diff --git "a/en-am/jw300-amharic-baseline/data/train.am" "b/en-am/jw300-amharic-baseline/data/train.am" new file mode 100644--- /dev/null +++ "b/en-am/jw300-amharic-baseline/data/train.am" @@ -0,0 +1,29054 @@ +target_sentence +17 አብራም ዕድሜው 99 ዓመት ሲሆን ይሖዋ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፦ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ። በፊቴ ተመላለስ፤ እንከን* የሌለብህ መሆንህንም አስመሥክር። +2 ከአንተ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤+ አንተንም እጅግ አበዛሃለሁ።”+ +3 በዚህ ጊዜ አብራም በግንባሩ ተደፋ፤ አምላክም እንዲህ በማለት እሱን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ +4 “በእኔ በኩል ከአንተ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳኔ እንደጸና ነው፤+ አንተም በእርግጥ የብዙ ብሔር አባት ትሆናለህ።+ +5 ከእንግዲህ ስምህ አብራም* አይባልም፤ የብዙ ብሔር አባት ስለማደርግህ ስምህ አብርሃም* ይሆናል። +6 እጅግ አበዛሃለሁ፤ ብዙ ብሔርም አደርግሃለሁ፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ።+ +7 “ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ አምላክ እሆን ዘንድ በእኔና በአንተ እንዲሁም መጪዎቹን ትውልዶቻቸውን ሁሉ ጨምሮ ከአንተ በኋላ በሚመጡት ዘሮችህ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አድርጌ እጠብቀዋለሁ።+ +8 ባዕድ ሆነህ የኖርክበትን አገር ይኸውም መላውን የከነአን ምድር ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ ዘላቂ ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”+ +9 በተጨማሪም አምላክ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “በአንተ በኩል፣ አንተም ሆንክ ከአንተ በኋላ የሚመጡት ዘሮችህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ቃል ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ። +10 እናንተም ሆናችሁ ከእናንተ በኋላ የሚመጡት ዘሮቻችሁ ልትጠብቁት የሚገባው በእኔና በእናንተ መካከል ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፦ በእናንተ መካከል ያለ ወንድ ሁሉ መገረዝ አለበት።+ +11 ሸለፈታችሁን መገረዝ አለባችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ቃል ኪዳን እንደ ምልክት ሆኖ ያገለግላል።+ +12 በትውልዶቻችሁ ሁሉ በመካከላችሁ ያለ ስምንት ቀን የሞላው ማንኛውም ወንድ መገረዝ አለበት፤+ በቤት የተወለደም ሆነ ዘርህ ያልሆነ ወይም ደግሞ ከባዕድ ሰው ላይ በገንዘብ የተገዛ ማንኛውም ወንድ ሁሉ ይገረዝ። +13 በቤትህ የተወለደ ማንኛውም ወንድ እንዲሁም በገንዘብህ የተገዛ ማንኛውም ወንድ መገረዝ አለበት፤+ በሥጋችሁ ላይ ያለው ይህ ምልክት ከእናንተ ጋር ለገባሁት ዘላቂ ቃል ኪዳን ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል። +14 ሸለፈቱ እንዲገረዝ የማያደርግ ያልተገረዘ ወንድ ካለ ያ ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።* ይህ ሰው ቃል ኪዳኔን አፍርሷል።” +15 ከዚያም አምላክ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “ሚስትህን ሦራን+ በተመለከተ ሦራ* ብለህ አትጥራት፤ ምክንያቱም ከእንግዲህ ስሟ ሣራ* ይሆናል። +16 እኔም እባርካታለሁ፤ ከእሷም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ።+ እባርካታለሁ፤ እሷም ብዙ ብሔር ትሆናለች፤ የሕዝቦች ነገሥታትም ከእሷ ይወጣሉ።” +17 በዚህ ጊዜ አብርሃም በግንባሩ ተደፋ፤ እየሳቀም በልቡ እንዲህ አለ፦+ “እንዲያው ምንስ ቢሆን 100 ዓመት የሆነው ሰው የልጅ አባት ሊሆን ይችላል? ዘጠና ዓመት የሆናት ሣራስ ብትሆን ልጅ ልትወልድ ትችላለች?”+ +18 ስለዚህ አብርሃም እውነተኛውን አምላክ “ምነው እስማኤልን ብቻ በባረክልኝ!”+ አለው። +19 አምላክም እንዲህ አለው፦ “ሚስትህ ሣራ በእርግጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ*+ ትለዋለህ። እኔም ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ ጭምር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እንዲሆን ከእሱ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ።+ +20 እስማኤልን በተመለከተም ልመናህን ሰምቻለሁ። እሱንም ቢሆን እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማ አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ። ደግሞም 12 አለቆች ከእሱ ይወጣሉ፤ ታላቅ ብሔርም አደርገዋለሁ።+ +21 ሆኖም የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ+ ከይስሐቅ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታ��ሁ።”+ +22 አምላክ ከአብርሃም ጋር ተነጋግሮ ሲያበቃ ከእሱ ተለይቶ ወደ ላይ ወጣ። +23 ከዚያም አብርሃም ልጁን እስማኤልን፣ በቤቱ የተወለዱትንና በገንዘቡ የገዛቸውን ወንዶች ሁሉ እንዲሁም በአብርሃም ቤት የሚገኙትን ወንዶች ሁሉ ወስዶ ልክ አምላክ በነገረው መሠረት በዚያኑ ዕለት ሸለፈታቸውን ገረዘ።+ +24 አብርሃም ሸለፈቱን ሲገረዝ የ99 ዓመት ሰው ነበር።+ +25 ልጁ እስማኤል ሸለፈቱን በተገረዘበት ጊዜ ደግሞ 13 ዓመቱ ነበር።+ +26 በዚሁ ዕለት አብርሃም ተገረዘ፤ ልጁ እስማኤልም ተገረዘ። +27 በተጨማሪም በቤቱ የሚገኙ ወንዶች ሁሉ፣ በቤት የተወለዱ ሁሉ እንዲሁም ከባዕድ ሰው በገንዘብ የተገዙ ሁሉ ከእሱ ጋር ተገረዙ። +30 ራሔል ለያዕቆብ ምንም ልጅ እንዳልወለደችለት ባየች ጊዜ በእህቷ ቀናች፤ ያዕቆብንም “ልጆች ስጠኝ፤ አለዚያ እሞታለሁ” ትለው ጀመር። +2 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ራሔልን በጣም ተቆጥቶ “እኔ፣ እንዳትወልጂ ያደረገሽን* አምላክ መሰልኩሽ እንዴ?” አላት። +3 እሷም በዚህ ጊዜ “ባሪያዬ ባላ+ ይችውልህ፤ ልጆች እንድትወልድልኝና* እኔም በእሷ አማካኝነት ልጆች እንዳገኝ ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጽም” አለችው። +4 በዚህ መሠረት አገልጋይዋን ባላን ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው፤ ያዕቆብም ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጸመ።+ +5 ባላም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። +6 ራሔልም “አምላክ ዳኛ ሆነልኝ፤ ቃሌንም ሰማ። በመሆኑም ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች። በዚህም የተነሳ ስሙን ዳን*+ አለችው። +7 የራሔል አገልጋይ ባላ በድጋሚ ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። +8 ራሔልም “ከእህቴ ጋር ብርቱ ትግል ገጠምኩ፤ አሸናፊም ሆንኩ!” አለች። በመሆኑም ስሙን ንፍታሌም*+ አለችው። +9 ሊያ ልጅ መውለድ እንዳቆመች ስትረዳ አገልጋይዋን ዚልጳን ለያዕቆብ ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው።+ +10 የሊያም አገልጋይ ዚልጳ ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። +11 ከዚያም ሊያ “ምንኛ መታደል ነው!” አለች። በመሆኑም ስሙን ጋድ*+ አለችው። +12 ከዚያ በኋላ የሊያ አገልጋይ ዚልጳ ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። +13 ከዚያም ሊያ “ምንኛ ደስተኛ ነኝ! በእርግጥም ከእንግዲህ ሴቶች ደስተኛ ይሉኛል”+ አለች። በመሆኑም ስሙን አሴር*+ አለችው። +14 የስንዴ መከር በሚሰበሰብበት ወቅት ሮቤል+ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከሜዳውም ላይ ፍሬ* ለቀመ። ለእናቱ ለሊያም አመጣላት። ከዚያም ራሔል ሊያን “እባክሽ፣ ልጅሽ ካመጣው ፍሬ የተወሰነ ስጪኝ” አለቻት። +15 በዚህ ጊዜ ሊያ “ባሌን የወሰድሽብኝ አነሰሽና+ አሁን ደግሞ ልጄ ያመጣውን ፍሬ መውሰድ ትፈልጊያለሽ?” አለቻት። በመሆኑም ራሔል “እሺ፣ ልጅሽ ባመጣው ፍሬ ፋንታ ዛሬ ማታ ከአንቺ ጋር ይደር” አለቻት። +16 ያዕቆብ የዚያን ቀን ምሽት ከእርሻ ሲመለስ ሊያ ወጥታ ተቀበለችውና “ልጄ ባመጣው ፍሬ ስለተከራየሁህ ዛሬ የምትተኛው ከእኔ ጋር ነው” አለችው። ስለሆነም በዚያ ሌሊት ከእሷ ጋር አደረ። +17 አምላክም ሊያን ሰማት፤ መልስም ሰጣት፤ እሷም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ አምስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። +18 ሊያም “አገልጋዬን ለባሌ ስለሰጠሁ አምላክ ደሞዜን* ከፈለኝ” አለች። በመሆኑም ስሙን ይሳኮር*+ አለችው። +19 ሊያም በድጋሚ ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ስድስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት።+ +20 ሊያም “አምላክ አድሎኛል፤ አዎ፣ መልካም ስጦታ ሰጥቶኛል። ለባሌ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለወለድኩለት+ ከእንግዲህ ይታገሠኛል”+ አለች። በመሆኑም ስሙን ዛብሎን*+ አለችው። +21 ከዚያ በኋላ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ዲና+ አለቻት። +22 በመጨረሻም አምላክ ራሔልን አሰባት፤ ልመናዋንም ሰምቶ መፀነስ እንድትችል በማድረግ* ጸሎቷን መለሰላት።+ +23 እሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። ከዚያም “አምላክ ነቀፋዬን አስወገደልኝ!”+ አለች። +24 በመሆኑም “ይሖዋ ሌላ ወንድ ልጅ ጨመረልኝ” በማለት ስሙን ዮሴፍ*+ አለችው። +25 ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ስፍራዬና ወደ ምድሬ እንድመለስ አሰናብተኝ።+ +26 ለእነሱ ስል ያገለገልኩህን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያህል እንዳገለገልኩህ በሚገባ ታውቃለህ።”+ +27 ከዚያም ላባ “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ ከእኔ ጋር ተቀመጥ፤ ይሖዋ እየባረከኝ ያለው በአንተ የተነሳ መሆኑን በንግርት* ተረድቻለሁ” አለው። +28 ከዚያም “ደሞዝህን አሳውቀኝና እሰጥሃለሁ”+ አለው። +29 በመሆኑም ያዕቆብ እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልኩህና መንጋህም ምን ያህል እየበዛልህ እንዳለ ታውቃለህ፤+ +30 እኔ ከመምጣቴ በፊት የነበረህ ነገር ጥቂት እንደሆነና እኔ ከመጣሁ በኋላ ግን ከብቶችህ በጣም እየበዙ እንደሄዱ፣ ይሖዋም እንደባረከህ ታውቃለህ። ታዲያ ለራሴ ቤት አንድ ነገር የማደርገው መቼ ነው?”+ +31 ከዚያም ላባ “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” አለው። ያዕቆብም እንዲህ አለ፦ “እኔ ምንም ነገር እንድትሰጠኝ አልፈልግም! የምጠይቅህን አንድ ነገር ብቻ የምታደርግልኝ ከሆነ መንጋህን መጠበቄንና መንከባከቤን እቀጥላለሁ።+ +32 ዛሬ በመንጎችህ ሁሉ መካከል እዘዋወራለሁ። አንተም ከመንጋው መካከል ጠቃጠቆ ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን በጎች ሁሉ፣ ከጠቦቶቹም መካከል ጥቁር ቡናማ የሆኑትን በጎች ሁሉ እንዲሁም ዥጉርጉር የሆኑትንና ጠቃጠቆ ያለባቸውን እንስት ፍየሎች ሁሉ ለይ። ከዚህ በኋላ እንዲህ ዓይነቶቹ የእኔ ደሞዝ ይሆናሉ።+ +33 ወደፊት ደሞዜን ለመመልከት በምትመጣበት ጊዜ ጽድቄ* ስለ እኔ ይናገራል፤ ከእንስት ፍየሎቹ መካከል ጠቃጠቆ የሌለበትና ዥጉርጉር ያልሆነ እንዲሁም ከጠቦቶቹ መካከል ጥቁር ቡናማ ያልሆነ በእኔ ዘንድ ከተገኘ ያ የተሰረቀ እንደሆነ ይቆጠራል።” +34 በዚህ ጊዜ ላባ “ይሄማ ጥሩ ነው! እንዳልከው ይሁን” አለው።+ +35 ከዚያም በዚያኑ ቀን ሽንትር ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን ተባዕት ፍየሎች ሁሉ፣ ጠቃጠቆ ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን እንስት ፍየሎች ሁሉ፣ ነጭ የሚባል ነገር ያለበትን ሁሉ እንዲሁም ከጠቦቶቹ መካከል ጥቁር ቡናማ የሆኑትን ሁሉ ለየ፤ እነዚህንም ወንዶች ልጆቹ እንዲጠብቋቸው ሰጣቸው። +36 ከዚህ በኋላ በእሱና በያዕቆብ መካከል የሦስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት እንዲኖር አደረገ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጎች ይጠብቅ ጀመር። +37 ከዚያም ያዕቆብ ከሊብነህ፣* ከአልሞንድና ከአርሞን* ዛፎች ላይ የተቆረጡ እርጥብ በትሮችን ወሰደ፤ በመቀጠልም በትሮቹን አለፍ አለፍ ብሎ በመላጥና ነጩ እንዲታይ በማድረግ ዥጉርጉር እንዲሆኑ አደረገ። +38 ከዚያም የላጣቸውን በትሮች ወስዶ መንጎቹ ውኃ ለመጠጣት ሲመጡ እንዲያዩአቸው በመንጎቹ ፊት ለፊት በቦዮቹ ማለትም ውኃ በሚጠጡባቸው ገንዳዎች ውስጥ አስቀመጣቸው፤ ይህን ያደረገውም መንጎቹ ውኃ ለመጠጣት ሲመጡ በበትሮቹ ፊት ለስሪያ እንዲነሳሱ ለማድረግ ነው። +39 ስለዚህ መንጎቹ በበትሮቹ ፊት ለስሪያ ይነሳሱ ነበር፤ መንጎቹም ሽንትርና ጠቃጠቆ ያለባቸውን እንዲሁም ዥጉርጉር የሆኑ ግልገሎችን ይወልዱ ነበር። +40 ከዚያም ያዕቆብ ጠቦቶቹን ለየ፤ ከዚያም መንጎቹ በላባ መንጎች መካከል ወዳሉት ሽንትር ወዳለባቸውና ጥቁር ቡናማ ወደሆኑት ሁሉ እንዲመለከቱ አደረገ። ከዚያም የራሱን መንጎች ለየ፤ ከላባ መንጎች ጋር አልቀላቀላቸውም። +41 ያዕቆብም ብርቱ የሆኑት እንስሳት ለስሪያ በተነሳሱ ቁጥር በትሮቹ�� በመንጎቹ ፊት ለፊት ገንዳዎቹ ውስጥ ያስቀምጣቸው ነበር፤ እንዲህ የሚያደርገው መንጎቹ በበትሮቹ አማካኝነት ለስሪያ እንዲነሳሱ ለማድረግ ነበር። +42 እንስሶቹ ደካማ ሲሆኑ ግን በትሮቹን ገንዳዎቹ ውስጥ አያስቀምጥም ነበር። ስለሆነም ደካማ ደካማዎቹ ለላባ ሲሆኑ ብርቱ ብርቱዎቹ ግን ለያዕቆብ ሆኑ።+ +43 በዚህ መንገድ ይህ ሰው እጅግ ባለጸጋ እየሆነ ሄደ፤ የብዙ መንጎች፣ የወንድና የሴት አገልጋዮች፣ የግመሎች እንዲሁም የአህዮች ባለቤት ሆነ።+ +35 ከዚያ በኋላ አምላክ ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ተነስተህ ወደ ቤቴል+ ውጣ፤ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከኤሳው እየሸሸህ+ ሳለህ ለተገለጠልህ ለእውነተኛው አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ።” +2 ከዚያም ያዕቆብ ቤተሰቡንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “በመካከላችሁ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤+ ራሳችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ቀይሩ፤ +3 ተነስተንም ወደ ቤቴል እንውጣ። በዚያም በጭንቀቴ ጊዜ ለሰማኝና በሄድኩበት ሁሉ* ከእኔ ላልተለየው+ ለእውነተኛው አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።” +4 በመሆኑም ባዕዳን አማልክታቸውን በሙሉ እንዲሁም በጆሯቸው ላይ ያደረጓቸውን ጉትቻዎች ለያዕቆብ ሰጡት፤ ያዕቆብም በሴኬም አቅራቢያ ባለው ትልቅ ዛፍ ሥር ቀበራቸው።* +5 በሚጓዙበት ጊዜም አምላክ በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ላይ ሽብር ይለቅባቸው ስለነበር የያዕቆብን ልጆች አላሳደዷቸውም። +6 በመጨረሻም ያዕቆብና አብረውት ያሉት ሰዎች በሙሉ በከነአን ምድር ወደምትገኘው ወደ ሎዛ+ ማለትም ወደ ቤቴል መጡ። +7 እሱም በዚያ መሠዊያ ሠራ፤ የቦታውንም ስም ኤልቤቴል* አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ በሸሸበት ጊዜ እውነተኛው አምላክ በዚያ ራሱን ገልጦለት ነበር።+ +8 በኋላም የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ+ ሞተች፤ በቤቴል አቅራቢያ በሚገኝ የባሉጥ ዛፍ ሥርም ተቀበረች። በመሆኑም ስሙን አሎንባኩት* አለው። +9 ያዕቆብ ከጳዳንአራም እየተመለሰ ሳለ አምላክ ዳግመኛ ተገለጠለትና ባረከው። +10 አምላክም “ስምህ ያዕቆብ ነው።+ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ከዚህ ይልቅ ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህ እስራኤል ብሎ ጠራው።+ +11 በተጨማሪም አምላክ እንዲህ አለው፦ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ።+ ብዛ፣ ተባዛ። ብሔራትና ብዙ ብሔራትን ያቀፈ ጉባኤ ከአንተ ይገኛሉ፤+ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ።*+ +12 ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህም ይህችን ምድር እሰጣለሁ።”+ +13 ከዚያም አምላክ ከእሱ ጋር ሲነጋገርበት ከነበረው ስፍራ ወደ ላይ ወጣ። +14 ስለዚህ ያዕቆብ ከአምላክ ጋር ሲነጋገር በነበረበት ስፍራ ላይ የድንጋይ ዓምድ አቆመ፤ ባቆመውም ዓምድ ላይ የመጠጥ መባና ዘይት አፈሰሰበት።+ +15 ያዕቆብም ከአምላክ ጋር የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል+ በሚለው በዚያው ስም ጠራው። +16 ከዚያም ከቤቴል ተነስተው ሄዱ። ኤፍራታ ለመድረስ የተወሰነ ርቀት ሲቀራቸው ራሔል ምጥ ያዛት፤ ምጡም እጅግ ጠናባት። +17 ምጡ እጅግ አስጨንቋት ሳለም አዋላጇ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ሌላ ወንድ ልጅ ልትገላገዪ ነው” አለቻት።+ +18 እሷ ግን ሕይወቷ ሊያልፍ በማጣጣር ላይ ሳለች* (ሞት አፋፍ ላይ ስለነበረች) የልጁን ስም ቤንኦኒ* አለችው፤ አባቱ ግን ስሙን ቢንያም*+ አለው። +19 ራሔልም ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ ይኸውም ወደ ቤተልሔም+ በሚወስደው መንገድ ላይ ተቀበረች። +20 ያዕቆብም በመቃብሯ ላይ ዓምድ አቆመ፤ ይህ የራሔል መቃብር ዓምድ እስከ ዛሬ ድረስ አለ። +21 ከዚያ በኋላ እስራኤል ከዚያ ተነስቶ በመሄድ ከኤዴር ማማ አለፍ ብሎ ድንኳኑን ተከለ። +22 አንድ ቀን፣ እስራኤል በዚያ ምድር ሰፍሮ ሳለ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር ተኛ፤ እስራኤልም ይህን ሰማ።+ ያዕቆብ 12 ወንዶች ልጆች ነበሩት። +23 ከሊያ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ የበኩር ልጁ ሮቤል+ ከዚያም ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር እና ዛብሎን ነበሩ። +24 ከራሔል የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዮሴፍና ቢንያም ነበሩ። +25 ከራሔል አገልጋይ ከባላ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዳንና ንፍታሌም ነበሩ። +26 ከሊያ አገልጋይ ከዚልጳ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ደግሞ ጋድና አሴር ነበሩ። እነዚህ ያዕቆብ በጳዳንአራም ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ናቸው። +27 ከጊዜ በኋላ ያዕቆብ አባቱ ይስሐቅ ወደነበረበት፣ አብርሃምና ይስሐቅ የባዕድ አገር ሰው ሆነው ወደኖሩበት+ በቂርያትአርባ ይኸውም በኬብሮን አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ማምሬ መጣ።+ +28 ይስሐቅ 180 ዓመት ኖረ።+ +29 ከዚያም ይስሐቅ የመጨረሻ እስትንፋሱን ተነፈሰ፤ ዕድሜ ጠግቦና በሕይወቱ ረክቶ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ፤* ልጆቹ ኤሳውና ያዕቆብም ቀበሩት።+ +31 ከጊዜ በኋላ ያዕቆብ፣ የላባ ልጆች “ያዕቆብ የአባታችንን ንብረት እንዳለ ወስዷል፤ ይህን ሁሉ ሀብት ያካበተው እኮ ከአባታችን ንብረት ነው”+ ሲሉ ሰማ። +2 ያዕቆብ የላባን ፊት ሲመለከት ፊቱ እንደተለወጠበት አስተዋለ።+ +3 በመጨረሻም ይሖዋ ያዕቆብን “ወደ አባቶችህና ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤+ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው። +4 ከዚያም ያዕቆብ ራሔልና ሊያ መንጎቹን ወዳሰማራበት መስክ እንዲመጡ መልእክት ላከባቸው፤ +5 እንዲህም አላቸው፦ “አባታችሁን ሳየው ፊቱ ተለውጦብኛል፤+ የአባቴ አምላክ ግን ከእኔ አልተለየም።+ +6 መቼም አባታችሁን ባለኝ አቅም ሁሉ እንዳገለገልኩት እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁ።+ +7 አባታችሁ ሊያጭበረብረኝ ሞክሯል፤ ደሞዜንም አሥር ጊዜ ቀያይሮብኛል፤ አምላክ ግን ጉዳት እንዲያደርስብኝ አልፈቀደለትም። +8 ‘ደሞዝህ ዥጉርጉር የሆኑት ይሆናሉ’ ሲለኝ መንጎቹ ሁሉ ዥጉርጉር ወለዱ፤ ‘ደሞዝህ ሽንትር ያለባቸው ይሆናሉ’ ሲለኝ ደግሞ መንጎቹ ሁሉ ሽንትር ያለባቸው ወለዱ።+ +9 ስለዚህ አምላክ የአባታችሁን ከብቶች ከእሱ እየወሰደ ለእኔ ይሰጠኝ ነበር። +10 በአንድ ወቅት፣ መንጎቹ ለስሪያ በሚነሳሱበት ጊዜ እንስቶቹን የሚያጠቁት አውራ ፍየሎች ሽንትር ያለባቸው፣ ዥጉርጉር የሆኑና ጠቃጠቆ ያለባቸው መሆናቸውን በሕልሜ አየሁ።+ +11 ከዚያም የእውነተኛው አምላክ መልአክ በሕልሜ ‘ያዕቆብ!’ ሲል ጠራኝ፤ እኔም ‘አቤት’ አልኩት። +12 እሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘እንስቶቹን የሚያጠቁት አውራ ፍየሎች ሁሉ ሽንትር ያለባቸው፣ ዥጉርጉር የሆኑና ጠቃጠቆ ያለባቸው መሆናቸውን እባክህ ቀና ብለህ ተመልከት፤ ምክንያቱም ላባ እየፈጸመብህ ያለውን ነገር ሁሉ ተመልክቻለሁ።+ +13 ዓምድ አቁመህ የቀባህበትና በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልክበት የቤቴል+ እውነተኛው አምላክ እኔ ነኝ።+ በል አሁን ተነስተህ ከዚህ ምድር ውጣ፤ ወደተወለድክበትም ምድር ተመለስ።’”+ +14 በዚህ ጊዜ ራሔልና ሊያ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “እንደው ለመሆኑ በአባታችን ቤት ልንወርሰው የምንችለው የቀረ ነገር ይኖራል? +15 እሱ እኛን የሸጠንና ለእኛ የተሰጠውን ገንዘብ የበላው እንደ ባዕድ ስለሚያየን አይደለም?+ +16 አምላክ ከአባታችን ላይ የወሰደበት ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው።+ ስለሆነም አምላክ አድርግ ያለህን ነገር ሁሉ አድርግ።”+ +17 ከዚያም ያዕቆብ ተነሳ፤ ልጆቹንና ሚስቶቹን ግመል ላይ አስቀመጣቸው፤+ +18 እንዲሁም መንጎቹን ሁሉና ያከማቸውን ንብረት ሁሉ፣+ በጳዳንአራም ሳለ ያገኛቸውንም ከብቶች ሁሉ እየነዳ በከነአን ምድር ወደሚገኘው ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ለመሄድ ጉዞ ጀመረ።+ +19 በዚህ ጊ�� ላባ በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር፤ ራሔልም የአባቷን+ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾች*+ ሰረቀች። +20 ያዕቆብም ቢሆን ለአራማዊው ለላባ ሳይነግረው ሊኮበልል በመነሳቱ አታሎታል። +21 ያዕቆብም ያለውን ሁሉ ይዞ ኮበለለ፤ ወንዙንም*+ ተሻግሮ ሄደ። ከዚያም ጊልያድ+ ወደተባለው ተራራማ አካባቢ አቀና። +22 በሦስተኛውም ቀን የያዕቆብ መኮብለል ለላባ ተነገረው። +23 በመሆኑም ላባ ያዕቆብ ላይ ለመድረስ ወንድሞቹን* አስከትሎ የሰባት ቀን መንገድ ተጓዘ፤ ከዚያም ጊልያድ በተባለው ተራራማ አካባቢ ደረሰበት። +24 ከዚያም አምላክ ለአራማዊው+ ለላባ ሌሊት በሕልም ተገልጦለት+ “ክፉም ሆነ ደግ ያዕቆብን ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ”* አለው።+ +25 ያዕቆብ በተራራው ላይ ድንኳኑን ተክሎ ሳለ ላባ ወደ ያዕቆብ ቀረበ፤ ላባም ከወንድሞቹ ጋር ጊልያድ በተባለው ተራራማ አካባቢ ሰፈረ። +26 ከዚያም ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ይህ ያደረግከው ነገር ምንድን ነው? እኔን ለማታለል የተነሳሳኸውና ሴት ልጆቼን በሰይፍ እንደተማረከ ምርኮኛ አስገድደህ የወሰድካቸው ለምንድን ነው? +27 ምንም ሳትነግረኝ ተደብቀህ የሸሸኸውና ያታለልከኝስ ለምንድን ነው? ነግረኸኝ ቢሆን ኖሮ በደስታና በዘፈን፣ በአታሞና በበገና እሸኝህ ነበር። +28 አንተ ግን የልጅ ልጆቼንና* ሴቶች ልጆቼን ስሜ እንድሰናበት እንኳ ዕድል አልሰጠኸኝም። የሠራኸው የሞኝነት ሥራ ነው። +29 እናንተን መጉዳት እችል ነበር፤ ሆኖም ትናንት ሌሊት የአባታችሁ አምላክ ‘ክፉም ሆነ ደግ ያዕቆብን ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ’ አለኝ።+ +30 እሺ፣ አንተ ለመሄድ የተነሳኸው ወደ አባትህ ቤት ለመመለስ ስለናፈቅክ ነው፤ ሆኖም አማልክቴን+ የሰረቅከው ለምንድን ነው?” +31 ያዕቆብ ለላባ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እንዲህ ያደረግኩት ‘ሴቶች ልጆችህን በኃይል ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ’ ብዬ ስለፈራሁ ነው። +32 አማልክትህን ያገኘህበት ማንኛውም ሰው ይገደል። በወንድሞቻችን ፊት ንብረቴን ፈትሽና የእኔ ነው የምትለውን ውሰድ።” ይሁንና ያዕቆብ ራሔል ጣዖቶቹን እንደሰረቀች አላወቀም ነበር። +33 በመሆኑም ላባ ወደ ያዕቆብ ድንኳን ገባ፤ ከዚያም ወደ ሊያ ድንኳን እንዲሁም ወደ ሁለቱ ሴት ባሪያዎች+ ድንኳን ገባ፤ ሆኖም ምንም አላገኘም። ከዚያም ከሊያ ድንኳን ወጥቶ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ። +34 በዚህ ጊዜ ራሔል የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹን በግመል ኮርቻ ላይ በሚገኘው የሴቶች ዕቃ ማስቀመጫ ውስጥ ከትታ በላያቸው ላይ ተቀምጣ ነበር። በመሆኑም ላባ ድንኳኑን በሙሉ በረበረ፤ ሆኖም ምንም አላገኘም። +35 ከዚያም ራሔል አባቷን “ጌታዬ፣ ስላልተነሳሁልህ አትቆጣ፤ የሴቶች ልማድ+ ደርሶብኝ ነው” አለችው። ስለዚህ ላባ በጥንቃቄ ፈተሸ፤ ይሁንና የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹን+ አላገኘም። +36 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ተቆጣ፤ ላባንም ወቀሰው። ከዚያም ላባን እንዲህ አለው፦ “እስቲ የፈጸምኩት በደል ምንድን ነው? እንደዚህ በቁጣ ገንፍለህ የምታሳድደኝ ምን ኃጢአት ሠርቼ ነው? +37 ይኸው ዕቃዬን ሁሉ ፈትሸሃል፤ ታዲያ የቤትህ ንብረት የሆነ ምን ነገር አገኘህ? እስቲ በወንድሞቼና በወንድሞችህ ፊት አስቀምጠውና እነሱ በሁለታችን መካከል ይፍረዱ። +38 ከአንተ ጋር አብሬ በኖርኩባቸው በእነዚህ 20 ዓመታት ውስጥ በጎችህና ፍየሎችህ ጨንግፈው አያውቁም፤+ እኔም ከመንጋህ መካከል አንዲት በግ እንኳ አልበላሁም። +39 አውሬ የቦጫጨቀውን እንስሳ+ አምጥቼልህ አላውቅም። ኪሳራውን በራሴ ላይ ቆጥሬ እከፍልህ ነበር። በቀንም ይሁን በሌሊት አንድ እንስሳ ቢሰረቅ ታስከፍለኝ ነበር። +40 ቀን በሐሩር፣ ሌሊት ደግሞ በቁር ስሠቃይ ኖሬአለሁ፤ እንቅልፍም በዓይኔ አይዞርም ነበር።+ +41 እንግዲ��� 20 ዓመት ሙሉ በቤትህ የኖርኩት በዚህ ሁኔታ ነበር። ለሁለት ሴቶች ልጆችህ ስል 14 ዓመት፣ ለመንጋህ ስል ደግሞ 6 ዓመት አገለገልኩህ። አንተ ግን ደሞዜን አሥር ጊዜ ትቀያይርብኝ ነበር።+ +42 የአባቴ አምላክ፣+ የአብርሃም አምላክና ይስሐቅ የሚፈራው አምላክ*+ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን ታሰናብተኝ ነበር። አምላክ ጉስቁልናዬንና ልፋቴን አየ፤ ትናንት ሌሊት የገሠጸህም ለዚህ ነው።”+ +43 ከዚያም ላባ ለያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ሴቶቹ የገዛ ልጆቼ ናቸው፤ ልጆቹም ቢሆኑ ልጆቼ ናቸው፤ መንጋውም ቢሆን የእኔው መንጋ ነው፤ የምታየው ነገር ሁሉ የእኔና የሴት ልጆቼ ነው። ታዲያ ዛሬ በእነዚህም ሆነ በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ምን ማድረግ እችላለሁ? +44 በል አሁን ና፣ እኔና አንተ ቃል ኪዳን እንጋባ፤ ይህም በእኔና በአንተ መካከል ምሥክር ሆኖ ያገለግላል።” +45 ስለዚህ ያዕቆብ ድንጋይ ወስዶ እንደ ዓምድ አቆመው።+ +46 ከዚያም ያዕቆብ ወንድሞቹን “ድንጋይ ሰብስቡ!” አላቸው። እነሱም ድንጋይ እያመጡ ከመሩ። በኋላም እዚያው ድንጋዩ ክምር ላይ በሉ። +47 ላባም የድንጋዩን ክምር ያጋርሳሃዱታ* አለው፤ ያዕቆብ ግን ጋልኢድ* ሲል ጠራው። +48 ከዚያም ላባ “ይህ የድንጋይ ክምር ዛሬ በእኔና በአንተ መካከል ምሥክር ነው” አለ። ከዚህም የተነሳ ያዕቆብ ጋልኢድ+ +49 እና መጠበቂያ ግንብ የሚል ስም አወጣለት፤ ምክንያቱም ላባ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “እርስ በርስ በማንተያይበት ጊዜ ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ጠባቂ ይሁን። +50 ልጆቼን ብትበድላቸውና በእነሱ ላይ ሌሎች ሚስቶችን ብታገባ ማንም ሰው ባያይም እንኳ አምላክ በእኔና በአንተ መካከል ምሥክር እንደሆነ አትርሳ።” +51 ላባም ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “የድንጋይ ክምሩ ይኸው፤ በእኔና በአንተ መካከል ያቆምኩት ዓምድም ይኸው። +52 እኔ አንተን ለመጉዳት ይህን የድንጋይ ክምር አልፌ ላልመጣ፣ አንተም እኔን ለመጉዳት ይህን የድንጋይ ክምርና ይህን ዓምድ አልፈህ ላትመጣ ይህ የድንጋይ ክምር ምሥክር ነው፤+ ዓምዱም ቢሆን ምሥክር ይሆናል። +53 የአብርሃም አምላክና*+ የናኮር አምላክ የሆነው የአባታቸው አምላክ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም አባቱ ይስሐቅ በሚፈራው አምላክ*+ ማለ። +54 ከዚያ በኋላ ያዕቆብ በተራራው ላይ መሥዋዕት አቀረበ። ወንድሞቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው። እነሱም ምግብ በሉ፤ በተራራውም ላይ አደሩ። +55 ላባም በማግስቱ ጠዋት ተነስቶ የልጅ ልጆቹንና*+ ሴቶች ልጆቹን ስሞ መረቃቸው።+ ተነስቶም ወደ ቤቱ ተመለሰ።+ +18 ከዚያም አብርሃም በጣም ሞቃታማ በሆነው የቀኑ ክፍለ ጊዜ ድንኳኑ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ሳለ ይሖዋ+ በማምሬ ትላልቅ ዛፎች+ አጠገብ ተገለጠለት። +2 ቀና ብሎም ሲመለከት እሱ ካለበት ትንሽ ራቅ ብሎ ሦስት ሰዎች ቆመው አየ።+ ሰዎቹን ባያቸው ጊዜም ከድንኳኑ ደጃፍ ተነስቶ ወደ እነሱ እየሮጠ ሄደ፤ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም ሰገደ። +3 ከዚያም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ፣ እንግዲህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ አገልጋይህን አልፈኸው አትሂድ። +4 እባካችሁ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤+ ከዚያም ከዛፉ ሥር አረፍ በሉ። +5 ወደ አገልጋያችሁ ከመጣችሁ አይቀር፣ ብርታት እንድታገኙ* ትንሽ እህል ላምጣላችሁና ቅመሱ፤ ከዚያም ጉዟችሁን ትቀጥላላችሁ።” በዚህ ጊዜ እነሱ “እሺ፣ እንዳልከው አድርግ” አሉት። +6 በመሆኑም አብርሃም ሣራ ወዳለችበት ወደ ድንኳኑ በፍጥነት ሄዶ “ቶሎ በይ! ሦስት መስፈሪያ* የላመ ዱቄት ወስደሽ አቡኪና ቂጣ ጋግሪ” አላት። +7 በመቀጠልም አብርሃም ወደ መንጋው ሮጦ በመሄድ ሥጋው ገር የሆነ ፍርጥም ያለ ወይፈን መረጠ። ለአገልጋዩም ሰጠው፤ እሱም ለማዘጋጀት ተጣደፈ። +8 ከዚያም ቅቤና ወተት እንዲሁም ያዘጋጀውን ወይፈን ወስዶ ምግቡን አቀረበላቸው። እየበሉ ሳሉም ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር።+ +9 እነሱም “ሚስትህ ሣራ+ የት አለች?” አሉት። እሱም “እዚህ ድንኳኑ ውስጥ ናት” አላቸው። +10 ከመካከላቸውም አንዱ ንግግሩን በመቀጠል “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ በእርግጥ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች”+ አለ። በዚህ ጊዜ ሣራ ከሰውየው በስተ ጀርባ ባለው በድንኳኑ ደጃፍ ላይ ሆና ታዳምጥ ነበር። +11 አብርሃምና ሣራ አርጅተው፣ ዕድሜያቸውም ገፍቶ ነበር።+ ሣራ ልጅ የመውለጃዋ ዕድሜ አልፎ ነበር።*+ +12 በመሆኑም ሣራ “አሁን እንዲህ አርጅቼ ጌታዬም ዕድሜው ገፍቶ እያለ በእርግጥ እንዲህ ዓይነት ደስታ ላገኝ እችላለሁ?”+ ብላ በማሰብ በልቧ ሳቀች። +13 ከዚያም ይሖዋ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “ሣራ ‘እንዲህ ካረጀሁ በኋላም እንኳ ልወልድ ነው ማለት ነው?’ በማለት የሳቀችው ለምንድን ነው? +14 ለይሖዋ የሚሳነው ነገር አለ?+ የዛሬ ዓመት በዚሁ በተወሰነው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች።” +15 ሣራ ግን ስለፈራች “ኧረ አልሳቅኩም!” ስትል ካደች። በዚህ ጊዜ “እንዴ! ሳቅሽ እንጂ” አላት። +16 ሰዎቹም ለመሄድ በተነሱና ቁልቁል ወደ ሰዶም+ በተመለከቱ ጊዜ አብርሃም ሊሸኛቸው አብሯቸው ሄደ። +17 ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “እኔ ላደርገው ያሰብኩትን ነገር ከአብርሃም ደብቄ አውቃለሁ?+ +18 አብርሃም በእርግጥ ታላቅና ኃያል ብሔር ይሆናል፤ የምድር ብሔራትም ሁሉ በእሱ አማካኝነት ይባረካሉ።*+ +19 እኔ ከአብርሃም ጋር የተዋወቅኩት ትክክለኛና ተገቢ የሆነውን ነገር በማድረግ የይሖዋን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእሱ በኋላ የሚመጣውን ቤተሰቡን እንዲያዝዝ ነው፤+ እንዲህ ካደረገ ይሖዋ አብርሃምን አስመልክቶ ቃል የገባውን ነገር ይፈጽምለታል።” +20 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ጩኸት በእርግጥም ታላቅ ነው፤+ ኃጢአታቸውም እጅግ ከባድ ሆኗል።+ +21 ድርጊታቸው እኔ ዘንድ እንደደረሰው ጩኸት መሆን አለመሆኑን ለማየት ወደዚያ እወርዳለሁ። ነገሩ እንደዚያ ካልሆነም ማወቅ እችላለሁ።”+ +22 ሰዎቹም ከዚያ ተነስተው ወደ ሰዶም አቀኑ፤ ይሖዋ+ ግን እዚያው ከአብርሃም ጋር ቀረ። +23 ከዚያም አብርሃም ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፦ “በእርግጥ ጻድቁን ከኃጢአተኛው ጋር አብረህ ታጠፋለህ?+ +24 እስቲ በከተማዋ ውስጥ 50 ጻድቅ ሰዎች አሉ እንበል። ታዲያ ሁሉንም ዝም ብለህ ታጠፋቸዋለህ? በውስጧ ስለሚኖሩት 50 ጻድቃን ስትል ስፍራውን አትምርም? +25 በጻድቁም ሆነ በኃጢአተኛው ላይ ተመሳሳይ ነገር እንዲደርስ የሚያደርግ እንዲህ ዓይነት እርምጃ በመውሰድ ጻድቁን ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ላይ ትገድላለህ ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የማይሆን ነገር ነው!+ ይህ በአንተ ዘንድ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው።+ የምድር ሁሉ ዳኛ ትክክል የሆነውን ነገር አያደርግም?”+ +26 ከዚያም ይሖዋ “በሰዶም ከተማ ውስጥ 50 ጻድቅ ሰዎች ባገኝ ስለ እነሱ ስል ስፍራውን በሙሉ እምራለሁ” አለ። +27 አብርሃም ግን እንደገና እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መቼም እኔ ትቢያና አመድ ሆኜ ሳለሁ አንዴ ደፍሬ ከይሖዋ ጋር መነጋገር ጀምሬያለሁ። +28 ከ50ዎቹ ጻድቃን መካከል አምስት ጎደሉ እንበል። ታዲያ በአምስቱ የተነሳ መላዋን ከተማ ታጠፋለህ?” እሱም “በዚያ 45 ባገኝ ከተማዋን አላጠፋም”+ አለ። +29 አብርሃም ግን በድጋሚ “በዚያ 40 ተገኙ እንበል” አለው። እሱም መልሶ “ስለ 40ዎቹ ስል አላደርገውም” አለ። +30 አብርሃም ግን በመቀጠል “ይሖዋ እባክህ፣ አትቆጣና+ አሁንም ልናገር፤ እንደው በዚያ 30 ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እሱም “በዚያ 30 ካገኘሁ አላደርገውም” ሲል መለሰ። +31 አብርሃም ግን እንዲህ በማለት ቀጠለ፦ “መቼም አንዴ ደፍሬ ከይሖዋ ጋር መነጋገር ጀምሬያለሁ፤ እንደው በዚያ 20 ብቻ ቢገኙስ?” እሱም መልሶ “ስለ 20ዎቹ ስል አላጠፋትም” አለ። +32 በመጨረሻም አብርሃም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እባክህ፣ አትቆጣና አንድ ጊዜ ብቻ ልናገር፤ በዚያ አሥር ብቻ ቢገኙስ?” እሱም መልሶ “ስለ አሥሩ ስል አላጠፋትም” አለ። +33 ይሖዋም ከአብርሃም ጋር ተነጋግሮ ሲጨርስ ጉዞውን ቀጠለ፤+ አብርሃም ደግሞ ወደ ስፍራው ተመለሰ። +23 ሣራም 127 ዓመት ኖረች፤ ሣራ በሕይወት የኖረችው ይህን ያህል ዓመት ነበር።+ +2 ሣራም በቂርያትአርባ+ ይኸውም በከነአን ምድር+ በሚገኘው በኬብሮን+ ሞተች፤ አብርሃምም በሣራ ሞት ያዝንና ያለቅስ ጀመር። +3 ከዚያም አብርሃም ከሚስቱ አስከሬን አጠገብ ተነሳ፤ የሄትንም+ ወንዶች ልጆች እንዲህ አላቸው፦ +4 “እኔ በመካከላችሁ የምኖር የባዕድ አገር ሰውና ሰፋሪ ነኝ።+ አስከሬኔን ወስጄ እንድቀብር በመካከላችሁ የመቃብር ቦታ የሚሆን መሬት ስጡኝ።” +5 በዚህ ጊዜ የሄት ወንዶች ልጆች ለአብርሃም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ +6 “ስማን ጌታዬ። አንተ እኮ በመካከላችን አምላክ የመረጠህ አለቃ* ነህ።+ ካሉን የመቃብር ስፍራዎች ምርጥ በሆነው ቦታ አስከሬንህን መቅበር ትችላለህ። ከእኛ መካከል አስከሬንህን እንዳትቀብር የመቃብር ቦታውን የሚከለክልህ ማንም የለም።” +7 በመሆኑም አብርሃም ተነሳ፤ ለዚያ አገር ሰዎች ይኸውም ለሄት+ ወንዶች ልጆች ሰገደ፤ +8 እንዲህም አላቸው፦ “አስከሬኔን ወስጄ እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ* አንዴ ስሙኝ፤ የጾሃር ልጅ የሆነውን ኤፍሮንን +9 በእርሻ ቦታው ዳርቻ ላይ የሚገኘውን የእሱ ንብረት የሆነውን የማክፈላ ዋሻ እንዲሸጥልኝ ለምኑልኝ። የመቃብር ስፍራ የሚሆን ርስት+ እንዲኖረኝ ቦታው የሚያወጣውን ብር+ በሙሉ ልስጠውና በእናንተ ፊት ይሽጥልኝ።” +10 ኤፍሮን በሄት ወንዶች ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር። ስለሆነም ሂታዊው ኤፍሮን የሄት ወንዶች ልጆች እየሰሙ በከተማው በር+ በሚገቡት ሰዎች ሁሉ ፊት ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ +11 “የለም ጌታዬ! አዳምጠኝ። የእርሻ ቦታውንም ሆነ በውስጡ ያለውን ዋሻ ሰጥቼሃለሁ። የሕዝቤ ልጆች በተገኙበት ለአንተ ሰጥቼሃለሁ። አስከሬንህን በዚያ ቅበር።” +12 በዚህ ጊዜ አብርሃም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ፤ +13 የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ኤፍሮንን እንዲህ አለው፦ “ፈቃድህ ከሆነ ስማኝ! የእርሻ ቦታው የሚያወጣውን ብር በሙሉ እሰጥሃለሁ። አስከሬኔን በዚያ እንድቀብር ብሩን ተቀበለኝ።” +14 ከዚያም ኤፍሮን ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰ፦ +15 “ጌታዬ እኔ የምልህን ስማኝ። የዚህ መሬት ዋጋ 400 የብር ሰቅል* ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በአንተ መካከል ያን ያህል ትልቅ ነገር ሆኖ ነው? ይልቁንስ አስከሬንህን በዚያ ቅበር።” +16 አብርሃም፣ ኤፍሮን ያለውን ሰማ፤ አብርሃምም ኤፍሮን በሄት ወንዶች ልጆች ፊት የተናገረውን የብር መጠን ሰጠው፤ በነጋዴዎቹ ዘንድ ተቀባይነት ባለው ሚዛን መሠረት 400 ሰቅል* ብር ለኤፍሮን መዘነለት።+ +17 በዚህ መንገድ በማምሬ ፊት ለፊት የነበረው በማክፈላ የሚገኘው የኤፍሮን የእርሻ ቦታ ይኸውም የእርሻ ቦታው፣ በውስጡ ያለው ዋሻና በእርሻ ቦታው ክልል ውስጥ የሚገኙት ዛፎች በሙሉ +18 አብርሃም የገዛቸው ንብረቶች መሆናቸው የሄት ወንዶች ልጆች በተገኙበት በከተማው በር በሚገቡት ሰዎች ሁሉ ፊት ተረጋገጠ። +19 ከዚያ በኋላ አብርሃም ሚስቱን ሣራን በማምሬ ይኸውም በከነአን ምድር ባለው በኬብሮን ፊት ለፊት በሚገኘው በማክፈላ የእርሻ ቦታ ውስጥ ባለው ዋሻ ቀበራት። +20 በዚህ መንገድ የእርሻ ቦታውና በውስ��� የሚገኘው ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከሄት ወንዶች ልጆች ለአብርሃም በርስትነት ተሰጠ።+ +34 ያዕቆብ ከሊያ የወለዳት ዲና+ የተባለችው ልጅ እዚያ አገር ካሉ ወጣት ሴቶች ጋር ጊዜ ለማሳለፍ* ትወጣ ነበር።+ +2 የአገሩ አለቃ የሆነው የሂዋዊው+ የኤሞር ልጅ ሴኬም ዲናን አያት፤ ከዚያም ወሰዳትና አብሯት ተኛ፤ አስገድዶም ደፈራት። +3 እሱም ልቡ* በያዕቆብ ልጅ በዲና ተማረከ፤ ወጣቷንም አፈቀራት፤ በሚያባብሉ ቃላትም አነጋገራት።* +4 በመጨረሻም ሴኬም አባቱን ኤሞርን+ “ከዚህች ልጅ ጋር አጋባኝ” አለው። +5 ያዕቆብ፣ ሴኬም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት በሰማ ጊዜ ወንዶች ልጆቹ በመስክ መንጎቹን እየጠበቁ ነበር። በመሆኑም ያዕቆብ ልጆቹ እስኪመለሱ ድረስ ዝም አለ። +6 በኋላም የሴኬም አባት ኤሞር ከያዕቆብ ጋር ለመነጋገር ወጣ። +7 ሆኖም የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ስለ ሁኔታው ሰሙ፤ ወዲያውኑም ከመስክ መጡ። ሴኬም የያዕቆብን ሴት ልጅ በመድፈር ፈጽሞ መደረግ የማይገባውን ድርጊት ስለፈጸመና+ በዚህም እስራኤልን ስላዋረደ በጣም ተበሳጩ፤ እጅግም ተቆጡ።+ +8 ኤሞርም እንዲህ አላቸው፦ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን በጣም ወዷታል።* እባካችሁ ሚስት እንድትሆነው ስጡት፤ +9 በጋብቻም እንዛመድ። ሴቶች ልጆቻችሁን ዳሩልን፤ የእኛንም ሴቶች ልጆች አግቡ።+ +10 አብራችሁንም መኖር ትችላላችሁ፤ አገራችን አገራችሁ ናት። ኑሩባት፤ ነግዱባት፤ ሀብትም አፍሩባት።” +11 ከዚያም ሴኬም አባቷንና ወንድሞቿን እንዲህ አላቸው፦ “በፊታችሁ ሞገስ ላግኝ እንጂ የምትጠይቁኝን ሁሉ እሰጣለሁ። +12 ብዙ ጥሎሽና ስጦታ ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ።+ እኔ የጠየቃችሁኝን ሁሉ ለመስጠት ፈቃደኛ ነኝ። ብቻ ይህችን ወጣት ሚስቴ እንድትሆን ስጡኝ።” +13 የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም ሴኬም እህታቸውን ዲናን ስላስነወረ ለእሱና ለአባቱ ለኤሞር ተንኮል ያዘለ መልስ ሰጧቸው። +14 እንዲህም አሏቸው፦ “እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አናደርግም፤ እህታችንን ላልተገረዘ ሰው አንሰጥም፤+ ምክንያቱም ይህ ለእኛ ውርደት ነው። +15 በሐሳባችሁ የምንስማማው እኛን ከመሰላችሁና የእናንተ የሆነው ወንድ ሁሉ እንዲገረዝ ካደረጋችሁ ብቻ ነው።+ +16 ከዚያም ሴቶች ልጆቻችንን እንድርላችኋለን፤ እኛም ሴቶች ልጆቻችሁን እናገባለን፤ አብረናችሁም እንኖራለን፤ አንድ ሕዝብም እንሆናለን። +17 የምንላችሁን የማትሰሙና ለመገረዝ ፈቃደኛ የማትሆኑ ከሆነ ግን ልጃችንን ይዘን እንሄዳለን።” +18 የተናገሩትም ነገር ኤሞርንና+ ልጁን ሴኬምን+ ደስ አሰኛቸው። +19 ወጣቱም ያሉትን ነገር ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም፤+ ምክንያቱም የያዕቆብን ልጅ ወዷት ነበር፤ ደግሞም በአባቱ ቤት ካሉት ሰዎች ሁሉ እጅግ የተከበረ ነበር። +20 በመሆኑም ኤሞርና ልጁ ሴኬም ወደ ከተማዋ በር በመሄድ በከተማቸው የሚኖሩትን ወንዶች+ እንዲህ አሏቸው፦ +21 “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር በሰላም መኖር ይፈልጋሉ። ምድሪቱ ለእነሱም ስለምትበቃ በምድሪቱ ይኑሩ፤ እንዲሁም ይነግዱ። ሴቶች ልጆቻቸውን ማግባት፣ የእኛንም ሴቶች ልጆች ለእነሱ መዳር እንችላለን።+ +22 ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋር አንድ ሕዝብ በመሆን አብረውን ለመኖር የሚስማሙት፣ ልክ እነሱ እንደተገረዙት የእኛ የሆኑ ወንዶች ሁሉ የሚገረዙ ከሆነ ብቻ ነው።+ +23 እንዲህ ብናደርግ ንብረታቸው፣ ሀብታቸውና ከብቶቻቸው ሁሉ የእኛ ሆኑ ማለት አይደለም? በመሆኑም ከእኛ ጋር ለመኖር ባቀረቡት ሐሳብ እንስማማ።” +24 በከተማው በር የሚወጡ ሁሉ ኤሞርና ልጁ ሴኬም ያሏቸውን ሰሙ፤ በከተማዋም በር የሚወጡ ወንዶች በሙሉ ተገረዙ። +25 ሆኖም በሦስተኛው ቀን፣ ሰዎቹ ገና ቆስለው እያሉ የዲና ወንድሞች+ የሆኑት ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ማለትም ስምዖንና ሌዊ ማንም ሳይጠረጥራቸው ሰይፋቸውን ይዘው ወደ ከተማዋ በመግባት ወንዶቹን ሁሉ ገደሉ።+ +26 ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን በሰይፍ ገደሏቸው፤ ከዚያም ዲናን ከሴኬም ቤት ይዘው ሄዱ። +27 ሌሎቹ የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም በሬሳ ላይ እየተረማመዱ ከተማዋን ዘረፉ፤ ይህን ያደረጉትም እህታቸው ስለተነወረች ነው።+ +28 እነሱም መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውን፣ አህዮቻቸውን እንዲሁም በከተማዋ ውስጥና በመስክ ያገኙትን ሁሉ ወሰዱ። +29 በተጨማሪም ንብረቶቻቸውን በሙሉ ወሰዱ፤ እንዲሁም ትናንሽ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ማረኩ፤ በየቤቱ ያገኙትን ሁሉ ዘረፉ። +30 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ፣ ስምዖንንና ሌዊን+ እንዲህ አላቸው፦ “በዚህች አገር በሚኖሩት በከነአናውያንና በፈሪዛውያን ዘንድ እንደ ጥምብ እንድቆጠር በማድረግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ከተታችሁኝ።* እኔ እንግዲህ በቁጥር አነስተኛ ነኝ፤ እነሱም በእኔ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ግንባር ፈጥረው መምጣታቸው አይቀርም፤ በዚ +31 እነሱ ግን “ታዲያ ማንም እህታችንን እንደ ዝሙት አዳሪ ቆጥሮ እንዲህ ያለ ድርጊት ይፈጽምባት?” አሉ። +19 ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። እሱም ባያቸው ጊዜ ተነስቶ ወደ እነሱ ሄደ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ።+ +2 እንዲህም አለ፦ “ጌቶቼ፣ እባካችሁ ወደ አገልጋያችሁ ቤት ጎራ በሉና እደሩ፤ እግራችሁንም ታጠቡ። ከዚያም በማለዳ ተነስታችሁ ጉዟችሁን ትቀጥላላችሁ።” እነሱም መልሰው “አይሆንም፣ አደባባዩ ላይ እናድራለን” አሉ። +3 እሱ ግን አጥብቆ ስለለመናቸው አብረውት ወደ ቤቱ ሄዱ። ከዚያም ግብዣ አደረገላቸው። ቂጣም ጋገረላቸው፤ እነሱም በሉ። +4 ከመተኛታቸውም በፊት የከተማዋ ሰዎች ማለትም በሰዶም ያሉ ወንዶች ሁሉ ከልጅ እስከ አዋቂ ድረስ ግልብጥ ብለው በመውጣት ቤቱን ከበቡት። +5 ሎጥንም ደጋግመው በመጥራት “በዚህ ምሽት ወደ አንተ የመጡት ሰዎች የት አሉ? ከእነሱ ጋር የፆታ ግንኙነት እንድንፈጽም ወደ ውጭ አውጣልን” ይሉት ጀመር።+ +6 ከዚያም ሎጥ ወደ እነሱ ወደ ውጭ ወጣ፤ በሩንም ከኋላው ዘጋው። +7 እንዲህም አላቸው፦ “እባካችሁ ወንድሞቼ፣ እንዲህ ያለ ክፉ ድርጊት አትፈጽሙ። +8 እባካችሁ፣ ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ። እባካችሁ፣ እነሱን ላውጣላችሁና መልካም መስሎ የታያችሁን አድርጉባቸው። እነዚህ ሰዎች ግን በጣሪያዬ ጥላ* ሥር ስለተጠለሉ በእነሱ ላይ ምንም ነገር አታድርጉ።”+ +9 በዚህ ጊዜ ሰዎቹ “ዞር በል!” አሉት። ከዚያም “ይህ ወገን የሌለው መጤ፣ ደግሞ በእኛ ላይ ዳኛ ልሁን ይላል እንዴ! በእነሱ ላይ ልናደርግ ካሰብነው የከፋ ነገር እንዳናደርግብህ” አሉት። ሎጥንም በኃይል ገፉት፤ በሩንም ሊሰብሩት ተቃረቡ። +10 ስለሆነም ውስጥ የነበሩት ሰዎች እጃቸውን ወደ ውጭ ዘርግተው ሎጥን እነሱ ወዳሉበት ወደ ቤት አስገቡት፤ በሩንም ዘጉት። +11 ሆኖም በቤቱ ደጃፍ ላይ የነበሩትን ሰዎች ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ አሳወሯቸው፤ በዚህም የተነሳ ሰዎቹ በሩን ለማግኘት ሲዳክሩ ደከሙ። +12 ከዚያም ሰዎቹ ሎጥን እንዲህ አሉት፦ “እዚህ የሚኖሩ ሌሎች ዘመዶች አሉህ? አማቾችህን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን እንዲሁም በከተማዋ ውስጥ የሚኖር ዘመድ አዝማድህን በሙሉ ከዚህ ስፍራ ይዘህ ውጣ! +13 ይህን ስፍራ ልናጠፋው ነው፤ ምክንያቱም ሕዝቦቿን በተመለከተ የሚሰማው ጩኸት በይሖዋ ፊት እየጨመረ ስለመጣ+ ይሖዋ ከተማዋን እንድናጠፋት ልኮናል።” +14 በመሆኑም ሎጥ ወጥቶ የሴት ልጆቹ እጮኛ የሆኑትን አማቾቹን “ተነሱ! ይሖዋ ከተማዋን ሊያጠፋት ስለሆነ ከዚህ ስፍራ ውጡ!” አላቸው። አማቾቹ ግን የ���ያሾፍ መሰላቸው።+ +15 ጎህ ሲቀድ መላእክቱ ሎጥን “ተነስ! በከተማዋ በደል የተነሳ እንዳትጠፋ ከአንተ ጋር ያሉትን ሚስትህንና ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ይዘህ ውጣ!” በማለት አቻኮሉት።+ +16 ሎጥ በዘገየ ጊዜ ይሖዋ ስለራራለት+ ሰዎቹ የእሱን እጅ፣ የሚስቱን እጅና የሁለቱን ሴቶች ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዋ አስወጡት።+ +17 ልክ ከተማዋ ዳርቻ ላይ እንዳደረሷቸውም ከእነሱ አንዱ እንዲህ አለ፦ “ሕይወትህን* ለማትረፍ ሽሽ! ወደ ኋላህ እንዳትመለከት፤+ አውራጃውንም+ ለቀህ እስክትወጣ ድረስ የትኛውም ቦታ ላይ እንዳትቆም! እንዳትጠፋ ወደ ተራራማው አካባቢ ሽሽ!” +18 ከዚያም ሎጥ እንዲህ አላቸው፦ “እባክህ ይሖዋ፣ ወደዚያስ አልሂድ! +19 መቼም አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ አግኝቷል፤ ሕይወቴን* በማትረፍ ታላቅ ደግነት* አሳይተኸኛል፤+ ሆኖም አደጋ እንዳይደርስብኝና እንዳልሞት ስለምፈራ+ ወደ ተራራማው አካባቢ ሸሽቼ ማምለጥ አልችልም። +20 እባክህ ይህች ከተማ ቅርብ ነች፤ ወደዚያ መሸሽ እችላለሁ፤ ትንሽ ስፍራ እኮ ናት። እባክህ፣ ወደዚያ መሸሽ እችላለሁ? ትንሽ ስፍራ እኮ ናት። እንደዚያ ከሆነ እተርፋለሁ።”* +21 እሱም እንዲህ አለው፦ “እሺ ይሁን፣ ያልካትን ከተማ ባለማጥፋት+ አሁንም አሳቢነት አሳይሃለሁ።+ +22 ፍጠን! አንተ እዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም ነገር ማድረግ ስለማልችል+ ወደዚያ ሽሽ!” ከተማዋን ዞአር*+ ብሎ የሰየማት ለዚህ ነው። +23 ሎጥ ዞአር ሲደርስ ፀሐይ በምድሩ ላይ ወጥታ ነበር። +24 ከዚያም ይሖዋ በሰዶምና በገሞራ ላይ እሳትና ድኝ አዘነበ፤ ይህም የመጣው ከሰማይ ከይሖዋ ዘንድ ነው።+ +25 እሱም እነዚህን ከተሞች ገለባበጠ፤ አዎ፣ የከተሞቹን ነዋሪዎችና የምድሪቱን ተክል+ ሁሉ ጨምሮ መላውን አውራጃ ገለባበጠ። +26 ሆኖም ከሎጥ በስተ ኋላ የነበረችው የሎጥ ሚስት ወደ ኋላ ዞራ መመልከት ጀመረች፤ እሷም የጨው ዓምድ ሆነች።+ +27 አብርሃምም በማለዳ ተነሳ፤ ቀደም ሲል በይሖዋ ፊት ቆሞ ወደነበረበትም ስፍራ ሄደ።+ +28 ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ እንዲሁም በአውራጃው ውስጥ ወዳሉት ከተሞች በሙሉ ቁልቁል ሲያይም የሚያስገርም ነገር ተመለከተ። ከእቶን እንደሚወጣ ያለ የሚትጎለጎል ጭስ ከምድሩ እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር!+ +29 አምላክ የአውራጃውን ከተሞች ባጠፋበት ጊዜ ሎጥ ይኖርባቸው ከነበሩትና አምላክ ካጠፋቸው ከተሞች ውስጥ ሎጥን በማውጣት አብርሃምን አሰበው።+ +30 በኋላም ሎጥ በዞአር+ መኖር ስለፈራ ከዞአር ወጥቶ ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራማው አካባቢ መኖር ጀመረ።+ ስለዚህ ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በዋሻ ውስጥ መኖር ጀመረ። +31 የመጀመሪያዋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፦ “አባታችን አርጅቷል፤ በመላው ምድር ላይ ባለው ልማድ መሠረት ከእኛ ጋር ግንኙነት የሚፈጽም ወንድ በዚህ አካባቢ የለም። +32 ነይ፣ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእሱ ጋር እንተኛ፤ እንዲህ በማድረግ ከአባታችን ዘር እናስቀር።” +33 በመሆኑም በዚያ ምሽት አባታቸውን ደጋግመው የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ከዚያም የመጀመሪያዋ ልጅ ገብታ ከአባቷ ጋር ተኛች። እሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም። +34 በማግስቱም የመጀመሪያዋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፦ “ይኸው እኔ ትናንት ሌሊት ከአባቴ ጋር ተኝቻለሁ። ዛሬ ማታም የወይን ጠጅ እናጠጣው። ከዚያም አንቺ ገብተሽ ከእሱ ጋር ትተኚያለሽ። እንዲህ በማድረግ ከአባታችን ዘር እናስቀር።” +35 በመሆኑም በዚያ ምሽትም አባታቸውን ደጋግመው የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ከዚያም ታናሽየዋ ልጅ ሄዳ ከአባቷ ጋር ተኛች። እሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሳ አላወቀም። +36 ስለሆነም ሁለቱም የሎጥ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። +37 ታላቅየዋም ወንድ ል�� ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ+ አለችው፤ እሱም ዛሬ ያሉት ሞዓባውያን አባት ነው።+ +38 ታናሽየዋም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ አለችው፤ እሱም ዛሬ ያሉት አሞናውያን አባት ነው።+ +20 አብርሃም ድንኳኑን+ ከዚያ ነቅሎ ወደ ኔጌብ ምድር ሄደ፤ በቃዴስና+ በሹር+ መካከልም መኖር ጀመረ። በጌራራ+ እየኖረ* ሳለ +2 በድጋሚ ሚስቱን ሣራን “እህቴ ናት” አለ።+ በመሆኑም የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ሰዎችን ልኮ ሣራን አስመጣት፤ ከዚያም ወሰዳት።+ +3 ከዚያም አምላክ ለአቢሜሌክ ሌሊት በሕልም ተገልጦለት “በወሰድካት ሴት የተነሳ ትሞታለህ፤+ ምክንያቱም እሷ ያገባችና ባለቤት ያላት ሴት ናት”+ አለው። +4 ሆኖም አቢሜሌክ ወደ እሷ አልቀረበም ነበር።* በመሆኑም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ፣ ምንም በደል ያልፈጸመን* ብሔር ታጠፋለህ? +5 እሱ ‘እህቴ ናት’ አላለኝም? እሷስ ብትሆን ‘ወንድሜ ነው’ አላለችም? ይህን ያደረግኩት በቅን ልቦናና በንጹሕ እጅ ነው።” +6 ከዚያም እውነተኛው አምላክ በሕልም ተገልጦለት እንዲህ አለው፦ “ይህን ያደረግከው በቅን ልቦና ተነሳስተህ እንደሆነ አውቃለሁ፤ በእኔም ላይ ኃጢአት እንዳትሠራ ጠብቄሃለሁ። እንድትነካት ያልፈቀድኩልህም ለዚህ ነው። +7 በል አሁን የሰውየውን ሚስት መልስ፤ እሱ ነቢይ ነውና፤+ ስለ አንተም ልመና ያቀርባል፤+ አንተም በሕይወት ትኖራለህ። እሷን ባትመልስ ግን በእርግጥ እንደምትሞት እወቅ፤ አንተም ሆንክ የአንተ የሆነው ሁሉ ትሞታላችሁ።” +8 አቢሜሌክ በማለዳ ተነሳ፤ አገልጋዮቹንም በሙሉ ጠርቶ የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፤ እነሱም በጣም ፈሩ። +9 ከዚያም አቢሜሌክ አብርሃምን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ይህ ያደረግክብን ነገር ምንድን ነው? በእኔም ሆነ በግዛቴ ላይ እንዲህ ያለውን ታላቅ ኃጢአት ያመጣህብን ለመሆኑ ምን በድዬህ ነው? ያደረግክብኝ ነገር ትክክል አይደለም።” +10 በመቀጠልም አቢሜሌክ አብርሃምን “ለመሆኑ ይህን ያደረግከው ምን አስበህ ነው?” አለው።+ +11 አብርሃምም እንዲህ አለው፦ “ይህን ያደረግኩት ‘በዚህ ስፍራ እንደሆነ ፈሪሃ አምላክ የሚባል ነገር የለም፤ ሰዎቹ ለሚስቴ ሲሉ ሊገድሉኝ ይችላሉ’ ብዬ ስለሰጋሁ ነው።+ +12 ደግሞም እኮ በእርግጥ እህቴ ናት፤ የእናቴ ልጅ ባትሆንም የአባቴ ልጅ ናት፤ እሷም ሚስቴ ሆነች።+ +13 በመሆኑም አምላክ ከአባቴ ቤት ወጥቼ ከአገር አገር እየዞርኩ እንድኖር በነገረኝ ጊዜ+ ‘በምንሄድበት ስፍራ ሁሉ “ወንድሜ ነው” ብለሽ በመናገር ታማኝ ፍቅር አሳዪኝ’ ብያት ነበር።”+ +14 ከዚያም አቢሜሌክ በጎችን፣ ከብቶችን እንዲሁም ወንድና ሴት አገልጋዮችን ለአብርሃም ሰጠው፤ ሚስቱን ሣራንም መለሰለት። +15 በተጨማሪም አቢሜሌክ “አገሬ አገርህ ናት፤ ደስ ባለህ ቦታ መኖር ትችላለህ” አለው። +"16 ሣራንም እንዲህ አላት፦ “ይኸው ለወንድምሽ+ 1,000 የብር ሰቅል እሰጠዋለሁ። ይህም አንቺ ንጹሕ ሰው መሆንሽን ከአንቺ ጋር ባሉት ሰዎች ሁሉ ፊትም ሆነ በሌሎች ሰዎች ፊት የሚያሳውቅ ምልክት ነው፤* አንቺም ከማንኛውም ነቀፋ ነፃ ነሽ።”" +17 አብርሃምም ወደ እውነተኛው አምላክ ልመና አቀረበ፤ አምላክም አቢሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት ባሪያዎቹን ፈወሳቸው፤ እነሱም ልጆች መውለድ ጀመሩ፤ +18 ምክንያቱም ይሖዋ በአብርሃም ሚስት በሣራ የተነሳ በአቢሜሌክ ቤት ያሉትን ሴቶች ሁሉ መሃን አድርጎ ነበር።*+ +3 እባብም+ ይሖዋ አምላክ ከሠራቸው የዱር እንስሳት ሁሉ እጅግ ጠንቃቃ* ነበር። በመሆኑም ሴቲቱን “በእርግጥ አምላክ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም ዛፍ አትብሉ’ ብሏችኋል?”+ ሲል ጠየቃት። +2 በዚህ ጊዜ ሴቲቱ እባቡን እንዲህ አለችው፦ “በአትክልቱ ስፍራ ካሉት ዛፎች ፍሬ መብላት እንችላለን።+ +3 ይሁንና በአትክልቱ ስፍራ መካከል የሚገኘውን ዛፍ+ ፍሬ በተመለከተ አምላክ ‘ከእሱ አትብሉ፤ ፈጽሞም አትንኩት፤ አለዚያ ትሞታላችሁ’ ብሏል።” +4 በዚህ ጊዜ እባቡ ሴቲቱን እንዲህ አላት፦ “መሞት እንኳ ፈጽሞ አትሞቱም።+ +5 አምላክ ከዛፉ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንደሚገለጡና መልካምና ክፉን በማወቅ ረገድ እንደ አምላክ እንደምትሆኑ+ ስለሚያውቅ ነው።” +6 በዚህም የተነሳ ሴቲቱ ዛፉ ለመብል መልካም፣ ሲያዩትም የሚያጓጓ እንደሆነ ተመለከተች፤ ዛፉ ለዓይን የሚማርክ ነበር። ስለሆነም ከዛፉ ፍሬ ወስዳ በላች።+ ባሏም አብሯት ሲሆን ለእሱም ሰጠችው፤ እሱም በላ።+ +7 ከዚያም የሁለቱም ዓይኖች ተገለጡ፤ ራቁታቸውን መሆናቸውንም አስተዋሉ። በመሆኑም የበለስ ቅጠል በመስፋት የሚያሸርጡት ነገር ለራሳቸው ሠሩ።+ +8 በኋላም ሰውየውና ሚስቱ ቀኑ ነፋሻማ በሆነበት ጊዜ ላይ ይሖዋ አምላክ በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ሲሄድ ድምፁን ሰሙ፤ እነሱም በአትክልቱ ስፍራ ባሉት ዛፎች መካከል በመግባት ከይሖዋ አምላክ ፊት ተደበቁ። +9 ይሖዋ አምላክም ሰውየውን በተደጋጋሚ በመጣራት “የት ነህ?” አለው። +10 በመጨረሻም ሰውየው “በአትክልቱ ስፍራ ድምፅህን ሰማሁ፤ ሆኖም ራቁቴን ስለነበርኩ ፈራሁ፤ ስለሆነም ተደበቅኩ” አለ። +11 እሱም “ራቁትህን+ እንደሆንክ ማን ነገረህ? እንዳትበላ ብዬ ካዘዝኩህ ዛፍ+ በላህ?” አለው። +12 ሰውየውም “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ይህች ሴት ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለ። +13 ከዚያም ይሖዋ አምላክ ሴቲቱን “ለመሆኑ ይህ ያደረግሽው ነገር ምንድን ነው?” አላት። ሴቲቱም “እባቡ አታለለኝና በላሁ”+ ስትል መለሰች። +14 ከዚያም ይሖዋ አምላክ እባቡን+ እንዲህ አለው፦ “ይህን ስላደረግክ ከቤት እንስሳት ሁሉ እንዲሁም ከዱር እንስሳት ሁሉ የተረገምክ ትሆናለህ። በሕይወትህ ዘመን ሁሉ በሆድህ እየተሳብክ ትሄዳለህ፤ እንዲሁም አፈር ትበላለህ። +15 በአንተና+ በሴቲቱ+ መካከል እንዲሁም በዘርህና+ በዘሯ+ መካከል ጠላትነት+ እንዲኖር አደርጋለሁ፤ እሱ ራስህን ይጨፈልቃል፤*+ አንተም ተረከዙን ታቆስላለህ።”*+ +16 ሴቲቱንም እንዲህ አላት፦ “በእርግዝናሽ ወቅት የሚሰማሽን ሕመም በእጅጉ አበዛለሁ፤ ልጆች የምትወልጂውም በሥቃይ ይሆናል፤ ምኞትሽ ሁሉ ባልሽ ይሆናል፤ እሱ ደግሞ ይገዛሻል።” +17 አዳምንም* እንዲህ አለው፦ “የሚስትህን ቃል ስለሰማህና ‘ከእሱ አትብላ’ ብዬ ካዘዝኩህ ዛፍ+ ወስደህ ስለበላህ በአንተ የተነሳ ምድር የተረገመች ትሁን።+ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ የምድርን ፍሬ በሥቃይ ትበላለህ።+ +18 ምድርም እሾህና አሜኬላ ታበቅልብሃለች፤ አንተም በሜዳ ላይ የሚበቅለውን ተክል ትበላለህ። +19 ከመሬት ስለተገኘህ+ ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ ላብህን እያንጠፈጠፍክ ምግብ ትበላለህ። አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ።”+ +20 ከዚህ በኋላ አዳም ሚስቱን ሔዋን* ብሎ ጠራት፤ ምክንያቱም እሷ የሕያዋን ሁሉ እናት ትሆናለች።+ +21 ይሖዋ አምላክም ረጅም ልብስ ከቆዳ ሠርቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።+ +22 ከዚያም ይሖዋ አምላክ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ሰውየው መልካምና ክፉን በማወቅ ረገድ ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል።+ አሁን ደግሞ እጁን በመዘርጋት ከሕይወት ዛፍ+ ፍሬ ወስዶ እንዳይበላና ለዘላለም እንዳይኖር አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ።” +23 ስለሆነም የተገኘበትን መሬት እንዲያርስ፣+ ይሖዋ አምላክ አዳምን ከኤደን የአትክልት ስፍራ+ አባረረው። +24 ሰውየውንም አስወጣው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤልና+ ያለማቋረጥ የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ አስቀመጠ። +24 አብርሃምም አረጀ፤ ዕድሜውም ገፋ፤ ይሖዋም አብርሃምን በሁሉ ነገር ባረከው።+ +2 አብርሃም ንብረቱን በሙሉ የሚያስተዳድርለትንና በቤቱ ውስጥ ካሉት አገልጋዮች ሁሉ አንጋፋ የሆነውን አገልጋዩን+ እንዲህ አለው፦ “እባክህ እጅህን ከጭኔ ሥር አድርግ፤ +3 በመካከላቸው ከምኖረው ከከነአናውያን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስት እንዳታመጣለት የሰማይና የምድር አምላክ በሆነው በይሖዋ አስምልሃለሁ።+ +4 ከዚህ ይልቅ ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ+ ሄደህ ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት አምጣለት።” +5 ይሁንና አገልጋዩ “ሴቲቱ ከእኔ ጋር ወደዚህ ምድር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ? ልጅህን አንተ ወደመጣህበት አገር+ መመለስ ይኖርብኛል?” አለው። +6 በዚህ ጊዜ አብርሃም እንዲህ አለው፦ “ልጄን ወደዚያ እንዳትወስደው ተጠንቀቅ።+ +7 ከአባቴ ቤትና ከዘመዶቼ አገር ያወጣኝ+ እንዲሁም ‘ይህን ምድር+ ለዘርህ+ እሰጣለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ+ የሰማይ አምላክ ይሖዋ መልአኩን ከፊትህ ይልካል፤+ አንተም ከዚያ አገር+ ለልጄ ሚስት ታመጣለታለህ። +8 ሆኖም ሴቲቱ ከአንተ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ሳትሆን ብትቀር ከዚህ መሐላ ነፃ ትሆናለህ። ልጄን ግን በምንም ዓይነት ወደዚያ እንዳትወስደው።” +9 ከዚያም አገልጋዩ እጁን ከጌታው ከአብርሃም ጭን ሥር አደረገ፤ ስለዚህ ጉዳይም ማለለት።+ +10 በመሆኑም አገልጋዩ ከጌታው ግመሎች መካከል አሥሩን ወሰደ፤ ከጌታውም ንብረት ምርጥ ምርጡን ሁሉ ይዞ ተነሳ። ከዚያም ከናኮር ከተማ ወደ ሜሶጶጣሚያ ጉዞ ጀመረ። +11 ከከተማዋ ውጭ ባለ አንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብም ግመሎቹን አንበረከከ። ጊዜውም ወደ ማምሻው አካባቢ ነበር፤ ይህ ጊዜ ደግሞ ሴቶች ውኃ ለመቅዳት የሚወጡበት ነው። +12 ከዚያም እንዲህ አለ፦ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ ይሖዋ፣ እባክህ በዚህ ዕለት ጉዳዬን አሳካልኝ፤ ለጌታዬ ለአብርሃምም ታማኝ ፍቅርህን አሳየው። +13 ይኸው እኔ እዚህ የውኃ ምንጭ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ የከተማዋ ሴቶች ልጆች ውኃ ለመቅዳት እየመጡ ነው። +14 እንግዲህ ‘እባክሽ፣ ውኃ እንድጠጣ እንስራሽን አውርጂልኝ’ ስላት ‘እንካ ጠጣ፤ ግመሎችህንም አጠጣልሃለሁ’ የምትለኝ ወጣት ለአገልጋይህ ለይስሐቅ የመረጥካት ትሁን፤ እንዲህ ካደረግክልኝ ለጌታዬ ታማኝ ፍቅር እንዳሳየኸው አውቃለሁ።” +15 እሱም ገና ንግግሩን ሳይጨርስ የባቱኤል+ ልጅ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ብቅ አለች፤ ባቱኤል የአብርሃም ወንድም የናኮር+ ሚስት ሚልካ+ የወለደችው ነው። +16 ወጣቷም በጣም ቆንጆና ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽማ የማታውቅ ድንግል ነበረች። እሷም ወደ ምንጩ ወርዳ በእንስራዋ ውኃ ሞልታ ተመለሰች። +17 አገልጋዩም ወዲያውኑ ወደ እሷ ሮጦ በመሄድ “እባክሽ ከእንስራሽ ውኃ ልጎንጭ” አላት። +18 እሷም መልሳ “ጌታዬ ጠጣ” አለችው። ከዚያም ፈጠን ብላ እንስራዋን ወደ እጇ በማውረድ የሚጠጣው ውኃ ሰጠችው። +19 ለእሱ ሰጥታው ከጠጣ በኋላ “ግመሎችህም ጠጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ውኃ እቀዳላቸዋለሁ” አለችው። +20 በእንስራዋ ውስጥ የነበረውን ውኃም በፍጥነት ገንዳ ውስጥ ገለበጠች፤ ከዚያም በሩጫ እየተመላለሰች ከጉድጓዱ ውኃ ትቀዳ ጀመር፤ ለግመሎቹም ሁሉ ቀዳች። +21 ይህ ሁሉ ሲሆን ሰውየው ይሖዋ ጉዞውን አሳክቶለት እንደሆነና እንዳልሆነ በማሰብ ዝም ብሎ በመገረም ይመለከታት ነበር። +22 ግመሎቹም ጠጥተው ሲጨርሱ ሰውየው ግማሽ ሰቅል* የሚመዝን የወርቅ የአፍንጫ ቀለበት እንዲሁም አሥር ሰቅል* የሚመዝኑ ሁለት የወርቅ አምባሮች አውጥቶ ሰጣት፤ +23 እንዲህም አላት፦ “እስቲ ንገሪኝ፣ ለመሆኑ የማን ልጅ ነሽ? በአባትሽ ቤት የምናድርበት ቦታ ይኖር ይሆን?” +24 እሷም መልሳ “ሚልካ ለናኮር+ የወለደችለ��� የባቱኤል ልጅ ነኝ”+ አለችው። +25 አክላም “ገለባና ብዙ ገፈራ እንዲሁም ለማደሪያ የሚሆን ስፍራ አለን” አለችው። +26 በዚህ ጊዜ ሰውየው በይሖዋ ፊት ተደፍቶ ሰገደ፤ +27 እንዲህም አለ፦ “ለጌታዬ ታማኝ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ያልነፈገው የጌታዬ የአብርሃም አምላክ ይወደስ። ይሖዋ ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት መራኝ።” +28 ወጣቷም የሆነውን ሁሉ ለእናቷ ቤተሰቦች ለመንገር እየሮጠች ሄደች። +29 ርብቃ፣ ላባ+ የሚባል ወንድም ነበራት። ላባም ከከተማዋ ውጭ በምንጩ አጠገብ ወዳለው ሰው እየሮጠ ሄደ። +30 የአፍንጫ ቀለበቱንና አምባሮቹን በእህቱ እጆች ላይ ሲመለከት እንዲሁም እህቱ ርብቃ “ሰውየው እንዲህ እንዲህ አለኝ” ብላ ስትናገር ሲሰማ በምንጩ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ የነበረውን ሰው ለማግኘት ወደ እሱ ሄደ። +31 እሱም ሰውየውን እንዳገኘው “አንተ ይሖዋ የባረከህ ሰው፣ ና እንጂ። ውጭ የቆምከው ለምንድን ነው? ቤቱን አዘጋጅቻለሁ፤ ለግመሎቹም ማደሪያ አለ” አለው። +32 ስለዚህ ሰውየው ወደ ቤት ገባ፤ እሱም* የግመሎቹን ጭነት አራገፈለት፤ ለግመሎቹም ገለባና ገፈራ ሰጣቸው። እንዲሁም ሰውየውና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበት ውኃ አቀረበላቸው። +33 ሆኖም ሰውየው የሚበላ ነገር ሲቀርብለት “የመጣሁበትን ጉዳይ ሳልናገር እህል አልቀምስም” አለ። በመሆኑም ላባ “እሺ፣ ተናገር!” አለው። +34 እሱም እንዲህ አለ፦ “እኔ የአብርሃም አገልጋይ ነኝ።+ +35 ይሖዋ ጌታዬን እጅግ ባርኮታል፤ በጎች፣ ከብቶች፣ ብር፣ ወርቅ፣ ወንድና ሴት አገልጋዮች እንዲሁም ግመሎችና አህዮች በመስጠት በጣም አበልጽጎታል።+ +36 በተጨማሪም የጌታዬ ሚስት ሣራ በስተርጅናዋ ለጌታዬ ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤+ ጌታዬም ያለውን ሁሉ ለእሱ ይሰጠዋል።+ +37 በመሆኑም ጌታዬ እንዲህ በማለት አስማለኝ፦ ‘በአገራቸው ከምኖረው ከከነአናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳታመጣለት።+ +38 ፈጽሞ እንዲህ እንዳታደርግ፤ ከዚህ ይልቅ ወደ አባቴ ቤትና ወደ ቤተሰቦቼ+ ሄደህ ለልጄ ሚስት አምጣለት።’+ +39 እኔ ግን ጌታዬን ‘ሴቲቱ ከእኔ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ?’ አልኩት።+ +40 እሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግኩት+ ይሖዋ መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፤+ ጉዞህን ያሳካልሃል፤ አንተም ከቤተሰቦቼና ከአባቴ ቤት+ ለልጄ ሚስት ታመጣለታለህ። +41 ወደ ቤተሰቦቼ ከሄድክና እነሱም ልጅቷን ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆኑ ከማልክልኝ መሐላ ነፃ ትሆናለህ። እንዲህ ካደረግክ ከመሐላህ ነፃ ትሆናለህ።’+ +42 “እኔም ዛሬ ምንጩ አጠገብ ስደርስ እንዲህ አልኩ፦ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ ይሖዋ፣ ጉዞዬን የምታሳካልኝ ከሆነ +43 ይኸው እዚህ የውኃ ምንጭ አጠገብ ቆሜአለሁ። አንዲት ወጣት ሴት+ ውኃ ለመቅዳት ስትመጣ “እባክሽ፣ ከእንስራሽ ትንሽ ውኃ አጠጪኝ” እላታለሁ፤ +44 እሷም “አንተም ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳላቸዋለሁ” ካለችኝ ይህች ሴት ይሖዋ ለጌታዬ ልጅ የመረጣት ትሁን።’+ +45 “እኔም ገና በልቤ ተናግሬ ሳልጨርስ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ብቅ አለች፤ እሷም ወደ ምንጩ ወርዳ ውኃ ቀዳች። ከዚያም እኔ ‘እባክሽ፣ ውኃ አጠጪኝ’ አልኳት።+ +46 እሷም ፈጠን ብላ እንስራዋን ከትከሻዋ በማውረድ ‘ጠጣ፤+ ግመሎችህንም አጠጣልሃለሁ’ አለችኝ። እኔም ጠጣሁ፤ ግመሎቹንም አጠጣች። +47 ከዚያም ‘ለመሆኑ የማን ልጅ ነሽ?’ ስል ጠየቅኳት፤ እሷም ‘ሚልካ ለናኮር የወለደችለት የባቱኤል ልጅ ነኝ’ አለችኝ። ስለዚህ ቀለበቱን በአፍንጫዋ ላይ፣ አምባሮቹን ደግሞ በእጆቿ ላይ አደረግኩላት።+ +48 እኔም በይሖዋ ፊት ተደፍቼ ሰገድኩ፤ የጌታዬን ወንድም ሴት ልጅ ለጌታዬ ልጅ እንድወስ���ለት በትክክለኛው መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ ይሖዋን አወደስኩ።+ +49 እንግዲህ አሁን ለጌታዬ ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ማሳየት የምትፈልጉ ከሆነ ንገሩኝ፤ ካልሆነ ግን ማድረግ ያለብኝን ነገር እንድወስን* ቁርጡን አሳውቁኝ።”+ +50 ከዚያም ላባና ባቱኤል እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “ይህ ነገር ከይሖዋ የመጣ ነው። እኛ እሺም ሆነ እንቢ ልንልህ አንችልም።* +51 ርብቃ ይቻትልህ። ይዘሃት ሂድ፤ ልክ ይሖዋ እንደተናገረውም ለጌታህ ልጅ ሚስት ትሁን።” +52 የአብርሃም አገልጋይም ያሉትን ሲሰማ ወዲያውኑ በይሖዋ ፊት መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። +53 ከዚያም አገልጋዩ የብርና የወርቅ ጌጣጌጦችን እንዲሁም ልብሶችን እያወጣ ለርብቃ ይሰጣት ጀመር፤ ለወንድሟና ለእናቷም ውድ የሆኑ ዕቃዎችን ሰጣቸው። +54 ከዚህ በኋላ እሱና ከእሱ ጋር ያሉት ሰዎች በሉ፣ ጠጡም፤ እዚያም አደሩ። እሱም ጠዋት ሲነሳ “በሉ እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድንሄድ አሰናብቱን” አላቸው። +55 በዚህ ጊዜ ወንድሟና እናቷ “ልጅቷ ከእኛ ጋር ቢያንስ ለአሥር ቀን ትቆይ። ከዚያ በኋላ መሄድ ትችላለች” አሉት። +56 እሱ ግን “ይሖዋ ጉዞዬን እንዳሳካልኝ እያያችሁ አታዘግዩኝ። ወደ ጌታዬ እንድሄድ አሰናብቱኝ” አላቸው። +57 እነሱም “ልጅቷን እንጥራና እንጠይቃት” አሉት። +58 ርብቃን ጠርተውም “ከዚህ ሰው ጋር ትሄጃለሽ?” አሏት። እሷም “አዎ፣ እሄዳለሁ” አለች። +59 ስለዚህ እህታቸውን ርብቃንና+ ሞግዚቷን*+ እንዲሁም የአብርሃምን አገልጋይና አብረውት የነበሩትን ሰዎች አሰናበቷቸው። +60 ርብቃንም “እህታችን ሆይ፣ ሺዎች ጊዜ አሥር ሺህ ሁኚ፤* ዘርሽም የጠላቶቹን በር* ይውረስ”+ ብለው መረቋት። +61 ከዚያም ርብቃና ሴት አገልጋዮቿ ተነሱ፤ በግመሎች ላይ ተቀምጠው ሰውየውን ተከተሉት። አገልጋዩም ርብቃን ይዞ ጉዞውን ቀጠለ። +62 ይስሐቅም በኔጌብ+ ምድር ይኖር ስለነበር ከብኤርላሃይሮዒ+ አቅጣጫ መጣ። +63 ይስሐቅም አመሻሹ ላይ ለማሰላሰል+ ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር። ቀና ብሎ ሲመለከትም ግመሎች ሲመጡ አየ! +64 ርብቃም ቀና ብላ ስትመለከት ይስሐቅን አየችው፤ ከዚያም ከግመሉ ላይ በፍጥነት ወረደች። +65 አገልጋዩንም “ከእኛ ጋር ለመገናኘት ሜዳውን አቋርጦ የሚመጣው ያ ሰው ማን ነው?” ስትል ጠየቀችው። አገልጋዩም “ጌታዬ ነው” አላት። በመሆኑም ዓይነ ርግቧን ወስዳ ራሷን ሸፈነች። +66 አገልጋዩም ያደረገውን ሁሉ ለይስሐቅ ነገረው። +67 ከዚያም ይስሐቅ ርብቃን ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን ይዟት ገባ።+ በዚህ መንገድ ሚስቱ አድርጎ ወሰዳት፤ እሱም ወደዳት፤+ ከእናቱም ሞት ተጽናና።+ +32 ከዚያም ያዕቆብ ጉዞውን ቀጠለ፤ የአምላክ መላእክትም አገኙት። +2 ያዕቆብም ልክ እንዳያቸው “ይህ የአምላክ ሰፈር ነው!” አለ። በመሆኑም የቦታውን ስም ማሃናይም* አለው። +3 ከዚያም ያዕቆብ በኤዶም+ ክልል* ሴይር+ በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ኤሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤ +4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “ጌታዬን ኤሳውን እንዲህ በሉት፦ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፦ “ከላባ ጋር እስካሁን ድረስ ለረጅም ጊዜ ኖሬአለሁ።*+ +5 አሁን በሬዎች፣ አህዮች፣ በጎች እንዲሁም ወንድና ሴት አገልጋዮች+ አሉኝ፤ ይህን መልእክት ለጌታዬ የላክሁት በፊትህ ሞገስ እንዳገኝ ለመጠየቅ ነው።”’” +6 ከተወሰነ ጊዜ በኋላም መልእክተኞቹ ወደ ያዕቆብ ተመልሰው በመምጣት እንዲህ አሉት፦ “ወንድምህን ኤሳውን አግኝተነው ነበር፤ እሱም ከአንተ ጋር ለመገናኘት ወደዚህ እየመጣ ነው፤ ከእሱም ጋር 400 ሰዎች አሉ።”+ +7 ያዕቆብም እጅግ ፈራ፤ በጭንቀትም ተዋጠ።+ በመሆኑም አብረውት ያሉትን ሰዎች፣ መንጎቹን፣ ከብቶቹንና ግመ���ቹን በሁለት ቡድን ከፈላቸው። +8 እሱም “ምናልባት ኤሳው በአንደኛው ቡድን ላይ ጥቃት ቢሰነዝር፣ ሌላኛው ቡድን ሊያመልጥ ይችላል” አለ። +9 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ አለ፦ “‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እኔም መልካም ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልከኝ የአባቴ የአብርሃም አምላክና የአባቴ የይስሐቅ አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+ +10 እኔ ባሪያህ ይህን ያህል ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ልታሳየኝ+ የሚገባኝ ሰው አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር ከበትር ሌላ ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ቡድን ሆኛለሁ።+ +11 ከወንድሜ ከኤሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤+ ምክንያቱም መጥቶ በእኔም ሆነ በእነዚህ እናቶችና በልጆቻቸው ላይ ጥቃት እንዳይሰነዝር ፈርቻለሁ።+ +12 አንተው ራስህ ‘በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፤ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሳ ሊቆጠር እንደማይችል የባሕር አሸዋ አደርገዋለሁ’ ብለኸኛል።”+ +13 እሱም በዚያ ሌሊት እዚያው አደረ። ከንብረቱም መካከል የተወሰነውን ወስዶ ለወንድሙ ለኤሳው ስጦታ አዘጋጀ፤+ +14 ስጦታውም የሚከተለው ነበር፦ 200 እንስት ፍየሎች፣ 20 ተባዕት ፍየሎች፣ 200 እንስት በጎች፣ 20 አውራ በጎች +15 እንዲሁም 30 የሚያጠቡ ግመሎች፣ 40 ላሞች፣ 10 በሬዎች፣ 20 እንስት አህዮችና 10 ተባዕት አህዮች።+ +16 እሱም በመንጋ በመንጋ ለይቶ ለአገልጋዮቹ ሰጣቸው። አገልጋዮቹንም “ቀድማችሁኝ ተሻገሩ፤ አንዱን መንጋ ከሌላው መንጋ አራርቁት” አላቸው። +17 በተጨማሪም የመጀመሪያውን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ወንድሜ ኤሳው ቢያገኝህና ‘ለመሆኑ አንተ የማን ነህ? የምትሄደው ወዴት ነው? እነዚህ የምትነዳቸው እንስሳትስ የማን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ +18 ‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው። ይህ ለጌታዬ ለኤሳው የተላከ ስጦታ ነው፤+ እንዲያውም እሱ ራሱ ከኋላችን እየመጣ ነው’ በለው።” +19 እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎቹን የሚነዱትን በሙሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ኤሳውን ስታገኙት ይህንኑ ንገሩት። +20 ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለት እንዳለባችሁም አትዘንጉ።” ይህን ያላቸው ‘ስጦታውን አስቀድሜ በመላክ ቁጣው እንዲበርድለት ካደረግኩ ከእሱ ጋር ስገናኝ በጥሩ ሁኔታ ይቀበለኝ ይሆናል’ ብሎ ስላሰበ ነው።+ +21 በመሆኑም ስጦታው ከእሱ ቀድሞ ተሻገረ፤ እሱ ግን እዚያው የሰፈረበት ቦታ አደረ። +22 በኋላም በዚያው ሌሊት ተነሳ፤ ሁለቱን ሚስቶቹን፣+ ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና+ 11ዱን ወንዶች ልጆቹን ይዞ በያቦቅ+ መልካ* ተሻገረ። +23 እነሱንም ወስዶ ወንዙን* አሻገራቸው፤ ያለውንም ነገር ሁሉ አሻገረ። +24 በመጨረሻም ያዕቆብ ብቻውን ቀረ። ከዚያም አንድ ሰው ጎህ እስኪቀድ ድረስ ሲታገለው ቆየ።+ +25 ሰውየውም ሊያሸንፈው እንዳልቻለ ሲያይ የጭኑን መጋጠሚያ ነካው፤ ያዕቆብም ከእሱ ጋር በሚታገልበት ጊዜ የጭኑ መጋጠሚያ ከቦታው ተናጋ።+ +26 በኋላም ሰውየው “ጎህ እየቀደደ ስለሆነ ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። እሱም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው።+ +27 በመሆኑም ሰውየው “ስምህ ማን ነው?” አለው፤ እሱም “ያዕቆብ” ሲል መለሰለት። +28 ሰውየውም “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል* እንጂ ያዕቆብ አይባልም፤+ ምክንያቱም ከአምላክም ሆነ ከሰዎች ጋር ታግለህ+ በመጨረሻ አሸንፈሃል” አለው። +29 ያዕቆብም መልሶ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” አለው። እሱ ግን “ስሜን የምትጠይቀኝ ለምንድን ነው?” አለው።+ እንዲህ ካለው በኋላም በዚያ ስፍራ ባረከው። +30 በመሆኑም ያዕቆብ “አምላክን ፊት ለፊት አይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፏል”*+ በማለት የቦታውን ስም ጰኒኤል*+ አለው። +31 ያዕቆብ ጰኑኤልን* እንዳለፈ ፀሐይ ወጣችበት��� እሱም ጭኑ በመጎዳቱ ምክንያት ያነክስ ነበር።+ +32 የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን ጅማት የማይበሉት ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ሰውየው በያዕቆብ ጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን ጅማት ነክቶ ነበር። +7 ከዚህ በኋላ ይሖዋ ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ትውልድ መካከል በፊቴ ጻድቅ ሆነህ ያገኘሁህ አንተን ስለሆነ+ አንተም ሆንክ መላው ቤተሰብህ ወደ መርከቡ ግቡ። +2 ከአንተም ጋር ንጹሕ ከሆነው ከእያንዳንዱ እንስሳ ሰባት ሰባት* ትወስዳለህ፤+ ተባዕትና እንስት ይሁኑ፤ ንጹሕ ካልሆነው ከእያንዳንዱ እንስሳ ደግሞ ሁለት ሁለት ውሰድ፤ ተባዕትና እንስት ይሁኑ፤ +3 በተጨማሪም በመላው ምድር ላይ ዘራቸው እንዲተርፍ+ በሰማይ ላይ ከሚበርሩ ፍጥረታት ሰባት ሰባት* አስገባ፤ ተባዕትና እንስት ይሁኑ። +4 ከሰባት ቀን በኋላ በምድር ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት+ ዝናብ አዘንባለሁ፤+ የሠራሁትንም ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ።”+ +5 ኖኅም ይሖዋ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። +6 የጥፋት ውኃው በምድር ላይ በወረደበት ወቅት ኖኅ 600 ዓመቱ ነበር።+ +7 ኖኅም የጥፋት ውኃው ከመጀመሩ በፊት ከወንዶች ልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር በመሆን ወደ መርከቡ ገባ።+ +8 እያንዳንዱ ንጹሕ እንስሳ፣ እያንዳንዱ ንጹሕ ያልሆነ እንስሳ እንዲሁም የሚበርሩ ፍጥረታትና በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ነገሮች ሁሉ+ +9 አምላክ ኖኅን ባዘዘው መሠረት ተባዕትና እንስት በመሆን ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ኖኅ ወዳለበት ወደ መርከቡ ገቡ። +10 ከሰባት ቀን በኋላም የጥፋት ውኃው በምድር ላይ ወረደ። +11 ኖኅ በተወለደ በ600ኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር ከወሩም በ17ኛው ቀን፣ በዚያ ቀን፣ ተንጣሎ የሚገኘው ጥልቅ ውኃ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማያት የውኃ በሮችም ተከፈቱ።+ +12 ዝናቡም ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት በምድር ላይ ወረደ። +13 በዚያው ቀን ኖኅ ከወንዶች ልጆቹ ከሴም፣ ከካምና ከያፌት+ እንዲሁም ከሚስቱና ከሦስቱ የልጆቹ ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገባ።+ +14 ከእነሱም ጋር እያንዳንዱ የዱር እንስሳ እንደየወገኑ፣ እያንዳንዱ የቤት እንስሳ እንደየወገኑ፣ በምድር ላይ ያለ መሬት ለመሬት የሚሄድ እያንዳንዱ እንስሳ እንደየወገኑ፣ እያንዳንዱ የሚበር ፍጥረት እንደየወገኑ እንዲሁም እያንዳንዱ ወፍና እያንዳንዱ ክንፍ ያለው ፍጡር ወደ መርከቡ ገባ። +15 የሕይወት እስትንፋስ* ያለው ሁሉም ዓይነት ሕያው ፍጡር ሁለት ሁለት ሆኖ ወደ ኖኅ በመምጣት መርከቡ ውስጥ ይገባ ጀመር። +16 በመሆኑም አምላክ ኖኅን ባዘዘው መሠረት ሁሉም ዓይነት ሕያው ፍጡር ተባዕትና እንስት እየሆነ ወደ መርከቡ ገባ። ከዚያም ይሖዋ ከበስተኋላው በሩን ዘጋበት። +17 የጥፋት ውኃው ለ40 ቀን በምድር ላይ ያለማቋረጥ ወረደ። ውኃው እየጨመረ ሲሄድ መርከቡን ወደ ላይ አነሳው፤ መርከቡም መሬቱን ለቆ መንሳፈፍ ጀመረ። +18 ውኃው በምድር ላይ እያየለና በእጅጉ እየጨመረ ሄደ፤ መርከቡ ግን በውኃው ላይ መንሳፈፉን ቀጠለ። +19 ውኃው በምድር ላይ በጣም እያየለ ከመሄዱ የተነሳ ከሰማይ በታች ያሉ ረጃጅም ተራሮች በሙሉ ተሸፈኑ።+ +20 ውኃው ከተራሮቹ በላይ 15 ክንድ* ያህል ከፍ አለ። +21 በመሆኑም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ* ይኸውም የሚበርሩ ፍጥረታት፣ የቤት እንስሳት፣ የዱር እንስሳት፣ የሚርመሰመሱ ፍጥረታትና ሰዎች በሙሉ+ ጠፉ።+ +22 በአፍንጫው የሕይወት እስትንፋስ*+ የነበረው በየብስ ላይ የሚኖር ፍጡር ሁሉ ሞተ። +23 እሱም ሰውን፣ እንስሳትን፣ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትንና በሰማይ ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትን ጨምሮ ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ገጽ ጠራርጎ አጠፋ። ሁሉም ከምድር ላይ ተጠራርገው ጠፉ��+ ከጥፋቱ የተረፉት ኖኅና ከእሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ብቻ ናቸው።+ +24 ውኃውም በምድር ላይ እንዳየለ ለ150 ቀናት ቆየ።+ +48 ይህ ከሆነ በኋላ ዮሴፍ “አባትህ ደክሟል” ተብሎ ተነገረው። ዮሴፍም ሁለቱን ወንዶች ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ።+ +2 ከዚያም ያዕቆብ “ልጅህ ዮሴፍ ወደ አንተ መጥቷል” ተብሎ ተነገረው። በመሆኑም እስራኤል እንደ ምንም ቀና ብሎ አልጋው ላይ ተቀመጠ። +3 ያዕቆብም ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በከነአን ምድር በምትገኘው በሎዛ ተገልጦልኝ ባረከኝ።+ +4 እሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘ፍሬያማ እያደረግኩህ ነው፤ ደግሞም አበዛሃለሁ፤ ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ጉባኤም አደርግሃለሁ፤+ ይህችን ምድር ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ ዘላቂ ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ።’+ +5 አንተ ወዳለህበት ወደ ግብፅ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር የወለድካቸው ሁለት ወንዶች ልጆች የእኔ ናቸው።+ ሮቤልና ስምዖን የእኔ እንደሆኑ ሁሉ ኤፍሬምና ምናሴም የእኔ ይሆናሉ።+ +6 ከእነሱ በኋላ የምትወልዳቸው ልጆች ግን የአንተ ይሆናሉ። እነሱም ርስት+ በሚሰጣቸው ጊዜ በወንድሞቻቸው ስም ይጠራሉ። +7 እኔም ከጳዳን ስመጣ ኤፍራታ ለመድረስ ረዘም ያለ መንገድ ሲቀረኝ ራሔል በከነአን ምድር ሞተችብኝ።+ በመሆኑም ወደ ኤፍራታ+ ማለትም ወደ ቤተልሔም+ በሚወስደው መንገድ ላይ ቀበርኳት።” +8 ከዚያም እስራኤል የዮሴፍን ወንዶች ልጆች ሲያይ “እነዚህ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀው። +9 ዮሴፍም አባቱን “እነዚህ አምላክ በዚህ ስፍራ የሰጠኝ ወንዶች ልጆቼ ናቸው”+ አለው። በዚህ ጊዜ “እባክህ እንድባርካቸው ወደ እኔ አቅርባቸው” አለው።+ +10 የእስራኤል ዓይኖች በእርጅና የተነሳ ደክመው ነበር፤ እሱም ማየት ተስኖት ነበር። ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን ወደ እሱ አቀረባቸው። እሱም ሳማቸው፤ እንዲሁም አቀፋቸው። +11 እስራኤልም ዮሴፍን “ዓይንህን አያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤+ አምላክ ግን ልጆችህንም ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው። +12 ከዚያም ዮሴፍ ልጆቹን ከእስራኤል ጉልበቶች መካከል አውጥቶ ፈቀቅ ካደረጋቸው በኋላ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። +13 ዮሴፍም ሁለቱን ልጆች ወስዶ ኤፍሬምን+ ከራሱ በስተ ቀኝ ከእስራኤል በስተ ግራ፣ ምናሴን+ ደግሞ ከራሱ በስተ ግራ ከእስራኤል በስተ ቀኝ አድርጎ ወደ እሱ አቀረባቸው። +14 ይሁን እንጂ እስራኤል ታናሽየው ኤፍሬም ቢሆንም ቀኝ እጁን በእሱ ራስ ላይ አደረገ፤ ግራ እጁን ደግሞ በምናሴ ራስ ላይ አደረገ። እንዲህ ያደረገው ሆን ብሎ ነው፤ ምክንያቱም ምናሴ የበኩር ልጅ ነበር።+ +15 ከዚያም ዮሴፍን ባረከው፤+ እንዲህም አለው፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የተመላለሱት+ እውነተኛው አምላክ፣እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ እረኛ የሆነልኝ እውነተኛው አምላክ፣+ +16 ከአደጋ ሁሉ ያዳነኝ መልአክ+ እነዚህን ልጆች ይባርክ።+ የእኔም ሆነ የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በእነሱ ይጠራ። በምድርም ላይ ቁጥራቸው እየበዛ ይሂድ።”+ +17 ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ እንዳደረገ ሲያይ ቅር ተሰኘ፤ ስለዚህ የአባቱን እጅ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንስቶ በምናሴ ራስ ላይ ሊያደርገው ሞከረ። +18 ዮሴፍም አባቱን “አባቴ፣ እንዲህ አይደለም፤ በኩሩ+ እኮ ይሄኛው ነው። ቀኝ እጅህን በእሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው። +19 አባቱ ግን “አውቄአለሁ ልጄ፣ አውቄአለሁ። እሱም ቢሆን ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል። ይሁን እንጂ ታናሽ ወንድሙ ከእሱ የበለጠ ይሆናል፤+ ዘሩም በዝቶ ብዙ ብሔር ለመሆን ይበቃል”+ በማለት እንቢ አለው። +20 በመሆኑም በዚያው ቀን እንዲህ ሲል እነሱን መባረኩን ቀጠለ፦+ “እስራኤል ��አንተ ስም እንዲህ በማለት ይባርክ፦ ‘አምላክ እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርግህ።’” በዚህ ሁኔታ ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው። +21 ከዚያም እስራኤል ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኔ የምሞትበት ጊዜ ቀርቧል።+ አምላክ ግን ከእናንተ እንደማይለይ እንዲሁም ወደ አባቶቻችሁ ምድር እንደሚመልሳችሁ የተረጋገጠ ነው።+ +22 በእኔ በኩል ከአሞራውያን እጅ በሰይፌና በቀስቴ የወሰድኩትን መሬት ከወንድሞችህ አንድ ድርሻ መሬት* አስበልጬ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።” +45 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩት አገልጋዮቹ ፊት ስሜቱን መቆጣጠር አልቻለም።+ በመሆኑም “ሁሉንም ሰው አስወጡልኝ!” በማለት ጮኸ። ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት+ ወቅት ከእሱ ጋር ማንም ሰው አልነበረም። +2 ከዚያም ጮክ ብሎ ማልቀስ ጀመረ፤ ግብፃውያንም ሰሙት፤ በፈርዖንም ቤት ተሰማ። +3 በመጨረሻም ዮሴፍ ወንድሞቹን “እኔ ዮሴፍ ነኝ። አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” አላቸው። ወንድሞቹ ግን በሁኔታው በጣም ስለደነገጡ ምንም ሊመልሱለት አልቻሉም። +4 ስለሆነም ዮሴፍ ወንድሞቹን “እባካችሁ ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው። እነሱም ወደ እሱ ቀረቡ። ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ።+ +5 አሁን ግን እኔን ወደዚህ በመሸጣችሁ አትዘኑ፤ እርስ በርሳችሁም አትወቃቀሱ፤ ምክንያቱም አምላክ ከእናንተ አስቀድሞ የላከኝ ሕይወት ለማዳን ሲል ነው።+ +6 ረሃቡ በምድር ላይ ከጀመረ ይህ ሁለተኛ ዓመቱ ነው፤+ ምንም የማይታረስባቸውና አዝመራ የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና ይቀራሉ። +7 አምላክ ግን በምድር ላይ ዘራችሁን ሊያስቀርና+ በታላቅ ማዳን ሕይወታችሁን ሊታደግ ከእናንተ አስቀድሞ ላከኝ። +8 ስለዚህ ለፈርዖን ዋና አማካሪ፣* በቤቱም ሁሉ ላይ ጌታ እንዲሁም በመላው የግብፅ ምድር ላይ ገዢ ሊያደርገኝ+ ወደዚህ የላከኝ እውነተኛው አምላክ እንጂ እናንተ አይደላችሁም። +9 “ቶሎ ብላችሁ ወደ አባቴ ሂዱና እንዲህ በሉት፦ ‘ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይላል፦ “አምላክ በመላው ግብፅ ላይ ጌታ አድርጎኛል።+ ሳትዘገይ ወደ እኔ ና።+ +10 ወንዶች ልጆችህን፣ የልጅ ልጆችህን፣ መንጎችህን፣ ከብቶችህንና ያለህን ነገር በሙሉ ይዘህ በመምጣት በአቅራቢያዬ በጎሸን ምድር ትኖራለህ።+ +11 ረሃቡ ገና ለአምስት ዓመታት ስለሚቀጥል እኔ የሚያስፈልግህን ምግብ እሰጥሃለሁ።+ አለዚያ አንተም ሆንክ ቤትህ እንዲሁም የአንተ የሆነው ሁሉ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።”’ +12 እንግዲህ አሁን እያናገርኳችሁ ያለሁት እኔው ራሴ መሆኔን እናንተም ሆናችሁ ወንድሜ ቢንያም በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል።+ +13 በመሆኑም በግብፅ ስላለኝ ክብር ሁሉ እንዲሁም ስላያችሁት ስለ ማንኛውም ነገር ለአባቴ ንገሩት። አሁንም በፍጥነት ሄዳችሁ አባቴን ወደዚህ ይዛችሁት ኑ።” +14 ከዚያም በወንድሙ በቢንያም አንገት ላይ ተጠምጥሞ አለቀሰ፤ ቢንያምም አንገቱን አቅፎት አለቀሰ።+ +15 የቀሩትን ወንድሞቹንም አንድ በአንድ እየሳመ አለቀሰ፤ ከዚህ በኋላም ወንድሞቹ ከእሱ ጋር ማውራት ጀመሩ። +16 “የዮሴፍ ወንድሞች መጥተዋል!” የሚለው ወሬ በፈርዖን ቤት ተሰማ። ፈርዖንና አገልጋዮቹም ደስ አላቸው። +17 ስለዚህ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “ወንድሞችህን እንዲህ በላቸው፦ ‘እንዲህ አድርጉ፦ የጋማ ከብቶቻችሁን ጫኑና ወደ ከነአን ምድር ሂዱ። +18 የግብፅን ምድር መልካም ነገሮች እንድሰጣችሁ አባታችሁንና ቤተሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ ከዚያም ለም* ከሆነው የምድሪቱ ክፍል ትበላላችሁ።’+ +19 አንተንም እንዲህ ብለህ እንድትነግራቸው አዝዤሃለሁ፦+ ‘እንዲህ አድርጉ፦ ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን የምታጓጉዙ��ቸውን ሠረገሎች ከግብፅ ምድር ውሰዱ፤+ አባታችሁንም በአንዱ ሠረገላ ላይ ጭናችሁ ወደዚህ ኑ።+ +20 ስለ ንብረታችሁ+ ምንም አትጨነቁ፤ ምክንያቱም በግብፅ ምድር ያለ ምርጥ ነገር ሁሉ የእናንተው ነው።’” +21 የእስራኤልም ወንዶች ልጆች እንደተባሉት አደረጉ፤ ዮሴፍ በፈርዖን ትእዛዝ መሠረት ሠረገሎችን ሰጣቸው፤ ለጉዟቸው የሚሆን ስንቅም አስያዛቸው። +22 ለእያንዳንዳቸው ቅያሪ ልብስ ሰጣቸው፤ ለቢንያም ግን 300 የብር ሰቅልና አምስት ቅያሪ ልብስ ሰጠው።+ +23 ለአባቱም የግብፅን ምድር መልካም ነገሮች የጫኑ አሥር አህዮችን እንዲሁም ለጉዞ ስንቅ እንዲሆነው እህል፣ ዳቦና ሌሎች ምግቦችን የጫኑ አሥር እንስት አህዮችን ላከ። +24 በዚህ መንገድ ወንድሞቹን ሸኛቸው፤ እነሱም ጉዞ ሲጀምሩ “ደግሞ በመንገድ ላይ እርስ በርስ እንዳትጣሉ” አላቸው።+ +25 እነሱም ከግብፅ ወጥተው ሄዱ፤ በከነአን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብም መጡ። +26 ከዚያም “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ ደግሞም በመላው የግብፅ ምድር ላይ ገዢ ሆኗል!”+ ሲሉ ነገሩት። እሱ ግን ክው ብሎ ቀረ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።+ +27 ዮሴፍ የነገራቸውን ነገር በሙሉ ሲነግሩትና ዮሴፍ እሱን ለመውሰድ የላካቸውን ሠረገሎች ሲያይ የአባታቸው የያዕቆብ መንፈስ ታደሰ። +28 እስራኤልም “በቃ አምኛችኋለሁ! ልጄ ዮሴፍ በሕይወት አለ! እንግዲህ ከመሞቴ በፊት ሄጄ ዓይኑን ማየት አለብኝ!” አላቸው።+ +12 ይሖዋም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ከአገርህ፣ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤት ወጥተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።+ +2 አንተን ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፤ አንተም በረከት ትሆናለህ።+ +3 የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግምህንም እረግማለሁ፤+ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በአንተ አማካኝነት ይባረካሉ።”*+ +4 ስለዚህ አብራም ልክ ይሖዋ በነገረው መሠረት ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን በወጣበት ጊዜ ዕድሜው 75 ዓመት ነበር።+ +5 አብራም ሚስቱን ሦራን፣+ የወንድሙን ልጅ ሎጥን+ እንዲሁም ያፈሩትን ንብረት ሁሉና+ በካራን አብረዋቸው የነበሩትን ሰዎች* በሙሉ ይዞ ተነሳ፤ እነሱም ወደ ከነአን ምድር አቀኑ።+ ከነአን ምድር በደረሱም ጊዜ +6 አብራም በሞሬ ትላልቅ ዛፎች+ አቅራቢያ እስከሚገኘው ሴኬም+ እስከሚባለው አካባቢ ድረስ ወደ ምድሪቱ ዘልቆ ገባ። በዚያን ጊዜ ከነአናውያን በምድሪቱ ይኖሩ ነበር። +7 ይሖዋም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ+ እሰጣለሁ”+ አለው። ስለዚህ አብራም ተገልጦለት ለነበረው ለይሖዋ በዚያ መሠዊያ ሠራ። +8 በኋላም ከዚያ ተነስቶ ከቤቴል+ በስተ ምሥራቅ ወደሚገኘው ተራራማ አካባቢ ተጓዘ፤ እሱም ቤቴልን በስተ ምዕራብ፣ ጋይን+ ደግሞ በስተ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ። በዚያም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ፤+ የይሖዋንም ስም ጠራ።+ +9 ከዚያ በኋላ አብራም ድንኳኑን ነቅሎ በየቦታው እየሰፈረ ወደ ኔጌብ+ ተጓዘ። +10 በምድሪቱም ላይ ረሃብ ተከሰተ፤ ረሃቡ በጣም አስከፊ ስለነበር+ አብራም ለተወሰነ ጊዜ* በግብፅ ለመኖር ወደዚያ ወረደ።+ +11 ወደ ግብፅ ለመግባት ሲቃረብም ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፦ “እባክሽ ስሚኝ፤ አንቺ በጣም ውብ ሴት ነሽ።+ +12 ስለሆነም ግብፃውያን አንቺን ሲያዩ ‘ይህች ሚስቱ ናት’ ማለታቸው አይቀርም። ከዚያም እኔን ይገድሉኛል፤ አንቺን ግን ይተዉሻል። +13 በአንቺ የተነሳ መልካም እንዲሆንልኝ እባክሽ፣ እህቴ እንደሆንሽ አድርገሽ ተናገሪ፤ እንዲህ ካደረግሽ ሕይወቴ ይተርፋል።”*+ +14 አብራምም ግብፅ እንደደረሰ ግብፃውያኑ ሴቲቱ እጅግ ውብ እንደሆነች ተመለከቱ። +15 የፈርዖንም መኳንንት ሴቲቱን አዩአት፤ ስለ እሷም ለፈርዖን በአድናቆት ነገሩት። በመሆኑም ሴቲቱ ወደ ፈርዖን ቤት ተወሰደች። +16 ፈርዖንም በእሷ ምክንያት አብራምን ተንከባከበው፤ በጎችን፣ ከብቶችን፣ ተባዕትና እንስት አህዮችን፣ ግመሎችን እንዲሁም ወንድና ሴት አገልጋዮችን ሰጠው።+ +17 ከዚያም ይሖዋ በአብራም ሚስት በሦራ+ የተነሳ ፈርዖንንና ቤተሰቡን በታላቅ መቅሰፍት መታ። +18 በመሆኑም ፈርዖን አብራምን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ይህ ያደረግክብኝ ነገር ምንድን ነው? ሚስትህ እንደሆነች ያልነገርከኝ ለምንድን ነው? +19 ‘እህቴ ናት’+ ያልከውስ ለምንድን ነው? እኔ እኮ ወስጄ ሚስቴ ላደርጋት ነበር። በል፣ ሚስትህ ይችውልህ፤ ይዘሃት ሂድ!” +20 ስለዚህ ፈርዖን አብራምን በተመለከተ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ እነሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋር አሰናበቱት።+ +1 በመጀመሪያ አምላክ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።+ +2 ምድርም ቅርጽ አልባና ባድማ ነበረች፤* ጥልቁም* ውኃ+ በጨለማ ተሸፍኖ ነበር፤ የአምላክም ኃይል*+ በውኃው ላይ ይንቀሳቀስ ነበር።+ +3 አምላክም “ብርሃን ይሁን” አለ። ብርሃንም ሆነ።+ +4 ከዚህ በኋላ አምላክ ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ አምላክም ብርሃኑን ከጨለማው ለየ። +5 አምላክም ብርሃኑን ‘ቀን’ ብሎ ጠራው፤ ጨለማውን ግን ‘ሌሊት’ ብሎ ጠራው።+ መሸ፣ ነጋም፤ የመጀመሪያ ቀን። +6 ከዚያም አምላክ “በውኃዎቹ መካከል ጠፈር+ ይሁን፣ ውኃዎቹም ከውኃዎቹ ይከፈሉ” አለ።+ +7 ከዚያም አምላክ ጠፈርን ሠራ፤ ከጠፈሩ በታች ያሉትንም ውኃዎች ከጠፈሩ በላይ ካሉት ውኃዎች ለየ።+ እንዳለውም ሆነ። +8 አምላክ ጠፈሩን ‘ሰማይ’ ብሎ ጠራው። መሸ፣ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን። +9 በመቀጠልም አምላክ “ከሰማያት በታች ያሉት ውኃዎች አንድ ቦታ ላይ ይሰብሰቡና ደረቁ መሬት ይገለጥ” አለ።+ እንዳለውም ሆነ። +10 አምላክ ደረቁን መሬት ‘የብስ’+ ብሎ ጠራው፤ አንድ ላይ የተሰበሰቡትን ውኃዎች ግን ‘ባሕር’+ ብሎ ጠራቸው። አምላክም ይህ መልካም እንደሆነ አየ።+ +11 ቀጥሎም አምላክ “ምድር ሣርን፣ ዘር የሚሰጡ ተክሎችን እንዲሁም ዘር ያለው ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ። እንዳለውም ሆነ። +12 ምድርም ሣርን፣ ዘር የሚሰጡ ተክሎችን+ እንዲሁም ዘር ያለው ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ማብቀል ጀመረች። ከዚያም አምላክ ይህ መልካም እንደሆነ አየ። +13 መሸ፣ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን። +14 አምላክም እንዲህ አለ፦ “ቀኑና ሌሊቱ እንዲለይ+ በሰማያት ጠፈር ላይ ብርሃን ሰጪ አካላት+ ይኑሩ፤ እነሱም ወቅቶችን፣ ቀናትንና ዓመታትን+ የሚጠቁሙ ምልክቶች ሆነው ያገለግላሉ። +15 በምድርም ላይ እንዲያበሩ በሰማያት ጠፈር ላይ ያሉ ብርሃን ሰጪ አካላት ሆነው ያገለግላሉ።” እንዳለውም ሆነ። +16 አምላክም ሁለቱን ታላላቅ ብርሃን ሰጪ አካላት ሠራ፤ ታላቁ ብርሃን ሰጪ አካል በቀን እንዲያይል፣+ ታናሹ ብርሃን ሰጪ አካል ደግሞ በሌሊት እንዲያይል አደረገ፤ ከዋክብትንም ሠራ።+ +17 በዚህ መንገድ አምላክ በምድር ላይ እንዲያበሩ በሰማያት ጠፈር ላይ አስቀመጣቸው፤ +18 በተጨማሪም በቀንና በሌሊት እንዲያይሉ እንዲሁም ብርሃኑን ከጨለማው እንዲለዩ አደረገ።+ አምላክም ይህ መልካም እንደሆነ አየ። +19 መሸ፣ ነጋም፤ አራተኛ ቀን። +20 ከዚያም አምላክ “ውኃዎቹ በሚርመሰመሱ ሕያዋን ፍጥረታት* ይሞሉ፤ እንዲሁም የሚበርሩ ፍጥረታት ከምድር በላይ በሰማያት ጠፈር ላይ ይብረሩ” አለ።+ +21 አምላክም ግዙፍ የባሕር ፍጥረታትን እንዲሁም በውኃዎቹ ውስጥ የሚንቀሳቀሱና የሚርመሰመሱ ሕያዋን ፍጥረታትን* ሁሉ እንደየወገናቸው ብሎም ክንፍ ያለውን እያንዳንዱን የሚበር ፍጥረት እንደየወገኑ ፈጠረ። አምላክ�� ይህ መልካም እንደሆነ አየ። +22 ከዚያም አምላክ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕሩንም ውኃ ሙሉት፤+ የሚበርሩ ፍጥረታትም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። +23 መሸ፣ ነጋም፤ አምስተኛ ቀን። +24 ቀጥሎም አምላክ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን* እንደየወገናቸው እንዲሁም የቤት እንስሳትን፣ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትንና* የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው ታውጣ” አለ።+ እንዳለውም ሆነ። +25 አምላክም በምድር ላይ ያሉ የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ የቤት እንስሳትን እንደየወገናቸው እንዲሁም መሬት ለመሬት የሚሄዱ ፍጥረታትን ሁሉ እንደየወገናቸው ሠራ። አምላክም ይህ መልካም እንደሆነ አየ። +26 ከዚያም አምላክ “ሰውን በመልካችን እንደ አምሳላችን+ እንሥራ፤+ እሱም በባሕር ዓሣዎች፣ በሰማያት ላይ በሚበርሩ ፍጥረታት፣ በቤት እንስሳትና በምድር ሁሉ እንዲሁም በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳት ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑረው”+ አለ። +27 አምላክም ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በአምላክ መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።+ +28 በተጨማሪም አምላክ ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤+ ግዟትም።+ እንዲሁም የባሕር ዓሣዎችን፣ በሰማያት ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትንና በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረታትን በሙሉ ግዟቸው።”+ +29 ቀጥሎም አምላክ እንዲህ አለ፦ “በመላው ምድር ላይ ያሉ ዘር የሚሰጡ ተክሎችን በሙሉ እንዲሁም ዘር ያለው ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን በሙሉ ይኸው ሰጥቻችኋለሁ። ምግብ ይሁኗችሁ።+ +30 በምድር ላይ ላለው የዱር እንስሳ ሁሉ፣ በሰማያት ላይ ለሚበር ፍጥረት ሁሉ እንዲሁም ሕይወት* ላለው በምድር ላይ ለሚንቀሳቀስ ነገር ሁሉ አረንጓዴ ተክሎችን በሙሉ ምግብ እንዲሆኗቸው ሰጥቻቸዋለሁ።”+ እንዳለውም ሆነ። +31 ከዚያ በኋላ አምላክ የሠራውን እያንዳንዱን ነገር ተመለከተ፤ እነሆ፣ እጅግ መልካም ነበር!+ መሸ፣ ነጋም፤ ስድስተኛ ቀን። +49 ያዕቆብም ወንዶች ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በኋለኞቹ ቀናት ምን እንደሚያጋጥማችሁ እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ። +2 እናንተ የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ተሰብሰቡና ስሙ፤ አዎ፣ አባታችሁን እስራኤልን አዳምጡ። +3 “ሮቤል፣+ አንተ የበኩር ልጄ ነህ፤+ ኃይሌና የብርታቴ የመጀመሪያ ፍሬ ነህ፤ የላቀ ክብርና የላቀ ኃይል ነበረህ። +4 እንደሚናወጥ ውኃ ስለምትዋልል የበላይ አትሆንም፤ ምክንያቱም አባትህ አልጋ ላይ ወጥተሃል።+ በዚያን ወቅት መኝታዬን አርክሰሃል። በእርግጥም አልጋዬ ላይ ወጥቷል! +5 “ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው።+ ሰይፎቻቸው የዓመፅ መሣሪያዎች ናቸው።+ +6 ነፍሴ* ሆይ፣ ከእነሱ ጋር አትወዳጂ። ክብሬ ሆይ፣ ከእነሱ ማኅበር ጋር አትተባበር፤ ምክንያቱም በቁጣ ተነሳስተው ሰዎችን ገድለዋል፤+ ደስ ስላላቸውም ብቻ የበሬዎችን ቋንጃ ቆርጠዋል። +7 ቁጣቸው ጨካኝ፣ ንዴታቸውም ምሕረት የለሽ ስለሆነ የተረገመ ይሁን።+ በያዕቆብ ልበትናቸው፤ በእስራኤልም ላሰራጫቸው።+ +8 “ይሁዳ+ ሆይ፣ ወንድሞችህ ያወድሱሃል።+ እጅህ የጠላቶችህን አንገት ያንቃል።+ የአባትህ ወንዶች ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።+ +9 ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው።+ ልጄ፣ በእርግጥም ያደንከውን በልተህ ትነሳለህ። እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ እንደ አንበሳ ይንጠራራል፤ ማንስ ሊያስነሳው ይደፍራል? +10 ሴሎ* እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣+ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤+ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል።+ +11 አህያውን በወይን ተክል ላይ፣ ውርንጭላውንም ምርጥ በሆነ የወይን ተክል ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጎናጸፊያውንም በወይን ፍሬ ጭማቂ ያጥባል። +12 ዓይ��ቹ ከወይን ጠጅ የተነሳ የቀሉ፣ ጥርሶቹም ከወተት የተነሳ የነጡ ናቸው። +13 “የዛብሎን+ መኖሪያ በባሕር ዳርቻ፣ መርከቦች መልሕቅ ጥለው በሚቆሙበት ዳርቻ ይሆናል፤+ የወሰኑም ጫፍ በሲዶና አቅጣጫ ይሆናል።+ +14 “ይሳኮር+ በመንታ ጭነት መካከል የሚተኛ አጥንተ ብርቱ አህያ ነው። +15 ማረፊያ ቦታው መልካም፣ ምድሩም አስደሳች መሆኑን ያያል። ሸክሙን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤ ለግዳጅ ሥራ ይንበረከካል። +16 “ከእስራኤል ነገዶች አንዱ የሆነው ዳን+ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል።+ +17 ዳን፣ ጋላቢው ወደ ኋላ እንዲወድቅ የፈረሱን ሰኮና የሚነክስ በመንገድ ዳር ያለ እባብ፣ በመተላለፊያ ላይ ያለ ቀንዳም እባብ ይሁን።+ +18 ይሖዋ ሆይ፣ የአንተን ማዳን እጠባበቃለሁ። +19 “ጋድ+ ደግሞ የወራሪዎች ቡድን አደጋ ይጥልበታል፤ እሱ ግን ዱካውን ተከታትሎ ይመታዋል።+ +20 “የአሴር+ ምግብ የተትረፈረፈ* ይሆናል፤ በንጉሥ ፊት የሚቀርብ ምግብ ያዘጋጃል።+ +21 “ንፍታሌም+ ሸንቃጣ የሜዳ ፍየል ነው። ከአፉም ያማሩ ቃላት ይወጣሉ።+ +22 “ዮሴፍ+ ፍሬያማ የሆነ ዛፍ ቀንበጥ ነው፤ ቅርንጫፎቹን በግንብ ላይ የሚሰድ በምንጭ ዳር ያለ ፍሬያማ የሆነ ዛፍ ቀንበጥ ነው። +23 ቀስተኞች ግን እረፍት ነሱት፤ ቀስታቸውንም ወረወሩበት፤ ለእሱም ጥላቻ አደረባቸው።+ +24 ሆኖም ቀስቱ ከቦታው ንቅንቅ አላለም፤+ እጆቹም ብርቱና ቀልጣፋ ናቸው።+ ይህም ከያዕቆብ ኃያል አምላክ እጆች፣ ከእረኛው፣ ከእስራኤል ዓለት የተገኘ ነው። +25 እሱ* ከአባትህ አምላክ የተገኘ ነው፤ አምላክም ይረዳሃል፤ እሱም ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ጋር ይሆናል። አምላክም ከላይ ከሰማያት በሚገኙ በረከቶች፣ ከታች ከጥልቁ በሚገኙ በረከቶች+ እንዲሁም ከጡትና ከማህፀን በሚገኙ በረከቶች ይባርክሃል። +26 የአባትህ በረከቶች ከዘላለማዊ ተራሮች ከሚመጡት በረከቶችና ጸንተው ከሚኖሩት ኮረብቶች ከሚገኙት መልካም ነገሮች የላቁ ይሆናሉ።+ በረከቶቹም በዮሴፍ ራስ ላይ፣ ከወንድሞቹ መካከል ተነጥሎ በወጣው በእሱ አናት ላይ ይሆናሉ።+ +27 “ቢንያም+ እንደ ተኩላ ይቦጫጭቃል።+ ያደነውን ጠዋት ላይ ይበላል፤ ምሽት ላይ ደግሞ ምርኮ ያከፋፍላል።”+ +28 እነዚህ ሁሉ 12ቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፤ አባታቸው በባረካቸው ጊዜ የነገራቸው ነገር ይህ ነው። ለእያንዳንዳቸውም የሚገባቸውን በረከት ሰጣቸው።+ +29 ከዚህ በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዛት ሰጣቸው፦ “እንግዲህ እኔ ወደ ወገኖቼ ልሰበሰብ* ነው።+ በሂታዊው በኤፍሮን እርሻ ውስጥ በሚገኘው ዋሻ+ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ +30 አብርሃም ለመቃብር ስፍራ ብሎ ከሂታዊው ከኤፍሮን በገዛው እርሻ ይኸውም በከነአን ምድር በማምሬ ፊት ለፊት በሚገኘው በማክፈላ እርሻ ውስጥ ባለው ዋሻ ቅበሩኝ። +31 አብርሃምንና ሚስቱን ሣራን የቀበሯቸው እዚያ ነው።+ ይስሐቅንና ሚስቱን ርብቃንም የቀበሯቸው እዚያ ነው፤+ እኔም ብሆን ሊያን የቀበርኳት እዚያው ነው። +32 እርሻውም ሆነ በውስጡ ያለው ዋሻ የተገዛው ከሄት ወንዶች ልጆች ነው።”+ +33 በዚህ መንገድ ያዕቆብ ለወንዶች ልጆቹ እነዚህን መመሪያዎች ሰጥቶ ጨረሰ። ከዚያም እግሮቹን ወደ አልጋው አውጥቶ የመጨረሻ እስትንፋሱን ተነፈሰ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።*+ +36 የኤሳው ማለትም የኤዶም + ታሪክ ይህ ነው። +2 ኤሳው ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ እነሱም የሂታዊው+ የኤሎን ልጅ አዳ+ እንዲሁም የአና ልጅና የሂዋዊው የጺብኦን የልጅ ልጅ የሆነችው ኦሆሊባማ+ ናቸው፤ +3 በተጨማሪም የእስማኤል ልጅ የሆነችውን የነባዮትን+ እህት ባሴማትን+ አገባ። +4 አዳ ለኤሳው ኤሊፋዝን ወለደችለት፤ ባሴማት ደግሞ ረኡዔልን ወለደች፤ +5 ኦሆሊባማ የኡሽን፣ ያላምን እና ቆሬን ወለደች።+ እነዚህ ኤሳው በከነአን ምድር ሳለ የተወለዱለት ልጆች ናቸው። +6 ከዚያም ኤሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ የቤተሰቡን አባላት* ሁሉ፣ መንጋውን፣ ሌሎቹን እንስሳት ሁሉና በከነአን ምድር ያፈራውን ሀብት ሁሉ+ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ርቆ ወደ ሌላ ምድር ሄደ።+ +7 ምክንያቱም ንብረታቸው በጣም ስለበዛ አብረው መኖር አልቻሉም፤ እንዲሁም ከመንጋቸው ብዛት የተነሳ ይኖሩበት* የነበረው ምድር ሊበቃቸው አልቻለም። +8 በመሆኑም ኤሳው በሴይር ተራራማ አካባቢ መኖር ጀመረ።+ ኤሳው ኤዶም ተብሎም ይጠራል።+ +9 በሴይር ተራራማ አካባቢ የሚኖረው የኤዶማውያን አባት የኤሳው ታሪክ ይህ ነው።+ +10 የኤሳው ወንዶች ልጆች ስም የሚከተለው ነው፦ የኤሳው ሚስት የአዳ ልጅ ኤሊፋዝና የኤሳው ሚስት የባሴማት ልጅ ረኡዔል ናቸው።+ +11 የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆች ደግሞ ቴማን፣+ ኦማር፣ ጸፎ፣ ጋታም እና ቀናዝ+ ናቸው። +12 ቲምና የኤሳው ልጅ የኤሊፋዝ ቁባት ሆነች። ከጊዜ በኋላም ለኤሊፋዝ አማሌቅን+ ወለደችለት። የኤሳው ሚስት የአዳ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። +13 የረኡዔል ወንዶች ልጆች ናሃት፣ ዛራ፣ ሻማህ እና ሚዛህ ናቸው። እነዚህም የኤሳው ሚስት የባሴማት+ ልጆች ነበሩ። +14 የአና ልጅና የጺብኦን የልጅ ልጅ የሆነችው የኤሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለኤሳው የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች የኡሽ፣ ያላም እና ቆሬ ናቸው። +15 የነገድ አለቆች* የሆኑት የኤሳው ወንዶች ልጆች+ የሚከተሉት ናቸው፦ የኤሳው የበኩር ልጅ የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆችም አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ጸፎ፣ አለቃ ቀናዝ፣+ +16 አለቃ ቆሬ፣ አለቃ ጋታም እና አለቃ አማሌቅ ናቸው። እነዚህ በኤዶም ምድር የነገድ አለቆች የሆኑት የኤሊፋዝ ልጆች+ ነበሩ። እነዚህ የአዳ ወንዶች ልጆች ናቸው። +17 የኤሳው ልጅ የረኡዔል ወንዶች ልጆች፣ አለቃ ናሃት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሻማህ እና አለቃ ሚዛህ ናቸው። እነዚህ በኤዶም ምድር የነገድ አለቆች የሆኑት የረኡዔል ልጆች+ ናቸው። እነዚህ የኤሳው ሚስት የባሴማት ወንዶች ልጆች ናቸው። +18 በመጨረሻም የኤሳው ሚስት የኦሆሊባማ ወንዶች ልጆች፣ አለቃ የኡሽ፣ አለቃ ያላም እና አለቃ ቆሬ ናቸው። እነዚህ የነገድ አለቆች የአና ልጅ የሆነችው የኤሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች ናቸው። +19 የኤሳው ማለትም የኤዶም+ ወንዶች ልጆችና አለቆቻቸው እነዚህ ናቸው። +20 በዚያ ምድር የሚኖሩት የሆራዊው የሴይር ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦+ ሎጣን፣ ሾባል፣ ጺብኦን፣ አና፣+ +21 ዲሾን፣ ኤጼር እና ዲሻን።+ እነዚህ በኤዶም ምድር የሆራውያን የነገድ አለቆች የሆኑት የሴይር ወንዶች ልጆች ናቸው። +22 የሎጣን ወንዶች ልጆች ሆሪ እና ሄማም ናቸው፤ የሎጣን እህት ቲምና ትባላለች።+ +23 የሾባል ወንዶች ልጆች አልዋን፣ ማናሃት፣ ኤባል፣ ሼፎ እና ኦናም ናቸው። +24 የጺብኦን+ ወንዶች ልጆች አያ እና አና ናቸው። ይህ አና የአባቱን የጺብኦንን አህዮች ሲጠብቅ በምድረ በዳ የፍል ውኃ ምንጮችን ያገኘው ነው። +25 የአና ልጆች ዲሾን እና የአና ሴት ልጅ ኦሆሊባማ ናቸው። +26 የዲሾን ወንዶች ልጆች ሄምዳን፣ ኤሽባን፣ ይትራን እና ኬራን ናቸው።+ +27 የኤጼር ወንዶች ልጆች ቢልሃን፣ ዛአዋን እና አቃን ናቸው። +28 የዲሻን ወንዶች ልጆች ዑጽ እና አራን ናቸው።+ +29 የሆራውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ናቸው፦ አለቃ ሎጣን፣ አለቃ ሾባል፣ አለቃ ጺብኦን፣ አለቃ አና፣ +30 አለቃ ዲሾን፣ አለቃ ኤጼር እና አለቃ ዲሻን።+ በሴይር ምድር የሆራውያን የነገድ አለቆች በየአለቆቻቸው ሲዘረዘሩ እነዚህ ናቸው። +31 እነዚህ በእስራኤላውያን* ላይ የትኛውም ንጉሥ መግዛት ከመጀመሩ በፊት+ በኤዶም ምድር ይገዙ የነበሩ ነገሥታት ናቸው።+ +32 የቢዖር ልጅ ቤላ በኤዶም ይገዛ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። +33 ቤላ ሲሞት የቦስራው የዛራ ልጅ ዮባብ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +34 ዮባብ ሲሞት ከቴማናውያን ምድር የመጣው ሁሻም በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +35 ሁሻም ሲሞት ምድያማውያንን+ በሞዓብ ክልል* ድል ያደረጋቸው የቤዳድ ልጅ ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ፤ የከተማውም ስም አዊት ይባል ነበር። +36 ሃዳድ ሲሞት የማስረቃው ሳምላ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +37 ሳምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለው የረሆቦቱ ሻኡል በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +38 ሻኡል ሲሞት የአክቦር ልጅ ባአልሀናን በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +39 የአክቦር ልጅ ባአልሀናን ሲሞት ሃዳር በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማው ስም ጳኡ ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣቤል ሲሆን እሷም የመዛሃብ ሴት ልጅ የማጥሬድ ልጅ ናት። +40 እንግዲህ የኤሳው ልጆች የሆኑ የነገድ አለቆች በየቤተሰባቸው፣ በየስፍራቸውና በየስማቸው ሲዘረዘሩ ስማቸው ይህ ነው፦ አለቃ ቲምና፣ አለቃ አልዋህ፣ አለቃ የቴት፣+ +41 አለቃ ኦሆሊባማ፣ አለቃ ኤላህ፣ አለቃ ፒኖን፣ +42 አለቃ ቀናዝ፣ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ሚብጻር፣ +43 አለቃ ማግዲኤል እና አለቃ ኢራም። ከኤዶም የተገኙት የነገድ አለቆች ርስት አድርገው በያዙት ምድር እንደየመኖሪያቸው ሲዘረዘሩ እነዚህ ናቸው።+ የኤዶማውያን አባት ኤሳው ይህ ነው።+ +29 ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ጉዞውን ቀጠለ፤ ወደ ምሥራቅ ሰዎች ምድርም ሄደ። +2 እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውኃ ጉድጓድ ተመለከተ፤ እረኞች የበግ መንጎቻቸውን ሁልጊዜ የሚያጠጡት ከዚያ የውኃ ጉድጓድ ስለነበር በአቅራቢያው ሦስት የበግ መንጎች ተኝተው አየ። በጉድጓዱም አፍ ላይ ትልቅ ድንጋይ ነበር። +3 መንጎቹ በሙሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ በውኃ ጉድጓዱ አፍ ላይ ያለውን ድንጋይ ያንከባልሉና መንጎቹን ያጠጣሉ፤ ከዚያም ድንጋዩን ወደ ቦታው በመመለስ የጉድጓዱን አፍ ይገጥሙታል። +4 ያዕቆብም “ወንድሞቼ፣ ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነሱም “ከካራን+ ነው የመጣነው” አሉት። +5 እሱም “የናኮርን+ የልጅ ልጅ ላባን+ ታውቁታላችሁ?” አላቸው፤ እነሱም “አዎ፣ እናውቀዋለን” አሉት። +6 እሱም “ለመሆኑ ደህና ነው?” አላቸው። እነሱም “አዎ፣ ደህና ነው። እንዲያውም ልጁ ራሔል+ ይኸው በጎች ይዛ እየመጣች ነው!” አሉት። +7 ከዚያም እሱ “እንደምታዩት ገና እኩለ ቀን ነው። አሁን እኮ መንጎች የሚገቡበት ሰዓት አይደለም፤ በጎቹን አጠጧቸውና ወደ ግጦሽ አሰማሯቸው” አላቸው። +8 እነሱም “መንጎቹ ሁሉ ካልተሰባሰቡና እረኞቹ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ላይ ካላንከባለሉት እንዲህ ማድረግ አንችልም፤ በጎቹን ማጠጣት የምንችለው ከዚያ በኋላ ነው” አሉት። +9 እሱም ገና ከእነሱ ጋር እየተነጋገረ ሳለ ራሔል እረኛ ስለነበረች የአባቷን በጎች እየነዳች መጣች። +10 ያዕቆብ የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የላባን በጎች ሲያይ ወዲያውኑ ወደ ጉድጓዱ ሄዶ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ላይ አንከባለለ፤ የእናቱን ወንድም የላባን በጎችም አጠጣ። +11 ከዚያም ያዕቆብ ራሔልን ሳማት፤ ጮክ ብሎም አለቀሰ። +12 ያዕቆብም ለራሔል የአባቷ ዘመድና* የርብቃ ልጅ መሆኑን ነገራት። እሷም እየሮጠች ሄዳ ለአባቷ ነገረችው። +13 ላባም+ የእህቱ ልጅ ስለሆነው ስለ ያዕቆብ ሲሰማ ወደ እሱ እየሮጠ ሄዶ አቅፎ ሳመው፤ ወደ ቤቱም አስገባው። ያዕቆብም ሁኔታውን ሁሉ ለላባ ነገረው። +14 ላባም “በእርግጥም አንተ የአጥንቴ ፍላጭ የሥጋዬ ቁራጭ* ነህ” አለው። በመሆኑም ያዕቆብ ከእሱ ጋር አንድ ወር ሙሉ ተቀመጠ። +15 ከዚያም ላባ ያዕቆብን “ዘመዴ*+ ስለሆንክ ብቻ እኔን በነፃ ልታገለግ���ኝ ይገባል? ንገረኝ፣ ደሞዝህ ምንድን ነው?”+ አለው። +16 ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት። የታላቋ ስም ሊያ ሲሆን የታናሿ ስም ደግሞ ራሔል ነበር።+ +17 ሊያ ዓይነ ልም* ነበረች፤ ራሔል ግን ዓይን የምትማርክ ውብ ሴት ነበረች። +18 ያዕቆብ ራሔልን ይወዳት ስለነበር “ለታናሿ ልጅህ ለራሔል ስል ሰባት ዓመት ላገለግልህ ፈቃደኛ ነኝ” አለው።+ +19 ላባም “ለሌላ ሰው ከምሰጣት ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ አብረኸኝ ተቀመጥ” አለው። +20 ያዕቆብም ለራሔል ሲል ሰባት ዓመት አገለገለ፤+ ይሁንና ራሔልን ይወዳት ስለነበር ሰባቱ ዓመታት ለእሱ እንደ ጥቂት ቀናት ነበሩ። +21 ከዚያም ያዕቆብ ላባን “እንግዲህ የተባባልነው ጊዜ ስላበቃ ሚስቴን ስጠኝ፤ ከእሷም ጋር ልተኛ” አለው። +22 ስለዚህ ላባ የአካባቢውን ሰዎች በሙሉ ጠራ፤ ግብዣም አደረገ። +23 ሆኖም ሲመሽ ላባ ልጁን ሊያን ወስዶ ከእሷ ጋር እንዲተኛ ለያዕቆብ ሰጠው። +24 በተጨማሪም ላባ የእሱ አገልጋይ የሆነችውን ዚልጳን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለሊያ ሰጣት።+ +25 በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ሊያ መሆኗን አወቀ! በመሆኑም ያዕቆብ ላባን “ያደረግክብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልኩህ ለራሔል ስል አልነበረም? ታዲያ ለምን አታለልከኝ?”+ አለው። +26 ላባም እንዲህ አለው፦ “በአካባቢያችን በኩሯ እያለች ታናሺቱን መዳር የተለመደ አይደለም። +27 ሳምንቱን ከዚህችኛዋ ጋር ተሞሸር። ከዚያም ለምታገለግለኝ ተጨማሪ ሰባት ዓመታት ሌላኛዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።”+ +28 ያዕቆብም እንደተባለው አደረገ፤ ሳምንቱን ከዚህችኛዋ ጋር ተሞሸረ። ከዚያም ላባ ልጁን ራሔልን ሚስት እንድትሆነው ሰጠው። +29 በተጨማሪም ላባ አገልጋዩ የሆነችውን ባላን+ አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለራሔል ሰጣት።+ +30 ከዚያም ያዕቆብ ከራሔል ጋር ተኛ፤ ራሔልንም ከሊያ ይልቅ ወደዳት። ላባንም ሌላ ሰባት ዓመት አገለገለው።+ +31 ይሖዋም ሊያ እንዳልተወደደች* ሲመለከት መፀነስ እንድትችል አደረጋት፤*+ ራሔል ግን መሃን ነበረች።+ +32 ሊያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ይህ የሆነው ይሖዋ መከራዬን ስላየልኝ ነው፤+ ከእንግዲህ ባሌ ይወደኛል” ስትል ስሙን ሮቤል*+ አለችው። +33 ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ይሖዋ እንዳልተወደድኩ ስለሰማ ይሄኛውንም ልጅ ሰጠኝ” አለች። ስሙንም ስምዖን*+ አለችው። +34 አሁንም ደግሞ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ሦስት ወንዶች ልጆች ስለወለድኩለት አሁን ባሌ ይቀርበኛል” አለች። በዚህም የተነሳ ሌዊ*+ ተባለ። +35 አሁንም እንደገና ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “አሁን ይሖዋን አወድሰዋለሁ” አለች። ስለሆነም ይሁዳ*+ አለችው። ከዚያ በኋላ መውለድ አቆመች። +28 በመሆኑም ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ ባረከውና እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳታገባ።+ +2 በጳዳንአራም ወደሚገኘው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድና ከእናትህ ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች+ መካከል አንዷን አግባ። +3 ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ይባርክሃል፤ ፍሬያማም ያደርግሃል፤ እንዲሁም ያበዛሃል፤ አንተም በእርግጥ ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ጉባኤ ትሆናለህ።+ +4 አምላክ ለአብርሃም የሰጠውን፣+ አንተም እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ የምትኖርበትን ምድር እንድትወርስ የአብርሃምን በረከት+ ለአንተና ከአንተ ጋር ላለው ዘርህ ይሰጣል።” +5 ስለሆነም ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ እሱም የያዕቆብና የኤሳው እናት የርብቃ ወንድም+ እንዲሁም የአራማዊው የባቱኤል ልጅ ወደሆነው ወደ ላባ+ ለመሄድ ወደ ጳዳንአራም ጉዞ ጀመረ። +6 ኤሳው፣ ይስሐቅ ያዕቆብን እንደባረከውና ሚስት እንዲያገባ ወደ ጳዳንአራም እንደላከው እንዲሁም በባረከው ጊዜ “ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳታገባ”+ ብሎ እንዳዘዘውና +7 ያዕቆብም አባቱንና እናቱን በመታዘዝ ወደ ጳዳንአራም እንደሄደ አወቀ።+ +8 በዚህ ጊዜ ኤሳው የከነአን ሴቶች ልጆች በአባቱ በይስሐቅ ዘንድ የተጠሉ መሆናቸውን ተገነዘበ፤+ +9 ስለዚህ ኤሳው ወደ እስማኤል ሄደ፤ ካሉትም ሚስቶች በተጨማሪ የአብርሃም ልጅ እስማኤል የወለዳትን የነባዮትን እህት ማሃላትን አገባ።+ +10 ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነስቶ ወደ ካራን አቀና።+ +11 ከዚያም ወደ አንድ ስፍራ ደረሰ፤ ፀሐይ ጠልቃ ስለነበረም እዚያ ለማደር አሰበ። በመሆኑም በአካባቢው ካሉት ድንጋዮች አንዱን አንስቶ በመንተራስ እዚያው ተኛ።+ +12 እሱም ሕልም አለመ፤ በሕልሙም በምድር ላይ የተተከለ ደረጃ* አየ፤ የደረጃውም ጫፍ እስከ ሰማያት ይደርስ ነበር፤ በላዩም ላይ የአምላክ መላእክት ይወጡና ይወርዱ ነበር።+ +13 ከደረጃውም በላይ ይሖዋ ነበር፤ እሱም እንዲህ አለ፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክና የይስሐቅ አምላክ ይሖዋ ነኝ።+ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ።+ +14 ዘርህም በእርግጥ እንደ ምድር አፈር ብዙ ይሆናል፤+ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ምሥራቅ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ትስፋፋለህ። የምድር ቤተሰቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካኝነት በእርግጥ ይባረካሉ።*+ +15 እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ።+ የገባሁልህን ቃል እስክፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።”+ +16 ከዚያም ያዕቆብ ከእንቅልፉ ነቅቶ “በእርግጥም በዚህ ስፍራ ይሖዋ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅኩም ነበር” አለ። +17 እሱም በፍርሃት ተዋጠ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ስፍራ እንዴት የሚያስፈራ ነው! ይህ የአምላክ ቤት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፤+ ይህ የሰማያት በር ነው።”+ +18 በመሆኑም ያዕቆብ በማለዳ ተነሳ፤ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ወስዶ እንደ ዓምድ አቆመው፤ በአናቱም ላይ ዘይት አፈሰሰበት።+ +19 ስለዚህ ያን ቦታ ቤቴል* አለው፤ የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ሎዛ+ ነበር። +20 ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ስእለት ተሳለ፦ “አምላክ ከእኔ ባይለይና በመንገዴ ቢጠብቀኝ እንዲሁም የምበላው ምግብና የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ፣ +21 ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብመለስ ይሖዋ አምላኬ መሆኑን አስመሠከረ ማለት ነው። +22 እንደ ዓምድ ያቆምኩት ይህ ድንጋይም የአምላክ ቤት ይሆናል፤+ አምላክ ሆይ፣ እኔም ከምትሰጠኝ ከማንኛውም ነገር አንድ አሥረኛውን ለአንተ እሰጣለሁ።” +38 በዚሁ ጊዜ አካባቢ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ በመውረድ ሂራ በሚባል አዱላማዊ ሰው አቅራቢያ ድንኳኑን ተከለ። +2 በዚያም ሹአ የሚባል የአንድ ከነአናዊ ሰው ሴት ልጅ+ አየ። እሷንም አገባትና ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ +3 እሷም ፀነሰች። ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኤር+ አለው። +4 ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኦናን አለችው። +5 በድጋሚም ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም አለችው። እሱም* ልጅ በወለደችለት ጊዜ አክዚብ+ በሚባል ቦታ ነበር። +6 ከጊዜ በኋላ ይሁዳ ለበኩር ልጁ ለኤር ሚስት አመጣለት፤ ስሟም ትዕማር+ ይባል ነበር። +7 ይሁንና የይሁዳ የበኩር ልጅ ኤር ይሖዋ ያዘነበት ሰው ነበር፤ በመሆኑም ይሖዋ በሞት ቀሰፈው። +8 በዚህ የተነሳ ይሁዳ ኦናንን “ከወንድምህ ሚስት ጋር ግንኙነት በመፈጸም የዋርሳነት ግዴታህን ተወጣ፤ ለወንድምህም ዘር ተካለት” አለው።+ +9 ኦናን ግን የሚወለደው ልጅ የእሱ ልጅ እንደሆነ ተደርጎ እንደማይቆጠር ያውቅ ነበር።+ በመሆኑም ለወንድሙ ዘር ላለመተካት ሲል ከወንድሙ ሚስት ጋር ግንኙነት በሚፈጽምበት ጊዜ ዘሩን መሬት ላይ ያፈስ ነበር።+ +10 እሱም ያደረገው ነገር በይሖዋ ፊት መጥፎ ስለነበር አምላክ በሞት ቀሰፈው።+ +11 ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን “ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ” አላት፤ ይህን ያላት ‘እሱም እንደ ወንድሞቹ ሊሞትብኝ ይችላል’ ብሎ ስላሰበ ነው።+ ስለዚህ ትዕማር ሄዳ በአባቷ ቤት መኖር ጀመረች። +12 የተወሰነ ጊዜ ካለፈ በኋላም የሹአ+ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳም ሐዘን ተቀምጦ ተነሳ፤ ከዚያም ከአዱላማዊው ወዳጁ ከሂራ+ ጋር በመሆን በጎቹን የሚሸልቱለት ሰዎች ወዳሉበት ወደ ቲምና+ ሄደ። +13 ትዕማርም “አማትሽ በጎቹን ለመሸለት ወደ ቲምና እየወጣ ነው” ተብሎ ተነገራት። +14 በዚህ ጊዜ የመበለትነት ልብሷን በማውለቅ የአንገት ልብስ ተከናንባና ፊቷን ተሸፍና ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ላይ በምትገኘው በኤናይም መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው ሴሎም ቢያድግም ለእሱ እንዳልተዳረች ስላየች ነው።+ +15 ይሁዳም ባያት ጊዜ ዝሙት አዳሪ መሰለችው፤ ምክንያቱም ፊቷን ሸፍና ነበር። +16 ስለሆነም ከመንገዱ ወጣ በማለት ወደ እሷ ጠጋ ብሎ “እባክሽ አብሬሽ እንድተኛ ፍቀጂልኝ” አላት፤ ይህን ያደረገውም ምራቱ መሆኗን ስላላወቀ ነው።+ ሆኖም እሷ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው። +17 እሱም “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እሷ ግን “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ መያዣ ትሰጠኛለህ?” አለችው። +18 እሱም “ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እሷም “የማኅተም ቀለበትህን+ ከነማንጠልጠያ ክሩ እንዲሁም በእጅህ የያዝከውን በትርህን ስጠኝ” አለችው። ከዚያም እነዚህን ነገሮች ሰጣት፤ ከእሷም ጋር ተኛ፤ ከእሱም ፀነሰች። +19 ከዚያ በኋላ ተነስታ ሄደች፤ የአንገት ልብሷንም አውልቃ የመበለትነት ልብሷን ለበሰች። +20 ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ለማስመለስ አዱላማዊ+ ወዳጁን የፍየል ጠቦት አስይዞ ወደ እሷ ላከው፤ እሱ ግን ፈጽሞ ሊያገኛት አልቻለም። +21 እሱም የአካባቢውን ሰዎች “ያቺ መንገድ ዳር የምትቀመጠው በኤናይም ያለች የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ የት አለች?” በማለት ጠየቀ። እነሱ ግን “ኧረ በዚህ አካባቢ የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ ታይታ አትታወቅም” አሉት። +22 በመጨረሻም ወደ ይሁዳ ተመልሶ እንዲህ አለው፦ “ሴቲቱን በፍጹም ላገኛት አልቻልኩም፤ ደግሞም የአካባቢው ሰዎች ‘በዚህ አካባቢ የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ ታይታ አትታወቅም’ አሉኝ።” +23 በመሆኑም ይሁዳ “በኋላ እኛ መሳለቂያ እንዳንሆን መያዣውን ትውሰደው። እኔ እንደሆነ ይህን ጠቦት ልኬላት ነበር፤ አንተ ግን ፈጽሞ ልታገኛት አልቻልክም” አለው። +24 ይሁን እንጂ ከሦስት ወር በኋላ ለይሁዳ “ምራትህ ትዕማር ዝሙት አዳሪ ሆናለች፤ ዝሙት በመፈጸሟም ፀንሳለች” ተብሎ ተነገረው። በዚህ ጊዜ ይሁዳ “አውጧትና በእሳት ትቃጠል” አለ።+ +25 እሷም ይዘዋት እየሄዱ ሳሉ ለአማቷ “የፀነስኩት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” የሚል መልእክት ላከችበት። በተጨማሪም “ይህ የማኅተም ቀለበትና ማንጠልጠያ ክሩ እንዲሁም ይህ በትር የማን እንደሆነ እስቲ አጣራ” አለችው።+ +26 ይሁዳም ዕቃዎቹን ከተመለከተ በኋላ “እሷ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ናት፤ ምክንያቱም ለልጄ ለሴሎም ልድራት ይገባኝ ነበር” አለ።+ ከእሷም ጋር ዳግመኛ የፆታ ግንኙነት አልፈጸመም። +27 የመውለጃዋም ጊዜ ሲደርስ በሆዷ ውስጥ መንታ ልጆች እንዳሉ ታወቀ። +28 በምትወልድበት ጊዜም አንደኛው ልጅ እጁን አወጣ፤ አዋላጇም “መጀመሪያ የወጣው ይህ ነው” በማለት ወዲያውኑ በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት። +29 ይሁን እንጂ ልጁ እጁን በመለሰ ጊዜ ወንድሙ ቀድሞ��� ወጣ፤ በመሆኑም አዋላጇ “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ?” አለች። በመሆኑም ስሙ ፋሬስ*+ ተባለ። +30 በኋላም እጁ ላይ ቀይ ክር የታሰረለት ወንድሙ ወጣ፤ ስሙም ዛራ+ ተባለ። +8 ሆኖም አምላክ ኖኅን እንዲሁም ከእሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን የዱር እንስሳትና የቤት እንስሳት ሁሉ አሰበ።+ አምላክም ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውኃውም መጉደል ጀመረ። +2 የጥልቁ ውኃ ምንጮችና የሰማያት የውኃ በሮች ተደፈኑ፤ በመሆኑም ከሰማያት የሚወርደው ዝናብ መዝነቡን አቆመ።*+ +3 ከዚያም ውኃው ቀስ በቀስ ከምድር ላይ እየቀነሰ ሄደ። ከ150 ቀናት በኋላም ውኃው ጎደለ። +4 በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ17ኛው ቀን መርከቡ በአራራት ተራሮች ላይ አረፈ። +5 ውኃውም እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ቀስ በቀስ እየቀነሰ ሄደ። በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የተራሮቹ አናት ታየ።+ +6 ከ40 ቀንም በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቡን መስኮት+ ከፍቶ +7 አንድ ቁራ ወደ ውጭ ላከ፤ ቁራው ከመርከቡ ውጭ ሲበር ይቆይና ተመልሶ ይመጣ ነበር፤ ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ እንዲሁ ያደርግ ነበር። +8 በኋላም ውኃው ከምድር ላይ መጉደሉን ለማረጋገጥ አንዲት ርግብ ላከ። +9 ርግቧ ምንም የምታርፍበት* ቦታ ስላላገኘች እሱ ወደነበረበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ምክንያቱም ውኃው ገና መላውን ምድር እንደሸፈነው ነበር።+ በመሆኑም እጁን ወደ ውጭ ዘርግቶ ተቀበላትና ወደ መርከቡ አስገባት። +10 ከዚያም ሌላ ሰባት ቀን ከጠበቀ በኋላ ርግቧን በድጋሚ ከመርከቡ አውጥቶ ለቀቃት። +11 ርግቧም አመሻሹ ላይ ወደ እሱ በመጣች ጊዜ አዲስ የተቀጠፈ ለምለም የወይራ ቅጠል በአፏ እንደያዘች አየ! ስለዚህ ኖኅ ውኃው ከምድር ላይ መጉደሉን+ አወቀ። +12 እንደገና ሌላ ሰባት ቀን ጠበቀ። ከዚያም ርግቧን አውጥቶ ለቀቃት፤ በዚህ ጊዜ ግን ርግቧ ወደ እሱ ተመልሳ አልመጣችም። +13 ኖኅ በተወለደ በ601ኛው ዓመት፣+ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ከመሬቱ ላይ ሸሸ፤ ኖኅም የመርከቡን ሽፋን አንስቶ ተመለከተ፤ በዚህ ጊዜ መሬቱ ደርቆ ነበር። +14 በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በ27ኛው ቀን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ደረቀች። +15 ከዚያም አምላክ ኖኅን እንዲህ አለው፦ +16 “አንተ፣ ሚስትህ፣ ወንዶች ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከመርከቡ ውጡ።+ +17 በምድር ላይ እንዲዋለዱ፣ እንዲራቡና በምድር ላይ እንዲባዙ*+ አብሮህ ያለውን እያንዳንዱን ዓይነት ሕያው ፍጡር ሁሉ+ ይኸውም የሚበርሩ ፍጥረታትን፣ እንስሳትን እንዲሁም በምድር ላይ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትን ይዘህ ውጣ።” +18 ስለዚህ ኖኅ ከወንዶች ልጆቹ፣+ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር አብሮ ወጣ። +19 እያንዳንዱ ሕያው ፍጡር፣ መሬት ለመሬት የሚሄድ እያንዳንዱ እንስሳና እያንዳንዱ የሚበር ፍጡር እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ነገር በወገን በወገኑ እየሆነ ከመርከቡ ወጣ።+ +20 ከዚያም ኖኅ ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ፤+ ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሁሉ እንዲሁም ንጹሕ ከሆኑት የሚበርሩ ፍጥረታት ሁሉ+ የተወሰኑትን ወስዶ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መባ አቀረበ።+ +21 ይሖዋም ደስ የሚያሰኘውን* መዓዛ አሸተተ። ስለዚህ ይሖዋ በልቡ እንዲህ አለ፦ “በሰው የተነሳ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ ምድርን አልረግምም፤+ ምክንያቱም የሰው የልብ ዝንባሌ ከልጅነቱ ጀምሮ መጥፎ ነው፤+ ደግሞም አሁን እንዳደረግኩት ሕያው ፍጡርን ሁሉ ፈጽሞ ዳግመኛ አላጠፋም።+ +22 ከአሁን ጀምሮ በምድር ላይ ዘር መዝራትና ማጨድ፣ ቅዝቃዜና ሙቀት፣ በጋና ክረምት እንዲሁም ቀንና ሌሊት ፈጽሞ አይቋረጡም።”+ +11 በዚህ ጊዜ፣ ምድር ሁሉ አንድ ቋንቋና ተመሳሳይ ቃላት ትጠቀም ነበር። +2 ወደ ምሥራቅ ሲ���ዙም በሰናኦር+ ምድር ወደሚገኝ አንድ ሸለቋማ ሜዳ ደረሱ፤ በዚያም መኖር ጀመሩ። +3 እርስ በርሳቸውም “ኑ! ጡብ እንሥራ፤ በእሳትም እንተኩሰው” ይባባሉ ጀመር። በመሆኑም በድንጋይ ፋንታ ጡብ፣ ለማያያዣም ቅጥራን ተጠቀሙ። +4 ከዚያም “ኑ! በመላው ምድር ላይ እንዳንበተን+ ከተማና ጫፉ ሰማይ የሚደርስ ግንብ ለራሳችን እንገንባ፤ ስማችንንም እናስጠራ” ተባባሉ። +5 ከዚያም ይሖዋ ሰዎች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። +6 ይሖዋም እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሰዎች አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ ናቸው፤+ ይኸው አሁን ደግሞ ይህን መሥራት ጀምረዋል። በዚህ ከቀጠሉ ያሰቡትን* ሁሉ ከማከናወን የሚያግዳቸው ምንም ነገር አይኖርም። +7 ና! እንውረድና*+ በቋንቋ እርስ በርስ እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እናዘበራርቅ።” +8 በመሆኑም ይሖዋ ከዚያ ቦታ ተነስተው በመላው ምድር ላይ እንዲበተኑ አደረገ፤+ እነሱም ቀስ በቀስ ከተማዋን መገንባታቸውን አቆሙ። +9 የከተማዋ ስም ባቤል*+ የተባለውም በዚህ የተነሳ ነው፤ ምክንያቱም ይሖዋ በዚያ የምድርን ሁሉ ቋንቋ አዘበራርቋል፤ እንዲሁም ይሖዋ ሰዎቹ ከዚያ ቦታ ተነስተው በመላው ምድር ላይ እንዲበተኑ አድርጓል። +10 የሴም+ ታሪክ ይህ ነው። ሴም የጥፋት ውኃ ከተከሰተ ከሁለት ዓመት በኋላ አርፋክስድን+ ሲወልድ የ100 ዓመት ሰው ነበር። +11 ሴም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።+ +12 አርፋክስድ 35 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሴሎምን+ ወለደ። +13 አርፋክስድ ሴሎምን ከወለደ በኋላ 403 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +14 ሴሎም 30 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ኤቤርን+ ወለደ። +15 ሴሎም ኤቤርን ከወለደ በኋላ 403 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +16 ኤቤር 34 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ፋሌቅን+ ወለደ። +17 ኤቤርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ 430 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +18 ፋሌቅ 30 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ረኡን+ ወለደ። +19 ፋሌቅ ረኡን ከወለደ በኋላ 209 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +20 ረኡ 32 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሴሮህን ወለደ። +21 ረኡ ሴሮህን ከወለደ በኋላ 207 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +22 ሴሮህ 30 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ናኮርን ወለደ። +23 ሴሮህ ናኮርን ከወለደ በኋላ 200 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +24 ናኮር 29 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ታራን+ ወለደ። +25 ናኮር ታራን ከወለደ በኋላ 119 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +26 ታራ 70 ዓመት ከኖረ በኋላ አብራምን፣+ ናኮርን+ እና ካራንን ወለደ። +27 የታራ ታሪክ ይህ ነው። ታራ አብራምን፣ ናኮርን እና ካራንን ወለደ፤ ካራን ደግሞ ሎጥን+ ወለደ። +28 ካራንም አባቱ ታራ ገና በሕይወት እያለ፣ በተወለደበት አገር በከለዳውያን+ ዑር+ ሞተ። +29 አብራምና ናኮር ሚስት አገቡ። የአብራም ሚስት ስሟ ሦራ+ ሲሆን የናኮር ሚስት ደግሞ ስሟ ሚልካ+ ነበር፤ እሷም የሚልካ እና የዪስካ አባት የሆነው የካራን ልጅ ናት። +30 በዚህ ጊዜ ሦራ መሃን ነበረች፤+ ልጅም አልነበራትም። +31 ከዚያም ታራ ልጁን አብራምንና የልጁ ልጅ የሆነውን የካራንን ልጅ ሎጥን+ እንዲሁም የልጁ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነአን ምድር+ ለመሄድ ከከለዳውያን ዑር ተነሳ። ከጊዜ በኋላም ወደ ካራን+ መጡ፤ በዚያም መኖር ጀመሩ። +32 ታራም 205 ዓመት ኖረ። ከዚያም በካራን ሞተ። +2 በዚህ መንገድ ሰማያትንና ምድርን እንዲሁም በውስጣቸው ያለውን ነገር ሁሉ* የመፍጠሩ ሥራ ተጠናቀቀ።+ +2 በሰባተኛውም ቀን አምላክ ይሠራው የነበረውን ሥራ አጠናቀቀ፤ በሰባተኛውም ቀን ይሠራው ከነበረው ሥራ ሁሉ ማረፍ ጀመረ።+ +3 አምላክም ሰ��ተኛውን ቀን ባረከው እንዲሁም ቀደሰው፤ ምክንያቱም አምላክ ከመፍጠር ሥራው ሁሉ፣ ሊሠራ ካሰበው ነገር ሁሉ ያረፈው ከዚያ ቀን አንስቶ ነው። +4 ሰማያትና ምድር በተፈጠሩበት ጊዜ፣ ይሖዋ* አምላክ ምድርንና ሰማይን በሠራበት+ ቀን የተከናወነው ነገር ይህ ነው። +5 በዚህ ጊዜ በምድር ላይ ምንም ዓይነት የሜዳ ቁጥቋጦ አልነበረም፤ እንዲሁም በሜዳ ላይ ምንም ዓይነት ተክል አልበቀለም፤ ምክንያቱም ይሖዋ አምላክ በምድር ላይ ዝናብ እንዲዘንብ አላደረገም ነበር፤ መሬቱን የሚያለማም ሰው አልነበረም። +6 ይሁንና ተን ከምድር እየተነሳ መላውን መሬት ያጠጣ ነበር። +7 ይሖዋ አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ሠራው፤+ በአፍንጫውም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፤+ ሰውየውም ሕያው ሰው* ሆነ።+ +8 በተጨማሪም ይሖዋ አምላክ በስተ ምሥራቅ፣ በኤደን የአትክልት ስፍራ ተከለ፤+ የሠራውንም ሰው+ በዚያ አስቀመጠው። +9 ከዚያም ይሖዋ አምላክ ለማየት የሚያስደስተውንና ለምግብነት መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከመሬት አበቀለ። በተጨማሪም በአትክልቱ ስፍራ መካከል የሕይወት ዛፍ+ እንዲሁም የመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ+ አበቀለ። +10 የአትክልቱን ስፍራ የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ወጥቶ ይፈስ ነበር፤ ከዚያም ተከፋፍሎ አራት ወንዝ* ሆነ። +11 የመጀመሪያው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ ይህ ወንዝ ወርቅ የሚገኝበትን መላውን የሃዊላ ምድር የሚከብ ነው። +12 የዚያ አገር ወርቅ ምርጥ ነው። በተጨማሪም በዚያ ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫና* የኦኒክስ ድንጋዮች ይገኛሉ። +13 የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ ይህ ወንዝ መላውን የኢትዮጵያ* ምድር የሚከብ ነው። +14 የሦስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ*+ ነው፤ ይህ ወንዝ ከአሦር+ በስተ ምሥራቅ የሚፈስ ነው። አራተኛው ወንዝ ደግሞ ኤፍራጥስ+ ነው። +15 ይሖዋ አምላክ ሰውየውን ወስዶ እንዲያለማውና እንዲንከባከበው በኤደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው።+ +16 በተጨማሪም ይሖዋ አምላክ ለሰውየው ይህን ትእዛዝ ሰጠው፦ “በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ሁሉ እስክትረካ ድረስ መብላት ትችላለህ።+ +17 ከመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ ግን አትብላ፤ ምክንያቱም ከዚህ ዛፍ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።”+ +18 ከዚያም ይሖዋ አምላክ “ሰውየው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም። ማሟያ የምትሆነውን ረዳት እሠራለታለሁ”+ አለ። +19 ይሖዋ አምላክም እያንዳንዱን የዱር እንስሳ እንዲሁም በሰማያት ላይ የሚበረውን እያንዳንዱን ፍጥረት ከአፈር ሠርቶ ነበር፤ ከዚያም ሰውየው እያንዳንዳቸውን ምን ብሎ እንደሚጠራቸው ለማየት ሁሉንም ወደ እሱ አመጣቸው፤ ሰውየው ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር* የሰጠው መጠሪያም የዚያ ፍጡር ስም ሆነ።+ +20 በመሆኑም ሰውየው ለቤት እንስሳት በሙሉ፣ በሰማያት ላይ ለሚበርሩ ፍጥረታት እንዲሁም ለዱር እንስሳት ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ለሰው ግን ማሟያ የሚሆን ረዳት አልነበረውም። +21 ስለሆነም ይሖዋ አምላክ በሰውየው ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ እንቅልፍ ወስዶት ሳለም ከጎድን አጥንቶቹ አንዷን ወሰደ፤ ቦታውንም በሥጋ ደፈነው። +22 ይሖዋ አምላክም ከሰውየው የወሰዳትን የጎድን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ሴቲቱንም ወደ ሰውየው አመጣት።+ +23 በዚህ ጊዜ ሰውየው እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ እሷ የአጥንቶቼ አጥንት፣የሥጋዬም ሥጋ ናት። እሷ ከወንድ ስለተገኘች+‘ሴት’ ትባላለች።” +24 በዚህም ምክንያት ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል።* ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።+ +25 ሰውየውም ሆነ ሚስቱ ራቁታቸውን ነበሩ፤+ እንደዚያም ሆኖ ኀፍረት አይሰማቸውም ነበር። +26 በአብርሃም ዘመን ከተከሰተው ከመጀመሪያው ረሃብ+ ሌላ በምድሪቱ ላይ ረሃብ ተከሰተ፤ ስለዚህ ይስሐቅ በጌራራ ወደሚገኘው ወደ ፍልስጤማውያን ንጉሥ ወደ አቢሜሌክ ሄደ። +2 ከዚያም ይሖዋ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፦ “ወደ ግብፅ አትውረድ። እኔ በማሳይህ ምድር ተቀመጥ። +3 በዚህ ምድር እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ ተቀመጥ፤+ እኔም ከአንተ ጋር መሆኔን እቀጥላለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ። ምክንያቱም ይህችን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤+ ደግሞም ለአባትህ ለአብርሃም እንዲህ ስል የማልሁለትን መሐላ እፈጽማለሁ፦+ +4 ‘ዘርህን በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤+ ይህችንም ምድር በሙሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤+ የምድርም ብሔራት ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።’+ +5 ይህን የማደርገውም አብርሃም ቃሌን ስለሰማ እንዲሁም ሥርዓቶቼን፣ ትእዛዛቴን፣ ደንቦቼንና ሕጎቼን ጠብቆ ስለኖረ ነው።”+ +6 በመሆኑም ይስሐቅ በጌራራ መኖሩን ቀጠለ።+ +7 የዚያ አገር ሰዎች ስለ ሚስቱ በተደጋጋሚ ሲጠይቁት “እህቴ ናት” ይላቸው ነበር።+ “የዚህ አገር ሰዎች በርብቃ የተነሳ ሊገድሉኝ ይችላሉ” ብሎ ስላሰበ “ሚስቴ ናት” ለማለት ፈርቶ ነበር፤ ምክንያቱም ርብቃ ቆንጆ ነበረች።+ +8 ከተወሰነ ጊዜ በኋላም የፍልስጤማውያን ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ወደ ውጭ ሲመለከት ይስሐቅ ለሚስቱ ለርብቃ ፍቅሩን ሲገልጽላት*+ አየ። +9 አቢሜሌክም ወዲያው ይስሐቅን ጠርቶ “መቼም እሷ ሚስትህ እንደሆነች ግልጽ ነው! ታዲያ ‘እህቴ ናት’ ያልከው ለምንድን ነው?” አለው። በዚህ ጊዜ ይስሐቅ “እንዲህ ያልኩት በእሷ የተነሳ ሕይወቴን እንዳላጣ ስለፈራሁ ነው” አለው።+ +10 አቢሜሌክ ግን “እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ታደርግብናለህ?+ ከእኛ ሰዎች አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ይችል ነበር፤ እኛንም በደለኞች አድርገህ ታስቆጥረን ነበር!”+ አለው። +11 ከዚያም አቢሜሌክ “ይህን ሰውም ሆነ ሚስቱን የነካ ማንኛውም ሰው ያለምንም ጥርጥር ይገደላል!” በማለት ለሕዝቡ ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ። +12 ይስሐቅም በዚያ ምድር ዘር መዝራት ጀመረ፤ ይሖዋም ስለባረከው በዚያ ዓመት፣ የዘራውን 100 እጥፍ አመረተ።+ +13 ሰውየውም ባለጸጋ ሆነ፤ እጅግ ባለጸጋ እስኪሆንም ድረስ በሀብት ላይ ሀብት እየጨመረ ሄደ። +14 የበግና የከብት መንጋው በዛለት፤ አገልጋዮቹም ብዙ ሆኑ፤+ ፍልስጤማውያንም ይቀኑበት ጀመር። +15 በመሆኑም ፍልስጤማውያን የአባቱ አገልጋዮች በአብርሃም ዘመን የቆፈሯቸውን የውኃ ጉድጓዶች+ በሙሉ አፈር በመሙላት ደፈኗቸው። +16 ከዚያም አቢሜሌክ ይስሐቅን “ከእኛ ይልቅ እየበረታህ ስለመጣህ አካባቢያችንን ለቅቀህ ሂድልን” አለው። +17 በመሆኑም ይስሐቅ ከዚያ ተነስቶ በመሄድ በጌራራ+ ሸለቆ* ሰፈረ፤ በዚያም መኖር ጀመረ። +18 ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ዘመን ተቆፍረው የነበሩትንና አብርሃም ከሞተ በኋላ ፍልስጤማውያን የደፈኗቸውን የውኃ ጉድጓዶች እንደገና ቆፈረ፤+ ቀደም ሲል አባቱ ባወጣላቸው ስምም ጠራቸው።+ +19 የይስሐቅ አገልጋዮችም በሸለቆው ውስጥ* ሲቆፍሩ ለመጠጥ የሚሆን ውኃ ያለበት አንድ ጉድጓድ አገኙ። +20 የጌራራ እረኞች “ውኃው የእኛ ነው!” በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ጠብ አነሱ። ከእሱ ጋር ስለተጣሉም የውኃ ጉድጓዱን ስም ኤሴቅ* አለው። +21 እነሱም ሌላ የውኃ ጉድጓድ ቆፈሩ፤ በዚህም ጉድጓድ ጠብ አነሱ። በመሆኑም የጉድጓዱን ስም ሲጥና* አለው። +22 ከዚያም ያን ቦታ ትቶ በመሄድ ሌላ የውኃ ጉድጓድ ቆፈረ፤ እነሱም በዚህ ጉድጓድ ጠብ አላነሱበትም። በመሆኑም “አሁን ይሖዋ ሰፊ ቦታ ሰጥቶናል፤ በምድርም ላይ እንድንበዛ አድርጎናል”+ በማለት የጉድጓዱን ስም ረሆቦት* አለው። +23 በኋላም ከዚያ ተነስቶ ወደ ቤርሳቤህ+ ወጣ። +24 ይሖዋም በዚያ ��ሊት ተገለጠለትና እንዲህ አለው፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ።+ እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ፤+ ስለ አገልጋዬ ስለ አብርሃም ስል እባርክሃለሁ እንዲሁም ዘርህን አበዛዋለሁ።”+ +25 በመሆኑም በዚያ መሠዊያ ሠራ፤ የይሖዋንም ስም ጠራ።+ እንዲሁም ይስሐቅ ድንኳኑን በዚያ ተከለ፤+ አገልጋዮቹም በዚያ የውኃ ጉድጓድ ቆፈሩ። +26 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አቢሜሌክ የግል አማካሪው ከሆነው ከአሁዛትና ከሠራዊቱ አዛዥ ከፊኮል+ ጋር በመሆን ከጌራራ ተነስቶ ወደ ይስሐቅ መጣ። +27 በዚህ ጊዜ ይስሐቅ “ጠልታችሁኝ ከአካባቢያችሁ ካባረራችሁኝ በኋላ አሁን ለምን ወደ እኔ መጣችሁ?” አላቸው። +28 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ይሖዋ ከአንተ ጋር እንደሆነ በግልጽ ማየት ችለናል።+ በመሆኑም እንዲህ አልን፦ ‘በእኛና በአንተ መካከል በመሐላ የጸና ስምምነት ይኑር፤ ከአንተም ጋር ቃል ኪዳን እንጋባ።+ +29 በአንተ ላይ ምንም ጉዳት እንዳላደረስንብህ ከዚህ ይልቅ በሰላም በማሰናበት መልካም እንዳደረግንልህ ሁሉ አንተም በእኛ ላይ ምንም መጥፎ ነገር እንደማታደርግብን ማልልን። አንተ አሁን ይሖዋ የባረከህ ሰው ነህ።’” +30 እሱም ግብዣ አዘጋጀላቸው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡም። +31 በማግስቱም በማለዳ ተነስተው እርስ በርሳቸው ተማማሉ።+ ከዚያም ይስሐቅ አሰናበታቸው፤ እነሱም ከእሱ ዘንድ በሰላም ሄዱ። +32 በዚያኑ ዕለት የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለቆፈሩት+ የውኃ ጉድጓድ ነገሩት፤ እነሱም “ውኃ እኮ አገኘን!” አሉት። +33 በመሆኑም የጉድጓዱን ስም ሳቤህ አለው። የከተማዋ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ+ ተብሎ የሚጠራው በዚህ የተነሳ ነው። +34 ኤሳው 40 ዓመት ሲሆነው የሂታዊውን የቤኤሪን ልጅ ዮዲትን እንዲሁም የሂታዊውን የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ።+ +35 እነሱም ይስሐቅንና ርብቃን ለከፍተኛ ሐዘን ዳረጓቸው።*+ +44 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ የቤቱ ኃላፊ የሆነውን ሰው እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “የቻሉትን ያህል እህል በየከረጢቶቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዳቸውንም ገንዘብ በየከረጢቶቻቸው አፍ ላይ አድርገው።+ +2 ሆኖም የእኔን ጽዋ ይኸውም የብር ጽዋዬን ውሰድና እህል ለመግዛት ካመጣው ገንዘብ ጋር አድርገህ በትንሹ ወንድማቸው ከረጢት አፍ ላይ አድርገው።” እሱም ልክ ዮሴፍ እንዳዘዘው አደረገ። +3 ሰዎቹም ማለዳ ላይ ጎህ ሲቀድ ከነአህዮቻቸው ተሸኙ። +4 እነሱም ከከተማዋ ብዙም ርቀው ሳይሄዱ ዮሴፍ የቤቱ ኃላፊ የሆነውን ሰው እንዲህ አለው፦ “ተነስ! ሰዎቹን ተከታተላቸው! ስትደርስባቸውም እንዲህ በላቸው፦ ‘ለተደረገላችሁ መልካም ነገር ክፉ የመለሳችሁት ለምንድን ነው? +5 ይህ ጌታዬ የሚጠጣበትና የሚጠነቁልበት ጽዋ አይደለም? የፈጸማችሁት ድርጊት በጣም አሳፋሪ ነው።’” +6 እሱም ተከታትሎ ደረሰባቸውና ልክ እንደተባለው አላቸው። +7 እነሱ ግን እንዲህ አሉት፦ “ጌታዬ እንዲህ ያለ ነገር የሚናገረው ለምንድን ነው? አገልጋዮችህ እንዲህ ያለ ነገር ያደርጋሉ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። +8 በከረጢቶቻችን አፍ ላይ ያገኘነውን ገንዘብ እንኳ ከከነአን ምድር ድረስ ይዘን ወደ አንተ መጥተን የለም?+ ታዲያ ከጌታህ ቤት ብር ወይም ወርቅ እንዴት እንሰርቃለን? +9 ከእኛ ከባሪያዎችህ መካከል የተገኘበት ቢኖር ያ ሰው ይገደል፤ የቀረነውም ለጌታዬ ባሪያዎች እንሆናለን።” +10 እሱም “እሺ፣ እንዳላችሁት ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው ባሪያዬ ይሆናል፤ የቀራችሁት ግን ነፃ ትሆናላችሁ” አላቸው። +11 ከዚያም እያንዳንዳቸው ወዲያውኑ ከረጢታቸውን መሬት አውርደው መፍታት ጀመሩ። +12 እሱም ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በጥንቃቄ ፈተሸ። በመጨረሻም ጽዋው በቢንያም ከረጢት ውስጥ ተገኘ።+ +13 በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ እያንዳንዳቸውም ጓዛቸውን መልሰው በአህዮቻቸው ላይ በመጫን ወደ ከተማዋ ተመለሱ። +14 ይሁዳና+ ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ሲገቡ ዮሴፍ ገና ከቤት አልወጣም ነበር፤ እነሱም በፊቱ መሬት ላይ ተደፉ።+ +15 ዮሴፍም “ይህ ያደረጋችሁት ነገር ምንድን ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ማንኛውንም ነገር በጥንቆላ የማወቅ ችሎታ እንዳለው አታውቁም?” አላቸው።+ +16 በዚህ ጊዜ ይሁዳ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ለጌታዬ ምን ማለት እንችላለን? ምንስ አፍ አለን? ጻድቅ መሆናችንን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? እውነተኛው አምላክ ባሪያዎችህ የፈጸሙትን ስህተት አጋልጧል።+ እንግዲህ እኛም ሆን ጽዋው የተገኘበት ሰው ለጌታዬ ባሪያዎች እንሆናለን!” +17 እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ይህንማ ፈጽሞ አላደርገውም! ባሪያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ነው።+ የቀራችሁት ግን ወደ አባታችሁ በሰላም ሂዱ።” +18 ይሁዳም ወደ እሱ ቀርቦ እንዲህ አለው፦ “እባክህ ጌታዬ እማጸንሃለሁ፤ ባሪያህ አንዲት ቃል ብቻ ይናገር፤ ጌታዬም ይስማው፤ እባክህ በባሪያህ ላይ አትቆጣ፤ ምክንያቱም አንተ ልክ እንደ ፈርዖን ነህ።+ +19 ጌታዬ እኛን ባሪያዎቹን ‘አባት ወይም ወንድም አላችሁ?’ በማለት ጠይቆን ነበር። +20 እኛም ለጌታዬ እንዲህ ስንል መለስንለት፦ ‘አረጋዊ አባት አለን፤ እንዲሁም በስተርጅናው የወለደው የሁላችንም ታናሽ የሆነ ወንድም አለን።+ ወንድሙ ግን ሞቷል፤+ በመሆኑም ከአንድ እናት ከተወለዱት መካከል የቀረው እሱ ብቻ ነው፤+ አባቱም በጣም ይወደዋል።’ +21 ከዚያም አንተ እኛን ባሪያዎችህን ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልከን።+ +22 እኛ ግን ጌታዬን ‘ልጁ ከአባቱ ሊለይ አይችልም። ከተለየው ደግሞ አባቱ ያለጥርጥር ይሞታል’+ አልነው። +23 አንተም እኛን ባሪያዎችህን ‘ትንሹን ወንድማችሁን ይዛችሁት ካልመጣችሁ ከእንግዲህ ፊቴን አታዩም’ አልከን።+ +24 “በመሆኑም ወደ ባሪያህ ወደ አባታችን ሄደን የጌታዬን ቃል ነገርነው። +25 ከጊዜ በኋላም አባታችን ‘ተመልሳችሁ ሂዱና ጥቂት እህል ግዙልን’ አለን።+ +26 እኛ ግን እንዲህ አልነው፦ ‘ወደዚያ መሄድ አንችልም። ትንሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ካልሄደ የሰውየውን ፊት ማየት ስለማንችል ትንሹ ወንድማችን አብሮን የሚሄድ ከሆነ ወደዚያ እንወርዳለን።’+ +27 በዚህ ጊዜ ባሪያህ አባታችን እንዲህ አለን፦ ‘ሚስቴ ከሁለት ወንዶች ልጆች ሌላ ምንም እንዳልወለደችልኝ እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁ።+ +28 ሆኖም አንዱ እንደወጣ በመቅረቱ “መቼም አውሬ ቦጫጭቆት መሆን አለበት!” አልኩ፤+ ይኸው ከዚያን ጊዜ ወዲህ አይቼው አላውቅም። +29 ይሄኛውንም ልጅ ከእኔ ለይታችሁ ብትወስዱትና አደጋ ደርሶበት ቢሞት ሽበቴን በሥቃይ+ ወደ መቃብር*+ ታወርዱታላችሁ።’ +30 “እንግዲህ ወደ ባሪያህ ወደ አባቴ ስመለስ ልጁ ከእኛ ጋር ከሌለ፣ የአባታችን ሕይወት* ከልጁ ሕይወት* ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ስለሆነ +31 አባታችን ልጁ አብሮን አለመኖሩን ሲያይ ይሞታል፤ ባሪያዎችህም የባሪያህን የአባታችንን ሽበት በሐዘን ወደ መቃብር* ያወርዱታል። +32 እኔ ባሪያህ ‘ልጁን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣው በአባቴ ፊት ለዘላለም በደለኛ ልሁን’ ብዬ ለአባቴ ቃል ገብቻለሁ።+ +33 ስለዚህ እባክህ ልጁ ከወንድሞቹ ጋር እንዲሄድ እኔ ባሪያህ በልጁ ፋንታ እዚሁ ቀርቼ ለጌታዬ ባሪያ ልሁን። +34 ልጁን ሳልይዝ እንዴት ወደ አባቴ እመለሳለሁ? በአባቴ ላይ እንዲህ ያለ መከራ ሲደርስ ማየት አልችልም!” +4 አዳምም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀነሰች።+ ቃየንንም+ በወለደች ጊዜ “በይሖዋ እርዳታ ወንድ ልጅ አፈራሁ”* አለች። +2 በኋላም ወንድሙን አቤልን+ ��ለደች። አቤል የበግ እረኛ ሆነ፤ ቃየን ግን አራሽ ሆነ። +3 ከጊዜ በኋላም ቃየን የተወሰኑ የምድር ፍሬዎችን ለይሖዋ መባ አድርጎ አቀረበ። +4 አቤል ግን ከመንጋው በኩራት+ መካከል የተወሰኑትን ከነስባቸው አቀረበ። ይሖዋ አቤልንና ያቀረበውን መባ+ በጥሩ ፊት ሲመለከት +5 ቃየንንና ያቀረበውን መባ ግን በጥሩ ፊት አልተመለከተም። በመሆኑም ቃየን በጣም ተናደደ፤ እጅግ አዘነ። +6 ከዚያም ይሖዋ ቃየንን እንዲህ አለው፦ “ለምን ተናደድክ? ለምንስ አዘንክ? +7 መልካም ወደ ማድረግ ብታዘነብል ኖሮ ሞገስ አታገኝም ነበር?* መልካም ወደ ማድረግ ካላዘነበልክ ግን ኃጢአት በደጅህ እያደባ ነው፤ ሊቆጣጠርህም ይፈልጋል፤ ታዲያ አንተ ትቆጣጠረው ይሆን?” +8 ከዚያ በኋላ ቃየን ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳው ላይ ሳሉም ቃየን ወንድሙን አቤልን ደብድቦ ገደለው።+ +9 በኋላም ይሖዋ ቃየንን “ወንድምህ አቤል የት ነው?” አለው፤ እሱም “እኔ አላውቅም። እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?” አለ። +10 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “ያደረግከው ነገር ምንድን ነው? ስማ! የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ እየጮኸ ነው።+ +11 እንግዲህ የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል+ አፏን ከከፈተችው ምድር እንድትሰደድ ተረግመሃል። +12 ምድርን በምታርስበትም ጊዜ ምርቷን* አትሰጥህም። በምድር ላይ ተንከራታችና ስደተኛ ትሆናለህ።” +13 በዚህ ጊዜ ቃየን ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “ለሠራሁት ጥፋት የምቀበለው ቅጣት ልሸከመው ከምችለው በላይ ነው። +14 ይኸው በዚህ ቀን ከምድሪቱ* ልታባርረኝ ነው፤ ከፊትህም እሰወራለሁ፤ እንዲሁም በምድር ላይ ተንከራታችና ስደተኛ እሆናለሁ፤ እንግዲህ በቃ፣ ያገኘኝ ሁሉ ይገድለኛል።” +15 ስለሆነም ይሖዋ “እንግዲያው ቃየንን የሚገድል ማንኛውም ሰው ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይቀበላል” አለው። በመሆኑም ያገኘው ማንም እንዳይገድለው ይሖዋ ለቃየን ምልክት አደረገለት።* +16 ከዚያም ቃየን ከይሖዋ ፊት ርቆ ሄደ፤ ከኤደን በስተ ምሥራቅ+ በሚገኘው በግዞት ምድር* መኖር ጀመረ። +17 ከዚህ በኋላ ቃየን ከሚስቱ+ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀነሰች፤ ሄኖክንም ወለደች። ከዚያም ቃየን ከተማ መገንባት ጀመረ፤ ከተማዋንም በልጁ በሄኖክ ስም ሰየማት። +18 ከጊዜ በኋላም ሄኖክ ኢራድን ወለደ። ኢራድም መሁያኤልን ወለደ፤ መሁያኤልም መቱሻኤልን ወለደ፤ መቱሻኤል ደግሞ ላሜህን ወለደ። +19 ላሜህም ሁለት ሚስቶች አገባ፤ የመጀመሪያዋ ስም አዳ ሲሆን የሁለተኛዋ ስም ደግሞ ጺላ ነበር። +20 አዳ ያባልን ወለደች። ያባል በድንኳን የሚኖሩና ከብት የሚያረቡ ሰዎች አባት ነበር። +21 የወንድሙ ስም ዩባል ነበር። እሱም የበገና ደርዳሪዎችና የእምቢልታ* ነፊዎች አባት ነበር። +22 ጺላ ደግሞ ቱባልቃይንን ወለደች፤ እሱም መዳብና ብረት እየቀጠቀጠ የተለያዩ መሣሪያዎችን ይሠራ ነበር። የቱባልቃይን እህት ናዕማ ትባል ነበር። +23 ከዚያም ላሜህ ለሚስቶቹ ለአዳና ለጺላ የሚከተለውን ተቀኘ፦ “እናንተ የላሜህ ሚስቶች፣ ቃሌን ስሙ፤የምላችሁንም አዳምጡ፦ አንድ ሰው ስላቆሰለኝ፣አዎ፣ አንድ ወጣት ስለመታኝ ገደልኩት። +24 ቃየንን የሚገድል 7 እጥፍ የበቀል ቅጣት+ የሚደርስበት ከሆነላሜህን የገደለማ 77 ጊዜ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል።” +25 አዳም ከሚስቱ ጋር በድጋሚ የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ወንድ ልጅ ወለደች። ስሙንም “ቃየን አቤልን ስለገደለው+ በእሱ ፋንታ አምላክ ሌላ ዘር ተክቶልኛል” በማለት ሴት*+ አለችው። +26 ሴት ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሄኖስ+ አለው። በዚያን ዘመን ሰዎች የይሖዋን ስም መጥራት ጀመሩ።* +41 ሁለት ድፍን ዓመታት ካለፉ በኋላ ፈርዖን በሕልሙ አባይ ���ንዝ ዳር ቆሞ አየ።+ +2 ከዚያም ቁመናቸው ያማረ ሰባት የሰቡ ላሞች ከአባይ ወንዝ ሲወጡ አየ፤ እነሱም አባይ ወንዝ ዳር ያለውን ሣር ይበሉ ነበር።+ +3 ከእነሱም ቀጥሎ አስቀያሚ መልክ ያላቸውና ከሲታ የሆኑ ሌሎች ሰባት ላሞች ከአባይ ወንዝ ወጡ፤ እነሱም አባይ ወንዝ ዳር ከነበሩት የሰቡ ላሞች አጠገብ ቆሙ። +4 ከዚያም አስቀያሚ መልክ ያላቸው ከሲታ የሆኑት ላሞች ያማረ ቁመና ያላቸውን የሰቡትን ሰባት ላሞች በሏቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ባነነ። +5 ከዚያም ፈርዖን በድጋሚ እንቅልፍ ወሰደው፤ ለሁለተኛ ጊዜም ሕልም አለመ። በሕልሙም በአንድ አገዳ ላይ የተንዠረገጉና ያማሩ ሰባት የእህል ዛላዎች ሲወጡ አየ።+ +6 ከእነሱም በኋላ የቀጨጩና በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት የእህል ዛላዎች በቀሉ። +7 የቀጨጩት የእህል ዛላዎች የተንዠረገጉትንና የፋፉትን ሰባት የእህል ዛላዎች ዋጧቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ባነነ፤ ሕልም እንደሆነም ተገነዘበ። +8 በነጋም ጊዜ መንፈሱ ተረበሸ። በመሆኑም በግብፅ የሚገኙ አስማተኛ ካህናትን በሙሉ እንዲሁም ጥበበኞቿን በሙሉ አስጠራ። ፈርዖንም ያያቸውን ሕልሞች ነገራቸው፤ ሆኖም ለፈርዖን ሕልሞቹን ሊፈታለት የቻለ አንድም ሰው አልነበረም። +9 በዚህ ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “ኃጢአቴን ዛሬ ልናዘዝ። +10 ፈርዖን በአገልጋዮቹ ተቆጥቶ ነበር። በመሆኑም እኔንና የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ በዘቦቹ አለቃ ቤት በሚገኘው ወህኒ ቤት ውስጥ አስሮን ነበር።+ +11 ከዚያም ሁለታችንም በአንድ ሌሊት ሕልም አለምን። እኔም ሆንኩ እሱ ያለምነው ሕልም የተለያየ ፍቺ ነበረው።+ +12 ከእኛም ጋር የዘቦቹ አለቃ አገልጋይ+ የሆነ አንድ ወጣት ዕብራዊ ነበር። ያየናቸውንም ሕልሞች በነገርነው ጊዜ+ የእያንዳንዳችንን ሕልም ፈታልን። +13 ነገሩ ሁሉ ልክ እሱ እንደፈታልን ሆነ። እኔ ወደ ሹመቴ ተመለስኩ፤ ሌላኛው ሰው ግን ተሰቀለ።”+ +14 ስለሆነም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ሰዎች ላከ፤+ እነሱም ከእስር ቤቱ* በፍጥነት ይዘውት መጡ።+ እሱም ተላጭቶና ልብሱን ለውጦ ወደ ፈርዖን ገባ። +15 ከዚያም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “ሕልም አይቼ ነበር፤ የሚፈታልኝ ሰው ግን አልተገኘም። አንተ ሕልም ሰምተህ መፍታት እንደምትችል ሰማሁ።”+ +16 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዖን “ኧረ እኔ እዚህ ግባ የምባል ሰው አይደለሁም! ለፈርዖን መልካም የሆነውን ነገር የሚያሳውቀው አምላክ ነው”+ ሲል መለሰለት። +17 ፈርዖንም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፦ “በሕልሜ አባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር። +18 ከዚያም ቁመናቸው ያማረ የሰቡ ሰባት ላሞች ከአባይ ወንዝ ሲወጡ አየሁ፤ እነሱም አባይ ወንዝ ዳር ያለውን ሣር ይበሉ ጀመር።+ +19 ከእነሱ ቀጥሎም የተጎሳቆሉ እንዲሁም አስቀያሚ ቁመና ያላቸውና ከሲታ የሆኑ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ በመላው የግብፅ ምድር እንደ እነሱ ያሉ አስቀያሚ ላሞች ፈጽሞ አይቼ አላውቅም። +20 ከዚያም ከሲታ የሆኑት አስቀያሚ ላሞች የመጀመሪያዎቹን ሰባት የሰቡ ላሞች በሏቸው። +21 ከበሏቸው በኋላም ግን ቁመናቸው ልክ እንደቀድሞው አስቀያሚ ስለነበር ማንም ሰው እንደበሏቸው እንኳ ሊያውቅ አይችልም ነበር። በዚህ ጊዜ ከእንቅልፌ ባነንኩ። +22 “ከዚያ በኋላ የፋፉና ያማሩ ሰባት የእህል ዛላዎች በአንድ አገዳ ላይ ሲወጡ በሕልሜ አየሁ።+ +23 ከእነሱም በኋላ የቀጨጩና በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት የጠወለጉ የእህል ዛላዎች በቀሉ። +24 ከዚያም የቀጨጩት የእህል ዛላዎች ያማሩትን ሰባት የእህል ዛላዎች ዋጧቸው። እኔም ሕልሜን አስማተኛ ለሆኑት ካህናት ነገርኳቸው፤+ ሆኖም ሊያብራራልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።”+ +25 ከዚያም ዮ��ፍ ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች አንድ ዓይነትና ተመሳሳይ ናቸው። እውነተኛው አምላክ ወደፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን አሳውቆታል።+ +26 ሰባቱ ያማሩ ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው። በተመሳሳይም ሰባቱ ያማሩ የእህል ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው። ሕልሞቹ አንድ ዓይነትና ተመሳሳይ ናቸው። +27 ከእነሱ በኋላ የመጡት ሰባቱ ከሲታና አስቀያሚ ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ በምሥራቅ ነፋስ የተመቱት ሰባቱ ፍሬ አልባ የእህል ዛላዎች ረሃብ የሚከሰትባቸው ሰባት ዓመታት ይሆናሉ። +28 ቀደም ብዬ ለፈርዖን እንደተናገርኩት እውነተኛው አምላክ ወደፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን አሳይቶታል። +29 “በመላው የግብፅ ምድር እህል እጅግ የሚትረፈረፍባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። +30 ከዚያ በኋላ ግን ረሃብ የሚከሰትባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። በግብፅ ምድር እህል የተትረፈረፈበት ዘመን ፈጽሞ ይረሳል፤ ረሃቡም ምድሪቱን በእጅጉ ይጎዳል።+ +31 ከዚያ በኋላ በሚከሰተው ረሃብ የተነሳ በምድሪቱ እህል የተትረፈረፈበት ጊዜ ፈጽሞ አይታወስም፤ ምክንያቱም ረሃቡ በጣም አስከፊ ይሆናል። +32 ሕልሙ ለፈርዖን ሁለት ጊዜ መታየቱ ነገሩ በእውነተኛው አምላክ ዘንድ የተቆረጠ መሆኑን ያሳያል፤ እውነተኛውም አምላክ ይህን በቅርቡ ይፈጽመዋል። +33 “ስለሆነም አሁን ፈርዖን ልባምና ጠቢብ የሆነ ሰው ይፈልግና በግብፅ ምድር ላይ ይሹም። +34 ፈርዖን በምድሪቱ ላይ የበላይ ተመልካቾችን በመሾም እርምጃ ይውሰድ፤ እህል በሚትረፈረፍባቸው ሰባት ዓመታትም በግብፅ ምድር ከሚገኘው ምርት አንድ አምስተኛውን ያከማች።+ +35 እነሱም በመጪዎቹ መልካም ዓመታት የሚገኘውን እህል በሙሉ ይሰብስቡ፤ ለምግብነት የሚሆነውንም እህል በፈርዖን ሥልጣን ሥር በየከተማው ያከማቹ፤ የተከማቸውንም እህል ይጠብቁት።+ +36 በግብፅ ምድር ረሃብ በሚከሰትባቸው ሰባት ዓመታት ምድሪቱ በረሃቡ እንዳትጠፋ የተከማቸው እህል ለአገሪቱ ነዋሪዎች ይሰጣል።”+ +37 ፈርዖንና አገልጋዮቹ በሙሉ ይህን ሐሳብ መልካም ሆኖ አገኙት። +38 በመሆኑም ፈርዖን አገልጋዮቹን “ታዲያ የአምላክ መንፈስ ያለበት እንዲህ ያለ ሌላ ሰው ሊገኝ ይችላል?” አላቸው። +39 ከዚያም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “አምላክ ይህን ሁሉ እንድታውቅ ስላደረገህ እንደ አንተ ያለ ልባምና ጠቢብ ሰው የለም። +40 አንተው ራስህ በቤቴ ላይ ትሾማለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ያላንዳች ማንገራገር ይታዘዝልሃል።+ እኔ ከአንተ የምበልጠው ንጉሥ በመሆኔ* ብቻ ይሆናል።” +41 በመቀጠልም ፈርዖን ዮሴፍን “ይኸው በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾሜሃለሁ” አለው።+ +42 ከዚያም ፈርዖን የማኅተም ቀለበቱን ከእጁ ላይ አውልቆ በዮሴፍ እጅ ላይ አደረገለት፤ ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስም አለበሰው፤ በአንገቱም ላይ የወርቅ ሐብል አጠለቀለት። +43 ከዚህም በላይ ከእሱ ቀጥሎ ባለው የክብር ሠረገላው ላይ አስቀመጠው፤ ሰዎችም ከፊት ከፊቱ እየሄዱ “አቭሬክ!”* እያሉ ይጮኹ ነበር። በዚህ መንገድ በመላው የግብፅ ምድር ላይ ሾመው። +44 በተጨማሪም ፈርዖን ዮሴፍን “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም ያለአንተ ፈቃድ ማንም ሰው በመላው የግብፅ ምድር ላይ ምንም ነገር ማድረግ* አይችልም” አለው።+ +45 ከዚያም ፈርዖን ለዮሴፍ ጸፍናትፓነህ የሚል ስም አወጣለት፤ የኦን* ካህን የሆነውን የጶጥፌራን ልጅ አስናትንም+ አጋባው። ዮሴፍም መላውን የግብፅ ምድር መቃኘት* ጀመረ።+ +46 ዮሴፍ በግብፁ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ* ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት+ ነበር። ከዚያም ዮሴፍ ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ መላውን የግብፅ ምድርም ተዘዋውሮ ተመለከተ። +47 እህል ይትረፈረፍባቸዋል በተባሉት ሰባት ዓመታት ምድሪ�� የተትረፈረፈ* ምርት ሰጠች። +48 በእነዚያ ሰባት ዓመታት በግብፅ ምድር የተገኘውንም እህል በሙሉ እየሰበሰበ በየከተሞቹ ያከማች ነበር። በእያንዳንዱ ከተማ ዙሪያ ከሚገኘው እርሻ የተሰበሰበውን እህል በየከተማው ያከማች ነበር። +49 በመጨረሻም ሰዎቹ እህሉን መስፈር አቅቷቸው መስፈራቸውን እስኪተዉ ድረስ ዮሴፍ እንደ ባሕር አሸዋ በጣም ብዙ የሆነ እህል አከማቸ። +50 ዮሴፍ የረሃቡ ዓመት ከመጀመሩ በፊት የኦን* ካህን ከሆነው ከጶጥፌራ ልጅ ከአስናት ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ።+ +51 ዮሴፍም “አምላክ የደረሰብኝን ችግር ሁሉና የአባቴን ቤት በሙሉ እንድረሳ አደረገኝ” በማለት ለበኩር ልጁ ምናሴ*+ የሚል ስም አወጣለት። +52 ሁለተኛውን ልጁን ደግሞ “መከራዬን ባየሁበት ምድር አምላክ ፍሬያማ አደረገኝ”+ በማለት ኤፍሬም*+ የሚል ስም አወጣለት። +53 ከዚያም በግብፅ ምድር እህል የተትረፈረፈባቸው ሰባት ዓመታት አበቁ፤+ +54 ልክ ዮሴፍ እንደተናገረውም ሰባቱ የረሃብ ዓመታት ጀመሩ።+ ረሃቡም በምድር ሁሉ ላይ እየሰፋ ሄደ፤ በመላው የግብፅ ምድር ግን ምግብ ነበር።+ +55 በመጨረሻም መላው የግብፅ ምድር በረሃቡ ተጠቃ፤ ሕዝቡም ምግብ ለማግኘት ወደ ፈርዖን ይጮኽ ጀመር።+ ፈርዖንም ግብፃውያንን ሁሉ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ የሚላችሁንም ሁሉ አድርጉ” ይላቸው ነበር።+ +56 ረሃቡም በመላው ምድር ላይ እየተስፋፋ ሄደ።+ ረሃቡ በግብፅ ምድር ላይ እየጸና ስለሄደ ዮሴፍ በመካከላቸው ያሉትን የእህል ጎተራዎች በሙሉ በመክፈት ለግብፃውያን እህል ይሸጥላቸው ጀመር።+ +57 በተጨማሪም ረሃቡ በመላው ምድር ላይ ክፉኛ ጸንቶ ስለነበር በመላው ምድር የሚኖሩ ሰዎች ከዮሴፍ እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ይመጡ ነበር።+ +46 በመሆኑም እስራኤል ያለውን* ሁሉ ይዞ ተነሳ። ቤርሳቤህ+ በደረሰ ጊዜም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ+ መሥዋዕቶችን አቀረበ። +2 ከዚያም አምላክ ለእስራኤል ሌሊት በራእይ ተገልጦለት “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ!” ሲል ጠራው፤ እሱም “አቤት!” አለ። +3 አምላክም እንዲህ አለው፦ “እኔ የአባትህ አምላክ የሆንኩት እውነተኛው አምላክ ነኝ።+ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ ምክንያቱም በዚያ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።+ +4 እኔ ራሴ ከአንተ ጋር ወደ ግብፅ እወርዳለሁ፤ ደግሞም እኔ ራሴ ከዚያ አወጣሃለሁ፤+ ዮሴፍም ዓይኖችህን በእጁ ይከድናል።”*+ +5 ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሳ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን፣ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን በላከለት ሠረገሎች ላይ አሳፍረው ጉዞ ጀመሩ። +6 እነሱም በከነአን ምድር ያፈሩትን ንብረትና መንጎቻቸውን ይዘው ሄዱ። ከዚያም ያዕቆብና ከእሱ ጋር የነበሩት ልጆቹ በሙሉ ወደ ግብፅ መጡ። +7 እሱም ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆቹንና ሴቶች የልጅ ልጆቹን ይኸውም ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ወደ ግብፅ መጣ። +8 ወደ ግብፅ የመጡት የእስራኤል ማለትም የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦+ የያዕቆብ የበኩር ልጅ ሮቤል።+ +9 የሮቤል ወንዶች ልጆች ሃኖክ፣ ፓሉ፣ ኤስሮን እና ካርሚ ነበሩ።+ +10 የስምዖን+ ወንዶች ልጆች የሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሃር እንዲሁም ከአንዲት ከነአናዊት የወለደው ሻኡል ነበሩ።+ +11 የሌዊ+ ወንዶች ልጆች ጌድሶን፣ ቀአት እና ሜራሪ ነበሩ።+ +12 የይሁዳ+ ወንዶች ልጆች ኤር፣ ኦናን፣ ሴሎም፣+ ፋሬስ+ እና ዛራ+ ነበሩ፤ ይሁንና ኤር እና ኦናን በከነአን ምድር ሞቱ።+ የፋሬስ ወንዶች ልጆች ኤስሮን እና ሃሙል ነበሩ።+ +13 የይሳኮር ወንዶች ልጆች ቶላ፣ ፑዋ፣ ዮብ እና ሺምሮን ነበሩ።+ +14 የዛብሎን+ ወንዶች ልጆች ሰሬድ፣ ኤሎን እና ያህልኤል ነበሩ።+ +15 ሴት ልጁን ዲናን+ ጨምሮ እነዚህ ሊያ ��ጳዳንአራም ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆች ናቸው። በአጠቃላይ ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ 33 ነበሩ።* +16 የጋድ+ ወንዶች ልጆች ጺፍዮን፣ ሃጊ፣ ሹኒ፣ ኤጽቦን፣ ኤሪ፣ አሮድ እና አርዔላይ ነበሩ።+ +17 የአሴር+ ወንዶች ልጆች ይምናህ፣ ይሽዋ፣ ይሽዊ እና በሪአ ሲሆኑ እህታቸውም ሴራህ ትባላለች። የበሪአ ወንዶች ልጆች ሄቤር እና ማልኪኤል ነበሩ።+ +18 ላባ ለልጁ ለሊያ የሰጣት ዚልጳ+ የተባለችው አገልጋይ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሷም ለያዕቆብ እነዚህን ወለደችለት፤ እነሱም በአጠቃላይ 16* ነበሩ። +19 የያዕቆብ ሚስት የራሔል ወንዶች ልጆች ዮሴፍና+ ቢንያም+ ነበሩ። +20 ዮሴፍ በግብፅ ምድር ሳለ ምናሴንና+ ኤፍሬምን*+ ወለደ፤ እነዚህም የኦን* ካህን የሆነው የጶጥፌራ ልጅ አስናት+ የወለደችለት ናቸው። +21 የቢንያም+ ወንዶች ልጆች ቤላ፣ ቤኬር፣ አሽቤል፣ ጌራ፣+ ንዕማን፣ ኤሂ፣ ሮሽ፣ ሙጲም፣ ሁፒም+ እና አርድ+ ነበሩ። +22 እነዚህ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ወንዶች ልጆች ናቸው፤ እነሱም በአጠቃላይ 14* ነበሩ። +23 የዳን+ ልጅ* ሁሺም+ ነበር። +24 የንፍታሌም+ ወንዶች ልጆች ያህጽኤል፣ ጉኒ፣ የጼር እና ሺሌም ነበሩ።+ +25 ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት ባላ የተባለችው አገልጋይ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሷም ለያዕቆብ እነዚህን ወለደችለት፤ እነሱም በአጠቃላይ ሰባት* ነበሩ። +26 የያዕቆብ ዝርያዎች የሆኑትና ከእሱ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች፣* የልጆቹን ሚስቶች ሳይጨምር በአጠቃላይ 66 ነበሩ።+ +27 ዮሴፍ በግብፅ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሁለት* ነበሩ። ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተሰቦች በአጠቃላይ 70* ነበሩ።+ +28 ያዕቆብ ወደ ጎሸን እየሄደ መሆኑን ለዮሴፍ እንዲነግረው ይሁዳን+ ከእሱ አስቀድሞ ላከው። ወደ ጎሸን ምድር+ በደረሱም ጊዜ +29 ዮሴፍ ሠረገላው እንዲዘጋጅለት ካደረገ በኋላ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጎሸን ሄደ። ባገኘውም ጊዜ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ረዘም ላለ ጊዜ አለቀሰ። +30 ከዚያም እስራኤል ዮሴፍን “ከእንግዲህ ብሞት አይቆጨኝም፤ ዓይንህን ለማየት በቅቻለሁ፤ በሕይወት መኖርህንም አረጋግጫለሁ” አለው። +31 ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተሰቦች እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ ሁኔታውን ልንገረው፤+ እንዲህም ልበለው፦ ‘በከነአን ምድር ይኖሩ የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተሰቦች ወደ እኔ መጥተዋል።+ +32 እነሱ እረኞችና+ ከብት አርቢዎች+ ናቸው፤ መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውንና ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።’+ +33 እንግዲህ ፈርዖን ጠርቶ ‘ሥራችሁ ምንድን ነው?’ ብሎ ሲጠይቃችሁ +34 ‘እኛ አገልጋዮችህም ሆን የቀድሞ አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ ከብት አርቢዎች ነን’ በሉት።+ ግብፃውያን በግ ጠባቂዎችን ስለሚጸየፉ+ በጎሸን ምድር እንድትኖሩ+ ይፈቅድላችኋል።” +37 ያዕቆብ አባቱ የባዕድ አገር ሰው ሆኖ ይኖርበት በነበረው በከነአን ምድር ኖረ።+ +2 የያዕቆብ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ+ የ17 ዓመት ወጣት ሳለ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዚልጳ ወንዶች ልጆች+ ጋር በጎች ይጠብቅ+ ነበር። እሱም ስለ ወንድሞቹ መጥፎ ድርጊት የሚገልጽ ወሬ ለአባታቸው ይዞለት መጣ። +3 እስራኤል ዮሴፍን የወለደው በስተርጅናው ስለነበር ከሌሎቹ ወንዶች ልጆቹ ሁሉ+ ይበልጥ ይወደው ነበር፤ ለእሱም ልዩ የሆነ ቀሚስ* አሠራለት። +4 ወንድሞቹም አባታቸው ከእነሱ አስበልጦ እንደሚወደው ሲያዩ ይጠሉት ጀመር፤ በሰላምም ሊያናግሩት አልቻሉም። +5 በኋላም ዮሴፍ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ነገራቸው፤+ እነሱም እሱን የሚጠሉበት ተጨማሪ ምክንያት አገኙ። +6 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እባካችሁ ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ�� ስሙኝ። +7 በእርሻ መካከል ነዶ እያሰርን ነበር፤ ከዚያም የእኔ ነዶ ተነስታ ቀጥ ብላ ስትቆም የእናንተ ነዶዎች ደግሞ የእኔን ነዶ ከበው ሰገዱላት።”+ +8 ወንድሞቹም “በእኛ ላይ ንጉሥ ልትሆንና ልትገዛን ታስባለህ ማለት ነው?” አሉት።+ በመሆኑም ያየው ሕልምና የተናገረው ነገር እሱን ይበልጥ እንዲጠሉት አደረጋቸው። +9 ከዚያም ሌላ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ “ሌላም ሕልም አለምኩ። አሁን ደግሞ ፀሐይ፣ ጨረቃና 11 ከዋክብት ሲሰግዱልኝ አየሁ።”+ +10 ሕልሙንም ለአባቱና ለወንድሞቹ ነገራቸው፤ አባቱም ገሠጸው፤ እንዲህም አለው፦ “ይህ ያለምከው ሕልም ፍቺ ምንድን ነው? እኔም ሆንኩ እናትህና ወንድሞችህ መጥተን መሬት ላይ ተደፍተን እንድንሰግድልህ ታስባለህ?” +11 ወንድሞቹም ይበልጥ ቀኑበት፤+ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው። +12 ወንድሞቹ የአባታቸውን መንጋ ለማሰማራት ሴኬም+ አቅራቢያ ወደሚገኝ ቦታ ሄደው ነበር። +13 በኋላም እስራኤል ዮሴፍን “ወንድሞችህ በሴኬም አቅራቢያ መንጎቹን እየጠበቁ እንዳሉ አውቀሃል አይደል? በል ና፣ ወደ እነሱ ልላክህ” አለው። እሱም “እሺ፣ እሄዳለሁ!” አለ። +14 በመሆኑም “እባክህ ሂድና ወንድሞችህ ደህና መሆናቸውን እይ። መንጋውም ደህና መሆኑን እይና መጥተህ ትነግረኛለህ” አለው። በዚህም መሠረት ከኬብሮን+ ሸለቆ* ወደዚያ ላከው፤ ዮሴፍም ወደ ሴኬም ሄደ። +15 በኋላም ዮሴፍ በሜዳ ላይ ሲባዝን አንድ ሰው አገኘው። ሰውየውም “ምን ፈልገህ ነው?” ሲል ጠየቀው። +16 እሱም “ወንድሞቼን እየፈለግኩ ነው። መንጎቹን እየጠበቁ ያሉት የት እንደሆነ እባክህ ንገረኝ” አለው። +17 ሰውየውም “ከዚህ ሄደዋል፤ ምክንያቱም ‘ወደ ዶታን እንሂድ’ ሲባባሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው። ስለዚህ ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ሄደ፤ ዶታን ላይም አገኛቸው። +18 እነሱም ከሩቅ ሲመጣ ተመለከቱት፤ አጠገባቸውም ከመድረሱ በፊት እሱን እንዴት እንደሚገድሉት ይመካከሩ ጀመር። +19 እነሱም እንዲህ ተባባሉ፦ “ያውና! ያ ሕልም አላሚ መጣ።+ +20 ኑ፣ እንግደለውና ከውኃ ጉድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም ኃይለኛ አውሬ በልቶታል እንላለን። እስቲ የሕልሞቹን መጨረሻ እናያለን።” +21 ሮቤል+ ይህን ሲሰማ ከእነሱ ሊያስጥለው አሰበ፤ በመሆኑም “ሕይወቱን* እንኳ አናጥፋ”+ አለ። +22 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ደም አታፍስሱ።+ በምድረ በዳ በሚገኘው በዚህ የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት እንጂ ጉዳት አታድርሱበት።”*+ ይህን ያላቸው ከእነሱ ሊያስጥለውና ወደ አባቱ ሊመልሰው አስቦ ነበር። +23 ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደደረሰም የለበሰውን ያን ልዩ ቀሚስ+ ገፈፉት፤ +24 ወስደውም የውኃ ጉድጓዱ ውስጥ ጣሉት። ጉድጓዱም ባዶ ነበር፤ ውኃም አልነበረበትም። +25 ከዚያም ሊበሉ ተቀመጡ። ቀና ብለው ሲመለከቱም እስማኤላውያን+ ነጋዴዎች ግመሎቻቸውን አግተልትለው ከጊልያድ ሲመጡ አዩ። እነሱም በግመሎቻቸው ላይ ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫ፣ በለሳንና ከርቤ+ ጭነው ወደ ግብፅ እየወረዱ ነበር። +26 በዚህ ጊዜ ይሁዳ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፦ “ወንድማችንን ብንገድለውና ደሙን ብንሸሽግ ምን እንጠቀማለን?+ +27 ኑ፣ ለእስማኤላውያን እንሽጠው፤+ እጃችንን አንሰንዝርበት። ደግሞም እኮ እሱ ወንድማችን፣ የገዛ ሥጋችን ነው።” እነሱም በወንድማቸው ሐሳብ ተስማሙ። +28 ምድያማውያን+ ነጋዴዎች በአጠገባቸው ሲያልፉም ዮሴፍን ከውኃ ጉድጓዱ አውጥተው በ20 የብር ሰቅል ለእስማኤላውያን ሸጡት።+ እነሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት። +29 በኋላም ሮቤል ወደ ውኃ ጉድጓዱ ተመልሶ ዮሴፍ በዚያ አለመኖሩን ሲመለከት ልብሱን ቀደደ። +30 ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ “ልጁ የለም! እንግዲህ ምንድን ነው የማደርገው?” አላቸው። +31 ስለዚህ የዮሴፍን ቀሚስ ወሰዱ፤ አንድ ፍየል ካረዱ በኋላም ቀሚሱን ደሙ ውስጥ ነከሩት። +32 ከዚያም ያን ልዩ ቀሚስ እንዲህ ከሚል መልእክት ጋር ወደ አባታቸው ላኩት፦ “ይህን አገኘን፤ እባክህ ይህ የልጅህ ቀሚስ መሆን አለመሆኑን እስቲ እየው።”+ +33 እሱም ልብሱን አገላብጦ ካየው በኋላ “ይሄማ የልጄ ቀሚስ ነው! ኃይለኛ አውሬ በልቶት መሆን አለበት! በቃ ዮሴፍን አውሬ ቦጫጭቆታል ማለት ነው!” አለ። +34 ከዚያም ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ በወገቡም ላይ ማቅ ታጥቆ ለብዙ ቀናት ለልጁ አለቀሰ። +35 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ሞከሩ፤ እሱ ግን ፈጽሞ ሊጽናና አልቻለም፤ “በልጄ ሐዘን እንደተቆራመድኩ ወደ መቃብር* እወርዳለሁ!”+ ይል ነበር። አባቱም ለልጁ ማልቀሱን አላቋረጠም። +36 በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ዮሴፍን ግብፅ ውስጥ ጶጢፋር ለተባለ ሰው ሸጡት፤ ይህ ሰው የፈርዖን የቤተ መንግሥት ባለሥልጣንና+ የዘቦች አለቃ+ ነበር። +40 ይህ ከሆነ በኋላ የግብፁ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና+ የዳቦ ጋጋሪዎች አለቃ ጌታቸውን የግብፁን ንጉሥ በደሉ። +2 በመሆኑም ፈርዖን በሁለቱ ሹማምንቱ ማለትም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃ ላይ እጅግ ተቆጣ፤+ +3 እሱም በዘቦች አለቃ+ ቤት በሚገኘው ወህኒ ቤት ይኸውም ዮሴፍ በታሰረበት እስር ቤት+ ውስጥ እንዲታሰሩ አደረገ። +4 ከዚያም የዘቦቹ አለቃ፣ ዮሴፍ ከእነሱ ጋር እንዲሆንና እንዲረዳቸው መደበው፤+ እነሱም ለተወሰነ ጊዜ* ወህኒ ቤት ውስጥ ቆዩ። +5 እስር ቤት ውስጥ ታስረው የነበሩት የግብፁ ንጉሥ መጠጥ አሳላፊና ዳቦ ጋጋሪ በአንድ ሌሊት ሕልም አለሙ፤ የእያንዳንዳቸውም ሕልም የተለያየ ፍቺ ነበረው። +6 በማግስቱ ጠዋት ዮሴፍ ገብቶ ሲያያቸው ተክዘው አገኛቸው። +7 በመሆኑም በጌታው ቤት ከእሱ ጋር የታሰሩትን የፈርዖንን ሹማምንት “ምነው ዛሬ ፊታችሁ በሐዘን ጠቆረ?” ሲል ጠየቃቸው። +8 እነሱም “ሁለታችንም ሕልም አልመን ነበር፤ ሕልማችንን የሚፈታልን ሰው ግን አላገኘንም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?+ እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው። +9 በመሆኑም የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፦ “በሕልሜ ከፊት ለፊቴ አንድ የወይን ተክል አየሁ። +10 በወይኑም ተክል ላይ ሦስት ቀንበጦች ነበሩ፤ ተክሉም በማቆጥቆጥ ላይ እያለ አበባ አወጣ፤ በዘለላዎቹም ላይ ያሉት ፍሬዎች በሰሉ። +11 እኔም የፈርዖንን ጽዋ በእጄ ይዤ ነበር፤ የወይን ፍሬዎቹንም ወስጄ በፈርዖን ጽዋ ውስጥ ጨመቅኳቸው። ከዚያም ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ሰጠሁት።” +12 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ እንዲህ አለው፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቀንበጦች ሦስት ቀናት ናቸው። +13 ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ከእስር ቤት ያስወጣሃል፤* ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል።+ አንተም የመጠጥ አሳላፊው በነበርክበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ሁሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።+ +14 ይሁንና ሁኔታዎች ሲስተካከሉልህ እኔን እንዳትረሳኝ። እባክህ ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤ ከዚህ እስር ቤት እንዲያስፈታኝም ስለ እኔ ለፈርዖን ንገረው። +15 በመሠረቱ እኔ ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት ተገድጄ ነው፤+ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት* ውስጥ የጣሉኝ ያለምንም ጥፋት ነው።”+ +16 የዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃም ዮሴፍ የተናገረው የሕልሙ ፍቺ መልካም መሆኑን ሲያይ እሱም እንዲህ አለው፦ “እኔም ሕልም አይቼ ነበር፤ በሕልሜም ነጭ ዳቦዎች የያዙ ሦስት ቅርጫቶች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ +17 ከላይ ባለው ቅርጫት ውስጥ ለፈርዖን የሚቀርቡ የተለያዩ የተጋገሩ ምግቦች ነበሩ፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከተሸከምኩት ቅርጫት ውስጥ ይበሉ ነበር።” +18 ከዚያም ዮሴፍ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቅርጫቶች ሦስት ቀናት ናቸው። +19 ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ከእስር ቤት ያስወጣሃል፤ ራስህንም ቆርጦ* በእንጨት ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበላሉ።”+ +20 ሦስተኛው ቀን ደግሞ ፈርዖን የልደት በዓሉን የሚያከብርበት ዕለት ነበር፤+ እሱም ለአገልጋዮቹ በሙሉ ግብዣ አዘጋጀ። አገልጋዮቹ ባሉበትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ከእስር ቤት አስወጣቸው።* +21 የመጠጥ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ መጠጥ አሳላፊነት ሹመቱ መለሰው፤ እሱም እንደቀድሞው ለፈርዖን ጽዋውን ይሰጠው ጀመር። +22 የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ግን ዮሴፍ ሕልማቸውን በፈታላቸው መሠረት ሰቀለው።+ +23 ይሁንና የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ጨርሶም ረሳው።+ +16 የአብራም ሚስት ሦራ ለአብራም ልጆች አልወለደችለትም ነበር፤+ ይሁንና አጋር+ የምትባል አንዲት ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። +2 በመሆኑም ሦራ አብራምን እንዲህ አለችው፦ “እንግዲህ እንደምታየው ይሖዋ ልጆች እንዳልወልድ አድርጎኛል። እባክህ ከአገልጋዬ ጋር ግንኙነት ፈጽም። ምናልባትም በእሷ አማካኝነት ልጆች ላገኝ እችላለሁ።”+ ስለሆነም አብራም የሦራን ቃል ሰማ። +3 አብራም በከነአን ምድር ለአሥር ዓመት ያህል ከኖረ በኋላ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋን አጋርን ወስዳ ሚስት እንድትሆነው ለባሏ ለአብራም ሰጠችው። +4 በመሆኑም አብራም ከአጋር ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀነሰች። መፀነሷን ባወቀች ጊዜም እመቤቷን መናቅ ጀመረች። +5 በዚህ ጊዜ ሦራ አብራምን እንዲህ አለችው፦ “ለደረሰብኝ በደል ተጠያቂው አንተ ነህ። አገልጋዬን በእቅፍህ ያደረግኩልህ እኔው ራሴ ነበርኩ፤ እሷ ግን መፀነሷን ባወቀች ጊዜ ትንቀኝ ጀመር። ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ።” +6 በመሆኑም አብራም ሦራን “እንግዲህ አገልጋይሽ እንደሆነች በእጅሽ ናት። መልካም መስሎ የታየሽን ነገር አድርጊባት” አላት። ከዚያም ሦራ አገልጋይዋን አዋረደቻት፤ ስለዚህም ጥላት ኮበለለች። +7 በኋላም የይሖዋ መልአክ አጋርን በምድረ በዳ በሚገኝ አንድ የውኃ ምንጭ አጠገብ ማለትም ወደ ሹር+ በሚወስደው መንገድ ላይ ባለው ምንጭ አጠገብ አገኛት። +8 እሱም “የሦራ አገልጋይ አጋር፣ ለመሆኑ የመጣሽው ከየት ነው? ወዴትስ እየሄድሽ ነው?” አላት። እሷም መልሳ “ከእመቤቴ ከሦራ ኮብልዬ እየሄድኩ ነው” አለች። +9 የይሖዋም መልአክ “ወደ እመቤትሽ ተመለሽ፤ ለእሷም በትሕትና ተገዢላት” አላት። +10 ከዚያም የይሖዋ መልአክ “ከብዛቱ የተነሳ የማይቆጠር እስኪሆን ድረስ ዘርሽን እጅግ አበዛዋለሁ”+ አላት። +11 በተጨማሪም የይሖዋ መልአክ እንዲህ አላት፦ “እንግዲህ ይኸው ፀንሰሻል፤ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ። ስሙንም እስማኤል* ትይዋለሽ፤ ምክንያቱም ይሖዋ የሥቃይ ጩኸትሽን ሰምቷል። +12 እሱም እንደ ዱር አህያ* ይሆናል። ባገኘው ሰው ሁሉ ላይ እጁን ያነሳል፤ ያገኘውም ሰው ሁሉ እጁን ያነሳበታል፤ ከወንድሞቹም ሁሉ ፊት ለፊት ይኖራል።”* +13 ከዚያም አጋር “የሚያየኝን አሁን በእርግጥ አየሁት ማለት ነው?” ብላ ስላሰበች እያነጋገራት የነበረውን ይሖዋን ስሙን ጠርታ “አንተ የምታይ አምላክ ነህ”+ አለች። +14 የውኃ ጉድጓዱ ብኤርላሃይሮዒ* ተብሎ የተጠራው በዚህ የተነሳ ነው። (ጉድጓዱም በቃዴስና በቤሬድ መካከል ይገኛል።) +15 ስለዚህ አጋር ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን ልጅ እስማኤል+ ብሎ ስም አወጣለት። +16 አጋር ለአብራም እስማኤልን በወለደችለት ጊዜ አብራም የ86 ዓመት ሰው ነበር። +6 ሰዎች በምድር ላይ ቁጥራቸው እየጨመረ ሲሄድ ሴቶች ልጆችን ወለዱ፤ +2 የእውነተኛው አምላክ ልጆችም*+ የሰዎች ሴቶች ልጆች ውብ እንደሆኑ አስተዋሉ። በመሆኑም የመረጧቸውን ሁሉ ለራሳቸው ሚስቶች አድርገው ወሰዱ። +3 ከዚያም ይሖዋ “ሰው ሥጋ ስለሆነ* መንፈሴ ሰውን ለዘላለም አይታገሥም።+ በመሆኑም ዘመኑ 120 ዓመት ይሆናል”+ አለ። +4 በዚያ ዘመንም ሆነ ከዚያ በኋላ ኔፍሊም* በምድር ላይ ነበሩ። በዚያ ጊዜም የእውነተኛው አምላክ ልጆች ከሰዎች ሴቶች ልጆች ጋር ግንኙነት ፈጸሙ፤ ሴቶቹም ወንዶች ልጆችን ወለዱላቸው። እነሱም በጥንት ዘመን በኃያልነታቸው ዝና ያተረፉ ሰዎች ነበሩ። +5 በዚህም የተነሳ ይሖዋ የሰው ልጅ ክፋት በምድር ላይ እንደበዛና የልቡም ሐሳብ ሁሉ ምንጊዜም ወደ መጥፎ ብቻ ያዘነበለ+ እንደሆነ ተመለከተ። +6 ይሖዋም ሰዎችን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤* ልቡም አዘነ።+ +7 በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “የፈጠርኳቸውን ሰዎች ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ ሰውን ጨምሮ የቤት እንስሳትን እንዲሁም መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትንና በሰማያት ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትን አጠፋለሁ፤ ምክንያቱም እነሱን በመፍጠሬ ተጸጽቻለሁ።” +8 ኖኅ ግን በይሖዋ ፊት ሞገስ አገኘ። +9 የኖኅ ታሪክ ይህ ነው። ኖኅ ጻድቅ ሰው ነበር።+ በዘመኑ* ከነበሩት ሰዎች መካከል እሱ እንከን* የሌለበት ሰው ነበር። ኖኅ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ይሄድ ነበር።+ +10 ኖኅ ከጊዜ በኋላ ሴም፣ ካምና ያፌት+ የተባሉ ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ። +11 ይሁንና ምድር በእውነተኛው አምላክ ፊት ተበላሽታ ነበር፤ እንዲሁም በዓመፅ ተሞልታ ነበር። +12 አዎ፣ አምላክ ምድርን ተመለከተ፤ ምድርም ተበላሽታ ነበር፤+ ሰው* ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበር።+ +13 ከዚህ በኋላ አምላክ ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በእነሱ የተነሳ ምድር በዓመፅ ስለተሞላች ሥጋን ሁሉ ለማጥፋት ወስኛለሁ፤ ስለሆነም እነሱን ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።+ +14 አንተ ከጎፈር እንጨት ለራስህ መርከብ* ሥራ።+ በመርከቡም ውስጥ የተለያዩ ክፍሎችን ሥራ፤ እንዲሁም መርከቡን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ቅጥራን*+ ለቅልቀው። +15 መርከቡንም የምትሠራው እንደሚከተለው ነው፦ የመርከቡ ርዝመት 300 ክንድ፣* ወርዱ 50 ክንድ እንዲሁም ከፍታው 30 ክንድ ይሁን። +16 በመርከቡም ላይ ከጣሪያው ሥር አንድ ክንድ ቁመት ያለው ብርሃን ማስገቢያ የሚሆን መስኮት* ሥራ፤ የመርከቡንም በር በጎኑ በኩል አድርግ፤+ መርከቡም ምድር ቤት እንዲሁም አንደኛና ሁለተኛ ፎቅ ይኑረው። +17 “እኔ ደግሞ ከሰማያት በታች የሕይወት እስትንፋስ* ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃ+ አመጣለሁ። በምድር ላይ ያለ ነገር ሁሉ ይጠፋል።+ +18 እኔም ከአንተ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ አንተም ወደ መርከቡ መግባት አለብህ፤ አንተ፣ ከአንተም ጋር ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና የልጆችህ ሚስቶች ወደ መርከቡ መግባት ይኖርባችኋል።+ +19 ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲተርፉ ከሁሉም ዓይነት ሕያው ፍጡር+ ተባዕትና እንስት እያደረግክ ሁለት ሁለት ወደ መርከቡ አስገባ፤+ +20 በሕይወት እንዲተርፉ የሚበርሩ ፍጥረታት እንደየወገናቸው፣ የቤት እንስሳት እንደየወገናቸው እንዲሁም በምድር ላይ ያሉ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳት ሁሉ እንደየወገናቸው ሁለት ሁለት እየሆኑ ከአንተ ጋር ይግቡ።+ +21 ለአንተም ሆነ ለእንስሳቱ ምግብ እንዲሆን ማንኛውንም ዓይነት ምግብ+ ሰብስበህ ይዘህ ትገባለህ።” +22 ኖኅም አምላክ ያዘዘውን ሁሉ በተባለው መሠረት አከናወነ። ልክ እንደዚሁ አደረገ።+ +25 አብርሃም ኬጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ። +2 እሷም ከጊዜ በኋላ ዚምራን���፣ ዮቅሻንን፣ ሚዳንን፣ ምድያምን፣+ ይሽባቅን እና ሹሃን+ ወለደችለት። +3 ዮቅሻንም ሳባን እና ዴዳንን ወለደ። የዴዳን ወንዶች ልጆች ደግሞ አሹሪም፣ ለጡሺም እና ለኡሚም ነበሩ። +4 የምድያም ወንዶች ልጆች ኤፋ፣ ኤፌር፣ ሃኖክ፣ አቢዳዕ እና ኤልዳዓ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ወንዶች ልጆች ነበሩ። +5 በኋላም አብርሃም ያለውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፤+ +6 ከቁባቶቹ ለወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ግን ስጦታ ሰጣቸው። ከዚያም ገና በሕይወት እያለ ከልጁ ከይስሐቅ እንዲርቁ በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ምሥራቅ ምድር ላካቸው።+ +7 አብርሃም በሕይወት የኖረበት ዘመን 175 ዓመት ነበር። +8 ከዚያም አብርሃም እስትንፋሱ ቀጥ አለ፤ ሸምግሎ፣ በሕይወቱ ረክቶና ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።* +9 ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤልም የሂታዊው የጾሃር ልጅ በሆነው በኤፍሮን የእርሻ ቦታ ውስጥ ባለው በማምሬ ፊት ለፊት በሚገኘው በማክፈላ ዋሻ ቀበሩት፤+ +10 ይህ የእርሻ ቦታ አብርሃም ከሄት ወንዶች ልጆች የገዛው ነው። አብርሃምም ከሚስቱ ከሣራ ጋር በዚያ ስፍራ ተቀበረ።+ +11 አብርሃም ከሞተ በኋላም አምላክ የአብርሃምን ልጅ ይስሐቅን መባረኩን ቀጠለ፤+ ይስሐቅ በብኤርላሃይሮዒ+ አቅራቢያ ይኖር ነበር። +12 የሣራ አገልጋይ የነበረችው ግብፃዊቷ አጋር+ ለአብርሃም የወለደችለት የአብርሃም ልጅ የእስማኤል+ ታሪክ ይህ ነው። +13 የእስማኤል ወንዶች ልጆች ስም በየስማቸውና በየቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው ሲዘረዘር የሚከተለው ነው፦ የእስማኤል የበኩር ልጅ ነባዮት+ ከዚያም ቄዳር፣+ አድበዔል፣ ሚብሳም፣+ +14 ሚሽማ፣ ዱማ፣ ማሳ፣ +15 ሃዳድ፣ ቴማ፣ የጡር፣ ናፊሽ እና ቄድማ። +16 የእስማኤል ወንዶች ልጆች በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው* ሲዘረዘሩ ስማቸው ይህ ነው፤ እነሱም በየነገዳቸው 12 የነገድ አለቆች ናቸው።+ +17 እስማኤል 137 ዓመት ኖረ። ከዚያም እስትንፋሱ ቀጥ አለና ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።* +18 እነሱም ከግብፅ አጠገብ በሹር+ አቅራቢያ ከምትገኘው ከሃዊላ+ አንስቶ እስከ አሦር ድረስ ባለው አካባቢ ሰፍረው ነበር። በወንድሞቹም ሁሉ አቅራቢያ ሰፈረ።*+ +19 የአብርሃም ልጅ+ የይስሐቅ ታሪክ ይህ ነው። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። +20 ይስሐቅ በጳዳንአራም የሚኖረውን የአራማዊውን የባቱኤልን ሴት ልጅ+ ማለትም የአራማዊውን የላባን እህት ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው 40 ዓመት ነበር። +21 ይስሐቅ ሚስቱ መሃን ስለነበረች ስለ እሷ አዘውትሮ ይሖዋን ይለምን ነበር፤ ይሖዋም ልመናውን ሰማው፤ ሚስቱ ርብቃም ፀነሰች። +22 በሆዷ ውስጥ ያሉት ልጆችም እርስ በርስ ይታገሉ ጀመር፤+ በመሆኑም “እንዲህ ከሆነስ ብሞት ይሻለኛል” አለች። ስለዚህ ይሖዋን ጠየቀች። +23 ይሖዋም እንዲህ አላት፦ “በማህፀንሽ ውስጥ ሁለት ብሔራት አሉ፤+ ከውስጥሽም ሁለት ሕዝቦች ተለያይተው ይወጣሉ።+ አንደኛው ብሔር ከሌላኛው ብሔር ይበረታል፤+ ታላቁም ታናሹን ያገለግላል።”+ +24 የመውለጃዋም ጊዜ ሲደርስ በማህፀኗ ውስጥ መንታ ልጆች ነበሩ። +25 መጀመሪያ የወጣው መልኩ ቀይ ሲሆን ፀጉራም ካባ የለበሰ ይመስል ሰውነቱ በሙሉ በፀጉር የተሸፈነ ነበር፤+ በመሆኑም ስሙን ኤሳው*+ አሉት። +26 ከዚያም ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የኤሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤+ በዚህም የተነሳ ስሙን ያዕቆብ* አለው።+ ርብቃ እነሱን ስትወልድ ይስሐቅ 60 ዓመቱ ነበር። +27 ልጆቹም እያደጉ ሲሄዱ ኤሳው ውጭ መዋል የሚወድ የተዋጣለት አዳኝ ሆነ፤+ ያዕቆብ ግን አብዛኛውን ጊዜውን በድንኳን የሚያሳልፍ+ ነቀፋ የሌለበት ሰው ነበር። +28 ይስሐቅ ኤሳውን ይወደው ነበር፤ ምክንያቱም እያደነ ያበላው ነበር፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወደው ነበር።+ +29 አንድ ቀን ኤሳው ውጭ ውሎ ��ጣም ደክሞት ሲመጣ ያዕቆብ ወጥ እየሠራ ነበር። +30 በመሆኑም ኤሳው ያዕቆብን “ቶሎ በል እባክህ፣ በጣም ስለደከመኝ* ከዚያ ከቀዩ ወጥ የተወሰነ* ስጠኝ!” አለው። ስሙ ኤዶም*+ የተባለውም በዚህ የተነሳ ነው። +31 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ “በመጀመሪያ የብኩርና መብትህን+ ሽጥልኝ!” አለው። +32 ኤሳውም “እኔ ለራሴ ልሞት ደርሻለሁ! ታዲያ የብኩርና መብት ምን ይጠቅመኛል?” አለው። +33 ያዕቆብም “በመጀመሪያ ማልልኝ!” አለው። እሱም ማለለት፤ የብኩርና መብቱንም ለያዕቆብ ሸጠለት።+ +34 ከዚያም ያዕቆብ ለኤሳው ዳቦና ምስር ወጥ ሰጠው፤ እሱም በላ፣ ጠጣም፤ ተነሥቶም ሄደ። በዚህ መንገድ ኤሳው የብኩርና መብቱን አቃለለ። +33 ያዕቆብም ቀና ብሎ ሲመለከት ኤሳው ሲመጣ አየ፤ ከእሱም ጋር 400 ሰዎች ነበሩ።+ በመሆኑም ልጆቹን ለሊያ፣ ለራሔልና ለሁለቱ ሴት አገልጋዮች+ አከፋፈላቸው። +2 እሱም ሴት አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውን ከፊት፣+ ሊያንና ልጆቿን ከእነሱ ቀጥሎ፣+ ራሔልንና ዮሴፍን+ ደግሞ ከእነሱ በኋላ እንዲሆኑ አደረገ። +3 ከዚያም እሱ ቀድሟቸው ሄደ፤ ወደ ወንድሙ ሲቀርብም ሰባት ጊዜ ወደ መሬት ዝቅ ብሎ ሰገደ። +4 ሆኖም ኤሳው ወደ እሱ እየሮጠ በመሄድ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። +5 ኤሳውም ቀና ብሎ ሴቶቹንና ልጆቹን ሲያይ እንዲህ አለ፦ “እነዚህ አብረውህ ያሉት እነማን ናቸው?” እሱም “አምላክ በቸርነቱ ለአገልጋይህ የሰጣቸው ልጆች ናቸው”+ አለው። +6 በዚህ ጊዜ ሴት አገልጋዮቹ ከልጆቻቸው ጋር ወደ ፊት ቀርበው ሰገዱ፤ +7 ሊያና ልጆቿም ወደ ፊት ቀርበው ሰገዱ። ከዚያም ዮሴፍና ራሔል ወደ ፊት ቀርበው ሰገዱ።+ +8 ኤሳውም “ቀደም ሲል ያገኘኋቸውን ሰዎችና እንስሳት የላክሃቸው ለምንድን ነው?” አለው።+ እሱም “በጌታዬ ፊት ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው።+ +9 ከዚያም ኤሳው “ወንድሜ ሆይ፣ እኔ ከበቂ በላይ አለኝ።+ የአንተ የሆነው ለራስህ ይሁን” አለው። +10 ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፦ “የለም፣ እንዲህማ አይሆንም። በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ ስጦታዬን ከእጄ መውሰድ አለብህ፤ ምክንያቱም ስጦታውን የላክሁት ፊትህን እንዳይ ብዬ ነው። እንዲህ በደስታ ተቀብለኸኝ የአንተን ፊት ማየቴ ራሱ ለእኔ የአምላክን ፊት የማየት ያህል ነው።+ +11 አምላክ ሞገስ ስላሳየኝና የሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ስላለኝ+ የመልካም ምኞት መግለጫ እንዲሆን ያመጣሁልህን ይህን ስጦታ እባክህ ተቀበለኝ።”+ ያዕቆብም አጥብቆ ለመነው፤ ስለዚህ ስጦታውን ወሰደ። +12 በኋላም ኤሳው “በል እንነሳና ጉዟችንን እንቀጥል፤ እኔም ከፊት ከፊትህ እሄዳለሁ” አለው። +13 እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “ልጆቹ አቅም እንደሌላቸው+ እንዲሁም የሚያጠቡ በጎችና ከብቶች እንዳሉኝ ጌታዬ ያውቃል። እንስሳቱ ለአንድ ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ መንጋው በሙሉ ያልቃል። +14 ስለዚህ ጌታዬ ከአገልጋዩ ቀድሞ ይሂድ፤ እኔ ግን ከጌታዬ ጋር እዚያው ሴይር እስከምንገናኝ+ ድረስ በምነዳቸው ከብቶች ፍጥነትና እንደ ልጆቹ እርምጃ ቀስ እያልኩ ላዝግም።” +15 ኤሳውም “እባክህ ከእኔ ጋር ካሉት ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን ልተውልህ” አለው። እሱም “ለምን ብለህ? በጌታዬ ፊት ሞገስ ማግኘቴ ብቻ ይበቃኛል” አለው። +16 በመሆኑም በዚያ ቀን ኤሳው ወደ ሴይር ለመመለስ ጉዞ ጀመረ። +17 ያዕቆብም ወደ ሱኮት+ ሄደ፤ በዚያም ለራሱ ቤት፣ ለመንጎቹም ዳስ ሠራ። የቦታውንም ስም ሱኮት* ያለው ለዚህ ነበር። +18 ያዕቆብ ከጳዳንአራም+ ተነስቶ በመጓዝ በከነአን+ ምድር ወደምትገኘው ወደ ሴኬም+ ከተማ በሰላም ደረሰ፤ በከተማዋም አቅራቢያ ሰፈረ። +19 ከዚያም ድንኳኑን የተከለበትን ቦታ ከሴኬም አባት ከኤሞር ወንዶች ልጆች እጅ በ100 ጥሬ ገንዘብ ገዛ።+ +20 ���ዚያም መሠዊያ አቆመ፤ መሠዊያውንም አምላክ፣ የእስራኤል አምላክ ብሎ ጠራው።+ +10 የኖኅ ወንዶች ልጆች የሆኑት የሴም፣ የካም እና የያፌት ታሪክ ይህ ነው። ከጥፋት ውኃ በኋላ ወንዶች ልጆች ወለዱ።+ +2 የያፌት ወንዶች ልጆች ጎሜር፣+ ማጎግ፣+ ማዳይ፣ ያዋን፣ ቱባል፣+ መሼቅ+ እና ቲራስ+ ነበሩ። +3 የጎሜር ወንዶች ልጆች አሽከናዝ፣+ ሪፋት እና ቶጋርማ+ ነበሩ። +4 የያዋን ወንዶች ልጆች ኤሊሻ፣+ ተርሴስ፣+ ኪቲም+ እና ዶዳኒም ነበሩ። +5 በደሴቶች ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች እንደየቋንቋቸውና እንደየቤተሰባቸው በየብሔራቸው በመሆን ወደየምድራቸው የተሰራጩት ከእነዚህ ነው። +6 የካም ወንዶች ልጆች ኩሽ፣ ሚጽራይም፣+ ፑጥ+ እና ከነአን+ ነበሩ። +7 የኩሽ ወንዶች ልጆች ሴባ፣+ ሃዊላ፣ ሳብታ፣ ራአማ+ እና ሳብተካ ነበሩ። የራአማ ወንዶች ልጆች ሳባ እና ዴዳን ነበሩ። +8 ኩሽ ናምሩድን ወለደ። እሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኃያል ሰው ነበር። +9 እሱም ይሖዋን የሚቃወም ኃያል አዳኝ ሆነ። በዚህም የተነሳ “እንደ ናምሩድ ያለ ይሖዋን የሚቃወም ኃያል አዳኝ” ይባል ነበር። +10 የግዛቱ መጀመሪያም* በሰናኦር+ ምድር የሚገኙት ባቤል፣+ ኤሬክ፣+ አካድ እና ካልኔ ነበሩ። +11 ከዚያ ምድር ተነስቶም ወደ አሦር+ በመሄድ ነነዌን፣+ ረሆቦትኢርን እና ካላህን ቆረቆረ፤ +12 እንዲሁም በነነዌና በካላህ መካከል የምትገኘውን ረሰንን ቆረቆረ፤ እሷም ታላቋ ከተማ ናት።* +13 ሚጽራይም ሉድን፣+ አናሚምን፣ ለሃቢምን፣ ናፊቱሂምን፣+ +14 ጳትሩሲምን፣+ ካስሉሂምን (ፍልስጤማውያን+ የተገኙት ከእሱ ነው) እንዲሁም ካፍቶሪምን+ ወለደ። +15 ከነአን የበኩር ልጁን ሲዶናን፣+ ሄትን+ +16 እንዲሁም ኢያቡሳዊውን፣+ አሞራዊውን፣+ ገርጌሻዊውን፣ +17 ሂዋዊውን፣+ አርቃዊውን፣ ሲናዊውን፣ +18 አርዋዳዊውን፣+ ጸማራዊውን እና ሃማታዊውን+ ወለደ። ከዚያ በኋላ የከነአናውያን ቤተሰቦች ተበተኑ። +19 በመሆኑም የከነአናውያን ወሰን ከሲዶና አንስቶ በጋዛ+ አቅራቢያ እስካለችው እስከ ጌራራ+ እንዲሁም እስከ ሰዶም፣ ገሞራ፣+ አድማህ እና በላሻ አቅራቢያ እስካለችው እስከ ጸቦይም+ ድረስ ያለው ነበር። +20 የካም ወንዶች ልጆች እንደየቤተሰባቸውና እንደየቋንቋቸው በየአገራቸውና በየብሔራቸው እነዚህ ነበሩ። +21 የኤቤር+ ወንዶች ልጆች ሁሉ ቅድመ አያትና የታላቅየው የያፌት ወንድም* የሆነው ሴምም ልጆች ወለደ። +22 የሴም ወንዶች ልጆች ኤላም፣+ አሹር፣+ አርፋክስድ፣+ ሉድ እና አራም+ ነበሩ። +23 የአራም ወንዶች ልጆች ዑጽ፣ ሁል፣ ጌተር እና ማሽ ነበሩ። +24 አርፋክስድ ሴሎምን+ ወለደ፤ ሴሎምም ኤቤርን ወለደ። +25 ኤቤር ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የአንደኛው ስም ፋሌቅ*+ ነበር፤ ምክንያቱም በእሱ የሕይወት ዘመን ምድር ተከፋፍላ* ነበር። የወንድሙ ስም ደግሞ ዮቅጣን+ ነበር። +26 ዮቅጣን አልሞዳድን፣ ሸሌፍን፣ ሃጻርማዌትን፣ ያራህን፣+ +27 ሃዶራምን፣ ዑዛልን፣ ዲቅላን፣ +28 ኦባልን፣ አቢማዔልን፣ ሳባን፣ +29 ኦፊርን፣+ ሃዊላን እና ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ነበሩ። +30 መኖሪያ ስፍራቸውም ከሜሻ አንስቶ እስከ ሰፋር ይኸውም እስከ ምሥራቅ ተራራማ አካባቢ ድረስ ይዘልቃል። +31 የሴም ወንዶች ልጆች እንደየቤተሰባቸውና እንደየቋንቋቸው በየአገራቸውና በየብሔራቸው እነዚህ ነበሩ።+ +32 የኖኅ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች እንደየዘር ሐረጋቸው በየብሔራቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውኃው በኋላ ብሔራት ሁሉ በምድር ላይ የተሰራጩት ከእነዚህ ነበር።+ +14 በዚያን ጊዜ የሰናኦር+ ንጉሥ አምራፌል፣ የኤላሳር ንጉሥ አርዮክ፣ የኤላም+ ንጉሥ ኮሎዶጎምር+ እና የጎይም ንጉሥ ቲድአል +2 ከሰዶም+ ንጉሥ ከቤራ፣ ከገሞራ+ ንጉሥ ከቢርሻ፣ ከአድማህ ንጉሥ ከሺንአብ፣ ከጸቦይም+ ንጉሥ ከሸሜበር እና ከቤላ ማለትም ከዞአር ንጉሥ ጋር ጦርነት ገጠሙ። +3 እነዚህ* ሁሉ በሲዲም ሸለቆ*+ ማለትም በጨው ባሕር*+ ሠራዊታቸውን አሰባሰቡ። +4 እነሱም ኮሎዶጎምርን 12 ዓመት አገለገሉት፤ በ13ኛው ዓመት ግን ዓመፁ። +5 ስለሆነም በ14ኛው ዓመት ኮሎዶጎምርና አብረውት የነበሩት ነገሥታት መጥተው ረፋይምን በአስተሮትቃርናይም፣ ዙዚምን በሃም፣ ኤሚምን+ በሻዌቂሪያታይም፣ +6 ሆራውያንን+ ደግሞ ሴይር+ ከሚባለው ተራራቸው አንስቶ በምድረ በዳ እስከሚገኘው እስከ ኤልጳራን ድረስ በሚዘልቀው ስፍራ ድል አደረጓቸው። +7 ከዚያም ቃዴስ+ ወደምትባለው ወደ ኤንሚሽጳጥ ተመልሰው በመምጣት መላውን የአማሌቃውያን+ ግዛትና በሃጻጾንታማር+ ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንን+ ድል አደረጉ። +8 በዚህ ጊዜ የሰዶም ንጉሥ፣ የገሞራ ንጉሥ፣ የአድማህ ንጉሥ፣ የጸቦይም ንጉሥ እንዲሁም የቤላ ማለትም የዞአር ንጉሥ ከእነሱ ጋር ለመዋጋት ሠራዊታቸውን አስተባብረው በሲዲም ሸለቆ* ውስጥ ለጦርነት ተሰለፉ፤ +9 የኤላምን ንጉሥ ኮሎዶጎምርን፣ የጎይምን ንጉሥ ቲድአልን፣ የሰናኦርን ንጉሥ አምራፌልን እንዲሁም የኤላሳርን+ ንጉሥ አርዮክን ለመውጋት ተነሱ፤ አራቱ ነገሥታት ከአምስቱ ጋር ተዋጉ። +10 የሲዲም ሸለቆ* በቅጥራን ጉድጓዶች የተሞላ ነበር፤ የሰዶምና የገሞራ ነገሥታት ሸሽተው ለማምለጥ ሲሞክሩ እነዚህ ጉድጓዶች ውስጥ ወደቁ፤ የቀሩት ደግሞ ወደ ተራራማው አካባቢ ሸሹ። +11 ከዚያም ድል አድራጊዎቹ የሰዶምንና የገሞራን ንብረት በሙሉ እንዲሁም ምግባቸውን ሁሉ ይዘው ሄዱ።+ +12 በተጨማሪም በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን+ ከነንብረቱ ይዘውት ሄዱ። +13 ከዚያም አንድ ያመለጠ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው። በዚያን ጊዜ አብራም የኤሽኮል እና የአኔር ወንድም በሆነው በአሞራዊው በማምሬ+ ትላልቅ ዛፎች አጠገብ ይኖር* ነበር።+ እነዚህ ሰዎች የአብራም አጋሮች ነበሩ። +14 በዚህ መንገድ አብራም ዘመዱ*+ በምርኮ መወሰዱን ሰማ። ስለሆነም በቤቱ የተወለዱትን 318 የሠለጠኑ አገልጋዮች ሰብስቦ ተነሳ፤ ወራሪዎቹንም ተከትሎ እስከ ዳን+ ድረስ ሄደ። +15 በሌሊትም ሠራዊቱን ከፋፈለ፤ እሱና አገልጋዮቹም በወራሪዎቹ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ድል አደረጓቸው። እሱም ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከምትገኘው እስከ ሆባ ድረስ አሳደዳቸው። +16 የወሰዷቸውን ንብረቶችም ሁሉ አስመለሰ፤ በተጨማሪም ዘመዱን ሎጥንና ንብረቶቹን እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎቹን ሰዎች አስመለሰ። +17 አብራም ኮሎዶጎምርንና ከእሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ድል አድርጎ ከተመለሰ በኋላ የሰዶም ንጉሥ ከአብራም ጋር ለመገናኘት ወደ ሻዌ ሸለቆ* ማለትም ወደ ንጉሡ ሸለቆ+ ወጣ። +18 የሳሌም ንጉሥ+ መልከጼዴቅም+ ምግብና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤ እሱም የልዑሉ አምላክ ካህን+ ነበር። +19 አብራምንም ባረከው፤ እንዲህም አለው፦ “ሰማይንና ምድርን የሠራውልዑሉ አምላክ አብራምን ይባርክ፤ +20 የሚጨቁኑህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠህ፣ልዑሉ አምላክ ይወደስ!” አብራምም ከሁሉም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።+ +21 ከዚያም የሰዶም ንጉሥ አብራምን “ሰዎቹን* ስጠኝ፤ ንብረቶቹን ግን ለራስህ ውሰድ” አለው። +22 አብራም ግን የሰዶምን ንጉሥ እንዲህ አለው፦ “ሰማይንና ምድርን ወደሠራው ወደ ልዑሉ አምላክ ወደ ይሖዋ እጄን አንስቼ እምላለሁ፣ +23 ‘አብራምን አበለጸግኩት’ እንዳትል የአንተ ከሆነው ነገር ምንም አልወስድም፤ ሌላው ቀርቶ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ አልወስድም። +24 ወጣቶቹ ከበሉት ምግብ በስተቀር ምንም ነገር አልወስድም። ከእኔ ጋር የዘመቱት አኔር፣ ኤሽኮልና ማምሬ+ ግን ድርሻቸውን ይውሰዱ።” +43 ረሃቡ በምድሪቱ ላይ በርትቶ ነበር።+ +2 ስለሆነም ከግብፅ ያመጡትን እህል በልተው ሲጨርሱ+ አባታቸው “ተመልሳችሁ ሂዱና ጥቂት እህል ግዙልን” አላቸው። +3 በዚህ ጊዜ ይሁዳ እንዲህ አለው፦ “ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁት ካልመጣችሁ በምንም ዓይነት ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ በማለት በግልጽ አስጠንቅቆናል።+ +4 ወንድማችንን ከእኛ ጋር የምትልከው ከሆነ ወደዚያ ወርደን እህል እንገዛልሃለን። +5 እሱን የማትልከው ከሆነ ግን ወደዚያ አንወርድም፤ ምክንያቱም ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁት ካልመጣችሁ በምንም ዓይነት ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎናል።”+ +6 እስራኤልም+ “ምነው እንዲህ ላለ ችግር ዳረጋችሁኝ? ሌላ ወንድም እንዳላችሁ ለምን ለሰውየው ነገራችሁት?” አላቸው። +7 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ሰውየው ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ?’ በማለት በቀጥታ ስለ እኛና ስለ ዘመዶቻችን ጠየቀን፤ እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው።+ ታዲያ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ኑ’ ይለናል ብለን እንዴት ልንጠረጥር እንችላለን?”+ +8 ከዚያም ይሁዳ አባቱን እስራኤልን እንዲህ በማለት ለመነው፦ “እኛም ሆን አንተ እንዲሁም ትናንሽ ልጆቻችን+ በረሃብ ከምናልቅ፣ በሕይወት እንድንተርፍ+ ልጁ ከእኔ ጋር እንዲሄድ ፍቀድና+ ተነስተን ወደዚያ እንሂድ። +9 የልጁን ደህንነት በተመለከተ ኃላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ።*+ አንድ ነገር ቢሆን እኔን ተጠያቂ ልታደርገኝ ትችላለህ። ልጁን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣውና ባላስረክብህ በሕይወቴ ሙሉ በፊትህ በደለኛ ልሁን። +10 ዝም ብለን ጊዜ ባናጠፋ ኖሮ እስካሁን ሁለት ጊዜ እዚያ ደርሰን በተመለስን ነበር።” +11 በመሆኑም አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ ሌላ አማራጭ ከጠፋ እንዲህ አድርጉ፦ ምድሪቱ ከምታፈራቸው ምርጥ ነገሮች መካከል ጥቂት በለሳን፣+ ጥቂት ማር፣ ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫ፣ ከርቤ፣+ ለውዝና አልሞንድ ለሰውየው ስጦታ+ እንዲሆን በከረጢቶቻችሁ ይዛችሁ ውረዱ። +12 በተጨማሪም እጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ በከረጢቶቻችሁ አፍ ላይ ተደርጎ የተመለሰላችሁንም ገንዘብ ይዛችሁ ሂዱ።+ ምናልባት በስህተት የመጣ ሊሆን ይችላል። +13 በሉ ተነሱና ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደ ሰውየው ሂዱ። +14 ሌላውን ወንድማችሁንና ቢንያምን እንዲለቅላችሁ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ የሰውየውን ልብ ያራራላችሁ። እንግዲህ ልጆቼን አጥቼ ለሐዘን ከተዳረግኩም ምን አደርጋለሁ፤ የመጣውን እቀበላለሁ!”+ +15 ስለዚህ ሰዎቹ ይህን ስጦታና እጥፍ ገንዘብ እንዲሁም ቢንያምን ይዘው ተነሱ። ወደ ግብፅም ወረዱ፤ እንደገናም ዮሴፍ ፊት ቀረቡ።+ +16 ዮሴፍ ቢንያምን ከእነሱ ጋር ሲያየው የቤቱ ኃላፊ የሆነውን ሰው ወዲያውኑ እንዲህ አለው፦ “ሰዎቹን ወደ ቤት ውሰዳቸው፤ አብረውኝ ምሳ ስለሚበሉ እንስሳ አርደህ ምግብ አዘጋጅ።” +17 ሰውየውም ወዲያውኑ ልክ ዮሴፍ እንዳለው አደረገ፤+ ሰዎቹንም ወደ ዮሴፍ ቤት ወሰዳቸው። +18 ሰዎቹ ግን ወደ ዮሴፍ ቤት ሲወሰዱ ፈሩ፤ እንዲህም ይሉ ጀመር፦ “ወደዚህ ያመጡን ባለፈው ጊዜ በከረጢቶቻችን ውስጥ በተመለሰው ገንዘብ የተነሳ ነው። በቃ አሁን ያሠቃዩናል፤ ባሪያ ያደርጉናል፤ አህዮቻችንንም ይቀሙናል!”+ +19 በመሆኑም የዮሴፍ ቤት ኃላፊ ወደሆነው ሰው ቀርበው በቤቱ በራፍ ላይ አነጋገሩት። +20 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ይቅርታ ጌታዬ! እኛ ባለፈው ጊዜ ወደዚህ የመጣነው እህል ለመግዛት ነበር።+ +21 ሆኖም የምናርፍበት ቦታ ደርሰን ከረጢቶቻችንን ስንከፍት የእያንዳንዳችንን ገንዘብ ምንም ሳይጎድል በየከረጢታችን አፍ ላይ አገኘነው።+ ስለዚህ ራሳችን ገንዘቡን መመለስ እንፈልጋለን። +22 እህል ለመግዛት ተጨማሪ ገንዘብ ይዘናል። ገንዘባችንን በከረጢታችን ውስጥ መልሶ ያስቀመጠው ማን እንደሆነ አናውቅም።”+ +23 እሱም “አይዟችሁ፣ አትፍሩ። ይህን ገንዘብ በከረጢቶቻችሁ ውስጥ ያስቀመጠላችሁ የእናንተ አምላክና የአባታችሁ አምላክ ነው። እኔ እንደሆነ ገንዘባችሁ ደርሶኛል” አላቸው። ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ ወደ እነሱ አመጣው።+ +24 ከዚያም ሰውየው ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባቸው፤ እግራቸውን እንዲታጠቡም ውኃ አቀረበላቸው፤ እንዲሁም ለአህዮቻቸው ገፈራ ሰጣቸው። +25 እነሱም እዚያው ምሳ እንደሚበሉ+ ስለሰሙ ዮሴፍ ቀትር ላይ ሲመጣ የሚሰጡትን ስጦታ+ ማዘገጃጀት ጀመሩ። +26 ዮሴፍ ወደ ቤት ሲገባ፣ ያዘጋጁትን ስጦታ ይዘው ወደ እሱ በመግባት አበረከቱለት፤ መሬት ላይም ተደፍተው ሰገዱለት።+ +27 ከዚያም ስለ ደህንነታቸው ጠየቃቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ “ባለፈው ጊዜ የነገራችሁኝ አረጋዊ አባታችሁ ደህና ነው? አሁንም በሕይወት አለ?”+ +28 እነሱም “አገልጋይህ አባታችን ደህና ነው። አሁንም በሕይወት አለ” አሉት። ከዚያም መሬት ላይ ተደፍተው ሰገዱ።+ +29 ዮሴፍም ቀና ብሎ ሲመለከት የእናቱን ልጅ ወንድሙን+ ቢንያምን አየ፤ እሱም “ባለፈው ጊዜ ስለ እሱ የነገራችሁኝ ትንሹ ወንድማችሁ ይሄ ነው?” አላቸው።+ ቢንያምንም “የእኔ ልጅ፣ አምላክ ሞገሱን ያሳይህ” አለው። +30 ዮሴፍ ወንድሙን ሲያይ ስሜቱን መቆጣጠር ስላቃተው በፍጥነት ወጣ፤ የሚያለቅስበትንም ቦታ ፈለገ። ብቻውን ወደ አንድ ክፍል ገብቶም አለቀሰ።+ +31 ከዚያም ፊቱን ተጣጥቦ ወጣ፤ እንደ ምንም ስሜቱን ተቆጣጥሮም “ምግብ ይቅረብ” አለ። +32 እነሱም ለዮሴፍ ለብቻው አቀረቡለት፤ ለእነሱም ለብቻቸው አቀረቡላቸው። እንዲሁም በቤቱ ለሚበሉት ግብፃውያን ለብቻቸው አቀረቡላቸው። ይህን ያደረጉት ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብረው ምግብ ስለማይበሉ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ለግብፃውያን አስጸያፊ ነገር ነው።+ +33 ወንድማማቾቹም* የበኩሩ እንደ ብኩርና መብቱ፣+ ታናሹም እንደ ታናሽነቱ በፊቱ ተቀመጡ፤ እርስ በርሳቸውም በመገረም ይተያዩ ነበር። +34 እሱም ፊቱ ከቀረበው ምግብ እየተነሳ ለእነሱ እንዲሰጣቸው ያደርግ ነበር፤ የቢንያም ድርሻ ግን ከሌሎቹ አምስት እጥፍ እንዲበልጥ ያደርግ ነበር።+ እነሱም እስኪጠግቡ ድረስ አብረውት በሉ፣ ጠጡም። +9 አምላክም ኖኅንና ወንዶች ልጆቹን ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት።+ +2 አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በምድር ላይ ባለ በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር፣ በሰማያት ላይ በሚበር በእያንዳንዱ ፍጡር እንዲሁም በመሬት ላይ በሚንቀሳቀስ ማንኛውም ፍጡርና በባሕር ውስጥ ባለ ዓሣ ሁሉ ላይ ይሁን። ይኸው ሁሉም በእጃችሁ ውስጥ* እንዲሆኑ ተሰጥተዋል።+ +3 በሕይወት የሚንቀሳቀስ እያንዳንዱ እንስሳ ምግብ ይሁናችሁ።+ የለመለመውን ተክል እንደሰጠኋችሁ ሁሉ እነዚህን በሙሉ ሰጥቻችኋለሁ።+ +4 ሕይወቱ* ማለትም ደሙ+ በውስጡ ያለበትን ሥጋ ብቻ አትብሉ።+ +5 ከዚህም በተጨማሪ ሕይወታችሁ የሆነውን ደማችሁን* የሚያፈሰውን ሁሉ ተጠያቂ አደርገዋለሁ። እያንዳንዱን ሕያው ፍጡር ተጠያቂ አደርገዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው ለወንድሙ ሕይወት ተጠያቂ አደርገዋለሁ።+ +6 አምላክ ሰውን በአምሳሉ ስለሠራው+ የሰውን ደም የሚያፈስ ማንም ሰው የእሱም ደም በሰው እጅ ይፈስሳል።+ +7 እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፤ ቁጥራችሁም በምድር ላይ እጅግ ይጨምር፤ ደግሞም ተባዙ።”+ +8 አምላክም ኖኅንና ከእሱ ጋር ያሉትን ወንዶች ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ +9 “እኔም አሁን፣ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጡት ዘሮቻችሁ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለ���፤+ +10 እንዲሁም ከእናንተ ጋር ካለው ከእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር* ማለትም ከወፎች፣ ከእንስሳት፣ አብረዋችሁ በምድር ላይ ከሚኖሩት ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ እንዲሁም ከመርከቡ ከወጡት ሁሉ ጋር ይኸውም በምድር ላይ ከሚገኝ ከእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ።+ +11 አዎ፣ ከእንግዲህ ሥጋ* ሁሉ በጥፋት ውኃ እንደማይጠፋ እንዲሁም የጥፋት ውኃ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን ፈጽሞ እንደማያጠፋት ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ።”+ +12 በተጨማሪም አምላክ እንዲህ አለ፦ “በእኔና በእናንተ እንዲሁም ከእናንተ ጋር ባለው በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር* መካከል ለመሠረትኩት ቃል ኪዳን ምልክቱ ይህ ነው፤ ይህም ቃል ኪዳን በመጪዎቹ ትውልዶች ሁሉ ጸንቶ ይኖራል። +13 ቀስተ ደመናዬን በደመናው ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት ሆኖ ያገለግላል። +14 ምድርን በደመና በጋረድኩ ጊዜ ሁሉ ቀስተ ደመናው በደመናው ላይ ይታያል። +15 እኔም ከእናንተ እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር* ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሥጋን ሁሉ ለማጥፋት የጥፋት ውኃ ፈጽሞ አይወርድም።+ +16 ቀስተ ደመናው በደመናው ላይ ይታያል፤ እኔም እሱን በማይበት ጊዜ በአምላክና በምድር ላይ በሚኖር በማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር* መካከል ያለውን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።” +17 አምላክም “በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ሁሉ መካከል ለመሠረትኩት ቃል ኪዳን ምልክቱ ይህ ነው”+ በማለት ለኖኅ በድጋሚ ነገረው። +18 ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ወንዶች ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ናቸው።+ ከጊዜ በኋላ ካም፣ ከነአንን ወለደ።+ +19 የኖኅ ወንዶች ልጆች እነዚህ ሦስቱ ነበሩ፤ የምድር ሕዝብ ሁሉ የተገኘው ከእነሱ ሲሆን በኋላም ወደተለያየ አካባቢ ተሰራጨ።+ +20 ኖኅም ገበሬ ሆነ፤ የወይን እርሻም አለማ። +21 አንድ ቀን ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ራቁቱን ሆነ። +22 የከነአን አባት ካምም የአባቱን እርቃን አየ፤ ውጭ ላሉት ሁለት ወንድሞቹም ነገራቸው። +23 ስለዚህ ሴምና ያፌት ልብስ ወስደው ትከሻቸው ላይ በማድረግ የኋሊት እየተራመዱ ገቡ። በዚህ መንገድም ፊታቸውን ወደ አባታቸው ሳያዞሩ እርቃኑን ሸፈኑ፤ በመሆኑም የአባታቸውን እርቃን አላዩም። +24 ኖኅ ከወይን ጠጅ ስካሩ ሲነቃ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ፤ +25 እንዲህም አለ፦ “ከነአን የተረገመ ይሁን።+ ለወንድሞቹም የባሪያ ባሪያ ይሁን።”+ +26 በተጨማሪም እንዲህ አለ፦ “የሴም አምላክ ይሖዋ ይወደስ፤ከነአንም የእሱ ባሪያ ይሁን።+ +27 አምላክ ለያፌት ሰፊ መሬት ይስጠው፤በሴም ድንኳኖች ውስጥም ይኑር። ከነአን ለእሱም ጭምር ባሪያ ይሁን።” +28 ኖኅ ከጥፋት ውኃው በኋላ 350 ዓመት ኖረ።+ +29 በመሆኑም ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። +27 ይስሐቅ ባረጀና ዓይኖቹ ደክመው ማየት በተሳናቸው ጊዜ ታላቁን ልጁን ኤሳውን ወደ እሱ ጠርቶ+ “ልጄ ሆይ!” አለው። እሱም “አቤት!” አለው። +2 ይስሐቅም እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አሁን አርጅቻለሁ። የምሞትበትንም ቀን አላውቅም። +3 ስለሆነም አሁን መሣሪያዎችህን፣ የቀስት ኮሮጆህንና ደጋንህን ይዘህ ወደ ዱር ሂድ፤ አድነህም አምጣልኝ።+ +4 እኔ የምወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ ሠርተህ አቅርብልኝ። ከመሞቴም በፊት እንድባርክህ* ልብላው።” +5 ይሁን እንጂ ይስሐቅ፣ ልጁን ኤሳውን ሲያነጋግረው ርብቃ ታዳምጥ ነበር። ኤሳው አደን አድኖ ለማምጣት ወደ ዱር ወጣ።+ +6 ርብቃም ልጇን ያዕቆብን እንዲህ አለችው፦+ “አባትህ ወንድምህን ኤሳውን እንዲህ ሲለው ሰምቻለሁ፦ +7 ‘እስቲ አደን አድነህ አምጣልኝና ጣ���ጭ ምግብ ሥራልኝ። እኔም ሳልሞት በይሖዋ ፊት እንድባርክህ ልብላ።’+ +8 እንግዲህ ልጄ፣ አሁን የምልህን በጥሞና አዳምጥ፤ የማዝህንም አድርግ።+ +9 አባትህ የሚወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ እንዳዘጋጅለት እባክህ ወደ መንጋው ሂድና ፍርጥም ያሉ ሁለት የፍየል ጠቦቶች አምጣልኝ። +10 ከዚያም ከመሞቱ በፊት እንዲባርክህ ምግቡን ለአባትህ ታቀርብለትና ይበላል።” +11 ያዕቆብ እናቱን ርብቃን እንዲህ አላት፦ “ወንድሜ ኤሳው ሰውነቱ ፀጉራም ነው፤+ የእኔ ሰውነት ግን ለስላሳ ነው። +12 አባቴ ቢዳብሰኝስ?+ በእሱ ላይ እያሾፍኩበት ያለሁ ሊመስል ይችላል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ በረከት ሳይሆን እርግማን አተርፋለሁ።” +13 በዚህ ጊዜ እናቱ “ልጄ፣ ለአንተ የታሰበው እርግማን ለእኔ ይሁን። ብቻ እኔ የምልህን አድርግ፤ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው።+ +14 ስለዚህ ሄዶ ጠቦቶቹን አመጣ፤ ለእናቱም ሰጣት፤ እናቱም አባቱ የሚወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ ሠራች። +15 ከዚያም ርብቃ ቤት ውስጥ ያስቀመጠችውን የታላቁን ልጇን የኤሳውን ምርጥ ልብስ ወስዳ ታናሹን ልጇን ያዕቆብን አለበሰችው።+ +16 በተጨማሪም የፍየል ጠቦቶቹን ቆዳ በእጆቹና ፀጉር በሌለው የአንገቱ ክፍል ላይ አደረገች።+ +17 ከዚያም የሠራችውን ጣፋጭ ምግብና ዳቦ ለልጇ ለያዕቆብ ሰጠችው።+ +18 እሱም ወደ አባቱ ገብቶ “አባቴ ሆይ!” አለው። እሱም መልሶ “አቤት! ለመሆኑ አንተ ማነህ ልጄ?” አለው። +19 ያዕቆብም አባቱን “እኔ የበኩር ልጅህ+ ኤሳው ነኝ። ልክ እንዳልከኝ አድርጌአለሁ። እንድትባርከኝ* እባክህ ቀና ብለህ ተቀመጥና አድኜ ካመጣሁት ብላ”+ አለው። +20 በዚህ ጊዜ ይስሐቅ ልጁን “እንዴት እንዲህ ቶሎ ቀናህ ልጄ?” አለው። እሱም መልሶ “አምላክህ ይሖዋ አምጥቶ እጄ ላይ ስለጣለልኝ ነው” አለው። +21 ከዚያም ይስሐቅ ያዕቆብን “ልጄ ሆይ፣ አንተ በእርግጥ ልጄ ኤሳው መሆንህን እንዳውቅ እስቲ ቀረብ በልና ልዳብስህ” አለው።+ +22 በመሆኑም ያዕቆብ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ቀረበ። እሱም ዳበሰውና “ድምፁ የያዕቆብ ድምፅ ነው፤ እጆቹ ግን የኤሳው እጆች ናቸው”+ አለ። +23 እጆቹ እንደ ወንድሙ እንደ ኤሳው እጆች ፀጉራም ስለነበሩ ማንነቱን አልለየውም። ስለዚህ ባረከው።+ +24 ከዚያም “በእርግጥ አንተ ልጄ ኤሳው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም “አዎ፣ ነኝ” አለው። +25 በመቀጠልም “በል እንግዲህ ልጄ፣ አድነህ ያመጣህልኝን እንድበላ አቅርብልኝ፤ ከዚያም እባርክሃለሁ”* አለው። እሱም አቀረበለትና በላ፤ እንዲሁም የወይን ጠጅ አመጣለትና ጠጣ። +26 ከዚያም አባቱ ይስሐቅ “ልጄ፣ እስቲ ቀረብ በልና ሳመኝ”+ አለው። +27 ስለዚህ ወደ እሱ ቀረበና ሳመው፤ ይስሐቅም የልጁን ልብስ ጠረን አሸተተ።+ ከዚያም ባረከው፤ እንዲህም አለው፦ “አቤት፣ የልጄ ጠረን ይሖዋ እንደባረከው መስክ መዓዛ ነው። +28 እውነተኛው አምላክ የሰማያትን ጠል፣+ የምድርን ለም አፈር+ እንዲሁም የተትረፈረፈ እህልና አዲስ የወይን ጠጅ ይስጥህ።+ +29 ሕዝቦች ያገልግሉህ፤ ብሔራትም ይስገዱልህ። የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ወንዶች ልጆች ይስገዱልህ።+ የሚረግሙህ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህም ሁሉ የተባረኩ ይሁኑ።”+ +30 ይስሐቅ ያዕቆብን ባርኮ እንዳበቃና ያዕቆብ ከአባቱ ከይስሐቅ ፊት እግሩ እንደወጣ ወንድሙ ኤሳው ከአደን ተመለሰ።+ +31 እሱም ደግሞ ጣፋጭ ምግብ አዘጋጅቶ ለአባቱ አቀረበለት፤ አባቱንም “እስቲ እንድትባርከኝ* አባቴ ይነሳና ልጁ አድኖ ካመጣለት ይብላ” አለው። +32 በዚህ ጊዜ አባቱ ይስሐቅ “አንተ ደግሞ ማን ነህ?” አለው። እሱም መልሶ “ልጅህ ነኛ! የበኩር ልጅህ ኤሳው”+ አለው። +33 ይስሐቅም በኃይል እየተንቀጠቀጠ “አደን አድኖ ያመጣልኝና ያቀረበልኝ ታዲያ ማን ነበር? እኔ እኮ አንተ ከመምጣትህ በፊት በላሁ፤ እንዲሁም ባረክሁት፤ ደግሞም የተባረከ ይሆናል!” አለው። +34 ኤሳው አባቱ የተናገረውን ሲሰማ ከፍ ባለ ድምፅ ምርር ብሎ እያለቀሰ አባቱን “አባቴ ባርከኝ፤ እኔንም ባርከኝ እንጂ!” አለው።+ +35 ይስሐቅ ግን “ወንድምህ ለአንተ የታሰበውን በረከት ለማግኘት አንድ ተንኮል ሠርቷል” አለው። +36 ኤሳውም እንዲህ አለ፦ “ስሙ ያዕቆብ* የተባለው መቼ ያለምክንያት ሆነ! የኔ የሆነውን ሲወስድብኝ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው።+ የብኩርና መብቴን መውሰዱ+ ሳያንሰው አሁን ደግሞ በረከቴን ቀማኝ!”+ ከዚያም “ለእኔ ምንም በረከት አላስቀረህልኝም?” አለው። +37 ይስሐቅ ግን ኤሳውን እንዲህ አለው፦ “በአንተ ላይ ጌታ አድርጌ ሾሜዋለሁ፤+ እንዲሁም ወንድሞቹን ሁሉ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ ሰጥቼዋለሁ። እህልና አዲስ የወይን ጠጅ እንዲበዛለት ባርኬዋለሁ፤+ ታዲያ ለአንተ ላደርግልህ የምችለው ምን የቀረ ነገር አለ ልጄ?” +38 ኤሳውም አባቱን “አባቴ ሆይ፣ ለእኔ የምትሆን አንዲት በረከት እንኳ የለችህም? አባቴ ባርከኝ። እኔንም ባርከኝ እንጂ!” አለው። ኤሳውም ከፍ ባለ ድምፅ ምርር ብሎ አለቀሰ።+ +39 ስለዚህ አባቱ ይስሐቅ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ መኖሪያህ ለም ከሆነው የምድር አፈር እንዲሁም በላይ ካሉት ሰማያት ጠል የራቀ ይሆናል።+ +40 በሰይፍህ ትኖራለህ፤+ ወንድምህንም ታገለግላለህ።+ ይሁንና እየተቅበጠበጥክ ባስቸገርክ ጊዜ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ ሰብረህ ትጥላለህ።”+ +41 ይሁን እንጂ ኤሳው አባቱ ያዕቆብን ስለባረከው ለያዕቆብ ከፍተኛ ጥላቻ አደረበት።+ ኤሳውም በልቡ “ለአባቴ ሐዘን የምንቀመጥበት ቀን ሩቅ አይደለም።+ ከዚያ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ” ይል ነበር። +42 ርብቃ ታላቁ ልጇ ኤሳው ያለው ነገር ሲነገራት ወዲያውኑ ለታናሹ ልጇ ለያዕቆብ እንዲህ የሚል መልእክት ላከችበት፦ “ወንድምህ ኤሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ እያሰበ ነው።* +43 እንግዲህ ልጄ እኔ የምልህን አድርግ። ተነስተህ በካራን ወደሚገኘው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ።+ +44 የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ እሱ ጋ ተቀመጥ፤ +45 ወንድምህ ንዴቱ እስኪበርድለትና ያደረግክበትን እስኪረሳ ድረስ እዚያ ቆይ። እኔም እልክብህና አስጠራሃለሁ። ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ለምን ልጣ?” +46 ከዚያ በኋላ ርብቃ ይስሐቅን እንዲህ ትለው ጀመር፦ “በሄት ሴቶች ልጆች የተነሳ ሕይወቴን ጠልቻለሁ።+ ያዕቆብም በዚህ አገር የሚገኙትን እንደነዚህ ያሉትን የሄት ሴቶች ልጆች የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምን ያደርግልኛል?”+ +47 ስለዚህ ዮሴፍ ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ እንዲሁም መንጎቻቸው፣ ከብቶቻቸውና የእነሱ የሆነው ሁሉ ከከነአን ምድር መጥተዋል፤ በጎሸን ምድር ይገኛሉ”+ አለው።+ +2 እሱም ከወንድሞቹ መካከል አምስቱን ወስዶ ፈርዖን ፊት አቀረባቸው።+ +3 ፈርዖንም የዮሴፍን ወንድሞች “ሥራችሁ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነሱም “እኛ አገልጋዮችህም ሆን የቀድሞ አባቶቻችን በግ አርቢዎች ነን” በማለት መለሱለት።+ +4 ከዚያም ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “ወደዚህ የመጣነው በምድሪቱ ላይ እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነን ለመኖር ነው፤+ ምክንያቱም በከነአን ምድር ረሃቡ በጣም ስለበረታ ለአገልጋዮችህ መንጋ የሚሆን የግጦሽ ቦታ የለም።+ ስለሆነም እባክህ አገልጋዮችህ በጎሸን ምድር እንዲኖሩ ፍቀድላቸው።”+ +5 በዚህ ጊዜ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “አባትህና ወንድሞችህ ወደ አንተ መጥተዋል። +6 የግብፅ ምድር እንደሆነ በእጅህ ነው። አባትህና ወንድሞችህ ምርጥ በሆነው የምድሪቱ ክፍል እንዲኖሩ አድርግ።+ በጎሸን ምድር ይኑሩ፤ ከእነሱ መካከል ጥሩ ችሎታ እንዳላቸው የምታውቃቸው ሰዎች ካሉ በከብቶቼ ላይ ኃላፊ አድርገህ ሹማቸው።” +7 ከዚያም ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን አስገብቶ ፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው። +8 ፈርዖንም ያዕቆብን “ለመሆኑ ዕድሜህ ስንት ነው?” ሲል ጠየቀው። +9 ያዕቆብም ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “ከቦታ ወደ ቦታ በመንከራተት* ያሳለፍኩት ዘመን 130 ዓመት ነው። የሕይወት ዘመኔ አጭርና ጭንቀት የበዛበት ነበር፤+ ደግሞም አባቶቼ ከቦታ ወደ ቦታ በመንከራተት* ያሳለፉትን ዘመን አያክልም።”+ +10 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ፈርዖንን መረቀው፤ ከፊቱም ወጥቶ ሄደ። +11 በመሆኑም ዮሴፍ፣ አባቱና ወንድሞቹ እንዲሰፍሩ አደረገ፤ ፈርዖንም ባዘዘው መሠረት ምርጥ ከሆነው የግብፅ ምድር፣ የራምሴስን ምድር ርስት አድርጎ ሰጣቸው።+ +12 ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተሰብ በትናንሽ ልጆቻቸው ቁጥር ልክ ቀለብ ይሰፍርላቸው ነበር። +13 በዚህ ወቅት ረሃቡ እጅግ በርትቶ ስለነበር በመላው ምድር እህል አልነበረም፤ የግብፅም ምድር ሆነ የከነአን ምድር በረሃቡ የተነሳ በጣም ተጎድተው ነበር።+ +14 ዮሴፍም ሰዎች እህል ሲገዙ የከፈሉትን በግብፅ ምድርና በከነአን ምድር የሚገኘውን ገንዘብ በሙሉ እየሰበሰበ ወደ ፈርዖን ቤት ያስገባ ነበር።+ +15 ከጊዜ በኋላ በግብፅ ምድርና በከነአን ምድር ያለው ገንዘብ አለቀ፤ ግብፃውያንም በሙሉ ወደ ዮሴፍ በመምጣት “እህል ስጠን! ገንዘብ ስለጨረስን ብቻ እንዴት ዓይንህ እያየ እንለቅ?” ይሉት ጀመር። +16 ዮሴፍም “ገንዘባችሁ ካለቀ ከብቶቻችሁን አምጡ፤ እኔም በከብቶቻችሁ ምትክ እህል እሰጣችኋለሁ” አላቸው። +17 በመሆኑም ከብቶቻቸውን ወደ ዮሴፍ ያመጡ ጀመር፤ ዮሴፍም በፈረሶቻቸው፣ በመንጎቻቸው፣ በከብቶቻቸውና በአህዮቻቸው ምትክ እህል ይሰጣቸው ነበር፤ በዚያም ዓመት በከብቶቻቸው ሁሉ ምትክ እህል ሲሰጣቸው ከረመ። +18 ያም ዓመት ካለቀ በኋላ በቀጣዩ ዓመት ሕዝቡ ወደ እሱ በመምጣት እንዲህ ይለው ጀመር፦ “ከጌታዬ የምንደብቀው ምንም ነገር የለም፤ ገንዘባችንንም ሆነ ከብቶቻችንን ለጌታዬ አስረክበናል። ከእኛ ከራሳችንና ከመሬታችን በስተቀር በጌታዬ ፊት ምንም የቀረን ነገር የለም። +19 ዓይንህ እያየ ለምን እንለቅ? መሬታችንስ ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንም ሆነ መሬታችንን በእህል ግዛን፤ እኛ ለፈርዖን ባሪያዎች እንሁን፤ መሬታችንም የእሱ ይሁን። በሕይወት እንድንኖርና እንዳንሞት እንዲሁም መሬታችን ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው እህል ስጠን።” +20 በመሆኑም ዮሴፍ የግብፃውያንን መሬት በሙሉ ለፈርዖን ገዛለት፤ ምክንያቱም ረሃቡ እጅግ ስለበረታባቸው ሁሉም ግብፃውያን መሬታቸውን ሸጠው ነበር፤ ስለዚህ ምድሪቱ የፈርዖን ሆነች። +21 ዮሴፍም በግብፅ ምድር ከዳር እስከ ዳር ያለው ሕዝብ ወደ ከተሞች እንዲገባ አደረገ።+ +22 ዮሴፍ ያልገዛው የካህናቱን መሬት ብቻ ነበር፤ ምክንያቱም ፈርዖን ለካህናቱ ቀለብ ይሰፍርላቸው ነበር፤+ እነሱም የሚኖሩት ፈርዖን በሚሰፍርላቸው ቀለብ ነበር። መሬታቸውን ያልሸጡትም ለዚህ ነው። +23 ከዚያም ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “ይኸው ዛሬ እናንተንም ሆነ መሬታችሁን ለፈርዖን ገዝቻለሁ። ዘር ይኸውላችሁ፤ እናንተም በመሬቱ ላይ ዝሩ። +24 ባፈራም ጊዜ አንድ አምስተኛውን ለፈርዖን ስጡ፤+ አራቱ እጅ ግን ለመሬታችሁ ዘር እንዲሁም ለራሳችሁ፣ በቤታችሁ ላሉትና ለልጆቻችሁ ምግብ እንዲሆናችሁ የእናንተ ይሆናል።” +25 እነሱም “አንተ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤+ በጌታዬ ፊት ሞገስ እናግኝ እንጂ እኛ ለፈርዖን ባሪያዎች እንሆናለን” አሉት።+ +26 ��ዚያም ዮሴፍ አንድ አምስተኛው ለፈርዖን እንዲሰጥ የሚያዝ ሕግ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ድረስ በግብፅ ምድር ይሠራበታል። የፈርዖን ያልሆነው የካህናቱ መሬት ብቻ ነበር።+ +27 እስራኤላውያንም በግብፅ አገር፣ በጎሸን ምድር መኖራቸውን ቀጠሉ።+ በዚያም ተደላድለው ይኖሩ ጀመር፤ ፍሬያማም ሆኑ፤ ቁጥራቸውም እጅግ እየበዛ ሄደ።+ +28 ያዕቆብም በግብፅ ምድር ለ17 ዓመት ኖረ፤ በመሆኑም ያዕቆብ በሕይወት የኖረበት ዘመን 147 ዓመት ሆነ።+ +29 እስራኤልም የሚሞትበት ቀን ሲቃረብ+ ልጁን ዮሴፍን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፤ ለእኔም ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት አሳየኝ። እባክህ በግብፅ አትቅበረኝ።+ +30 በምሞትበት* ጊዜ ከግብፅ አውጥተህ በአባቶቼ መቃብር ቅበረኝ።”+ እሱም “እሺ፣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለው። +31 ያዕቆብም “በል ማልልኝ” አለው፤ እሱም ማለለት።+ በዚህ ጊዜ እስራኤል በአልጋው ራስጌ ላይ ሰገደ።+ +50 ከዚያም ዮሴፍ አባቱ ላይ ተደፍቶ አለቀሰ፤+ አባቱንም ሳመው። +2 በኋላም ዮሴፍ መድኃኒት ቀማሚ የሆኑ አገልጋዮቹን የአባቱን አስከሬን መድኃኒት እንዲቀቡ+ አዘዛቸው። መድኃኒት ቀማሚዎቹም እስራኤልን መድኃኒት ቀቡት፤ +3 ይህም 40 ቀን ሙሉ ፈጀባቸው፤ ምክንያቱም አስከሬን መድኃኒት መቀባት ይህን ያህል ጊዜ ይወስድ ነበር፤ ግብፃውያንም 70 ቀን አለቀሱለት። +4 የሐዘኑም ጊዜ ሲያበቃ ዮሴፍ የፈርዖንን ቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት* እንዲህ አላቸው፦ “በፊታችሁ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባካችሁ ለፈርዖን ይህን መልእክት ንገሩልኝ፦ +5 ‘አባቴ “እንግዲህ እኔ የምሞትበት ጊዜ ቀርቧል።+ በመሆኑም በከነአን ምድር ባዘጋጀሁት+ የመቃብር ስፍራ ቅበረኝ”+ ሲል አስምሎኛል።+ ስለዚህ እባክህ ልውጣና አባቴን ልቅበር፤ ከዚያም እመለሳለሁ።’” +6 ፈርዖንም “እንግዲህ ባስማለህ መሠረት+ ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው። +7 በመሆኑም ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ወጣ፤ ከእሱም ጋር የፈርዖን አገልጋዮች በሙሉ ሄዱ፤ በቤተ መንግሥቱም ያሉ ሽማግሌዎች፣+ በግብፅ ምድር የሚገኙ ሽማግሌዎች በሙሉ፣ +8 በዮሴፍ ቤት ያሉ ሁሉ፣ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰቦች ሄዱ።+ በጎሸን ምድር የቀሩት ትናንሽ ልጆቻቸው፣ መንጎቻቸውና ከብቶቻቸው ብቻ ነበሩ። +9 ሠረገሎችና+ ፈረሰኞችም አብረውት ወጡ፤ ያጀበውም ሰው እጅግ ብዙ ነበር። +10 ከዚያም በዮርዳኖስ ክልል ወደሚገኘው አጣድ የተባለ አውድማ ደረሱ፤ በዚያም እየጮኹ ምርር ብለው አለቀሱ፤ እሱም ለአባቱ ሰባት ቀን ለቅሶ ተቀመጠ። +11 በዚያ የሚኖሩ ከነአናውያንም ሰዎቹ በአጣድ አውድማ ሲያለቅሱ ሲመለከቱ “መቼም ይህ ለግብፃውያን ከባድ ሐዘን መሆን አለበት!” አሉ። በዮርዳኖስ ክልል የሚገኘው የዚህ ስፍራ ስም አቤልምጽራይም* የተባለው በዚህ የተነሳ ነው። +12 በመሆኑም ልጆቹ ልክ በሰጣቸው መመሪያ መሠረት አደረጉለት።+ +13 ወንዶች ልጆቹም ወደ ከነአን ምድር ወስደው አብርሃም ለመቃብር ቦታ ብሎ ከሂታዊው ከኤፍሮን በገዛው ከማምሬ ፊት ለፊት በሚገኘው እርሻ ማለትም በማክፈላ እርሻ ውስጥ ባለው ዋሻ ቀበሩት።+ +14 ዮሴፍም አባቱን ከቀበረ በኋላ ከወንድሞቹና ለአባቱ ቀብር አብረውት ከሄዱት ሁሉ ጋር ወደ ግብፅ ተመለሰ። +15 የዮሴፍ ወንድሞች አባታቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ “ምናልባት እኮ ዮሴፍ በፈጸምንበት በደል የተነሳ ቂም ይዞ ይበቀለን ይሆናል” አሉ።+ +16 ስለዚህ ለዮሴፍ እንዲህ የሚል መልእክት ላኩበት፦ “አባትህ ከመሞቱ በፊት እንዲህ የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር፦ +17 ‘ዮሴፍን እንዲህ በሉት፦ “የወንድሞችህን በደል እንዲሁም በአንተ ላይ እንዲህ ያለ ጉዳት በማድረስ የ��ሩትን ኃጢአት ይቅር እንድትል እማጸንሃለሁ።”’ እናም እባክህ የአባትህን አምላክ አገልጋዮች በደል ይቅር በል።” ዮሴፍም እንዲህ ሲሉት አለቀሰ። +18 ከዚያም ወንድሞቹ መጡ፤ በፊቱም ተደፍተው በመስገድ “እኛ የአንተ ባሪያዎች ነን!” አሉት።+ +19 ዮሴፍም እንዲህ አላቸው፦ “አይዟችሁ አትፍሩ። ለመሆኑ እኔን በአምላክ ቦታ ያስቀመጠኝ ማን ነው? +20 ምንም እንኳ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ የነበረ ቢሆንም+ አምላክ ግን ይኸው ዛሬ እንደምታዩት ነገሩን ለመልካም አደረገው፤ የብዙ ሰዎችንም ሕይወት ለማዳን ተጠቀመበት።+ +21 ስለሆነም አትፍሩ። ለእናንተም ሆነ ለትናንሽ ልጆቻችሁ የሚያስፈልገውን እህል እሰጣችኋለሁ።”+ እሱም በዚህ መንገድ አጽናናቸው፤ እንዲሁም አረጋጋቸው። +22 ዮሴፍ ከአባቱ ቤተሰቦች ጋር በግብፅ መኖሩን ቀጠለ፤ ዮሴፍም 110 ዓመት ኖረ። +23 እሱም የኤፍሬምን ወንዶች ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ አየ፤+ እንዲሁም የምናሴን ልጅ የማኪርን ወንዶች ልጆች አየ።+ እነዚህ የተወለዱት በዮሴፍ ጭን ላይ ነበር።* +24 ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ የምሞትበት ጊዜ ቀርቧል፤ ይሁንና አምላክ ፊቱን ወደ እናንተ እንደሚመልስ የተረጋገጠ ነው፤+ ደግሞም ያለጥርጥር ከዚህ ምድር አውጥቶ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር ያስገባችኋል።”+ +25 በመሆኑም ዮሴፍ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች “አምላክ ፊቱን ወደ እናንተ እንደሚመልስ ጥርጥር የለውም። አደራ፣ በዚያን ጊዜ አፅሜን ከዚህ ይዛችሁ እንድትወጡ” በማለት አስማላቸው።+ +26 ዮሴፍም በ110 ዓመቱ ሞተ፤ እነሱም አስከሬኑን መድኃኒት ቀቡት፤+ ከዚያም በሬሳ ሣጥን ውስጥ አድርገው በግብፅ አስቀመጡት። +13 ከዚያም አብራም ሚስቱንና ያለውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከሎጥ ጋር በመሆን ከግብፅ ወጥቶ ወደ ኔጌብ ሄደ።+ +2 አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ እጅግ በልጽጎ ነበር።+ +3 እሱም ከኔጌብ ተነስቶ ወደ ቤቴል በሚጓዝበት ጊዜ ድንኳኑን ተክሎበት ወደነበረው በቤቴልና በጋይ+ መካከል ወደሚገኘው ስፍራ እስኪደርስ ድረስ በየቦታው ይሰፍር ነበር፤ +4 ይህም ቀደም ሲል መሠዊያ ሠርቶበት የነበረው ስፍራ ነው። በዚያም አብራም የይሖዋን ስም ጠራ። +5 ከአብራም ጋር ይጓዝ የነበረው ሎጥም በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት። +6 በመሆኑም ሁሉም አንድ ላይ ለመኖር ምድሪቱ አልበቃቻቸውም፤ ንብረታቸው በጣም እየበዛ ስለመጣ አብረው መኖር አልቻሉም። +7 በዚህም ምክንያት በአብራም እረኞችና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነሳ። (በወቅቱ ከነአናውያንና ፈሪዛውያን በምድሪቱ ይኖሩ ነበር።)+ +8 ስለዚህ አብራም ሎጥን+ እንዲህ አለው፦ “እባክህ በእኔና በአንተ እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ምንም ዓይነት ጠብ አይኑር፤ እኛ እኮ ወንድማማቾች ነን። +9 ምድሪቱ ሁሉ በእጅህ አይደለችም? እባክህ ከእኔ ተለይ። አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ ደግሞ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።” +10 ሎጥም ዓይኑን አቅንቶ መላውን የዮርዳኖስ አውራጃ እስከ ዞአር+ ድረስ ተመለከተ፤+ (ይሖዋ ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ በፊት) አካባቢው ልክ እንደ ይሖዋ የአትክልት ስፍራ፣+ ልክ እንደ ግብፅ ምድር ውኃ የጠገበ ነበር። +11 ከዚያም ሎጥ መላውን የዮርዳኖስ አውራጃ ለራሱ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ሄዶ ሰፈረ። በዚህ መንገድ አንዳቸው ከሌላው ተለዩ። +12 አብራም በከነአን ምድር ኖረ፤ ሎጥ ግን በአውራጃው በሚገኙ ከተሞች አቅራቢያ ኖረ።+ በመጨረሻም በሰዶም አቅራቢያ ድንኳን ተከለ። +13 የሰዶም ሰዎች በይሖዋ ፊት ከባድ ኃጢአት የሚፈጽሙ ክፉ ሰዎች ነበሩ።+ +14 ሎጥ ከአብራም ከተለየ በኋላ ይሖዋ አብራምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ካለህበት ቦታ ሆነህ ዓይንህን አቅንተህ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት፤ +15 ምክንያቱም የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘለቄታው ርስት አድርጌ እሰጣለሁ።+ +16 ዘርህን እንደ ምድር አፈር አበዛዋለሁ፤ ማንም ሰው የምድርን አፈር መቁጠር ከቻለ የአንተም ዘር ሊቆጠር ይችላል።+ +17 ተነሳ፣ ይህችን ምድር ልሰጥህ ስለሆነ በምድሪቱ ስፋትና ርዝመት ሂድ።” +18 በመሆኑም አብራም ሄደ፤ በድንኳን መኖሩንም ቀጠለ። ከጊዜ በኋላም በኬብሮን+ ወደሚገኙት የማምሬ+ ትላልቅ ዛፎች መጥቶ መኖር ጀመረ፤ በዚያም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ።+ +5 የአዳምን ታሪክ የያዘው መጽሐፍ ይህ ነው። አምላክ አዳምን በፈጠረበት ቀን፣ በአምላክ አምሳል ሠራው።+ +2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።+ በተፈጠሩበትም+ ቀን ባረካቸው፤ እንዲሁም ሰው* ብሎ ጠራቸው። +3 አዳም 130 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም እሱን የሚመስል ወንድ ልጅ በራሱ አምሳያ ወለደ፤ ስሙንም ሴት+ አለው። +4 አዳም ሴትን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +5 ስለዚህ አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ።+ +6 ሴት 105 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሄኖስን+ ወለደ። +7 ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +8 ስለዚህ ሴት በአጠቃላይ 912 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። +9 ሄኖስ 90 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ቃይናንን ወለደ። +10 ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +11 ስለዚህ ሄኖስ በአጠቃላይ 905 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። +12 ቃይናን 70 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም መላልኤልን+ ወለደ። +13 ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +14 ስለዚህ ቃይናን በአጠቃላይ 910 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። +15 መላልኤል 65 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ያሬድን+ ወለደ። +16 መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ 830 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +17 ስለዚህ መላልኤል በአጠቃላይ 895 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። +18 ያሬድ 162 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሄኖክን+ ወለደ። +19 ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +20 ስለዚህ ያሬድ በአጠቃላይ 962 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። +21 ሄኖክ 65 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ማቱሳላን+ ወለደ። +22 ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ ለ300 ዓመት ከእውነተኛው አምላክ* ጋር መሄዱን ቀጠለ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +23 ስለዚህ ሄኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ። +24 ሄኖክ ከእውነተኛው አምላክ ጋር መሄዱን ቀጠለ።+ አምላክ ስለወሰደውም ከዚያ በኋላ አልተገኘም።+ +25 ማቱሳላ 187 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ላሜህን+ ወለደ። +26 ማቱሳላም ላሜህን ከወለደ በኋላ 782 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +27 ስለዚህ ማቱሳላ በአጠቃላይ 969 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። +28 ላሜህ 182 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ወንድ ልጅ ወለደ። +29 እሱም “ይህ ልጅ፣ ይሖዋ በረገማት ምድር+ የተነሳ ከምንለፋው ልፋትና ከምንደክመው ድካም በማሳረፍ ያጽናናናል”* በማለት ስሙን ኖኅ*+ ብሎ ጠራው። +30 ላሜህም ኖኅን ከወለደ በኋላ 595 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። +31 ስለዚህ ላሜህ በአጠቃላይ 777 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። +32 ኖኅ 500 ዓመት ከሆነው በኋላ ሴምን፣+ ካምንና+ ያፌትን+ ወለደ። +21 ይሖዋ ልክ በተናገረው መሠረት ሣራን አሰባት፤ ይሖዋም ለሣራ ቃል የገባላትን አደረገላት።+ +2 በመሆኑም ሣራ ፀነሰች፤+ ለአብርሃምም አምላክ ቃል በገባለት በተወሰነው ጊዜ ላይ በስተርጅናው ወንድ ልጅ ወለደችለት።+ +3 አብርሃም ሣራ የወለደችለትን ልጅ ይስሐቅ ብሎ ጠራው።+ +4 አብርሃምም ልክ አምላክ ባዘዘው መሠረት ልጁ ይስሐቅ ስምንት ቀን ሲሆነው ገረዘው።+ +5 አብርሃም ልጁ ይስሐቅ ሲወለድ ዕድሜው 100 ዓመት ነበር። +6 ከዚያም ሣራ “አምላክ በደስታ እንድስቅ አድርጎኛል፤ ይህን የሰማም ሁሉ ከእኔ ጋር አብሮ ይስቃል”* አለች። +7 አክላም “ለመሆኑ ለአብርሃም ‘ሣራ ልጆች ታጠባለች’ ማን ብሎት ያውቃል? እኔ ግን ይኸው በስተርጅናው ወንድ ልጅ ወለድኩለት” አለች። +8 ልጁም አደገ፤ ጡትም ጣለ፤ አብርሃምም ይስሐቅ ጡት በጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣ አደረገ። +9 ሣራም ግብፃዊቷ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት ልጅ+ በይስሐቅ ላይ እንደሚያፌዝበት+ በተደጋጋሚ አስተዋለች። +10 ስለዚህ አብርሃምን “ይህችን ባሪያና ልጇን ከዚህ አባር፤ ምክንያቱም የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር ወራሽ አይሆንም!”+ አለችው። +11 አብርሃም ግን ሣራ ስለ ልጁ የተናገረችው ነገር በጣም ቅር አሰኘው።+ +12 ከዚያም አምላክ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “ሣራ ስለ ልጁና ስለ ባሪያህ እየነገረችህ ያለው ነገር ምንም ቅር አያሰኝህ። ዘርህ የሚጠራልህ በይስሐቅ በኩል ስለሆነ የምትልህን* ስማ።+ +13 የባሪያይቱም ልጅ+ ቢሆን ልጅህ ስለሆነ ከእሱ አንድ ብሔር እንዲገኝ አደርጋለሁ።”+ +14 ስለዚህ አብርሃም በማለዳ ተነሳ፤ ለአጋርም ምግብና የውኃ አቁማዳ ሰጣት። እነዚህንም በትከሻዋ አሸከማት፤ ከዚያም ከልጁ ጋር አሰናበታት።+ እሷም ሄደች፤ በቤርሳቤህ+ ምድረ በዳም ትንከራተት ጀመር። +15 በመጨረሻም በአቁማዳው ውስጥ የነበረው ውኃ አለቀ፤ እሷም ልጁን አንዱ ቁጥቋጦ ሥር ጣለችው። +16 ከዚያም “ልጁ ሲሞት ማየት አልፈልግም” ብላ የቀስት ውርወራ ያህል ርቃ ተቀመጠች። እሷም ትጮኽና ታለቅስ ጀመር። +17 በዚህ ጊዜ አምላክ የልጁን ድምፅ ሰማ፤+ የአምላክም መልአክ ከሰማይ አጋርን ጠርቶ እንዲህ አላት፦+ “አጋር፣ ምን ሆነሻል? ልጁ ካለበት ቦታ ሆኖ ሲያለቅስ አምላክ ስለሰማ አይዞሽ አትፍሪ። +18 ተነሽ፣ ልጁንም አንስተሽ በእጅሽ ያዢው፤ ምክንያቱም እኔ ታላቅ ብሔር አደርገዋለሁ።”+ +19 ከዚያም አምላክ ዓይኖቿን ከፈተላት፤ የውኃ ጉድጓድም ተመለከተች። ወደዚያም ሄዳ በአቁማዳው ውኃ ሞላች፤ ልጁንም አጠጣችው። +20 ልጁም እያደገ ሄደ፤ አምላክም ከልጁ+ ጋር ነበር። እሱም የሚኖረው በምድረ በዳ ነበር፤ ቀስተኛም ሆነ። +21 እሱም በፋራን ምድረ በዳ+ ኖረ፤ እናቱም ከግብፅ ምድር ሚስት አመጣችለት። +22 በዚያን ጊዜ አቢሜሌክ ከሠራዊቱ አዛዥ ከፊኮል ጋር ሆኖ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “በምታደርገው ነገር ሁሉ አምላክ ከአንተ ጋር ነው።+ +23 ስለዚህ እኔንም ሆነ ልጆቼንና ዘሮቼን እንደማትክድ እንዲሁም ለእኔም ሆነ ለምትኖርባት ምድር እኔ ያሳየሁህ ዓይነት ታማኝ ፍቅር እንደምታሳይ በአምላክ ስም ማልልኝ።”+ +24 አብርሃምም “እሺ፣ እምላለሁ” አለ። +25 ሆኖም አብርሃም የአቢሜሌክ አገልጋዮች በጉልበት ስለወሰዱት የውኃ ጉድጓድ ለአቢሜሌክ ቅሬታውን ገለጸለት።+ +26 አቢሜሌክም መልሶ “ይህን ያደረገው ማን እንደሆነ አላውቅም፤ አንተም ብትሆን ስለዚህ ጉዳይ አልነገርከኝም፤ ስለዚህ ነገር ያለዛሬ አልሰማሁም” አለው። +27 በዚህ ጊዜ አብርሃም በጎችንና ከብቶችን ወስዶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን ገቡ። +28 አብርሃም ሰባት እንስት በጎችን ከመንጋው ለይቶ ለብቻቸው እንዲሆኑ ባደረገ ጊዜ +29 አቢሜሌክ አብርሃምን “እነዚህን ሰባት እንስት በጎች ለብቻቸው የለየኸው ለምንድን ነው?” አለው። +30 እሱም “ይህን ጉድጓድ የቆፈርኩት እኔ ለመሆኔ ምሥክር እንዲሆን እነዚህን ሰባት እንስት በጎች ከእጄ ውሰድ” አለው። +31 የቦታውን ስም ��ርሳቤህ*+ ብሎ የጠራው በዚህ የተነሳ ነው፤ ምክንያቱም በዚያ ሁለቱ ተማምለዋል። +32 ስለዚህ በቤርሳቤህ ቃል ኪዳን ገቡ፤+ ከዚያም አቢሜሌክ ከሠራዊቱ አዛዥ ከፊኮል ጋር ሆኖ ወደ ፍልስጤማውያን+ ምድር ተመለሰ። +33 ከዚያም በኋላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከለ፤ በዚያም የዘላለማዊውን አምላክ+ የይሖዋን ስም ጠራ።+ +34 አብርሃምም በፍልስጤማውያን ምድር ረዘም ላለ ጊዜ* ኖረ።*+ +15 ከዚህ በኋላ የይሖዋ ቃል በራእይ ወደ አብራም መጥቶ “አብራም አትፍራ።+ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ።+ የምታገኘውም ሽልማት እጅግ ታላቅ ይሆናል”+ አለው። +2 አብራምም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ያለልጅ እንደቀረሁና ቤቴን የሚወርሰው የደማስቆ ሰው የሆነው ኤሊዔዘር+ እንደሆነ ታያለህ፤ ታዲያ ምን ትሰጠኛለህ?” +3 በተጨማሪም አብራም “እንግዲህ ዘር አልሰጠኸኝም፤+ ደግሞም ወራሼ የሚሆነው በቤቴ ያለው አገልጋይ* ነው” አለ። +4 ሆኖም እንዲህ የሚል የይሖዋ ቃል ወደ እሱ መጣ፦ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ከዚህ ይልቅ የገዛ ልጅህ* ወራሽህ ይሆናል።”+ +5 ወደ ውጭም ካወጣው በኋላ “እባክህ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስቲ መቁጠር ከቻልክ ከዋክብቱን ቁጠራቸው” አለው። ከዚያም “የአንተም ዘር እንዲሁ ይሆናል”+ አለው። +6 አብራምም በይሖዋ አመነ፤+ አምላክም ይህን ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት።+ +7 ደግሞም እንዲህ አለው፦ “ይህችን ምድር ርስት አድርጌ ልሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እኔ ይሖዋ ነኝ።”+ +8 አብራምም “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ይህችን ምድር ርስት አድርጌ እንደምወርስ እንዴት አውቃለሁ?” አለ። +9 እሱም መልሶ “አንዲት የሦስት ዓመት ጊደር፣ አንዲት የሦስት ዓመት ፍየል፣ አንድ የሦስት ዓመት አውራ በግ እንዲሁም አንድ ዋኖስና አንድ የርግብ ጫጩት ውሰድ” አለው። +10 እሱም እነዚህን እንስሳት ሁሉ ወስዶ ለሁለት ሰነጠቃቸው፤ ከዚያም አንዱን ግማሽ ከሌላኛው ግማሽ ትይዩ አድርጎ አስቀመጠ። ወፎቹን ግን አልሰነጠቃቸውም። +11 አሞሮችም በበድኖቹ ላይ መውረድ ጀመሩ፤ አብራም ግን ያባርራቸው ነበር። +12 ፀሐይ ልትጠልቅ ስትቃረብም አብራም ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ ታላቅና የሚያስፈራ ጨለማም ወረደበት። +13 አምላክም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ዘሮችህ በባዕድ አገር ባዕዳን ሆነው እንደሚኖሩ እንዲሁም በዚያ ያሉት ሰዎች ለ400 ዓመት በባርነት እንደሚገዟቸውና እንደሚያጎሳቁሏቸው በእርግጥ እወቅ።+ +14 ይሁንና በባርነት በሚገዛቸው ብሔር ላይ እፈርዳለሁ፤+ እነሱም ብዙ ንብረት ይዘው ይወጣሉ።+ +15 አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፤ ዕድሜ ጠግበህም ወደ መቃብር ትወርዳለህ።+ +16 ሆኖም በአራተኛው ትውልድ ወደዚህ ይመለሳሉ፤+ ምክንያቱም የአሞራውያን በደል ጽዋው ገና አልሞላም።”