diff --git "a/en-am/jw300-amharic-baseline/test.am" "b/en-am/jw300-amharic-baseline/test.am" new file mode 100644--- /dev/null +++ "b/en-am/jw300-amharic-baseline/test.am" @@ -0,0 +1,1001 @@ +target_sentence +36 አዎ፣ ሌሎች ደግሞ መዘባበቻ በመሆንና በመገረፍ ይባስ ብሎም በመታሰርና ወህኒ ቤት በመጣል+ ፈተና ደርሶባቸዋል። +37 በድንጋይ ተወግረዋል፤+ ተፈትነዋል፤ በመጋዝ ለሁለት ተሰንጥቀዋል፤ በሰይፍ ተቀልተዋል፤+ እየተቸገሩ፣ መከራ እየተቀበሉና+ እየተንገላቱ+ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ተንከራተዋል፤+ +38 ዓለም እንዲህ ዓይነት ሰዎች የሚገቡት ሆኖ አልተገኘም። በየበረሃው፣ በየተራራው፣ በየዋሻውና+ በምድር ውስጥ ባሉ ጉድጓዶች ተቅበዝብዘዋል። +39 ይሁንና እነዚህ ሁሉ በእምነታቸው ምክንያት በመልካም የተመሠከረላቸው ቢሆኑም እንኳ የተስፋውን ቃል ፍጻሜ አላዩም፤ +40 ምክንያቱም አምላክ ያለእኛ ወደ ፍጽምና እንዲደርሱ ዓላማው ስላልነበረ ለእኛ የተሻለ ነገር ለመስጠት አስቀድሞ አስቧል።+ +2 ቀስ በቀስ እንዳንወሰድ+ ለሰማናቸው ነገሮች ከወትሮው የበለጠ ትኩረት መስጠታችን አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው።+ +2 በመላእክት አማካኝነት የተነገረው ቃል+ የጸና መሆኑ ከተረጋገጠ እንዲሁም ማንኛውም አለመታዘዝና መተላለፍ ከፍትሕ ጋር የሚስማማ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ+ +3 እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንል እንዴት ከቅጣት ልናመልጥ እንችላለን?+ ይህ መዳን መጀመሪያ ጌታችን የተናገረው+ ሲሆን እሱን የሰሙት ሰዎችም ለእኛ አረጋግጠውልናል፤ +4 አምላክም በምልክቶች፣ በድንቅ ነገሮች፣ በተለያዩ ተአምራትና+ ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን በማደል መሥክሯል።+ +5 ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለም+ያስገዛው ለመላእክት አይደለምና። +6 ነገር ግን አንድ ምሥክር፣ አንድ ቦታ ላይ እንዲህ ብሏል፦ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ወይስ ትንከባከበው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?+ +7 ከመላእክት ጥቂት አሳነስከው፤ የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፋህለት፤ እንዲሁም በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምከው። +8 ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዛህለት።”+ አምላክ ሁሉንም ነገር ለእሱ ስላስገዛ፣+ ያላስገዛለት ምንም ነገር የለም።+ ይሁንና በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት አናይም።+ +9 ነገር ግን ከመላእክት በጥቂቱ እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ+ እስከ ሞት ድረስ መከራ በመቀበሉ+ አሁን የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፍቶ እናየዋለን፤ እሱ በአምላክ ጸጋ ለሰው ሁሉ ሲል ሞትን ቀምሷል።+ +10 ሁሉ ነገር የሚኖረው ለአምላክ ነው፤ የሚኖረውም በእሱ አማካኝነት ነው። ስለዚህ አምላክ ብዙ ልጆችን ክብር ለማጎናጸፍ+ ሲል ለመዳን የሚያበቃቸውን “ዋና ወኪል”+ በመከራ አማካኝነት ፍጹም ማድረጉ የተገባ ነበር።+ +11 የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሰዎች፣+ ሁሉም ከአንድ አባት የመጡ ናቸውና፤+ ከዚህም የተነሳ እነሱን ወንድሞች ብሎ ለመጥራት አያፍርም፤+ +12 ምክንያቱም “ስምህን ለወንድሞቼ አሳውቃለሁ፤ በጉባኤ መካከልም በመዝሙር አወድስሃለሁ” ይላል።+ +13 ደግሞም “እኔ እምነቴን በእሱ ላይ እጥላለሁ” ይላል።+ እንደገናም “እነሆ! እኔና ይሖዋ* የሰጠኝ ልጆች” ይላል።+ +14 ስለዚህ እነዚህ “ልጆች” ሥጋና ደም ስለሆኑ እሱም ሥጋና ደም ሆነ፤+ ይህም የሆነው ለሞት የመዳረግ አቅም ያለውን+ ዲያብሎስን በሞቱ አማካኝነት እንዳልነበረ ያደርገው ዘንድ ነው፤+ +15 እንዲሁም ሞትን በመፍራታቸው በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ በባርነት ቀንበር የተያዙትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ ነው።+ +16 እሱ እየረዳ ያለው መላእክትን እንዳልሆነ የታወቀ ነውና፤ ከዚህ ይልቅ እየረዳ ያለው የአብርሃምን ዘር ነው።+ +17 ስለሆነም ለሕዝቡ ኃጢአት የማስተሰረያ መሥዋዕት ለማቅረብ*+ በአምላክ አገልግሎት መሐሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ይሆን ዘንድ በሁሉ ረገድ እንደ “ወንድሞቹ” መ��ን አስፈለገው።+ +18 በተፈተነ ጊዜ እሱ ራሱ መከራ ስለደረሰበት+ በፈተና ላይ ላሉት ሊደርስላቸው ይችላል።+ +4 ስለዚህ ወደ እረፍቱ የመግባት ተስፋ አሁንም ስላለ ከእናንተ መካከል ማንም ለዚያ የማይበቃ ሆኖ እንዳይገኝ እንጠንቀቅ።*+ +2 ለአባቶቻችን ተሰብኮ እንደነበረው ሁሉ ምሥራቹ ለእኛም ተሰብኳልና፤+ እነሱ ግን ሰምተው የታዘዙት ሰዎች የነበራቸው ዓይነት እምነት ስላልነበራቸው የሰሙት ቃል አልጠቀማቸውም። +3 እኛ ግን እምነት በማሳየታችን ወደዚህ እረፍት እንገባለን። ምንም እንኳ የእሱ ሥራ ዓለም ከተመሠረተበት* ጊዜ ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም+ “‘ወደ እረፍቴ አይገቡም’ ብዬ በቁጣዬ ማልኩ” ብሏል።+ +4 በአንድ ቦታ ላይ ሰባተኛውን ቀን አስመልክቶ “አምላክም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ አረፈ” ብሏልና፤+ +5 እንደገና እዚህ ላይ “ወደ እረፍቴ አይገቡም” ብሏል።+ +6 ስለዚህ ገና ወደ እረፍቱ የሚገቡ ስላሉና መጀመሪያ ምሥራቹ የተሰበከላቸው ባለመታዘዛቸው ምክንያት ሳይገቡ ስለቀሩ+ +7 ከረጅም ጊዜ በኋላ በዳዊት መዝሙር ላይ “ዛሬ” በማለት እንደገና አንድን ቀን መደበ፤ ይህም ቀደም ሲል “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ ልባችሁን አታደንድኑ” እንደተባለው ነው።+ +8 ኢያሱ+ ወደ እረፍት ቦታ እየመራ አስገብቷቸው ቢሆን ኖሮ አምላክ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር። +9 ስለዚህ የአምላክ ሕዝብ የሰንበት እረፍት ገና ይቀረዋል።+ +10 ወደ አምላክ እረፍት የገባ ሰው አምላክ ከሥራው እንዳረፈ ሁሉ እሱም ከሥራው አርፏልና።+ +11 ስለዚህ ማንም የእነዚያን ያለመታዘዝ ምሳሌ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደዚያ እረፍት ለመግባት የተቻለንን ሁሉ እናድርግ።+ +12 የአምላክ ቃል ሕያውና ኃይለኛ ነው፤+ በሁለት በኩል ስለት ካለው ከየትኛውም ሰይፍ የበለጠ ስለታም ነው፤+ ነፍስንና* መንፈስን* እንዲሁም መገጣጠሚያንና መቅኒን እስኪለያይ ድረስ ሰንጥቆ ይገባል፤ የልብንም ሐሳብና ዓላማ መረዳት ይችላል። +13 ደግሞም ከአምላክ እይታ የተሰወረ አንድም ፍጥረት የለም፤+ ይልቁንም ተጠያቂዎች በሆንበት+ በእሱ ዓይኖች ፊት ሁሉም ነገር የተራቆተና ገሃድ የወጣ ነው። +14 እንግዲህ ወደ ሰማያት የገባ ታላቅ ሊቀ ካህናት ይኸውም የአምላክ ልጅ+ ኢየሱስ እንዳለን ስለምናውቅ በእሱ ላይ እምነት እንዳለን ምንጊዜም በይፋ እንናገር።+ +15 ያለን ሊቀ ካህናት በድካማችን ሊራራልን የማይችል አይደለምና፤+ ከዚህ ይልቅ እንደ እኛው በሁሉም ረገድ የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁንና እሱ ኃጢአት የለበትም።+ +16 እንግዲህ እርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትና ጸጋ እናገኝ ዘንድ ያለምንም ፍርሃት* ወደ ጸጋው ዙፋን እንቅረብ።+ +6 ስለዚህ ስለ ክርስቶስ ከተማርነው መሠረታዊ ትምህርት አልፈን ስለሄድን+ ወደ ጉልምስና ለመድረስ እንጣጣር፤+ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፤ ይኸውም ከሞቱ ሥራዎች ንስሐ ስለ መግባት፣ በአምላክ ስለ ማመን፣ +2 እንዲሁም ስለ ጥምቀቶች፣ እጆችን ስለ መጫን፣+ ስለ ሙታን ትንሣኤና+ ስለ ዘላለማዊ ፍርድ የሚገልጹ ትምህርቶችን ደግመን አንማር። +3 አምላክ ከፈቀደ ይህን እናደርጋለን። +4 ቀደም ሲል ብርሃን በርቶላቸው የነበሩትን፣+ ሰማያዊውን ነፃ ስጦታ የቀመሱትን፣ መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉትን፣ +5 መልካም የሆነውን የአምላክ ቃልና በሚመጣው ሥርዓት* የሚገኙትን በረከቶች* የቀመሱትን፣ +6 በኋላ ግን ከእምነት ጎዳና የራቁትን+ እንደገና ወደ ንስሐ መመለስ አይቻልም፤ ምክንያቱም የአምላክን ልጅ ለራሳቸው እንደገና በእንጨት ላይ ይቸነክሩታል፤ እንዲሁም በአደባባይ ያዋርዱታል።+ +7 በየጊዜው በላዩ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የሚጠጣና ለአራሾቹ መብል የሚሆን አትክልት የሚያ���ራ መሬት ከአምላክ በረከትን ያገኛልና። +8 እሾህና አሜኬላ የሚያበቅል ከሆነ ግን የተተወና ለመረገም የተቃረበ ይሆናል፤ በመጨረሻም በእሳት ይቃጠላል። +9 ይሁን እንጂ የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ምንም እንኳ እንደዚህ ብለን ብንናገርም እናንተ በተሻለ ሁኔታ ላይ ይኸውም ወደ መዳን በሚያደርስ ሁኔታ ላይ እንደምትገኙ እርግጠኞች ነን። +10 አምላክ ቅዱሳንን በማገልገልም* ሆነ ወደፊትም ማገልገላችሁን በመቀጠል የምታከናውኑትን ሥራ እንዲሁም ለስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር+ በመርሳት ፍትሕ አያዛባም። +11 ይሁንና ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ የሆነውን ተስፋ+ እስከ መጨረሻው መያዝ እንድትችሉ+ እያንዳንዳችሁ ያንኑ ትጋት እንድታሳዩ እንመኛለን፤ +12 ይህም አምላክ ቃል የገባቸውን ነገሮች በእምነትና በትዕግሥት የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ነው።+ +13 አምላክ ለአብርሃም ቃል በገባለት ጊዜ ሊምልበት የሚችል ከእሱ የሚበልጥ ሌላ ማንም ስለሌለ በራሱ ስም ማለ፤+ +14 እንዲህም አለ፦ “በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በእርግጥ አበዛዋለሁ።”+ +15 በመሆኑም አብርሃም በትዕግሥት ከጠበቀ በኋላ ይህን የተስፋ ቃል አገኘ። +16 ሰዎች ከእነሱ በሚበልጥ ይምላሉ፤ መሐላቸውም እንደ ሕጋዊ ዋስትና ስለሆነ ማንኛውም ሙግት በመሐላው ይቋጫል።+ +17 በተመሳሳይም አምላክ ዓላማው ፈጽሞ የማይለወጥ መሆኑን ለተስፋው ቃል ወራሾች+ ይበልጥ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ለማሳየት በወሰነ ጊዜ የተስፋውን ቃል በመሐላ አረጋገጠ። +18 ይህን ያደረገው መጠጊያ ለማግኘት ወደ እሱ የሸሸን እኛ፣ አምላክ ሊዋሽ በማይችልባቸው፣+ ፈጽሞ በማይለወጡት በእነዚህ ሁለት ነገሮች አማካኝነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን እንድንይዝ የሚረዳንን ከፍተኛ ማበረታቻ እንድናገኝ ነው። +19 እኛ ለነፍሳችን* እንደ መልሕቅ አስተማማኝና ጽኑ የሆነ ይህ ተስፋ አለን፤+ ተስፋውም መጋረጃውን አልፈን ወደ ውስጥ እንድንገባ ያስችለናል፤+ +20 ከመልከጼዴቅ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ለዘላለም ሊቀ ካህናት+ የሆነው ኢየሱስ+ ፈር ቀዳጅ ሆኖ ስለ እኛ ወደዚያ ገብቷል። +10 ሕጉ ወደፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ+ ነው እንጂ የእነዚህ ነገሮች እውነተኛ አካል አይደለም፤ ስለዚህ ሕጉ ከዓመት ዓመት እነዚያኑ መሥዋዕቶች በማቅረብ አምላክን የሚያመልኩትን ሰዎች ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም።*+ +2 ቢችልማ ኖሮ መሥዋዕት ማቅረቡን ይተዉት አልነበረም? ምክንያቱም ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርቡት ሰዎች አንዴ ከነጹ በኋላ ሕሊናቸው በጥፋተኝነት ስሜት አይወቅሳቸውም ነበር። +3 ይሁንና እነዚህ መሥዋዕቶች ከዓመት ዓመት ኃጢአት እንዲታወስ ያደርጋሉ፤+ +4 የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ማስወገድ አይችልምና። +5 ስለዚህ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ እንዲህ አለ፦ “‘መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤ ከዚህ ይልቅ አካል አዘጋጀህልኝ። +6 ሙሉ በሙሉ በሚቃጠል መባና ለኃጢአት በሚቀርብ መባ ደስ አልተሰኘህም።’+ +7 በዚህ ጊዜ ‘እነሆ፣ አምላክ ሆይ፣ (ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል እንደተጻፈ) ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ’ አልኩ።”+ +8 በመጀመሪያ እንዲህ አለ፦ “መሥዋዕትን፣ መባን፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባንና ለኃጢአት የሚቀርብ መባን አልፈለግክም፤ እንዲሁም ደስ አልተሰኘህበትም።” እነዚህ መሥዋዕቶች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የሚቀርቡ ናቸው። +9 ከዚያም “እነሆ፣ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ።+ ሁለተኛውን ለማቋቋም የመጀመሪያውን ያስወግዳል። +10 በዚህ “ፈቃድ”+ መሠረት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት ሆኖ በቀረበው የኢየሱስ ክርስቶስ አካል አማካኝነት ተቀድሰናል።+ +11 በተጨማሪም እያንዳንዱ ካህን ቅዱስ አገልግሎት ለማቅረብና*+ ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የማይችሉትን+ እነዚያኑ መሥዋዕቶች በየጊዜው ለማቅረብ+ ዕለት ዕለት በቦታው ይገኛል። +12 ይህ ሰው ግን ስለ ኃጢአት ለሁልጊዜ የሚሆን አንድ መሥዋዕት አቅርቦ በአምላክ ቀኝ ተቀምጧል፤+ +13 ከዚያን ጊዜ አንስቶ ጠላቶቹ የእግሩ መርገጫ እስኪደረጉ ድረስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።+ +14 እነዚያን የሚቀደሱትን ለሁልጊዜ ፍጹማን ያደረጋቸው አንድ መሥዋዕት በማቅረብ ነውና።+ +15 ከዚህ በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስም ስለ እኛ ይመሠክራል፤ በመጀመሪያ እንዲህ ይላልና፦ +16 “‘ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው’ ይላል ይሖዋ።* ‘ሕግጋቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ፤ በአእምሯቸውም ላይ እጽፋቸዋለሁ።’”+ +17 በመቀጠልም “ኃጢአታቸውንና የዓመፅ ድርጊታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም” ይላል።+ +18 እንግዲህ እነዚህ ይቅር ከተባሉ፣ ከዚህ በኋላ ለኃጢአት መባ ማቅረብ አያስፈልግም። +19 ስለዚህ ወንድሞች፣ በኢየሱስ ደም አማካኝነት ወደ ቅዱሱ ስፍራ በሚወስደው መንገድ ለመግባት የሚያስችል ድፍረት* አግኝተናል፤+ +20 እሱ የከፈተልን* ይህ መንገድ ወደ ሕይወት የሚመራ አዲስ መንገድ ነው። ይህን ያደረገው በመጋረጃው+ ማለትም በሥጋው በኩል በማለፍ ነው፤ +21 በተጨማሪም በአምላክ ቤት ላይ የተሾመ ታላቅ ሊቀ ካህናት ስላለን+ +22 ከክፉ ሕሊና ለመንጻት+ ልባችንን ተረጭተን እንዲሁም ሰውነታችንን በንጹሕ ውኃ ታጥበን+ በቅን ልቦና እና በሙሉ እምነት ወደ አምላክ እንቅረብ። +23 የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ስለሆነ ተስፋችንን በይፋ ለማወጅ የሚያስችለንን አጋጣሚ ያላንዳች ማወላወል አጥብቀን እንያዝ።+ +24 እንዲሁም እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት* እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤*+ +25 አንዳንዶች ልማድ እንዳደረጉት መሰብሰባችንን* ቸል አንበል፤+ ከዚህ ይልቅ እርስ በርስ እንበረታታ፤+ ደግሞም ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስናይ ከበፊቱ ይበልጥ ይህን እናድርግ።+ +26 የእውነትን ትክክለኛ እውቀት ካገኘን በኋላ ሆን ብለን በኃጢአት ጎዳና ብንመላለስ+ ለኃጢአታችን የሚቀርብ ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤+ +27 ከዚህ ይልቅ አስፈሪ ፍርድ ይጠብቀናል፤ አምላክን የሚቃወሙትን የሚበላ የሚነድ ቁጣም ይኖራል።+ +28 የሙሴን ሕግ የጣሰ ማንኛውም ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሠከሩበት ያለርኅራኄ ይገደል ነበር።+ +29 ታዲያ የአምላክን ልጅ የረገጠ፣ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳኑን ደም+ እንደ ተራ ነገር የቆጠረና የጸጋን መንፈስ በንቀት ያጥላላ ሰው ምን ያህል የከፋ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?+ +30 “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና። ደግሞም “ይሖዋ* ሕዝቡን ይዳኛል።”+ +31 በሕያው አምላክ እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነገር ነው። +32 ይሁን እንጂ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ+ በመከራ ውስጥ በከፍተኛ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀድሞውን ጊዜ ዘወትር አስታውሱ። +33 በአደባባይ ለነቀፋና ለመከራ የተጋለጣችሁባቸው* ጊዜያት ነበሩ፤ ደግሞም እንዲህ ዓይነት ሁኔታ የደረሰባቸውን ሰዎች መከራ የተጋራችሁባቸው* ጊዜያት ነበሩ። +34 እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ዘላቂ የሆነ ንብረት እንዳላችሁ ስለምታውቁ+ በእስር ላይ ላሉት ራራችሁላቸው፤ እንዲሁም ንብረታችሁ ሲዘረፍ ሁኔታውን በደስታ ተቀበላችሁ።+ +35 እንግዲህ ትልቅ ወሮታ የሚያስገኘውን በድፍረት የመናገር ነፃነታችሁን አሽቀንጥራችሁ አትጣሉት።+ +36 የአምላክን ፈቃድ ከፈጸማችሁ በኋላ የተስፋው ቃል ሲፈጸም ማየት እንድትችሉ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።+ +37 ምክንያቱም “ለጥቂት ጊዜ ነው”+ እንጂ “የሚመጣው እ�� ይመጣል፤ ደግሞም አይዘገይም።”+ +38 “ሆኖም ጻድቅ አገልጋዬ በእምነት ይኖራል”፤+ ደግሞም “ወደኋላ ቢያፈገፍግ በእሱ ደስ አልሰኝም።”*+ +39 እንግዲህ እኛ በሕይወት የሚያኖር* እምነት እንዳላቸው ሰዎች ነን እንጂ ወደ ጥፋት እንደሚያፈገፍጉ ሰዎች አይደለንም።+ +9 የቀድሞው ቃል ኪዳን በበኩሉ ቅዱስ አገልግሎት የሚከናወንባቸው ደንቦችና በምድር ላይ የራሱ ቅዱስ ስፍራ+ ነበረው። +2 መቅረዙ፣+ ጠረጴዛውና በአምላክ ፊት የቀረበው ኅብስት+ የሚገኙበት የድንኳኑ የመጀመሪያው ክፍል ተሠርቶ ነበር፤ ይህም ቅድስት ይባላል።+ +3 ከሁለተኛው መጋረጃ+ በስተ ኋላ ግን ቅድስተ ቅዱሳን የሚባለው የድንኳኑ ክፍል ይገኝ ነበር።+ +4 በዚህ ክፍል ውስጥ የወርቅ ጥና+ እና ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠው+ የቃል ኪዳኑ ታቦት+ ይገኙ ነበር፤ በታቦቱ ውስጥም መና የያዘው የወርቅ ማሰሮ፣+ ያቆጠቆጠችው የአሮን በትርና+ የቃል ኪዳኑ ጽላቶች+ ነበሩ፤ +5 በላዩ ላይ ደግሞ የስርየት መክደኛውን* የሚጋርዱ ክብራማ ኪሩቦች ነበሩ።+ ይሁንና ስለ እነዚህ ነገሮች በዝርዝር ለመናገር አሁን ጊዜው አይደለም። +6 እነዚህ ነገሮች በዚህ መንገድ ከተሠሩ በኋላ ካህናቱ ቅዱስ አገልግሎቶችን ለማከናወን ወደ ድንኳኑ የመጀመሪያ ክፍል ሁልጊዜ ይገባሉ፤+ +7 ወደ ሁለተኛው ክፍል የሚገባው ግን ሊቀ ካህናቱ ብቻ ነበር፤ የሚገባውም በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤+ ደግሞም ለራሱና+ ሕዝቡ+ ባለማወቅ ለፈጸመው ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም።+ +8 በዚህ መንገድ፣ የመጀመሪያው ድንኳን* ተተክሎ ሳለ ወደ ቅዱሱ ስፍራ* የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ግልጽ አድርጓል።+ +9 ይህ ድንኳን ለአሁኑ ዘመን ምሳሌ+ ሲሆን ከዚህ ዝግጅት ጋር በሚስማማ ሁኔታ ስጦታዎችና መሥዋዕቶች ይቀርባሉ።+ ይሁን እንጂ እነዚህ ነገሮች ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርበው ሰው ፍጹም በሆነ መንገድ ንጹሕ ሕሊና እንዲኖረው ሊያደርጉ አይችሉም።+ +10 እነዚህ ነገሮች ከምግብ፣ ከመጠጥና ከተለያዩ የመንጻት ሥርዓቶች* ጋር ብቻ የተያያዙ ናቸው።+ ደግሞም አካልን የሚመለከቱ ደንቦች+ ሲሆኑ በሥራ ላይ የዋሉትም፣ ሁኔታዎች የሚስተካከሉበት የተወሰነው ጊዜ እስኪመጣ ድረስ ነበር። +11 ይሁን እንጂ ክርስቶስ አሁን ላሉት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ በመጣ ጊዜ በሰው እጅ ወዳልተሠራው ይኸውም ከዚህ ፍጥረት ወዳልሆነው ይበልጥ ታላቅና ፍጹም ወደሆነው ድንኳን ገብቷል። +12 ወደ ቅዱሱ ስፍራ የገባው የፍየሎችንና የወይፈኖችን ደም ይዞ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የገዛ ራሱን ደም ይዞ+ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገባ፤ ደግሞም ለእኛ ዘላለማዊ መዳን* አስገኘልን።+ +13 የፍየሎችና የኮርማዎች ደም+ እንዲሁም በረከሱ ሰዎች ላይ የሚረጭ የጊደር አመድ ሥጋን በማንጻት የሚቀድስ ከሆነ+ +14 በዘላለማዊ መንፈስ አማካኝነት ራሱን ያላንዳች እንከን ለአምላክ ያቀረበው የክርስቶስ ደም+ ሕያው ለሆነው አምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንድናቀርብ+ ሕሊናችንን ከሞቱ ሥራዎች እንዴት አብልጦ አያነጻም?+ +15 የአዲስ ቃል ኪዳን መካከለኛ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው።+ መካከለኛ የሆነውም የተጠሩት የዘላለማዊውን ውርሻ+ ተስፋ ይቀበሉ ዘንድ ነው። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በሞቱ የተነሳ ሲሆን በእሱ ሞት አማካኝነት በቀድሞው ቃል ኪዳን ሥር ሆነው ሕግ በመተላለፍ ከፈጸሟቸው ድርጊቶች በቤዛ ነፃ ወጥተዋል።+ +16 ቃል ኪዳን ሲኖር ቃል ኪዳኑን የፈጸመው ሰው* መሞቱ መረጋገጥ አለበት፤ +17 ምክንያቱም ቃል ኪዳኑን የፈጸመው ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ቃል ኪዳኑ መቼም ተፈጻሚ ሊሆን ስለማይችል ቃል ኪዳን የሚጸናው ሞትን መሠረት በማድረግ ነው። +18 ከዚህም የተነሳ የቀድሞ��� ቃል ኪዳንም ያለደም ሥራ ላይ መዋል አልጀመረም።* +19 ሙሴ በሕጉ ላይ የሰፈረውን እያንዳንዱን ትእዛዝ ለሕዝቡ ሁሉ ከተናገረ በኋላ የወይፈኖችንና የፍየሎችን ደም ከውኃ፣ ከቀይ ሱፍና ከሂሶጵ ጋር ወስዶ መጽሐፉንና* ሕዝቡን ሁሉ ረጭቷል፤ +20 የረጨውም “አምላክ እንድትጠብቁት ያዘዛችሁ የቃል ኪዳኑ ደም ይህ ነው” ብሎ ነው።+ +21 በተመሳሳይም በድንኳኑና ቅዱስ አገልግሎት* በሚቀርብባቸው ዕቃዎች ሁሉ ላይ ደም ረጭቷል።+ +22 አዎ፣ በሕጉ መሠረት ሁሉም ነገር ማለት ይቻላል በደም ይነጻል፤+ ደም ካልፈሰሰ በስተቀር ይቅርታ ማግኘት አይቻልም።+ +23 ስለዚህ በሰማያት ላሉት ነገሮች ዓይነተኛ አምሳያ+ የሆኑት ሁሉ በዚህ መንገድ መንጻታቸው+ የግድ አስፈላጊ ነበር፤ በሰማያት ያሉት ነገሮች ግን የተሻሉ መሥዋዕቶች ያስፈልጓቸዋል። +24 ክርስቶስ የገባው በሰው እጅ ወደተሠራውና የእውነተኛው ቅዱስ ስፍራ አምሳያ+ ወደሆነው ስፍራ አይደለምና፤+ ከዚህ ይልቅ አሁን ስለ እኛ በአምላክ ፊት ይታይ ዘንድ+ ወደ ሰማይ ገብቷል።+ +25 የገባው ግን ሊቀ ካህናቱ የራሱን ሳይሆን የእንስሳ ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይገባ እንደነበረው ራሱን ብዙ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ አይደለም።+ +26 አለዚያማ ዓለም ከተመሠረተ* ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ኃጢአትን ለማስወገድ በሥርዓቶቹ* መደምደሚያ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ራሱን ገልጧል።+ +27 ሰው ሁሉ አንድ ጊዜ መሞቱ አይቀርም፤ ከዚያ በኋላ ግን ፍርድ ይቀበላል፤ +28 በተመሳሳይም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለመሸከም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት ሆኖ ቀርቧል፤+ ለሁለተኛ ጊዜ የሚገለጠውም ኃጢአትን ለማስወገድ አይደለም፤ መዳን ለማግኘት እሱን በጉጉት የሚጠባበቁትም ያዩታል።+ +13 እርስ በርሳችሁ እንደ ወንድማማች መዋደዳችሁን ቀጥሉ።+ +2 እንግዳ መቀበልን* አትርሱ፤+ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ ሳያውቁት መላእክትን አስተናግደዋልና።+ +3 በእስር ላይ ያሉትን ከእነሱ ጋር ታስራችሁ እንዳላችሁ አድርጋችሁ በማሰብ+ ሁልጊዜ አስታውሷቸው፤+ እናንተም ራሳችሁ ገና በሥጋ ያላችሁ በመሆናችሁ* እንግልት እየደረሰባቸው ያሉትን አስቡ። +4 ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፣ መኝታውም ከርኩሰት የጸዳ ይሁን፤+ አምላክ ሴሰኞችንና* አመንዝሮችን ይፈርድባቸዋልና።+ +5 አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን፤+ ባሏችሁ ነገሮች ረክታችሁ ኑሩ።+ እሱ “ፈጽሞ አልተውህም፤ በምንም ዓይነት አልጥልህም” ብሏልና።+ +6 ስለዚህ በሙሉ ልብ “ይሖዋ* ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።+ +7 የአምላክን ቃል የነገሯችሁን በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ፤+ ደግሞም ምግባራቸው ያስገኘውን ውጤት በሚገባ በማጤን በእምነታቸው ምሰሏቸው።+ +8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ለዘላለምም ያው ነው። +9 በልዩ ልዩና እንግዳ በሆኑ ትምህርቶች አትወሰዱ፤ ልባችን በምግብ* ሳይሆን በአምላክ ጸጋ ቢጠናከር መልካም ነውና፤ በዚህ የተጠመዱ ምንም አልተጠቀሙም።+ +10 እኛ መሠዊያ ያለን ሲሆን በድንኳኑ ውስጥ ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርቡት ከመሠዊያው ላይ ወስደው መብላት አይፈቀድላቸውም።+ +11 ምክንያቱም ሊቀ ካህናቱ የእንስሳቱን ደም የኃጢአት መባ አድርጎ ወደ ቅዱሱ ስፍራ* የሚወስደው ሲሆን ሥጋው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል።+ +12 ስለዚህ ኢየሱስም ሕዝቡን በገዛ ራሱ ደም ለመቀደስ+ ከከተማው በር ውጭ መከራ ተቀበለ።+ +13 እንግዲህ እኛም እሱ የተሸከመውን ነቀፋ ተሸክመን ከሰፈር ውጭ እሱ ወዳለበት እንሂድ፤+ +14 በዚህ ቋሚ ከተማ የለንምና፤ ከዚህ ይልቅ ወደፊት የምትመጣዋን ከተማ በጉጉት እንጠባበቃለን።+ +15 ስለዚህ በኢየሱስ አማካኝነት የውዳሴ መሥዋዕት ዘወትር ለአምላክ እናቅርብ፤+ ይህም ስሙን በይፋ የምናውጅበት+ የከንፈራችን ፍሬ ነው።+ +16 በተጨማሪም መልካም ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤+ አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታልና።+ +17 ተግተው ስለሚጠብቋችሁና* ይህን በተመለከተ ስሌት ስለሚያቀርቡ+ በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ታዘዙ+ እንዲሁም ተገዙ፤+ ይህን የምታደርጉት ሥራቸውን በደስታ እንጂ በሐዘን እንዳያከናውኑ ነው፤ አለዚያ ሥራቸውን የሚያከናውኑት በሐዘን ይሆናል፤ ይህ ደግሞ እናንተን ይጎዳችኋል። +18 ለእኛ መጸለያችሁን ቀጥሉ፤ ምክንያቱም ሐቀኛ* ሕሊና እንዳለን እናምናለን፤ ደግሞም በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር እንፈልጋለን።+ +19 በተለይ ደግሞ ወደ እናንተ በፍጥነት ተመልሼ እንድመጣ ትጸልዩልኝ ዘንድ አሳስባችኋለሁ። +20 እንግዲያው ታላቅ የበጎች እረኛ+ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ የዘላለማዊውን ቃል ኪዳን ደም ይዞ ከሞት እንዲነሳ ያደረገው የሰላም አምላክ +21 ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ እሱ በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን ነገር እንድናደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ያነሳሳናል። ለእሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። +22 እንግዲህ ወንድሞች፣ የጻፍኩላችሁ ደብዳቤ አጭር ስለሆነ ይህን የማበረታቻ ቃል በትዕግሥት እንድታዳምጡ አሳስባችኋለሁ። +23 ወንድማችን ጢሞቴዎስ መፈታቱን እንድታውቁ እፈልጋለሁ። ቶሎ ከመጣ አብረን መጥተን እናያችኋለን። +24 በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ሁሉና ለቀሩት ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጣሊያን+ ያሉት ሰላምታ ልከውላችኋል። +25 የአምላክ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን። +5 ከሰዎች መካከል የተመረጠ እያንዳንዱ ሊቀ ካህናት ለኃጢአት መባና መሥዋዕት ያቀርብ ዘንድ+ እነሱን በመወከል የአምላክን አገልግሎት ለማከናወን ይሾማል።+ +2 እሱ ራሱ ድክመት ስላለበት* አላዋቂ የሆኑትንና የሚሳሳቱትን* በርኅራኄ* ሊይዛቸው ይችላል፤ +3 በዚህም የተነሳ ለሕዝቡ የኃጢአት መባ እንደሚያቀርብ ሁሉ ለራሱም ለማቅረብ ይገደዳል።+ +4 አንድ ሰው ይህን የክብር ቦታ የሚያገኘው እንደ አሮን፣ አምላክ ሲጠራው ብቻ ነው እንጂ በራሱ ፈቃድ አይደለም።+ +5 ክርስቶስም ሊቀ ካህናት በመሆን ራሱን ከፍ ከፍ አላደረገም፤+ ከዚህ ይልቅ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ”+ ብሎ ስለ እሱ የተናገረው፣ ከፍ ከፍ አደረገው። +6 ደግሞም በሌላ ቦታ ላይ “እንደ መልከጼዴቅ፣ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሏል።+ +7 ክርስቶስ በምድር ላይ በኖረበት ዘመን* ከሞት ሊያድነው ለሚችለው በከፍተኛ ለቅሶና እንባ ምልጃና ልመና አቀረበ፤+ አምላካዊ ፍርሃት ስለነበረውም ጸሎቱ ተሰማለት። +8 ልጅ ቢሆንም እንኳ ከደረሰበት መከራ መታዘዝን ተማረ።+ +9 በዚህም ፍጹም ከሆነ በኋላ+ የሚታዘዙት ሁሉ ዘላለማዊ መዳን እንዲያገኙ ምክንያት ሆነላቸው፤+ +10 ምክንያቱም ከመልከጼዴቅ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ አምላክ ሊቀ ካህናት አድርጎ ሾሞታል።+ +11 እሱን በተመለከተ ብዙ የምንናገረው ነገር አለን፤ ይሁንና ጆሯችሁ ስለደነዘዘ ለማስረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው። +12 በአሁኑ ጊዜ* አስተማሪዎች ልትሆኑ ይገባችሁ የነበረ ቢሆንም የአምላክን ቅዱስ መልእክት መሠረታዊ ነገሮች እንደገና ከመጀመሪያ ጀምሮ የሚያስተምራችሁ ሰው ትፈልጋላችሁ፤+ ደግሞም ጠንካራ ምግብ ከመመገብ ይልቅ እንደገና ወተት መፈለግ ጀምራችኋል። +13 ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለሆነ ከጽድቅ ቃል ጋር ትውውቅ የለውም።+ +14 ጠንካራ ምግብ ግን ትክክልና ስህተት የሆ���ውን ነገር መለየት እንዲችሉ የማስተዋል ችሎታቸውን በማሠራት ላሠለጠኑ* ጎልማሳ ሰዎች ነው። +3 ወንድሞቼ ሆይ፣ ከእናንተ መካከል ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ፤ ምክንያቱም እኛ የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል* ታውቃላችሁ።+ +2 ሁላችንም ብዙ ጊዜ እንሰናከላለንና።*+ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር ይህ ሰው መላ ሰውነቱንም መቆጣጠር* የሚችል ፍጹም ሰው ነው። +3 ፈረሶች እንዲታዘዙልን አፋቸው ውስጥ ልጓም ካስገባን መላ ሰውነታቸውንም መምራት እንችላለን። +4 መርከቦችንም ተመልከቱ፦ በጣም ትልቅና በኃይለኛ ነፋስ የሚነዱ ቢሆኑም የመርከቡ ነጂ በትንሽ መሪ ወደሚፈልገው አቅጣጫ ሁሉ ይመራቸዋል። +5 ልክ እንደዚሁም ምላስ ትንሽ የአካል ክፍል ሆና ሳለ ጉራዋን ትነዛለች። በጣም ሰፊ የሆነን ጫካ በእሳት ለማያያዝ ትንሽ እሳት ብቻ ይበቃል! +6 ምላስም እሳት ናት።+ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የክፋትን ዓለም ትወክላለች፤ መላ ሰውነትን ታረክሳለችና፤+ እንዲሁም መላውን የሕይወት ጎዳና* ታቃጥላለች፤ እሷም በገሃነም* ትቃጠላለች። +7 ማንኛውም ዓይነት የዱር እንስሳ፣ ወፍ፣ በምድር ላይ የሚሳብ ፍጥረትና በባሕር ውስጥ የሚኖር ፍጥረት በሰዎች ሊገራ ይችላል፤ ደግሞም ተገርቷል። +8 ምላስን ግን ሊገራ የሚችል አንድም ሰው የለም። ምላስ ገዳይ መርዝ የሞላባት፣ ለመቆጣጠር የምታስቸግር ጎጂ ነገር ናት።+ +9 በምላሳችን አባት የሆነውን ይሖዋን* እናወድሳለን፤ ይሁንና በዚህችው ምላሳችን “በአምላክ አምሳል” የተፈጠሩትን ሰዎች+ እንረግማለን። +10 ከአንድ አፍ በረከትና እርግማን ይወጣሉ። ወንድሞቼ፣ ይህ መሆኑ ተገቢ አይደለም።+ +11 አንድ ምንጭ ከዚያው ጉድጓድ ጣፋጭና መራራ ውኃ ያፈልቃል? +12 ወንድሞቼ፣ የበለስ ዛፍ ወይራን ወይም ደግሞ የወይን ተክል በለስን ሊያፈራ ይችላል?+ ከጨዋማ ውኃም ጣፋጭ ውኃ ሊገኝ አይችልም። +13 ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ ሰው ማን ነው? ሥራውን የሚያከናውነው ከጥበብ በመነጨ ገርነት* መሆኑን በመልካም ምግባሩ ያሳይ። +14 ሆኖም በልባችሁ ውስጥ መራራ ቅናትና+ ጠበኝነት*+ ካለ አትኩራሩ፤+ እንዲሁም በእውነት ላይ አትዋሹ። +15 ይህ ከሰማይ የሚመጣ ጥበብ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ምድራዊ፣+ እንስሳዊና አጋንንታዊ ነው። +16 ቅናትና ጠበኝነት* ባለበት ሁሉ ብጥብጥና መጥፎ ነገሮችም ይኖራሉ።+ +17 ከሰማይ የሆነው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ+ ነው፤ ከዚያም ሰላማዊ፣+ ምክንያታዊ፣+ ለመታዘዝ ዝግጁ የሆነ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬዎች የሞሉበት+ እንዲሁም አድልዎና+ ግብዝነት የሌለበት+ ነው። +18 ከዚህም በላይ የጽድቅ ፍሬ ሰላም ፈጣሪ ለሆኑ ሰዎች*+ ሰላማዊ በሆኑ ሁኔታዎች+ ይዘራል። +1 የአምላክና የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የሆነው ያዕቆብ፣+ በየቦታው ለተበተኑት ለ12ቱ ነገዶች፦ ሰላምታ ይድረሳችሁ! +2 ወንድሞቼ ሆይ፣ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት፤+ +3 ይህን ስታደርጉ ተፈትኖ የተረጋገጠው እምነታችሁ ጽናት እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ።+ +4 ይሁንና በሁሉም ረገድ ምንም የማይጎድላችሁ ፍጹማንና* እንከን የለሽ እንድትሆኑ ጽናት ሥራውን ሙሉ በሙሉ ይፈጽም።+ +5 እንግዲህ ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤+ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ* ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤+ ይህም ሰው ይሰጠዋል።+ +6 ሆኖም ምንም ሳይጠራጠር በእምነት መለመኑን ይቀጥል፤+ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ እንደሚገፋና እንደሚናወጥ የባሕር ማዕበል ነውና። +7 እንዲያውም እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከይሖዋ* አንዳች ነገር አገኛለሁ ብሎ መጠበቅ የለበትም፤ +8 ይህ ሰው በሁለት ሐሳብ የሚዋልልና በመንገዱ ሁሉ የሚወላውል ነው።+ +9 ይሁንና ዝቅ ያለው ወንድም ከፍ በመደረጉ ደስ ይበለው፤*+ +10 እንዲሁም ባለጸጋ የሆነው ዝቅ በመደረጉ+ ደስ ይበለው፤ ምክንያቱም ባለጸጋ ሰው እንደ ሜዳ አበባ ይረግፋል። +11 ፀሐይ ወጥታ በኃይለኛ ሙቀቷ ተክሉን ታጠወልጋለች፤ አበባውም ይረግፋል፤ ውበቱም ይጠፋል፤ ባለጸጋ ሰውም ልክ እንደዚሁ በዕለት ተዕለት ተግባሩ ሲዋትት ከስሞ ይጠፋል።+ +12 ፈተናን በጽናት ተቋቁሞ የሚኖር ሰው ደስተኛ ነው፤+ ምክንያቱም ይህ ሰው በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት በሚያገኝበት ጊዜ፣ ይሖዋ* እሱን ለሚወዱት ቃል የገባውን የሕይወት አክሊል ይቀበላል።+ +13 ማንም ሰው ፈተና ሲደርስበት “አምላክ እየፈተነኝ ነው” አይበል። አምላክ በክፉ ነገር ሊፈተን አይችልምና፤ እሱ ራሱም ማንንም በክፉ ነገር አይፈትንም። +14 ሆኖም እያንዳንዱ ሰው በራሱ ምኞት ሲማረክና ሲታለል* ይፈተናል።+ +15 ከዚያም ምኞት ከፀነሰች በኋላ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአት ሲፈጸም ደግሞ ሞት ያስከትላል።+ +16 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ አትታለሉ። +17 መልካም ስጦታ ሁሉና ፍጹም ገጸ በረከት ሁሉ ከላይ ነው፤+ ይህ የሚወርደው ከሰማይ ብርሃናት አባት+ ሲሆን እሱ ደግሞ ቦታውን እንደሚቀያይር ጥላ አይለዋወጥም።+ +18 ፈቃዱ ስለሆነም ከፍጥረታቱ መካከል እኛ እንደ በኩራት እንድንሆን+ በእውነት ቃል አማካኝነት ወለደን።+ +19 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን እወቁ፦ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየና+ ለቁጣ የዘገየ መሆን አለበት፤+ +20 የሰው ቁጣ የአምላክ ጽድቅ እንዲፈጸም አያደርግምና።+ +21 ስለዚህ ጸያፍ የሆነውን ነገር ሁሉና ክፋትን ሁሉ* አስወግዳችሁ+ እናንተን* ሊያድን የሚችለውን በውስጣችሁ የሚተከለውን ቃል በገርነት ተቀበሉ። +22 ሆኖም ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ+ እንጂ የውሸት ምክንያት እያቀረባችሁ ራሳችሁን በማታለል ሰሚዎች ብቻ አትሁኑ። +23 ማንም ሰው ቃሉን የሚሰማ እንጂ የማያደርገው ከሆነ+ የገዛ ፊቱን በመስተዋት እያየ ካለ ሰው ጋር ይመሳሰላል። +24 ይህ ሰው ራሱን ካየ በኋላ ይሄዳል፤ ወዲያውም ምን እንደሚመስል ይረሳል። +25 ሆኖም ነፃ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ+ በትኩረት የሚመለከትና በዚያ የሚጸና ሰው ሰምቶ የሚረሳ ሳይሆን በሥራ ላይ የሚያውል ሰው ነው፤ በሚያደርገውም ነገር ደስተኛ ይሆናል።+ +26 አንድ ሰው አምላክን እያመለከ እንዳለ* ቢያስብም እንኳ አንደበቱን የማይገታ* ከሆነ+ ይህ ሰው የገዛ ልቡን ያታልላል፤ አምልኮውም ከንቱ ነው። +27 በአምላካችንና በአባታችን ዓይን ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ* ‘ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና+ መበለቶችን+ በመከራቸው መርዳት+ እንዲሁም ከዓለም እድፍ ራስን መጠበቅ’ ነው።+ +2 ወንድሞቼ ሆይ፣ በአንድ በኩል ክብር በተጎናጸፈው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የምታምኑ ሆናችሁ በሌላ በኩል ደግሞ አድልዎ ታደርጋላችሁ?+ +2 በጣቶቹ ላይ የወርቅ ቀለበቶች ያደረገና ያማረ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ስብሰባችሁ ቢመጣና ያደፈ ልብስ የለበሰ ድሃ ሰውም እንደዚሁ ወደ ስብሰባው ቢገባ +3 ያማረ ልብስ ለለበሰው ሰው አክብሮት በማሳየት “እዚህ የተሻለው ቦታ ላይ ተቀመጥ” ድሃውን ደግሞ “አንተ እዚያ ቁም” ወይም “እዚህ ከእግሬ ማሳረፊያ በታች ተቀመጥ” ትሉታላችሁ?+ +4 እንዲህ የምትሉ ከሆነ በመካከላችሁ የመደብ ልዩነት እንዲኖር ማድረጋችሁ አይደለም?+ ደግሞስ ክፉ ፍርድ የምትፈርዱ ፈራጆች መሆናችሁ አይደለም?+ +5 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ስሙ። አምላክ በእምነት ባለጸጋ እንዲሆኑና+ እሱን ለሚወዱ ቃል የገባውን መንግሥት እንዲወርሱ ከዓለም አመለካከት አንጻር ድሆች የሆኑትን አልመረጠም?+ +6 እናንተ ግን ድሃውን ሰው አዋረዳችሁ። እናንተን የሚጨቁኗችሁና+ ጎትተው ፍርድ ���ት የሚያቀርቧችሁ ሀብታሞች አይደሉም? +7 እናንተ የተጠራችሁበትን መልካም ስም የሚሳደቡት እነሱ አይደሉም? +8 እንግዲያው በቅዱስ መጽሐፉ መሠረት “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ የሚለውን ንጉሣዊ ሕግ ተግባራዊ የምታደርጉ ከሆነ መልካም እያደረጋችሁ ነው። +9 ማዳላታችሁን የማትተዉ ከሆነ+ ግን ኃጢአት እየሠራችሁ ነው፤ ሕጉም ሕግ ተላላፊዎች ናችሁ ብሎ ይፈርድባችኋል።*+ +10 አንድ ሰው ሕጉን ሁሉ የሚጠብቅ ሆኖ ሳለ አንዱን ትእዛዝ ሳይጠብቅ ቢቀር ሁሉንም እንደጣሰ ይቆጠራል።+ +11 “አታመንዝር”+ ያለው እሱ “አትግደል”+ የሚል ትእዛዝም ሰጥቷልና። እንግዲህ ምንዝር ባትፈጽምም እንኳ ከገደልክ ሕግ ተላላፊ ሆነሃል። +12 ነፃ በሆኑ ግለሰቦች ሕግ* የሚዳኙ ሰዎች በሚናገሩበት መንገድ መናገራችሁንና እነሱ እንደሚያደርጉት ማድረጋችሁን ቀጥሉ።+ +13 ምሕረት የማያደርግ ሰው ያለምሕረት ይፈረድበታልና።+ ምሕረት በፍርድ ላይ ድል ይቀዳጃል። +14 ወንድሞቼ ሆይ፣ አንድ ሰው እምነት አለኝ ቢል ነገር ግን እምነቱ በሥራ የተደገፈ ባይሆን ምን ጥቅም ይኖረዋል?+ እምነቱ ሊያድነው ይችላል?+ +15 አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት የሚለብሱት ቢያጡና* ለዕለት የሚያስፈልጋቸውን በቂ ምግብ ባያገኙ +16 ሆኖም ከመካከላችሁ አንዱ “በሰላም ሂዱ፤ ይሙቃችሁ፤ ጥገቡም” ቢላቸው ለሰውነታቸው የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ግን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል?+ +17 ስለዚህ በሥራ ያልተደገፈ እምነትም በራሱ የሞተ ነው።+ +18 ይሁን እንጂ አንድ ሰው እንዲህ ይላል፦ “አንተ እምነት አለህ፤ እኔ ደግሞ ሥራ አለኝ። እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔ ደግሞ እምነቴን በሥራ አሳይሃለሁ።” +19 አንድ አምላክ እንዳለ ታምናለህ አይደል? ማመንህ መልካም ነው። ይሁንና አጋንንትም ያምናሉ፤ በፍርሃትም ይንቀጠቀጣሉ።+ +20 አንተ ከንቱ ሰው፣ እምነት ያለሥራ እንደማይጠቅም ማረጋገጥ ትፈልጋለህ? +21 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ ካቀረበ በኋላ የጸደቀው በሥራ አይደለም?+ +22 እምነቱ ከሥራው ጋር አብሮ ይሠራ እንደነበረና ሥራው እምነቱን ፍጹም እንዳደረገው ትገነዘባለህ፤+ +23 ደግሞም “አብርሃም በይሖዋ* አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት”+ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፤ እሱም የይሖዋ* ወዳጅ ለመባል በቃ።+ +24 እንግዲህ ሰው የሚጸድቀው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም ጭምር እንደሆነ ትገነዘባላችሁ። +25 ዝሙት አዳሪዋ ረዓብም መልእክተኞቹን በጥሩ ሁኔታ ተቀብላ ካስተናገደቻቸውና በሌላ መንገድ ከላከቻቸው በኋላ በሥራ አልጸደቀችም?+ +26 በእርግጥም አካል ያለመንፈስ* የሞተ እንደሆነ ሁሉ+ እምነትም ያለሥራ የሞተ ነው።+ +4 በእናንተ መካከል ያለው ጦርነትና ጠብ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ* ከሚዋጉት ሥጋዊ ፍላጎቶቻችሁ የመነጨ አይደለም?+ +2 ትመኛላችሁ ሆኖም አታገኙም። ትገድላላችሁ እንዲሁም ትጎመጃላችሁ፤* ይሁንና ማግኘት አትችሉም። ትጣላላችሁ እንዲሁም ትዋጋላችሁ።+ ስለማትጠይቁም አታገኙም። +3 በምትጠይቁበት ጊዜም አታገኙም፤ ምክንያቱም የምትጠይቁት ለተሳሳተ ዓላማ ይኸውም ሥጋዊ ፍላጎታችሁን ለማርካት ነው። +4 አመንዝሮች ሆይ፣* ከዓለም ጋር መወዳጀት ከአምላክ ጋር ጠላትነት መፍጠር እንደሆነ አታውቁም? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ ራሱን የአምላክ ጠላት ያደርጋል።+ +5 ወይስ ቅዱስ መጽሐፉ “በውስጣችን ያደረው መንፈስ በቅናት ሁልጊዜ ይመኛል” ያለው ያለምክንያት ይመስላችኋል?+ +6 ይሁን እንጂ አምላክ የሚሰጠው ጸጋ እንዲህ ካለው መንፈስ የላቀ ነው። በመሆኑም ቅዱስ መጽሐፉ “አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤+ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ይላ��።+ +7 ስለዚህ ራሳችሁን ለአምላክ አስገዙ፤+ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙት፤+ እሱም ከእናንተ ይሸሻል።+ +8 ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።+ እናንተ ኃጢአተኞች እጆቻችሁን አንጹ፤+ እናንተ ወላዋዮች ልባችሁን አጥሩ።+ +9 ተጨነቁ፣ እዘኑ፣ አልቅሱ።+ ሳቃችሁ ወደ ሐዘን፣ ደስታችሁም ወደ ተስፋ መቁረጥ ይለወጥ። +10 በይሖዋ* ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤+ እሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል።+ +11 ወንድሞች፣ አንዳችሁ ሌላውን መንቀፋችሁን ተዉ።+ ወንድሙን የሚነቅፍ ወይም በወንድሙ ላይ የሚፈርድ ሁሉ ሕግን ይነቅፋል እንዲሁም በሕግ ላይ ይፈርዳል። በሕግ ላይ የምትፈርድ ከሆነ ደግሞ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም። +12 ሕግ የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ብቻ ነው፤+ እሱ ማዳንም ሆነ ማጥፋት ይችላል።+ ታዲያ በባልንጀራህ* ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?+ +13 እንግዲህ እናንተ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ከተማ እንሄዳለን፤ እዚያም ዓመት እንቆያለን፤ እንነግዳለን እንዲሁም እናተርፋለን” የምትሉ ስሙ፤+ +14 ሕይወታችሁ ነገ ምን እንደሚሆን እንኳ አታውቁም።+ ለጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁና።+ +15 ከዚህ ይልቅ “ይሖዋ* ከፈቀደ+ በሕይወት እንኖራለን፤ ደግሞም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል። +16 አሁን ግን እናንተ ከልክ በላይ ጉራ በመንዛት ትኩራራላችሁ። እንዲህ ያለው ጉራ ሁሉ ክፉ ነው። +17 ስለዚህ አንድ ሰው ትክክል የሆነውን ነገር እንዴት ማድረግ እንዳለበት እያወቀ ሳያደርገው ቢቀር ኃጢአት ይሆንበታል።+ +5 እናንተ ሀብታሞች እንግዲህ ስሙ፤ እየመጣባችሁ ባለው መከራ አልቅሱ እንዲሁም ዋይ ዋይ በሉ።+ +2 ሀብታችሁ በስብሷል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል።+ +3 ወርቃችሁና ብራችሁ ሙሉ በሙሉ ዝጓል፤ ዝገቱም በእናንተ ላይ ይመሠክራል፤ ሥጋችሁንም ይበላል። ያከማቻችሁት ነገር በመጨረሻዎቹ ቀናት እንደ እሳት ይሆናል።*+ +4 እነሆ፣ በእርሻችሁ ላይ ያለውን ሰብል ለሰበሰቡት ሠራተኞች ሳትከፍሏቸው የቀራችሁት ደሞዝ ይጮኻል፤ አጫጆቹም ለእርዳታ የሚያሰሙት ጥሪ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ ይሖዋ* ጆሮ ደርሷል።+ +5 በምድር ላይ በቅንጦት ኖራችኋል፤ የራሳችሁንም ፍላጎት ለማርካት ትጥሩ ነበር። በእርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል።+ +6 ጻድቁን ኮነናችሁት፤ ደግሞም ገደላችሁት። እሱ እየተቃወማችሁ አይደለም?* +7 እንግዲህ ወንድሞች፣ ጌታ እስከሚገኝበት ጊዜ+ ድረስ በትዕግሥት ጠብቁ። እነሆ፣ ገበሬ የመጀመሪያውና የኋለኛው ዝናብ እስኪመጣ ድረስ በመታገሥ የምድርን መልካም ፍሬ ይጠባበቃል።+ +8 እናንተም በትዕግሥት ጠብቁ፤+ ጌታ የሚገኝበት ጊዜ ስለተቃረበ ልባችሁን አጽኑ።+ +9 ወንድሞች፣ እንዳይፈረድባችሁ አንዳችሁ በሌላው ላይ አታጉረምርሙ።*+ እነሆ፣ ፈራጁ ደጃፍ ላይ ቆሟል። +10 ወንድሞች፣ በይሖዋ* ስም የተናገሩትን ነቢያት+ መከራ በመቀበልና ትዕግሥት በማሳየት+ ረገድ አርዓያ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው።+ +11 እነሆ፣ የጸኑትን ደስተኞች* እንደሆኑ አድርገን እንቆጥራቸዋለን።+ ስለ ኢዮብ ጽናት ሰምታችኋል፤+ በውጤቱም ይሖዋ* ያደረገለትን አይታችኋል፤+ በዚህም ይሖዋ* እጅግ አፍቃሪና* መሐሪ እንደሆነ ተመልክታችኋል።+ +12 ከሁሉም በላይ ወንድሞቼ፣ በሰማይም ሆነ በምድር ወይም በሌላ መሐላ መማላችሁን ተዉ። ከዚህ ይልቅ “አዎ” ካላችሁ አዎ ይሁን፤ “አይደለም” ካላችሁ አይደለም ይሁን፤+ አለዚያ ለፍርድ ትዳረጋላችሁ። +13 ከእናንተ መካከል መከራ እየደረሰበት ያለ ሰው አለ? መጸለዩን ይቀጥል።+ ደስ የተሰኘ አለ? የምስጋና መዝሙር ይዘምር።+ +14 ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የጉባኤ ሽማግሌዎችን ወደ እሱ ይጥራ፤+ እነሱም በ���ሖዋ* ስም ዘይት ቀብተው+ ይጸልዩለት። +15 በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን* ሰው ይፈውሰዋል፤ ይሖዋም* ያስነሳዋል። በተጨማሪም ኃጢአት ሠርቶ ከሆነ ይቅር ይባላል። +16 ስለዚህ ፈውስ ማግኘት እንድትችሉ አንዳችሁ ለሌላው ኃጢአታችሁን በግልጽ ተናዘዙ፤+ እንዲሁም አንዳችሁ ለሌላው ጸልዩ። ጻድቅ ሰው የሚያቀርበው ምልጃ ታላቅ ኃይል አለው።+ +17 ኤልያስ እንደ እኛው ዓይነት ስሜት ያለው ሰው ነበር፤ ያም ሆኖ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ በጸለየ ጊዜ በምድሩ ላይ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር ዝናብ አልዘነበም።+ +18 ከዚያም እንደገና ጸለየ፤ ሰማዩም ዝናብ ሰጠ፤ ምድሩም ፍሬ አፈራ።+ +19 ወንድሞቼ፣ ከእናንተ መካከል አንድ ሰው ከእውነት መንገድ ስቶ ቢወጣና ሌላ ሰው ቢመልሰው፣ +20 ኃጢአተኛን ከስህተት ጎዳናው የሚመልስ ማንኛውም ሰው+ ኃጢአተኛውን* ከሞት እንደሚያድንና ብዙ ኃጢአትን እንደሚሸፍን እወቁ።+ +3 በተመሳሳይም እናንተ ሚስቶች፣ ለቃሉ የማይታዘዙ ባሎች ካሉ ያለቃል በሚስቶቻቸው ምግባር እንዲማረኩ+ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤+ +2 ሊማረኩ የሚችሉትም ንጹሕ ምግባራችሁንና+ የምታሳዩትን ጥልቅ አክብሮት ሲመለከቱ ነው። +3 ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በማጌጥ ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ የወርቅ ጌጣጌጦች በማድረግ+ ወይም ያማረ ልብስ በመልበስ አይሁን፤ +4 ከዚህ ይልቅ ውበታችሁ የማይጠፋውን ጌጥ ይኸውም በአምላክ ፊት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የሰከነና ገር መንፈስ የተላበሰ+ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁን። +5 ተስፋቸውን በአምላክ ላይ የጣሉ በቀድሞ ጊዜ የነበሩ ቅዱሳን ሴቶች ራሳቸውን ለባሎቻቸው በማስገዛት በዚህ ዓይነት ሁኔታ ራሳቸውን ያስውቡ ነበርና፤ +6 ሣራም አብርሃምን ጌታዬ እያለች በመጥራት ትታዘዘው ነበር።+ እናንተም መልካም ማድረጋችሁን ከቀጠላችሁና በፍርሃት ካልተሸነፋችሁ+ ልጆቿ ናችሁ። +7 በተመሳሳይም እናንተ ባሎች ከእነሱ ጋር በእውቀት* አብራችሁ ኑሩ። እነሱም ከእናንተ ጋር የሕይወትን ጸጋ አብረው ስለሚወርሱ+ ጸሎታችሁ እንዳይታገድ ከእናንተ ይበልጥ እንደ ተሰባሪ ዕቃ የሆኑትን ሴቶችን አክብሯቸው።+ +8 በመጨረሻም ሁላችሁም የአስተሳሰብ አንድነት* ይኑራችሁ፤+ የሌላውን ስሜት የምትረዱ ሁኑ፤ የወንድማማች መዋደድ ይኑራችሁ፤ ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ፤+ ትሑታን ሁኑ።