+ +17 ፀሐይዋ ከጠለቀችና ድቅድቅ ጨለማ አካባቢውን ከዋጠው በኋላ የሚጨስ ምድጃ ታየ፤ ለሁለት በተከፈለውም ሥጋ መካከል የሚንቦገቦግ ችቦ አለፈ። +18 በዚያ ቀን ይሖዋ እንዲህ ሲል ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገባ፦+ “ከግብፅ ወንዝ አንስቶ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ+ ድረስ ያለውን ይህን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤+ +19 የቄናውያንን፣+ የቀኒዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣ +20 የሂታውያንን፣+ የፈሪዛውያንን፣+ የረፋይምን፣+ +21 የአሞራውያንን፣ የከነአናውያንን፣ የገርጌሻውያንንና የኢያቡሳውያንን+ ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።” +22 ከዚህ በኋላ እውነተኛው አምላክ አብርሃምን ፈተነው፤+ “አብርሃም!” ሲል ጠራው፤ እሱም መልሶ “አቤት!” አለ። +2 ከዚያም አምላክ እንዲህ አለው፦ “እባክህ ልጅህን፣ በጣም የምትወደውን አንድ ልጅህን+ ይስሐቅን+ ይዘህ ወደ ሞሪያ+ ምድር ሂድ፤ በዚያም እኔ በማሳይህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መባ አድርገህ አቅርበው።” +3 ስለዚህ አብርሃም በማለዳ ተነስቶ አህያውን ከጫነ በኋላ ከአገልጋዮቹ መካከል ሁለቱን ከልጁ ከይስሐቅ ጋር ይዞ ለመሄድ ተነሳ። ለሚቃጠል መባ የሚሆን እንጨትም ፈለጠ፤ ከዚያም ተነስቶ እውነተኛው አምላክ ወዳሳየው ስፍራ ተጓዘ። +4 በሦስተኛውም ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ቦታውን ከሩቅ ተመለከተ። +5 በዚህ ጊዜ አብርሃም አገልጋዮቹን “እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ በመሄድ በአምላክ ፊት ሰግደን ወደ እናንተ እንመለሳለን” አላቸው። +6 ስለዚህ አብርሃም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንጨት ወስዶ ልጁን ይስሐቅን አሸከመው። እሱ ደግሞ እሳቱንና ቢላውን* ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ። +7 ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን “አባዬ!” ሲል ጠራው። እሱም መልሶ “አቤት ልጄ!” አለው። ይስሐቅም “እሳቱና እንጨቱ ይኸውና፤ ለሚቃጠል መባ የሚሆነው በግ ግን የት አለ?” አለው። +8 በዚህ ጊዜ አብርሃም “ልጄ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን በግ+ አምላክ ራሱ ያዘጋጃል” አለው። ሁለቱም አብረው ጉዟቸውን ቀጠሉ። +9 በመጨረሻም እውነተኛው አምላክ ወዳሳየው ስፍራ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያ ሠርቶ እንጨቱን ረበረበበት። ልጁን ይስሐቅንም እጁንና እግሩን አስሮ በመሠዊያው ላይ በተረበረበው እንጨት ላይ አጋደመው።+ +10 ከዚያም አብርሃም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላውን* አነሳ።+ +11 ሆኖም የይሖዋ መልአክ ከሰማይ ጠርቶት “አብርሃም፣ አብርሃም!” አለው፤ እሱም መልሶ “አቤት!” አለ። +12 መልአኩም እንዲህ አለው፦ “በልጁ ላይ እጅህን አታሳርፍበት፤ ምንም ነገር አታድርግበት፤ ምክንያቱም ልጅህን፣ አንድ ልጅህን ለእኔ ለመስጠት ስላልሳሳህ አምላክን የምትፈራ ሰው እንደሆንክ አሁን በእርግጥ አውቄአለሁ።”+ +13 በዚህ ጊዜ አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ከእሱ ትንሽ እልፍ ብሎ ቀንዶቹ በጥሻ የተያዙ አውራ በግ አየ። በመሆኑም አብርሃም አውራውን በግ ካመጣ በኋላ በልጁ ምትክ የሚቃጠል መባ አድርጎ አቀረበው። +14 አብርሃምም ያን ስፍራ ይሖዋ ይርኤ* ብሎ ጠራው። እስከ ዛሬም ድረስ “ይሖዋ በተራራው ላይ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ያቀርባል”+ የሚባለው በዚህ የተነሳ ነው። +15 የይሖዋም መልአክ ከሰማይ ለሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ጠራው፤ +16 እንዲህም አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በራሴ እምላለሁ፤+ ይህን ስላደረግክ እንዲሁም ልጅህን፣ አንድ ልጅህን ለመስጠት ስላልሳሳህ+ +17 በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በእርግጥ አበዛዋለሁ፤+ ዘርህም የጠላቶቹን በር* ይወርሳል።+ +18 ቃሌን ስለሰማህ የምድር ብሔራት ሁሉ በዘርህ+ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።’”+ +19 ከዚያ በኋላ አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰ፤ ተነስተውም አብረው ወደ ቤርሳቤህ+ ተመለሱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ መኖሩን ቀጠለ። +20 ከዚህ በኋላ ለአብርሃም እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “ሚልካም ለወንድምህ ለናኮር+ ወንዶች ልጆችን ወልዳለታለች፤ +21 እነሱም የበኩር ልጁ ዑጽ፣ ወንድሙ ቡዝ፣ የአራም አባት የሆነው ቀሙኤል፣ +22 ኬሰድ፣ ሃዞ፣ ፒልዳሽ፣ ይድላፍ እና ባቱኤል+ ናቸው።” +23 ባቱኤልም ርብቃን+ ወለደ። ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር እነዚህን ስምንቱን ወለደችለት። +24 ቁባቱ የሆነችው ረኡማም ተባህ፣ ጋሃም፣ ታሃሽ እና ማአካ የተባሉ ወንዶች ልጆችን ወለደች። +42 ያዕቆብ በግብፅ እህል መኖሩን+ ባወቀ ጊዜ ወንዶች ልጆቹን “ለምን ዝም ብላችሁ እርስ በርስ ትተያያላችሁ?” አላቸው። +2 ከዚያም “በግብፅ እህል እንዳለ ሰምቻለሁ። በሕይወ�� እንድንኖር ወደዚያ ወርዳችሁ እህል ግዙልን፤ አለዚያ ማለቃችን ነው” አላቸው።+ +3 ስለሆነም አሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች+ እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ወረዱ። +4 ሆኖም ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ቢንያምን+ “ምናልባት አደጋ ሊደርስበትና ሊሞትብኝ ይችላል” ብሎ ስላሰበ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር አላከውም።+ +5 ረሃቡ እስከ ከነአን ምድር ድረስ ተስፋፍቶ ስለነበር የእስራኤል ወንዶች ልጆች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ከሚመጡት ሰዎች ጋር አብረው መጡ።+ +6 በዚያን ጊዜ በምድሩ ላይ አስተዳዳሪ የነበረውና+ ለምድር ሕዝቦች ሁሉ እህል የሚሸጠው ዮሴፍ ነበር።+ በመሆኑም የዮሴፍ ወንድሞች መጥተው መሬት ላይ በመደፋት ሰገዱለት።+ +7 ዮሴፍም ወንድሞቹን ሲያያቸው ወዲያውኑ አወቃቸው፤ እሱ ግን ማንነቱን ከእነሱ ደበቀ።+ በመሆኑም “የመጣችሁት ከየት ነው?” በማለት በቁጣ ተናገራቸው፤ እነሱም “እህል ለመግዛት ከከነአን ምድር ነው የመጣነው” አሉት።+ +8 ዮሴፍ ወንድሞቹን ያወቃቸው ቢሆንም እነሱ ግን አላወቁትም። +9 ዮሴፍም ስለ እነሱ ያያቸው ሕልሞች ወዲያው ትዝ አሉት፤+ እሱም “እናንተ ሰላዮች ናችሁ! የመጣችሁት ምድሪቱ በየት በኩል ለጥቃት እንደተጋለጠች* ለማየት ነው!” አላቸው። +10 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ኧረ እንደዚያ አይደለም ጌታዬ፤ እኛ አገልጋዮችህ የመጣነው እህል ለመግዛት ነው። +11 ሁላችንም የአንድ ሰው ልጆች ነን። እኛ ንጹሐን ሰዎች ነን። አገልጋዮችህ ሰላዮች አይደለንም።” +12 እሱ ግን “በፍጹም አይደለም! የመጣችሁት ምድሪቱ በየት በኩል ለጥቃት እንደተጋለጠች ለማየት ነው!” አላቸው። +13 በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ 12 ወንድማማቾች ነን።+ በከነአን ምድር የሚኖር የአንድ ሰው ልጆች ነን፤+ ትንሹ ወንድማችን አሁን ከአባታችን ጋር ነው፤+ አንደኛው ግን የለም።”+ +14 ይሁን እንጂ ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ “‘እናንተ ሰላዮች ናችሁ!’ አልኳችሁ እኮ፤ +15 እንግዲህ ሰላዮች መሆን አለመሆናችሁ በዚህ ይረጋገጣል፤ በፈርዖን ሕይወት እምላለሁ፣ ትንሹ ወንድማችሁ ወደዚህ ካልመጣ በስተቀር ከዚህች ንቅንቅ አትሉም።+ +16 እናንተ እዚሁ ታስራችሁ እያላችሁ ከመካከላችሁ አንዱን ላኩትና ወንድማችሁን ይዞት ይምጣ። በዚህ መንገድ የተናገራችሁት ነገር እውነት መሆን አለመሆኑ ይረጋገጣል። አለዚያ ግን በፈርዖን ሕይወት እምላለሁ፣ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።” +17 ከዚያም ለሦስት ቀን አንድ ላይ እስር ቤት አቆያቸው። +18 በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ አምላክን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ። +19 እንዳላችሁት ንጹሐን ሰዎች ከሆናችሁ ከመካከላችሁ አንዱ ወንድማችሁ እዚሁ እስር ቤት ውስጥ ይቆይ፤ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁ መሄድ ትችላላችሁ።+ +20 የተናገራችሁት ቃል እውነት መሆኑ እንዲረጋገጥና ከሞት እንድትተርፉ ትንሹን ወንድማችሁን ወደ እኔ ይዛችሁት ኑ።” እነሱም እንደተባሉት አደረጉ። +21 ከዚያም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “ይህ ሁሉ እየደረሰብን ያለው በወንድማችን ላይ በፈጸምነው ግፍ የተነሳ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፤+ ምክንያቱም ተጨንቆ* እንድንራራለት ሲማጸነን እኛ ግን አልሰማነውም። ይህ ሁሉ መከራ እየደረሰብን ያለው በዚህ ምክንያት ነው።” +22 በዚህ ጊዜ ሮቤል እንዲህ አላቸው፦ “‘በዚህ ልጅ ላይ ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብያችሁ አልነበረም? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም።+ ይኸው አሁን ደሙ ከእጃችን እየተፈለገ ነው።”+ +23 ይሁንና ዮሴፍ ያነጋገራቸው በአስተርጓሚ ስለነበር ምን እየተባባሉ እንዳለ እንደሚሰማ አላወቁም ነበር። +24 በመሆኑም ከፊታቸው ዞር ብ�� አለቀሰ።+ ከዚያም ወደ እነሱ ተመልሶ በመምጣት በድጋሚ ካነጋገራቸው በኋላ ስምዖንን+ ከእነሱ ለይቶ በመውሰድ ዓይናቸው እያየ አሰረው።+ +25 በኋላም ዮሴፍ በየከረጢቶቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው አዘዘ፤ በተጨማሪም የእያንዳንዳቸውን ገንዘብ በየከረጢቶቻቸው መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዟቸው የሚሆን ስንቅ እንዲሰጧቸው ትእዛዝ አስተላለፈ። ልክ እንዳለውም ተደረገላቸው። +26 እነሱም እህላቸውን በአህዮቻቸው ላይ ጭነው ጉዞ ጀመሩ። +27 ከእነሱ መካከል አንዱ ባረፉበት ቦታ ለአህያው መኖ ለመስጠት ከረጢቱን ሲፈታ ገንዘቡን ከረጢቱ አፍ ላይ አገኘው። +28 እሱም በዚህ ጊዜ ወንድሞቹን “ኧረ ገንዘቤ ተመልሶልኛል፤ ይኸው እዚህ ከረጢቴ ውስጥ አገኘሁት!” አላቸው። እነሱም ልባቸው በፍርሃት ራደ፤ እየተንቀጠቀጡም እርስ በርሳቸው “አምላክ ያደረገብን ይህ ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ። +29 በከነአን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ በደረሱም ጊዜ ያጋጠማቸውን ሁሉ እንዲህ በማለት ነገሩት፦ +30 “የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው በቁጣ ተናገረን፤+ አገሪቱን ለመሰለል እንደሄድን አድርጎም ቆጠረን። +31 እኛ ግን እንዲህ አልነው፦ ‘እኛ ንጹሐን ሰዎች ነን። ሰላዮች አይደለንም።+ +32 እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆን 12 ወንድማማቾች ነን።+ አንዱ የለም፤+ ትንሹ ወንድማችን ደግሞ አሁን ከአባታችን ጋር በከነአን ምድር ይገኛል’፤+ +33 ሆኖም የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው እንዲህ አለን፦ ‘እንግዲህ ንጹሐን ሰዎች መሆን አለመሆናችሁን በዚህ አውቃለሁ፤ አንዱ ወንድማችሁ እዚህ እኔ ጋ እንዲቆይ አድርጉ።+ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ የሆነ ነገር ይዛችሁ ሂዱ።+ +34 ንጹሐን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁንም እንዳውቅ ትንሹን ወንድማችሁን ወደ እኔ ይዛችሁት ኑ። ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ መነገድ ትችላላችሁ።’” +35 እያንዳንዳቸውም ከረጢታቸውን ሲያራግፉ ገንዘባቸውን እንደተቋጠረ በከረጢታቸው ውስጥ አገኙት። እነሱም ሆኑ አባታቸው የተቋጠረውን ገንዘብ ሲያዩ ደነገጡ። +36 አባታቸው ያዕቆብም “ለሐዘን የዳረጋችሁት እኔን ነው!+ ዮሴፍ የለም፤+ ስምዖንም የለም፤+ አሁን ደግሞ ቢንያምን ልትወስዱት ነው! ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው። +37 ሮቤል ግን አባቱን “ልጁን መልሼ ባላመጣልህ ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ግደላቸው።+ ለእኔ በኃላፊነት ስጠኝ፤ እኔ ራሴ መልሼ አስረክብሃለሁ” አለው።+ +38 እሱ ግን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ከእናንተ ጋር ወደዚያ አይወርድም። ምክንያቱም ወንድሙ ሞቷል፤ አሁን የቀረው እሱ ብቻ ነው።+ ከእናንተ ጋር አብሮ ሲሄድ መንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበትና ቢሞት ሽበቴን በሐዘን+ ወደ መቃብር*+ ታወርዱታላችሁ።” +39 ዮሴፍም ወደ ግብፅ ተወሰደ፤+ የፈርዖን የቤተ መንግሥት ባለሥልጣንና የዘቦች አለቃ የሆነ ጶጢፋር+ የሚባል አንድ ግብፃዊ ወደዚያ ይዘውት ከወረዱት እስማኤላውያን+ እጅ ዮሴፍን ገዛው። +2 ሆኖም ይሖዋ ከዮሴፍ ጋር ነበር።+ በዚህም የተነሳ ስኬታማ ሆነ፤ በግብፃዊው ጌታው ቤትም ላይ ኃላፊ ሆኖ ተሾመ። +3 ጌታውም ይሖዋ ከዮሴፍ ጋር እንደሆነና የሚሠራውንም ነገር ሁሉ ይሖዋ እንደሚያሳካለት አየ። +4 ዮሴፍም በፊቱ ሞገስ እያገኘ ሄደ፤ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። በመሆኑም በቤቱ ላይ ሾመው፤ የእሱ የሆነውንም ነገር ሁሉ በኃላፊነት ሰጠው። +5 በቤቱና ባለው ነገር ሁሉ ላይ ከሾመው ጊዜ አንስቶ ይሖዋ በዮሴፍ ምክንያት የግብፃዊውን ቤት ባረከ፤ ይሖዋም በቤትና በመስክ ያለውን ነገር ሁሉ ባረከለት።+ +6 ከጊዜ በኋላም ያለውን ነገር ሁሉ ለዮሴፍ በኃላፊነት ሰጠው፤ እሱም ከሚመገበው ምግብ በስተቀር ስለ ሌላው ነገር ���ንም አይጨነቅም ነበር። ደግሞም ዮሴፍ ሰውነቱ እየዳበረና መልኩ እያማረ ሄደ። +7 በኋላም የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይኗን ጣለችበት፤ እሷም “ከእኔ ጋር ተኛ” ትለው ጀመር። +8 እሱ ግን ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ የጌታውን ሚስት እንዲህ አላት፦ “ጌታዬ በዚህ ቤት በእኔ እጅ ስላለው ነገር ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ ያለውንም ነገር ሁሉ በአደራ ሰጥቶኛል። +9 በዚህ ቤት ውስጥ ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ጌታዬ ከአንቺ በስተቀር ምንም ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ ይህን ያደረገውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለውን እጅግ መጥፎ ድርጊት በመፈጸም በአምላክ ላይ እንዴት ኃጢአት እሠራለሁ?”+ +10 እሷም ዮሴፍን በየቀኑ ትወተውተው ነበር፤ እሱ ግን ከእሷ ጋር ለመተኛትም ሆነ አብሯት ለመሆን ፈጽሞ ፈቃደኛ አልሆነም። +11 ይሁንና አንድ ቀን ዮሴፍ ሥራውን ለማከናወን ወደ ቤት ሲገባ ከቤቱ አገልጋዮች መካከል አንዳቸውም በዚያ አልነበሩም። +12 እሷም ልብሱን አፈፍ አድርጋ ይዛ “አብረኸኝ ተኛ!” አለችው። እሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ወደ ውጭ ሸሽቶ ወጣ። +13 እሷም ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ወደ ውጭ እንደሸሸ ባየች ጊዜ +14 የቤቷን ሰዎች ጮኻ በመጣራት እንዲህ አለቻቸው፦ “አያችሁ! ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ መሳለቂያ ሊያደርገን ነው። መጥቶ አብሬሽ ካልተኛሁ አለኝ፤ እኔ ግን ጩኸቴን አቀለጥኩት። +15 ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ልብሱን አጠገቤ ጥሎ ወደ ውጭ ሸሽቶ ወጣ።” +16 ከዚያም ጌታው ወደ ቤቱ እስኪመለስ ድረስ ልብሱን አጠገቧ አቆየችው። +17 ከዚያም እንዲህ ስትል ያንኑ ነገር ነገረችው፦ “ይህ ያመጣህብን ዕብራዊ አገልጋይ እኔ ወዳለሁበት ገብቶ መሳለቂያ ሊያደርገኝ ነበር። +18 ሆኖም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ልብሱን አጠገቤ ጥሎ ወደ ውጭ ሸሽቶ ወጣ።” +19 ጌታውም “ይኸውልህ፣ አገልጋይህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ሲሰማ ቁጣው ነደደ። +20 በመሆኑም የዮሴፍ ጌታ ዮሴፍን ወስዶ የንጉሡ እስረኞች የታሰሩበት እስር ቤት አስገባው፤ ዮሴፍም እዚያው እስር ቤት ውስጥ ቆየ።+ +21 ይሁን እንጂ ይሖዋ ከዮሴፍ አልተለየም፤ እንደወትሮው ሁሉ ለእሱ ታማኝ ፍቅር ከማሳየት ወደኋላ አላለም፤ በእስር ቤቱ አለቃም ፊት ሞገስ ሰጠው።+ +22 በመሆኑም የእስር ቤቱ አለቃ ዮሴፍን በእስር ቤቱ ውስጥ ባሉት እስረኞች ሁሉ ላይ ኃላፊ አደረገው፤ በእስር ቤቱ ውስጥ እስረኞቹ የሚያከናውኑትን ማንኛውንም ሥራ የሚቆጣጠረው እሱ ነበር።+ +23 ይሖዋ ከዮሴፍ ጋር ስለነበርና የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ይሖዋ ስለሚያሳካለት የእስር ቤቱ አለቃ በዮሴፍ ኃላፊነት ሥር ስላለው ስለ ማንኛውም ነገር ምንም አይጨነቅም ነበር።+ +17 መላው የእስራኤል ማኅበረሰብም ከሲን ምድረ በዳ+ ተነስቶ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት+ ከቦታ ወደ ቦታ ሲጓዝ ከቆየ በኋላ በረፊዲም+ ሰፈረ። ሆኖም ሕዝቡ የሚጠጣው ውኃ አልነበረም። +2 በመሆኑም ሕዝቡ “የሚጠጣ ውኃ ስጠን” በማለት ከሙሴ ጋር ይጣላ ጀመር።+ ሙሴ ግን “ከእኔ ጋር የምትጣሉት ለምንድን ነው? ይሖዋንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?”+ አላቸው። +3 ሆኖም ሕዝቡ ውኃ በጣም ተጠምቶ ስለነበር “እኛና ልጆቻችን እንዲሁም ከብቶቻችን በውኃ ጥም እንድናልቅ ከግብፅ ያወጣኸን ለምንድን ነው?” በማለት በሙሴ ላይ ማጉረምረሙን ቀጠለ።+ +4 በመጨረሻም ሙሴ “ይህን ሕዝብ ምን ባደርገው ይሻለኛል? ትንሽ ቆይተው እኮ ይወግሩኛል!” በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ። +5 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑትን ምረጥና የአባይን ወንዝ የመታህበትን በትር+ ይዘህ ከሕዝቡ ፊት ፊት ሂድ። በትሩን በእጅህ ይዘህ ሂድ። +6 እኔም በዚያ በኮሬብ በሚገ��ው ዓለት ላይ ፊትህ እቆማለሁ። አንተም ዓለቱን ትመታዋለህ፤ ውኃም ከውስጡ ይፈልቃል፤ ሕዝቡም ይጠጣሉ።”+ ሙሴም የእስራኤል ሽማግሌዎች እያዩ እንደተባለው አደረገ። +7 እሱም እስራኤላውያን ስለተጣሉትና “ለመሆኑ ይሖዋ በመካከላችን አለ ወይስ የለም?” በማለት ይሖዋን ስለተፈታተኑት+ የቦታውን ስም ማሳህ*+ እና መሪባ*+ አለው። +8 ከዚያም አማሌቃውያን+ መጥተው በረፊዲም እስራኤላውያንን ወጉ።+ +9 በዚህ ጊዜ ሙሴ ኢያሱን+ እንዲህ አለው፦ “ሰዎች ምረጥልንና ከአማሌቃውያን ጋር ለመዋጋት ውጣ። እኔም በነገው ዕለት የእውነተኛውን አምላክ በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው አናት ላይ እቆማለሁ።” +10 ከዚያም ኢያሱ ልክ ሙሴ እንዳለው አደረገ፤+ ከአማሌቃውያንም ጋር ተዋጋ። ሙሴ፣ አሮንና ሁርም+ ወደ ኮረብታው አናት ወጡ። +11 ሙሴ እጆቹን ወደ ላይ አንስቶ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ያይሉ፣ እጆቹን በሚያወርድበት ጊዜ ግን አማሌቃውያን ያይሉ ነበር። +12 የሙሴ እጆች በዛሉ ጊዜ ድንጋይ ወስደው ከሥሩ አስቀመጡለት፤ እሱም በድንጋዩ ላይ ተቀመጠ። ከዚያም አሮንና ሁር አንዱ በአንደኛው በኩል፣ ሌላው ደግሞ በሌላኛው በኩል ሆነው እጆቹን ደገፉለት፤ በመሆኑም ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ እጆቹ ባሉበት ጸኑ። +13 በዚህ መንገድ ኢያሱ አማሌቅንና ሕዝቦቹን በሰይፍ ድል አደረገ።+ +14 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መታሰቢያ* እንዲሆን ይህን በመጽሐፍ ጻፈው፤ ለኢያሱም ‘የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ሙሉ በሙሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ’+ በማለት ይህን ደግመህ ንገረው።” +15 ከዚያም ሙሴ መሠዊያ ሠርቶ ስሙን ‘ይሖዋ ንሲ’* ብሎ ሰየመው፤ +16 እንዲህም ያለው “እጁ በያህ+ ዙፋን ላይ ስለተነሳ ይሖዋ ከአማሌቅ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዋጋል”+ በማለት ነው። +30 “ዕጣን የሚጨስበት መሠዊያ ትሠራለህ፤+ ከግራር እንጨትም ትሠራዋለህ።+ +2 ርዝመቱ አንድ ክንድ፣* ወርዱ አንድ ክንድ ሆኖ አራቱም ጎኖቹ እኩል ይሁኑ፤ ቁመቱ ደግሞ ሁለት ክንድ ይሁን። ቀንዶቹም ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሆናሉ።+ +3 ላዩን፣ ሁሉንም ጎኖቹን እንዲሁም ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ ዙሪያውንም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ። +4 በተጨማሪም በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ትሠራለታለህ፤ ቀለበቶቹም መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች የሚገቡባቸው ይሆናሉ። +5 መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። +6 ራሴን ለአንተ ከምገልጥበት+ ከምሥክሩ ታቦት+ አጠገብ ካለው መጋረጃ በፊት ይኸውም ምሥክሩን ከሚጋርደው መከለያ በፊት ታስቀምጠዋለህ። +7 “አሮንም+ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ያጨስበታል፤+ በየማለዳው መብራቶቹን+ በሚያዘገጃጅበት ጊዜም ዕጣኑ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። +8 በተጨማሪም አሮን አመሻሹ ላይ* መብራቶቹን በሚያበራበት ጊዜ ዕጣኑን ያጨሰዋል። ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘወትር በይሖዋ ፊት የሚቀርብ የዕጣን መባ ነው። +9 በዚህ መሠዊያ ላይ ያልተፈቀደ ዕጣን+ ወይም የሚቃጠል መባ አሊያም የእህል መባ አታቅርቡ፤ እንዲሁም በላዩ ላይ የመጠጥ መባ አታፍስሱ። +10 አሮንም በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተሰረያ ያድርግ።+ ለማስተሰረያ ከቀረበው የኃጢአት መባ ላይ የተወሰነ ደም ወስዶ+ በዓመት አንድ ጊዜ ለመሠዊያው ማስተሰረያ ያደርጋል፤ ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይደረጋል። ይህ ለይሖዋ እጅግ የተቀደሰ ነው።” +11 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +12 “የሕዝብ ቆጠራ በማካሄድ የእስራኤልን ልጆች በምትቆጥርበት+ ጊዜ ሁሉ እያንዳንዱ ሰው በቆጠራው ወቅት ለይሖዋ ስለ ሕይወቱ* ቤዛ መስጠት አለበት። ይህን የሚያደርጉት በሚመዘገቡበት ጊዜ መቅሰፍት እንዳይመጣባቸው ነው። +13 የተመዘገቡት ሁሉ የሚሰጡት ይህን ነው፦ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* መሠረት+ ግማሽ ሰቅል* ይሰጣሉ። አንድ ሰቅል ሃያ ጌራ* ነው። ለይሖዋ የሚሰጠው መዋጮ ግማሽ ሰቅል ነው።+ +14 ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ሁሉ ለይሖዋ መዋጮ ይሰጣሉ።+ +15 ለሕይወታችሁ* ማስተሰረያ እንዲሆን ለይሖዋ መዋጮ በምትሰጡበት ጊዜ ባለጸጋው ከግማሽ ሰቅል* አብልጦ፣ ችግረኛውም ከግማሽ ሰቅል አሳንሶ አይስጥ። +16 ለሕይወታችሁ* ማስተሰረያ በመሆን በይሖዋ ፊት ለእስራኤላውያን እንደ መታሰቢያ ሆኖ እንዲያገለግል ለማስተሰረያ የቀረበውን የብር ገንዘብ ከእስራኤላውያን ወስደህ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለሚቀርበው አገልግሎት ትሰጠዋለህ።” +17 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +18 “ለመታጠቢያ እንዲሆን ከመዳብ ገንዳና ማስቀመጫውን ሥራ፤+ በመገናኛ ድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠው፤ ውኃም ጨምርበት።+ +19 አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡበታል።+ +20 ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገቡበት ወይም ለማገልገልና በእሳት የሚቀርብ መባ ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ እንዳይሞቱ በውኃ ይታጠባሉ። +21 እንዳይሞቱ እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡ፤ ይህም ለእሱና ለዘሮቹ በትውልዶቻቸው ሁሉ ዘላለማዊ ሥርዓት ሆኖ ያገልግል።”+ +22 ይሖዋም እንዲህ በማለት ሙሴን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ +23 “አንተም ጥሩ መዓዛ ያላቸውን የሚከተሉትን ምርጥ ቅመሞች ውሰድ፦ 500 ሰቅል የረጋ ከርቤ፣ የዚህን ግማሽ ይኸውም 250 ሰቅል ጣፋጭ ቀረፋ፣ 250 ሰቅል ጥሩ መዓዛ ያለው ጠጅ ሣር፣ +24 እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* መሠረት+ 500 ሰቅል ብርጉድ* እንዲሁም አንድ ሂን* የወይራ ዘይት። +25 ከእነዚህም ቅዱስ የቅብዓት ዘይት አዘጋጅ፤ በብልሃት የተቀመመ መሆን ይኖርበታል።+ ይህም ቅዱስ የቅብዓት ዘይት ይሆናል። +26 “አንተም የመገናኛ ድንኳኑንና+ የምሥክሩን ታቦት +27 እንዲሁም ጠረጴዛውንና ዕቃዎቹን በሙሉ፣ መቅረዙንና ዕቃዎቹን፣ የዕጣን መሠዊያውን፣ +28 የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያና ዕቃዎቹን በሙሉ እንዲሁም የውኃ ገንዳውንና ማስቀመጫውን በዘይቱ ትቀባለህ። +29 እጅግ ቅዱስ እንዲሆኑም ቀድሳቸው።+ የሚነካቸው ማንኛውም ሰው ቅዱስ መሆን አለበት።+ +30 አንተም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትቀባቸዋለህ፤+ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም+ ትቀድሳቸዋለህ። +31 “አንተም ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ ‘በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ምንጊዜም ለእኔ ቅዱስ የቅብዓት ዘይት ይሆናል።+ +32 ይህ ማንም ሰው ሰውነቱን የሚቀባው አይደለም፤ እንዲሁም በተመሳሳይ መንገድ በመቀመም እንዲህ ያለ ቅባት ማዘጋጀት የለባችሁም። ይህ የተቀደሰ ነገር ነው። ለእናንተም ምንጊዜም የተቀደሰ ይሆናል። +33 ይህን የመሰለ ቅባት የሚሠራና ያልተፈቀደለትን ሰው* የሚቀባ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።’”+ +34 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተም ጥሩ መዓዛ ካላቸው ቅመሞች+ ይኸውም ከሚንጠባጠብ ሙጫ፣ ከኦኒካ፣* ከሚሸት ሙጫ እንዲሁም ከንጹሕ ነጭ ዕጣን እኩል መጠን ውሰድ። +35 ከዚያም ዕጣን አድርገህ አዘጋጀው፤+ ይህም ዕጣን በብልሃት የተቀመመ፣ ጨው የተጨመረበት፣+ ንጹሕና ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። +36 ከእሱም የተወሰነውን ወቅጠህ በማላም ራሴን ለአንተ በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ባለው ምሥክር ፊት ታስቀምጠዋለህ። ይህም ለእናንተ እጅግ ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። +37 በተመሳሳይ መንገድ የተቀመመ ዕጣን ለራስህ ማዘጋጀት የለብህም።+ ለይሖዋ የተቀደሰ እንደሆነ አድርገህ ልትመለከተው ይገባል። +38 በመዓዛው ለመደሰት ሲል ይህን የመሰለ ዕጣን የሚያዘጋጅ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።” +35 በኋላም ሙሴ የእስራኤልን ማኅበረሰብ ሁሉ አንድ ላይ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንድትፈጽሟቸው ያዘዛችሁ ነገሮች እነዚህ ናቸው፦+ +2 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእናንተ የተቀደሰ ይሆናል፤ ለይሖዋም ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል።+ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራ ማንም ሰው ይገደላል።+ +3 በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በሰንበት ቀን እሳት አታቀጣጥሉ።” +4 ከዚያም ሙሴ ለእስራኤል ማኅበረሰብ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦ +5 ‘ካላችሁ ነገር ለይሖዋ መዋጮ አምጡ።+ ልቡ ያነሳሳው+ ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን ነገሮች ለይሖዋ መዋጮ አድርጎ ያምጣ፦ ወርቅ፣ ብር፣ መዳብ፣ +6 ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣+ +7 ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር እንጨት፣ +8 ለመብራት የሚሆን ዘይት፣ ለቅብዓት ዘይትና ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆን የበለሳን ዘይት፣+ +9 በኤፉዱና በደረት ኪሱ+ ላይ የሚቀመጡ የኦኒክስ ድንጋዮችና+ ሌሎች ድንጋዮች። +10 “‘በመካከላችሁ ያሉ ጥሩ ችሎታ* ያላቸው+ ሰዎች ሁሉ መጥተው ይሖዋ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ይሥሩ፤ +11 እነዚህም የማደሪያ ድንኳኑ ከተለያየ ቁሳቁሱና ከመደረቢያው ጋር፣ ማያያዣዎቹ፣ አራት ማዕዘን ቋሚዎቹ፣ አግዳሚ እንጨቶቹ፣ ዓምዶቹ፣ መሰኪያዎቹ፣ +12 ታቦቱና+ መሎጊያዎቹ፣+ መክደኛው፣+ ለመከለያ የሚሆነው መጋረጃ፣+ +13 ጠረጴዛው+ እንዲሁም መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ በሙሉ፣ ገጸ ኅብስቱ፣+ +14 የመብራት መቅረዙና+ ዕቃዎቹ፣ መብራቶቹ፣ ለመብራቱ የሚሆነው ዘይት፣+ +15 የዕጣን መሠዊያውና+ መሎጊያዎቹ፣ የቅብዓት ዘይቱና ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን፣+ ለማደሪያ ድንኳኑ መግቢያ የሚሆነው መከለያ፣* +16 የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያ+ እንዲሁም የመዳብ ፍርግርጉ፣ መሎጊያዎቹና ዕቃዎቹ በሙሉ፣ ገንዳውና ማስቀመጫው፣+ +17 የግቢው መጋረጃ+ እንዲሁም ቋሚዎቹና መሰኪያዎቹ፣ ለግቢው መግቢያ የሚሆነው መከለያ፣* +18 የማደሪያ ድንኳኑ ካስማዎችና የግቢው ካስማዎች እንዲሁም ገመዶቻቸው፣+ +19 በመቅደሱ ለማገልገል የሚለበሱት በጥሩ ሁኔታ የተሸመኑት ልብሶች፣+ የካህኑ የአሮን ቅዱስ ልብሶች+ እንዲሁም ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸው ልብሶች ናቸው።’” +20 ከዚያም የእስራኤል ማኅበረሰብ በሙሉ ከሙሴ ፊት ሄደ። +21 ከዚያም ልባቸው የገፋፋቸውና+ መንፈሳቸው ያነሳሳቸው ሁሉ መጥተው ለመገናኛ ድንኳኑ ሥራና በዚያ ለሚከናወነው ማንኛውም አገልግሎት እንዲሁም ለቅዱሶቹ ልብሶች እንዲሆን መዋጮአቸውን ለይሖዋ አመጡ። +22 ፈቃደኛ ልብ ያላቸው ሁሉ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የደረት ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ ቀለበትና ሌላ ጌጣጌጥ እንዲሁም ሁሉንም ዓይነት ከወርቅ የተሠራ ጌጣጌጥ ይዘው ይመጡ ነበር። ሁሉም የወርቅ መባዎቻቸውን* ለይሖዋ አቀረቡ።+ +23 ደግሞም ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ እንዲሁም የአቆስጣ ቆዳ ያላቸው ሁሉ እነዚህን አመጡ። +24 ብርና መዳብ የሚያዋጡ ሁሉ ለይሖዋ የሚሆነውን መዋጮ አመጡ፤ ለመገናኛው ድንኳን ሥራ የሚውል የግራር እንጨት ያላቸውም ሁሉ ይህን አመጡ። +25 ጥሩ ችሎታ ያላቸው ሴቶችም+ ሁሉ በእጃቸው ይፈትሉ ነበር፤ እነሱም የሚከተሉትን ነገሮች ፈትለው አመጡ፦ ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣ ደ���ቅ ቀይ ማግ እንዲሁም ጥሩ በፍታ። +26 ጥሩ ችሎታ ያላቸው ልባቸው ያነሳሳቸው ሴቶች ሁሉ የፍየል ፀጉሩን ይፈትሉ ነበር። +27 አለቆቹም በኤፉዱና በደረት ኪሱ+ ላይ የሚቀመጡ የኦኒክስ ድንጋዮችንና ሌሎች ድንጋዮችን፣ +28 የበለሳን ዘይቱን እንዲሁም ለመብራት፣ ለቅብዓት ዘይቱና+ ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን+ የሚሆነውን ዘይት አመጡ። +29 ልባቸው ያነሳሳቸው ወንዶችና ሴቶች በሙሉ ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት እንዲከናወን ላዘዘው ሥራ የሚውሉ ነገሮችን አመጡ፤ እስራኤላውያኑ ይህን በፈቃደኝነት የሚቀርብ መባ አድርገው ለይሖዋ አመጡ።+ +30 ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፦ “እንደምታዩት ይሖዋ ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሁር ልጅ ዖሪ+ የወለደውን ባስልኤልን መርጦታል። +31 ደግሞም በማንኛውም ዓይነት የእጅ ሙያ ማስተዋል፣ ጥበብና እውቀት በመስጠት በአምላክ መንፈስ ሞልቶታል። +32 ይኸውም የተለያዩ ንድፎችን እንዲያወጣ እንዲሁም በወርቅ፣ በብርና በመዳብ የተለያዩ ነገሮችን እንዲሠራ፣ +33 ፈርጥ የሚሆኑትን ድንጋዮች እንዲቀርጽና በቦታቸው እንዲያስቀምጥ እንዲሁም ድንቅ የሆኑ ልዩ ልዩ የእንጨት ቁሳቁሶችን እንዲሠራ ነው። +34 አምላክም ለእሱና ከዳን ነገድ ለሆነው ለአሂሳማክ ልጅ ለኤልያብ+ ሌሎችን የማስተማር ችሎታ ሰጥቷቸዋል። +35 የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ የጥልፍ ባለሙያ እንዲሁም በሰማያዊ ክር፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ በደማቅ ቀይ ማግና በጥሩ በፍታ የሚሸምን የጥበብ ባለሙያ ብሎም የሽመና ባለሙያ የሚያከናውኗቸውን ሥራዎች በሙሉ እንዲሠሩ ጥሩ ችሎታ* ሰጥቷቸዋል።+ እነዚህ ሰዎች ሁሉንም ዓይነት ሥራዎች የሚሠሩና ሁሉንም ዓይነት ንድፎች የሚ +31 ይሖዋ እንዲህ በማለት ሙሴን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ +2 “እንግዲህ እኔ ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሁር ልጅ ዖሪ+ የወለደውን ባስልኤልን+ መርጬዋለሁ።* +3 ደግሞም ጥበብ፣ ማስተዋልና እውቀት በመስጠት በማንኛውም ዓይነት የእጅ ሙያ የተካነ እንዲሆን በአምላክ መንፈስ እሞላዋለሁ፤ +4 ይህን የማደርገው የተለያዩ ንድፎችን እንዲያወጣ፣ በወርቅ፣ በብርና በመዳብ የተለያዩ ነገሮችን እንዲሠራ፣ +5 ፈርጥ የሚሆኑትን ድንጋዮች እንዲቀርጽና በቦታቸው እንዲያስቀምጥ+ እንዲሁም ከእንጨት ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን እንዲሠራ ነው።+ +6 በተጨማሪም ከዳን ነገድ የሆነውን የአሂሳማክን ልጅ ኤልያብን+ ረዳት እንዲሆነው መርጬዋለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን የሚከተሉትን ነገሮች በሙሉ እንዲሠሩ ጥሩ ችሎታ* ባላቸው ሰዎች ሁሉ ልብ ውስጥ ጥበብን አኖራለሁ፦+ +7 የመገናኛ ድንኳኑን፣+ የምሥክሩን ታቦትና+ በላዩ ላይ ያለውን መክደኛ፣+ የድንኳኑን ዕቃዎች በሙሉ፣ +8 ጠረጴዛውንና+ ዕቃዎቹን፣ ከንጹሕ ወርቅ የሚሠራውን መቅረዝና ዕቃዎቹን በሙሉ፣+ የዕጣን መሠዊያውን፣+ +9 የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያና+ ዕቃዎቹን በሙሉ፣ መታጠቢያ ገንዳውንና መቆሚያውን፣+ +10 ጥሩ ሆነው የተሸመኑትን ልብሶች፣ የካህኑን የአሮንን ቅዱስ ልብሶች፣ ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸውን ልብሶች፣+ +11 የቅብዓት ዘይቱንና ለመቅደሱ የሚሆነውን ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን።+ ማንኛውንም ነገር ልክ እኔ ባዘዝኩህ መሠረት ይሠሩታል።” +12 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +13 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እናንተን የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ መሆኔን እንድታውቁ የሚያደርግ፣ በትውልዶቻችሁ ሁሉ በእኔና በእናንተ መካከል ያለ ምልክት ስለሆነ በተለይ ሰንበቴን ማክበር አለባችሁ።+ +14 ለእናንተ የተቀደሰ ስለሆነ ሰንበትን አክብሩ።+ ሰንበትን የሚያረክስ ሰው ይገደል። ማንም ሰው በዚያ ቀን ሥራ ቢሠራ ያ ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረ�� አለበት።+ +15 ስድስት ቀን ሥራ መሥራት ይቻላል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ነው።+ ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። በሰንበት ቀን ሥራ የሚሠራ ማንም ሰው ይገደል። +16 እስራኤላውያን ሰንበትን መጠበቅ አለባቸው፤ በትውልዶቻቸው ሁሉ ሰንበትን ማክበር አለባቸው። ይህ ዘላቂ ቃል ኪዳን ነው። +17 በእኔና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ያለ ዘላለማዊ ምልክት ነው፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ሠርቶ በማጠናቀቅ ሥራውን ያቆመውና ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነው።’”+ +18 በሲና ተራራ ላይ ከእሱ ጋር ተነጋግሮ እንደጨረሰ የምሥክሩን ሁለት ጽላቶች+ ይኸውም በአምላክ ጣት+ የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች ለሙሴ ሰጠው። +18 የምድያም ካህን የሆነው የሙሴ አማት ዮቶር+ አምላክ ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገውን ነገር ሁሉ ይኸውም ይሖዋ እስራኤልን ከግብፅ እንዴት እንዳወጣ ሰማ።+ +2 የሙሴ አማት ዮቶር የሙሴ ሚስት ሲፓራ ወደ እሱ ተመልሳ በተላከች ጊዜ እሷንና +3 ሁለቱን ወንዶች ልጆቿን+ ይዞ ተነሳ። ሙሴ “በባዕድ አገር የምኖር የባዕድ አገር ሰው ሆንኩ” ብሎ ስለነበር የአንደኛው ልጅ ስም ጌርሳም*+ ነበር፤ +4 እንዲሁም ሙሴ “ከፈርዖን ሰይፍ+ ያዳነኝ የአባቴ አምላክ ረዳቴ ነው” ብሎ ስለነበር የሌላኛው ልጁ ስም ኤሊዔዘር* ነበር። +5 በመሆኑም የሙሴ አማት ዮቶር ከሙሴ ሚስትና ወንዶች ልጆች ጋር በመሆን የእውነተኛው አምላክ ተራራ+ በሚገኝበት ምድረ በዳ ሰፍሮ ወደነበረው ወደ ሙሴ መጣ። +6 ከዚያም ዮቶር “እኔ አማትህ ዮቶር፣+ ከሚስትህና ከሁለቱ ወንዶች ልጆቿ ጋር ወደ አንተ እየመጣሁ ነው” የሚል መልእክት ወደ ሙሴ ላከ። +7 ሙሴም ወዲያውኑ አማቱን ሊቀበለው ወጣ፤ እሱም ሰገደለት፤ ከዚያም ሳመው። እርስ በርሳቸውም ስለ ደህንነታቸው ተጠያየቁ፤ በኋላም ወደ ድንኳኑ ገቡ። +8 ሙሴም ይሖዋ ለእስራኤል ሲል በፈርዖንና በግብፅ ላይ ያደረገውን ሁሉ+ እንዲሁም በጉዟቸው ያጋጠሟቸውን አስቸጋሪ ሁኔታዎችና+ ይሖዋ እንዴት እንዳዳናቸው ለአማቱ ተረከለት። +9 ዮቶርም ይሖዋ እስራኤልን ከግብፅ እጅ በማዳን ለእነሱ ሲል ባደረገላቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ተደሰተ። +10 ከዚያም ዮቶር እንዲህ አለ፦ “ከግብፅና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ እንዲሁም ሕዝቡን ከግብፅ እጅ ነፃ ያወጣው ይሖዋ ይወደስ። +11 ይሖዋ በሕዝቡ ላይ የእብሪት ድርጊት በፈጸሙ ሰዎች ላይ እንዲህ ያለ እርምጃ በመውሰዱ ከሌሎች አማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ+ አሁን አውቄአለሁ።” +12 ከዚያም የሙሴ አማት ዮቶር የሚቃጠል መባና መሥዋዕቶችን ለአምላክ አመጣ፤ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ከሙሴ አማት ጋር በእውነተኛው አምላክ ፊት ምግብ ለመብላት መጡ። +13 በማግስቱም ሙሴ እንደተለመደው ሕዝቡን በዳኝነት ለማገልገል ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ከጠዋት አንስቶ እስከ ማታ ድረስ እየመጣ በሙሴ ፊት ይቆም ነበር። +14 የሙሴ አማትም ሙሴ ለሕዝቡ የሚያደርገውን ሁሉ ባየ ጊዜ “ይህ ለሕዝቡ እያደረግክ ያለኸው ነገር ምንድን ነው? አንተ ብቻህን ለመዳኘት የምትቀመጠውና ይህ ሁሉ ሕዝብ ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ ፊትህ የሚቆመው ለምንድን ነው?” አለው። +15 ሙሴም አማቱን እንዲህ አለው፦ “ምክንያቱም ሕዝቡ አምላክን ለመጠየቅ ያለማቋረጥ ወደ እኔ ይመጣል። +16 አንድ ጉዳይ በሚነሳበት ጊዜ ጉዳዩ ወደ እኔ ይቀርባል፤ እኔ ደግሞ ባለጉዳዮቹን እዳኛለሁ፤ እንዲሁም የእውነተኛውን አምላክ ውሳኔዎችና ሕጎች አሳውቃለሁ።”+ +17 በዚህ ጊዜ የሙሴ አማት እንዲህ አለው፦ “እያደረግክ ያለኸው ነገር መልካም አይደለም። +18 ይህ ሥራ ለአንተ ከባድ ሸክም ስለሚሆን አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያለው ይህ ሕዝብ መድከማች��� አይቀርም፤ ደግሞም ብቻህን ልትሸከመው አትችልም። +19 እንግዲህ አሁን የምልህን ስማ። አንድ ነገር ልምከርህ፤ አምላክም ከአንተ ጋር ይሆናል።+ አንተ በእውነተኛው አምላክ ፊት የሕዝቡ ተወካይ ሆነህ ታገለግላለህ፤+ ጉዳያቸውንም ወደ እውነተኛው አምላክ ታቀርባለህ።+ +20 ሥርዓቶቹና ሕጎቹ ምን እንደሆኑ በመንገር ማሳሰቢያ ትሰጣቸዋለህ፤+ እንዲሁም የሚሄዱበትን መንገድና የሚያከናውኑትን ነገር ታሳውቃቸዋለህ። +21 ሆኖም ከመላው ሕዝብ መካከል አምላክን የሚፈሩትንና ብቃት ያላቸውን+ እንዲሁም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የማይፈልጉትንና እምነት የሚጣልባቸውን ሰዎች+ ምረጥ፤ እነዚህንም የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች አድርገህ በሕዝቡ ላይ ሹማቸው።+ +22 እነሱም የተለያዩ ጉዳዮች በሚነሱበት ጊዜ* ሕዝቡን ይዳኙ፤ ከበድ ያሉ ጉዳዮች ሲያጋጥሟቸው ወደ አንተ ያምጡ፤+ ቀለል ያሉ ጉዳዮችን ግን ራሳቸው ይዳኙ። ሸክሙን እንዲጋሩህ በማድረግ በአንተ ላይ ያለውን ጫና አቅልል።+ +23 ይህን ነገር ከአምላክ እንደተቀበልከው ትእዛዝ አድርገህ ብትፈጽም ውጥረቱ ይቀንስልሃል፤ እያንዳንዱም ሰው ተደስቶ ወደ ቤቱ ይሄዳል።” +24 ሙሴም ወዲያውኑ አማቱን በመስማት ያለውን ሁሉ አደረገ። +25 ሙሴም ከመላው እስራኤል ብቃት ያላቸውን ወንዶች መርጦ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች አድርጎ በሕዝቡ ላይ ሾማቸው። +26 በመሆኑም እነዚህ ሰዎች የተለያዩ ጉዳዮች በሚነሱበት ጊዜ ሕዝቡን ይዳኙ ነበር። ከበድ ያለ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው ወደ ሙሴ ያመጡ+ የነበረ ሲሆን ቀለል ያሉ ጉዳዮችን ግን ራሳቸው ይዳኙ ነበር። +27 ከዚያም ሙሴ አማቱን ሸኘው፤+ እሱም ወደ አገሩ ሄደ። +23 “የሐሰት ወሬ አትንዛ።*+ ተንኮል የሚሸርብ ምሥክር በመሆን ከክፉ ሰው ጋር አትተባበር።+ +2 ብዙኃኑን ተከትለህ ክፉ ነገር አታድርግ፤ ከብዙኃኑ ጋር ለመስማማት ስትል የተዛባ* ምሥክርነት በመስጠት ፍትሕን አታጣም። +3 ችግረኛው ሙግት ሲኖረው አታድላለት።+ +4 “የጠላትህ በሬ ወይም አህያ ሲባዝን ብታገኘው ወደ እሱ ልትመልሰው ይገባል።+ +5 የሚጠላህ ሰው አህያ ጭነቱ ከብዶት ወድቆ ብታይ ዝም ብለህ አትለፈው። ከዚህ ይልቅ ጭነቱን ከእንስሳው ላይ ለማውረድ እርዳው።+ +6 “በመካከልህ ያለ ድሃ ሙግት ሲኖረው ፍርድ አታጣምበት።+ +7 “ከሐሰት ክስ* ራቅ፤ እኔ ክፉውን ሰው ጻድቅ እንደሆነ አድርጌ ስለማልቆጥር*+ ንጹሑንና ጻድቁን ሰው አትግደል። +8 “ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ አጥርተው የሚያዩ ሰዎችን ዓይን ያሳውራል፤ እንዲሁም የጻድቅ ሰዎችን ቃል ሊያዛባ ይችላል።+ +9 “የባዕድ አገር ሰውን አትጨቁን። እናንተ ራሳችሁ በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ስለነበራችሁ የባዕድ አገር ሰው መሆን ምን ስሜት እንደሚያሳድር* ታውቃላችሁ።+ +10 “ለስድስት ዓመት መሬትህ ላይ ዘር ዝራ፤ አዝመራውንም ሰብስብ።+ +11 በሰባተኛው ዓመት ግን መሬትህን አትረሰው፤ እንዲሁ ተወው። በሕዝብህ መካከል ያሉ ድሆች ከዚያ ይበላሉ፤ ከእነሱ የተረፈውንም የዱር አራዊት ይበሉታል። በወይን እርሻህም ሆነ በወይራ ዛፍ እርሻህ እንደዚሁ ታደርጋለህ። +12 “ለስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ሆኖም በሬህና አህያህ እንዲያርፉ እንዲሁም የሴት ባሪያህ ልጅና የባዕድ አገሩ ሰው ጉልበታቸውን እንዲያድሱ በሰባተኛው ቀን ሥራ አትሥራ።+ +13 “የነገርኳችሁን ነገሮች በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽሙ፤+ እንዲሁም የሌሎች አማልክትን ስም አታንሱ፤ እንዲህ ዓይነቱ ነገር ከአፍህ ሲወጣ ሊሰማ አይገባም።+ +14 “በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓል ታከብርልኛለህ።+ +15 የቂጣን በዓል ታከብራለህ።+ በአቢብ* ���ር+ በተወሰነው ጊዜ፣ ባዘዝኩህ መሠረት ለሰባት ቀናት ቂጣ ትበላለህ፤ ምክንያቱም ከግብፅ የወጣኸው በዚህ ጊዜ ነው። ማንም ባዶ እጁን ፊቴ አይቅረብ።+ +16 በተጨማሪም በእርሻህ ላይ በዘራኸው መጀመሪያ በሚደርሰው የድካምህ ፍሬ የመከርን በዓል* አክብር፤+ ከእርሻህ ላይ የድካምህን ፍሬ በምትሰበስብበት በዓመቱ ማብቂያ ላይ የአዝመራ መክተቻን በዓል* አክብር።+ +17 የአንተ የሆኑ ሰዎች* ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእውነተኛው ጌታ በይሖዋ ፊት ይቅረቡ።+ +18 “የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ከገባበት ከማንኛውም ነገር ጋር አብረህ አታቅርብ። በበዓሎቼም ላይ የሚቀርቡት የስብ መሥዋዕቶች እስከ ጠዋት ድረስ ማደር የለባቸውም። +19 “በምድርህ ላይ የሚገኘውን መጀመሪያ የደረሰውን ምርጥ ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አምጣ።+ “የፍየል ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።+ +20 “በመንገድ ላይ እንዲጠብቅህና ወዳዘጋጀሁት ስፍራ እንዲያመጣህ በፊትህ መልአክ እልካለሁ።+ +21 የሚልህን ስማ፤ ቃሉንም ታዘዝ። መተላለፋችሁን ይቅር ስለማይል+ በእሱ ላይ አታምፁ፤ ምክንያቱም እሱ ስሜን ተሸክሟል። +22 ይሁን እንጂ ቃሉን በጥንቃቄ ብትታዘዝና የምልህን ሁሉ ብታደርግ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ። +23 ምክንያቱም መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ እንዲሁም ወደ አሞራውያን፣ ሂታውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ከነአናውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ያመጣሃል፤ እኔም ጠራርጌ አጠፋቸዋለሁ።+ +24 ለአማልክታቸው አትስገድ፤ ወይም ተታለህ እነሱን አታገልግል፤ የሚያደርጉትን ነገር አታድርግ።+ ከዚህ ይልቅ አውድማቸው፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውንም ሰባብር።+ +25 አምላካችሁን ይሖዋን አገልግሉ፤+ እሱም ምግብህንና ውኃህን ይባርክልሃል።+ እኔም ከመካከልህ በሽታን አስወግዳለሁ።+ +26 በምድርህ ላይ የሚኖሩ ሴቶች አያስወርዳቸውም ወይም መሃን አይሆኑም፤+ ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ። +27 “አንተ ከመድረስህ በፊት ስለ እኔ ሰምተው ይፈራሉ፤+ የምታገኛቸውም ሕዝቦች ሁሉ ግራ እንዲጋቡ አደርጋለሁ። ጠላቶችህም ሁሉ ድል ተመተው ከፊትህ እንዲሸሹ* አደርጋለሁ።+ +28 ከአንተ አስቀድሜ ጭንቀት* እልካለሁ፤+ ሂዋውያንን፣ ከነአናውያንንና ሂታውያንን ከፊትህ አባሮ ያስወጣቸዋል።+ +29 ምድሩ ባድማ እንዳይሆንና የዱር አራዊት በዝተው እንዳያስቸግሩህ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፊትህ አባርሬ አላስወጣቸውም።+ +30 ቁጥርህ እስኪበዛና ምድሩን እስክትቆጣጠር ድረስ ጥቂት በጥቂት ከፊትህ አባርሬ አስወጣቸዋለሁ።+ +31 “ወሰንህንም ከቀይ ባሕር አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ባሕር እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ አደርገዋለሁ።+ ምክንያቱም የምድሩን ነዋሪዎች በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ አንተም ከፊትህ አባረህ ታስወጣቸዋለህ።+ +32 ከእነሱም ሆነ ከአማልክታቸው ጋር ቃል ኪዳን መግባት የለብህም።+ +33 በእኔ ላይ ኃጢአት እንድትሠራ እንዳያደርጉህ በምድርህ ላይ መኖር የለባቸውም። አማልክታቸውን ብታገለግል ወጥመድ ይሆንብሃል።”+ +34 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጥረብ፤+ እኔም በጽላቶቹ ላይ አንተ በሰበርካቸው+ በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ።+ +2 አንተም በጠዋት ወደ ሲና ተራራ ወጥተህ በዚያ በተራራው አናት ላይ በፊቴ ስለምትቆም በጠዋት ለመሄድ ተዘጋጅ።+ +3 ሆኖም ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይውጣ፤ ደግሞም በተራራው ላይ በየትኛውም ቦታ ሌላ ማንም ሰው አይታይ። ሌላው ቀርቶ በጎችም ሆኑ ከብቶች እንኳ በተራራው ፊት ለፊት አይሰማሩ።”+ +4 በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት የመ���መሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ከጠረበ በኋላ በጠዋት ተነስቶ ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ይዞ ነበር። +5 ከዚያም ይሖዋ በደመና ውስጥ ወርዶ+ በዚያ ከእሱ ጋር ሆነ፤ ይሖዋ የተባለውንም ስሙን አወጀ።+ +6 ይሖዋም በፊቱ እያለፈ እንዲህ ሲል አወጀ፦ “ይሖዋ፣ ይሖዋ፣ መሐሪና+ ሩኅሩኅ*+ የሆነ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየ፣+ ታማኝ ፍቅሩና*+ እውነቱ*+ እጅግ ብዙ የሆነ፣ +7 ታማኝ ፍቅርን ለሺዎች የሚያሳይ፣+ ስህተትን፣ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል፣+ ጥፋተኛውን ግን በምንም ዓይነት ሳይቀጣ የማያልፍ+ እንዲሁም አባቶች ለሠሩት ስህተት በልጆች፣ በልጅ ልጆች፣ በሦስተኛና በአራተኛ ትውልድ ላይ ቅጣትን የሚያመጣ።”+ +8 ሙሴም ወዲያውኑ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። +9 ከዚያም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ ይሖዋ፣ እኛ ግትር* ሕዝብ ብንሆንም+ በመካከላችን ሆነህ አብረኸን ሂድ፤+ ደግሞም ስህተታችንንና ኃጢአታችንን ይቅር በል፤+ እንደ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።” +10 እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኔ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፦ በመላው ምድርም ሆነ በብሔራት ሁሉ መካከል ፈጽሞ ተደርገው* የማያውቁ ድንቅ ነገሮችን በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ፤+ ለአንተ ስል የማደርገው ነገር የሚያስፈራ ስለሆነ በመካከላቸው የምትኖረው ሕዝቦች ሁሉ የይሖዋን ሥራ ያ +11 “እኔ ዛሬ የማዝህን ነገር ልብ በል።+ እኔም አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ሂታውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ አስወጣቸዋለሁ።+ +12 በምትሄድበት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤+ አለዚያ ወጥመድ ይሆንብሃል።+ +13 ከዚህ ይልቅ መሠዊያዎቻቸውን ታፈራርሳላችሁ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ትሰባብራላችሁ፤ እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ትቆራርጣላችሁ።+ +14 ይሖዋ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ* አምላክ በመሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ ለሌላ አምላክ አትስገድ።+ አዎ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።+ +15 ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም እነሱ አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር በሚፈጽሙበትና ለአማልክታቸው በሚሠዉበት+ ጊዜ ከመካከላቸው አንዱ አንተን መጋበዙ አይቀርም፣ አንተም ካቀረበው መሥዋዕት ትበላለህ።+ +16 ከዚያም ሴቶች ልጆቻቸውን ከወንዶች ልጆችህ ጋር ታጋባለህ፤+ ሴቶች ልጆቻቸውም አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር መፈጸማቸው እንዲሁም ወንዶች ልጆችህ የእነሱን አማልክት በማምለክ ምንዝር እንዲፈጽሙ ማድረጋቸው አይቀርም።+ +17 “ከቀለጠ ብረት አማልክት አትሥራ።+ +18 “የቂጣን በዓል ታከብራለህ።+ ልክ ባዘዝኩህ መሠረት ቂጣ ትበላለህ፤ ከግብፅ የወጣኸው በአቢብ* ወር+ ስለሆነ በአቢብ ወር በተወሰነው ጊዜ ላይ ለሰባት ቀን ይህን ታደርጋለህ። +19 “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* የእኔ ነው፤+ ደግሞም የመንጋህ በኩር ሁሉ፣ በኩር የሆነ በሬም ሆነ ተባዕት በግ የእኔ ነው።+ +20 የአህያን በኩር በበግ ዋጀው። የማትዋጀው ከሆነ ግን አንገቱን ስበረው። ከወንዶች ልጆችህ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ ትዋጀዋለህ።+ ማንም ባዶ እጁን ፊቴ አይቅረብ። +21 “ስድስት ቀን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ።*+ በሚታረስበትም ሆነ አዝመራ በሚሰበሰብበት ወቅትም እንኳ ታርፋለህ። +22 “የሳምንታት በዓልህን መጀመሪያ በደረሰው የስንዴ በኩር አክብር፤ የአዝመራ መክተቻን በዓልም* በዓመቱ ማብቂያ ላይ አክብር።+ +23 “የአንተ የሆነ ሰው* ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ የእስራኤል አምላክ በሆነው በእውነተኛው ጌታ በይሖዋ ፊት ይቅረ��።+ +24 ብሔራትን ከፊትህ አስወጣለሁና፤+ ክልልህንም ሰፊ አደርገዋለሁ፤ የአምላክህን የይሖዋን ፊት ለማየት በዓመት ሦስቴ በምትወጣበት ጊዜ ማንም ምድርህን አይመኝም። +25 “የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ከገባበት ከማንኛውም ነገር ጋር አድርገህ አታቅርብ።+ የፋሲካ በዓል መሥዋዕት እስከ ጠዋት ድረስ መቆየት የለበትም።+ +26 “መጀመሪያ የደረሰውን የአፈርህን ምርጥ ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አምጣ።+ “የፍየልን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።”+ +27 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ከአንተም ሆነ ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን የምገባው+ በእነዚህ ቃላት መሠረት ስለሆነ እነዚህን ቃላት ጻፍ”+ አለው። +28 እሱም በዚያ ከይሖዋ ጋር 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆየ። እህል አልቀመሰም፤ ውኃም አልጠጣም።+ እሱም* በጽላቶቹ ላይ የቃል ኪዳኑን ቃላት ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት* ጻፈ።+ +29 ከዚያም ሙሴ ከሲና ተራራ ወረደ፤ ሁለቱንም የምሥክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ነበር።+ ከአምላክ ጋር ሲነጋገር ስለቆየ ከተራራው በወረደበት ጊዜ ፊቱ እንደሚያንጸባርቅ አላወቀም ነበር። +30 አሮንና እስራኤላውያን ሁሉ ሙሴን ሲያዩት ፊቱ እንደሚያንጸባርቅ አስተዋሉ፤ ወደ እሱ ለመቅረብም ፈሩ።+ +31 ሙሴ ግን ጠራቸው፤ በመሆኑም አሮንና የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ ወደ እሱ መጡ፤ ሙሴም አነጋገራቸው። +32 ከዚያም እስራኤላውያን በሙሉ ወደ እሱ ቀረቡ፤ እሱም ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ የሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ ሰጣቸው።+ +33 ሙሴም ከእነሱ ጋር ተነጋግሮ ሲጨርስ ፊቱን በመሸፈኛ ይሸፍን ነበር።+ +34 ሙሴ፣ ይሖዋ ፊት ቀርቦ ከእሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ግን ከዚያ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያነሳ ነበር።+ ከዚያም ወጥቶ የተቀበለውን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን ይነግራቸው ነበር።+ +35 እስራኤላውያንም የሙሴ ፊት እንደሚያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ ከዚያም ሙሴ አምላክን* ለማነጋገር ወደ ውስጥ እስከሚገባበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን መልሶ ፊቱ ላይ አደረገው።+ +19 እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በሦስተኛው ወር በዚያው ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። +2 ከረፊዲም+ ተነስተው ወደ ሲና ምድረ በዳ በመምጣት በምድረ በዳው ሰፈሩ። እስራኤላውያን በዚያ ከተራራው ፊት ለፊት ሰፈሩ።+ +3 ከዚያም ሙሴ ወደ እውነተኛው አምላክ ወጣ፤ ይሖዋም ከተራራው ጠርቶት እንዲህ አለው፦+ “ለያዕቆብ ቤት የምትለው፣ ለእስራኤላውያንም የምትነግረው ይህ ነው፦ +4 ‘እናንተን በንስር ክንፎች ተሸክሜ+ ወደ እኔ ለማምጣት ስል በግብፃውያን ላይ ያደረግኩትን ሁሉ እናንተው ራሳችሁ አይታችኋል።+ +5 አሁንም ቃሌን በጥብቅ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ መላው ምድር የእኔ ስለሆነ+ እናንተ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተመረጣችሁ ልዩ ንብረቶቼ* ትሆናላችሁ።+ +6 እናንተ ለእኔ የካህናት መንግሥትና ቅዱስ ብሔር ትሆናላችሁ።’+ ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።” +7 በመሆኑም ሙሴ ሄዶ የሕዝቡን ሽማግሌዎች ጠራ፤ ይሖዋ ያዘዘውንም ይህን ቃል ነገራቸው።+ +8 ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ በአንድ ድምፅ “ይሖዋ የተናገረውን ሁሉ ለመፈጸም ፈቃደኞች ነን”+ ብለው መለሱ። ሙሴም ወዲያውኑ የሕዝቡን ምላሽ ይዞ ወደ ይሖዋ ሄደ። +9 ይሖዋም ሙሴን “ሕዝቡ ከአንተ ጋር ስነጋገር እንዲሰማና ምንጊዜም በአንተ ላይ እምነት እንዲጥል በጥቁር ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ” አለው። ከዚያም ሙሴ የሕዝቡን ቃል ለይሖዋ ተናገረ። +10 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ሕዝቡ ሄደህ ዛሬና ነገ ቀድሳቸው፤ እነሱም ልብሳቸውን ይጠቡ። +11 ለሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ ምክንያቱም በሦስተኛው ቀን ይሖዋ ሕዝቡ ሁሉ እያዩ በሲና ተራራ ላይ ይወርዳል። +12 በተራራው ዙሪያ ለሕዝቡ ወሰን አብጅ፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ፣ ድንበሩንም እንኳ እንዳትነኩ ተጠንቀቁ። ተራራውን የሚነካ ማንኛውም ሰው ይገደላል። +13 ይህን ሰው ማንም እንዳይነካው፤ ከዚህ ይልቅ በድንጋይ ይወገር ወይም ደግሞ ይወጋ።* እንስሳም ሆነ ሰው በሕይወት እንዲኖር አይተውም።’+ ሆኖም የቀንደ መለከቱ ድምፅ+ በሚሰማበት ጊዜ ወደ ተራራው ሊወጡ ይችላሉ።” +14 ከዚያም ሙሴ ከተራራው ወርዶ ወደ ሕዝቡ ሄደ፤ ሕዝቡንም ይቀድስ ጀመር፤ እነሱም ልብሳቸውን አጠቡ።+ +15 ሕዝቡንም “ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ። የፆታ ግንኙነት ከመፈጸምም ተቆጠቡ”* አላቸው። +16 በሦስተኛውም ቀን ጠዋት ነጎድጓድ መሰማትና መብረቅ መታየት ጀመረ፤ በተራራውም ላይ ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር፤+ ከፍተኛ የቀንደ መለከት ድምፅም ተሰማ፤ በሰፈሩም ውስጥ ያለው ሕዝብ በሙሉ በፍርሃት ተንቀጠቀጠ።+ +17 በዚህ ጊዜ ሙሴ ከእውነተኛው አምላክ ጋር እንዲገናኙ ሕዝቡን ከሰፈሩ ይዞ ወጣ፤ እነሱም በተራራው ግርጌ ቆሙ። +18 የሲና ተራራ ይሖዋ በእሳት ስለወረደበት ዙሪያውን ጨሰ፤+ ጭሱም እንደ እቶን ጭስ እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ በኃይል ተናወጠ።+ +19 የቀንደ መለከቱም ድምፅ ይበልጥ እየጨመረ ሲመጣ ሙሴ ተናገረ፤ የእውነተኛውም አምላክ ድምፅ መለሰለት። +20 በመሆኑም ይሖዋ በሲና ተራራ አናት ላይ ወረደ። ከዚያም ይሖዋ ሙሴን ወደ ተራራው አናት ጠራው፤ ሙሴም ወጣ።+ +21 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ሂድ ውረድ፤ ሕዝቡ ይሖዋን ለማየት ሲሉ አልፈው ለመምጣት እንዳይሞክሩ አስጠንቅቃቸው፤ ካልሆነ ግን ብዙዎቹ ለጥፋት ይዳረጋሉ። +22 ዘወትር ወደ ይሖዋ የሚቀርቡት ካህናትም ይሖዋ እንዳይቀስፋቸው ራሳቸውን ይቀድሱ።”+ +23 ከዚያም ሙሴ ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “አንተ ‘በተራራው ዙሪያ ወሰን አድርግ፤ እሱንም ቀድሰው’ በማለት ስላስጠነቀቅከን ሕዝቡ ወደ ሲና ተራራ መቅረብ አይችልም።”+ +24 ሆኖም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ሂድ፣ ውረድና ከአሮን ጋር ተመልሰህ ወደዚህ ውጣ፤ ነገር ግን ካህናቱም ሆኑ ሕዝቡ አልፈው ወደ ይሖዋ ለመምጣት እንዳይሞክሩና እንዳይቀስፋቸው ከልክላቸው።”+ +25 ስለሆነም ሙሴ ወደ ሕዝቡ ወርዶ ነገራቸው። +20 ከዚያም አምላክ ይህን ቃል ሁሉ ተናገረ፦+ +2 “ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ።+ +3 ከእኔ በቀር* ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።+ +4 “በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን ቅርጽ ወይም የተሠራን ምስል ለራስህ አታድርግ።+ +5 አትስገድላቸው፤ ተታለህም እነሱን አታገልግል፤+ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና+ በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤ +6 ሆኖም ለሚወዱኝና ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ታማኝ ፍቅር የማሳይ አምላክ ነኝ።+ +7 “የአምላክህን የይሖዋን ስም በከንቱ አታንሳ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ስሙን በከንቱ የሚያነሳውን ሳይቀጣ አይተወውም።+ +8 “የሰንበትን ቀን ቅዱስ አድርገህ መጠበቅ እንዳለብህ አትርሳ።+ +9 ሥራህንና የምታከናውናቸውን ነገሮች በሙሉ በስድስት ቀን ሠርተህ አጠናቅ፤+ +10 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ የቤት እንስሳህም ሆነ በሰፈርህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ።+ +11 ምክንያቱም ይሖዋ ሰማያትን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ ሠርቶ ካጠናቀቀ በኋላ በሰባተኛው ቀን ማረፍ ጀምሯል።+ ይሖዋ የሰንበትን ቀን የባረከውና የቀደሰው ለዚህ ነው። +12 “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም+ አባትህንና እናትህን አክብር።+ +13 “አትግደል።*+ +14 “አታመንዝር።+ +15 “አትስረቅ።+ +16 “በባልንጀራህ ላይ ምሥክር ሆነህ ስትቀርብ በሐሰት አትመሥክር።+ +17 “የባልንጀራህን ቤት አትመኝ። የባልንጀራህን ሚስት፣+ ወንድ ባሪያውን፣ ሴት ባሪያውን፣ በሬውን ወይም አህያውን አሊያም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።”+ +18 ሕዝቡም ሁሉ የነጎድጓዱንና የቀንደ መለከቱን ድምፅ ሰሙ፤ እንዲሁም የመብረቁን ብልጭታና የተራራውን ጭስ ተመለከቱ፤ ይህም በፍርሃት እንዲንቀጠቀጡና ርቀው እንዲቆሙ አደረጋቸው።+ +19 በመሆኑም ሙሴን “አንተ አነጋግረን፤ እኛም እናዳምጥሃለን፤ ሆኖም እንዳንሞት ስለምንፈራ አምላክ አያነጋግረን” አሉት።+ +20 ሙሴም ሕዝቡን “አትፍሩ፤ ምክንያቱም እውነተኛው አምላክ የመጣው እናንተን ለመፈተን+ ይኸውም ዘወትር እሱን በመፍራት ኃጢአት ከመሥራት እንድትቆጠቡ ለማድረግ ነው”+ አላቸው። +21 ሕዝቡም እዚያው ርቆ ባለበት ቆመ፤ ሙሴ ግን እውነተኛው አምላክ ወዳለበት ጥቁር ደመና ቀረበ።+ +22 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከሰማይ ሆኜ እንዳነጋገርኳችሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል።+ +23 እኔን የሚቀናቀኑ ከብር የተሠሩ አማልክት አይኑሯችሁ፤ ከወርቅ የተሠሩ አማልክትም አይኑሯችሁ።+ +24 ከጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፤ በእሱም ላይ የሚቃጠሉ መባዎችህን፣ የኅብረት መሥዋዕቶችህን፣* መንጎችህንና ከብቶችህን ሠዋ። ስሜ እንዲታወስ በማደርግበት ቦታ ሁሉ+ ወደ አንተ እመጣለሁ፣ ደግሞም እባርክሃለሁ። +25 ከድንጋይ መሠዊያ የምትሠራልኝ ከሆነ በተጠረቡ ድንጋዮች አትሥራው።+ ምክንያቱም ድንጋዮቹን በመሮህ ከጠረብካቸው ታረክሳቸዋለህ። +26 ኀፍረተ ሥጋህ* በእሱ ላይ እንዳይጋለጥ ወደ መሠዊያዬ በደረጃ አትውጣ።’ +3 ሙሴ የምድያም ካህን የሆነው የአማቱ የዮቶር+ መንጋ እረኛ ሆነ። እሱም መንጋውን እየመራ ወደ ምድረ በዳው ምዕራባዊ ክፍል ከተጓዘ በኋላ በመጨረሻ ወደ እውነተኛው አምላክ ተራራ ወደ ኮሬብ+ ደረሰ። +2 ከዚያም የይሖዋ መልአክ በቁጥቋጦ መሃል በሚነድ የእሳት ነበልባል ውስጥ ተገለጠለት።+ እሱም ትኩር ብሎ ሲመለከት ቁጥቋጦው በእሳት ቢያያዝም አለመቃጠሉን አስተዋለ። +3 ስለዚህ ሙሴ “ይህ እንግዳ ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅና ቁጥቋጦው የማይቃጠለው ለምን እንደሆነ ለማየት እስቲ ቀረብ ልበል” አለ። +4 ይሖዋም ሙሴ ሁኔታውን ለማየት ቀረብ ማለቱን ሲመለከት ከቁጥቋጦው መሃል “ሙሴ! ሙሴ!” ሲል ጠራው፤ እሱም “አቤት” አለ። +5 ከዚያም አምላክ “ከዚህ በላይ እንዳትቀርብ። የቆምክበት ስፍራ ቅዱስ መሬት ስለሆነ ጫማህን አውልቅ” አለው። +6 እሱም በመቀጠል “እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣+ የይስሐቅ አምላክና+ የያዕቆብ አምላክ+ ነኝ” አለው። በዚህ ጊዜ ሙሴ እውነተኛውን አምላክ ለማየት ስለፈራ ፊቱን ከለለ። +7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “በግብፅ የሚኖረውን የሕዝቤን መከራ በእርግጥ አይቻለሁ፤ አስገድደው በሚያሠሯቸው ሰዎች የተነሳ የሚያሰሙትን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ እየደረሰባቸው ያለውንም ሥቃይ በሚገባ አውቃለሁ።+ +8 እኔም ከግብፃውያን እጅ ልታደጋቸው+ እንዲሁም ከዚያ ምድር አውጥቼ ወደ ከነአናውያን፣ ወደ ሂታውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፈሪዛውያን፣ ወደ ሂዋውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ግዛት ይኸውም ወተትና ማር ወደምታፈሰው መልካምና ሰፊ ምድር+ ላስ���ባቸው እወርዳለሁ።+ +9 እነሆ የእስራኤል ሕዝብ የሚያሰማው ጩኸት ወደ እኔ ደርሷል፤ ግብፃውያኑ እነሱን በመጨቆን እያደረሱባቸው ያለውን በደል ተመልክቻለሁ።+ +10 ስለዚህ አሁን ና፤ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ፤ አንተም ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ታወጣለህ።”+ +11 ይሁን እንጂ ሙሴ እውነተኛውን አምላክ “ወደ ፈርዖን የምሄደውና እስራኤላውያንን ከግብፅ የማወጣው ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ?” አለው። +12 እሱም በዚህ ጊዜ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤+ የላክሁህ እኔ ለመሆኔም ምልክቱ ይህ ነው፦ ሕዝቡን ከግብፅ ካወጣሃቸው በኋላ እውነተኛውን አምላክ በዚህ ተራራ ላይ ታገለግላላችሁ”*+ አለው። +13 ሆኖም ሙሴ እውነተኛውን አምላክ “ወደ እስራኤላውያን ሄጄ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ ስላቸው እነሱ ደግሞ ‘ስሙ ማን ነው?’+ ብለው ቢጠይቁኝ ምን ልበላቸው?” አለው። +14 በዚህ ጊዜ አምላክ ሙሴን “መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ”*+ አለው። በመቀጠልም “እስራኤላውያንን ‘“እሆናለሁ” ወደ እናንተ ልኮኛል’+ በላቸው” አለው። +15 ከዚያም አምላክ ሙሴን በድጋሚ እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣+ የይስሐቅ አምላክና+ የያዕቆብ አምላክ+ የሆነው ይሖዋ ወደ እናንተ ልኮኛል።’ ይህ ለዘላለም ስሜ ነው፤+ ከትውልድ እስከ ትውልድ የምታወሰውም በዚህ ነው። +16 አሁን ሄደህ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ የሆነው ይሖዋ ተገልጦልኝ እንዲህ አለኝ፦ “እናንተንም ሆነ ግብፅ ውስጥ እየደረሰባችሁ ያለውን ነገር በእርግጥ ተመልክቻለሁ።+ +17 በመሆኑም እንዲህ አልኩ፦ ግብፃውያን ከሚያደርሱባችሁ መከራ አውጥቼ+ ከነአናውያን፣ ሂታውያን፣ አሞራውያን፣+ ፈሪዛውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን+ ወደሚኖሩባት ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ አስገባችኋለሁ።”’ +18 “እነሱም በእርግጥ ቃልህን ይሰማሉ፤+ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎችም ወደ ግብፁ ንጉሥ ሄዳችሁ እንዲህ በሉት፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ+ አነጋግሮን ነበር። በመሆኑም እባክህ ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳ እንድንጓዝ ፍቀድልን።’+ +19 ይሁንና የግብፁ ንጉሥ ኃያል የሆነ ክንድ ካላስገደደው በስተቀር እንድትሄዱ እንደማይፈቅድላችሁ እኔ ራሴ በሚገባ አውቃለሁ።+ +20 በመሆኑም እጄን እዘረጋለሁ፤ ግብፅንም በመካከሏ በምፈጽማቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ እመታለሁ፤ ከዚያ በኋላ ይለቃችኋል።+ +21 እኔም ለዚህ ሕዝብ በግብፃውያን ፊት ሞገስ እሰጠዋለሁ፤ በምትወጡበትም ጊዜ በምንም ዓይነት ባዶ እጃችሁን አትሄዱም።+ +22 እያንዳንዷ ሴት ከጎረቤቷና ቤቷ ካረፈችው ሴት የብርና የወርቅ ዕቃዎችን እንዲሁም ልብሶችን ትጠይቅ፤ እነዚህንም ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻችሁ ታደርጉላቸዋላችሁ፤ ግብፃውያኑንም ትበዘብዛላችሁ።”+ +24 ሙሴንም እንዲህ አለው፦ “አንተ፣ አሮን፣ ናዳብ፣ አቢሁና+ 70ዎቹ የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ይሖዋ ውጡ፤ ከሩቅ ሆናችሁም ስገዱ። +2 ሙሴ ብቻውን ወደ ይሖዋ ይቅረብ፤ ሌሎቹ ግን መቅረብ የለባቸውም፤ ሕዝቡም ከእሱ ጋር መውጣት የለበትም።”+ +3 ከዚያም ሙሴ መጥቶ የይሖዋን ቃል ሁሉ እንዲሁም ድንጋጌዎቹን በሙሉ ለሕዝቡ ነገራቸው፤+ ሕዝቡም ሁሉ “ይሖዋ የተናገረውን ቃል በሙሉ ለመፈጸም ፈቃደኞች ነን”+ ሲሉ በአንድ ድምፅ መለሱ። +4 ስለሆነም ሙሴ የይሖዋን ቃል ሁሉ በጽሑፍ አሰፈረ።+ በማለዳም ተነስቶ በተራራው ግርጌ መሠዊያና 12ቱን የእስራኤል ነገዶች የሚወክሉ 12 ዓምዶች ሠራ። +5 ከዚያም ወጣት እስራኤላውያን ወንዶችን ላከ፤ እነሱም የሚቃጠሉ መባዎችን አቀረቡ፤ እንዲሁም በሬዎችን የኅብረት መሥዋዕቶች+ አድርገው ለይሖዋ ሠዉ። +6 ሙሴም ከደሙ ግማሹን ወስዶ በሳህኖች ውስጥ አስቀመጠው፤ ግማሹን ደም ደግሞ በመሠዊያው ላይ ረጨው። +7 ከዚያም የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለሕዝቡ አነበበ።+ ሕዝቡም “ይሖዋ የተናገረውን ሁሉ ለመፈጸምና ለመታዘዝ ፈቃደኞች ነን” አሉ።+ +8 በመሆኑም ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው፤+ እንዲህም አለ፦ “በእነዚህ ቃላት መሠረት ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ደም ይህ ነው።”+ +9 ሙሴ፣ አሮን፣ ናዳብ፣ አቢሁና 70ዎቹ የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ላይ ወጡ፤ +10 የእስራኤልንም አምላክ አዩ።+ ከእግሩም ሥር እንደ ሰማይ የጠራ የሰንፔር ንጣፍ የሚመስል ነገር ነበር።+ +11 እሱም በእስራኤል አለቆች+ ላይ ጉዳት አላደረሰባቸውም፤ እነሱም እውነተኛውን አምላክ በራእይ ተመለከቱ፤ በሉ፣ ጠጡም። +12 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣና በዚያ ቆይ። ለሕዝቡ መመሪያ እንዲሆን እኔ የጻፍኩትን ሕግና ትእዛዝ የያዙትን የድንጋይ ጽላቶች እሰጥሃለሁ።”+ +13 በመሆኑም ሙሴ ከአገልጋዩ ከኢያሱ+ ጋር ተነስቶ ወደ እውነተኛው አምላክ ተራራ ወጣ።+ +14 ሽማግሌዎቹን ግን እንዲህ አላቸው፦ “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ እዚሁ ጠብቁን።+ አሮንና ሁር+ አብረዋችሁ ናቸው። ሙግት ያለው ሰው ቢኖር እነሱ ፊት መቅረብ ይችላል።”+ +15 ሙሴም ወደ ተራራው ሲወጣ ደመናው ተራራውን ሸፍኖት ነበር።+ +16 የይሖዋም ክብር+ በሲና ተራራ ላይ እንዳረፈ ነበር፤+ ደመናውም ለስድስት ቀናት ተራራውን ሸፍኖት ነበር። በሰባተኛውም ቀን ከደመናው መሃል ሙሴን ጠራው። +17 ሁኔታውን ይከታተሉ ለነበሩት እስራኤላውያን የይሖዋ ክብር በተራራው አናት ላይ እንዳለ የሚባላ እሳት ሆኖ ታያቸው። +18 ከዚያም ሙሴ ወደ ደመናው ገባ፤ ወደ ተራራውም ወጣ።+ ሙሴም በተራራው ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆየ።+ +32 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ላይ ሳይወርድ እንደቆየ አየ።+ በመሆኑም አሮንን ከበው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት ስለማናውቅ በል ተነስተህ ከፊት ከፊታችን የሚሄድ አምላክ ሥራልን።”+ +2 አሮንም “በሚስቶቻችሁ እንዲሁም በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ጆሮዎች ላይ ያሉትን የወርቅ ጉትቻዎች+ አውልቃችሁ አምጡልኝ” አላቸው። +3 በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ በጆሮዎቻቸው ላይ የነበሩትን የወርቅ ጉትቻዎች እያወለቁ ወደ አሮን ያመጡ ጀመር። +4 እሱም ወርቁን ከእነሱ ወስዶ በቅርጽ ማውጫ ቅርጽ አወጣለት፤ የጥጃ ሐውልትም* አድርጎ ሠራው።+ እነሱም “እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው” ይሉ ጀመር።+ +5 አሮንም ይህን ሲያይ በምስሉ ፊት መሠዊያ ሠራ። ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ “ነገ ለይሖዋ የሚከበር በዓል አለ” ሲል ተናገረ። +6 በመሆኑም በማግስቱ በማለዳ ተነስተው የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርቡ ጀመር። ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ። ከዚያም ሊጨፍሩ ተነሱ።+ +7 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብፅ ምድር መርተህ ያወጣኸው ሕዝብህ ምግባረ ብልሹ+ ስለሆነ ሂድ፣ ውረድ። +8 እንዲሄዱበት ካዘዝኳቸው መንገድ+ ፈጥነው ዞር ብለዋል። ለራሳቸውም የጥጃ ሐውልት* ሠርተዋል፤ ለእሱም እየሰገዱና መሥዋዕት እያቀረቡ ‘እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው’ እያሉ ነው።” +9 ይሖዋም በመቀጠል ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ ግትር* መሆኑን ተመልክቻለሁ።+ +10 እንግዲህ አሁን ቁጣዬ እንዲነድባቸውና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ አንተ��� በእነሱ ምትክ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።”+ +11 ሙሴም አምላኩን ይሖዋን ተማጸነ፤+ እንዲህም አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በታላቅ ኃይልና በብርቱ እጅ ከግብፅ ምድር ካወጣሃቸው በኋላ በሕዝብህ ላይ ቁጣህ የሚነደው ለምንድን ነው?+ +12 ግብፃውያንስ ‘ቀድሞውንም ቢሆን መርቶ ያወጣቸው ተንኮል አስቦ ነው። በተራሮች ላይ ሊገድላቸውና ከምድር ገጽ ሊያጠፋቸው ፈልጎ ነው’ ለምን ይበሉ?+ ከሚነደው ቁጣህ ተመለስ፤ በሕዝብህ ላይ ይህን ጥፋት ለማምጣት ያደረግከውን ውሳኔ እስቲ እንደገና አስበው።* +13 ‘ዘራችሁን በሰማያት ላይ እንዳሉት ከዋክብት አበዛዋለሁ፤+ ለዘላለም ርስት አድርጎ እንዲወርሰውም ለዘራችሁ ለመስጠት ያሰብኩትን ይህን ምድር በሙሉ እሰጠዋለሁ’+ በማለት በራስህ የማልክላቸውን አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን አስታውስ።” +14 በመሆኑም ይሖዋ በሕዝቡ ላይ እንደሚያመጣ የተናገረውን ጥፋት እንደገና አሰበበት።*+ +15 ከዚያም ሙሴ ሁለቱን የምሥክር ጽላቶች+ በእጁ እንደያዘ+ ተመልሶ ከተራራው ወረደ። ጽላቶቹም በሁለቱም በኩል ተቀርጾባቸው ነበር፤ በፊትም ሆነ በጀርባ ተጽፎባቸው ነበር። +16 ጽላቶቹ የአምላክ ሥራ ነበሩ፤ በጽላቶቹ ላይ የተቀረጸው ጽሑፍም የአምላክ ጽሑፍ ነበር።+ +17 ኢያሱም ሕዝቡ ይጮኽ ስለነበር ጫጫታውን ሲሰማ ሙሴን “በሰፈሩ ውስጥ የጦርነት ሁካታ ይሰማል” አለው። +18 ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “ይህ ድምፅ የድል መዝሙር አይደለም፤ ይህ ድምፅ በሽንፈት ምክንያት የሚሰማ የለቅሶ ድምፅም አይደለም፤ ይህ የምሰማው ድምፅ የተለየ መዝሙር ድምፅ ነው።” +19 ሙሴም ወደ ሰፈሩ ሲቃረብ ጥጃውንና+ ጭፈራውን አየ፤ በዚህ ጊዜ ቁጣው ነደደ። ጽላቶቹንም ከእጁ ወርውሮ በተራራው ግርጌ ሰባበራቸው።+ +20 የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ሰባብሮም ዱቄት አደረገው፤+ ከዚያም በውኃው ላይ በመበተን እስራኤላውያን እንዲጠጡት አደረገ።+ +21 ሙሴም አሮንን “ይህን ከባድ ኃጢአት ያመጣህበት ይህ ሕዝብ ምን ቢያደርግህ ነው?” አለው። +22 በዚህ ጊዜ አሮን እንዲህ አለ፦ “ጌታዬ አትቆጣ። መቼም ይህ ሕዝብ ወደ ክፋት ያዘነበለ እንደሆነ አንተ ራስህ በሚገባ ታውቃለህ።+ +23 ስለዚህ ‘ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት ስለማናውቅ ከፊት ከፊታችን የሚሄድ አምላክ ሥራልን’ አሉኝ።+ +24 በመሆኑም ‘ወርቅ ያለው ሁሉ አውልቆ ይስጠኝ’ አልኳቸው። ከዚያም ወርቁን እሳቱ ውስጥ ጣልኩት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።” +25 በተቃዋሚዎቻቸው ፊት መሳለቂያ እንዲሆኑ አሮን ሕዝቡን መረን ስለለቀቃቸው ሙሴ ሕዝቡ መረን እንደተለቀቀ አስተዋለ። +26 ከዚያም ሙሴ በሰፈሩ መግቢያ ላይ ቆሞ “ከይሖዋ ጎን የሚቆም ማን ነው? ወደ እኔ ይምጣ!”+ አለ። በዚህ ጊዜ ሌዋውያን በሙሉ በዙሪያው ተሰበሰቡ። +27 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ሰይፋችሁን ታጠቁ፤ ከአንዱ በር ወደ ሌላው በር በመሄድና በሰፈሩ ውስጥ በማለፍ እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን፣ ጎረቤቱንና የቅርብ ጓደኛውን ይግደል።’”+ +"28 ሌዋውያኑም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ። በመሆኑም በዚያ ዕለት 3,000 ገደማ የሚሆኑ ወንዶች ተገደሉ።" +29 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እያንዳንዳችሁ በገዛ ልጃችሁና በገዛ ወንድማችሁ ላይ ስለተነሳችሁ+ ዛሬ ራሳችሁን ለይሖዋ ለዩ፤* እሱም ዛሬ በረከትን ያፈስላችኋል።”+ +30 በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “ከባድ ኃጢአት ሠርታችኋል፤ እንግዲህ አሁን ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ አንድ ነገር ማድረግ እችል እንደሆነ ለማየት ወደ ይሖዋ እወጣለሁ።”+ +31 በመሆኑም ሙሴ ወደ ይሖዋ ተመልሶ እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ ���ፈጸመው ኃጢአት ምንኛ ከባድ ነው! የወርቅ አምላክ ሠርተዋል።+ +32 ሆኖም አሁን ፈቃድህ ከሆነ ኃጢአታቸውን ይቅር በል፤+ ካልሆነ ግን እባክህ እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ ላይ ደምስሰኝ።”+ +33 ይሁንና ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በእኔ ላይ ኃጢአት የሠራውን ሁሉ ከመጽሐፌ ላይ እደመስሰዋለሁ። +34 በል አሁን ሄደህ ሕዝቡን ወደነገርኩህ ስፍራ እየመራህ ውሰዳቸው። እነሆ መልአኬ ከፊት ከፊትህ ይሄዳል፤+ ሕዝቡን በምመረምርበትም ቀን ስለሠሩት ኃጢአት ቅጣት አመጣባቸዋለሁ።” +35 ከዚያም ይሖዋ፣ በሠሩት ጥጃ ይኸውም አሮን በሠራላቸው ጥጃ ምክንያት ሕዝቡን በመቅሰፍት መታ። +7 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አድርጌሃለሁ፤* የገዛ ወንድምህ አሮን ደግሞ የአንተ ነቢይ ይሆናል።+ +2 አንተም የማዝህን ሁሉ ደግመህ ትናገራለህ፤ ወንድምህ አሮንም ለፈርዖን ይነግረዋል፤ እሱም እስራኤላውያን ከምድሩ እንዲወጡ ይለቃቸዋል። +3 እኔ ደግሞ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤+ በግብፅ ምድርም ምልክቶቼንና ተአምራቴን አበዛለሁ።+ +4 ፈርዖን ግን አይሰማችሁም፤ እኔም በግብፅ ምድር ላይ እጄን አሳርፋለሁ፤ ሠራዊቴን ይኸውም ሕዝቤ የሆኑትን እስራኤላውያንን በታላቅ ፍርድ ከግብፅ ምድር አወጣቸዋለሁ።+ +5 በግብፅ ላይ እጄን ስዘረጋና እስራኤላውያንን ከመካከላቸው ሳወጣ ግብፃውያን እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።”+ +6 ሙሴና አሮን ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ልክ እንደተባሉት አደረጉ። +7 ከፈርዖን ጋር በተነጋገሩበት ጊዜ ሙሴ የ80 ዓመት ሰው፣ አሮን ደግሞ የ83 ዓመት ሰው ነበር።+ +8 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +9 “ምናልባት ፈርዖን ‘እስቲ ተአምር አሳዩ’ ቢላችሁ አሮንን ‘በትርህን ወስደህ በፈርዖን ፊት ጣለው’ በለው። በትሩም ትልቅ እባብ ይሆናል።”+ +10 ስለሆነም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው ልክ ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ። አሮንም በትሩን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት ጣለው፤ በትሩም ትልቅ እባብ ሆነ። +11 ይሁንና ፈርዖን ጠቢባኑንና መተተኞቹን ጠራ፤ አስማት የሚሠሩ የግብፅ ካህናትም+ በአስማታቸው* ተመሳሳይ ነገር አደረጉ።+ +12 እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፤ በትሮቹም ትላልቅ እባቦች ሆኑ፤ ይሁን እንጂ የአሮን በትር የእነሱን በትሮች ዋጠ። +13 ያም ሆኖ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤+ ልክ ይሖዋ እንዳለውም ያሉትን ነገር አልሰማቸውም። +14 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የፈርዖን ልብ ደንድኗል።+ እሱም ሕዝቡን ለመልቀቅ እንቢተኛ ሆኗል። +15 በማለዳ ወደ ፈርዖን ሂድ። እሱም ወደ ውኃው ይወርዳል! አንተም እሱን ለማግኘት በአባይ ወንዝ ዳር ቁም፤ ወደ እባብ ተለውጦ የነበረውንም በትር በእጅህ ያዝ።+ +16 እንዲህም በለው፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ ወደ አንተ ልኮኛል፤+ እሱም “በምድረ በዳ እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ” ብሎሃል፤ ይኸው አንተ ግን እስካሁን ድረስ አልታዘዝክም። +17 እንግዲህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በዚህ ታውቃለህ።+ ይኸው በበትሬ በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለውን ውኃ እመታለሁ፤ ውኃውም ወደ ደም ይለወጣል። +18 በአባይ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ይሞታሉ፤ አባይም ይከረፋል፤ ግብፃውያንም ከአባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት አይችሉም።”’” +19 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘የግብፅ ውኃዎች ይኸውም ወንዞቿ፣ የመስኖ ቦዮቿ፣* ረግረጋማ ቦታዎቿና+ የተጠራቀሙት ውኃዎቿ ሁሉ ወደ ደም እንዲለወጡ በትርህን ወስደህ በእነሱ ላይ እጅህን ዘርጋ።’+ በመላው የግብፅ ምድር ላይ ሌላው ቀርቶ ከእንጨትና ከድንጋይ በተሠሩ ዕቃ +20 ሙሴ�� አሮን ወዲያውኑ ልክ ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እሱም ፈርዖንና አገልጋዮቹ እያዩ በትሩን አንስቶ በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለውን ውኃ መታ፤ በወንዙ ውስጥ የነበረውም ውኃ በሙሉ ወደ ደም ተለወጠ።+ +21 በወንዙ ውስጥ የነበሩት ዓሣዎች ሞቱ፤+ ወንዙም መከርፋት ጀመረ፤ ግብፃውያንም ከአባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት አልቻሉም፤+ በመላው የግብፅ ምድር ላይም ደም ነበር። +22 ይሁንና አስማት የሚሠሩ የግብፅ ካህናትም በሚስጥራዊ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር አደረጉ፤+ በመሆኑም የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንዳለውም እነሱን ለመስማት እንቢተኛ ሆነ።+ +23 ከዚያም ፈርዖን ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ፤ ይህን ከቁም ነገር አልቆጠረውም። +24 ግብፃውያን ሁሉ ከአባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት ስላልቻሉ የሚጠጣ ውኃ ለማግኘት የአባይን ዳርቻ ተከትለው ጉድጓዶችን ይቆፍሩ ነበር። +25 ይሖዋ አባይን ከመታ ሰባት ቀን አለፈ። +12 ይሖዋም ሙሴንና አሮንን በግብፅ ምድር እንዲህ አላቸው፦ +2 “ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሆንላችኋል። ከዓመቱም ወሮች የመጀመሪያው ይሆንላችኋል።+ +3 ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲህ ብላችሁ ንገሩ፦ ‘ይህ ወር በገባ በአሥረኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው ለአባቱ ቤት አንድ በግ ይኸውም ለአንድ ቤት አንድ በግ+ ይውሰድ። +4 ሆኖም ቤተሰቡ ለአንድ በግ የሚያንስ ከሆነ እነሱና የእነሱ* የቅርብ ጎረቤቶች በጉን በየቤታቸው ባሉት ሰዎች* ቁጥር ልክ ይከፋፈሉት። በምታሰሉበት ጊዜም እያንዳንዱ ሰው ከበጉ ምን ያህል እንደሚበላ ወስኑ። +5 የምትመርጡት በግ እንከን የሌለበት፣+ ተባዕትና አንድ ዓመት የሞላው መሆን ይኖርበታል። ከበግ ጠቦቶች ወይም ከፍየሎች መካከል መምረጥ ትችላላችሁ። +6 እስከዚህ ወር 14ኛ ቀን+ ድረስ እየተንከባከባችሁ አቆዩት፤ መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ጉባኤም አመሻሹ ላይ* ይረደው።+ +7 ከደሙም ወስደው በጉን በሚበሉበት ቤት በር በሁለቱ መቃኖችና በጉበኑ ላይ ይርጩት።+ +8 “‘ሥጋውንም በዚያው ሌሊት ይብሉት።+ ሥጋውን በእሳት ጠብሰው ከቂጣና*+ ከመራራ ቅጠል+ ጋር ይብሉት። +9 የትኛውንም የሥጋውን ብልት ጥሬውን ወይም ቅቅሉን አትብሉ፤ ነገር ግን ጭንቅላቱን ከእግሩና ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት ጥበሱት። +10 እስከ ጠዋት ድረስ ምንም አታስተርፉ፤ ሳይበላ ያደረ ካለ ግን በእሳት አቃጥሉት።+ +11 የምትበሉትም ወገባችሁን ታጥቃችሁ፣ ጫማችሁን አድርጋችሁና በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ መሆን አለበት፤ በጥድፊያም ብሉት። ይህ የይሖዋ ፋሲካ* ነው። +12 ምክንያቱም በዚህ ሌሊት በግብፅ ምድር አልፋለሁ፤ ከሰው አንስቶ እስከ እንስሳ ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ እመታለሁ፤+ በግብፅ አማልክት ሁሉ ላይም የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +13 ደሙም እናንተ ያላችሁበትን ቤት የሚጠቁም ምልክት ሆኖ ያገለግላል፤ እኔም ደሙን ሳይ እናንተን አልፌ እሄዳለሁ፤ የግብፅን ምድር በምመታበት ጊዜ መቅሰፍቱ መጥቶ እናንተን አያጠፋም።+ +14 “‘ይህ ቀን ለእናንተ መታሰቢያ ይሆናል፤ እናንተም በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ የይሖዋ በዓል አድርጋችሁ አክብሩት። ይህን ዘላቂ ደንብ አድርጋችሁ አክብሩት። +15 ለሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ።+ አዎ፣ በመጀመሪያው ቀን ከቤታችሁ እርሾ አስወግዱ፤ ምክንያቱም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ ሰባተኛው ቀን ድረስ እርሾ የገባበትን ነገር የሚበላ ማንኛውም ሰው* ከእስራኤል መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል። +16 በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ፤ በሰባተኛውም ቀን ሌላ ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። በእነዚህ ቀናት ምንም ዓይነት ሥራ መሠራት የለበትም።+ እያንዳንዱ ሰው* የሚበላውን ነገር ከማዘጋጀት ውጭ ሌላ ምንም ነገ��� አትሥሩ። +17 “‘የቂጣን በዓል አክብሩ፤+ ምክንያቱም በዚህ ቀን ሠራዊታችሁን ከግብፅ ምድር አወጣለሁ። እናንተም ይህን ዕለት በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘላቂ ደንብ አድርጋችሁ አክብሩት። +18 በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም ከ14ኛው ቀን ምሽት አንስቶ እስከ ወሩ 21ኛ ቀን ምሽት ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ።+ +19 ለሰባት ቀናት እርሾ የሚባል ነገር በቤታችሁ ውስጥ አይገኝ፤ ምክንያቱም እርሾ ያለበትን ነገር የሚበላ ማንኛውም ሰው የባዕድ አገር ሰውም ሆነ የአገሩ ተወላጅ፣+ ያ ሰው* ከእስራኤል ማኅበረሰብ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል።+ +20 እርሾ ያለበት ምንም ነገር አትብሉ። በቤታችሁ ሁሉ ቂጣ ብሉ።’” +21 ሙሴም ወዲያው የእስራኤልን ሽማግሌዎች+ በሙሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሂዱ፣ ለየቤተሰባችሁ የሚሆን ጠቦት መርጣችሁ የፋሲካን መሥዋዕት እረዱ። +22 ከዚያም አንድ እስር ሂሶጵ ወስዳችሁ በሳህን ባለው ደም ውስጥ ከነከራችሁ በኋላ ደሙን በበራችሁ ጉበንና በሁለቱ መቃኖች ላይ እርጩት፤ ከእናንተም መካከል አንድም ሰው እስኪነጋ ድረስ ከቤቱ መውጣት የለበትም። +23 ይሖዋ ግብፃውያንን በመቅሰፍት ሊመታ በሚያልፍበት ጊዜ በበራችሁ ጉበንና በሁለቱ መቃኖች ላይ ያለውን ደም ሲያይ ይሖዋ በእርግጥ በሩን አልፎ ይሄዳል፤ የሞት መቅሰፍቱ* ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይፈቅድም።+ +24 “እናንተም ይህን ነገር ለእናንተና ለልጆቻችሁ ዘላቂ ሥርዓት አድርጋችሁ አክብሩት።+ +25 ልክ ይሖዋ በተናገረው መሠረትም ወደሚሰጣችሁ ምድር በምትገቡበት ጊዜ ይህን በዓል አክብሩ።+ +26 ልጆቻችሁ ‘ይህን በዓል የምታከብሩት ለምንድን ነው?’ ብለው ሲጠይቋችሁ+ +27 እንዲህ በሏቸው፦ ‘ግብፃውያንን በመቅሰፍት በመታበት ጊዜ በግብፅ ያሉትን የእስራኤላውያንን ቤቶች አልፎ በመሄድ ቤቶቻችንን ላተረፈልን ለይሖዋ የሚቀርብ የፋሲካ መሥዋዕት ነው።’” ከዚያም ሕዝቡ ተደፍቶ ሰገደ። +28 እስራኤላውያንም ሄደው ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።+ ልክ እንደተባሉት አደረጉ። +29 እኩለ ሌሊት ላይ ይሖዋ፣ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኩር ልጅ አንስቶ በእስር ቤት* እስከሚገኘው እስረኛ የበኩር ልጅ ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ መታ፤ የእያንዳንዱን እንስሳ በኩርም መታ።+ +30 ከዚያም ፈርዖን በዚያ ሌሊት ተነሳ፤ እሱ ብቻ ሳይሆን አገልጋዮቹ ሁሉና ሌሎቹ ግብፃውያን በሙሉ ተነሱ፤ ሰው ያልሞተበት አንድም ቤት ስላልነበር በግብፃውያን መካከል ታላቅ ዋይታ ሆነ።+ +31 እሱም ወዲያውኑ ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ+ እንዲህ አላቸው፦ “ተነሱ፣ እናንተም ሆናችሁ ሌሎቹ እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ። ሂዱ፣ እንዳላችሁት ይሖዋን አገልግሉ።+ +32 ባላችሁትም መሠረት መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ይዛችሁ ሂዱ።+ እኔን ግን ባርኩኝ።” +33 ግብፃውያኑም “በዚህ ዓይነት እኮ ሁላችንም ማለቃችን ነው!”+ በማለት ሕዝቡ በአስቸኳይ ምድሪቱን ለቆ እንዲሄድላቸው ያጣድፉት ጀመር።+ +34 ስለዚህ ሕዝቡ ያልቦካውን ሊጥ በየቡሃቃው አድርጎ በልብሱ ከጠቀለለ በኋላ በትከሻው ተሸከመው። +35 እስራኤላውያንም ሙሴ የነገራቸውን አደረጉ፤ የብርና የወርቅ ዕቃዎችን እንዲሁም ልብሶችን እንዲሰጧቸውም ግብፃውያንን ጠየቁ።+ +36 ይሖዋም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስ ሰጣቸው፤ በመሆኑም የጠየቁትን ሁሉ ሰጧቸው፤ ግብፃውያኑንም በዘበዟቸው።+ +"37 ከዚያም እስራኤላውያን ከራምሴስ+ ተነስተው ወደ ሱኮት+ ሄዱ፤ ልጆችን ሳይጨምር እግረኛ የሆኑት ወንዶች ወደ 600,000 ገደማ ነበሩ።+" +38 ከእነሱም ጋር እጅግ ብዙ ድብልቅ ሕዝብ*+ እንዲሁም መንጎችና ከብቶች ይኸውም እጅግ ብዙ እንስሳ አብሮ ወጣ። +39 እነሱም ከግብፅ ይዘው በወጡት ሊጥ ቂጣ ጋገሩ። ይህም የሆነው ሊጡ ስላልቦካ ነበር፤ ምክንያቱም ከግብፅ እንዲወጡ የተደረገው በድንገት ስለነበር ለራሳቸው ስንቅ ማዘጋጀት አልቻሉም።+ +40 በግብፅ የኖሩት እስራኤላውያን+ የኖሩበት ዘመን 430 ዓመት ነበር።+ +41 አራት መቶ ሠላሳው ዓመት በተፈጸመበት በዚያው ዕለት መላው የይሖዋ ሠራዊት ከግብፅ ምድር ወጣ። +42 ይህ ሌሊት ይሖዋ ከግብፅ ምድር ስላወጣቸው የሚያከብሩት ሌሊት ነው። ይህ ሌሊት መላው የእስራኤል ሕዝብ በመጪዎቹ ትውልዶች ሁሉ ለይሖዋ የሚያከብረው ሌሊት ነው።+ +43 ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “የፋሲካው ደንብ ይህ ነው፦ ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ከፋሲካው አይብላ።+ +44 ሆኖም አንድ ሰው በገንዘብ የተገዛ ባሪያ ካለው ግረዘው።+ መብላት የሚችለው ይህ ከሆነ ብቻ ነው። +45 ሰፋሪና ቅጥር ሠራተኛ ከዚያ ላይ መብላት የለባቸውም። +46 በአንድ ቤት ውስጥ መበላት አለበት። ከሥጋውም ላይ የትኛውንም ቢሆን ከቤት ውጭ ይዘህ አትውጣ፤ ከአጥንቱም አንዱንም አትስበሩ።+ +47 መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ይህን በዓል ማክበር አለበት። +48 በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለና ለይሖዋ ፋሲካን ማክበር ከፈለገ የእሱ የሆኑት ወንዶች ሁሉ መገረዝ አለባቸው። ከዚያ በኋላ በዓሉን ለማክበር መቅረብ ይችላል፤ እሱም እንደ አገሩ ተወላጅ ይሆናል። ነገር ግን ማንኛውም ያልተገረዘ ሰው ከፋሲካው ምግብ መብላት አይችልም።+ +49 ለአገሩ ተወላጅም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ሕጉ አንድ ዓይነት ነው።”+ +50 በመሆኑም እስራኤላውያን በሙሉ ይሖዋ ሙሴን እና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ። ልክ እንደተባሉት አደረጉ። +51 በዚሁ ቀን ይሖዋ እስራኤላውያንን ከነሠራዊታቸው ከግብፅ ምድር አወጣቸው። +1 ቤተሰባቸውን ይዘው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የመጡት የእስራኤል ወንዶች ልጆች ስም የሚከተለው ነው፦+ +2 ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣+ +3 ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ቢንያም፣ +4 ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር።+ +5 ከያዕቆብ አብራክ የወጡት* በጠቅላላ 70* ነበሩ፤ ዮሴፍ ግን ቀድሞውኑም እዚያው ግብፅ ነበር።+ +6 ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ ሞተ፤+ ወንድሞቹም ሁሉ ሞቱ፤ ያም ትውልድ በሙሉ ሞተ። +7 እስራኤላውያንም* ተዋለዱ፤ በጣም ብዙ ሆኑ፤ ቁጥራቸውም በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረና ኃያል እየሆኑ ሄዱ፤ ከዚህም የተነሳ ምድሪቱን ሞሏት።+ +8 ከጊዜ በኋላ ዮሴፍን የማያውቅ አዲስ ንጉሥ በግብፅ ተነሳ። +9 እሱም ሕዝቦቹን እንዲህ አላቸው፦ “ይኸው እንደምታዩት የእስራኤል ሕዝብ ከእኛ ይልቅ እጅግ ብዙና ኃያል ነው።+ +10 እንግዲህ እነሱን በተመለከተ አንድ መላ እንፍጠር። ካልሆነ ግን ቁጥራቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ደግሞም ጦርነት ከተነሳ ከጠላቶቻችን ጋር ወግነው እኛን መውጋታቸውና አገሪቱን ጥለው መኮብለላቸው አይቀርም።” +11 በመሆኑም ከባድ ሥራ በማሠራት እንዲያስጨንቋቸው የግዳጅ ሥራ የሚያሠሩ አለቆችን ሾሙባቸው፤+ እነሱም ጲቶም እና ራምሴስ+ የተባሉ ለማከማቻ የሚሆኑ ከተሞችን ለፈርዖን ገነቡ። +12 ሆኖም ይበልጥ በጨቆኗቸው መጠን ይበልጥ እየበዙና በምድሩ ላይ ይበልጥ እየተስፋፉ ስለሄዱ ግብፃውያን በእስራኤላውያን የተነሳ ከፍተኛ ፍርሃት አደረባቸው።+ +13 በመሆኑም ግብፃውያን እስራኤላውያንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በባርነት ይገዟቸው ጀመር።+ +14 የሸክላ ጭቃ በማስቦካት፣ ጡብ በማሠራትና በእርሻ ላይ ማንኛውንም ዓይነት የባርነት ሥራ እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን መራራ አደረጉባቸው። አዎ፣ ማንኛውንም ዓይነት የባርነት ሥራ በማሠራት በጭካኔ ያንገላቷቸው ነበር።+ +15 በኋላም የግብፅ ንጉሥ፣ ሺፍራ እና ፑሃ የተባሉትን ዕብራውያን አዋላጆች አነጋገራቸው፤ +16 እንዲህም አላቸው፦ “ዕብራውያን ሴቶችን በምታዋልዱበት ጊዜ+ በማዋለጃው ዱካ ላይ ተቀምጠው ስታዩ የሚወለደው ልጅ ወንድ ከሆነ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።” +17 ይሁን እንጂ አዋላጆቹ እውነተኛውን አምላክ ስለፈሩ የግብፅ ንጉሥ ያላቸውን አላደረጉም። ከዚህ ይልቅ ወንዶቹን ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ይተዉአቸው ነበር።+ +18 ከጊዜ በኋላም የግብፅ ንጉሥ አዋላጆቹን ጠርቶ “ወንዶቹን ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ የተዋችኋቸው ለምንድን ነው?” አላቸው። +19 አዋላጆቹም ፈርዖንን “ዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብፃውያን ሴቶች አይደሉም። እነሱ ብርቱዎች ስለሆኑ አዋላጇ ከመድረሷ በፊት በራሳቸው ይወልዳሉ” አሉት። +20 ስለሆነም አምላክ ለአዋላጆቹ መልካም ነገር አደረገላቸው፤ ሕዝቡም እየበዛና እጅግ ኃያል እየሆነ ሄደ። +21 አዋላጆቹ እውነተኛውን አምላክ በመፍራታቸው፣ አምላክ ከጊዜ በኋላ ቤተሰብ ሰጣቸው። +22 በመጨረሻም ፈርዖን ሕዝቡን ሁሉ “አዲስ የሚወለዱትን የዕብራውያንን ወንዶች ልጆች ሁሉ አባይ ወንዝ ውስጥ ጣሏቸው፤ ሴቶቹን ልጆች ሁሉ ግን በሕይወት እንዲኖሩ ተዉአቸው” ሲል አዘዘ።+ +36 “ባስልኤል ከኤልያብና ጥሩ ችሎታ* ካላቸው ወንዶች ሁሉ ጋር ይሠራል፤ እነዚህ ወንዶች ቅዱስ ከሆነው አገልግሎት ጋር የተያያዘው ሥራ በሙሉ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት እንዴት እንደሚከናወን ማወቅ ይችሉ ዘንድ ይሖዋ ጥበብና ማስተዋል የሰጣቸው ናቸው።”+ +2 ከዚያም ሙሴ ባስልኤልንና ኤልያብን እንዲሁም ይሖዋ በልባቸው ጥበብን ያኖረላቸውን ጥሩ ችሎታ ያላቸውን ወንዶች+ ሁሉ ይኸውም ሥራውን ለመሥራት በፈቃደኝነት ራሳቸውን እንዲያቀርቡ ልባቸው ያነሳሳቸውን+ ሁሉ ጠራ። +3 እነሱም እስራኤላውያን ለቅዱሱ አገልግሎት ሥራ ያመጡትን መዋጮ+ በሙሉ ከሙሴ ወሰዱ። ሕዝቡ ግን በየማለዳው የፈቃደኝነት መባ ወደ እሱ ያመጣ ነበር። +4 ቅዱሱን ሥራ ከጀመሩም በኋላ ጥሩ ችሎታ ያላቸው ሠራተኞች ሁሉ አንድ በአንድ ይመጡ ነበር፤ +5 ሙሴንም “ሕዝቡ፣ ይሖዋ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ከሚፈለገው በላይ እያመጣ ነው” አሉት። +6 ስለዚህ ሙሴ በሰፈሩ ሁሉ እንዲህ የሚል ማስታወቂያ እንዲነገር አዘዘ፦ “ወንዶችም ሆናችሁ ሴቶች፣ ከእንግዲህ ለቅዱሱ መዋጮ የሚሆን ተጨማሪ ነገር አታምጡ።” በመሆኑም ሕዝቡ ምንም ነገር ከማምጣት ተገታ። +7 የመጣውም ነገር ሥራውን ሁሉ ለማከናወን በቂ፣ እንዲያውም ከበቂ በላይ ነበር። +8 ጥሩ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች+ ሁሉ በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍና ከደማቅ ቀይ ማግ ከተሠሩ አሥር የድንኳን ጨርቆች የማደሪያ ድንኳኑን ሠሩ፤+ እሱም* በጨርቆቹ ላይ ኪሩቦችን ጠለፈባቸው።+ +9 የእያንዳንዱ የድንኳን ጨርቅ ርዝመት 28 ክንድ* ወርዱ ደግሞ 4 ክንድ ነበር። ሁሉም የድንኳን ጨርቆች መጠናቸው እኩል ነበር። +10 ከዚያም አምስቱን የድንኳን ጨርቆች አንድ ላይ ቀጣጠላቸው፤ ሌሎቹን አምስት የድንኳን ጨርቆችም እንዲሁ አንድ ላይ ቀጣጠላቸው። +11 ከዚህ በኋላ አንደኛው የድንኳን ጨርቅ ከሌላኛው ጋር በሚጋጠምበት ጠርዝ ላይ ከሰማያዊ ክር ማቆላለፊያዎችን ሠራ። ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት በመጨረሻው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይም እንዲሁ አደረገ። +12 በአንደኛው የድንኳን ጨርቅ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ፤ ማቆላለፊያዎቹም ትይዩ እንዲሆኑ ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት የድንኳኑ ጨርቅ ጠርዝ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ። +13 በመጨረሻም 50 የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርቶ የድንኳኑን ጨርቆች በማያያዣዎቹ አማካኝነት እርስ በርስ አጋጠማቸው፤ በዚህም ��ንገድ የማደሪያ ድንኳኑ አንድ ወጥ ሆነ። +14 ከዚያም ለማደሪያ ድንኳኑ ልባስ የሚሆኑ የድንኳን ጨርቆችን ከፍየል ፀጉር ሠራ። አሥራ አንድ የድንኳን ጨርቆችን ሠራ።+ +15 የእያንዳንዱ የድንኳን ጨርቅ ርዝመት 30 ክንድ ወርዱ ደግሞ 4 ክንድ ነበር። አሥራ አንዱም የድንኳን ጨርቆች መጠናቸው እኩል ነበር። +16 ከዚያም አምስቱን የድንኳን ጨርቆች አንድ ላይ፣ ሌሎቹን ስድስት የድንኳን ጨርቆች ደግሞ አንድ ላይ ቀጣጠላቸው። +17 በመቀጠልም አንደኛው የድንኳን ጨርቅ ከሌላኛው ጋር በሚጋጠምበት በመጨረሻው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ፤ እንዲሁም ከዚህኛው ጋር በሚጋጠመው በሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ሠራ። +18 ከዚያም ድንኳኑን በማያያዝ አንድ ወጥ እንዲሆን ለማድረግ 50 የመዳብ ማያያዣዎችን ሠራ። +19 እሱም ቀይ ቀለም ከተነከረ የአውራ በግ ቆዳ ለድንኳኑ መደረቢያ ሠራ፤ እንዲሁም ከአቆስጣ ቆዳ በላዩ ላይ የሚደረብ መደረቢያ ሠራ።+ +20 ከዚያም የግራር እንጨት+ ጣውላዎችን በማገጣጠም የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች ሠራ።+ +21 እያንዳንዱ ቋሚ ቁመቱ አሥር ክንድ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር። +22 እያንዳንዱ ቋሚም እርስ በርስ የተያያዙ ሁለት ጉጦች ነበሩት። ሁሉንም የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች የሠራው በዚህ መንገድ ነበር። +23 በመሆኑም በስተ ደቡብ በኩል ለሚገኘው፣ ፊቱ በደቡብ አቅጣጫ ላለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ቋሚዎችን ይኸውም 20 ቋሚዎችን ሠራ። +24 ከዚያም በ20ዎቹ ቋሚዎች ሥር የሚሆኑ 40 የብር መሰኪያዎችን ሠራ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ላሉት ሁለት ጉጦች የሚሆኑ ሁለት መሰኪያዎችን፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ላሉት ሁለት ጉጦች የሚሆኑ ሁለት መሰኪያዎችን አደረገ።+ +25 በስተ ሰሜን በኩል ላለው ለሌላኛውም የማደሪያ ድንኳኑ ጎን 20 ቋሚዎችን ሠራ፤ +26 እንዲሁም 40 የብር መሰኪያዎቻቸውን ሠራ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎችን፣ በተቀረው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎችን አደረገ። +27 በስተ ምዕራብ በኩል ለሚገኘው ለኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ስድስት ቋሚዎችን ሠራ።+ +28 በማደሪያ ድንኳኑ በስተ ኋላ በኩል ባሉት ሁለት ማዕዘኖች ላይ የማዕዘን ቋሚዎች የሚሆኑ ሁለት ቋሚዎችን ሠራ። +29 ቋሚዎቹም ከታች አንስቶ የመጀመሪያው ቀለበት እስከሚገኝበት እስከ ላይ ድረስ ድርብ ነበሩ። ሁለቱን የማዕዘን ቋሚዎች የሠራቸው በዚህ መንገድ ነበር። +30 በመሆኑም ስምንት ቋሚዎች የነበሩ ሲሆን እነሱም ከብር የተሠሩ 16 መሰኪያዎች ነበሯቸው፤ ይህም በእያንዳንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያ ማለት ነው። +31 ከዚያም ከግራር እንጨት አግዳሚ እንጨቶችን ሠራ፤ በአንዱ ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን፣+ +32 በሌላኛው ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች ደግሞ አምስት አግዳሚ እንጨቶችን እንዲሁም በስተ ምዕራብ በሚገኘው በኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ላሉት ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን ሠራ። +33 በቋሚዎቹ መሃል ላይ ከጫፍ እስከ ጫፍ እንዲዘልቅ መካከለኛውን አግዳሚ እንጨት ሠራ። +34 ቋሚዎቹንም በወርቅ ለበጣቸው፤ አግዳሚ እንጨቶቹን የሚሸከሙትን ቀለበቶችም ከወርቅ ሠራቸው። አግዳሚ እንጨቶቹንም በወርቅ ለበጣቸው።+ +35 ከዚያም ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር መጋረጃ ሠራ።+ በላዩም ላይ ኪሩቦች+ እንዲጠለፉበት አደረገ።+ +36 ከዚያም ለመጋረጃው ከግራር እንጨት አራት ዓምዶችን ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው፤ ማንጠልጠያዎቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ ለዓምዶቹም ከብር የተሠሩ አራት መሰኪያዎችን አዘጋጀ። +37 በመቀጠልም ለ��ንኳኑ መግቢያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር የተሸመነ መከለያ* ሠራ፤+ +38 እንዲሁም አምስቱን ዓምዶችና ማንጠልጠያዎቹን ሠራ። አናታቸውንና ማያያዣዎቻቸውንም* በወርቅ ለበጣቸው፤ አምስቱ መሰኪያዎቻቸው ግን ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ። +29 “ለእኔ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነሱን ለመቀደስ የምታደርገው ነገር ይህ ነው፦ እንከን የሌለበትን አንድ ወይፈንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት አውራ በጎች ውሰድ፤+ +2 እንዲሁም ቂጣ፣* በዘይት ከተለወሰ ሊጥ የተጋገረ የቀለበት ቅርጽ ያለው እርሾ ያልገባበት ዳቦና ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ውሰድ።+ እነዚህንም ከላመ የስንዴ ዱቄት ጋግረህ +3 በቅርጫት ውስጥ ታደርጋቸዋለህ፤ በቅርጫት ውስጥ አድርገህም+ ከወይፈኑና ከሁለቱ አውራ በጎች ጋር ታቀርባቸዋለህ። +4 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ+ ታቀርባቸዋለህ፤ በውኃም ታጥባቸዋለህ።+ +5 ከዚያም ልብሶቹን+ ወስደህ ረጅሙን ቀሚስ፣ እጅጌ የሌለውን የኤፉዱን ቀሚስ፣ ኤፉዱንና የደረት ኪሱን አሮንን አልብሰው፤ በሽመና የተሠራውን የኤፉዱን መቀነትም ወገቡ ላይ ጠበቅ አድርገህ ታስርለታለህ።+ +6 ጥምጥሙንም በራሱ ላይ ታደርግለታለህ፤ በጥምጥሙም ላይ ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየውን ቅዱስ ምልክት* ታደርጋለህ፤+ +7 የቅብዓት ዘይቱንም+ ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ትቀባዋለህ።+ +8 “ከዚያም ወንዶች ልጆቹን አምጥተህ ረጃጅሞቹን ቀሚሶች አልብሳቸው፤+ +9 አሮንንና ወንዶች ልጆቹን መቀነቱን አስታጥቃቸው፤ የራስ ቆባቸውንም አድርግላቸው፤ ክህነቱም ዘላለማዊ ደንብ ሆኖ የእነሱ ይሆናል።+ በዚህም መንገድ አሮንና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ ትሾማቸዋለህ።*+ +10 “ከዚያም ወይፈኑን በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ታቀርበዋለህ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጭናሉ።+ +11 ወይፈኑንም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት እረደው።+ +12 ከወይፈኑም ደም ላይ የተወሰነውን ወስደህ በጣትህ በመሠዊያው ቀንዶች+ ላይ አድርግ፤ የቀረውንም ደም በሙሉ መሠዊያው ሥር አፍስሰው።+ +13 ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብ+ ሁሉ፣ በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ ውሰድ፤ በመሠዊያውም ላይ እንዲጨሱ አቃጥላቸው።+ +14 የወይፈኑን ሥጋ፣ ቆዳውንና ፈርሱን ግን ከሰፈሩ ውጭ አውጥተህ በእሳት ታቃጥለዋለህ። ይህ የኃጢአት መባ ነው። +15 “ከዚያም አንዱን አውራ በግ ውሰድ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ።+ +16 አንተም አውራውን በግ እረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ እርጨው።+ +17 አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራርጠው፤ ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም እጠባቸው፤+ ከዚያም የተቆራረጡትን ብልቶች ከጭንቅላቱ ጋር አሰናድተህ አስቀምጣቸው። +18 አውራውንም በግ ሙሉ በሙሉ በማቃጠል በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አድርገው። ይህም ለይሖዋ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ+ ነው። ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። +19 “ከዚያም ሌላኛውን አውራ በግ ትወስዳለህ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጭኑበታል።+ +20 አንተም አውራውን በግ እረደው፤ ከደሙም ወስደህ የአሮንን የቀኝ ጆሮ ጫፍና የወንዶች ልጆቹን የቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጃቸውን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ቀባ፤ ደሙንም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ እርጨው። +21 በመሠዊያው ላይ ካለው ደምና ከቅብዓት ዘይቱ+ ውሰድ፤ ከዚያም አሮንና ልብሶቹ እንዲሁም ወንዶች ልጆቹና ልብሶቻቸ�� ቅዱስ እንዲሆኑ በአሮንና በልብሶቹ እንዲሁም በወንዶች ልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ እርጨው።+ +22 “አውራው በግ የክህነት ሹመት ሥርዓት በሚካሄድበት ጊዜ የሚቀርብ+ ስለሆነ ከአውራው በግ ላይ ስቡን፣ ላቱን፣ አንጀቱን የሚሸፍነውን ስብ፣ የጉበቱን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ+ እንዲሁም ቀኝ እግሩን ውሰድ። +23 በተጨማሪም በይሖዋ ፊት ካለው ቂጣ ከተቀመጠበት ቅርጫት ውስጥ ቂጣውን፣ በዘይት ከተለወሰ ሊጥ የተጋገረውን የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦና ስሱን ቂጣ ውሰድ። +24 ሁሉንም በአሮን እጅና በወንዶች ልጆቹ እጅ ላይ አስቀምጣቸው፤ ከዚያም በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዝውዛቸው። +25 በይሖዋም ፊት ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ እንዲሆን ከእጃቸው ላይ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይ ታቃጥላቸዋለህ። ይህ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። +26 “ከዚያም ለአሮን የክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርበውን አውራ በግ+ ፍርምባ ወስደህ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዝውዘው፤ እሱም የአንተ ድርሻ ይሆናል። +27 ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የክህነት ሹመት ሥርዓት ከቀረበው አውራ በግ+ ተወስዶ ለሚወዘወዝ መባ የቀረበውን ፍርምባና የተቀደሰ ድርሻ እንዲሆን የተወዘወዘውን እግር ትቀድሳቸዋለህ። +28 ይህም የተቀደሰ ድርሻ ስለሆነ የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል፤ ይህም እስራኤላውያን የሚፈጽሙት ዘላለማዊ ሥርዓት ነው፤ ይህ ድርሻ እስራኤላውያን የሚያቀርቡት የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል።+ ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ ለይሖዋ የሚሰጥ የተቀደሰ ድርሻቸው ነው።+ +29 “የአሮን ቅዱስ ልብሶችም+ ከእሱ በኋላ የሚመጡት ወንዶች ልጆቹ በሚቀቡበትና ካህናት ሆነው በሚሾሙበት ጊዜ ይገለገሉባቸዋል።+ +30 ከወንዶች ልጆቹ መካከል እሱን የሚተካውና በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል ወደ መገናኛ ድንኳኑ የሚገባው ካህን ለሰባት ቀን ይለብሳቸዋል።+ +31 “ለክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርበውን አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ።+ +32 አሮንና ወንዶች ልጆቹ የአውራውን በግ ሥጋና በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ቂጣ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ይበሉታል።+ +33 እነሱን ካህናት አድርጎ ለመሾምና* ለመቀደስ ማስተሰረያ ሆነው የቀረቡትን ነገሮች ይበላሉ። ሆኖም እነዚህ ነገሮች የተቀደሱ ስለሆኑ ያልተፈቀደለት ሰው* ሊበላቸው አይችልም።+ +34 ለክህነት ሹመት ሥርዓቱ መሥዋዕት ሆኖ ከቀረበው ሥጋና ቂጣ ተርፎ ያደረ ካለ የተረፈውን በእሳት አቃጥለው።+ የተቀደሰ ስለሆነ መበላት የለበትም። +35 “እኔ ባዘዝኩህ ሁሉ መሠረት ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ በዚሁ መንገድ ታደርግላቸዋለህ። እነሱን ካህናት አድርገህ ለመሾም* ሰባት ቀን ይፈጅብሃል።+ +36 ለማስተሰረያ እንዲሆን የኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ በየዕለቱ ታቀርባለህ፤ ለመሠዊያውም ማስተሰረያ በማቅረብ መሠዊያውን ከኃጢአት ታነጻዋለህ፤ መሠዊያውን ለመቀደስም ቀባው።+ +37 መሠዊያውን ለማስተሰረይ ሰባት ቀን ይፈጅብሃል፤ እጅግ ቅዱስ መሠዊያ እንዲሆንም ቀድሰው።+ መሠዊያውን የሚነካ ማንኛውም ሰው ቅዱስ መሆን አለበት። +38 “በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው እነዚህን ይሆናል፦ አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት የበግ ጠቦቶችን በየቀኑ ሳታቋርጥ ታቀርባለህ።+ +39 አንደኛውን የበግ ጠቦት ጠዋት ላይ ታቀርበዋለህ፤ ሌላኛውን የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ* ታቀርበዋለህ።+ +40 ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን* ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ* አንድ አሥረኛ የላመ ዱቄትና ለመጠጥ መባ የሚሆን አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋር ይቅረብ። +41 ሁለተኛውንም የበግ ጠቦት ልክ ማለዳ ላይ ከምታቀርባቸው ጋር ተመሳሳይ ከሆኑ የእህልና የመጠጥ መባዎች ጋር አመሻሹ ላይ* ታቀርበዋለህ። ይህን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርገህ ታቀርበዋለህ። +42 ይህም እኔ እናንተን ለማነጋገር ራሴን በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ+ መግቢያ ላይ በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ በይሖዋ ፊት ዘወትር የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይሆናል። +43 “እኔም በዚያ ራሴን ለእስራኤላውያን እገልጣለሁ፤ ያም ስፍራ በክብሬ+ የተቀደሰ ይሆናል። +44 መገናኛ ድንኳኑንና መሠዊያውን እቀድሰዋለሁ፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እቀድሳቸዋለሁ።+ +45 እኔም በእስራኤል ሕዝብ መካከል እኖራለሁ፤* አምላካቸውም እሆናለሁ።+ +46 እነሱም በመካከላቸው እኖር ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው እኔ አምላካቸው ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።+ እኔ አምላካቸው ይሖዋ ነኝ። +28 “አንተም ለእኔ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ+ ወንድምህን አሮንን ከወንዶች ልጆቹ ጋር ከእስራኤላውያን መካከል ለይተህ ትጠራዋለህ፤ አሮንን+ እንዲሁም የአሮንን ወንዶች ልጆች+ ናዳብን፣ አቢሁን፣+ አልዓዛርንና ኢታምርን+ ትጠራቸዋለህ። +2 ለወንድምህ ለአሮንም ክብርና ውበት የሚያጎናጽፉትን ቅዱስ ልብሶች ትሠራለታለህ።+ +3 የጥበብ መንፈስ የሞላሁባቸውን ጥሩ ችሎታ* ያላቸውን ሰዎች+ ሁሉ አንተ ራስህ ታናግራቸዋለህ፤ እነሱም አሮን ለእኔ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ እሱን ለመቀደስ ልብሶቹን ይሠሩለታል። +4 “የሚሠሯቸው ልብሶችም እነዚህ ናቸው፦ የደረት ኪስ፣+ ኤፉድ፣+ እጅጌ የሌለው ቀሚስ፣+ በካሬ ንድፍ የተሸመነ ረጅም ቀሚስ፣ ጥምጥምና+ መቀነት፤+ ወንድምህ አሮንና ወንዶች ልጆቹ ካህን ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነዚህን ቅዱስ ልብሶች ይሠሩላቸዋል። +5 እነዚህ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ወርቁን፣ ሰማያዊውን ክር፣ ሐምራዊውን ሱፍ፣ ደማቁን ቀይ ማግና ጥሩውን በፍታ ተጠቅመው ይሠሯቸዋል። +6 “ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ኤፉዱን ያዘጋጃሉ፤ ኤፉዱም ጥልፍ የተጠለፈበት ይሁን።+ +7 ኤፉዱ ላዩ ላይ የተጣበቁ ሁለት የትከሻ ጥብጣቦች የሚኖሩት ሲሆን እነሱም ኤፉዱን በሁለቱ ጫፎቹ ላይ ያያይዙታል። +8 ኤፉዱ ወዲያ ወዲህ እንዳይንቀሳቀስ ለማሰር የሚያገለግለው ከኤፉዱ ጋር የተያያዘው በሽመና የተሠራው መቀነት+ ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ መሆን ይኖርበታል። +9 “ሁለት የኦኒክስ ድንጋዮችን+ ወስደህ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች+ ትቀርጽባቸዋለህ፤ +10 በትውልዳቸው ቅደም ተከተል መሠረት የስድስቱን ስሞች በአንዱ ድንጋይ ላይ፣ የቀሩትን የስድስቱን ስሞች ደግሞ በሌላኛው ድንጋይ ላይ ትቀርጻለህ። +11 አንድ ቅርጽ አውጪ በድንጋይ ላይ ማኅተም እንደሚቀርጽ ሁሉ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ይቀርጽባቸዋል።+ ከዚያም በወርቅ አቃፊዎች ውስጥ እንዲቀመጡ ታደርጋለህ። +12 ለእስራኤል ልጆች እንደ መታሰቢያ ድንጋዮች ሆነው እንዲያገለግሉ ሁለቱን ድንጋዮች በኤፉዱ የትከሻ ጥብጣቦች ላይ ታስቀምጣቸዋለህ፤+ አሮንም እንደ መታሰቢያ ሆነው እንዲያገለግሉ ስሞቻቸውን በሁለቱ የትከሻ ጥብጣቦች ላይ በይሖዋ ፊት ይሸከማል። +13 አንተም የወርቅ አቃፊዎችን +14 እንዲሁም እንደ ገመድ የተገመዱ ሁለት ሰንሰለቶችን ከንጹሕ ወርቅ ትሠራለህ፤+ የተገመዱትንም ሰንሰለቶች ከአቃፊዎቹ ጋር አያይዛቸው።+ +15 “የፍርዱን የደረት ኪስ የጥልፍ ባለሙያ እንዲሠራው ታደርጋለህ።+ የ���ረት ኪሱ ልክ እንደ ኤፉዱ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ መሠራት ይኖርበታል።+ +16 ለሁለት በሚታጠፍበትም ጊዜ ቁመቱ አንድ ስንዝር፣* ወርዱ ደግሞ አንድ ስንዝር የሆነ ካሬ ይሁን። +17 የከበሩ ድንጋዮችን* በአራት ረድፍ በማቀፊያ ውስጥ ታደርግበታለህ። በመጀመሪያው ረድፍ ሩቢ፣ ቶጳዝዮንና መረግድ ይደርደር። +18 በሁለተኛው ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና ኢያስጲድ ይደርደር። +19 በሦስተኛው ረድፍ ለሼም፣ አካትምና አሜቴስጢኖስ ይደርደር። +20 በአራተኛውም ረድፍ ክርስቲሎቤ፣ ኦኒክስና ጄድ ይደርደር። በወርቅ አቃፊዎችም ውስጥ ይቀመጡ። +21 ድንጋዮቹም የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች ማለትም 12ቱን በየስማቸው የሚወክሉ ይሆናሉ። ለ12ቱም ነገዶች ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ይቀረጽላቸው። +22 “በደረት ኪሱም ላይ ከንጹሕ ወርቅ እንደተሠሩ ገመዶች የተጎነጎኑ ሰንሰለቶችን ትሠራለህ።+ +23 ለደረት ኪሱም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህ ሁለቱን ቀለበቶች ከሁለቱ የደረት ኪሱ ጫፎች ጋር ታያይዛቸዋለህ። +24 ሁለቱን የወርቅ ገመዶችም በደረት ኪሱ ዳርና ዳር ባሉት ጫፎች ላይ በሚገኙት በሁለቱ ቀለበቶች ውስጥ ታስገባቸዋለህ። +25 የሁለቱን ገመዶች ሁለት ጫፎች በሁለቱ አቃፊዎች ውስጥ ታስገባለህ፤ እነሱንም ከኤፉዱ የትከሻ ጥብጣቦች ጋር በፊት በኩል ታያይዛቸዋለህ። +26 ሁለት የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርተህ በኤፉዱ በኩል በሚውለው በደረት ኪሱ ውስጠኛ ጠርዝ ላይ ባሉት ሁለት ጫፎች ላይ ታደርጋቸዋለህ።+ +27 ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርተህ በኤፉዱ በፊት በኩል ከሁለቱ የትከሻ ጥብጣቦች በታች ኤፉዱ በተጋጠመበት ቦታ አካባቢ፣ በሽመና ከተሠራው የኤፉዱ መቀነት በላይ አድርጋቸው።+ +28 የደረት ኪሱ ከቦታው እንዳይንቀሳቀስ የደረት ኪሱ ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ መያያዝ ይኖርባቸዋል። ይህም የደረት ኪሱ ከመቀነቱ በላይ ከኤፉዱ ላይ ሳይንቀሳቀስ እንዲቀመጥ ያደርገዋል። +29 “አሮን ወደ ቅድስቱ በሚገባበት ጊዜ በይሖዋ ፊት ቋሚ መታሰቢያ እንዲሆን በልቡ ላይ በሚገኘው የፍርድ የደረት ኪስ የእስራኤልን ልጆች ስሞች ይሸከም። +30 ኡሪሙንና ቱሚሙን*+ በፍርድ የደረት ኪሱ ውስጥ ታስቀምጣቸዋለህ፤ አሮን በይሖዋ ፊት ለመቅረብ በሚገባበት ጊዜ በልቡ ላይ መሆን አለባቸው፤ አሮን በይሖዋ ፊት በሚቀርብበት ጊዜ ለእስራኤላውያን ፍርድ መስጫውን ዘወትር በልቡ ላይ ይሸከም። +31 “እጅጌ የሌለውን የኤፉዱን ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ክር ትሠራዋለህ።+ +32 ከላይ በኩል መሃል ላይ የአንገት ማስገቢያ ይኖረዋል። የአንገት ማስገቢያውም ዙሪያውን በሽመና ባለሙያ የተሠራ ቅምቅማት ይኑረው። የአንገት ማስገቢያውም እንዳይቀደድ እንደ ጥሩር አንገትጌ ሆኖ ይሠራ። +33 በታችኛው ጠርዝ ዙሪያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍና ከደማቅ ቀይ ማግ የተሠሩ ሮማኖችን አድርግ፤ በመሃል በመሃላቸውም የወርቅ ቃጭሎች አድርግ። +34 እጅጌ በሌለው ቀሚስ በታችኛው ጠርዝ ዙሪያ የወርቅ ቃጭል ከዚያም ሮማን፣ የወርቅ ቃጭል ከዚያም ሮማን እያፈራረቅክ አንጠልጥልበት። +35 አሮን በሚያገለግልበት ጊዜ ይህን ልብስ መልበስ አለበት፤ በይሖዋ ፊት ለመቅረብ ወደ መቅደሱ በሚገባበትና ከዚያ በሚወጣበት ጊዜ እንዳይሞት የቃጭሎቹ ድምፅ መሰማት አለበት።+ +36 “ከንጹሕ ወርቅም የሚያብረቀርቅ ጠፍጣፋ ወርቅ ሠርተህ ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ‘ቅድስና የይሖዋ ነው’+ ብለህ ትቀርጽበታለህ። +37 እሱንም በሰማያዊ ገመድ በጥምጥሙ ላይ እሰረው፤+ በጥምጥሙ ላይ ከፊት በኩል ይሆናል። +38 በአሮን ��ንባር ላይ ይሆናል፤ አሮንም አንድ ሰው ቅዱስ ከሆኑ ነገሮች ይኸውም እስራኤላውያን ቅዱስ ስጦታ አድርገው በሚያቀርቧቸው ጊዜ ከሚቀድሷቸው ነገሮች ጋር በተያያዘ ለሚፈጽመው ስህተት ተጠያቂ ይሆናል።+ በይሖዋም ፊት ተቀባይነት እንዲያገኙ ዘወትር በግንባሩ ላይ መሆን ይኖርበታል። +39 “ከጥሩ በፍታ ረጅም ቀሚስ በካሬ ንድፍ ትሸምንለታለህ፤ እንዲሁም ከጥሩ በፍታ ጥምጥም ትሠራለህ፤ በተጨማሪም በሽመና የተሠራ መቀነት ትሠራለህ።+ +40 “ለአሮን ወንዶች ልጆችም ክብርና ውበት የሚያጎናጽፏቸውን+ ረጃጅም ቀሚሶች፣ መቀነቶችና የራስ ቆቦች ትሠራላቸዋለህ።+ +41 ወንድምህን አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ፤ እንዲሁም ትቀባቸዋለህ፣+ ትሾማቸዋለህ*+ ደግሞም ትቀድሳቸዋለህ፤ እነሱም ካህናት ሆነው ያገለግሉኛል። +42 እርቃናቸውን የሚሸፍኑበት የበፍታ ቁምጣም ትሠራላቸዋለህ።+ ቁምጣውም ከወገባቸው እስከ ጭናቸው የሚደርስ ይሆናል። +43 በደል እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ አሮንና ወንዶች ልጆቹ ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገቡበት ጊዜ ወይም ቅዱስ በሆነው ስፍራ ለማገልገል ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ እነዚህን ልብሶች መልበስ አለባቸው። ይህ ለእሱም ሆነ ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ ዘላለማዊ ደንብ ነው። +38 እሱም የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ። ርዝመቱ አምስት ክንድ፣* ወርዱም አምስት ክንድ ሲሆን አራቱም ጎኖቹ እኩል ነበሩ፤ ከፍታው ደግሞ ሦስት ክንድ ነበር።+ +2 ከዚያም በአራቱ ማዕዘኖች ላይ ቀንዶቹን ሠራለት። ቀንዶቹም ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ። በመቀጠልም በመዳብ ለበጠው።+ +3 ከዚህ በኋላ የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ ይኸውም ባልዲዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ ሳህኖቹን፣ ሹካዎቹንና መኮስተሪያዎቹን ሠራ። ዕቃዎቹን በሙሉ ከመዳብ ሠራቸው። +4 በተጨማሪም ለመሠዊያው ከጠርዙ ወደ ታች ወረድ ብሎ ወደ መሃል አካባቢ እንደ መረብ ያለ የመዳብ ፍርግርግ ሠራለት። +5 መሎጊያዎቹን ለመያዝ የሚያገለግሉትንም አራት ቀለበቶች ከመዳብ ፍርግርጉ አጠገብ በአራቱ ማዕዘኖች ላይ ሠራ። +6 በኋላም መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርቶ በመዳብ ለበጣቸው። +7 ከዚያም መሠዊያውን ለመሸከም እንዲያገለግሉ መሎጊያዎቹን በመሠዊያው ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። መሠዊያውንም ባዶ ሣጥን አስመስሎ ከሳንቃዎች ሠራው። +8 ከዚያም የመዳቡን ገንዳና+ ከመዳብ የተሠራውን ማስቀመጫውን ሠራ፤ ለዚህም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በተደራጀ መልክ ያገለግሉ የነበሩትን ሴት አገልጋዮች መስተዋቶች* ተጠቀመ። +9 ከዚያም ግቢውን ሠራ።+ በስተ ደቡብ በኩል ለሚገኘው፣ ፊቱ በደቡብ አቅጣጫ ላለው የግቢው ጎን በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ርዝመታቸው 100 ክንድ የሆነ መጋረጃዎች ሠራ።+ +10 ከመዳብ የተሠሩ 20 ቋሚዎችና 20 መሰኪያዎች ነበሩ፤ በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው* ደግሞ ከብር የተሠሩ ነበሩ። +11 በተጨማሪም በስተ ሰሜን በኩል ባለው ጎን ያሉት መጋረጃዎች ርዝመታቸው 100 ክንድ ነበር። ሃያዎቹ ቋሚዎቻቸውና 20ዎቹ መሰኪያዎቻቸው ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ። በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው* ደግሞ ከብር የተሠሩ ነበሩ። +12 በስተ ምዕራብ በኩል ባለው ጎን ያሉት መጋረጃዎች ግን ርዝመታቸው 50 ክንድ ነበር። አሥር ቋሚዎችና አሥር መሰኪያዎች ነበሩ፤ በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው* ከብር የተሠሩ ነበሩ። +13 በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይኸውም በፀሐይ መውጫ በኩል ያለው ጎን ርዝመቱ 50 ክንድ ነበር። +14 በአንደኛው በኩል ያሉት የመግቢያው መጋረጃዎች ርዝመታቸው 15 ክንድ ሲሆን ሦስት ቋሚዎችና ሦ���ት መሰኪያዎች ነበሯቸው። +15 በሌላኛው በኩል ያሉት የግቢው መግቢያ መጋረጃዎችም ርዝመታቸው 15 ክንድ ሲሆን ሦስት ቋሚዎችና ሦስት መሰኪያዎች ነበሯቸው። +16 በግቢው ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች በሙሉ በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠሩ ነበሩ። +17 የቋሚዎቹ መሰኪያዎች ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ፤ በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው* ከብር የተሠሩ ሲሆኑ አናታቸውም በብር የተለበጠ ነበር። የግቢው ቋሚዎች በሙሉ ከብር የተሠሩ ማያያዣዎች ነበሯቸው።+ +18 የግቢው መግቢያ መከለያ* ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር ተሸምኖ የተሠራ ነበር። ርዝመቱ 20 ክንድ ሲሆን ከፍታው ደግሞ ልክ እንደ ግቢው መጋረጃዎች 5 ክንድ ነበር።+ +19 አራቱ ቋሚዎቻቸውና አራቱ መሰኪያዎቻቸው ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ። ማንጠልጠያዎቻቸውና ማያያዣዎቻቸው* ከብር የተሠሩ ሲሆኑ አናታቸው ደግሞ በብር የተለበጠ ነበር። +20 የማደሪያ ድንኳኑና በግቢው ዙሪያ የሚገኙት ካስማዎች በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ።+ +21 በሙሴ ትእዛዝ መሠረት ተቆጥረው የተመዘገቡት የማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም የምሥክሩ የማደሪያ ድንኳን+ ዕቃዎች የሚከተሉት ናቸው፤ ይህን ያከናወኑት ሌዋውያኑ+ ሲሆኑ መሪያቸውም የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታምር+ ነበር። +22 ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሁር ልጅ የዖሪ ልጅ ባስልኤል+ ይሖዋ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። +23 ከእሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳማክ ልጅ ኤልያብ+ ነበር፤ እሱም የእጅ ባለሙያና የጥልፍ ባለሙያ እንዲሁም በሰማያዊ ክር፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ በደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በጥሩ በፍታ የሚሸምን የሽመና ባለሙያ ነበር። +24 በአጠቃላይ በቅዱሱ ስፍራ ለተከናወነው ሥራ የዋለው ወርቅ በሙሉ መባ*+ ሆኖ ከቀረበው ወርቅ ጋር ተመጣጣኝ ነበር፤ ይህም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* 29 ታላንት* ከ730 ሰቅል* ነበር። +"25 ከማኅበረሰቡ መካከል ከተመዘገቡት ሰዎች የተገኘው ብር ደግሞ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል 100 ታላንት ከ1,775 ሰቅል ነበር።" +"26 ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗቸው ከተመዘገቡት 603,550+ ሰዎች መካከል የሆነ እያንዳንዱ ግለሰብ የሰጠው ግማሽ ሰቅል፣ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* ግማሽ ሰቅል ነበር።+ " +27 የቅዱሱን ስፍራ መሰኪያዎችና ለመጋረጃው ቋሚዎች የሚሆኑትን መሰኪያዎች ለመሥራት የዋለው 100 ታላንት ብር ነበር፤ 100 መሰኪያዎች 100 ታላንት ነበሩ፤ ይህም ለእያንዳንዱ መሰኪያ አንድ ታላንት ማለት ነው።+ +"28 ለቋሚዎቹ ከ1,775 ሰቅል ብር ማንጠልጠያዎችን ሠራ፤ አናታቸውንም ከለበጠ በኋላ እርስ በርስ አያያዛቸው። " +"29 መባ* ሆኖ የቀረበው መዳብ ደግሞ 70 ታላንት ከ2,400 ሰቅል ነበር።" +30 በዚህም የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መሰኪያዎች፣ የመዳብ መሠዊያውንና የመዳብ ፍርግርጉን እንዲሁም የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ ሠራ፤ +31 እንዲሁም በግቢው ዙሪያ ያሉትን መሰኪያዎች፣ ለግቢው መግቢያ የሚሆኑትን መሰኪያዎች እንዲሁም የማደሪያ ድንኳኑን ካስማዎች በሙሉና በግቢው ዙሪያ ያሉትን የድንኳን ካስማዎች+ በሙሉ ሠራ። +8 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ገብተህ እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ።+ +2 እነሱን ለመልቀቅ አሁንም ፈቃደኛ የማትሆን ከሆነ ምድርህን በሙሉ በእንቁራሪት መቅሰፍት እመታለሁ።+ +3 የአባይም ወንዝ በእንቁራሪቶች ይሞላል፤ እነሱም ወጥተው ወደ ቤትህ፣ ወደ መኝታ ክፍልህ ይገባሉ፤ አልጋህም ላይ ይወጣሉ፤ እንዲሁም ወደ አገልጋዮችህ ቤቶች ይገባሉ፤ ሕዝብህም ���ይ ይወጣሉ፤ መጋገሪያ ምድጃዎችህና ቡሃቃዎችህም ውስጥ ይገባሉ።+ +4 እንቁራሪቶቹ በአንተ፣ በሕዝብህና በአገልጋዮችህ ሁሉ ላይ ይወጡባችኋል።”’” +5 በኋላም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘እጅህን ሰንዝረህ ወንዞቹን፣ የአባይ ወንዝ የመስኖ ቦዮቹንና ረግረጋማ ቦታዎቹን በበትርህ በመምታት እንቁራሪቶቹ በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አድርግ።’” +6 ስለዚህ አሮን በግብፅ ውኃዎች ላይ እጁን ሰነዘረ፤ እንቁራሪቶቹም እየወጡ የግብፅን ምድር መውረር ጀመሩ። +7 ይሁን እንጂ አስማተኞቹ ካህናትም በሚስጥራዊ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር ፈጸሙ፤ እነሱም እንቁራሪቶች በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አደረጉ።+ +8 ከዚያም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ሕዝቡ ለይሖዋ መሥዋዕት እንዲያቀርብ መልቀቅ ስለምፈልግ እንቁራሪቶቹን ከእኔም ሆነ ከሕዝቤ ላይ እንዲያስወግድ ይሖዋን ለምኑልኝ”+ አላቸው። +9 ከዚያም ሙሴ ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “እንቁራሪቶቹ ከአንተ፣ ከአገልጋዮችህ፣ ከሕዝብህና ከቤቶችህ ይወገዱ ዘንድ አምላክን እንድለምንልህ የምትፈልገው መቼ እንደሆነ የመወሰኑን ጉዳይ ለአንተ ትቼዋለሁ። እንቁራሪቶቹ በአባይ ወንዝ ውስጥ ብቻ ተወስነው ይቀራሉ።” +10 እሱም “ነገ ይሁን” አለው። በመሆኑም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ ያለ ማንም እንደሌለ+ እንድታውቅ ልክ እንዳልከው ይሆናል። +11 እንቁራሪቶቹ ከአንተ፣ ከቤቶችህ፣ ከአገልጋዮችህና ከሕዝቦችህ ይወገዳሉ። በአባይ ወንዝ ውስጥ ብቻ ተወስነው ይቀራሉ።”+ +12 ሙሴና አሮንም ከፈርዖን ፊት ወጥተው ሄዱ፤ ሙሴም ይሖዋ በፈርዖን ላይ ያመጣቸውን እንቁራሪቶች አስመልክቶ ወደ እሱ ጮኸ።+ +13 ይሖዋም ሙሴ እንደጠየቀው አደረገ፤ እንቁራሪቶቹም በየቤቱ፣ በየግቢውና በየሜዳው መሞት ጀመሩ። +14 እነሱም እንቁራሪቶቹን በየቦታው ከመሯቸው፤ ምድሪቱም መግማት ጀመረች። +15 ፈርዖንም ችግሩ ጋብ ማለቱን ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንደተናገረውም እነሱን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም።+ +16 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘በትርህን ሰንዝረህ የምድርን አቧራ ምታ፤ አቧራውም በመላው የግብፅ ምድር ላይ ትንኝ ይሆናል።’” +17 እነሱም እንዲሁ አደረጉ። አሮን በእጁ የያዘውን በትር ሰንዝሮ የምድርን አቧራ መታ፤ ትንኞቹም ሰዉንም እንስሳውንም ወረሩ። በምድሪቱ ያለው አቧራ ሁሉ በመላው የግብፅ ምድር ላይ ትንኝ ሆነ።+ +18 አስማተኞቹ ካህናትም ተመሳሳይ ነገር ለመፈጸምና በሚስጥራዊ ጥበባቸው ትንኞች እንዲፈሉ ለማድረግ ሞከሩ፤+ ሆኖም አልቻሉም። ትንኞቹ ሰዉንም እንስሳውንም ወርረው ነበር። +19 በመሆኑም አስማተኞቹ ካህናት ፈርዖንን “ይህ የአምላክ ጣት ነው!”+ አሉት። የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንዳለውም እነሱን አልሰማቸውም። +20 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በማለዳ ተነስተህ ፈርዖን ፊት ቁም። እሱም ወደ ውኃው ይወርዳል! አንተም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። +21 ሕዝቤን የማትለቅ ከሆነ ግን በአንተ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ እንዲሁም በቤቶችህ ውስጥ ተናካሽ ዝንብ እለቃለሁ፤ ዝንቦቹም በግብፅ ያሉትን ቤቶች ይሞላሉ፤ አልፎ ተርፎም የቆሙበትን* መሬት ይሸፍናሉ። +22 በዚያ ቀን ሕዝቤ የሚኖርበትን የጎሸንን ምድር እለያለሁ። በዚያ ምንም ተናካሽ ዝንብ አይኖርም፤+ ይህን በማድረጌም እኔ ይሖዋ በምድሪቱ መካከል እንዳለሁ ታውቃለህ።+ +23 እኔም በሕዝቤና በሕዝብህ መካከል ልዩነት እንዲኖር አደርጋለሁ። ይህ ምልክት ነገ ይፈጸማል።”’” +24 ይሖዋም እን��ለው አደረገ፤ የተናካሽ ዝንብ መንጋም የፈርዖንን ቤትና የአገልጋዮቹን ቤቶች እንዲሁም መላውን የግብፅ ምድር መውረር ጀመረ።+ በተናካሽ ዝንቦቹም የተነሳ ምድሪቱ ክፉኛ ተበላሸች።+ +25 በመጨረሻም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ሂዱ፤ በምድሪቱም ለአምላካችሁ መሥዋዕት ሠዉ” አላቸው። +26 ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “ይሄማ ተገቢ አይደለም፤ ምክንያቱም እኛ ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት የምናደርገው ነገር ለግብፃውያን አስጸያፊ ነው።+ ታዲያ ግብፃውያን የሚጸየፉትን መሥዋዕት እዚያው እነሱ እያዩን ብናቀርብ አይወግሩንም? +27 ስለዚህ ወደ ምድረ በዳው የሦስት ቀን መንገድ እንጓዛለን፤ በዚያም አምላካችን ይሖዋ ባለን መሠረት ለእሱ መሥዋዕት እናቀርባለን።”+ +28 በዚህ ጊዜ ፈርዖን እንዲህ አለ፦ “በምድረ በዳ ለአምላካችሁ ለይሖዋ መሥዋዕት እንድታቀርቡ እለቃችኋለሁ። ብቻ ብዙ ርቃችሁ መሄድ የለባችሁም። ስለ እኔም ለምኑልኝ።”+ +29 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አሁን ከአንተ ተለይቼ እወጣለሁ፤ ይሖዋንም እለምናለሁ፤ ተናካሽ ዝንቦቹም በነገው ዕለት ከፈርዖን፣ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ይወገዳሉ። ሆኖም ፈርዖን፣ ሕዝቡ ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ እንዳይሄድ በመከልከል ሊያታልለን* መሞከሩን ይተው።”+ +30 ከዚያም ሙሴ ከፈርዖን ፊት ወጥቶ በመሄድ ይሖዋን ለመነ።+ +31 ይሖዋም ሙሴ እንዳለው አደረገ፤ ተናካሽ ዝንቦቹም ከፈርዖን፣ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ተወገዱ። አንድም ዝንብ አልቀረም። +32 ሆኖም ፈርዖን እንደገና ልቡን አደነደነ፤ ሕዝቡንም ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም። +11 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ አንድ ተጨማሪ መቅሰፍት አመጣለሁ። ከዚያ በኋላ ከዚህ እንድትሄዱ ይለቃችኋል።+ ደግሞም በሚለቃችሁ ጊዜ አንዳችሁንም ሳያስቀር ከዚህ ያባርራችኋል።+ +2 እንግዲህ አሁን ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ ሁሉ ከየጎረቤቶቻቸው የብርና የወርቅ ዕቃዎችን እንዲጠይቁ ለሕዝቡ ንገር።”+ +3 ይሖዋም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስ ሰጣቸው። ሙሴ ራሱም ቢሆን በፈርዖን አገልጋዮችና በሕዝቡ ፊት በግብፅ ምድር እጅግ የተከበረ ሰው ሆኖ ነበር። +4 ሙሴም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኩለ ሌሊት ገደማ በግብፅ መሃል እወጣለሁ፤+ +5 በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኩር ልጅ አንስቶ የወፍጮ መጅ እስከምትገፋው ባሪያ የበኩር ልጅ ድረስ በግብፅ ምድር ያለ በኩር ሁሉ ይሞታል፤+ የእንስሳም በኩር ሁሉ ይሞታል።+ +6 በመላው የግብፅ ምድርም ከዚያ በፊት በጭራሽ ሆኖ የማያውቅ ከዚያ በኋላም ፈጽሞ ዳግመኛ የማይከሰት ታላቅ ዋይታ ይሆናል።+ +7 ሆኖም ይሖዋ በግብፃውያንና በእስራኤላውያን መካከል ልዩነት ማድረግ እንደሚችል እንድታውቁ በእስራኤላውያን ላይ፣ በሰዎቹም ሆነ በእንስሶቻቸው ላይ ውሻ እንኳ አይጮኽም።’*+ +8 አገልጋዮችህም ሁሉ ወደ እኔ ወርደው ‘አንተም ሆንክ አንተን የሚከተሉ ሰዎች ሁሉ ከዚህ ሂዱልን’ በማለት ይሰግዱልኛል።+ ከዚያ በኋላም እወጣለሁ።” ሙሴም ይህን ተናግሮ በታላቅ ቁጣ ከፈርዖን ፊት ወጣ። +9 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ተአምራቶቼ በግብፅ ምድር ላይ እንዲበዙ+ ፈርዖን እናንተን አይሰማችሁም” አለው።+ +10 ሙሴና አሮንም እነዚህን ሁሉ ተአምራት በፈርዖን ፊት ፈጸሙ፤+ ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ስለፈቀደ ፈርዖን እስራኤላውያን ከምድሩ እንዲሄዱ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም።+ +2 በዚያን ጊዜ ከሌዊ ነገድ የሆነ አንድ ሰው የሌዊን ልጅ አገባ።+ +2 ሴቲቱም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጁም በጣም የሚያምር መሆኑን ስታይ ለሦስት ወር ደብቃ አቆየችው።+ +3 ከዚያ በላይ ደብቃ ልታቆየው እንደማትችል+ ስታውቅ ግን የደንገል ቅርጫት* ወስዳ ቅርጫቱን በቅጥራንና በዝፍት ለቀለቀችው፤ ከዚያም ልጁን በቅርጫቱ ውስጥ አድርጋ በአባይ ወንዝ ዳር በሚገኘው ቄጠማ መሃል አስቀመጠችው። +4 እህቱ+ ግን የሕፃኑ መጨረሻ ምን እንደሚሆን ለማወቅ ራቅ ብላ ቆማ ሁኔታውን ትከታተል ነበር። +5 በዚህ ጊዜ የፈርዖን ሴት ልጅ ገላዋን ልትታጠብ ወደ አባይ ወረደች፤ ደንገጡሮቿም በአባይ ወንዝ ዳር ዳር ይሄዱ ነበር። እሷም በቄጠማው መሃል ቅርጫቱን አየች። ወዲያውኑም ቅርጫቱን እንድታመጣላት ባሪያዋን ላከቻት።+ +6 ቅርጫቱንም ስትከፍት ሕፃኑን አየችው፤ ሕፃኑም እያለቀሰ ነበር። እሷም “ይህ ልጅ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች፤ ያም ሆኖ ለሕፃኑ አዘነችለት። +7 ከዚያም የሕፃኑ እህት የፈርዖንን ልጅ “ከዕብራውያን ሴቶች መካከል ልጁን እያጠባች የምታሳድግልሽ ሞግዚት ልጥራልሽ?” አለቻት። +8 የፈርዖንም ልጅ “አዎ፣ ሂጂ!” አለቻት። ልጅቷም ወዲያውኑ ሄዳ የሕፃኑን እናት+ ጠራቻት። +9 የፈርዖን ልጅም ሴትየዋን “ይህን ሕፃን ወስደሽ እያጠባሽ አሳድጊልኝ፤ እኔም እከፍልሻለሁ” አለቻት። በመሆኑም ሴትየዋ ልጁን ወስዳ እያጠባች ታሳድገው ጀመር። +10 ልጁም ባደገ ጊዜ አምጥታ ለፈርዖን ልጅ ሰጠቻት፤ እሱም ልጇ ሆነ።+ እሷም “ከውኃ ውስጥ አውጥቼዋለሁ” በማለት ስሙን ሙሴ* አለችው።+ +11 ሙሴ በጎለመሰ ጊዜ* ወንድሞቹ የተጫነባቸውን ሸክም+ ለማየት ወደ እነሱ ወጣ፤ ከዚያም ከወንድሞቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ አንድ ግብፃዊ ሲደበድበው አየ። +12 በመሆኑም ወዲያና ወዲህ ተመልክቶ ማንም አለመኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ግብፃዊውን ገድሎ አሸዋ ውስጥ ደበቀው።+ +13 ሆኖም በማግስቱ ሲወጣ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ ተመለከተ። እሱም ጥፋተኛውን “የገዛ ወገንህን የምትመታው ለምንድን ነው?” አለው።+ +14 በዚህ ጊዜ “አንተን በእኛ ላይ አለቃና ፈራጅ ማን አደረገህ? ግብፃዊውን እንደገደልከው እኔንም ልትገድለኝ ታስባለህ?” አለው።+ ሙሴም “ይህ ነገር ታውቋል ማለት ነው!” ብሎ በማሰብ ፈራ። +15 ከዚያም ፈርዖን ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴንም ሊገድለው ሞከረ፤ ይሁን እንጂ ሙሴ ከፈርዖን ሸሽቶ በምድያም+ ምድር ለመኖር ሄደ፤ እዚያም በአንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ። +16 በምድያም የነበረው ካህን+ ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነሱም ውኃ ቀድተው ገንዳውን በመሙላት የአባታቸውን መንጋ ውኃ ለማጠጣት መጡ። +17 ሆኖም እንደወትሮው እረኞቹ መጥተው ሴቶቹን አባረሯቸው። በዚህ ጊዜ ሙሴ ተነስቶ ለሴቶቹ አገዘላቸው፤* መንጋቸውንም አጠጣላቸው። +18 ሴቶቹም ወደ ቤት፣ ወደ አባታቸው ወደ ረኡዔል*+ በተመለሱ ጊዜ አባታቸው “ዛሬ እንዴት ቶሎ መጣችሁ?” ሲል በመገረም ጠየቃቸው። +19 እነሱም “አንድ ግብፃዊ+ ከእረኞቹ እጅ አዳነን፤ እንዲያውም ውኃ ቀድቶ መንጋችንን አጠጣልን” አሉት። +20 እሱም ልጆቹን “ታዲያ ሰውየው የት አለ? ለምን ትታችሁት መጣችሁ? አብሮን ይበላ ዘንድ ጥሩት” አላቸው። +21 ከዚያ በኋላ ሙሴ ከሰውየው ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ሰውየውም ልጁን ሲፓራን+ ለሙሴ ዳረለት። +22 እሷም ከጊዜ በኋላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም “በባዕድ አገር የምኖር የባዕድ አገር ሰው ሆንኩ”+ በማለት ስሙን ጌርሳም*+ አለው። +23 ከረጅም ጊዜ* በኋላ የግብፁ ንጉሥ ሞተ፤+ እስራኤላውያን ግን ካሉበት የባርነት ሕይወት የተነሳ መቃተታቸውንና እሮሮ ማሰማታቸውን አላቆሙም ነበር፤ ከባርነት ሕይወታቸው የተነሳ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙት ጩኸት ወደ እውነተኛው አምላክ ወጣ።+ +24 ከጊዜ በኋላም አምላክ በመቃተት የሚያሰሙትን ጩኸት አዳመጠ፤+ እንዲሁም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳኑን አሰበ።+ +25 በመሆኑም አምላክ እስራኤላውያንን አየ፤ ያሉበትንም ሁኔታ ተመለከተ። +26 “በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ እንዲሁም ከደማቅ ቀይ ማግ ከተዘጋጁ አሥር የድንኳን ጨርቆች የማደሪያ ድንኳኑን+ ትሠራለህ። በጨርቆቹ ላይ ኪሩቦችን+ ትጠልፍባቸዋለህ።+ +2 የእያንዳንዱ የድንኳን ጨርቅ ርዝመት 28 ክንድ* ወርዱ ደግሞ 4 ክንድ ይሆናል። ሁሉም የድንኳን ጨርቆች መጠናቸው እኩል ይሆናል።+ +3 አምስቱ የድንኳን ጨርቆች አንድ ላይ ይቀጣጠላሉ፤ የቀሩት አምስቱ የድንኳን ጨርቆችም እንዲሁ አንድ ላይ ይቀጣጠላሉ። +4 እርስ በርስ ከተቀጣጠሉት የድንኳን ጨርቆች በመጨረሻው ጨርቅ ጠርዝ ላይ ከሰማያዊ ክር የተሠሩ ማቆላለፊያዎችን ታደርጋለህ፤ እርስ በርስ የተቀጣጠለው ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት የመጨረሻው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይም እንዲሁ ታደርጋለህ። +5 በአንደኛው የድንኳን ጨርቅ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ትሠራለህ፤ በሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ጠርዝ ላይም 50 ማቆላለፊያዎችን ታደርጋለህ፤ ማቆላለፊያዎቹም የሚጋጠሙበት ቦታ ላይ እርስ በርሳቸው ትይዩ ይሆናሉ። +6 ከዚያም 50 የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርተህ የድንኳን ጨርቆቹን በማያያዣዎቹ አማካኝነት እርስ በርስ ታጋጥማቸዋለህ፤ በዚህ መንገድ ማደሪያ ድንኳኑ አንድ ወጥ ይሆናል።+ +7 “በተጨማሪም ለማደሪያ ድንኳኑ ልባስ የሚሆኑ ጨርቆችን ከፍየል ፀጉር+ ትሠራለህ። አሥራ አንድ የድንኳን ጨርቆችን ትሠራለህ።+ +8 የእያንዳንዱ የድንኳን ጨርቅ ርዝመት 30 ክንድ ወርዱ ደግሞ 4 ክንድ ይሆናል። የአሥራ አንዱም የድንኳን ጨርቆች መጠን እኩል ይሆናል። +9 አምስቱን የድንኳን ጨርቆች አንድ ላይ ትቀጣጥላቸዋለህ፤ የቀሩትን ስድስቱን የድንኳን ጨርቆች ደግሞ አንድ ላይ ትቀጣጥላቸዋለህ፤ ስድስተኛውን የድንኳን ጨርቅ በድንኳኑ ፊት በኩል ታጥፈዋለህ። +10 እርስ በርስ ከተቀጣጠሉት የድንኳን ጨርቆች በመጨረሻው ጠርዝ ላይ 50 ማቆላለፊያዎችን ትሠራለህ፤ እርስ በርስ የተቀጣጠለው ሌላኛው የድንኳን ጨርቅ ከዚህኛው ጋር በሚጋጠምበት ጨርቅ ጠርዝ ላይም 50 ማቆላለፊያዎችን ታደርጋለህ። +11 ከዚያም 50 የመዳብ ማያያዣዎችን ትሠራለህ፤ ማያያዣዎቹንም ማቆላለፊያዎቹ ውስጥ በማስገባት ድንኳኑን ታጋጥመዋለህ፤ በዚህ መንገድ የድንኳኑ ጨርቅ አንድ ወጥ ይሆናል። +12 ከድንኳኑ ጨርቆች ትርፍ ሆኖ የወጣው እንደተንጠለጠለ ይተዋል። ትርፍ ሆኖ የወጣው ግማሹ የድንኳን ጨርቅ በማደሪያ ድንኳኑ ጀርባ ላይ ይንጠለጠላል። +13 ትርፍ ሆኖ የወጣው አንድ አንድ ክንድ ጨርቅ ድንኳኑን እንዲሸፍን በማደሪያ ድንኳኑ ጎንና ጎን ይንጠለጠላል። +14 “በተጨማሪም ቀይ ቀለም ከተነከረ የአውራ በግ ቆዳ ለድንኳኑ መደረቢያ ትሠራለህ፤ በዚያ ላይ የሚደረግ መደረቢያም ከአቆስጣ ቆዳ ትሠራለህ።+ +15 “የግራር እንጨት ጣውላዎችን በማገጣጠም ለማደሪያ ድንኳኑ የሚሆኑ አራት ማዕዘን ቋሚዎችን ትሠራለህ።+ +16 የእያንዳንዱ ቋሚ ቁመት አሥር ክንድ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ይሆናል። +17 እያንዳንዱ ቋሚም እርስ በርስ የተያያዙ ሁለት ጉጦች ይኑሩት። ለማደሪያ ድንኳኑ የሚያገለግሉትን ቋሚዎች በሙሉ በዚህ መንገድ ሥራቸው። +18 በስተ ደቡብ በኩል ለሚገኘው ፊቱ በደቡብ አቅጣጫ ላለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን 20 ቋሚዎችን ትሠራለህ። +19 “ከ20ዎቹ ቋሚዎች ሥር የሚሆኑ 40 የብር መሰኪያዎችን+ ትሠራለህ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ያሉት ሁለት ጉጦች ሁለት መሰኪያዎች፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ቋሚ ሥር ያሉት ሁለት ጉጦችም+ ሁለት መሰኪያዎች ይኖሯቸዋል። +20 በስተ ሰሜን በኩል ላለው ለሌላኛውም የማደሪያ ድንኳኑ ጎን 20 ቋሚዎችን ሥራ፤ +21 እንዲሁም 40 የብር መሰኪያዎቻቸውን ሥራ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች ይኑሩ። +22 በስተ ምዕራብ በኩል ለሚገኘው ለኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ስድስት ቋሚዎችን ትሠራለህ።+ +23 በማደሪያ ድንኳኑ በስተ ኋላ በኩል የማዕዘን ቋሚዎች እንዲሆኑ ሁለት ቋሚዎችን ትሠራለህ። +24 ቋሚዎቹም ከታች አንስቶ የመጀመሪያው ቀለበት እስከሚገኝበት እስከ ላይ ድረስ ድርብ መሆን አለባቸው። ሁለቱም በዚህ መንገድ መሠራት አለባቸው፤ እነሱም ሁለት የማዕዘን ቋሚዎች ሆነው ያገለግላሉ። +25 ስምንት ቋሚዎችና ከብር የተሠሩ 16 መሰኪያዎች ይኸውም በአንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች ይኖራሉ። +26 “ከግራር እንጨት አግዳሚ እንጨቶችን ታዘጋጃለህ፤ በአንዱ ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን፣+ +27 በሌላኛው ጎን ላሉት የማደሪያ ድንኳኑ ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን እንዲሁም በስተ ምዕራብ በኩል ባለው በኋለኛው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ላሉት ቋሚዎች አምስት አግዳሚ እንጨቶችን ታዘጋጃለህ። +28 በቋሚዎቹ መሃል ላይ የሚያርፈው መካከለኛው አግዳሚ እንጨት ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚዘልቅ መሆን ይኖርበታል። +29 “ቋሚዎቹን በወርቅ ትለብጣቸዋለህ፤+ አግዳሚ እንጨቶቹን የሚሸከሙትን የቋሚዎቹን ቀለበቶች ከወርቅ ትሠራቸዋለህ፤ አግዳሚ እንጨቶቹንም በወርቅ ትለብጣቸዋለህ። +30 የማደሪያ ድንኳኑን በተራራው ላይ ተገልጦልህ ባየኸው ንድፍ መሠረት ትከለው።+ +31 “ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር መጋረጃ+ ትሠራለህ። በላዩም ላይ ኪሩቦች ይጠለፉበታል። +32 መጋረጃውንም በወርቅ በተለበጡ አራት የግራር እንጨት ዓምዶች ላይ ታንጠለጥለዋለህ። ማንጠልጠያዎቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ። ዓምዶቹም ከብር በተሠሩ አራት መሰኪያዎች ላይ ይቆማሉ። +33 መጋረጃውን ከማያያዣዎቹ በታች ታንጠለጥለዋለህ፤ የምሥክሩንም ታቦት+ በመጋረጃው ውስጥ ታስቀምጠዋለህ። መጋረጃውም ቅድስቱንና+ ቅድስተ ቅዱሳኑን+ ለመለየት ያገለግላችኋል። +34 መክደኛውንም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ በሚገኘው በምሥክሩ ታቦት ላይ ግጠመው። +35 “ጠረጴዛውንም ከመጋረጃው ውጭ ታስቀምጠዋለህ፤ መቅረዙን+ በስተ ደቡብ በኩል ባለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ ታስቀምጠዋለህ፤ ጠረጴዛውን ደግሞ በስተ ሰሜን በኩል ታስቀምጠዋለህ። +36 ለድንኳኑ መግቢያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር የተሸመነ መከለያ* ትሠራለህ።+ +37 ለመከለያውም* አምስት ዓምዶችን ከግራር እንጨት ትሠራለህ፤ በወርቅም ትለብጣቸዋለህ። ማንጠልጠያዎቹም ከወርቅ የተሠሩ ይሆናሉ፤ ለዓምዶቹም አምስት የመዳብ መሰኪያዎችን ትሠራለህ። +4 ሆኖም ሙሴ “‘ይሖዋ አልተገለጠልህም’ ቢሉኝና ባያምኑኝስ? ቃሌንስ ባይሰሙ?”+ አለው። +2 ይሖዋም “በእጅህ የያዝከው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። እሱም መልሶ “በትር ነው” አለ። +3 እሱም “መሬት ላይ ጣለው” አለው። እሱም መሬት ላይ ጣለው፤ በትሩም እባብ ሆነ፤+ ሙሴም ከእባቡ ሸሸ። +4 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን “እጅህን ዘርግተህ ጅራቱን ያዘው” አለው። እሱም እጁን ዘርግቶ ያዘው፤ እባቡም በእጁ ላይ እንደገና በትር ሆነ። +5 ከዚያም አምላክ “ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ይሖዋ+ እንደተገለጠልህ እንዲያምኑ ነው” አለው።+ +6 ይሖዋም በድጋሚ “እባክህ እጅህን ወዳጣፋኸው ��ብስ ውስጥ አስገባ” አለው። እሱም እጁን ወዳጣፋው ልብስ ውስጥ አስገባ። ባወጣውም ጊዜ እጁ በለምጽ ተመቶ ልክ እንደ በረዶ ነጭ ሆኖ ነበር!+ +7 ከዚያም “እጅህን ወዳጣፋኸው ልብስ ውስጥ መልሰህ አስገባው” አለው። እሱም እጁን መልሶ ልብሱ ውስጥ አስገባው። እጁንም ከልብሱ ውስጥ ባወጣው ጊዜ እጁ ተመልሶ እንደ ሌላው የሰውነቱ ክፍል ሆነ! +8 እሱም እንዲህ አለው፦ “ባያምኑህ ወይም የመጀመሪያውን ተአምራዊ ምልክት ችላ ቢሉ እንኳ የኋለኛውን ተአምራዊ ምልክት በእርግጥ አምነው ይቀበላሉ።+ +9 እንደዛም ሆኖ እነዚህን ሁለት ምልክቶች ባያምኑና ቃልህን ለመስማት ፈቃደኛ ባይሆኑ ከአባይ ወንዝ ውኃ ቀድተህ በደረቁ መሬት ላይ አፍስሰው፤ ከአባይ የቀዳኸው ውኃ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል።”+ +10 ሙሴም ይሖዋን “ይሖዋ ሆይ፣ ይቅርታ አድርግልኝ፤ እኔ ከዚህ በፊትም ሆነ አንተ አገልጋይህን ካነጋገርክበት ጊዜ ጀምሮ ፈጽሞ አንደበተ ርቱዕ አይደለሁም፤ ንግግር የማልችልና* ተብታባ ሰው ነኝ” አለው።+ +11 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “ለሰው አፍ የፈጠረለት ማን ነው? ሰዎችን ዱዳ፣ ደንቆሮ ወይም ዕውር የሚያደርግ አሊያም ለሰዎች የዓይን ብርሃን የሚሰጥ ማን ነው? እኔ ይሖዋ አይደለሁም? +12 በል አሁን ሂድ፤ በምትናገርበት ጊዜ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤* የምትናገረውንም ነገር አስተምርሃለሁ።”+ +13 እሱ ግን “ይሖዋ ሆይ፣ ይቅርታ አድርግልኝ፤ እባክህ መላክ የፈለግከውን ሌላ ማንኛውንም ሰው ላክ” አለው። +14 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በሙሴ ላይ ነደደ፤ እንዲህም አለው፦ “እሺ ሌዋዊው ወንድምህ አሮንስ?+ እሱ በደንብ መናገር እንደሚችል አውቃለሁ። ደግሞም አንተን ለማግኘት አሁን ወደዚህ እየመጣ ነው። በሚያይህም ጊዜ ልቡ በደስታ ይሞላል።+ +15 ስለሆነም እሱን አነጋግረው፤ ቃላቱንም በአንደበቱ አኑር፤+ በምትናገሩበትም ጊዜ ከአንተና ከእሱ ጋር እሆናለሁ፤+ ምን ማድረግ እንዳለባችሁም አስተምራችኋለሁ። +16 እሱም አንተን ወክሎ ለሕዝቡ ይናገራል፤ እንደ ቃል አቀባይም ይሆንልሃል፤ አንተም ለእሱ እንደ አምላክ ትሆናለህ።*+ +17 ይህን በትር በእጅህ ይዘህ ትሄዳለህ፤ በእሱም ተአምራዊ ምልክቶቹን ትፈጽማለህ።”+ +18 ስለዚህ ሙሴ ወደ አማቱ ወደ ዮቶር+ ተመልሶ በመሄድ “እስካሁን በሕይወት መኖር አለመኖራቸውን አይ ዘንድ እባክህ በግብፅ ወዳሉት ወንድሞቼ ተመልሼ ልሂድ” አለው። ዮቶርም ሙሴን “በሰላም ሂድ” አለው። +19 ከዚያ በኋላ ይሖዋ ሙሴን በምድያም ሳለ “ሂድ፤ ወደ ግብፅ ተመለስ፤ ነፍስህን ለማጥፋት የሚፈልጉት ሰዎች በሙሉ ሞተዋል” አለው።+ +20 ከዚያም ሙሴ ሚስቱንና ልጆቹን በአህያ ላይ አስቀምጦ ወደ ግብፅ ምድር ለመመለስ ጉዞ ጀመረ። የእውነተኛውን አምላክ በትርም በእጁ ይዞ ነበር። +21 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ግብፅ ከተመለስክ በኋላ፣ በሰጠሁህ ኃይል የምታከናውናቸውን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ።+ እኔ ግን ልቡ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤+ እሱም ሕዝቡን አይለቅም።+ +22 ፈርዖንንም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ልጄ ነው፤ አዎ፣ የበኩር ልጄ ነው።+ +23 እንግዲህ ‘እንዲያገለግለኝ ልጄን ልቀቅ’ ብዬሃለሁ። ለመልቀቅ ፈቃደኛ ካልሆንክ ግን ልጅህን፣ አዎ የበኩር ልጅህን እገድላለሁ።”’”+ +24 ይሖዋም+ በመንገድ ላይ ባለው የእንግዳ ማረፊያ ስፍራ አገኘው፤ እሱንም ሊገድለው ፈልጎ ነበር።+ +25 በመጨረሻም ሲፓራ+ ባልጩት ወስዳ ልጇን ገረዘችው፤ ሸለፈቱን እግሩን ካስነካች በኋላም “ይህ የሆነው አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ስለሆንክ ነው” አለች። +26 ስለሆነም እንዲሄድ ፈቀደለት። እሷም በዚህ ጊዜ በግርዛቱ ��ተነሳ “የደም ሙሽራ” አለች። +27 ይሖዋም አሮንን “ሙሴን ለማግኘት ወደ ምድረ በዳ ሂድ” አለው።+ እሱም ሄደ፤ በእውነተኛውም አምላክ ተራራ+ ላይ አገኘው፤ ከዚያም ሳመው። +28 ሙሴም ይሖዋ እንዲናገር የላከውን ቃል ሁሉ+ እንዲሁም እንዲፈጽማቸው ያዘዘውን ተአምራዊ ምልክቶች ሁሉ+ ለአሮን ነገረው። +29 ከዚህ በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው የእስራኤልን ሽማግሌዎች በሙሉ ሰበሰቡ።+ +30 አሮንም ይሖዋ ለሙሴ የነገረውን ቃል ሁሉ ነገራቸው፤ እሱም በሕዝቡ ፊት ተአምራዊ ምልክቶቹን አደረገ።+ +31 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ አመነ።+ ይሖዋ ፊቱን ወደ እስራኤላውያን እንደመለሰና+ ሥቃያቸውንም እንዳየ+ ሲሰሙ ተደፍተው ሰገዱ። +37 ከዚያም ባስልኤል+ ከግራር እንጨት ታቦቱን+ ሠራ። ርዝመቱ ሁለት ክንድ* ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ከፍታው ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር።+ +2 ውስጡንና ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት።+ +3 ከአራቱ እግሮቹ በላይ የሚሆኑ አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራለት፤ ሁለቱን ቀለበቶች በአንድ ጎኑ፣ ሁለቱን ቀለበቶች ደግሞ በሌላኛው ጎኑ በኩል አደረጋቸው። +4 ከዚያም ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሠራ፤ በወርቅም ለበጣቸው።+ +5 ታቦቱንም ለመሸከም እንዲያገለግሉ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎንና ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው።+ +6 እሱም ከንጹሕ ወርቅ መክደኛውን ሠራ።+ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር።+ +7 በተጨማሪም በመክደኛው+ ጫፍና ጫፍ ላይ ከተጠፈጠፈ ወርቅ ሁለት ኪሩቦችን+ ሠራ። +8 አንዱ ኪሩብ በአንዱ ጫፍ ሌላኛው ኪሩብ ደግሞ በሌላኛው ጫፍ ላይ ነበር። ኪሩቦቹን በሁለቱም የመክደኛው ጫፎች ላይ ሠራቸው። +9 ሁለቱ ኪሩቦችም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት መክደኛውን በክንፎቻቸው ከልለውት ነበር።+ እርስ በርስ ትይዩ ነበሩ፤ ፊታቸውንም ወደ መክደኛው አጎንብሰው ነበር።+ +10 ከዚያም ከግራር እንጨት ጠረጴዛውን ሠራ።+ ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ ከፍታው ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል ነበር።+ +11 በንጹሕ ወርቅም ለበጠው፤ ዙሪያውንም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። +12 ከዚያም በዙሪያው አንድ ጋት* ስፋት ያለው ጠርዝ ሠራለት፤ ለጠርዙም ዙሪያውን የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። +13 በተጨማሪም አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠራለት፤ ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮቹ በሚገኙባቸው አራት ማዕዘኖች ላይ አደረጋቸው። +14 ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች የሚይዙት ቀለበቶች በጠርዙ አጠገብ ነበሩ። +15 ከዚያም ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። +16 በኋላም በጠረጴዛው ላይ የሚሆኑትን ዕቃዎች ይኸውም ሳህኖቹንና ጽዋዎቹን እንዲሁም ለመጠጥ መባ ማፍሰሻ የሚያገለግሉትን ጎድጓዳ ሳህኖቹንና ማንቆርቆሪያዎቹን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።+ +17 ከዚያም መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።+ መቅረዙን ጠፍጥፎ ሠራው። የመቅረዙ መቆሚያ፣ ግንዱ፣ አበባ አቃፊዎቹ፣ እንቡጦቹና የፈኩት አበቦች ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ።+ +18 መቅረዙ ከግንዱ ላይ የወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ነበሩት፤ ሦስቱ ቅርንጫፎቹ ከአንዱ ጎን ሦስቱ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ከሌላው ጎን የወጡ ነበሩ። +19 በአንዱ በኩል ባሉት ቅርንጫፎች በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎች ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር በማፈራረቅ ተሠርተው ነበር፤ በሌላኛው በኩል ባሉት ቅርንጫፎችም በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎች ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር +20 በመቅረዙም ግንድ ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ አራት የአበባ አቃፊዎች ከእን���ጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር በማፈራረቅ ተሠርተው ነበር። +21 ከግንዱ በሚወጡት በመጀመሪያዎቹ ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ፣ ቀጥሎ ባሉት ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ እንዲሁም ቀጥሎ ባሉት ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ ነበር፤ ከመቅረዙ ግንድ ለሚወጡት ስድስት ቅርንጫፎች እንዲሁ ተደርጎላቸው ነበር። +22 እንቡጦቹም ሆኑ ቅርንጫፎቹ፣ መላው መቅረዙ ከንጹሕ ወርቅ ተጠፍጥፎ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር። +23 ከዚያም ሰባቱን መብራቶች+ እንዲሁም መቆንጠጫዎቹንና መኮስተሪያዎቹን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። +24 መቅረዙን ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር የሠራው ከአንድ ታላንት* ንጹሕ ወርቅ ነበር። +25 ከዚያም ከግራር እንጨት የዕጣን መሠዊያውን+ ሠራ። ርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ ሆኖ አራቱም ጎኖቹ እኩል ሲሆኑ ከፍታው ደግሞ ሁለት ክንድ ነበር። ቀንዶቹ ከዚያው ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ።+ +26 እሱም ላዩን፣ ሁሉንም ጎኖቹን እንዲሁም ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ሠራለት። +27 መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች እንዲይዙም በሁለቱ ተቃራኒ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራለት። +28 ከዚያ በኋላ መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። +29 በተጨማሪም ቅዱሱን የቅብዓት ዘይትና+ በብልሃት የተቀመመውን ጥሩ መዓዛ ያለውን ንጹሕ ዕጣን+ አዘጋጀ። +40 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የማደሪያ ድንኳኑን ይኸውም የመገናኛ ድንኳኑን ትከል።+ +3 የምሥክሩን ታቦት በውስጡ ካስቀመጥክ+ በኋላ ታቦቱን በመጋረጃው ከልለው።+ +4 ጠረጴዛውንም+ ካስገባህ በኋላ በላዩ ላይ የሚቀመጡትን ነገሮች አስተካክለህ አስቀምጥ፤ መቅረዙንም+ አስገብተህ መብራቶቹን+ አብራቸው። +5 ከዚያም ለዕጣን የሚሆነውን የወርቅ መሠዊያ+ ከምሥክሩ ታቦት በፊት አስቀምጠው፤ ለማደሪያ ድንኳኑ መግቢያ የሚሆነውን መከለያም* በቦታው አድርገው።+ +6 “የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያም+ በማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ፊት አድርገው፤ +7 ገንዳውንም በመገናኛ ድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አድርገህ ውኃ ጨምርበት።+ +8 በመገናኛ ድንኳኑም ዙሪያ ግቢ ከልልለት፤+ ለግቢውም መግቢያ መከለያ*+ አድርግለት። +9 የማደሪያ ድንኳኑም የተቀደሰ እንዲሆን የቅብዓት ዘይቱን+ ወስደህ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች በሙሉ ትቀባቸዋለህ፤+ ድንኳኑንም ሆነ ዕቃዎቹን በሙሉ ትቀድሳለህ። +10 የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትም መሠዊያ እጅግ ቅዱስ እንዲሆን መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ ትቀባቸዋለህ፤ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ።+ +11 ገንዳውንና ማስቀመጫውንም ቀባ፤ ቀድሰውም። +12 “ከዚያም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ አቅርባቸው፤ በውኃም እጠባቸው።+ +13 አሮንንም ቅዱስ የሆኑትን ልብሶች ካለበስከው+ በኋላ ቀባው፤+ እንዲሁም ቀድሰው፤ እሱም ካህን ሆኖ ያገለግለኛል። +14 ከዚያም ወንዶች ልጆቹን አቅርበህ ረጃጅሞቹን ቀሚሶች አልብሳቸው።+ +15 ካህናት ሆነውም እንዲያገለግሉኝ አባታቸውን እንደቀባኸው ሁሉ እነሱንም ቀባቸው፤+ መቀባታቸውም ክህነታቸው ለትውልዶቻቸው ሁሉ በዘላቂነት እንዲቀጥል ያስችላል።”+ +16 ሙሴም ይሖዋ ባዘዘው መሠረት አደረገ።+ ልክ እንደዚሁ አደረገ። +17 በሁለተኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የማደሪያ ድንኳኑ ተተከለ።+ +18 ሙሴም የማደሪያ ድንኳኑን ሲተክል መሰኪያዎቹን+ ከሥር በማስቀመጥ አራት ማዕዘን ቋሚዎቹን+ አደረገባቸው፤ አግዳሚ እንጨቶቹንም+ አስገባቸው፤ ዓምዶቹንም አቆማቸው። +19 ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የማደሪያ ድንኳኑን በድንኳኑ ጨርቅ አለበሰው፤+ በላዩም ላይ የድንኳኑን መደረቢያ ደረበበት።+ +20 ቀጥሎም የምሥክሩን ጽላቶች+ ወስዶ በታቦቱ+ ውስጥ አስቀመጣቸው፤ የታቦቱንም መሎጊያዎች+ አስገባቸው፤ መክደኛውንም+ በታቦቱ ላይ አደረገው።+ +21 ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ታቦቱን ወደ ማደሪያ ድንኳኑ አስገባው፤ የመግቢያው መከለያ የሆነውን መጋረጃ+ በቦታው በማድረግ የምሥክሩን ታቦት ከለለው።+ +22 በመቀጠልም ጠረጴዛውን+ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በስተ ሰሜን በኩል ባለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን ከመጋረጃው ውጭ አደረገው፤ +23 በላዩም ላይ ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የተነባበረውን ኅብስት በይሖዋ ፊት አስቀመጠ።+ +24 መቅረዙንም+ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ከጠረጴዛው ትይዩ፣ በስተ ደቡብ በኩል ባለው የማደሪያ ድንኳኑ ጎን አስቀመጠው። +25 ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት መብራቶቹን+ በይሖዋ ፊት አበራቸው። +26 የወርቅ መሠዊያውንም+ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ከመጋረጃው በፊት አስቀመጠው፤ +27 ይህን ያደረገውም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ እንዲጨስበት+ ነው። +28 ቀጥሎም የማደሪያ ድንኳኑን መግቢያ መከለያ*+ በቦታው አደረገው። +29 ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የሚቃጠለውን መባና የእህሉን መባ በላዩ ላይ እንዲያቀርብበት የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ+ በማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ አደረገው። +30 በመቀጠልም ገንዳውን በመገናኛ ድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አደረገው፤ ለመታጠቢያ የሚሆን ውኃም ጨመረበት።+ +31 ሙሴ እንዲሁም አሮንና ወንዶች ልጆቹ እጃቸውንና እግራቸውን ታጠቡበት። +32 ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገቡበትና ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ ሁሉ ይታጠቡ ነበር።+ +33 በመጨረሻም በማደሪያ ድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ግቢውን ከለለ፤+ ለግቢውም መግቢያ መከለያ* አደረገለት።+ በዚህ መንገድ ሙሴ ሥራውን አጠናቀቀ። +34 ደመናውም የመገናኛ ድንኳኑን ሸፈነው፤ የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ሞላው።+ +35 ደመናው በመገናኛ ድንኳኑ ላይ አርፎ ስለነበርና የይሖዋም ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ስለሞላው ሙሴ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግባት አልቻለም ነበር።+ +36 እስራኤላውያንም በጉዟቸው ወቅት ሁሉ ደመናው ከማደሪያ ድንኳኑ ላይ በሚነሳበት ጊዜ ድንኳናቸውን ነቅለው ይንቀሳቀሱ ነበር።+ +37 ሆኖም ደመናው ካልተነሳ፣ ደመናው እስከሚነሳበት ቀን ድረስ ድንኳናቸውን ነቅለው አይንቀሳቀሱም ነበር።+ +38 መላው የእስራኤል ቤት በሚጓዝበት ወቅት ሁሉ ቀን ቀን የይሖዋ ደመና፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ እሳት በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ሆኖ ያይ ነበር።+ +16 ከኤሊም ከተነሱ በኋላም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ከግብፅ ምድር በወጣ በሁለተኛው ወር በ15ኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወደሚገኘው ወደ ሲን ምድረ በዳ+ መጣ። +2 ከዚያም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ በምድረ በዳ ሳለ በሙሴና በአሮን ላይ ማጉረምረም ጀመረ።+ +3 እስራኤላውያንም እንዲህ ይሏቸው ነበር፦ “በግብፅ ምድር በሥጋው ድስት አጠገብ ተቀምጠን ሳለንና እስክንጠግብ ድረስ ዳቦ ስንበላ በነበረበት ጊዜ ምነው በይሖዋ እጅ ሞተን ባረፍነው ኖሮ።+ እናንተ ግን ይህን ጉባኤ በሙሉ በረሃብ ልትጨርሱት ወደዚህ ምድረ በዳ አመጣችሁን።”+ +4 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኔ ከሰማይ ምግብ አዘንብላችኋለሁ፤+ ሕዝቡም ይውጣ፤ እያንዳንዱም ሰው ወጥቶ የሚበቃውን ያህል በየዕለቱ ይሰብስብ፤+ በዚህም ሕጌን አክብረው ይመላለሱ እንደሆነና እን���ልሆነ እፈትናቸዋለሁ።+ +5 በስድስተኛው ቀን+ የሰበሰቡትን በሚያዘጋጁበት ጊዜ ግን በሌሎቹ ቀናት ከሚሰበስቡት እጥፍ ይሁን።”+ +6 በመሆኑም ሙሴና አሮን እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አሏቸው፦ “ከግብፅ ምድር ያወጣችሁ ይሖዋ መሆኑን በዚህ ምሽት በእርግጥ ታውቃላችሁ።+ +7 ጠዋት ላይ የይሖዋን ክብር ታያላችሁ፤ ምክንያቱም ይሖዋ በእሱ ላይ ማጉረምረማችሁን ሰምቷል። በእኛ ላይ የምታጉረመርሙት ለመሆኑ እኛ ማን ነን?” +8 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ምሽት ላይ፣ የምትበሉት ሥጋ ጠዋት ላይ ደግሞ የምትፈልጉትን ያህል ዳቦ ሲሰጣችሁ ይሖዋ በእሱ ላይ ያጉረመረማችሁትን ማጉረምረም እንደሰማ ታያላችሁ። ታዲያ እኛ ማን ነን? ያጉረመረማችሁት በእኛ ላይ ሳይሆን በይሖዋ ላይ ነው።”+ +9 ሙሴም አሮንን “ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ‘ማጉረምረማችሁን ስለሰማ ኑ በይሖዋ ፊት ቅረቡ’ በላቸው” አለው።+ +10 አሮን ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ወደ ምድረ በዳው ዞሮ ቆመ፤ በዚህ ጊዜ የይሖዋ ክብር በደመናው ውስጥ ተገለጠ።+ +11 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +12 “የእስራኤላውያንን ማጉረምረም ሰምቻለሁ።+ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘አመሻሹ ላይ* ሥጋ ትበላላችሁ፤ ጠዋት ላይ ደግሞ ዳቦ ትጠግባላችሁ፤+ እኔም አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ታውቃላችሁ።’”+ +13 በዚህም መሠረት ምሽት ላይ ድርጭቶች መጥተው ሰፈሩን አለበሱት፤+ ጠዋት ላይም በሰፈሩ ውስጥ ሁሉ ጤዛ ወርዶ ነበር። +14 በኋላም ጤዛው ሲተን በምድረ በዳው ላይ እንደ አመዳይ ደቃቅ የሆነ ቅርፊት የሚመስል ስስ ነገር+ መሬቱ ላይ ታየ። +15 እስራኤላውያንም ባዩት ጊዜ ምን እንደሆነ ስላላወቁ እርስ በርሳቸው “ይህ ነገር ምንድን ነው?” ይባባሉ ጀመር። ስለሆነም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንድትበሉት የሰጣችሁ ምግብ ነው።+ +16 ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦ ‘እያንዳንዱ ሰው የሚበላውን ያህል ይሰብስብ። እያንዳንዳችሁ በድንኳናችሁ ውስጥ ባሉት ሰዎች ቁጥር* ልክ ለእያንዳንዱ ሰው አንድ ኦሜር*+ ሰፍራችሁ ውሰዱ።’” +17 እስራኤላውያንም እንደተባሉት አደረጉ፤ ይሰበስቡም ጀመር፤ አንዳንዶቹ ብዙ ሌሎቹ ደግሞ ትንሽ ሰበሰቡ። +18 የሰበሰቡትን በኦሜር ሲሰፍሩት ብዙ የሰበሰበው ምንም ትርፍ አላገኘም፤ ጥቂት የሰበሰበውም ምንም አልጎደለበትም።+ እያንዳንዳቸው የሰበሰቡት የሚበሉትን ያህል ነበር። +19 ከዚያም ሙሴ “ማንም ሰው እስከ ጠዋት ድረስ ምንም ማስተረፍ የለበትም”+ አላቸው። +20 እነሱ ግን ሙሴን አልሰሙትም። አንዳንዶቹ ከሰበሰቡት ውስጥ የተወሰነውን አሳደሩት፤ ሆኖም ተልቶ መሽተት ጀመረ፤ በመሆኑም ሙሴ በእነሱ ላይ እጅግ ተቆጣ። +21 በየማለዳው እያንዳንዱ ሰው የሚበላውን ያህል ይሰበስብ ነበር። ፀሐዩ እየበረታ በሚሄድበት ጊዜም ይቀልጥ ነበር። +22 በስድስተኛውም ቀን ሁለት እጥፍ ምግብ+ ይኸውም ለአንድ ሰው ሁለት ኦሜር ሰበሰቡ። በመሆኑም የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ መጥተው ሁኔታውን ለሙሴ ነገሩት። +23 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ይሄማ ይሖዋ የተናገረው ነገር ነው። ነገ ሙሉ በሙሉ የእረፍት ቀን* ይኸውም ለይሖዋ ቅዱስ ሰንበት ይሆናል።+ የምትጋግሩትን ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤+ የተረፈውን ሁሉ አስቀምጡ፤ እስከ ጠዋትም ድረስ አቆዩት።” +24 እነሱም ልክ ሙሴ ባዘዛቸው መሠረት እስከ ጠዋት ድረስ አቆዩት፤ ምግቡም አልሸተተም ወይም አልተላም። +25 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ዛሬ ይህን ብሉ፤ ምክንያቱም ዛሬ የይሖዋ ሰንበት ነው። ዛሬ ሜዳው ላይ አታገኙትም። +26 ስድስት ቀን ትሰበስባላችሁ፤ በሰባተኛው ቀን ይኸውም በሰንበት ቀን+ ግን ምንም አይገኝም��” +27 ይሁንና ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ በሰባተኛው ቀን ሊሰበስቡ ወጡ፤ ሆኖም ምንም አላገኙም። +28 በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ሰዎች ትእዛዛቴንና ሕጎቼን ለማክበር እንቢተኛ የምትሆኑት እስከ መቼ ነው?+ +29 ይሖዋ ሰንበትን እንደሰጣችሁ ልብ በሉ።+ በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚሆን ምግብ የሰጣችሁም ለዚህ ነው። እያንዳንዱ ሰው ባለበት ስፍራ መቆየት አለበት፤ በሰባተኛውም ቀን ማንም ሰው ካለበት ቦታ መውጣት የለበትም።” +30 ሕዝቡም በሰባተኛው ቀን ሰንበትን አከበረ።*+ +31 የእስራኤልም ቤት ምግቡን “መና”* አሉት። እሱም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ ሲሆን ጣዕሙም ማር እንደተቀባ ቂጣ ነበር።+ +32 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንዲህ ሲል አዟል፦ ‘ከግብፅ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ እንድትበሉት የሰጠኋችሁን ምግብ እንዲያዩ ከእሱ አንድ ኦሜር ሰፍራችሁ ለሚመጡት ትውልዶቻችሁ ሁሉ አስቀምጡ።’”+ +33 በመሆኑም ሙሴ አሮንን “ማሰሮ ወስደህ አንድ ኦሜር መና ጨምርበት፤ ለሚመጡት ትውልዶቻችሁ ሁሉ ተጠብቆ እንዲቆይ በይሖዋ ፊት አስቀምጠው” አለው።+ +34 አሮንም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተጠብቆ እንዲቆይ መናውን በምሥክሩ*+ ፊት አስቀመጠው። +35 እስራኤላውያንም ወደሚኖሩበት ምድር እስከሚመጡ ድረስ+ ለ40 ዓመት+ መናውን በሉ። ወደ ከነአን ምድር ድንበር+ እስከሚደርሱ ድረስ መናውን በሉ። +36 አንድ ኦሜር፣ የኢፍ መስፈሪያ* አንድ አሥረኛ ነው። +6 በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ።+ በኃያል ክንድ ተገዶ ይለቃቸዋል፤ በኃያል ክንድ ተገዶም ከምድሩ እንዲወጡ ያደርጋቸዋል” አለው።+ +2 ከዚያም አምላክ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ ይሖዋ ነኝ። +3 ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሁሉን ቻይ አምላክ+ ሆኜ እገለጥላቸው ነበር፤ ይሖዋ የሚለውን ስሜን+ በተመለከተ ግን ራሴን ሙሉ በሙሉ አልገለጥኩላቸውም።+ +4 በተጨማሪም የከነአንን ምድር ማለትም የባዕድ አገር ሰው ሆነው የኖሩባትን ምድር ልሰጣቸው ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።+ +5 እንግዲህ አሁን ግብፃውያን በባርነት እየገዟቸው ያሉት የእስራኤል ሰዎች እያሰሙት ያለውን የሥቃይ ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም አስባለሁ።+ +6 “ስለዚህ እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከግብፃውያን ከባድ ሸክም ነፃ አወጣችኋለሁ፤ ከጫኑባችሁም የባርነት ቀንበር አላቅቃችኋለሁ፤+ በተዘረጋ* ክንድና በታላቅ ፍርድ እታደጋችኋለሁ።+ +7 የራሴ ሕዝብ አድርጌ እወስዳችኋለሁ፤ አምላካችሁም እሆናለሁ፤+ እናንተም ከግብፃውያን ከባድ ሸክም ነፃ የማወጣችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ታውቃላችሁ። +8 ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት እጄን አንስቼ ወደማልኩላቸው ምድር አስገባችኋለሁ፤ ርስት አድርጌም እሰጣችኋለሁ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።’”+ +9 ከዚያም ሙሴ ለእስራኤላውያን ይህን መልእክት ነገራቸው፤ እነሱ ግን ተስፋ ከመቁረጣቸውና አስከፊ ከሆነው የባርነት ሕይወታቸው የተነሳ ሊሰሙት ፈቃደኞች አልሆኑም።+ +10 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +11 “ወደ ግብፁ ንጉሥ ወደ ፈርዖን ገብተህ እስራኤላውያንን ከምድሩ እንዲያሰናብታቸው ንገረው።” +12 ሆኖም ሙሴ “እንግዲህ እስራኤላውያን ሊሰሙኝ ፈቃደኛ አልሆኑም፤+ ታዲያ የመናገር ችግር ያለብኝን* እኔን፣ ፈርዖን እንዴት ብሎ ሊሰማኝ ይችላል?”+ በማለት ለይሖዋ መለሰ። +13 ይሖዋ ግን እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ለማውጣት ለእነሱና ለግብፁ ንጉሥ ለፈርዖን ማስተላለፍ ያለባቸውን ትእዛዝ ለሙሴና ለአሮን በድጋሚ ነገራቸው። +14 የአባቶቻቸው ቤት መሪዎችም እነዚህ ናቸው፦ ���እስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል+ ወንዶች ልጆች ሃኖክ፣ ፓሉ፣ ኤስሮን እና ካርሚ ነበሩ።+ እነዚህ የሮቤል ቤተሰቦች ናቸው። +15 የስምዖን ወንዶች ልጆች የሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሃር እና ከአንዲት ከነአናዊት የወለደው ሻኡል ነበሩ።+ እነዚህ የስምዖን ቤተሰቦች ናቸው። +16 የሌዊ+ ወንዶች ልጆች በየቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው ስማቸው ይህ ነው፦ ጌድሶን፣ ቀአት እና ሜራሪ።+ ሌዊ 137 ዓመት ኖረ። +17 የጌድሶን ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸው ሊብኒ እና ሺምአይ ነበሩ።+ +18 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣ ኬብሮን እና ዑዚኤል ነበሩ።+ ቀአት 133 ዓመት ኖረ። +19 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ። የሌዋውያን ቤተሰቦች በየቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው እነዚህ ነበሩ።+ +20 አምራም የአባቱን እህት ዮካቤድን አገባ።+ እሷም አሮንንና ሙሴን ወለደችለት።+ አምራም 137 ዓመት ኖረ። +21 የይጽሃር ወንዶች ልጆች ቆሬ፣+ ኔፌግ እና ዚክሪ ነበሩ። +22 የዑዚኤል ወንዶች ልጆች ሚሳኤል፣ ኤሊጻፋን+ እና ሲትሪ ነበሩ። +23 አሮን የነአሶን+ እህት የሆነችውን የአሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ። እሷም ናዳብን፣ አቢሁን፣ አልዓዛርን እና ኢታምርን ወለደችለት።+ +24 የቆሬ ወንዶች ልጆች አሲር፣ ሕልቃና እና አቢያሳፍ ነበሩ።+ የቆሬያውያን ቤተሰቦች እነዚህ ናቸው።+ +25 የአሮን ልጅ አልዓዛር+ ከፑቲኤል ልጆች መካከል አንዷን አገባ። እሷም ፊንሃስን+ ወለደችለት። የሌዋውያን የአባቶች ቤት መሪዎች በየቤተሰባቸው እነዚህ ናቸው።+ +26 ይሖዋ “የእስራኤልን ሕዝብ በቡድን በቡድን* በማድረግ ከግብፅ ምድር ይዛችሁ ውጡ”+ ብሎ የነገራቸው አሮንና ሙሴ እነዚህ ናቸው። +27 የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ለማውጣት የግብፁን ንጉሥ ፈርዖንን ያነጋገሩት ሙሴና አሮን ነበሩ።+ +28 ይሖዋ በግብፅ ምድር ሙሴን ባነጋገረበት በዚያ ዕለት +29 ይሖዋ ሙሴን “እኔ ይሖዋ ነኝ። የምነግርህን ሁሉ ለግብፁ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው” አለው። +30 ከዚያም ሙሴ ይሖዋን “እኔ እንደሆነ የመናገር ችግር አለብኝ፤* ታዲያ ፈርዖን እንዴት ብሎ ይሰማኛል?” አለው።+ +25 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ለእስራኤላውያን መዋጮ እንዲያመጡልኝ ንገራቸው፤ ለመስጠት ልቡ ካነሳሳው ከእያንዳንዱ ሰው መዋጮዬን ትቀበላላችሁ።+ +3 ከእነሱ የምትቀበሉት መዋጮም ይህ ነው፦ ወርቅ፣+ ብር፣+ መዳብ፣+ +4 ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣* ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣ +5 ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር እንጨት፣+ +6 ለመብራት የሚሆን ዘይት፣+ ለቅብዓት ዘይትና+ ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን+ የሚሆን በለሳን፣ +7 ለኤፉዱ+ እንዲሁም ለደረት ኪሱ+ የሚሆኑ የኦኒክስ ድንጋዮችና ሌሎች ድንጋዮች። +8 ለእኔም መቅደስ ይሠሩልኛል፤ እኔም በመካከላቸው እኖራለሁ።*+ +9 የማደሪያ ድንኳኑንም ሆነ በውስጡ የሚቀመጡትን ቁሳቁሶች ሁሉ እኔ በማሳይህ ንድፍ መሠረት ትሠሯቸዋላችሁ።+ +10 “ርዝመቱ ሁለት ክንድ* ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል እንዲሁም ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት* ከግራር እንጨት ይሠራሉ።+ +11 ከዚያም በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ።+ ውስጡንና ውጭውን ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ።+ +12 አራት የወርቅ ቀለበቶች ትሠራለታለህ፤ ከዚያም ሁለቱን ቀለበቶች በአንዱ በኩል ሁለቱን ቀለበቶች ደግሞ በሌላው በኩል በማድረግ ከአራቱ እግሮቹ በላይ ታያይዛቸዋለህ። +13 ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ትሠራለህ፤ በወርቅም ትለብጣቸዋለህ።+ +14 ታቦቱን ለመሸከም እንዲያገለግሉ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎንና ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ ታስገባቸዋለህ። +15 መሎጊያዎቹ በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ እንዳሉ ይቀመጣሉ፤ ከዚያ መውጣት የለባቸውም።+ +16 የምሰጥህንም ምሥክር በታቦቱ ውስጥ ታስቀምጠዋለህ።+ +17 “እንዲሁም ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ትሠራለህ።+ +18 ሁለት የወርቅ ኪሩቦችን ትሠራለህ፤ ወርቁን በመጠፍጠፍም በመክደኛው ጫፍና ጫፍ ላይ ወጥ አድርገህ ትሠራቸዋለህ።+ +19 በሁለቱ የመክደኛው ጫፎች ላይ ኪሩቦቹን ሥራ፤ አንዱን ኪሩብ በዚህኛው ጫፍ፣ ሌላኛውን ኪሩብ ደግሞ በዚያኛው ጫፍ ላይ ሥራ። +20 ኪሩቦቹ ሁለቱን ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይከልሉታል፤+ እነሱም ትይዩ ይሆናሉ። የኪሩቦቹ ፊት ወደ መክደኛው ያጎነበሰ ይሆናል። +21 መክደኛውንም+ በታቦቱ ላይ ትገጥመዋለህ፤ የምሰጥህንም ምሥክር በታቦቱ ውስጥ ታስቀምጠዋለህ። +22 እኔም በዚያ እገለጥልሃለሁ፤ ከመክደኛውም በላይ ሆኜ አነጋግርሃለሁ።+ በምሥክሩ ታቦት ላይ በሚገኙት በሁለቱ ኪሩቦች መካከል ሆኜ እስራኤላውያንን በተመለከተ የማዝህንም ሁሉ አሳውቅሃለሁ። +23 “በተጨማሪም ርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ከፍታው ደግሞ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር እንጨት ትሠራለህ።+ +24 በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ። +25 ዙሪያውንም አንድ ጋት* ስፋት ያለው ጠርዝ ታበጅለታለህ፤ በጠርዙም ዙሪያ የወርቅ ክፈፍ ታደርግለታለህ። +26 አራት የወርቅ ቀለበቶች ትሠራለታለህ፤ ከዚያም ቀለበቶቹን አራቱ እግሮቹ በሚገኙባቸው አራት ማዕዘኖች ላይ ታደርጋቸዋለህ። +27 ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች እንዲይዙ ቀለበቶቹ በጠርዙ አጠገብ ይሆናሉ። +28 መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ትለብጣቸዋለህ፤ ጠረጴዛውንም በእነሱ አማካኝነት ትሸከማለህ። +29 “ለመጠጥ መባ ማፍሰሻ የሚያገለግሉትን ሳህኖቹን፣ ጽዋዎቹን፣ ማንቆርቆሪያዎቹንና ጎድጓዳ ሳህኖቹን ትሠራለህ። ከንጹሕ ወርቅ ትሠራቸዋለህ።+ +30 ገጸ ኅብስቱን በጠረጴዛው ላይ ሁልጊዜ በፊቴ ታስቀምጣለህ።+ +31 “ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ+ ትሠራለህ። መቅረዙም ወጥ ከሆነ ወርቅ ተጠፍጥፎ የተሠራ ይሁን። የመቅረዙ መቆሚያ፣ ግንድ፣ ቅርንጫፎች፣ አበባ አቃፊዎች፣ እንቡጦችና የፈኩት አበቦች ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሆናሉ።+ +32 በመቅረዙ ጎንና ጎን ስድስት ቅርንጫፎች ይኖራሉ፤ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች ከአንዱ ጎን፣ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች ደግሞ ከሌላው ጎን የወጡ ይሆናሉ። +33 በአንዱ በኩል ባሉት ቅርንጫፎች በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎችን ከእንቡጦቹና ከፈኩት አበቦች ጋር እያፈራረቅክ ትሠራለህ፤ በሌላኛው በኩል ባሉት ቅርንጫፎችም በእያንዳንዳቸው ላይ የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ ሦስት የአበባ አቃፊዎችን ከእንቡጦቹና ከፈኩት አበቦች ጋር +34 በግንዱ ላይም የአልሞንድ አበባ የሚመስሉ አራት የአበባ አቃፊዎችን ከእንቡጦቹና ከፈኩት አበቦች ጋር እያፈራረቅክ ትሠራለህ። +35 ከግንዱ በሚወጡት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቅርንጫፎች ሥር አንድ እንቡጥ ይኖራል፤ በቀጣዮቹ ሁለት ቅርንጫፎች ሥርም አንድ እንቡጥ ይኖራል፤ በቀጣዮቹ ሁለት ቅርንጫፎች ሥርም እንዲሁ አንድ እንቡጥ ይኖራል፤ ከግንዱ የሚወጡት ስድስቱም ቅርንጫፎች በዚሁ መንገድ ይሠራሉ። +36 እንቡጦቹና ቅርንጫፎቻቸው እንዲሁም የመቅረዙ ሁለመና ንጹሕ ከሆነ አንድ ወጥ ወርቅ ተጠፍጥፈው የተሠሩ ይሆናሉ።+ +37 ሰባት መብራቶች ትሠራለታለህ፤ መብራቶቹ በሚለኮሱበት ጊዜ ከፊት ለፊቱ ላለው አካባቢ ብርሃን ይሰጣሉ።+ +38 መቆንጠጫዎቹና መኮስተሪያዎቹ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ይሁኑ።+ +39 ቁሳቁሶቹ ሁሉ ከአንድ ታላንት* ንጹሕ ወርቅ ይሠሩ። +40 በተራራው ላይ ተገልጦልህ ባየኸው ንድፍ መሠረት ተጠንቅቀህ ሥራቸው።+ +33 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብፅ መርተህ ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህ ተነስተህ ሂድ። ‘ለዘርህ እሰጠዋለሁ’ በማለት ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማልኩላቸውም ምድር ተጓዝ።+ +2 እኔም ከአንተ አስቀድሜ መልአክ በመላክ+ ከነአናውያንን፣ አሞራውያንን፣ ሂታውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን አስወጣለሁ።+ +3 ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ ሂዱ። ሆኖም እናንተ ግትር* ሕዝብ ስለሆናችሁ+ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋችሁ+ በመካከላችሁ ሆኜ አብሬያችሁ አልሄድም።” +4 ሕዝቡም ይህን ኃይለኛ ንግግር ሲሰሙ በሐዘን ተዋጡ፤ ከመካከላቸውም ማንም ጌጡን አላደረገም። +5 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እናንተ ግትር* ሕዝብ ናችሁ።+ ለአንድ አፍታ በመካከላችሁ አልፌ ላጠፋችሁ እችል ነበር።+ በእናንተ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እስክወስን ድረስ ጌጣጌጣችሁን አውልቁ።’” +6 ስለዚህ እስራኤላውያን ከኮሬብ ተራራ አንስቶ ጌጣጌጣቸውን ማድረግ ተዉ። +7 ሙሴም የራሱን ድንኳን ወስዶ ከሰፈሩ ውጭ ማለትም ከሰፈሩ ትንሽ ራቅ አድርጎ ተከለው፤ ድንኳኑንም የመገናኛ ድንኳን ብሎ ጠራው። ይሖዋን የሚጠይቅ+ ማንኛውም ሰው ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው የመገናኛ ድንኳን ይሄድ ነበር። +8 ሙሴ ወደ ድንኳኑ ሲሄድ ሕዝቡ በሙሉ ተነስተው በየድንኳናቸው መግቢያ ላይ በመቆም ሙሴ ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ትክ ብለው ይመለከቱት ነበር። +9 ሙሴ ወደ ድንኳኑ ገብቶ አምላክ ከሙሴ ጋር በሚነጋገርበት+ ጊዜ የደመናው ዓምድ+ ወርዶ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ይቆማል። +10 ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሞ ሲመለከት እያንዳንዳቸው ተነስተው በየድንኳናቸው መግቢያ ላይ ይሰግዱ ነበር። +11 አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር እንደሚነጋገር ይሖዋ ከሙሴ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገር ነበር።+ ሙሴ ወደ ሰፈሩ በሚመለስበት ጊዜ አገልጋዩና ረዳቱ+ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ+ ከድንኳኑ አይለይም ነበር። +12 ሙሴም ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ ‘ይህን ሕዝብ ምራ’ እያልከኝ ነው፤ ሆኖም ከእኔ ጋር ማንን እንደምትልክ አላሳወቅከኝም። ከዚህም በላይ ‘በስም አውቄሃለሁ፤* ደግሞም በፊቴ ሞገስ አግኝተሃል’ ብለኸኝ ነበር። +13 እባክህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እንዳውቅህና በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንድኖር መንገድህን አሳውቀኝ።+ እንዲሁም ይህ ብሔር ሕዝብህ እንደሆነ አስብ።”+ +14 በመሆኑም እሱ “እኔ ራሴ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤*+ እረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው።+ +15 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “አንተ ራስህ ከእኛ ጋር የማትሄድ* ከሆነ ይህን ቦታ ለቅቀን እንድንሄድ አታድርገን። +16 ታዲያ እኔም ሆንኩ ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ እንዳገኘን የሚታወቀው እንዴት ነው? እኔም ሆንኩ ሕዝብህ በምድር ላይ ካሉ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተለየን እንድንሆን+ ስትል አብረኸን በመሄድህ አይደለም?”+ +17 ይሖዋም ሙሴን “በፊቴ ሞገስ ስላገኘህና በስም ስላወቅኩህ የጠየቅከውን ይህን ነገር እፈጽማለሁ” አለው። +18 እሱም በዚህ ጊዜ “እባክህ ክብርህን አሳየኝ” አለው። +19 ሆኖም እሱ እንዲህ አለው፦ “እኔ ራሴ ጥሩነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ ይሖዋ የተባለውንም ስሜን በፊትህ አውጃለሁ።+ ሞገስ ላሳየው የምፈልገውን ሞገስ አሳየዋለሁ፤ ልምረው የምፈልገውን ደግሞ እምረዋለሁ።”+ +20 ሆኖም “ማንም ሰው አይቶኝ በሕይወት መኖር ስለማይችል ፊቴን ማየት አትችልም” አለው። +21 በተጨማሪም ይሖዋ ���ንዲህ አለው፦ “ይኸው አጠገቤ ቦታ አለ። አንተም በዓለቱ ላይ ቁም። +22 ክብሬ በዚያ በሚያልፍበትም ጊዜ በዓለቱ ዋሻ ውስጥ አስቀምጥሃለሁ፤ እስከማልፍም ድረስ በእጄ እጋርድሃለሁ። +23 ከዚያም እጄን አነሳለሁ፤ አንተም ጀርባዬን ታያለህ። ፊቴ ግን አይታይም።”+ +10 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ ምክንያቱም የእሱም ሆነ የአገልጋዮቹ ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤+ ይህን የማደርገውም እነዚህን ተአምራዊ ምልክቶቼን በፊቱ እንዳሳይ+ +2 እንዲሁም ግብፅን እንዴት አድርጌ እንደቀጣሁና በመካከላቸው ተአምራዊ ምልክቶቼን እንዴት እንዳሳየሁ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ እንድታውጅ ነው፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በእርግጥ ታውቃላችሁ።” +3 በመሆኑም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለመሆኑ ለእኔ ለመገዛት ፈቃደኛ የማትሆነው እስከ መቼ ነው?+ እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። +4 አሁንም ሕዝቤን ለመልቀቅ ፈቃደኛ የማትሆን ከሆነ ግን በነገው ዕለት በግዛትህ ላይ አንበጦችን አመጣለሁ። +5 አንበጦቹም ምድሪቱን ይሸፍናሉ፤ መሬቱንም ማየት አይቻልም። እነሱም ከበረዶው ያመለጠውንና የቀረላችሁን ነገር ሁሉ ሙልጭ አድርገው ይበሉታል፤ በመስክ ላይ እየበቀሉ ያሉትን ዛፎቻችሁን በሙሉ ይበሏቸዋል።+ +6 አንበጦቹ አባቶችህና አያቶችህ በዚህች ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ አይተውት በማያውቁት ሁኔታ+ ቤቶችህን፣ የአገልጋዮችህን ቤቶች ሁሉና የግብፅን ቤቶች ሁሉ ይሞላሉ።’” እሱም ይህን ከተናገረ በኋላ ፊቱን አዙሮ ከፈርዖን ፊት ወጥቶ ሄደ። +7 ከዚያም የፈርዖን አገልጋዮች ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው ወጥመድ የሚሆንብን እስከ መቼ ነው? አምላካቸውን ይሖዋን እንዲያገለግሉ ሰዎቹን ልቀቃቸው። ግብፅ እየጠፋች እንደሆነ እስካሁን አልተገነዘብክም?” +8 በመሆኑም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ተመልሰው እንዲመጡ ተደረገ፤ እሱም “ሂዱ፤ አምላካችሁን ይሖዋን አገልግሉ። ይሁንና የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው። +9 በዚህ ጊዜ ሙሴ “ለይሖዋ የምናከብረው በዓል+ ስላለን ወጣቶቻችንን፣ አዛውንቶቻችንን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን እንዲሁም በጎቻችንንና ከብቶቻችንን ይዘን እንሄዳለን” አለ።+ +10 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተንና ልጆቻችሁን ከለቀኩማ በእርግጥም ይሖዋ ከእናንተ ጋር ነው!+ መቼም የሆነ ተንኮል እንዳሰባችሁ ግልጽ ነው። +11 ይሄማ አይሆንም! ወንዶቹ ብቻ ሄደው ይሖዋን ያገልግሉ፤ ምክንያቱም የጠየቃችሁት ይህንኑ ነው።” ከዚያም ከፈርዖን ፊት እንዲወጡ ተደረገ። +12 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንበጦች መጥተው የግብፅን ምድር እንዲወሩና ከበረዶ የተረፈውን በምድሩ ላይ ያለውን ማንኛውንም ተክል ጠራርገው እንዲበሉ በግብፅ ምድር ላይ እጅህን ዘርጋ።” +13 ሙሴም ወዲያው በግብፅ ምድር ላይ በትሩን ሰነዘረ፤ ይሖዋም በዚያን ዕለት ቀኑንና ሌሊቱን ሙሉ በምድሩ ላይ የምሥራቅ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ። ሲነጋም የምሥራቁ ነፋስ አንበጦችን አመጣ። +14 አንበጦቹም በመላው የግብፅ ምድር ላይ መውጣትና በግብፅ ግዛት ሁሉ ላይ መስፈር ጀመሩ።+ ሁኔታው እጅግ አስከፊ ነበር፤+ ከዚህ በፊት ያን ያህል ብዛት ያለው አንበጣ ታይቶ አያውቅም፤ ዳግመኛም ያን ያህል ብዛት ያለው አንበጣ ፈጽሞ አይከሰትም። +15 አንበጦቹም መላውን ምድር ሸፈኑት፤ ምድሪቱም በእነሱ የተነሳ ጨለመች፤ እነሱም ከበረዶው የተረፈውን በምድሩ ላይ ያለውን ተክል ሁሉ እንዲሁም በዛፎች ላይ ያለውን ፍሬ ሁሉ ጠራርገው በሉት፤ በመላው የግብፅ ምድር በዛፎችም ሆነ በመስክ ባሉ ተክሎች ላይ አንድም ለምለም ቅጠል አልተረፈም። +16 በመሆኑም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን በአስቸኳይ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በይሖዋም ሆነ በእናንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁ። +17 ስለሆነም አሁን እባካችሁ ይህን ኃጢአቴን ብቻ ይቅር በሉኝ፤ ይህን ገዳይ መቅሰፍት ከእኔ ላይ እንዲያስወግድልኝም አምላካችሁን ይሖዋን ለምኑልኝ።” +18 እሱም* ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ ይሖዋንም ለመነ።+ +19 ከዚያም ይሖዋ ነፋሱ እንዲቀየር አደረገ፤ ነፋሱም ኃይለኛ የምዕራብ ነፋስ ሆነ፤ ነፋሱም አንበጦቹን ወስዶ ቀይ ባሕር ውስጥ ከተታቸው። በመላው የግብፅ ግዛት አንድም አንበጣ አልቀረም። +20 ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤+ እሱም እስራኤላውያንን አለቀቀም። +21 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “በግብፅ ምድር ላይ ጨለማ ይኸውም የሚዳሰስ የሚመስል ድቅድቅ ጨለማ እንዲከሰት እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው። +22 ሙሴም ወዲያውኑ እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በመላው የግብፅ ምድር ላይም ለሦስት ቀን ያህል ድቅድቅ ጨለማ ተከሰተ።+ +23 እነሱም እርስ በርስ አይተያዩም ነበር፤ ለሦስት ቀን ማናቸውም ካሉበት ቦታ ንቅንቅ ማለት አልቻሉም፤ ሆኖም እስራኤላውያን ሁሉ በሚኖሩበት ስፍራ ብርሃን ነበር።+ +24 ከዚያም ፈርዖን ሙሴን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ሂዱ፣ ይሖዋን አገልግሉ።+ በጎቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ እዚሁ ይቀራሉ። ልጆቻችሁም አብረዋችሁ መሄድ ይችላሉ።” +25 ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “እንግዲያውስ ለመሥዋዕቶችና ለሚቃጠሉ መባዎች የሚሆኑትን እንስሳት አንተው ራስህ ትሰጠንና ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገን እናቀርባቸዋለን።+ +26 ከብቶቻችንም አብረውን መሄድ አለባቸው። አምላካችንን ይሖዋን ስናመልክ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹን መሥዋዕት አድርገን ስለምናቀርብ አንድም እንስሳ* እዚህ መቅረት የለበትም፤ ደግሞም እኛ ራሳችን ለይሖዋ አምልኮ ምን መሥዋዕት ማቅረብ እንዳለብን የምናውቀው እዚያ ስንደርስ ነው።” +27 ይሖዋም የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እሱም ሊለቃቸው ፈቃደኛ አልሆነም።+ +28 ስለሆነም ፈርዖን “ከፊቴ ጥፋ! ዳግመኛ ፊቴን ለማየት እንዳትሞክር፤ ፊቴን የምታይበት ቀን መሞቻህ እንደሚሆን እወቅ” አለው። +29 በዚህ ጊዜ ሙሴ “እሺ፣ እንዳልከው ይሁን፤ ዳግመኛ ፊትህን አላይም” አለው። +14 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ወደ ኋላ ተመልሰው በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በበዓልጸፎን ትይዩ በሚገኘው በፊሃሂሮት ፊት ለፊት እንዲሰፍሩ ለእስራኤላውያን ንገራቸው።+ በበዓልጸፎን ፊት ለፊት በባሕሩ አጠገብ ስፈሩ። +3 ፈርዖንም ስለ እስራኤላውያን ‘ግራ ተጋብተው በምድሪቱ ላይ እየተንከራተቱ ነው። ምድረ በዳው ጋሬጣ ሆኖባቸዋል’ ማለቱ አይቀርም። +4 እኔም የፈርዖን ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤+ እሱም ያሳድዳቸዋል፤ እኔም ፈርዖንንና ሠራዊቱን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን እጎናጸፋለሁ፤+ ግብፃውያንም እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።”+ እነሱም ልክ እንዲሁ አደረጉ። +5 በኋላም ለግብፁ ንጉሥ ሕዝቡ እንደኮበለለ ተነገረው። ፈርዖንና አገልጋዮቹም ስለ ሕዝቡ የነበራቸውን ሐሳብ ወዲያው በመቀየር+ “ምን ማድረጋችን ነው? እስራኤላውያን ባሪያ ሆነው እንዳያገለግሉን የለቀቅናቸው ምን ነክቶን ነው?” አሉ። +6 በመሆኑም ፈርዖን የጦር ሠረገሎቹ እንዲዘጋጁለት አደረገ፤ ሠራዊቱንም ከጎኑ አሰለፈ።+ +7 ከዚያም 600 የተመረጡ ሠረገሎችንና ሌሎች የግብፅ ሠረገሎችን ሁሉ ይዞ ተነሳ፤ በእያንዳንዱም ሠረገላ ላይ ተዋጊዎች ነበሩ። +8 በዚህ መንገድ ይሖዋ የግብፁ ንጉሥ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ እስራኤላው��ን ወጥተው በልበ ሙሉነት* እየሄዱ ሳሉ ፈርዖን እነሱን ማሳደዱን ተያያዘው።+ +9 ግብፃውያኑ ተከታተሏቸው፤+ እስራኤላውያን በበዓልጸፎን ፊት ለፊት በባሕሩ አጠገብ ባለው በፊሃሂሮት ሰፍረው ሳሉም የፈርዖን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞቹና ሠራዊቱ በሙሉ ደረሱባቸው። +10 ፈርዖን ወደ እነሱ ሲቀርብ እስራኤላውያን ቀና ብለው ተመለከቱ፤ ግብፃውያኑ እነሱን እየተከታተሏቸው ነበር። እስራኤላውያንም ተሸበሩ፤ ወደ ይሖዋም ይጮኹ ጀመር።+ +11 እነሱም ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እዚህ ምድረ በዳ ውስጥ እንድንሞት ያመጣኸን በግብፅ የመቃብር ቦታ ጠፍቶ ነው?+ ከግብፅ መርተህ በማውጣት ምን ያደረግክልን ነገር አለ? +12 በግብፅ ሳለን ‘እባክህ ተወን፤ አርፈን ግብፃውያንን እናገልግል’ ብለንህ አልነበረም? እዚህ ምድረ በዳ ውስጥ ከመሞት ግብፃውያንን ብናገለግል ይሻለን ነበር።”+ +13 በዚህ ጊዜ ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ።+ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በዛሬው ዕለት ይሖዋ ለእናንተ ሲል የሚፈጽመውን የእሱን ማዳን እዩ።+ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያን ዳግመኛ አታዩአቸውም፤ በጭራሽ አታዩአቸውም።+ +14 ይሖዋ ራሱ ስለ እናንተ ይዋጋል፤+ ብቻ እናንተ ዝም በሉ።” +15 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለምን ወደ እኔ ትጮኻለህ? እስራኤላውያን ድንኳናቸውን ነቅለው እንዲጓዙ ንገራቸው። +16 አንተም እስራኤላውያን በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት እንዲሻገሩ በትርህን አንሳና እጅህን በባሕሩ ላይ ሰንዝር፤ ባሕሩንም ክፈለው። +17 እኔ ደግሞ የግብፃውያን ልብ እንዲደነድን ስለምፈቅድ እስራኤላውያንን ተከትለው ይገባሉ፤ እኔም ፈርዖንን፣ ሠራዊቱን ሁሉ፣ የጦር ሠረገሎቹንና ፈረሰኞቹን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን እጎናጸፋለሁ።+ +18 ፈርዖንን፣ የጦር ሠረገሎቹንና ፈረሰኞቹን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን በምጎናጸፍበት ጊዜ ግብፃውያን እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።”+ +19 ከዚያም ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ፊት ይሄድ የነበረው የእውነተኛው አምላክ መልአክ+ ከዚያ ተነስቶ ወደ ኋላቸው ሄደ፤ ከፊታቸው የነበረውም የደመና ዓምድ ወደ ኋላቸው ሄዶ በስተ ጀርባቸው ቆመ።+ +20 በመሆኑም የደመናው ዓምድ በግብፃውያንና በእስራኤላውያን መካከል ሆነ።+ ዓምዱ በአንደኛው በኩል ጭልም ያለ ደመና ነበር። በሌላኛው በኩል ደግሞ ለሌሊቱ ብርሃን ይሰጥ ነበር።+ ስለሆነም ሌሊቱን ሙሉ አንደኛው ወገን ወደ ሌላኛው ወገን መቅረብ አልቻለም። +21 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤+ ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፤ የባሕሩንም ወለል ወደ ደረቅ መሬት ለወጠው፤+ ውኃውም ተከፈለ።+ +22 በመሆኑም እስራኤላውያን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ+ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተሻገሩ።+ +23 ግብፃውያኑም እነሱን ማሳደዳቸውን ተያያዙት፤ የፈርዖን ፈረሶች፣ የጦር ሠረገሎችና ፈረሰኞች ሁሉ ተከትለዋቸው ወደ ባሕሩ መሃል ገቡ።+ +24 በማለዳውም ክፍለ ሌሊት* ይሖዋ በእሳትና በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፤+ የግብፃውያንም ሠራዊት ግራ እንዲጋባ አደረገ። +25 ሠረገሎቻቸውን መንዳት አስቸጋሪ እንዲሆንባቸው የሠረገሎቻቸውን መንኮራኩሮች* አወላለቀባቸው፤ ግብፃውያኑም “ይሖዋ እስራኤላውያንን በመደገፍ ግብፃውያንን እየተዋጋላቸው ስለሆነ ከእስራኤላውያን ፊት እንሽሽ” አሉ።+ +26 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ውኃው በግብፃውያን፣ በጦር ሠረገሎቻቸውና በፈረሰኞቻቸው ላይ ተመልሶ እንዲመጣባቸው እጅህን በባሕሩ ላይ ሰንዝር” አለው። +27 ሙሴም ወዲያውኑ እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤ ሊነጋጋ ሲልም ባሕሩ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ��መለሰ። ግብፃውያንም ውኃው እንዳይደርስባቸው ለመሸሽ ሲሞክሩ ይሖዋ ግብፃውያኑን ባሕሩ መሃል ጣላቸው።+ +28 ውኃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ተከትለው የገቡትን የጦር ሠረገሎችና ፈረሰኞች እንዲሁም የፈርዖንን ሠራዊት በሙሉ አለበሳቸው።+ ከእነሱም መካከል አንድም የተረፈ የለም።+ +29 እስራኤላውያን ግን ውኃው በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ቆሞ+ በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተጓዙ።+ +30 በዚህ መንገድ ይሖዋ በዚያ ቀን እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ አዳነ፤+ እስራኤላውያንም የግብፃውያን ሬሳ በባሕሩ ዳርቻ ላይ ወድቆ ተመለከቱ። +31 በተጨማሪም እስራኤላውያን ይሖዋ ግብፃውያንን የመታበትን ኃያል ክንድ ተመለከቱ፤ ሕዝቡም ይሖዋን መፍራት ጀመረ፤ በይሖዋና በአገልጋዩ በሙሴም አመነ።+ +9 ስለሆነም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ገብተህ እንዲህ በለው፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ።+ +2 እነሱን ለመልቀቅ እንቢተኛ የምትሆንና እንዳይሄዱ የምትከለክላቸው ከሆነ +3 የይሖዋ እጅ+ በመስክ ያሉትን ከብቶችህን ይመታል። በፈረሶች፣ በአህዮች፣ በግመሎች፣ በበሬዎች፣ በላሞችና በመንጎች ላይ አጥፊ መቅሰፍት ይወርዳል።+ +4 ይሖዋም በእስራኤል ከብቶችና በግብፅ ከብቶች መካከል ልዩነት እንዲኖር ያደርጋል፤ ከእስራኤላውያን ከብቶች መካከል አንድ እንኳ አይሞትም።”’”+ +5 ከዚህም በላይ ይሖዋ “በነገው ዕለት እኔ ይሖዋ በምድሪቱ ላይ ይህን አደርጋለሁ” በማለት ቀን ቆርጧል። +6 ይሖዋም በማግስቱ ይህን አደረገ፤ የግብፅ ከብት ሁሉ ይሞት ጀመር፤+ ከእስራኤላውያን ከብቶች መካከል ግን አንድ እንኳ አልሞተም። +7 ፈርዖንም ሁኔታውን ሲያጣራ ከእስራኤላውያን ከብቶች መካከል አንድ እንኳ አለመሞቱን ተገነዘበ። ያም ሆኖ ግን የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ሕዝቡንም አለቀቀም።+ +8 ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “ከሸክላ መተኮሻ ምድጃ እፍኝ ሙሉ ጥቀርሻ ውሰዱ፤ ሙሴም ጥቀርሻውን በፈርዖን ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው። +9 ጥቀርሻውም በመላው የግብፅ ምድር ላይ አቧራ ይሆናል፤ ከዚያም በመላው የግብፅ ምድር ባለ ሰውና እንስሳ ላይ መግል የያዘ እባጭ ሆኖ ይወጣል።” +10 እነሱም ከሸክላ መተኮሻ ምድጃ ጥቀርሻ ወስደው ፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ጥቀርሻውን ወደ ሰማይ በተነው፤ ጥቀርሻውም በሰውና በእንስሳ ላይ መግል የያዘ እባጭ ሆኖ ወጣ። +11 አስማተኞቹ ካህናት በእባጩ የተነሳ ሙሴ ፊት ሊቆሙ አልቻሉም፤ ምክንያቱም እባጩ በአስማተኞቹ ካህናትና በሁሉም ግብፃውያን ላይ ወጥቶ ነበር።+ +12 ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ ፈርዖንም ልክ ይሖዋ ለሙሴ እንደነገረው እነሱን አልሰማቸውም።+ +13 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በማለዳ ተነስተህ ፈርዖን ፊት ቁም፤ እንዲህም በለው፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። +14 ምክንያቱም በመላው ምድር ላይ እንደ እኔ ያለ ማንም እንደሌለ እንድታውቅ+ ልብህን፣ አገልጋዮችህንና ሕዝብህን ለመምታት መቅሰፍቴን በሙሉ አሁን አወርዳለሁ። +15 እስካሁን እጄን ዘርግቼ አንተንም ሆነ ሕዝብህን አጥፊ በሆነ መቅሰፍት በመታኋችሁ ነበር፤ አንተም ከምድር ገጽ ተጠራርገህ በጠፋህ ነበር። +16 ሆኖም ኃይሌን እንዳሳይህና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ስል በሕይወት አቆይቼሃለሁ።+ +17 ሕዝቤን አለቅም በማለት አሁንም በእነሱ ላይ እንደታበይክ ነህ? +18 እንግዲህ በነገው ዕለት በዚህ ሰዓት ገደማ ግብፅ ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ የማያውቅ እጅግ ታላቅ የበረዶ ውርጅብኝ አዘንባለሁ። +19 ስለዚህ አሁን መልእክት ልከህ በመስክ ላይ የተሰማሩትን ከብቶችህንና የአንተ የሆኑትን ሁሉ ወደ መጠለያ እንዲገቡ አድርግ። በመስክ የተገኘና ወደ ቤት ያልገባ ማንኛውም ሰውና እንስሳ በረዶው ይወርድበትና ይሞታል።”’” +20 ከፈርዖን አገልጋዮች መካከል የይሖዋን ቃል የፈሩ ሁሉ አገልጋዮቻቸውንና ከብቶቻቸውን በፍጥነት ወደ ቤት አስገቡ፤ +21 ሆኖም የይሖዋን ቃል ከቁም ነገር ያልቆጠሩት ሁሉ አገልጋዮቻቸውንና ከብቶቻቸውን እዚያው መስክ ላይ እንዳሉ ተዉአቸው። +22 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን “በመላው የግብፅ ምድር ላይ ይኸውም በሰው፣ በእንስሳና በግብፅ ምድር ላይ በበቀለው ተክል ሁሉ ላይ በረዶ እንዲወርድ+ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው።+ +23 በመሆኑም ሙሴ በትሩን ወደ ሰማይ አነሳ፤ ይሖዋም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፤ እሳትም* በምድር ላይ ወረደ፤ ይሖዋ በግብፅ ምድር ላይ ያለማቋረጥ በረዶ እንዲወርድ አደረገ። +24 በረዶም ወረደ፤ በበረዶውም መካከል የእሳት ብልጭታ ነበር። በረዶውም እጅግ ከባድ ነበር፤ ግብፅ እንደ አገር ሆና ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ በዚያች ምድር ላይ እንዲህ ያለ በረዶ ተከስቶ አያውቅም።+ +25 በረዶው ከሰው አንስቶ እስከ እንስሳ ድረስ በግብፅ ምድር በመስክ ላይ የነበረውን ማንኛውንም ነገር መታ፤ ዕፀዋቱን ሁሉና በሜዳ ላይ ያለውን ዛፍ በሙሉ አወደመ።+ +26 በረዶ ያልወረደው እስራኤላውያን በሚኖሩበት በጎሸን ምድር ብቻ ነበር።+ +27 ስለሆነም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “አሁንስ በድያለሁ። ይሖዋ ጻድቅ ነው፤ ጥፋተኞቹ እኔና ሕዝቤ ነን። +28 አምላክ ያመጣው ነጎድጓድና በረዶ እንዲቆም ይሖዋን ለምኑልኝ። እኔም እናንተን ለመልቀቅ ፈቃደኛ እሆናለሁ፤ ከአሁን በኋላ እዚህ አትቆዩም።” +29 በመሆኑም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “ልክ ከከተማዋ እንደወጣሁ እጆቼን በይሖዋ ፊት እዘረጋለሁ። ምድር የይሖዋ እንደሆነች እንድታውቅም ነጎድጓዱ ይቆማል፤ በረዶውም ከዚያ በኋላ አይወርድም።+ +30 ሆኖም አንተም ሆንክ አገልጋዮችህ ይህ ከሆነ በኋላም እንኳ ይሖዋ አምላክን እንደማትፈሩ አውቃለሁ።” +31 በዚህ ጊዜ ገብሱ አሽቶ፣ ተልባውም አብቦ ስለነበር ተልባውና ገብሱ ከጥቅም ውጭ ሆኑ። +32 ስንዴውና አጃው ግን ወቅታቸው ገና ስለነበር ጉዳት አልደረሰባቸውም። +33 ሙሴም ከፈርዖን ተለይቶ ከከተማዋ ወጣ፤ እጆቹንም በይሖዋ ፊት ዘረጋ፤ ነጎድጓዱና በረዶውም ቆመ፤ ዝናቡም በምድር ላይ መዝነቡን አቆመ።+ +34 ፈርዖንም ዝናቡ፣ በረዶውና ነጎድጓዱ መቆሙን ባየ ጊዜ እንደገና ኃጢአት ሠራ፤ እሱም ሆነ አገልጋዮቹ ልባቸውን አደነደኑ።+ +35 የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት እንደተናገረውም እስራኤላውያንን አለቀቀም።+ +27 “ርዝመቱ አምስት ክንድ፣* ወርዱም አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ትሠራለህ።+ መሠዊያው አራቱም ጎኖቹ እኩል፣ ከፍታው ደግሞ ሦስት ክንድ መሆን አለበት።+ +2 በአራቱ ማዕዘኖቹ ላይ ቀንዶች+ ትሠራለታለህ፤ ቀንዶቹም የመሠዊያው ክፍል ይሆናሉ፤ መሠዊያውንም በመዳብ ትለብጠዋለህ።+ +3 አመዱን* ማስወገጃ ባልዲዎችን፣ አካፋዎችን፣ ሳህኖችን፣ ሹካዎችንና መኮስተሪያዎችን ትሠራለህ፤ ዕቃዎቹንም ሁሉ ከመዳብ ትሠራቸዋለህ።+ +4 ለመሠዊያው እንደ መረብ አድርገህ የመዳብ ፍርግርግ ትሠራለታለህ፤ በፍርግርጉ በአራቱም ማዕዘኖቹ ላይ አራት የመዳብ ቀለበቶችን ትሠራለታለህ። +5 ፍርግርጉንም ከመሠዊያው ጠርዝ ወደ ታች ወረድ አድርገህ ታስቀምጠዋለህ፤ ፍርግርጉም መሠዊያው መሃል አካባቢ ይሆናል። +6 ለመሠዊያው የሚሆኑ መሎጊያዎችን ከግራር እንጨት ትሠራለህ፤ በመዳብም ትለብጣቸዋለህ። +7 መሎጊያዎቹም ቀለበቶቹ ውስጥ ይገባሉ፤ መሠዊያውን በምትሸከሙበትም ጊዜ መሎጊያዎቹ በሁለቱ ጎኖቹ በኩል ይሆናሉ።+ +8 መሠዊያውንም ባዶ ሣጥን አስመስለህ ከሳንቃ ትሠራዋለህ። ልክ ተራራው ላይ ባሳየህ መሠረት ይሠራ።+ +9 “የማደሪያ ድንኳኑን ግቢ ትሠራለህ።+ በስተ ደቡብ በኩል የሚገኘው፣ ፊቱ በደቡብ አቅጣጫ ያለው የግቢው ጎን በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ይኖሩታል፤ የአንዱ ጎን ርዝመት 100 ክንድ ይሆናል።+ +10 ግቢው 20 ቋሚዎችና ከመዳብ የተሠሩ 20 መሰኪያዎች ይኖሩታል። በቋሚዎቹ ላይ ያሉት ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎቻቸው* ደግሞ ከብር የተሠሩ ይሆናሉ። +11 በስተ ሰሜን በኩል በሚገኘው ጎን ያሉት መጋረጃዎችም ርዝመታቸው 100 ክንድ ይሆናል፤ እንዲሁም 20 ቋሚዎችና ለቋሚዎቹ የሚሆኑ ከመዳብ የተሠሩ 20 መሰኪያዎች ይኖራሉ፤ በቋሚዎቹም ላይ ማንጠልጠያዎችና ማያያዣዎች* ይኖራሉ። +12 በስተ ምዕራብ አቅጣጫ በግቢው ወርድ ልክ 50 ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖራሉ፤ አሥር ቋሚዎችና አሥር መሰኪያዎችም ይኖሯቸዋል። +13 በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በፀሐይ መውጫ በኩል ያለው የግቢው ወርድ 50 ክንድ ነው። +14 በአንዱ በኩል 15 ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖራሉ፤ ሦስት ቋሚዎችና ሦስት መሰኪያዎችም ይኖሯቸዋል።+ +15 በሌላኛውም በኩል 15 ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖራሉ፤ ሦስት ቋሚዎችና ሦስት መሰኪያዎችም ይኖሯቸዋል። +16 “የግቢው መግቢያ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግ እንዲሁም በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ የበፍታ ድር+ ተሸምኖ የተሠራ 20 ክንድ ርዝመት ያለው መከለያ* ይኑረው፤ አራት ቋሚዎችና ለቋሚዎቹ የሚሆኑ አራት መሰኪያዎችም ይኑሩት።+ +17 በግቢው ዙሪያ ያሉት ቋሚዎች በሙሉ ከብር የተሠሩ መቆንጠጫዎችና ከብር የተሠሩ ማንጠልጠያዎች ይኖሯቸዋል፤ መሰኪያዎቻቸው ግን ከመዳብ የተሠሩ ይሆናሉ።+ +18 ግቢው ርዝመቱ 100 ክንድ፣+ ወርዱ 50 ክንድ ሆኖ በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠሩ 5 ክንድ ከፍታ ያላቸው መጋረጃዎች ይኖሩታል፤ ከመዳብ የተሠሩ መሰኪያዎችም ይኑሩት። +19 በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ ለሚቀርበው አገልግሎት የሚውሉት ቁሳቁሶችና ዕቃዎች በሙሉ እንዲሁም የድንኳኑ ካስማዎችና የግቢው ካስማዎች በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ይሆናሉ።+ +20 “አንተም መብራቶቹ ያለማቋረጥ እንዲበሩ ለመብራት የሚሆን ተጨቅጭቆ የተጠለለ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን ታዛቸዋለህ።+ +21 አሮንና ወንዶች ልጆቹ መብራቶቹ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በምሥክሩ+ አጠገብ ካለው መጋረጃ ውጭ ከምሽት አንስቶ እስከ ጠዋት ድረስ በይሖዋ ፊት+ እንዲበሩ ያደርጋሉ። ይህ እስራኤላውያን በትውልዶቻቸው ሁሉ የሚፈጽሙት ዘላቂ ደንብ ነው።+ +13 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ከእስራኤል ሕዝብ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ።* ከሰውም ሆነ ከእንስሳ መካከል በኩር የሆነው ወንድ ሁሉ* የእኔ ነው።”+ +3 ከዚያም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ከግብፅ ከባርነት ቤት የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስቡ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ በኃያል ክንድ ከዚህ አውጥቷችኋል።+ በመሆኑም እርሾ የገባበት ምንም ነገር መበላት የለበትም። +4 ይኸው በዛሬው ዕለት በአቢብ* ወር ከዚህ ለቃችሁ እየወጣችሁ ነው።+ +5 ይሖዋ ለአንተ ይሰጥህ ዘንድ ለቀድሞ አባቶችህ ወደማለላቸው+ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ ይኸውም ወደ ከነአናውያን፣ ሂታውያን፣ አሞራውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ምድር+ ሲያስገባህ አንተ ደግሞ በዚህ ወር ይህን በዓል ማክበር አለብህ። +6 ለሰባት ቀን ቂጣ ትበላለህ፤+ በሰባተኛውም ቀን ለይሖዋ በዓል ይከበራል። +7 በእነዚህ ሰባት ቀናት መበላት ያለበት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ነው፤+ በአንተ ዘንድ እርሾ የገባበት ምንም ነገር መገኘት የለበትም፤+ በወሰንህም ውስጥ ሁሉ ምንም እርሾ መገኘት የለበትም። +8 በዚያ ቀን ለልጅህ ‘ይህን የማደርገው ከግብፅ በወጣሁበት ጊዜ ይሖዋ ባደረገልኝ ነገር የተነሳ ነው’ ብለህ ንገረው።+ +9 የይሖዋ ሕግ በአፍህ ላይ እንዲሆን ይህ በዓል በእጅህ ላይ እንደታሰረ ምልክትና በግንባርህ* ላይ እንዳለ መታሰቢያ* ሆኖ ያገለግልሃል፤+ ምክንያቱም ይሖዋ በኃያል ክንድ ከግብፅ አውጥቶሃል። +10 አንተም ይህን ደንብ በየዓመቱ በተወሰነለት ጊዜ አክብረው።+ +11 “ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአንተም ሆነ ለቀድሞ አባቶችህ ወደማለላችሁ+ ወደ ከነአናውያን ምድር ሲያስገባህ +12 በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ* እንዲሁም የአንተ ከሆነው እንስሳ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለይሖዋ መስጠት አለብህ። ወንዶቹ ሁሉ የይሖዋ ናቸው።+ +13 የእያንዳንዱን አህያ በኩር በበግ ዋጀው፤ የማትዋጀው ከሆነ ግን አንገቱን ስበረው። ከወንዶች ልጆችህ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ ልትዋጀው ይገባል።+ +14 “ምናልባት ወደፊት ልጅህ ‘ይህን የምታደርገው ለምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ በኃያል ክንድ ከግብፅ ከባርነት ቤት አወጣን።+ +15 ፈርዖን እኛን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆን ግትር አቋም በያዘ ጊዜ+ ይሖዋ ከሰው በኩር አንስቶ እስከ እንስሳ በኩር ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ ገደለ።+ በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ* ለይሖዋ የምሠዋው እንዲሁም ከወንዶች ልጆቼ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ የምዋጀው ለዚህ ነው።’ +16 ይሖዋ በኃያል ክንድ ከግብፅ ስላወጣን ይህ በዓል በእጅህ ላይ እንዳለ ምልክትና በግንባርህ* ላይ እንደታሰረ ነገር ሆኖ ያገልግል።”+ +17 ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ አምላክ ምንም እንኳ አቋራጭ ቢሆንም ወደ ፍልስጤማውያን ምድር በሚወስደው መንገድ አልመራቸውም። ምክንያቱም “ሕዝቡ ጦርነት ቢያጋጥመው ሐሳቡን ለውጦ ወደ ግብፅ ሊመለስ ይችላል” በማለት አስቦ ነበር። +18 በመሆኑም አምላክ ሕዝቡ በቀይ ባሕር አቅራቢያ ባለው ምድረ በዳ በኩል ዞሮ እንዲሄድ አደረገ።+ እስራኤላውያንም ከግብፅ ምድር የወጡት የጦርነት አሰላለፍ ተከትለው ነበር። +19 በተጨማሪም ሙሴ የዮሴፍን አፅም ይዞ ነበር፤ ምክንያቱም ዮሴፍ እስራኤላውያንን “አምላክ ፊቱን ወደ እናንተ መመለሱ አይቀርም፤ በመሆኑም አፅሜን ከዚህ ይዛችሁ ውጡ” በማለት በጥብቅ አስምሏቸው ነበር።+ +20 እነሱም ከሱኮት ተነስተው በምድረ በዳው ዳርቻ ላይ በሚገኘው በኤታም ሰፈሩ። +21 ይሖዋ የሚሄዱበትን መንገድ ይመራቸው ዘንድ ቀን ቀን በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፤+ ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን እንዲያገኙ ለማድረግ በእሳት ዓምድ ውስጥ ሆኖ ይመራቸው ነበር፤+ በመሆኑም ቀንም ሆነ ሌሊት ይጓዙ ነበር። +22 ቀን ቀን የደመናው ዓምድ ሌሊት ሌሊት ደግሞ የእሳቱ ዓምድ ከሕዝቡ ፊት አይለይም ነበር።+ +5 ከዚያ በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያከብርልኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይላል።” +2 ፈርዖን ግን እንዲህ አለ፦ “የእሱን ቃል ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለመሆኑ ይሖዋ ማነው?+ እኔ ይሖዋ የምትሉትን ፈጽሞ አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም።”+ +3 ሆኖም እነሱ እንዲህ አሉት፦ “የዕብራውያን አምላክ አነጋግሮን ነበር። በመሆኑም እባክህ የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳ ተጉዘን ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት ማቅረብ እንፈልጋለን፤+ ካልሆነ ግን በበሽታ ወይም በሰይፍ ይጨርሰናል።” +4 የግብፅም ንጉሥ “ሙሴና አሮን፣ ሕዝቡን ሥራ የምታስፈቱት ለ���ንድን ነው? አርፋችሁ ወደ ጉልበት ሥራችሁ ተመለሱ!” አላቸው።+ +5 ፈርዖንም በመቀጠል “የምድሩ ሕዝብ ምን ያህል ብዙ እንደሆነ ተመልከት፤ አንተ ደግሞ ሥራ ልታስፈታቸው ነው” አለ። +6 ፈርዖንም በዚያኑ ዕለት የሥራ ኃላፊዎቹንና አሠሪዎቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ +7 “ከአሁን በኋላ ለጡብ መሥሪያ የሚሆን ጭድ ለሕዝቡ እንዳትሰጡ።+ ራሳቸው ሄደው ጭድ ይሰብስቡ። +8 ሆኖም በፊት ይሠሩት የነበረውን ያህል ጡብ ሠርተው እንዲያስረክቡ አድርጉ። ዘና እያሉ ስለሆነ* ማስረከብ ከሚጠበቅባቸው ጡብ ምንም እንዳትቀንሱላቸው። ‘መሄድ እንፈልጋለን፤ ሄደን ለአምላካችን መሥዋዕት ማቅረብ እንፈልጋለን!’ እያሉ የሚጮኹት ለዚህ ነው። +9 ለሐሰት ወሬ ጆሯቸውን እንዳይሰጡ ሥራውን አክብዱባቸው፤ እንዲሁም ፋታ አሳጧቸው።” +10 ስለዚህ የሥራ ኃላፊዎቹና+ አሠሪዎቹ ወጥተው ለሕዝቡ እንዲህ አሉ፦ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ ‘ከእንግዲህ ጭድ አላቀርብላችሁም። +11 ራሳችሁ ሄዳችሁ ከየትም ፈልጋችሁ ጭድ አምጡ፤ ሥራችሁ ግን በምንም ዓይነት አይቀነስም።’” +12 ከዚያም ሕዝቡ እንደ ጭድ ሆኖ የሚያገለግለውን የእህል ቆረን* ለመሰብሰብ በመላው የግብፅ ምድር ተሰማራ። +13 የሥራ ኃላፊዎቹም “እያንዳንዳችሁ ጭድ ይቀርብላችሁ በነበረበት ጊዜ ታደርጉት እንደነበረው ሁሉ አሁንም በየዕለቱ የሚጠበቅባችሁን ሥራ ሠርታችሁ ማጠናቀቅ አለባችሁ” እያሉ ያስገድዷቸው ነበር። +14 በተጨማሪም የፈርዖን የሥራ ኃላፊዎች የሾሟቸው የእስራኤላውያን አሠሪዎች ተገረፉ።+ እነሱንም “ቀደም ሲል ሠርታችሁ ታስረክቡት የነበረውን ያህል ጡብ ሠርታችሁ ያላስረከባችሁት ለምንድን ነው? ትናንትም ሆነ ዛሬ እንዲህ አላደረጋችሁም” ብለው ጠየቋቸው። +15 በመሆኑም የእስራኤላውያን አሠሪዎች ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ በማለት እሮሯቸውን አሰሙ፦ “በአገልጋዮችህ ላይ እንዲህ ያለ ድርጊት የምትፈጽመው ለምንድን ነው? +16 ለእኛ ለአገልጋዮችህ ምንም ጭድ አይሰጠንም፤ እነሱ ግን ‘ጡብ ሥሩ!’ ይሉናል። ጥፋቱ የገዛ ሰዎችህ ሆኖ ሳለ እኛ አገልጋዮችህ እንገረፋለን።” +17 እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እኮ ተዝናንታችኋል፤* አዎ፣ ዘና እያላችሁ ነው!*+ ‘መሄድ እንፈልጋለን፤ ሄደን ለይሖዋ መሥዋዕት ማቅረብ እንፈልጋለን!’ የምትሉት ለዚህ ነው።+ +18 በሉ አሁን ወደ ሥራችሁ ተመለሱ! ምንም ጭድ አይቀርብላችሁም፤ ሆኖም የሚጠበቅባችሁን ያህል ጡብ መሥራት አለባችሁ።” +19 የእስራኤል አሠሪዎችም “በየዕለቱ ማስረከብ ከሚጠበቅባችሁ ጡብ ምንም ማጉደል የለባችሁም” የሚለውን ትእዛዝ ሲሰሙ ከባድ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ተረዱ። +20 እነሱም ፈርዖንን አነጋግረው ሲወጡ በዚያ ቆመው ይጠብቋቸው የነበሩትን ሙሴንና አሮንን አገኟቸው። +21 እነሱም እንዲህ አሏቸው፦ “በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት እንድንጠላ ስላደረጋችሁና* እንዲገድሉን በእጃቸው ሰይፍ ስለሰጣችኋቸው ይሖዋ ይይላችሁ፤ ደግሞም ይፍረድባችሁ።”+ +22 በዚህ ጊዜ ሙሴ ወደ ይሖዋ ተመልሶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ሕዝብ ለመከራ የዳረግከው ለምንድን ነው? እኔንስ የላክኸኝ ለምንድን ነው? +23 ፈርዖን በስምህ ለመናገር ወደ እሱ ከገባሁበት+ ጊዜ አንስቶ ይህን ሕዝብ ይበልጥ ማንገላታቱን ቀጥሏል፤+ አንተም ብትሆን ሕዝብህን አላዳንክም።”+ +21 “ለእነሱ የምትነግራቸው ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፦+ +2 “ዕብራዊ ባሪያ ከገዛህ+ ለስድስት ዓመት ባሪያ ሆኖ ያገለግልሃል፤ በሰባተኛው ዓመት ግን ያለምንም ክፍያ ነፃ ይወጣል።+ +3 የመጣው ብቻውን ከሆነ ብቻውን ነፃ ይወጣል። ሚስት ካለችው ግን ሚስቱም አብራው ነፃ ትውጣ። +4 ጌታው ሚስት ቢያጋባውና ሚስቱ ��ንዶች ወይም ሴቶች ልጆችን ብትወልድለት ሚስቱና ልጆቿ የጌታዋ ይሆናሉ፤ እሱም ብቻውን ነፃ ይወጣል።+ +5 ሆኖም ባሪያው ‘ጌታዬን፣ ሚስቴንና ልጆቼን እወዳለሁ፤ ነፃ መውጣት አልፈልግም’+ በማለት በአቋሙ ከጸና +6 ጌታው በእውነተኛው አምላክ ፊት ያቅርበው። ከዚያም ጌታው ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ አምጥቶ ጆሮውን በወስፌ ይበሳዋል፤ እሱም ዕድሜውን ሙሉ ባሪያው ይሆናል። +7 “አንድ ሰው ሴት ልጁን ባሪያ አድርጎ ቢሸጣት ነፃ የምትወጣው ወንድ ባሪያ ነፃ በሚወጣበት መንገድ አይደለም። +8 ጌታዋ ደስ ባይሰኝባትና ቁባቱ እንድትሆን ባይፈልግ ከዚህ ይልቅ ሌላ ሰው እንዲገዛት* ቢያደርግ እሷን ለባዕድ አገር ሰው የመሸጥ መብት አይኖረውም፤ ምክንያቱም ክህደት ፈጽሞባታል። +9 ለወንድ ልጁ እንድትሆን ከመረጣት ደግሞ አንዲት ልጅ ማግኘት የሚገባትን መብት እንድታገኝ ያድርግ። +10 ሌላ ሚስት ካገባም የመጀመሪያ ሚስቱ ምግቧ፣ ልብሷና የጋብቻ መብቷ ሊጓደልባት አይገባም።+ +11 እነዚህን ሦስት ነገሮች የማያሟላላት ከሆነ ግን ምንም ገንዘብ ሳትከፍል እንዲሁ ነፃ ትውጣ። +12 “አንድ ሰው ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል ገዳዩ ይገደል።+ +13 ሆኖም የገደለው ሆን ብሎ ባይሆንና እውነተኛው አምላክ ይህ ነገር እንዲሆን ቢፈቅድ ገዳዩ የሚሸሽበት ቦታ እኔ አዘጋጅልሃለሁ።+ +14 አንድ ሰው በባልንጀራው ላይ እጅግ ቢቆጣና ሆን ብሎ ቢገድለው+ ይህን ሰው ከመሠዊያዬ አጠገብም እንኳ ቢሆን ወስደህ ግደለው።+ +15 አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ይገደል።+ +16 “ማንኛውም ግለሰብ አንድን ሰው አፍኖ ቢወስድና+ ቢሸጠው ወይም ይህን ሰው ይዞት ቢገኝ+ ይገደል።+ +17 “አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ይገደል።+ +18 “ሰዎች ተጣልተው አንደኛው ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ* ቢመታውና ተመቺው ባይሞት ከዚህ ይልቅ አልጋ ላይ ቢውል መደረግ ያለበት ነገር ይህ ነው፦ +19 ሰውየው ከአልጋው በመነሳት ከቤት ወጥቶ በምርኩዝ መንቀሳቀስ ከቻለ የመታው ሰው ከቅጣት ነፃ ይሆናል። ተጎጂው ሙሉ በሙሉ እስኪድን ድረስ ከሥራ በመስተጓጎሉ ለባከነበት ጊዜ ብቻ ካሳ ይከፍላል። +20 “አንድ ሰው ወንድ ባሪያውን ወይም ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታና እጁ ላይ ቢሞትበት ወይም ብትሞትበት ይህ ሰው የበቀል ቅጣት መቀጣት አለበት።+ +21 ሆኖም ባሪያው ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን በሕይወት ከቆየ የበቀል ቅጣት መቀጣት የለበትም፤ ምክንያቱም ይህ ሰው በጌታው ገንዘብ የተገዛ ነው። +22 “ሰዎች እርስ በርስ ሲታገሉ በአንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ላይ ጉዳት ቢያደርሱባትና ያለጊዜዋ ብትወልድ*+ ሆኖም ለሞት* የተዳረገ ባይኖር ጉዳት ያደረሰው ሰው የሴትየዋ ባል የጠየቀውን ካሳ መክፈል አለበት፤ ፈራጆቹ የወሰኑበትን ካሳ መክፈል ይኖርበታል።+ +23 ሆኖም ለሞት የተዳረገ ካለ ሕይወት ስለ ሕይወት፣*+ +24 ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፣ እጅ ስለ እጅ፣ እግር ስለ እግር፣+ +25 መቃጠል ስለ መቃጠል፣ ቁስል ስለ ቁስል እንዲሁም ምት ስለ ምት እንዲመለስ ማድረግ አለብህ። +26 “አንድ ሰው የወንድ ባሪያውን ወይም የሴት ባሪያውን ዓይን ቢመታና ዓይኑን ቢያጠፋው ለዓይኑ ካሳ እንዲሆን ባሪያውን ነፃ ሊያወጣው ይገባል።+ +27 የወንድ ባሪያውን ወይም የሴት ባሪያውን ጥርስ ቢያወልቅ ለጥርሱ ካሳ እንዲሆን ከባርነቱ ነፃ አድርጎ ሊያሰናብተው ይገባል። +28 “አንድ በሬ አንድን ወንድ ወይም አንዲትን ሴት ቢወጋና የተወጋው ሰው ቢሞት በሬው በድንጋይ ተወግሮ ይገደል፤+ ሥጋውም መበላት የለበትም። የበሬው ባለቤት ግን ከቅጣት ነፃ ነው። +29 በሬው የመዋጋት አመል እንዳለው የሚታወቅ ከሆነና ለባለቤቱም ስለ በሬው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ከነበረ በሬውን ሳይጠብቀው ቀርቶ አንድን ወንድ ወይም አንዲትን ሴት ቢገድል፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም ይገደል። +30 ቤዛ* እንዲከፍል ከተጠየቀ ለሕይወቱ* መዋጃ የሚሆነውን ዋጋ ይክፈል፤ የተጠየቀውንም ሁሉ ይስጥ። +31 በሬው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ቢወጋ የበሬው ባለቤት በዚሁ ድንጋጌ መሠረት ሊፈረድበት ይገባል። +32 በሬው የወጋው አንድን ወንድ ባሪያ ወይም አንዲትን ሴት ባሪያ ከሆነ የበሬው ባለቤት ለባሪያው ጌታ 30 ሰቅል* ይሰጠዋል፤ በሬውም በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል። +33 “አንድ ሰው ጉድጓድ ከፍቶ ወይም ቆፍሮ ጉድጓዱን ሳይከድነው ቢተወውና አንድ በሬ ወይም አንድ አህያ ጉድጓዱ ውስጥ ቢወድቅ +34 የጉድጓዱ ባለቤት ካሳ መክፈል አለበት።+ ዋጋውን ለእንስሳው ባለቤት መስጠት ይኖርበታል፤ የሞተውም እንስሳ የእሱ ይሆናል። +35 የአንድ ሰው በሬ በሌላው ሰው በሬ ላይ ጉዳት ቢያደርስና በሬው ቢሞት ሰዎቹ በሕይወት ያለውን በሬ ሸጠው ገንዘቡን ይካፈሉ፤ የሞተውንም በሬ ይካፈሉ። +36 ወይም በሬው የመዋጋት አመል እንዳለበት እየታወቀ ባለቤቱ ሳይጠብቀው ቀርቶ ከሆነ ባለቤቱ በበሬ ፋንታ በሬ ካሳ መክፈል አለበት፤ የሞተውም በሬ የእሱ ይሆናል። +15 በዚያን ጊዜ ሙሴና እስራኤላውያን የሚከተለውን መዝሙር ለይሖዋ ዘመሩ፦+ “በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ስላለ ለይሖዋ እዘምራለሁ።+ ፈረሱንና ፈረሰኛውን ባሕር ውስጥ ጣላቸው።+ +2 አዳኜ ስለሆነልኝ ያህ* ብርታቴና ኃይሌ ነው።+ እሱ አምላኬ ነው፤ አወድሰዋለሁ፤+ የአባቴ አምላክ ነው፤+ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።+ +3 ይሖዋ ኃያል ተዋጊ ነው።+ ስሙ ይሖዋ ነው።+ +4 የፈርዖንን ሠረገሎችና ሠራዊቱን ባሕር ውስጥ ወረወራቸው፣+ ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎቹም ቀይ ባሕር ውስጥ ሰመጡ።+ +5 ማዕበሉም ከደናቸው፤ እነሱም እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ሰመጡ።+ +6 ይሖዋ ሆይ፣ ቀኝ እጅህ እጅግ ኃያል ነው፤+ ይሖዋ ሆይ፣ ቀኝ እጅህ ጠላትን ያደቃል። +7 እጅግ ታላቅ በሆነው ግርማህ በአንተ ላይ የሚነሱትን ሁሉ ቁልቁል ታሽቀነጥራቸዋለህ፤+ የሚነደውን ቁጣህን ትልካለህ፤ እነሱንም እንደ ገለባ* ይበላቸዋል። +8 በአፍንጫህ እስትንፋስ ውኃዎች ተቆለሉ፤ ወራጁንም ውኃ ገድበው ቀጥ ብለው ቆሙ፤ ማዕበሉም በባሕሩ ልብ ውስጥ ረጋ። +9 ጠላትም ‘አሳድዳቸዋለሁ! አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ! እስክጠግብም* ድረስ ምርኮን እከፋፈላለሁ! ሰይፌን እመዛለሁ! እጄም ታንበረክካቸዋለች!’ አለ።+ +10 አንተም እስትንፋስህን እፍ አልክ፤ ባሕሩም ከደናቸው፤+ እነሱም ኃያል በሆኑ ውኃዎች ውስጥ እንደ አረር ሰመጡ። +11 ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ በቅድስናው ኃያል መሆኑን የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ የምትፈራና የምትወደስ፣ ድንቅ ነገሮችን የምታደርግ አንተ ነህ።+ +12 ቀኝ እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው።+ +13 የታደግካቸውን+ ሕዝቦች በታማኝ ፍቅርህ መራሃቸው፤ በብርታትህም ወደ ቅዱስ መኖሪያህ ትመራቸዋለህ። +14 ሕዝቦችም ይሰማሉ፤+ ይንቀጠቀጣሉ፤ የፍልስጤም ነዋሪዎችም ምጥ ይይዛቸዋል። +15 በዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ይሸበራሉ፤ የሞዓብ ኃያላን ገዢዎች ብርክ ይይዛቸዋል።+ የከነአን ነዋሪዎችም ሁሉ ልባቸው ይከዳቸዋል።+ +16 ፍርሃትና ድንጋጤ ይወድቅባቸዋል።+ ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝቦችህ አልፈው እስኪሄዱ ድረስ፣ አንተ የፈጠርካቸው ሕዝቦች+ አልፈው እስኪሄዱ ድረስ፣+ ከክንድህ ታላቅነት የተነሳ እንደ ድንጋይ ደርቀው ይቀራሉ። +17 አምጥተህ በርስትህ ተራራ ላይ ትተክላቸዋለህ፤+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ራስህ ልትኖርበት ባዘጋጀኸው ጸንቶ የተመሠረተ ቦታ፣ ይሖዋ ሆይ፣ እጆችህ በመሠረቱት መቅደስ ትተክላቸዋለህ። +18 ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።+ +19 ���ፈርዖን ፈረሶች፣ የጦር ሠረገሎቹና ፈረሰኞቹ ወደ ባሕሩ በገቡ ጊዜ፣+ ይሖዋ የባሕሩን ውኃ ላያቸው ላይ መለሰባቸው፤+ የእስራኤል ሕዝብ ግን በባሕሩ መሃል በደረቅ መሬት ተሻገረ።”+ +20 ከዚያም የአሮን እህት ነቢዪቱ ሚርያም አታሞ አነሳች፤ ሴቶቹም ሁሉ አታሞ እየመቱና እየጨፈሩ ተከተሏት። +21 ሚርያምም ከወንዶቹ ጋር እየተቀባበለች እንዲህ ስትል ዘመረች፦ “በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ስላለ ለይሖዋ ዘምሩ።+ ፈረሱንና ፈረሰኛውን ባሕር ውስጥ ጣላቸው።”+ +22 ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን ከቀይ ባሕር እየመራ ይዟቸው ወጣ፤ እነሱም ወደ ሹር ምድረ በዳ ሄዱ፤ በምድረ በዳውም ለሦስት ቀን ያህል ተጓዙ፤ ሆኖም ውኃ አላገኙም ነበር። +23 በኋላም ወደ ማራ*+ መጡ፤ ያም ሆኖ በማራ ያለው ውኃ መራራ ስለነበር ሊጠጡት አልቻሉም። የቦታውን ስም ማራ ያለውም በዚህ የተነሳ ነው። +24 በመሆኑም ሕዝቡ “እንግዲህ ምን ልንጠጣ ነው?” እያለ በሙሴ ላይ ማጉረምረም ጀመረ።+ +25 እሱም ወደ ይሖዋ ጮኸ፤+ ይሖዋም ወደ አንዲት ዛፍ መራው። ሙሴም ዛፏን ውኃው ውስጥ ሲጥላት ውኃው ጣፋጭ ሆነ። እሱም በዚያ የሚመሩበት ሥርዓትና ለፍርድ መሠረት የሚሆን መመሪያ አወጣላቸው፤ በዚያም ፈተናቸው።+ +26 እንዲህም አላቸው፦ “የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል በጥንቃቄ ብታዳምጡ፣ በእሱ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ብታደርጉ፣ ለትእዛዛቱ ጆሯችሁን ብትሰጡና ሥርዓቶቹን በሙሉ ብታከብሩ+ በግብፃውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤+ ምክንያቱም እኔ ይሖዋ እፈውሳችኋለሁ።”+ +27 ከዚያም 12 የውኃ ምንጮችና 70 የዘንባባ ዛፎች ወዳሉበት ወደ ኤሊም መጡ። በዚያም በውኃው አጠገብ ሰፈሩ። +22 “አንድ ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅና ቢያርደው ወይም ቢሸጠው ለበሬው አምስት በሬዎችን ለበጉ ደግሞ አራት በጎችን ካሳ መክፈል አለበት።+ +2 (“አንድ ሌባ+ ሰብሮ ሲገባ ቢያዝና ተመቶ ቢሞት ማንም ስለ እሱ በደም ዕዳ ተጠያቂ አይሆንም። +3 ይህ የሆነው ግን ፀሐይ ከወጣች በኋላ ከሆነ ገዳዩ በደም ዕዳ ተጠያቂ ይሆናል።) “ሌባው ካሳ መክፈል አለበት። ምንም የሚከፍለው ነገር ከሌለው ግን ለሰረቃቸው ነገሮች ካሳ እንዲከፍል እሱ ራሱ ይሸጥ። +4 የሰረቀው ነገር በሬም ሆነ አህያ ወይም በግ በሕይወት እንዳለ በእጁ ላይ ከተገኘ እጥፍ አድርጎ ካሳ መክፈል አለበት። +5 “አንድ ሰው ከብቶቹን በእርሻ ወይም በወይን ቦታ አሰማርቶ የሌላ ሰው እርሻ ውስጥ ገብተው ሲግጡ ዝም ቢላቸው ይህ ሰው ምርጥ ከሆነው ከራሱ እርሻ ወይም ምርጥ ከሆነው ከራሱ የወይን ቦታ ካሳ መክፈል አለበት። +6 “እሳት ተነስቶ ወደ ቁጥቋጦ ቢዛመትና ነዶዎችን ወይም ያልታጨደን እህል አሊያም አዝመራን ቢያወድም እሳቱን ያስነሳው ሰው ለተቃጠለው ነገር ካሳ መክፈል አለበት። +7 “አንድ ሰው ገንዘብ ወይም ንብረት እንዲያስቀምጥለት ለባልንጀራው ቢሰጠውና ገንዘቡ ወይም ንብረቱ ከባልንጀራው ቤት ቢሰረቅ፣ ሌባው ከተያዘ እጥፍ አድርጎ ካሳ መክፈል አለበት።+ +8 ሌባው ካልተያዘ ግን የቤቱ ባለቤት በባልንጀራው ንብረት ላይ እጁን አሳርፎ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማረጋገጥ በእውነተኛው አምላክ ፊት እንዲቀርብ መደረግ አለበት።+ +9 አላግባብ በባለቤትነት የተያዘን ንብረት ይኸውም በሬን፣ አህያን፣ በግን፣ ልብስን ወይም ጠፍቶ የነበረን ማንኛውንም ነገር በተመለከተ ‘ይህ ንብረት የእኔ ነው!’ በሚል ክርክር ቢነሳ፣ ሁለቱም ሰዎች ጉዳያቸውን በእውነተኛው አምላክ ፊት ያቅርቡ።+ አምላክ ጥፋተኛ ነው ብሎ የሚፈርድበት ግለሰብ እጥፍ አድርጎ +10 “አንድ ሰው አህያ ወይም በሬ ወይም በግ አሊያም ሌላ ማንኛውንም የቤት እንስሳ ለባልንጀራው በአደራ ቢሰጥና እ��ስሳው ቢሞት ወይም ከባድ ጉዳት ቢደርስበት አሊያም ማንም ሰው ሳያይ ተነድቶ ቢወሰድ +11 አደራ ተቀባዩ በባልንጀራው ንብረት ላይ እጁን እንዳላሳረፈ ለማረጋገጥ በይሖዋ ፊት ይማልለት፤ የንብረቱ ባለቤትም መሐላውን መቀበል አለበት። ያም ሰው ካሳ እንዲከፍል አይጠየቅም።+ +12 እንስሳው ተሰርቆበት ከሆነ ግን ለባለቤቱ ካሳ መክፈል አለበት። +13 በአውሬ ተበልቶ ከሆነ ደግሞ ከአውሬ የተረፈውን ማስረጃ አድርጎ ያቅርብ። አውሬ ለበላው ካሳ መክፈል አይጠበቅበትም። +14 “ሆኖም ማንኛውም ሰው ከባልንጀራው እንስሳ ቢዋስና እንስሳው ባለቤቱ በሌለበት ከባድ ጉዳት ቢደርስበት ወይም ቢሞት የተዋሰው ሰው ካሳ መክፈል አለበት። +15 ጉዳቱ የደረሰው ባለቤቱ አብሮ እያለ ከሆነ ግን ካሳ መክፈል የለበትም። እንስሳው በኪራይ መልክ የተወሰደ ከሆነ የደረሰው ጉዳት በኪራዩ ዋጋ ይሸፈናል። +16 “አንድ ወንድ አንዲትን ያልታጨች ድንግል አባብሎ አብሯት ቢተኛ የማጫዋን ዋጋ ከፍሎ ሚስቱ ሊያደርጋት ይገባል።+ +17 የልጅቷ አባት ልጁን ለእሱ ለመስጠት ፈጽሞ ፈቃደኛ ሳይሆን ቢቀር ይህ ሰው ለደናግል የሚከፈለውን የማጫ ዋጋ መክፈል አለበት። +18 “መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ።+ +19 “ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት የሚፈጽም ማንም ሰው ያለጥርጥር ይገደል።+ +20 “ለይሖዋ ካልሆነ በቀር ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ይገደል።+ +21 “የባዕድ አገር ሰውን አትበድል ወይም አትጨቁን፤+ ምክንያቱም እናንተ ራሳችሁ በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ።+ +22 “መበለቲቱን ወይም አባት የሌለውን* ልጅ አታጎሳቁሉ።+ +23 ብታጎሳቁለውና ወደ እኔ ቢጮኽ እኔ በእርግጥ ጩኸቱን እሰማለሁ፤+ +24 ቁጣዬም ይነድዳል። እናንተንም በሰይፍ እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የሌላቸው ልጆች ይሆናሉ። +25 “ከሕዝቤ መካከል አብሮህ ላለ ችግረኛ ገንዘብ ብታበድር እንደ አራጣ አበዳሪ አትሁንበት። ወለድም አትጠይቁት።+ +26 “የባልንጀራህን ልብስ መያዣ አድርገህ ብትይዝ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ልትመልስለት ይገባል።+ +27 ምክንያቱም የሚለብሰው ልብስ ይኸውም ሰውነቱ ላይ የሚጥለው ልብስ እሱ ብቻ ነው፤ አለዚያ ምን ለብሶ ይተኛል?+ እሱም ወደ እኔ በሚጮኽበት ጊዜ በእርግጥ እሰማዋለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሩኅሩኅ* ነኝ።+ +28 “አምላክን አትራገም፤+ በሕዝብህ መካከል ያለውን አለቃም* አትራገም።+ +29 “ከተትረፈረፈው ምርትህና ሞልቶ ከሚፈሰው መጭመቂያህ* መባ ለማቅረብ አትሳሳ።+ የወንዶች ልጆችህን በኩር ለእኔ መስጠት አለብህ።+ +30 የበሬህንና የበግህን በኩር በተመለከተ ልታደርገው የሚገባህ ነገር ይህ ነው፦+ ለሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቆይ። በስምንተኛው ቀን ለእኔ መስጠት አለብህ።+ +31 “እናንተ ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ሆናችሁ መገኘት አለባችሁ፤+ አውሬ ዘንጥሎት ሜዳ ላይ የተገኘን የማንኛውንም እንስሳ ሥጋ አትብሉ።+ ለውሾች ጣሉት። +39 በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል የሚለበሱትን በጥሩ ሁኔታ የተሸመኑትን ልብሶች ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍና ከደማቅ ቀይ ማግ ሠሩ።+ ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረትም የአሮንን ቅዱስ ልብሶች ሠሩ።+ +2 እሱም ኤፉዱን+ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠራው። +3 እነሱም ወርቁን በመቀጥቀጥ በስሱ ጠፈጠፉት፤ እሱም ከሰማያዊው ክር፣ ከሐምራዊው ሱፍ፣ ከደማቁ ቀይ ማግና ከጥሩው በፍታ ጋር አብሮ እንዲሠራው ወርቁን እንደ ክር በቀጫጭኑ ሰነጣጠቀው፤ ከዚያም በወርቁ ጥልፍ ጠለፈበት። +4 ለኤፉዱም ላዩ ላይ የሚጣበቁ የትከሻ ጥብጣቦች የሠሩለት ሲሆን ኤፉዱም ከትከሻ ጥብጣቦቹ ጋር የሚያያዘው በሁለቱ ጫፎቹ ላይ ነበር። +5 ኤፉዱ ወዲያ ወዲህ እንዳይንቀሳቀስ ለማሰር የሚያገለግለው ከኤፉዱ ጋር የተያያዘው በሽመና የተሠራው መቀነትም + ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት እንደ ኤፉዱ ሁሉ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ተሠራ። +6 ከዚያም የኦኒክስ ድንጋዮቹን በወርቅ አቃፊዎቹ ውስጥ አስቀመጧቸው፤ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞችም ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ቀረጹባቸው።+ +7 እሱም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤል ልጆች እንደ መታሰቢያ ድንጋዮች ሆነው እንዲያገለግሉ+ በኤፉዱ የትከሻ ጥብጣቦች ላይ አስቀመጣቸው። +8 ከዚያም የደረት ኪሱን+ የጥልፍ ባለሙያ እንደሚሠራው አድርጎ ልክ ኤፉዱ በተሠራበት መንገድ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠራው።+ +9 ለሁለት በሚታጠፍበት ጊዜም አራቱም ጎኖቹ እኩል ነበሩ። ለሁለት በሚታጠፍበት ጊዜ ቁመቱም ሆነ ወርዱ አንድ ስንዝር* የሆነውን የደረት ኪስ ሠሩ። +10 በላዩም ላይ አራት ረድፍ ድንጋዮችን አደረጉበት። በመጀመሪያው ረድፍ ሩቢ፣ ቶጳዝዮንና መረግድ ተደረደረ። +11 በሁለተኛው ረድፍ ደግሞ በሉር፣ ሰንፔርና ኢያስጲድ ተደረደረ። +12 በሦስተኛው ረድፍ ለሼም፣ አካትምና አሜቴስጢኖስ ተደረደረ። +13 በአራተኛውም ረድፍ ክርስቲሎቤ፣ ኦኒክስና ጄድ ተደረደረ። በወርቅ አቃፊዎችም ውስጥ ተቀመጡ። +14 ድንጋዮቹም 12ቱን የእስራኤል ወንዶች ልጆች ስሞች የሚወክሉ ነበሩ፤ ስሞቹም ልክ ማኅተም በሚቀረጽበት መንገድ ተቀረጹ፤ እያንዳንዱ ስም ከ12ቱ ነገዶች አንዱን የሚወክል ነበር። +15 ከዚያም በደረት ኪሱ ላይ እንደ ገመድ የተጎነጎነ ሰንሰለት ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ።+ +16 በመቀጠልም ሁለት የወርቅ አቃፊዎችንና ሁለት ቀለበቶችን ሠሩ፤ ሁለቱን ቀለበቶችም በደረት ኪሱ ሁለት ማዕዘኖች ላይ አያያዟቸው። +17 በኋላም ሁለቱን የወርቅ ገመዶች በደረት ኪሱ ማዕዘኖች ላይ በሚገኙት ሁለት ቀለበቶች ውስጥ አስገቧቸው። +18 ከዚያም የሁለቱን ገመዶች ሁለት ጫፎች በሁለቱ አቃፊዎች ውስጥ አስገቧቸው፤ በኤፉዱ በፊት በኩል በትከሻ ጥብጣቦቹ ላይ አያያዟቸው። +19 በመቀጠልም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው በኤፉዱ በኩል በሚውለው በደረት ኪሱ ውስጠኛ ጠርዝ ሁለት ጫፎች ላይ አደረጓቸው።+ +20 ከዚያም ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው በኤፉዱ ላይ ከፊት በኩል ከሁለቱ የትከሻ ጥብጣቦች በታች፣ መጋጠሚያው አጠገብ፣ በሽመና ከተሠራው የኤፉዱ መቀነት በላይ አደረጓቸው። +21 በመጨረሻም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ላይ ሳይንቀሳቀስ፣ ተሸምኖ ከተሠራው መቀነት በላይ እንዲውል የደረት ኪሱን ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ አያያዟቸው። +22 ከዚያም እጅጌ የሌለውን የኤፉዱን ቀሚስ የሽመና ባለሙያ ሙሉ በሙሉ በሰማያዊ ክር ሸምኖ እንዲሠራው አደረገ።+ +23 የቀሚሱ አንገት ማስገቢያ ልክ እንደ ጥሩር አንገት ማስገቢያ መሃል ላይ ነበር። የአንገት ማስገቢያውም እንዳይቀደድ ዙሪያውን ተቀምቅሞ ነበር። +24 ከዚያም ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍና ደማቅ ቀይ ማግ አንድ ላይ በመግመድ በታችኛው የቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ዘርፍ የሚሆኑ ሮማኖችን ሠሩ። +25 በተጨማሪም ከንጹሕ ወርቅ ቃጭሎችን ሠሩ፤ ቃጭሎቹንም በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ በሮማኖቹ መሃል መሃል አደረጓቸው። +26 ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረትም ለአገልግሎት በሚውለው ቀሚስ የታችኛው ጠርዝ ዙሪያ ቃጭል ከዚያም ሮማን፣ ቃጭል ከዚያም ሮማን እያፈራረቁ አደረጉበት። +27 ከዚያም ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ከጥ�� በፍታ ረጅም ቀሚስ በሽመና ባለሙያ አሠሩላቸው፤+ +28 በተጨማሪም ጥምጥሙን+ ከጥሩ በፍታ፣ ጌጠኛ የራስ ቆቦቹንም+ ከጥሩ በፍታ፣ የበፍታ ቁምጣውን+ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ +29 እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት መቀነቱን በቀጭኑ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ፣ ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍና ከደማቅ ቀይ ማግ ሸምነው ሠሩት። +30 በመጨረሻም የሚያብረቀርቀውን ጠፍጣፋ ወርቅ ይኸውም ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየውን ቅዱስ ምልክት* ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ፤ አንድ ሰው ማኅተም በሚቀርጽበት መንገድ “ቅድስና የይሖዋ ነው” የሚል ጽሑፍ በላዩ ላይ ቀረጹበት።+ +31 ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት በጥምጥሙ ላይ እንዲውል ለማድረግ ሰማያዊ ገመድ አሰሩበት። +32 የማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም የመገናኛ ድንኳኑ ሥራ በሙሉ ተጠናቀቀ፤ እስራኤላውያን ይሖዋ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ ሠሩ።+ ልክ እንደታዘዙትም አደረጉ። +33 እነሱም የማደሪያ ድንኳኑን+ ወደ ሙሴ አመጡ፤ ድንኳኑንና+ ዕቃዎቹን በሙሉ ማለትም ማያያዣዎቹን፣+ አራት ማዕዘን ቋሚዎቹን፣+ አግዳሚ እንጨቶቹን፣+ ዓምዶቹን፣ መሰኪያዎቹን፣+ +34 ለመደረቢያ የሚሆነውን ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና+ ለመደረቢያ የሚሆነውን የአቆስጣ ቆዳ፣ ለመግቢያው መከለያ የሚሆነውን መጋረጃ፣+ +35 የምሥክሩን ታቦት እንዲሁም መሎጊያዎቹንና+ መክደኛውን፣+ +36 ጠረጴዛውን እንዲሁም ዕቃዎቹን+ በሙሉና ገጸ ኅብስቱን፣ +37 ከንጹሕ ወርቅ የተሠራውን መቅረዝ+ እንዲሁም በመደዳ የተደረደሩትን መብራቶቹንና ዕቃዎቹን+ በሙሉ፣ የመብራቱን ዘይት፣+ +38 የወርቅ መሠዊያውን፣+ የቅብዓት ዘይቱን፣+ ጥሩ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣+ ለድንኳኑ መግቢያ የሚሆነውን መከለያ፣*+ +39 የመዳብ መሠዊያውንና+ የመዳብ ፍርግርጉን እንዲሁም መሎጊያዎቹንና+ ዕቃዎቹን+ በሙሉ፣ ገንዳውንና ማስቀመጫውን፣+ +40 የግቢውን መጋረጃዎች እንዲሁም ቋሚዎቹን፣ መሰኪያዎቹን፣+ ለግቢው መግቢያ የሚሆነውን መከለያ፣*+ የድንኳኑን ገመዶች፣ የድንኳኑን ካስማዎችና+ በማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ለሚከናወነው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች በሙሉ፣ +41 በመቅደሱ ለማገልገል የሚለበሱትን በጥሩ ሁኔታ ተሸምነው የተሠሩትን ልብሶች፣ የካህኑን የአሮንን ቅዱስ ልብሶች+ እንዲሁም ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸውን ልብሶች አመጡ። +42 እስራኤላውያን ሥራውን በሙሉ ያከናወኑት ይሖዋ ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።+ +43 ሙሴም ሥራቸውን በሙሉ ሲመለከት ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት እንደሠሩ አየ፤ ከዚያም ባረካቸው። +17 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲሁም እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ ያዘዘው ይህ ነው፦ +3 “‘“ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው በሬ ወይም የበግ ጠቦት አሊያም ፍየል በሰፈሩ ውስጥ ወይም ከሰፈሩ ውጭ ቢያርድና +4 በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊት ለይሖዋ መባ አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ባያመጣ ያ ሰው በደም ዕዳ ይጠየቃል። ሰውየው ደም አፍስሷል፤ በመሆኑም ይህ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። +5 ይህም እስራኤላውያን በሜዳ ላይ እየሠዉ ያሉትን መሥዋዕት ወደ ይሖዋ፣ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያና ወደ ካህኑ እንዲያመጡ ነው። እነዚህንም ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕቶች አድርገው መሠዋት አለባቸው።+ +6 ካህኑም ደሙን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ባለው የይሖዋ መሠዊያ ላይ ይረጨዋል፤ ስቡንም ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ አድርጎ ያጨሰዋል።+ +7 ከእንግዲህ ወዲህ፣ አብረዋቸው ምንዝር ለሚፈጽሙት+ ፍየል የሚመስሉ አጋንንት*+ አይሠ���ም። ይህም በመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል።”’ +8 “እንዲህም በላቸው፦ ‘የሚቃጠል መባ ወይም መሥዋዕት የሚያቀርብ ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው +9 ይህን ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ባያመጣ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት።+ +10 “‘ከእስራኤል ቤት የሆነ ማንኛውም ሰው ወይም በመካከላችሁ የሚኖር የትኛውም የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ደም ቢበላ፣+ ደም በሚበላው ሰው* ላይ በእርግጥ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። +11 ምክንያቱም የሥጋ ሕይወት* ያለው በደሙ ውስጥ ነው፤+ ለራሳችሁም* ማስተሰረያ እንዲሆን እኔ ራሴ ደሙን ለእናንተ ስል ለመሠዊያው ሰጥቼዋለሁ፤+ ምክንያቱም በውስጡ ባለው ሕይወት* አማካኝነት የሚያስተሰርየው ደሙ ነው።+ +12 እስራኤላውያንን “ማንኛችሁም ደም መብላት የለባችሁም፤* እንዲሁም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው+ ደም አይብላ”+ ያልኳቸው ለዚህ ነው። +13 “‘አንድ እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር አንድ የባዕድ አገር ሰው ለመብልነት የተፈቀደ እንስሳ ወይም ወፍ አድኖ ቢይዝ ደሙን ያፍሰው፤+ አፈርም ያልብሰው። +14 የሥጋ ሁሉ ሕይወት* ደሙ ነውና፤ ምክንያቱም በውስጡ ሕይወት* አለ። በዚህም የተነሳ እስራኤላውያንን እንዲህ አልኳቸው፦ “የሥጋ ሁሉ ሕይወት* ደሙ ስለሆነ የማንኛውንም ሥጋ ደም አትብሉ። ደም የሚበላ ማንኛውም ሰው ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል።”+ +15 የአገሬው ተወላጅም ይሁን የባዕድ አገር ሰው፣ ማንኛውም ሰው* ሞቶ የተገኘን ወይም አውሬ የቦጫጨቀውን እንስሳ+ ሥጋ ቢበላ ልብሶቹን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሁን፤+ ከዚያም ንጹሕ ይሆናል። +16 ሆኖም ልብሶቹን ካላጠበና ሰውነቱን ካልታጠበ በሠራው ጥፋት ይጠየቅበታል።’”+ +18 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።+ +3 ትኖሩበት በነበረው በግብፅ ምድር ያሉ ሰዎች እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነአን ምድር ያሉ ሰዎች እንደሚያደርጉትም አታድርጉ።+ እንዲሁም እነሱ የሚከተሏቸውን ደንቦች አትከተሉ። +4 ድንጋጌዎቼን ተግባር ላይ አውሉ፤ ደንቦቼንም በመጠበቅ በእነሱ ሂዱ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +5 ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ጠብቁ፤ እንዲህ የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +6 “‘ከመካከላችሁ ማንም ሰው የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ አይቅረብ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +7 ከአባትህ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ከእናትህም ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ እናትህ ናት፤ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። +8 “‘ከአባትህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።+ ይህ አባትህን ለኀፍረት መዳረግ ነው።* +9 “‘የአባትህ ልጅም ሆነች የእናትህ ልጅ ወይም በቤት የተወለደችም ሆነች በውጭ፣ ከእህትህ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።+ +10 “‘ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እነሱ የአንተው እርቃን ናቸው። +11 “‘የአባትህ ልጅ ከሆነችው ከአባትህ ሚስት ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እሷ እህትህ ናት። +12 “‘ከአባትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። እሷ የአባትህ የሥጋ ዘመድ ናት።+ +13 “‘ከእናትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም እሷ የእናትህ የሥጋ ዘመድ ናት። +14 “‘ከአባትህ ወንድም ሚስት ጋር ��ፆታ ግንኙነት በመፈጸም እሱን ለኀፍረት አትዳርገው።* እሷ ዘመድህ ናት።+ +15 “‘ከልጅህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።+ እሷ የልጅህ ሚስት ናት፤ ከእሷ ጋር ግንኙነት መፈጸም የለብህም። +16 “‘ከወንድምህ ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤+ ምክንያቱም ይህ ወንድምህን ለኀፍረት መዳረግ ነው።* +17 “‘ከአንዲት ሴትና ከሴት ልጇ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም።+ ከወንድ ልጇ ሴት ልጅም ሆነ ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም እነሱን አትውሰድ። እነሱ የእሷ የቅርብ ዘመዶች ናቸው፤ ይህ ጸያፍ ድርጊት* ነው። +18 “‘እህቷ ጣውንቷ እንዳትሆን+ ሚስትህ በሕይወት እያለች ከእህቷ ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም። +19 “‘አንዲት ሴት በወር አበባዋ ረክሳ እያለች ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ እሷ አትቅረብ።+ +20 “‘ከጓደኛህ* ሚስት ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም ራስህን አታርክስ።+ +21 “‘ከልጆችህ መካከል የትኛውንም ለሞሎክ እንዲሰጥ* አታድርግ።+ በዚህ መንገድ የአምላክህን ስም አታርክስ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +22 “‘ከሴት ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ።+ ይህ አስጸያፊ ድርጊት ነው። +23 “‘አንድ ወንድ ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈጸም ራሱን አያርክስ፤ ሴትም ብትሆን ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ራሷን ለእንስሳ አታቅርብ።+ ይህ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ነገር ነው። +24 “‘ከእነዚህ ነገሮች በየትኛውም ራሳችሁን አታርክሱ፤ ምክንያቱም ከእናንተ ፊት አባርሬ የማስወጣቸው ብሔራት ራሳቸውን በእነዚህ ነገሮች አርክሰዋል።+ +25 ስለሆነም ምድሪቱ ረክሳለች፤ እኔም ለሠራችው ስህተት ቅጣት አመጣባታለሁ፤ ምድሪቱም ነዋሪዎቿን ትተፋቸዋለች።+ +26 እናንተ ግን ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ጠብቁ፤+ ከእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች መካከል የትኛውንም ማድረግ የለባችሁም፤ የአገራችሁ ሰውም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው እንዲህ ማድረግ የለበትም።+ +27 ምክንያቱም ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ፈጽመዋል፤+ በዚህም የተነሳ አሁን ምድሪቱ ረክሳለች። +28 እናንተ ግን ምድሪቱን ስለማታረክሷት ከእናንተ በፊት የነበሩትን ብሔራት እንደተፋቻቸው እናንተን አትተፋችሁም። +29 ማንኛውም ሰው ከእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች መካከል የትኛውንም ቢፈጽም ይህን የፈጸመው ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። +30 ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች ይከተሏቸው ከነበሩት አስጸያፊ ልማዶች በመራቅ ለእኔ የገባችሁትን ግዴታ ፈጽሙ፤+ አለዚያ በእነሱ ምክንያት ራሳችሁን ታረክሳላችሁ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” +23 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ልታውጇቸው የሚገቡት+ በየወቅቱ የሚከበሩ የይሖዋ በዓላት+ ቅዱስ ጉባኤዎች ናቸው። በየወቅቱ የሚከበሩት የእኔ በዓላት የሚከተሉት ናቸው፦ +3 “‘ለስድስት ቀን ሥራ መሥራት ይቻላል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት+ ይኸውም ቅዱስ ጉባኤ ነው። ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ይህ የይሖዋ ሰንበት ነው።+ +4 “‘በተወሰነላቸው ጊዜ ላይ ልታውጇቸው የሚገቡት በየወቅቱ የሚከበሩ የይሖዋ በዓላት ማለትም ቅዱስ ጉባኤዎች የሚከተሉት ናቸው፦ +5 በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን+ አመሻሹ ላይ* ለይሖዋ ፋሲካ* ይከበራል።+ +6 “‘በዚህ ወር 15ኛ ቀን ላይ የቂጣ በዓል ለይሖዋ ይከበራል።+ ለሰባት ቀንም ቂጣ መብላት ይኖርባችኋል።+ +7 በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ።+ ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። +8 ��ኖም ለሰባት ቀን ያህል ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ታቀርባላችሁ። በሰባተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም።’” +9 በመቀጠልም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +10 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ የምድሪቱን አዝመራ በምታጭዱበት ጊዜ ከአዝመራችሁ መጀመሪያ የደረሰውን+ እህል ነዶ ለካህኑ ማምጣት አለባችሁ።+ +11 እሱም ተቀባይነት እንድታገኙ ነዶውን በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዝውዘው። ካህኑ በሰንበት ማግስት ነዶውን ወዲያና ወዲህ ሊወዘውዘው ይገባል። +12 ነዶው ወዲያና ወዲህ እንዲወዘወዝ በምታደርጉበት ቀን አንድ ዓመት ገደማ የሆነው እንከን የሌለበት ጠቦት ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ማቅረብ አለባችሁ። +13 ከዚህም ጋር ሁለት አሥረኛ ኢፍ* በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። በተጨማሪም አንድ አራተኛ ሂን* የወይን ጠጅ ከዚያ ጋር የመጠጥ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። +14 የአምላካችሁን መባ እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ ምንም ዓይነት ዳቦም ሆነ ቆሎ ወይም እሸት መብላት የለባችሁም። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው። +15 “‘ከሰንበት ማግስት ይኸውም ለሚወዘወዝ መባ የሚሆነውን ነዶ ካመጣችሁበት ቀን ጀምሮ ሰባት ሰንበቶችን ቁጠሩ።+ እነሱም ሙሉ ሳምንታት መሆን አለባቸው። +16 እስከ ሰባተኛው ሰንበት ማግስት ድረስ 50 ቀን+ ቁጠሩ፤ ከዚያም ለይሖዋ አዲስ የእህል መባ አቅርቡ።+ +17 ከምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁለት ቂጣዎችን ለሚወዘወዝ መባ ማምጣት ይኖርባችኋል። እነሱም ከሁለት አሥረኛ ኢፍ* የላመ ዱቄት የተዘጋጁ መሆን አለባቸው። ለይሖዋ የሚቀርቡ መጀመሪያ የደረሱ ፍሬዎች+ እንደመሆናቸው መጠን እርሾ ገብቶባቸው+ መጋገር ይኖርባቸዋል። +18 ከቂጣዎቹም ጋር እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸውና እንከን የሌለባቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች አቅርቡ።+ እነዚህም ከእህል መባቸውና ከመጠጥ መባዎቻቸው ጋር ለይሖዋ የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ሆነው ይቀርባ +19 እንዲሁም ለኃጢአት መባ እንዲሆን ከፍየሎች መካከል አንድ ግልገል፣+ ለኅብረት መሥዋዕት+ እንዲሆኑ ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን አቅርቡ። +20 ካህኑም መጀመሪያ ከደረሱ ፍሬዎች ከተዘጋጁት ቂጣዎችና ከሁለቱ ተባዕት ጠቦቶች ጋር በይሖዋ ፊት የሚወዘወዝ መባ አድርጎ ወዲያና ወዲህ ይወዝውዛቸው። እነዚህም ለይሖዋ የተቀደሱ ነገሮች ናቸው፤ የካህኑም ድርሻ ይሆናሉ።+ +21 በዚህ ቀን ለእናንተ ቅዱስ ጉባኤ ታውጃላችሁ።+ ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው። +22 “‘የምድራችሁን አዝመራ በምታጭዱበት ጊዜ የእርሻችሁን ዳርና ዳር ሙልጭ አድርጋችሁ አትጨዱት፤ የእርሻችሁን ቃርሚያም አትልቀሙ።+ እነዚህን ለድሃውና*+ ለባዕድ አገሩ ሰው+ ተዉለት። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” +23 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +24 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘በሰባተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን መለከት በመንፋት የሚታሰብ+ ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ። +25 ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ፤ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ታቀርባላችሁ።’” +26 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +27 “ሆኖም የዚህ የሰባተኛው ወር አሥረኛ ቀን የስርየት ቀን ነው።+ ቅዱስ ጉባኤ አክብሩ፣ ራሳችሁን አጎሳቁሉ*+ እንዲሁም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አቅርቡ። +28 ይህ ቀን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ለእናንተ ማስተሰረያ+ የሚቀርብበት የስርየት ቀን ስለሆነ በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። +29 በዚህ ቀን ራሱን የማያጎሳቁል* ማንኛውም ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል።+ +30 በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ የሚሠራን ሰው* ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። +31 ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው። +32 ይህ እናንተ ሙሉ በሙሉ የምታርፉበት ሰንበት ነው፤ በወሩም ዘጠነኛ ቀን ምሽት ላይ ራሳችሁን* ታጎሳቁላላችሁ።+ ሰንበታችሁንም ከዚያ ዕለት ምሽት አንስቶ እስከ ቀጣዩ ቀን ምሽት ድረስ አክብሩ።” +33 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +34 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘በዚህ በሰባተኛው ወር ከ15ኛው ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀን ያህል ለይሖዋ የዳስ* በዓል ይከበራል።+ +35 በመጀመሪያው ቀን ላይ ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል፤ እናንተም ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። +36 ለሰባት ቀን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ማቅረብ ይኖርባችኋል። በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ፤+ ለይሖዋም በእሳት የሚቀርብ መባ ማቅረብ አለባችሁ። ይህ የተቀደሰ ጉባኤ ነው። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ። +37 “‘ለይሖዋ በእሳት የሚቀርበውን መባ ማለትም የሚቃጠለውን መባ፣+ ከመሥዋዕቱ ጋር የሚቀርበውን የእህል መባና+ በየዕለቱ እንዲቀርቡ የተመደቡትን የመጠጥ መባዎች+ ለማቅረብ ቅዱስ ጉባኤዎች+ እንደሆኑ አድርጋችሁ የምታውጇቸው በየወቅቱ የሚከበሩት የይሖዋ በዓላት+ እነዚህ ናቸው። +38 እነዚህ ለይሖዋ ልትሰጧቸው ከሚገቡት በይሖዋ ሰንበቶች+ ላይ ከሚቀርቡት፣ ከስጦታዎቻችሁ፣+ ስእለት ለመፈጸም ከምታቀርቧቸው መባዎችና+ ከፈቃደኝነት መባዎቻችሁ+ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ናቸው። +39 ይሁን እንጂ የምድራችሁን ፍሬ በምትሰበስቡበት ጊዜ በሰባተኛው ወር ላይ ከ15ኛው ቀን ጀምሮ የይሖዋን በዓል ለሰባት ቀን ታከብራላችሁ።+ የመጀመሪያው ቀን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል፤ ስምንተኛውም ቀን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል።+ +40 በመጀመሪያውም ቀን የተንዠረገጉ ዛፎችን ፍሬ፣ የዘንባባ ዝንጣፊዎችን፣+ የለመለሙ ዛፎችን ቅርንጫፎችና በሸለቆ* የሚበቅሉ የአኻያ ዛፎችን ውሰዱ፤ በአምላካችሁም በይሖዋ ፊት ለሰባት ቀን+ ተደሰቱ።+ +41 ይህን በዓል በየዓመቱ ለሰባት ቀን ለይሖዋ የሚከበር በዓል አድርጋችሁ ታከብሩታላችሁ።+ በትውልዶቻችሁም ሁሉ ዘላቂ ደንብ አድርጋችሁ በሰባተኛው ወር አክብሩት። +42 ለሰባት ቀን በዳስ ውስጥ ተቀመጡ።+ በእስራኤል የሚኖሩ የአገሩ ተወላጆች በሙሉ በዳስ ውስጥ ይቀመጡ፤ +43 ይህን የሚያደርጉት እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ በዳስ ውስጥ እንዲቀመጡ እንዳደረግኩ መጪዎቹ ትውልዶቻችሁ እንዲያውቁ+ ነው።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” +44 ስለዚህ ሙሴ በየወቅቱ የሚከበሩትን የይሖዋን በዓላት ለእስራኤላውያን አስታወቀ። +19 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል።+ +3 “‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤*+ ሰንበቶቼንም ይጠብቅ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +4 ከንቱ ወደሆኑ አማልክት ዞር አትበሉ፤+ ወይም ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልክትን አትሥሩ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +5 “‘ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕ�� የምታቀርቡ+ ከሆነ ተቀባይነት በሚያስገኝላችሁ መንገድ አቅርቡት።+ +6 መሥዋዕቱም በዚያው ባቀረባችሁበት ዕለትና በቀጣዩ ቀን መበላት ይኖርበታል፤ ተርፎ እስከ ሦስተኛው ቀን የቆየ ካለ ግን በእሳት መቃጠል አለበት።+ +7 ይሁንና ከተረፈው ላይ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የሌለው አስጸያፊ ነገር ይሆናል። +8 የበላውም ሰው የይሖዋን ቅዱስ ነገር ስላረከሰ በጥፋቱ ይጠየቃል፤ ያም ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። +9 “‘የምድራችሁን አዝመራ በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ዳር ዳር ያለውን ሙልጭ አድርጋችሁ አትጨዱት፤ የእርሻችሁን ቃርሚያም አትልቀሙ።+ +10 በተጨማሪም በወይን እርሻህ ላይ የተረፈውን አትሰብስብ፤ በወይን እርሻህ ላይ የወዳደቀውን የወይን ፍሬ አትልቀም። እነዚህን ለድሃውና* ለባዕድ አገሩ ሰው ተውለት።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +11 “‘አትስረቁ፤+ አታታሉ፤+ አንዳችሁ በሌላው ላይ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት አትፈጽሙ። +12 በስሜ በሐሰት አትማሉ፤+ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ። እኔ ይሖዋ ነኝ። +13 ባልንጀራህን አታጭበርብር፤+ አትዝረፈውም።+ የቅጥር ሠራተኛውን ደሞዝ ሳትከፍል አታሳድር።+ +14 “‘መስማት የተሳነውን አትርገም ወይም በዓይነ ስውሩ ፊት እንቅፋት አታስቀምጥ፤+ አምላክህን ፍራ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +15 “‘ፍርድ አታዛቡ። ለድሃው አታዳላ ወይም ባለጸጋውን ከሌሎች አስበልጠህ አትመልከት።+ ለባልንጀራህ ፍትሐዊ ፍርድ ፍረድ። +16 “‘በሕዝብህ መካከል እየዞርክ ስም አታጥፋ።+ የባልንጀራህን ሕይወት* ለማጥፋት አትነሳ።*+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +17 “‘ወንድምህን በልብህ አትጥላው።+ የባልንጀራህ ኃጢአት ተባባሪ እንዳትሆን ተግሣጽ በሚያስፈልገው ጊዜ ሁሉ ገሥጸው።+ +18 “‘የሕዝብህን ልጆች አትበቀል፤+ በእነሱም ላይ ቂም አትያዝ፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +19 “‘የሚከተሉትን ደንቦቼን ጠብቁ፦ ሁለት ዓይነት እንስሳትን አታዳቅል። በእርሻህ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ፤+ ከሁለት የተለያዩ የክር ዓይነቶች የተሠራ ልብስ አትልበስ።+ +20 “‘አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም፣ ሴቲቱ ደግሞ ለሌላ ወንድ የታጨች ሆኖም ገና ያልተዋጀች ወይም ነፃ ያልወጣች ባሪያ ብትሆን የቅጣት እርምጃ መወሰድ አለበት። ይሁንና ይህች ሴት ገና ነፃ ስላልወጣች መገደል የለባቸውም። +21 ሰውየው የበደል መባውን ይኸውም ለበደል መባ የሚሆነውን አውራ በግ ወደ ይሖዋ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ያምጣ።+ +22 ካህኑም ሰውየው ለሠራው ኃጢአት የበደል መባ እንዲሆን በቀረበው አውራ በግ በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል፤ የሠራውም ኃጢአት ይቅር ይባልለታል። +23 “‘እናንተም ወደ ምድሪቱ ብትገቡና ለምግብ የሚሆን ዛፍ ብትተክሉ ፍሬውን ርኩስና የተከለከለ* አድርጋችሁ ቁጠሩት። ለሦስት ዓመት ከእሱ መብላት የለባችሁም።* ፍሬው መበላት የለበትም። +24 በአራተኛው ዓመት ግን ፍሬው በሙሉ በይሖዋ ፊት የምትደሰቱበት ቅዱስ ነገር ይሆናል።+ +25 ከዚያም በአምስተኛው ዓመት ፍሬውን መብላት ትችላላችሁ፤ ይህን ካደረጋችሁ ምርታችሁ ይበዛላችኋል። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +26 “‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ነገር አትብሉ።+ “‘አታስጠንቁሉ ወይም አስማት አትሥሩ።+ +27 “‘ጆሮ ግንዳችሁ አካባቢ ያለውን ፀጉር አትላጩ* ወይም የጢማችሁን ዳር ዳር አትላጩ።+ +28 “‘ለሞተ ሰው* ብላችሁ አካላችሁን አትተልትሉ+ ወይም ሰውነታችሁን አትነቀሱ። እኔ ይሖዋ ነኝ። +29 “‘ምድሪቱ ዝሙት እንዳትፈጽምና ልቅ በሆነ ምግባር እንዳትሞላ+ ሴት ልጅህን ዝሙት አዳሪ በማድረግ አታዋርዳት።+ +30 “‘ሰንበቶቼን ጠብቁ፤+ ለመቅደሴ አክብሮት* ይኑራችሁ። እኔ ይሖዋ ነኝ። +31 “‘ወደ መናፍስት ጠሪዎች አትሂዱ፤+ ጠንቋዮችንም አትጠይቁ፤+ እንዲህ ካደረጋችሁ በእነሱ ትረክሳላችሁ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +32 “‘በሸበተው ሰው ፊት ተነስ፤+ አረጋዊውንም አክብር፤+ አምላክህን ፍራ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +33 “‘በምድራችሁ አብሯችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለ አትበድሉት።+ +34 አብሯችሁ የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው እንደ አገራችሁ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፤+ እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁም ውደዱት፤ ምክንያቱም እናንተም በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +35 “‘ርዝመትን፣ ክብደትን ወይም መጠንን ስትለኩ በተጭበረበረ መለኪያ አትጠቀሙ።+ +36 ትክክለኛ ሚዛን፣ ትክክለኛ የሚዛን ድንጋዮች፣ ትክክለኛ የደረቅ ነገር መስፈሪያና* ትክክለኛ የፈሳሽ ነገር መለኪያ* ሊኖራችሁ ይገባል።+ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +37 ስለሆነም ደንቦቼን ሁሉና ድንጋጌዎቼን በሙሉ ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።’” +20 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ልጁን ለሞሎክ የሚሰጥ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም እስራኤል ውስጥ የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ይገደል።+ የአገሩ ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉት። +3 ልጆቹን ለሞሎክ ስለሰጠ እንዲሁም ቅዱሱን ስፍራዬን ስላረከሰና+ ቅዱሱን ስሜን ስላቃለለ እኔ ራሴ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቁርበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። +4 የአገሩ ሰዎች ሰውየው ልጁን ለሞሎክ በመስጠት የፈጸመውን ድርጊት አይተው እንዳላዩ ቢሆኑና ሳይገድሉት ቢቀሩ+ +5 እኔ ራሴ በዚህ ሰውና በቤተሰቡ ላይ እነሳባቸዋለሁ።+ ያንን ሰውም ሆነ ከሞሎክ ጋር ምንዝር በመፈጸም የእሱን ፈለግ የተከተሉትን ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋቸዋለሁ። +6 “‘አንድ ሰው* ከመናፍስት ጠሪዎችና+ ከጠንቋዮች+ ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ወደ እነሱ ቢሄድ እኔ በዚያ ሰው* ላይ በእርግጥ እነሳበታለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።+ +7 “‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆንኩ ራሳችሁን ቀድሱ፤ ቅዱሳንም ሁኑ።+ +8 ደንቦቼን ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+ የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ።+ +9 “‘አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ማንኛውም ሰው ይገደል።+ አባቱን ወይም እናቱን ስለረገመ ደሙ በራሱ ላይ ነው። +10 “‘ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽምን ሰው በተመለከተ እንዲህ ይደረግ፦ ከባልንጀራው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሰው ይገደል፤ አመንዝራውም ሆነ አመንዝራይቱ ይገደሉ።+ +11 ከአባቱ ሚስት ጋር የተኛ ሰው አባቱን ለኀፍረት ዳርጎታል።*+ ሁለቱም ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። +12 አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ቢተኛ ሁለቱም ይገደሉ። ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ድርጊት ፈጽመዋል። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።+ +13 “‘አንድ ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱም አስጸያፊ ድርጊት ፈጽመዋል።+ ስለዚህ ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። +14 “‘አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቷን ቢያገባ፣ ይህ ጸያፍ ድርጊት* ነው።+ ይህ ጸያፍ ምግባር በመካከላችሁ እንዳይቀጥል እሱንም ሆነ እነሱን በእሳት ያቃጥሏቸው።+ +15 “‘አንድ ሰው ከእንስሳ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም ይገደል፤ እንስሳውንም ግደሉት።+ +16 አንዲት ሴት የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ ማንኛውም እንስሳ ብትቀርብ+ ሴትየዋንም ሆነ እንስሳውን ግደል፤ ሁለቱም ይገደሉ። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው። +17 “‘አንድ ሰው ከእህቱ ማለትም ከአባቱ ሴት ልጅ ወይም ከእናቱ ሴት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽምና እርቃኗን ቢያይ፣ እሷም የእሱን እርቃን ብታይ ይህ አሳፋሪ ድርጊት ነው።+ በሕዝቦቻቸው ልጆች ፊት እንዲጠፉ ይደረጉ። እህቱን ለኀፍረት ዳርጓል።* ለፈጸመው ጥፋት ይጠየቅበታል። +18 “‘አንድ ሰው በወር አበባዋ ወቅት ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም እሱም ሆነ እሷ የሚፈሰውን ደሟን ገልጠዋል።+ ስለሆነም ሁለቱም ከሕዝቦቻቸው መካከል ተለይተው እንዲጠፉ ይደረጉ። +19 “‘ከእናትህ እህት ወይም ከአባትህ እህት ጋር የፆታ ግንኙነት አትፈጽም፤ ምክንያቱም ይህ የሥጋ ዘመድን ለኀፍረት መዳረግ ነው።+ ለፈጸሙት ጥፋት ይጠየቁበታል። +20 ከአጎቱ ሚስት ጋር የተኛ ሰው አጎቱን ለኀፍረት ዳርጓል።*+ ለፈጸሙት ኃጢአት ይጠየቁበታል። ልጅ ሳይኖራቸው ይሙቱ። +21 አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ቢወስድ ይህ አስጸያፊ ድርጊት ነው።+ ወንድሙን ለኀፍረት ዳርጓል።* ያለልጅም ይቅሩ። +22 “‘ትኖሩባት ዘንድ እናንተን የማስገባባት ምድር እንዳትተፋችሁ+ ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን ሁሉ ጠብቁ፤+ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+ +23 ከፊታችሁ አባርሬ የማስወጣቸው ብሔራት በሚመሩባቸው ደንቦች አትሂዱ፤+ ምክንያቱም እነሱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርገዋል፤ እኔም እጸየፋቸዋለሁ።+ +24 በመሆኑም እንዲህ አልኳችሁ፦ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እኔ ደግሞ ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር+ እንድትወርሷት እሰጣችኋለሁ። ከሕዝቦች የለየኋችሁ አምላካችሁ ይሖዋ እኔ ነኝ።”+ +25 ንጹሕ በሆነውና ርኩስ በሆነው እንስሳ እንዲሁም ርኩስ በሆነውና ንጹሕ በሆነው ወፍ መካከል ልዩነት አድርጉ፤+ እኔ ርኩስ ነው ብዬ በለየሁላችሁ እንስሳ ወይም ወፍ አሊያም መሬት ለመሬት በሚሄድ ማንኛውም ነገር ራሳችሁን* አታርክሱ።+ +26 እኔ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እናንተም ለእኔ ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል፤+ የእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ሕዝቦች ለየኋችሁ።+ +27 “‘መናፍስት ጠሪ ወይም ጠንቋይ የሆነ ወንድ ወይም የሆነች ሴት ካሉ ይገደሉ።+ ሕዝቡ በድንጋይ ወግሮ ይግደላቸው። ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።’” +3 “‘አንድ ሰው የሚያቀርበው መባ የኅብረት መሥዋዕት*+ ቢሆንና ከከብቶች መካከል ወስዶ የሚያቀርብ ከሆነ እንስሳው ተባዕትም ሆነ እንስት እንከን የሌለበትን በይሖዋ ፊት ማቅረብ ይኖርበታል። +2 እሱም መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ እንስሳውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ይታረዳል፤ ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይረጩታል። +3 እሱም ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤+ ይኸውም አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣+ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣ +4 ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳዋል።+ +5 የአሮን ወንዶች ልጆችም በመሠዊያው ላይ ይኸውም በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ ላይ ያጨሱታል፤+ ይህም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።+ +6 “‘ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው መባ ከመንጋው መካከል የተወሰደ ከሆነ እንስሳው ተባዕትም ሆነ እንስት እንከን የሌለበትን ያቀርባል።+ +7 የበግ ጠቦት መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ ይሖዋ ፊት ያቀርበዋል። +8 እሱም መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ እንስሳውም በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ለፊት ይታረዳል። የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይረጩታል። +9 ከኅብረት መሥዋዕቱ ላ���ም ስቡን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል።+ ከጀርባ አጥንቱ አጠገብ ያለውን ላት በሙሉ፣ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ ያነሳዋል፤ +10 ደግሞም ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያነሳዋል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል።+ +11 ካህኑም እንደ ምግብ* ይኸውም ለይሖዋ በእሳት እንደሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል።+ +12 “‘ፍየል መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ ይሖዋ ፊት ያቀርበዋል። +13 እጁንም በራሱ ላይ ይጭንበታል፤ በመገናኛ ድንኳኑም ፊት ይታረዳል፤ የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት። +14 ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ የሚያቀርበውም እነዚህን ነው፦ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣+ +15 ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል። +16 ካህኑም እንደ ምግብ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሳቸዋል። ስቡ ሁሉ የይሖዋ ነው።+ +17 “‘ስብም ሆነ ደም+ ፈጽሞ አትብሉ። ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተም ሆነ ለትውልዶቻችሁ ዘላቂ ደንብ ነው።’” +24 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “መብራቱ ያለማቋረጥ እንዲበራ ለማድረግ ለመብራቱ የሚሆን ተጨቅጭቆ የተጠለለ ንጹሕ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን እዘዛቸው።+ +3 ከምሽት አንስቶ እስከ ጠዋት ድረስ መብራቱ በይሖዋ ፊት ያለማቋረጥ እንዲበራ አሮን በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ካለው ከምሥክሩ መጋረጃ ውጭ ያስቀምጠው። በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላለማዊ ደንብ ነው። +4 ዘወትር በይሖዋ ፊት እንዲሆኑ መብራቶቹን ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው መቅረዝ+ ላይ በቦታ በቦታቸው ያስቀምጣቸው። +5 “አንተም የላመ ዱቄት ወስደህ የቀለበት ቅርጽ ያላቸው 12 ዳቦዎችን ጋግር። እያንዳንዱ ዳቦ ከሁለት አሥረኛ ኢፍ* ዱቄት የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል። +6 እነዚህንም በይሖዋ ፊት ባለው ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ+ ላይ ስድስት ስድስት አድርገህ በማነባበር በሁለት ረድፍ ታስቀምጣቸዋለህ።+ +7 ተነባብሮ በተቀመጠው በእያንዳንዱ ረድፍ ላይም ንጹሕ ነጭ ዕጣን አድርግ፤ ይህም ለምግቡ መታሰቢያ እንዲሆን+ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ይሆናል። +8 እሱም በየሰንበቱ ዘወትር በይሖዋ ፊት ይደርድረው።+ ይህ በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ያለ ዘላቂ ቃል ኪዳን ነው። +9 ይህም የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል፤+ ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች መካከል ለእሱ እጅግ ቅዱስ ነገር ስለሆነ ቅዱስ በሆነ ቦታ ይበሉታል፤+ ይህ ዘላቂ ሥርዓት ነው።” +10 በእስራኤላውያን መካከል በእናቱ እስራኤላዊ በአባቱ ግን ግብፃዊ የሆነ አንድ ሰው ነበር፤+ በሰፈሩም ውስጥ በእሱና በአንድ እስራኤላዊ መካከል ጠብ ተነሳ። +11 የእስራኤላዊቷም ልጅ የአምላክን ስም* መሳደብና መራገም ጀመረ።+ በመሆኑም ወደ ሙሴ አመጡት።+ የእናትየውም ስም ሸሎሚት ነበር፤ እሷም ከዳን ነገድ የሆነው የዲብራይ ልጅ ነበረች። +12 እነሱም የይሖዋ ውሳኔ ግልጽ እስኪሆንላቸው ድረስ በጥበቃ ሥር እንዲቆይ አደረጉት።+ +13 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +14 “የተራገመውን ሰው ከሰፈሩ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሰዎች ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ መላው ጉባኤም በድንጋይ ይውገረው።+ +15 ለእስራኤላውያንም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ማንኛውም ሰው አምላኩን ቢራገም ለሠራው ኃጢአት ይጠየቅበታል። +16 ስለሆነም የይሖዋን ስም የተሳደበው ሰው ይገደል።+ መላው ጉባኤም በድንጋይ ይውገረው። የባዕድ አገሩም ሰው የአምላክን ስም ከተሳደበ ልክ እንደ አገሩ ተወላጅ ይገደል። +17 “‘አንድ ሰው የሰው ሕይወት ካጠፋ* ይገደል።+ +18 የቤት እንስሳን የገደለ* ሰው፣ ሕይወት ስለ ሕይወት* ካሳ አድርጎ መክፈል ይኖርበታል። +19 አንድ ሰው በባልንጀራው ላይ ጉዳት ቢያደርስ ልክ እሱ ያደረሰው ዓይነት ጉዳት በራሱ ላይ እንዲደርስ ይደረግ።+ +20 ስብራት ስለ ስብራት፣ ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ ይሁን፤ በሰውየው ላይ ያደረሰው ዓይነት ጉዳት በእሱ ላይ እንዲደርስ ይደረግ።+ +21 እንስሳን መትቶ የገደለ ስለ እንስሳው ካሳ መክፈል ይኖርበታል፤+ ሰውን መትቶ የገደለ ግን መገደል አለበት።+ +22 “‘ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ፣ ለሁላችሁም የሚሠራው አንድ ዓይነት ድንጋጌ ነው፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” +23 ከዚያም ሙሴ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ እነሱም የተራገመውን ሰው ከሰፈሩ ውጭ አውጥተው በድንጋይ ወገሩት።+ በዚህ መንገድ እስራኤላውያን ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። +7 “‘የበደል መባ ሕግ ይህ ነው፦+ ይህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው። +2 ለበደል መባ የሚሆነውን እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንስሳ በሚያርዱበት ቦታ ያርዱታል፤ ደሙም+ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ መረጨት ይኖርበታል።+ +3 ስቡን በሙሉ ይኸውም ላቱን፣ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣+ +4 ሁለቱን ኩላሊቶች፣ በሽንጡ አካባቢ ካለው ስባቸው ጋር ያቅርብ። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳዋል።+ +5 ካህኑ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሳቸዋል።+ ይህ የበደል መባ ነው። +6 ካህን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል፤+ ቅዱስ በሆነ ስፍራም መበላት ይኖርበታል። ይህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው።+ +7 ስለ ኃጢአት መባው የወጣው ሕግ ለበደል መባውም ይሠራል፤ መባውም በመባው ለሚያስተሰርየው ካህን ይሆናል።+ +8 “‘ካህኑ ለአንድ ሰው የሚቃጠል መባ በሚያቀርብበት ጊዜ የሚቃጠል መባ ሆኖ ለካህኑ የቀረበው እንስሳ ቆዳ+ የእሱ ይሆናል። +9 “‘በመጋገሪያ ምድጃ የተጋገረ ወይም በድስት የተዘጋጀ አሊያም በምጣድ የተጋገረ የእህል መባ+ ሁሉ መባውን ለሚያቀርበው ካህን ይሆናል። መባው የእሱ ይሆናል።+ +10 በዘይት የተለወሰው+ ወይም ደረቅ የሆነው+ የእህል መባ ግን ለአሮን ወንዶች ልጆች በሙሉ ይከፋፈላል፤ እያንዳንዳቸውም እኩል ድርሻ ይኖራቸዋል። +11 “‘አንድ ሰው ለይሖዋ የሚያቀርበውን የኅብረት መሥዋዕት+ በተመለከተ ደግሞ ሕጉ ይህ ነው፦ +12 ሰውየው መሥዋዕቱን የሚያቀርበው አመስጋኝነቱን ለመግለጽ+ ከሆነ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋር በዘይት ተለውሶ የተጋገረ እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ፣ ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣና በዘይት በደንብ ከራሰና ከተለወሰ የላመ ዱቄት የተጋገረ የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ አብሮ ያቀርባል። +13 መባውንም እርሾ ገብቶባቸው ከተጋገሩ የቀለበት ቅርጽ ያላቸው ዳቦዎችና የምስጋና መሥዋዕት አድርጎ ከሚያቀርባቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ጋር አብሮ ያቀርባል። +14 ከዚያም ላይ ከእያንዳንዱ መባ አንድ አንድ በማንሳት ለይሖዋ የተቀደሰ ድርሻ አድርጎ ያቀርባል፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቶቹን ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል።+ +15 የምስጋና መሥዋዕት እንዲሆኑ ያቀረባቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ሥጋ፣ መሥዋዕቱን ባቀረበበት ቀን መበላት ይኖርበታል። ከዚያ ላይ ምንም ማስቀረትና ማሳደር የለበትም።+ +16 “‘መባ አድርጎ የሚያቀርበው መሥዋዕት ስእለት+ ወይም የፈቃደኝነት መባ+ ከሆነ መሥዋዕቱን ባቀረበበት ቀን መበላት አለበት፤ የተረፈውም በማግስቱ ሊበላ ይችላል። +17 ለመሥዋዕት ከቀረበው ሥጋ ተርፎ እስከ ሦስተኛው ቀን የቆየው ግን በእሳት መቃጠል አለበት።+ +18 ይሁን እንጂ የኅብረት መሥዋዕት እንዲሆን ያቀረበው ማንኛውም ሥጋ በሦስተኛው ቀን ቢበላ መሥዋዕቱን ያቀረበው ሰው ተቀባይነት አያገኝም። ያደረገውም ነገር አይታሰብለትም፤ ይህ አስጸያፊ ነገር ነው፤ ከዚያም ላይ የበላው ሰው* ለፈጸመው ስህተት ይጠየቅበታል።+ +19 ርኩስ የሆነን ማንኛውንም ነገር የነካ ሥጋ መበላት የለበትም። በእሳት መቃጠል አለበት። ንጹሕ የሆነ ማንኛውም ሰው ንጹሕ የሆነውን ሥጋ ሊበላ ይችላል። +20 “‘ሆኖም ማንኛውም ሰው* ርኩስ ሆኖ ሳለ ለይሖዋ ከቀረበው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ያ ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።*+ +21 አንድ ሰው* ርኩስ የሆነ ነገር ይኸውም የሰውን ርኩሰት+ ወይም ርኩስ የሆነን እንስሳ+ ወይም ርኩስ የሆነን ማንኛውንም አስጸያፊ ነገር+ ቢነካና ለይሖዋ ከቀረበው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ያ ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።’” +22 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +23 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ማንኛውንም ዓይነት የበሬ፣ የበግ ጠቦት ወይም የፍየል ስብ አትብሉ።+ +24 ሞቶ የተገኘ እንስሳ ስብና አውሬ የገደለው እንስሳ ስብ ለሌላ ለማንኛውም አገልግሎት ሊውል ይችላል፤ እናንተ ግን ፈጽሞ እንዳትበሉት።+ +25 ማንኛውም ሰው ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ከሚያቀርበው እንስሳ ላይ ስብ ቢበላ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። +26 “‘በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ የወፍም ይሁን የእንስሳ፣ ማንኛውንም ደም አትብሉ።+ +27 ደም የሚበላ ማንኛውም ሰው* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።’”+ +28 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +29 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የኅብረት መሥዋዕቱን ለይሖዋ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ከኅብረት መሥዋዕቱ መባ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ ያቀርባል።+ +30 እሱም ስቡን+ ከፍርምባው ጋር ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ እንዲሆን በራሱ እጆች ያመጣል፤ የሚወዘወዝ መባ+ አድርጎም በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዘውዘዋል። +31 ካህኑ ስቡን በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል፤+ ፍርምባው ግን የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል።+ +32 “‘ከኅብረት መሥዋዕቶቻችሁም ላይ ቀኝ እግሩን ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻ አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ።+ +33 የኅብረት መሥዋዕቱን ደምና ስቡን የሚያቀርበው የአሮን ልጅ የእንስሳውን ቀኝ እግር እንደ ድርሻው አድርጎ ይወስዳል።+ +34 እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የተቀደሰ ድርሻ ሆኖ የቀረበውን እግር እወስዳለሁ፤ ለእስራኤላውያንም ዘላቂ ሥርዓት እንዲሆን ለካህኑ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ እሰጣቸዋለሁ።+ +35 “‘ካህናት ሆነው ይሖዋን ለማገልገል በሚቀርቡበት ቀን፣ ለይሖዋ በእሳት ከቀረቡት መባዎች ላይ ለካህናቱ ይኸውም ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የሚመደብላቸው ድርሻ ይህ ነው።+ +36 ይሖዋ በቀባቸው+ ቀን ይህ ድርሻ ከእስራኤላውያን ተወስዶ እንዲሰጣቸው አዟል። ይህ ለትውልዶቻቸው ዘላለማዊ ደንብ ነው።’” +37 የሚቃጠል መባን፣+ የእህል መባን፣+ የኃጢአት መባን፣+ የበደል መባን፣+ ለክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርብ መሥዋዕትንና+ የኅብረት መሥዋዕትን+ በተመለከተ የተሰጠው ሕግ ይህ ነው፤ +38 ይህም እስራኤላውያን በሲና ምድረ በዳ መባዎቻቸውን ለይሖዋ እንዲያቀርቡ+ ባዘዛቸው ቀን ይሖዋ ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ባዘዘው+ መሠረት የሚፈጸም ነው። +12 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንዲት ሴት ብታረግዝና* ወንድ ል�� ብትወልድ በወር አበባዋ ወቅት እንደምትረክሰው ሁሉ ለሰባት ቀን ትረክሳለች።+ +3 ሕፃኑም በስምንተኛው ቀን ይገረዛል።+ +4 እሷም ከደም ራሷን ለማንጻት ለቀጣዮቹ 33 ቀናት ትቆያለች። የምትነጻባቸው ቀናት እስኪያበቁ ድረስ ምንም ዓይነት ቅዱስ ነገር መንካትም ሆነ ወደ ቅዱሱ ስፍራ መግባት የለባትም። +5 “‘ሴት ልጅ ከወለደች ደግሞ በወር አበባዋ ወቅት እንደምትረክሰው ሁሉ ለ14 ቀን ትረክሳለች። ከደም ራሷን ለማንጻትም ለቀጣዮቹ 66 ቀናት ትቆያለች። +6 ሴትየዋ ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ ወልዳ የመንጻቷ ጊዜ ሲያበቃ ለሚቃጠል መባ እንዲሆን አንድ ዓመት ገደማ የሆነው የበግ ጠቦት፣+ ለኃጢአት መባ እንዲሆን ደግሞ አንድ የርግብ ጫጩት ወይም አንድ ዋኖስ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወደ ካህኑ ታመጣለች። +7 እሱም መባዎቹን በይሖዋ ፊት በማቅረብ ያስተሰርይላታል፤ እሷም ከሚፈሳት ደም ትነጻለች። ወንድ ልጅም ሆነ ሴት ልጅ ለወለደች ሴት የሚሠራው ሕግ ይህ ነው። +8 ሆኖም ሴትየዋ በግ ለማቅረብ አቅሟ የማይፈቅድላት ከሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ታምጣ፤+ አንዱ ለሚቃጠል መባ ሌላው ደግሞ ለኃጢአት መባ ይሆናል። ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እሷም ንጹሕ ትሆናለች።’” +1 ይሖዋም ሙሴን ጠርቶ ከመገናኛ ድንኳኑ+ እንዲህ ሲል አናገረው፦ +2 “እስራኤላውያንን* አናግራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ከእናንተ መካከል ማንኛችሁም ከቤት እንስሳት ለይሖዋ መባ ማቅረብ ከፈለጋችሁ መባችሁን ከከብቶች ወይም ከመንጎች መካከል ማቅረብ አለባችሁ።+ +3 “‘የሰውየው መባ ከከብቶች መካከል ተወስዶ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ከሆነ እንከን የሌለበትን ተባዕት እንስሳ ማቅረብ ይኖርበታል።+ መባውን በራሱ ፈቃድ ተነሳስቶ+ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት ማቅረብ ይኖርበታል። +4 ለሚቃጠል መባ በሚቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ መባውም ለሰውየው ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። +5 “‘ከዚያም ወይፈኑ በይሖዋ ፊት ይታረድ፤ ካህናት+ የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን ያቅርቡት፤ እንዲሁም ደሙን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው መሠዊያ ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።+ +6 የሚቃጠለውም መባ መገፈፍና መቆራረጥ ይኖርበታል።+ +7 ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም በመሠዊያው ላይ እሳት ያንድዱ፤+ በእሳቱም ላይ እንጨት ይረብርቡበት። +8 እነሱም ተቆራርጦ የተዘጋጀውን መባ+ ከጭንቅላቱና ከሞራው* ጋር በመሠዊያው ላይ ባለው እሳት ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ ይደርድሩት። +9 ሆድ ዕቃውና እግሮቹም በውኃ ይታጠቡ፤ ካህኑም የሚቃጠል መባ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ ሙሉውን በመሠዊያው ላይ ያጭሰው።+ +10 “‘ሰውየው የሚቃጠል መባ እንዲሆን የሚያቀርበው መባ ከመንጋው+ ማለትም ከበግ ጠቦቶቹ ወይም ከፍየሎቹ መካከል የተወሰደ ከሆነ እንከን የሌለበትን ተባዕት ያቅርብ።+ +11 በስተ ሰሜን በኩል ባለው የመሠዊያው ጎን በይሖዋ ፊት ይታረድ፤ ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።+ +12 እሱም ጭንቅላቱንና ሞራውን* ጨምሮ እንስሳውን በየብልቱ ይቆራርጠዋል፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ ባለው እሳት ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ ይደረድራቸዋል። +13 ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ ያጥባቸዋል፤ ካህኑም ሙሉውን ያቀርበዋል፤ እንዲሁም በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ይህም የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። +14 “‘ሆኖም ሰውየው አእዋፋትን ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ መባውን ከዋኖሶች ወይም ከርግብ ጫጩቶች መካከል ያቀርባል።+ +15 ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል፤ እንዲሁም አንገቱ ላይ ቦጭቆ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ደሙ ግን በመሠዊያው ጎን ይንጠፍጠፍ። +16 ቋቱንና ላባዎቹንም ከለየ በኋላ ከመሠዊያው አጠገብ በስተ ምሥራቅ በኩል ወዳለው አመድ* ወደሚደፋበት ቦታ ይወርውራቸው።+ +17 ሙሉ በሙሉ ለሁለት ሳይለያየው ክንፎቹን ይዞ ይሰነጥቀዋል። ከዚያም ካህኑ በመሠዊያው ላይ ይኸውም በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ይህም የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። +8 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “አሮንን፣ ከእሱም ጋር ወንዶች ልጆቹን+ እንዲሁም ልብሶቹን፣+ የቅብዓት ዘይቱን፣+ ለኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ፣ ሁለቱን አውራ በጎችና ቂጣ ያለበትን ቅርጫት+ ውሰድ፤ +3 መላው ማኅበረሰብም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ እንዲሰበሰብ አድርግ።” +4 ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበረሰቡም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ተሰበሰበ። +5 ሙሴም ለማኅበረሰቡ “ይሖዋ እንድናደርግ ያዘዘን ነገር ይህ ነው” አላቸው። +6 በመሆኑም ሙሴ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን አቀረባቸው፤ በውኃም አጠባቸው።+ +7 ከዚያም ለአሮን ረጅሙን ቀሚስ+ አጠለቀለት፤ መቀነቱንም+ አሰረለት፤ እጅጌ የሌለውን ቀሚስም+ አለበሰው፤ ኤፉዱንም+ አደረገለት፤ ኤፉዱንም ተሸምኖ በተሠራው የኤፉዱ መቀነት+ ጠበቅ አድርጎ አሰረው። +8 በመቀጠልም የደረት ኪሱን+ አደረገለት፤ በደረት ኪሱም ውስጥ ኡሪሙንና ቱሚሙን+ አስቀመጠ። +9 ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ጥምጥሙን+ በራሱ ላይ አደረገለት፤ በጥምጥሙም ከፊት በኩል፣ የሚያብረቀርቀውን ጠፍጣፋ ወርቅ ይኸውም ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየውን ቅዱስ ምልክት*+ አደረገለት። +10 ሙሴም የቅብዓት ዘይቱን ወስዶ የማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች በሙሉ ቀባቸው፤+ እንዲሁም ቀደሳቸው። +11 ከዚያም ይቀድሳቸው ዘንድ ከዘይቱ የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ በመርጨት መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ እንዲሁም የውኃ ገንዳውንና ማስቀመጫውን ቀባቸው። +12 በመጨረሻም ከቅብዓት ዘይቱ የተወሰነውን ወስዶ በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰው፤ የተቀደሰም ይሆን ዘንድ ቀባው።+ +13 ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት የአሮንን ወንዶች ልጆች አቀረባቸው፤ ረጅሞቹን ቀሚሶችም አለበሳቸው፤+ መቀነቶቹንም አሰረላቸው፤ የራስ ቆቡንም ደፋላቸው። +14 ከዚያም ለኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን ለኃጢአት መባ በሚሆነው በሬ ራስ ላይ ጫኑ።+ +15 ሙሴም በሬውን አረደው፤ ደሙንም+ በጣቱ ወስዶ በሁሉም የመሠዊያው ጎኖች ላይ ያሉትን ቀንዶች ቀባ፤ መሠዊያውንም ከኃጢአት አነጻው፤ የቀረውንም ደም መሠዊያው ማስተሰረያ ይቀርብበት ዘንድ መሠዊያውን ለመቀደስ በሥሩ አፈሰሰው። +16 ከዚያም ሙሴ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣ በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ።+ +17 ሙሴም ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ከበሬው የቀረውን፣ ቆዳውን፣ ሥጋውንና ፈርሱን ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለው።+ +18 እሱም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ጫኑ።+ +19 ከዚያም ሙሴ አውራውን በግ አረደው፤ ደሙንም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። +20 አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራረጠው፤ ቀጥሎም ጭንቅላቱን፣ ብልቶቹንና ሞራውን* አጨሰው። +21 ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠባቸው፤ ሙሴም አውራው በ��� በሙሉ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። ይህም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ ነበር። ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነበር። +22 ከዚያም ሁለተኛውን አውራ በግ ይኸውም ለክህነት ሹመት ሥርዓት+ የሚቀርበውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ።+ +23 ከዚያም ሙሴ አውራውን በግ አረደው፤ ከደሙም የተወሰነውን ወስዶ የአሮንን የቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ቀባ። +24 በመቀጠልም ሙሴ የአሮንን ወንዶች ልጆች ወደ ፊት አቀረባቸው፤ ከደሙም የተወሰነውን ወስዶ የቀኝ ጆሯቸውን ጫፍ፣ የቀኝ እጃቸውን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ቀባ፤ የቀረውን ደም ግን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው።+ +25 ከዚያም ስቡን፣ ላቱን፣ አንጀቱን የሚሸፍነውን ስብ በሙሉ፣ የጉበቱን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ እንዲሁም ቀኝ እግሩን ወሰደ።+ +26 በይሖዋ ፊት ካለው ቂጣዎች ከተቀመጡበት ቅርጫት ውስጥም እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦ፣+ ዘይት የተቀባ የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦና+ አንድ ስስ ቂጣ ወሰደ። ከዚያም በስቦቹና በቀኝ እግሩ ላይ አደረጋቸው። +27 በመቀጠልም ሁሉንም በአሮን መዳፍና በወንዶች ልጆቹ መዳፍ ላይ አስቀመጣቸው፤ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባም ወዲያና ወዲህ ወዘወዛቸው። +28 ከዚያም ሙሴ ከእጃቸው ላይ ወስዶ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይ እንዲጨሱ አደረገ። እነዚህም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ የሚሰጡ የክህነት ሹመት መሥዋዕት ናቸው። ይህም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነበር። +29 ሙሴም ፍርምባውን ወስዶ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዘወዘው።+ ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረትም ለክህነት ሹመት ሥርዓት ከሚቀርበው አውራ በግ ላይ ይህ የእሱ ድርሻ ሆነ።+ +30 ሙሴም ከቅብዓት ዘይቱና+ በመሠዊያው ላይ ካለው ደም የተወሰነውን ወስዶ በአሮንና በልብሶቹ እንዲሁም ከእሱ ጋር በነበሩት ወንዶች ልጆቹና በወንዶች ልጆቹ ልብሶች ላይ ረጨው። በዚህ መንገድ አሮንንና ልብሶቹን እንዲሁም ወንዶች ልጆቹንና+ ልብሶቻቸውን ቀደሰ።+ +31 ከዚያም ሙሴ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ “ሥጋውን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ቀቅሉት፤+ ‘አሮንና ወንዶች ልጆቹ ይበሉታል’ ተብዬ በታዘዝኩት መሠረት ሥጋውንም ሆነ በክህነት ሹመት ሥርዓቱ ቅርጫት ውስጥ ያለውን ቂጣ እዚያ ትበሉታላችሁ።+ +32 ከሥጋውም ሆነ ከቂጣው የተረፈውን በእሳት ታቃጥሉታላችሁ።+ +33 ለክህነት ሹመታችሁ ሥርዓት የተመደቡት ቀናት እስከሚያበቁ ድረስ ይኸውም ለሰባት ቀን ያህል በመገናኛ ድንኳኑ ደጃፍ ቆዩ፤ ምክንያቱም እናንተን ካህን አድርጎ መሾም* ሰባት ቀን ይፈጃል።+ +34 ለእናንተ ለማስተሰረይ+ ዛሬ ያደረግነውን ነገር እንድናደርግ ይሖዋ አዟል። +35 በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ቀንና ሌሊት ለሰባት ቀን ያህል ትቆያላችሁ፤+ እንዳትሞቱም ለይሖዋ የገባችሁትን ግዴታ ፈጽሙ፤+ ምክንያቱም እንዲህ እንዳደርግ ታዝዣለሁ።” +36 አሮንና ወንዶች ልጆቹም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ያዘዛቸውን ነገሮች በሙሉ አደረጉ። +11 ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በሏቸው፦ ‘በምድር ላይ ካሉ ሕያዋን ፍጥረታት* መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦+ +3 ሰኮናው የተሰነጠቀውንና ስንጥቁም ሙሉ በሙሉ የተከፈለውን እንዲሁም የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ። +4 “‘ሆኖም የሚያመሰኩትን ወይም ሰኮናቸው የተሰነጠቀውን እነዚህን እንስሳ�� መብላት የለባችሁም፦ ግመል የሚያመሰኳ ቢሆንም ሰኮናው የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነው።+ +5 ሽኮኮም+ መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም የሚያመሰኳ ቢሆንም ሰኮናው የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነው። +6 ጥንቸልም ብትሆን መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም የምታመሰኳ ብትሆንም ሰኮናዋ የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነች። +7 አሳማም+ መብላት የለባችሁም፤ ሰኮናው የተሰነጠቀና ስንጥቁ ሙሉ በሙሉ የተከፈለ ቢሆንም እንኳ አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። +8 የእነዚህን እንስሳት ሥጋ አትብሉ ወይም በድናቸውን አትንኩ። እነዚህ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።+ +9 “‘በውኃዎች ውስጥ ካሉት መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦ በባሕርም ሆነ በወንዞች፣ በውኃዎች ውስጥ ካሉት መካከል ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ሁሉ መብላት ትችላላችሁ።+ +10 በውኃዎች ውስጥ ካሉ የሚርመሰመሱ ፍጥረታትና ሌሎች ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት* ሁሉ መካከል በባሕርና በወንዞች ውስጥ የሚገኙ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ ግን ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። +11 አዎ፣ እነዚህን ልትጸየፏቸው ይገባል፤ ሥጋቸውን ፈጽሞ አትብሉ፤+ በድናቸውንም ተጸየፉት። +12 በውኃዎች ውስጥ የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። +13 “‘ልትጸየፏቸው የሚገቡ በራሪ ፍጥረታት እነዚህ ናቸው፤ አስጸያፊ በመሆናቸው መበላት የለባቸውም፦ ንስር፣+ ዓሣ በል ጭላት፣ ጥቁር ጥምብ አንሳ፣+ +14 ቀይ ጭልፊት፣ ማንኛውም ዓይነት ጥቁር ጭልፊት፣ +15 ማንኛውም ዓይነት ቁራ፣ +16 ሰጎን፣ ጉጉት፣ ዓሣ አዳኝ፣ ማንኛውም ዓይነት ሲላ፣ +17 ትንሿ ጉጉት፣ ለማሚት፣ ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉት፣ +18 ዝይ፣ ሻላ፣ ጥምብ አንሳ፣ +19 ራዛ፣ ማንኛውም ዓይነት ሽመላ፣ ጅንጅላቴና የሌሊት ወፍ። +20 በአራቱም እግሩ የሚሄድ ክንፍ ያለው የሚርመሰመስ ፍጡር* ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ነው። +21 “‘በአራቱም እግራቸው ከሚሄዱ ክንፍ ካላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት መካከል መብላት የምትችሉት ከእግሮቻቸው በላይ በመሬት ላይ ለመፈናጠር የሚያገለግል የሚተጣጠፍ ቅልጥም ያላቸውን ብቻ ነው። +22 ከእነዚህም መካከል የሚከተሉትን መብላት ትችላላችሁ፦ የተለያየ ዓይነት የሚፈልስ አንበጣ፣ ሌሎች የሚበሉ አንበጦች፣+ እንጭራሪቶችና ፌንጣዎች። +23 አራት እግር ኖሯቸው ክንፍ ያላቸው ሌሎች የሚርመሰመሱ ፍጥረታት ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። +24 በእነዚህ ራሳችሁን ታረክሳላችሁ። በድናቸውን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ +25 ከእነዚህ መካከል የማናቸውንም በድን የሚያነሳ ሁሉ ልብሶቹን ይጠብ፤+ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +26 “‘ሰኮናው የተሰነጠቀ፣ ስንጥቁ ግን ሙሉ በሙሉ ያልተከፈለ እንዲሁም የማያመሰኳ ማንኛውም እንስሳ ለእናንተ ርኩስ ነው። የሚነካቸውም ሁሉ ርኩስ ይሆናል።+ +27 በአራቱም እግራቸው ከሚሄዱ ፍጥረታት መካከል በመዳፋቸው የሚሄዱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። በድናቸውን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። +28 በድናቸውን የሚያነሳ ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤+ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ እነዚህ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። +29 “‘ለእናንተ ርኩስ የሆኑት በምድር ላይ የሚርመሰመሱ ፍጥረታት እነዚህ ናቸው፦ ፍልፈል፣ አይጥ፣+ ማንኛውም ዓይነት እንሽላሊት፣ +30 ጌኮ፣ ገበሎ፣ የውኃ እንሽላሊት፣ የአሸዋ እንሽላሊትና እስስት። +31 እነዚህ የሚርመሰመሱ ፍጥረታት ለእናንተ ርኩስ ናቸው።+ በድናቸውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ +32 “‘በሚሞቱበት ጊዜ የወደቁበት ማንኛውም ነገር ይኸውም የእንጨት ዕቃም ሆነ ልብስ ወይም ቆዳ አሊያም ደግሞ በርኖስ ርኩስ ይሆናል። አገልግሎት ላይ የሚውል ማንኛውም ዕቃ ውኃ ውስጥ ይነከር፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም ይነጻል። +33 በሸክላ ዕቃ ውስጥ ከወደቁ ዕቃውን ሰባብሩት፤ በውስጡ ያለውም ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል።+ +34 እንዲህ ባለ ዕቃ ውስጥ የነበረ ውኃ የነካው ማንኛውም ዓይነት ምግብ ርኩስ ይሆናል፤ በእንዲህ ዓይነቱ ዕቃ ውስጥ የነበረ የሚጠጣ ማንኛውም ዓይነት መጠጥም ርኩስ ይሆናል። +35 በድናቸው የወደቀበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል። መጋገሪያ ምድጃም ይሁን አነስተኛ ምድጃ ይሰበር። እነዚህ ነገሮች ርኩስ ናቸው፤ ለእናንተም ርኩስ ይሆናሉ። +36 ምንጭና የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ብቻ ንጹሕ ይሆናሉ፤ ይሁንና በድኑን የነካ ማንኛውም ሰው ርኩስ ይሆናል። +37 በድናቸው በሚዘራ ዘር ላይ ቢወድቅ ዘሩ ንጹሕ ነው። +38 ይሁንና በዘሩ ላይ ውኃ ተደርጎበት ሳለ የበድናቸው አንዱ ክፍል ዘሩ ላይ ቢወድቅ ዘሩ ለእናንተ ርኩስ ይሆናል። +39 “‘እንድትበሉ ከተፈቀደላችሁ እንስሳ አንዱ ቢሞት የእንስሳውን በድን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ +40 ከበድኑ የበላ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ በድኑን ያነሳ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +41 በምድር ላይ የሚርመሰመስ ማንኛውም ፍጥረት አስጸያፊ ነው።+ መበላት የለበትም። +42 በሆዱ የሚሳብን ማንኛውም ፍጥረት፣ በአራቱም እግሩ የሚሄድን ማንኛውም ፍጥረት ወይም ብዙ እግሮች ያሉትን በምድር ላይ የሚርመሰመስ ማንኛውም ፍጥረት መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም አስጸያፊ ናቸው።+ +43 በምድር ላይ በሚርመሰመስ በማንኛውም ፍጥረት ራሳችሁን* አስጸያፊ አታድርጉ፤ በእነሱም ራሳችሁን በመበከል አትርከሱ።+ +44 እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝና፤+ እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ+ እናንተም ራሳችሁን ልትቀድሱና ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል።+ በምድር ላይ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም የሚርመሰመስ ፍጥረት ራሳችሁን* አታርክሱ። +45 አምላካችሁ መሆኔን ለማስመሥከር ከግብፅ ምድር መርቼ ያወጣኋችሁ እኔ ይሖዋ ነኝና፤+ እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ+ እናንተም ቅዱሳን መሆን አለባችሁ።+ +46 “‘እንስሳትን፣ የሚበርሩ ፍጥረታትን፣ በውኃዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስን ማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር* እንዲሁም በምድር ላይ የሚርመሰመስን ፍጡር* ሁሉ በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፤ +47 ርኩስ የሆነውንና ንጹሕ የሆነውን እንዲሁም ለመብል የሚሆነውንና ለመብል የማይሆነውን ሕያው ፍጡር ለመለየት ሕጉ ይህ ነው።’”+ +2 “‘አንድ ሰው* ለይሖዋ የእህል መባ+ የሚያቀርብ ከሆነ መባው የላመ ዱቄት መሆን አለበት፤ በላዩም ላይ ዘይት ያፍስበት፤ ነጭ ዕጣንም ያስቀምጥበት።+ +2 ከዚያም ካህናት ወደሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች ያመጣዋል፤ ካህኑም ከላዩ ላይ አንድ እፍኝ የላመ ዱቄትና ዘይት፣ ነጭ ዕጣኑንም በሙሉ ይወስዳል፤ ይህንም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ+ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። +3 ከእህል መባው የተረፈው ማንኛውም ነገር የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤+ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው።+ +4 “‘በመጋገሪያ ምድጃ የተጋገረ የእህል መባ የምታቀርብ ከሆነ ከላመ ዱቄት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ ወይም ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ* መሆን ይኖርበታል።+ +5 “‘መባህ በምጣድ የተጋገረ የእህል መባ+ ከሆነ በዘይት ከተለወሰ እርሾ ያልገባበት የላመ ዱቄት የተጋገረ መሆን ይኖር���ታል። +6 መቆራረስ አለበት፤ ዘይትም አፍስበት።+ ይህ የእህል መባ ነው። +7 “‘መባህ በድስት የተዘጋጀ የእህል መባ ከሆነ ከላመ ዱቄትና ከዘይት የተሠራ መሆን ይኖርበታል። +8 ከእነዚህ ነገሮች የተዘጋጀውን የእህል መባ ወደ ይሖዋ ማምጣት ይኖርብሃል፤ ወደ መሠዊያው ለሚያቀርበውም ካህን ይሰጠው። +9 ካህኑም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ+ እንዲሆን ከእህል መባው ላይ የተወሰነውን በማንሳት ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል።+ +10 ከእህል መባው የተረፈው የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው።+ +11 “‘እርሾ ወይም ማር ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ ማጨስ ስለሌለባችሁ ለይሖዋ ከምታቀርቡት የእህል መባ ውስጥ እርሾ የገባበት ምንም ነገር አይኑር።+ +12 “‘እነዚህንም የፍሬ በኩራት መባ+ አድርጋችሁ ለይሖዋ ልታቀርቧቸው ትችላላችሁ፤ ሆኖም ደስ እንደሚያሰኝ* መዓዛ ሆነው ወደ መሠዊያው መምጣት የለባቸውም። +13 “‘የምታቀርበው የእህል መባ በሙሉ በጨው መቀመም አለበት፤ የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨውም ከእህል መባህ ላይ አይጥፋ። ከማንኛውም መባህ ጋር ጨው አብረህ ታቀርባለህ።+ +14 “‘መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ የእህል መባ አድርገህ ለይሖዋ የምታቀርብ ከሆነ የደረሰውን ሆኖም ገና እሸት የሆነውን በእሳት የተጠበሰና የተከካ እህል መጀመሪያ ላይ እንደደረሰው ፍሬህ የእህል መባ አድርገህ አቅርብ።+ +15 በላዩም ላይ ዘይት ትጨምርበታለህ፤ ነጭ ዕጣንም ታስቀምጥበታለህ። ይህ የእህል መባ ነው። +16 ካህኑም ከተከካው እህልና ከዘይቱ የተወሰነውን፣ ነጭ ዕጣኑንም በሙሉ ወስዶ አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ+ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ ያጨሰዋል። +26 “‘ትሰግዱላቸው ዘንድ+ ለራሳችሁ ከንቱ አማልክትን አትሥሩ፤+ እንዲሁም ለራሳችሁ የተቀረጸ ምስል+ ወይም የማምለኪያ ዓምድ አታቁሙ፤ በምድራችሁም ከድንጋይ የተቀረጸ ምስል አታኑሩ፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +2 ሰንበቶቼን ጠብቁ፤ ለመቅደሴም አክብሮት* ይኑራችሁ። እኔ ይሖዋ ነኝ። +3 “‘ባወጣኋቸው ደንቦች መሠረት ብትሄዱና ትእዛዛቴን ብትጠብቁ እንዲሁም ብትፈጽሙ+ +4 ዝናብን በወቅቱ አዘንብላችኋለሁ፤+ ምድሪቱም ምርቷን ትሰጣለች፤+ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጣሉ። +5 ገና እህላችሁን ወቅታችሁ ሳትጨርሱ ወይናችሁን የምትሰበስቡበት ጊዜ ይደርሳል፤ ገና ወይኑን ሰብስባችሁ ሳትጨርሱ ደግሞ ዘር የምትዘሩበት ጊዜ ይመጣል፤ ምግባችሁን እስክትጠግቡ ድረስ ትበላላችሁ፤ በምድራችሁም ያለስጋት ትቀመጣላችሁ።+ +6 በምድሪቱ ሰላም አሰፍናለሁ፤+ እናንተም ማንም ሳያስፈራችሁ ትተኛላችሁ፤+ እኔም አደገኛ አውሬዎች በምድሪቱ እንዳይኖሩ አደርጋለሁ፤ በምድራችሁም የጦርነት ሰይፍ አያልፍም። +7 እናንተም በእርግጥ ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ እነሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። +"8 አምስታችሁ 100 ሰዎችን ታሳድዳላችሁ፤ መቶዎቻችሁ ደግሞ 10,000 ሰዎችን ታሳድዳላችሁ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ " +9 “‘እኔም ሞገስ አሳያችኋለሁ፤* ፍሬያማ እንድትሆኑና እንድትበዙ አደርጋችኋለሁ፤+ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳኔን እጠብቃለሁ።+ +10 እናንተም ያለፈውን ዓመት እህል ገና በልታችሁ ሳትጨርሱ ለዘንድሮው እህል ቦታ ለማግኘት ያለፈውን ዓመት እህል ታስለቅቃላችሁ። +11 የማደሪያ ድንኳኔን በመካከላችሁ እተክላለሁ፤+ እኔም አልተዋችሁም።* +12 በመካከላችሁ እሄዳለሁ፤ አምላካችሁም እሆናለሁ፤+ ���ናንተ ደግሞ ሕዝቦቼ ትሆናላችሁ።+ +13 የግብፃውያን ባሪያዎች ሆናችሁ እንዳትቀሩ ከዚያ ምድር ያወጣኋችሁና ቀንበራችሁን ሰብሬ ራሳችሁን ቀና አድርጋችሁ* እንድትሄዱ ያደረግኳችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +14 “‘ይሁን እንጂ የማትሰሙኝ ወይም እነዚህን ትእዛዛት በሙሉ የማትፈጽሙ ከሆነ+ +15 እንዲሁም ደንቦቼን ችላ የምትሉና+ ትእዛዛቴን በሙሉ ላለመፈጸም ድንጋጌዎቼን የምትጸየፉ፣* ቃል ኪዳኔንም የምታፈርሱ ከሆነ+ +16 እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፦ ዓይናችሁ እንዲጠፋና ሕይወታችሁ* እንዲመነምን የሚያደርግ የሳንባ ነቀርሳና ኃይለኛ ትኩሳት በእናንተ ላይ በማምጣት በጭንቀት እቀጣችኋለሁ። ዘራችሁን የምትዘሩት እንዲሁ በከንቱ ይሆናል፤ ምክንያቱም የሚበሉት ጠላቶቻችሁ ናቸው።+ +17 እኔም በእርግጥ ፊቴን አጠቁርባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ድል ያደርጓችኋል፤+ የሚጠሏችሁም ሰዎች ይረግጧችኋል፤+ እንዲሁም ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።+ +18 “‘እነዚህ ሁሉ ነገሮች ደርሰውባችሁም የማትሰሙኝ ከሆነ ለሠራችሁት ኃጢአት ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ። +19 ኃይለኛ የሆነውን ትዕቢታችሁን እሰብረዋለሁ፤ ሰማያችሁን እንደ ብረት፣+ ምድራችሁን ደግሞ እንደ መዳብ አደርገዋለሁ። +20 ምድራችሁ ምርቷን ስለማትሰጥና የምድርም ዛፍ ፍሬ ስለማያፈራ ኃይላችሁን እንዲሁ በከንቱ ታባክናላችሁ።+ +21 “‘ሆኖም እኔን መቃወማችሁን ከቀጠላችሁና እኔን ለመስማት ፈቃደኞች ሳትሆኑ ከቀራችሁ እንደ ኃጢአታችሁ መጠን ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ። +22 የዱር አራዊትን እሰድባችኋለሁ፤+ እነሱም ልጆቻችሁን ይነጥቋችኋል፤+ የቤት እንስሶቻችሁንም ይበሉባችኋል፤ ቁጥራችሁም እንዲመናመን ያደርጋሉ፤ መንገዶቻችሁም ጭር ይላሉ።+ +23 “‘እነዚህ ሁሉ ነገሮች ደርሰውባችሁም እርማቴን ባትቀበሉና+ እኔን መቃወማችሁን ብትገፉበት +24 እኔም እናንተን በመቃወም እመጣባችኋለሁ፤ ለኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ። +25 ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን ስላፈረሳችሁ+ በላያችሁ ላይ የበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ። በከተሞቻችሁ ውስጥ ከተሰበሰባችሁ በመካከላችሁ በሽታ እልክባችኋለሁ፤+ እናንተም ለጠላት እጅ ትሰጣላችሁ።+ +26 የዳቦ እጥረት እንዲከሰትባችሁ+ በማደርግበት ጊዜ* አሥር ሴቶች በአንድ ምድጃ ብቻ ዳቦ ይጋግሩላችኋል፤ ዳቦውንም እየመዘኑ ያከፋፍሏችኋል፤+ እናንተም ትበላላችሁ፤ ነገር ግን አትጠግቡም።+ +27 “‘ይሁን እንጂ በዚህም እኔን ለመስማት ፈቃደኛ ካልሆናችሁና እኔን መቃወማችሁን ከገፋችሁበት +28 በኃይል እቃወማችኋለሁ፤+ እኔ ራሴም ለኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ። +29 በመሆኑም የወንድ ልጆቻችሁን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴት ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ።+ +30 በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉትን ቅዱስ ስፍራዎቻችሁን+ አጠፋለሁ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁንም አስወግዳለሁ፤ በድናችሁንም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ* በድን ላይ እከምረዋለሁ፤+ እኔም ተጸይፌያችሁ ከእናንተ ዞር እላለሁ።*+ +31 ከተሞቻችሁን ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ፤+ መቅደሶቻችሁንም ባዶ አደርጋቸዋለሁ፤ የመሥዋዕቶቻችሁን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ አላሸትም። +32 እኔ ራሴ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤+ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁም በመደነቅ ይመለከቷታል።+ +33 እናንተንም በብሔራት መካከል እበትናችኋለሁ፤+ ሰይፍም መዝዤ አሳድዳችኋለሁ፤+ ምድራችሁ ባድማ ትሆናለች፤+ ከተሞቻችሁም ይፈራርሳሉ። +34 “‘በጠላቶቻችሁ ምድር ሆናችሁ ምድሪቱ ባድማ ሆና በምትቆይባቸው ጊዜያት ሁሉ የሰንበት ዕዳዋን ትከፍላለች። በዚያን ጊዜ ምድሪቱ የሰንበት ዕዳዋን መክፈል ስላለባት ታርፋለች።*+ +35 ምድሪቱ ትኖሩባት በ���በረው ጊዜ በሰንበታችሁ ወቅት ስላላረፈች ባድማ ሆና በምትቆይባቸው ጊዜያት ሁሉ ታርፋለች። +36 “‘ከእናንተ መካከል በሕይወት የሚተርፉትም+ በጠላቶቻቸው ምድር ልባቸው ተስፋ እንዲቆርጥ አደርጋለሁ፤ የቅጠል ኮሽታ እንኳ ያስበረግጋቸዋል፤ ከሰይፍ እንደሚሸሽ ሰው ይፈረጥጣሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።+ +37 ከሰይፍ እንደሚሸሹ ሰዎች እነሱም ማንም ሳያሳድዳቸው እርስ በርሳቸው እየተደነቃቀፉ ይወድቃሉ። እናንተም ጠላቶቻችሁን መቋቋም ይሳናችኋል።+ +38 በብሔራት መካከል ትጠፋላችሁ፤+ የጠላቶቻችሁም ምድር ትበላችኋለች። +39 ከእናንተ መካከል የሚተርፉትም በሠሩት ስህተት የተነሳ በጠላቶቻችሁ ምድር ይበሰብሳሉ።+ አዎ፣ በአባቶቻቸው ስህተት የተነሳ ይበሰብሳሉ።+ +40 ከዚያም የገዛ ራሳቸውን ስህተት እንዲሁም አባቶቻቸው የፈጸሙትን ስህተትና ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ይናዘዛሉ፤+ እንዲሁም እኔን በመቃወም ታማኝ ሳይሆኑ መቅረታቸውን አምነው ይቀበላሉ።+ +41 እኔም እነሱን ወደ ጠላቶቻቸው ምድር በማምጣት+ እቃወማቸዋለሁ።+ “‘ምናልባትም ያልተገረዘው* ልባቸው በዚያ ጊዜ ትሑት ይሆናል፤+ የስህተታቸውንም ዋጋ ይከፍላሉ። +42 እኔም ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳንና ከይስሐቅ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስባለሁ፤+ እንዲሁም ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤+ ምድሪቱንም አስባለሁ። +43 እነሱም ምድሪቱን ትተዋት በሄዱበት ጊዜ ምድሪቱ የሰንበት ዕዳዋን ትከፍላለች፤+ ያለእነሱም ባድማ ሆና ትቆያለች፤ እነሱም ድንጋጌዎቼን ችላ ስላሉና ደንቦቼን ስለተጸየፉ*+ የስህተታቸውን ዋጋ ይከፍላሉ። +44 ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን በጠላቶቻቸው ምድር በሚቆዩበት ጊዜ ሁሉ እርግፍ አድርጌ አልተዋቸውም፤+ ፈጽሜ እስካጠፋቸውም ድረስ አልጥላቸውም፤ እንዲህ ባደርግ ከእነሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ማፍረስ ይሆንብኛል፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካቸው ይሖዋ ነኝ። +45 አምላካቸው መሆኔን አስመሠክር ዘንድ ብሔራት በዓይናቸው እያዩ ከግብፅ ምድር ካወጣኋቸው አባቶቻቸው+ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ስለ እነሱ ስል አስባለሁ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።’” +46 ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ በሙሴ አማካኝነት በራሱና በእስራኤላውያን መካከል ያስቀመጣቸው ሥርዓቶች፣ ድንጋጌዎችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።+ +4 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ሰው* ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ+ ኃጢአት ቢሠራ እንዲህ መደረግ ይኖርበታል፦ +3 “‘የተቀባው ካህን+ ኃጢአት+ ቢሠራና ሕዝቡ በደለኛ እንዲሆን ቢያደርግ ለፈጸመው ኃጢአት እንከን የሌለበትን ወይፈን የኃጢአት መባ አድርጎ ለይሖዋ ያቅርብ።+ +4 ወይፈኑን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ+ ወደ ይሖዋ ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናል፤ ወይፈኑንም በይሖዋ ፊት ያርደዋል።+ +5 ከዚያም የተቀባው ካህን+ ከወይፈኑ ደም የተወሰነ ወስዶ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይዞ ይገባል፤ +6 ካህኑም ጣቱን ደሙ ውስጥ ነክሮ+ ደሙን በቅዱሱ ስፍራ መጋረጃ ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።+ +7 በተጨማሪም ካህኑ ከደሙ የተወሰነውን ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በይሖዋ ፊት የሚገኘውን ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤+ ከዚያም የተረፈውን የወይፈኑን ደም በሙሉ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሰዋል።+ +8 “‘ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብና በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ ጨምሮ ለኃጢአት መባ የቀረበውን ወይፈን ስብ በሙሉ ከላዩ ላይ ያነሳል፤ +9 እንዲሁም ሁለቱን ���ላሊቶችና በላያቸው ላይ ያለውን በሽንጡ አካባቢ የሚገኝ ስብ ያነሳል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል።+ +10 ይህም ለኅብረት መሥዋዕት+ ከሚቀርበው በሬ ላይ ከሚነሳው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። ካህኑም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል። +11 “‘ሆኖም የወይፈኑን ቆዳ እንዲሁም ሥጋውን በሙሉ ከጭንቅላቱ፣ ከእግሮቹ፣ ከሆድ ዕቃውና ከፈርሱ ጋር+ +12 እንዲሁም ከወይፈኑ የቀረውን በሙሉ ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው አመድ* ወደሚደፋበት ንጹሕ የሆነ ቦታ ይወስደዋል፤ በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ አድርጎም ያቃጥለዋል።+ አመዱ በሚደፋበት ቦታ ላይ ይቃጠል። +13 “‘መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ባለማወቅ ኃጢአት በመሥራቱ በደለኛ ቢሆንና+ ጉባኤው ግን ይሖዋ አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን መፈጸሙን ባይገነዘብ፣+ +14 በኋላም ኃጢአቱ ቢታወቅ ጉባኤው ለኃጢአት መባ የሚሆን ወይፈን ያቅርብ፤ ወደ መገናኛ ድንኳኑም ፊት ያምጣው። +15 የማኅበረሰቡ ሽማግሌዎች በይሖዋ ፊት እጃቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናሉ፤ ወይፈኑም በይሖዋ ፊት ይታረዳል። +16 “‘ከዚያም የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም የተወሰነ ወስዶ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይዞ ይገባል። +17 ካህኑም ጣቱን ደሙ ውስጥ ነክሮ የተወሰነውን በመጋረጃው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።+ +18 የተወሰነውንም ደም ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በይሖዋ ፊት የሚገኘውን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤+ ከዚያም የተረፈውን ደም በሙሉ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሰዋል።+ +19 ስቡንም በሙሉ አንስቶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል።+ +20 በወይፈኑ ላይ ለኃጢአት መባ እንዲሆን በቀረበው በሌላኛው ወይፈን ላይ እንዳደረገው ሁሉ ያደርጋል። በዚህኛውም ላይ የሚያደርገው ይህንኑ ይሆናል፤ ካህኑም ለእነሱ ያስተሰርይላቸዋል፤+ እነሱም ይቅር ይባላሉ። +21 ወይፈኑንም ከሰፈሩ ውጭ እንዲወሰድ ካደረገ በኋላ ልክ የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለው ሁሉ ይሄኛውንም ያቃጥለዋል።+ ይህ ስለ ጉባኤው የሚቀርብ የኃጢአት መባ ነው።+ +22 “‘አንድ አለቃ+ አምላኩ ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ሠርቶ በደለኛ ቢሆን +23 ወይም ትእዛዙን በመተላለፍ ኃጢአት እንደሠራ ቢያውቅ እንከን የሌለበትን ተባዕት የፍየል ጠቦት መባ አድርጎ ያምጣ። +24 እጁንም በፍየል ጠቦቱ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም የሚቃጠለው መባ በይሖዋ ፊት ዘወትር በሚታረድበት ስፍራ ያርደዋል።+ ይህ የኃጢአት መባ ነው። +25 ካህኑም ለኃጢአት መባ ከቀረበው እንስሳ ደም ላይ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤+ ከዚያም የተረፈውን ደሙን የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ሥር ያፈሳል።+ +26 ስቡንም በሙሉ ልክ እንደ ኅብረት መሥዋዕቱ ስብ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል፤+ ካህኑም የእሱን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። +27 “‘በምድሩ ከሚኖሩ ሕዝቦች መካከል ማንኛውም ሰው* ይሖዋ መደረግ የለባቸውም ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ቢሆን፣+ +28 በኋላም የሠራውን ኃጢአት ቢያውቅ ለፈጸመው ኃጢአት እንከን የሌለባትን እንስት የፍየል ጠቦት መባ አድርጎ ያምጣ። +29 እጁንም ለኃጢአት መባ በቀረበችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም ለኃጢአት መባ የቀረበችውን እንስሳ የሚቃጠለው መባ በሚታረድበት ስፍራ ያርዳታል።+ +30 ካህኑም ከደሙ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበ��ን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤ ከዚያም የተረፈውን ደሙን በሙሉ በመሠዊያው ሥር ያፈሰዋል።+ +31 ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይ ስቡ+ እንደሚነሳ ሁሉ ከዚህ ላይም ስቡን በሙሉ ያነሳዋል፤+ ካህኑም ስቡ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ እንዲሰጥ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል፤ ካህኑም ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። +32 “‘ሆኖም የኃጢአት መባ አድርጎ የሚያቀርበው የበግ ጠቦት ከሆነ እንከን የሌለባትን እንስት የበግ ጠቦት ማምጣት አለበት። +33 እጁንም ለኃጢአት መባ በቀረበችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ እንዲሁም እንስሳዋን የሚቃጠለው መባ በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአት መባ አድርጎ ያርዳታል።+ +34 ካህኑም ለኃጢአት መባ ከቀረበችው እንስሳ ደም ላይ የተወሰነውን በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ ቀንዶች ይቀባል፤+ ከዚያም የተረፈውን ደሙን በሙሉ በመሠዊያው ሥር ያፈሰዋል። +35 የኅብረት መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርበው የበግ ጠቦት ላይ ስቡ እንደሚነሳ ሁሉ ከዚህ ላይም ስቡን በሙሉ ያነሳዋል፤ እሱም በመሠዊያው ላይ ባሉት ለይሖዋ በእሳት በሚቀርቡት መባዎች ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል።+ ካህኑም ሰውየው የሠራውን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።+ +16 ሁለቱ የአሮን ወንዶች ልጆች ይሖዋ ፊት በመቅረባቸው የተነሳ ከሞቱ+ በኋላ ይሖዋ ሙሴን አነጋገረው። +2 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “እኔ ከመክደኛው በላይ+ በደመና ውስጥ+ ስለምገለጥ በመጋረጃው ውስጥ+ ወዳለው ቅዱስ ስፍራ+ ይኸውም በታቦቱ ላይ ወዳለው መክደኛ ፊት በፈለገው ጊዜ እንዳይገባና በዚህም የተነሳ እንዳይሞት+ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው። +3 “አሮን ወደተቀደሰው ስፍራ በሚገባበት ጊዜ ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ ወይፈንና+ ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ አውራ በግ+ ይዞ ይምጣ። +4 ቅዱሱን የበፍታ ቀሚስ+ ይልበስ፤ በበፍታ ቁምጣዎቹም+ ሰውነቱን ይሸፍን፤ የበፍታ መቀነቱንም+ ይታጠቅ፤ ራሱም ላይ የበፍታ ጥምጥሙን+ ይጠምጥም። እነዚህ ቅዱስ ልብሶች+ ናቸው። እሱም ገላውን በውኃ ታጥቦ+ ይለብሳቸዋል። +5 “ከእስራኤል ማኅበረሰብም ሁለት ተባዕት የፍየል ጠቦቶችን ለኃጢአት መባ፣ አንድ አውራ በግ ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይውሰድ።+ +6 “ከዚያም አሮን ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያቅርብ፤ ለራሱም+ ሆነ ለቤቱ ያስተሰርያል። +7 “ሁለቱን ፍየሎች ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት እንዲቆሙ ያደርጋል። +8 አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥላል፤ አንደኛው ዕጣ ለይሖዋ ሌላኛው ዕጣ ደግሞ ለአዛዜል* ይሆናል። +9 አሮንም ለይሖዋ እንዲሆን ዕጣ+ የወጣበትን ፍየል ያቀርባል፤ የኃጢአትም መባ ያደርገዋል። +10 ለአዛዜል እንዲሆን ዕጣ የወጣበት ፍየል ግን በእሱ አማካኝነት ስርየት እንዲፈጸምበት ከነሕይወቱ መጥቶ በይሖዋ ፊት እንዲቆም ይደረግ፤ ከዚያም ለአዛዜል እንዲሆን ወደ ምድረ በዳ ይለቀቃል።+ +11 “አሮንም ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያቀርባል፤ ለራሱም ሆነ ለቤቱ ያስተሰርያል፤ ከዚያም ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያርዳል።+ +12 “በይሖዋ ፊት ካለው መሠዊያ ላይ የተወሰደ ፍም+ የሞላበትን ዕጣን ማጨሻና+ ሁለት እፍኝ ሙሉ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ይወስዳል፤ እነዚህንም ይዞ ወደ መጋረጃው ውስጥ ይገባል።+ +13 እንዳይሞትም ዕጣኑን በይሖዋ ፊት+ ባለው እሳት ላይ ይጨምረዋል፤ የዕጣኑም ጭስ ከምሥክሩ+ በላይ ያለውን የታቦቱን መክደኛ+ ይሸፍነዋል። +14 “ከወይፈኑም ደም+ የተወሰነውን ወስዶ ከመክደኛው ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ በኩል በጣቱ ይረጨዋል፤ የተወሰነውን ደም ደግሞ ከመክደኛው ፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።+ +15 “ከዚያም ለሕዝቡ የኃጢ��ት መባ+ የሚሆነውን ፍየል ያርደዋል፤ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ይዞ በመግባት+ ልክ በወይፈኑ ደም+ እንዳደረገው በዚህኛውም ደም ያደርጋል፤ ደሙንም ወደ መክደኛውና በመክደኛው ፊት ይረጨዋል። +16 “እስራኤላውያን ስለፈጸሙት ርኩሰት፣ ስለ መተላለፋቸውና ስለ ኃጢአታቸው+ ለቅዱሱ ስፍራ ያስተሰርይ፤ በእነሱ ዘንድ በርኩሰታቸው መካከል ለሚገኘው ለመገናኛ ድንኳኑም ይህንኑ ያድርግ። +17 “ለማስተሰረይ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ገብቶ እስኪወጣ ድረስ ሌላ ማንም ሰው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ መገኘት የለበትም። እሱም ለራሱ፣ ለቤቱና+ ለመላው የእስራኤል ጉባኤ+ ያስተሰርያል። +18 “ከዚያም በይሖዋ ፊት ወዳለው መሠዊያ ይወጣል፤+ ለመሠዊያውም ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑ ደም የተወሰነውን እንዲሁም ከፍየሉ ደም የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ያሉትን ቀንዶች ይቀባል። +19 በተጨማሪም ከደሙ የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ላይ በጣቱ ሰባት ጊዜ በመርጨት እስራኤላውያን ከፈጸሙት ርኩሰት ያነጻዋል እንዲሁም ይቀድሰዋል። +20 “ለቅዱሱ ስፍራ፣ ለመገናኛ ድንኳኑና ለመሠዊያው+ ካስተሰረየ+ በኋላ በሕይወት ያለውንም ፍየል ያቀርባል።+ +21 ከዚያም አሮን ሁለቱንም እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ በመጫን እስራኤላውያን የሠሩትን ስህተት ሁሉ፣ መተላለፋቸውን ሁሉና ኃጢአታቸውን ሁሉ ይናዘዝበታል፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ያደርጋል፤+ ፍየሉንም ለዚህ በተመደበው* ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል። +22 ፍየሉም ስህተቶቻቸውን በሙሉ ተሸክሞ+ ወደ በረሃ ይሄዳል፤+ እሱም ፍየሉን ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል።+ +23 “ከዚያም አሮን ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይገባል፤ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ሲገባ ለብሷቸው የነበሩትንም የበፍታ ልብሶች ያወልቃል፤ ልብሶቹንም እዚያው ይተዋቸዋል። +24 ገላውንም በቅዱስ ስፍራ በውኃ ይታጠብ፤+ ልብሶቹንም ይልበስ፤+ ከዚያም ወጥቶ የራሱን የሚቃጠል መባ+ እንዲሁም የሕዝቡን የሚቃጠል መባ+ ያቀርባል፤ ለራሱና ለሕዝቡም ያስተሰርያል።+ +25 የኃጢአት መባው ስብም በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። +26 “ለአዛዜል+ ሲል ፍየሉን የለቀቀውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል። +27 “ደማቸው ለማስተሰረያ እንዲሆን ወደ ቅዱሱ ስፍራ የገባው የኃጢአት መባው ወይፈንና የኃጢአት መባው ፍየል ከሰፈሩ ውጭ ይወሰዳሉ፤ ቆዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸውም በእሳት ይቃጠላል።+ +28 እነዚህን ያቃጠለው ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል። +29 “ይህም ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል፦ በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ራሳችሁን አጎሳቁሉ፤* ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ፤+ የአገራችሁ ሰውም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ሥራ አይሥራ። +30 በዚህ ቀን፣ ንጹሕ መሆናችሁን ለማሳወቅ ለእናንተ ማስተሰረያ+ ይቀርባል። በይሖዋም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ንጹሕ ትሆናላችሁ።+ +31 ይህ ሙሉ በሙሉ የምታርፉበት ሰንበት ነው፤ እናንተም ራሳችሁን* አጎሳቁሉ።+ ይህም ዘላቂ ደንብ ነው። +32 “አባቱን ተክቶ+ በክህነት እንዲያገለግል የሚቀባውና የሚሾመው*+ ካህን ያስተሰርያል፤ እንዲሁም ቅዱስ የሆኑትን የበፍታ ልብሶች+ ይለብሳል። +33 ለቅዱሱ መቅደስ፣+ ለመገናኛ ድንኳኑና+ ለመሠዊያው+ ያስተሰርያል፤ እንዲሁም ለካህናቱና ለጉባኤው ሕዝብ በሙሉ ያስተሰርያል።+ +34 ይህም የእስራኤላውያንን ኃጢአት በሙሉ በዓመት አንድ ጊዜ+ ለማስተሰረይ የሚያገለግል ዘላቂ ደንብ ይሆናል።”+ እሱም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረገ። +6 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “አንድ ሰው* በአደራ እንዲይዝ ወይም እንዲያስቀምጥ ከተሰጠው ነገር ጋር በተያያዘ+ ባልንጀራውን በማታለል ኃጢአት ቢሠራና በይሖዋ ላይ ታማኝነት የማጉደል ተግባር ቢፈጽም+ አሊያም ባልንጀራውን ቢሰርቅ ወይም ቢያጭበረብር +3 አሊያም ደግሞ የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ብሎ ቢዋሽና ሰውየው ከእነዚህ ኃጢአቶች መካከል አንዱንም እንዳልሠራ አድርጎ በሐሰት ቢምል+ እንዲህ ማድረግ አለበት፦ +4 ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ሆኖ ቢገኝ የሰረቀውን፣ ቀምቶ ወይም አጭበርብሮ የወሰደውን አሊያም በአደራ ተሰጥቶት የነበረውን ወይም ደግሞ ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፤ +5 አሊያም በሐሰት የማለበትን ማንኛውንም ነገር ይመልስ፤ ሙሉ ካሳ ይክፈል፤+ የዋጋውንም አንድ አምስተኛ ይጨምርበት። በደለኛ መሆኑ በተረጋገጠበትም ዕለት ለባለቤቱ ይሰጠዋል። +6 በተተመነውም ዋጋ መሠረት እንከን የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው መካከል በመውሰድ የበደል መባው አድርጎ ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ ካህኑ ያመጣዋል።+ +7 ካህኑም በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል፤ እሱም በደለኛ እንዲሆን ያደረገው ማንኛውም ነገር ይቅር ይባልለታል።”+ +8 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +9 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ‘የሚቃጠል መባ ሕግ ይህ ነው፦+ የሚቃጠለው መባ ሌሊቱን ሙሉ እስኪነጋ ድረስ በመሠዊያው ላይ ባለው ማንደጃ ላይ ይቀመጣል፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ሲነድ ያድራል። +10 ካህኑ ከበፍታ የተሠራውን የክህነት ልብሱን+ ይለብሳል፤ እርቃኑንም ለመሸፈን ከበፍታ የተሠራውን ቁምጣ+ ያደርጋል። ከዚያም በመሠዊያው ላይ ከነበረው በእሳት ከነደደው የሚቃጠል መባ የወጣውን አመድ*+ ያነሳል፤ በመሠዊያውም ጎን ያደርገዋል። +11 ከዚያም ልብሱን አውልቆ+ ሌላ ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ከሰፈሩ ውጭ ወደሚገኝ ንጹሕ የሆነ ቦታ ይወስደዋል።+ +12 እሳቱ በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል። መጥፋትም የለበትም። ካህኑም በየማለዳው እንጨት ይማግድበት፤+ በላዩም ላይ የሚቃጠለውን መባ ይረብርብበት፤ የኅብረት መሥዋዕቶቹንም ስብ በላዩ ላይ ያጨስበታል።+ +13 በመሠዊያውም ላይ ያለማቋረጥ እሳት ይነድዳል። መጥፋትም የለበትም። +14 “‘የእህል መባ ሕግ ደግሞ ይህ ነው፦+ እናንተ የአሮን ወንዶች ልጆች በመሠዊያው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ታቀርቡታላችሁ። +15 ከመካከላቸው አንዱ ለእህል መባ ከቀረበው የላመ ዱቄት ላይ ከነዘይቱ አንድ እፍኝ ያነሳል፤ እንዲሁም በእህል መባው ላይ ያለውን ነጭ ዕጣን በሙሉ ይወስዳል። አምላክ መላውን መባ እንዲያስበውም ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል።+ +16 ከዚያ የተረፈውን አሮንና ወንዶች ልጆቹ ይበሉታል፤+ እንደ ቂጣ ተጋግሮ በቅዱስ ስፍራ ይበላል። በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ይበሉታል።+ +17 ያለእርሾ መጋገር አለበት።+ ለእኔ በእሳት ከሚቀርቡልኝ መባዎች ውስጥ ይህን ድርሻቸው አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።+ እንደ ኃጢአት መባና እንደ በደል መባ ሁሉ ይህም እጅግ ቅዱስ ነገር ነው።+ +18 የአሮን ዘር የሆኑ ወንዶች ሁሉ ይበሉታል።+ ይህ ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡ መባዎች ውስጥ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእነሱ የሚሰጥ ዘላለማዊ ድርሻ ነው።+ የሚነካቸውም* ነገር ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።’” +19 ይሖዋም በድጋሚ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +20 “አሮን በሚቀባበት+ ቀን እሱና ወንዶች ልጆቹ ለይሖዋ የሚያቀርቡት መባ ይህ ነው፦ የኢፍ አንድ አሥረኛ*+ የላመ ዱቄት በቋሚነት የሚቀርብ የእህል መባ አድርገው ያቅርቡ፤+ ግማሹን ጠዋት፣ ግማሹን ደግሞ ምሽት ላይ ያቅርቡ። +21 በዘይት ከተለወሰ በኋላም በምጣድ ላይ ይጋገራል።+ ከዚያም በደንብ በዘይት ለውሰህ ታመጣዋለህ፤ ���ተጋገረውንም የእህል መባ ቆራርሰህ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ይሆን ዘንድ ለይሖዋ ታቀርበዋለህ። +22 ከወንዶች ልጆቹ መካከል እሱን የሚተካው የተቀባው ካህንም ያቀርበዋል።+ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባም ሆኖ ለይሖዋ እንዲጨስ ይደረጋል፤ ይህም ዘላቂ ሥርዓት ነው። +23 አንድ ካህን የሚያቀርበው እያንዳንዱ የእህል መባ ሙሉ በሙሉ መቃጠል ይኖርበታል። መበላት የለበትም።” +24 ይሖዋ በድጋሚ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +25 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የኃጢአት መባ ሕግ ይህ ነው፦+ ለኃጢአት መባ የሚሆነውም እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነው እንስሳ በሚታረድበት ቦታ+ በይሖዋ ፊት ይታረዳል። ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው። +26 ይህን ለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው ካህን ይበላዋል።+ በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ይበላል።+ +27 “‘ሥጋውን የሚነካ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ይሆናል፤ ማንም ሰው የእንስሳውን ደም በልብሱ ላይ ቢረጭ ደም የተረጨበትን ልብስ በቅዱስ ስፍራ እጠበው። +28 ሥጋው የተቀቀለበት የሸክላ ዕቃም መሰባበር አለበት። የተቀቀለው ከመዳብ በተሠራ ዕቃ ከሆነ ግን ዕቃው ፍትግ ተደርጎ በውኃ መታጠብ አለበት። +29 “‘ካህን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል።+ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው።+ +30 ይሁን እንጂ በቅዱሱ ስፍራ ለማስተሰረያ እንዲሆን ደሙ ወደ መገናኛ ድንኳኑ የገባ የኃጢአት መባ መበላት የለበትም።+ በእሳት መቃጠል አለበት። +25 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ አለው፦ +2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በምትገቡበት ጊዜ+ ምድሪቱ ለይሖዋ ሰንበትን ማክበር ይኖርባታል።+ +3 ስድስት ዓመት በእርሻህ ላይ ዘር ዝራ፤ ስድስት ዓመት ወይንህን ግረዝ፤ እንዲሁም የምድሪቱን ምርት ሰብስብ።+ +4 ሰባተኛው ዓመት ግን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ የምታርፍበት ሰንበት ይኸውም የይሖዋ ሰንበት ይሁን። በእርሻህ ላይ ዘር አትዝራ ወይም ወይንህን አትግረዝ። +5 በማሳህ ላይ የበቀለውን ገቦ* አትጨድ፤ ያልተገረዘውን ወይንህን ፍሬ አትልቀም። ምድሪቱ ለአንድ ዓመት ሙሉ በሙሉ ማረፍ ይኖርባታል። +6 ሆኖም ምድሪቱ በሰንበት እረፍቷ ጊዜ የምታበቅለውን እህል መብላት ትችላለህ፤ አንተ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ፣ ቅጥር ሠራተኛህና አብረውህ የሚኖሩ ባዕዳን ሰፋሪዎች ልትበሉት ትችላላችሁ፤ +7 እንዲሁም በምድርህ ለሚኖሩ የቤትና የዱር እንስሳት ምግብ ይሁን። ምድሪቱ የምትሰጠው ምርት ሁሉ ለምግብነት ሊውል ይችላል። +8 “‘ሰባት የሰንበት ዓመታትን ማለትም ሰባት ጊዜ ሰባት ዓመታትን ትቆጥራለህ፤ ሰባቱ የሰንበት ዓመታትም 49 ዓመታት ይሆናሉ። +9 ከዚያም በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ቀንደ መለከቱን ድምፁን ከፍ አድርገህ ትነፋዋለህ፤ በስርየት ቀን+ የቀንደ መለከቱ ድምፅ በምድራችሁ ሁሉ እንዲሰማ ማድረግ አለባችሁ። +10 ሃምሳኛውን ዓመት ቀድሱ፤ በምድሪቱም ለሚኖሩ ሁሉ ነፃነት አውጁ።+ ለእናንተ ኢዮቤልዩ ይሆንላችኋል፤ ከእናንተ እያንዳንዱ ወደየርስቱ ይመለሳል፤ ከእናንተም እያንዳንዱ ወደየቤተሰቡ ይመለስ።+ +11 ሃምሳኛው ዓመት ለእናንተ ኢዮቤልዩ ይሆንላችኋል። ዘር አትዘሩም ወይም ማሳ ላይ የበቀለውን ገቦ አታጭዱም አሊያም ያልተገረዘውን የወይን ፍሬ አትሰበስቡም።+ +12 ምክንያቱም ይህ ኢዮቤልዩ ነው። ለእናንተም ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። ምድሪቱ በራሷ የምታበቅለውን ብቻ መብላት ትችላላችሁ።+ +13 “‘በዚህ የኢዮቤልዩ ዓመት ከእናንተ እያንዳንዱ ወደየርስቱ ይመለስ።+ +14 ለባልንጀራችሁ አንድ ነገር ብትሸጡ ወይም ከባልንጀራችሁ እጅ አንድ ነገር ብትገዙ አንዳችሁ ሌላውን መጠቀሚያ አታድርጉ።+ +15 ከባልንጀራህ ላይ መሬት ስትገዛ ከኢዮቤልዩ በኋላ ያሉትን ዓመታት ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብሃል፤ እሱም ሲሸጥልህ እህል የሚሰበሰብባቸውን የቀሩትን ዓመታት ማስላት ይኖርበታል።+ +16 ብዙ ዓመታት የሚቀሩ ከሆነ ዋጋውን መጨመር ይችላል፤ የሚቀሩት ዓመታት ጥቂት ከሆኑ ደግሞ ዋጋውን መቀነስ ይኖርበታል፤ ምክንያቱም የሚሸጥልህ አዝመራ የሚሰበሰብበትን ጊዜ አስልቶ ነው። +17 ከእናንተ መካከል ማንም ባልንጀራውን መጠቀሚያ ማድረግ የለበትም፤+ አምላክህን ፍራ፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።+ +18 ደንቦቼን ብትፈጽሙና ድንጋጌዎቼን ብትጠብቁ በምድሪቱ ላይ ያለስጋት ትኖራላችሁ።+ +19 ምድሪቱ ፍሬዋን ትሰጣለች፤+ እናንተም እስክትጠግቡ ድረስ ትበላላችሁ፤ በዚያም ያለስጋት ትኖራላችሁ።+ +20 “‘ሆኖም ‘ዘር ካልዘራን ወይም እህል ካልሰበሰብን በሰባተኛው ዓመት ምን እንበላለን?’ ብትሉ+ +21 እኔ በስድስተኛው ዓመት በረከቴን እልክላችኋለሁ፤ ምድሪቱም ለሦስት ዓመት የሚበቃ እህል ታፈራለች።+ +22 ከዚያም በስምንተኛው ዓመት ዘር ትዘራላችሁ፤ እስከ ዘጠነኛውም ዓመት ድረስ ቀድሞ ከሰበሰባችሁት ትበላላችሁ። እህሉ እስኪደርስ ድረስ ቀድሞ የሰበሰባችሁትን ትበላላችሁ። +23 “‘ምድሪቱ የእኔ ስለሆነች+ መሬት ለዘለቄታው መሸጥ አይኖርበትም።+ ምክንያቱም እናንተ በእኔ አመለካከት የባዕድ አገር ሰዎችና ሰፋሪዎች ናችሁ።+ +24 በርስትነት በያዛችሁት ምድር ሁሉ መሬትን መልሶ መግዛት የሚያስችል መብት እንዲኖር አድርጉ። +25 “‘ወንድምህ ቢደኸይና ከርስቱ የተወሰነውን ለመሸጥ ቢገደድ የሚዋጅ የቅርብ ዘመዱ መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን መልሶ ይግዛ።+ +26 አንድ ሰው የሚዋጅለት ቢያጣ ሆኖም እሱ ራሱ ሀብት ቢያገኝና መሬቱን ለመዋጀት የሚያስችል አቅም ቢኖረው +27 መሬቱን ከሸጠበት ጊዜ አንስቶ ያሉትን ዓመታት በመቁጠር ዋጋውን ያስላ፤ የዋጋውንም ልዩነት ለሸጠለት ሰው ይመልስ። ከዚያም ወደ ርስቱ መመለስ ይችላል።+ +28 “‘ሆኖም መሬቱን ከሰውየው ላይ ለማስመለስ የሚያስችል አቅም ባይኖረው የሸጠው መሬት እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ በገዢው እጅ ይቆያል፤+ መሬቱም በኢዮቤልዩ ይመለስለታል፤ እሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል።+ +29 “‘አንድ ሰው በቅጥር በታጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኝን መኖሪያ ቤት ቢሸጥ ከሸጠበት ጊዜ አንስቶ እስከ አንድ ዓመት ድረስ የመዋጀት መብቱ እንደተጠበቀ ይቆያል፤ የመዋጀት መብቱ+ ለአንድ ዓመት ሙሉ እንደተጠበቀ ይቆያል። +30 ይሁንና ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት መልሶ ሊገዛው ካልቻለ በቅጥር በታጠረው ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቤት ለዘለቄታው የገዢው ንብረት ሆኖ በትውልዶቹ ሁሉ ይቀጥላል። በኢዮቤልዩ ነፃ አይለቀቅም። +31 ቅጥር በሌላቸው መንደሮች ውስጥ የሚገኙ ቤቶች ግን በገጠራማ አካባቢ የሚገኝ የእርሻ መሬት ክፍል እንደሆኑ ይቆጠራሉ። የመዋጀት መብታቸው እንደተጠበቀ ይቆይ፤ በኢዮቤልዩም ነፃ ይለቀቁ። +32 “‘በሌዋውያን ከተሞች+ ውስጥ ያሉትን የሌዋውያን ቤቶች በተመለከተ ግን ሌዋውያኑ እነዚህን ቤቶች የመዋጀት መብታቸው ምንጊዜም የተጠበቀ ነው። +33 የሌዋውያን ንብረት ተመልሶ ካልተገዛ የእነሱ በሆነው ከተማ ውስጥ የሚገኘው የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ነፃ ይለቀቃል፤+ ምክንያቱም በሌዋውያኑ ከተሞች ውስጥ የሚገኙት ቤቶች በእስራኤላውያን መካከል ያሉ የሌዋውያኑ ንብረቶች ናቸው።+ +34 ከዚህም በላይ በከተሞቻቸው ዙሪያ ያለው የግጦሽ መሬት+ ዘላለማዊ ርስታቸው ስለሆነ መሸጥ አይኖርበትም። +35 “‘በአቅራቢያህ ያለ ወንድምህ ቢደኸይና ራሱን ማስተዳደር ቢያቅተው አብሮህ በሕይወት ይኖር ዘንድ አንድን የባዕድ አገ��� ሰውና ሰፋሪ+ እንደምትረዳ ሁሉ ልትረዳው ይገባል።+ +36 ከእሱ ወለድ ወይም ትርፍ* አትቀበል።+ ከዚህ ይልቅ አምላክህን ፍራ፤+ ወንድምህም አብሮህ በሕይወት ይኖራል። +37 ገንዘብህን በወለድ አታበድረው+ ወይም እህል ስታበድረው ትርፍ አትጠይቀው። +38 የከነአንን ምድር በመስጠት አምላካችሁ መሆኔን አስመሠክር ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።+ +39 “‘በአቅራቢያህ የሚኖር ወንድምህ ቢደኸይና ራሱን ለአንተ ለመሸጥ ቢገደድ+ እንደ ባሪያ እንዲሠራ አታስገድደው።+ +40 እንደ ቅጥር ሠራተኛና እንደ ሰፋሪ ሊታይ ይገባዋል።+ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያገልግልህ። +41 ከዚያም እሱም ሆነ አብረውት ያሉት ልጆቹ* ትተውህ ይሄዳሉ፤ ወደ ዘመዶቹም ይመለሳሉ። እሱም ወደ ቀድሞ አባቶቹ ርስት ይመለስ።+ +42 ምክንያቱም እነሱ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸው።+ እንደ ባሪያ ራሳቸውን መሸጥ የለባቸውም። +43 የጭካኔ ድርጊት ልትፈጽምበት አይገባም፤+ አምላክህን መፍራት ይኖርብሃል።+ +44 ወንድ ባሪያዎቻችሁና ሴት ባሪያዎቻችሁ በዙሪያችሁ ካሉት ብሔራት የመጡ ይሁኑ፤ ከእነሱ መካከል ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ መግዛት ትችላላችሁ። +45 በተጨማሪም ከእናንተ ጋር ከሚኖሩት ባዕዳን ሰፋሪዎች+ እንዲሁም እነሱ በምድራችሁ ከወለዷቸው ቤተሰቦቻቸው መካከል ባሪያዎችን መግዛት ትችላላችሁ፤ እነሱም የእናንተ ንብረት ይሆናሉ። +46 እነሱንም እንደ ቋሚ ንብረት አድርጋችሁ ከእናንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆቻችሁ ማውረስ ትችላላችሁ። ባሪያ አድርጋችሁ ልታሠሯቸው ትችላላችሁ፤ ወንድሞቻችሁ የሆኑትን እስራኤላውያንን ግን በጭካኔ አትግዟቸው።+ +47 “‘በመካከልህ ያለ የባዕድ አገር ሰው ወይም ሰፋሪ ሀብታም ቢሆንና ከእሱ ጋር ያለው ወንድምህ ደግሞ ደህይቶ ለባዕድ አገሩ ሰው ወይም ሰፋሪ አሊያም ከባዕድ አገሩ ሰው ቤተሰብ መካከል ለአንዱ ራሱን ለመሸጥ ቢገደድ +48 ይህ ሰው ራሱን ከሸጠም በኋላ የመዋጀት መብቱ የተጠበቀ ይሆናል። ከወንድሞቹ አንዱ መልሶ ሊገዛው ይችላል፤+ +49 ወይም ደግሞ አጎቱ አሊያም የአጎቱ ልጅ መልሶ ሊገዛው ይችላል፤ አሊያም ደግሞ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ* ማለትም ከቤተሰቦቹ አንዱ መልሶ ሊገዛው ይችላል። “‘ወይም ደግሞ ሰውየው ራሱ ሀብት ካገኘ ራሱን መልሶ ሊገዛ ይችላል።+ +50 እሱም ራሱን ከሸጠበት ዓመት አንስቶ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያለውን+ ጊዜ ከገዛው ሰው ጋር በመሆን ያስላ፤ የተሸጠበትም ገንዘብ ከዓመታቱ ብዛት ጋር የሚመጣጠን ይሁን።+ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሉት የሥራ ቀናት የሚሰሉት የአንድ ቅጥር ሠራተኛ የሥራ ቀናት በሚሰሉበት መንገድ ይሆናል።+ +51 ገና ብዙ ዓመታት የሚቀሩ ከሆነ እሱን ለመግዛት ከተከፈለው ገንዘብ ላይ የቀሪዎቹን ዓመታት ብዛት ግምት ውስጥ በማስገባት ራሱን የሚዋጅበትን ዋጋ ይክፈል። +52 እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የሚቀሩት ዓመታት ጥቂት ከሆኑ ደግሞ ይህን ለራሱ ያስላ፤ በቀሩት ዓመታት ብዛት ልክም የሚዋጅበትን ዋጋ ይክፈል። +53 ከእሱም ጋር በሚቆይበት ጊዜ ከዓመት እስከ ዓመት እንደ ቅጥር ሠራተኛ ሆኖ ያገልግለው፤ አንተም የጭካኔ ድርጊት እንዳይፈጽምበት ተከታተል።+ +54 ሆኖም ከእነዚህ መንገዶች በአንዱ ራሱን መልሶ መግዛት ካልቻለ በኢዮቤልዩ ዓመት ነፃ ይለቀቃል፤+ እሱም ሆነ ልጆቹ* አብረውት ነፃ ይለቀቁ። +55 “‘እስራኤላውያን የእኔ ባሪያዎች ናቸው። እነሱ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸው።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። +10 በኋላም የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብና አቢሁ+ እያንዳንዳቸው የዕጣን ማጨሻቸውን አምጥተው በላዩ ላይ እሳት አደረጉበት፤ በእሳቱም ላይ ዕጣን ጨመሩበት።+ ከዚያም ይሖዋ እንዲያደርጉ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ እሳት+ በፊቱ አቀረቡ። +2 በዚህ ጊዜ እሳት ከይሖዋ ፊት ወጥቶ በላቸው፤+ እነሱም በይሖዋ ፊት ሞቱ።+ +3 ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ ሰዎች መካከል እቀደሳለሁ፤+ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከበራለሁ’ ብሏል።” አሮንም ዝም አለ። +4 ሙሴም የአሮን አጎት የዑዚኤል+ ልጆች የሆኑትን ሚሳኤልንና ኤሊጻፋንን ጠርቶ “ኑ፣ ወንድሞቻችሁን ከቅዱሱ ስፍራ ፊት ለፊት አንስታችሁ ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው ቦታ አውጧቸው” አላቸው። +5 ስለዚህ መጥተው ልክ ሙሴ በነገራቸው መሠረት ሟቾቹን ከነቀሚሳቸው ተሸክመው ከሰፈሩ ውጭ አወጧቸው። +6 ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲሁም ሌሎቹን የአሮን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እንዳትሞቱ እንዲሁም አምላክ በመላው ማኅበረሰብ ላይ እንዳይቆጣ ፀጉራችሁን አታንጨብርሩ ወይም ልብሶቻችሁን አትቅደዱ።+ ሆኖም ወንድሞቻችሁ ይኸውም መላው የእስራኤል ቤት ይሖዋ በእሳት ለገደላቸው ያለቅሱላቸዋል። +7 የይሖዋ የቅብዓት ዘይት በላያችሁ ላይ ስላለ ከመገናኛ ድንኳኑ ደጃፍ መራቅ የለባችሁም፤+ አለዚያ ትሞታላችሁ።” እነሱም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ። +8 ከዚያም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ +9 “እንዳትሞቱ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ስትገቡ አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶች ልጆችህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ።+ ይህ ትእዛዝ ለትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘላለማዊ ደንብ ነው። +10 ይህም ቅዱስ የሆነውን ከረከሰው ነገር እንዲሁም ንጹሕ ያልሆነውን ንጹሕ ከሆነው ነገር ለመለየት+ +11 እንዲሁም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት የሰጣቸውን ሥርዓቶች በሙሉ ለእስራኤላውያን ለማስተማር ነው።”+ +12 ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲሁም የተረፉትን የአሮን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈውን የእህል መባ ወስዳችሁ ያለእርሾ በማዘጋጀት በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤+ ምክንያቱም ይህ እጅግ ቅዱስ ነገር ነው።+ +13 ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች ላይ ይህ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ስለሆነ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ብሉት፤+ ምክንያቱም እንዲህ እንዳደርግ ታዝዣለሁ። +14 እንዲሁም የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የቅዱሱን ድርሻ+ እግር አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ንጹሕ በሆነ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤+ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ሆነው የተሰጡ ናቸው። +15 እነሱም የቅዱሱን ድርሻ እግርና የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባ በእሳት ከሚቀርቡት የስብ መባዎች ጋር ያመጣሉ፤ ይህን የሚያደርጉት የሚወዘወዘውን መባ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ለመወዝወዝ ነው፤ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረትም ይህ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉት ወንዶች ልጆችህ ዘላለማዊ ድርሻ ሆኖ ያገለግላል።”+ +16 ሙሴም ለኃጢአት መባ የሚሆነውን ፍየል በደንብ አፈላለገ፤+ በኋላም ፍየሉ መቃጠሉን ተረዳ። በመሆኑም የተረፉትን የአሮን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን ተቆጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ +17 “ይህ መባ እጅግ ቅዱስ ነገር ሆኖ ሳለና መባውንም የሰጣችሁ የማኅበረሰቡን ኃጢአት እንድትሸከሙ እንዲሁም በይሖዋ ፊት እንድታስተሰርዩላቸው ሆኖ ሳለ የኃጢአት መባውን በቅዱሱ ስፍራ ያልበላችሁት+ ለምንድን ነው? +18 ይኸው ደሙ ወደ ቅዱሱ ስፍራ አልገባም።+ ልክ እንደታዘዝኩት በቅዱሱ ስፍራ ልትበሉት ይገባችሁ ነበር።” +19 በዚህ ጊዜ አሮን ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እነሱ በዛሬው ዕለት የኃጢአት መባቸውንና የሚቃጠል መባቸውን በይ��ዋ ፊት ያቀረቡት+ እኔ እንዲህ ያለ ነገር ደርሶብኝ እያለ ነው። ታዲያ ዛሬ የኃጢአት መባውን በልቼ ቢሆን ኖሮ ይሖዋ ይደሰት ነበር?” +20 ሙሴም ይህን ሲሰማ ነገሩ አጥጋቢ ሆኖ አገኘው። +14 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “የሥጋ ደዌ ያለበት አንድ ሰው መንጻቱን ለማረጋገጥ ካህኑ ፊት እንዲቀርብ+ በሚደረግበት ዕለት የሚኖረው ሕግ ይህ ነው። +3 ካህኑ ከሰፈሩ ውጭ ወጥቶ ሰውየውን ይመረምረዋል። የሥጋ ደዌ ይዞት የነበረው ሰው ከሥጋ ደዌው ከዳነ +4 ካህኑ ሰውየው ራሱን ለማንጻት በሕይወት ያሉ ሁለት ንጹሕ ወፎችን፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል።+ +5 እንዲሁም ካህኑ አንደኛዋ ወፍ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ውስጥ እንድትታረድ ትእዛዝ ይሰጣል። +6 በሕይወት ያለችውን ወፍ ደግሞ ከአርዘ ሊባኖስ እንጨቱ፣ ከደማቁ ቀይ ማግና ከሂሶጱ ጋር ወስዶ ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ ላይ በታረደችው ወፍ ደም ውስጥ ይንከራቸው። +7 ከዚያም ራሱን ከሥጋ ደዌ በሚያነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፤ ሰውየውም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል፤ በሕይወት ያለችውንም ወፍ ሜዳ ላይ ይለቃታል።+ +8 “ራሱን የሚያነጻውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ፀጉሩንም በሙሉ ይላጭ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል። ይህን ካደረገ በኋላ ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል፤ ሆኖም ለሰባት ቀን ከድንኳኑ ውጭ ይቀመጣል። +9 በሰባተኛው ቀን በራሱ ላይ ያለውን ፀጉር፣ ጺሙንና ቅንድቡን በሙሉ ይላጭ። ፀጉሩን በሙሉ ከተላጨ በኋላ ልብሶቹን ያጥባል እንዲሁም ገላውን በውኃ ይታጠባል፤ ከዚያም ንጹሕ ይሆናል። +10 “በስምንተኛው ቀን እንከን የሌለባቸውን ሁለት የበግ ጠቦቶች፣ አንድ ዓመት ገደማ የሆናትን እንከን የሌለባት አንዲት እንስት የበግ ጠቦት፣+ የእህል መባ እንዲሆን በዘይት የተለወሰ ሦስት አሥረኛ ኢፍ* የላመ ዱቄትና+ አንድ የሎግ መስፈሪያ* ዘይት ያመጣል፤+ +11 ሰውየው ንጹሕ መሆኑን የሚያስታውቀው ካህንም ራሱን የሚያነጻውን ሰው ከመባዎቹ ጋር በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት ያቀርበዋል። +12 ካህኑም አንደኛውን የበግ ጠቦት ወስዶ ከአንዱ የሎግ መስፈሪያ ዘይት ጋር በማድረግ የበደል መባ እንዲሆን ያቀርበዋል፤+ እነዚህንም የሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዘውዛቸዋል።+ +13 ከዚያም የበግ ጠቦቱን የኃጢአት መባውና የሚቃጠል መባው ዘወትር በሚታረዱበት ቦታ+ ይኸውም ቅዱስ በሆነ ስፍራ ያርደዋል፤ ምክንያቱም እንደ ኃጢአት መባው ሁሉ የበደል መባውም የካህኑ ድርሻ ነው።+ ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው።+ +14 “ካህኑም ከበደል መባው ደም ላይ የተወሰነውን ይወስዳል፤ ከዚያም ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል። +15 ካህኑም ከአንዱ የሎግ መስፈሪያ ዘይት+ ላይ የተወሰነውን በራሱ የግራ እጅ መዳፍ ላይ ያንቆረቁረዋል። +16 ከዚያም የቀኝ እጁን ጣት በግራ እጁ መዳፍ ላይ ባለው ዘይት ውስጥ ይነክራል፤ ከዘይቱም የተወሰነውን በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጨዋል። +17 በእጁም መዳፍ ላይ ከቀረው ዘይት ላይ የተወሰነውን ወስዶ ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል፤ በበደል መባው ደም ላይ ደርቦ ይቀባዋል። +18 ካህኑም በእጁ መዳፍ ላይ የቀረውን ዘይት ራሱን በሚያነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሰዋል፤ ለሰውየውም በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል።+ +19 “ካህኑ ለኃጢአት መባ የሚሆነውን እንስሳ ይሠዋል፤+ ራሱን ከርኩሰቱ ለሚያነጻውም ሰው ያስተሰርይለታል፤ ከዚያም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንስሳ ያርዳል። +20 ካህኑም የሚቃጠለውን መባና የእህሉን መባ+ በመሠዊያው ላይ ያቀርባል፤ ለሰውየውም ያስተሰርይለታል፤+ እሱም ንጹሕ ይሆናል።+ +21 “ሆኖም ሰውየው ድሃ ከሆነና ይህን ለማቅረብ አቅሙ ካልፈቀደለት ለራሱ ማስተሰረያ እንዲሆንለት ለሚወዘወዝ መባ አንድ የበግ ጠቦት የበደል መባ አድርጎ ያመጣል፤ በተጨማሪም ለእህል መባ እንዲሆን በዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ* የላመ ዱቄት፣ አንድ የሎግ መስፈሪያ ዘይት +22 እንዲሁም ከሁለት ዋኖሶች ወይም ከሁለት የርግብ ጫጩቶች አቅሙ የቻለውን ያቀርባል፤ አንደኛው ለኃጢአት መባ ሌላኛው ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይሆናል።+ +23 መንጻቱን ለማረጋገጥም በስምንተኛው ቀን+ እነዚህን ይዞ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት ወዳለው ወደ ካህኑ ይመጣል።+ +24 “ካህኑም ለበደል መባ እንዲሆን የቀረበውን የበግ ጠቦትና+ አንዱን የሎግ መስፈሪያ ዘይት ይወስዳል፤ እነዚህንም የሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዘውዛቸዋል።+ +25 ከዚያም ለበደል መባ እንዲሆን የቀረበውን የበግ ጠቦት ያርዳል፤ ከበደል መባው ደም ላይ የተወሰነውን ወስዶ ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል።+ +26 ካህኑም ከዘይቱ የተወሰነውን በራሱ የግራ እጅ መዳፍ ላይ ያንቆረቁረዋል።+ +27 በግራ እጁ መዳፍ ላይ ካለው ዘይት የተወሰነውን በቀኝ እጁ ጣት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። +28 በእጁ መዳፍ ላይ ካለው ዘይት የተወሰነውን ወስዶ የበደል መባውን ደም በቀባበት ቦታ ላይ ማለትም ራሱን በሚያነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት እንዲሁም በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል። +29 ከዚያም በእጁ መዳፍ ላይ የቀረውን ዘይት ራሱን በሚያነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሰዋል፤ ይህን የሚያደርገው በይሖዋ ፊት እንዲያስተሰርይለት ነው። +30 “ካህኑም ሰውየው አቅሙ ፈቅዶ ካመጣቸው ዋኖሶች ወይም የርግብ ጫጩቶች መካከል አንዱን ያቀርባል፤+ +31 አቅሙ ፈቅዶ ካመጣቸውም መካከል አንዱን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ+ አድርጎ ከእህል መባው ጋር ያቀርባል፤ ካህኑም ራሱን ለሚያነጻው ሰው በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል።+ +32 “የሥጋ ደዌ የነበረበትን ሆኖም መንጻቱን ለማረጋገጥ የሚያስፈልገውን ነገር ለማቅረብ አቅሙ የማይፈቅድለትን ሰው በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው።” +33 ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +34 “ርስት አድርጌ ወደምሰጣችሁ+ ወደ ከነአን ምድር+ በምትገቡበት ጊዜ በምድራችሁ ውስጥ የሚገኝን አንድ ቤት በደዌ ብበክለው+ +35 የቤቱ ባለቤት ወደ ካህኑ መጥቶ ‘አንድ የሚበክል ነገር ቤቴ ውስጥ ታይቷል’ በማለት ይንገረው። +36 ካህኑም ቤቱ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ርኩስ ነው እንዳይል የሚበክለውን ነገር ለመመርመር ወደ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ በሙሉ እንዲያወጡ ትእዛዝ ይሰጣል፤ ከዚያም ካህኑ ቤቱን ለመመርመር ወደ ውስጥ ይገባል። +37 እሱም ብክለቱ የታየበትን ቦታ ይመረምራል፤ በቤቱም ግድግዳ ላይ ወደ ቢጫነት ያደላ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ የተቦረቦረ ምልክት ቢታይና ይህም ከላይ ወደ ውስጥ ዘልቆ የገባ ከሆነ +38 ካህኑ ከቤቱ ውስጥ ወደ ደጃፉ ወጥቶ ቤቱን ለሰባት ቀን ያሽገዋል።+ +39 “ከዚያም ካህኑ በሰባተኛው ቀን ተመልሶ በመምጣት ቤቱን ይመረምረዋል። ቤቱን የበከለው ነገር በግድግዳው ላይ ተስፋፍቶ ከሆነ +40 ካህኑ ትእዛዝ ይሰጣል፤ የተበከሉትም ድንጋዮች ተሰርስረው መውጣትና ከከተማዋ ውጭ ወዳለ ርኩስ የሆነ ስፍራ መጣል አለባቸው። +41 ከዚያም ቤቱ ከውስጥ በኩል በደንብ እንዲፈቀፈቅ ያደርጋል፤ ተፈቅፍቆ የተነሳው ልስንና ምርጊትም ��ከተማዋ ውጭ በሚገኝ ርኩስ የሆነ ስፍራ ይደፋ። +42 ባወጧቸውም ድንጋዮች ቦታ ሌሎች ድንጋዮችን ያስገቡ፤ ቤቱም በአዲስ ምርጊት እንዲለሰን ያድርግ። +43 “ድንጋዮቹ ተሰርስረው ከወጡና ቤቱ ተፈቅፍቆ ዳግመኛ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ እንደገና ተመልሶ በቤቱ ላይ ከታየ +44 ካህኑ ገብቶ ይመረምረዋል። ብክለቱ በቤቱ ውስጥ ተስፋፍቶ ከሆነ ይህ በቤቱ ላይ የወጣ አደገኛ ደዌ+ ነው። ቤቱ ርኩስ ነው። +45 ቤቱ ይኸውም ድንጋዮቹ፣ እንጨቶቹ፣ ልስኑና ምርጊቱ እንዲፈርስ ያደርጋል፤ ከከተማዋ ውጭ በሚገኝ ርኩስ የሆነ ስፍራም እንዲጣል ያደርጋል።+ +46 ሆኖም ቤቱ ታሽጎ+ በነበረበት በየትኛውም ቀን ወደዚያ ቤት የገባ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤+ +47 እዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ እንዲሁም እዚያ ቤት ውስጥ የበላ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል። +48 “ይሁንና ካህኑ መጥቶ ሲያየው ቤቱ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ በቤቱ ውስጥ ካልተስፋፋ ቤቱ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል፤ ምክንያቱም ብክለቱ ጠፍቷል። +49 ቤቱንም ከርኩሰት* ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ ይወስዳል።+ +50 አንደኛዋንም ወፍ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ውስጥ ያርዳታል። +51 ከዚያም የአርዘ ሊባኖስ እንጨቱን፣ ሂሶጱን፣ ደማቁን ቀይ ማግና በሕይወት ያለችውን ወፍ ወስዶ በታረደችው ወፍ ደምና ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ ውስጥ ይነክራቸዋል፤ ወደ ቤቱም ሰባት ጊዜ ይርጨው።+ +52 ቤቱንም በወፏ ደም፣ ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ፣ በሕይወት ባለችው ወፍ፣ በአርዘ ሊባኖስ እንጨቱ፣ በሂሶጱና በደማቁ ቀይ ማግ ከርኩሰት* ያነጻዋል። +53 በሕይወት ያለችውንም ወፍ ከከተማዋ ውጭ ወደ ሜዳ ይለቃታል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል። +54 “ከማንኛውም ዓይነት የሥጋ ደዌ፣ በራስ ቆዳ ወይም በጢም ላይ ከሚወጣ ቁስል፣+ +55 በልብስ+ ወይም በቤት+ ላይ ከሚወጣ ደዌ፣ +56 ከእባጭ፣ ከእከክና ከቋቁቻ+ ጋር በተያያዘ +57 አንድ ነገር ርኩስ ወይም ንጹሕ መሆኑን ለመወሰን የሚያገለግለው ሕግ ይህ ነው።+ የሥጋ ደዌን በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው።”+ +9 በስምንተኛውም ቀን+ ሙሴ አሮንን፣ ወንዶች ልጆቹንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራ። +2 አሮንንም እንዲህ አለው፦ “ለኃጢአት መባ+ አንድ ጥጃ፣ ለሚቃጠል መባ ደግሞ አንድ አውራ በግ ለራስህ ውሰድ፤ እንከን የሌለባቸው ይሁኑ፤ በይሖዋም ፊት አቅርባቸው። +3 እስራኤላውያንን ግን እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘ለኃጢአት መባ አንድ ተባዕት ፍየል፣ ለሚቃጠል መባ ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸውና እንከን የሌለባቸው አንድ ጥጃና አንድ የበግ ጠቦት ውሰዱ፤ +4 የኅብረት መሥዋዕት+ ሆነው በይሖዋ ፊት እንዲሠዉም አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ውሰዱ፤ እንዲሁም በዘይት የተለወሰ የእህል መባ+ አቅርቡ፤ ምክንያቱም ይሖዋ ዛሬ ለእናንተ ይገለጣል።’”+ +5 ስለዚህ ሙሴ ያዘዛቸውን ነገሮች በሙሉ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ፊት አመጡ። ከዚያም መላው ማኅበረሰብ መጥቶ በይሖዋ ፊት ቆመ። +6 ሙሴም “የይሖዋ ክብር ይገለጥላችሁ+ ዘንድ ይሖዋ እንድታደርጉት ያዘዛችሁ ነገር ይህ ነው” አለ። +7 ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአት መባህንና+ የሚቃጠል መባህን አቅርብ፤ ለራስህና ለቤትህም አስተሰርይ፤+ ይሖዋ ባዘዘውም መሠረት የሕዝቡን መባ አቅርብ፤+ እንዲሁም ለእነሱ አስተሰርይ።”+ +8 አሮንም ወዲያው ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ የኃጢአት መባ ሆኖ የሚቀርበውን ጥጃ አረደ።+ +9 ከዚያም ወንዶች ልጆቹ ደሙን አቀረቡለት፤+ እሱም ጣቱን ደሙ ውስጥ በመንከር የመሠዊያውን ���ንዶች ቀባ፤ የቀረውንም ደም በመሠዊያው ሥር አፈሰሰው።+ +10 ይሖዋ ሙሴን ባዘዘውም መሠረት ከኃጢአት መባው ላይ ስቡን፣ ኩላሊቶቹንና በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ ወስዶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ።+ +11 ሥጋውንና ቆዳውንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለው።+ +12 ከዚያም የሚቃጠል መባ ሆኖ የሚቀርበውን እንስሳ አረደው፤ ወንዶች ልጆቹም ደሙን ሰጡት፤ እሱም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው።+ +13 እነሱም የሚቃጠለውን መባ ብልቶች ከነጭንቅላቱ ሰጡት፤ እሱም በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ። +14 በተጨማሪም ሆድ ዕቃውንና እግሮቹን አጠባቸው፤ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይም እንዲጨሱ አደረገ። +15 በመቀጠልም የሕዝቡን መባ አቀረበ፤ ለሕዝቡ የኃጢአት መባ ሆኖ የሚቀርበውን ፍየል ወስዶ አረደው፤ እንደ መጀመሪያው ሁሉ በዚህኛውም የኃጢአት መባ አቀረበ። +16 ከዚያም የሚቃጠለውን መባ አቀረበ፤ በተለመደውም አሠራር መሠረት አቀረበው።+ +17 በመቀጠልም የእህል መባውን+ አቀረበ፤ ከላዩ ላይም እፍኝ ሙሉ አንስቶ ጠዋት ላይ ከሚቀርበው የሚቃጠል መባ በተጨማሪ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ።+ +18 በኋላም ለሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑትን በሬውንና አውራውን በግ አረዳቸው። ወንዶች ልጆቹም ደሙን ሰጡት፤ እሱም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው።+ +19 ከዚያም የበሬውን ስቦች፣+ የአውራውን በግ ላት፣ ሆድ ዕቃውን የሸፈነውን ስብ፣ ኩላሊቶቹንና የጉበቱን ሞራ+ +20 ማለትም ስቡን ሁሉ በፍርምባዎቹ ላይ አደረጉ፤ ስቡም ሁሉ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ።+ +21 ሆኖም አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ እግሩን ልክ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እንደሚወዘወዝ መባ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ወዘወዛቸው።+ +22 ከዚያም አሮን እጆቹን ወደ ሕዝቡ በማንሳት ባረካቸው፤+ የኃጢአት መባውን፣ የሚቃጠል መባውንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን ካቀረበ በኋላ ወረደ። +23 በመጨረሻም ሙሴና አሮን ወደ መገናኛ ድንኳኑ ገቡ፤ ከዚያም ወጥተው ሕዝቡን ባረኩ።+ በዚህ ጊዜ የይሖዋ ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ፤+ +24 እሳትም ከይሖዋ ፊት ወጥቶ+ በመሠዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠል መባና ስብ በላ። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያይ እልል አለ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ።+ +27 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘አንድ ሰው የአንድን ግለሰብ* የተተመነ ዋጋ ለይሖዋ ለማቅረብ ልዩ ስእለት ቢሳል+ +3 ከ20 ዓመት እስከ 60 ዓመት ድረስ ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኝ ወንድ የሚተመነው ዋጋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* 50 የብር ሰቅል* ይሆናል። +4 ሴት ከሆነች ግን የሚተመንላት ዋጋ 30 ሰቅል ይሆናል። +5 ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወንድ ከሆነ የሚተመንለት ዋጋ 20 ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች ደግሞ 10 ሰቅል ይሆናል። +6 ከአንድ ወር እስከ አምስት ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወንድ ከሆነ የሚተመንለት ዋጋ አምስት የብር ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች ደግሞ ሦስት የብር ሰቅል ይሆናል። +7 “‘ዕድሜው ከ60 ዓመት በላይ ለሆነ ወንድ ደግሞ የሚተመንለት ዋጋ 15 ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች 10 ሰቅል ይሆናል። +8 ሆኖም ሰውየው በጣም ድሃ ቢሆንና የተተመነውን ዋጋ መስጠት ባይችል+ ግለሰቡ ካህኑ ፊት ይቆማል፤ ካህኑም ለሰውየው ዋጋ ይተምንለታል። ካህኑ ስእለት የተሳለውን ሰው አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ለሰውየው ዋጋ ይተምንለታል።+ +9 “‘ስእለቱ ለይሖዋ መባ ሆኖ መቅረብ የሚችል እንስሳ ከሆነ ለይሖዋ የሚሰጠው ማንኛውም ነገር የተቀደሰ ይሆናል። +10 እንስሳውን በሌላ መተካትም ሆነ መጥፎውን በጥሩ፣ ጥ���ውን በመጥፎ መለወጥ አይችልም። እንስሳውን በሌላ እንስሳ መለወጥ ካለበት ግን የመጀመሪያው እንስሳም ሆነ ተለዋጭ ሆኖ የቀረበው እንስሳ የተቀደሱ ይሆናሉ። +11 ሰውየው ያቀረበው እንስሳ ለይሖዋ መባ ሆኖ ሊቀርብ የማይችል ርኩስ እንስሳ+ ከሆነ እንስሳውን ካህኑ ፊት ያቁመው። +12 ካህኑ እንስሳው ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ ይተምንለት። ካህኑ የተመነውም ዋጋ ይጸናል። +13 ሆኖም ሰውየው እንስሳውን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት።+ +14 “‘አንድ ሰው ቤቱን ቅዱስ አድርጎ ለይሖዋ ቢሰጥ ካህኑ ቤቱ ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ ይተምንለት። የቤቱ ዋጋ ካህኑ የተመነው ዋጋ ይሆናል።+ +15 ሆኖም ቤቱን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ሰው ቤቱን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ የገንዘቡን አንድ አምስተኛ ጨምሮ መስጠት አለበት፤ ቤቱም የእሱ ይሆናል። +16 “‘አንድ ሰው ርስት አድርጎ ከያዘው እርሻ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ ቅዱስ አድርጎ ቢሰጥ ዋጋው መተመን ያለበት የሚዘራበትን ዘር መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል፤ ለአንድ ሆሜር* የገብስ ዘር 50 የብር ሰቅል ይሆናል። +17 ሰውየው እርሻውን ከኢዮቤልዩ ዓመት+ አንስቶ ቅዱስ አድርጎ ከሰጠ የተተመነለት ዋጋ ይጸናል። +18 ሰውየው እርሻውን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ኢዮቤልዩ ካለፈ በኋላ ከሆነ ካህኑ እስከ ቀጣዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የቀሩትን ዓመታት ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋውን ያስላለት፤ ከተተመነውም ዋጋ ላይ መቀነስ አለበት።+ +19 ሆኖም እርሻውን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ሰው እርሻውን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ የገንዘቡን አንድ አምስተኛ ጨምሮ መስጠት አለበት፤ ከዚያም እርሻው የእሱ ንብረት እንደሆነ ይጸናል። +20 ሰውየው እርሻውን መልሶ ባይገዛውና እርሻው ለሌላ ሰው ቢሸጥ ሰውየው መልሶ ሊገዛው አይችልም። +21 እርሻው በኢዮቤልዩ ነፃ በሚለቀቅበት ጊዜ ለይሖዋ እንደተሰጠ እርሻ ተቆጥሮ ለእሱ የተቀደሰ ይሆናል። የካህናቱም ንብረት ይሆናል።+ +22 “‘አንድ ሰው በውርስ ያገኘው ንብረት ክፍል ያልሆነውን በገንዘቡ የገዛውን እርሻ+ ለይሖዋ ቅዱስ አድርጎ ቢሰጥ +23 ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የሚያወጣውን ዋጋ ይተምንለት፤ እሱም የተተመነውን ዋጋ በዚያው ቀን ይስጥ።+ ይህ ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። +24 በኢዮቤልዩ ዓመት እርሻው ለሻጩ ይኸውም ለመሬቱ ባለቤት ይመለሳል።+ +25 “‘እያንዳንዱ ዋጋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት መተመን አለበት። አንዱ ሰቅል 20 ጌራ* መሆን ይኖርበታል። +26 “‘ይሁንና ማንም ሰው ከእንስሳት መካከል በኩር የሆነውን ቅዱስ አድርጎ መስጠት የለበትም፤ ምክንያቱም በኩሩ የይሖዋ ነው።+ በሬም ሆነ በግ ቀድሞውንም የይሖዋ ነው።+ +27 በኩሩ ርኩስ ከሆኑት እንስሳት መካከል ከሆነና በተተመነለት ዋጋ መሠረት ከዋጀው በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት።+ ሰውየው መልሶ የማይገዛው ከሆነ ግን በተተመነው ዋጋ መሠረት ይሸጥ። +28 “‘አንድ ሰው የራሱ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ ያለምንም ገደብ ለይሖዋ የሰጠው ማንኛውም ተለይቶ የተሰጠ ነገር ይኸውም የእሱ ንብረት የሆነ ሰውም ሆነ እንስሳ አሊያም እርሻ ሊሸጥም ሆነ ተመልሶ ሊገዛ አይችልም። ተለይቶ የተሰጠ ማንኛውም ነገር ለይሖዋ እጅግ የተቀደሰ ነው።+ +29 በተጨማሪም እንዲጠፋ የተበየነበት ማንኛውም ለጥፋት የተለየ ሰው አይዋጅም፤+ ከዚህ ይልቅ መገደል አለበት።+ +30 “‘እርሻው ከሚሰጠው ምርትም ሆነ ዛፉ ከሚያፈራው ፍሬ ውስጥ የምድሩ አንድ አሥረኛ*+ ሁሉ የይሖዋ ነው። ይ��� ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። +31 አንድ ሰው አንድ አሥረኛ አድርጎ የሰጠውን ማንኛውንም ነገር መልሶ መግዛት ቢፈልግ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት። +32 ከከብቶቹና ከመንጋው መካከል አንድ አሥረኛው ማለትም በበትሩ ሥር ከሚያልፉት መካከል አሥረኛው እንስሳ* ለይሖዋ የተቀደሰ መሆን አለበት። +33 ከዚህ በኋላ እንስሳው ጥሩ ይሁን መጥፎ መመርመር የለበትም፤ በሌላ ሊለውጠውም አይገባም። እንስሳውን በሌላ መለወጥ ካሰበ ግን የመጀመሪያው እንስሳም ሆነ ተለዋጭ ሆኖ የቀረበው እንስሳ የተቀደሱ ይሆናሉ።+ ተመልሶ ሊገዛ አይችልም።’” +34 ይሖዋ በሲና ተራራ+ ላይ በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ትእዛዛት እነዚህ ናቸው። +13 ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +2 “አንድ ሰው በቆዳው ላይ እብጠት፣ እከክ ወይም ቋቁቻ ቢወጣበትና ወደ ሥጋ ደዌነት*+ ቢለወጥበት ወደ ካህኑ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ወንዶች ልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።+ +3 ካህኑም በቆዳው ላይ ያለውን ቁስል ይመረምራል። ቁስሉ ባለበት ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠና ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ ይህ የሥጋ ደዌ ነው። ካህኑ ቁስሉን ከመረመረ በኋላ ግለሰቡ ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። +4 ሆኖም በቆዳው ላይ ያለው ቋቁቻ ነጭ ከሆነና ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ እንዲሁም በዚያ ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ካልተለወጠ ካህኑ ቁስል የወጣበትን ሰው ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል።+ +5 ከዚያም በሰባተኛው ቀን ካህኑ ሰውየውን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ ባለበት ከቆመና በቆዳው ላይ ካልተስፋፋ ካህኑ ሰውየውን ለተጨማሪ ሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። +6 “ካህኑም በሰባተኛው ቀን እንደገና ሰውየውን ይመርምረው፤ ቁስሉ ከከሰመና በቆዳው ላይ ካልተስፋፋ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል፤+ ይህ እከክ ነው። ከዚያም ሰውየው ልብሶቹን ያጥባል፤ ንጹሕም ይሆናል። +7 ሆኖም ሰውየው መንጻቱን ለማረጋገጥ ካህኑ ፊት ከቀረበ በኋላ እከኩ* በቆዳው ላይ እየተስፋፋ ከሄደ እንደገና ካህኑ ፊት ይቀርባል። +8 ካህኑም ይመረምረዋል፤ እከኩ በቆዳው ላይ ተስፋፍቶ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ የሥጋ ደዌ ነው።+ +9 “አንድ ሰው የሥጋ ደዌ ቢይዘው ወደ ካህኑ እንዲቀርብ ይደረግ፤ +10 ካህኑም ይመረምረዋል።+ በቆዳው ላይ ነጭ እብጠት ካለና በዚያ ቦታ ላይ ያለውን ፀጉር ወደ ነጭነት ከለወጠው እንዲሁም በእብጠቱ ላይ አፉን የከፈተ ቁስል+ ካለ +11 ይህ በቆዳው ላይ የወጣ ሥር የሰደደ የሥጋ ደዌ ነው፤ ካህኑም ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ሰውየው ርኩስ ስለሆነም ለተወሰነ ጊዜ ተገልሎ እንዲቆይ+ ማድረግ አያስፈልገውም። +12 የሥጋ ደዌው በቆዳው ሁሉ ላይ ቢወጣና የሥጋ ደዌው ካህኑ ሊያየው እስከሚችለው ድረስ ግለሰቡን ከራሱ አንስቶ እስከ እግሮቹ ድረስ ቢያለብሰው +13 እንዲሁም ካህኑ ሲመረምረው የሥጋ ደዌው ቆዳውን ሁሉ አልብሶት ቢያይ ቁስሉ የወጣበት ግለሰብ ንጹሕ* መሆኑን ያስታውቃል። ቆዳው ሙሉ በሙሉ ወደ ነጭነት ተለውጧል፤ ሰውየውም ንጹሕ ነው። +14 ሆኖም በቆዳው ላይ አፉን የከፈተ ቁስል በወጣበት በማንኛውም ጊዜ ሰውየው ርኩስ ይሆናል። +15 ካህኑ አፉን የከፈተ ቁስል ካየ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል።+ አፉን የከፈተው ቁስል ርኩስ ነው። ይህ የሥጋ ደዌ ነው።+ +16 ሆኖም አፉን የከፈተው ቁስል እንደገና ወደ ነጭነት ከተለወጠ ሰውየው ወደ ካህኑ ይመጣል። +17 ካህኑም ይመረምረዋል፤+ ቁስሉ ወደ ነጭነት ከተለወጠ ካህኑ ቁስሉ የወጣበት ግለሰብ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። ሰውየው ንጹሕ ነው። +18 “አንድ ሰው በቆዳው ላይ እባጭ ቢወጣበትና ቢድን +19 ሆኖም እባጩ በነበረበት ቦታ ላይ ነጭ እብጠት ወይም ነጣ ያለ ቀይ ቋቁቻ ቢወጣ ሰውየው ራሱን ለካህን ያሳይ። +20 ካህኑም ቁስሉን ይመረምረዋል፤+ ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነና በዚያ ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ በእባጩ ላይ የወጣ የሥጋ ደዌ ነው። +21 ይሁንና ካህኑ ቁስሉን ሲመረምረው በላዩ ላይ ነጭ ፀጉር ከሌለና ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ እንዲሁም እየከሰመ ከሆነ ካህኑ ሰውየውን ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል።+ +22 ቁስሉ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ ደዌ ነው። +23 ይሁን እንጂ ቋቁቻው ባለበት ከቆመና ካልተስፋፋ ይህ እባጩ ያስከተለው ቁስል ነው፤ ካህኑም ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል።+ +24 “ወይም አንድ ሰው እሳት አቃጥሎት በሰውነቱ ቆዳ ላይ ጠባሳ ቢተውና ጠባሳው ላይ ያለው ያልሻረ ቁስል ነጣ ያለ ቀይ ወይም ነጭ ቋቁቻ ቢሆን +25 ካህኑ ቁስሉን ይመረምረዋል። በቋቁቻው ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠና ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ ይህ በጠባሳው ላይ የወጣ የሥጋ ደዌ ነው፤ ካህኑም ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ የሥጋ ደዌ ነው። +26 ይሁንና ካህኑ ሲመረምረው በቋቁቻው ላይ ነጭ ፀጉር ከሌለና ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ እንዲሁም እየከሰመ ከሆነ ካህኑ ሰውየውን ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል።+ +27 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ሰውየውን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ የሥጋ ደዌ ነው። +28 ይሁንና ቋቁቻው ባለበት ከቆመና በቆዳው ላይ ካልተስፋፋ እንዲሁም ከከሰመ ይህ ጠባሳው ያስከተለው እብጠት ነው፤ ይህ የጠባሳው ቁስል ስለሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። +29 “በአንድ ወንድ ወይም በአንዲት ሴት ራስ ወይም አገጭ ላይ ቁስል ቢወጣ +30 ካህኑ ቁስሉን ይመረምረዋል።+ ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ እንዲሁም በዚያ ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ቢጫ ከሆነና ከሳሳ ካህኑ ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል፤ ይህ በራስ ቆዳ ወይም በጢም ላይ የሚወጣ ቁስል ነው። ይህ የራስ ወይም የአገጭ የሥጋ ደዌ ነው። +31 ሆኖም ካህኑ ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ አለመሆኑንና በዚያ ቦታ ላይ ጥቁር ፀጉር አለመኖሩን ካየ ቁስሉ የወጣበትን ሰው ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያድርገው።+ +32 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቁስሉን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ ካልተስፋፋና በዚያ ቦታ ላይ ቢጫ ፀጉር ካልወጣ እንዲሁም ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ +33 ሰውየው ፀጉሩን ይላጭ፤ ቁስሉ ያለበትን ቦታ ግን አይላጨውም። ከዚያም ካህኑ ቁስሉ የወጣበትን ሰው ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። +34 “ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቁስሉ ያለበትን ቦታ እንደገና ይመረምረዋል፤ ቁስሉ በቆዳው ላይ ካልተስፋፋና ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ ሰውየውም ልብሶቹን ይጠብ፤ ንጹሕም ይሁን። +35 ሆኖም ሰውየው ከነጻ በኋላ ቁስሉ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ መሆኑ በግልጽ ከታየ +36 ካህኑ ይመረምረዋል፤ ቁስሉ በቆዳው ላይ ከተስፋፋ ካህኑ ቢጫ ፀጉር መኖር አለመኖሩን ማየት አያስፈልገውም፤ ሰውየው ርኩስ ነው። +37 ሆኖም ካህኑ ሲመረምረው ቁስሉ ካልተስፋፋና በዚያ ቦታ ጥቁር ፀጉር ከበቀለ ቁስሉ ድኗል ማለት ነው። ሰውየው ንጹሕ ነው፤ ካህኑም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል።+ +38 “አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በቆዳቸው ላይ ቋቁቻ ቢወጣና ቋቁቻው ደግሞ ነጭ ቢሆን +39 ካህኑ ይመረምራቸዋል።+ በቆዳው ላይ የወጣው ቋቁቻ ደብዘዝ ያለ ነጭ ከሆነ ይህ ቆዳው ላይ የወጣ ጉዳት የሌለው ሽፍታ ነው። ሰውየው ንጹሕ ነው። +40 “አንድ ወንድ ራሱ ቢመለጥና ራሰ በራ ቢሆን ሰውየው ንጹሕ ነው። +41 ሰውየው ከፊት በኩል ቢመለጥና ራሰ በራ ቢሆን ንጹሕ ነው። +42 ሆኖም በራሱ ወይም በግንባሩ ላይ ባለው በራ ላይ ቀላ ያለ ነጭ ቁስል ቢወጣበት ይህ በራሱ ወይም በግንባሩ ላይ የወጣ ሥጋ ደዌ ነው። +43 ካህኑም ሰውየውን ይመረምረዋል፤ በአናቱ ወይም በግንባሩ ላይ ባለው በራ ላይ የወጣው ቁስል ያስከተለው እብጠት ቀላ ያለ ነጭ ከሆነና በቆዳው ላይ ሲታይ የሥጋ ደዌ የሚመስል ከሆነ +44 ሰውየው የሥጋ ደዌ በሽተኛ ነው። ርኩስ ነው፤ በራሱም ላይ ባለው ደዌ የተነሳ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ። +45 የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው ልብሶቹ የተቀዳደዱ ይሁኑ፤ ፀጉሩም ይንጨብረር፤ አፍንጫው ሥር እስካለው ጢም ድረስ ተሸፋፍኖ ‘ርኩስ ነኝ፣ ርኩስ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ። +46 ሰውየው ደዌው በላዩ ላይ ባለበት ጊዜ ሁሉ ርኩስ ይሆናል። ርኩስ ስለሆነም ከሰዎች ተገልሎ መኖር አለበት። መኖሪያውም ከሰፈሩ ውጭ ይሆናል።+ +47 “ደዌው ከሱፍም ሆነ ከበፍታ የተሠራን ልብስ ቢበክል +48 ወይም የበፍታውንም ሆነ የሱፉን ድር ወይም ማግ አሊያም ቁርበትን ወይም ደግሞ ከቆዳ የተሠራን ማንኛውንም ነገር ቢበክል +49 እንዲሁም ደዌው ያስከተለው ወደ ቢጫነት ያደላ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ ምልክት ልብሱን፣ ቆዳውን፣ ድሩን፣ ማጉን ወይም ደግሞ ከቆዳ የተሠራውን የትኛውንም ዕቃ ቢበክል ይህ በደዌ ምክንያት የተከሰተ ብክለት ነው፤ ካህኑ እንዲያየው መደረግ አለበት። +50 ካህኑም ደዌውን ይመረምረዋል፤ ደዌው ያለበትም ነገር ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቀመጥ ያድርግ።+ +51 በሰባተኛው ቀን ደዌውን ሲመረምረው ደዌው በልብሱ፣ በድሩ፣ በማጉ ወይም በቆዳው ላይ (ቆዳው ለማንኛውም ዓይነት አገልግሎት የሚውል ይሁን) ተስፋፍቶ ቢገኝ ደዌው አደገኛ ደዌ ነው፤ ዕቃውም ርኩስ ነው።+ +52 እሱም ደዌው ያለበትን ልብስ ወይም የሱፍም ሆነ የበፍታ ድር ወይም ማግ አሊያም ደግሞ ከቆዳ የተሠራ ማንኛውም ዕቃ ያቃጥል፤ ምክንያቱም ይህ አደገኛ ደዌ ነው። በእሳት መቃጠል ይኖርበታል። +53 “ሆኖም ካህኑ ሲመረምረው ደዌው በልብሱ ወይም በድሩ አሊያም በማጉ ወይም ደግሞ ከቆዳ በተሠራው በማንኛውም ዕቃ ላይ ካልተስፋፋ +54 ካህኑ ደዌው ያለበትን ነገር እንዲያጥቡት ያዛል፤ ከዚያም እንደገና ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቀመጥ ያደርጋል። +55 የተበከለው ዕቃ በደንብ ከታጠበ በኋላ ካህኑ ይመረምረዋል። ደዌው ባይስፋፋም እንኳ ብክለቱ መልኩን ካልቀየረ ዕቃው ርኩስ ነው። ዕቃው ከውስጡ ወይም ከውጭው ስለተበላ በእሳት አቃጥለው። +56 “ሆኖም ዕቃው በደንብ ከታጠበ በኋላ ካህኑ ሲመረምረው የተበከለው ክፍል ከደበዘዘ ያን ቦታ ከልብሱ ወይም ከቆዳው አሊያም ከድሩ ወይም ደግሞ ከማጉ ላይ ቀዶ ያወጣዋል። +57 ይሁንና ደዌው በልብሱ ወይም በድሩ አሊያም በማጉ ወይም ደግሞ ከቆዳ በተሠራው በማንኛውም ዕቃ ላይ በሌላ ቦታ አሁንም ከታየ ደዌው እየተስፋፋ ነው፤ ስለዚህ በደዌው የተበከለውን ማንኛውንም ዕቃ በእሳት አቃጥለው።+ +58 ሆኖም በልብሱ ወይም በድሩ አሊያም በማጉ ወይም ደግሞ ከቆዳ በተሠራው በማንኛውም ዕቃ ላይ የተከሰተው ብክለት ስታጥበው ከለቀቀ ዕቃው ለሁለተኛ ጊዜ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል። +59 “ከሱፍ ወይም ከበፍታ በተሠራ ልብስ አሊያም በድር ወይም በማግ አሊያም ደግሞ ከቆዳ በተሠራ በማንኛውም ዕቃ ላይ የወጣን ደዌ በተመለከተ ዕቃው ንጹሕ ነው ብሎ ለማስታወቅም ሆነ ርኩስ ነው ለማለት ሕጉ ይህ ነው።” +5 “‘አንድ ሰው* ሰዎች የምሥክርነት ቃል እንዲሰጡ ጥሪ+ ���የቀረበ መሆኑን ቢሰማና* እሱ መመሥከር እየቻለ ወይም ደግሞ ጉዳዩን አይቶ አሊያም አውቆ ሳለ ሳይናገር ቢቀር በሠራው ጥፋት ይጠየቅበታል። +2 “‘ወይም አንድ ሰው* ርኩስ የሆነን ማንኛውንም ነገር ይኸውም ርኩስ የሆነን የዱር አውሬ ወይም ርኩስ የሆነን የቤት እንስሳ አሊያም ርኩስ የሆነን የሚርመሰመስ ፍጥረት በድን ቢነካ፣+ ይህን ያደረገው ባለማወቅ ቢሆንም እንኳ ይህ ሰው ርኩስ ነው፤ በደለኛም ይሆናል። +3 ወይም አንድ ሰው ባለማወቅ የሰውን ርኩሰት+ ይኸውም እንዲረክስ ሊያደርገው የሚችለውን ማንኛውንም ርኩስ ነገር ቢነካና በኋላም ይህን ቢያውቅ በደለኛ ይሆናል። +4 “‘አሊያም ደግሞ አንድ ሰው* ነገሩ ምንም ሆነ ምን ክፉ ወይም መልካም ለማድረግ በችኮላ ቢምልና ይህን ያደረገው ባለማወቅ ቢሆን ሆኖም የማለው በችኮላ መሆኑን በኋላ ላይ ቢገነዘብ በደለኛ ይሆናል።*+ +5 “‘ከእነዚህ ነገሮች በአንዱ በደለኛ ሆኖ ቢገኝ በምን መንገድ ኃጢአት እንደሠራ መናዘዝ+ አለበት። +6 ለሠራው ኃጢአት የበደል መባ+ ማለትም ከመንጋው መካከል እንስት የበግ ጠቦት ወይም እንስት የፍየል ግልገል የኃጢአት መባ አድርጎ ለይሖዋ ያመጣል። ከዚያም ካህኑ ኃጢአቱን ያስተሰርይለታል። +7 “‘በግ ለማምጣት አቅሙ የማይፈቅድለት ከሆነ ግን ለሠራው ኃጢአት የበደል መባ እንዲሆኑ ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ለይሖዋ ያምጣ፤+ አንዱ ለኃጢአት መባ ሌላኛው ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይሆናል።+ +8 ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤ ካህኑም በቅድሚያ ለኃጢአት መባ የሚሆነውን ያቀርባል፤ አንገቱን ሙሉ በሙሉ ሳይቆርጥ ከፊት በኩል አንገቱን በመቦጨቅ ያቀርበዋል። +9 ከኃጢአት መባው ደም ላይ የተወሰነውን በመሠዊያው ጎን ላይ ይረጨዋል፤ የተረፈው ደም ግን በመሠዊያው ሥር ይንጠፈጠፋል።+ ይህ የኃጢአት መባ ነው። +10 ሌላኛውን ደግሞ በተለመደው አሠራር መሠረት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤+ ካህኑም ለሠራው ኃጢአት ማስተሰረያ ያቀርብለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።+ +11 “‘ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ለማምጣት አቅሙ የማይፈቅድለት ከሆነ ደግሞ ለሠራው ኃጢአት፣ የኃጢአት መባ እንዲሆን አንድ አሥረኛ ኢፍ*+ የላመ ዱቄት መባ አድርጎ ያምጣ። የኃጢአት መባ ስለሆነ ዘይት አይጨምርበት ወይም ነጭ ዕጣን አያድርግበት። +12 ወደ ካህኑም ያመጣዋል፤ ካህኑም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው ለማድረግ ከላዩ ላይ አንድ እፍኝ አንስቶ በመሠዊያው ላይ ባሉት ለይሖዋ በእሳት በሚቀርቡት መባዎች ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። ይህ የኃጢአት መባ ነው። +13 ካህኑም ሰውየው ከእነዚህ ኃጢአቶች ውስጥ ለሠራው ለየትኛውም ኃጢአት ማስተሰረያ ያቀርብለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።+ እንደ እህል መባው+ ሁሉ ከመባው የተረፈውም የካህኑ ይሆናል።’”+ +14 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +15 “አንድ ሰው* ለይሖዋ በተቀደሱት ነገሮች ላይ ባለማወቅ ኃጢአት በመሥራት ታማኝነቱን ቢያጎድል+ ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበትን አውራ በግ የበደል መባ አድርጎ ለይሖዋ ያመጣል፤+ ዋጋው በብር ሰቅል* የሚተመነው እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* መሠረት ነው።+ +16 በቅዱሱ ስፍራ ላይ ለፈጸመው ኃጢአት ካሳ ይከፍላል፤ የዋጋውንም አንድ አምስተኛ ይጨምርበታል።+ ካህኑ ለበደል መባ በቀረበው አውራ በግ አማካኝነት እንዲያስተሰርይለትም ለካህኑ ይሰጠዋል፤+ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።+ +17 “አንድ ሰው* ይሖዋ እንዳይደረጉ ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ኃጢአት ቢሠራ፣ እንዲህ ያደረገው ባለማወቅ ቢሆንም እንኳ በደለኛ ይሆናል፤ በሠራውም ጥፋት ይጠየቅበታል።+ +18 የበደል መባ እንዲሆንም የተተመነለትን ዋጋ ያህል የሚያወጣ እንከን የሌለበት አውራ በግ ከመንጋው መካከል ወስዶ ለካህኑ ያምጣ።+ ከዚያም ካህኑ፣ ሰውየው ባለማወቅ ለፈጸመው ስህተት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። +19 ይህ የበደል መባ ነው። በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለፈጸመ በእርግጥ በደለኛ ይሆናል።” +21 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለካህናቱ ማለትም ለአሮን ወንዶች ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ማንም ሰው ከሕዝቦቹ መካከል ለሞተ ሰው* ራሱን አያርክስ።*+ +2 ይሁንና ለቅርብ የሥጋ ዘመዱ ይኸውም ለእናቱ፣ ለአባቱ፣ ለወንድ ልጁ፣ ለሴት ልጁ፣ ለወንድሙ እንዲህ ማድረግ ይችላል፤ +3 እንዲሁም ድንግል ለሆነች፣ ለምትቀርበውና ላላገባች እህቱ ሲል ራሱን ማርከስ ይችላል። +4 ከሕዝቡ መካከል ባል ላገባች ሴት ሲል ራሱን ማርከስና ማዋረድ የለበትም። +5 ራሳቸውን መላጨት+ ወይም የጢማቸውን ዳር ዳር መላጨት አሊያም ሰውነታቸውን መተልተል የለባቸውም።+ +6 የአምላካቸው ምግብ* የሆኑትን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች የሚያቀርቡት እነሱ ስለሆኑ ለአምላካቸው ቅዱሳን መሆንና+ የአምላካቸውን ስም ከማርከስ መራቅ አለባቸው፤+ ቅዱሳን መሆን ይኖርባቸዋል።+ +7 ዝሙት አዳሪ የሆነችን ይኸውም የረከሰችን ሴት ወይም ከባሏ የተፋታችን ሴት አያግቡ፤+ ምክንያቱም ካህኑ ለአምላኩ ቅዱስ ነው። +8 የአምላክህን ምግብ የሚያቀርበው እሱ ስለሆነ ቀድሰው።+ እናንተን የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እሱም በአንተ ፊት ቅዱስ ሆኖ መገኘት አለበት።+ +9 “‘የአንድ ካህን ሴት ልጅ ዝሙት አዳሪ በመሆን ራሷን ብታረክስ አባቷን ታረክሳለች። ስለዚህ በእሳት መቃጠል አለባት።+ +10 “‘ከወንድሞቹ መካከል ሊቀ ካህናት በመሆን በራሱ ላይ የቅብዓት ዘይት የሚፈስበትና+ የክህነት ልብሶቹን እንዲለብስ+ የተሾመው* ካህን ፀጉሩን ማንጨብረር ወይም ልብሶቹን መቅደድ የለበትም።+ +11 ወደ ሞተ ሰው* አይጠጋ።+ ሌላው ቀርቶ ለአባቱ ወይም ለእናቱ ሲል ራሱን አያርክስ። +12 ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየው ምልክት ይኸውም የአምላኩ የቅብዓት ዘይት+ በላዩ ላይ ስላለ ከመቅደሱ መውጣትም ሆነ የአምላኩን መቅደስ ማርከስ የለበትም።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +13 “‘የሚያገባው ድንግል የሆነችን ሴት መሆን ይኖርበታል።+ +14 ባል የሞተባትን፣ ከባሏ የተፋታችን፣ የረከሰችን ወይም ዝሙት አዳሪ የሆነችን ሴት አያግባ፤ ሆኖም ከሕዝቡ መካከል ድንግል የሆነችውን ያግባ። +15 እሱን የምቀድሰው እኔ ይሖዋ ስለሆንኩ በሕዝቡ መካከል ዘሩን ማርከስ የለበትም።’”+ +16 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +17 “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘ከዘርህ መካከል በትውልዶቹ ሁሉ በሰውነቱ ላይ እንከን ያለበት ማንም ሰው የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ አይምጣ። +18 እንደሚከተሉት ያሉ እንከኖች ያሉበት ማንም ሰው መቅረብ የለበትም፦ ዓይነ ስውር ወይም አንካሳ አሊያም የፊቱ ገጽታ የተበላሸ* ወይም አንዱ እግሩ ወይም አንዱ እጁ የረዘመ +19 አሊያም እግሩ የተሰበረ ወይም እጁ የተሰበረ ሰው +20 አሊያም ጀርባው ላይ ጉብር ያለበት ወይም ድንክ የሆነ* አሊያም የዓይን ችግር ያለበት ወይም ችፌ የያዘው አሊያም ጭርት ያለበት ወይም የዘር ፍሬው የተጎዳ አይቅረብ።+ +21 ከካህኑ ከአሮን ዘር እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው በእሳት የሚቀርቡትን የይሖዋን መባዎች ለማቅረብ አይምጣ። ይህ ሰው እንከን ስላለበት የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ መምጣት አይችልም። +22 እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮችና+ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች+ የአምላኩን ምግብ መብላት ይችላል። +23 ሆኖም እንከን ስላለበት ወደ መጋረጃው+ አይቅረብ፤ ወደ መሠዊያውም+ አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው+ እኔ ይሖዋ ስለሆንኩ መቅደሴን+ አያርክስ።’” +24 ስለዚህ ሙሴ ይህን ለአሮን፣ ለወንዶች ልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ ነገራቸው። +15 ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብላችሁ ንገሯቸው፦ ‘አንድ ወንድ ከብልቱ* ፈሳሽ የሚወጣ ከሆነ ይህ ፈሳሽ ርኩስ ያደርገዋል።+ +3 ሰውየው በፈሳሹ የተነሳ ርኩስ ነው፤ ፈሳሹ ከብልቱ እየፈሰሰ ቢሆንም ወይም ብልቱን ቢዘጋው ሰውየው ርኩስ ነው። +4 “‘ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የተኛበት አልጋም ርኩስ ይሆናል፤ ይህ ሰው የተቀመጠበት ማንኛውም ነገርም ርኩስ ይሆናል። +5 የሰውየውን አልጋ የነካ ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ +6 እንዲሁም ፈሳሽ የሚወጣው ሰው ተቀምጦበት በነበረ ነገር ላይ የተቀመጠ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +7 ፈሳሽ የሚወጣውን ሰው፣ ሰውነት የነካ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +8 ፈሳሽ የሚወጣው ሰው ንጹሕ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ የተተፋበት ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +9 ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የተቀመጠበት ኮርቻ ርኩስ ይሆናል። +10 ይህ ሰው የተቀመጠበትን የትኛውንም ነገር የነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እነዚህን ነገሮች የያዘ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +11 ፈሳሽ የሚወጣው ሰው+ እጆቹን በውኃ ሳይታጠብ አንድን ሰው ቢነካ የተነካው ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +12 ፈሳሽ የሚወጣው ሰው የነካው የሸክላ ዕቃ ይሰበር፤ ማንኛውም የእንጨት ዕቃ ደግሞ በውኃ ይታጠብ።+ +13 “‘እንግዲህ ፈሳሹ ቢቆምና ሰውየው ከፈሳሹ ቢነጻ ንጹሕ ለመሆን ሰባት ቀን ይቁጠር፤ ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።+ +14 በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ይውሰድ፤+ እነዚህንም ይዞ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት በመቅረብ ለካህኑ ይስጥ። +15 ካህኑም አንዱን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም ስለ ፈሳሹ ለሰውየው በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል። +16 “‘አንድ ወንድ ዘር ቢፈሰው ገላውን በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ +17 የፈሰሰው ዘር የነካውን ማንኛውንም ዓይነት ልብስ ወይም ቁርበት በውኃ ማጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +18 “‘አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ቢተኛና ዘሩ ቢፈስ ገላቸውን በውኃ መታጠብ አለባቸው፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናሉ።+ +19 “‘አንዲት ሴት ከሰውነቷ ደም ቢፈሳት በወር አበባዋ የተነሳ ርኩስ እንደሆነች ለሰባት ቀን ትቀጥላለች፤+ እንዲሁም እሷን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ +20 በወር አበባዋ የተነሳ ርኩስ በሆነችባቸው ጊዜያት የተኛችበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም የተቀመጠችበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል።+ +21 አልጋዋን የነካ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +22 እሷ ተቀምጣበት የነበረውን የትኛውንም ነገር የነካ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +23 የተቀመጠችው አልጋ ላይም ይሁን ሌላ ነገር ላይ ሰውየው ያን መንካቱ እስከ ማታ ድረስ እንዲረክስ ያደርገዋል።+ +24 አንድ ወንድ ከእሷ ጋር ቢተኛና በወር አበባዋ ቢረክስ+ ሰውየው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤ የተኛበት አልጋም ርኩስ ይሆናል። +25 “‘አንዲት ሴት የወር አበባዋ ከሚመጣበት ከተለመደው ጊዜ ውጭ ለብዙ ቀናት ደም ቢፈሳት+ ወይም በወር አበባዋ ወቅት ከወትሮው ረዘም ላለ ጊዜ ደም ቢፈሳት+ የወር አበባዋ በሚመጣባቸው ቀናት እንደሚሆነው ፈሳሽ በሚፈሳት ጊዜ ሁሉ ርኩስ ትሆናለች። +26 ፈሳሽ በሚፈሳት ቀናት ሁሉ የተኛችበት አልጋ በወር አበባዋ የተነሳ ርኩስ በሆነችባቸው ጊዜያት እንደተኛችበት አልጋ ይሆናል፤+ እንዲሁም የተቀመጠችበት ማንኛውም ነገር በወር አበባዋ ወቅት ርኩስ እንደሚሆን ሁሉ በዚህ ጊዜም ርኩስ ይሆናል። +27 እነዚህን ነገሮች የነካ ማንኛውም ሰው ርኩስ ይሆናል፤ ልብሶቹንም ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።+ +28 “‘ይሁን እንጂ ይፈሳት ከነበረው ፈሳሽ በምትነጻበት ጊዜ ለራሷ ሰባት ቀን ትቆጥራለች፤ ከዚያ በኋላ ንጹሕ ትሆናለች።+ +29 በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ትውሰድ፤+ እነዚህንም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወዳለው ወደ ካህኑ ታመጣቸዋለች።+ +30 ካህኑም አንዱን ለኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ ለሚቃጠል መባ ያደርገዋል፤ ካህኑም የሚፈሳትን ርኩስ ፈሳሽ አስመልክቶ ለሴትየዋ በይሖዋ ፊት ያስተሰርይላታል።+ +31 “‘በመካከላቸው ያለውን የማደሪያ ድንኳኔን በማርከስ በርኩሰታቸው እንዳይሞቱ በዚህ መንገድ እስራኤላውያንን ከርኩሰታቸው ለዩአቸው።+ +32 “‘ፈሳሽ የሚወጣውን ወንድ፣ ዘሩ በመፍሰሱ የተነሳ ርኩስ የሆነውን ወንድ፣+ +33 በወር አበባዋ ላይ በመሆኗ ርኩስ የሆነችን ሴት፣+ ወንድም ሆነ ሴት ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣውን ማንኛውንም ሰው+ እንዲሁም ርኩስ ከሆነች ሴት ጋር የተኛን ወንድ በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው።’” +22 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ፣ እስራኤላውያን የሚያመጧቸውን ቅዱስ ነገሮች የሚይዙበትን መንገድ በተመለከተ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና* ለእኔ የተቀደሱ አድርገው በለዩአቸው ነገሮች+ ቅዱስ ስሜን እንዳያረክሱ+ ንገራቸው። እኔ ይሖዋ ነኝ። +3 እንዲህ በላቸው፦ ‘በትውልዶቻችሁ ሁሉ ከልጆቻችሁ መካከል ረክሶ እያለ እስራኤላውያን ለይሖዋ የተቀደሱ አድርገው ወደለዩአቸው ቅዱስ ነገሮች የሚቀርብ ሰው ካለ ያ ሰው* ከፊቴ እንዲጠፋ ይደረግ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +4 ከአሮን ልጆች መካከል የሥጋ ደዌ+ ያለበት ወይም ፈሳሽ የሚወጣው+ ማንኛውም ሰው ንጹሕ እስኪሆን ድረስ+ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት የለበትም፤ የሞተን ሰው* በመንካት የረከሰን ሰው+ የነካ ወይም ከሰውነቱ የዘር ፈሳሽ የሚወጣው+ +5 አሊያም ርኩስ የሆነን የሚርመሰመስ ፍጡር የነካ+ ወይም ደግሞ ሊያረክሰው በሚችል በማንኛውም ዓይነት ነገር የረከሰን ሰው የነካ+ ሰው ከእነዚህ ነገሮች አይብላ። +6 እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን የነካ ማንኛውም ሰው* እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውንም በውኃ እስካልታጠበ+ ድረስ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት አይችልም። +7 ፀሐይ በምትጠልቅበት ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያ በኋላ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት ይችላል፤ ምክንያቱም ይህ ምግቡ ነው።+ +8 በተጨማሪም እንዳይረክስ ሞቶ የተገኘን ወይም አውሬ የቦጫጨቀውን የማንኛውንም እንስሳ ሥጋ መብላት የለበትም።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +9 “‘ለእኔ የገቡትን ግዴታ ባለመጠበቅ በራሳቸው ላይ ኃጢአት እንዳያመጡና በዚህም የተ���ሳ ቅዱስ የሆነውን ነገር በማርከስ እንዳይሞቱ የገቡትን ግዴታ መጠበቅ አለባቸው። የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ ነኝ። +10 “‘ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው* ቅዱስ የሆነውን የትኛውንም ነገር መብላት የለበትም።+ ካህኑ ቤት በእንግድነት ያረፈ ሰው ወይም ቅጥር ሠራተኛ ቅዱስ ከሆነው ነገር መብላት የለበትም። +11 ሆኖም አንድ ካህን በገዛ ገንዘቡ አንድ ሰው* ቢገዛ ያ ሰው ከምግቡ መካፈል ይችላል። በቤቱ የተወለዱ ባሪያዎችም ከእሱ ምግብ መካፈል ይችላሉ።+ +12 የአንድ ካህን ሴት ልጅ፣ ካህን ያልሆነን ሰው ብታገባ* በመዋጮ ከተሰጡት ቅዱስ የሆኑ ነገሮች መብላት አትችልም። +13 ይሁንና የአንድ ካህን ሴት ልጅ፣ ባሏ ቢሞት ወይም ብትፋታና ልጅ ባይኖራት እንደ ወጣትነቷም ጊዜ ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ ከአባቷ ምግብ መብላት ትችላለች፤+ ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው* ግን ከዚያ መብላት የለበትም። +14 “‘አንድ ሰው ቅዱስ ከሆነው ነገር ባለማወቅ ቢበላ የቅዱሱን ነገር ዋጋ አንድ አምስተኛ በመጨመር ቅዱስ የሆነውን መባ ለካህኑ ይስጥ።+ +15 ካህናቱ፣ እስራኤላውያን ለይሖዋ መዋጮ አድርገው የሰጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ማርከስ+ +16 እንዲሁም ሕዝቡ ያመጣቸውን ቅዱስ ነገሮች እንዲበላና በራሱ ላይ ቅጣት የሚያስከትል በደል እንዲፈጽም ማድረግ የለባቸውም፤ ምክንያቱም የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ ነኝ።’” +17 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +18 “ለአሮን፣ ለወንዶች ልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ስእለቱን ለመፈጸም ወይም የፈቃደኝነት መባ ለማቅረብ+ ሲል የሚቃጠል መባውን ለይሖዋ የሚያቀርብ አንድ እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል ውስጥ የሚኖር አንድ የባዕድ አገር ሰው+ +19 ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፈለገ መሥዋዕቱ ከመንጋው፣ ከጠቦቶቹ ወይም ከፍየሎቹ መካከል የተወሰደ እንከን የሌለበት ተባዕት+ መሆን ይኖርበታል። +20 ተቀባይነት ስለማያስገኝላችሁ እንከን ያለበትን ማንኛውንም ነገር አታቅርቡ።+ +21 “‘አንድ ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም የፈቃደኝነት መባ ለመስጠት ሲል ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት+ ቢያቀርብ መሥዋዕቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከከብቶቹ ወይም ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበትን ማቅረብ ይኖርበታል። ምንም ዓይነት እንከን ሊኖርበት አይገባም። +22 መባ ሆኖ የሚቀርበው እንስሳ ዕውር ወይም ሰባራ አሊያም ቆራጣ ወይም ደግሞ ኪንታሮት አሊያም እከክ ወይም ጭርት ያለበት መሆን የለበትም፤ እንዲህ ያለውን እንስሳ ለይሖዋ ማቅረብ የለባችሁም ወይም እንዲህ ያለውን መባ ለይሖዋ በመሠዊያው ላይ ማቅረብ የለባችሁም። +23 አንዱ እግሩ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬ ወይም በግ የፈቃደኝነት መባ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ የስእለት መባ አድርጋችሁ ብታቀርቡት ግን ተቀባይነት አይኖረውም። +24 የዘር ፍሬው ጉዳት የደረሰበትን ወይም የተቀጠቀጠን አሊያም ተሰንጥቆ የወጣን ወይም የተቆረጠን እንስሳ ለይሖዋ ማቅረብ የለባችሁም፤ በምድራችሁ እነዚህን የመሰሉ እንስሳትን ማቅረብ አይኖርባችሁም። +25 እነዚህ ጉድለትና እንከን ስላለባቸው ከመካከላቸው የትኛውንም ከባዕድ ሰው እጅ በመቀበል የአምላካችሁ ምግብ አድርጋችሁ ማቅረብ የለባችሁም። ተቀባይነት አያገኙላችሁም።’” +27 “ጥጃ ወይም የበግ ግልገል አሊያም የፍየል ግልገል በሚወለድበት ጊዜ ለሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቆይ፤+ ከስምንተኛው ቀን አንስቶ ግን መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ሆኖ ቢቀርብ ተቀባይነት ይኖረዋል። +28 ላምን ከጥጃዋ ወይም በግን ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ።+ +29 “ለይሖዋ የምሥጋና መሥዋዕት+ የምትሠዉ ከሆነ ተቀባይነት በሚያስገኝላችሁ መንገድ ልትሠዉት ይገባል። +30 መሥዋዕቱ በዚያው ዕለት መበላት ይኖርበታል። ከእሱም ላይ ምንም አስተርፋችሁ አታሳድሩ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +31 “እናንተም ትእዛዛቴን ጠብቁ፤ እንዲሁም ፈጽሟቸው።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። +32 ቅዱሱን ስሜን አታርክሱ፤+ እኔ በእስራኤላውያን መካከል ልቀደስ ይገባኛል።+ የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ነኝ፤+ +33 አምላክ መሆኔን ለእናንተ ለማሳየት ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ነኝ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።” +17 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን አናግራቸው፤ ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት ከእያንዳንዱ የአባቶች ቤት አለቃ+ ላይ አንድ አንድ በትር ይኸውም በአጠቃላይ 12 በትሮችን ከእነሱ ላይ ውሰድ። የእያንዳንዳቸውንም ስም በየበትራቸው ላይ ጻፍ። +3 ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት መሪ የሚኖረው አንድ በትር ስለሆነ የአሮንን ስም በሌዊ በትር ላይ ጻፍ። +4 በትሮቹን ራሴን ዘወትር ለእናንተ በምገልጥበት+ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በምሥክሩ+ ፊት ለፊት አስቀምጣቸው። +5 ከዚያም እኔ የምመርጠው+ ሰው በትር ያቆጠቁጣል፤ እኔም እስራኤላውያን በእናንተ ላይ በማጉረምረም+ በእኔ ላይ እያሰሙ ያሉት ማጉረምረም+ እንዲያበቃ አደርጋለሁ።” +6 በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያንን አነጋገራቸው፤ አለቆቻቸውም በሙሉ በትሮቹን ይኸውም ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት አለቃ አንድ በትር ማለትም 12 በትሮችን ሰጡት፤ የአሮንም በትር ከእነሱ በትሮች ጋር ነበር። +7 ከዚያም ሙሴ በትሮቹን በምሥክሩ ድንኳን ውስጥ በይሖዋ ፊት አስቀመጣቸው። +8 በማግስቱም ሙሴ ወደ ምሥክሩ ድንኳን ሲገባ የሌዊን ቤት የሚወክለውን የአሮንን በትር አቆጥቁጦ፣ እንቡጥ አውጥቶ፣ አበባ አብቦና የደረሰ የአልሞንድ ፍሬ አፍርቶ አገኘው። +9 ከዚያም ሙሴ በትሮቹን በሙሉ ከይሖዋ ፊት አውጥቶ ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ አመጣቸው። እነሱም በትሮቹን አዩ፤ እያንዳንዱም ሰው የራሱን በትር ወሰደ። +10 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለዓመፀኞቹ ልጆች+ ምልክት ሆኖ እንዲያገለግል+ የአሮንን በትር+ መልሰህ ምሥክሩ ፊት አስቀምጠው፤ ይህም የሚሆነው በእኔ ላይ ማጉረምረማቸውን እንዲተዉና እንዳይሞቱ ነው።” +11 ሙሴም ወዲያውኑ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ። ልክ እንደተባለውም አደረገ። +12 ከዚያም እስራኤላውያን ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ መሞታችን ነው፤ በቃ ማለቃችን ነው፤ ሁላችንም ማለቃችን ነው! +13 ወደ ይሖዋ የማደሪያ ድንኳን የሚቀርብ ማንኛውም ሰው ይሞታል!+ በቃ በዚህ መንገድ ሁላችንም መሞታችን ነው?”+ +30 ከዚያም ሙሴ የእስራኤላውያን የነገድ መሪዎችን+ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ የሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፦ +2 አንድ ሰው ለይሖዋ ስእለት ቢሳል+ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ ራሱን* ግዴታ ውስጥ ቢያስገባ+ ቃሉን ማጠፍ የለበትም።+ አደርገዋለሁ ብሎ የማለውን ነገር ሁሉ መፈጸም አለበት።+ +3 “በአባቷ ቤት የምትኖር አንዲት ወጣት ለይሖዋ ስእለት ብትሳል ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ብታስገባ +4 አባቷ ስእለት መሳሏን ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን* በመሐላ ግዴታ ውስጥ ማስገባቷን ሰምቶ ካልተቃወማት ስእለቶቿ በሙሉ ይጸናሉ፤ እንዲሁም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችው ማንኛውም ግዴታ ይጸናል። +5 ሆኖም አባቷ ስእለት መሳሏን ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ማስገባቷን ሲሰማ ቢከለክላት ስእለቱ አይጸናም። አባቷ ስለከለከላት ይሖዋ ይቅር ይላታል።+ +6 “ይሁን እንጂ ይህች ሴት ስእለት ተስላ ወይም ሳታስብበት ራሷን ግዴታ ውስጥ የሚያስገባ ቃል ተናግራ እያለ ባል ብታገባ፣ +7 ባሏም ይህን ቢሰማና በሰማበት ቀን ዝም ቢላት ስእለቶቿ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባቻቸው ግዴታዎች ይጸናሉ። +8 ሆኖም ባሏ ይህን በሰማበት ቀን ቢከለክላት የተሳለችውን ስእለት ወይም ሳታስብበት ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ቃል ያፈርሰዋል፤+ ይሖዋም ይቅር ይላታል። +9 “ሆኖም አንዲት መበለት ወይም ከባሏ የተፋታች አንዲት ሴት ስእለት ብትሳል ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች በሙሉ ይጸኑባታል። +10 “ይሁን እንጂ አንዲት ሴት ስእለት የተሳለችው ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ያስገባችው በባሏ ቤት እያለች ከሆነና +11 ባሏም ሰምቶ ይህን ካልተቃወማት ወይም ካልከለከላት የተሳለቻቸው ስእለቶች በሙሉ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባቻቸው ግዴታዎች ሁሉ ይጸናሉ። +12 ይሁንና ባሏ የተሳለችውን ማንኛውንም ስእለት ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችውን የትኛውንም ግዴታ በሰማበት ቀን ሙሉ በሙሉ ቢያፈርስባት ስእለቶቹ አይጸኑም።+ ባሏ ስእለቶቿን አፍርሷቸዋል፤ ይሖዋም ይቅር ይላታል። +13 የትኛውንም ስእለት ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችውን ግዴታ አሊያም ራሷን* ለማጎሳቆል የገባችውን ቃል ባሏ ሊያጸናው ወይም ሊያፈርሰው ይችላል። +14 ሆኖም ባሏ ቀናት እያለፉ ሲሄዱ ጨርሶ ካልተቃወማት ስእለቶቿን በሙሉ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችውን ግዴታ ሁሉ አጽንቶታል ማለት ነው። ስእለት መሳሏን በሰማበት ቀን ስላልተቃወማት እንዳጸናቸው ይቆጠራል። +15 ስእለቶቹን ሰምቶ የተወሰኑ ቀናት ካለፉ በኋላ ስእለቶቹን ካፈረሰ ግን የእሷ በደል የሚያስከትላቸውን መዘዞች እሱ ይሸከማል።+ +16 “ከባልና ከሚስት እንዲሁም ከአባትና በቤቱ ከምትኖር ወጣት ልጁ ጋር በተያያዘ ይሖዋ ለሙሴ የሰጣቸው ደንቦች እነዚህ ናቸው።” +35 ይሖዋ ሙሴን በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ+ ላይ እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን ከሚወርሱት ርስት ላይ ለሌዋውያኑ መኖሪያ የሚሆኑ ከተሞችን እንዲሰጧቸው እዘዛቸው፤+ በከተሞቹም ዙሪያ ያለውን የግጦሽ መሬት ለሌዋውያኑ መስጠት አለባቸው።+ +3 ከተሞቹ ለእነሱ መኖሪያ፣ የግጦሽ ቦታዎቹ ደግሞ ለከብቶቻቸውና ለዕቃዎቻቸው እንዲሁም ለሌሎች እንስሶቻቸው ይሆናሉ። +"4 ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው የከተሞቹ የግጦሽ ቦታዎች ከከተማው ቅጥር በሁሉም አቅጣጫ 1,000 ክንድ* ይሆናል።" +"5 ከተማውን መካከል ላይ በማድረግ ከከተማው ውጭ በምሥራቅ በኩል 2,000 ክንድ፣ በደቡብ በኩል 2,000 ክንድ፣ በምዕራብ በኩል 2,000 ክንድ እንዲሁም በሰሜን በኩል 2,000 ክንድ ለኩ። እነዚህም የከተሞቻቸው የግጦሽ መሬት ይሆናሉ። " +6 “ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው ከተሞች ነፍስ ያጠፋ ሰው ሸሽቶ የሚሸሸግባቸውን+ 6 የመማጸኛ ከተሞችና+ ሌሎች 42 ከተሞችን ነው። +7 በጠቅላላ 48 ከተሞችን ከነግጦሽ መሬታቸው ለሌዋውያኑ ትሰጧቸዋላችሁ።+ +8 ከተሞቹን የምትሰጧቸው ከእስራኤላውያን ርስት ላይ ወስዳችሁ ነው።+ ተለቅ ካለው ቡድን ላይ ብዙ ትወስዳላችሁ፤ አነስ ካለው ቡድን ላይ ደግሞ ጥቂት ትወስዳላችሁ።+ እያንዳንዱ ቡድን በወረሰው ርስት መጠን ካሉት ከተሞች ላይ የተወሰኑትን ለሌዋውያኑ መስጠት ይኖርበታል።” +9 ይሖዋ በመቀጠል ሙሴን እንዲህ አለው፦ +10 “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እንግዲህ ወደ ከነአን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው።+ +11 ሳያስበው ሰው የገደለ* ሰው ሸሽቶ የሚጠጋባቸው አመቺ የሆኑ የመማጸኛ ከተሞችን ለራሳችሁ ምረጡ።+ +12 እነዚህ ከተሞች ነፍስ ያጠፋው ሰው በማኅበረሰቡ ፊት ለፍርድ ከመቅረቡ በፊት+ እንዳይሞት ከደም ተበቃዩ+ የሚሸሸግባቸው ከተሞች ይሆኑላችኋል። +13 እናንተ የምትሰጧቸው ስድስቱ የመማጸኛ ከተሞች ለዚህ ዓላማ ያገለግላሉ። +14 የመማጸኛ ከተሞች ሆነው እንዲያገለግሉ ከዮርዳኖስ ወዲህ ሦስት ከተሞችን፣+ በከነአን ምድር ደግሞ ሦስት ከተሞችን+ ትሰጣላችሁ። +15 እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤላውያንም ሆነ ለባዕድ አገር ሰው+ አሊያም በመካከላቸው ለሚኖር ሰፋሪ ሳያስበው ሰው የገደለ* ማንኛውም ሰው ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ከተሞች ሆነው ያገለግላሉ።+ +16 “‘ሆኖም ሰውየው ግለሰቡን በብረት መሣሪያ ቢመታውና ቢገድለው ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው። ነፍሰ ገዳዩ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት።+ +17 ሰውየው ግለሰቡን ሊገድለው በሚችል ድንጋይ ቢመታውና ቢገድለው ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው። ነፍሰ ገዳዩ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት። +18 ሰውየው ግለሰቡን ሊገድለው በሚችል ከእንጨት የተሠራ መሣሪያ ቢመታውና ቢገድለው ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው። ነፍሰ ገዳዩ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት። +19 “‘ነፍሰ ገዳዩን መግደል ያለበት ደም ተበቃዩ ይሆናል። ባገኘው ጊዜ እሱ ራሱ ይግደለው። +20 አንድ ሰው ሌላውን በጥላቻ ተገፋፍቶ ቢገፈትረው ወይም ተንኮል አስቦ* የሆነ ነገር ቢወረውርበትና ግለሰቡ ቢሞት+ +21 አሊያም በጥላቻ ተነሳስቶ በእጁ ቢመታውና ቢሞት መቺው ያለምንም ጥርጥር ይገደላል። እሱ ነፍሰ ገዳይ ነው። ደም ተበቃዩም ነፍሰ ገዳዩን ባገኘው ጊዜ ይገድለዋል። +22 “‘ይሁን እንጂ ሰውየው ግለሰቡን የገፈተረው በጥላቻ ተነሳስቶ ሳይሆን ሳያስበው ከሆነ ወይም ዕቃ የወረወረበት ተንኮል አስቦ* ካልሆነ+ +23 አሊያም ግለሰቡ ሳያየው ድንጋይ ቢጥልበትና ቢሞት ሆኖም ሰውየው ከግለሰቡ ጋር ጠላትነት ባይኖረውና ይህን ያደረገው እሱን ለመጉዳት አስቦ ባይሆን +24 ማኅበረሰቡ እነዚህን ደንቦች መሠረት በማድረግ በገዳዩና በደም ተበቃዩ መካከል ፍርድ ይስጥ።+ +25 ማኅበረሰቡም ነፍሰ ገዳዩን ከደም ተበቃዩ እጅ ታድጎ ሸሽቶበት ወደነበረው የመማጸኛ ከተማ ይመልሰው፤ እሱም በቅዱስ ዘይት የተቀባው+ ሊቀ ካህናት እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቆይ። +26 “‘ይሁንና ገዳዩ ሸሽቶ ከገባበት የመማጸኛ ከተማ ወሰን ቢወጣና +27 ደም ተበቃዩም ገዳዩን ከመማጸኛ ከተማው ወሰን ውጭ አግኝቶ ቢገድለው በደም ዕዳ አይጠየቅም። +28 ምክንያቱም ሊቀ ካህናቱ እስኪሞት ድረስ በመማጸኛ ከተማው ውስጥ መቆየት ይገባዋል። ሊቀ ካህናቱ ከሞተ በኋላ ግን ገዳዩ ወደ ርስቱ መመለስ ይችላል።+ +29 እነዚህም በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ፍርድ ለመስጠት እንደሚያገለግል ደንብ ይሁኗችሁ። +30 “‘ሰው* የገደለ ማንኛውም ሰው ምሥክሮች ከመሠከሩበት*+ እንደ ነፍሰ ገዳይ ተቆጥሮ ይገደል፤+ ይሁን እንጂ ማንም ሰው* አንድ ግለሰብ በሚሰጠው ምሥክርነት ብቻ በሞት መቀጣት የለበትም። +31 ሞት ለሚገባው ነፍሰ ገዳይ ሕይወት* ቤዛ አትቀበሉ፤ ምክንያቱም ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት።+ +32 እንዲሁም ሸሽቶ ወደ መማጸኛ ከተማው ለገባ ሰው* ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ ምድሩ ተመልሶ እንዲኖር ለማድረግ ቤዛ አትቀበሉ። +33 “‘ደም ምድሪቱን ስለሚበክል ያላችሁባትን ምድር አትበክሉ፤+ ደም ባፈሰሰው ሰው ደም ካልሆነ በስተቀር በምድሪቱ ላይ ለፈሰሰው ደም ስርየት ሊኖር አይችልም።+ +34 የምትኖሩባትን፣ እኔም የምኖርባትን ምድር አታርክሱ፤ እኔ ይሖዋ በእስራኤል ሕዝብ መካከል እኖራለሁና።’”+ +31 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ለእስራኤላውያን ምድያማውያንን+ ተበቀልላቸው።+ ከዚያ በኋላ ወደ ወገኖችህ ትሰበሰባለህ።”*+ +3 በመሆኑም ሙሴ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ በምድያም ላይ የሚወስደውን የበቀል እርምጃ ለማስፈጸም ከምድያም ጋር ለሚደረገው ጦርነት* ከመካከላችሁ ወንዶችን አስታጥቁ። +"4 ከሁሉም የእስራኤል ነገድ ከእያንዳንዱ 1,000 ወንዶችን ወደ ጦርነቱ ላኩ።”" +"5 ስለዚህ በሺዎች ከሚቆጠሩት እስራኤላውያን+ መካከል ከአንድ ነገድ 1,000 ወንዶች ተመርጠው በአጠቃላይ 12,000 ወንዶች ለጦርነቱ* ታጠቁ። " +6 ከዚያም ሙሴ ከየነገዱ የተውጣጡትን አንድ አንድ ሺህ ወንዶች ወደ ጦርነቱ ላካቸው፤ ከእነሱም ጋር የሠራዊቱ ካህን የሆነውን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሃስን+ ላከው፤ ቅዱስ የሆኑት ዕቃዎችና በጦርነት ጊዜ የሚነፉት መለከቶች+ በእሱ እጅ ነበሩ። +7 እነሱም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት በምድያም ላይ ጦርነት ከፈቱ፤ ወንዶቹንም ሁሉ ገደሉ። +8 ከተገደሉትም መካከል ኤዊ፣ ራቄም፣ ጹር፣ ሁር እና ረባ የተባሉት አምስቱ የምድያም ነገሥታት ይገኙበታል። እንዲሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን+ በሰይፍ ገደሉ። +9 ሆኖም እስራኤላውያን የምድያምን ሴቶችና ትናንሽ ልጆች ማርከው ወሰዱ። በተጨማሪም የቤት እንስሶቻቸውን፣ ከብቶቻቸውን እንዲሁም ንብረታቸውን በሙሉ ዘረፉ። +10 ይኖሩባቸው የነበሩትን ከተሞችና ሰፈሮቻቸውን* ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። +11 ሰውም ሆነ እንስሳ የማረኩትንና የዘረፉትን በሙሉ ወሰዱ። +12 ከዚያም የማረኳቸውን ሰዎችና የዘረፉትን ንብረት በኢያሪኮ፣ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ+ ላይ ወደሚገኘው ሰፈር ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛርና ወደ እስራኤል ማኅበረሰብ አመጡ። +13 ከዚያም ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛርና የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ ከእነሱ ጋር ለመገናኘት ከሰፈሩ ውጭ ወጡ። +14 ሆኖም ሙሴ ከጦርነቱ በተመለሱት የሠራዊቱ አዛዦች ይኸውም በሺህ አለቆቹና በመቶ አለቆቹ ላይ ተቆጣ። +15 እንዲህም አላቸው፦ “ሴቶቹን በሙሉ እንዴት ሳትገድሉ ተዋችኋቸው? +16 የበለዓምን ቃል ሰምተው እስራኤላውያን በፌጎር በተከሰተው ነገር+ የተነሳ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት እንዲፈጽሙ ያሳቷቸውና+ በዚህም ምክንያት በይሖዋ ማኅበረሰብ ላይ መቅሰፍት እንዲመጣ ያደረጉት እነሱ አይደሉም?+ +17 በሉ አሁን ከልጆች መካከል ወንዶቹን በሙሉ እንዲሁም ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት የፈጸሙ ሴቶችን በሙሉ ግደሉ። +18 ሆኖም ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁትን ወጣት ሴቶች ሁሉ+ በሕይወት እንዲተርፉ ልታደርጉ ትችላላችሁ። +19 እናንተም ለሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጭ ቆዩ። ከመካከላችሁ ሰው* የገደለም ሆነ የሞተ ሰው የነካ+ ማንኛውም ሰው በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፤+ እናንተም ሆናችሁ የማረካችኋቸው ሰዎች ራሳችሁን አንጹ። +20 ማንኛውንም ልብስ፣ ማንኛውንም ከቆዳ የተሠራ ነገር፣ ማንኛውንም ከፍየል ፀጉር የተሠራ ነገር እንዲሁም ማንኛውንም ከእንጨት የተሠራ ነገር ከኃጢአት አንጹ።” +21 ከዚያም ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነቱ ሄደው የነበሩትን ወንዶች እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ ሙሴን ያዘዘው የሕጉ ደንብ ይህ ነው፦ +22 ‘ወርቁን፣ ብሩን፣ መዳቡን፣ ብረቱን፣ ቆርቆሮውንና እርሳሱን ብቻ +23 ይኸውም እሳትን መቋቋም የሚችለውን ማንኛውንም ነገር በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አድርጉ፤ እሱም ንጹሕ ይሆናል። ያም ሆኖ ለማንጻት በሚያገለግለው ውኃ መንጻት አለበት።+ እሳትን መቋቋም የማይችሉ ነገሮችን በሙሉ በውኃ ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ አለባችሁ። +24 በሰባተኛውም ቀን ልብሶቻችሁን እጠቡ፤ ንጹሕም ሁኑ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ትችላላችሁ።’”+ +25 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +26 “የምርኮውን ብዛት ቁጠር፤ ሰዎችም ሆኑ እንስሳት የተማረኩትን ሁሉ ቁጠር፤ ይህንም ከካህኑ ከአልዓዛርና ከማኅበረሰቡ የአባቶች ቤት መሪዎች ጋር አድርግ። +27 ምርኮውንም በጦርነቱ ለተካ���ሉት ተዋጊዎችና ለቀረው ማኅበረሰብ ሁሉ እንዲከፋፈል ለሁለት ክፈለው።+ +28 ለይሖዋም ግብር እንዲሆን በጦርነቱ ከተካፈሉት ተዋጊዎች ላይ ከሰውም ሆነ ከከብት፣ ከአህያም ሆነ ከመንጋ ከ500 አንድ ነፍስ* ውሰድ። +29 ለእነሱ ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ ወስዳችሁ ለካህኑ ለአልዓዛር የይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ስጡት።+ +30 ለእስራኤላውያን ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ ደግሞ ከሰውም ሆነ ከከብት፣ ከአህያም ሆነ ከመንጋ እንዲሁም ከማንኛውም እንስሳ ከ50 አንድ ወስደህ ከይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ጋር በተያያዘ ያለባቸውን ኃላፊነት+ ለሚወጡት ለሌዋውያኑ ስጥ።”+ +31 በመሆኑም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። +"32 በውጊያው የተካፈሉት ሰዎች ማርከው ካመጡት ምርኮ ውስጥ የቀሩት 675,000 በጎች፣" +"33 72,000 ከብቶች" +"34 እንዲሁም 61,000 አህዮች ነበሩ።" +"35 ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁት ሴቶች*+ በአጠቃላይ 32,000 ነበሩ።" +"36 በውጊያው ለተሳተፉት ተከፍሎ የተሰጣቸው ድርሻ በአጠቃላይ 337,500 በግ ነበር።" +37 ከበጎቹ መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 675 ነበሩ። +"38 ከብቶቹ ደግሞ 36,000 ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 72 ነበሩ።" +"39 አህዮቹ 30,500 ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 61 ነበሩ።" +"40 ሰዎቹ* ደግሞ 16,000 ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል ለይሖዋ ግብር ተደርገው የተሰጡት 32 ሰዎች* ነበሩ።" +41 ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ግብሩን ለይሖዋ መዋጮ እንዲሆን ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው።+ +42 ሙሴም በጦርነቱ የተካፈሉት ሰዎች ካመጡት ላይ ከፍሎ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፦ +"43 ሙሴ ከፍሎ የሰጣቸው ድርሻ 337,500 በግ፣" +"44 36,000 ከብት፣" +"45 30,500 አህያ" +"46 እንዲሁም 16,000 ሰው* ነበር።" +47 ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን ተከፍሎ ከተሰጣቸው ድርሻ ላይ ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ከ50 አንድ ወስዶ በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን የተጣለባቸውን ኃላፊነት+ ለሚወጡት ሌዋውያን ሰጠ።+ +48 ከዚያም በሠራዊቱ ክፍሎች ውስጥ የተሾሙት አዛዦች ይኸውም የሺህ አለቆቹና+ የመቶ አለቆቹ ወደ ሙሴ ቀርበው +49 እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ በሥራችን ያሉትን ተዋጊዎች ቆጥረናል፤ ከመካከላችን አንድም የጎደለ የለም።+ +50 ስለዚህ እያንዳንዳችን በይሖዋ ፊት ለራሳችን* ማስተሰረያ እንዲሆኑልን፣ ያገኘናቸውን ነገሮች ይኸውም የወርቅ ጌጣጌጦችን፣ የእግር አልቦዎችን፣ የእጅ አምባሮችን፣ የማኅተም ቀለበቶችን፣ የጆሮ ጉትቻዎችንና ሌሎች ጌጣጌጦችን ለይሖዋ መባ አድርገን ማቅረብ እንፈልጋለን።” +51 በመሆኑም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ይኸውም ጌጣጌጡን ሁሉ ተቀበሏቸው። +"52 ከሺህ አለቆቹና ከመቶ አለቆቹ ተቀብለው ለይሖዋ መዋጮ እንዲሆን የሰጡት ወርቅ በጠቅላላ 16,750 ሰቅል* ሆነ።" +53 በሠራዊቱ ውስጥ ያሉት ወንዶች እያንዳንዳቸው ከምርኮው ላይ ድርሻቸውን ወስደው ነበር። +54 ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁን ከሺህ አለቆቹና ከመቶ አለቆቹ ተቀብለው በይሖዋ ፊት ለእስራኤል ሕዝብ ማስታወሻ* እንዲሆን ወደ መገናኛ ድንኳኑ አስገቡት። +18 ከዚያም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ከመቅደሱ+ ጋር በተያያዘ ለሚፈጸመው ማንኛውም በደል አንተ፣ ከአንተም ጋር ወንዶች ልጆችህና የአባትህ ቤት ተጠያቂ ትሆናላችሁ፤ ከክህነታችሁ ጋር በተያያዘ ለሚፈጸመው ማንኛውም በደል አንተ፣ ከአንተም ጋር ወንዶች ልጆችህ ተጠያቂ ትሆናላችሁ።+ +2 በተጨማሪም በምሥክሩ ድንኳን+ ፊት ከአንተ ጋር አብረው እንዲሆኑ እንዲሁም አንተንና ወንዶች ልጆችህን እንዲያገለግሉ+ ከአባትህ ነገድ ይኸው��� ከሌዊ ነገድ የሆኑትን ወንድሞችህን አቅርባቸው። +3 ከአንተም ሆነ በአጠቃላይ ከድንኳኑ ጋር በተያያዘ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ይወጡ።+ ይሁንና አንተም ሆንክ እነሱ እንዳትሞቱ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ዕቃዎችና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ።+ +4 እነሱም ከእናንተ ጋር በመሆን ከመገናኛ ድንኳኑና በድንኳኑ ከሚከናወነው አገልግሎት ሁሉ ጋር በተያያዘ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ይወጣሉ፤ ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው* ወደ እናንተ መቅረብ የለበትም።+ +5 እናንተም በእስራኤል ሕዝብ ላይ ዳግም ቁጣ እንዳይመጣ+ ከቅዱሱ ስፍራና ከመሠዊያው+ ጋር በተያያዘ የተጣለባችሁን ኃላፊነት ተወጡ።+ +6 እኔ ራሴ ወንድሞቻችሁ የሆኑትን ሌዋውያን ከእስራኤላውያን መካከል ወስጄ ለእናንተ ስጦታ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ።+ እነሱም በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ የሚከናወነውን አገልግሎት እንዲፈጽሙ ለይሖዋ የተሰጡ ናቸው።+ +7 ከመሠዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ካለው+ ነገር ጋር የተያያዙትን የክህነት ሥራዎቻችሁን የማከናወኑ ኃላፊነት የተጣለው በአንተና በወንዶች ልጆችህ ላይ ነው፤ እናንተም ይህን አገልግሎት ታከናውናላችሁ።+ የክህነት አገልግሎቱን ለእናንተ ስጦታ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ወደዚያ የሚቀርብ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው* +8 በተጨማሪም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለእኔ በሚቀርቡት መዋጮዎች+ ላይ እኔ ራሴ ኃላፊ አድርጌ ሾሜሃለሁ። እስራኤላውያን የሚያዋጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ሁሉ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ቋሚ ድርሻችሁ ነው።+ +9 በእሳት ከሚቀርቡት እጅግ ቅዱስ የሆኑ መባዎች ውስጥ የሚከተሉት የአንተ ይሆናሉ፦ ለእኔ የሚያመጡትን የእህል መባቸውን፣+ የኃጢአት መባቸውንና+ የበደል መባቸውን+ ጨምሮ የሚያቀርቡት ማንኛውም መባ የአንተ ይሆናል። ይህ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ እጅግ የተቀደሰ ነገር ነው። +10 እጅግ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ብላው።+ እያንዳንዱ ወንድ ይብላው። ይህ ለአንተ የተቀደሰ ነገር ነው።+ +11 እስራኤላውያን ከሚወዘወዝ መባቸው+ ሁሉ ጋር መዋጮ አድርገው የሚያመጧቸው ስጦታዎች+ የአንተ ይሆናሉ። እነዚህን ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለወንዶች ልጆችህና ለሴቶች ልጆችህ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ።+ በቤትህ ያለ ማንኛውም ንጹሕ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል።+ +12 “ለይሖዋ የሚሰጡትን ምርጥ የሆነውን ዘይት ሁሉ፣ ምርጥ የሆነውን አዲስ የወይን ጠጅና እህል ሁሉ ይኸውም የፍሬያቸውን በኩራት+ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።+ +13 በምድራቸው ላይ መጀመሪያ የደረሰው ለይሖዋ የሚያመጡት ፍሬ ሁሉ የአንተ ይሆናል።+ በቤትህ ያለ ማንኛውም ንጹሕ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል። +14 “በእስራኤል ውስጥ ቅዱስ ለሆነ ዓላማ የተለየ ማንኛውም ነገር* የአንተ ይሆናል።+ +15 “ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ለይሖዋ የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ሕይወት ያለው ነገር* በኩር ሁሉ+ የአንተ መሆን ይኖርበታል። ሆኖም ከሰው በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይኖርብሃል፤+ እንዲሁም ርኩስ ከሆነ እንስሳ በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይገባሃል።+ +16 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሲሆነው እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል*+ መሠረት በተተመነለት ዋጋ ይኸውም በአምስት የብር ሰቅል* ወጆ ልትዋጀው ይገባል። አንዱ ሰቅል 20 ጌራ* ነው። +17 በኩር የሆነውን በሬ፣ በኩር የሆነውን ተባዕት በግና በኩር የሆነውን ፍየል ግን መዋጀት የለብህም።+ እነዚህ የተቀደሱ ነገሮች ናቸው። ደማቸውን በመሠዊያው ላይ እርጨው፤+ ስባቸውን ደግሞ ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ የሚሰጥ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርገህ አጭሰው።+ +18 ሥጋቸው የአንተ ይሆናል። እንደሚወዘወዘው መባ ፍርምባና እንደ ቀ��� እግር ሁሉ ይህም የአንተ ይሆናል።+ +19 እስራኤላውያን ለይሖዋ የሚያዋጧቸውን ቅዱስ መዋጮዎች+ በሙሉ ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለወንዶች ልጆችህና ለሴቶች ልጆችህ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ።+ ይህም በይሖዋ ፊት ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለዘሮችህ የተገባ ዘላቂ የጨው ቃል ኪዳን* ነው።” +20 ይሖዋም በመቀጠል አሮንን እንዲህ አለው፦ “አንተ በምድራቸው ውርሻ አይኖርህም፤ በመካከላቸውም ርስት አይኖርህም።+ በእስራኤላውያን መካከል የአንተ ድርሻም ሆነ ውርሻ እኔ ነኝ።+ +21 “እንግዲህ የሌዊ ወንዶች ልጆች ለሚያከናውኑት አገልግሎት ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ለሚሰጡት አገልግሎት በእስራኤል ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር አንድ አሥረኛ ውርሻ አድርጌ እንደሰጠኋቸው+ ልብ በል። +22 ከእንግዲህ እስራኤላውያን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መቅረብ አይችሉም፤ ከቀረቡ ግን ኃጢአት ሆኖባቸው ይሞታሉ። +23 በመገናኛ ድንኳኑ የሚቀርበውን አገልግሎት ማከናወን ያለባቸው ሌዋውያኑ ራሳቸው ናቸው፤ ሕዝቡ ለሚፈጽመው ስህተት ተጠያቂ የሚሆኑት እነሱ ናቸው።+ በእስራኤላውያን መካከል በውርስ የሚያገኙት ርስት አይኖራቸውም፤+ ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ የሚቀጥል ዘላቂ ደንብ ነው። +24 ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ መዋጮ አድርጎ ለይሖዋ የሚያዋጣውን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ ውርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። እኔም ‘በእስራኤላውያን መካከል በውርስ የሚያገኙት ርስት አይኖራቸውም’ ያልኳቸው ለዚህ ነው።”+ +25 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +26 “ሌዋውያኑን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእስራኤላውያን ላይ ውርሻችሁ አድርጌ የሰጠኋችሁን አንድ አሥረኛ ከእነሱ እጅ ትቀበላላችሁ፤+ እናንተ ደግሞ የአንድ አሥረኛውን አንድ አሥረኛ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ።+ +27 ይህ ለእናንተ እንደ መዋጮ ይኸውም ከአውድማ እንደገባ እህል+ ወይም ከወይን መጭመቂያ አሊያም ከዘይት መጭመቂያ እንደተገኘ የተትረፈረፈ ምርት ተደርጎ ይታሰብላችኋል። +28 በዚህ መንገድ እናንተም ከእስራኤላውያን ከምትቀበሉት አንድ አሥረኛ ሁሉ ላይ ለይሖዋ መዋጮ ታዋጣላችሁ፤ ከእሱም ላይ የይሖዋን መዋጮ ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ። +29 ከምትቀበሏቸው ስጦታዎች+ ሁሉ ላይ ምርጥ የሆነውን እንደ ቅዱስ ነገር አድርጋችሁ ለይሖዋ ሁሉንም ዓይነት መዋጮ ታዋጣላችሁ።’ +30 “እንዲህም በላቸው፦ ‘ከስጦታዎቹ ላይ ምርጥ የሆነውን በምታዋጡበት ጊዜ ይህ ለእናንተ ለሌዋውያኑ ከአውድማ እንደገባ ምርት እንዲሁም ከወይን መጭመቂያ ወይም ከዘይት መጭመቂያ እንደተገኘ ምርት ተደርጎ ይታሰብላችኋል። +31 ይህ በመገናኛ ድንኳኑ ለምታከናውኑት አገልግሎት የተሰጠ ደሞዛችሁ ስለሆነ እናንተም ሆናችሁ ቤተሰባችሁ በየትኛውም ቦታ ልትበሉት ትችላላችሁ።+ +32 ከስጦታዎቹ ላይ ምርጥ የሆነውን መዋጮ እስካደረጋችሁ ድረስ ኃጢአት አይሆንባችሁም፤ የእስራኤላውያንን ቅዱስ ነገሮች ማርከስ የለባችሁም፤ እንዲህ ካደረጋችሁ ግን ትሞታላችሁ።’”+ +23 ከዚያም በለዓም ባላቅን “እዚህ ቦታ ላይ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፤+ እንዲሁም ሰባት በሬዎችና ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅልኝ” አለው። +2 ባላቅም ወዲያውኑ በለዓም እንዳለው አደረገ። ባላቅና በለዓም በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረቡ።+ +3 ከዚያም በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “አንተ እዚህ የሚቃጠለው መባህ አጠገብ ቆይ፤ እኔ ግን ልሂድ። ምናልባት ይሖዋ ይገለጥልኝ ይሆናል። እሱ የሚገልጥልኝን ማንኛውንም ነገር እነግርሃለሁ።” በመሆኑም በለዓም ወደ አንድ ገላጣ ኮረብታ ሄደ። +4 በለዓምም ከአምላክ ጋር በተገናኘ ጊዜ+ “ሰባቱን መሠዊያዎች በመደዳ አቁሜያቸዋለሁ፤ በእያንዳንዱም መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቅርቤያለሁ” አለው። +5 ይሖዋም በበለዓም አፍ ላይ ይህን ቃል አስቀመጠ፦+ “ወደ ባላቅ ተመለስና እንዲህ ብለህ ንገረው።” +6 በመሆኑም በለዓም ተመለሰ፤ እሱም ባላቅን ከሞዓብ መኳንንት ሁሉ ጋር በሚቃጠለው መባው አጠገብ ቆሞ አየው። +7 ከዚያም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+ “የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ከአራም፣+ከምሥራቅ ተራሮች አመጣኝ፤ ‘ና፣ ያዕቆብን እርገምልኝ። አዎ ና፣ እስራኤልን አውግዝልኝ’ አለኝ።+ + 8 አምላክ ያልረገመውን እኔ እንዴት ልረግም እችላለሁ? ይሖዋ ያላወገዘውንስ እኔ እንዴት ላወግዝ እችላለሁ?+ + 9 ከዓለቶቹ አናት ላይ ሆኜ አያቸዋለሁ፤ከኮረብቶቹም ላይ ሆኜ እመለከታቸዋለሁ። በዚያ እንደ አንድ ሕዝብ ብቻቸውን ሰፍረዋል፤+ከሌሎች ብሔራት እንደ አንዱ አድርገው ራሳቸውን አይቆጥሩም።+ +10 ከብዛቱ የተነሳ እንደ አፈር የሆነውን ያዕቆብን ማን ሊቆጥረው ይችላል?+የእስራኤልንስ ሩብ ማን ይቆጥረዋል? የቅኖች ዓይነት አሟሟት ልሙት፤*መጨረሻዬም እንደ እነሱ ይሁን።” +11 ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? እኔ እኮ ያመጣሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነው፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አልፈየድክልኝም።”+ +12 እሱም መልሶ “እኔ መናገር ያለብኝ ይሖዋ በአፌ ላይ ያስቀመጠውን ብቻ አይደለም?” አለ።+ +13 ከዚያም ባላቅ እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ እነሱን ማየት ወደምትችልበት ሌላ ቦታ አብረን እንሂድ። እርግጥ ሁሉንም አታያቸውም፤ የምታያቸው በከፊል ብቻ ነው። እዚያ ሆነህ እርገምልኝ።”+ +14 እሱም በጲስጋ አናት+ ላይ ወደሚገኘው የጾፊም ሜዳ ወሰደው፤ በዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረበ።+ +15 በለዓምም ባላቅን “እኔ ከእሱ ጋር ለመገናኘት ወደዚያ ስሄድ አንተ እዚሁ የሚቃጠለው መባህ አጠገብ ቆይ” አለው። +16 ይሖዋም ከበለዓም ጋር ተገናኘ፤ በአፉም ላይ ይህን ቃል አስቀመጠ፦+ “ወደ ባላቅ ተመለስና እንዲህ ብለህ ንገረው።” +17 በመሆኑም በለዓም ወደ ባላቅ ተመለሰ፤ ባላቅንም በሚቃጠለው መባው አጠገብ ሲጠብቀው አገኘው፤ የሞዓብ መኳንንትም ከእሱ ጋር ነበሩ። ከዚያም ባላቅ “ለመሆኑ ይሖዋ ምን አለ?” ሲል ጠየቀው። +18 በለዓምም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+ “ባላቅ ተነስ፤ አዳምጥ። የሴፎር ልጅ ሆይ፣ ጆሮህን ስጠኝ። +19 አምላክ እንደ ሰው አይዋሽም፤+እንደ ሰው ልጅም ሐሳቡን አይለውጥም።*+ እሱ ያለውን አያደርገውም? የተናገረውንስ አይፈጽመውም?+ +20 እንግዲህ የእኔ ተልእኮ መባረክ ነው፤እሱ እንደሆነ ባርኳል፤+ እኔ ደግሞ ልለውጠው አልችልም።+ +21 ያዕቆብን ለማጥቃት የታሰበን ማንኛውንም አስማታዊ ኃይል ዝም ብሎ አያልፍም፤በእስራኤል ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንዲደርስ አይፈቅድም። አምላኩ ይሖዋ ከእነሱ ጋር ነው፤+በመካከላቸውም እንደ ንጉሥ ከፍ ባለ ድምፅ ይወደሳል። +22 አምላክ ከግብፅ አውጥቷቸዋል።+ እሱም ለእነሱ ልክ እንደ ጎሽ ቀንዶች ነው።+ +23 በያዕቆብ ላይ የሚሠራ ምንም ዓይነት ድግምት የለምና፤+በእስራኤልም ላይ የሚሠራ ምንም ዓይነት ሟርት የለም።+ በዚህ ጊዜ ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል ‘አምላክ ያደረገውን ተመልከቱ!’ ይባላል። +24 ልክ እንደ አንበሳ የሚነሳው ሕዝብ ይህ ነው፤እሱም እንደ አንበሳ ተነስቶ ይቆማል።+ ያደነውን እስኪበላ፣የተገደሉትንም ደማቸውን እስኪጠጣ ድረስ አይተኛም።” +25 ከዚያም ባላቅ በለዓምን “እንግዲያው ልትረግመው ካልቻልክ ልትባርከውም አይገባም” አለው። +26 በለዓምም መልሶ ባላቅን “‘እኔ የማደርገው ይሖዋ የሚናገረውን ብቻ ነው’ ብዬህ አልነበረም?” አለው።+ +27 ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ና፤ እስቲ አሁንም ወደ ሌላ ቦታ ልውሰድህ። ምናልባትም እውነተኛው አምላክ እዚያ ሆነህ እሱን እንድትረግምልኝ ይፈቅድ ይሆናል።”+ +28 ስለዚህ ባላቅ በለዓምን፣ የሺሞንን* ፊት ለፊት ማየት ወደሚቻልበት ወደ ፌጎር አናት ወሰደው።+ +29 ከዚያም በለዓም ባላቅን “እዚህ ቦታ ላይ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፤ እንዲሁም ሰባት በሬዎችና ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅልኝ” አለው።+ +30 ባላቅም በለዓም እንዳለው አደረገ፤ ከዚያም በእያንዳንዱ መሠዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረበ። +34 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ለእስራኤላውያን ይህን መመሪያ ስጣቸው፦ ‘ወደ ከነአን ምድር ስትገቡ+ ርስት አድርጋችሁ የምትወርሷት ምድር ይኸውም የከነአን ምድር ከነወሰኖቿ ይህች ናት።+ +3 “‘በስተ ደቡብ ያለው ወሰናችሁ ከጺን ምድረ በዳ ተነስቶ እስከ ኤዶም ጠረፍ ድረስ ይዘልቃል፤ በስተ ምሥራቅ ያለው ደቡባዊ ወሰናችሁ ደግሞ ከጨው ባሕር* ዳርቻ ጀምሮ ያለው ይሆናል።+ +4 ወሰናችሁ አቅጣጫውን በመቀየር ከአቅራቢም አቀበት+ በስተ ደቡብ አድርጎ እስከ ጺን ድረስ ይዘልቃል፤ መጨረሻውም ከቃዴስበርኔ+ በስተ ደቡብ ይሆናል። ከዚያም ወደ ሃጻርአዳር+ ይሄድና ወደ አጽሞን ይዘልቃል። +5 ወሰኑ አጽሞን ላይ ሲደርስ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ ግብፅ ደረቅ ወንዝ* ይሄዳል፤ መጨረሻውም ባሕሩ* ይሆናል።+ +6 “‘ምዕራባዊ ወሰናችሁ ደግሞ ታላቁ ባሕርና* የባሕሩ ዳርቻ ይሆናል። ይህ ምዕራባዊ ወሰናችሁ ይሆናል።+ +7 “‘ሰሜናዊ ወሰናችሁ የሚከተለው ይሆናል፦ ከታላቁ ባሕር አንስቶ እስከ ሆር ተራራ ድረስ ምልክት በማድረግ ወሰናችሁን ከልሉ። +8 ከሆር ተራራም አንስቶ እስከ ሌቦሃማት*+ ድረስ ወሰኑን ምልክት አድርጉ፤ የወሰኑም መጨረሻ ጼዳድ+ ይሆናል። +9 ወሰኑም እስከ ዚፍሮን ድረስ ይዘልቃል፤ መጨረሻውም ሃጻርኤናን+ ይሆናል። ይህ ሰሜናዊ ወሰናችሁ ይሆናል። +10 “‘ከዚያም በስተ ምሥራቅ በኩል ወሰናችሁን ከሃጻርኤናን አንስቶ እስከ ሸፋም ድረስ ምልክት አድርጉ። +11 ወሰኑም ከሸፋም አንስቶ ከአይን በስተ ምሥራቅ እስከሚገኘው እስከ ሪብላ ድረስ ይዘልቃል፤ ከዚያም ቁልቁል ወርዶ የኪኔሬትን ባሕር* ምሥራቃዊ ዳርቻ አቋርጦ ያልፋል።+ +12 ወሰኑ ወደ ዮርዳኖስ ይወርድና መጨረሻው ጨው ባሕር ይሆናል።+ እንግዲህ ምድራችሁ+ በዙሪያዋ ካሉት ወሰኖቿ ጋር ይህች ናት።’” +13 በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ይሖዋ ለዘጠኙ ነገዶችና ለግማሹ ነገድ እንዲሰጥ ባዘዘው መሠረት ርስት አድርጋችሁ በዕጣ የምትከፋፈሏት+ ምድር ይህች ናት። +14 የሮቤላውያን ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፣ የጋዳውያን ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስቀድመው ርስታቸውን ወስደዋልና።+ +15 ሁለቱ ነገድና ግማሹ ነገድ በኢያሪኮ አቅራቢያ ከዮርዳኖስ ክልል በስተ ምሥራቅ በፀሐይ መውጫ አቅጣጫ ርስታቸውን አግኝተዋል።”+ +16 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +17 “ምድሪቱን ለእናንተ ርስት አድርገው የሚያከፋፍሏችሁ ካህኑ አልዓዛርና+ የነዌ ልጅ ኢያሱ+ ናቸው። +18 ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ ለማከፋፈል ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አንድ አለቃ ትወስዳላችሁ።+ +19 የሰዎቹም ስም የሚከተለው ነው፦ ከይሁዳ ነገድ+ የየፎኒ ልጅ ካሌብ፣+ +20 ከስምዖን ልጆች ነገድ+ የአሚሁድ ልጅ ሸሙኤል፣ +21 ከቢንያም ነገድ+ የኪስሎን ልጅ ኤሊዳድ፣ +22 ከዳን ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የዮግሊ ልጅ ቡቂ፣ +23 ከዮሴፍ ልጆች+ መካከል ከምናሴ ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የኤፎድ ልጅ ሃኒ���ል፣ +24 ከኤፍሬም ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የሺፍጣን ልጅ ቀሙኤል፣ +25 ከዛብሎን ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የፓርናክ ልጅ ኤሊጻፋን፣ +26 ከይሳኮር ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የአዛን ልጅ ፓልጢኤል፣ +27 ከአሴር ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የሸሎሚ ልጅ አሂሑድ፣ +28 ከንፍታሌም ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የአሚሁድ ልጅ ፐዳሄል።” +29 ይሖዋ በከነአን ምድር ለእስራኤላውያን መሬቱን እንዲያከፋፍሉ ያዘዛቸው እነዚህ ናቸው።+ +19 ይሖዋ ሙሴንና አሮንን በድጋሚ እንዲህ አላቸው፦ +2 “ይሖዋ ያዘዘው የሕጉ ደንብ ይህ ነው፦ ‘እንከን የሌለባትና+ ቀንበር ተጭኖባት የማታውቅ በጥሩ ሁኔታ ላይ የምትገኝ አንዲት ቀይ ላም እንዲያመጡልህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። +3 ለካህኑ ለአልዓዛርም ስጡት፤ እሱም ከሰፈሩ ውጭ ይወስዳትና በፊቱ ትታረዳለች። +4 ከዚያም ካህኑ አልዓዛር ከደሙ ላይ በጣቱ ወስዶ ደሙን በቀጥታ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።+ +5 ከዚያም ላሟ ዓይኑ እያየ ትቃጠላለች። ቆዳዋ፣ ሥጋዋና ደሟ ከፈርሷ ጋር አብሮ ይቃጠላል።+ +6 ካህኑም የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ሂሶጵና+ ደማቅ ቀይ ማግ ወስዶ ላሟ የምትቃጠልበት እሳት ውስጥ ይጨምራል። +7 ከዚያም ካህኑ ልብሶቹን በውኃ ያጥባል፤ ገላውንም ይታጠባል፤ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል፤ ሆኖም ካህኑ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። +8 “‘ላሟን ያቃጠለውም ሰው ልብሶቹን በውኃ ያጥባል፤ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። +9 “‘ንጹሕ የሆነ ሰው የላሟን አመድ+ አፍሶ ከሰፈሩ ውጭ ባለ ንጹሕ ቦታ ያጠራቅመዋል፤ የእስራኤል ማኅበረሰብም ለማንጻት የሚያገለግለውን ውኃ+ ለማዘጋጀት እንዲውል አመዱን ያስቀምጠው። ይህ የኃጢአት መባ ነው። +10 የላሟን አመድ የሚያፍሰው ሰው ልብሶቹን ያጥባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። “‘ይህም ለእስራኤላውያንና በመካከላቸው ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል።+ +11 የሞተ ሰው* የነካ ማንኛውም ሰው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።+ +12 ይህ ሰው በሦስተኛው ቀን ራሱን በውኃው ያንጻ፤ በሰባተኛውም ቀን ንጹሕ ይሆናል። በሦስተኛው ቀን ራሱን ካላነጻ ግን በሰባተኛው ቀን ንጹሕ አይሆንም። +13 የሞተ ሰው* የነካና ራሱን ያላነጻ ሰው ሁሉ የይሖዋን የማደሪያ ድንኳን አርክሷል፤+ ይህ ሰው* ከእስራኤል መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት።+ የሚያነጻው ውኃ+ ስላልተረጨበት ርኩስ ነው። አሁንም ከርኩሰቱ አልነጻም። +14 “‘አንድ ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፦ ወደ ድንኳኑ የሚገባም ሆነ ቀድሞውኑም በድንኳኑ ውስጥ የነበረ ሰው ሁሉ ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል። +15 መክደኛው ላዩ ላይ ያልታሰረ ክፍት ዕቃ ሁሉ ርኩስ ነው።+ +16 በሰይፍ የተገደለን ወይም በድንን ወይም አፅምን ወይም መቃብርን የነካ በሜዳ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ለሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።+ +17 ለረከሰውም ሰው ከተቃጠለው የኃጢአት መባ አመድ ላይ ወስደው በዕቃ በማድረግ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ይጨምሩበት። +18 ከዚያም ንጹሕ የሆነ ሰው+ ሂሶጵ+ ወስዶ ውኃው ውስጥ ከነከረ በኋላ በድንኳኑ፣ በዕቃዎቹ ሁሉ፣ እዚያ በነበረው ሰው* ሁሉና አፅሙን ወይም የተገደለውን ሰው አሊያም በድኑን ወይም መቃብሩን በነካው ሰው ላይ ይረጨዋል። +19 ንጹሕ የሆነውም ሰው ውኃውን በረከሰው ሰው ላይ በሦስተኛው ቀንና በሰባተኛው ቀን ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ከኃጢአት ያነጻዋል፤+ ከዚያም ሰውየው ልብሶቹን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ ማታም ላይ ንጹሕ ይሆናል። +20 “‘ሆኖም የረከሰውና ራሱን ያላነጻው ሰው የይሖዋን መቅደስ ስላረከሰ ይህ ���ው* ከጉባኤው መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት።+ የሚያነጻው ውኃ ስላልተረጨበት ሰውየው ርኩስ ነው። +21 “‘ይህ ለእነሱ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል፦ የሚያነጻውን ውኃ+ የሚረጨው ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ የሚያነጻውን ውኃ የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። +22 የረከሰው ሰው የሚነካው ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል፤ ይህን የነካ ሰውም* እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።’”+ +20 በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ወደ ጺን ምድረ በዳ መጣ፤ ሕዝቡም በቃዴስ+ ተቀመጠ። ሚርያም+ የሞተችውም ሆነ የተቀበረችው በዚያ ነበር። +2 በዚያ ለማኅበረሰቡ የሚሆን ውኃ አልነበረም፤+ ሕዝቡም ሙሴንና አሮንን በመቃወም በእነሱ ላይ ተሰበሰበ። +3 ሕዝቡም እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣላ፦+ “ምነው ወንድሞቻችን በይሖዋ ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ሞተን ባረፍነው ኖሮ! +4 እኛም ሆንን ከብቶቻችን እዚህ እንድናልቅ የይሖዋን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት ለምንድን ነው?+ +5 ከግብፅ አውጥታችሁ ወደዚህ መጥፎ ቦታ እየመራችሁ ያመጣችሁን ለምንድን ነው?+ ይህ ቦታ እህልም ሆነ በለስ፣ የወይን ፍሬም ሆነ ሮማን የሌለበት ነው፤ የሚጠጣ ውኃም የለም።”+ +6 ከዚያም ሙሴና አሮን ከጉባኤው ፊት ተነስተው ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በመሄድ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ፤ የይሖዋም ክብር ተገለጠላቸው።+ +7 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +8 “በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበረሰቡን ሰብስቡ፤ ዓለቱም ውኃውን እንዲሰጥ በእነሱ ፊት ተናገሩት፤ አንተም ከዓለቱ ውኃ ታፈልቅላቸዋለህ፤ ማኅበረሰቡም ሆነ ከብቶቻቸው እንዲጠጡም ትሰጣቸዋለህ።”+ +9 ሙሴም ልክ እንደታዘዘው በትሩን ከይሖዋ ፊት ወሰደ።+ +10 ከዚያም ሙሴና አሮን ጉባኤውን በዓለቱ ፊት ሰበሰቡ፤ እሱም “እናንተ ዓመፀኞች ስሙ! ከዚህ ዓለት ለእናንተ ውኃ ማፍለቅ አለብን?” አላቸው።+ +11 ሙሴም ይህን ካለ በኋላ እጁን አንስቶ ዓለቱን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ውኃውም ይንዶለዶል ጀመር፤ ማኅበረሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ።+ +12 በኋላም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “በእስራኤል ሕዝብ ፊት በእኔ ስላልታመናችሁና እኔን ስላልቀደሳችሁ ይህን ጉባኤ እኔ ወደምሰጠው ምድር ይዛችሁ አትገቡም።”+ +13 ይሖዋ በመካከላቸው ይቀደስ ዘንድ እስራኤላውያን ከእሱ ጋር የተጣሉባቸው የመሪባ*+ ውኃዎች እነዚህ ናቸው። +14 ከዚያም ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት ከቃዴስ መልእክተኞችን ላከ፦+ “ወንድምህ እስራኤል+ እንዲህ ይላል፦ ‘መቼም የደረሰብንን መከራ ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ። +15 አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወርደው ነበር፤+ እኛም በግብፅ ለብዙ ዓመታት* ኖርን፤+ ግብፃውያኑም በእኛም ሆነ በአባቶቻችን ላይ በደል ይፈጽሙብን ነበር።+ +16 በመጨረሻም ወደ ይሖዋ ጮኽን፤+ እሱም ጩኸታችንን ሰምቶ መልአክ በመላክ+ ከግብፅ አወጣን፤ ይኸው አሁን ድንበርህ ላይ ባለችው በቃዴስ ከተማ እንገኛለን። +17 እናም አሁን እባክህ በምድርህ እንለፍ። በየትኛውም እርሻ ወይም በየትኛውም የወይን ቦታ አቋርጠን አንሄድም፤ ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር ሳንል በንጉሡ መንገድ እንሄዳለን።’”+ +18 ኤዶም ግን “ክልላችንን አቋርጠህ ማለፍ አትችልም። እንዲህ ካደረግክ ወጥቼ በሰይፍ እገጥምሃለሁ” አለው። +19 እስራኤላውያንም መልሰው እንዲህ አሉት፦ “አውራ ጎዳናውን ይዘን እናቀናለን፤ እኛም ሆን ከብቶቻችን ከውኃህ ከጠጣን ዋጋውን እንከፍልሃለን።+ በእግራችን አልፈን ከመሄድ በስተቀር ሌላ ምንም ነገር አንፈልግም።”+ +20 እሱ ግን አሁንም “በዚህ ማለፍ አትችልም”+ ሲል መልስ ሰጠ። ከዚያም ኤዶም ብዙ ሕዝብና ኃያል ሠራዊት* ይዞ ሊገጥመው ወጣ። +21 በዚህ መንገድ ኤዶም እስራኤል በክልሉ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ስለዚህ እስራኤል ከእሱ ተመለሰ።+ +22 የእስራኤል ሕዝብ ይኸውም መላው ማኅበረሰብ ከቃዴስ ተነስቶ ወደ ሆር ተራራ+ መጣ። +23 ከዚያም ይሖዋ በኤዶም ምድር ወሰን ላይ ባለው በሆር ተራራ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +24 “አሮን ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል።*+ ሁለታችሁም ከመሪባ ውኃ ጋር በተያያዘ በሰጠሁት ትእዛዝ ላይ ስላመፃችሁ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ምድር አይገባም።+ +25 አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሆር ተራራ ውጣ። +26 የአሮንን ልብስ አውልቀህ+ ልጁን አልዓዛርን+ አልብሰው፤ አሮንም በዚያ ይሞታል።”* +27 በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ እነሱም መላው ማኅበረሰብ እያየ ወደ ሆር ተራራ ወጡ። +28 ሙሴም የአሮንን ልብስ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው። ከዚያም አሮን እዚያው ተራራው አናት ላይ ሞተ።+ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ወረዱ። +29 መላው ማኅበረሰብም አሮን መሞቱን አየ፤ በዚህ ጊዜ የእስራኤል ቤት በሙሉ ለአሮን 30 ቀን አለቀሰለት።+ +3 ይሖዋ በሲና ተራራ+ ላይ ከሙሴ ጋር በተነጋገረ ጊዜ የአሮንና የሙሴ የቤተሰብ ሐረግ* ይህ ነበር። +2 የአሮን ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦ የበኩር ልጁ ናዳብ፣ አቢሁ፣+ አልዓዛርና+ ኢታምር።+ +3 የአሮን ወንዶች ልጆች ስም ይኸውም ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ የተሾሙት* ቅቡዕ የሆኑት ካህናት ስም ይህ ነበር።+ +4 ይሁንና ናዳብና አቢሁ በሲና ምድረ በዳ በይሖዋ ፊት ያልተፈቀደ እሳት ባቀረቡ ጊዜ በይሖዋ ፊት ሞቱ፤+ እነሱም ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም። አልዓዛርና+ ኢታምር+ ግን ከአባታቸው ከአሮን ጋር በክህነት ማገልገላቸውን ቀጠሉ። +5 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +6 “የሌዊን ነገድ+ አምጥተህ በካህኑ በአሮን ፊት አቁመው፤ እነሱም ያገልግሉት።+ +7 ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ የሚያከናውኑትን አገልግሎት በመፈጸም ለእሱም ሆነ ለመላው ማኅበረሰብ ያለባቸውን ኃላፊነት በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ይወጡ። +8 የመገናኛ ድንኳኑን ዕቃዎች በሙሉ በኃላፊነት መቆጣጠርና+ ከማደሪያ ድንኳኑ ጋር የተያያዘውን አገልግሎት በማከናወን ለእስራኤል ልጆች ያለባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል።+ +9 ሌዋውያኑን ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ስጣቸው። እነሱ የተሰጡ ናቸው፤ ከእስራኤላውያን መካከል ለእሱ የተሰጡ ናቸው።+ +10 አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ሹማቸው፤ እነሱም የክህነት ኃላፊነታቸውን ይወጡ፤+ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው* ወደ መቅደሱ ቢቀርብ ይገደል።”+ +11 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +12 “በእስራኤላውያን በኩሮች ሁሉ* ምትክ ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል እወስዳለሁ፤+ ሌዋውያኑም የእኔ ይሆናሉ። +13 ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነው።+ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን+ በእስራኤላውያን መካከል ያለውን የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ለራሴ ቀድሻለሁ።+ እነሱ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ።” +14 በተጨማሪም ይሖዋ በሲና ምድረ በዳ+ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +15 “የሌዊን ወንዶች ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶችና በየቤተሰባቸው መዝግብ። አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ መዝግብ።”+ +16 በመሆኑም ሙሴ ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ልክ እንደታዘዘው መዘገባቸው። +17 የሌዊ ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦ ጌድሶን፣ ቀአትና ሜራሪ።+ +18 የጌድሶን ወንዶች ልጆች ስም በየቤተሰባቸው ይህ ነበር፦ ሊብኒ እና ሺምአይ።+ +19 የቀአት ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸው አምራም፣ ይጽሃር፣ ኬብ��ንና ዑዚኤል ነበሩ።+ +20 የሜራሪ ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸው ማህሊ+ እና ሙሺ+ ነበሩ። የሌዋውያኑ ቤተሰቦች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ነበሩ። +21 የሊብናውያን+ ቤተሰብና የሺምአያውያን ቤተሰብ የተገኘው ከጌድሶን ነበር። የጌድሶናውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ። +"22 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው 7,500 ነበር።+" +23 የጌድሶናውያን ቤተሰቦች የሰፈሩት ከማደሪያ ድንኳኑ በስተ ኋላ+ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ነበር። +24 የጌድሶናውያን የአባቶች ቤት አለቃ የላኤል ልጅ ኤሊያሳፍ ነበር። +25 የጌድሶን ልጆች+ በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ያለባቸው ኃላፊነት ከማደሪያ ድንኳኑ፣ ከድንኳኑ ጨርቅ፣+ ከመደረቢያው፣+ ከመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ መከለያ፣*+ +26 ከግቢው መጋረጃዎች፣+ በማደሪያ ድንኳኑ ዙሪያ በሚገኘው ግቢ መግቢያ ላይ ካለው መከለያ፣*+ ከመሠዊያው፣ ከድንኳኑ ገመዶችና ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ካለው አገልግሎት ሁሉ ጋር የተያያዘ ነበር። +27 የአምራማውያን ቤተሰብ፣ የይጽሃራውያን ቤተሰብ፣ የኬብሮናውያን ቤተሰብና የዑዚኤላውያን ቤተሰብ የተገኘው ከቀአት ነበር። የቀአታውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ።+ +"28 አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው 8,600 ነበር፤ እነሱም ቅዱሱን ስፍራ የመንከባከብ ኃላፊነት ነበረባቸው።+" +29 የቀአት ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች ከማደሪያ ድንኳኑ በስተ ደቡብ በኩል ሰፍረው ነበር።+ +30 የቀአታውያን ቤተሰቦች የአባቶች ቤት አለቃ የዑዚኤል+ ልጅ ኤሊጻፋን ነበር። +31 ኃላፊነታቸውም ከታቦቱ፣+ ከጠረጴዛው፣+ ከመቅረዙ፣+ ከመሠዊያዎቹ፣+ በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል ከሚጠቀሙባቸው ዕቃዎች፣+ ከመከለያውና*+ ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ካለው አገልግሎት ሁሉ ጋር የተያያዘ ነበር።+ +32 የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር+ ሲሆን እሱም ከቅዱሱ ስፍራ ጋር በተያያዘ ኃላፊነት የተጣለባቸውን በበላይነት ይከታተል ነበር። +33 የማህላውያን ቤተሰብና የሙሻውያን ቤተሰብ የተገኘው ከሜራሪ ነበር። የሜራሪ ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ።+ +"34 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው 6,200 ነበር።+" +35 የሜራሪ ቤተሰቦች የአባቶች ቤት አለቃ የአቢሃይል ልጅ ጹሪኤል ነበር። እነሱም ከማደሪያ ድንኳኑ በስተ ሰሜን በኩል ሰፍረው ነበር።+ +36 የሜራሪ ወንዶች ልጆች የተጣለባቸው ኃላፊነት የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች፣+ አግዳሚ እንጨቶቹን፣+ ዓምዶቹን፣+ መሰኪያዎቹን፣ ዕቃዎቹን በሙሉ፣+ ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ያለውን አገልግሎት ሁሉ+ +37 እንዲሁም በግቢው ዙሪያ ያሉትን ዓምዶች፣ መሰኪያዎቻቸውን፣+ የድንኳን ካስማዎቻቸውንና የድንኳን ገመዶቻቸውን በበላይነት መቆጣጠር ነበር። +38 በማደሪያ ድንኳኑ ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ፀሐይ በምትወጣበት አቅጣጫ የሰፈሩት ሙሴና አሮን እንዲሁም የአሮን ወንዶች ልጆች ነበሩ። እስራኤላውያንን ወክለው እንዲያከናውኑ የተጣለባቸው ግዴታም መቅደሱን የመንከባከብ ኃላፊነት ነበር። ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው* ወደ +"39 ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ሙሴና አሮን በየቤተሰባቸው የመዘገቧቸው አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች በሙሉ 22,000 ነበሩ። " +40 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤላውያን መካከል አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸውን+ በኩር የሆኑ ወንዶች በሙሉ መዝግብ፤ ከቆጠርካቸውም በኋላ ስማቸውን በዝርዝር ጻፍ። +41 ከእስራኤላውያን መካከል በኩር በሆኑት ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ለይልኝ፤+ የሌዋውያኑን የቤት እንስሳትም ከእስራኤላውያን የቤት እንስሳት መካከል በኩር በሆኑት ሁሉ ምትክ ለይልኝ፤+ እኔ ይሖዋ ነኝ።” +42 ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ከእስራኤላውያን መካከል በኩር የሆኑትን ሁሉ መዘገበ። +"43 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው በየስማቸው የተመዘገቡት በኩር የሆኑ ወንዶች ብዛታቸው 22,273 ነበር። " +44 ይሖዋ እንዲህ በማለት ሙሴን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ +45 “ከእስራኤላውያን መካከል በኩር በሆኑት ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ለይ፤ የሌዋውያኑን የቤት እንስሳትም በቤት እንስሶቻቸው ሁሉ ምትክ ለይ፤ ሌዋውያኑ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ። +46 ቁጥራቸው ከሌዋውያኑ ቁጥር የበለጠውን 273+ እስራኤላውያን በኩሮች ለመዋጀት+ +47 ለእያንዳንዱ ግለሰብ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል* መሠረት አምስት ሰቅል* ውሰድ።+ አንድ ሰቅል 20 ጌራ* ነው።+ +48 አንተም ገንዘቡን ቁጥራቸው ከሌዋውያኑ ቁጥር የተረፈውን ሰዎች ለመዋጀት የተከፈለ ዋጋ አድርገህ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ስጥ።” +49 በመሆኑም ሙሴ ቁጥራቸው ከሌዋውያኑ ቁጥር የተረፈውን ሰዎች ለመዋጀት የመዋጃውን ገንዘብ ሰበሰበ። +"50 እሱም ገንዘቡን ይኸውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 1,365 ሰቅል ከእስራኤላውያኑ በኩሮች ላይ ወሰደ።" +51 ከዚያም ሙሴ በይሖዋ ቃል* መሠረት ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው የመዋጃውን ገንዘብ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ሰጣቸው። +24 በለዓምም ይሖዋ እስራኤልን መባረክ እንደወደደ* ሲያይ ዳግመኛ ድግምት ፍለጋ አልሄደም፤+ ከዚህ ይልቅ ፊቱን ወደ ምድረ በዳ አቀና። +2 በለዓም አሻግሮ ሲመለከት እስራኤል በየነገዱ እንደሰፈረ አየ፤+ ከዚያም የአምላክ መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ።+ +3 በመሆኑም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+ “የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣ + 4 የአምላክን ቃል የሰማው፣ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ ያየውዓይኖቹ ሳይከደኑ የሰገደው ሰው ቃል ይህ ነው፦+ + 5 ያዕቆብ ሆይ፣ ድንኳኖችህ፣እስራኤል ሆይ፣ የማደሪያ ድንኳኖችህ እንዴት ያማሩ ናቸው!+ + 6 እንደ ሸለቆዎች፣*በወንዝም ዳር እንዳሉ የአትክልት ስፍራዎች በረጅሙ ተዘርግተዋል።+ይሖዋ እንደተከላቸው እሬቶች፣በውኃም ዳር እንዳሉ አርዘ ሊባኖሶች ሆነዋል። + 7 ከሁለቱም አቁማዳዎቹ ውኃ ይንጠባጠባል፤ዘሩም በብዙ ውኃዎች አጠገብ ተዘርቷል።+ ንጉሡም+ ከአጋግ+ የላቀ ይሆናል፤መንግሥቱም ከፍ ከፍ ይላል።+ + 8 አምላክ ከግብፅ አወጣው፤ለእነሱ ልክ እንደ ጎሽ ቀንዶች ነው። የሚጨቁኑትን ብሔራት ይበላል፤+አጥንቶቻቸውንም ይቆረጣጥማል፤ በፍላጻዎቹም ያደቃቸዋል። + 9 አድብቷል፤ እንደ አንበሳም ተጋድሟል፤እንደ አንበሳስ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል? አንተን የሚባርኩህ የተባረኩ ናቸው፤የሚረግሙህም የተረገሙ ናቸው።”+ +10 በዚህ ጊዜ ባላቅ በበለዓም ላይ በጣም ተቆጣ። ባላቅም በንቀት እጆቹን አጨብጭቦ በለዓምን እንዲህ አለው፦ “የጠራሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤+ አንተ ግን ይኸው ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው እንጂ ምንም የፈየድከው ነገር የለም። +11 በል አሁን ቶሎ ብለህ ወደ ቤትህ ሂድ። እኔ እንኳ ታላቅ ክብር ላጎናጽፍህ አስቤ ነበር፤+ ይሖዋ ግን ክብር ነፈገህ።” +12 በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞች እንዲህ ብዬ ነገሬአቸው አልነበረም? +13 ‘ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላውን ቤቱን ቢሰጠኝ እንኳ ከይሖዋ ትእዛዝ ውጭ በገዛ ፈቃዴ* መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር ማድረግ አልችልም። እኔ የምናገረው ይሖዋ የሚነግረኝን ብቻ ነው።’+ +14 እንግዲህ አሁን ወደ ሕዝቤ ልሄድ ነው። ይልቅስ መጥተህ ወደፊት* ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚ��ደርገውን ልንገርህ።” +15 ስለዚህ ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+ “የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣+ +16 የአምላክን ቃል የሰማው፣የልዑሉን አምላክ እውቀት የሚያውቀው ሰው ቃል ይህ ነው፤ዓይኖቹ ሳይከደኑ እየሰገደ ሳለሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ አየ፦ +17 አየዋለሁ፣ አሁን ግን አይደለም፤እመለከተዋለሁ፣ በቅርቡ ግን አይደለም። ኮከብ+ ከያዕቆብ ይወጣል፤በትረ መንግሥትም+ ከእስራኤል ይነሳል።+ የሞዓብን ግንባር፣*የሁከት ልጆችንም ሁሉ ራስ ቅል ይፈረካክሳል።+ +18 እስራኤል ጀግንነቱን ሲያሳይኤዶም ርስቱ ይሆናል፤+ሴይርም+ የጠላቶቹ ርስት ይሆናል።+ +19 ከያዕቆብም አንዱ ድል እያደረገ ይወጣል፤+የተረፉትንም የከተማዋን ነዋሪዎች ሁሉ ያጠፋል።” +20 አማሌቅንም ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “አማሌቅ ከብሔራት መካከል የመጀመሪያ ነበር፤+ሆኖም በመጨረሻ ይጠፋል።”+ +21 ቄናውያንንም+ ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ ጎጆህም በቋጥኝ ላይ የተሠራ ነው። +22 ሆኖም አንድ ሰው ቄይንን ያቃጥላታል። አሦር ማርኮ እስኪወስዳችሁ ድረስ ምን ያህል ትቆዩ ይሆን?” +23 እሱም እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “አቤት! አምላክ ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ማን ይተርፍ ይሆን? +24 ከኪቲም+ የባሕር ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፤አሦርንም ያጠቃሉ፤+ደግሞም ኤቤርን ያሠቃያሉ። ሆኖም እሱም ፈጽሞ ይጠፋል።” +25 ከዚያም በለዓም+ ተነስቶ ወደ ስፍራው ተመለሰ። ባላቅም መንገዱን ቀጠለ። +32 የሮቤል ልጆችና+ የጋድ ልጆች+ እጅግ በጣም ብዙ ከብት ነበራቸው። እነሱም የያዜር+ እና የጊልያድ ምድር ለከብቶች የሚስማማ ስፍራ እንደሆነ አዩ። +2 በመሆኑም የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች መጥተው ሙሴን፣ ካህኑን አልዓዛርንና የማኅበረሰቡን አለቆች እንዲህ አሏቸው፦ +3 “የአጣሮት፣ የዲቦን፣ የያዜር፣ የኒምራ፣ የሃሽቦን፣+ የኤልዓሌ፣ የሰባም፣ የነቦ+ እና የቤኦን+ ምድር +4 ይሖዋ በእስራኤል ማኅበረሰብ ፊት ድል ያደረገው+ ሲሆን ለከብቶች ምቹ ነው፤ አገልጋዮችህ ደግሞ ብዙ ከብት አላቸው።”+ +5 አክለውም እንዲህ አሉ፦ “እንግዲህ በፊትህ ሞገስ ካገኘን ይህ ምድር ለአገልጋዮችህ ርስት ተደርጎ ይሰጥ። ዮርዳኖስን እንድንሻገር አታድርገን።” +6 ከዚያም ሙሴ የጋድን ልጆችና የሮቤልን ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እዚህ ተቀምጣችሁ ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት እንዲሄዱ ትፈልጋላችሁ? +7 የእስራኤል ልጆች ይሖዋ ወደሚሰጣቸው ምድር እንዳይሻገሩ ተስፋ የምታስቆርጧቸው ለምንድን ነው? +8 አባቶቻችሁ ምድሪቱን እንዲያዩ ከቃዴስበርኔ በላክኋቸው ጊዜ ያደረጉት ይህንኑ ነበር።+ +9 ወደ ኤሽኮል ሸለቆ*+ አቅንተው ምድሪቱን ካዩ በኋላ የእስራኤልን ሕዝብ ይሖዋ ወደሚሰጠው ምድር እንዳይገባ ተስፋ አስቆረጡት።+ +10 በዚያ ቀን የይሖዋ ቁጣ ነደደ፤ እንዲህም ሲል ማለ፦+ +11 ‘ከግብፅ ምድር ከወጡት መካከል 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማልኩላቸውን+ ምድር አያዩም፤+ ምክንያቱም በሙሉ ልባቸው አልተከተሉኝም፤ +12 ይሖዋን በሙሉ ልባቸው ከተከተሉት+ ከቀኒዛዊው ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና+ ከነዌ ልጅ ከኢያሱ+ በስተቀር አንዳቸውም ምድሪቱን አያዩም።’ +13 በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በይሖዋ ፊት ክፉ ድርጊት የፈጸመው ያ ትውልድ በሙሉ እስኪያልቅ ድረስ+ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው።+ +14 እናንተ የኃጢአተኞች ልጆች ደግሞ ይኸው በአባቶቻችሁ እግር ተተክታችሁ ይሖዋ በእስራኤል ላይ ይበልጥ እንዲቆጣ ታደርጋላችሁ። +15 እንግዲህ እናንተ እሱን ከመከተል ዞር ካላችሁ እሱም እንደገና በምድረ በዳ ይተዋቸዋል፤ እናንተም በዚህ ሁሉ ሕዝብ ላይ ጥፋት ታመጣላችሁ።” +16 በኋላም ወደ እሱ ቀርበው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲያው እዚሁ ለከብቶቻችን በድንጋይ ካብ በረት እንሥራ፤ ለልጆቻችንም ከተሞች እንገንባ። +17 ይሁን እንጂ ወደ ስፍራቸው እስክናስገባቸው ድረስ ለጦርነት ታጥቀን+ በእስራኤላውያን ፊት እንሄዳለን፤ በዚህም ጊዜ ልጆቻችን ከምድሪቱ ነዋሪዎች ተጠብቀው በተመሸጉት ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ። +18 እኛም እያንዳንዱ እስራኤላዊ የራሱን ርስት እስኪያገኝ ድረስ ወደ ቤታችን አንመለስም።+ +19 እኛ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው አካባቢ ርስት ካገኘን ከዮርዳኖስ ማዶና ከዚያ ባሻገር ባለው አካባቢ ከእነሱ ጋር ርስት አንካፈልም።”+ +20 ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ብታደርጉ ይኸውም በጦርነቱ ለመካፈል በይሖዋ ፊት ታጥቃችሁ ብትነሱ+ +21 እንዲሁም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ+ እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያችሁን ይዛችሁ በይሖዋ ፊት ዮርዳኖስን ብትሻገሩና +22 ምድሪቱ በይሖዋ ፊት እስክትገዛ ድረስ+ በዚያ ብትቆዩ፣ ከዚያ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፤+ በይሖዋም ሆነ በእስራኤላውያን ዘንድ ከበደል ነፃ ትሆናላችሁ። ከዚያም ይህች ምድር በይሖዋ ፊት የእናንተ ርስት ትሆናለች።+ +23 ይህን ባታደርጉ ግን በይሖዋ ላይ ኃጢአት ትሠራላችሁ። ለሠራችሁትም ኃጢአት ተጠያቂ እንደምትሆኑ እወቁ። +24 ስለዚህ ለልጆቻችሁ ከተሞችን መገንባትና ለመንጎቻችሁ በረት መሥራት የምትችሉ+ ቢሆንም የገባችሁትን ቃል መፈጸም ይኖርባችኋል።” +25 የጋድ ልጆችና የሮቤል ልጆችም ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ ጌታችን እንዳዘዘን እናደርጋለን። +26 ልጆቻችን፣ ሚስቶቻችን፣ ከብቶቻችንና እንስሶቻችን በሙሉ በጊልያድ ከተሞች ውስጥ ይቆያሉ፤+ +27 ሆኖም እኛ አገልጋዮችህ ይኸውም በይሖዋ ፊት ጦርነት ለመግጠም የታጠቅን እያንዳንዳችን ልክ ጌታችን በተናገረው መሠረት እንሻገራለን።”+ +28 በመሆኑም ሙሴ ለካህኑ ለአልዓዛር፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና ለእስራኤል ነገዶች የአባቶች ቤት መሪዎች እነሱን በተመለከተ ትእዛዝ ሰጠ። +29 ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “የጋድ ልጆችና የሮቤል ልጆች ይኸውም በይሖዋ ፊት ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ሰው ከእናንተ ጋር ዮርዳኖስን ከተሻገረ፣ ምድሪቱም በፊታችሁ ከተገዛች የጊልያድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጧቸዋላችሁ።+ +30 ሆኖም የጦር መሣሪያ ታጥቀው ከእናንተ ጋር ካልተሻገሩ በከነአን ምድር በመካከላችሁ ይኖራሉ።” +31 በዚህ ጊዜ የጋድ ልጆችና የሮቤል ልጆች እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ይሖዋ ለአገልጋዮችህ የተናገረውን እንፈጽማለን። +32 እኛ ራሳችን የጦር መሣሪያ ታጥቀን በይሖዋ ፊት ወደ ከነአን ምድር እንሻገራለን፤+ የምንወርሰው ርስት ግን ከዮርዳኖስ ወዲህ ያለውን ይሆናል።” +33 ስለዚህ ሙሴ ለጋድ ልጆችና ለሮቤል ልጆች+ እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ+ የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንን ግዛትና+ የባሳንን ንጉሥ የኦግን ግዛት+ ይኸውም በክልሎቹ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ይዞታ የሆነውን ምድር እንዲሁም በዙሪያው ባለው ምድር ያሉትን ከተሞች ሰጣቸው። +34 የጋድ ልጆችም ዲቦን፣+ አጣሮት፣+ አሮዔር፣+ +35 አትሮትሾፋን፣ ያዜር፣+ ዮግበሃ፣+ +36 ቤትኒምራ+ እና ቤትሃራን+ የተባሉትን የተመሸጉ ከተሞች ገነቡ፤ ለመንጎቹም በድንጋይ ካብ በረት ሠሩ። +37 የሮቤል ልጆች ደግሞ ሃሽቦንን፣+ ኤልዓሌን፣+ ቂርያታይምን፣+ +38 ስማቸው የተለወጠውን ነቦን+ እና በዓልመዖንን+ እንዲሁም ሲብማን ገነቡ፤ እነሱም መልሰው ለገነቧቸው ከተሞች አዲስ ስም አወ��ላቸው። +39 የምናሴ ልጅ የማኪር+ ልጆች በጊልያድ ላይ ዘምተው ምድሪቱን ያዙ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያን አስወጧቸው። +40 በመሆኑም ሙሴ ጊልያድን ለምናሴ ልጅ ለማኪር ሰጠው፤ እሱም በዚያ መኖር ጀመረ።+ +41 የምናሴ ልጅ ያኢርም በእነሱ ላይ ዘምቶ የድንኳን ሰፈሮቻቸውን ያዘ፤ እነሱንም ሃዎትያኢር* ብሎ ጠራቸው።+ +42 ኖባህም ዘምቶ ቄናትንና በሥሯ* ያሉትን ከተሞች ያዘ፤ እነሱንም በራሱ ስም ኖባህ ብሎ ሰየማቸው። +7 ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑን ተክሎ በጨረሰበት ቀን+ የማደሪያ ድንኳኑን ከቁሳቁሶቹ ሁሉና ከመሠዊያው እንዲሁም ከዕቃዎቹ ሁሉ+ ጋር ቀባው፤+ ደግሞም ቀደሰው። እነዚህን ነገሮች በቀባቸውና በቀደሳቸው+ ጊዜ +2 የእስራኤል አለቆች+ ማለትም የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች መባ አቀረቡ። ምዝገባውን በበላይነት ሲቆጣጠሩ የነበሩት እነዚህ የየነገዱ አለቆች +3 ስድስት ባለ ሽፋን ሠረገሎችንና 12 በሬዎችን ይኸውም ሁለት አለቆች አንድ ሠረገላ፣ እያንዳንዳቸውም አንድ አንድ በሬ መባ አድርገው ወደ ይሖዋ ፊት አመጡ፤ እነዚህንም በማደሪያ ድንኳኑ ፊት አቀረቡ። +4 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +5 “በመገናኛ ድንኳኑ ለሚከናወነው አገልግሎት እንዲውሉ እነዚህን ከእነሱ ተቀበል፤ ለሌዋውያኑም ለእያንዳንዳቸው ለሥራቸው እንደሚያስፈልጋቸው ስጣቸው።” +6 ስለሆነም ሙሴ ሠረገሎቹንና ከብቶቹን ተቀብሎ ለሌዋውያኑ ሰጣቸው። +7 ለጌድሶን ወንዶች ልጆች ለሥራቸው እንደሚያስፈልጋቸው ሁለት ሠረገሎችና አራት በሬዎች ሰጣቸው፤+ +8 ለሜራሪ ወንዶች ልጆች ደግሞ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ሆነው ለሚያከናውኑት ሥራ እንደሚያስፈልጋቸው አራት ሠረገሎችና ስምንት በሬዎች ሰጣቸው።+ +9 ለቀአት ወንዶች ልጆች ግን ምንም አልሰጣቸውም፤ ምክንያቱም ሥራቸው በቅዱሱ ስፍራ ከሚቀርበው አገልግሎት ጋር የተያያዘ+ ሲሆን ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች የሚሸከሙት ደግሞ በትከሻቸው ነበር።+ +10 አለቆቹም መሠዊያው በተቀባበት ዕለት በምርቃቱ*+ ላይ መባቸውን አቀረቡ። አለቆቹ መባቸውን በመሠዊያው ፊት ባቀረቡ ጊዜ +11 ይሖዋ ሙሴን “በየቀኑ አንድ አንድ አለቃ ለመሠዊያው ምርቃት የሚሆነውን መባውን ያቅርብ” አለው። +12 በመጀመሪያው ቀን መባውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የሆነው የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን+ ነበር። +13 መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል*+ መሠረት 130 ሰቅል* የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +14 እንዲሁም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +15 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +16 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +17 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚናዳብ+ ልጅ ነአሶን ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +18 በሁለተኛውም ቀን የይሳኮር አለቃ የሆነው የጹአር ልጅ ናትናኤል+ መባ አቀረበ። +19 መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +20 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +21 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በ��ና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +22 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +23 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የጹአር ልጅ ናትናኤል ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +24 በሦስተኛውም ቀን የዛብሎን ልጆች አለቃ የሆነው የሄሎን ልጅ ኤልያብ+ +25 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +26 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +27 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +28 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +29 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የሄሎን ልጅ ኤልያብ+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +30 በአራተኛውም ቀን የሮቤል ልጆች አለቃ የሆነው የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር+ +31 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +32 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +33 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +34 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +35 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +36 በአምስተኛውም ቀን የስምዖን ልጆች አለቃ የሆነው የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል+ +37 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +38 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +39 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +40 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +41 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +42 በስድስተኛውም ቀን የጋድ ልጆች አለቃ የሆነው የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ+ +43 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +44 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +45 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወ���ፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +46 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +47 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +48 በሰባተኛውም ቀን የኤፍሬም ልጆች አለቃ የሆነው የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ+ +49 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +50 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +51 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +52 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +53 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +54 በስምንተኛውም ቀን የምናሴ ልጆች አለቃ የሆነው የፐዳጹር ልጅ ገማልያል+ +55 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +56 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +57 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +58 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +59 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የፐዳጹር ልጅ ገማልያል+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +60 በዘጠነኛውም ቀን የቢንያም ልጆች አለቃ+ የሆነው የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን+ +61 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +62 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +63 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +64 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +65 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +66 በአሥረኛውም ቀን የዳን ልጆች አለቃ የሆነው የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ +67 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +68 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +69 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +70 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +71 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +72 በ11ኛውም ቀን የአሴር ልጆች አለቃ የሆነው የኦክራን ልጅ ፓጊኤል+ +73 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +74 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +75 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +76 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +77 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የኦክራን ልጅ ፓጊኤል+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +78 በ12ኛውም ቀን የንፍታሌም ልጆች አለቃ የሆነው የኤናን ልጅ አሂራ+ +79 መባ አቀረበ፤ መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 130 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ +80 በተጨማሪም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ +81 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ +82 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ +83 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የኤናን ልጅ አሂራ+ ያቀረበው መባ ይህ ነበር። +84 የእስራኤል አለቆች መሠዊያው በተቀባበት ጊዜ ያቀረቡት የመሠዊያው ምርቃት መባ+ የሚከተለው ነው፦ 12 የብር ሳህኖች፣ 12 የብር ጎድጓዳ ሳህኖች፣ 12 የወርቅ ጽዋዎች፣+ +"85 እያንዳንዱ የብር ሳህን 130 ሰቅል፣ እያንዳንዱም ጎድጓዳ ሳህን 70 ሰቅል ይመዝን ነበር፤ ዕቃዎቹ የተሠሩበት ብር በአጠቃላይ፣ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት 2,400 ሰቅል ነበር፤" +86 ዕጣን የተሞሉት 12 የወርቅ ጽዋዎች ሲመዘኑ እያንዳንዱ ጽዋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 10 ሰቅል ነበር፤ ጽዋዎቹ የተሠሩበት ወርቅ በአጠቃላይ 120 ሰቅል ነበር። +87 የእህል መባዎቻቸውን ጨምሮ ለሚቃጠል መባ የቀረቡት ከብቶች በአጠቃላይ 12 በሬዎች፣ 12 አውራ በጎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 12 ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ፤ ለኃጢአት መባ የቀረቡት 12 የፍየል ጠቦቶች ነበሩ፤ +88 ለኅብረት መሥዋዕት የቀረቡት ከብቶች በአጠቃላይ 24 በሬዎች፣ 60 አውራ በጎች፣ 60 ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 60 ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ+ በኋላ የቀረበው የመሠዊያው ምርቃት መባ+ ይህ ነበር። +89 ሙሴ ከአምላክ* ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛ ድንኳኑ በሚገባበት ጊዜ+ ሁሉ ከምሥክሩ ታቦት መክደኛ በላይ ድምፅ ሲያነጋግረው ይሰማ ነበር፤+ እሱም ከሁለቱ ኪሩ��ች መካከል ያነጋግረው ነበር።+ +12 ሙሴ ኩሻዊት ሴት አግብቶ ስለነበር ባገባት ኩሻዊት ሴት+ የተነሳ ሚርያምና አሮን ይነቅፉት ጀመር። +2 እነሱም “ለመሆኑ ይሖዋ የሚናገረው በሙሴ አማካኝነት ብቻ ነው? በእኛስ በኩል አልተናገረም?”+ ይሉ ነበር። ይሖዋም ይህን ይሰማ ነበር።+ +3 ሙሴ በምድር ላይ ከነበሩ ሰዎች ሁሉ ይልቅ በጣም የዋህ ነበር።*+ +4 ይሖዋም ድንገት ሙሴን፣ አሮንንና ሚርያምን “ሦስታችሁም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ውጡ” አላቸው። በመሆኑም ሦስቱም ወጡ። +5 ይሖዋም በደመና ዓምድ ወርዶ+ በድንኳኑ መግቢያ ላይ በመቆም አሮንንና ሚርያምን ጠራቸው። በዚህ ጊዜ ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ። +6 እሱም እንዲህ አለ፦ “እባካችሁ ቃሌን ስሙ። አንድ የይሖዋ ነቢይ በመካከላችሁ ቢኖር በራእይ አማካኝነት+ ራሴን አሳውቀው በሕልምም+ አነጋግረው ነበር። +7 አገልጋዬን ሙሴን በተመለከተ ግን እንዲህ አይደለም! እሱ በቤቴ ሁሉ ላይ አደራ የተጣለበት* ሰው ነው።+ +8 እኔ እሱን የማነጋግረው ፊት ለፊት*+ በግልጽ እንጂ በእንቆቅልሽ አይደለም፤ እሱም የይሖዋን አምሳል ያያል። ታዲያ አገልጋዬን ሙሴን ስትነቅፉት ምነው አልፈራችሁም?” +9 በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ በእነሱ ላይ ነደደ፤ ትቷቸውም ሄደ። +10 ከዚያም ደመናው ከድንኳኑ ላይ ተነሳ፤ በዚህ ጊዜ ሚርያም በሥጋ ደዌ ተመታ እንደ በረዶ ነጭ ሆና ነበር።+ አሮንም ወደ ሚርያም ዞር ሲል በሥጋ ደዌ ተመታ አየ።+ +11 አሮንም ወዲያውኑ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይቅርታ አድርግልኝ ጌታዬ! እባክህ ይህን ኃጢአት አትቁጠርብን! የፈጸምነው የሞኝነት ድርጊት ነው። +12 እባክህ፣ ግማሽ አካሉ ተበልቶ የተወለደ ጭንጋፍ መስላ እንድትቀር አታድርግ!” +13 ሙሴም “አምላክ ሆይ፣ እባክህ ፈውሳት! እባክህ!” በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ።+ +14 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባቷ ፊቷ ላይ ቢተፋባት ለሰባት ቀን ተዋርዳ ትቆይ አልነበረም? አሁንም ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀን ተገልላ እንድትቆይ ይደረግ፤+ ከዚያ በኋላ እንድትመለስ ማድረግ ይቻላል።” +15 ስለዚህ ሚርያም ለሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጭ ተገልላ እንድትቆይ ተደረገ፤+ ሕዝቡም ሚርያም ተመልሳ እንድትቀላቀል እስኪደረግ ድረስ ጉዞውን አልቀጠለም። +16 ከዚያም ሕዝቡ ከሃጼሮት+ ተነስቶ በፋራን ምድረ በዳ+ ሰፈረ። +1 ይሖዋም እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት ሁለተኛ ወር፣ የመጀመሪያ ቀን+ ላይ በሲና ምድረ በዳ+ በመገናኛ ድንኳኑ+ ውስጥ ሙሴን አነጋገረው። እንዲህም አለው፦ +2 “የእስራኤልን ማኅበረሰብ* በሙሉ በየቤተሰባቸው፣ በየአባቶቻቸው ቤትና በስም በተዘረዘሩት ወንዶች ሁሉ ቁጥር መሠረት በግለሰብ ደረጃ ቁጠር።+ +3 አንተና አሮን ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን+ በእስራኤል ውስጥ ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉትን ሁሉ በየምድባቸው* መዝግቡ። +4 “ከየነገዱ አንድ ሰው ውሰድ፤ እያንዳንዳቸውም ለየአባቶቻቸው ቤት መሪ ይሆናሉ።+ +5 ከአንተ ጋር የሚቆሙትም ወንዶች ስም የሚከተለው ነው፦ ከሮቤል ነገድ የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር፣+ +6 ከስምዖን ነገድ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል፣+ +7 ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፣+ +8 ከይሳኮር ነገድ የጹአር ልጅ ናትናኤል፣+ +9 ከዛብሎን ነገድ የሄሎን ልጅ ኤልያብ፣+ +10 ከዮሴፍ ወንዶች ልጆች ይኸውም ከኤፍሬም+ ነገድ የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ፣ ከምናሴ ነገድ ደግሞ የፐዳጹር ልጅ ገማልያል፣ +11 ከቢንያም ነገድ የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን፣+ +12 ከዳን ነገድ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር፣+ +13 ከአሴር ነገድ የኦክራን ልጅ ፓጊኤል፣+ +14 ከጋድ ነገድ የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ+ +15 እንዲሁም ከንፍታሌም ነገድ የኤናን ልጅ አሂራ።+ +16 እነዚህ ከማኅበረሰቡ የተመረጡ ናቸ���። እነሱም የአባቶቻቸው ነገዶች መሪዎች+ ማለትም የእስራኤል የሺህ አለቆች+ ናቸው።” +17 በመሆኑም ሙሴና አሮን በስም የተጠቀሱትን እነዚህን ወንዶች ወሰዱ። +18 እነሱም ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ+ የሆኑት በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በግለሰብ ደረጃ እንዲመዘገቡ ለማድረግ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ላይ መላውን ማኅበረሰብ ሰበሰቡ፤ +19 ይህን ያደረጉት ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነው። እሱም በሲና ምድረ በዳ መዘገባቸው።+ +20 የእስራኤል የበኩር ልጅ+ ዝርያዎች የሆኑት የሮቤል ልጆች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በግለሰብ ደረጃ ተቆጠሩ፤ +"21 ከሮቤል ነገድ የተመዘገቡት 46,500 ነበሩ። " +22 የስምዖን+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በግለሰብ ደረጃ ተቆጠሩ፤ +"23 ከስምዖን ነገድ የተመዘገቡት 59,300 ነበሩ። " +24 የጋድ+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"25 ከጋድ ነገድ የተመዘገቡት 45,650 ነበሩ። " +26 የይሁዳ+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"27 ከይሁዳ ነገድ የተመዘገቡት 74,600 ነበሩ። " +28 የይሳኮር+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"29 ከይሳኮር ነገድ የተመዘገቡት 54,400 ነበሩ። " +30 የዛብሎን+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"31 ከዛብሎን ነገድ የተመዘገቡት 57,400 ነበሩ። " +32 በኤፍሬም+ በኩል ያሉት የዮሴፍ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"33 ከኤፍሬም ነገድ የተመዘገቡት 40,500 ነበሩ። " +34 የምናሴ+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"35 ከምናሴ ነገድ የተመዘገቡት 32,200 ነበሩ። " +36 የቢንያም+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"37 ከቢንያም ነገድ የተመዘገቡት 35,400 ነበሩ። " +38 የዳን+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"39 ከዳን ነገድ የተመዘገቡት 62,700 ነበሩ። " +40 የአሴር+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"41 ከአሴር ነገድ የተመዘገቡት 41,500 ነበሩ። " +42 የ��ፍታሌም+ ዝርያዎች በየስማቸው፣ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በዝርዝር ተመዘገቡ። ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ተቆጠሩ፤ +"43 ከንፍታሌም ነገድ የተመዘገቡት 53,400 ነበሩ። " +44 ሙሴ ከአሮንና እያንዳንዳቸው የአባቶቻቸውን ቤት ከሚወክሉት ከ12 የእስራኤል አለቆች ጋር በመሆን የመዘገባቸው እነዚህ ናቸው። +45 በእስራኤል ውስጥ ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የሚችሉት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት እስራኤላውያን ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ተመዘገቡ፤ +"46 የተመዘገቡትም ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር 603,550 ነበር።+ " +47 ይሁን እንጂ ሌዋውያኑ+ ሌሎቹ እንደተመዘገቡት በየአባቶቻቸው ነገድ መሠረት አልተመዘገቡም።+ +48 ስለዚህ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +49 “የሌዊን ነገድ ብቻ አትመዝግብ፤ ቁጥራቸውም በሌሎቹ እስራኤላውያን ቁጥር ውስጥ እንዲካተት አታድርግ።+ +50 ሌዋውያኑን በምሥክሩ+ የማደሪያ ድንኳን፣ በዕቃዎቹ ሁሉና ከዚያ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ነገሮች ሁሉ ላይ ሹማቸው።+ እነሱም የማደሪያ ድንኳኑንና ዕቃዎቹን በሙሉ ይሸከማሉ፤+ በዚያም ያገለግላሉ፤+ በማደሪያ ድንኳኑም ዙሪያ ይሰፍራሉ።+ +51 የማደሪያ ድንኳኑ ከቦታ ወደ ቦታ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሁሉ ሌዋውያኑ ይንቀሉት፤+ የማደሪያ ድንኳኑ በሚተከልበት ጊዜም ሌዋውያኑ ይትከሉት። ያልተፈቀደለት ማንኛውም ሰው* ወደዚያ ቢቀርብ ይገደል።+ +52 “እያንዳንዱ እስራኤላዊ በየተመደበበት ሰፈር ድንኳኑን ይትከል፤ እያንዳንዱም ሰው ሦስት ነገዶችን ባቀፈው ቡድኑ*+ ውስጥ በየምድቡ* ይስፈር። +53 በእስራኤል ማኅበረሰብ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያኑ በምሥክሩ የማደሪያ ድንኳን ዙሪያ ይስፈሩ፤+ ሌዋውያኑም የምሥክሩን የማደሪያ ድንኳን የመንከባከብ* ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።”+ +54 እስራኤላውያንም ይሖዋ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። ልክ እንደዚያው አደረጉ። +36 ከዮሴፍ ልጆች ቤተሰቦች የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣+ የጊልያድ ተወላጆች የአባቶች ቤት መሪዎች ወደ ሙሴና የእስራኤላውያን የአባቶች ቤት መሪዎች ወደሆኑት አለቆች ቀርበው ተናገሩ፤ +2 እንዲህም አሉ፦ “ይሖዋ ጌታዬን ምድሪቱን ለእስራኤላውያን ርስት አድርጎ በዕጣ እንዲያከፋፍል አዞት ነበር፤+ ደግሞም የወንድማችንን የሰለጰአድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ እንዲሰጥ ይሖዋ ጌታዬን አዞት ነበር።+ +3 እነዚህ ሴቶች ከሌሎች የእስራኤል ነገዶች ባሎችን ቢያገቡ የእነሱ ውርስ ከአባቶቻችን ውርስ ላይ ተወስዶ በሚያገቡት ሰው ነገድ ውርስ ላይ ይጨመራል፤ በመሆኑም በዕጣ ከተሰጠን ውርስ ላይ ይቀነሳል። +4 የእስራኤል ሕዝብ የኢዮቤልዩ+ ዓመት በሚደርስበት ጊዜ የሴቶቹ ውርስ በሚያገቡት ሰው ነገድ ውርስ ላይ ለዘለቄታው ይጨመራል፤ በመሆኑም የእነሱ ውርስ ከአባቶቻችን ነገድ ውርስ ላይ ይቀነሳል።” +5 ከዚያም ሙሴ ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “የዮሴፍ ልጆች ነገድ የተናገረው ነገር ትክክል ነው። +6 ይሖዋ የሰለጰአድን ሴቶች ልጆች በተመለከተ እንዲህ ሲል አዟል፦ ‘የፈለጉትን ሰው ማግባት ይችላሉ። ሆኖም ከአባታቸው ነገድ ቤተሰብ የሆነን ሰው ማግባት ይኖርባቸዋል። +7 የትኛውም የእስራኤላውያን ውርስ ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ መተላለፍ የለበትም፤ ምክንያቱም እስራኤላውያን እያንዳንዳቸው የአባቶቻቸውን ነገድ ውርስ አጽንተው መያዝ አለባቸው። +8 እስራኤላውያን የቀደሙትን አባቶቻቸውን ውርስ ጠብቀው ማቆየት እንዲችሉ በእስራኤል ነገዶች መካከል ውርስ ያላት የትኛዋም ልጅ የአባቷ ነገድ ተወላጅ የሆነ ሰው ማግባት ይኖርባታል።+ +9 የትኛውም ውርስ ከአን�� ነገድ ወደ ሌላው ነገድ መተላለፍ የለበትም፤ ምክንያቱም የእስራኤል ነገዶች እያንዳንዳቸው የየራሳቸውን ውርስ አጽንተው መያዝ አለባቸው።’” +10 የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።+ +11 ስለሆነም የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች+ የሆኑት ማህላ፣ ቲርጻ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ኖኅ የአባታቸውን ወንድሞች ልጆች አገቡ። +12 ውርሻቸው በአባታቸው ቤተሰብ ነገድ ሥር እንደሆነ እንዲቀጥል የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ልጆች ቤተሰቦች የሆኑ ወንዶችን አገቡ። +13 ይሖዋ በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ለነበሩት እስራኤላውያን በሙሴ አማካኝነት የሰጣቸው ትእዛዛትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው።+ +29 “‘በሰባተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም።+ ይህም መለከት የምትነፉበት ቀን ነው።+ +2 እናንተም አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ +3 ከእነዚህም ጋር ለወይፈኑ ሦስት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ +4 ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ +5 እንዲሁም ለእናንተ ማስተሰረያ እንዲሆን አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። +6 ይህም በተለመደው አሠራር መሠረት ከሚቀርቡት ከወርሃዊው የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባ፣+ ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባ+ እንዲሁም ከመጠጥ መባዎቻቸው+ በተጨማሪ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። +7 “‘በዚሁ በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ፤+ ራሳችሁን አጎሳቁሉ።* ምንም ዓይነት ሥራ አትሥሩ።+ +8 አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል።+ +9 ከእነዚህም ጋር ለወይፈኑ ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ +10 እንዲሁም ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ +11 ለማስተሰረያ ከሚሆነው የኃጢአት መባ፣+ ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባ እንዲሁም ከመጠጥ መባዎቻቸው በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። +12 “‘በሰባተኛው ወር በ15ኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ፤ ለሰባት ቀንም ለይሖዋ በዓል አክብሩ።+ +13 እንዲሁም 13 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መባ+ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል።+ +14 ከእነዚህም ጋር ለ13ቱ ወይፈኖች ለእያንዳንዳቸው ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለ2ቱ አውራ በጎች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ አቅርቡ�� +15 እንዲሁም ለ14ቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት አቅርቡ፤ +16 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +17 “‘በሁለተኛው ቀን 12 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤+ +18 ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ +19 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባ እንዲሁም ከመጠጥ መባዎቻቸው በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +20 “‘በሦስተኛው ቀን 11 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤+ +21 ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ +22 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +23 “‘በአራተኛው ቀን 10 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤+ +24 ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ +25 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +26 “‘በአምስተኛው ቀን 9 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤+ +27 ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ +28 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +29 “‘በስድስተኛውም ቀን 8 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤+ +30 ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ +31 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብረውት ከሚቀርቡት የእህል መባና የመጠጥ መባዎች በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +32 “‘በሰባተኛው ቀን 7 ወይፈኖች፣ 2 አውራ በጎች እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው 14 ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤+ +33 ለወይፈኖቹ፣ ለአውራ በጎቹና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ +34 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +35 “‘በ���ምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም።+ +36 አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መባ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤+ +37 ለወይፈኑ፣ ለአውራው በግና ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ በተለመደው አሠራር መሠረት በቁጥራቸው ልክ የእህል መባቸውንና የመጠጥ መባዎቻቸውን አቅርቡ፤ +38 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሁም አብሮት ከሚቀርበው የእህል መባና የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +39 “‘እነዚህም የሚቃጠሉ መባዎች፣+ የእህል መባዎች፣+ የመጠጥ መባዎችና+ የኅብረት መሥዋዕቶች+ አድርጋችሁ ከምታቀርቧቸው የስእለት መባዎችና+ የፈቃደኝነት መባዎች+ በተጨማሪ በየወቅቱ በምታከብሯቸው በዓላት+ ላይ ለይሖዋ የምታቀርቧቸው ናቸው።’” +40 ሙሴም ይሖዋ ያዘዘውን ነገር በሙሉ ለእስራኤላውያን ነገራቸው። +28 በመቀጠልም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን እዘዛቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ምግቤን ይኸውም መባዬን ለእኔ ማቅረባችሁን እንዳትዘነጉ። ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ እንዲሰጡ በእሳት የሚቀርቡት መባዎቼ በተወሰነላቸው ጊዜ መቅረብ አለባቸው።’+ +3 “እንዲህም በላቸው፦ ‘ለይሖዋ የምታቀርቡት በእሳት የሚቃጠል መባ ይህ ነው፦ በየቀኑ፣ አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ዘወትር አቅርቡ።+ +4 አንደኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ጠዋት ላይ፣ ሌላኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ* አቅርቡ፤+ +5 ከእነዚህም ጋር ተጨቅጭቆ በተጠለለ አንድ አራተኛ ሂን* ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ* የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +6 ይህም በሲና ተራራ ላይ በወጣው ደንብ መሠረት ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው ዘወትር የሚቀርብ የሚቃጠል መባ+ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው፤ +7 ከዚህም ጋር የመጠጥ መባውን ይኸውም ለእያንዳንዱ ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አራተኛ ሂን አቅርቡ።+ የሚያሰክረውን መጠጥ ለይሖዋ እንደሚቀርብ የመጠጥ መባ አድርጋችሁ በቅዱሱ ስፍራ አፍሱት። +8 ሌላኛውን ተባዕት የበግ ጠቦት ደግሞ አመሻሹ ላይ* አቅርቡት። ከእሱም ጋር ማለዳ ላይ የሚቀርበውን ዓይነት የእህል መባና ከእሱ ጋር አብሮ የሚቀርበውን ዓይነት የመጠጥ መባ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ።+ +9 “‘ይሁንና በሰንበት ቀን፣+ አንድ ዓመት የሆናቸውን እንከን የሌለባቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች እንዲሁም በዘይት የተለወሰ ሁለት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ከመጠጥ መባው ጋር ታቀርባላችሁ። +10 ይህ ዘወትር ከሚቀርበው የሚቃጠል መባና ከመጠጥ መባው ጋር በየሰንበቱ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ነው።+ +11 “‘በየወሩም* መባቻ ላይ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤+ +12 ለእያንዳንዱ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ+ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤+ +13 ለእያንዳንዱም ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ የሚቃጠል መባ+ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። +14 በተጨማሪም ከእነዚህ ጋር ለአንድ ወይፈን ግማሽ ሂን፣+ ለአውራው በግ አንድ ሦስተኛ ሂን+ እንዲሁም ለአንድ ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አራተኛ ሂን+ የወይን ጠጅ የመጠጥ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። ይህም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚቀርብ ወርሃዊ የሚቃጠል መባ ነው። +15 እንዲሁም ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና አብሮት ከሚቀርበው የመጠጥ መባ በተጨማሪ አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ ሆኖ ለይሖዋ መቅረብ አለበት። +16 “‘በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን የይሖዋ ፋሲካ ይከበራል።+ +17 በዚሁ ወር በ15ኛው ቀን በዓል ይሆናል። ለሰባት ቀን ቂጣ ይበላል።+ +18 በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። +19 ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። እንከን የሌለባቸውን እንስሳት ማቅረብ አለባችሁ።+ +20 ከእነዚህም ጋር ለአንድ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ+ አድርጋችሁ አቅርቡ። +21 ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ ታቀርባላችሁ፤ +22 እንዲሁም ለእናንተ ማስተሰረያ እንዲሆን አንድ ፍየል የኃጢአት መባ አድርጋችሁ አቅርቡ። +23 ለዘወትሩ የሚቃጠል መባ እንዲሆን ጠዋት ላይ ከሚቀርበው የሚቃጠል መባ በተጨማሪ እነዚህን ታቀርባላችሁ። +24 እነዚህንም በተመሳሳይ መንገድ በየቀኑ ለሰባት ቀን እንደ ምግብ፣ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ። ይህም ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና ከመጠጥ መባው ጋር ይቅረብ። +25 በሰባተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ።+ ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም።+ +26 “‘መጀመሪያ የሚደርሰው ፍሬ በሚሰበሰብበት ቀን+ ለይሖዋ አዲስ የእህል መባ ስታቀርቡ+ በሳምንታት በዓላችሁ ላይ ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ።+ ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም።+ +27 ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤+ +28 ከእነዚህም ጋር ለእያንዳንዱ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ +29 እንዲሁም ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ +30 በተጨማሪም ለእናንተ ማስተሰረያ እንዲሆን አንድ የፍየል ጠቦት ታቀርባላችሁ።+ +31 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና ከእህል መባው በተጨማሪ እነዚህን ታቀርባላችሁ። እንስሳቱም እንከን የሌለባቸው መሆን አለባቸው፤+ ከመጠጥ መባቸውም ጋር መቅረብ ይኖርባቸዋል። +8 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ለአሮን ‘መብራቶቹን በምታበራበት ጊዜ ሰባቱ መብራቶች በመቅረዙ ፊት ለፊት ላለው አካባቢ ብርሃን መስጠት ይኖርባቸዋል’ ብለህ ንገረው።”+ +3 አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመቅረዙ+ ፊት ለፊት ያለው አካባቢ ብርሃን እንዲያገኝ የመቅረዙን መብራቶች ለኮሳቸው። +4 የመቅረዙ አሠራር ይህ ነበር፦ አንድ ወጥ ከሆነ ወርቅ ተጠፍጥፎ የተሠራ ነበር፤ ግንዱም ሆነ የፈኩት አበቦቹ ወጥ ከሆነ ወርቅ ተጠፍጥፈው የተሠሩ ነበሩ።+ መቅረ��� የተሠራው ይሖዋ ለሙሴ ባሳየው ራእይ መሠረት ነበር።+ +5 ይሖዋ ሙሴን ዳግመኛ እንዲህ አለው፦ +6 “ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል ወስደህ አንጻቸው።+ +7 እነሱንም የምታነጻቸው በሚከተለው መንገድ ነው፦ ከኃጢአት የሚያነጻ ውኃ እርጫቸው፤ እነሱም ሰውነታቸውን በሙሉ በምላጭ ይላጩ፤ እንዲሁም ልብሳቸውን ይጠቡ፤ ራሳቸውንም ያንጹ።+ +8 ከዚያም አንድ ወይፈንና+ አብሮት የሚቀርበውን በዘይት ከተለወሰ የላመ ዱቄት የተዘጋጀ የእህል መባ+ ይወስዳሉ፤ አንተም ለኃጢአት መባ+ እንዲሆን ሌላ ወይፈን ትወስዳለህ። +9 እንዲሁም ሌዋውያኑን በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ታቀርባቸዋለህ፤ መላውን የእስራኤል ማኅበረሰብ ትሰበስባለህ።+ +10 ሌዋውያኑን በይሖዋ ፊት በምታቀርባቸው ጊዜ እስራኤላውያን በሌዋውያኑ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ።+ +11 አሮንም ከእስራኤላውያን መካከል ሌዋውያኑን እንደሚወዘወዝ መባ+ አድርጎ በይሖዋ ፊት ያቅርባቸው፤* እነሱም ለይሖዋ የሚቀርበውን አገልግሎት ያከናውናሉ።+ +12 “ከዚያም ሌዋውያኑ በወይፈኖቹ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጭናሉ።+ ይህን ካደረጉ በኋላ ለእነሱ ማስተሰረያ እንዲሆኑ+ አንደኛውን ወይፈን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርገው ለይሖዋ ያቀርባሉ። +13 ሌዋውያኑንም በአሮንና በወንዶች ልጆቹ ፊት እንዲቆሙ ካደረግክ በኋላ እንደሚወዘወዝ መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርባቸው።* +14 ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል ለያቸው፤ ሌዋውያኑም የእኔ ይሆናሉ።+ +15 ከዚህ በኋላ ሌዋውያኑ በመገናኛ ድንኳኑ ለማገልገል ይመጣሉ። እነሱን የምታነጻቸውና እንደሚወዘወዝ መባ አድርገህ የምታቀርባቸው* በዚህ መንገድ ነው። +16 ምክንያቱም እነሱ የተሰጡ ይኸውም ከእስራኤላውያን መካከል ለእኔ የተሰጡ ናቸው። በእስራኤላውያን በኩሮች ሁሉ* ምትክ+ እነሱን ለራሴ እወስዳቸዋለሁ። +17 ምክንያቱም ሰውም ሆነ እንስሳ ከእስራኤላውያን መካከል በኩር የሆነ ሁሉ የእኔ ነው።+ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን እነሱን ለራሴ ቀድሻቸዋለሁ።+ +18 ሌዋውያኑን በእስራኤላውያን በኩር ሁሉ ምትክ እወስዳቸዋለሁ። +19 የእስራኤል ሕዝብ ወደ ቅዱሱ ስፍራ በመቅረቡ የተነሳ በመካከሉ መቅሰፍት እንዳይከሰት+ በእስራኤላውያን ምትክ በመገናኛ ድንኳኑ ያገለግሉና+ ለእነሱ ያስተሰርዩ ዘንድ ከእስራኤላውያን መካከል ሌዋውያኑን ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የተሰጡ አድርጌ እሰጣቸዋለሁ።” +20 ሙሴ፣ አሮንና መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ሁሉ ለሌዋውያኑ እንዲሁ አደረጉ። እስራኤላውያንም ይሖዋ ሌዋውያኑን አስመልክቶ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። +21 በመሆኑም ሌዋውያኑ ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሶቻቸውንም አጠቡ፤+ በመቀጠልም አሮን እንደሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት አቀረባቸው።*+ ከዚያም አሮን እነሱን ለማንጻት ማስተሰረያ አቀረበላቸው።+ +22 ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ሌዋውያኑ በመገናኛ ድንኳኑ በአሮንና በወንዶች ልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ገቡ። ይሖዋ ሌዋውያኑን በተመለከተ ሙሴን ባዘዘው መሠረት እንዲሁ አደረጉላቸው። +23 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +24 “ሌዋውያኑን በተመለከተ የተደረገው ዝግጅት የሚከተለው ነው፦ አንድ ወንድ ዕድሜው 25 ዓመትና ከዚያ በላይ ከሆነ በመገናኛ ድንኳኑ ከሚያገለግለው ቡድን ጋር ይቀላቀላል። +25 ዕድሜው 50 ዓመት ከሞላ ግን ከሚያገለግልበት ቡድን ጡረታ ይወጣል፤ ከዚያ በኋላ ማገልገል አይጠበቅበትም። +26 ይህ ሰው በመገናኛ ድንኳኑ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉትን ወንድሞቹን ሊያገለግል ይችላል፤ ሆኖም በዚያ ማገልገል የለበትም። ሌዋውያኑንና የተጣለባቸውን ኃላፊነት በተመለከተ ማድረግ ያ��ብህ ይህን ነው።”+ +11 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ፣ ስለደረሰበት ችግር በይሖዋ ፊት ክፉኛ ማጉረምረም ጀመረ። ይሖዋ ይህን ሲሰማ ቁጣው ነደደ፤ ከይሖዋም የመጣ እሳት በእነሱ ላይ ተቀጣጠለ፤ በሰፈሩ ዳርቻ ያሉትን የተወሰኑ ሰዎችም በላ። +2 ሕዝቡ ወደ ሙሴ መጮኽ ሲጀምር ሙሴ ይሖዋን ተማጸነ፤+ እሳቱም ከሰመ። +3 ከይሖዋ የመጣ እሳት በእነሱ ላይ ስለነደደም የዚያ ቦታ ስም ታበራ* ተባለ።+ +4 እስራኤላውያንም በመካከላቸው የነበረው ድብልቅ ሕዝብ*+ ሲስገበገብ+ ሲያዩ እንዲህ በማለት እንደገና ያለቅሱ ጀመር፦ “እንግዲህ አሁን የምንበላው ሥጋ ማን ይሰጠናል?+ +5 በግብፅ እያለን በነፃ እንበላው የነበረው ዓሣ እንዲሁም ኪያሩ፣ ሐብሐቡ፣ ባሮ ሽንኩርቱ፣ ቀይ ሽንኩርቱና ነጭ ሽንኩርቱ በዓይናችን ላይ ዞሯል!+ +6 አሁን ግን ዝለናል።* ከዚህ መና በስተቀር ሌላ የምናየው ነገር የለም።”+ +7 መናው+ እንደ ድንብላል ዘር+ ነበር፤ መልኩም ሙጫ* ይመስል ነበር። +8 ሕዝቡም ሜዳ ላይ ወጥቶ መናውን ከለቀመ በኋላ በወፍጮ ይፈጨው ወይም በሙቀጫ ይወቅጠው ነበር። ከዚያም በድስት ይቀቅሉት ወይም እንደ ቂጣ ይጋግሩት ነበር፤+ ጣዕሙም በዘይት ተለውሶ እንደተጋገረ ጣፋጭ ቂጣ ነበር። +9 ሌሊት በሰፈሩ ላይ ጤዛ በሚወርድበት ጊዜ መናውም በላዩ ላይ ይወርድ ነበር።+ +10 ሙሴም ሕዝቡ ይኸውም እያንዳንዱ ሰው በድንኳኑ ደጃፍ ላይ ሆኖ ከቤተሰቡ ጋር ሲያለቅስ ሰማ። ይሖዋም እጅግ ተቆጣ፤+ ሙሴም በጣም አዘነ። +11 ከዚያም ሙሴ ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “አገልጋይህን የምታጎሳቁለው ለምንድን ነው? በፊትህ ሞገስ ያጣሁትና የዚህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ የጫንከው ለምንድን ነው?+ +12 ይህን ሁሉ ሕዝብ የፀነስኩት እኔ ነኝ? ለአባቶቻቸው ለመስጠት ቃል ወደገባህላቸው ምድር እንዳስገባቸው ‘የሚጠባን ሕፃን እንደሚታቀፍ ሞግዚት በጉያህ እቀፋቸው’ የምትለኝ የወለድኳቸው እኔ ነኝ?+ +13 ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ሥጋ ከየት ነው የማመጣው? ይኸው እነሱ ‘የምንበላው ሥጋ ስጠን!’ በማለት እያለቀሱብኝ ነው። +14 ይህን ሁሉ ሕዝብ እኔ ብቻዬን ልሸከመው አልችልም፤ ከአቅሜ በላይ ነው።+ +15 እንዲህስ ከምታደርገኝ እባክህ አሁኑኑ ግደለኝ።+ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ ከእንግዲህ መከራ እንዳይ አታድርገኝ።” +16 ይሖዋም መልሶ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል የሕዝቡ ሽማግሌዎችና አለቆች+ የመሆን ብቃት አላቸው የምትላቸውን 70 ሰዎች ሰብስብልኝ፤ እነሱንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ውሰዳቸውና በዚያ ከአንተ ጋር ይቁሙ። +17 እኔም ወርጄ+ በዚያ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፤+ በአንተ ላይ ካለው መንፈስ+ ወስጄ በእነሱ ላይ አደርጋለሁ፤ እነሱም የሕዝቡን ሸክም ብቻህን እንዳትሸከም ይረዱሃል።+ +18 ሕዝቡንም እንዲህ በለው፦ ‘ሥጋ ስለምትበሉ ለነገ ራሳችሁን ቀድሱ፤+ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት አልቅሳችኋል፤+ ደግሞም “የምንበላው ሥጋ ማን ይሰጠናል? በግብፅ የነበርንበት ሁኔታ የተሻለ ነበር”+ ብላችኋል። ይሖዋ በእርግጥ ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ትበላላችሁ።+ +19 የምትበሉትም ለአንድ ቀን ወይም ለ2 ቀን ወይም ለ5 ቀን ወይም ለ10 ቀን ወይም ለ20 ቀን አይደለም፤ +20 ከዚህ ይልቅ በአፍንጫችሁ እስኪወጣና እስኪያንገፈግፋችሁ+ ድረስ ወር ሙሉ ትበላላችሁ፤ ምክንያቱም በመካከላችሁ ያለውን ይሖዋን ትታችኋል፤ እንዲሁም “ከግብፅ የወጣነው ለምንድን ነው?” በማለት በፊቱ አልቅሳችኋል።’”+ +"21 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እኔ በመካከሉ የምገኘው ሕዝብ 600,000 እግረኛ ወንዶች+ ያሉበት ነው፤ አንተ ደግሞ ‘ሥጋ እሰጣቸዋለሁ፤ ወር ሙሉ እስኪጠግቡ ይበላሉ’ ትላለህ።" +22 በጎቹና ከብቶቹ ሁሉ ቢታረዱ እንኳ ይበቃቸዋል? የባሕር ዓሣዎች ሁሉ ቢያዙስ ሊበቃቸው ይችላል?” +23 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ለመሆኑ የይሖዋ እጅ አጭር ነው?+ እንግዲህ ያልኩት ነገር ይፈጸምልህ እንደሆነና እንዳልሆነ ታያለህ” አለው። +24 ሙሴም ወጥቶ የይሖዋን ቃል ለሕዝቡ ተናገረ። እንዲሁም ከሕዝቡ ሽማግሌዎች መካከል 70 ሰዎችን ሰብስቦ በድንኳኑ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ።+ +25 ከዚያም ይሖዋ በደመና ወርዶ+ አነጋገረው፤+ በሙሴ ላይ ከነበረውም መንፈስ+ ወስዶ በ70ዎቹ ሽማግሌዎች ላይ አደረገ። እነሱም ወዲያው መንፈሱ እንዳረፈባቸው እንደ ነቢያት አደረጋቸው፤*+ ሆኖም ዳግመኛ እንደዚያ አልሆኑም። +26 በዚህ ጊዜ ከሰዎቹ መካከል ሁለቱ በሰፈሩ ውስጥ ቀርተው ነበር። ስማቸውም ኤልዳድና ሞዳድ ነበር። እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳ ወደ ድንኳኑ ባይሄዱም ስማቸው ከተመዘገቡት ሰዎች መካከል ስለነበሩ መንፈሱ በእነሱም ላይ ወረደ። በመሆኑም እነሱም በሰፈሩ ውስጥ እንደ ነቢያት ሆኑ። +27 አንድ ወጣትም እየሮጠ በመሄድ “ኤልዳድና ሞዳድ በሰፈሩ ውስጥ እንደ ነቢያት እየሆኑ ነው!” ሲል ለሙሴ ነገረው። +28 በዚህ ጊዜ ከወጣትነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ+ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ፣ እነዚህን ሰዎች ከልክላቸው እንጂ!”+ ሲል ተናገረ። +29 ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “ስለ እኔ ተቆርቁረህ ነው? አትቆርቆር፤ የይሖዋ ሕዝቦች በሙሉ ነቢያት ቢሆኑና ይሖዋ መንፈሱን ቢሰጣቸው እንዴት ደስ ባለኝ!” +30 በኋላም ሙሴ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር ወደ ሰፈሩ ተመለሰ። +31 ከዚያም ነፋስ ከይሖዋ ዘንድ ወጥቶ ድርጭቶችን ከባሕሩ እየነዳ በማምጣት በሰፈሩ ዙሪያ በተናቸው፤+ ድርጭቶቹም የአንድ ቀን መንገድ ያህል በአንድ በኩል፣ የአንድ ቀን መንገድ ያህል ደግሞ በሌላ በኩል በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ተበትነው ነበር፤ መሬት ላይም ሁለት ክንድ* ከፍታ ያህል ተቆልለው ነበር። +32 ሕዝቡም በዚያን ዕለት ቀኑን ሙሉና ሌሊቱን ሙሉ እንዲሁም በማግስቱ ቀኑን ሙሉ ድርጭቶቹን ሲሰበስብ ዋለ። ከአሥር ሆሜር* ያነሰ የሰበሰበ አልነበረም፤ የሰበሰቧቸውንም በሰፈሩ ዙሪያ አሰጧቸው። +33 ሆኖም ሥጋውን ገና ሳያኝኩት፣ በጥርሳቸው መካከል እያለ የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ ይሖዋም ሕዝቡን ክፉኛ ፈጀ።+ +34 እነሱም ሲስገበገቡ+ የነበሩትን ሰዎች በዚያ ስለቀበሯቸው የቦታውን ስም ቂብሮትሃታባ*+ አሉት። +35 ሕዝቡም ከቂብሮትሃታባ ተነስቶ ወደ ሃጼሮት+ ተጓዘ፤ በሃጼሮትም ተቀመጠ። +2 ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +2 “እስራኤላውያን ሦስት ነገዶችን ላቀፈው ምድባቸው+ በተሰጠው ቦታ ይስፈሩ፤ እያንዳንዱም ሰው ለአባቶቹ ቤት በቆመው ዓርማ* አጠገብ ይስፈር። ፊታቸውን ወደ መገናኛ ድንኳኑ አድርገው ዙሪያውን ይስፈሩ። +3 “በስተ ምሥራቅ ፀሐይ በምትወጣበት አቅጣጫ በየምድቡ* የሚሰፍረው ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የይሁዳ ምድብ ይሆናል፤ የይሁዳ ልጆች አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን+ ነው። +"4 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 74,600 ናቸው።+" +5 ከእሱም ቀጥሎ የሚሰፍረው የይሳኮር ነገድ ይሆናል፤ የይሳኮር ልጆች አለቃ የጹአር ልጅ ናትናኤል+ ነው። +"6 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 54,400 ናቸው።+" +7 ከዚያ ቀጥሎ የዛብሎን ነገድ ይስፈር፤ የዛብሎን ልጆች አለቃ የሄሎን ልጅ ኤልያብ+ ነው። +"8 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 57,400 ናቸው።+ " +"9 “በይሁዳ ምድብ በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 186,400 ናቸው። መጀመሪያ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ይሆናሉ።+ " +10 “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የሮቤል+ ምድብ በየምድቡ* በመሆን በስተ ደቡብ አቅጣጫ ይስፈር፤ የሮቤል ልጆች አለቃ የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር+ ነው። +"11 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 46,500 ናቸው።+" +12 ���እሱ ቀጥሎ የሚሰፍረው የስምዖን ነገድ ይሆናል፤ የስምዖን ልጆች አለቃ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል+ ነው። +"13 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 59,300 ናቸው።+" +14 ከዚያ ቀጥሎ የጋድ ነገድ ይስፈር፤ የጋድ ልጆች አለቃ የረኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ+ ነው። +"15 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 45,650 ናቸው።+ " +"16 “በሮቤል ምድብ በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 151,450 ናቸው፤ በሁለተኛ ደረጃ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ናቸው።+ " +17 “የመገናኛ ድንኳኑ ከቦታ ወደ ቦታ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ+ የሌዋውያኑ ሰፈር በሌሎቹ ሰፈሮች መሃል መሆን ይኖርበታል። “እነሱም ልክ በሰፈሩበት ሁኔታ እያንዳንዳቸው ቦታቸውን ጠብቀው+ ሦስት ነገድ ባቀፈው ምድባቸው መሠረት መጓዝ ይኖርባቸዋል። +18 “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የኤፍሬም ምድብ በየምድቡ* በመሆን በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ይስፈር፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ+ ነው። +"19 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 40,500 ናቸው።+" +20 ከእሱም ቀጥሎ የምናሴ+ ነገድ ይስፈር፤ የምናሴ ልጆች አለቃ የፐዳጹር ልጅ ገማልያል+ ነው። +"21 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 32,200 ናቸው።+" +22 ከዚያ ቀጥሎ የቢንያም ነገድ ይስፈር፤ የቢንያም ልጆች አለቃ የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን+ ነው። +"23 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 35,400 ናቸው።+ " +"24 “በኤፍሬም ምድብ በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 108,100 ናቸው፤ በሦስተኛ ደረጃ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ናቸው።+ " +25 “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የዳን ምድብ በየምድቡ* በመሆን በስተ ሰሜን አቅጣጫ ይስፈር፤ የዳን ልጆች አለቃ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ ነው። +"26 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 62,700 ናቸው።+" +27 ከእሱም ቀጥሎ የሚሰፍረው የአሴር ነገድ ይሆናል፤ የአሴር ልጆች አለቃ የኦክራን ልጅ ፓጊኤል+ ነው። +"28 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 41,500 ናቸው።+" +29 ከዚያ ቀጥሎ የንፍታሌም ነገድ ይስፈር፤ የንፍታሌም ልጆች አለቃ የኤናን ልጅ አሂራ+ ነው። +"30 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 53,400 ናቸው።+ " +"31 “በዳን ምድብ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 157,600 ናቸው። ሦስት ነገዶችን ባቀፈው ምድባቸው መሠረት መጨረሻ ላይ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ናቸው።”+ " +"32 በአባቶቻቸው ቤት መሠረት የተመዘገቡት እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፤ ወደ ሠራዊቱ ለመቀላቀል በሰፈሩ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 603,550 ነበሩ።+" +33 ሌዋውያኑ ግን ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር+ አልተመዘገቡም።+ +34 እስራኤላውያንም ይሖዋ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። እያንዳንዳቸው በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በመሆን ሦስት ነገዶችን ባቀፈው ምድባቸው+ መሠረት የሰፈሩትም ሆነ ድንኳናቸውን ነቅለው የተነሱት በዚህ መንገድ ነው።+ +26 ከመቅሰፍቱ በኋላ+ ይሖዋ ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፦ +2 “ከመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ መካከል ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን በየአባቶቻቸው ቤት ቁጠሩ፤ በእስራኤል የጦር ሠራዊት ውስጥ ገብተው ማገልገል የሚችሉትን ሁሉ ቁጠሩ።”+ +3 በመሆኑም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር+ ከኢያሪኮ ማዶ+ በዮርዳኖስ አጠገብ በሚገኘው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ+ ላይ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፦ +4 “ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን ቁጠሩ።”+ ከግብፅ ምድር የወጡት የእስራኤል ልጆች የሚከተሉት ነበሩ፦ +5 የእስራኤል የበኩር ልጅ ሮቤል፤+ የሮቤል ልጆች+ እነዚህ ነበሩ፦ ከሃኖክ የሃኖካውያን ቤተሰብ፣ ከፓሉ የፓላውያን ቤተሰብ፣ +6 ከኤስሮን የኤስሮናውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከካርሚ ��ካርማውያን ቤተሰብ። +"7 የሮቤላውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 43,730 ነበሩ።+ " +8 የፓሉ ልጅ ኤልያብ ነበር። +9 የኤልያብ ልጆች ደግሞ ነሙኤል፣ ዳታን እና አቤሮን ነበሩ። እዚህ ላይ የተጠቀሱት ዳታን እና አቤሮን ቆሬና ግብረ አበሮቹ+ በይሖዋ ላይ ባመፁበት ወቅት+ ከእነሱ ጋር በማበር በሙሴና በአሮን ላይ የተነሱ የማኅበረሰቡ ተወካዮች ነበሩ።+ +10 ከዚያም ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻቸው። ቆሬም እሳት ወርዶ 250 ሰዎችን በበላ ጊዜ ከነግብረ አበሮቹ ሞተ።+ እነሱም የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆኑ።+ +11 ይሁንና የቆሬ ልጆች አልሞቱም።+ +12 የስምዖን ልጆች+ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከነሙኤል የነሙኤላውያን ቤተሰብ፣ ከያሚን የያሚናውያን ቤተሰብ፣ ከያኪን የያኪናውያን ቤተሰብ፣ +13 ከዛራ የዛራውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሻኡል የሻኡላውያን ቤተሰብ። +"14 የስምዖናውያን ቤተሰቦች እነዚህ ሲሆኑ እነሱም 22,200 ነበሩ።+ " +15 የጋድ ልጆች+ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከጸፎን የጸፎናውያን ቤተሰብ፣ ከሃጊ የሃጋውያን ቤተሰብ፣ ከሹኒ የሹናውያን ቤተሰብ፣ +16 ከኦዝኒ የኦዝናውያን ቤተሰብ፣ ከኤሪ የኤራውያን ቤተሰብ፣ +17 ከአሮድ የአሮዳውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከአርዔላይ የአርዔላውያን ቤተሰብ። +"18 የጋድ ልጆች ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 40,500 ነበሩ።+ " +19 የይሁዳ ልጆች+ ኤር እና ኦናን ነበሩ።+ ሆኖም ኤር እና ኦናን በከነአን ምድር ሞቱ።+ +20 የይሁዳ ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሴሎም+ የሴሎማውያን ቤተሰብ፣ ከፋሬስ+ የፋሬሳውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከዛራ+ የዛራውያን ቤተሰብ። +21 የፋሬስ ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከኤስሮን+ የኤስሮናውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሃሙል+ የሃሙላውያን ቤተሰብ። +"22 የይሁዳ ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 76,500 ነበሩ።+ " +23 የይሳኮር ልጆች+ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከቶላ+ የቶላውያን ቤተሰብ፣ ከፑዋ የፑዋውያን ቤተሰብ፣ +24 ከያሹብ የያሹባውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሺምሮን የሺምሮናውያን ቤተሰብ። +"25 የይሳኮር ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 64,300 ነበሩ።+ " +26 የዛብሎን ልጆች+ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሰሬድ የሰሬዳውያን ቤተሰብ፣ ከኤሎን የኤሎናውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከያህልኤል የያህልኤላውያን ቤተሰብ። +"27 የዛብሎናውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 60,500 ነበሩ።+ " +28 የዮሴፍ ልጆች+ በየቤተሰባቸው ምናሴና ኤፍሬም ነበሩ።+ +29 የምናሴ ልጆች+ እነዚህ ነበሩ፦ ከማኪር+ የማኪራውያን ቤተሰብ፤ ማኪር ጊልያድን ወለደ፤+ ከጊልያድ የጊልያዳውያን ቤተሰብ። +30 የጊልያድ ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከኢዔዝር የኢዔዝራውያን ቤተሰብ፣ ከሄሌቅ የሄሌቃውያን ቤተሰብ፣ +31 ከአስሪዔል የአስሪዔላውያን ቤተሰብ፣ ከሴኬም የሴኬማውያን ቤተሰብ፣ +32 ከሸሚዳ የሸሚዳውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሄፌር የሄፌራውያን ቤተሰብ። +33 የሄፌር ልጅ ሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤+ የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች+ ስም ማህላ፣ ኖኅ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበር። +"34 የምናሴ ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 52,700 ነበሩ።+ " +35 የኤፍሬም ልጆች+ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሹተላ+ የሹተላውያን ቤተሰብ፣ ከቤኬር የቤኬራውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከታሃን የታሃናውያን ቤተሰብ። +36 የሹተላ ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከኤራን የኤራናውያን ቤተሰብ። +"37 የኤፍሬም ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 32,500 ነበሩ።+ የዮሴፍ ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚ�� ነበሩ። " +38 የቢንያም ልጆች+ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከቤላ+ የቤላውያን ቤተሰብ፣ ከአሽቤል የአሽቤላውያን ቤተሰብ፣ ከአሂራም የአሂራማውያን ቤተሰብ፣ +39 ከሼፉፋም የሼፉፋማውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሁፋም የሁፋማውያን ቤተሰብ። +40 የቤላ ልጆች አርድ እና ንዕማን ነበሩ፤+ ከአርድ የአርዳውያን ቤተሰብ፣ ከንዕማን ደግሞ የንዕማናውያን ቤተሰብ። +"41 የቢንያም ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 45,600 ነበሩ።+ " +42 የዳን ልጆች+ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሹሃም የሹሃማውያን ቤተሰብ። የዳን ቤተሰቦች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ። +"43 ከሹሃማውያን ቤተሰቦች በሙሉ የተመዘገቡት 64,400 ነበሩ።+ " +44 የአሴር ልጆች+ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከይምናህ የይምናሃውያን ቤተሰብ፣ ከይሽዊ የይሽዋውያን ቤተሰብ፣ ከበሪአ የበሪአውያን ቤተሰብ፤ +45 ከበሪአ ልጆች፦ ከሄቤር የሄቤራውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከማልኪኤል የማልኪኤላውያን ቤተሰብ። +46 የአሴር ሴት ልጅ ስም ሴራህ ነበር። +"47 የአሴር ልጆች ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 53,400 ነበሩ።+ " +48 የንፍታሌም ልጆች+ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከያህጽኤል የያህጽኤላውያን ቤተሰብ፣ ከጉኒ የጉናውያን ቤተሰብ፣ +49 ከየጼር የየጼራውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሺሌም የሺሌማውያን ቤተሰብ። +"50 የንፍታሌም ቤተሰቦች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 45,400 ነበሩ።+ " +"51 ከእስራኤላውያን መካከል የተመዘገቡት በጠቅላላ 601,730 ነበሩ።+ " +52 ከዚህ በኋላ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +53 “ምድሪቱ ለእነዚህ በስማቸው ዝርዝር መሠረት ርስት ሆና ትከፋፈል።+ +54 ተለቅ ላሉት ቡድኖች በዛ ያለ ውርሻ ትሰጣቸዋለህ፤ አነስ ላሉት ቡድኖች ደግሞ አነስ ያለ ውርሻ ትሰጣቸዋለህ።+ የእያንዳንዱ ቡድን ውርሻ በተመዘገቡት ሰዎች ብዛት ተመጣጥኖ መሰጠት አለበት። +55 ይሁን እንጂ ምድሪቱ መከፋፈል ያለባት በዕጣ ነው።+ ውርሻቸውንም ማግኘት ያለባቸው በአባቶቻቸው ነገዶች ስም መሠረት ነው። +56 እያንዳንዱ ውርሻ የሚወሰነው በዕጣ ሲሆን በኋላም ውርሻው እንደ ቡድኑ ትልቅነትና ትንሽነት ይከፋፈላል።” +57 ከሌዋውያኑ መካከል በየቤተሰባቸው የተመዘገቡት እነዚህ ነበሩ፦+ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ቤተሰብ፣ ከቀአት+ የቀአታውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሜራሪ የሜራራውያን ቤተሰብ። +58 የሌዋውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፦ የሊብናውያን ቤተሰብ፣+ የኬብሮናውያን ቤተሰብ፣+ የማህላውያን ቤተሰብ፣+ የሙሻውያን ቤተሰብ+ እና የቆሬያውያን ቤተሰብ።+ ቀአት አምራምን ወለደ።+ +59 የአምራም ሚስት ስሟ ዮካቤድ ነበር፤+ እሷም የሌዊ ሚስት በግብፅ ለሌዊ የወለደችለት ናት። ዮካቤድም ለአምራም አሮንን፣ ሙሴንና እህታቸውን ሚርያምን ወለደችለት።+ +60 አሮንም ናዳብን፣ አቢሁን፣ አልዓዛርን እና ኢታምርን ወለደ።+ +61 ሆኖም ናዳብና አቢሁ በይሖዋ ፊት ያልተፈቀደ እሳት በማቅረባቸው ሞቱ።+ +"62 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ወንዶች በአጠቃላይ 23,000 ነበሩ።+ እነዚህ በእስራኤላውያን መካከል ርስት ስለማይሰጣቸው+ ከእስራኤላውያን ጋር አልተመዘገቡም።+ " +63 እነዚህም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ በሚገኘው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ እስራኤላውያንን በመዘገቡበት ወቅት የመዘገቧቸው ናቸው። +64 ሆኖም ከእነዚህ መካከል ሙሴና ካህኑ አሮን እስራኤላውያንን በሲና ምድረ በዳ በቆጠሩበት ወቅት ተመዝግቦ የነበረ አንድም ሰው አልነበረም።+ +65 ምክንያቱም ይሖዋ እነሱን በተመለከተ “በእርግጥ በምድረ በዳው ላይ ያልቃሉ”+ በማ��ት ተናግሮ ነበር። በመሆኑም ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር አንድም የተረፈ ሰው አልነበረም።+ +4 ይሖዋም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +2 “ከሌዊ ልጆች መካከል የቀአትን ወንዶች ልጆች+ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች መሠረት ቁጠሩ፤ +3 በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ እንዲሠራ በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉትን ዕድሜያቸው ከ30+ እስከ 50 ዓመት+ የሆኑትን ሁሉ ቁጠሩ።+ +4 “የቀአት ወንዶች ልጆች በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ የሚያከናውኑት አገልግሎት ይህ ነው።+ ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው፦ +5 ሰፈሩ በሚነሳበት ጊዜ አሮንና ወንዶች ልጆቹ መጥተው ታቦቱን+ የሚከልለውን መጋረጃ+ ያወርዱታል፤ የምሥክሩንም ታቦት በእሱ ይሸፍኑታል። +6 በላዩም ላይ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛ ይደርቡበታል፤ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ሰማያዊ የሆነ ጨርቅ ያለብሱታል፤ ለመሸከሚያ የሚያገለግሉትንም መሎጊያዎች+ በቦታቸው ላይ ያደርጓቸዋል። +7 “ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥበትንም ጠረጴዛ+ ሰማያዊ ጨርቅ ያለብሱታል፤ በላዩም ላይ ሳህኖቹን፣ ጽዋዎቹን፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹንና ለመጠጥ መባ የሚሆኑትን ማንቆርቆሪያዎች ያስቀምጣሉ፤+ የዘወትሩም የቂጣ መባ+ ከላዩ ላይ አይነሳ። +8 ደማቅ ቀይ ጨርቅ ያለብሷቸዋል፤ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛም ይደርቡበታል፤ እንዲሁም ለመሸከሚያ የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች+ በቦታቸው ላይ ያደርጓቸዋል። +9 ከዚያም ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው የመብራቱን መቅረዝ+ ከመብራቶቹ፣+ ከመቆንጠጫዎቹና ከመኮስተሪያዎቹ+ እንዲሁም ዘወትር ዘይት እንዲኖር ለማድረግ ከሚያገለግሉት ዘይት የሚቀመጥባቸው ዕቃዎች ሁሉ ጋር ይሸፍኑታል። +10 መቅረዙን ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር ከአቆስጣ ቆዳ በተሠራ መሸፈኛ ይጠቀልሉታል፤ በመሸከሚያ ሳንቃ ላይም ያስቀምጡታል። +11 የወርቁን መሠዊያም+ ሰማያዊ ጨርቅ ያለብሱታል፤ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛም ይደርቡበታል፤ ለመሸከሚያ የሚያገለግሉትንም መሎጊያዎች+ በቦታቸው ላይ ያደርጓቸዋል። +12 ከዚያም በቅዱሱ ስፍራ ዘወትር የሚጠቀሙባቸውን መገልገያ ዕቃዎች በሙሉ+ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ ይጠቀልሏቸዋል፤ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛም ይደርቡባቸዋል፤ በመሸከሚያ ሳንቃ ላይም ያስቀምጧቸዋል። +13 “አመዱን* ከመሠዊያው ላይ ያስወግዱ፤+ መሠዊያውንም ሐምራዊ የሱፍ ጨርቅ ያልብሱት። +14 እንዲሁም በመሠዊያው ላይ ለማገልገል የሚጠቀሙባቸውን ዕቃዎች በሙሉ ይኸውም መኮስተሪያዎቹን፣ ሹካዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹንና የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ በላዩ ላይ ያደርጉበታል፤+ ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መሸፈኛም ይደርቡበታል፤ ለመሸከሚያ የሚያገለግሉትንም መሎጊያዎች+ በቦታቸው ላይ ያደርጓቸዋል +15 “አሮንና ወንዶች ልጆቹ ሰፈሩ ከመነሳቱ በፊት በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮችና የቅዱሱን ስፍራ ዕቃዎች በሙሉ ሸፍነው መጨረስ አለባቸው።+ ከዚያም የቀአት ወንዶች ልጆች ለመሸከም ይመጣሉ፤+ ሆኖም በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮች መንካት የለባቸውም፤ ከነኩ ግን ይሞታሉ።+ ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ እነ +16 “የመብራቱን ዘይት፣+ ጥሩ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣+ ዘወትር የሚቀርበውን የእህል መባና የቅብዓት ዘይቱን+ የመቆጣጠሩ ኃላፊነት የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር+ ነው። ቅዱሱን ስፍራና ዕቃዎቹን ጨምሮ የማደሪያ ድንኳኑን ሁሉና በውስጡ ያለውን ነገር በሙሉ የመቆጣጠሩ ኃላፊነት የእሱ ነው።” +17 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +18 “የቀአታውያን+ ቤተሰቦች ነገድ ከሌዋውያን መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ አታድርጉ። +19 እጅግ ቅዱስ ወደሆኑት ነገሮች+ በመቅረባቸው የተነሳ እንዳይሞቱ፣ ከዚህ ይልቅ በሕይወት እንዲኖሩ ይህን አድርጉላቸው። አሮንና ወንዶች ልጆቹ ገብተው ለእያንዳንዳቸው ሥራቸውንና የሚሸከሙትን ነገር ይመድቡላቸው። +20 ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች ለአፍታ እንኳ ገብተው ማየት የለባቸውም፤ ካዩ ግን ይሞታሉ።”+ +21 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +22 “የጌድሶንን ወንዶች ልጆች+ በየአባቶቻቸው ቤቶችና በየቤተሰባቸው ቁጠር። +23 በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉትን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑትን ሁሉ መዝግብ። +24 የጌድሶናውያን ቤተሰቦች እንዲንከባከቡና እንዲሸከሙ+ የተመደቡት እነዚህን ነገሮች ነው፦ +25 እነሱም የማደሪያ ድንኳኑን የድንኳን ጨርቆች፣+ የመገናኛ ድንኳኑን ጨርቆች፣ መደረቢያውንና ከእሱ በላይ ያለውን ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መደረቢያ+ እንዲሁም የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መከለያ*+ ይሸከማሉ፤ +26 በተጨማሪም የግቢውን መጋረጃዎች፣+ በማደሪያ ድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ግቢ መግቢያ ላይ የሚገኘውን መከለያ፣*+ የድንኳን ገመዶቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን በሙሉ እንዲሁም ለአገልግሎቱ የሚውሉትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። የሥራ ምድባቸው ይህ ነው። +27 ጌድሶናውያን+ የሚያከናውኑትን አገልግሎትና የሚሸከሟቸውን ነገሮች ሁሉ የሚቆጣጠሩት አሮንና ወንዶች ልጆቹ ናቸው፤ እነዚህን ነገሮች ሁሉ የመሸከሙን ኃላፊነት ለእነሱ ትሰጣቸዋለህ። +28 የጌድሶናውያን ቤተሰቦች በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ የሚያከናውኑት አገልግሎት ይህ ነው፤+ ኃላፊነታቸውንም የሚወጡት በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር+ አመራር ሥር ሆነው ነው። +29 “የሜራሪን ወንዶች ልጆችም+ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት ትመዘግባቸዋለህ። +30 በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉትን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑትን ሁሉ ትመዘግባለህ። +31 በመገናኛ ድንኳኑ ከሚያከናውኑት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ነገሮች የመሸከም ኃላፊነት+ ተጥሎባቸዋል፦ የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች፣+ አግዳሚ እንጨቶቹን፣+ ዓምዶቹን፣+ መሰኪያዎቹን፣+ +32 በግቢው ዙሪያ ያሉትን ቋሚዎች፣+ መሰኪያዎቻቸውን፣+ የድንኳን ካስማዎቻቸውን፣+ የድንኳን ገመዶቻቸውን እንዲሁም ቁሳቁሶቻቸውንና ከዚህ አገልግሎት ጋር የተያያዙትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። በኃላፊነት የሚሸከሙትንም ዕቃ በስም ጠቅሰህ ትመድብላቸዋለህ። +33 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች+ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ሆነው በመገናኛ ድንኳኑ የሚያገለግሉት በዚህ መሠረት ነው።”+ +34 ከዚያም ሙሴ፣ አሮንና የማኅበረሰቡ አለቆች+ የቀአታውያንን ወንዶች ልጆች+ በየቤተሰቦቻቸውና በየአባቶቻቸው ቤት መዘገቡ፤ +35 በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉትን ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑትን ሁሉ መዘገቡ።+ +"36 በየቤተሰባቸው የተመዘገቡትም በአጠቃላይ 2,750 ነበሩ።+" +37 ከቀአታውያን ቤተሰቦች መካከል የተመዘገቡትና በመገናኛ ድንኳኑ የሚያገለግሉት በአጠቃላይ እነዚህ ነበሩ። ሙሴና አሮንም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት መዘገቧቸው።+ +38 የጌድሶን ወንዶች ልጆችም+ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት ተመዘገቡ፤ +39 በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉት ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑት ሁሉ ተመዘገቡ። +"40 በየቤተሰቦቻቸውና በየአባቶቻቸው ቤት የተመዘገቡት በአጠቃላይ 2,630 ነበሩ።+" +41 በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግሉ የተመዘገቡት የጌድሶን ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች በአጠቃላይ እነዚህ ነበሩ። ሙሴና አሮንም ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት መዘገቧቸው።+ +42 የሜራሪ ���ንዶች ልጆች በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት ተመዘገቡ፤ +43 በመገናኛ ድንኳኑ እንዲያገለግል በተመደበው ቡድን ውስጥ ያሉት ዕድሜያቸው ከ30 እስከ 50 ዓመት የሆኑት ሁሉ ተመዘገቡ።+ +"44 ከእነሱ መካከል በየቤተሰባቸው የተመዘገቡት በአጠቃላይ 3,200 ነበሩ።+" +45 ሙሴና አሮን ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት የመዘገቧቸው የሜራሪ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ።+ +46 ሙሴ፣ አሮንና የእስራኤል አለቆች እነዚህን ሌዋውያን ሁሉ በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች መዘገቧቸው፤ +47 እነሱም ከ30 እስከ 50 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ሁሉም ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ እንዲያገለግሉና ሸክም እንዲሸከሙ ተመድበው ነበር።+ +"48 የተመዘገቡትም በአጠቃላይ 8,580 ነበሩ።+" +49 እነሱም ይሖዋ በሙሴ በኩል ባስተላለፈው ትእዛዝ መሠረት ተመዝግበው ነበር፤ የተመዘገቡትም እያንዳንዳቸው በሚያከናውኑት አገልግሎትና በሚሸከሙት ሸክም መሠረት ነበር፤ እነሱም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተመዘገቡ። +16 ከዚያም የሌዊ+ ልጅ፣ የቀአት+ ልጅ፣ የይጽሃር+ ልጅ ቆሬ+ ከሮቤል ልጆች አንዱ ከሆነው ከኤልያብ+ ልጆች ከዳታንና ከአቤሮን እንዲሁም ከሮቤል+ ልጆች አንዱ ከሆነው ከፐሌት ልጅ ከኦን ጋር በመሆን ተነሳ። +2 እነሱም ከማኅበረሰቡ አለቆች ይኸውም ከጉባኤው መካከል ከተመረጡት ታዋቂ የሆኑ 250 እስራኤላውያን ወንዶች ጋር በማበር በሙሴ ላይ ተነሱ። +3 እነሱም ሙሴንና አሮንን ለመቃወም+ ተሰብስበው መጡ፤ እንዲህም አሏቸው፦ “ምነው፣ አላበዛችሁትም እንዴ! መላው ማኅበረሰብ እኮ ቅዱስ ነው፤+ ሁሉም ቅዱስ ናቸው፤ ይሖዋም በመካከላቸው ነው።+ ታዲያ በይሖዋ ጉባኤ ላይ ራሳችሁን ከፍ ከፍ የምታደርጉት ለምንድን ነው?” +4 ሙሴ ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ በግንባሩ ተደፋ። +5 ከዚያም ቆሬንና ግብረ አበሮቹን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “ጠዋት ላይ ይሖዋ የእሱ የሆነውን፣+ ቅዱስ የሆነውንና ወደ እሱ መቅረብ የሚችለውን+ ሰው ያሳውቃል፤ እሱ የመረጠውም+ ሰው ወደ እሱ ይቀርባል። +6 ስለዚህ እንዲህ አድርጉ፦ ቆሬ፣ አንተም ሆንክ ግብረ አበሮችህ+ በሙሉ የዕጣን ማጨሻዎች+ ውሰዱ፤ +7 ከዚያም በነገው ዕለት እሳት ካደረጋችሁባቸው በኋላ በይሖዋ ፊት ዕጣን ጨምሩባቸው፤ ይሖዋ የሚመርጠውም ሰው፣+ እሱ ቅዱስ ይሆናል። እናንተ የሌዊ ልጆች፣+ በጣም አብዝታችሁታል!” +8 ከዚያም ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፦ “እናንተ የሌዊ ልጆች፣ እባካችሁ አዳምጡ። +9 የእስራኤል አምላክ እናንተን ከእስራኤል ማኅበረሰብ+ መለየቱ እንዲሁም በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን የሚከናወነውን አገልግሎት ትፈጽሙና በማኅበረሰቡ ፊት ቆማችሁ እነሱን ታገለግሉ ዘንድ ወደ እሱ እንድትቀርቡ መፍቀዱ እንደ ቀላል ነገር የሚታይ ነው?+ +10 ደግሞስ አንተንና የሌዊ ልጆች የሆኑትን ወንድሞችህን በሙሉ ወደ እሱ እንድትቀርቡ ማድረጉ ቀላል ነገር ነው? ታዲያ የክህነት አገልግሎቱንም ለመጠቅለል መሞከር ይገባችኋል?+ +11 ስለዚህ አንተም ሆንክ አብረውህ የተሰበሰቡት ግብረ አበሮችህ በሙሉ ይሖዋን እየተቃወማችሁ ነው። በአሮን ላይ የምታጉረመርሙት እሱ ምን ስለሆነ ነው?”+ +12 ከዚያም ሙሴ የኤልያብን ልጆች ዳታንንና አቤሮንን+ አስጠራቸው፤ እነሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “አንመጣም! +13 በምድረ በዳ ልትገድለን ወተትና ማር ከምታፈሰው ምድር ያወጣኸን አይበቃህም?+ አሁን ደግሞ በእኛ ላይ ፈላጭ ቆራጭ* ልትሆን ያምርሃል? +14 ደግሞም ወተትና ማር ወደምታፈስ ምድር+ አላስገባኸንም፤ ወይም እርሻና የወይን የአትክልት ቦታዎችን ርስት አድርገህ አልሰጠኸንም። ታዲያ የእነዚያን ሰዎች ዓይን ልታወጣ ነው? እኛ እንደሆነ አንመጣም!” +15 ስለዚህ ሙሴ እጅግ ተቆጣ፤ ይሖዋንም እንዲህ አለው፦ “የእህል መባቸውን አትመልከት። ከእነዚህ ሰዎች አንድ አህያ እንኳ አልወሰድኩም፤ አንዳቸውንም ቢሆን አልበደልኩም።”+ +16 ከዚያም ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፦ “አንተና ግብረ አበሮችህ በሙሉ ነገ በይሖዋ ፊት ቅረቡ፤ አንተም ሆንክ እነሱ እንዲሁም አሮን መቅረብ ይኖርባችኋል። +17 እያንዳንዱ ሰው የየራሱን የዕጣን ማጨሻ ይያዝ፤ በላዩም ላይ ዕጣን ያድርግበት፤ አንተንና አሮንን ጨምሮ እያንዳንዱ ሰው በይሖዋ ፊት የዕጣን ማጨሻውን ያቀርባል፤ ይህም በአጠቃላይ 250 የዕጣን ማጨሻዎች ማለት ነው፤ እያንዳንዱም የየራሱን የዕጣን ማጨሻ ይዞ ይቀርባል።” +18 ስለዚህ እያንዳንዳቸው የዕጣን ማጨሻቸውን ይዘው መጡ፤ በላዩም ላይ እሳትና ዕጣን አደረጉበት፤ ከዚያም ከሙሴና ከአሮን ጋር በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሙ። +19 ቆሬ፣ ግብረ አበሮቹ+ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ሙሴንና አሮንን በመቃወም እንዲሰበሰቡ ባደረገ ጊዜ የይሖዋ ክብር ለመላው ማኅበረሰብ ተገለጠ።+ +20 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +21 “በአንዴ ጠራርጌ እንዳጠፋቸው ራሳችሁን ከዚህ ቡድን ለዩ።”+ +22 እነሱም በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ፣ አንተ የሰው ሁሉ መንፈስ* አምላክ ነህ፤+ ታዲያ አንድ ሰው በሠራው ኃጢአት የተነሳ በመላው ማኅበረሰብ ላይ ትቆጣለህ?”+ +23 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +24 “ለማኅበረሰቡ ‘ከቆሬ፣ ከዳታንና ከአቤሮን+ ድንኳኖች አካባቢ ራቁ!’ ብለህ ንገራቸው።” +25 ሙሴም ተነስቶ ወደ ዳታንና አቤሮን ሄደ፤ የእስራኤል ሽማግሌዎችም+ አብረውት ሄዱ። +26 ከዚያም ማኅበረሰቡን እንዲህ አላቸው፦ “በኃጢአታቸው ተጠራርጋችሁ እንዳትጠፉ እባካችሁ፣ ከእነዚህ ክፉ ሰዎች ድንኳኖች ራቁ፤ የእነሱ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትንኩ።” +27 እነሱም ወዲያውኑ ከቆሬ፣ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳኖች፣ ከዙሪያቸውም ሁሉ ራቁ፤ ዳታንና አቤሮንም ወጥተው ከሚስቶቻቸው፣ ከልጆቻቸውና ከሕፃኖቻቸው ጋር በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ላይ ቆሙ። +28 ሙሴም እንዲህ አለ፦ “እነዚህን ነገሮች ሁሉ የማደርገው ከልቤ አመንጭቼ ሳይሆን* ይሖዋ ልኮኝ መሆኑን በዚህ ታውቃላችሁ፦ +29 እነዚህ ሰዎች እንደ ማንኛውም ሰው አሟሟት የሚሞቱ ከሆነና የሚደርስባቸውም ቅጣት በሌሎች ሰዎች ሁሉ ላይ የሚደርስ ዓይነት ከሆነ እኔን ይሖዋ አላከኝም ማለት ነው።+ +30 ሆኖም ይሖዋ በእነሱ ላይ እንግዳ የሆነ ነገር ቢያደርግና መሬት አፏን ከፍታ እነሱንም ሆነ የእነሱ የሆነውን ነገር ሁሉ ብትውጥ፣ በሕይወት እንዳሉም ወደ መቃብር* ቢወርዱ፣ እነዚህ ሰዎች ይሖዋን እንደናቁ በእርግጥ ታውቃላችሁ።” +31 እሱም ይህን ተናግሮ እንደጨረሰ፣ የቆሙባት ምድር ተሰነጠቀች።+ +32 ምድሪቱም አፏን ከፍታ እነሱን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ የቆሬ የሆነውን ማንኛውንም ሰውና+ ንብረታቸውን ሁሉ ዋጠች። +33 በዚህ መንገድ እነሱም ሆኑ የእነሱ የሆኑት ሁሉ በሕይወት እንዳሉ ወደ መቃብር* ወረዱ፤ ምድርም ተከደነችባቸው፤ ስለዚህ ከጉባኤው መካከል ጠፉ።+ +34 በዙሪያቸው የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ጩኸታቸውን ሲሰሙ “ኧረ ምድሪቱ እኛንም እንዳትውጠን!” በማለት መሸሽ ጀመሩ። +35 ከዚያም ከይሖዋ ዘንድ እሳት መጥቶ+ ዕጣን ሲያጥኑ የነበሩትን 250 ሰዎች በላ።+ +36 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +37 “የዕጣን ማጨሻዎቹ+ ቅዱስ ስለሆኑ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ከእሳቱ ውስጥ እንዲያወጣቸው ንገረው። በተጨማሪም እሳቱን ራቅ አድርጎ እንዲበትነው ንገረው። +38 ኃጢአት በመሥራታቸው የተነሳ ሕይወታቸውን የከፈሉት* ሰዎች ይዘዋቸው የነበሩ�� የዕጣን ማጨሻዎች ቅዱስ ስለሆኑ ለመሠዊያው መለበጫ+ እንዲያገለግሉ በስሱ ይጠፍጠፉ፤ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት ስላቀረቧቸው ቅዱስ ሆነዋል። ለእስራኤላውያንም ምልክት ሆነው ያገልግሉ።”+ +39 ስለሆነም ካህኑ አልዓዛር በእሳት የተቃጠሉት ሰዎች ያቀረቧቸውን የመዳብ የዕጣን ማጨሻዎች ወሰደ፤ ከዚያም መሠዊያውን ለመለበጥ በስሱ ጠፈጠፋቸው፤ +40 ይህን ያደረገውም ይሖዋ በሙሴ በኩል ለእሱ በነገረው መሠረት ነው። ይህም የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው* በይሖዋ ፊት ዕጣን ለማጨስ እንዳይቀርብ+ እንዲሁም ማንም ሰው እንደ ቆሬና እንደ ግብረ አበሮቹ እንዳይሆን ለእስራኤላውያን ማሳሰቢያ እንዲሆን ነው።+ +41 በማግስቱም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ “እናንተ ሰዎች የይሖዋን ሕዝብ ገድላችኋል” በማለት በሙሴና በአሮን ላይ ያጉረመርም ጀመር።+ +42 የእስራኤልም ማኅበረሰብ ሙሴንና አሮንን በመቃወም በተሰበሰበ ጊዜ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ዞር ብሎ ሲመለከት፣ መገናኛ ድንኳኑን ደመና ሸፍኖት አየ፤ የይሖዋም ክብር ተገለጠ።+ +43 ሙሴና አሮንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ፊት መጡ፤+ +44 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +45 “በአንዴ እንዳጠፋቸው+ ራሳችሁን ከዚህ ማኅበረሰብ ለዩ።” እነሱም በዚህ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።+ +46 ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “የዕጣን ማጨሻ ውሰድና ከመሠዊያው ላይ እሳት አድርግበት፤+ በላዩም ላይ ዕጣን ጨምርበት፤ ፈጥነህም ወደ ማኅበረሰቡ በመሄድ አስተሰርይላቸው፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ተቆጥቷል። መቅሰፍቱ ጀምሯል!” +47 አሮን ልክ ሙሴ እንዳለው ወዲያውኑ የዕጣን ማጨሻውን ይዞ ወደ ጉባኤው መካከል እየሮጠ ገባ፤ መቅሰፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር። በመሆኑም ዕጣኑን በዕጣን ማጨሻው ላይ በማድረግ ለሕዝቡ ማስተሰረይ ጀመረ። +48 እሱም በሞቱትና በሕይወት ባሉት መካከል ቆመ፤ መቅሰፍቱም ቀስ በቀስ ቆመ። +"49 በቆሬ ምክንያት የሞቱትን ሳይጨምር በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች ብዛት 14,700 ነበር።" +50 በመጨረሻም አሮን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ወደነበረው ወደ ሙሴ ሲመለስ መቅሰፍቱ ቆሞ ነበር። +6 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ለይሖዋ ናዝራዊ*+ ሆነው ለመኖር ልዩ ስእለት ቢሳሉ +3 ስእለት የተሳለው ሰው ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር ሌላ መጠጥ መራቅ ይኖርበታል። የወይን ጠጅ ኮምጣጤ ወይም የማንኛውም ዓይነት የሚያሰክር መጠጥ ኮምጣጤ አይጠጣ።+ ከወይን ፍሬ የተዘጋጀን ማንኛውንም መጠጥ አይጠጣ፤ የወይን ፍሬም ሆነ ዘቢብ አይብላ። +4 ናዝራዊ ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ ከወይን ተክል የተዘጋጀን ማንኛውንም ነገር፣ ያልበሰለውን የወይን ፍሬም ሆነ ግልፋፊውን ፈጽሞ መብላት የለበትም። +5 “‘ናዝራዊ ሆኖ ለመቆየት በተሳለበት ጊዜ ሁሉ ራሱን ምላጭ አይንካው።+ ለይሖዋ የተለየበት ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ የራስ ፀጉሩን በማሳደግ ቅዱስ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል። +6 ራሱን ለይሖዋ በለየበት ጊዜ ሁሉ ወደ ሞተ ሰው* አይቅረብ።* +7 ለአምላኩ ናዝራዊ መሆኑን የሚያሳየው ምልክት በራሱ ላይ ስላለ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እህቱ ቢሞቱ እንኳ በእነሱ ራሱን አያርክስ።+ +8 “‘ናዝራዊ ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ ለይሖዋ ቅዱስ ይሆናል። +9 ይሁንና አንድ ሰው ድንገት አጠገቡ ቢሞትና+ ለአምላክ የተለየ መሆኑን የሚያሳየውን ፀጉሩን ቢያረክስ* መንጻቱን በሚያረጋግጥበት ቀን ራሱን ይላጭ።+ በሰባተኛውም ቀን ፀጉሩን ይላጨው። +10 በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወደሚገኘው ካህን ያምጣ። +11 ካ���ኑም አንዱን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርጎ በማዘጋጀት ከሞተ ሰው* ጋር በተያያዘ ስለሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል።+ ከዚያም በዚያ ቀን ራሱን ይቀድስ። +12 ናዝራዊ ሆኖ ለሚቆይበት ጊዜ እንደገና ራሱን ለይሖዋ ይለይ፤ አንድ ዓመት ገደማ የሆነው የበግ ጠቦት የበደል መባ አድርጎ ያምጣ። ሆኖም ናዝራዊነቱን ስላረከሰ የቀድሞዎቹ ጊዜያት አይታሰቡለትም። +13 “‘እንግዲህ ናዝራዊን በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፦ ናዝራዊ ሆኖ የሚቆይበትን ጊዜ ሲያጠናቅቅ+ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ እንዲመጣ ይደረግ። +14 በዚያም የሚከተሉትን ለይሖዋ መባ አድርጎ ያቅርብ፦ ለሚቃጠል መባ አንድ ዓመት ገደማ የሆነውን እንከን የሌለበት አንድ የበግ ጠቦት፣+ ለኃጢአት መባ አንድ ዓመት ገደማ የሆናትን እንከን የሌለባት አንዲት ጠቦት፣+ ለኅብረት መሥዋዕት እንከን የሌለበትን አንድ አውራ በግ፣+ +15 በዘይት ከተለወሰ የላመ ዱቄት የተዘጋጁ እርሾ ያልገባባቸው አንድ ቅርጫት የቀለበት ቅርጽ ያላቸው ዳቦዎችና ዘይት የተቀቡ ስስ ቂጣዎች* እንዲሁም የእህል መባዎቻቸውንና+ የመጠጥ መባዎቻቸውን።+ +16 ካህኑም እነዚህን በይሖዋ ፊት ያቀርባቸዋል፤ የሰውየውን የኃጢአት መባና የሚቃጠል መባም ያቀርባል። +17 አውራውንም በግ በቅርጫቱ ውስጥ ካሉት ቂጣዎች ጋር የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለይሖዋ ያቀርበዋል፤ ካህኑም የእህል መባውንና+ የመጠጥ መባውን ያቀርበዋል። +18 “‘ከዚያም ናዝራዊው ያልተቆረጠውን ፀጉሩን*+ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ይላጭ፤ ናዝራዊ ሆኖ በቆየበት ጊዜ ያደገውን የራሱን ፀጉር ወስዶ ከኅብረት መሥዋዕቱ ሥር ባለው እሳት ውስጥ ይጨምረው። +19 ናዝራዊው የናዝራዊነት ምልክቱን ከተላጨ በኋላ ካህኑ የአውራውን በግ አንድ የተቀቀለ+ የፊት እግር፣ ከቅርጫቱም ውስጥ እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦ እንዲሁም አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ በናዝራዊው መዳፍ ላይ ያድርጋቸው። +20 ካህኑም እነዚህን የሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዝውዛቸው።+ ይህም ከሚወዘወዘው መባ ፍርምባና መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው እግር ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ይሆናል።+ ከዚህ በኋላ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት ይችላል። +21 “‘ስእለት የሚሳልን ናዝራዊ+ በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፦ ናዝራዊው ስእለት ከተሳለና በናዝራዊነት ከሚጠበቅበት በተጨማሪ ለይሖዋ መባ ለማቅረብ አቅሙ የሚፈቅድለት ከሆነ ለናዝራዊነቱ ሕግ ካለው አክብሮት የተነሳ ስእለቱን መፈጸም ይገባዋል።’” +22 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +23 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤልን ሕዝብ የምትባርኩት+ በዚህ መንገድ ነው። እንዲህ በሏቸው፦ +24 “ይሖዋ ይባርክህ፤+ ደግሞም ይጠብቅህ። +25 ይሖዋ ፊቱን ያብራልህ፤+ ሞገሱንም ያሳይህ። +26 ይሖዋ ፊቱን ወደ አንተ ይመልስ፤ ሰላምም ይስጥህ።”’+ +27 እኔም እንድባርካቸው+ ስሜን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያድርጉ።”+ +25 እስራኤላውያን በሺቲም+ ይኖሩ በነበረበት ጊዜ ሕዝቡ ከሞዓብ ሴቶች ጋር የፆታ ብልግና መፈጸም ጀመረ።+ +2 ሴቶቹም ለአማልክታቸው ወደተሠዉት መሥዋዕቶች ሕዝቡን ጠሩ፤+ ሕዝቡም ከመሥዋዕቱ መብላት እንዲሁም ለእነሱ አማልክት መስገድ ጀመረ።+ +3 ስለዚህ እስራኤል የፌጎርን ባአል በማምለክ ተባበረ፤*+ ይሖዋም በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ። +4 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እየነደደ ያለው የይሖዋ ቁጣ ከእስራኤል ላይ እንዲመለስ የዚህን ሕዝብ መሪዎች* ሁሉ ወስደህ በጠራራ ፀሐይ* በይሖዋ ፊት ስቀላቸው።” +5 ከዚያም ሙሴ የእስራኤልን ዳኞች+ “እያንዳንዳችሁ በፌጎር ባአል አምልኮ የተባበረውን* የየራሳችሁን ሰው ግደሉ” አላቸው።+ +6 ሆኖም ልክ በዚህ ጊዜ አንድ እስራኤላዊ፣ ሙሴና በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ እያለቀሰ ያለው የእስራኤል ማኅበረሰብ በሙሉ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት+ ይዞ ወደ ወንድሞቹ መጣ። +7 የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ+ ይህን ሲመለከት ከማኅበረሰቡ መሃል ወዲያው ብድግ ብሎ ጦር አነሳ። +8 ከዚያም እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ በመግባት ሁለቱንም ወጋቸው፤ እስራኤላዊውን ወጋው፤ እሷንም ሆዷ* ላይ ወጋት። በዚህ ጊዜ መቅሰፍቱ ከእስራኤል ልጆች ላይ ተወገደ።+ +"9 በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች 24,000 ነበሩ።+ " +10 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +11 “የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ+ በመካከላቸው እኔን የሚቀናቀነኝን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ ቁጣዬ ከእስራኤል ሕዝብ ላይ እንዲመለስ አድርጓል።+ ስለዚህ እስራኤላውያንን እኔን ብቻ ለምን አላመለካችሁም ብዬ ጠራርጌ አላጠፋኋቸውም።+ +12 በዚህም የተነሳ ከእሱ ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እንደምገባ ንገረው። +13 ይህም አምላኩን የሚቀናቀነውን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ+ እንዲሁም ለእስራኤል ሕዝብ በማስተሰረዩ ለእሱና ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ+ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ሆኖ ያገለግላል።” +14 ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው ሟቹ እስራኤላዊ የስምዖናውያን አባቶች ቤት አለቃ የሆነው የሳሉ ልጅ ዚምሪ ነበር። +15 የተገደለችውም ምድያማዊት ሴት የጹር+ ልጅ ኮዝቢ ነበረች፤ ጹር በምድያም ካሉት የአባቶች ቤት ጎሳዎች የአንዱ መሪ ነበር።+ +16 በኋላም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +17 “ምድያማውያንን አንገላቷቸው፤ እንዲሁም ፍጇቸው፤+ +18 ምክንያቱም እነሱ ከፌጎርና+ ከእህታቸው ከኮዝቢ ጋር በተያያዘ በፈጸሙባችሁ ተንኮል የተነሳ አንገላተዋችኋል፤ ኮዝቢ ከፌጎር ጋር በተያያዘ የተከሰተው መቅሰፍት በመጣበት ዕለት+ የተገደለች የምድያማዊው አለቃ ልጅ ነች።”+ +33 የእስራኤል ሕዝብ በሙሴና በአሮን መሪነት+ በየምድቡ*+ በመሆን ከግብፅ ምድር በወጣ ጊዜ+ የተጓዘው በዚህ መልክ ነበር። +2 ሙሴም በጉዟቸው ላይ ሳሉ ያረፉባቸውን ቦታዎች ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይመዘግብ ነበር፤ ከአንዱ ስፍራ ተነስተው ወደ ሌላው የተጓዙት በሚከተለው ሁኔታ ነበር፦+ +3 በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ15ኛው ቀን+ ከራምሴስ ተነሱ።+ ልክ በፋሲካ በዓል+ ማግስት እስራኤላውያን ግብፃውያን ሁሉ እያዩአቸው በልበ ሙሉነት* ወጡ። +4 በዚህ ጊዜ ግብፃውያን ይሖዋ በመቅሰፍት የመታቸውን በኩሮቻቸውን ሁሉ እየቀበሩ ነበር፤+ ምክንያቱም ይሖዋ በአማልክታቸው ላይ የቅጣት እርምጃ ወስዶ ነበር።+ +5 በመሆኑም እስራኤላውያን ከራምሴስ ተነስተው በሱኮት+ ሰፈሩ። +6 ከዚያም ከሱኮት ተነስተው በምድረ በዳው ዳርቻ ላይ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ።+ +7 በመቀጠልም ከኤታም ተነስተው በበዓልጸፎን+ ትይዩ ወደምትገኘው ወደ ፊሃሂሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም+ ፊት ለፊት ሰፈሩ። +8 ከዚያም ከፊሃሂሮት ተነስተው ባሕሩን በማቋረጥ+ ወደ ምድረ በዳው+ ሄዱ፤ በኤታም ምድረ በዳ+ የሦስት ቀን መንገድ ከተጓዙ በኋላ በማራ+ ሰፈሩ። +9 ከዚያም ከማራ ተነስተው ወደ ኤሊም መጡ። በኤሊም 12 የውኃ ምንጮችና 70 የዘንባባ ዛፎች ነበሩ፤ በመሆኑም በዚያ ሰፈሩ።+ +10 በመቀጠል ደግሞ ከኤሊም ተነስተው በቀይ ባሕር አጠገብ ሰፈሩ። +11 ከዚያ በኋላ ከቀይ ባሕር ተነስተው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ።+ +12 ከሲን ምድረ በዳ ተነስተው ደግሞ በዶፍቃ ሰፈሩ። +13 በኋላም ከዶፍቃ ተነስተው በአሉሽ ሰፈሩ። +14 በመቀጠልም ከአሉሽ ተነስተው በረፊዲም+ ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጣው ውኃ አልነበረም። +15 ከዚያ በኋላ ከረፊዲም ተነስተው በሲ��� ምድረ በዳ ሰፈሩ።+ +16 ከሲና ምድረ በዳም ተነስተው በቂብሮትሃታባ+ ሰፈሩ። +17 ከዚያም ከቂብሮትሃታባ ተነስተው በሃጼሮት+ ሰፈሩ። +18 በኋላም ከሃጼሮት ተነስተው በሪትማ ሰፈሩ። +19 በመቀጠል ደግሞ ከሪትማ ተነስተው በሪሞንጰሬጽ ሰፈሩ። +20 ከዚያም ከሪሞንጰሬጽ ተነስተው በሊብና ሰፈሩ። +21 ከሊብናም ተነስተው በሪሳ ሰፈሩ። +22 በመቀጠልም ከሪሳ ተነስተው በቀሄላታ ሰፈሩ። +23 ከዚያም ከቀሄላታ ተነስተው በሸፈር ተራራ ሰፈሩ። +24 በኋላም ከሸፈር ተራራ ተነስተው በሃራዳ ሰፈሩ። +25 ከዚያም ከሃራዳ ተነስተው በማቅሄሎት ሰፈሩ። +26 ቀጥሎም ከማቅሄሎት ተነስተው+ በታሃት ሰፈሩ። +27 ከዚያ በኋላም ከታሃት ተነስተው በታራ ሰፈሩ። +28 ከዚያም ከታራ ተነስተው በሚትቃ ሰፈሩ። +29 በኋላም ከሚትቃ ተነስተው በሃሽሞና ሰፈሩ። +30 ከሃሽሞናም ተነስተው በሞሴሮት ሰፈሩ። +31 ከዚያም ከሞሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን+ ሰፈሩ። +32 በኋላም ከብኔያዕቃን ተነስተው በሆርሃጊድጋድ ሰፈሩ። +33 ከዚያም ከሆርሃጊድጋድ ተነስተው በዮጥባታ+ ሰፈሩ። +34 ከዮጥባታም ተነስተው በአብሮና ሰፈሩ። +35 ከዚያም ከአብሮና ተነስተው በዔጽዮንጋብር+ ሰፈሩ። +36 በኋላም ከዔጽዮንጋብር ተነስተው በጺን ምድረ በዳ+ በምትገኘው በቃዴስ ሰፈሩ። +37 ከቃዴስም ተነስተው በኤዶም ምድር ወሰን ላይ በሚገኘው በሆር ተራራ+ ሰፈሩ። +38 እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡ በ40ኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ካህኑ አሮን ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ወደ ሆር ተራራ ወጣ፤ በዚያም ሞተ።+ +39 አሮን በሆር ተራራ ላይ በሞተበት ጊዜ ዕድሜው 123 ዓመት ነበር። +40 በከነአን ምድር በኔጌብ ይኖር የነበረው ከነአናዊው የአራድ ንጉሥ+ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ። +41 ከጊዜ በኋላም ከሆር ተራራ+ ተነስተው በጻልሞና ሰፈሩ። +42 ከዚያም ከጻልሞና ተነስተው በጱኖን ሰፈሩ። +43 በመቀጠልም ከጱኖን ተነስተው በኦቦት+ ሰፈሩ። +44 ከኦቦትም ተነስተው በሞዓብ ድንበር+ ላይ በምትገኘው በኢዬዓባሪም ሰፈሩ። +45 በኋላም ከኢይም ተነስተው በዲቦንጋድ+ ሰፈሩ። +46 በመቀጠልም ከዲቦንጋድ ተነስተው በአልሞንዲብላታይም ሰፈሩ። +47 ከአልሞንዲብላታይም ተነስተው ደግሞ በነቦ+ ፊት ለፊት በአባሪም+ ተራሮች ሰፈሩ። +48 በመጨረሻም ከአባሪም ተራሮች ተነስተው በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ሰፈሩ።+ +49 በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሺቲም+ በሚገኘው ስፍራ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ሰፈሩ። +50 ይሖዋ በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +51 “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እንግዲህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደ ከነአን ምድር ልትገቡ ነው።+ +52 የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አባሯቸው፤ የተቀረጹ የድንጋይ ምስሎቻቸውንም+ ሁሉ አጥፉ፤ ከብረት የተሠሩ ሐውልቶቻቸውንም*+ በሙሉ አስወግዱ፤ በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉ ቅዱስ ስፍራዎቻቸውን+ ሁሉ አፍርሱ። +53 ምድሪቱን ርስት አድርጌ ስለምሰጣችሁ ምድሪቱን ወርሳችሁ በዚያ ትኖራላችሁ።+ +54 ምድሪቱንም በየቤተሰባችሁ ውርስ አድርጋችሁ በዕጣ+ ተከፋፈሉ። ተለቅ ላለው ቡድን በዛ ያለውን፣ አነስ ላለው ቡድን ደግሞ አነስ ያለውን ውርስ አድርጋችሁ ስጡት።+ ሁሉም በወጣለት ዕጣ መሠረት የተሰጠውን ቦታ ይወርሳል። በየአባቶቻችሁ ነገዶች ርስታችሁን ውርስ አድርጋችሁ ትቀበላላችሁ።+ +55 “‘የምድሪቱን ነዋሪዎች ከፊታችሁ ሳታባርሩ እዚያው ከተዋችኋቸው+ ግን ዓይናችሁ ውስጥ እንደገባ ጉድፍ እንዲሁም ጎናችሁ ላይ እንደተሰካ እሾህ ይሆኑባችኋል፤ ደግሞ�� በምትኖሩበት ምድር ያንገላቷችኋል።+ +56 እኔም በእነሱ ላይ ለማድረግ ያሰብኩትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።’”+ +10 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ሁለት መለከቶችን+ ለራስህ ሥራ፤ ወጥ ከሆነ ብር ጠፍጥፈህ ሥራቸው፤ መለከቶቹንም ማኅበረሰቡን ለመሰብሰብና ሕዝቡ ከሰፈረባቸው ቦታዎች ተነስቶ እንዲሄድ ምልክት ለመስጠት ተጠቀምባቸው። +3 ሁለቱም መለከቶች ሲነፉ መላው ማኅበረሰብ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ወደ አንተ ይሰብሰብ።+ +4 አንዱ መለከት ብቻ ከተነፋ ግን የእስራኤል የሺህ አለቆች ብቻ ወደ አንተ ይሰብሰቡ።+ +5 “ድምፁን እያለዋወጣችሁ መለከቱን ስትነፉ በስተ ምሥራቅ+ የሰፈሩት ተነስተው ይጓዙ። +6 ለሁለተኛ ጊዜ ድምፁን እያለዋወጣችሁ መለከቱን ስትነፉ በስተ ደቡብ+ የሰፈሩት ተነስተው ይጓዙ። ከመካከላቸው አንዱ ምድብ ተነስቶ በተጓዘ ቁጥር መለከቱን በዚህ መንገድ ይንፉ። +7 “ጉባኤውን አንድ ላይ በምትሰበስቡበት ጊዜ መለከቶቹን መንፋት+ ይኖርባችኋል፤ በዚህ ጊዜ ግን ድምፁን እያለዋወጣችሁ መንፋት የለባችሁም። +8 ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች መለከቶቹን ይንፉ፤+ መለከቶቹን በዚህ መንገድ መጠቀም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል። +9 “ግፍ ከሚፈጽምባችሁ ጨቋኝ ጠላት ጋር በምድራችሁ ጦርነት ብትገጥሙ በመለከቶቹ አማካኝነት የክተት ጥሪ አሰሙ፤+ አምላካችሁ ይሖዋም ያስባችኋል፤ ከጠላቶቻችሁም ያድናችኋል። +10 “እንዲሁም በደስታችሁ ወቅት+ ይኸውም በበዓላት ወቅቶችና+ የወር መባቻን ስታከብሩ በሚቃጠሉ መባዎቻችሁ+ እንዲሁም በኅብረት መሥዋዕቶቻችሁ+ ላይ መለከቶቹን ንፉ፤ እነሱም በአምላካችሁ ፊት ለእናንተ እንደ መታሰቢያ ሆነው ያገለግላሉ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።”+ +11 በሁለተኛው ዓመት ሁለተኛ ወር፣ ከወሩም በ20ኛው ቀን+ ደመናው ከምሥክሩ የማደሪያ ድንኳን ላይ ተነሳ።+ +12 እስራኤላውያንም በወጣላቸው የጉዞ ቅደም ተከተል መሠረት ከሲና ምድረ በዳ ተነስተው መጓዝ ጀመሩ፤+ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ+ ቆመ። +13 ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ተነስተው ሲጓዙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር።+ +14 ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የይሁዳ ልጆች ምድብ በየምድቡ* በመሆን በመጀመሪያ ተነስቶ ተጓዘ፤ የምድቡም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን+ ነበር። +15 የይሳኮር ልጆች ነገድ ምድብ አለቃም የጹአር ልጅ ናትናኤል+ ነበር። +16 የዛብሎን ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የሄሎን ልጅ ኤልያብ+ ነበር። +17 የማደሪያ ድንኳኑ በተነቀለም ጊዜ+ የማደሪያ ድንኳኑን የሚሸከሙት የጌድሶን ወንዶች ልጆችና+ የሜራሪ ወንዶች ልጆች+ ተነስተው ተጓዙ። +18 ከዚያም ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የሮቤል ምድብ በየምድቡ* በመሆን ተነስቶ ተጓዘ፤ የምድቡም አለቃ የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር+ ነበር። +19 የስምዖን ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል+ ነበር። +20 የጋድ ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የደኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ+ ነበር። +21 ከዚያም የመቅደሱን ዕቃዎች የሚሸከሙት ቀአታውያን+ ተነስተው ተጓዙ። እነሱ በሚደርሱበት ጊዜ የማደሪያ ድንኳኑ ተተክሎ ይቆያል። +22 ቀጥሎም ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የኤፍሬም ምድብ በየምድቡ* በመሆን ተነስቶ ተጓዘ፤ የምድቡም አለቃ የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ+ ነበር። +23 የምናሴ ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የፐዳጹር ልጅ ገማልያል+ ነበር። +24 የቢንያም ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን+ ነበር። +25 ከዚያም ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የዳን ልጆች ምድብ ለሁሉም ምድቦች የኋላ ደጀን በመሆን በየምድቡ* ተነስቶ ተጓዘ፤ የሠራዊቱም አለቃ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ ነበር። +26 የአሴር ል��ች ነገድ ምድብ አለቃ የኦክራን ልጅ ፓጊኤል+ ነበር። +27 የንፍታሌም ልጆች ነገድ ምድብ አለቃ የኤናን ልጅ አሂራ+ ነበር። +28 እስራኤላውያን በየምድባቸው* በመሆን ተነስተው የሚጓዙበት የጉዞ ቅደም ተከተል ይህ ነበር።+ +29 ከዚያም ሙሴ የአማቱን የምድያማዊውን የረኡዔልን*+ ልጅ ሆባብን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኛ ይሖዋ ‘ለእናንተ እሰጣችኋለሁ’+ ወዳለን ምድር ተነስተን መጓዛችን ነው። አንተም ከእኛ ጋር ና፤+ ይሖዋ ለእስራኤል መልካም ነገር ለማድረግ ቃል ስለገባ+ እኛም መልካም ነገር እናደርግልሃለን።” +30 እሱ ግን “አብሬያችሁ አልሄድም። እኔ ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እመለሳለሁ” አለው። +31 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “በምድረ በዳው የት መስፈር እንዳለብን ስለምታውቅ እባክህ ትተኸን አትሂድ፤ መንገድም ልትመራን* ትችላለህ። +32 ከእኛ ጋር የምትሄድ ከሆነ+ ይሖዋ የሚያደርግልንን መልካም ነገር ሁሉ እኛም በእርግጥ ለአንተ እናደርግልሃለን።” +33 በመሆኑም የሦስት ቀን መንገድ ለመጓዝ ከይሖዋ ተራራ+ ተነስተው ጉዞ ጀመሩ፤ የሦስት ቀኑን ጉዞ በሚጓዙበት ጊዜም የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት+ ለእነሱ የማረፊያ ቦታ ለመፈለግ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር።+ +34 ከሰፈሩበት ቦታ በሚነሱበት ጊዜ የይሖዋ ደመና+ ቀን ቀን በላያቸው ይሆን ነበር። +35 ታቦቱ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሁሉ ሙሴ “ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ፤+ ጠላቶችህ ይበታተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር። +36 ታቦቱ በሚያርፍበትም ጊዜ “ይሖዋ ሆይ፣ በሺዎች ወደሚቆጠሩት ስፍር ቁጥር የሌላቸው እስራኤላውያን*+ ተመለስ” ይል ነበር። +14 ከዚያም ማኅበረሰቡ ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ሕዝቡም ሌሊቱን ሙሉ ሲጮኽና ሲያለቅስ አደረ።+ +2 እስራኤላውያንም በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ ያጉረመርሙ ጀመር፤+ መላው ማኅበረሰብ እንዲህ አላቸው፦ “ምነው በግብፅ ምድር ሳለን ሞተን ባረፍነው፤ ወይም ምናለ በዚህ ምድረ በዳ በሞትን! +3 ይሖዋ በሰይፍ እንድንሞት ወደዚህ ምድር ያመጣን ለምንድን ነው?+ እንግዲህ ሚስቶቻችንና ልጆቻችን ይማረካሉ።+ ታዲያ ወደ ግብፅ ብንመለስ አይሻለንም?”+ +4 እንዲያውም እርስ በርሳቸው “መሪ እንሹምና ወደ ግብፅ እንመለስ” ይባባሉ ጀመር።+ +5 በዚህ ጊዜ ሙሴና አሮን በተሰበሰበው በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ። +6 ምድሩን ከሰለሉት ሰዎች መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና+ የየፎኒ ልጅ ካሌብ+ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ +7 ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብም እንዲህ አሉ፦ “ተዘዋውረን የሰለልናት ምድር እጅግ በጣም ጥሩ ምድር ናት።+ +8 ይሖዋ በእኛ ከተደሰተ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ወደዚህች ምድር+ በእርግጥ ያስገባናል፤ ደግሞም ይህችን ምድር ይሰጠናል። +9 ብቻ እናንተ በይሖዋ ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ስለምንጎርሳቸው የምድሪቱን ሕዝቦች አትፍሯቸው።+ ጥላቸው ተገፏል፤ ደግሞም ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው።+ ፈጽሞ አትፍሯቸው።” +10 ይሁን እንጂ መላው ማኅበረሰብ በድንጋይ ሊወግራቸው ተማከረ።+ ሆኖም የይሖዋ ክብር በመገናኛ ድንኳኑ ላይ ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ተገለጠ።+ +11 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ የሚንቀኝ እስከ መቼ ነው?+ በመካከላቸው ይህን ሁሉ ተአምራዊ ምልክት እያሳየሁ የማያምኑብኝስ እስከ መቼ ነው?+ +12 እንግዲህ በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ ደግሞም እደመስሳቸዋለሁ፤ አንተን ግን ከእነሱ ይልቅ ታላቅና ኃያል ብሔር አደርግሃለሁ።”+ +13 ሙሴ ግን ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “እንዲህ ካደረግክ ይህን ሕዝብ በኃይልህ ከመካከላቸው ስታወጣ ያዩ ግብፃውያን መስማታቸው አይቀርም፤+ +14 እነሱ ደግሞ የሰሙትን ነገር ለዚህ ምድር ነዋሪዎች ይናገራሉ። እነሱም ቢሆኑ አንተ ይሖዋ በዚህ ሕዝብ መካከል እንዳለህና+ ፊት ለፊት+ እንደተገለጥክላቸው ሰምተዋል። አንተ ይሖዋ ነህ፤ ደመናህም በላያቸው ላይ ቆሟል፤ ቀን ቀን በደመና ዓምድ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ በእሳት ዓምድ ከፊት ከፊታቸው ትሄዳለህ።+ +15 እንግዲህ ይህን ሕዝብ በሙሉ በአንዴ ብትፈጀው* የአንተን ዝና የሰሙ ብሔራት እንዲህ ማለታቸው አይቀርም፦ +16 ‘ይሖዋ ይህን ሕዝብ፣ ሊሰጠው ወደማለለት ምድር ሊያስገባው ስላልቻለ በምድረ በዳ ፈጀው።’+ +17 አሁንም እባክህ ይሖዋ እንዲህ በማለት ቃል በገባኸው መሠረት ኃይልህ ታላቅ ይሁን፦ +18 ‘ይሖዋ ለቁጣ የዘገየ፣ ታማኝ ፍቅሩ* የበዛ፣+ ስህተትንና መተላለፍን ይቅር የሚል፣ በደለኛውን ግን በምንም ዓይነት ሳይቀጣ የማያልፍ እንዲሁም አባቶች ለሠሩት ስህተት በልጆች፣ በሦስተኛና በአራተኛ ትውልድ ላይ ቅጣትን የሚያመጣ ነው።’+ +19 ይህን ሕዝብ ከግብፅ አንስቶ እስካሁን ድረስ ይቅር ስትለው እንደቆየህ ሁሉ አሁንም እባክህ፣ የዚህን ሕዝብ ስህተት ታላቅ በሆነው ታማኝ ፍቅርህ ይቅር በል።”+ +20 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “ባልከኝ መሠረት ይቅር እላቸዋለሁ።+ +21 በሌላ በኩል ግን በሕያውነቴ እምላለሁ፣ መላዋ ምድር በይሖዋ ክብር ትሞላለች።+ +22 ይሁን እንጂ ክብሬንና በግብፅም ሆነ በምድረ በዳ የፈጸምኳቸውን ተአምራዊ ምልክቶች+ የተመለከቱት ሆኖም አሥር ጊዜ የተፈታተኑኝና+ ቃሌን ያልሰሙት+ ሰዎች አንዳቸውም ቢሆኑ +23 ለአባቶቻቸው የማልኩላቸውን ምድር ፈጽሞ አያዩም። አዎ፣ የናቁኝ ሰዎች አንዳቸውም ቢሆኑ ያን ምድር አያዩም።+ +24 አገልጋዬ ካሌብ+ ግን የተለየ መንፈስ እንዳለው ስላሳየና በሙሉ ልቡ ስለተከተለኝ ሄዶባት ወደነበረው ምድር በእርግጥ አስገባዋለሁ፤ ዘሮቹም ያቺን ምድር ይወርሳሉ።+ +25 አማሌቃውያንና ከነአናውያን+ በሸለቆው ውስጥ* ስለሚኖሩ በነገው ዕለት ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳው ሂዱ።”+ +26 ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ +27 “ይህ ክፉ ማኅበረሰብ በእኔ ላይ እንዲህ የሚያጉረመርመው እስከ መቼ ነው?+ እስራኤላውያን በእኔ ላይ የሚያጉረመርሙትን ሰምቻለሁ።+ +28 እንዲህ በሏቸው፦ ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “እናንተው ራሳችሁ ስትናገሩ የሰማሁትን ነገር አደርግባችኋለሁ!+ +29 ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗችሁ የተመዘገባችሁትና የተቆጠራችሁት ሁሉ አዎ፣ በእኔ ላይ ያጉረመረማችሁት+ ሁሉ ሬሳችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል።+ +30 ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር+ አንዳችሁም ብትሆኑ በዚያ እንደማኖራችሁ ወደማልኩላችሁ* ምድር አትገቡም።+ +31 “‘“ለምርኮ ይዳረጋሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን+ ግን አስገባቸዋለሁ፤ እናንተ የናቃችኋትንም ምድር+ በሚገባ ያውቋታል። +32 የእናንተ ሬሳ ግን በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል። +33 እንግዲህ ልጆቻችሁ በምድረ በዳ ለ40 ዓመት እረኞች ይሆናሉ፤+ እነሱም የእናንተ የመጨረሻው ሬሳ በምድረ በዳ እስኪወድቅ ድረስ+ እናንተ ለፈጸማችሁት ታማኝነት የጎደለው ድርጊት* መልስ ይሰጣሉ። +34 እኔን መቃወም* ምን ማለት እንደሆነ እንድታውቁ ምድሪቱን በሰለላችሁባቸው 40 ቀናት+ ልክ ይኸውም አንዱ ቀን እንደ አንድ ዓመት ተቆጥሮ፣ ለሠራችኋቸው ስህተቶች ለ40 ዓመት+ መልስ ትሰጣላችሁ። +35 “‘“እኔ ይሖዋ ተናግሬአለሁ። በእኔ ላይ ተባብሮ በተነሳው በዚህ ክፉ ማኅበረሰብ ላይ በእርግጥ ይህን አደርጋለሁ፦ መጨረሻቸው በዚህ ምድረ በዳ ይሆናል፤ እዚሁም ይሞታሉ።+ +36 ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸውና ስለ ምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው በመምጣት መላው ማኅበረሰብ በእሱ ላይ እንዲያጉረመርም ያደረጉት ሰዎች+ +37 አዎ፣ ስለ ምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው የመጡት ሰዎች በይሖዋ ፊት ተቀስፈው ይሞታሉ።+ +38 ምድሪቱን ለመሰለል ከሄዱት ሰዎች መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የየፎኒ ልጅ ካሌብ ግን በሕይወት ይኖራሉ።”’”+ +39 ሙሴም ለእስራኤላውያን በሙሉ ይህን ሲነግራቸው ሕዝቡ እጅግ አዘነ። +40 ከዚያም በጠዋት ወደ ተራራው አናት ለመውጣት ተነሱ፤ እነሱም “ኃጢአት ስለሠራን ይሖዋ ወደተናገረለት ቦታ ለመውጣት ይኸው ዝግጁ ነን” አሉ።+ +41 ሙሴ ግን እንዲህ አለ፦ “የይሖዋን ትእዛዝ የምትጥሱት ለምንድን ነው? ይህ አይሳካላችሁም። +42 ይሖዋ ከእናንተ ጋር ስላልሆነ አትውጡ፤ በጠላቶቻችሁ ድል ትመታላችሁ።+ +43 ምክንያቱም አማሌቃውያንና ከነአናውያን በዚያ ይገጥሟችኋል፤+ እናንተም በሰይፍ ትወድቃላችሁ። ምክንያቱም ይሖዋን ከመከተል ዞር ስላላችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር አይሆንም።”+ +44 እነሱ ግን በትዕቢት ወደ ተራራው አናት ወጡ፤+ ሆኖም የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦትና ሙሴ ከሰፈሩ መካከል ንቅንቅ አላሉም።+ +45 ከዚያም በዚያ ተራራ የሚኖሩት አማሌቃውያንና ከነአናውያን ወርደው መቷቸው፤ እስከ ሆርማም ድረስ በታተኗቸው።+ +9 ከግብፅ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር+ ይሖዋ ሙሴን በሲና ምድረ በዳ እንዲህ በማለት አነጋገረው፦ +2 “እስራኤላውያን የፋሲካን* መሥዋዕት+ በተወሰነለት ጊዜ ያዘጋጁ።+ +3 በዚህ ወር በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ* በተወሰነለት ጊዜ አዘጋጁት። ደንቦቹን ሁሉና ሥርዓቱን ሁሉ ተከትላችሁ አዘጋጁት።”+ +4 በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያን የፋሲካን መሥዋዕት እንዲያዘጋጁ ነገራቸው። +5 እነሱም በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ* የፋሲካን መሥዋዕት በሲና ምድረ በዳ አዘጋጁ። እስራኤላውያንም ሁሉንም ነገር ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ። +6 የሞተ ሰው ነክተው* በመርከሳቸው+ የተነሳ በዚያ ቀን የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት ያልቻሉ ሰዎች ነበሩ። በመሆኑም እነዚህ ሰዎች በዚያ ቀን ሙሴና አሮን ፊት ቀረቡ፤+ +7 እንዲህም አሉት፦ “እኛ የሞተ ሰው በመንካታችን* የተነሳ ረክሰናል። ይሁንና ከእስራኤላውያን ጋር መባውን በተወሰነለት ጊዜ ለይሖዋ እንዳናቀርብ የምንከለከለው ለምንድን ነው?”+ +8 በዚህ ጊዜ ሙሴ “ይሖዋ እናንተን በተመለከተ የሚሰጠውን ትእዛዝ እስክሰማ ድረስ እዚያ ጠብቁ”+ አላቸው። +9 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +10 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእናንተ ወይም ከመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ መካከል ማንኛውም ሰው የሞተ ሰው በመንካቱ* ቢረክስ+ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ ለይሖዋ የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት ይጠበቅበታል። +11 እነሱም በሁለተኛው ወር+ በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ* ያዘጋጁት። ይህንም ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት።+ +12 ከእሱም ላይ እስከ ጠዋት ድረስ ምንም ማስተረፍ+ ወይም ከአጥንቱ ውስጥ አንዱንም መስበር+ የለባቸውም። ፋሲካን በተመለከተ የወጣውን ደንብ ሁሉ ተከትለው ያዘጋጁት። +13 ይሁንና አንድ ሰው ንጹሕ ሆኖ ሳለ ወይም ሩቅ መንገድ ሳይሄድ በቸልተኝነት የፋሲካን መሥዋዕት ሳያዘጋጅ ቢቀር፣ ያ ሰው* የይሖዋን መባ በተወሰነለት ጊዜ ስላላቀረበ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ።+ ይህ ሰው ለሠራው ኃጢአት ይጠየቅበታል። +14 “‘በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለ እሱም ለይሖዋ የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት አለበት።+ ይህን በፋሲካው ደንብና በወጣለት ሥርዓት መሠረት ማድረግ አለበት።+ ለሁላችሁም ማለትም ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ አንድ ዓይነት ደንብ ይኑር።’”+ +15 የማደሪያ ድንኳኑ በተተከለበት ቀን+ ደመናው የማደሪያ ድንኳኑን ይኸውም የምሥክሩ��� ድንኳን ሸፈነው፤ ሆኖም ከምሽት ጀምሮ እስከ ጠዋት ድረስ በማደሪያ ድንኳኑ ላይ እሳት የሚመስል ነገር ታየ።+ +16 ሁልጊዜም እንዲህ ይሆን ነበር፦ ቀን ቀን ደመናው ድንኳኑን ይሸፍነው ነበር፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ እሳት የሚመስል ነገር ይታይ ነበር።+ +17 ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሳበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ወዲያውኑ ተነስተው ይጓዙ ነበር፤+ ደመናው በሚቆምበት ቦታ ደግሞ እስራኤላውያን ይሰፍሩ ነበር።+ +18 እስራኤላውያን ተነስተው የሚጓዙት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር፤ የሚሰፍሩትም በይሖዋ ትእዛዝ ነበር።+ ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ በሚቆይባቸው ቀናት ሁሉ እነሱም በሰፈሩበት ቦታ ይቆዩ ነበር። +19 ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ረዘም ላሉ ቀናት በሚቆይበትም ጊዜ እስራኤላውያን ይሖዋን በመታዘዝ ባሉበት ይቆዩ ነበር።+ +20 አንዳንድ ጊዜ ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ የሚቆየው ለጥቂት ቀናት ነበር። እነሱም የሚሰፍሩት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር፤ ተነስተው የሚጓዙትም በይሖዋ ትእዛዝ ነበር። +21 አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደመናው የሚቆየው ከምሽት እስከ ጠዋት ድረስ ብቻ ነበር፤ ጠዋት ላይ ደመናው ሲነሳ እነሱም ተነስተው ይጓዛሉ። ቀንም ሆነ ሌሊት ደመናው በሚነሳበት ጊዜ እነሱም ተነስተው ይጓዛሉ።+ +22 እስራኤላውያን ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ እስካለ ድረስ ለሁለት ቀንም ይሁን ለአንድ ወር ወይም ረዘም ላለ ጊዜ በሰፈሩበት ይቆያሉ እንጂ ተነስተው አይጓዙም። ደመናው በሚነሳበት ጊዜ ግን ተነስተው ይጓዛሉ። +23 እነሱም የሚሰፍሩት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር፤ ተነስተውም የሚጓዙት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር። ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይሖዋ የጣለባቸውን ግዴታ ይወጡ ነበር። +27 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ቤተሰቦች የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የሄፌር ልጅ የሆነው የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች+ ቀረቡ። የሴት ልጆቹም ስም ማህላ፣ ኖኅ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበር። +2 እነሱም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በአለቆቹ+ እንዲሁም በመላው ማኅበረሰብ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦ +3 “አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ይሁንና እሱ በይሖዋ ላይ ለማመፅ ከተባበሩት ከቆሬ ግብረ አበሮች+ አንዱ አልነበረም፤ እሱ የሞተው በራሱ ኃጢአት ነው፤ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም። +4 ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ስለሌለው ብቻ ስሙ ከቤተሰቡ መካከል ለምን ይጥፋ? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስት ስጡን።” +5 ስለዚህ ሙሴ ጉዳያቸውን በይሖዋ ፊት አቀረበ።+ +6 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +7 “የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ትክክል ናቸው። በአባታቸው ወንድሞች መካከል ርስታቸውን ውርስ አድርገህ ልትሰጣቸው ይገባል፤ የአባታቸውም ውርስ ለእነሱ እንዲተላለፍ ማድረግ አለብህ።+ +8 እስራኤላውያንንም እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ውርሱ ለሴት ልጆቹ እንዲተላለፍ ማድረግ አለባችሁ። +9 ሴት ልጅ ከሌለው ደግሞ ውርሱን ለወንድሞቹ ትሰጣላችሁ። +10 ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ለአባቱ ወንድሞች ትሰጣላችሁ። +11 አባቱ ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ከቤተሰቡ መካከል ቅርብ ለሆነው የሥጋ ዘመዱ ትሰጣላችሁ፤ እሱም ርስት አድርጎ ይወስደዋል። ይህም ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን የተደነገገ ደንብ ሆኖ ያገለግላል።’” +12 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደዚህ ወደ አባሪም ተራራ+ ውጣና ለእስራኤላውያን የምሰጠውን ምድር ተመልከት።+ +13 ካየኸውም በኋላ እንደ ወንድምህ እንደ አሮን+ አንተም ወደ ወገኖችህ ትሰበሰባለህ፤*+ +14 ምክንያቱም ማኅበረሰቡ በጺን ምድረ በዳ ከእኔ ጋር በተጣላ ጊዜ ከውኃዎቹ ጋር በተያያዘ በ���ታቸው ሳትቀድሱኝ በመቅረታችሁ ትእዛዜን ተላልፋችኋል።+ እነዚህም በጺን ምድረ በዳ+ በቃዴስ+ የሚገኙት የመሪባ ውኃዎች+ ናቸው። +15 ከዚያም ሙሴ ይሖዋን እንዲህ አለው፦ +16 “የሰው* ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነው ይሖዋ በማኅበረሰቡ ላይ አንድ ሰው ይሹም፤ +17 እሱም የይሖዋ ማኅበረሰብ እረኛ እንደሌላቸው በጎች እንዳይሆን በፊታቸው የሚወጣና የሚገባ እንዲሁም እነሱን መርቶ የሚያወጣና የሚያስገባ ይሆናል።” +18 በመሆኑም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መንፈስ ያለበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት።+ +19 ከዚያም በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበረሰብ ፊት አቁመው፤ በፊታቸውም ሹመው።+ +20 መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ እንዲሰማውም+ ከሥልጣንህ* የተወሰነውን ስጠው።+ +21 እሱም በኡሪም+ አማካኝነት የይሖዋን ፍርድ በሚጠይቅለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል። እሱም ሆነ ከእሱ ጋር ያሉት እስራኤላውያን እንዲሁም መላው ማኅበረሰብ በእሱ ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በእሱ ትእዛዝ ይገባሉ።” +22 በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ። ኢያሱንም ወስዶ በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበረሰብ ፊት አቆመው፤ +23 ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በተናገረውም መሠረት+ እጆቹን በእሱ ላይ በመጫን ሾመው።+ +13 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነአንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎችን ላክ። ከእያንዳንዱ የአባቶች ነገድ አንድ አንድ ሰው ይኸውም ከመካከላቸው አለቃ+ የሆነውን ሰው ትልካለህ።”+ +3 በመሆኑም ሙሴ ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ከፋራን ምድረ በዳ+ ላካቸው። ሰዎቹ በሙሉ የእስራኤላውያን መሪዎች ነበሩ። +4 ስማቸውም የሚከተለው ነው፦ ከሮቤል ነገድ የዛኩር ልጅ ሻሙአ፣ +5 ከስምዖን ነገድ የሆሪ ልጅ ሻፋጥ፣ +6 ከይሁዳ ነገድ የየፎኒ ልጅ ካሌብ፣+ +7 ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ይግዓል፣ +8 ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ ሆሺአ፣+ +9 ከቢንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፓልጢ፣ +10 ከዛብሎን ነገድ የሶዲ ልጅ ጋዲኤል፣ +11 ከዮሴፍ+ ነገድ መካከል ለምናሴ+ ነገድ የሱሲ ልጅ ጋዲ፣ +12 ከዳን ነገድ የገማሊ ልጅ አሚዔል፣ +13 ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፣ +14 ከንፍታሌም ነገድ የዎፍሲ ልጅ ናህቢ +15 እንዲሁም ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጌኡዔል። +16 ሙሴ ምድሪቱን እንዲሰልሉ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴም ለነዌ ልጅ ለሆሺአ፣ ኢያሱ*+ የሚል ስም አወጣለት። +17 ሙሴ የከነአንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎቹን ሲልካቸው እንዲህ አላቸው፦ “በዚህ አድርጋችሁ ወደ ኔጌብ አቅኑ፤ ከዚያም ወደ ተራራማው አካባቢ ሂዱ።+ +18 ምድሪቱ ምን እንደምትመስል፣+ ነዋሪዎቿም ብርቱ ወይም ደካማ፣ ጥቂት ወይም ብዙ መሆናቸውን እዩ፤ +19 እንዲሁም ምድሪቱ መልካም ወይም መጥፎ መሆኗን ከተሞቹም በግንብ የታጠሩ ወይም ያልታጠሩ መሆናቸውን ተመልከቱ። +20 ምድሪቱም ለም* ወይም ደረቅ* መሆኗን፣+ በዚያም ዛፎች መኖር አለመኖራቸውን አጣሩ። እንዲሁም በድፍረት+ ከምድሪቱ ፍሬ ጥቂት ይዛችሁ ኑ።” ደግሞም ጊዜው የመጀመሪያው የወይን ፍሬ የሚደርስበት ወቅት ነበር።+ +21 ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው ምድሪቱን ከጺን ምድረ በዳ+ አንስተው በሌቦሃማት*+ አቅራቢያ እስከምትገኘው እስከ ሬሆብ+ ድረስ ሰለሉ። +22 በኔጌብ በኩል ሽቅብ ሲወጡም ኤናቃውያኑ+ አሂማን፣ ሸሻይ እና ታልማይ+ ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን+ ደረሱ። ኬብሮን የተቆረቆረችው በግብፅ ያለችው ጾዓን ከመቆርቆሯ ከሰባት ዓመት በፊት ነበር። +23 ወደ ኤሽኮል ሸለቆ*+ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላዎችን ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ከዚያ ቆረጡ፤ ከሰዎቹም መካከል ሁለቱ በዱላ ተሸከሙት፤ በተጨማሪም ጥቂት የሮማን ፍሬዎችንና የበለስ ፍሬዎችን ያዙ���+ +24 እስራኤላውያን ከዚያ በቆረጡት ዘለላ የተነሳ ያን ቦታ የኤሽኮል* ሸለቆ*+ ብለው ጠሩት። +25 ምድሪቱንም ሰልለው ከ40 ቀን+ በኋላ ተመለሱ። +26 በቃዴስ+ ባለው በፋራን ምድረ በዳ ወደሚገኙት ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ተመልሰው መጡ። ያዩትንም ሁሉ ለመላው ማኅበረሰብ ተናገሩ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው። +27 ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “ወደላክኸን ምድር ገብተን ነበር፤ በእርግጥም ምድሪቱ ወተትና ማር የምታፈስ ናት፤+ የምድሪቱም ፍሬ+ ይህን ይመስላል። +28 ይሁንና በምድሪቱ የሚኖሩት ሰዎች ብርቱዎች ናቸው፤ በግንብ የታጠሩት ከተሞችም ቢሆኑ በጣም ታላላቅ ናቸው። ደግሞም ኤናቃውያንን በዚያ አይተናል።+ +29 አማሌቃውያን+ በኔጌብ+ ምድር ይኖራሉ፤ ሂታውያን፣ ኢያቡሳውያንና+ አሞራውያን+ ደግሞ በተራራማው አካባቢ ይኖራሉ፤ በባሕሩ አካባቢና+ በዮርዳኖስ ዳርቻ ደግሞ ከነአናውያን+ ይኖራሉ።” +30 ከዚያም ካሌብ “በድፍረት እንውጣ፤ ድል እንደምናደርግ ምንም ጥርጥር ስለሌለው ምድሪቱን እንወርሳለን” በማለት በሙሴ ፊት የቆመውን ሕዝብ ሊያረጋጋ ሞከረ።+ +31 ከእሱ ጋር የወጡት ሰዎች ግን “ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለሆኑ ወጥተን ልንዋጋቸው አንችልም” አሉ።+ +32 እንዲሁም የሰለሏትን ምድር በተመለከተ ለእስራኤላውያን እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ+ አወሩ፦ “በውስጧ ተዘዋውረን የሰለልናት ምድር ነዋሪዎቿን የምትበላ ምድር ናት፤ እዚያ ያየናቸውም ሰዎች በሙሉ እጅግ ግዙፎች ናቸው።+ +33 በዚያም ኔፍሊሞችን ይኸውም የኔፍሊም ዝርያ የሆኑትን የኤናቅን ልጆች+ አይተናል፤ እኛ ከእነሱ ጋር ስንነጻጸር በእኛም ሆነ በእነሱ ዓይን ልክ እንደ ፌንጣ ነበርን።” +5 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን የሥጋ ደዌ ያለበትን፣+ ፈሳሽ የሚወጣውንና+ በሞተ ሰው* የረከሰን+ ማንኛውንም ሰው ከሰፈሩ እንዲያስወጡ እዘዛቸው። +3 ወንድም ሆነ ሴት አስወጧቸው። እኔ በመካከላቸው ስለምኖር*+ ሕዝቤ የሚኖርባቸውን ሰፈሮች እንዳይበክሉ+ ከሰፈሩ አስወጧቸው።” +4 በመሆኑም እስራኤላውያን እንደተባሉት አደረጉ፤ ሰዎቹንም ከሰፈሩ አስወጧቸው። እስራኤላውያን ልክ ይሖዋ ለሙሴ እንደነገረው አደረጉ። +5 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +6 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የሰው ልጆች ከሚፈጽሟቸው ኃጢአቶች ውስጥ የትኛውንም ቢሠሩና በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ቢፈጽሙ ይህን ያደረገው ሰው* በደለኛ ይሆናል።+ +7 እሱም* የሠራውን ኃጢአት መናዘዝና+ ለፈጸመው በደል ካሳ አድርጎ ሙሉ ዋጋውን መመለስ አለበት፤ የዚህን አንድ አምስተኛም ይጨምርበት፤+ በደል ለፈጸመበትም ሰው ይስጠው። +8 ሆኖም በደል የተፈጸመበት ሰው ቢሞትና ካሳውን የሚቀበልለት የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ካህኑ የግለሰቡን በደል ከሚያስተሰርይበት አውራ በግ በስተቀር ካሳው ለይሖዋ ይመለስ፤ የካህኑም ይሆናል።+ +9 “‘እስራኤላውያን ለካህኑ የሚያቀርቧቸው ቅዱስ መዋጮዎች+ በሙሉ የእሱ ይሆናሉ።+ +10 እያንዳንዱ ሰው የሚያቀርባቸው ቅዱስ የሆኑ ነገሮች የእሱ ይሆናሉ። እያንዳንዱ ሰው ለካህኑ የሚሰጠው ማንኛውም ነገር የካህኑ ይሆናል።’” +11 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ +12 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የአንድ ሰው ሚስት ከትክክለኛው መንገድ ዞር በማለት ለባሏ ታማኝ ሳትሆን ብትቀርና +13 ሌላ ወንድ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም፣+ ባሏ ግን ይህን ነገር ባያውቅና ጉዳዩ ተሰውሮ ቢቀር፣ ይህች ሴት በዚህ መንገድ ራሷን ብታረክስም የሚመሠክርባት ሰው ባይገኝና እጅ ከፍንጅ ባትያዝ፣ +14 ባሏም ሚስቱ ራሷን አርክሳ ሳለ የቅናት መንፈስ ቢያድርበትና የሚስቱን ታማኝነት ቢጠራጠር ወይም ደግሞ ራሷን ሳታረክስ የቅናት መንፈስ ቢያድርበትና ታማኝነቷን ቢጠራጠር +15 ሰውየው ሚስቱን ለእሷ ከሚቀርበው መባ ይኸውም ከአንድ አሥረኛ ኢፍ* የገብስ ዱቄት ጋር ወደ ካህኑ ያምጣ። ይህ የቅናት የእህል መባ ይኸውም በደል እንዲታወስ የሚያደርግ የእህል መባ ስለሆነ በላዩ ላይ ዘይት አያፍስበት ወይም ነጭ ዕጣን አያድርግበት። +16 “‘ካህኑ ሴትየዋን አምጥቶ ይሖዋ ፊት እንድትቆም ያደርጋል።+ +17 ከዚያም ካህኑ የተቀደሰ ውኃ በሸክላ ዕቃ ይወስዳል፤ ከማደሪያ ድንኳኑም ወለል ላይ ጥቂት አፈር ወስዶ ውኃው ውስጥ ይጨምረዋል። +18 ካህኑም ሴትየዋ በይሖዋ ፊት እንድትቆም ያደርጋል፤ ፀጉሯንም ይፈታል፤ ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል መባ ይኸውም የቅናት የእህል መባውን+ በእጆቿ ላይ ያደርጋል፤ ካህኑም እርግማን የሚያመጣውን መራራ ውኃ በእጁ ይይዛል።+ +19 “‘ካህኑም ሴትየዋን እንዲህ በማለት ያስምላታል፦ “በባልሽ ሥልጣን ሥር ሆነሽ ሳለ+ ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር የፆታ ግንኙነት ካልፈጸመ አንቺም ከትክክለኛው መንገድ ዞር ካላልሽና ካልረከስሽ እርግማን የሚያስከትለው ይህ ውኃ ምንም ጉዳት አያድርስብሽ። +20 ይሁንና በባልሽ ሥልጣን ሥር ሆነሽ ሳለ ራስሽን በማርከስ ከትክክለኛው መንገድ ዞር ብለሽ ከሆነና ከሌላ ወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመሽ+ ከሆነ . . . ” +21 ካህኑም ሴትየዋን እርግማን ያለበት መሐላ ያስምላታል፤ እንዲህም ይላታል፦ “ይሖዋ ጭንሽ* እንዲሰልና* ሆድሽ እንዲያብጥ በማድረግ፣ ይሖዋ በሕዝብሽ መካከል የእርግማንና የመሐላ ምሳሌ ያድርግሽ። +22 እርግማን የሚያመጣው ይህ ውኃ ወደ አንጀትሽ ገብቶ ሆድሽን ያሳብጠው፤ መሃንም ያድርግሽ።” በዚህ ጊዜ ሴትየዋ “አሜን! አሜን!”* ትበል። +23 “‘ከዚያም ካህኑ እነዚህን እርግማኖች በመጽሐፍ ይጻፋቸው፤ በመራራውም ውኃ አጥቦ ያጥፋቸው። +24 እርግማን የሚያመጣውን መራራ ውኃም እንድትጠጣ ያድርግ፤ ውኃውም ወደ ሰውነቷ ገብቶ መራራ ሥቃይ ያስከትልባት። +25 ካህኑም የቅናት የእህል መባውን+ ከሴትየዋ እጅ ላይ ወስዶ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዝውዘው፤ ወደ መሠዊያውም ያምጣው። +26 ካህኑም ከእህል መባው ላይ አንድ እፍኝ በመውሰድ የመባው መታሰቢያ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጭሰው፤+ ከዚያ በኋላ ሴትየዋ ውኃውን እንድትጠጣ ያድርግ። +27 ውኃውን እንድትጠጣ በሚያደርግበትም ጊዜ ሴትየዋ ራሷን አርክሳና በባሏ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጽማ ከሆነ እርግማን የሚያመጣው ውኃ ወደ ሰውነቷ ገብቶ መራራ ሥቃይ ያስከትልባታል፤ ሆዷም ያብጣል፤ ጭኗም* ይሰልላል፤* እሷም በሕዝቧ መካከል የእርግማን ምሳሌ ትሆናለች። +28 ይሁንና ሴትየዋ ራሷን ካላረከሰችና ንጹሕ ከሆነች እንዲህ ካለው ቅጣት ነፃ ትሆናለች፤ እንዲሁም መጸነስና ልጆች ማፍራት ትችላለች። +29 “‘እንግዲህ ቅናትን በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፤+ አንዲት ሴት በባሏ ሥልጣን ሥር ሆና ሳለ ከትክክለኛው መንገድ ዞር ብትልና ራሷን ብታረክስ +30 ወይም አንድ ሰው የቅናት መንፈስ ቢያድርበትና የሚስቱን ታማኝነት ቢጠራጠር ሕጉ ይህ ነው፤ እሱም ሚስቱ በይሖዋ ፊት እንድትቆም ያድርግ፤ ካህኑም ይህ ሕግ በሙሉ በእሷ ላይ እንዲፈጸም ያድርግ። +31 ሰውየው ከበደል ነፃ ይሆናል፤ ሚስቱ ግን ስለ በደሏ ትጠየቃለች።’” +21 በኔጌብ የሚኖረው ከነአናዊው የአራድ ንጉሥ+ እስራኤላውያን በአታሪም መንገድ እየመጡ መሆናቸውን በሰማ ጊዜ በእነሱ ላይ ጥቃት ሰነዘረ፤ ከመካከላቸውም የተወሰኑትን በምርኮ ወሰደ። +2 ስለዚህ እስራኤል “ይህን ሕዝብ በእጄ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ከሆነ ከተሞቻቸውን ጠራርጌ ���ጠፋለሁ” በማለት ለይሖዋ ስእለት ተሳለ። +3 በመሆኑም ይሖዋ የእስራኤልን ጩኸት ሰማ፤ ከነአናውያንንም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነሱም ሕዝቡንና ከተሞቻቸውን ጠራርገው አጠፉ። ስለሆነም የቦታውን ስም ሆርማ*+ አሉት። +4 እስራኤላውያን ከሆር ተራራ+ በመነሳት በኤዶም ምድር ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ የቀይ ባሕርን መንገድ ይዘው ተጓዙ፤+ ከጉዞውም የተነሳ ሕዝቡ* ዛለ። +5 ሕዝቡም እንዲህ በማለት በአምላክና በሙሴ ላይ ያማርር ጀመር፦+ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብፅ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ፣ ውኃ የለ፤+ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል።”*+ +6 በመሆኑም ይሖዋ በሕዝቡ ላይ መርዘኛ* እባቦችን ሰደደባቸው፤ እባቦቹም ሰዎቹን ስለነደፏቸው ብዙ እስራኤላውያን ሞቱ።+ +7 ስለሆነም ሕዝቡ ወደ ሙሴ መጥቶ “በይሖዋና በአንተ ላይ በማማረራችን ኃጢአት ሠርተናል።+ እባቦቹን ከመካከላችን እንዲያስወግድልን ይሖዋን ተማጸንልን” አለ። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ተማጸነ።+ +8 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመርዛማ* እባብ ምስል ሠርተህ እንጨት ላይ ስቀለው። ማንኛውም ሰው በሚነደፍበት ጊዜ በሕይወት እንዲኖር ምስሉን ማየት አለበት።” +9 ሙሴም ወዲያው የመዳብ እባብ+ ሠርቶ እንጨት ላይ ሰቀለው፤+ አንድ ሰው እባብ ሲነድፈው ከመዳብ ወደተሠራው እባብ ከተመለከተ ይድን ነበር።+ +10 ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ከነበሩበት ተነስተው በመጓዝ በኦቦት ሰፈሩ።+ +11 ከዚያም ከኦቦት ተነስተው በምሥራቅ አቅጣጫ በሞዓብ ፊት ለፊት በሚገኘው ምድረ በዳ በኢዬዓባሪም+ ሰፈሩ። +12 ከዚያ ተነስተው ደግሞ በዘረድ ሸለቆ*+ ሰፈሩ። +13 ከዘረድ ሸለቆ ተነስተው ከአሞራውያን ድንበር ጀምሮ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በሚገኘው በአርኖን ክልል+ ሰፈሩ፤ ምክንያቱም አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል የሚገኝ የሞዓብ ድንበር ነው። +14 የይሖዋ የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ በማለት የሚናገረው ለዚህ ነው፦ “በሱፋ የሚገኘው ዋሄብ፣ የአርኖን ሸለቆዎች* +15 እንዲሁም ኤር ወደሚገኝበት አቅጣጫ የሚዘረጋውና የሞዓብን ድንበር የሚያዋስነው የሸለቆዎች* ቁልቁለት።”* +16 ከዚያም ወደ በኤር ተጓዙ። ይሖዋ ሙሴን “ሕዝቡን ሰብስብ፤ እኔም ውኃ እሰጣቸዋለሁ” ያለው ይህን የውኃ ጉድጓድ አስመልክቶ ነው። +17 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ዘመሩ፦ “አንተ ጉድጓድ፣ ውኃ አፍልቅ! እናንተም መልሱለት!* +18 መኳንንት ለቆፈሩት፣ በሕዝቡ መካከል ያሉ ታላላቅ ሰዎች ለማሱት፣በገዢ ዘንግና በራሳቸው በትሮች ላዘጋጁት የውኃ ጉድጓድ ዘምሩለት።” ከዚያም ከምድረ በዳው ተነስተው ወደ ማታናህ ተጓዙ፤ +19 ከማታናህ ተነስተው ደግሞ ወደ ናሃሊኤል፣ ከናሃሊኤልም ተነስተው ወደ ባሞት+ ተጓዙ። +20 ከባሞትም ተነስተው የሺሞንን*+ ቁልቁል ማየት ወደሚቻልበት በጲስጋ+ አናት ላይ ወደሚገኘውና በሞዓብ ክልል*+ ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ። +21 እስራኤላውያን የአሞራውያን ንጉሥ ወደሆነው ወደ ሲሖን እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፦+ +22 “ምድርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን። ወደ የትኛውም እርሻ ወይም ወደ የትኛውም የወይን ቦታ አንገባም። ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ በንጉሡ መንገድ ቀጥ ብለን እንሄዳለን።”+ +23 ሲሖን ግን እስራኤላውያን ክልሉን አቋርጠው እንዲያልፉ አልፈቀደላቸውም። ከዚህ ይልቅ ሲሖን ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ሄደ፤ ያሃጽ በደረሰ ጊዜም ከእስራኤላውያን ጋር ውጊያ ገጠመ።+ +24 እስራኤላውያን ግን በሰይፍ ድል አደረጉት፤+ ምድሩንም ከአርኖን+ አንስቶ በአሞናውያን አቅራቢያ እስከሚገኘው እስከ ያቦቅ+ ድ��ስ ያዙ፤+ ሆኖም ያዜር+ የአሞናውያን ወሰን+ ስለሆነ ከዚያ አላለፉም። +25 በመሆኑም እስራኤላውያን እነዚህን ከተሞች ሁሉ ያዙ፤ ከዚያም በአሞራውያን+ ከተሞች ይኸውም በሃሽቦንና በሥሯ* ባሉት ከተሞች ሁሉ መኖር ጀመሩ። +26 ምክንያቱም ሃሽቦን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖን ከተማ ነበረች፤ እሱም ከሞዓብ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድር ከእጁ ወስዶበት ነበር። +27 እንዲህ የሚለውን ቅኔ በመቀኘት የተሳለቁበት በዚህ የተነሳ ነው፦ “ወደ ሃሽቦን ኑ። የሲሖን ከተማ ትገንባ፤ ጸንታም ትቁም። +28 እሳት ከሃሽቦን፣ ነበልባልም ከሲሖን ከተማ ወጥቷልና። የሞዓብን ኤር፣ የአርኖንን ኮረብቶች ጌቶች በላ። +29 ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! እናንተ የከሞሽ+ ሕዝቦች ሆይ፣ ድምጥማጣችሁ ይጠፋል። ወንዶች ልጆቹን ለስደት ይዳርጋል፤ ሴቶች ልጆቹንም ለአሞራውያን ንጉሥ ለሲሖን ምርኮኛ አድርጎ ይሰጣል። +30 በመሆኑም ጥቃት እንሰንዝርባቸው፤ሃሽቦን እስከ ዲቦን+ ድረስ ይደመሰሳል፤እስከ ኖፋ ድረስ እንደምስሰው፤እስከ መደባም+ ድረስ እሳት ይዛመታል።” +31 ስለዚህ እስራኤላውያን በአሞራውያን ምድር መኖር ጀመሩ። +32 ከዚያም ሙሴ ያዜርን እንዲሰልሉ የተወሰኑ ሰዎችን ላከ።+ እነሱም በሥሯ* ያሉትን ከተሞች ተቆጣጠሩ፤ በዚያ የነበሩትንም አሞራውያን አባረሩ። +33 ከዚህ በኋላ ተመልሰው በባሳን መንገድ ወጡ። የባሳን ንጉሥ ኦግም+ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በመሆን ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥማቸው ወጣ።+ +34 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እሱንም ሆነ ሕዝቡን ሁሉ እንዲሁም ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ አትፍራው፤+ አንተም በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግከው በእሱም ላይ ታደርግበታለህ።”+ +35 በመሆኑም ኦግን ከወንዶች ልጆቹና ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አንድም ሰው ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ፤+ ምድሩንም ወረሱ።+ +15 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እንድትኖሩባት ወደምሰጣችሁ ምድር በምትገቡበትና+ +3 ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ+ እንዲሆን የሚቃጠል መባም+ ሆነ ለየት ያለ ስእለት ለመሳል የሚቀርብ መሥዋዕት ወይም የፈቃደኝነት መባ+ አሊያም በየወቅቱ በምታከብሯቸው በዓላት+ ላይ የሚቀርብ መባ፣ ከከብታችሁ ወይም ከመንጋችሁ በመውሰድ ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ በምታቀርቡበት ጊዜ +4 መባውን የሚያቀርበው ሰው በአንድ አራተኛ ሂን* ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ* የላመ ዱቄትም+ የእህል መባ አድርጎ ለይሖዋ ማቅረብ ይኖርበታል። +5 እንዲሁም ከሚቃጠለው መባ ወይም ከተባዕት የበግ ጠቦት መሥዋዕቱ ጋር አንድ አራተኛ ሂን የወይን ጠጅ የመጠጥ መባ አድርገህ ማቅረብ አለብህ።+ +6 ወይም ከአውራ በግ ጋር በአንድ ሦስተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ ሁለት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርገህ አቅርብ። +7 እንዲሁም አንድ ሦስተኛ ሂን የወይን ጠጅ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የመጠጥ መባ አድርገህ ማቅረብ አለብህ። +8 “‘ሆኖም ከመንጋው መካከል አንድ ወይፈን የሚቃጠል መባ+ ወይም ለየት ያለ ስእለት+ ለመሳል የሚቀርብ መሥዋዕት አሊያም የኅብረት መሥዋዕት አድርገህ ለይሖዋ የምታቀርብ+ ከሆነ +9 ከወይፈኑ ጋር በግማሽ ሂን ዘይት የተለወሰ ሦስት አሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት የእህል መባ+ አድርገህ ማቅረብ ይኖርብሃል። +10 እንዲሁም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የመጠጥ መባ+ እንዲሆን ግማሽ ሂን የወይን ጠጅ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርገህ ማቅረብ አለብህ። +11 ለእያንዳንዱ በሬ ወይም ለእያንዳንዱ አውራ በግ ወይም ለእያንዳንዱ ተባዕት የበግ ጠቦት ወይም ለእያንዳንዱ ፍየል እንዲሁ መደረግ አለበት። +12 የምታቀርቡት ብዛቱ ምንም ያህል ይሁን ምን ለእያንዳንዱ እንደየብዛቱ እንዲህ ማድረግ ይኖርባችኋል። +13 የአገሩ ተወላጅ የሆነ እያንዳንዱ እስራኤላዊ ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ የሚያቀርበው በዚህ መንገድ ነው። +14 “‘ከእናንተ ጋር እየኖረ ያለ ወይም ለብዙ ትውልድ በመካከላችሁ ሲኖር የነበረ የባዕድ አገር ሰው ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቃጠል መባ ቢያቀርብ ልክ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ።+ +15 የጉባኤው ክፍል የሆናችሁት እናንተም ሆናችሁ አብሯችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው አንድ ዓይነት ደንብ ይኖራችኋል። ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘላቂ ደንብ ይሆናል። የባዕድ አገሩ ሰው በይሖዋ ፊት ልክ እንደ እናንተ ይታያል።+ +16 ለእናንተም ሆነ ከእናንተ ጋር ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው አንድ ዓይነት ሕግና አንድ ዓይነት ድንጋጌ ይኑር።’” +18 “እስራኤላውያንን አናግራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ወደማመጣችሁ ምድር በምትገቡበትና +19 ከምድሪቱ ማንኛውንም ምግብ በምትበሉበት+ ጊዜ ለይሖዋ መዋጮ ማድረግ አለባችሁ። +20 ከተፈጨው የእህላችሁ በኩር+ ላይ የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ በማዘጋጀት መዋጮ ማድረግ ይኖርባችኋል። ይህን ማዋጣት የሚኖርባችሁ ከአውድማ ላይ የሚገኘውን መዋጮ በምታዋጡበት መንገድ ነው። +21 በትውልዶቻችሁ ሁሉ፣ ከተፈጨው የእህላችሁ በኩር ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ መስጠት ይኖርባችኋል። +22 “‘ምናልባት ስህተት ብትሠሩና ይሖዋ ለሙሴ የተናገራቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ሳትፈጽሙ ብትቀሩ +23 ይኸውም ይሖዋ ትእዛዙን ከሰጠበት ዕለት አንስቶ ሥራ ላይ የዋለውንና በትውልዶቻችሁ ሁሉ ጸንቶ የሚኖረውን ይሖዋ በሙሴ በኩል ያስተላለፈላችሁን ትእዛዝ ሁሉ ባትፈጽሙና +24 ይህን ያደረጋችሁት ደግሞ በስህተትና ማኅበረሰቡ ሳያውቅ ቢሆን መላው ማኅበረሰብ አንድ ወይፈን ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቅርብ፤ ከእሱም ጋር በተለመደው አሠራር መሠረት+ የእህል መባውንና የመጠጥ መባውን እንዲሁም አንድ የፍየል ጠቦት የኃጢአት መባ አድርጎ ያቅርብ።+ +25 ካህኑም ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ያስተሰርያል፤ ኃጢአቱም ባለማወቅ የተፈጸመ ስለሆነና ለሠሩትም ስህተት መባቸውን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርገው ስላቀረቡ እንዲሁም በይሖዋ ፊት የኃጢአት መባቸውን ስላቀረቡ ይቅር ይባልላቸዋል።+ +26 ይህም ሕዝቡ ሁሉ ባለማወቅ የፈጸመው ስለሆነ መላው የእስራኤል ማኅበረሰብም ሆነ በመካከላቸው የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ይቅር ይባላል። +27 “‘ማንኛውም ሰው* ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ አንድ ዓመት ገደማ የሆናት አንዲት ፍየል የኃጢአት መባ አድርጎ ያቅርብ።+ +28 ከዚያም ባለማወቅ በይሖዋ ፊት ኃጢአት በመሥራት የተሳሳተው ሰው* ኃጢአቱ ይሰረይለት ዘንድ ካህኑ ማስተሰረያ ያቀርብለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።+ +29 ባለማወቅ ከሚፈጸም ነገር ጋር በተያያዘ በእስራኤላውያን መካከል ለሚገኝ የአገሬው ተወላጅም ሆነ በመካከላቸው ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው አንድ ዓይነት ሕግ ይኑራችሁ።+ +30 “‘ይሁን እንጂ ሆን ብሎ ኃጢአት የሚሠራ ሰው*+ የአገሬው ተወላጅም ይሁን የባዕድ አገር ሰው ይሖዋን እንደተሳደበ ስለሚቆጠር ከሕዝቡ ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት። +31 የይሖዋን ቃል ስላቃለለና የእሱን ትእዛዝ ስለጣሰ ያ ሰው* ያለምንም ጥርጥር ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት።+ ጥፋቱ የራሱ ነው።’”+ +32 እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሳሉ አንድ ሰው በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም አገኙ።+ +33 ሰዎቹም እንጨት ሲለቅም ያገኙትን ሰው ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው ማኅበረሰብ አመጡት። +34 ሰውየው ምን መደረግ እንዳለበት በግልጽ የተቀመጠ ነገር ስላልነበረ በጥበቃ ሥር እንዲቆይ አደረጉ።+ +35 ይሖዋም ሙሴን “ሰውየው ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት፤+ መላው ማኅበረሰብም ከሰፈሩ ውጭ በድንጋይ ይውገረው”+ አለው። +36 ስለዚህ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት መላው ማኅበረሰብ ሰውየውን ከሰፈሩ ውጭ አውጥቶ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ወገረው። +37 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ +38 “እስራኤላውያን በትውልዶቻቸው ሁሉ በልብሳቸው ጫፍ ላይ ዘርፍ እንዲያደርጉ ንገራቸው፤ ልብሳቸውም ከዘርፉ በላይ ሰማያዊ ጥለት ይኑረው።+ +39 ‘ይህን ዘርፍ በልብሳችሁ ላይ አድርጉ፤ ምክንያቱም እሱን ስታዩ የይሖዋን ትእዛዛት ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ እንዲሁም ትፈጽማላችሁ።+ ወደ መንፈሳዊ ምንዝር የሚመራችሁን የገዛ ልባችሁንና ዓይናችሁን አትከተሉ።+ +40 ይህን መመሪያ የሰጠኋችሁ ትእዛዛቴን በሙሉ እንድታስታውሱና እንድትፈጽሙ ነው፤ ለአምላካችሁም የተቀደሳችሁ ትሆናላችሁ።+ +41 አምላካችሁ መሆኔን ለማስመሥከር ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።+ አዎ፣ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’”+ +22 እስራኤላውያንም ከዚያ ተነስተው በመጓዝ ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ በሚገኘው በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ሰፈሩ።+ +2 የሴፎር ልጅ ባላቅ+ እስራኤላውያን በአሞራውያን ላይ ያደረጉትን ሁሉ አየ፤ +3 ሞዓብም ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ በጣም ፈራ፤ በእርግጥም ሞዓብ በእስራኤላውያን ምክንያት በፍርሃት ታውኮ ነበር።+ +4 ስለዚህ ሞዓብ የምድያምን+ ሽማግሌዎች “በሬ በሜዳ ላይ ያለን ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ ይህም ጉባኤ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ ያጠፋል” አላቸው። በዚያን ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበር። +5 እሱም የቢዖርን ልጅ በለዓምን እንዲጠሩት መልእክተኞችን ላከ፤ በለዓም የሚኖረው በትውልድ አገሩ ባለው ወንዝ* ዳር በምትገኘው በጰቶር ነበር።+ እንዲህም ብለው እንዲነግሩት ላካቸው፦ “ከግብፅ ወጥቶ የመጣ አንድ ሕዝብ አለ። ይኸው የምድሪቱን* ገጽ* ሸፍኗል፤+ ደግሞም መጥቶ አፍንጫዬ ሥር ሰፍሯል። +6 እነሱ ከእኔ ይልቅ ኃያላን ስለሆኑ እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ እርገምልኝ።+ ምናልባትም ድል አድርጌ ከምድሪቱ ላባርራቸው እችላለሁ፤ ምክንያቱም አንተ የባረክኸው ሁሉ የተባረከ፣ የረገምከውም ሁሉ የተረገመ እንደሚሆን በሚገባ አውቃለሁ።” +7 በመሆኑም የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎች ለሟርት የሚከፈለውን ዋጋ ይዘው ወደ በለዓም+ ሄዱ፤ የባላቅንም መልእክት ነገሩት። +8 እሱም “እንግዲህ እዚህ እደሩና ይሖዋ የሚለኝን ማንኛውንም ነገር መልሼ እነግራችኋለሁ” አላቸው። ስለዚህም የሞዓብ መኳንንት በለዓም ዘንድ አደሩ። +9 ከዚያም አምላክ ወደ በለዓም መጥቶ+ “ከአንተ ጋር ያሉት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?” አለው። +10 በለዓምም እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለው፦ “የሞዓብ ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ የሚል መልእክት ልኮብኛል፦ +11 ‘ከግብፅ ወጥቶ የመጣው ሕዝብ የምድሪቱን* ገጽ* ሸፍኗል። ስለዚህ መጥተህ እነሱን እርገምልኝ።+ ምናልባትም ድል አድርጌ ከምድሪቱ ላባርራቸው እችላለሁ።’” +12 ሆኖም አምላክ በለዓምን “ከእነሱ ጋር እንዳትሄድ። ሕዝቡ የተባረከ ስለሆነ እንዳትረግመው” አለው።+ +13 በለዓም በጠዋት ተነስቶ የባላቅን መኳንንት “ይሖዋ ከእናንተ ጋር እንዳልሄድ ስለከለከለኝ ወደ አገራችሁ ሂዱ” አላቸው። +14 በመሆኑም የሞዓብ መኳንንት ተነስተው ወደ ባላቅ ተመለሱ፤ እንዲህም አሉት፦ “በለዓም ከእኛ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ አልሆነም።” +15 ሆኖም ባ���ቅ ከበፊቶቹ ይልቅ ቁጥራቸው የበዛና ይበልጥ የተከበሩ ሌሎች መኳንንት እንደገና ላከ። +16 እነሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፦ “የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ይላል፦ ‘እባክህ ወደ እኔ ከመምጣት ምንም ነገር እንዲያግድህ አትፍቀድ። +17 እኔም ከፍ ያለ ክብር አጎናጽፍሃለሁ፤ የምትለኝንም ሁሉ አደርጋለሁ። ስለሆነም እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ እርገምልኝ።’” +18 ሆኖም በለዓም ለባላቅ አገልጋዮች እንዲህ የሚል መልስ ሰጣቸው፦ “ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላውን የገዛ ቤቱን ቢሰጠኝ እንኳ ከአምላኬ ከይሖዋ ትእዛዝ ወጥቼ ትንሽም ሆነ ትልቅ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም።+ +19 ሆኖም እባካችሁ፣ ይሖዋ ሌላ የሚለኝ ነገር ካለ እንዳውቅ ዛሬም እዚህ እደሩ።”+ +20 ከዚያም አምላክ በሌሊት ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፦ “እነዚህ ሰዎች የመጡት አንተን ለመጥራት ከሆነ አብረሃቸው ሂድ። ይሁንና የምትናገረው እኔ የምልህን ብቻ ነው።”+ +21 ስለዚህ በለዓም በጠዋት ተነስቶ አህያውን ከጫነ በኋላ ከሞዓብ መኳንንት ጋር ሄደ።+ +22 ይሁን እንጂ በለዓም ጉዞ በመጀመሩ የአምላክ ቁጣ ነደደ፤ የይሖዋም መልአክ በለዓምን ሊቃወመው መንገዱ ላይ ቆመ። በዚህ ጊዜ በለዓም በአህያው ላይ ተቀምጦ እየተጓዘ ነበር፤ ሁለት አገልጋዮቹም አብረውት ነበሩ። +23 አህያዋም የይሖዋ መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ መንገዱ ላይ መቆሙን ስታይ ከመንገዱ ወጥታ ወደ እርሻ ለመግባት ሞከረች። ሆኖም በለዓም አህያዋን ወደ መንገዱ ለመመለስ ይደበድባት ጀመር። +24 ከዚያም የይሖዋ መልአክ በዚህም በዚያም በኩል በግንብ በታጠሩ ሁለት የወይን እርሻዎች መካከል በሚገኝ ጠባብ መንገድ ላይ ቆመ። +25 አህያዋም የይሖዋን መልአክ ስታይ ግንቡን መታከክ ጀመረች፤ የበለዓምንም እግር ከግንቡ ጋር አጣበቀችው፤ በለዓምም እንደገና ይደበድባት ጀመር። +26 የይሖዋም መልአክ እንደገና አልፎ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ መፈናፈን በማያስችል ጠባብ ቦታ ላይ ቆመ። +27 አህያዋም የይሖዋን መልአክ ስታይ በለዓም ላይዋ ላይ እንዳለ ተኛች፤ በዚህ ጊዜ በለዓም እጅግ ተቆጣ፤ አህያዋንም በዱላው ይቀጠቅጣት ጀመር። +28 በመጨረሻም ይሖዋ አህያዋ እንድትናገር አደረገ፤*+ እሷም በለዓምን “ሦስት ጊዜ እንዲህ የመታኸኝ ምን አድርጌህ ነው?”+ አለችው። +29 በለዓምም አህያዋን “ስለተጫወትሽብኝ ነዋ! በእጄ ሰይፍ ይዤ ቢሆንማ ኖሮ እገድልሽ ነበር!” አላት። +30 ከዚያም አህያዋ በለዓምን “እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወትህ ሙሉ የተቀመጥክብኝ አህያህ አይደለሁም? ከዚህ በፊት እንዲህ አድርጌህ አውቃለሁ?” አለችው። እሱም “በጭራሽ!” አላት። +31 ከዚያም ይሖዋ የበለዓምን ዓይኖች ገለጠ፤+ እሱም የይሖዋ መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ መንገዱ ላይ ቆሞ አየ። ወዲያውኑም በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደ። +32 ከዚያም የይሖዋ መልአክ እንዲህ አለው፦ “አህያህን ሦስት ጊዜ እንዲህ አድርገህ የመታሃት ለምንድን ነው? መንገድህ ከፈቃዴ ጋር ስለሚቃረን እኔ ራሴ ከጉዞህ ልገታህ መጥቻለሁ።+ +33 አህያዋ አይታኝ ሦስቱንም ጊዜ ከፊቴ ዞር ለማለት ሞከረች።+ እሷ ከፊቴ ዞር ባትልማ ኖሮ ምን ይከሰት እንደነበር አስብ! ይሄን ጊዜ አንተን ገድዬህ አህያዋን በሕይወት በተውኳት ነበር።” +34 በዚህ ጊዜ በለዓም የይሖዋን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ምክንያቱም አንተ እኔን ለማግኘት መንገድ ላይ እንደቆምክ አላወቅኩም ነበር። አሁንም ቢሆን መሄዴ ጥሩ መስሎ ካልታየህ እመለሳለሁ።” +35 ሆኖም የይሖዋ መልአክ በለዓምን “ከሰዎቹ ጋር መሄዱን እንኳ ሂድ፤ የምትናገረው ግን እኔ የምልህን ብቻ ነው” አለው። በመሆኑም በለዓም ከባላቅ መኳንንት ��ር ጉዞውን ቀጠለ። +36 ባላቅ የበለዓምን መምጣት ሲሰማ በክልሉ ወሰን ላይ በሚገኘው በአርኖን ዳርቻ ባለው በሞዓብ ከተማ ሊቀበለው ወዲያውኑ ወጣ። +37 ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እንድትመጣ ልኬብህ አልነበረም? ታዲያ ወደ እኔ ያልመጣኸው ለምንድን ነው? ለመሆኑ እኔ አንተን ታላቅ ክብር ማጎናጸፍ የሚያቅተኝ ይመስልሃል?”+ +38 በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “ይኸው አሁን ወደ አንተ መጥቻለሁ። ይሁንና ያሻኝን መናገር የምችል ይመስልሃል? እኔ መናገር የምችለው አምላክ በአፌ ላይ የሚያደርገውን ቃል ብቻ ነው።”+ +39 በመሆኑም በለዓም ከባላቅ ጋር ሄደ፤ ወደ ቂርያትሁጾትም መጡ። +40 ባላቅም ከብቶችንና በጎችን ሠዋ፤ የተወሰነውንም ለበለዓምና ከእሱ ጋር ለነበሩት መኳንንት ላከ። +41 ጠዋት ላይም ባላቅ በለዓምን ይዞት ወደ ባሞትበዓል ወጣ፤ እዚያ ሆኖ ሕዝቡን ሁሉ ማየት ይችል ነበር።+ +17 “እንከን ወይም ማንኛውም ዓይነት ጉድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለይሖዋ አትሠዋ፤ ምክንያቱም ይህ ለአምላክህ ለይሖዋ አስጸያፊ ነው።+ +2 “አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዱ ውስጥ በአምላክህ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር የሚፈጽምና ቃል ኪዳኑን የሚያፈርስ ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ+ +3 እሱም ሄዶ ሌሎች አማልክትን በማምለክ እንዲሁም ለእነሱ ወይም ለፀሐይ አሊያም ለጨረቃ ወይም ደግሞ ለሰማይ ሠራዊት በሙሉ በመስገድ+ እኔ ያላዘዝኩትን ነገር ቢያደርግ+ +4 አንተም ይህ ነገር ቢነገርህ ወይም ሁኔታውን ብትሰማ ጉዳዩን በጥንቃቄ አጣራ። ይህ አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ውስጥ መፈጸሙ እውነት እንደሆነ ቢረጋገጥ+ +5 እንዲህ ያለ መጥፎ ድርጊት የፈጸመውን ያንን ሰው ወይም ያቺን ሴት ወደ ከተማዋ በር አውጣቸው፤ ከዚያም ሰውየው ወይም ሴትየዋ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ይወገሩ።+ +6 ሞት የሚገባው ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በሚሰጡት ምሥክርነት*+ ይገደል። አንድ ምሥክር በሚሰጠው ቃል ብቻ መገደል የለበትም።+ +7 እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጃቸውን የሚያነሱት ምሥክሮቹ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ያንሳበት። ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+ +8 “ከከተሞችህ በአንዱ ውስጥ ለመዳኘት አስቸጋሪ የሆነ ክርክር ቢነሳ ለምሳሌ፣ ጉዳዩ ደም ማፍሰስን+ የሚመለከትም ይሁን ለሕግ አቤቱታ ማቅረብን ወይም የዓመፅ ድርጊትን አሊያም ሌሎች አለመግባባቶችን የሚመለከት ቢሆን ተነስተህ አምላክህ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ውጣ።+ +9 ወደ ሌዋውያን ካህናትና በዚያን ጊዜ ዳኛ ሆኖ ወደሚያገለግለው ሰው+ ሄደህ ጠይቅ፤ እነሱም ውሳኔውን ይነግሩሃል።+ +10 አንተም እነዚህ ሰዎች ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ ሆነው በነገሩህ ውሳኔ መሠረት እርምጃ ውሰድ። የሰጡህንም መመሪያ በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም። +11 በሚሰጡህ ሕግና በሚነግሩህ ውሳኔ መሠረት እርምጃ ውሰድ።+ እነሱ ካሳለፉት ውሳኔ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል።+ +12 አምላክህን ይሖዋን የሚያገለግለውን ካህን ወይም ዳኛውን ባለመስማት እብሪተኛ የሚሆን ሰው ካለ ይገደል።+ ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል አስወግድ።+ +13 ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲሰማ ይፈራል፤ ከእንግዲህም የእብሪት ድርጊት አይፈጽምም።+ +14 “አምላክህ ይሖዋ የሚሰጥህን ምድር ገብተህ ከወረስካት በኋላ በዚያ መኖር ስትጀምር ‘በዙሪያዬ እንዳሉት ብሔራት ሁሉ እኔም በላዬ ላይ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል+ +15 አምላክህ ይሖዋ የሚመርጠውን ንጉሥ ታነግሣለህ። የምታነግሠውም ንጉሥ ከወንድሞችህ መካከል መሆን ይኖርበታል።+ ወንድምህ ያልሆነን ባዕድ ሰው በላይህ ላይ ማንገሥ አይገባህም። +16 ይሁን እንጂ ንጉሡ ለራሱ ፈረሶች ማብዛት+ ወይም የፈረ���ቹን ቁጥር ለመጨመር ሲል ሕዝቡ ወደ ግብፅ እንዲመለስ ማድረግ የለበትም፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ‘በዚህ መንገድ ፈጽሞ ዳግመኛ አንዳትመለሱ’ ብሏችኋል። +17 ልቡ ከትክክለኛው መንገድ ዞር እንዳይል ለራሱ ሚስቶች አያብዛ፤+ ለራሱም ብርና ወርቅ አያከማች።+ +18 በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ በሌዋውያን ካህናት እጅ ካለው ላይ ወስዶ የዚህን ሕግ ቅጂ ለራሱ በመጽሐፍ* ላይ ይጻፍ።+ +19 “አምላኩን ይሖዋን መፍራትን እንዲማር እንዲሁም በዚህ ሕግና በእነዚህ ሥርዓቶች ላይ የሰፈሩትን ቃላት በሙሉ በመፈጸም እንዲጠብቃቸው ይህ መጽሐፍ ከእሱ ጋር ይሁን፤+ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ያንብበው።+ +20 ይህን ካደረገ ልቡ በወንድሞቹ ላይ አይታበይም፤ ከትእዛዛቱም ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አይልም፤ ይህም እሱም ሆነ ልጆቹ በእስራኤል መካከል በመንግሥቱ ላይ ረጅም ዘመን እንዲቆዩ ያስችላቸዋል። +30 “ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን+ በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር+ ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት* ጊዜ+ +2 እንዲሁም አንተም ሆንክ ልጆችህ እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ በምትመለሱበትና ቃሉን በምትሰሙበት ጊዜ+ +3 አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤+ ምሕረትም ያሳይሃል፤+ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል።+ +4 ሕዝብህ እስከ ሰማያት ዳርቻ ድረስ ቢበተን እንኳ አምላክህ ይሖዋ ከዚያ ይሰበስብሃል፤ ከዚያም መልሶ ያመጣሃል።+ +5 አምላክህ ይሖዋ አባቶችህ ወርሰዋት ወደነበሩት ምድር ያስገባሃል፤ አንተም ትወርሳታለህ፤ እሱም ከአባቶችህ ይበልጥ ያበለጽግሃል፤ እንዲሁም ያበዛሃል።+ +6 በሕይወትም ትኖር ዘንድ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ* እንድትወደው+ አምላክህ ይሖዋ ልብህን እንዲሁም የልጆችህን ልብ ያነጻል።*+ +7 ከዚያም አምላክህ ይሖዋ እነዚህን እርግማኖች ሁሉ በሚጠሉህና በሚያሳድዱህ ጠላቶችህ ላይ ያመጣል።+ +8 “አንተም ተመልሰህ የይሖዋን ቃል ትሰማለህ፤ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዛቱን ሁሉ ትፈጽማለህ። +9 አምላክህ ይሖዋ በአባቶችህ ደስ እንደተሰኘ+ ሁሉ ይሖዋ አንተንም በማበልጸግ ስለሚደሰት የሆድህን ፍሬ፣ እንስሶችህንና የምድርህን ፍሬ በማብዛት በእጅህ ሥራ ሁሉ እጅግ እንድትበለጽግ ያደርግሃል።+ +10 ይህም የሚሆነው የአምላክህን የይሖዋን ቃል ስለምትሰማ፣ በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዛቱንና ደንቦቹን ስለምትጠብቅ እንዲሁም በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ* ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ስለምትመለስ ነው።+ +11 “እኔ ዛሬ የማዝህ ይህ ትእዛዝ ለአንተ ያን ያህል ከባድ አይደለም፤ ከአንተም የራቀ አይደለም።+ +12 ‘ሰምተን እንድንፈጽመው ወደ ሰማይ ወጥቶ ማን ያምጣልን?’ እንዳትል ትእዛዙ ያለው በሰማይ አይደለም።+ +13 ደግሞም ‘ሰምተን እንድንፈጽመው ባሕሩን ተሻግሮ ማን ያምጣልን?’ እንዳትል ትእዛዙ ያለው ከባሕሩ ማዶ አይደለም። +14 ቃሉ ትፈጽመው ዘንድ+ ለአንተ በጣም ቅርብ ነውና፤ ደግሞም በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው።+ +15 “እንግዲህ እኔ ዛሬ ሕይወትንና መልካም ነገርን እንዲሁም ሞትንና መጥፎ ነገርን በፊትህ አስቀምጫለሁ።+ +16 አምላክህን ይሖዋን በመውደድ፣+ በመንገዶቹ በመሄድ እንዲሁም ትእዛዛቱን፣ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን በመጠበቅ እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ብትሰማ በሕይወት ትኖራለህ፤+ ደግሞም ትበዛለህ፤ አምላክህ ይሖዋም በምትወርሳት ምድር ውስጥ ይባርክሃል።+ +17 “ሆኖም ልብህ ቢሸፍትና+ ለመስማት ፈቃደኛ ባትሆን እንዲሁም ተታለህ ለሌሎች አማልክት ብትሰግድና ብታገለግላቸው+ +18 በእርግጥ እንደምትጠፉ+ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ። ደግሞም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁ ያጥራል። +19 ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና እርግማንን በፊታችሁ እንዳስቀመጥኩ+ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምሥክሮች አድርጌ እጠራባችኋለሁ፤ እንግዲህ አንተም ሆንክ ዘሮችህ+ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤+ +20 ይህን የምታደርገው አምላክህን ይሖዋን በመውደድ፣+ ቃሉን በመስማትና ከእሱ ጋር በመጣበቅ ነው፤+ ምክንያቱም እሱ ሕይወትህ ነው፤ ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ የምትኖረውም በእሱ ነው።”+ +31 ከዚያም ሙሴ ወጥቶ እነዚህን ቃላት ለመላው እስራኤል ተናገረ፤ +2 እንዲህም አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ አሁን 120 ዓመት ሆኖኛል።+ ይሖዋ ‘የዮርዳኖስን ወንዝ አትሻገርም’+ ስላለኝ ከእንግዲህ ልመራችሁ* አልችልም። +3 ከፊትህ የሚሻገረው አምላክህ ይሖዋ ነው፤ እሱ ራሱም እነዚህን ብሔራት ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ታባርራቸዋለህ።+ ልክ ይሖዋ በተናገረውም መሠረት እየመራ የሚያሻግርህ ኢያሱ ነው።+ +4 ይሖዋ የአሞራውያንን ነገሥታት ሲሖንን+ እና ኦግን+ እንዲሁም ምድራቸውን ባጠፋ ጊዜ በእነሱ ላይ እንዳደረገው ሁሉ በእነዚህም ብሔራት ላይ እንዲሁ ያደርግባቸዋል።+ +5 ይሖዋ እነሱን ድል ያደርግላችኋል፤ እናንተም እኔ በሰጠኋችሁ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት ታደርጉባቸዋላችሁ።+ +6 ደፋርና ብርቱ ሁኑ።+ ከእናንተ ጋር የሚሄደው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው ወይም በፊታቸው አትሸበሩ።+ እሱ አይጥላችሁም ወይም አይተዋችሁም።”+ +7 ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በመላው እስራኤል ፊት እንዲህ አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤+ ምክንያቱም ይህን ሕዝብ ይሖዋ ለአባቶቻቸው ሊሰጣቸው ወደማለላቸው ምድር የምታስገባው አንተ ነህ፤ ደግሞም ይህን ምድር ርስት አድርገህ ትሰጣቸዋለህ።+ +8 በፊትህ የሚሄደው ይሖዋ ነው፤ እሱ ምንጊዜም ከአንተ ጋር ይሆናል።+ አይጥልህም ወይም አይተውህም። አትፍራ ወይም አትሸበር።”+ +9 ከዚያም ሙሴ ይህን ሕግ ጽፎ+ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ለሚሸከሙት ሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ሰጣቸው። +10 ሙሴ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “በየሰባት ዓመቱ መጨረሻ፣ በዓመቱ ውስጥ ዕዳ በሚሰረዝበት+ በተወሰነው ጊዜ ላይ ማለትም የዳስ* በዓል+ ሲከበር +11 መላው እስራኤል አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በፊቱ በሚሰበሰብበት+ ጊዜ ይህን ሕግ እስራኤላውያን በሙሉ እንዲሰሙት አንብብላቸው።+ +12 ስለ አምላካችሁ ስለ ይሖዋ ይሰሙና ይማሩ እንዲሁም እሱን ይፈሩ ዘንድ ብሎም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ እንዲፈጽሙ ሕዝቡን ማለትም ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችንና* በከተሞችህ ውስጥ* የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው ሰብስብ።+ +13 ከዚያም ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸው ይሰማሉ፤+ እንዲሁም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ አምላካችሁን ይሖዋን መፍራት ይማራሉ።”+ +14 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ የምትሞትበት ጊዜ ቀርቧል።+ ኢያሱን ጥራውና መሪ አድርጌ እንድሾመው በመገናኛ ድንኳኑ ተገኙ።”*+ በመሆኑም ሙሴና ኢያሱ ሄደው በመገናኛ ድንኳኑ ተገኙ። +15 ከዚያም ይሖዋ በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ በድንኳኑ ላይ ተገለጠ፤ የደመናውም ዓምድ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆመ።+ +16 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ መሞትህ ነው፤* ይህም ሕዝብ በሚሄድበት ምድር በዙሪያው ካሉ ባዕዳን አማልክት ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ይፈጽማል።+ እኔንም ይተዉኛል፤+ ከእነሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።+ +17 በዚያን ጊዜ ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል፤+ እኔም እተዋቸዋለሁ፤+ ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰሱም ድረስ ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ።+ ከዚያም ብዙ መከራና ችግር ይደርስባቸዋል፤+ እነሱም ‘ይህ ሁሉ መከራ የደረሰብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደል?’+ ይላሉ። +18 ሆኖም ወደ ሌሎች አማልክት ዞር በማለት ከፈጸሙት መጥፎ ድርጊት ሁሉ የተነሳ በዚያ ቀን ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ።+ +19 “እንግዲህ አሁን ይህን መዝሙር ለራሳችሁ ጻፉ፤+ ለእስራኤላውያንም አስተምሯቸው።+ ይህ መዝሙር በእስራኤል ሕዝብ ላይ ምሥክሬ ሆኖ ያገለግል ዘንድ እንዲማሩት አድርጉ።*+ +20 ምክንያቱም ለአባቶቻቸው ወደማልኩላቸው+ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ በማስገባቸው ጊዜ በልተው ሲጠግቡና ሲበለጽጉ*+ ወደ ሌሎች አማልክት ዞር ይላሉ፤ እንዲሁም እነሱን ያገለግላሉ፤ እኔንም ይንቁኛል፤ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ።+ +21 ብዙ መከራና ችግር በሚደርስባቸው ጊዜ+ ይህ መዝሙር ምሥክር ይሆንባቸዋል፤ (ምክንያቱም ዘሮቻቸው ይህን መዝሙር ሊዘነጉት አይገባም፤) እኔ እንደሆነ ወደማልኩላቸው ምድር ገና ሳላስገባቸው ምን ዓይነት ዝንባሌ እንዳዳበሩ አውቄአለሁ።”+ +22 ስለዚህ ሙሴ ይህን መዝሙር በዚያን ቀን ጻፈው፤ እስራኤላውያንንም አስተማራቸው። +23 እሱም* የነዌን ልጅ ኢያሱን ሾመው፤+ እንዲህም አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤+ ምክንያቱም እስራኤላውያንን ወደማልኩላቸው ምድር የምታስገባቸው አንተ ነህ፤+ እኔም ምንጊዜም ከአንተ ጋር እሆናለሁ።” +24 ሙሴም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ላይ ጽፎ+ እንደጨረሰ +25 የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያኑን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ +26 “ይህን የሕግ መጽሐፍ+ ወስዳችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት+ አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በዚያ በእናንተ ላይ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል። +27 ምክንያቱም እናንተ ዓመፀኛና+ ግትር*+ መሆናችሁን በሚገባ አውቃለሁ። እኔ ዛሬ ከእናንተ ጋር በሕይወት እያለሁ በይሖዋ ላይ እንዲህ ካመፃችሁ ከሞትኩ በኋላማ ምን ያህል ታምፁ! +28 የነገዶቻችሁን ሽማግሌዎችና አለቆቻችሁን በሙሉ ሰብስቡልኝ፤ እኔም ጆሯቸው እየሰማ እነዚህን ቃላት ልናገር፤ ሰማይንና ምድርንም በእነሱ ላይ ምሥክሮች አድርጌ ልጥራ።+ +29 ምክንያቱም እኔ ከሞትኩ በኋላ ክፉ ድርጊት እንደምትፈጽሙና ካዘዝኳችሁ መንገድ ዞር እንደምትሉ በሚገባ አውቃለሁ።+ በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ስለምትፈጽሙና በእጆቻችሁ ሥራ ስለምታስቆጡት ወደፊት መከራ ይደርስባችኋል።”+ +30 ከዚያም ሙሴ መላው የእስራኤል ጉባኤ እየሰማ የዚህን መዝሙር ቃላት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዲህ ሲል ተናገረ፦+ +18 “ሌዋውያኑ ካህናት አልፎ ተርፎም መላው የሌዊ ነገድ ከእስራኤል ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ አይኖራቸውም። የእሱ ድርሻ የሆኑትን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች ይበላሉ።+ +2 በመሆኑም በወንድሞቻቸው መካከል ውርሻ ሊኖራቸው አይገባም። አስቀድሞ በነገራቸው መሠረት ውርሻቸው ይሖዋ ነው። +3 “ካህናት ከሕዝቡ ሊያገኙ የሚገባቸው ድርሻ የሚከተለው ይሆናል፦ በሬም ሆነ በግ መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው የእንስሳውን ወርች፣ መንገጭላውንና ሆድ ዕቃውን ለካህኑ ይስጥ። +4 የእህልህን በኩር፣ አዲስ የወይን ጠጅህንና ዘይትህን እንዲሁም ከመንጋህ በመጀመሪያ የተሸለተውን ፀጉር ስጠው።+ +5 አምላክህ ይሖዋ ከነገዶችህ ሁሉ መካከል በይሖዋ ስም ሁልጊዜ እንዲያገለግል የመረጠው እሱንና ወንዶች ልጆቹን ነው።+ +6 “ሆኖም አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት በእስራኤል ከሚገኙ ከተሞችህ+ ከአንዱ ወጥቶ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ*+ መሄድ ቢፈልግ* +7 በይሖዋ ፊት ቆመው እንደሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ ሁሉ እሱም በዚያ በአምላኩ በይሖዋ ስም ሊያገለግል ይችላል።+ +8 የአባቶቹን ርስት በመሸጥ ከሚያገኘው ገንዘብ በተጨማሪ ከእነሱ እኩል ምግብ ይሰጠዋል።+ +9 “አምላክህ ይሖዋ ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ በዚያ የሚገኙ ብሔራት የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ነገሮች አታድርግ።+ +10 ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፣+ ሟርተኛ፣+ አስማተኛ፣+ ሞራ ገላጭ፣+ ምትሃተኛ፣+ +11 ድግምተኛ፣ መናፍስት ጠሪ፣+ ጠንቋይ+ ወይም ሙታን አነጋጋሪ+ በመካከልህ አይገኝ። +12 ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤ አምላክህ ይሖዋም እነሱን ከፊትህ የሚያባርራቸው በእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች የተነሳ ነው። +13 በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንከን የለሽ ሆነህ መገኘት አለብህ።+ +14 “አንተ ከምድራቸው የምታስለቅቃቸው እነዚህ ብሔራት አስማተኞችንና+ ሟርተኞችን+ ይሰማሉ፤ አንተ ግን እንዲህ እንድታደርግ አምላክህ ይሖዋ አልፈቀደልህም። +15 አምላክህ ይሖዋ ከወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል። እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል።+ +16 ይህም የሚሆነው በኮሬብ ተሰብስባችሁ+ በነበረበት ዕለት ‘እንዳልሞት የአምላኬን የይሖዋን ድምፅ ከእንግዲህ አልስማ ወይም ይህን ታላቅ እሳት ከእንግዲህ አልይ’+ በማለት አምላካችሁን ይሖዋን በጠየቃችሁት መሠረት ነው። +17 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘የተናገሩት ነገር መልካም ነው። +18 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሳላቸዋለሁ፤+ ቃሌንም በአፉ ላይ አደርጋለሁ፤+ እሱም እኔ የማዘውን ሁሉ ይነግራቸዋል።+ +19 በእኔ ስም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው በእርግጥ ተጠያቂ አደርገዋለሁ።+ +20 “‘እኔ እንዲናገር ያላዘዝኩትን ቃል በእብሪት ተነሳስቶ በስሜ የሚናገር ወይም በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ካለ ያ ነቢይ ይገደል።+ +21 ሆኖም አንተ በልብህ “ታዲያ ቃሉን ይሖዋ እንዳልተናገረው እንዴት እናውቃለን?” ብለህ ታስብ ይሆናል። +22 ነቢዩ በይሖዋ ስም ቢናገርና የተናገረው ቃል ባይፈጸም ወይም እውነት ሆኖ ባይገኝ ይህን ቃል የተናገረው ይሖዋ አይደለም። ይህ ቃል ነቢዩ በእብሪት ተነሳስቶ የተናገረው ነው። እሱን ልትፈራው አይገባም።’ +23 “የዘር ፍሬው ተቀጥቅጦ የተኮላሸ ወይም ብልቱ የተቆረጠ ማንኛውም ሰው ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግባ።+ +2 “ዲቃላ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግባ።+ ሌላው ቀርቶ እስከ አሥረኛ ትውልድ ድረስ ዘሮቹ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ። +3 “አሞናውያንም ሆኑ ሞዓባውያን ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ።+ ሌላው ቀርቶ እስከ አሥረኛ ትውልድ ድረስ ዘሮቻቸው ፈጽሞ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ፤ +4 ምክንያቱም እነሱ ከግብፅ ወጥታችሁ እየተጓዛችሁ በነበረበት ጊዜ ምግብና ውኃ በመስጠት አልረዷችሁም፤+ ደግሞም በሜሶጶጣሚያ በምትገኘው በጰቶር የሚኖረው የቢዖር ልጅ በለዓም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ቀጥረውት ነበር።+ +5 አምላክህ ይሖዋ ግን በለዓምን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም።+ ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ሲል እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው፤+ ይህን ያደረገው አምላክህ ይሖዋ ስለወደደህ ነው።+ +6 በዘመንህ ሁሉ መቼም ቢሆን ለእነሱ ሰላምን ወይም ብልጽግናን አትመኝ።+ +7 “ወንድምህ ስለሆነ ኤዶማዊውን አትጥላው።+ “የባዕድ አገር ሰው ሆነህ በአገሩ ትኖር ስለነበር ግብፃዊውን አትጥላው።+ +8 ለእነሱ የሚወለዱላቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆ��� ወደ ይሖዋ ጉባኤ መግባት ይችላሉ። +9 “ጠላትህን ለመውጋት ወጥተህ በምትሰፍርበት ጊዜ ከማንኛውም መጥፎ* ነገር መራቅ ይኖርብሃል።+ +10 አንድ ሰው ዘሩ በመፍሰሱ ምክንያት ቢረክስ+ ከሰፈሩ ውጭ ይውጣ፤ ወደ ሰፈሩም ተመልሶ አይግባ። +11 አመሻሹ ላይ በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ወደ ሰፈሩ ተመልሶ መግባት ይችላል።+ +12 ለመጸዳጃ የሚሆን ቦታ ከሰፈሩ ውጭ አዘጋጅ፤ አንተም መሄድ ያለብህ ወደዚያ ነው። +13 ከመሣሪያዎችህም ጋር መቆፈሪያ ያዝ። ውጭ በምትጸዳዳበትም ጊዜ በመቆፈሪያው ጉድጓድ ቆፍር፤ ከዚያም በዓይነ ምድርህ ላይ አፈሩን መልስበት። +14 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሊታደግህና ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈሩ ውስጥ ይዘዋወራል፤+ በመሆኑም ነውር የሆነ ምንም ነገር እንዳያይብህና ከአንተ ጋር መሄዱን እንዳይተው ሰፈርህ ቅዱስ መሆን አለበት።+ +15 “አንድ ባሪያ ከጌታው አምልጦ ወደ አንተ ቢመጣ መልሰህ ለጌታው አትስጠው። +16 ከከተሞችህ መካከል በመረጠውና ደስ ባለው ቦታ አብሮህ ሊኖር ይችላል። በደል አትፈጽምበት።+ +17 “ከእስራኤል ሴቶች ልጆች መካከል የትኛዋም የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ አትሁን፤+ ከእስራኤል ወንዶች ልጆችም መካከል የትኛውም የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ አይሁን።+ +18 ለሴት ዝሙት አዳሪ የተከፈለን ዋጋም ሆነ ለወንድ ዝሙት አዳሪ* የተከፈለን ዋጋ* አንድን ስእለት ለመፈጸም ስትል ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አታምጣ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሁለቱንም ይጸየፋቸዋል። +19 “ወንድምህን ወለድ አታስከፍለው፤+ ከገንዘብም ሆነ ከእህል ወይም ወለድ ሊያስከፍል ከሚችል ከማንኛውም ነገር ወለድ አታስከፍለው። +20 ከባዕድ አገር ሰው ወለድ መጠየቅ ትችላለህ፤+ ሆኖም አምላክህ ይሖዋ ገብተህ በምትወርሳት ምድር በሥራህ ሁሉ እንዲባርክህ+ ወንድምህን ወለድ አታስከፍለው።+ +21 “ለአምላክህ ለይሖዋ ስእለት ከተሳልክ+ ለመፈጸም አትዘግይ።+ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በእርግጥ ከአንተ ይፈልገዋል፤ አለዚያ ኃጢአት ይሆንብሃል።+ +22 ሳትሳል ከቀረህ ግን ኃጢአት አይሆንብህም።+ +23 ከአፍህ የወጣውን ቃል ጠብቅ፤+ ለአምላክህ ለይሖዋ የፈቃደኝነት መባ አድርገህ ለማቅረብ በገዛ አንደበትህ የተሳልከውን ፈጽም።+ +24 “ወደ ባልንጀራህ የወይን እርሻ ከገባህ እስክትጠግብ* ድረስ ወይን መብላት ትችላለህ፤ በዕቃህ ግን ምንም ይዘህ አትሂድ።+ +25 “ወደ ባልንጀራህ የእህል ማሳ ከገባህ እሸት ቀጥፈህ መብላት ትችላለህ፤ ሆኖም የባልንጀራህን እህል በማጭድ ማጨድ የለብህም።+ +34 ከዚያም ሙሴ ከሞዓብ በረሃማ ሜዳ ተነስቶ ወደ ነቦ ተራራ+ ይኸውም በኢያሪኮ+ ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ጲስጋ አናት+ ወጣ። ይሖዋም ምድሪቱን በሙሉ አሳየው፤ ይኸውም ከጊልያድ እስከ ዳን፣+ +2 ንፍታሌምን በሙሉ፣ የኤፍሬምንና የምናሴን ምድር፣ በስተ ምዕራብ በኩል እስካለው ባሕር* ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር በሙሉ፣+ +3 ኔጌብን፣+ የዮርዳኖስን አውራጃ+ እንዲሁም የዘንባባ ዛፍ ከተማ በሆነችው በኢያሪኮ ካለው ሸለቋማ ሜዳ አንስቶ እስከ ዞአር+ ድረስ አሳየው። +4 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’+ በማለት የማልኩላቸው ምድር ይህች ናት። በዓይንህ እንድታያት አድርጌሃለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም።”+ +5 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴም ልክ ይሖዋ እንደተናገረው በዚያው በሞዓብ ምድር ሞተ።+ +6 እሱም ከቤትጰኦር ትይዩ በሞዓብ ምድር በሚገኘው ሸለቆ ቀበረው፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩ የት እንደሚገኝ የሚያውቅ የለም።+ +7 ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው 120 ዓመት ነበር።+ ዓይኖቹ አልፈዘዙም፤ ጉልበቱም አልደከመም ነበር። +8 እስራኤላውያንም በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ለሙሴ 30 ቀን አለቀሱለት።+ በመጨረሻም ለሙሴ የሚለቀስበትና የሚታዘንበት ጊዜ አበቃ። +9 የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴ እጁን ስለጫነበት+ የጥበብ መንፈስ ተሞልቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም እሱን ይሰሙት ጀመር፤ እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።+ +10 ሆኖም ይሖዋ ፊት ለፊት እንዳወቀው+ እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነቢይ እስካሁን በእስራኤል ተነስቶ አያውቅም።+ +11 ይሖዋ በግብፅ ምድር በፈርዖን፣ በአገልጋዮቹ ሁሉና በምድሩ ሁሉ ፊት እንዲፈጽም የላከውን ምልክቶችና ተአምራት በሙሉ ፈጸመ፤+ +12 ከዚህም በተጨማሪ ሙሴ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት በኃያል ክንድ ታላቅና አስፈሪ ድርጊት ፈጸመ።+ +19 “አምላክህ ይሖዋ ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥህን ብሔራት፣ ይሖዋ በሚያጠፋቸውና አንተም እነሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው መኖር በምትጀምርበት ጊዜ+ +2 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ሦስት ከተሞችን ለይ።+ +3 አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት የሚሰጥህን ምድር ሦስት ቦታ ከፋፍላት፤ እንዲሁም ነፍስ ያጠፋ ማንኛውም ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ መሸሽ እንዲችል መንገድ አዘጋጅ። +4 “እዚያ ለመኖር ሸሽቶ የሄደን፣ ነፍስ ያጠፋ ሰው በተመለከተ መደረግ ያለበት ነገር ይህ ነው፦ ለባልንጀራው የቆየ ጥላቻ የሌለው አንድ ሰው ሳያስበው ባልንጀራውን መትቶ ቢገድለው፣+ +5 ለምሳሌ ከባልንጀራው ጋር እንጨት ለመቁረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፣ ዛፉንም ለመቁረጥ መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ላይ ወልቆ ባልንጀራውን ቢመታውና ቢገድለው ነፍሰ ገዳዩ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።+ +6 አለዚያ በንዴት የበገነው* ደም ተበቃይ+ ከተማዋ ሩቅ ከመሆኗ የተነሳ ነፍሰ ገዳዩን አሳዶ ሊደርስበትና ሊገድለው ይችላል። ይሁን እንጂ ይህ ሰው ለባልንጀራው የቆየ ጥላቻ ስለሌለው መሞት አይገባውም።+ +7 ‘ሦስት ከተሞችን ለይ’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው። +8 “አምላክህ ይሖዋ ለአባቶችህ በማለላቸው መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህና+ ለእነሱ ለመስጠት ቃል የገባላቸውን ምድር በሙሉ ሲሰጥህ+ +9 ይኸውም አምላክህን ይሖዋን እንድትወድና ዘወትር በመንገዶቹ እንድትሄድ እኔ ዛሬ የማዝህን ይህን ትእዛዝ ሁሉ በመጠበቅህ+ ግዛትህን ሲያሰፋልህ ከእነዚህ ሦስት ከተሞች በተጨማሪ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትለያለህ።+ +10 ይህም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ንጹሕ ደም እንዳይፈስና+ በደም ዕዳ ተጠያቂ እንዳትሆን ነው።+ +11 “ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣+ አድብቶም ለሞት የሚያበቃ ጉዳት ቢያደርስበትና ሰውየው ቢሞት፣ ገዳዩም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ ቢሸሽ +12 የሚኖርበት ከተማ ሽማግሌዎች ሰውየውን ከዚያ በማስመጣት ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት፤ ይህ ሰው ሞት ይገባዋል።+ +13 አትዘንለት፤* መልካም እንዲሆንልህ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የሚመጣን በደል ከእስራኤል አስወግድ።+ +14 “አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ርስትህን በምትቀበልበት ጊዜ የቀድሞ አባቶችህ የከለሉትን ወሰን በማለፍ የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንካ።+ +15 “አንድ ሰው የትኛውንም ስህተት ወይም የትኛውንም ኃጢአት ቢፈጽም ግለሰቡን ጥፋተኛ ለማድረግ አንድ ምሥክር አይበቃም።+ ጉዳዩ የሚጸናው ሁለት ምሥክሮች ወይም ሦስት ምሥክሮች በሚሰጡት የምሥክርነት ቃል* ነው።+ +16 ተንኮል ያሰበ አንድ ምሥክር አንድን ግለሰብ የሆነ በደል ፈጽሟል በማለት ቢመሠክርበት+ +17 ክርክር የገጠሙት ሁለቱ ሰዎች በይሖዋ ፊት፣ በካህናቱና በዚያን ጊዜ ዳኛ ሆነው በሚያገ���ግሉት ሰዎች ፊት ይቆማሉ።+ +18 ዳኞቹም ጉዳዩን በጥንቃቄ ይመረምራሉ፤+ ምሥክሩ ሐሰተኛ ምሥክር ከሆነና ወንድሙን የወነጀለው በሐሰት ከሆነ +19 በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያቀደውን ነገር በራሱ ላይ አድርጉበት፤+ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+ +20 ሌሎችም ይህን ሲሰሙ ይፈራሉ፤ በመካከልህም እንዲህ ያለ መጥፎ ነገር ፈጽሞ ዳግመኛ አያደርጉም።+ +21 አዘኔታ አታሳይ፤+ ሕይወት* ስለ ሕይወት፣* ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፣ እጅ ስለ እጅ እንዲሁም እግር ስለ እግር ይሁን።+ +20 “ከጠላቶችህ ጋር ጦርነት ለመግጠም ብትሄድና ፈረሶቻቸው፣ ሠረገሎቻቸውና ሠራዊታቸው ከአንተ ይልቅ እጅግ ብዙ መሆናቸውን ብታይ አትፍራቸው፤ ምክንያቱም ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ነው።+ +2 ወደ ውጊያው ለመግባት በምትቀርቡበትም ጊዜ ካህኑ መጥቶ ሕዝቡን ማነጋገር አለበት።+ +3 እንዲህም ይበላቸው፦ ‘እስራኤላውያን ሆይ፣ ስሙ፤ እንግዲህ ዛሬ ከጠላቶቻችሁ ጋር ጦርነት ልትገጥሙ ነው። ልባችሁ አይራድ። በእነሱ ምክንያት አትፍሩ፣ አትሸበሩ ወይም አትንቀጥቀጡ፤ +4 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ ጠላቶቻችሁን ሊዋጋላችሁና ሊያድናችሁ አብሯችሁ ይወጣል።’+ +5 “አለቆቹም ሕዝቡን እንዲህ ይበሉ፦ ‘ከመካከላችሁ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለ? ወደ ቤቱ ይመለስ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ቤቱን ሌላ ሰው ሊያስመርቀው ይችላል። +6 ወይን ተክሎ ገና ከዚያ ያልበላ አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊበላው ይችላል። +7 አንዲት ሴት አጭቶ ገና ያላገባት ሰው አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።+ አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊያገባት ይችላል።’ +8 በተጨማሪም አለቆቹ ለሕዝቡ እንዲህ በማለት ይናገሩ፦ ‘ከመካከላችሁ የፈራና ልቡ የራደ አለ?+ ልክ እንደ ራሱ ልብ የወንድሞቹንም ልብ እንዳያቀልጥ+ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።’ +9 አለቆቹም ለሕዝቡ ተናግረው ሲጨርሱ ሕዝቡን እንዲመሩ የሠራዊቱን አለቆች ይሹሙ። +10 “አንዲትን ከተማ ለመውጋት ወደ እሷ ስትቀርብ ለከተማዋ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ።+ +11 ከተማዋ የሰላም ጥሪህን ከተቀበለችና በሯን ከከፈተችልህ ነዋሪዎቿ ሁሉ የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሕዝቦች ይሆኑልሃል፤ አንተንም ያገለግሉሃል።+ +12 ይሁን እንጂ የሰላም ጥሪህን ካልተቀበለችና ከአንተ ጋር ውጊያ ለመግጠም ከተነሳች ከተማዋን ክበባት፤ +13 አምላክህ ይሖዋ ከተማዋን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አንተም በውስጧ የሚኖሩትን ወንዶች ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው። +14 ሆኖም ሴቶቹን፣ ትናንሽ ልጆቹን፣ እንስሳቱንና በከተማዋ ውስጥ የተገኘውን ነገር ሁሉ ማርከህ ለራስህ መውሰድ ትችላለህ፤+ አምላክህ ይሖዋ በእጅህ አሳልፎ የሰጠህን ከጠላቶችህ ያገኘኸውን ምርኮም ትበላለህ።+ +15 “በአቅራቢያህ የሚገኙት ብሔራት ከተሞች ባልሆኑ ከአንተ ርቀው በሚገኙ ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርገው ይህንኑ ነው። +16 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ እነዚህ ሕዝቦች በሚኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ ግን እስትንፋስ ያለውን ማንኛውንም ነገር በሕይወት አታስቀር።+ +17 ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ሂታውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ሙሉ በሙሉ አጥፋ፤+ +18 ይህን የምታደርጉት ለአማልክታቸው የሚያደርጓቸውን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ እንዳያስተምሯችሁና በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንድትሠሩ እንዳያደርጓችሁ ነው።+ +19 “አንዲትን ከተማ ከበህ ከብዙ ቀናት ውጊያ በኋላ በቁጥጥርህ ሥር ብታውላት ዛፎቿን በመጥረቢያ አትጨፍጭፍ። ፍሬያቸውን ልትበላ ትችላለህ፤ ሆኖም አትቁረ��ቸው።+ ደግሞስ ሰው ይመስል የሜዳን ዛፍ ከበህ ማጥፋት አለብህ? +20 ለምግብነት እንደማይሆን የምታውቀውን ዛፍ ብቻ ማጥፋት ትችላለህ። ዛፉንም ቆርጠህ ከአንተ ጋር ውጊያ የገጠመችው ከተማ እስክትወድቅ ድረስ ዙሪያዋን ልታጥርበት ትችላለህ። +3 “ከዚያም ተመልሰን በባሳን መንገድ ወጣን። የባሳን ንጉሥ ኦግም ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በመሆን ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥመን ወጣ።+ +2 በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እሱንም ሆነ ሕዝቡን ሁሉ እንዲሁም ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ አትፍራው፤ አንተም በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግከው ሁሉ በእሱም ላይ ታደርግበታለህ።’ +3 ስለዚህ አምላካችን ይሖዋ የባሳንን ንጉሥ ኦግንና ሕዝቡን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም ከሕዝቡ መካከል አንድም ሰው ሳናስቀር ሁሉንም ደመሰስን። +4 ከዚያም ከተሞቹን በሙሉ ያዝን። ከእነሱ ያልወሰድነው አንድም ከተማ አልነበረም፤ በባሳን ባለው በኦግ መንግሥት ሥር የሚገኘውን የአርጎብን ክልል በሙሉ ይኸውም 60 ከተሞችን ወሰድን።+ +5 እነዚህ ከተሞች በሙሉ በረጃጅም ቅጥሮች የታጠሩ እንዲሁም በሮችና መቀርቀሪያዎች ያሏቸው ነበሩ፤ ከእነዚህም በተጨማሪ በጣም ብዙ የገጠር ከተሞች ነበሩ። +6 ሆኖም እያንዳንዱን ከተማ እንዲሁም ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን+ በማጥፋት በሃሽቦን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግነው ሁሉ እነዚህንም ሙሉ በሙሉ ደመሰስናቸው።+ +7 ከብቶቹንና ከየከተማው የማረክናቸውን ነገሮች ሁሉ ለራሳችን ወሰድን። +8 “በዚያን ጊዜም ከአርኖን ሸለቆ* አንስቶ እስከ ሄርሞን ተራራ+ ድረስ ባለው በዮርዳኖስ ክልል ከነበሩት ከሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት እጅ ምድራቸውን ወሰድን፤+ +9 (ሲዶናውያን የሄርሞንን ተራራ ሲሪዮን ብለው ሲጠሩት አሞራውያን ደግሞ ሰኒር ብለው ይጠሩት ነበር፤) +10 በባሳን ባለው በኦግ መንግሥት ሥር የሚገኙትን ከተሞች ይኸውም በአምባው ላይ የሚገኙትን ከተሞች በሙሉ፣ ጊልያድን በሙሉ፣ ባሳንን በሙሉ እስከ ሳልካ ድረስ እንዲሁም ኤድራይን+ ወሰድን። +11 ከረፋይም ወገን የተረፈው የባሳን ንጉሥ ኦግ ብቻ ነበር። ቃሬዛው እንኳ የብረት* ቃሬዛ* ነበር፤ አሁንም የአሞናውያን ከተማ በሆነችው በራባ ይገኛል። በሰው ክንድ* ሲለካ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ስፋቱ ደግሞ አራት ክንድ ነበር። +12 በዚያን ጊዜ ይህችን ምድር ወረስን፤ በአርኖን ሸለቆ* አጠገብ ከምትገኘው ከአሮዔር+ አንስቶ ያለውን ምድር እንዲሁም የጊልያድን ተራራማ አካባቢ እኩሌታ ከነከተሞቹ ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው።+ +13 የቀረውን የጊልያድን ክፍልና በኦግ ግዛት ሥር ያለውን ባሳንን በሙሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ።+ የባሳን ይዞታ የሆነው የአርጎብ አካባቢ በሙሉ የረፋይም ምድር ተብሎ ይጠራ ነበር። +14 “የምናሴ ልጅ ያኢር+ የአርጎብን ክልል+ በሙሉ እስከ ገሹራውያን እና እስከ ማአካታውያን+ ወሰን ድረስ ያለውን ወሰደ፤ በባሳን የሚገኙትን እነዚህን መንደሮች በራሱ ስም ሃዎትያኢር*+ ብሎ ሰየማቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሚጠሩት በዚህ ስም ነው። +15 ጊልያድን ደግሞ ለማኪር ሰጠሁት።+ +16 ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን+ የአርኖንን ሸለቆ* መሃል ወሰን በማድረግ ከጊልያድ አንስቶ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ እንዲሁም የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው ሸለቆ ማለትም እስከ ያቦቅ ድረስ ሰጠኋቸው፤ +17 እንዲሁም ከኪኔሬት አንስቶ በአረባ እስከሚገኘው ባሕር ይኸውም በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በጲስጋ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ ጨው ባሕር* ድረስ ያለውን አረባን፣ ዮርዳኖስንና ወሰኑን ሰጠኋቸው።+ +18 “ከዚያም ይህን ትእዛዝ ሰጠኋችሁ፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ ይህችን ም��ር ርስት አድርጋችሁ እንድትወርሷት ሰጥቷችኋል። ብርቱ የሆናችሁት ወንዶች ሁሉ የጦር መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ በእስራኤላውያን ፊት ትሻገራላችሁ።+ +19 ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ (መቼም ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁ አውቃለሁ) በሰጠኋችሁ ከተሞች ውስጥ ይቀራሉ፤ +20 ይህም ይሖዋ ልክ ለእናንተ እንዳደረገላችሁ ሁሉ ለወንድሞቻችሁም እረፍት እስኪሰጣቸው እንዲሁም አምላካችሁ ይሖዋ ከዮርዳኖስ ማዶ የሚሰጣቸውን ምድር ርስት አድርገው እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚያ በኋላ እያንዳንዳችሁ ወደሰጠኋችሁ ወደየራሳችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።’+ +21 “በዚያን ጊዜ ለኢያሱ ይህን ትእዛዝ ሰጠሁት፦+ ‘አምላክህ ይሖዋ በእነዚህ ሁለት ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ በገዛ ዓይንህ አይተሃል። ይሖዋ አልፈሃቸው በምትሄደው መንግሥታት ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋል።+ +22 ስለ እናንተ የሚዋጋው+ አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው።’ +23 “እኔም በዚያን ጊዜ ይሖዋን እንዲህ በማለት ተማጸንኩት፦ +24 ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህ ታላቅነትህንና ብርቱ ክንድህን እንዲያይ አድርገሃል፤+ አንተ እንደምታደርጋቸው ያሉ ታላላቅ ነገሮችን መፈጸም የሚችለው በሰማይም ሆነ በምድር ያለ የትኛው አምላክ ነው?+ +25 እባክህ ከዮርዳኖስ ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር፣ አዎ ውብ የሆነችውን ይህችን ተራራማ አካባቢና ሊባኖስን ተሻግሬ እንዳይ ፍቀድልኝ።’+ +26 ይሖዋ ግን በእናንተ የተነሳ በጣም ተቆጥቶኝ ስለነበር+ አልሰማኝም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘በቃ! ዳግመኛ ስለዚህ ጉዳይ እንዳታነሳብኝ። +27 ይህን ዮርዳኖስን ስለማትሻገር ወደ ጲስጋ አናት ውጣና+ ዓይንህን አቅንተህ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ ተመልከት።+ +28 በዚህ ሕዝብ ፊት የሚሻገረውም+ ሆነ አንተ ያየሃትን ምድር እንዲወርሱ የሚያደርገው ኢያሱ ስለሆነ እሱን መሪ አድርገህ ሹመው፤+ አደፋፍረው፤ አበረታታውም።’ +29 ይህ ሁሉ የሆነው በቤትጰኦር+ ፊት ለፊት በሚገኘው ሸለቆ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ነው። +24 “አንድ ሰው አንዲት ሴት ቢያገባ ሆኖም ነውር የሆነ ነገር አግኝቶባት ቅር ቢሰኝ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት+ ከቤቱ ያሰናብታት።+ +2 እሷም ከእሱ ቤት ከወጣች በኋላ የሌላ ሰው ሚስት መሆን ትችላለች።+ +3 በኋላ ያገባትም ሰው ቢጠላትና የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ቢያሰናብታት ወይም አግብቷት የነበረው ሁለተኛው ሰው ቢሞት +4 ከቤቱ አሰናብቷት የነበረው የመጀመሪያው ባለቤቷ ከረከሰች በኋላ እንደገና ሚስቱ አድርጎ እንዲወስዳት አይፈቀድለትም፤ ምክንያቱም ይህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ። +5 “አንድ ሰው አዲስ ሙሽራ ከሆነ በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የለበትም፤ ወይም ምንም ዓይነት ሌላ ሥራ ሊሰጠው አይገባም። ለአንድ ዓመት ያህል ከምንም ነገር ነፃ ሆኖ ይቆይ፤ በቤቱም ተቀምጦ ሚስቱን ያስደስታት።+ +6 “ማንም ሰው ወፍጮን ወይም መጅን የብድር መያዣ አድርጎ መውሰድ የለበትም፤ ምክንያቱም የሰውየውን መተዳደሪያ* መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆንበታል።+ +7 “አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ መካከል አንዱን አፍኖ በመውሰድ በደል ሲፈጽምበትና ሲሸጠው+ ቢገኝ አፍኖ የወሰደው ሰው ይገደል።+ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+ +8 “የሥጋ ደዌ* ቢከሰት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጧችሁን መመሪያዎች ሁሉ በጥንቃቄ ተከተሉ።+ እኔ የሰጠኋቸውንም ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽሙ። +9 ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አምላካችሁ ይሖዋ በሚርያም ላይ ያደረገውን አስታውሱ።+ +10 ���ለባልንጀራህ ማንኛውንም ነገር ብታበድር+ መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ለመውሰድ ወደ ቤቱ አትግባ። +11 ውጭ ቆመህ ጠብቅ፤ ያበደርከውም ሰው መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ውጭ ድረስ ያምጣልህ። +12 ሰውየው ከተቸገረ መያዣ አድርጎ የሰጠህን ነገር አንተ ጋ አታሳድር።+ +13 ልክ ፀሐይ ስትጠልቅ መያዣውን ልትመልስለት ይገባል፤ እሱም ለብሶት ይተኛል፤+ ደግሞም ይባርክሃል፤ በአምላክህም በይሖዋ ፊት እንደ ጽድቅ ይቆጠርልሃል። +14 “ከወንድሞችህም ሆነ በምድርህ ይኸውም በከተሞችህ* ውስጥ ከሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች መካከል የተቸገረውንና ድሃ የሆነውን ቅጥር ሠራተኛ አታታል።+ +15 ደሞዙን በዕለቱ ስጠው፤+ ችግረኛ በመሆኑና ሕይወቱ* የተመካው በደሞዙ ላይ ስለሆነ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ስጠው። አለዚያ በአንተ የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻል፤ አንተም በኃጢአት ትጠየቃለህ።+ +16 “አባቶች ልጆቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም አባቶቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም።+ አንድ ሰው መገደል ያለበት በገዛ ኃጢአቱ ብቻ ነው።+ +17 “የባዕድ አገሩን ሰው ወይም አባት የሌለውን* ልጅ ፍርድ አታዛባ፤+ የመበለቲቱን ልብስ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ።+ +18 አንተም በግብፅ ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ ከዚያ እንደተቤዠህ አስታውስ።+ እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው። +19 “በማሳህ ላይ ያለውን እህል በምታጭድበት ጊዜ በማሳው ላይ ነዶ ብትረሳ ያን ለመውሰድ አትመለስ። አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ እንዲሆን እዚያው ተወው።+ +20 “የወይራ ዛፍህን በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ሙልጭ አድርገህ አታራግፈው። የቀረው ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ ይሁን።+ +21 “ከወይን እርሻህ ላይ የወይን ፍሬህን በምትሰበስብበት ጊዜ ተመልሰህ ቃርሚያውን አትልቀም። ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ መተው አለበት። +22 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክ አስታውስ። እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው። +32 “ሰማያት ሆይ፣ ጆሯችሁን ስጡኝ፤ እኔም እናገራለሁ፤ምድርም የአፌን ቃል ትስማ። + 2 ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይወርዳል፤ካፊያ ሣር ላይ እንደሚወርድ፣የሚያረሰርስ ዝናብም ተክልን እንደሚያጠጣ፣ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠባል። + 3 የይሖዋን ስም አውጃለሁና።+ ስለ አምላካችን ታላቅነት ተናገሩ!+ + 4 እሱ ዓለት፣ የሚያደርገውም ነገር ሁሉ ፍጹም ነው፤+መንገዶቹ ሁሉ ፍትሕ ናቸውና።+ እሱ ፈጽሞ ፍትሕን የማያጓድል+ ታማኝ+ አምላክ ነው፤ጻድቅና ትክክለኛ ነው።+ + 5 ምግባረ ብልሹ የሆኑት እነሱ ናቸው።+ ልጆቹ አይደሉም፤ ጉድለቱ የራሳቸው ነው።+ ጠማማና ወልጋዳ ትውልድ ናቸው!+ + 6 እናንተ ሞኞችና ጥበብ የጎደላችሁ ሰዎች ሆይ፣+በይሖዋ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋላችሁ?+ ወደ ሕልውና ያመጣህ አባትህ እሱ አይደለም?+የሠራህና አጽንቶ ያቆመህስ እሱ አይደለም? + 7 የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤ያለፉት ትውልዶች የኖሩባቸውን ዓመታት መለስ ብለህ አስብ። አባትህን ጠይቅ፤ ሊነግርህ ይችላል፤+ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ይነግሩሃል። + 8 ልዑሉ ለብሔራት ርስታቸውን ሲሰጥ፣+የአዳምን ልጆች* አንዱን ከሌላው ሲለያይ፣+በእስራኤል ልጆች ቁጥር ልክ+የሕዝቦችን ወሰን ደነገገ።+ + 9 የይሖዋ ሕዝብ ድርሻው ነው፤+ያዕቆብ ርስቱ ነው።+ +10 እሱን ምድረ በዳ በሆነ ምድር፣+ነፋስ በሚያፏጭበት ጭው ያለ በረሃ አገኘው።+ ሊጠብቀውም ዙሪያውን ከበበው፤ ተንከባከበው፤+እንደ ዓይኑም ብሌን ጠበቀው።+ +11 ንስር ጎጆዋን እንደም���ነቀንቅናከጫጩቶቿ በላይ እንደምታንዣብብ፣ክንፎቿን ዘርግታ እንደምትይዛቸው፣በላባዎቿም እንደምትሸከማቸው ሁሉ+ +12 ይሖዋ ብቻውን መራው፤*+ከእሱም ጋር ምንም ባዕድ አምላክ አልነበረም።+ +13 በምድር ላይ በሚገኙ ከፍ ያሉ ቦታዎች እንዲሄድ አደረገው፤+ስለሆነም የእርሻውን ምርት በላ።+ ከዓለት ማር አበላው፤ከባልጩትም ዘይት መገበው፤ +14 የላሞቹን ቅቤና የመንጋውን ወተትምርጥ ከሆነው በግ* ጋር ሰጠው፤የባሳንን አውራ በጎችና አውራ ፍየሎችከምርጥ ስንዴ* ጋር ሰጠው፤+አንተም ከወይን ፍሬው ደም* የወይን ጠጅ ጠጣህ። +15 የሹሩን* ሲወፍር በዓመፀኝነት ተራገጠ። ሰባህ፤ ፈረጠምክ፤ ደለብክ።+ ስለሆነም የሠራውን አምላክ ተወ፤+አዳኝ የሆነለትን ዓለት ናቀ። +16 በባዕዳን አማልክት አስቆጡት፤+በአስጸያፊ ነገሮችም አሳዘኑት።+ +17 ለአምላክ ሳይሆን ለአጋንንት፣+ለማያውቋቸው አማልክት፣በቅርቡ ለተነሱ ለአዲሶች፣አባቶቻችሁ ለማያውቋቸው አማልክት ይሠዉ ነበር። +18 አባት የሆነህን ዓለት ረሳኸው፤+የወለደህንም አምላክ አላስታወስክም።+ +19 ይሖዋ ይህን ሲያይ ተዋቸው፤+ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ አሳዝነውት ነበርና። +20 ስለዚህ እንዲህ አለ፦ ‘ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ፤+ምን እንደሚሆኑም አያለሁ። ምክንያቱም እነሱ ጠማማ ትውልድ ናቸው፤+ታማኝነት የሚባል ነገር የማያውቁ ልጆች ናቸው።+ +21 እነሱ አምላክ ባልሆነው አስቆጡኝ፤+ከንቱ በሆኑ ጣዖቶቻቸው አሳዘኑኝ።+ በመሆኑም እኔ ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤+ሞኝ በሆነ ብሔር አበሳጫቸዋለሁ።+ +22 ምክንያቱም ቁጣዬ እሳት አቀጣጥሏል፤+እሱም እስከ መቃብር* ጥልቀት ድረስ ዘልቆ ይነድዳል፤+ምድርንና ምርቷን ይበላል፤የተራሮችንም መሠረት ያቃጥላል። +23 መከራቸውን አበዛዋለሁ፤ቀስቶቼን በእነሱ ላይ እጨርሳለሁ። +24 በረሃብ ይዳከማሉ፤+በሚያቃጥል ትኩሳትና በመራራ ጥፋት ይበላሉ።+ የአራዊትን ጥርስ፣በምድር ላይ የሚሳቡ እንስሳትንም መርዝ እልክባቸዋለሁ።+ +25 ወጣቱንም ሆነ ልጃገረዲቱን፣ጨቅላውንም ሆነ ሽማግሌውን፣+በውጭ፣ ሰይፍ ለሐዘን ይዳርጋቸዋል፤+በቤት ውስጥ ደግሞ ሽብር አለ።+ +26 እኔም “እበትናቸዋለሁ፤መታሰቢያቸውም ከሰዎች ዘንድ እንዲጠፋ አደርጋለሁ” ባልኩ ነበር፤ +27 ነገር ግን የጠላትን ምላሽ ፈራሁ፤+ምክንያቱም ባላጋራዎቼ በተሳሳተ መንገድ ሊረዱት ይችላሉ።+ “ክንዳችን የበላይ ሆነ፤+ይህን ሁሉ ያደረገው ይሖዋ አይደለም” ሊሉ ይችላሉ። +28 እነሱ ማመዛዘን የጎደለው* ብሔር ናቸው፤በመካከላቸውም ማስተዋል የሚባል ነገር የለም።+ +29 ምነው ጥበበኛ በሆኑ ኖሮ!+ ይህን ሁሉ ያሰላስሉ ነበር።+ የሚደርስባቸውንም ያስቡ ነበር።+ +"30 ዓለታቸው ካልሸጣቸውና+ይሖዋ ለምርኮ ካልዳረጋቸው በስተቀር አንድ ሰው 1,000 ሊያሳድድ፣ሁለት ሰው ደግሞ 10,000 ሊያባርር እንዴት ይችላል?+ " +31 የእነሱ ዓለት እንደ እኛ ዓለት አይደለም፤+ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን ተረድተዋል።+ +32 ወይናቸው ከሰዶም የወይን ተክልናከገሞራ የእርሻ ቦታ የተገኘ ነው።+ የወይን ፍሬያቸው መርዛማ የወይን ፍሬ ነው፤ዘለላቸው መራራ ነው።+ +33 የወይን ጠጃቸው የእባቦች መርዝ፣የጉበናም* ምሕረት የለሽ መርዝ ነው። +34 ይህ እኔ ጋ ያለ፣በግምጃ ቤቴ ውስጥ ማኅተም ታትሞበት የተቀመጠ አይደለም?+ +35 በቀልም ሆነ ቅጣት የእኔ ነው፤+አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ እግራቸው ይከዳቸዋል፤+የሚጠፉበት ቀን ቀርቧልና፤የሚጠብቃቸውም ነገር በፍጥነት ይመጣል።’ +36 ይሖዋ ሕዝቡን ይዳኛል፤+አገልጋዮቹ አቅም እንዳነሳቸው፣ረዳት የለሽና ደካማ የሆኑት ብቻ እንደቀሩ ሲያይለእነሱ ያዝንላቸዋል።*+ +37 ከዚያም እንዲህ ይላል፦ ‘አማልክታቸው የት አሉ?+መሸሸጊያ እንዲሆናቸው የተጠጉት ዓለትስ የት አለ? +38 የመሥዋዕቶቻቸውን ስብ* ይበላ፣የመጠጥ መባዎቻቸውንም የወይን ጠጅ ይጠጣ የነበረው የት አለ?+ እስቲ ተነስተው ይርዷችሁ። እስቲ መሸሸጊያ ስፍራ ይሁኑላችሁ። +39 እንግዲህ እኔ እሱ እንደሆንኩ እዩ፤+ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት የሉም።+ እኔ እገድላለሁ፤ እኔ ሕያው አደርጋለሁ።+ እኔ አቆስላለሁ፤+ እኔው እፈውሳለሁ፤+ከእጄም ማዳን የሚችል የለም።+ +40 እጄን ወደ ሰማይ አንስቼ፣“በዘላለማዊ ሕያውነቴ” ብዬ እምላለሁ፤+ +41 የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ከሳልኩናእጄን ለፍርድ ካዘጋጀሁ፣+ተቃዋሚዎቼን እበቀላለሁ፤+የሚጠሉኝንም እቀጣለሁ። +42 በታረዱና በተማረኩ ሰዎች ደም፣በጠላት መሪዎች ራስ፣ቀስቶቼን በደም አሰክራለሁ፤ሰይፌም ሥጋ ይበላል።’ +43 እናንተ ብሔራት ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤+እሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳልና፤+ተቃዋሚዎቹንም ይበቀላል፤+ለሕዝቡም ምድር ያስተሰርይለታል።”* +44 ሙሴም ከነዌ ልጅ ከሆሺአ*+ ጋር መጥቶ የዚህን መዝሙር ቃላት በሙሉ ሕዝቡ እየሰማ ተናገረ።+ +45 ሙሴ እነዚህን ቃላት በሙሉ ለመላው እስራኤል ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ +46 እንዲህ አላቸው፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዟቸው+ እኔ በዛሬው ዕለት እናንተን ለማስጠንቀቅ የምነግራችሁን ቃል ሁሉ ልብ በሉ።+ +47 ይህ ቃል ለእናንተ ሕይወታችሁ እንጂ እንዲሁ ባዶ ቃል አይደለም፤+ ይህ ቃል ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁን ሊያረዝምላችሁ ይችላል።” +48 ይሖዋ በዚያው ዕለት ሙሴን እንዲህ አለው፦ +49 “በኢያሪኮ ትይዩ በሞዓብ ምድር ወደሚገኘው ወደዚህ የአባሪም ተራራ+ ይኸውም ወደ ነቦ ተራራ+ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነአንን ምድር ተመልከት።+ +50 ወንድምህ አሮን በሆር ተራራ ላይ ሞቶ+ ወደ ወገኖቹ እንደተሰበሰበ* ሁሉ አንተም በምትወጣበት በዚህ ተራራ ላይ ትሞታለህ፤ ወደ ወገኖችህም ትሰበሰባለህ፤ +51 ምክንያቱም ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ በሚገኘው በቃዴስ፣ በመሪባ ውኃዎች+ አጠገብ በእስራኤላውያን መካከል ለእኔ ታማኝ ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ እንዲሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት እኔን አልቀደሳችሁኝም።+ +52 ምድሪቱን ከሩቅ ታያታለህ፤ ሆኖም ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።”+ +7 “አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ ወደምትወርሳት ምድር ሲያመጣህ+ ብዙ ሕዝብ ያላቸውን ብሔራት ይኸውም ከአንተ ይልቅ ብዙ ሕዝብ ያላቸውንና ኃያላን የሆኑትን ሰባት ብሔራት+ ማለትም ሂታውያንን፣ ገርጌሻውያንን፣ አሞራውያንን፣+ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንን እና ኢያቡሳውያንን+ ከፊትህ ያስወግድል +2 አምላክህ ይሖዋ እነሱን አሳልፎ ይሰጥሃል፤ ድልም ታደርጋቸዋለህ።+ አንተም ሙሉ በሙሉ ደምስሳቸው።+ ከእነሱ ጋር ምንም ዓይነት ቃል ኪዳን አትጋባ፤ አትራራላቸውም።+ +3 ከእነሱ ጋር በጋብቻ አትዛመድ። ሴቶች ልጆችህን ለወንዶች ልጆቻቸው አትዳር ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆችህ አትውሰድ።+ +4 ምክንያቱም ልጆችህ ሌሎች አማልክትን ያገለግሉ ዘንድ እኔን ከመከተል ዞር እንዲሉ ያደርጓቸዋል፤+ ከዚያም የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ አንተንም ወዲያው ያጠፋሃል።+ +5 “ከዚህ ይልቅ እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ሰባብሩ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ቆራርጡ፤+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።+ +6 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ* እንድትሆን መርጦሃል።+ +7 “ይሖዋ እናንተን የወደዳችሁና የመረጣችሁ+ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ይልቅ ቁጥራችሁ ስለበዛ አይደለም፤ ቁጥራችሁማ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ አነስተኛ ነበር።+ +8 ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እናንተን ከባርነት ቤት ይኸውም ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ ይታደጋችሁ ዘንድ ይሖዋ በብርቱ እጅ ያወጣችሁ+ ስለወደዳችሁና ለአባቶቻችሁ የማለላቸውን መሐላ ስለጠበቀ ነው።+ +9 አንተም አምላክህ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ፣ ታማኝ አምላክ እንዲሁም ለሚወዱትና ትእዛዛቱን ለሚጠብቁ ሁሉ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ መሆኑን በሚገባ ታውቃለህ።+ +10 የሚጠሉትን ግን በማጥፋት በግልጽ ይበቀላቸዋል።+ በሚጠሉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ አይዘገይም፤ በግልጽ ይበቀላቸዋል። +11 ስለዚህ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች በማክበር በጥንቃቄ ጠብቃቸው። +12 “እነዚህን ድንጋጌዎች ብትሰሙና ብትጠብቋቸው እንዲሁም ብትፈጽሟቸው አምላካችሁ ይሖዋ ለአባቶቻችሁ በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳንና ታማኝ ፍቅር ይጠብቃል። +13 ይወድሃል፣ ይባርክሃል እንዲሁም ያበዛሃል። አዎ፣ ለአንተ ሊሰጥህ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር ላይ የሆድህን ፍሬ፣+ የመሬትህን ምርት፣ እህልህን፣ አዲሱን የወይን ጠጅህን፣ ዘይትህን፣+ የከብቶችህን ጥጆችና የመንጋህን ግልገሎች ይባርክልሃል።+ +14 አንተም ከሕዝቦች ሁሉ ይበልጥ የተባረክ ትሆናለህ፤+ በመካከልህ ልጅ የሌለው ወንድ ወይም ሴት አይገኝም፤ እንስሶችህም ግልገል የሌላቸው አይሆኑም።+ +15 ይሖዋ በሽታን ሁሉ ያስወግድልሃል፤ በግብፅ ሳለህ ታውቃቸው ከነበሩት አሰቃቂ በሽታዎች አንዱንም በአንተ ላይ አያመጣም።+ ከዚህ ይልቅ በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል። +16 አምላክህ ይሖዋ አሳልፎ የሚሰጥህን ሕዝቦች ሁሉ ታጠፋለህ።+ አትዘንላቸው፤*+ አማልክታቸውንም አታገልግል፤+ ምክንያቱም እንዲህ ማድረግህ ወጥመድ ይሆንብሃል።+ +17 “ምናልባት በልብህ ‘እነዚህ ብሔራት እኮ ከእኛ ይልቅ ብዙ ናቸው። ታዲያ እንዴት ላባርራቸው እችላለሁ?’ ትል ይሆናል፤+ +18 ሆኖም አትፍራቸው።+ አምላክህ ይሖዋ በፈርዖንና በግብፅ ሁሉ ላይ ያደረገውን አስታውስ፤+ +19 ዓይኖችህ ያዩአቸውን ታላላቅ የፍርድ እርምጃዎች* እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ አንተን ለማውጣት የተጠቀመባቸውን ድንቅ ምልክቶች፣ ተአምራት፣+ ብርቱ እጅና የተዘረጋ ክንድ አስብ።+ አምላክህ ይሖዋ በምትፈራቸው ሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚያደርገው ይህንኑ ነው።+ +20 አምላክህ ይሖዋ በሕይወት የተረፉትና ከፊትህ የተሸሸጉት እስኪጠፉ ድረስ ጭንቀት* ይለቅባቸዋል።+ +21 ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ+ የሆነው አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለሆነ+ በእነሱ የተነሳ አትሸበር። +22 “አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት በጥቂት በጥቂቱ ከፊትህ ያባርራቸዋል።+ የዱር አራዊት እንዳይበዙብህ በአንድ ጊዜ ጠራርገህ እንድታጠፋቸው አይፈቀድልህም። +23 አምላክህ ይሖዋ እነሱን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ እስኪጠፉም ድረስ ሙሉ በሙሉ ድል ታደርጋቸዋለህ።+ +24 እሱም ነገሥታታቸውን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤+ አንተም ስማቸውን ከሰማይ በታች ትደመስሳለህ።+ ድምጥማጣቸውን እስክታጠፋ+ ድረስ ማንም አይቋቋምህም።+ +25 የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች በእሳት አቃጥሉ።+ ወጥመድ ሊሆንብህ ስለሚችል በእነሱ ላይ ያለውን ብርም ሆነ ወርቅ አትመኝ ወይም ለራስህ አትውሰድ፤+ ምክንያቱም ይህ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነገር ነው።+ +26 አስጸያፊ ነገር ወደ ቤትህ በማምጣት ልክ እንደ እሱ ራስህን ለጥፋት አትዳርግ። ለጥፋት የተለየ ነገር ስለሆነ ፈጽመህ ጥላው፤ ሙሉ በሙሉም ተጸየፈው። +12 ���የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ እንድትወርሷት በሚሰጣችሁ ምድር ላይ በሕይወት በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ በጥንቃቄ ልትፈጽሟቸው የሚገቡ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው። +2 ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩባቸው የነበሩትን ቦታዎች በሙሉ፣ በረጃጅም ተራሮችም ሆነ በኮረብቶች ላይ ወይም በተንዠረገጉ ዛፎች ሥር ያሉትን ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ አጥፉ።+ +3 መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም* በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤+ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።+ +4 “እነሱ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት መንገድ አምላካችሁን ይሖዋን አታምልኩ።+ +5 ከዚህ ይልቅ በነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ስሙን ሊያጸናበትና ማደሪያ ስፍራው ሊያደርገው በሚመርጠው በማንኛውም ቦታ አምላካችሁን ይሖዋን ፈልጉ፤ ወደዚያም ስፍራ ሂዱ።+ +6 የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣+ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣+ ከእጃችሁ የሚዋጣውን መዋጮ፣+ የስእለት መባዎቻችሁን፣ የፈቃደኝነት መባዎቻችሁን+ እንዲሁም የከብታችሁንና የመንጋችሁን በኩራት+ የምትወስዱት ወደዚያ ስፍራ ነው። +7 እናንተም ሆናችሁ ቤተሰቦቻችሁ በዚያ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ብሉ፤+ አምላካችሁ ይሖዋ ስለባረካችሁ በሥራችሁ ሁሉ ተደሰቱ።+ +8 “ዛሬ እዚህ እያደረግን እንዳለነው እያንዳንዳችሁ በራሳችሁ አመለካከት ትክክል መስሎ የታያችሁን ማድረግ የለባችሁም፤ +9 ምክንያቱም አሁን ይህን የምታደርጉት ወደምታርፉበት ቦታና+ አምላካችሁ ይሖዋ ወደሚሰጣችሁ ርስት ገና ስላልገባችሁ ነው። +10 ዮርዳኖስን በምትሻገሩበትና+ አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ በዙሪያችሁ ካሉ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ያሳርፋችኋል፤ እናንተም ያለስጋት ትቀመጣላችሁ።+ +11 የማዛችሁንም ነገር በሙሉ ይኸውም የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣+ የእጃችሁን መዋጮና ለይሖዋ የተሳላችሁትን ማንኛውንም የስእለት መባ አምላካችሁ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ታመጣላችሁ።+ +12 እናንተ፣ ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ሴቶች ልጆቻችሁ፣ ወንድ ባሪያዎቻችሁ፣ ሴት ባሪያዎቻችሁ እንዲሁም በከተሞቻችሁ* ውስጥ የሚኖሩ ሌዋውያን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ትደሰታላችሁ፤+ ምክንያቱም ሌዋውያኑ በእናንተ መካከል ድርሻም ሆነ ውርሻ የላቸውም።+ +13 የሚቃጠሉ መባዎችህን በፈለግከው በየትኛውም ቦታ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ።+ +14 ከዚህ ይልቅ የሚቃጠሉ መባዎችህን ይሖዋ በሚመርጠው የነገዶችህ ይዞታ በሆነው ቦታ ብቻ አቅርብ፤ በዚያም እኔ የማዝህን ነገር ሁሉ አድርግ።+ +15 “አምላክህ ይሖዋ በሰጠህ በረከት መጠን በከተሞችህ ሁሉ* አንተን ባሰኘህ* በማንኛውም ጊዜ እንስሳትን አርደህ ሥጋ መብላት ትችላለህ።+ የሜዳ ፍየልና ርኤም* እንደምትበላ ሁሉ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል። +16 ደሙን ግን እንዳትበሉ፤+ ከዚህ ይልቅ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍሱት።+ +17 የእህልህን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አንድ አሥረኛ፣ የከብትህንና የመንጋህን በኩር፣+ የምትሳለውን ማንኛውንም የስእለት መባ፣ የፈቃደኝነት መባዎችህን ወይም የእጅህን መዋጮ በከተሞችህ* ውስጥ እንድትበላ አይፈቀድልህም። +18 እነዚህንም አንተ፣ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህ፣ ሴት አገልጋይህ እንዲሁም በከተሞችህ* የሚኖሩ ሌዋውያን አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ+ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትበሏቸዋላችሁ፤ አንተም በሥራህ ሁሉ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትደሰታለህ። +19 በምድርህ ላይ በሕይወት እስካለህ ድረስ ሌዋውያንን ቸል እንዳትል ተጠንቀቅ።+ +20 “አምላክህ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት+ ግዛትህን በሚያሰፋልህ ጊዜ+ ሥጋ መብላት ፈልገህ* ‘ሥጋ አማረኝ’ ብትል ባሰኘህ* ጊዜ ሁሉ ሥጋ ብላ።+ +21 አምላክህ ይሖዋ ስሙ እንዲኖርበት የሚመርጠው ስፍራ+ አንተ ካለህበት የራቀ ከሆነ ይሖዋ ከሰጠህ ከከብትህ ወይም ከመንጋህ መካከል እኔ ባዘዝኩህ መሠረት አርደህ ባሰኘህ* ጊዜ ሁሉ በከተሞችህ* ውስጥ ብላ። +22 የሜዳ ፍየልንና ርኤምን እንደምትበላው ሁሉ ይህንም ልትበላው ትችላለህ፤+ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል። +23 ብቻ ደሙን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ፤+ ምክንያቱም ደም ሕይወት* ነው፤+ ሕይወትን* ደግሞ ከሥጋ ጋር መብላት የለብህም። +24 ደሙን ፈጽሞ እንዳትበላ። ከዚህ ይልቅ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍስሰው።+ +25 ደሙን አትብላ፤ ምክንያቱም እንዲህ ስታደርግ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ትፈጽማለህ፤ ይህን የምታደርገው ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ ነው። +26 ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ስትመጣ የአንተ የሆኑትን ቅዱስ ነገሮችና የስእለት መባዎችህን ብቻ መያዝ ይኖርብሃል። +27 የሚቃጠሉ መባዎችህን፣ ሥጋውንና ደሙን+ በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ላይ ታቀርባለህ፤ የመሥዋዕቶችህም ደም በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ላይ መፍሰስ ይኖርበታል፤+ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ። +28 “እኔ የማዝህን እነዚህን ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም፤ ምክንያቱም እንዲህ ስታደርግ በአምላክህ በይሖዋ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ትፈጽማለህ፤ ይህን የምታደርገው ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ምንጊዜም መልካም እንዲሆንላችሁ ነው። +29 “ከምድራቸው የምታስለቅቃቸውን ብሔራት አምላክህ ይሖዋ ሲያጠፋቸውና+ በምድራቸው ላይ ስትኖር +30 እነሱ ከጠፉ በኋላ በእነሱ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ። ‘እነዚህ ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩ የነበረው እንዴት ነው? ቆይ እኔም እንደ እነሱ አደርጋለሁ’ ብለህ ስለ አማልክታቸው አትጠይቅ።+ +31 አንተ በአምላክህ በይሖዋ ላይ ይህን ማድረግ የለብህም፤ ምክንያቱም እነሱ ይሖዋ የሚጠላውን አስጸያፊ ነገር ሁሉ ለአማልክታቸው ያደርጋሉ፤ ሌላው ቀርቶ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአማልክታቸው በእሳት ያቃጥላሉ።+ +32 እናንተ እኔ የማዛችሁን እያንዳንዱን ነገር በጥንቃቄ ፈጽሙ።+ በእሱ ላይ ምንም አትጨምሩ፤ ከእሱም ላይ ምንም አትቀንሱ።+ +1 ሙሴ በዮርዳኖስ ክልል በሚገኘው ምድረ በዳ ይኸውም በፋራን፣ በጦፌል፣ በላባ፣ በሃጼሮት እና በዲዛሃብ መካከል ከሚገኘው ከሱፈ ፊት ለፊት ባለው በረሃማ ሜዳ ላይ ለነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ የተናገረው ቃል ይህ ነው። +2 ወደ ሴይር ተራራ በሚወስደው መንገድ በኩል ከኮሬብ እስከ ቃዴስበርኔ+ የ11 ቀን መንገድ ነው። +3 በ40ኛው ዓመት፣+ በ11ኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሙሴ ለእስራኤላውያን* እንዲነግራቸው ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ነገራቸው። +4 ይህን ያደረገው በሃሽቦን ይኖር የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን+ ድል ካደረገና በአስታሮት ይኖር የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ኦግን+ ኤድራይ+ ላይ* ካሸነፈ በኋላ ነው። +5 በዮርዳኖስ ክልል፣ በሞዓብ ምድር ሙሴ ይህን ሕግ እንዲህ በማለት ያብራራ ጀመር፦+ +6 “ይሖዋ አምላካችን በኮሬብ እንዲህ አለን፦ ‘በዚህ ተራራማ አካባቢ ለረጅም ጊዜ ቆይታችኋል።+ +7 ተነስታችሁ ወደ አሞራውያን+ ተራራማ አካባቢ እንዲሁም በአረባ፣+ በተራራማው አካባቢ፣ በሸፌላ፣ በኔጌብ እና በባሕሩ ዳርቻ+ ወደሚገኙት ጎረቤቶቻቸው ሁሉ ብሎም ወደ ከነአናውያን ምድርና ወደ ሊባኖስ*+ በመጓዝ እስከ ታላቁ ወንዝ ማለትም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ+ ድረስ ሂዱ። +8 እነሆ በፊታችሁ ይህችን ምድር አስቀምጫለሁ። ይሖዋ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና+ ለያዕቆብ+ እንዲሁም ከእነሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቻቸው ሊሰጣቸው የማለላቸውን ምድር+ ገብታችሁ ውረሱ።’ +9 “እኔም በዚያን ጊዜ እንዲህ አልኳችሁ፦ ‘እኔ ብቻዬን እናንተን ልሸከማችሁ አልችልም።+ +10 ይሖዋ አምላካችሁ ቁጥራችሁን አብዝቶታል፤ ይኸው ዛሬ ከብዛታችሁ የተነሳ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት ሆናችኋል።+ +11 የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ ሺህ ጊዜ ያብዛችሁ፤+ ደግሞም በገባላችሁ ቃል መሠረት ይባርካችሁ።+ +12 ይሁንና እኔ ብቻዬን የእናንተን ሸክምና ጫና እንዲሁም ጠብ እንዴት መሸከም እችላለሁ?+ +13 ከየነገዶቻችሁ ጥበበኛና አስተዋይ የሆኑ እንዲሁም ተሞክሮ ያካበቱ ወንዶችን ምረጡ፤ እኔም በእናንተ ላይ መሪ አድርጌ እሾማቸዋለሁ።’+ +14 እናንተም ‘አድርጉ ያልከን ነገር መልካም ነው’ በማለት መለሳችሁልኝ። +15 እኔም ጥበበኛ የሆኑትንና ተሞክሮ ያካበቱትን የየነገዳችሁን መሪዎች ወስጄ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች እንዲሁም የየነገዶቻችሁ ሹማምንት አድርጌ በእናንተ ላይ ሾምኳቸው።+ +16 “በዚያን ጊዜ ለዳኞቻችሁ ይህን መመሪያ ሰጠኋቸው፦ ‘በወንድሞቻችሁ መካከል የተፈጠረን አንድ ጉዳይ በምትሰሙበት ጊዜ በሰውየውና በወንድሙ ወይም በባዕድ አገሩ ሰው መካከል+ በጽድቅ ፍረዱ።+ +17 በምትፈርዱበት ጊዜ አታዳሉ።+ ትንሹንም ሆነ ትልቁን እኩል ስሙ።+ ፍርድ የአምላክ ስለሆነ+ ሰውን አትፍሩ፤+ አንድ ጉዳይ ከከበዳችሁ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እሰማዋለሁ።’+ +18 በዚያን ጊዜ ማድረግ ስላለባችሁ ነገር ሁሉ መመሪያ ሰጠኋችሁ። +19 “ከዚያም ይሖዋ አምላካችን ባዘዘን መሠረት ከኮሬብ በመነሳት ያን ያያችሁትን ጭልጥ ያለና የሚያስፈራ ምድረ በዳ+ አቋርጠን ወደ አሞራውያን ተራራማ አካባቢዎች+ በሚወስደው መንገድ ተጓዝን፤ በመጨረሻም ቃዴስበርኔ+ ደረስን። +20 እኔም እንዲህ አልኳችሁ፦ ‘አምላካችን ይሖዋ ወደሚሰጠን ወደ አሞራውያን ተራራማ አካባቢዎች ደርሳችኋል። +21 ይኸው አምላካችሁ ይሖዋ ምድሪቱን ለእናንተ ሰጥቷችኋል። የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ በነገራችሁ መሠረት ተነሱና ውረሷት።+ አትፍሩ ወይም አትሸበሩ።’ +22 “ሆኖም እናንተ ሁላችሁም ወደ እኔ መጥታችሁ እንዲህ አላችሁኝ፦ ‘ምድሪቱን እንዲሰልሉልን እንዲሁም በየትኛው መንገድ መሄድ እንደሚኖርብንና ምን ዓይነት ከተሞች እንደሚያጋጥሙን አይተው እንዲነግሩን ሰዎችን አስቀድመን እንላክ።’+ +23 ይህም ሐሳብ መልካም መስሎ ታየኝ፤ በመሆኑም ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አንድ ሰው ይኸውም ከመካከላችሁ 12 ሰዎችን መረጥኩ።+ +24 እነሱም ተነስተው ወደ ተራራማው አካባቢ ሄዱ፤+ እስከ ኤሽኮል ሸለቆ* ድረስ በመዝለቅም ምድሪቱን ሰለሉ። +25 ምድሪቱ ከምታፈራው ፍሬም የተወሰነ ይዘው ወደ እኛ መጡ፤ እንዲሁም ‘አምላካችን ይሖዋ የሚሰጠን ምድር መልካም ናት’ ብለው ነገሩን።+ +26 እናንተ ግን ወደዚያ ለመውጣት ፈቃደኞች አልሆናችሁም፤ በአምላካችሁ በይሖዋ ትእዛዝም ላይ ዓመፃችሁ።+ +27 በየድንኳኖቻችሁ ውስጥ ሆናችሁ እንዲህ በማለት አጉተመተማችሁ፦ ‘ይሖዋ ስለጠላን አሞራውያን እንዲያጠፉን ለእነሱ አሳልፎ ሊሰጠን ከግብፅ ምድር አወጣን። +28 ታዲያ የምንሄደው ወዴት ነው? ወንድሞቻችን “ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱና ረጃጅሞች ናቸው፤ ከተሞቻቸውም ቢሆኑ ታላላቅና እስከ ሰማይ በሚደርስ ቅጥር የታጠሩ ናቸው፤+ እንዲያውም በዚያ የኤናቅን+ ልጆች አይተናል” በማለት ልባችን እንዲቀልጥ አድርገዋል።’+ +29 “በመሆኑም እኔ እንዲህ አልኳችሁ፦ ‘በእነሱ የተነሳ በፍርሃት አትራዱ ወይም አትሸበሩ።+ +30 አምላካችሁ ይሖዋ በፊታችሁ ይሄዳል፤ የገዛ ዓይናችሁ እያየ በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ይዋጋላችኋል።+ +31 በምድረ በዳም ተጉዛችሁ እዚህ እስክትደርሱ ድረስ አንድ አባት ልጁን እንደሚሸከም አምላካችሁ ይሖዋም በሄዳችሁበት ሁሉ እንዴት እንደተሸከማችሁ አይታችኋል።’ +32 እናንተ ግን ይህ ሁሉ ተደርጎላችሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እምነት አላሳደራችሁም፤+ +33 እሱ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ ከፊት ከፊታችሁ ይሄድ ነበር። በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባችሁ ለማሳየትም ሌሊት ሌሊት በእሳት፣ ቀን ቀን ደግሞ በደመና ይመራችሁ ነበር።+ +34 “በዚህ ጊዜ ይሖዋ ያላችሁትን ሰማ፤ ተቆጥቶም እንዲህ ሲል ማለ፦+ +35 ‘ለአባቶቻችሁ ለመስጠት የማልኩላቸውን መልካሚቱን ምድር ከዚህ ክፉ ትውልድ መካከል አንድም ሰው አያያትም፤+ +36 ከየፎኒ ልጅ ከካሌብ በስተቀር ማንም አያያትም። እሱ ያያታል፤ ይሖዋን በሙሉ ልቡ ስለተከተለም የረገጣትን ምድር ለእሱና ለልጆቹ እሰጣታለሁ።+ +37 (ይሖዋ በእናንተ የተነሳ በእኔም ላይ እንኳ ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “አንተም ብትሆን ወደዚያ አትገባም።+ +38 ወደ ምድሪቱ የሚገባው+ በፊትህ የሚቆመው የነዌ ልጅ ኢያሱ ነው።+ እስራኤላውያን ምድሪቱን እንዲወርሱ የሚያደርገው እሱ ስለሆነ አበርታው።”)*+ +39 በተጨማሪም ለምርኮ ይዳረጋሉ+ ያላችኋቸው ልጆቻችሁ እንዲሁም ዛሬ ክፉና ደጉን የማያውቁት ወንዶች ልጆቻችሁ ወደዚያ ይገባሉ፤ እኔም ምድሪቱን እንዲወርሷት ለእነሱ እሰጣታለሁ።+ +40 እናንተ ግን አቅጣጫ በመቀየር ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ አድርጋችሁ ወደ ምድረ በዳው ሂዱ።’+ +41 “እናንተም በዚህ ጊዜ እንዲህ አላችሁኝ፦ ‘በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል። በቃ፣ አምላካችን ይሖዋ ባዘዘን መሠረት ወጥተን እንዋጋለን!’ በመሆኑም እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያዎቻችሁን ታጠቃችሁ፤ ወደ ተራራው መውጣት ቀላል መስሎ ታይቷችሁ ነበር።+ +42 ይሁንና ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እንዲህ በላቸው፦ “እኔ አብሬያችሁ ስለማልሆን ወጥታችሁ ውጊያ እንዳትገጥሙ።+ እንዲህ ብታደርጉ ግን ጠላቶቻችሁ ድል ያደርጓችኋል።”’ +43 እኔም ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም። ከዚህ ይልቅ በይሖዋ ትእዛዝ ላይ በማመፅ በእብሪት ወደ ተራራው ለመውጣት ሞከራችሁ። +44 ከዚያም በተራራው ላይ ይኖሩ የነበሩት አሞራውያን እናንተን ለመግጠም ወጡ፤ እነሱም ልክ እንደ ንብ እየተከታተሉ አሳደዷችሁ፤ ከሴይር አንስቶ እስከ ሆርማ ድረስም በታተኗችሁ። +45 ስለሆነም ተመልሳችሁ በይሖዋ ፊት ማልቀስ ጀመራችሁ፤ ሆኖም ይሖዋ ጩኸታችሁን አልሰማም፤ ጆሮውንም አልሰጣችሁም። +46 እነዚያን ሁሉ ቀናት በቃዴስ የተቀመጣችሁትም ለዚህ ነው። +29 ይሖዋ በኮሬብ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ ሙሴ በሞዓብ ምድር ከእነሱ ጋር እንዲገባ ያዘዘው ቃል ኪዳን ቃላት እነዚህ ናቸው።+ +2 ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን በሙሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ በግብፅ ምድር በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ እንዲሁም በመላ ምድሩ ላይ ያደረገውን ነገር ሁሉ በገዛ ዓይናችሁ ተመልክታችኋል፤+ +3 ደግሞም እነዚያን ታላላቅ የፍርድ እርምጃዎች፣* ድንቅ ምልክቶችና ተአምራት+ በዓይናችሁ አይታችኋል። +4 ሆኖም ይሖዋ እስከ ዛሬ ድረስ የሚያስተውል ልብ፣ የሚያይ ዓይንና የሚሰማ ጆሮ አልሰጣችሁም።+ +5 ‘በምድረ በዳ ለ40 ዓመታት+ በመራኋችሁ ጊዜ ልብሳችሁ ላያችሁ ላይ አላለቀም፤ ጫማችሁም እግራችሁ ላይ አላለቀም።+ +6 እኔ አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን ታውቁ ዘንድ ዳቦ አልበላችሁም፤ የወይን ��ጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም።’ +7 በኋላም ወደዚህ ስፍራ መጣችሁ፤ የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን+ እና የባሳን ንጉሥ ኦግ+ ሊወጉን ወጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው።+ +8 ከዚያም ምድራቸውን ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠናቸው።+ +9 በመሆኑም የምታደርጉት ነገር ሁሉ መልካም እንዲሆንላችሁ የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት ጠብቁ፤ ደግሞም ታዘዙ።+ +10 “እናንተ ሁላችሁ ይኸውም የየነገዶቻችሁ መሪዎች፣ ሽማግሌዎቻችሁ፣ አለቆቻችሁና በእስራኤል ያለ ወንድ ሁሉ በዛሬው ዕለት በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ቆማችኋል፤ +11 እንዲሁም ልጆቻችሁ፣ ሚስቶቻችሁና+ ከእንጨት ለቃሚዎቻችሁ አንስቶ እስከ ውኃ ቀጂዎቻችሁ ድረስ፣ በሰፈራችሁ የሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች+ ሁሉ በፊቱ ቆመዋል። +12 አሁን እዚህ የተገኘኸው አምላክህ ይሖዋ በዛሬው ዕለት ከአንተ ጋር ወደሚገባው ይኸውም በመሐላ ወደሚያጸናው ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቃል ኪዳን እንድትገባ ነው፤+ +13 ይህም ለአንተ ቃል በገባውና ለአባቶችህ ለአብርሃም፣+ ለይስሐቅና+ ለያዕቆብ+ በማለላቸው መሠረት በዛሬው ዕለት አንተን ሕዝቡ አድርጎ+ ያጸናህ እንዲሁም አምላክህ ይሆን ዘንድ+ ነው። +14 “እኔ አሁን ይህን ቃል ኪዳን የምገባውም ሆነ ይህን መሐላ የምምለው ለእናንተ ብቻ አይደለም፤ +15 ከዚህ ይልቅ በዛሬው ዕለት በይሖዋ ፊት አብረውን ለቆሙትና በዚህ ዕለት ከእኛ ጋር ለሌሉት ጭምር ነው። +16 (በግብፅ እንዴት እንኖር እንደነበረና በጉዟችንም ላይ የተለያዩ ብሔራትን እንዴት አቋርጠን እንዳለፍን በሚገባ ታውቃላችሁና።+ +17 በመካከላቸው የነበሩትን የሚያስጠሉ ነገሮች እንዲሁም ከእንጨት፣ ከድንጋይ፣ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውንም*+ አይታችኋል።) +18 የእነዚያን ብሔራት አማልክት ለማገልገል ከአምላካችን ከይሖዋ ልቡ የሚሸፍት+ ወንድ ወይም ሴት ወይም ቤተሰብ አሊያም ነገድ በዛሬው ዕለት በመካከላችሁ እንዳይገኝ እንዲሁም መርዛማና መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ።+ +19 “አንድ ሰው ይህን የመሐላ ቃል ቢሰማና በመንገዱ ላይ ያገኘውን ሁሉ* ጠራርጎ ለማጥፋት በማሰብ ‘እንዳሻኝ ብሆን እንኳ በሰላም እኖራለሁ’ እያለ በልቡ ቢኩራራ +20 ይሖዋ ይቅር ሊለው ፈቃደኛ አይሆንም።+ ከዚህ ይልቅ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በዚያ ሰው ላይ ይነድዳል፤ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉት እርግማኖች በሙሉ ይወርዱበታል፤+ ይሖዋም የዚህን ሰው ስም ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል። +21 ከዚያም በዚህ የሕግ መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው በቃል ኪዳኑ እርግማን ሁሉ መሠረት ይሖዋ ከሌሎቹ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ እሱን ለጥፋት ይለየዋል። +22 “መጪው የልጆቻችሁ ትውልድና ከሩቅ ምድር የሚመጡት የባዕድ አገር ሰዎች በምድሪቱ ላይ የወረዱትን መቅሰፍቶች ይኸውም ይሖዋ በላይዋ ላይ ያመጣውን በሽታ +23 እንዲሁም ይሖዋ በቁጣውና በመዓቱ ሰዶምንና ገሞራን፣+ አድማህንና ጸቦይምን+ እንደገለባበጠ ሁሉ መላዋ ምድር እንዳይዘራባት፣ እንዳታቆጠቁጥ ወይም ምንም ዓይነት ተክል እንዳታበቅል የላከውን ድኝ፣ ጨውና እሳት ሲመለከቱ +24 እነሱም ሆኑ ሁሉም ብሔራት ‘ይሖዋ በዚህች ምድር ላይ እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?+ ይህን ታላቅ ቁጣስ ምን አመጣው?’ ይላሉ። +25 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ከግብፅ ምድር ባወጣቸው+ ጊዜ ከእነሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን በማፍረሳቸው ነው።+ +26 ሄደውም ሌሎችን አማልክት ይኸውም የማያውቋቸውንና እሱ እንዲያመልኳቸው ያልፈቀደላቸውን* አማልክት አገለገሉ፤ ደግሞም ሰገዱላቸው።+ +27 ይሖዋም በዚህ መጽሐፍ ላይ የተጻፉት��� እርግማኖች በሙሉ እስኪያመጣባት ድረስ ቁጣው በምድሪቱ ላይ ነደደ።+ +28 በመሆኑም ይሖዋ በታላቅ ቁጣውና በኃይለኛው ንዴቱ ከምድራቸው ላይ ነቅሎ+ አሁን ወዳሉበት ሌላ ምድር አፈለሳቸው።’+ +29 “የተሰወሩት ነገሮች የአምላካችን የይሖዋ ናቸው፤+ የተገለጡት ነገሮች ግን በዚህ ሕግ ውስጥ ያሉትን ቃላት በሙሉ እንፈጽም ዘንድ ለዘላለም የእኛና የዘሮቻችን ናቸው።+ +28 “እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ሁሉ በጥንቃቄ በመፈጸም ቃሉን በእርግጥ ብትሰማ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።+ +2 የአምላክህን የይሖዋን ቃል ከሰማህ እነዚህ ሁሉ በረከቶች ይወርዱልሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦+ +3 “በከተማ የተባረክ ትሆናለህ፤ በእርሻም የተባረክ ትሆናለህ።+ +4 “የሆድህ ፍሬ፣+ የመሬትህ ፍሬ፣ የቤት እንስሳህ ግልገል፣ ጥጃህና የበግህ ግልገል የተባረከ ይሆናል።+ +5 “ቅርጫትህና+ ቡሃቃህ+ የተባረከ ይሆናል። +6 “ስትገባ የተባረክ ትሆናለህ፤ ስትወጣም የተባረክ ትሆናለህ። +7 “ይሖዋ በአንተ ላይ የሚነሱ ጠላቶችህ በፊትህ ድል እንዲሆኑ ያደርጋል።+ ከአንድ አቅጣጫ ጥቃት ይሰነዝሩብሃል፤ ሆኖም በሰባት አቅጣጫ ከፊትህ ይሸሻሉ።+ +8 ይሖዋ በጎተራህና በምታከናውነው ሥራ ሁሉ ላይ በረከት እንዲፈስልህ ያዛል፤+ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል። +9 የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ከጠበቅክና በመንገዶቹ ከሄድክ ይሖዋ በማለልህ መሠረት+ ለእሱ ቅዱስ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል።+ +10 የምድር ሕዝቦች ሁሉ የይሖዋ ስም በአንተ አማካኝነት እንደሚጠራ ያያሉ፤+ እነሱም ይፈሩሃል።+ +11 “ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር+ ላይ ይሖዋ የሆድህ ፍሬ እንዲበዛ፣ የቤት እንስሶችህ እንዲረቡና መሬትህ ፍሬያማ እንዲሆን+ በማድረግ ያበለጽግሃል። +12 ይሖዋ በምድርህ ላይ በወቅቱ ዝናብን ለማዝነብና የእጅህን ሥራ ሁሉ ለመባረክ ሲል መልካም የሆነውን ጎተራውን ይኸውም ሰማይን ይከፍትልሃል።+ አንተም ለብዙ ብሔራት ታበድራለህ፤ አንተ ግን አትበደርም።+ +13 ይሖዋ ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ትጠብቃቸውና ትፈጽማቸው ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ከፈጸምክ መቼም ቢሆን ከላይ+ እንጂ ከታች አትሆንም። +14 ሌሎች አማልክትን ለማገልገል+ ብላችሁ እነሱን በመከተል እኔ ዛሬ ከምሰጣችሁ ትእዛዛት ሁሉ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበሉ።+ +15 “እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች በሙሉ በጥንቃቄ የማትፈጽምና የአምላክህን የይሖዋን ቃል የማትሰማ ከሆነ ግን እነዚህ ሁሉ እርግማኖች ይወርዱብሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦+ +16 “በከተማ የተረገምክ ትሆናለህ፤ በእርሻም የተረገምክ ትሆናለህ።+ +17 “ቅርጫትህና+ ቡሃቃህ+ የተረገመ ይሆናል። +18 “የሆድህ ፍሬ፣+ የመሬትህ ፍሬ፣ ጥጃህና የበግህ ግልገል የተረገመ ይሆናል።+ +19 “ስትገባ የተረገምክ ትሆናለህ፤ ስትወጣም የተረገምክ ትሆናለህ። +20 “ይሖዋ በፈጸምካቸው መጥፎ ድርጊቶችና እኔን በመተውህ የተነሳ ፈጥነህ እስክትደመሰስ እንዲሁም እስክትጠፋ ድረስ፣ በምታከናውነው በማንኛውም ሥራ ላይ እርግማንን፣ ግራ መጋባትንና ቅጣትን ያመጣብሃል።+ +21 ይሖዋ ከምትወርሳት ምድር ላይ ጨርሶ እስኪያጠፋህ ድረስ በሽታ እንዲጣበቅብህ ያደርጋል።+ +22 ይሖዋ በሳንባ በሽታ፣ በኃይለኛ ትኩሳት፣+ ሰውነትን በሚያስቆጣ በሽታ፣ በሚያነድ ትኩሳት፣ በሰይፍ፣+ ሰብል በሚለበልብ ነፋስና በዋግ+ ይመታሃል፤ እነሱም እስክትጠፋ ድረስ ያሳድዱሃል። +23 ከራስህ በላይ ያለው ሰማይ መዳብ፣ ከበታችህ ያለውም ምድር ብረት ይሆንብሃል።+ +24 ይሖዋ በምድርህ ላይ የሚዘንበውን ዝናብ ትቢያና አቧራ ያደርገዋል፤ ይህም እስክትጠፋ ድረስ ከሰማይ ይወርድብሃል። +25 ይሖዋ በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል።+ በአንድ አቅጣጫ ጥቃት ትሰነዝርባቸዋለህ፤ ሆኖም በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ የምድርም መንግሥታት ሁሉ በአንተ ላይ የደረሰውን ሲያዩ በፍርሃት ይርዳሉ።+ +26 ሬሳህ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ምግብ ይሆናል፤ አስፈራርቶ የሚያባርራቸውም አይኖርም።+ +27 “ይሖዋ ፈውስ ልታገኝ በማትችልበት የግብፅ እባጭ፣ ኪንታሮት፣ ችፌና ሽፍታ ይመታሃል። +28 ይሖዋ በእብደት፣ በዕውርነትና+ በግራ መጋባት ይመታሃል። +29 ጨለማ የዋጠው ዓይነ ስውር በዳበሳ እንደሚሄድ ሁሉ አንተም በእኩለ ቀን በዳበሳ ትሄዳለህ፤+ የምታደርገው ነገር ሁሉ አይሳካልህም፤ ሁልጊዜ ትጭበረበራለህ፤ እንዲሁም ትዘረፋለህ፤ የሚያስጥልህም የለም።+ +30 አንዲትን ሴት ታጫለህ፤ ሆኖም ሌላ ሰው ይደፍራታል። ቤት ትሠራለህ፤ ሆኖም አትኖርበትም።+ ወይን ትተክላለህ፤ ግን አትበላውም።+ +31 በሬህ ዓይንህ እያየ ይታረዳል፤ ሆኖም ከእሱ ላይ ምንም አትቀምስም። አህያህም ከፊትህ ተዘርፎ ይወሰዳል፤ ሆኖም አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚደርስልህ ግን የለም። +32 ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ዓይንህ እያየ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤+ አንተም ሁልጊዜ የእነሱን መመለስ ትናፍቃለህ፤ ሆኖም እጆችህ ምንም ኃይል አይኖራቸውም። +33 የምድርህን ፍሬና ያመረትከውን ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል፤+ አንተም ሁልጊዜ ትጭበረበራለህ፤ ደግሞም ትረገጣለህ። +34 ዓይንህ የሚያየውም ነገር ያሳብድሃል። +35 “ይሖዋ በሚያሠቃይና ሊድን በማይችል እባጭ ጉልበቶችህንና እግሮችህን ይመታል፤ እባጩም ከእግር ጥፍርህ እስከ ራስ ቅልህ ድረስ ይወርስሃል። +36 ይሖዋ አንተንና በላይህ ያነገሥከውን ንጉሥ፣ አንተም ሆንክ አባቶችህ ወደማታውቁት ብሔር ይወስዳችኋል፤+ እዚያም ሌሎች አማልክትን ይኸውም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክትን ታገለግላለህ።+ +37 ይሖዋ በሚያስገባህ ሕዝብ ሁሉ መካከል ማስፈራሪያ፣ መቀለጃና* መሳለቂያ ትሆናለህ።+ +38 “ወደ እርሻህ ብዙ ዘር ይዘህ ትወጣለህ፤ የምትሰበስበው ግን ጥቂት ይሆናል፤+ ምክንያቱም አንበጦች ያወድሙታል። +39 ወይን ትተክላለህ፤ ታለማለህም፤ ይሁንና ምንም የወይን ጠጅ አትጠጣም፤ እንዲሁም አንዳች አትሰበስብም፤+ ምክንያቱም ትል ይበላዋል። +40 በግዛትህ ሁሉ የወይራ ዛፍ ይኖርሃል፤ ሰውነትህን የምትቀባው ዘይት ግን አይኖርህም፤ ምክንያቱም የወይራ ፍሬዎችህ ይረግፋሉ። +41 ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ትወልዳለህ፤ ሆኖም በምርኮ ስለሚወሰዱ የአንተ አይሆኑም።+ +42 ዛፎችህንና የምድርህን ፍሬ ሁሉ የሚርመሰመሱ ነፍሳት ይወሩታል። +43 አንተ ዝቅ ዝቅ እያልክ ስትሄድ በመካከልህ የሚኖረው የባዕድ አገር ሰው ግን በአንተ ላይ ከፍ ከፍ እያለ ይሄዳል። +44 እሱ ያበድርሃል እንጂ አንተ አታበድረውም።+ እሱ ራስ ይሆናል፤ አንተ ግን ጅራት ትሆናለህ።+ +45 “አምላክህ ይሖዋ ያዘዘህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች ባለመጠበቅ ቃሉን ስላልሰማህ እነዚህ እርግማኖች ሁሉ+ እስክትጠፋ ድረስ ይወርዱብሃል፤+ ያሳድዱሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል።+ +46 እነሱም በአንተና በልጆችህ ላይ ለዘላለም ምልክትና ማስጠንቀቂያ ይሆናሉ፤+ +47 ምክንያቱም ሁሉም ነገር ተትረፍርፎልህ ሳለ አምላክህን ይሖዋን በደስታና በሐሴት አላገለገልከውም።+ +48 ይሖዋ ጠላቶችህን በአንተ ላይ ያስነሳቸዋል፤ አንተም ተርበህ፣+ ተጠምተህ፣ ተራቁተህና ሁሉን ነገር አጥተህ እያለ ታገለግላቸዋለህ።+ እሱም እስኪያጠፋህ ��ረስ በአንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭንብሃል። +49 “ይሖዋ ቋንቋውን የማትረዳውን+ በሩቅ ያለን አንድ ብሔር ከምድር ጫፍ አስነስቶ ያመጣብሃል፤+ እሱም እንደ ንስር ተምዘግዝጎ ይወርድብሃል፤+ +50 ይህ ብሔር ለሽማግሌ የማያዝን ወይም ለወጣት የማይራራ ፊቱ የሚያስፈራ ብሔር ነው።+ +51 እስክትጠፋም ድረስ የእንስሶችህን ግልገልና የምድርህን ፍሬ ይበላሉ። አንተንም እስኪያጠፉህ ድረስ ምንም እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅም ሆነ ዘይት፣ ጥጃም ሆነ የበግ ግልገል አያስተርፉልህም።+ +52 የምትተማመንባቸው ረጃጅምና የተመሸጉ ቅጥሮችህ እስኪወድቁም ድረስ በከተሞችህ* ውስጥ እንዳለህ ዘግተውብህ ይከቡሃል። አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህም ምድር ሁሉ ላይ በከተሞችህ ውስጥ እንዳለህ ይከቡሃል።+ +53 ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በአንተ ላይ ከሚያደርሰው ሥቃይ የተነሳ አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን የሆድህን ፍሬ ይኸውም የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።+ +54 “ሌላው ቀርቶ በመካከልህ ያለ በምቾትና በቅምጥልነት ይኖር የነበረ ሰው እንኳ በወንድሙ፣ በሚወዳት ሚስቱ ወይም በተረፉት ልጆቹ ላይ ይጨክናል፤ +55 ከሚበላው የልጆቹ ሥጋ ላይ ምንም ነገር አያካፍላቸውም፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ የሚተርፈው ምንም ነገር አይኖረውም።+ +56 ከቅምጥልነቷ የተነሳ መሬት ለመርገጥ እንኳ ትጸየፍ የነበረች+ በመካከልህ ያለች ቅምጥልና በምቾት የምትኖር ሴትም በምትወደው ባሏ፣ በወንድ ልጇ ወይም በሴት ልጇ ላይ ትጨክናለች፤ +57 ሌላው ቀርቶ ከወሊድ በኋላ ከእግሮቿ መካከል በሚወጣው ነገር ሁሉና በምትወልዳቸው ልጆች ላይ ትጨክናለች፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ በድብቅ ትበላቸዋለች። +58 “በዚህ መጽሐፍ ላይ የተጻፈውን የዚህን ሕግ+ ቃላት ሁሉ በጥንቃቄ የማትጠብቅ እንዲሁም ክብራማና አስፈሪ የሆነውን የአምላክህን የይሖዋን ስም+ የማትፈራ ከሆነ +59 ይሖዋ በአንተና በልጆችህ ላይ ከባድ የሆኑ መቅሰፍቶችን ይኸውም ታላቅና ለረጅም ጊዜ የሚዘልቁ መቅሰፍቶችን እንዲሁም አስከፊና ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ በሽታዎችን+ ያመጣል። +60 ትፈራቸው የነበሩትን የግብፅ በሽታዎች ሁሉ መልሶ ያመጣብሃል፤ እነሱም በአንተ ላይ ይጣበቃሉ። +61 በተጨማሪም ይሖዋ በዚህ የሕግ መጽሐፍ ውስጥ ያልተጻፉ በሽታዎችን ወይም መቅሰፍቶችን ሁሉ እስክትጠፋ ድረስ በአንተ ላይ ያመጣብሃል። +62 ብዛታችሁ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት+ የነበረ ቢሆንም የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ስላልሰማችሁ የምትቀሩት በጣም ጥቂት ትሆናላችሁ።+ +63 “ይሖዋ እናንተን በማበልጸግና በማብዛት እጅግ ይደሰት እንደነበረው ሁሉ ይሖዋ እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስም እጅግ ይደሰታል፤ ገብታችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ። +64 “ይሖዋ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ በብሔራት ሁሉ መካከል ይበትንሃል፤+ እዚያም አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት ታገለግላለህ።+ +65 በእነዚያም ብሔራት መካከል ሰላም አይኖርህም፤+ ወይም ለእግርህ ማሳረፊያ የሚሆን ቦታ አታገኝም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ በዚያ ልብህ እንዲሸበር፣+ ዓይንህ እንዲፈዝና በተስፋ መቁረጥ እንድትዋጥ ያደርጋል።*+ +66 ሕይወትህ ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣል፤ ሌሊትና ቀንም በፍርሃት ትዋጣለህ፤ ለሕይወትህም ዋስትና ታጣለህ። +67 በልብህ ውስጥ ካለው ፍርሃትና በዓይንህ ከምታየው ነገር የተነሳ ጠዋት ላይ ‘ምነው በመሸ!’ ትላለህ፤ ምሽት ላይ ደግሞ ‘ምነው በነጋ!’ ትላለህ። +68 ��ዳግመኛ አታያትም’ ባልኩህ መንገድ ይሖዋ ወደ ግብፅ በመርከቦች ይመልስሃል፤ በዚያም ራሳችሁን ለጠላቶቻችሁ ወንድ ባሪያዎችና ሴት ባሪያዎች አድርጋችሁ ለመሸጥ ትገደዳላችሁ፤ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።” +8 “በሕይወት እንድትኖሩና+ እንድትበዙ እንዲሁም ይሖዋ ለአባቶቻችሁ የማለላቸውን ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ ዛሬ የማዛችሁን እያንዳንዱን ትእዛዝ በጥንቃቄ ጠብቁ።+ +2 አምላክህ ይሖዋ በልብህ ምን እንዳለ+ ይኸውም ትእዛዛቱን ትጠብቅ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ ይፈትንህና ትሑት ያደርግህ ዘንድ+ በእነዚህ 40 ዓመታት በምድረ በዳ እንድትጓዝበት ያደረገህን ረጅሙን መንገድ አስታውስ።+ +3 ትሑት እንድትሆን አደረገህ፤ ካስራበህም+ በኋላ አንተ የማታውቀውን፣ አባቶችህም የማያውቁትን መና መገበህ፤+ ይህን ያደረገው፣ ሰው ከይሖዋ አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ ሊኖር እንደማይችል ሊያሳውቅህ ነው።+ +4 በእነዚህ 40 ዓመታት፣ የለበስከው ልብስ አላለቀም፤ እግርህም አላበጠም።+ +5 አንድ ሰው ለልጁ እርማት እንደሚሰጥ ሁሉ አምላክህ ይሖዋም እርማት ይሰጥህ+ እንደነበር ልብህ በሚገባ ያውቃል። +6 “እንግዲህ አንተ በመንገዶቹ በመሄድና እሱን በመፍራት የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ጠብቅ። +7 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መልካም ወደሆነች ምድር ሊያስገባህ ነው፤+ ይህች ምድር ጅረቶች* ያሏት፣ በሸለቋማ ሜዳዋና በተራራማ አካባቢዋ ምንጮች የሚፈልቁባትና ውኃዎች የሚንዶለዶሉባት፣ +8 ስንዴ፣ ገብስ፣ ወይን፣ በለስና ሮማን+ የሚበቅልባት፣ የወይራ ዘይትና ማር የሚገኝባት፣+ +9 የምግብ እጥረት የሌለባት፣ ምንም ነገር የማታጣባት፣ ብረት ያለባቸው ድንጋዮች የሚገኙባት እንዲሁም ከተራሮቿ መዳብ ቆፍረህ የምታወጣባት ምድር ናት። +10 “በልተህ በምትጠግብበት ጊዜ ስለሰጠህ ስለ መልካሚቱ ምድር አምላክህን ይሖዋን አመስግነው።+ +11 እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛት፣ ድንጋጌዎችና ደንቦች ችላ በማለት አምላክህን ይሖዋን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ። +12 በልተህ ስትጠግብ፣ ጥሩ ጥሩ ቤቶችን ሠርተህ በዚያ መኖር ስትጀምር፣+ +13 ከብትህና መንጋህ ሲበዛ፣ ብርህና ወርቅህ ሲበራከት እንዲሁም የአንተ የሆነው ሁሉ እየበዛ ሲሄድ +14 ልብህ እንዳይታበይና+ ከግብፅ ምድር ይኸውም ከባርነት ቤት ያወጣህን አምላክህን ይሖዋን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ፤+ +15 መርዛማ እባቦችና ጊንጦች በሞሉበት እንዲሁም ውኃ የተጠማ ደረቅ ምድር ባለበት በዚያ ጭልጥ ያለና የሚያስፈራ ምድረ በዳ+ አቋርጠህ እንድታልፍ ያደረገህን አምላክህን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ። እሱ ከጠንካራ ዓለት* ውኃ አፍልቆልሃል፤+ +16 እንዲሁም ወደፊት መልካም እንዲሆንልህ አንተን ትሑት ለማድረግና ለመፈተን ሲል+ አባቶችህ የማያውቁትን መና በምድረ በዳ መግቦሃል።+ +17 በልብህም ‘ይህን ሀብት ያፈራሁት በራሴ ኃይልና በእጄ ብርታት ነው’+ ብለህ ብታስብ +18 ሀብት እንድታፈራ ኃይል የሰጠህ አምላክህ ይሖዋ መሆኑን አስታውስ፤+ ይህን ያደረገው ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ለአባቶችህ በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ነው።+ +19 “አምላክህን ይሖዋን ብትረሳና ሌሎች አማልክትን ብትከተል እንዲሁም እነሱን ብታገለግልና ለእነሱ ብትሰግድ፣ በእርግጥ እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ እመሠክርባችኋለሁ።+ +20 የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ስላልሰማችሁ ይሖዋ ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው ብሔራት እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።+ +11 “አንተም አምላክህን ይሖዋን ውደድ፤+ ለእሱ ያለብህንም ግዴታ ምንጊዜም ተወጣ፤ እንዲሁም ደንቦቹን፣ ድንጋጌዎቹንና ትእዛዛቱን ሁልጊዜ ጠብቅ። +2 ዛሬ እየተናገርኩ ያለሁት ለእናንተ እንጂ የአም���ካችሁን የይሖዋን ተግሣጽ፣+ የእሱን ታላቅነት፣+ የእሱን ብርቱ እጅና+ የተዘረጋ ክንድ ላላወቁት ወይም ላላዩት ለልጆቻችሁ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። +3 እነሱ በግብፅ ይኸውም በግብፁ ንጉሥ በፈርዖን ፊትና በመላው ምድሩ ላይ ያሳየውን ተአምራዊ ምልክትም ሆነ ያደረገውን ነገር አልተመለከቱም፤+ +4 ወይም እናንተን እያሳደዱ ሳሉ በቀይ ባሕር ውስጥ በሰጠሙት በግብፅ ሠራዊት፣ በፈርዖን ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች ላይ ያደረገውን አላዩም፤ ይሖዋም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ* አጠፋቸው።+ +5 እናንተ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን ነገር አልተመለከቱም፤ +6 ወይም ደግሞ የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንን እና አቤሮንን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ድንኳኖቻቸውንና ከእነሱ ጋር ያበረውን ማንኛውንም ሕያው ፍጡር እስራኤላውያን ሁሉ እያዩ ምድር ተከፍታ በዋጠቻቸው ጊዜ በእነሱ ላይ ያደረገውን ነገር አልተመለከቱም።+ +7 እናንተ፣ ይሖዋ ያደረጋቸውን ታላላቅ ሥራዎች በሙሉ በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል። +8 “ብርታት እንድታገኙና ወደምትወርሷት ምድር ተሻግራችሁ እንድትገቡ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ፤ +9 ይሖዋ ለአባቶቻችሁና ለዘሮቻቸው ለመስጠት በማለላቸው+ ወተትና ማር በምታፈሰው ምድር+ ላይ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም+ እነዚህን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ። +10 “የምትወርሳት ምድር ዘር ትዘራባት እንዲሁም ልክ እንደ አትክልት ስፍራ በእግርህ* በመስኖ ታጠጣት እንደነበረችው እንደወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም። +11 ከዚህ ይልቅ ተሻግራችሁ የምትወርሷት ምድር ተራሮችና ሸለቋማ ሜዳዎች ያሉባት ምድር ናት።+ የሰማይን ዝናብ የምትጠጣ ምድር ናት፤+ +12 አምላክህ ይሖዋ የሚንከባከባት ምድር ናት። የአምላክህም የይሖዋ ዓይን ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ መጨረሻው ድረስ ዘወትር በእሷ ላይ ነው። +13 “እኔ ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዛቴን በትጋት ብትፈጽሙ፣ አምላካችሁን ይሖዋን ብትወዱት እንዲሁም በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ* ብታገለግሉት፣+ +14 እኔ ደግሞ ለምድራችሁ በወቅቱ ዝናብን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እሰጣለሁ፤ አንተም እህልህን፣ አዲስ የወይን ጠጅህንና ዘይትህን ትሰበስባለህ።+ +15 ለእንስሶችህም በሜዳህ ላይ ዕፀዋት አበቅልልሃለሁ፤ አንተም በልተህ ትጠግባለህ።+ +16 ልባችሁ እንዳይታለልና ዞር ብላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ እንዲሁም እንዳትሰግዱላቸው ተጠንቀቁ።+ +17 አለዚያ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ ዝናብ ዘንቦ ምድሪቱ ምርት እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤+ እናንተም ይሖዋ ከሚሰጣችሁ መልካም ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።+ +18 “እነዚህን ቃሎቼን በልባችሁና በነፍሳችሁ* ላይ አትሟቸው፤ በእጃችሁም ላይ እንደ ማስታወሻ እሰሯቸው፤ በግንባራችሁም ላይ* እንደታሰረ ነገር ይሁኑ።+ +19 በቤታችሁ ስትቀመጡ፣ በመንገድ ላይ ስትሄዱ፣ ስትተኙና ስትነሱ ስለ እነሱ በመናገር ለልጆቻችሁ አስተምሯቸው።+ +20 በቤታችሁ መቃኖችና በግቢያችሁ በሮች ላይ ጻፏቸው፤ +21 ይህን ካደረጋችሁ ሰማይ ከምድር በላይ እስካለ ድረስ ይሖዋ ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር+ ላይ የእናንተም ሆነ የልጆቻችሁ ዕድሜ ይረዝማል።+ +22 “አምላካችሁን ይሖዋን እንድትወዱ፣+ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄዱና ከእሱ ጋር እንድትጣበቁ የሰጠኋችሁን እነዚህን ሁሉ ትእዛዛት በጥብቅ ብትከተሉና ብትፈጽሟቸው+ +23 ይሖዋም እነዚህን ሁሉ ብሔራት ከፊታችሁ ያባርራቸዋል፤+ እናንተም ከእናንተ ይልቅ ታላቅ የሆኑትንና ብዙ ሕዝብ ያላቸውን ብሔራት ታስለቅቃላችሁ።+ +24 እግራችሁ የረገጠው ቦታ ሁሉ የእናንተ ይሆናል።+ ወሰናችሁም ከ���ድረ በዳው አንስቶ እስከ ሊባኖስ እንዲሁም ከወንዙ ይኸውም ከኤፍራጥስ ወንዝ አንስቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር* ድረስ ይሆናል።+ +25 ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም።+ አምላካችሁ ይሖዋም ቃል በገባላችሁ መሠረት በምትረግጡት ምድር ሁሉ ላይ ሽብርና ፍርሃት ይለቃል።+ +26 “እንግዲህ ዛሬ ይህን በረከትና እርግማን በፊታችሁ አስቀምጫለሁ፦+ +27 እኔ ዛሬ የማዛችሁን የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ከፈጸማችሁ በረከቱን ታገኛላችሁ፤+ +28 የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ካልፈጸማችሁና እኔ ዛሬ እንድትከተሉት ከማዛችሁ መንገድ ዞር በማለት የማታውቋቸውን አማልክት ከተከተላችሁ ግን እርግማኑ ይደርስባችኋል።+ +29 “አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጋችሁ ወደምትወርሷት ምድር በሚያስገባችሁ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ ላይ እርግማኑን ደግሞ በኤባል ተራራ ላይ ታውጃላችሁ።*+ +30 እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ፣* በአረባ በሚኖሩት በከነአናውያን ምድር ከጊልጋል ትይዩ በሞሬ ትላልቅ ዛፎች አጠገብ አይደለም?+ +31 አሁን አምላካችሁ ይሖዋ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው።+ እንግዲህ ምድሪቱን ወርሳችሁ በእሷ ላይ ስትኖሩ +32 ዛሬ በፊታችሁ ያስቀመጥኳቸውን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽሙ።+ +2 ከዚያም ልክ ይሖዋ በነገረኝ መሠረት ተመልሰን ወደ ቀይ ባሕር የሚወስደውን መንገድ በመከተል ወደ ምድረ በዳው ተጓዝን፤+ በሴይር ተራራ አካባቢም ለብዙ ቀናት ተንከራተትን። +2 በመጨረሻም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ +3 ‘እንግዲህ በዚህ ተራራ አካባቢ ብዙ ተንከራታችኋል። አሁን ወደ ሰሜን አቅኑ። +4 ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዝ፦ “እንግዲህ በሴይር በሚኖሩት+ በወንድሞቻችሁ በኤሳው ዘሮች+ ድንበር አልፋችሁ ልትሄዱ ነው፤ እነሱም ይፈሯችኋል፤+ ቢሆንም ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ። +5 ከምድራቸው ላይ የእግር መርገጫ የምታክል መሬት እንኳ ስለማልሰጣችሁ ከእነሱ ጋር እንዳትጣሉ፤* ምክንያቱም የሴይርን ተራራ ለኤሳው ርስት አድርጌ ሰጥቼዋለሁ።+ +6 ለምትበሉት ምግብም ሆነ ለምትጠጡት ውኃ ገንዘብ ክፈሏቸው።+ +7 አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና። በዚህ ጭልጥ ያለ ምድረ በዳ እንደተጓዝክ በሚገባ ያውቃል። በእነዚህ 40 ዓመታት አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለነበር ምንም የጎደለብህ ነገር የለም።”’+ +8 ስለዚህ በሴይር በሚኖሩት ወንድሞቻችን በኤሳው ዘሮች በኩል አልፈን ሄድን፤+ ወደ አረባ ከሚወስደው መንገድ፣ ከኤላት እና ከዔጽዮንጋብር ርቀን ተጓዝን።+ “በመቀጠልም ተነስተን ወደ ሞዓብ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተጓዝን።+ +9 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ከሞዓብ ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ ስለማልሰጥህ ከእሱ ጋር አትጣላ ወይም ጦርነት አትግጠም፤ ምክንያቱም ኤርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።+ +10 (ታላቅና ብዙ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን ቁመተ ረጃጅም የሆኑት ኤሚማውያን+ ቀደም ሲል በዚያ ይኖሩ ነበር። +11 ረፋይማውያንም+ ልክ እንደ ኤናቃውያን+ ይቆጠሩ ነበር፤ ሞዓባውያንም ኤሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። +12 ሆራውያን+ ቀደም ሲል በሴይር ይኖሩ ነበር፤ እስራኤላውያን ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጣቸው ምድር ላይ እንደሚያደርጉት ሁሉ የኤሳውም ዘሮች ሆራውያንን በማስለቀቅና በማጥፋት በምድራቸው ላይ መኖር ጀመሩ።)+ +13 በሉ አሁን ተነሱና የዘረድን ሸለቆ* አቋርጣችሁ ሂዱ።’ ስለዚህ የዘረድን ሸለቆ*+ አቋርጠን ሄድን። +14 ከቃዴስበርኔ ተነስተን የዘረድን ሸለቆ* እስክናቋርጥ ድረስ 38 ዓመት ፈጅቶብናል፤ በዚህ ጊዜም ይሖዋ ለእነሱ በማለላቸው መሠረት ለጦርነት ብቁ የሆነው ትውልድ በሙሉ ከሕዝቡ መካከል አለቀ።+ +15 ሙሉ በሙሉ እስኪጠፉም ድረስ የይሖዋ እጅ ከሕዝቡ መካከል ሊያጠፋቸው በእነሱ ላይ ነበር።+ +16 “ለጦርነት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ሞተው እንዳለቁ+ +17 ይሖዋ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፦ +18 ‘ዛሬ በሞዓብ ክልል ይኸውም በኤር በኩል ታልፋለህ። +19 ወደ አሞናውያን በቀረብክ ጊዜ እነሱን አታስቆጣቸው ወይም አትተናኮላቸው፤ ምክንያቱም ምድሪቱን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ስለሰጠኋቸው ከአሞን ልጆች ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ አልሰጥህም።+ +20 ይህችም ምድር የረፋይማውያን+ ምድር ተደርጋ ትቆጠር ነበር። (ቀደም ሲል ረፋይማውያን በዚያ ይኖሩ ነበር፤ አሞናውያንም ዛምዙሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። +21 እነሱም ታላቅና ቁጥራቸው የበዛ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን+ ቁመተ ረጃጅሞች ነበሩ፤ ይሖዋ ግን ከአሞናውያን ፊት አጠፋቸው፤ እነሱም ምድራቸውን አስለቅቀው በዚያ ሰፈሩ። +22 አሁን በሴይር ለሚኖሩት+ የኤሳው ዘሮች ሆራውያንን+ ከፊታቸው ባጠፋላቸው ጊዜ ያደረገላቸው ይህንኑ ነበር፤ በዚህም የተነሳ የኤሳው ዘሮች እነሱን አስለቅቀው እስከ ዛሬ ድረስ በምድራቸው ላይ እየኖሩ ነው። +23 አዊማውያን ደግሞ ከካፍቶር* የተገኙት ካፍቶሪማውያን+ እነሱን አጥፍተው በምድራቸው ላይ መኖር እስከጀመሩበት ጊዜ ድረስ እስከ ጋዛ+ በሚገኙት መንደሮች ይኖሩ ነበር።) +24 “‘ተነሱና የአርኖንን ሸለቆ*+ አቋርጣችሁ ሂዱ። ይኸው የሃሽቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሲሖንን+ በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ። በመሆኑም ምድሩን መውረስ ጀምሩ፤ ከእሱም ጋር ጦርነት ግጠሙ። +25 በዚህች ዕለት፣ ስለ እናንተ የሰሙ ከሰማይ በታች ያሉ ሕዝቦች ሁሉ እንዲሸበሩና በፍርሃት እንዲርዱ አደርጋለሁ። በእናንተም የተነሳ ይታወካሉ፤ ምጥም ይይዛቸዋል።’+ +26 “ከዚያም እኔ ከቀደሞት+ ምድረ በዳ ለሃሽቦን ንጉሥ ለሲሖን እንዲህ የሚል የሰላም መልእክት እንዲነግሩት መልእክተኞችን ላክሁበት፦+ +27 ‘ምድርህን አቋርጬ እንዳልፍ ፍቀድልኝ። ከመንገዱ አልወጣም፤ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አልልም።+ +28 በገንዘብ የምትሸጥልኝን ምግብ ብቻ እበላለሁ፤ በገንዘብ የምትሰጠኝንም ውኃ ብቻ እጠጣለሁ። ምድሩን ረግጬ እንዳልፍ ብቻ ፍቀድልኝ፤ +29 አምላካችን ይሖዋ ወደሚሰጠን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በሴይር የሚኖሩት የኤሳው ዘሮችና በኤር የሚኖሩት ሞዓባውያን እንዲሁ አድርገውልኛል።’ +30 የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን ግን በእሱ በኩል አቋርጠን እንድናልፍ አልፈቀደልንም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሐሳበ ግትር እንዲሆንና ልቡ እንዲደነድን ፈቅዶ ነበር፤+ ይህን ያደረገው ይኸው ዛሬ እንደምታዩት እጃችሁ ላይ እንዲወድቅ ነው።+ +31 “ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እነሆ ሲሖንን እና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ። እንግዲህ ምድሩን ለመውረስ ተነስ።’+ +32 ሲሖንም ከመላው ሕዝቡ ጋር በመሆን ያሃጽ+ ላይ እኛን ለመውጋት በወጣ ጊዜ +33 አምላካችን ይሖዋ በእጃችን አሳልፎ ሰጠው፤ ስለዚህ እሱንም ሆነ ልጆቹን እንዲሁም ሕዝቡን በሙሉ ድል አደረግናቸው። +34 በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ እያንዳንዱን ከተማ ሙሉ በሙሉ አጠፋን። ማንንም በሕይወት አላስተረፍንም።+ +35 ለራሳችን ማርከን የወሰድነው እንስሶችንና በያዝናቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘነውን ንብረት ብቻ ነው። +36 በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ካለችው ከአሮዔር+ (በሸለቆው ውስጥ የምትገኘውን ከተማ ጨምሮ) እስከ ጊልያድ ድረስ ከእጃችን ያመለጠ አንድም ከተማ አልነበረም። አምላካችን ይሖዋ ሁሉንም በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶን ነበር።+ +37 ሆኖም ወደ አሞናውያን ምድር፣+ ወደ ያቦቅ ሸለቆ*+ ዳርቻ ሁሉና በተራራማው አካባቢ ወደሚገኙት ከተሞች ወይም አምላካችን ይሖዋ ወደከለከለን ወደ ሌላ ማንኛውም ቦታ አልቀረባችሁም። +26 “አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር ገብተህ ስትወርስና በዚያ መኖር ስትጀምር +2 አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ይኸውም ምድሪቱ ከምታፈራው ፍሬ ሁሉ በኩር የሆነውን ወስደህ በቅርጫት ውስጥ በማድረግ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።+ +3 በወቅቱ ወደሚያገለግለው ካህን ሄደህ ‘ይሖዋ ለእኛ ለመስጠት ለአባቶቻችን ወደማለላቸው ምድር መግባቴን ዛሬ ለአምላክህ ለይሖዋ አሳውቃለሁ’ በለው።+ +4 “ከዚያም ካህኑ ቅርጫቱን ከእጅህ ላይ ወስዶ በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ፊት ያስቀምጠዋል። +5 አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘አባቴ ዘላን* አራማዊ+ ነበር፤ እሱም ወደ ግብፅ ወርዶ+ በቁጥር አነስተኛ ከሆነው ቤተሰቡ+ ጋር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ መኖር ጀመረ። ሆኖም በዚያ ሲኖር ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ታላቅ ብሔር ሆነ።+ +6 ግብፃውያንም ክፉኛ ያንገላቱንና ይጨቁኑን እንዲሁም በላያችን ላይ ከባድ የባርነት ቀንበር ይጭኑብን ነበር።+ +7 እኛም ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ ይሖዋ ጮኽን፤ ይሖዋም ጩኸታችንን ሰማ፤ ጉስቁልናችንን፣ መከራችንንና የደረሰብንን ጭቆናም ተመለከተ።+ +8 በመጨረሻም ይሖዋ በኃያል እጅና በተዘረጋ ክንድ፣+ አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ እንዲሁም ድንቅ ምልክቶችን በማሳየትና ተአምራትን በመፈጸም ከግብፅ አወጣን።+ +9 ከዚያም ወደዚህ ስፍራ አምጥቶ ይህችን ምድር ይኸውም ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ሰጠን።+ +10 ይኸው አሁን ይሖዋ የሰጠኝ ምድር ካፈራችው ፍሬ በኩር የሆነውን አምጥቻለሁ።’+ “ይህን በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስቀምጠው፤ አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት ስገድ። +11 ከዚያም አንተ፣ ሌዋዊውና በመካከልህ የሚኖረው የባዕድ አገር ሰው አምላክህ ይሖዋ ለአንተና ለቤተሰብህ በሰጠው መልካም ነገር ሁሉ ትደሰታላችሁ።+ +12 “የአሥራት ዓመት በሆነው በሦስተኛው ዓመት የምርትህን አንድ አሥረኛ አሥራት+ እንዲሆን ለይተህ ካስቀመጥክ በኋላ ለሌዋዊው፣ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው* ልጅና ለመበለቲቱ ትሰጣለህ፤ እነሱም በከተሞችህ* ውስጥ እስኪጠግቡ ድረስ ይበሉታል።+ +13 ከዚያም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ትላለህ፦ ‘በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ቅዱስ የሆነውን ነገር ከቤት አውጥቼ ለሌዋዊው፣ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ+ ሰጥቻለሁ። ትእዛዛትህን አልጣስኩም ወይም ችላ አላልኩም። +14 ሐዘን ላይ በተቀመጥኩበት ጊዜ ከእሱ አልበላሁም፤ ወይም ረክሼ ባለሁበት ጊዜ ከእሱ ላይ ምንም ነገር አላነሳሁም፤ አሊያም ለሞተ ሰው ከእሱ ላይ ምንም ነገር አልሰጠሁም። የአምላኬን የይሖዋን ቃል ታዝዣለሁ፤ ያዘዝከኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። +15 እንግዲህ አሁን ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማያት ሆነህ ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረት+ የሰጠኸንን ምድር ይኸውም ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ባርክ።’