+ +9 ክፉን በክፉ+ ወይም ስድብን በስድብ አትመልሱ።+ ከዚህ ይልቅ ባርኩ፤+ የተጠራችሁት ይህን ጎዳና በመከተል በረከትን እንድትወርሱ ነውና። +10 ስለዚህ “ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ማየት የሚፈልግ ሰው በምላሱ ክፉ ነገር ከመናገር፣+ በከንፈሩም ከማታለል ይቆጠብ። +11 ክፉ ከሆነ ነገር ይራቅ፤+ መልካም የሆነውንም ያድርግ፤+ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተለውም።+ +12 የይሖዋ* ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮዎቹም ምልጃቸውን ይሰማሉ፤+ የይሖዋ* ፊት ግን ክፉ ነገሮችን በሚያደርጉ ላይ ነው።”+ +13 መልካም ነገር ለማድረግ ቀናተኞች ብትሆኑ ጉዳት የሚያደርስባችሁ ማን ነው?+ +14 ሆኖም ለጽድቅ ስትሉ መከራ ብትቀበሉ ደስተኞች ናችሁ።+ ይሁን እንጂ እነሱ የሚፈሩትን እናንተ አትፍሩ፤* ደግሞም አትሸበሩ።+ +15 ነገር ግን ክርስቶስን እንደ ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ፣ ምክንያት እንድታቀርቡ ለሚጠይቃችሁ ሰው ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር ዝግጁ ሁኑ፤ ይህን ስታደርጉ ግን በገርነት* መንፈስና+ በጥልቅ አክብሮት ይሁን።+ +16 ስለ እናንተ መጥፎ ነገር የሚናገሩ ሰዎች፣ የክርስቶስ ተከታዮች እንደመሆናችሁ መጠን በምታሳዩት መልካም ምግባር+ የተነሳ ስለ እናንተ በሚናገሩት በማንኛውም መጥፎ ነገር እንዲያፍሩ+ ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ።+ +17 ክፉ ነገር ሠርታችሁ መከራ ከምትቀበሉ+ ይልቅ የአምላክ ፈቃድ ከሆነ፣ መልካም ነገር ሠርታችሁ መከራ ብትቀበሉ ይሻላልና።+ +18 ጻድቅ የሆነው ክርስቶስ እንኳ ለዓመፀኞች+ ሲል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመሞት+ ከኃጢአት ነፃ አውጥቷቸዋልና። ይህን ያደረገው እናንተን ወደ አምላክ ለመምራት ነው።+ ሥጋ ሆኖ ተገደለ፤+ ሆኖም መንፈስ ሆኖ ሕያው ሆነ።+ +19 በዚህ ሁኔታ እያለም ሄዶ በእስር ላሉት መናፍስት ሰበከላቸው፤*+ +20 እነዚህ መናፍስት ቀደም ሲል ማለትም በኖኅ ዘመን ጥቂት ሰዎች ይኸውም ስምንት ነፍሳት* በውኃው መካከል አልፈው የዳኑበት+ መርከብ እየተሠራ በነበረበት ጊዜ፣+ አምላክ በትዕግሥት እየጠበቀ ሳለ* ሳይታዘዙ የቀሩ ናቸው።+ +21 አሁንም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነው ጥምቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካኝነት እናንተን እያዳናችሁ ነው። ጥምቀት የሰውነትን እድፍ የሚያስወግድ ሳይሆን ጥሩ ሕሊና ለማግኘት ለአምላክ የሚቀርብ ልመና ነው።+ +22 ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሄደ ሲሆን አሁን በአምላክ ቀኝ ይገኛል፤+ እንዲሁም መላእክት፣ ሥልጣናትና ኃይላት እንዲገዙለት ተደርጓል።+ +1 የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጴጥሮስ፤+ በጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣+ በእስያና በቢቲኒያ ተበትነው ለሚገኙ፣ ጊዜያዊ ነዋሪዎች ለሆኑ የአምላክ ምርጦች፣ +2 ይኸውም አባት የሆነው አምላክ አስቀድሞ ባወቀው መሠረት ለተመረጡት+ ደግሞም ታዛዥ እንዲሆኑና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንዲረጩ+ በመንፈስ ለተቀደሱት፦+ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። +3 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይወደስ፤ እሱ በታላቅ ምሕረቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ+ አማካኝነት ለሕያው ተስፋ+ እንደ አዲስ ወልዶናልና፤+ +4 እንዲሁም ለማይበሰብስ፣ ለማይረክስና ለማይጠፋ ርስት ወልዶናል።+ ይህም በሰማይ ለእናንተ ተጠብቆላችኋል፤+ +5 እናንተንም አምላክ በዘመኑ መጨረሻ ለሚገለጠው መዳን በእምነት አማካኝነት በኃይሉ እየጠበቃችሁ ነው። +6 አሁን ለአጭር ጊዜ በልዩ ልዩ ፈተናዎች መጨነቃችሁ የግድ ቢሆንም በእነዚህ ሁሉ ነገሮች የተነሳ እጅግ እየተደሰታችሁ ነው፤+ +7 እነዚህ ፈተናዎች የሚደርሱባችሁ፣ በእሳት የተፈተነ ቢሆንም እንኳ ሊጠፋ ከሚችለው ወርቅ እጅግ የላቀ ዋጋ ያለውና ተፈትኖ* የተረጋገጠው እምነታችሁ+ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፣ ግርማንና ክብርን ያስገኝ ዘንድ ነው።+ +8 እሱን አይታችሁት ባታውቁም ትወዱታላችሁ። አሁን ባታዩትም እንኳ በእሱ ላይ እምነት እያሳያችሁና በቃላት ሊገለጽ በማይችል ታላቅ ደስታ እጅግ ሐሴት እያደረጋችሁ ነው፤ +9 ምክንያቱም የእምነታችሁ ግብ ላይ እንደምትደርሱ ይኸውም ራሳችሁን* እንደምታድኑ ታውቃላችሁ።+ +10 ለእናንተ ስለሚሰጠው ጸጋ የተነበዩት ነቢያት ይህን መዳን በተመለከተ ትጋት የተሞላበት ምርምርና ጥልቅ ጥናት አካሂደዋል።+ +11 በውስጣቸው ያለው መንፈስ በክርስቶስ ላይ ስለሚደርሱት መከራዎችና+ ከዚያ በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ ሲመሠክር ከክርስቶስ ጋር በተያያዘ ስለ የትኛው ጊዜ ወይም ወቅት እያመለከተ እንዳለ ይመረምሩ ነበር።+ +12 እነሱ ራሳቸውን እያገለገሉ እንዳልሆነ ተገልጦላቸው ነበር። ከዚህ ይልቅ ከሰማይ በተላከ መንፈስ ቅዱስ+ ምሥራቹን ባበሰሩላችሁ ሰዎች አማካኝነት ከተነገሯችሁ ነገሮች ጋር በተያያዘ እናንተን እያገለገሉ ነበር። መላእክትም እነዚህን ነገሮች ለማየት ይጓጓሉ። +13 በመሆኑም አእምሯችሁን ዝግጁ በማድረግ ለሥራ ታጠቁ፤+ የማስተዋል ስሜታችሁን በሚገባ ጠብቁ፤+ ተስፋችሁን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ በምታገኙት ጸጋ ላይ አድርጉ። +14 ታዛዥ ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን ቀድሞ እውቀት ባልነበራችሁ ጊዜ ትከተሉት በነበረው ምኞት መሠረት መቀረጻችሁን አቁሙ፤ +15 ከዚህ ይልቅ የጠራችሁ ቅዱስ አምላክ፣ ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ እናንተም በምግባራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤+ +16 “እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ተብሎ ተጽፏልና።+ +17 ደግሞም ምንም ሳያዳላ+ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት የምትለምኑ ከሆነ ጊዜያዊ ነዋሪዎች ሆናችሁ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ አምላክን በመፍራት ኑሩ።+ +18 እናንተ ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት* ከንቱ አኗኗር ነፃ የወጣችሁት*+ ሊበላሹ በሚችሉ ነገሮች ይኸውም በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁና። +19 ከዚህ ይልቅ ነፃ የወጣችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ+ ደም ባለ ውድ ደም+ ይኸውም በክርስቶስ ደም ነው።+ +20 እርግጥ እሱ አስቀድሞ የታወቀው፣ ዓለም ከመመሥረቱ* በፊት+ ነው፤ ሆኖም ለእናንተ ሲባል በዘመናት መጨረሻ ላይ እንዲገለጥ ተደረገ።+ +21 እናንተም እምነታችሁና ተስፋችሁ በአምላክ ላይ ይሆን ዘንድ እሱን ከሞት ባስነሳውና+ ክብር ባጎናጸፈው+ አምላክ ያመናችሁት በእሱ አማካኝነት ነው።+ +22 እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ራሳችሁን* ስላነጻችሁ ግብዝነት የሌለበት የወንድማማች መዋደድ አላችሁ፤+ በመሆኑም እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ።+ +23 ሕያው በሆነውና ጸንቶ በሚኖረው አምላክ ቃል አማካኝነት እንደ አዲስ የተወለዳችሁት+ በሚበሰብስ ሳይሆን በማይበሰብስ ዘር*+ ነው።+ +24 “ሥጋ ሁሉ* እንደ ሣር ነውና፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው፤ ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤ +25 የይሖዋ* ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”+ ለእናንተም የተሰበከላችሁ ምሥራች ይህ “ቃል” ነው።+ +2 እንግዲህ ክፋትን ሁሉ፣ ማታለልን፣ ግብዝነትን፣ ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ።+ +2 ገና እንደተወለዱ ሕፃናት+ በአምላክ ቃል ውስጥ ለሚገኘው ያልተበረዘ* ወተት ጉጉት አዳብሩ፤ ይህም በእሱ አማካኝነት ወደ መዳን ማደግ እንድትችሉ ነው፤+ +3 ጌታ ደግ መሆኑን ቀምሳችኋልና።* +4 በሰዎች ወደተናቀው+ በአምላክ ግን ወደተመረጠውና በፊቱ ክቡር ወደሆነው ወደ እሱ ይኸውም ሕያው ወደሆነው ድንጋይ+ በመምጣት +5 እናንተ ራሳችሁ ቅዱሳን ካህናት ለመሆን እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ለመሆን እየተገነባችሁ ነው፤+ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መንፈሳዊ መሥዋዕት ማቅረብ ትችሉ ዘንድ ነው።+ +6 ምክንያቱም ቅዱስ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በጽዮን የተመረጠ ድንጋይ ይኸውም ክቡር የሆነ የማዕዘን የመሠረት ድንጋይ አኖራለሁ፤ ደግሞም በእሱ የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አያፍርም።”+ +7 በመሆኑም እናንተ አማኞች ስለሆናችሁ እሱ ለእናንተ ክቡር ነው፤ የማያምኑትን በተመለከተ ግን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፦ “ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣+ እሱ የማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ”፤+ +8 እንዲሁም “የሚያደናቅፍ ድንጋይና የሚያሰናክል ዓለት ሆነ።”+ እነሱ የሚሰናከሉት ለቃሉ ስለማይታዘዙ ነው። እነዚህ ሰዎች የሚጠብቃቸው ነገር ይኸው ነው። +9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን+ የእሱን “ድንቅ ባሕርያት* በየቦታው እንድታውጁ+ የተመረጠ ዘር፣ ንጉሣዊ ካህናት፣ ቅዱስ ብሔር፣+ ልዩ ንብረት እንዲሆን የተለየ ሕዝብ”+ ናችሁ። +10 እናንተ በአንድ ወቅት የአምላክ ሕዝብ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የአምላክ ሕዝብ ናችሁ፤+ ቀደም ሲል ምሕረት አልተደረገላችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረት አግኝታችኋል።+ +11 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ የባዕድ አገር ሰዎችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች+ እንደመሆናችሁ መጠን እናንተን ከሚዋጉት* ሥጋዊ ፍላጎቶች+ ምንጊዜም እንድትርቁ አሳስባችኋለሁ።+ +12 ክፉ አድራጊዎች እንደሆናችሁ አድርገው ሲከሷችሁ መልካም ሥራችሁን በዓይናቸው ማየት እንዲችሉ+ ብሎም አምላክ ለመመርመር በሚመጣበት ቀን እሱን እንዲያከብሩ በዓለም ባሉ ሰዎች መካከል መልካም ምግባር ይኑራችሁ።+ +13 ለጌታ ብላችሁ ለሰብዓዊ ሥልጣን* ሁሉ ተገዙ፦+ የበላይ ስለሆነ ለንጉሥ ተገዙ፤+ +14 ደግሞም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት፣ መልካም የሚያደርጉትን ግን ለማመስገን በእሱ የተላኩ ስለሆኑ ለገዢዎች ተገዙ።+ +15 የአምላክ ፈቃድ፣ መልካም ነገር በማድረግ ከንቱ ንግግር የሚናገሩትን ምክንያታዊ ያልሆኑ ሰዎች አፍ ዝም እንድታሰኙ* ነውና።+ +16 እንደ ነፃ ሰዎች ኑሩ፤+ ነፃነታችሁን እንደ አምላክ ባሪያዎች+ ሆናችሁ ተጠቀሙበት እንጂ ለክፋት መሸፈኛ* አታድርጉት።+ +17 ሁሉንም ዓይነት ሰው አክብሩ፤+ ለመላው የወንድማማች ማኅበር ፍቅር ይኑራችሁ፤+ አምላክን ፍሩ፤+ ንጉሥን አክብሩ።+ +18 አገልጋዮች ጥሩና ምክንያታዊ ለሆኑት ብቻ ሳይሆን በቀላሉ ለማይደሰቱ ጌቶቻቸውም እንኳ ተገቢ ፍርሃት በማሳየት ይገዙ።+ +19 አንድ ሰው በአምላክ ፊት ንጹሕ ሕሊና እንዲኖረው ሲል መከራን* ችሎ ቢያሳልፍና ግፍ ቢደርስበት ይህ ደስ የሚያሰኝ ነውና።+ +20 ኃጢአት በመሥራታችሁ የሚደርስባችሁን ዱላ ብትቋቋሙ ምን ጥቅም አለው?+ መልካም ነገር በማድረጋችሁ መከራ ሲደርስባችሁ ችላችሁ ብታሳልፉ ግን ይህ አምላክ ደስ የሚሰኝበት ነገር ነው።+ +21 ደግሞም የተጠራችሁት በዚህ ጎዳና እንድትሄዱ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስም እንኳ የእሱን ፈለግ በጥብቅ እንድትከተሉ አርዓያ ትቶላችሁ+ ስለ እናንተ መከራ ተቀብሏል።+ +22 እሱ ምንም ኃጢአት አልሠራም፤+ በአንደበቱም የማታለያ ቃል አልተገኘም።+ +23 ሲሰድቡት+ መልሶ አልተሳደበም።+ መከራ ሲደርስበት+ አልዛተም፤ ከዚህ ይልቅ በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን በአደራ ሰጠ።+ +24 ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እሱ ራሱ በገዛ አካሉ ኃጢአታችንን በእንጨት* ላይ+ ተሸከመ።+ ደግሞም “በእሱ ቁስል እናንተ ተፈወሳችሁ።”+ +25 እናንተ እንደባዘኑ በጎች ነበራችሁና፤+ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ* እረኛና+ ጠባቂ* ተመልሳችኋል። +4 ክርስቶስ በሥጋ መከራ ስለተቀበለ+ እናንተም ይህንኑ አስተሳሰብ* ለማንጸባረቅ ዝግጁ ሁኑ፤ ምክንያቱም በሥጋ መከራ የተቀበለ ሰው ኃጢአት መሥራት አቁሟል፤+ +2 ይኸውም ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ በሚኖርበት ቀሪ ሕይወቱ ለሰው ፍላጎት ሳይሆን+ ለአምላክ ፈቃድ መኖር ይችል ዘንድ ነው።+ +3 ዓይን ባወጣ ምግባር፣* ልቅ በሆነ የሥጋ ፍላጎት፣ ከልክ በላይ በመጠጣት፣ መረን በለቀቀ ድግስ፣ በመጠጥ ግብዣዎችና በአስጸያፊ የጣዖት አምልኮ በመካፈል የአሕዛብን ፈቃድ የፈጸማችሁበት+ ያለፈው ጊዜ ይበቃል።+ +4 ይህን በመሰለው ያዘቀጠ ወራዳ ሕይወት ከእነሱ ጋር መሮጣችሁን ስለማትቀጥሉ ግራ ይጋባሉ፤ በመሆኑም ይሰድቧችኋል።+ +5 ይሁንና እነዚህ ሰዎች በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።+ +6 እንዲያውም ምሥራቹ ለሙታንም* የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤+ በመሆኑም ከሰው አመለካከት አንጻር በሥጋ የሚፈረድባቸው ቢሆንም ከአምላክ አመለካከት አንጻር ከመንፈስ ጋር በሚስማማ ሁኔታ መኖር ይችላሉ። +7 ሆኖም የሁሉም ነገር መጨረሻ ቀርቧል። ስለዚህ ጤናማ አስተሳሰብ ይኑራችሁ፤+ እንዲሁም በጸሎት ረገድ ንቁዎች ሁኑ።+ +8 ከሁሉም በላይ አንዳችሁ ለሌላው የጠለቀ ፍቅር ይኑራችሁ፤+ ምክንያቱም ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል።+ +9 ሳታጉረመርሙ አንዳችሁ ለሌላው የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ አሳዩ።+ +10 በልዩ ልዩ መንገዶች የተገለጸው የአምላክ ጸጋ መልካም መጋቢዎች እንደመሆናችሁ መጠን፣ እያንዳንዳችሁ በ��ቀበላችሁት ስጦታ መሠረት የተሰጣችሁን ስጦታ አንዳችሁ ሌላውን ለማገልገል ተጠቀሙበት።+ +11 የሚናገር ማንም ቢኖር ከአምላክ የተቀበለውን ቃል እየተናገረ እንዳለ ሆኖ ይናገር፤ የሚያገለግል ማንም ቢኖር አምላክ በሚሰጠው ኃይል ተማምኖ ያገልግል፤+ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት አምላክ በሁሉም ነገር እንዲከበር ነው።+ ክብርና ኃይል ለዘላለም የእሱ ነው። አሜን። +12 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እንደ እሳት ባሉ ከባድ ፈተናዎች ስትፈተኑ እንግዳ የሆነ ነገር እየደረሰባችሁ እንዳለ አድርጋችሁ በማሰብ አትደነቁ።+ +13 ከዚህ ይልቅ ክርስቶስ በክብሩ በሚገለጥበት ወቅት+ እናንተም እንድትደሰቱና እጅግ ሐሴት እንድታደርጉ እሱ የተቀበለው መከራ ተካፋዮች+ በመሆናችሁ ምንጊዜም ደስ ይበላችሁ።+ +14 ለክርስቶስ ስም ስትሉ ብትነቀፉ* ደስተኞች ናችሁ፤+ ምክንያቱም የክብር መንፈስ ይኸውም የአምላክ መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋል። +15 ይሁን እንጂ ከእናንተ መካከል ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ ወይም በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ጣልቃ የሚገባ ሆኖ መከራ አይቀበል።+ +16 ይሁንና ማንም ሰው ክርስቲያን በመሆኑ መከራ ቢደርስበት ምንም ኀፍረት አይሰማው፤+ ይልቁንም ይህን ስም ተሸክሞ አምላክን ያክብር። +17 ፍርድ ከአምላክ ቤት+ የሚጀምርበት አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ይህ ነውና። እንግዲህ ፍርድ በእኛ የሚጀምር ከሆነ+ ለአምላክ ምሥራች ታዛዥ ያልሆኑ ሰዎች መጨረሻ ምን ይሆን?+ +18 “እንግዲህ ጻድቅ በጭንቅ የሚድን ከሆነ ኃጢአተኛውና ፈሪሃ አምላክ የሌለው ሰውማ ምን ይውጠው ይሆን?”+ +19 ስለዚህ የአምላክን ፈቃድ በማድረጋቸው መከራ የሚደርስባቸው ሰዎች መልካም እያደረጉ ራሳቸውን* ታማኝ ለሆነው ፈጣሪ አደራ ይስጡ።+ +5 ስለዚህ እኔም እንደ እነሱ ሽማግሌ እንዲሁም የክርስቶስ መከራ ምሥክርና ወደፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ እንደመሆኔ መጠን+ በመካከላችሁ ያሉትን ሽማግሌዎች እንዲህ በማለት አጥብቄ እለምናለሁ፦* +2 የበላይ ተመልካቾች ሆናችሁ በማገልገል* በአደራ የተሰጣችሁን የአምላክን መንጋ እንደ እረኛ ጠብቁ፤+ ሥራችሁን በግዴታ ሳይሆን በአምላክ ፊት በፈቃደኝነት ተወጡ፤+ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በመመኘት ሳይሆን+ ለማገልገል በመጓጓት፣ +3 የአምላክ ንብረት በሆኑት ላይ ሥልጣናችሁን በማሳየት ሳይሆን+ ለመንጋው ምሳሌ በመሆን ጠብቁ።+ +4 የእረኞች አለቃ+ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋ የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።+ +5 በተመሳሳይም እናንተ ወጣቶች፣ ለሽማግሌዎች ተገዙ።+ ይሁንና እርስ በርስ ባላችሁ ግንኙነት ሁላችሁም ትሕትናን ልበሱ፤* ምክንያቱም አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።+ +6 ስለዚህ በተገቢው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው የአምላክ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤+ +7 የሚያስጨንቃችሁንም* ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ፤+ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።+ +8 የማስተዋል ስሜታችሁን ጠብቁ፤ ንቁ ሆናችሁ ኑሩ!+ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይንጎራደዳል።+ +9 ሆኖም በዓለም ዙሪያ በመላው የወንድማማች ማኅበር ውስጥ ያሉት ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እየደረሰባቸው እንዳለ ተገንዝባችሁ+ በእምነት ጸንታችሁ በመቆም ተቃወሙት።+ +10 ከክርስቶስ ጋር ባላችሁ አንድነት ወደ ዘላለማዊ ክብሩ የጠራችሁ+ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እሱ ራሱ ሥልጠናችሁ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል። ጽኑ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፤+ ደግሞም ያጠነክራችኋል፤+ አጽንቶም ያቆማችኋል። +11 ኃይል ለዘላለም የእሱ ይሁን። አሜን። +12 እኔ ታማኝ ወንድም አድርጌ በምቆጥረ�� በስልዋኖስ*+ አማካኝነት ይህን በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍኩላችሁም እናንተን ለማበረታታትና ይህ የአምላክ እውነተኛ ጸጋ እንደሆነ አጥብቄ ለመመሥከር ነው። ይህን ጸጋ አጥብቃችሁ ያዙ። +13 እንደ እናንተ የተመረጠችው በባቢሎን የምትገኘው ሰላምታ ታቀርብላችኋለች፤ ልጄ ማርቆስም+ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። +14 በፍቅር እርስ በርስ በመሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ። ከክርስቶስ ጋር አንድነት ያላችሁ ሁሉ፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን። +3 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ይህ አሁን የምጽፍላችሁ ሁለተኛ ደብዳቤ ነው። በመጀመሪያው ደብዳቤዬ እንዳደረግሁት አሁንም ልጽፍላችሁ የተነሳሁት ማሳሰቢያ በመስጠት በትክክል ማሰብ እንድትችሉ ለማነቃቃት ሲሆን+ +2 ይህም ቀደም ሲል ቅዱሳን ነቢያት የተናገሩትን ቃል* እንዲሁም ጌታችንና አዳኛችን በሐዋርያት* አማካኝነት የሰጠውን ትእዛዝ እንድታስታውሱ ለመርዳት ነው። +3 ከሁሉ አስቀድሞ ይህን እወቁ፦ በመጨረሻዎቹ ቀናት የራሳቸውን ምኞት እየተከተሉ የሚያፌዙ ፌዘኞች ይመጣሉ።+ +4 እነዚህ ፌዘኞች “‘እገኛለሁ’ ያለው ታዲያ የት አለ?+ አባቶች በሞት ካንቀላፉበት ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ነገር ከፍጥረት መጀመሪያ አንስቶ እንዳለ ይቀጥላል” ይላሉ።+ +5 በጥንት ዘመን ሰማያት እንደነበሩ እንዲሁም ደረቁ ምድር በአምላክ ቃል ከውኃ በላይ ጸንቶ እንደቆመና በውኃ መካከል እንደነበረ የሚያረጋግጠውን ሐቅ ሆን ብለው ችላ ይላሉ።+ +6 በዚያ ጊዜ የነበረው ዓለም በእነዚህ ነገሮች ጠፍቷል። ይህም የሆነው መላዋ ምድር በውኃ በተጥለቀለቀች ጊዜ ነው።+ +7 ሆኖም በዚያው ቃል አሁን ያሉት ሰማያትም ሆኑ ምድር ለእሳትና ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች ለሚጠፉበት የፍርድ ቀን ተጠብቀው ይቆያሉ።+ +8 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እናንተ ግን በይሖዋ* ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፣ ሺህ ዓመት ደግሞ እንደ አንድ ቀን መሆኑን ልትዘነጉ አይገባም።+ +9 አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ይሖዋ* የገባውን ቃል ለመፈጸም አይዘገይም፤+ ከዚህ ይልቅ እናንተን የታገሠው፣ ሁሉ ለንስሐ እንዲበቃ እንጂ ማንም እንዲጠፋ ስለማይፈልግ ነው።+ +10 ይሁንና የይሖዋ* ቀን+ እንደ ሌባ ይመጣል፤+ በዚያም ቀን ሰማያት በነጎድጓድ ድምፅ* ያልፋሉ፤+ ንጥረ ነገሮቹም በኃይለኛ ሙቀት ይቀልጣሉ፤ ምድርና በላይዋ የተሠሩ ነገሮችም ይጋለጣሉ።+ +11 እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚቀልጡ ከሆነ ቅዱስ ሥነ ምግባር በመከተልና ለአምላክ ያደራችሁ መሆናችሁን የሚያሳዩ ተግባሮች በመፈጸም ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባችሁ ልታስቡበት ይገባል! +12 ሰማያት በእሳት ተቃጥለው የሚጠፉበትንና+ ንጥረ ነገሮቹም በኃይለኛ ሙቀት የሚቀልጡበትን የይሖዋን* ቀን መምጣት* እየጠበቃችሁና በአእምሯችሁ አቅርባችሁ እየተመለከታችሁ* ልትኖሩ ይገባል!+ +13 በሌላ በኩል ግን አምላክ በገባው ቃል መሠረት አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር እንጠባበቃለን፤+ በእነዚህም ውስጥ ጽድቅ ይሰፍናል።+ +14 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እነዚህን ነገሮች እየተጠባበቃችሁ ስለሆነ በመጨረሻ በእሱ ፊት ቆሻሻና እድፍ ሳይኖርባችሁ በሰላም እንድትገኙ የተቻላችሁን ጥረት አድርጉ።+ +15 በተጨማሪም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ በተሰጠው ጥበብ እንደጻፈላችሁ የጌታችንን ትዕግሥት እንደ መዳን ቁጠሩት፤+ +16 እንዲያውም በሁሉም ደብዳቤዎቹ ላይ ስለ እነዚህ ነገሮች ጽፏል። ይሁንና በደብዳቤዎቹ ውስጥ ለመረዳት የሚከብዱ አንዳንድ ነገሮች አሉ፤ እውቀት የጎደላቸውና* የሚወላውሉ ሰዎች ሌሎቹን ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ ሁሉ እነዚህንም ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ። +17 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ይህን አስቀድማችሁ ስላወ��ችሁ ሕግ የሚተላለፉ ሰዎች በሚፈጽሙት ስህተት ከእነሱ ጋር ተታልላችሁ እንዳትወሰዱና ጽኑ አቋማችሁ እንዳይናጋ ተጠንቀቁ።+ +18 ከዚህ ይልቅ በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እድገት አድርጉ። አሁንም ሆነ ለዘላለም ለእሱ ክብር ይሁን። አሜን። +1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፣ በአምላካችን ጽድቅ እንዲሁም በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ አማካኝነት እኛ ያገኘነውን ዓይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉ፦ +2 ስለ አምላክና ስለ ጌታችን ኢየሱስ በምትቀስሙት ትክክለኛ እውቀት+ አማካኝነት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። +3 መለኮታዊ ኃይሉ፣ በገዛ ክብሩና በጎነቱ ስለጠራን አምላክ ባገኘነው ትክክለኛ እውቀት+ ለአምላክ ያደርን ሆነን ለመኖር የሚረዱንን ነገሮች ሁሉ ሰጥቶናል።* +4 በእነዚህ ነገሮች አማካኝነት ክቡርና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋ ሰጥቶናል፤*+ ይህን ያደረገውም የመጥፎ ምኞት* ውጤት ከሆነው ከዓለም ብልሹ ምግባር አምልጣችሁ፣ በዚህ ተስፋ አማካኝነት ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ ነው።+ +5 በመሆኑም ልባዊ ጥረት በማድረግ+ በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ጨምሩ፤+ በበጎነት ላይ እውቀትን፣+ +6 በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፣+ ራስን በመግዛት ላይ ጽናትን፣ በጽናት ላይ ለአምላክ ማደርን፣+ +7 ለአምላክ በማደር ላይ ወንድማዊ መዋደድን፣ በወንድማዊ መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።+ +8 እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ ቢኖሩና ቢትረፈረፉ፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ትክክለኛ እውቀት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ይጠብቋችኋል።+ +9 እነዚህ ነገሮች የሚጎድሉት ማንኛውም ሰው ብርሃን ላለማየት ዓይኑን የጨፈነ ዕውር ሰው* ነው፤+ ደግሞም ከቀድሞ ኃጢአቱ መንጻቱን ረስቷል።+ +10 በመሆኑም ወንድሞች፣ መጠራታችሁንና+ መመረጣችሁን አስተማማኝ ለማድረግ ከበፊቱ ይበልጥ ትጉ፤ እነዚህን ነገሮች የምታደርጉ ከሆነ ፈጽሞ አትወድቁምና።+ +11 እንዲያውም በእጅጉ ትባረካላችሁ፤ ጌታችንና አዳኛችን ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥትም+ ትገባላችሁ።+ +12 ስለዚህ ምንም እንኳ እነዚህን ነገሮች የምታውቁና በተማራችሁት እውነት ጸንታችሁ የቆማችሁ ብትሆኑም፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ሁልጊዜ እናንተን ከማሳሰብ ወደኋላ አልልም። +13 በዚህ ድንኳን*+ እስካለሁ ድረስ እናንተን በማሳሰብ ማነቃቃት ተገቢ ይመስለኛል፤+ +14 ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጽ እንዳሳወቀኝ ይህ ድንኳን የሚወገድበት ጊዜ እንደቀረበ አውቃለሁ።+ +15 እኔ ከሄድኩ በኋላ እነዚህን ነገሮች ማስታወስ* እንድትችሉ ሁልጊዜ አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ አደርጋለሁ። +16 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መገኘት ያሳወቅናችሁ በብልሃት የተፈጠረ ተረት ተከትለን ሳይሆን ግርማውን በገዛ ዓይናችን አይተን ነው።+ +17 ከግርማዊው ክብር “እኔ ራሴ በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው”+ የሚል ቃል* ለእሱ በተነገረ ጊዜ ከአባታችንና ከአምላካችን ክብርና ሞገስ ተቀብሏል። +18 ከእሱ ጋር በቅዱሱ ተራራ በነበርንበት ጊዜ ይህ ቃል ከሰማይ ሲመጣ ሰምተናል። +19 በመሆኑም ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ጎህ እስኪቀድና የንጋት ኮከብ+ እስኪወጣ ድረስ በጨለማ ቦታ፣ በልባችሁ ውስጥ ለሚበራ መብራት+ የምትጠነቀቁትን ያህል ለትንቢታዊው ቃል ትኩረት መስጠታችሁ መልካም ነው። +20 በመጀመሪያ ደረጃ፣ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ያለው ትንቢት ሁሉ በሰው ሐሳብ ላይ የተመሠረተ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። +21 መቼም ቢሆን ትንቢት በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤+ ከዚህ ይልቅ ሰዎች ከአምላክ የተቀበሉት��� ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍተው* ተናገሩ።+ +2 ይሁን እንጂ በሕዝቡ መካከል ሐሰተኛ ነቢያት እንደነበሩ ሁሉ በእናንተም መካከል ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይነሳሉ።+ እነዚህ ሰዎች ጥፋት የሚያስከትል ኑፋቄ በስውር ያስገባሉ፤ የዋጃቸውን+ ጌታ እንኳ ሳይቀር ክደው በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋት ያመጣሉ። +2 በተጨማሪም ብዙዎች እነሱ የሚፈጽሙትን ዓይን ያወጣ ምግባር* ይከተላሉ፤+ በዚህም ምክንያት የእውነት መንገድ ይሰደባል።+ +3 እነዚህ ሐሰተኛ አስተማሪዎች አስመሳይ ቃላት በመናገር እናንተን በስግብግብነት ይበዘብዟችኋል። ሆኖም ከብዙ ዘመን በፊት የተበየነባቸው ፍርድ+ አይዘገይም፤ ጥፋት እንደሚደርስባቸውም ጥርጥር የለውም።*+ +4 ደግሞም አምላክ ኃጢአት የሠሩትን መላእክት ከመቅጣት ወደኋላ አላለም፤+ ይልቁንም በድቅድቅ ጨለማ አስሮ* በማስቀመጥ ፍርዳቸውን እንዲጠባበቁ+ ወደ እንጦሮጦስ* ጣላቸው።+ +5 እንዲሁም የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን+ ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ+ ፈሪሃ አምላክ ባልነበራቸው ሰዎች በተሞላው ዓለም ላይ የጥፋት ውኃ ባመጣ ጊዜ+ የጥንቱን ዓለም ከመቅጣት ወደኋላ አላለም።+ +6 ደግሞም ፈሪሃ አምላክ ለሌላቸው ሰዎች ለወደፊቱ ምሳሌ እንዲሆኑ+ የሰዶምና የገሞራ ከተሞችን አመድ በማድረግ ፈርዶባቸዋል።+ +7 ሆኖም ለሕግ የማይገዙ ሰዎች በሚፈጽሙት ዓይን ያወጣ ምግባር* እጅግ እየተሳቀቀ ይኖር የነበረውን ጻድቁን ሎጥን አድኖታል።+ +8 ይህ ጻድቅ ሰው ዕለት ተዕለት በመካከላቸው ሲኖር በሚያየውና በሚሰማው መረን የለቀቀ ድርጊታቸው ጻድቅ ነፍሱን* ያስጨንቅ ነበር። +9 በመሆኑም ይሖዋ፣* ለአምላክ ያደሩ ሰዎችን ከፈተና እንዴት እንደሚያድንና+ ዓመፀኞችን ደግሞ በፍርድ ቀን ለሚደርስባቸው ጥፋት እንዴት ጠብቆ እንደሚያቆይ ያውቃል።+ +10 በተለይ ደግሞ ሰዎችን ለማርከስ+ ሲሉ ከእነሱ ጋር የፆታ ብልግና ለመፈጸም የሚመኙትንና ሥልጣን ያላቸውን የሚንቁትን*+ ለፍርድ ጠብቆ ያቆያቸዋል። ደፋሮችና በራሳቸው የሚመሩ ከመሆናቸውም በላይ የተከበሩትን ሲሳደቡ አይፈሩም። +11 ይሁንና መላእክት፣ ከእነሱ የላቀ ብርታትና ኃይል ያላቸው ቢሆንም ለይሖዋ* ካላቸው አክብሮት የተነሳ* ሐሰተኛ አስተማሪዎቹን በመስደብ አልነቀፏቸውም።+ +12 እነዚህ ሰዎች ግን ተይዘው ለመገደል እንደተወለዱ፣ በደመ ነፍስ እንደሚንቀሳቀሱ አእምሮ የሌላቸው እንስሳት ናቸው፤ በማያውቁት ነገር እየገቡ ይሳደባሉ።+ በሚከተሉት የጥፋት ጎዳና የተነሳ ለጥፋት ይዳረጋሉ። +13 በሠሩት ክፉ ድርጊት የተነሳ በራሳቸው ላይ ክፉ ነገር በማምጣት ብድራታቸውን ይቀበላሉ። በጠራራ ፀሐይ የሥጋ ፍላጎታቸውን ማርካትን እንደ ደስታ ይቆጥሩታል።+ እነዚህ ሰዎች እንደ ቆሻሻና እድፍ ናቸው፤ ከእናንተ ጋር በግብዣ ላይ ሲገኙ አታላይ በሆኑ ትምህርቶቻቸው ሌሎችን በማሳት እጅግ ይደሰታሉ።+ +14 አመንዝራ ዓይን+ ያላቸው በመሆኑ ኃጢአት ከመሥራት መታቀብ አይችሉም፤ ጸንተው ያልቆሙትንም* ያማልላሉ። መስገብገብ የለመደ ልብ አላቸው። የተረገሙ ልጆች ናቸው። +15 ቀናውን መንገድ ትተው በተሳሳተ ጎዳና ሄደዋል። ለጥቅም ሲል ክፉ ድርጊት መፈጸም የመረጠውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለዋል።+ +16 በለዓም ግን ትክክለኛውን መመሪያ በመጣሱ ተወቅሷል።+ መናገር የማትችል አህያ እንደ ሰው ተናግራ የነቢዩን የእብደት አካሄድ ለመግታት ሞከረች።+ +17 እነዚህ ሰዎች የደረቁ ምንጮችና በአውሎ ነፋስ የሚነዱ ደመናዎች ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማም ይጠብቃቸዋል።+ +18 በከንቱ ጉራ ይነዛሉ። በተሳሳተ ጎዳና ከሚመላለሱ ሰዎች መካከል በቅርቡ ያመለጡትን በሥጋ ምኞቶችና+ ዓይን ባወጣ ምግባር* ያማልላሉ።+ +19 እነ�� ራሳቸው የመጥፎ ሥነ ምግባር ባሪያዎች ሆነው ሳሉ ነፃ ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤+ ማንም ሰው በሌላ ሰው ከተሸነፈ የዚያ ሰው ባሪያ ይሆናልና።*+ +20 ስለ ጌታችንና አዳኛችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ባገኙት ትክክለኛ እውቀት አማካኝነት ከዓለም ርኩሰት ካመለጡ በኋላ+ ተመልሰው በዚሁ ነገር ከተጠመዱና ከተሸነፉ ከመጀመሪያው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታቸው የከፋ እንደሚሆንባቸው ምንም ጥርጥር የለውም።+ +21 የጽድቅን መንገድ በትክክል ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደኋላ ከሚሉ ቀድሞውኑ ባያውቁት ይሻላቸው ነበር።+ +22 “ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፤ የታጠበች አሳማም ተመልሳ ጭቃ ላይ ትንከባለላለች”+ የሚለው እውነተኛ ምሳሌ በእነሱ ላይ ተፈጽሟል። +3 የአምላክ ልጆች ተብለን እንድንጠራ+ አብ ምን ያህል ታላቅ ፍቅር እንዳሳየን ተመልከቱ!+ ደግሞም ልጆቹ ነን። ዓለም እኛን የማያውቀን ለዚህ ነው፤+ ምክንያቱም ዓለም እሱን አላወቀውም።+ +2 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እኛ አሁን የአምላክ ልጆች ነን፤+ ሆኖም ወደፊት ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም።+ እሱ በሚገለጥበት ጊዜ እንደ እሱ እንደምንሆን እናውቃለን፤ ምክንያቱም እሱን በእርግጥ እናየዋለን። +3 በእሱ ላይ እንዲህ ያለ ተስፋ ያላቸው ሁሉ እሱ ንጹሕ እንደሆነ እነሱም ራሳቸውን ያነጻሉ።+ +4 በኃጢአት ጎዳና የሚመላለስ ሁሉ ዓመፀኛ ነው፤ ኃጢአትም ዓመፅ ነው። +5 በተጨማሪም እሱ እንዲገለጥ የተደረገው ኃጢአታችንን እንዲያስወግድ መሆኑን ታውቃላችሁ፤+ እሱ ደግሞ ኃጢአት የለበትም። +6 ከእሱ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ የሚኖር ሁሉ በኃጢአት ጎዳና አይመላለስም፤+ በኃጢአት ጎዳና የሚመላለስ ሁሉ እሱን አላየውም ደግሞም አላወቀውም። +7 ልጆቼ ሆይ፣ ማንም አያሳስታችሁ፤ እሱ ጻድቅ እንደሆነ ሁሉ በጽድቅ ጎዳና የሚመላለስ ሰውም ጻድቅ ነው። +8 በኃጢአት ጎዳና የሚመላለስ የዲያብሎስ ወገን ነው፤ ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያው አንስቶ* ኃጢአት ሲሠራ ቆይቷል።+ የአምላክ ልጅ የተገለጠው የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ* ነው።+ +9 ከአምላክ የተወለደ ሁሉ በኃጢአት ጎዳና አይመላለስም፤+ የአምላክ ዘር* እንዲህ ባለው ሰው ውስጥ ይኖራልና፤ በኃጢአት ጎዳናም ሊመላለስ አይችልም፤ ይህ ሰው ከአምላክ የተወለደ ነውና።+ +10 የአምላክ ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ በግልጽ ይታወቃሉ፦ በጽድቅ ጎዳና የማይመላለስ ሁሉ የአምላክ ወገን አይደለም፤ ወንድሙን የማይወድም የአምላክ ወገን አይደለም።+ +11 ከመጀመሪያ የሰማችሁት መልእክት እርስ በርሳችን መዋደድ አለብን የሚል ነውና፤+ +12 ከክፉው* ወገን እንደሆነውና ወንድሙን በጭካኔ እንደገደለው እንደ ቃየን መሆን የለብንም።+ ቃየን ወንድሙን በጭካኔ የገደለው በምን ምክንያት ነበር? የእሱ ሥራ ክፉ፣+ የወንድሙ ሥራ ግን ጽድቅ ስለነበረ ነው።+ +13 ወንድሞች፣ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ።+ +14 እኛ ወንድሞችን ስለምንወድ+ ከሞት ወደ ሕይወት እንደተሻገርን እናውቃለን።+ ወንድሙን የማይወድ በሞት ውስጥ ይኖራል።+ +15 ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፤+ ነፍሰ ገዳይ የሆነ ሁሉ ደግሞ የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ።+ +16 እሱ ሕይወቱን* ለእኛ አሳልፎ ስለሰጠ በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤+ እኛም ሕይወታችንን* ለወንድሞቻችን አሳልፈን የመስጠት ግዴታ አለብን።+ +17 ይሁን እንጂ የዚህ ዓለም ቁሳዊ ንብረት ያለው ሰው ወንድሙ ሲቸገር ተመልክቶ ሳይራራለት ቢቀር ‘የአምላክ ፍቅር በእሱ ውስጥ አለ’ እንዴት ሊባል ይችላል?+ +18 ልጆቼ ሆይ፣ በተግባርና+ በእውነት+ እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።+ +19 ከእውነት ወገን መሆናችንን በዚህ እናውቃለን፤ ልባችንም በፊቱ እንዲረጋጋ* እናደርጋለን፤ +20 ይህን የምናደርገው ልባችን እኛን በሚኮንንበት ነገር ሁሉ ነው፤ ምክንያቱም አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው፤ ደግሞም ሁሉንም ነገር ያውቃል።+ +21 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ልባችን የማይኮንነን ከሆነ ከአምላክ ጋር በነፃነት መነጋገር እንችላለን፤+ +22 እንዲሁም ትእዛዛቱን ስለምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኙትን ነገሮች ስለምናደርግ የምንጠይቀውን ሁሉ ከእሱ እንቀበላለን።+ +23 በእርግጥም ትእዛዙ ይህ ነው፦ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናምንና+ እሱ ባዘዘን መሠረት እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነው።+ +24 በተጨማሪም ትእዛዛቱን የሚጠብቅ ሰው ከእሱ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ ይኖራል፤ እሱም እንዲህ ካለው ሰው ጋር አንድነት ይኖረዋል።+ እሱ ከእኛ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ እንደሚኖር በሰጠን መንፈስ አማካኝነት እናውቃለን።+ +1 ከመጀመሪያ የነበረውን፣ የሰማነውን፣ በዓይናችን ያየነውን፣ በትኩረት የተመለከትነውንና በእጃችን የዳሰስነውን የሕይወትን ቃል በተመለከተ እንጽፍላችኋለን፤+ +2 (አዎ፣ ይህ ሕይወት ተገልጧል፤ እኛም አይተናል፤ ደግሞም እየመሠከርን ነው፤+ እንዲሁም በአብ ዘንድ የነበረውንና ለእኛ የተገለጠውን የዘላለም ሕይወት+ ለእናንተ እየነገርናችሁ ነው፤) +3 እናንተም ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ* ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተም እየነገርናችሁ ነው።+ ደግሞም ይህ ኅብረታችን ከአብና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።+ +4 እነዚህን ነገሮች የምንጽፍላችሁ ደስታችን የተሟላ እንዲሆን ነው። +5 ከእሱ የሰማነውና ለእናንተ የምናሳውቀው መልእክት ይህ ነው፦ አምላክ ብርሃን ነው፤+ በእሱም ዘንድ* ጨለማ ፈጽሞ የለም። +6 “ከእሱ ጋር ኅብረት አለን” ብለን እየተናገርን በጨለማ የምንመላለስ ከሆነ እየዋሸን ነው፤ እውነትንም ሥራ ላይ እያዋልን አይደለም።+ +7 ይሁን እንጂ እሱ ራሱ በብርሃን እንዳለ ሁሉ እኛም በብርሃን የምንመላለስ ከሆነ እርስ በርሳችን ኅብረት ይኖረናል፤ እንዲሁም የልጁ የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።+ +8 “ኃጢአት የለብንም” ብለን የምንናገር ከሆነ ራሳችንን እያታለልን ነው፤+ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። +9 ኃጢአታችንን የምንናዘዝ ከሆነ እሱ ታማኝና ጻድቅ ስለሆነ ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል፤ እንዲሁም ከክፋት ሁሉ ያነጻናል።+ +10 “ኃጢአት አልሠራንም” ብለን የምንናገር ከሆነ እሱን ውሸታም እያደረግነው ነው፤ ቃሉም በውስጣችን የለም። +2 የተወደዳችሁ ልጆቼ፣ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ኃጢአት* እንዳትሠሩ ነው። ማንም ኃጢአት ቢሠራ ግን በአብ ዘንድ ረዳት* አለን፤ እሱም ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።+ +2 እሱ ለእኛ ኃጢአት+ የቀረበ የማስተሰረያ* መሥዋዕት ነው፤+ ሆኖም ለእኛ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሁሉ ኃጢአት ጭምር ነው።+ +3 ደግሞም ትእዛዛቱን መፈጸማችንን ከቀጠልን እሱን የምናውቅ መሆናችንን በዚህ እንረዳለን። +4 “እሱን አውቀዋለሁ” እያለ ትእዛዛቱን የማይፈጽም ሰው ቢኖር ውሸታም ነው፤ እውነትም በዚህ ሰው ውስጥ የለም። +5 ሆኖም የእሱን ቃል የሚጠብቅ ማንም ቢኖር የአምላክ ፍቅር በእርግጥ በዚህ ሰው ላይ ፍጹም በሆነ መንገድ ይታያል።+ ከእሱ ጋር አንድነት እንዳለንም በዚህ እናውቃለን።+ +6 ከእሱ ጋር ያለኝን አንድነት ጠብቄ እኖራለሁ የሚል፣ እሱ በተመላለሰበት መንገድ የመመላለስ ግዴታ አለበት።+ +7 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ የምጽፍላችሁ ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበራችሁን የቆየውን ትእዛዝ እንጂ አዲስ ትእዛዝ አይደለም።+ ይህ የቆየው ትእዛዝ የሰማችሁት ቃል ነው። +8 ይሁንና በእሱም ሆነ በእናንተ ዘንድ እውነት የሆነውን አ���ስ ትእዛዝ እጽፍላችኋለሁ፤ ምክንያቱም ጨለማው እያለፈና እውነተኛው ብርሃን አሁንም እንኳ እያበራ ነው።+ +9 በብርሃን ውስጥ እንዳለ እየተናገረ ወንድሙን የሚጠላ+ አሁንም በጨለማ ውስጥ ነው።+ +10 ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ውስጥ ይኖራል፤+ በእሱም ዘንድ ምንም የሚያሰናክል ነገር የለም። +11 ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ ውስጥ ነው፤ በጨለማም ይመላለሳል፤+ ደግሞም ጨለማው ዓይኑን ስላሳወረው ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።+ +12 ልጆቼ ሆይ፣ የምጽፍላችሁ ለእሱ ስም ሲባል ኃጢአታችሁ ይቅር ስለተባለላችሁ ነው።+ +13 አባቶች ሆይ፣ የምጽፍላችሁ ከመጀመሪያ ያለውን እሱን ስላወቃችሁት ነው። እናንተ ወጣት ወንዶች፣ የምጽፍላችሁ ክፉውን ስላሸነፋችሁት ነው።+ ልጆች ሆይ፣ የምጽፍላችሁ አብን ስላወቃችሁት ነው።+ +14 አባቶች ሆይ፣ የምጽፍላችሁ ከመጀመሪያ ያለውን እሱን ስላወቃችሁት ነው። እናንተ ወጣት ወንዶች፣ የምጽፍላችሁ ጠንካሮች ስለሆናችሁ፣+ የአምላክ ቃል በልባችሁ ስለሚኖርና+ ክፉውን ስላሸነፋችሁት ነው።+ +15 ዓለምንም ሆነ በዓለም ውስጥ ያሉትን ነገሮች አትውደዱ።+ ማንም ዓለምን የሚወድ ከሆነ የአብ ፍቅር በውስጡ የለም፤+ +16 ምክንያቱም በዓለም ያለው ነገር ሁሉ ይኸውም የሥጋ ምኞት፣+ የዓይን አምሮትና+ ኑሮዬ ይታይልኝ ማለት* ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመነጭ አይደለም። +17 ከዚህም በተጨማሪ ዓለምም ሆነ ምኞቱ ያልፋሉ፤+ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።+ +18 ልጆቼ ሆይ፣ ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ እንደሰማችሁትም ፀረ ክርስቶስ እየመጣ ነው፤+ አሁንም እንኳ ብዙ ፀረ ክርስቶሶች መጥተዋል፤+ ከዚህም በመነሳት ይህ የመጨረሻው ሰዓት መሆኑን እናውቃለን። +19 በእኛ መካከል ነበሩ፤ ሆኖም ከእኛ ወገን ስላልነበሩ ትተውን ሄደዋል።+ ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር። ሆኖም ከእኛ ወገን የሆኑት ሁሉም አለመሆናቸው በግልጽ ይታይ ዘንድ ከእኛ ተለይተው ወጡ።+ +20 እናንተ ግን ቅዱስ ከሆነው ከእሱ የመንፈስ ቅብዓት አግኝታችኋል፤+ ደግሞም ሁላችሁም እውቀት አላችሁ። +21 የምጽፍላችሁ እውነትን+ ስለማታውቁ ሳይሆን እውነትን ስለምታውቁና ከእውነት ምንም ዓይነት ውሸት ስለማይወጣ ነው።+ +22 ኢየሱስን፣ ክርስቶስ አይደለም ብሎ ከሚክድ በቀር ውሸታም ማን ነው?+ ይህ አብንና ወልድን የሚክደው ፀረ ክርስቶስ ነው።+ +23 ወልድን የሚክድ ሁሉ በአብ ዘንድም ተቀባይነት የለውም።+ ወልድን አምኖ የሚቀበል ሁሉ+ ግን በአብም ዘንድ ተቀባይነት አለው።+ +24 በእናንተ በኩል ግን ከመጀመሪያ የሰማችሁት በልባችሁ ይኑር።+ ከመጀመሪያ የሰማችሁት በልባችሁ የሚኖር ከሆነ እናንተም ከወልድና ከአብ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ትኖራላችሁ። +25 ከዚህም በተጨማሪ እሱ ራሱ የገባልን የተስፋ ቃል የዘላለም ሕይወት ነው።+ +26 እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ሊያሳስቷችሁ ከሚሞክሩት ሰዎች የተነሳ ነው። +27 እናንተ ግን ከእሱ የተቀበላችሁት የመንፈስ ቅብዓት+ በውስጣችሁ ይኖራል፤ በመሆኑም ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ከእሱ ያገኛችሁት ይህ ቅብዓት ስለ ሁሉም ነገር እያስተማራችሁ ነው፤+ ደግሞም እውነት እንጂ ውሸት አይደለም። ይህ ቅብዓት ባስተማራችሁ መሠረት ከእሱ ጋር ያላችሁን አንድ +28 እንግዲህ ልጆቼ፣ እሱ በሚገለጥበት ጊዜ የመናገር ነፃነት+ እንዲኖረንና እሱ በሚገኝበት ወቅት ለኀፍረት ተዳርገን ከእሱ እንዳንርቅ ከእሱ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ኑሩ። +29 እሱ ጻድቅ መሆኑን ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእሱ የተወለደ መሆኑን ታውቃላችሁ።+ +4 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ በመንፈስ የተነገረን ቃል* ሁሉ አትመኑ፤+ ከዚህ ይልቅ በመንፈስ የተነገሩት ቃላት* ከአምላክ የመነጩ መሆን አለመሆናቸውን መርምሩ፤+ ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።+ +2 በመንፈስ የተነገረው ቃል ከአምላክ የመነጨ መሆኑን በዚህ ማወቅ ትችላላችሁ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የሚመሠክር በመንፈስ የተነገረ ቃል ሁሉ ከአምላክ የመነጨ ነው።+ +3 ሆኖም ስለ ኢየሱስ የማይመሠክር በመንፈስ የተነገረ ቃል ሁሉ ከአምላክ የሚመነጭ አይደለም።+ ይህ በመንፈስ የተነገረ ቃል ከፀረ ክርስቶስ የሚመነጭ ነው፤ ፀረ ክርስቶስ እንዲህ ያሉ ነገሮችን እንደሚናገር ሰምታችኋል፤+ አሁንም እንኳ ይህ ቃል በዓለም ላይ እየተነገረ ነው።+ +4 ልጆቼ ሆይ፣ እናንተ ከአምላክ ወገን ናችሁ፤ እነሱንም* አሸንፋችኋል፤+ ምክንያቱም ከእናንተ ጎን ያለው፣+ ከዓለም ጎን ካለው ይበልጣል።+ +5 እነሱ የዓለም ወገን ናቸው፤+ ከዓለም የሚመነጨውን ነገር የሚናገሩትና ዓለምም የሚሰማቸው ለዚህ ነው።+ +6 እኛ ከአምላክ ወገን ነን። አምላክን የሚያውቅ ሁሉ ይሰማናል፤+ ከአምላክ ወገን ያልሆነ ሁሉ አይሰማንም።+ በመንፈስ የተነገረውን የእውነት ቃልና በመንፈስ የተነገረውን የስህተት ቃል ለይተን የምናውቀው በዚህ መንገድ ነው።+ +7 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እርስ በርስ መዋደዳችንን እንቀጥል፤+ ምክንያቱም ፍቅር ከአምላክ ነው፤ ፍቅር የሚያሳይ ሁሉ ከአምላክ የተወለደ ሲሆን አምላክን ያውቃል።+ +8 ፍቅር የማያሳይ አምላክን አያውቅም፤ ምክንያቱም አምላክ ፍቅር ነው።+ +9 የአምላክ ፍቅር ከእኛ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በዚህ መንገድ ተገልጧል፤ እኛ በእሱ አማካኝነት ሕይወት ማግኘት እንድንችል+ አምላክ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታል።+ +10 ይህ ፍቅር የተገለጠው በዚህ መንገድ ነው፦ እኛ አምላክን ስለወደድነው ሳይሆን እሱ ስለወደደንና ለኃጢአታችን የማስተሰረያ መሥዋዕት* እንዲሆን+ ልጁን ስለላከ ነው።+ +11 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ አምላክ የወደደን በዚህ መንገድ ከሆነ እኛም እርስ በርሳችን የመዋደድ ግዴታ አለብን።+ +12 መቼም ቢሆን አምላክን ያየው ማንም የለም።+ እርስ በርስ መዋደዳችንን ከቀጠልን አምላክ ከእኛ ጋር ይሆናል፤ ፍቅሩም በመካከላችን ፍጹም ይሆናል።+ +13 እሱ መንፈሱን ስለሰጠን እኛ ከእሱ ጋር አንድነት እንዳለንና እሱም ከእኛ ጋር አንድነት እንዳለው እናውቃለን። +14 ከዚህ በተጨማሪ አብ ልጁን የዓለም አዳኝ አድርጎ እንደላከው እኛ ራሳችን አይተናል፤ ደግሞም እየመሠከርን ነው።+ +15 ማንም ሰው ኢየሱስ የአምላክ ልጅ መሆኑን የሚመሠክር+ ከሆነ አምላክ እንዲህ ካለው ሰው ጋር አንድነት ይኖረዋል፤ እሱም ከአምላክ ጋር አንድነት ይኖረዋል።+ +16 ደግሞም አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል፤ እንዲሁም አምነናል።+ አምላክ ፍቅር ነው፤+ በፍቅር የሚኖር ከአምላክ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ ይኖራል፤ አምላክም ከእሱ ጋር አንድነት ይኖረዋል።+ +17 በመሆኑም በፍርድ ቀን የመናገር ነፃነት* ይኖረን ዘንድ+ ፍቅር በእኛ መካከል ፍጹም የሆነው በዚህ መንገድ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ ዓለም ውስጥ እኛ ራሳችን እንደ እሱ* ነን። +18 በፍቅር ፍርሃት የለም፤+ እንዲያውም ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፤* ምክንያቱም ፍርሃት ወደኋላ እንድንል ያደርገናል። ደግሞም የሚፈራ ሰው ፍጹም የሆነ ፍቅር የለውም።+ +19 እሱ አስቀድሞ ስለወደደን እኛም ፍቅር እናሳያለን።+ +20 ማንም “አምላክን እወደዋለሁ” እያለ ወንድሙን የሚጠላ ከሆነ ይህ ሰው ውሸታም ነው።+ ያየውን ወንድሙን የማይወድ+ ያላየውን አምላክ ሊወድ አይችልምና።+ +21 እሱም “አምላክን የሚወድ ሁሉ ወንድሙንም መውደድ ይገባዋል” የሚለውን ይህን ትእዛዝ ሰጥ��ናል።+ +5 ኢየሱስ በእርግጥ ክርስቶስ እንደሆነ የሚያምን ሁሉ ከአምላክ ተወልዷል፤+ አባቱን የሚወድ ሁሉ ደግሞ ከእሱ የተወለደውንም ይወዳል። +2 አምላክን ስንወድና ትእዛዛቱን ስንፈጽም የአምላክን ልጆች+ እንደምንወድ በዚህ እናውቃለን። +3 አምላክን መውደድ ማለት ትእዛዛቱን መጠበቅ ማለት ነውና፤+ ትእዛዛቱ ደግሞ ከባድ አይደሉም፤+ +4 ምክንያቱም ከአምላክ የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል።+ ዓለምን ድል እንድናደርግ ያስቻለን እምነታችን ነው።+ +5 ዓለምን ሊያሸንፍ የሚችል ማን ነው?+ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ እንደሆነ የሚያምን ሰው አይደለም?+ +6 በውኃና በደም አማካኝነት የመጣው፣ እሱ ይኸውም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ የመጣውም ከውኃ ጋር ብቻ ሳይሆን+ ከውኃና ከደም ጋር ነው።