+ +16 “አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እንድትጠብቅ ዛሬ ያዝሃል። አንተም በሙሉ ልብህና+ በሙሉ ነፍስህ* ፈጽማቸው፤ ጠብቃቸውም። +17 ይሖዋ በመንገዶቹ ከሄድክ እንዲሁም ሥርዓቶቹን፣+ ትእዛዛቱንና+ ድንጋጌዎቹን+ ከጠበቅክና ቃሉን ከሰማህ አምላክህ እንደሚሆን ዛሬ ነግሮሃል። +18 አንተም ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት ሕዝቡ ማለትም ልዩ ንብረቱ*+ እንደምትሆንና ትእዛዛቱን በሙሉ እንደምትጠብቅ የተናገርከውን ቃ��� በዛሬው ዕለት ሰምቷል፤ +19 አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ+ ሆነህ ስትገኝ እሱ ደግሞ በገባው ቃል መሠረት ውዳሴ፣ ዝናና ክብር በማጎናጸፍ፣ ከፈጠራቸው ሌሎች ብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።”+ +4 “አሁንም እስራኤል ሆይ፣ በሕይወት እንድትኖሩና+ የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፣ ትጠብቋቸው ዘንድ የማስተምራችሁን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች አዳምጡ። +2 እኔ የማዛችሁን የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ጠብቁ፤ በምሰጣችሁ ትእዛዝ ላይ ምንም ነገር አትጨምሩ፤ ከዚያም ላይ ምንም አትቀንሱ።+ +3 “ይሖዋ ከፌጎር ባአል ጋር በተያያዘ ምን እንዳደረገ በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል፤ አምላክህ ይሖዋ የፌጎርን ባአል የተከተለውን እያንዳንዱን ሰው ከመካከልህ አጥፍቶታል።+ +4 አምላካችሁን ይሖዋን የሙጥኝ ያላችሁት እናንተ ሁላችሁ ግን ይኸው ዛሬም በሕይወት አላችሁ። +5 እኔም አምላኬ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ሥርዓቶችንና ድንጋጌዎችን+ ያስተማርኳችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ እንድትጠብቋቸው ነው። +6 እነዚህንም በጥንቃቄ ጠብቋቸው፤+ ፈጽሟቸውም፤ እንዲህ ብታደርጉ ስለ እነዚህ ሥርዓቶች ሁሉ በሚሰሙ ሕዝቦች ፊት እንደ ጥበበኞችና+ እንደ አስተዋዮች+ ትቆጠራላችሁ፤ እነሱም ‘ይህ ታላቅ ብሔር በእርግጥም ጥበበኛና አስተዋይ ሕዝብ ነው’+ ይላሉ። +7 በምንጠራው ጊዜ ሁሉ ለእኛ ቅርብ እንደሆነው እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ፣ ለእሱ ቅርብ የሆኑ አማልክት ያሉት ታላቅ ብሔር የትኛው ነው?+ +8 ዛሬ በፊታችሁ እንዳስቀመጥኩት እንደዚህ ሕግ ያለ የጽድቅ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ያሉት የትኛው ታላቅ ብሔር ነው?+ +9 “ዓይኖቻችሁ ያዩአቸውን ነገሮች እንዳትረሱና በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ከልባችሁ እንዳይጠፉ ተጠንቀቁ፤ ራሳችሁንም ጠብቁ።* እነዚህንም ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ንገሯቸው።+ +10 በኮሬብ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት በቆማችሁበት ቀን ይሖዋ ‘በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት+ ይማሩና ልጆቻቸውንም ያስተምሩ+ ዘንድ ቃሌን እንዲሰሙ+ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ’ ብሎኝ ነበር። +11 “በመሆኑም እናንተ መጥታችሁ በተራራው ግርጌ ቆማችሁ፤ ተራራውም እስከ ሰማያት ድረስ* እየነደደ ነበር፤ ጨለማ፣ ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ሆኖ ነበር።+ +12 ይሖዋም ከእሳቱ ውስጥ ያነጋግራችሁ ጀመር።+ እናንተም ድምፅ ከመስማት በስተቀር መልክ አላያችሁም፤+ የሰማችሁት ድምፅ ብቻ ነበር።+ +13 እሱም እንድትጠብቁት ያዘዛችሁን ቃል ኪዳኑን ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት* ገለጸላችሁ።+ ከዚያም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው።+ +14 በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ ገብታችሁ በምትወርሷት ምድር የምትፈጽሟቸውን ሥርዓቶችና ደንቦች እንዳስተምራችሁ አዘዘኝ። +15 “በመሆኑም ይሖዋ በኮሬብ በእሳቱ መካከል ሆኖ ባነጋገራችሁ ቀን ምንም መልክ ስላላያችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤* +16 ይኸውም ምግባረ ብልሹ በመሆን በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን የትኛውንም ዓይነት ምስል፣ የወንድ ወይም የሴት ምስል፣+ +17 በምድር ላይ ያለን የማንኛውንም እንስሳ ምስል ወይም በሰማይ ላይ የሚበርን የማንኛውንም ወፍ ምስል፣+ +18 መሬት ለመሬት የሚሄድን የማንኛውንም ነገር ምስል አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ያለን የማንኛውንም ዓሣ ምስል ለራሳችሁ እንዳትሠሩ ነው።+ +19 እንዲሁም ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ይኸውም የሰማይን ሠራዊት በሙሉ በምታይበት ጊዜ ተታለህ እንዳትሰግድላቸውና እንዳታገለግላቸው።+ እነዚህ አምላክህ ይሖዋ ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸው ናቸው። +20 እናንተን ግን ልክ እንደ ዛሬው ሁሉ ይሖዋ የእሱ የግል ንብረት*+ እንድትሆኑ የብረት ማቅለጫ ምድጃ ከሆነችው ከግብፅ አውጥቶ አመጣችሁ። +21 “ይሖዋ በእናንተ የተነሳ እኔን ተቆጣኝ፤+ ዮርዳኖስን እንደማልሻገርም ሆነ አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንደማልገባ ማለ።+ +22 እንግዲህ እኔ የምሞተው በዚህ አገር ነው፤ ዮርዳኖስን አልሻገርም፤+ እናንተ ግን ተሻግራችሁ ይህችን መልካም ምድር ትወርሳላችሁ። +23 አምላካችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ+ እንዲሁም አምላካችሁ ይሖዋ የከለከላችሁን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል ለራሳችሁ እንዳትሠሩ ተጠንቀቁ።+ +24 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የሚባላ እሳት፣+ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።+ +25 “ልጆችና የልጅ ልጆች ስታፈሩ፣ በምድሪቱም ላይ ረጅም ዘመን ስትኖሩ፣ የጥፋት ጎዳና ወደመከተል ዞር ብትሉና የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል+ ብትሠሩ እንዲሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ክፉ ነገር በመፈጸም እሱን ብታስቆጡት+ +26 ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ያለጥርጥር ወዲያውኑ እንደምትደመሰሱ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምሥክር አድርጌ እጠራባችኋለሁ። በምድሪቱ ላይ ረጅም ዘመን ከመኖር ይልቅ ሙሉ በሙሉ ትደመሰሳላችሁ።+ +27 ይሖዋም በሕዝቦች መካከል ይበትናችኋል፤+ ይሖዋ በሚበትናችሁ ብሔራትም መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ።+ +28 እዚያም ማየትም ሆነ መስማት፣ መብላትም ሆነ ማሽተት የማይችሉ በሰው እጅ የተሠሩ የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን ታገለግላላችሁ።+ +29 “እዚያ ሆናችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ብትፈልጉት፣ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ብትሹት በእርግጥ ታገኙታላችሁ።+ +30 ከጊዜ በኋላ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ስትገባና እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአንተ ላይ ሲደርሱ ያኔ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ትመለሳለህ፤ ድምፁንም ትሰማለህ።+ +31 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መሐሪ አምላክ ነው።+ አይተውህም፣ አያጠፋህም ወይም ለአባቶችህ በመሐላ ያጸናላቸውን ቃል ኪዳን አይረሳም።+ +32 “እንግዲህ ከአንተ ዘመን በፊት ስለነበሩት ስለ ቀደሙት ጊዜያት ይኸውም አምላክ ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ቀን አንስቶ ስላለው ዘመን ጠይቅ፤ ከአንዱ የሰማይ ጥግ እስከ ሌላኛው የሰማይ ጥግ ድረስ እስቲ መርምር። እንዲህ ያለ እጅግ ታላቅ ነገር ተደርጎ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ተሰምቶ ያውቃል?+ +33 ልክ እንደ አንተ፣ አምላክ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሰማና በሕይወት የኖረ ሌላ ሕዝብ አለ?+ +34 ወይስ አምላካችሁ ይሖዋ የገዛ ዓይኖቻችሁ እያዩ ለእናንተ በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ በፍርድ እርምጃዎች፣* ድንቅ በሆኑ ምልክቶች፣ በተአምራት፣+ በጦርነት፣+ በብርቱ እጅ፣+ በተዘረጋ ክንድና አስፈሪ በሆኑ ሥራዎች+ ከሌላ ብሔር መካከል ለራሱ ብሔር ለመውሰድ ሞክሯል? +35 እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ መሆኑን ታውቅ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እንድታይ ተደርገሃል፤+ ከእሱ ሌላ ማንም የለም።+ +36 አንተን ለማረም ከሰማያት ድምፁን እንድትሰማ አደረገህ፤ በምድርም ላይ የእሱን ታላቅ እሳት እንድታይ አደረገህ፤ ድምፁንም ከእሳቱ ውስጥ ሰማህ።+ +37 “እሱ አባቶችህን ስለወደደና ከእነሱ በኋላ የሚመጣውን ዘራቸውን ስለመረጠ+ ከአንተ ጋር በመሆን በታላቅ ኃይሉ ከግብፅ አወጣህ። +38 እንዲሁም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ወደ ምድራቸው ሊያስገባህና ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሊሰጥህ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆኑትን ብሔራት ከፊትህ አባረራቸው።+ +39 እንግዲህ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ እንደሆነ ዛሬ እወቅ፤ እንዲሁም ልብ በል።+ ሌላ ማንም የለ��።+ +40 ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁና አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ለረጅም ዘመን እንድትኖር እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ሥርዓትና ትእዛዛት ጠብቅ።”+ +41 በዚያን ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ።+ +42 ነፍስ ያጠፋ ማንኛውም ግለሰብ ባልንጀራውን የገደለው ሆን ብሎ ካልሆነና የቆየ ጥላቻ ካልነበረው+ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ በዚያ መኖር ይችላል።+ +43 ከተሞቹም ለሮቤላውያን በአምባው ላይ ባለው ምድረ በዳ የምትገኘው ቤጼር፣+ ለጋዳውያን በጊልያድ የምትገኘው ራሞት+ እንዲሁም ለምናሴያውያን በባሳን+ ያለችው ጎላን+ ናቸው። +44 ሙሴ በእስራኤል ሕዝብ ፊት ያስቀመጠው ሕግ+ ይህ ነው። +45 እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ሙሴ የሰጣቸው ማሳሰቢያዎች፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤+ +46 ይህን የነገራቸው በዮርዳኖስ ክልል ከቤትጰኦር+ ባሻገር በሚገኘው ሸለቆ ይኸውም ሙሴና እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ድል ባደረጉት በሃሽቦን+ ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ምድር ነበር።+ +47 እነሱም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው ክልል የነበሩትን የሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ምድር ማለትም የሲሖንን ምድርና የባሳንን ንጉሥ የኦግን+ ምድር ወረሱ፤ +48 ይህም ምድር በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ከሚገኘው ከአሮዔር+ አንስቶ እስከ ሲዎን ተራራ ይኸውም እስከ ሄርሞን+ ድረስ ያለውን አካባቢ ይሸፍናል፤ +49 እንዲሁም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን የአረባን ምድርና በጲስጋ+ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ አረባ ባሕር* ድረስ ያለውን አካባቢ ይጨምራል። +16 “አምላክህ ይሖዋ ከግብፅ በሌሊት ያወጣህ በአቢብ* ወር ስለሆነ የአቢብን ወር አስብ፤+ እንዲሁም ለአምላክህ ለይሖዋ ፋሲካን* አክብር።+ +2 ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በመረጠው ስፍራ+ ከመንጋህና ከከብትህ+ ለአምላክህ ለይሖዋ የፋሲካን መባ ሠዋ።+ +3 ከእሱም ጋር እርሾ የገባበት ምንም ነገር አትብላ፤+ ከግብፅ ምድር የወጣኸው በጥድፊያ ስለነበር+ ለሰባት ቀን ቂጣ* ይኸውም የመከራ ቂጣ ብላ። ይህን የምታደርገው ከግብፅ ምድር የወጣህበትን ዕለት በሕይወት ዘመንህ ሁሉ እንድታስታውስ ነው።+ +4 ለሰባት ቀን በግዛትህ ሁሉ እርሾ አይገኝ፤+ በመጀመሪያው ቀን ምሽት ላይ ከምታቀርበው መሥዋዕት ላይም ቢሆን ምንም ሥጋ ማደር የለበትም።+ +5 የፋሲካውን መባ አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ከተሞች አንተ በፈለግከው በአንዱ ውስጥ መሠዋት አይገባህም። +6 ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ መቅረብ ይኖርበታል። የፋሲካውን መባ ምሽት ላይ ፀሐይ እንደጠለቀች፣+ ከግብፅ በወጣህበት በዚያው ጊዜ ሠዋው። +7 አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ቦታ+ አብስለህ ብላው፤+ ሲነጋም ተመልሰህ ወደ ድንኳንህ መሄድ ትችላለህ። +8 ለስድስት ቀን ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለይሖዋ የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ሥራ አትሥራ።+ +9 “ሰባት ሳምንት ቁጠር። በማሳህ ላይ ያለውን እህል ለማጨድ ማጭድህን ካነሳህበት ጊዜ አንስቶ ሰባት ሳምንት ቁጠር።+ +10 ከዚያም አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን+ በምታቀርበው የፈቃደኝነት መባ አማካኝነት ለአምላክህ ለይሖዋ የሳምንታት በዓልን ታከብራለህ።+ +11 በአምላክህ በይሖዋ ፊት ደስ ይበልህ፤ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ* የሚኖር ሌዋዊ፣ በመካከልህ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው* ልጅና መበለቲቱ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በመረጠው ስፍራ ደስ ይበላችሁ።+ +12 አንተም በግብፅ ባሪያ ���ንደነበርክ አስታውስ፤+ እነዚህንም ሥርዓቶች ጠብቅ እንዲሁም ፈጽም። +13 “እህልህን ከአውድማህ፣ ዘይትህንና የወይን ጠጅህን ከመጭመቂያህ በምታስገባበት ጊዜ የዳስ* በዓልን+ ለሰባት ቀን አክብር። +14 በዓልህን በምታከብርበት ወቅት ደስ ይበልህ፤+ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ፣ የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው ልጅና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ። +15 አምላክህ ይሖዋ ምርትህንና የእጅህን ሥራ ሁሉ ስለሚባርክልህ+ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለይሖዋ ሰባት ቀን በዓሉን ታከብራለህ፤+ አንተም እጅግ ትደሰታለህ።+ +16 “በመካከልህ ያሉ ወንዶች ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ ይኸውም በቂጣ በዓል+ ቀን፣ በሳምንታት በዓል+ ቀን እንዲሁም በዳስ* በዓል+ ቀን አምላክህ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ፊቱ ይቅረቡ፤ ማናቸውም ባዶ እጃቸውን ይሖዋ ፊት አይቅረቡ። +17 እያንዳንዱ ሰው የሚያመጣው ስጦታ አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን መሆን አለበት።+ +18 “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለእያንዳንዱ ነገድ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤+ እነሱም ለሕዝቡ የጽድቅ ፍርድ ይፍረዱ። +19 ፍርድን አታዛባ፤+ አድልዎ አትፈጽም+ ወይም ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራል፤+ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማል። +20 በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ ይሖዋ የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ ፍትሕን፣ አዎ ፍትሕን ተከታተል።+ +21 “ለአምላክህ ለይሖዋ በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የማምለኪያ ግንድ*+ እንዲሆን ማንኛውንም ዓይነት ዛፍ አትትከል። +22 “አምላክህ ይሖዋ አጥብቆ የሚጠላውን የማምለኪያ ዓምድ ለራስህ አታቁም።+ +6 “አምላካችሁ ይሖዋ ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ ትጠብቋቸው ዘንድ እንዳስተምራችሁ የሰጠኝ ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤ +2 ይህም አንተ፣ ልጅህና የልጅ ልጅህ+ ዕድሜያችሁ ይረዝም ዘንድ በሕይወታችሁ ዘመን ሁሉ አምላካችሁን ይሖዋን እንድትፈሩ እንዲሁም እኔ የማዛችሁን የእሱን ደንቦችና ትእዛዛት ሁሉ እንድትጠብቁ ነው።+ +3 እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ ይሖዋ በገባልህ ቃል መሠረት ወተትና ማር በምታፈሰው ምድር እንድትበለጽግና እጅግ እንድትበዛ እነዚህን በጥንቃቄ ጠብቅ። +4 “እስራኤል ሆይ ስማ፣ አምላካችን ይሖዋ አንድ ይሖዋ ነው።+ +5 አንተም አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና*+ በሙሉ ኃይልህ ውደድ።+ +6 እኔ ዛሬ የማዝህን እነዚህን ትእዛዛት በልብህ ያዝ፤ +7 በልጆችህም ውስጥ ቅረጻቸው፤*+ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድ ላይ ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሳ ስለ እነሱ ተናገር።+ +8 በእጅህም ላይ እንደ ማስታወሻ እሰራቸው፤ በግንባርህም ላይ* እንደታሰረ ነገር ይሁኑ።+ +9 በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው። +10 “አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር+ ሲያስገባህና በዚያም አንተ ያልገነባሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞች፣+ +11 አንተ ባልደከምክባቸው የተለያዩ መልካም ነገሮች የተሞሉ ቤቶችን፣ አንተ ያልቦረቦርካቸውን የውኃ ማጠራቀሚያዎች እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ስታገኝ፣ በልተህም ስትጠግብ+ +12 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ይሖዋን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።+ +13 ይሖዋ አምላክህን ፍራ፤+ እሱን አገልግል፤+ በስሙም ማል።+ +14 ሌሎች አማልክትን ይኸውም በዙሪያችሁ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን የትኞቹንም አማልክት አትከተሉ፤+ +15 ምክንያቱም በመካከልህ ያለው አምላክህ ይሖዋ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።+ አለዚያ የአምላክህ የይሖዋ ቁጣ በላይህ ይነድዳል፤+ ከምድርም ገጽ ጠራርጎ ያጠፋሃል።+ +16 “በማሳህ እንደተፈታተናችሁት+ አምላካችሁን ይሖዋን አትፈታተኑት።+ +17 አምላካችሁ ይሖዋ እንድትጠብቋቸው ያዘዛችሁን ትእዛዛት እንዲሁም ማሳሰቢያዎቹንና ሥርዓቶቹን በጥንቃቄ ጠብቁ። +18 እንድትበለጽግና ይሖዋ ለአባቶችህ የማለላቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ እንድትወርስ በይሖዋ ፊት ትክክልና መልካም የሆነውን አድርግ፤+ +19 ይሖዋ በገባው ቃል መሠረት ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ አባረህ አስወጣ።+ +20 “ወደፊት ልጅህ ‘አምላካችን ይሖዋ የሰጣችሁ ማሳሰቢያዎች፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ትርጉም ምንድን ነው?’ ብሎ ሲጠይቅህ +21 እንዲህ ትለዋለህ፦ ‘እኛ በግብፅ የፈርዖን ባሪያዎች ሆነን ነበር፤ ይሖዋ ግን በብርቱ ክንድ ከግብፅ አወጣን። +22 ይሖዋም በግብፅ፣ በፈርዖንና በቤተሰቡ ሁሉ ላይ+ ታላላቅና አጥፊ የሆኑ ድንቅ ምልክቶችንና ተአምራትን+ ዓይናችን እያየ ፈጸመ። +23 እኛንም ለአባቶቻችን የማለላቸውን ምድር ሊሰጠን ከዚያ አውጥቶ ወደዚህ አመጣን።+ +24 ከዚያም ይሖዋ ምንጊዜም መልካም ይሆንልን ዘንድ እነዚህን ሥርዓቶች ሁሉ እንድንፈጽምና አምላካችንን ይሖዋን እንድንፈራ አዘዘን፤+ ይህም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ በሕይወት እንድንኖር ነው።+ +25 አምላካችንን ይሖዋን በመታዘዝ* ልክ እሱ በሰጠን መመሪያ መሠረት እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ በጥንቃቄ ብንፈጽም ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።’+ +25 “በሰዎች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ሰዎቹ ዳኞች ፊት መቅረብ ይችላሉ፤+ እነሱም ይዳኟቸዋል፤ ጻድቅ የሆነውን ንጹሕ፣ ጥፋተኛ የሆነውን ደግሞ በደለኛ ይሉታል።+ +2 ጥፋተኛው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ+ ዳኛው መሬት ላይ እንዲያስተኙትና እሱ ባለበት እንዲገረፍ ያደርጋል። የግርፋቱም ቁጥር ከሠራው ጥፋት ጋር የሚመጣጠን ይሁን። +3 እስከ 40 ግርፋት ሊገርፈው ይችላል፤+ ከዚያ ማስበለጥ ግን የለበትም። ከዚህ የበለጠ ብዙ ግርፋት ከገረፈው ግን ወንድምህ በፊትህ ይዋረዳል። +4 “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር።+ +5 “ወንድማማቾች አንድ ላይ ሲኖሩ ቆይተው ከመካከላቸው አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ የሆነ ሰው ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ወደ እሷ በመሄድ ሚስቱ አድርጎ ይውሰዳት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።+ +6 መጀመሪያ የምትወልደው ልጅ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራል፤+ ይህ የሚሆነው የሟቹ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ነው።+ +7 “ሰውየው የሟች ወንድሙን ሚስት ለማግባት ፈቃደኛ ካልሆነ መበለት የሆነችው ሴት በከተማዋ በር ወደሚገኙት ሽማግሌዎች ሄዳ ‘የባሌ ወንድም የወንድሙ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም። የዋርሳነት ግዴታውን ሊፈጽምልኝ አልተስማማም’ ትበላቸው። +8 የከተማዋ ሽማግሌዎችም ጠርተው ያናግሩት። እሱም ‘እኔ እሷን ማግባት አልፈልግም’ ብሎ በሐሳቡ ከጸና +9 የወንድሙ ሚስት በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እሱ ቀርባ ጫማውን ከእግሩ ላይ ታውልቅ፤+ ከዚያም ፊቱ ላይ ትትፋበትና ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ የሚደረግበት እንዲህ ነው’ ትበል። +10 ከዚያ በኋላ የዚያ ሰው ቤተሰብ ስም* በእስራኤል ውስጥ ‘ጫማው የወለቀበት ሰው ቤት’ ይባላል። +11 “ሁለት ሰዎች ቢደባደቡና የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል ስትል እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዝ +12 እጇን ቁረጠው። ልታዝንላት አይገባም።* +13 “በከረጢትህ ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት የሚዛን ድንጋዮች አይኑሩህ።+ +14 በቤትህም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት መስፈሪያዎች* ���ይኑሩህ።+ +15 አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም ትክክለኛና ሐቀኛ ሚዛን እንዲሁም ትክክለኛና ሐቀኛ መስፈሪያ ይኑርህ።+ +16 ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ነገሮችን በማድረግ ፍትሕ የጎደለው ድርጊት የሚፈጽም ሰው ሁሉ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው።+ +17 “ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አማሌቃውያን ያደረጉባችሁን ነገር አስታውሱ፤+ +18 በጉዞ ላይ ሳለህ ደክመህና ዝለህ በነበረበት ጊዜ አግኝተውህ ከኋላ ከኋላህ እያዘገሙ በነበሩት ሁሉ ላይ እንዴት ጥቃት እንደሰነዘሩ አስታውስ። አምላክንም አልፈሩም። +19 አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ አምላክህ ይሖዋ በዙሪያህ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ በሚያሳርፍህ ጊዜ+ አማሌቃውያንን ከሰማይ በታች ጨርሶ እንዳይታወሱ አድርገህ ጠራርገህ አጥፋቸው።+ ይህን አትርሳ። +33 የእውነተኛው አምላክ ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት እስራኤላውያንን የባረካቸው በረከት ይህ ነው።+ +2 እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ከሲና መጣ፤+ከሴይርም ሆኖ አበራባቸው። ከፋራን ተራራማ አካባቢዎችም በክብር አበራ፤+ከእሱም ጋር አእላፋት ቅዱሳን* ነበሩ፤+በቀኙም ተዋጊዎቹ አሉ።+ + 3 እሱ ሕዝቡን ይወዳል፤+ቅዱስ የሆነው ሕዝብ ሁሉ እጅህ ውስጥ ነው።+ እነሱም እግርህ ሥር ተቀምጠዋል፤+ቃልህንም ይሰማሉ።+ + 4 (ሙሴ ትእዛዝን ይኸውም ሕግን ሰጠን፤+ይህም ለያዕቆብ ጉባኤ እንደ ርስት ነው።)+ + 5 የሕዝቡ መሪዎች ከመላው የእስራኤል ነገድ ጋር+አንድ ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ፣+አምላክ በየሹሩን*+ ላይ ንጉሥ ሆነ። + 6 ሮቤል በሕይወት ይኑር፣ አይሙት፤+የወገኖቹም ቁጥር አይቀንስ።”+ + 7 ይሁዳንም እንዲህ ሲል ባረከው፦+ “ይሖዋ ሆይ፣ የይሁዳን ድምፅ ስማ፤+ወደ ሕዝቦቹም መልሰህ አምጣው። እጆቹ የእሱ ለሆነው ይከላከላሉ፤*አንተም ጠላቶቹን እንዲዋጋ እርዳው።”+ + 8 ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦+ “የአንተ* ቱሚምና ኡሪም+ ለአንተ ታማኝ ለሆነ፣+በማሳህ ለፈተንከው ሰው ይሆናል፤+ በመሪባ ውኃዎች አጠገብ ተጣላኸው፤+ + 9 ሰውየው አባቱንና እናቱን በተመለከተ ‘ስለ እነሱ ግድ የለኝም’ አለ። ሌላው ቀርቶ ወንድሞቹን እንኳ አልተቀበለም፤+የገዛ ልጆቹንም ችላ አለ። ቃልህን ታዘዋልና፤ቃል ኪዳንህንም ጠብቀዋል።+ +10 ለያዕቆብ ድንጋጌህን፣+ለእስራኤልም ሕግህን ያስተምሩ።+ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሸትህ ዕጣን ያቅርቡልህ፤+በመሠዊያህም ላይ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባ ይሠዉልህ።+ +11 ይሖዋ ሆይ፣ ጉልበቱን ባርክለት፤በእጆቹም ሥራ ደስ ይበልህ። እሱን የሚጠሉት ዳግመኛ እንዳያንሰራሩበእሱ ላይ የሚነሱትን እግራቸውን* አድቅቅ።” +12 ስለ ቢንያም እንዲህ አለ፦+ “ይሖዋ የወደደው ያለስጋት አብሮት ይኑር፤ቀኑን ሙሉ ይከልለዋልና፤በትከሻዎቹም መካከል ይኖራል።” +13 ስለ ዮሴፍ እንዲህ አለ፦+ “ይሖዋ ከሰማይ በሚወርዱ ምርጥ ነገሮች፣በጤዛና ከታች በሚመነጩ ውኃዎች+ምድሩን ይባርክ፤+ +14 እንዲሁም ፀሐይ በምታስገኛቸው ምርጥ ነገሮች፣በየወሩ በሚገኝ ምርጥ ፍሬ፣+ +15 ጥንታዊ ከሆኑ ተራሮች* በሚገኙ ምርጥ ነገሮች፣+ጸንተው ከሚኖሩት ኮረብቶች በሚገኙ ምርጥ ነገሮች፣ +16 ከምድር በሚገኙ ምርጥ ነገሮችና ምድርን በሞሉ ምርጥ ነገሮች፣+በቁጥቋጦው ውስጥ በተገለጠው በእሱ ሞገስ ይባርክ።+ እነዚህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ፣ከወንድሞቹ መካከል ተነጥሎ በወጣው አናት ላይ ይውረዱ።+ +17 ግርማው እንደ በኩር በሬ ነው፤ቀንዶቹም የዱር በሬ ቀንድ ናቸው። በእነሱም ሰዎችን፣ሕዝቦችን ሁሉ እስከ ምድር ዳርቻ ይገፋል።* እነሱ የኤፍሬም አሥር ሺዎች ናቸው፤+የምናሴም ሺዎች ናቸው።” +18 ስለ ዛብሎን እንዲህ አለ፦+ “ዛብሎን ሆይ፣ በመውጣት�� ደስ ይበልህ፤አንተም ይሳኮር፣ በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ።+ +19 ሰዎችን ወደ ተራራው ይጠራሉ። በዚያም የጽድቅ መሥዋዕቶችን ያቀርባሉ። ምክንያቱም በባሕሮች ውስጥ ካለው የተትረፈረፈ ሀብት፣በአሸዋም ውስጥ ተሰውሮ ከተከማቸው ነገር* ዝቀው ያወጣሉ።” +20 ስለ ጋድ እንዲህ አለ፦+ “የጋድን ድንበሮች የሚያሰፋ የተባረከ ነው።+ በዚያ እንደ አንበሳ ይተኛል፤ክንድን፣ አዎ አናትን ለመዘነጣጠል ተዘጋጅቶ ይጠብቃል። +21 የመጀመሪያውን መርጦ ለራሱ ይወስዳል፤+በዚያ የሕግ ሰጪው ድርሻ ተለይቶ ተቀምጧልና።+ የሕዝቡ መሪዎች አንድ ላይ ይሰበሰባሉ። የይሖዋን ጽድቅና ድንጋጌዎች፣በእስራኤል ያስፈጽማል።” +22 ስለ ዳን እንዲህ አለ፦+ “ዳን የአንበሳ ደቦል ነው።+ ከባሳን ዘሎ ይወጣል።”+ +23 ስለ ንፍታሌም እንዲህ አለ፦+ “ንፍታሌም በይሖዋ ሞገስ ረክቷል፤በእሱም በረከት ተሞልቷል። ምዕራቡንና ደቡቡን ውረስ።” +24 ስለ አሴር እንዲህ አለ፦+ “አሴር በልጆች የተባረከ ነው። በወንድሞቹ ፊት ሞገስ ያግኝ፤እግሩንም ዘይት ውስጥ ይንከር።* +25 የበርህ መቀርቀሪያ ብረትና መዳብ ናቸው፤+በዘመንህ ሁሉ ያለስጋት ትኖራለህ።* +26 አንተን ለመርዳት በሰማይ ውስጥ የሚጋልብ፣በግርማው በደመና ላይ የሚገሰግስ፣+እንደ እውነተኛው የየሹሩን+ አምላክ ያለ ማንም የለም።+ +27 አምላክ ከጥንት ጀምሮ መሸሸጊያ ነው፤+ዘላለማዊ ክንዶቹ ከበታችህ ናቸው።+ ጠላትን ከፊትህ ያባርራል፤+እንዲሁም ‘አጥፋቸው!’ ይላል።+ +28 እህልና አዲስ የወይን ጠጅ ባለበት ምድር፣+ሰማያቱ ጠል በሚያንጠባጥቡበት+እስራኤል ያለስጋት ይቀመጣል፤የያዕቆብም ምንጭ የተገለለ ይሆናል። +29 እስራኤል ሆይ፣ ደስተኛ ነህ!+ የይሖዋን ማዳን ያየ፣+እንደ አንተ ያለ ሕዝብ ማን አለ?+እሱ የሚከልል ጋሻህና+ታላቅ ሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፤+አንተም በጀርባቸው* ላይ ትራመዳለህ።” +10 “በዚያን ጊዜ ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጠርበህ+ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፤ የእንጨት ታቦትም* ለራስህ ሥራ። +2 እኔም በጽላቶቹ ላይ አንተ በሰበርካቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፋለሁ፤ አንተም ጽላቶቹን በታቦቱ ውስጥ አስቀምጣቸው።’ +3 ስለዚህ ከግራር እንጨት ታቦት ሠራሁ፤ ከዚያም እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ የድንጋይ ጽላቶችን ከቀረጽኩ በኋላ ሁለቱን ጽላቶች ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ።+ +4 እሱም በጽላቶቹ ላይ ቀደም ሲል ጽፏቸው የነበሩትን ቃላት+ ይኸውም ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን+ ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ+ ለእናንተ ነግሯችሁ የነበሩትን አሥርቱን ትእዛዛት*+ ጻፈባቸው፤ ይሖዋም ጽላቶቹን ለእኔ ሰጠኝ። +5 እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድኩ፤+ ይሖዋም ባዘዘኝ መሠረት ጽላቶቹን፣ በሠራሁት ታቦት ውስጥ አስቀመጥኳቸው። እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይገኛሉ። +6 “ከዚያም እስራኤላውያን ከበኤሮት ብኔያዕቃን ተነስተው ወደ ሞሴራ ሄዱ። አሮንም በዚያ ቦታ ሞቶ ተቀበረ፤+ ልጁ አልዓዛርም በእሱ ምትክ ካህን ሆኖ ማገልገል ጀመረ።+ +7 ከዚያም ተነስተው ወደ ጉድጎዳ ተጓዙ፤ ከጉድጎዳም ተነስተው ጅረቶች* ወደሚፈስሱባት ምድር ወደ ዮጥባታ+ ሄዱ። +8 “በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፣+ ይሖዋን ለማገልገል በፊቱ እንዲቆምና እስከ ዛሬ እንደሚያደርገው በስሙ እንዲባርክ+ የሌዊን ነገድ ለየ።+ +9 ሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ለዚህ ነው። አምላክህ ይሖዋ በነገረው መሠረት ይሖዋ ርስቱ ነው።+ +10 እኔም እንደ መጀመሪያው ጊዜ ሁሉ በተራራው ላይ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት ቆየሁ፤+ በዚህ ጊዜም ደግሞ ይሖዋ ሰማ��።+ ይሖዋ ሊያጠፋህ አልፈለገም። +11 ከዚያም ይሖዋ ‘ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማልኩላቸውን ምድር ገብተው እንዲወርሱ ተነስና ከሕዝቡ ፊት ፊት ሂድ’ አለኝ።+ +12 “እንግዲህ እስራኤል ሆይ፣ አምላክህ ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?+ አምላክህን ይሖዋን እንድትፈራው፣+ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ፣+ እንድትወደው፣ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ* እንድታገለግለው+ +13 እንዲሁም ለገዛ ጥቅምህ ስትል እኔ ዛሬ የማዝህን የይሖዋን ትእዛዛትና ደንቦች እንድትጠብቅ ብቻ ነው።+ +14 እነሆ ሰማያት፣ ሌላው ቀርቶ ሰማየ ሰማያት* እንዲሁም ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ የአምላክህ የይሖዋ ናቸው።+ +15 ይሁንና ይሖዋ የቀረበውና ፍቅሩን የገለጸው ለአባቶችህ ብቻ ነው፤ ስለሆነም ይኸው ዛሬ እንደሆነው የእነሱ ዘር የሆናችሁትን እናንተን ከሕዝቦች ሁሉ መካከል መረጠ።+ +16 ስለዚህ ልባችሁን አንጹ፤*+ ከእንግዲህም ወዲህ ግትር መሆናችሁን ተዉ።*+ +17 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የአማልክት አምላክና+ የጌቶች ጌታ እንዲሁም ታላቅ፣ ኃያል፣ የሚያስፈራ፣ ለማንም የማያዳላና+ ጉቦ የማይቀበል አምላክ ነው። +18 አባት ለሌለው* ልጅና ለመበለት ይፈርዳል፤+ እንዲሁም የባዕድ አገሩን ሰው ይወደዋል፤+ ምግብና ልብስም ይሰጠዋል። +19 እናንተም የባዕድ አገሩን ሰው ውደዱ፤ ምክንያቱም በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ።+ +20 “አምላክህን ይሖዋን ፍራ፤ አገልግለው፤+ ከእሱም ጋር ተጣበቅ፤ በስሙም ማል። +21 ልታወድሰው የሚገባህ እሱን ነው።+ እሱ በዓይኖችህ ያየሃቸውን እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ሁሉ ያደረገልህ አምላክህ ነው።+ +22 አባቶችህ ወደ ግብፅ ሲወርዱ 70* ነበሩ፤+ አሁን ግን አምላክህ ይሖዋ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት ቁጥርህን አብዝቶታል።+ +14 “እናንተ የአምላካችሁ የይሖዋ ልጆች ናችሁ። ለሞተ ሰው ብላችሁ ሰውነታችሁን አትተልትሉ፤+ ቅንድባችሁንም* አትላጩ።+ +2 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤+ ይሖዋም በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ* እንድትሆን መርጦሃል።+ +3 “ማንኛውንም አስጸያፊ ነገር አትብላ።+ +4 የምትበሏቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው፦+ በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣ +5 ርኤም፣ የሜዳ ፍየል፣ ድኩላ፣ የዱር ፍየል፣ አጋዘን፣ የዱር በግ እና የተራራ በግ። +6 ለሁለት የተከፈለ የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውን እንዲሁም የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ። +7 ሆኖም ከሚያመሰኩት ወይም የተሰነጠቀ ሰኮና ካላቸው እንስሳት መካከል እነዚህን አትብሉ፦ ግመል፣ ጥንቸልና ሽኮኮ፤ ምክንያቱም እነዚህ እንስሳት ቢያመሰኩም ሰኮናቸው ስንጥቅ አይደለም። እነሱ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።+ +8 አሳማም እንደዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ሰኮናው ስንጥቅ ቢሆንም አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። ሥጋቸውን መብላትም ሆነ በድናቸውን መንካት የለባችሁም። +9 “በውኃ ውስጥ ከሚኖሩ መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ሁሉ መብላት ትችላላችሁ።+ +10 ሆኖም ክንፍና ቅርፊት የሌለውን ማንኛውንም ነገር አትብሉ። ለእናንተ ርኩስ ነው። +11 “ንጹሕ የሆነውን ወፍ ሁሉ መብላት ትችላላችሁ። +12 እነዚህን ግን አትብሉ፦ ንስር፣ ዓሣ በል ጭላት፣ ጥቁር ጥምብ አንሳ፣+ +13 ቀይ ጭልፊትም ሆነ ጥቁር ጭልፊት እንዲሁም ሁሉንም ዓይነት ሌሎች ጭልፊቶች፣ +14 ማንኛውንም ዓይነት ቁራ፣ +15 ሰጎን፣ ጉጉት፣ ዓሣ አዳኝ ወፍ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሲላ፣ +16 ትንሿ ጉጉት፣ ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉት፣ ዝይ፣ +17 ሻላ፣ ጥምብ አንሳ፣ ለማሚት፣ +18 ራዛ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሽመላ፣ ጅንጅ��ቴና የሌሊት ወፍ። +19 በተጨማሪም ክንፍ ያላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት* በሙሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። መበላት የለባቸውም። +20 ንጹሕ የሆነን ማንኛውንም የሚበር ፍጥረት መብላት ትችላላችሁ። +21 “ሞቶ የተገኘን ማንኛውንም እንስሳ አትብሉ።+ ከዚህ ይልቅ በከተሞችህ* ውስጥ ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ልትሰጠውና እሱ ሊበላው ይችላል፤ አሊያም ለባዕድ አገር ሰው ሊሸጥ ይችላል። ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ። “የፍየልን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።+ +22 “በየዓመቱ ከእርሻህ ላይ ከምታገኘው ምርት ሁሉ አንድ አሥረኛውን* መስጠት አለብህ።+ +23 ዘወትር አምላክህን ይሖዋን መፍራትን+ እንድትማር የእህልህን፣ የአዲስ የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አንድ አሥረኛ እንዲሁም የከብትህንና የመንጋህን በኩራት በአምላክህ በይሖዋ ፊት ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ ብላ።+ +24 “ሆኖም አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን የሚመርጠው ስፍራ+ አንተ ካለህበት ቦታ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ መንገዱ በጣም ቢረዝምብህና (አምላክህ ይሖዋ ስለባረከህ) እዚያ ድረስ ተሸክመኸው መሄድ ባትችል +25 ወደ ገንዘብ ልትቀይረው ትችላለህ፤ ገንዘቡንም ይዘህ አምላክህ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ። +26 ከዚያም በገንዘቡ የምትሻውን* ነገር ይኸውም ከብት፣ በግ፣ ፍየል፣ የወይን ጠጅ፣ ሌላ የሚያሰክር መጠጥና የሚያስደስትህን* ማንኛውንም ነገር መግዛት ትችላለህ፤ አንተና ቤተሰብህም በአምላክህ በይሖዋ ፊት በዚያ ብሉ፤ ተደሰቱም።+ +27 በከተሞችህ ውስጥ የሚኖረውን ሌዋዊ ችላ አትበለው፤+ ምክንያቱም እሱ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ የለውም።+ +28 “በየሦስት ዓመቱ መጨረሻ ላይ በዚያ ዓመት ያገኘኸውን ምርት አንድ አሥረኛ በሙሉ አምጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች።+ +29 አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ የሌለው ሌዋዊ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች፣ አባት የሌላቸው* ልጆችና መበለቶች መጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ይብሉ።+ +9 “እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ እንግዲህ ዛሬ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆኑ ብሔራትን+ እንዲሁም ታላላቅና እስከ ሰማያት የሚደርስ ቅጥር ያላቸውን ከተሞች+ በማስለቀቅ ወደ ምድሪቱ ለመግባት ዮርዳኖስን ልትሻገር ነው፤+ +2 ‘የኤናቅን ልጆች ማን ሊቋቋማቸው ይችላል?’ ሲባልላቸው የሰማኸውን፣ አንተ ራስህ የምታውቃቸውን ታላቅ ሕዝብና ቁመተ ረጃጅም የሆኑትን የኤናቅን ልጆችም+ ልታስለቅቅ ነው። +3 ስለሆነም አምላክህ ይሖዋ ዛሬ ከአንተ ቀድሞ እንደሚሻገር እወቅ።+ እሱ የሚባላ እሳት ነው፤+ ደግሞም ያጠፋቸዋል። ልክ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት በፍጥነት ታባርራቸውና* ታጠፋቸው ዘንድ ዓይንህ እያየ ድል ያደርጋቸዋል።+ +4 “አምላክህ ይሖዋ እነሱን ከፊትህ በሚያባርራቸው ጊዜ በልብህ ‘ይሖዋ ይህችን ምድር እንድወርስ ወደዚህ ያመጣኝ እኮ በራሴ ጽድቅ ነው’ አትበል፤+ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው በራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው።+ +5 የእነሱን ምድር ገብተህ የምትወርሰው ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሳ አይደለም። ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው ከራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው፤+ እንዲሁም ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣+ ለይስሐቅና+ ለያዕቆብ+ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም ሲል ነው። +6 ስለዚህ አምላክህ ይሖዋ ይህችን መልካም ምድር እንድትወርሳት የሚሰጥህ ከጽድቅህ የተነሳ እንዳልሆነ እወቅ፤ ምክንያቱም አንተ ግትር* ሕዝብ ነህ።+ +7 “በምድረ በዳ አምላክህን ይሖዋን እንዴት እንዳስቆጣኸው+ አስታውስ፤ ፈጽሞም አትርሳ። ከግብፅ ምድር ከወጣችሁበት ጊዜ አንስቶ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ በይሖዋ ላይ ዓምፃችኋል።+ +8 በኮሬብም እንኳ ይሖዋን አስቆጥታችሁት ነበር፤ ይሖዋም በእናንተ ላይ እጅግ ከመቆጣቱ የተነሳ እናንተን ለማጥፋት አስቦ ነበር።+ +9 እኔም የድንጋይ ጽላቶቹን+ ይኸውም ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን የተጻፈባቸውን ጽላቶች+ ለመቀበል ወደ ተራራው በወጣሁ ጊዜ እህል ሳልበላና ውኃ ሳልጠጣ በተራራው ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆይቼ ነበር።+ +10 ከዚያም ይሖዋ በአምላክ ጣት የተጻፈባቸውን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፤ በእነሱም ላይ ይሖዋ እዚያ ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የነገራችሁ ነገር ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር።+ +11 ከ40 ቀንና ከ40 ሌሊት በኋላ ይሖዋ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ይኸውም የቃል ኪዳኑን ጽላቶች ሰጠኝ፤ +12 ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ ‘ተነስ፤ ቶሎ ብለህ ውረድ፤ ምክንያቱም ከግብፅ ያወጣኸው ሕዝብህ የጥፋት ጎዳና እየተከተለ ነው።+ እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ፈጥነው ዞር ብለዋል። ከብረት የተሠራ ምስልም* ለራሳቸው አበጅተዋል።’+ +13 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ፤ በእርግጥም ግትር* ሕዝብ ነው።+ +14 አጠፋቸውና ስማቸውን ከሰማይ በታች እደመስሰው ዘንድ ተወኝ፤ አንተን ግን ከእነሱ ይልቅ ኃያልና ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ብሔር አደርግሃለሁ።’+ +15 “እኔም ተራራው በእሳት እየተቀጣጠለ+ እያለ ተመልሼ ከተራራው ወረድኩ፤ ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶችም በእጆቼ ይዤ ነበር።+ +16 ከዚያም ስመለከት በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንደፈጸማችሁ አየሁ! ለራሳችሁም የብረት* ጥጃ ሠርታችሁ ነበር። ይሖዋ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ዞር ብላችሁ ነበር።+ +17 ስለዚህ ሁለቱን ጽላቶች አሽቀንጥሬ በመወርወር ዓይናችሁ እያየ ሰባበርኳቸው።+ +18 ከዚያም እንደ መጀመሪያው ጊዜ ሁሉ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት በይሖዋ ፊት ተደፋሁ። በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በማድረግና እሱን በማስቆጣት በፈጸማችሁት ኃጢአት ሁሉ የተነሳ እህል አልቀመስኩም፤ ውኃም አልጠጣሁም።+ +19 ምክንያቱም ይሖዋ በእናንተ ላይ እጅግ ከመቆጣቱ የተነሳ ሊያጠፋችሁ ስለተዘጋጀ+ ፈርቼ ነበር። ይሁንና ይሖዋ በዚያን ጊዜም ሰማኝ።+ +20 “ይሖዋ አሮንን ለማጥፋት እስኪያስብ ድረስ በእሱ ላይ ተቆጥቶ ነበር፤+ ሆኖም በዚያን ጊዜ ስለ አሮንም ምልጃ አቀረብኩ። +21 ከዚያም የኃጢአት ሥራችሁን ይኸውም ጥጃውን+ ወስጄ በእሳት አቃጠልኩት፤ ሰባበርኩት፤ እንደ አቧራ ብናኝ እስኪሆንም ድረስ ፈጨሁት፤ ብናኙንም ከተራራው በሚወርደው ጅረት ውስጥ በተንኩት።+ +22 “በተጨማሪም በታበራ፣+ በማሳህ+ እና በቂብሮትሃታባ+ ይሖዋን አስቆጣችሁት። +23 ይሖዋ ከቃዴስበርኔ+ በላካችሁና ‘ውጡ፤ የምሰጣችሁንም ምድር ውረሱ!’ ባላችሁ ጊዜ በአምላካችሁ በይሖዋ ትእዛዝ ላይ በድጋሚ ዓመፃችሁ፤+ በእሱ አልታመናችሁም፤+ እንዲሁም አልታዘዛችሁትም። +24 እኔ እናንተን ካወቅኩበት ጊዜ አንስቶ በይሖዋ ላይ እንዳመፃችሁ ነው። +25 “በመሆኑም 40 ቀንና 40 ሌሊት በይሖዋ ፊት ተደፋሁ፤+ እንዲህ በፊቱ የተደፋሁት፣ ይሖዋ እንደሚያጠፋችሁ ተናግሮ ስለነበር ነው። +26 ከዚያም እንዲህ በማለት ይሖዋን መማጸን ጀመርኩ፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን አታጥፋ። እነሱ በታላቅነትህ የታደግካቸውና በኃያል ክንድህ ከግብፅ ያወጣሃቸው+ የግል ንብረቶችህ*+ ናቸው። +27 አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስብ።+ የዚህን ሕዝብ ግትርነት፣ ክፋትና ኃጢአት አትመልከት።+ +28 አለዚያ እኛን ባወጣህበት ምድር የሚገኙ ሰዎች “ይሖዋ ���ል ወደገባላቸው ምድር ሊያስገባቸው ስላልቻለና ስለጠላቸው በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው” ሊሉ ይችላሉ።+ +29 እነሱ በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋ ክንድህ ያወጣሃቸው+ ሕዝቦችህና የግል ንብረቶችህ*+ ናቸው።’ +27 ከዚያም ሙሴ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “እኔ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ። +2 አምላካችሁ ይሖዋ ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በምትሻገሩበት ቀን ትላልቅ ድንጋዮችን አቁማችሁ ለስኗቸው።*+ +3 ከዚያም የአባቶችህ አምላክ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት አምላክህ ይሖዋ ወደሚሰጥህ ምድር ይኸውም ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ ለመግባት በምትሻገርበት ጊዜ የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ ጻፍባቸው። +4 ዮርዳኖስን ስትሻገሩ ዛሬ በሰጠኋችሁ ትእዛዝ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በኤባል ተራራ+ ላይ አቁሟቸው፤ ደግሞም ለስኗቸው።* +5 በዚያም ለአምላክህ ለይሖዋ መሠዊያ ይኸውም የድንጋይ መሠዊያ ሥራ። ድንጋዮቹንም የብረት መሣሪያ አታስነካቸው።+ +6 የአምላክህን የይሖዋን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥራ፤ በላዩም ላይ ለአምላክህ ለይሖዋ የሚቃጠሉ መባዎችን አቅርብ። +7 የኅብረት መሥዋዕቶችንም አቅርብ፤+ መሥዋዕቶቹንም እዚያው ብላቸው፤+ አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት ደስ ይልሃል።+ +8 በድንጋዮቹም ላይ የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በግልጽ ጻፍባቸው።”+ +9 ከዚያም ሙሴና ሌዋውያኑ ካህናት እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አሏቸው፦ “እስራኤል ሆይ፣ ጸጥ ብለህ አዳምጥ። በዛሬው ቀን አንተ የአምላክህ የይሖዋ ሕዝብ ሆነሃል።+ +10 የአምላክህን የይሖዋን ቃል ስማ፤ እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ሥርዓቶች ፈጽም።”+ +11 ሙሴም በዚያ ቀን ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፦ +12 “ዮርዳኖስን በምትሻገሩበት ጊዜ በገሪዛን ተራራ+ ላይ ቆመው ሕዝቡን የሚባርኩት ነገዶች ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍ እና ቢንያም ናቸው። +13 እርግማኑን ለማሰማት በኤባል ተራራ+ ላይ የሚቆሙት ደግሞ ሮቤል፣ ጋድ፣ አሴር፣ ዛብሎን፣ ዳን እና ንፍታሌም ናቸው። +14 ሌዋውያኑም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ለእያንዳንዱ እስራኤላዊ እንዲህ ብለው ይናገራሉ፦+ +15 “‘ይሖዋ የሚጠላውን አስጸያፊ ነገር+ ይኸውም የአንድ የእጅ ጥበብ ባለሙያ* የእጅ ሥራ ውጤት የሆነውን የተቀረጸ ምስል+ ወይም ከብረት የተሠራ ሐውልት*+ የሚሠራና በስውር የሚያስቀምጥ ሰው የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’* ብሎ ይመልሳል።) +16 “‘አባቱን ወይም እናቱን የሚንቅ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +17 “‘የጎረቤቱን የወሰን ምልክት የሚገፋ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +18 “‘ዓይነ ስውሩን መንገድ የሚያሳስት የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +19 “‘የባዕድ አገሩን ሰው፣ አባት የሌለውን* ልጅ ወይም የመበለቲቱን ፍርድ የሚያዛባ+ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +20 “‘ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ አባቱን ስላዋረደ* የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +21 “‘ከማንኛውም ዓይነት እንስሳ ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +22 “‘የአባቱ ልጅ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው ከእህቱ ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +23 “‘ከሚስቱ እናት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +24 “‘ጎረቤቱን አድብቶ በመጠበቅ የሚገድል የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +25 “‘ንጹሑን ሰው* ለመግደል ሲል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +26 “‘የዚህን ሕግ ቃል ተግባራዊ በማድረግ የማይጠብቅ ሰው የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) +13 “አንድ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ከመካከልህ ተነስቶ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር እንደሚያሳይ ቢነግርህና +2 የነገረህ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር ቢፈጸም፣ እሱም ‘ሌሎች አማልክትን ይኸውም አንተ የማታውቃቸውን አማልክት እንከተል፤ እናገልግላቸውም’ ቢልህ፣ +3 የዚያን ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቃል እንዳትሰማ፤+ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ* አምላካችሁን ይሖዋን ትወዱት+ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ እየፈተናችሁ ነው።+ +4 እናንተ አምላካችሁን ይሖዋን ተከተሉ፤ እሱን ፍሩ፤ ትእዛዛቱን ጠብቁ፤ ቃሉን ስሙ፤ እሱን አገልግሉ፤ እንዲሁም እሱን አጥብቃችሁ ያዙ።+ +5 ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ግን ይገደል፤+ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ ዞር እንድትሉ፣ ከግብፅ ምድር ባወጣችሁና ከባርነት ቤት በታደጋችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እንድታምፁ አበረታቷችኋል። አንተም ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።+ +6 “የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ አሊያም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ጓደኛህ* ‘ሌሎች አማልክትን እናምልክ’+ በማለት በሚስጥር ሊያባብልህ ቢሞክርና እነዚህ አማልክት ደግሞ አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸው +7 እንዲሁም በቅርብም ሆነ በሩቅ፣ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ የሚገኙ በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸው አማልክት ቢሆኑ +8 እሺ አትበለው ወይም አትስማው+ አሊያም አትዘንለት ወይም ደግሞ አትራራለት፤ ከለላም አትሁነው፤ +9 ከዚህ ይልቅ ያለማመንታት ግደለው።+ እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጅህን መሰንዘር ያለብህ አንተ ነህ፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ይሰንዝርበት።+ +10 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከይሖዋ ዞር እንድትል ሊያደርግህ ስለሞከረ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።+ +11 ከዚያም እስራኤላውያን ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ በመካከልህም እንዲህ ያለ መጥፎ ነገር ዳግመኛ አያደርጉም።+ +12 “አምላክህ ይሖዋ እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ትሰማ ይሆናል፦ +13 ‘እናንተ የማታውቋቸውን “ሌሎች አማልክት ሄደን እናምልክ” እያሉ የከተማቸውን ነዋሪዎች ለማሳት የሚሞክሩ የማይረቡ ሰዎች ከመካከልህ ተነስተዋል’፤ +14 በዚህ ጊዜ ጉዳዩን በጥልቀት በመመርመርና በማጣራት ስለ ሁኔታው ማወቅ ይኖርብሃል፤+ ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ ተፈጽሞ ከሆነና ነገሩ እውነት መሆኑ ከተረጋገጠ +15 የከተማዋን ነዋሪዎች በሰይፍ ግደላቸው።+ እንስሶቿን ጨምሮ ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ በሰይፍ ሙሉ በሙሉ አጥፋ።+ +16 ከዚያም በከተማዋ ውስጥ የተገኘውን ምርኮ በሙሉ በአደባባይዋ ላይ ሰብስብ፤ ከተማዋን በእሳት አቃጥል፤ በውስጧ የተገኘው ምርኮ ደግሞ ለአምላክህ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባ ይሆናል። እሷም ለዘላለም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች። ፈጽሞ ተመልሳ አትገነባም። +17 ይሖዋ ከሚነድ ቁጣው እንዲመለስ፣ ለአባቶችህ በማለላቸው መሠረት+ ምሕረት እንዲያደርግልህና እንዲራራልህ እንዲሁም እንዲያበዛህ ከፈለግክ፣ እንዲጠፉ ከተለዩት ነገሮች መካከል እጅህ ምንም አይውሰድ።+ +18 እኔ ዛሬ የምሰጥህን የእሱን ትእዛዛት በሙሉ በመጠበቅ አምላክህን ይሖዋን ታዘዝ፤* በዚህ መንገድ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ታደርጋለህ።+ +5 ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን በሙሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እስራኤላውያን፣ በ���ሬው ዕለት የምነግራችሁን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ስሙ፤ እወቋቸው፤ በጥንቃቄም ፈጽሟቸው። +2 አምላካችን ይሖዋ በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ገብቷል።+ +3 ይሖዋ ይህን ቃል ኪዳን የገባው ከአባቶቻችን ጋር ሳይሆን ዛሬ በሕይወት እዚህ ካለነው ከእኛ ከሁላችን ጋር ነው። +4 ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ከእናንተ ጋር ፊት ለፊት ተነጋገረ።+ +5 በዚያ ወቅት እኔ የይሖዋን ቃል ለእናንተ ለመንገር በይሖዋና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር፤+ ምክንያቱም እናንተ ከእሳቱ የተነሳ ፈርታችሁ ወደ ተራራው አልወጣችሁም።+ እሱም እንዲህ አለ፦ +6 “‘ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ።+ +7 ከእኔ በቀር* ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።+ +8 “‘በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸ ቅርጽም+ ሆነ የተሠራ ምስል ለራስህ አታብጅ። +9 ለእነሱ አትስገድ፤ አታገልግላቸውም፤+ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና+ በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤+ +10 ሆኖም ለሚወዱኝና ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ታማኝ ፍቅር* የማሳይ አምላክ ነኝ። +11 “‘የአምላክህን የይሖዋን ስም በከንቱ አታንሳ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ስሙን በከንቱ የሚያነሳውን ሳይቀጣ አይተወውም።+ +12 “‘አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ቅዱስ አድርገህ ትጠብቀው ዘንድ የሰንበትን ቀን አክብር።+ +13 ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ትሠራለህ፤+ +14 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው።+ በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ በሬህም ሆነ አህያህ ወይም ማንኛውም የቤት እንስሳህ አሊያም በከተሞችህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው+ ምንም ሥራ አትሥሩ፤+ ይህም አንተ እንደምታርፈው ወ +15 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ በብርቱ እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ እንዳወጣህ አስታውስ።+ አምላክህ ይሖዋ የሰንበትን ቀን እንድታከብር ያዘዘህ ለዚህ ነው። +16 “‘አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ+ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።+ +17 “‘አትግደል።+ +18 “‘አታመንዝር።+ +19 “‘አትስረቅ።+ +20 “‘በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመሥክር።+ +21 “‘የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ።+ የባልንጀራህን ቤት፣ እርሻውን፣ ወንድ ባሪያውን፣ ሴት ባሪያውን፣ በሬውን፣ አህያውን ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።’+ +22 “ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳቱ መካከል በደመናውና በድቅድቅ ጨለማው+ ውስጥ ሆኖ እነዚህን ትእዛዛት* ከፍ ባለ ድምፅ ለመላው ጉባኤያችሁ ተናገረ፤ ከእነዚህም ሌላ ምንም አልጨመረም፤ ከዚያም እነዚህን በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጽፎ ሰጠኝ።+ +23 “ይሁን እንጂ ተራራው በእሳት እየነደደ ሳለ+ ከጨለማው ውስጥ ድምፅ ሲወጣ ስትሰሙ የነገድ መሪዎቻችሁና ሽማግሌዎቹ በሙሉ ወደ እኔ መጡ። +24 ከዚያም እንዲህ አላችሁ፦ ‘ይኸው አምላካችን ይሖዋ ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፤ ድምፁንም ከእሳቱ ውስጥ ሰምተናል።+ አምላክ ከሰው ጋር መነጋገር እንደሚችልና ያም ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል።+ +25 ታዲያ አሁን ለምን እንሙት? ምክንያቱም ይህ ታላቅ እሳት ሊበላን ይችላል። የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅ መስማት ከቀጠልን እንደምንሞት የተረጋገጠ ነው። +26 ለመሆኑ ከሥጋ* ሁሉ መካከል ልክ ��ኛ እንደሰማነው ሕያው የሆነው አምላክ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር ሰምቶ በሕይወት የኖረ ማን አለ? +27 አንተው ራስህ ቀርበህ አምላካችን ይሖዋ የሚናገረውን ሁሉ ስማ፤ ከዚያም አምላካችን ይሖዋ የነገረህን ሁሉ ትነግረናለህ፤ እኛም እንሰማለን፤ ደግሞም የተባልነውን እናደርጋለን።’+ +28 “ከዚያም ይሖዋ ያላችሁኝን ነገር ሰማ፤ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ ‘ይህ ሕዝብ ምን እንዳለህ ሰምቻለሁ። የተናገሩት ነገር ሁሉ መልካም ነው።+ +29 ምንጊዜም እኔን የሚፈራና+ ትእዛዛቴን ሁሉ የሚጠብቅ ልብ+ ቢኖራቸው ምናለ፤ እንዲህ ቢሆን ለእነሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም ይሆንላቸው ነበር!+ +30 ሂድና “ወደየድንኳናችሁ ተመለሱ” በላቸው። +31 አንተ ግን እዚሁ እኔ ጋ ቆይ፤ እኔም ርስት አድርገው እንዲወርሷት በምሰጣቸው ምድር ውስጥ ይጠብቋቸው ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች በሙሉ እነግርሃለሁ።’ +32 እንግዲህ አምላካችሁ ይሖዋ ያዘዛችሁን በጥንቃቄ ፈጽሙ።+ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበሉ።+ +33 ርስት አድርጋችሁ በምትወርሷት ምድር በሕይወት እንድትኖሩ፣ እንድትበለጽጉና ዕድሜያችሁ እንዲረዝም+ አምላካችሁ ይሖዋ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።+ +21 “አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር አንድ ሰው ሜዳ ላይ ተገድሎ ቢገኝና ማን እንደገደለው ባይታወቅ +2 ሽማግሌዎችህና ዳኞችህ+ ወጥተው የሞተው ሰው ከተገኘበት ስፍራ አንስቶ በዙሪያው እስከሚገኙት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ። +3 ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ምንም ሥራ ያልተሠራባትንና ቀንበር ተጭኖባት የማያውቅን ጊደር ከከብቶች መካከል ይውሰዱ፤ +4 የከተማዋም ሽማግሌዎች ጊደሯን ከዚህ ቀደም ታርሶ ወይም ዘር ተዘርቶበት ወደማያውቅ ወራጅ ውኃ ወዳለበት ሸለቆ* ይውሰዷት፤ በሸለቆውም ውስጥ የጊደሯን አንገት ይስበሩ።+ +5 “ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ ይቅረቡ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ እሱን እንዲያገለግሉና በይሖዋ ስም እንዲባርኩ+ የመረጠው እነሱን ነው።+ ደግሞም የኃይል ጥቃትን በተመለከተ ለሚነሳ ለማንኛውም ክርክር እልባት የሚሰጡት እነሱ ናቸው።+ +6 ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆኑት የከተማዋ ሽማግሌዎች በሙሉ በሸለቆው ውስጥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤+ +7 እንዲህ ብለውም ይናገሩ፦ ‘እጆቻችን ይህን ደም አላፈሰሱም፤ ዓይኖቻችንም ይህ ደም ሲፈስ አላዩም። +8 ይሖዋ ሆይ፣ የታደግከውን+ ሕዝብህን እስራኤልን በዚህ ድርጊት ተጠያቂ አታድርገው፤ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመ በደልም በሕዝብህ በእስራኤል መካከል እንዲኖር አትፍቀድ።’+ እነሱም በደም ዕዳው ተጠያቂ አይሆኑም። +9 በዚህ መንገድ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመን በደል ከመካከልህ በማስወገድ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ። +10 “ከጠላቶችህ ጋር ብትዋጋ፣ አምላክህ ይሖዋም እነሱን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህ፣ አንተም ምርኮኛ አድርገህ ብትወስዳቸውና+ +11 ከምርኮኞቹ መካከል አንዲት የምታምር ሴት አይተህ ብትወዳት፣ ሚስትህም ልታደርጋት ብትፈልግ +12 ወደ ቤትህ ልትወስዳት ትችላለህ። እሷም ፀጉሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቁረጥ፤ +13 የምርኮኛነት ልብሷን ታውልቅ፤ በቤትህም ትቀመጥ። ለአባቷና ለእናቷ አንድ ወር ሙሉ ታልቅስ፤+ ከዚህ በኋላ ከእሷ ጋር ግንኙነት መፈጸም ትችላለህ፤ አንተ ባሏ ትሆናለህ፤ እሷም ሚስትህ ትሆናለች። +14 በእሷ ካልተደሰትክ ግን ወደፈለገችበት* እንድትሄድ አሰናብታት።+ ሆኖም ለውርደት ስለዳረግካት በገንዘብ ልትሸጣት ወይም ግፍ ልትፈጽምባት አይገባም። +15 “አንድ ሰው ሁለት ሚስ��ች ቢኖሩትና አንደኛዋን ከሌላኛዋ አስበልጦ የሚወዳት ቢሆን፣* ሁለቱም ወንዶች ልጆች ቢወልዱለትና በኩሩ የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ+ ቢሆን +16 ውርሱን ለወንዶች ልጆቹ በሚያስተላልፍበት ቀን ከማይወዳት ሚስቱ የተወለደውን በኩር የሆነውን ወንድ ልጅ ትቶ ከሚወዳት ሚስቱ የተወለደውን ወንድ ልጅ እንደ በኩር ልጁ አድርጎ መቁጠር የለበትም። +17 ከዚህ ይልቅ ከማይወዳት ሚስቱ ለተወለደው ወንድ ልጅ፣ ካለው ከማንኛውም ነገር ላይ ሁለት እጥፍ በመስጠት የልጁን ብኩርና መቀበል ይኖርበታል፤ ምክንያቱም የጎልማሳነቱ ብርታት መጀመሪያ ይህ ልጅ ነው። የብኩርና መብቱ የእሱ ነው።+ +18 “አንድ ሰው እልኸኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው ልጁም አባቱንም ሆነ እናቱን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ቢል፣+ እነሱም እርማት ሊሰጡት ቢሞክሩና እሱ ግን ሊሰማቸው ፈቃደኛ ባይሆን+ +19 አባትና እናቱ እሱ ባለበት ከተማ በር ላይ ወዳሉት ሽማግሌዎች ያምጡት፤ +20 ሽማግሌዎቹንም ‘ይህ ልጃችን እልኸኛና ዓመፀኛ ነው፤ ሊታዘዘንም ፈቃደኛ አይደለም። ሆዳምና+ ሰካራም+ ነው’ ይበሏቸው። +21 ከዚያም የከተማዋ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ።+ +22 “አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ሠርቶ ቢገደልና+ በእንጨት ላይ ብትሰቅለው+ +23 በድኑ በእንጨቱ ላይ አይደር።+ ከዚህ ይልቅ በዚያው ዕለት ቅበረው፤ ምክንያቱም እንጨት ላይ የሚሰቀለው፣ አምላክ የረገመው ነው፤+ አንተም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር አታርክስ።+ +15 “በየሰባት ዓመቱ መጨረሻ የሌሎችን ዕዳ መሰረዝ ይኖርብሃል።+ +2 ዕዳ የሚሰረዘው በሚከተለው መንገድ ነው፦ እያንዳንዱ አበዳሪ ባልንጀራው ያለበትን ዕዳ ይሰርዝለታል። ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ክፍያ መጠየቅ የለበትም፤ ምክንያቱም ለይሖዋ ሲባል ዕዳ እንዲሰረዝ ይታወጃል።+ +3 ከባዕድ አገር ሰው ክፍያ መጠየቅ ትችላለህ፤+ ወንድምህ ለአንተ መመለስ ያለበትን ማንኛውንም ነገር ግን ተውለት። +4 ይሁንና አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ ይሖዋ ስለሚባርክህ+ ከእናንተ መካከል ማንም ድሃ አይሆንም፤ +5 ይህ የሚሆነው ግን የአምላክህን የይሖዋን ቃል በትኩረት የምትሰማና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዛት በሙሉ በጥንቃቄ የምትፈጽም ከሆነ ነው።+ +6 አምላክህ ይሖዋ በገባልህ ቃል መሠረት ይባርክሃልና፤ አንተም ለብዙ ብሔራት ታበድራለህ* እንጂ አትበደርም፤+ ብዙ ብሔራትን ትገዛለህ እንጂ አንተን አይገዙህም።+ +7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+ +8 ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤+ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው።* +9 ‘ዕዳ የሚሰረዝበት ሰባተኛው ዓመት ቀርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ በልብህ አድሮ ለድሃው ወንድምህ ከመለገስ ወደኋላ እንዳትልና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር ተጠንቀቅ።+ እሱ በአንተ ላይ ቅር ተሰኝቶ ወደ ይሖዋ ቢጮኽ ኃጢአት ይሆንብሃል።+ +10 በልግስና ስጠው፤+ ስትሰጠው ልብህ ቅር እያለው መሆን የለበትም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በሥራህ ሁሉና በምታከናውነው በማንኛውም ነገር የሚባርክህ በዚህ የተነሳ ነው።+ +11 መቼም ቢሆን ከምድሪቱ ላይ ድሆች አይጠፉምና።+ ‘በምድርህ ላይ ለሚኖር ጎስቋላና ድሃ ወንድምህ በልግስና እጅህን ዘርጋለት’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው።+ +12 “ከወንድሞችህ አንዱ ይኸውም አንድ ዕብራዊ ወይም አንዲት ዕብራዊ፣ ለአንተ ቢሸጥና ስድስት ዓመት ቢያገለግልህ በሰባተኛው ዓመት ነፃ አውጣው።+ +13 ነፃ የምታወጣው ከሆነ ባዶ እጁን አትስደደው። +14 ከመንጋህና ከአውድማህ እንዲሁም ከዘይትና ከወይን መጭመቂያህ በልግስና ስጠው። አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን ስጠው። +15 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ እንደተቤዠህ አስታውስ። እኔ ዛሬ ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው። +16 “ሆኖም ይህ ሰው ከአንተ ጋር በነበረበት ጊዜ ደስተኛ ስለነበር አንተንና ቤተሰብህን በመውደድ ‘ፈጽሞ ከአንተ አልለይም!’ ቢልህ+ +17 ጆሮውን በር ላይ አስደግፈህ በወስፌ ብሳው፤ እሱም ዕድሜ ልኩን የአንተ ባሪያ ይሆናል። ሴት ባሪያህንም በተመለከተ እንደዚሁ አድርግ። +18 ባሪያህን ነፃ አድርጎ ማሰናበት ሊከብድህ አይገባም፤ ምክንያቱም እሱ በስድስት ዓመት ውስጥ የሰጠህ አገልግሎት በቅጥር ሠራተኛ ደሞዝ ቢሰላ እጥፍ ዋጋ ያስወጣህ ነበር፤ ደግሞም አምላክህ ይሖዋ በምትሠራው ነገር ሁሉ ባርኮሃል። +19 “ከከብትህና ከመንጋህ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለአምላክህ ለይሖዋ ቀድሰው።+ በከብትህ* በኩር ምንም ሥራ አትሥራበት፤ የመንጋህንም በኩር አትሸልት። +20 አንተም ሆንክ ቤተሰብህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በየዓመቱ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ብሉት።+ +21 ይሁንና እንስሳው እንከን ካለበት ይኸውም አንካሳ ወይም ዕውር ከሆነ አሊያም ሌላ ዓይነት ከባድ ጉድለት ካለበት ለአምላክህ ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርበው።+ +22 በከተሞችህ* ውስጥ ብላው፤ እንደ ሜዳ ፍየል ወይም እንደ ርኤም* ሁሉ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል።+ +23 ሆኖም ደሙን አትብላ፤+ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍስሰው።+ +22 “የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ካየህ እንዳላየ ሆነህ አትለፍ።+ ከዚህ ይልቅ ወደ ወንድምህ መልሰህ ልትወስደው ይገባል። +2 ሆኖም ወንድምህ በአቅራቢያህ የማይኖር ወይም እሱን የማታውቀው ከሆነ እንስሳውን ወደ ቤትህ አምጣው፤ ወንድምህ እሱን ፈልጎ እስኪመጣም ድረስ አንተ ጋ ይቆይ። ከዚያም መልስለት።+ +3 አህያውንም ሆነ ልብሱን ወይም ወንድምህ ጠፍቶበት ያገኘኸውን ማንኛውንም ነገር በተመለከተ እንዲሁ ማድረግ ይኖርብሃል። አይተህ ዝም ብለህ ማለፍ የለብህም። +4 “የወንድምህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታይ እንዳላየ ሆነህ አትለፍ። ከዚህ ይልቅ እንስሳው ተነስቶ እንዲቆም በማድረግ ሰውየውን ልትረዳው ይገባል።+ +5 “ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድ ደግሞ የሴት ልብስ አይልበስ። ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው። +6 “መንገድ ላይ ስትሄድ ጫጩቶች ወይም እንቁላሎች ያሉበት የወፍ ጎጆ፣ ዛፍ ላይ ወይም መሬት ላይ ብታገኝና እናትየው ጫጩቶቹን ወይም እንቁላሎቹን ታቅፋ ቢሆን እናትየውን ከጫጩቶቿ ጋር አብረህ አትውሰድ።+ +7 እናትየውን ልቀቃት፤ ጫጩቶቹን ግን መውሰድ ትችላለህ። ይህን የምታደርገው መልካም እንዲሆንልህና ዕድሜህ እንዲረዝም ነው። +8 “አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ አንድ ሰው ከጣሪያህ ላይ ወድቆ በቤትህ ላይ የደም ዕዳ እንዳታመጣ በጣሪያህ ዙሪያ መከታ ሥራ።+ +9 “በወይን እርሻህ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ።+ እንዲህ ካደረግክ ከዘራኸው ዘር የሚገኘው ምርትም ሆነ የወይን እርሻህ ምርት በሙሉ በቤተ መቅደሱ ተቀባይነት ያጣል። +10 “በሬና አህያ አንድ ላይ ጠምደህ አትረስ።+ +11 “ከሱፍና ከበፍታ ተቀላቅሎ የተሠራ ልብስ አትልበስ።+ +12 “በምትለብሰው ልብስ ላይ በአራቱም ማዕዘን ዘርፍ አድርግ።+ +13 “አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ከእ�� ጋር ግንኙነት ከፈጸመ በኋላ ቢጠላት፣ +14 መጥፎ ምግባር እንዳላት አድርጎ ቢከሳትና ‘ይህችን ሴት አግብቼ ነበር፤ ሆኖም ከእሷ ጋር ግንኙነት ስፈጽም የድንግልናዋን ማስረጃ አላገኘሁም’ በማለት መጥፎ ስም ቢሰጣት +15 የልጅቷ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዋ በር ወደሚገኙት ሽማግሌዎች ይምጡ። +16 የልጅቷም አባት ሽማግሌዎቹን እንዲህ ይበላቸው፦ ‘ልጄን ለዚህ ሰው ድሬለት ነበር፤ እሱ ግን ጠላት፤ +17 እንዲሁም “ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም” በማለት መጥፎ ምግባር እንዳላት አድርጎ እየከሰሳት ነው። እንግዲህ የልጄ የድንግልና ማስረጃ ይኸውላችሁ።’ እነሱም ልብሱን በከተማዋ ሽማግሌዎች ፊት ይዘርጉት። +18 የዚያች ከተማ ሽማግሌዎችም+ ሰውየውን ወስደው ይቅጡት።+ +19 እነሱም 100 የብር ሰቅል* ያስከፍሉታል፤ ከዚያም ገንዘቡን ለልጅቷ አባት ይስጡት፤ ምክንያቱም ይህ ሰው የአንዲትን እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቷል፤+ እሷም ሚስቱ ሆና ትኖራለች። በሕይወት ዘመኑም ሁሉ እንዲፈታት አይፈቀድለትም። +20 “ሆኖም ክሱ እውነት ከሆነና ልጅቷ ድንግል እንደነበረች የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካልተገኘ +21 ልጅቷን ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያውጧት፤ በአባቷ ቤት የፆታ ብልግና በመፈጸም በእስራኤል ውስጥ አስነዋሪ ድርጊት ስለፈጸመች+ የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+ +22 “አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ከሴትየዋ ጋር የተኛው ሰውም ሆነ ሴትየዋ ሁለቱም ይገደሉ።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል አስወግድ። +23 “አንድ ሰው ለሌላ ሰው የታጨችን አንዲት ድንግል ከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእሷ ጋር ቢተኛ +24 ልጅቷ በከተማው ውስጥ ስላልጮኸች፣ ሰውየው ደግሞ የባልንጀራውን ሚስት ስላዋረደ ሁለቱንም ወደ ከተማዋ በር አውጥታችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ። +25 “ይሁንና ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ያገኛት ሜዳ ላይ ቢሆንና በጉልበት አስገድዶ አብሯት ቢተኛ እሱ ብቻ ይገደል፤ +26 በልጅቷ ላይ ምንም አታድርግ። ልጅቷ ሞት የሚገባው ኃጢአት አልሠራችም። ይህ ጉዳይ በባልንጀራው ላይ ጥቃት ሰንዝሮ ከሚገድል* ሰው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ነው።+ +27 ምክንያቱም ሰውየው ልጅቷን ያገኛት ሜዳ ላይ ሲሆን የታጨችው ልጅ ብትጮኽም እንኳ ማንም አልደረሰላትም። +28 “አንድ ሰው ያልታጨችን አንዲት ድንግል አግኝቶ ቢይዛትና አብሯት ቢተኛ፣ በኋላም ቢጋለጡ+ +29 ሰውየው ለልጅቷ አባት 50 የብር ሰቅል ይስጥ፤ እሷም ሚስቱ ትሆናለች።+ ስላዋረዳትም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እንዲፈታት አይፈቀድለትም። +30 “ማንም ሰው አባቱን እንዳያዋርድ* የአባቱን ሚስት አያግባ።+ +17 ከዚያም ዕጣው+ ለምናሴ+ ነገድ ወጣ፤ ምክንያቱም እሱ የዮሴፍ የበኩር ልጅ ነበር።+ የጊልያድ አባት የሆነው የምናሴ የበኩር ልጅ ማኪር+ ጦረኛ ሰው ስለነበር ጊልያድን እና ባሳንን+ ወሰደ። +2 ለቀሩት የምናሴ ዘሮችም በየቤተሰባቸው ይኸውም ለአቢዔዜር+ ልጆች፣ ለሄሌቅ ልጆች፣ ለአስሪዔል ልጆች፣ ለሴኬም ልጆች፣ ለሄፌር ልጆችና ለሸሚዳ ልጆች ዕጣ ወጣ። የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ዘሮች ወንዶቹ በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ።+ +3 ሆኖም የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የሄፌር ልጅ ሰለጰአድ+ ሴቶች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የሴቶች ልጆቹም ስም ማህላ፣ ኖኅ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበር። +4 እነሱም ወደ ካህኑ አልዓዛር፣+ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ አለቆቹ ቀርበው “ይሖዋ በወንድሞቻችን መካከል ርስት እንዲሰጠን ሙሴን አዞት ነበር” አሏቸው።+ ስለዚህ ኢያሱ ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በአባታቸው ወንድሞች መካከል ርስት ሰጣቸው።+ +5 ምናሴ በዮርዳኖስ ማዶ* ከነበሩት ከጊልያድና ከባሳን በተጨማሪ አሥር ድርሻዎች ወጡለት፤+ +6 ምክንያቱም የምናሴ ሴቶች ልጆች በወንዶች ልጆቹ መካከል ርስት ተሰጥቷቸው ነበር፤ የጊልያድም ምድር የቀሩት የምናሴ ዘሮች ርስት ሆነ። +7 የምናሴ ወሰን ከአሴር አንስቶ ከሴኬም+ ፊት ለፊት እስከምትገኘው እስከ ሚክመታት+ ድረስ ነበር፤ ወሰኑ በስተ ደቡብ* በኩል የኤንታጱአ ነዋሪዎች እስከሚገኙበት ምድር ይዘልቃል። +8 የታጱአ+ ምድር የምናሴ ሆነች፤ በምናሴ ወሰን ላይ የምትገኘው የታጱአ ከተማ ግን የኤፍሬም ዘሮች ነበረች። +9 ወሰኑ ወደ ቃና ሸለቆ ይኸውም ከሸለቆው በስተ ደቡብ ቁልቁል ይወርዳል። በምናሴ ከተሞች መካከል የሚገኙ የኤፍሬም ከተሞች የነበሩ ሲሆን+ የምናሴ ወሰን በሸለቆው ሰሜናዊ ክፍል አድርጎ ባሕሩ ጋ ሲደርስ ያበቃል።+ +10 በስተ ደቡብ በኩል ያለው የኤፍሬም፣ በስተ ሰሜን በኩል ያለው ደግሞ የምናሴ ነበር፤ ባሕሩም የእሱ ወሰን ነበር፤+ እነሱም* በስተ ሰሜን እስከ አሴር፣ በስተ ምሥራቅ ደግሞ እስከ ይሳኮር ይደርሱ ነበር። +11 በይሳኮርና በአሴር ግዛቶች ውስጥ ለምናሴ የተሰጡት የሚከተሉት ናቸው፦ ቤትሼንና በሥሯ* ያሉት ከተሞች፣ ይብለአምና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ የዶር+ ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉት ከተሞች እንዲሁም የኤንዶር+ ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ የታአናክ+ ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ የመጊዶ ነዋሪዎችና በሥሯ +12 ሆኖም የምናሴ ዘሮች እነዚህን ከተሞች መውረስ አልቻሉም፤ ከነአናውያን ይህን ምድር ላለመልቀቅ ቆርጠው ነበር።+ +13 እስራኤላውያን እያየሉ በሄዱ ጊዜ ከነአናውያንን የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው፤+ ይሁን እንጂ ሙሉ በሙሉ አላባረሯቸውም።*+ +14 የዮሴፍ ዘሮችም ኢያሱን “አንድ ዕጣና+ አንድ ድርሻ ብቻ ርስት አድርገህ የሰጠኸን ለምንድን ነው?* ይሖዋ እስካሁን ድረስ ስለባረከን የሕዝባችን ቁጥር በዝቷል”+ አሉት። +15 ኢያሱም “ቁጥራችሁ ይህን ያህል ብዙ ከሆነ የኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ በጣም ስለሚጠብባችሁ ወደ ጫካው በመውጣት በፈሪዛውያንና+ በረፋይም+ ምድር የሚገኘውን አካባቢ ለራሳችሁ መንጥሩ” አላቸው። +16 ከዚያም የዮሴፍ ዘሮች እንዲህ አሉት፦ “ተራራማው አካባቢ አይበቃንም፤ ደግሞም በሸለቆው* ምድር ማለትም በቤትሼን+ እና በሥሯ* በሚገኙት ከተሞች እንዲሁም በኢይዝራኤል ሸለቆ+ ውስጥ* የሚኖሩት ከነአናውያን በሙሉ የብረት ማጭድ የተገጠመላቸው የጦር ሠረገሎች* አሏቸው።”+ +17 በመሆኑም ኢያሱ ለዮሴፍ ቤት ይኸውም ለኤፍሬምና ለምናሴ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ብዙ ሕዝብ ናችሁ፤ ታላቅ ኃይልም አላችሁ። ድርሻችሁ አንድ ዕጣ ብቻ አይሆንም፤+ +18 ከዚህ ይልቅ ተራራማው አካባቢ የእናንተ ይሆናል።+ አካባቢው ጫካ ቢሆንም ትመነጥሩታላችሁ፤ የግዛታችሁም ወሰን ይሆናል። ምክንያቱም ከነአናውያን የብረት ማጭድ የተገጠመላቸው የጦር ሠረገሎች* ያሏቸውና ብርቱዎች ቢሆኑም እንኳ ከምድሩ ታባርሯቸዋላችሁ።”+ +18 ከዚያም መላው የእስራኤላውያን ማኅበረሰብ በሴሎ+ ተሰበሰበ፤ በዚህ ጊዜ ምድሪቱ በፊታቸው ተገዝታላቸው+ ስለነበር የመገናኛ ድንኳኑን በዚያ ተከሉ።+ +2 ይሁንና ከእስራኤላውያን መካከል ገና ርስት ያልተሰጣቸው ሰባት ነገዶች ነበሩ። +3 በመሆኑም ኢያሱ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፦ “የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ የሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ችላ የምትሉት እስከ መቼ ነው?+ +4 ከእያንዳንዱ ነገድ ሦስት ሦስት ወንዶችን ስጡኝ፤ እኔም እልካቸዋለሁ፤ እነሱም ሄደው ምድሪቱን ተዘዋውረው ከተመለከ��� በኋላ በሚወርሱት ድርሻ መሠረት ይሸነሽኗታል። ከዚያም ተመልሰው ወደ እኔ ይመጣሉ። +5 ምድሪቱንም ሰባት ቦታ ይከፋፈሏታል።+ ይሁዳ በስተ ደቡብ ያለውን ክልሉን ይዞ ይኖራል፤+ የዮሴፍ ቤት ደግሞ በስተ ሰሜን ያለውን ክልሉን ይዞ ይኖራል።+ +6 እናንተ ግን ምድሪቱን ሰባት ቦታ ትሸነሽኗታላችሁ፤ ከዚያም የሸነሸናችሁትን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እዚህ በአምላካችን በይሖዋ ፊት ዕጣ አወጣላችኋለሁ።+ +7 ሌዋውያኑ ግን ለይሖዋ የሚያቀርቡት የክህነት አገልግሎት ውርሻቸው ስለሆነ+ በመካከላችሁ ድርሻ አይኖራቸውም፤+ ጋድ፣ ሮቤልና የምናሴ ነገድ እኩሌታም+ ቢሆኑ የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ በሰጣቸው መሠረት ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ርስታቸውን አስቀድመው ወስደዋል።” +8 ሰዎቹም ለመሄድ ተነሱ፤ ኢያሱም ምድሪቱን ለመሸንሸን የሚሄዱትን ሰዎች “ሂዱና ምድሪቱን ተዘዋውራችሁ በማየት ሸንሽኗት፤ ከዚያም ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እዚሁ በሴሎ በይሖዋ ፊት ዕጣ አወጣላችኋለሁ”+ ሲል አዘዛቸው። +9 ሰዎቹም ሄደው በምድሪቱ ተዘዋወሩ፤ ከዚያም በከተማ በከተማ ሰባት ቦታ ሸንሽነው በመጽሐፍ አሰፈሩት። በኋላም በሴሎ ባለው ሰፈር ወደሚገኘው ወደ ኢያሱ ተመልሰው መጡ። +10 ኢያሱም በሴሎ በይሖዋ ፊት ዕጣ አወጣላቸው።+ በዚያም ኢያሱ ምድሪቱን ለእስራኤላውያን በየድርሻቸው አከፋፈላቸው።+ +11 የመጀመሪያውም ዕጣ ለቢንያም ነገድ በየቤተሰቡ ወጣ፤ በዕጣ የደረሳቸውም ክልል በይሁዳ ሰዎችና+ በዮሴፍ ሰዎች+ መካከል የሚገኘው ነበር። +12 በሰሜን በኩል ያለው ወሰናቸው ከዮርዳኖስ ተነስቶ በስተ ሰሜን ወዳለው የኢያሪኮ+ ሸንተረር ይወጣና በስተ ምዕራብ ወደ ተራራው ያቀናል፤ ከዚያም ወደ ቤትአዌን+ ምድረ በዳ ይዘልቃል። +13 ከዚያ ደግሞ ወሰኑ ቤቴል+ ወደምትባለው ወደ ሎዛ ማለትም ወደ ሎዛ ደቡባዊ ሸንተረር ያቀናል፤ በመቀጠልም ከታችኛው ቤትሆሮን+ በስተ ደቡብ በሚገኘው ተራራ ላይ አድርጎ ወደ አጣሮትዓዳር+ ይወርዳል። +14 በስተ ምዕራብ ያለው ወሰንም በስተ ደቡብ በኩል ከቤትሆሮን ትይዩ ከሆነው ተራራ በመነሳት ወደ ደቡብ ይታጠፋል፤ ከዚያም የይሁዳ ከተማ የሆነችው ቂርያትበአል ይኸውም ቂርያትየአሪም + ጋ ሲደርስ ያበቃል። ይህ ምዕራባዊው ወሰን ነው። +15 በስተ ደቡብ ያለው ወሰን ደግሞ ከቂርያትየአሪም ጫፍ ተነስቶ ወደ ምዕራብ ይዘልቃል፤ ከዚያም ወደ ነፍቶአ+ የውኃ ምንጭ ይወጣል። +16 ከዚያም ከሂኖም ልጅ ሸለቆ+ ፊት ለፊት ወደሚገኘውና በረፋይም ሸለቆ*+ ሰሜናዊ ጫፍ ወዳለው ተራራ ግርጌ ይወርዳል፤ በመቀጠልም ወደ ሂኖም ሸለቆ ይኸውም በስተ ደቡብ ወደሚገኘው ወደ ኢያቡሳውያን+ ሸንተረር ይወርድና እስከ ኤንሮጌል+ ይዘልቃል። +17 ከዚያም ወደ ሰሜን በማቅናት ወደ ኤንሼሜሽ ያልፍና ከአዱሚም አቀበት+ ፊት ለፊት እስከምትገኘው እስከ ገሊሎት ይደርሳል፤ በመቀጠልም የሮቤል ልጅ የቦሃን+ ድንጋይ+ እስካለበት ድረስ ይወርዳል። +18 ወሰኑ አረባ ፊት ለፊት ወዳለው ሰሜናዊ ሸንተረር ይሄድና ቁልቁል ወደ አረባ ይወርዳል። +19 ከዚያም ወደ ቤትሆግላ+ ሰሜናዊ ሸንተረር ይዘልቅና በዮርዳኖስ ደቡባዊ ጫፍ፣ የጨው ባሕር*+ ሰሜናዊ ዳርቻ ላይ ሲደርስ ያበቃል። ደቡባዊው ወሰን ይህ ነበር። +20 በስተ ምሥራቅ በኩል ወሰኑ ዮርዳኖስ ነበር። የቢንያም ዘሮች በየቤተሰባቸው ያገኙት ርስት ወሰን ዙሪያውን ይህ ነበር። +21 የቢንያም ነገድ በየቤተሰቡ ያገኛቸው ከተሞች እነዚህ ናቸው፦ ኢያሪኮ፣ ቤትሆግላ፣ ኤሜቀጺጽ፣ +22 ቤትአረባ፣+ ጸማራይም፣ ቤቴል፣+ +23 አዊም፣ ጳራ፣ ኦፍራ፣ +24 ከፋርአሞናይ፣ ኦፍኒ እና ጌባ፤+ በአጠቃላይ 12 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +25 ገባኦን፣+ ራማ፣ በኤሮት፣ +26 ምጽጳ፣ ከፊ���፣ ሞጻ፣ +27 ራቄም፣ ይርጰኤል፣ ታራላ፣ +28 ጸላህ፣+ ኤሌፍ፣ ኢያቡስ ማለትም ኢየሩሳሌም፣+ ጊብዓ+ እና ቂርያት፤ በአጠቃላይ 14 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። የቢንያም ዘሮች በየቤተሰባቸው ያገኙት ርስት ይህ ነበር። +23 ይሖዋ እስራኤላውያንን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ካሳረፋቸው+ ከብዙ ጊዜ በኋላ፣ ኢያሱም አርጅቶና ዕድሜው ገፍቶ ሳለ+ +2 ኢያሱ እስራኤላውያንን በሙሉ፣ ሽማግሌዎቻቸውን፣ መሪዎቻቸውን፣ ዳኞቻቸውንና አለቆቻቸውን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦+ “እንግዲህ እኔ አርጅቻለሁ፤ ዕድሜዬም ገፍቷል። +3 አምላካችሁ ይሖዋ ለእናንተ ሲል በእነዚህ ብሔራት ላይ ያደረገውን ሁሉ ራሳችሁ አይታችኋል፤ ምክንያቱም ለእናንተ እየተዋጋላችሁ የነበረው አምላካችሁ ይሖዋ ነው።+ +4 እኔም ከዮርዳኖስ አንስቶ በስተ ምዕራብ* እስከሚገኘው እስከ ታላቁ ባሕር* ድረስ ያጠፋኋቸውን ብሔራት ሁሉ ምድር+ ጨምሮ የቀሩትን ብሔራት ምድር+ ለየነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆን በዕጣ አከፋፍዬ+ ሰጥቻችኋለሁ። +5 እነሱን ከፊታችሁ ያባረራቸው አምላካችሁ ይሖዋ ነው፤+ እሱም ለእናንተ ሲል አባረራቸው፤* እናንተም አምላካችሁ ይሖዋ በገባላችሁ ቃል መሠረት ምድራቸውን ወረሳችሁ።+ +6 “እንግዲህ በሙሴ የሕግ መጽሐፍ+ ውስጥ ከተጻፈው ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ፈጽሞ ዞር ሳትሉ+ ሕጉን ሁሉ ለመጠበቅና ለመፈጸም ደፋሮች ሁኑ፤ +7 እንዲሁም በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ ብሔራት ጋር አትቀላቀሉ።+ ሌላው ቀርቶ የአማልክታቸውን ስም አታንሱ፤+ በእነሱም አትማሉ፤ ፈጽሞ አታገልግሏቸው እንዲሁም አትስገዱላቸው።+ +8 ከዚህ ይልቅ እስከዚህ ቀን ድረስ እንዳደረጋችሁት ሁሉ ከአምላካችሁ ከይሖዋ ጋር ተጣብቃችሁ ኑሩ።+ +9 ይሖዋ ታላላቅና ኃያላን ብሔራትን ከፊታችሁ ያባርራቸዋል፤+ እስከዚህ ቀን ድረስ አንድም ሰው ሊቋቋማችሁ አልቻለም።+ +10 አምላካችሁ ይሖዋ በገባላችሁ ቃል መሠረት+ ለእናንተ ስለሚዋጋላችሁ+ ከእናንተ አንዱ፣ ሺህ ሰው ያሳድዳል።+ +11 ስለዚህ አምላካችሁን ይሖዋን በመውደድ+ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ።*+ +12 “ይሁንና ወደ ኋላ ዞር ብትሉና ከእነዚህ ብሔራት መካከል ተርፈው ከእናንተ ጋር ከቀሩት+ ሰዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ብትመሠርቱ፣ በጋብቻ ብትዛመዱ+ እንዲሁም እናንተ ከእነሱ ጋር ብትወዳጁ፣ እነሱም ከእናንተ ጋር ወዳጅነት ቢመሠርቱ +13 አምላካችሁ ይሖዋ ከዚህ በኋላ ለእናንተ ሲል እነዚህን ብሔራት እንደማያባርራቸው* በእርግጥ እወቁ።+ እነሱም አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር ላይ እስክትጠፉ ድረስ ወጥመድ፣ አሽክላ፣ ለጀርባችሁ ጅራፍ እንዲሁም በዓይናችሁ ውስጥ እንዳለ እሾህ ይሆኑባችኋል።+ +14 “እንግዲህ እኔ መሞቻዬ ተቃርቧል፤* አምላካችሁ ይሖዋ ከገባላችሁ መልካም ቃል ሁሉ አንዲቷም እንኳ ሳትፈጸም እንዳልቀረች በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ* ታውቃላችሁ። ሁሉም ተፈጽሞላችኋል። ከመካከላቸው ሳይፈጸም የቀረ አንድም ቃል የለም።+ +15 ሆኖም አምላካችሁ ይሖዋ የገባላችሁ መልካም ቃል በሙሉ እንደተፈጸመላችሁ ሁሉ ይሖዋ አመጣባችኋለሁ ብሎ+ የተናገረውን ጥፋት ሁሉ* ያመጣባችኋል፤ አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድርም ያጠፋችኋል።+ +16 አምላካችሁ ይሖዋ እንድትጠብቁት ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን ካፈረሳችሁ እንዲሁም ሄዳችሁ ሌሎች አማልክትን ካገለገላችሁና ለእነሱ ከሰገዳችሁ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤+ ከሰጣችሁም መልካም ምድር ላይ በፍጥነት ትጠፋላችሁ።”+ +19 ከዚያም ሁለተኛው ዕጣ+ ለስምዖን ይኸውም ለስምዖን+ ነገድ በየቤተሰቡ ወጣ። ርስታቸውም በይሁዳ ርስት መካከል ነበር።+ +2 ርስታቸውም የሚከተለው ነበር፦ ቤርሳቤህ+ ከሳባ ጋር፣ ሞላዳ፣+ +3 ሃጻርሹአል፣+ ባላህ፣ ኤጼም፣+ +4 ኤልቶላድ፣+ በቱል፣ ሆርማ፣ +5 ጺቅላግ፣+ ቤትማርካቦት፣ ሃጻርሱሳ፣ +6 ቤትለባኦት+ እና ሻሩሄን፤ በአጠቃላይ 13 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው፤ +7 አይን፣ ሪሞን፣ ኤቴር እና አሻን፤+ በአጠቃላይ አራት ከተሞች ከነመንደሮቻቸው፤ +8 እንዲሁም በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ የነበሩትን መንደሮች በሙሉ እስከ ባዓላትበኤር ይኸውም በስተ ደቡብ እስከምትገኘው እስከ ራማ ድረስ ያሉትን አካባቢዎች ይጨምራል። የስምዖን ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር። +9 ለስምዖን ዘሮች ርስት የተሰጠው ከይሁዳ ልጆች ድርሻ ላይ ተወስዶ ነበር፤ ምክንያቱም የይሁዳ ዘሮች ድርሻቸው በጣም በዝቶባቸው ነበር። በመሆኑም የስምዖን ልጆች ርስት ያገኙት በእነሱ ርስት መካከል ነው።+ +10 በመቀጠል ሦስተኛው ዕጣ+ ለዛብሎን+ ዘሮች በየቤተሰባቸው ወጣ፤ የርስታቸውም ወሰን እስከ ሳሪድ ድረስ ይዘልቃል። +11 በስተ ምዕራብም ወደ ማረአል ይወጣና እስከ ዳባሼት ይደርሳል፤ ከዚያም በዮቅነአም ፊት ለፊት እስካለው ሸለቆ* ድረስ ይሄዳል። +12 ከሳሪድ ተነስቶ በስተ ምሥራቅ ወደ ፀሐይ መውጫ አቅጣጫ እስከ ኪስሎትታቦር ድንበር ድረስ ይሄድና ወደ ዳብራት+ ከዚያም ወደ ያፊአ ይወጣል። +13 ከዚያም ተነስቶ በስተ ምሥራቅ በፀሐይ መውጫ አቅጣጫ ወደ ጋትሔፌር፣+ ወደ ኢትቃጺን ከሄደ በኋላ ወደ ሪሞን ወጥቶ እስከ ኒአ ይዘልቃል። +14 በመቀጠልም በስተ ሰሜን ዞሮት ወደ ሃናቶን ያመራል፤ ወሰኑ የሚያበቃው ይፍታህኤል ሸለቆ፣ +15 ቃጣት፣ ናሃላል፣ ሺምሮን፣+ ይዳላ እና ቤተልሔም + ጋ ሲደርስ ነው፤ በአጠቃላይ 12 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +16 የዛብሎን ዘሮች ርስት በየቤተሰባቸው ይህ ነበር።+ ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። +17 አራተኛው ዕጣ+ የወጣው ለይሳኮር+ ይኸውም ለይሳኮር ዘሮች በየቤተሰባቸው ነበር። +18 ወሰናቸውም እስከ ኢይዝራኤል፣+ ከሱሎት፣ ሹነም፣+ +19 ሃፋራይም፣ ሺኦን፣ አናሃራት፣ +20 ራቢት፣ ቂሾን፣ ኤቤጽ፣ +21 ረመት፣ ኤንጋኒም፣+ ኤንሃዳ እና ቤትጳጼጽ ድረስ ነበር። +22 ከዚያም እስከ ታቦር፣+ ሻሃጺማ እና ቤትሼሜሽ ይዘልቅ ነበር፤ ወሰናቸውም ዮርዳኖስ ጋ ሲደርስ ያበቃል፤ በአጠቃላይ 16 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +23 የይሳኮር ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር፤+ ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። +24 ከዚያም አምስተኛው ዕጣ+ ለአሴር+ ነገድ በየቤተሰቡ ወጣ። +25 ወሰናቸውም ሄልቃት፣+ ሃሊ፣ ቤጤን፣ አክሻፍ፣ +26 አላሜሌክ፣ አምዓድ እና ሚሽአል ነበር። በስተ ምዕራብም እስከ ቀርሜሎስና+ እስከ ሺሆርሊብናት ይደርስ ነበር፤ +27 ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ቤትዳጎን ተመልሶ እስከ ዛብሎን እንዲሁም በስተ ሰሜን እስከ ይፍታህኤል ሸለቆ ይደርስና እስከ ቤትኤሜቅ እንዲሁም እስከ ነኢኤል ይዘልቃል፤ በመቀጠልም በስተ ግራ በኩል ወደ ካቡል ይሄዳል፤ +28 ከዚያም ወደ ኤብሮን፣ ሬሆብ፣ ሃሞን እና ቃና ሄዶ እስከ ታላቋ ሲዶና+ ድረስ ይደርሳል። +29 ወሰኑ ወደ ራማ ተመልሶ እስከተመሸገችው ከተማ እስከ ጢሮስ+ ይዘልቃል። ከዚያም ወደ ሆሳ ይመለስና በአክዚብ ክልል የሚገኘው ባሕር፣ +30 ዑማ፣ አፌቅ+ እና ሬሆብ+ ጋ ሲደርስ ያበቃል፤ በአጠቃላይ 22 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +31 የአሴር ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነው።+ ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። +32 ስድስተኛው ዕጣ+ የወጣው ለንፍታሌም ዘሮች ይኸውም ለንፍታሌም ዘሮች በየቤተሰባቸው ነበር። +33 ወሰናቸውም ከሄሌፍ፣ በጻናኒም ከሚገኘው ትልቅ ዛፍ፣+ ከአዳሚኔቄብ እና ከያብነኤል አንስቶ እስከ ላቁም ይደርሳል፤ ዮርዳኖስ ጋ ሲደርስም ያበቃል። +34 ወሰኑ በስተ ምዕራብ ወደ አዝኖትታቦር ��መለሳል፤ ከዚያም በመነሳት ወደ ሁቆቃ ይሄድና በስተ ደቡብ እስከ ዛብሎን፣ በስተ ምዕራብ እስከ አሴር፣ በስተ ምሥራቅ ደግሞ በዮርዳኖስ እስከሚገኘው እስከ ይሁዳ ይደርሳል። +35 የተመሸጉት ከተሞች እነዚህ ነበሩ፦ ጺዲም፣ ጸር፣ ሃማት፣+ ራቃት፣ ኪኔሬት፣ +36 አዳማ፣ ራማ፣ ሃጾር፣+ +37 ቃዴሽ፣+ ኤድራይ፣ ኤንሃጾር፣ +38 ይርኦን፣ ሚግዳልኤል፣ ሆሬም፣ ቤትአናት እና ቤትሼሜሽ፤+ በአጠቃላይ 19 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +39 የንፍታሌም ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር፤+ ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። +40 ሰባተኛው ዕጣ+ ለዳን+ ነገድ በየቤተሰቡ ወጣ። +41 የርስታቸውም ወሰን ጾራ፣+ ኤሽታዖል፣ ኢርሻሜሽ፣ +42 ሻአላቢን፣+ አይሎን፣+ ይትላ፣ +43 ኤሎን፣ ቲምና፣+ ኤቅሮን፣+ +44 ኤልተቄ፣ ጊበቶን፣+ ባዓላት፣ +45 የሁድ፣ ብኔበራቅ፣ ጋትሪሞን፣+ +46 መሃይያርቆን፣ ራቆን እና ከኢዮጴ+ ትይዩ ያለው ድንበር ነበር። +47 የዳን ዘሮች ርስታቸው በጣም ጠቧቸው ነበር።+ በመሆኑም ወጥተው ለሸምን+ ወጉ፤ ከተማዋንም በመቆጣጠር በሰይፍ መቷት። ከዚያም ከተማዋን ርስት አድርገው በመያዝ በዚያ መኖር ጀመሩ፤ ለሸምንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት።+ +48 የዳን ነገድ ርስት በየቤተሰቡ ይህ ነበር። ከተሞቹና መንደሮቻቸው እነዚህ ነበሩ። +49 በዚህ መንገድ ምድሪቱን በየክልሉ በርስትነት አከፋፍለው ጨረሱ። ከዚያም እስራኤላውያን ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት። +50 እነሱም የጠየቀውን ከተማ ማለትም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ቲምናትሰራን+ በይሖዋ ትእዛዝ መሠረት ሰጡት፤ እሱም ከተማዋን ገንብቶ በዚያ ተቀመጠ። +51 ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገዶች የአባቶች ቤት መሪዎች በሴሎ+ በይሖዋ ፊት በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ+ ርስት አድርገው በዕጣ ያከፋፈሉት ድርሻ ይህ ነበር።+ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን አከፋፍለው ጨረሱ። +20 ከዚያም ይሖዋ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ +2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘በሙሴ አማካኝነት በነገርኳችሁ መሠረት ለራሳችሁ የመማጸኛ ከተሞችን+ ምረጡ፤ +3 ሳያስበው ወይም በድንገት* ሰው የገደለ* ግለሰብ ወደነዚህ ከተሞች መሸሽ ይችላል። እነሱም ከደም ተበቃዩ+ መሸሸጊያ ሆነው ያገለግሏችኋል። +4 ገዳዩ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ+ በከተማዋ በር ላይ ቆሞ+ ለከተማዋ ሽማግሌዎች ጉዳዩን ይናገር። እነሱም ወደ ከተማቸው አስገብተው መኖሪያ ይስጡት፤ እሱም አብሯቸው ይኖራል። +5 ደም ተበቃዩ ቢያሳድደው ሰዎቹ ነፍሰ ገዳዩን አሳልፈው አይስጡት፤ ምክንያቱም ግለሰቡ ባልንጀራውን የገደለው የቆየ ጥላቻ ኖሮት ሳይሆን በድንገት* ነው።+ +6 ስለሆነም በማኅበረሰቡ ፊት ለፍርድ እስኪቀርብ+ ድረስ በከተማዋ ውስጥ ይኑር፤ በዚያ ጊዜ የሚያገለግለው ሊቀ ካህናት እስኪሞት ድረስም ከዚያ መውጣት የለበትም።+ ከዚያ በኋላ ገዳዩ ሸሽቶ ወደወጣባት ከተማ መመለስ እንዲሁም ወደ ከተማውና ወደ ቤቱ መግባት ይችላል።’”+ +7 በመሆኑም በንፍታሌም ተራራማ አካባቢ በገሊላ የምትገኘውን ቃዴሽን፣+ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ሴኬምንና+ በይሁዳ ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ቂርያትአርባን+ ማለትም ኬብሮንን ለዚህ ዓላማ ቀደሱ።* +8 ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ ባለው የዮርዳኖስ ክልል ደግሞ ከሮቤል ነገድ ርስት በአምባው ላይ በሚገኘው ምድረ በዳ ላይ ያለችውን ቤጼርን፣+ ከጋድ ነገድ ርስት በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትን+ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ ርስት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን+ መረጡ።+ +9 ሳያስበው ሰው* የገደለ ማንኛውም ግለሰብ በማኅበረሰቡ ፊት ለፍርድ ከመቅረቡ በፊት ደም ተበቃዩ አግኝቶ እንዳይገ���ለው ሸሽቶ እንዲሸሸግባቸው+ ለእስራኤላውያን በሙሉ ወይም በመካከላቸው ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው የተለዩት ከተሞች እነዚህ ናቸው።+ +3 ከዚያም ኢያሱ በማለዳ ተነሳ፤ እሱም ሆነ እስራኤላውያን* በሙሉ ከሺቲም+ ተነስተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ። ወደ ማዶም ሳይሻገሩ እዚያው አደሩ። +2 ከሦስት ቀን በኋላም አለቆቹ+ በሰፈሩ ውስጥ በመዘዋወር +3 ሕዝቡን እንዲህ በማለት አዘዙ፦ “ሌዋውያን የሆኑት ካህናት+ የአምላካችሁን የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ስታዩ ከሰፈራችሁበት ቦታ ተነስታችሁ ታቦቱን ተከተሉት። +"4 ሆኖም ወደ እሱ አትቅረቡ፤ በእናንተና በታቦቱ መካከል 2,000 ክንድ* ያህል ርቀት ይኑር፤ ከዚህ በፊት በዚህ አቅጣጫ ሄዳችሁ ስለማታውቁ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባችሁ በዚህ ትረዳላችሁ።” " +5 ኢያሱም ሕዝቡን “ይሖዋ በነገው ዕለት በመካከላችሁ ድንቅ ነገሮችን ስለሚያደርግ+ ራሳችሁን ቀድሱ”+ አላቸው። +6 ከዚያም ኢያሱ ካህናቱን “የቃል ኪዳኑን ታቦት አንስታችሁ+ ከሕዝቡ ቀድማችሁ ሂዱ” አላቸው። በመሆኑም ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት በማንሳት ከሕዝቡ ቀድመው ሄዱ። +7 ይሖዋም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ ሁሉ+ ከአንተም ጋር መሆኔን እንዲያውቁ+ በዛሬው ዕለት አንተን በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።+ +8 አንተም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙትን ካህናት ‘ዮርዳኖስ ውኃ ዳር ስትደርሱ እዚያው ዮርዳኖስ ውስጥ ባላችሁበት ቁሙ’ ብለህ እዘዛቸው።”+ +9 ኢያሱም እስራኤላውያንን “ወደዚህ ቀርባችሁ የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ስሙ” አላቸው። +10 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ በመካከላችሁ ሕያው አምላክ እንዳለና+ እሱም ከነአናውያንን፣ ሂታውያንን፣ ሂዋውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ገርጌሻውያንን፣ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን በእርግጥ ከፊታችሁ እንደሚያባርራቸው በዚህ ታውቃላችሁ።+ +11 የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳን ታቦት ቀድሟችሁ ወደ ዮርዳኖስ ይገባል። +12 እናንተም ከእስራኤል ነገዶች 12 ሰዎችን ይኸውም ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አንድ ሰው ምረጡ፤+ +13 የምድር ሁሉ ጌታ የሆነውን የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙት ካህናት እግር የዮርዳኖስን ውኃ ሲነካ* ከላይ የሚወርደው ውኃ ይቋረጣል፤ ውኃውም ልክ እንደ ግድብ* ቀጥ ብሎ ይቆማል።”+ +14 ስለዚህ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ለመሻገር ድንኳኑን ነቅሎ ሲነሳ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት+ ሕዝቡን ቀድመው ሄዱ። +15 ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት ዮርዳኖስ ጋ ሲደርሱና እግራቸውን ውኃው ዳር ሲያጠልቁ (ወቅቱ መከር ስለነበር በመከር ጊዜ እንደሚሆነው ሁሉ የዮርዳኖስ ወንዝ ሞልቶ ዳርቻውን አጥለቅልቆት ነበር)+ +16 ከላይ ይወርድ የነበረው ውኃ ቆመ። ውኃውም በሩቅ ይኸውም በጻረታን አጠገብ በምትገኘው በአዳም ከተማ እንደ ግድብ* ተቆልሎ ቆመ፤ በአረባ ወደሚገኘው ባሕር ይኸውም ወደ ጨው ባሕር* የሚወርደውም ውኃ ደረቀ። ውኃው ተቋርጦ ስለነበር ሕዝቡ ከኢያሪኮ ማዶ ወዳለው ስፍራ ተሻገረ። +17 እስራኤላውያን በሙሉ በደረቅ መሬት እስኪሻገሩ+ ይኸውም መላው ብሔር ዮርዳኖስን ተሻግሮ እስኪያበቃ ድረስ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙት ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ላይ ባሉበት ቆመው ነበር።+ +24 ከዚያም ኢያሱ የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ በሴኬም አንድ ላይ ሰበሰባቸው፤ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች፣ መሪዎች፣ ዳኞችና አለቆች+ ጠራ፤ እነሱም በእውነተኛው አምላክ ፊት ቆሙ። +2 ኢያሱም ሕዝቡን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የአብርሃምና የናኮር አባት የሆነውን ታራን ጨምሮ አባቶቻችሁ+ ከረጅም ጊዜ በፊት+ ከወንዙ* ማዶ ይኖሩ ነበር፤ እነሱም ሌሎች አማልክትን ያገለግሉ ነበር።+ +3 “‘እኔም ከጊዜ በኋላ አባታችሁን አብርሃምን+ ከወንዙ* ማዶ አምጥቼ በመላው የከነአን ምድር እንዲዘዋወር አደረግኩት፤ ዘሩንም አበዛሁለት።+ ይስሐቅን ሰጠሁት፤+ +4 ከዚያም ለይስሐቅ ያዕቆብንና ኤሳውን ሰጠሁት።+ በኋላም ለኤሳው ሴይር ተራራን ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤+ ያዕቆብና ልጆቹ ደግሞ ወደ ግብፅ ወረዱ።+ +5 በኋላም ሙሴንና አሮንን ላክኋቸው፤+ ግብፅንም በመካከላቸው በፈጸምኩት ነገር በመቅሰፍት መታኋት፤+ ከዚያም እናንተን አወጣኋችሁ። +6 አባቶቻችሁን ከግብፅ ባወጣኋቸውና+ ወደ ባሕሩ በደረሳችሁ ጊዜ ግብፃውያኑ የጦር ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን አሰልፈው አባቶቻችሁን እየተከታተሉ እስከ ቀይ ባሕር ድረስ መጡ።+ +7 እነሱም ወደ ይሖዋ መጮኽ ጀመሩ፤+ በመሆኑም በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ እንዲኖር አደረገ፤ ባሕሩንም በላያቸው ላይ በመመለስ አሰመጣቸው፤+ በግብፅ ያደረግኩትንም የገዛ ዓይኖቻችሁ አይተዋል።+ ከዚያም በምድረ በዳ ለብዙ ዓመታት* ኖራችሁ።+ +8 “‘ከዮርዳኖስ ማዶ* ይኖሩ ወደነበሩት ወደ አሞራውያንም ምድር አመጣኋችሁ፤ እነሱም ተዋጓችሁ።+ ሆኖም ምድራቸውን እንድትወርሱ እነሱን በእጃችሁ አሳልፌ ሰጠኋችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።+ +9 ከዚያም የሞዓብ ንጉሥ የሆነው የሴፎር ልጅ ባላቅ ተነስቶ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ። የቢዖርን ልጅ በለዓምንም እናንተን እንዲረግም አስጠራው።+ +10 እኔ ግን በለዓምን ልሰማው አልፈለግኩም።+ በመሆኑም ደጋግሞ ባረካችሁ፤+ እኔም ከእጁ አዳንኳችሁ።+ +11 “‘ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ+ ወደ ኢያሪኮ መጣችሁ።+ የኢያሪኮ መሪዎች* የሆኑት አሞራውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ከነአናውያን፣ ሂታውያን፣ ገርጌሻውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ተዋጓችሁ፤ እኔ ግን እነሱን በእጃችሁ አሳልፌ ሰጠኋችሁ።+ +12 ከእናንተ አስቀድሜ ጭንቀት* ላክሁ፤ ሁለቱንም የአሞራውያን ነገሥታት ከፊታችሁ አባረራቸው።+ ይህም የሆነው በሰይፋችሁ ወይም በቀስታችሁ አይደለም።+ +13 ስለዚህ ያልደከማችሁበትን ምድር፣ ያልገነባችኋቸውንም ከተሞች ሰጠኋችሁ፤+ እናንተም በዚያ መኖር ጀመራችሁ። ካልተከላችሁት የወይን ተክልና የወይራ ዛፍ እየበላችሁ ነው።’+ +14 “ስለዚህ ይሖዋን ፍሩ፤ በንጹሕ አቋምና* በታማኝነትም* አገልግሉት፤+ አባቶቻችሁ ከወንዙ* ማዶና በግብፅ ምድር ያገለገሏቸውን አማልክት አስወግዱ፤+ ይሖዋን አገልግሉ። +15 ይሖዋን ማገልገል መጥፎ መስሎ ከታያችሁ ደግሞ የምታገለግሉትን ዛሬውኑ ምረጡ፤+ ከወንዙ* ማዶ የነበሩት አባቶቻችሁ ያገለገሏቸውን አማልክትም+ ይሁን አሁን በምትኖሩበት ምድር ያሉት አሞራውያን የሚያገለግሏቸውን አማልክት+ መምረጥ ትችላላችሁ። እኔና ቤተሰቤ ግን ይሖዋን እናገለግላለን።” +16 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “በእኛ በኩል ይሖዋን መተውና ሌሎች አማልክትን ማገልገል ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። +17 እኛንም ሆነ አባቶቻችንን ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣን፣+ እነዚህን ታላላቅ ምልክቶች በፊታችን የፈጸመው+ እንዲሁም በሄድንበት መንገድ ሁሉና አቋርጠን ባለፍናቸው ሕዝቦች ሁሉ መካከል የጠበቀን+ አምላካችን ይሖዋ ነው። +18 ይሖዋ አሞራውያንን ጨምሮ ከእኛ በፊት በምድሪቱ ላይ ይኖሩ የነበሩትን ሕዝቦች በሙሉ አባረረ። ስለዚህ እኛም ይሖዋን እናገለግላለን፤ ምክንያቱም እሱ አምላካችን ነው።” +19 ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ አምላክን ማገልገል አትችሉም፤ ምክንያቱም እሱ ቅዱስ አምላክ ነው፤+ እንዲሁም እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።+ መተላለፋችሁንና* ኃጢአታችሁን ይቅር ���ይልም።+ +20 ይሖዋን ትታችሁ ባዕዳን አማልክትን ብታገለግሉ እሱም መልካም ነገር ካደረገላችሁ በኋላ በእናንተ ላይ ይዞርባችኋል፤ ደግሞም ያጠፋችኋል።”+ +21 ሕዝቡ ግን ኢያሱን “በፍጹም፣ እኛ ይሖዋን እናገለግላለን!” አሉት።+ +22 ስለዚህ ኢያሱ ሕዝቡን “በራሳችሁ ፍላጎት ይሖዋን ለማገልገል ስለመረጣችሁ እናንተ በራሳችሁ ላይ ምሥክሮች ናችሁ” አላቸው።+ እነሱም “አዎ፣ ምሥክሮች ነን” አሉ። +23 “እንግዲህ አሁን በመካከላችሁ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ ይሖዋ አዘንብሉ።” +24 ሕዝቡም ኢያሱን “አምላካችንን ይሖዋን እናገለግላለን፤ ቃሉንም እንሰማለን!” አለው። +25 በመሆኑም ኢያሱ በዚያ ቀን ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን ገባ፤ ለእነሱም በሴኬም ሥርዓትና ደንብ ደነገገላቸው። +26 ከዚያም ኢያሱ እነዚህን ቃላት በአምላክ የሕግ መጽሐፍ+ ላይ ጻፋቸው፤ ትልቅ ድንጋይም ወስዶ+ በይሖዋ መቅደስ አጠገብ በሚገኘው ትልቅ ዛፍ ሥር አቆመው። +27 ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ ይህ ድንጋይ ይሖዋ የነገረንን ሁሉ ስለሰማ በእኛ ላይ እንደ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል፤+ እንዲሁም አምላካችሁን እንዳትክዱ በእናንተ ላይ እንደ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል።” +28 ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ፣ እያንዳንዱን ወደየርስቱ አሰናበተ።+ +29 ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣ የይሖዋ አገልጋይ የሆነው የነዌ ልጅ ኢያሱ በ110 ዓመቱ ሞተ።+ +30 እነሱም ከጋአሽ ተራራ በስተ ሰሜን በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ በሚገኘው ርስቱ ውስጥ በቲምናትሰራ+ ቀበሩት። +31 እስራኤላውያን ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ እንዲሁም ከኢያሱ በኋላ በሕይወት በኖሩትና ይሖዋ ለእስራኤላውያን ሲል ያደረገውን ነገር በሙሉ በሚያውቁት ሽማግሌዎች ሁሉ ዘመን ይሖዋን ማገልገላቸውን ቀጠሉ።+ +32 እስራኤላውያን ከግብፅ ይዘውት የወጡት የዮሴፍ አፅም + ያዕቆብ ከሴኬም አባት ከኤሞር+ ልጆች ላይ በ100 ጥሬ ገንዘብ በገዛው+ በሴኬም በሚገኘው እርሻ ውስጥ ተቀብሮ ነበር፤ ይህም የዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።+ +33 የአሮን ልጅ አልዓዛርም ሞተ።+ እነሱም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ለልጁ ለፊንሃስ+ ተሰጥቶት በነበረው ኮረብታ ቀበሩት። +7 ይሁን እንጂ ከይሁዳ ነገድ የሆነው የዛራ ልጅ፣ የዛብዲ ልጅ፣ የካርሚ ልጅ አካን+ ለጥፋት ከተለየው ነገር ላይ በመውሰዱ እስራኤላውያን ለጥፋት ከተለየው ነገር ጋር በተያያዘ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጸሙ።+ በዚህም የተነሳ የይሖዋ ቁጣ በእስራኤላውያን ላይ ነደደ።+ +2 ከዚያም ኢያሱ “ወጥታችሁ ምድሪቱን ሰልሉ” በማለት ከቤቴል+ በስተ ምሥራቅ በቤትአዌን አቅራቢያ ወደምትገኘው ወደ ጋይ+ ሰዎችን ላከ። በመሆኑም ሰዎቹ ወጥተው ጋይን ሰለሉ። +3 ሰዎቹም ወደ ኢያሱ ተመልሰው እንዲህ አሉት፦ “ሕዝቡ ሁሉ መውጣት አያስፈልገውም። ጋይን ድል ለማድረግ ሁለት ሺህ ወይም ሦስት ሺህ ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ብቻ ይበቃሉ። ነዋሪዎቿ ጥቂት ስለሆኑ መላው ሕዝብ እንዲሄድ በማድረግ ሕዝቡን አታድክም።” +"4 በመሆኑም 3,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ወደዚያ ወጡ፤ ይሁን እንጂ ከጋይ ሰዎች ፊት ለመሸሽ ተገደዱ።+" +5 የጋይ ሰዎችም 36 ሰዎችን ገደሉ፤ ከከተማዋ በር አንስቶ እስከ ሸባሪም* ድረስ በማሳደድ ቁልቁለቱ ላይ መቷቸው። በዚህም የተነሳ የሕዝቡ ልብ ቀለጠ፤ እንደ ውኃም ፈሰሰ። +6 በዚህ ጊዜ ኢያሱ ልብሱን ቀደደ፤ እስከ ምሽትም ድረስ በይሖዋ ታቦት ፊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እሱም ሆነ የእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲሁ አደረጉ፤ በራሳቸውም ላይ አቧራ ይበትኑ ነበር። +7 ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ወዮ! ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ይህን ሁሉ ሕዝብ ዮርዳኖስን አሻግረህ እዚህ ��ረስ ያመጣኸው ለአሞራውያን አሳልፈህ በመስጠት እንድንጠፋ ለማድረግ ነው? እዚያው በዮርዳኖስ ማዶ* አርፈን ብንቀመጥ ይሻለን ነበር! +8 አቤቱ ይሖዋ ሆይ ይቅር በለኝ፣ እንግዲህ እስራኤል ከጠላቶቹ ፊት እንዲህ የሚሸሽ* ከሆነ ምን ማለት እችላለሁ? +9 ከነአናውያንና የምድሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ ይህን ሲሰሙ መጥተው ይከቡንና ስማችንን ከምድር ገጽ ያጠፉታል፤ ታዲያ አንተ ለታላቁ ስምህ ስትል ምን ታደርግ ይሆን?”+ +10 ይሖዋም ለኢያሱ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ተነስ! በግንባርህ የተደፋኸው ለምንድን ነው? +11 እስራኤላውያን ኃጢአት ሠርተዋል። እንዲጠብቁት ያዘዝኳቸውን ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል።+ ለጥፋት ከተለየው ነገር ላይም ሰርቀው+ ወስደዋል፤+ ከራሳቸው ዕቃዎችም ጋር በመቀላቀል ደብቀው አስቀምጠውታል።+ +12 ስለዚህ እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን መቋቋም አይችሉም። ዞረውም ከጠላቶቻቸው ፊት ይሸሻሉ፤ ምክንያቱም እነሱ ራሳቸው ለጥፋት የተለዩ ሆነዋል። ለጥፋት የተለየውን ነገር ከመካከላችሁ ካላስወገዳችሁ በስተቀር ከእንግዲህ እኔ ከእናንተ ጋር አልሆንም።+ +13 ተነስና ሕዝቡን ቀድስ!+ እንዲህም በላቸው፦ ‘ነገ ራሳችሁን ቀድሱ፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “እስራኤል ሆይ፣ በመካከልህ ለጥፋት የተለየ ነገር አለ። ለጥፋት የተለየውን ነገር ከመካከልህ ካላስወገድክ ጠላቶችህን መቋቋም አትችልም። +14 ማለዳ ላይ በነገድ በነገድ ሆናችሁ ትቀርባላችሁ፤ ይሖዋ የሚመርጠውም ነገድ+ ወደ ፊት ይቀርባል፤ ከዚያም በወገን በወገኑ ሆኖ ይቀርባል፤ ይሖዋ የሚመርጠውም ወገን ወደ ፊት ይቀርባል፤ ከዚያም በቤተሰብ በቤተሰብ ሆኖ ይቀርባል፤ ይሖዋ የሚመርጠውም ቤተሰብ ወደ ፊት ይቀርባል፤ ከዚያም በግለሰብ በግለሰብ ሆ +15 ለጥፋት የተለየውን ነገር ወስዶ የተገኘውም ሰው በእሳት ይቃጠላል፤+ እሱም ሆነ የእሱ የሆነው ሁሉ ይቃጠላሉ፤ ምክንያቱም ይህ ሰው የይሖዋን ቃል ኪዳን አፍርሷል፤+ እንዲሁም በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪ ተግባር ፈጽሟል።”’” +16 ስለሆነም ኢያሱ በሚቀጥለው ቀን በማለዳ ተነስቶ እስራኤላውያን በነገድ በነገድ ሆነው ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ የይሁዳም ነገድ ተመረጠ። +17 የይሁዳ ወገኖች ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከመካከላቸውም የዛራውያን+ ወገን ተመረጠ፤ ከዚያም ከዛራውያን ወገን የሆኑት ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም ዛብዲ ተመረጠ። +18 በመጨረሻም የዛብዲ ቤተሰብ በግለሰብ በግለሰብ ሆኖ ወደ ፊት እንዲቀርብ አደረገ፤ ከዚያም ከይሁዳ ነገድ የዛራ ልጅ፣ የዛብዲ ልጅ፣ የካርሚ ልጅ አካን ተመረጠ።+ +19 ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ፣ እባክህ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን አክብር፤ ለእሱም ተናዘዝ። እባክህ ያደረግከውን ንገረኝ። አትደብቀኝ።” +20 አካንም ለኢያሱ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “በእርግጥም በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ላይ ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ፤ እንግዲህ ያደረግኩት ይህ ነው፦ +21 ከምርኮው መካከል ከሰናኦር+ የመጣ የሚያምር የክብር ልብስ፣ 200 ሰቅል* ብርና 50 ሰቅል የሚመዝን ጥፍጥፍ ወርቅ አይቼ ስለተመኘሁ ወሰድኳቸው። አሁንም ገንዘቡ ከታች ሆኖ ድንኳኔ ውስጥ መሬት ውስጥ ተቀብረው ይገኛሉ።” +22 ኢያሱም ወዲያውኑ መልእክተኞች ላከ፤ እነሱም ወደ ድንኳኑ እየሮጡ ሄዱ፤ ልብሱንም ድንኳኑ ውስጥ ተደብቆ አገኙት፤ ገንዘቡም ከልብሱ ሥር ነበር። +23 ከዚያም ከድንኳኑ አውጥተው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤላውያን ሁሉ አመጧቸው፤ በይሖዋም ፊት አስቀመጧቸው። +24 በኋላም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ የዛራን ልጅ አካንን፣+ ብሩን፣ የክብር ልብሱን፣ ጥፍጥፍ ወርቁን፣+ ወንዶች ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹን፣ በሬውን፣ አህያውን፣ መንጋውን፣ ድንኳኑንና የእሱ የሆነውን ሁሉ ወደ አኮር ሸለቆ*+ አመጡ። +25 ኢያሱም አካንን “መዓት* ያመጣህብን ለምንድን ነው?+ ይሖዋም በዛሬው ዕለት መዓት ያመጣብሃል” አለው። ከዚያም እስራኤላውያን በሙሉ በድንጋይ ወገሩት፤+ በእሳትም አቃጠሏቸው።+ በዚህ መንገድ ሁሉንም በድንጋይ ወግረው ገደሏቸው። +26 በእሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታየውን የድንጋይ ቁልል ከመሩበት። በዚህ ጊዜ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በረደ።+ የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር* ሸለቆ የሚባለው በዚህ የተነሳ ነው። +12 እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን ምድራቸውን ይኸውም ከአርኖን ሸለቆ*+ አንስቶ እስከ ሄርሞን ተራራ+ ድረስ ያለውን እንዲሁም በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን አረባን በሙሉ የወረሱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦+ +2 በሃሽቦን የሚኖረውና በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ላይ በምትገኘው በአሮዔር+ ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን፤+ እሱም በአርኖን ሸለቆ+ መሃል ካለው ስፍራ አንስቶ የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ሸለቆ* ድረስ ያለውን የጊልያድን እኩሌታ ይገዛ ነበር። +3 በተጨማሪም ምሥራቃዊ አረባን እስከ ኪኔሬት ባሕር*+ ድረስ፣ በስተ ምሥራቅ በቤትየሺሞት አቅጣጫ እስካለው የአረባ ባሕር ይኸውም እስከ ጨው ባሕር* ድረስና በስተ ደቡብ እስከ ጲስጋ+ ሸንተረር ድረስ ያለውን አካባቢ ይገዛ ነበር። +4 እንዲሁም በአስታሮትና በኤድራይ ይኖር የነበረውንና ከመጨረሻዎቹ የረፋይም+ ወገኖች አንዱ የሆነውን የባሳንን ንጉሥ የኦግን+ ግዛት፤ +5 እሱም የሄርሞንን ተራራ፣ ሳልካን፣ ባሳንን+ በሙሉ እስከ ገሹራውያንና እስከ ማአካታውያን+ ወሰን ድረስ እንዲሁም እስከ ሃሽቦን+ ንጉሥ እስከ ሲሖን ግዛት ድረስ ያለውን የጊልያድን እኩሌታ ይገዛ ነበር። +6 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ነገሥታት ድል አደረጓቸው፤+ ከዚያም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ምድራቸውን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጠ።+ +7 ኢያሱና እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸው ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ያሉት የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ+ ከሚገኘው ከበዓልጋድ+ አንስቶ ወደ ሴይር+ ሽቅብ እስከሚወጣው እስከ ሃላቅ ተራራ+ ድረስ ነው፤ ከዚያም ኢያሱ ምድራቸውን ለእስራኤል ነገዶች እንደየድርሻቸው ርስት አድርጎ +8 ይህም በተራራማው አካባቢ፣ በሸፌላ፣ በአረባ፣ በሸንተረሮቹ ላይ፣ በምድረ በዳውና በኔጌብ+ የሚኖሩት የሂታውያን፣ የአሞራውያን፣+ የከነአናውያን፣ የፈሪዛውያን፣ የሂዋውያንና የኢያቡሳውያን+ ምድር ነው፤ ነገሥታቱም የሚከተሉት ናቸው፦ + 9 የኢያሪኮ ንጉሥ፣+ አንድ፤ በቤቴል አጠገብ የነበረችው የጋይ ንጉሥ፣+ አንድ፤ +10 የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ አንድ፤ የኬብሮን ንጉሥ፣+ አንድ፤ +11 የያርሙት ንጉሥ፣ አንድ፤ የለኪሶ ንጉሥ፣ አንድ፤ +12 የኤግሎን ንጉሥ፣ አንድ፤ የጌዜር ንጉሥ፣+ አንድ፤ +13 የደቢር ንጉሥ፣+ አንድ፤ የጌዴር ንጉሥ፣ አንድ፤ +14 የሆርማ ንጉሥ፣ አንድ፤ የአራድ ንጉሥ፣ አንድ፤ +15 የሊብና ንጉሥ፣+ አንድ፤ የአዱላም ንጉሥ፣ አንድ፤ +16 የመቄዳ ንጉሥ፣+ አንድ፤ የቤቴል ንጉሥ፣+ አንድ፤ +17 የታጱአ ንጉሥ፣ አንድ፤ የሄፌር ንጉሥ፣ አንድ፤ +18 የአፌቅ ንጉሥ፣ አንድ፤ የላሻሮን ንጉሥ፣ አንድ፤ +19 የማዶን ንጉሥ፣ አንድ፤ የሃጾር ንጉሥ፣+ አንድ፤ +20 የሺምሮንመሮን ንጉሥ፣ አንድ፤ የአክሻፍ ንጉሥ፣ አንድ፤ +21 የታአናክ ንጉሥ፣ አንድ፤ የመጊዶ ንጉሥ፣ አንድ፤ +22 የቃዴሽ ንጉሥ፣ አንድ፤ በቀርሜሎስ የምትገኘው የዮቅነአም ንጉሥ፣+ አንድ፤ +23 በዶር+ ሸንተረሮች የምትገኘው የዶር ንጉሥ፣ አንድ፤ በጊልጋል የምትገኘው የጎይም ንጉሥ፣ አንድ፤ +24 የቲርጻ ንጉሥ፣ አንድ፤ በአጠቃላይ 31 ነገሥታት ናቸው። +1 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ ይሖዋ የሙሴ አገልጋይ+ የነበረውን የነዌን ልጅ ኢያሱን*+ እንዲህ አለው፦ +2 “አገልጋዬ ሙሴ ሞቷል።+ እንግዲህ አንተም ሆንክ ይህ ሕዝብ ተነስታችሁ ዮርዳኖስን በመሻገር ለእስራኤላውያን ወደምሰጣቸው ምድር ግቡ።+ +3 ለሙሴ በገባሁት ቃል መሠረት እግራችሁ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ እሰጣችኋለሁ።+ +4 ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስና እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ይኸውም መላው የሂታውያን+ ምድር እንዲሁም በስተ ምዕራብ* እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር* ድረስ ይሆናል።+ +5 በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም።+ ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ ሁሉ ከአንተም ጋር እሆናለሁ።+ አልጥልህም ወይም አልተውህም።+ +6 ይህን ሕዝብ ለአባቶቻቸው ልሰጣቸው ወደማልኩላቸው ምድር+ የምታስገባው አንተ ስለሆንክ ደፋርና ብርቱ ሁን።+ +7 “ብቻ አንተ ደፋርና ብርቱ ሁን፤ አገልጋዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም። በምትሄድበት በየትኛውም ቦታ ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን እንድትችል+ ከዚህ ሕግ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል።+ +8 ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤+ በውስጡ የተጻፈውንም በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችል ቀንም ሆነ ሌሊት በለሆሳስ አንብበው፤*+ እንዲህ ካደረግክ መንገድህ ይቃናልሃል፤ እንዲሁም ማንኛውንም ነገር በጥበብ ማከናወን ትችላለህ።+ +9 ደፋርና ብርቱ ሁን ብዬ አዝዤህ አልነበረም? አምላክህ ይሖዋ በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር ስለሆነ አትሸበር፤ አትፍራ።”+ +10 ከዚያም ኢያሱ የሕዝቡን አለቆች እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ +11 “በሰፈሩ ውስጥ በመዘዋወር ሕዝቡን እንዲህ በማለት እዘዙ፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ ለመውረስ በሦስት ቀን ውስጥ ዮርዳኖስን ስለምትሻገሩ ስንቃችሁን አዘጋጁ።’”+ +12 ኢያሱም ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ እንዲህ አላቸው፦ +13 “የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ እንዲህ በማለት ያዘዛችሁን ቃል አስታውሱ፦+ ‘አምላካችሁ ይሖዋ እረፍት ሰጥቷችኋል፤ ይህን ምድር አውርሷችኋል። +14 ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ በሰጣችሁ ከዮርዳኖስ ወዲህ ባለው ምድር* ላይ ይቀመጣሉ፤+ ሆኖም ብርቱ የሆናችሁት ተዋጊዎች በሙሉ+ የጦርነት አሰላለፍ በመከተል ወንድሞቻችሁን ቀድማችሁ ትሻገራላችሁ።+ እነሱን መርዳት ይገባችኋል፤ +15 ይሖዋ ለእናንተ እንዳደረገው ሁሉ ለወንድሞቻችሁም እረፍት እስከሚሰጣቸውና አምላካችሁ ይሖዋ የሚሰጣቸውን ምድር እስከሚወርሱ ድረስ ይህን ማድረግ ይኖርባችኋል። ከዚያም እንድትይዟትና እንድትወርሷት ወደተሰጠቻችሁ ይኸውም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ወደሰጣችሁ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ወደምትገኘው ምድር ትመለሳላ +16 እነሱም ለኢያሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “የምታዘንን ሁሉ እንፈጽማለን፤ ወደምትልከንም ሁሉ እንሄዳለን።+ +17 ሙሴ የሚለንን ማንኛውንም ነገር እንሰማ እንደነበር ሁሉ አንተንም እንሰማለን። ብቻ አምላክህ ይሖዋ ከሙሴ ጋር እንደነበረ ሁሉ ከአንተም ጋር ይሁን።+ +18 መመሪያህን አልታዘዝም የሚልና የምትሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ የማይሰማ ማንኛውም ሰው ይገደል።+ ብቻ አንተ ደፋርና ብርቱ ሁን።”+ +8 ከዚያም ይሖዋ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “አትፍራ ወይም አትሸበር።+ ተዋጊዎቹን ሁሉ ይዘህ በጋይ ላይ ዝመት። እነሆ፣ የጋይን ንጉሥ፣ ሕዝቡን፣ ከተማውንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ።+ +2 በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ ያደረግከውን ሁሉ በጋይና በንጉሥዋም ላይ አድርግ፤+ የማረካችኋቸውን ነገሮችና ከብቶቿን ግን ለራሳችሁ ውሰዱ። ከከተማዋም በስተ ጀርባ የደፈጣ ተዋጊዎችን አስቀምጥ።” +"3 ስለዚህ ኢያሱና ተዋጊዎቹ በሙሉ ጋይን ለመውጋት ወጡ። ኢያሱም 30,000 ኃያል ተዋጊዎችን መርጦ በሌሊት ላካቸው።" +4 እንዲህም ሲል አዘዛቸው፦ “እንግዲህ እናንተ ከከተማዋ በስተ ጀርባ አድፍጣችሁ ትጠብቃላችሁ። ከከተማዋ ብዙ አትራቁ፤ ሁላችሁም በተጠንቀቅ ጠብቁ። +5 እኔና አብሮኝ ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማዋ እንቀርባለን፤ እነሱም ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ ሊወጉን ሲወጡ+ እኛ ከፊታቸው እንሸሻለን። +6 እነሱም ‘ከዚህ በፊት እንዳደረጉት አሁንም ከፊታችን እየሸሹ ነው’+ በማለት ይከታተሉናል፤ በዚህ መንገድ ከከተማዋ እንዲርቁ እናደርጋቸዋለን። እኛም ከእነሱ እንሸሻለን። +7 እናንተም ካደፈጣችሁበት ቦታ ተነስታችሁ ከተማዋን ትቆጣጠራላችሁ፤ አምላካችሁ ይሖዋም ከተማዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል። +8 ከተማዋን እንደያዛችሁም በእሳት አቃጥሏት።+ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት አድርጉ። እንግዲህ እኔ አዝዣችኋለሁ።” +9 ከዚያም ኢያሱ ሰዎቹን ላካቸው፤ እነሱም አድፍጠው ወደሚጠባበቁበት ቦታ ሄዱ፤ ከጋይ በስተ ምዕራብ በቤቴልና በጋይ መካከል በሚገኘው ስፍራም አደፈጡ፤ ኢያሱ ግን ያን ሌሊት እዚያው ከሕዝቡ ጋር አደረ። +10 ከዚያም ኢያሱ በማለዳ ተነስቶ ሠራዊቱን ከሰበሰበ በኋላ እሱና የእስራኤል ሽማግሌዎች እየመሯቸው ወደ ጋይ ይዘዋቸው ሄዱ። +11 ከእሱም ጋር የነበሩት ተዋጊዎች በሙሉ+ ገስግሰው ወደ ከተማዋ ፊት ቀረቡ። እነሱም ከጋይ በስተ ሰሜን ሰፈሩ፤ በእነሱና በጋይ መካከልም ሸለቆ ነበር። +"12 በዚህ ጊዜ ኢያሱ 5,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎችን ወስዶ ከከተማዋ በስተ ምዕራብ በኩል በቤቴልና+ በጋይ መካከል አድፍጠው እንዲጠብቁ+ አድርጎ ነበር።" +13 ሕዝቡም ዋና ሰፈሩን ከከተማዋ በስተ ሰሜን አደረገ፤+ የኋላ ደጀን የሆነውን ሠራዊት ደግሞ ከከተማዋ በስተ ምዕራብ አደረገ፤+ ኢያሱም በዚያ ሌሊት ወደ ሸለቆው* መሃል ሄደ። +14 የጋይም ንጉሥ ይህን ባየ ጊዜ እሱና የከተማዋ ሰዎች ማልደው በመነሳት ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት በረሃማውን ሜዳ ቁልቁል ማየት ወደሚያስችላቸው ስፍራ በፍጥነት ገሰገሱ። ሆኖም ንጉሡ ከከተማዋ በስተ ጀርባ በእሱ ላይ ያደፈጠ ሠራዊት መኖሩን አላወቀም ነበር። +15 የጋይ ሰዎችም ጥቃት በሰነዘሩ ጊዜ ኢያሱና መላው እስራኤል ድል የተመቱ በማስመሰል ወደ ምድረ በዳው የሚወስደውን መንገድ ይዘው ሸሹ።+ +16 ከዚያም በከተማዋ ውስጥ የነበረው ሕዝብ በሙሉ ወጥቶ እንዲያሳድዳቸው ተጠራ፤ እነሱም ኢያሱን እያሳደዱ ከከተማዋ ርቀው ሄዱ። +17 ከጋይም ሆነ ከቤቴል እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ አንድም ወንድ አልነበረም። ከተማዋንም ወለል አድርገው ከፍተው በመሄድ እስራኤልን ማሳደዳቸውን ተያያዙት። +18 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ኢያሱን “ከተማዋን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ+ የያዝከውን ጦር ወደ ጋይ አቅጣጫ ሰንዝር”+ አለው። ኢያሱም ይዞት የነበረውን ጦር ወደ ከተማዋ አቅጣጫ ሰነዘረ። +19 ያደፈጠውም ሠራዊት ኢያሱ እጁን በሰነዘረበት ቅጽበት ወዲያውኑ ከቦታው ተነስቶ ወደ ከተማዋ ሮጦ በመግባት ያዛት። ከዚያም በፍጥነት ከተማዋን በእሳት አያያዟት።+ +20 የጋይ ሰዎች ዞረው ሲመለከቱ የከተማዋ ጭስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደየትኛውም አቅጣጫ መሸሽ የሚችሉበት አቅም አልነበራቸውም። ወደ ምድረ በዳው እየሸሹ የነበሩትም ሰዎች ወደ አሳዳጆቻቸው ዞሩ። +21 ኢያሱና እስራኤላውያን በሙሉ፣ አድፍጦ የነበረው ሠራዊት ከተማዋን በቁጥጥር ሥር ማዋሉንና የከተማዋ ጭስ ��ደ ላይ መውጣቱን ሲመለከቱ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ማጥቃት ጀመሩ። +22 ከተማዋን ተቆጣጥረው የነበሩትም ሰዎች እነሱን ለመግጠም ከከተማዋ ወጡ፤ በመሆኑም የጋይ ሰዎች በሁለቱም በኩል ባሉት እስራኤላውያን መካከል አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ፤ እነሱም ፈጇቸው፤ ከመካከላቸው የተረፈም ሆነ ያመለጠ አንድም እንኳ አልነበረም።+ +23 የጋይን ንጉሥ+ ግን ከነሕይወቱ ይዘው ወደ ኢያሱ አመጡት። +24 እስራኤላውያን የጋይን ነዋሪዎች በሙሉ ሜዳ ላይ ይኸውም ሲያሳድዷቸው በነበረው ምድረ በዳ ላይ ፈጇቸው፤ አንድም ሳይቀር ሁሉም በሰይፍ አለቁ። ከዚያም እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ጋይ ተመልሰው ከተማዋን በሰይፍ መቱ። +"25 ወንድ ሴት ሳይል በዚያን ቀን የሞቱት የጋይ ሰዎች በጠቅላላ 12,000 ነበሩ።" +26 ኢያሱም የጋይን ነዋሪዎች በሙሉ ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ+ ጦር የሰነዘረበትን እጁን አልመለሰውም።+ +27 እስራኤላውያንም ይሖዋ ለኢያሱ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት የከተማዋን ምርኮና ከብቶች ለራሳቸው ወሰዱ።+ +28 ኢያሱም ጋይን በእሳት አጋያት፤ ከተማዋንም የፍርስራሽ ክምር ሆና እንድትቀር አደረጋት፤+ እስከ ዛሬም ድረስ ባድማ ናት። +29 የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ እንጨት* ላይ ሰቀለው፤ ከዚያም ኢያሱ ፀሐይ ልትጠልቅ ስትል በድኑን ከእንጨቱ ላይ እንዲያወርዱት ትእዛዝ ሰጠ።+ እነሱም በድኑን በከተማዋ በር ላይ ጣሉት፤ በእሱም ላይ ትልቅ የድንጋይ ቁልል ከመሩበት፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ እዚያው ይገኛል። +30 ኢያሱም በኤባል ተራራ+ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ መሠዊያ የሠራው በዚያን ጊዜ ነበር፤ +31 መሠዊያውንም የሠራው የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ለእስራኤላውያን በሰጠው ትእዛዝና በሙሴ የሕግ መጽሐፍ+ ላይ በተጻፈው “መሠዊያው የብረት መሣሪያ ካልነካው ያልተጠረበ ድንጋይ የተሠራ ይሁን”+ በሚለው መመሪያ መሠረት ነው። በዚያም ላይ የሚቃጠሉ መባዎችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን ለይሖዋ አቀረቡ።+ +32 ከዚያም በድንጋዮቹ ላይ ሙሴ በእስራኤላውያን ፊት የጻፈውን ሕግ ቅጂ+ ጻፈባቸው።+ +33 እስራኤላውያን በሙሉ፣ ሽማግሌዎቻቸው፣ አለቆቻቸውና ዳኞቻቸው የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት በሚሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ከታቦቱ ወዲህና ወዲያ ቆመው ነበር። የባዕድ አገር ሰዎችም ሆኑ የአገሬው ተወላጆች በዚያ ነበሩ።+ የእስራኤልን ሕዝብ ለመባረክ (የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ቀደም ሲል ባዘዘው መሠረት) +34 ከዚህ በኋላ ኢያሱ በሕጉ መጽሐፍ+ ላይ በተጻፈው መሠረት የሕጉን ቃላት በሙሉ ይኸውም በረከቱንና+ እርግማኑን+ ድምፁን ከፍ አድርጎ አነበበ። +35 ኢያሱ፣ ሙሴ ከሰጠው ትእዛዝ ውስጥ፣ ሴቶችንና ልጆችን እንዲሁም በመካከላቸው የሚኖሩ+ የባዕድ አገር ሰዎችን+ ጨምሮ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ድምፁን ከፍ አድርጎ ያላነበበው አንድም ቃል አልነበረም።+ +11 የሃጾር ንጉሥ ያቢን ይህን ሲሰማ ወደ ማዶን ንጉሥ+ ወደ ዮባብ፣ ወደ ሺምሮን ንጉሥ፣ ወደ አክሻፍ ንጉሥ+ +2 እንዲሁም በስተ ሰሜን በሚገኘው ተራራማ አካባቢ፣ በደቡብ ኪኔሬት ባሉት ሜዳዎችና* በሸፌላ ወደሚገኙት እንዲሁም በስተ ምዕራብ በዶር+ ሸንተረሮች ወዳሉት ነገሥታት፣ +3 በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ወዳሉት ከነአናውያን፣+ ወደ አሞራውያን፣+ ወደ ሂታውያን፣ ወደ ፈሪዛውያን፣ በተራራማው አካባቢ ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሳውያን እንዲሁም በምጽጳ ምድር በሄርሞን+ ግርጌ ወደሚገኙት ወደ ሂዋውያን+ መልእክት ላከ። +4 እነሱም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ ከሆነው ሠራዊታቸው ሁሉ ጋር ወጡ፤ እጅግ ብዙ ፈረሶችና የጦር ሠረገሎችም ነበሯቸው። +5 እነዚህም ነገሥታት በሙሉ አንድ ላይ ለመገናኘት ተስማሙ፤ ከዚያም እስራኤልን ለመውጋት መጥተ��� በመሮም ውኃ አጠገብ አንድ ላይ ሰፈሩ። +6 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ሰዓት ገደማ ሁሉንም ለእስራኤላውያን አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍሯቸው፤+ እናንተም ትፈጇቸዋላችሁ። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ቁረጡ፣+ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።” +7 ከዚያም ኢያሱና አብረውት የነበሩት ተዋጊዎች በሙሉ በመሮም ውኃ አጠገብ ድንገተኛ ጥቃት ሰነዘሩባቸው። +8 ይሖዋም ለእስራኤላውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤+ እነሱም ድል አደረጓቸው፤ እስከ ታላቋ ሲዶና፣+ እስከ ሚስረፎትማይምና+ በስተ ምሥራቅ እስካለው እስከ ምጽጳ ሸለቆ ድረስም አሳደዷቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት ሳያስቀሩ መቷቸው።+ +9 ከዚያም ኢያሱ ልክ ይሖዋ እንደነገረው አደረገባቸው፤ የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ቆረጠ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።+ +10 ከዚህም በተጨማሪ ኢያሱ ተመልሶ ሃጾርን ተቆጣጠረ፤ ንጉሥዋንም በሰይፍ መትቶ ገደለው፤+ ምክንያቱም ሃጾር ቀደም ሲል የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ የበላይ ነበረች። +11 እነሱም በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ በሰይፍ በመምታት ፈጽመው አጠፉ።+ እስትንፋስ ያለው አንድም ነገር አላስቀሩም።+ ከዚያም ሃጾርን በእሳት አቃጠላት። +12 ኢያሱ የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች በሙሉ በቁጥጥር ሥር አዋለ፤ ነገሥታታቸውንም ሁሉ በሰይፍ ድል አደረገ።+ የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ባዘዘውም መሠረት ፈጽሞ አጠፋቸው።+ +13 ሆኖም እስራኤላውያን ኢያሱ ካቃጠላት ከሃጾር በስተቀር በኮረብቶቻቸው ላይ ካሉት ከተሞች አንዱንም አላቃጠሉም ነበር። +14 እስራኤላውያን ከእነዚህ ከተሞች ያገኙትን ምርኮና የቤት እንስሳ ሁሉ ለራሳቸው ወሰዱ።+ ሰዎቹን ግን አንድ በአንድ በሰይፍ መተው ሁሉንም አጠፏቸው።+ እስትንፋስ ያለው አንድም ሰው አላስቀሩም።+ +15 ይሖዋ አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ሙሴም ኢያሱን አዞት ነበር፤+ ኢያሱም እንደተባለው አደረገ። ኢያሱ፣ ይሖዋ ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ሳይፈጽም የቀረው አንድም ነገር አልነበረም።+ +16 ኢያሱ ይህን ምድር በሙሉ ይኸውም ተራራማውን አካባቢ፣ ኔጌብን+ በሙሉ፣ የጎሸንን ምድር ሁሉ፣ ሸፌላን፣+ አረባን፣+ የእስራኤልን ተራራማና ቆላማ አካባቢዎች በሙሉ ድል አደረገ፤ +17 ወደ ሴይር ሽቅብ ከሚወጣው ከሃላቅ ተራራ አንስቶ በሄርሞን ተራራ+ ግርጌ በሊባኖስ ሸለቆ እስከሚገኘው እስከ በዓልጋድ+ ድረስ ያለውን አካባቢ በሙሉ ድል አደረገ፤ ነገሥታታቸውን ሁሉ በቁጥጥር ሥር አዋለ፤ ድል አደረጋቸው፤ ገደላቸውም። +18 ኢያሱ ከእነዚህ ሁሉ ነገሥታት ጋር ለተወሰነ ጊዜ ተዋጋ። +19 በገባኦን ከሚኖሩት ሂዋውያን በስተቀር ከእስራኤላውያን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት የፈጠረ አንድም ከተማ አልነበረም።+ ሌሎቹን ሁሉ በጦርነት ድል አደረጓቸው።+ +20 በእስራኤል ላይ ጦርነት እንዲከፍቱና ምንም ሳይራራላቸው ፈጽሞ ያጠፋቸው+ ዘንድ ልባቸው እንዲደነድን የፈቀደው ይሖዋ ነው።+ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሙሉ በሙሉ መጥፋት ነበረባቸው።+ +21 በዚያን ጊዜ ኢያሱ ከተራራማው አካባቢ ከኬብሮን፣ ከደቢር፣ ከአናብ እንዲሁም ከይሁዳ ተራራማ አካባቢዎች ሁሉና ከእስራኤል ተራራማ አካባቢዎች ሁሉ ኤናቃውያንን+ ጠራርጎ አጠፋ። ኢያሱ እነሱንም ሆነ ከተሞቻቸውን ሙሉ በሙሉ አጠፋቸው።+ +22 በእስራኤላውያን ምድር የተረፈ አንድም ኤናቃዊ አልነበረም፤ ኤናቃውያን የነበሩት በጋዛ፣+ በጌት+ እና በአሽዶድ+ ብቻ ነበር።+ +23 ስለዚህ ኢያሱ ይሖዋ ለሙሴ በገባው ቃል መሠረት ምድሩን ሁሉ ተቆጣጠረ፤+ ከዚያም ኢያሱ ለእስራኤላውያን በየነገዳቸው ድርሻቸውን ርስት አድርጎ ሰጣቸው።+ ምድሪቱም ከጦርነት አረፈች።+ +2 ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ ከሺቲም+ ሁለት ሰላዮችን በድብቅ ላከ። እነሱንም “እስቲ ሄዳችሁ ምድሪቱን በተለይም ኢያሪኮን አይታችሁ ኑ” አላቸው። ሰዎቹም ሄደው ረዓብ+ ወደተባለች አንዲት ዝሙት አዳሪ ቤት ገቡ፤ በዚያም አረፉ። +2 የኢያሪኮም ንጉሥ “እስራኤላውያን የሆኑ ሰዎች ምድሪቱን ለመሰለል ዛሬ ማታ ወደዚህ መጥተዋል” ተብሎ ተነገረው። +3 በዚህ ጊዜ የኢያሪኮ ንጉሥ ወደ ረዓብ እንዲህ የሚል መልእክት ላከባት፦ “ቤትሽ መጥተው ያረፉትን ሰዎች አውጪ፤ ምክንያቱም ወደዚህ የመጡት ምድሪቱን በሙሉ ለመሰለል ነው።” +4 ሴትየዋ ግን ሁለቱን ሰዎች ደበቀቻቸው። ከዚያም እንዲህ አለች፦ “በእርግጥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተው ነበር፤ ሆኖም ከየት እንደመጡ አላወቅኩም። +5 ምሽት ላይ የከተማዋ በር ሊዘጋ ሲል ወጥተው ሄደዋል። ወዴት እንደሄዱ አላውቅም፤ ሆኖም ፈጥናችሁ ከተከታተላችኋቸው ልትደርሱባቸው ትችላላችሁ።” +6 (ይሁንና ሰዎቹን ጣሪያ ላይ ይዛቸው ወጥታ በተረበረበ የተልባ እግር ውስጥ ደብቃቸው ነበር።) +7 ሰዎቹም ሰላዮቹን በመከታተል ወደ ዮርዳኖስ አቅጣጫ በመልካው*+ በኩል ሄዱ፤ አሳዳጆቹ ወጥተው እንደሄዱም የከተማዋ በር ተዘጋ። +8 እሷም ሰላዮቹ ከመተኛታቸው በፊት እነሱ ወዳሉበት ወደ ጣሪያው ወጣች። +9 እንዲህም አለቻቸው፦ “ይሖዋ ምድሪቱን እንደሚሰጣችሁ አውቃለሁ፤+ እኛም እናንተን በመፍራት ተሸብረናል።+ የምድሪቱ ነዋሪዎች በሙሉ በእናንተ የተነሳ ልባቸው ከድቷቸዋል፤+ +10 ምክንያቱም ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ ይሖዋ ቀይ ባሕርን በፊታችሁ እንዴት እንዳደረቀው+ እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ* በደመሰሳችኋቸው በሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት፣ በሲሖንና+ በኦግ+ ላይ ምን እንዳደረጋችሁ ሰምተናል። +11 ይህን ስንሰማ ልባችን ቀለጠ፤ በእናንተም የተነሳ ወኔ ያልከዳው ማንም አልነበረም፤ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ ነው።+ +12 እንግዲህ እኔ ታማኝ ፍቅር እንዳሳየኋችሁ ሁሉ እናንተም ለአባቴ ቤት ታማኝ ፍቅር እንደምታሳዩ እባካችሁ በይሖዋ ማሉልኝ፤ እንዲሁም አስተማማኝ ምልክት ስጡኝ። +13 አባቴን፣ እናቴን፣ ወንድሞቼን፣ እህቶቼንና የእነሱ የሆነውን ሁሉ አትርፉልኝ፤ ከሞትም ታደጉን።”*+ +14 በዚህ ጊዜ ሰዎቹ እንዲህ አሏት፦ “በእናንተ ምትክ ሕይወታችንን እንሰጣለን!* ስለ ተልእኳችን ካልተናገራችሁ ይሖዋ ምድሪቱን በሚሰጠን ጊዜ ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት እናሳያችኋለን።” +15 እሷም ሰዎቹን በመስኮት በኩል በገመድ አወረደቻቸው፤ ምክንያቱም ቤቷ ከከተማው ቅጥር ጋር ተያይዞ የተሠራ ነበር። እንዲያውም የምትኖረው ቅጥሩ ላይ ነበር።+ +16 ከዚያም እንዲህ አለቻቸው፦ “የሚያሳድዷችሁ ሰዎች እንዳያገኟችሁ ወደ ተራራማው አካባቢ ሄዳችሁ ለሦስት ቀን ተደበቁ። ከዚያም የሚያሳድዷችሁ ሰዎች ከተመለሱ በኋላ ወደምትፈልጉት ቦታ መሄድ ትችላላችሁ።” +17 ሰዎቹም እንዲህ አሏት፦ “እንደሚከተለው ካላደረግሽ ባስማልሽን በዚህ መሐላ ተጠያቂ አንሆንም፦+ +18 ወደ ምድሪቱ በምንገባበት ጊዜ ይህን ቀይ ገመድ እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል አንጠልጥይው። እንዲሁም አባትሽ፣ እናትሽ፣ ወንድሞችሽና የአባትሽ ቤት በሙሉ ቤትሽ ውስጥ እንዲሰበሰቡ ማድረግ አለብሽ።+ +19 ከቤትሽ ወጥቶ ደጅ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ እኛም ከበደል ነፃ እንሆናለን። ሆኖም ከአንቺ ጋር ቤት ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ጉዳት ቢደርስበት* ደሙ በእኛ ላይ ይሆናል። +20 ስለ ተልእኳችን ከተናገርሽ+ ግን ባስማልሽን በዚህ መሐላ ተጠያቂ አንሆንም።” +21 እሷም “እንዳላችሁት ይሁን” አለቻቸው። ከዚያም አሰናበተቻቸው፤ እነሱም ሄዱ። እሷም ቀዩን ገመድ መስኮቱ ላይ አሰረችው። +22 እነሱም ወደ ተራራማው አካባቢ ሄደው ��ሳዳጆቹ እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ለሦስት ቀን ተቀመጡ። አሳዳጆቹም በየመንገዱ ሁሉ ፈለጓቸው፤ ሆኖም አላገኟቸውም። +23 ከዚያም ሁለቱ ሰዎች ከተራራማው አካባቢ ወርደው ወንዙን በመሻገር ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ። ያጋጠማቸውንም ሁሉ ነገሩት። +24 ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “ይሖዋ ምድሪቱን በሙሉ በእጃችን ሰጥቶናል።+ እንዲያውም የምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ በእኛ የተነሳ ልባቸው ከድቷቸዋል።”+ +4 መላው ብሔር ዮርዳኖስን እንደተሻገረ ይሖዋ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ +2 “ከሕዝቡ መካከል 12 ሰዎችን ይኸውም ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አንድ ሰው ምረጥ፤+ +3 እነሱንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ‘ከዮርዳኖስ ወንዝ መሃል ይኸውም የካህናቱ እግር ከቆመበት ስፍራ+ 12 ድንጋዮችን ውሰዱ፤ ድንጋዮቹንም ይዛችሁ በመሄድ በምታድሩበት ስፍራ አስቀምጧቸው።’”+ +4 በመሆኑም ኢያሱ ከእስራኤላውያን መካከል የሾማቸውን 12 ሰዎች ይኸውም ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አንድ ሰው ጠራ፤ +5 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “የአምላካችሁን የይሖዋን ታቦት ቀድማችሁ ወደ ዮርዳኖስ መሃል ሂዱ፤ እያንዳንዳችሁም በእስራኤላውያን ነገዶች ቁጥር ልክ አንድ አንድ ድንጋይ አንስታችሁ በትከሻችሁ ተሸከሙ፤ +6 ይህም በመካከላችሁ እንደ ምልክት ሆኖ ያገለግላል። ምናልባት ወደፊት ልጆቻችሁ* ‘እነዚህን ድንጋዮች እዚህ ያስቀመጣችኋቸው ለምንድን ነው?’ ብለው ቢጠይቋችሁ+ +7 እንዲህ በሏቸው፦ ‘የዮርዳኖስ ውኃ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተቋርጦ ስለነበር ነው።+ ታቦቱ ዮርዳኖስን ሲሻገር የዮርዳኖስ ውኃ ተቋረጠ። እነዚህ ድንጋዮች ለእስራኤላውያን በዘላቂነት እንደ መታሰቢያ* ሆነው ያገለግላሉ።’”+ +8 እስራኤላውያንም ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እነሱም ይሖዋ ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ከዮርዳኖስ መሃል በእስራኤላውያን ነገዶች ቁጥር ልክ 12 ድንጋዮችን አነሱ። ከዚያም ወደሚያድሩበት ስፍራ ይዘዋቸው በመሄድ እዚያ አስቀመጧቸው። +9 በተጨማሪም ኢያሱ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት እግር ቆሞበት በነበረው በዮርዳኖስ መሃል ባለው ቦታ+ ላይ 12 ድንጋዮችን አስቀምጦ ነበር፤ እነዚህም ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ። +10 ሙሴ ለኢያሱ በሰጠው መመሪያ መሠረት ይሖዋ፣ ኢያሱ ለሕዝቡ እንዲናገር ያዘዘው ነገር በሙሉ እስኪፈጸም ድረስ ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት በዮርዳኖስ መሃል ቆመው ነበር። በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ፈጥኖ ተሻገረ። +11 ሕዝቡ ሁሉ ተሻግሮ እንዳበቃ የይሖዋ ታቦትና ካህናቱ ሕዝቡ እያያቸው ተሻገሩ።+ +12 ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ ሙሴ በሰጣቸው መመሪያ መሠረት+ የጦርነት አሰላለፍ ተከትለው+ ሌሎቹን እስራኤላውያን ቀድመው ተሻገሩ። +"13 ወደ 40,000 የሚሆኑ ለጦርነት የታጠቁ ሰዎች ወደ ኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ በይሖዋ ፊት ተሻገሩ። " +14 በዚያ ዕለት ይሖዋ ኢያሱን በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤+ እነሱም ሙሴን በጥልቅ ያከብሩት እንደነበር ሁሉ እሱንም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በጥልቅ አከበሩት።*+ +15 ከዚያም ይሖዋ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ +16 “የምሥክሩን ታቦት+ የተሸከሙትን ካህናት ከዮርዳኖስ እንዲወጡ እዘዛቸው።” +17 በመሆኑም ኢያሱ ካህናቱን “ከዮርዳኖስ ውጡ” በማለት አዘዛቸው። +18 የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙት ካህናት+ ከዮርዳኖስ መሃል ሲወጡና የካህናቱ እግር ከውኃው ወጥቶ ደረቁን መሬት ሲረግጥ የዮርዳኖስ ውኃ እንደቀድሞው መፍሰሱንና ዳርቻውን ሁሉ ማጥለቅለቁን ቀጠለ።+ +19 ሕዝቡም በመጀመሪያው ወር በአሥረኛው ቀን ላይ ከዮርዳኖስ ወጥቶ በኢያሪኮ ምሥራቃዊ ወሰን ላይ በምትገኘው በጊልጋል ሰፈረ።+ +20 ኢያሱም ከዮርዳኖስ ያወጧቸ��ን 12 ድንጋዮች በጊልጋል አቆማቸው።+ +21 ከዚያም እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፦ “ወደፊት ልጆቻችሁ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ+ +22 ልጆቻችሁን እንዲህ በሏቸው፦ ‘እስራኤል ዮርዳኖስን በደረቅ ምድር ተሻገረ፤+ +23 ይህም የሆነው አምላካችሁ ይሖዋ ቀይ ባሕርን እስኪሻገሩ ድረስ ባሕሩን በፊታቸው እንዳደረቀው ሁሉ እኛም ዮርዳኖስን እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ ይሖዋ የዮርዳኖስን ውኃ በፊታችን ስላደረቀው ነው።+ +24 ይህን ያደረገው የምድር ሕዝቦች ሁሉ የይሖዋ ክንድ ምን ያህል ኃያል መሆኑን እንዲያውቁና+ እናንተም አምላካችሁን ይሖዋን ሁልጊዜ እንድትፈሩ ነው።’” +16 ለዮሴፍ ዘሮች+ በዕጣ የተሰጣቸው ምድር+ በኢያሪኮ አጠገብ ካለው ከዮርዳኖስ አንስቶ ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ እስካሉት ውኃዎች ድረስ ሲሆን ከኢያሪኮ ሽቅብ የሚወጣውን ምድረ በዳ አቋርጦ እስከ ተራራማው የቤቴል አካባቢ ድረስ ይዘልቃል።+ +2 እንዲሁም በሎዛ ከምትገኘው ከቤቴል አንስቶ በአጣሮት እስካለው የአርካውያን ወሰን ድረስ ይሄዳል፤ +3 ከዚያም በስተ ምዕራብ ወደ ያፍለጣውያን ወሰን ቁልቁል በመውረድ እስከ ታችኛው ቤትሆሮን+ ወሰንና እስከ ጌዜር+ ይደርሳል፤ ባሕሩም ጋ ሲደርስ ያበቃል። +4 ስለሆነም የዮሴፍ ዘሮች+ ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸው የሆነውን መሬት ወሰዱ።+ +5 የኤፍሬም ዘሮች ወሰን በየቤተሰባቸው የሚከተለው ነው፦ በስተ ምሥራቅ በኩል የርስታቸው ወሰን አጣሮትዓዳር+ ሲሆን እስከ ላይኛው ቤትሆሮንም+ ይደርሳል፤ +6 ከዚያም እስከ ባሕሩ ድረስ ይዘልቃል። ወሰኑ በስተ ሰሜን ሚክመታት+ ሲሆን በስተ ምሥራቅ በኩል ዞሮ ወደ ታአናትሺሎ ይሄድና በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ያኖአህ ይዘልቃል። +7 ከያኖአህ ተነስቶም ወደ አጣሮትና ወደ ናዕራ ቁልቁል በመውረድ ኢያሪኮ+ ይደርስና ወደ ዮርዳኖስ ይዘልቃል። +8 ከዚያም ከታጱአ+ ተነስቶ በስተ ምዕራብ በኩል እስከ ቃና ሸለቆ በመዝለቅ ባሕሩ ጋ ሲደርስ ያበቃል።+ የኤፍሬም ነገድ በየቤተሰቡ ያገኘው ርስት ይህ ነው፤ +9 የኤፍሬም ዘሮች በምናሴ+ ርስት ውስጥም የተከለሉ ከተሞች ነበሯቸው፤ ከተሞቹ በሙሉ ከነመንደሮቻቸው የእነሱ ነበሩ። +10 ሆኖም በጌዜር+ ይኖሩ የነበሩትን ከነአናውያን አላባረሯቸውም፤ ከነአናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በኤፍሬም መካከል ይኖራሉ፤+ የግዳጅ ሥራ የመሥራት ግዴታም ተጥሎባቸዋል።+ +6 ኢያሪኮ በእስራኤላውያን የተነሳ ጥርቅም ተደርጋ ተዘግታ ነበር፤ ወደ ውጭ የሚወጣም ሆነ ወደ ውስጥ የሚገባ አልነበረም።+ +2 ይሖዋም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ ኢያሪኮን፣ ንጉሥዋንና ኃያል ተዋጊዎቿን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ።+ +3 ተዋጊ የሆናችሁት ወንዶችም ሁሉ ከተማዋን ዙሪያዋን በመሄድ አንድ ጊዜ ዙሯት። ለስድስት ቀን እንዲህ አድርጉ። +4 ሰባት ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት* ይዘው በታቦቱ ፊት ይሂዱ። በሰባተኛው ቀን ግን ከተማዋን ሰባት ጊዜ ዙሯት፤ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።+ +5 ቀንደ መለከቱ ሲነፋና የቀንደ መለከቱን ድምፅ* ስትሰሙ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ የጦርነት ጩኸት ያሰማ። ከዚያም የከተማዋ ቅጥር ይፈራርሳል፤+ ሕዝቡም ሁሉ፣ እያንዳንዱም ሰው ቀጥ ብሎ ወደ ፊት ይሂድ።” +6 ስለዚህ የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን አንድ ላይ ጠርቶ “የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሱ፤ ሰባት ካህናትም ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በይሖዋ ታቦት ፊት ይሂዱ” አላቸው።+ +7 ሕዝቡንም “እናንተ ተነሱና ከተማዋን ዙሩ፤ የታጠቁት ተዋጊዎችም+ ከይሖዋ ታቦት ቀድመው ይሄዳሉ” አላቸው። +8 ኢያሱ ለሕዝቡ በተናገረው መሠረት ሰባት ቀንደ መለከት የያዙት ሰባት ካህናት በይሖዋ ፊት ቀድመው በመሄድ ቀንደ መለከታቸውን ነፉ፤ ���ይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦትም ይከተላቸው ነበር። +9 የታጠቁትም ተዋጊዎች ቀንደ መለከቱን ከሚነፉት ካህናት ቀድመው ሄዱ፤ የኋላው ደጀን ደግሞ ታቦቱን ይከተል ነበር፤ በዚህ ጊዜ ሁሉ ቀንደ መለከቱ ያለማቋረጥ ይነፋ ነበር። +10 ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “መጮኽም ሆነ ድምፃችሁን ማሰማት የለባችሁም። እኔ ‘ጩኹ!’ ብዬ እስከማዛችሁ ቀን ድረስ ከአፋችሁ አንድም ቃል መውጣት የለበትም። ከዚያ በኋላ ትጮኻላችሁ።” +11 እሱም የይሖዋ ታቦት በከተማዋ ዙሪያ በመሄድ ከተማዋን አንድ ጊዜ እንዲዞር አደረገ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ ተመልሰው በዚያ አደሩ። +12 በሚቀጥለው ቀን ኢያሱ በማለዳ ተነሳ፤ ካህናቱም የይሖዋን ታቦት አነሱ፤+ +13 ሰባት ቀንደ መለከት የያዙ ሰባት ካህናት ያለማቋረጥ መለከታቸውን እየነፉ ከይሖዋ ታቦት ፊት ፊት ይሄዱ ነበር። የታጠቁት ተዋጊዎችም ከእነሱ ፊት ይሄዱ ነበር፤ የኋላው ደጀን ደግሞ የይሖዋን ታቦት ይከተል ነበር፤ በዚህ ጊዜ ሁሉ ቀንደ መለከቱ ያለማቋረጥ ይነፋ ነበር። +14 በሁለተኛውም ቀን ከተማዋን አንድ ጊዜ ዞሯት፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ ተመለሱ። ለስድስት ቀን ልክ እንደዚሁ አደረጉ።+ +15 በሰባተኛው ቀን ገና ጎህ ሲቀድ ተነስተው ከተማዋን በዚሁ መንገድ ሰባት ጊዜ ዞሯት። ከተማዋን ሰባት ጊዜ የዞሯት በዚያ ቀን ብቻ ነበር።+ +16 በሰባተኛው ዙር ላይ ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ነፉ፤ ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ከተማዋን አሳልፎ ስለሰጣችሁ ጩኹ!+ +17 ከተማዋም ሆነች በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ መጥፋት አለበት፤+ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ የይሖዋ ነች። በሕይወት የሚተርፉት ዝሙት አዳሪዋ ረዓብና+ ከእሷ ጋር በቤቱ ውስጥ ያሉት ብቻ ናቸው፤ ምክንያቱም እሷ የላክናቸውን መልእክተኞች ደብቃለች።+ +18 እናንተ ግን ለጥፋት የተለየው ነገር እንዳያጓጓችሁና እንዳትወስዱት፣ በእስራኤልም ሰፈር ላይ መዓት* በማምጣት ሰፈሩን ለጥፋት የተለየ እንዳታደርጉት+ ለጥፋት ከተለየው ነገር ራቁ።+ +19 ሆኖም ብሩ፣ ወርቁ እንዲሁም ከመዳብና ከብረት የተሠሩት ዕቃዎች ሁሉ ለይሖዋ የተቀደሱ ናቸው።+ ወደ ይሖዋ ግምጃ ቤት መግባት አለባቸው።”+ +20 ከዚያም ቀንደ መለከቱ ሲነፋ ሕዝቡ ጮኸ።+ ሕዝቡ የቀንደ መለከቱን ድምፅ ሰምቶ ታላቅ የጦርነት ጩኸት ሲያሰማ ቅጥሩ ፈረሰ።+ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣ እያንዳንዱም ሰው በቀጥታ ወደ ከተማዋ በመግባት ከተማዋን ያዛት። +21 እነሱም በከተማዋ ውስጥ የነበረውን በሙሉ ይኸውም ወንዱንና ሴቱን፣ ወጣቱንና ሽማግሌውን እንዲሁም በሬውን፣ በጉንና አህያውን በሰይፍ ሙሉ በሙሉ አጠፉ።+ +22 ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉትን ሁለቱን ሰዎች “ወደ ዝሙት አዳሪዋ ቤት ገብታችሁ በማላችሁላት መሠረት ሴትየዋንና የእሷ የሆነውን ሁሉ ከዚያ አውጡ” አላቸው።+ +23 በመሆኑም ወጣቶቹ ሰላዮች ገብተው ረዓብን፣ አባቷን፣ እናቷን፣ ወንድሞቿንና የእሷ የሆነውን ሁሉ አዎ፣ ቤተሰቧን በሙሉ+ አውጥተው ከእስራኤል ሰፈር ውጭ ወዳለ ስፍራ በሰላም አመጧቸው። +24 ከዚያም ከተማዋንና በውስጧ የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። ብሩን፣ ወርቁን እንዲሁም ከመዳብና ከብረት የተሠሩትን ዕቃዎች ግን ወደ ይሖዋ ግምጃ ቤት አስገቡ።+ +25 ኢያሱ በሕይወት እንዲተርፉ ያደረገው ዝሙት አዳሪዋን ረዓብን፣ የአባቷን ቤተሰብና የእሷ የሆነውን ብቻ ነበር፤+ እሷም እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤል መካከል ትኖራለች፤+ ምክንያቱም ኢያሱ ኢያሪኮን እንዲሰልሉ የላካቸውን መልእክተኞች ደብቃ ነበር።+ +26 በዚያን ጊዜ ኢያሱ ይህን ቃለ መሐላ አወጀ፦* “ይህችን የኢያሪኮን ከተማ ለመገንባት የሚነሳ ሰው በይሖዋ ፊት የተረገመ ይሁን። የከተማዋን መሠረት ሲጥል የበኩር ልጁ ይጥፋ፤ በሮቿንም ሲያቆም የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ።”+ +27 ይሖዋም ከኢያሱ ጋር ነበር፤+ በመላውም ምድር ላይ ዝነኛ ሆነ።+ +10 የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ኢያሱ ጋይን እንደተቆጣጠራትና እንደደመሰሳት፣ በኢያሪኮና በንጉሥዋ+ ላይ እንዳደረገው ሁሉ በጋይና በንጉሥዋም+ ላይ እንዳደረገ እንዲሁም የገባኦን ነዋሪዎች ከእስራኤላውያን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት+ ፈጥረው በመካከላቸው እየኖሩ እንዳሉ ሲሰማ +2 በጣም ደነገጠ፤+ ምክንያቱም ገባኦን በንጉሥ እንደሚተዳደሩት ከተሞች ሁሉ ታላቅ ከተማ ነበረች። ይህች ከተማ ከጋይ+ ትበልጥ የነበረ ሲሆን ነዋሪዎቿም በሙሉ ጦረኞች ነበሩ። +3 በመሆኑም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ለኬብሮን+ ንጉሥ ለሆሐም፣ ለያርሙት ንጉሥ ለፒራም፣ ለለኪሶ ንጉሥ ለያፊአ እና ለኤግሎን ንጉሥ+ ለደቢር እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ +4 “መጥታችሁ እርዱኝና በገባኦን ላይ ጥቃት እንሰንዝር፤ ምክንያቱም ገባኦን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ፈጥራለች።”+ +5 በዚህ ጊዜ አምስቱ የአሞራውያን+ ነገሥታት ይኸውም የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ የኬብሮን ንጉሥ፣ የያርሙት ንጉሥ፣ የለኪሶ ንጉሥና የኤግሎን ንጉሥ ከነሠራዊታቸው አንድ ላይ ተሰብስበው በመዝመት ገባኦንን ለመውጋት ከበቧት። +6 የገባኦን ሰዎችም በጊልጋል+ በሚገኘው ሰፈር ወደነበረው ወደ ኢያሱ እንዲህ የሚል መልእክት ላኩበት፦ “እኛን ባሪያዎችህን አትተወን።+ ፈጥነህ ድረስልን! አድነን፤ እርዳን! በተራራማው አካባቢ የሚኖሩት የአሞራውያን ነገሥታት በሙሉ እኛን ለመውጋት ተሰብስበዋል።” +7 በመሆኑም ኢያሱ ተዋጊዎቹንና ኃያላን የሆኑትን ጦረኞች+ በሙሉ ይዞ ከጊልጋል ወጣ። +8 ከዚያም ይሖዋ ኢያሱን “በእጅህ አሳልፌ ስለሰጠኋቸው+ አትፍራቸው።+ አንዳቸውም እንኳ ሊቋቋሙህ አይችሉም”+ አለው። +9 ኢያሱም ከጊልጋል በመነሳት ሌሊቱን ሙሉ ሲገሰግስ አድሮ ድንገት መጣባቸው። +10 ይሖዋም በእስራኤላውያን ፊት ግራ እንዲጋቡ አደረጋቸው፤+ እነሱም ገባኦን ላይ ክፉኛ ጨፈጨፏቸው፤ ወደ ቤትሆሮን አቀበት በሚወስደው መንገድ ላይ በማሳደድ እስከ አዜቃ እና እስከ መቄዳ ድረስ መቷቸው። +11 እነሱም ከእስራኤላውያን በመሸሽ የቤትሆሮንን ቁልቁለት እየወረዱ ሳሉ እስከ አዜቃ ድረስ ይሖዋ ከሰማይ ትላልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ እነሱም ሞቱ። እንዲያውም በእስራኤላውያን ሰይፍ ከሞቱት ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት ይበልጣሉ። +12 ይሖዋ አሞራውያንን ከእስራኤላውያን ፊት ባባረረበት ዕለት ኢያሱ በእስራኤላውያን ፊት ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “ፀሐይ ሆይ፣ በገባኦን ላይ ቁሚ፤+ አንቺም ጨረቃ ሆይ፣ በአይሎን ሸለቆ* ላይ ቀጥ በይ!” +13 በመሆኑም ብሔሩ ጠላቶቹን እስኪበቀል ድረስ ፀሐይ ባለችበት ቆመች፤ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህስ በያሻር መጽሐፍ+ ላይ ተጽፎ የሚገኝ አይደለም? ፀሐይ በሰማይ መካከል ባለችበት ቆመች፤ ለአንድ ቀን ያህል ለመጥለቅ አልቸኮለችም። +14 ይሖዋ የሰውን ቃል የሰማበት+ እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ ፈጽሞ አልነበረም፤ ምክንያቱም ይሖዋ ለእስራኤል እየተዋጋ ነበር።+ +15 ከዚያ በኋላ ኢያሱና መላው እስራኤል በጊልጋል ወደሚገኘው ሰፈር+ ተመለሱ። +16 በዚህ ጊዜ አምስቱ ነገሥታት ሸሽተው በመቄዳ+ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው ነበር። +17 ከዚያም ኢያሱ “አምስቱ ነገሥታት በመቄዳ+ በሚገኘው ዋሻ ውስጥ ተደብቀው ተገኝተዋል” የሚል መልእክት ደረሰው። +18 እሱም እንዲህ አለ፦ “ትላልቅ ድንጋዮች አንከባላችሁ የዋሻውን አፍ ግጠሙትና እነሱን የሚጠብቁ ሰዎች መድቡ። +19 የተቀራችሁት ግን ዝም ብላችሁ አትቁሙ። ጠላቶቻችሁን እያሳደዳችሁ ከኋላ ምቷቸው።+ አምላካችሁ ይሖዋ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣቸው ወደ ከተሞቻቸው እንዲገቡ አትፍቀዱላቸው።” +20 ኢያሱና እስራኤላውያን፣ አምልጠው ወደተመሸጉት ከተሞች ከገቡት ጥቂት ሰዎች በቀር ጠላቶቻቸውን እስኪጠፉ ድረስ ክፉኛ ከጨፈጨፏቸው በኋላ +21 ሕዝቡ ሁሉ በመቄዳ በሚገኘው ሰፈር ወደነበረው ወደ ኢያሱ በሰላም ተመለሰ። በእስራኤላውያን ላይ አንዲት ቃል ሊናገር የደፈረ* ሰው አልነበረም። +22 ከዚያም ኢያሱ “የዋሻውን አፍ ከፍታችሁ አምስቱን ነገሥታት ከዋሻው አውጥታችሁ ወደ እኔ አምጧቸው” አለ። +23 ስለሆነም እነዚህን አምስት ነገሥታት ማለትም የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፣ የኬብሮንን ንጉሥ፣ የያርሙትን ንጉሥ፣ የለኪሶን ንጉሥና የኤግሎንን ንጉሥ ከዋሻው አውጥተው ወደ እሱ አመጧቸው።+ +24 ኢያሱም እነዚህን ነገሥታት ወደ እሱ ባመጧቸው ጊዜ የእስራኤልን ሰዎች በሙሉ ጠርቶ አብረውት የሄዱትን የሠራዊቱን አዛዦች “ወደዚህ ቅረቡ። እግራችሁን በእነዚህ ነገሥታት ማጅራት ላይ አድርጉ” አላቸው። እነሱም ቀርበው እግራቸውን በማጅራታቸው ላይ አደረጉ።+ +25 ከዚያም ኢያሱ እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ ወይም አትሸበሩ።+ ይሖዋ በምትዋጓቸው ጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲህ ስለሚያደርግ ደፋርና ብርቱ ሁኑ።”+ +26 ከዚያም ኢያሱ መትቶ ገደላቸው፤ በአምስት እንጨቶችም* ላይ ሰቀላቸው፤ በእንጨቶቹም ላይ እንደተሰቀሉ እስከ ምሽት ድረስ ቆዩ። +27 ፀሐይም ልትጠልቅ ስትቃረብ ኢያሱ፣ አስከሬኖቻቸው ከእንጨቶቹ ላይ እንዲወርዱና+ ተደብቀውበት በነበረው ዋሻ ውስጥ እንዲጣሉ ትእዛዝ ሰጠ። ከዚያም በዋሻው አፍ ላይ ትላልቅ ድንጋዮችን አደረጉ፤ እነዚህም እስከ ዛሬ ድረስ እዚያው ይገኛሉ። +28 ኢያሱም በዚያን ዕለት መቄዳን+ በመቆጣጠር ሕዝቡን በሰይፍ ፈጀ። ንጉሥዋንና በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ አንድም ሳያስቀር ፈጽሞ አጠፋ።+ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ እንዳደረገውም ሁሉ በመቄዳ ንጉሥ+ ላይ አደረገ። +29 ከዚያም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከመቄዳ ወደ ሊብና በመሄድ ሊብናን+ ወጓት። +30 ይሖዋም ከተማዋንና ንጉሥዋን+ በእስራኤላውያን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነሱም ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ በሰይፍ መቱ። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ እንዳደረጉትም ሁሉ በንጉሥዋ ላይ አደረጉ።+ +31 በመቀጠልም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከሊብና ወደ ለኪሶ+ ሄዱ፤ እሷንም ከበው ወጓት። +32 ይሖዋም ለኪሶን ለእስራኤላውያን አሳልፎ ሰጣት፤ እነሱም በሁለተኛው ቀን ያዟት። በሊብና ላይ እንዳደረጉትም ሁሉ ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ በሰይፍ መቱ።+ +33 በዚህ ጊዜ የጌዜር+ ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት ወጣ፤ ሆኖም ኢያሱ እሱንና ሕዝቡን አንድም ሳያስቀር መታቸው። +34 በመቀጠልም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከለኪሶ ወደ ኤግሎን+ በመሄድ ከበው ወጓት። +35 እነሱም በዚያን ቀን ከተማዋን በመቆጣጠር በሰይፍ መቷት። በለኪሶ ላይ እንዳደረጉት ሁሉ በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ በዚያኑ ዕለት ሙሉ በሙሉ አጠፉ።+ +36 ከዚያም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከኤግሎን ወደ ኬብሮን+ በመውጣት ኬብሮንን ወጓት። +37 እሷንም ተቆጣጥረው ከተማዋን፣ ንጉሥዋንና በዙሪያዋ ያሉትን አነስተኛ ከተሞች እንዲሁም በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ በሰይፍ መቱ። በኤግሎንም ላይ እንዳደረገው ሁሉ ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ሰው* ሁሉ ሙሉ በሙሉ አጠፋ። +38 በመጨረሻም ኢያሱና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ደቢር+ በመዞር ወጓት። +39 ከተማዋን፣ ንጉሥዋንና በዙሪያዋ ያሉትን አነስተኛ ከተሞች ተቆ��ጠረ፤ እነሱንም በሰይፍ መቷቸው፤ በውስጧ ያለውንም ሰው* ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ+ ፈጽመው አጠፉ።+ በኬብሮን እንዲሁም በሊብና እና በንጉሥዋ ላይ እንዳደረገው ሁሉ በደቢርና በንጉሥዋ ላይ አደረገ። +40 ኢያሱም ምድሩን ሁሉ ይኸውም ተራራማውን አካባቢ፣ ኔጌብን፣ ሸፌላን፣+ ሸንተረሮቹንና ነገሥታታቸውን በሙሉ ድል አደረገ፤ አንድም ሰው አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ባዘዘውም መሠረት+ እስትንፋስ ያለውን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።+ +41 ኢያሱ ከቃዴስበርኔ+ አንስቶ እስከ ጋዛ+ ድረስ እንዲሁም የጎሸንን+ ምድር በሙሉ እስከ ገባኦን+ ድረስ ድል አደረገ። +42 ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን በሙሉ በአንድ ጊዜ ተቆጣጠረ፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ለእስራኤላውያን እየተዋጋላቸው ነበር።+ +43 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን በሙሉ በጊልጋል+ ወደሚገኘው ሰፈር ተመለሱ። +14 እንግዲህ እስራኤላውያን በከነአን ምድር ርስት አድርገው የወረሱት ይኸውም ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገዶች የአባቶች ቤት መሪዎች ያወረሷቸው ምድር ይህ ነው።+ +2 ይሖዋ ዘጠኙን ነገድና ግማሹን ነገድ+ አስመልክቶ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ርስታቸው የተከፋፈለው በዕጣ ነበር።+ +3 ሙሴ ለሌሎቹ ሁለት ነገዶችና ለሌላኛው ግማሽ ነገድ ከዮርዳኖስ ማዶ* ርስት ሰጥቷቸው ነበር፤+ ለሌዋውያኑ ግን በእነሱ መካከል ርስት አልሰጣቸውም።+ +4 የዮሴፍ ዘሮች እንደ ሁለት ነገድ ተደርገው ይቆጠሩ+ የነበረ ሲሆን እነሱም ምናሴና ኤፍሬም ናቸው፤+ ለሌዋውያኑም ከሚኖሩባቸው ከተሞች እንዲሁም ለከብቶቻቸውና ለንብረቶቻቸው ከሚሆን መሬት በስተቀር በምድሪቱ ውስጥ ድርሻ አልሰጧቸውም።+ +5 በመሆኑም እስራኤላውያን ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ምድሪቱን ተከፋፈሉ። +6 ከዚያም የይሁዳ ሰዎች በጊልጋል+ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ የቀኒዛዊው የየፎኒ ልጅ ካሌብም+ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ በቃዴስበርኔ+ ስለ እኔና ስለ አንተ ለእውነተኛው አምላክ ሰው ለሙሴ+ ምን እንዳለው በሚገባ ታውቃለህ።+ +7 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ምድሪቱን እንድሰልል ከቃዴስበርኔ ሲልከኝ የ40 ዓመት ሰው ነበርኩ፤+ እኔም ትክክለኛውን መረጃ* ይዤ መጣሁ።+ +8 አብረውኝ የወጡት ወንድሞቼ የሕዝቡ ልብ እንዲቀልጥ ቢያደርጉም እኔ ግን አምላኬን ይሖዋን በሙሉ ልቤ ተከተልኩት።+ +9 ሙሴም በዚያ ዕለት ‘አምላኬን ይሖዋን በሙሉ ልብህ ስለተከተልከው እግርህ የረገጣት ምድር ለዘለቄታው የአንተና የልጆችህ ርስት ትሆናለች’ ብሎ ማለ።+ +10 እስራኤል በምድረ በዳ እየተጓዘ ሳለ+ ይሖዋ ለሙሴ ይህን ቃል ከገባለት ጊዜ አንስቶ ይሖዋ በገባው ቃል መሠረት+ እነዚህን 45 ዓመታት በሕይወት አቆይቶኛል፤+ ይኸው ዛሬ 85 ዓመት ሆኖኛል። +11 ደግሞም ሙሴ በላከኝ ጊዜ የነበረኝ ብርታት ዛሬም አለኝ። ልክ እንደዚያን ጊዜ ሁሉ አሁንም ወደ ጦርነት ለመሄድም ሆነ ሌሎች ነገሮችን ለማከናወን የሚያስችል ጥንካሬ አለኝ። +12 ስለዚህ ይሖዋ በዚያ ዕለት ቃል የገባውን ይህን ተራራማ አካባቢ ስጠኝ። የተመሸጉ ታላላቅ ከተሞች+ ያሏቸው ኤናቃውያን+ በአካባቢው እንደሚኖሩ በዚያ ቀን ሰምተህ የነበረ ቢሆንም ይሖዋ ከእኔ ጋር እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፤+ ይሖዋም በገባው ቃል መሠረት ድል አድርጌ አባርራቸዋለሁ።”+ +13 በመሆኑም ኢያሱ ባረከው፤ ኬብሮንንም ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርጎ ሰጠው።+ +14 ኬብሮን ለቀኒዛዊው ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ እስከ ዛሬ ድረስ ርስት የሆነችው ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም እሱ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን በሙሉ ልቡ ተከትሏል።+ +15 ኬብሮን ከዚያ በፊት ቂርያትአርባ+ ተብላ ትጠራ ነበር (አርባ በኤናቃውያን መካከል ታላቅ ሰ��� ነበር)። ምድሪቱም ከጦርነት አረፈች።+ +9 ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ+ በተራራማው አካባቢ፣ በሸፌላ፣ በመላው የታላቁ ባሕር*+ ዳርቻ እንዲሁም በሊባኖስ ፊት ለፊት የነበሩት ነገሥታት ሁሉ ይኸውም ሂታውያን፣ አሞራውያን፣ ከነአናውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ሂዋውያንና ኢያቡሳውያን ይህን ሲሰሙ+ +2 ኢያሱንና እስራኤልን ለመውጋት ግንባር ፈጠሩ።+ +3 የገባኦን+ ነዋሪዎችም ኢያሱ በኢያሪኮና+ በጋይ+ ላይ ምን እንዳደረገ ሰሙ። +4 በመሆኑም ብልሃት ፈጠሩ፤ ስንቃቸውን ባረጁ ከረጢቶች ውስጥ ከከተቱ በኋላ ተቀዳደው ከተጠጋገኑ ያረጁ የወይን ጠጅ አቁማዳዎች ጋር በአህያዎቻቸው ላይ ጫኑ፤ +5 በተጨማሪም ያደረጉት ነጠላ ጫማ ያለቀና የተጠጋገነ፣ የለበሱትም ልብስ ያረጀ ነበር። ለስንቅ የያዙትም ዳቦ በሙሉ የደረቀና የተፈረፈረ ነበር። +6 እነሱም በጊልጋል+ በሚገኘው ሰፈር ወደነበረው ወደ ኢያሱ ሄደው እሱንና የእስራኤልን ሰዎች “የመጣነው ከሩቅ አገር ነው። እንግዲህ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ግቡ” አሏቸው። +7 ይሁን እንጂ የእስራኤል ሰዎች ሂዋውያኑን+ “ይህን ጊዜ እኮ የምትኖሩት እዚሁ አጠገባችን ይሆናል። ታዲያ ከእናንተ ጋር እንዴት ቃል ኪዳን እንገባለን?” አሏቸው።+ +8 እነሱም መልሰው ኢያሱን “እኛ የአንተ አገልጋዮች* ነን” አሉት። ከዚያም ኢያሱ “እናንተ እነማን ናችሁ? የመጣችሁትስ ከየት ነው?” አላቸው። +9 በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ ለአምላክህ ለይሖዋ ስም ካለን አክብሮት የተነሳ ከሩቅ አገር የመጣን ነን፤+ ምክንያቱም ዝናውንና በግብፅ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል፤+ +10 እንዲሁም ከዮርዳኖስ ማዶ* በነበሩት በሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ይኸውም በሃሽቦን ንጉሥ በሲሖንና+ በአስታሮት በነበረው በባሳን ንጉሥ በኦግ+ ላይ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል። +11 በመሆኑም ሽማግሌዎቻችንና የአገራችን ነዋሪዎች በሙሉ እንዲህ አሉን፦ ‘ለጉዟችሁ የሚሆን ስንቅ ይዛችሁ ወደ እነዚህ ሰዎች ሂዱ። ከዚያም “አገልጋዮቻችሁ እንሆናለን።+ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ግቡ”+ በሏቸው።’ +12 ለስንቅ እንዲሆነን የያዝነው ይህ ዳቦ ወደዚህ ወደ እናንተ ለመምጣት ከቤታችን በወጣንበት ቀን ትኩስ ነበር። አሁን ግን ይኸው እንደምታዩት ደርቋል፤ ደግሞም ተፈርፍሯል።+ +13 እነዚህ የወይን ጠጅ አቁማዳዎች ያን ጊዜ ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ አሁን ግን ይኸው እንደምታዩአቸው ተቀዳደዋል።+ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችንም ረጅም መንገድ ከመጓዛችን የተነሳ አልቀዋል።” +14 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሰዎች ከስንቃቸው ላይ ጥቂት ወሰዱ፤* ስለ ጉዳዩ ግን ይሖዋን አልጠየቁም።+ +15 በመሆኑም ኢያሱ ከእነሱ ጋር በሰላም ለመኖር ተስማማ፤+ እንደማያጠፋቸውም ቃል ኪዳን ገባላቸው፤ የማኅበረሰቡም አለቆች ይህንኑ በመሐላ አጸኑላቸው።+ +16 እስራኤላውያንም ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ከገቡ ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሰዎች እዚያው በአቅራቢያቸው የሚኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ሰሙ። +17 ከዚያም እስራኤላውያን ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባኦን፣+ ከፊራ፣ በኤሮት እና ቂርያትየአሪም+ ነበሩ። +18 ይሁን እንጂ የማኅበረሰቡ አለቆች በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ምለውላቸው+ ስለነበር እስራኤላውያን ጥቃት አልሰነዘሩባቸውም። ስለሆነም መላው ማኅበረሰብ በአለቆቹ ላይ ማጉረምረም ጀመረ። +19 በዚህ ጊዜ አለቆቹ በሙሉ መላውን ማኅበረሰብ እንዲህ አሉ፦ “በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ስም ስለማልንላቸው ጉዳት ልናደርስባቸው አንችልም። +20 እንግዲህ የምናደርገው ነገር ቢኖር በማልንላቸው መሐላ የተነሳ ቁጣ እንዳይመጣብን በሕይወት እንዲኖሩ መተው ብቻ ነው።”+ +21 ከዚያም ��ለቆቹ “በሕይወት ይኑሩ፤ ሆኖም ለማኅበረሰቡ በሙሉ እንጨት ለቃሚዎችና ውኃ ቀጂዎች ይሁኑ” አሉ። አለቆቹም ይህንኑ ቃል ገቡላቸው። +22 ኢያሱም እነሱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “የምትኖሩት እዚሁ አጠገባችን ሆኖ ሳለ ‘የምንኖረው ከእናንተ በጣም ርቆ በሚገኝ ቦታ ነው’ በማለት ያታለላችሁን ለምንድን ነው?+ +23 ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ የተረገማችሁ ናችሁ፤+ ለአምላኬም ቤት እንጨት ለቃሚዎችና ውኃ ቀጂዎች በመሆን ምንጊዜም እንደ ባሪያ ታገለግላላችሁ።” +24 እነሱም መልሰው ኢያሱን እንዲህ አሉት፦ “ይህን ያደረግነው አምላክህ ይሖዋ አገልጋዩን ሙሴን ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንዲሰጣችሁና ነዋሪዎቿን በሙሉ ከፊታችሁ እንዲያጠፋላችሁ አዞት እንደነበር ለእኛ ለአገልጋዮችህ በግልጽ ስለተነገረን ነው።+ ስለሆነም በእናንተ የተነሳ ለሕይወታችን* በጣም ፈራን፤+ ይህ +25 ይኸው አሁን በእጅህ ነን። መልካምና ትክክል መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግብን።” +26 እሱም እንዲሁ አደረገባቸው፤ ከእስራኤላውያን እጅ አዳናቸው፤ እነሱም አልገደሏቸውም። +27 ሆኖም በዚያን ዕለት ኢያሱ አምላክ በሚመርጠው ስፍራ+ ለማኅበረሰቡና ለይሖዋ መሠዊያ እንጨት ለቃሚዎችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው፤+ እነሱም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ያደርጋሉ።+ +13 ኢያሱም ዕድሜው ገፍቶና አርጅቶ ነበር።+ በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ ዕድሜህ ገፍቷል፤ አርጅተሃል፤ ሆኖም መወረስ* ያለበት ገና ሰፊ ምድር ይቀራል። +2 የሚቀረውም ምድር ይህ ነው፦+ የፍልስጤማውያንና የገሹራውያን+ ምድር በሙሉ +3 (ከግብፅ ፊት ለፊት ከሚገኘው ከአባይ ወንዝ ቅርንጫፍ* አንስቶ በሰሜን እስከ ኤቅሮን ወሰን ድረስ ያለው ክልል የከነአናውያን ግዛት እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር)+ እንዲሁም በጋዛ፣ በአሽዶድ፣+ በአስቀሎን፣+ በጌት+ እና በኤቅሮን+ የሚኖሩትን የአምስቱን የፍልስጤም ገዢዎች+ ምድር የሚጨምር ሲሆን የአ +4 እነሱም በደቡብ በኩል ይኖሩ ነበር፤ መላው የከነአናውያን ምድር፤ የሲዶናውያን+ ይዞታ የሆነችው መአራ፣ እንዲሁም በአሞራውያን ወሰን ላይ እስከሚገኘው እስከ አፌቅ ድረስ ያለው አካባቢ፤ +5 የጌባላውያን+ ምድር፣ በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ያለው መላው ሊባኖስ ይኸውም በሄርሞን ተራራ ግርጌ ከሚገኘው ከበዓልጋድ አንስቶ እስከ ሌቦሃማት*+ ድረስ ያለው አካባቢ፤ +6 በተራራማው አካባቢ፣ ከሊባኖስ+ እስከ ሚስረፎትማይም+ ባለው ምድር የሚኖሩት ነዋሪዎች በሙሉ እንዲሁም ሲዶናውያን+ በሙሉ ናቸው። እነሱንም ከእስራኤላውያን ፊት አባርራቸዋለሁ።+ አንተም ባዘዝኩህ መሠረት ምድሩን ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ ስጥ።+ +7 እንግዲህ ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገዶችና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ አከፋፍል።”+ +8 የተቀረው የምናሴ ነገድ እኩሌታና ሮቤላውያን እንዲሁም ጋዳውያን የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ በሰጣቸው መሠረት ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ርስታቸውን ወስደዋል፤+ +9 ይህም በአርኖን ሸለቆ*+ መካከል የምትገኘውን ከተማና የመደባን አምባ በሙሉ ጨምሮ በሸለቆው ዳርቻ ላይ ከምትገኘው ከአሮዔር+ አንስቶ እስከ ዲቦን ድረስ ያለውን አካባቢ፣ +10 በሃሽቦን ሆኖ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንን ከተሞች በሙሉ እስከ አሞናውያን+ ወሰን ድረስ፣ +11 ጊልያድን፣ የገሹራውያንንና የማአካታውያንን+ ግዛት፣ የሄርሞንን ተራራ በሙሉ፣ ባሳንን+ በሙሉ እስከ ሳልካ+ ድረስ +12 እንዲሁም በአስታሮት እና በኤድራይ ሆኖ ይገዛ የነበረውን በባሳን ያለውን የኦግን ንጉሣዊ ግዛት በሙሉ ያጠቃልላል። (እሱም በሕይወት ከተረፉት የመጨረሻዎቹ የረፋይም ዘሮች አንዱ ነበር።)+ ሙሴም ድል አድርጎ አባረራቸው።+ +13 ሆኖም እስራኤላውያን ገሹራውያንንና ማአካታውያንን ከምድራቸው አላስለቀቋቸውም፤+ ምክንያቱም ገሹራውያንና ማአካታውያን እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤል መካከል አሉ። +14 ውርስ ያልሰጠው ለሌዋውያን ነገድ ብቻ ነበር።+ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ቃል በገባላቸው መሠረት+ ለእሱ በእሳት የሚቀርቡት መባዎች የእነሱ ውርሻ ናቸው።+ +15 ከዚያም ሙሴ ለሮቤላውያን ነገድ በየቤተሰባቸው ርስት ሰጣቸው፤ +16 ግዛታቸውም በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ላይ ከምትገኘው ከአሮዔር አንስቶ ያለው ሲሆን በሸለቆው መካከል የምትገኘውን ከተማ፣ የመደባን አምባ በሙሉ፣ +17 ሃሽቦንንና በአምባው ላይ ያሉትን ከተሞቿን በሙሉ፣+ ዲቦንን፣ ባሞትበዓልን፣ ቤትበዓልመዖንን፣+ +18 ያሃጽን፣+ ቀደሞትን፣+ መፋአትን፣+ +19 ቂርያታይምን፣ ሲብማን፣+ በሸለቆው* አጠገብ ባለው ኮረብታ ላይ የምትገኘውን ጸሬትሻሃርን፣ +20 ቤትጰኦርን፣ የጲስጋን ሸንተረሮች፣+ ቤትየሺሞትን፣+ +21 በአምባው ላይ የሚገኙትን ከተሞች ሁሉ እንዲሁም በሃሽቦን+ ሆኖ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንን ንጉሣዊ ግዛት በሙሉ ያጠቃልላል። ሙሴም ይህን ንጉሥና+ በምድሪቱ ይኖሩ የነበሩትን የምድያም አለቆች፣ ኤዊን፣ ራቄምን፣ ጹርን፣ ሁርን እና ረባን+ እንዲሁም የሲሖንን መሳፍንት* ድል አድርጓቸው +22 እስራኤላውያን በሰይፍ ከገደሏቸው መካከል ሟርተኛው+ የቢዖር ልጅ በለዓም+ ይገኝበታል። +23 የሮቤላውያን ወሰን ዮርዳኖስ ነበር፤ ከተሞቹንና መንደሮቹን ጨምሮ ይህ ግዛት ሮቤላውያን በየቤተሰባቸው የያዙት ርስት ነው። +24 በተጨማሪም ሙሴ ለጋድ ነገድ ይኸውም ለጋዳውያን በየቤተሰባቸው ርስት ሰጣቸው፤ +25 ግዛታቸውም ያዜርን፣+ የጊልያድን ከተሞች በሙሉ፣ ከራባ+ ፊት ለፊት እስከምትገኘው እስከ አሮዔር የሚደርሰውን የአሞናውያንን+ ምድር እኩሌታ፣ +26 ከሃሽቦን+ እስከ ራማትምጽጳ እና እስከ በጦኒም እንዲሁም ከማሃናይም+ እስከ ደቢር ወሰን ድረስ ያለውን አካባቢ፣ +27 በሸለቆው ውስጥ* ደግሞ ቤትሃራምን፣ ቤትኒምራን፣+ ሱኮትን፣+ ጻፎንን እና ወሰኑ ዮርዳኖስ ሆኖ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ከሚገኘው ከኪኔሬት ባሕር*+ የታችኛው ጫፍ ጀምሮ ያለውን ቀሪውን የሃሽቦንን ንጉሥ የሲሖንን ንጉሣዊ ግዛት+ ያጠቃልላል። +28 ከተሞቹንና መንደሮቹን ጨምሮ ጋዳውያን በየቤተሰባቸው የያዙት ርስት ይህ ነው። +29 በተጨማሪም ሙሴ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኸውም ለግማሹ የምናሴ ነገድ በየቤተሰባቸው ርስት ሰጠ።+ +30 ግዛታቸውም ከማሃናይም+ አንስቶ ያለው ሲሆን ባሳንን በሙሉ፣ የባሳንን ንጉሥ የኦግን ንጉሣዊ ግዛት በሙሉ፣ በባሳን የሚገኙትን የያኢር+ የድንኳን ሰፈሮች በሙሉ፣ 60 ከተሞችን ያጠቃልላል። +31 የጊልያድ እኩሌታ እንዲሁም በባሳን የሚገኙት የኦግ ንጉሣዊ ግዛት ከተሞች ማለትም አስታሮትና ኤድራይ+ የምናሴ ልጅ ለሆነው ለማኪር+ ልጆች ይኸውም ለማኪር ልጆች እኩሌታ በየቤተሰባቸው ተሰጡ። +32 ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ በሞዓብ በረሃማ ሜዳ የሰጣቸው ርስት ይህ ነበር።+ +33 ሆኖም ሙሴ ለሌዋውያን ነገድ ርስት አልሰጠም።+ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ቃል በገባላቸው መሠረት ርስታቸው እሱ ነው።+ +5 ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ* የሚገኙት የአሞራውያን+ ነገሥታት ሁሉ እንዲሁም በባሕሩ አጠገብ ያሉት የከነአናውያን+ ነገሥታት በሙሉ ይሖዋ እስራኤላውያን ዮርዳኖስን እስኪሻገሩ ድረስ የወንዙን ውኃ በፊታቸው እንዳደረቀው ሲሰሙ ልባቸው ቀለጠ፤+ በእስራኤላውያንም የተነሳ ወኔ ከድቷቸው ነበር።*+ +2 በዚያን ጊዜ ይሖዋ ኢያሱን “የባልጩት ቢላ ሠርተህ እስራኤላውያን ወንዶችን እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው”+ አለው። +3 ስለሆነም ኢያሱ የባልጩት ቢላ ሠርቶ እስራኤላውያን ወንዶችን ጊብዓትሃራሎት* በተባለ ስፍራ ገረዛቸው።+ +4 ኢያሱ የገረዛቸው በዚህ የተነሳ ነው፦ ከግብፅ በወጣው ሕዝብ መካከል የነበሩት ወንዶች ሁሉ ይኸውም ለውጊያ ብቁ የሆኑት* ወንዶች በሙሉ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በጉዞ ላይ ሳሉ በምድረ በዳ ሞተዋል።+ +5 ከግብፅ የወጣው ሕዝብ ሁሉ ተገርዞ ነበር፤ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በጉዞ ላይ ሳሉ በምድረ በዳ የተወለደው ሕዝብ ግን አልተገረዘም ነበር። +6 መላው ብሔር ይኸውም የይሖዋን ቃል ያልታዘዙት+ ከግብፅ የወጡት ለውጊያ ብቁ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ሞተው እስኪያልቁ ድረስ እስራኤላውያን በምድረ በዳ 40 ዓመት ተጓዙ።+ ይሖዋም ለእኛ ለመስጠት ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር+ ይኸውም ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር+ እንዲያዩ ፈጽሞ እንደማይፈቅድላቸው ይሖ +7 በመሆኑም በእነሱ ምትክ ወንዶች ልጆቻቸውን አስነሳ።+ ኢያሱም እነዚህን ገረዛቸው፤ ምክንያቱም በጉዞ ላይ ሳሉ ስላልገረዟቸው ከነሸለፈታቸው ነበሩ። +8 እነሱም መላውን ብሔር ገርዘው ሲጨርሱ የተገረዙት ከቁስላቸው እስኪያገግሙ ድረስ እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ቆዩ። +9 ከዚያም ይሖዋ ኢያሱን “በዛሬው ዕለት የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ” አለው። በመሆኑም የዚያ ስፍራ ስም ጊልጋል*+ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሚታወቀው በዚሁ ስሙ ነው። +10 እስራኤላውያንም በጊልጋል እንደሰፈሩ ቆዩ፤ ወሩ በገባ በ14ኛው ቀን ምሽት ላይም በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ የፋሲካን* በዓል አከበሩ።+ +11 ከፋሲካውም ቀን በኋላ በዚያው ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ማለትም ቂጣና*+ የተጠበሰ እሸት በሉ። +12 ከምድሪቱ ፍሬ በበሉበት ቀን ማግስት መናው ተቋረጠ፤+ ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን መና አልወረደላቸውም፤ ከዚህ ይልቅ በዚያ ዓመት የከነአንን ምድር ፍሬ መብላት ጀመሩ።+ +13 ኢያሱ በኢያሪኮ አቅራቢያ ሳለ፣ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ+ አንድ ሰው ፊት ለፊቱ ቆሞ አየ።+ ኢያሱም ወደ እሱ ሄዶ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው። +14 እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “አይደለሁም፤ እኔ አሁን የመጣሁት የይሖዋ ሠራዊት አለቃ ሆኜ ነው።”+ በዚህ ጊዜ ኢያሱ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ በመስገድ “ታዲያ ጌታዬ ለአገልጋዩ የሚነግረው ምንድን ነው?” አለው። +15 የይሖዋ ሠራዊት አለቃም ኢያሱን “የቆምክበት ስፍራ ቅዱስ ስለሆነ ጫማህን አውልቅ” አለው። ኢያሱም ወዲያውኑ እንደተባለው አደረገ።+ +21 የሌዋውያን አባቶች ቤቶች መሪዎች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፣+ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ነገዶች አባቶች ቤቶች መሪዎች ቀርበው +2 በከነአን ምድር በሴሎ+ እንዲህ አሏቸው፦ “ይሖዋ የምንኖርባቸው ከተሞች ለከብቶቻችን ከሚሆኑት የግጦሽ መሬቶቻቸው ጋር እንዲሰጡን በሙሴ በኩል አዝዞ ነበር።”+ +3 በመሆኑም እስራኤላውያን ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ከራሳቸው ርስት ላይ እነዚህን ከተሞችና የግጦሽ መሬቶቻቸውን ለሌዋውያኑ ሰጡ።+ +4 ከዚያም ዕጣው ለቀአታውያን ቤተሰቦች+ ወጣ፤ የካህኑ የአሮን ዘሮች የሆኑት ሌዋውያንም ከይሁዳ ነገድ፣+ ከስምዖን ነገድና+ ከቢንያም ነገድ+ ላይ 13 ከተሞች በዕጣ ተሰጧቸው። +5 ለቀሩት ቀአታውያንም ከኤፍሬም ነገድ፣+ ከዳን ነገድና ከምናሴ ነገድ+ እኩሌታ ቤተሰቦች ላይ አሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጧቸው። +6 ለጌድሶናውያንም+ ከይሳኮር ነገድ፣ ከአሴር ነገድ፣ ከንፍታሌም ነገድና በባሳን+ ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ቤተሰቦች ላይ 13 ከተሞች በዕጣ ተሰጧቸው። +7 ለሜራራውያንም+ በየቤተሰባቸው ከሮቤል ነገድ፣ ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድ+ ላይ 12 ከተሞች ተሰጧቸው። +8 በመሆኑም እስራኤላውያን ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ለሌዋውያኑ እነዚህን ከተሞችና የግጦሽ መሬቶቻቸውን በዕጣ ሰጧቸው።+ +9 ከይሁዳ ነገድና ከስምዖን ነገድ ላይ ደግሞ እዚህ ላይ በስም የተጠቀሱትን እነዚህን ከተሞች ሰጧቸው፤+ +10 እነዚህም ከሌዋውያን መካከል የቀአታውያን ቤተሰብ ለሆኑት ለአሮን ልጆች ተሰጡ፤ ምክንያቱም የመጀመሪያው ዕጣ የወጣው ለእነሱ ነበር። +11 እነሱም በይሁዳ ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ቂርያትአርባን+ (አርባ የኤናቅ አባት ነበር) ይኸውም ኬብሮንን+ እና በዙሪያዋ ያለውን የግጦሽ መሬት ሰጧቸው። +12 ይሁንና የከተማዋን እርሻና መንደሮቿን ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።+ +13 ለካህኑ ለአሮን ልጆችም ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ+ የሆነችውን ኬብሮንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ሊብናን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ +14 ያቲርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ኤሽተሞዓን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ +15 ሆሎንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ደቢርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ +16 አይንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ዩጣን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ቤትሼሜሽን ከነግጦሽ መሬቷ ሰጡ፤ ከእነዚህ ሁለት ነገዶች ላይ ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ። +17 ከቢንያም ነገድ ገባኦንን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ጌባን ከነግጦሽ መሬቷ፣+ +18 አናቶትን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም አልሞንን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጧቸው። +19 ለካህናቱ ለአሮን ዘሮች የተሰጡት ከተሞች በአጠቃላይ 13 ከተሞች ከነግጦሽ መሬቶቻቸው ነበሩ።+ +20 ከሌዋውያን መካከል ለሆኑት ለቀሩት የቀአታውያን ቤተሰቦች ደግሞ ከኤፍሬም ነገድ ርስት ላይ ከተሞች በዕጣ ተሰጧቸው። +21 ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ የሆነችውን+ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ሴኬምን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ጌዜርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ +22 ቂብጻይምን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ቤትሆሮንን+ ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጧቸው። +23 ከዳን ነገድ ላይ ኤልተቄን ከነግጦሽ መሬቷ፣ ጊበቶንን ከነግጦሽ መሬቷ፣ +24 አይሎንን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ጋትሪሞንን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጧቸው። +25 ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ ታአናክን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ጋትሪሞንን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም ሁለት ከተሞችን ሰጧቸው። +26 ለቀሩት የቀአታውያን ቤተሰቦች የተሰጧቸው ከተሞች ከነግጦሽ መሬቶቻቸው በአጠቃላይ አሥር ነበሩ። +27 የሌዋውያን ቤተሰቦች የሆኑት ጌድሶናውያንም+ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ የሆነችውን በባሳን የምትገኘውን ጎላንን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም በኤሽተራን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም ሁለት ከተሞችን ወሰዱ። +28 ከይሳኮር ነገድ+ ላይ ቂሾንን ከነግጦሽ መሬቷ፣ ዳብራትን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ +29 ያርሙትን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ኤንጋኒምን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጡ። +30 ከአሴር ነገድ+ ላይ ሚሽአልን ከነግጦሽ መሬቷ፣ አብዶንን ከነግጦሽ መሬቷ፣ +31 ሄልቃትን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ሬሆብን+ ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጡ። +32 ከንፍታሌም ነገድ ላይ ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ+ የሆነችውን በገሊላ የምትገኘውን ቃዴሽን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ሃሞትዶርን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ቃርታንን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም ሦስት ከተሞችን ሰጡ። +33 የጌድሶናውያን ከተሞች በየቤተሰባቸው በአጠቃላይ 13 ከተሞች ከነግጦሽ መሬቶቻቸው ነበሩ። +34 የሜራራውያን ቤተሰቦች+ የሆኑት የቀሩት ሌዋውያን ደግሞ ከዛብሎን ነገድ+ ላይ ዮቅነአምን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ቃርታን ከነግጦሽ መሬቷ፣ +35 ዲምናን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ናሃላልን+ ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ወሰዱ። +36 ከሮቤል ነገድ ላይ ቤጼርን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ያሃጽን ከነግጦሽ መሬቷ፣+ +37 ቀደሞትን ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም መፋአትን ከነግጦሽ መሬቷ ይኸውም አራት ከተሞችን ሰጡ። +38 ከጋድ ነገድ+ ላይ ደግሞ ነፍስ ላጠፋ ሰው የመማጸኛ ከተማ የሆነችውን በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ ማሃናይምን+ ከነግጦሽ መሬቷ፣ +39 ሃሽቦንን+ ከነግጦሽ መሬቷ እንዲሁም ያዜርን+ ከነግጦሽ መሬቷ በአጠቃላይ አራት ከተሞችን ሰጡ። +40 ከሌዋውያን ቤተሰቦች ለቀሩት ሜራራውያን በየቤተሰባቸው በዕጣ የተሰጧቸው ከተሞች በአጠቃላይ 12 ከተሞች ነበሩ። +41 በእስራኤላውያን ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች በአጠቃላይ 48 ከተሞች ከነግጦሽ መሬቶቻቸው ነበሩ።+ +42 እነዚህ ከተሞች በሙሉ እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው የግጦሽ መሬት ነበራቸው። +43 በመሆኑም ይሖዋ ለእስራኤላውያን፣ ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማለላቸውን ምድር+ በሙሉ ሰጣቸው፤ እነሱም ምድሪቱን ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።+ +44 በተጨማሪም ይሖዋ ለአባቶቻቸው በማለላቸው+ በእያንዳንዱ ነገር መሠረት በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ እረፍት ሰጣቸው፤ ከጠላቶቻቸው መካከል ሊቋቋማቸው የቻለ አንድም አልነበረም።+ ይሖዋ ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።+ +45 ይሖዋ ለእስራኤል ቤት ከገባው መልካም ቃል ሁሉ ሳይፈጸም የቀረ አንድም ቃል የለም፤ ሁሉም ተፈጽሟል።+ +15 ለይሁዳ ነገድ ለየቤተሰቡ በዕጣ የተሰጠው ርስት+ እስከ ኤዶም+ ይኸውም እስከ ጺን ምድረ በዳና እስከ ኔጌብ ደቡባዊ ጫፍ ድረስ ይዘልቃል። +2 ደቡባዊው ወሰናቸው ከጨው ባሕር* ዳርቻ+ ይኸውም ከባሕሩ ደቡባዊ ወሽመጥ ይነሳል። +3 ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ አቅራቢም አቀበት+ ድረስ ይዘልቅና ወደ ጺን ይሻገራል፤ በመቀጠልም ከደቡብ ወደ ቃዴስበርኔ+ ይወጣና በኤስሮን በኩል አልፎ ወደ አዳር ከሄደ በኋላ ወደ ቃርቃ ይዞራል። +4 ከዚያም ወደ አጽሞን+ ይዘልቅና ወደ ግብፅ ሸለቆ*+ ይቀጥላል፤ ወሰኑም ባሕሩ* ጋ ሲደርስ ያበቃል። ደቡባዊ ወሰናቸው ይህ ነበር። +5 ምሥራቃዊው ወሰን ደግሞ ጨው ባሕር* ሲሆን ይህም እስከ ዮርዳኖስ ጫፍ ይደርሳል፤ በስተ ሰሜን በኩል ያለው ወሰን በዮርዳኖስ ጫፍ ላይ የሚገኘው የባሕሩ ወሽመጥ ነበር።+ +6 ከዚያም ወሰኑ ወደ ቤትሆግላ+ ይወጣና ከቤትአረባ+ በስተ ሰሜን በኩል ያልፋል፤ የሮቤል ልጅ የቦሃን ድንጋይ+ እስካለበትም ድረስ ይዘልቃል። +7 በመቀጠልም በአኮር ሸለቆ*+ ወደምትገኘው ወደ ደቢር ይወጣና በስተ ሰሜን ወደ ጊልጋል+ ይኸውም ከሸለቆው በስተ ደቡብ ከሚገኘው ከአዱሚም አቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ቦታ ይታጠፋል፤ ከዚያም ወደ ኤንሼሜሽ+ ውኃዎች ይሄድና ኤንሮጌል+ ላይ ያበቃል። +8 ወሰኑ እስከ ሂኖም ልጅ ሸለቆ+ ይኸውም በስተ ደቡብ እስከሚገኘው እስከ ኢያቡሳውያን+ ሸንተረር ማለትም እስከ ኢየሩሳሌም+ ድረስ ይወጣል፤ በተጨማሪም በረፋይም ሸለቆ* ሰሜናዊ ጫፍ ላይ እስከሚገኘውና ከሂኖም ሸለቆ ምዕራባዊ ክፍል ትይዩ እስካለው ተራራ አናት ድረስ ይዘልቃል። +9 ከዚያም ከተራራው አናት ተነስቶ እስከ ነፍቶአ+ የውኃ ምንጮች ድረስ ይሄዳል፤ እንዲሁም በኤፍሮን ተራራ ላይ እስካሉት ከተሞች ይዘልቃል፤ በመቀጠልም እስከ ባዓላ ማለትም እስከ ቂርያትየአሪም+ ይሄዳል። +10 ወሰኑ ከባዓላ ተነስቶ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በመዞር ወደ ሴይር ተራራ ይሄዳል፤ ከዚያም በስተ ሰሜን ወደ የአሪም ተራራ ሸንተረር ማለትም ወደ ከሳሎን ያልፋል፤ በመቀጠልም ወደ ቤትሼሜሽ+ በመውረድ ወደ ቲምና+ ይዘልቃል። +11 ወደ ሰሜን አቅጣጫ ወደ ኤቅሮን+ ሸንተረር ከወጣም በኋላ ወደ ሺከሮን ይሄዳል፤ ከዚያም ባዓላ ተራራን አልፎ ወደ ያብነኤል ይወጣል፤ ��ሕሩም ጋ ሲደርስ ያበቃል። +12 ምዕራባዊው ወሰን ታላቁ ባሕርና*+ ዳርቻው ነበር። እንግዲህ የይሁዳ ዘሮች በየቤተሰባቸው ወሰናቸው ዙሪያውን ይህ ነበር። +13 ኢያሱ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ+ በይሁዳ ዘሮች መካከል የምትገኘውን ኬብሮን+ የተባለችውን ቂርያትአርባን ድርሻ አድርጎ ሰጠው (አርባ የኤናቅ አባት ነበር)። +14 በመሆኑም ካሌብ የኤናቅ+ ዘሮች የሆኑትን ሦስቱን የኤናቅ ልጆች ማለትም ሸሻይን፣ አሂማንን እና ታልማይን+ ከዚያ አባረራቸው። +15 ከዚያ ተነስቶም በደቢር ነዋሪዎች ላይ ዘመተ።+ (ደቢር ቀደም ሲል ቂርያትሰፈር ትባል ነበር።) +16 ካሌብም “ቂርያትሰፈርን መትቶ በቁጥጥር ሥር ላደረጋት ሰው ሴት ልጄን አክሳን እድርለታለሁ” አለ። +17 የካሌብ ወንድም የሆነው የቀናዝ+ ልጅ ኦትኒኤልም+ ከተማዋን በቁጥጥር ሥር አደረጋት። ስለሆነም ካሌብ ሴት ልጁን አክሳን+ ዳረለት። +18 እሷም ወደ ባሏ ቤት እየሄደች ሳለ ባሏን ከአባቷ መሬት እንዲጠይቅ ወተወተችው። ከዚያም ከአህያዋ ላይ ወረደች።* በዚህ ጊዜ ካሌብ “ምን ፈለግሽ?” ሲል ጠየቃት።+ +19 እሷም “የሰጠኸኝ በስተ ደቡብ* ያለ ቁራሽ መሬት ስለሆነ እባክህ ባርከኝ፤ ጉሎትማይምንም* ስጠኝ” አለችው። ስለዚህ ላይኛውን ጉሎት እና ታችኛውን ጉሎት ሰጣት። +20 የይሁዳ ነገድ በየቤተሰባቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነበር። +21 በኤዶም+ ወሰን በኩል ባለው የይሁዳ ነገድ ክልል ደቡባዊ ጫፍ ላይ የሚገኙት ከተሞች እነዚህ ናቸው፦ ቃብጽኤል፣ ኤዴር፣ ያጉር፣ +22 ቂና፣ ዲሞና፣ አድዓዳ፣ +23 ቃዴሽ፣ ሃጾር፣ ይትናን፣ +24 ዚፍ፣ ተሌም፣ በዓሎት፣ +25 ሃጾርሃዳታ፣ ቀሪዮትሄጽሮን ማለትም ሃጾር፣ +26 አማም፣ ሼማ፣ ሞላዳ፣+ +27 ሃጻርጋዳ፣ ሄሽሞን፣ ቤትጳሌጥ፣+ +28 ሃጻርሹአል፣ ቤርሳቤህ፣+ ቢዝዮትያ፣ +29 ባዓላ፣ ኢዪም፣ ኤጼም፣ +30 ኤልቶላድ፣ ከሲል፣ ሆርማ፣+ +31 ጺቅላግ፣+ ማድማና፣ ሳንሳና፣ +32 ለባኦት፣ ሺልሂም፣ አይን እና ሪሞን፤+ በአጠቃላይ 29 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +33 በሸፌላ+ የነበሩት ከተሞች እነዚህ ናቸው፦ ኤሽታዖል፣ ጾራ፣+ አሽና፣ +34 ዛኖሃ፣ ኤንጋኒም፣ ታጱአ፣ ኤናም፣ +35 ያርሙት፣ አዱላም፣+ ሶኮህ፣ አዜቃ፣+ +36 ሻአራይም፣+ አዲታይም፣ ገዴራ እና ገዴሮታይም፤* በአጠቃላይ 14 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +37 ጸናን፣ ሃዳሻ፣ ሚግዳልጋድ፣ +38 ዲልአን፣ ምጽጳ፣ ዮቅተኤል፣ +39 ለኪሶ፣+ ቦጽቃት፣ ኤግሎን፣ +40 ካቦን፣ ላህማም፣ ኪትሊሽ፣ +41 ገዴሮት፣ ቤትዳጎን፣ ናዕማ እና መቄዳ፤+ በአጠቃላይ 16 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +42 ሊብና፣+ ኤቴር፣ አሻን፣+ +43 ይፍታህ፣ አሽና፣ ነጺብ፣ +44 ቀኢላ፣ አክዚብ እና ማሬሻህ፤ በአጠቃላይ ዘጠኝ ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +45 ኤቅሮን እንዲሁም በሥሯ* ያሉት ከተሞችና መንደሮቿ። +46 ከኤቅሮን በስተ ምዕራብ በአሽዶድ በኩል ያሉት አካባቢዎች በሙሉና መንደሮቻቸው። +47 አሽዶድ+ እንዲሁም በሥሯ* ያሉት ከተሞችና መንደሮቿ፤ ጋዛ+ እንዲሁም በሥሯ ያሉት ከተሞችና መንደሮቿ እስከ ግብፅ ሸለቆ፣ እስከ ታላቁ ባሕርና* በባሕሩ ጠረፍ እስካለው አካባቢ ድረስ።+ +48 በተራራማው አካባቢ የነበሩት ከተሞች እነዚህ ናቸው፦ ሻሚር፣ ያቲር፣+ ሶኮህ፣ +49 ዳና፣ ቂርያትሳና ማለትም ደቢር፣ +50 አናብ፣ ኤሽተሞህ፣+ አኒም፣ +51 ጎሸን፣+ ሆሎን እና ጊሎ፤+ በአጠቃላይ 11 ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +52 ዓረብ፣ ዱማ፣ ኤሽዓን፣ +53 ያኒም፣ ቤትታጱአ፣ አፌቃ፣ +54 ሁምጣ፣ ቂርያትአርባ ማለትም ኬብሮን+ እና ጺኦር፤ በአጠቃላይ ዘጠኝ ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +55 ማኦን፣+ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣+ ዩጣ፣ +56 ኢይዝራኤል፣ ዮቅደአም፣ ዛኖሃ፣ +57 ቄይን፣ ጊብዓ እና ቲምና፤+ በ���ጠቃላይ አሥር ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +58 ሃልሁል፣ ቤትጹር፣ ጌዶር፣ +59 ማአራት፣ ቤትአኖት እና ኤልተቆን፤ በአጠቃላይ ስድስት ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +60 ቂርያትበኣል ማለትም ቂርያትየአሪም+ እና ራባ፤ በአጠቃላይ ሁለት ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +61 በምድረ በዳው የነበሩት ከተሞች እነዚህ ናቸው፦ ቤትአረባ፣+ ሚዲን፣ ሰካካ፣ +62 ኒብሻን፣ የጨው ከተማ እና ኤንገዲ፤+ በአጠቃላይ ስድስት ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። +63 የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩትን+ ኢያቡሳውያንን+ ሊያባርሯቸው አልቻሉም ነበር፤+ ስለሆነም ኢያቡሳውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሰዎች ጋር በኢየሩሳሌም ይኖራሉ። +22 ከዚያም ኢያሱ ሮቤላውያንን፣ ጋዳውያንንና የምናሴን ነገድ እኩሌታ ጠርቶ +2 እንዲህ አላቸው፦ “የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ሁሉ ፈጽማችኋል፤+ እኔም ባዘዝኳችሁ ነገር ሁሉ ቃሌን ሰምታችኋል።+ +3 በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት እስከ ዛሬ ድረስ ወንድሞቻችሁን አልተዋችሁም፤+ አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ትእዛዝ ጋር በተያያዘ ግዴታችሁን ተወጥታችኋል።+ +4 እንግዲህ አሁን አምላካችሁ ይሖዋ ለወንድሞቻችሁ ቃል በገባላቸው መሠረት እረፍት ሰጥቷቸዋል።+ በመሆኑም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ* ርስት አድርጎ በሰጣችሁ ምድር ወደሚገኙት ድንኳኖቻችሁ መመለስ ትችላላችሁ።+ +5 ብቻ እናንተ አምላካችሁን ይሖዋን በመውደድ፣+ በመንገዶቹ ሁሉ በመሄድ፣+ ትእዛዛቱን በመጠበቅ፣+ ከእሱ ጋር በመጣበቅ+ እንዲሁም በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ እሱን በማገልገል+ የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ የሰጣችሁን ትእዛዝና ሕግ በጥንቃቄ ፈጽሙ።”+ +6 ከዚያም ኢያሱ ባረካቸውና አሰናበታቸው፤ እነሱም ወደ ድንኳኖቻቸው ሄዱ። +7 ሙሴ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በባሳን ርስት ሰጥቶ ነበር፤+ ኢያሱ ደግሞ ለቀረው የነገዱ እኩሌታ ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ከወንድሞቻቸው ጋር መሬት ሰጣቸው።+ በተጨማሪም ኢያሱ ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ ባሰናበታቸው ጊዜ ባረካቸው፤ +8 እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ሀብት፣ እጅግ ብዙ ከብት፣ ብር፣ ወርቅ፣ መዳብ፣ ብረትና እጅግ ብዙ ልብስ ይዛችሁ ወደየድንኳኖቻችሁ ተመለሱ።+ ከጠላቶቻችሁ ያገኛችሁትን ምርኮ ወስዳችሁ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”+ +9 ከዚህ በኋላ ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ በከነአን ምድር በምትገኘው በሴሎ ከነበሩት ከሌሎቹ እስራኤላውያን ተለይተው ወደ ጊልያድ ምድር+ ይኸውም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ርስት አድርገው ወደሰፈሩባት ምድር ተመለሱ።+ +10 ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ በከነአን ምድር ወዳለው የዮርዳኖስ ክልል ሲደርሱ በዮርዳኖስ አጠገብ ግዙፍ የሆነ አስደናቂ መሠዊያ ሠሩ። +11 በኋላም ሌሎቹ እስራኤላውያን “እነሆ፣ ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ የእስራኤላውያን ክልል በሆነው በከነአን ምድር ወሰን ላይ በሚገኘው የዮርዳኖስ ክልል መሠዊያ ሠርተዋል” የሚል ወሬ ሰሙ።+ +12 እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ መላው የእስራኤላውያን ማኅበረሰብ እነሱን ለመውጋት በሴሎ+ ተሰበሰበ። +13 ከዚያም እስራኤላውያን የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሃስን+ በጊልያድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤላውያን፣ ወደ ጋዳውያን እና ወደ ምናሴ ነገድ እኩሌታ ላኩት፤ +14 ከእሱም ጋር አሥር አለቆችን ይኸውም ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች ከእያንዳንዱ የአባቶች ቤት አንድ አንድ አለቃ አብረው ላኩ፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው ከእስራኤል የሺህ አለቆች* መካከል የሆኑ የአባቶች ቤት መሪዎች ነበሩ።+ +15 እነሱም በጊልያድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤላውያን፣ ወደ ��ዳውያንና ወደ ምናሴ ነገድ እኩሌታ መጥተው እንዲህ አሏቸው፦ +16 “መላው የይሖዋ ጉባኤ እንዲህ ይላል፦ ‘በእስራኤል አምላክ ላይ እንዲህ ያለ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት የፈጸማችሁት ለምንድን ነው?+ ለራሳችሁ መሠዊያ በመሥራትና በይሖዋ ላይ በማመፅ ይኸው ዛሬ ይሖዋን ከመከተል ዞር ብላችኋል።+ +17 በፌጎር የሠራነው ስህተት አንሶ ነው? ምንም እንኳ ያኔ በይሖዋ ጉባኤ ላይ መቅሰፍት ቢወርድም ይኸው እስከ ዛሬ ድረስ ከዚህ ነገር ራሳችንን አላነጻንም።+ +18 እናንተ ደግሞ ዛሬ ይሖዋን ከመከተል ዞር ትላላችሁ! ዛሬ እናንተ በይሖዋ ላይ ብታምፁ ነገ ደግሞ እሱ በመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ላይ ይቆጣል።+ +19 የወረሳችኋት ምድር ረክሳ ከሆነ የይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ወደሚገኝበት+ የይሖዋ ርስት ወደሆነው ምድር ተሻግራችሁ+ በመካከላችን ኑሩ፤ ሆኖም ከአምላካችን ከይሖዋ መሠዊያ ሌላ ለራሳችሁ መሠዊያ በመሥራት በይሖዋ ላይ አታምፁ፣ እኛንም ዓመፀኞች አታድርጉን።+ +20 የዛራ ልጅ አካን+ ለጥፋት ከተለየው ነገር ጋር በተያያዘ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት በፈጸመ ጊዜ በመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ላይ ቁጣ አልወረደም?+ በሠራው ስህተት የሞተው እሱ ብቻ አልነበረም።’”+ +21 በዚህ ጊዜ ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል የሺህ* አለቆች እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦+ +22 “የአማልክት አምላክ፣ ይሖዋ!* የአማልክት አምላክ፣ ይሖዋ!+ እሱ ያውቃል፤ እስራኤልም ቢሆን ያውቃል። በይሖዋ ላይ ዓምፀንና ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጽመን ከሆነ ዛሬ አይታደገን። +23 ለራሳችን መሠዊያ የሠራነው ይሖዋን ከመከተል ዞር ለማለት ወይም በላዩ ላይ የሚቃጠሉ መባዎችንና የእህል መባዎችን ለማቅረብ አሊያም የኅብረት መሥዋዕቶችን ለመሠዋት ብለን ከሆነ ይሖዋ ይቅጣን።+ +24 እኛ ግን ይህን ያደረግነው ወደፊት ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እንዲህ ማለታቸው አይቀርም ብለን ስለሰጋን ነው፦ ‘ከእስራኤል አምላክ ከይሖዋ ጋር ምን ግንኙነት አላችሁ? +25 ይሖዋ ሮቤላውያንና ጋዳውያን በሆናችሁት በእናንተና በእኛ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጓል። እናንተ በይሖዋ ዘንድ ምንም ድርሻ የላችሁም።’ ልጆቻችሁም ልጆቻችን ይሖዋን እንዳያመልኩ* እንቅፋት ይሆኑባቸዋል።” +26 “በመሆኑም እንዲህ አልን፦ ‘እንግዲህ አንድ እርምጃ መውሰድ አለብን፤ መሠዊያ እንሥራ፤ ይህም የሚቃጠል መባ ወይም መሥዋዕት የሚቀርብበት አይደለም፤ +27 ከዚህ ይልቅ የሚቃጠሉ መባዎቻችንን፣ መሥዋዕቶቻችንንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችንን+ ይዘን በመምጣት በይሖዋ ፊት አገልግሎት እንደምናቀርብ ለማሳየት በእኛና በእናንተ እንዲሁም ከእኛ በኋላ በሚመጡት ዘሮቻችን* መካከል ምሥክር የሚሆን ነው፤+ ስለዚህ ወደፊት ልጆቻችሁ ልጆቻችንን “እናንተ በይሖዋ ዘንድ ምንም +28 ስለዚህ እኛ እንዲህ አልን፦ ‘ወደፊት እኛንም ሆነ ዘሮቻችንን* እንዲህ ቢሉ እኛ ደግሞ “የሚቃጠል መባ ወይም መሥዋዕት የሚቀርብበት ሳይሆን በእኛና በእናንተ መካከል ምሥክር እንዲሆን አባቶቻችን የይሖዋን መሠዊያ አስመስለው የሠሩት መሠዊያ ይኸውና” እንላቸዋለን።’ +29 በማደሪያ ድንኳኑ ፊት ካለው ከአምላካችን ከይሖዋ መሠዊያ ሌላ የሚቃጠል መባ፣ የእህል መባና መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ በመሥራት+ ዛሬ በይሖዋ ላይ ማመፅና ይሖዋን ከመከተል ወደኋላ ማለት+ በእኛ በኩል ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው!” +30 ካህኑ ፊንሃስና ከእሱ ጋር የነበሩት የማኅበረሰቡ አለቆች ይኸውም የእስራኤል የሺህ* አለቆች የሮቤል፣ የጋድና የምናሴ ዘሮች የተናገሩትን በሰሙ ጊዜ ነገሩን አሳማኝ ሆኖ አገኙት።+ +31 በመሆኑም የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ የሮቤልን፣ የጋድንና የምናሴን ዘሮች እንዲህ አላቸው፦ “በይሖዋ ላይ እንዲህ ያለ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ስላልፈጸማችሁ ይሖዋ በመካከላችን እንዳለ ዛሬ አውቀናል። እነሆ እስራኤላውያንን ከይሖዋ እጅ ታድጋችኋል።” +32 ከዚያም የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስና አለቆቹ በጊልያድ ምድር ከሰፈሩት ከሮቤላውያንና ከጋዳውያን ዘንድ ተመልሰው በከነአን ምድር ወደሚገኙት ወደ ሌሎቹ እስራኤላውያን በመምጣት ስለ ሁኔታው ነገሯቸው። +33 እስራኤላውያንም ነገሩን አሳማኝ ሆኖ አገኙት። ከዚያም እስራኤላውያን አምላክን ባረኩ፤ ከዚያ በኋላም በሮቤላውያንና በጋዳውያን ላይ ስለመዝመትም ሆነ የሚኖሩባትን ምድር ስለማጥፋት አንስተው አያውቁም። +34 ስለሆነም ሮቤላውያንና ጋዳውያን “ይህ መሠዊያ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ ስለመሆኑ በመካከላችን ያለ ምሥክር ነው” በማለት ለመሠዊያው ስም* አወጡለት። +17 በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ የሚኖር ሚክያስ የተባለ አንድ ሰው ነበር። +"2 እሱም እናቱን እንዲህ አላት፦ “1,100 የብር ሰቅል ተወስዶብሽ የሰረቀውን ሰው ስትራገሚ ሰምቼ ነበር፤ ብሩ ያለው እኔ ጋ ነው። የወሰድኩት እኔ ነበርኩ።” በዚህ ጊዜ እናቱ “ልጄ፣ ይሖዋ ይባርክህ” አለችው።" +"3 በመሆኑም 1,100ውን የብር ሰቅል ለእናቱ መለሰላት፤ እናቱ ግን “የተቀረጸ ምስልና ከብረት የተሠራ ሐውልት* + እንዲሠራበት ለልጄ ስል ብሩን ከእጄ ለይሖዋ እቀድሰዋለሁ። ለአንተም መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው። " +4 እሱም ብሩን ለእናቱ ከመለሰላት በኋላ እናቱ 200 የብር ሰቅል ወስዳ ለብር አንጥረኛው ሰጠችው። እሱም የተቀረጸ ምስልና ከብረት የተሠራ ሐውልት* ሠራበት፤ እነሱም በሚክያስ ቤት ተቀመጡ። +5 ሚክያስ የተባለው ይህ ሰው የአማልክት ቤት ነበረው፤ እሱም ኤፉድና+ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾች* + ሠራ፤ ከወንዶች ልጆቹም መካከል አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው።* + +6 በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም።+ እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ትክክል መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።+ +7 በዚያ ጊዜ በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም+ የሚኖር ከይሁዳ ቤተሰብ የሆነ አንድ ወጣት ነበር። እሱም ሌዋዊ+ ሲሆን በዚያ ለተወሰነ ጊዜ ተቀምጦ ነበር። +8 ይህም ሰው የሚኖርበት ስፍራ ለመፈለግ በይሁዳ የምትገኘውን የቤተልሔምን ከተማ ለቆ ሄደ። እየተጓዘም ሳለ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ሚክያስ+ ቤት ደረሰ። +9 ከዚያም ሚክያስ “ከየት ነው የመጣኸው?” ሲል ጠየቀው። እሱም መልሶ “በይሁዳ ከምትገኘው ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የምኖርበት ስፍራ ለመፈለግ እየሄድኩ ነው” አለው። +10 በመሆኑም ሚክያስ “እንግዲያው እኔ ጋ ተቀመጥ፤ እንደ አባትና* እንደ ካህንም ሆነህ አገልግለኝ። እኔ ደግሞ በዓመት አሥር የብር ሰቅል እንዲሁም ልብስና ምግብህን እሰጥሃለሁ” አለው። ስለዚህ ሌዋዊው ገባ። +11 በዚህ መንገድ ሌዋዊው ከሰውየው ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት። +12 በተጨማሪም ሚክያስ ሌዋዊውን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው፤* + እሱም በሚክያስ ቤት ኖረ። +13 ከዚያም ሚክያስ “ሌዋዊ፣ ካህን ስለሆነልኝ ይሖዋ መልካም እንደሚያደርግልኝ አሁን ተረድቻለሁ” አለ። +18 በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም።+ በዚያ ጊዜ የዳናውያን ነገድ+ የሚሰፍርበት ርስት እየፈለገ ነበር፤ ምክንያቱም ዳናውያን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልተሰጣቸውም ነበር።+ +2 ዳናውያን ከቤተሰባቸው መካከል ብቃት ያላቸውን አምስት ወንዶች መርጠው ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲቃኙ ከጾራና ከኤሽታዖል+ ላኳቸው። እነሱንም “ሂዱ፣ ምድሪቱን ቃኙ” አሏቸው። እነሱም በኤፍ��ም ተራራማ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ሚክያስ+ ቤት ሲደርሱ እዚያ አደሩ። +3 ወደ ሚክያስ ቤት በቀረቡም ጊዜ የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ* ለዩት፤ በመሆኑም ወደ እሱ ገብተው “ለመሆኑ እዚህ ማን አመጣህ? ደግሞስ እዚህ ምን ትሠራለህ? እዚህ እንድትቆይ ያደረገህስ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። +4 እሱም መልሶ “ሚክያስ ይህን ይህን አደረገልኝ፤ ካህን ሆኜ እንዳገለግለውም ቀጠረኝ”+ አላቸው። +5 ከዚያም እነሱ “መንገዳችን የተቃና መሆን አለመሆኑን እባክህ አምላክን ጠይቅልን” አሉት። +6 ካህኑም “በሰላም ሂዱ። በመንገዳችሁ ሁሉ ይሖዋ ከእናንተ ጋር ነው” አላቸው። +7 ስለሆነም አምስቱ ሰዎች ጉዟቸውን በመቀጠል ወደ ላይሽ+ መጡ። የከተማዋም ሰዎች ልክ እንደ ሲዶናውያን ራሳቸውን ችለው እንደሚኖሩ ተመለከቱ። እነዚህ ሰዎች ያለምንም ስጋት ተረጋግተው የተቀመጡ+ ከመሆናቸውም ሌላ በምድሪቱ ላይ እነሱን የሚያውክ ጨቋኝ ቅኝ ገዢ አልነበረም። በተጨማሪም የሚኖሩት ከሲዶናውያን +8 እነሱም በጾራና በኤሽታዖል+ ወደሚገኙት ወንድሞቻቸው በተመለሱ ጊዜ ወንድሞቻቸው “የሄዳችሁበት ጉዳይ እንዴት ሆነ?” በማለት ጠየቋቸው። +9 እነሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ምድሪቱ በጣም ጥሩ ምድር መሆኗን ስላየን ተነሱ፣ እንዝመትባቸው። ለምን ታመነታላችሁ? ገብታችሁ ምድሪቱን ለመውረስ አትዘግዩ። +10 እዚያ ስትደርሱ ያለምንም ስጋት የተቀመጠ+ ሕዝብ ታገኛላችሁ፤ ምድሪቱም በጣም ሰፊ ነች። አምላክም በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ነገር የማይታጣበትን ስፍራ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷችኋል።”+ +11 ከዚያም ከዳናውያን ቤተሰብ የሆኑና ለጦርነት የታጠቁ 600 ሰዎች ከጾርና ከኤሽታዖል+ ተንቀሳቀሱ። +12 እነሱም ወጥተው በይሁዳ በምትገኘው በቂርያትየአሪም+ ሰፈሩ። ከቂርያትየአሪም በስተ ምዕራብ የሚገኘው ያ ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ማሃነህዳን* + ተብሎ የሚጠራው በዚህ የተነሳ ነው። +13 ከዚያም ተነስተው ወደ ኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ተጓዙ፤ ወደ ሚክያስም+ ቤት መጡ። +14 በኋላም ላይሽን+ ለመሰለል ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ወንድሞቻቸውን “እነዚህ ቤቶች ውስጥ ኤፉድ፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾች፣* የተቀረጸ ምስልና ከብረት የተሠራ ሐውልት* እንዳለ ታውቃላችሁ?+ እንግዲህ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ አስቡ” አሏቸው። +15 እነሱም በሚክያስ ቤት ወደሚገኘው ወደ ወጣቱ ሌዋዊ+ ቤት ጎራ ብለው ስለ ደህንነቱ ጠየቁት። +16 በዚህ ጊዜ ሁሉ ለጦርነት የታጠቁት 600ዎቹ የዳን ሰዎች+ መግቢያው በር ላይ ቆመው ነበር። +17 ምድሪቱን ለመሰለል+ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎችም የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣+ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹንና* + ከብረት የተሠራውን ምስል* + ለመውሰድ ወደ ውስጥ ገቡ። (ካህኑም+ ለጦርነት ከታጠቁት 600 ሰዎች ጋር መግቢያው በር ላይ ቆሞ ነበር።) +18 እነሱም ወደ ሚክያስ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹንና* ከብረት የተሠራውን ምስል* ወሰዱ። ካህኑም “ምን እያደረጋችሁ ነው?” አላቸው። +19 እነሱ ግን እንዲህ አሉት፦ “ዝም በል። ምንም ቃል አትናገር፤ ይልቅስ ከእኛ ጋር ሄደህ አባትና* ካህን ሁነን። ለአንድ ሰው ቤት ካህን ብትሆን ይሻልሃል+ ወይስ በእስራኤል ለሚገኝ አንድ ነገድና+ ቤተሰብ ካህን ብትሆን?” +20 በዚህ ጊዜ የካህኑ ልብ ደስ ተሰኘ፤ እሱም ኤፉዱን፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹንና* የተቀረጸውን ምስል+ ይዞ ከሕዝቡ ጋር ሄደ። +21 ከዚያም ልጆቹን፣ ከብቶቹንና ውድ የሆኑትን ነገሮች ከፊት አስቀድመው ጉዟቸውን ለመቀጠል ተነሱ። +22 ከሚክያስ ቤት የተወሰነ መንገድ ርቀው ከሄዱም በኋላ በሚክያስ ቤት አቅራቢያ በሚገኙ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አንድ ላይ ተሰበሰቡ፤ ዳናውያንንም ተከታትለው ደረሱባቸው። +23 ከዚያም ጮኸው ሲጠሯቸው ዳናውያኑ ዞር በማለት ሚክያስን “ምን ሆነሃል? ተሰባስባችሁ የመጣችሁትስ ለምንድን ነው?” አሉት። +24 እሱም “የሠራኋቸውን አማልክቴን ወሰዳችሁ፤ ካህኑንም ይዛችሁ ሄዳችሁ። እንግዲህ ምን ቀረኝ? ታዲያ እንዴት ‘ምን ሆነሃል?’ ትሉኛላችሁ?” አላቸው። +25 በዚህ ጊዜ ዳናውያኑ “አትጩኽብን፤ አለዚያ የተቆጡ ሰዎች* ጉዳት ያደርሱባችኋል፤ ይህም የገዛ ሕይወትህንና* የቤተሰብህን ሕይወት* ሊያሳጣህ ይችላል” አሉት። +26 ዳናውያኑም ጉዟቸውን ቀጠሉ፤ ሚክያስም እነሱ ከእሱ ይልቅ ብርቱዎች እንደሆኑ ስለተረዳ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ። +27 እነሱም ሚክያስ የሠራቸውን ነገሮችና የእሱን ካህን ከወሰዱ በኋላ ወደ ላይሽ+ ይኸውም ያለምንም ስጋት ተረጋግተው ይኖሩ ወደነበሩት+ ሰዎች ሄዱ። እነሱንም በሰይፍ መቷቸው፤ ከተማዋንም በእሳት አቃጠሉ። +28 ከተማዋ የምትገኘው ከሲዶና ርቃ ስለነበርና ነዋሪዎቿም ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ስላልነበራቸው ማንም የሚያድናት አልነበረም፤ ላይሽ የምትገኘው በቤትሬሆብ+ ባለው ሸለቋማ ሜዳ* ላይ ነበር። እነሱም ከተማዋን ዳግመኛ ገንብተው በዚያ መኖር ጀመሩ። +29 በተጨማሪም ከተማዋን ለእስራኤል በተወለደለት+ በአባታቸው በዳን ስም ዳን+ ብለው ጠሯት። የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ላይሽ ነበር።+ +30 ከዚያም ዳናውያን የተቀረጸውን ምስል+ ለራሳቸው አቆሙት፤ የሙሴ ልጅ የሆነው የጌርሳም+ ልጅ ዮናታንና+ ወንዶች ልጆቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች በግዞት እስከተወሰዱበት ጊዜ ድረስ የዳናውያን ነገድ ካህናት ሆኑ። +31 ሚክያስ የሠራውንም የተቀረጸ ምስል አቆሙት፤ ምስሉም የእውነተኛው አምላክ ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ በዚያ ነበር።+ +19 በእስራኤል ንጉሥ ባልነበረበት+ በዚያ ዘመን በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ ራቅ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚኖር አንድ ሌዋዊ በይሁዳ ካለችው ከቤተልሔም+ አንዲት ቁባት አገባ። +2 ቁባቱ ግን ለእሱ ታማኝ አልነበረችም፤ ከዚያም ትታው በይሁዳ ባለችው ቤተልሔም ወደሚገኘው ወደ አባቷ ቤት ሄደች። እሷም በዚያ ለአራት ወር ተቀመጠች። +3 ባሏም እንድትመለስ ሊያግባባት ተነስቶ ወደ እሷ ሄደ፤ ወደዚያም የሄደው አገልጋዩንና ሁለት አህዮቹን ይዞ ነበር። እሷም ወደ አባቷ ቤት አስገባችው። አባቷም ባየው ጊዜ እሱን በማግኘቱ ተደሰተ። +4 ስለሆነም አማቱ ማለትም የወጣቷ አባት ሰውየውን ለሦስት ቀን እሱ ጋ እንዲቆይ አግባባው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡም፤ እሱም እዚያው አደረ። +5 በአራተኛው ቀን በማለዳ ለመሄድ ሲነሱ የወጣቷ አባት አማቹን “ብርታት እንድታገኙ* ትንሽ እህል ቅመሱ፤ ከዚያ በኋላ ትሄዳላችሁ” አለው። +6 በመሆኑም ተቀመጡ፤ እነሱም አብረው በሉ፤ ጠጡም፤ ከዚያም የወጣቷ አባት ሰውየውን “እባክህ እዚሁ እደር፤ ልብህም ደስ ይበለው” አለው። +7 ሰውየውም ለመሄድ ሲነሳ አማቱ ይለምነው ነበር፤ ስለዚህ ዳግመኛ እዚያው አደረ። +8 በአምስተኛውም ቀን ለመሄድ በማለዳ ሲነሳ የወጣቷ አባት “ብርታት እንድታገኝ* እባክህ ትንሽ እህል ቅመስ” አለው። እነሱም ቀኑ እስኪገባደድ ድረስ እዚያው ዋሉ፤ አብረውም ሲበሉ ቆዩ። +9 ሰውየውም ከቁባቱና ከአገልጋዩ ጋር ለመሄድ ሲነሳ አማቱ ማለትም የወጣቷ አባት እንዲህ አለው፦ “አሁን እኮ እየመሸ ነው! እባካችሁ እዚሁ እደሩ። ቀኑ እየተገባደደ ነው። እዚሁ እደሩና ልባችሁ ደስ ይበለው። ነገ በማለዳ ተነስታችሁ ትጓዛላችሁ፤ ወደ ቤታችሁም* ትሄዳላችሁ።” +10 ሆኖም ሰውየው እዚያ ለማደር አልፈለገም፤ ስለሆነም ተነስቶ እስከ ኢያቡስ ማለትም እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ተጓዘ።+ ከእሱም ጋር ጭነት የተጫኑት ሁለቱ አህዮች፣ ���ባቱና አገልጋዩ ነበሩ። +11 ወደ ኢያቡስም በቀረቡ ጊዜ ቀኑ መሸትሸት ብሎ ነበር። በመሆኑም አገልጋዩ ጌታውን “ወደዚህች የኢያቡሳውያን ከተማ ጎራ ብለን ብናድር አይሻልም?” አለው። +12 ጌታው ግን “እስራኤላውያን ወዳልሆኑ ባዕድ ሰዎች ከተማ መግባት የለብንም። ከዚህ ይልቅ እስከ ጊብዓ+ ድረስ እንሂድ” አለው። +13 ከዚያም አገልጋዩን “ና፣ ከእነዚህ ስፍራዎች ወደ አንዱ ለመድረስ እንሞክር፤ ጊብዓ ወይም ራማ+ እናድራለን” አለው። +14 በመሆኑም ጉዟቸውን ቀጠሉ፤ የቢንያም ወደሆነችው ወደ ጊብዓ በተቃረቡም ጊዜ ፀሐይዋ መጥለቅ ጀመረች። +15 ስለዚህ በጊብዓ ለማደር ወደዚያ ጎራ አሉ። ገብተውም በከተማዋ አደባባይ ተቀመጡ፤ ሆኖም ሊያሳድራቸው ወደ ቤቱ የወሰዳቸው ማንም ሰው አልነበረም።+ +16 በመጨረሻም ምሽት ላይ ከእርሻ ሥራው እየተመለሰ ያለ አንድ አረጋዊ ሰው መጣ። ይህ ሰው የኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ ሰው ነበር፤ በጊብዓም መኖር ከጀመረ የተወሰነ ጊዜ ሆኖታል፤ የከተማዋ ነዋሪዎች ግን ቢንያማውያን+ ነበሩ። +17 አረጋዊውም ቀና ብሎ መንገደኛውን ሰው በከተማዋ አደባባይ ሲያየው “ወዴት ነው የምትሄደው? የመጣኸውስ ከየት ነው?” አለው። +18 እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እኛ በይሁዳ ከምትገኘው ቤተልሔም ተነስተን በኤፍሬም ተራራማ አካባቢዎች ራቅ ብሎ ወደሚገኝ ስፍራ እየተጓዝን ነው፤ እኔ የዚያ አካባቢ ሰው ነኝ። በይሁዳ ወደምትገኘው ቤተልሔም+ ሄጄ ነበር፤ አሁን ወደ ይሖዋ ቤት እየሄድኩ ነው፤* ይሁንና ወደ ቤቱ የሚያስገባኝ ሰው አላገኘሁ +19 ለአህዮቻችን የሚሆን በቂ ገለባና ገፈራ አለን፤+ በተጨማሪም ለእኔም ሆነ ለሴትየዋ እንዲሁም ለአገልጋያችን የሚሆን ምግብና+ የወይን ጠጅ አለን። ምንም የጎደለ ነገር የለም።” +20 ሆኖም አረጋዊው ሰው “ሰላም ለአንተ ይሁን! የሚያስፈልጋችሁን ማንኛውንም ነገር እኔ አሟላላችኋለሁ። ብቻ እዚህ አደባባይ ላይ አትደሩ” አለው። +21 ስለዚህ ወደ ቤቱ ይዞት ገባ፤ ለአህዮቹም ገፈራ ሰጣቸው። ሰዎቹም እግራቸውን ታጠቡ፤ በሉ፣ ጠጡም። +22 እነሱም እየተደሰቱ ሳለ በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ የተወሰኑ ጋጠወጥ ወንዶች ቤቱን ከበው እርስ በርስ እየተገፈታተሩ በሩን ይደበድቡ ጀመር፤ የቤቱ ባለቤት የሆነውንም አረጋዊ “ከእሱ ጋር የፆታ ግንኙነት እንድንፈጽም ቤትህ የገባውን ሰው ወደ ውጭ አውጣልን” ይሉት ነበር።+ +23 በዚህ ጊዜ የቤቱ ባለቤት ወደ እነሱ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞቼ ተዉ፤ ይህን መጥፎ ድርጊት አትፈጽሙ። እባካችሁ ይህ ሰው የእኔ እንግዳ ነው። እንዲህ ያለውን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ። +24 ይኸው ድንግል የሆነች ልጄና የሰውየው ቁባት አሉ። እንግዲህ አሻፈረኝ ካላችሁ እነሱን ላውጣላችሁና ልታዋርዷቸው ትችላላችሁ።* + በዚህ ሰው ላይ ግን እንዲህ ያለውን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ።” +25 ሰዎቹ ግን ሊሰሙት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ በመሆኑም ሰውየው ቁባቱን+ ይዞ ወደ ውጭ አወጣላቸው። እነሱም ደፈሯት፤ እስኪነጋም ድረስ ሌሊቱን ሙሉ ሲጫወቱባት አደሩ። ከዚያም ጎህ ሲቀድ ለቀቋት። +26 ሴትየዋም በማለዳ መጥታ ጌታዋ ባለበት የሰውየው ቤት በር ላይ ተዘረረች፤ ብርሃን እስኪሆንም ድረስ እዚያው ወድቃ ቀረች። +27 በኋላም ጌታዋ ጉዞውን ለመቀጠል በጠዋት ተነስቶ የቤቱን በሮች ሲከፍት ሴትየዋ ማለትም ቁባቱ እጇ ደፉ ላይ ተዘርግቶ የቤቱ በር ላይ ወድቃ ተመለከተ። +28 እሱም “ተነሽ፤ እንሂድ” አላት። ነገር ግን ምንም መልስ አልነበረም። ከዚያም ሰውየው እሷን በአህያው ላይ አድርጎ ወደ ቤቱ ሄደ። +29 ቤቱም እንደደረሰ ቢላ አንስቶ ቁባቱን በአጥንቶቿ መገጣጠሚያ ላይ 12 ቦታ ቆራረጣት፤ ከዚያም ወደ እያንዳንዱ የእስራኤል ክ��ል አንድ ቁራጭ ላከ። +30 ይህን ያየ ሰው ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ ታይቶም፣ ተሰምቶም አያውቅም። ይህን ጉዳይ በቁም ነገር አስቡበት፤* ተመካከሩበት፤+ ከዚያም ምን መደረግ እንዳለበት ንገሩን።” +20 በመሆኑም ከዳን+ አንስቶ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ እንዲሁም በጊልያድ ምድር+ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ አንድ ላይ* በመውጣት በምጽጳ+ በይሖዋ ፊት ተሰበሰቡ። +"2 የሕዝቡና የእስራኤል ነገዶች አለቆች ሁሉ በእውነተኛው አምላክ ሕዝብ ጉባኤ መካከል ቦታ ቦታቸውን ይዘው ቆሙ፤ ሰይፍ የታጠቁት እግረኛ ወታደሮች 400,000 ነበሩ።+ " +3 ቢንያማውያንም የእስራኤል ሰዎች ወደ ምጽጳ መውጣታቸውን ሰሙ። ከዚያም የእስራኤል ሰዎች “ይህ ክፉ ነገር እንዴት ሊፈጸም እንደቻለ እስቲ ንገሩን?”+ አሏቸው። +4 በዚህ ጊዜ የተገደለችው ሴት ባል የሆነው ሌዋዊ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔና ቁባቴ የቢንያም በሆነችው በጊብዓ ለማደር ወደዚያ መጥተን ነበር።+ +5 የጊብዓ ነዋሪዎችም* በእኔ ላይ ተነሱብኝ፤ በሌሊት መጥተውም ቤቱን ከበቡ። ለመግደል ያሰቡት እኔን ነበር፤ ሆኖም ቁባቴን ደፈሯት፤ እሷም ሞተች።+ +6 እኔም የቁባቴን አስከሬን ወስጄ ቆራረጥኩት፤ ከዚያም ወደ እያንዳንዱ የእስራኤል ርስት ላክሁት፤+ ምክንያቱም እነሱ በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪና አስነዋሪ ድርጊት ፈጽመዋል። +7 እንግዲህ እናንተ እስራኤላውያን ሁሉ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ያላችሁን ሐሳብና አስተያየት ስጡ።”+ +8 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ አንድ ላይ* ሆኖ በመነሳት እንዲህ አለ፦ “ከመካከላችን ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ አይሄድም ወይም ወደ ቤቱ አይመለስም። +9 እንግዲህ በጊብዓ ላይ የምናደርገው ይህ ነው፦ ዕጣ እናወጣና እንዘምትባታለን።+ +"10 የቢንያም ግዛት የሆነችው የጊብዓ ነዋሪዎች በእስራኤል ውስጥ በፈጸሙት አሳፋሪ ድርጊት የተነሳ በእሷ ላይ ዘምቶ ተገቢውን እርምጃ ለሚወስደው ሠራዊት ስንቅ እንዲያዘጋጁ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ከ100ው 10፣ ከ1,000ው 100፣ ከ10,000ው ደግሞ 1,000 ሰዎችን እንወስዳለን።”" +11 በዚህ መንገድ የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ግንባር በመፍጠር በከተማዋ ላይ በአንድነት* ወጡ። +12 ከዚያም የእስራኤል ነገዶች ወደ ቢንያም ነገድ መሪዎች ሁሉ እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፦ “በመካከላችሁ የተፈጸመው ይህ ዘግናኝ ድርጊት ምንድን ነው? +13 በሉ አሁን በጊብዓ ያሉትን እነዚያን ጋጠወጥ ሰዎች+ እንድንገድላቸውና ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል እንድናስወግድ ሰዎቹን አሳልፋችሁ ስጡን።”+ ቢንያማውያን ግን ወንድሞቻቸውን እስራኤላውያንን ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም። +14 ከዚያም ቢንያማውያን ከእስራኤል ሰዎች ጋር ለመዋጋት ከየከተሞቹ ወጥተው በጊብዓ ተሰባሰቡ። +"15 ከተመረጡት 700 የጊብዓ ሰዎች በተጨማሪ በዚያ ቀን ሰይፍ የታጠቁ 26,000 ቢንያማውያን ከየከተሞቻቸው ተሰባሰቡ።" +16 በሠራዊቱም መካከል የተመረጡ 700 ግራኞች ነበሩ። እያንዳንዳቸውም ድንጋይ ወንጭፈው ፀጉር እንኳ የማይስቱ ነበሩ። +"17 የእስራኤል ሰዎች ደግሞ ቢንያምን ሳይጨምር ሰይፍ የታጠቁ 400,000 ሰዎች አሰባሰቡ፤+ እያንዳንዳቸውም ልምድ ያላቸው ተዋጊዎች ነበሩ።" +18 እነሱም አምላክን ለመጠየቅ ተነስተው ወደ ቤቴል ወጡ።+ ከዚያም የእስራኤል ሰዎች “ከቢንያማውያን ጋር ለሚደረገው ውጊያ ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። ይሖዋም “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ሲል መለሰ። +19 ከዚያም እስራኤላውያን በማለዳ ተነስተው ጊብዓን ከበቡ። +20 የእስራኤል ሰዎችም ቢንያምን ለመውጋት ወጡ፤ የእስራኤል ሰዎች እነሱን ጊብዓ ላይ ለመውጋት የጦ���ነት አሰላለፍ ይዘው ቆሙ። +"21 ቢንያማውያንም ከጊብዓ በመውጣት በዚያን ቀን ከእስራኤላውያን መካከል 22,000 ሰዎችን ገደሉ።" +22 ሆኖም የእስራኤላውያን ሠራዊት ልክ እንደ መጀመሪያው ቀን የጦርነት አሰላለፍ ይዞ አሁንም እዚያው ቦታ ላይ በድፍረት ቆመ። +23 ከዚያም እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በይሖዋ ፊት አለቀሱ፤ ይሖዋንም “ከወንድሞቻችን ከቢንያም ሰዎች ጋር ለመዋጋት እንደገና እንውጣ?” በማለት ጠየቁ።+ ይሖዋም “አዎ፣ በእነሱ ላይ ውጡ” አላቸው። +24 በመሆኑም እስራኤላውያን በሁለተኛው ቀን ወደ ቢንያማውያን ተጠጉ። +"25 ቢንያማውያንም በሁለተኛው ቀን እነሱን ለመግጠም ከጊብዓ ወጡ፤ ከእስራኤላውያንም መካከል ሰይፍ የታጠቁ ተጨማሪ 18,000 ሰዎችን ገደሉ።+" +26 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ወደ ቤቴል ወጡ። በዚያም እያለቀሱ በይሖዋ ፊት ተቀመጡ፤+ እንዲሁም በዚያ ቀን እስኪመሽ ድረስ ጾሙ፤+ በይሖዋም ፊት የሚቃጠሉ መባዎችንና+ የኅብረት መባዎችን+ አቀረቡ። +27 ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ይሖዋን ጠየቁ፤+ ምክንያቱም በዚያ ዘመን የእውነተኛው አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት የሚገኘው እዚያ ነበር። +28 የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስም+ በዚያ ዘመን በታቦቱ ፊት ያገለግል* ነበር። እነሱም “ወንድሞቻችንን የቢንያምን ሰዎች ለመውጋት እንደገና እንውጣ ወይስ እንቅር?” ሲሉ ጠየቁ።+ ይሖዋም “በነገው ዕለት እነሱን በእጃችሁ አሳልፌ ስለምሰጣችሁ ውጡ” በማለት መለሰላቸው። +29 ከዚያም እስራኤላውያን በጊብዓ ዙሪያ አድፍጠው የሚጠባበቁ+ ሰዎች አስቀመጡ። +30 በሦስተኛውም ቀን እስራኤላውያን ቢንያማውያንን ለመውጋት ወጡ፤ እንደ ሌሎቹ ጊዜያት ሁሉ ጊብዓን ለመውጋት የጦርነት አሰላለፍ ይዘው ቆሙ።+ +31 ቢንያማውያንም ሠራዊቱን ለመግጠም በወጡ ጊዜ ከከተማዋ ራቁ።+ ከዚያም እንደ ሌሎቹ ጊዜያት ሁሉ በአውራ ጎዳናዎቹ ማለትም ወደ ቤቴልና ወደ ጊብዓ በሚወስዱት አውራ ጎዳናዎች ላይ በነበሩት ሰዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር የተወሰኑ ሰዎችን ገደሉ፤ ወደ 30 ገደማ የሚሆኑ የእስራኤል ሰዎችን በሜዳው ላይ ገደሉ። +32 በመሆኑም ቢንያማውያን “እንደ በፊቱ ሁሉ አሁንም ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ።+ እስራኤላውያን ግን “እየሸሸን ከከተማው ርቀው ወደ አውራ ጎዳናዎቹ እንዲመጡ እናድርጋቸው” አሉ። +33 ስለሆነም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ከነበሩበት ተነስተው በመሄድ በዓልታማር ላይ የጦርነት አሰላለፍ ይዘው ቆሙ፤ በዚህ ጊዜ አድፍጠው የነበሩት እስራኤላውያን ተደብቀውበት ከነበረው ከጊብዓ አቅራቢያ ተንደርድረው ወጡ። +"34 በዚህ መንገድ ከመላው እስራኤል የተውጣጡ 10,000 የተመረጡ ወንዶች ወደ ጊብዓ ፊት ለፊት መጡ፤ ከባድ ውጊያም ተካሄደ። ሆኖም ቢንያማውያን ጥፋት እያንዣበበባቸው መሆኑን አላወቁም ነበር። " +"35 ይሖዋ ቢንያምን በእስራኤል ፊት ድል አደረገው፤+ በዚያም ቀን እስራኤላውያን ሰይፍ የታጠቁ 25,100 ቢንያማውያንን ገደሉ።+ " +36 ይሁንና ቢንያማውያን የእስራኤል ሰዎች ከእነሱ ሲያፈገፍጉ ድል እያደረጓቸው ያሉ መስሏቸው ነበር፤+ ሆኖም እስራኤላውያን ያፈገፈጉት በጊብዓ ላይ ባደፈጡት ሰዎች ተማምነው ነበር።+ +37 አድፍጠው የነበሩትም ሰዎች በፍጥነት እየተንደረደሩ ወደ ጊብዓ ሄዱ። ከዚያም በየቦታው ተሰራጭተው ከተማዋን በሙሉ በሰይፍ መቱ። +38 የእስራኤልም ሰዎች አድፍጠው በከተማዋ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩት ተዋጊዎች ከከተማዋ ጭስ እንዲወጣ በማድረግ ምልክት እንዲያሳዩአቸው ተስማምተው ነበር። +39 እስራኤላውያንም ከውጊያው ሲያፈገፍጉ የቢንያም ሰዎች ጥቃት በመሰንዘር ከእስራኤላውያን መካከል ወደ 30 ገደማ የሚሆኑ ሰዎችን ገደሉ፤+ እነሱም “ልክ እንደ መጀመሪያው ውጊያ ሁሉ አሁንም ድል እያደረግናቸው መሆኑ ግልጽ ነው” ይሉ ነበር።+ +40 ሆኖም ምልክት ሆኖ የሚያገለግለው ጭስ እንደ ዓምድ በመሆን ከከተማዋ ይወጣ ጀመር። የቢንያምም ሰዎች ዞር ብለው ሲመለከቱ የመላ ከተማዋ ነበልባል ወደ ሰማይ ሲንቀለቀል አዩ። +41 ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ የቢንያምም ሰዎች መጥፊያቸው እንደቀረበ ስላወቁ ተደናገጡ። +42 በመሆኑም ከእስራኤል ሰዎች በመሸሽ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ ሆኖም ከከተሞቹ የወጡትም ሰዎች በእነሱ ላይ ጥቃት መሰንዘር ስለጀመሩ ከውጊያው ማምለጥ አልቻሉም። +43 እነሱም ቢንያማውያኑን ከበቧቸው፤ ያለእረፍትም አሳደዷቸው። ከዚያም ጊብዓ ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ባለው ስፍራ ደመሰሷቸው። +"44 በመጨረሻም 18,000 የቢንያም ሰዎች ረገፉ፤ ሁሉም ኃያል ተዋጊዎች ነበሩ።+ " +"45 የቢንያም ሰዎችም ዞረው በምድረ በዳው ወደሚገኘው የሪሞን ዓለት+ ሸሹ፤ እስራኤላውያንም 5,000 ሰዎችን በአውራ ጎዳናዎቹ ላይ ገደሉባቸው፤* እስከ ጊድኦምም ድረስ አሳደዷቸው፤ በመሆኑም ተጨማሪ 2,000 ሰዎችን ገደሉ።" +"46 በዚያ ቀን የተገደሉት ሰይፍ የታጠቁ ቢንያማውያን ቁጥር በአጠቃላይ 25,000 ደረሰ፤+ ሁሉም ኃያል ተዋጊዎች ነበሩ።" +47 ሆኖም 600 ሰዎች በምድረ በዳው ወደሚገኘው የሪሞን ዓለት ሸሹ፤ በሪሞን ዓለትም ለአራት ወር ተቀመጡ። +48 የእስራኤልም ሰዎች በቢንያማውያን ላይ ተመልሰው በመምጣት ከሰው አንስቶ እስከ እንስሳ ድረስ በከተማዋ ውስጥ የቀረውን ሁሉ በሰይፍ መቱ። በተጨማሪም በመንገዳቸው ላይ ያገኟቸውን ከተሞች በሙሉ በእሳት አቃጠሉ። +3 ይሖዋ ከከነአን ጋር በተደረገው ጦርነት ያልተካፈሉትን እስራኤላውያን ሁሉ እንዲፈትኗቸው+ ሲል በምድሪቱ ላይ እንዲኖሩ የፈቀደላቸው ብሔራት እነዚህ ናቸው +2 (ይህን ያደረገው ከዚህ በፊት ተዋግተው የማያውቁት በኋላ ላይ የመጡት የእስራኤላውያን ትውልዶች የውጊያ ልምድ እንዲያገኙ ነው)፦ +3 አምስቱ የፍልስጤም+ ገዢዎች፣ ከነአናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያን+ እንዲሁም ከበዓልሄርሞን ተራራ አንስቶ እስከ ሌቦሃማት* + ድረስ በሚዘልቀው የሊባኖስ+ ተራራ የሚኖሩት ሂዋውያን።+ +4 እነዚህ ብሔራት እስራኤላውያን ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ለአባቶቻቸው የሰጣቸውን ትእዛዛት ይጠብቁ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ የእስራኤላውያን መፈተኛ ሆነው አገልግለዋል።+ +5 በመሆኑም እስራኤላውያን በከነአናውያን፣ በሂታውያን፣ በአሞራውያን፣ በፈሪዛውያን፣ በሂዋውያን እና በኢያቡሳውያን መካከል ይኖሩ ነበር።+ +6 እነሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ያገቡ፣ የራሳቸውንም ሴቶች ልጆች ለእነሱ ወንዶች ልጆች ይድሩ የነበረ ሲሆን የእነሱን አማልክትም ማገልገል ጀመሩ።+ +7 ስለዚህ እስራኤላውያን በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤ አምላካቸውን ይሖዋንም ረሱ፤ ባአልንና+ የማምለኪያ ግንዶችን* + አገለገሉ። +8 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ለሜሶጶጣሚያው* ንጉሥ ለኩሻንሪሻታይምም አሳልፎ ሸጣቸው። እስራኤላውያን ኩሻንሪሻታይምን ለስምንት ዓመት አገለገሉት። +9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ +10 የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤+ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን* ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት። +11 ከዚያ በኋላ ምድሪቱ ለ40 ዓመት አረፈች።* ከዚያም የቀናዝ ልጅ ኦትኒኤል ሞተ። +12 እስራኤላውያንም እንደገና በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር ማድረግ ጀመሩ።+ ስለዚህ ይሖዋ የሞዓብ+ ንጉሥ ኤግሎን በእስራኤላውያን ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ፤ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አድርገው ነበር። +13 በተጨማሪም አሞናውያንንና+ አማሌቃውያንን+ በእነሱ ላይ አመጣባቸው። እነሱም በእስራኤላውያን ላይ ጥቃት በመሰንዘር የዘንባባ ዛፎች ከተማን+ ያዙ። +14 እስራኤላውያንም የሞዓብን ንጉሥ ኤግሎንን 18 ዓመት አገለገሉ።+ +15 ከዚያም እስራኤላውያን ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ ጮኹ፤+ ይሖዋም ግራኝ+ የሆነውን ቢንያማዊውን+ የጌራን ልጅ ኤሁድን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳላቸው።+ ከጊዜ በኋላ እስራኤላውያን በእሱ በኩል ለሞዓብ ንጉሥ ለኤግሎን ግብር ላኩ። +16 በዚህ ጊዜ ኤሁድ ርዝመቱ አንድ ክንድ* የሆነ በሁለት በኩል ስለት ያለው ሰይፍ ሠርቶ ከልብሱ ሥር በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው። +17 ከዚያም ግብሩን ለሞዓብ ንጉሥ ለኤግሎን አቀረበ። ኤግሎን በጣም ወፍራም ነበር። +18 ኤሁድ ግብሩን ሰጥቶ እንደጨረሰ ግብሩን ተሸክመው የመጡትን ሰዎች አሰናበታቸው። +19 እሱ ግን በጊልጋል+ የሚገኙት የተቀረጹ ምስሎች* ጋ ሲደርስ ተመልሶ በመሄድ “ንጉሥ ሆይ፣ በሚስጥር የምነግርህ አንድ መልእክት አለኝ” አለ። ንጉሡም “እስቲ አንዴ ጸጥታ!” አለ። በዚህ ጊዜ አገልጋዮቹ ሁሉ ጥለውት ወጡ። +20 ንጉሡ፣ ሰገነት ላይ በሚገኘው ቀዝቀዝ ያለ የግል ክፍሉ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ወደ እሱ ቀረበ። ከዚያም ኤሁድ “ከአምላክ ዘንድ ለአንተ የመጣ መልእክት አለኝ” አለው። በዚህ ጊዜ ንጉሡ ከዙፋኑ* ተነሳ። +21 ስለዚህ ኤሁድ ግራ እጁን ሰዶ በቀኝ ጭኑ በኩል የነበረውን ሰይፍ በመምዘዝ በንጉሡ ሆድ ውስጥ ሻጠው። +22 ከስለቱ በኋላም እጀታው ሆዱ ውስጥ ገባ፤ ኤሁድ ሰይፉን ከሆዱ መልሶ ስላላወጣው ስለቱ በስብ ተሸፈነ፤ ፈርሱም ተዘረገፈ። +23 ኤሁድም በበረንዳው* በኩል ወጣ፤ ሰገነት ላይ ያለውን ክፍል በሮች ግን ዘግቶ ቆልፏቸው ነበር። +24 እሱም ከሄደ በኋላ አገልጋዮቹ መጥተው ሲያዩ ሰገነት ላይ ያለው ክፍል በሮች ተቆልፈው ነበር። በመሆኑም “ቀዝቀዝ ባለው ውስጠኛ ክፍል እየተጸዳዳ* ይሆናል” አሉ። +25 እነሱም እስኪያፍሩ ድረስ ጠበቁ፤ ሆኖም ሰገነት ላይ የሚገኘውን ክፍል በሮች እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ ቁልፉን ወስደው በሮቹን ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ ወለል ላይ ተዘርሮ ተመለከቱ! +26 ኤሁድ ግን እነሱ ቆመው ሲጠባበቁ ሳለ አመለጠ፤ በተቀረጹት ምስሎች* + በኩል አድርጎም በሰላም ወደ ሰኢራ ደረሰ። +27 እዚያም እንደደረሰ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ ቀንደ መለከት ነፋ፤+ እስራኤላውያንም ከተራራማው አካባቢ ወጥተው በእሱ መሪነት አብረውት ወረዱ። +28 ከዚያም “ይሖዋ ጠላቶቻችሁን ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ተከተሉኝ” አላቸው። እነሱም ተከትለውት በመሄድ ሞዓባውያን እንዳይሻገሩ የዮርዳኖስን መልካዎች* ያዙባቸው፤ አንድም ሰው እንዲሻገር አልፈቀዱም። +"29 በዚያን ጊዜም ጠንካራና ጀግና የሆኑ 10,000 ሞዓባውያንን ገደሉ፤+ አንድም ሰው አላመለጠም።+" +30 በዚያ ቀን ሞዓብ በእስራኤል እጅ ተንበረከከ፤ ምድሪቱም ለ80 ዓመት አረፈች።* + +31 ከእሱ በኋላ፣ 600 ፍልስጤማውያንን+ በከብት መውጊያ+ የገደለው የአናት ልጅ ሻምጋር+ ተነሳ፤ እሱም እስራኤልን አዳነ። +7 ከዚያም የሩባአል የተባለው ጌድዮንና+ ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በሙሉ በማለዳ ተነስተው በሃሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ፤ የምድያማውያን ሰፈር ደግሞ ከእሱ በስተ ሰሜን በሞሬ ኮረብታ በሸለቋማው ሜዳ* ላይ ይገኝ ነበር። +2 ይሖዋም ጌድዮንን እንዲህ አለው፦ “ምድያማውያንን በእጃቸው አሳልፌ እንዳልሰጥ አብረውህ ያሉት ሰዎች በጣም ብዙ ናቸው።+ ይህን ባደርግ እስራኤላውያን ‘የገዛ እጄ አዳ��ኝ’+ ብለው ይታበዩብኛል። +"3 በመሆኑም እባክህ ሕዝቡ በተሰበሰበበት ‘ከመካከላችሁ የፈራና የተሸበረ ካለ ወደ ቤት ይመለስ’ ብለህ ተናገር።”+ ስለዚህ ጌድዮን ፈተናቸው። በዚህ ጊዜ ከሕዝቡ መካከል 22,000 ሰዎች ወደ ቤታቸው ተመለሱና 10,000 ብቻ ቀሩ። " +4 ይሖዋም እንደገና ጌድዮንን እንዲህ አለው፦ “አሁንም ሰዎቹ በጣም ብዙ ናቸው። በዚያ እነሱን እንድፈትንልህ ወደ ውኃው ይዘሃቸው ውረድ። እኔም ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሄዳል’ የምልህ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሄድም’ የምልህ ግን ከአንተ ጋር አይሄድም።” +5 እሱም ሰዎቹን ወደ ውኃው ይዟቸው ወረደ። ከዚያም ይሖዋ ጌድዮንን “ልክ እንደ ውሻ ውኃውን በምላሱ እየጨለፈ የሚጠጣውን ሁሉ በጉልበታቸው ተንበርክከው ከሚጠጡት ለይ” አለው። +6 ውኃውን በእጃቸው እየጨለፉ የሚጠጡት ሰዎች ቁጥር 300 ነበር። የቀሩት ሰዎች ሁሉ ግን ውኃ ለመጠጣት በጉልበታቸው ተንበረከኩ። +7 ይሖዋም ጌድዮንን እንዲህ አለው፦ “ውኃውን በእጃቸው እየጨለፉ በጠጡት 300 ሰዎች አድናችኋለሁ፤ ምድያማውያንንም በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።+ የቀሩት ሰዎች ሁሉ ግን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አሰናብታቸው።” +8 በመሆኑም ከሕዝቡ ላይ ስንቃቸውንና ቀንደ መለከታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ጌድዮን 300ዎቹን ብቻ አስቀርቶ ሌሎቹን እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው። የምድያማውያኑ ሰፈር የሚገኘው ከእሱ በታች በሸለቋማው ሜዳ ላይ ነበር።+ +9 በዚያ ምሽት ይሖዋ ጌድዮንን እንዲህ አለው፦ “ተነስ፤ በእጅህ አሳልፌ ስለሰጠሁህ በሰፈሩ ላይ ጥቃት ሰንዝር።+ +10 በሰፈሩ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ከፈራህ ግን ከአገልጋይህ ከፑራ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ። +11 የሚናገሩትንም ነገር አዳምጥ፤ ከዚያም በሰፈሩ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ድፍረት ታገኛለህ።”* ስለዚህ እሱና አገልጋዩ ፑራ ወርደው ሠራዊቱ ወደሰፈረበት ቦታ ተጠጉ። +12 ምድያማውያንና አማሌቃውያን እንዲሁም የምሥራቅ ሰዎች በሙሉ+ ሸለቋማውን ሜዳ ልክ እንደ አንበጣ መንጋ ወረውት ነበር፤ ግመሎቻቸውም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ለቁጥር የሚያታክቱ ነበሩ።+ +13 ጌድዮንም እዚያ ደረሰ፤ በዚህ ጊዜ አንድ ሰው ለጓደኛው እንዲህ በማለት አንድ ሕልም እየነገረው ነበር፦ “ያለምኩት ሕልም ይህ ነው። አንድ የገብስ ዳቦ እየተንከባለለ ወደ ምድያም ሰፈር መጣ። ከዚያም ወደ አንድ ድንኳን በመምጣት በኃይል መትቶ ጣለው።+ ድንኳኑንም ገለበጠው፤ ድንኳኑም መሬት ላይ ተነጠፈ። +14 ጓደኛውም እንዲህ አለው፦ “ይሄማ ከዮአስ ልጅ ከእስራኤላዊው ከጌድዮን ሰይፍ በስተቀር ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም።+ አምላክ ምድያማውያንንና ሰፈሩን በሙሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶታል።”+ +15 ጌድዮንም ሕልሙንና ፍቺውን ሲሰማ ለአምላክ ሰገደ።+ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ተመልሶ “ተነሱ፤ ይሖዋ የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷችኋል” አላቸው። +16 በመቀጠልም 300ዎቹን ሰዎች በሦስት ቡድን ከፈላቸው፤ ለሁሉም ቀንደ መለከትና+ በውስጣቸው ችቦ ያለባቸው ትላልቅ ባዶ ማሰሮዎች ሰጣቸው። +17 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ልብ ብላችሁ ተመልከቱኝ፤ እኔ የማደርገውንም አድርጉ። ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በምጠጋበት ጊዜ ልክ እኔ እንደማደርገው አድርጉ። +18 እኔና ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከቶቻችንን ስንነፋ እናንተም በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለከቶቻችሁን ነፍታችሁ ‘ለይሖዋና ለጌድዮን!’ ብላችሁ ጩኹ።” +19 ከዚያም ጌድዮንና ከእሱ ጋር የነበሩት 100 ሰዎች በመካከለኛው ክፍለ ሌሊት* መጀመሪያ ላይ ዘብ ጠባቂዎቹ ገና እንደተቀያየሩ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ ተጠጉ። እነሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤+ የያዟቸውንም ትላልቅ የውኃ ማሰሮዎች ሰባበሩ።+ +20 በዚህ ጊዜ ሦስቱም ቡድኖች ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ ትላልቆቹንም ማሰሮዎች ሰባበሩ። ችቦዎቹን በግራ እጃቸው ይዘው በቀኝ እጃቸው የያዟቸውን ቀንደ መለከቶች እየነፉ “የይሖዋና የጌድዮን ሰይፍ!” በማለት ጮኹ። +21 እያንዳንዱም ሰው በሰፈሩ ዙሪያ ቦታ ቦታውን ይዞ ቆሞ ነበር፤ ሠራዊቱም ሁሉ ሮጠ፤ እየጮኸም ሸሸ።+ +22 ሦስት መቶዎቹ ሰዎችም ቀንደ መለከቶቹን መንፋታቸውን ቀጠሉ፤ ይሖዋም በሰፈሩ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤+ ሠራዊቱም በጸሬራህ አቅጣጫ እስከ ቤትሺጣ እንዲሁም ከጣባት አጠገብ እስከምትገኘው እስከ አቤልምሆላ+ ዳርቻ ድረስ ሸሸ። +23 እስራኤላውያንም ከንፍታሌም፣ ከአሴርና ከመላው ምናሴ+ ተጠርተው አንድ ላይ በመሰባሰብ ምድያማውያንን አሳደዷቸው። +24 ጌድዮንም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሁሉ “በምድያማውያን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ውረዱ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያሉትን ውኃዎችና ዮርዳኖስን ያዙ” ብለው እንዲነግሯቸው መልእክተኞችን ላከ። በመሆኑም የኤፍሬም ሰዎች በሙሉ ተጠሩ፤ እነሱም እስከ ቤትባራ ድረስ ያሉትን ውኃዎችና ዮርዳኖስን ያዙ። +25 በተጨማሪም ሁለቱን የምድያም መኳንንት ማለትም ኦሬብን+ እና ዜብን ያዙ፤ ኦሬብን በኦሬብ ዓለት ላይ ገደሉት፤ ዜብን ደግሞ በዜብ የወይን መጭመቂያ ላይ ገደሉት። ምድያማውያንንም ማሳደዳቸውን ተያያዙት፤+ የኦሬብን እና የዜብን ጭንቅላት በዮርዳኖስ አካባቢ ወደነበረው ወደ ጌድዮን አመጡ። +12 ከዚያም የኤፍሬም ሰዎች አንድ ላይ ተሰባስበው ወደ ጻፎን* በመሻገር ዮፍታሔን “አሞናውያንን ለመውጋት ስትሻገር አብረንህ እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምንድን ነው?+ ቤትህን በላይህ ላይ በእሳት እናቃጥለዋለን” አሉት። +2 ዮፍታሔ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እኔና ሕዝቤ ከአሞናውያን ጋር በከፍተኛ ሁኔታ ተጋጭተን ነበር። እኔም እንድትረዱኝ ጠርቻችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ከእጃቸው አላዳናችሁኝም። +3 እኔም እንደማታድኑኝ ስመለከት ሕይወቴን አደጋ ላይ ጥዬ* በአሞናውያን ላይ ለመዝመት ወሰንኩ፤+ ይሖዋም እነሱን በእጄ አሳልፎ ሰጣቸው። ታዲያ ዛሬ ልትወጉኝ የወጣችሁት ለምንድን ነው?” +4 ከዚያም ዮፍታሔ የጊልያድን+ ሰዎች ሁሉ አሰባስቦ ከኤፍሬም ጋር ተዋጋ፤ የጊልያድም ሰዎች ኤፍሬማውያንን ድል አደረጓቸው፤ ኤፍሬማውያን የጊልያድን ሰዎች “በኤፍሬምና በምናሴ የምትኖሩ እናንተ የጊልያድ ሰዎች፣ እናንተ እኮ ከኤፍሬም ሸሽታችሁ ያመለጣችሁ ስደተኞች ናችሁ” ይሏቸው ነበር። +5 ጊልያዳውያንም ከኤፍሬማውያን ፊት ለፊት የሚገኘውን የዮርዳኖስን+ መልካ* ተቆጣጠሩ፤ የኤፍሬምም ሰዎች ለማምለጥ በሚሞክሩበት ጊዜ “እንድሻገር ፍቀዱልኝ” ይላሉ፤ በዚህ ጊዜ የጊልያድ ሰዎች እያንዳንዱን ሰው “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ እሱም “አይ፣ አይደለሁም” ብሎ ሲመልስላቸው +"6 “እስቲ ሺቦሌት በል” ይሉታል። እሱ ግን ቃሉን በትክክል መጥራት ስለማይችል “ሲቦሌት” ይላል። እነሱም ይዘው እዚያው ዮርዳኖስ መልካ ላይ ይገድሉታል። በመሆኑም በዚያን ጊዜ 42,000 ኤፍሬማውያን አለቁ። " +7 ዮፍታሔም በእስራኤል ውስጥ ለስድስት ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ፤ ከዚያም ጊልያዳዊው ዮፍታሔ ሞተ፤ በጊልያድ በምትገኘው ከተማውም ተቀበረ። +8 ከእሱም በኋላ የቤተልሔሙ ኢብጻን በእስራኤል ውስጥ ፈራጅ ሆኖ አገለገለ።+ +9 ኢብጻን 30 ወንዶችና 30 ሴቶች ልጆች ነበሩት። እሱም ሴቶች ልጆቹን ከጎሳው ውጭ የሆኑ ሰዎችን እንዲያገቡ ላካቸው፤ እንዲሁም ከወንዶች ልጆቹ ጋር እንዲጋቡ ከጎሳው ውጭ የሆኑ 30 ሴቶችን አስመጣ። በእስራኤልም ውስጥ ለሰ���ት ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። +10 ከዚያም ኢብጻን ሞተ፤ በቤተልሔምም ተቀበረ። +11 ከእሱም በኋላ ዛብሎናዊው ኤሎን በእስራኤል ውስጥ ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። እሱም በእስራኤል ውስጥ ለአሥር ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። +12 ከዚያም ዛብሎናዊው ኤሎን ሞተ፤ በዛብሎን ምድር በአይሎንም ተቀበረ። +13 ከእሱም በኋላ የጲራቶናዊው የሂሌል ልጅ አብዶን በእስራኤል ውስጥ ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። +14 እሱም በ70 አህዮች የሚጋልቡ 40 ወንዶች ልጆችና 30 የልጅ ልጆች ነበሩት። በእስራኤልም ውስጥ ለስምንት ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። +15 ከዚያም የጲራቶናዊው የሂሌል ልጅ አብዶን ሞተ፤ በአማሌቃውያን+ ተራራ በኤፍሬም ምድር በምትገኘው በጲራቶንም ተቀበረ። +1 ኢያሱ+ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን* “ከከነአናውያን ጋር ለመዋጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” በማለት ይሖዋን ጠየቁ።+ +2 ይሖዋም “ይሁዳ ይውጣ።+ እኔም ምድሪቱን በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ”* አለ። +3 ከዚያም ይሁዳ ወንድሙን ስምዖንን “ከከነአናውያን ጋር ለመዋጋት ወደተመደበልኝ ርስት* + አብረኸኝ ውጣ። እኔም ደግሞ በዕጣ ወደደረሰህ ርስት አብሬህ እሄዳለሁ” አለው። ስለዚህ ስምዖን አብሮት ሄደ። +"4 ይሁዳም በወጣ ጊዜ ይሖዋ ከነአናውያንንና ፈሪዛውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤+ በመሆኑም ቤዜቅ ላይ 10,000 ሰዎችን ድል አደረጉ።" +5 አዶኒቤዜቅን ቤዜቅ ላይ ባገኙት ጊዜ በዚያ ከእሱ ጋር ተዋጉ፤ ከነአናውያንንና+ ፈሪዛውያንንም+ ድል አደረጉ። +6 አዶኒቤዜቅም በሸሸ ጊዜ አሳደው ያዙት፤ ከዚያም የእጆቹንና የእግሮቹን አውራ ጣቶች ቆረጡ። +7 አዶኒቤዜቅም እንዲህ አለ፦ “የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣቶች የተቆረጡባቸው ከገበታዬ ሥር ሆነው ፍርፋሪ የሚለቃቅሙ 70 ነገሥታት ነበሩ። አምላክም ልክ እኔ እንዳደረግኩት አደረገብኝ።” ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤+ እሱም በዚያ ሞተ። +8 በተጨማሪም የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወግተው በቁጥጥር ሥር አዋሏት፤+ ከተማዋንም በሰይፍ መትተው በእሳት አቃጠሏት። +9 ከዚያም የይሁዳ ሰዎች በተራራማው አካባቢ፣ በኔጌብና በሸፌላ+ ከሚኖሩት ከነአናውያን ጋር ለመዋጋት ወረዱ። +10 በመሆኑም ይሁዳ በኬብሮን ይኖሩ በነበሩት ከነአናውያን ላይ ዘመተ (ኬብሮን ቀደም ሲል ቂርያትአርባ ተብላ ትጠራ ነበር)፤ እነሱም ሸሻይን፣ አሂማንን እና ታልማይን መቱ።+ +11 ከዚያም ተነስተው በደቢር ነዋሪዎች ላይ ዘመቱ።+ (ደቢር ቀደም ሲል ቂርያትሰፈር ትባል ነበር።)+ +12 ካሌብም+ “ቂርያትሰፈርን መትቶ በቁጥጥር ሥር ላደረጋት ሰው ሴት ልጄን አክሳን እድርለታለሁ” አለ።+ +13 የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነው የቀናዝ+ ልጅ ኦትኒኤልም+ ከተማዋን በቁጥጥር ሥር አደረጋት። ስለሆነም ካሌብ ሴት ልጁን አክሳን ዳረለት። +14 እሷም ወደ ባሏ ቤት እየሄደች ሳለ ባሏን ከአባቷ መሬት እንዲጠይቅ ወተወተችው። ከዚያም ከአህያዋ ላይ ወረደች።* በዚህ ጊዜ ካሌብ “ምን ፈለግሽ?” ሲል ጠየቃት። +15 እሷም “የሰጠኸኝ በስተ ደቡብ* ያለ ቁራሽ መሬት ስለሆነ እባክህ ባርከኝ፤ ጉሎትማይምንም* ስጠኝ” አለችው። በመሆኑም ካሌብ ላይኛውን ጉሎት እና ታችኛውን ጉሎት ሰጣት። +16 የቄናዊው+ የሙሴ አማት+ ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባ ዛፎች ከተማ+ ወጥተው ከአራድ+ በስተ ደቡብ ወደሚገኘው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ አቀኑ። እነሱም ወደዚያ ሄደው ከሕዝቡ ጋር መኖር ጀመሩ።+ +17 ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር በመዝመት በጸፋት በሚኖሩት ከነአናውያን ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ ከተማዋንም ሙሉ በሙሉ ደመሰሱ።+ በመሆኑም ከተማዋን ሆርማ* + ብለው ሰየሟት። +18 ከዚያም ይሁዳ ጋዛንና+ ግዛቶቿን፣ አስቀሎንንና+ ግዛቶቿን እንዲሁም ኤቅ���ንንና+ ግዛቶቿን ተቆጣጠረ። +19 ይሖዋ ከይሁዳ ጋር ስለነበር ይሁዳ ተራራማውን አካባቢ ወረሰ፤ በሜዳው* ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ግን ማባረር አልቻሉም፤ ምክንያቱም እነሱ የብረት ማጭድ የተገጠመላቸው የጦር ሠረገሎች* ነበሯቸው።+ +20 ሙሴ ቃል በገባው መሠረት ኬብሮንን ለካሌብ ሰጡት፤+ እሱም ሦስቱን የኤናቅ ልጆች ከዚያ አባረራቸው።+ +21 ቢንያማውያን ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከዚያ አላስወጧቸውም ነበር፤ በመሆኑም ኢያቡሳውያኑ ከቢንያማውያን ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም አብረው ይኖራሉ።+ +22 በዚህ ጊዜ የዮሴፍ ቤት+ ቤቴልን ለመውጋት ወጣ፤ ይሖዋም ከእነሱ ጋር ነበር።+ +23 የዮሴፍ ቤት ቤቴልን እየሰለለ ነበር (ቤቴል ቀደም ሲል ሎዛ ተብላ ትጠራ ነበር)፤+ +24 ሰላዮቹም አንድ ሰው ከከተማዋ ሲወጣ አዩ። በመሆኑም “እባክህ ወደ ከተማዋ የሚያስገባውን መንገድ አሳየን፤ እኛም ደግነት እናደርግልሃለን”* አሉት። +25 በመሆኑም ሰውየው ወደ ከተማዋ የሚያስገባውን መንገድ አሳያቸው፤ እነሱም የከተማዋን ነዋሪዎች በሰይፍ መቱ፤ ይሁንና ሰውየውንና ቤተሰቡን በሙሉ ነፃ ለቀቋቸው።+ +26 ሰውየውም ወደ ሂታውያን ምድር ሄዶ ከተማ ገነባ፤ ከተማዋንም ሎዛ ብሎ ጠራት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ስሟ ይኸው ነው። +27 ምናሴ ቤትሼንንና በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ ታአናክንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች፣ የዶርን ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉትን ከተሞች፣ የይብለአምን ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም የመጊዶን ነዋሪዎችና በሥሯ ያሉትን ከተሞች አልወረሰም ነበር።+ ከነአናውያን ይህን ምድር ላለመልቀቅ ቆርጠው ነበር። +28 እስራኤላውያንም እያየሉ በሄዱ ጊዜ ከነአናውያንን የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው+ እንጂ ሙሉ በሙሉ አላባረሯቸውም።+ +29 ኤፍሬምም ቢሆን በጌዜር ይኖሩ የነበሩትን ከነአናውያን አላባረራቸውም። ከነአናውያን በጌዜር አብረዋቸው ይኖሩ ነበር።+ +30 ዛብሎንም የቂትሮንን ነዋሪዎችና የናሃሎልን+ ነዋሪዎች አላባረራቸውም። ከነአናውያን አብረዋቸው ይኖሩ የነበረ ሲሆን የግዳጅ ሥራም እንዲሠሩ ተገደው ነበር።+ +31 አሴር የአኮን ነዋሪዎች እንዲሁም የሲዶናን፣+ የአህላብን፣ የአክዚብን፣+ የሄልባን፣ የአፊቅን+ እና የሬሆብን+ ነዋሪዎች አላባረራቸውም። +32 በመሆኑም አሴራውያን በምድሩ ይኖሩ ከነበሩት ከነአናውያን ጋር አብረው መኖራቸውን ቀጠሉ፤ ምክንያቱም አላባረሯቸውም ነበር። +33 ንፍታሌም የቤትሼሜሽን ነዋሪዎችና የቤትአናትን ነዋሪዎች+ አላባረራቸውም፤ ከዚህ ይልቅ በምድሩ ይኖሩ ከነበሩት ከነአናውያን ጋር አብረው ኖሩ።+ የቤትሼሜሽ ነዋሪዎችና የቤትአናት ነዋሪዎች የግዳጅ ሥራ ይሠሩላቸው ነበር። +34 ዳናውያን ወደ ሜዳው* እንዲወርዱ አሞራውያን ስላልፈቀዱላቸው በተራራማው አካባቢ ተወስነው ለመኖር ተገደዱ።+ +35 አሞራውያን የሃሬስ ተራራን፣ አይሎንን+ እና ሻአልቢምን+ አንለቅም በማለት በዚያ መኖራቸውን ቀጠሉ። ይሁንና የዮሴፍ ቤት ኃይሉ* እየጨመረ* በመጣ ጊዜ የጉልበት ሥራ ለመሥራት ተገደዱ። +36 የአሞራውያን ክልል ከአቅራቢም አቀበትና+ ከሴላ አንስቶ ወደ ላይ ያለው ነበር። +8 ከዚያም የኤፍሬም ሰዎች ጌድዮንን “እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ታደርግብናለህ? ከምድያማውያን ጋር ለመዋጋት ስትወጣ ያልጠራኸን ለምንድን ነው?”