+ ምሥክርነት የሚሰጠውም መንፈስ ነው፤+ ምክንያቱም መንፈስ እውነት ነው። +7 ምሥክርነት የሚሰጡ ሦስት ነገሮች አሉ፦ +8 እነሱም መንፈሱ፣+ ውኃውና+ ደሙ+ ናቸው፤ እነዚህ ሦስቱ ደግሞ ይስማማሉ። +9 ሰዎች የሚሰጡትን ምሥክርነት ከተቀበልን አምላክ የሚሰጠው ምሥክርነት ደግሞ ከዚያ የላቀ ነው። ምክንያቱም አምላክ የሰጠው ምሥክርነት ስለ ልጁ የሰጠው የምሥክርነት ቃል ነው። +10 በአምላክ ልጅ የሚያምን የምሥክርነቱ ቃል በልቡ አለው። በአምላክ የማያምን ግን አምላክ ስለ ልጁ የሰጠውን ምሥክርነት ስላላመነ እሱን ውሸታም አድርጎታል።+ +11 ምሥክርነቱም ይህ ነው፤ አምላክ የዘላለም ሕይወት ሰጠን፤+ ይህም ሕይወት የተገኘው በልጁ ነው።+ +12 ልጁ ያለው ይህ ሕይወት አለው፤ የአምላክ ልጅ የሌለው ይህ ሕይወት የለውም።+ +13 እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ በአምላክ ልጅ ስም የምታምኑት+ እናንተ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ነው።+ +14 በእሱ ላይ ያለን ትምክህት* ይህ ነው፤+ የምንጠይቀው ነገር ምንም ይሁን ምን ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ እስከለመንን ድረስ ይሰማናል።+ +15 የምንጠይቀውንም ነገር ሁሉ እንደሚሰማን ስለምናውቅ የምንጠይቀውን ነገር እንደምናገኝ እርግጠኞች ነን።+ +16 ማንም ሰው ወንድሙ ለሞት የማያበቃ ኃጢአት ሲሠራ ቢያየው ስለ እሱ ይለምናል፤ አምላክም ሕይወት ይሰጠዋል።+ ይህ የሚሆነው ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ላልሠሩ ሰዎች ነው። ይሁን እንጂ ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት አለ።+ እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ለሠራ ግለሰብ ማንም ሰው ይጸልይ አልልም። +17 ጽድቅ ያልሆነ ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው፤+ ይሁንና ለሞት የማያበቃ ኃጢአት አለ። +18 ከአምላክ የተወለደ ሁሉ በኃጢአት ጎዳና እንደማይመላለስ እናውቃለን፤ ይልቁንም ከአምላክ የተወለደው* ይጠብቀዋል፤ ክፉውም* ምንም ሊያደርገው አይችልም።+ +19 እኛ ከአምላክ ወገን መሆናችንን እናውቃለን፤ መላው ዓለም ግን በክፉው ቁጥጥር ሥር ነው።+ +20 ይሁንና የአምላክ ልጅ እንደመጣ እናውቃለን፤+ እሱም ስለ እውነተኛው አምላክ እውቀት ማግኘት እንድንችል ማስተዋል* ሰጥቶናል። እኛም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ከእሱ ጋር አንድነት አለን።+ አዎ፣ እሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።+ +21 ልጆቼ ሆይ፣ ከጣዖቶች ራቁ።+ +1 ከሽማግሌው፣ ለተመረጠችው እመቤትና* ለልጆቿ፦ ከልብ እወዳችኋለሁ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን ያወቁ ሁሉ ይወዷችኋል፤ +2 የምንወዳችሁ በውስጣችን በሚኖረው እውነት የተነሳ ነው፤ ይህም እውነት አብሮን ለዘላለም ይኖራል። +3 አባት ከሆነው አምላክና የአብ ልጅ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ እውነትንና ፍቅርን ጨምሮ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም እናገኛለን። +4 ከልጆችሽ መካከል አንዳንዶቹ ከአብ በተቀበልነው ትእዛዝ መሠረት በእውነት እየተመላለሱ መሆናቸውን ስላወቅኩ እጅግ ደስ ብሎኛል።+ +5 ስለሆነም እመቤት ���ይ፣ እርስ በርስ እንዋደድ ዘንድ እለምንሻለሁ። (እየጻፍኩልሽ ያለሁት አዲስ ትእዛዝ ሳይሆን ከመጀመሪያ ጀምሮ የተቀበልነው ነው።)+ +6 ፍቅር ሲባል ደግሞ በትእዛዛቱ መሠረት መመላለስ ማለት ነው።+ እናንተ ከመጀመሪያ እንደሰማችሁት ትእዛዙ በፍቅር መመላለሳችሁን እንድትቀጥሉ ነው። +7 ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መምጣቱን+ አምነው የማይቀበሉ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋልና።+ እንዲህ ያለ ሰው አሳችና ፀረ ክርስቶስ ነው።+ +8 ሙሉ ሽልማት እንድታገኙ እንጂ የደከምንባቸውን ነገሮች እንዳታጡ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።+ +9 ከክርስቶስ ትምህርት አልፎ የሚሄድና በትምህርቱ ጸንቶ የማይኖር ሁሉ አምላክ የለውም።+ በዚህ ትምህርት ጸንቶ የሚኖር ሰው ግን አብና ወልድ አሉት።+ +10 ማንም ሰው ወደ እናንተ ቢመጣና ይህን ትምህርት ይዞ ባይመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት+ ወይም ሰላም አትበሉት። +11 ሰላም የሚለው ሰው የክፉ ሥራው ተባባሪ ይሆናልና። +12 የምነግራችሁ ብዙ ነገር ቢኖረኝም በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ደስታችሁ የተሟላ እንዲሆን ወደ እናንተ መጥቼ ፊት ለፊት እንደማነጋግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። +13 የተመረጠችው የእህትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል። +1 ከሽማግሌው፣ ከልብ ለምወደው ለተወዳጁ ጋይዮስ። +2 የተወደድክ ወንድም፣ አሁን በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለህ* ሁሉ፣ በሁሉም ነገር እንዲሳካልህና ጥሩ ጤንነት እንዲኖርህ እጸልያለሁ። +3 ወንድሞች መጥተው እውነትን አጥብቀህ እንደያዝክ ሲመሠክሩ በመስማቴ እጅግ ደስ ብሎኛልና፤ ደግሞም በእውነት ውስጥ እየተመላለስክ መሆኑ በጣም አስደስቶኛል።+ +4 ልጆቼ በእውነት ውስጥ እየተመላለሱ መሆናቸውን ከመስማት የበለጠ ደስታ የለኝም።*+ +5 የተወደድክ ወንድም፣ በግል ባታውቃቸውም እንኳ ለወንድሞች በምታደርገው ነገር ታማኝ መሆንህን እያሳየህ ነው።+ +6 እነሱም በጉባኤው ፊት ስለ አንተ ፍቅር መሥክረዋል። እባክህ፣ አምላክ ደስ በሚሰኝበት ሁኔታ ሸኛቸው።+ +7 ከአሕዛብ ምንም ሳይቀበሉ የወጡት ለስሙ ሲሉ ነውና።+ +8 ስለዚህ በእውነት ውስጥ አብረን የምንሠራ እንሆን ዘንድ እንዲህ ላሉ ሰዎች የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ የማሳየት ግዴታ አለብን።+ +9 ለጉባኤው የጻፍኩት ነገር ነበር፤ ሆኖም በመካከላቸው የመሪነት ቦታ መያዝ የሚፈልገው+ ዲዮጥራጢስ ከእኛ በአክብሮት የሚቀበለው ምንም ነገር የለም።+ +10 በመሆኑም እኔ ከመጣሁ ስለ እኛ መጥፎ ወሬ በማናፈስ* የሚሠራውን ሥራ ይፋ አወጣለሁ።+ ይህም አልበቃ ብሎት ወንድሞችን በአክብሮት አይቀበልም፤+ እነሱን መቀበል የሚፈልጉትንም ለመከልከልና ከጉባኤ ለማባረር ይጥራል። +11 ወዳጄ ሆይ፣ መጥፎ የሆነውን አትከተል፤ ይልቁንም ጥሩ የሆነውን ተከተል።+ መልካም የሚያደርግ የአምላክ ወገን ነው።+ መጥፎ የሚያደርግ አምላክን አላየውም።*+ +12 ሁሉም ወንድሞች ስለ ድሜጥሮስ በሚገባ መሥክረዋል፤ እውነት ራሱም ይህን አረጋግጧል። እንዲያውም እኛም ጭምር ስለ እሱ እየመሠከርን ነው፤ የምንሰጠው ምሥክርነት ደግሞ እውነት እንደሆነ ታውቃለህ። +13 ብዙ የምነግርህ ነገር ነበረኝ፤ ሆኖም ከዚህ በላይ በብዕርና በቀለም ልጽፍልህ አልፈልግም። +14 ከዚህ ይልቅ በቅርቡ እንደማይህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በዚያን ጊዜ ፊት ለፊት እንነጋገራለን። ሰላም ለአንተ ይሁን። ወዳጆች ሰላምታ ያቀርቡልሃል። በግለሰብ ደረጃ ሰላምታዬን ለወዳጆች አቅርብልኝ። +1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና የያዕቆብ+ ወንድም ከሆነው ከይሁዳ፣ ለተጠሩትና+ አባታችን በሆነው አምላክ ለተወደዱት እንዲሁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ይሆኑ ዘንድ ጥበቃ ለተደረገላቸው፦+ +2 ምሕረት፣ ሰላምና ፍቅር ይብ��ላችሁ። +3 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ሁላችንም ስለምናገኘው መዳን+ ልጽፍላችሁ እጅግ ጓጉቼ የነበረ ቢሆንም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅዱሳን ስለተሰጠው እምነት ብርቱ ተጋድሎ እንድታደርጉ+ ለማሳሰብ ልጽፍላችሁ ተገደድኩ። +4 ይህን ያደረግኩት ፍርድ እንደሚጠብቃቸው በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አስቀድሞ የተነገረላቸው አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ስለገቡ ነው፤ እነዚህ ሰዎች ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው፣ በአምላካችን ጸጋ እያሳበቡ ዓይን ያወጣ ምግባር*+ የሚፈጽሙ እንዲሁም የዋጀንንና እሱ ብቻ ጌታችን* የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ +5 ምንም እንኳ ይህን ሁሉ አስቀድማችሁ በሚገባ ታውቁ የነበረ ቢሆንም ይሖዋ* ሕዝቡን ከግብፅ ምድር እንዳዳነ፣+ በኋላም እምነት ያላሳዩትን እንዳጠፋ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።+ +6 በተጨማሪም መጀመሪያ የነበራቸውን ቦታ ያልጠበቁትንና ተገቢ የሆነውን የመኖሪያ ስፍራቸውን የተዉትን መላእክት+ በታላቁ ቀን ለሚፈጸምባቸው ፍርድ በዘላለም እስራት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ አቆይቷቸዋል።+ +7 በተመሳሳይም ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በዙሪያቸው የነበሩ ከተሞች ራሳቸውን ልቅ ለሆነ የፆታ ብልግና* አሳልፈው የሰጡ ከመሆኑም ሌላ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሥጋ ፍላጎታቸውን ያሳድዱ ነበር፤+ በመሆኑም በዘላለም እሳት ፍርድ ተቀጥተው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆነዋል።+ +8 ያም ሆኖ ግን እነዚህ ሕልም አላሚዎች ሥጋን ያረክሳሉ፤ ሥልጣንን ይንቃሉ፤ የተከበሩትንም ይሳደባሉ።+ +9 ይሁንና የመላእክት አለቃ+ ሚካኤል+ የሙሴን ሥጋ+ በተመለከተ ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ የስድብ ቃል በመናገር ሊፈርድበት አልደፈረም፤+ ከዚህ ይልቅ “ይሖዋ* ይገሥጽህ” አለው።+ +10 እነዚህ ሰዎች ግን ስለማያውቁት ነገር ሁሉ ትችት ይሰነዝራሉ።+ ደግሞም አእምሮ እንደሌላቸው እንስሳት፣+ በደመ ነፍስ የሚረዷቸውን ነገሮች ሁሉ ሲያደርጉ የራሳቸውን ሥነ ምግባር ያበላሻሉ። +11 በቃየን+ መንገድ ስለሄዱ፣ ለጥቅም ሲሉ የበለዓምን+ የተሳሳተ መንገድ በጭፍን ስለተከተሉና በቆሬ+ የዓመፅ ንግግር+ ስለጠፉ ወዮላቸው! +12 እነዚህ ሰዎች ፍቅራችሁን ለመግለጽ በምታዘጋጁት ግብዣ ላይ ተገኝተው አብረዋችሁ ሲመገቡ ልክ በባሕር ውስጥ እንደተደበቀ ዓለት+ ከመሆናቸውም ሌላ ያላንዳች ኀፍረት ለሆዳቸው ብቻ የሚያስቡ እረኞች ናቸው፤+ በነፋስ ወዲያና ወዲህ የሚነዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች+ እንዲሁም በመከር ጊዜ ፍሬ የማይገኝባቸው፣ +13 አረፋ እንደሚደፍቅ ኃይለኛ የባሕር ማዕበል አሳፋሪ ድርጊታቸውን ይገልጣሉ፤+ ለዘላለም ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚጣሉ ተንከራታች ከዋክብት ናቸው።+ +14 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖክ+ ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ሲል ተንብዮአል፦ “እነሆ! ይሖዋ* ከአእላፋት* ቅዱሳን መላእክቱ ጋር መጥቷል፤+ +15 የመጣውም በሁሉ ላይ ለመፍረድ፣+ ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች ለአምላክ አክብሮት በጎደለው መንገድ የፈጸሙትን ክፉ ድርጊትና ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ኃጢአተኞች በእሱ ላይ የተናገሩትን ክፉ ቃል ለማጋለጥ ነው።”+ +16 እነዚህ ሰዎች የሚያጉረመርሙና+ ኑሯቸውን የሚያማርሩ እንዲሁም የራሳቸውን ምኞት የሚከተሉ ናቸው፤+ ጉራ መንዛት ይወዳሉ፤ ለጥቅማቸው ሲሉም ሌሎችን ይክባሉ።+ +17 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እናንተ ግን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት አስቀድመው የነገሯችሁን ቃል* አስታውሱ፤ +18 እነሱ “በመጨረሻው ዘመን መጥፎ ምኞታቸውን የሚከተሉ ዘባቾች ይነሳሉ” ይሏችሁ ነበር።+ +19 እነዚህ ሰዎች ክፍፍል የሚፈጥሩ፣+ የእንስሳ ባሕርይ ያላቸውና* መንፈሳዊ ያልሆኑ* ናቸው። +20 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እናንተ ግን እጅግ ቅዱስ በሆነው ��ምነታችሁ ላይ ራሳችሁን ገንቡ፤ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ጸልዩ፤+ +21 ይህን የምታደርጉት የዘላለም ሕይወት የሚያስገኝላችሁን+ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት እየተጠባበቃችሁ ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ እንድትኖሩ ነው።+ +22 በተጨማሪም ጥርጣሬ ላደረባቸው+ ምሕረት አሳዩ፤+ +23 ከእሳት ነጥቃችሁ በማውጣት አድኗቸው።+ ለሌሎች ምሕረት ማሳየታችሁንም ቀጥሉ፤ ሆኖም ይህን ስታደርጉ ለራሳችሁ መጠንቀቅና በሥጋ ሥራ ያደፈውን ልብሳቸውን መጥላት ይኖርባችኋል።+ +24 እንዳትሰናከሉ ሊጠብቃችሁና ነቀፋ የሌለባችሁ አድርጎ በታላቅ ደስታ፣ በክብሩ ፊት ሊያቆማችሁ ለሚችለው፣+ +25 አዳኛችን ለሆነው ብቸኛው አምላክ ከዘመናት ሁሉ በፊት፣ አሁንና እስከ ዘላለም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ክብር፣ ግርማ፣ ኃይልና ሥልጣን ይሁን። አሜን። +17 ሰባቱን ሳህኖች ይዘው ከነበሩት ሰባት መላእክት+ አንዱ መጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “ና፣ በብዙ ውኃዎች ላይ በምትቀመጠው በታላቂቱ አመንዝራ ላይ የተበየነውን ፍርድ አሳይሃለሁ፤+ +2 የምድር ነገሥታት ከእሷ ጋር አመነዘሩ፤*+ የምድር ነዋሪዎች ደግሞ በዝሙቷ* ወይን ጠጅ ሰከሩ።”+ +3 እሱም በመንፈስ ኃይል ወደ ምድረ በዳ ወሰደኝ። በዚያም አንዲት ሴት አምላክን የሚሰድቡ ስሞች በሞሉበት እንዲሁም ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ባሉት ደማቅ ቀይ አውሬ ላይ ተቀምጣ አየሁ። +4 ሴቲቱ ሐምራዊና+ ደማቅ ቀይ ልብስ ለብሳ እንዲሁም በወርቅ፣ በከበሩ ድንጋዮችና በዕንቁዎች አጊጣ ነበር፤+ በእጇም አስጸያፊ ነገሮችና የዝሙቷ* ርኩሰት የሞላበት የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር። +5 በግንባሯ ላይ “ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና+ የምድር አስጸያፊ ነገሮች እናት”+ የሚል ሚስጥራዊ ስም ተጽፎ ነበር። +6 እኔም ሴቲቱ በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምሥክሮች ደም ሰክራ አየኋት።+ ባየኋትም ጊዜ እጅግ ተደነቅኩ። +7 መልአኩም እንዲህ አለኝ፦ “የተደነቅከው ለምንድን ነው? የሴቲቱን+ እንዲሁም እሷ የተቀመጠችበትን ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉት አውሬ+ ሚስጥር እነግርሃለሁ፦ +8 ያየኸው አውሬ ከዚህ በፊት ነበር፤ አሁን ግን የለም፤ ይሁንና በቅርቡ ከጥልቁ+ ይወጣል፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል። ዓለም ከተመሠረተበት* ጊዜ አንስቶ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል+ ላይ ያልተጻፈው የምድር ነዋሪዎች አውሬው ከዚህ በፊት እንደነበረ፣ አሁን ግን እንደሌለና ወደፊት እንደሚኖር ሲያዩ በአድናቆ +9 “ይህ ነገር ጥበብ ያለው አእምሮ* ይጠይቃል፦ ሰባቱ ራሶች+ ሴቲቱ የተቀመጠችባቸውን ሰባት ተራሮች ያመለክታሉ። +10 ደግሞም ሰባት ነገሥታት ናቸው፦ አምስቱ ወድቀዋል፤ አንዱ አለ፤ ሌላው ደግሞ ገና አልመጣም፤ በሚመጣበት ጊዜ ግን ለአጭር ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል። +11 ከዚህ በፊት የነበረው፣ አሁን ግን የሌለው አውሬም+ ስምንተኛ ንጉሥ ነው፤ የሚወጣው ግን ከሰባቱ ነው፤ እሱም ወደ ጥፋት ይሄዳል። +12 “ያየሃቸው አሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታትን ያመለክታሉ፤ ይሁንና ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንዲነግሡ ሥልጣን ይቀበላሉ። +13 እነዚህ አንድ ዓይነት ሐሳብ አላቸው፤ በመሆኑም ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውን ለአውሬው ይሰጣሉ። +14 እነዚህ ከበጉ+ ጋር ይዋጋሉ፤ ሆኖም በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ+ ስለሆነ ድል ይነሳቸዋል።+ ከእሱ ጋር ያሉት የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ድል ያደርጋሉ።”+ +15 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “አመንዝራዋ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውኃዎች ወገኖችን፣ ብዙ ሕዝብን፣ ብሔራትንና ቋንቋዎችን ያመለክታሉ።+ +16 ያየሃቸው አሥሩ ቀንዶችና+ አውሬውም+ አመንዝራዋን+ ይጠሏታል፤ ከዚያም ይበዘብዟታል፤ ራቁቷንም ያስቀሯታል፤ እንዲሁም ሥጋዋን ይበላሉ፤ ሙሉ በሙሉም በእሳት ያቃጥሏታል።+ +17 አምላክ ቃሉ ፍጻሜውን እስኪያገኝ ድረስ ሐሳቡን ዳር እንዲያደርሱ+ አዎ፣ መንግሥታቸውን ለአውሬው+ በመስጠት አንድ የሆነውን የራሳቸውን ሐሳብ እንዲፈጽሙ ይህን በልባቸው አኑሯልና። +18 ያየሃትም ሴት+ በምድር ነገሥታት ላይ መንግሥት ያላትን ታላቂቱን ከተማ ታመለክታለች።” +18 ከዚህ በኋላ ከፍተኛ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሳ ምድር በብርሃን ደመቀች። +2 እሱም በኃይለኛ ድምፅ እንዲህ ሲል ጮኸ፦ “ወደቀች! ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች!+ የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩስ መንፈስ ሁሉ* እንዲሁም የርኩሳንና የተጠሉ ወፎች ሁሉ መሰወሪያ ሆነች!+ +3 ብሔራት ሁሉ የዝሙቷ* የፍትወት* ወይን ጠጅ ሰለባ ሆነዋል፤+ የምድር ነገሥታትም ከእሷ ጋር አመንዝረዋል፤+ የምድር ነጋዴዎችም * ያላንዳች ኀፍረት ባከማቸቻቸው ውድ ነገሮች በልጽገዋል።” +4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “ሕዝቤ ሆይ፣ የኃጢአቷ ተባባሪ መሆን የማትፈልጉና የሚደርስባት መቅሰፍት ተካፋይ መሆን የማትፈልጉ ከሆነ ከእሷ ውጡ።+ +5 ኃጢአቷ እስከ ሰማይ ድረስ ተቆልሏልና፤+ አምላክም የፈጸመቻቸውን ኢፍትሐዊ ድርጊቶች* አስቧል።+ +6 በሌሎች ላይ በፈጸመችው በዚያው መንገድ ብድራቷን መልሱላት፤+ አዎ፣ ለሠራቻቸው ነገሮች እጥፍ ክፈሏት፤+ በቀላቀለችበት ጽዋ+ እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት።+ +7 ለራሷ ክብር የሰጠችውንና ያላንዳች ኀፍረት ውድ ነገሮች በማከማቸት የተቀማጠለችውን ያህል፣ በዚያው ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጧት። ሁልጊዜ በልቧ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ፈጽሞ አይደርስብኝም’ ትላለችና።+ +8 መቅሰፍቶቿ ይኸውም ሞትና ሐዘን እንዲሁም ረሃብ በአንድ ቀን የሚመጡባት ለዚህ ነው፤ ሙሉ በሙሉም በእሳት ትቃጠላለች፤+ ምክንያቱም የፈረደባት ይሖዋ* አምላክ ብርቱ ነው።+ +9 “ከእሷ ጋር ያመነዘሩና* ያላንዳች ኀፍረት ከእሷ ጋር በቅንጦት የኖሩ የምድር ነገሥታትም እሷ ስትቃጠል የሚወጣውን ጭስ በሚያዩበት ጊዜ ስለ እሷ ያለቅሳሉ እንዲሁም በሐዘን ደረታቸውን ይደቃሉ። +10 ደግሞም ሥቃይዋን በመፍራት በሩቅ ቆመው ‘አንቺ ታላቂቱ ከተማ፣+ አንቺ ብርቱ የሆንሽው ከተማ ባቢሎን፣ እንዴት ያሳዝናል! እንዴት ያሳዝናል! ፍርድሽ በአንድ ሰዓት ተፈጽሟልና’ ይላሉ። +11 “የምድር ነጋዴዎችም ከዚህ በኋላ ብዛት ያለውን ሸቀጣቸውን የሚገዛቸው ስለማይኖር ስለ እሷ ያለቅሳሉ እንዲሁም ያዝናሉ፤ +12 ብዛት ያለው ሸቀጣቸውም ወርቅን፣ ብርን፣ የከበሩ ድንጋዮችን፣ ዕንቁን፣ ጥሩ በፍታን፣ ሐምራዊ ጨርቅን፣ ሐርንና ደማቅ ቀይ ጨርቅን ያካተተ ነው፤ በተጨማሪም ጥሩ መዓዛ ካለው እንጨት የተሠራ ነገር ሁሉ፣ ከዝሆን ጥርስ፣ ውድ ከሆነ እንጨት፣ ከመዳብ፣ ከብረትና ከእብነ በረድ የተሠራ ማንኛውም ዓይነት ዕቃ +13 ደግሞም ቀረፋ፣ የሕንድ ቅመም፣ ዕጣን፣ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት፣ ነጭ ዕጣን፣ የወይን ጠጅ፣ የወይራ ዘይት፣ የላመ ዱቄት፣ ስንዴ፣ ከብቶች፣ በጎች፣ ፈረሶች፣ ሠረገላዎች፣ ባሪያዎችና ሰዎች* ይገኙበታል። +14 አዎ፣ የተመኘሽው* ጥሩ ፍሬ ከአንቺ ርቋል፤ ምርጥና ማራኪ የሆኑ ነገሮችም ሁሉ ከአንቺ ጠፍተዋል፤ ዳግመኛም አይገኙም። +15 “እነዚህን ነገሮች በመሸጥ በእሷ የበለጸጉ ነጋዴዎች ሥቃይዋን በመፍራት በሩቅ ቆመው እያለቀሱና እያዘኑ +16 እንዲህ ይላሉ፦ ‘ጥሩ በፍታ፣ ሐምራዊና ደማቅ ቀይ ልብስ የለበሰችው እንዲሁም በወርቅ ጌጣጌጥ፣ በከበሩ ድንጋዮችና በዕንቁዎች የተንቆጠቆጠችው+ ታላቂቱ ከተማ፣ እንዴት ያሳዝናል! እንዴት ያሳዝናል! +17 ምክንያቱም ያ ሁሉ ታላቅ ሀብት በአንድ ሰዓት ውስ�� እንዳልነበረ ሆኗል።’ “የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በባሕር ላይ የሚጓዙ ሁሉ፣ መርከበኞችና መተዳደሪያቸው በባሕር ላይ የተመሠረተ ሁሉ በሩቅ ቆመው +18 እሷ ስትቃጠል የሚወጣውን ጭስ እያዩ ‘እንደ ታላቂቱ ከተማ ያለ ከተማ የት ይገኛል?’ በማለት ጮኹ። +19 በራሳቸው ላይ አቧራ በትነው እያለቀሱና እያዘኑ እንዲህ ሲሉ ጮኹ፦ ‘በባሕር ላይ መርከቦች ያሏቸውን ሁሉ በሀብቷ ያበለጸገችው ታላቂቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ውስጥ መጥፋቷ እንዴት ያሳዝናል! እንዴት ያሳዝናል!’+ +20 “ሰማይ ሆይ፣ በእሷ ላይ በደረሰው ነገር ደስ ይበልህ፤+ ደግሞም እናንተ ቅዱሳን፣+ ሐዋርያትና ነቢያት ደስ ይበላችሁ፤ ምክንያቱም አምላክ ለእናንተ ሲል ፈርዶባታል!”+ +21 አንድ ብርቱ መልአክም ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስል ድንጋይ አንስቶ ወደ ባሕር በመወርወር እንዲህ አለ፦ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ በፍጥነት ቁልቁል ትወረወራለች፤ ዳግመኛም አትገኝም።+ +22 በተጨማሪም ራሳቸውን በበገና የሚያጅቡ ዘማሪዎች፣ የሙዚቀኞች፣ የዋሽንት ነፊዎችና የመለከት ነፊዎች ድምፅ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ፈጽሞ አይሰማም። ደግሞም የማንኛውም ዓይነት የእጅ ጥበብ ባለሙያ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ እንዲሁም የወፍጮ ድምፅ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም። +23 የመብራት ብርሃን ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽሪት ድምፅም ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ይህም የሚሆነው ነጋዴዎችሽ የምድር ታላላቅ ሰዎች ስለነበሩና በመናፍስታዊ ድርጊቶችሽ+ ብሔራት ሁሉ ስለተሳሳቱ ነው። +24 በእሷም ውስጥ የነቢያት፣ የቅዱሳንና+ በምድር ላይ የታረዱ ሰዎች ሁሉ ደም ተገኝቷል።”+ +19 ከዚህ በኋላ በሰማይ እንደ ብዙ ሠራዊት ድምፅ ያለ ታላቅ ድምፅ ሰማሁ። እንዲህም አሉ፦ “ያህን አወድሱ!*+ ማዳን፣ ክብርና ኃይል የአምላካችን ነው፤ +2 ምክንያቱም ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸው።+ ምድርን በዝሙቷ* ባረከሰችው በታላቂቱ አመንዝራ ላይ የፍርድ እርምጃ ወስዷልና፤ እንዲሁም ስለ ባሪያዎቹ ደም ተበቅሏታል።”*+ +3 ወዲያውኑም ለሁለተኛ ጊዜ “ያህን አወድሱ!*+ ከእሷ የሚወጣው ጭስም ለዘላለም ወደ ላይ ይወጣል” አሉ።+ +4 ደግሞም 24ቱ ሽማግሌዎችና+ አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት+ ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው አምላክ ሰገዱ፤ እንዲሁም “አሜን! ያህን አወድሱ!”* አሉ።+ +5 በተጨማሪም ከዙፋኑ የወጣ አንድ ድምፅ “እሱን የምትፈሩ ባሪያዎቹ ሁሉ፣+ ታናናሾችና ታላላቆች፣+ አምላካችንን አወድሱ” አለ። +6 እንደ ብዙ ሠራዊት ድምፅ፣ እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅና እንደ ኃይለኛ ነጎድጓድ ድምፅ ያለ ነገር ሰማሁ። እንዲህም አሉ፦ “ያህን አወድሱ፤*+ ምክንያቱም ሁሉን ቻይ የሆነው አምላካችን ይሖዋ*+ ነግሦአል!+ +7 የበጉ ሠርግ ስለደረሰና ሙሽራዋ ራሷን ስላዘጋጀች እንደሰት፤ ሐሴትም እናድርግ፤ ለእሱም ክብር እንስጠው። +8 አዎ፣ የሚያንጸባርቅና ንጹሕ የሆነ ጥሩ በፍታ እንድትለብስ ተሰጥቷታል፤ ይህ ጥሩ በፍታ የቅዱሳንን የጽድቅ ተግባር ያመለክታልና።”+ +9 እሱም “ይህን ጻፍ፦ ወደ በጉ ሠርግ+ የራት ግብዣ የተጠሩ ደስተኞች ናቸው” አለኝ። ደግሞም “እነዚህ እውነተኛ የአምላክ ቃሎች ናቸው” አለኝ። +10 እኔም በዚህ ጊዜ ልሰግድለት በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እሱ ግን “ተጠንቀቅ! ፈጽሞ እንዳታደርገው!+ እኔ ከአንተም ሆነ ስለ ኢየሱስ የመመሥከር ሥራ ካላቸው ወንድሞችህ ጋር አብሬ የማገለግል ባሪያ ነኝ።+ ለአምላክ ስገድ!+ ትንቢት የሚነገረው ስለ ኢየሱስ ለመመሥከር ነውና” አለኝ።+ +11 እኔም ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም፣ ነጭ ፈረስ ነበር።+ በእሱም ላይ የተቀመጠው “ታማኝና+ እውነተኛ”+ ተብሎ ይጠራል፤ እሱም በጽድቅ ይፈርዳል እንዲሁም ይዋጋል።