+ አሉት። የመረረ ጥልም ተጣሉት።+ +2 እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ካደረጋችሁት ጋር ሲነጻጸር እኔ ምን አደረግኩ? የኤፍሬም ቃርሚያ+ ከአቢዔዜር+ የወይን መከር አይሻልም? +3 አምላክ የምድያማውያንን መኳንንት ኦሬብን እና ዜብን አሳልፎ የሰጠው ለእናንተ ነው፤+ ታዲያ እናንተ ካደረጋችሁት ጋር ሲነጻጸር እኔ ��ን አደረግኩ?” እነሱም በዚህ መንገድ ሲያነጋግራቸው* ቁጣቸው በረደ።* +4 ከዚያም ጌድዮን ወደ ዮርዳኖስ መጥቶ ወንዙን ተሻገረ። እሱም ሆነ ከእሱ ጋር የነበሩት 300 ሰዎች ደክሟቸው የነበረ ቢሆንም ጠላቶቻቸውን ከማሳደድ ወደኋላ አላሉም ነበር። +5 ስለዚህ ጌድዮን የሱኮትን ሰዎች “የምድያማውያን ነገሥታት የሆኑትን ዘባህን እና ጻልሙናን በማሳደድ ላይ ስለሆንኩና የሚከተሉኝም ሰዎች ስለደከማቸው እባካችሁ ዳቦ ስጧቸው” አላቸው። +6 የሱኮት መኳንንት ግን “ለሠራዊትህ ዳቦ የምንሰጠው ለመሆኑ የዘባህ እና የጻልሙና መዳፍ እጅህ ገብቷል?” አሉት። +7 በዚህ ጊዜ ጌድዮን “እንግዲያው ይሖዋ ዘባህን እና ጻልሙናን በእጄ አሳልፎ ሲሰጠኝ በምድረ በዳ እሾህና አሜኬላ ሥጋችሁን እተለትላለሁ”+ አላቸው። +8 ከዚያም ወደ ጰኑኤል ወጣ፤ ለእነሱም ተመሳሳይ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ የጰኑኤል ሰዎችም የሱኮት ሰዎች የሰጡትን ዓይነት መልስ ሰጡት። +9 ስለዚህ የጰኑኤልንም ሰዎች “በሰላም በምመለስበት ጊዜ ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ”+ አላቸው። +"10 በዚህ ጊዜ ዘባህ እና ጻልሙና ከሠራዊታቸው ጋር በቃርቆር ሰፍረው ነበር፤ የሠራዊቱም ቁጥር ወደ 15,000 ገደማ ነበር። ቀደም ሲል 120,000 የሚያህሉ ሰይፍ የታጠቁ ወንዶች ተገድለው ስለነበር ከመላው የምሥራቅ ሰዎች+ ሠራዊት የቀሩት እነዚህ ብቻ ነበሩ።" +11 ጌድዮንም ከኖባህ እና ከዮግበሃ+ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ ወጣ፤ የጠላት ሠራዊት ተዘናግቶ ባለበትም ወቅት በሰፈሩ ላይ ጥቃት ሰነዘረ። +12 ሁለቱ ምድያማውያን ነገሥታት ማለትም ዘባህ እና ጻልሙና በሸሹም ጊዜ አሳዶ ያዛቸው፤ መላውን ሠራዊትም አሸበረው። +13 ከዚያም የዮአስ ልጅ ጌድዮን ወደ ሄሬስ ሽቅብ በሚያስወጣው መንገድ በኩል አድርጎ ከውጊያው ተመለሰ። +14 እሱም በመንገድ ላይ የሱኮት ሰው የሆነ አንድ ወጣት ያዘ፤ እሱንም መረመረው። በመሆኑም ወጣቱ የሱኮት መኳንንትና ሽማግሌዎች የሆኑ የ77 ሰዎችን ስም ጻፈለት። +15 ጌድዮንም ወደ ሱኮት ሰዎች ሄዶ “‘ለደከሙት ሰዎችህ ዳቦ የምንሰጠው ለመሆኑ የዘባህ እና የጻልሙና መዳፍ እጅህ ገብቷል?’ በማለት የተሳለቃችሁብኝ ዘባህ እና ጻልሙና እነዚሁላችሁ” አላቸው።+ +16 ከዚያም የከተማዋን ሽማግሌዎች ወሰደ፤ በምድረ በዳ እሾህና አሜኬላም ለሱኮት ሰዎች ትምህርት ሰጣቸው።+ +17 እንዲሁም የጰኑኤልን ግንብ አፈረሰ፤+ የከተማዋንም ሰዎች ገደለ። +18 ጌድዮንም ዘባህን እና ጻልሙናን “ለመሆኑ በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች ምን ዓይነት ነበሩ?” አላቸው። እነሱም መልሰው “እንደ አንተ ዓይነት ነበሩ፤ እያንዳንዳቸውም የንጉሥ ልጅ ይመስሉ ነበር” አሉት። +19 በዚህ ጊዜ “እነሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ነበሩ። ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ በሕይወት ትታችኋቸው ቢሆን ኖሮ አልገድላችሁም ነበር” አላቸው። +20 ከዚያም የበኩር ልጁን የቴርን “ተነስ፤ ግደላቸው” አለው። ወጣቱ ግን ሰይፉን አልመዘዘም፤ ምክንያቱም ገና ወጣት ስለሆነ ፈርቶ ነበር። +21 በመሆኑም ዘባህ እና ጻልሙና “የሰው ማንነት የሚለካው በኃይሉ ስለሆነ አንተው ራስህ ተነስና ግደለን” አሉት። በመሆኑም ጌድዮን ተነስቶ ዘባህን እና ጻልሙናን+ ገደላቸው፤ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበሩትንም የሩብ ጨረቃ ቅርጽ ያላቸው ጌጣጌጦች ወሰደ። +22 ከጊዜ በኋላም የእስራኤል ሰዎች ጌድዮንን “ከምድያማውያን እጅ ስለታደግከን አንተ፣ ልጆችህና የልጅ ልጆችህ ግዙን” አሉት።+ +23 ጌድዮን ግን “እኔ አልገዛችሁም፤ ልጄም ቢሆን አይገዛችሁም። የሚገዛችሁ ይሖዋ ነው”+ አላቸው። +24 ከዚያም ጌድዮን “አንድ ነገር ልጠይቃችሁ፦ እያንዳንዳችሁ በምርኮ ካገኛችሁት ላይ የአፍንጫ ሎቲዎችን ስጡኝ” አላቸው። (ምክንያቱም ድል የሆኑት ሕዝቦች እስማኤላውያን+ ስለነበሩ የወርቅ የአፍንጫ ሎቲዎች ነበሯቸው።) +25 እነሱም “በደስታ እንሰጣለን” አሉት። ከዚያም መጎናጸፊያ አነጠፉ፤ እያንዳንዱም ሰው በምርኮ ካገኘው ውስጥ የአፍንጫ ሎቲውን እዚያ ላይ ጣለ። +"26 የሩብ ጨረቃ ቅርጽ ካላቸው ጌጣጌጦች፣ ከአንገት ሐብል ማጫወቻዎች፣ የምድያም ነገሥታት ይለብሷቸው ከነበሩት ቀይ ሐምራዊ ቀለም የተነከሩ የሱፍ ልብሶች እንዲሁም በግመሎቹ ላይ ከነበሩት የአንገት ጌጦች በተጨማሪ እንዲሰጡት የጠየቃቸው የወርቅ የአፍንጫ ሎቲዎች ክብደት 1,700 የወርቅ ሰቅል* ነበር።+ " +27 ጌድዮንም በወርቁ ኤፉድ+ ሠራ፤ ሰዎች እንዲያዩትም በከተማው በኦፍራ+ አስቀመጠው፤ እስራኤላውያንም በሙሉ በዚያ ከእሱ ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ፈጸሙ፤+ ኤፉዱም ለጌድዮንና ለቤተሰቡ ወጥመድ ሆነ።+ +28 በዚህ መንገድ ምድያማውያን+ ለእስራኤላውያን ተገዙ፤ ከዚያ በኋላም ተገዳድረዋቸው አያውቁም፤* በጌድዮን ዘመን ምድሪቱ ለ40 ዓመት አረፈች።* + +29 የዮአስ ልጅ የሩባአልም+ ወደ ቤቱ ተመልሶ በዚያ መኖሩን ቀጠለ። +30 ጌድዮንም ብዙ ሚስቶች ስለነበሩት 70 ወንዶች ልጆች* ነበሩት። +31 በሴኬም የነበረችው ቁባቱም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ እሱም ስሙን አቢሜሌክ+ አለው። +32 የዮአስ ልጅ ጌድዮንም ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ የአቢዔዜራውያን+ በሆነችው በኦፍራ በሚገኘው በአባቱ በዮአስ መቃብር ተቀበረ። +33 እስራኤላውያን ጌድዮን ከሞተ ብዙም ሳይቆይ እንደገና ከባአል ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ፈጸሙ፤+ ባአልበሪትንም አምላካቸው አደረጉት።+ +34 እስራኤላውያንም በዙሪያቸው ከነበሩት ጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ የታደጋቸውን+ አምላካቸውን ይሖዋን አላስታወሱም፤+ +35 እንዲሁም የሩባአል የተባለው ጌድዮን ለእስራኤል ያደረገውን ጥሩ ነገር ሁሉ አስበው ለቤተሰቡ ታማኝ ፍቅር አላሳዩም።+ +11 ጊልያዳዊው ዮፍታሔ+ ኃያል ተዋጊ ነበር፤ እሱም የአንዲት ዝሙት አዳሪ ልጅ የነበረ ሲሆን አባቱ ጊልያድ ነበር። +2 ይሁንና የጊልያድ ሚስትም ለጊልያድ ወንዶች ልጆች ወለደችለት። የዚህችኛዋ ሚስቱ ልጆች ሲያድጉም ዮፍታሔን “አንተ ከሌላ ሴት የተወለድክ ስለሆንክ በአባታችን ቤት ምንም ውርሻ አይኖርህም” በማለት አባረሩት። +3 በመሆኑም ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ሸሽቶ በጦብ ምድር መኖር ጀመረ። ሥራ ፈት ሰዎችም ከእሱ ጋር በመተባበር ተከተሉት። +4 ከተወሰነ ጊዜ በኋላም አሞናውያን ከእስራኤላውያን ጋር ተዋጉ።+ +5 አሞናውያን ከእስራኤላውያን ጋር በሚዋጉበት ጊዜ የጊልያድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር መልሰው ለማምጣት ወዲያውኑ ወደዚያ ሄዱ። +6 ዮፍታሔንም “አሞናውያንን መውጋት እንድንችል መጥተህ አዛዣችን ሁን” አሉት። +7 ዮፍታሔ ግን የጊልያድን ሽማግሌዎች “እኔን እጅግ ከመጥላታችሁ የተነሳ ከአባቴ ቤት ያባረራችሁኝ እናንተ አይደላችሁም?+ ታዲያ አሁን ጭንቅ ውስጥ ስትገቡ ወደ እኔ የምትመጡት ለምንድን ነው?” አላቸው። +8 በዚህ ጊዜ የጊልያድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን እንዲህ አሉት፦ “አሁን ወደ አንተ ተመልሰን የመጣነውም ለዚህ ነው። ከእኛ ጋር አብረኸን በመሄድ ከአሞናውያን ጋር የምትዋጋ ከሆነ ለጊልያድ ነዋሪዎች በሙሉ መሪ ትሆናለህ።”+ +9 ዮፍታሔም የጊልያድን ሽማግሌዎች “እንግዲህ ከአሞናውያን ጋር እንድዋጋ ወደዚያ ብትመልሱኝና ይሖዋ እነሱን ድል ቢያደርግልኝ በእርግጥ እኔ መሪያችሁ እሆናለሁ!” አላቸው። +10 የጊልያድ ሽማግሌዎችም ዮፍታሔን “እንዳልከው ካላደረግን ይሖዋ በመካከላችን ምሥክር* ይሁን” አሉት። +11 በመሆኑም ዮፍታሔ ከጊልያድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም መሪና አዛዥ አደረገው። ��ፍታሔም የተናገረውን ነገር ሁሉ በምጽጳ+ በይሖዋ ፊት ደገመው። +12 ከዚያም ዮፍታሔ ለአሞናውያን+ ንጉሥ “ምድሬን ልትወጋ የመጣኸው ከእኔ ጋር ምን ጠብ ቢኖርህ ነው?”* ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞች ላከ። +13 የአሞናውያን ንጉሥም የዮፍታሔን መልእክተኞች እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ያደረግኩት እስራኤል ከግብፅ በወጣበት ጊዜ ከአርኖን+ አንስቶ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ+ ድረስ ያለውን መሬቴን ስለወሰደብኝ ነው።+ አሁንም መሬቴን በሰላም መልሱልኝ።” +14 ዮፍታሔ ግን መልእክተኞቹን እንደገና ወደ አሞናውያን ንጉሥ በመላክ +15 እንዲህ አለው፦ “ዮፍታሔ እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤል የሞዓባውያንን+ ምድርና የአሞናውያንን+ ምድር አልወሰደም፤ +16 ምክንያቱም እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ ጊዜ በምድረ በዳው አልፈው እስከ ቀይ ባሕርና+ እስከ ቃዴስ+ ድረስ መጡ። +17 ከዚያም እስራኤል ለኤዶም+ ንጉሥ “እባክህ ምድርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን” ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ላከ፤ የኤዶም ንጉሥ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም። ለሞዓብም+ ንጉሥ መልእክት ላኩ፤ እሱም ቢሆን በዚህ ሐሳብ አልተስማማም። ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ+ ተቀመጠ። +18 በምድረ በዳው በተጓዙበት ጊዜ በኤዶም ምድርና በሞዓብ ምድር ዳርቻ አልፈው ሄዱ።+ ከሞዓብ ምድር በስተ ምሥራቅ ተጉዘውም+ በአርኖን ክልል ሰፈሩ፤ ወደ ሞዓብ ወሰንም አልገቡም፤+ ምክንያቱም አርኖን የሞዓብ ወሰን ነበር። +19 “‘ከዚያም እስራኤል ወደ አሞራውያን ንጉሥ ማለትም ወደ ሃሽቦን ንጉሥ ወደ ሲሖን መልእክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም “እባክህ ምድርህን አቋርጠን ወደ ገዛ ስፍራችን እንድናልፍ ፍቀድልን” አለው።+ +20 ሲሖን ግን በግዛቱ አቋርጦ እንዲያልፍ ለመፍቀድ እስራኤልን አላመነውም፤ በመሆኑም ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት ሰብስቦ በያሃጽ ሰፈረ፤ ከእስራኤልም ጋር ውጊያ ገጠመ።+ +21 በዚህ ጊዜ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሲሖንንና ሕዝቡን ሁሉ ለእስራኤላውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ በመሆኑም ድል አደረጓቸው፤ እስራኤላውያንም በዚያ የሚኖሩትን የአሞራውያንን ምድር በሙሉ ወረሱ።+ +22 በዚህ መንገድ ከአርኖን አንስቶ እስከ ያቦቅ እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ያለውን የአሞራውያንን ግዛት በሙሉ ወረሱ።+ +23 “‘እንግዲህ አሞራውያንን ከሕዝቡ ከእስራኤላውያን ፊት ያባረራቸው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ነው፤+ እና አሁን አንተ ደግሞ እነሱን ልታባርራቸው ነው? +24 አንተስ ብትሆን አምላክህ ከሞሽ+ እንድትወርሰው የሰጠህን ሁሉ አትወርስም? ስለዚህ እኛም አምላካችን ይሖዋ ከፊታችን ያባረራቸውን ሁሉ እናባርራለን።+ +25 ደግሞስ አንተ የሞዓብ ንጉሥ ከሆነው ከሴፎር ልጅ ከባላቅ+ ትበልጣለህ? ለመሆኑ እሱ እስራኤልን ለመገዳደር ሞክሮ ያውቃል? ወይስ ከእነሱ ጋር ውጊያ ገጥሞ ያውቃል? +26 እስራኤል በሃሽቦንና በሥሯ* ባሉት ከተሞች፣+ በአሮዔርና በሥሯ ባሉት ከተሞች እንዲሁም በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ በሚገኙት ከተሞች ሁሉ ለ300 ዓመት ተቀምጦ በነበረበት ጊዜ እነዚያን ቦታዎች መልሳችሁ ለመውሰድ ያልሞከራችሁት ለምንድን ነው?+ +27 እንግዲህ እኔ ምንም የበደልኩህ ነገር የለም፤ አንተም ብትሆን በእኔ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መነሳትህ ተገቢ አይደለም። ፈራጁ ይሖዋ+ በእስራኤል ሕዝብና በአሞን ሕዝብ መካከል ዛሬ ይፍረድ።’” +28 የአሞናውያን ንጉሥ ግን ዮፍታሔ የላከበትን መልእክት ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም። +29 የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤+ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ+ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ። +30 ከዚያም ዮፍታሔ እንዲህ ሲል ለይሖዋ ስእለት ተሳለ፦+ “አሞናውያንን በእጄ አሳልፈህ ከሰጠኸኝ +31 ከአሞናውያን ዘንድ በሰላም በምመለስበት ጊዜ ሊቀበለኝ ከቤቴ በር የሚወጣው ማንኛውም ሰው የይሖዋ ይሆናል፤+ እኔም የሚቃጠል መባ አድርጌ አቀርበዋለሁ።”+ +32 በመሆኑም ዮፍታሔ ከአሞናውያን ጋር ለመዋጋት ሄደ፤ ይሖዋም እነሱን በእጁ አሳልፎ ሰጠው። +33 እሱም ከአሮዔር አንስቶ እስከ ሚኒት ድረስ ማለትም 20 ከተሞችን፣ ከዚያም አልፎ እስከ አቤልከራሚም ድረስ ፈጽሞ ደመሰሳቸው። በዚህ መንገድ አሞናውያን ለእስራኤላውያን ተገዙ። +34 በመጨረሻም ዮፍታሔ በምጽጳ+ ወደሚገኘው ቤቱ መጣ፤ በዚህ ጊዜ ሴት ልጁ አታሞ እየመታችና እየጨፈረች ልትቀበለው ወጣች! ልጁ እሷ ብቻ ነበረች። ከእሷ ሌላ ወንድም ሆነ ሴት ልጅ አልነበረውም። +35 እሱም ባያት ጊዜ ልብሱን ቀደደ፤ እንዲህም አለ፦ “ወዮ፣ ልጄ! ልቤን ሰበርሽው፤* እንግዲህ ከቤት የማስወጣው አንቺን ነው። አንዴ ለይሖዋ ቃል ገብቻለሁ፤ ልመልሰውም አልችልም።”+ +36 እሷም እንዲህ አለችው፦ “አባቴ ሆይ፣ ለይሖዋ ቃል ከገባህ፣ የገባኸውን ቃል በእኔ ላይ ፈጽምብኝ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ጠላቶችህን አሞናውያንን ተበቅሎልሃል።” +37 እሷም በመቀጠል አባቷን እንዲህ አለችው፦ “እንዲህ ይደረግልኝ፦ ለሁለት ወር ያህል ብቻዬን ልሁን፤ ወደ ተራሮቹም ልሂድ፤ ከሴት ባልንጀሮቼም ጋር ሆኜ ስለ ድንግልናዬ ላልቅስ።”* +38 በዚህ ጊዜ “እሺ ሂጂ!” አላት፤ ለሁለት ወርም አሰናበታት፤ እሷም ስለ ድንግልናዋ ለማልቀስ ከባልንጀሮቿ ጋር ወደ ተራሮቹ ሄደች። +39 ከሁለት ወር በኋላም ወደ አባቷ ተመለሰች፤ አባቷም እሷን በተመለከተ የተሳለውን ስእለት ፈጸመ።+ እሷም ከወንድ ጋር ግንኙነት ፈጽማ አታውቅም ነበር። ይህም በእስራኤል ውስጥ ልማድ* ሆነ፦ +40 የእስራኤል ወጣት ሴቶች የጊልያዳዊውን የዮፍታሔን ሴት ልጅ ለማመስገን በየዓመቱ ለአራት ቀን ያህል ይሄዱ ነበር። +2 የይሖዋም መልአክ+ ከጊልጋል+ ወደ ቦኪም ወጣ፤ እንዲህም አለ፦ “ከግብፅ አውጥቼ ለአባቶቻችሁ ወደማልኩላቸው ምድር አስገባኋችሁ።+ በተጨማሪም እንዲህ አልኩ፦ ‘እኔ ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ፈጽሞ አላፈርስም።+ +2 እናንተም ከዚህች ምድር ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ፤+ መሠዊያዎቻቸውንም አፈራርሱ።’+ እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም።+ እንዲህ ያደረጋችሁት ለምንድን ነው? +3 በዚህም የተነሳ ‘እነሱን ከፊታችሁ አላስወጣቸውም፤+ ለእናንተም ወጥመድ ይሆኑባችኋል፤+ አማልክታቸውም ያታልሏችኋል’+ አልኩ።” +4 የይሖዋም መልአክ ለእስራኤላውያን በሙሉ ይህን በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ። +5 ስለሆነም የዚያን ስፍራ ስም ቦኪም* አሉት፤ በዚያም ለይሖዋ መሥዋዕት አቀረቡ። +6 ኢያሱ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ እያንዳንዱ እስራኤላዊ ምድሪቱን ለመውረስ ወደየርስቱ ሄደ።+ +7 ሕዝቡም ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ እንዲሁም ከኢያሱ በኋላ በሕይወት በኖሩትና ይሖዋ ለእስራኤል ሲል ያደረገውን ታላቅ ነገር በሙሉ በተመለከቱት ሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ ይሖዋን አገለገለ።+ +8 ከዚያም የይሖዋ አገልጋይ የሆነው የነዌ ልጅ ኢያሱ በ110 ዓመቱ ሞተ።+ +9 እነሱም ከጋአሽ ተራራ+ በስተ ሰሜን በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ በሚገኘው ርስቱ በቲምናትሄረስ+ ቀበሩት። +10 ያም ትውልድ ሁሉ ወደ አያቶቹ ተሰበሰበ፤* ከእነሱም በኋላ ይሖዋንም ሆነ እሱ ለእስራኤል ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሳ። +11 በመሆኑም እስራኤላውያን በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤ ባአልንም አገለገሉ።* + +12 በዚህ መንገድ ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ተዉ።+ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን ሌሎች አማልክት ተከተሉ፤+ ለእነሱም በመስገድ ይሖዋን አስቆጡት።+ +13 ይሖዋን ትተው ባአልንና የአስታሮትን ምስሎች አገለገሉ።+ +14 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በመሆኑም ለሚዘርፏቸው ዘራፊዎች አሳልፎ ሰጣቸው።+ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው፤+ ከዚያ ወዲህ ጠላቶቻቸውን መቋቋም አልቻሉም።+ +15 ይሖዋ አስቀድሞ በተናገረውና ይሖዋ ለእነሱ በማለው መሠረት+ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ጥፋት ያመጣባቸው+ ዘንድ የይሖዋ እጅ በእነሱ ላይ ነበር፤ እነሱም በከባድ ጭንቀት ተውጠው ነበር።+ +16 በመሆኑም ይሖዋ ከዘራፊዎቻቸው እጅ የሚያድኗቸውን መሳፍንት አስነሳላቸው።+ +17 እነሱ ግን መሳፍንቱን እንኳ ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ እንዲያውም ከሌሎች አማልክት ጋር አመነዘሩ፤ ለእነሱም ሰገዱ። የይሖዋን ትእዛዛት ያከብሩ የነበሩ አባቶቻቸው ከሄዱበት መንገድ ፈጥነው ዞር አሉ።+ እነሱ እንዳደረጉት ማድረግ ሳይችሉ ቀሩ። +18 ይሖዋ መሳፍንትን በሚያስነሳላቸው+ ጊዜ ሁሉ ይሖዋ ከመስፍኑ ጋር ይሆን ነበር፤ በመስፍኑም ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ ያድናቸው ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ በሚጨቁኗቸውና+ በሚያንገላቷቸው ሰዎች የተነሳ ሲቃትቱ ያዝናል።*+ +19 መስፍኑ በሚሞትበት ጊዜ ግን ሌሎች አማልክትን በመከተልና በማገልገል እንዲሁም ለእነሱ በመስገድ በድጋሚ ከአባቶቻቸው ይበልጥ መጥፎ ድርጊት ይፈጽማሉ።+ መጥፎ ሥራቸውን ያልተዉ ከመሆኑም ሌላ በእንቢተኝነታቸው ገፍተውበታል። +20 በመጨረሻም የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤+ እንዲህም አለ፦ “ይህ ብሔር ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ስላፈረሰና+ ቃሌን ስላልሰማ+ +21 እኔም ኢያሱ በሞተ ጊዜ ሳያጠፋ ከተዋቸው ብሔራት መካከል አንዳቸውንም ከፊቱ አላባርርም።+ +22 ይህን የማደርገው እስራኤላውያን አባቶቻቸው እንዳደረጉት እነሱም በይሖዋ መንገድ በመሄድ መንገዱን ይጠብቁ እንደሆነና እንዳልሆነ ለመፈተን ነው።”+ +23 ስለዚህ ይሖዋ እነዚህ ብሔራት እዚያው እንዲኖሩ ፈቀደ። ወዲያውኑም አላስወጣቸውም፤ ለኢያሱም አሳልፎ አልሰጣቸውም። +4 ሆኖም ኤሁድ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን እንደገና በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ።+ +2 በመሆኑም ይሖዋ በሃጾር ሆኖ ይገዛ ለነበረው ለከነአን ንጉሥ ለያቢን አሳልፎ ሸጣቸው።+ የሠራዊቱም አለቃ በሃሮሼትጎይም+ የሚኖረው ሲሳራ ነበር። +3 ያቢን* የብረት ማጭድ የተገጠመላቸው 900 የጦር ሠረገሎች* + ስለነበሩትና ለ20 ዓመት ክፉኛ ስለጨቆናቸው+ እስራኤላውያን ወደ ይሖዋ ጮኹ።+ +4 በዚያን ጊዜ የላጲዶት ሚስት ነቢዪቱ ዲቦራ+ በእስራኤል ውስጥ ፈራጅ ሆና ታገለግል ነበር። +5 እሷም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ፣ በራማና+ በቤቴል+ መካከል ባለው የዲቦራ ዘንባባ ዛፍ ሥር ትቀመጥ ነበር፤ እስራኤላውያንም ለፍርድ ወደ እሷ ይወጡ ነበር። +"6 እሷም የአቢኖዓምን ልጅ ባርቅን+ ከቃዴሽንፍታሌም+ አስጠርታ እንዲህ አለችው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ የሚል ትእዛዝ ሰጥቶ የለም? ‘ሂድና ወደ ታቦር ተራራ ዝመት፤* ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን 10,000 ወንዶችን ውሰድ።" +7 እኔም የያቢን ሠራዊት አለቃ የሆነውን ሲሳራን ከጦር ሠረገሎቹና ከሠራዊቱ ጋር ወደ ቂሾን ጅረት* + ወደ አንተ አመጣዋለሁ፤ እሱንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።’”+ +8 በዚህ ጊዜ ባርቅ “አብረሽኝ የምትሄጂ ከሆነ እሄዳለሁ፤ አብረሽኝ የማትሄጂ ከሆነ ግን አልሄድም” አላት። +9 እሷም እንዲህ አለችው፦ “በእርግጥ አብሬህ እሄዳለሁ። ይሁንና ይሖዋ ሲሳራን በሴት እጅ አሳልፎ ስለሚሰጠው የምታካሂደው ዘመቻ ለአንተ ክብር አያስገኝልህም።”+ ከዚያም ዲቦራ ���ነስታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴሽ+ ሄደች። +"10 ባርቅም ዛብሎንንና ንፍታሌምን+ ወደ ቃዴሽ ጠራቸው፤ 10,000 ሰዎችም የእሱን ዱካ ተከተሉ። ዲቦራም አብራው ወጣች። " +11 እንደ አጋጣሚ ሆኖ ቄናዊው+ ሄቤር፣ የሙሴ አማት+ የሆባብ ዘሮች ከሆኑት ከቄናውያን ተለይቶ በቃዴሽ በሚገኘው በጻናኒም ትልቅ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተክሎ ነበር። +12 ከዚያም የአቢኖዓም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ+ እንደወጣ ለሲሳራ ነገሩት። +13 ሲሳራም ወደ ቂሾን ጅረት* + ለመሄድ ወዲያውኑ የጦር ሠረገሎቹን በሙሉ ይኸውም የብረት ማጭድ የተገጠመላቸውን 900 የጦር ሠረገሎች* እንዲሁም ከእሱ ጋር የነበረውን ሠራዊት ሁሉ ከሃሮሼትጎይም አሰባሰበ። +"14 በዚህ ጊዜ ዲቦራ ባርቅን እንዲህ አለችው፦ “ይሖዋ ሲሳራን በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ይህ ስለሆነ ተነስ! ይሖዋ በፊትህ ቀድሞ ይወጣ የለም?” ባርቅም 10,000 ሰዎችን አስከትሎ ከታቦር ተራራ ወረደ።" +15 ይሖዋም ሲሳራንና የጦር ሠረገሎቹን በሙሉ እንዲሁም ሠራዊቱን ሁሉ ግራ እንዲጋቡ አደረጋቸው፤+ በባርቅም ሰይፍ አጠፋቸው። በመጨረሻም ሲሳራ ከሠረገላው ላይ ወርዶ በእግሩ መሸሽ ጀመረ። +16 ባርቅም የጦር ሠረገሎቹንና ሠራዊቱን እስከ ሃሮሼትጎይም ድረስ አሳደዳቸው። በመሆኑም የሲሳራ ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ወደቀ፤ አንድም የተረፈ ሰው አልነበረም።+ +17 ሆኖም ሲሳራ የቄናዊው የሄቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ኢያዔል+ ድንኳን በእግሩ ሸሸ፤ ምክንያቱም በሃጾር ንጉሥ በያቢንና+ በቄናዊው በሄቤር+ ቤት መካከል ሰላማዊ ግንኙነት ነበር። +18 ኢያዔልም ሲሳራን ልትቀበለው ወጣች፤ ከዚያም “ጌታዬ ና፤ ወደዚህ ግባ። አትፍራ” አለችው። በመሆኑም ወደ እሷ ድንኳን ገባ። እሷም ብርድ ልብስ አለበሰችው። +19 ከዚያም “እባክሽ ስለጠማኝ የምጠጣው ትንሽ ውኃ ስጪኝ” አላት። እሷም የወተት አቁማዳውን ፈትታ የሚጠጣውን ሰጠችው፤+ ከዚያም በድጋሚ ሸፈነችው። +20 እሱም “ድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፤ ማንም ሰው መጥቶ ‘እዚህ ሰው አለ?’ ብሎ ቢጠይቅሽ ‘የለም!’ በይ” አላት። +21 የሄቤር ሚስት ኢያዔል ግን የድንኳን ካስማና መዶሻ ወሰደች። ከዚያም ሲሳራ ደክሞት ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዶት ሳለ በቀስታ ወደ እሱ ሄዳ ካስማውን ሰሪሳራዎቹ* ላይ በመቸንከር ከመሬት ጋር አጣበቀችው። እሱም ሞተ።+ +22 ባርቅ ሲሳራን እያሳደደ ወደዚያ አካባቢ ሄደ፤ ኢያዔልም እሱን ለማግኘት ወጣች፤ ከዚያም “ና፣ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው። እሱም ከእሷ ጋር ወደ ውስጥ ገባ፤ ሲሳራንም ካስማው ሰሪሳራዎቹ ላይ እንደተቸነከረ ሞቶ አገኘው። +23 በመሆኑም አምላክ በዚያን ዕለት የከነአን ንጉሥ ያቢን ለእስራኤላውያን እንዲንበረከክ አደረገ።+ +24 እስራኤላውያን የከነአንን+ ንጉሥ ያቢንን እስኪያጠፉት ድረስ እጃቸው በከነአን ንጉሥ በያቢን ላይ ይበልጥ እየበረታ ሄደ።+ +16 አንድ ቀን ሳምሶን ወደ ጋዛ ሄደ፤ በዚያም አንዲት ዝሙት አዳሪ አይቶ ወደ እሷ ገባ። +2 ከዚያም ጋዛውያን “ሳምሶን እዚህ መጥቷል” የሚል ወሬ ደረሳቸው። እነሱም ከበውት በከተማዋ በር ላይ ሌሊቱን ሙሉ አድፍጠው ሲጠባበቁ አደሩ። ለራሳቸውም “ጎህ ሲቀድ እንገድለዋለን” በማለት ሌሊቱን ሙሉ ድምፃቸውን አጥፍተው አደሩ። +3 ይሁንና ሳምሶን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ተኛ። ከዚያም እኩለ ሌሊት ላይ ተነስቶ የከተማዋን በሮች ያዘ፤ በሮቹን ከነመቃኖቹና ከነመቀርቀሪያዎቹ ነቀለ። በትከሻው ከተሸከማቸውም በኋላ በኬብሮን ትይዩ እስከሚገኘው ተራራ አናት ድረስ ይዟቸው ወጣ። +4 ከዚህ በኋላ ሳምሶን በሶረቅ ሸለቆ* የምትገኝ ደሊላ+ የምትባል አንዲት ሴት ወደደ። +"5 የፍልስጤም ገዢዎችም ወደ እሷ ቀርበው እንዲህ አሏት፦ “እስቲ አታለሽ* + እንዲህ ያለ ከፍተኛ ጥንካሬ የሰጠው ምን እንደሆነ እንዲሁም እንዴት ልናሸንፈው፣ ልናስረውና በቁጥጥር ሥር ልናውለው እንደምንችል ለማወቅ ሞክሪ። ይህን ካደረግሽ እያንዳንዳችን 1,100 የብር ሰቅል እንሰጥሻለን።” " +6 ከጊዜ በኋላም ደሊላ ሳምሶንን “የታላቅ ኃይልህ ሚስጥር ምን እንደሆነ እንዲሁም አንተን በምን ማሰርና በቁጥጥር ሥር ማዋል እንደሚቻል እስቲ ንገረኝ” አለችው። +7 ሳምሶንም “ገና እርጥብ በሆኑ ባልደረቁ ሰባት ጅማቶች ቢያስሩኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። +8 በመሆኑም የፍልስጤም ገዢዎች ገና እርጥብ የሆኑ ያልደረቁ ሰባት ጅማቶች አመጡላት፤ እሷም በጅማቶቹ አሰረችው። +9 እነሱም በውስጠኛው ክፍል ውስጥ አድፍጠው ይጠባበቁ ነበር፤ እሷም “ሳምሶን፣ ፍልስጤማውያን መጡብህ!” ብላ ጮኸች። በዚህ ጊዜ ሳምሶን የተፈተለ የበፍታ ክር* እሳት ሲነካው በቀላሉ እንደሚበጣጠስ ጅማቶቹን በጣጠሳቸው።+ የኃይሉም ሚስጥር ሊታወቅ አልቻለም። +10 ደሊላም ሳምሶንን “አሞኝተኸኛል፣ ደግሞም ዋሽተኸኛል።* እሺ አሁን በምን ልትታሰር እንደምትችል እባክህ ንገረኝ” አለችው። +11 እሱም “ሥራ ላይ ባልዋሉ አዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። +12 ደሊላም አዲስ ገመዶች ወስዳ አሰረችው፤ ከዚያም “ሳምሶን፣ ፍልስጤማውያን መጡብህ!” ብላ ጮኸች። (በዚህ ጊዜ ሁሉ በውስጠኛው ክፍል ውስጥ አድፍጠው የሚጠባበቁ ሰዎች ነበሩ።) ሳምሶንም ገመዶቹን ልክ እንደ ክር ከእጆቹ ላይ በጣጠሳቸው።+ +13 ከዚህ በኋላ ደሊላ ሳምሶንን “አሁንም አሞኘኸኝ፤ ዋሸኸኝ።+ በምን ልትታሰር እንደምትችል ንገረኝ” አለችው። እሱም “የራስ ፀጉሬን ሰባት ጉንጉኖች በመሸመኛ ላይ ከድር ጋር አብረሽ ሸምኛቸው” አላት። +14 በመሆኑም ደሊላ ጉንጉኖቹን በሸማኔ ዘንግ አጠበቀቻቸው፤ ከዚያም “ሳምሶን፣ ፍልስጤማውያን መጡብህ!” ብላ ጮኸች። እሱም ከእንቅልፉ ነቃ፤ ዘንጉንና ድሩንም መዞ አወጣው። +15 እሷም “ልብህ ከእኔ ጋር ሳይሆን እንዴት ‘እወድሻለሁ’+ ትለኛለህ? ይኸው ሦስት ጊዜ አሞኘኸኝ፤ የታላቁ ኃይልህን ሚስጥር አልነገርከኝም”+ አለችው። +16 ዕለት ዕለት ስለነዘነዘችውና ለጭንቀት ስለዳረገችው ሞቱን እስኪመኝ ድረስ ተመረረ።* + +17 በመጨረሻም የልቡን ሁሉ አውጥቶ እንዲህ ሲል ነገራት፦ “ከተወለድኩበት ጊዜ አንስቶ* ለአምላክ ናዝራዊ ስለሆንኩ ራሴን ምላጭ ነክቶት አያውቅም።+ ፀጉሬን ከተላጨሁ ኃይሌን አጣለሁ፤ አቅምም አይኖረኝም፤ እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ እሆናለሁ።” +18 ደሊላም ሳምሶን የልቡን ሁሉ አውጥቶ እንደነገራት ስታውቅ “የልቡን ሁሉ አውጥቶ ስለነገረኝ በቃ አሁን መምጣት ትችላላችሁ” በማለት የፍልስጤም ገዢዎችን+ ወዲያውኑ አስጠራቻቸው። የፍልስጤም ገዢዎችም ገንዘቡን ይዘው ወደ እሷ መጡ። +19 እሷም ሳምሶንን ጭኗ ላይ አስተኛችው፤ ሰውየውንም ጠርታ የራስ ፀጉሩን ሰባት ጉንጉኖች እንዲላጫቸው አደረገች። ከዚያ በኋላ ኃይሉ ከእሱ ስለተለየ በቁጥጥሯ ሥር አዋለችው። +20 እሷም “ሳምሶን፣ ፍልስጤማውያን መጡብህ!” አለችው። በዚህ ጊዜ ከእንቅልፉ ነቅቶ “እንደ ሌላው ጊዜ እወጣለሁ፤+ ራሴንም ነፃ አደርጋለሁ” አለ። ሆኖም ይሖዋ እንደተወው አላወቀም ነበር። +21 በመሆኑም ፍልስጤማውያን ይዘው ዓይኖቹን አወጡ። ከዚያም ወደ ጋዛ ይዘውት በመውረድ ከመዳብ በተሠሩ ሁለት የእግር ብረቶች አሰሩት፤ እሱም እስር ቤት ውስጥ እህል ፈጪ ሆነ። +22 ሆኖም ተላጭቶ የነበረው የሳምሶን ፀጉር እንደገና ማደግ ጀመረ።+ +23 የፍልስጤም ገዢዎች “አምላካችን ጠላታችንን ሳምሶንን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን!” በማለት ለአምላካቸው ለዳጎን+ ታላቅ መሥዋዕት ለመሠዋትና ለመደሰት አንድ ላይ ተሰብስበው ነበር። +24 ሕዝቡም ሳምሶንን ባዩት ጊዜ “አምላካችን ምድራችንን ያጠፋውንና+ ብዙ ወገኖቻችንን የገደለብንን+ ጠላታችንን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን” በማለት አምላካቸውን አወደሱ። +25 እነሱም ልባቸው ሐሴት በማድረጉ “እስቲ ሳምሶንን ጥሩትና ትንሽ ያዝናናን” አሉ። በመሆኑም እንዲያዝናናቸው ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠሩት፤ በዓምዶቹም መካከል አቆሙት። +26 ከዚያም ሳምሶን እጁን ይዞት የነበረውን ልጅ “ቤቱ የቆመባቸውን ዓምዶች አስይዘኝና ልደገፍባቸው” አለው። +"27 (እንደ አጋጣሚ ሆኖ ቤቱ በወንዶችና በሴቶች ተሞልቶ ነበር። የፍልስጤም ገዢዎችም በሙሉ እዚያ ነበሩ፤ በተጨማሪም ሳምሶን ሕዝቡን ሲያዝናና ይመለከቱ የነበሩ 3,000 ወንዶችና ሴቶች ጣሪያው ላይ ነበሩ።) " +28 ሳምሶንም+ እንዲህ በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ አስበኝ፤ አምላክ ሆይ፣ እባክህ ለአሁን ብቻ አንድ ጊዜ ብርታት ስጠኝና+ ከሁለቱ ዓይኖቼ+ ስለ አንዱ ፍልስጤማውያንን ልበቀላቸው።” +29 ከዚያም ሳምሶን ቤቱን ደግፈው ያቆሙትን መሃል ላይ የሚገኙትን ሁለቱን ዓምዶች፣ አንዱን በቀኝ እጁ ሌላውን ደግሞ በግራ እጁ አቅፎ ተደገፈባቸው። +30 እሱም “ከፍልስጤማውያን ጋር ልሙት!”* ብሎ ጮኸ። ከዚያም ዓምዶቹን ባለ በሌለ ኃይሉ ገፋቸው፤ ቤቱም በገዢዎቹና በውስጡ በነበሩት ሰዎች ሁሉ ላይ ወደቀ።+ በመሆኑም ሳምሶን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው ሰዎች ይልቅ በሞተበት ጊዜ የገደላቸው ሰዎች በለጡ።+ +31 በኋላም ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰቦች በሙሉ ሊወስዱት ወደዚያ ወረዱ። እነሱም ወስደው በጾራ+ እና በኤሽታዖል መካከል በሚገኘው በአባቱ በማኑሄ+ የመቃብር ስፍራ ቀበሩት። እሱም በእስራኤል ውስጥ ለ20 ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ።+ +6 እስራኤላውያን ግን እንደገና በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ በመሆኑም ይሖዋ ለሰባት ዓመት ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው።+ +2 የምድያማውያን እጅ በእስራኤል ላይ በረታ።+ እስራኤላውያን በምድያማውያን የተነሳ በተራሮች ላይ፣ በዋሻዎች ውስጥና በቀላሉ በማይደረስባቸው ስፍራዎች ለመደበቂያ የሚሆኑ ቦታዎችን* ለራሳቸው አዘጋጁ።+ +3 እነሱም ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ሁሉ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና+ የምሥራቅ ሰዎች+ ጥቃት ይሰነዝሩባቸው ነበር። +4 እንዲሁም በዙሪያቸው በመስፈር እስከ ጋዛ ድረስ ያለውን የምድሩን ሰብል ያጠፉ ነበር፤ ለእስራኤላውያን የሚበሉት ምንም ነገር አያስተርፉላቸውም፤ በግም ሆነ ከብት ወይም አህያ አያስቀሩላቸውም ነበር።+ +5 ምክንያቱም ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው እንደ አንበጣ መንጋ ብዙ ሆነው ይመጡ ነበር፤+ እነሱም ሆኑ ግመሎቻቸው ለቁጥር የሚያታክቱ ነበሩ፤+ ወደዚያም የሚመጡት ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር። +6 በመሆኑም እስራኤላውያን በምድያማውያን የተነሳ ለከፍተኛ ድህነት ተዳረጉ፤ እነሱም ይሖዋ እንዲረዳቸው መጮኽ ጀመሩ።+ +7 እስራኤላውያን በምድያማውያን የተነሳ ለእርዳታ ወደ ይሖዋ በጮኹ ጊዜ+ +8 ይሖዋ ነቢይ ላከላቸው፤ እሱም እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከግብፅ አወጣኋችሁ፤ በዚህ መንገድ ከባርነት ቤት አላቀኳችሁ።+ +9 ከግብፅ እጅና ከሚጨቁኗችሁ ሁሉ ታደግኳችሁ፤ እነሱንም ከፊታችሁ በማባረር ምድራቸውን ሰጠኋችሁ።+ +10 እንዲሁም “እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።+ በምድራቸው ላይ የምትኖሩባቸው አሞራውያን የሚያመልኳቸውን አማልክት አትፍሩ” አልኳችሁ።+ እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም።’”+ +11 በኋላም የይሖዋ መልአክ መጥቶ+ በኦፍራ በሚገኘው በአቢዔዜራዊው+ በዮአስ ትልቅ ዛፍ ሥር ተቀመጠ። የዮአስም ል��� ጌድዮን+ ከምድያማውያን ተደብቆ በወይን መጭመቂያው ስፍራ ስንዴ እየወቃ ነበር። +12 ከዚያም የይሖዋ መልአክ ተገለጠለትና “አንተ ኃያል ተዋጊ፣ ይሖዋ ከአንተ ጋር ነው”+ አለው። +13 ጌድዮንም እንዲህ አለው፦ “ይቅርታ ጌታዬ፤ ታዲያ ይሖዋ ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ሁሉ የሚደርስብን ለምንድን ነው?+ አባቶቻችን ‘ይሖዋ ከግብፅ ምድር አላወጣንም?’+ እያሉ ይነግሩን የነበረው ድንቅ ሥራው ሁሉ የት አለ?+ አሁን ይሖዋ ትቶናል፤+ ለምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል።” +14 ይሖዋም ፊት ለፊቱ ቆመና እንዲህ አለው፦ “በል ባለህ ኃይል ሂድ፤ እስራኤልንም ከምድያማውያን እጅ ታድናለህ።+ የምልክህ እኔ አይደለሁም?” +15 ጌድዮንም መልሶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ይቅርታ አድርግልኝ፤ እኔ እንዴት እስራኤልን ላድን እችላለሁ? የእኔ ጎሳ* እንደሆነ ከምናሴ ነገድ የመጨረሻው ነው፤ እኔም ብሆን በአባቴ ቤት ውስጥ እዚህ ግባ የምባል አይደለሁም።” +16 ሆኖም ይሖዋ “እኔ ከአንተ ጋር ስለምሆን+ ምድያማውያንን ልክ እንደ አንድ ሰው ትመታቸዋለህ” አለው። +17 ከዚያም ጌድዮን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ ከእኔ ጋር እየተነጋገርክ ያለኸው አንተ ስለመሆንህ አንድ ምልክት አሳየኝ። +18 ደግሞም ተመልሼ መጥቼ ስጦታዬን በፊትህ እስካቀርብ ድረስ እባክህ ከዚህ አትሂድ”+ አለው። እሱም “እስክትመለስ ድረስ እዚሁ እጠብቅሃለሁ” አለው። +19 ጌድዮንም ገብቶ አንድ የፍየል ጠቦትና ከአንድ ኢፍ* ዱቄት ቂጣ* አዘጋጀ።+ ሥጋውን በቅርጫት፣ መረቁን ደግሞ በድስት አድርጎ ወደ እሱ ይዞ በመምጣት በትልቁ ዛፍ ሥር አቀረበለት። +20 የእውነተኛው አምላክ መልአክም “ሥጋውንና ቂጣውን ወስደህ እዚያ ባለው ዓለት ላይ አስቀምጣቸው፤ መረቁንም አፍስሰው” አለው። እሱም እንዲሁ አደረገ። +21 ከዚያም የይሖዋ መልአክ በእጁ ይዞት የነበረውን በትር ዘርግቶ በጫፉ ሥጋውንና ቂጣውን ነካ፤ በዚህ ጊዜ እሳት ከዓለቱ ወጥቶ ሥጋውንና ቂጣውን በላ።+ ከዚያም የይሖዋ መልአክ ከእይታው ተሰወረ። +22 በዚህ ጊዜ ጌድዮን የይሖዋ መልአክ እንደነበር አስተዋለ።+ ወዲያውኑም “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ የይሖዋን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና ወዮልኝ!” አለ።+ +23 ሆኖም ይሖዋ “ሰላም ለአንተ ይሁን። አትፍራ፤+ አትሞትም” አለው። +24 ጌድዮንም በዚያ ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያውም እስከ ዛሬ ድረስ ‘ይሖዋ ሻሎም’* + ተብሎ ይጠራል። አሁንም ድረስ የአቢዔዜራውያን በሆነችው በኦፍራ ይገኛል። +25 በዚያ ምሽት ይሖዋ ጌድዮንን እንዲህ አለው፦ “የአባትህ ንብረት የሆነውን ሰባት ዓመት የሞላውን ሁለተኛውን ወይፈን ውሰድ፤ የአባትህ የሆነውን የባአልን መሠዊያም አፈራርስ፤ አጠገቡም የሚገኘውን የማምለኪያ ግንድ* ሰባብር።+ +26 በዚህ ምሽግ አናት ላይ ድንጋይ ደርድረህ ለአምላክህ ለይሖዋ መሠዊያ ከሠራህ በኋላ ሁለተኛውን ወይፈን ወስደህ በምትሰባብረው የማምለኪያ ግንድ* እንጨት ላይ የሚቃጠል መባ አድርገህ አቅርበው።” +27 ስለዚህ ጌድዮን ከአገልጋዮቹ መካከል አሥር ሰዎችን ወስዶ ልክ ይሖዋ እንዳለው አደረገ። ይሁንና የአባቱን ቤትና የከተማዋን ሰዎች በጣም ስለፈራ ይህን ያደረገው በቀን ሳይሆን በሌሊት ነበር። +28 የከተማዋ ሰዎች በማግስቱ በማለዳ ሲነሱ የባአል መሠዊያ ፈራርሶ፣ አጠገቡ የነበረው የማምለኪያ ግንድም* ተሰባብሮ እንዲሁም ሁለተኛው ወይፈን በተሠራው መሠዊያ ላይ ተሠውቶ ተመለከቱ። +29 እነሱም እርስ በርሳቸው “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ተባባሉ። ሁኔታውንም ካጣሩ በኋላ “ይህን ያደረገው የዮአስ ልጅ ጌድዮን ነው” አሉ። +30 በመሆኑም የከተማዋ ሰዎች ዮአስን “ልጅህ የባአልን ���ሠዊያ ስላፈራረሰና አጠገቡ የነበረውን የማምለኪያ ግንድ* ስለሰባበረ ወደዚህ አውጣው፤ መሞት አለበት” አሉት። +31 ከዚያም ዮአስ+ እሱን የሚቃወሙትን ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “ለባአል መሟገት ይኖርባችኋል? እሱን ለማዳን መሞከርስ ይገባችኋል? ለእሱ የሚሟገት ማንኛውም ሰው በዚህ ጠዋት መሞት ይገባዋል።+ እሱ አምላክ ከሆነ አንድ ሰው መሠዊያውን ስላፈረሰበት ለራሱ ይሟገት።”+ +32 እሱም “ባአል አንድ ሰው መሠዊያውን ስላፈረሰበት ለራሱ ይሟገት” በማለት ጌድዮንን በዚያ ቀን የሩባአል* ብሎ ጠራው። +33 ምድያማውያን፣+ አማሌቃውያንና+ የምሥራቅ ሰዎች በሙሉ ግንባር ፈጥረው+ ወደ ኢይዝራኤል ሸለቆ* በመሻገር በዚያ ሰፈሩ። +34 የይሖዋም መንፈስ በጌድዮን ላይ ወረደ፤* + እሱም ቀንደ መለከት ነፋ፤+ አቢዔዜራውያንም+ እሱን በመደገፍ ተከትለውት ወጡ። +35 ከዚያም በመላው ምናሴ መልእክተኞችን ላከ፤ እነሱም እሱን በመደገፍ ተከትለውት ወጡ። በተጨማሪም ወደ አሴር፣ ወደ ዛብሎንና ወደ ንፍታሌም መልእክተኞችን ላከ፤ እነሱም ከእሱ ጋር ለመገናኘት ወጡ። +36 ከዚያም ጌድዮን እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለው፦ “ቃል በገባኸው መሠረት በእኔ አማካኝነት እስራኤልን የምታድን ከሆነ+ +37 ይኸው አውድማው ላይ የተባዘተ የበግ ፀጉር አስቀምጣለሁ። በዙሪያው ያለው ምድር በሙሉ ደረቅ ሆኖ የበግ ፀጉሩ ላይ ብቻ ጤዛ ከተገኘ ቃል በገባኸው መሠረት በእኔ አማካኝነት እስራኤልን እንደምታድን አውቃለሁ።” +38 ልክ እንደዚሁም ሆነ። በማግስቱ በማለዳ ተነስቶ የበግ ፀጉሩን ሲጨምቀው ከበግ ፀጉሩ ላይ የወጣው ውኃ በትልቅ ጎድጓዳ ሳህን ሙሉ ሆነ። +39 ሆኖም ጌድዮን እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለው፦ “እባክህ ቁጣህ በእኔ ላይ አይንደድ፤ አንድ ጊዜ ብቻ እንድናገር ፍቀድልኝ። ከበግ ፀጉሩ ጋር በተያያዘ አንድ ሌላ ሙከራ ብቻ ላድርግ። እባክህ የበግ ፀጉሩ ብቻ ደረቅ ሆኖ ምድሩ በሙሉ ጤዛ እንዲሆን አድርግ።” +40 በመሆኑም አምላክ በዚያ ሌሊት እንደዚሁ አደረገ፤ የበግ ፀጉሩ ብቻ ደረቅ ሆኖ ምድሩ በሙሉ ጤዛ ሆነ። +10 ከአቢሜሌክ በኋላ የዶዶ ልጅ፣ የፑሃ ልጅ የይሳኮር ሰው የሆነው ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሳ።+ እሱም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢዎች በምትገኘው በሻሚር ይኖር ነበር። +2 በእስራኤልም ውስጥ ለ23 ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። ከዚያም ሞተ፤ በሻሚርም ተቀበረ። +3 ከእሱም በኋላ ጊልያዳዊው ያኢር ተነሳ፤ በእስራኤልም ውስጥ ለ22 ዓመት ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። +4 ያኢር በ30 አህዮች የሚጋልቡ 30 ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነሱም እስከ ዛሬ ድረስ ሃዎትያኢር+ ተብለው የሚጠሩ 30 ከተሞች ነበሯቸው፤ ከተሞቹም የሚገኙት በጊልያድ ምድር ነው። +5 ከዚያም ያኢር ሞተ፤ በቃሞንም ተቀበረ። +6 እስራኤላውያንም በይሖዋ ፊት እንደገና መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ ባአልን፣+ የአስታሮትን ምስሎች፣ የአራምን* አማልክት፣ የሲዶናን አማልክት፣ የሞዓብን አማልክት፣+ የአሞናውያንን አማልክትና+ የፍልስጤማውያንን አማልክት+ ማገልገል ጀመሩ። ይሖዋን ተዉት፤ እሱንም አላገለገሉም። +7 የይሖዋም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ እነሱንም ለፍልስጤማውያንና ለአሞናውያን ሸጣቸው።+ +8 ስለሆነም በዚያ ዓመት እስራኤላውያንን አደቀቋቸው፤ ክፉኛም ጨቆኗቸው፤ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በጊልያድ በሚገኘው በአሞራውያን ምድር የነበሩትን እስራኤላውያን በሙሉ ለ18 ዓመት ጨቆኗቸው። +9 በተጨማሪም አሞናውያን ይሁዳን፣ ቢንያምንና የኤፍሬምን ቤት ለመውጋት ዮርዳኖስን ይሻገሩ ነበር፤ እስራኤላውያንም እጅግ ተጨንቀው ነበር። +10 ከዚያም እስራኤላውያን “አንተን አምላካችንን ትተን ባአልን በማገልገላችን+ በአንተ ላ�� ኃጢአት ሠርተናል” በማለት ይሖዋ እንዲረዳቸው ጮኹ።+ +11 ሆኖም ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፦ “ግብፃውያን፣+ አሞራውያን፣+ አሞናውያን፣ ፍልስጤማውያን፣+ +12 ሲዶናውያን፣ አማሌቃውያንና ምድያማውያን በጨቆኗችሁ ጊዜ አላዳንኳችሁም? ወደ እኔ ስትጮኹ ከእጃቸው ታደግኳችሁ። +13 እናንተ ግን እኔን ትታችሁ ሌሎች አማልክትን አገለገላችሁ።+ ዳግመኛ የማላድናችሁም በዚህ የተነሳ ነው።+ +14 ወደመረጣችኋቸው አማልክት ሂዱና እንዲረዷችሁ ጠይቋቸው።+ በጭንቀታችሁ ጊዜ እነሱ ያድኗችሁ።”+ +15 እስራኤላውያን ግን ይሖዋን “ኃጢአት ሠርተናል። መልካም መስሎ የታየህን ማንኛውንም ነገር አድርግብን። እባክህ፣ የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት። +16 እነሱም ከመካከላቸው ባዕዳን አማልክትን አስወግደው ይሖዋን አገለገሉ፤+ በመሆኑም በእስራኤል ላይ እየደረሰ የነበረውን መከራ ሊታገሥ አልቻለም።* + +17 ከጊዜ በኋላም አሞናውያን+ ተሰባስበው በጊልያድ ሰፈሩ። በመሆኑም እስራኤላውያን ተሰባስበው በምጽጳ ሰፈሩ። +18 የጊልያድ ሕዝብና መኳንንት እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “ከአሞናውያን ጋር የሚደረገውን ውጊያ ግንባር ቀደም ሆኖ የሚመራው ማን ነው?+ ይህ ሰው በጊልያድ ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሁን።” +14 ከዚያም ሳምሶን ወደ ቲምና ወረደ፤ በቲምናም አንዲት ፍልስጤማዊት ሴት አየ። +2 ወጥቶም አባቱንና እናቱን “በቲምና ያለች አንዲት ፍልስጤማዊት ዓይኔን ማርካዋለች፤ እሷን እንድታጋቡኝ እፈልጋለሁ” አላቸው። +3 ሆኖም አባቱና እናቱ “ከዘመዶችህና ከእኛ ሕዝብ መካከል ለአንተ የምትሆን ሴት አጥተህ ነው?+ የግድ ሄደህ ካልተገረዙት ፍልስጤማውያን መካከል ሚስት ማግባት አለብህ?” አሉት። ሳምሶን ግን አባቱን “ልቤን የማረከችው እሷ ስለሆነች እሷን አጋባኝ” አለው። +4 በዚያን ጊዜ በእስራኤል ላይ ይገዙ የነበሩት ፍልስጤማውያን ስለነበሩ አባቱና እናቱ ነገሩ ከይሖዋ መሆኑንና እሱም ከፍልስጤማውያን ጋር ግጭት የሚፈጠርበትን አጋጣሚ እየፈለገ እንደነበር አላወቁም።+ +5 ስለዚህ ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ። በቲምና ወዳለው የወይን እርሻ ሲደርስም አንድ ደቦል አንበሳ እያገሳ መጣበት። +6 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ አንድ ሰው በባዶ እጁ የፍየልን ጠቦት ለሁለት እንደሚገነጥል እሱም አንበሳውን ለሁለት ገነጠለው። ሆኖም ያደረገውን ነገር ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም። +7 ከዚያም ወርዶ ሴቲቱን አነጋገራት፤ አሁንም የሳምሶን ልብ በእሷ እንደተማረከ ነበር።+ +8 ከተወሰነ ጊዜ በኋላም ወደ ቤቱ ሊያመጣት+ ተመልሶ ሲሄድ የአንበሳውን በድን ለማየት ከመንገድ ዞር አለ፤ በአንበሳውም በድን ውስጥ የንብ መንጋና ማር ነበር። +9 እሱም ማሩን ዛቅ አድርጎ መዳፉ ላይ በማድረግ በመንገድ ላይ እየበላ ሄደ። ከአባቱና ከእናቱ ጋር እንደተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነሱም በሉ። ሆኖም ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን ውስጥ እንደሆነ አልነገራቸውም ነበር። +10 አባቱም ወደ ሴቲቱ ወረደ፤ ሳምሶንም በዚያ ግብዣ አዘጋጀ፤ ምክንያቱም ወጣቶች እንዲህ የማድረግ ልማድ ነበራቸው። +11 እነሱም ባዩት ጊዜ አብረውት እንዲሆኑ 30 ሚዜዎችን አመጡ። +12 ሳምሶንም እንዲህ አላቸው፦ “እስቲ አንድ እንቆቅልሽ ልንገራችሁ። ግብዣው በሚቆይበት በዚህ ሰባት ቀን ውስጥ ፍቺውን ካወቃችሁና መልሱን ከነገራችሁኝ 30 የበፍታ ልብሶችንና 30 የክት ልብሶችን እሰጣችኋለሁ። +13 መልሱን ልትነግሩኝ ካልቻላችሁ ግን 30 የበፍታ ልብሶችንና 30 የክት ልብሶችን ትሰጡኛላችሁ።” እነሱም “እንቆቅልሽህን ንገረን፤ እስቲ እንስማው” አሉት። +14 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ከበ���ተኛው መብል ወጣ፤ ከብርቱውም ውስጥ ጣፋጭ ነገር ወጣ።”+ እነሱም እስከ ሦስት ቀን ድረስ እንቆቅልሹን ሊፈቱት አልቻሉም። +15 በአራተኛውም ቀን የሳምሶንን ሚስት እንዲህ አሏት፦ “ባልሽን አታለሽ+ የእንቆቅልሹን ፍቺ እንዲነግረን አድርጊ። አለዚያ አንቺንም ሆነ የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን። እዚህ የጋበዛችሁን ንብረታችንን ልትዘርፉን ነው?” +16 የሳምሶንም ሚስት ላዩ ላይ እያለቀሰች “አንተ ትጠላኛለህ፤ ደግሞም አትወደኝም።+ ለሕዝቤ አንድ እንቆቅልሽ ነግረሃቸው ነበር፤ መልሱን ግን ለእኔ አልነገርከኝም” አለችው። እሱም በዚህ ጊዜ “እንዴ፣ ለገዛ አባቴና እናቴ እንኳ አልነገርኳቸውም! ታዲያ ለአንቺ ለምን እነግርሻለሁ?” አላት። +17 እሷ ግን ግብዣው እስከቆየበት እስከ ሰባተኛው ቀን ድረስ ስታለቅስበት ሰነበተች። በመጨረሻም አጥብቃ ስለነዘነዘችው በሰባተኛው ቀን ነገራት። እሷም የእንቆቅልሹን ፍቺ ለሕዝቧ ነገረች።+ +18 የከተማዋም ሰዎች ሳምሶንን በሰባተኛው ቀን ፀሐይዋ ከመጥለቋ በፊት* እንዲህ አሉት፦ “ከማር ይልቅ የሚጣፍጥ ምን ተገኝቶ?ከአንበሳስ ይልቅ የበረታ ከየት መጥቶ?”+ እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “በጊደሬ ባላረሳችሁ፣+እንቆቅልሼን ባልፈታችሁ።” +19 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ ለሳምሶን ኃይል ሰጠው፤+ እሱም ወደ አስቀሎን+ ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል 30ውን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፎ እንቆቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው።+ ቁጣው እንደነደደም ወደ አባቱ ቤት ወጣ። +20 የሳምሶንም ሚስት+ አብረውት ከነበሩት ሚዜዎች ለአንዱ ተዳረች።+ +9 ከጊዜ በኋላ የየሩባአል ልጅ አቢሜሌክ+ በሴኬም ወደሚገኙት የእናቱ ወንድሞች ሄዶ እነሱንና የአያቱን ቤተሰብ* በሙሉ እንዲህ አላቸው፦ +2 “እባካችሁ የሴኬምን መሪዎች* ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ጠይቋቸው፦ ‘70ዎቹ የየሩባአል ልጆች+ በሙሉ ቢገዟችሁ ይሻላችኋል ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ? ደግሞም እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ፣ የሥጋችሁ ቁራጭ* መሆኔን አስታውሱ።’” +3 በመሆኑም የእናቱ ወንድሞች እሱን ወክለው ለሴኬም መሪዎች በሙሉ ይህንኑ ነገሯቸው፤ እነሱም “እሱ እኮ የገዛ ወንድማችን ነው” በማለት ልባቸው አቢሜሌክን ወደመከተል አዘነበለ። +4 እነሱም ከባአልበሪት+ ቤት* 70 የብር ሰቅል ሰጡት፤ አቢሜሌክም ተከታዮቹ እንዲሆኑ በዚህ ገንዘብ ሥራ ፈቶችንና ወሮበሎችን ቀጠረበት። +5 ከዚያም በኦፍራ+ ወደሚገኘው ወደ አባቱ ቤት ሄዶ ወንድሞቹን ማለትም 70ዎቹን የየሩባአል ልጆች በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላቸው።+ በሕይወት የተረፈው የሁሉም ታናሽ የሆነው የየሩባአል ልጅ ኢዮዓታም ብቻ ነበር፤ ምክንያቱም እሱ ተደብቆ ነበር። +6 ከዚያም የሴኬም መሪዎች ሁሉ እንዲሁም የቤትሚሎ ሰዎች በሙሉ በአንድነት ተሰብስበው በመሄድ አቢሜሌክን በትልቁ ዛፍ አጠገብ ይኸውም በሴኬም በነበረው ዓምድ አጠገብ አነገሡት።+ +7 ኢዮዓታምም ይህን በነገሩት ጊዜ ወዲያውኑ ሄዶ በገሪዛን ተራራ+ አናት ላይ ቆመ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሴኬም መሪዎች እኔን ስሙኝ፤ ከዚያም አምላክ ይሰማችኋል። +8 “ከዕለታት አንድ ቀን ዛፎች በላያቸው የሚነግሥ ንጉሥ ለመቀባት ሄዱ። በመሆኑም የወይራ ዛፍን ‘በእኛ ላይ ንገሥ’+ አሉት። +9 ሆኖም የወይራ ዛፍ ‘ሄጄ ከሌሎች ዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል አምላክንና ሰዎችን ለማክበር የሚጠቀሙበትን ዘይቴን* መስጠት ልተው?’ አላቸው። +10 ከዚያም ዛፎቹ የበለስን ዛፍ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት። +11 የበለስ ዛፍ ግን ‘ሄጄ ከሌሎች ዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል ጣፋጭና መልካም ፍሬዬን መስጠት ልተው?’ አላቸው። +12 በመቀጠልም ዛፎቹ የወይን ተክልን ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት። +13 የወይን ተክልም መልሶ ‘ሄጄ ከሌሎች ዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል አምላክንና ሰዎችን የሚያስደስተውን አዲስ የወይን ጠጅ መስጠቴን ልተው?’ አላቸው። +14 በመጨረሻም ሌሎቹ ዛፎች ሁሉ የእሾህ ቁጥቋጦን ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’+ አሉት። +15 በዚህ ጊዜ የእሾህ ቁጥቋጦው ዛፎቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘በእናንተ ላይ ንጉሥ እንድሆን የምትቀቡኝ እውነት ከልባችሁ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ። ካልሆነ ግን እሳት ከእሾህ ቁጥቋጦው ወጥቶ አርዘ ሊባኖሶችን ያቃጥል።’ +16 “ለመሆኑ አቢሜሌክን ንጉሥ ያደረጋችሁት+ በየዋህነትና በቅንነት ነው? ለየሩባአልና ለቤተሰቡ ጥሩነት አሳይታችኋል? የሚገባውን ውለታስ መልሳችሁለታል? +17 አባቴ ለእናንተ ሲል በተዋጋ ጊዜ+ እናንተን ከምድያማውያን እጅ ለመታደግ ሕይወቱን* አደጋ ላይ ጥሏል።+ +18 እናንተ ግን ዛሬ በአባቴ ቤተሰብ ላይ ተነሳችሁ፤ 70 ልጆቹንም በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላችኋቸው።+ ወንድማችሁ ስለሆነ ብቻ ከባሪያይቱ የወለደውን ልጁን አቢሜሌክን+ በሴኬም መሪዎች ላይ አነገሣችሁት። +19 በዛሬው ዕለት ለየሩባአልና ለቤተሰቡ ይህን ያደረጋችሁት በየዋህነትና በቅንነት ከሆነ በአቢሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እሱም በእናንተ ደስ ይበለው። +20 ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቢሜሌክ ወጥቶ የሴኬምን መሪዎችና ቤትሚሎን+ ያቃጥል፤ እንዲሁም እሳት ከሴኬም መሪዎችና ከቤትሚሎ ወጥቶ አቢሜሌክን ያቃጥል።”+ +21 ከዚያም ኢዮዓታም+ ወደ በኤር ሸሽቶ አመለጠ፤ በወንድሙ በአቢሜሌክ የተነሳም በዚያ ኖረ። +22 አቢሜሌክም በእስራኤል ላይ ሦስት ዓመት ገዛ።* +23 ከዚያም አምላክ በአቢሜሌክና በሴኬም መሪዎች መካከል ቅራኔ እንዲፈጠር አደረገ፤* እነሱም በአቢሜሌክ ላይ ተንኮል አሴሩበት። +24 ይህም የሆነው ወንድሞቹን የገደለውን አቢሜሌክንና ወንድሞቹን እንዲገድል የረዱትን የሴኬምን መሪዎች በሞቱት ሰዎች ደም ተጠያቂ በማድረግ+ በ70ዎቹ የየሩባአል ልጆች ላይ የተፈጸመውን ግፍ ለመበቀል ነው። +25 በመሆኑም የሴኬም መሪዎች አድብተው እሱን የሚጠባበቁ ሰዎችን በተራሮች አናት ላይ መደቡ፤ እነሱም በአጠገባቸው የሚያልፈውን መንገደኛ ሁሉ ይዘርፉ ነበር። በኋላም ሁኔታው ለአቢሜሌክ ተነገረው። +26 ከዚያም የኤቤድ ልጅ ገአል ከወንድሞቹ ጋር ወደ ሴኬም ተሻገረ፤+ የሴኬምም መሪዎች እምነት ጣሉበት። +27 እነሱም ወደ እርሻ ወጥተው የወይን ፍሬያቸውን ከሰበሰቡ በኋላ ጨመቁት፤ በዓልም አከበሩ፤ ከዚያም ወደ አምላካቸው+ ቤት ገብተው በሉ፤ ጠጡም፤ አቢሜሌክንም ረገሙ። +28 ከዚያም የኤቤድ ልጅ ገአል እንዲህ አለ፦ “ለመሆኑ አቢሜሌክ ማን ነው? እናገለግለውስ ዘንድ ሴኬም ማን ነው? እሱ የየሩባአል+ ልጅ አይደለም? የእሱ ተወካይስ ዘቡል አይደለም? የሴኬምን አባት የኤሞርን ሰዎች አገልግሉ! አቢሜሌክን የምናገለግለው ለምንድን ነው? +29 ይህን ሕዝብ የማዘው እኔ ብሆን ኖሮ አቢሜሌክን አስወግደው ነበር።” ከዚያም አቢሜሌክን “ብዙ ሠራዊት አሰባስበህ ና ውጣ” አለው። +30 የከተማዋ ገዢ የሆነው ዘቡል የኤቤድ ልጅ ገአል የተናገረውን ነገር በሰማ ጊዜ ቁጣው ነደደ። +31 በመሆኑም ለአቢሜሌክ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት በሚስጥር መልእክተኞችን ላከ፦* “እነሆ፣ የኤቤድ ልጅ ገአልና ወንድሞቹ ወደ ሴኬም መጥተዋል፤ ከተማዋም በአንተ ላይ እንድታምፅ እያነሳሱ ነው። +32 በመሆኑም አንተም ሆንክ አብረውህ ያሉት ሰዎች በሌሊት ወጥታችሁ ሜዳው ላይ አድፍጡ። +33 ጠዋት ላይ ልክ ፀሐይ ስትወጣ፣ ማልደህ በመነሳት በከተማዋ ላይ ጥቃት ሰንዝር፤ እሱና አብረውት ያሉት ሰዎች አንተን ለመውጋት ሲወጡም እሱን ድል ለመምታት የቻልከውን ሁሉ አድርግ።”* +34 በመሆ���ም አቢሜሌክና አብረውት ያሉት ሰዎች በሙሉ በሌሊት ተነሱ፤ በአራት ቡድንም ሆነው በሴኬም ላይ አደፈጡ። +35 የኤቤድ ልጅ ገአል ወጥቶ በከተማዋ መግቢያ በር ላይ በቆመ ጊዜ አቢሜሌክና አብረውት ያሉት ሰዎች ካደፈጡበት ቦታ ተነሱ። +36 ገአልም ሰዎቹን ባያቸው ጊዜ ዘቡልን “ተመልከት፣ ከተራሮቹ አናት ላይ ሰዎች እየወረዱ ነው” አለው። ዘቡል ግን “ሰው መስሎ የታየህ የተራሮቹ ጥላ ነው” አለው። +37 በኋላም ገአል “ተመልከት፤ ከምድሩ መሃል ሰዎች እየወረዱ ነው፤ አንደኛው ቡድን በመኦነኒም ትልቅ ዛፍ በኩል አድርጎ እየመጣ ነው” አለ። +38 ዘቡልም “‘እናገለግለው ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው?’+ እያልክ ጉራህን ስትነዛ አልነበረም? የናቅከው ሕዝብ ይህ አይደለም? እስቲ አሁን ውጣና ግጠማቸው” ሲል መለሰለት። +39 በመሆኑም ገአል ከሴኬም መሪዎች ፊት ፊት በመሄድ ከአቢሜሌክ ጋር ተዋጋ። +40 አቢሜሌክም አሳደደው፤ ገአልም ከፊቱ ሸሸ፤ እስከ ከተማዋም መግቢያ በር ድረስ ብዙ ሰው ተረፈረፈ። +41 አቢሜሌክም በአሩማ መኖሩን ቀጠለ፤ ዘቡልም+ ገአልንና ወንድሞቹን ከሴኬም አስወጣቸው። +42 በማግስቱም ሕዝቡ ከከተማዋ ወጣ፤ ይህም ለአቢሜሌክ ተነገረው። +43 እሱም ሰዎቹን ወስዶ በሦስት ቡድን በመክፈል ሜዳ ላይ አድፍጦ ይጠባበቅ ጀመር። ሕዝቡም ከከተማዋ መውጣቱን ተመለከተ፤ በዚህ ጊዜም በእነሱ ላይ ጥቃት ሰነዘረ፤ መታቸውም። +44 አቢሜሌክና አብረውት የነበሩት ቡድኖች በፍጥነት ወደ ፊት በመገስገስ በከተማዋ መግቢያ በር ላይ ቆሙ፤ ሁለቱ ቡድኖች ደግሞ ከከተማዋ ውጭ ባሉት ሰዎች ሁሉ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ መቷቸውም። +45 አቢሜሌክም ያን ቀን ሙሉ ከተማዋን ሲወጋ ዋለ፤ በመጨረሻም በቁጥጥሩ ሥር አዋላት። በከተማዋም ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ገደለ፤ ከዚያም ከተማዋን አፈራረሳት፤+ በላይዋም ጨው ዘራባት። +46 የሴኬም ግንብ መሪዎች በሙሉ ይህን ሲሰሙ ወዲያውኑ በኤልበሪት+ ቤት* ወደሚገኘው መሸሸጊያ ቦታ* ሄዱ። +47 የሴኬም ግንብ መሪዎች በሙሉ አንድ ላይ እንደተሰባሰቡ ለአቢሜሌክ በተነገረውም ጊዜ +48 አቢሜሌክና አብረውት የነበሩት ሰዎች በሙሉ ወደ ጻልሞን ተራራ ወጡ። አቢሜሌክም መጥረቢያ ይዞ የዛፍ ቅርንጫፍ ከቆረጠ በኋላ አንስቶ በትከሻው ተሸከመው፤ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች “እኔ ሳደርግ ያያችሁትን ፈጥናችሁ አድርጉ!” አላቸው። +"49 በመሆኑም ሰዎቹ ሁሉ ቅርንጫፎች ቆርጠው በመያዝ አቢሜሌክን ተከተሉት። ከዚያም ቅርንጫፎቹን መሸሸጊያ ቦታው ላይ በመቆለል መሸሸጊያ ቦታውን በእሳት አያያዙት። በዚህም የተነሳ የሴኬም ግንብ ሰዎች በሙሉ ይኸውም 1,000 ገደማ የሚሆኑ ወንዶችና ሴቶች ሞቱ። " +50 ከዚያም አቢሜሌክ ወደ ቴቤጽ ሄደ፤ ቴቤጽንም ከቦ በቁጥጥር ሥር አዋላት። +51 በከተማዋ መሃል ጠንካራ ግንብ ስለነበር ወንዶችና ሴቶች በሙሉ እንዲሁም የከተማዋ መሪዎች በሙሉ ወደዚያ ሸሹ። እነሱም ከውስጥ ሆነው በሩን ከዘጉት በኋላ የግንቡ አናት ላይ ወጡ። +52 አቢሜሌክም ወደ ግንቡ ሄደ፤ ጥቃትም ሰነዘረበት። ግንቡንም በእሳት ለማቃጠል ወደ መግቢያው ተጠጋ። +53 ከዚያም አንዲት ሴት በአቢሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ በመልቀቅ ጭንቅላቱን ፈረከሰችው።+ +54 እሱም ጋሻ ጃግሬውን ወዲያውኑ ጠርቶ “‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉኝ ሰይፍህን ምዘዝና ግደለኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬውም ወጋው፤ እሱም ሞተ። +55 የእስራኤል ሰዎች አቢሜሌክ መሞቱን ሲያዩ ሁሉም ወደቤታቸው ተመለሱ። +56 በዚህ መንገድ አምላክ፣ አቢሜሌክ 70 ወንድሞቹን በመግደል በአባቱ ላይ ለፈጸመው ክፉ ነገር የእጁን እንዲያገኝ አደረገ።+ +57 በተጨማሪም አምላክ የሴኬም ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ እንዲደርስ አደረገ። በመሆኑ�� የየሩባአል+ ልጅ የኢዮዓታም+ እርግማን ደረሰባቸው። +13 እስራኤላውያን እንደገና በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ ይሖዋም ለ40 ዓመት በፍልስጤማውያን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።+ +2 በዚህ ጊዜ ከዳናውያን+ ቤተሰብ የሆነ ስሙ ማኑሄ+ የሚባል አንድ የጾራ+ ሰው ነበር። ሚስቱ መሃን ስለነበረች ልጅ አልነበራትም።+ +3 ከጊዜ በኋላ የይሖዋ መልአክ ለሴቲቱ ተገለጠላትና እንዲህ አላት፦ “እነሆ አንቺ መሃን ነሽ፤ ልጅም የለሽም። ነገር ግን ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ።+ +4 እንግዲህ ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤+ እንዲሁም ምንም ዓይነት ርኩስ ነገር አትብዪ።+ +5 እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ይህ ልጅ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ* የአምላክ ናዝራዊ* ስለሚሆን ራሱን ምላጭ አይንካው፤+ እሱም እስራኤልን ከፍልስጤማውያን እጅ በማዳን ረገድ ግንባር ቀደም ይሆናል።”+ +6 ከዚያም ሴቲቱ ሄዳ ባሏን እንዲህ አለችው፦ “የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደ እኔ መጥቶ ነበር፤ መልኩም የእውነተኛውን አምላክ መልአክ ይመስላል፤ በጣም የሚያስፈራ ነበር። ከየት እንደመጣ አልጠየቅኩትም፤ እሱም ቢሆን ስሙን አልነገረኝም።+ +7 ሆኖም እንዲህ አለኝ፦ ‘እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ። እንግዲህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ እንዲሁም ምንም ዓይነት ርኩስ ነገር አትብዪ፤ ምክንያቱም ልጁ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ* እስከሚሞትበት ዕለት ድረስ የአምላክ ናዝራዊ ይሆናል።’” +8 ማኑሄም “ይቅርታ አድርግልኝ ይሖዋ። እባክህ ልከኸው የነበረው ያ የእውነተኛው አምላክ ሰው እንደገና ወደ እኛ ይምጣና የሚወለደውን ልጅ በተመለከተ ምን ማድረግ እንዳለብን መመሪያ ይስጠን” በማለት ይሖዋን ተማጸነ። +9 በመሆኑም እውነተኛው አምላክ የማኑሄን ቃል ሰማ፤ የእውነተኛው አምላክ መልአክም ሴቲቱ ሜዳ ላይ ተቀምጣ ሳለ ዳግመኛ ወደ እሷ መጣ፤ ባሏ ማኑሄ ግን አብሯት አልነበረም። +10 ሴቲቱም በፍጥነት እየሮጠች ሄዳ ባሏን “ባለፈው ጊዜ ወደ እኔ መጥቶ የነበረው ሰው ተገለጠልኝ” አለችው።+ +11 ከዚያም ማኑሄ ተነስቶ ከሚስቱ ጋር ሄደ። ሰውየውንም ሲያገኘው “ሚስቴን ያነጋገርካት አንተ ነህ?” አለው፤ እሱም “አዎ፣ እኔ ነኝ” አለ። +12 ማኑሄም “እንግዲህ እንደ ቃልህ ይሁንልን! ይሁንና ልጁን ማሳደግ የሚኖርብን እንዴት ነው? የእሱስ ሥራ ምን ይሆናል?” አለው።+ +13 የይሖዋም መልአክ ማኑሄን እንዲህ አለው፦ “ሚስትህ ከነገርኳት ነገር ሁሉ ራሷን ትጠብቅ።+ +14 ከወይን ተክል የሚገኝ ማንኛውንም ነገር አትብላ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤+ እንዲሁም ምንም ዓይነት ርኩስ ነገር አትብላ።+ ያዘዝኳትን ሁሉ ትጠብቅ።” +15 ማኑሄም የይሖዋን መልአክ “እባክህ አንድ የፍየል ጠቦት አዘጋጅተን እስክናቀርብልህ ድረስ ቆይ” አለው።+ +16 ሆኖም የይሖዋ መልአክ ማኑሄን “ብቆይም እንኳ የምታቀርበውን ምግብ አልበላም፤ ይሁንና ለይሖዋ የሚቃጠል መባ ማቅረብ የምትፈልግ ከሆነ እሱን አቅርበው” አለው። ማኑሄ ይህ ሰው የይሖዋ መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። +17 ከዚያም ማኑሄ የይሖዋን መልአክ “የተናገርከው ቃል ሲፈጸም እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?”+ በማለት ጠየቀው። +18 ሆኖም የይሖዋ መልአክ “ስሜ የሚያስደንቅ ሆኖ ሳለ ለምን ስሜን ትጠይቀኛለህ?” አለው። +19 ከዚያም ማኑሄ የፍየል ጠቦቱንና የእህል መባውን ወስዶ በዓለቱ ላይ ለይሖዋ አቀረበው። እሱም ማኑሄና ሚስቱ እየተመለከቱ አስደናቂ ነገር አደረገ። +20 የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ የይሖዋ መልአክ ማኑሄና ሚስቱ እያዩት ከመሠዊያው በወጣው ነ��ልባል ውስጥ ሆኖ አረገ። እነሱም ወዲያውኑ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ። +21 የይሖዋም መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ዳግመኛ አልተገለጠላቸውም። ማኑሄ ሰውየው የይሖዋ መልአክ እንደነበር የተገነዘበው ያን ጊዜ ነበር።+ +22 ከዚያም ማኑሄ ሚስቱን “ያየነው አምላክን ስለሆነ መሞታችን አይቀርም” አላት።+ +23 ሚስቱ ግን “ይሖዋ ሊገድለን ቢፈልግማ ኖሮ የሚቃጠል መባና የእህል መባ ከእጃችን ባልተቀበለ ነበር፤+ ደግሞም ይህን ሁሉ ነገር ባላሳየንና እንዲህ ያለውንም ነገር ባልነገረን ነበር” አለችው። +24 በኋላም ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሳምሶን+ አለችው፤ ልጁም እያደገ ሄደ፤ ይሖዋም ባረከው። +25 ከጊዜ በኋላም በጾራ እና በኤሽታዖል+ መካከል በምትገኘው በማሃነህዳን+ ሳለ የይሖዋ መንፈስ ይገፋፋው ጀመር።+ +5 በዚያን ቀን ዲቦራ+ ከአቢኖዓም ልጅ ከባርቅ+ ጋር ሆና ይህን መዝሙር ዘመረች፦+ + 2 “በእስራኤል ስላለው የተለቀቀ ፀጉር፣*ሕዝቡም ፈቃደኛ ስለሆነ፣+ይሖዋን አወድሱ! + 3 እናንተ ነገሥታት ስሙ! እናንተ ገዢዎች ጆሯችሁን ስጡ! ለይሖዋ እዘምራለሁ። ለእስራኤል አምላክ+ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+ + 4 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከሴይር+ በወጣህ ጊዜ፣ከኤዶም ክልል እየገሰገስክ በመጣህ ጊዜ፣ምድር ተናወጠች፤ ሰማያትም ውኃ አወረዱ፤ደመናትም ውኃ አንዠቀዠቁ። + 5 ተራሮች በይሖዋ ፊት ቀለጡ፣*+ሲናም ሳይቀር በእስራኤል አምላክ+ በይሖዋ ፊት ቀለጠ።+ + 6 በአናት ልጅ በሻምጋር+ ዘመን፣በኢያዔል+ ዘመን ጎዳናዎቹ ጭር ያሉ ነበሩ፤ተጓዦችም በውስጥ ለውስጥ መንገዶች ይሄዱ ነበር። + 7 እኔ ዲቦራ+ እስክነሳ ድረስ፣እኔ በእስራኤል እናት ሆኜ እስክነሳ ድረስ፣+የመንደር ነዋሪዎች ከእስራኤል ደብዛቸው ጠፋ። +" 8 እነሱ አዳዲስ አማልክትን መረጡ፤+በበሮቹም ላይ ጦርነት ነበር።+ በ40,000 የእስራኤል ወንዶች መካከል፣አንድ ጋሻ ወይም አንድ ጦር ሊታይ አልቻለም። " + 9 ልቤ ከእስራኤል አዛዦች፣+ከሕዝቡ ጋር በፈቃደኝነት ከወጡት ጋር ነው።+ ይሖዋን አወድሱ! +10 እናንተ፣ ነጣ ባሉ ቡናማ አህዮች የምትጋልቡ፣እናንተ፣ ባማሩ ምንጣፎች ላይ የምትቀመጡ፣እናንተ፣ በመንገድ ላይ የምትሄዱ፣ይህን ልብ በሉ! +11 የውኃ ቀጂዎች ድምፅ በውኃ መቅጃው ስፍራ ተሰማ፤እነሱም በዚያ የይሖዋን የጽድቅ ሥራዎች፣በእስራኤል መንደሮች ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦቹን የጽድቅ ሥራዎች መተረክ ጀመሩ። የይሖዋም ሕዝቦች ወደ በሮቹ ወረዱ። +12 ዲቦራ+ ሆይ፣ ንቂ፣ ንቂ! ንቂ፣ ንቂ፣ መዝሙርም ዘምሪ!+ የአቢኖዓም ልጅ ባርቅ+ ሆይ፣ ተነስ! ምርኮኞችህን እየመራህ ሂድ! +13 የተረፉትም ሰዎች ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤የይሖዋ ሕዝቦች ኃያላኑን ለመውጋት ወደ እኔ ወረዱ። +14 በሸለቆው* የነበሩ ሰዎች ምንጫቸው ኤፍሬም ነበር፤ቢንያም ሆይ፣ እነሱ በሕዝቦችህ መካከል እየተከተሉህ ነው። ከማኪር+ አዛዦች፣ከዛብሎንም የመልማዮችን በትር የያዙ* ሰዎች ወረዱ። +15 የይሳኮር መኳንንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤እንደ ይሳኮር ሁሉ ባርቅም+ ከእሷ ጋር ነበር። እሱም በእግር ወደ ሸለቋማው ሜዳ* ተላከ።+ የሮቤል ቡድኖች ልባቸው በእጅጉ አመንትቶ ነበር። +16 አንተ በመንታ ጭነት መካከል የተቀመጥከው ለምንድን ነው?ለመንጎቹ ዋሽንታቸውን ሲነፉ ለማዳመጥ ነው?+ የሮቤል ቡድኖች እንደሆነ ልባቸው በእጅጉ አመንትቷል። +17 ጊልያድ ከዮርዳኖስ ማዶ አርፎ ተቀምጧል፤+ዳን ከመርከቦች ጋር የተቀመጠው ለምንድን ነው?+ አሴር በባሕር ዳርቻ ላይ ሥራ ፈቶ ተቀምጧል፤በወደቦቹም ላይ ይኖራል።+ +18 ዛብሎን እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን ለአደጋ የሚያጋልጥ* ሕዝብ ነበር፤ንፍታሌምም ቢሆን+ በገላጣ ኮረብቶች ላይ ነው።+ +19 ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤በዚያን ጊዜ የከነአን ነገሥታት፣+በመጊዶ+ ውኃዎች አጠገብ በታአናክ ተዋጉ። ምንም ብር ማርከው አልወሰዱም።+ +20 ከዋክብት ከሰማይ ተዋጉ፤በምሕዋራቸው ላይ ሆነው ከሲሳራ ጋር ተዋጉ። +21 የቂሾን ወንዝ፣ጥንታዊው ወንዝ፣ የቂሾን ወንዝ ጠራርጎ ወሰዳቸው።+ ነፍሴ* ሆይ፣ ብርቱዎቹን ረገጥሽ። +22 የፈረሶች ኮቴ ሲረግጥ የተሰማው ያን ጊዜ ነበር፣ድንጉላ ፈረሶቹ በኃይል ይጋልቡ ነበር።+ +23 የይሖዋ መልአክ እንዲህ አለ፦ ‘መሮዝን እርገሙ፤ነዋሪዎቿንም እርገሙ፣ይሖዋን ለመርዳት አልመጡምና፣ይሖዋን ለመርዳት ከኃያላኑ ጋር አልመጡም።’ +24 የቄናዊው የሄቤር+ ሚስት ኢያዔል+ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተባረከች ነች፤ በድንኳን ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ነች። +25 ውኃ ጠየቀ፣ ወተት ሰጠችው። ለመኳንንት በሚቀርብበት ጎድጓዳ ሳህን እርጎ ሰጠችው።+ +26 እጇን ዘርግታ የድንኳን ካስማ አነሳች፣በቀኝ እጇም የሠራተኛ መዶሻ ያዘች። ሲሳራንም ቸነከረችው፣ ጭንቅላቱንም ፈረከሰችው፣ሰሪሳራውንም ተረከከችው፤ በሳችው።+ +27 እሱም በእግሮቿ መካከል ተደፋ፤ በወደቀበት በዚያው ቀረ፤በእግሮቿ መካከል ተደፋ፣ ወደቀ፤እዚያው በተደፋበት ተሸንፎ ቀረ። +28 አንዲት ሴት በመስኮት ተመለከተች፣የሲሳራ እናት በፍርግርጉ አጮልቃ ወደ ውጭ ተመለከተች፣‘የጦር ሠረገሎቹ ሳይመጡ ለምን ዘገዩ? የሠረገሎቹ ኮቴ ድምፅስ ምነው ይህን ያህል ዘገየ?’+ +29 ጥበበኛ የሆኑት የተከበሩ ወይዛዝርቷ ይመልሱላታል፤አዎ፣ እሷም ለራሷ እንዲህ ትላለች፣ +30 ‘ያገኙትን ምርኮ እየተከፋፈሉ መሆን አለበት፣ለእያንዳንዱ ተዋጊ አንድ ልጃገረድ* እንዲያውም ሁለት ልጃገረዶች፣*ለሲሳራም ከምርኮው ላይ ቀለም የተነከሩ ልብሶች፣ አዎ ቀለም የተነከሩ ልብሶች፣ምርኮውን ለማረኩት ሰዎች አንገት፣ቀለም የተነከረ ባለ ጥልፍ ልብስ፣ እንዲያውም ሁለት ባለ ጥልፍ ልብስ እየተሰጠ +31 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፣+አንተን የሚወዱ ግን ደምቃ እንደምትወጣ ፀሐይ ይሁኑ።” ከዚያ በኋላ ምድሪቱ ለ40 ዓመት አረፈች።* + +21 የእስራኤል ሰዎች በምጽጳ+ ተሰብስበው “ከእኛ መካከል ማንም ሰው ሴት ልጁን ከቢንያም ወገን ለሆነ ሰው መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር።+ +2 በመሆኑም እስራኤላውያን ወደ ቤቴል+ መጥተው በዚያ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አምርረው እያለቀሱ በእውነተኛው አምላክ ፊት እስከ ምሽት ድረስ ተቀመጡ። +3 እነሱም “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ በእስራኤል ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር እንዲከሰት ለምን ፈቀድክ? ዛሬ ከእስራኤል መካከል አንድ ነገድ እንዴት ይጥፋ?” ይሉ ነበር። +4 በማግስቱም ሕዝቡ በማለዳ ተነስቶ የሚቃጠሉ መባዎችንና የኅብረት መባዎችን+ ለማቅረብ በዚያ መሠዊያ ሠራ። +5 የእስራኤል ሰዎችም በምጽጳ በይሖዋ ፊት ያልተገኘ ሰው ሁሉ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት በማለት በጥብቅ ተማምለው ስለነበር “ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል በይሖዋ ፊት ለመሰብሰብ ያልወጣው ማን ነው?” በማለት ጠየቁ። +6 የእስራኤል ሰዎችም በወንድማቸው በቢንያም ላይ በደረሰው ነገር አዘኑ። እንዲህም አሉ፦ “እነሆ ዛሬ ከእስራኤል መካከል አንድ ነገድ ተቆርጧል። +7 እንግዲህ እኛ ሴት ልጆቻችንን ለእነሱ ላለመዳር በይሖዋ ምለናል፤+ ታዲያ የተረፉት ወንዶች ሚስት ማግኘት እንዲችሉ ምን ብናደርግ ይሻላል?”+ +8 እነሱም “ከእስራኤል ነገዶች መካከል በምጽጳ በይሖዋ ፊት ለመቅረብ ያልወጣው የትኛው ነው?”+ በማለት ጠየቁ። ከኢያቢስጊልያድ ጉባኤው ወደነበረበት ሰፈር የመጣ ማንም ሰው አልነበረም። +9 ሕዝቡ በተቆጠረበት ጊዜ ከኢያቢስጊልያድ ነዋሪዎች መካከል አንድም ሰው እንዳልነበር ተገነዘቡ። +"10 በመሆኑም ማኅበረሰቡ እጅግ ኃያል ከሆኑት ተዋጊዎች መካከል 12,000 ሰዎችን ወደዚያ ላከ። እንዲህም ሲሉ አዘዟቸው፦ “ሂዱ፤ የኢያቢስጊልያድን ነዋሪዎች በሰይፍ ምቱ፤ ሴቶችንና ልጆችንም እንኳ አታስቀሩ።+" +11 እንግዲህ እንዲህ አድርጉ፦ እያንዳንዱን ወንድ እንዲሁም ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የሚያውቁ ሴቶችን ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ።” +12 እነሱም ከኢያቢስጊልያድ ነዋሪዎች መካከል ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁ 400 ደናግል ሴቶችን አገኙ። እነሱንም በከነአን ምድር በሴሎ+ ወደሚገኘው ሰፈር አመጧቸው። +13 ከዚያም መላው ማኅበረሰብ በሪሞን በሚገኘው ዓለት+ ወዳሉት ቢንያማውያን መልእክት በመላክ የሰላም ጥሪ አቀረበላቸው። +14 በመሆኑም በዚህ ጊዜ ቢንያማውያን ወደ ምድራቸው ተመለሱ። ከኢያቢስጊልያድ ሴቶች መካከል በሕይወት እንዲተርፉ የተዉአቸውንም ሴቶች ሰጧቸው፤+ ሆኖም በቂ ሴቶች አላገኙላቸውም። +15 ሕዝቡም ይሖዋ በእስራኤል ነገዶች መካከል ክፍፍል እንዲኖር በማድረጉ የተነሳ በቢንያማውያን ላይ በደረሰው ነገር አዘነ።+ +16 የማኅበረሰቡም ሽማግሌዎች “ቢንያማውያን ሴቶች በሙሉ ስላለቁ ለተረፉት ወንዶች ሚስት ለማግኘት ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉ። +17 እነሱም እንዲህ በማለት መለሱ፦ “ከእስራኤል መካከል አንድ ነገድ ሙሉ በሙሉ እንዳይጠፋ በሕይወት ለተረፉት ቢንያማውያን ርስት ሊኖራቸው ይገባል። +18 ሆኖም እኛ ሴቶች ልጆቻችንን ለእነሱ መዳር አይፈቀድልንም፤ ምክንያቱም የእስራኤል ሰዎች ‘ለቢንያም ልጁን የሚድር የተረገመ ነው’ ብለው ምለዋል።”+ +19 ከዚያም “ከቤቴል በስተ ሰሜንና ከቤቴል ወደ ሴኬም ከሚወስደው አውራ ጎዳና በስተ ምሥራቅ እንዲሁም ከለቦና በስተ ደቡብ በምትገኘው በሴሎ+ በየዓመቱ ለይሖዋ የሚከበር በዓል አለ” አሉ። +20 በመሆኑም የቢንያምን ሰዎች እንዲህ በማለት አዘዟቸው፦ “ሂዱና በወይን እርሻው ውስጥ አድፍጣችሁ ጠብቁ። +21 የሴሎ ወጣት ሴቶች ክብ ሠርተው ለመጨፈር ሲወጡ ስታዩ እያንዳንዳችሁ ከወይን እርሻው ውስጥ ወጥታችሁ ከሴሎ ወጣት ሴቶች መካከል ለራሳችሁ ሚስት ጠልፋችሁ ውሰዱ፤ ከዚያም ወደ ቢንያም ምድር ተመለሱ። +22 አባቶቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው መጥተው በእኛ ላይ ስሞታ ቢያሰሙ እንዲህ እንላቸዋለን፦ ‘ባደረግነው ጦርነት ለእያንዳንዳቸው የሚሆኑ ሚስቶችን ማግኘት ስላልቻልን ለእነሱ ስትሉ ውለታ ዋሉልን፤+ እናንተም ብትሆኑ ሴቶቹን ፈቅዳችሁ ስላልሰጣችኋቸው በጥፋተኝነት አትጠየቁም።’”+ +23 በመሆኑም የቢንያም ሰዎች እንደተባሉት አደረጉ፤ እያንዳንዳቸውም ከሚጨፍሩት ሴቶች መካከል ሚስቶችን ጠልፈው ወሰዱ። ከዚያም ወደየርስታቸው ተመልሰው በመሄድ ከተሞቻቸውን በድጋሚ ገንብተው+ በዚያ መኖር ጀመሩ። +24 በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን እያንዳንዳቸው ወደየነገዳቸውና ወደየቤተሰባቸው በመሄድ ከዚያ አካባቢ ተበተኑ፤ እያንዳንዳቸውም ከዚያ ተነስተው ወደየርስታቸው ሄዱ። +25 በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም።+ እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ትክክል መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር። +15 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወቅት ሳምሶን አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደ። እሱም “ሚስቴ ወዳለችበት መኝታ ቤት* መግባት እፈልጋለሁ” አለ። አባቷ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም። +2 ከዚያም አባትየው እንዲህ አለው፦ “እኔ እኮ ‘ፈጽሞ ጠልተሃታል’ ብዬ አስቤ ነበር።+ ስለሆነም ለሚዜህ ዳርኳት።+ ታናሽ እህቷ ከእሷ ይልቅ ቆንጆ አይደለችም? እባክህ በዚያችኛዋ ፋንታ ይህችኛዋን አግባት።” +3 ሳምሶን ግን “ከእንግዲህ ፍልስጤማውያን ለማደርስባቸው ጉዳት ተጠያቂ ሊያደርጉኝ አይችሉም” አላቸው። +4 ሳምሶንም ሄዶ 300 ቀበሮዎችን ያዘ። ከዚያም ችቦዎች አመጣ፤ ቀበሮዎቹንም ፊታቸውን አዙሮ ጭራና ጭራቸውን አንድ ላይ ካሰረ በኋላ በጭራቸው መሃል አንድ አንድ ችቦ አደረገ። +5 በመቀጠልም ችቦዎቹን በእሳት በመለኮስ ቀበሮዎቹን በፍልስጤማውያን እርሻ ላይ ባለው ያልታጨደ እህል ውስጥ ለቀቃቸው። ከነዶው አንስቶ እስካልታጨደው እህል ድረስ እንዲሁም የወይን እርሻዎችንና የወይራ ዛፎችን አቃጠለ። +6 ፍልስጤማውያኑም “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ጠየቁ። እነሱም “የቲምናዊው አማች ሳምሶን ነው፤ ይህን ያደረገውም ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው ስለሰጠበት ነው” ተብሎ ተነገራቸው።+ በዚህ ጊዜ ፍልስጤማውያን ሄደው እሷንና አባቷን በእሳት አቃጠሉ።+ +7 ሳምሶንም “እንግዲህ እናንተ ይህን ካደረጋችሁ እኔ ደግሞ እናንተን ሳልበቀል አርፌ አልቀመጥም” አላቸው።+ +8 ከዚያም አንድ በአንድ እየመታ* ረፈረፋቸው፤ ከዚህ በኋላ ወርዶ በኤጣም በሚገኝ አንድ የዓለት ዋሻ* ውስጥ ተቀመጠ። +9 በኋላም ፍልስጤማውያን ወጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ የሊሃይንም+ አካባቢ ያስሱ ጀመር። +10 የይሁዳም ሰዎች “እኛን ልትወጉ የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አሏቸው፤ እነሱም መልሰው “እኛ የመጣነው ሳምሶንን ለመያዝና* እሱ እንዳደረገብን ሁሉ እኛም እንድናደርግበት ነው” አሉ። +"11 በመሆኑም 3,000 የይሁዳ ሰዎች በኤጣም ወደሚገኘው የዓለት ዋሻ* ወርደው ሳምሶንን “ፍልስጤማውያን ገዢዎቻችን መሆናቸውን አታውቅም?+ ታዲያ እንዲህ ያለ ነገር የፈጸምክብን ለምንድን ነው?” አሉት። እሱም “እነሱ እንዳደረጉብኝ እኔም አደረግኩባቸው” አላቸው።" +12 እነሱ ግን “አሁን የመጣነው ይዘን* ለፍልስጤማውያን ልናስረክብህ ነው” አሉት። ከዚያም ሳምሶን “እናንተ ራሳችሁ ምንም ጥቃት እንደማታደርሱብኝ ማሉልኝ” አላቸው። +13 እነሱም “አስረን ብቻ ለእነሱ እናስረክብሃለን እንጂ አንገድልህም” አሉት። በመሆኑም በሁለት አዳዲስ ገመዶች አስረው ከዓለቱ ውስጥ አወጡት። +14 እሱም ሊሃይ ሲደርስ ፍልስጤማውያኑ እሱን በማግኘታቸው በድል አድራጊነት ጮኹ። በዚህ ጊዜ የይሖዋ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ እጆቹ የታሰሩባቸውም ገመዶች እሳት እንደበላው የበፍታ ክር ሆኑ፤ ማሰሪያዎቹም ከእጆቹ ላይ ቀልጠው ወደቁ።+ +"15 እሱም በቅርቡ የሞተ የአንድ አህያ መንጋጋ አገኘ፤ መንጋጋውንም አንስቶ በእሱ 1,000 ሰው ገደለ።+" +"16 ከዚያም ሳምሶን እንዲህ አለ፦ “በአህያ መንጋጋ በክምር ላይ ክምር አነባባሪ፤ በአህያ መንጋጋ 1,000 ሰው ዘራሪ!”+ " +17 እሱም ይህን ተናግሮ ሲጨርስ የአህያውን መንጋጋ ወረወረው፤ ያንንም ቦታ ራማትሊሃይ* + ብሎ ጠራው። +18 ከዚያም በጣም ተጠማ፤ ወደ ይሖዋም እንዲህ ሲል ጮኸ፦ “ይህ ታላቅ መዳን በአገልጋይህ እጅ እንዲፈጸም ያደረግከው አንተ ነበርክ። ታዲያ አሁን በውኃ ጥም ልሙት? በእነዚህ ባልተገረዙ ሰዎች እጅስ ልውደቅ?” +19 በመሆኑም አምላክ በሊሃይ የሚገኝ አንድ ዓለት ነደለ፤ ውኃም ከዓለቱ መውጣት ጀመረ።+ እሱም በጠጣ ጊዜ መንፈሱ* ተመለሰ፤ ብርታትም አገኘ። እስከ ዛሬ ድረስ በሊሃይ የሚገኘውን ያንን ቦታ ኤንሃቆሬ* ሲል የጠራው ለዚህ ነው። +20 እሱም በፍልስጤማውያን ዘመን ለ20 ዓመት በእስራኤል ውስጥ ፈራጅ ሆኖ አገለገለ።+ +3 ከዚያም አማቷ ናኦሚ እንዲህ አለቻት፦ “ልጄ ሆይ፣ መልካም ይሆንልሽ ዘንድ ቤት* ልፈልግልሽ አይገባም?+ +2 ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለም?+ አብረሻቸው የነበርሽው ወጣት ሴቶች የእሱ ናቸው። ዛሬ ማታ በአውድማው ላይ ገብስ ያዘራል። +3 ስለዚህ ተነስተሽ ተጣጠቢና ሰውነትሽን ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ተቀቢ፤ ከዚያም ልብስሽን ለባብሰሽ* ወደ አውድማው ውረጂ። ሰውየው በልቶና ጠ���ቶ እስኪጨርስ ድረስ እዚያ መኖርሽን እንዲያውቅ ማድረግ የለብሽም። +4 ሲተኛም የሚተኛበትን ቦታ ልብ ብለሽ እዪ፤ ከዚያም ሄደሽ እግሩን ገልጠሽ ተኚ። እሱም ምን ማድረግ እንዳለብሽ ይነግርሻል።” +5 እሷም “ያልሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አለቻት። +6 ስለዚህ ሩት ወደ አውድማው በመውረድ ሁሉንም ነገር ልክ አማቷ እንዳዘዘቻት አደረገች። +7 ቦዔዝም ከበላና ከጠጣ በኋላ ልቡ በደስታ ተሞላ። ከዚያም ሄዶ የተቆለለው እህል አጠገብ ተኛ። ሩትም በቀስታ መጥታ እግሩን ገልጣ ተኛች። +8 እኩለ ሌሊትም ሲሆን ቦዔዝ እየተንቀጠቀጠ ከእንቅልፉ ባነነ፤ ቀና ሲልም አንዲት ሴት እግሩ ሥር ተኝታ ተመለከተ። +9 እሱም “ለመሆኑ አንቺ ማን ነሽ?” አላት። እሷም መልሳ “እኔ አገልጋይህ ሩት ነኝ። መቤዠት+ የሚገባህ አንተ ስለሆንክ መጎናጸፊያህን በአገልጋይህ ላይ ጣል” አለችው። +10 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላት፦ “ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ ይባርክሽ። ሀብታምም ሆኑ ድሃ፣ ወጣት ወንዶችን ተከትለሽ ባለመሄድሽ ከበፊቱ ይልቅ+ አሁን ያሳየሽው ታማኝ ፍቅር በለጠ። +11 ስለዚህ የእኔ ልጅ፣ አትፍሪ። አንቺ ምግባረ መልካም ሴት መሆንሽን የከተማው* ሰው ሁሉ ስለሚያውቅ ያልሽውን ሁሉ አደርግልሻለሁ።+ +12 እኔ መቤዠት+ እንዳለብኝ የማይካድ ቢሆንም ከእኔ ይልቅ የቅርብ ዘመድ የሆነ መቤዠት የሚችል ሰው አለ።+ +13 ዛሬ እዚሁ እደሪ፤ ሲነጋም ሰውዬው የሚቤዥሽ ከሆነ፣ መልካም! እሱ ይቤዥሽ።+ ሊቤዥሽ የማይፈልግ ከሆነ ግን ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ እኔው ራሴ እቤዥሻለሁ። እስከ ማለዳ ድረስ ግን እዚሁ ተኚ።” +14 በመሆኑም እስኪነጋ ድረስ እግሩ ሥር ተኛች፤ ከዚያም ጎህ ቀዶ ሰውን በውል መለየት የሚያስችል ብርሃን ከመውጣቱ በፊት ተነሳች። እሱም “አንዲት ሴት ወደ አውድማው መጥታ እንደነበር ማንም አይወቅ” አለ። +15 በተጨማሪም “የለበስሽውን ኩታ ዘርግተሽ ያዢው” አላት። ስትዘረጋለትም ስድስት መስፈሪያ* ገብስ ሰፈረላትና አሸከማት፤ በኋላም ወደ ከተማ ሄደ። +16 እሷም ወደ አማቷ ሄደች፤ አማቷም “ልጄ ሆይ፣ እንዴት ሆነልሽ?”* አለቻት። ሩትም ሰውየው ያደረገላትን ሁሉ አንድ በአንድ ነገረቻት። +17 እንዲሁም “‘ወደ አማትሽ ባዶ እጅሽን አትሂጂ’ ብሎ ይህን ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰጠኝ” አለቻት። +18 በዚህ ጊዜ ናኦሚ እንዲህ አለቻት፦ “ልጄ ሆይ፣ ከዚህ በኋላ ቁርጡ እስኪታወቅ ድረስ ዝም ብለሽ ተቀመጪ፤ ምክንያቱም ሰውየው ዛሬውኑ ለጉዳዩ እልባት ሳያበጅ ዝም ብሎ አይቀመጥም።” +1 መሳፍንት+ ፍትሕን ያስፈጽሙ* በነበረበት ዘመን በምድሪቱ ላይ ረሃብ ተከሰተ፤ አንድ ሰው ከሚስቱና ከሁለት ወንዶች ልጆቹ ጋር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ ለመኖር በይሁዳ ከምትገኘው ከቤተልሔም+ ተነስቶ ወደ ሞዓብ+ ምድር አቀና። +2 የሰውየው ስም ኤሊሜሌክ፣* የሚስቱ ስም ናኦሚ፣* የሁለቱ ወንዶች ልጆቹ ስም ደግሞ ማህሎን* እና ኪሊዮን* ነበር። እነሱም በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም የሚኖሩ ኤፍራታውያን ነበሩ። ወደ ሞዓብም መጥተው በዚያ መኖር ጀመሩ። +3 ከጊዜ በኋላም የናኦሚ ባል ኤሊሜሌክ ሞተ፤ ስለሆነም ናኦሚ ከሁለት ልጆቿ ጋር ቀረች። +4 በኋላም ልጆቿ ሞዓባውያን ሴቶችን አገቡ፤ የአንደኛዋ ስም ዖርፋ፣ የሌላኛዋ ደግሞ ሩት+ ነበር። በዚያም ለአሥር ዓመት ያህል ኖሩ። +5 ከዚያም ሁለቱ ወንዶች ልጆቿ ማህሎንና ኪሊዮን ሞቱ፤ ናኦሚም ሁለት ልጆቿንና ባሏን አጥታ ብቻዋን ቀረች። +6 እሷም በሞዓብ ምድር ሳለች ይሖዋ ለሕዝቡ እህል በመስጠት ፊቱን ወደ እነሱ እንደመለሰ ስለሰማች ከምራቶቿ ጋር ወደ አገሯ ለመመለስ ከሞዓብ ተነሳች። +7 ከሁለቱ ምራቶቿም ጋር ትኖርበት የነበረውን ቦታ ትታ ሄደች። ወደ ይሁዳ ምድር ለመመለስ ወደ��ያ የሚወስደውን መንገድ ይዘው እየሄዱ ሳሉም +8 ናኦሚ ሁለቱን ምራቶቿን እንዲህ አለቻቸው፦ “ሂዱ፣ ሁለታችሁም ወደ እናቶቻችሁ ቤት ተመለሱ። ለሞቱት ባሎቻችሁና ለእኔ ታማኝ ፍቅር+ እንዳሳያችሁ ሁሉ ይሖዋም ለእናንተ ታማኝ ፍቅር ያሳያችሁ። +9 ይሖዋ በየባላችሁ ቤት+ ያለስጋት እንድትኖሩ ያድርጋችሁ።”* ከዚያም ሳመቻቸው፤ እነሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ማልቀስ ጀመሩ። +10 እንዲህም አሏት፦ “በፍጹም! ከአንቺ ጋር ወደ ወገኖችሽ እንሄዳለን።” +11 ናኦሚ ግን እንዲህ አለቻቸው፦ “ልጆቼ፣ ተመለሱ። ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ለእናንተ ባሎች ሊሆኑ የሚችሉ ወንዶች ልጆች አሁንም ልወልድ የምችል ይመስላችኋል?+ +12 ልጆቼ፣ ተመለሱ። እኔ እንደሆነ በጣም ስላረጀሁ ከእንግዲህ ባል ላገባ አልችልም፤ ስለዚህ ሂዱ። ዛሬ ማታ ባል የማግኘትና ልጆች የመውለድ ተስፋ ቢኖረኝ እንኳ +13 እስኪያድጉ ድረስ ትጠብቃላችሁ? እነሱን በመጠበቅስ ባል ሳታገቡ ትቆያላችሁ? ልጆቼ፣ ይሄማ አይሆንም፤ የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ስለተነሳ የእናንተን ሁኔታ ሳስብ ሕይወቴ መራራ ይሆንብኛል።”+ +14 እነሱም እንደገና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ከዚያም ዖርፋ አማቷን ስማ ተሰናበተቻት። ሩት ግን ከእሷ ላለመለየት የሙጥኝ አለች። +15 ናኦሚም “ተመልከች፣ መበለት የሆነችው የባልሽ ወንድም ሚስት ወደ ወገኖቿና ወደ አማልክቷ ተመልሳለች። አብረሻት ተመለሽ” አለቻት። +16 ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ከአንቺ እንድለይና ትቼሽ እንድመለስ አትማጸኚኝ፤ እኔ እንደሆነ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምታድሪበት አድራለሁ። ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል።+ +17 በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በዚያም እቀበራለሁ። ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ቢኖር ይሖዋ አንዳች ነገር ያምጣብኝ፤ ከዚያም የከፋ ያድርግብኝ።” +18 ናኦሚ፣ ሩት ከእሷ ጋር ለመሄድ እንደቆረጠች ስታውቅ መወትወቷን አቆመች። +19 ከዚያም ወደ ቤተልሔም ጉዟቸውን ቀጠሉ።+ ቤተልሔም እንደደረሱም በእነሱ ምክንያት መላ ከተማዋ ታመሰች፤ ሴቶቹም “ይህች ናኦሚ አይደለችም እንዴ?” ይሉ ነበር። +20 እሷም እንዲህ ትላቸው ነበር፦ “ናኦሚ* ብላችሁ አትጥሩኝ። ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሕይወቴን መራራ አድርጎታልና ማራ* ብላችሁ ጥሩኝ።+ +21 ከዚህ ስወጣ ሙሉ ነበርኩ፤ ይሖዋ ግን ባዶ እጄን እንድመለስ አደረገኝ። ይሖዋ ተቃውሞኝና ሁሉን የሚችለው አምላክ መከራ አምጥቶብኝ ሳለ ለምን ናኦሚ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ?”+ +22 እንግዲህ ናኦሚ ምራቷ ከሆነችው ከሞዓባዊቷ ሩት ጋር ከሞዓብ ምድር+ የተመለሰችው በዚህ ሁኔታ ነበር። ቤተልሔም የደረሱትም የገብስ አዝመራ መሰብሰብ በጀመረበት ወቅት ነበር።+ +2 ናኦሚ በባሏ በኩል ሀብታም የሆነ የቅርብ ዘመድ ነበራት፤ ይህ ሰው ቦዔዝ+ የሚባል ሲሆን የኤሊሜሌክ ቤተሰብ ነበር። +2 ሞዓባዊቷም ሩት ናኦሚን “እባክሽ ወደ እርሻ ቦታዎቹ ልሂድና ሞገስ የሚያሳየኝ ሰው ካገኘሁ እህል ልቃርም”+ አለቻት። ናኦሚም “ልጄ ሆይ፣ ሂጂ” አለቻት። +3 ሩትም ሄደች፤ በማሳውም ውስጥ ከአጫጆቹ ኋላ እየተከተለች መቃረም ጀመረች። እንደ አጋጣሚ ሆኖ የገባችው የኤሊሜሌክ ቤተሰብ+ ወደሆነው ወደ ቦዔዝ+ እርሻ ነበር። +4 በዚህ ጊዜ ቦዔዝ ከቤተልሔም መጣ፤ አጫጆቹንም “ይሖዋ ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው። እነሱም “ይሖዋ ይባርክህ” ብለው መለሱለት። +5 ከዚያም ቦዔዝ የአጫጆቹ አለቃ የሆነውን ወጣት “ይህች ወጣት የማን ነች?” ሲል ጠየቀው። +6 የአጫጆቹ አለቃ የሆነው ወጣትም እንዲህ በማለት መለሰ፦ “ወጣቷ፣ ናኦሚ ከሞዓብ ምድር+ ስትመለስ አብራት የመጣች ሞዓባዊት+ ነች። +7 እሷም ‘እባክህ፣ ከአጫጆቹ ኋላ እየተከተልኩ የወደቁትን ዛላዎች* መቃረም+ እችላለሁ?’ አለችኝ። ይኸው ወደዚህ ከመጣችበት ከጠዋት አንስቶ ወደ ዳሱ ገብታ ጥቂት አረፍ እስካለችበት እስካሁን ድረስ አንዴም እንኳ ቁጭ አላለችም።” +8 ከዚያም ቦዔዝ ሩትን እንዲህ አላት፦ “ልጄ ሆይ፣ ስሚኝ። ለመቃረም ወደ ሌላ እርሻ አትሂጂ፤ የትም አትሂጂ፤ ከወጣት ሴት ሠራተኞቼም አትራቂ።+ +9 የሚያጭዱበትን ማሳ እያየሽ አብረሻቸው ሂጂ። ወጣቶቹም ወንዶች እንዳይነኩሽ* አዝዣቸዋለሁ። ውኃ ሲጠማሽ ወደ እንስራዎቹ ሄደሽ ወጣቶቹ ቀድተው ካስቀመጡት ጠጪ።” +10 እሷም መሬት ላይ በግንባሯ ተደፍታ በመስገድ “እኔ የባዕድ አገር ሰው ሆኜ+ ሳለሁ በፊትህ ሞገስ ላገኝ የበቃሁትና ትኩረት ልትሰጠኝ የቻልከው እንዴት ነው?” አለችው። +11 ቦዔዝም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ባልሽ ከሞተ በኋላ ለአማትሽ ያደረግሽላትን ሁሉ እንዲሁም አባትሽን፣ እናትሽንና ዘመዶችሽ የሚኖሩበትን አገር ትተሽ ቀድሞ ወደማታውቂው ሕዝብ እንዴት እንደመጣሽ በሚገባ ሰምቻለሁ።+ +12 ላደረግሽው ሁሉ ይሖዋ ብድራትሽን ይመልስልሽ፤+ በክንፎቹ ሥር ለመጠለል+ ብለሽ ወደ እሱ የመጣሽበት የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሙሉ ዋጋሽን* ይክፈልሽ።” +13 እሷም መልሳ “ጌታዬ ሆይ፣ እኔ ከሴት አገልጋዮችህ አንዷ ባልሆንም እንኳ ስላጽናናኸኝና እኔን አገልጋይህን በሚያበረታታ መንገድ ስላነጋገርከኝ* ምንጊዜም በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለችው። +14 የምግብ ሰዓትም ሲደርስ ቦዔዝ “ወደዚህ ቀረብ በይ፤ ዳቦ ወስደሽ ብዪ፤ የቆረስሽውንም ሆምጣጤ ውስጥ አጥቅሺ” አላት። በመሆኑም ከአጫጆቹ ጋር ተቀመጠች። እሱም ቆሎ ዘግኖ ሰጣት፤ እሷም እስክትጠግብ ድረስ በላች፤ የተወሰነም ተረፋት። +15 ለመቃረም+ በተነሳች ጊዜም ቦዔዝ ወጣቶቹን ወንዶች እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ከታጨዱት ዛላዎች* ላይ እንኳ ሳይቀር ትቃርም፤ ምንም እንዳትበድሏት።+ +16 ከታሰረው ነዶ ላይም የተወሰኑ ዛላዎችን እየመዘዛችሁ ጣሉላትና ትቃርም፤ ማንም እንዳይከለክላት።” +17 እሷም እስከ ማታ ድረስ ስትቃርም ቆየች።+ የቃረመችውንም ገብስ በወቃችው ጊዜ አንድ የኢፍ* መስፈሪያ ያህል ሆነ። +18 እህሉንም ይዛ ወደ ከተማ ሄደች፤ አማቷም ምን ያህል እንደቃረመች አየች። በተጨማሪም ሩት በልታ ከጠገበች በኋላ አስተርፋ ያመጣችውን ምግብ+ አውጥታ ለአማቷ ሰጠቻት። +19 በዚህ ጊዜ አማቷ “ዛሬ የቃረምሽው የት ነው? የትስ ስትሠሪ ዋልሽ? ትኩረት የሰጠሽ ሰው የተባረከ ይሁን” አለቻት።+ እሷም “ዛሬ ስሠራ የዋልኩት ቦዔዝ በተባለ ሰው እርሻ ውስጥ ነው” በማለት ከማን ጋር ስትሠራ እንደዋለች ለአማቷ ነገረቻት። +20 ናኦሚም ምራቷን “ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ታማኝ ፍቅሩን ከማሳየት ወደኋላ የማይለው ይሖዋ ይባርከው” አለቻት።+ አክላም “ሰውየው ዘመዳችን ነው።+ ከሚቤዡን ሰዎች አንዱ ነው”* አለች።+ +21 ከዚያም ሞዓባዊቷ ሩት “ደግሞም ‘ወጣቶቹ ሠራተኞቼ አዝመራዬን በሙሉ ሰብስበው እስኪጨርሱ ድረስ ከእነሱ አትራቂ’ ብሎኛል” አለቻት።+ +22 ናኦሚም ምራቷን ሩትን “ልጄ ሆይ፣ ወደ ሌላ እርሻ ብትሄጂ ሊተናኮሉሽ ስለሚችሉ ከእሱ ሴት ሠራተኞች ጋር አብረሽ መሆን ይሻልሻል” አለቻት። +23 ስለዚህ ሩት የገብሱ አዝመራና+ የስንዴው አዝመራ ተሰብስቦ እስኪያልቅ ድረስ ከቦዔዝ ሴት ሠራተኞች ሳትርቅ ስትቃርም ቆየች። ከአማቷም ጋር መኖሯን ቀጠለች።+ +4 ከዚያም ቦዔዝ ወደ ከተማዋ በር+ ሄዶ በዚያ ተቀመጠ። በዚህ ጊዜ ቦዔዝ ቀደም ሲል ጠቅሶት የነበረው የሚቤዠው ሰው+ በዚያ ሲያልፍ ተመለከተ። ቦዔዝም “እገሌ፣ አንዴ ወደዚህ ና፤ እዚህ ተቀመጥ” አለው። ሰውየውም መጥቶ ተቀመጠ። +2 ከዚያም ቦዔዝ ከከተማዋ ሽማግሌዎች+ መካከል አሥር ሰ���ች አምጥቶ “እዚህ ተቀመጡ” አላቸው። እነሱም ተቀመጡ። +3 ቦዔዝም የሚቤዠውን+ ሰው እንዲህ አለው፦ “ከሞዓብ ምድር+ የተመለሰችው ናኦሚ የወንድማችንን የኤሊሜሌክን+ የእርሻ ቦታ ልትሸጠው ነው። +4 ስለዚህ ጉዳዩን ለአንተ ላሳውቅህና እንዲህ ልልህ አሰብኩ፦ ‘እዚህ በተሰበሰቡት ነዋሪዎችና በአገሬ ሽማግሌዎች ፊት ግዛው።+ ልትቤዠው የምትፈልግ ከሆነ ተቤዠው። ልትቤዠው የማትፈልግ ከሆነ ግን ንገረኝና ልወቀው፤ ምክንያቱም በቅድሚያ የመቤዠት መብት ያለህ አንተ ነህ፤ እኔ ደግሞ ከአንተ ቀጥሎ ነኝ።’” ሰ +5 ከዚያም ቦዔዝ “መሬቱን ከናኦሚ በምትገዛበት ቀን ውርሱ በሟቹ ስም እንዲጠራ ለማድረግ የሟቹ ሚስት ከሆነችው ከሞዓባዊቷ ሩት ላይም መግዛት እንዳለብህ እወቅ” አለው።+ +6 የሚቤዠውም ሰው “የገዛ ርስቴን አደጋ ላይ ልጥል ስለምችል ልቤዠው አልችልም። እኔ ልቤዠው ስለማልችል በእኔ የመቤዠት መብት ተጠቅመህ አንተ ለራስህ ተቤዠው” አለው። +7 በጥንት ዘመን በእስራኤል ውስጥ በነበረው ልማድ መሠረት ከመቤዠት መብትም ሆነ ይህን መብት ለሌላ ሰው ከማስተላለፍ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ዓይነት ስምምነት የሚጸድቀው አንድ ሰው ጫማውን አውልቆ+ ለሌላው ወገን ሲሰጥ ነበር፤ በእስራኤል ውስጥ አንድ ውል* የሚጸናው በዚህ መንገድ ሲከናወን ነበር። +8 በመሆኑም የሚቤዠው ሰው ቦዔዝን “አንተ ለራስህ ግዛው” በማለት ጫማውን አወለቀ። +9 ከዚያም ቦዔዝ ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “የኤሊሜሌክ የሆነውን ሁሉ እንዲሁም የኪሊዮንና የማህሎን የሆነውን ሁሉ ከናኦሚ ለመግዛቴ ዛሬ እናንተ ምሥክሮች ናችሁ።+ +10 በተጨማሪም የሟቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል እንዲሁም ከሚኖርባት ከተማ በር እንዳይጠፋ የሟቹን ስም ዳግም በርስቱ ለማስጠራት+ የማህሎን ሚስት የሆነችውን ሞዓባዊቷን ሩትን ሚስት አድርጌ ወስጃታለሁ። ለዚህም እናንተ ዛሬ ምሥክሮች ናችሁ።”+ +11 በዚህ ጊዜ በከተማዋ በር ላይ የነበሩት ሰዎች ሁሉና ሽማግሌዎቹ እንዲህ አሉ፦ “እኛ ምሥክሮች ነን! ይሖዋ ወደ ቤትህ የምትገባውን ሚስት የእስራኤልን ቤት እንደገነቡት እንደ ራሔልና እንደ ሊያ ያድርጋት።+ አንተም በኤፍራታ+ የበለጸግክ ሁን፤ በቤተልሔምም+ መልካም ስም አትርፍ።* +12 እንዲሁም ይሖዋ ከዚህች ወጣት ሴት በሚሰጥህ ዘር አማካኝነት ቤትህ ትዕማር ለይሁዳ እንደወለደችለት እንደ ፋሬስ+ ቤት ይሁን።”+ +13 በመሆኑም ቦዔዝ ሩትን ወሰዳት፤ ሚስቱም ሆነች። ከእሷም ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ ይሖዋም እንድትፀንስ አደረጋት፤ ወንድ ልጅም ወለደች። +14 ሴቶቹም ናኦሚን እንዲህ አሏት፦ “ዛሬ የሚቤዥ ሰው ያላሳጣሽ ይሖዋ ይወደስ። ስሙም በእስራኤል ይታወጅ! +15 የምትወድሽና+ ከሰባት ወንዶች ልጆች የምትበልጥብሽ ምራትሽ የወለደችው ስለሆነ እሱ* ሕይወትሽን* የሚያድስ ይሆናል፤ በእርጅናሽም ዘመን ይጦርሻል።” +16 ናኦሚም ልጁን ወስዳ አቀፈችው፤ ትንከባከበውም ጀመር።* +17 ከዚያም ጎረቤቶቿ የሆኑ ሴቶች ስም አወጡለት። እንዲሁም “ለናኦሚ ወንድ ልጅ ተወለደላት” አሉ፤ ስሙንም ኢዮቤድ+ አሉት። እሱም የዳዊት አባት የሆነው የእሴይ+ አባት ነው። +18 እንግዲህ የፋሬስ+ የትውልድ ሐረግ ይህ ነው፦ ፋሬስ ኤስሮንን+ ወለደ፤ +19 ኤስሮንም ራምን ወለደ፤ ራምም አሚናዳብን ወለደ፤+ +20 አሚናዳብም+ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ +21 ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ +22 ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤+ እሴይም ዳዊትን+ ወለደ። +17 ፍልስጤማውያን+ ሠራዊታቸውን ለውጊያ አሰባሰቡ። እነሱም በይሁዳ በምትገኘው በሶኮህ+ ከተሰባሰቡ በኋላ በሶኮህ እና በአዜቃ+ መካከል በምትገኘው በኤፌስዳሚም+ ሰፈሩ። +2 ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ደግሞ ተሰባስበው በኤላህ ሸለቆ*+ ውስጥ ሰፈሩ፤ እነሱም ለጦርነት ተሰልፈው ፍልስጤማውያንን ለመግጠም ወጡ። +3 ፍልስጤማውያን በአንድ በኩል ያለውን ተራራ ያዙ፣ እስራኤላውያን ደግሞ በሌላ በኩል ያለውን ተራራ ያዙ፤ በመካከላቸውም ሸለቆ ነበር። +4 በዚህ ጊዜ አንድ ኃያል ተዋጊ ከፍልስጤማውያን ሰፈር ብቅ አለ፤ እሱም የጌት+ ሰው ሲሆን ስሙ ጎልያድ+ ይባላል፤ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከአንድ ስንዝር* ነበር። +"5 እሱም ከመዳብ የተሠራ የራስ ቁር ደፍቶ ነበር፤ እንዲሁም ከተነባበሩ ጠፍጣፋ መዳቦች የተሠራ ጥሩር ለብሶ ነበር። የጥሩሩም+ ክብደት 5,000 ሰቅል* ነበር።" +6 ቅልጥሙ ላይ ከመዳብ የተሠራ ገምባሌ አድርጎ ነበር፤ በትከሻውና በትከሻውም መካከል ከመዳብ የተሠራ ጦር+ አንግቶ ነበር። +7 የጭሬውም ዘንግ የሸማኔ መጠቅለያ ያህል ነበር፤+ ከብረት የተሠራው የጭሬው ጫፍ 600 ሰቅል* ነበር፤ ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር። +8 ከዚያም ጎልያድ ከቆመበት ቦታ ሆኖ የተሰለፈውን የእስራኤል ሠራዊት+ በመጣራት እንዲህ አላቸው፦ “ለውጊያ ተሰልፋችሁ የወጣችሁት ለምንድን ነው? እኔ ፍልስጤማዊ፣ እናንተ ደግሞ የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁም? እንግዲህ አንድ ሰው ምረጡና ወደ እኔ ይውረድ። +9 ከእኔ ጋር ተዋግቶ እኔን መግደል ከቻለ እኛ የእናንተ አገልጋዮች እንሆናለን። እኔ ባሸንፈውና ብገድለው ግን እናንተ የእኛ አገልጋዮች ትሆናላችሁ፤ እኛንም ታገለግላላችሁ።” +10 በመቀጠልም ፍልስጤማዊው “ዛሬ፣ ለውጊያ የተሰለፈውን የእስራኤል ሠራዊት እሳለቅበታለሁ።*+ በሉ አሁን አንድ ሰው ምረጡና እንጋጠም!” አለ። +11 ሳኦልና እስራኤላውያን በሙሉ ፍልስጤማዊው የተናገረውን ይህን ቃል ሲሰሙ ተሸበሩ፤ እንዲሁም በጣም ፈሩ። +12 ዳዊት በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም+ የሚኖረው የኤፍራታዊው+ የእሴይ ልጅ ነበር፤ እሴይ+ ስምንት ወንዶች ልጆች+ የነበሩት ሲሆን በሳኦል የንግሥና ዘመን ዕድሜው ገፍቶ ነበር። +13 ሦስቱ የእሴይ ትላልቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ውጊያው ሄደው ነበር።+ ወደ ውጊያው የሄዱት ሦስቱ ወንዶች ልጆቹ የበኩር ልጁ ኤልያብ፣+ ሁለተኛ ልጁ አቢናዳብና+ ሦስተኛ ልጁ ሻማህ+ ነበሩ። +14 ዳዊት የሁሉም ታናሽ ነበር፤+ ትላልቆቹ ሦስቱ ሳኦልን ተከትለው ሄደው ነበር። +15 ዳዊት ሳኦልን ያገለግል እንዲሁም ከዚያ እየተመላለሰ በቤተልሔም የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር።+ +16 ይህ በእንዲህ እንዳለ ፍልስጤማዊው 40 ቀን ሙሉ ጠዋትና ማታ ወደ እነሱ በመቅረብ ፊታቸው ቆሞ ይገዳደራቸው ነበር። +17 ከዚያም እሴይ ልጁን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “እስቲ እባክህ ይህን አንድ የኢፍ* መስፈሪያ ቆሎና እነዚህን አሥር ዳቦዎች ይዘህ በጦር ሰፈሩ ውስጥ ላሉት ወንድሞችህ ቶሎ አድርስላቸው። +18 እንዲሁም ይህን አሥር የአይብ ጥፍጥፍ ለሺህ አለቃው ውሰድለት፤ በተጨማሪም ወንድሞችህ እንዴት እንደሆኑ አይተህ ደህንነታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘህ ና።” +19 የዳዊት ወንድሞች ከሳኦልና ከሌሎቹ የእስራኤል ሰዎች ጋር ሆነው በኤላህ ሸለቆ*+ ከፍልስጤማውያን ጋር እየተዋጉ ነበር።+ +20 በመሆኑም ዳዊት በማለዳ ተነስቶ በጎቹን ለጠባቂ ሰጠ፤ ከዚያም ዕቃዎቹን ይዞ እሴይ ባዘዘው መሠረት ሄደ። እሱም ወደ ጦር ሰፈሩ ሲደርስ የጦር ሠራዊቱ እየፎከረ ወደ ጦር ግንባሩ እየወጣ ነበር። +21 ለጦርነት የተሰለፉት እስራኤላውያንና ፍልስጤማውያንም ፊት ለፊት ተፋጠው ነበር። +22 ዳዊትም ወዲያውኑ ዕቃውን ስንቅ ጠባቂው ጋ አስቀምጦ ወደ ጦር ግንባሩ እየሮጠ ሄደ። እዚያም ሲደርስ የወንድሞቹን ደህንነት መጠየቅ ጀመረ።+ +23 እሱም ከእነሱ ጋር እየተነጋገረ ሳለ የጌት ሰው የሆ��ው ጎልያድ+ የተባለው ኃያል ፍልስጤማዊ ተዋጊ መጣ። እሱም ለውጊያ ከተሰለፉት ፍልስጤማውያን መካከል ብቅ ብሎ እንደ በፊቱ መደንፋት ጀመረ፤+ ዳዊትም ሰማው። +24 የእስራኤልም ሰዎች በሙሉ ሰውየውን ሲመለከቱት እጅግ ተሸብረው ከፊቱ ሸሹ።+ +25 እነሱም እንዲህ ይሉ ነበር፦ “እየመጣ ያለውን ይህን ሰው አያችሁት? የሚመጣው እኮ በእስራኤል ላይ ለመሳለቅ ነው።+ እሱን ለሚገድል ሰው ንጉሡ ብዙ ሀብት ይሰጠዋል፤ ሴት ልጁንም ይድርለታል፤+ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ውስጥ ከማንኛውም ዓይነት ግዴታ ነፃ እንዲሆን ያደርጋል።” +26 ዳዊትም አጠገቡ ቆመው የነበሩትን ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “ለመሆኑ ያን ፍልስጤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ላይ ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጤማዊ ሕያው በሆነው አምላክ ሠራዊት ላይ የሚሳለቀው ማን ስለሆነ ነው?”+ +27 ሰዎቹም “ለሚገድለው ሰውማ እንዲህ እንዲህ ይደረግለታል” በማለት ቀደም ሲል የተናገሩትን ነገር ደገሙለት። +28 ታላቅ ወንድሙ ኤልያብም+ ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ሲሰማ በእሱ ላይ እጅግ ተቆጥቶ እንዲህ አለው፦ “ወደዚህ የወረድከው ለምንድን ነው? ለመሆኑ እነዚያን ጥቂት በጎች ምድረ በዳ ላይ ለማን ተውካቸው?+ እኔ ትዕቢትህንና የልብህን ክፉ ሐሳብ መች አጣሁት፤ ወደዚህ የመጣኸው ለሌላ ሳይሆን ውጊያውን ለማየ +29 ዳዊትም መልሶ “ቆይ አሁን ምን አጠፋሁ? ጥያቄ እኮ ነው የጠየቅኩት!” አለ። +30 ከዚያም ከእሱ ዞር ብሎ ያንኑ ጥያቄ ሌላ ሰው ጠየቀ፤+ ሰዎቹም እንደቀድሞው ያንኑ መልስ ሰጡት።+ +31 ዳዊት የተናገረው ነገር ተሰማ፤ ለሳኦልም ተነገረው። ስለዚህ ሳኦል ልኮ አስጠራው። +32 ዳዊትም ሳኦልን “በዚህ ሰው የተነሳ የማንም ሰው ልብ አይቅለጥ።* አገልጋይህ ሄዶ ከዚህ ፍልስጤማዊ ጋር ይዋጋል” አለው።+ +33 ሳኦል ግን ዳዊትን “አንተ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነህ፤+ እሱ ግን ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነው፤ ስለዚህ ይህን ፍልስጤማዊ ልትገጥመው አትችልም” አለው። +34 ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “አገልጋይህ የአባቱን መንጋ በሚጠብቅበት ጊዜ አንበሳ+ እንዲሁም ድብ ይመጣና ከመንጋው መካከል አንድ በግ ነጥቆ ይወስድ ነበር። +35 እኔም ተከትዬው በመሄድ እመታውና በጉን ከአፉ አስጥለው ነበር። ሊያጠቃኝ በተነሳ ጊዜም ጉሮሮውን አንቄ* በመምታት እገድለው ነበር። +36 አገልጋይህ አንበሳውንም ሆነ ድቡን ገድሏል፤ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጤማዊም ሕያው በሆነው አምላክ ሠራዊት ላይ ስለተሳለቀ መጨረሻው ከእነሱ እንደ አንዱ ይሆናል።”+ +37 ዳዊትም በመቀጠል “ከአንበሳና ከድብ ጥፍር የታደገኝ ይሖዋ አሁንም ከዚህ ፍልስጤማዊ እጅ ይታደገኛል” አለ።+ በዚህ ጊዜ ሳኦል ዳዊትን “እሺ ሂድ፤ ይሖዋ ከአንተ ጋር ይሁን” አለው። +38 ከዚያም ሳኦል ለዳዊት የራሱን ልብሶች አለበሰው። በራሱም ላይ ከመዳብ የተሠራ ቁር ደፋለት፤ ጥሩርም አለበሰው። +39 በኋላም ዳዊት ሰይፉን በልብሱ ላይ ታጥቆ ለመራመድ ሞከረ፤ ሆኖም ከዚህ በፊት እንደዚህ ዓይነት ትጥቅ ታጥቆ ስለማያውቅ መራመድ አልቻለም። ዳዊትም ሳኦልን “እንዲህ ያሉ ትጥቆችን ታጥቄ ስለማላውቅ እነሱን አድርጌ መራመድ አልቻልኩም” አለው። በመሆኑም ዳዊት ከላዩ ላይ አወለቃቸው። +40 ከዚያም በትሩን በእጁ ያዘ፤ አምስት ድቡልቡል ድንጋዮችንም ከወንዝ* ከመረጠ በኋላ በእረኛ ኮሮጆው ውስጥ ጨመራቸው፤ በእጁም ወንጭፉን+ ይዞ ነበር። ከዚያም ወደ ፍልስጤማዊው ቀረበ። +41 ፍልስጤማዊውም ወደ ዳዊት እየቀረበ መጣ፤ ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር። +42 ፍልስጤማዊውም ዳዊትን ትኩር ብሎ ሲያየው ዳዊት የቀይ ዳማና መልከ መልካም የሆነ አንድ ፍ��� ልጅ+ ስለነበር ናቀው። +43 በመሆኑም ፍልስጤማዊው ዳዊትን “በትር ይዘህ ወደ እኔ የምትመጣው እኔ ውሻ ነኝ?”+ አለው። በአማልክቱም ስም ረገመው። +44 ከዚያም “እስቲ ወደ እኔ ና፤ ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው። +45 ዳዊትም መልሶ ፍልስጤማዊውን እንዲህ አለው፦ “አንተ ሰይፍ፣ ጭሬና ጦር+ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተሳለቅክበት፣+ የእስራኤል ተዋጊዎች አምላክ በሆነው በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ስም+ እመጣብሃለሁ። +46 ዛሬ ይሖዋ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጥሃል፤+ እኔም አንተን ገድዬ ራስህን እቆርጠዋለሁ፤ በዚህ ቀን የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ሬሳ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ በመላው ምድር የሚኖሩ ሰዎችም በእስራኤል አምላክ እንዳለ ያውቃሉ።+ +47 እዚህ የተሰበሰቡትም ሁሉ ይሖዋ የሚያድነው በሰይፍ ወይም በጦር እንዳልሆነ ያውቃሉ፤+ ምክንያቱም ውጊያው የይሖዋ ነው፤+ እሱም ሁላችሁንም በእጃችን አሳልፎ ይሰጣችኋል።”+ +48 ፍልስጤማዊውም ተነስቶ ዳዊትን ለመግጠም ወደ እሱ እየተራመደ መጣ፤ ዳዊትም ፍልስጤማዊውን ለመግጠም ወደ ጦር ግንባሩ እየተንደረደረ ሄደ። +49 ከዚያም ዳዊት እጁን ወደ ኮሮጆው በመስደድ አንድ ድንጋይ አውጥቶ ወነጨፈው። ፍልስጤማዊውንም ግንባሩ ላይ መታው፤ ድንጋዩም ግንባሩ ውስጥ ገብቶ ተቀረቀረ፤ ሰውየውም በአፍጢሙ መሬት ላይ ተደፋ።+ +50 በዚህ ሁኔታ ዳዊት ፍልስጤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፤ ዳዊት በእጁ ሰይፍ ባይዝም ፍልስጤማዊውን መትቶ ገደለው።+ +51 ከዚያም ዳዊት እየሮጠ ሄዶ ላዩ ላይ ቆመ። የፍልስጤማዊውንም ሰይፍ+ ከሰገባው ውስጥ በመምዘዝ አንገቱን ቆርጦ ገደለው። ፍልስጤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ሲያዩ ሸሹ።+ +52 በዚህ ጊዜ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነስተው እየጮኹ ፍልስጤማውያኑን ከሸለቆው+ አንስቶ እስከ ኤቅሮን+ በሮች ድረስ አሳደዷቸው፤ የፍልስጤማውያኑም ሬሳ ከሻአራይም+ አንስቶ እስከ ጌት እና እስከ ኤቅሮን ድረስ በየመንገዱ ወድቆ ነበር። +53 እስራኤላውያን ፍልስጤማውያኑን ከማሳደድ ከተመለሱ በኋላ ሰፈሮቻቸውን በዘበዙ። +54 ዳዊትም የፍልስጤማዊውን ራስ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የፍልስጤማዊውን የጦር መሣሪያዎች ግን በራሱ ድንኳን ውስጥ አስቀመጣቸው።+ +55 ዳዊት፣ ፍልስጤማዊውን ለመግጠም በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ዳዊትን ተመልክቶ የሠራዊቱን አዛዥ አበኔርን+ “አበኔር፣ ለመሆኑ ይህ የማን ልጅ ነው?”+ አለው። አበኔርም መልሶ “ንጉሥ ሆይ፣ በሕያውነትህ እምላለሁ፣* አላውቅም!” አለው። +56 ንጉሡም “ይህ ወጣት የማን ልጅ እንደሆነ አጣራ” አለው። +57 ስለዚህ ዳዊት ፍልስጤማዊውን ገድሎ ሲመለስ አበኔር ዳዊትን ወስዶ የፍልስጤማዊውን ራስ+ በእጁ እንደያዘ ንጉሡ ፊት አቀረበው። +58 ሳኦልም “አንተ ወጣት፣ የማን ልጅ ነህ?” ሲል ጠየቀው፤ ዳዊትም መልሶ “የቤተልሔም+ ሰው የሆነው የአገልጋይህ የእሴይ+ ልጅ ነኝ” አለው። +30 በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ+ ሲመጡ አማሌቃውያን+ በስተ ደቡብ* ያለውን አካባቢና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ እነሱም በጺቅላግ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ በእሳትም አቃጠሏት። +2 ሴቶችንና+ በዚያ የነበሩትንም ሁሉ ትንሽ ትልቅ ሳይሉ ማርከው ወሰዱ። አንድም ሰው አልገደሉም፤ ከዚህ ይልቅ ሁሉንም ይዘው ሄዱ። +3 ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ ሲመጡ ከተማዋ በእሳት ተቃጥላ አገኟት፤ ሚስቶቻቸውም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በምርኮ ተወስደው ነበር። +4 በመሆኑም ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ለማልቀስ አቅም እስኪያጡ ድረስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። +5 ሁለቱ የዳዊት ሚስቶችም ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አኪኖዓም እና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢጋኤል በምርኮ ተወስደው ነበር።+ +6 ዳዊት ሰዎቹ ሊወግሩት እየተማከሩ ስለነበር እጅግ ተጨነቀ፤ ምክንያቱም ሰዎቹ* ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በመወሰዳቸው ተመርረው ነበር። ይሁንና ዳዊት በአምላኩ በይሖዋ ራሱን አበረታ።+ +7 ከዚያም ዳዊት የአሂሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን+ “እባክህ፣ ኤፉዱን አምጣልኝ”+ አለው። አብያታርም ኤፉዱን ለዳዊት አመጣለት። +8 ዳዊትም “ይህን ወራሪ ቡድን ላሳደው? እደርስበት ይሆን?” ሲል ይሖዋን ጠየቀ።+ እሱም “በእርግጥ ስለምትደርስባቸውና የወሰዱትን ሁሉ ከእጃቸው ስለምታስጥል ሂድ አሳዳቸው” አለው።+ +9 ዳዊትም ወዲያውኑ አብረውት ከነበሩት 600 ሰዎች+ ጋር ወጣ፤ እነሱም እስከ በሶር ሸለቆ* ድረስ ሄዱ፤ በዚያም የተወሰኑ ሰዎች ወደ ኋላ ቀሩ። +10 ዳዊትም ከ400 ሰዎች ጋር ሆኖ ማሳደዱን ቀጠለ፤ በጣም ከመድከማቸው የተነሳ የበሶርን ሸለቆ መሻገር ያልቻሉት 200 ሰዎች ግን እዚያው ቀሩ።+ +11 ከዚያም ሜዳ ላይ አንድ ግብፃዊ አግኝተው ወደ ዳዊት አመጡት። የሚበላው ምግብና የሚጠጣው ውኃ ሰጡት። +12 በተጨማሪም ቁራሽ የበለስ ጥፍጥፍና ሁለት የዘቢብ ቂጣ ሰጡት። እሱም ከበላ በኋላ ብርታት አገኘ፤* ምክንያቱም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ሙሉ እህልም ሆነ ውኃ አልቀመሰም ነበር። +13 ዳዊትም “ለመሆኑ አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው?” አለው፤ እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እኔ ለአንድ አማሌቃዊ ባሪያ የሆንኩ ግብፃዊ ነኝ፤ ሆኖም ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ ስለነበር ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ። +14 የከሪታውያንን+ ምድር ደቡባዊ ክፍል፣* የይሁዳን ግዛትና የካሌብን+ ደቡባዊ ክፍል* ወረርን፤ ጺቅላግንም በእሳት አጋየናት።” +15 በዚህ ጊዜ ዳዊት “ይህ ወራሪ ቡድን ወዳለበት መርተህ ትወስደኛለህ?” አለው። እሱም “ብቻ እንደማትገድለኝና ለጌታዬ አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ በአምላክ ማልልኝ እንጂ ወራሪው ቡድን ወዳለበት መርቼ አደርስሃለሁ” አለው። +16 በመሆኑም ሰዎቹ ከፍልስጤማውያን ምድርና ከይሁዳ ምድር በወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሳ በየቦታው ተበታትነው ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ይደሰቱ ወደነበረበት ቦታ መርቶ ወሰደው። +17 ከዚያም ዳዊት ጎህ ሳይቀድ ጀምሮ እስከ ማግስቱ ምሽት ድረስ መታቸው፤ ፈጽሞም አጠፋቸው፤ በግመል ተቀምጠው ከሸሹት 400 ሰዎች በስተቀር አንድም ሰው አላመለጠም።+ +18 ዳዊትም አማሌቃውያን የወሰዱትን ሁሉ አስጣለ፤+ ሁለቱን ሚስቶቹንም አስመለሰ። +19 ከትንሽ እስከ ትልቅ ምንም የጎደለ ነገር አልነበረም። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ሆነ ዘርፈው የወሰዱባቸውን ንብረት ሁሉ አስመለሱ፤+ ዳዊት የወሰዱትን ሁሉ አስመለሰ። +20 በመሆኑም ዳዊት መንጎቹንና ከብቶቹን በሙሉ ወሰደ፤ እነሱም ከራሳቸው ከብቶች ፊት ፊት ነዷቸው። እነሱም “ይህ የዳዊት ምርኮ ነው” አሉ። +21 ከዚያም ዳዊት በጣም ከመድከማቸው የተነሳ አብረውት ሊሄዱ ወዳልቻሉትና በበሶር ሸለቆ+ ቀርተው ወደነበሩት 200 ሰዎች መጣ፤ እነሱም ዳዊትንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ለመቀበል ወጡ። ዳዊትም ወደ ሰዎቹ በቀረበ ጊዜ ስለ ደህንነታቸው ጠየቃቸው። +22 ሆኖም ከዳዊት ጋር አብረው ከሄዱት መካከል ክፉ የሆኑትና የማይረቡት ሰዎች “እነዚህ ሰዎች አብረውን ስላልሄዱ እያንዳንዳቸው ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካመጣነው ምርኮ ላይ ምንም ነገር አንሰጣቸውም” አሉ። +23 ዳዊት ግን እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼ ይሖዋ በሰጠን ነገርማ እንዲህ ማድረግ የለባችሁም። የጠበቀንና የመጣብንን ወራሪ ቡድን በእጃችን አሳልፎ የሰጠን እሱ ነው።+ +24 ታዲያ አሁን ይህን የምትሉትን ማን ይሰማችኋል? ወደ ውጊያ የዘ��ተው ሰው የሚያገኘው ድርሻና ጓዝ የጠበቀው ሰው የሚያገኘው ድርሻ እኩል ነው።+ ሁሉም ድርሻ ይኖረዋል።”+ +25 ዳዊትም ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከዚህ ዕለት ድረስ ይህን ለእስራኤል ሥርዓትና ደንብ አድርጎ አጸደቀው። +26 ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በተመለሰ ጊዜ “ከይሖዋ ጠላቶች ከተገኘው ምርኮ የተሰጠ ስጦታ* ይኸውላችሁ” በማለት ወዳጆቹ ለሆኑት የይሁዳ ሽማግሌዎች ከምርኮው ላይ የተወሰነውን ላከ። +27 ስጦታውንም በቤቴል፣+ በኔጌብ* ራሞት፣ በያቲር፣+ +28 በአሮዔር፣ በሲፍሞት፣ በኤሽተሞዓ፣+ +29 በራካል፣ በየራህምኤል+ ከተሞች፣ በቄናውያን+ ከተሞች፣ +30 በሆርማ፣+ በቦርአሻን፣ በአታክ፣ +31 በኬብሮን+ እንዲሁም ዳዊትና ሰዎቹ በሚያዘወትሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለነበሩት ላከ። +31 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል ጋር እየተዋጉ ነበር።+ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦአ+ ተራራ ላይ ተገደሉ። +2 ፍልስጤማውያንም ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን እግር በእግር ተከታተሏቸው፤ ፍልስጤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንን፣+ አቢናዳብንና ሜልኪሳን መትተው ገደሏቸው።+ +3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታ፤ ቀስተኞቹም አገኙት፤ እነሱም ክፉኛ አቆሰሉት።+ +4 ከዚያም ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ ያልተገረዙ+ ሰዎች መጥተው እንዳይወጉኝና በጭካኔ እንዳያሠቃዩኝ* ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበር ፈቃደኛ አልሆነም። በመሆኑም ሳኦል ሰይፉን ወስዶ በላዩ ላይ ወድቆ ሞተ።+ +5 ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ሲያይ+ እሱም በራሱ ሰይፍ ላይ ወድቆ ከእሱ ጋር ሞተ። +6 ስለዚህ ሳኦል፣ ሦስቱ ወንዶች ልጆቹ፣ ጋሻ ጃግሬውና የእሱ ሰዎች በሙሉ በዚያ ቀን አብረው ሞቱ።+ +7 በሸለቆውና* በዮርዳኖስ አካባቢ የነበሩት እስራኤላውያን፣ የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን እንዲሁም ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቹን ጥለው ሸሹ፤+ ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው ከተሞቹን ያዙ። +8 በማግስቱ ፍልስጤማውያን የሞቱትን ሰዎች ልብስና ትጥቅ ለመግፈፍ ሲመጡ ሳኦልንና ሦስቱን ወንዶች ልጆቹን በጊልቦአ+ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው። +9 ስለሆነም የሳኦልን ራስ ከቆረጡና የጦር ትጥቁን ከገፈፉ በኋላ ወሬው በጣዖቶቻቸው+ ቤቶችና* በሕዝቡ ሁሉ መካከል እንዲሰራጭ+ ለማድረግ በመላው የፍልስጤም ምድር መልእክት ላኩ። +10 ከዚያም የጦር ትጥቁን በአስታሮት ምስሎች ቤት አስቀመጡት፣ አስከሬኑን ደግሞ በቤትሻን+ ግንብ ላይ ቸነከሩት። +11 የኢያቢስጊልያድ+ ነዋሪዎችም ፍልስጤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን ሲሰሙ +12 ተዋጊዎቹ ሁሉ ተነስተው ሌሊቱን ሙሉ ሲጓዙ አደሩ፤ ከዚያም የሳኦልንና የልጆቹን አስከሬን ከቤትሻን ግንብ ላይ አወረዱ። ወደ ኢያቢስ ተመልሰውም በዚያ አቃጠሏቸው። +13 ከዚያም አፅማቸውን+ ወስደው በኢያቢስ+ በሚገኝ የታማሪስክ ዛፍ ሥር ቀበሩት፤ ለሰባት ቀንም ጾሙ። +18 ዳዊት ከሳኦል ጋር ተነጋግሮ እንደጨረሰ ዮናታንና+ ዳዊት የጠበቀ ወዳጅነት መሠረቱ፤* ዮናታንም እንደ ራሱ* ወደደው።+ +2 ከዚያን ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊት ከእሱ ጋር እንዲኖር አደረገ፤ ወደ አባቱም ቤት እንዲመለስ አልፈቀደለትም።+ +3 ዮናታንም ዳዊትን እንደ ራሱ* ስለወደደው+ ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን ተጋቡ።+ +4 ከዚያም ዮናታን ለብሶት የነበረውን መደረቢያ አውልቆ ለዳዊት ሰጠው፤ እንዲሁም ልብሶቹን ሌላው ቀርቶ ሰይፉን፣ ቀስቱንና ቀበቶውን ሰጠው። +5 ዳዊትም ለውጊያ ይወጣ ጀመር፤ ሳኦል በሚልከው በማንኛውም ቦታ ተልእኮውን በተሳካ ሁኔታ* ይፈጽም ነበር።+ በመሆኑም ሳኦል በሠራዊቱ ላይ ሾመው፤+ ይህም ሕዝቡንና የሳኦልን አገልጋዮች በሙሉ አስደሰታቸው። +6 ዳዊትና አብረውት ያሉት ሰዎች ፍልስጤማውያንን መትተው በተመለሱ ጊዜ በመላው የእስራኤል ከተሞች የሚገኙ ሴቶች አታሞና+ ባለ ሦስት አውታር መሣሪያ ይዘው በደስታ እየዘፈኑና+ እየጨፈሩ ንጉሥ ሳኦልን ለመቀበል ወጡ። +7 እየጨፈሩ የነበሩት ሴቶችም እንዲህ እያሉ ዘፈኑ፦ “ሳኦል ሺዎችን ገደለ፤ዳዊት ደግሞ አሥር ሺዎችን ገደለ።”+ +8 ሳኦልም እጅግ ተቆጣ፤+ ዘፈኑም አላስደሰተውም፤ በመሆኑም “ለዳዊት አሥር ሺህ አሉለት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ፤ ያልተሰጠው ነገር እኮ መንግሥት ብቻ ነው!” አለ።+ +9 ከዚያች ዕለት አንስቶ ሳኦል ዳዊትን በጥርጣሬ ዓይን ይመለከተው ጀመር። +10 በማግስቱም ከአምላክ የመጣ መጥፎ መንፈስ ሳኦልን ያዘው፤+ ዳዊት በፊት እንደሚያደርገው ሁሉ በገና እየደረደረ+ ሳለ ሳኦል ቤቱ ውስጥ እንግዳ ባሕርይ ያሳይ* ጀመር። ሳኦልም በእጁ ጦር ይዞ ነበር፤+ +11 እሱም ‘ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ!’ ብሎ በማሰብ ጦሩን በኃይል ወረወረው።+ ዳዊት ግን ሁለት ጊዜ ከእሱ አመለጠ። +12 ይሖዋ ከሳኦል ተለይቶ+ ከዳዊት ጋር ስለነበር+ ሳኦል ዳዊትን ፈራው። +13 በመሆኑም ሳኦል ከፊቱ እንዲርቅ አደረገው፤ የሺህ አለቃ አድርጎም ሾመው፤ ዳዊትም ሠራዊቱን እየመራ ወደ ጦርነት ይሄድ ነበር።*+ +14 ዳዊት የሚያከናውነው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር፤*+ ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር።+ +15 ሳኦልም ዳዊት ስኬታማ እንደሆነ ሲያይ ፈራው። +16 መላው እስራኤልና ይሁዳ ግን ዳዊትን ወደዱት፤ ምክንያቱም ወደ ጦርነት ሲወጡ የሚመራቸው እሱ ነበር። +17 በኋላም ሳኦል ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ ትልቋ ልጄ ሜሮብ+ አለች። እሷን እድርልሃለሁ።+ ሆኖም ጀግንነትህን ለእኔ ከማሳየት ወደኋላ ማለት የለብህም፤ የይሖዋንም ጦርነቶች መዋጋት ይኖርብሃል።”+ ሳኦል ይህን ያለው ‘እጄን በዚህ ሰው ላይ አላሳርፍም። ከዚህ ይልቅ በፍልስጤማውያን እጅ ይሙት’ ብ +18 በዚህ ጊዜ ዳዊት ሳኦልን “ለንጉሡ አማች እሆን ዘንድ እኔም ሆንኩ የአባቴ ቤተሰቦች የሆኑት ዘመዶቼ በእስራኤል ውስጥ ከቶ ማን ሆነን ነው?” አለው።+ +19 ሆኖም የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለዳዊት ልትሰጥ የነበረበት ጊዜ ሲደርስ እሷ ቀድሞውኑ ለመሆላታዊው ለአድሪዔል+ ተድራ ነበር። +20 የሳኦል ልጅ ሜልኮል+ ዳዊትን ትወደው ነበር፤ ይህን ለሳኦል ነገሩት፤ እሱም ነገሩ ደስ አሰኘው። +21 በመሆኑም ሳኦል “ወጥመድ እንድትሆነውና የፍልስጤማውያን እጅ በእሱ ላይ እንዲሆን እሷን እሰጠዋለሁ” አለ።+ ከዚያም ሳኦል ለሁለተኛ ጊዜ ዳዊትን “በዛሬዋ ዕለት በዚህች በሁለተኛዋ ሴት አማካኝነት ከእኔ ጋር በጋብቻ ትዛመዳለህ”* አለው። +22 በተጨማሪም ሳኦል አገልጋዮቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ለዳዊት እንዲህ ብላችሁ በሚስጥር ንገሩት፦ ‘ንጉሡ በአንተ ደስ ብሎታል፤ አገልጋዮቹም በሙሉ ይወዱሃል። ስለሆነም አሁን ከንጉሡ ጋር በጋብቻ ተዛመድ።’” +23 የሳኦልም አገልጋዮች ይህን በነገሩት ጊዜ ዳዊት “እዚህ ግባ ለማልባል ለእንደኔ ዓይነቱ ድሃ ከንጉሡ ጋር በጋብቻ መዛመድ እንዲህ ቀላል ነገር ይመስላችኋል?” አላቸው።+ +24 ከዚያም የሳኦል አገልጋዮች “ዳዊት እኮ እንዲህ እንዲህ አለ” ብለው ነገሩት። +25 በዚህ ጊዜ ሳኦል እንዲህ አለ፦ “ዳዊትን እንዲህ በሉት፦ ‘ንጉሡ ከአንተ የሚፈልገው ጥሎሽ+ ሳይሆን ጠላቶቹን መበቀል እንዲችል የ100 ፍልስጤማውያንን ሸለፈት+ ብቻ ነው።’” ሳኦል ይህን ያለው ዳዊት በፍልስጤማውያን እጅ እንዲወድቅ ተንኮል አስቦ ስለነበር ነው። +26 በመሆኑም አገልጋዮቹ ይህንኑ ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም ከንጉሡ ጋር በጋብቻ የመዛመዱ ጉዳይ አስደሰተው።+ ስለሆነም የተሰጠው ጊዜ ከማብቃቱ በፊት +27 ዳዊት አብረውት ከነበሩት ሰዎች ጋር በመሄድ 200 ፍልስጤማው���ንን መታ፤ ዳዊት ከንጉሡ ጋር በጋብቻ ለመዛመድ የገደላቸውን ሰዎች ሸለፈት በሙሉ አምጥቶ ለንጉሡ ሰጠው። በመሆኑም ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ዳረለት።+ +28 ሳኦል ይሖዋ ከዳዊት ጋር እንደነበርና+ ልጁ ሜልኮልም ዳዊትን እንደወደደችው+ ተረዳ። +29 በዚህም ምክንያት ሳኦል ዳዊትን ከበፊቱ ይልቅ ፈራው፤ በመሆኑም ዕድሜውን ሙሉ የዳዊት ጠላት ሆነ።+ +30 የፍልስጤም መኳንንትም ለውጊያ ይወጡ ነበር፤ ሆኖም ለውጊያ በወጡ ቁጥር ዳዊት ከሳኦል አገልጋዮች ሁሉ ይበልጥ ይሳካለት ነበር፤*+ ስሙም እየገነነ መጣ።+ +23 ከጊዜ በኋላም ዳዊት “ፍልስጤማውያን በቀኢላ+ ላይ ውጊያ ከፍተው በየአውድማው ያለውን እህል እየዘረፉ ነው” ተብሎ ተነገረው። +2 ስለሆነም ዳዊት “ሄጄ እነዚህን ፍልስጤማውያን ልምታ?” በማለት ይሖዋን ጠየቀ።+ ይሖዋም ዳዊትን “ሂድ፣ ፍልስጤማውያንን ምታ፤ ቀኢላንም አድናት” አለው። +3 የዳዊት ሰዎች ግን “እዚህ በይሁዳ እያለን እንኳ ፈርተናል፤+ የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመውጋት ወደ ቀኢላ ከሄድንማ ምን ያህል እንፈራ!”+ አሉት። +4 በመሆኑም ዳዊት እንደገና ይሖዋን ጠየቀ።+ ይሖዋም “ፍልስጤማውያንን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ+ ተነስተህ ወደ ቀኢላ ውረድ” ሲል መለሰለት። +5 ስለዚህ ዳዊት ከሰዎቹ ጋር በመሆን ወደ ቀኢላ ሄዶ ከፍልስጤማውያን ጋር ተዋጋ፤ ከብቶቻቸውን እየነዳ ወሰደ፤ ብዙ ሰውም ገደለባቸው፤ በዚህ መንገድ ዳዊት የቀኢላን ነዋሪዎች ታደጋቸው።+ +6 የአሂሜሌክ ልጅ አብያታር+ በቀኢላ ወደነበረው ወደ ዳዊት በሸሸ ጊዜ ኤፉድ ይዞ ነበር። +7 ሳኦል “ዳዊት ወደ ቀኢላ መጥቷል” የሚል ወሬ ደረሰው። ሳኦልም “ዳዊት በሮችና መቀርቀሪያዎች ወዳሏት ከተማ በመግባት ራሱን ወጥመድ ውስጥ ከቷል፤ ስለሆነም አምላክ እሱን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶታል”*+ አለ። +8 በመሆኑም ሳኦል ወደ ቀኢላ በመውረድ ዳዊትንና ሰዎቹን ከቦ ለመያዝ ሕዝቡን ሁሉ ለጦርነት አሰባሰበ። +9 ዳዊትም ሳኦል ሴራ እየጠነሰሰበት መሆኑን ሲያውቅ ካህኑን አብያታርን “ኤፉዱን ወደዚህ አምጣው” አለው።+ +10 ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ሳኦል ወደ ቀኢላ መጥቶ በእኔ የተነሳ ከተማዋን ለማጥፋት+ ማሰቡን አገልጋይህ በእርግጥ ሰምቷል። +11 ታዲያ የቀኢላ መሪዎች* ለእሱ አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? አገልጋይህ እንደሰማውስ ሳኦል ወደዚህ ይወርድ ይሆን? የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ለአገልጋይህ አሳውቀው።” በዚህ ጊዜ ይሖዋ “አዎ፣ ይወርዳል” አለው። +12 ዳዊትም “የቀኢላ መሪዎች እኔንና ሰዎቼን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡን ይሆን?” በማለት ጠየቀ። ይሖዋም “አዎ፣ አሳልፈው ይሰጧችኋል” ሲል መለሰለት። +13 ዳዊትም 600 ገደማ+ ከሚሆኑት የራሱ ሰዎች ጋር ወዲያውኑ ተነሳ፤ ከቀኢላም ወጥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ። ሳኦልም ዳዊት ከቀኢላ መሸሹ ሲነገረው እሱን ለማሳደድ መውጣቱን ተወው። +14 ዳዊትም በምድረ በዳው ውስጥ በሚገኙ በቀላሉ በማይደረስባቸው ቦታዎች፣ በዚፍ+ ምድረ በዳ ባለው ተራራማ አካባቢ ተቀመጠ። ሳኦል ሁልጊዜ ይፈልገው ነበር፤+ ይሖዋ ግን በእጁ አሳልፎ አልሰጠውም። +15 ዳዊት በሆሬሽ በሚገኘው በዚፍ ምድረ በዳ ሳለ ሳኦል የእሱን ሕይወት* ለመፈለግ መውጣቱን አውቆ* ነበር። +16 የሳኦል ልጅ ዮናታንም በሆሬሽ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት ሄደ፤ እሱም በይሖዋ ላይ ያለው ትምክህት እንዲጠናከር ረዳው።*+ +17 እንዲህም አለው፦ “አባቴ ሳኦል ስለማያገኝህ አትፍራ፤ አንተ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆናለህ፤+ እኔ ደግሞ ከአንተ ቀጥዬ ሁለተኛ ሰው እሆናለሁ፤ አባቴ ሳኦልም ቢሆን ይህን ያውቃል።”+ +18 ከዚያም ሁለቱም በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ተጋቡ፤+ ��ዊትም በሆሬሽ ተቀመጠ፤ ዮናታን ደግሞ ወደ ቤቱ ተመለሰ። +19 በኋላም የዚፍ ሰዎች በጊብዓ+ ወደነበረው ወደ ሳኦል ወጥተው እንዲህ አሉት፦ “ዳዊት እዚሁ አጠገባችን ከየሺሞን*+ በስተ ደቡብ፣* በሃኪላ ኮረብታ+ ላይ በሆሬሽ+ በሚገኙት በቀላሉ የማይደረስባቸው ስፍራዎች ተደብቆ የለም?+ +20 አሁንም ንጉሥ ሆይ፣ ወደዚህ ለመውረድ* በምትፈልግበት በማንኛውም ጊዜ ወደዚህ ና፤ እኛም እሱን ለንጉሡ አሳልፈን እንሰጣለን።”+ +21 በዚህ ጊዜ ሳኦል እንዲህ አላቸው፦ “ለእኔ ስለተቆረቆራችሁ ይሖዋ ይባርካችሁ። +22 አሁንም እባካችሁ ሂዱና ያለበትን ትክክለኛ ቦታም ሆነ በዚያ ያየውን ሰው ማንነት ለይታችሁ ለማወቅ ጥረት አድርጉ፤ ምክንያቱም እሱ በጣም ተንኮለኛ ሰው እንደሆነ ሰምቻለሁ። +23 የሚደበቅባቸውን ቦታዎች በሙሉ በደንብ አጣሩ፤ ከዚያም ተጨባጭ ማስረጃ ይዛችሁልኝ ኑ። እኔም አብሬያችሁ እሄዳለሁ፤ በዚያ አገር የሚገኝ ከሆነ ከይሁዳ ሺዎች* ሁሉ መካከል የገባበት ገብቼ አወጣዋለሁ።” +24 በመሆኑም ሰዎቹ ተነሱ፤ ከሳኦልም ቀድመው ወደ ዚፍ+ ሄዱ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ከየሺሞን በስተ ደቡብ በሚገኘው በአረባ፣+ በማኦን+ ምድረ በዳ ነበሩ። +25 ሳኦልም ዳዊትን ለመፈለግ ከሰዎቹ ጋር መጣ።+ ዳዊትም ይህ በተነገረው ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ዓለቱ+ ወርዶ በማኦን ምድረ በዳ ተቀመጠ። ሳኦል ይህን ሲሰማ ዳዊትን እያሳደደ ወደ ማኦን ምድረ በዳ ሄደ። +26 ከዚያም ሳኦል ከተራራው በአንደኛው በኩል ሲሆን ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ ከተራራው በሌላኛው በኩል ሆኑ። ዳዊት ከሳኦል ለማምለጥ እየተጣደፈ ነበር፤+ ይሁን እንጂ ሳኦልና አብረውት የነበሩት ሰዎች ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ተቃርበው ነበር።+ +27 ሆኖም አንድ መልእክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ “ፍልስጤማውያን ምድሪቱን ስለወረሯት ቶሎ ድረስ!” አለው። +28 በዚህ ጊዜ ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱን ትቶ+ ፍልስጤማውያንን ለመግጠም ሄደ። ያ ቦታ ‘የመለያያ ዓለት’ የተባለው በዚህ የተነሳ ነው። +29 ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ በኤንገዲ+ በሚገኙ በቀላሉ በማይደረስባቸው ስፍራዎች ተቀመጠ። +19 በኋላም ሳኦል፣ ዳዊት እንዲገደል ማሰቡን ለልጁ ለዮናታንና ለአገልጋዮቹ በሙሉ ነገራቸው።+ +2 የሳኦል ልጅ ዮናታን ዳዊትን በጣም ይወደው+ ስለነበር ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “አባቴ ሳኦል ሊገድልህ ይፈልጋል። ስለዚህ እባክህ ጠዋት ላይ ተጠንቀቅ፤ ወደ አንድ ሰዋራ ቦታም ሄደህ ተሸሽገህ ቆይ። +3 እኔም እወጣና አንተ ባለህበት ሜዳ ከአባቴ አጠገብ እቆማለሁ። ከእሱም ጋር ስለ አንተ እነጋገራለሁ፤ የሆነ ነገር እንዳለ ከተረዳሁ እነግርሃለሁ።”+ +4 በመሆኑም ዮናታን ለአባቱ ለሳኦል ስለ ዳዊት መልካም ነገር ነገረው።+ እንዲህም አለው፦ “ንጉሡ በአገልጋዩ በዳዊት ላይ ኃጢአት አይሥራ፤ ምክንያቱም እሱ በአንተ ላይ የሠራው ኃጢአት የለም፤ ያደረገልህም ነገር ቢሆን ለአንተ የሚበጅ ነው። +5 ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ* ፍልስጤማዊውን መታ፤+ ይሖዋም ለመላው እስራኤል ታላቅ ድል አጎናጸፈ።* አንተም ይህን አይተህ በጣም ተደስተህ ነበር። ታዲያ ያለምንም ምክንያት ዳዊትን በመግደል በንጹሕ ሰው ደም ላይ ለምን ኃጢአት ትሠራለህ?”+ +6 ሳኦልም የዮናታንን ቃል ሰማ፤ እሱም “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ ዳዊት አይገደልም” ሲል ማለ። +7 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን ጠርቶ ሁሉንም ነገር ነገረው። ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን ወደ ሳኦል አመጣው፤ እሱም እንደቀድሞው ሳኦልን ማገልገሉን ቀጠለ።+ +8 ከጊዜ በኋላ ሌላ ጦርነት ተነሳ፤ ዳዊትም ወጥቶ ከፍልስጤማውያን ጋር ተዋጋ፤ ክፉኛም ጨፈጨፋቸው፤ እነሱም ከፊቱ ሸሹ። +9 ሳኦል ጦሩን ይዞ ቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ሳለ ከይሖዋ የመጣ መጥፎ መንፈስ ወረደበት፤+ በዚህ ጊዜ ዳዊት በገና እየደረደረ ነበር።+ +10 ሳኦልም ዳዊትን በጦሩ ከግድግዳው ጋር ሊያጣብቀው ሞከረ፤ ዳዊት ግን ከሳኦል ፊት ዞር በማለቱ ጦሩ ግድግዳው ላይ ተሰካ። ዳዊትም በዚያ ሌሊት ሸሽቶ አመለጠ። +11 በኋላም ሳኦል የዳዊትን ቤት ከበው በንቃት በመጠባበቅ ጠዋት ላይ እንዲገድሉት መልእክተኞችን ላከ፤+ ሆኖም የዳዊት ሚስት ሜልኮል “ዛሬ ሌሊት ካላመለጥክ* ነገ ትገደላለህ” አለችው። +12 ሜልኮልም ዳዊት ሸሽቶ እንዲያመልጥ ወዲያውኑ በመስኮት አሾልካ አወረደችው። +13 ከዚያም የተራፊም ቅርጹን* ወስዳ አልጋው ላይ አጋደመች፤ በራስጌውም ከፍየል ፀጉር የተሠራ እንደ መረብ ያለ ጨርቅ አደረገች፤ በልብስም ሸፈነችው። +14 ሳኦልም ዳዊትን እንዲይዙት መልእክተኞችን ላከ፤ እሷ ግን “አሞታል” አለቻቸው። +15 በመሆኑም ሳኦል ዳዊትን እንዲያዩት መልእክተኞቹን ላከ፤ እነሱንም “ዳዊትን እንድገድለው በአልጋው ላይ እንዳለ አምጡልኝ” አላቸው።+ +16 መልእክተኞቹም ሲገቡ አልጋው ላይ ያገኙት የተራፊም ቅርጹን* ነበር፤ በራስጌውም ከፍየል ፀጉር የተሠራ እንደ መረብ ያለ ጨርቅ ነበር። +17 ሳኦልም ሜልኮልን “እንዲህ ያታለልሽኝና ጠላቴ+ ሸሽቶ እንዲያመልጥ ያደረግሽው ለምንድን ነው?” አላት። ሜልኮልም “‘እንዳመልጥ እርጂኝ፣ አለዚያ እገድልሻለሁ!’ አለኝ” አለችው። +18 ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፤ በራማ+ ወደሚገኘው ወደ ሳሙኤልም መጣ። ሳኦል ያደረገበትንም ነገር ሁሉ ነገረው። ከዚያም እሱና ሳሙኤል ሄደው በናዮት+ መኖር ጀመሩ። +19 ከጊዜ በኋላም ሳኦል “ዳዊት እኮ ያለው በራማ በምትገኘው በናዮት ነው!” የሚል ወሬ ደረሰው። +20 ሳኦልም ዳዊትን እንዲይዙት ወዲያውኑ መልእክተኞችን ላከ። የሳኦል መልእክተኞችም አረጋውያን የሆኑት ነቢያት ትንቢት ሲናገሩ፣ ሳሙኤል ደግሞ እንደ መሪያቸው ሆኖ ቆሞ ሲያዩ የአምላክ መንፈስ ወረደባቸው፤ እነሱም እንደ ነቢያት ያደርጋቸው ጀመር። +21 ይህን ለሳኦል በነገሩት ጊዜ ወዲያውኑ ሌሎች መልእክተኞችን ላከ፤ እነሱም እንደ ነቢያት ያደርጋቸው ጀመር። በመሆኑም ሳኦል ለሦስተኛ ጊዜ መልእክተኞችን ላከ፤ እነሱም እንደ ነቢያት ያደርጋቸው ጀመር። +22 በመጨረሻም እሱ ራሱ ወደ ራማ ሄደ። በሰኩ ወደሚገኘው ትልቅ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ እንደደረሰም “ለመሆኑ ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ሲል ጠየቀ። እነሱም “በራማ ባለችው በናዮት+ ይገኛሉ” ብለው መለሱለት። +23 ሳኦልም በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት እየሄደ ሳለ የአምላክ መንፈስ በእሱም ላይ ወረደበት፤ እሱም በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት እስኪደርስ ድረስ እንደ ነቢይ አደረገው። +24 ልብሱንም አወለቀ፤ በሳሙኤልም ፊት እንደ ነቢይ አደረገው፤ ቀኑንና ሌሊቱን ሙሉ ራቁቱን* ሆኖ በዚያ ተጋደመ። እነሱም “ሳኦልም ከነቢያቱ አንዱ ነው እንዴ?”+ ያሉት በዚህ የተነሳ ነው። +20 ከዚያም ዳዊት በራማ ከምትገኘው ከናዮት ሸሸ። ሆኖም ወደ ዮናታን መጥቶ “ምን አደረግኩ?+ የፈጸምኩትስ በደል ምንድን ነው? አባትህ ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚፈልገው በእሱ ላይ ምን ኃጢአት ሠርቼ ነው?” አለው። +2 ዮናታንም እንዲህ አለው፦ “ይሄማ የማይታሰብ ነው!+ ፈጽሞ አትሞትም! አባቴ እንደሆነ ትልቅም ሆነ ትንሽ፣ ለእኔ ሳይነግረኝ ምንም ነገር አያደርግም። ታዲያ አባቴ ይህን ነገር ከእኔ የሚደብቅበት ምን ምክንያት አለው? እንዲህማ አይሆንም።” +3 ዳዊት ግን እንደገና ማለለት፤ እንዲህም አለው፦ “አባትህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን+ በሚገባ ስለሚያውቅ ‘ዮናታን ሊያዝን ስለሚችል ይህን ነገር ማወቅ የለበትም’ ብሎ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ* እምላለሁ፣ በእኔና በ���ት መካከል ያለው አንድ እርምጃ ብቻ ነው!”+ +4 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን “የምትለውን* ማንኛውንም ነገር አደርግልሃለሁ” አለው። +5 በዚህ ጊዜ ዳዊት ዮናታንን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፣ ነገ አዲስ ጨረቃ+ የምትወጣበት ቀን ነው፤ እኔም ከንጉሡ ጋር ለመመገብ በማዕድ መቀመጥ ይጠበቅብኛል፤ አንተ ካሰናበትከኝ ግን እስከ ሦስተኛው ቀን ምሽት ድረስ ወደ ሜዳ ሄጄ እደበቃለሁ። +6 ምናልባት አባትህ አለመኖሬን አስተውሎ ከጠየቀ ‘ዳዊት በከተማው በቤተልሔም+ ለመላ ቤተሰቡ የሚቀርብ ዓመታዊ መሥዋዕት ስላለ ቶሎ ወደዚያ ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት ለመነኝ’ በለው።+ +7 እሱም ‘ጥሩ ነው!’ ካለ አገልጋይህን የሚያሰጋው ነገር የለም ማለት ነው። ከተቆጣ ግን በእኔ ላይ ጉዳት ለማድረስ እንደቆረጠ እወቅ። +8 አገልጋይህ ከአንተ ጋር በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን እንዲገባ ያደረግከው+ አንተ ስለሆንክ ለአገልጋይህ ታማኝ ፍቅር አሳየው።+ በእኔ ላይ ጥፋት ከተገኘ+ ግን አንተው ራስህ ግደለኝ። ለምን ለአባትህ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ?” +9 በዚህ ጊዜ ዮናታን “እንዲህ ብለህ ማሰብማ የለብህም! አባቴ በአንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ መቁረጡን ባውቅ እንዴት ሳልነግርህ ዝም እላለሁ?” አለው።+ +10 ከዚያም ዳዊት ዮናታንን “ታዲያ አባትህ ክፉ ቃል ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል?” አለው። +11 ዮናታንም ዳዊትን “ና፣ ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው። በመሆኑም ተያይዘው ወደ ሜዳ ወጡ። +12 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ጊዜ ወይም ከነገ ወዲያ አባቴ ያለውን አመለካከት ባላጣራ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ምሥክር ይሁንብኝ። እሱ ለዳዊት ጥሩ አመለካከት ካለው ወደ አንተ ልኬ የማላሳውቅህ ይመስልሃል? +13 አባቴ በአንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ አስቦ ቢሆንና እኔ ግን ይህን ሳላሳውቅህ ብቀር እንዲሁም በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ ይሖዋ በዮናታን ላይ ይህን ያድርግበት፤ ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣበት። ይሖዋ ከአባቴ ጋር እንደነበር+ ሁሉ ከአንተም ጋር ይሁን።+ +14 አንተስ ብትሆን በሕይወት ሳለሁም ሆነ ስሞት የይሖዋን ታማኝ ፍቅር አታሳየኝም?+ +15 ይሖዋ የዳዊትን ጠላቶች በሙሉ ከምድር ገጽ ጠራርጎ በሚያጠፋበት ጊዜም ለቤተሰቤ+ ታማኝ ፍቅርህን ከማሳየት ፈጽሞ ወደኋላ አትበል።” +16 ስለዚህ ዮናታን “ይሖዋ የዳዊትን ጠላቶች ይፋረዳቸዋል” በማለት ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን ገባ። +17 በመሆኑም ዮናታን ዳዊት ለእሱ ባለው ፍቅር እንደገና እንዲምልለት አደረገ፤ ምክንያቱም ዳዊትን እንደ ራሱ* ይወደው ነበር።+ +18 ዮናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ነገ አዲስ ጨረቃ+ የምትወጣበት ቀን ነው፤ የምትቀመጥበት ቦታ ባዶ ስለሚሆን አለመኖርህ ይታወቃል። +19 በሦስተኛውም ቀን፣ አለመኖርህ ይበልጥ ግልጽ ይሆናል፤ አንተም ያን ቀን* ተደብቀህበት ወደነበረው ቦታ ሂድ፤ እዚህ ድንጋይ አጠገብም ቆይ። +20 እኔም ዒላማ የምመታ አስመስዬ በድንጋዩ አጠገብ ሦስት ቀስቶችን አስፈነጥራለሁ። +21 አገልጋዩንም ‘ሂድ፣ ፍላጻዎቹን አምጣቸው’ ብዬ እልከዋለሁ። አገልጋዩን ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ በዚህኛው በኩል ናቸው፤ አምጣቸው’ ካልኩት ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ ሁሉ ነገር ሰላም ስለሆነና ምንም የሚያሰጋህ ነገር ስለሌለ ተመልሰህ መምጣት ትችላለህ። +22 ሆኖም ልጁን ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ ወዲያ ናቸው’ ካልኩት ይሖዋ አሰናብቶሃልና ሂድ። +23 እኔና አንተ የተጋባነውን ቃል+ በተመለከተም ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ለዘላለም ምሥክር ይሁን።”+ +24 በመሆኑም ዳዊት ወደ ሜዳ ሄዶ ተደበቀ። አዲስ ጨረቃ ስትወጣም ንጉሡ ለመብላት በማዕድ ተቀመጠ።+ +25 ንጉሡ እንደተለመደው በግድግዳው በኩል ባለው መቀመጫው ላይ ተቀምጦ ነበር። ዮናታን ከፊት ለፊቱ፣ አበኔር+ ደግሞ ከሳኦል ጎን ተቀምጠው ነበር፤ የዳዊት ቦታ ግን ባዶ ነበር። +26 ሳኦል ‘መቼም ዳዊት እንዳይነጻ+ የሚያደርገው የሆነ ነገር ገጥሞት መሆን ይኖርበታል። አዎ፣ ረክሶ መሆን አለበት’ ብሎ ስላሰበ በዚያን ቀን ምንም አልተናገረም። +27 አዲስ ጨረቃ በወጣችበት ቀን ማግስት ይኸውም በሁለተኛው ቀን የዳዊት ቦታ ክፍት እንደሆነ ነበር። ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን “የእሴይ+ ልጅ ትናንትም፣ ዛሬም ማዕድ ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” አለው። +28 ዮናታንም ለሳኦል እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ዳዊት ወደ ቤተልሔም ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት ለመነኝ።+ +29 እንዲህም አለኝ፦ ‘ቤተሰባችን በከተማዋ ውስጥ መሥዋዕት ስለሚያቀርብና ወንድሜም በዚያ እንድገኝ ስለጠራኝ እባክህ እንድሄድ ፍቀድልኝ። እንግዲህ በፊትህ ሞገስ ካገኘሁ እባክህ ወንድሞቼን አይ ዘንድ ሹልክ ብዬ ልሂድ።’ ዳዊት በንጉሡ ማዕድ ላይ ያልተገኘው ለዚህ ነው።” +30 በዚህ ጊዜ ሳኦል በዮናታን ላይ እጅግ ተቆጣ፤ እንዲህም አለው፦ “አንተ የዚያች ዓመፀኛ ሴት ልጅ፣ በራስህም ሆነ በእናትህ* ላይ ውርደት ለማምጣት ከእሴይ ልጅ ጋር መወገንህን የማላውቅ መሰለህ? +31 የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተም ሆንክ መንግሥትህ አትጸኑም።+ እሱ መሞት ስላለበት* በል አሁኑኑ ልከህ አስመጣልኝ።”+ +32 ዮናታን ግን አባቱን ሳኦልን “ለምን ይገደላል?+ ጥፋቱስ ምንድን ነው?” አለው። +33 በዚህ ጊዜ ሳኦል እሱን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት፤+ ስለሆነም ዮናታን አባቱ፣ ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ መነሳቱን አወቀ።+ +34 ዮናታንም ወዲያውኑ በታላቅ ቁጣ ከማዕዱ ላይ ተነሳ፤ በዳዊት ምክንያት በጣም ስላዘነና+ የገዛ አባቱም ስላዋረደው አዲስ ጨረቃ በወጣች በሁለተኛው ቀን ምንም ምግብ አልቀመሰም። +35 ዮናታንም በማለዳ ተነስቶ ከዳዊት ጋር ወደተቀጣጠሩበት ቦታ ሄደ፤ አንድ ወጣት አገልጋይም አብሮት ነበር።+ +36 እሱም አገልጋዩን “ሂድ፣ ሩጥ፤ የምወነጭፋቸውንም ፍላጻዎች ፈልግ” አለው። ከዚያም አገልጋዩ ሮጠ፤ ዮናታንም ፍላጻውን ከእሱ አሳልፎ ወነጨፈው። +37 አገልጋዩም ዮናታን የወነጨፈው ፍላጻ ያረፈበት ቦታ ሲደርስ ዮናታን አገልጋዩን ጠርቶ “ፍላጻው ያለው ከአንተ ወዲያ አይደለም?” አለው። +38 ዮናታንም በድጋሚ አገልጋዩን ጠርቶ “ፍጠን እንጂ! ቶሎ በል! አትዘግይ!” አለው። የዮናታን አገልጋይም ፍላጻዎቹን አንስቶ ወደ ጌታው ተመለሰ። +39 አገልጋዩ ስለ ጉዳዩ የሚያውቀው ነገር አልነበረም፤ የዚህ ትርጉም ምን እንደሆነ የሚያውቁት ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነበሩ። +40 ከዚያም ዮናታን የጦር መሣሪያዎቹን ለአገልጋዩ ሰጥቶ “ሂድ፣ ወደ ከተማ ይዘሃቸው ተመለስ” አለው። +41 አገልጋዩም ሲሄድ ዳዊት በስተ ደቡብ በኩል ከሚገኝ በአቅራቢያው ካለ ስፍራ ተነስቶ መጣ። ሦስት ጊዜም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ እጅ ነሳ፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱ፤ ይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር። +42 ዮናታንም ዳዊትን “ሁለታችንም ‘ይሖዋ በእኔና በአንተ፣ በዘሮቼና በዘሮችህ መካከል ለዘላለም ይሁን’+ ብለን በይሖዋ ስም ስለተማማልን+ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነስቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማዋ ተመለሰ። +3 ይህ በእንዲህ እንዳለ ብላቴናው ሳሙኤል በኤሊ ፊት ይሖዋን ያገለግል ነበር፤+ ይሁን እንጂ በዚያ ዘመን ከይሖዋ የሚመጣ ቃል ብርቅ ነበር፤ ራእይ+ ማየትም ቢሆን ብዙ የተለመደ አልነበረም። +2 አንድ ቀን ኤሊ የተለመደው ቦታው ላይ ተኝቶ ነበር፤ ዓይኖቹ ስለደከሙ ማየት ተስኖታል።+ +3 የአምላክም መብራት+ ገና አልጠፋም፤ ሳሙኤልም የአምላክ ታቦት ባለበት የይሖዋ ቤተ መቅደስ*+ ውስጥ ተኝቶ ነበር። +4 ከዚያም ይሖዋ ሳሙኤልን ጠራው። እሱም “አቤት” አለ። +5 ወደ ኤሊም እየሮጠ ሄዶ “አቤት፣ ጠራኸኝ?” አለው። እሱ ግን “አይ፣ አልጠራሁህም። ተመልሰህ ተኛ” አለው። በመሆኑም ሄዶ ተኛ። +6 ይሖዋም እንደገና “ሳሙኤል!” ሲል ጠራው። በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ኤሊ በመሄድ “አቤት፣ ጠራኸኝ?” አለው። እሱ ግን “ኧረ አልጠራሁህም ልጄ። ተመልሰህ ተኛ” አለው። +7 (ሳሙኤል ይሖዋን ገና አላወቀውም ነበር፤ የይሖዋም ቃል ቢሆን ገና አልተገለጠለትም ነበር።)+ +8 በመሆኑም ይሖዋ ለሦስተኛ ጊዜ እንደገና “ሳሙኤል!” ሲል ጠራው። እሱም ተነስቶ ወደ ኤሊ በመሄድ “አቤት፣ ጠራኸኝ?” አለው። ኤሊም ብላቴናውን እየጠራው ያለው ይሖዋ መሆኑን አስተዋለ። +9 በመሆኑም ኤሊ ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ሂድና ተኛ፤ እንደገና ከጠራህ ‘ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህ እየሰማ ስለሆነ ተናገር’ በል።” ሳሙኤልም ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ። +10 ይሖዋም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ እንደ ሌላው ጊዜም “ሳሙኤል፣ ሳሙኤል!” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም “አገልጋይህ እየሰማ ስለሆነ ተናገር” አለ። +11 ይሖዋ ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ለሰሚው ሁሉ ጆሮ የሚሰቀጥጥ ነገር በእስራኤል ውስጥ አደርጋለሁ።+ +12 በዚያ ቀን ስለ ኤሊ ቤት የተናገርኩትን ነገር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በእሱ ላይ እፈጽማለሁ።+ +13 እሱ በሚያውቀው ጥፋት የተነሳ በቤቱ ላይ ለዘለቄታው እንደምፈርድ ንገረው፤+ ምክንያቱም ልጆቹ አምላክን ረግመዋል፤+ እሱ ግን አልገሠጻቸውም።+ +14 በዚህም የተነሳ የኤሊ ቤት የፈጸመው ጥፋት መሥዋዕት ወይም መባ በማቅረብ ፈጽሞ እንደማይሰረይ ለኤሊ ቤት ምያለሁ።”+ +15 ሳሙኤልም እስከ ንጋት ድረስ ተኛ፤ ከዚያም የይሖዋን ቤት በሮች ከፈተ። ሳሙኤል ራእዩን ለኤሊ መንገር ፈርቶ ነበር። +16 ኤሊ ግን ሳሙኤልን ጠርቶ “ልጄ፣ ሳሙኤል!” አለው። እሱም “አቤት” አለው። +17 ኤሊም እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ “ለመሆኑ የነገረህ መልእክት ምንድን ነው? እባክህ አትደብቀኝ። እሱ ከነገረህ ነገር ውስጥ አንዲት ቃል እንኳ ብትደብቀኝ አምላክ እንዲህ ያድርግብህ፤ ከዚያም የከፋ ነገር ያምጣብህ።” +18 በመሆኑም ሳሙኤል እሱ የነገረውን በሙሉ ምንም ሳይደብቅ ነገረው። ኤሊም “ይህ ከይሖዋ ነው። እሱ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ” አለ። +19 ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር፤+ የሚናገረውም ቃል ሁሉ እንዲፈጸም ያደርግ* ነበር። +20 ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል ተቀባይነት ያገኘ የይሖዋ ነቢይ እንደሆነ ተገነዘቡ። +21 ይሖዋም በሴሎ ይገለጥ ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ በሴሎ በይሖዋ ቃል አማካኝነት ራሱን ለሳሙኤል ገልጦለት ነበር።+ +24 ሳኦል ፍልስጤማውያንን አሳዶ እንደተመለሰ “ዳዊት በኤንገዲ+ ምድረ በዳ ይገኛል” ብለው ነገሩት። +"2 ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ 3,000 ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ የተራራ ፍየሎች ወደሚገኙበት ዓለታማ ገደላ ገደል ሄደ።" +3 ሳኦልም በመንገዱ ዳር ወዳለ ከድንጋይ የተሠራ የበጎች ጉረኖ ደረሰ፤ በዚያም አንድ ዋሻ ነበር፤ በመሆኑም ሳኦል ለመጸዳዳት* ወደ ዋሻው ገባ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ በዋሻው+ ውስጠኛ ክፍል ተቀምጠው ነበር። +4 ከዚያም የዳዊት ሰዎች “ይሖዋ ‘ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤+ አንተም ደስ ያለህን ታደርግበታለህ’ ያለህ ቀን ይህ ነው” አሉት። ስለሆነም ዳዊት ተነሳ፤ የሳኦልንም ልብስ ጫፍ በቀስታ ቆርጦ ወሰደ። +5 በኋላ ላይ ግን ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቁረጡ ልቡ* ወቀሰው።+ +6 አብረውት የነበሩትንም ሰዎች “ይሖዋ በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን በማንሳት እንዲህ ያለውን ድርጊት መፈጸም በይሖዋ ዓይን ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው፤ ምክንያቱም እሱ ይሖዋ የቀባው ነው”+ አላቸው። +7 ስለዚህ ዳዊት ይህን በማለት ሰዎቹን ከለከላቸው፤* በሳኦል ላይ ጉዳት እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ተነስቶ ከዋሻው ወጥቶ ሄደ። +8 ከዚያም ዳዊት ከዋሻው በመውጣት “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!”+ በማለት ሳኦልን ጠራው። ሳኦልም ወደኋላው ዞር ብሎ ሲመለከት ዳዊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። +9 ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “‘ዳዊት የአንተን ክፉ ማየት ይፈልጋል’ የሚሉትን ሰዎች ወሬ ለምን ትሰማለህ?+ +10 በዛሬዋ ዕለት በዋሻው ውስጥ ይሖዋ አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ሰጥቶኝ እንደነበር በገዛ ዓይንህ አይተሃል። አንድ ሰው እንድገድልህ ገፋፍቶኝ+ የነበረ ቢሆንም እኔ ግን ለአንተ በማዘን ‘ይሖዋ የቀባው+ ስለሆነ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሳም’ አልኩ። +11 አሁንም አባቴ ሆይ፣ ተመልከት፣ በእጄ የያዝኩትን የልብስህን ቁራጭ እይ፤ የልብስህን ጫፍ በቆረጥኩ ጊዜ ልገድልህ እችል ነበር፤ ግን አልገደልኩህም። እንግዲህ አንተን ለመጉዳትም ሆነ በአንተ ላይ ለማመፅ ፈጽሞ እንዳላሰብኩ ከዚህ ማየትና መረዳት ትችላለህ፤ ምንም እንኳ ሕይወቴን* ለማጥፋት እያሳደድከኝ+ +12 ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤+ ይሖዋ አንተን ይበቀልልኝ+ እንጂ እኔ በምንም ዓይነት እጄን በአንተ ላይ አላነሳም።+ +13 ‘ከክፉ ሰው ክፉ ነገር ይወጣል’ የሚል የጥንት አባባል አለ፤ እኔ ግን በምንም ዓይነት እጄን በአንተ ላይ አላነሳም። +14 ለመሆኑ የእስራኤል ንጉሥ የወጣው ማንን ፍለጋ ነው? የምታሳድደውስ ማንን ነው? አንድን የሞተ ውሻ? ወይስ አንዲትን ቁንጫ?+ +15 አሁንም ይሖዋ ዳኛ ሆኖ በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤ ጉዳዩንም ተመልክቶ ስለ እኔ ይሟገትልኝ፤+ እሱ ይፍረድልኝ፣ ከእጅህም ያድነኝ።” +16 ዳዊት ይህን ተናግሮ ሲጨርስ ሳኦል “ልጄ ዳዊት፣ ይህ የአንተ ድምፅ ነው?”+ አለው። ከዚያም ሳኦል ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ። +17 ዳዊትንም እንዲህ አለው፦ “አንተ መልካም ስታደርግልኝ እኔ ግን ክፉ መለስኩልህ፤ ስለሆነም አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።+ +18 አዎ፣ ይሖዋ እኔን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህም ሳትገድለኝ በመቅረት ለእኔ ያደረግከውን መልካም ነገር ይኸው ዛሬ ነገርከኝ።+ +19 ለመሆኑ ጠላቱን አግኝቶ ጉዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ሰው ይኖራል? ዛሬ አንተ ለእኔ መልካም ስላደረግክልኝ ይሖዋም ለአንተ መልካም በማድረግ ወሮታህን ይመልስልህ።+ +20 ደግሞም አንተ በእርግጥ ንጉሥ ሆነህ እንደምትገዛ አውቃለሁ፤+ የእስራኤልም መንግሥት በእጅህ ይጸናል። +21 በመሆኑም አሁን ከእኔ በኋላ የሚመጡትን ዘሮቼን እንደማታጠፋና ስሜንም ከአባቴ ቤት+ እንደማትደመስስ በይሖዋ ማልልኝ።”+ +22 ስለዚህ ዳዊት ለሳኦል ማለለት፤ ከዚያም ሳኦል ወደ ቤቱ ሄደ።+ ዳዊትና ሰዎቹ ግን ወደ ምሽጉ ወጡ።+ +7 በመሆኑም የቂርያትየአሪም ሰዎች መጥተው የይሖዋን ታቦት በኮረብታው ላይ ወደሚገኘው ወደ አቢናዳብ ቤት+ ወሰዱት፤ የይሖዋን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት። +2 ታቦቱም ወደ ቂርያትየአሪም ከመጣ ረጅም ጊዜ ይኸውም በአጠቃላይ 20 ዓመት አለፈው፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ይሖዋን መፈለግ* ጀመረ።+ +3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ “በሙሉ ልባችሁ+ ወደ ይሖዋ የምትመለሱ ከሆነ ባዕዳን አማልክትንና+ የአስታሮትን ምስሎች+ ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ልባችሁንም ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ ስጡ፤ እሱን ብቻ አገልግሉ፤+ እሱም ከፍልስጤማውያን እጅ ይታደጋችኋል”+ አላቸው። +4 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን የባአልንና የአስታሮትን ምስሎች አስወግደው ይሖዋን ብቻ አገለገሉ።+ +5 ከዚያም ��ሙኤል “እስራኤልን ሁሉ በምጽጳ+ ሰብስቡ፤ እኔም ስለ እናንተ ወደ ይሖዋ እጸልያለሁ”+ አለ። +6 እነሱም በምጽጳ ተሰበሰቡ፤ ከዚያም ውኃ ቀድተው በይሖዋ ፊት አፈሰሱ፤ ያን ዕለትም ሲጾሙ ዋሉ።+ በዚያም “በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል” አሉ።+ ሳሙኤልም በምጽጳ በእስራኤላውያን ላይ ፈራጅ ሆኖ ማገልገል ጀመረ።+ +7 ፍልስጤማውያንም እስራኤላውያን በምጽጳ አንድ ላይ መሰብሰባቸውን በሰሙ ጊዜ የፍልስጤም ገዢዎች+ እስራኤልን ለመውጋት ወጡ። እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ፍልስጤማውያንን ፈሩ። +8 ስለሆነም እስራኤላውያን ሳሙኤልን “አምላካችን ይሖዋ እንዲረዳንና ከፍልስጤማውያን እጅ እንዲያድነን ወደ እሱ መጮኽህን አታቁም” አሉት።+ +9 ከዚያም ሳሙኤል አንድ የሚጠባ ግልገል ወስዶ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ+ አድርጎ አቀረበው፤ ሳሙኤልም ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲረዳቸው ተማጸነ፤ ይሖዋም መለሰለት።+ +10 ሳሙኤል የሚቃጠለውን መባ እያቀረበ ሳለ ፍልስጤማውያን እስራኤላውያንን ለመውጋት ቀረቡ። ይሖዋም በዚያን ዕለት በፍልስጤማውያን ላይ ኃይለኛ የነጎድጓድ ድምፅ ለቀቀባቸው፤+ ግራ እንዲጋቡም አደረጋቸው፤+ እነሱም በእስራኤላውያን ፊት ድል ተመቱ።+ +11 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሰዎች ከምጽጳ ወጥተው ፍልስጤማውያንን ማሳደዳቸውን ተያያዙት፤ ከቤትካር በስተ ደቡብ እስከሚገኘው አካባቢም ድረስ መቷቸው። +12 ከዚያም ሳሙኤል አንድ ድንጋይ+ ወስዶ በምጽጳ እና በየሻና መካከል አስቀመጠው፤ ስሙንም ኤቤንዔዘር* አለው፤ ይህን ያለው “ይሖዋ እስካሁን ድረስ ረድቶናል”+ ሲል ነው። +13 በዚህ ሁኔታ ፍልስጤማውያን ድል ተመቱ፤ ዳግመኛም ወደ እስራኤላውያን ክልል መጥተው አያውቁም፤+ በሳሙኤል ዘመን ሁሉ የይሖዋ እጅ በፍልስጤማውያን ላይ ነበር።+ +14 በተጨማሪም ፍልስጤማውያን ከእስራኤላውያን ላይ የወሰዷቸው ከኤቅሮን እስከ ጌት ያሉት ከተሞች ለእስራኤላውያን ተመለሱላቸው፤ እንዲሁም እስራኤላውያን በእነዚህ ከተሞች ሥር ያሉትን ክልሎች ከፍልስጤማውያን እጅ አስለቀቁ። በእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከልም ሰላም ወረደ።+ +15 ሳሙኤልም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለእስራኤላውያን ፈራጅ ሆኖ አገለገለ።+ +16 በየዓመቱም በቤቴል፣+ በጊልጋል+ እና በምጽጳ+ በመዘዋወር በእነዚህ አካባቢዎች ሁሉ ለሚገኙ እስራኤላውያን ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። +17 ሆኖም ቤቱ የሚገኘው በራማ+ ስለነበር ወደዚያ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ለእስራኤላውያን ፈራጅ ሆኖ አገለገለ። በዚያም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ።+ +12 በመጨረሻም ሳሙኤል እስራኤላውያንን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ ያላችሁኝን ሁሉ አድርጌአለሁ፤* የሚገዛችሁም ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ።+ +2 የሚመራችሁ* ንጉሥ ይኸው!+ እኔ ዕድሜዬ ገፍቷል፤ ፀጉሬም ሸብቷል፤ እነሆ፣ ልጆቼ አብረዋችሁ ናቸው፤+ እኔ እንደሆንኩ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ ስመራችሁ ቆይቻለሁ።+ +3 አሁንም ያለሁት በፊታችሁ ነው። እስቲ የምከሰስበት ነገር ካለ በይሖዋና እሱ በቀባው+ ፊት ንገሩኝ፦ የማንን በሬ ወይም የማንን አህያ ወስጃለሁ?+ ወይስ ማንን አታልያለሁ? ደግሞስ በማን ላይ ግፍ ፈጽሜአለሁ? አይቼ እንዳላየሁ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀብያለሁ?+ እንዲህ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ። +4 በዚህ ጊዜ እነሱ “አታለኸንም ሆነ ግፍ ፈጽመህብን ወይም ደግሞ ከማንም ሰው እጅ ምንም ነገር ተቀብለህ አታውቅም” አሉት። +5 በመሆኑም ሳሙኤል “እኔን የምትከሱበት ምንም ነገር እንዳላገኛችሁ* ይሖዋም ሆነ እሱ የቀባው ዛሬ በእናንተ ላይ ምሥክሮች ናቸው” አላቸው። እነሱም “እሱ ምሥክር ነው” አሉ። +6 ሳሙኤልም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ሙሴንና አሮን�� የመረጠው እንዲሁም አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ያወጣው+ ይሖዋ ምሥክር ነው። +7 እንግዲህ እናንተ ባላችሁበት ቁሙ፤ እኔም ይሖዋ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ባደረጋቸው የጽድቅ ሥራዎች መሠረት በይሖዋ ፊት እፋረዳችኋለሁ። +8 “ያዕቆብ ወደ ግብፅ በገባና+ አባቶቻችሁም ይሖዋ እንዲረዳቸው በጮኹ ጊዜ+ ይሖዋ አባቶቻችሁን ከግብፅ መርተው እንዲያወጧቸውና በዚህ ስፍራ እንዲያኖሯቸው+ ሙሴንና አሮንን ላከ።+ +9 እነሱ ግን አምላካቸውን ይሖዋን ረሱ፤ እሱም የሃጾር ሠራዊት አለቃ ለነበረው ለሲሳራ፣+ ለፍልስጤማውያንና ለሞዓብ+ ንጉሥ እጅ+ አሳልፎ ሸጣቸው፤+ እነሱም ወጓቸው። +10 በዚህ ጊዜ ይሖዋ እንዲረዳቸው ጮኹ፤+ እንዲህም አሉ፦ ‘ባአልንና+ የአስታሮትን+ ምስሎች ለማገልገል ስንል ይሖዋን ስለተውን ኃጢአት ሠርተናል፤+ ስለሆነም እንድናገለግልህ አሁን ከጠላቶቻችን እጅ ታደገን።’ +11 ከዚያም ይሖዋ ያለስጋት መኖር እንድትችሉ የሩባአልን፣+ ቤዳንን፣ ዮፍታሔንና+ ሳሙኤልን+ ልኮ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ እጅ ታደጋችሁ።+ +12 የአሞናውያን ንጉሥ የሆነው ናሃሽ+ በእናንተ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እንደመጣ ስታዩ ምንም እንኳ አምላካችሁ ይሖዋ ንጉሣችሁ ቢሆንም+ ‘አይሆንም፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን!’ አላችሁኝ።+ +13 እንግዲህ የመረጣችሁትና የጠየቃችሁት ንጉሥ ይኸውላችሁ። እነሆ፣ ይሖዋ በላያችሁ ንጉሥ አንግሦአል።+ +14 ይሖዋን ብትፈሩና+ ብታገለግሉ፣+ ቃሉን ብትታዘዙና+ በይሖዋ ትእዛዝ ላይ ባታምፁ እንዲሁም እናንተም ሆናችሁ በላያችሁ የሚገዛው ንጉሥ አምላካችሁን ይሖዋን ብትከተሉ መልካም ይሆንላችኋል። +15 ሆኖም የይሖዋን ቃል ባትታዘዙና በይሖዋ ትእዛዝ ላይ ብታምፁ የይሖዋ እጅ በእናንተና በአባቶቻችሁ ላይ ይሆናል።+ +16 ስለሆነም አሁን ባላችሁበት ቆማችሁ ይሖዋ ዓይናችሁ እያየ የሚፈጽመውን ይህን ታላቅ ነገር ተመልከቱ። +17 ዛሬ የስንዴ መከር የሚታጨድበት ጊዜ አይደለም? ይሖዋን ነጎድጓድና ዝናብ እንዲልክ እጠይቀዋለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቅ በይሖዋ ፊት ምን ያህል ታላቅ በደል እንደፈጸማችሁ ታውቃላችሁ፤ ደግሞም ታስተውላላችሁ።”+ +18 ከዚያም ሳሙኤል ይሖዋን ጠየቀ፤ ይሖዋም በዚያ ቀን ነጎድጓድና ዝናብ ላከ፤ በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ ይሖዋንና ሳሙኤልን እጅግ ፈራ። +19 ሕዝቡም ሳሙኤልን “ሌላው ኃጢአታችን ሳያንሰን ንጉሥ እንዲነግሥልን በመለመን ተጨማሪ በደል ስለፈጸምን እንዳንሞት ስለ አገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ጸልይልን”+ አለው። +20 በመሆኑም ሳሙኤል ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “አትፍሩ። እርግጥ ይህን ሁሉ ክፋት ፈጽማችኋል። ብቻ ይሖዋን ከመከተል ዞር አትበሉ፤+ ይሖዋንም በሙሉ ልባችሁ አገልግሉት።+ +21 ምንም ዋጋ የሌላቸውንና+ ማዳን የማይችሉ ከንቱ+ ነገሮችን* ወደ መከተል ዞር አትበሉ፤ ምክንያቱም እነሱ ከንቱ* ነገሮች ናቸው። +22 ይሖዋ ስለ ታላቁ ስሙ ሲል+ ሕዝቡን አይተውም፤+ ምክንያቱም ይሖዋ እናንተን የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ፈልጓል።+ +23 እኔም ብሆን ስለ እናንተ መጸለዬን በመተው በይሖዋ ላይ ኃጢአት መሥራት ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው፤ እንዲሁም መልካምና ትክክለኛ የሆነውን መንገድ እናንተን ማስተማሬን እቀጥላለሁ። +24 ብቻ እናንተ ይሖዋን ፍሩ፤+ በሙሉ ልባችሁም በታማኝነት* አገልግሉት፤ ለእናንተ ያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች አስታውሱ።+ +25 ሆኖም በግትርነት መጥፎ ነገር ማድረጋችሁን ብትቀጥሉ እናንተም ሆናችሁ ንጉሣችሁ+ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ።”+ +1 በኤፍሬም+ ተራራማ አካባቢ በምትገኘው በራማታይምጾፊም+ የሚኖር ሕልቃና+ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ኤፍሬማዊ ሲሆን የጹፍ ል���፣ የቶሁ ልጅ፣ የኤሊሁ ልጅ፣ የየሮሃም ልጅ ነበር። +2 እሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ የአንደኛዋ ስም ሐና ሲሆን የሌላኛዋ ደግሞ ፍናና ነበር። ፍናና ልጆች ነበሯት፤ ሐና ግን ምንም ልጅ አልነበራትም። +3 ያም ሰው አምልኮ ለማቅረብና* ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ መሥዋዕት ለመሠዋት በየዓመቱ ከከተማው ወደ ሴሎ ይወጣ ነበር።+ በዚያም ሁለቱ የኤሊ ልጆች ሆፍኒ እና ፊንሃስ+ ለይሖዋ ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር።+ +4 አንድ ቀን ሕልቃና መሥዋዕት ሲያቀርብ ለሚስቱ ለፍናና እንዲሁም ለወንዶች ልጆቿና ለሴቶች ልጆቿ በሙሉ ድርሻቸውን ሰጣቸው፤+ +5 ሆኖም ሐናን ይወዳት ስለነበር ልዩ የሆነ ድርሻ ሰጣት፤ ይሁንና ይሖዋ ለሐና ልጅ አልሰጣትም ነበር።* +6 በተጨማሪም ይሖዋ ልጅ ስላልሰጣት ጣውንቷ እሷን ለማበሳጨት ዘወትር ትሳለቅባት ነበር። +7 እሷም በየዓመቱ እንዲህ ታደርግባት ነበር፤ ሐና ወደ ይሖዋ ቤት+ በወጣች ቁጥር፣ እስክታለቅስና መብላት እስኪያቅታት ድረስ ጣውንቷ ትሳለቅባት ነበር። +8 ባሏ ሕልቃና ግን “ሐና፣ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበይም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከአሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽም?” አላት። +9 ከዚያም ሐና በሴሎ ከበሉና ከጠጡ በኋላ ተነሳች። በዚህ ጊዜ ካህኑ ኤሊ በይሖዋ ቤተ መቅደስ*+ መቃን አጠገብ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር። +10 እሷም በጣም ተማርራ* ነበር፤ ስቅስቅ ብላም እያለቀሰች ወደ ይሖዋ ትጸልይ ጀመር።+ +11 እንዲህም ስትል ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህ እየደረሰባት ያለውን መከራ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት+ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለይሖዋ እሰጠዋለሁ፤ ራሱንም ምላጭ አይነካውም።”+ +12 ሐና በይሖዋ ፊት ለረጅም ሰዓት ስትጸልይ ኤሊ አፏን ይመለከት ነበር። +13 ሐና የምትናገረው በልቧ ነበር፤ በመሆኑም ከንፈሯ ሲንቀጠቀጥ ቢታይም ድምፅዋ አይሰማም ነበር። በመሆኑም ኤሊ የሰከረች መሰለው። +14 ስለዚህ “ስካሩ የማይለቅሽ እስከ መቼ ነው? የወይን ጠጅሽን መጠጣት ተይ” አላት። +15 ሐናም መልሳ እንዲህ አለች፦ “አልሰከርኩም ጌታዬ! እኔ ብዙ ጭንቀት ያለብኝ ሴት* ነኝ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም፤ ይልቅስ ነፍሴን* በይሖዋ ፊት እያፈሰስኩ ነው።+ +16 እኔ እስካሁን ድረስ እየተናገርኩ ያለሁት በውስጤ ካለው ብሶትና ጭንቀት የተነሳ ስለሆነ አገልጋይህን እንደማትረባ ሴት አትቁጠራት።” +17 ከዚያም ኤሊ “በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ነገር ይስጥሽ” አላት።+ +18 እሷም “አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ ታግኝ” አለችው። ከዚያም ተነስታ ሄደች፤ ምግብም በላች፤ ዳግመኛም በፊቷ ላይ ሐዘን አልታየም። +19 እነሱም በማለዳ ተነስተው በይሖዋ ፊት ሰገዱ፤ ከዚያም በራማ+ ወደሚገኘው ቤታቸው ተመለሱ። ሕልቃናም ከሚስቱ ከሐና ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ ይሖዋም አሰባት።+ +20 ከዚያም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ* ሐና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ እሷም “ከይሖዋ የለመንኩት ነው” በማለት ስሙን+ ሳሙኤል* አለችው። +21 ከጊዜ በኋላም ሕልቃና ለይሖዋ ዓመታዊውን መሥዋዕት ለመሠዋትና+ የስእለት መባውን ለማቅረብ ቤተሰቡን ሁሉ ይዞ ወጣ። +22 ሐና ግን አልወጣችም፤+ ምክንያቱም ለባሏ “ሕፃኑ ጡት እንደጣለ አመጣዋለሁ፤ እሱም ይሖዋ ፊት ይቀርባል፤ ዕድሜውንም ሙሉ በዚያ ይኖራል” በማለት ነግራው ነበር።+ +23 ባሏ ሕልቃናም “መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ። ልጁን ጡት እስክታስጥዪው ድረስ ቤት ሁኚ። ይሖዋም ያልሽውን ይፈጽም” ብሏት ነበር። በመሆኑም ሐና ቤት ተቀመጠች፤ ልጇንም ጡት እስክታስጥለው ድረስ ተንከባከበችው። +24 እሷም ልክ ልጁን ጡት እንዳስጣለችው ከልጁ ጋር የሦስት ዓመት ወይፈን፣ አንድ የኢፍ መስፈሪያ* ዱቄትና አንድ እንስራ የወይን ጠጅ ይዛ ወጣች፤+ ልጁንም በሴሎ+ ወደሚገኘው ወደ ይሖዋ ቤት ይዛው መጣች። +25 እነሱም ወይፈኑን ካረዱ በኋላ ልጁን ወደ ኤሊ አመጡት። +26 እሷም እንዲህ አለች፦ “ጌታዬ ሆይ፣ በሕያውነትህ* እምላለሁ፤ ጌታዬ ሆይ፣ እኔ ወደ ይሖዋ ለመጸለይ ከአንተ ጋር እዚህ ቦታ ቆሜ የነበርኩት ሴት ነኝ።+ +27 ይህን ልጅ እንዲሰጠኝ ጸልዬ ነበር፤ ይሖዋም የለመንኩትን ሰጠኝ።+ +28 እኔ ደግሞ በበኩሌ ልጁን ለይሖዋ እሰጠዋለሁ።* በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለይሖዋ የተሰጠ ይሆናል።” እሱም* በዚያ ለይሖዋ ሰገደ። +29 ፍልስጤማውያን+ ሠራዊታቸውን በሙሉ በአፌቅ አሰባሰቡ፤ እስራኤላውያን ደግሞ በኢይዝራኤል+ በሚገኘው ምንጭ አጠገብ ሰፍረው ነበር። +2 የፍልስጤም ገዢዎችም በመቶዎችና በሺዎች እየሆኑ አለፉ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ+ ጋር ሆነው ከኋላ ተሰልፈው ይሄዱ ነበር። +3 የፍልስጤም መኳንንት ግን “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ያደርጋሉ?” አሉ። በዚህ ጊዜ አንኩስ የፍልስጤምን መኳንንት “ይህ ሰው ከእኔ ጋር ለአንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ አብሮኝ የኖረው የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ የሆነው ዳዊት ነው።+ ወደ እኔ ከተጠጋበት ቀን አንስቶ እስከዚህች ዕለት ድረስ +4 የፍልስጤም መኳንንት ግን በእሱ ላይ ተቆጥተው እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው እንዲመለስ አድርግ።+ ወደሰጠኸውም ስፍራ ይመለስ። በውጊያው ወቅት እኛኑ ዞሮ እንዳይወጋን+ አብሮን ወደ ጦርነቱ እንዲሄድ ማድረግ የለብህም። ደግሞስ ከጌታው ጋር ለመታረቅ የእኛን ሰዎች ራስ ቆርጦ ከመውሰድ በስተቀር ምን የተሻለ ነ +5 ይህ ሰው ‘ሳኦል ሺዎችን ገደለ፤ዳዊት ደግሞ አሥር ሺዎችን ገደለ’ በማለት እየዘፈኑ የጨፈሩለት ዳዊት አይደለም?”+ +6 በመሆኑም አንኩስ+ ዳዊትን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ አንተ ቅን ሰው ነህ፤ በእኔ በኩል ከሠራዊቴ ጋር አብረህ ብትዘምት ደስ ባለኝ፤+ ምክንያቱም ወደ እኔ ከመጣህበት ቀን አንስቶ እስከዚህች ዕለት ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁብህም።+ ሆኖም ገዢዎቹ አላመኑህም።+ +7 ስለዚህ በሰላም ተመለስ፤ የፍልስጤም ገዢዎችን ቅር የሚያሰኝ ምንም ነገር አታድርግ።” +8 ዳዊት ግን አንኩስን “ምን አደረግኩ? ወደ አንተ ከመጣሁበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህች ዕለት ድረስ በአገልጋይህ ላይ ምን ጥፋት አግኝተህበታል? ከአንተ ጋር የማልሄደውና ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋር የማልዋጋው ለምንድን ነው?” አለው። +9 አንኩስም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “በእኔ በኩል አንተ እንደ አምላክ መልአክ ጥሩ ሰው ነህ።+ የፍልስጤም መኳንንት ግን ‘ከእኛ ጋር ለጦርነት እንዲወጣ አታድርግ’ አሉኝ። +10 አሁንም አብረውህ ከመጡት የጌታህ አገልጋዮች ጋር በማለዳ ተነሱ፤ ልክ ጎህ ሲቀድ ጉዞ ጀምሩ።” +11 በመሆኑም ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ፍልስጤማውያን ምድር ለመመለስ በጠዋት ተነሱ፤ ፍልስጤማውያንም ወደ ኢይዝራኤል+ ወጡ። +28 በዚያም ዘመን ፍልስጤማውያን ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ሠራዊታቸውን አሰባሰቡ።+ በመሆኑም አንኩስ ዳዊትን “መቼም አንተና ሰዎችህ አብራችሁኝ ወደ ጦርነት እንደምትወጡ ታውቃለህ” አለው።+ +2 ዳዊትም አንኩስን “አገልጋይህ ምን እንደሚያደርግ አንተ በእርግጥ ታውቃለህ” አለው። ከዚያም አንኩስ ዳዊትን “እኔም በቋሚነት የግል ጠባቂዬ* እንድትሆን የምሾምህ ለዚህ ነው” አለው።+ +3 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም ሁሉ አልቅሰውለት በገዛ ከተማው በራማ+ ቀብረውት ነበር። ሳኦልም መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድሪቱ አስወግዶ ነበር።+ +4 ፍልስጤማውያንም ተሰብስበ��� በመምጣት በሹነም+ ሰፈሩ። ሳኦል ደግሞ እስራኤላውያንን በሙሉ አሰባሰበ፤ እነሱም በጊልቦአ+ ሰፈሩ። +5 ሳኦል የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ባየ ጊዜ ፈራ፤ ልቡም እጅግ ተሸበረ።+ +6 ሳኦል ይሖዋን ቢጠይቅም+ ይሖዋ በሕልምም ሆነ በኡሪም+ አሊያም በነቢያት በኩል መልስ አልሰጠውም። +7 በመጨረሻም ሳኦል አገልጋዮቹን “መናፍስት ጠሪ+ ፈልጉልኝ፤ እኔም ሄጄ ምክር እጠይቃታለሁ” አላቸው። አገልጋዮቹም “በኤንዶር+ አንዲት መናፍስት ጠሪ አለች” በማለት መለሱለት። +8 በመሆኑም ሳኦል ማንነቱን ሰውሮና ሌላ ልብስ ለብሶ ከሁለት ሰዎች ጋር በመሆን በሌሊት ወደ ሴትየዋ ሄደ። እሱም “እባክሽ፣ መናፍስትን ጠርተሽ+ ጠንቁይልኝ፤ የምነግርሽንም ሰው አስነሺልኝ” አላት። +9 ሆኖም ሴትየዋ እንዲህ አለችው፦ “ሳኦል መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድሪቱ በማስወገድ ምን እንዳደረገ አንተ ራስህ በሚገባ ታውቃለህ።+ ታዲያ እኔ እንድገደል ልታጠምደኝ* የምትሞክረው ለምንድን ነው?”+ +10 ከዚያም ሳኦል “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ በዚህ ጉዳይ በጥፋተኝነት አትጠየቂም!” በማለት በይሖዋ ማለላት። +11 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ “እሺ ማንን ላስነሳልህ?” አለችው። እሱም “ሳሙኤልን አስነሺልኝ” አላት። +12 ሴትየዋም “ሳሙኤልን”*+ ስታየው በኃይል ጮኸች፤ ከዚያም ሳኦልን “ያታለልከኝ ለምንድን ነው? አንተ ሳኦል አይደለህ!” አለችው። +13 ንጉሡም “አትፍሪ፤ ለመሆኑ ምን እያየሽ ነው?” አላት። ሴትየዋም ለሳኦል “አማልክትን የሚመስል ከምድር ሲወጣ አያለሁ” ስትል መለሰችለት። +14 እሱም ወዲያውኑ “ምን ይመስላል?” አላት፤ እሷም “የወጣው አንድ አረጋዊ ሰው ነው፤ እጅጌ የሌለው ቀሚስ ለብሷል”+ አለችው። በዚህ ጊዜ ሳኦል የወጣው “ሳሙኤል” እንደሆነ ተገነዘበ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። +15 ከዚያም “ሳሙኤል” ሳኦልን “እንድነሳ በማድረግ ለምን ትረብሸኛለህ?” አለው። ሳኦልም እንዲህ አለው፦ “ከባድ ጭንቅ ውስጥ ገብቻለሁ። ፍልስጤማውያን እየወጉኝ ነው፤ አምላክም ከእኔ ርቋል፤ በነቢያትም ሆነ በሕልም አማካኝነት መልስ አይሰጠኝም፤+ ስለሆነም ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንድትነግረኝ ጠራሁህ።”+ +16 “ሳሙኤልም” እንዲህ አለው፦ “ታዲያ ይሖዋ ከራቀህና+ ጠላት ከሆነብህ እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? +17 ይሖዋ በእኔ በኩል አስቀድሞ የተናገረውን ይፈጽማል፦ ይሖዋ መንግሥትን ከእጅህ ነጥቆ ከባልንጀሮችህ አንዱ ለሆነው ለዳዊት ይሰጠዋል።+ +18 የይሖዋን ቃል ስላልሰማህና በአማሌቃውያን ላይ የነደደውን ቁጣውን ስላላስፈጸምክ+ ይሖዋ በዚህ ቀን ይህን ያደርግብሃል። +19 ይሖዋ አንተንም ሆነ እስራኤላውያንን ለፍልስጤማውያን+ አሳልፎ ይሰጣችኋል፤ ነገ አንተና+ ልጆችህ+ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ። በተጨማሪም ይሖዋ የእስራኤልን ሠራዊት ለፍልስጤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”+ +20 በዚህ ጊዜ ሳኦል በቁመቱ መሬት ላይ ተዘረረ፤ “ሳሙኤል” በተናገረውም ቃል የተነሳ በከፍተኛ ፍርሃት ተዋጠ። ደግሞም ሙሉ ቀንና ሙሉ ሌሊት እህል ስላልቀመሰ አቅሙ ተሟጠጠ። +21 ሴትየዋም ወደ ሳኦል መጥታ በጣም እንደተረበሸ ስታይ እንዲህ አለችው፦ “እንግዲህ እኔ አገልጋይህ ቃልህን ሰምቻለሁ፤ ሕይወቴን አደጋ ላይ ጥዬም*+ እንዳደርገው የነገርከኝን ፈጽሜአለሁ። +22 አሁንም እባክህ፣ የአገልጋይህን ቃል ስማ። ትንሽ ምግብ ላቅርብልህና ብላ፤ ከዚያም ለመሄድ የሚያስችል ብርታት ታገኛለህ።” +23 እሱ ግን “አልበላም” በማለት እንቢ አለ። ሆኖም አገልጋዮቹና ሴትየዋ አጥብቀው ለመኑት። በመጨረሻም ቃላቸውን በመስማት ከመሬት ተነስቶ አልጋ ላይ ተቀመጠ። +24 ሴትየዋም ቤት ውስጥ አንድ የሰባ ጥጃ ነበ���ት፤ ስለዚህ ፈጠን ብላ ጥጃውን አረደችው፤* ከዚያም ዱቄት ወስዳ ካቦካች በኋላ ቂጣ ጋገረች። +25 ለሳኦልና ለአገልጋዮቹም አቀረበችላቸው፤ እነሱም በሉ። ከዚያም ተነስተው በሌሊት ሄዱ።+ +8 ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ውስጥ ፈራጆች ሆነው እንዲያገለግሉ ሾማቸው። +2 የበኩር ልጁ ስም ኢዩኤል ሲሆን የሁለተኛው ልጁ ስም ደግሞ አቢያህ+ ነበር፤ እነሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ። +3 ይሁንና ልጆቹ የእሱን ፈለግ አልተከተሉም፤ ከዚህ ይልቅ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም+ ለማግኘት ይጥሩ፣ ጉቦ ይቀበሉ+ እንዲሁም ፍርድ ያጣምሙ+ ነበር። +4 ከጊዜ በኋላ የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ አንድ ላይ ተሰብስበው በራማ ወደሚገኘው ወደ ሳሙኤል መጡ። +5 እንዲህም አሉት፦ “እንግዲህ አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህ ደግሞ የአንተን ፈለግ እየተከተሉ አይደለም። ስለዚህ እንደ ሌሎቹ ብሔራት ሁሉ በእኛ ላይ ፈራጅ የሚሆን ንጉሥ ሹምልን።”+ +6 ይሁንና “በእኛ ላይ ፈራጅ የሚሆን ንጉሥ ሹምልን” ማለታቸው ሳሙኤልን አላስደሰተውም።* ሳሙኤልም ወደ ይሖዋ ጸለየ፤ +7 ይሖዋም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቡ የሚልህን ሁሉ ስማ፤ አልቀበልም ያሉት አንተን አይደለም፤ ይልቁንም ንጉሣቸው አድርገው መቀበል ያልፈለጉት እኔን ነው።+ +8 እየፈጸሙ ያሉት ነገር ከግብፅ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከዚህች ዕለት ድረስ ሲያደርጉ የነበሩትን ነው፤ እኔን ትተው+ ሌሎች አማልክትን አገለገሉ፤+ በአንተም ላይ እያደረጉ ያሉት ይህንኑ ነው። +9 ስለዚህ የሚሉህን ስማ። ይሁን እንጂ በጥብቅ አስጠንቅቃቸው፤ በላያቸው የሚነግሠው ንጉሥ ምን እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት እንዳለው ንገራቸው።” +10 በመሆኑም ሳሙኤል ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ለጠየቁት ሰዎች የይሖዋን ቃል ሁሉ ነገራቸው። +11 እንዲህ አላቸው፦ “በእናንተ ላይ የሚነግሠው ንጉሥ እንዲህ እንዲደረግለት የመጠየቅ መብት አለው፦+ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ+ ሠረገላው ውስጥ ያስቀምጣቸዋል፤+ ፈረሰኞችም+ ያደርጋቸዋል፤ የተወሰኑትንም ከሠረገሎቹ ፊት ፊት እንዲሮጡ ያደርጋል። +12 ለራሱም የሺህ አለቆችንና+ የሃምሳ አለቆችን+ ይሾማል፤ አንዳንዶቹም መሬቱን ያርሳሉ፣+ እህሉን ያጭዳሉ+ እንዲሁም የጦር መሣሪያዎቹንና ለሠረገሎቹ+ የሚሆኑትን ዕቃዎች ይሠራሉ። +13 ሴቶች ልጆቻችሁንም ወስዶ ቅባት ቀማሚዎች፣* ምግብ አብሳዮችና ዳቦ ጋጋሪዎች+ ያደርጋቸዋል። +14 እንዲሁም ከማሳችሁ፣ ከወይን እርሻችሁና ከወይራ ዛፎቻችሁ+ ምርጥ የሆነውን ይወስዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይሰጣቸዋል። +15 ከእህል ማሳችሁና ከወይን እርሻችሁ ላይ አንድ አሥረኛውን ወስዶ ለቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱና ለአገልጋዮቹ ይሰጣል። +16 ወንድ አገልጋዮቻችሁንና ሴት አገልጋዮቻችሁን፣ ከከብቶቻችሁ መካከል ምርጥ የሆኑትን እንዲሁም አህዮቻችሁን ይወስዳል፤ ለራሱ ሥራም ይጠቀምባቸዋል።+ +17 ከመንጋችሁ መካከል አንድ አሥረኛውን ይወስዳል፤+ እናንተም የእሱ አገልጋዮች ትሆናላችሁ። +18 ለራሳችሁ ከመረጣችሁት ንጉሥ የተነሳ የምትጮኹበት ቀን ይመጣል፤+ ሆኖም በዚያ ቀን ይሖዋ አይመልስላችሁም።” +19 ሕዝቡ ግን ሳሙኤል የተናገረውን ለመስማት አሻፈረኝ አለ፤ እንዲህም አለ፦ “አይሆንም፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን። +20 ከዚያም እንደ ሌሎች ብሔራት እንሆናለን፤ ንጉሣችንም ፈራጅ ይሆንልናል፣ ይመራናል እንዲሁም ጦርነት ሲገጥመን ይዋጋልናል።” +21 ሳሙኤልም ሕዝቡ ያለውን ሁሉ ከሰማ በኋላ የተናገሩትን ነገር ይሖዋ እየሰማ በድጋሚ ተናገረ። +22 ይሖዋም ሳሙኤልን “የሚሉህን ስማ፤ በላያቸው የሚገዛ ንጉሥም አንግሥላቸው”+ አለው። ከዚያም ሳሙኤል የእስራኤልን ሰዎች “እያንዳንዳ���ሁ ወደ ከተማችሁ ተመለሱ” አላቸው። +11 ከዚያም አሞናዊው+ ናሃሽ ወጥቶ በጊልያድ የምትገኘውን ኢያቢስን ከበባት። የኢያቢስ+ ሰዎች በሙሉ ናሃሽን “ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ግባ፤* እኛም እናገለግልሃለን” አሉት። +2 አሞናዊው ናሃሽም “ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የምገባው የእያንዳንዳችሁ ቀኝ ዓይን ከወጣ ነው። ይህን የማደርገውም መላውን እስራኤል ለማዋረድ ስል ነው” አላቸው። +3 የኢያቢስ ሽማግሌዎችም “ወደ መላው የእስራኤል ግዛት መልእክተኞችን እንድንልክ የሰባት ቀን ጊዜ ስጠን። ከዚያም የሚያድነን ሰው ከሌለ ለአንተ እጃችንን እንሰጣለን” ሲሉ መለሱለት። +4 መልእክተኞቹም ሳኦል ወደሚገኝበት ወደ ጊብዓ+ መጥተው ይህን መልእክት ለሕዝቡ ተናገሩ፤ ሕዝቡም ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ። +5 ሳኦል ግን መንጋውን እየነዳ ከመስክ በመምጣት ላይ ነበር፤ ሳኦልም “ሕዝቡ የሚያለቅሰው ምን ሆኖ ነው?” አለ። እነሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሏቸውን ነገሩት። +6 ሳኦልም ይህን ሲሰማ የአምላክ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ ቁጣውም ነደደ። +7 እሱም ጥንድ በሬዎችን ወስዶ ቆራረጣቸው፤ እነዚህንም በመልእክተኞቹ እጅ አስይዞ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ማንኛውም ሰው ከብቱ እንዲህ ይቆራረጣል!” በማለት እንዲናገሩ ወደ መላው የእስራኤል ግዛት ላካቸው። በሕዝቡም ላይ የይሖዋ ፍርሃት ስለወደቀ ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ። +"8 ከዚያም ሳኦል ሰዎቹን ቤዜቅ ላይ ቆጠራቸው፤ እነሱም 300,000 እስራኤላውያንና 30,000 የይሁዳ ሰዎች ነበሩ።" +9 የመጡትንም መልእክተኞች እንዲህ አሏቸው፦ “በጊልያድ ባለችው በኢያቢስ የሚኖሩትን ሰዎች ‘በነገው ዕለት ፀሐይዋ በምትከርበት ጊዜ መዳን ታገኛላችሁ’ በሏቸው።” ከዚያም መልእክተኞቹ መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሯቸው፤ እነሱም በደስታ ፈነደቁ። +10 ስለሆነም የኢያቢስ ሰዎች “ነገ እጃችንን ለእናንተ እንሰጣለን፤ እናንተም መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ ልታደርጉብን ትችላላችሁ” አሏቸው።+ +11 በማግስቱ ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ቡድን ከፈለው፤ እነሱም በማለዳው ክፍለ ሌሊት* ወደ አሞናውያን+ ሰፈር ገብተው ፀሐይዋ እስክትከር ድረስ መቷቸው። የተረፉትም ቢሆኑ ሁለቱ እንኳ አንድ ላይ መሆን እስከማይችሉ ድረስ ተበታተኑ። +12 ከዚያም ሕዝቡ ሳሙኤልን “‘አሁን ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሊሆን ነው?’ ሲሉ የነበሩት እነማን ናቸው?+ እነዚህን ሰዎች ስጡንና እንግደላቸው” አለው። +13 ሳኦል ግን “ይህ ዕለት ይሖዋ እስራኤልን ያዳነበት ስለሆነ በዚህ ቀን ማንም ሰው መገደል የለበትም” አለ።+ +14 በኋላም ሳሙኤል ሕዝቡን “ኑ፣ ወደ ጊልጋል+ እንውጣና ንግሥናውን እንደገና እናጽና” አለ።+ +15 በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጊልጋል ሄደ፤ በጊልጋልም ሳኦልን በይሖዋ ፊት አነገሡት። በዚያም በይሖዋ ፊት የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረቡ፤+ ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እጅግ ተደሰቱ።+ +2 ከዚያም ሐና እንዲህ ስትል ጸለየች፦ “ልቤ በይሖዋ ሐሴት አደረገ፤+ቀንዴም* በይሖዋ ከፍ ከፍ አለ። አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፣በማዳን ሥራዎችህ ደስ ብሎኛልና። + 2 እንደ ይሖዋ ያለ ቅዱስ ማንም የለም፣ያለአንተ ማንም የለም፤+እንደ አምላካችን ያለ ዓለት የለም።+ + 3 በትዕቢት መናገራችሁን ተዉ፤የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፣ይሖዋ ሁሉን የሚያውቅ አምላክ ነውና፣+ተግባርን ሁሉ በትክክል የሚመዝን እሱ ነው። + 4 የኃያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፣የተንገዳገዱት ግን ብርታት አግኝተዋል።+ + 5 ጠግበው የነበሩት ለምግብ ሲሉ ተቀጥረው ለመሥራት ተገደዱ፤የተራቡት ግን ከእንግዲህ አይራቡም።+ መሃን የነበረችው ሴት ሰባት ልጆች ወለደች፤+ብዙ ወንዶች ልጆች የነበሯት ግን ብቻዋን ���ረች።* + 6 ይሖዋ ይገድላል፤ ሕይወትንም ያድናል፤*ወደ መቃብር* ያወርዳል፤ ከዚያም ያወጣል።+ + 7 ይሖዋ ያደኸያል፤ እንዲሁም ያበለጽጋል፤+እሱ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።+ + 8 ችግረኛውን ከአቧራ ላይ ያነሳል፤ድሃውንም ከአመድ ቁልል* ላይ ያነሳል፤+ከመኳንንትም ጋር ያስቀምጣቸዋል፤የክብር ወንበርም ይሰጣቸዋል። የምድር ምሰሶዎች የይሖዋ ናቸው፤+ፍሬያማ የሆነችውን ምድር በእነሱ ላይ አስቀምጧል። + 9 እሱ የታማኞቹን እርምጃ ይጠብቃል፤+ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ጸጥ እንዲሉ ይደረጋሉ፤+ሰው የበላይ የሚሆነው በኃይሉ አይደለምና።+ +10 ይሖዋ ከእሱ ጋር የሚዋጉትን ያደቃቸዋል፤*+እሱም ከሰማይ ነጎድጓድ ይለቅባቸዋል።+ ይሖዋ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይፈርዳል፤+ለንጉሡ ኃይል ይሰጣል፤+የእሱ ቅቡዕ የሆነውንም ቀንዱን* ከፍ ከፍ ያደርጋል።”+ +11 ከዚያም ሕልቃና በራማ ወደሚገኘው ቤቱ ሄደ፤ ልጁ ግን በካህኑ በኤሊ ፊት የይሖዋ አገልጋይ ሆነ።*+ +12 የኤሊ ወንዶች ልጆች ምግባረ ብልሹ ነበሩ፤+ ለይሖዋ አክብሮት አልነበራቸውም። +13 ከሕዝቡ ላይ የካህናቱን ድርሻ በሚቀበሉበት ጊዜ እንዲህ ያደርጉ ነበር፦+ ማንኛውም ሰው መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለው ሹካ ይዞ ይመጣና +14 ሹካውን ወደ ሰታቴው ወይም ወደ ምንቸቱ ወይም ወደ አፍላሉ* ወይም ወደ ባለ አንድ ጆሮው ድስት ይከተዋል። መንሹ ይዞ የሚወጣውንም ካህኑ ለራሱ ይወስድ ነበር። ወደ ሴሎ በሚመጡት እስራኤላውያን ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጉ ነበር። +15 ሌላው ቀርቶ መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው ስቡን ከማቃጠሉ+ በፊት የካህኑ አገልጋይ መጥቶ “ለካህኑ የሚጠበስ ሥጋ ስጠው። ጥሬ ሥጋ ብቻ እንጂ የተቀቀለ ሥጋ ከአንተ አይቀበልም” ይለው ነበር። +16 ሰውየውም “በመጀመሪያ ስቡን ያቃጥሉ፤+ ከዚያ በኋላ የፈለግከውን* ውሰድ” ይለው ነበር። እሱ ግን “አይሆንም፤ አሁኑኑ ስጠኝ፤ ካልሆነ ግን ነጥቄ እወስዳለሁ!” ይለዋል። +17 ሰዎቹ የይሖዋን መባ ያቃልሉ ስለነበር የአገልጋዮቹ ኃጢአት በይሖዋ ፊት እጅግ ታላቅ ሆነ።+ +18 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ገና አንድ ፍሬ ልጅ የነበረ ቢሆንም ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ+ ለብሶ* በይሖዋ ፊት ያገለግል ነበር።+ +19 እናቱም ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብ ከባሏ ጋር ስትወጣ እጅጌ የሌለው ትንሽ ቀሚስ እየሠራች በየዓመቱ ታመጣለት ነበር።+ +20 ኤሊም ሕልቃናንና ሚስቱን እንዲህ ሲል ባረካቸው፦ “ለይሖዋ በተሰጠው* ልጅ ምትክ ይሖዋ ከዚህች ሚስትህ ልጅ ይስጥህ” አለው።+ እነሱም ወደ ቤታቸው ተመለሱ። +21 ይሖዋም ሐናን አሰባት፤ እሷም ፀነሰች፤+ ሌሎች ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችም ወለደች። ብላቴናው ሳሙኤልም በይሖዋ ፊት እያደገ ሄደ።+ +22 በዚህ ጊዜ ኤሊ በጣም አርጅቶ ነበር፤ ሆኖም ወንዶች ልጆቹ በሁሉም እስራኤላውያን ላይ ምን እንደሚያደርጉ+ እንዲሁም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደሚተኙ+ አንድም ሳይቀር ሰምቶ ነበር። +23 እሱም እንዲህ ይላቸው ነበር፦ “እንዲህ ያለ ነገር ለምን ታደርጋላችሁ? ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መጥፎ ነገር ሲናገሩ እሰማለሁ። +24 ልጆቼ፣ ትክክል አይደላችሁም፤ በይሖዋ ሕዝቦች መካከል ሲናፈስ የምሰማው ወሬ ጥሩ አይደለም። +25 አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል ሌላ ሰው ይሖዋን ይለምንለት ይሆናል፤* ሆኖም አንድ ሰው ይሖዋን ቢበድል+ ማን ሊጸልይለት ይችላል?” እነሱ ግን የአባታቸውን ቃል ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ምክንያቱም ይሖዋ ሊገድላቸው ወስኖ ነበር።+ +26 ይህ በእንዲህ እንዳለ ብላቴናው ሳሙኤል በይሖዋም ሆነ በሰዎች ፊት በአካል እያደገና ይበልጥ ሞገስ እያገኘ ሄደ።+ +27 አንድ የአምላክ ሰው ወደ ኤሊ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የአባትህ ቤት በግብፅ በፈርዖን ቤት በባርነት ያገለግል በነበረበት ጊዜ ራሴን በይፋ ገልጬለት አልነበረም?+ +28 ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ፣ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፣+ ዕጣን እንዲያጥንና* በፊቴ ኤፉድ እንዲለብስ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ተመርጦ ነበር፤+ እኔም እስራኤላውያን* በእሳት የሚያቀርቧቸውን መባዎች በሙሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።+ +29 ታዲያ እናንተ በማደሪያዬ እንዲቀርብ ያዘዝኩትን መሥዋዕቴንና መባዬን የናቃችሁት* ለምንድን ነው?+ ሕዝቤ እስራኤል ከሚያመጣው ከእያንዳንዱ መባ ላይ ምርጡን ወስዳችሁ ራሳችሁን በማደለብ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ያከበርከው ለምንድን ነው?+ +30 “‘ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የይሖዋ ቃል እንዲህ ይላል፦ “የአንተ ቤትና የአባትህ ቤት ምንጊዜም በፊቴ እንደሚሄዱ ተናግሬ ነበር።”+ አሁን ግን ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው፤ ምክንያቱም የሚያከብሩኝን አከብራለሁ፤+ የሚንቁኝ ግን ይናቃሉ።” +31 በቤትህ እስከ ሽምግልና ድረስ በሕይወት የሚቆይ ሰው እንዳይኖር የአንተንም ሆነ የአባትህን ቤት ብርታት* የምቆርጥበት ቀን ይመጣል።+ +32 ለእስራኤል በተደረገው ብዙ መልካም ነገር መካከል በማደሪያዬ ውስጥ ተቀናቃኝ ታያለህ፤+ በቤትህም ዳግመኛ አረጋዊ የሚባል አይገኝም። +33 በመሠዊያዬ ፊት እንዲያገለግል የምተወው የአንተ የሆነ ሰው ዓይኖችህ እንዲፈዙና ለሐዘን እንድትዳረግ* ያደርጋል፤ ከቤትህ ሰዎች መካከል ግን አብዛኞቹ በሰዎች ሰይፍ ይሞታሉ።+ +34 በሁለቱ ልጆችህ በሆፍኒ እና በፊንሃስ ላይ የሚደርሰው ነገር ምልክት ይሆንሃል፦ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።+ +35 ከዚያም ለራሴ ታማኝ የሆነ ካህን አስነሳለሁ።+ እሱም ከልቤ ፍላጎት* ጋር የሚስማማ ተግባር ይፈጽማል፤ እኔም ዘላቂ የሆነ ቤት እሠራለታለሁ፤ እሱም እኔ በቀባሁት ፊት ሁልጊዜ ይሄዳል። +36 ከቤትህ የሚተርፍ ሰው ቢኖር የሚከፈለው ገንዘብና ቁራሽ ዳቦ ለማግኘት ሲል መጥቶ ይሰግድለታል፤ ከዚያም “እባክህ፣ ቁራሽ ዳቦ እንዳገኝ በማንኛውም የክህነት ሥራ ላይ መድበኝ” ይላል።’”+ +26 ከጊዜ በኋላ የዚፍ+ ሰዎች በጊብዓ+ ወደሚገኘው ወደ ሳኦል መጥተው “ዳዊት በየሺሞን*+ ፊት ለፊት በሚገኘው በሃኪላ ኮረብታ ተደብቆ የለም?” አሉት። +"2 ስለሆነም ሳኦል ከእስራኤል የተመረጡ 3,000 ሰዎችን በማስከተል ዳዊትን በዚፍ ምድረ በዳ ለመፈለግ ወደዚያ ወረደ።+" +3 ሳኦልም ከየሺሞን ፊት ለፊት በሚገኘው በሃኪላ ኮረብታ ላይ መንገድ ዳር ሰፈረ። በዚህ ጊዜ ዳዊት በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ዳዊትም ሳኦል እሱን ለመፈለግ ወደ ምድረ በዳ እንደመጣ ሰማ። +4 በመሆኑም ሳኦል በእርግጥ መጥቶ እንደሆነ ለማወቅ ሰላዮችን ላከ። +5 በኋላም ዳዊት ሳኦል ወደሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አዛዥ የሆነው የኔር ልጅ አበኔር+ የተኙበትንም ቦታ አየ፤ ሳኦል በሰፈሩ መሃል ተኝቶ ነበር፤ ሠራዊቱም ዙሪያውን ሰፍሮ ነበር። +6 ከዚያም ዳዊት ሂታዊውን+ አሂሜሌክንና የኢዮዓብ ወንድም የሆነውን የጽሩያን+ ልጅ አቢሳን+ “ሳኦል ወደሰፈረበት ቦታ አብሮኝ የሚወርድ ማን ነው?” አላቸው። አቢሳም “እኔ አብሬህ እወርዳለሁ” አለ። +7 ስለዚህ ዳዊትና አቢሳ በሌሊት ሠራዊቱ ወዳለበት ሄዱ፤ ሳኦልም ጦሩን ራስጌው አጠገብ መሬት ላይ ሰክቶ በሰፈሩ መሃል ተኝቶ አገኙት፤ አበኔርና ሠራዊቱም በዙሪያው ተኝተው ነበር። +8 አቢሳም ዳዊትን “አምላክ ዛሬ ጠላትህን እጅህ ላይ ጥሎታል።+ እባክህ አሁን አንድ ጊዜ ብቻ በጦር ወግቼ ከመሬት ጋር ላጣብቀው፤ መድገም አያስፈልገኝም” አለው። +9 ሆኖም ዳዊት አቢሳን “ጉዳት እንዳታደርስበት፤ ለመሆኑ ይሖዋ በቀባው+ ላይ እጁን አንስቶ ከበደል ነፃ የሚሆን ማን ነው?”+ አለው። +10 ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለው፦ “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ ይሖዋ ራሱ ይቀስፈዋል፤+ ወይም ደግሞ እንደ ማንኛውም ሰው አንድ ቀን ይሞታል፤+ አሊያም ወደ ጦርነት ወርዶ እዚያ ይገደላል።+ +11 በእኔ በኩል ይሖዋ በቀባው ላይ እጄን ማንሳት በይሖዋ ዓይን ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው!+ በል አሁን ራስጌው አጠገብ ያለውን ጦርና የውኃ መያዣውን አንሳና እንሂድ።” +12 በመሆኑም ዳዊት ጦሩንና የውኃ መያዣውን ከሳኦል ራስጌ ወሰደ፤ ከዚያም ሄዱ። ሁሉም ተኝተው ስለነበር ያያቸውም ሆነ ልብ ያላቸው ወይም ከእንቅልፉ የነቃ አንድም ሰው አልነበረም፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ከባድ እንቅልፍ ጥሎባቸው ነበር። +13 ከዚያም ዳዊት ወደ ማዶ ተሻግሮ በተራራው ጫፍ ላይ ራቅ ብሎ ቆመ፤ በመካከላቸውም ያለው ርቀት ሰፊ ነበር። +14 ዳዊትም ወደ ሠራዊቱና ወደ ኔር ልጅ ወደ አበኔር+ ተጣርቶ “አበኔር፣ የማትመልስልኝ ለምንድን ነው?” አለ። አበኔርም “ንጉሡን የምትጣራው አንተ ማን ነህ?” ሲል መለሰለት። +15 ዳዊትም አበኔርን እንዲህ አለው፦ “አንተ ወንድ አይደለህም? ደግሞስ በእስራኤል ውስጥ እንደ አንተ ያለ ማን አለ? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን በንቃት ያልጠበቅከው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ከወታደሮቹ አንዱ ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር።+ +16 ይህ ያደረግከው ነገር ጥሩ አይደለም። ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ ይሖዋ የቀባውን+ ጌታችሁን በንቃት ስላልጠበቃችሁ ሞት ይገባችኋል። እስቲ ዙሪያህን ተመልከት! በንጉሡ ራስጌ አጠገብ የነበረው የንጉሡ ጦርና የውኃ መያዣ+ የት አለ?” +17 ሳኦልም የዳዊት ድምፅ መሆኑን ስለለየ “ልጄ ዳዊት ሆይ፣ ይህ የአንተ ድምፅ ነው?” አለው።+ ዳዊትም መልሶ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ አዎ የእኔ ድምፅ ነው” አለ። +18 አክሎም እንዲህ አለ፦ “ጌታዬ አገልጋዩን የሚያሳድደው ለምንድን ነው?+ ምን አድርጌ ነው? የተገኘብኝስ በደል ምንድን ነው?+ +19 ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እባክህ የአገልጋይህን ቃል ስማ፦ በእኔ ላይ እንድትነሳ ያደረገህ ይሖዋ ከሆነ የማቀርበውን የእህል መባ ይቀበል።* ሆኖም እንዲህ እንድታደርግ ያነሳሱህ ሰዎች ከሆኑ+ በይሖዋ ፊት የተረገሙ ይሁኑ፤ ምክንያቱም ‘ሂድ፣ ሌሎች አማልክትን አገልግል!’ ብለው በይሖዋ ርስት+ ውስጥ ድርሻ እን +20 አሁንም ደሜ ከይሖዋ ፊት ርቆ መሬት ላይ እንዲፈስ አታድርግ፤ ምክንያቱም የእስራኤል ንጉሥ በተራራ ላይ ቆቅ የሚያሳድድ ይመስል አንዲት ቁንጫ+ ለመፈለግ ወጥቷል።” +21 ሳኦልም መልሶ እንዲህ አለው፦ “በእርግጥ ኃጢአት ሠርቻለሁ።+ ልጄ ዳዊት ሆይ፣ ከእንግዲህ ምንም ጉዳት ስለማላደርስብህ ተመለስ፤ ምክንያቱም በዛሬው ዕለት ሕይወቴን* ውድ አድርገህ+ ተመልክተሃታል። በእርግጥም የሞኝነት ድርጊት ፈጽሜአለሁ፤ ትልቅ ስህተት ሠርቻለሁ።” +22 ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “የንጉሡ ጦር ይኸውና። ከወጣቶቹ መካከል አንዱ ይምጣና ይውሰደው። +23 ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና+ እንደ ታማኝነቱ የሚከፍለው ይሖዋ ነው፤ ይኸው ዛሬ ይሖዋ እጄ ላይ ጥሎህ ነበር፤ እኔ ግን ይሖዋ በቀባው ላይ እጄን ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆንኩም።+ +24 እነሆ፣ ዛሬ የአንተ ሕይወት* በፊቴ ውድ እንደሆነች ሁሉ የእኔም ሕይወት* በይሖዋ ፊት ውድ ትሁን፤ ከመከራም ሁሉ ያድነኝ።”+ +25 ሳኦልም ዳዊትን “ልጄ ዳዊት ሆይ፣ የተባረክ ሁን። አንተ ታላላቅ ሥራዎችን ታከናውናለህ፤ ድል አድራጊም ትሆናለህ” አለው።+ ከዚያም ዳዊት መንገዱን ቀጠለ፤ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።+ +4 የሳሙኤልም ቃል ለእስራኤላውያን ሁሉ ደረሰ። ከዚያ��� እስራኤላውያን ከፍልስጤማውያን ጋር ለመዋጋት ወጡ፤ ኤቤንዔዘርም አጠገብ ሰፈሩ፤ ፍልስጤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፍረው ነበር። +"2 ፍልስጤማውያን እስራኤላውያንን ለመግጠም ተሰልፈው ወጡ፤ ውጊያውም እየተፋፋመ ሄደ፤ እስራኤላውያንም ውጊያው በተደረገበት ግንባር 4,000 ሰው በገደሉባቸው በፍልስጤማውያን ድል ተመቱ።" +3 ሠራዊቱ ወደ ሰፈሩ በተመለሰ ጊዜ የእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ አሉ፦ “ይሖዋ በዛሬው ዕለት በፍልስጤማውያን ፊት ድል እንድንመታ የፈቀደው ለምንድን ነው?*+ አብሮን እንዲሆንና ከጠላቶቻችን እጅ እንዲያድነን የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ ይዘነው እንሂድ።”+ +4 በመሆኑም ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ላከ፤ እነሱም ከኪሩቤል በላይ* ዙፋን ላይ የተቀመጠውን+ የሠራዊት ጌታ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከዚያ ተሸክመው መጡ። ሁለቱ የኤሊ ልጆች ሆፍኒ እና ፊንሃስም+ ከእውነተኛው አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ጋር አብረው ነበሩ። +5 የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈሩ ሲገባ እስራኤላውያን ሁሉ ምድር እስክትናወጥ ድረስ ጮኹ። +6 ፍልስጤማውያንም ጩኸቱን ሲሰሙ “በዕብራውያን ሰፈር የሚሰማው ይህ ሁሉ ጩኸት ምንድን ነው?” አሉ። በመጨረሻም የይሖዋ ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደገባ አወቁ። +7 ፍልስጤማውያንም “አምላክ ወደ ሰፈሩ ገብቷል!”+ በማለት በፍርሃት ተዋጡ። በመሆኑም እንዲህ አሉ፦ “ወየው ጉዳችን! እንዲህ ዓይነት ነገር ሆኖ አያውቅም! +8 ወየው ጉዳችን! ከዚህ ባለ ግርማ አምላክ እጅ ማን ያድነናል? ግብፃውያንን በምድረ በዳ በተለያዩ መቅሰፍቶች የመታቸው አምላክ እኮ ይህ ነው።+ +9 እናንተ ፍልስጤማውያን አይዟችሁ፣ ወንድነታችሁን አሳዩ፤ አለዚያ ዕብራውያን የእናንተ አገልጋዮች እንደነበሩ ሁሉ እናንተም የእነሱ አገልጋዮች ትሆናላችሁ።+ ወንድነታችሁን አሳዩ፤ ተዋጉ!” +"10 በመሆኑም ፍልስጤማውያን ተዋጉ፤ እስራኤላውያንም ድል ተመቱ፤+ እያንዳንዱም ሰው ወደየድንኳኑ ሸሸ። በጣም ብዙ ሕዝብ አለቀ፤ ከእስራኤላውያንም ወገን 30,000 እግረኛ ወታደር ሞተ።" +11 የአምላክም ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱ የኤሊ ልጆች ሆፍኒ እና ፊንሃስም ሞቱ።+ +12 አንድ ቢንያማዊ ልብሱን ቀዶና በራሱ ላይ አቧራ ነስንሶ+ ከጦር ግንባሩ እየሮጠ በዚያው ቀን ሴሎ ደረሰ። +13 ሰውየውም ሲደርስ ኤሊ በእውነተኛው አምላክ ታቦት+ የተነሳ ልቡ ስለተረበሸ መንገድ ዳር ወንበር ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወሬውን ለመንገር ወደ ከተማዋ ገባ፤ መላ ከተማዋም በጩኸት ትናወጥ ጀመር። +14 ኤሊም ጩኸቱን ሲሰማ “ይህ ሁሉ ጩኸት ምንድን ነው?” በማለት ጠየቀ። ሰውየውም በፍጥነት ወደ እሱ ሄዶ ወሬውን ነገረው። +15 (በዚህ ወቅት ኤሊ ዕድሜው 98 ዓመት ነበር፤ ኤሊ ማየት ተስኖት የነበረ ቢሆንም ዓይኖቹ ፊት ለፊት ትኩር ብለው ይመለከቱ ነበር።)+ +16 ከዚያም ሰውየው ኤሊን “ከጦር ግንባሩ የመጣሁት ሰው እኔ ነኝ! ከጦር ግንባሩ ሸሽቼ የመጣሁትም ዛሬ ነው” አለው። በዚህ ጊዜ ኤሊ “ልጄ፣ ለመሆኑ የተከሰተው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። +17 ወሬውን ያመጣውም ሰው እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያን ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሽተዋል፤ ሕዝቡም ከፍተኛ ሽንፈት ደርሶበታል፤+ ሁለቱ ልጆችህ ሆፍኒ እና ፊንሃስም ሞተዋል፤+ የእውነተኛው አምላክ ታቦትም ተማርኳል።”+ +18 ሰውየው ስለ እውነተኛው አምላክ ታቦት በተናገረበት ቅጽበት ኤሊ በሩ አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ወደኋላው ወደቀ፤ በዕድሜ የገፋ ከመሆኑም ሌላ ሰውነቱ ከባድ ስለነበር አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እሱም ለ40 ዓመት በእስራኤል ላይ ፈራጅ ሆኖ አገልግሏል። +19 የኤሊ ምራት የፊንሃስ ሚስት ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር። እሷም የእውነተኛው አምላክ ታቦት እንደተማረከ እንዲሁም አማቷና ባሏ እንደሞቱ ስትሰማ ሆዷን ይዛ ጎንበስ አለች፤ ድንገትም ምጥ ያዛትና ወለደች። +20 እሷም ልትሞት በምታጣጥርበት ጊዜ አጠገቧ ቆመው የነበሩት ሴቶች “አይዞሽ፣ ወንድ ልጅ ወልደሻል” አሏት። እሷ ግን መልስ አልሰጠችም፤ ልብም አላለችውም። +21 ሆኖም የእውነተኛው አምላክ ታቦት በመማረኩ እንዲሁም በአማቷና በባሏ ላይ በደረሰው ነገር+ የተነሳ “ክብር ከእስራኤል በግዞት ተወሰደ”+ ስትል ለልጁ ኢካቦድ*+ የሚል ስም አወጣችለት። +22 “የእውነተኛው አምላክ ታቦት ስለተማረከ ክብር ከእስራኤል በግዞት ተወሰደ”+ አለች። +16 ከጊዜ በኋላ ይሖዋ ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ሳኦል በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን አልፈለግኩም፤+ ታዲያ አንተ ለእሱ የምታዝነው እስከ መቼ ነው?+ በል ቀንድህን ዘይት ሙላና+ ሂድ። የቤተልሔም ሰው ወደሆነው ወደ እሴይ+ እልክሃለሁ፤ ምክንያቱም ከወንዶች ልጆቹ መካከል ንጉሥ የሚሆንልኝ ሰው መርጫለሁ። +2 ሳሙኤል ግን “እንዴት መሄድ እችላለሁ? ሳኦል ይህን ከሰማ ይገድለኛል”+ አለ። ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድ፤ ከዚያም ‘የመጣሁት ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ ነው’ በል። +3 እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ ጥራው፤ እኔም ምን ማድረግ እንዳለብህ አሳውቅሃለሁ። አንተም እኔ የምመርጥልህን ሰው ትቀባልኛለህ።”+ +4 ሳሙኤልም ይሖዋ የነገረውን አደረገ። ቤተልሔም+ እንደደረሰም የከተማዋ ሽማግሌዎች ባገኙት ጊዜ እየተንቀጠቀጡ “የመጣኸው በሰላም ነው?” አሉት። +5 እሱም “አዎ በሰላም ነው። የመጣሁት ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ ነው። ራሳችሁን ቀድሱ፤ ወደ መሥዋዕቱም አብራችሁኝ ሂዱ” አላቸው። ከዚያም እሴይንና ልጆቹን ቀደሳቸው፤ ወደ መሥዋዕቱ እንዲመጡም ጠራቸው። +6 እነሱም እዚያ በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ኤልያብን+ ሲያየው “መቼም ይሖዋ የሚቀባው ሰው ይህ መሆን አለበት” አለ። +7 ሆኖም ይሖዋ ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “እኔ ስላልተቀበልኩት መልኩንና የቁመቱን ርዝማኔ አትይ።+ አምላክ የሚያየው ሰው በሚያይበት መንገድ አይደለም፤ ምክንያቱም ሰው የሚያየው ውጫዊ ገጽታን ነው፤ ይሖዋ ግን የሚያየው ልብን ነው።”+ +8 ከዚያም እሴይ አቢናዳብን+ ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገ፤ እሱ ግን “ይሄኛውንም ይሖዋ አልመረጠውም” አለ። +9 ቀጥሎም እሴይ ሻማህ+ እንዲቀርብ አደረገ፤ እሱ ግን “ይሄኛውንም ይሖዋ አልመረጠውም” አለ። +10 በመሆኑም እሴይ ሰባቱም ወንዶች ልጆቹ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን እሴይን “ይሖዋ ከእነዚህ መካከል ማናቸውንም አልመረጠም” አለው። +11 በመጨረሻም ሳሙኤል እሴይን “ወንዶች ልጆችህ እነዚሁ ብቻ ናቸው?” አለው። እሱም “ታናሽየው+ ገና ይቀራል፤ በጎች እየጠበቀ ነው” አለ።+ ከዚያም ሳሙኤል እሴይን “በል ልከህ አስመጣው፤ ምክንያቱም እሱ ሳይመጣ ምግብ ለመብላት መቀመጥ አንችልም” አለው። +12 በመሆኑም ልኮ አስመጣው። እሱም የቀይ ዳማ፣ ዓይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበር።+ ከዚያም ይሖዋ “ተነስ፣ ቀባው፤ የመረጥኩት እሱን ነው!” አለው።+ +13 ስለዚህ ሳሙኤል የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያም ቀን አንስቶ የይሖዋ መንፈስ ለዳዊት ኃይል ሰጠው።+ በኋላም ሳሙኤል ተነስቶ ወደ ራማ+ ሄደ። +14 በዚህ ጊዜ የይሖዋ መንፈስ ከሳኦል ራቀ፤+ ከይሖዋ የመጣ መጥፎ መንፈስም ይረብሸው ጀመር።+ +15 የሳኦል አገልጋዮችም እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ ከአምላክ የመጣ መጥፎ መንፈስ እየረበሸህ ነው። +16 ጌታችን በፊቱ የቆሙትን አገልጋዮቹን በገና የሚደረድር ጥሩ ችሎታ ያለው ሰው እንዲፈልጉ ይዘዝ።+ ከአምላክ የመጣው መጥፎ መንፈስ በአንተ ላይ ሲወርድ ይህ ሰው በገና ይጫወትልሃል፤ አንተም ደህና ትሆናለህ።” +17 ስለዚህ ሳኦል አገልጋዮቹን “እንግዲያው እባካችሁ ጥሩ አድርጎ በገና የሚደረድር ሰው ፈልጋችሁ አምጡልኝ” አላቸው። +18 ከአገልጋዮቹም አንዱ እንዲህ አለ፦ “የቤተልሔሙ ሰው የእሴይ ልጅ በገና የመደርደር ጥሩ ችሎታ እንዳለው አይቻለሁ፤ እሱም ደፋርና ኃያል ተዋጊ ነው።+ ደግሞም አንደበተ ርቱዕና መልከ መልካም+ ሲሆን ይሖዋም ከእሱ ጋር ነው።”+ +19 ከዚያም ሳኦል ወደ እሴይ መልእክተኞችን ልኮ “በጎች የሚጠብቀውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ” አለው።+ +20 በመሆኑም እሴይ ዳቦና በወይን ጠጅ የተሞላ አቁማዳ በአህያ አስጭኖ እንዲሁም የፍየል ግልገል አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው። +21 በዚህ መንገድ ዳዊት ወደ ሳኦል መጣ፤ እሱንም ያገለግለው ጀመር።+ ሳኦልም እጅግ እየወደደው ሄደ፤ ጋሻ ጃግሬውም ሆነ። +22 ሳኦልም “ዳዊት በፊቴ ሞገስ ስላገኘ እባክህ እዚሁ እኔ ጋ ሆኖ እንዲያገለግለኝ ፍቀድልኝ” በማለት ወደ እሴይ መልእክት ላከ። +23 ከአምላክ የሚመጣ መጥፎ መንፈስ በሳኦል ላይ በሚወርድበት ጊዜ ሁሉ ዳዊት በገናውን አንስቶ ይደረድር ነበር፤ ሳኦልም ቀለል ይለውና ደህና ይሆን ነበር፤ መጥፎው መንፈስም ከእሱ ይርቅ ነበር።+ +6 የይሖዋ ታቦት+ በፍልስጤማውያን ምድር ሰባት ወር ቆየ። +2 ፍልስጤማውያኑም ካህናትንና ሟርተኞችን+ ጠርተው “የይሖዋን ታቦት ምን ብናደርገው ይሻላል? ወደ ስፍራው እንዴት እንደምንመልሰው አሳውቁን” አሏቸው። +3 እነሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ያለመባ እንዳትመልሱት። ከበደል መባ ጋር አድርጋችሁ ወደ እሱ መመለስ ይኖርባችኋል።+ የምትፈወሱት እንዲህ ካደረጋችሁ ብቻ ነው፤ ደግሞም እጁ ከእናንተ ላይ ያልተመለሰው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ።” +4 ስለዚህ “ወደ እሱ መላክ የሚኖርብን የበደል መባ ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁ። እነሱም እንዲህ አሏቸው፦ “እናንተንም ሆነ ገዢዎቻችሁን ያሠቃየው መቅሰፍት ተመሳሳይ ስለሆነ በፍልስጤም ገዢዎች+ ቁጥር ልክ አምስት የወርቅ ኪንታሮቶችንና* አምስት የወርቅ አይጦችን ላኩ። +5 ምድሪቱን እያጠፉ ባሉት ኪንታሮቶቻችሁና አይጦቻችሁ+ አምሳያ ምስሎችን ሥሩ፤ የእስራኤልንም አምላክ አክብሩ። ምናልባትም በእናንተ፣ በአምላካችሁና በምድራችሁ ላይ የከበደውን እጁን ያቀልላችሁ ይሆናል።+ +6 ግብፅና ፈርዖን ልባቸውን እንዳደነደኑት እናንተም ለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ?+ እሱ ክፉኛ በቀጣቸው+ ጊዜ እስራኤላውያንን ለቀቋቸው፤ እነሱም ሄዱ።+ +7 ስለዚህ አሁን አዲስ ሠረገላ እንዲሁም እንቦሶች ያሏቸውና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት ላሞች አዘጋጁ። ከዚያም ሠረገላውን ጥመዱባቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ከእነሱ ነጥላችሁ ወደ ቤት መልሷቸው። +8 የይሖዋን ታቦት ወስዳችሁ ሠረገላው ላይ አስቀምጡት፤ እንዲሁም ለእሱ የበደል መባ አድርጋችሁ የምትልኳቸውን የወርቅ ምስሎች በሣጥን አድርጋችሁ ታቦቱ አጠገብ አስቀምጡ።+ ከዚያም መንገዱን ይዞ እንዲሄድ ላኩት፤ +9 ልብ ብላችሁም ተመልከቱ፦ ታቦቱ ወደ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ+ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ከሄደ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እሱ ነው ማለት ነው። ካልሆነ ግን የእሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን፤ ይህ የደረሰብንም እንዲያው በአጋጣሚ ነው።” +10 ሰዎቹም እንዲሁ አደረጉ። እንቦሶች ያሏቸውን ሁለት ላሞች ወስደው ሠረገላውን ጠመዱባቸው፤ እንቦሶቹንም በረት ውስጥ ዘጉባቸው። +11 ከዚያም የይሖዋን ታቦት እንዲሁም የወርቅ አይጦቹንና የኪንታሮቶቻቸውን ምስል የ���ዘውን ሣጥን ሠረገላው ላይ ጫኑ። +12 ላሞቹም ወደ ቤትሼሜሽ በሚወስደው መንገድ ቀጥ ብለው ሄዱ።+ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሳይሉ አንዱን ጎዳና ተከትለው ‘እምቧ’ እያሉ ተጓዙ፤ በዚህ ጊዜ ሁሉ የፍልስጤም ገዢዎች እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ድረስ ከኋላ ከኋላቸው ይከተሏቸው ነበር። +13 የቤትሼሜሽ ሰዎች በሸለቋማው ሜዳ* ላይ ስንዴ እያጨዱ ነበር። እነሱም ቀና ብለው ታቦቱን ተመለከቱ፤ እሱን በማየታቸውም በጣም ተደሰቱ። +14 ሠረገላውም ወደ ቤትሼሜሻዊው ኢያሱ ማሳ ገብቶ እዚያ በሚገኝ አንድ ትልቅ ዓለት አጠገብ ቆመ። ሰዎቹም የሠረገላውን እንጨት ፈልጠው ላሞቹን+ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርገው አቀረቡ። +15 ሌዋውያኑም+ የይሖዋን ታቦትና አብሮት የነበረውን የወርቅ ምስሎቹን የያዘውን ሣጥን አውርደው በትልቁ ዓለት ላይ አስቀመጧቸው። በዚያም ቀን የቤትሼሜሽ+ ሰዎች ለይሖዋ የሚቃጠሉ መባዎችን አቀረቡ፤ መሥዋዕቶችንም ሠዉ። +16 አምስቱ የፍልስጤም ገዢዎችም ይህን ሲያዩ በዚያው ቀን ወደ ኤቅሮን ተመለሱ። +17 ፍልስጤማውያን ለይሖዋ የበደል መባ አድርገው የላኳቸው የወርቅ ኪንታሮቶች እነዚህ ናቸው፦+ ለአሽዶድ+ አንድ፣ ለጋዛ አንድ፣ ለአስቀሎን አንድ፣ ለጌት+ አንድ እንዲሁም ለኤቅሮን+ አንድ። +18 የወርቅ አይጦቹ ቁጥር አምስቱ የፍልስጤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው ከተሞች ሁሉ ይኸውም በተመሸጉት ከተሞችና በሥራቸው በሚገኙ አውላላ ሜዳ ላይ ባሉ መንደሮች ቁጥር ልክ ነበር። የይሖዋን ታቦት ያስቀመጡበት በቤትሼሜሻዊው ኢያሱ ማሳ ውስጥ የሚገኘው ትልቅ ዓለት እስከ ዛሬ ድረስ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል። +"19 ይሁንና አምላክ የይሖዋን ታቦት ስለተመለከቱ የቤትሼሜሽን ሰዎች መታቸው። ከሕዝቡ መካከል 50,070 ሰዎችን* መታ፤ ሰዎቹም ይሖዋ ብዙ ሕዝብ ስለፈጀባቸው ያለቅሱ ጀመር።+" +20 በመሆኑም የቤትሼሜሽ ሰዎች “ታዲያ በዚህ ቅዱስ አምላክ+ በይሖዋ ፊት ማን ሊቆም ይችላል? ምናለ ከእኛ ላይ ዞር ቢልና ወደ ሌሎች ቢሄድ?” አሉ።+ +21 ስለዚህ ወደ ቂርያትየአሪም+ ነዋሪዎች መልእክተኞችን ልከው “ፍልስጤማውያን የይሖዋን ታቦት መልሰዋል። ወደዚህ ውረዱና ይዛችሁት ውጡ” አሏቸው።+ +25 ከጊዜ በኋላም ሳሙኤል+ ሞተ፤ እስራኤላውያንም በሙሉ ሊያለቅሱለትና በራማ+ በሚገኘው ቤቱ ሊቀብሩት ተሰበሰቡ። ከዚያም ዳዊት ተነስቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ። +"2 በማኦን+ የሚኖር እጅግ ባለጸጋ የሆነ አንድ ሰው ነበር። ይህ ሰው የሚሠራው በቀርሜሎስ*+ ሲሆን 3,000 በጎችና 1,000 ፍየሎች ነበሩት፤ በዚያን ወቅት በቀርሜሎስ በጎቹን እየሸለተ ነበር።" +3 የሰውየው ስም ናባል፣+ የሚስቱ ስም ደግሞ አቢጋኤል+ ነበር። እሷም በጣም አስተዋይና ውብ ሴት ነበረች፤ ከካሌብ+ ወገን የሆነው ባሏ ግን ኃይለኛና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበር።+ +4 ዳዊት በምድረ በዳ ሳለ ናባል በጎቹን እየሸለተ መሆኑን ሰማ። +5 ስለዚህ ዳዊት አሥር ወጣቶችን ወደ እሱ ላከ፤ ዳዊትም ወጣቶቹን እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ቀርሜሎስ ወጥታችሁ ናባልን ስታገኙት በስሜ ስለ ደህንነቱ ጠይቁት። +6 ከዚያም ናባልን እንዲህ በሉት፦ ‘ረጅም ዕድሜና ጤና* እመኝልሃለሁ፤ ለመላ ቤተሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ሰላም ይሁን። +7 በጎችህን እየሸለትክ እንዳለህ ሰምቻለሁ። እረኞችህም ከእኛ ጋር በነበሩበት ጊዜ ምንም ዓይነት ጉዳት አላደረስንባቸውም፤+ በቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ምንም ነገር አልጠፋባቸውም። +8 ወጣቶችህን ጠይቅ፤ ይነግሩሃል። እንግዲህ የመጣነው በደስታ* ቀን ስለሆነ ወጣቶቼ በፊትህ ሞገስ ያግኙ። እባክህ ለአገልጋዮችህና ለልጅህ ለዳዊት የቻልከውን ያህል ስጥ።’”+ +9 በመሆኑም ዳዊት የላካቸው ወጣቶች ሄደው ይህን ሁሉ በዳዊት ስም ለናባ��� ነገሩት። ተናግረው እንዳበቁም +10 ናባል የዳዊትን አገልጋዮች እንዲህ አላቸው፦ “ለመሆኑ ዳዊት ማን ነው? ደግሞስ የእሴይ ልጅ ማን ነው? በአሁኑ ጊዜ እንደሆነ ከጌቶቻቸው የሚኮበልሉ+ አገልጋዮች ብዙ ናቸው። +11 ታዲያ ዳቦዬን፣ ውኃዬንና ለሚሸልቱልኝ ሰዎች ያረድኩትን ሥጋ ከየት እንደመጡ እንኳ ለማላውቃቸው ሰዎች መስጠት ይኖርብኛል?” +12 ዳዊት የላካቸው ወጣቶችም ወደመጡበት ተመልሰው በመሄድ የተባሉትን ሁሉ ነገሩት። +13 ዳዊትም ወዲያውኑ አብረውት ላሉት ሰዎች “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ!”+ አላቸው። በመሆኑም ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም ሰይፉን ታጠቀ፤ ወደ 400 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ከዳዊት ጋር ሲወጡ 200ዎቹ ግን ጓዙን ለመጠበቅ እዚያው ቀሩ። +14 ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአገልጋዮቹ አንዱ ለናባል ሚስት ለአቢጋኤል እንዲህ አላት፦ “እነሆ፣ ዳዊት ለጌታችን መልካም ምኞቱን ለመግለጽ መልእክተኞችን ከምድረ በዳ ልኮ ነበር፤ እሱ ግን የስድብ ናዳ አወረደባቸው።+ +15 ሰዎቹ ለእኛ እጅግ ጥሩ ነበሩ። ምንም ዓይነት ጉዳት አድርሰውብን አያውቁም፤ በመስክ ከእነሱ ጋር አብረን በነበርንባቸው ጊዜያት ሁሉ አንድም ነገር ጠፍቶብን አያውቅም።+ +16 መንጋውን እየጠበቅን ከእነሱ ጋር በቆየንባቸው ጊዜያት ሁሉ ሌሊትም ሆነ ቀን በዙሪያችን እንደ መከላከያ ቅጥር ሆነውልን ነበር። +17 እንግዲህ አሁን በጌታችንና በቤቱ ሁሉ ላይ ጥፋት+ መምጣቱ ስለማይቀር ምን ማድረግ እንዳለብሽ ወስኚ፤ እሱ እንደሆነ የማይረባ*+ ሰው ስለሆነ ማንም ሊያናግረው አይችልም።” +18 ስለሆነም አቢጋኤል+ ወዲያውኑ 200 ዳቦ፣ ሁለት እንስራ የወይን ጠጅ፣ ታርደው የተሰናዱ አምስት በጎች፣ አምስት የሲህ መስፈሪያ* ቆሎ፣ 100 የዘቢብ ቂጣ እንዲሁም 200 የበለስ ጥፍጥፍ ወስዳ ሁሉንም በአህዮች ላይ ጫነች።+ +19 ከዚያም አገልጋዮቿን “ቀድማችሁኝ ሂዱ፤ እኔም እከተላችኋለሁ” አለቻቸው። ለባሏ ለናባል ግን ምንም አልነገረችውም። +20 አቢጋኤልም አህያ ላይ እንደተቀመጠች በተራራው ተከልላ እየወረደች ሳለ ዳዊትና ሰዎቹም ወደ እሷ እየወረዱ ነበር፤ እሷም አገኘቻቸው። +21 ዳዊትም እንዲህ ብሎ ነበር፦ “በምድረ በዳ የዚህን ሰው ንብረት የጠበቅኩለት ለካስ እንዲያው በከንቱ ነበር። ደግሞም ከንብረቱ መካከል አንድም ነገር አልጠፋበትም፤+ እሱ ግን ደግ በሠራሁለት ክፉ መለሰልኝ።+ +22 የእሱ ከሆኑት ወንዶች* መካከል እስከ ነገ ጠዋት ድረስ አንድ ሰው እንኳ ባስቀር አምላክ በዳዊት ጠላቶች ላይ* ይህን ያድርግ፤ ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣ።” +23 አቢጋኤልም ዳዊትን ባየችው ጊዜ፣ ከተቀመጠችበት አህያ ላይ በፍጥነት በመውረድ በዳዊት ፊት በግንባሯ ተደፍታ ሰገደች። +24 ከዚያም እግሩ ላይ ወድቃ እንዲህ አለችው፦ “ጌታዬ ሆይ፣ ጥፋቱ በእኔ ላይ ይሁን፤ እባክህ አገልጋይህ እንድታናግርህ ፍቀድላት፤ የአገልጋይህንም ቃል ስማ። +25 እባክህ ጌታዬ፣ ናባል የተባለውን ይህን የማይረባ+ ሰው ከቁብ አትቁጠረው፤ እሱ ልክ እንደ ስሙ ነውና። ስሙ ናባል* ነው፤ ደግሞም ማስተዋል የጎደለው ሰው ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ወጣቶች አላየሁም። +26 እናም አሁን ጌታዬ፣ ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ* እምላለሁ፣ በደም ዕዳ ተጠያቂ+ ከመሆንና በራስህ እጅ ከመበቀል* የጠበቀህ+ ይሖዋ ነው። አሁንም ጠላቶችህና ጌታዬን ሊጎዱ የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ። +27 ስለዚህ አገልጋይህ ለጌታዬ ያመጣችው ይህ ስጦታ*+ ጌታዬን ለሚከተሉት ወጣቶች+ ይሰጥ። +28 ጌታዬ እየተዋጋ ያለው የይሖዋን ጦርነት+ ስለሆነ ይሖዋ የጌታዬን ቤት ለዘለቄታው ያጸናለታል፤+ ስለሆነም እባክህ የአገልጋይህን መተላለፍ ይቅር በል፤ በሕይ��ት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህ።+ +29 ማንም ሰው አንተን ለማሳደድ ቢነሳና ሕይወትህን* ለማጥፋት ቢፈልግ የጌታዬ ሕይወት* በአምላክህ በይሖዋ ዘንድ በደንብ በታሰረ የሕይወት ከረጢት ውስጥ ትቀመጣለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት* ግን ከወንጭፍ እንደሚወረወር ድንጋይ ይወነጭፈዋል። +30 ይሖዋ ቃል የገባለትን መልካም ነገር ሁሉ ለጌታዬ በሚፈጽምለትና በእስራኤል ላይ መሪ አድርጎ በሚሾመው+ ጊዜ +31 ጌታዬ ያለምክንያት ደም በማፍሰሱና እጁን ለበቀል በማንሳቱ* ልቡን የሚቆጨው ወይም የሚጸጽተው* ነገር አይኖርም።+ ይሖዋ ለጌታዬ መልካም ነገር በሚያደርግለት ጊዜ አገልጋይህን አስባት።” +32 በዚህ ጊዜ ዳዊት አቢጋኤልን እንዲህ አላት፦ “ዛሬ እኔን እንድታገኚኝ የላከሽ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ! +33 ማስተዋልሽም የተባረከ ይሁን! በዚህ ዕለት በራሴ ላይ የደም ዕዳ እንዳላመጣና+ በገዛ እጄ እንዳልበቀል* ስለጠበቅሽኝ አንቺም የተባረክሽ ሁኚ። +34 በአንቺ ላይ ጉዳት ከማድረስ በጠበቀኝ+ ሕያው በሆነው በእስራኤል አምላክ በይሖዋ እምላለሁ፣ እኔን ለማግኘት ፈጥነሽ ባትመጪ ኖሮ+ እስከ ነገ ጠዋት ድረስ የናባል የሆነ አንድም ወንድ* ባልተረፈ ነበር።”+ +35 ከዚያም ዳዊት ያመጣችለትን ነገር ከእጇ ተቀብሎ “ወደ ቤትሽ በሰላም ሂጂ። ይኸው ቃልሽን ሰምቻለሁ፤ የጠየቅሽኝንም እፈጽምልሻለሁ” አላት። +36 በኋላም አቢጋኤል በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ታላቅ ግብዣ አዘጋጅቶ ወደነበረው ወደ ናባል ተመለሰች፤ ናባልም ልቡ በሐሴት ተሞልቶ በጣም ሰክሮ ነበር። እሷም እስኪነጋ ድረስ ምንም ነገር አልነገረችውም። +37 ጠዋት ላይ ናባል ስካሩ ሲበርድለት ሚስቱ የሆነውን ሁሉ ነገረችው። ልቡም እንደ ሞተ ሰው ልብ ሆነ፤ ሰውነቱም እንደ ድንጋይ በድን ሆነ። +38 ከአሥር ቀን ገደማ በኋላም ይሖዋ ናባልን ስለቀሰፈው ሞተ። +39 ዳዊት፣ ናባል መሞቱን ሲሰማ እንዲህ አለ፦ “ከናባል የደረሰብኝን ነቀፋ+ የተሟገተልኝና+ አገልጋዩን መጥፎ ድርጊት ከመፈጸም የጠበቀው+ ይሖዋ ይወደስ፤ ይሖዋ የናባልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰው!” ከዚያም ዳዊት አቢጋኤል ሚስት እንድትሆነው ጥያቄ ለማቅረብ መልእክት ላከ። +40 በመሆኑም የዳዊት አገልጋዮች በቀርሜሎስ ወዳለችው ወደ አቢጋኤል መጥተው “ዳዊት ሊያገባሽ ስለፈለገ ወደ አንቺ ልኮናል” አሏት። +41 እሷም ወዲያውኑ ተነሳች፤ በግንባሯም ተደፍታ በመስገድ “ባሪያህ እንደ አገልጋይ በመሆን የጌታዬን አገልጋዮች እግር ለማጠብ+ ዝግጁ ነች” አለች። +42 ከዚያም አቢጋኤል+ ፈጥና ተነሳች፤ አምስት ሴት አገልጋዮቿንም በማስከተል በአህያ ላይ ተቀምጣ ጉዞ ጀመረች፤ ከዳዊት መልእክተኞችም ጋር አብራ ሄደች፤ የዳዊትም ሚስት ሆነች። +43 በተጨማሪም ዳዊት ከኢይዝራኤል+ አኪኖዓምን+ አግብቶ ነበር፤ ሁለቱም ሴቶች ሚስቶቹ ሆኑ።+ +44 ሳኦል ግን የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን+ የጋሊም ሰው ለሆነው ለላይሽ ልጅ ለፓልጢ+ ድሯት ነበር። +10 ሳሙኤልም የዘይት ዕቃውን አንስቶ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው።+ ከዚያም ሳመውና እንዲህ አለው፦ “በርስቱ+ ላይ መሪ እንድትሆን ይሖዋ ቀብቶህ የለም?+ +2 ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ በቢንያም ግዛት ውስጥ በምትገኘው በጸልጻህ ባለው የራሔል መቃብር+ አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ፤ እነሱም እንዲህ ይሉሃል፦ ‘ስትፈልጋቸው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋል፤ አባትህ ግን ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ+ ስለ እናንተ እየተጨነቀ ነው። ደግሞም “የልጄን ነገር ምን ባደርግ +3 አንተም ከዚያ ተነስተህ ታቦር የሚገኘው ትልቅ ዛፍ አጠገብ እስክትደርስ ድረስ ጉዞህን ቀጥል፤ እዚያም ሦስት ሰዎች በቤቴል+ ወደሚገኘው ወደ እውነተኛው አምላክ ሲወጡ ታገኛለህ፤ እነሱም አንደኛው ሦስት የፍየል ግልገል፣ ሌላኛው ሦስት ዳቦ፣ ሌላኛው ደግሞ በእንስራ የወይን ጠጅ ይዘዋል። +4 እነዚህ ሰዎች ስለ ደህንነትህ ከጠየቁህ በኋላ ሁለት ዳቦ ይሰጡሃል፤ አንተም ዳቦዎቹን ተቀበላቸው። +5 ከዚህ በኋላ የፍልስጤማውያን የጦር ሰፈር ወዳለበት ወደ እውነተኛው አምላክ ኮረብታ ትመጣለህ። ወደ ከተማዋም በምትደርስበት ጊዜ ትንቢት እየተናገረ ከኮረብታው የሚወርድ አንድ የነቢያት ቡድን ታገኛለህ፤ ከፊት ከፊቱም ባለ አውታር መሣሪያ፣ አታሞ፣ ዋሽንትና በገና የሚጫወቱ ሰዎች ይሄዳሉ። +6 የይሖዋ መንፈስ ኃይል ይሰጥሃል፤+ አንተም ከእነሱ ጋር ትንቢት ትናገራለህ፤ ተለውጠህም እንደ ሌላ ሰው ትሆናለህ።+ +7 እነዚህ ምልክቶች ሲፈጸሙ ስታይ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ፤ ምክንያቱም እውነተኛው አምላክ ከአንተ ጋር ነው። +8 ከዚያም ከእኔ ቀድመህ ወደ ጊልጋል+ ውረድ፤ እኔም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን ለማቅረብ አንተ ወዳለህበት እወርዳለሁ። እኔ ወደ አንተ እስክመጣ ድረስ ሰባት ቀን መጠበቅ አለብህ። ከዚያም ምን ማድረግ እንዳለብህ አሳውቅሃለሁ።” +9 ሳኦልም ከሳሙኤል ተለይቶ ለመሄድ ፊቱን ሲያዞር አምላክ የሳኦል ልብ ወደ ሌላ ሰው ልብ እንዲለወጥ አደረገ፤ እነዚህም ሁሉ ምልክቶች በዚያው ቀን ተፈጸሙ። +10 በመሆኑም ከዚያ ተነስተው ወደ ኮረብታው ሄዱ፤ አንድ የነቢያት ቡድንም አገኘው። ወዲያውም የአምላክ መንፈስ ኃይል ሰጠው፤+ እሱም አብሯቸው ትንቢት መናገር ጀመረ።+ +11 ቀደም ሲል ያውቁት የነበሩት ሁሉ ከነቢያቱ ጋር ሆኖ ትንቢት ሲናገር ሲያዩት እርስ በርሳቸው “የቂስ ልጅ ምን ሆኗል? ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ?” ተባባሉ። +12 ከዚያም የአካባቢው ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው “ለመሆኑ የእነሱስ አባት ማን ነው?” አለ። “ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ?” የሚል ምሳሌያዊ አባባል የኖረው በዚህ የተነሳ ነው።+ +13 እሱም ትንቢት ተናግሮ ሲጨርስ ወደ ኮረብታው መጣ። +14 በኋላም የሳኦል አባት ወንድም ሳኦልንና አገልጋዩን “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ሳኦልም “አህዮቹን ፍለጋ ሄደን ነበር፤+ ሆኖም በዚያ ልናገኛቸው ስላልቻልን ወደ ሳሙኤል ሄድን” አለው። +15 የሳኦልም አጎት “እስቲ ንገረኝ፣ ሳሙኤል ምን አላችሁ?” አለው። +16 ሳኦልም መልሶ አጎቱን “አህዮቹ መገኘታቸውን በትክክል ነገረን” አለው። ይሁን እንጂ ሳሙኤል ስለ ንግሥና የነገረውን ነገር አልነገረውም። +17 ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን በምጽጳ+ በይሖዋ ፊት እንዲሰበሰብ ከጠራ በኋላ +18 እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤልን ከግብፅ ያወጣሁት እንዲሁም ከግብፅ እጅና+ ይጨቁኗችሁ ከነበሩት መንግሥታት ሁሉ እጅ የታደግኳችሁ እኔ ነኝ። +19 ዛሬ ግን እናንተ ከመከራችሁና ከጭንቀታችሁ ሁሉ ያዳናችሁን አምላካችሁን አንቀበልም በማለት+ “አይሆንም፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን” አላችሁ። ስለዚህ አሁን በየነገዳችሁና በየሺህ ምድባችሁ* ሆናችሁ በይሖዋ ፊት ቁሙ።’” +20 ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤል ነገዶች በሙሉ እንዲቀርቡ አደረገ፤+ ከእነሱም መካከል የቢንያም ነገድ ተመረጠ።+ +21 ከዚያም የቢንያም ነገድ በየቤተሰቡ ሆኖ እንዲቀርብ አደረገ፤ የማጥራውያን ቤተሰብም ተመረጠ። በመጨረሻም የቂስ ልጅ ሳኦል ተመረጠ።+ ሆኖም ፈልገው ሊያገኙት አልቻሉም። +22 ስለዚህ “ለመሆኑ ሰውየው እዚህ መጥቷል?” በማለት ይሖዋን ጠየቁ።+ ይሖዋም “ያውላችሁ፣ ጓዙ መካከል ተደብቋል” አላቸው። +23 በመሆኑም ሮጠው ከዚያ አመጡት። እሱም በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜ ከትከሻው በላይ ዘለ��� ብሎ በቁመት ከሌሎቹ ሰዎች ሁሉ በልጦ ይታይ ነበር።+ +24 ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ “ይሖዋ የመረጠውን ሰው አያችሁት?+ ከሕዝቡ ሁሉ መካከል እንደ እሱ ያለ የለም” አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” በማለት መጮኽ ጀመረ። +25 ሳሙኤልም ለነገሥታት ምን ሊደረግላቸው እንደሚገባ ለሕዝቡ ተናገረ፤+ እንዲሁም በመጽሐፍ ጽፎ በይሖዋ ፊት አስቀመጠው። ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን ሁሉ ወደየቤቱ አሰናበተ። +26 ሳኦልም ይሖዋ ልባቸውን ባነሳሳው ተዋጊዎች ታጅቦ በጊብዓ ወዳለው ቤቱ ሄደ። +27 አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች ግን “ይህ ሰው እንዴት ሊያድነን ይችላል?” አሉ።+ በመሆኑም ናቁት፤ ምንም ዓይነት ስጦታም አላመጡለትም።+ እሱ ግን ዝም አለ።* +14 አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን+ ጋሻ ጃግሬውን “ና፣ በዚያ በኩል ወዳለው የፍልስጤማውያን የጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ይህን ግን ለአባቱ አልነገረውም። +2 ሳኦልም በጊብዓ+ ዳርቻ በሚግሮን በሚገኘው የሮማን ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር፤ ከእሱም ጋር 600 ሰዎች ነበሩ።+ +3 (በሴሎ+ የይሖዋ ካህን የሆነው የኤሊ+ ልጅ፣ የፊንሃስ+ ልጅ፣ የኢካቦድ+ ወንድም የአኪጡብ+ ልጅ አኪያህ ኤፉድ ለብሶ ነበር።)+ ሕዝቡም ዮናታን መሄዱን አላወቀም። +4 ዮናታን ወደ ፍልስጤማውያን የጦር ሰፈር ለመሻገር ባሰበባቸው መተላለፊያዎች መካከል በአንደኛው በኩል እንደ ጥርስ የሾለ ዓለት፣ በሌላኛውም በኩል እንደ ጥርስ የሾለ ዓለት ነበር፤ የአንደኛው ስም ቦጼጽ ሲሆን የሌላኛው ስም ደግሞ ሴኔ ነበር። +5 አንደኛው ዓለት በሚክማሽ ትይዩ በስተ ሰሜን እንደ ዓምድ ቆሞ ነበር፤ ሌላኛው ደግሞ በጊብዓ+ ትይዩ በስተ ደቡብ ቆሞ ነበር። +6 በመሆኑም ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን “ና፣ ወደ እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች የጦር ሰፈር እንሻገር።+ ይሖዋ በብዙም ሆነ በጥቂት ሰዎች ተጠቅሞ ከማዳን የሚያግደው ነገር ስለሌለ ምናልባት ይሖዋ ስለ እኛ ሲል እርምጃ ይወስድ ይሆናል” አለው።+ +7 በዚህ ጊዜ ጋሻ ጃግሬው “ልብህ ያነሳሳህን ማንኛውንም ነገር አድርግ። ወደፈለግክበት ሂድ፤ እኔም ልብህ ወዳነሳሳህ ወደየትኛውም ቦታ ተከትዬህ እሄዳለሁ” አለው። +8 ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው፦ “እንግዲያውስ ወደ እነዚያ ሰዎች እንሻገርና እንታያቸው። +9 እነሱም ‘ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ ባላችሁበት ጠብቁን’ ካሉን ባለንበት ሆነን እንጠብቃቸዋለን፤ ወደ እነሱም አንወጣም። +10 ይሁንና ‘ውጡና ግጠሙን!’ ካሉን ወደዚያ እንወጣለን፤ ምክንያቱም ይሖዋ እነሱን በእጃችን አሳልፎ ይሰጠናል። እንግዲህ ይህ ምልክት ይሆነናል።”+ +11 ከዚያም ሁለቱ ወጥተው ለፍልስጤማውያን የጦር ሰፈር ታዩ። ፍልስጤማውያኑም “አያችሁ፣ ዕብራውያኑ ከተደበቁባቸው ጉድጓዶች እየወጡ ነው” አሉ።+ +12 በመሆኑም በጦር ሰፈሩ የነበሩት ሰዎች ዮናታንንና ጋሻ ጃግሬውን “ኑ፣ ወደ እኛ ውጡ፤ እናሳያችኋለን!” አሏቸው።+ ዮናታንም ወዲያውኑ ጋሻ ጃግሬውን “ይሖዋ እስራኤላውያን እጅ ላይ ስለሚጥላቸው ተከተለኝ” አለው።+ +13 ዮናታንም በእጁና በእግሩ እየቧጠጠ ወጣ፤ ጋሻ ጃግሬውም ይከተለው ነበር፤ ዮናታንም በፍልስጤማውያን ላይ ጥቃት ሰነዘረ፤ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው እየተከተለ ገደላቸው። +14 ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው መጀመሪያ ላይ በሰነዘሩት ጥቃት አንድ ጥማድ በሚያውል የእርሻ መሬት ላይ ግማሽ ትልም በሚያህል ቦታ 20 ሰው ገደሉ። +15 ከዚያም በእርሻው ውስጥ በሰፈረው ሠራዊትና በጦር ሰፈሩ ውስጥ በነበረው ሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ተነዛ፤ ሌላው ቀርቶ ወራሪ ቡድኖቹ+ እንኳ ተሸበሩ። ምድሪቱም መንቀጥቀጥ ጀመረች፤ ከአምላክ የመጣ ሽብርም ወረደባቸው። +16 በቢንያም ግዛት በምትገኘው በጊብዓ+ የነበሩት የሳኦል ጠባቂዎችም በየአቅጣጫው ሁከት መሰራጨቱን አዩ።+ +17 ሳኦልም አብረውት የነበሩትን ሰዎች “እስቲ ሕዝቡን ቁጠሩና ትቶን የሄደው ማን እንደሆነ እወቁ” አላቸው። እነሱም ሲቆጥሩ ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው እዚያ እንዳልነበሩ ተረዱ። +18 ሳኦልም አኪያህን+ “የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ወደዚህ አምጣ!” አለው። (በዚያ ጊዜ* የእውነተኛው አምላክ ታቦት በእስራኤላውያን ዘንድ ነበር።) +19 ሳኦል ካህኑን እያነጋገረ ሳለ በፍልስጤማውያን ሰፈር የነበረው ትርምስ ይበልጥ እየጨመረ ሄደ። ከዚያም ሳኦል ካህኑን “እያደረግክ ያለኸውን ነገር ተው”* አለው። +20 በመሆኑም ሳኦልና አብረውት የነበሩት ሰዎች በሙሉ ተሰባስበው ውጊያው ወደሚደረግበት ቦታ ሄዱ፤ እዚያ ሲደርሱም ፍልስጤማውያኑ እርስ በርሳቸው በሰይፍ ሲጨፋጨፉ አገኟቸው፤ ከፍተኛ ትርምስ ተፈጥሮ ነበር። +21 ቀደም ሲል ከፍልስጤማውያን ጋር ወግነው የነበሩትና አብረዋቸው ወደ ሰፈሩ የመጡት ዕብራውያንም በሳኦልና በዮናታን ሥር ከነበሩት እስራኤላውያን ጋር ተቀላቀሉ። +22 በተጨማሪም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ተደብቀው+ የነበሩት የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ፍልስጤማውያን እየሸሹ መሆኑን ሰሙ፤ እነሱም ከሌሎቹ ጋር በመተባበር ፍልስጤማውያንን ማሳደዱን ተያያዙት። +23 በዚህ መንገድ ይሖዋ በዚያ ቀን እስራኤልን አዳነ፤+ ውጊያውም እስከ ቤትአዌን+ ድረስ ዘለቀ። +24 ሆኖም ሳኦል “ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት እስከ ማታ ድረስ እህል የሚቀምስ ሰው የተረገመ ይሁን!” በማለት ሕዝቡን አስምሎ ስለነበር በዚያ ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ። በመሆኑም ከሕዝቡ መካከል አንድም ሰው እህል አልቀመሰም።+ +25 ሕዝቡም* ሁሉ ወደ ጫካው ገባ፤ መሬቱም ላይ ማር ነበር። +26 ሕዝቡም ወደ ጫካው ሲገባ ማሩ ሲንጠባጠብ አየ፤ ሆኖም ሁሉም መሐላውን ስለፈሩ እጁን ወደ አፉ ያነሳ አንድም ሰው አልነበረም። +27 ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን ሲያስምል አልሰማም ነበር፤+ በመሆኑም በእጁ የነበረውን በትር ዘርግቶ ጫፉን የማር እንጀራው ውስጥ አጠቀሰ። ከዚያም እጁን ወደ አፉ ሲመልስ ዓይኑ በራ። +28 በዚህ ጊዜ ከሕዝቡ መካከል አንዱ “አባትህ እኮ ‘በዛሬው ዕለት እህል የሚቀምስ ሰው የተረገመ ይሁን!’+ በማለት ሕዝቡን በጥብቅ አስምሏል። ሕዝቡ በጣም የተዳከመው ለዚህ ነው” አለው። +29 ዮናታን ግን እንዲህ አለ፦ “አባቴ በምድሪቱ ላይ ከባድ ችግር አምጥቷል። እኔ ይህችን ማር በመቅመሴ ዓይኖቼ እንዴት እንደበሩ እስቲ ተመልከቱ። +30 ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው ከወሰዱት ምርኮ ዛሬ በነፃነት በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ የተሻለ ይሆን ነበር!+ የተገደሉት ፍልስጤማውያንም ቁጥር ከዚህ እጅግ በበለጠ ነበር።” +31 በዚያም ዕለት ፍልስጤማውያንን ከሚክማሽ አንስተው እስከ አይሎን+ ድረስ መቷቸው፤ ሕዝቡም በጣም ተዳከመ። +32 ስለሆነም ሕዝቡ ምርኮውን በመስገብገብ ተሻምቶ ወሰደ፤ በጎችን፣ ከብቶችንና ጥጆችን ወስደው መሬት ላይ አረዷቸው፤ ሥጋውንም ከነደሙ በሉት።+ +33 በመሆኑም ሳኦል “ይኸው ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት+ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እየሠራ ነው” ተብሎ ተነገረው። እሱም በዚህ ጊዜ “እምነት እንደሌላችሁ የሚያሳይ ድርጊት ፈጽማችኋል። በሉ አሁኑኑ አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ አምጡልኝ” አለ። +34 አክሎም እንዲህ አለ፦ “በሕዝቡ መሃል ተበታትናችሁ እንዲህ በሏቸው፦ ‘እያንዳንዳችሁ በሬያችሁንና በጋችሁን አምጡ፤ በዚህም ስፍራ አርዳችሁ ብሉ። ሥጋውን ከነደሙ በመብላት በይሖዋ ላይ ኃጢአት አትሥሩ።’”+ በመሆኑም በዚያ ምሽት እያንዳንዱ ሰው በሬውን አምጥቶ በዚያ ስፍራ አረደው። +35 ሳኦልም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ።+ ይህ መሠዊያ ሳኦል ለይሖዋ የሠራው የመጀመሪያ መሠዊያ ነው። +36 በኋላም ሳኦል “በሌሊት ፍልስጤማውያንን ተከታትለን በመውረድ እስኪነጋ ድረስ እንበዝብዛቸው። አንድም ሰው በሕይወት አናስተርፍም” አለ። በዚህ ጊዜ ሕዝቡ “መልካም መስሎ የታየህን ማንኛውንም ነገር አድርግ” አሉት። ከዚያም ካህኑ “እዚሁ ወደ እውነተኛው አምላክ እንቅረብ” አለ።+ +37 ሳኦልም “ፍልስጤማውያንን ተከትዬ ልውረድ?+ በእስራኤላውያን እጅ እንዲወድቁ ታደርጋለህ?” በማለት አምላክን ጠየቀ። አምላክ ግን በዚያ ዕለት አልመለሰለትም። +38 በመሆኑም ሳኦል እንዲህ አለ፦ “እናንተ የሕዝቡ አለቆች ሁሉ ወደዚህ ቅረቡ፤ በዛሬው ዕለት ምን ኃጢአት እንደተፈጸመ አጣሩ። +39 እስራኤልን ባዳነው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ ይህን ኃጢአት የሠራው ልጄ ዮናታን ሆኖ ቢገኝ እንኳ መሞት አለበት።” ሆኖም ከሕዝቡ መካከል መልስ የሰጠው አንድም ሰው አልነበረም። +40 ከዚያም እስራኤላውያንን በሙሉ “እናንተ በአንድ በኩል ትሆናላችሁ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በሌላኛው በኩል እንሆናለን” አላቸው። በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሳኦልን “መልካም መስሎ የታየህን ማንኛውንም ነገር አድርግ” አለው። +41 ሳኦልም ይሖዋን “የእስራኤል አምላክ ሆይ፣ በቱሚም+ አማካኝነት መልስ ስጠን!” አለው። ከዚያም ዮናታንና ሳኦል ተመረጡ፤ ሕዝቡም ነፃ ሆነ። +42 በዚህ ጊዜ ሳኦል “ከእኔና ከልጄ ከዮናታን ማን እንደሆነ ለመለየት ዕጣ ጣሉ”+ አለ። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወጣ። +43 ሳኦልም ዮናታንን “ንገረኝ፣ ያደረግከው ነገር ምንድን ነው?” አለው። በመሆኑም ዮናታን “በእጄ ይዤው በነበረው በትር ጫፍ ትንሽ ማር ቀምሻለሁ።+ እንግዲህ ይኸው ለመሞት ዝግጁ ነኝ!” በማለት መለሰለት። +44 በዚህ ጊዜ ሳኦል “ዮናታን፣ እንደው አንተ ካልሞትክ አምላክ ይፍረድብኝ፤ የከፋም ነገር ያድርግብኝ” አለ።+ +45 ሕዝቡ ግን ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል*+ ያስገኘው ዮናታን መሞት ይገባዋል? ይሄማ ፈጽሞ የማይሆን ነገር ነው! ሕያው በሆነው በይሖዋ እንምላለን፣ ከራስ ፀጉሩ አንዷ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም፤ ምክንያቱም በዚህ ዕለት ይህን ያደረገው ከአምላክ ጋር ሆኖ ነው።”+ በዚህ መንገ +46 ሳኦልም ፍልስጤማውያንን ማሳደዱን ተወ፤ ፍልስጤማውያንም ወደ ክልላቸው ሄዱ። +47 ሳኦልም በእስራኤል ላይ ንግሥናውን አጸና፤ በዙሪያው ከነበሩት ጠላቶቹ ማለትም ከሞዓባውያን፣+ ከአሞናውያን፣+ ከኤዶማውያን፣+ ከጾባህ+ ነገሥታትና ከፍልስጤማውያን+ ጋር ተዋጋ፤ በሄደበትም ሁሉ ድል ያደርጋቸው ነበር። +48 እንዲሁም በጀግንነት በመዋጋት አማሌቃውያንን+ ድል አደረገ፤ እስራኤላውያንንም ከዘራፊዎቻቸው እጅ አዳነ። +49 የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን፣ ይሽዊ እና ሜልኪሳ+ ነበሩ። እሱም ሁለት ሴቶች ልጆች የነበሩት ሲሆን የትልቋ ስም ሜሮብ፣+ የትንሿ ደግሞ ሜልኮል+ ነበር። +50 የሳኦል ሚስት የአኪማዓስ ልጅ አኪኖዓም ነበረች። የሠራዊቱ አዛዥ ደግሞ አበኔር+ ሲሆን እሱም የሳኦል አጎት የኔር ልጅ ነበር። +51 የሳኦል አባት ቂስ+ ነበር፤ የአበኔር አባት ኔር+ ደግሞ የአቢዔል ልጅ ነበር። +52 በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጤማውያን ጋር ከባድ ውጊያ ይደረግ ነበር።+ ሳኦልም ብርቱ ወይም ደፋር ሰው ሲያገኝ ወደ ሠራዊቱ እንዲቀላቀል ይመለምለው ነበር።+ +9 የቢንያም ሰው የሆነ ቂስ+ የተባለ አንድ እጅግ ባለጸጋ ሰው ነበር፤ እሱም የቢንያማዊው+ የአፊያ ልጅ፣ የቤኮራት ልጅ፣ የጸሮር ልጅ፣ የአቢዔል ልጅ ነበር። +2 ይህ ሰው ሳኦል+ የተባለ መልከ መልካም ወጣት ልጅ ነበረው፤ ከእስራኤላውያንም መካከል እንደ እሱ ያለ መልከ መልካም ወንድ አልነበረም፤ እሱም ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ ሲሆን ���መቱ ከሌሎቹ ሁሉ ይበልጥ ነበር። +3 የሳኦል አባት ቂስ አህዮቹ* በጠፉበት ጊዜ ልጁን ሳኦልን “እባክህ ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልጋቸው” አለው። +4 እነሱም የኤፍሬምን ተራራማ አካባቢና የሻሊሻን ምድር አቋርጠው ሄዱ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኟቸውም። ከዚያም የሻአሊምን ምድር አቋርጠው ተጓዙ፤ አህዮቹ ግን በዚያ አልነበሩም። እነሱም መላውን የቢንያማውያንን ምድር አቋርጠው ሄዱ፤ ይሁንና አህዮቹን አላገኟቸውም። +5 እነሱም ወደ ጹፍ ምድር መጡ፤ ሳኦልም አብሮት የነበረውን አገልጋዩን “አባቴ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ እንዳይጀምር፣ ና እንመለስ” አለው።+ +6 አገልጋዩ ግን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፣ በዚህ ከተማ የሚኖር አንድ የተከበረ የአምላክ ሰው አለ። የሚናገረው ነገር በሙሉ መሬት ጠብ አይልም።+ ስለዚህ ወደዚያ እንሂድ። ምናልባት በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ሊነግረን ይችላል።” +7 በዚህ ጊዜ ሳኦል አገልጋዩን እንዲህ አለው፦ “መሄዱንስ እንሂድ፤ ግን ለሰውየው ምን ይዘንለት እንሄዳለን? በከረጢታችን ውስጥ የያዝነው ዳቦ እንደሆነ አልቋል፤ ለእውነተኛው አምላክ ሰው ስጦታ አድርገን የምንሰጠው ምንም ነገር የለንም። ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” +8 አገልጋዩም መልሶ ሳኦልን “እንግዲህ ሩብ ሰቅል* ብር በእጄ አለ። ይህን ለእውነተኛው አምላክ ሰው እሰጠዋለሁ፤ እሱም በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረናል” አለው። +9 (ቀደም ባሉት ጊዜያት በእስራኤል ውስጥ አንድ ሰው አምላክን ለመፈለግ ሲሄድ “ኑ፣ ወደ ባለ ራእዩ+ እንሂድ” ይል ነበር። ምክንያቱም በዛሬው ጊዜ ነቢይ የሚባለው ቀደም ባሉት ጊዜያት ባለ ራእይ ይባል ነበር።) +10 ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን “የተናገርከው ነገር መልካም ነው። በል ና፣ እንሂድ” አለው። በመሆኑም የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደሚገኝበት ከተማ ሄዱ። +11 እነሱም ወደ ከተማዋ የሚወስደውን አቀበት እየወጡ ሳለ ውኃ ለመቅዳት የወጡ ልጃገረዶችን አገኙ። በመሆኑም “ባለ ራእዩ+ እዚህ ነው ያለው?” አሏቸው። +12 እነሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “አዎ እዚህ ነው። እነሆ፣ ከፊታችሁ ነው ያለው! ፈጠን ብላችሁ ሂዱ፣ በዛሬው ዕለት ሕዝቡ ከፍ ባለው ቦታ+ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ+ ወደ ከተማዋ መጥቷል። +13 ልክ ወደ ከተማዋ እንደገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን የሚባርከው እሱ ስለሆነ ሕዝቡ እሱ ካልመጣ መብላት አይጀምርም። ከዚያ በኋላ የተጋበዙት ይበላሉ። በሉ አሁኑኑ ውጡ፤ ታገኙታላችሁ።” +14 ስለዚህ ወደ ከተማዋ ወጡ። ከተማዋ መሃል ሲደርሱም ሳሙኤል ከእነሱ ጋር ተገናኝቶ ወደ ኮረብታው ለመውጣት ወደ እነሱ እየመጣ ነበር። +15 ይሖዋ፣ ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት ለሳሙኤል እንዲህ ብሎት* ነበር፦ +16 “ነገ በዚህ ጊዜ ገደማ ከቢንያም ምድር+ የመጣ አንድ ሰው ወደ አንተ እልካለሁ። አንተም በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አድርገህ ቀባው፤+ እሱም ሕዝቤን ከፍልስጤማውያን እጅ ያድናቸዋል። ምክንያቱም የሕዝቤን መከራ አይቻለሁ፤ ጩኸታቸውም ወደ እኔ ደርሷል።”+ +17 ሳሙኤል፣ ሳኦልን ባየው ጊዜ ይሖዋ “‘ሕዝቤን የሚገዛው* እሱ ነው’ ብዬ የነገርኩህ ሰው ይህ ነው” አለው።+ +18 ከዚያም ሳኦል በሩ መሃል ላይ ወደነበረው ወደ ሳሙኤል ቀርቦ “እባክህ፣ የባለ ራእዩ ቤት የት እንደሆነ ትነግረኛለህ?” አለው። +19 ሳሙኤልም ለሳኦል እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ። ከእኔ ቀድመህ ወደ ኮረብታው ውጣ፤ ዛሬ አብራችሁኝ ትበላላችሁ።+ በማለዳም አሰናብትሃለሁ፤ ማወቅ የምትፈልገውንም ነገር ሁሉ* እነግርሃለሁ። +20 ከሦስት ቀን በፊት ስለጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ፤+ ምክንያቱም ተገኝተዋል። በእስራኤል ውስጥ ያለው ምርጥ ነገር ሁሉ የማን ነው? የአንተና የመላው የአባትህ ቤት አይደለም?”+ +21 በዚህ ጊዜ ሳኦል እንዲህ አለው፦ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ አነስተኛ ከሆነው ከቢንያም ነገድ የተገኘሁ ቢንያማዊ አይደለሁም?+ ቤተሰቤስ ቢሆን ከቢንያም ነገድ ቤተሰቦች መካከል እዚህ ግባ የሚባል ሆኖ ነው? ታዲያ እንዲህ የምትለኝ ለምንድን ነው?” +22 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ መመገቢያ አዳራሹ ይዟቸው ሄደ፤ እነሱንም በተጋበዙት ሰዎች ፊት በክብር ቦታ አስቀመጣቸው፤ ተጋባዦቹም 30 ገደማ ነበሩ። +23 ሳሙኤልም ምግብ የሚያበስለውን ሰው “‘ለይተህ አስቀምጠው’ ብዬ የሰጠሁህን ድርሻ አምጣው” አለው። +24 በዚህ ጊዜ ምግብ የሚያበስለው ሰው ጭኑንና ላዩ ላይ የነበረውን አንስቶ ሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም እንዲህ አለው፦ “ተለይቶ ተቀምጦ የነበረው ፊትህ ቀርቦልሃል። ይህ ለዚህ ጊዜ ብለው ለይተው ያስቀመጡልህ ስለሆነ ብላ። ምክንያቱም ‘እንግዶች ጋብዣለሁ’ ብዬ ነግሬያቸዋለሁ።” በመሆኑም ሳኦል በዚያ +25 ከዚያም ከኮረብታው+ ወደ ከተማው ወረዱ፤ ሳሙኤልም ከሳኦል ጋር በቤቱ ሰገነት ላይ ሲነጋገር ቆየ። +26 እነሱም በማለዳ ተነሱ፤ ጎህ እንደቀደደም ሳሙኤል ሳኦልን ወደ ቤቱ ሰገነት ጠርቶ “በል ተዘጋጅና ላሰናብትህ” አለው። ስለዚህ ሳኦል ተዘጋጀ፤ ከዚያም እሱና ሳሙኤል ወደ ውጭ ወጡ። +27 እነሱም በከተማዋ ዳርቻ ቁልቁል እየወረዱ ሳሉ ሳሙኤል ሳኦልን “አገልጋይህ+ ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ እሱም ቀድሞ ሄደ። ሳሙኤልም “አንተ ግን የአምላክን ቃል እንዳሰማህ እዚሁ ቁም” አለው። +27 ሆኖም ዳዊት በልቡ እንዲህ አለ፦ “አንድ ቀን በሳኦል እጅ መጥፋቴ አይቀርም። የሚያዋጣኝ ወደ ፍልስጤማውያን ምድር መሸሽ ነው፤+ ሳኦልም ተስፋ ቆርጦ በእስራኤል ግዛት ሁሉ እኔን መፈለጉን ያቆማል፤+ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ።” +2 በመሆኑም ዳዊት አብረውት ከነበሩት 600 ሰዎች+ ጋር ተነስቶ የጌት ንጉሥ ወደሆነው ወደ ማኦክ ልጅ ወደ አንኩስ+ ተሻገረ። +3 ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰባቸው ጌት ውስጥ አንኩስ ዘንድ ተቀመጡ። ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ማለትም ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪኖዓም+ እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢጋኤል+ ጋር ነበር። +4 ሳኦልም ዳዊት ወደ ጌት መሸሹ ሲነገረው እሱን መፈለጉን ተወ።+ +5 ከዚያም ዳዊት አንኩስን “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ በገጠር ካሉ ከተሞች በአንዱ እንድኖር ቦታ እንዲሰጡኝ አድርግ። አገልጋይህ ለምን በንጉሥ ከተማ ከአንተ ጋር ይኖራል?” አለው። +6 በመሆኑም አንኩስ በዚያ ቀን ጺቅላግን+ ሰጠው። ጺቅላግ እስካሁንም ድረስ የይሁዳ ነገሥታት ይዞታ የሆነችው በዚህ ምክንያት ነው። +7 ዳዊት በፍልስጤማውያን ገጠራማ አካባቢ የኖረበት ጊዜ* አንድ ዓመት ከአራት ወር ነበር።+ +8 ዳዊትም ከሰዎቹ ጋር በመሆን ገሹራውያንን፣+ ጊዝራውያንን እና አማሌቃውያንን+ ለመውረር ይወጣ ነበር፤ ምክንያቱም እነዚህ ሕዝቦች ከቴላም አንስቶ እስከ ሹር+ እና እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ባለው አካባቢ ይኖሩ ነበር። +9 ዳዊት በምድሪቱ ላይ ጥቃት በሚሰነዝርበት ጊዜ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አያስቀርም ነበር፤+ ሆኖም መንጎችን፣ ከብቶችን፣ አህዮችን፣ ግመሎችንና ልብሶችን ወስዶ ወደ አንኩስ ይመለስ ነበር። +10 አንኩስም “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ይለው ነበር። ዳዊትም “በይሁዳ ደቡባዊ ክፍል*+ ላይ ዘምተን ነበር” ወይም “በየራህምኤላውያን+ ምድር ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነበር” አሊያም “በቄናውያን+ ምድር ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነ���ር” በማለት ይመልስለት ነበር። +11 ዳዊት “‘እሱ እንዲህ አደረገ’ በማለት ስለ እኛ ሊነግሯቸው ይችላሉ” ብሎ ስላሰበ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስተርፎ ወደ ጌት አያመጣም ነበር። (ዳዊት በፍልስጤም ገጠራማ አካባቢ በኖረበት ዘመን ሁሉ እንዲህ የማድረግ ልማድ ነበረው።) +12 ስለዚህ አንኩስ ‘በእርግጥም ይህ ሰው በገዛ ሕዝቦቹ በእስራኤላውያን ዘንድ እንደ ጥንብ ተቆጥሯል፤ ስለሆነም ዕድሜ ልኩን አገልጋዬ ይሆናል’ ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው። +13 ሳኦል በነገሠ ጊዜ ዕድሜው . . .* ነበር፤+ እሱም በእስራኤል ላይ ሁለት ዓመት ገዛ። +"2 ሳኦል ከእስራኤላውያን መካከል 3,000 ሰዎችን መረጠ፤ ከእነዚህም መካከል 2,000ዎቹ በሚክማሽና በቤቴል ተራራማ አካባቢ ከሳኦል ጋር ሆኑ፤ ሌሎቹ 1,000 ሰዎች ደግሞ በቢንያም ግዛት በጊብዓ+ ከዮናታን+ ጋር ሆኑ። የቀሩትን ሰዎች እያንዳንዳቸውን ወደየድንኳናቸው አሰናበታቸው።" +3 ዮናታንም በጌባ+ የነበረውን የፍልስጤማውያንን+ የጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም “ዕብራውያን ይስሙ!” በማለት በምድሩ ሁሉ ቀንደ መለከት አስነፋ።+ +4 እስራኤላውያን በሙሉ “ሳኦል የፍልስጤማውያንን የጦር ሰፈር መታ፤ እስራኤላውያንም በፍልስጤማውያን ዘንድ እንደ ግም ተቆጠሩ” ሲባል ሰሙ። በመሆኑም ሕዝቡ ሳኦልን ለመከተል በጊልጋል ተሰበሰበ።+ +"5 ፍልስጤማውያንም 30,000 የጦር ሠረገሎች፣ 6,000 ፈረሰኞችና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ይዘው ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት ተሰባሰቡ፤+ እነሱም ወጥተው ከቤትአዌን+ በስተ ምሥራቅ በሚክማሽ ሰፈሩ።" +6 የእስራኤል ሰዎችም አደጋ እንደተጋረጠባቸው ስላዩ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብተው ነበር፤ በመሆኑም ሕዝቡ በየዋሻው፣ በየጉድጓዱ፣ በየዓለቱ፣ በየጎሬውና በየውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዱ ውስጥ ተደበቀ።+ +7 እንዲያውም አንዳንድ ዕብራውያን ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ጊልያድ+ ምድር ሄዱ። ሳኦል ግን እዚያው ጊልጋል ነበር፤ የተከተሉት ሰዎችም ሁሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር። +8 እሱም ሳሙኤል የቀጠረው ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ለሰባት ቀን ጠበቀ፤ ሳሙኤል ግን ወደ ጊልጋል አልመጣም፤ ሕዝቡም ሳኦልን ትቶ መበታተን ጀመረ። +9 በመጨረሻም ሳኦል “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቶቹን አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።+ +10 ሆኖም ሳኦል የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርቦ እንደጨረሰ ሳሙኤል መጣ። በመሆኑም ሳኦል ሊቀበለውና ሊባርከው ወጣ። +11 ከዚያም ሳሙኤል “ያደረግከው ነገር ምንድን ነው?” አለው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ሕዝቡ ትቶኝ መበታተን እንደጀመረና+ አንተም በተቀጠረው ጊዜ እንዳልመጣህ እንዲሁም ፍልስጤማውያኑ በሚክማሽ+ እየተሰባሰቡ መሆናቸውን አየሁ። +12 በመሆኑም ‘እንግዲህ ፍልስጤማውያን ወደ ጊልጋል ወርደው ሊወጉኝ ነው፤ እኔ ደግሞ ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳየኝ አለመንኩም’ ብዬ አሰብኩ። ስለሆነም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።” +13 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “የፈጸምከው የሞኝነት ድርጊት ነው። አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅክም።+ ጠብቀህ ቢሆን ኖሮ ይሖዋ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ባጸናልህ ነበር። +14 አሁን ግን መንግሥትህ አይዘልቅም።+ ይሖዋ እንደ ልቡ የሚሆንለት ሰው ያገኛል፤+ ይሖዋም በሕዝቡ ላይ መሪ አድርጎ ይሾመዋል፤+ ምክንያቱም አንተ የይሖዋን ትእዛዝ አልጠበቅክም።”+ +15 ከዚያም ሳሙኤል ተነስቶ ከጊልጋል በቢንያም ግዛት ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ ወጣ፤ ሳኦልም ሕዝቡን ቆጠረ፤ አብረውት ያሉት ሰዎች ብዛታቸው 600 ገደማ ነበር።+ +16 ��ኦልና ልጁ ዮናታን እንዲሁም አብረዋቸው የቀሩት ሰዎች በቢንያም ግዛት በምትገኘው በጌባ+ ሰፍረው የነበረ ሲሆን ፍልስጤማውያን ደግሞ በሚክማሽ+ ሰፍረው ነበር። +17 በሦስት ምድብ የተከፈለው የወራሪዎች ቡድን ከፍልስጤማውያን ሰፈር ይወጣል። አንደኛው ቡድን ወደ ሹአል ምድር ወደ ኦፍራ ወደሚወስደው መንገድ ያቀናል፤ +18 ሌላኛው ቡድን ወደ ቤትሆሮን+ ወደሚወስደው መንገድ ይሄዳል፤ ሦስተኛው ቡድን ደግሞ የጸቦይምን ሸለቆ ቁልቁል ወደሚያሳየው ወሰን ይኸውም ወደ ምድረ በዳው ወደሚወስደው መንገድ ያቀናል። +19 በመላው የእስራኤል ምድር አንድም ብረት ቀጥቃጭ አልነበረም፤ ምክንያቱም ፍልስጤማውያን “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር እንዳይሠሩ” ብለው ነበር። +20 ስለዚህ እስራኤላውያን በሙሉ ማረሻቸውን ወይም ዶማቸውን አሊያም መጥረቢያቸውን ወይም ማጭዳቸውን ለማሳል ወደ ፍልስጤማውያን ይወርዱ ነበር። +21 ማረሻ፣ ዶማ፣ መንሽና መጥረቢያ ለማሳል እንዲሁም የበሬ መውጊያ ለማሳሰር ዋጋው አንድ ፊም* ነበር። +22 ውጊያው በተደረገበት ቀን ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ባሉት ሰዎች እጅ አንድም ሰይፍ ወይም ጦር አልተገኘም፤ መሣሪያ የነበራቸው ሳኦልና ልጁ ዮናታን ብቻ ነበሩ።+ +23 በዚህ ጊዜ አንደኛው የፍልስጤማውያን ጦር በሚክማሽ+ ወደሚገኝ ጠባብ ሸለቆ ወጥቶ ነበር። +5 ፍልስጤማውያኑ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ከማረኩ+ በኋላ ከኤቤንዔዘር ወደ አሽዶድ አመጡት። +2 እነሱም የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ወስደው ወደ ዳጎን ቤት* አስገቡት፤ ከዳጎን+ አጠገብም አስቀመጡት። +3 በማግስቱም አሽዶዳውያን በማለዳ ሲነሱ ዳጎን በይሖዋ ታቦት ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት።+ በመሆኑም ዳጎንን አንስተው ወደ ቦታው መለሱት።+ +4 በሚቀጥለውም ቀን ማለዳ ሲነሱ ዳጎን በይሖዋ ታቦት ፊት በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት። የዳጎን ራስና መዳፎቹም ተቆርጠው ደፉ ላይ ወድቀው ነበር። ባለበት የቀረው የዓሣው ክፍል ብቻ* ነበር። +5 እስከ ዛሬም ድረስ የዳጎን ካህናትና ወደ ዳጎን ቤት የሚገቡ ሁሉ በአሽዶድ የሚገኘውን የዳጎንን ደፍ የማይረግጡት ለዚህ ነው። +6 የይሖዋም እጅ በአሽዶዳውያን ላይ ከበደባቸው፤ እሱም አሽዶድንና ግዛቶቿን በኪንታሮት*+ በመምታት አጠፋቸው። +7 የአሽዶድ ሰዎች የተከሰተውን ነገር ሲያዩ “የእስራኤል አምላክ ታቦት በመካከላችን እንዲቆይ አታድርጉ፤ ምክንያቱም እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጨክኖብናል” አሉ። +8 በመሆኑም ሰዎችን ልከው የፍልስጤምን ገዢዎች በሙሉ በመሰብሰብ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ምን ብናደርገው ይሻላል?” ብለው ጠየቋቸው። እነሱም “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት+ ይወሰድ” ሲሉ መለሱላቸው። ስለሆነም የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደዚያ ወሰዱት። +9 ታቦቱንም ወደዚያ ከወሰዱት በኋላ የይሖዋ እጅ በከተማዋ ላይ ሆነ፤ ታላቅ ሽብርም ለቀቀባቸው። እሱም የከተማዋን ሰዎች ከትንሽ እስከ ትልቅ መታቸው፤ ኪንታሮትም ወጣባቸው።+ +10 በመሆኑም የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ወደ ኤቅሮን+ ላኩት፤ ሆኖም የእውነተኛው አምላክ ታቦት ኤቅሮን ሲደርስ ኤቅሮናውያን “እኛንም ሆነ ሕዝባችንን ለማስፈጀት የእስራኤልን አምላክ ታቦት ይኸው ወደ እኛ ደግሞ አመጡብን!” በማለት ይጮኹ ጀመር።+ +11 ከዚያም ሰዎችን ልከው የፍልስጤምን ገዢዎች በሙሉ በመሰብሰብ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ እኛም ሆንን ሕዝባችን እንዳናልቅ ወደ ቦታው እንዲመለስ አድርጉ” አሏቸው። ምክንያቱም መላ ከተማዋ በሞት ፍርሃት ተውጣ ነበር፤ የእውነተኛውም አምላክ እጅ በዚያ በጣም ከብዶ ነበር፤+ +12 ያልሞቱት ሰዎችም በኪንታሮት ተመቱ። ከተማዋ እ��ዳታ ለማግኘት የምታሰማው ጩኸትም ወደ ሰማይ ወጣ። +21 በኋላም ዳዊት ካህኑ አሂሜሌክ ወደሚገኝበት ወደ ኖብ+ መጣ። አሂሜሌክም ዳዊትን ሲያገኘው ተንቀጠቀጠ፤ እሱም “ምነው ብቻህን? ሰው አብሮህ የለም?” አለው።+ +2 ዳዊትም ለካህኑ ለአሂሜሌክ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ንጉሡ አንድ ጉዳይ እንዳስፈጽም አዞኝ ነበር፤ ሆኖም ‘ስለሰጠሁህ ተልእኮና ስላዘዝኩህ ነገር ማንም ሰው ምንም ነገር እንዳያውቅ’ ብሎኛል። ከሰዎቼም ጋር የሆነ ቦታ ላይ ለመገናኘት ተቀጣጥረናል። +3 ስለዚህ አሁን እጅህ ላይ አምስት ዳቦ ካለ ወይም የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ስጠኝ።” +4 ካህኑ ግን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ማንኛውም ሰው የሚበላው ዓይነት ዳቦ የለኝም፤ ሰሞኑን ሰዎቹ ራሳቸውን ከሴት ጠብቀው*+ ከሆነ ግን የተቀደሰው ኅብስት አለ።”+ +5 ስለዚህ ዳዊት ካህኑን እንዲህ አለው፦ “ከዚህ በፊት ለውጊያ እንደወጣሁባቸው ጊዜያት ሁሉ አሁንም ፈጽሞ ሴቶች ወደ እኛ አልቀረቡም።+ ተራ በሆነ ተልእኮም እንኳ የሰዎቹ አካል ቅዱስ ከነበረ ታዲያ ዛሬማ እንዴት ይበልጥ ቅዱስ አይሆን!” +6 በመሆኑም ካህኑ የተቀደሰውን ኅብስት ሰጠው፤+ ምክንያቱም ትኩስ ኅብስት በሚተካበት ቀን ከይሖዋ ፊት ከተነሳው ገጸ ኅብስት በስተቀር ሌላ ዳቦ አልነበረም። +7 ከሳኦል አገልጋዮች አንዱ በይሖዋ ፊት እንዲቆይ በመገደዱ ያን ቀን እዚያ ነበር። ዶይቅ+ የተባለው ይህ ኤዶማዊ+ የሳኦል እረኞች አለቃ ነበር። +8 ከዚያም ዳዊት አሂሜሌክን “ንጉሡ የሰጠኝ ተልእኮ አስቸኳይ ስለነበር ሰይፌንም ሆነ የጦር መሣሪያዎቼን አልያዝኩም፤ እዚህ አንተ ጋ ጦር ወይም ሰይፍ ይኖራል?” አለው። +9 ካህኑም “በኤላህ ሸለቆ*+ አንተ የገደልከው የፍልስጤማዊው የጎልያድ ሰይፍ+ አለ፤ ያውልህ ከኤፉዱ+ ኋላ በጨርቅ ተጠቅልሎ ተቀምጧል። ከእሱ ሌላ እዚህ ምንም ስለሌለ ከፈለግክ እሱን ውሰደው” አለው። ዳዊትም “ከእሱ የተሻለማ የትም አይገኝም። እሱኑ ስጠኝ” አለው። +10 በዚያም ቀን ዳዊት ተነስቶ ከሳኦል ሸሸ፤+ ከጊዜ በኋላም ወደ ጌት+ ንጉሥ ወደ አንኩስ መጣ። +11 የአንኩስ አገልጋዮችም እንዲህ አሉት፦ “ይህ የምድሪቱ ንጉሥ፣ ዳዊት አይደለም?‘ሳኦል ሺዎችን ገደለ፤ዳዊት ደግሞ አሥር ሺዎችን ገደለ’+ በማለት እየዘፈኑ የጨፈሩለትስ ለዚህ ሰው አይደለም?” +12 ዳዊትም ይህን ቃል በቁም ነገር ተመለከተው፤ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው።+ +13 በመሆኑም በፊታቸው አእምሮውን እንደሳተ ሰው ሆነ፤+ በመካከላቸውም* እንደአበደ ሰው አደረገው። የከተማዋን በሮች ይቦጫጭር እንዲሁም ለሃጩን በጢሙ ላይ ያዝረበርብ ጀመር። +14 አንኩስም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ “እስቲ ተመልከቱ፣ ሰውየው እኮ እብድ ነው! ታዲያ ወደ እኔ ያመጣችሁት ለምንድን ነው? +15 ይህን ሰው ፊቴ እንዲህ እንዲያብድ ያመጣችሁት እኔ እብድ አጥቼ ነው? ይህስ ሰው ቤቴ መግባት ይገባዋል?” +15 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ እንድቀባህ የላከው እኔን ነበር፤+ እንግዲህ አሁን ይሖዋ ምን እንደሚል ስማ።+ +2 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ ጊዜ በመንገድ ላይ እነሱን በመቃወም ለፈጸሙት ድርጊት አማሌቃውያንን እቀጣቸዋለሁ።+ +3 በል አሁን ሂድ፤ አማሌቃውያንን+ ምታቸው፤ እነሱንም ካላቸው ነገር ሁሉ ጋር ፈጽመህ አጥፋቸው።+ አንዳቸውንም አታስቀር፤* ወንድም ሆነ ሴት፣ ልጅም ሆነ ሕፃን፣ በሬም ሆነ በግ፣ ግመልም ሆነ አህያ ሁሉንም ግደል።’”+ +"4 ሳኦልም ሕዝቡን በጤላይም ሰብስቦ ቆጠረ፤ በዚያም 200,000 እግረኛ ወታደሮችና 10,000 የይሁዳ ሰዎች ነበሩ።+ " +5 ከዚያም ሳኦል እስከ አማሌቃውያን ከ���ማ ድረስ በመጠጋት በሸለቆው* ውስጥ አደፈጠ። +6 ሳኦልም ቄናውያንን+ “ከአማሌቃውያን ጋር አብሬ እንዳላጠፋችሁ+ ሂዱ፣ ከእነሱ መካከል ውጡ። ምክንያቱም እናንተ እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡበት ጊዜ ለሕዝቡ በሙሉ ታማኝ ፍቅር አሳይታችኋል”+ አላቸው። በመሆኑም ቄናውያን ከአማሌቃውያን መካከል ወጡ። +7 ከዚያም ሳኦል አማሌቃውያንን+ ከሃዊላ+ አንስቶ በግብፅ አጠገብ እስከምትገኘው እስከ ሹር+ ድረስ መታቸው። +8 እሱም የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን+ ከነሕይወቱ ማረከው፤ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ግን በሰይፍ ፈጽሞ አጠፋ።+ +9 ሆኖም ሳኦልና ሕዝቡ አጋግን እንዲሁም ከመንጋው፣ ከከብቱ፣ ከደለቡት እንስሳትና ከአውራ በጎቹ መካከል ምርጥ የሆኑትንና ጥሩ ጥሩ የሆነውን ነገር ሁሉ ሳያጠፉ ተዉ።+ እነዚህን ሊያጠፏቸው አልፈለጉም። የማይረባውንና የማይፈለገውን ነገር ሁሉ ግን ፈጽመው አጠፉ። +10 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሳሙኤል መጣ፦ +11 “ሳኦልን ንጉሥ በማድረጌ ተጸጽቻለሁ፤* ምክንያቱም እሱ እኔን ከመከተል ዞር ብሏል፤ ቃሌንም አልፈጸመም።”+ ሳሙኤልም በጣም ስለተረበሸ ሌሊቱን ሙሉ ወደ ይሖዋ ሲጮኽ አደረ።+ +12 ሳሙኤል ሳኦልን ለማግኘት በማለዳ ተነስቶ ሲሄድ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ+ ሄዶ በዚያ ለራሱ የመታሰቢያ ሐውልት አቁሟል።+ ከዚያም ተመልሶ ወደ ጊልጋል ወርዷል” ተብሎ ተነገረው። +13 በመጨረሻም ሳሙኤል ወደ ሳኦል ሲመጣ ሳኦል “ይሖዋ ይባርክህ። የይሖዋን ቃል ፈጽሜአለሁ” አለው። +14 ሳሙኤል ግን “ታዲያ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎችና የከብቶች ድምፅ ምንድን ነው?” አለው።+ +15 በዚህ ጊዜ ሳኦል “ሕዝቡ ከአማሌቃውያን ላይ ወስዶ ያመጣቸው ናቸው፤ ከመንጋውና ከከብቶቹ መካከል ምርጥ የሆኑትን ለአምላክህ ለይሖዋ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳያጠፉ ተዉአቸው፤* የቀረውን ግን ሙሉ በሙሉ አጥፍተናል” አለው። +16 ሳሙኤልም ሳኦልን “ተው በቃ! ትናንት ማታ ይሖዋ ምን እንዳለኝ ልንገርህ” አለው።+ እሱም “እሺ ንገረኝ!” አለው። +17 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፦ “በእስራኤል ነገዶች ላይ መሪ ሆነህ በተሾምክበትና ይሖዋ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ በቀባህ+ ጊዜ አንተ ራስህ እዚህ ግባ የማትባል ሰው እንደሆንክ ተሰምቶህ አልነበረም?+ +18 በኋላም ይሖዋ ‘ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው።+ ጨርሰህ እስክታጠፋቸውም ድረስ ከእነሱ ጋር ተዋጋ’ በማለት ላከህ።+ +19 ታዲያ የይሖዋን ቃል ያልታዘዝከው ለምንድን ነው? ከዚህ ይልቅ ለምርኮው በመስገብገብ+ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አድርገሃል!” +20 ሳኦል ግን ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “እኔ እኮ የይሖዋን ቃል ታዝዣለሁ! ይሖዋ የሰጠኝን ተልእኮ ለመፈጸም ሄጃለሁ፤ የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ይዤ አምጥቻለሁ፤ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ።+ +21 ሕዝቡ ግን በጊልጋል ለአምላክህ ለይሖዋ ለመሠዋት ከምርኮው ላይ በጎችንና ከብቶችን ይኸውም ለጥፋት ከተለየው ነገር ላይ ምርጥ የሆነውን ወሰደ።”+ +22 ከዚያም ሳሙኤል እንዲህ አለ፦ “ይሖዋን ይበልጥ የሚያስደስተው የትኛው ነው? የሚቃጠሉ መባዎችንና መሥዋዕቶችን+ ማቅረብ ወይስ የይሖዋን ቃል መታዘዝ? እነሆ፣ መታዘዝ ከመሥዋዕት፣+ መስማትም ከአውራ በግ ስብ+ ይበልጣል፤ +23 ምክንያቱም ዓመፀኝነት+ ሟርት+ ከመፈጸም አይተናነስም፤ እብሪተኝነትም ቢሆን ከጥንቆላና ከጣዖት አምልኮ* ተለይቶ አይታይም። አንተ የይሖዋን ቃል ስላልተቀበልክ+ እሱም የአንተን ንግሥና አልተቀበለውም።”+ +24 ከዚያም ሳኦል ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ሕዝቡን በመፍራትና ቃላቸውን በመስማት የይሖዋን ትእዛዝም ሆነ የአንተን ቃል ጥሻለሁ። +25 አሁንም እ��ክህ ኃጢአቴን ይቅር በል፤ ለይሖዋም እንድሰግድ አብረኸኝ ተመለስ።”+ +26 ሳሙኤል ግን ሳኦልን “አንተ የይሖዋን ቃል ስላልተቀበልክና ይሖዋም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆነህ እንድትቀጥል ስላልፈቀደ ከአንተ ጋር አልመለስም” አለው።+ +27 ሳሙኤል ለመሄድ ዞር ሲል ሳኦል የሳሙኤልን ልብስ ጫፍ አፈፍ አድርጎ ያዘ፤ ልብሱም ተቀደደ። +28 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ የእስራኤልን ንጉሣዊ አገዛዝ በዛሬው ዕለት ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተ ለሚሻል ባልንጀራህም አሳልፎ ይሰጠዋል።+ +29 ደግሞም የእስራኤል ክቡር+ አይዋሽም+ ወይም ሐሳቡን አይቀይርም፤* ምክንያቱም እሱ ሐሳቡን ይቀይር* ዘንድ+ የሰው ልጅ አይደለም።” +30 እሱም “ኃጢአት ሠርቻለሁ። ሆኖም እባክህ በሕዝቤ ሽማግሌዎችና በእስራኤል ፊት አክብረኝ። አብረኸኝ ተመለስ፤ እኔም ለአምላክህ ለይሖዋ እሰግዳለሁ”+ አለው። +31 በመሆኑም ሳሙኤል ሳኦልን ተከትሎት ተመለሰ፤ ሳኦልም በይሖዋ ፊት ሰገደ። +32 ሳሙኤልም “የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግም “መቼም የሞትን መራራ ጽዋ የምቀምስበት ጊዜ አልፏል” ብሎ ስላሰበ ፈራ ተባ እያለ* ወደ እሱ ሄደ። +33 ሆኖም ሳሙኤል “በአንተ ሰይፍ የተነሳ ልጆቻቸውን ያጡ ሴቶች እንዳዘኑ ሁሉ የአንተም እናት ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ ታዝናለች” አለው። ከዚያም ሳሙኤል በጊልጋል በይሖዋ ፊት አጋግን ቆራረጠው።