+ +12 ዓይኖቹ የእሳት ነበልባል ናቸው፤+ በራሱም ላይ ብዙ ዘውዶች አሉ። ከራሱ በቀር ማንም የማያውቀው ስም ተጽፎበታል፤ +13 ደም የነካው* መደረቢያም ለብሷል፤ ደግሞም “የአምላክ ቃል”+ በሚል ስም ይጠራል። +14 በተጨማሪም በሰማይ ያሉት ሠራዊቶች በነጭ ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር፤ እነሱም ነጭና ንጹሕ የሆነ ጥሩ በፍታ ለብሰው ነበር። +15 እሱም ብሔራትን ይመታበት ዘንድ ከአፉ ረጅም ስለታም ሰይፍ+ ይወጣል፤ እንደ እረኛም በብረት በትር ይገዛቸዋል።*+ በተጨማሪም ሁሉን ቻይ የሆነውን የአምላክን የመዓቱን የቁጣ ወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል።+ +16 በመደረቢያው አዎ፣ በጭኑ ላይ “የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ”+ የሚል ስም ተጽፏል። +17 በተጨማሪም አንድ መልአክ በፀሐይ መካከል ቆሞ አየሁ፤ እሱም በታላቅ ድምፅ ጮኾ በሰማይ መካከል* ለሚበርሩት ወፎች ሁሉ እንዲህ አለ፦ “ወደዚህ ኑ፤ ወደ ታላቁ የአምላክ ራት ተሰብሰቡ፤+ +18 የነገሥታትን ሥጋ፣ የጦር አዛዦችን ሥጋ፣ የብርቱ ሰዎችን ሥጋ፣+ የፈረሶችንና የፈረሰኞችን ሥጋ+ እንዲሁም የሁሉንም ሥጋ ይኸውም የነፃ ሰዎችንና የባሪያዎችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ ብሉ።” +19 ከዚህ በኋላ አውሬው፣ የምድር ነገሥታትና ሠራዊታቸው በፈረሱ ላይ ከተቀመጠውና ከሠራዊቱ ጋር ለመዋጋት ተሰብስበው አየሁ።+ +20 አውሬውም ተያዘ፤ በፊቱ ተአምራዊ ምልክቶች የፈጸመው ሐሰተኛው ነቢይም+ ከእሱ ጋር ተያዘ፤ ይህ ነቢይ በእነዚህ ምልክቶች አማካኝነት፣ የአውሬውን ምስል የተቀበሉትንና+ ለምስሉ የሰገዱትን+ አስቷል። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በድኝ ወደሚነደው የእሳት ሐይቅ ተወረወሩ።+ +21 የቀሩት ግን በፈረሱ ላይ ከተቀመጠው አፍ በወጣው ረጅም ሰይፍ ተገደሉ።+ ወፎችም ሁሉ ሥጋቸውን በልተው ጠገቡ።+ +20 እኔም የጥልቁን ቁልፍና+ ታላቅ ሰንሰለት በእጁ የያዘ አንድ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። +"2 እሱም ዘንዶውን+ ያዘውና ለ1,000 ዓመት አሰረው፤ ይህም ዘንዶ ዲያብሎስና+ ሰይጣን+ የሆነው የጥንቱ እባብ+ ነው።" +"3 ደግሞም ይህ 1,000 ዓመት እስኪያበቃ ድረስ ከእንግዲህ ሕዝቦችን እንዳያሳስት ወደ ጥልቁ+ ወረወረውና ዘጋበት፤ በማኅተምም አሸገው። ከዚያ በኋላ ለጥቂት ጊዜ ሊፈታ ይገባዋል።+ " +4 ዙፋኖችንም አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው። ስለ ኢየሱስ በመመሥከራቸውና ስለ አምላክ በመናገራቸው የተነሳ የተገደሉትን* ሰዎች ነፍሳት* እንዲሁም አውሬውን ወይም ምስሉን ያላመለኩትንና ምልክቱን በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች አየሁ።+ እነሱም ሕያው ሆ +"5 (የቀሩት ሙታን+ ይህ 1,000 ዓመት እስኪያበቃ ድረስ ሕያው አልሆኑም።) ይህ የመጀመሪያው ትንሣኤ ነው።+" +"6 በመጀመሪያው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑ ሁሉ ደስተኞችና ቅዱሳን ናቸው፤+ ሁለተኛው ሞት+ በእነዚህ ላይ ሥልጣን የለውም፤+ ከዚህ ይልቅ የአምላክና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤+ ከእሱም ጋር ለ1,000 ዓመት ይነግሣሉ።+ " +"7 ይህ 1,000 ዓመት እንዳበቃም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤" +8 እሱም በአራቱም የምድር ማዕዘናት ያሉትን ብሔራት፣ ጎግንና ማጎግን ለማሳሳትና ለጦርነቱ አንድ ላይ ለመሰብሰብ ይወጣል። የእነዚህም ቁጥር በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነው። +9 እነሱም በምድር ሁሉ ተሰራጩ፤ እንዲሁም የቅዱሳኑን ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ። ሆኖም እሳት ከሰማይ ወርዶ በላቸው።+ +10 ሲያሳስታቸው የነበረው ዲያብሎስም፣ አውሬውና+ ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ድኙ ሐይቅ ተወረወረ፤+ እነሱም ለዘላለም ቀንና ሌሊት ይሠቃያሉ።* +11 እኔም አንድ ትልቅ ነጭ ዙፋንና በዙፋኑ ላይ የተ���መጠውን አየሁ።+ ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፤+ ስፍራም አልተገኘላቸውም። +12 ከዚያም ሙታንን፣ ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ የመጽሐፍ ጥቅልሎችም ተከፈቱ። ሌላም ጥቅልል ተከፈተ፤ ይህም የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ነው።+ ሙታን በጥቅልሎቹ ውስጥ በተጻፉት ነገሮች መሠረት እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው።+ +13 ባሕርም በውስጡ ያሉትን ሙታን ሰጠ፤ ሞትና መቃብርም* በውስጣቸው ያሉትን ሙታን ሰጡ፤ እነሱም እያንዳንዳቸው እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው።+ +14 ሞትና መቃብርም* ወደ እሳቱ ሐይቅ ተወረወሩ።+ ይህም የእሳት ሐይቅ+ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል።+ +15 በተጨማሪም በሕይወት መጽሐፍ+ ላይ ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳቱ ሐይቅ ተወረወረ።+ +3 “በሰርዴስ ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ሰባቱ የአምላክ መናፍስት+ ያሉትና ሰባቱን ከዋክብት+ የያዘው እንዲህ ይላል፦ ‘ሥራህን አውቃለሁ፤ ሕያው ነው የሚል ስም አለህ፤ ነገር ግን ሞተሃል።+ +2 ሥራህን በአምላኬ ፊት በተሟላ ሁኔታ ተጠናቆ ስላላገኘሁት ንቃ፤+ ሊሞቱ የተቃረቡትን የቀሩትን ነገሮችም አጠናክር። +3 ስለዚህ የተቀበልከውንና የሰማኸውን ምንጊዜም አስብ፤ እንዲሁም ዘወትር ጠብቀው፤ ንስሐም ግባ።+ ካልነቃህ ግን እንደ ሌባ እመጣለሁ፤+ በየትኛው ሰዓት ከተፍ እንደምልብህም ፈጽሞ አታውቅም።+ +4 “‘ይሁን እንጂ ልብሳቸውን ያላረከሱ+ ጥቂት ሰዎች* ከአንተ ጋር በሰርዴስ አሉ፤ እነሱም የሚገባቸው ስለሆኑ ነጭ ልብስ+ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ። +5 ድል የሚነሳም+ልክ እንዲሁ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤+ እኔም ስሙን ከሕይወት መጽሐፍ+ በምንም ዓይነት አልደመስስም፤* ከዚህ ይልቅ በአባቴ ፊትና በመላእክቱ ፊት ለስሙ እመሠክራለሁ።+ +6 መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።’ +7 “በፊላደልፊያ ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ቅዱስና+ እውነተኛ የሆነው፣+ የዳዊት ቁልፍ ያለው፣+ ማንም እንዳይዘጋ፣ የሚከፍተው እንዲሁም ማንም እንዳይከፍት፣ የሚዘጋው እሱ እንዲህ ይላል፦ +8 ‘ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ፣ ማንም ሊዘጋው የማይችል የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌአለሁ።+ ደግሞም ጥቂት ኃይል እንዳለህ አውቃለሁ፤ ቃሌንም ጠብቀሃል፤ ስሜንም አልካድክም። +9 እነሆ፣ አይሁዳውያን ሳይሆኑ አይሁዳውያን ነን እያሉ የሚዋሹት፣+ ከሰይጣን ምኩራብ የሆኑት ወደ አንተ መጥተው በእግርህ ፊት እንዲሰግዱ* አደርጋለሁ፤ እንዲሁም እንደወደድኩህ እንዲያውቁ አደርጋለሁ። +10 ስለ ጽናቴ የተነገረውን ቃል ስለጠበቅክ*+ እኔም በምድር ላይ የሚኖሩትን ለመፈተን በመላው ምድር ላይ ከሚመጣው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ።+ +11 ቶሎ እመጣለሁ።+ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን ምንጊዜም አጥብቀህ ያዝ።+ +12 “‘ድል የሚነሳውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዓምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያ በኋላም በምንም ዓይነት ከዚያ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና+ ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን የአምላኬን ከተማ የአዲሲቱን ኢየሩሳሌም+ ስም እንዲሁም የእኔን አዲስ ስም በእሱ ላይ እጽፋለሁ።+ +13 መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።’ +14 “በሎዶቅያ ላለው ጉባኤ+ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፣+ ታማኝና እውነተኛ+ ምሥክር+ እንዲሁም ከአምላክ ፍጥረት የመጀመሪያ የሆነው+ እንዲህ ይላል፦ +15 ‘ሥራህን አውቃለሁ፤ ወይ ቀዝቃዛ ወይ ትኩስ አይደለህም። ቀዝቃዛ ወይም ደግሞ ትኩስ ብትሆን ደስ ባለኝ ነበር። +16 ለብ ያልክ እንጂ ትኩስም+ ሆነ ቀዝቃዛ+ ስላልሆንክ ከአፌ አውጥቼ ልተፋህ ነው። +17 ምክንያቱም “ሀብታም ነኝ፤+ ደግሞም ብዙ ሀብት አከማችቻለሁ፤ ምንም ነገር አያስፈልገኝም” ��ላለህ፤ ነገር ግን ጎስቋላ፣ ምስኪን፣ ድሃ፣ ዕውርና የተራቆትክ መሆንህን አታውቅም፤ +18 ሀብታም እንድትሆን በእሳት የነጠረ ወርቅ፣ ልብስ እንድትለብስና ለኀፍረት የሚዳርገው እርቃንህ እንዲሸፈን+ ነጭ ልብስ እንዲሁም ማየት እንድትችል+ ዓይንህን የምትኳለው ኩል+ ከእኔ እንድትገዛ እመክርሃለሁ። +19 “‘እኔ፣ የምወዳቸውን ሁሉ እወቅሳለሁ እንዲሁም እገሥጻለሁ።+ ስለዚህ ቀናተኛ ሁን፤ ንስሐም ግባ።+ +20 እነሆ፣ በር ላይ ቆሜ እያንኳኳሁ ነው። ማንም ድምፄን ሰምቶ በሩን ከከፈተልኝ ወደ ቤቱ እገባለሁ፤ ከእሱም ጋር ራት እበላለሁ፤ እሱም ከእኔ ጋር ይበላል። +21 እኔ ድል ነስቼ ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥኩ ሁሉ+ ድል የሚነሳውንም+ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።+ +22 መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።’” +7 ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱ የምድር ማዕዘናት ቆመው አየሁ፤ እነሱም በምድር ወይም በባሕር ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ ምንም ነፋስ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳት አጥብቀው ይዘው ነበር። +2 እንዲሁም የሕያው አምላክ ማኅተም ያለው ሌላ መልአክ ከፀሐይ መውጫ* ወደ ላይ ሲወጣ አየሁ፤ እሱም ምድርንና ባሕርን እንዲጎዱ ሥልጣን የተሰጣቸውን አራቱን መላእክት በታላቅ ድምፅ +3 እንዲህ አላቸው፦ “የአምላካችንን ባሪያዎች ግንባራቸው ላይ ማኅተም እስክናደርግባቸው ድረስ+ ምድርን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጉዱ።”+ +"4 የታተሙትን ሰዎች ቁጥር ሰማሁ፤ ቁጥራቸው 144,000+ ሲሆን የታተሙትም ከእያንዳንዱ የእስራኤል ልጆች ነገድ ነበር፦+ " +"5 ከይሁዳ ነገድ 12,000 ታተሙ፤ከሮቤል ነገድ 12,000፣ከጋድ ነገድ 12,000፣" +"6 ከአሴር ነገድ 12,000፣ከንፍታሌም ነገድ 12,000፣ከምናሴ+ ነገድ 12,000፣" +"7 ከስምዖን ነገድ 12,000፣ከሌዊ ነገድ 12,000፣ከይሳኮር ነገድ 12,000፣" +"8 ከዛብሎን ነገድ 12,000፣ከዮሴፍ ነገድ 12,000፣ከቢንያም ነገድ 12,000 ታተሙ። " +9 ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም፣ ከሁሉም ብሔራት፣ ነገዶች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች የተውጣጡ+ አንድም ሰው ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሕዝብ ነጭ ልብስ ለብሰው+ በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው ነበር፤ የዘንባባ ዝንጣፊዎችንም በእጆቻቸው ይዘው ነበር።+ +10 በታላቅም ድምፅ እየጮኹ “መዳን ያገኘነው በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው+ ከአምላካችን እንዲሁም ከበጉ+ ነው” ይሉ ነበር። +11 መላእክቱ ሁሉ በዙፋኑ፣ በሽማግሌዎቹና+ በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት ዙሪያ ቆመው ነበር፤ እነሱም በዙፋኑ ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ለአምላክ ሰገዱ፤ +12 እንዲህም አሉ፦ “አሜን! ውዳሴ፣ ግርማ፣ ጥበብ፣ ምስጋና፣ ክብር፣ ኃይልና ብርታት ለዘላለም ለአምላካችን ይሁን።+ አሜን።” +13 ከሽማግሌዎቹ አንዱ መልሶ “እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱት+ እነማን ናቸው? ከወዴትስ የመጡ ናቸው?” አለኝ። +14 እኔም ወዲያውኑ “ጌታዬ፣ የምታውቀው አንተ ነህ” አልኩት። እሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ታላቁን መከራ+ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል።+ +15 በአምላክ ዙፋን ፊት ያሉትም ለዚህ ነው፤ በቤተ መቅደሱም ቀንና ሌሊት ቅዱስ አገልግሎት እያቀረቡለት ነው፤ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውም+ ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል።+ +16 ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም እንዲሁም አይጠሙም፤ ፀሐይ አይመታቸውም፤ ሐሩሩም አያቃጥላቸውም፤+ +17 ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ+ እረኛቸው ይሆናል፤+ ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭም ይመራቸዋል።+ አምላክም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።”*+ +12 ከዚያም በሰማይ ታላቅ ምልክት ታየ፦ አንዲት ሴት+ ፀሐይን ተጎናጽፋ* ነበር፤ ጨረቃም ከእግሯ ሥር ነበረች፤ በራሷም ላይ 12 ከዋክብት ያሉ��� አክሊል ነበር፤ +2 እሷም ነፍሰ ጡር ነበረች። ልትወልድ ስትል ምጥ ይዟት በጭንቅ ትጮኽ ነበር። +3 ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ። እነሆ፣ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉት፣ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች የደፋ፣ ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ታላቅ ዘንዶ+ ታየ፤ +4 ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት+ አንድ ሦስተኛ ጎትቶ ወደ ምድር ወረወረ።+ ዘንዶውም በምትወልድበት ጊዜ ልጇን ለመዋጥ ፈልጎ ልትወልድ በተቃረበችው ሴት+ ፊት ቆሞ ይጠብቅ ነበር። +5 እሷም ብሔራትን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛውን*+ ልጅ አዎ፣ ወንድ ልጅ ወለደች።+ ልጇም ወደ አምላክና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። +"6 ሴቲቱም 1,260 ቀን በዚያ እንዲመግቧት አምላክ ወዳዘጋጀላት ስፍራ ወደ ምድረ በዳ ሸሸች።+ " +7 በሰማይም ጦርነት ተነሳ፦ ሚካኤልና*+ መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም ተዋጓቸው፤ +8 ነገር ግን አልቻሏቸውም፤* ከዚያ በኋላም በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። +9 ስለሆነም ታላቁ ዘንዶ+ ይኸውም መላውን ዓለም እያሳሳተ ያለው+ ዲያብሎስና+ ሰይጣን+ ተብሎ የሚጠራው የጥንቱ እባብ+ ወደ ታች ተወረወረ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤+ መላእክቱም ከእሱ ጋር ተወረወሩ። +10 በሰማይ እንዲህ የሚል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፦ “አሁን የአምላካችን ማዳን፣+ ኃይልና መንግሥት+ እንዲሁም የእሱ መሲሕ ሥልጣን ሆኗል፤ ምክንያቱም ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ወደ ታች ተወርውሯል!+ +11 እነሱም ከበጉ ደም+ የተነሳና ከምሥክርነታቸው ቃል+ የተነሳ ድል ነሱት፤+ እስከ ሞት ድረስ እንኳ ለነፍሳቸው* አልሳሱም።+ +12 ስለዚህ እናንተ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ምድርና ባሕር+ ግን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ዲያብሎስ ጥቂት ጊዜ እንደቀረው+ ስላወቀ በታላቅ ቁጣ ተሞልቶ ወደ እናንተ ወርዷል።” +13 ዘንዶውም ወደ ምድር እንደተወረወረ+ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ በወለደችው ሴት ላይ ስደት አደረሰባት።+ +14 ሆኖም ሴቲቱ ከእባቡ+ ፊት ርቃ ለአንድ ዘመን፣ ለዘመናትና ለግማሽ ዘመን*+ ወደምትመገብበት በምድረ በዳ ወደተዘጋጀላት ስፍራ በርራ መሄድ እንድትችል የታላቅ ንስር ሁለት ክንፎች+ ተሰጧት። +15 እባቡም ሴቲቱ በወንዝ ውስጥ እንድትሰምጥ ከአፉ የወጣ እንደ ወንዝ ያለ ውኃ ከኋላዋ ለቀቀባት። +16 ይሁን እንጂ ምድሪቱ ለሴቲቱ ደረሰችላት፤ ምድሪቱም አፏን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ የለቀቀውን ወንዝ ዋጠች። +17 ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ እጅግ ተቆጥቶ የአምላክን ትእዛዛት የሚጠብቁትንና ስለ ኢየሱስ የመመሥከር ሥራ+ የተሰጣቸውን ከዘሯ+ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ። +1 በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊፈጸሙ የሚገባቸውን ነገሮች ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ+ አምላክ ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውና+ እሱ የገለጠው ራእይ* ይህ ነው። ኢየሱስም መልአኩን ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ+ በምልክቶች ገለጠለት፤ +2 ዮሐንስም አምላክ ስለሰጠው ቃልና ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰጠው ምሥክርነት ይኸውም ስላያቸው ነገሮች ሁሉ መሥክሯል። +3 የዚህን ትንቢት ቃል ጮክ ብሎ የሚያነብ ደስተኛ ነው፤ እንዲሁም ቃሉን የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፉትን ነገሮች የሚጠብቁት ደስተኞች ናቸው፤+ የተወሰነው ጊዜ ቀርቧልና። +4 ከዮሐንስ፣ በእስያ አውራጃ ለሚገኙ ለሰባቱ ጉባኤዎች፦+ “ካለው፣ ከነበረውና ከሚመጣው”+ እንዲሁም በዙፋኑ ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት+ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ +5 በተጨማሪም “ታማኝ ምሥክር፣”+ “ከሙታን በኩር”+ እና “የምድር ነገሥታት ገዢ”+ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደንና+ በገዛ ደሙ አማካኝነት ከኃጢአታችን ነፃ ላወጣን፣+ +6 ነገሥታት*+ እንዲሁም ለአምላኩና ለአባቱ ካህናት+ ላደረገን ለእሱ ክብርና ኃይል ለዘላለም ይሁን። አሜን። +7 እነሆ፣ ከደመናት ጋር ይመጣል፤+ ዓይኖች ሁሉ፣ የወጉትም ያዩታል፤ በእሱም የተነሳ የምድር ነገዶች ሁሉ በሐዘን ደረታቸውን ይደቃሉ።+ አዎ፣ ይህ በእርግጥ ይሆናል። አሜን። +8 “እኔ አልፋና ኦሜጋ፣*+ ያለው፣ የነበረውና የሚመጣው፣ ሁሉን ቻይ ነኝ” ይላል ይሖዋ* አምላክ።+ +9 የኢየሱስ ተከታይ በመሆኔ+ ከእናንተ ጋር የመከራው፣+ የመንግሥቱና+ የጽናቱ+ ተካፋይ የሆንኩ እኔ ወንድማችሁ ዮሐንስ፣ ስለ አምላክ በመናገሬና ስለ ኢየሱስ በመመሥከሬ ጳጥሞስ በምትባል ደሴት ነበርኩ። +10 በመንፈስ ወደ ጌታ ቀን ተወሰድኩ፤ ከኋላዬም እንደ መለከት ያለ ኃይለኛ ድምፅ ሰማሁ፤ +11 እንዲህም አለኝ፦ “የምታየውን በመጽሐፍ ጥቅልል ላይ ጽፈህ በኤፌሶን፣+ በሰምርኔስ፣+ በጴርጋሞን፣+ በትያጥሮን፣+ በሰርዴስ፣+ በፊላደልፊያና+ በሎዶቅያ+ ለሚገኙት ለሰባቱ ጉባኤዎች ላከው።” +12 እኔም እያናገረኝ ያለው ማን እንደሆነ ለማየት ዞር አልኩ፤ በዚህ ጊዜም ሰባት የወርቅ መቅረዞች ተመለከትኩ፤+ +13 በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስል አየሁ፤+ እሱም እስከ እግሩ የሚደርስ ልብስ የለበሰና ደረቱ ላይ የወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር። +14 በተጨማሪም ራሱና ፀጉሩ እንደ ነጭ ሱፍ፣ እንደ በረዶም ነጭ ነበር፤ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤+ +15 እግሮቹም እቶን ውስጥ እንደጋለ የጠራ መዳብ ነበሩ፤+ ድምፁም እንደ ውኃ ፏፏቴ ነበር። +16 በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤+ ከአፉም በሁለቱም በኩል ስለት ያለው ረጅም ሰይፍ+ ወጣ፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሐይ ነበር።+ +17 ባየሁት ጊዜ እንደሞተ ሰው ሆኜ እግሩ ሥር ወደቅኩ። እሱም ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፦ “አትፍራ። እኔ የመጀመሪያውና+ የመጨረሻው ነኝ፤+ +18 ሕያው የሆነውም እኔ ነኝ፤+ ሞቼም ነበር፤+ አሁን ግን ለዘላለም እኖራለሁ፤+ የሞትና የመቃብር* ቁልፎችም አሉኝ።+ +19 ስለዚህ ያየሃቸውን ነገሮች፣ አሁን እየተከናወኑ ያሉትንና ከእነዚህ በኋላ የሚፈጸሙትን ነገሮች ጻፍ። +20 በቀኝ እጄ ላይ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብት እንዲሁም የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ቅዱስ ሚስጥር ይህ ነው፦ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱን ጉባኤዎች መላእክት* ያመለክታሉ፤ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱን ጉባኤዎች ያመለክታሉ።+ +8 ሰባተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ+ በሰማይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ጸጥታ ሰፈነ። +2 እኔም በአምላክ ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፤+ ሰባት መለከትም ተሰጣቸው። +3 የወርቅ ጥና* የያዘ ሌላ መልአክ መጥቶ በመሠዊያው+ አጠገብ ቆመ፤ እሱም የቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት እየተሰማ በነበረበት ወቅት በዙፋኑ ፊት ባለው በወርቁ መሠዊያ+ ላይ እንዲያቀርበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዕጣን+ ተሰጠው። +4 በመልአኩ እጅ ያለው የዕጣኑ ጭስ እንዲሁም የቅዱሳኑ ጸሎት+ በአምላክ ፊት ወደ ላይ ወጣ። +5 ሆኖም መልአኩ ወዲያውኑ ጥናውን ይዞ ከመሠዊያው ላይ እሳት በመውሰድ ጥናውን ሞላውና እሳቱን ወደ ምድር ወረወረው። ከዚያም ነጎድጓድ፣ ድምፅ፣ የመብረቅ ብልጭታና+ የምድር ነውጥ ተከሰተ። +6 ሰባቱን መለከቶች የያዙት ሰባቱ መላእክትም+ ሊነፉ ተዘጋጁ። +7 የመጀመሪያው መለከቱን ነፋ። ከደም ጋር የተቀላቀለ በረዶና እሳት ታየ፤ ወደ ምድርም ተወረወረ፤+ የምድር አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የዛፎችም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የለመለሙ ተክሎችም ሁሉ ተቃጠሉ።+ +8 ሁለተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። በእሳት የተቀጣጠለ ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገርም ወደ ባሕር ተወረወረ።+ የባሕሩም አንድ ሦስተኛ ደም ሆነ፤+ +9 በባሕር ውስጥ ካሉ ሕያዋን ፍጥረታትም* አንድ ሦስተኛው ሞተ፤+ ከመርከቦችም አንድ ሦስተኛው ወደመ። +10 ሦስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። እንደ መብራት ቦግ ያለ አንድ ትልቅ ኮከብም ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞች አንድ ሦስተኛና በውኃ ምንጮች ላይ ወደቀ።+ +11 ኮከቡ ጭቁኝ ይባላል። የውኃውም አንድ ሦስተኛ እንደ ጭቁኝ መራራ ሆነ፤ ውኃውም መራራ+ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ሰዎች በውኃው ጠንቅ ሞቱ። +12 አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፣+ የጨረቃ አንድ ሦስተኛና የከዋክብት አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ይህም የሆነው የእነዚህ አካላት አንድ ሦስተኛው እንዲጨልም+ እንዲሁም የቀኑ አንድ ሦስተኛና የሌሊቱ አንድ ሦስተኛ ብርሃን እንዳያገኝ ነው። +13 እኔም አየሁ፤ አንድ ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “መለከቶቻቸውን ሊነፉ የተዘጋጁት ሦስቱ መላእክት+ በሚያሰሟቸው በቀሩት ኃይለኛ የመለከት ድምፆች የተነሳ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!”+ +11 እኔም ዘንግ* የሚመስል ሸምበቆ+ ተሰጠኝ፤ እንዲህም አለኝ፦ “ተነስና የአምላክን ቤተ መቅደስ ቅዱስ ስፍራ፣* መሠዊያውንና በዚያ የሚያመልኩትን ለካ። +2 ሆኖም ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ውጭ ያለውን ግቢ ሙሉ በሙሉ ተወው፤ አትለካው፤ ምክንያቱም ለአሕዛብ ተሰጥቷል፤ እነሱም የተቀደሰችውን ከተማ+ ለ42 ወራት ይረግጧታል።+ +"3 እኔም ሁለቱ ምሥክሮቼ ማቅ ለብሰው ለ1,260 ቀናት ትንቢት እንዲናገሩ አደርጋለሁ።”" +4 እነዚህ በሁለቱ የወይራ ዛፎችና+ በሁለቱ መቅረዞች ተመስለዋል፤+ እነሱም በምድር ጌታ ፊት ቆመዋል።