+ +34 ሳሙኤል ወደ ራማ ሄደ፤ ሳኦልም በጊብዓ ወደሚገኘው ቤቱ አቀና። +35 ሳሙኤልም ለሳኦል እጅግ አዘነ፤+ እስከ ዕለተ ሞቱም ድረስ ሳኦልን ዳግመኛ አላየውም። ይሖዋም ሳኦልን በእስራኤል ላይ ንጉሥ በማድረጉ ተጸጸተ።+ +22 ዳዊትም ከዚያ ተነስቶ+ ወደ አዱላም+ ዋሻ ሸሸ። ወንድሞቹና መላው የአባቱ ቤት ይህን ሲሰሙ እሱ ወዳለበት ወደዚያ ወረዱ። +2 ችግር ያጋጠማቸው፣ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ* ሰዎች ሁሉ ወደ እሱ ተሰበሰቡ፤ እሱም አለቃቸው ሆነ። ከእሱም ጋር 400 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ነበሩ። +3 በኋላም ዳዊት ከዚያ ተነስቶ በሞዓብ ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ የሞዓብንም+ ንጉሥ “አምላክ የሚያደርግልኝን ነገር እስካውቅ ድረስ እባክህ አባቴና እናቴ አንተ ጋ ይሁኑ” አለው። +4 በመሆኑም የሞዓብ ንጉሥ ጋ አስቀመጣቸው፤ እነሱም ዳዊት በተራራው ላይ ምሽግ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ሁሉ እዚያ ተቀመጡ።+ +5 ከጊዜ በኋላም ነቢዩ ጋድ+ ዳዊትን “እዚህ ምሽግ ውስጥ መቆየት የለብህም። ሄደህ ወደ ይሁዳ ምድር ግባ” አለው።+ በመሆኑም ዳዊት ሄዶ ወደ ሄሬት ጫካ ገባ። +6 ሳኦልም ዳዊትና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች መገኘታቸውን ሰማ። በዚህ ጊዜ ሳኦል በጊብዓ+ በኮረብታው ላይ ባለው የታማሪስክ ዛፍ ሥር ጦሩን ይዞ ተቀምጦ ነበር፤ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር። +7 ከዚያም ሳኦል በዙሪያው የቆሙትን አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ቢንያማውያን፣ እስቲ ስሙኝ፤ ለመሆኑ የእሴይ+ ልጅ እንደ እኔ፣ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁም ይሰጣችኋል? ሁላችሁንስ የሺህ አለቆችና የመቶ አለቆች አድርጎ ይሾማችኋል?+ +8 እናንተ ሁላችሁ በእኔ ላይ ደባ ፈጽማችሁብኛል! የገዛ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ቃል ኪዳን ሲጋባ+ አንድም ሰው አልነገረኝም! ይኸው አሁን እንደምታዩት የገዛ ልጄ፣ አገልጋዬን በእኔ ላይ እንዲያደባብኝ ማነሳሳቱን አንዳችሁም ብትሆኑ ስለ እኔ ተቆርቁራችሁ አልነገራችሁኝም።” +9 ከዚያም በሳኦል አገልጋዮች ላይ ተሹሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦+ “የእሴይ ልጅ በኖብ ወደሚገኘው ወደ አኪጡብ+ ልጅ ወደ አሂሜሌክ ሲመጣ አይቻለሁ። +10 አሂሜሌክም ይሖዋን ጠየቀለት፤ ስንቅም ሰጠው። ሌላው ቀርቶ የፍልስጤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው።”+ +11 ንጉሡም ��ዲያውኑ ሰዎች ልኮ የካህኑን የአኪጡብን ልጅ አሂሜሌክንና በኖብ በአባቱ ቤት የነበሩትን ካህናት በሙሉ አስጠራ። በመሆኑም ሁሉም ወደ ንጉሡ መጡ። +12 ሳኦልም “አንተ የአኪጡብ ልጅ፣ እስቲ ስማኝ!” አለው፤ እሱም መልሶ “እሺ ጌታዬ፣ እየሰማሁ ነው” አለ። +13 ከዚያም ሳኦል “ለእሴይ ልጅ ምግብና ሰይፍ በመስጠት እንዲሁም ስለ እሱ አምላክን በመጠየቅ አንተም ሆንክ እሱ ደባ የፈጸማችሁብኝ ለምንድን ነው? ይኸው አሁን እንደሚታየው እየተቃወመኝና እያደባብኝ ነው” አለው። +14 በዚህ ጊዜ አሂሜሌክ ንጉሡን እንዲህ አለው፦ “እንደው ለመሆኑ ከአገልጋዮችህ ሁሉ መካከል እንደ ዳዊት ያለ እምነት የሚጣልበት* ማን አለ?+ እሱ የንጉሡ አማች፣+ የክብር ዘቦችህ አለቃና በቤትህ የተከበረ ሰው ነው።+ +15 ስለ እሱ አምላክን ስጠይቅ+ ዛሬ የመጀመሪያዬ ነው? የምትናገረው ነገር ፈጽሞ ያላሰብኩትን ነው! ንጉሡ አገልጋዩንም ሆነ የአባቴን ቤት በሙሉ ጥፋተኛ አያድርግ፤ ምክንያቱም አገልጋይህ ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።”+ +16 ንጉሡ ግን “አሂሜሌክ፣ አንተም ሆንክ የአባትህ ቤት+ በሙሉ በእርግጥ ትሞታላችሁ”+ አለው። +17 ከዚያም ንጉሡ በዙሪያው ቆመው የነበሩትን ጠባቂዎች* “ከዳዊት ጋር ስላበሩ ዙሩና የይሖዋን ካህናት ግደሉ! ዳዊት መኮብለሉን እያወቁ አልነገሩኝም!” አላቸው። የንጉሡ አገልጋዮች ግን የይሖዋን ካህናት ለመግደል እጃቸውን ማንሳት አልፈለጉም። +18 ንጉሡም ዶይቅን+ “እንግዲያውስ አንተ ዙርና ካህናቱን ግደላቸው!” አለው። ኤዶማዊው+ ዶይቅም ወዲያውኑ ሄዶ ካህናቱን ገደላቸው። በዚያን ቀን፣ ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ የለበሱ 85 ሰዎችን ገደለ።+ +19 እንዲሁም የካህናቱን ከተማ ኖብን+ በሰይፍ መታ፤ ወንድም ሆነ ሴት፣ ልጅም ሆነ ጨቅላ ሕፃን፣ በሬም ሆነ አህያ ወይም በግ አንድም ሳያስቀር ሁሉንም በሰይፍ ገደለ። +20 ሆኖም ከአኪጡብ ልጅ ከአሂሜሌክ ልጆች አንዱ የሆነው አብያታር+ አምልጦ ዳዊትን ለመከተል እሱ ወዳለበት እየሮጠ ሄደ። +21 አብያታር ለዳዊት “ሳኦል እኮ የይሖዋን ካህናት ገደላቸው” ሲል ነገረው። +22 በዚህ ጊዜ ዳዊት አብያታርን እንዲህ አለው፦ “ያን ቀን ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያ ስለነበር ይህን ለሳኦል እንደሚነግረው አውቄአለሁ።+ በአባትህ ቤት ላሉት ሰዎች* ሁሉ ሞት ተጠያቂው እኔ ራሴ ነኝ። +23 አሁን እኔ ጋ ቆይ። የአንተን ሕይወት* የሚፈልግ የእኔን ሕይወት* የሚፈልግ ስለሆነ አትፍራ፤ እኔ ከለላ እሆንሃለሁ።”+ +"17 ከዚያም አኪጦፌል አቢሴሎምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ 12,000 ሰዎች ልምረጥና ተነስቼ ዛሬ ማታ ዳዊትን ላሳደው።" +2 በደከመውና አቅም ባጣ* ጊዜ ድንገት እደርስበታለሁ፤+ ሽብርም እለቅበታለሁ፤ አብረውት ያሉት ሰዎችም ሁሉ ይሸሻሉ፤ ንጉሡን ብቻ እመታለሁ።+ +3 ከዚያም ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ። የሕዝቡ ሁሉ መመለስ የተመካው አንተ የምትፈልገው ሰው በሚደርስበት ነገር ላይ ነው። ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ሰላም ያገኛል።” +4 ይህ ሐሳብም በአቢሴሎምና በእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ ፊት መልካም ሆኖ ተገኘ። +5 ሆኖም አቢሴሎም “እስቲ አርካዊውን ኩሲን+ ጥሩትና እሱ ደግሞ የሚለውን እንስማ” አለ። +6 በመሆኑም ኩሲ ወደ አቢሴሎም ገባ። ከዚያም አቢሴሎም “አኪጦፌል እንዲህ የሚል ምክር ሰጥቷል። ታዲያ እሱ እንዳለው እናድርግ? ካልሆነ የአንተን ሐሳብ ንገረን” አለው። +7 ኩሲም አቢሴሎምን “እዚህ ላይ እንኳ አኪጦፌል የሰጠው ምክር የሚያዋጣ አይደለም!” አለው።+ +8 አክሎም ኩሲ እንዲህ አለ፦ “መቼም አባትህም ሆነ አብረውት ያሉት ሰዎች ኃያል ተዋጊዎችና+ በሜዳ እንዳለች ግልገሎቿን ያጣች ድብ+ ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ* ��ሆናቸውን በሚገባ ታውቃለህ። ደግሞም አባትህ ጦረኛ ነው፤+ ሌሊት ከሕዝቡ ጋር አያድርም። +9 ይህን ጊዜ እኮ አንድ ዋሻ* ውስጥ ወይም ሌላ ቦታ ተደብቋል፤+ እሱ ቀድሞ ጥቃት ከሰነዘረ ይህን የሰሙ ሁሉ ‘አቢሴሎምን የተከተሉት ሰዎች ድል ተመቱ!’ ብለው ያወራሉ። +10 ልቡ እንደ አንበሳ+ የሆነ ደፋር ሰው እንኳ በፍርሃት መራዱ አይቀርም፤ ምክንያቱም አባትህ ኃያል ተዋጊ፣ አብረውት ያሉትም ሰዎች ጀግኖች+ መሆናቸውን መላው እስራኤል ያውቃል። +11 እንግዲህ እኔ የምመክርህ ይህ ነው፦ ከብዛቱ የተነሳ በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ+ የሆነው ከዳን አንስቶ እስከ ቤርሳቤህ+ ድረስ ያለው የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ወደ አንተ ይሰብሰብ፤ አንተ ራስህም እየመራህ ወደ ውጊያ ውሰዳቸው። +12 እኛም የገባበት ገብተን ጥቃት እንሰነዝርበታለን፤ በመሬት ላይ እንደሚወርድ ጤዛም እንወርድበታለን፤ እሱም ሆነ ከእሱ ጋር ያሉት ሰዎች አንዳቸውም አያመልጡም። +13 ወደ አንድ ከተማ ቢሸሽ እንኳ መላው እስራኤል ወደ ከተማዋ ገመድ ይዞ በመሄድ፣ ከተማዋን ጎትተን አንዲት ጠጠር ሳናስቀር ሸለቆ ውስጥ እንከታታለን።” +14 ከዚያም አቢሴሎምና የእስራኤል ሰዎች በሙሉ “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የኩሲ ምክር ይሻላል!” አሉ።+ ምክንያቱም ይሖዋ በአቢሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት ሲል ይሖዋ መልካም የሆነውን የአኪጦፌልን+ ምክር ለማክሸፍ ወስኖ* ነበር።+ +15 በኋላም ኩሲ ካህናት የሆኑትን ሳዶቅንና አብያታርን+ እንዲህ አላቸው፦ “አኪጦፌል እንዲህ እንዲህ በማለት አቢሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች መክሯቸው ነበር፤ እኔ ደግሞ እንዲህ እንዲህ ብዬ መክሬያቸዋለሁ። +16 አሁንም ለዳዊት ፈጥናችሁ መልእክት በመላክ እንዲህ ብላችሁ አስጠንቅቁት፦ ‘ዛሬ ሌሊት በምድረ በዳው ባሉት መልካዎች* እንዳታድር፤ የግድ መሻገር አለብህ፤ አለዚያ ንጉሡና አብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ያልቃል።’”*+ +17 ዮናታንና+ አኪማዓስም+ በኤንሮጌል+ ተቀምጠው ነበር፤ በመሆኑም አንዲት አገልጋይ ሄዳ መልእክቱን ነገረቻቸው፤ እነሱም ሁኔታውን ለንጉሥ ዳዊት ለመንገር ሄዱ። ምክንያቱም ወደ ከተማዋ ከገባን እንታያለን ብለው ፈርተው ነበር። +18 ይሁንና አንድ ወጣት አያቸውና ለአቢሴሎም ነገረው። ስለሆነም ሁለቱም በፍጥነት ከዚያ በመሄድ በባሁሪም+ ወደሚገኝ አንድ ሰው ቤት መጡ፤ እሱም ግቢው ውስጥ የውኃ ጉድጓድ ነበረው። እነሱም እዚያ ውስጥ ገቡ፤ +19 የሰውየውም ሚስት በጉድጓዱ አፍ ላይ ማስጫ ዘርግታ የተከካ እህል አሰጣችበት፤ ይህን ያወቀ ማንም ሰው አልነበረም። +20 የአቢሴሎም አገልጋዮችም ወደ ሴትየዋ ቤት መጥተው “አኪማዓስና ዮናታን የት አሉ?” አሏት። እሷም “በዚህ አልፈው ወደ ወንዙ ሄደዋል” አለቻቸው።+ ሰዎቹም ፍለጋቸውን ቀጠሉ፤ ሆኖም ሊያገኟቸው አልቻሉም፤ ስለዚህ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። +21 ሰዎቹ ከሄዱም በኋላ አኪማዓስና ዮናታን ከጉድጓዱ ወጥተው ወደ ንጉሥ ዳዊት በመሄድ “እናንተ ሰዎች፣ ተነስታችሁ በፍጥነት ወንዙን ተሻገሩ፤ ምክንያቱም አኪጦፌል ስለ እናንተ እንዲህ እንዲህ የሚል ምክር ሰጥቷል” አሉት።+ +22 ዳዊትና አብሮት የነበረው ሕዝብ በሙሉ ወዲያውኑ ተነስተው ዮርዳኖስን ተሻገሩ። ጎህ ሲቀድም ዮርዳኖስን ሳይሻገር የቀረ አንድም ሰው አልነበረም። +23 አኪጦፌል፣ የሰጠው ምክር ተቀባይነት እንዳላገኘ ሲያይ አህያውን ጭኖ በሚኖርባት ከተማ ወደሚገኘው ቤቱ ሄደ።+ ከዚያም ለቤተሰቡ አንዳንድ መመሪያዎችን ከሰጠ+ በኋላ ታንቆ ሞተ።+ በአባቶቹም የመቃብር ቦታ ተቀበረ። +24 ይህ በእንዲህ እንዳለ ዳዊት ወደ ማሃናይም+ ሄደ፤ አቢሴሎም ደግሞ ከእስራኤል ሰዎች ሁሉ ጋር ዮርዳኖስን ተሻገረ። +25 አቢሴሎም በኢዮዓብ+ ቦታ አሜሳይን+ በሠራዊቱ ላይ ሾመው፤ አሜሳይ የእስራኤላዊው የይትራ ልጅ ነበር፤ ይትራ የኢዮዓብ እናት ከሆነችው ከጽሩያ እህት ከአቢጋኤል+ ጋር ግንኙነት ነበረው፤ አቢጋኤል የናሃሽ ልጅ ነበረች። +26 እስራኤላውያንና አቢሴሎም በጊልያድ+ ምድር ሰፈሩ። +27 ዳዊት ማሃናይም ሲደርስ የአሞናውያን ከተማ ከሆነችው ከራባ+ የመጣው የናሃሽ ልጅ ሾባይ፣ ከሎደባር የመጣው የአሚዔል ልጅ ማኪርና+ ከሮገሊም የመጣው ጊልያዳዊው ቤርዜሊ+ +28 ለመኝታ የሚሆኑ ነገሮች፣ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ የሸክላ ዕቃዎች፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ዱቄት፣ ቆሎ፣ ባቄላ፣ ምስር፣ የተጠበሰ እሸት፣ +29 ማር፣ ቅቤ፣ በግና አይብ* ይዘው መጡ። ይህን ሁሉ ይዘው የመጡት “መቼም ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፣ ደክሟል፣ ተጠምቷል” ብለው በማሰብ ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች እንዲበሉት ነው።+ +18 ከዚያም ዳዊት አብረውት የነበሩትን ሰዎች ቆጠረ፤ በእነሱም ላይ የሺህ አለቆችና የመቶ አለቆች ሾመ።+ +2 በተጨማሪም ዳዊት ከሰዎቹ መካከል አንድ ሦስተኛውን በኢዮዓብ+ አመራር* ሥር፣ አንድ ሦስተኛውን ደግሞ የኢዮዓብ ወንድም በሆነው በጽሩያ+ ልጅ በአቢሳ+ አመራር ሥር እንዲሁም አንድ ሦስተኛውን በጌታዊው በኢታይ+ አመራር ሥር አድርጎ ላከ። ንጉሡም ሰዎቹን “እኔም አብሬያችሁ እወጣለሁ” አላቸው። +3 እነሱ ግን እንዲህ አሉት፦ “አንተማ መውጣት የለብህም፤+ ለመሸሽ ብንገደድ እንኳ እነሱ ስለ እኛ ደንታ አይሰጣቸውም፤* ግማሾቻችን ብንሞትም ግድ የላቸውም፤ ምክንያቱም አንተ ከእኛ ከአሥሩ ሺህ ትበልጣለህ።+ ስለዚህ ከተማው ውስጥ ሆነህ ድጋፍ ብትሰጠን ይሻላል።” +4 ንጉሡም “እሺ፣ እናንተ የተሻለ ነው ያላችሁትን አደርጋለሁ” አላቸው። በመሆኑም ንጉሡ በከተማዋ በር አጠገብ ቆመ፤ ሰዎቹም ሁሉ በመቶዎችና በሺዎች እየሆኑ ወጡ። +5 ንጉሡም ኢዮዓብን፣ አቢሳንና ኢታይን “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ በአቢሴሎም ላይ አትጨክኑበት” ሲል አዘዛቸው።+ ንጉሡ አቢሴሎምን አስመልክቶ ለአለቆቹ በሙሉ ትእዛዝ ሲሰጥ ሰዎቹ ሁሉ ሰሙ። +6 ሰዎቹም ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት ወደ ሜዳው ወጡ፤ ውጊያውም በኤፍሬም ጫካ ውስጥ ተካሄደ።+ +"7 በዚያም የእስራኤል ሰዎች+ በዳዊት አገልጋዮች ድል ተመቱ፤+ በዚያም ቀን ታላቅ እልቂት ሆነ፤ ከመካከላቸውም 20,000 ሰው ተገደለ።" +8 ውጊያውም በአካባቢው ሁሉ ተዛመተ። በዚያን ቀን ሰይፍ ከበላው ይልቅ ጫካ የበላው ሰው በለጠ። +9 በኋላም አቢሴሎም ከዳዊት አገልጋዮች ጋር ድንገት ተገናኘ። አቢሴሎም በበቅሎ ላይ ተቀምጦ ይሄድ ነበር፤ በቅሎዋም ጥቅጥቅ ያለ ቅርንጫፍ ባለው አንድ ትልቅ ዛፍ ሥር ስታልፍ ዛፉ የአቢሴሎምን ፀጉር ያዘው፤ በመሆኑም የተቀመጠባት በቅሎ ስታልፍ እሱ አየር ላይ* ተንጠልጥሎ ቀረ። +10 ከዚያም አንድ ሰው ይህን አይቶ ለኢዮዓብ+ “አቢሴሎምን አንድ ትልቅ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት!” ብሎ ነገረው። +11 በዚህ ጊዜ ኢዮዓብ ይህን የነገረውን ሰው “እና ካየኸው ያኔውኑ መትተህ መሬት ላይ ያልጣልከው ለምንድን ነው? እንዲህ ብታደርግ ኖሮ አሥር ሰቅል ብርና ቀበቶ እሸልምህ ነበር” አለው። +"12 ሰውየው ግን ኢዮዓብን እንዲህ አለው፦ “1,000 የብር ሰቅል ቢሰጠኝ* እንኳ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሳም፤ ምክንያቱም ንጉሡ አንተን፣ አቢሳንና ኢታይን ‘ማናችሁም ብትሆኑ በወጣቱ በአቢሴሎም ላይ ጉዳት እንዳታደርሱበት ተጠንቀቁ’ ብሎ ሲያዛችሁ ሰምተናል።+" +13 ትእዛዙን በመተላለፍ የልጁን ሕይወት አጥፍቼ* ቢሆን ኖሮ ይህ ጉዳይ ከንጉሡ ተሰውሮ ሊቀር አይችልም ነበር፤ አንተም ብትሆን ልታስጥለኝ አትችልም።” +14 ኢዮዓብም “ከዚህ በላይ ከአንተ ጋር ጊዜ አላጠፋም!” አለው። ከዚያም ሦስት ቀስቶች* ይዞ በመሄድ አቢሴሎም በትልቁ ዛፍ መሃል ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ቀስቶቹን ልቡ ላይ ሰካቸው። +15 ከዚያም ከኢዮዓብ ጋሻ ጃግሬዎች አሥሩ መጥተው አቢሴሎምን መትተው ገደሉት።+ +16 ኢዮዓብም ቀንደ መለከት ነፋ፤ ሰዎቹም እስራኤላውያንን ከማሳደድ ተመለሱ፤ በዚህ መንገድ ኢዮዓብ ሰዎቹን አስቆማቸው። +17 እነሱም አቢሴሎምን ወስደው ጫካው ውስጥ በሚገኝ አንድ ትልቅ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በላዩም ላይ በጣም ትልቅ የድንጋይ ቁልል ከመሩበት።+ እስራኤላውያንም በሙሉ ወደየቤታቸው ሸሹ። +18 አቢሴሎም በሕይወት ሳለ “ስሜ የሚታወስበት ልጅ የለኝም”+ በማለት በንጉሡ ሸለቆ*+ ለራሱ ዓምድ አቁሞ ነበር። ዓምዱንም በራሱ ስም ሰይሞት ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ የአቢሴሎም ሐውልት በመባል ይጠራል። +19 የሳዶቅ ልጅ አኪማዓስም+ “ይሖዋ ንጉሡን ከጠላቶቹ እጅ ነፃ በማውጣት ስለፈረደለት+ እባክህ እየሮጥኩ ሄጄ ወሬውን ልንገረው” አለ። +20 ኢዮዓብ ግን “ዛሬ ወሬውን የምትነግረው አንተ አይደለህም። ወሬውን ሌላ ቀን ትነግረዋለህ፤ የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ ዛሬ ወሬውን መናገር የለብህም” አለው።+ +21 ከዚያም ኢዮዓብ አንድ ኩሻዊ+ ጠርቶ “ሂድ፣ ያየኸውን ነገር ለንጉሡ ንገረው” አለው። በዚህ ጊዜ ኩሻዊው ለኢዮዓብ ከሰገደ በኋላ እየሮጠ ሄደ። +22 የሳዶቅ ልጅ አኪማዓስም እንደገና ኢዮዓብን “እባክህ፣ የመጣው ይምጣ እኔም ኩሻዊውን ተከትዬ ልሩጥ” አለው። ሆኖም ኢዮዓብ “ልጄ ሆይ፣ የምትናገረው ነገር ሳይኖር ለምን ትሮጣለህ?” አለው። +23 እሱ ግን አሁንም “ምንም ይሁን ምን፣ እባክህ ልሩጥ” አለው። ስለዚህ ኢዮዓብ “በቃ ሩጥ!” አለው። አኪማዓስም የዮርዳኖስን አውራጃ* አቋርጦ የሚያልፈውን መንገድ ይዞ መሮጥ ጀመረ፤ በኋላም ኩሻዊውን አልፎት ሄደ። +24 በዚህ ጊዜ ዳዊት በሁለቱ የከተማዋ በሮች+ መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂውም+ ከቅጥሩ ጋር ተያይዞ ወደተሠራው የበሩ ሰገነት ወጣ። ቀና ብሎም ሲመለከት ብቻውን የሚሮጥ አንድ ሰው አየ። +25 ጠባቂውም ተጣርቶ ይህንኑ ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም “ብቻውን ከሆነ ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ። ሰውየውም እየቀረበ ሲመጣ +26 ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ ተመለከተ። በመሆኑም የበር ጠባቂውን ተጣርቶ “ይኸው ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለው። ንጉሡም “ይህም ሰው ቢሆን ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ። +27 ጠባቂውም “የመጀመሪያው ሰው አሯሯጥ የሳዶቅን ልጅ የአኪማዓስን+ አሯሯጥ ይመስላል” አለ፤ በመሆኑም ንጉሡ “እሱማ ጥሩ ሰው ነው፤ ምሥራች ሳይዝ አይመጣም” አለው። +28 አኪማዓስም ንጉሡን ተጣርቶ “ሁሉም ነገር ሰላም ነው!” አለው። ከዚያም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ ሰገደ። ቀጥሎም “በጌታዬ በንጉሡ ላይ ያመፁትን* ሰዎች አሳልፎ የሰጠህ አምላክህ ይሖዋ ይወደስ!” አለ።+ +29 ሆኖም ንጉሡ “ለመሆኑ ወጣቱ አቢሴሎም ደህና ነው?” አለው። በዚህ ጊዜ አኪማዓስ “ኢዮዓብ የንጉሡን አገልጋይና እኔን አገልጋይህን በላከ ጊዜ ከፍተኛ ትርምስ አይቻለሁ፤ ምን እንደሆነ ግን አላወቅኩም” አለ።+ +30 ንጉሡም “እሺ፣ እልፍ በልና እዚያ ቁም” አለው። እሱም እልፍ ብሎ ቆመ። +31 ከዚያም ኩሻዊው ደረሰ፤+ እሱም “ጌታዬ ንጉሡ፣ ያመጣሁትን ይህን ወሬ ይስማ፦ ዛሬ ይሖዋ፣ በአንተ ላይ ካመፁብህ ሰዎች ሁሉ እጅ ነፃ በማውጣት ፈርዶልሃል” አለ።+ +32 ይሁንና ንጉሡ ኩሻዊውን “ለመሆኑ ወጣቱ አቢሴሎም ደህና ነው?” አለው። በዚህ ጊዜ ኩሻዊው “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶች ሁሉና በአንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ ያመፁብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ!” አለ።+ +33 ይህም ንጉሡን ረበሸው፤ በውጭው በር ሰገነት ላይ ወዳለው ክፍ���ም ወጥቶ አለቀሰ፤ ወዲያ ወዲህ እያለም “ልጄ አቢሴሎም፣ ልጄ፣ ልጄ አቢሴሎም! ምነው በአንተ ፋንታ እኔ በሞትኩ፤ ልጄ አቢሴሎም፣ ልጄ!” ይል ነበር።+ +23 የዳዊት የመጨረሻ ቃላት እነዚህ ናቸው፦+ “የእሴይ ልጅ የዳዊት ቃል፣+ከፍ ከፍ የተደረገው ሰው ቃል፣+የያዕቆብ አምላክ የቀባው፣+የእስራኤል መዝሙሮች ተወዳጅ ዘማሪ።*+ + 2 የይሖዋ መንፈስ በእኔ ተናገረ፤+ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።+ + 3 የእስራኤል አምላክ ተናገረ፣የእስራኤል ዓለት+ እንዲህ አለኝ፦ ‘የሰው ልጆችን የሚገዛው ጻድቅ ሲሆን፣+አምላክን በመፍራት ሲገዛ፣+ + 4 ፀሐይ በምትፈነጥቅበት ጊዜ እንደሚኖረው የማለዳ ብርሃን፣+ደመና እንደሌለበት ማለዳ ይሆናል። ሣርን ከምድር እንደሚያበቅል፣+ዝናብ ካባራ በኋላ ፍንትው ብሎ እንደሚወጣ የፀሐይ ብርሃን ነው።’ + 5 የእኔስ ቤት በአምላክ ፊት እንዲሁ አይደለም? እሱ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ገብቷልና፤+ቃል ኪዳኑም የተስተካከለና አስተማማኝ ነው። ምክንያቱም ይህ ለእኔ የተሟላ መዳንና ፍጹም ደስታ ነው፤ደግሞስ ቤቴ እንዲለመልም የሚያደርገው ለዚህ አይደለም?+ + 6 የማይረቡ ሰዎች ሁሉ ልክ እንደ እሾህ ቁጥቋጦ ወዲያ ይጣላሉ፤+በእጅ ሊሰበሰቡ አይችሉምና። + 7 የሚነካቸው ሰውየብረት መሣሪያ መታጠቅና የጦር ዘንግ መያዝ አለበት፤እነሱም ባሉበት ሙሉ በሙሉ በእሳት መቃጠል አለባቸው።” +8 የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች+ ስም ይህ ነው፦ የሦስቱ መሪ+ የሆነው ታህክሞናዊው ዮሼብባሼቤት። እሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ጊዜ 800 ሰው ገደለ። +9 ከእሱ ቀጥሎ የአሆሐይ ልጅ የሆነው የዶዶ+ ልጅ አልዓዛር+ ነበር፤ እሱም ፍልስጤማውያንን በተገዳደሩበት ጊዜ ከዳዊት ጋር ከነበሩት ሦስት ኃያላን ተዋጊዎች አንዱ ነው። ፍልስጤማውያንም በዚያ ለጦርነት ተሰብስበው ነበር፤ የእስራኤል ሰዎች ባፈገፈጉ ጊዜ +10 እሱ ካለበት ንቅንቅ ሳይል እጁ እስኪዝልና ከጨበጠው ሰይፍ ላይ መላቀቅ እስኪያቅተው ድረስ ፍልስጤማውያንን ጨፈጨፋቸው።+ በመሆኑም ይሖዋ በዚያ ቀን ታላቅ ድል አጎናጸፈ፤*+ ሕዝቡም ከተገደሉት ሰዎች ላይ ለመግፈፍ ከእሱ ኋላ ተመልሶ መጣ። +11 ከእሱ ቀጥሎ የሃራራዊው የአጌ ልጅ ሻማህ ነበር። ፍልስጤማውያን ሊሃይ በተባለ ስፍራ ምስር በሞላበት አንድ ማሳ ውስጥ ተሰብስበው ነበር፤ ሕዝቡም በፍልስጤማውያን የተነሳ ሸሸ። +12 እሱ ግን በእርሻው መካከል ካለበት ንቅንቅ ሳይል መሬቱ እንዳይያዝ አደረገ፤ ፍልስጤማውያንንም መታቸው፤ በመሆኑም ይሖዋ ታላቅ ድል አጎናጸፈ።*+ +13 በመከር ወቅት ከ30ዎቹ መሪዎች መካከል ሦስቱ ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ አዱላም+ ዋሻ ወረዱ፤ አንድ የፍልስጤማውያን ቡድንም* በረፋይም ሸለቆ*+ ሰፍሮ ነበር። +14 በዚህ ጊዜ ዳዊት በምሽጉ+ ውስጥ ነበር፤ የፍልስጤማውያንም የጦር ሰፈር በቤተልሔም ነበር። +15 ከዚያም ዳዊት “በቤተልሔም በር አቅራቢያ ካለው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ የምጠጣው ውኃ ባገኝ ምንኛ ደስ ባለኝ!” በማለት ምኞቱን ገለጸ። +16 በዚህ ጊዜ ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች ወደ ፍልስጤማውያን ሰፈር ጥሰው በመግባት በቤተልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውኃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ እሱ ግን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ውኃውን ለይሖዋ አፈሰሰው።+ +17 ከዚያም “ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ማድረግ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው! ሕይወታቸውን* አደጋ ላይ ጥለው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም ልጠጣ ይገባል?”+ አለ። በመሆኑም ውኃውን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም። ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎቹ ያደረጓቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ። +18 የጽሩያ+ ልጅ የኢዮዓብ ወንድም አቢሳ+ የሌሎች ሦስት ሰዎች መሪ ነበር፤ እሱም ጦሩን ሰብቆ 300 ሰ�� ገደለ፤ እንደ ሦስቱም ሰዎች ዝነኛ ነበር።+ +19 ምንም እንኳ ከሌሎቹ ሦስት ሰዎች ይበልጥ ታዋቂና የእነሱ አለቃ የነበረ ቢሆንም የመጀመሪያዎቹን ሦስት ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም። +20 የዮዳሄ ልጅ በናያህ+ በቃብጽኤል+ ብዙ ጀብዱ የፈጸመ ደፋር ሰው* ነበር። እሱም የሞዓቡን የአርዔልን ሁለት ወንዶች ልጆች ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በሚጥልበት ዕለት ወደ አንድ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።+ +21 በተጨማሪም እጅግ ግዙፍ የሆነ ግብፃዊ ገደለ። ግብፃዊው በእጁ ጦር ይዞ የነበረ ቢሆንም እሱ ግን በትር ብቻ ይዞ በመሄድ ገጠመው፤ የግብፃዊውንም ጦር ከእጁ ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደለው። +22 የዮዳሄ ልጅ በናያህ ያደረጋቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ፤ እሱም እንደ ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች ዝነኛ ነበር። +23 ከሠላሳዎቹ ይበልጥ ታዋቂ የነበረ ቢሆንም የሦስቱን ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም። ይሁን እንጂ ዳዊት የራሱ የክብር ዘብ አለቃ አድርጎ ሾመው። +24 የኢዮዓብ ወንድም አሳሄል+ ከሠላሳዎቹ አንዱ ነበር፤ ከኃያላኑ ሰዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የቤተልሔሙ+ የዶዶ ልጅ ኤልሃናን፣ +25 ሃሮዳዊው ሻማህ፣ ሃሮዳዊው ኤሊቃ፣ +26 ጳሌጣዊው ሄሌጽ፣+ የተቆአዊው የኢቄሽ ልጅ ኢራ፣+ +27 አናቶታዊው+ አቢዔዜር፣+ ሁሻዊው መቡናይ፣ +28 አሆሐያዊው ጻልሞን፣ ነጦፋዊው ማህራይ፣+ +29 የነጦፋዊው የባአናህ ልጅ ሄሌብ፣ ከቢንያማውያን የጊብዓው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣ +30 ጲራቶናዊው በናያህ፣+ የጋአሽ+ ደረቅ ወንዞች* ሰው የሆነው ሂዳይ፣ +31 አርባዊው አቢዓልቦን፣ ባርሁማዊው አዝማዌት፣ +32 ሻአልቢማዊው ኤሊያህባ፣ የያሼን ልጆች፣ ዮናታን፣ +33 ሃራራዊው ሻማህ፣ የሃራራዊው የሻራር ልጅ አሂዓም፣ +34 የማአካታዊው ልጅ፣ የአሃስባይ ልጅ ኤሊፌሌት፣ የጊሎአዊው የአኪጦፌል+ ልጅ ኤሊያም፣ +35 ቀርሜሎሳዊው ሄጽሮ፣ ዓረባዊው ፓአራይ፣ +36 የጾባህዊው የናታን ልጅ ይግዓል፣ ጋዳዊው ባኒ፣ +37 አሞናዊው ጼሌቅ፣ የጽሩያ ልጅ የኢዮዓብ ጋሻ ጃግሬ በኤሮታዊው ናሃራይ፣ +38 ይትራዊው ኢራ፣ ይትራዊው+ ጋሬብ +39 እንዲሁም ሂታዊው ኦርዮ፤+ በአጠቃላይ 37 ነበሩ። +19 ለኢዮዓብ “ንጉሡ ለአቢሴሎም እያለቀሰና እያዘነ ነው” ተብሎ ተነገረው።+ +2 ሕዝቡ ሁሉ ንጉሡ በልጁ ምክንያት ማዘኑን ሲሰማ ያን ዕለት የተገኘው ድል* ወደ ሐዘን ተለወጠ። +3 በዚያን ቀን ሕዝቡ ከጦርነት በመሸሹ ምክንያት በኀፍረት እንደተሸማቀቀ ሕዝብ ድምፁን አጥፍቶ ወደ ከተማዋ ገባ።+ +4 ንጉሡም ፊቱን ተከናንቦ “ልጄ አቢሴሎም! ልጄ አቢሴሎም፣ ልጄ!” እያለ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያለቅስ ነበር።+ +5 ከዚያም ኢዮዓብ ቤቱ ውስጥ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ገብቶ እንዲህ አለው፦ “በዛሬው ዕለት የአንተን፣ የወንዶች ልጆችህን፣+ የሴቶች ልጆችህን፣+ የሚስቶችህንና የቁባቶችህን+ ሕይወት* የታደጉትን አገልጋዮችህን ሁሉ አሳፍረሃቸዋል። +6 አንተ የሚጠሉህን ትወዳለህ፣ የሚወዱህን ደግሞ ትጠላለህ፤ የጦር አለቆችህም ሆኑ አገልጋዮችህ ለአንተ ምንህም እንዳይደሉ ይኸው ዛሬ በግልጽ አሳይተሃል፤ በዛሬው ቀን አቢሴሎም ብቻ በሕይወት ተርፎ እኛ ሁላችን አልቀን ቢሆን ኖሮ ደስ ይልህ እንደነበር እርግጠኛ ነኝ። +7 በል አሁን ተነስተህ ውጣና አገልጋዮችህን አበረታታቸው፤* ባትወጣ ግን በይሖዋ እምላለሁ፣ ዛሬ አንድም ሰው አብሮህ አያድርም። ይህ ደግሞ ከልጅነትህ አንስቶ እስካሁን ድረስ ከደረሰብህ ጉዳት ሁሉ የከፋ ይሆናል።” +8 በመሆኑም ንጉሡ ተነስቶ በከተማዋ በር አጠገብ ተቀመጠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ “ንጉሡ በሩ አጠገብ ተቀምጧል” ተብሎ ተነገረው። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ንጉሡ መጣ። እስራኤላውያን ግን ወደየቤታቸው ሸሽተው ነበር።+ +9 በመላው የ���ስራኤል ነገዶች መካከል ያለው ሕዝብ እንዲህ በማለት ይከራከር ነበር፦ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን አዳነን፤+ ከፍልስጤማውያንም ታደገን፤ አሁን ግን በአቢሴሎም የተነሳ ከአገሩ ሸሽቶ ሄዷል።+ +10 በላያችን እንዲነግሥ የቀባነው+ አቢሴሎም እንደሆነ በውጊያው ሞቷል።+ ታዲያ ንጉሡን ለመመለስ አንድ ነገር የማታደርጉት ለምንድን ነው?” +11 ንጉሥ ዳዊት ለካህናቱ ለሳዶቅና+ ለአብያታር+ እንዲህ የሚል መልእክት ላከባቸው፦ “የይሁዳን ሽማግሌዎች+ እንዲህ በሏቸው፦ ‘እስራኤላውያን በሙሉ የተናገሩት ነገር በቤቱ ውስጥ ወዳለው ወደ ንጉሡ ደርሶ ሳለ እናንተ ንጉሡን ወደ ቤቱ ለመመለስ እንዴት የመጨረሻዎቹ ሰዎች ትሆናላችሁ? +12 እናንተ ወንድሞቼ ናችሁ፤ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቁራጭ* ናችሁ። ታዲያ ንጉሡን ለመመለስ እንዴት የመጨረሻዎቹ ሰዎች ትሆናላችሁ?’ +13 አሜሳይንም+ ‘አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቁራጭ አይደለህም? ከአሁን ጀምሮ በኢዮዓብ+ ምትክ የሠራዊቴ አለቃ ባትሆን አምላክ እንዲህ ያድርግብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጣብኝ’ በሉት።” +14 በመሆኑም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ልብ ልክ እንደ አንድ ሰው ልብ ማረከ፤* እነሱም ወደ ንጉሡ “አንተም ሆንክ አገልጋዮችህ በሙሉ ተመለሱ” የሚል መልእክት ላኩበት። +15 ንጉሡም ለመመለስ ጉዞ ጀመረ፤ እስከ ዮርዳኖስም ድረስ መጣ፤ የይሁዳም ሰዎች ንጉሡን ለመቀበልና እስከ ዮርዳኖስ ማዶ ድረስ ለመሸኘት ወደ ጊልጋል+ መጡ። +16 የባሁሪም ሰው የሆነው ቢንያማዊው የጌራ ልጅ ሺምአይ+ ንጉሥ ዳዊትን ለማግኘት ከይሁዳ ሰዎች ጋር በፍጥነት ወረደ፤ +"17 ከእሱም ጋር ከቢንያም የመጡ 1,000 ሰዎች ነበሩ። በተጨማሪም የሳኦል ቤት አገልጋይ የሆነው ሲባ+ ከ15 ወንዶች ልጆቹና ከ20 አገልጋዮቹ ጋር በመሆን ከንጉሡ ቀድሞ በፍጥነት ወደ ዮርዳኖስ ወረደ።" +18 እሱም* የንጉሡን ቤተሰብ ለማሻገርና ንጉሡ ደስ የሚያሰኘውን ለማድረግ መልካውን* ተሻገረ። የጌራ ልጅ ሺምአይ ግን ንጉሡ ዮርዳኖስን ሊሻገር ሲል በፊቱ ተደፋ። +19 ንጉሡንም እንዲህ አለው፦ “ጌታዬ በደሌን አይቁጠርብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም በወጣበት ቀን አገልጋይህ የፈጸመውን በደል አያስብ።+ ንጉሡም በልቡ አይያዘው፤ +20 ምክንያቱም እኔ አገልጋይህ ኃጢአት እንደሠራሁ በሚገባ አውቃለሁ፤ በመሆኑም ዛሬ ጌታዬን ንጉሡን ወርጄ ለመቀበል ከመላው የዮሴፍ ቤት ቀድሜ መጥቻለሁ።” +21 በዚህ ጊዜ የጽሩያ+ ልጅ አቢሳ+ “ሺምአይ ይሖዋ የቀባውን በመራገም ለፈጸመው በደል ሞት አይገባውም?” አለ።+ +22 ዳዊት ግን እንዲህ አለ፦ “እናንተ የጽሩያ ልጆች፣+ ይህ ጉዳይ ምን ይመለከታችኋልና ነው ዛሬ እኔን ተቃውማችሁ የተነሳችሁት? በዛሬው ዕለት እስራኤል ውስጥ ሰው መገደል ይገባዋል? በእስራኤል ላይ ንጉሥ መሆኔን ያወቅኩት ዛሬ አይደለም?” +23 ንጉሡ አክሎ ሺምአይን “አይዞህ፣ አትሞትም” አለው። ከዚያም ንጉሡ ማለለት።+ +24 የሳኦል የልጅ ልጅ የሆነው ሜፊቦስቴም+ ንጉሡን ለመቀበል ወረደ። እሱም ንጉሡ ከሄደበት ቀን አንስቶ በሰላም እስከተመለሰበት ዕለት ድረስ ለእግሩ ተገቢውን እንክብካቤ አላደረገም፣ ጢሙን አልተከረከመም፤ ልብሱንም አላጠበም። +25 እሱም ንጉሡን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም* በመጣ ጊዜ ንጉሡ “ሜፊቦስቴ፣ አብረኸኝ ያልሄድከው ለምንድን ነው?” አለው። +26 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ አገልጋዬ+ አታለለኝ። እኔ አገልጋይህ ሽባ+ ስለሆንኩ ‘በአህያዬ ላይ ተቀምጬ ከንጉሡ ጋር እንድሄድ አህያዬን ጫኑልኝ’ ብዬ ነበር። +27 ሆኖም እሱ በጌታዬ በንጉሡ ፊት የእኔን የአገልጋይህን ስም አጥፍቷል።+ ይሁን እንጂ ጌታዬ ንጉሡ እንደ እውነተኛው አምላክ መልአክ ስለሆነ መልካም መስሎ ���ታየህን አድርግ። +28 የአባቴ ቤት በሙሉ በንጉሡ በጌታዬ ሞት ሊፈረድበት ይገባ ነበር፤ አንተ ግን አገልጋይህን ከማዕድህ ከሚበሉት አንዱ አደረግከው።+ ታዲያ ንጉሡን ተጨማሪ ነገር የመጠየቅ ምን መብት አለኝ?” +29 ሆኖም ንጉሡ “ለምን ዝም ብለህ ነገር ታስረዝማለህ? እርሻውን አንተና ሲባ እንድትካፈሉ ወስኛለሁ” አለው።+ +30 በዚህ ጊዜ ሜፊቦስቴ ንጉሡን “ጌታዬ ንጉሡ ወደ ቤቱ እንኳን በሰላም ተመለሰ እንጂ እሱ ሁሉንም ይውሰደው” አለው። +31 ከዚያም ጊልያዳዊው ቤርዜሊ+ ንጉሡን ወደ ዮርዳኖስ ለመሸኘት ከሮገሊም ወደ ዮርዳኖስ ወረደ። +32 ቤርዜሊ የ80 ዓመት አረጋዊ ነበር፤ እጅግ ባለጸጋም ስለነበር ንጉሡ በማሃናይም ይኖር በነበረበት ጊዜ ቀለብ አምጥቶለት ነበር።+ +33 በመሆኑም ንጉሡ ቤርዜሊን “አብረኸኝ ተሻገር፤ እኔም በኢየሩሳሌም ቀለብ እሰጥሃለሁ” አለው።+ +34 ቤርዜሊ ግን ንጉሡን እንዲህ አለው፦ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የምወጣው ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ ነው? +35 አሁን የ80 ዓመት ሰው ነኝ።+ ታዲያ መልካምና መጥፎውን መለየት እችላለሁ? እኔ አገልጋይህ የምበላውንና የምጠጣውን ማጣጣም እችላለሁ? ደግሞስ የወንድና የሴት ዘፋኞችን ድምፅ መስማት እችላለሁ?+ ታዲያ አገልጋይህ ለጌታዬ ለንጉሡ ለምን ተጨማሪ ሸክም ይሆናል? +36 አገልጋይህ ንጉሡን እስከ ዮርዳኖስ ድረስ መሸኘት ከቻለ ይበቃዋል። ታዲያ ንጉሡ ይህን ወሮታ የሚመልስልኝ ለምንድን ነው? +37 እባክህ እኔ አገልጋይህ ልመለስና በገዛ ከተማዬ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ ልሙት።+ ሆኖም አገልጋይህ ኪምሃም+ ይኸውልህ። እሱ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር ይሻገር፤ አንተም መልካም መስሎ የታየህን አድርግለት።” +38 በመሆኑም ንጉሡ “እንግዲያው ኪምሃም አብሮኝ ይሻገራል፤ እኔም መልካም መስሎ የታየህን አደርግለታለሁ፤ ለአንተም የምትጠይቀኝን ማንኛውንም ነገር አደርግልሃለሁ” አለው። +39 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን መሻገር ጀመረ፤ ንጉሡም ሊሻገር ሲል ቤርዜሊን ስሞ ባረከው፤+ ቤርዜሊም ወደ ቤቱ ተመለሰ። +40 ንጉሡ ወደ ጊልጋል+ ሲሻገር ኪምሃምም አብሮት ተሻገረ። እንዲሁም የይሁዳ ሰዎች በሙሉና ግማሹ የእስራኤል ሕዝብ ንጉሡን አሻገሩት።+ +41 ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ቀርበው “ወንድሞቻችን የሆኑት የይሁዳ ሰዎች ሹልክ ብለው ይዘውህ በመሄድ ንጉሡንና ቤተሰቡን ከዳዊት ሰዎች ሁሉ ጋር ዮርዳኖስን ያሻገሩት ለምንድን ነው?” አሉት።+ +42 በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የእስራኤልን ሰዎች “ይህን ያደረግነው ንጉሡ ዘመዳችን ስለሆነ ነው።+ ታዲያ ይህ እናንተን ያስቆጣችሁ ለምንድን ነው? በንጉሡ ወጪ የበላነው ነገር አለ? ወይስ ስጦታ መጥቶልን ያውቃል?” አሏቸው። +43 ሆኖም የእስራኤል ሰዎች የይሁዳን ሰዎች እንዲህ አሏቸው፦ “እኛ እኮ ከንጉሡ አሥር እጅ ድርሻ አለን፤ ስለሆነም በዳዊት ላይ ከእናንተ የበለጠ መብት ያለን እኛ ነን። ታዲያ የናቃችሁን ለምንድን ነው? ንጉሣችንን ለመመለስ ቅድሚያ ሊሰጠን አይገባም ነበር?” ይሁንና ከእስራኤል ሰዎች ቃል ይልቅ የይሁዳ ሰዎ +20 በዚህ ጊዜ የቢንያማዊው የቢክሪ ልጅ የሆነ ሳባ+ የሚባል አንድ አስቸጋሪ ሰው ነበር። እሱም ቀንደ መለከት በመንፋት+ “እኛ ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ጋር ምንም ውርሻ የለንም።+ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንድህ ወደ አማልክትህ* ተመለስ!” አለ።+ +2 ስለዚህ የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ዳዊትን መከተል ትተው የቢክሪን ልጅ ሳባን መከተል ጀመሩ፤+ የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንስቶ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ከንጉሣቸው አልተለዩም።+ +3 ዳዊት በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤቱ*+ ሲመጣ ንጉሡ ቤቱን እንዲጠብቁ ትቷቸው ሄዶ የነበሩትን አሥሩን ቁባቶቹን+ ወስዶ በዘብ በሚጠበቅ አንድ ቤት ውስጥ አስገባቸው። በየጊዜው ቀለብ ይሰጣቸው የነበረ ቢሆንም ከእነሱ ጋር ምንም ግንኙነት አልፈጸመም።+ እነሱም ባላቸው በሕይወት ያለ ቢሆንም እስከ ዕለተ ሞታቸ +4 ንጉሡም አሜሳይን+ “የይሁዳን ሰዎች በሦስት ቀን ውስጥ ጠርተህ ወደ እኔ ሰብስብልኝ፤ አንተም እዚህ መገኘት ይኖርብሃል” አለው። +5 ስለዚህ አሜሳይ የይሁዳን ሕዝብ ለመሰብሰብ ሄደ፤ ሆኖም ንጉሡ ከቀጠረለት ጊዜ ዘገየ። +6 ከዚያም ዳዊት አቢሳን+ “ከአቢሴሎም ይልቅ የቢክሪ ልጅ ሳባ+ የከፋ ጉዳት ሊያደርስብን ይችላል።+ ስለሆነም የተመሸጉ ከተሞች አግኝቶ እንዳያመልጠን የጌታህን አገልጋዮች ይዘህ አሳደው” አለው። +7 በመሆኑም የኢዮዓብ+ ሰዎች፣ ከሪታውያን፣ ጴሌታውያን+ እና ኃያላን የሆኑት ሰዎች በሙሉ ተከትለውት ሄዱ፤ የቢክሪን ልጅ ሳባን ለማሳደድም ከኢየሩሳሌም ወጡ። +8 እነሱም በገባኦን+ በሚገኘው ትልቅ ድንጋይ አጠገብ ሲደርሱ አሜሳይ+ ሊገናኛቸው መጣ። ኢዮዓብ የጦር ልብሱን ለብሶ፣ ወገቡም ላይ ሰይፉን ከነሰገባው ታጥቆ ነበር። ወደ ፊት ራመድ ሲልም ሰይፉ ከሰገባው ወደቀ። +9 ኢዮዓብም አሜሳይን “ወንድሜ ሆይ፣ ደህና ነህ?” አለው። ከዚያም ኢዮዓብ የሚስመው አስመስሎ በቀኝ እጁ የአሜሳይን ጢም ያዘ። +10 አሜሳይ፣ በኢዮዓብ እጅ ከነበረው ሰይፍ ራሱን አልጠበቀም፤ ኢዮዓብም በሰይፉ ሆዱ ላይ ወጋው፤+ አንጀቱም መሬት ላይ ተዘረገፈ። ዳግመኛ መውጋት እንኳ ሳያስፈልገው አንዴ ብቻ ወግቶ ገደለው። ከዚያም ኢዮዓብና ወንድሙ አቢሳ የቢክሪን ልጅ ሳባን ማሳደዳቸውን ቀጠሉ። +11 ከኢዮዓብ ወጣቶች መካከል አንዱ አሜሳይ አጠገብ ቆሞ “ከኢዮዓብ ጎን የሚቆምና የዳዊት የሆነ ማንኛውም ሰው ኢዮዓብን ይከተል!” ይል ነበር። +12 በዚህ ጊዜ አሜሳይ መንገዱ መሃል ላይ በደም ተጨማልቆ ይንፈራገጥ ነበር። ሰውየውም ሰዉ ሁሉ እዚያ ሲደርስ እንደሚቆም ሲያይ አሜሳይን ከመንገዱ ላይ ወደ ሜዳው ገለል አደረገው። ይሁንና ሰዉ ሁሉ አሁንም እሱ ጋ ሲደርስ እንደሚቆም ሲያይ ልብስ ጣል አደረገበት። +13 አሜሳይን ከመንገዱ ላይ ካነሳው በኋላ ሰዉ ሁሉ የቢክሪን ልጅ ሳባን+ ለማሳደድ ኢዮዓብን ተከትሎ ሄደ። +14 ሳባም የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ አልፎ ወደ ቤትማዓካዋ አቤል+ ሄደ። ቢክሪያውያንም ተሰብስበው ተከተሉት። +15 ኢዮዓብና ሰዎቹም* መጥተው ሳባን በቤትማዓካዋ አቤል እንዳለ ከበቡት፤ በከተማዋም ዙሪያ የአፈር ቁልል ደለደሉ፤ ከተማዋም በአፈር ቁልሉ መሃል ነበረች። ከኢዮዓብም ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ የከተማዋን ቅጥር ለመጣል ከሥሩ ይሰረስሩ ነበር። +16 ከከተማዋም ውስጥ አንዲት ብልህ ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “ስሙ፣ እናንተ ሰዎች ስሙ! እባካችሁ ኢዮዓብን ‘ወደዚህ ቅረብና ላነጋግርህ’ በሉት” አለች። +17 እሱም ወደ እሷ ቀረበ፤ ከዚያም ሴትየዋ “ኢዮዓብ አንተ ነህ?” አለችው፤ እሱም “አዎ፣ እኔ ነኝ” አላት። በዚህ ጊዜ “አገልጋይህ የምትልህን ስማ” አለችው። እሱም መልሶ “እሺ እየሰማሁ ነው” አላት። +18 እሷም እንዲህ አለች፦ “ቀደም ባሉት ጊዜያት ሰዎች ‘በአቤል ከተማ ይጠይቁ፤ ጉዳያቸውም እልባት ያገኛል’ ይሉ ነበር። +19 እኔ የእስራኤልን ሰላማዊና ታማኝ ሰዎች እወክላለሁ። አንተ በእስራኤል ውስጥ እንደ እናት የሆነችን ከተማ ልትደመስስ ትፈልጋለህ። የይሖዋን ውርሻ የምታጠፋው* ለምንድን ነው?”+ +20 ኢዮዓብም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ከተማዋን ማጥፋትም ሆነ መደምሰስ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው። +21 ነገሩ እንደዚያ አይደለም። ሆኖም ከኤፍሬም ተራራማ አካባቢ+ የመጣውና የቢክሪ ልጅ የሆነው ሳባ+ በንጉሥ ዳዊት ላይ ዓምፆአ��።* ይህን ሰው አሳልፋችሁ ከሰጣችሁኝ ከተማዋን ትቼ እሄዳለሁ።” ከዚያም ሴትየዋ ኢዮዓብን “እንግዲህ የሰውየው ራስ በቅጥሩ ላይ ይወረወርልሃል!” አለችው። +22 ብልህ የሆነችው ሴትም ወዲያውኑ ወደ ሕዝቡ ሄደች፤ እነሱም የቢክሪን ልጅ የሳባን ራስ ቆርጠው ለኢዮዓብ ወረወሩለት። በዚህ ጊዜ ኢዮዓብ ቀንደ መለከት ነፋ፤ እነሱም ከተማዋን ትተው በየአቅጣጫው ተበታተኑ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደቤቱ ሄደ፤+ ኢዮዓብም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ንጉሡ ተመለሰ። +23 ኢዮዓብ የመላው የእስራኤል ሠራዊት አዛዥ ነበር፤+ የዮዳሄ+ ልጅ በናያህ+ ደግሞ በከሪታውያንና በጴሌታውያን+ ላይ የበላይ ነበር። +24 አዶራም+ የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ በተመለመሉት ላይ የበላይ ነበር፤ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ ደግሞ ታሪክ ጸሐፊ ነበር። +25 ሻዌ ጸሐፊ ነበር፤ ሳዶቅና+ አብያታር+ ደግሞ ካህናት ነበሩ። +26 በተጨማሪም ያኢራዊው ኢራ ዋና ኃላፊ* ሆኖ ዳዊትን ያገለግል ነበር። +3 በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል የሚደረገው ውጊያ ለረጅም ጊዜ ዘለቀ፤ ዳዊት እየበረታ+ ሲሄድ የሳኦል ቤት ግን እየተዳከመ+ መጣ። +2 በዚህ መሃል ዳዊት በኬብሮን ወንዶች ልጆች ተወለዱለት።+ የበኩር ልጁ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪኖዓም+ የወለደው አምኖን+ ነበር። +3 ሁለተኛው ልጁ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢጋኤል+ የወለደው ኪልአብ ሲሆን ሦስተኛው ልጁ ደግሞ የገሹር ንጉሥ የታልማይ+ ልጅ የሆነችው የማአካ ልጅ አቢሴሎም+ ነበር። +4 አራተኛው ልጁ የሃጊት ልጅ አዶንያስ፣+ አምስተኛው ልጁ ደግሞ የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያህ ነበር። +5 ስድስተኛው ልጁ ኤግላ ከተባለችው ሚስቱ የወለደው ይትረአም ነበር። እነዚህ ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ናቸው። +6 በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል የነበረው ጦርነት በቀጠለበት ወቅት አበኔር+ በሳኦል ቤት ውስጥ የነበረውን ቦታ እያጠናከረ ሄደ። +7 ሳኦል የአያ ልጅ የሆነች ሪጽፋ+ የተባለች ቁባት ነበረችው። በኋላም ኢያቡስቴ+ አበኔርን “ከአባቴ ቁባት ጋር ግንኙነት የፈጸምከው ለምንድን ነው?” አለው።+ +8 አበኔርም በኢያቡስቴ ንግግር እጅግ ተቆጥቶ እንዲህ አለ፦ “እኔ ከይሁዳ ወገን የሆንኩ የውሻ ጭንቅላት ነኝ? እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ለአባትህ ለሳኦል ቤት፣ ለወንድሞቹና ለቅርብ ወዳጆቹ ታማኝ ፍቅር ከማሳየት ወደኋላ አላልኩም፤ አንተንም ለዳዊት አሳልፌ አልሰጠሁህም፤ ይኸው አንተ ግን ዛሬ በአንዲት ሴት +9 ይሖዋ ለዳዊት እንደማለለት+ ሳላደርግለት ብቀር አምላክ በአበኔር ላይ ይህን ያድርግበት፤ ከዚህ የከፋም ያምጣበት፤ +10 አምላክ መንግሥትን ከሳኦል ቤት እንደሚወስድ እንዲሁም የዳዊትን ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ላይ ከዳን አንስቶ እስከ ቤርሳቤህ+ ድረስ እንደሚያጸና ምሏል።” +11 ኢያቡስቴም አበኔርን ስለፈራው አንዲት ቃል እንኳ ሊመልስለት አልደፈረም።+ +12 አበኔርም ወዲያውኑ ወደ ዳዊት መልእክተኞችን ልኮ “ምድሪቱ የማን ናት? ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን ግባ፤ መላው እስራኤል ከአንተ ጎን እንዲቆም የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ”* አለው።+ +13 እሱም እንዲህ አለው፦ “መልካም! ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ። ብቻ አንድ ነገር እንድታደርግልኝ እጠይቅሃለሁ፤ ወደ እኔ ስትመጣ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን+ ይዘህ ካልመጣህ በቀር ፊቴን እንደማታይ እወቅ” አለው። +14 ከዚያም ዳዊት ለሳኦል ልጅ ለኢያቡስቴ+ “በ100 የፍልስጤማውያን ሸለፈት ያጨኋትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ላከ።+ +15 በመሆኑም ኢያቡስቴ መልእክተኛ ልኮ ሜልኮልን የላይሽ ልጅ ከሆነው ከባሏ ከፓልጢኤል+ ወሰዳት። +16 ባሏ ግን እስከ ባሁሪም+ ድረስ እያለቀሰ ተከትሏት ሄደ። ከዚያ�� አበኔር “በቃ ሂድ፣ ተመለስ!” አለው። እሱም ተመለሰ። +17 ይህ በእንዲህ እንዳለ አበኔር ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “ቀድሞውንም ቢሆን ዳዊት በላያችሁ እንዲነግሥ ትፈልጉ ነበር። +18 ይሖዋ ዳዊትን ‘ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጤማውያንና ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ የምታደገው በአገልጋዬ በዳዊት እጅ ነው’+ ስላለው በሉ አሁን እርምጃ ውሰዱ።” +19 ከዚያም አበኔር ቢንያማውያንን+ አነጋገራቸው። በተጨማሪም አበኔር እስራኤልና መላው የቢንያም ቤት ለማድረግ የተስማሙትን ነገር በኬብሮን ላለው ለዳዊት በግል ሊነግረው ወደ እሱ ሄደ። +20 አበኔር ከ20 ሰዎች ጋር ሆኖ በኬብሮን ወዳለው ወደ ዳዊት ሲመጣ ዳዊት ለአበኔርና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ግብዣ አደረገላቸው። +21 ከዚያም አበኔር ዳዊትን “እስራኤላውያን ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ ተነስቼ ልሂድና ሁሉንም ወደ ጌታዬ ወደ ንጉሡ ልሰብስባቸው፤ አንተም በፈለግከው* ሁሉ ላይ ንጉሥ ትሆናለህ” አለው። በመሆኑም ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ እሱም በሰላም ሄደ። +22 በዚህ ጊዜ የዳዊት አገልጋዮችና ኢዮዓብ በጣም ብዙ ምርኮ ይዘው ከዘመቻ ተመለሱ። አበኔር ግን ዳዊት በሰላም አሰናብቶት ስለሄደ በኬብሮን ከእሱ ጋር አልነበረም። +23 ኢዮዓብና+ አብሮት የነበረው ሠራዊት ሁሉ እዚያ ሲደርስ “የኔር+ ልጅ አበኔር+ ወደ ንጉሡ መጥቶ ነበር፤ ንጉሡም አሰናበተው፤ እሱም በሰላም ሄደ” ብለው ለኢዮዓብ ነገሩት። +24 በመሆኑም ኢዮዓብ ወደ ንጉሡ ገብቶ እንዲህ አለው፦ “ምን ማድረግህ ነው? አበኔር ወደ አንተ መጥቶ ነበር። ታዲያ በሰላም እንዲሄድ ያሰናበትከው ለምንድን ነው? +25 የኔርን ልጅ አበኔርን በሚገባ ታውቀዋለህ! ወደዚህ የመጣው አንተን ለማታለል እንዲሁም መውጫ መግቢያህን ለማወቅና የምታደርገውን ነገር ሁሉ ለመሰለል ነው።” +26 በመሆኑም ኢዮዓብ ከዳዊት ዘንድ ወጥቶ መልእክተኞችን ወደ አበኔር ላከ፤ እነሱም ሲራ ከተባለው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ጋ መለሱት፤ ዳዊት ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም። +27 አበኔር ወደ ኬብሮን+ በተመለሰ ጊዜ ኢዮዓብ ከእሱ ጋር በግል ለመነጋገር ነጠል አድርጎ ወደ ቅጥሩ በር ይዞት ገባ። ሆኖም በዚያ ሳሉ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው፤+ ይህን ያደረገው የወንድሙን የአሳሄልን ደም ለመበቀል ነው።+ +28 ዳዊትም ይህን ሲሰማ እንዲህ አለ፦ “እኔም ሆንኩ መንግሥቴ በኔር ልጅ በአበኔር ደም በይሖዋ ፊት ለዘላለም ተጠያቂ አይደለንም።+ +29 ደሙ በኢዮዓብ ራስና በመላው የአባቱ ቤት ራስ ላይ ይሁን።+ ከኢዮዓብም ቤት ፈሳሽ የሚወጣው+ ሰው ወይም የሥጋ ደዌ+ ያለበት አሊያም እንዝርት የሚያሾር ወንድ* ወይም በሰይፍ የሚወድቅ አሊያም የሚበላው ያጣ ረሃብተኛ አይጥፋ!”+ +30 በመሆኑም ኢዮዓብና ወንድሙ አቢሳ+ በገባኦን በተደረገው ውጊያ ላይ ወንድማቸውን አሳሄልን ስለገደለባቸው+ አበኔርን+ ገደሉት። +31 ከዚያም ዳዊት ኢዮዓብንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች በሙሉ “ልብሳችሁን ቀድዳችሁና ማቅ አሸርጣችሁ ለአበኔር አልቅሱለት” አላቸው። ንጉሥ ዳዊትም ራሱ ከቃሬዛው ኋላ ይሄድ ነበር። +32 አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም በአበኔር መቃብር ላይ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ አለቀሰ። +33 ንጉሡም ለአበኔር ይህን የሐዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፦ “አበኔርም እንደማይረባ ሰው ይሙት? +34 እጆችህ አልታሰሩም፤እግሮችህም እግር ብረት* ውስጥ አልገቡም። በወንጀለኞች* ፊት እንደሚወድቅ ሰው ወደቅክ።”+ በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ለእሱ እንደገና አለቀሱ። +35 በኋላም ሕዝቡ ሁሉ ገና ቀን ሳለ፣ ዳዊትን ለማጽናናት ምግብ* ይዞ መጣ፤ ሆኖም ዳዊት “ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ምግብ ወይም ማንኛውንም ነገር ብቀምስ አምላክ እንዲህ ያድርግብኝ፤ ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣብኝ!” በማለት ማለ።+ +36 ሕዝቡም ሁሉ የሆነውን ነገር ተመለከተ፤ ይህም ደስ አሰኛቸው። ንጉሡ ያደረገው ማንኛውም ነገር እንዳስደሰታቸው ሁሉ ይህም ደስ አሰኛቸው። +37 በመሆኑም ሰዎቹ ሁሉና መላው እስራኤል ንጉሡ በኔር ልጅ በአበኔር ሞት እጁ እንደሌለበት በዚያ ቀን አወቁ።+ +38 ከዚያም ንጉሡ አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ “በዛሬው ዕለት በእስራኤል ውስጥ አለቃና ታላቅ ሰው እንደወደቀ አታውቁም?+ +39 ምንም እንኳ ንጉሥ ሆኜ የተቀባሁ+ ብሆንም እኔ ዛሬ ደካማ ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ+ ልጆች እጅግ ጨካኝ ሆነውብኛል።+ ይሖዋ ለክፉ አድራጊው እንደ ክፋቱ ይመልስለት።”+ +24 ዳዊትንም “ሂድ፣ እስራኤልንና ይሁዳን+ ቁጠር”+ ብሎ በእነሱ ላይ ባነሳሳው* ጊዜ የይሖዋ ቁጣ እንደገና በእስራኤል ላይ ነደደ።+ +2 ንጉሡም ከእሱ ጋር አብሮት የነበረውን የሠራዊቱን አለቃ ኢዮዓብን+ “የሕዝቡን ብዛት እንዳውቅ እስቲ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ+ ባሉት በሁሉም የእስራኤል ነገዶች መካከል ተዘዋውራችሁ ሕዝቡን መዝግቡ” አለው። +3 ኢዮዓብ ግን ንጉሡን “አምላክህ ይሖዋ ሕዝቡን 100 እጥፍ ያብዛው፤ የጌታዬ የንጉሡም ዓይኖች ይህን ይዩ፤ ሆኖም ጌታዬ ንጉሡ ይህን ማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” አለው። +4 ሆኖም የንጉሡ ቃል ኢዮዓብንና የሠራዊቱን አዛዦች አሸነፋቸው። በመሆኑም ኢዮዓብና የሠራዊቱ አዛዦች የእስራኤልን ሕዝብ ለመመዝገብ+ ከንጉሡ ፊት ወጥተው ሄዱ። +5 እነሱም ዮርዳኖስን ተሻግረው በሸለቆ* ውስጥ ከምትገኘው ከተማ በስተ ቀኝ* ባለችው በአሮዔር+ ሰፈሩ፤ ከዚያም ወደ ጋዳውያን፣ ወደ ያዜር+ ሄዱ። +6 በኋላም ወደ ጊልያድና+ ወደ ታህቲምሆድሺ ምድር ሄዱ፤ ከዚያም ወደ ዳንየዓን ቀጠሉ፤ ዞረውም ወደ ሲዶና+ ሄዱ። +7 ከዚያም ወደ ጢሮስ+ ምሽግ እንዲሁም ወደ ሂዋውያንና+ ወደ ከነአናውያን ከተሞች በሙሉ ሄዱ፤ በመጨረሻም በይሁዳ ባለችው በኔጌብ+ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ+ መጡ። +8 በዚህ መንገድ በመላው ምድር ሲዘዋወሩ ቆይተው ከዘጠኝ ወር ከሃያ ቀን በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። +"9 ኢዮዓብም የተመዘገበውን የሕዝቡን ቁጥር ለንጉሡ ሰጠው። በእስራኤል ውስጥ ሰይፍ የታጠቁ 800,000 ተዋጊዎች ነበሩ፤ የይሁዳ ሰዎች ደግሞ 500,000 ነበሩ።+ " +10 ሆኖም ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ልቡ* ወቀሰው።+ ከዚያም ዳዊት ይሖዋን “ይህን በማድረጌ ከባድ ኃጢአት ሠርቻለሁ።+ አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤+ ታላቅ የሞኝነት ድርጊት ፈጽሜአለሁና” አለው።+ +11 ዳዊት ጠዋት ላይ ሲነሳ እንዲህ የሚል የይሖዋ ቃል የዳዊት ባለ ራእይ ወደሆነው ወደ ነቢዩ ጋድ+ መጣ፦ +12 “ሂድና ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ “ሦስት ምርጫዎችን ሰጥቼሃለሁ። በአንተ ላይ አመጣብህ ዘንድ አንዱን ምረጥ” ይላል።’”+ +13 ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ገብቶ እንዲህ አለው፦ “በምድርህ ላይ ለሰባት ዓመት ረሃብ+ ይሁን ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ለሦስት ወር ከእነሱ ብትሸሽ ይሻልሃል?+ ወይስ ደግሞ በምድርህ ላይ ለሦስት ቀን ቸነፈር ይምጣ?+ እንግዲህ አሁን ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ በጥሞና አስብበት።” +14 ስለዚህ ዳዊት ጋድን “ሁኔታው በጣም አስጨንቆኛል። ምሕረቱ ታላቅ ስለሆነ+ እባክህ በይሖዋ እጅ እንውደቅ፤+ ሰው እጅ ላይ ግን አትጣለኝ”+ አለው። +"15 ከዚያም ይሖዋ ከጠዋት አንስቶ እስከተወሰነው ጊዜ ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር ላከ፤+ በዚህም የተነሳ ከዳን አንስቶ እስከ ቤርሳቤህ+ ድረስ ካለው ሕዝብ መካከል 70,000 ሰዎች ሞቱ።+" +16 መልአኩም ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን ወደ እሷ በዘረጋ ጊዜ ይሖዋ በደረሰው ጥፋት ተጸጸተ፤*+ በመሆኑም በሕዝቡ ላይ ጥፋት እያመጣ የነበረውን መልአክ “ይብቃ! አሁን እጅህን መልስ” አለው። የይሖዋ መልአክ በኢያቡሳዊው+ በአረውና+ አውድማ አጠገብ ነበር። +17 ዳዊትም ሕዝቡን እየገደለ ያለውን መልአክ ሲያይ ይሖዋን “ኃጢአት የሠራሁት እኮ እኔ ነኝ፤ ያጠፋሁትም እኔ ነኝ፤ ታዲያ እነዚህ በጎች+ ምን አደረጉ? እባክህ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን”+ አለው። +18 በመሆኑም ጋድ በዚያው ቀን ወደ ዳዊት መጥቶ “ውጣና በኢያቡሳዊው በአረውና አውድማ ላይ ለይሖዋ መሠዊያ ሥራ” አለው።+ +19 ስለዚህ ዳዊት፣ ጋድ በነገረው መሠረት ይሖዋ እንዳዘዘው ተነስቶ ወጣ። +20 አረውናም ቁልቁል ሲመለከት ንጉሡና አገልጋዮቹ ወደ እሱ ሲመጡ አየ፤ እሱም ወዲያውኑ ወጥቶ በግንባሩ መሬት ላይ በመደፋት ለንጉሡ ሰገደ። +21 ከዚያም አረውና “ጌታዬ ንጉሡ ወደ አገልጋዩ የመጣው ለምንድን ነው?” አለው። ዳዊትም “በሕዝቡ ላይ እየወረደ ያለው መቅሰፍት እንዲቆም+ ለይሖዋ መሠዊያ ለመሥራት ይህን አውድማ ከአንተ ላይ ለመግዛት ነው” አለው። +22 አረውና ግን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ጌታዬ ንጉሡ አውድማውን ወስዶ መልካም መስሎ የታየውን ነገር ያቅርብበት። ለሚቃጠል መባ የሚሆኑት ከብቶች እነዚሁልህ፣ ማሄጃውና* ከብቶቹ ላይ የሚውሉት መሣሪያዎች ደግሞ ለማገዶ ይሁኑ። +23 ንጉሥ ሆይ፣ አረውና እነዚህን ሁሉ ለንጉሡ ሰጥቷል።” አክሎም አረውና ንጉሡን “አምላክህ ይሖዋ ሞገስ ያሳይህ” አለው። +24 ሆኖም ንጉሡ አረውናን “በፍጹም አይሆንም! ዋጋውን ልከፍልህ ይገባል። ደግሞም ምንም ያልከፈልኩበትን ነገር ለአምላኬ ለይሖዋ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም” አለው። ስለዚህ ዳዊት አውድማውንና ከብቶቹን በ50 የብር ሰቅል* ገዛ።+ +25 ዳዊትም በዚያ ለይሖዋ መሠዊያ+ ሠርቶ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረበ። ይሖዋም ስለ ምድሪቱ የቀረበውን ልመና ሰማ፤+ በእስራኤል ላይ ይወርድ የነበረው መቅሰፍትም ቆመ። +7 ንጉሡ በራሱ ቤት* መኖር በጀመረና+ ይሖዋም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ እረፍት በሰጠው ጊዜ +2 ነቢዩ ናታንን+ “የእውነተኛው አምላክ ታቦት በድንኳን ውስጥ+ ተቀምጦ ሳለ ይኸው እኔ ከአርዘ ሊባኖስ በተሠራ+ ቤት ውስጥ እየኖርኩ ነው” አለው። +3 ናታንም ንጉሡን “ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለሆነ ሄደህ በልብህ ያለውን ነገር ሁሉ አድርግ” አለው።+ +4 በዚያው ሌሊት የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ናታን መጣ፦ +5 “ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተ የምኖርበትን ቤት መሥራት ይኖርብሃል?+ +6 እስራኤላውያንን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ ድንኳን እጓዝ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርኩም።+ +7 ከእስራኤላውያን* ሁሉ ጋር በተጓዝኩበት ጊዜ በሙሉ ሕዝቤን እስራኤልን እረኛ ሆነው እንዲጠብቁ ከሾምኳቸው የነገድ መሪዎች መካከል ‘በአርዘ ሊባኖስ ቤት ያልሠራህልኝ ለምንድን ነው?’ ያልኩት ማን አለ?”’ +8 አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን+ መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ+ ወሰድኩህ። +9 እኔም በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤+ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋለሁ፤+ ስምህንም በምድር ላይ እንዳሉ ታላላቅ ሰዎች ስም ገናና አደርገዋለሁ።+ +10 ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ተረጋግተው እንዲቀመጡም አደርጋለሁ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም የሚረብሻቸው አይኖርም፤ ክፉዎች እንደቀድሞው ዳግመኛ አይጨቁኗቸውም፤+ +11 በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሳፍንትን ከሾምኩበት+ ጊዜ አንስቶ ሲያደርጉ እንደነበሩት አያደርጉባቸውም። እኔም ከጠላቶችህ ሁሉ እረፍት እሰጥሃለሁ።+ “‘“በተጨማሪም ይሖዋ ቤት* እንደሚሠራልህ ይሖዋ ራሱ ነግሮሃል።+ +12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ +13 ለስሜ የሚሆን ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።+ +14 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ጥፋት በሚያጠፋበት ጊዜም በሰዎች በትር፣ በሰው* ልጆች አለንጋ እቀጣዋለሁ።+ +15 ከፊትህ ካስወገድኩት ከሳኦል ላይ ታማኝ ፍቅሬን እንደወሰድኩ+ ከእሱ ላይ አይወሰድም። +16 ቤትህና መንግሥትህ ለዘላለም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም ለዘላለም የጸና ይሆናል።”’”+ +17 ናታንም ይህን ቃል ሁሉና ይህን ራእይ በሙሉ ለዳዊት ነገረው።+ +18 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ገብቶ በይሖዋ ፊት ተቀመጠ፤ እንዲህም አለ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ኧረ ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ? እስከዚህ ድረስ ያደረስከኝስ ቤቴ ምን ስለሆነ ነው?+ +19 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሳያንስ ስለ አገልጋይህ ቤት ገና ወደፊት የሚሆነውንም ነገር ተናገርክ፤ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ለሰው ዘር ሁሉ የተሰጠ መመሪያ* ነው። +20 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ታዲያ አገልጋይህ ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? አንተ በሚገባ ታውቀኝ የለ?+ +21 ለቃልህ ስትል፣ ከልብህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ* እነዚህን ሁሉ ታላላቅ ነገሮች ፈጽመሃል፤ እንዲሁም ለአገልጋይህ ገልጠህለታል።+ +22 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በእርግጥም ታላቅ+ የሆንከው ለዚህ ነው። እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤+ ከአንተ በቀር አምላክ የለም፤+ በጆሯችን የሰማነው ነገር ሁሉ ይህን ያረጋግጣል። +23 በምድር ላይ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ሌላ ብሔር ማን አለ?+ አምላክ ሄዶ ለእነሱ ሲል ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን+ በመፈጸም እንዲሁም ስሙን በማስጠራት+ ሕዝቡ አድርጎ ዋጃቸው።+ ከግብፅ ለዋጀኸው ሕዝብ ስትል ብሔራትንና አማልክታቸውን አባረርክ። +24 ሕዝብህን እስራኤልን እስከ ወዲያኛው የራስህ ሕዝብ አድርገህ አጸናኸው፤+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተም አምላኩ ሆንክ።+ +25 “አሁንም ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ አገልጋይህንና ቤቱን በተመለከተ የገባኸውን ቃል እስከ ወዲያኛው ፈጽም፤ ቃል እንደገባኸውም አድርግ።+ +26 ሰዎች ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በእስራኤል ላይ አምላክ ነው’ እንዲሉ ስምህ ለዘላለም ከፍ ከፍ ይበል፤+ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን።+ +27 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ‘ለአንተ ቤት* እሠራልሃለሁ’+ በማለት ለአገልጋይህ ራእይ ገልጠህለታል። አገልጋይህ ይህን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት* ያገኘው በዚህ ምክንያት ነው። +28 አሁንም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ እውነተኛው አምላክ አንተ ነህ፤ ቃልህ እውነት ነው፤+ ለአገልጋይህም እነዚህን መልካም ነገሮች ለማድረግ ቃል ገብተህለታል። +29 በመሆኑም የአገልጋይህን ቤት እባክህ ባርክ፤ በፊትህም ለዘላለም የጸና ይሁን፤+ ምክንያቱም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ራስህ ቃል ገብተሃል፤ በአንተም በረከት የአገልጋይህ ቤት ለዘላለም የተባረከ ይሁን።”+ +12 በመሆኑም ይሖዋ ናታንን+ ወደ ዳዊት ላከው። እሱም ወደ ዳዊት መጥቶ+ እንዲህ አለው፦ “በአንዲት ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንደኛው ሀብታም ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ድሃ ነበር። +2 ሀብታሙ ሰው እጅግ ብዙ በጎችና ከብቶች ነበሩት፤+ +3 ድሃው ሰው ግን ከገዛት አንዲት ትንሽ የበግ ጠቦት ሌላ ምንም አልነበረውም።+ እሱም ይንከባከባት ነበር፤ እሷም ከእሱና ከወ��ዶች ልጆቹ ጋር አብራ እየኖረች አደገች። ያለችውን ጥቂት ምግብ አብራ ትበላ፣ ከጽዋውም ትጠጣ እንዲሁም በእቅፉ ትተኛ ነበር። ለእሱም እንደ ሴት ልጁ ነበረች። +4 አንድ ቀን ሀብታሙ ሰው እንግዳ መጣበት፤ ሆኖም ይህ ሰው ወደ እሱ ለመጣው መንገደኛ የሚበላ ነገር ለማዘጋጀት ከራሱ በጎችና ከብቶች ላይ አልወሰደም። ከዚህ ይልቅ የድሃውን ሰው የበግ ጠቦት ወስዶ ወደ እሱ ለመጣው እንግዳ አዘጋጅቶ አቀረበለት።”+ +5 በዚህ ጊዜ ዳዊት በሰውየው ላይ እጅግ ተቆጥቶ ናታንን እንዲህ አለው፦ “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣+ ይህን ያደረገው ሰው ሞት ይገባዋል! +6 ይህ ሰው እንዲህ ያለውን ነገር ስላደረገና ርኅራኄ ስላላሳየ በበግ ጠቦቷ ምትክ አራት እጥፍ መክፈል አለበት።”+ +7 ከዚያም ናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ያ ሰው አንተ ነህ! የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እኔ ራሴ ቀባሁህ፤+ ከሳኦልም እጅ ታደግኩህ።+ +8 የጌታህን ቤት ልሰጥህ፣+ የጌታህንም ሚስቶች+ በእቅፍህ ላደርግልህ ፈቃደኛ ነበርኩ፤ የእስራኤልንና የይሁዳንም ቤት ሰጠሁህ።+ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ ነገር ላደርግልህ ፈቃደኛ ነበርኩ።+ +9 ታዲያ በፊቱ መጥፎ ነገር በመሥራት የይሖዋን ቃል ያቃለልከው ለምንድን ነው? ሂታዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታኸው!+ በአሞናውያን ሰይፍ ከገደልከውም+ በኋላ ሚስቱን ወስደህ ሚስትህ አደረግካት።+ +10 ስለዚህ የሂታዊውን የኦርዮን ሚስት ወስደህ ሚስትህ በማድረግ እኔን ስለናቅክ ሰይፍ ከቤትህ ፈጽሞ አይለይም።’+ +11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከገዛ ቤትህ መከራ አመጣብሃለሁ፤+ ዓይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለሌላ ሰው* እሰጣቸዋለሁ፤+ እሱም በቀን ብርሃን* ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።+ +12 አንተ ይህን በድብቅ ብታደርገውም+ እኔ ግን በመላው እስራኤል ፊት በቀን ብርሃን* አደርገዋለሁ።’” +13 ከዚያም ዳዊት ናታንን “በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁ” አለው።+ ናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ይሖዋም ኃጢአትህን ይቅር ይላል።*+ አትሞትም።+ +14 ይሁንና ይህን ድርጊት በመፈጸም ይሖዋን እጅግ ስለናቅክ አሁን የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።” +15 ከዚያም ናታን ወደ ቤቱ ሄደ። ይሖዋም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ በመቅሰፍት መታው፤ ልጁም ታመመ። +16 ዳዊትም ስለ ልጁ እውነተኛውን አምላክ ተማጸነ። ምንም ነገር ሳይቀምስም ጾመ፤ ወደ ክፍሉ ገብቶም ሌሊቱን ሙሉ መሬት ላይ ተኝቶ አደረ።+ +17 በቤቱ ያሉ ሽማግሌዎችም መጥተው አጠገቡ ቆሙ፤ ከመሬት ሊያነሱትም ሞከሩ። እሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ አብሯቸውም ምግብ አልበላም። +18 በሰባተኛው ቀን ልጁ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮች ግን የልጁን መሞት ለእሱ መንገር ፈሩ። እነሱም እንዲህ አሉ፦ “ልጁ በሕይወት ሳለ ዳዊትን አነጋግረነው ነበር፤ እሱ ግን ሊሰማን ፈቃደኛ አልሆነም። ታዲያ አሁን ልጁ መሞቱን እንዴት እንነግረዋለን? መቼም ይህን ብንነግረው መጥፎ ነገር ሊያደርግ ይችላል።” +19 ዳዊት አገልጋዮቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ሲያይ ልጁ እንደሞተ ገባው። በመሆኑም አገልጋዮቹን “ልጁ ሞተ?” አላቸው። እነሱም “አዎ፣ ሞቷል” ብለው መለሱለት። +20 በዚህ ጊዜ ዳዊት ከመሬት ተነሳ። ከታጠበ፣ ዘይት ከተቀባና+ ልብሱን ከቀየረ በኋላም ወደ ይሖዋ ቤት+ ሄዶ ሰገደ። ወደ ቤቱም* ሄዶ ምግብ እንዲያቀርቡለት ጠየቀ፤ ከዚያም በላ። +21 አገልጋዮቹም “እንዲህ ያደረግከው ለምንድን ነው? ልጁ በሕይወት ሳለ ስትጾምና ስታለቅስ ነበር፤ ልጁ ሲሞት ግን ወዲያውኑ ተነሳህ፤ ምግብም በላህ” አሉት። +22 እሱም እንዲህ አለ፦ “ልጁ በሕይወት ሳለ ‘ማን ያውቃል፣ ይሖዋ ይራራልኝና ልጁን በሕይወት ያኖርልኝ ይሆናል’+ ብዬ ስላሰብኩ ጾምኩ፤+ እንዲሁም አለቀስኩ። +23 አሁን ግን ልጁ ሞቷል፤ ታዲያ የምጾመው ለምንድን ነው? መልሼ ላመጣው እችላለሁ?+ እኔ ወደ እሱ እሄዳለሁ+ እንጂ እሱ ወደ እኔ አይመለስም።”+ +24 ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን+ አጽናናት። ወደ እሷም ገብቶ አብሯት ተኛ። ከጊዜ በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙም ሰለሞን*+ ተባለ። ይሖዋም ወደደው፤+ +25 በነቢዩ ናታን+ በኩል መልእክት ልኮም ለይሖዋ ሲል ስሙን ይዲድያህ* አለው። +26 ኢዮአብ የአሞናውያን+ ከተማ የሆነችውን ራባን+ መውጋቱን ቀጠለ፤ የነገሥታቱንም* ከተማ ተቆጣጠረ።+ +27 በመሆኑም ኢዮአብ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ፦ “ከራባ+ ጋር ተዋግቼ የውኃዎችን ከተማ* ይዣለሁ። +28 በል አሁን የቀረውን ሠራዊት ሰብስብና ከተማዋን ከበህ በቁጥጥርህ ሥር አድርጋት። አለዚያ ከተማዋን እይዛትና ክብሩ ለእኔ ይሆናል።”* +29 በመሆኑም ዳዊት ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ራባ ሄደ፤ ከተማዋንም ወግቶ በቁጥጥር ሥር አደረጋት። +30 ከዚያም የማልካምን* ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። የዘውዱም ክብደት አንድ ታላንት* ወርቅ ነበር፤ በላዩም ላይ የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ፤ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተደረገ። በተጨማሪም ከከተማዋ+ በጣም ብዙ ምርኮ ወሰደ።+ +31 ነዋሪዎቿንም አውጥቶ ድንጋይ እንዲቆርጡ፣ ስለት ባላቸው የብረት መሣሪያዎችና በብረት መጥረቢያዎች እንዲሠሩ እንዲሁም ጡብ እንዲያመርቱ አደረጋቸው። በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። በመጨረሻም ዳዊትና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። +1 ሳኦል ከሞተ በኋላ ዳዊት አማሌቃውያንን ድል አድርጎ* ሲመለስ በጺቅላግ+ ሁለት ቀን ቆየ። +2 በሦስተኛውም ቀን አንድ ሰው ልብሱን ቀዶና በራሱ ላይ አቧራ ነስንሶ ከሳኦል ሰፈር መጣ። እሱም ዳዊት ጋ ሲደርስ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። +3 ዳዊትም “ከየት ነው የመጣኸው?” ሲል ጠየቀው፤ እሱም “ከእስራኤል ሰፈር አምልጬ ነው” በማለት መለሰለት። +4 ዳዊትም “እስቲ የሆነውን ነገር ንገረኝ” አለው። እሱም “ሰዎቹ ከውጊያው ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹም ወድቀዋል፤ ሞተዋል። ሳኦልና ልጁ ዮናታንም እንኳ ሞተዋል” አለው።+ +5 ከዚያም ዳዊት ወሬውን ያመጣለትን ወጣት “ለመሆኑ ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት አወቅክ?” ሲል ጠየቀው። +6 ወጣቱም እንዲህ አለው፦ “እንደ አጋጣሚ ሆኖ ጊልቦአ+ ተራራ ላይ ነበርኩ፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተመርኩዞ ቆሞ ነበር፤ ሠረገሎቹና ፈረሰኞቹም ደረሱበት።+ +7 ወደ ኋላም ዞር ብሎ ሲያየኝ ጠራኝ፤ እኔም ‘አቤት!’ አልኩት። +8 እሱም ‘አንተ ማን ነህ?’ አለኝ፤ እኔም ‘አማሌቃዊ+ ነኝ’ አልኩት። +9 ከዚያም ‘ሕይወቴ ያላለፈች* ቢሆንም ከባድ ሥቃይ ላይ ስለሆንኩ እባክህ ላዬ ላይ ቁምና ግደለኝ’ አለኝ። +10 በመሆኑም መቼም ቆስሎ ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅኩ ላዩ ላይ ቆሜ ገደልኩት።+ ከዚያም ራሱ ላይ ያለውን ዘውድና ክንዱ ላይ የነበረውን አምባር ወስጄ ወደ ጌታዬ ይዤ መጣሁ።” +11 በዚህ ጊዜ ዳዊት ልብሱን ቀደደ፤ አብረውት ያሉትም ሰዎች ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ። +12 ከዚያም ለሳኦል፣ ለልጁ ለዮናታን፣ ለይሖዋ ሕዝብና ለእስራኤል ቤት+ እስከ ማታ ድረስ ጮኹ፣ አለቀሱ እንዲሁም ጾሙ፤+ በሰይፍ ወድቀዋልና። +13 ዳዊትም ወሬውን ያመጣለትን ወጣት “የየት አገር ሰው ነህ?” አለው። እሱም “የባዕድ አገር ሰው የሆነ የአንድ አማሌቃዊ ልጅ ነኝ” አለው። +14 ከዚያም ዳዊት “ይሖዋ የቀባውን ለመግደል እጅህን ስታነሳ እንዴት አልፈራህም?” አለው።+ +15 ዳዊትም ከወጣቶቹ መካከል አንዱን ጠርቶ “በል ቅረብና ምታው” አለው። እሱም መታው፤ ወጣቱም ሞተ።+ +16 ከዚያም ዳዊት “‘ይሖዋ የቀባውን እኔ ራሴ ገድዬዋለሁ’ በማለት የገዛ አፍህ ስለመሠከረብህ ደምህ በራስህ ላይ ነው” አለው።+ +17 ዳዊትም ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን ይህን የሐዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፤+ +18 እንዲሁም በያሻር መጽሐፍ+ ተጽፎ የሚገኘውን “ቀስት” የተባለውን ሙሾ* የይሁዳ ልጆች እንዲማሩ አዘዘ። +19 “እስራኤል ሆይ፣ ውበት በኮረብቶችህ ላይ ተገድሎ ተጋድሟል።+ ኃያላኑ እንዴት እንዲህ ይውደቁ! +20 ይህን በጌት አትናገሩ፤+በአስቀሎን ጎዳናዎችም ላይ አታውጁ፤አለዚያ የፍልስጤም ሴቶች ልጆች ይደሰታሉ፣የእነዚያ ያልተገረዙ ሰዎች ሴቶች ልጆችም ይፈነድቃሉ። +21 እናንተ የጊልቦአ ተራሮች፣+ጠል አያረስርሳችሁ ወይም ዝናብ አይዝነብባችሁ፣ለቅዱስ መዋጮዎች የሚሆን እህል የሚያበቅሉ ማሳዎችም አይገኙባችሁ፣+በዚያ የኃያላኑ ጋሻ ረክሷልና፣የሳኦልም ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም። +22 ከተገደሉት ሰዎች ደም፣ ከኃያላኑ ስብ፣የዮናታን ቀስት አልተመለሰም፤+የሳኦልም ሰይፍ ድል ሳያደርግ አይመለስም።+ +23 ሳኦልና ዮናታን+ በሕይወት ሳሉ የሚወደዱና የሚደነቁ* ነበሩ፤ሲሞቱም አልተለያዩም።+ ከንስር ይልቅ ፈጣኖች፣+ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።+ +24 እናንተ የእስራኤል ሴቶች ልጆች፣የተንቆጠቆጡ ደማቅ ቀይ ልብሶችን ላለበሳችሁ፣ልብሶቻችሁንም በወርቅ ላስጌጠላችሁ ለሳኦል አልቅሱ። +25 ኃያላኑ በጦርነት ላይ እንዴት እንዲህ ይውደቁ! ዮናታን በኮረብቶችህ ላይ ተገድሎ ተጋድሟል!+ +26 ወንድሜ ዮናታን፣ በአንተ የተነሳ ተጨንቄአለሁ፤አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተወደድክ ነበርክ።+ የአንተ ፍቅር ለእኔ ከሴት ፍቅር ይበልጥ ነበር።+ +27 ኃያላኑ እንዴት እንዲህ ይውደቁ፤የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት እንዲህ ይጥፉ!” +8 ከጊዜ በኋላም ዳዊት ፍልስጤማውያንን+ ድል በማድረግ በቁጥጥር ሥር አዋላቸው፤+ መተግአማህንም ከፍልስጤማውያን እጅ ወሰደ። +2 ሞዓባውያንንም ድል አደረጋቸው፤+ እነሱንም መሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው። ይህን ያደረገው በገመዱ ርዝመት ሁለት እጅ የሚሆኑትን ለመግደል እንዲሁም በገመዱ ርዝመት አንድ እጅ የሚሆኑትን በሕይወት ለመተው ነው።+ ሞዓባውያንም የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ ግብርም ገበሩለት።+ +3 የሬሆብ ልጅ የሆነው የጾባህ+ ንጉሥ ሃዳድኤዜር በኤፍራጥስ ወንዝ+ ላይ ያለውን የበላይነት ዳግመኛ ለማረጋገጥ በሄደ ጊዜ ዳዊት ድል አደረገው። +"4 ዳዊትም ከእሱ ላይ 1,700 ፈረሰኞችንና 20,000 እግረኛ ወታደሮችን ማረከ። ከዚያም ዳዊት 100 የሠረገላ ፈረሶችን ብቻ አስቀርቶ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቆረጠ።+ " +"5 የደማስቆዎቹ ሶርያውያን፣+ የጾባህን ንጉሥ ሃዳድኤዜርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን መካከል 22,000 ሰዎችን ገደለ።+" +6 ከዚያም ዳዊት በደማስቆ ሶርያ የጦር ሰፈሮች አቋቋመ፤ ሶርያውያንም የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ ግብርም ገበሩለት። ይሖዋ ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።*+ +7 በተጨማሪም ዳዊት ከሃዳድኤዜር አገልጋዮች ላይ ከወርቅ የተሠሩ ክብ ጋሻዎችን ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው።+ +8 ደግሞም ንጉሥ ዳዊት የሃዳድኤዜር ከተሞች ከሆኑት ከቤጣህ እና ከበሮታይ እጅግ ብዙ መዳብ ወሰደ። +9 በዚህ ጊዜ የሃማት+ ንጉሥ ቶአይ ዳዊት የጾባህን ንጉሥ የሃዳድኤዜርን+ ሠራዊት በሙሉ ድል እንዳደረገ ሰማ። +10 በመሆኑም ቶአይ የንጉሥ ዳዊትን ደህንነት እንዲጠይቅና ከሃዳድኤዜር ጋር ተዋግቶ ድል በማድረጉ የተሰማውን ደስታ እንዲገልጽለት ልጁን ዮራምን ወደ ዳዊት ላከው (ምክንያቱም ሃዳድኤዜር ከቶአይ ጋር ብዙ ጊዜ ይዋጋ ነበር)፤ እሱም ከብር፣ ከወርቅና ከመዳብ የተሠሩ ዕቃዎችን ይዞ መጣ። +11 ንጉሥ ዳዊት እነዚህን ዕቃ���ች ተገዢዎቹ ካደረጋቸው ብሔራት ሁሉ ላይ ወስዶ ከቀደሰው ብርና ወርቅ ጋር አብሮ ለይሖዋ ቀደሳቸው፤+ +12 ዕቃዎቹም ከሶርያ፣ ከሞዓብ፣+ ከአሞናውያን፣ ከፍልስጤማውያንና+ ከአማሌቃውያን+ ላይ የወሰዳቸው እንዲሁም የሬሆብ ልጅ ከሆነው ከጾባህ ንጉሥ ከሃዳድኤዜር+ ላይ የማረካቸው ናቸው። +"13 ዳዊት በጨው ሸለቆ 18,000 ኤዶማውያንን ገድሎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ።+" +14 በኤዶምም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ። በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን ከማቋቋሙም ሌላ ኤዶማውያን ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ።+ ይሖዋም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።*+ +15 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ መግዛቱን ቀጠለ፤+ ለሕዝቡም ሁሉ+ ፍትሕንና ጽድቅን አሰፈነላቸው።+ +16 የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ+ የሠራዊቱ አዛዥ ነበር፤ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ ታሪክ ጸሐፊ ነበር። +17 የአኪጡብ ልጅ ሳዶቅና+ የአብያታር ልጅ አሂሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሰራያህ ደግሞ ጸሐፊ ነበር። +18 የዮዳሄ ልጅ በናያህ+ የከሪታውያንና የጴሌታውያን+ አዛዥ ነበር። የዳዊት ወንዶች ልጆችም ዋና ኃላፊዎች* ሆኑ። +11 በዓመቱ መባቻ፣* ነገሥታት ለውጊያ በሚዘምቱበት ወቅት ዳዊት አሞናውያንን እንዲያጠፉ ኢዮዓብን፣ አገልጋዮቹንና መላውን የእስራኤል ሠራዊት ላከ፤ እነሱም ራባን+ ከበቡ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።+ +2 አንድ ቀን ምሽት፣* ዳዊት ከአልጋው ተነስቶ በንጉሡ ቤት* ሰገነት ላይ ይንጎራደድ ነበር። በሰገነቱ ላይ ሳለም አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ እሷም በጣም ውብ ነበረች። +3 ዳዊትም ስለ ሴትየዋ ማንነት እንዲጠይቅ አንድ ሰው ላከ፤ ሰውየውም “ሴቲቱ የኤሊያም+ ልጅ፣ የሂታዊው+ የኦርዮ+ ሚስት ቤርሳቤህ+ ናት” ብሎ ነገረው። +4 ከዚያም ዳዊት ሴትየዋን እንዲያመጧት መልእክተኞችን ላከ።+ እሷም ወደ እሱ ገባች፤ አብሯትም ተኛ።+ (ይህ የሆነው ራሷን ከርኩሰቷ* እያነጻች ሳለ ነበር።)+ በኋላም ሴትየዋ ወደ ቤቷ ተመለሰች። +5 ሴትየዋም ፀነሰች፤ ለዳዊትም “አርግዣለሁ” የሚል መልእክት ላከችበት። +6 በዚህ ጊዜ ዳዊት “ሂታዊውን ኦርዮን ወደ እኔ ላከው” በማለት ወደ ኢዮዓብ መልእክት ላከበት። በመሆኑም ኢዮዓብ ኦርዮን ወደ ዳዊት ላከው። +7 ኦርዮም በመጣ ጊዜ ዳዊት ስለ ኢዮዓብ ደህንነት፣ ስለ ሠራዊቱ ሁኔታና ጦርነቱ እንዴት እየተካሄደ እንዳለ ጠየቀው። +8 ከዚያም ዳዊት ኦርዮን “እንግዲህ ወደ ቤትህ ውረድና ዘና በል”* አለው። ኦርዮ ከንጉሡ ቤት ወጥቶ በሄደ ጊዜ የንጉሡ የደግነት ስጦታ* ተላከለት። +9 ኦርዮ ግን ከሌሎቹ የጌታው አገልጋዮች ጋር በንጉሡ ቤት ደጃፍ ላይ ተኛ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም። +10 በመሆኑም ለዳዊት “ኦርዮ እኮ ወደ ቤቱ አልወረደም” ብለው ነገሩት። በዚህ ጊዜ ዳዊት ኦርዮን “ከመንገድ ገና መግባትህ አይደለም እንዴ? ታዲያ ወደ ቤትህ ያልወረድከው ለምንድን ነው?” አለው። +11 ኦርዮም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ታቦቱም+ ሆነ እስራኤልና ይሁዳ ያሉት ዳስ ውስጥ ነው፤ ጌታዬ ኢዮዓብና የጌታዬ አገልጋዮችም አውላላ ሜዳ ላይ ሰፍረዋል። ታዲያ እኔ ለመብላትና ለመጠጣት፣ ከሚስቴም ጋር ለመተኛት ወደ ቤቴ ልሂድ?+ በአንተና በሕያውነትህ* እምላለሁ ይህን ፈጽሞ አላደርገውም!” +12 ከዚያም ዳዊት ኦርዮን “እንግዲያውስ ዛሬን እዚህ ቆይና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። በመሆኑም ኦርዮ ያን ቀንና ቀጣዩን ቀን ኢየሩሳሌም ቆየ። +13 ዳዊትም አብሮት እንዲበላና እንዲጠጣ አስጠራው፤ አሰከረውም። ሆኖም ኦርዮ ምሽት ላይ ከጌታው አገልጋዮች ጋር ለመተኛት ወጥቶ ወደ መኝታው ሄደ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም። +14 ሲነጋም ዳዊት ለኢዮዓብ ደብዳቤ ጽፎ በኦርዮ እጅ ላከለት። +15 በደብዳቤውም ላይ “ኦርዮን ውጊያው በ��ፋፋመበት ግንባር መድበው። እሱም ተመቶ እንዲሞት እናንተ ከኋላው አፈግፍጉ” ብሎ ጻፈ።+ +16 ኢዮዓብም ከተማዋን በጥንቃቄ ይመለከት ነበር፤ ኦርዮንም ኃይለኛ ተዋጊዎች እንዳሉበት በሚያውቀው ግንባር መደበው። +17 የከተማዋም ሰዎች ወጥተው ከኢዮዓብ ጋር ሲዋጉ ከዳዊት አገልጋዮች መካከል አንዳንዶቹ ወደቁ፤ ከሞቱትም ሰዎች መካከል ሂታዊው ኦርዮ ይገኝበታል።+ +18 ከዚያም ኢዮዓብ የጦርነቱን አጠቃላይ ሁኔታ የሚገልጽ ወሬ ለዳዊት ላከ። +19 መልእክተኛውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “አጠቃላይ የጦርነቱን ሁኔታ ለንጉሡ ነግረህ ስትጨርስ +20 ንጉሡ ሊቆጣና እንዲህ ሊልህ ይችላል፦ ‘ከተማዋን ለመውጋት ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው? ቅጥሩ አናት ላይ ሆነው እንደሚወነጭፉባችሁ አታውቁም? +21 የየሩቤሼትን+ ልጅ አቢሜሌክን የገደለው ማን ሆነና ነው?+ በቅጥሩ አናት ላይ ሆና መጅ በመልቀቅ በቴቤጽ የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችም? ታዲያ እናንተ ይህን ያህል ወደ ቅጥሩ የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ በዚህ ጊዜ ‘አገልጋይህ ሂታዊው ኦርዮም ሞቷል’ በለው።” +22 በመሆኑም መልእክተኛው ተነስቶ ሄደ፤ ኢዮዓብ የላከውንም መልእክት ሁሉ ለዳዊት ነገረው። +23 መልእክተኛውም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ሰዎቹ አየሉብን፤ እኛንም ለመውጋት ወደ ሜዳው ወጡ፤ እኛ ግን እስከ ከተማው መግቢያ ድረስ እንዲያፈገፍጉ አደረግናቸው። +24 ቀስተኞቹም ቅጥሩ አናት ላይ ሆነው በአገልጋዮችህ ላይ ቀስት ያስወነጭፉ ጀመር፤ በዚህም የተነሳ ከንጉሡ አገልጋዮች መካከል አንዳንዶቹ ተገደሉ፤ አገልጋይህ ሂታዊው ኦርዮም ሞተ።”+ +25 በዚህ ጊዜ ዳዊት መልእክተኛውን “ኢዮዓብን እንዲህ በለው፦ ‘መቼም ሰይፍ አንዱን እንደሚበላ ሁሉ ሌላውንም ስለሚበላ ይህ ሁኔታ አይረብሽህ። ብቻ አንተ በከተማዋ ላይ ውጊያህን በማፋፋም በቁጥጥር ሥር አውላት።’+ አንተም አበረታታው” አለው። +26 የኦርዮ ሚስት ባሏ መሞቱን ስትሰማ ለባለቤቷ አለቀሰችለት። +27 የሐዘኑ ጊዜ እንዳበቃም ዳዊት ልኮ ወደ ቤቱ አስመጣት፤ እሷም ሚስቱ ሆነች፤+ ወንድ ልጅም ወለደችለት። ሆኖም ዳዊት ያደረገው ነገር ይሖዋን በጣም አሳዝኖት* ነበር።+ +2 ከዚህ በኋላ ዳዊት “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዱ ልውጣ?” በማለት ይሖዋን ጠየቀ።+ ይሖዋም “ውጣ” አለው። ዳዊትም “ወዴት ብሄድ ይሻላል?” አለ። እሱም “ወደ ኬብሮን”+ አለው። +2 በመሆኑም ዳዊት ከሁለቱ ሚስቶቹ ማለትም ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪኖዓም+ እና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢጋኤል+ ጋር ወደዚያ ወጣ። +3 በተጨማሪም ዳዊት አብረውት የነበሩትን ሰዎች+ እያንዳንዳቸውን ከነቤተሰባቸው ይዞ ወጣ፤ እነሱም በኬብሮን ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ መኖር ጀመሩ። +4 ከዚያም የይሁዳ ሰዎች መጥተው በዚያ ዳዊትን በይሁዳ ቤት ላይ ንጉሥ አድርገው ቀቡት።+ ለዳዊትም “ሳኦልን የቀበሩት የኢያቢስጊልያድ ሰዎች ናቸው” ብለው ነገሩት። +5 በመሆኑም ዳዊት ወደ ኢያቢስጊልያድ ሰዎች መልእክተኞችን በመላክ እንዲህ አላቸው፦ “ጌታችሁን ሳኦልን በመቅበር ለእሱ ታማኝ ፍቅር ስላሳያችሁ ይሖዋ ይባርካችሁ።+ +6 ይሖዋ ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ያሳያችሁ። እኔም ይህን ስላደረጋችሁ ደግነት አደርግላችኋለሁ።+ +7 እንግዲህ አሁን ጌታችሁ ሳኦል ስለሞተና የይሁዳም ቤት እኔን በላያቸው ንጉሥ አድርገው ስለቀቡኝ እጆቻችሁን አበርቱ፤ ደፋሮችም ሁኑ።” +8 የሳኦል ሠራዊት አለቃ የሆነው የኔር ልጅ አበኔር+ ግን የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን+ ወስዶ ወደ ማሃናይም+ አሻገረው፤ +9 እሱንም በጊልያድ፣+ በአሱራውያን፣ በኢይዝራኤል፣+ በኤፍሬምና+ በቢንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ ላይ አነገሠው። +10 ��ሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በእስራኤል ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 40 ዓመት ነበር፤ እሱም ለሁለት ዓመት ገዛ። የይሁዳ ቤት ግን ዳዊትን ደገፈ።+ +11 ዳዊት በኬብሮን ንጉሥ ሆኖ በይሁዳ ቤት ላይ የገዛበት ጊዜ* ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበር።+ +12 ከጊዜ በኋላ የኔር ልጅ አበኔርና የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ አገልጋዮች ከማሃናይም+ ወደ ገባኦን+ ወጡ። +13 የጽሩያ+ ልጅ ኢዮዓብና+ የዳዊት አገልጋዮችም ወጥተው በገባኦን ኩሬ አጠገብ አገኟቸው፤ አንደኛው ቡድን ከኩሬው በዚህኛው በኩል ሌላኛው ቡድን ደግሞ ከኩሬው በዚያኛው በኩል ተቀመጠ። +14 በመጨረሻም አበኔር ኢዮዓብን “እስቲ ወጣቶቹ ይነሱና በፊታችን ይፋለሙ”* አለው። ኢዮዓብም “እሺ ይነሱ” አለ። +15 በመሆኑም ተነሱ፤ ከሳኦል ልጅ ከኢያቡስቴ 12 ቢንያማውያን፣ ከዳዊት አገልጋዮችም 12 ሰዎች ተቆጥረው ተሻገሩ። +16 ከዚያም አንዱ የሌላውን ራስ በመያዝ ሰይፉን በባላጋራው ጎን እየሻጠ ሁሉም ተያይዘው ወደቁ። ስለዚህ በገባኦን የሚገኘው ያ ቦታ ሄልቃትሃጽጹሪም ተባለ። +17 በዚያን ዕለት የተነሳው ውጊያ እጅግ ከባድ ነበር፤ በመጨረሻም አበኔርና የእስራኤል ሰዎች በዳዊት አገልጋዮች ፊት ተሸነፉ። +18 ሦስቱ የጽሩያ+ ልጆች ኢዮዓብ፣+ አቢሳ+ እና አሳሄል+ እዚያ ነበሩ፤ አሳሄል በመስክ ላይ እንዳለች የሜዳ ፍየል ፈጣን ሯጭ ነበር። +19 አሳሄልም አበኔርን ማሳደዱን ተያያዘው፤ እሱን ከማሳደድ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አላለም። +20 አበኔርም ወደ ኋላ ዞር ብሎ ተመለከተና “አሳሄል፣ አንተ ነህ?” ሲል ጠየቀ፤ እሱም “አዎ፣ እኔ ነኝ” አለው። +21 ከዚያም አበኔር “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ዞር ብለህ ከወጣቶቹ መካከል አንዱን ያዝና ያለውን ነጥቀህ ለራስህ ውሰድ” አለው። አሳሄል ግን እሱን ማሳደዱን መተው አልፈለገም። +22 በመሆኑም አበኔር አሳሄልን እንደገና “እኔን ማሳደድህን ተው። እኔስ ለምን ልግደልህ? የወንድምህን የኢዮዓብንስ ፊት እንዴት ብዬ አያለሁ?” አለው። +23 እሱ ግን ለመተው ፈቃደኛ አልሆነም፤ በመሆኑም አበኔር በጦሩ የኋላ ጫፍ ሆዱን ወጋው፤+ ጦሩም በጀርባው ዘልቆ ወጣ፤ እሱም እዚያው ወድቆ ወዲያውኑ ሞተ። በዚያ የሚያልፍ ሰው ሁሉ አሳሄል ወድቆ የሞተበት ስፍራ ሲደርስ ቆም ይል ነበር። +24 ከዚያም ኢዮዓብና አቢሳ አበኔርን ማሳደድ ጀመሩ። ወደ ገባኦን ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ላይ ከጊያህ ፊት ለፊት ያለው የአማ ኮረብታ ጋ ሲደርሱ ፀሐይ ጠለቀች። +25 በዚያም ቢንያማውያን በአበኔር ዙሪያ ተሰበሰቡ፤ እነሱም ግንባር በመፍጠር በአንድ ኮረብታ አናት ላይ ቆሙ። +26 ከዚያም አበኔር ኢዮዓብን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ይህ ሰይፍ ያለገደብ ሰው መብላት አለበት? ውጤቱስ መራራ እንደሚሆን አንተ ራስህ ሳታውቀው ቀርተህ ነው? ሰዎቹ ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንዲመለሱ የማትነግራቸው እስከ መቼ ነው?” +27 በዚህ ጊዜ ኢዮዓብ “ሕያው በሆነው በእውነተኛው አምላክ እምላለሁ፣ አንተ ይህን ባትናገር ኖሮ ሰዎቹ እስኪነጋ ድረስ ወንድሞቻቸውን ማሳደዳቸውን አያቆሙም ነበር” አለ። +28 ኢዮዓብም ቀንደ መለከት ነፋ፤ የእሱ ሰዎችም እስራኤልን ማሳደዳቸውን ተዉ፤ ውጊያውም አቆመ። +29 ከዚያም አበኔርና ሰዎቹ ሌሊቱን ሙሉ በአረባ+ ሲጓዙ አደሩ፤ ዮርዳኖስንም በመሻገር ሸለቆውን* ሁሉ አቋርጠው በመጨረሻ ማሃናይም+ደረሱ። +30 ኢዮዓብም አበኔርን ከማሳደድ ተመልሶ ሕዝቡን በሙሉ አንድ ላይ ሰበሰበ። ከዳዊትም አገልጋዮች መካከል አሳሄልን ጨምሮ 19 ሰዎች መጉደላቸው ታወቀ። +31 የዳዊት አገልጋዮች ግን ቢንያማውያንንና የአበኔርን ሰዎች ድል ያደረጓቸው ከመሆኑም ሌላ ከእነሱ መካከል 360 ሰዎችን ገድለው ነበር። +32 እነሱም አሳሄልን+ ወስደው ��ቤተልሔም+ በሚገኘው በአባቱ የመቃብር ቦታ ቀበሩት። ከዚያም ኢዮዓብና ሰዎቹ ሌሊቱን ሙሉ ሲገሰግሱ አድረው ንጋት ላይ ኬብሮን+ ደረሱ። +4 የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ፣*+ አበኔር በኬብሮን መሞቱን+ ሲሰማ ወኔ ከዳው፤* እስራኤላውያንም በሙሉ ተረበሹ። +2 የሳኦል ልጅ የሚመራቸው ወራሪ ቡድኖች አለቃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ የአንደኛው ስም ባአናህ ሲሆን የሌላኛው ስም ደግሞ ሬካብ ነበር። እነሱም ከቢንያም ነገድ የሆነው የበኤሮታዊው የሪሞን ልጆች ነበሩ። (ምክንያቱም በኤሮት+ ከቢንያም ወገን እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር። +3 በኤሮታውያን ወደ ጊታይም+ ሸሹ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ የባዕድ አገር ሰው ሆነው ይኖራሉ።) +4 የሳኦል ልጅ ዮናታን+ እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው።+ እሱም ስለ ሳኦልና ስለ ዮናታን የሚገልጸው ወሬ ከኢይዝራኤል+ በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፤ ሞግዚቱም አንስታው መሸሽ ጀመረች፤ ሆኖም በድንጋጤ ሸሽታ ስትሮጥ ከእጇ ላይ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜፊቦስቴ+ ነበር። +5 የበኤሮታዊው የሪሞን ልጆች ሬካብ እና ባአናህ ሞቃታማ በሆነው የቀኑ ክፍለ ጊዜ ወደ ኢያቡስቴ ቤት ሄዱ፤ እሱም ቀትር ላይ አረፍ ብሎ ነበር። +6 እነሱም ስንዴ የሚወስዱ ሰዎች መስለው ወደ ቤቱ ውስጥ ዘልቀው ገቡ፤ ኢያቡስቴንም ሆዱ ላይ ወጉት፤ ከዚያም ሬካብ እና ወንድሙ ባአናህ+ ሸሽተው አመለጡ። +7 ወደ ቤት ሲገቡ ኢያቡስቴ መኝታ ቤቱ ውስጥ አልጋው ላይ ጋደም ብሎ ነበር፤ እነሱም መትተው ገደሉት፤ ከዚያም ራሱን ቆርጠው በመውሰድ ወደ አረባ በሚወስደው መንገድ ሌሊቱን ሙሉ ሲጓዙ አደሩ። +8 የኢያቡስቴንም+ ራስ በኬብሮን ወዳለው ወደ ዳዊት አምጥተው ንጉሡን “ሕይወትህን* ሲፈልጋት+ የነበረው የጠላትህ+ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ። ይሖዋ በዛሬው ዕለት ሳኦልንና ዘሮቹን ለጌታዬ ለንጉሡ ተበቀለለት” አሉት። +9 ሆኖም ዳዊት ለበኤሮታዊው ለሪሞን ልጆች ለሬካብ እና ለወንድሙ ለባአናህ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሕይወቴን ከመከራ ሁሉ በታደገልኝ*+ ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ +10 አንድ ሰው ምሥራች ያበሰረኝ መስሎት ‘ሳኦል እኮ ሞተ’+ ብሎ በነገረኝ ጊዜ ጺቅላግ ላይ ገደልኩት።+ መልእክተኛው ከእኔ ያገኘው ሽልማት ይህ ነበር! +11 ታዲያ በገዛ ቤቱ አልጋው ላይ ተኝቶ የነበረውን ጻድቅ ሰው የገደሉ ክፉ ሰዎችማ እንዴት ከዚህ የባሰ ነገር አይጠብቃቸው! እና አሁን ደሙን ከእጃችሁ መጠየቅም+ ሆነ እናንተን ከምድር ገጽ ማጥፋት አይገባኝም?” +12 ከዚያም ዳዊት እንዲገድሏቸው ለወጣቶቹ ትእዛዝ ሰጠ።+ እነሱም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ቆርጠው በኬብሮን በሚገኘው ኩሬ አጠገብ ሰቀሏቸው።+ የኢያቡስቴን ራስ ግን ወስደው በኬብሮን ባለው በአበኔር የመቃብር ቦታ ቀበሩት። +16 ዳዊት የተራራውን ጫፍ+ አልፎ ጥቂት እንደሄደ ሲባ+ የተባለው የሜፊቦስቴ+ አገልጋይ 200 ዳቦዎች፣ 100 የዘቢብ ቂጣዎች፣ ከበጋ ፍሬ* የተዘጋጁ 100 ቂጣዎችና አንድ እንስራ የወይን ጠጅ የተጫነባቸው ሁለት አህዮች እየነዳ ሊያገኘው መጣ።+ +2 ንጉሡም ሲባን “እነዚህን ነገሮች ያመጣኸው ለምንድን ነው?” አለው። ሲባም “አህዮቹን የንጉሡ ቤተሰብ እንዲቀመጥባቸው፣ ዳቦውንና የበጋ ፍሬውን ደግሞ ወጣቶቹ እንዲበሏቸው፣ የወይን ጠጁንም በምድረ በዳ የደከሙ ሰዎች እንዲጠጡት ነው” ሲል መለሰ።+ +3 ንጉሡም “የጌታህ ልጅ* የት አለ?” አለው።+ በዚህ ጊዜ ሲባ ንጉሡን “‘ዛሬ የእስራኤል ቤት የአባቴን ንጉሣዊ ሥልጣን ይመልስልኛል’ ብሎ ስላሰበ ኢየሩሳሌም ቀርቷል” አለው።+ +4 ንጉሡም ሲባን “እንግዲህ የሜፊቦስቴ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው” አለው።+ ሲባም “በፊትህ እሰግዳለሁ። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በአንተ ዘንድ ሞገስ ላግኝ” ሲል መለሰ።+ +5 ንጉሥ ዳዊትም ባሁሪም ሲደርስ ከሳኦል ቤት የሆነ ሺምአይ+ የተባለ ሰው ከዚያ ወጥቶ እየተራገመ+ ወደ እነሱ ቀረበ፤ እሱም የጌራ ልጅ ነበር። +6 ሺምአይ በንጉሥ ዳዊትና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ እንዲሁም በንጉሡ ግራና ቀኝ በነበረው ሕዝብ ሁሉና በኃያላኑ ላይ ድንጋይ ይወረውር ነበር። +7 ሺምአይም እንዲህ እያለ ይራገም ነበር፦ “ውጣ፣ ከዚህ ውጣ፣ አንተ የደም ሰው! አንተ የማትረባ ሰው! +8 ንግሥናውን በወሰድክበት በሳኦል ቤት የተነሳ ያለብህን የደም ዕዳ በሙሉ ይሖዋ በአንተ ላይ እያመጣብህ ነው፤ ይሖዋም መንግሥትህን ለልጅህ ለአቢሴሎም አሳልፎ ይሰጠዋል። የደም ሰው ስለሆንክ ይኸው መከራህን እያየህ ነው!”+ +9 ከዚያም የጽሩያ+ ልጅ አቢሳ ንጉሡን “ይህ የሞተ ውሻ+ ጌታዬን ንጉሡን የሚራገመው ለምንድን ነው?+ እባክህ ልሂድና ራሱን ልቁረጠው”+ አለው። +10 ንጉሡ ግን “እናንተ የጽሩያ ልጆች፣ ከእናንተ ጋር ምን የሚያገናኘኝ ጉዳይ አለ?+ ተዉት ይርገመኝ፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ‘ዳዊትን እርገመው!’ ብሎታል።+ ታዲያ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ማን ሊለው ይችላል?” አለው። +11 ከዚያም ዳዊት አቢሳንና አገልጋዮቹን በሙሉ እንዲህ አላቸው፦ “ከአብራኬ የወጣው የገዛ ልጄ እንኳ ይኸው ሕይወቴን* እየፈለገ አይደል?+ ታዲያ አንድ ቢንያማዊ+ እንዲህ ቢያደርግ ምን ያስደንቃል! ተዉት ይርገመኝ፤ ይሖዋ እርገመው ብሎት ነው! +12 ምናልባትም ይሖዋ መከራዬን ያይልኝና+ በዛሬው እርግማን ፋንታ ይሖዋ መልካም ነገር ያደርግልኝ ይሆናል።”+ +13 ከዚያም ዳዊትና ሰዎቹ መንገዱን ይዘው ቁልቁል ወረዱ፤ ሺምአይም በተራራው ጥግ ከዳዊት ጎን ጎን እየሄደ ይራገም፣+ ድንጋይ ይወረውርና አቧራ ይበትን ነበር። +14 በኋላም ንጉሡና አብሮት የነበረው ሕዝብ በሙሉ ወዳሰቡበት ቦታ ደረሱ፤ እነሱም በጣም ደክሟቸው ነበር፤ በዚያም አረፉ። +15 ይህ በእንዲህ እንዳለ አቢሴሎምና የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ኢየሩሳሌም ደረሱ፤ አኪጦፌልም+ አብሮት ነበር። +16 የዳዊት ወዳጅ* አርካዊው+ ኩሲም+ ልክ ወደ አቢሴሎም እንደገባ አቢሴሎምን “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!+ ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” አለው። +17 በዚህ ጊዜ አቢሴሎም ኩሲን “ለወዳጅህ ታማኝ ፍቅር የምታሳየው በዚህ መንገድ ነው? ከወዳጅህ ጋር አብረህ ያልሄድከው ለምንድን ነው?” አለው። +18 ኩሲም አቢሴሎምን እንዲህ አለው፦ “በጭራሽ፣ እንዲህማ አላደርግም፤ ይሖዋ፣ ይህ ሕዝብና የእስራኤል ሰዎች በሙሉ ከመረጡት ሰው ጎን እቆማለሁ። ከእሱም ጋር እቀመጣለሁ። +19 ደግሜ ይህን እናገራለሁ፣ ማገልገል ያለብኝ ማንን ነው? ልጁን አይደለም? አባትህን እንዳገለገልኩ ሁሉ አንተንም አገለግላለሁ።”+ +20 ከዚያም አቢሴሎም አኪጦፌልን “እስቲ ምክር ስጡኝ።+ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለው። +21 አኪጦፌልም አቢሴሎምን “አባትህ፣ ቤቱን* እንዲጠብቁ ከተዋቸው+ ቁባቶቹ ጋር ግንኙነት ፈጽም።+ ከዚያም እስራኤላውያን ሁሉ ራስህን በአባትህ ዘንድ እንደ ጥንብ እንዳስቆጠርክ ይሰማሉ፤ አንተንም የሚደግፉ ብርታት ያገኛሉ” አለው። +22 በመሆኑም ለአቢሴሎም በጣሪያው ላይ ድንኳን ተከሉለት፤+ አቢሴሎምም እስራኤላውያን ሁሉ እያዩት+ ከአባቱ ቁባቶች ጋር ግንኙነት ፈጸመ።+ +23 በዚያ ዘመን አኪጦፌል+ የሚሰጠው ምክር እንደ እውነተኛው አምላክ ቃል ተደርጎ* ይቆጠር ነበር። ዳዊትም ሆነ አቢሴሎም የአኪጦፌልን ምክር ሁሉ የሚያዩት እንደዚያ ነበር። +"6 ዳዊትም በእስራኤል ውስጥ ያሉትን ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎች በሙሉ በድጋሚ ሰበሰበ፤ ብዛታቸውም 30,000 ነበር።" +2 ከዚያም አብሮት ከነበረው ሕዝብ ሁሉ ጋር ተነስቶ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት+ ለማምጣት በዙፋን ላይ ከኪ��ቤል በላይ የተቀመጠው*+ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ+ ስም ወደተጠራበት ወደ በዓለይሁዳ ሄደ። +3 ይሁን እንጂ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በኮረብታ ላይ ካለው ከአቢናዳብ+ ቤት ለማምጣት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፤+ የአቢናዳብ ልጆች የሆኑት ዖዛ እና አሂዮም አዲሱን ሠረገላ ይነዱ ነበር። +4 በመሆኑም የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በኮረብታ ላይ ከነበረው ከአቢናዳብ ቤት ይዘው ጉዞ ጀመሩ፤ አሂዮም ከታቦቱ ፊት ፊት ይሄድ ነበር። +5 ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት ከጥድ እንጨት በተሠሩ የተለያዩ መሣሪያዎች፣ በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎች፣+ በአታሞ፣+ በጸናጽልና በሲምባል*+ ታጅበው በይሖዋ ፊት በደስታ ይጨፍሩ ነበር። +6 ወደ ናኮን አውድማ ሲደርሱ ግን ከብቶቹ ታቦቱን ሊጥሉት ተቃርበው ስለነበር ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ያዘ።+ +7 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ በመሆኑም ዖዛ እንዲህ ያለ የድፍረት ድርጊት+ በመፈጸሙ እውነተኛው አምላክ እዚያው ቀሰፈው፤+ እሱም በእውነተኛው አምላክ ታቦት አጠገብ እዚያው ሞተ። +8 ሆኖም የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ስለነደደ ዳዊት ተበሳጨ፤* ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ጴሬዝዖዛ* ተብሎ ይጠራል። +9 ዳዊትም በዚያን ዕለት ይሖዋን ፈርቶ+ “ታዲያ የይሖዋ ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?” አለ።+ +10 ዳዊትም የይሖዋ ታቦት እሱ ወዳለበት ወደ ዳዊት ከተማ+ እንዲመጣ አልፈለገም። ይልቁንም ታቦቱ የጌት ሰው ወደሆነው ወደ ኦቤድዔዶም+ ቤት እንዲወሰድ አደረገ። +11 የይሖዋም ታቦት የጌት ሰው በሆነው በኦቤድዔዶም ቤት ለሦስት ወር ተቀመጠ፤ ይሖዋም ኦቤድዔዶምን እና ቤተሰቡን በሙሉ ባረከ።+ +12 በመጨረሻም ዳዊት “ይሖዋ በእውነተኛው አምላክ ታቦት የተነሳ የኦቤድዔዶምን ቤትና የእሱ የሆነውን ነገር ሁሉ ባርኳል” ተብሎ ተነገረው። ስለሆነም ዳዊት የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ከኦቤድዔዶም ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በታላቅ ደስታ ለማምጣት ሄደ።+ +13 የይሖዋን ታቦት የተሸከሙት+ ሰዎች ስድስት እርምጃ ከተራመዱ በኋላ ዳዊት አንድ በሬና አንድ የሰባ ጥጃ ሠዋ። +14 ዳዊትም በሙሉ ኃይሉ በይሖዋ ፊት ይጨፍር ነበር፤ በዚህ ጊዜ ሁሉ ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ* ነበር።+ +15 ዳዊትና የእስራኤል ቤት በሙሉ የይሖዋን ታቦት+ በእልልታና+ በቀንደ መለከት+ አጅበው አመጡት። +16 ይሁንና የይሖዋ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በመጣ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል+ በመስኮት ሆና ወደ ታች ተመለከተች፤ እሷም ንጉሥ ዳዊት በይሖዋ ፊት ሲዘልና ሲጨፍር አይታ በልቧ ናቀችው።+ +17 በዚህ መንገድ የይሖዋን ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ በተዘጋጀለት ቦታ ላይ አስቀመጡት።+ ከዚያም ዳዊት የሚቃጠሉ መባዎችንና+ የኅብረት መሥዋዕቶችን+ በይሖዋ ፊት አቀረበ።+ +18 ዳዊት የሚቃጠሉትን መባዎችና የኅብረት መሥዋዕቶቹን አቅርቦ ሲጨርስ ሕዝቡን በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ስም ባረከ። +19 በተጨማሪም ለሕዝቡ ሁሉ ይኸውም ለተሰበሰቡት እስራኤላውያን በሙሉ፣ ለእያንዳንዱ ወንድና ሴት አንድ ዳቦ፣ አንድ የቴምር ጥፍጥፍና አንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ አከፋፈለ፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ወደየቤቱ ሄደ። +20 በዚህ ጊዜ ዳዊት የራሱን ቤት ለመባረክ ተመለሰ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮልም+ ዳዊትን ልትቀበለው ወጥታ “ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ እንደ አንድ ተራ ሰው በአገልጋዮቹ ሴት ባሪያዎች ፊት እርቃኑን በመሆኑ እንዴት ራሱን አስከብሯል!” አለችው።+ +21 በዚህ ጊዜ ዳዊት ሜልኮልን እንዲህ አላት፦ “የጨፈርኩት እኮ ከአባትሽና በቤቱ ካሉት ሁሉ ይልቅ እኔን መርጦ በይሖዋ ሕዝብ በእስራኤል ላይ መሪ አድርጎ በሾመኝ በይሖዋ ፊት ነው፤+ አሁንም ቢሆን በይሖዋ ፊት እጨፍራለሁ። +22 እንዲያው�� ከዚህ የባሰ ራሴን አዋርዳለሁ፤ ራሴንም እንቃለሁ። ሆኖም አንቺ በጠቀስሻቸው ሴት ባሪያዎች ፊት እከበራለሁ።” +23 የሳኦል ልጅ ሜልኮልም+ እስከሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም። +10 ከጊዜ በኋላ የአሞናውያን+ ንጉሥ ሞተ፤ ልጁ ሃኑንም በእሱ ፋንታ ነገሠ።+ +2 በዚህ ጊዜ ዳዊት “አባቱ ታማኝ ፍቅር እንዳሳየኝ ሁሉ እኔም ለናሃሽ ልጅ ለሃኑን ታማኝ ፍቅር አሳየዋለሁ” አለ። ስለሆነም ዳዊት፣ በአባቱ ሞት ከደረሰበት ሐዘን እንዲያጽናኑት አገልጋዮቹን ወደ ሃኑን ላከ። ሆኖም የዳዊት አገልጋዮች ወደ አሞናውያን ምድር ሲደርሱ +3 የአሞናውያን መኳንንት ጌታቸውን ሃኑንን “ዳዊት አጽናኞችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃል? ዳዊት አገልጋዮቹን ወደ አንተ የላከው ከተማዋን በሚገባ ለማጥናት፣ ለመሰለልና ለመገልበጥ አይደለም?” አሉት። +4 በመሆኑም ሃኑን የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ ግማሹን ጢማቸውን ላጫቸው፤+ ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ላካቸው። +5 ዳዊትም ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ መልእክተኞችን ወደ ሰዎቹ ላከ፤ ምክንያቱም በኀፍረት ተውጠው ነበር፤ ንጉሡም “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ+ ቆዩ፤ ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው። +"6 ውሎ አድሮ አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ጥንብ እንደተቆጠሩ ተገነዘቡ፤ በመሆኑም አሞናውያን፣ ሰዎችን በመላክ ከቤትሬሆብ+ ሶርያውያንና ከጾባህ+ ሶርያውያን 20,000 እግረኛ ተዋጊዎችን፣ የማአካን+ ንጉሥ ከ1,000 ሰዎች ጋር እንዲሁም ከኢሽጦብ* 12,000 ሰዎችን ቀጠሩ።+" +7 ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን እንዲሁም እጅግ ኃያላን የሆኑትን ተዋጊዎቹን+ ጨምሮ መላውን ሠራዊት ላከ። +8 አሞናውያንም ወጥተው በከተማዋ መግቢያ ላይ ለውጊያ ተሰለፉ፤ የጾባህና የሬሆብ ሶርያውያን ደግሞ ከኢሽጦብና* ከማአካ ጋር ሆነው ለብቻቸው ሜዳ ላይ ተሰለፉ። +9 ኢዮዓብ ወታደሮቹ ከፊትና ከኋላ ጥቃት ለመሰንዘር ወደ እሱ እየገሰገሱ መምጣታቸውን ሲያይ በእስራኤል ካሉት ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎች መካከል የተወሰኑትን መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው።+ +10 የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ+ አመራር ሥር* ሆነው አሞናውያንን+ እንዲገጥሙ አሰለፋቸው። +11 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ ትደርስልኛለህ፤ አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ እደርስልሃለሁ። +12 ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል ብርቱና ደፋር መሆን አለብን፤+ ይሖዋም በፊቱ መልካም የሆነውን ነገር ያደርጋል።”+ +13 ከዚያም ኢዮዓብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሶርያውያንን ለመግጠም ወደ እነሱ ሲገሰግሱ ሶርያውያኑ ከፊታቸው ሸሹ።+ +14 አሞናውያንም ሶርያውያን እንደ ሸሹ ሲያዩ ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማዋ ገቡ። ከዚያም ኢዮዓብ አሞናውያንን ከመውጋት ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። +15 ሶርያውያንም በእስራኤላውያን ድል እንደተመቱ ሲያዩ በአዲስ መልክ ተደራጁ።+ +16 በመሆኑም ሃዳድኤዜር+ በወንዙ*+ አካባቢ ወደነበሩት ሶርያውያን መልእክተኞችን ላከ፤ እነሱም የሃዳድኤዜር ሠራዊት አለቃ በሆነው በሾባክ መሪነት ወደ ሄላም መጡ። +17 ዳዊት ወሬው በተነገረው ጊዜ ወዲያውኑ እስራኤላውያንን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን በመሻገር ወደ ሄላም መጣ። ሶርያውያንም ዳዊትን ለመግጠም ተሰለፉ፤ ከእሱም ጋር ተዋጉ።+ +"18 ሆኖም ሶርያውያን ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን መካከል 700 ሠረገለኞችንና 40,000 ፈረሰኞችን ገደለ፤ የሠራዊታቸው አለቃ የሆነውን ሾባክንም መታው፤ እሱም እዚያው ሞተ።+" +19 የሃዳድኤዜር አገልጋዮች የሆኑት ነገሥታት በሙሉ እስራኤላውያን እንዳሸነፏቸው ባዩ ጊዜ ወዲያውኑ ከ���ስራኤላውያን ጋር እርቅ በመፍጠር ለእነሱ ተገዙ፤+ ሶርያውያንም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አሞናውያንን መርዳት ፈሩ። +14 የጽሩያ+ ልጅ ኢዮዓብ የንጉሡ ልብ አቢሴሎምን እንደናፈቀ ተረዳ።+ +2 በመሆኑም ኢዮአብ ወደ ተቆአ፣+ ሰው ልኮ አንዲት ብልህ ሴት አስመጣ፤ እንዲህም አላት፦ “እባክሽ፣ ሐዘንተኛ ምሰዪ፤ የሐዘን ልብስ ልበሺ፤ ዘይትም አትቀቢ።+ ሰው ሞቶባት ለረጅም ጊዜ እንዳዘነች ሴት ሁኚ። +3 ወደ ንጉሡም ገብተሽ እንዲህ በይው።” ከዚያም ኢዮዓብ ምን እንደምትል ነገራት። +4 ተቆአዊቷም ሴት ወደ ንጉሡ ከገባች በኋላ በግንባሯ ተደፍታ በመስገድ “ንጉሥ ሆይ፣ እርዳኝ!” አለች። +5 ንጉሡም “ምን ሆነሽ ነው?” አላት። እሷም እንዲህ አለችው፦ “እኔ ባሌ የሞተብኝ መበለት ነኝ። +6 እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ እነሱም ሜዳ ላይ ተደባደቡ። ገላጋይም ስላልነበረ አንደኛው ሌላኛውን መትቶ ገደለው። +7 በኋላም ቤተ ዘመድ ሁሉ በእኔ በአገልጋይህ ላይ ተነስቶ ‘ወራሹን ማጥፋት ቢሆንብንም እንኳ የወንድሙን ሕይወት* ስላጠፋ እሱን እንድንገድለው ገዳዩን አሳልፈሽ ስጪን’ ይለኝ ጀመር።+ በመሆኑም የቀረችኝን አንዲት ፍም* በማጥፋት ባሌን በምድር ላይ ያለስምና ያለዘር ሊያስቀሩት ነው።” +8 ከዚያም ንጉሡ ሴትየዋን “በቃ አንቺ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ የአንቺን ጉዳይ በተመለከተ ትእዛዝ እሰጣለሁ” አላት። +9 በዚህ ጊዜ ተቆአዊቷ ሴት ንጉሡን “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ንጉሡና ዙፋኑ ንጹሐን ስለሆኑ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ይሁን” አለችው። +10 ከዚያም ንጉሡ “ከዚህ በኋላ ማንም ሰው ቢናገርሽ ወደ እኔ አምጪው፤ ዳግመኛም አያስቸግርሽም” አላት። +11 እሷ ግን “ደም ተበቃዩ+ በልጄ ላይ ጉዳት እንዳያደርስበትና እንዳይገድለው እባክህ ንጉሡ አምላኩን ይሖዋን ያስብ” አለችው። እሱም “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣+ ከልጅሽ ራስ ላይ አንዲት ፀጉር እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አላት። +12 ሴትየዋም “እባክህ አገልጋይህ ለጌታዬ ለንጉሡ አንዲት ቃል እንድትናገር ፍቀድላት” አለች። እሱም “እሺ፣ ተናገሪ!” አላት። +13 ከዚያም ሴትየዋ እንዲህ አለች፦ “ታዲያ አንተ በአምላክ ሕዝብ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ለማድረግ ያሰብከው ለምንድን ነው?+ ንጉሡ የተሰደደውን የገዛ ልጁን ባለመመለሱ እንዲህ ብሎ ሲናገር ራሱን በደለኛ እያደረገ ነው።+ +14 ሁላችንም መሞታችን አይቀርም፤ የፈሰሰ ውኃ እንደማይታፈስ ሁሉ እኛም እንደዚሁ እንሆናለን። ሆኖም አምላክ ሕይወት* አያጠፋም፤ እንዲሁም የተሰደደ ሰው ከእሱ ርቆ በዚያው ተሰዶ እንዳይቀር እሱን ለመመለስ ምክንያት ይፈልጋል። +15 አሁንም ለጌታዬ ለንጉሡ ይህን ነገር ለመናገር የመጣሁት ሕዝቡ ስላስፈራኝ ነው። በመሆኑም አገልጋይህ እንዲህ ብላ አሰበች፦ ‘እንግዲህ አሁን ንጉሡን ላነጋግረው። ምናልባትም ንጉሡ ባሪያው የጠየቀችውን ነገር ይፈጽምላት ይሆናል። +16 ንጉሡ ቃሌን ሰምቶ እኔንም ሆነ አንድ ልጄን አምላክ ከሰጠን ርስት ላይ ሊያጠፋን ከሚፈልገው ሰው እጅ ባሪያውን ይታደጋት ይሆናል።’+ +17 ከዚያም አገልጋይህ ‘የጌታዬ የንጉሡ ቃል እረፍት ይስጠኝ’ አለች፤ ምክንያቱም ጌታዬ ንጉሡ ጥሩውን ከመጥፎው በመለየት ረገድ እንደ እውነተኛው አምላክ መልአክ ነው። አምላክህ ይሖዋም ከአንተ ጋር ይሁን።” +18 ንጉሡም መልሶ ሴትየዋን “እባክሽ፣ የምጠይቅሽን ነገር አንድም ሳትደብቂ ንገሪኝ” አላት። ሴትየዋም “እሺ፣ ንጉሡ ጌታዬ ይናገር” አለች። +19 ከዚያም ንጉሡ “በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ የኢዮዓብ እጅ አለበት?” ሲል ጠየቃት።+ ሴትየዋም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በሕያውነትህ* እምላለሁ፣ ጌታዬ ንጉሡ እንደተ���ገረው ነው፤* ይህን እንዳደርግ ያዘዘኝና አገልጋይህ የተናገረችውን ነገር ሁሉ የነገራት አገልጋይህ ኢዮዓብ ነው። +20 አገልጋይህ ኢዮዓብ ይህን ያደረገው ሁኔታውን ለመለወጥ ሲል ነው፤ ሆኖም ጌታዬ እንደ እውነተኛው አምላክ መልአክ ዓይነት ጥበብ አለው፤ በምድሪቱ ላይ የሚከናወነውንም ነገር ሁሉ ያውቃል።” +21 ከዚያም ንጉሡ ኢዮዓብን “እሺ፣ ይህን አደርጋለሁ።+ በል ሂድና ወጣቱን አቢሴሎምን መልሰህ አምጣው” አለው።+ +22 በዚህ ጊዜ ኢዮዓብ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ በመስገድ ንጉሡን አመሰገነ። ከዚያም “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ንጉሡ አገልጋዩ የጠየቀውን ነገር ስለፈጸመለት ዛሬ እኔ አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ እንዳገኘሁ አወቅኩ” አለ። +23 ኢዮዓብም ተነስቶ ወደ ገሹር+ ሄደ፤ አቢሴሎምንም ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው። +24 ሆኖም ንጉሡ “ወደ ራሱ ቤት ይመለስ፤ ፊቴን እንዳያይ” አለ። በመሆኑም አቢሴሎም ወደ ራሱ ቤት ተመለሰ፤ የንጉሡንም ፊት አላየም። +25 መቼም በመልኩ ማማር የአቢሴሎምን ያህል የተወደሰ አንድም ወንድ በመላው እስራኤል አልነበረም። ከእግር ጥፍሩ አንስቶ እስከ ራስ ፀጉሩ ድረስ ምንም እንከን አይወጣለትም ነበር። +26 የራስ ፀጉሩን ሲቆረጠው ፀጉሩ በቤተ መንግሥቱ የድንጋይ ሚዛን* 200 ሰቅል* ይመዝን ነበር፤ ፀጉሩም በጣም ስለሚከብደው ሁልጊዜ በዓመቱ መጨረሻ ላይ መቆረጥ ነበረበት። +27 አቢሴሎም ትዕማር የምትባል አንዲት ሴት ልጅና ሦስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።+ ትዕማር በጣም ቆንጆ ነበረች። +28 አቢሴሎምም በኢየሩሳሌም ድፍን ሁለት ዓመት ተቀመጠ፤ ሆኖም የንጉሡን ፊት አላየም።+ +29 በመሆኑም አቢሴሎም ወደ ንጉሡ ሊልከው ስለፈለገ ኢዮዓብን አስጠራው፤ ኢዮዓብ ግን ወደ እሱ ሳይመጣ ቀረ። ለሁለተኛ ጊዜም ሰው ላከበት፤ እሱ ግን አሁንም ለመምጣት ፈቃደኛ አልሆነም። +30 በመጨረሻም አቢሴሎም አገልጋዮቹን “የኢዮዓብ እርሻ የሚገኘው ከእኔ እርሻ አጠገብ ነው፤ በእርሻው ላይም የገብስ አዝመራ አለ። ሂዱና እሳት ልቀቁበት” አላቸው። በመሆኑም የአቢሴሎም አገልጋዮች በእርሻው ላይ እሳት ለቀቁበት። +31 በዚህ ጊዜ ኢዮዓብ ተነስቶ ወደ አቢሴሎም ቤት በመምጣት “አገልጋዮችህ እርሻዬን በእሳት ያቃጠሉት ለምንድን ነው?” አለው። +32 አቢሴሎምም ኢዮዓብን እንዲህ አለው፦ “ወደ እኔ ናና ለንጉሡ ‘“ከገሹር የመጣሁት ለምንድን ነው?+ እዚያው ብሆን ይሻለኝ ነበር። አሁንም ቢሆን የንጉሡን ፊት ማየት እፈልጋለሁ፤ ጥፋት ከተገኘብኝም ይግደለኝ” ብለህ እንድትነግርልኝ ልላክህ’ ብዬ መልእክት ላክሁብህ።” +33 በመሆኑም ኢዮዓብ ወደ ንጉሡ ገብቶ ይህንኑ ነገረው። ንጉሡም አቢሴሎምን ጠራው፤ አቢሴሎምም ወደ ንጉሡ ገብቶ በንጉሡ ፊት በግንባሩ መሬት ላይ በመደፋት ሰገደ። ንጉሡም አቢሴሎምን ሳመው።+ +9 ከዚያም ዳዊት “ለመሆኑ ለዮናታን ስል ታማኝ ፍቅር ላሳየው የምችል ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው ይኖራል?” አለ።+ +2 በዚህ ጊዜ የሳኦል ቤት አገልጋይ የሆነ ሲባ+ የሚባል ሰው ነበር። እሱንም ወደ ዳዊት እንዲመጣ ጠሩት፤ ንጉሡም “ሲባ የምትባለው አንተ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም “አዎ፣ እኔ አገልጋይህ ሲባ ነኝ” በማለት መለሰ። +3 ከዚያም ንጉሡ “እንደው የአምላክን ታማኝ ፍቅር ላሳየው የምችል ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው ይኖራል?” አለው። ሲባም ንጉሡን “ሁለቱም እግሮቹ ሽባ+ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” አለው። +4 ንጉሡም “ለመሆኑ የት ነው ያለው?” አለው። ሲባም ንጉሡን “ሎደባር ባለው በአሚዔል ልጅ በማኪር+ ቤት ይገኛል” አለው። +5 ንጉሥ ዳዊትም ወዲያውኑ መልእክተኞችን ልኮ ሎደባር ከሚገኘው ከአሚዔል ልጅ ከማኪር ቤት አስመጣው። +6 የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜፊቦስቴ ወደ ዳዊት ሲገባ ወዲያውኑ በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደ። ከዚያም ዳዊት “ሜፊቦስቴ!” ብሎ ጠራው፤ እሱም “አቤት ጌታዬ” አለ። +7 ዳዊትም “ለአባትህ ለዮናታን ስል ታማኝ ፍቅር ስለማሳይህ አትፍራ፤+ የአያትህን የሳኦልንም መሬት በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ አንተም ዘወትር ከማዕዴ ትበላለህ”+ አለው። +8 እሱም ከሰገደ በኋላ “እንደ እኔ ላለ የሞተ ውሻ+ ሞገስ ታሳይ ዘንድ ለመሆኑ እኔ አገልጋይህ ማን ነኝ?” አለው። +9 ከዚያም ንጉሡ ለሳኦል አገልጋይ ለሲባ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “የሳኦልና የቤተሰቡ የሆነውን ነገር ሁሉ ለጌታህ የልጅ ልጅ ሰጥቼዋለሁ።+ +10 አንተ፣ ልጆችህና አገልጋዮችህ መሬቱን ታርሱለታላችሁ፤ ምርቱንም ታስገቡለታላችሁ፤ ይህም ለጌታህ የልጅ ልጅ ቤተሰቦች መብል ይሆናል። የጌታህ የልጅ ልጅ ሜፊቦስቴ ግን ዘወትር ከማዕዴ ይመገባል።”+ ሲባ 15 ልጆችና 20 አገልጋዮች ነበሩት።+ +11 ከዚያም ሲባ ንጉሡን “እኔ አገልጋይህ፣ ጌታዬ ንጉሡ ያዘዘኝን ሁሉ እፈጽማለሁ” አለው። ስለዚህ ሜፊቦስቴ ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት* ማዕድ በላ። +12 ሜፊቦስቴም ሚካ+ የሚባል ትንሽ ልጅ ነበረው፤ በሲባ ቤት የሚኖሩም ሁሉ የሜፊቦስቴ አገልጋዮች ሆኑ። +13 ሜፊቦስቴም ዘወትር ከንጉሡ ማዕድ ይበላ+ ስለነበር የሚኖረው በኢየሩሳሌም ነበር፤ ሁለቱም እግሮቹ ሽባ ነበሩ።+ +13 የዳዊት ልጅ አቢሴሎም ትዕማር+ የምትባል ቆንጆ እህት ነበረችው፤ የዳዊት ልጅ አምኖንም+ ወደዳት። +2 አምኖን በእህቱ በትዕማር ምክንያት በጣም ከመጨነቁ የተነሳ ታመመ፤ ምክንያቱም ድንግል ስለነበረች በእሷ ላይ ምንም ነገር ማድረግ እንደማይችል ሆኖ ተሰምቶት ነበር። +3 አምኖን፣ ኢዮናዳብ+ የተባለ ጓደኛ ነበረው፤ እሱም የዳዊት ወንድም የሆነው የሺምአህ+ ልጅ ነው፤ ኢዮናዳብም ብልህ ሰው ነበር። +4 እሱም አምኖንን “አንተ የንጉሥ ልጅ፣ በየቀኑ እንዲህ የምትጨነቀው ለምንድን ነው? ለምን አትነግረኝም?” አለው። አምኖንም “የወንድሜን የአቢሴሎምን እህት+ ትዕማርን አፍቅሬ ነው” አለው። +5 በዚህ ጊዜ ኢዮናዳብ እንዲህ አለው፦ “የታመምክ መስለህ አልጋህ ላይ ተኛ። አባትህም ሊጠይቅህ ሲመጣ ‘እባክህ፣ እህቴ ትዕማር መጥታ ምግብ ትስጠኝ። ለታመመ ሰው የሚሆነውን ምግብ* እዚሁ እያየኋት ታዘጋጅልኝና በእጇ ታጉርሰኝ’ በለው።” +6 ስለዚህ አምኖን የታመመ መስሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊጠይቀው መጣ። ከዚያም አምኖን ንጉሡን “እባክህ፣ እህቴ ትዕማር ትምጣና እዚሁ እያየኋት ሁለት ቂጣ* ጋግራ በእጇ ታጉርሰኝ” አለው። +7 ዳዊትም “እባክሽ፣ ወደ ወንድምሽ ወደ አምኖን ቤት ሄደሽ ምግብ* አዘጋጂለት” ብለው ለትዕማር እንዲነግሯት ወደ ቤት መልእክት ላከ። +8 በመሆኑም ትዕማር ወደ ወንድሟ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፤ እሱም እዚያ ተኝቶ ነበር። እሷም ሊጥ ካቦካች በኋላ እዚያው እያየ ጠፍጥፋ ጋገረችው። +9 ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ ቂጣውን አቀረበችለት። አምኖን ግን ለመብላት ፈቃደኛ አልሆነም፤ እሱም “ሁሉንም ሰው ከዚህ አስወጡልኝ!” አለ። ስለዚህ ሁሉም ሰው ትቶት ወጣ። +10 በዚህ ጊዜ አምኖን ትዕማርን “በእጅሽ እንድታጎርሺኝ ምግቡን* ወደ መኝታ ክፍል አምጪልኝ” አላት። ትዕማርም የጋገረችውን ቂጣ ይዛ ወንድሟ አምኖን ወደነበረበት መኝታ ክፍል ገባች። +11 እሷም ምግቡን እንዲበላ ስታቀርብለት አፈፍ አድርጎ ያዛትና “እህቴ ሆይ፣ ነይ፣ አብረሽኝ ተኚ” አላት። +12 እሷ ግን እንዲህ አለችው፦ “ወንድሜ ሆይ፣ ይሄማ ፈጽሞ አይሆንም! እባክህ አታዋርደኝ፤ በእስራኤል ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር ተደርጎ አያውቅም።+ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽም።+ +13 እኔስ ብሆን ይህን ነውሬን ተሸክሜ እንዴት እኖራ��ሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል ውስጥ ካሉት ወራዳ ሰዎች እንደ አንዱ ትቆጠራለህ። ስለዚህ አሁን፣ እባክህ ንጉሡን አነጋግረው፤ እሱም ቢሆን እኔን አይከለክልህም።” +14 እሱ ግን ሊሰማት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ኃይል ተጠቅሞ በማስነወር አዋረዳት። +15 ከዚያም አምኖን እጅግ በጣም ጠላት፤ ለእሷ ያደረበት ጥላቻም ለእሷ ከነበረው ፍቅር በለጠ። አምኖንም “ተነሽ ውጭልኝ!” አላት። +16 በዚህ ጊዜ “ወንድሜ ሆይ፣ ይሄማ አይሆንም፤ አሁን እኔን ማባረርህ ቀደም ሲል ከፈጸምክብኝ ነገር የከፋ ይሆናል!” አለችው። እሱ ግን ሊሰማት ፈቃደኛ አልሆነም። +17 ከዚያም አምኖን የሚያገለግለውን ወጣት ጠርቶ “እባክህ ይህችን ሴት ከፊቴ አስወጣና በሩን ዝጋባት” አለው። +18 (እሷም የሚያምር* ልብስ ለብሳ ነበር፤ ምክንያቱም ድንግል የሆኑት የንጉሡ ሴቶች ልጆች እንዲህ ዓይነት ልብስ ይለብሱ ነበር።) በመሆኑም አገልጋዩ ወደ ውጭ አስወጥቶ በሩን ዘጋባት። +19 ከዚያም ትዕማር ራሷ ላይ አመድ ነሰነሰች፤+ የለበሰችውንም የሚያምር ቀሚስ ቀደደች፤ በእጇም ራሷን ይዛ እያለቀሰች ሄደች። +20 በዚህ ጊዜ ወንድሟ አቢሴሎም+ “ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበር? እህቴ ሆይ፣ በቃ አሁን ዝም በይ። እንግዲህ እሱ ወንድምሽ ነው።+ ይህን ነገር በልብሽ አታብሰልስዪው” አላት። ከዚያም ትዕማር ከሌሎች ተገልላ በወንድሟ በአቢሴሎም ቤት ተቀመጠች። +21 ንጉሥ ዳዊት የሆነውን ነገር ሁሉ ሲሰማ እጅግ ተቆጣ።+ ሆኖም አምኖን የበኩር ልጁ በመሆኑ በጣም ይወደው ስለነበር ሊያስቀይመው አልፈለገም። +22 አቢሴሎምም አምኖንን ክፉም ሆነ ደግ አልተናገረውም፤ ምክንያቱም አቢሴሎም፣ አምኖን እህቱን ትዕማርን ስላዋረዳት+ ጠልቶት ነበር።+ +23 ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ እንዲህ ሆነ፤ አቢሴሎም በኤፍሬም+ አቅራቢያ ባለችው በበዓልሃጾር በጎቹን ያሸልት ነበር፤ አቢሴሎምም የንጉሡን ወንዶች ልጆች በሙሉ ጋበዘ።+ +24 በመሆኑም አቢሴሎም ወደ ንጉሡ ገብቶ “አገልጋይህ በጎቹን እያሸለተ ነው። እባክህ፣ ንጉሡና አገልጋዮቹ ከእኔ ጋር ይሂዱ” አለው። +25 ንጉሡ ግን አቢሴሎምን “የእኔ ልጅ፣ ይሄማ አይሆንም! ሁላችንም ከሄድን ሸክም እንሆንብሃለን” አለው። አቢሴሎም አጥብቆ ቢለምነውም ንጉሡ ለመሄድ ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ባረከው። +26 ከዚያም አቢሴሎም “እሺ አንተ ካልሄድክ እባክህ ወንድሜ አምኖን አብሮን ይሂድ”+ አለው። ንጉሡም “ከአንተ ጋር የሚሄደው ለምንድን ነው?” አለው። +27 አቢሴሎም ግን አጥብቆ ለመነው፤ በመሆኑም ዳዊት አምኖንንና የንጉሡን ወንዶች ልጆች በሙሉ ላካቸው። +28 ከዚያም አቢሴሎም አገልጋዮቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፣ እኔም አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሞቅ ሲለው ‘አምኖንን ምቱት!’ እላችኋለሁ። እናንተም ትገድሉታላችሁ። አትፍሩ፤ የማዛችሁ እኔ አይደለሁም? በርቱ! ደፋሮች ሁኑ!” +29 በመሆኑም የአቢሴሎም አገልጋዮች በአምኖን ላይ ልክ አቢሴሎም እንዳዘዛቸው አደረጉበት፤ ከዚያም ሌሎቹ የንጉሡ ልጆች በሙሉ ተነስተው በየበቅሏቸው ላይ በመቀመጥ ሸሹ። +30 ገና በመንገድ ላይ ሳሉም ዳዊት “አቢሴሎም የንጉሡን ልጆች በሙሉ ፈጃቸው፤ አንድም የተረፈ ሰው የለም” የሚል ወሬ ደረሰው። +31 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተነሳ፤ ልብሱንም ቀዶ መሬት ላይ ተዘረረ፤ አገልጋዮቹም በሙሉ ልብሳቸውን ቀደው አጠገቡ ቆመው ነበር። +32 ሆኖም የዳዊት ወንድም የሺምአህ+ ልጅ የሆነው ኢዮናዳብ+ እንዲህ አለ፦ “ጌታዬ ወጣቶቹን የንጉሡን ወንዶች ልጆች በሙሉ እንደገደሏቸው አድርጎ አያስብ፤ ምክንያቱም የሞተው አምኖን ብቻ ነው።+ ይህም በአቢሴሎም ትእዛዝ የተፈጸመ ነው፤ እሱ፣ አ��ኖን እህቱን+ ትዕማርን+ ካስነወረበት ቀን አንስቶ ይህን ነገ +33 አሁንም ጌታዬ ንጉሡ ‘የንጉሡ ወንዶች ልጆች በሙሉ አልቀዋል’ ለሚለው ወሬ ጆሮ አይስጥ፤ የሞተው አምኖን ብቻ ነው።” +34 ይህ በእንዲህ እንዳለ አቢሴሎም ሸሸ።+ በኋላም ጠባቂው ቀና ብሎ ሲመለከት ከኋላው ባለው ከተራራው አጠገብ በሚገኘው መንገድ ላይ ብዙ ሰዎች ሲመጡ አየ። +35 በዚህ ጊዜ ኢዮናዳብ+ ንጉሡን “ይኸው፣ የንጉሡ ወንዶች ልጆች ተመልሰው መጥተዋል። የሆነውም ነገር ልክ አገልጋይህ እንደተናገረው ነው” አለው። +36 እሱም ተናግሮ እንደጨረሰ የንጉሡ ወንዶች ልጆች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እያለቀሱ ገቡ፤ ንጉሡና አገልጋዮቹም በሙሉ አምርረው አለቀሱ። +37 አቢሴሎም ግን ኮብልሎ የገሹር ንጉሥ ወደሆነው ወደ አሚሁድ ልጅ ወደ ታልማይ+ ሄደ። ዳዊትም ለልጁ ብዙ ቀናት አለቀሰ። +38 አቢሴሎም ሸሽቶ ወደ ገሹር+ ከሄደ በኋላ በዚያ ሦስት ዓመት ተቀመጠ። +39 በመጨረሻም የንጉሥ ዳዊት ነፍስ አቢሴሎምን ለማየት ናፈቀች፤ ምክንያቱም ዳዊት የአምኖን ሞት ካስከተለበት ሐዘን ተጽናንቶ ነበር። +5 ከጊዜ በኋላ የእስራኤል ነገዶች በሙሉ በኬብሮን+ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ፣ የሥጋህም ቁራጭ ነን።*+ +2 ባለፉት ዘመናት ሳኦል ንጉሣችን በነበረበት ጊዜ እስራኤል ወደ ጦርነት ሲወጣ የምትመራው* አንተ ነበርክ።+ ይሖዋም ‘ሕዝቤን እስራኤልን እረኛ ሆነህ ትጠብቃለህ፣ በእስራኤልም ላይ መሪ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”+ +3 በመሆኑም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ንጉሡ ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም በኬብሮን ከእነሱ ጋር በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ገባ።+ እነሱም ዳዊትን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ቀቡት።+ +4 ዳዊት በነገሠ ጊዜ 30 ዓመቱ ነበር፤ ለ40 ዓመትም ገዛ።+ +5 በኬብሮን ተቀምጦ በይሁዳ ላይ ለ7 ዓመት ከ6 ወር ገዛ፤ በኢየሩሳሌም+ ሆኖ ደግሞ በመላው እስራኤልና ይሁዳ ላይ ለ33 ዓመት ገዛ። +6 ዳዊትና ሰዎቹም በምድሪቱ የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን+ ለመውጋት ወደ ኢየሩሳሌም ዘመቱ። እነሱም ዳዊትን “ፈጽሞ ወደዚህ አትገባም! ዕውሮችና ሽባዎች እንኳ ያባርሩሃል” በማለት ተሳለቁበት። ይህን ያሉት ‘ዳዊት ፈጽሞ ወደዚህ አይገባም’ ብለው ስላሰቡ ነበር።+ +7 ይሁን እንጂ ዳዊት በአሁኑ ጊዜ የዳዊት ከተማ+ ተብላ የምትጠራውን የጽዮንን ምሽግ ያዘ። +8 ስለሆነም በዚያን ቀን ዳዊት “በኢያቡሳውያን ላይ ጥቃት የሚሰነዝር ማንኛውም ሰው ዳዊት የሚጠላቸውን* ‘ሽባዎችንና ዕውሮችን’ ለመምታት በውኃ መውረጃው ቦይ በኩል ማለፍ አለበት!” አለ። “ዕውርና ሽባ ፈጽሞ ወደ ቤት አይገቡም” የሚባለውም በዚህ የተነሳ ነው። +9 ከዚያም ዳዊት በምሽጉ ውስጥ መኖር ጀመረ፤ ስፍራውም የዳዊት ከተማ ተብሎ ይጠራ ነበር፤* እሱም ከጉብታው*+ አንስቶ ወደ ውስጥ ዙሪያውን መገንባት ጀመረ።+ +10 በዚህ ሁኔታ ዳዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ ሄደ፤+ የሠራዊት አምላክ ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር።+ +11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም+ መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ፤ እንዲሁም የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎችን፣+ አናጺዎችንና ለቅጥር የሚሆን ድንጋይ የሚጠርቡ ሰዎችን ላከ፤ እነሱም ለዳዊት ቤት* መሥራት ጀመሩ።+ +12 ዳዊትም ይሖዋ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናውና+ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤል ሲል+ መንግሥቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት+ አወቀ። +13 ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ቁባቶችን+ አስቀመጠ፤ እንዲሁም ሌሎች ሚስቶችን አገባ፤ ተጨማሪ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።+ +14 በኢየሩሳሌም ሳለ የተወለዱለት ልጆች ስም ይህ ነው፦ ሻሙአ፣ ሾባብ፣ ናታን፣+ ሰለሞን፣+ +15 ይብሃር፣ ኤሊሹዓ፣ ኔፌግ፣ ያፊአ፣ +16 ኤሊሻማ፣ ኤሊያዳ እና ኤሊፌሌት። +17 ፍልስጤማውያንም በሙሉ ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን+ ሲሰሙ እሱን ፍለጋ ወጡ።+ ዳዊትም ይህን ሲሰማ ወደ ምሽጉ ወረደ።+ +18 ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው በረፋይም ሸለቆ*+ ተበታትነው ሰፈሩ። +19 ዳዊትም “ወጥቼ ፍልስጤማውያንን ልግጠም? አንተስ በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ?” ሲል ይሖዋን ጠየቀ።+ ይሖዋም ዳዊትን “አዎ ውጣ፤ እኔም በእርግጥ ፍልስጤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ” አለው።+ +20 በመሆኑም ዳዊት ወደ በዓልጰራጺም መጥቶ በዚያ መታቸው። እሱም “ይሖዋ፣ ውኃ እንደጣሰው ግድብ ጠላቶቼን በፊቴ ደረማመሳቸው” አለ።+ ከዚህም የተነሳ ያን ቦታ በዓልጰራጺም*+ ብሎ ጠራው። +21 ፍልስጤማውያንም ጣዖቶቻቸውን በዚያ ጥለው ሸሹ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዷቸው።* +22 ከጊዜ በኋላ ፍልስጤማውያን እንደገና ወደ ረፋይም ሸለቆ*+ መጥተው ተበታትነው ሰፈሩ። +23 ዳዊትም ይሖዋን ጠየቀ፤ እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “በቀጥታ አትውጣ። ይልቁንም ከኋላቸው ዞረህ በባካ* ቁጥቋጦዎቹ ፊት ለፊት ግጠማቸው። +24 በባካ ቁጥቋጦዎቹ አናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ቆራጥ እርምጃ ውሰድ፤ ምክንያቱም ይህ በሚሆንበት ጊዜ ይሖዋ የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመምታት በፊትህ ወጥቷል ማለት ነው።” +25 በመሆኑም ዳዊት ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ ፍልስጤማውያንንም ከጌባ+ አንስቶ እስከ ጌዜር+ ድረስ መታቸው።+ +21 በዳዊት ዘመን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ረሃብ ሆነ፤+ ስለዚህ ዳዊት ይሖዋን ምክር ጠየቀ፤ ይሖዋም “ሳኦል ገባኦናውያንን ስለገደለ እሱም ሆነ ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ።+ +2 በመሆኑም ንጉሡ ገባኦናውያንን+ ጠርቶ አነጋገራቸው። (እርግጥ ገባኦናውያን ከአሞራውያን+ የተረፉ ናቸው እንጂ እስራኤላውያን አልነበሩም፤ እስራኤላውያንም እንደማያጠፏቸው ምለውላቸው ነበር፤+ ይሁንና ሳኦል ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ ባለው ቅንዓት ተነሳስቶ ሊያጠፋቸው ፈልጎ ነበር።) +3 ዳዊትም ገባኦናውያንን “የይሖዋን ርስት እንድትባርኩ ምን ላድርግላችሁ? ማስተሰረይስ የምችለው እንዴት ነው?” አላቸው። +4 ገባኦናውያንም “ከሳኦልና ከእሱ ቤት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ችግር በብርና በወርቅ የሚፈታ አይደለም፤+ ደግሞም በእስራኤል ውስጥ ማንንም ሰው የመግደል መብት የለንም” አሉት። በዚህ ጊዜ ዳዊት “ያላችሁትን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” አላቸው። +5 እነሱም ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ለጥፋት ከዳረገንና በየትኛውም የእስራኤል ግዛት ውስጥ እንዳንኖር እኛን ለመደምሰስ ሴራ ከጠነሰሰብን ሰው+ +6 ወንዶች ልጆች መካከል ሰባቱ ይሰጡን። እኛም በይሖዋ የተመረጠው የሳኦል+ አገር በሆነችው በጊብዓ+ በድናቸውን በይሖዋ ፊት እንሰቅላለን።”*+ ከዚያም ንጉሡ “እሺ፣ እሰጣችኋለሁ” አላቸው። +7 ሆኖም ንጉሡ እሱና የሳኦል ልጅ ዮናታን በይሖዋ ፊት በተማማሉት መሐላ የተነሳ የሳኦል ልጅ ለሆነው ለዮናታን+ ልጅ ለሜፊቦስቴ+ ራራለት። +8 በመሆኑም ንጉሡ የአያ ልጅ ሪጽፋ+ ለሳኦል የወለደችለትን ሁለት ወንዶች ልጆች ማለትም አርሞኒንና ሜፊቦስቴን እንዲሁም የሳኦል ልጅ ሜልኮል*+ የመሆላታዊው የቤርዜሊ ልጅ ለሆነው ለአድሪዔል+ የወለደችለትን አምስት ወንዶች ልጆች ወሰደ። +9 ከዚያም ለገባኦናውያኑ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነሱም በድናቸውን በተራራው ላይ በይሖዋ ፊት ሰቀሉ።+ ሰባቱም አንድ ላይ ሞቱ፤ የተገደሉትም አዝመራ በሚሰበሰብባቸው የመጀመሪያዎቹ ቀናት ይኸውም የገብስ አዝመራ መሰብሰብ በሚጀምርበት ጊዜ ነበር። +10 ከዚያም የአያ ልጅ ሪጽፋ+ ከመከር ወቅት መጀመሪያ አንስቶ በበድኖቹ ላይ ከሰማይ ዝናብ እስከሚወርድበት ጊዜ ድረስ ማቅ ወስዳ በዓለቱ ላይ አነጠፈች፤ ቀን የሰማይ አሞሮች እንዲያርፉባቸው፣ ሌሊት ደግሞ የዱር አራዊት እንዲጠጓቸው አልፈቀደችም። +11 በኋላም የሳኦል ቁባት የሆነችው የአያ ልጅ ሪጽፋ ያደረገችው ነገር ለዳዊት ተነገረው። +12 ስለዚህ ዳዊት ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አፅም ከኢያቢስጊልያድ+ መሪዎች* ላይ ወሰደ፤ እነዚህ ሰዎች አፅሙን ፍልስጤማውያን ሳኦልን በጊልቦአ+ በገደሉበት ቀን እሱንና ዮናታንን ከሰቀሉበት ከቤትሻን አደባባይ ሰርቀው ወስደው ነበር። +13 እሱም የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አፅም ከዚያ አመጣ፤ በተጨማሪም የተገደሉትን* ሰዎች አፅም ሰበሰቡ።+ +14 ከዚያም የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አፅም በቢንያም ምድር በጸላ+ በሚገኘው በሳኦል አባት በቂስ+ የመቃብር ስፍራ ቀበሩት። ንጉሡ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ከፈጸሙም በኋላ አምላክ ስለ ምድሪቱ ያቀረቡትን ልመና ሰማ።+ +15 በፍልስጤማውያንና በእስራኤላውያን መካከል እንደገና ጦርነት ተነሳ።+ በመሆኑም ዳዊትና አገልጋዮቹ ወርደው ፍልስጤማውያንን ወጉ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት ዛለ። +16 ከረፋይም+ ዘር የሆነው እንዲሁም 300 ሰቅል*+ የሚመዝን የመዳብ ጦርና አዲስ ሰይፍ የታጠቀው ይሽቢብኖብ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። +17 የጽሩያ ልጅ አቢሳም+ ወዲያውኑ ደረሰለት፤+ ፍልስጤማዊውንም መትቶ ገደለው። በዚያን ጊዜ የዳዊት ሰዎች “ከአሁን በኋላ ከእኛ ጋር ወደ ውጊያ መውጣት የለብህም!+ የእስራኤልን መብራት አታጥፋ!”+ በማለት ማሉለት። +18 ከዚህም በኋላ እንደገና ከፍልስጤማውያን ጋር በጎብ ጦርነት ተከፈተ።+ በዚህ ጊዜ ሁሻዊው ሲበካይ+ የረፋይም+ ዘር የሆነውን ሳፍን ገደለው። +19 ዳግመኛም ከፍልስጤማውያን ጋር በጎብ ጦርነት ተቀሰቀሰ፤+ የቤተልሔማዊው የያአሬዖርጊም ልጅ ኤልሃናን የሸማኔ መጠቅለያ የሚመስል ዘንግ ያለው ጦር ይዞ የነበረውን ጌታዊውን ጎልያድን ገደለው።+ +20 እንደገናም በጌት ጦርነት ተቀሰቀሰ፤ በዚያም በእጆቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች በእግሮቹም ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች፣ በድምሩ 24 ጣቶች ያሉት በጣም ግዙፍ የሆነ ሰው ነበር፤ እሱም የረፋይም ዘር ነበር።+ +21 ይህ ሰው እስራኤልን ይገዳደር+ ስለነበር የዳዊት ወንድም የሺምአይ+ ልጅ ዮናታን ገደለው። +22 እነዚህ አራቱ በጌት የሚኖሩ የረፋይም ዘሮች ነበሩ፤ እነሱም በዳዊት እጅና በአገልጋዮቹ እጅ ወደቁ።+ +15 ከዚህ ሁሉ በኋላ አቢሴሎም ሠረገላ፣ ፈረሶችና ከፊቱ የሚሮጡ 50 ሰዎች አዘጋጀ።+ +2 አቢሴሎምም በጠዋት ተነስቶ ወደ ከተማዋ በር+ በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆም ነበር። ማንም ሰው ሙግት ኖሮት ፍርድ ለማግኘት+ ወደ ንጉሡ በሚመጣበት ጊዜ አቢሴሎም ይጠራውና “ለመሆኑ አንተ የየትኛው ከተማ ሰው ነህ?” ይለው ነበር፤ እሱም “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች መካከል ከአንዱ ነው” ይለዋል። +3 አቢሴሎምም “አቤቱታህ ትክክልና ተገቢ ነው፤ ግን ምን ያደርጋል፣ ከንጉሡ ዘንድ ጉዳይህን የሚሰማልህ አንድም ሰው አታገኝም” ይለው ነበር። +4 ከዚያም አቢሴሎም “ምነው በምድሪቱ ላይ ዳኛ ሆኜ በተሾምኩ! ሙግት ያለው ወይም ፍርድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወደ እኔ መጥቶ ፍትሕ ማግኘት ይችል ነበር” ይል ነበር። +5 እንዲሁም አንድ ሰው ሊሰግድለት ወደ እሱ በሚቀርብበት ጊዜ አቢሴሎም እጁን ዘርግቶ ይይዘውና ይስመው ነበር።+ +6 አቢሴሎምም ፍርድ ለማግኘት ወደ ንጉሡ ለሚመጣው እስራኤላዊ በሙሉ እንዲህ ያደርግ ነበር፤ በዚህ መንገድ አቢሴሎም የእስራኤልን ሰዎች ልብ ሰረቀ።+ +7 በአራቱ* ዓመት ማብቂያ ላይ አቢሴሎም ንጉሡን እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ ለይሖዋ የተሳልኩትን ስእለት ለማድረስ ወደ ኬብሮን+ ልሂድ። +8 ምክንያቱም እኔ አገልጋ���ህ በሶርያ ባለችው በገሹር+ በነበርኩበት ጊዜ ‘ይሖዋ ወደ ኢየሩሳሌም ከመለሰኝ ለይሖዋ መባ* አቀርባለሁ’ በማለት ተስዬ+ ነበር።” +9 በመሆኑም ንጉሡ “በሰላም ሂድ” አለው። እሱም ተነስቶ ወደ ኬብሮን ሄደ። +10 አቢሴሎምም “የቀንደ መለከት ድምፅ ስትሰሙ ‘አቢሴሎም በኬብሮን ነገሠ!’+ ብላችሁ አውጁ” በማለት በመላው የእስራኤል ነገዶች መካከል ሰላዮችን አሰማራ። +11 በዚህ ጊዜ ከኢየሩሳሌም 200 ሰዎች ከአቢሴሎም ጋር ወደዚያ ሄደው ነበር፤ ጥሪ ቀርቦላቸው የሄዱት እነዚህ ሰዎች ምንም የጠረጠሩትና የሚያውቁት ነገር አልነበረም። +12 በተጨማሪም አቢሴሎም መሥዋዕቶቹን በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊትን አማካሪ+ ጊሎአዊውን አኪጦፌልን+ ከከተማው ከጊሎ+ ልኮ አስጠራው። አቢሴሎም የጠነሰሰው ሴራ እየተጠናከረ ሄደ፤ ከአቢሴሎም ጎን የተሰለፈውም ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ መጣ።+ +13 በኋላም አንድ ሰው ወደ ዳዊት መጥቶ “የእስራኤል ሰዎች ልብ ወደ አቢሴሎም ሸፍቷል” ሲል ነገረው። +14 ዳዊትም በኢየሩሳሌም አብረውት የነበሩትን አገልጋዮቹን በሙሉ ወዲያውኑ እንዲህ አላቸው፦ “ተነሱ፣ እንሽሽ፤+ አለዚያ አንዳችንም ከአቢሴሎም እጅ አናመልጥም! በፍጥነት መጥቶ እንዳይዘንና እንዳያጠፋን፣ ከተማዋንም በሰይፍ እንዳይመታ ቶሎ ብለን ከዚህ እንሂድ!”+ +15 የንጉሡ አገልጋዮችም ንጉሡን “እኛ አገልጋዮችህ ጌታዬ ንጉሡ የወሰነውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን” አሉት።+ +16 በመሆኑም ንጉሡ ቤተሰቡን ሁሉ አስከትሎ ወጣ፤ ሆኖም ቤቱን* እንዲጠብቁ አሥር ቁባቶቹን እዚያው አስቀረ።+ +17 ንጉሡም ሕዝቡን ሁሉ አስከትሎ ተጓዘ፤ እነሱም ቤትሜርሃቅ ሲደርሱ ቆሙ። +18 ከዚያም አብረውት የሄዱት* አገልጋዮቹ በሙሉ፣ ከሪታውያን በሙሉ፣ ጴሌታውያን+ በሙሉ እንዲሁም ከጌት+ ተከትለውት የመጡት 600 ጌታውያን+ ንጉሡ እያያቸው አለፉ።* +19 ንጉሡም ጌታዊውን ኢታይን+ እንዲህ አለው፦ “ከእኛ ጋር የምትሄደው ለምንድን ነው? በል ተመለስና ከአዲሱ ንጉሥ ጋር ተቀመጥ፤ አንተ ለራስህ ከአገርህ ተሰደህ የመጣህ የባዕድ አገር ሰው ነህ። +20 የመጣኸው ገና ትናንት ነው፤ ታዲያ ዛሬ እኔ ወደምሄድበት ቦታ ሁሉ አብረህ እንድትሄድ በማድረግ ከእኛ ጋር እንድትንከራተት ላድርግ? በል አሁን ወንድሞችህን ይዘህ ተመለስ፤ ይሖዋም ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ያሳይህ!”+ +21 ኢታይ ግን ለንጉሡ “ሕያው በሆነው በይሖዋና ሕያው በሆነው በጌታዬ በንጉሡ እምላለሁ፣ በሕይወት ብኖርም ሆነ ብሞት ጌታዬ ንጉሡ በሚገኝበት በማንኛውም ቦታ ሁሉ እኔ አገልጋይህም በዚያ እሆናለሁ!” ሲል መለሰ።+ +22 በዚህ ጊዜ ዳዊት ኢታይን+ “እሺ፣ እለፍ” አለው። በመሆኑም ጌታዊው ኢታይ ከሰዎቹና ከልጆቹ ሁሉ ጋር አለፈ። +23 እነዚህ ሁሉ ሰዎች በሚያልፉበት ጊዜ በአካባቢው ያሉ ሰዎች በሙሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያለቅሱ ነበር፤ ንጉሡም በቄድሮን ሸለቆ+ አጠገብ ቆሞ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳው ወደሚወስደው መንገድ ተሻገረ። +24 ሳዶቅም+ በዚያ ነበር፤ የእውነተኛውን አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት+ የተሸከሙት ሌዋውያንም+ በሙሉ ከእሱ ጋር ነበሩ፤ እነሱም የእውነተኛውን አምላክ ታቦት አስቀመጡት፤ ሕዝቡ ሁሉ ከተማዋን ለቆ ከተሻገረም በኋላ አብያታር+ ወጣ። +25 ሆኖም ንጉሡ ሳዶቅን እንዲህ አለው፦ “የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ወደ ከተማዋ መልሱት።+ በይሖዋ ፊት ሞገስ ካገኘሁ እንድመለስና ታቦቱንም ሆነ ማደሪያ ስፍራውን እንዳይ ያደርገኝ ይሆናል።+ +26 ይሁንና እሱ ‘በአንተ አልተደሰትኩም’ ካለኝ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግብኝ።” +27 ንጉሡም ካህኑን ሳዶቅን እንዲህ አለው፦ “አንተ ባለ ራእይ አይደለህም?+ በል እንግዲህ ወደ ከተማዋ በሰላም ተመለስ፤ ሁለቱን ልጆቻችሁን ማለትም የገዛ ልጅህን አኪማዓስንና የአብያታርን ልጅ ዮናታንን+ ይዘህ ተመለስ። +28 እኔም ከእናንተ አንድ መልእክት እስኪመጣልኝ ድረስ በምድረ በዳው በሚገኙት መልካዎች* አጠገብ እቆያለሁ።”+ +29 ስለዚህ ሳዶቅና አብያታር የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ እነሱም በዚያ ተቀመጡ። +30 ዳዊት የደብረ ዘይትን ተራራ*+ ሽቅብ ሲወጣ እያለቀሰ ነበር፤ እሱም ራሱን ተከናንቦ ባዶ እግሩን ይሄድ ነበር። አብረውት የነበሩት ሰዎችም ሁሉ ራሳቸውን ተከናንበው እያለቀሱ ሽቅብ ወጡ። +31 ከዚያም ዳዊት “ከአቢሴሎም+ ጋር ካሴሩት+ ሰዎች አንዱ እኮ አኪጦፌል ነው” ተብሎ ተነገረው። በዚህ ጊዜ ዳዊት “ይሖዋ ሆይ፣+ እባክህ የአኪጦፌልን ምክር የሞኝ ምክር+ አድርገው!” አለ። +32 ዳዊት ሕዝቡ ለአምላክ ይሰግድበት ወደነበረው የተራራ ጫፍ ሲደርስ አርካዊው+ ኩሲ+ ልብሱን ቀዶና በራሱ ላይ አቧራ ነስንሶ እሱን ለማግኘት በዚያ ይጠባበቅ ነበር። +33 ዳዊት ግን እንዲህ አለው፦ “አብረኸኝ የምትሻገር ከሆነ ሸክም ትሆንብኛለህ። +34 ከዚህ ይልቅ ወደ ከተማዋ ተመልሰህ አቢሴሎምን ‘ንጉሥ ሆይ፣ እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ።+ ቀደም ሲል የአባትህ አገልጋይ ነበርኩ፤ አሁን ግን የአንተ አገልጋይ ነኝ’ ብትለው የአኪጦፌልን ምክር ታከሽፍልኛለህ።+ +35 ካህናት የሆኑት ሳዶቅና አብያታር እዚያው ከአንተ ጋር አይደሉም? ከንጉሡ ቤት የምትሰማውን ነገር ሁሉ ካህናት ለሆኑት ለሳዶቅና ለአብያታር ንገራቸው።+ +36 ከእነሱም ጋር ሁለቱ ልጆቻቸው ማለትም የሳዶቅ ልጅ አኪማዓስና+ የአብያታር ልጅ ዮናታን+ አሉ፤ እናንተም የምትሰሙትን ማንኛውንም ነገር በእነሱ በኩል ልካችሁ አሳውቁኝ።” +37 በመሆኑም አቢሴሎም ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የዳዊት ወዳጅ*+ የሆነው ኩሲ ወደ ከተማዋ ሄደ። +22 ዳዊት፣ ይሖዋ ከጠላቶቹ ሁሉ እጅና ከሳኦል እጅ+ በታደገው+ ቀን የዚህን መዝሙር ቃል ለይሖዋ ዘመረ።+ +2 እንዲህም አለ፦ “ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና+ ታዳጊዬ ነው።+ + 3 አምላኬ የምሸሸግበት ዓለቴ ነው፤+ጋሻዬ፣+ የመዳኔ ቀንድና* አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤+መሸሻዬና+ አዳኜ ነው፤+ አንተ ከዓመፅ ታድነኛለህ። + 4 ውዳሴ የሚገባውን ይሖዋን እጠራለሁ፤ከጠላቶቼም እድናለሁ። + 5 የሞት ማዕበል ዙሪያዬን ከቦኛል፤+የማይረቡ ሰዎች የለቀቁት ድንገተኛ ጎርፍ አሸበረኝ።+ + 6 የመቃብር* ገመድ ተጠመጠመብኝ፤+የሞት ወጥመድ ተጋረጠብኝ።+ + 7 በጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ይሖዋን ጠራሁት፤+አምላኬን ደጋግሜ ጠራሁት። እሱም በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፣እርዳታ ለማግኘት የማሰማውም ጩኸት ወደ ጆሮው ደረሰ።+ + 8 ምድርም ወዲያና ወዲህ ትናወጥና ትንቀጠቀጥ ጀመር፤+የሰማያት መሠረቶች ተንቀጠቀጡ፤+እሱ ስለተቆጣም ራዱ።+ + 9 ከአፍንጫው ጭስ ወጣ፤የሚባላም እሳት ከአፉ ወጣ፤+ፍምም ከእሱ ፈለቀ። +10 ወደ ታች ሲወርድ ሰማያት እንዲያጎነብሱ አደረገ፤+ከእግሮቹም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር።+ +11 በኪሩብ ላይ ተቀምጦ+ እየበረረ መጣ። በመንፈስ ክንፎችም* ላይ ሆኖ ይታይ ነበር።+ +12 ከዚያም ጨለማን በዙሪያው እንደ መጠለያ አደረገ፣+ጨለማውም ጥቁር ውኃና ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረው። +13 በፊቱ ካለው ብርሃን ፍም ፈለቀ። +14 ከዚያም ይሖዋ ከሰማይ ያንጎደጉድ ጀመር፤+ልዑሉ አምላክ ድምፁን አሰማ።+ +15 ፍላጻዎቹን+ አስፈንጥሮ በታተናቸው፤መብረቁን አብርቆ ግራ አጋባቸው።+ +16 በይሖዋ ተግሣጽ፣ ከአፍንጫውም በሚወጣው ኃይለኛ እስትንፋስ+የባሕር ወለሎች ታዩ፤+የምድር መሠረቶችም ተገለጡ። +17 ከላይ ሆኖ እጁን ሰደደ፤ከጥልቅ ውኃ ውስጥም አወጣኝ።+ +18 ከብርቱ ጠላቴ አዳነኝ፤+ከእኔ ይበልጥ ብርቱዎች ከሆኑት፣ ከሚጠሉኝ ሰዎች ታደገኝ። +19 ችግር ላይ በወደቅኩበት ቀን ተነሱብኝ፤+ይሖዋ ግን ድጋፍ ሆነልኝ። +20 ደህንነት ወደሚገኝበት ስፍራ* አመጣኝ፤+በእኔ ስለተደሰተ ታደገኝ።+ +21 ይሖዋ እንደ ጽድቄ ወሮታ ይከፍለኛል፤+እንደ እጄ ንጽሕና ብድራት ይመልስልኛል።+ +22 የይሖዋን መንገድ ጠብቄአለሁና፤አምላኬን በመተው ክፉ ድርጊት አልፈጸምኩም። +23 ፍርዱ+ ሁሉ በፊቴ ነው፤ደንቦቹን+ አልተላለፍም። +24 በፊቱ እንከን የለሽ+ ሆኜ እኖራለሁ፤ራሴንም ከስህተት እጠብቃለሁ።+ +25 ይሖዋ እንደ ጽድቄ፣+በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራት ይመልስልኝ።+ +26 ታማኝ ለሆነ ሰው ታማኝ ትሆናለህ፤+እንከን የለሽ ለሆነ ኃያል ሰው እንከን የለሽ ትሆናለህ፤+ +27 ከንጹሕ ሰው ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤+ጠማማ ለሆነ ሰው ግን ብልህ መሆንህን ታሳያለህ።*+ +28 ትሑት የሆኑትን ታድናለህና፤+ዓይኖችህ ግን በትዕቢተኞች ላይ ናቸው፤ አንተም ታዋርዳቸዋለህ።+ +29 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ መብራቴ ነህና፤+ጨለማዬን ብርሃን የሚያደርገው ይሖዋ ነው።+ +30 በአንተ እርዳታ ወራሪውን ቡድን መጋፈጥ እችላለሁ፤በአምላክ ኃይል ቅጥር መውጣት እችላለሁ።+ +31 የእውነተኛው አምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤+የይሖዋ ቃል የነጠረ ነው።+ እሱ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው።+ +32 ደግሞስ ከይሖዋ ሌላ አምላክ ማን ነው?+ ከአምላካችንስ በቀር ዓለት ማን ነው?+ +33 እውነተኛው አምላክ ጠንካራ ምሽጌ ነው፤+መንገዴንም ፍጹም ያደርግልኛል።+ +34 እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤በከፍታ ቦታዎች ላይ ያቆመኛል።+ +35 እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ክንዶቼ የመዳብ ደጋን ማጠፍ ይችላሉ። +36 የመዳን ጋሻህን ትሰጠኛለህ፤ትሕትናህም ታላቅ ያደርገኛል።+ +37 ለእርምጃዬ መንገዱን ታሰፋልኛለህ፤እግሮቼ* አያዳልጣቸውም።+ +38 ጠላቶቼን አሳድጄ አጠፋቸዋለሁ፤ተጠራርገው እስኪጠፉ ድረስ ወደ ኋላ አልመለስም። +39 እንዳያንሰራሩም ጠራርጌ አጠፋቸዋለሁ፣ አደቃቸዋለሁ፤+እግሬ ሥር ይወድቃሉ። +40 ለውጊያው ብርታት ታስታጥቀኛለህ፤+ጠላቶቼ ሥሬ እንዲወድቁ ታደርጋለህ።+ +41 ጠላቶቼ ከእኔ እንዲሸሹ ታደርጋለህ፤*+እኔም የሚጠሉኝን አጠፋለሁ።*+ +42 እርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ ሆኖም የሚያድናቸው የለም፤ወደ ይሖዋም ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስላቸውም።+ +43 በምድር ላይ እንዳለ አቧራ አደቃቸዋለሁ፤በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ እረግጣቸዋለሁ፤ አደቃቸዋለሁ። +44 ስህተት ከሚለቃቅሙት ሕዝቦቼ ታድነኛለህ።+ የብሔራት መሪ እንድሆን ትጠብቀኛለህ፤+የማላውቀው ሕዝብ ያገለግለኛል።+ +45 ባዕዳንም ተሸማቀው ወደ ፊቴ ይቀርባሉ፤+ስለ እኔ የሚሰሙትም እንዲታዘዙኝ ያደርጋቸዋል።* +46 የባዕድ አገር ሰዎች ወኔ ይከዳቸዋል፤*ከምሽጎቻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ። +47 ይሖዋ ሕያው ነው! ዓለቴ ይወደስ!+ የመዳኔ ዓለት የሆነው አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።+ +48 እውነተኛው አምላክ ይበቀልልኛል፤+ሕዝቦችንም ከበታቼ ያስገዛልኛል፤+ +49 እሱ ከጠላቶቼ ያድነኛል። ከሚያጠቁኝ ሰዎች በላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤+ከዓመፀኛ ሰው ታድነኛለህ።+ +50 ይሖዋ ሆይ፣ በብሔራት መካከል የማመሰግንህ ለዚህ ነው፤+ለስምህም እንዲህ ብዬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፦+ +51 ለንጉሡ ታላላቅ የማዳን ሥራዎችን ያከናውናል፤*+ለቀባውም ታማኝ ፍቅር ያሳያል፤ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይህን ያደርጋል።”+ +17 በዚህ ጊዜ ከጊልያድ+ ነዋሪዎች አንዱ የሆነው ቲሽባዊው ኤልያስ*+ አክዓብን “በማገለግለውና* ሕያው በሆነው በእስራኤል አምላክ በይሖዋ እምላለሁ፣ በእኔ ትእዛዝ ካልሆነ በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠል ወይም ዝናብ አይኖርም!” አለው።+ +2 የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ +3 “ከዚህ ተነስተህ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ሂድ፤ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በከሪት ሸለቆም* ተደበቅ። +4 ከጅረቱ ትጠጣለህ፤ ቁራዎችም እዚያ ምግብ እንዲያመጡልህ አዛለሁ።”+ +5 እሱም ወዲያውኑ ሄዶ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ ሄዶም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በከሪት ሸለቆ* ተቀመጠ። +6 ቁራዎቹም ጠዋትና ማታ ምግብና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ እሱም ከጅረቱ ይጠጣ ነበር።+ +7 ሆኖም በምድሪቱ ላይ ዝናብ ስላልዘነበ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ጅረቱ ደረቀ።+ +8 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ +9 “ተነስተህ በሲዶና ወደምትገኘው ወደ ሰራፕታ ሂድ፤ እዚያም ተቀመጥ። እኔም በዚያ አንዲት መበለት እንድትመግብህ አዛለሁ።”+ +10 ኤልያስም ተነስቶ ወደ ሰራፕታ ሄደ። ወደ ከተማዋ መግቢያ በደረሰም ጊዜ አንዲት መበለት ጭራሮ ስትለቅም አገኘ። መበለቲቱንም ጠርቶ “እባክሽ የምጠጣው ትንሽ ውኃ በዕቃ ስጪኝ” አላት።+ +11 ልታመጣለት ስትሄድም ጠራትና “እባክሽ ቁራሽ ዳቦም ይዘሽልኝ ነይ” አላት። +12 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለችው፦ “ሕያው በሆነው አምላክህ በይሖዋ እምላለሁ፣ በማድጋው ውስጥ ካለው አንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮው ውስጥ ካለው ጥቂት ዘይት በስተቀር ምንም ዳቦ የለኝም።+ ለእኔና ለልጄ የሆነች ነገር ለማዘጋጀት ጭራሮ እየለቀምኩ ነው። እኛም እሷን ቀምሰን እንሞታለን።” +13 ከዚያም ኤልያስ እንዲህ አላት፦ “አይዞሽ ስጋት አይግባሽ። ወደ ቤት ገብተሽ እንዳልሽው አድርጊ። ብቻ በመጀመሪያ ከዚያችው ካለችሽ ላይ ትንሽ ቂጣ ጋግረሽ አምጪልኝ። ከዚያ በኋላ ለአንቺና ለልጅሽ የሆነ ነገር ማዘጋጀት ትችያለሽ። +14 ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይሖዋ በምድሪቱ ላይ ዝናብ እስከሚያዘንብበት ዕለት ድረስ ከማድጋው ዱቄት አይጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አያልቅም።’”+ +15 ስለሆነም ሄዳ ኤልያስ እንዳላት አደረገች፤ እሷም ሆነች እሱ እንዲሁም ቤተሰቧ ለብዙ ቀናት ሲመገቡ ቆዩ።+ +16 ይሖዋ በኤልያስ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት ከማድጋው ዱቄት አልጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አላለቀም። +17 ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ የቤቱ ባለቤት፣ ልጇ ታመመ፤ ሕመሙም እጅግ ስለጠናበት እስትንፋሱ ቀጥ አለ።+ +18 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ኤልያስን “የእውነተኛው አምላክ ሰው ሆይ፣ ምን አደረግኩህ?* የመጣኸው በደሌን ልታስታውሰኝና ልጄን ልትገድል ነው?” አለችው።+ +19 እሱ ግን “ልጅሽን ስጪኝ” አላት። ከዚያም ልጁን ከእቅፏ ወስዶ እሱ ወዳረፈበት በሰገነቱ ላይ ወዳለው ክፍል ይዞት ወጣ፤ ልጁንም በራሱ አልጋ ላይ አስተኛው።+ +20 እሱም “አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣+ እኔን ያሳረፈችኝ የዚህች መበለት ልጅ እንዲሞት በማድረግ በእሷም ላይ መከራ ታመጣባታለህ?” በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ። +21 ከዚያም ልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ከተዘረጋበት በኋላ “አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ የዚህ ልጅ ሕይወት ይመለስለት”* ብሎ ወደ ይሖዋ ጮኸ። +22 ይሖዋም የኤልያስን ልመና ሰማ፤+ የልጁም ሕይወት ተመለሰለት፤* እሱም ሕያው ሆነ።+ +23 ከዚያም ኤልያስ ልጁን ይዞት ሰገነት ላይ ካለው ክፍል ወደ ቤት ከወረደ በኋላ ለእናቱ ሰጣት፤ ኤልያስም “ይኸው፣ ልጅሽ ሕያው ሆኗል” አላት።+ +24 በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ኤልያስን “አንተ በእርግጥ የአምላክ ሰው+ እንደሆንክ በአንደበትህም ያለው የይሖዋ ቃል እውነት እንደሆነ አሁን አወቅኩ” አለችው። +18 ከተወሰነ ጊዜ በኋላም በሦስተኛው ዓመት+ የይሖዋ ቃል “ሂድና አክዓብ ፊት ቅረብ፤ እኔም በምድሩ ላይ ዝናብ አዘንባለሁ”+ ሲል ወደ ኤልያስ መጣ። +2 ስለሆነም ኤልያስ አክዓብ ፊት ለመቅረብ ሄደ፤ በዚህ ወቅት ረሃቡ በሰማርያ ክፉኛ ጸንቶ ነበር።+ +3 በዚህ ጊዜ አክዓብ በቤቱ ላይ አዛዥ የነበረውን አብድዩን ጠራው። (አብድዩ ይሖዋን በጣም ይፈራ ነበር፤ +4 ኤልዛቤል+ የይሖዋን ነቢያት እያጠፋች በነበረበት ጊዜም አብድዩ 100 ነቢያትን ወስዶ 50ውን በአንድ ዋሻ 50ውን ደግሞ በሌላ ዋሻ ውስጥ ከደበቃቸው በኋላ ምግብና ውኃ ይሰጣቸው ነበር።) +5 ከዚያም አክዓብ አብድዩን እንዲህ አለው፦ “በምድሪቱ ላይ ወደሚገኙት የውኃ ምንጮች ሁሉና ሸለቆዎች* ሁሉ ሂድ። እንስሶቻችን በሙሉ እንዳያልቁ፣ ፈረሶቹንና በቅሎዎቹን በሕይወት ማቆየት የሚያስችል በቂ ሣር እናገኝ ይሆናል።” +6 በመሆኑም አቋርጠውት የሚሄዱትን ምድር ተከፋፈሉ። አክዓብ ለብቻው በአንድ በኩል፣ አብድዩም ለብቻው በሌላ በኩል ሄደ። +7 አብድዩ እየተጓዘ ሳለ ኤልያስን መንገዱ ላይ አገኘው። እሱም ወዲያውኑ ስላወቀው በግንባሩ ተደፋ፤ ከዚያም “ጌታዬ ኤልያስ ሆይ፣ በእርግጥ አንተ ነህ?” አለው።+ +8 ኤልያስም “አዎ፣ እኔ ነኝ። ሄደህ ለጌታህ ‘ኤልያስ እዚህ አለ’ ብለህ ንገረው” አለው። +9 እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “እኔ አገልጋይህ እንድሞት ለአክዓብ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ምን ኃጢአት ሠርቼ ነው? +10 ሕያው በሆነው አምላክህ በይሖዋ እምላለሁ፣ ጌታዬ አንተን ፍለጋ ሰው ያልላከበት አንድም ብሔር ሆነ መንግሥት የለም። እነሱም ‘እዚህ የለም’ ባሉት ጊዜ ያ መንግሥትም ሆነ ብሔር አንተን አለማግኘቱን በመሐላ እንዲያረጋግጥለት ያደርግ ነበር።+ +11 አንተ ደግሞ አሁን ‘ሄደህ ለጌታህ “ኤልያስ እዚህ አለ” ብለህ ንገረው’ ትለኛለህ። +12 ከአንተ ተለይቼ ስሄድ የይሖዋ መንፈስ ወደማላውቀው ቦታ ይወስድሃል፤+ ለአክዓብ ብነግረውና ሳያገኝህ ቢቀር እንደሚገድለኝ የታወቀ ነው። ነገር ግን እኔ አገልጋይህ ከወጣትነቴ ጀምሮ ይሖዋን ስፈራ ኖሬአለሁ። +13 ኤልዛቤል የይሖዋን ነቢያት በገደለች ጊዜ ከይሖዋ ነቢያት መካከል 100ዎቹን ወስጄ ሃምሳ ሃምሳ በማድረግ ዋሻ ውስጥ እንደደበቅኳቸው እንዲሁም ምግብና ውኃ እሰጣቸው እንደነበር ጌታዬ አልሰማም?+ +14 አሁን ግን አንተ ‘ሄደህ ለጌታህ “ኤልያስ እዚህ አለ” ብለህ ንገረው’ ትለኛለህ። እሱም በእርግጠኝነት ይገድለኛል።” +15 ሆኖም ኤልያስ “በማገለግለው* ሕያው በሆነው በሠራዊት ጌታ በይሖዋ እምላለሁ፣ ዛሬ እሱ ፊት እቀርባለሁ” አለ። +16 ስለዚህ አብድዩ ወደ አክዓብ ሄዶ ነገረው፤ አክዓብም ኤልያስን ለማግኘት ሄደ። +17 አክዓብም ልክ ኤልያስን ሲያየው “በእስራኤል ላይ ከፍተኛ ችግር የምትፈጥረው* አንተ ነህ?” አለው። +18 በዚህ ጊዜ ኤልያስ እንዲህ አለው፦ “የይሖዋን ትእዛዛት በመተውና ባአልን በመከተል በእስራኤል ላይ ችግር የምትፈጥሩት+ አንተና የአባትህ ቤት እንጂ እኔ አይደለሁም። +19 ይልቅስ አሁን እስራኤላውያንን በሙሉ፣ ከኤልዛቤል ማዕድ ከሚበሉት 450 የባአል ነቢያትና 400 የማምለኪያ ግንድ*+ ነቢያት ጋር በቀርሜሎስ+ ተራራ ላይ ሰብስብልኝ።” +20 በመሆኑም አክዓብ ወደ እስራኤል ሰዎች ሁሉ መልእክት ላከ፤ ነቢያቱንም በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ሰበሰበ። +21 ከዚያም ኤልያስ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ “በሁለት ሐሳብ የምታነክሱት እስከ መቼ ነው?+ እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ ከሆነ እሱን ተከተሉ፤+ ባአል ከሆነ ደግሞ እሱን ተከተሉ!” አላቸው። ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል አልመለሰለትም። +22 ከዚያም ኤልያስ እንዲህ አላቸው፦ “ከይሖዋ ነቢያት መካከል የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤+ የባአል ነቢያት ግን 450 ናቸው። +23 እንግዲህ አሁን ሁለት ወይፈኖች ይስጡን፤ እነሱም አንድ ወይፈን መርጠው በየብልቱ እየቆራረጡ በእንጨቱ ላይ ያድርጉት፤ ሆኖም እሳት አያንድዱበት። እኔ ደግሞ ሌላኛውን ወይፈን አዘጋጅቼ በእንጨቱ ላይ አደርገዋለሁ�� ሆኖም እሳት አላነድበትም። +24 ከዚያም እናንተ የአምላካችሁን ስም ትጠራላችሁ፤+ እኔም የይሖዋን ስም እጠራለሁ። እሳት በመላክ መልስ የሚሰጠው አምላክ እሱ እውነተኛው አምላክ እንደሆነ ያሳያል።”+ በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “ያልከው ነገር ጥሩ ነው” አሉ። +25 ኤልያስም የባአል ነቢያትን “እናንተ ብዙ ስለሆናችሁ በቅድሚያ አንድ ወይፈን መርጣችሁ አዘጋጁ። ከዚያም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ ሆኖም እሳት አታንድዱበት” አላቸው። +26 በመሆኑም የተሰጣቸውን ወይፈን ወስደው አዘጋጁ፤ ከጠዋት አንስቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስም “ባአል ሆይ፣ መልስልን!” እያሉ የባአልን ስም ጠሩ። ሆኖም ድምፅ የለም፤ የሚመልስም አልነበረም።+ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ዞሩ። +27 እኩለ ቀን ገደማም ኤልያስ እንዲህ በማለት ያፌዝባቸው ጀመር፦ “ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ እንጂ! አምላክ እኮ ነው!+ ምናልባት በሐሳብ ተውጦ ይሆናል፤ ወይም ሊጸዳዳ ሄዶ ይሆናል።* አሊያም ደግሞ ተኝቶ ሊሆን ስለሚችል የሚቀሰቅሰው ያስፈልገው ይሆናል!” +28 እነሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኹ እንደ ልማዳቸውም ደም በደም እስኪሆኑ ድረስ ሰውነታቸውን በጩቤና በጦር ይተለትሉ ነበር። +29 እኩለ ቀን አልፎ የእህል መባ እስከሚቀርብበትም ጊዜ ድረስ እንደ እብድ* ሲያደርጋቸው ቆየ፤ ሆኖም ምንም ድምፅ የለም፤ የሚመልስም የለም፤ ትኩረት የሰጠም አልነበረም።+ +30 በኋላም ኤልያስ ሕዝቡን ሁሉ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ ወደ እሱ ቀረቡ። ከዚያም ፈርሶ የነበረውን የይሖዋን መሠዊያ ጠገነ።+ +31 በመቀጠልም ኤልያስ “ስምህ እስራኤል ይባላል”+ የሚል የይሖዋ ቃል በመጣለት በያዕቆብ ወንዶች ልጆች ነገዶች ቁጥር ልክ 12 ድንጋዮችን ወሰደ። +32 በድንጋዮቹም በይሖዋ ስም መሠዊያ ሠራ።+ በመሠዊያውም ዙሪያ ሁለት የሲህ መስፈሪያ* ዘር ሊያዘራ የሚችል ስፋት ያለው ቦይ ቆፈረ። +33 ከዚያም እንጨቶቹን ረበረበ፤ ወይፈኑንም በየብልቱ ቆራርጦ በእንጨቶቹ ላይ አደረገ።+ ቀጥሎም “በአራት ጋኖች ውኃ ሞልታችሁ በሚቃጠለው መባና በእንጨቱ ላይ አፍስሱ” አለ። +34 ከዚያም “አሁንም ድገሙ” አለ። እነሱም ደገሙ። “ለሦስተኛ ጊዜ ድገሙ” አላቸው። እነሱም ለሦስተኛ ጊዜ ደገሙ። +35 ውኃውም መሠዊያውን ዙሪያውን አጥለቀለቀው፤ ቦዩንም በውኃ ሞላው። +36 ነቢዩ ኤልያስም የምሽቱ የእህል መባ በሚቀርብበት ጊዜ+ ገደማ ወደ ፊት ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፦ “የአብርሃም፣+ የይስሐቅና+ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በእስራኤል ውስጥ አምላክ እንደሆንክ፣ እኔም አገልጋይህ እንደሆንኩና እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረግኩት በአንተ ቃል እንደሆነ ዛሬ ይታወቅ።+ +37 ይሖዋ ሆይ፣ መልስልኝ! እነዚህ ሰዎች አንተ ይሖዋ እውነተኛው አምላክ እንደሆንክና ልባቸውን ወደ አንተ እየመለስክ መሆንህን እንዲያውቁ መልስልኝ።”+ +38 በዚህ ጊዜ የይሖዋ እሳት ወርዶ የሚቃጠለውን መባ፣ እንጨቱን፣ ድንጋዮቹንና አፈሩን በላ፤+ በቦዩ ውስጥ የነበረውንም ውኃ ላሰ።+ +39 ሕዝቡ ሁሉ ይህን ሲያዩ ወዲያውኑ በግንባራቸው ተደፉ፤ ከዚያም “እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ነው! እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ነው!” አሉ። +40 በዚህ ጊዜ ኤልያስ “የባአልን ነቢያት ያዟቸው! አንዳቸውም እንዳያመልጡ!” አላቸው። እነሱም ወዲያውኑ ያዟቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ጅረት*+ ይዟቸው በመውረድ በዚያ አረዳቸው።+ +41 ኤልያስም አክዓብን “የከባድ ዝናብ ድምፅ እያጉረመረመ ስለሆነ ሂድ ብላ፤ ጠጣም” አለው።+ +42 በመሆኑም አክዓብ ሊበላና ሊጠጣ ሲወጣ ኤልያስ ደግሞ ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱንም በጉልበቶቹ መካከል አድርጎ ወደ መሬት አቀረቀረ።+ +43 ከዚያም አገልጋዩን “እባክህ ውጣና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት” አለው። እሱም ወጥቶ ተመለከተና “ኧረ ምንም የለም” አለ። ኤልያስም ሰባት ጊዜ “ተመልሰህ ሂድ” አለው። +44 በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ “እነሆ! የሰው እጅ የምታክል ትንሽ ደመና ከባሕሩ እየወጣች ነው” አለ። ኤልያስም “ሄደህ አክዓብን ‘ሠረገላህን አዘጋጅ! ዝናቡ እንዳያግድህ ወደዚያ ውረድ!’ በለው” አለው። +45 በዚህ ጊዜ ሰማዩ በደመና ጠቆረ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ከባድ ዝናብም ይጥል ጀመር፤+ አክዓብም እየጋለበ ወደ ኢይዝራኤል+ ሄደ። +46 ሆኖም የይሖዋ እጅ በኤልያስ ላይ መጣ፤ እሱም ልብሱን ጠቅልሎ መቀነቱ ውስጥ በመሸጎጥ* ከአክዓብ ፊት ፊት እየሮጠ እስከ ኢይዝራኤል ድረስ ሄደ። +19 ከዚያም አክዓብ+ ኤልያስ ያደረገውን ሁሉና ነቢያቱን በሙሉ እንዴት በሰይፍ እንደገደለ+ ለኤልዛቤል+ ነገራት። +2 በዚህ ጊዜ ኤልዛቤል “ነገ በዚህ ሰዓት ከእነሱ እንደ አንዱ ሳላደርግህ* ብቀር አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጡብኝ!” ብሎ ለኤልያስ እንዲነግረው መልእክተኛ ላከችበት። +3 በዚህ ጊዜ ኤልያስ ፈራ፤ በመሆኑም ሕይወቱን* ለማትረፍ ሸሸ።+ በይሁዳ ወደምትገኘው+ ወደ ቤርሳቤህም+ መጣ፤ አገልጋዩንም እዚያ ተወው። +4 ከዚያም በምድረ በዳው የአንድ ቀን መንገድ ከተጓዘ በኋላ ወደ አንድ የክትክታ ዛፍ ሲደርስ ሥሩ ተቀመጠ፤ እንዲሞትም* መለመን ጀመረ። እንዲህም አለ፦ “አሁንስ በቅቶኛል! ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ሕይወቴን* ውሰዳት።”+ +5 ከዚያም በክትክታው ዛፍ ሥር ጋደም አለ፤ እንቅልፍም ወሰደው። ሆኖም ድንገት አንድ መልአክ ነካ አደረገውና+ “ተነስና ብላ” አለው።+ +6 እሱም ቀና ብሎ ሲመለከት ራስጌው አጠገብ በጋሉ ድንጋዮች ላይ የተቀመጠ ዳቦ እንዲሁም በውኃ መያዣ ዕቃ ውስጥ ያለ ውኃ አየ። እሱም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተመልሶ ተኛ። +7 በኋላም የይሖዋ መልአክ ለሁለተኛ ጊዜ መጥቶ ነካ አደረገውና “ሩቅ መንገድ ስለምትጓዝ ተነስና ብላ” አለው። +8 ስለሆነም ተነስቶ በላ፤ ጠጣም፤ ከምግቡም ባገኘው ብርታት እስከ እውነተኛው አምላክ ተራራ እስከ ኮሬብ+ ድረስ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት ተጓዘ። +9 እዚያም ሲደርስ ወደ አንድ ዋሻ+ ገብቶ አደረ፤ በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቃል ወደ እሱ መጥቶ “ኤልያስ እዚህ ምን ታደርጋለህ?” አለው። +10 እሱም እንዲህ አለ፦ “እኔ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ እጅግ ቀንቻለሁ፤+ ምክንያቱም የእስራኤል ሰዎች ቃል ኪዳንህን ትተዋል፤+ መሠዊያዎችህንም አፈራርሰዋል፤ ነቢያትህን በሰይፍ ገድለዋል፤+ እንግዲህ የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ። ይኸው አሁን ደግሞ የእኔንም ሕይወት* ለማጥፋት እየፈለጉ ነው።”+ +11 እሱ ግን “ውጣና ተራራው ላይ ይሖዋ ፊት ቁም” አለው። በዚህ ጊዜ ይሖዋ እያለፈ+ ነበር፤ ታላቅና ኃይለኛ ነፋስም በይሖዋ ፊት ተራሮቹን ሰነጣጠቀ፤+ ዓለቶቹንም ፈረካከሰ፤ ይሖዋ ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱ ቀጥሎ ደግሞ የምድር መናወጥ ተከሰተ፤ ይሖዋ ግን በምድር መናወጡ+ ውስጥ አልነበረም። +12 ከምድር መናወጡ በኋላም እሳት+ መጣ፤ ይሖዋ ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱ በኋላ ደግሞ ዝግ ያለና ለስለስ ያለ ድምፅ ተሰማ።+ +13 ኤልያስ ይህን ድምፅ ሲሰማ ወዲያውኑ በለበሰው የነቢይ ልብስ ፊቱን ሸፈነ፤+ ወጥቶም ዋሻው ደጃፍ ላይ ቆመ። ከዚያም አንድ ድምፅ “ኤልያስ እዚህ ምን ታደርጋለህ?” ሲል ጠየቀው። +14 እሱም እንዲህ አለ፦ “እኔ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ እጅግ ቀንቻለሁ፤ ምክንያቱም የእስራኤል ሰዎች ቃል ኪዳንህን ትተዋል፤+ መሠዊያዎችህንም አፈራርሰዋል፤ ነቢያትህን በሰይፍ ገድለዋል፤ እንግዲህ የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ። ይኸው አሁን ደግሞ የእኔንም ሕይወት* ለማጥፋት እየፈለጉ ነው።”+ +15 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “ወደ ደማስቆ ምድረ በዳ ተመልሰህ ሂድ። እዚያም ስትደርስ ሃዛኤልን+ በሶርያ ላይ ንጉሥ አድርገህ ቀባው። +16 እንዲሁም የኒምሺን የልጅ ልጅ ኢዩን+ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገህ ቀባው፤ የአቤልምሆላ ሰው የሆነውን የሻፋጥን ልጅ ኤልሳዕን* ደግሞ በአንተ ምትክ ነቢይ አድርገህ ቀባው።+ +17 ከሃዛኤል ሰይፍ+ ያመለጠውን ኢዩ ይገድለዋል፤+ ከኢዩ ሰይፍ ያመለጠውን ደግሞ ኤልሳዕ ይገድለዋል።+ +"18 እኔም ለባአል ያልተንበረከኩና+ እሱን ያልሳሙ+ በእስራኤል ውስጥ የቀሩ 7,000 ሰዎች አሉኝ።”+ " +19 ኤልያስም ከዚያ ወጥቶ ሄደ፤ የሻፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን ከፊቱ 12 ጥማድ በሬዎች እያረሱ፣ እሱም በ12ኛው ጥማድ በሬ እያረሰ አገኘው። ኤልያስም ወደ እሱ በመሄድ የራሱን የነቢይ ልብስ+ አውልቆ ላዩ ላይ ጣል አደረገበት። +20 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን እዚያው በመተው ኤልያስን ተከትሎ እየሮጠ “እባክህ፣ አባቴንና እናቴን ስሜ እንድመጣ ፍቀድልኝ። ከዚያ በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። እሱም “ሂድ ተመለስ፤ እኔ መቼ ከለከልኩህ?” አለው። +21 በመሆኑም ተመለሰ፤ ከዚያም አንድ ጥማድ በሬ ወስዶ መሥዋዕት አደረገ፤ በእርሻ መሣሪያዎቹም የበሬዎቹን ሥጋ በመቀቀል ለሕዝቡ ሰጠ፤ እነሱም በሉ። ይህን ካደረገ በኋላም ተነስቶ ኤልያስን ተከተለው፤ እሱንም ያገለግለው ጀመር።+ +20 በዚህ ጊዜ የሶርያ+ ንጉሥ ቤንሃዳድ+ ጦር ሠራዊቱን በሙሉ አሰባሰበ፤ በተጨማሪም ሌሎች 32 ነገሥታትን ከነፈረሶቻቸውና ከነሠረገሎቻቸው አሰባሰበ፤ ወጥቶም ሰማርያን+ በመክበብ+ ውጊያ ከፈተባት። +2 ከዚያም በከተማዋ ውስጥ ወደሚገኘው ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ+ መልእክተኞች ልኮ እንዲህ አለው፦ “ቤንሃዳድ እንዲህ ይላል፦ +3 ‘ብርህና ወርቅህ እንዲሁም ከሚስቶችህና ከልጆችህ መካከል ምርጥ የሆኑት የእኔ ናቸው።’” +4 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ አንተ እንዳልከው እኔም ሆንኩ የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነን” ሲል መለሰለት።+ +5 በኋላም መልእክተኞቹ ተመልሰው በመምጣት እንዲህ አሉት፦ “ቤንሃዳድ እንዲህ ይላል፦ ‘እንዲህ የሚል መልእክት ልኬብህ ነበር፦ “ብርህን፣ ወርቅህን፣ ሚስቶችህንና ልጆችህን ትሰጠኛለህ።” +6 ሆኖም ነገ በዚህ ሰዓት ገደማ አገልጋዮቼን ወደ አንተ እልካለሁ፤ እነሱም የአንተን ቤትና የአገልጋዮችህን ቤት አንድ በአንድ ይበረብራሉ፤ ለአንተ ትልቅ ዋጋ ያለውን ነገር ሁሉ እጃቸው በማስገባት ይወስዳሉ።’” +7 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ በምድሪቱ ያሉትን ሽማግሌዎች በሙሉ ጠርቶ “እንግዲህ ይህ ሰው በእኛ ላይ መከራ ለማምጣት ቆርጦ እንደተነሳ ልብ በሉ፤ ሚስቶቼን፣ ልጆቼን፣ ብሬንና ወርቄን እንድሰጠው ላከብኝ፤ እኔም አልከለከልኩትም” አላቸው። +8 ከዚያም ሽማግሌዎቹ ሁሉና ሕዝቡ በሙሉ “እሺ አትበለው፤ በዚህ አትስማማ” አሉት። +9 በመሆኑም የቤንሃዳድን መልእክተኞች “ጌታዬ ንጉሡን እንዲህ በሉት፦ ‘እኔ አገልጋይህ መጀመሪያ ላይ የጠየቅከኝን ነገር ሁሉ እፈጽማለሁ፤ ይህን ግን መፈጸም አልችልም’” አላቸው። መልእክተኞቹም ይህን መልእክት ይዘው ወደ እሱ ሄዱ። +10 ቤንሃዳድም “የሰማርያ አፈር ለሚከተለኝ ሕዝብ ሁሉ አንድ አንድ እፍኝ እንኳ ቢደርሰው አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ ከዚህ የከፋም ያምጡብኝ!” የሚል መልእክት ላከበት። +11 የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ “ቤንሃዳድን እንዲህ በሉት፦ ‘ለጦርነት እየታጠቀ ያለ ሰው ጦርነቱን ድል አድርጎ ትጥቁን እንደሚፈታ ሰው መደንፋት የለበትም’” አለ።+ +12 ቤንሃዳድና ነገሥታቱ በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው እየጠጡ ሳለ ቤንሃዳድ ይህን ምላሽ ሲሰማ አገልጋዮቹን “ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጁ!” አላቸው። በመሆኑም በከተማዋ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጁ። +13 ሆኖም አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ+ ቀርቦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን እጅግ ብዙ ሕዝብ ትመለከታለህ? እኔ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ’” አለው።+ +14 አክዓብም “በማን አማካኝነት?” ሲል ጠየቀ፤ እሱም መልሶ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በአውራጃዎቹ መኳንንት አገልጋዮች አማካኝነት’” አለው። ስለሆነም አክዓብ “ታዲያ ውጊያውን የሚያስጀምረው ማን ነው?” አለ፤ እሱም “አንተ ነህ!” አለው። +"15 ከዚያም አክዓብ የአውራጃዎቹን መኳንንት አገልጋዮች ቆጠረ፤ እነሱም 232 ነበሩ፤ በመቀጠልም የእስራኤልን ወንዶች በሙሉ ቆጠረ፤ እነሱም 7,000 ነበሩ።" +16 እነሱም እኩለ ቀን ላይ ቤንሃዳድ ረዳቶቹ ከሆኑት 32 ነገሥታት ጋር በድንኳኖቹ ውስጥ ሆኖ ሰክሮ ሳለ ወደዚያ ሄዱ። +17 የአውራጃዎቹ መኳንንት አገልጋዮች ቀድመው በወጡ ጊዜ ቤንሃዳድ ወዲያውኑ መልእክተኞችን ላከ። እነሱም “ከሰማርያ የመጡ ሰዎች አሉ” ብለው ነገሩት። +18 በዚህ ጊዜ ቤንሃዳድ “ሰዎቹ የመጡት ለሰላም ከሆነ በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው፤ የመጡት ለጦርነት ከሆነም በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው” አለ። +19 ሆኖም እነዚህ ማለትም የአውራጃዎቹ መኳንንት አገልጋዮችና እነሱን ይከተላቸው የነበረው ሠራዊት ከከተማዋ ሲወጡ +20 እያንዳንዳቸው ሊገጥማቸው የመጣውን ሰው ገደሉ። ከዚያም ሶርያውያን ሸሹ፤+ እስራኤላውያንም አሳደዷቸው፤ የሶርያ ንጉሥ ቤንሃዳድ ግን በፈረስ ላይ ሆኖ ከተወሰኑ ፈረሰኞች ጋር አመለጠ። +21 ሆኖም የእስራኤል ንጉሥ ወጥቶ ፈረሶቹንና ሠረገሎቹን መታ፤ በሶርያውያንም ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጀ።* +22 በኋላም ነቢዩ+ ወደ እስራኤል ንጉሥ ቀርቦ “የሶርያ ንጉሥ በሚቀጥለው ዓመት መባቻ* ላይ ስለሚመጣብህ+ ሄደህ ራስህን አጠናክር፤ ምን ማድረግ እንደምትችልም አስብ”+ አለው። +23 በዚህ ጊዜ የሶርያን ንጉሥ አገልጋዮቹ እንዲህ አሉት፦ “አምላካቸው የተራሮች አምላክ ነው። በእኛ ላይ ያየሉብንም ለዚህ ነው። ሆኖም ሜዳ ላይ ብንገጥማቸው እናሸንፋቸዋለን። +24 በተጨማሪም እንዲህ አድርግ፦ ነገሥታቱን በሙሉ ከቦታቸው አንስተህ+ በምትካቸው አስተዳዳሪዎች አስቀምጥ። +25 ከዚያም ከተደመሰሰብህ ሠራዊት ጋር የሚመጣጠን ሠራዊት ሰብስብ፤* በፈረሱ ፋንታ ፈረስ፣ በሠረገላውም ፋንታ ሠረገላ ተካ። ከዚያም ሜዳ ላይ እንግጠማቸው፤ ያለምንም ጥርጥር እናሸንፋቸዋለን።” ንጉሡም የሰጡትን ምክር ሰማ፤ እንዳሉትም አደረገ። +26 በዓመቱ መባቻ* ላይም ቤንሃዳድ ሶርያውያንን አሰባስቦ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ወደ አፌቅ+ ወጣ። +27 የእስራኤል ሰዎችም ከተሰባሰቡና ስንቅ ከተሰጣቸው በኋላ እነሱን ለመግጠም ወጡ። የእስራኤል ሰዎች ፊት ለፊታቸው ሰፍረው ሲታዩ ሁለት ትናንሽ የፍየል መንጋ ይመስሉ ነበር፤ ሶርያውያኑ ግን መላውን ምድር አጥለቅልቀውት ነበር።+ +28 ከዚያም የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደ እስራኤል ንጉሥ ቀርቦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሶርያውያን “ይሖዋ የተራሮች አምላክ እንጂ የሜዳ አምላክ አይደለም” ስላሉ ይህን እጅግ ብዙ ሕዝብ በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ታውቃላችሁ’”+ አለው። +"29 እነሱም ለሰባት ቀን ያህል እንደተፋጠጡ ቆዩ። በሰባተኛውም ቀን ውጊያው ተጀመረ። የእስራኤል ሰዎችም በአንድ ቀን 100,000 ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን ገደሉ።" +"30 የተረፉትም ወደ ከተማዋ ወደ አፌቅ+ ሸሹ። ሆኖም ከተረፉት ሰዎች መካከል በ27,000ዎቹ ላይ ቅጥሩ ተንዶ ወደቀባቸው። ቤንሃዳድም ሸሽቶ ወደ ከተማዋ ገባ፤ አንድ ክፍል ውስጥ ገብቶም ተሸሸገ። " +31 በመሆኑም አገልጋዮቹ እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል ቤት ነገሥታት መሐሪዎች እንደሆኑ* ሰምተናል። እንግዲህ ወገባችንን በማቅ ታጥቀንና ራሳችን ላይ ገመድ አስረን ወደ እስራኤል ንጉሥ እንውጣ። ምናልባት ሕይወትህን* ያተርፍልህ ይሆናል።”+ +32 ስለሆነም ወገባቸውን በማቅ ታጥቀውና ራሳቸው ላይ ገመድ አስረው ወደ እስራኤል ንጉሥ በመምጣት “አገልጋይህ ቤንሃዳድ ‘እባክህ፣ ሕይወቴን* አታጥፋ’ ይላል” አሉት። ንጉሡም “እስካሁን በሕይወት አለ? ወንድሜ እኮ ነው” አለ። +33 ሰዎቹ ይህን እንደ ጥሩ ገድ በመመልከትና ንጉሡ የተናገረውን በማመን “አዎ፣ ቤንሃዳድ እኮ ወንድምህ ነው” አሉ። ንጉሡም “በሉ ሄዳችሁ አምጡት” አለ። ከዚያም ቤንሃዳድ ወደ እሱ መጣ፤ እሱም ወዲያውኑ ሠረገላው ላይ እንዲወጣ አደረገው። +34 ቤንሃዳድም “አባቴ ከአባትህ ላይ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልሳለሁ፤ አባቴ በሰማርያ እንዳደረገው ሁሉ አንተም በደማስቆ ለራስህ ገበያ ማቋቋም* ትችላለህ” አለው። አክዓብም “በዚህ ስምምነት* መሠረት አሰናብትሃለሁ” አለው። በዚህም መሠረት ከእሱ ጋር ስምምነት አድርጎ አሰናበተው። +35 ከነቢያት ልጆች*+ አንዱ በይሖዋ ቃል ታዞ ጓደኛውን “እባክህ ምታኝ” አለው። ሰውየው ግን ሊመታው ፈቃደኛ አልሆነም። +36 ስለዚህ “የይሖዋን ቃል ስላልሰማህ ከእኔ ተለይተህ እንደሄድክ አንበሳ አግኝቶ ይገድልሃል” አለው። ከእሱ ተለይቶም ሲሄድ አንበሳ አግኝቶ ገደለው። +37 ከዚያም ሌላ ሰው አግኝቶ “እባክህ ምታኝ” አለው። በመሆኑም ሰውየው መትቶ አቆሰለው። +38 ከዚያም ይህ ነቢይ ሄዶ ንጉሡን መንገድ ዳር ቆሞ ጠበቀው፤ ማንነቱም እንዳይታወቅ ዓይኖቹን በመጠምጠሚያ ሸፍኖ ነበር። +39 ንጉሡም በዚያ ሲያልፍ ነቢዩ ጮክ ብሎ ንጉሡን በመጣራት እንዲህ አለ፦ “እኔ አገልጋይህ ወደተፋፋመው ጦርነት ገብቼ ነበር፤ በዚህ ጊዜ አንድ ሰው ከዚያ ወጥቶ የሆነ ሰው ወደ እኔ ይዞ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፦ ‘ይህን ሰው ጠብቀው። ይህ ሰው ቢጠፋ በእሱ ሕይወት ፋንታ የአንተ ሕይወት ይተካል፤*+ ወይም ደ +40 ታዲያ እኔ አገልጋይህ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያ ወዲህ ስል ሰውየው ድንገት አምልጦ ሄደ።” የእስራኤልም ንጉሥ “እንግዲህ በራስህ ላይ ፈርደሃል፤ አንተው ራስህ ውሳኔውን አስተላልፈሃል” አለው። +41 ከዚያም ፈጠን ብሎ መጠምጠሚያውን ከዓይኖቹ ላይ አነሳ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ይህ ሰው ከነቢያት አንዱ+ መሆኑን አወቀ። +42 ነቢዩም “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ መጥፋት አለበት ያልኩት ሰው ከእጅህ እንዲያመልጥ ስላደረግክ+ በእሱ ሕይወት ፋንታ የአንተ ሕይወት ይተካል፤*+ በእሱም ሕዝብ ፋንታ የአንተ ሕዝብ ይተካል’”+ አለው። +43 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ፊቱ ጠቁሮና አዝኖ ወደ ቤቱ ወደ ሰማርያ+ ሄደ። +3 ሰለሞን ከግብፁ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር በጋብቻ ተዛመደ። የፈርዖንን ሴት ልጅ አገባ፤*+ እሷንም የራሱን ቤት፣ የይሖዋን ቤትና+ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር+ ገንብቶ እስኪጨርስ ድረስ+ ወደ ዳዊት ከተማ+ አመጣት። +2 ሆኖም እስከዚያን ጊዜ ድረስ ለይሖዋ ስም የተሠራ ቤት ስላልነበረ+ ሕዝቡ መሥዋዕት ያቀርብ የነበረው ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች+ ላይ ነበር። +3 ሰለሞን መሥዋዕቶችንና የሚቃጠሉ መባዎችን ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ከማቅረቡ በስተቀር በአባቱ በዳዊት ደንቦች መሠረት በመሄድ ይሖዋን እንደሚወድ አሳይቷል።+ +"4 ይበልጥ ታዋቂ* የሆነው ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ ገባኦን ስለነበር ንጉሡ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ።+ ሰለሞን በዚያ መሠዊያ ላይ 1,000 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን አቀረበ።+" +5 በገባኦንም ይሖዋ ለሰለሞን ሌሊት በሕ��ም ተገለጠለት፤ አምላክም “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ጠይቅ” አለው።+ +6 በዚህ ጊዜ ሰለሞን እንዲህ አለ፦ “አገልጋይህ አባቴ ዳዊት በፊትህ በታማኝነት፣ በጽድቅና በቅን ልቦና ስለሄደ ጥልቅ የሆነ ታማኝ ፍቅር አሳይተኸዋል። በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ በመስጠት እስከ ዛሬም ድረስ ለእሱ ይህን ጥልቅ የሆነ ታማኝ ፍቅር አሳይተሃል።+ +7 አሁንም አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ገና አንድ ፍሬ ልጅና ተሞክሮ የሌለኝ*+ ብሆንም አገልጋይህን በአባቴ በዳዊት ምትክ አንግሠኸዋል። +8 አገልጋይህ አንተ በመረጥከው፣+ ከብዛቱም የተነሳ ሊቆጠር በማይችለው ሕዝብ መካከል ይገኛል። +9 ስለሆነም አገልጋይህ ሕዝብህን መዳኘት እንዲሁም መልካምና ክፉ የሆነውን ነገር መለየት+ እንዲችል ታዛዥ ልብ ስጠው፤+ አለዚያማ ስፍር ቁጥር የሌለውን* ይህን ሕዝብህን ማን ሊዳኝ ይችላል?” +10 ሰለሞን ይህን መጠየቁ ይሖዋን ደስ አሰኘው።+ +11 ከዚያም አምላክ እንዲህ አለው፦ “ይህን ነገር ስለጠየቅክ እንዲሁም ለራስህ ረጅም ዕድሜ* ወይም ብልጽግና አሊያም የጠላቶችህን ሞት* ሳይሆን የፍርድ ጉዳዮችን መዳኘት እንድትችል ማስተዋልን ስለጠየቅክ+ +12 የጠየቅከውን አደርግልሃለሁ።+ ከአንተ በፊት ማንም ሰው ያልነበረውን+ ከአንተ በኋላም ማንም ሰው የማያገኘውን ጥበበኛና አስተዋይ ልብ እሰጥሃለሁ።+ +13 በተጨማሪም በሕይወት ዘመንህ* ሁሉ ከነገሥታት መካከል አንተን የሚተካከል እንዳይኖር+ አንተ ያልጠየቅከውን+ ብልጽግናና ክብር+ እሰጥሃለሁ። +14 አባትህ ዳዊት እንዳደረገው+ ሥርዓቶቼንና ትእዛዛቴን በመጠበቅ በመንገዶቼ ከሄድክ ረጅም ዕድሜም እሰጥሃለሁ።”*+ +15 ሰለሞንም ከእንቅልፉ ሲነቃ ሕልም መሆኑን ተረዳ። ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መባዎችን+ አቀረበ፤ ለአገልጋዮቹም በሙሉ ግብዣ አዘጋጀ። +16 በዚህ ጊዜ ሁለት ዝሙት አዳሪዎች ወደ ንጉሡ መጥተው ፊቱ ቆሙ። +17 የመጀመሪያዋም ሴት እንዲህ አለች፦ “ጌታዬ ሆይ፣ እኔና ይህች ሴት የምንኖረው አንድ ቤት ውስጥ ነው፤ እሷም ቤት ውስጥ እያለች ልጅ ወለድኩ። +18 እኔ ከወለድኩ ከሦስት ቀን በኋላ ይህችም ሴት ልጅ ወለደች። ሁለታችን አብረን ነበርን፤ ከሁለታችን በስተቀር ቤቱ ውስጥ ማንም አብሮን አልነበረም። +19 ሌሊት ላይ ይህች ሴት ልጇ ላይ ስለተኛችበት ልጇ ሞተ። +20 ስለሆነም እኩለ ሌሊት ላይ ተነስታ እኔ አገልጋይህ ተኝቼ እያለሁ ልጄን ከአጠገቤ በመውሰድ በእቅፏ አስተኛችው፤ የሞተውን ልጇን ደግሞ በእኔ እቅፍ ውስጥ አስተኛችው። +21 እኔም በማለዳ ልጄን ለማጥባት ስነሳ ልጁ ሞቷል። ስለሆነም በማለዳ ብርሃን ልጁን ትክ ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድኩት ልጅ አለመሆኑን ተረዳሁ።” +22 ሆኖም ሌላኛዋ ሴት “በፍጹም፣ በሕይወት ያለው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው!” አለች። በዚህ ጊዜ የመጀመሪያዋ ሴት “በጭራሽ፣ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ በሕይወት ያለው የእኔ ልጅ ነው” አለች። እነሱም እንዲህ እያሉ በንጉሡ ፊት ተጨቃጨቁ። +23 በመጨረሻም ንጉሡ “ይህችኛዋ ‘ይህ በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው!’ ትላለች፤ ያቺኛዋ ደግሞ ‘በፍጹም፣ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ በሕይወት ያለው የእኔ ልጅ ነው!’ ትላለች” አለ። +24 ከዚያም ንጉሡ “እንግዲያውስ ሰይፍ አምጡልኝ” አለ። በመሆኑም ለንጉሡ ሰይፍ አመጡለት። +25 ንጉሡም “በሉ በሕይወት ያለውን ልጅ ለሁለት ሰንጥቁትና ግማሹን ለአንደኛዋ ሴት ግማሹን ደግሞ ለሌላኛዋ ስጡ” አለ። +26 በሕይወት ያለው ልጅ እናት ለልጇ ስለራራች ወዲያውኑ ንጉሡን “እባክህ ጌታዬ! በሕይወት ያለውን ልጅ ለእሷ ስጧት! በፍ��ም አትግደሉት!” በማለት ተማጸነችው። ሌላኛዋ ሴት ግን “ልጁ የእኔም የአንቺም አይሆንም! ለሁለት ይሰንጥቁት!” ትል ነበር። +27 ንጉሡም መልሶ “በሕይወት ያለውን ልጅ ለመጀመሪያዋ ሴት ስጧት! እናቱ እሷ ስለሆነች በፍጹም አትግደሉት” አለ። +28 እስራኤላውያንም ሁሉ ንጉሡ የሰጠውን ፍርድ ሰሙ፤ ንጉሡ ፍትሐዊ ፍርድ መስጠት ይችል ዘንድ የአምላክን ጥበብ እንደታደለ+ ስለተመለከቱ ለንጉሡ አክብሮታዊ ፍርሃት አደረባቸው።+ +7 ሰለሞንም የራሱን ቤት*+ ሙሉ በሙሉ ሠርቶ ለማጠናቀቅ 13 ዓመት ፈጀበት።+ +2 እሱም የሊባኖስ ደን+ የተባለውን ርዝመቱ 100 ክንድ፣* ወርዱ 50 ክንድ፣ ቁመቱ ደግሞ 30 ክንድ የሆነ ቤት በአራት ረድፍ በተደረደሩ የአርዘ ሊባኖስ ዓምዶች ገነባ፤ በዓምዶቹም ላይ የአርዘ ሊባኖስ ወራጆች+ ነበሩ። +3 ቤቱም በዓምዶቹ ላይ ባረፉት አግዳሚዎች ላይ የተረበረቡ የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች ነበሩት፤ ዓምዶቹም* 45 ሲሆኑ በአንዱ ረድፍ ላይ 15 ነበሩ። +4 በሦስት ረድፍ የተሠሩ ባለ ክፈፍ መስኮቶች ነበሩ፤ በሦስቱም ደርቦች ላይ እያንዳንዱ መስኮት ከሌላኛው መስኮት ጋር ትይዩ ነበር። +5 በሦስቱ ደርቦች ላይ ያሉት ትይዩ የሆኑ መስኮቶች ከፊት ለፊት ሲታዩ አራት ማዕዘን እንደሆኑ ሁሉ መግቢያዎቹና መቃኖቹም በሙሉ እንዲሁ ነበሩ። +6 እሱም ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 30 ክንድ የሆነ የዓምዶች መተላለፊያ* ሠራ፤ ከፊት ለፊቱም ዓምዶችና ታዛ ያለው በረንዳ ነበር። +7 በተጨማሪም ፍርድ የሚሰጥበትን የዙፋን+ አዳራሽ* ይኸውም የፍርድ+ አዳራሹን ሠራ፤ አዳራሹንም ከወለሉ አንስቶ እስከ ወራጆቹ ድረስ በአርዘ ሊባኖስ ለበጡት። +8 በሌላኛው ግቢ+ ያለው ራሱ የሚኖርበት ቤት* የሚገኘው ከአዳራሹ* ጀርባ ሲሆን አሠራራቸውም ተመሳሳይ ነበር። በተጨማሪም ሰለሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ከዚህ አዳራሽ ጋር የሚመሳሰል ቤት ሠርቶላት ነበር።+ +9 እነዚህ ሁሉ ከውጭ አንስቶ እስከ ትልቁ ግቢ+ ድረስ፣ ከመሠረቱ እስከ ድምድማቱ፣ በውስጥም በውጭም ተለክተው በተጠረቡና በድንጋይ መጋዝ በተቆረጡ ውድ ድንጋዮች የተሠሩ ነበሩ።+ +10 መሠረቱ የተጣለው ውድ በሆኑ ትላልቅ ድንጋዮች ነበር፤ አንዳንዶቹ ድንጋዮች ባለ አሥር ክንድ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ባለ ስምንት ክንድ ነበሩ። +11 በእነዚህም ላይ ተለክተው የተጠረቡ ውድ ድንጋዮችና የአርዘ ሊባኖስ እንጨቶች ነበሩ። +12 ለይሖዋ ቤት ውስጠኛ ግቢና+ ለቤቱ በረንዳ+ እንደተደረገው ሁሉ የትልቁ ግቢ አጥር የተሠራው በሦስት ረድፍ ጥርብ ድንጋይና በአንድ ረድፍ የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃ ነበር። +13 ንጉሥ ሰለሞን መልእክተኛ ልኮ ኪራምን+ ከጢሮስ አስመጣው። +14 ኪራም ከንፍታሌም ነገድ የሆነች የአንዲት መበለት ልጅ ነበር፤ አባቱ የጢሮስ ሰው ሲሆን የመዳብ ሥራ ባለሙያ+ ነበር፤ ኪራም ከማንኛውም የመዳብ* ሥራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችሎታ፣ ማስተዋልና+ ልምድ ነበረው። በመሆኑም ወደ ንጉሥ ሰለሞን መጥቶ ሥራዎቹን ሁሉ አከናወነለት። +15 እሱም ሁለቱን ዓምዶች+ ከቀለጠ መዳብ ሠራ፤ እያንዳንዱም ዓምድ ቁመቱ 18 ክንድ ነበር፤ ሁለቱ ዓምዶች እያንዳንዳቸው በመለኪያ ገመድ ሲለኩ መጠነ ዙሪያቸው 12 ክንድ ነበር።+ +16 እንዲሁም በዓምዶቹ አናት ላይ የሚሆኑ ሁለት የዓምድ ራሶችን ከመዳብ ሠራ። የአንደኛው የዓምድ ራስ ቁመት አምስት ክንድ የሌላኛው የዓምድ ራስ ቁመትም አምስት ክንድ ነበር። +17 በእያንዳንዱ ዓምድ አናት ላይ ያለው የዓምድ ራስ በሰንሰለት ጉንጉን የተሠሩ መረቦች ነበሩት፤+ በአንደኛው የዓምድ ራስ ላይ ሰባት በሌላኛው የዓምድ ራስ ላይም ሰባት ነበሩ። +18 በዓምዶቹ አናት ላይ ያሉትን የዓምድ ራሶች ለማስጌጥ በአንደኛው መረብ ዙሪያ ሮማኖችን በሁለት ረድፍ ሠራ፤ በ���ለቱም የዓምድ ራሶች ላይ እንዲሁ አደረገ። +19 በረንዳው አጠገብ በሚገኙት ዓምዶች አናት ላይ ያሉት የዓምድ ራሶች አራት ክንድ ቁመት ያለው የአበባ ቅርጽ ነበራቸው። +20 የዓምድ ራሶቹ በሁለቱ ዓምዶች ላይ፣ ልክ ከመረብ ሥራው ቀጥሎ ካለው ከሆዱ በላይ ነበሩ፤ በእያንዳንዱ የዓምድ ራስ ዙሪያ 200 ሮማኖች በረድፍ ተደርድረው ነበር።+ +21 እሱም የቤተ መቅደሱን* በረንዳ ዓምዶች አቆመ።+ በስተ ቀኝ* ያለውን ዓምድ አቁሞ ያኪን* ብሎ ሰየመው፤ ከዚያም በስተ ግራ* ያለውን ዓምድ አቁሞ ቦዔዝ* ብሎ ሰየመው።+ +22 የዓምዶቹም አናቶች የአበባ ቅርጽ ነበራቸው። በዚህ መንገድ የዓምዶቹ ሥራ ተጠናቀቀ። +23 ከዚያም ባሕሩን* በቀለጠ ብረት ሠራ።+ ባሕሩ ክብ ቅርጽ የነበረው ሲሆን ከአንዱ ጠርዝ እስከ ሌላኛው ጠርዝ 10 ክንድ፣ ከፍታው ደግሞ 5 ክንድ ነበር፤ መጠነ ዙሪያውም በመለኪያ ገመድ ሲለካ 30 ክንድ ሆነ።+ +24 በባሕሩም ዙሪያ ከጠርዙ ዝቅ ብሎ በእያንዳንዱ ክንድ ላይ በቅል ቅርጽ+ የተሠሩ አሥር ጌጦች ነበሩ፤ ቅሎቹም በሁለት ረድፍ ከባሕሩ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር። +25 ባሕሩ 3ቱ ወደ ሰሜን፣ 3ቱ ወደ ምዕራብ፣ 3ቱ ወደ ደቡብ እንዲሁም 3ቱ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ፊታቸውን ባደረጉ 12 በሬዎች+ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ባሕሩም ላያቸው ላይ ነበር፤ የሁሉም ሽንጥ ወደ መሃል ገባ ያለ ነበር። +"26 የውኃ ማጠራቀሚያው ውፍረት አንድ ጋት* ነበር፤ ጠርዙ የጽዋ ከንፈር ይመስል የነበረ ሲሆን በአበባ ቅርጽ የተሠራ ነበር። የውኃ ማጠራቀሚያውም 2,000 የባዶስ መስፈሪያ* ይይዝ ነበር። " +27 ከዚያም አሥር የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችን*+ ከመዳብ ሠራ። እያንዳንዱ ጋሪ ርዝመቱ አራት ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ፣ ቁመቱ ደግሞ ሦስት ክንድ ነበር። +28 የጋሪዎቹ አሠራር እንዲህ ነበር፦ ጋሪዎቹ የጎን መከለያ ነበራቸው፤ የጎን መከለያዎቹም በፍርግርግ መካከል ነበሩ። +29 በፍርግርጎቹ መሃል በነበሩት የጎን መከለያዎች ላይ የአንበሶች፣+ የበሬዎችና የኪሩቦች+ ምስል ነበር፤ በፍርግርጎቹም ላይ እንዲሁ ዓይነት ምስል ነበር። ከአንበሶቹና ከበሬዎቹ በላይና በታች፣ የተንጠለጠሉ የአበባ ጉንጉኖች የሚመስሉ ቅርጾች ነበሩ። +30 እያንዳንዱ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪ አራት የመዳብ መንኮራኩሮችና* የመዳብ ዘንጎች ነበሩት፤ በአራቱ ማዕዘኖች ላይ ያሉት ቋሚዎች ደግሞ ድጋፍ ይሆኗቸው ነበር። ድጋፎቹ ከገንዳው በታች ነበሩ፤ እያንዳንዳቸውም በጎናቸው ወጥ ሆኖ የተሠራ የአበባ ጉንጉን የሚመስል ቅርጽ ነበራቸው። +31 የገንዳው አፍ ያለው በጋሪው አናት ውስጥ ሲሆን አንድ ክንድ ከፍታ ነበረው፤ የጋሪው አፍ ክብ ነበር፤ በአፉ ላይ ያለው ማስቀመጫ አንድ ክንድ ተኩል ከፍታ ነበረው፤ በአፉም ላይ የተቀረጹ ምስሎች ነበሩ። የጎን መከለያዎቹም አራት ማዕዘን እንጂ ክብ አልነበሩም። +32 አራቱ መንኮራኩሮች ከጎን መከለያዎቹ በታች ነበሩ፤ የመንኮራኩሮቹ ድጋፎች ከጋሪው ጋር ተያይዘው ነበር፤ የእያንዳንዱ መንኮራኩር ቁመት አንድ ክንድ ተኩል ነበር። +33 የመንኮራኩሮቹ አሠራር ከሠረገላ መንኮራኩር* አሠራር ጋር ተመሳሳይ ነበር። የመንኮራኩሮቹ ድጋፎች፣ ክፈፎች፣* ራጂዎችና አቃፊዎች ሁሉ ከቀለጠ ብረት የተሠሩ ነበሩ። +34 በእያንዳንዱ ጋሪ አራት ማዕዘኖች ላይ አራት ድጋፎች ነበሩ፤ ድጋፎቹም የጋሪው ክፍል ሆነው* የተሠሩ ነበሩ። +35 በጋሪው አናት ላይ ቁመቱ ግማሽ ክንድ የሆነ ክብ ክፈፍ ነበር፤ እንዲሁም በጋሪው አናት ላይ የሚገኙት ፍርግርጎችና የጎን መከለያዎች የጋሪው ክፍል ሆነው* የተሠሩ ነበሩ። +36 በፍርግርጎቹና በጎን መከለያዎቹም ላይ እንደ ስፋታቸው ኪሩቦችን፣ አንበሶችንና የዘንባባ ዛፍ ምስሎችን ቀረጸባቸው፤ ዙሪያውንም የአበባ ጉን���ን ምስል ሠራበት።+ +37 አሥሩን ጋሪዎች+ የሠራው በዚህ መንገድ ነበር፤ ሁሉም አንድ ዓይነት መጠንና ቅርጽ እንዲኖራቸው ተደርገው በተመሳሳይ መንገድ ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ።+ +38 እሱም አሥር የመዳብ ገንዳዎችን+ ሠራ፤ እያንዳንዱ ገንዳ 40 የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር። እያንዳንዱ ገንዳ አራት ክንድ ነበር።* በአሥሩም ጋሪዎች ላይ አንድ አንድ ገንዳ ነበር። +39 ከዚያም አምስቱን ጋሪዎች ከቤቱ በስተ ቀኝ በኩል አምስቱን ጋሪዎች ደግሞ ከቤቱ በስተ ግራ በኩል አደረጋቸው፤ ባሕሩንም ከቤቱ በስተ ቀኝ በኩል፣ በስተ ደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ አስቀመጠው።+ +40 በተጨማሪም ኪራም+ ገንዳዎቹን፣ አካፋዎቹንና+ ጎድጓዳ ሳህኖቹን+ ሠራ። ኪራምም በይሖዋ ቤት ለንጉሥ ሰለሞን ያከናውን የነበረውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።+ የሠራቸውም ነገሮች እነዚህ ነበሩ፦ +41 ሁለቱ ዓምዶች፣+ በሁለቱ ዓምዶች አናት ላይ የነበሩት የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸው የዓምድ ራሶች፣ በዓምዶቹ አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸውን ሁለቱን ክብ የዓምድ ራሶች የሚያስጌጡት ሁለት መረቦች፣+ +42 ለሁለቱ መረቦች የተሠሩት 400 ሮማኖች+ ማለትም በሁለቱ ዓምዶች አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸው የዓምድ ራሶች ለማስጌጥ የተሠሩት በእያንዳንዱ መረብ ላይ በሁለት ረድፍ የተደረደሩት ሮማኖች፣ +43 አሥሩ ጋሪዎችና+ በጋሪዎቹ ላይ የነበሩት አሥር የውኃ ገንዳዎች፣+ +44 ባሕሩና+ ከሥሩ የነበሩት 12 በሬዎች፣ +45 አመድ ማጠራቀሚያዎቹ፣ አካፋዎቹ፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹና ኪራም ለይሖዋ ቤት እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰለሞን ከተወለወለ መዳብ የሠራቸው ዕቃዎች በሙሉ። +46 ንጉሡ እነዚህ ነገሮች በዮርዳኖስ አውራጃ በሱኮትና በጻረታን መካከል በሚገኝ ስፍራ ከሸክላ በተሠሩ ቅርጽ ማውጫዎች ውስጥ ቀልጠው እንዲሠሩ አደረገ። +47 ሰለሞን ዕቃዎቹ ሁሉ እንዲመዘኑ አላደረገም፤ ምክንያቱም ዕቃዎቹ እጅግ ብዙ ነበሩ። የመዳቡ ክብደት ምን ያህል እንደሆነ አልታወቀም።+ +48 ሰለሞንም ለይሖዋ ቤት መገልገያ የሚሆኑትን የሚከተሉትን ነገሮች ሠራ፦ የወርቅ መሠዊያውን፣+ ገጸ ኅብስት የሚቀመጥበትን የወርቅ ጠረጴዛ፣+ +49 በውስጠኛው ክፍል ፊት በቀኝና በግራ የሚቀመጡትን ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ+ አምስት አምስት መቅረዞች፣+ ከወርቅ የተሠሩትን የፈኩ አበቦች፣+ መብራቶችና መቆንጠጫዎች፣ +50 ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩትን ሳህኖች፣ የእሳት ማጥፊያዎች፣+ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ ጽዋዎችና+ መኮስተሪያዎች+ እንዲሁም ከወርቅ የተሠሩትን የውስጠኛው ክፍል+ ማለትም የቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና የመቅደሱ በሮች+ የሚሽከረከሩባቸውን መቆሚያዎች። +51 በዚህ ሁኔታ ንጉሥ ሰለሞን ከይሖዋ ቤት ጋር በተያያዘ መሥራት የሚገባውን ሥራ በሙሉ አጠናቀቀ። ከዚያም ሰለሞን አባቱ ዳዊት የቀደሳቸውን ነገሮች ወደዚያ አስገባ፤+ ብሩን፣ ወርቁንና ዕቃዎቹን በይሖዋ ቤት ግምጃ ቤቶች ውስጥ አስቀመጠ።+ +12 ሮብዓም እስራኤላውያን በሙሉ ሊያነግሡት+ ወደ ሴኬም+ መጥተው ስለነበር እሱም ወደ ሴኬም ሄደ። +2 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን እንደሰማ (ምክንያቱም ኢዮርብዓም ከንጉሥ ሰለሞን ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ስለነበር በወቅቱ በዚያ ይገኝ ነበር)፣+ +3 ልከው አስጠሩት። ከዚያም ኢዮርብዓምና መላው የእስራኤል ጉባኤ መጥተው ሮብዓምን እንዲህ አሉት፦ +4 “አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር።+ አንተ ግን አባትህ የሰጠንን አስቸጋሪ ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ* ቀንበር የምታቀልልን ከሆነ እናገለግልሃለን።” +5 በዚህ ጊዜ “እንግዲያው ሂዱና ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” አላቸው። በመሆኑም ሕዝቡ ሄደ።+ +6 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም አባቱ ሰለሞን በሕይወት በነበረበት ጊዜ ሲያገለግሉት የነበሩትን ሽማግሌዎች “ለዚህ ሕዝብ ምን ምላሽ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” በማለት ምክር ጠየቀ። +7 እነሱም “ዛሬ አንተ የዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆንና የጠየቁህን ብትፈጽምላቸው እንዲሁም መልካም ምላሽ ብትሰጣቸው ምንጊዜም አገልጋዮችህ ይሆናሉ” በማለት መለሱለት። +8 ሆኖም ሮብዓም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ አብሮ አደጎቹ ከነበሩትና አሁን የእሱ አገልጋዮች ከሆኑት ወጣቶች ጋር ተማከረ።+ +9 እሱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚለኝ ለዚህ ሕዝብ ምን ምላሽ እንድንሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” +10 አብሮ አደጎቹ የሆኑት ወጣቶችም እንዲህ አሉት፦ “‘አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚልህ ለዚህ ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች። +11 አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ግን ቀንበራችሁን የባሰ አከብደዋለሁ። አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ።’” +12 ኢዮርብዓምና መላው ሕዝብ ንጉሡ “በሦስተኛው ቀን ተመልሳችሁ ኑ” ባላቸው መሠረት በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ።+ +13 ንጉሡ ግን ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ ለሕዝቡ መጥፎ ምላሽ ሰጠ። +14 ወጣቶቹም በሰጡት ምክር መሠረት “አባቴ ቀንበራችሁን አክብዶባችሁ ነበር፤ እኔ ግን ቀንበራችሁን የባሰ አከብደዋለሁ። አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ” አላቸው። +15 በመሆኑም ንጉሡ ሕዝቡን ሳይሰማ ቀረ፤ ይህም የሆነው ይሖዋ በሴሎናዊው በአኪያህ+ አማካኝነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ይሖዋ እነዚህ ነገሮች በዚህ መንገድ እንዲከናወኑ ስላደረገ ነው።+ +16 እስራኤላውያን ሁሉ ንጉሡ ሊሰማቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን ሲያዩ ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ምንም ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፣ ወደ አማልክትህ ተመለስ። ዳዊት ሆይ፣ እንግዲህ የገዛ ቤትህን ጠብቅ!” ከዚያም እስራኤላውያን ወደየቤታቸው* ተመለሱ።+ +17 ይሁንና ሮብዓም በይሁዳ ከተሞች በሚኖሩት እስራኤላውያን ላይ መግዛቱን ቀጠለ።+ +18 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ የተመለመሉት ሰዎች አለቃ የነበረውን አዶራምን+ ላከው፤ ሆኖም እስራኤላውያን በሙሉ በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሥ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ።+ +19 እስራኤላውያንም እስከዚህ ቀን ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንዳመፁ+ ናቸው። +20 እስራኤላውያን በሙሉ ኢዮርብዓም መመለሱን እንደሰሙ ወደ ማኅበረሰቡ ካስጠሩት በኋላ በመላው እስራኤል ላይ አነገሡት።+ ከይሁዳ ነገድ በስተቀር ከሕዝቡ መሃል የዳዊትን ቤት የተከተለ ማንም አልነበረም።+ +"21 ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከእስራኤል ቤት ጋር ተዋግተው ንግሥናውን ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም እንዲያስመልሱ ከመላው የይሁዳ ቤትና ከቢንያም ነገድ የተውጣጡ 180,000 የሠለጠኑ* ተዋጊዎች ወዲያውኑ ሰበሰበ።+" +22 ከዚያም የእውነተኛው አምላክ ቃል የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደሆነው ወደ ሸማያህ+ እንዲህ ሲል መጣ፦ +23 “ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም፣ ለይሁዳ ቤት ሁሉ፣ ለቢንያምና ለቀረው ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ +24 ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት አትውጡ። ይህ እንዲሆን ያደረግኩት እኔ ስለሆንኩ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ።”’”+ ስለዚህ የይሖዋን ቃል ሰሙ፤ ይሖዋ እንደነገራቸውም ወደየቤታቸው ተመለሱ። +25 ከዚያም ኢዮርብዓም በኤፍሬም ��ራራማ አካባቢ ሴኬምን+ ገንብቶ* በዚያ መኖር ጀመረ። ከዚያ ወጥቶ በመሄድ ጰኑኤልን+ ገነባ።* +26 ኢዮርብዓም በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፦ “እንግዲህ አሁን መንግሥቱ ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል።+ +27 ይህ ሕዝብ በኢየሩሳሌም በሚገኘው የይሖዋ ቤት+ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ መውጣቱን ከቀጠለ የዚህ ሕዝብ ልብ ጌታው ወደሆነው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ይመለሳል። እኔንም ይገድለኛል፤ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓምም ይመለሳል።” +28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ +29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው። +30 ይህም ለኃጢአት ዳረጋቸው፤+ ሕዝቡም በዳን የሚገኘውን ጥጃ ለማምለክ እስከዚያ ድረስ ይሄድ ነበር። +31 እሱም በኮረብቶቹ ላይ የአምልኮ ቤቶችን ሠራ፤ ከሕዝቡም መካከል ሌዋውያን ያልሆኑ ሰዎችን ካህናት አድርጎ ሾመ።+ +32 በተጨማሪም ኢዮርብዓም በስምንተኛው ወር ከወሩም በ15ኛው ቀን በይሁዳ ይከበር የነበረው ዓይነት በዓል እንዲቋቋም አደረገ።+ ለሠራቸውም ጥጆች በቤቴል+ በሠራው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ በቤቴል ለሠራቸው ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችም ካህናት መደበ። +33 በቤቴል በሠራው መሠዊያም ላይ ራሱ በመረጠው ወር ይኸውም በስምንተኛው ወር በ15ኛው ቀን መባዎችን ማቅረብ ጀመረ፤ ለእስራኤል ሰዎችም በዓል አቋቋመ፤ እንዲሁም መባዎችንና የሚጨሱ መሥዋዕቶችን ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ። +1 ንጉሥ ዳዊት አረጀ፤+ ዕድሜውም እየገፋ ሄደ፤ ልብስ ቢደራርቡለትም እንኳ ሊሞቀው አልቻለም። +2 በመሆኑም አገልጋዮቹ “ለጌታዬ ለንጉሡ አንዲት ልጃገረድ ትፈለግለት፤ እሷም ንጉሡን እንደ ሞግዚት ሆና ትንከባከበው። ጌታዬ ንጉሡ እንዲሞቀው በእቅፉ ትተኛለች” አሉት። +3 ስለዚህ በመላው የእስራኤል ግዛት በመዘዋወር ቆንጆ ልጃገረድ ፈለጉ፤ ሹነማዊቷን+ አቢሻግንም+ አገኙ፤ ወደ ንጉሡም አመጧት። +4 እሷም እጅግ ውብ ነበረች፤ የንጉሡም ሞግዚት ሆነች፤ ትንከባከበውም ጀመር፤ ሆኖም ንጉሡ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት አልፈጸመም። +5 በዚህ ጊዜ የሃጊት ልጅ አዶንያስ+ “ንጉሥ እሆናለሁ!” በማለት ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ጀመር። ለራሱም ሠረገላ ከነፈረሰኞቹ እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሮጡ 50 ሰዎች እንዲዘጋጁለት አደረገ።+ +6 አባቱ ግን አንድም ቀን “ይህን ያደረግከው ለምንድን ነው?” በማለት ተቃውሞት* አያውቅም ነበር። በተጨማሪም አዶንያስ እጅግ መልከ መልካም ነበር፤ እናቱ እሱን የወለደችው ከአቢሴሎም በኋላ ነበር። +7 እሱም ከጽሩያ ልጅ ከኢዮዓብና ከካህኑ ከአብያታር+ ጋር ተመካከረ፤ እነሱም እርዳታና ድጋፍ አደረጉለት።+ +8 ሆኖም ካህኑ ሳዶቅ፣+ የዮዳሄ ልጅ በናያህ፣+ ነቢዩ ናታን፣+ ሺምአይ፣+ ረአይና የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች+ አዶንያስን አልደገፉትም። +9 በኋላም አዶንያስ በኤንሮጌል አቅራቢያ በሚገኘው በጾሃለት ድንጋይ አጠገብ በጎችን፣ ከብቶችንና የሰቡ እንስሳትን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤+ የንጉሡ ልጆች የሆኑትን ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም የንጉሡ አገልጋዮች የሆኑትን የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠራ። +10 ይሁን እንጂ ነቢዩ ናታንን፣ በናያህን፣ የዳዊትን ኃያላን ተዋጊዎች ወይም ወንድሙን ሰለሞንን አልጠራም። +11 ከዚያም ናታን+ የሰለሞንን እናት+ ቤርሳቤህን+ እንዲህ አላት፦ “የሃጊት ልጅ አዶንያስ+ ንጉሥ እንደሆነና ጌታችን ዳዊት ደግሞ ስለ ጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ አልሰማሽም? +12 ስለዚህ አሁን ነይ፣ የራስሽንም ሆነ የልጅሽን የሰለሞንን ሕይወት* ማዳን እንድትችይ አንድ ነገር ልምከርሽ።+ +13 ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ እንዲህ በዪው፦ ‘“ልጅሽ ሰለሞን ከእኔ በኋላ ንጉሥ ይሆናል፤ በዙፋኔም ላይ የሚቀመጠው እሱ ነው”+ በማለት ለአገልጋይህ የማልክላት አንተ ንጉሡ ጌታዬ አልነበርክም? ታዲያ አዶንያስ ንጉሥ የሆነው ለምንድን ነው?’ +14 አንቺም እዚያው ገና ከንጉሡ ጋር እየተነጋገርሽ ሳለ እኔ ተከትዬሽ እገባና ያልሽው ትክክል መሆኑን እናገራለሁ።” +15 በመሆኑም ቤርሳቤህ ንጉሡ ወዳለበት ወደ ውስጠኛው ክፍል ገባች። ንጉሡ በጣም አርጅቶ ነበር፤ ሹነማዊቷ አቢሻግም+ ንጉሡን እየተንከባከበች ነበር። +16 ከዚያም ቤርሳቤህ በንጉሡ ፊት ተደፍታ ሰገደች፤ ንጉሡም “ጥያቄሽ ምንድን ነው?” አላት። +17 እሷም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “ጌታዬ ሆይ፣ ‘ልጅሽ ሰለሞን ከእኔ በኋላ ንጉሥ ይሆናል፤ በዙፋኔም ላይ የሚቀመጠው እሱ ነው’ በማለት ለአገልጋይህ በአምላክህ በይሖዋ የማልክላት አንተ ነበርክ።+ +18 ይኸው አሁን ግን አዶንያስ ንጉሥ ሆኗል፤ ጌታዬ ንጉሡም ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።+ +19 እሱም በጣም ብዙ በሬዎችን፣ የሰቡ እንስሳትንና በጎችን መሥዋዕት አድርጓል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ ካህኑን አብያታርንና የሠራዊቱን አለቃ ኢዮዓብን ጠርቷል፤+ አገልጋይህን ሰለሞንን ግን አልጠራውም።+ +20 አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እስራኤላውያን በሙሉ ከጌታዬ ከንጉሡ በኋላ በዙፋኑ ላይ የሚቀመጠው ማን እንደሆነ እንድታሳውቃቸው ዓይኖቻቸው አንተ ላይ ናቸው። +21 አለዚያ ግን ጌታዬ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር በሚያንቀላፋበት ጊዜ እኔና ልጄ ሰለሞን እንደ ከዳተኞች ተደርገን እንቆጠራለን።” +22 እሷም ገና ከንጉሡ ጋር እየተነጋገረች ሳለ ነቢዩ ናታን ገባ።+ +23 ወዲያውም ለንጉሡ “ነቢዩ ናታን መጥቷል!” ብለው ነገሩት። ናታንም ንጉሡ ፊት ቀርቦ በግንባሩ መሬት ላይ በመደፋት ሰገደ። +24 ከዚያም ናታን እንዲህ አለ፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ‘አዶንያስ ከእኔ በኋላ ንጉሥ ይሆናል፤ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውም እሱ ነው’ ብለህ ተናግረሃል እንዴ?+ +25 ይኸው ዛሬ በጣም ብዙ በሬዎችን፣ የሰቡ እንስሳትንና በጎችን ለመሠዋት ወርዷል፤+ እንዲሁም የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ የሠራዊቱን አለቆችና ካህኑን አብያታርን ጠርቷል።+ እነሱም በዚያ ከእሱ ጋር እየበሉና እየጠጡ ‘ንጉሥ አዶንያስ ለዘላለም ይኑር!’ እያሉ ነው። +26 ሆኖም እኔን አገልጋይህን ወይም ካህኑን ሳዶቅን አሊያም የዮዳሄን ልጅ በናያህን+ ወይም አገልጋይህን ሰለሞንን አልጠራም። +27 ጌታዬ ንጉሡ ከእሱ በኋላ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ የሚቀመጠው ማን እንደሆነ ለአገልጋዩ ሳይነግረው ይህ እንዲደረግ ፈቅዷል?” +28 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ዳዊት “ቤርሳቤህን ጥሩልኝ” አለ። እሷም ገብታ ንጉሡ ፊት ቆመች። +29 ንጉሡም እንዲህ ሲል ማለ፦ “ከመከራ ሁሉ ባዳነኝ*+ ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ +30 ‘ልጅሽ ሰለሞን ከእኔ በኋላ ንጉሥ ይሆናል፤ በእኔ ምትክ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውም እሱ ነው!’ በማለት በእስራኤል አምላክ በይሖዋ በማልኩልሽ መሠረት ዛሬም ይህ እንዲፈጸም አደርጋለሁ።” +31 ከዚያም ቤርሳቤህ በግንባሯ መሬት ላይ ተደፍታ ለንጉሡ በመስገድ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም ይኑር!” አለች። +32 ንጉሥ ዳዊትም ወዲያውኑ “በሉ አሁን ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንንና የዮዳሄን+ ልጅ በናያህን+ ጥሩልኝ” አለ። እነሱም ገብተው ንጉሡ ፊት ቀረቡ። +33 ንጉሡም እንዲህ አላቸው፦ “የጌታችሁን አገልጋዮች ውሰዱና ልጄን ሰለሞንን በበቅሎዬ*+ ላይ አስቀምጣችሁ ወደ ግዮን+ ይዛችሁት ውረዱ። +34 በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቀቡታል፤+ ከዚያም ቀንደ መለከ�� እየነፋችሁ ‘ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!’+ በሉ። +35 አጅባችሁትም ተመለሱ፤ እሱም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል፤ በእኔም ምትክ ንጉሥ ይሆናል፤ እኔም በእስራኤልና በይሁዳ ላይ መሪ አድርጌ እሾመዋለሁ።” +36 የዮዳሄ ልጅ በናያህም ወዲያውኑ ንጉሡን እንዲህ አለው፦ “አሜን! የጌታዬ የንጉሡ አምላክ ይሖዋ ይህን ያጽናው። +37 ይሖዋ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር እንደነበረ ሁሉ ከሰለሞንም ጋር ይሁን፤+ ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሥ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርገው።”+ +38 ከዚያም ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያህ፣+ ከሪታውያንና ጴሌታውያን+ ወርደው ሰለሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ ላይ አስቀመጡት፤+ ወደ ግዮንም+ አመጡት። +39 ካህኑ ሳዶቅም ከድንኳኑ+ ውስጥ የዘይቱን ቀንድ+ ወስዶ ሰለሞንን ቀባው፤+ እነሱም ቀንደ መለከት መንፋት ጀመሩ፤ ሕዝቡም ሁሉ “ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!” እያለ ይጮኽ ጀመር። +40 ከዚያም ሕዝቡ በሙሉ ዋሽንት እየነፋና በደስታ እየፈነደቀ ተከትሎት ወጣ፤ ከጩኸታቸውም የተነሳ ምድሪቱ ተሰነጠቀች።+ +41 አዶንያስና የጋበዛቸው ሰዎች ሁሉ በልተው ሲጨርሱ ይህን ድምፅ ሰሙ።+ ኢዮዓብ የቀንደ መለከቱን ድምፅ ሲሰማ “በከተማዋ ውስጥ የሚሰማው ይህ ሁሉ ሁካታ ምንድን ነው?” አለ። +42 እሱም ገና እየተናገረ ሳለ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን+ መጣ። ከዚያም አዶንያስ “መቼም አንተ ጥሩ* ሰው ስለሆንክ ምሥራች ሳትይዝ አትመጣምና ግባ” አለው። +43 ዮናታን ግን ለአዶንያስ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ምሥራች ይዤስ አልመጣሁም! ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰለሞንን አንግሦታል። +44 ንጉሡም ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያህ፣ ከሪታውያንና ጴሌታውያን አብረውት እንዲሄዱ አደረገ፤ እነሱም በንጉሡ በቅሎ ላይ አስቀመጡት።+ +45 ከዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት። እነሱም ከዚያ እየተደሰቱ መጡ፤ ከተማዋ በጩኸት እየተናወጠች ነው። እናንተም የሰማችሁት ይህን ድምፅ ነው። +46 ከዚህም በላይ ሰለሞን በነገሥታቱ ዙፋን ላይ ተቀምጧል። +47 የንጉሡ አገልጋዮችም ‘አምላክህ የሰለሞንን ስም ከአንተ ስም በላይ ታላቅ ያድርገው፤ ዙፋኑንም ከአንተ ዙፋን የበለጠ ያድርገው’ በማለት ለጌታችን ለንጉሥ ዳዊት ደስታቸውን ለመግለጽ መጥተዋል። በዚህ ጊዜ ንጉሡ አልጋው ላይ ሰገደ። +48 ከዚያም ንጉሡ ‘ዛሬ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጥ ሰው የሰጠኝና ዓይኖቼም ይህን እንዲያዩ ያደረገው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ!’ አለ።” +49 አዶንያስ የጋበዛቸው ሰዎችም ሁሉ ተሸበሩ፤ እያንዳንዳቸውም ተነስተው በየፊናቸው ሄዱ። +50 አዶንያስም ሰለሞንን ስለፈራው ተነስቶ በመሄድ የመሠዊያውን ቀንዶች ያዘ።+ +51 በኋላም ሰለሞን “አዶንያስ ንጉሥ ሰለሞንን ፈርቶታል፤ ‘በመጀመሪያ ንጉሥ ሰለሞን አገልጋዩን በሰይፍ እንደማይገድል ይማልልኝ’ በማለት የመሠዊያውን ቀንዶች ይዟል” ተብሎ ተነገረው። +52 በዚህ ጊዜ ሰለሞን “ጸባዩን ካሳመረ ከራስ ፀጉሩ አንዲቷም እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም፤ መጥፎ ነገር ከተገኘበት+ ግን ይሞታል” አለ። +53 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን አዶንያስን ከመሠዊያው ላይ እንዲያወርዱት ሰዎች ላከ። ከዚያም አዶንያስ መጥቶ ለንጉሥ ሰለሞን ሰገደ፤ ሰለሞንም “ወደ ቤትህ ሂድ” አለው። +8 በዚህ ጊዜ ሰለሞን የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የነገዶቹን መሪዎች ሁሉና የእስራኤልን የአባቶች ቤት አለቆች+ ሰበሰበ።+ እነሱም የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ+ ማለትም ከጽዮን+ ለማምጣት በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ንጉሥ ሰለሞን መጡ። +2 የእስራኤል ሰዎች በሙሉ በሰባተኛው ወር ማለትም በኤታኒም* ወር በሚከበረው በዓል* ላይ ንጉሥ ሰ��ሞን ፊት ተሰበሰቡ።+ +3 የእስራኤል ሽማግሌዎችም በሙሉ መጡ፤ ካህናቱም ታቦቱን አነሱ።+ +4 የይሖዋን ታቦት፣ የመገናኛ ድንኳኑንና+ በድንኳኑ ውስጥ የነበሩትን ቅዱስ ዕቃዎች በሙሉ አመጡ። እነዚህንም ያመጡት ካህናቱና ሌዋውያኑ ናቸው። +5 ንጉሥ ሰለሞንና ወደ እሱ እንዲመጣ የተጠራው መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ታቦቱ ፊት ነበሩ። ከብዛታቸው የተነሳ ሊቆጠሩ የማይችሉ ብዙ በጎችና ከብቶች መሥዋዕት ሆነው ቀረቡ።+ +6 ከዚያም ካህናቱ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት አምጥተው ቦታው+ ላይ ማለትም በቤቱ ውስጠኛ ክፍል ይኸውም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ከኪሩቦቹ ክንፎች በታች አስቀመጡት።+ +7 የኪሩቦቹ ክንፎች ታቦቱ ባለበት ቦታ ላይ ተዘርግተው ስለነበር ኪሩቦቹ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን ከላይ ከልለዋቸው ነበር።+ +8 መሎጊያዎቹ+ ረጅም ስለነበሩ የመሎጊያዎቹን ጫፎች ከውስጠኛው ክፍል ፊት ለፊት ባለው በቅድስቱ ውስጥ ሆኖ ማየት ይቻል ነበር፤ ከውጭ ግን አይታዩም ነበር። እስከ ዛሬም ድረስ እዚያው ይገኛሉ። +9 የእስራኤል ሰዎች ከግብፅ ምድር ሲወጡ+ ይሖዋ ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባበት ጊዜ+ ሙሴ በኮሬብ ታቦቱ ውስጥ ካስቀመጣቸው+ ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች+ በስተቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም አልነበረም። +10 ካህናቱ ከቅዱሱ ስፍራ በወጡ ጊዜ ደመናው+ የይሖዋን ቤት ሞላው።+ +11 የይሖዋ ክብር የይሖዋን ቤት ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ከደመናው የተነሳ በዚያ ቆመው ማገልገል አልቻሉም።+ +12 በዚህ ጊዜ ሰለሞን እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ በድቅድቅ ጨለማ+ ውስጥ እንደሚኖር ተናግሯል። +13 እኔም እጅግ ከፍ ያለ ቤት፣ ለዘላለም የምትኖርበት ጸንቶ የተመሠረተ ቦታ+ ገንብቼልሃለሁ።” +14 ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ ቆሞ ሳለ ንጉሡ ዞሮ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ መባረክ ጀመረ።+ +15 እንዲህም አለ፦ “ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ እንዲህ ብሎ ቃል የገባውና ይህን በራሱ እጅ የፈጸመው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ፦ +16 ‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ዕለት አንስቶ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ስሜ የሚጠራበት ቤት እንዲሠራበት አንድም ከተማ አልመረጥኩም፤+ ዳዊትን ግን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዢ እንዲሆን መረጥኩ።’ +17 አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ለመሥራት ከልቡ ተመኝቶ ነበር።+ +18 ሆኖም ይሖዋ አባቴን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ ‘ለስሜ ቤት ለመሥራት ከልብህ ተመኝተህ ነበር፤ ይህን በልብህ መመኘትህም መልካም ነው። +19 ይሁንና ቤቱን የምትሠራው አንተ አይደለህም፤ ሆኖም ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ የሚወለድልህ የገዛ ልጅህ* ይሆናል።’+ +20 ይሖዋ የገባውን ቃል ፈጽሟል፤ ልክ ይሖዋ ቃል በገባው መሠረት አባቴን ዳዊትን ተክቼ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀምጫለሁና። በተጨማሪም ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ሠርቻለሁ፤+ +21 እንዲሁም አባቶቻችንን ከግብፅ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ይሖዋ ከእነሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን የያዘው ታቦት+ የሚያርፍበትን ቦታ በዚያ አዘጋጅቻለሁ።” +22 ከዚያም ሰለሞን በይሖዋ መሠዊያ ፊት፣ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ለፊት ቆሞ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤+ +23 እንዲህም አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ በፊቱ በሙሉ ልባቸው ለሚመላለሱ+ አገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር+ የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ አምላክ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር የለም።+ +24 ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቀሃል። በገዛ አፍህ ቃል ገባህ፤ ዛሬ ደግሞ በራስህ እጅ ፈጸምከው።+ +25 አሁንም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ ‘አንተ በፊቴ እንደተመላለስከው ሁሉ ልጆችህም በጥንቃቄ በፊቴ ከተመላለሱ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከፊቴ ፈጽሞ አይታጣም’ በማለት ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቅ።+ +26 አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ፣ እባክህ ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸው ቃል ይፈጸም። +27 “በእርግጥ አምላክ በምድር ላይ ይኖራል?+ እነሆ ሰማያት፣ አዎ ሰማየ ሰማያት እንኳ ሊይዙህ አይችሉም፤+ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤትማ ምንኛ ያንስ!+ +28 እንግዲህ አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመና በትኩረት ስማ፤ አገልጋይህ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰማውን ጩኸትና በዛሬው ዕለት በፊትህ የሚያቀርበውን ጸሎት አዳምጥ። +29 አገልጋይህ ወደዚህ ስፍራ የሚያቀርበውን ጸሎት ለመስማት ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’+ ወዳልከው ወደዚህ ቤት ዓይኖችህ ቀንና ሌሊት ይመልከቱ።+ +30 አገልጋይህ ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመናና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ በመጸለይ የሚያቀርበውን ልመና አዳምጥ፤ በሰማያት ባለው ማደሪያህ ሆነህ ስማ፤+ ሰምተህም ይቅር በል።+ +31 “አንድ ሰው ባልንጀራውን በድሎ እንዲምል ቢደረግ፣* በመሐላውም* ተጠያቂ ቢሆን፣ በዳዩም በዚህ መሐላ* ሥር ሆኖ እዚህ ቤት ውስጥ ባለው መሠዊያህ ፊት ቢቀርብ፣+ +32 አንተ በሰማያት ሆነህ ስማ፤ ክፉውን ጥፋተኛ* በማለትና እንደ ሥራው በመመለስ፣ ጻድቁንም ንጹሕ* መሆኑን በማሳወቅና እንደ ጽድቁ ወሮታውን በመክፈል እርምጃ ውሰድ፤ አገልጋዮችህንም ዳኝ።+ +33 “ሕዝብህ እስራኤላውያን አንተን ከመበደላቸው የተነሳ በጠላት ድል ቢነሱና+ ወደ አንተ ተመልሰው ስምህን ቢያወድሱ+ እንዲሁም በዚህ ቤት ወደ አንተ ቢጸልዩና ሞገስ ለማግኘት ልመና ቢያቀርቡ+ +34 ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ለአባቶቻቸው ወደሰጠኸው ምድርም መልሳቸው።+ +35 “ሕዝቡ አንተን በመበደሉ የተነሳ+ ሰማያት ተዘግተው ዝናብ ቢጠፋ፣+ እነሱም አንተ ስላዋረድካቸው* ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩና ስምህን ቢያወድሱ እንዲሁም ከኃጢአታቸው ቢመለሱ+ +36 ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የአገልጋዮችህን፣ የሕዝብህን የእስራኤላውያንን ኃጢአት ይቅር በል፤ ስለሚሄዱበት ቀና መንገድ ታስተምራቸዋለህና፤+ ለሕዝብህ ርስት አድርገህ ባወረስከው ምድርህም ላይ ዝናብ አዝንብ።+ +37 “በምድሪቱ ላይ ረሃብ+ ወይም ቸነፈር፣ የሚለበልብና የሚያደርቅ ነፋስ ወይም ዋግ+ ቢከሰት፣ የአንበጣ መንጋ ወይም የማይጠግብ አንበጣ* ቢመጣ አሊያም ጠላቶቻቸው በምድሪቱ ላይ ባለ በየትኛውም ከተማ* ውስጥ ሳሉ ቢከቧቸው ወይም ደግሞ ማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት አሊያም ማንኛውም ዓይነት በሽታ ቢከሰትና+ +38 ማንኛውም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል በሙሉ (እያንዳንዱ የልቡን ጭንቀት ያውቃልና)+ ወደ አንተ ለመጸለይ ወይም ሞገስ እንድታሳየው ልመና+ ለማቅረብ እጁን ወደዚህ ቤት ቢዘረጋ +39 አንተ ከመኖሪያ ቦታህ+ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ ደግሞም ይቅር በል፤+ እርምጃም ውሰድ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው ብድራቱን ክፈለው፤+ ምክንያቱም አንተ ልቡን ታውቃለህ (የሰውን ልብ በሚገባ የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ)፤+ +40 ይህም ለአባቶቻችን በሰጠኸው ምድር ላይ በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አንተን እንዲፈሩ ነው። +41 “በተጨማሪም ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ የባዕድ አገር ሰው በስምህ* የተነሳ ከሩቅ አገር ቢመጣ፣+ +42 (መቼም ስለ ታላቁ ስምህ፣+ ስለ ኃያሉ እጅህና ስለተዘረጋው ክንድህ መስማታቸው አይቀርም) ወደዚህም ቤት መጥቶ ቢጸልይ +43 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት+ ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና እንዲፈሩህ+ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ �� የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት። +44 “ሕዝብህ ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትልካቸው መንገድ ለጦርነት ቢወጡና+ አንተ ወደመረጥከው ከተማ+ እንዲሁም ለስምህ ወደሠራሁት ቤት አቅጣጫ+ ወደ ይሖዋ ቢጸልዩ+ +45 ከሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡትን ልመና ስማ፤ ፍረድላቸውም። +46 “በአንተ ላይ ኃጢአት ቢሠሩ (መቼም ኃጢአት የማይሠራ ሰው የለም)፣+ አንተም በእነሱ እጅግ ተቆጥተህ ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው፣ ጠላቶቻቸውም ራቅ ወዳለ ወይም ቅርብ ወደሆነ የጠላት ምድር ምርኮኛ አድርገው ቢወስዷቸው+ +47 እነሱም በምርኮ በተወሰዱበት ምድር ወደ ልቦናቸው ቢመለሱና+ ወደ አንተ ዞር በማለት+ ‘ኃጢአት ሠርተናል፤ አጥፍተናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል’+ በማለት በተማረኩበት ምድር+ ሆነው ሞገስ ለማግኘት ወደ አንተ ልመና ቢያቀርቡ፣ +48 ማርከው በወሰዷቸው ጠላቶቻቸውም ምድር ሆነው በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው* ወደ አንተ ቢመለሱ+ እንዲሁም ለአባቶቻቸው በሰጠሃቸው ምድር፣ አንተ በመረጥካት ከተማና ለስምህ በሠራሁት ቤት አቅጣጫ ወደ አንተ ቢጸልዩ+ +49 ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት ያቀረቡትን ልመና ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ+ ስማ፤ ፍረድላቸውም፤ +50 በአንተ ላይ የፈጸሙትን በደል ሁሉ ይቅር በማለት በአንተ ላይ ኃጢአት የሠራውን ሕዝብህን ይቅር በል። የማረኳቸውም ሰዎች እንዲያዝኑላቸው ታደርጋለህ፤ እነሱም ያዝኑላቸዋል+ +51 (ምክንያቱም እነሱ እንደ ብረት ማቅለጫ+ ከሆነችው ከግብፅ ያወጣሃቸው+ ሕዝቦችህና ርስትህ+ ናቸው)። +52 አገልጋይህም ሆነ ሕዝብህ እስራኤል ወደ አንተ በሚጮኹበት ጊዜ ሁሉ ስማቸው፤ ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡትንም ልመና+ ዓይኖችህ ይመልከቱ።+ +53 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አባቶቻችንን ከግብፅ ባወጣሃቸው ጊዜ በአገልጋይህ በሙሴ በኩል በተናገርከው መሠረት ከምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ርስትህ አድርገህ ለይተሃቸዋልና።”+ +54 ሰለሞንም ይህን ሁሉ ጸሎትና ልመና ወደ ይሖዋ አቅርቦ እንደጨረሰ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ከተንበረከከበት ከይሖዋ መሠዊያ ፊት ተነሳ።+ +55 ከዚያም ቆሞ የእስራኤልን ጉባኤ በሙሉ ጮክ ብሎ እንዲህ ሲል ባረከ፦ +56 “በገባው ቃል መሠረት ለሕዝቡ ለእስራኤል የእረፍት ቦታ የሰጠው ይሖዋ ይወደስ።+ በአገልጋዩ በሙሴ አማካኝነት ከሰጠው መልካም ተስፋ ሁሉ መካከል ሳይፈጸም የቀረ አንድም ቃል የለም።+ +57 አምላካችን ይሖዋ ከአባቶቻችን ጋር እንደነበረ ሁሉ ከእኛም ጋር ይሁን።+ አይተወን፤ ደግሞም አይጣለን።+ +58 በመንገዱ ሁሉ እንድንሄድ እንዲሁም አባቶቻችን እንዲጠብቁ ያዘዛቸውን ትእዛዛቱን፣ ሥርዓቱንና ድንጋጌዎቹን እንድንጠብቅ ልባችንን ወደ እሱ ያዘንብል።+ +59 ሞገስ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ያቀረብኩት ይህ ልመና በአምላካችን በይሖዋ ፊት ቀንና ሌሊት ይታወስ፤ ለአገልጋዩና ለሕዝቡ ለእስራኤልም በየዕለቱ የሚያስፈልገውን ፍርድ ይፍረድላቸው፤ +60 ይህም የምድር ሕዝቦች ሁሉ እውነተኛው አምላክ ይሖዋ መሆኑን እንዲያውቁ ነው።+ ከእሱ ሌላ ማንም የለም!+ +61 በመሆኑም እንደ ዛሬው ዕለት ሁሉ በአምላካችን በይሖዋ ሥርዓቶች በመሄድና ትእዛዛቱን በመጠበቅ ልባችሁ በእሱ ዘንድ ሙሉ ይሁን።”*+ +62 ከዚያም ንጉሡና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ በይሖዋ ፊት ታላቅ መሥዋዕት አቀረቡ።+ +"63 ሰለሞን 22,000 ከብቶችና 120,000 በጎች ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት+ አድርጎ አቀረበ። በዚህ መንገድ ንጉሡና እስራኤላውያን በሙሉ የይሖዋን ቤት መረቁ።+" +64 ንጉሡም በዚያ ቀን በይሖዋ ቤት ፊት የሚገኘውን የግቢውን መሃል መቀደስ አስፈልጎት ነበር፤ ምክንያቱም የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶች፣ ���እህል መባዎቹንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን በዚያ ማቅረብ ነበረበት፤ ይህም የሆነው በይሖዋ ፊት ያለው የመዳብ መሠዊያ+ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶች፣ የእህል መባዎቹንና የኅብረት መሥ +65 በዚያ ጊዜ ሰለሞን ከመላው እስራኤል ጋር ይኸውም ከሌቦሃማት* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ ድረስ ካለው ምድር ከመጣው ታላቅ ጉባኤ ጋር በመሆን በአምላካችን በይሖዋ ፊት ለ7 ቀን፣ ከዚያም ለተጨማሪ 7 ቀን በአጠቃላይ ለ14 ቀን በዓሉን አከበረ።+ +66 በቀጣዩም* ቀን ሕዝቡን አሰናበተ፤ እነሱም ንጉሡን ባረኩ፤ ይሖዋ ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ባሳየው ጥሩነት ሁሉ እየተደሰቱና ከልባቸው እየፈነደቁ+ ወደየቤታቸው ሄዱ። +11 ይሁንና ንጉሥ ሰለሞን ከፈርዖን ልጅ+ ሌላ ብዙ የባዕድ አገር ሴቶችን+ ማለትም ሞዓባውያን፣+ አሞናውያን፣+ ኤዶማውያን፣ ሲዶናውያንና+ ሂታውያን+ ሴቶችን አፈቀረ። +2 እነሱም ይሖዋ ለእስራኤላውያን “ከእነሱ ጋር አትቀላቀሉ፤* እነሱም ከእናንተ ጋር አይቀላቀሉ፤ አለዚያ ያለምንም ጥርጥር ልባችሁ አማልክታቸውን ወደ መከተል እንዲያዘነብል ያደርጉታል”+ ብሎ ከነገራቸው ብሔራት ወገን ነበሩ። ሆኖም ሰለሞን ከእነሱ ጋር ተጣበቀ፤ ደግሞም አፈቀራቸው። +3 እሱም ልዕልቶች የሆኑ 700 ሚስቶች እንዲሁም 300 ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ቀስ በቀስ ልቡ ወደ ሌላ እንዲያዘነብል አደረጉት።* +4 ሰለሞን በሸመገለ+ ጊዜ ሚስቶቹ ልቡ ሌሎች አማልክትን ወደ መከተል እንዲያዘነብል* አደረጉት፤+ ልቡ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ በአምላኩ በይሖዋ ዘንድ ሙሉ* አልነበረም። +5 ሰለሞን የሲዶናውያንን እንስት አምላክ አስታሮትንና+ አስጸያፊ የሆነውን የአሞናውያንን አምላክ ሚልኮምን+ ተከተለ። +6 ሰለሞንም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ይሖዋን ሙሉ በሙሉ አልተከተለም።+ +7 ሰለሞን አስጸያፊ ለሆነው የሞዓብ አምላክ ለከሞሽና አስጸያፊ ለሆነው ለአሞናውያን+ አምላክ ለሞሎክ+ ኢየሩሳሌም ፊት ለፊት በሚገኘው ተራራ ላይ ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ+ የሠራው በዚህ ጊዜ ነበር። +8 ለአማልክታቸው የሚጨስ መሥዋዕት ለሚያቀርቡትና ለሚሠዉት የባዕድ አገር ሚስቶቹ ሁሉ ልክ እንደዚሁ አደረገ። +9 ሰለሞን ሁለት ጊዜ ከተገለጠለት+ ከእስራኤል አምላክ ከይሖዋ ልቡ ስለሸፈተ+ ይሖዋ በሰለሞን ላይ ተቆጣ፤ +10 ደግሞም ሌሎች አማልክትን እንዳይከተል በማዘዝ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ አስጠንቅቆት ነበር።+ እሱ ግን ይሖዋ ያዘዘውን ነገር አልጠበቀም። +11 በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “ይህን ስላደረግክ እንዲሁም ባዘዝኩህ መሠረት ቃል ኪዳኔንና ደንቦቼን ስላልጠበቅክ መንግሥትህን ቀድጄ ከአንተ እወስደዋለሁ፤ ከአገልጋዮችህም መካከል ለአንዱ እሰጠዋለሁ።+ +12 ሆኖም ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ዘመን ይህን አላደርግም። መንግሥትህን ከልጅህ እጅ ላይ እቀደዋለሁ፤+ +13 ይሁንና መንግሥቱን በሙሉ ቀድጄ አልወስድም።+ ስለ አገልጋዬ ስለ ዳዊትና ስለመረጥኳት+ ስለ ኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ።”+ +14 ከዚያም ይሖዋ ከኤዶም+ ንጉሣዊ ቤተሰብ የሆነውን ኤዶማዊውን ሃዳድን በሰለሞን ላይ ተቃዋሚ አድርጎ አስነሳው።+ +15 ዳዊት ኤዶምን+ ድል ባደረገበት ጊዜ የሠራዊቱ አለቃ የሆነው ኢዮዓብ የተገደሉትን ለመቅበር ወጥቶ የነበረ ሲሆን በኤዶም የሚገኘውን እያንዳንዱን ወንድ ለመግደል ሞክሮ ነበር። +16 (ምክንያቱም ኢዮዓብ በኤዶም የሚገኘውን እያንዳንዱን ወንድ ገድሎ እስኪጨርስ ድረስ ከመላው እስራኤል ጋር በዚያ ለስድስት ወር ተቀምጦ ነበር።) +17 ሆኖም ሃዳድ የአባቱ አገልጋዮች ከሆኑ የተወሰኑ ኤዶማውያን ጋር ሸሸ፤ እነሱም ���ደ ግብፅ ሄዱ፤ በወቅቱ ሃዳድ ገና ትንሽ ልጅ ነበር። +18 እነሱም ከምድያም ተነስተው ወደ ፋራን ሄዱ። ከፋራንም+ ሰዎች ይዘው ወደ ግብፅ ይኸውም ወደ ግብፁ ንጉሥ ወደ ፈርዖን መጡ፤ ፈርዖንም ቤትና መሬት ሰጠው፤ ቀለብም እንዲሰፈርለት አደረገ። +19 ሃዳድም በፈርዖን ፊት ሞገስ ስላገኘ ፈርዖን የገዛ ሚስቱን እህት ማለትም የንግሥት ጣፍኔስን እህት ዳረለት። +20 ከጊዜ በኋላ የጣፍኔስ እህት፣ ጌኑባት የተባለ ልጅ ወለደችለት፤ ጣፍኔስም ልጁን በፈርዖን ቤት ውስጥ አሳደገችው፤* ጌኑባት በፈርዖን ቤት ከፈርዖን ልጆች ጋር ኖረ። +21 ሃዳድ በግብፅ ሳለ ዳዊት ከአባቶቹ ጋር እንዳንቀላፋ+ እንዲሁም የሠራዊቱ አለቃ ኢዮዓብ እንደሞተ ሰማ።+ በመሆኑም ሃዳድ ፈርዖንን “ወደ አገሬ እንድሄድ አሰናብተኝ” አለው። +22 ፈርዖን ግን “እዚህ እኔ ጋር እያለህ ምን ጎደለብህና ነው ወደ አገርህ መሄድ የፈለግከው?” አለው። እሱም “ምንም የጎደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ እንድሄድ አሰናብተኝ” አለው። +23 በተጨማሪም አምላክ ከጌታው ከጾባህ ንጉሥ ከሃዳድኤዜር+ የኮበለለውን የኤሊያዳን ልጅ ረዞንን በሰለሞን ላይ ተቃዋሚ አድርጎ አስነሳው።+ +24 እሱም ዳዊት የጾባህን ሰዎች ድል ባደረገበት ጊዜ* ሰዎችን አሰባስቦ የአንድ ወራሪ ቡድን አለቃ ሆነ።+ በመሆኑም ወደ ደማስቆ+ ሄደው በዚያ ሰፈሩ፤ በደማስቆም መግዛት ጀመሩ። +25 ሃዳድ በእስራኤል ላይ ካስከተለው ጉዳት በተጨማሪ ረዞንም በሰለሞን ዘመን ሁሉ የእስራኤል ተቃዋሚ ሆነ፤ በሶርያ ላይ በነገሠበትም ዘመን ሁሉ ለእስራኤል ከፍተኛ ጥላቻ ነበረው። +26 እንዲሁም የሰለሞን አገልጋይ+ የሆነ ኢዮርብዓም+ የተባለ አንድ ኤፍሬማዊ ነበር፤ እሱም ከጸሬዳህ ወገን ሲሆን የናባጥ ልጅ ነበር፤ እናቱም ጽሩዓ የምትባል መበለት ነበረች። እሱም በንጉሡ ላይ ማመፅ* ጀመረ።+ +27 በንጉሡ ላይ ያመፀውም በዚህ የተነሳ ነው፦ ሰለሞን ጉብታውን*+ ሠርቶ እንዲሁም በአባቱ በዳዊት ከተማ+ ቅጥር ላይ የነበረውን ክፍተት ዘግቶ ነበር። +28 ኢዮርብዓም ከፍተኛ ችሎታ ያለው ሰው ነበር። ሰለሞንም ወጣቱ ጠንካራ ሠራተኛ መሆኑን ሲያይ በዮሴፍ ቤት በሚከናወነው የግዳጅ ሥራ ሁሉ ላይ የበላይ ተመልካች አደረገው።+ +29 በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ወጣ፤ ሴሎናዊው ነቢዩ አኪያህም መንገድ ላይ አገኘው። አኪያህ+ አዲስ ልብስ ለብሶ ነበር፤ በሜዳውም ላይ ሁለቱ ብቻቸውን ነበሩ። +30 አኪያህም ለብሶት የነበረውን አዲስ ልብስ ይዞ 12 ቦታ ቀደደው። +31 ከዚያም ኢዮርብዓምን እንዲህ አለው፦ “አሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እንግዲህ መንግሥቱን ከሰለሞን እጅ እቀደዋለሁ፤ ለአንተም አሥር ነገዶችን እሰጥሃለሁ።+ +32 ሆኖም ስለ አገልጋዬ ስለ ዳዊትና+ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ስለመረጥኳት ከተማ+ ስለ ኢየሩሳሌም ስል አንዱ ነገድ የእሱ እንደሆነ ይቀጥላል።+ +33 ይህን የማደርገው እኔን ትተው+ ለሲዶናውያን እንስት አምላክ ለአስታሮት፣ ለሞዓብ አምላክ ለከሞሽና ለአሞናውያን አምላክ ለሚልኮም ስለሰገዱ ነው፤ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ እንዲሁም ደንቦቼንና ድንጋጌዎቼን በመጠበቅ በመንገዴ አልሄዱም። +34 ሆኖም ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ስለጠበቀው ስለመረጥኩት አገልጋዬ ስለ ዳዊት+ ስል መንግሥቱን በሙሉ ከእጁ አልወስድም፤ ደግሞም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ አለቃ አደርገዋለሁ። +35 ይሁን እንጂ መንግሥቱን ይኸውም አሥሩን ነገድ ከልጁ እጅ ወስጄ ለአንተ እሰጥሃለሁ።+ +36 አገልጋዬ ዳዊት ስሜ እንዲኖርባት ለራሴ በመረጥኳት ከተማ በኢየሩሳሌም ዘወትር በፊቴ መብራት እንዲኖረው+ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ። +37 እኔም እወስድሃለሁ፤ አንተም በተመኘኸው* ሁሉ ላይ ትገዛለህ፤ በእስራኤልም ላይ ንጉሥ ትሆናለህ። +38 አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው+ ያዘዝኩህን ሁሉ ብትፈጽም እንዲሁም ደንቦቼንና ትእዛዛቴን በመጠበቅ በመንገዶቼ ብትሄድና በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር ብታደርግ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ። ለዳዊት እንዳደረግኩለት ሁሉ ለአንተም ጸንቶ የሚኖር ቤት እሠራልሃለሁ፤+ እስራኤልንም እሰጥሃለሁ። +39 በዚህም የተነሳ የዳዊትን ዘር አዋርዳለሁ፤+ ይህን የማደርገው ግን ለሁልጊዜ አይደለም።’”+ +40 በመሆኑም ሰለሞን ኢዮርብዓምን ሊገድለው ሞከረ፤ ሆኖም ኢዮርብዓም ተነስቶ ወደ ግብፅ፣+ ወደ ንጉሥ ሺሻቅ+ ሸሸ፤ ሰለሞን እስኪሞትም ድረስ በግብፅ ተቀመጠ። +41 የቀረው የሰለሞን ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉና ጥበቡ በሰለሞን የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?+ +42 ሰለሞን በኢየሩሳሌም ሆኖ በመላው እስራኤል ላይ የገዛበት የጊዜ ርዝመት* 40 ዓመት ነበር። +43 ከዚያም ሰለሞን ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ሮብዓም+ ነገሠ። +2 ዳዊት የሚሞትበት ቀን ሲቃረብ ልጁን ሰለሞንን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ +2 “እንግዲህ እኔ የምሞትበት ጊዜ ቀርቧል።* ስለሆነም በርታ፤+ ወንድ ሁን።+ +3 በሙሴ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት በመንገዶቹ በመሄድ እንዲሁም ደንቦቹን፣ ትእዛዛቱን፣ ፍርዶቹንና ማሳሰቢያዎቹን በመጠበቅ ለአምላክህ ለይሖዋ ያለብህን ግዴታ ፈጽም፤+ ይህን ካደረግክ የምታከናውነው ሁሉ ይሳካልሃል፤ በምትሄድበትም ሁሉ ይቃናልሃል። +4 ይሖዋም እንዲህ በማለት የገባልኝን ቃል ይፈጽማል፦ ‘ልጆችህ፣ በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው*+ በፊቴ በታማኝነት በመመላለስ መንገዳቸውን ከጠበቁ ከዘር ሐረግህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይታጣም።’+ +5 “የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ በእኔ ላይ ያደረገውን ነገር ይኸውም በሁለቱ የእስራኤል ሠራዊት አለቆች ማለትም በኔር ልጅ በአበኔርና+ በየቴር ልጅ በአሜሳይ+ ላይ ያደረገውን በሚገባ ታውቃለህ። ይህ ሰው እነዚህን ሰዎች በመግደል ጦርነት ሳይኖር በሰላሙ ጊዜ ደም አፍስሷል፤+ እንዲሁም በወገቡ ላይ የታጠቀው ቀበቶና +6 እንግዲህ እንደ ጥበብህ አድርግ፤ ሽበቱ በሰላም ወደ መቃብር* እንዲወርድ አታድርግ።+ +7 “ሆኖም ለቤርዜሊ+ ልጆች ታማኝ ፍቅር አሳያቸው፤ እነሱም ከማዕድህ ከሚበሉ ሰዎች መካከል ይሁኑ፤ ምክንያቱም ከወንድምህ ከአቢሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ+ እነሱም ከጎኔ ቆመው ነበር።+ +8 “በተጨማሪም ከባሁሪም የመጣው ቢንያማዊው የጌራ ልጅ ሺምአይ አብሮህ አለ። ወደ ማሃናይም በሄድኩበት ዕለት+ ከባድ እርግማን የረገመኝ እሱ ነው፤+ ሆኖም እኔን ለማግኘት ወደ ዮርዳኖስ በወረደ ጊዜ ‘በሰይፍ አልገድልህም’ ብዬ በይሖዋ ማልኩለት።+ +9 አንተ ጥበበኛ ስለሆንክና በእሱ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብህ ስለምታውቅ ሳትቀጣ አትተወው፤+ ሽበቱ በደም ወደ መቃብር* እንዲወርድ አድርግ።”+ +10 ከዚያም ዳዊት ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም+ ተቀበረ። +11 ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ የገዛው ለ40 ዓመት ነበር። በኬብሮን+ ለ7 ዓመት፣ በኢየሩሳሌም ደግሞ ለ33 ዓመት ነገሠ።+ +12 ከዚያም ሰለሞን በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ቀስ በቀስም ንግሥናው እየጸና ሄደ።+ +13 ከጊዜ በኋላም የሃጊት ልጅ አዶንያስ ወደ ሰለሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ መጣ። እሷም “የመጣኸው በሰላም ነው?” አለችው፤ እሱም “አዎ፣ በሰላም ነው” አላት። +14 ከዚያም “አንድ የምነግርሽ ጉዳይ አለኝ” አላት። እሷም “እሺ፣ ንገረኝ” አለችው። +15 እሱም እንዲህ አላት፦ “ንግሥናው የእኔ ሊሆን እን���ነበረና እስራኤልም ሁሉ ይነግሣል ብለው ይጠብቁ እንደነበር* በሚገባ ታውቂያለሽ፤+ ይሁንና ንግሥናው የእኔ መሆኑ ቀርቶ የወንድሜ ሆነ፤ ምክንያቱም ይሖዋ ንግሥናው የእሱ እንዲሆን ወስኖ ነበር።+ +16 ሆኖም አሁን አንድ የምጠይቅሽ ነገር አለ። መቼም አታሳፍሪኝም።” እሷም “እሺ ንገረኝ” አለችው። +17 እሱም “እባክሽ፣ ንጉሥ ሰለሞን የጠየቅሽውን እንቢ ስለማይልሽ ሹነማዊቷን አቢሻግን+ እንዲድርልኝ ጠይቂው” አላት። +18 በዚህ ጊዜ ቤርሳቤህ “መልካም! ንጉሡን አነጋግርልሃለሁ” አለችው። +19 በመሆኑም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሥ ሰለሞን ገባች። ንጉሡም ወዲያውኑ ሊቀበላት ተነሳ፤ ሰገደላትም። ከዚያም ዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ የንጉሡም እናት በቀኙ እንድትቀመጥ ዙፋን አስመጣላት። +20 እሷም “አንዲት ትንሽ ነገር ልጠይቅህ አስቤ ነበር። መቼም እንቢ አትለኝም” አለችው። ንጉሡም “እናቴ ሆይ፣ ንገሪኝ፤ የጠየቅሽኝን እንቢ አልልሽም” አላት። +21 እሷም “ሹነማዊቷ አቢሻግ ለወንድምህ ለአዶንያስ ትዳርለት” አለችው። +22 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ሰለሞን ለእናቱ እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ለአዶንያስ ሹነማዊቷን አቢሻግን ብቻ ለምን ትጠይቂለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ+ ስለሆነ ንግሥናም ጠይቂለት እንጂ፤+ ካህኑ አብያታርና የጽሩያ+ ልጅ ኢዮዓብም+ እየደገፉት ነው።” +23 ከዚያም ንጉሥ ሰለሞን እንዲህ ሲል በይሖዋ ማለ፦ “አዶንያስ ይህን በመጠየቁ ሕይወቱን ሳያጣ ቢቀር* አምላክ ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣብኝ። +24 አሁንም በሚገባ ባጸናኝ፣+ በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ ባስቀመጠኝና በገባው ቃል መሠረት ቤት በሠራልኝ*+ ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ አዶንያስ በዛሬዋ ዕለት ይገደላል።”+ +25 ንጉሥ ሰለሞንም ወዲያውኑ የዮዳሄን ልጅ በናያህን+ ላከው፤ እሱም ወጥቶ አዶንያስን መታው፤* እሱም ሞተ። +26 ንጉሡም ካህኑን አብያታርን+ እንዲህ አለው፦ “በአናቶት+ ወደሚገኘው እርሻህ ሂድ! አንተ ሞት የሚገባህ ሰው ነህ፤ ሆኖም በአባቴ በዳዊት ፊት የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ታቦት ስለተሸከምክና+ በአባቴ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ ስለተጋራህ ዛሬ አልገድልህም።”+ +27 በመሆኑም ይሖዋ በሴሎ፣+ በኤሊ ቤት+ ላይ እንደሚደርስ የተናገረው ነገር ይፈጸም ዘንድ ሰለሞን አብያታርን የይሖዋ ካህን ሆኖ እንዳያገለግል አባረረው። +28 ኢዮዓብ ቀደም ሲል ከአቢሴሎም+ጋር ወግኖ ያልነበረ ቢሆንም አዶንያስን+ ደግፎ ስለነበር ይህን ወሬ ሲሰማ ወደ ይሖዋ ድንኳን+ በመሸሽ የመሠዊያውን ቀንዶች ያዘ። +29 ከዚያም ንጉሥ ሰለሞን “ኢዮዓብ ወደ ይሖዋ ድንኳን ሸሽቶ እዚያ በመሠዊያው አጠገብ ይገኛል” ተብሎ ተነገረው። በመሆኑም ሰለሞን የዮዳሄን ልጅ በናያህን “ሂድና ግደለው!” ብሎ ላከው። +30 ስለዚህ በናያህ ወደ ይሖዋ ድንኳን ሄዶ ኢዮዓብን “ንጉሡ ‘ና ውጣ!’ ብሎሃል” አለው። እሱ ግን “እዚሁ እሞታታለሁ እንጂ በፍጹም አልወጣም!” አለ። በዚህ ጊዜ በናያህ “ኢዮዓብ እንዲህ እንዲህ ብሏል፤ እንዲህም ሲል መልሶልኛል” በማለት ለንጉሡ ተናገረ። +31 ከዚያም ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በል ልክ እንዳለው አድርግ፤ ግደለውና ቅበረው፤ ኢዮዓብ አላግባብ ካፈሰሰውም ደም እኔንና የአባቴን ቤት አንጻ።+ +32 ኢዮዓብ አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእሱ ይልቅ ጻድቅና የተሻሉ የነበሩትን ሁለት ሰዎች ማለትም የእስራኤል ሠራዊት አለቃ+ የነበረውን የኔርን ልጅ አበኔርንና+ የይሁዳ ሠራዊት አለቃ+ የነበረውን የየቴርን ልጅ አሜሳይን+ በሰይፍ መትቶ በመግደሉ ይሖዋ ደሙን በራሱ ላይ ይመልስበታል። +33 ደማቸውም ለዘላለም በኢዮዓብ ራስና በዘሮቹ ራስ ላይ ይሆናል፤+ በዳዊት፣ በዘሮቹ፣ በቤቱና በ���ፋኑ ላይ ግን የይሖዋ ሰላም ለዘላለም ይሁን።” +34 ከዚያም የዮዳሄ ልጅ በናያህ ወጥቶ ኢዮዓብን መትቶ ገደለው፤ እሱም በምድረ በዳ በሚገኘው በራሱ ቤት ተቀበረ። +35 ከዚያም ንጉሡ በኢዮዓብ ምትክ የዮዳሄን ልጅ በናያህን+ በሠራዊቱ ላይ ሾመው፤ በአብያታር ቦታ ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን+ ሾመው። +36 ንጉሡም ሺምአይን+ አስጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ኢየሩሳሌም ውስጥ ቤት ሠርተህ በዚያ ኑር፤ ከዚያም ወጥተህ ወደ ሌላ ቦታ አትሂድ። +37 ከዚያ ወጥተህ የቄድሮንን ሸለቆ+ የተሻገርክ ቀን ግን እንደምትሞት እወቅ። ደምህ በራስህ ላይ ይሆናል።” +38 ሺምአይም ንጉሡን “ጥሩ ሐሳብ ነው። አገልጋይህ፣ ጌታዬ ንጉሡ እንዳለው ያደርጋል” አለው። ስለሆነም ሺምአይ በኢየሩሳሌም ለብዙ ጊዜ ተቀመጠ። +39 ሆኖም ከሦስት ዓመት በኋላ ከሺምአይ ባሪያዎች መካከል ሁለቱ የጌት ንጉሥ ወደሆነው ወደ ማአካ ልጅ ወደ አንኩስ+ ኮበለሉ። ሺምአይም “ባሪያዎችህ ያሉት ጌት ነው” ተብሎ ሲነገረው +40 ወዲያውኑ አህያውን ጭኖ ባሪያዎቹን ለመፈለግ በጌት ወዳለው ወደ አንኩስ አቀና። ሺምአይ ባሪያዎቹን ይዞ ከጌት ሲመለስ +41 ለሰለሞን “ሺምአይ ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ወደ ጌት ሄዶ ነበር፤ አሁን ግን ተመልሷል” ተብሎ ተነገረው። +42 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ሺምአይን አስጠርቶ እንዲህ አለው፦ “‘ከዚህ ወጥተህ ወደ ሌላ ቦታ በሄድክ ቀን እንደምትሞት እወቅ’ ብዬ በይሖዋ አስምዬህና አስጠንቅቄህ አልነበረም? አንተስ ብትሆን ‘ጥሩ ሐሳብ ነው፤ እንዳልከኝ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ አልነበረም?+ +43 ታዲያ በይሖዋ ፊት የገባኸውን መሐላና የሰጠሁህን ትእዛዝ ያልጠበቅከው ለምንድን ነው?” +44 ከዚያም ንጉሡ፣ ሺምአይን እንዲህ አለው፦ “በአባቴ በዳዊት ላይ ያደረግከውን ክፉ ነገር ሁሉ ልብህ ያውቀዋል፤+ ይሖዋም ያደረግከውን ክፉ ነገር በራስህ ላይ ይመልስብሃል።+ +45 ንጉሥ ሰለሞን ግን ይባረካል፤+ የዳዊትም ዙፋን በይሖዋ ፊት ለዘላለም ይጸናል።” +46 ከዚያም ንጉሡ የዮዳሄን ልጅ በናያህን አዘዘው፤ እሱም ወጥቶ ሺምአይን መትቶ ገደለው።+ በዚህ መንገድ መንግሥቱ በሰለሞን እጅ ጸና።+ +4 ንጉሥ ሰለሞን መላውን እስራኤል ይገዛ ነበር።+ +2 ከፍተኛ ባለሥልጣናቱ* እነዚህ ነበሩ፦ የሳዶቅ+ ልጅ አዛርያስ ካህን ነበር፤ +3 የሺሻ ልጆች ኤሌሆሬፍና አኪያህ ጸሐፊዎች ነበሩ፤+ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ ታሪክ ጸሐፊ ነበር፤ +4 የዮዳሄ ልጅ በናያህ+ የሠራዊቱ አዛዥ ነበር፤ ሳዶቅና አብያታር+ ካህናት ነበሩ፤ +5 የናታን+ ልጅ አዛርያስ የአስተዳዳሪዎቹ ኃላፊ ነበር፤ የናታን ልጅ ዛቡድ ካህንና የንጉሡ ወዳጅ ነበር፤+ +6 አሂሻር የቤቱ አዛዥ ነበር፤ የአብዳ ልጅ አዶኒራም+ የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ በተመለመሉት+ ላይ አዛዥ ነበር። +7 ሰለሞን በመላው እስራኤል ላይ የተሾሙ ለንጉሡና ለቤተሰቡ ቀለብ የሚያቀርቡ 12 አስተዳዳሪዎች ነበሩት። እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር።+ +8 ስማቸውም የሚከተለው ነው፦ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የሁር ልጅ፣ +9 በማቃጽ፣ በሻአልቢም፣+ በቤትሼሜሽ እና በኤሎንቤትሃናን የዴቀር ልጅ፣ +10 በአሩቦት የሄሴድ ልጅ (ሶኮህ እና የሄፌር ምድር በሙሉ በሥሩ ነበሩ)፣ +11 በዶር ሸንተረር በሙሉ የአቢናዳብ ልጅ (እሱም የሰለሞንን ልጅ ጣፋትን አግብቶ ነበር)፣ +12 በታአናክ እና በመጊዶ+ እንዲሁም ከኢይዝራኤል በታች ከጸረታን አጠገብ በሚገኘው በቤትሼን+ በሙሉና ከቤትሼን አንስቶ በዮቅመአም+ እስከሚገኘው እስከ አቤልምሆላ ድረስ የአሂሉድ ልጅ ባአና፣ +13 በራሞትጊልያድ+ የጌቤር ልጅ (በጊልያድ+ የሚገኙት የምናሴ ልጅ የያኢር+ የድንኳን ሰፈሮች በእሱ ሥር ነበሩ፤ እንዲሁም በባሳን+ የ���ገኘው የአርጎብ ክልል+ ይኸውም በቅጥር የታጠሩና የመዳብ መቀርቀሪያ ያላቸው 60 ትላልቅ ከተሞች በእሱ ሥር ነበሩ)፣ +14 በማሃናይም+ የኢዶ ልጅ አሂናዳብ፣ +15 በንፍታሌም አኪማዓስ (እሱም ሌላኛዋን የሰለሞንን ልጅ፣ ባሴማትን አግብቶ ነበር)፣ +16 በአሴርና በበዓሎት የኩሲ ልጅ ባአና፣ +17 በይሳኮር የፓሩህ ልጅ ኢዮሳፍጥ፣ +18 በቢንያም+ የኤላ ልጅ ሺምአይ+ +19 እንዲሁም የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖን+ እና የባሳን ንጉሥ የኦግ+ ምድር በሆነው በጊልያድ+ ምድር የዖሪ ልጅ ጌቤር። በተጨማሪም በምድሪቱ አስተዳዳሪዎች ሁሉ ላይ የተሾመ አንድ አስተዳዳሪ ነበር። +20 ይሁዳና እስራኤል ከብዛታቸው የተነሳ እንደ ባሕር አሸዋ ነበሩ፤+ እነሱም ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ይደሰቱ ነበር።+ +21 ሰለሞን ከወንዙ*+ አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ምድርና እስከ ግብፅ ወሰን ድረስ ባሉት መንግሥታት ሁሉ ላይ ገዛ። እነሱም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ግብር ያመጡለት እንዲሁም ያገለግሉት ነበር።+ +22 ሰለሞን በየቀኑ የሚገባለት ቀለብ ይህ ነበር፦ 30 የቆሮስ መስፈሪያ* የላመ ዱቄት፣ 60 የቆሮስ መስፈሪያ ዱቄት +23 እንዲሁም 10 ቅልብ ከብቶች፣ ከግጦሽ የመጡ 20 ከብቶች፣ 100 በጎችና የተወሰኑ የርኤም* ዝርያዎች፣ የሜዳ ፍየሎችና የሰቡ ወፎች። +24 እሱም ከወንዙ ወዲህ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ጨምሮ ከቲፍሳ አንስቶ እስከ ጋዛ+ ድረስ የሚገኙትን ከወንዙ+ ወዲህ* ያሉትን አካባቢዎች በሙሉ ተቆጣጥሮ ነበር፤ በዙሪያው ባለው አካባቢ ሁሉ ሰላም ሰፍኖለት ነበር።+ +25 በሰለሞን ዘመን ከዳን አንስቶ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ በይሁዳና በእስራኤል የሚገኝ እያንዳንዱ ሰው ከገዛ ወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ያለስጋት ይኖር ነበር። +"26 ሰለሞን ሠረገሎቹን ለሚጎትቱት ፈረሶች የሚሆኑ 4,000* ጋጣዎችና 12,000 ፈረሶች* ነበሩት።+ " +27 እነዚህ አስተዳዳሪዎች ለንጉሥ ሰለሞንና ከንጉሥ ሰለሞን ማዕድ ለሚመገቡት ሁሉ ቀለብ ያቀርቡ ነበር። እያንዳንዳቸውም በተመደበላቸው ወር የሚጠበቅባቸውን ያቀርቡ የነበረ ሲሆን ምንም ነገር እንዳይጓደል ጥንቃቄ ያደርጉ ነበር።+ +28 እንዲሁም እያንዳንዳቸው በተመደበላቸው ድርሻ መሠረት ለፈረሶቹና ለሰንጋ ፈረሶቹ የሚሆነውን ገብስና ገለባ ወደተፈለገው ቦታ ያመጡ ነበር። +29 አምላክም ለሰለሞን እጅግ ታላቅ ጥበብና ማስተዋል እንዲሁም በባሕር ዳርቻ ላይ እንዳለ አሸዋ፣ ሰፊ ልብ* ሰጠው።+ +30 የሰለሞን ጥበብ ከምሥራቅ ሰዎች ሁሉ ጥበብና ከግብፅ ሁሉ ጥበብ የላቀ ነበር።+ +31 እሱም ከማንኛውም ሰው ይልቅ ጥበበኛ ነበር፤ ከዛራዊው ከኤታን+ እንዲሁም የማሆል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፣+ ከካልኮል+ እና ከዳርዳ ይልቅ ጥበበኛ ነበር፤ ዝናውም በዙሪያው ባሉት ብሔራት ሁሉ ዘንድ ተሰማ።+ +"32 እሱም 3,000 ምሳሌዎችን+ አቀናበረ፤* የመዝሙሮቹም+ ብዛት 1,005 ነበር።" +33 በሊባኖስ ከሚገኘው አርዘ ሊባኖስ አንስቶ በቅጥር ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ+ ድረስ ስለ ዛፎች ተናግሯል፤ እንዲሁም ስለ እንስሳት፣+ ስለ አእዋፍ፣*+ መሬት ለመሬት ስለሚሄዱ ፍጥረታትና*+ ስለ ዓሣዎች ተናግሯል። +34 ስለ እሱ ጥበብ ሲወራ የሰሙ በተለያየ የምድር ክፍል የሚገኙ ነገሥታትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ብሔራት፣ ሰዎች የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ይመጡ ነበር።+ +16 ከዚያም በባኦስ ላይ የተነገረው የይሖዋ ቃል የሃናኒ+ ልጅ ወደሆነው ወደ ኢዩ+ እንዲህ ሲል መጣ፦ +2 “ከአቧራ ላይ አንስቼ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አደረግኩህ፤+ አንተ ግን የኢዮርብዓምን መንገድ ተከተልክ፤ ሕዝቤ እስራኤልም ኃጢአት እንዲሠራ አደረግክ፤ እነሱም በኃጢአታቸው አስቆጡኝ።+ +3 ስለሆነም ባኦስንና ቤቱን ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ፤ ቤቱንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም+ ቤት አደርገዋለሁ። +4 ከባኦስ ወገን የሆነውን በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ሁሉ ውሾች ይበሉታል፤ ከእሱ ወገን የሆነውን በሜዳ ላይ የሚሞተውን ሁሉ ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል።” +5 የቀረው የባኦስ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮችና ኃያልነቱ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +6 በመጨረሻም ባኦስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቲርጻም+ ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኤላህ ነገሠ። +7 በተጨማሪም ባኦስ ልክ እንደ ኢዮርብዓም ቤት በእጁ በሠራቸው ነገሮች ይሖዋን በማስቆጣት በፊቱ መጥፎ የሆነውን ነገር ሁሉ ስለፈጸመ እንዲሁም እሱን* ስለገደለ የይሖዋ ቃል የሃናኒ ልጅ በሆነው በነቢዩ ኢዩ አማካኝነት በባኦስና በቤቱ ላይ መጣ።+ +8 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ26ኛው ዓመት የባኦስ ልጅ ኤላህ በቲርጻ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሁለት ዓመትም ገዛ። +9 የግማሹ የሠረገላ ሠራዊት አለቃ የሆነው አገልጋዩ ዚምሪ በእሱ ላይ አሴረ፤ በዚህ ጊዜ ኤላህ በቲርጻ የሚገኘው የንጉሡ ቤት ኃላፊ በነበረው በአርጻ ቤት ጠጥቶ ሰክሮ ነበር። +10 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ27ኛው ዓመት ዚምሪ ገብቶ ኤላህን መትቶ ገደለው፤+ በእሱም ምትክ ነገሠ። +11 እሱም ነግሦ ገና በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠ የባኦስን ቤት ሁሉ መታ። ከዘመዶቹም* ሆነ ከወዳጆቹ መካከል አንድም ወንድ* አላስተረፈም። +12 በዚህ መንገድ ይሖዋ በነቢዩ ኢዩ+ አማካኝነት በባኦስ ላይ በተናገረው ቃል መሠረት ዚምሪ መላውን የባኦስን ቤት አጠፋ። +13 ይህም የሆነው ባኦስ እና ልጁ ኤላህ በፈጸሙት ኃጢአት እንዲሁም ከንቱ በሆኑት ጣዖቶቻቸው አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን በማስቆጣት እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረጉት ኃጢአት የተነሳ ነው።+ +14 የቀረው የኤላህ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +15 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ27ኛው ዓመት፣ ሠራዊቱ የፍልስጤማውያን የሆነችውን ጊበቶንን+ ከቦ በነበረበት ወቅት ዚምሪ በቲርጻ ለሰባት ቀን ነገሠ። +16 በኋላም ከተማዋን ከቦ የነበረው ሠራዊት “ዚምሪ ሴራ በመጠንሰስ ንጉሡን ገድሎታል” የሚል ወሬ ሰማ። በመሆኑም መላው እስራኤል የሠራዊቱ አለቃ የሆነውን ኦምሪን+ በዚያን ቀን በሰፈሩ ውስጥ በእስራኤል ላይ አነገሡት። +17 ኦምሪና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከጊበቶን ወጥተው ቲርጻን ከበቡ። +18 ዚምሪም ከተማዋ መያዟን ሲያይ በንጉሡ ቤት* ወዳለው የማይደፈር ማማ ገብቶ በውስጡ እንዳለ ቤቱን በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም የተነሳ ሞተ።+ +19 ይህም የሆነው የኢዮርብዓምን መንገድ በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም በሠራው በገዛ ኃጢአቱና እስራኤላውያን እንዲሠሩ ባደረገው ኃጢአት የተነሳ ነው።+ +20 የቀረው የዚምሪ ታሪክና የጠነሰሰው ሴራ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም? +21 የእስራኤል ሕዝብ በሁለት አንጃ የተከፈለው በዚህ ጊዜ ነበር። አንደኛው ወገን የጊናትን ልጅ ቲብኒን ለማንገሥ ስለፈለገ የእሱ ተከታይ ሆነ፤ ሌላኛው ወገን ደግሞ ኦምሪን ተከተለ። +22 ሆኖም ኦምሪን የተከተለው ሕዝብ የጊናትን ልጅ ቲብኒን በተከተለው ሕዝብ ላይ አየለ። በመሆኑም ቲብኒ ሞተ፤ ኦምሪም ነገሠ። +23 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ31ኛው ዓመት ኦምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለ12 ዓመትም ገዛ። በቲርጻም ሆኖ ለስድስት ዓመት ገዛ። +24 እሱም የሰማርያን ተራራ ከሼሜር ላይ በሁለት ታላንት* ብር ገዛ፤ በተራራውም ላይ ከተማ ገነባ። የገነባትንም ከተማ ��ተራራው ጌታ በሆነው በሼሜር ስም ሰማርያ*+ ብሎ ሰየማት። +25 ኦምሪም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ቀጠለ፤ ከእሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸመ።+ +26 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ፤ እንዲሁም ኢዮርብዓም እስራኤላውያን በከንቱ ጣዖቶቻቸው አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን እንዲያስቆጡት በማድረግ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና ተመላለሰ።+ +27 የቀረው የኦምሪ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮችና በኃያልነቱ የፈጸማቸው ጀብዱዎች በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +28 በመጨረሻም ኦምሪ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ አክዓብ+ ነገሠ። +29 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ38ኛው ዓመት የኦምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ የኦምሪ ልጅ አክዓብ በሰማርያ+ ሆኖ በእስራኤል ላይ ለ22 ዓመት ገዛ። +30 የኦምሪ ልጅ አክዓብ ከእሱ በፊት የነበሩት ሁሉ ከፈጸሙት የከፋ ድርጊት በይሖዋ ፊት ፈጸመ።+ +31 አክዓብ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና መመላለሱ ሳያንሰው የሲዶናውያን+ ንጉሥ የኤትባዓል ልጅ የሆነችውን ኤልዛቤልን+ አገባ፤ እንዲሁም ባአልን ማገልገልና+ ለእሱ መስገድ ጀመረ። +32 እንዲሁም በሰማርያ ለባአል በሠራው ቤት+ ውስጥ* ለባአል መሠዊያ አቆመ። +33 በተጨማሪም አክዓብ የማምለኪያ ግንድ* ሠራ።+ እንዲሁም ከእሱ በፊት ከነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን የሚያስቆጣ ድርጊት ፈጸመ። +34 በአክዓብ ዘመን የቤቴል ሰው የሆነው ሂኤል ኢያሪኮን መልሶ ገነባ። ይሖዋ በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት የከተማዋን መሠረት ሲጥል የበኩር ልጁ አቤሮን ሞተ፤ በሮቿን ሲያቆም ደግሞ የመጨረሻ ልጁ ሰጉብ ሞተ።+ +6 እስራኤላውያን* ከግብፅ ምድር በወጡ+ በ480ኛው ዓመት ይኸውም ሰለሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ዚፍ*+ በተባለው በሁለተኛው ወር ሰለሞን የይሖዋን ቤት መሥራት ጀመረ።*+ +2 ንጉሥ ሰለሞን ለይሖዋ የሠራው ቤት ርዝመቱ 60 ክንድ፣* ወርዱ 20 ክንድ፣ ቁመቱ ደግሞ 30 ክንድ ነበር።+ +3 ከቅድስቱ* ፊት ለፊት ያለው በረንዳ+ ርዝመቱ* 20 ክንድ ሲሆን ይህም ከቤቱ ወርድ ጋር እኩል ነው። በረንዳው ከቤቱ አሥር ክንድ ወደ ፊት ወጣ ያለ ነበር። +4 ለቤቱም እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች*+ ያሏቸውን መስኮቶች ሠራ። +5 በተጨማሪም በቤቱ ግድግዳ ዙሪያ ተቀጥላ ቤት ሠራ። ቤቱ የተሠራው በቤቱ ግድግዳ ዙሪያ ይኸውም በቤተ መቅደሱና* በውስጠኛው ክፍል+ ግድግዳ ዙሪያ ነበር፤ በዚህ መንገድ በዙሪያው ተቀጥላ ክፍሎችን ሠራ።+ +6 የታችኛው ተቀጥላ ክፍል ወርድ አምስት ክንድ፣ የመካከለኛው ወርድ ስድስት ክንድ፣ የላይኛው ወርድ ደግሞ ሰባት ክንድ ነበር፤ ከቤቱ ግድግዳ ጋር የሚያያዝ ምንም ነገር እንዳይኖር በቤቱ ግድግዳ ዙሪያ ተሸካሚዎችን* ሠርቶ ነበር።+ +7 ቤቱ የተገነባው ሁሉ ነገር ባለቀለት ተፈልፍሎ በወጣ ድንጋይ ነበር፤+ በመሆኑም ቤቱ በተገነባበት ጊዜ የመዶሻ ወይም የመጥረቢያ አሊያም የማንኛውም የብረት መሣሪያ ድምፅ ቤቱ ውስጥ አልተሰማም። +8 የታችኛው ተቀጥላ ክፍል መግቢያ የሚገኘው በስተ ደቡብ* በኩል ባለው የቤቱ ጎን ነበር፤+ በተጨማሪም ከታችኛው ወደ መካከለኛው ደርብ እንዲሁም ከመካከለኛው ወደ ላይኛው ደርብ የሚያስወጣ ጠመዝማዛ ደረጃ ነበር። +9 እሱም ቤቱን ገንብቶ አጠናቀቀ፤+ ቤቱንም ከአርዘ ሊባኖስ በተሠሩ ተሸካሚዎችና ርብራቦች ከደነው።+ +10 በቤቱ ዙሪያ እያንዳንዳቸው ቁመታቸው አምስት ክንድ የሆነ ተቀጥላ ክፍሎችን ሠራ፤+ ክፍሎቹም ከቤቱ ጋር በአ��ዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች ተያይዘው ነበር። +11 ይህ በእንዲህ እንዳለ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሰለሞን መጣ፦ +12 “በደንቦቼ ብትሄድ፣ ፍርዶቼን ብትፈጽምና በትእዛዛቴ መሠረት በመሄድ ሁሉንም ብትጠብቃቸው+ እኔም እየገነባህ ያለኸውን ይህን ቤት በተመለከተ ለአባትህ ለዳዊት የገባሁለትን ቃል እፈጽምልሃለሁ፤+ +13 እንዲሁም በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤+ ሕዝቤን እስራኤልንም አልተውም።”+ +14 ሰለሞንም ቤቱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የግንባታ ሥራውን ገፋበት። +15 ውስጠኛውን የቤቱን ግድግዳ በአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች ሠራ። ቤቱንም ከወለሉ አንስቶ እስከ ኮርኒሱ ወራጆች ድረስ በሳንቃ ለበጠ፤ የቤቱንም ወለል በጥድ ጣውላ ለበጠው።