+ +5 ማንም እነሱን ሊጎዳ ቢፈልግ እሳት ከአፋቸው ወጥቶ ጠላቶቻቸውን ይበላል። ማንም ሊጎዳቸው ቢፈልግ በዚህ ዓይነት ሁኔታ መገደል አለበት። +6 እነዚህ ሰዎች ትንቢት በሚናገሩባቸው ቀናት ምንም ዝናብ እንዳይዘንብ+ ሰማይን የመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤+ እንዲሁም ውኃዎችን ወደ ደም የመለወጥና+ የፈለጉትን ጊዜ ያህል፣ በማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት ምድርን የመምታት ሥልጣን አላቸው። +7 የምሥክርነት ሥራቸውን ባጠናቀቁ ጊዜ፣ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ውጊያ ይከፍትባቸዋል፤ ድል ይነሳቸዋል፤ እንዲሁም ይገድላቸዋል።+ +8 አስከሬናቸውም በመንፈሳዊ ሁኔታ ሰዶምና ግብፅ ተብላ በምትጠራውና የእነሱም ጌታ በእንጨት ላይ በተሰቀለባት በታላቂቱ ከተማ አውራ ጎዳና ላይ ይጋደማል። +9 ከተለያዩ ሕዝቦች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ብሔራት የተውጣጡ ሰዎችም ለሦስት ቀን ተኩል አስከሬናቸውን ያያሉ፤+ አስከሬናቸውም እንዲቀበር አይፈቅዱም። +10 እነዚህ ሁለት ነቢያት በምድር ላይ የሚኖሩትን አሠቃይተው ስለነበር በምድር ላይ የሚኖሩት በእነሱ ሞት ይደሰታሉ፤ ሐሴትም ያደርጋሉ እንዲሁም እርስ በርሳቸው ስጦታ ይሰጣጣሉ። +11 ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከአምላክ የመጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤+ በእግሮቻቸውም ቆሙ፤ ያዩአቸውም ሰዎች በታላቅ ፍርሃት ተዋጡ። +12 ከሰማይም አንድ ታላቅ ድምፅ “ወደዚህ ውጡ” ሲላቸው ሰሙ። እነሱም በደመና ውስጥ ሆነው ወደ ሰማይ ወጡ፤ ጠላቶቻቸውም አዩአቸው።* +"13 በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር ነውጥ ተከሰተ፤ የከተማዋ አንድ አሥረኛም ወደቀ፤ በምድር ነውጡም 7,000 ሰዎች ሞቱ፤ የቀሩትም ፍርሃት አደረባቸው፤ ለሰማይ አምላክም ክብር ሰጡ። " +14 ሁለተኛው ወዮታ+ አልፏል። እነሆ፣ ሦስተኛው ወዮታ በፍጥነት ይመጣል። +15 ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ።+ በሰማይም ታላላቅ ድምፆች እንዲህ ሲሉ ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና+ የእሱ መሲሕ+ መንግሥት ሆነ፤ እሱም ለዘላለም ይነግሣል።”+ +16 በአምላክ ፊት በዙፋኖቻቸው ላይ ተቀምጠው የነበሩት 24ቱ ሽማግሌዎችም+ በግንባራቸው ተደፍተው ለአምላክ ሰገዱ፤ +17 እንዲህም አሉ፦ “ያለህና+ የነበርክ፣ ሁሉን ��ይ የሆንከው ይሖዋ* አምላክ ሆይ፣ ታላቅ ኃይልህን ስለያዝክና ንጉሥ ሆነህ መግዛት ስለጀመርክ+ እናመሰግንሃለን። +18 ሆኖም ብሔራት ተቆጡ፤ የአንተም ቁጣ መጣ፤ በሙታን ላይ የምትፈርድበት፣ ለባሪያዎችህ ለነቢያት፣+ ለቅዱሳንና ስምህን ለሚፈሩ ለታናናሾችና ለታላላቆች ወሮታ የምትከፍልበት+ እንዲሁም ምድርን እያጠፉ ያሉትን+ የምታጠፋበት* የተወሰነው ጊዜ መጣ።” +19 በሰማይ ያለው የአምላክ ቤተ መቅደስ ቅዱስ ስፍራ* ተከፍቶ ነበር፤ የቃል ኪዳኑ ታቦትም በቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ታየ።+ እንዲሁም የመብረቅ ብልጭታ፣ ድምፅ፣ ነጎድጓድ፣ የምድር ነውጥና ታላቅ በረዶ ተከሰተ። +2 “በኤፌሶን ላለው ጉባኤ+ መልአክ+ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ሰባቱን ከዋክብት በቀኝ እጁ የያዘውና በሰባቱ የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚመላለሰው+ እንዲህ ይላል፦ +2 ‘ሥራህን፣ ድካምህንና ጽናትህን አውቃለሁ፤ ደግሞም መጥፎ ሰዎችን መታገሥ እንደማትችል እንዲሁም ሐዋርያት ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን የሚሉትን+ ፈትነህ ውሸታሞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ። +3 በተጨማሪም በአቋምህ ጸንተሃል፤ ስለ ስሜም ስትል ብዙ ችግሮችን ተቋቁመሃል፤+ ደግሞም አልታከትክም።+ +4 ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ይኸውም መጀመሪያ ላይ የነበረህን ፍቅር ትተሃል። +5 “‘ስለዚህ ከየት እንደወደቅክ አስታውስ፤ ንስሐም ግባ፤+ ቀድሞ ታደርገው የነበረውንም ነገር አድርግ። አለዚያ እመጣብሃለሁ፤ ንስሐ ካልገባህ+ መቅረዝህን+ ከስፍራው አነሳዋለሁ። +6 ያም ሆኖ አንድ የሚያስመሰግንህ ነገር አለ፦ እኔም የምጠላውን የኒቆላውያንን+ ሥራ* ትጠላለህ። +7 መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፦+ ድል ለሚነሳ+ በአምላክ ገነት ውስጥ ካለው የሕይወት ዛፍ እንዲበላ እፈቅድለታለሁ።’+ +8 “በሰምርኔስ ላለው ጉባኤ መልአክም እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ‘የመጀመሪያውና የመጨረሻው፣’+ ሞቶ የነበረውና ዳግም ሕያው የሆነው+ እንዲህ ይላል፦ +9 ‘መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፤ ይሁንና ሀብታም ነህ፤+ አይሁዳውያን ሳይሆኑ አይሁዳውያን ነን የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ፤ እነሱ የሰይጣን ምኩራብ ናቸው።+ +10 ሊደርስብህ ያለውን መከራ አትፍራ።+ እነሆ፣ ሙሉ በሙሉ እንድትፈተኑና ለአሥር ቀን መከራ እንድትቀበሉ ዲያብሎስ አንዳንዶቻችሁን እስር ቤት ይከታል። እስከ ሞት ድረስ ታማኝነትህን አስመሥክር፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።+ +11 መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፦+ ድል የሚነሳ+ በሁለተኛው ሞት+ ከቶ አይጎዳም።’ +12 “በጴርጋሞን ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ በሁለቱም በኩል ስለት ያለው ረጅም ሰይፍ+ የያዘው እንዲህ ይላል፦ +13 ‘የምትኖረው የሰይጣን ዙፋን ባለበት እንደሆነ አውቃለሁ፤ ያም ሆኖ ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል፤+ ሰይጣን በሚኖርበት፣ እናንተ ባላችሁበት ቦታ በተገደለው+ በታማኙ ምሥክሬ+ በአንቲጳስ ዘመን እንኳ በእኔ ላይ ያለህን እምነት አልካድክም።+ +14 “‘ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገሮች አሉኝ፤ የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሠዉ ነገሮችን እንዲበሉና የፆታ ብልግና* እንዲፈጽሙ+ በፊታቸው ማሰናከያ እንዲያስቀምጥ ባላቅን+ ያስተማረውን የበለዓምን ትምህርት+ አጥብቀው የሚከተሉ በመካከልህ አሉ። +15 እንደዚሁም የኒቆላዎስን የኑፋቄ ትምህርት+ አጥብቀው የሚከተሉ ሰዎች በመካከልህ አሉ። +16 ስለዚህ ንስሐ ግባ። አለዚያ በፍጥነት ወደ አንተ እመጣለሁ፤ በአፌም ረጅም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።+ +17 “‘መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፦+ ድል ለሚነሳ+ ከተሰወረው መና ላይ እሰጠዋለሁ፤+ እንዲሁም ነጭ ጠጠር እሰጠዋለሁ፤ በጠጠሩም ላይ ከሚቀበለው ሰው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም ተጽፎበታል።’ +18 “በትያጥሮን+ ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖችና+ እንደጠራ መዳብ ያሉ እግሮች+ ያሉት የአምላክ ልጅ እንዲህ ይላል፦ +19 ‘ሥራህን፣ ፍቅርህን፣ እምነትህን፣ አገልግሎትህንና ጽናትህን አውቃለሁ፤ ደግሞም ከመጀመሪያው ሥራህ ይልቅ የአሁኑ እንደሚበልጥ አውቃለሁ። +20 “‘ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ራሷን ነቢዪት ብላ የምትጠራውን ያቺን ሴት ኤልዛቤልን+ ችላ ብለሃታል፤ እሷም የፆታ ብልግና* እንዲፈጽሙና+ ለጣዖት የተሠዉ ነገሮችን እንዲበሉ ባሪያዎቼን ታስተምራለች እንዲሁም ታሳስታለች። +21 እኔም ንስሐ እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት፤ እሷ ግን ለፈጸመችው የፆታ ብልግና* ንስሐ ለመግባት ፈቃደኛ አይደለችም። +22 እነሆ፣ የአልጋ ቁራኛ ላደርጋት ነው፤ ከእሷ ጋር ምንዝር የሚፈጽሙትም ከሥራዋ ንስሐ ካልገቡ ታላቅ መከራ አመጣባቸዋለሁ። +23 እንዲሁም እኔ የውስጥ ሐሳብንና* ልብን የምመረምር እንደሆንኩ ጉባኤዎቹ ሁሉ እንዲያውቁ ልጆቿን በገዳይ መቅሰፍት እፈጃለሁ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።+ +24 “‘ነገር ግን ይህን ትምህርት ለማትከተሉ ሁሉና “የሰይጣን ጥልቅ ነገሮች”+ የሚባሉትን ለማታውቁ፣ በትያጥሮን ለምትገኙ ለቀራችሁት ይህን እላለሁ፦ በእናንተ ላይ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ሸክም አልጭንባችሁም። +25 ብቻ እኔ እስክመጣ ድረስ ያላችሁን አጥብቃችሁ ያዙ።+ +26 ደግሞም ድል ለሚነሳና በሥራዬ እስከ መጨረሻ ለሚጸና በብሔራት ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ፤+ +27 ይህም ከአባቴ የተቀበልኩት ዓይነት ሥልጣን ነው። ድል የነሳውም ሕዝቦችን እንደ ሸክላ ዕቃ እንዲደቅቁ በብረት በትር ይገዛቸዋል።*+ +28 እኔም አጥቢያ ኮከብ+ እሰጠዋለሁ። +29 መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።’ +4 ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም፣ በሰማይ የተከፈተ በር ነበር፤ በመጀመሪያ ሲያናግረኝ የሰማሁት ድምፅ እንደ መለከት ድምፅ ያለ ነበር፤ እንዲህም አለኝ፦ “ና ወደዚህ ውጣ፤ መፈጸም ያለባቸውን ነገሮች አሳይሃለሁ።” +2 ከዚያም ወዲያውኑ የአምላክ መንፈስ ወረደብኝ፦ እነሆም፣ በሰማይ አንድ ዙፋን ተቀምጦ ነበር፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠ ነበር።+ +3 በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው የኢያስጲድ ድንጋይና+ የሰርድዮን ድንጋይ ዓይነት መልክ ነበረው፤ በዙፋኑም ዙሪያ መረግድ የሚመስል ቀስተ ደመና ነበር።+ +4 በዙፋኑ ዙሪያ 24 ዙፋኖች ነበሩ፤ በእነዚህም ዙፋኖች ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ 24 ሽማግሌዎች+ ተቀምጠው አየሁ። +5 ከዙፋኑ መብረቅ፣+ ድምፅና ነጎድጓድ ይወጣ ነበር፤+ በዙፋኑም ፊት የሚነድዱ ሰባት የእሳት መብራቶች ነበሩ፤ እነዚህም ሰባቱን የአምላክ መናፍስት ያመለክታሉ።+ +6 በዙፋኑ ፊት የክሪስታል መልክ ያለው እንደ ብርጭቆ ያለ ባሕር+ የሚመስል ነገር ነበር። በዙፋኑ መካከል* እና በዙፋኑ ዙሪያ ከፊትም ሆነ ከኋላ በዓይኖች የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጥረታት ነበሩ።+ +7 የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ይመስላል፤+ ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ወይፈን ይመስላል፤+ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር+ የሰው ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛው ሕያው ፍጡር+ ደግሞ የሚበር ንስር ይመስላል።+ +8 እነዚህ አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች አሏቸው፤ ክንፎቹ በዙሪያቸውና በውስጥ በኩል በዓይኖች የተሞሉ ናቸው።+ ያለማቋረጥም ቀንና ሌሊት “የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፣+ ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ* አምላክ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው”+ ይላሉ። +9 ሕያዋን ፍጥረታቱ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውንና ለዘላ��ም የሚኖረውን+ ከፍ ከፍ ባደረጉ ቁጥር እንዲሁም እሱን ባከበሩና ባመሰገኑ ቁጥር +10 ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች+ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ተደፍተው ለዘላለም ለሚኖረው አምልኮ ያቀርባሉ፤ እንዲሁም አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት ጥለው እንዲህ ይላሉ፦ +11 “ይሖዋ* አምላካችን፣ ሁሉንም ነገሮች ስለፈጠርክ+ እንዲሁም ወደ ሕልውና የመጡትም ሆነ የተፈጠሩት በአንተ ፈቃድ ስለሆነ ግርማ፣+ ክብርና+ ኃይል+ ልትቀበል ይገባሃል።” +16 እኔም ከቅዱሱ ስፍራ*+ የወጣ ታላቅ ድምፅ ሰባቱን መላእክት “ሂዱና የአምላክን ቁጣ የያዙትን ሰባቱን ሳህኖች በምድር ላይ አፍስሱ” ሲል ሰማሁ።+ +2 የመጀመሪያው መልአክ ሄዶ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በምድር ላይ አፈሰሰው።+ በዚህ ጊዜም የአውሬው ምልክት በነበራቸውና+ ምስሉን ያመልኩ በነበሩት ሰዎች+ ላይ ጉዳት የሚያስከትልና አስከፊ የሆነ ቁስል+ ወጣባቸው። +3 ሁለተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን ወደ ባሕር አፈሰሰው።+ ባሕሩም እንደሞተ ሰው ደም ሆነ፤+ በባሕሩም+ ውስጥ ያለ ሕያው ፍጡር* ሁሉ ሞተ። +4 ሦስተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን ወደ ወንዞችና ወደ ውኃ ምንጮች አፈሰሰው።+ እነሱም ደም ሆኑ።+ +5 እኔም በውኃዎች ላይ ሥልጣን ያለው መልአክ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “ያለህና የነበርክ+ ታማኝ አምላካችን፣+ እነዚህን የፍርድ ውሳኔዎች ስላስተላለፍክ አንተ ጻድቅ ነህ፤+ +6 ምክንያቱም የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም አፍስሰዋል፤+ አንተም ደም እንዲጠጡ ሰጥተሃቸዋል፤+ ደግሞም ይገባቸዋል።”+ +7 መሠዊያውም “አዎ፣ ሁሉን ቻይ የሆንከው ይሖዋ* አምላክ ሆይ፣+ ፍርድህ ሁሉ እውነትና ጽድቅ ነው”+ ሲል ሰማሁ። +8 አራተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰው፤+ ፀሐይም ሰዎችን በእሳት እንድትለበልብ ተፈቀደላት። +9 ሰዎቹም በኃይለኛ ሙቀት ተለበለቡ፤ ሆኖም እነሱ በእነዚህ መቅሰፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን አምላክ ስም ተሳደቡ እንጂ ንስሐ አልገቡም፤ ለእሱም ክብር አልሰጡም። +10 አምስተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰው። መንግሥቱም በጨለማ ተዋጠ፤+ እነሱም ከሥቃያቸው የተነሳ ምላሳቸውን ያኝኩ ጀመር፤ +11 ይሁንና ከሥቃያቸውና ከቁስላቸው የተነሳ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ከሥራቸውም ንስሐ አልገቡም። +12 ስድስተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ላይ አፈሰሰው፤+ ከፀሐይ መውጫ* ለሚመጡት ነገሥታት መንገድ እንዲዘጋጅላቸውም+ የወንዙ ውኃ ደረቀ።+ +13 እኔም እንቁራሪት የሚመስሉ በመንፈስ የተነገሩ ሦስት ርኩሳን ቃላት* ከዘንዶው+ አፍና ከአውሬው አፍ እንዲሁም ከሐሰተኛው ነቢይ አፍ ሲወጡ አየሁ። +14 እንዲያውም እነዚህ በአጋንንት መንፈስ የተነገሩ ቃላት ናቸው፤ ተአምራዊ ምልክቶችም ይፈጽማሉ፤+ እነሱም ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን+ ወደሚካሄደው ጦርነት ሊሰበስቧቸው+ ወደ ዓለም ነገሥታት ሁሉ ይወጣሉ። +15 “እነሆ፣ እንደ ሌባ እመጣለሁ።+ ራቁቱን እንዳይሄድና ሰዎች ኀፍረቱን እንዳያዩበት+ ነቅቶ የሚኖርና+ መደረቢያውን የሚጠብቅ ሰው ደስተኛ ነው።” +16 እነሱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን*+ ወደሚባል ስፍራ ሰበሰቧቸው። +17 ሰባተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በአየር ላይ አፈሰሰው። በዚህ ጊዜ ከቅዱሱ ስፍራ፣* ከዙፋኑ “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምፅ ወጣ።+ +18 እንዲሁም የመብረቅ ብልጭታ፣ ድምፅና ነጎድጓድ ተከሰተ፤ ሰው በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ታይቶ የማያውቅ ታላቅ የምድር ነውጥም ተከሰተ፤+ የምድር ነውጡ መጠነ ሰፊና እጅግ ታላቅ ነበር። +19 ታላቂቱ ከተማ+ ለሦስት ተከፈለች፤ የብሔራት ከተሞችም ፈራረሱ፤ አምላክም የመዓ���ን የቁጣ ወይን ጠጅ የያዘውን ጽዋ ይሰጣት ዘንድ+ ታላቂቱ ባቢሎንን+ አስታወሳት። +20 ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ፤ ተራሮችም ሊገኙ አልቻሉም።+ +21 ከዚያም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ከሰማይ በሰዎች ላይ ወረደ፤+ እያንዳንዱ የበረዶ ድንጋይ አንድ ታላንት* ይመዝን ነበር፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ስለነበር ሰዎቹ ከበረዶው መቅሰፍት+ የተነሳ አምላክን ተሳደቡ። +6 እኔም በጉ+ ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን ሲከፍት አየሁ፤+ ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታትም+ አንዱ እንደ ነጎድጓድ ባለ ድምፅ “ና!” ሲል ሰማሁ። +2 እኔም አየሁ፣ እነሆ ነጭ ፈረስ ነበር፤+ በእሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤+ እሱም ድል እያደረገ ወጣ፤ ድሉንም ለማጠናቀቅ ወደ ፊት ገሰገሰ።+ +3 ሁለተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ሁለተኛው ሕያው ፍጡር+ “ና!” ሲል ሰማሁ። +4 ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ሌላ ፈረስ ወጣ፤ በእሱም ላይ ለተቀመጠው ሰዎች እርስ በርሳቸው ይተራረዱ ዘንድ ሰላምን ከምድር እንዲወስድ ተፈቀደለት፤ እንዲሁም ትልቅ ሰይፍ ተሰጠው።+ +5 ሦስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ+ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር+ “ና!” ሲል ሰማሁ። እኔም አየሁ፣ እነሆ ጥቁር ፈረስ ነበር፤ በእሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር። +6 ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት መካከል እንደ ድምፅ ያለ ነገር “አንድ እርቦ* ስንዴ በዲናር፣*+ ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፤ ደግሞም የወይራ ዘይቱንና የወይን ጠጁን አትጉዳ” ሲል ሰማሁ።+ +7 አራተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ አራተኛው ሕያው ፍጡር+ “ና!” ሲል ሰማሁ። +8 እኔም አየሁ፣ እነሆ ግራጫ ፈረስ ነበር፤ በእሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበር። መቃብርም* በቅርብ ይከተለው ነበር። ሞትና መቃብርም በረጅም ሰይፍ፣ በምግብ እጥረት፣+ በገዳይ መቅሰፍትና በምድር አራዊት እንዲገድሉ በምድር አንድ አራተኛ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።+ +9 አምስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ በአምላክ ቃል የተነሳና በሰጡት ምሥክርነት የተነሳ የታረዱትን ሰዎች ነፍሳት*+ ከመሠዊያው በታች+ አየሁ።+ +10 እነሱም “ቅዱስና እውነተኛ የሆንከው ሉዓላዊ ጌታ ሆይ፣+ በምድር በሚኖሩት ላይ የማትፈርደውና ደማችንን የማትበቀለው እስከ መቼ ነው?”+ ብለው በታላቅ ድምፅ ጮኹ። +11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤+ እንዲሁም ወደፊት እንደ እነሱ የሚገደሉት ባልንጀሮቻቸው የሆኑ ባሪያዎችና የወንድሞቻቸው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እንዲጠብቁ ተነገራቸው።+ +12 ስድስተኛውንም ማኅተም ሲከፍት አየሁ፤ ታላቅ የምድር ነውጥም ተከሰተ፤ ፀሐይም ከፀጉር* እንደተሠራ ማቅ ጠቆረች፤ ጨረቃም ሙሉ በሙሉ ደም መሰለች፤+ +13 ኃይለኛ ነፋስ የበለስን ዛፍ ሲያወዛውዝ ያልበሰሉት ፍሬዎች ከዛፉ ላይ እንደሚረግፉ፣ የሰማይ ከዋክብትም ወደ ምድር ወደቁ። +14 ሰማይም እየተጠቀለለ እንዳለ የመጽሐፍ ጥቅልል ከቦታው ተነሳ፤+ እንዲሁም ተራሮች ሁሉና ደሴቶች ሁሉ ከቦታቸው ተወገዱ።+ +15 ከዚያም የምድር ነገሥታት፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የጦር አዛዦች፣ ሀብታሞች፣ ብርቱዎች፣ ባሪያዎች ሁሉና ነፃ ሰዎች ሁሉ በዋሻዎች ውስጥና ተራራ ላይ ባሉ ዓለቶች መካከል ተደበቁ።+ +16 ተራሮቹንና ዓለቶቹንም እንዲህ እያሉ ተማጸኑ፦ “በላያችን ውደቁና+ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው+ ፊትና ከበጉ+ ቁጣ ሰውሩን፤ +17 ምክንያቱም ቁጣቸውን የሚገልጹበት ታላቁ ቀን መጥቷል፤+ ማንስ ሊቆም ይችላል?”+ +10 እኔም ደመና የተጎናጸፈ* ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበር፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ፣+ ቅልጥሞቹም* እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፤ +2 በእጁም የተከፈተች ትንሽ ጥቅልል ይዞ ነበር። እሱም ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ፣ ግራ እግሩን ደግሞ በምድር ላይ አሳረፈ፤ +3 እንደሚያገሣ አንበሳም በታላቅ ድምፅ ጮኸ።+ በጮኸም ጊዜ የሰባቱ ነጎድጓዶች ድምፆች+ ተናገሩ። +4 ሰባቱ ነጎድጓዶች በተናገሩም ጊዜ ለመጻፍ ተዘጋጀሁ፤ ሆኖም ከሰማይ+ “ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሯቸውን ነገሮች በማኅተም አሽጋቸው* እንጂ አትጻፋቸው” የሚል ድምፅ ሰማሁ። +5 በባሕሩና በምድሩ ላይ ቆሞ ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አነሳ፤ +6 ሰማይንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች፣ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች እንዲሁም ባሕርንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች በፈጠረውና+ ለዘላለም በሚኖረው+ በመማል እንዲህ አለ፦ “ከእንግዲህ ወዲህ መዘግየት አይኖርም። +7 ሆኖም ሰባተኛው መልአክ+ መለከቱን ሊነፋ+ በተዘጋጀባቸው ቀኖች አምላክ የገዛ ራሱ ባሪያዎች ለሆኑት ለነቢያት+ እንደ ምሥራች ያበሰረው ቅዱስ ሚስጥር+ በእርግጥ ይፈጸማል።” +8 ከሰማይ የመጣውም ድምፅ+ እንደገና ሲያናግረኝ ሰማሁ፤ እንዲህም አለኝ፦ “ሂድ፣ በባሕሩና በምድሩ ላይ በቆመው መልአክ እጅ ያለችውን የተከፈተች ጥቅልል ውሰድ።”+ +9 እኔም ወደ መልአኩ ሄጄ ትንሿን ጥቅልል እንዲሰጠኝ ጠየቅኩት። እሱም “ውሰድና ብላት፤+ ሆድህን መራራ ታደርገዋለች፤ አፍህ ላይ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች” አለኝ። +10 ትንሿን ጥቅልል ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላኋት፤+ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠች፤+ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ። +11 እነሱም “ሕዝቦችን፣ ብሔራትን፣ ቋንቋዎችንና ብዙ ነገሥታትን በተመለከተ እንደገና ትንቢት መናገር አለብህ” አሉኝ። +"14 ከዚያም አየሁ፤ እነሆ፣ በጉ+ በጽዮን ተራራ+ ላይ ቆሟል፤ ከእሱም ጋር የእሱ ስምና የአባቱ ስም+ በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው 144,000+ ነበሩ።" +2 ከሰማይ እንደ ብዙ ውኃዎችና እንደ ኃይለኛ የነጎድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ ሲወጣ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ በገናቸውን እየደረደሩ የሚዘምሩ ዘማሪዎች ዓይነት ድምፅ ነው። +"3 እነሱም በዙፋኑ ፊት እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና+ በሽማግሌዎቹ+ ፊት አዲስ የሚመስል መዝሙር እየዘመሩ ነበር፤+ ከምድር ከተዋጁት ከ144,000ዎቹ+ በስተቀር ማንም ይህን መዝሙር ጠንቅቆ ሊያውቀው አልቻለም።" +4 እነዚህ ራሳቸውን በሴቶች ያላረከሱ ናቸው፤ እንዲያውም ደናግል ናቸው።+ ምንጊዜም በጉ በሄደበት ሁሉ ይከተሉታል።+ እነዚህ ለአምላክና ለበጉ እንደ በኩራት+ ሆነው ከሰዎች መካከል ተዋጅተዋል፤+ +5 በአፋቸውም የማታለያ ቃል አልተገኘም፤ ምንም ዓይነት እንከን የለባቸውም።+ +6 ሌላም መልአክ በሰማይ መካከል* ሲበር አየሁ፤ እሱም በምድር ላይ ለሚኖር ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ ሁሉ የሚያበስረው የዘላለም ምሥራች ይዞ ነበር።+ +7 እሱም በታላቅ ድምፅ “አምላክን ፍሩ፤ ክብርም ስጡት፤ ምክንያቱም የሚፈርድበት ሰዓት ደርሷል፤+ በመሆኑም ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና የውኃ ምንጮችን የሠራውን+ አምልኩ” አለ። +8 ሌላ ሁለተኛ መልአክ “ወደቀች! ብሔራት ሁሉ የዝሙቷን* የፍትወት* ወይን ጠጅ እንዲጠጡ ያደረገችው+ ታላቂቱ ባቢሎን+ ወደቀች!”+ እያለ ተከተለው። +9 ሌላ ሦስተኛ መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፦ “ማንም አውሬውንና+ ምስሉን የሚያመልክና በግንባሩ ወይም በእጁ ላይ ምልክት የሚቀበል ከሆነ+ +10 እሱም፣ ሳይበረዝ ወደ ቁጣው ጽዋ የተቀዳውን የአምላክ የቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤+ እንዲሁም በቅዱሳኑ መላእክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በድኝ ይሠቃያል።+ +11 የሥቃያቸውም ጭስ ለዘላለም ወደ ላይ ይወጣል፤+ ደግሞም አውሬውንና ምስሉን የሚያመልኩ እንዲሁም የስሙን ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ምንም እረፍት አይኖራቸውም።+ +12 የአምላክን ትእዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስን እምነት አጥብቀ��� የሚከተሉ+ ቅዱሳን፣+ መጽናት የሚያስፈልጋቸው እዚህ ላይ ነው።” +13 ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፦ “ይህን ጻፍ፦ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከጌታ ጋር ያላቸውን አንድነት ጠብቀው የሚሞቱ+ ደስተኞች ናቸው። መንፈስም ‘አዎ፣ ያከናወኑት ሥራ ወዲያው ስለሚከተላቸው* ከድካማቸው ይረፉ’ ይላል።” +14 ከዚያም አየሁ፤ እነሆም፣ ነጭ ደመና ነበር፤ በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጧል፤+ እሱም በራሱ ላይ የወርቅ አክሊል ደፍቷል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዟል። +15 ሌላ መልአክ ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ* ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የአጨዳው ሰዓት ስለደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ ምክንያቱም የምድር መከር ደርሷል” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።+ +16 በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደ፤ ምድርም ታጨደች። +17 አሁንም ሌላ መልአክ በሰማይ ካለው ቤተ መቅደስ ቅዱስ ስፍራ ወጣ፤ እሱም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር። +18 እንደገናም ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጣ፤ እሱም በእሳቱ ላይ ሥልጣን ነበረው። በታላቅ ድምፅ ጮኾም ስለታም ማጭድ የያዘውን መልአክ “የምድሪቱ የወይን ፍሬዎች ስለበሰሉ ስለታም ማጭድህን ስደድና የምድርን የወይን ዘለላዎች ሰብስብ” አለው።+ +19 መልአኩ ማጭዱን ወደ ምድር በመስደድ የምድርን ወይን ሰበሰበ፤ ከዚያም ወደ ታላቁ የአምላክ የቁጣ ወይን መጭመቂያ ወረወረው።+ +20 ወይኑ ከከተማው ውጭ ተረገጠ፤ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስ ከፍታ ያለውና 296 ኪሎ ሜትር ገደማ* ርቀት ያለው ደም ወጣ። +9 አምስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ።+ እኔም ከሰማይ ወደ ምድር የወደቀ አንድ ኮከብ አየሁ፤ ለእሱም የጥልቁ መግቢያ ቁልፍ+ ተሰጠው። +2 የጥልቁንም መግቢያ ከፈተው፤ በመግቢያውም በኩል ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጭስ ያለ ጭስ ወጣ፤ ከዚያ በወጣው ጭስም ፀሐይ ጨለመች፤+ አየሩም ጠቆረ። +3 ከጭሱም አንበጦች ወጥተው ወደ ምድር ወረዱ፤+ እነሱም በምድር ላይ ያሉ ጊንጦች ያላቸው ዓይነት ሥልጣን ተሰጣቸው። +4 የአምላክ ማኅተም በግንባራቸው ላይ የሌላቸውን ሰዎች ብቻ እንጂ ማንኛውንም የምድር ተክል ወይም ማንኛውንም ዕፀዋት ወይም ማንኛውንም ዛፍ እንዳይጎዱ ተነገራቸው።+ +5 አንበጦቹም ሰዎቹን እንዲገድሏቸው ሳይሆን ለአምስት ወር እንዲያሠቃዩአቸው ተፈቀደላቸው፤ በእነሱም ላይ የሚደርሰው ሥቃይ ጊንጥ+ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዓይነት ሥቃይ ነው። +6 በእነዚያ ቀኖች ሰዎች ሞትን ይሻሉ፤ ሆኖም ፈጽሞ አያገኙትም፤ ለመሞት ይመኛሉ፤ ሞት ግን ከእነሱ ይሸሻል። +7 የአንበጦቹም ገጽታ ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶች ይመስል ነበር፤+ በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊሎች የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ፤ ፊታቸው ደግሞ የሰው ፊት ይመስል ነበር፤ +8 ፀጉራቸው የሴት ፀጉር ይመስል ነበር። ጥርሳቸው ግን የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር፤+ +9 የብረት ጥሩር የሚመስል ጥሩርም ነበራቸው። የክንፎቻቸው ድምፅም ወደ ጦርነት የሚገሰግሱ በፈረስ የሚጎተቱ ሠረገላዎች ድምፅ ይመስል ነበር።+ +10 በተጨማሪም የጊንጥ ዓይነት ተናዳፊ ጅራት አላቸው፤ ደግሞም ሰዎቹን ለአምስት ወር የሚጎዱበት ሥልጣን በጅራታቸው ላይ ነበር።+ +11 በእነሱ ላይ የተሾመ ንጉሥ አላቸው፤ እሱም የጥልቁ መልአክ ነው።+ በዕብራይስጥ ስሙ አባዶን* ሲሆን በግሪክኛ ደግሞ ስሙ አጶልዮን* ነው። +12 አንዱ ወዮታ አልፏል። እነሆ፣ ከዚህ በኋላ ሌሎች ሁለት ወዮታዎች+ ይመጣሉ። +13 ስድስተኛው መልአክ+ መለከቱን ነፋ።+ ደግሞም በአምላክ ፊት ካለው የወርቅ መሠዊያ+ ቀንዶች የወጣ አንድ ድምፅ ሰማሁ፤ +14 ድምፁም መለከት የያዘውን ስድስተኛውን መልአክ “በታላቁ ወንዝ፣ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራ��ን መላእክት ፍታቸው” አለው።+ +15 ለዚህ ሰዓት፣ ቀን፣ ወርና ዓመት ተዘጋጅተው የነበሩት አራቱ መላእክትም ከሰዎቹ አንድ ሦስተኛውን እንዲገድሉ ተፈቱ። +16 የፈረሰኞቹ ሠራዊት ብዛት ሁለት እልፍ ጊዜ እልፍ* ነበር፤ ቁጥራቸውንም ሰማሁ። +17 በራእዩ ላይ ያየኋቸው ፈረሶችና በላያቸው የተቀመጡት ይህን ይመስሉ ነበር፦ እንደ እሳት ቀይ፣ እንደ ያክንት ሰማያዊና እንደ ድኝ ቢጫ የሆነ ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበር፤+ ከአፋቸውም እሳት፣ ጭስና ድኝ ወጣ። +18 ከአፋቸው በወጡት በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች ይኸውም በእሳቱ፣ በጭሱና በድኙ ከሰዎቹ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ተገደሉ። +19 የፈረሶቹ ሥልጣን ያለው በአፋቸውና በጅራታቸው ላይ ነውና፤ ጅራታቸው እባብ የሚመስል ሲሆን ራስም አለው፤ ጉዳት የሚያደርሱትም በዚህ ነው። +20 ሆኖም በእነዚህ መቅሰፍቶች ያልተገደሉት የቀሩት ሰዎች ከእጃቸው ሥራ ንስሐ አልገቡም፤ ደግሞም አጋንንትን እንዲሁም ማየት፣ መስማትም ሆነ መሄድ የማይችሉትን ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመዳብ፣ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩትን ጣዖቶች ማምለካቸውን አልተዉም።+ +21 እንዲሁም ከፈጸሙት የነፍስ ግድያ፣ ከመናፍስታዊ ድርጊቶቻቸው፣ ከፆታ ብልግናቸውም* ሆነ ከሌብነታቸው ንስሐ አልገቡም። +13 እሱም* በባሕር አሸዋ ላይ ቆመ። እኔም አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ያሉት አንድ አውሬ+ ከባሕር+ ሲወጣ አየሁ፤ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች የነበሩት ሲሆን በራሶቹ ላይ አምላክን የሚሰድቡ ስሞች ነበሩት። +2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ ግን የድብ እግር፣ አፉ ደግሞ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ዘንዶውም+ለአውሬው ኃይልና ዙፋን እንዲሁም ታላቅ ሥልጣን ሰጠው።+ +3 እኔም አየሁ፤ ከአውሬው ራሶች አንዱ የሞተ ያህል እስኪሆን ድረስ ቆስሎ ነበር፤ ሆኖም ለሞት የሚዳርገው ቁስሉ ዳነ፤+ ምድርም ሁሉ አውሬውን በአድናቆት ተከተለው። +4 ሰዎችም ዘንዶው ለአውሬው ሥልጣን ስለሰጠው ዘንዶውን አመለኩ፤ እንዲሁም “እንደ አውሬው ያለ ማን ነው? ከእሱስ ጋር ማን ሊዋጋ ይችላል?” በማለት አውሬውን አመለኩ። +5 እሱም የትዕቢት ቃል የሚናገርበትና አምላክን የሚሳደብበት አፍ ተሰጠው፤ ደግሞም ለ42 ወር የፈለገውን እንዲያደርግ ሥልጣን ተሰጠው።+ +6 አምላክን ለመሳደብ+ ይኸውም የአምላክን ስምና የአምላክን መኖሪያ እንዲሁም በሰማይ የሚኖሩትን ለመሳደብ አፉን ከፈተ።+ +7 ቅዱሳኑን እንዲዋጋና ድል እንዲያደርጋቸው ተፈቀደለት፤+ ደግሞም በነገድ፣ በሕዝብ፣ በቋንቋና በብሔር ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው። +8 በምድር ላይ የሚኖሩም ሁሉ ያመልኩታል። ዓለም ከተመሠረተበት* ጊዜ ጀምሮ የአንዳቸውም ስም በታረደው በግ+ የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል+ ላይ አልሰፈረም። +9 ጆሮ ያለው ካለ ይስማ።+ +10 ማንም ሰው መማረክ ካለበት ይማረካል። በሰይፍ የሚገድል ካለ* በሰይፍ መገደል አለበት።+ ቅዱሳን+ ጽናትና+ እምነት ማሳየት+ የሚያስፈልጋቸው እዚህ ላይ ነው። +11 ከዚያም ሌላ አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤ እሱም እንደ በግ ሁለት ቀንዶች ነበሩት፤ ሆኖም እንደ ዘንዶ+ መናገር ጀመረ። +12 በመጀመሪያው አውሬ ፊት የመጀመሪያውን አውሬ+ ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀማል። ምድርና የምድር ነዋሪዎች፣ ለሞት የሚዳርገው ቁስል የዳነለትን+ የመጀመሪያውን አውሬ እንዲያመልኩ ያደርጋል። +13 በሰው ልጆችም ፊት ታላላቅ ምልክቶችን ይፈጽማል፤ እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር ያወርዳል። +14 በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በሰይፍ ቆስሎ ለነበረው በኋላ ግን ላገገመው+ አውሬ፣ ምስል+ እንዲሠሩ እያዘዘ በአውሬው ፊት እንዲፈጽማቸው በተፈቀዱለት ምልክቶች አማካኝነት በምድር ላይ ��ሚኖሩትን ያስታል። +15 እንዲሁም ለአውሬው ምስል እስትንፋስ* እንዲሰጠው ተፈቀደለት፤ ይህም የሆነው የአውሬው ምስል መናገር እንዲችልና የአውሬውን ምስል የማያመልኩትን ሁሉ እንዲያስገድል ነው። +16 ሰዎች ሁሉ ማለትም ታናናሾችና ታላላቆች፣ ሀብታሞችና ድሆች እንዲሁም ነፃ ሰዎችና ባሪያዎች በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ላይ ምልክት እንዲደረግባቸው አስገደደ፤+ +17 ይህም የሆነው ምልክቱ ይኸውም የአውሬው ስም+ ወይም የስሙ ቁጥር+ ካለው ሰው በስተቀር ማንም መግዛት ወይም መሸጥ እንዳይችል ነው። +18 ጥበብ የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው፦ የማስተዋል ችሎታ ያለው ሰው የአውሬውን ቁጥር ያስላ፤ ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነውና፤ ቁጥሩም 666 ነው።+ +5 እኔም በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው+ በሁለቱም በኩል* የተጻፈበትና በሰባት ማኅተሞች በደንብ የታሸገ ጥቅልል በቀኝ እጁ ይዞ ተመለከትኩ። +2 አንድ ብርቱ መልአክም በታላቅ ድምፅ “ማኅተሞቹን ሊያነሳና ጥቅልሉን ሊከፍት የሚገባው ማን ነው?” ብሎ ሲያውጅ አየሁ። +3 ሆኖም በሰማይም ሆነ በምድር እንዲሁም ከምድር በታች ጥቅልሉን ሊከፍትም ሆነ ውስጡን ሊመለከት የሚችል ማንም አልነበረም። +4 ጥቅልሉን ሊከፍትም ሆነ ውስጡን ሊመለከት የሚገባው ማንም ባለመገኘቱ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። +5 ሆኖም ከሽማግሌዎቹ አንዱ “አታልቅስ። እነሆ፣ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፣+ የዳዊት+ ሥር+ ድል ስላደረገ+ ሰባቱን ማኅተሞችና ጥቅልሉን ሊከፍት ይችላል” አለኝ። +6 በዙፋኑ መካከል፣ በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት መካከልና በሽማግሌዎቹ+ መካከል የታረደ+ የሚመስል በግ+ ቆሞ አየሁ፤ በጉም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች አሉት፤ ዓይኖቹም ወደ መላው ምድር የተላኩትን ሰባቱን የአምላክ መናፍስት+ ያመለክታሉ። +7 እሱም ወዲያውኑ ወደ ፊት ቀርቦ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው+ ቀኝ እጅ ጥቅልሉን ወሰደ። +8 ጥቅልሉን በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና 24ቱ ሽማግሌዎች+ በበጉ ፊት ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም በገናና ዕጣን የተሞሉ የወርቅ ሳህኖች ነበሯቸው። (ዕጣኑ የቅዱሳኑን ጸሎት ያመለክታል።)+ +9 እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፦+ “ጥቅልሉን ልትወስድና ማኅተሞቹን ልትከፍት ይገባሃል፤ ታርደሃልና፤ በደምህም ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ+ ሰዎችን ለአምላክ ዋጅተሃል፤+ +10 እንዲሁም ለአምላካችን መንግሥትና+ ካህናት እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤+ በምድርም ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ።”+ +11 እኔም አየሁ፤ ደግሞም በዙፋኑ፣ በሕያዋን ፍጥረታቱና በሽማግሌዎቹ ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቁጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና* ሺዎች ጊዜ ሺዎች ነበር፤+ +12 እነሱም በታላቅ ድምፅ “ታርዶ የነበረው በግ+ ኃይል፣ ብልጽግና፣ ጥበብ፣ ብርታት፣ ክብር፣ ግርማና በረከት ሊቀበል ይገባዋል” አሉ።+ +13 እንዲሁም በሰማይ፣ በምድር፣ ከምድር በታችና+ በባሕር ያለ ፍጡር ሁሉ፣ አዎ በውስጣቸው ያሉ ነገሮች ሁሉ “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና+ ለበጉ+ በረከት፣ ክብር፣+ ግርማና ኃይል ለዘላለም ይሁን” ብለው ሲናገሩ ሰማሁ።+ +14 አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት “አሜን!” ይሉ ነበር፤ ሽማግሌዎቹም ተደፍተው ሰገዱ። +21 እኔም አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤+ የቀድሞው ሰማይና የቀድሞው ምድር አልፈዋልና፤+ ባሕሩም+ ከእንግዲህ ወዲህ የለም። +2 ደግሞም ቅድስቲቱ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከአምላክ ዘንድ ስትወርድ አየሁ፤+ እሷም ለባሏ እንዳጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ ነበር።+ +3 በዚህ ጊዜ ከዙፋኑ አንድ ታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “እነሆ፣ የአምላክ ድንኳን ከሰዎች ጋር ነው፤ እሱም ከእነሱ ጋር ይኖራል፤ እነሱም ሕዝቡ ይሆናሉ። አምላክ ራሱ�� ከእነሱ ጋር ይሆናል።+ +4 እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤*+ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤+ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።+ ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።” +5 በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው+ “እነሆ፣ ሁሉንም ነገር አዲስ አደርጋለሁ” አለ።+ ደግሞም “እነዚህ ቃላት አስተማማኝና* እውነት ስለሆኑ ጻፍ” አለኝ። +6 እንዲህም አለኝ፦ “እነዚህ ነገሮች ተፈጽመዋል! እኔ አልፋና ኦሜጋ፣* የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ።+ ለተጠማ ሁሉ ከሕይወት ውኃ ምንጭ በነፃ* እሰጣለሁ።+ +7 ድል የሚነሳ ሁሉ እነዚህን ነገሮች ይወርሳል፤ እኔ አምላክ እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል። +8 ይሁን እንጂ የፈሪዎች፣ የእምነት የለሾች፣+ ርኩስና አስጸያፊ የሆኑ ሰዎች፣ የነፍሰ ገዳዮች፣+ የሴሰኞች፣*+ መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ የጣዖት አምላኪዎችና የውሸታሞች+ ሁሉ ዕጣ ፋንታቸው በእሳትና በድኝ በሚቃጠል ሐይቅ ውስጥ መጣል ነው።+ ይህ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል።”+ +9 በሰባቱ የመጨረሻ መቅሰፍቶች የተሞሉትን ሰባቱን ሳህኖች ይዘው ከነበሩት ሰባት መላእክት+ አንዱ መጥቶ “ና፣ የበጉን ሚስት፣ ሙሽራይቱን+ አሳይሃለሁ” አለኝ። +10 ከዚያም በመንፈስ ኃይል ወደ አንድ ትልቅና ረጅም ተራራ ወሰደኝና ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከአምላክ ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤+ +11 እሷም የአምላክን ክብር ተላብሳ ነበር።+ የብርሃኗም ድምቀት እጅግ እንደከበረ ድንጋይ ይኸውም እንደ ኢያስጲድ ነበር፤ ደግሞም እንደ ክሪስታል ጥርት ብሎ ያንጸባርቅ ነበር።+ +12 ትልቅና ረጅም የግንብ አጥር እንዲሁም 12 በሮች ነበሯት፤ በበሮቹም ላይ 12 መላእክት ነበሩ፤ የ12ቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስም በበሮቹ ላይ ተቀርጾ ነበር። +13 በምሥራቅ ሦስት በሮች፣ በሰሜን ሦስት በሮች፣ በደቡብ ሦስት በሮችና በምዕራብ ሦስት በሮች ነበሩ።+ +14 በተጨማሪም የከተማዋ የግንብ አጥር 12 የመሠረት ድንጋዮች ነበሩት፤ በእነሱም ላይ የ12ቱ የበጉ ሐዋርያት 12 ስሞች+ ተጽፈው ነበር። +15 እያነጋገረኝ የነበረው መልአክም ከተማዋን፣ በሮቿንና የግንብ አጥሯን ለመለካት የሚያገለግል የወርቅ ዘንግ ይዞ ነበር።+ +"16 ከተማዋ አራት ማዕዘን ቅርጽ ያላት ሲሆን ርዝመቷ ከወርዷ ጋር እኩል ነው። እሱም ከተማዋን በዘንጉ ሲለካት 2,220 ኪሎ ሜትር ገደማ* ሆና ተገኘች፤ ርዝመቷ፣ ወርዷና ከፍታዋ እኩል ነው።" +17 በተጨማሪም የግንብ አጥሯን ለካ፤ አጥሩም በሰው መለኪያ፣ በመልአክም መለኪያ 144 ክንድ* ሆኖ ተገኘ። +18 የከተማዋ የግንብ አጥር የተገነባው ከኢያስጲድ ነበር፤+ ከተማዋም የጠራ መስተዋት የሚመስል ንጹሕ ወርቅ ነበረች። +19 የከተማዋ የግንብ አጥር መሠረቶች በተለያዩ የከበሩ ድንጋዮች* ያጌጡ ነበሩ፦ የመጀመሪያው መሠረት ኢያስጲድ፣ ሁለተኛው ሰንፔር፣ ሦስተኛው ኬልቄዶን፣ አራተኛው መረግድ፣ +20 አምስተኛው ሰርዶንክስ፣ ስድስተኛው ሰርድዮን፣ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፣ ስምንተኛው ቢረሌ፣ ዘጠነኛው ቶጳዝዮን፣ አሥረኛው ክርስጵራስስ፣ አሥራ አንደኛው ያክንትና አሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበር። +21 በተጨማሪም 12ቱ በሮች 12 ዕንቁዎች ነበሩ፤ እያንዳንዱ በር ከአንድ ዕንቁ የተሠራ ነበር። የከተማዋ አውራ ጎዳናም ብርሃን እንደሚያስተላልፍ መስተዋት ንጹሕ ወርቅ ነበር። +22 በከተማዋ ውስጥ ቤተ መቅደስ አላየሁም፤ ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ* አምላክና+ በጉ ቤተ መቅደሷ ናቸውና። +23 ከተማዋ የፀሐይም ሆነ የጨረቃ ብርሃን አላስፈለጋትም፤ የአምላክ ክብር ብርሃን ሰጥቷታልና፤+ በጉም መብራቷ ነበር።+ +24 ብሔራትም በእሷ ብርሃን ይጓዛሉ፤+ የምድር ነገሥታትም ክብራቸውን ወደ እሷ ያመጣሉ። +25 በሮ��� በቀን አይዘጉም፤ በዚያም ሌሊት ፈጽሞ አይኖርም።+ +26 የብሔራትን ግርማና ክብርም ወደ እሷ ያመጣሉ።+ +27 ሆኖም የረከሰ ማንኛውም ነገር እንዲሁም አስጸያፊ ነገር የሚያደርግና የሚያታልል ማንኛውም ሰው በምንም ዓይነት ወደ እሷ አይገባም፤+ ወደ እሷ የሚገቡት በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ላይ የተጻፉ ብቻ ናቸው።+ +15 እኔም ሌላ ታላቅና አስደናቂ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ ሰባት መቅሰፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት+ ነበሩ። የአምላክ ቁጣ የሚደመደመው በእነዚህ ስለሆነ እነዚህ መቅሰፍቶች የመጨረሻዎቹ ናቸው።+ +2 እኔም ከእሳት ጋር የተቀላቀለ የብርጭቆ ባሕር+ የሚመስል ነገር አየሁ፤ እንዲሁም አውሬውን፣ ምስሉንና+ የስሙን ቁጥር+ ድል የነሱት+ የአምላክን በገናዎች ይዘው በብርጭቆው ባሕር አጠገብ ቆመው ነበር። +3 የአምላክን ባሪያ የሙሴን መዝሙርና+ የበጉን+ መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፦ “ሁሉን ቻይ የሆንከው ይሖዋ* አምላክ ሆይ፣+ ሥራዎችህ ታላቅና አስደናቂ ናቸው።+ የዘላለም ንጉሥ ሆይ፣+ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው።+ +4 ይሖዋ* ሆይ፣ ለመሆኑ አንተን የማይፈራና ስምህን ከፍ ከፍ የማያደርግ ማን ነው? አንተ ብቻ ታማኝ ነህና!+ የጽድቅ ድንጋጌዎችህ ስለተገለጡ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”+ +5 ከዚህ በኋላ አየሁ፤ የምሥክሩ ድንኳን+ ቅዱስ ስፍራ* በሰማይ ተከፍቶ ነበር፤+ +6 ሰባቱን መቅሰፍቶች የያዙት ሰባቱ መላእክትም+ ንጹሕና የሚያንጸባርቅ በፍታ ለብሰው እንዲሁም ደረታቸውን በወርቅ መታጠቂያ ታጥቀው ከቅዱሱ ስፍራ ወጡ። +7 ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት አንዱ ለዘላለም በሚኖረው አምላክ ቁጣ+ የተሞሉ ሰባት የወርቅ ሳህኖችን ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው። +8 ቅዱሱ ስፍራም ከአምላክ ክብርና+ ከኃይሉ የተነሳ በጭስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባት መቅሰፍቶች+ እስኪፈጸሙ ድረስም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ማንም መግባት አልቻለም። +22 መልአኩም ከአምላክና ከበጉ+ ዙፋን ወጥቶ የሚፈሰውን እንደ ክሪስታል የጠራ የሕይወት ውኃ ወንዝ አሳየኝ፤+ +2 ወንዙም በከተማዋ አውራ ጎዳና መካከል ቁልቁል ይፈስ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ በየወሩ እያፈሩ በዓመት 12 ጊዜ ፍሬ የሚሰጡ የሕይወት ዛፎች ነበሩ። የዛፎቹም ቅጠሎች ሕዝቦችን ለመፈወስ የሚያገለግሉ ነበሩ።+ +3 በዚያም ከእንግዲህ እርግማን አይኖርም። ከዚህ ይልቅ የአምላክና የበጉ ዙፋን+ በከተማዋ ውስጥ ይሆናል፤ ባሪያዎቹም ቅዱስ አገልግሎት ያቀርቡለታል፤ +4 ፊቱንም ያያሉ፤+ ስሙም በግንባራቸው ላይ ይሆናል።+ +5 በተጨማሪም ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤+ ይሖዋ* አምላክ በእነሱ ላይ ብርሃን ስለሚፈነጥቅ የመብራት ብርሃንም ሆነ የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤+ ደግሞም ለዘላለም ይነግሣሉ።+ +6 መልአኩም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ቃላት አስተማማኝና* እውነት ናቸው፤+ አዎ፣ ነቢያት በመንፈስ መሪነት እንዲናገሩ የሚያደርገው ይሖዋ* አምላክ፣+ በቅርብ ጊዜ ውስጥ መፈጸም ያለባቸውን ነገሮች ለባሪያዎቹ ለማሳየት መልአኩን ልኳል። +7 እነሆ፣ እኔ ቶሎ እመጣለሁ።+ በዚህ ጥቅልል ውስጥ የሚገኙትን የትንቢት ቃላት የሚጠብቅ ማንኛውም ሰው ደስተኛ ነው።”+ +8 እነዚህን ነገሮች ስሰማና ስመለከት የነበርኩት እኔ ዮሐንስ ነኝ። እነዚህን ነገሮች በሰማሁና ባየሁ ጊዜ እያሳየኝ ለነበረው መልአክ ልሰግድ እግሩ ሥር ተደፋሁ። +9 እሱ ግን “ተጠንቀቅ! ፈጽሞ እንዳታደርገው! እኔ ከአንተም ሆነ ነቢያት ከሆኑት ወንድሞችህና በዚህ ጥቅልል ውስጥ የሰፈሩትን ቃላት ከሚጠብቁት ሁሉ ጋር አብሬ የማገለግል ባሪያ ነኝ። ለአምላክ ስገድ” አለኝ።+ +10 ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ “የተወሰነው ጊዜ ስለቀረበ በዚህ ጥቅልል ውስጥ የሰፈ��ትን የትንቢት ቃላት በማኅተም አታሽጋቸው። +11 ጻድቅ ያልሆነ፣ በዓመፅ ጎዳናው ይቀጥል፤ ርኩስ የሆነውም በርኩሰቱ ይቀጥል፤ ጻድቅ የሆነው ግን በጽድቅ ጎዳና መመላለሱን ይቀጥል፤ ቅዱስ የሆነውም በቅድስና ይቀጥል። +12 “‘እነሆ፣ እኔ ቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ብድራት ከእኔ ጋር ነው።+ +13 እኔ አልፋና ኦሜጋ፣*+ ፊተኛውና ኋለኛው፣ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ። +14 ከሕይወት ዛፎች ፍሬ የመብላት መብት እንዲያገኙና+ በበሮቿ+ በኩል ወደ ከተማዋ መግባት እንዲፈቀድላቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ+ ደስተኞች ናቸው። +15 ውሾች፣* መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ ሴሰኞች፣* ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች እንዲሁም ውሸትን የሚወዱና የሚዋሹ ሁሉ ከከተማዋ ውጭ አሉ።’+ +16 “‘እኔ ኢየሱስ ለጉባኤዎቹ ጥቅም ስል ስለ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ለመመሥከር መልአኬን ልኬአለሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር+ እንዲሁም ደማቅ አጥቢያ ኮከብ+ ነኝ።’” +17 መንፈሱና ሙሽራይቱም+ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም ሁሉ “ና!” ይበል፤ የተጠማም ሁሉ ይምጣ፤+ የሚፈልግ ሁሉ የሕይወትን ውኃ በነፃ ይውሰድ።+ +18 “በዚህ ጥቅልል ላይ የሰፈሩትን የትንቢት ቃላት ለሚሰማ ሁሉ እመሠክራለሁ፦ ማንም በእነዚህ ነገሮች ላይ አንዲት ነገር ቢጨምር+ አምላክ በዚህ ጥቅልል ውስጥ የተጻፉትን መቅሰፍቶች ይጨምርበታል፤+ +19 ማንም በዚህ የትንቢት መጽሐፍ ጥቅልል ላይ ከሰፈሩት ቃላት አንዲት ነገር ቢያጎድል አምላክ በዚህ ጥቅልል ላይ ከተጠቀሱት የሕይወት ዛፎችና+ ከቅድስቲቱ ከተማ+ ዕጣ ፋንታውን ይወስድበታል። +20 “ስለ እነዚህ ነገሮች የሚመሠክረው ‘አዎ፣ ቶሎ እመጣለሁ’+ ይላል።” “አሜን! ጌታ ኢየሱስ፣ ና።” +21 የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከቅዱሳኑ ጋር ይሁን።