+ +16 እንዲሁም ከቤቱ በስተ ኋላ በኩል ከወለሉ አንስቶ እስከ ወራጁ ድረስ በአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች የተሠራ ባለ 20 ክንድ ክፍል ገነባ፤ በውስጡም፣* የውስጠኛውን ክፍል+ ይኸውም ቅድስተ ቅዱሳኑን+ ሠራ። +17 ከፊቱ ያለው የቤቱ ክፍል ይኸውም ቤተ መቅደሱ*+ 40 ክንድ ነበር። +18 በቤቱ በውስጠኛው በኩል ያለው አርዘ ሊባኖስ የቅሎችና+ የፈኩ አበቦች+ ምስል ተቀርጾበት ነበር። ሙሉ በሙሉ በአርዘ ሊባኖስ የተሠራ ነበር፤ ምንም የሚታይ ድንጋይ አልነበረም። +19 እሱም የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት+ በዚያ ለማስቀመጥ ቤቱ ውስጥ የውስጠኛውን ክፍል+ አዘጋጀ። +20 ውስጠኛው ክፍል ርዝመቱ 20 ክንድ፣ ወርዱ 20 ክንድ እንዲሁም ቁመቱ 20 ክንድ ነበር፤+ በንጹሕ ወርቅም ለበጠው፤ መሠዊያውንም+ በአርዘ ሊባኖስ ለበጠው። +21 ሰለሞን ቤቱን ከውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤+ በወርቅ በተለበጠው በውስጠኛው ክፍል+ ፊት ለፊትም የወርቅ ሰንሰለት ዘረጋ። +22 ቤቱ ሙሉ በሙሉ እስኪለበጥ ድረስ ቤቱን በሙሉ በወርቅ ለበጠው፤ በውስጠኛው ክፍል አጠገብ ያለውን መሠዊያም+ ሙሉ በሙሉ በወርቅ ለበጠው። +23 በውስጠኛው ክፍል ውስጥ እያንዳንዳቸው አሥር ክንድ ቁመት ያላቸውን+ ሁለት ኪሩቦች+ ከጥድ እንጨት* ሠራ። +24 የኪሩቡ አንድ ክንፍ አምስት ክንድ ሲሆን ሌላኛውም ክንፉ አምስት ክንድ ነበር። ከአንዱ ክንፍ ጫፍ እስከ ሌላው ክንፍ ጫፍ አሥር ክንድ ነበር። +25 ሁለተኛውም ኪሩብ አሥር ክንድ ነበር። ሁለቱ ኪሩቦች ተመሳሳይ መጠንና ቅርጽ ነበራቸው። +26 የአንደኛው ኪሩብ ቁመት አሥር ክንድ ነበር፤ የሌላኛውም ኪሩብ እንደዚሁ ነበር። +27 ከዚያም ኪሩቦቹን+ ውስጠኛው ክፍል* ውስጥ አስቀመጣቸው። የኪሩቦቹም ክንፎች ተዘርግተው ስለነበር የአንደኛው ኪሩብ ክንፍ አንደኛው ግድግዳ ጋ፣ የሌላኛው ኪሩብ ክንፍ ደግሞ ሌላኛው ግድግዳ ጋ ይደርስ ነበር፤ ወደ ቤቱ መሃል የተዘረጉት ክንፎቻቸው ደግሞ ይነካኩ ነበር። +28 ኪሩቦቹንም በወርቅ ለበጣቸው። +29 በቤቱ ግድግዳ ሁሉ ላይ ይኸውም በውስጠኛውና በውጨኛው ክፍሎች ዙሪያ ሁሉ የኪሩቦችን፣+ የዘንባባ ዛፎችንና+ የፈኩ አበቦችን+ ምስል ቀረጸ፤ +30 የቤቱን ወለል ይኸውም የውስጠኛውንም ሆነ የውጨኛውን ክፍሎች ወለል በወርቅ ለበጠው። +31 ለውስጠኛው ክፍል መግቢያ የሚሆኑ በሮችን፣ በጎንና በጎን የሚቆሙ ዓምዶችንና መቃኖችን አንድ አምስተኛ* አድርጎ ከጥድ እንጨት ሠራ። +32 ሁለቱ በሮች ከጥድ እንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ በበሮቹም ላይ የኪሩቦችን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችን ምስል ቀረጸባቸው፤ በወርቅም ለበጣቸው፤ ደግሞም ወርቁን በኪሩቦቹና በዘንባባ ዛፎቹ ላይ ጠፈጠፈው። +33 ለቤተ መቅደሱ* መግቢያ የሚሆኑትንና የአንድ አራተኛው* ክፍል የሆኑትን የጥድ እንጨት መቃኖች የሠራው በዚሁ መንገድ ነበር። +34 እሱም ከጥድ እንጨት ሁለት በሮች ሠራ። ሁለት ታጣፊ ሳንቃዎች ያሉት አንዱ በር በመሽከርከሪያዎቹ ላይ፣ ሁለት ታጣፊ ሳንቃዎች ያሉት ሌላኛውም በር በመሽከርከሪያዎቹ ላይ ተገጥሞ ነበር።+ +35 እሱም ኪሩቦችን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችን ምስል ቀረጸ፤ ቅርጾቹንም በወርቅ ለበጣቸው። +36 የውስጠኛውንም ግቢ+ ወደ ላይ በተነባበረ ሦስት ረድፍ ጥርብ ድንጋይና በአንድ ረድፍ የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃ ሠራው።+ +37 በ4ኛው ዓመት በዚፍ* ወር የይሖዋ ቤት መሠረት ተጣለ፤+ +38 በ11ኛው ዓመት በቡል* ወር (ማለትም በስምንተኛው ወር) የቤቱ እያንዳንዱ ነገር በንድፉ መሠረት ተሠርቶ ተጠናቀቀ።+ በመሆኑም ቤቱን ገንብቶ ለመጨረስ ሰባት ዓመት ፈጀበት። +10 የሳባ ንግሥት ስለ ሰለሞን ዝና እንዲሁም ከይሖዋ ስም ጋር ስላለው ግንኙነት ሰማች፤+ በመሆኑም አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች* ልትፈትነው መጣች።+ +2 እሷም እጅግ ታላቅ አጀብ አስከትላ+ እንዲሁም የበለሳን ዘይት፣+ በጣም ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮች በግመል አስጭና ኢየሩሳሌም ደረሰች። ወደ ሰለሞንም ገብታ በልቧ ያለውን ሁሉ ነገረችው። +3 ሰለሞንም ጥያቄዎቿን ሁሉ መለሰላት። ንጉሡ ሊያብራራላት ያልቻለው* ምንም ነገር አልነበረም። +4 የሳባ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ+ ሁሉና የሠራውን ቤት ስትመለከት፣+ +5 በገበታው ላይ የሚቀርበውን ምግብ፣+ የአገልጋዮቹን አቀማመጥ፣ አስተናጋጆቹ በማዕድ ላይ የሚያስተናግዱበትን መንገድና አለባበሳቸውን፣ መጠጥ አሳላፊዎቹን እንዲሁም በይሖዋ ቤት ዘወትር የሚያቀርባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ስታይ በመገረም ፈዛ ቀረች።* +6 በመሆኑም ንጉሡን እንዲህ አለችው፦ “ስላከናወንካቸው ነገሮችና* ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ነገር እውነት ነው። +7 ይሁንና እኔ ራሴ መጥቼ በገዛ ዓይኔ እስከማይ ድረስ የተነገረኝን ነገር አላመንኩም ነበር። እንደዚያም ሆኖ ግማሹ እንኳ አልተነገረኝም! በጥበብም ሆነ በብልጽግና ከሰማሁት ሁሉ እጅግ የላቅክ ነህ። +8 አብረውህ ያሉ ሰዎች ደስተኞች ናቸው፤ ዘወትር በፊትህ ቆመው ጥበብህን የሚሰሙት አገልጋዮችህም እጅግ ደስተኞች ናቸው!+ +9 አንተን በእስራኤል ዙፋን ላይ በማስቀመጥ በአንተ ደስ የተሰኘው አምላክህ ይሖዋ ይወደስ።+ ይሖዋ ለእስራኤል ካለው ዘላለማዊ ፍቅር የተነሳ ፍትሕንና ጽድቅን እንድታሰፍን ንጉሥ አድርጎ ሾሞሃል።” +10 ከዚያም ለንጉሡ 120 ታላንት* ወርቅ እንዲሁም እጅግ ብዙ የበለሳን ዘይትና+ የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው።+ የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰለሞን የሰጠችውን የሚያህል መጠን ያለው የበለሳን ዘይት ከዚያ በኋላ መጥቶ አያውቅም። +11 ከኦፊር ወርቅ ጭነው የመጡት የኪራም መርከቦች ከኦፊር+ እጅግ ብዙ የሰንደል ዛፍ ሳንቃዎችንና+ የከበሩ ድንጋዮችንም+ አምጥተው ነበር። +12 ንጉሡም ከሰንደል ዛፍ ሳንቃዎቹ ለይሖዋ ቤትና ለንጉሡ ቤት* ድጋፎችን እንዲሁም ለዘማሪዎቹ የሚሆኑ በገናዎችንና ሌሎች ባለ አውታር መሣሪያዎችን ሠራ።+ ይህን ያህል ብዛት ያለው የሰንደል ዛፍ ሳንቃ እስከ ዛሬ ድረስ መጥቶም ሆነ ታይቶ አያውቅም። +13 ንጉሥ ሰለሞንም ለሳባ ንግሥት በልግስና ተነሳስቶ* ከሰጣት ሌላ የፈለገችውንና የጠየቀችውን ነገር ሁሉ ሰጣት። ከዚያም ተነስታ አገልጋዮቿን በማስከተል ወደ አገሯ ተመለሰች።+ +14 ሰለሞን በየዓመቱ 666 ታላንት ወርቅ ይመጣለት ነበር፤+ +15 ይህም ከነጋዴዎች፣ ከሸቃጮች ከሚገኘው ትርፍ፣ ከዓረብ ነገሥታት ሁሉና ከአገረ ገዢዎች የሚሰበሰበውን ሳይጨምር ነው። +16 ንጉሥ ሰለሞን ከቅይጥ ወርቅ 200 ትላልቅ ጋሻዎችን ሠራ፤+ (እያንዳንዱ ጋሻ በ600 ሰቅል* ወርቅ ተለብጦ ነበር)፤+ +17 እንዲሁም ከቅይጥ ወርቅ 300 ትናንሽ ጋሻዎችን* ሠራ፤ (እያንዳንዱ ትንሽ ጋሻ በሦስት ምናን* ወርቅ ተለብጦ ነበር)። ከዚያም ንጉሡ የሊባኖስ ደን+ በተባለው ቤት አስቀመጣቸው። +18 በተጨማሪም ንጉሡ ከዝሆን ጥርስ ትልቅ ዙፋን ሠርቶ+ በተጣራ ወርቅ ለበጠው።+ +19 ወደ ዙፋኑ የሚያስወጡ ስድስት ደረጃዎች ነበሩ፤ ዙፋኑም ከኋላው በኩል ክብ ከለላ ነበረው፤ መቀመጫውም በጎንና በጎኑ የእጅ መደገፊያዎች ያሉት ሲሆን ከእጅ መደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች+ ቆመው ነበር። +20 በስድስቱ ደረጃዎች ዳርና ዳር አንድ አንድ አንበሳ፣ በአጠቃላይ 12 አንበሶች ቆመው ነበር። እንዲህ ያለ ዙፋን የሠራ አንድም ሌላ መንግሥት አልነበረም። +21 የንጉሥ ሰለሞን የመጠጫ ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ የሊባኖስ ደን በተባለው ቤት+ የነበሩት ዕቃዎችም በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ። ከብር የተሠራ ምንም ነገር አልነበረም፤ በሰለሞን ዘመን ብር እንደ ተራ ነገር ይቆጠር ነበር።+ +22 ንጉሡ ከኪራም መርከቦች ጋር አብረው በባሕር ላይ የሚጓዙ የተርሴስ+ መርከቦች ነበሩት። እነዚህ የተርሴስ መርከቦች በሦስት ዓመት አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብር፣ የዝሆን ጥርስ፣+ ጦጣና ጣዎስ* ጭነው ይመጡ ነበር። +23 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን በብልጽግናና+ በጥበብ+ ምድር ላይ ካሉ ሌሎች ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ ነበር። +24 የምድር ሕዝቦችም ሁሉ አምላክ በሰለሞን ልብ ውስጥ ያኖረውን ጥበብ+ ይሰሙ ዘንድ ከእሱ ጋር ለመገናኘት ይጓጉ ነበር።* +25 ወደ እሱ የሚመጡትም ሰዎች በየዓመቱ የብር ዕቃዎች፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ ልብሶች፣ የጦር ትጥቆች፣ የበለሳን ዘይት፣ ፈረሶችና በቅሎዎች ስጦታ አድርገው ያመጡ ነበር። +"26 ሰለሞንም ሠረገሎችንና ፈረሶችን* መሰብሰቡን ቀጠለ፤ እሱም 1,400 ሠረገሎችና 12,000 ፈረሶች*+ ነበሩት፤ እነሱንም በሠረገላ ከተሞችና በኢየሩሳሌም በንጉሡ አቅራቢያ አኖራቸው።+ " +27 ንጉሡ በኢየሩሳሌም ያለውን ብር ከብዛቱ የተነሳ በየቦታው እንደሚገኝ ድንጋይ አደረገው፤ አርዘ ሊባኖሱንም ከብዛቱ የተነሳ በሸፌላ እንደሚገኘው የሾላ ዛፍ አደረገው።+ +28 የሰለሞን ፈረሶች ከግብፅ ያስመጣቸው ነበሩ፤ የንጉሡ ነጋዴዎችም የፈረሶቹን መንጋ አንዴ በተተመነው ዋጋ ይገዙ ነበር።*+ +29 ከግብፅ የሚመጣው እያንዳንዱ ሠረገላ 600 የብር ሰቅል ያወጣ ነበር፤ አንድ ፈረስ ደግሞ 150 ሰቅል ያወጣል፤ እነሱ ደግሞ በተራቸው ለሂታውያን+ ነገሥታትና ለሶርያ ነገሥታት ሁሉ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይሸጡ ነበር። +14 በዚህ ጊዜ የኢዮርብዓም ልጅ አቢያህ ታመመ። +2 በመሆኑም ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፦ “እባክሽ፣ ተነሺና የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን እንዳያውቁ ራስሽን ለውጠሽ ወደ ሴሎ ሂጂ። ነቢዩ አኪያህ ያለው እዚያ ነው። እኔ በዚህ ሕዝብ ላይ ንጉሥ እንደምሆን የተናገረው እሱ ነው።+ +3 አሥር ዳቦና የተቀቡ ቂጣዎች እንዲሁም አንድ ገንቦ ማር ይዘሽ ወደ እሱ ሂጂ። እሱም በልጁ ላይ የሚደርሰውን ነገር ይነግርሻል።” +4 የኢዮርብዓምም ሚስት እንዳላት አደረገች። ተነስታ ወደ ሴሎ+ በመሄድ ወደ አኪያህ ቤት መጣች። አኪያህ ከማርጀቱ የተነሳ ማየት ተስኖት የነበረ ቢሆንም ዓይኖቹ ፊት ለፊት ትኩር ብለው ይመለከቱ ነበር። +5 ይሖዋ ግን አኪያህን እንዲህ አለው፦ “የኢዮርብዓም ሚስት ልጇ ስለታመመ ስለ እሱ ልትጠይቅህ እየመጣች ነው። እኔም ምን እንደምትላት እነግርሃለሁ።* እሷም እዚህ ስትደርስ ማንነቷ እንዳይታወቅ ራሷን ትለውጣለች።” +6 አኪያህም በሩ ጋ ስትደርስ የእግሯን ኮቴ ሰምቶ እንዲህ አላት፦ “የኢዮርብዓም ሚስት ግቢ። ማንነትሽ እንዳይታወቅ ራስሽን የለወጥሽው ለምንድን ነው? መጥፎ ዜና እንድነግርሽ ታዝዣለሁ። +7 ሂጂና ኢዮርብዓምን እንዲህ በዪው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ከሕዝብህ መካከል አስነሳሁህ።+ +8 ከዚያም መንግሥቱን ከዳዊት ቤት ላይ ቀድጄ ለአንተ ሰጠሁህ።+ አንተ ግን በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር ብቻ በማድረግ ትእዛዛቴን እንደጠበቀውና በሙሉ ልቡ እንደተከተለኝ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት አልሆንክም።+ +9 ከዚህ ይልቅ ከአንተ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸምክ፤ እኔንም ለማስቆጣት ለራስህ ሌላ አምላክና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን* ሠራህ፤+ ጀርባህንም ሰጠኸኝ።+ +10 በዚህም የተነሳ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ጥፋት አመጣለሁ፤ በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን ጨምሮ የኢዮርብዓም የሆነውን ወንድ* ሁሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ አንድ ሰው ፋንድያን ሙልጭ አድርጎ በመጥረግ እንደሚያስወግድ ሁሉ እኔም የኢዮርብዓምን ቤት ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ!+ +11 ከኢዮርብዓም ወገን የሆነውን በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ሁሉ ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞተውን ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል፤ ይሖዋ ይህን ተናግሯልና።”’ +12 “እንግዲህ አሁን ተነስተሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ። እግርሽ ከተማዋን እንደረገጠ ልጁ ይሞታል። +13 ከኢዮርብዓም ቤተሰብ መካከል በመቃብር ቦታ የሚቀበረው እሱ ብቻ ስለሆነ እስራኤል ሁሉ አልቅሰው ይቀብሩታል፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ከኢዮርብዓም ቤት ሁሉ አንድ መልካም ነገር ያገኘበት እሱን ብቻ ነው። +14 ይሖዋም ከዚያን ቀን ጀምሮ እንዲያውም አሁኑኑ፣ የኢዮርብዓምን ቤት+ የሚያስወግድ በእስራኤል ላይ የሚነግሥ ንጉሥ ለራሱ ያስነሳል። +15 ይሖዋ በውኃ ውስጥ እንደሚወዛወዝ ሸምበቆ እስራኤልን ይመታል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንን ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው ከዚህ መልካም ምድር ላይ ይነቅላቸዋል፤+ ከወንዙም* ማዶ ይበትናቸዋል፤+ ምክንያቱም የማምለኪያ ግንዶችን*+ ለራሳቸው በማቆም ይሖዋን አስቆጥተውታል። +16 እሱም ኢዮርብዓም በሠራው ኃጢአትና እስራኤላውያን እንዲሠሩ ባደረገው ኃጢአት የተነሳ እስራኤልን ይተዋል።”+ +17 በዚህ ጊዜ የኢዮርብዓም ሚስት ተነስታ በመሄድ ወደ ቲርጻ መጣች። ቤቱ ደጃፍ ላይ ስትደርስም ልጁ ሞተ። +18 ይሖዋ በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያህ አማካኝነት በተናገረውም መሠረት ቀበሩት፤ እስራኤልም ሁሉ አለቀሰለት። +19 ኢዮርብዓም ስላደረገው ውጊያና+ ስለ አገዛዙ የሚናገረው የቀረው ታሪኩ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል። +20 ኢዮርብዓም የገዛበት የጊዜ ርዝመት* 22 ዓመት ነበር፤ ከዚያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በእሱም ምትክ ልጁ ናዳብ ነገሠ።+ +21 ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር። ሮብዓም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 41 ዓመት ነበር፤ እሱም ይሖዋ ስሙ እንዲኖርባት+ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል በመረጣት ከተማ+ በኢየሩሳሌም ሆኖ ለ17 ዓመት ገዛ። እናቱም ናዕማ የተባለች አሞናዊት+ ነበረች። +22 ይሁዳም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤+ እነሱም በፈጸሙት ኃጢአት የተነሳ ከአባቶቻቸው ይበልጥ አስቆጡት።+ +23 እነሱም ቢሆኑ በእያንዳንዱ ኮረብታ+ ላይና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ+ ሥር ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን፣ የማምለኪያ ዓምዶችንና የማምለኪያ ግንዶችን*+ ለራሳቸው ሠሩ። +24 ሌላው ቀርቶ በምድሪቱ ላይ የቤተ መቅደስ ቀላጮች* ነበሩ።+ ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት አባሮ ያስወጣቸው ብሔራት ይፈጽሟቸው የነበሩትን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ አደረጉ። +25 ንጉሥ ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፁ ንጉሥ ሺሻቅ+ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት መጣ።+ +26 እሱም በይሖዋ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶችና በንጉሡ ቤት* የነበሩትን ውድ ንብረቶች ወሰደ።+ ሰለሞን የሠራቸውን የወርቅ ጋሻዎች ጨምሮ ሁሉንም ነገር ወሰደ።+ +27 በመሆኑ�� ንጉሥ ሮብዓም በእነሱ ምትክ የመዳብ ጋሻዎችን ሠርቶ የንጉሡን ቤት በር ለሚጠብቁት የዘብ* አለቆች ሰጣቸው። +28 ዘቦቹም ንጉሡ ወደ ይሖዋ ቤት በመጣ ቁጥር ጋሻዎቹን ያነግቡ ነበር፤ ከዚያም ወደ ዘቦቹ ክፍል ይመልሷቸው ነበር። +29 የቀረው የሮብዓም ታሪክና ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?+ +30 በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር።+ +31 በመጨረሻም ሮብዓም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም+ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። እናቱ ናዕማ የተባለች አሞናዊት+ ነበረች። በእሱም ምትክ ልጁ አብያም*+ ነገሠ። +9 ሰለሞን የይሖዋን ቤትና የንጉሡን ቤት*+ እንዲሁም ለመሥራት የፈለገውን ነገር ሁሉ ገንብቶ እንደጨረሰ+ +2 ይሖዋ በገባኦን እንደተገለጠለት አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠለት።+ +3 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “በፊቴ የጸለይከውን ጸሎትና ሞገስ ለማግኘት ያቀረብከውን ልመና ሰምቻለሁ። የገነባኸውን ይህን ቤት ስሜ ለዘለቄታው እንዲጠራበት በማድረግ+ ቀድሼዋለሁ፤ ዓይኔም ሆነ ልቤ ሁልጊዜ በዚያ ይሆናል።+ +4 አንተም አባትህ ዳዊት እንዳደረገው ያዘዝኩህን ሁሉ በመፈጸም+ በንጹሕ ልብና+ በቅንነት+ በፊቴ ብትሄድ+ እንዲሁም ሥርዓቶቼንና ፍርዴን ብትጠብቅ+ +5 ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘር ሐረግህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይታጣም’ በማለት በገባሁለት ቃል መሠረት የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።+ +6 ሆኖም እናንተም ሆናችሁ ልጆቻችሁ እኔን ከመከተል ዞር ብትሉ እንዲሁም በፊታችሁ ያስቀመጥኳቸውን ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ባትጠብቁ፣ ሄዳችሁም ሌሎች አማልክትን ብታገለግሉና ለእነሱ ብትሰግዱ+ +7 እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ላይ አጠፋቸዋለሁ፤+ ለስሜ የቀደስኩትንም ቤት ከፊቴ አስወግደዋለሁ፤+ እስራኤላውያንም በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መቀለጃና* መሳለቂያ ይሆናሉ።+ +8 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል።+ በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’+ በማለት ያፏጫሉ። +9 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው አባቶቻቸውን ከግብፅ ምድር ያወጣውን አምላካቸውን ይሖዋን ትተው ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ለእነሱ ስለሰገዱ እንዲሁም እነሱን ስላገለገሉ ነው። ይሖዋ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣባቸው ለዚህ ነው።’”+ +10 ሰለሞን ሁለቱን ቤቶች ይኸውም የይሖዋን ቤትና የንጉሡን ቤት* ገንብቶ በጨረሰበት በ20ኛው ዓመት ማብቂያ ላይ+ +11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም+ ለሰለሞን የሚፈልገውን ያህል የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎች፣ የጥድ ዛፍ ሳንቃዎችና ወርቅ ሰጠው፤+ ንጉሥ ሰለሞን ደግሞ ለኪራም በገሊላ ምድር የሚገኙ 20 ከተሞችን ሰጠው። +12 ስለሆነም ኪራም ሰለሞን የሰጠውን ከተሞች ለማየት ከጢሮስ ወጥቶ ሄደ፤ ሆኖም በከተሞቹ አልተደሰተም። +13 እሱም “ወንድሜ ሆይ፣ የሰጠኸኝ ምን ዓይነት ከተሞችን ነው?” አለው። ስለዚህ እነዚህ ከተሞች እስከ ዛሬ ድረስ የካቡል ምድር* ተብለው ይጠራሉ። +14 ይህ በእንዲህ እንዳለ ኪራም ለንጉሡ 120 ታላንት* ወርቅ ላከለት።+ +15 ንጉሥ ሰለሞን የይሖዋን ቤት፣+ የራሱን ቤት፣* ጉብታውን፣*+ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ ሃጾርን፣+ መጊዶንና+ ጌዜርን+ እንዲገነቡ ስለመለመላቸው የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሠራተኞች+ የሚገልጸው ዘገባ ይህ ነው። +16 (የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ ጌዜርን ያዘ፤ በእሳትም አቃጠላት፤ በተጨማሪም በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩትን ከነአናውያን+ ገደለ። ከተማዋንም የሰለሞን ሚስት ለሆነችው ለልጁ ጎጆ መውጫ* አድርጎ ሰጣት።)+ +17 ሰለሞንም ጌዜርንና ታችኛውን ቤትሆሮንን+ ሠራ፤ +18 በተጨማሪም ባዓላትን፣+ በምድሩ በሚገኘው ምድረ በዳ ውስጥ ያለችውን ትዕማርን +19 እንዲሁም የሰለሞንን የእህልና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች በሙሉ፣ የሠረገላ ከተሞቹን፣+ የፈረሰኞቹን ከተሞች እንዲሁም ሰለሞን በኢየሩሳሌም፣ በሊባኖስና በእሱ ግዛት ውስጥ ባለው ምድር ሁሉ መገንባት የፈለጋቸውን ነገሮች በሙሉ ሠራ። +20 ከእስራኤላውያን ወገን ያልሆኑትን+ ከአሞራውያን፣ ከሂታውያን፣ ከፈሪዛውያን፣ ከሂዋውያንና ከኢያቡሳውያን+ የተረፉትን ሕዝቦች በሙሉ +21 ይኸውም እስራኤላውያን ፈጽመው ሊያጠፏቸው ያልቻሏቸውን በምድሪቱ ላይ የቀሩትን ዘሮቻቸውን ሰለሞን እንደ ባሪያ ሆነው የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ መልምሏቸው ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ ይሠራሉ።+ +22 ሆኖም ሰለሞን ከእስራኤላውያን መካከል አንዳቸውንም ባሪያ አላደረገም፤+ ምክንያቱም እነሱ ተዋጊዎቹ፣ አገልጋዮቹ፣ መኳንንቱ፣ የጦር መኮንኖቹ እንዲሁም የሠረገለኞቹና የፈረሰኞቹ አለቆች ነበሩ። +23 ሰለሞን የሚያሠራውን ሥራ የሚከታተሉት ይኸውም ሥራውን የሚሠሩትን ሰዎች በቅርብ የሚቆጣጠሩት የበታች ተቆጣጣሪዎቹ አለቆች 550 ነበሩ።+ +24 የፈርዖን ሴት ልጅ+ ግን ከዳዊት ከተማ+ ወጥታ ሰለሞን ወዳሠራላት ወደ ራሷ ቤት መጣች፤ ከዚያም ጉብታውን*+ ሠራ። +25 ሰለሞን በዓመት ሦስት ጊዜ+ ለይሖዋ በሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን ያቀርብ ነበር፤+ በተጨማሪም በይሖዋ ፊት በነበረው መሠዊያ ላይ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ ቤቱንም አጠናቀቀ።+ +26 እንዲሁም ንጉሥ ሰለሞን በኤዶም ምድር+ በቀይ ባሕር ዳርቻ በኤሎት አጠገብ በምትገኘው በዔጽዮንጋብር+ መርከቦችን ሠራ። +27 ኪራምም ከሰለሞን አገልጋዮች ጋር አብረው እንዲሠሩ አገልጋዮቹን ይኸውም ልምድ ያላቸውን ባሕረኞች ከእነዚህ መርከቦች ጋር ላከ።+ +28 እነሱም ወደ ኦፊር+ በመሄድ 420 ታላንት ወርቅ አምጥተው ለንጉሥ ሰለሞን ሰጡት። +13 ኢዮርብዓም በመሠዊያው+ አጠገብ የሚጨስ መሥዋዕት ለማቅረብ ቆሞ ሳለ አንድ የአምላክ ሰው+ በይሖዋ ቃል በታዘዘው መሠረት ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ። +2 ከዚያም በይሖዋ ቃል በታዘዘው መሠረት መሠዊያውን በመቃወም እንዲህ ሲል ተጣራ፦ “መሠዊያ ሆይ! መሠዊያ ሆይ! ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ኢዮስያስ+ የተባለ ልጅ ለዳዊት ቤት ይወለዳል! እሱም በአንተ ላይ የሚጨስ መሥዋዕት እያቀረቡ ያሉትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ካህናት በላይህ ይሠዋቸዋል፤ በአ +3 እሱም በዚያ ቀን እንዲህ በማለት ምልክት* ሰጠ፦ “ይሖዋ የሰጠው ምልክት* ይህ ነው፦ እነሆ፣ መሠዊያው ይሰነጠቃል፤ በላዩም ላይ ያለው አመድ* ይፈስሳል።” +4 ንጉሡ ኢዮርብዓምም የእውነተኛው አምላክ ሰው በቤቴል የሚገኘውን መሠዊያ በመቃወም የተናገረውን ቃል ሲሰማ እጁን ከመሠዊያው ላይ አንስቶ በመዘርጋት “ያዙት!” አላቸው።+ ወዲያውኑም ወደ እሱ የዘረጋው እጁ ደረቀ፤* እጁንም ሊያጥፈው አልቻለም።+ +5 ከዚያም የእውነተኛው አምላክ ሰው በይሖዋ ቃል ታዞ በሰጠው ምልክት* መሠረት መሠዊያው ተሰነጠቀ፤ አመዱም ከመሠዊያው ላይ ፈሰሰ። +6 በዚህ ጊዜ ንጉሡ የእውነተኛውን አምላክ ሰው “እባክህ፣ የአምላክህን የይሖዋን ሞገስ እንዳገኝ ለምንልኝ፤ እጄም ወደ ቦታው እንዲመለስ ጸልይልኝ” አለው።+ በዚህ ጊዜ የእውነተኛው አምላክ ሰው የይሖዋን ሞገስ እንዲያገኝ ለመነለት፤ የንጉሡም እጅ ተመልሶ እንደቀድሞው ሆነ። +7 ከዚያም ንጉሡ የእውነተኛውን አምላክ ሰው “አብረኸኝ ወደ ቤት ሂድና ምግብ ብላ፤ ስጦታም ልስጥህ” አለው። +8 ሆኖም የእውነተኛው አምላክ ሰው ንጉሡን እንዲ�� አለው፦ “የቤትህን ግማሽ ብትሰጠኝ እንኳ ከአንተ ጋር አልሄድም፤ በዚህም ቦታ ምግብ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም። +9 ምክንያቱም የይሖዋ ቃል ‘ምግብ እንዳትበላ፤ ውኃም እንዳትጠጣ፤ በሄድክበትም መንገድ እንዳትመለስ’ ሲል አዞኛል።” +10 በመሆኑም በሌላ መንገድ ሄደ፤ ወደ ቤቴል በመጣበትም መንገድ አልተመለሰም። +11 በዚህ ጊዜ በቤቴል የሚኖር አንድ አረጋዊ ነቢይ ነበር፤ ልጆቹም ወደ ቤት መጥተው የእውነተኛው አምላክ ሰው በዚያ ቀን በቤቴል ያደረገውን ነገር ሁሉና ለንጉሡ የተናገረውን ቃል ነገሩት። ይህን ለአባታቸው ከተረኩለት በኋላ +12 አባታቸው “ለመሆኑ የሄደው በየት በኩል ነው?” ሲል ጠየቃቸው። ልጆቹም ከይሁዳ የመጣው የእውነተኛው አምላክ ሰው የሄደበትን መንገድ አሳዩት። +13 እሱም ልጆቹን “በሉ አህያውን ጫኑልኝ” አላቸው። እነሱም አህያውን ጫኑለት፤ እሱም አህያው ላይ ተቀመጠ። +14 ከዚያም የእውነተኛውን አምላክ ሰው ተከተለው፤ በአንድ ትልቅ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው። እሱም “ከይሁዳ የመጣኸው የእውነተኛው አምላክ ሰው አንተ ነህ?” አለው፤+ እሱም “አዎ፣ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት። +15 ከዚያም “አብረን ወደ ቤት እንሂድና ምግብ ብላ” አለው። +16 እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “ከአንተ ጋር ተመልሼ ልሄድ ወይም ያቀረብክልኝን ግብዣ ልቀበል አልችልም፤ ደግሞም በዚህ ቦታ ከአንተ ጋር ምግብም ሆነ ውኃ አልቀምስም። +17 ምክንያቱም የይሖዋ ቃል ‘እዚያ ምግብ እንዳትበላ፤ ውኃም እንዳትጠጣ። በመጣህበትም መንገድ እንዳትመለስ’ በማለት አዞኛል።” +18 በዚህ ጊዜ አረጋዊው ሰው “እኔም እኮ እንደ አንተው ነቢይ ነኝ፤ አንድ መልአክ ‘ምግብ እንዲበላና ውኃ እንዲጠጣ መልሰህ ወደ ቤትህ አምጣው’ በማለት የይሖዋን ቃል ነግሮኛል” አለው። (እሱም አታለለው።) +19 በመሆኑም እሱ ቤት ምግብ ለመብላትና ውኃ ለመጠጣት አብሮት ተመለሰ። +20 እነሱም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ የይሖዋ ቃል የእውነተኛውን አምላክ ሰው መልሶ ወዳመጣው ነቢይ መጣ፤ +21 ከዚያም ከይሁዳ የመጣውን የእውነተኛውን አምላክ ሰው ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በይሖዋ መመሪያ ላይ ስላመፅክና አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን ትእዛዝ ስላልጠበቅክ፣ +22 ከዚህ ይልቅ ምግብ ለመብላትና ውኃ ለመጠጣት ስትል “ምግብ እንዳትበላ፤ ውኃም እንዳትጠጣ” ወደተባልክበት ቦታ ስለተመለስክ ሬሳህ በአባቶችህ የመቃብር ቦታ አይቀበርም።’”+ +23 የእውነተኛው አምላክ ሰውም ከበላና ከጠጣ በኋላ አረጋዊው ነቢይ ከመንገድ መልሶ ላመጣው ለዚያ ነቢይ አህያውን ጫነለት። +24 ከዚያም መንገዱን ቀጠለ፤ ሆኖም አንድ አንበሳ መንገድ ላይ አግኝቶ ገደለው።+ ሬሳውም መንገዱ ላይ ተጋድሞ፣ አህያው ደግሞ አጠገቡ ቆሞ ነበር፤ አንበሳውም ሬሳው አጠገብ ቆሞ ነበር። +25 በዚያ የሚያልፉ ሰዎችም ሬሳው መንገድ ላይ ተጋድሞ፣ አንበሳው ደግሞ አጠገቡ ቆሞ አዩ። ከዚያም መጥተው ይህን ነገር አረጋዊው ነቢይ በሚኖርበት ከተማ አወሩ። +26 ከመንገድ መልሶ ያመጣውም ነቢይ ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ “ይህ ሰው በይሖዋ መመሪያ ላይ ያመፀው የእውነተኛው አምላክ ሰው ነው፤+ ይሖዋ በነገረው ቃል መሠረት እንዲቦጫጭቀውና እንዲገድለው ይሖዋ ለአንበሳ አሳልፎ ሰጥቶታል” አለ።+ +27 እሱም ልጆቹን “በሉ አህያውን ጫኑልኝ” አላቸው። እነሱም ጫኑለት። +28 ከዚያም ሄደ፤ ሬሳው መንገድ ላይ ተጋድሞ፣ አህያውና አንበሳውም አጠገቡ ቆመው አገኛቸው። አንበሳው ሬሳውን አልበላውም፤ አህያውንም ቢሆን አልቦጫጨቀውም። +29 ነቢዩም የእውነተኛውን አምላክ ሰው ሬሳ አንስቶ አህያው ላይ ከጫነ በኋላ አልቅሶ ሊቀብረው ስላሰበ ወደሚኖርበት ከተማ ይዞት ��መለሰ። +30 ከዚያም ሬሳውን በራሱ የመቃብር ቦታ ቀበረው፤ እነሱም “ወይኔ ወንድሜን!” እያሉ አለቀሱለት። +31 እሱንም ከቀበረው በኋላ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ “እኔም ስሞት የእውነተኛው አምላክ ሰው በተቀበረበት የመቃብር ቦታ ቅበሩኝ። አጥንቶቼንም ከአጥንቶቹ አጠገብ ቅበሯቸው።+ +32 በይሖዋ ቃል በታዘዘው መሠረት በቤቴል በሚገኘው መሠዊያና በሰማርያ ከተሞች በሚገኙት ኮረብቶች ላይ ባሉት የአምልኮ ቤቶች+ ሁሉ ላይ የተናገረው ቃል ያለጥርጥር ይፈጸማል።”+ +33 ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላ ቢሆን ኢዮርብዓም ከመጥፎ መንገዱ አልተመለሰም፤ ከዚህ ይልቅ ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ከሕዝቡ መካከል ካህናት መሾሙን ቀጠለ።+ እንዲሁም ካህን ለመሆን የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው “ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህን ይሁን” በማለት ይሾመው* ነበር።+ +34 ይህም ኃጢአት የኢዮርብዓም+ ቤት ከምድር ገጽ እንዲጠፋና እንዲደመሰስ ምክንያት ሆነ።+ +5 የጢሮስ+ ንጉሥ ኪራም ሰለሞን በአባቱ ምትክ ንጉሥ ሆኖ እንደተቀባ ሲሰማ አገልጋዮቹን ወደ እሱ ላከ፤ ምክንያቱም ኪራም ምንጊዜም የዳዊት ወዳጅ ነበር።*+ +2 ሰለሞንም በምላሹ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ኪራም+ ላከ፦ +3 “አባቴ ዳዊት ከተለያየ አቅጣጫ ጦርነት ይከፈትበት ስለነበር ይሖዋ ጠላቶቹን ከእግሩ በታች እስኪያደርግለት ድረስ ለአምላኩ ለይሖዋ ስም የሚሆን ቤት መሥራት እንዳልቻለ በሚገባ ታውቃለህ።+ +4 አሁን ግን አምላኬ ይሖዋ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ ሁሉ እረፍት ሰጥቶኛል።+ የሚቃወመኝም ሆነ እየተፈጸመ ያለ ምንም መጥፎ ነገር የለም።+ +5 በመሆኑም ይሖዋ ለአባቴ ለዳዊት ‘ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ በአንተ ምትክ በዙፋንህ ላይ የማስቀምጠው ልጅህ ነው’ ሲል በገባው ቃል መሠረት ለአምላኬ ለይሖዋ ስም ቤት ለመሥራት አስቤአለሁ።+ +6 ስለሆነም አገልጋዮችህ አርዘ ሊባኖስ+ እንዲቆርጡልኝ ትእዛዝ ስጥ። አገልጋዮቼም ከአገልጋዮችህ ጋር ይሠራሉ፤ የአገልጋዮችህንም ደሞዝ አንተ በወሰንከው መሠረት እከፍላለሁ፤ መቼም ከመካከላችን እንደ ሲዶናውያን ዛፍ መቁረጥ የሚችል አንድም ሰው እንደሌለ ታውቃለህ።”+ +7 ኪራም የሰለሞንን መልእክት ሲሰማ እጅግ በመደሰቱ “ይህን ታላቅ* ሕዝብ እንዲመራ ለዳዊት ጥበበኛ ልጅ ስለሰጠው ዛሬ ይሖዋ ይወደስ!” አለ።+ +8 ስለዚህ ኪራም እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ሰለሞን ላከ፦ “የላክብኝ መልእክት ደርሶኛል። የአርዘ ሊባኖስና የጥድ ሳንቃዎች በማቅረብ ረገድ የፈለግከውን ሁሉ አደርጋለሁ።+ +9 አገልጋዮቼ ሳንቃዎቹን ከሊባኖስ ወደ ባሕሩ ያወርዷቸዋል፤ እኔም በባሕር ላይ ተንሳፈው አንተ ወደምትለኝ ቦታ እንዲደርሱ አንድ ላይ አስሬ እልካቸዋለሁ። እዚያም ሲደርሱ እንዲፈቱ አደርጋለሁ፤ ከዚያ ልትወስዳቸው ትችላለህ። አንተ ደግሞ በምላሹ የጠየቅኩህን ቀለብ ለቤተሰቤ ታቀርባለህ።”+ +10 በመሆኑም ኪራም፣ ሰለሞን የፈለገውን ያህል የአርዘ ሊባኖስና የጥድ ሳንቃ አቀረበለት። +"11 ሰለሞን ደግሞ ለኪራም ቤተሰብ ቀለብ እንዲሆን 20,000 የቆሮስ መስፈሪያ* ስንዴና 20 የቆሮስ መስፈሪያ ምርጥ የወይራ ዘይት* ለኪራም ሰጠው። ሰለሞን ለኪራም በየዓመቱ ይህን ይሰጠው ነበር።+" +12 ይሖዋም ቃል በገባለት መሠረት ለሰለሞን ጥበብ ሰጠው።+ በኪራምና በሰለሞን መካከል ሰላም ነበር፤ እንዲሁም የስምምነት ውል ተዋዋሉ።* +"13 ሰለሞንም ከመላው እስራኤል የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሰዎችን መለመለ፤ የተመለመሉትም ሰዎች ብዛታቸው 30,000 ነበር።+" +14 እነሱንም በየወሩ አሥር አሥር ሺህ እያደረገ በየተራ ወደ ሊባኖስ ይልካቸው ነበር። እነሱም ለአንድ ወር በሊባኖስ፣ ለሁለት ወር ደግሞ ቤታቸው ይቀመጡ ነበር፤ የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ ��ተመለመሉት ሰዎች አለቃ አዶኒራም+ ነበር። +"15 ሰለሞን በተራሮቹ ላይ 70,000 ተራ የጉልበት ሠራተኞችና* 80,000 ድንጋይ ጠራቢዎች+ ነበሩት፤+" +"16 በተጨማሪም ከሰለሞን መኳንንት መካከል አስተዳዳሪዎች+ ሆነው የሚያገለግሉት 3,300 ሰዎች ሠራተኞቹን ይቆጣጠሩ ነበር።" +17 የቤቱን መሠረት በተጠረቡ ድንጋዮች ለመጣል+ በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ውድ የሆኑ ትላልቅ ድንጋዮችን+ ፈልፍለው አወጡ።+ +18 ስለዚህ የሰለሞን ግንበኞች፣ የኪራም ግንበኞችና ጌባላውያን+ ድንጋዮቹን ጠረቡ፤ እንዲሁም ቤቱን ለመገንባት የሚያስፈልጉትን ሳንቃዎችና ድንጋዮች አዘጋጁ። +21 እነዚህ ነገሮች ከተከናወኑ በኋላ ከኢይዝራኤላዊው ከናቡቴ የወይን እርሻ ጋር በተያያዘ አንድ ሁኔታ ተከሰተ፤ የወይን እርሻው የሚገኘው በኢይዝራኤል+ ውስጥ ከሰማርያው ንጉሥ ከአክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ ነበር። +2 አክዓብ ናቡቴን እንዲህ አለው፦ “የወይን እርሻህ ከቤቴ አጠገብ ስለሚገኝ የአትክልት ቦታ እንዳደርገው ስጠኝ። እኔም በምትኩ ከዚህ የተሻለ የወይን እርሻ እሰጥሃለሁ። ከፈለግክ ደግሞ የቦታውን ዋጋ እሰጥሃለሁ።” +3 ናቡቴ ግን አክዓብን “የአባቶቼን ርስት ለአንተ መስጠት በይሖዋ ፊት ተገቢ ስላልሆነ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው” አለው።+ +4 በመሆኑም አክዓብ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ “የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም” ስላለው ፊቱ ጠቁሮና አዝኖ ወደ ቤቱ ገባ። ከዚያም ፊቱን ወደ ግድግዳ አዙሮ ተኛ፤ ምግብ ለመብላትም ፈቃደኛ አልሆነም። +5 ሚስቱ ኤልዛቤልም+ ወደ እሱ ገብታ “ምግብ አልበላ እስኪልህ ድረስ እንዲህ ያዘንከው* ለምንድን ነው?” አለችው። +6 እሱም እንዲህ አላት፦ “ኢይዝራኤላዊውን ናቡቴን ‘የወይን እርሻህን በገንዘብ ሽጥልኝ። ከፈለግክ ደግሞ በምትኩ ሌላ የወይን እርሻ ልስጥህ’ ብዬው ነበር። እሱ ግን ‘የወይን እርሻዬን አልሰጥህም’ አለኝ።” +7 ሚስቱ ኤልዛቤልም “በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆነህ የምትገዛው አንተ አይደለህም? በል ተነስና እህል ቅመስ፤ ልብህም ደስ ይበለው። የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን እርሻ እኔ እሰጥሃለሁ” አለችው።+ +8 ስለሆነም በአክዓብ ስም ደብዳቤዎች ጽፋ በእሱ ማኅተም አተመቻቸው፤+ ደብዳቤዎቹንም ናቡቴ በሚኖርበት ከተማ ወደሚገኙት ሽማግሌዎችና+ ታላላቅ ሰዎች ላከቻቸው። +9 በደብዳቤዎቹም ላይ እንዲህ ስትል ጻፈች፦ “ጾም አውጁ፤ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት በክብር ቦታ ላይ አስቀምጡት። +10 ሁለት የማይረቡ ሰዎችንም አምጥታችሁ ከፊት ለፊቱ አስቀምጡና ‘አምላክንና ንጉሡን ተራግመሃል!’+ በማለት እንዲመሠክሩበት አድርጉ።+ ከዚያም አውጥታችሁ በድንጋይ በመውገር ግደሉት።”+ +11 በመሆኑም የከተማዋ ሰዎች ማለትም እሱ በሚኖርበት ከተማ ያሉት ሽማግሌዎችና ታላላቅ ሰዎች ኤልዛቤል በላከችላቸው ደብዳቤዎች ላይ በተጻፈው መሠረት አደረጉ። +12 እነሱም ጾም አወጁ፤ ናቡቴም በሕዝቡ ፊት በክብር ቦታ ላይ እንዲቀመጥ አደረጉ። +13 ከዚያም ሁለት የማይረቡ ሰዎች መጥተው ፊት ለፊቱ ተቀመጡ፤ እነሱም በሕዝቡ ፊት ‘ናቡቴ አምላክንና ንጉሡን ተራግሟል!’ እያሉ በናቡቴ ላይ ይመሠክሩበት ጀመር።+ ከዚያም ወደ ከተማዋ ዳርቻ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።+ +14 እነሱም “ናቡቴ በድንጋይ ተወግሮ ሞቷል” በማለት ወደ ኤልዛቤል መልእክት ላኩባት።+ +15 ኤልዛቤልም ናቡቴ በድንጋይ ተወግሮ መሞቱን እንደሰማች አክዓብን “ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ በገንዘብ ሊሸጥልህ ያልፈለገውን የወይን እርሻውን ተነስና ውረስ፤+ ምክንያቱም ናቡቴ በሕይወት የለም፤ ሞቷል” አለችው። +16 አክዓብም ናቡቴ መሞቱን እንደሰማ ተነስቶ የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን እርሻ ለመውረስ ወደዚያ ወረ��። +17 ሆኖም የይሖዋ ቃል ወደ ቲሽባዊው ወደ ኤልያስ+ እንዲህ ሲል መጣ፦ +18 “በሰማርያ+ የሚገኘውን የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ለማግኘት ተነስተህ ወደዚያ ውረድ። እሱም የናቡቴን የወይን እርሻ ለመውረስ ሄዶ እዚያ ይገኛል። +19 እንዲህም በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሰው ገድለህ+ ንብረቱን ወሰድክ+ አይደል?”’ ከዚያም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም ደም ይልሱታል።”’”+ +20 አክዓብም ኤልያስን “ጠላቴ ሆይ፣ አገኘኸኝ?” አለው፤+ እሱም እንዲህ አለው፦ “አዎ፣ አግኝቼሃለሁ። ‘እንግዲህ አንተ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ቆርጠህ ስለተነሳህ*+ +21 ጥፋት አመጣብሃለሁ፤ እየተከታተልኩም ሙልጭ አድርጌ እጠርግሃለሁ፤ እንዲሁም በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን+ ጨምሮ የአክዓብ የሆነውን ወንድ* ሁሉ አጠፋለሁ።+ +22 ቁጣዬን ስላነሳሳህና እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲፈጽሙ ስላደረግክ ቤትህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም+ ቤትና እንደ አኪያህ ልጅ እንደ ባኦስ+ ቤት አደርገዋለሁ።’ +23 ኤልዛቤልን በተመለከተም ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ ‘ውሾች በኢይዝራኤል በሚገኘው ቁራሽ መሬት ላይ ኤልዛቤልን ይበሏታል።+ +24 ከአክዓብ ወገን የሆነውን፣ በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞተውን ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል።+ +25 በእርግጥም በሚስቱ በኤልዛቤል ተነድቶ+ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ* እንደ አክዓብ ያለ አንድም ሰው የለም።+ +26 ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ያሳደዳቸው አሞራውያን እንዳደረጉት ሁሉ እሱም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶችን* በመከተል እጅግ አስነዋሪ ነገር አደረገ።’”+ +27 አክዓብም ይህን እንደሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለበሰ፤ ጾመ፤ እንዲሁም ማቅ ላይ ይተኛና በሐዘን ተኮራምቶ ይሄድ ነበር። +28 ከዚያም የይሖዋ ቃል ወደ ቲሽባዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ +29 “አክዓብ ስለ እሱ በተናገርኩት ነገር የተነሳ ራሱን እንዴት እንዳዋረደ ተመለከትክ?+ ራሱን በፊቴ ስላዋረደ ላመጣበት የነበረውን ጥፋት በእሱ ዘመን አላመጣም። ከዚህ ይልቅ በእሱ ቤት ላይ ጥፋት የማመጣው በልጁ ዘመን ነው።”+ +15 የናባጥ ልጅ ንጉሥ ኢዮርብዓም+ በነገሠ በ18ኛው ዓመት አብያም በይሁዳ ላይ ነገሠ።+ +2 እሱም በኢየሩሳሌም ለሦስት ዓመት ገዛ። የእናቱ ስም ማአካ+ ሲሆን እሷም የአቢሴሎም የልጅ ልጅ ነበረች። +3 እሱም አባቱ ከእሱ በፊት በሠራው ኃጢአት ሁሉ መመላለሱን ቀጠለ፤ ልቡ እንደቀድሞ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ በአምላኩ በይሖዋ ዘንድ ሙሉ* አልነበረም። +4 ሆኖም በዳዊት+ የተነሳ አምላኩ ይሖዋ ከእሱ በኋላ ልጁን በማስነሳትና ኢየሩሳሌም ጸንታ እንድትኖር በማድረግ በኢየሩሳሌም መብራት ሰጠው።+ +5 ምክንያቱም ዳዊት በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርጓል፤ እንዲሁም ከሂታዊው ከኦርዮ ጋር በተያያዘ ከፈጸመው ነገር በስተቀር በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እሱ ከሰጠው ከየትኛውም ትእዛዝ ፈቀቅ አላለም።+ +6 በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበር።+ +7 የቀረው የአብያም ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?+ በአብያምና በኢዮርብዓም መካከልም ጦርነት ነበር።+ +8 በመጨረሻም አብያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም ቀበሩት፤ በእሱም ምትክ+ ልጁ አሳ+ ነገሠ። +9 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በ20ኛው ዓመት አሳ በይሁዳ ላይ መግዛት ጀመረ። +10 እሱም በኢየሩሳሌም ለ41 ዓመት ገዛ። የአያቱም ስም ማአካ+ ሲሆን እሷም የአቢሴሎም የልጅ ልጅ ነበረች። +11 አሳ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ +12 እሱም የቤተ መቅደስ ቀላጮችን* ከምድሪቱ አባረረ፤+ እንዲሁም አባቶቹ የሠሯቸውን አስጸያፊ ጣዖቶች* በሙሉ አስወገደ።+ +13 ሌላው ቀርቶ አያቱ ማአካ+ ለማምለኪያ ግንዱ* አምልኮ ጸያፍ ጣዖት ሠርታ ስለነበር ከእመቤትነቷ* ሻራት። አሳ፣ አያቱ የሠራችውን ጸያፍ ጣዖት ቆርጦ+ በቄድሮን ሸለቆ+ አቃጠለው። +14 ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች ግን አልተወገዱም ነበር።+ ያም ሆኖ አሳ በሕይወት ዘመኑ* ሁሉ ልቡ በይሖዋ ዘንድ ሙሉ* ነበር። +15 እሱና አባቱ የቀደሷቸውን ነገሮች ይኸውም ብሩን፣ ወርቁንና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ወደ ይሖዋ ቤት አስገባ።+ +16 በአሳና የእስራኤል ንጉሥ በሆነው በባኦስ+ መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር። +17 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ ዘመተ፤ እሱም ማንም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ እንዳይገባና እንዳይወጣ* ለማድረግ ራማን+ መገንባት* ጀመረ።+ +18 በዚህ ጊዜ አሳ በይሖዋ ቤት ግምጃ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤት የቀረውን ብርና ወርቅ ሁሉ አውጥቶ ለአገልጋዮቹ ሰጣቸው። ከዚያም ንጉሥ አሳ እነዚህን አገልጋዮቹን በደማስቆ ወደሚገኘው የሶርያ ንጉሥ+ ማለትም የሄዝዮን ልጅ፣ የታብሪሞን ልጅ ወደሆነው ወደ ቤንሃዳድ እንዲህ ሲል ላካቸው፦ +19 “በእኔና በአንተ እንዲሁም በአባቴና በአባትህ መካከል ውል* አለ። እኔ የብርና የወርቅ ስጦታ ልኬልሃለሁ። ስለዚህ ና፣ የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ከእኔ እንዲርቅ ከእሱ ጋር የገባኸውን ውል* አፍርስ።” +20 ቤንሃዳድ የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀብሎ የጦር ሠራዊቱን አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ፤ እነሱም ኢዮንን፣+ ዳንን፣+ አቤልቤትማዓካን እንዲሁም ኪኔሬትን ሁሉና መላውን የንፍታሌም ምድር መቱ። +21 ባኦስም ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ ራማን መገንባቱን* አቁሞ በቲርጻ+ መኖሩን ቀጠለ። +22 ከዚያም ንጉሥ አሳ ማንንም ሳያስቀር የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ እነሱም ባኦስ እየገነባባቸው የነበሩትን የራማን ድንጋዮችና ሳንቃዎች አጋዙ፤ ንጉሥ አሳም በድንጋዮቹና በሳንቃዎቹ በቢንያም የምትገኘውን ጌባንና+ ምጽጳን+ ገነባ።* +23 የቀረው የአሳ ታሪክ ሁሉ፣ ኃያልነቱ ሁሉ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉና የገነባቸው* ከተሞች በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? ሆኖም አሳ ባረጀ ጊዜ በእግር ሕመም ይሠቃይ ነበር።+ +24 በመጨረሻም አሳ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማም ከእነሱ ጋር ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮሳፍጥ+ ነገሠ። +25 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ናዳብ+ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ እሱም በእስራኤል ላይ ለሁለት ዓመት ገዛ። +26 በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ገፋበት፤ የአባቱንም መንገድ ተከተለ፤+ እንዲሁም አባቱ እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረገው ኃጢአት ተመላለሰ።+ +27 ከይሳኮር ቤት የሆነው የአኪያህ ልጅ ባኦስ በእሱ ላይ አሴረ፤ ናዳብና እስራኤል ሁሉ የፍልስጤማውያን ከተማ የሆነችውን ጊበቶንን+ ከበው ሳሉ ባኦስ ጊበቶን ላይ ናዳብን ገደለው። +28 በመሆኑም ባኦስ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ናዳብን ገድሎ በምትኩ ነገሠ። +29 እሱም እንደነገሠ ወዲያውኑ የኢዮርብዓምን ቤት ሁሉ ፈጀ። ከኢዮርብዓም ቤት እስትንፋስ ያለውን አንድም ሰው አላስቀረም፤ ይሖዋ በአገልጋዩ በሴሎናዊው በአኪያህ በኩል በተናገረው መሠረት ሁሉንም ደመሰሳቸው።+ +30 ይህም የሆነው ኢዮርብዓም በፈጸመው ኃጢአትና እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረገው ኃጢአት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ክፉኛ ስላስቆጣው ነው። +31 የቀረው የናዳብ ታሪክና ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +32 በአሳና የእስራኤል ንጉሥ በሆነው በባኦስ መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር።+ +33 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአኪያህ ልጅ ባኦስ በቲርጻ ሆኖ በመላው እስራኤል ላይ ለ24 ዓመት ገዛ።+ +34 ሆኖም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ገፋበት፤+ የኢዮርብዓምን መንገድ ተከተለ፤ እንዲሁም ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረገው ኃጢአት ተመላለሰ።+ +22 በሶርያና በእስራኤል መካከል ለሦስት ዓመት ጦርነት አልነበረም። +2 በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ+ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወረደ።+ +3 የእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮቹን “ራሞትጊልያድ+ የእኛ እንደሆነች ታውቃላችሁ አይደል? ሆኖም እሷን ከሶርያ ንጉሥ እጅ ለማስመለስ እያመነታን ነው” አላቸው። +4 ከዚያም ኢዮሳፍጥን “በራሞትጊልያድ ለመዋጋት ከእኔ ጋር አብረህ ትሄዳለህ?” አለው። በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ ለእስራኤል ንጉሥ “እኔ ማለት እኮ አንተ ማለት ነህ። ሕዝቤ ሕዝብህ ነው። የእኔ ፈረሶችም የአንተ ፈረሶች ናቸው” በማለት መለሰለት።+ +5 ሆኖም ኢዮሳፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ “እባክህ፣ በመጀመሪያ ይሖዋ ምን እንደሚል+ ጠይቅ”+ አለው። +6 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ 400 ገደማ የሚሆኑ ነቢያትን አንድ ላይ ሰብስቦ “ራሞትጊልያድን ለመውጋት ልዝመት ወይስ ይቅርብኝ?” አላቸው። እነሱም “ዝመት፤ ይሖዋ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” አሉት። +7 ከዚያም ኢዮሳፍጥ “በዚህ ቦታ የይሖዋ ነቢይ የለም? ካለ በእሱም አማካኝነት እንጠይቅ” አለ።+ +8 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “በእሱ አማካኝነት ይሖዋን ልንጠይቅ የምንችልበት አንድ ሰው ይቀራል፤+ ሆኖም ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ መልካም ነገር ፈጽሞ ስለማይተነብይ በጣም እጠላዋለሁ።+ እሱም የይምላ ልጅ ሚካያህ ነው” አለው። ኢዮሳፍጥ ግን “ንጉሡ እንዲህ ሊል አይገባም” አለ። +9 ስለሆነም የእስራኤል ንጉሥ አንድ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን ጠርቶ “የይምላን ልጅ ሚካያህን በአስቸኳይ ይዘኸው ና” አለው።+ +10 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ የንግሥና ልብሳቸውን ለብሰው በሰማርያ መግቢያ በር ላይ በሚገኘው አውድማ ላይ በየዙፋናቸው ተቀምጠው ነበር፤ ነቢያቱም ሁሉ በፊታቸው ትንቢት ይናገሩ ነበር።+ +11 ከዚያም የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስ የብረት ቀንዶች ሠርቶ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’”* አለ። +12 ሌሎቹ ነቢያትም ሁሉ “ወደ ራሞትጊልያድ ውጣ፤ ይሳካልሃል፤ ይሖዋም እሷን በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” በማለት ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር። +13 ሚካያህን ለመጥራት የሄደው መልእክተኛም “እነሆ፣ ነቢያቱ ሁሉ በአንድ ድምፅ ለንጉሡ የተናገሩት ነገር ጥሩ ነው። እባክህ፣ የአንተም ቃል እንደ እነሱ ይሁን፤ አንተም ጥሩ ነገር ተናገር” አለው።+ +14 ሚካያህ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ የምናገረው ይሖዋ የሚለኝን ብቻ ነው” አለ። +15 ከዚያም ወደ ንጉሡ ገባ፤ ንጉሡም “ሚካያህ፣ ራሞትጊልያድን ለመውጋት እንዝመት ወይስ ይቅርብን?” ሲል ጠየቀው። እሱም ወዲያውኑ “ውጡ፤ ይቀናችኋል፤ ይሖዋ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” በማለት መለሰለት። +16 በዚህ ጊዜ ንጉሡ “በይሖዋ ስም ከእውነት በስተቀር ሌላ አንዳች ነገር እንዳትነግረኝ የማስምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው። +17 በመሆኑም ሚካያህ እንዲህ በማለት ተ���ገረ፦ “እስራኤላውያን ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበታትነው አያለሁ።+ ይሖዋም ‘እነዚህ ጌታ የላቸውም። እያንዳንዳቸው በሰላም ወደየቤታቸው ይመለሱ’ ብሏል።” +18 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “‘ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ ጥሩ ነገር አይተነብይም’ ብዬህ አልነበረም?” አለው።+ +19 በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ+ የሰማያት ሠራዊትም ሁሉ በቀኙና በግራው አጠገቡ ቆመው+ አየሁ። +20 ከዚያም ይሖዋ ‘በራሞትጊልያድ ላይ ዘምቶ እዚያው እንዲሞት አክዓብን ማን ያሞኘዋል?’ አለ። በዚህ ጊዜ አንዱ አንድ ነገር፣ ሌላው ደግሞ ሌላ ነገር ተናገረ። +21 ከዚያም አንድ መንፈስ*+ ወደ ፊት ወጥቶ ይሖዋ ፊት በመቆም ‘እኔ አሞኘዋለሁ’ አለ። ይሖዋም ‘እንዴት አድርገህ?’ አለው። +22 ‘እኔ እወጣና በነቢያቱ ሁሉ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ እሆናለሁ’ አለ።+ እሱም ‘እንግዲያው ታሞኘዋለህ፤ ደግሞም ይሳካልሃል። ውጣና እንዳልከው አድርግ’ አለው። +23 ይሖዋም በእነዚህ ነቢያትህ ሁሉ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ አኑሯል፤+ ሆኖም ይሖዋ ጥፋት እንደሚመጣብህ ተናግሯል።”+ +24 የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስም ወደ ሚካያህ ቀርቦ በጥፊ መታውና “ለመሆኑ የይሖዋ መንፈስ እኔን በየት በኩል አልፎ ነው አንተን ያናገረህ?” አለው።+ +25 ሚካያህም “በየት በኩል እንዳለፈማ፣ ለመደበቅ ወደ ውስጠኛው ክፍል በምትገባበት ቀን ታውቀዋለህ” አለው። +26 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ እንዲህ አለ፦ “ሚካያህን ወስዳችሁ ለከተማው አለቃ ለአምዖን እና የንጉሡ ልጅ ለሆነው ለዮአስ አስረክቡት። +27 እንዲህም በሏቸው፦ ‘ንጉሡ “በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ይህን ሰው እስር ቤት አቆዩት፤+ ጥቂት ምግብና ውኃ ብቻ ስጡት” ብሏል።’” +28 ሚካያህ ግን “እውነት አንተ በሰላም ከተመለስክ ይሖዋ በእኔ አልተናገረም ማለት ነው!” አለ።+ ከዚያም “እናንተ ሰዎች፣ ሁላችሁም ልብ በሉ” አለ። +29 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ወደ ራሞትጊልያድ+ ወጡ። +30 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “እኔ ማንነቴ እንዳይታወቅ ራሴን ለውጬ ወደ ውጊያው እገባለሁ፤ አንተ ግን ንጉሣዊ ልብስህን ልበስ” አለው። ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ማንነቱ እንዳይታወቅ ራሱን ለውጦ+ ወደ ውጊያው ገባ። +31 በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ 32ቱን የሠረገላ አዛዦች+ “ከእስራኤል ንጉሥ በስተቀር ከትንሹም ሆነ ከትልቁ፣ ከማንም ጋር እንዳትዋጉ” በማለት አዟቸው ነበር። +32 የሠረገሎቹ አዛዦችም ኢዮሳፍጥን ባዩት ጊዜ “ያለጥርጥር ይህ የእስራኤል ንጉሥ ነው” ብለው አሰቡ። በመሆኑም ሊወጉት ወደ እሱ ዞሩ፤ በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ እርዳታ ለማግኘት ጮኸ። +33 የሠረገሎቹ አዛዦችም የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን ሲያዩ ወዲያውኑ እሱን ማሳደዳቸውን ትተው ተመለሱ። +34 ይሁንና አንድ ሰው በነሲብ* ቀስቱን ሲያስወነጭፍ የእስራኤልን ንጉሥ የጥሩሩ መጋጠሚያ ላይ ወጋው። ስለሆነም ንጉሡ ሠረገላ ነጂውን “ክፉኛ ስለቆሰልኩ ሠረገላውን አዙረህ ከጦርነቱ* ይዘኸኝ ውጣ” አለው።+ +35 ያን ቀን ሙሉ የተፋፋመ ውጊያ ተካሄደ፤ ንጉሡንም ሠረገላው ውስጥ እንዳለ ፊቱን ወደ ሶርያውያን አዙረው ደግፈው አቆሙት። ከቁስሉ የሚወጣውም ደም በጦር ሠረገላው ውስጥ ይፈስ ነበር፤ አመሻሹም ላይ ሞተ።+ +36 ፀሐይ ልትጠልቅም ስትል በሰፈሩ መካከል “እያንዳንዱ ሰው ወደ ከተማው፣ እያንዳንዱም ሰው ወደ ምድሩ ይመለስ!” የሚል ጥሪ አስተጋባ።+ +37 በዚህ መንገድ ንጉሡ ሞተ፤ ወደ ሰማርያም ተወሰደ፤ ንጉሡንም በሰማርያ ቀበሩት። +38 እነሱም የጦር ሠረገላውን በሰማርያ ኩሬ ባጠቡት ጊዜ ይሖዋ በተናገረው መሠረት ውሾች ደሙን ላሱት፤ ዝሙት አዳሪዎችም በዚያ ገላቸውን እየታጠቡ ነበር።*+ +39 ስለቀረው የአክዓብ ታሪክ፣ ስላደረጋቸው ነገሮች ሁሉ፣ በዝሆን ጥርስ ስለሠራው ቤትና*+ ስለገነባቸው ከተሞች ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም? +40 በመጨረሻም አክዓብ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በእሱም ምትክ ልጁ አካዝያስ+ ነገሠ። +41 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ በይሁዳ ላይ ነገሠ። +42 ኢዮሳፍጥ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 35 ዓመት የነበረ ሲሆን በኢየሩሳሌም 25 ዓመት ገዛ። እናቱ የሺልሂ ልጅ አዙባ ነበረች። +43 እሱም በአባቱ በአሳ+ መንገድ ሁሉ ሄደ። ከዚያ ፈቀቅ አላለም፤ በይሖዋም ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ ይሁን እንጂ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር፤ ሕዝቡም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ መሠዋቱንና የሚጨስ መሥዋዕት ማቅረቡን አልተወም ነበር።+ +44 ኢዮሳፍጥ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ነበረው።+ +45 የቀረው የኢዮሳፍጥ ታሪክ፣ በኃያልነቱ የፈጸማቸው ጀብዱዎችና ያደረጋቸው ውጊያዎች በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +46 ኢዮሳፍጥ ከአባቱ ከአሳ+ ዘመን የተረፉትን የቤተ መቅደስ ቀላጮች*+ ከምድሪቱ ላይ አስወግዶ ነበር። +47 በዚያ ዘመን በኤዶም+ ንጉሥ አልነበረም፤ እንደ ንጉሥ ሆኖ የሚገዛው አስተዳዳሪው ነበር።+ +48 በተጨማሪም ኢዮሳፍጥ ወርቅ ለማምጣት ወደ ኦፊር የሚሄዱ የተርሴስ መርከቦች* ሠርቶ ነበር፤+ ሆኖም መርከቦቹ በዔጽዮንጋብር+ ስለተሰበሩ ወደዚያ አልሄዱም። +49 የአክዓብ ልጅ አካዝያስ ኢዮሳፍጥን “አገልጋዮቼ ከአገልጋዮችህ ጋር በመርከቦቹ ይሂዱ” ያለው በዚህ ጊዜ ነበር፤ ኢዮሳፍጥ ግን በዚህ አልተስማማም። +50 በመጨረሻም ኢዮሳፍጥ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በአባቱ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮራም+ ነገሠ። +51 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ17ኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ+ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ሁለት ዓመት ገዛ። +52 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ቀጠለ፤ በአባቱና+ በእናቱ+ መንገድ እንዲሁም እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲፈጽሙ ባደረጋቸው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ ሄደ።+ +53 ባአልን ማገልገሉንና+ ለእሱ መስገዱን ቀጠለ፤ አባቱም እንዳደረገው ሁሉ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን አስቆጣ።+ +17 የይሁዳ ንጉሥ አካዝ በነገሠ በ12ኛው ዓመት የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እሱም ለዘጠኝ ዓመት ገዛ። +2 ከእሱ በፊት የነበሩትን የእስራኤል ነገሥታት ያህል አይሁን እንጂ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። +3 የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር በእሱ ላይ መጣ፤+ ሆሺአም አገልጋዩ ሆነ፤ ገበረለትም።+ +4 ሆኖም የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር ሆሺአ እንዳሴረበት አወቀ፤ ምክንያቱም ሆሺአ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሶህ መልእክተኞች ልኮ ነበር፤+ ደግሞም ቀደም ባሉት ዓመታት ያደርግ እንደነበረው ለአሦር ንጉሥ መገበሩን አቁሞ ነበር። ስለሆነም የአሦር ንጉሥ እስር ቤት ውስጥ አስሮ አስቀመጠው። +5 የአሦር ንጉሥ መላ አገሪቱን ወረረ፤ ወደ ሰማርያም መጥቶ ከተማዋን ለሦስት ዓመት ከበባት። +6 ሆሺአ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ።+ ከዚያም የእስራኤልን ሕዝብ ወደ አሦር በግዞት+ በመውሰድ በሃላህ፣ በጎዛን+ ወንዝ አጠገብ በምትገኘው በሃቦርና በሜዶናውያን ከተሞች አሰፈራቸው።+ +7 ይህ የሆነው የእስራኤል ሰዎች ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ቀንበርና ከግብፅ ምድር ነፃ ባወጣቸው በአምላካቸው በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠሩ ነው።+ እነሱም ሌሎች አማልክትን አመለኩ፤*+ +8 ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ያባረራቸውን ብሔራት ልማዶች ተከተሉ፤ ደግሞም የእስራኤል ነገሥታት ያቋቋሟቸውን ልማዶች ተከተሉ። +9 እስራኤላውያን በአምላካቸው በይሖዋ ፊት ትክክል ያልሆኑ ነገሮችን ያደርጉ ነበር። ከመጠበቂያው ግንብ አንስቶ እስከተመሸገው ከተማ ድረስ በሁሉም ከተሞቻቸው* ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን ሠሩ።+ +10 በእያንዳንዱ ኮረብታ ላይና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ ሥር+ የማምለኪያ ዓምዶችንና የማምለኪያ ግንዶችን*+ ለራሳቸው አቆሙ፤ +11 ይሖዋ ከፊታቸው አሳዶ በግዞት እንዲወሰዱ ያደረጋቸው ብሔራት ያደርጉ እንደነበረው ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ሁሉ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር።+ ይሖዋን ለማስቆጣት ክፉ ነገሮችን ማድረጋቸውን ቀጠሉ። +12 ይሖዋ “አታድርጉ!”+ ያላቸውን ነገር በማድረግ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶችን* አገለገሉ፤+ +13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። +14 እነሱ ግን አልሰሙም፤ በአምላካቸው በይሖዋ እንዳላመኑት አባቶቻቸው እነሱም ግትሮች ሆኑ።*+ +15 ሥርዓቶቹን፣ ከአባቶቻቸው ጋር የገባውን ቃል ኪዳንና+ እነሱን ለማስጠንቀቅ የሰጣቸውን ማሳሰቢያዎች ችላ አሉ፤+ ደግሞም ይሖዋ የእነሱን ምሳሌ እንዳይከተሉ ያዘዛቸውን+ በዙሪያቸው ያሉትን ብሔራት በመምሰል ከንቱ ጣዖቶችን ተከተሉ፤+ እነሱ ራሳቸውም ከንቱ ሆኑ።+ +16 የአምላካቸውን የይሖዋን ትእዛዛት በሙሉ ተዉ፤ ለራሳቸውም ከብረት የተሠሩ ሁለት የጥጃ ሐውልቶችን* አበጁ፤+ የማምለኪያም ግንድ*+ ሠሩ፤ ለሰማያት ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፤+ እንዲሁም ባአልን አገለገሉ።+ +17 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ለእሳት አሳልፈው ሰጡ፤+ ሟርተኞችና ጠንቋዮች ሆኑ፤+ ይሖዋንም ያስቆጡት ዘንድ በእሱ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ራሳቸውን ሰጡ።* +18 በመሆኑም ይሖዋ በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ፤ ስለሆነም ከፊቱ አስወገዳቸው።+ ከይሁዳ ነገድ ሌላ ማንንም አላስቀረም። +19 የይሁዳም ሰዎች ቢሆኑ የአምላካቸውን የይሖዋን ትእዛዛት አልጠበቁም፤+ እነሱም እስራኤላውያን በተከተሏቸው ልማዶች ተመላለሱ።+ +20 ይሖዋም የእስራኤልን ዘሮች ሁሉ ተወ፤ ከፊቱም እስኪያስወግዳቸው ድረስ አዋረዳቸው፤ ለሚበዘብዟቸውም ሰዎች አሳልፎ ሰጣቸው። +21 እስራኤልን ከዳዊት ቤት ለየ፤ እነሱም የናባጥን ልጅ ኢዮርብዓምን አነገሡት።+ ሆኖም ኢዮርብዓም እስራኤላውያን ይሖዋን ከመከተል ዞር እንዲሉና ከባድ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረገ። +22 የእስራኤልም ሰዎች ኢዮርብዓም የፈጸማቸውን ኃጢአቶች ሁሉ ሠሩ።+ ከዚያ ዞር አላሉም፤ +23 ይህም የሆነው ይሖዋ በአገልጋዮቹ በነቢያት ሁሉ አማካኝነት በተናገረው መሠረት እስራኤልን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ ነው።+ በመሆኑም እስራኤላውያን ከገዛ ምድራቸው ወደ አሦር በግዞት ተወሰዱ፤+ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይገኛሉ። +24 የአሦርም ንጉሥ ሰዎችን ከባቢሎን፣ ከኩታ፣ ከአዋ፣ ከሃማትና ከሰፋርዊም+ አምጥቶ በእስራኤላውያን ምትክ በሰማርያ ከተሞች አሰፈራቸው፤ እነሱም ሰማርያን ወርሰው በከተሞቿ መኖር ጀመሩ። +25 በዚያ መኖር እንደጀመሩ አካባቢ ይሖዋን አይፈሩም* ነበር። በመሆኑም ይሖዋ በመካከላቸው አንበሶችን ላከባቸው፤+ እነሱም የተወሰኑ ሰዎችን ���ደሉ። +26 የአሦርም ንጉሥ እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “በግዞት ወስደህ በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ ያደረግካቸው ብሔራት የዚያች ምድር አምላክ እንዴት እንደሚመለክ* አላወቁም። ስለዚህ በመካከላቸው አንበሶችን ላከባቸው፤ አንዳቸውም የዚያች ምድር አምላክ እንዴት እንደሚመለክ ስለማያውቁ አንበሶቹ እየገደሏቸው ነው።” +27 በዚህ ጊዜ የአሦር ንጉሥ “ከዚያ በግዞት ከወሰዳችኋቸው ካህናት መካከል አንዱ ተመልሶ አብሯቸው በመኖር የዚያች ምድር አምላክ እንዴት እንደሚመለክ ያስተምራቸው” ሲል አዘዘ። +28 ስለሆነም ከሰማርያ በግዞት ከወሰዷቸው ካህናት መካከል አንዱ ተመልሶ በመምጣት በቤቴል+ መኖር ጀመረ፤ እሱም ይሖዋን እንዴት መፍራት* እንዳለባቸው ያስተምራቸው ጀመር።+ +29 ይሁንና እያንዳንዱ ብሔር የየራሱን አምላክ* በመሥራት ሳምራውያን ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ በሠሯቸው ቤቶች ውስጥ አስቀምጦ ነበር፤ እያንዳንዱ ብሔር በሚኖርባቸው ከተሞች ውስጥ እንዲህ አደረገ። +30 በመሆኑም የባቢሎን ሰዎች ሱኮትቤኖትን፣ የኩት ሰዎች ኔርጋልን፣ የሃማት+ ሰዎች ደግሞ አሺማን ሠሩ፤ +31 አዋውያንም ኒብሃዝን እና ታርታቅን ሠሩ። ሰፋርዊማውያን+ ደግሞ አድራሜሌክና አናሜሌክ ለተባሉት የሰፋርዊም አማልክት ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ነበር። +32 ይሖዋን ይፈሩ የነበረ ቢሆንም ከሕዝቡ መካከል፣ ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች የሚያገለግሉ ካህናትን ሾሙ፤ እነዚህ ካህናትም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች በሚገኙት የአምልኮ ቤቶች የእነሱ አገልጋዮች ሆኑ።+ +33 በአንድ በኩል ይሖዋን ይፈሩ ነበር፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከመፈናቀላቸው በፊት የነበሩባቸው ብሔራት ያመልኩ እንደነበረው* የራሳቸውን አማልክት ያመልኩ ነበር።+ +34 እስከ ዛሬ ድረስ አምልኳቸውን የሚያከናውኑት በፊት ያደርጉት እንደነበረው* ነው። ይሖዋን የሚያመልክ* ብሎም ደንቦቹን፣ ድንጋጌዎቹን እንዲሁም ይሖዋ እስራኤል የሚል ስም ላወጣለት ለያዕቆብ+ ልጆች የሰጣቸውን ሕግና ትእዛዝ የሚከተል አንድም ሰው አልነበረም። +35 ይሖዋ ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን በተጋባበት ወቅት+ እንዲህ ሲል አዟቸው ነበር፦ “ሌሎች አማልክትን አትፍሩ፤ አትስገዱላቸው፤ አታገልግሏቸው፤ አትሠዉላቸው።+ +36 ከዚህ ይልቅ መፍራት+ ያለባችሁ በታላቅ ኃይልና በተዘረጋ ክንድ ከግብፅ ምድር ያወጣችሁን ይሖዋን ነው፤+ መስገድ ያለባችሁ ለእሱ ነው፤ መሠዋት ያለባችሁም ለእሱ ነው። +37 የጻፈላችሁን ሥርዓቶች፣ ድንጋጌዎች፣ ሕግና ትእዛዛት ምንጊዜም በጥንቃቄ ጠብቁ፤+ ሌሎች አማልክትን አትፍሩ። +38 ደግሞም ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አትርሱ፤+ ሌሎች አማልክትንም አትፍሩ። +39 ይልቁንም ከጠላቶቻችሁ ሁሉ እጅ የሚታደጋችሁ እሱ ስለሆነ መፍራት ያለባችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ነው።” +40 እነሱ ግን አልታዘዙም፤ አምልኳቸውንም የሚያከናውኑት በፊት ያደርጉት እንደነበረው* ነው።+ +41 እነዚህ ብሔራት ይሖዋን ይፈሩ+ የነበረ ቢሆንም የራሳቸውን የተቀረጹ ምስሎችም ያገለግሉ ነበር። ልጆቻቸውም ሆኑ የልጅ ልጆቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ የሚያደርጉት አባቶቻቸው እንዳደረጉት ነው። +18 የእስራኤል ንጉሥ የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ+ ልጅ ሕዝቅያስ+ ነገሠ። +2 እሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ አቢ* ትባል ነበር፤ እሷም የዘካርያስ ልጅ ነበረች።+ +3 አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ +4 ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎች ያስወገደው፣+ የማምለኪያ ዓምዶቹን ያደቀቀውና+ የማምለኪያ ግንዱን* የቆራረጠው እ��� ነበር። በተጨማሪም ሙሴ ሠርቶት የነበረውን የመዳብ እባብ አደቀቀ፤+ የእስራኤል ሕዝብ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ለእባቡ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበርና፤ ይህም ጣዖት የመዳብ እባብ* ተብሎ ይጠ +5 እሱም በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ታመነ፤+ ከእሱ በኋላም ሆነ ከእሱ በፊት ከተነሱት የይሁዳ ነገሥታት መካከል እንደ እሱ ያለ አልተገኘም። +6 ከይሖዋ ጋር ተጣበቀ።+ እሱንም ከመከተል ዞር አላለም፤ ይሖዋ ለሙሴ የሰጠውን ትእዛዝ ጠብቆ ኖረ። +7 ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር። የሚያደርገውንም ነገር ሁሉ በጥበብ ያከናውን ነበር። በኋላም በአሦር ንጉሥ ላይ ዓመፀ፤ እሱንም ለማገልገል ፈቃደኛ አልሆነም።+ +8 በተጨማሪም እስከ ጋዛና እስከ ክልሎቿ ድረስ በመዝለቅ ፍልስጤማውያንን+ ከመጠበቂያ ግንቡ አንስቶ እስከተመሸገው ከተማ* ድረስ ድል አደረገ። +9 ሕዝቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ማለትም የእስራኤል ንጉሥ የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር በሰማርያ ላይ ዘምቶ ከበባት።+ +10 በሦስተኛው ዓመት ማብቂያ ላይ ከተማዋን ያዟት፤+ ሕዝቅያስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት ይኸውም የእስራኤል ንጉሥ ሆሺአ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰማርያ ተያዘች። +11 ከዚያም የአሦር ንጉሥ እስራኤላውያንን ወደ አሦር በግዞት ወስዶ+ በሃላህ፣ በጎዛን ወንዝ አጠገብ በምትገኘው በሃቦርና በሜዶናውያን ከተሞች አሰፈራቸው።+ +12 ይህ የሆነው የአምላካቸውን የይሖዋን ድምፅ ከመስማት ይልቅ ቃል ኪዳኑን ስላፈረሱ ይኸውም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸውን ትእዛዝ በሙሉ ስላልጠበቁ ነው።+ አልሰሙም፤ ደግሞም አልታዘዙም። +13 ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም+ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ዘምቶ ያዛቸው።+ +14 በመሆኑም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ በለኪሶ ወደነበረው ወደ አሦር ንጉሥ “በድያለሁ። እባክህ ከእኔ ተመለስ፤ እኔም የምትጠይቀኝን ነገር ሁሉ እሰጣለሁ” የሚል መልእክት ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ 300 የብር ታላንትና* 30 የወርቅ ታላንት ቅጣት ጣለበት። +15 በመሆኑም ሕዝቅያስ በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች የተገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው።+ +16 በዚህ ጊዜ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ራሱ የለበጣቸውን*+ የይሖዋን ቤተ መቅደስ በሮችና+ መቃኖች ነቃቅሎ* ለአሦር ንጉሥ ሰጠው። +17 ከዚያም የአሦር ንጉሥ ታርታኑን፣* ራብሳሪሱንና* ራብሻቁን* ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ+ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ላካቸው።+ እነሱም ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ልብስ አጣቢው እርሻ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ በሚገኘው በላይኛው ኩሬ የውኃ መውረጃ ቦይ አጠገብ ቆሙ።+ +18 ንጉሡ እንዲመጣ በተጣሩ ጊዜ የንጉሡ ቤት* ኃላፊ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣+ ጸሐፊው ሸብናህ+ እና ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአህ ወደ እነሱ ወጡ። +19 ራብሻቁም እንዲህ አላቸው፦ “እስቲ ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፦ ‘ታላቁ ንጉሥ፣ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “ለመሆኑ እንዲህ እንድትተማመን ያደረገህ ምንድን ነው?+ +20 ‘የጦር ስልትና ለመዋጋት የሚያስችል ኃይል አለኝ’ ትላለህ፤ ይሁንና ይህ ከንቱ ወሬ ነው። ለመሆኑ በእኔ ላይ ለማመፅ የደፈርከው በማን ተማምነህ ነው?+ +21 እነሆ፣ ሰው ቢመረኮዘው እጁ ላይ ሊሰነቀርና ሊወጋው ከሚችለው ከዚህ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ፣ ከግብፅ ድጋፍ አገኛለሁ ብለህ ተማምነሃል።+ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው። +22 ‘እኛ የምንታመነው በአምላካችን በይሖዋ ነው’+ የምትሉኝ ከሆነ ደግሞ፣ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ‘መስገድ ያለባችሁ በኢየሩሳሌም በሚገኘው በዚህ መሠዊያ ፊት ���ው’+ ብሎ የእሱን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችና መሠዊያዎች አስወግዶ የለም?”’+ +"23 በል እስቲ፣ አሁን ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተወራረድ፦ ጋላቢዎች ማግኘት የምትችል ከሆነ 2,000 ፈረሶች እሰጥሃለሁ።+" +24 አንተ የምትታመነው በግብፅ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ነው፤ ታዲያ ከጌታዬ አገልጋዮች መካከል ዝቅተኛ ደረጃ ያለውን አንዱን አለቃ እንኳ እንዴት መመከት ትችላለህ? +25 ለመሆኑ ይህን አካባቢ ለማጥፋት የመጣሁት ይሖዋ ሳይፈቅድልኝ ይመስልሃል? ይሖዋ ራሱ ‘በዚህ ምድር ላይ ዘምተህ አጥፋው’ ብሎኛል።” +26 በዚህ ጊዜ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ሸብናህ+ እና ዮአህ ራብሻቁን+ እንዲህ አሉት፦ “እባክህ፣ እኛ አገልጋዮችህ ቋንቋውን ስለምናውቅ በአረማይክ* ቋንቋ+ አናግረን፤ በቅጥሩ ላይ ያለው ሕዝብ በሚሰማው በአይሁዳውያን ቋንቋ አታነጋግረን።”+ +27 ራብሻቁ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ጌታዬ ይህን ቃል እንድናገር የላከኝ ለጌታህና ለአንተ ብቻ ነው? ከእናንተ ጋር የገዛ ራሳቸውን እዳሪ ለሚበሉትና የገዛ ራሳቸውን ሽንት ለሚጠጡት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎች ጭምር አይደለም?” +28 ከዚያም ራብሻቁ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ በአይሁዳውያን ቋንቋ እንዲህ አለ፦ “የታላቁን ንጉሥ፣ የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ።+ +29 ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ ‘ሕዝቅያስ አያታላችሁ፤ እሱ ከእጄ ሊታደጋችሁ አይችልምና።+ +30 ደግሞም ሕዝቅያስ “ይሖዋ በእርግጥ ይታደገናል፤ ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትወድቅም” እያለ በይሖዋ እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።+ +31 ሕዝቅያስን አትስሙት፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፦ “ከእኔ ጋር ሰላም ፍጠሩ፤ እጃችሁንም ስጡ፤* እያንዳንዳችሁም ከራሳችሁ ወይንና ከራሳችሁ በለስ ትበላላችሁ፤ ከራሳችሁም የውኃ ጉድጓድ ትጠጣላችሁ፤ +32 ይህም የሚሆነው መጥቼ የእናንተን ምድር ወደምትመስለው፣ እህልና አዲስ የወይን ጠጅ፣ ዳቦና የወይን እርሻ፣ የወይራ ዛፍና ማር ወደሚገኝባት ምድር እስክወስዳችሁ ድረስ ነው።+ በዚያን ጊዜ በሕይወት ትኖራላችሁ እንጂ አትሞቱም። ሕዝቅያስን አትስሙት፤ ‘ይሖዋ ይታደገናል’ እያለ ያታልላችኋልና። +33 ከብሔራት አማልክት መካከል ምድሩን ከአሦር ንጉሥ እጅ ያስጣለ አለ? +34 የሃማትና+ የአርጳድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዊም፣+ የሄና እና የኢዋ አማልክትስ የት አሉ? ሰማርያን ከእጄ ማስጣል ችለዋል?+ +35 ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ ምድሩን ከእጄ ማስጣል የቻለ የትኛው ነው? ታዲያ ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ከእጄ ሊያስጥላት ይችላል?”’”+ +36 ሕዝቡ ግን ንጉሡ “ምንም መልስ አትስጡት” ብሎ አዝዞ ስለነበር ዝም አለ፤ አንድም ቃል አልመለሰለትም።+ +37 ይሁንና የቤቱ* አስተዳዳሪ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሐፊው ሸብናህ እና ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአህ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ ራብሻቁ ያለውንም ነገሩት። +23 ንጉሡም መልእክት ላከ፤ እነሱም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠሩ።+ +2 ከዚያ በኋላ ንጉሡ ከይሁዳ ሰዎች፣ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣ ከካህናቱ፣ ከነቢያቱ እንዲሁም ትልቅ ትንሽ ሳይባል ከሕዝቡ ሁሉ ጋር ወደ ይሖዋ ቤት ወጣ። እሱም በይሖዋ ቤት የተገኘውን+ የቃል ኪዳኑን+ መጽሐፍ+ ቃል ሁሉ የተሰበሰቡት ሰዎች እየሰሙ አነበበላቸው። +3 ንጉሡ ዓምዱ አጠገብ ቆሞ በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈሩትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት በመፈጸም በሙሉ ልቡና በሙሉ ነፍሱ* ይሖዋን ለመከተል እንዲሁም ትእዛዛቱን፣ ማሳሰቢያዎቹንና ደንቦቹን ለመጠበቅ በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ገባ።*+ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳኑ ተስማማ።+ +4 ከዚያም ንጉሡ ሊቀ ካህናቱን ኬልቅያስን፣+ በሁለተኛ ማዕረግ ያሉትን ካህናትና በር ጠባቂዎቹን ለባ���ል፣ ለማምለኪያ ግንዱና* ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ የተሠሩትን ዕቃዎች በሙሉ ከይሖዋ ቤተ መቅደስ እንዲያወጡ አዘዛቸው።+ ከዚያም ከኢየሩሳሌም ውጭ በቄድሮን ተዳፋት ላይ አቃጠላቸው፤ አመዱንም ወደ ቤቴል+ ወሰደው +5 የይሁዳ ነገሥታት በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ዙሪያ በነበሩት ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ላይ የሚጨስ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ የሾሟቸውን የባዕድ አምላክ ካህናት አባረረ፤ በተጨማሪም ለባአል፣ ለፀሐይ፣ ለጨረቃ፣ ዞዲያክ ለተባለው ኅብረ ከዋክብትና ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ+ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርቡ የነበሩትን +6 የማምለኪያ ግንዱን* ከይሖዋ ቤት አውጥቶ+ ወደ ኢየሩሳሌም ዳርቻ ወደ ቄድሮን ሸለቆ በመውሰድ በዚያ አቃጠለው፤+ አድቅቆም አመድ አደረገው፤ አመዱንም በሕዝቡ መቃብር ላይ በተነው።+ +7 እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ የነበሩትንና ሴቶች ለማምለኪያ ግንዱ* ቤተ መቅደስ የሚሆኑ ድንኳኖችን ይሸምኑባቸው የነበሩትን የቤተ መቅደስ ቀላጮች*+ ቤቶች አፈራረሰ። +8 ከዚያም ካህናቱን ሁሉ ከይሁዳ ከተሞች አስወጣ፤ እንዲሁም ካህናቱ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን ከጌባ+ አንስቶ እስከ ቤርሳቤህ+ ድረስ የሚገኙትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች አረከሰ። በተጨማሪም የከተማዋ አለቃ በሆነው በኢያሱ መግቢያ በር ላይ ይኸውም አንድ ሰው በከተማዋ በር ሲገባ በስተ ግ +9 ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች ካህናት፣ በኢየሩሳሌም በሚገኘው የይሖዋ መሠዊያ አያገልግሉ+ እንጂ ከወንድሞቻቸው ጋር ቂጣ* ይበሉ ነበር። +10 እሱም በሂኖም ልጆች ሸለቆ*+ ውስጥ የነበረውን ቶፌትን+ አረከሰ፤ ይህን ያደረገው ማንም ሰው በዚያ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት አሳልፎ እንዳይሰጥ ነው።+ +11 ደግሞም የይሁዳ ነገሥታት ለፀሐይ የሰጧቸው ፈረሶች የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን በሆነው በናታንሜሌክ ክፍል* ይኸውም በመተላለፊያዎቹ መሃል ባለው ክፍል በኩል አድርገው ወደ ይሖዋ ቤት እንዳይገቡ ከለከለ፤ የፀሐይንም+ ሠረገሎች በእሳት አቃጠለ። +12 እንዲሁም ንጉሡ የይሁዳ ነገሥታት በአካዝ ሰገነት ጣሪያ ላይ+ የሠሯቸውን መሠዊያዎችና ምናሴ በይሖዋ ቤት ሁለት ግቢዎች ውስጥ የሠራቸውን መሠዊያዎች አፈራረሰ።+ ከዚያም አደቀቃቸው፤ የደቀቀውንም በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ በተነው። +13 በተጨማሪም ንጉሡ፣ የእስራኤል ንጉሥ ሰለሞን ለሲዶናውያን አስጸያፊ የሴት አምላክ ለአስታሮት፣ ለሞዓባውያን አስጸያፊ አምላክ ለከሞሽ እንዲሁም ለአሞናውያን አስጸያፊ አምላክ+ ለሚልኮም+ የሠራቸውን በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት ከጥፋት ተራራ* በስተ ደቡብ* የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች አረከሰ። +14 የማምለኪያ ዓምዶቹን ሰባበረ፤ የማምለኪያ ግንዶቹንም* ቆራረጠ፤+ ቦታውንም በሰው አፅም ሞላው። +15 በቤቴል የነበረውንም መሠዊያ ይኸውም እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲሠሩ ያደረገው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም የሠራውን ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ አፈረሰ።+ ያን መሠዊያና ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ ካፈረሰ በኋላ ቦታውን አቃጠለው፤ ፈጭቶም አመድ አደረገው፤ የማምለኪያ ግንዱንም* አቃጠለ።+ +16 ኢዮስያስ ዞር ብሎ በተራራው ላይ ያሉትን መቃብሮች ባየ ጊዜ አፅሞቹን ከመቃብሮቹ ውስጥ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በማቃጠል እነዚህ ነገሮች እንደሚሆኑ አስቀድሞ የተናገረው የእውነተኛው አምላክ ሰው ባወጀው የይሖዋ ቃል መሠረት መሠዊያውን አረከሰ።+ +17 ከዚያም “እዚያ ጋ የማየው የመቃብር ሐውልት የማን ነው?” አለ። በዚህ ጊዜ የከተማዋ ሰዎች “ከይሁዳ የመጣውና በቤቴል በሚገኘው መሠዊያ ላይ አንተ ያደረግካቸውን እነዚህን ነገሮች አስቀድሞ የተናገረው የእውነተኛው አምላክ ሰው+ መቃብር ነው” አሉ��። +18 እሱም “በሉ ይረፍ ተዉት። ማንም ሰው አፅሙን አይረብሸው” አለ። በመሆኑም የእሱንም ሆነ ከሰማርያ የመጣውን ነቢይ አፅም ሳይነኩ ተዉት።+ +19 በተጨማሪም ኢዮስያስ የእስራኤል ነገሥታት አምላክን ለማስቆጣት በሰማርያ ከተሞች ውስጥ የሠሯቸውን ከፍ ባሉ የማምለኪያ ቦታዎች ላይ የሚገኙ የአምልኮ ቤቶች በሙሉ አስወገደ፤+ በቤቴል ያደረገውንም ሁሉ በእነሱ ላይ አደረገ።+ +20 በዚህም መሠረት በዚያ የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ካህናት በሙሉ በመሠዊያዎቹ ላይ ሠዋ፤ በላያቸውም ላይ የሰው አፅም አቃጠለ።+ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። +21 ንጉሡም ሕዝቡን ሁሉ “በዚህ የቃል ኪዳን መጽሐፍ ላይ በተጻፈው መሠረት ለአምላካችሁ ለይሖዋ ፋሲካን* አክብሩ”+ ሲል አዘዘ።+ +22 መሳፍንት እስራኤልን ያስተዳድሩ በነበረበት ዘመንም ሆነ በእስራኤል ነገሥታትና በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ሁሉ እንዲህ ያለ ፋሲካ ተከብሮ አያውቅም።+ +23 ንጉሥ ኢዮስያስ በነገሠ በ18ኛው ዓመት ግን ይህ ፋሲካ በኢየሩሳሌም ለይሖዋ ተከበረ። +24 በተጨማሪም ኢዮስያስ ካህኑ ኬልቅያስ በይሖዋ ቤት ውስጥ ባገኘው መጽሐፍ+ ላይ የተጻፈውን የሕጉን ቃል ይፈጽም ዘንድ+ መናፍስት ጠሪዎችን፣ ጠንቋዮችን፣+ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾችን፣*+ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶችን* እንዲሁም በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም የነበሩ አስጸያፊ ነገሮችን በሙሉ አስወገደ። +25 በሙሴ ሕግ መሠረት በሙሉ ልቡ፣ በሙሉ ነፍሱና*+ በሙሉ ኃይሉ ወደ ይሖዋ የተመለሰ እንደ እሱ ያለ ንጉሥ ከእሱ በፊት አልነበረም፤ ከእሱ በኋላም እንደ እሱ ያለ ንጉሥ አልተነሳም። +26 ይሁንና ይሖዋ፣ ምናሴ እሱን ያስቆጣው ዘንድ በፈጸማቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ በይሁዳ ላይ ከነደደው ቁጣው አልተመለሰም ነበር።+ +27 ይሖዋ “እስራኤልን እንዳስወገድኩ+ ሁሉ ይሁዳንም ከፊቴ አስወግዳለሁ፤+ የመረጥኳትን ይህችን ከተማ ኢየሩሳሌምን እንዲሁም ‘ስሜ በዚያ ይኖራል’+ ብዬ የተናገርኩለትን ቤት እተዋለሁ” አለ። +28 የቀረው የኢዮስያስ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +29 በእሱ ዘመን የግብፁ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ ከአሦር ንጉሥ ጋር ለመገናኘት በኤፍራጥስ ወንዝ በኩል መጣ፤ ንጉሥ ኢዮስያስም ሊገጥመው ወጣ፤ ኒካዑም ባየው ጊዜ መጊዶ ላይ ገደለው።+ +30 በመሆኑም አገልጋዮቹ አስከሬኑን በሠረገላ ከመጊዶ ወደ ኢየሩሳሌም በማምጣት በራሱ መቃብር ውስጥ ቀበሩት። ከዚያም የምድሪቱ ሕዝብ የኢዮስያስን ልጅ ኢዮዓካዝን ቀብተው በአባቱ ምትክ አነገሡት።+ +31 ኢዮዓካዝ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 23 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ገዛ። እናቱ ሀሙጣል ትባል ነበር፤+ እሷም የሊብና ሰው የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። +32 አባቶቹ እንዳደረጉት ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +33 ፈርዖን ኒካዑ፣+ ኢዮዓካዝ በኢየሩሳሌም ሆኖ እንዳይገዛ በሃማት ምድር በምትገኘው በሪብላ+ አሰረው፤ በምድሪቱም ላይ 100 የብር ታላንትና* አንድ የወርቅ ታላንት ቅጣት ጣለ።+ +34 በተጨማሪም ፈርዖን ኒካዑ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ ምትክ አነገሠው፤ ስሙንም ቀይሮ ኢዮዓቄም አለው፤ ኢዮዓካዝን ግን ወደ ግብፅ ወሰደው፤+ እሱም በመጨረሻ በዚያ ሞተ።+ +35 ኢዮዓቄም ብሩንና ወርቁን ለፈርዖን ሰጠው፤ ይሁንና ፈርዖን የጠየቀውን ብር ለመስጠት በምድሪቱ ላይ ቀረጥ መጣል አስፈልጎት ነበር። እሱም እያንዳንዱ የምድሪቱ ነዋሪ ለፈርዖን ኒካዑ እንዲሰጥ ተገምቶ በተጣለበት ቀረጥ መሠረት ብርና ወርቅ እንዲከፍል አደረገ። +36 ኢዮዓቄም+ በነገ��� ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ።+ እናቱ ዘቢዳ ትባል ነበር፤ እሷም የሩማ ሰው የሆነው የፐዳያህ ልጅ ነበረች። +37 አባቶቹ እንዳደረጉት+ ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +19 ንጉሥ ሕዝቅያስ ይህን እንደሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶም ወደ ይሖዋ ቤት ገባ።+ +2 ከዚያም የቤቱ* አስተዳዳሪ የሆነውን ኤልያቄምን፣ ጸሐፊውን ሸብናህን እንዲሁም የካህናቱን ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ+ እንዲሄዱ ላካቸው። +3 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የዘለፋና* የውርደት ቀን ነው፤ መውለጃዋ ደርሶ* ለማማጥ የሚያስችል አቅም እንዳጣች ሴት ሆነናል።+ +4 ምናልባት አምላክህ ይሖዋ፣ ሕያው የሆነውን አምላክ እንዲያቃልል ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራብሻቁን ቃል ሁሉ ይሰማ ይሆናል፤+ ደግሞም አምላክህ ይሖዋ፣ የተናገረውን ቃል ሰምቶ ተጠያቂ ያደርገው ይሆናል። ስለዚህ በሕይወት ለተረፉት ቀሪዎች ጸልይ።’”+ +5 በመሆኑም የንጉሥ ሕዝቅያስ አገልጋዮች ወደ ኢሳይያስ ሄዱ፤+ +6 ኢሳይያስም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታችሁን እንዲህ በሉት፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች እኔን በመሳደብ የተናገሩትን ቃል በመስማትህ አትፍራ።+ +7 እነሆ፣ በአእምሮው አንድ ሐሳብ አስገባለሁ፤* እሱም ወሬ ሰምቶ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ በገዛ አገሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።”’”+ +8 ራብሻቁም የአሦር ንጉሥ ለኪሶን+ ለቆ እንደሄደ ሲሰማ ወደ ንጉሡ ተመለሰ፤ ከሊብናም ጋር ሲዋጋ አገኘው።+ +9 ንጉሡ የኢትዮጵያው ንጉሥ ቲርሃቅ “ከአንተ ጋር ሊዋጋ ወጥቷል” የሚል ወሬ ሰምቶ ነበር። በመሆኑም ለሕዝቅያስ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት በድጋሚ መልእክተኞች ላከ፦+ +10 “የይሁዳን ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፦ ‘የምትታመንበት አምላክህ “ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትወድቅም” ብሎ አያታልህ።+ +11 እነሆ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን አገሮች ሁሉ ፈጽመው በማጥፋት ያደረጉትን ነገር ሰምተሃል።+ ታዲያ አንተ ብቻ ከዚህ የምታመልጥ ይመስልሃል? +12 አባቶቼ ያጠፏቸውን ብሔራት አማልክታቸው ታድገዋቸዋል? ጎዛን፣ ካራን፣+ ረጼፍና በቴልአሳር የነበሩት የኤደን ሕዝቦች የት አሉ? +13 የሃማት ንጉሥ፣ የአርጳድ ንጉሥ፣ የሰፋርዊም ከተሞች ንጉሥ እንዲሁም የሄና እና የኢዋ+ ነገሥታት የት አሉ?’” +14 ሕዝቅያስ ደብዳቤዎቹን ከመልእክተኞቹ እጅ ተቀብሎ አነበበ። ከዚያም ወደ ይሖዋ ቤት ወጥቶ ደብዳቤዎቹን* በይሖዋ ፊት ዘረጋ።+ +15 ሕዝቅያስም በይሖዋ ፊት እንዲህ ሲል ጸለየ፦+ “ከኪሩቤል በላይ* የምትቀመጥ፣+ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ እውነተኛ አምላክ አንተ ብቻ ነህ።+ ሰማያትንና ምድርን ሠርተሃል። +16 ይሖዋ ሆይ፣ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ!+ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይንህን ገልጠህ እይ!+ ሰናክሬም ሕያው የሆነውን አምላክ ለማቃለል የላከውን ቃል ስማ። +17 ይሖዋ ሆይ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን ብሔራትና ምድራቸውን እንዳጠፉ አይካድም።+ +18 አማልክታቸውንም እሳት ውስጥ ጨምረዋል፤ ምክንያቱም የሰው እጅ ሥራ፣+ እንጨትና ድንጋይ እንጂ አማልክት አይደሉም።+ ሊያጠፏቸው የቻሉት በዚህ ምክንያት ነው። +19 አሁን ግን አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ፣ አንተ ብቻ አምላክ እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ከእጁ አድነን።”+ +20 ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ሕዝቅያስ ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ ያቀረብከውን ጸሎት ሰምቻለሁ።+ +21 ይሖዋ በእሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ “ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ትንቅሃለች፤ ደግሞም ታፌዝብሃለች። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ራሷን ትነቀንቅብሃለች። +22 ያቃለልከውና የሰደብከው ማንን ነው?+ ድምፅህን ከፍ ያደረግከው፣+እብሪተኛ ዓይንህንም ያነሳኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ እኮ ነው!+ +23 በመልእክተኞችህ+ በኩል ይሖዋን አቃለሃል፤+ እንዲህም ብለሃል፦‘ብዛት ባላቸው የጦር ሠረገሎቼ፣ወደ ተራሮች ከፍታ፣ርቀው ወደሚገኙትም የሊባኖስ ስፍራዎች እወጣለሁ። ረጃጅሞቹን አርዘ ሊባኖሶች፣ ምርጥ የሆኑትንም የጥድ ዛፎች እቆርጣለሁ። ርቆ ወደሚገኘው ማረፊያ ቦታ፣ በጣም ጥቅጥቅ ወዳለው ጫካ እገባለሁ። +24 ጉድጓድ ቆፍሬ የባዕድ አገር ውኃዎችን እጠጣለሁ፤የግብፅንም ጅረቶች* ሁሉ በእግሬ ረግጬ አደርቃለሁ።’ +25 አልሰማህም? ይህ ከጥንት ዘመን ጀምሮ የተወሰነ* ነው።+ ከድሮ ጀምሮ ይህን አስቤአለሁ።*+ አሁን እንዲፈጸም አደርጋለሁ።+ አንተም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር ታደርጋለህ።+ +26 ነዋሪዎቻቸው አቅመ ቢስ ይሆናሉ፤ይሸበራሉ፤ ደግሞም ያፍራሉ። እንደ ሜዳ ተክል፣ እንደ ለምለም ሣር፣+እንዲሁም የምሥራቅ ነፋስ እንዳቃጠለው በጣሪያ ላይ የበቀለ ሣር ይሆናሉ። +27 ይሁንና መቼ እንደምትቀመጥ፣ መቼ እንደምትወጣና መቼ እንደምትገባ፣እንዲሁም መቼ በእኔ ላይ እንደተቆጣህ በሚገባ አውቃለሁ፤+ +28 ምክንያቱም በእኔ ላይ የተቆጣኸው ቁጣና+ ጩኸትህ ወደ ጆሮዬ ደርሷል።+ ስለዚህ ስናጌን በአፍንጫህ፣ ልጓሜንም+ በአፍህ አስገባለሁ፤በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።”+ +29 “‘ይህም ምልክት ይሆንሃል፦* በዚህ ዓመት የገቦውን እህል* ትበላላችሁ፤ በሁለተኛውም ዓመት ከዚያው ላይ የበቀለውን እህል ትበላላችሁ፤+ በሦስተኛው ዓመት ግን ዘር ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁም፤ እንዲሁም ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።+ +30 ከይሁዳ ቤት ያመለጡትና በሕይወት የቀሩት ሰዎች+ ወደ ታች ሥር ይሰዳሉ፤ ወደ ላይም ያፈራሉ። +31 ከኢየሩሳሌም ቀሪዎች፣ ከጽዮን ተራራም በሕይወት የተረፉ ሰዎች ይወጣሉና። የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።+ +32 “‘ስለዚህ ይሖዋ ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦+ “ወደዚህች ከተማ አይመጣም፤+ፍላጻም አይወረውርባትም፤ጋሻም ይዞ አይመጣባትም፤ከበባ ለማድረግም በዙሪያዋ የአፈር ቁልል አይደለድልም።+ +33 በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤ወደዚህች ከተማ አይገባም” ይላል ይሖዋ። +34 “ስለ እኔና+ ስለ አገልጋዬ ስለ ዳዊት ስል+ይህችን ከተማ እጠብቃታለሁ፤+ ደግሞም አድናታለሁ።”’” +"35 በዚያም ሌሊት የይሖዋ መልአክ ወጥቶ በአሦራውያን ሰፈር የነበሩትን 185,000 ሰዎች ገደለ።+ ሰዎችም በማለዳ ሲነሱ ሬሳውን አዩ።+" +36 በመሆኑም የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከዚያ ተነስቶ ወደ ነነዌ+ ተመለሰ፤ በዚያም ተቀመጠ።+ +37 ሰናክሬም በአምላኩ በኒስሮክ ቤት* እየሰገደ ሳለ አድራሜሌክና ሳሬጸር የተባሉት የገዛ ልጆቹ በሰይፍ መትተው ገደሉት፤+ ከዚያም ወደ አራራት+ ምድር ሸሽተው ሄዱ። ልጁም ኤሳርሃደን+ በእሱ ምትክ ነገሠ። +20 በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ሞት አፋፍ ደርሶ ነበር።+ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህ ስለማይቀር ለቤተሰብህ መመሪያ ስጥ።’”+ +2 በዚህ ጊዜ ፊቱን ወደ ግድግዳው አዙሮ ወደ ይሖዋ መጸለይ ጀመረ፦ +3 “እባክህ ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትና በሙሉ ልብ በፊትህ እንዴት እንደተመላለስኩ እንዲሁም በዓይኖችህ ፊት መልካም የሆነውን ነገር እንዳደረግኩ እንድታስታውስ አጥብቄ እለምንሃለሁ።”+ ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ። +4 ኢሳይያስ ገና ወደ መካከለኛው ግቢ ሳይወጣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦+ +5 “ተመልሰህ ሂድና የሕዝቤ መሪ የሆነውን ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ። እንባህንም አይቻለሁ።+ ስለሆነም እፈውስሃለሁ።+ በሦስተኛው ቀን ወደ ይሖዋ ቤት ትወጣለህ።+ +6 እኔም በዕድሜህ* ላይ 15 ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ ደግሞም አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤+ ስለ ራሴና ስለ አገልጋዬ ስለ ዳዊት ስል ከተማዋን እጠብቃታለሁ።”’”+ +7 ከዚያም ኢሳይያስ “የደረቀ የበለስ ጥፍጥፍ አምጡ” አለ። ጥፍጥፉንም አምጥተው እባጩ ላይ አደረጉለት፤ እሱም ቀስ በቀስ እየተሻለው ሄደ።+ +8 ሕዝቅያስ ኢሳይያስን “ይሖዋ እንደሚፈውሰኝና በሦስተኛው ቀን ወደ ይሖዋ ቤት እንደምወጣ ማወቅ የምችልበት ምልክት ምንድን ነው?”+ ሲል ጠየቀው። +9 ኢሳይያስም መልሶ “ይሖዋ የተናገረውን ቃል እንደሚፈጽም የሚያሳየው ይሖዋ የሰጠህ ምልክት ይህ ነው፦ ጥላው በደረጃው* ላይ አሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ትፈልጋለህ ወይስ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ?” አለው።+ +10 ሕዝቅያስም “ጥላው አሥር ደረጃ ወደ ፊት መሄዱ ቀላል ነገር ነው፤ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ መመለሱ ግን ቀላል አይደለም” አለ። +11 ስለዚህ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ይሖዋ ጮኸ፤ እሱም በአካዝ ደረጃ ላይ ወደ ታች ወርዶ የነበረው ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ።+ +12 በዚያን ጊዜ የባላዳን ልጅ የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ቤሮዳክባላዳን ሕዝቅያስ መታመሙን ሰምቶ ስለነበር ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።+ +13 ሕዝቅያስም ለመልእክተኞቹ ጥሩ አቀባበል አደረገላቸው፤* ከዚያም ግምጃ ቤቱን ሁሉ ይኸውም ብሩን፣ ወርቁን፣ የበለሳን ዘይቱን፣ ሌላውን ምርጥ ዘይት፣ የጦር መሣሪያውንና በግምጃ ቤቶቹ ውስጥ ያለውን ንብረት በሙሉ አሳያቸው።+ ሕዝቅያስ በቤቱም* ሆነ በግዛቱ ሁሉ ያላሳያቸው ምንም ነገር አልነበረም። +14 ከዚያ በኋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ መጥቶ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? የመጡትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “የመጡት ከሩቅ አገር፣ ከባቢሎን ነው” አለው።+ +15 ቀጥሎም “በቤትህ* ያዩት ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “በቤቴ* ያለውን ነገር ሁሉ አይተዋል። በግምጃ ቤቶቼ ውስጥ ካለው ንብረት ሁሉ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” ሲል መለሰለት። +16 በዚህ ጊዜ ኢሳይያስ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፦ “የይሖዋን ቃል ስማ፦+ +17 ‘እነሆ፣ በቤትህ* ያለው ሁሉና አባቶችህ እስካሁን ድረስ ያከማቹት ነገር ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚጋዝበት ቀን ይመጣል።+ አንድም የሚቀር ነገር አይኖርም’ ይላል ይሖዋ። +18 ‘ከአንተ ከሚወለዱት ከገዛ ልጆችህ መካከልም አንዳንዶቹ ይወሰዳሉ፤+ በባቢሎን ንጉሥ ቤተ መንግሥትም ባለሥልጣናት ይሆናሉ።’”+ +19 በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ ኢሳይያስን “የተናገርከው የይሖዋ ቃል መልካም ነው”+ አለው። አክሎም “በእኔ የሕይወት ዘመን* ሰላምና መረጋጋት* መኖሩ መልካም ነው” አለ።+ +20 የቀረው የሕዝቅያስ ታሪክ፣ ኃያልነቱ ሁሉ እንዲሁም ኩሬውንና+ ቦዩን ሠርቶ ውኃው ወደ ከተማዋ እንዲመጣ ያደረገበት መንገድ+ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም? +21 በመጨረሻም ሕዝቅያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በእሱም ምትክ ልጁ ምናሴ+ ነገሠ።+ +3 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ18ኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ ኢዮራም+ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እሱም ለ12 ዓመት ገዛ። +2 ኢዮራም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ ሆኖም አባቱ ወይም እናቱ ያደረጉትን ያህል ክፉ ድርጊት አልፈጸመም፤ አባቱ የሠራውን የባአል የማምለኪያ ዓምድ አስወግዶ ነበርና።+ +3 ይሁንና የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲሠሩ በማድረግ+ የተከተለውን የኃጢአት ጎዳና የሙጥኝ አለ። ከዚያ ፈቀቅ አላለም። +"4 የሞዓብ ንጉሥ ሜሻ በግ አርቢ ነበር፤ እሱም ለእስራኤል ንጉሥ 100,000 የበግ ጠቦቶችንና 100,000 ያልተሸለቱ አውራ በጎችን ይገብር ነበር።" +5 አክዓብ እንደሞተ+ የሞዓብ ንጉሥ በእስራኤል ንጉሥ ላይ ዓመፀ።+ +6 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ኢዮራም ከሰማርያ ወጥቶ በመሄድ እስራኤልን ሁሉ አሰለፈ። +7 በተጨማሪም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሳፍጥ “የሞዓብ ንጉሥ ዓምፆብኛል። ሞዓብን ለመውጋት አብረኸኝ ትሄዳለህ?” የሚል መልእክት ላከበት። እሱም “አብሬህ እሄዳለሁ።+ እኔ ማለት እኮ አንተ ማለት ነህ። ሕዝቤ፣ ሕዝብህ ነው። ፈረሶቼም ፈረሶችህ ናቸው” አለው።+ +8 ከዚያም “ታዲያ በየትኛው መንገድ ብንወጣ ይሻላል?” ብሎ ጠየቀው። እሱም “ወደ ኤዶም ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ” አለው። +9 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ከይሁዳ ንጉሥና ከኤዶም+ ንጉሥ ጋር አብሮ ሄደ። ለሰባት ቀን ያህል በሌላ አቅጣጫ ዞረው ከሄዱ በኋላ ለሠራዊቱም ሆነ እየተከተሏቸው ለነበሩት የቤት እንስሳት የሚሆን ውኃ አጡ። +10 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ “በጣም አስደንጋጭ ነው! ይሖዋ እነዚህን ሦስት ነገሥታት የጠራው ለሞዓብ አሳልፎ ለመስጠት ነው!” አለ። +11 በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ “በእሱ አማካኝነት ይሖዋን ልንጠይቅ የምንችልበት የይሖዋ ነቢይ እዚህ የለም?” አለ።+ ከእስራኤል ንጉሥ አገልጋዮች አንዱ “ኤልያስን+ እጅ ያስታጥብ የነበረው* የሻፋጥ ልጅ ኤልሳዕ+ እዚህ አለ” ሲል መለሰ። +12 ከዚያም ኢዮሳፍጥ “የይሖዋ ቃል እሱ ዘንድ ይገኛል” አለ። በዚህም መሠረት የእስራኤል ንጉሥ፣ ኢዮሳፍጥና የኤዶም ንጉሥ ወደ እሱ ወረዱ። +13 ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ “እኔና አንተን ምን የሚያገናኘን ነገር አለ?+ ወደ አባትህ ነቢያትና ወደ እናትህ ነቢያት ሂድ”+ አለው። የእስራኤል ንጉሥ ግን “ይሄማ አይሆንም፤ ይሖዋ እኮ እነዚህን ሦስት ነገሥታት ጠርቶ በሞዓብ እጅ አሳልፎ ሊሰጣቸው ነው” አለው። +14 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ እንዲህ አለ፦ “በማገለግለውና* ሕያው በሆነው በሠራዊት ጌታ በይሖዋ እምላለሁ፣ ለማከብረው ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮሳፍጥ+ ብዬ ነው እንጂ ዓይንህን አላይም፣ ጉዳዬም አልልህም ነበር።+ +15 በሉ አሁን በገና የሚደረድር ሰው*+ አምጡልኝ።” በገና የሚደረድረውም ሰው መጫወት ሲጀምር የይሖዋ እጅ በኤልሳዕ ላይ መጣ።+ +16 እሱም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህ ሸለቆ* ውስጥ ብዙ ቦዮች ቆፍሩ፤ +17 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ነፋስም ሆነ ዝናብ አታዩም፤ ይሁንና ይህ ሸለቆ* በውኃ ይሞላል፤+ እናንተም ሆናችሁ ከብቶቻችሁ እንዲሁም ሌሎች እንስሶቻችሁ ከዚያ ትጠጣላችሁ።”’ +18 ይህ ለይሖዋ በጣም ቀላል ነገር ነው፤+ ሞዓብንም በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋልና።+ +19 እናንተም እያንዳንዱን የተመሸገ ከተማና+ እያንዳንዱን የተመረጠ ከተማ ትመታላችሁ፤ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ትቆርጣላችሁ፤ የውኃ ምንጮችን በሙሉ ትደፍናላችሁ፤ ጥሩውንም መሬት ሁሉ በድንጋይ ታበላሻላችሁ።”+ +20 በነጋታውም የጠዋት የእህል መባ+ በሚቀርብበት ጊዜ በድንገት ውኃ ከኤዶም አቅጣጫ መጣ፤ ምድሪቱም በውኃው ተጥለቀለቀች። +21 ሞዓባውያንም ነገሥታቱ ሊወጓቸው እንደመጡ ሲሰሙ የጦር መሣሪያ መታጠቅ የሚችሉ* ሰዎችን ሁሉ ሰብስበው ድንበሩ ላይ ቆሙ። +22 በማለዳ ሲነሱም ፀሐይዋ በውኃው ላይ ታንጸባርቅ ነበር፤ ማዶ ለነበሩት ሞዓባውያንም ውኃው እንደ ደም ቀልቶ ታያቸው። +23 እነሱም “ይሄ�� ደም ነው! ነገሥታቱ ያለጥርጥር እርስ በርሳቸው በሰይፍ ተራርደዋል። ስለዚህ ሞዓብ ሆይ፣ ወደ ምርኮህ+ ሂድ!” አሉ። +24 እነሱም ወደ እስራኤል ሰፈር ሲመጡ እስራኤላውያን ተነስተው ሞዓባውያንን መምታት ጀመሩ፤ እነሱም ከፊታቸው ሸሹ።+ እስራኤላውያንም ሞዓባውያንን እየመቱ ወደ ሞዓብ ገሰገሱ። +25 ከተሞቹንም ደመሰሱ፤ እያንዳንዱም ሰው ድንጋይ እየጣለ ጥሩውን መሬት ሁሉ በድንጋይ ሞላው፤ የውኃ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤+ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቆረጡ።+ በመጨረሻም የቂርሃረሰት+ የድንጋይ ግንቦች ብቻ ቆመው ቀሩ፤ ወንጭፍ የሚወነጭፉትም ዙሪያዋን ከበው መቷት። +26 የሞዓብ ንጉሥ በውጊያው እንደተሸነፈ ባየ ጊዜ ወደ ኤዶም ንጉሥ+ ጥሶ ለመግባት ሰይፍ የታጠቁ 700 ሰዎችን ወሰደ፤ ሆኖም አልተሳካላቸውም። +27 ስለዚህ በእሱ ምትክ የሚነግሠውን የበኩር ልጁን ወስዶ ቅጥሩ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው።+ በእስራኤልም ላይ ታላቅ ቁጣ ሆነ፤ በመሆኑም አካባቢውን ለቀው ወደ ምድራቸው ተመለሱ። +24 በኢዮዓቄም ዘመን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ ምድሪቱን ወረረ፤ ኢዮዓቄምም ለሦስት ዓመት የእሱ አገልጋይ ሆነ። ሆኖም ሐሳቡን ለውጦ ዓመፀበት። +2 ከዚያም ይሖዋ የከለዳውያንን፣+ የሶርያውያንን፣ የሞዓባውያንንና የአሞናውያንን ወራሪ ቡድኖች ይልክበት ጀመር። ይሖዋ አገልጋዮቹ በሆኑት በነቢያት አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት+ ይሁዳን እንዲያጠፉ እነዚህን ቡድኖች ይልክባቸው ነበር። +3 ይህ ነገር ይሖዋ ባዘዘው መሠረት በይሁዳ ላይ የደረሰው ይሁዳን ከፊቱ ለማጥፋት ነው፤+ ይህም የሆነው ምናሴ በሠራቸው ኃጢአቶች ሁሉ የተነሳ ነው፤+ +4 ንጹሕ ደም በማፍሰስ ኢየሩሳሌም በንጹሕ ደም እንድትጥለቀለቅ በማድረጉ ነው፤+ ይሖዋም ይቅር ለማለት ፈቃደኛ አልሆነም።+ +5 የቀረው የኢዮዓቄም ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?+ +6 በመጨረሻም ኢዮዓቄም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በእሱም ምትክ ልጁ ዮአኪን ነገሠ። +7 የባቢሎን ንጉሥ ከግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ አንስቶ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ+ ድረስ የሚገኘውን የግብፅን ንጉሥ+ ምድር ሁሉ ወስዶ ስለነበር የግብፅ ንጉሥ ዳግመኛ ከምድሩ ለመውጣት አልደፈረም። +8 ዮአኪን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 18 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ገዛ።+ እናቱ ነሁሽታ ትባል ነበር፤ እሷም የኢየሩሳሌም ሰው የሆነው የኤልናታን ልጅ ነበረች። +9 አባቱ እንዳደረገው ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። +10 በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የናቡከደነጾር አገልጋዮች በኢየሩሳሌም ላይ ዘመቱ፤ ከተማዋም ተከበበች።+ +11 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹ ከተማዋን ከበው ሳሉ ወደ ከተማዋ መጣ። +12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ+ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ+ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።+ +13 ከዚያም በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* የነበሩትን ውድ ዕቃዎች ሁሉ ወሰደ።+ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሰለሞን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ የሠራቸውን የወርቅ ዕቃዎች በሙሉ ሰባበራቸው።+ ይህ የሆነው ይሖዋ አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው። +"14 ኢየሩሳሌምን በሙሉ፣ መኳንንቱን በሙሉ፣+ ኃያላን ተዋጊዎቹን ሁሉ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን*+ በአጠቃላይ 10,000 ሰዎችን በግዞት ወሰደ። በጣም ድሃ ከሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች በስተቀር በዚያ የቀረ አልነበረም።+" +15 በዚህ መንገድ ዮአኪንን+ ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤+ በተጨማሪም የ���ጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ። +"16 ደግሞም የባቢሎን ንጉሥ ኃያላን የሆኑና ለጦርነት የሠለጠኑ ወንዶችን በሙሉ ይኸውም 7,000 ተዋጊዎችን እንዲሁም 1,000 የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን* ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።" +17 ከዚያም የዮአኪንን አጎት ማታንያህን+ በእሱ ምትክ አነገሠው፤ ስሙንም ቀይሮ ሴዴቅያስ+ አለው። +18 ሴዴቅያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 21 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ። እናቱ ሀሙጣል ትባል ነበር፤+ እሷም የሊብና ሰው የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። +19 ኢዮዓቄም እንዳደረገው ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +20 እነዚህ ነገሮች በኢየሩሳሌምና በይሁዳ የተፈጸሙት ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ ነው፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው።+ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዓመፀ።+ +7 ኤልሳዕም እንዲህ አለ፦ “የይሖዋን ቃል ስሙ። ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ነገ በዚህ ሰዓት ገደማ በሰማርያ በር* ላይ አንድ የሲህ መስፈሪያ* የላመ ዱቄት በአንድ ሰቅል* እንዲሁም ሁለት የሲህ መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል ይሸጣል።’”+ +2 በዚህ ጊዜ ንጉሡ የሚተማመንበት የጦር መኮንን የእውነተኛውን አምላክ ሰው “ይሖዋ የሰማይን የውኃ በሮች ቢከፍት እንኳ እንዲህ ያለ ነገር* ሊፈጸም ይችላል?”+ አለው። ኤልሳዕም “ይህን በገዛ ዓይኖችህ ታያለህ፤+ ሆኖም ከዚያ ምንም አትቀምስም”+ አለው። +3 በከተማዋ መግቢያ በር ላይ በሥጋ ደዌ የተያዙ አራት ሰዎች ነበሩ፤+ እነሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “እስክንሞት ድረስ እዚህ ቁጭ የምንለው ለምንድን ነው? +4 ‘ወደ ከተማዋ እንግባ’ ብንል ከተማዋ ውስጥ ረሃብ+ ስላለ እዚያ መሞታችን አይቀርም። እዚህም ብንቀመጥ ያው የሚጠብቀን ሞት ነው። ስለዚህ ዝም ብለን ወደ ሶርያውያን ሰፈር እንሂድ። ካልገደሉን ሕይወታችን ይተርፋል፤ ከገደሉንም ያው ሞቶ መገላገል ነው።” +5 ከዚያም ጨለምለም ሲል ተነስተው ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄዱ። ወደ ሶርያውያን ሰፈር ዳርቻ በደረሱ ጊዜ በዚያ አንድም ሰው አልነበረም። +6 ምክንያቱም ይሖዋ የሶርያውያን ሰፈር የጦር ሠረገሎችን ድምፅ፣ የፈረሶችን ድምፅና የታላቅ ሠራዊት ድምፅ እንዲሰማ አድርጎ ነበር።+ በመሆኑም እርስ በርሳቸው “የእስራኤል ንጉሥ እኛን ለመውጋት የሂታውያንንና የግብፅን ነገሥታት ቀጥሮብናል!” ተባባሉ። +7 እነሱም ወዲያውኑ ተነስተው በምሽት ሸሹ፤ ድንኳኖቻቸውን፣ ፈረሶቻቸውንና አህዮቻቸውን እንዲሁም ሰፈሩን እንዳለ ትተው ሕይወታቸውን* ለማዳን እግሬ አውጪኝ አሉ። +8 በሥጋ ደዌ የተያዙት እነዚህ ሰዎች ወደ ሰፈሩ ዳርቻ ከደረሱ በኋላ ወደ አንዱ ድንኳን ገብተው መብላትና መጠጣት ጀመሩ። ከዚያም ብር፣ ወርቅና ልብስ ይዘው በመሄድ ደበቁት። ከዚያም ተመልሰው መጥተው ወደ ሌላ ድንኳን በመግባት የተለያዩ ነገሮችን ወሰዱ፤ እነዚህንም ይዘው በመሄድ ደበቁ። +9 በመጨረሻም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “እያደረግን ያለነው ነገር ትክክል አይደለም። ይህ ቀን እኮ ምሥራች የሚነገርበት ቀን ነው! የምናመነታና እስኪነጋ ድረስ የምንጠብቅ ከሆነ መቀጣታችን አይቀርም። በመሆኑም አሁን ወደ ንጉሡ ቤት ሄደን ይህን ነገር እንናገር።” +10 ስለሆነም ሄደው የከተማዋን በር ጠባቂዎች በመጥራት እንዲህ አሏቸው፦ “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ገብተን ነበር፤ ሆኖም በዚያ አንድም ሰው አልነበረም፤ የአንድም ሰው ድምፅ አልሰማንም። እዚያ የነበሩት የታሰሩ ፈረሶችና አህዮች ብቻ ናቸው፤ ድንኳኖቹም እንዳሉ ነበሩ።” +11 የከተማዋ በር ጠባቂዎችም ወዲያውኑ ይህን አስተጋቡ፤ ወሬውም በንጉሡ ቤት ተሰማ። +12 ንጉሡም ወዲያውኑ በሌሊት ተነስቶ አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ “ሶርያውያን ምን እንዳደረጉብን ልንገራችሁ። እንደተራብን+ ያውቃሉ፤ በመሆኑም ‘እነሱ ከተማዋን ለቀው ይወጣሉ፤ እኛም በሕይወት እንዳሉ እንይዛቸዋለን፤ ወደ ከተማዋም እንገባለን’ በማለት በዱር ለመደበቅ ከሰፈሩ ወጥተው ሄደዋል።”+ +13 ከዚያም ከአገልጋዮቹ አንዱ እንዲህ አለ፦ “የተወሰኑ ሰዎች በከተማዋ ውስጥ ከቀሩት ፈረሶች አምስቱን ይዘው ይሂዱ። እነዚህ ሰዎች እንደሆነ እዚህ ከሚቀረው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የተለየ ምንም አይደርስባቸውም። የሚጠብቃቸው ነገር ቢኖር በዚህ እንዳለቁት እስራኤላውያን መሆን ነው። ስለሆነም እንላካቸውና የ +14 ስለዚህ ሁለት ሠረገሎችን ከፈረሶች ጋር ወሰዱ፤ ንጉሡም “ሄዳችሁ እዩ” በማለት ወደ ሶርያውያን ሰፈር ላካቸው። +15 እነሱም ዮርዳኖስ ድረስ ተከትለዋቸው ሄዱ፤ ሶርያውያን በድንጋጤ ሲሸሹ ጥለዋቸው የሄዱት ልብሶችና ዕቃዎች መንገዱን ሁሉ ሞልተውት ነበር። መልእክተኞቹም ተመልሰው በመምጣት ሁኔታውን ለንጉሡ ነገሩት። +16 ከዚያም ሕዝቡ ወጥቶ የሶርያውያንን ሰፈር በዘበዘ፤ በመሆኑም ይሖዋ በተናገረው መሠረት አንድ የሲህ መስፈሪያ የላመ ዱቄት በአንድ ሰቅል እንዲሁም ሁለት የሲህ መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል ተሸጠ።+ +17 ንጉሡ፣ የሚተማመንበትን የጦር መኮንን የከተማዋ በር ኃላፊ አድርጎ ሾመው፤ ይሁንና ሕዝቡ በሩ ላይ የጦር መኮንኑን ረጋገጠው፤ የእውነተኛው አምላክ ሰው ንጉሡ ወደ እሱ በወረደ ጊዜ በተናገረው መሠረት ሞተ። +18 የእውነተኛው አምላክ ሰው “ነገ በዚህ ሰዓት በሰማርያ በር ላይ ሁለት የሲህ መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል እንዲሁም አንድ የሲህ መስፈሪያ የላመ ዱቄት በአንድ ሰቅል ይሸጣል”+ በማለት ለንጉሡ የተናገረው ነገር ተፈጸመ። +19 የጦር መኮንኑ ግን የእውነተኛውን አምላክ ሰው “ይሖዋ የሰማይን የውኃ በሮች ቢከፍት እንኳ ይህ የተባለው ነገር* ይፈጸማል?” ብሎት ነበር። በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ “ይህን በገዛ ዓይኖችህ ታያለህ፤ ሆኖም ከዚያ ምንም አትቀምስም” ብሎት ነበር። +20 የጦር መኮንኑ፣ ሕዝቡ በሩ ላይ ረጋግጦት ስለሞተ ልክ እንደተባለው ደረሰበት። +12 ኢዩ+ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮዓስ+ ነገሠ፤ እሱም በኢየሩሳሌም ሆኖ 40 ዓመት ገዛ። እናቱ ጺብያ የተባለች የቤርሳቤህ ተወላጅ ነበረች።+ +2 ኢዮዓስ ካህኑ ዮዳሄ ያስተምረው በነበረበት ዘመን ሁሉ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ። +3 ይሁን እንጂ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች+ አልተወገዱም፤ ደግሞም ሕዝቡ አሁንም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ይሠዋ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። +4 ኢዮዓስ ካህናቱን እንዲህ አላቸው፦ “ቅዱስ መባ+ ሆኖ ወደ ይሖዋ ቤት የሚመጣውን ገንዘብ በሙሉ ማለትም እያንዳንዱ ሰው የሚጠበቅበትን ገንዘብ፣+ አንድ ሰው* እንዲከፍል የተተመነበትን ገንዘብና እያንዳንዱ ሰው ልቡ አነሳስቶት ወደ ይሖዋ ቤት የሚያመጣውን ገንዘብ በሙሉ ውሰዱ።+ +5 ካህናቱ በግል ቀርበው ገንዘቡን ከለጋሾቻቸው* ላይ መቀበል ይችላሉ፤ ከዚያም በቤቱ ውስጥ የፈረሰውን* ሁሉ ለመጠገን ይጠቀሙበት።”+ +6 ንጉሥ ኢዮዓስ በነገሠ በ23ኛው ዓመት ካህናቱ በቤቱ ውስጥ የፈረሰውን ነገር ገና አልጠገኑም ነበር።+ +7 በመሆኑም ንጉሥ ኢዮዓስ ካህኑን ዮዳሄንና+ ሌሎቹን ካህናት ጠርቶ “በቤቱ ውስጥ የፈረሰውን ነገር ያልጠገናችሁት ለምንድን ነው? ስለዚህ ገንዘቡ ቤቱን ለማደስ ሥራ ላይ እስካልዋለ ድረስ ከለጋሾች ላይ ከዚህ በላይ ገንዘብ አትቀበሉ” አላቸው።+ +8 በዚህ ጊዜ ካህናቱ ከሕዝቡ ላይ ተጨማ�� ገንዘብ ላለመቀበልና ቤቱን የማደሱን ኃላፊነት ላለመውሰድ ተስማሙ። +9 ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ አንድ ሣጥን+ ወስዶ መክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀ፤ ሣጥኑንም አንድ ሰው ወደ ይሖዋ ቤት ሲገባ በስተ ቀኝ በኩል በሚያገኘው መሠዊያ አጠገብ አስቀመጠው። በር ጠባቂዎች ሆነው የሚያገለግሉት ካህናት ወደ ይሖዋ ቤት የሚመጣውን ገንዘብ በሙሉ እዚያ ይጨምሩት ነበር።+ +10 እነሱም ሣጥኑ ውስጥ ብዙ ገንዘብ መኖሩን በሚያዩበት ጊዜ ሁሉ የንጉሡ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ መጥተው ይሰበስቡታል፤* ከዚያም ወደ ይሖዋ ቤት የመጣውን ገንዘብ ይቆጥሩታል።+ +11 የተቆጠረውን ገንዘብ በይሖዋ ቤት በሚከናወነው ሥራ ላይ ለተሾሙት ሰዎች ይሰጧቸዋል። እነሱ ደግሞ ገንዘቡን በይሖዋ ቤት ለሚሠሩት አናጺዎችና የግንባታ ባለሙያዎች ይከፍሉ ነበር፤+ +12 በተጨማሪም ለግንበኞችና ለድንጋይ ጠራቢዎች ይከፍሉ ነበር። ደግሞም በይሖዋ ቤት ውስጥ የፈረሰውን ለመጠገን የሚውሉ ሳንቃዎችንና ጥርብ ድንጋዮችን ለመግዛት እንዲሁም ቤቱን ለመጠገን የሚያስፈልጉትን ሌሎች ወጪዎች ለመሸፈን ያውሉት ነበር። +13 ይሁን እንጂ ወደ ይሖዋ ቤት ከገባው ገንዘብ ውስጥ ለይሖዋ ቤት የሚሆኑ የብር ገንዳዎችን፣ የእሳት ማጥፊያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳህኖችን፣ መለከቶችን+ አሊያም ማንኛውንም ዓይነት የወርቅ ወይም የብር ዕቃ ለመሥራት የዋለ ገንዘብ አልነበረም።+ +14 ገንዘቡን የሚሰጡት ሥራውን ለሚሠሩት ሰዎች ብቻ ነበር፤ እነሱም በገንዘቡ የይሖዋን ቤት ጠገኑ። +15 ለሠራተኞቹ እንዲከፍሉ ገንዘብ በሚሰጧቸው ሰዎች ላይ ቁጥጥር አያደርጉም ነበር፤ ምክንያቱም ሰዎቹ እምነት የሚጣልባቸው ነበሩ።+ +16 ይሁን እንጂ ለበደል መባዎች+ የሚሰጠው ገንዘብና ለኃጢአት መባዎች የሚሰጠው ገንዘብ የካህናቱ ንብረት+ ስለሆነ ወደ ይሖዋ ቤት እንዲገባ አይደረግም ነበር። +17 የሶርያ ንጉሥ ሃዛኤል+ ጌትን+ ለመውጋት የወጣው በዚህ ጊዜ ነበር፤ እሱም በቁጥጥር ሥር አዋላት፤ ከዚያም በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወሰነ።*+ +18 በዚህ ጊዜ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓስ የይሁዳ ነገሥታት የነበሩት አባቶቹ ኢዮሳፍጥ፣ ኢዮራምና አካዝያስ የቀደሷቸውን ቅዱስ መባዎች ሁሉ፣ የራሱን ቅዱስ መባዎች እንዲሁም በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወስዶ ለሶርያ ንጉሥ ለሃዛኤል ላከለት።+ በመሆኑም ሃዛኤል ኢየሩሳሌምን ከመ +19 የቀረው የኢዮዓስ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +20 ይሁንና አገልጋዮቹ በኢዮዓስ ላይ በማሴር+ ወደ ሲላ ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ላይ በጉብታው+ ቤት* ገደሉት። +21 ኢዮዓስን መትተው የገደሉት፣ አገልጋዮቹ የነበሩት የሺምዓት ልጅ ዮዛካር እና የሾሜር ልጅ የሆዛባድ ነበሩ።+ እነሱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፤ በእሱም ምትክ ልጁ አሜስያስ ነገሠ።+ +1 አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞዓብ+ በእስራኤል ላይ ዓመፀ። +2 በዚህ ወቅት አካዝያስ በሰማርያ በሚገኘው ቤቱ ሰገነት ላይ ካለው ክፍል በርብራቡ ሾልኮ በመውደቁ ጉዳት ደርሶበት ነበር። በመሆኑም “ከደረሰብኝ ጉዳት እድን እንደሆነና እንዳልሆነ ማወቅ እንድችል ሄዳችሁ የኤቅሮንን+ አምላክ ባአልዜቡብን ጠይቁልኝ” በማለት መልእክተኞች ላከ።+ +3 የይሖዋ መልአክ ግን ቲሽባዊውን ኤልያስን*+ እንዲህ አለው፦ “ተነስተህ የሰማርያን ንጉሥ መልእክተኞች ለማግኘት ውጣ፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘የኤቅሮንን አምላክ ባአልዜቡብን ለመጠየቅ የምትሄዱት በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነው?+ +4 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከተኛህበት አልጋ ላይ አትነሳም፤ በእርግጥ ትሞታለህ።”’” ከዚያም ኤልያስ ሄደ። +5 መልእክተኞቹ ወደ እሱ ተመልሰው ሲመጡ አካዝያስ “ለምን ተመልሳችሁ መጣችሁ?” አላቸው። +6 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “እኛን ለማግኘት የመጣ አንድ ሰው ነበር፤ እሱም እንዲህ አለን፦ ‘ሂዱ፣ ወደላካችሁ ንጉሥ ተመልሳችሁ እንዲህ በሉት፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የኤቅሮንን አምላክ ባአልዜቡብን ለመጠየቅ መልእክተኛ የምትልከው በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነው? ስለዚህ ከተኛህበት አልጋ ላይ አትነሳም፤ +7 በዚህ ጊዜ አካዝያስ “እናንተን ለማግኘት የመጣውና ይህን የነገራችሁ ሰው ምን ይመስላል?” ብሎ ጠየቃቸው። +8 እነሱም “ሰውየው ፀጉራም ልብስ የለበሰ+ ሲሆን ወገቡም ላይ የቆዳ ቀበቶ ታጥቋል”+ አሉት። እሱም ወዲያውኑ “ይሄማ ቲሽባዊው ኤልያስ ነው” አለ። +9 ከዚያም ንጉሡ አንድ ሃምሳ አለቃ በሥሩ ካሉት 50 ሰዎች ጋር ላከ። ሃምሳ አለቃው ወደ እሱ ሲወጣ ኤልያስ ተራራው አናት ላይ ተቀምጦ ነበር። ሃምሳ አለቃውም “አንተ የእውነተኛው አምላክ ሰው፣+ ንጉሡ ‘ና ውረድ’ ብሎሃል” አለው። +10 ኤልያስ ግን ሃምሳ አለቃውን “እኔ የአምላክ ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ+ አንተንና ከአንተ ጋር ያሉትን 50 ሰዎች ይብላ” አለው። ከዚያም እሳት ከሰማይ ወርዶ እሱንና 50ዎቹን ሰዎች በላ። +11 በመሆኑም ንጉሡ እንደገና ሌላ ሃምሳ አለቃ በሥሩ ካሉት 50 ሰዎች ጋር ወደ ኤልያስ ላከ። እሱም ሄዶ ኤልያስን “አንተ የእውነተኛው አምላክ ሰው፣ ንጉሡ ‘ና ፈጥነህ ውረድ’ ብሎሃል” አለው። +12 ኤልያስ ግን “እኔ የእውነተኛው አምላክ ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ከአንተ ጋር ያሉትን 50 ሰዎች ይብላ” አላቸው። ከዚያም የአምላክ እሳት ከሰማይ ወርዶ እሱንና 50ዎቹን ሰዎች በላ። +13 ከዚያም ንጉሡ እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ አንድ ሃምሳ አለቃ በሥሩ ካሉት 50 ሰዎች ጋር ላከ። ሆኖም ሦስተኛው ሃምሳ አለቃ ወጥቶ በኤልያስ ፊት በጉልበቱ ተንበርክኮ ሰገደ፤ ሞገስ እንዲያሳየውም እየለመነ እንዲህ አለው፦ “አንተ የእውነተኛው አምላክ ሰው፣ እባክህ የእኔም ሕይወት ሆነ የእነዚህ 50 አገልጋዮ +14 ከዚህ በፊት እሳት ከሰማይ ወርዶ ሁለቱን ሃምሳ አለቆችና አብረዋቸው የነበሩትን ሃምሳ ሃምሳ ሰዎች በልቷል፤ አሁን ግን ነፍሴ በፊትህ የከበረች ትሁን።” +15 በዚህ ጊዜ የይሖዋ መልአክ ኤልያስን “አብረኸው ውረድ። አትፍራው” አለው። በመሆኑም ኤልያስ ተነስቶ አብሮት ወደ ንጉሡ ወረደ። +16 ከዚያም ኤልያስ ንጉሡን እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የኤቅሮንን+ አምላክ ባአልዜቡብን ለመጠየቅ መልእክተኞች ልከሃል። ይህን ያደረግከው በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነው?+ ለምን የእስራኤልን አምላክ አልጠየቅክም? ስለዚህ ከተኛህበት አልጋ ላይ አትነሳም፤ በእርግጥ ትሞታለህ።’” +17 በመሆኑም ይሖዋ በኤልያስ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት ሞተ፤ አካዝያስ ወንድ ልጅ ስላልነበረው ኢዮራም*+ በምትኩ ነገሠ፤ ይህ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዮራም በነገሠ+ በሁለተኛው ዓመት ነው። +18 የቀረው የአካዝያስ+ ታሪክ፣ ያደረገው ነገር በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም? +8 ኤልሳዕ፣ ልጇን ከሞት ያስነሳላትን+ ሴት “ተነስተሽ ከቤተሰብሽ ጋር የባዕድ አገር ሰው ሆነሽ መኖር ወደምትችዪበት ቦታ ሂጂ፤ ይሖዋ ረሃብ እንደሚከሰት ተናግሯልና፤+ ደግሞም ረሃቡ በምድሪቱ ላይ ለሰባት ዓመት ይቆያል” አላት። +2 በመሆኑም ሴትየዋ ተነስታ የእውነተኛው አምላክ ሰው እንደነገራት አደረገች። እሷም ከመላ ቤተሰቧ ጋር ሄደች፤ በፍልስጤማውያንም+ ምድር ለሰባት ዓመት ተቀመጠች። +3 በሰባቱ ዓመት ማብ��ያ ላይ ሴትየዋ ከፍልስጤማውያን ምድር ተመልሳ መጣች፤ ከዚያም ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ለንጉሡ አቤቱታ ለማቅረብ ሄደች። +4 በዚህ ጊዜ ንጉሡ የእውነተኛው አምላክ ሰው አገልጋይ የሆነውን ግያዝን “እስቲ ኤልሳዕ ያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች በሙሉ ተርክልኝ” እያለው ነበር።+ +5 እሱም ኤልሳዕ የሞተውን ልጅ እንዴት እንዳስነሳው+ ለንጉሡ እየተረከለት ሳለ ኤልሳዕ ልጇን ከሞት ያስነሳላት ሴት ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ለንጉሡ አቤቱታ ለማቅረብ መጣች።+ ግያዝም ወዲያውኑ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ሴትየዋ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ያስነሳው ልጇም ይሄ ነው” አለው። +6 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ሴትየዋን ጠየቃት፤ እሷም ታሪኩን ነገረችው። ከዚያም ንጉሡ ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ አንዱን “የእሷ የሆነውን በሙሉ እንዲሁም መሬቷን ከለቀቀችበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ መሬቱ ያፈራውን ምርት ሁሉ መልስላት” የሚል መመሪያ በመስጠት መደበላት። +7 የሶርያ ንጉሥ ቤንሃዳድ+ ታሞ ሳለ ኤልሳዕ ወደ ደማስቆ+ መጣ። በመሆኑም “የእውነተኛው አምላክ ሰው+ ወደዚህ መጥቷል” ተብሎ ተነገረው። +8 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ሃዛኤልን+ “ስጦታ ይዘህ ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው+ ሂድ። በእሱም አማካኝነት ይሖዋን ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁ?’ ብለህ ጠይቀው” አለው። +9 ሃዛኤልም በደማስቆ ከሚገኘው ምርጥ ነገር ሁሉ 40 የግመል ጭነት ስጦታ ይዞ ሊያገኘው ሄደ። እሱም መጥቶ በፊቱ በመቆም “ልጅህ የሶርያ ንጉሥ ቤንሃዳድ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁ?’ በማለት ወደ አንተ ልኮኛል” አለው። +10 ኤልሳዕም “ሂድና ‘በእርግጥ ትድናለህ’ በለው፤ ሆኖም መሞቱ እንደማይቀር ይሖዋ አሳይቶኛል”+ ሲል መለሰለት። +11 ደግሞም እስኪያፍር ድረስ ትኩር ብሎ ተመለከተው። ከዚያም የእውነተኛው አምላክ ሰው አለቀሰ። +12 ሃዛኤልም “ጌታዬ የሚያለቅሰው ለምንድን ነው?” በማለት ጠየቀው። እሱም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “በእስራኤል ሕዝብ ላይ ምን ዓይነት ጉዳት እንደምታደርስ ስለማውቅ ነው።+ የተመሸጉ ስፍራዎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ምርጥ የሆኑ ሰዎቻቸውን በሰይፍ ትገድላለህ፤ ልጆቻቸውንም ትፈጠፍጣለህ፤ ነፍሰ ጡር የሆኑ +13 ሃዛኤልም “ለመሆኑ ተራ ውሻ የሆነው አገልጋይህ እንዲህ ያለ ነገር እንዴት ሊያደርግ ይችላል?” አለው። ኤልሳዕ ግን “አንተ በሶርያ ላይ ንጉሥ እንደምትሆን ይሖዋ አሳይቶኛል” አለው።+ +14 ከዚያም ከኤልሳዕ ተለይቶ በመሄድ ወደ ጌታው መጣ፤ ቤንሃዳድም “ለመሆኑ ኤልሳዕ ምን አለህ?” አለው። እሱም “በእርግጥ እንደምትድን ነግሮኛል” ሲል መለሰለት።+ +15 በማግስቱ ግን ሃዛኤል የአልጋ ልብስ ወስዶ ውኃ ውስጥ ከነከረ በኋላ የንጉሡን ፊት ሸፈነው፤ ንጉሡም ሞተ።+ ሃዛኤልም በምትኩ ነገሠ።+ +16 የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም+ በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዮራም ነገሠ፤+ በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ በይሁዳ ንጉሥ ሆኖ ይገዛ ነበር። +17 ኢዮራም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 32 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ስምንት ዓመት ገዛ። +18 የአክዓብን ልጅ አግብቶ+ ስለነበር ከአክዓብ ቤት የሆኑት እንዳደረጉት+ ሁሉ እሱም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤+ በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +19 ሆኖም ይሖዋ ለአገልጋዩ ለዳዊት ሲል ይሁዳን ማጥፋት አልፈለገም፤+ ምክንያቱም ለእሱና ለልጆቹ ለሁልጊዜ የሚኖር መብራት እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር።+ +20 በእሱ ዘመን ኤዶም በይሁዳ ላይ ዓምፆ+ የራሱን ንጉሥ አነገሠ።+ +21 በመሆኑም ኢዮራም ሠረገሎቹን ሁሉ ይዞ ወደ ጻኢር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እሱንና የሠረገሎቹን አዛዦች ከበው የነበሩትን ኤዶማውያን ድል አደረገ፤ ሠራዊቱም ሸሽቶ ወደየድንኳኑ ሄደ። +22 ሆኖም ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው። ሊብናም+ በዚሁ ጊዜ ዓመፀ። +23 የቀረው የኢዮራም ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +24 በመጨረሻም ኢዮራም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ከአባቶቹም ጋር በዳዊት ከተማ ተቀበረ።+ በእሱም ምትክ ልጁ አካዝያስ+ ነገሠ። +25 የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በ12ኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ።+ +26 አካዝያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም ጎቶልያ+ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የኦምሪ+ የልጅ ልጅ* ነበረች። +27 እሱም ከአክዓብ ቤተሰብ ጋር በጋብቻ ተሳስሮ ስለነበር የአክዓብን ቤት መንገድ ተከተለ፤ እንዲሁም የአክዓብ ቤት እንዳደረገው ሁሉ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +28 በመሆኑም አካዝያስ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሆኖ ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል ጋር ለመዋጋት ወደ ራሞትጊልያድ+ ሄደ፤ ሆኖም ሶርያውያን ኢዮራምን አቆሰሉት።+ +29 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል ጋር በተዋጋበት ጊዜ ሶርያውያን በራማ ካቆሰሉት ቁስል ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል+ ተመለሰ።+ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም ቆስሎ* ስለነበር እሱን ለማየት ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። +11 የአካዝያስ እናት ጎቶልያ+ ልጇ መሞቱን+ ባየች ጊዜ ተነስታ የንጉሣውያኑን ቤተሰብ* በሙሉ አጠፋች።+ +2 ይሁንና የአካዝያስ እህት የሆነችው የንጉሥ ኢዮራም ልጅ የሆሼባ ሊገደሉ ከነበሩት የንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮዓስን+ ሰርቃ በመውሰድ እሱንና ሞግዚቱን በውስጠኛው መኝታ ክፍል አስቀመጠቻቸው። እነሱም ጎቶልያ እንዳታየው ደብቀው አቆዩት፤ በመሆኑም ሳይገደል ቀረ። +3 እሱም ከእሷ ጋር ለስድስት ዓመት በይሖዋ ቤት ተደብቆ ቆየ፤ በዚህ ጊዜ ጎቶልያ በምድሪቱ ላይ ትገዛ ነበር። +4 በሰባተኛው ዓመት ዮዳሄ መልእክት ልኮ ካራውያን ጠባቂዎቹንና የቤተ መንግሥቱን ዘቦች* የሚያዙትን መቶ አለቆች+ እሱ ወዳለበት ወደ ይሖዋ ቤት አስመጣ። ከዚያም ከእነሱ ጋር ስምምነት* አደረገ፤ እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ አስማላቸው፤ ይህን ካደረገም በኋላ የንጉሡን ልጅ አሳያቸው።+ +5 እንዲህም ሲል አዘዛቸው፦ “እናንተም እንዲህ ታደርጋላችሁ፦ ከመካከላችሁ አንድ ሦስተኛ የምትሆኑት በሰንበት ቀን ገብታችሁ የንጉሡን ቤት*+ በተጠንቀቅ ትጠብቃላችሁ፤ +6 አንድ ሦስተኛ የምትሆኑት ደግሞ በመሠረት በር ላይ ትሆናላችሁ፤ ሌላው አንድ ሦስተኛ ከቤተ መንግሥቱ ዘቦች ኋላ ባለው በር ላይ ይሆናል። ቤቱን በየተራ ትጠብቃላችሁ። +7 ከመካከላችሁ በሰንበት ቀን ከሥራ ነፃ የሚሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ንጉሡን ከጥቃት ለመከላከል የይሖዋን ቤት በተጠንቀቅ ይጠብቁ። +8 እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ ንጉሡን ዙሪያውን ክበቡት። ረድፉን ጥሶ የገባ ማንኛውም ሰው ይገደላል። ንጉሡ በሚሄድበት ሁሉ* አብራችሁት ሁኑ።” +9 መቶ አለቆቹ+ ልክ ካህኑ ዮዳሄ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እያንዳንዳቸውም በሰንበት ቀን ተረኛ የሚሆኑትንና በሰንበት ቀን ከሥራ ነፃ የሚሆኑትን የራሳቸውን ሰዎች ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ።+ +10 ከዚያም ካህኑ በይሖዋ ቤት የነበሩትን የንጉሥ ዳዊት ጦሮችና ክብ ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው። +11 የቤተ መንግሥቱ ዘቦችም+ እያንዳንዳቸው የጦር መሣሪያቸውን ይዘው በስተ ቀኝ በኩል ካለው የቤቱ ጎን አንስቶ በስተ ግራ በኩል እስካለው የቤቱ ጎን ድረስ በመሠዊያውና+ በቤቱ አጠገብ በንጉሡ ዙሪያ ቆ��። +12 ከዚያም ዮዳሄ የንጉሡን ልጅ+ አውጥቶ አክሊሉን* ጫነበት፤ ምሥክሩንም*+ ሰጠው፤ በዚህም መንገድ አነገሡት፤ ደግሞም ቀቡት። እያጨበጨቡም “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” ይሉ ጀመር።+ +13 ጎቶልያ ሕዝቡ ሲሯሯጥ ስትሰማ ወዲያውኑ በይሖዋ ቤት ወዳለው ሕዝብ መጣች።+ +14 ከዚያም በነበረው ልማድ መሠረት ንጉሡ ዓምዱ አጠገብ ቆሞ አየች።+ አለቆቹና መለከት ነፊዎቹ+ ከንጉሡ ጋር ነበሩ፤ የምድሪቱም ሕዝብ ሁሉ እጅግ እየተደሰተና መለከት እየነፋ ነበር። በዚህ ጊዜ ጎቶልያ ልብሷን ቀዳ “ይህ ሴራ ነው! ሴራ ነው!” በማለት ጮኸች። +15 ካህኑ ዮዳሄ ግን በሠራዊቱ ላይ የተሾሙትን መቶ አለቆች+ “ከረድፉ መካከል አውጧት፤ እሷን ተከትሎ የሚመጣ ሰው ካለ በሰይፍ ግደሉት!” በማለት አዘዛቸው። ካህኑ “በይሖዋ ቤት ውስጥ እንዳትገድሏት” ብሎ ነበር። +16 በመሆኑም ያዟት፤ ፈረሶች ወደ ንጉሡ ቤት*+ የሚገቡበት ቦታ ላይ ስትደርስ ተገደለች። +17 ከዚያም ዮዳሄ የይሖዋ ሕዝብ ሆነው እንዲቀጥሉ ይሖዋ፣ ንጉሡና ሕዝቡ ቃል ኪዳን እንዲጋቡ አደረገ፤+ በተጨማሪም ንጉሡና ሕዝቡ ቃል ኪዳን እንዲጋቡ አደረገ።+ +18 ከዚህም በኋላ የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ወደ ባአል ቤት* መጥቶ መሠዊያዎቹን አፈራረሰ፤+ ምስሎቹንም እንክትክት አድርጎ ሰባበረ፤+ የባአል ካህን የነበረውን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ገደሉት።+ ከዚያም ካህኑ በይሖዋ ቤት ላይ የበላይ ተመልካቾችን ሾመ።+ +19 በተጨማሪም ንጉሡን አጅበው ከይሖዋ ቤት ወደ ታች እንዲያመጡት መቶ አለቆቹን፣+ ካራውያን ጠባቂዎቹን፣ የቤተ መንግሥት ዘቦቹንና+ የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ ሰበሰበ፤ እነሱም ወደ ቤተ መንግሥቱ ዘቦች በር በሚወስደው መንገድ በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጡ።* እሱም በነገሥታቱ ዙፋን ላይ ተቀመጠ።+ +20 በመሆኑም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እጅግ ተደሰተ፤ ጎቶልያንም በንጉሡ ቤት በሰይፍ ስለገደሏት ከተማዋ ጸጥታ ሰፈነባት። +21 ኢዮዓስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር።+ +2 ይሖዋ ኤልያስን+ በአውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ የሚወስድበት ጊዜ ሲደርስ+ ኤልያስና ኤልሳዕ+ ከጊልጋል+ ተነስተው ጉዞ ጀመሩ። +2 ኤልያስም ኤልሳዕን “ይሖዋ ወደ ቤቴል እንድሄድ ስለላከኝ እባክህ አንተ እዚህ ቆይ” አለው። ኤልሳዕ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ* እምላለሁ፣ ከአንተ አልለይም” አለው። በመሆኑም አብረው ወደ ቤቴል+ ወረዱ። +3 ከዚያም በቤቴል የነበሩት የነቢያት ልጆች* ወጥተው ኤልሳዕን “ይሖዋ በአንተ ላይ ራስ የነበረውን ጌታህን ዛሬ ሊወስደው እንደሆነ አውቀሃል?”+ አሉት። እሱም “አዎ፣ አውቄአለሁ። ዝም በሉ” አለ። +4 ኤልያስም “ኤልሳዕ፣ ይሖዋ ወደ ኢያሪኮ+ እንድሄድ ስለላከኝ እባክህ አንተ እዚህ ቆይ” አለው። ኤልሳዕ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ* እምላለሁ፣ ከአንተ አልለይም” አለው። በመሆኑም አብረው ወደ ኢያሪኮ መጡ። +5 ከዚያም በኢያሪኮ የነበሩት የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ቀርበው “ይሖዋ በአንተ ላይ ራስ የነበረውን ጌታህን ዛሬ ሊወስደው እንደሆነ አውቀሃል?” አሉት። እሱም “አዎ፣ አውቄአለሁ። ዝም በሉ” አለ። +6 ኤልያስም ኤልሳዕን “ይሖዋ ወደ ዮርዳኖስ እንድሄድ ስለላከኝ እባክህ አንተ እዚህ ቆይ” አለው። ኤልሳዕ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ* እምላለሁ፣ ከአንተ አልለይም” አለው። በመሆኑም አብረው ሄዱ። +7 ከነቢያት ልጆች መካከል 50ዎቹ ተከትለዋቸው በመሄድ ራቅ ብለው ቆመው ያዩአቸው ነበር፤ በዚህ ጊዜ ሁለቱ ዮርዳኖስ አጠገብ ቆመው ነበር። +8 ከዚያም ኤልያስ የነቢይ ልብሱን+ አውልቆ በመጠቅለል ውኃውን መታው፤ ውኃውም ግራና ቀኝ ተከፈለ፤ ሁለቱም በደረቅ መሬት ተሻገሩ።+ +9 ዮርዳኖስን እንደ��ሻገሩ ኤልያስ ኤልሳዕን “ከአንተ ከመወሰዴ በፊት እንዳደርግልህ የምትፈልገውን ጠይቀኝ” አለው። ኤልሳዕም “እባክህ፣ መንፈስህ+ በእጥፍ* ይሰጠኝ”+ አለው። +10 ኤልያስም “የጠየቅከው አስቸጋሪ ነገር ነው። ከአንተ ስወሰድ ካየኸኝ እንዳልከው ይሆንልሃል፤ አለዚያ ግን አይሆንልህም” አለው። +11 ሁለቱ እየተጨዋወቱ በመሄድ ላይ ሳሉ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች+ ድንገት መጥተው ለያዩአቸው፤ ኤልያስም በአውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ወደ ሰማይ ወጣ።+ +12 ኤልሳዕ ይህን ሲመለከት “አባቴ፣ አባቴ፣ እነሆ የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኞቹ!”+ በማለት ጮኸ። ኤልያስ ከዓይኑ ሲሰወርበትም የራሱን ልብስ ይዞ ለሁለት ቀደደው።+ +13 ከዚያም ከኤልያስ ላይ የወደቀውን የነቢይ ልብስ+ አነሳ፤ ተመልሶም በዮርዳኖስ ዳርቻ ቆመ። +14 እሱም ከኤልያስ ላይ በወደቀው የነቢይ ልብስ ውኃውን መታና እንዲህ አለ፦ “የኤልያስ አምላክ ይሖዋ የት አለ?” ውኃውንም ሲመታው ግራና ቀኝ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።+ +15 በኢያሪኮ የሚኖሩ የነቢያት ልጆች ኤልሳዕን ከሩቅ ሲመለከቱት “የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ አርፏል”+ አሉ። በመሆኑም እሱን ለማግኘት ሄዱ፤ በፊቱም መሬት ላይ ተደፍተው እጅ ነሱት። +16 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “እነሆ፣ ከአገልጋዮችህ ጋር ብቁ የሆኑ 50 ሰዎች አሉ። እባክህ ይሂዱና ጌታህን ይፈልጉት። ምናልባት የይሖዋ መንፈስ* ወደ ላይ አንስቶት ከተራሮቹ በአንዱ ላይ ወይም ከሸለቆዎቹ በአንዱ ውስጥ ጥሎት ይሆናል።”+ እሱ ግን “አትላኳቸው” አላቸው። +17 ሆኖም እነሱ እስኪያፍር ድረስ ወተወቱት፤ እሱም “እሺ፣ ላኳቸው” አለ። እነሱም 50ዎቹን ሰዎች ላኩ፤ ሰዎቹም ለሦስት ቀን ያህል ፈለጉት፤ ሆኖም ሊያገኙት አልቻሉም። +18 ወደ ኤልሳዕ በተመለሱም ጊዜ ኤልሳዕ በኢያሪኮ+ ነበር። እሱም “‘አትሂዱ’ ብያችሁ አልነበረም?” አላቸው። +19 ከጊዜ በኋላም የከተማዋ ሰዎች ኤልሳዕን “ጌታዬ፣ ይኸው እንደምታየው ከተማዋ የምትገኘው ጥሩ ቦታ ላይ ነው፤+ ሆኖም ውኃው መጥፎ ነው፤ ምድሪቱም ፍሬ አትሰጥም”* አሉት። +20 እሱም “አነስ ባለ አዲስ ጎድጓዳ ሳህን ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ” አለ። እነሱም አመጡለት። +21 ከዚያም ውኃው ወደሚመነጭበት ቦታ ሄዶ ጨው ረጨበትና+ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ። ከእንግዲህ ለሞት ምክንያት አይሆንም፤ ምድሪቱንም ፍሬ እንዳትሰጥ* አያደርጋትም’” አለ። +22 ኤልሳዕ በተናገረውም ቃል መሠረት ውኃው እስከ ዛሬ ድረስ እንደተፈወሰ ነው። +23 እሱም ከዚያ ተነስቶ ወደ ቤቴል ወጣ። በዚህ ጊዜ ከከተማዋ የወጡ ልጆች “አንተ መላጣ፣ ውጣ! አንተ መላጣ፣ ውጣ!” እያሉ ያፌዙበት ጀመር።+ +24 በመጨረሻም ዞር ብሎ ተመለከታቸውና በይሖዋ ስም ረገማቸው። ከዚያም ሁለት እንስት ድቦች+ ከጫካው ወጥተው 42 ልጆችን ቦጫጨቁ።+ +25 እሱም ጉዞውን በመቀጠል ወደ ቀርሜሎስ ተራራ+ ሄደ፤ ከዚያ ደግሞ ወደ ሰማርያ ተመለሰ። +4 ከነቢያት ልጆች+ መካከል የአንዱ ሚስት ወደ ኤልሳዕ መጥታ እንዲህ ስትል ጮኸች፦ “አገልጋይህ ባለቤቴ ሞቷል፤ አገልጋይህ ምንጊዜም ይሖዋን የሚፈራ ሰው እንደነበር በሚገባ ታውቃለህ።+ አሁን ግን አንድ አበዳሪ መጥቶ ሁለቱንም ልጆቼን ባሪያዎቹ አድርጎ ሊወስዳቸው ነው።” +2 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ “ታዲያ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? ንገሪኝ፣ ቤት ውስጥ ምን አለሽ?” አላት። እሷም “አገልጋይህ ከአንድ ማሰሮ ዘይት በስተቀር ቤት ውስጥ ምንም ነገር የላትም”+ ብላ መለሰችለት። +3 ከዚያም እንዲህ አላት፦ “እንግዲያው ሂጂና ከጎረቤቶችሽ ሁሉ ባዶ ዕቃዎች ለምኚ። የቻልሽውን ያህል ብዙ ዕቃ ለምኚ። +4 ከዚያም ገብተሽ በሩን በአንቺና በልጆችሽ ላ��� ዝጊው። ዕቃዎቹንም ሁሉ በዘይት ሙዪ፤ የሞሉትንም ለብቻ አስቀምጫቸው።” +5 እሷም ወጥታ ሄደች። በሩን በራሷና በልጆቿ ላይ ከዘጋች በኋላ ልጆቿ ዕቃዎቹን ሲያቀርቡላት እሷ ትቀዳባቸው ጀመር።+ +6 ዕቃዎቹ ሲሞሉ ከልጆቿ መካከል አንዱን “ሌላ ዕቃ አምጣልኝ”+ አለችው። እሱ ግን “የቀረ ዕቃ የለም” አላት። በዚህ ጊዜ ዘይቱ መውረዱን አቆመ።+ +7 እሷም ሄዳ ለእውነተኛው አምላክ ሰው ነገረችው፤ እሱም “ሂጂ፤ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን ክፈዪ፤ የተረፈው ደግሞ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ ይሁን” አላት። +8 አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሹነም+ ሄደ፤ በዚያም አንዲት ታዋቂ ሴት ነበረች፤ እሷም ምግብ እንዲበላ አጥብቃ ለመነችው።+ እሱም በዚያ ባለፈ ቁጥር ምግብ ለመብላት ወደዚያ ጎራ ይል ነበር። +9 በመሆኑም ሴትየዋ ባሏን እንዲህ አለችው፦ “ይህ በየጊዜው በዚህ መንገድ የሚያልፈው ሰው ቅዱስ የአምላክ ሰው እንደሆነ አውቃለሁ። +10 እባክህ በሰገነቱ ላይ ትንሽ ክፍል+ ሠርተን አልጋ፣ ጠረጴዛ፣ ወንበርና መቅረዝ እናስገባለት። ከዚያም ወደ እኛ በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ እዚያ ማረፍ ይችላል።”+ +11 ኤልሳዕም አንድ ቀን ወደዚያ መጣ፤ ጋደም ለማለትም በሰገነቱ ላይ ወዳለው ክፍል ሄደ። +12 ከዚያም አገልጋዩን ግያዝን+ “እስቲ ሹነማዊቷን+ ሴት ጥራት” አለው። እሱም ጠራት፤ እሷም መጥታ ፊቱ ቆመች። +13 ከዚያም ኤልሳዕ ግያዝን እንዲህ አለው፦ “እባክህ እንዲህ በላት፦ ‘እንግዲህ ለእኛ ስትዪ ብዙ ተቸግረሻል።+ ታዲያ ምን እንዲደረግልሽ ትፈልጊያለሽ?+ ንጉሡን ወይም የሠራዊቱን አለቃ የማነጋግርልሽ ነገር አለ?’”+ እሷ ግን “እኔ እኮ የምኖረው በገዛ ወገኖቼ መካከል ነው” ብላ መለሰች። +14 እሱም “ታዲያ ምን ቢደረግላት ይሻላል?” አለ። ግያዝም “ለነገሩማ ሴትየዋ ወንድ ልጅ የላትም፤+ ባሏ ደግሞ አርጅቷል” አለው። +15 ኤልሳዕም ወዲያውኑ “በል ጥራት” አለው። እሱም ጠራት፤ እሷም በራፉ ላይ ቆመች። +16 ከዚያም “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት።+ እሷ ግን “የእውነተኛው አምላክ ሰው ጌታዬ ሆይ፣ ይሄማ አይሆንም! አገልጋይህን መዋሸት እንዳይሆንብህ” አለችው። +17 ይሁንና ሴትየዋ ፀነሰች፤ ኤልሳዕ በነገራትም መሠረት በቀጣዩ ዓመት በዚያው ጊዜ ወንድ ልጅ ወለደች። +18 ልጁም አደገ፤ ከዚያም አንድ ቀን ከአጫጆቹ ጋር ወደነበረው ወደ አባቱ ወጣ። +19 አባቱንም “ራሴን! ወይኔ ራሴን!” አለው። ከዚያም አባቱ አገልጋዩን “ተሸክመህ ወደ እናቱ ውሰደው” አለው። +20 እሱም ተሸክሞ ወደ እናቱ ወሰደው፤ ልጁም እስከ እኩለ ቀን ድረስ እናቱ ጭን ላይ ተቀመጠ፤ ከዚያም ሞተ።+ +21 እሷም ወደ ላይ ወጥታ ልጁን በእውነተኛው አምላክ ሰው አልጋ+ ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታ ሄደች። +22 ባሏንም ጠርታ “እባክህ አንድ አገልጋይና አንድ አህያ ላክልኝና ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው በፍጥነት ደርሼ ልመለስ” አለችው። +23 እሱ ግን “ዛሬ ወደ እሱ መሄድ ለምን አስፈለገሽ? አዲስ ጨረቃ+ ወይም ሰንበት አይደለም” አላት። እሷ ግን “ግድ የለም፣ ደርሼ ልምጣ” አለችው። +24 ስለዚህ አህያዋን ከጫነች በኋላ አገልጋይዋን “ቶሎ ቶሎ ሂድ። እኔ ቀስ በል እስካላልኩህ ድረስ ለእኔ ብለህ ፍጥነትህን እንዳትቀንስ” አለችው። +25 በመሆኑም በቀርሜሎስ ተራራ ወደሚገኘው ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው ሄደች። የእውነተኛውም አምላክ ሰው ከሩቅ እንዳያት አገልጋዩን ግያዝን እንዲህ አለው፦ “ተመልከት! ሹነማዊቷ ሴት ያቻትና። +26 እባክህ ሮጠህ ወደ እሷ ሂድና ‘ምነው፣ ደህና አይደለሽም? ባልሽ ደህና አይደለም እንዴ? ልጁስ ደህና አይደለም?’ በላት።” እሷም “ሁሉም ነገር ደህና ነው” አለች። +27 ተራራው ላይ ���ዳለው ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው እንደደረሰች እግሩ ላይ ተጠመጠመች።+ በዚህ ጊዜ ግያዝ ሊያስለቅቃት ሲመጣ የእውነተኛው አምላክ ሰው “ተዋት፣ እጅግ ተጨንቃለች፤* ይሖዋም ነገሩን ከእኔ ደብቆታል፤ የነገረኝ ነገር የለም” አለው። +28 እሷም “ለመሆኑ ጌታዬ ልጅ እንዲሰጠኝ ጠይቄ ነበር? ደግሞስ ‘የማይሆን ተስፋ አትስጠኝ’ አላልኩም?” አለችው።+ +29 እሱም ወዲያውኑ ግያዝን “ልብስህን ወገብህ ላይ ታጠቅ፤+ በትሬን ያዝና ሩጥ። መንገድ ላይ ሰው ብታገኝ ሰላም አትበል፤ ማንም ሰው ሰላም ቢልህም መልስ አትስጠው። ሂድና በትሬን በልጁ ፊት ላይ አድርገው” አለው። +30 በዚህ ጊዜ የልጁ እናት “ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ* እምላለሁ፣ ፈጽሞ ትቼህ አልሄድም” አለችው።+ ስለሆነም ተነስቶ አብሯት ሄደ። +31 ግያዝ ቀድሟቸው በመሄድ በትሩን በልጁ ፊት ላይ አደረገው፤ ሆኖም ድምፅም ሆነ ምላሽ አልነበረም።+ እሱም ወደ ኤልሳዕ ተመልሶ በመምጣት “ልጁ አልነቃም” አለው። +32 ኤልሳዕ ወደ ቤት ሲገባ ልጁ ሞቶ በእሱ አልጋ ላይ ተጋድሞ አገኘው።+ +33 ከዚያም ወደ ውስጥ ገብቶ በሩን በራሱና በልጁ ላይ ከዘጋ በኋላ ወደ ይሖዋ መጸለይ ጀመረ።+ +34 ከዚያም አልጋው ላይ ወጥቶ ልጁ ላይ በመተኛት አፉን በአፉ፣ ዓይኑን በዓይኑ እንዲሁም መዳፉን በመዳፉ ላይ አድርጎ ላዩ ላይ ተደፋበት፤ የልጁም ሰውነት መሞቅ ጀመረ።+ +35 ኤልሳዕ ተነስቶ ቤቱ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይል ጀመር፤ ደግሞም እንደገና አልጋው ላይ ወጥቶ ላዩ ላይ ተደፋበት። ልጁም ሰባት ጊዜ ካስነጠሰው በኋላ ዓይኖቹን ገለጠ።+ +36 ኤልሳዕም ግያዝን ጠርቶ “ሹነማዊቷን ሴት ጥራት” አለው። እሱም ጠራት፤ እሷም ወደ እሱ ገባች። ከዚያም ኤልሳዕ “ልጅሽን አንሺው” አላት።+ +37 እሷም ገብታ እግሩ ሥር በመውደቅ ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ ነሳች፤ ልጇንም አንስታ ወጣች። +38 ኤልሳዕ ወደ ጊልጋል ሲመለስ በምድሪቱ ላይ ረሃብ ነበር።+ የነቢያት ልጆች+ በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ አገልጋዩንም+ “ትልቁን ድስት ጣደውና ለነቢያት ልጆች ወጥ ሥራላቸው” አለው። +39 አንድ ሰው ቅጠላ ቅጠል ለማምጣት ወደ ሜዳ ወጣ፤ እሱም ዱር በቀል ሐረግ አገኘ፤ ከሐረጉም ላይ የዱር ቅል ለቅሞ በልብሱ ሙሉ ይዞ ተመለሰ። ከዚያም ምንነታቸውን ሳያውቅ ከትፎ ድስቱ ውስጥ ጨመራቸው። +40 በኋላም ሰዎቹ እንዲበሉ አቀረቡላቸው፤ እነሱ ግን ወጡን ገና እንደቀመሱት “የእውነተኛው አምላክ ሰው ሆይ፣ ድስቱ ውስጥ ገዳይ መርዝ አለ” ብለው ጮኹ። ሊበሉትም አልቻሉም። +41 እሱም “ዱቄት አምጡልኝ” አለ። ዱቄቱንም ድስቱ ውስጥ ከጨመረው በኋላ “ለሰዎቹ አቅርቡላቸው” አለ። በድስቱም ውስጥ ጉዳት የሚያስከትል ምንም ነገር አልተገኘም።+ +42 ከበዓልሻሊሻ+ የመጣ አንድ ሰው ነበር፤ እሱም ለእውነተኛው አምላክ ሰው ከፍሬው በኩራት የተዘጋጁ 20 የገብስ ዳቦዎችና+ አንድ ከረጢት የእሸት ዛላዎች ይዞለት መጣ።+ ከዚያም ኤልሳዕ “ሰዎቹ እንዲበሉ ስጣቸው” አለው። +43 ሆኖም አገልጋዩ “ይህን እንዴት አድርጌ ለ100 ሰው አቀርባለሁ”+ አለው። በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ “ሰዎቹ እንዲበሉ ስጣቸው፤ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ይበላሉ፤ ደግሞም ይተርፋቸዋል’”+ አለው። +44 ከዚያም አቀረበላቸው፤ እነሱም በሉ፤ ይሖዋም በተናገረው መሠረት ተረፋቸው።+ +16 የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ በነገሠ በ17ኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓታም ልጅ አካዝ+ ነገሠ። +2 አካዝ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 20 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በአምላኩ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አላደረገም።+ +3 ከዚህ ይልቅ የእስራኤልን ነገሥታት መንገድ ተከተለ፤+ ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሙ የነበረውን አስጸያፊ ድርጊት በመከተል+ የገዛ ልጁን እንኳ ሳይቀር ለእሳት አሳልፎ ሰጠ።+ +4 ደግሞም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች፣+ በኮረብቶቹና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ ሥር+ ይሠዋ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። +5 የሶርያ ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የሆነው የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ የመጡት በዚህ ጊዜ ነበር።+ አካዝንም ከበቡት፤ ሆኖም ከተማዋን መያዝ አልቻሉም። +6 በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ረጺን አይሁዳውያንን* ከኤላት+ ካባረረ በኋላ ኤላትን ለኤዶም መለሰ። ኤዶማውያንም ወደ ኤላት ገቡ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይኖራሉ። +7 በመሆኑም አካዝ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር+ መልእክተኞች ልኮ “እኔ አገልጋይህና ልጅህ ነኝ። መጥተህ በእኔ ላይ ጥቃት ከሚሰነዝሩት ከሶርያ ንጉሥ እጅና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ” አለው። +8 ከዚያም አካዝ በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች ያለውን ብርና ወርቅ በመውሰድ ለአሦር ንጉሥ ጉቦ ሰጠ።+ +9 የአሦርም ንጉሥ ልመናውን በመስማት ወደ ደማስቆ ወጥቶ ከተማዋን ያዛት፤ ሕዝቧንም ወደ ቂር በግዞት ወሰደ፤+ ረጺንንም ገደለው።+ +10 ከዚያም ንጉሥ አካዝ የአሦርን ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶርን ለማግኘት ወደ ደማስቆ ሄደ። በደማስቆ የነበረውን መሠዊያ ባየ ጊዜ ንጉሥ አካዝ የመሠዊያውን ንድፍና እንዴት እንደተሠራ የሚያሳይ መግለጫ ለካህኑ ለዑሪያህ ላከለት።+ +11 ካህኑ ዑሪያህ+ ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ በላከለት መመሪያ መሠረት መሠዊያውን ሠራ።+ ካህኑ ዑሪያህ ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ ከመመለሱ በፊት ሠርቶ አጠናቀቀ። +12 ንጉሡ ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ መሠዊያውን አየው፤ ወደ መሠዊያውም ቀርቦ በላዩ ላይ መባ አቀረበ።+ +13 እንዲሁም በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መባውና የእህል መባው እንዲጨስ አደረገ፤ የመጠጥ መባውንም አፈሰሰ፤ የኅብረት መሥዋዕቶቹንም ደም ረጨ። +14 ከዚያም በይሖዋ ፊት የነበረውን የመዳብ መሠዊያ+ ከቤቱ ፊት ለፊት ከነበረበት ቦታ ይኸውም እሱ ከሠራው መሠዊያና ከይሖዋ ቤት መሃል አንስቶ ከእሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን አስቀመጠው። +15 ንጉሥ አካዝም ካህኑን ዑሪያህን+ እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ጠዋት ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መባ፣ ማታ ላይ የሚቀርበውን የእህል መባ፣+ የንጉሡን የሚቃጠል መባና የእህል መባ እንዲሁም የሕዝቡን ሁሉ የሚቃጠል መባ፣ የእህል መባና የመጠጥ መባ በታላቁ መሠዊያ ላይ አቅርብ።+ በተጨማሪም የሚቃጠለውን መባ ደ +16 ካህኑ ዑሪያህም ንጉሥ አካዝ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።+ +17 በተጨማሪም ንጉሥ አካዝ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎቹን+ የጎን መከለያዎች ቆራረጠ፤ የውኃ ገንዳዎቹንም ከላያቸው ላይ አነሳ፤+ ባሕሩንም ከተቀመጠበት የመዳብ በሬዎች+ ላይ አውርዶ በድንጋይ ንጣፍ ላይ አስቀመጠው።+ +18 እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ ሠርተውት የነበረውን ለሰንበት ቀን የሚያገለግለውን መጠለያና በውጭ ያለውን የንጉሡን መግቢያ በአሦር ንጉሥ የተነሳ ወደ ሌላ ቦታ ወሰደው። +19 የቀረው የአካዝ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?+ +20 በመጨረሻም አካዝ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ሕዝቅያስ*+ ነገሠ። +6 የነቢያት ልጆች+ ኤልሳዕን እንዲህ አሉት፦ “ይኸው እንደምታየው አብረንህ የምንኖርበት ስፍራ በጣም ጠቦናል። +2 እባክህ ወደ ዮርዳኖስ እንሂድ። እያንዳንዳችን ከዚያ እንጨት እንቁረጥ፤ በዚያም የምንቀመጥበት መኖሪያ እንሥራ።” እሱም “እሺ ሂዱ” አላቸው። +3 ከመካከላቸው አንዱ “አንተስ ከአገልጋ��ችህ ጋር ለመሄድ ፈቃደኛ ነህ?” አለው። እሱም “እሺ እሄዳለሁ” አለ። +4 ስለዚህ አብሯቸው ሄደ፤ ወደ ዮርዳኖስም መጥተው ዛፍ መቁረጥ ጀመሩ። +5 ከእነሱ አንዱ ዛፍ እየቆረጠ ሳለ የመጥረቢያው አናት ወልቆ ውኃው ውስጥ ወደቀ። ሰውየውም “ወየው ጌታዬ፣ ተውሼ ያመጣሁት መጥረቢያ እኮ ነው!” በማለት ጮኸ። +6 የእውነተኛው አምላክ ሰውም “የት ነው የወደቀው?” አለው። ሰውየውም ቦታውን አሳየው። እሱም እንጨት ቆርጦ ውኃው ውስጥ በመጣል የመጥረቢያው አናት እንዲንሳፈፍ አደረገ። +7 ከዚያም “በል አውጣው” አለው። ሰውየውም እጁን ዘርግቶ ወሰደው። +8 በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ እስራኤልን ለመውጋት ዘምቶ ነበር።+ ከአገልጋዮቹ ጋር ከተማከረ በኋላ “እዚህ እዚህ ቦታ አብሬያችሁ እሰፍራለሁ” አለ። +9 ከዚያም የእውነተኛው አምላክ ሰው+ “ሶርያውያን በዚህ እየወረዱ ስለሆነ በዚህ በኩል እንዳታልፍ ተጠንቀቅ” በማለት ወደ እስራኤል ንጉሥ መልእክት ላከ። +10 የእስራኤልም ንጉሥ፣ የእውነተኛው አምላክ ሰው እንዳይሄድ ወዳስጠነቀቀው ስፍራ መልእክት ላከ። በዚህ መንገድ ኤልሳዕ ንጉሡን በተደጋጋሚ ጊዜ* ያስጠነቅቀው የነበረ ሲሆን ንጉሡም ከዚያ አካባቢ ይርቅ ነበር።+ +11 ይህ ጉዳይ የሶርያን ንጉሥ* እጅግ አበሳጨው፤ በመሆኑም አገልጋዮቹን ጠርቶ “ከመካከላችን ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የወገነ ካለ ንገሩኝ!” አላቸው። +12 ከዚያም ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱ “ንጉሡ ጌታዬ ሆይ፣ ኧረ ማንም የለም! አንተ መኝታ ቤትህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን ነገር ለእስራኤል ንጉሥ የሚነግረው በእስራኤል ያለው ነቢዩ ኤልሳዕ ነው”+ አለው። +13 ንጉሡም “በሉ ሰዎች ልኬ እንዳስይዘው ሄዳችሁ የት እንደሚገኝ አጣሩ” አላቸው። በኋላም “ዶታን+ ነው ያለው” የሚል ወሬ ደረሰው። +14 እሱም ወዲያውኑ ፈረሶችን፣ የጦር ሠረገሎችንና ብዙ ሠራዊት ወደዚያ ላከ፤ እነሱም በሌሊት መጥተው ከተማዋን ከበቡ። +15 የእውነተኛው አምላክ ሰው አገልጋይ በማለዳ ተነስቶ ወደ ውጭ ሲወጣ በፈረሶችና በጦር ሠረገሎች የተጠናከረ ሠራዊት ከተማዋን መክበቡን አየ። አገልጋዩም ወዲያውኑ “ወየው ጌታዬ! ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለ። +16 ኤልሳዕ ግን “አይዞህ፣ አትፍራ!+ ከእነሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ”+ አለው። +17 ከዚያም ኤልሳዕ “ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን ክፈትለት”+ በማለት ጸለየ። ይሖዋም ወዲያውኑ የአገልጋዩን ዓይኖች ከፈተ፤ እሱም አየ፤ እነሆ የእሳት ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች+ በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራማውን አካባቢ ሞልተውት ነበር።+ +18 ሶርያውያኑ ወደ ኤልሳዕ መውረድ ሲጀምሩ ኤልሳዕ “እባክህ፣ ይህን ሕዝብ አሳውረው”+ በማለት ወደ ይሖዋ ጸለየ። እሱም ኤልሳዕ በጠየቀው መሠረት አሳወራቸው። +19 ኤልሳዕም “መንገዱ ይሄ አይደለም፤ ከተማዋም ይህች አይደለችም። ወደምትፈልጉት ሰው መርቼ እንዳደርሳችሁ እኔን ተከተሉኝ” አላቸው። ይሁን እንጂ ኤልሳዕ የወሰዳቸው ወደ ሰማርያ+ ነበር። +20 እነሱም ሰማርያ ሲደርሱ ኤልሳዕ “ይሖዋ ሆይ፣ እንዲያዩ ዓይኖቻቸውን ክፈት” አለ። ስለዚህ ይሖዋ ዓይኖቻቸውን ከፈተላቸው፤ እነሱም ሰማርያ ውስጥ መሆናቸውን አዩ። +21 የእስራኤል ንጉሥ ባያቸው ጊዜ ኤልሳዕን “አባቴ ሆይ፣ ልግደላቸው? ልፍጃቸው?” አለው። +22 እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “አትግደላቸው። ለመሆኑ በሰይፍህ ወይም በቀስትህ ማርከህ የወሰድካቸውን ሰዎች ትገድላለህ? በል አሁን እንዲበሉና እንዲጠጡ ምግብና ውኃ ስጣቸው፤+ ከዚያም ወደ ጌታቸው ይመለሱ።” +23 በመሆኑም ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡም፤ ከዚያም ወደ ጌታቸው እንዲመለሱ አሰናበታቸው። ከዚያ በኋላ የሶርያ��ያን+ ወራሪ ቡድን ወደ እስራኤል ምድር ተመልሶ አልመጣም። +24 ከጊዜ በኋላ የሶርያ ንጉሥ ቤንሃዳድ ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ በመውጣት ሰማርያን ከበበ።+ +25 በመሆኑም በሰማርያ ታላቅ ረሃብ ተከሰተ፤+ ከተማዋን ከበው በነበረበት ጊዜም አንድ የአህያ ጭንቅላት+ 80 የብር ሰቅል እንዲሁም አንድ አራተኛ የቃብ መስፈሪያ* የርግብ ኩስ 5 የብር ሰቅል እስኪያወጣ ድረስ ረሃቡ ጸንቶ ነበር። +26 የእስራኤል ንጉሥ በቅጥሩ ላይ ሲያልፍ አንዲት ሴት “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እርዳን!” በማለት ወደ እሱ ጮኸች። +27 ንጉሡም “ይሖዋ ካልረዳሽ እኔ ከየት አምጥቼ ልረዳሽ እችላለሁ? ከአውድማው ነው ወይስ ከወይኑ ወይስ ከዘይት መጭመቂያው?” አላት። +28 ከዚያም “ለመሆኑ ችግርሽ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት። እሷም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “ይህች ሴት ‘ዛሬ የአንቺን ልጅ እንድንበላው አምጪው፤ ነገ ደግሞ የእኔን ልጅ እንበላለን’ አለችኝ።+ +29 በመሆኑም ልጄን ቀቅለን በላነው።+ በማግስቱ ‘የአንቺን ልጅ እንድንበላው አምጪው’ አልኳት። እሷ ግን ልጇን ደበቀችው።” +30 ንጉሡ ሴትየዋ ያለችውን ሲሰማ ልብሱን ቀደደ።+ በቅጥሩም ላይ በሚያልፍበት ጊዜ ሕዝቡ ንጉሡ ከልብሶቹ ሥር ማቅ መልበሱን አየ። +31 ከዚያም “የሻፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ጭንቅላት ዛሬ አንገቱ ላይ ካደረ አምላክ እንዲህ ያድርግብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጣብኝ!” አለ።+ +32 ኤልሳዕ ቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ ሽማግሌዎቹም አብረውት ተቀምጠው ነበር። ንጉሡ አንድ ሰው ከፊቱ አስቀድሞ ላከ፤ ሆኖም መልእክተኛው ከመድረሱ በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “ይህ የነፍሰ ገዳይ ልጅ+ ጭንቅላቴን ሊያስቆርጥ ሰው እንደላከ ታያላችሁ? በሉ መልእክተኛው ሲመጣ በሩን ዝጉት፤ ደ +33 እሱም ገና ከእነሱ ጋር እየተነጋገረ ሳለ መልእክተኛው ወደ እሱ ደረሰ፤ ንጉሡም “ይህ ከይሖዋ የመጣ ጥፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ይሖዋን ለምን እጠብቃለሁ?” አለ። +25 ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ ሠራዊቱን ሁሉ አስከትሎ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ።+ በዙሪያዋም ሰፈረ፤ ደግሞም በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ቆለለ፤+ +2 ከተማዋም እስከ ንጉሥ ሴዴቅያስ 11ኛ ዓመት ድረስ ተከበበች። +3 በአራተኛው ወር፣ ዘጠነኛ ቀን በከተማዋ ውስጥ ረሃቡ እጅግ ከፋ፤+ በምድሪቱ የሚኖሩትም ሰዎች የሚላስ የሚቀመስ አጡ።+ +4 የከተማዋ ቅጥር ተደረመሰ፤+ ከለዳውያን ከተማዋን ከበው ሳለም ወታደሮቹ ሁሉ በንጉሡ የአትክልት ቦታ አቅራቢያ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ወጥተው ሸሹ፤ ንጉሡም ወደ አረባ በሚወስደው መንገድ ሄደ።+ +5 ይሁንና የከለዳውያን ሠራዊት ንጉሡን አሳደደ፤ እሱንም በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት፤ ወታደሮቹም ሁሉ ጥለውት ተበታተኑ። +6 ከዚያም ንጉሡን ይዘው+ በሪብላ ወደነበረው የባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ ደግሞም ፈረዱበት። +7 የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አረዷቸው፤ ከዚያም ናቡከደነጾር የሴዴቅያስን ዓይን አሳወረ፤ በመዳብ የእግር ብረት አስሮም ወደ ባቢሎን ወሰደው።+ +8 በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በሰባተኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ናቡከደነጾር በነገሠ በ19ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃና የባቢሎን ንጉሥ አገልጋይ የሆነው ናቡዛራዳን+ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።+ +9 እሱም የይሖዋን ቤት፣+ የንጉሡን ቤትና*+ በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ የታዋቂ ሰዎችንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አጋየ።+ +10 ከዘቦቹ አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር አፈረሰ።+ +11 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን በከተማዋ የ���ሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎች፣ ከድተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የሄዱትን ሰዎችና የቀረውን ሕዝብ በግዞት ወሰደ።+ +12 ሆኖም የዘቦቹ አለቃ በምድሪቱ ከነበሩት ያጡ የነጡ ድሆች መካከል አንዳንዶቹ የወይን አትክልት ሠራተኞች ሆነው እንዲያገለግሉና የግዳጅ አገልግሎት እንዲሰጡ እዚያው ተዋቸው።+ +13 ከለዳውያኑም የይሖዋን ቤት የመዳብ ዓምዶች+ እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ የነበሩትን የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችና+ የመዳብ ባሕር+ ሰባብረው መዳቡን ወደ ባቢሎን አጋዙ።+ +14 በተጨማሪም አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ የእሳት ማጥፊያዎቹን፣ ጽዋዎቹንና ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉትን የመዳብ ዕቃዎች ሁሉ ወሰዱ። +15 የዘቦቹ አለቃ ከንጹሕ ወርቅና ብር የተሠሩትን መኮስተሪያዎችና ጎድጓዳ ሳህኖች ወሰደ።+ +16 ንጉሥ ሰለሞን ለይሖዋ ቤት ያሠራቸው ሁለቱ ዓምዶች፣ ባሕሩና የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎቹ የተሠሩበት መዳብ ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የሚችል አልነበረም።+ +17 የእያንዳንዱ ዓምድ ቁመት 18 ክንድ* ነበር፤+ በዓምዱ አናት ላይ ያለው ጌጥ ከመዳብ የተሠራ ሲሆን የጌጡ ርዝማኔ ሦስት ክንድ ነበር፤ በጌጡ ዙሪያ ያሉት ሮማኖችና መረቡ በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ።+ ሁለተኛው ዓምድና መረቡም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነበር። +18 በተጨማሪም የዘቦቹ አለቃ የካህናት አለቃ የሆነውን ሰራያህን፣+ ሁለተኛውን ካህን ሶፎንያስንና+ ሦስቱን የበር ጠባቂዎች ወሰዳቸው።+ +19 ደግሞም ከከተማዋ የወታደሮቹ ኃላፊ የሆነን አንድ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን፣ በከተማዋ ውስጥ የነበሩትን አምስቱን የንጉሡ የቅርብ ሰዎች፣ የምድሪቱን ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ እንዲሁም ከተማዋ ውስጥ የተገኙትን በምድሪቱ የሚኖሩ 60 ተራ ሰዎች ወሰደ። +20 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ እነዚህን ሰዎች ይዞ በሪብላ ወዳለው ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጣቸው።+ +21 የባቢሎን ንጉሥ በሃማት+ ምድር ባለችው በሪብላ ሰዎቹን መትቶ ገደላቸው። በዚህ መንገድ ይሁዳ ከምድሩ በግዞት ተወሰደ።+ +22 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በይሁዳ ምድር በተዋቸው ሰዎች ላይ የሳፋን+ ልጅ፣ የአኪቃም+ ልጅ የሆነውን ጎዶልያስን+ አለቃ አድርጎ ሾመው።+ +23 የሠራዊቱ አለቆች በሙሉና አብረዋቸው ያሉት ሰዎች የባቢሎን ንጉሥ ጎዶልያስን አለቃ አድርጎ እንደሾመው ሲሰሙ ወዲያውኑ በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም የነታንያህ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ የነጦፋዊው የታንሁመት ልጅ ሰራያህና የማአካታዊው ልጅ ያአዛንያህ እንዲሁም አብረዋቸው የ +24 ጎዶልያስ ለእነሱና አብረዋቸው ለነበሩት ሰዎች “የከለዳውያን አገልጋይ መሆን አያስፈራችሁ። በምድሪቱ ላይ ኑሩ፤ የባቢሎንንም ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካምም ይሆንላችኋል”+ ሲል ማለላቸው። +25 በሰባተኛውም ወር፣ ከንጉሣውያን ቤተሰብ* የሆነው የኤሊሻማ ልጅ፣ የነታንያህ ልጅ እስማኤል+ ከሌሎች አሥር ሰዎች ጋር መጣ፤ እነሱም ጎዶልያስን መቱት፤ እሱም በምጽጳ አብረውት ከነበሩት አይሁዳውያንና ከለዳውያን ጋር ሞተ።+ +26 ከዚያ በኋላ የሠራዊቱን አለቆች ጨምሮ ትልቅ ትንሽ ሳይባል ሕዝቡ ሁሉ ተነስተው ወደ ግብፅ ሄዱ፤+ ከለዳውያንን ፈርተው ነበርና።+ +27 የባቢሎን ንጉሥ ኤዊልሜሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን+ ከእስር ቤት ፈታው፤* ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በግዞት በተወሰደ በ37ኛው ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በ27ኛው ቀን ነበር።+ +28 በርኅራኄም አናገረው፤ ዙፋኑንም በባቢሎን ከእሱ ጋር ከነበሩት ከሌሎች ነገሥታት ዙፋን ይበልጥ ከፍ ከፍ አደረገለት። +29 በመሆኑም ዮአኪን የእስር ቤት ልብሱን አወለቀ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ በቋሚ��ት ከንጉሡ ማዕድ ይመገብ ነበር። +30 ንጉሡም ለዮአኪን በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሳያቋርጥ ቀለቡን በየዕለቱ ይሰጠው ነበር። +10 አክዓብ+ በሰማርያ 70 ወንዶች ልጆች ነበሩት። በመሆኑም ኢዩ ደብዳቤዎች ጽፎ በሰማርያ ወደሚገኙት የኢይዝራኤል መኳንንትና ሽማግሌዎች እንዲሁም ወደ አክዓብ ልጆች ሞግዚቶች* ላከ፤+ መልእክቱ እንዲህ የሚል ነበር፦ +2 “አሁን ይህ ደብዳቤ ሲደርሳችሁ የጌታችሁ ወንዶች ልጆች ከእናንተ ጋር ይሆናሉ፤ እንዲሁም የጦር ሠረገሎች፣ ፈረሶች፣ የተመሸገች ከተማና የጦር መሣሪያ ይኖራችኋል። +3 በመሆኑም ከጌታችሁ ወንዶች ልጆች መካከል የተሻለውንና ብቃት ያለውን* መርጣችሁ በአባቱ ዙፋን ላይ አስቀምጡት። ከዚያም ለጌታችሁ ቤት ተዋጉ።” +4 እነሱ ግን በፍርሃት ተውጠው “ሁለት ነገሥታት በፊቱ ሊቆሙ ካልቻሉ+ እኛ እንዴት ልንቆም እንችላለን?” አሉ። +5 በመሆኑም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ፣* የከተማዋ ገዢ፣ ሽማግሌዎቹና ሞግዚቶቹ “እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን፤ አንተ ያልከንን ሁሉ እናደርጋለን። ማንንም አናነግሥም። አንተ ራስህ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” በማለት ወደ ኢዩ መልእክት ላኩ። +6 ከዚያም ኢዩ “የእኔ ከሆናችሁና እኔን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ከሆናችሁ የጌታችሁን ወንዶች ልጆች ራስ ቆርጣችሁ ነገ በዚህ ሰዓት ወደ ኢይዝራኤል ይዛችሁልኝ ኑ” የሚል ሁለተኛ ደብዳቤ ጻፈላቸው። በዚህ ጊዜ 70ዎቹ የንጉሡ ልጆች አሳዳጊዎቻቸው ከሆኑት ታዋቂ የከተማዋ ሰዎች ጋር ነበሩ። +7 እነሱም ደብዳቤው እንደደረሳቸው 70ዎቹን የንጉሡን ልጆች ወስደው አረዷቸው፤+ ከዚያም ጭንቅላታቸውን በቅርጫቶች ውስጥ አድርገው ወደ ኢይዝራኤል ላኩለት። +8 መልእክተኛውም ገብቶ “የንጉሡን ልጆች ጭንቅላት አምጥተዋል” አለው። እሱም “በከተማዋ መግቢያ በር ላይ ሁለት ቦታ ቆልላችሁ እስከ ጠዋት ድረስ አቆዩአቸው” አለ። +9 ከዚያም ጠዋት ላይ ሲወጣ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ቆሞ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ንጹሐን* ናችሁ። በጌታዬ ላይ ያሴርኩትና የገደልኩት እኔ ነኝ፤+ እነዚህን ሁሉ ግን የገደላቸው ማን ነው? +10 እንግዲህ ይሖዋ በአክዓብ ቤት ላይ ከተናገረው የይሖዋ ቃል አንዱም እንኳ ሳይፈጸም እንደማይቀር* እወቁ፤+ ይሖዋ በአገልጋዩ በኤልያስ አማካኝነት የተናገረውን ቃል ፈጽሟል።”+ +11 በተጨማሪም ኢዩ በኢይዝራኤል ከአክዓብ ቤት የቀሩትን ሁሉ እንዲሁም ታዋቂ የሆኑ ሰዎቹን፣ ወዳጆቹንና ካህናቱን አንድም ሳያስቀር ገደላቸው።+ +12 ከዚያም ተነስቶ ወደ ሰማርያ አቀና። በመንገዱ ላይም የእረኞች ማቆያ ቤት* ይገኝ ነበር። +13 በዚያም ኢዩ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን+ ወንድሞች አገኛቸው፤ እሱም “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲላቸው “እኛ የአካዝያስ ወንድሞች ነን፤ የንጉሡን ልጆችና የንጉሡን እናት* ልጆች ደህንነት ለመጠየቅ እየወረድን ነው” አሉት። +14 እሱም ወዲያውኑ “በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው!” አለ። በመሆኑም በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው፤ በእረኞች ማቆያው ቤት አጠገብ በሚገኘው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ 42ቱን ሰዎች አረዷቸው። ከመካከላቸው አንድም ሰው አላስተረፈም።+ +15 ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ የሬካብን+ ልጅ ኢዮናዳብን+ ወደ እሱ ሲመጣ አገኘው። ኢዩም ሰላምታ ሰጥቶት* “የእኔ ልብ ከልብህ ጋር እንደሆነው ሁሉ የአንተስ ልብ ሙሉ በሙሉ* ከእኔ ጋር ነው?” አለው። ኢዮናዳብም “አዎ ነው” ሲል መለሰለት። ኢዩም “እንደዚያ ከሆነ እጅህን ስጠኝ” አለው። እሱም እጁን ሰጠው፤ +16 ከዚያም “አብረኸኝ ሂድና ይሖዋን የሚቀናቀንን ማንኛውንም ነገር እንደማልታገሥ* እይ”+ አለው። እነሱም በጦር ሠረገላው አብሮት እንዲሄድ አደረጉ። +17 ከዚያም ወደ ሰማርያ መጣ፤ ደግሞም ይሖዋ ለኤልያስ በነገረው ቃል መሠረት+ ኢዩ በሰማርያ የሚገኙትን ከአክዓብ ቤት የቀሩትን በሙሉ ጠራርጎ እስኪያጠፋቸው ድረስ መታቸው።+ +18 በተጨማሪም ኢዩ ሕዝቡን ሁሉ አንድ ላይ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “አክዓብ ባአልን ያመለከው በትንሹ ነው፤+ ኢዩ ግን በላቀ ሁኔታ ያመልከዋል። +19 በመሆኑም የባአልን ነቢያት+ ሁሉ፣ አምላኪዎቹን ሁሉና ካህናቱን+ ሁሉ ጥሩልኝ። ለባአል ታላቅ መሥዋዕት ስለማቀርብ አንድም ሰው እንዳይቀር። የሚቀር ካለ በሕይወት አይኖርም።” ሆኖም ኢዩ ይህን ያለው የባአልን አምላኪዎች ለማጥፋት ተንኮል አስቦ ነው። +20 በመቀጠልም ኢዩ “ለባአል የተቀደሰ ጉባኤ አውጁ”* አለ። እነሱም ይህንኑ አወጁ። +21 ከዚያም ኢዩ በመላው እስራኤል መልእክት ላከ፤ የባአል አምላኪዎችም በሙሉ መጡ። ሳይመጣ የቀረ አንድም ሰው አልነበረም። እነሱም ወደ ባአል ቤት*+ ገቡ፤ የባአልም ቤት ከአፍ እስከ ገደፉ ሞላ። +22 ኢዩም የልብስ ቤቱን ኃላፊ “ለባአል አምላኪዎች ሁሉ ልብስ አውጣላቸው” አለው። እሱም ልብሶቹን አወጣላቸው። +23 ከዚያም ኢዩና የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ+ ወደ ባአል ቤት ገቡ። የባአልንም አምላኪዎች “ከባአል አምላኪዎች በስተቀር አንድም የይሖዋ አምላኪ እዚህ አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ” አላቸው። +24 በመጨረሻም መሥዋዕቶችንና የሚቃጠሉ መባዎችን ለማቅረብ ገቡ። ኢዩም የራሱ የሆኑ 80 ሰዎችን ውጭ አቁሞ “በእጃችሁ አሳልፌ ከምሰጣችሁ ሰዎች መካከል አንድ ሰው ቢያመልጥ የእናንተ ሕይወት በዚያ ሰው ሕይወት* ይተካል” አላቸው። +25 ኢዩም የሚቃጠለውን መባ አቅርቦ እንደጨረሰ ጠባቂዎቹንና* የጦር መኮንኖቹን “ግቡና ጨፍጭፏቸው! አንድም ሰው እንዳያመልጥ!”+ አላቸው። ጠባቂዎቹና የጦር መኮንኖቹም በሰይፍ ጨፈጨፏቸው፤ ሬሳቸውንም ወደ ውጭ ጣሉ፤ እስከ ባአል ቤት ውስጠኛ መቅደስም * ድረስ ዘልቀው ገቡ። +26 ከዚያም የባአልን ቤት የማምለኪያ ዓምዶች+ አውጥተው አንድ በአንድ አቃጠሉ።+ +27 የባአልን የማምለኪያ ዓምድ ፈረካከሱ፤+ የባአልንም ቤት+ በማፈራረስ መጸዳጃ ቦታ እንዲሆን አደረጉ፤ እስከ ዛሬም ድረስ እንደዚያው ነው። +28 በዚህ መንገድ ኢዩ ባአልን ከእስራኤል አስወገደ። +29 ሆኖም የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኃጢአት ይኸውም በቤቴልና በዳን ከነበሩት የወርቅ ጥጆች+ ጋር በተያያዘ እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ያደረገውን ኃጢአት ከመከተል ዞር አላለም። +30 ስለሆነም ይሖዋ ኢዩን “በአክዓብ ቤት ላይ በልቤ ያሰብኩትን+ ሁሉ በመፈጸም በፊቴ መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስላደረግክ ልጆችህ እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ”+ አለው። +31 ኢዩ ግን በሙሉ ልቡ በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ሕግ ይሄድ ዘንድ አልተጠነቀቀም።+ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ካደረጋቸው ኃጢአቶች ዞር አላለም።+ +32 በዚያ ዘመን ይሖዋ የእስራኤልን ግዛት መቆራረስ* ጀመረ። ሃዛኤል በሁሉም የእስራኤል ግዛት ጥቃት ይሰነዝር ነበር፤+ +33 ይህም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን የጊልያድ ምድር ሁሉ ማለትም ጋዳውያን፣ ሮቤላውያንና ምናሴያውያን+ የሚኖሩበትን ምድር እንዲሁም ከአርኖን ሸለቆ* አጠገብ ካለው ከአሮዔር አንስቶ እስከ ጊልያድና እስከ ባሳን+ ድረስ ያለውን አካባቢ ያጠቃልላል። +34 የቀረው የኢዩ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉና ኃያልነቱ ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +35 በመጨረሻም ኢዩ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ እነሱም በሰማርያ ቀበሩት፤ ልጁ ኢዮዓካዝም+ በምትኩ ነገሠ። +36 ኢዩ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ የገዛበት ዘመን ርዝመት* 28 ዓመት ነበር። +14 የእስራ���ል ንጉሥ የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ+ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ ነገሠ። +2 አሜስያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ የሆዓዲን የተባለች የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች።+ +3 እሱም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ባይሆንም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ፈጸመ።+ ሁሉንም ነገር አባቱ ኢዮዓስ እንዳደረገው አደረገ።+ +4 ሆኖም ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር፤+ ሕዝቡ አሁንም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ይሠዋ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።+ +5 እሱም መንግሥቱ በእጁ እንደጸናለት፣ ንጉሥ የነበረውን አባቱን የገደሉትን አገልጋዮቹን+ ገደላቸው። +6 ይሁንና “አባቶች በልጆቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም በአባቶቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ይልቁንም እያንዳንዱ ሰው በገዛ ኃጢአቱ ይገደል”+ በሚለው በሙሴ የሕግ መጽሐፍ ላይ በተጻፈው የይሖዋ ትእዛዝ መሠረት የገዳዮቹን ልጆች አልገደላቸውም። +"7 እሱም 10,000 ኤዶማውያንን+ በጨው ሸለቆ+ መታ፤ ተዋግቶም ሴላን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፤+ እሷም እስከ ዛሬ ድረስ ዮቅተኤል ተብላ ትጠራለች። " +8 ከዚያም አሜስያስ የእስራኤል ንጉሥ ወደሆነው ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮዓካዝ ልጅ ወደ ኢዮዓስ “ና፤ ውጊያ እንግጠም”* በማለት መልእክተኞች ላከ።+ +9 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ደግሞ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ይህን መልእክት ላከ፦ “በሊባኖስ የሚገኘው ኩርንችት በሊባኖስ ወደሚገኘው አርዘ ሊባኖስ ‘ሴት ልጅህን ለወንድ ልጄ ዳርለት’ የሚል መልእክት ላከ። ይሁን እንጂ በሊባኖስ የነበረ አንድ የዱር አውሬ በዚያ ሲያልፍ ያን ኩርንችት ረገጠው። +10 እርግጥ ኤዶምን መተሃል፤+ በመሆኑም ልብህ ታብዮአል። ክብርህን ጠብቀህ አርፈህ ቤትህ* ተቀመጥ። በራስህ ላይ ለምን ጥፋት ትጋብዛለህ? ደግሞስ ራስህንም ሆነ ይሁዳን ለምን ለውድቀት ትዳርጋለህ?” +11 አሜስያስ ግን አልሰማም።+ በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ወጣ፤ እሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ በምትገኘው በቤትሼሜሽ+ ተጋጠሙ።+ +12 ይሁዳ በእስራኤል ድል ተመታ፤ እያንዳንዳቸውም ወደየቤታቸው* ሸሹ። +13 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ የአካዝያስ ልጅ፣ የኢዮዓስ ልጅ የሆነውን የይሁዳን ንጉሥ አሜስያስን ቤትሼሜሽ ላይ ያዘው። ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ እሱም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ ከኤፍሬም በር+ አንስቶ እስከ ማዕዘን በር+ ድረስ አፈረሰ፤ ርዝመቱም 400 ክንድ* ያህል ነበር። +14 በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች የተገኘውን ወርቅ፣ ብርና ዕቃ ሁሉ እንዲሁም የታገቱትን ሰዎች ወሰደ። ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ። +15 የቀረው የኢዮዓስ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮችና ኃያልነቱ እንዲሁም ከይሁዳ ንጉሥ ከአሜስያስ ጋር እንዴት እንደተዋጋ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +16 በመጨረሻም ኢዮዓስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ከእስራኤልም ነገሥታት ጋር በሰማርያ ተቀበረ፤+ ልጁም ኢዮርብዓም*+ በእሱ ምትክ ነገሠ። +17 የእስራኤል ንጉሥ የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ+ ከሞተ በኋላ፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ+ 15 ዓመት ኖረ።+ +18 የቀረው የአሜስያስ ታሪክ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም? +19 ከጊዜ በኋላ ኢየሩሳሌም ውስጥ በእሱ ላይ ሴራ ተጠነሰሰ፤+ እሱም ወደ ለኪሶ ሸሸ፤ እነሱ ግን ተከታትለው እንዲይዙት ሰዎችን ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት። +20 ከዚያም በፈረሶች ላይ ጭነው አመጡት፤ እሱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር በኢየሩሳሌም ተቀበረ።+ +21 ከዚያም የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ በወቅቱ የ16 ዓመት+ ልጅ የነበረውን አዛርያስን*+ ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ምትክ አነገሡት።+ +22 እሱም፣ ንጉሡ* ከአባቶቹ ጋር ካንቀላፋ በኋላ ኤላትን+ መልሶ በመገንባት ወደ ይሁዳ መለሳት።+ +23 የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ በነገሠ በ15ኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ ኢዮርብዓም+ በሰማርያ ነገሠ፤ እሱም 41 ዓመት ገዛ። +24 በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ካደረጋቸው ኃጢአት ሁሉ ዞር አላለም።+ +25 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ የጋትሔፌር+ ነቢይ በሆነው በአሚታይ ልጅ፣ በአገልጋዩ በዮናስ+ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት ከሌቦሃማት*+ አንስቶ እስከ አረባ ባሕር*+ ድረስ ያለውን የእስራኤልን ወሰን አስመለሰ። +26 ይሖዋ በእስራኤል ላይ እየደረሰ ያለውን ከባድ ሥቃይ ተመልክቶ ነበርና።+ በዚያም እስራኤልን ሌላው ቀርቶ ምስኪኑንና ደካማውን የሚረዳ አልነበረም። +27 ሆኖም ይሖዋ የእስራኤልን ስም ከሰማይ በታች ጠራርጎ እንደማያጠፋ ቃል ገብቶ ነበር።+ በመሆኑም በኢዮዓስ ልጅ በኢዮርብዓም አማካኝነት አዳናቸው።+ +28 የቀረው የኢዮርብዓም ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉና ኃያልነቱ እንዲሁም እንዴት እንደተዋጋ ብሎም ደማስቆንና ሃማትን+ ለይሁዳና ለእስራኤል እንዴት እንዳስመለሰ+ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +29 በመጨረሻም ኢዮርብዓም ከአባቶቹ ከእስራኤል ነገሥታት ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ዘካርያስ+ በእሱ ምትክ ነገሠ። +9 ከዚያም ነቢዩ ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ልብስህን በወገብህ ታጠቅና ይህን የዘይት ዕቃ ይዘህ ወደ ራሞትጊልያድ+ በፍጥነት ሂድ። +2 እዚያም ስትደርስ የኒምሺን ልጅ፣ የኢዮሳፍጥን ልጅ ኢዩን+ ፈልገው፤ ከዚያም ገብተህ ከወንድሞቹ መካከል አስነሳውና ወደ ውስጠኛው ክፍል ውሰደው። +3 የዘይቱንም ዕቃ ወስደህ ዘይቱን በራሱ ላይ አፍስ፤ እንዲህም በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ ቀብቼሃለሁ።”’+ ከዚያም በሩን ከፍተህ በፍጥነት ሽሽ።” +4 በመሆኑም የነቢዩ አገልጋይ ወደ ራሞትጊልያድ አቀና። +5 እዚያም ሲደርስ የሠራዊቱ አለቆች ተቀምጠው አገኛቸው። እሱም “አለቃ ሆይ፣ የምነግርህ መልእክት አለኝ” አለ። ኢዩም “ለማናችን ነው?” ሲል ጠየቀው። እሱም “አለቃ ሆይ፣ ለአንተ ነው” አለው። +6 በመሆኑም ኢዩ ተነስቶ ወደ ቤት ገባ፤ አገልጋዩም ዘይቱን በኢዩ ራስ ላይ በማፍሰስ እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን በይሖዋ ሕዝብ፣ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ ቀብቼሃለሁ።+ +7 አንተም የጌታህን የአክዓብን ቤት ትመታለህ፤ እኔም የአገልጋዮቼን የነቢያትን ደምና በኤልዛቤል እጅ የሞቱትን የይሖዋን አገልጋዮች ሁሉ ደም እበቀላለሁ።+ +8 የአክዓብም ቤት በጠቅላላ ይጠፋል፤ ደግሞም በእስራኤል ውስጥ ያለውን ምስኪኑንም ሆነ ደካማውን ጨምሮ ከአክዓብ ቤት ወንድ የተባለውን ሁሉ* ጠራርጌ አጠፋለሁ።+ +9 የአክዓብንም ቤት እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤትና+ እንደ አኪያህ ልጅ እንደ ባኦስ ቤት+ አደርገዋለሁ። +10 ኤልዛቤልን ደግሞ ኢይዝራኤል ውስጥ በሚገኝ የእርሻ ቦታ ውሾች ይበሏታል፤+ የሚቀብራትም አይኖርም።’” ይህን ከተናገረም በኋላ በሩን ከፍቶ ሸሸ።+ +11 ኢዩ ወጥቶ ወደ ጌታው አገልጋዮች ሲሄድ “ሁሉም ነገር ደህና ነው? ይህ እብድ ወደ አንተ የመጣው ለምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። እሱም “መቼም ሰውየውንም ሆነ የሚናገ���ውን ነገር ታውቁታላችሁ” አላቸው። +12 እነሱ ግን “ይሄ እንኳ ትክክል አይደለም! ይልቅስ እውነቱን ንገረን” አሉት። ከዚያም ኢዩ “እንግዲህ የነገረኝ ይህ ነው፤ ደግሞም እንዲህ ብሏል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ ቀብቼሃለሁ።”’”+ +13 በዚህ ጊዜ እያንዳንዳቸው ቶሎ ብለው ልብሳቸውን በማውለቅ ደረጃዎቹ ላይ አነጠፉለት፤+ ቀንደ መለከትም ነፍተው “ኢዩ ነግሦአል!” አሉ።+ +14 ከዚያም የኒምሺ ልጅ፣ የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዩ+ በኢዮራም ላይ አሴረ። ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል+ የተነሳ ከእስራኤል ሁሉ ጋር ሆኖ ራሞትጊልያድን+ እየጠበቀ ነበር። +15 በኋላም ንጉሥ ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል ጋር በተዋጋበት ጊዜ ሶርያውያን ካደረሱበት ቁስል ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል+ ተመለሰ።+ ኢዩም “እንግዲህ ከተስማማችሁ* ወደ ኢይዝራኤል ሄዶ ይህን ወሬ የሚያቀብል ሰው እንዳይኖር ማንም ሰው ከከተማዋ ሾልኮ እንዳይወጣ ጠብቁ” አለ። +16 ከዚያም ኢዩ ሠረገላው ላይ ወጥቶ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ ምክንያቱም ኢዮራም ቆስሎ በዚያ ተኝቶ ነበር፤ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም ኢዮራምን ለመጠየቅ ወደዚያ ወርዶ ነበር። +17 ጠባቂውም በኢይዝራኤል ማማ ላይ ቆሞ ሳለ የኢዩ ሰዎች ግር ብለው ሲመጡ አየ። ወዲያውኑም “ሰዎች ግር ብለው ሲመጡ ይታየኛል” አለ። ኢዮራምም “አንድ ፈረሰኛ ጠርተህ ወደ እነሱ ላክ፤ እሱም ‘የመጣችሁት በሰላም ነው?’ ይበላቸው” አለ። +18 ስለሆነም አንድ ፈረሰኛ ወደ ኢዩ ሄዶ “ንጉሡ ‘የመጣችሁት በሰላም ነው?’ ይላል” አለው። ኢዩ ግን “አንተ ስለ ‘ሰላም’ ምን ይመለከትሃል? ይልቅስ ከኋላዬ ተሰለፍ!” አለው። ጠባቂውም “መልእክተኛው እነሱ ጋ ደርሷል፤ ሆኖም አልተመለሰም” በማለት ተናገረ። +19 በመሆኑም ሁለተኛ ፈረሰኛ ላከ፤ እሱም እነሱ ጋ ሲደርስ “ንጉሡ ‘የመጣችሁት በሰላም ነው?’ ይላል” አለ። ኢዩ ግን “አንተ ስለ ‘ሰላም’ ምን ይመለከትሃል? ይልቅስ ከኋላዬ ተሰለፍ!” አለው። +20 ጠባቂውም “መልእክተኛው እነሱ ጋ ደርሷል፤ ሆኖም አልተመለሰም፤ ሰውየው ሠረገላ አነዳዱ የኒምሺን የልጅ ልጅ* የኢዩን ይመስላል፤ የሚነዳው ልክ እንደ እብድ ነውና” በማለት ተናገረ። +21 ኢዮራምም “ሠረገላዬን አዘጋጁልኝ!” አለ። በመሆኑም የጦር ሠረገላው ተዘጋጀለት፤ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም+ በየራሳቸው የጦር ሠረገላ ሆነው ኢዩን ለመገናኘት ወጡ። በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የእርሻ ቦታ+ ላይ ከእሱ ጋር ተገናኙ። +22 ኢዮራምም ኢዩን እንዳየው “ኢዩ፣ የመጣኸው በሰላም ነው?” አለው። እሱ ግን “የእናትህ የኤልዛቤል+ ምንዝርና መተት+ እያለ ምን ሰላም አለ?” አለው። +23 ኢዮራምም ለመሸሽ ወዲያውኑ ሠረገላውን አዙሮ አካዝያስን “አካዝያስ ተታለናል!” አለው። +24 ኢዩም ቀስቱን አስፈንጥሮ ኢዮራምን በትከሻዎቹ መካከል ወጋው፤ ቀስቱም በልቡ በኩል ወጣ፤ ኢዮራምም እዚያው ጦር ሠረገላው ውስጥ ወደቀ። +25 ኢዩም የጦር መኮንኑን ቢድቃርን እንዲህ አለው፦ “አንስተህ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የእርሻ ቦታ ላይ ጣለው።+ እኔና አንተ በሠረገሎች ሆነን አባቱን አክዓብን እንከተለው በነበረ ጊዜ ይሖዋ ራሱ በእሱ ላይ ይህን ፍርድ እንዳስተላለፈ አስታውስ፦+ +26 ‘“ትናንት የናቡቴን ደምና የልጆቹን ደም እንዳየሁ ሁሉ”+ ይላል ይሖዋ፣ “በዚህ የእርሻ ቦታ ላይ ዋጋህን እከፍልሃለሁ”+ ይላል ይሖዋ።’ በመሆኑም ይሖዋ በተናገረው ቃል መሠረት አንስተህ እርሻው ላይ ጣለው።”+ +27 የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ+ ይህን ሲያይ በአትክልት ቤቱ በኩል ባለው መንገድ ሸሸ። (በኋላም ኢዩ እሱን እያሳደደው “እሱንም ግደሉት!” አለ። እነሱም በይብለአም+ አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ጉር ሽቅብ በሚያስወጣው መንገድ ላይ ሠረገላው ውስጥ እንዳለ አቆሰሉት። እሱ ግን ወደ መጊዶ ሸሸ፤ በዚያም ሞተ። +28 ከዚያም አገልጋዮቹ በሠረገላ ጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዳዊት ከተማ+ ከአባቶቹ ጋር በራሱ መቃብር ቀበሩት። +29 አካዝያስ+ በይሁዳ ላይ የነገሠው የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በ11ኛው ዓመት ነበር።) +30 ከዚያም ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል+ መጣ፤ ኤልዛቤልም+ ይህን ሰማች። በመሆኑም ዓይኖቿን ተኩላና ፀጉሯን አሰማምራ በመስኮት ቁልቁል ትመለከት ጀመር። +31 ኢዩም በቅጥሩ በር በኩል ሲገባ ኤልዛቤል “ጌታውን የገደለው ዚምሪ ምን እንደደረሰበት አታውቅም?” አለችው።+ +32 እሱም ወደ መስኮቱ ቀና ብሎ በመመልከት “ከእኔ ጎን የቆመ ማን ነው? ማን ነው?”+ አለ። ወዲያውኑ ሁለት ወይም ሦስት የሚሆኑ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ቁልቁል ተመለከቱት። +33 እሱም “ወደ ታች ወርውሯት!” አላቸው። እነሱም ወረወሯት፤ ደሟም በግድግዳውና በፈረሶቹ ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በፈረሶቹ ረጋገጣት። +34 ከዚያም ገብቶ በላ፤ ጠጣም። በኋላም “እባካችሁ ይህችን የተረገመች ሴት አንስታችሁ ቅበሯት። ምንም ቢሆን የንጉሥ ልጅ ናት”+ አላቸው። +35 ሊቀብሯት ሲሄዱ ግን ከራስ ቅሏ፣ ከእግሮቿና ከእጆቿ መዳፍ በስተቀር ምኗንም አላገኙም።+ +36 እነሱም ተመልሰው በነገሩት ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ይህ እኮ ይሖዋ በአገልጋዩ በቲሽባዊው በኤልያስ አማካኝነት እንዲህ በማለት የተናገረው ቃል ፍጻሜ ነው፦+ ‘በኢይዝራኤል በሚገኘው የእርሻ ቦታ ውሾች የኤልዛቤልን ሥጋ ይበላሉ።+ +37 ሰዎች “ይህች እኮ ኤልዛቤል ናት” እንዳይሉ የኤልዛቤል በድን በኢይዝራኤል የእርሻ ቦታ ላይ እንደ ፍግ ይሆናል።’” +13 የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስ+ ልጅ ኢዮዓስ+ በነገሠ በ23ኛው ዓመት የኢዩ+ ልጅ ኢዮዓካዝ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በሰማርያም ሆኖ ለ17 ዓመት ገዛ። +2 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ እንዲሁም የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ያደረገውን ኃጢአት መሥራቱን ቀጠለ።+ ከዚያም አልራቀም። +3 በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ+ በእስራኤል ላይ ነደደ፤+ በዘመናቸውም ሁሉ በሶርያ ንጉሥ በሃዛኤል+ እጅና በሃዛኤል ልጅ በቤንሃዳድ+ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። +4 ከጊዜ በኋላ ኢዮዓካዝ የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት ለመነ፤ ይሖዋም ሰማው፤ ምክንያቱም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ ያደረሰውን ጭቆና አይቶ ነበር።+ +5 ስለሆነም ይሖዋ ለእስራኤላውያን ከሶርያውያን እጅ ነፃ የሚያወጣ አዳኝ ሰጣቸው፤+ እስራኤላውያንም እንደቀድሟቸው በየቤታቸው መኖር ጀመሩ።* +6 (እነሱ ግን የኢዮርብዓም ቤት እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ካደረገው ኃጢአት ዞር አላሉም።+ ይህን ኃጢአት መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤* የማምለኪያ ዓምዱም*+ በሰማርያ እንደቆመ ነበር።) +"7 ኢዮዓካዝ የቀረው 50 ፈረሰኞች፣ 10 ሠረገሎችና 10,000 እግረኛ ወታደሮች ብቻ ያሉት ሠራዊት ነበር፤ ምክንያቱም የሶርያ ንጉሥ በአውድማ ላይ እንዳለ እብቅ ረጋግጦ ደምስሷቸው ነበር።+ " +8 የቀረው የኢዮዓካዝ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉና ኃያልነቱ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +9 በመጨረሻም ኢዮዓካዝ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ቀበሩት፤+ ልጁም ኢዮዓስ በምትኩ ነገሠ። +10 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓስ+ በነገሠ በ37ኛው ዓመት የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በሰማርያም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። +11 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሟቸው ካደረጋቸው ኃጢአቶች ሁሉ ዞር አላለም���+ እነዚህን ኃጢአቶች መፈጸሙን* ቀጠለ። +12 የቀረው የኢዮዓስ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉና ኃያልነቱ እንዲሁም ከይሁዳ ንጉሥ ከአሜስያስ ጋር እንዴት እንደተዋጋ+ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +13 በመጨረሻም ኢዮዓስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ኢዮርብዓምም*+ በዙፋኑ ተቀመጠ። ኢዮዓስም ከእስራኤል ነገሥታት ጋር በሰማርያ ተቀበረ።+ +14 ኤልሳዕ+ ለሞት በዳረገው በሽታ ተይዞ በነበረበት ወቅት የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ወደ እሱ ወርዶ “አባቴ፣ አባቴ! የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኞች!”+ በማለት ላዩ ላይ ተደፍቶ አለቀሰ። +15 ኤልሳዕም “በል ደጋንና ቀስቶች አምጣ” አለው። እሱም ደጋንና ቀስቶች አመጣ። +16 ከዚያም ኤልሳዕ የእስራኤልን ንጉሥ “ደጋኑን በእጅህ ያዝ” አለው። ንጉሡም ደጋኑን በእጁ ያዘ፤ በመቀጠልም ኤልሳዕ እጆቹን በንጉሡ እጆች ላይ ጫነ። +17 ከዚያም “በምሥራቅ በኩል ያለውን መስኮት ክፈት” አለው። እሱም ከፈተ። ኤልሳዕም “አስፈንጥር!” አለው። እሱም አስፈነጠረ። ኤልሳዕም “የይሖዋ የድል* ቀስት፤ በሶርያ ላይ የሚወነጨፍ የድል* ቀስት! ሶርያውያንን ድምጥማጣቸውን እስክታጠፋ ድረስ አፌቅ+ ላይ ትመታቸዋለህ”* አለው። +18 ኤልሳዕ በመቀጠል “ቀስቶቹን ያዝ” አለው፤ እሱም ያዘ። ከዚያም የእስራኤልን ንጉሥ “መሬቱን ውጋ” አለው። እሱም መሬቱን ሦስት ጊዜ ወግቶ አቆመ። +19 በዚህ ጊዜ የእውነተኛው አምላክ ሰው በእሱ ላይ ተቆጥቶ እንዲህ አለው፦ “መሬቱን አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መውጋት ነበረብህ! እንደዚያ ብታደርግ ኖሮ ሶርያውያንን ሙሉ በሙሉ ድምጥማጣቸውን ታጠፋ ነበር፤ አሁን ግን ሶርያን የምትመታው ሦስት ጊዜ ብቻ ነው”+ አለው። +20 ከዚያም ኤልሳዕ ሞተ፤ ተቀበረም። በዓመቱ መጀመሪያ* ላይ ወደ ምድሪቱ ዘልቀው የሚገቡ የሞዓባውያን ወራሪ ቡድኖች+ ነበሩ። +21 የተወሰኑ ሰዎች አንድ ሰው ሊቀብሩ ሲሉ ወራሪውን ቡድን ተመለከቱ፤ ስለዚህ ሰውየውን ኤልሳዕ የተቀበረበት ቦታ ውስጥ ወርውረው እየሮጡ ሄዱ። ሰውየውም የኤልሳዕን አፅም በነካ ጊዜ ሕያው ሆነ፤+ በእግሩም ቆመ። +22 የሶርያ ንጉሥ ሃዛኤል+ በኢዮዓካዝ ዘመን ሁሉ እስራኤልን ይጨቁን ነበር።+ +23 ሆኖም ይሖዋ ከአብርሃም፣+ ከይስሐቅና+ ከያዕቆብ+ ጋር ስለገባው ቃል ኪዳን ሲል ሞገስና አሳቢነት አሳያቸው፤ ምሕረትም አደረገላቸው።+ ሊያጠፋቸው አልፈለገም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከፊቱ አላስወገዳቸውም። +24 የሶርያ ንጉሥ ሃዛኤል በሞተ ጊዜ ልጁ ቤንሃዳድ በእሱ ምትክ ነገሠ። +25 ከዚያም የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ፣ ሃዛኤል ከአባቱ ከኢዮዓካዝ ላይ በጦርነት የወሰዳቸውን ከተሞች ከሃዛኤል ልጅ ከቤንሃዳድ አስመለሰ። ኢዮዓስ ሦስት ጊዜ መታው፤*+ የእስራኤልንም ከተሞች መልሶ ያዘ። +5 የሶርያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃ የሆነው ንዕማን በጌታው ፊት የተከበረና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሰው ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ ለሶርያ ድል ያጎናጸፈው* በእሱ አማካኝነት ነበር። ይህ ሰው የሥጋ ደዌ በሽተኛ* ቢሆንም ኃያል ተዋጊ ነበር። +2 ሶርያውያን በአንድ ወቅት ወረራ ሲያካሂዱ ከእስራኤል ምድር አንዲት ትንሽ ልጅ ማርከው ወስደው ነበር፤ እሷም የንዕማን ሚስት አገልጋይ ሆነች። +3 ይህች ልጅ እመቤቷን “ጌታዬ በሰማርያ ወዳለው ነቢይ+ ቢሄድ እኮ ጥሩ ነው! ከሥጋ ደዌው ይፈውሰው ነበር”+ አለቻት። +4 እሱም* ወደ ጌታው ሄዶ ከእስራኤል ምድር የመጣችው ልጅ ያለችውን ነገረው። +"5 የሶርያም ንጉሥ “እንግዲያው ሂድ! እኔም ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እልክለታለሁ” አለ። እሱም አሥር ታላንት* ብር፣ 6,000 ሰቅል ወርቅና አሥር ቅያሪ ልብሶች ይዞ ሄደ።" +6 ���እስራኤልም ንጉሥ “አገልጋዬን ንዕማንን ከሥጋ ደዌው እንድትፈውሰው ከዚህ ደብዳቤ ጋር ወደ አንተ ልኬዋለሁ” የሚለውን ደብዳቤ ሰጠው። +7 የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን እንዳነበበ ልብሱን ቀደደ፤ ከዚያም “ይህን ሰው ከሥጋ ደዌው እንድፈውስ ወደ እኔ የሚልከው እኔ መግደልና ማዳን የምችል አምላክ ሆኜ ነው?+ እንግዲህ ነገር ሲፈልገኝ እዩ” አለ። +8 ይሁንና የእውነተኛው አምላክ ሰው ኤልሳዕ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን እንደቀደደ ሲሰማ ወዲያውኑ “ልብስህን የቀደድከው ለምንድን ነው? በእስራኤል ነቢይ መኖሩን እንዲያውቅ እባክህ ወደ እኔ ላከው”+ የሚል መልእክት ወደ ንጉሡ ላከ። +9 በመሆኑም ንዕማን ፈረሶቹንና የጦር ሠረገሎቹን ይዞ መጣ፤ በኤልሳዕም ቤት ደጃፍ ላይ ቆመ። +10 ሆኖም ኤልሳዕ “ሄደህ ዮርዳኖስ ውስጥ ሰባት ጊዜ+ ታጠብ፤+ ሥጋህም ይፈወሳል፤ ንጹሕም ትሆናለህ” ብሎ እንዲነግረው መልእክተኛ ላከ። +11 በዚህ ጊዜ ንዕማን ተቆጥቶ ለመሄድ ተነሳ፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ እኮ ‘ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የይሖዋን ስም እየጠራ ቁስሉ ያለበትን ቦታ በመዳሰስ ከያዘኝ የሥጋ ደዌ ይፈውሰኛል’ ብዬ አስቤ ነበር። +12 ለዚህ ለዚህማ የደማስቆ+ ወንዞች አባና እና ፋርፋር በእስራኤል ከሚገኙ ውኃዎች ሁሉ የተሻሉ አይደሉም? እነሱ ውስጥ ታጥቤ መንጻት አልችልም ነበር?” ከዚያም በቁጣ ተመልሶ ሄደ። +13 አገልጋዮቹም ቀርበው “አባቴ ሆይ፣ ነቢዩ ያልተለመደ ነገር እንድታደርግ ቢነግርህ ኖሮ አታደርገውም ነበር? ታዲያ ‘ታጠብና ንጻ’ ቢልህ ምኑ ከበደህ?” አሉት። +14 በዚህ ጊዜ ንዕማን የእውነተኛው አምላክ ሰው በነገረው መሠረት ወርዶ ዮርዳኖስ ውስጥ ሰባት ጊዜ ጠለቀ።+ ከዚያም ሥጋው እንደ ትንሽ ልጅ ሥጋ ሆነ፤+ ደግሞም ነጻ።+ +15 ከዚያ በኋላ አጃቢዎቹን አስከትሎ ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው ተመለሰ፤+ በፊቱም ቆሞ “በእስራኤል እንጂ በምድር ላይ በሌላ በየትኛውም ቦታ አምላክ እንደሌለ አሁን አውቄአለሁ።+ እባክህ ከአገልጋይህ ስጦታ* ተቀበል” አለው። +16 እሱ ግን “በማገለግለውና* ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ ምንም ነገር አልቀበልም”+ አለው። ንዕማን እንዲቀበለው ቢወተውተውም ፈቃደኛ አልሆነም። +17 በመጨረሻም ንዕማን እንዲህ አለው፦ “እንግዲያው የማትቀበለኝ ከሆነ፣ አገልጋይህ ከአሁን በኋላ ለይሖዋ እንጂ ለሌሎች አማልክት የሚቃጠል መባም ሆነ መሥዋዕት ስለማያቀርብ እባክህ ለአገልጋይህ ከዚህ ቦታ የሁለት በቅሎ ጭነት አፈር ይሰጠው። +18 ይሁንና ይሖዋ ስለ አንድ ነገር ብቻ አገልጋይህን ይቅር ይበለው፤ ይኸውም ጌታዬ ለመስገድ ወደ ሪሞን ቤት* በሚገባበት ጊዜ ክንዴን ይደገፋል፤ እኔም በሪሞን ቤት መስገዴ አይቀርም። በሪሞን ቤት በምሰግድበት ጊዜ ይሖዋ ይህን ነገር አገልጋይህን ይቅር ይበለው።” +19 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ “በሰላም ሂድ” አለው። ከእሱ ተለይቶ የተወሰነ ርቀት እንደተጓዘ +20 የእውነተኛው አምላክ ሰው+ የኤልሳዕ አገልጋይ የሆነው ግያዝ+ ‘ጌታዬ ሶርያዊው ንዕማን+ ያመጣውን ነገር ሳይቀበለው እንዲሁ አሰናበተው። ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ ተከትዬው ሮጬ የሆነ ነገር እቀበለዋለሁ’ ብሎ አሰበ። +21 ስለዚህ ግያዝ ንዕማንን ተከተለው። ንዕማንም አንድ ሰው በሩጫ እየተከተለው እንዳለ ሲያይ ሰውየውን ለማግኘት ከሠረገላው ላይ ወርዶ “በደህና ነው?” አለው። +22 በዚህ ጊዜ ግያዝ እንዲህ አለው፦ “አዎ፣ በደህና ነው። ጌታዬ ‘ከነቢያት ልጆች መካከል ሁለት ወጣቶች ከተራራማው ከኤፍሬም አካባቢ አሁን ድንገት ወደ እኔ መጡ። ስለሆነም እባክህ አንድ ታላንት ብርና ሁለት ቅያሪ ልብስ ስጣቸው’+ ብዬ እንድነግርህ ልኮኝ ነው።” +23 ንዕማ��ም “እባክህ፣ ሁለት ታላንት ውሰድ” አለው። አጥብቆም ለመነው፤+ ከዚያም ሁለት ታላንት ብር በሁለት ከረጢት ጠቅልሎ እንዲሁም ሁለት ቅያሪ ልብስ ጨምሮ ለሁለቱ አገልጋዮቹ ሰጣቸው፤ እነሱም ተሸክመው ከፊት ከፊቱ ሄዱ። +24 እሱም ኦፌል* በደረሰ ጊዜ ዕቃዎቹን ከእጃቸው ላይ ወስዶ ቤት ውስጥ ካስቀመጠ በኋላ ሰዎቹን አሰናበታቸው። እነሱም ከሄዱ በኋላ +25 ገብቶ ጌታው አጠገብ ቆመ። ኤልሳዕም “ግያዝ፣ ከየት ነው የመጣኸው?” አለው። እሱ ግን “ኧረ አገልጋይህ የትም አልሄደም” አለ።+ +26 ኤልሳዕም እንዲህ አለው፦ “ሰውየው አንተን ለማግኘት ከሠረገላው ላይ ሲወርድ ልቤ በዚያ ከአንተ ጋር አልነበረም? ለመሆኑ ጊዜው ብር ወይም ልብስ፣ የወይራ ወይም የወይን እርሻ፣ በግ ወይም ከብት አሊያም ደግሞ ወንድ ወይም ሴት አገልጋዮች የሚቀበሉበት ነው?+ +27 ስለሆነም የንዕማን የሥጋ ደዌ+ በአንተና በዘርህ ላይ ለዘላለም ይጣበቃል።” ግያዝም በሥጋ ደዌ የተነሳ እንደ በረዶ ነጭ ሆኖ ወዲያውኑ ከፊቱ ወጣ።+ +21 ምናሴ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 12 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ55 ዓመት ገዛ።+ የእናቱ ስም ሄፍጺባ ነበር። +2 እሱም ይሖዋ ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሟቸው የነበሩትን አስጸያፊ ልማዶች በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +3 አባቱ ሕዝቅያስ አስወግዷቸው የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች መልሶ ገነባ፤+ እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለባአል መሠዊያዎችን አቆመ፤+ የማምለኪያ ግንድም* ሠራ።+ ለሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ሰገደ፤ እነሱንም አገለገለ።+ +4 በተጨማሪም ይሖዋ “ስሜን በኢየሩሳሌም አኖራለሁ”+ ብሎ በተናገረለት በይሖዋ ቤት ውስጥ መሠዊያዎችን ሠራ።+ +5 ደግሞም በይሖዋ ቤት በሚገኙት በሁለቱ ግቢዎች+ ውስጥ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ።+ +6 የገዛ ልጁን ለእሳት አሳልፎ ሰጠ፤ አስማተኛና መተተኛም ሆነ፤+ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ቀጠረ።+ ይሖዋን ያስቆጣው ዘንድ በእሱ ፊት በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሠራ። +7 የሠራውንም የማምለኪያ ግንድ* የተቀረጸ ምስል ይሖዋ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን እንዲህ ብሎ በተናገረለት ቤት ውስጥ አስቀመጠው፦+ “በዚህ ቤትና ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በመረጥኳት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለቄታው አኖራለሁ።+ +8 እነሱ ያዘዝኳቸውን ሁሉ ይኸውም አገልጋዬ ሙሴ እንዲከተሉት ያዘዛቸውን ሕግ በሙሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ+ እንጂ ከእንግዲህ የእስራኤላውያን እግር ለአባቶቻቸው ከሰጠሁት ምድር ወጥቶ እንዲንከራተት አላደርግም።”+ +9 እነሱ ግን አልታዘዙም፤ ምናሴም ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው ብሔራት የበለጠ ክፉ ነገር እንዲሠሩ አሳታቸው።+ +10 ይሖዋ አገልጋዮቹ በሆኑት ነቢያት አማካኝነት በተደጋጋሚ እንዲህ ይላቸው ነበር፦+ +11 “የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች አድርጓል፤ ከእሱ በፊት ከነበሩት አሞራውያን+ ሁሉ ይበልጥ ክፉ ድርጊት ፈጽሟል፤+ አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቹም* ይሁዳ ኃጢአት እንዲሠራ አድርጓል። +12 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለሚሰማው ሰው ሁሉ ጆሮ የሚሰቀጥጥ* ጥፋት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ አመጣለሁ።+ +13 በሰማርያ ላይ ተጠቅሜበት የነበረውን የመለኪያ ገመድ+ በኢየሩሳሌም ላይ እዘረጋለሁ፤+ እንዲሁም በአክዓብ ቤት+ ላይ ተጠቅሜበት የነበረውን ውኃ ልክ* በእሷ ላይ እጠቀማለሁ፤ አንድ ሰው ሳህኑን እንደሚወለውል ሁሉ እኔም ኢየሩሳሌምን ከወለወልኩ በኋላ እገለብጣታለሁ።+ +14 የርስቴን ቀሪዎች እተዋቸዋለሁ፤+ በጠላቶቻቸውም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እነሱም በጠላቶቻቸው ሁሉ ይበዘበዛሉ፤ እንዲሁም ለጠላቶቻቸው ምርኮ ይሆናሉ፤+ +15 ይህን የማደርገው አባቶቻቸው ከግብፅ ከወጡበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በፊቴ መጥፎ የሆነውን ነገር ስላደረጉና በተደጋጋሚ ስላስቆጡኝ ነው።’”+ +16 ምናሴ፣ ይሁዳ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም ኃጢአት እንዲሠራ በማድረግ ከሠራው ኃጢአት በተጨማሪ ኢየሩሳሌም ከዳር እስከ ዳር በደም እስክትሞላ ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደም አፍስሷል።+ +17 የቀረው የምናሴ ታሪክና ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ እንዲሁም የሠራው ኃጢአት በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +18 በመጨረሻም ምናሴ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቤቱም በሚገኘው የአትክልት ስፍራ ይኸውም በዑዛ የአትክልት ስፍራ ተቀበረ፤+ ልጁም አምዖን በእሱ ምትክ ነገሠ። +19 አምዖን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሁለት ዓመት ገዛ።+ እናቱ ሜሹሌሜት ትባል ነበር፤ እሷም የዮጥባ ሰው የሆነው የሃሩጽ ልጅ ነበረች። +20 አምዖን አባቱ ምናሴ እንዳደረገው በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +21 አባቱ በሄደበት መንገድ ሁሉ ተመላለሰ፤ ደግሞም አባቱ ያገለግላቸው የነበሩትን አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶች አገለገለ፤ ለእነሱም ሰገደ።+ +22 የአባቶቹንም አምላክ ይሖዋን ተወ፤ በይሖዋም መንገድ አልሄደም።+ +23 ከጊዜ በኋላም የንጉሥ አምዖን አገልጋዮች በእሱ ላይ አሲረው በገዛ ቤቱ ውስጥ ገደሉት። +24 ሆኖም የምድሪቱ ሕዝብ በንጉሥ አምዖን ላይ ያሴሩትን ሁሉ ገደላቸው፤ በእሱም ምትክ ልጁን ኢዮስያስን አነገሠው።+ +25 የቀረው የአምዖን ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +26 እሱንም በዑዛ የአትክልት ስፍራ በሚገኘው መቃብሩ ቀበሩት፤+ ልጁም ኢዮስያስ+ በምትኩ ነገሠ። +15 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም* በነገሠ በ27ኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የአሜስያስ+ ልጅ አዛርያስ*+ ነገሠ።+ +2 እሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 16 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ52 ዓመት ገዛ። እናቱ ይኮልያ የተባለች የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች። +3 እሱም አባቱ አሜስያስ እንዳደረገው ሁሉ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ +5 ይሖዋ ንጉሡን ቀሰፈው፤ እስከ ዕለተ ሞቱም ድረስ የሥጋ ደዌ+ በሽተኛ ሆኖ ኖረ፤ በአንድ የተለየ ቤትም ውስጥ ተገልሎ ተቀመጠ፤+ በዚህ ጊዜ የንጉሡ ልጅ ኢዮዓታም+ በቤቱ* ላይ ተሹሞ በምድሪቱ በሚኖረው ሕዝብ ላይ ይፈርድ ነበር።+ +6 የቀረው የአዛርያስ ታሪክ፣+ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +7 በመጨረሻም አዛርያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ እነሱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮዓታም ነገሠ። +8 የይሁዳ ንጉሥ አዛርያስ+ በነገሠ በ38ኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ+ በሰማርያ፣ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለስድስት ወርም ገዛ። +9 አባቶቹ እንዳደረጉት በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሟቸው ካደረጋቸው ኃጢአቶች ዞር አላለም።+ +10 ከዚያም የኢያቢስ ልጅ ሻሉም በእሱ ላይ በማሴር ይብለአም+ ላይ መትቶ ገደለው።+ ከገደለው በኋላ በእሱ ምትክ ነገሠ። +11 የቀረው የዘካርያስ ታሪክ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል። +12 ይህም ይሖዋ ለኢዩ “ልጆችህ+ እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ” በማለት የተናገረው ቃል ፍጻሜ ነው።+ የሆነውም ልክ እንደዚሁ ነው። +13 የይሁዳ ንጉሥ ዖዝያ+ በነገሠ በ39ኛው ዓመት የኢያቢስ ልጅ ሻሉም ነገሠ፤ እሱም በሰማርያ ሆኖ ድፍን አንድ ወር ገዛ። +14 ከዚያም የጋዲ ልጅ መናሄም ከቲርጻ+ ወደ ሰማርያ መጥቶ የኢያቢስን ልጅ ሻሉምን ሰማርያ ላይ መትቶ ገደለው።+ ከገደለውም በኋላ በእሱ ምትክ ነገሠ። +15 የቀረው የሻሉም ታሪክና የጠነሰሰው ሴራ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል። +16 በዚያን ጊዜ መናሄም ከቲርጻ ወጥቶ ቲፍሳን እንዲሁም በውስጧና በዙሪያዋ የነበሩትን ሁሉ መታ፤ ይህን ያደረገው በሮቿን ለእሱ ለመክፈት ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው። እሱም ቲፍሳን መታት፤ የነፍሰ ጡሮቿንም ሆድ ቀደደ። +17 የይሁዳ ንጉሥ አዛርያስ በነገሠ በ39ኛው ዓመት የጋዲ ልጅ መናሄም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ በሰማርያም ሆኖ ለአሥር ዓመት ገዛ። +18 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። በዘመኑም ሁሉ፣ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሟቸው ካደረጋቸው ኃጢአቶች ዞር አላለም።+ +"19 በዚህ ጊዜ የአሦር ንጉሥ ፑል+ ወደ ምድሩ መጣ፤ መናሄምም መንግሥቱን ለማጽናት ድጋፍ እንዲሰጠው ለፑል 1,000 የብር ታላንት* ሰጠው።+" +20 መናሄም ብሩን ያገኘው ከእስራኤላውያን ይኸውም ስመ ጥርና ሀብታም የሆኑ ሰዎች እንዲያዋጡ በማስገደድ ነው።+ በእያንዳንዱ ሰው 50 የብር ሰቅል* አስቦ ለአሦር ንጉሥ ሰጠው። ከዚያም የአሦር ንጉሥ ተመልሶ ሄደ፤ በምድሪቱም አልቆየም። +21 የቀረው የመናሄም+ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +22 በመጨረሻም መናሄም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ፈቃህያህ በእሱ ምትክ ነገሠ። +23 የይሁዳ ንጉሥ አዛርያስ በነገሠ በ50ኛው ዓመት የመናሄም ልጅ ፈቃህያህ በሰማርያ፣ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሁለት ዓመትም ገዛ። +24 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሟቸው ካደረጋቸው ኃጢአቶች ዞር አላለም።+ +25 ከዚያም የረማልያህ ልጅ የሆነው የጦር መኮንኑ ፋቁሄ+ ከአርጎብ እና ከአርያ ጋር በማበር በእሱ ላይ አሴረ፤ በሰማርያ፣ በንጉሡ ቤት* በሚገኘው የማይደፈር ማማ ላይ ሳለም መትቶ ገደለው። ከእሱ ጋር 50 የጊልያድ ሰዎች ነበሩ፤ እሱን ከገደለ በኋላም በምትኩ ነገሠ። +26 የቀረው የፈቃህያህ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈዋል። +27 የይሁዳ ንጉሥ አዛርያስ በነገሠ በ52ኛው ዓመት የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ+ በሰማርያ፣ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለ20 ዓመትም ገዛ። +28 እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሟቸው ካደረጋቸው ኃጢአቶች ዞር አላለም።+ +29 በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሄ ዘመን የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ ወረራ በማካሄድ ኢዮንን፣ አቤልቤትማዓካን፣+ ያኖአህን፣ ቃዴሽን፣+ ሃጾርን፣ ጊልያድን+ እንዲሁም ገሊላን ይኸውም መላውን የንፍታሌም+ ምድር ያዘ፤ ነዋሪዎቹንም በግዞት ወደ አሦር ወሰደ።+ +30 በመጨረሻም የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በረማልያህ ልጅ በፋቁሄ ላይ በማሴር መትቶ ገደለው፤ እሱም የዖዝያ ልጅ ኢዮዓታም+ በነገሠ በ20ኛው ዓመት በፋቁሄ ምትክ ነገሠ። +31 የቀረው የፋቁሄ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈዋል። +32 የእስራኤል ንጉሥ የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የዖዝያ+ ልጅ ኢዮዓታም+ ነገሠ። +33 እሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። እናቱም የሩሻ ትባል ነበር፤ እሷም የሳዶቅ ልጅ ነበረች።+ +34 እሱም አባቱ ዖዝያ እንዳደረገው ሁሉ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ +35 ሆኖም ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር፤ ሕዝቡ አሁንም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ ይሠዋ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።+ የይሖዋን ቤት የላይኛውን በር የሠራው እሱ ነበር።+ +36 የቀረው የኢዮዓታም ታሪክና ያደረጋቸው ነገሮች በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +37 በዚያ ዘመን ይሖዋ በይሁዳ ላይ የሶርያን ንጉሥ ረጺንን እና የረማልያህን ልጅ ፋቁሄን+ ላከ።+ +38 በመጨረሻም ኢዮዓታም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። በእሱም ምትክ ልጁ አካዝ ነገሠ። +22 ኢዮስያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ31 ዓመት ገዛ።+ እናቱ ይዲዳ ትባል ነበር፤ እሷም የቦጽቃት+ ሰው የሆነው የአዳያህ ልጅ ነበረች። +2 ኢዮስያስም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤+ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አላለም። +3 ንጉሥ ኢዮስያስ፣ በነገሠ በ18ኛው ዓመት የመሹላም ልጅ፣ የአዜልያ ልጅ የሆነውን ጸሐፊውን ሳፋንን እንዲህ ሲል ወደ ይሖዋ ቤት ላከው፦+ +4 “ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኬልቅያስ+ ሂድ፤ በር ጠባቂዎቹ ከሕዝቡ ላይ የሰበሰቡትንና ወደ ይሖዋ ቤት የገባውን ገንዘብ በአጠቃላይ እንዲሰበስብ አድርግ።+ +5 ገንዘቡን በይሖዋ ቤት የሚከናወነውን ሥራ እንዲቆጣጠሩ ለተሾሙት ሰዎች ይስጧቸው፤ እነሱ ደግሞ በይሖዋ ቤት ውስጥ የፈረሰውን* ለሚጠግኑት ሠራተኞች ይስጡ፤+ +6 ይኸውም ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹ፣ ለግንባታ ባለሙያዎቹና ለግንበኞቹ ያስረክቡ፤ እነሱም ገንዘቡን ለቤቱ ጥገና የሚያስፈልጉትን ሳንቃዎችና ጥርብ ድንጋዮች ለመግዛት ይጠቀሙበታል።+ +7 ነገር ግን ሰዎቹ እምነት የሚጣልባቸው ስለሆኑ ለተሰጣቸው ገንዘብ ስሌት እንዲያቀርቡ መጠየቅ አያስፈልግም።”+ +8 በኋላም ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ ጸሐፊውን ሳፋንን+ “የሕጉን መጽሐፍ+ በይሖዋ ቤት ውስጥ አገኘሁት” አለው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው፤ እሱም ያነበው ጀመር።+ +9 ከዚያም ጸሐፊው ሳፋን ወደ ንጉሡ ሄዶ “አገልጋዮችህ በቤቱ ውስጥ የተገኘውን ገንዘብ በሙሉ አውጥተው በይሖዋ ቤት የሚከናወነውን ሥራ እንዲቆጣጠሩ ለተሾሙት ሰዎች አስረክበዋል” አለው።+ +10 በተጨማሪም ጸሐፊው ሳፋን ንጉሡን “ካህኑ ኬልቅያስ የሰጠኝ አንድ መጽሐፍ+ አለ” አለው። ከዚያም ሳፋን መጽሐፉን በንጉሡ ፊት ማንበብ ጀመረ። +11 ንጉሡ የሕጉን መጽሐፍ ቃል ሲሰማ ልብሱን ቀደደ።+ +12 ከዚያም ንጉሡ ካህኑን ኬልቅያስን፣ የሳፋንን ልጅ አኪቃምን፣+ የሚካያህን ልጅ አክቦርን፣ ጸሐፊውን ሳፋንን እና የንጉሡን አገልጋይ አሳያህን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ +13 “ሄዳችሁ በተገኘው በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን ቃል በተመለከተ እኔን፣ ሕዝቡንና መላውን ይሁዳ ወክላችሁ ይሖዋን ጠይቁ፤ ምክንያቱም አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ ላይ እኛን አስመልክቶ የሰፈረውን ቃል ስላልታዘዙ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በእኛ ላይ ነዷል።”+ +14 በመሆኑም ካህኑ ኬልቅያስ፣ አኪቃም፣ አክቦር፣ ሳፋንና አሳያህ ወደ ነቢዪቱ ሕልዳና+ ሄዱ። ሕልዳና የሃርሐስ ልጅ፣ የቲቅዋ ልጅ፣ የአልባሳት ጠባቂው የሻሉም ሚስት ስትሆን ኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው ክፍል ትኖር ነበር፤ እነሱም በዚያ አነጋገሯት።+ +15 እሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ እኔ የላካችሁን ሰው እንዲህ በሉት፦ +16 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ መከራ አመጣለሁ፤ የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ+ ላይ የሰፈረውን ቃል ሁሉ እፈጽማለሁ። +17 እኔን በመተው በእጆቻቸው ሥራ+ ሁሉ ያስቆጡኝ ዘንድ ለሌሎች አማልክት የሚጨስ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡ+ ቁጣዬ በዚህ ቦታ ላይ ይነዳል፤ ደግሞም አይጠፋም።’”+ +18 ይሖዋን እንድትጠይቁ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ ግን እንዲህ በሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማኸውን ቃል በተመለከተ፣ +19 ይህን ቦታም ሆነ ነዋሪዎቹን መቀጣጫ እንደማደርግና እንደምረግም የተናገርኩትን ነገር ስትሰማ ልብህ ስለተነካ፣* በይሖዋም ፊት ራስህን ስላዋረድክ+ እንዲሁም ልብስህን ስለቀደድክና+ በፊቴ ስላለቀስክ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል ይሖዋ። +20 ወደ አባቶችህ የምሰበስብህ* በዚህ የተነሳ ነው፤ አንተም በሰላም በመቃብርህ ታርፋለህ፤ በዚህ ቦታ ላይ የማመጣውን መከራ ሁሉ ዓይኖችህ አያዩም።’”’” ከዚያም ሰዎቹ መልሱን ለንጉሡ አመጡለት። +17 ዳዊት በራሱ ቤት መኖር እንደጀመረ ነቢዩ ናታንን+ “የይሖዋ የቃል ኪዳኑ ታቦት በድንኳን ውስጥ ተቀምጦ+ ሳለ ይኸው እኔ ከአርዘ ሊባኖስ+ በተሠራ ቤት ውስጥ እየኖርኩ ነው” አለው። +2 ናታንም ዳዊትን “እውነተኛው አምላክ ከአንተ ጋር ስለሆነ በልብህ ያለውን ነገር ሁሉ አድርግ” አለው። +3 በዚያው ሌሊት የአምላክ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ናታን መጣ፦ +4 “ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም።+ +5 እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ድንኳን፣ ከአንዱም የማደሪያ ድንኳን ወደ ሌላው የማደሪያ ድንኳን እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርኩም።+ +6 ከመላው እስራኤል ጋር በተጓዝኩበት ጊዜ ሁሉ ሕዝቤን እረኛ ሆነው እንዲጠብቁ ከሾምኳቸው የእስራኤል ፈራጆች መካከል ‘በአርዘ ሊባኖስ፣ ቤት ያልሠራህልኝ ለምንድን ነው?’ ያልኩት ማን አለ?” ’ +7 “አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ ወሰድኩህ።+ +8 እኔም በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤+ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋለሁ፤+ ስምህንም በምድር ላይ እንዳሉ ታላላቅ ሰዎች ስም አደርገዋለሁ።+ +9 ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ተረጋግተው እንዲቀመጡም አደርጋለሁ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም የሚረብሻቸው አይኖርም፤ ክፉዎችም እንደቀድሞው ዳግመኛ አይጨቁኗቸውም፤+ +10 በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሳፍንትን ከሾምኩበት+ ጊዜ አንስቶ ሲያደርጉ እንደነበሩት አያደርጉባቸውም። ጠላቶቻችሁም ሁሉ እንዲገዙላችሁ አደርጋለሁ።+ በተጨማሪም ‘ይሖዋ ቤት እንደሚሠራልህ’ እነግርሃለሁ። +11 “ ‘ “የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ ከአባቶችህ ጋር ለመሆን በምትሄድበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ዘርህን ይኸውም ከወንዶች ልጆችህ መካከል አንዱን አስነሳለሁ፤+ ንግሥናውንም አጸናለሁ።+ +12 ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አጸናለሁ።+ +13 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ታማኝ ፍቅሬንም ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድኩ+ ከእሱ ላይ አልወስድም።+ +14 በቤቴና በንጉሣዊ ግዛቴ ላይ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር አደርገዋለሁ፤+ ዙፋኑም ለዘላለም ይዘልቃል።” ’ ”+ +15 ናታንም ይህን ቃል ሁሉና ይህን ራእይ በሙሉ ለዳዊት ነገረው። +16 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ገብቶ በይሖዋ ፊት ተቀመጠ፤ እንዲህም አለ፦ “ይሖ�� አምላክ ሆይ፣ ኧረ ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ? እስከዚህ ድረስ ያደረስከኝስ ቤቴ ምን ስለሆነ ነው?+ +17 አምላክ ሆይ፣ ይህ ሳያንስ ስለ አገልጋይህ ቤት ገና ወደፊት የሚሆነውንም ነገር ተናገርክ፤+ ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ከዚህ በላይ ከፍ ከፍ ሊደረግ እንደሚገባ ሰው አድርገህ ተመልክተኸኛል። +18 ስለሰጠኸኝ ክብር አገልጋይህ ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? አንተ አገልጋይህን በሚገባ ታውቀው የለ?+ +19 ይሖዋ ሆይ፣ ለአገልጋይህ ስትል፣ ከልብህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ታላቅነትህን በመግለጥ እነዚህን ሁሉ ታላላቅ ነገሮች ፈጽመሃል።+ +20 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤+ ከአንተ በቀር አምላክ የለም፤+ በጆሯችን የሰማነው ነገር ሁሉ ይህን ያረጋግጣል። +21 በምድር ላይ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ሌላ ብሔር ማን አለ?+ እውነተኛው አምላክ ሄዶ ሕዝቡ አድርጎ ዋጀው።+ ብሔራትን ከግብፅ ከዋጀኸው ሕዝብህ ፊት አባረህ+ ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን በመፈጸም ስምህን አስጠራህ።+ +22 ሕዝብህን እስራኤልን እስከ ወዲያኛው የራስህ ሕዝብ አደረግከው፤+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተም አምላኩ ሆንክ።+ +23 አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህንና ቤቱን በተመለከተ የገባኸው ቃል እስከ ወዲያኛው የጸና ይሁን፤ ቃል እንደገባኸውም አድርግ።+ +24 ሰዎች ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ለእስራኤል አምላክ ነው’ እንዲሉ ስምህ የጸና ይሁን፤ ደግሞም ለዘላለም ከፍ ከፍ ይበል፤+ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን።+ +25 አምላኬ ሆይ፣ አንተ ለአገልጋይህ ቤት የመሥራት ዓላማ እንዳለህ አሳውቀኸዋልና። አገልጋይህ ይህን ጸሎት በልበ ሙሉነት ወደ አንተ የሚያቀርበው በዚህ ምክንያት ነው። +26 አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ እውነተኛው አምላክ አንተ ነህ፤ ለአገልጋይህም እነዚህን መልካም ነገሮች ለማድረግ ቃል ገብተህለታል። +27 በመሆኑም የአገልጋይህን ቤት እባክህ ባርክ፤ በፊትህም ለዘላለም የጸና ይሁን፤ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ቀድሞውንም ባርከኸዋልና፤ ለዘላለምም የተባረከ ይሆናል።” +18 ከጊዜ በኋላም ዳዊት ፍልስጤማውያንን ድል በማድረግ በቁጥጥር ሥር አዋላቸው፤ ጌትንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞችም ከፍልስጤማውያን እጅ ወሰደ።+ +2 ከዚያም ሞዓብን ድል አደረገ፤+ ሞዓባውያንም የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ ግብርም ገበሩለት።+ +3 የጾባህ+ ንጉሥ ሃዳድኤዜር+ በኤፍራጥስ ወንዝ+ ላይ ያለውን የበላይነት ለማጠናከር በሄደ ጊዜ ዳዊት በሃማት+ አቅራቢያ ድል አደረገው። +"4 ዳዊት ከእሱ ላይ 1,000 ሠረገሎች፣ 7,000 ፈረሰኞችና 20,000 እግረኛ ወታደሮች ማረከ።+ ከዚያም ዳዊት 100 የሠረገላ ፈረሶችን ብቻ አስቀርቶ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቆረጠ።+" +"5 የደማስቆዎቹ ሶርያውያን፣ የጾባህን ንጉሥ ሃዳድኤዜርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን መካከል 22,000 ሰዎችን ገደለ።+" +6 ከዚያም ዳዊት በደማስቆ ሶርያ የጦር ሰፈሮች አቋቋመ፤ ሶርያውያንም የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ ግብርም ገበሩለት። ይሖዋ ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።+ +7 በተጨማሪም ዳዊት ከሃዳድኤዜር አገልጋዮች ላይ ከወርቅ የተሠሩ ክብ ጋሻዎችን ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። +8 ዳዊት የሃዳድኤዜር ከተሞች ከሆኑት ከጢብሃትና ከኩን እጅግ ብዙ መዳብ ወሰደ። ሰለሞን የመዳቡን ባሕር፣+ ዓምዶቹንና የመዳብ ዕቃዎቹን የሠራው በዚህ ነበር።+ +9 የሃማት ንጉሥ ቶዑ፣ ዳዊት የጾባህን ንጉሥ የሃዳድኤዜርን ሠራዊት በሙሉ ድል እንዳደረገ በሰማ ጊዜ+ +10 ደህንነቱን እንዲጠይቅና ከሃዳድኤዜር ጋር ተዋግቶ ድል በማድረጉ የተሰማውን ደስታ እንዲገልጽለት ልጁን ሃዶራምን ወዲያውኑ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው (ሃዳድኤዜር ከቶዑ ጋር ብዙ ጊዜ ይዋጋ ነበርና)፤ እሱም ከወርቅ፣ ከብርና ከመዳብ የተሠሩ ብዙ ዓይነት ዕቃዎችን ይዞ መጣ። +11 ንጉሥ ዳዊት እነዚህን ዕቃዎች ከሁሉም ብሔራት ይኸውም ከኤዶም፣ ከሞዓብ፣ ከአሞናውያን፣+ ከፍልስጤማውያንና+ ከአማሌቃውያን+ ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር ለይሖዋ ቀደሰ።+ +"12 የጽሩያ ልጅ+ አቢሳ+ በጨው ሸለቆ 18,000 ኤዶማውያንን ገደለ።+" +13 እሱም በኤዶም የጦር ሰፈሮች አቋቋመ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ።+ ይሖዋ ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።+ +14 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ መግዛቱን ቀጠለ፤+ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕንና ጽድቅን አሰፈነላቸው።+ +15 የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ የሠራዊቱ አዛዥ ነበር፤+ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ ታሪክ ጸሐፊ ነበር፤ +16 የአኪጡብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አሂሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሻውሻ ደግሞ ጸሐፊ ነበር። +17 የዮዳሄ ልጅ በናያህ የከሪታውያንና+ የጴሌታውያን+ አዛዥ ነበር። የዳዊት ወንዶች ልጆችም ከንጉሡ ቀጥሎ ዋና ባለሥልጣናት ነበሩ። +23 ዳዊት በሸመገለና የሕይወቱ ፍጻሜ በተቃረበ ጊዜ ልጁን ሰለሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።+ +2 ከዚያም የእስራኤልን መኳንንት፣ ካህናቱንና+ ሌዋውያኑን+ ሁሉ ሰበሰበ። +"3 ዕድሜያቸው 30 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሌዋውያን ተቆጠሩ፤+ እያንዳንዱ ወንድ በነፍስ ወከፍ ሲቆጠር 38,000 ነበር።" +"4 ከእነዚህም መካከል 24,000ዎቹ የይሖዋን ቤት ሥራ በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር፤ በተጨማሪም 6,000 አለቆችና ዳኞች ነበሩ፤+" +"5 ደግሞም 4,000 በር ጠባቂዎች+ እንዲሁም ዳዊት “ውዳሴ ለማቅረብ የሠራኋቸው ናቸው” ባላቸው መሣሪያዎች ለይሖዋ ውዳሴ+ የሚያቀርቡ 4,000 ሰዎች ነበሩ። " +6 ከዚያም ዳዊት በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀአት እና በሜራሪ+ ምድብ አደራጃቸው።+ +7 ከጌድሶናውያን ወገን ላዳን እና ሺምአይ ነበሩ። +8 የላዳን ወንዶች ልጆች መሪው የሂኤል፣ ዜታም እና ኢዩኤል+ ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። +9 የሺምአይ ወንዶች ልጆች ሸሎሞት፣ ሃዚኤል እና ካራን ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። እነዚህ የላዳን ወገን የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ነበሩ። +10 የሺምአይ ወንዶች ልጆች ያሃት፣ ዚና፣ የኡሽ እና በሪአ ነበሩ። እነዚህ አራቱ የሺምአይ ወንዶች ልጆች ነበሩ። +11 መሪው ያሃት ነበር፤ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛህ ነበር። የኡሽ እና በሪአ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች ስላልነበሯቸው በአንድ የሥራ መደብ እንደ አንድ የአባቶች ቤት ሆነው ተቆጠሩ። +12 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣+ ኬብሮን እና ዑዚኤል+ ሲሆኑ በአጠቃላይ አራት ነበሩ። +13 የአምራም ወንዶች ልጆች አሮን+ እና ሙሴ+ ነበሩ። ሆኖም አሮንና ወንዶች ልጆቹ ቅድስተ ቅዱሳኑን እንዲቀድሱ፣ በይሖዋ ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ እሱን እንዲያገለግሉና ምንጊዜም በስሙ እንዲባርኩ+ በቋሚነት ተለይተው ነበር።+ +14 የእውነተኛው አምላክ ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆች የሌዋውያን ነገድ ክፍል ሆነው ተቆጠሩ። +15 የሙሴ ወንዶች ልጆች ጌርሳም+ እና ኤሊዔዘር+ ነበሩ። +16 ከጌርሳም ወንዶች ልጆች መካከል መሪው ሸቡኤል+ ነበር። +17 ከኤሊዔዘር ዘሮች መካከል መሪው ረሃቢያህ+ ነበር፤ ኤሊዔዘር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ይሁንና የረሃብያህ ወንዶች ልጆች እጅግ ብዙ ነበሩ። +18 ከይጽሃር+ ወንዶች ልጆች መካከል መሪው ሸሎሚት+ ነበር። +19 የኬብሮን ወንዶች ልጆች መሪ የሆነው የሪያ፣ ሁለተኛው አማርያህ፣ ሦስተኛው ያሃዚኤል እና አራተኛው የቃምአም+ ነበሩ። +20 የዑዚኤል ወንዶች ልጆች+ መሪ የሆነው ሚክያስ እና ሁለተኛው ይሽሺያህ ነበሩ። +21 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ።+ የማህሊ ወንዶች ልጆች አልዓዛር እና ቂስ ነበሩ። +22 ሆኖም አልዓዛር ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ። በመሆኑም ዘመዶቻቸው የቂስ ልጆች አገቧቸው። +23 የሙሺ ወንዶች ልጆች ማህሊ፣ ኤዴር እና የሬሞት ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። +24 በአባቶቻቸው ቤት ይኸውም በአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ተቆጥረውና በስም ተዘርዝረው የተመዘገቡት በይሖዋ ቤት ያለውን አገልግሎት ያከናውኑ የነበሩ 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው የሌዊ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። +25 ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡ እረፍት ሰጥቷል፤+ እሱም በኢየሩሳሌም ለዘላለም ይኖራል።+ +26 ሌዋውያኑም የማደሪያ ድንኳኑን ወይም በውስጡ ያሉትን ለአምልኮ የሚያገለግሉ ዕቃዎች ሁሉ መሸከም አያስፈልጋቸውም።”+ +27 ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት ከሌዊ ልጆች መካከል የተቆጠሩት 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች እነዚህ ነበሩ። +28 የሌዋውያኑ ተግባር በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ይኸውም ቅጥር ግቢዎቹንና+ የመመገቢያ ክፍሎቹን፣ ቅዱስ የሆነውን ነገር ሁሉ የማንጻቱን ሥራና በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚከናወኑትን አስፈላጊ ሥራዎች ሁሉ ኃላፊነት ወስደው በመሥራት የአሮንን ልጆች+ መርዳት ነበር። +29 ደግሞም የሚነባበረውን ዳቦ፣+ ለእህል መባ የሚያገለግለውን የላመ ዱቄት፣ እርሾ ያልገባበትን ስስ ቂጣ፣+ በምጣድ የሚጋገረውን ቂጣና በዘይት የሚለወሰውን ሊጥ+ በማዘጋጀት እንዲሁም ከሁሉም ዓይነት መለኪያዎችና መስፈሪያዎች ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በማከናወን ያግዟቸው ነበር። +30 ለይሖዋ ምስጋናና ውዳሴ ለማቅረብ ጠዋት ጠዋትም+ ሆነ ማታ ማታ+ ይቆሙ ነበር። +31 ሕጉ በሚያዘው ቁጥር መሠረት ዘወትር በይሖዋ ፊት በየሰንበቱ፣+ በየወር መባቻውና+ በበዓላት ወቅት+ ለይሖዋ የሚቃጠል መሥዋዕት በቀረበ ጊዜ ሁሉ ያግዟቸው ነበር። +32 በተጨማሪም በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ከመገናኛ ድንኳኑ፣ ከቅዱሱ ስፍራና ወንድሞቻቸው ከሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች ጋር በተያያዘ ያሉባቸውን ኃላፊነቶች ይወጡ ነበር። +19 ከጊዜ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናሃሽ ሞተ፤ በእሱም ፋንታ ልጁ ነገሠ።+ +2 በዚህ ጊዜ ዳዊት “አባቱ ታማኝ ፍቅር+ ስላሳየኝ እኔም ለናሃሽ ልጅ ለሃኑን ታማኝ ፍቅር አሳየዋለሁ” አለ። በመሆኑም ዳዊት በአባቱ ሞት ከደረሰበት ሐዘን እንዲያጽናኑት መልእክተኞችን ላከ። ሆኖም የዳዊት አገልጋዮች ሃኑንን ለማጽናናት ወደ አሞናውያን+ ምድር ሲደርሱ +3 የአሞናውያን መኳንንት ሃኑንን እንዲህ አሉት፦ “ዳዊት አጽናኞችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃል? አገልጋዮቹ ወደ አንተ የመጡት ምድሪቱን በሚገባ ለማጥናትና በውስጧ ያለውን ነገር ለመሰለል እንዲሁም አንተን ለመገልበጥ አይደለም?” +4 በመሆኑም ሃኑን የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ ላጫቸው፤+ ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ላካቸው። +5 በአገልጋዮቹ ላይ የደረሰውን ነገር ለዳዊት በነገሩት ጊዜ ሰዎቹ በኀፍረት ተውጠው ስለነበር ዳዊት ወዲያውኑ መልእክተኞችን ወደ እነሱ ላከ፤ ንጉሡም “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ+ ቆዩ፤ ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው። +"6 ውሎ አድሮ አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ጥንብ እንደተቆጠሩ ተገነዘቡ፤ በመሆኑም ሃኑን እና አሞናውያን ከሜሶጶጣሚያ፣ ከአራምመዓካና ከጾባህ+ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ለመቅጠር 1,000 የብር ታላንት ላኩ።" +"7 በዚህ መንገድ 32,000 ሠረገሎችን፣ የማአካን ንጉሥና ሕዝቡን ለራሳቸው ቀጠሩ። እነሱም መጥተው በመደባ+ ፊት ለፊት ሰፈሩ። አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት መጡ። " +8 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን+ እንዲሁም እጅግ ኃያላን የሆኑትን ��ዋጊዎቹን ጨምሮ መላውን ሠራዊት ላከ።+ +9 አሞናውያንም ወጥተው በከተማዋ መግቢያ ላይ ለውጊያ ተሰለፉ፤ የመጡት ነገሥታት ደግሞ ለብቻቸው ሜዳ ላይ ተሰለፉ። +10 ኢዮዓብ ወታደሮቹ ከፊትና ከኋላ ጥቃት ለመሰንዘር ወደ እሱ እየገሰገሱ መምጣታቸውን ሲያይ በእስራኤል ካሉት ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎች መካከል የተወሰኑትን መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው።+ +11 የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ+ አመራር ሥር ሆነው አሞናውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው። +12 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ሶርያውያን+ ከበረቱብኝ አንተ ትደርስልኛለህ፤ አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ እደርስልሃለሁ። +13 ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል ብርቱና ደፋር መሆን አለብን፤+ ይሖዋም በፊቱ መልካም የሆነውን ነገር ያደርጋል።” +14 ከዚያም ኢዮዓብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሶርያውያንን ለመግጠም ወደ እነሱ ሲገሰግሱ ሶርያውያኑ ከፊቱ ሸሹ።+ +15 አሞናውያንም ሶርያውያን እንደ ሸሹ ሲያዩ እነሱም ከወንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማዋ ገቡ። ከዚያም ኢዮዓብ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። +16 ሶርያውያን በእስራኤላውያን ድል እንደተመቱ ሲያዩ መልእክተኞች ልከው በወንዙ+ አካባቢ የነበሩትን ሶርያውያን አስጠሩ፤ የሃዳድኤዜር ሠራዊት አለቃ የሆነውም ሾፋክ ይመራቸው ነበር።+ +17 ዳዊት ወሬው በተነገረው ጊዜ ወዲያውኑ እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን በመሻገር ወደ እነሱ መጣ፤ ተዋጊዎቹንም በእነሱ ላይ አሰለፈ። ዳዊት ሶርያውያንን ለመግጠም ተዋጊዎቹን ባሰለፈ ጊዜ ከእሱ ጋር ተዋጉ።+ +"18 ይሁንና ሶርያውያን ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን መካከል 7,000 ሠረገለኞችንና 40,000 እግረኛ ወታደሮችን ገደለ፤ የሠራዊቱ አዛዥ የሆነውን ሾፋክንም ገደለው።" +19 የሃዳድኤዜር አገልጋዮች በእስራኤል እንደተሸነፉ+ ባዩ ጊዜ ወዲያውኑ ከዳዊት ጋር እርቅ በመፍጠር ለእሱ ተገዙ፤+ ሶርያም ከዚህ በኋላ አሞናውያንን ለመርዳት ፈቃደኛ አልሆነችም። +20 በዓመቱ መባቻ፣ ነገሥታት ለውጊያ በሚዘምቱበት ወቅት ኢዮዓብ+ የጦር ሠራዊቱን በመምራት የአሞናውያንን ምድር አወደመ፤ ወደ ራባ+ ሄዶም ከበባት፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።+ ኢዮዓብም በራባ ላይ ጥቃት ሰንዝሮ አፈራረሳት።+ +2 ከዚያም ዳዊት የማልካምን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱም ክብደት አንድ ታላንት ወርቅ ነበር፤ በላዩም ላይ የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ፤ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተደረገ። በተጨማሪም ከከተማዋ በጣም ብዙ ምርኮ ወሰደ።+ +3 ነዋሪዎቿንም አውጥቶ ድንጋይ እንዲቆርጡ፣ ስለት ባላቸው የብረት መሣሪያዎችና በመጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው።+ ዳዊት በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። በመጨረሻም ዳዊትና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። +4 ከዚህ በኋላ ከፍልስጤማውያን ጋር በጌዜር ጦርነት ተከፈተ። በዚህ ጊዜ ሁሻዊው ሲበካይ+ የረፋይም+ ዘር የሆነውን ሲፓይን ገደለው፤ ፍልስጤማውያንም ድል ተመቱ። +5 ዳግመኛም ከፍልስጤማውያን ጋር ጦርነት ተካሄደ፤ የያኢር ልጅ ኤልሃናን የሸማኔ መጠቅለያ+ የሚመስል ዘንግ ያለው ጦር ይዞ የነበረውን የጎልያድን+ ወንድም ጌታዊውን ላህሚን ገደለው። +6 እንደገናም በጌት+ ጦርነት ተቀሰቀሰ፤ በዚያም በእጆቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች በእግሮቹም ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች፣ በድምሩ 24 ጣቶች ያሉት በጣም ግዙፍ የሆነ ሰው ነበር፤+ እሱም የረፋይም ዘር+ ነበር። +7 ይህ ሰው እስራኤልን ይገዳደር+ ስለነበር የዳዊት ወንድም የሺምአ+ ልጅ ዮናታን ገደለው። +8 እነዚህ በጌት+ የሚኖሩ የረፋይም+ ዘሮች ነበሩ፤ እነሱም በዳዊት እጅና በአገልጋዮቹ እጅ ወደቁ። +3 ዳዊት ��ኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦+ የበኩር ልጁ አምኖን፤+ እናቱ ኢይዝራኤላዊቷ አኪኖዓም+ ነበረች፤ ሁለተኛው ልጁ ዳንኤል፤ እናቱ ቀርሜሎሳዊቷ አቢጋኤል+ ነበረች፤ +2 የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማአካ የወለደው ሦስተኛው ልጁ አቢሴሎም፤+ ከሃጊት የወለደው አራተኛው ልጁ አዶንያስ፤+ +3 አምስተኛው ልጁ ሰፋጥያህ፤ እናቱ አቢጣል ነበረች፤ ስድስተኛው ልጁ ይትረአም፤ እናቱ የዳዊት ሚስት ኤግላ ነበረች። +4 እነዚህ ስድስቱ በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ናቸው፤ በዚያም ለ7 ዓመት ከ6 ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌም ደግሞ 33 ዓመት ነገሠ።+ +5 በኢየሩሳሌም የተወለዱለት እነዚህ ናቸው፦+ ሺምአ፣ ሾባብ፣ ናታን+ እና ሰለሞን፤+ የእነዚህ የአራቱ ልጆች እናት የአሚዔል ልጅ ቤርሳቤህ+ ነበረች። +6 ሌሎቹ ዘጠኝ ወንዶች ልጆች ደግሞ ይብሃር፣ ኤሊሻማ፣ ኤሊፌሌት፣ +7 ኖጋ፣ ኔፌግ፣ ያፊአ፣ +8 ኤሊሻማ፣ ኤሊያዳ እና ኤሊፌሌት ናቸው። +9 ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ የዳዊት ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ እህታቸውም ትዕማር+ ትባል ነበር። +10 የሰለሞን ልጅ ሮብዓም፣+ የሮብዓም ልጅ አቢያህ፣+ የአቢያህ ልጅ አሳ፣+ የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ፣+ +11 የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዮራም፣+ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣+ የአካዝያስ ልጅ ኢዮዓስ፣+ +12 የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ፣+ የአሜስያስ ልጅ አዛርያስ፣+ የአዛርያስ ልጅ ኢዮዓታም፣+ +13 የኢዮዓታም ልጅ አካዝ፣+ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣+ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ፣+ +14 የምናሴ ልጅ አምዖን፣+ የአምዖን ልጅ ኢዮስያስ።+ +15 የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ዮሃናን፣ ሁለተኛው ልጁ ኢዮዓቄም፣+ ሦስተኛው ልጁ ሴዴቅያስ+ እና አራተኛው ልጁ ሻሉም ነበሩ። +16 የኢዮዓቄም ወንዶች ልጆች ልጁ ኢኮንያን+ እና ልጁ ሴዴቅያስ ነበሩ። +17 የእስረኛው የኢኮንያን ወንዶች ልጆች ሰላትያል፣ +18 ማልኪራም፣ ፐዳያህ፣ ሸናጻር፣ የቃምያህ፣ ሆሻማ እና ነዳብያህ ነበሩ። +19 የፐዳያህ ወንዶች ልጆች ዘሩባቤል+ እና ሺምአይ ነበሩ፤ የዘሩባቤል ወንዶች ልጆችም መሹላም እና ሃናንያህ ነበሩ (ሸሎሚትም እህታቸው ነበረች)፤ +20 ሌሎቹ አምስት ወንዶች ልጆች ደግሞ ሃሹባ፣ ኦሄል፣ ቤራክያህ፣ ሃሳድያህ እና ዮሻብሄሴድ ነበሩ። +21 የሃናንያህ ወንዶች ልጆች ደግሞ ጰላጥያህ እና የሻያህ ነበሩ፤ የየሻያህ ልጅ ረፋያህ ነበር፤ የረፋያህ ልጅ አርናን ነበር፤ የአርናን ልጅ አብድዩ ነበር፤ የአብድዩ ልጅ ሸካንያህ ነበር፤ +22 የሸካንያህ ዘሮች ሸማያህና የሸማያህ ልጆች ናቸው፤ እነሱም ሃጡሽ፣ ይግዓል፣ ባሪያህ፣ ነአርያህ እና ሻፋጥ ሲሆኑ በአጠቃላይ ስድስት ነበሩ። +23 የነአርያህ ወንዶች ልጆች ኤሊዮዔናይ፣ ሂዝቅያህ እና አዝሪቃም ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። +24 የኤሊዮዔናይ ወንዶች ልጆች ደግሞ ሆዳውያህ፣ ኤልያሺብ፣ ፐላያህ፣ አቁብ፣ ዮሃናን፣ ደላያህ እና አናኒ ሲሆኑ በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ። +24 የአሮን ዘሮች ምድብ ይህ ነበር፦ የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብ፣ አቢሁ፣+ አልዓዛር እና ኢታምር+ ነበሩ። +2 ይሁንና ናዳብ እና አቢሁ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤+ ወንዶች ልጆችም አልነበሯቸውም፤ አልዓዛር+ እና ኢታምር ግን ካህናት ሆነው ማገልገላቸውን ቀጠሉ። +3 ዳዊት፣ ከአልዓዛር ወንዶች ልጆች አንዱ ከሆነው ከሳዶቅ+ እንዲሁም ከኢታምር ወንዶች ልጆች አንዱ ከሆነው ከአሂሜሌክ ጋር ሆኖ የአሮንን ዘሮች በተሰጣቸው የአገልግሎት ኃላፊነት መሠረት መደባቸው። +4 የአልዓዛር ወንዶች ልጆች፣ ከኢታምር ወንዶች ልጆች ይልቅ ብዙ መሪዎች ስለነበሯቸው መሪዎቹን በዚሁ መሠረት መደቧቸው፦ የአልዓዛር ወንዶች ልጆች የየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች የሆኑ 16 መሪዎች፣ የኢታምር ወንዶች ልጆች ደግሞ የየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች የሆኑ 8 መሪዎች ነበሯቸው። +5 በተጨማሪም ከአልዓዛር ወንዶች ልጆችም ሆነ ከኢታምር ወንዶች ልጆች መካከል በቅዱሱ ስፍራ የሚያገለግሉ አለቆችና እውነተኛውን አምላክ የሚያገለግሉ አለቆች ስለነበሩ አንደኛውን ቡድን ከሌላው ቡድን ጋር በዕጣ+ መደቧቸው። +6 ከዚያም የሌዋውያን ጸሐፊ የሆነው የናትናኤል ልጅ ሸማያህ በንጉሡ፣ በመኳንንቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣+ በአብያታር+ ልጅ በአሂሜሌክ+ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤት መሪዎች ፊት ስማቸውን መዘገበ፤ አንድ የአባቶች ቤት ከአልዓዛር ወገን ሲመረጥ፣ አንድ የአባቶች ቤት ደግሞ ከኢታምር ወገን ተመረጠ። +7 የመጀመሪያው ዕጣ ለየሆያሪብ ወጣ፤ ሁለተኛው ለየዳያህ፣ +8 ሦስተኛው ለሃሪም፣ አራተኛው ለሰኦሪም፣ +9 አምስተኛው ለማልኪያህ፣ ስድስተኛው ለሚያሚን፣ +10 ሰባተኛው ለሃቆጽ፣ ስምንተኛው ለአቢያህ፣+ +11 ዘጠነኛው ለየሹዋ፣ አሥረኛው ለሸካንያህ፣ +12 አሥራ አንደኛው ለኤልያሺብ፣ አሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣ +13 አሥራ ሦስተኛው ለሁፓ፣ አሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፣ +14 አሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፣ አሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፣ +15 አሥራ ሰባተኛው ለሄዚር፣ አሥራ ስምንተኛው ለሃፒጼጽ፣ +16 አሥራ ዘጠነኛው ለፐታያህ፣ ሃያኛው ለየሄዝቄል፣ +17 ሃያ አንደኛው ለያኪን፣ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣ +18 ሃያ ሦስተኛው ለደላያህ እና ሃያ አራተኛው ለማአዝያህ ወጣ። +19 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት አባታቸው አሮን ወደ ይሖዋ ቤት ሲገቡ የአገልግሎት ኃላፊነታቸውን+ የሚያከናውኑበትን ሥርዓት በተመለከተ ያወጣው ደንብ ይህ ነበር። +20 ከቀሩት ሌዋውያን መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ ከአምራም+ ወንዶች ልጆች መካከል ሹባኤል፤+ ከሹባኤል ወንዶች ልጆች መካከል የህድያ፤ +21 ከረሃቢያህ፦+ ከረሃቢያህ ወንዶች ልጆች መካከል፣ መሪ የሆነው ይሽሺያህ፤ +22 ከይጽሃራውያን መካከል ሸሎሞት፤+ ከሸሎሞት ወንዶች ልጆች መካከል ያሃት፤ +23 ከኬብሮን ወንዶች ልጆች መካከል፣ መሪ የሆነው የሪያ፣+ ሁለተኛው አማርያህ፣ ሦስተኛው ያሃዚኤል እና አራተኛው የቃምአም፤ +24 ከዑዚኤል ወንዶች ልጆች መካከል ሚክያስ፤ ከሚክያስ ወንዶች ልጆች መካከል ሻሚር። +25 ይሽሺያህ የሚክያስ ወንድም ነበር፤ ከይሽሺያህ ወንዶች ልጆች መካከል ዘካርያስ። +26 የሜራሪ+ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ፤ የያአዚያሁ ልጅ ቤኖ። +27 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፦ ከያአዚያሁ ልጆች መካከል ቤኖ፣ ሾሃም፣ ዛኩር እና ኢብሪ፤ +28 ከማህሊ ልጆች መካከል አልዓዛር፤ እሱ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤+ +29 ከቂስ፦ የቂስ ልጅ የራህምኤል፤ +30 የሙሺ ወንዶች ልጆች ማህሊ፣ ኤዴር እና የሪሞት ነበሩ። በአባቶቻቸው ቤት መሠረት የተዘረዘሩት የሌዊ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ። +31 እነሱም ወንድሞቻቸው የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች እንዳደረጉት በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአሂሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤት መሪዎች ፊት ዕጣ+ ጣሉ። በዚህ ረገድ በመሪው አባት ቤት ወይም በትልቁ ቤተሰብ መሪና በታናሽ ወንድሙ አባት ቤት ወይም በአነስተኛው ቤተሰብ መሪ መካከል ምንም +7 የይሳኮር ወንዶች ልጆች ቶላ፣ ፑሃ፣ ያሹብና ሺምሮን+ ሲሆኑ በአጠቃላይ አራት ነበሩ። +"2 የቶላም ወንዶች ልጆች ዑዚ፣ ረፋያህ፣ የሪኤል፣ ያህማይ፣ ይብሳም እና ሸሙኤል ሲሆኑ የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ነበሩ። የቶላ ዘሮች ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ፤ በዳዊት ዘመን ቁጥራቸው 22,600 ነበር።" +3 የዑዚ ዘሮች ይዝራህያህ እና የይዝራህያህ ወንዶች ልጆች ይኸውም ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤልና ይሽሺያህ ናቸው፤ አምስቱም አለቆች ነበሩ። +"4 እነሱም ብዙ ሚስቶችና ወንዶች ልጆች ስለነበሯቸው በየትውልድ ሐረጋቸው ከየአባቶቻቸው ቤት ለመዋጋት ዝግጁ የሆኑ 36,000 ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት ነበራቸው።" +"5 ከይሳኮር ቤተሰቦች በሙሉ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የሰፈሩት ኃያላን ተዋጊዎች የሆኑት ወንድሞቻቸው በአጠቃላይ 87,000 ነበሩ።+ " +6 የቢንያም+ ወንዶች ልጆች ቤላ፣+ ቤኬር+ እና የዲአዔል+ ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። +"7 የቤላ ወንዶች ልጆች ኤጽቦን፣ ዑዚ፣ ዑዚኤል፣ የሪሞት እና ኢሪ ሲሆኑ በአጠቃላይ አምስት ነበሩ፤ እነሱም የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች እንዲሁም ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ፤ በትውልድ ሐረግ መዝገቡም ላይ የሰፈሩት 22,034 ነበሩ።+" +8 የቤኬር ወንዶች ልጆች ዘሚራ፣ ኢዮአስ፣ ኤሊዔዘር፣ ኤሊዮዔናይ፣ ኦምሪ፣ የሬሞት፣ አቢያህ፣ አናቶት እና አለሜት ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ወንዶች ልጆች ናቸው። +"9 በየትውልድ ሐረጋቸውና በየዘሮቻቸው የተመዘገቡት በየአባቶቻቸው ቤት ያሉት መሪዎች 20,200 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ።" +10 የየዲአዔል+ ወንዶች ልጆች ቢልሃን እና የቢልሃን ወንዶች ልጆች ይኸውም የኡሽ፣ ቢንያም፣ ኤሁድ፣ ኬናአና፣ ዜታን፣ ተርሴስ እና አሂሻሐር ነበሩ። +"11 እነዚህ ሁሉ የየዲአዔል ወንዶች ልጆች ሲሆኑ የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች እንዲሁም ሠራዊቱን ተቀላቅለው ለመዋጋት ዝግጁ የሆኑ 17,200 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ። " +12 የሹፒምና የሁፒም ቤተሰቦች የኢር+ ልጆች ነበሩ፤ የሁሺም ልጆች ደግሞ የአሄር ዘሮች ነበሩ። +13 የንፍታሌም ወንዶች ልጆች+ ያህጺኤል፣ ጉኒ፣ የጼር እና ሻሉም ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች የባላ+ ዘሮች ነበሩ። +14 የምናሴ ልጆች፦+ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት አስሪዔል። (እሷ የጊልያድን አባት ማኪርን+ ወለደች። +15 ማኪር፣ ሁፒምንና ሹፒምን ሚስት አጋባቸው፤ የእህቱም ስም ማአካ ይባላል።) ሁለተኛው ሰለጰአድ+ ተብሎ ይጠራል፤ ሆኖም ሰለጰአድ የወለደው ሴት ልጆችን ብቻ ነበር።+ +16 የማኪር ሚስት ማአካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፔሬሽ አለችው፤ የወንድሙም ስም ሼሬሽ ይባል ነበር፤ ወንዶች ልጆቹም ዑላም እና ራቄም ነበሩ። +17 የዑላም ልጅ ቤዳን ነበር። እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ የጊልያድ ዘሮች ነበሩ። +18 እህቱም ሞሌኬት ትባል ነበር። እሷም ኢሽሆድን፣ አቢዔዜርንና ማህላን ወለደች። +19 የሸሚዳ ወንዶች ልጆችም አሂያን፣ ሴኬም፣ ሊቅሂ እና አኒዓም ነበሩ። +20 ሹተላ የኤፍሬም+ ልጅ ነበር፤ የሹተላ+ ልጅ ቤሬድ፣ የቤሬድ ልጅ ታሃት፣ የታሃት ልጅ ኤልዓዳ፣ የኤልዓዳ ልጅ ታሃት፣ +21 የታሃት ልጅ ዛባድ፣ የዛባድ ልጅ ሹተላ ነበር፤ ኤጼር እና ኤልዓድም የኤፍሬም ልጆች ነበሩ። እነሱም መንጎች ለመዝረፍ በወረዱ ጊዜ የምድሪቱ ተወላጆች የሆኑት የጌት+ ሰዎች ገደሏቸው። +22 አባታቸው ኤፍሬም ለብዙ ቀናት አለቀሰ፤ ወንድሞቹም እሱን ለማጽናናት ይመጡ ነበር። +23 ከዚያም ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። ሆኖም እሷ በወለደች ጊዜ በቤተሰቡ ላይ መከራ ደርሶ ስለነበር ስሙን በሪአ አለው። +24 የሴት ልጁም ስም ሼኢራ ሲሆን እሷም የታችኛውንና+ የላይኛውን ቤትሆሮንን+ እንዲሁም ዑዜንሼራን የገነባች ነች። +25 ሬፋህ እና ሬሼፍ ወንዶች ልጆቹ ነበሩ፤ ሬሼፍ ቴላህን ወለደ፤ ቴላህ ታሃንን ወለደ፤ +26 ታሃን ላዳንን ወለደ፤ ላዳን አሚሁድን ወለደ፤ አሚሁድ ኤሊሻማን ወለደ፤ +27 ኤሊሻማ ነዌን ወለደ፤ ነዌ ኢያሱን+ ወለደ። +28 ርስታቸውና ሰፈራቸው ቤቴልንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች፣ በስተ ምሥራቅ ናአራንን፣ በስተ ምዕራብ ደግሞ ጌዜርንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ሴኬምንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች ጨምሮ እስከ አያህና በሥሯ እስካሉት ከተሞች ይደርሳል፤ +29 በምናሴም ዘሮች ወሰን በኩል ቤትሼንና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ ታአናክና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ መጊዶና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች እንዲሁም ዶርና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች ነበሩ። በእነዚህ ስፍራዎች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር። +30 የአሴር ወንዶች ልጆች ይምናህ፣ ይሽዋ፣ ይሽዊ እና በሪአ+ ሲሆኑ እህታቸውም ሴራህ ትባላለች።+ +31 የበሪአ ወንዶች ልጆች ሄቤር እና የቢርዛይት አባት የሆነው ማልኪኤል ነበሩ። +32 ሄቤር ያፍሌጥን፣ ሾሜርን፣ ሆታምንና እህታቸውን ሹአን ወለደ። +33 የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች ፓሳክ፣ ቢምሃል እና አሽዋት ነበሩ። እነዚህ የያፍሌጥ ልጆች ነበሩ። +34 የሼሜር ወንዶች ልጆች አሂ፣ ሮህጋ፣ የሁባ እና አራም ነበሩ። +35 የወንድሙ የሄሌም ወንዶች ልጆች ጾፋ፣ ይምና፣ ሼሌሽ እና አማል ነበሩ። +36 የጾፋ ወንዶች ልጆች ሱአ፣ ሃርኔፌር፣ ሹአል፣ ቤሪ፣ ይምራ፣ +37 ቤጼር፣ ሆድ፣ ሻማ፣ ሺልሻ፣ ይትራን እና ቤኤራ ነበሩ። +38 የየቴር ወንዶች ልጆች የፎኒ፣ ፒስጳ እና አራ ነበሩ። +39 የዑላ ወንዶች ልጆች ኤራ፣ ሃኒኤል እና ሪጽያ ነበሩ። +"40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ወንዶች ልጆችና የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ናቸው፤ እንዲሁም የተመረጡ ኃያላን ተዋጊዎች ሲሆኑ የሠራዊቱ አለቆች መሪዎች ነበሩ፤ ደግሞም በቤተሰባቸው መዝገብ ላይ እንደተጻፈው+ ለውጊያ ዝግጁ የሆኑ 26,000 ሰዎች+ በሠራዊቱ ውስጥ ይገኙ ነበር።" +12 ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል የተነሳ ተደብቆ ይኖር+ በነበረበት ጊዜ እሱ ወዳለበት ወደ ጺቅላግ+ የመጡት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ እነሱም በጦርነት ከረዱት ኃያላን ተዋጊዎች መካከል ነበሩ።+ +2 ቀስት የታጠቁ ነበሩ፤ በቀኝ እጃቸውም ሆነ በግራ እጃቸው+ ድንጋይ መወንጨፍ+ ወይም ፍላጻ ማስፈንጠር ይችሉ ነበር። እነሱ ከቢንያም ነገድ+ ሲሆኑ የሳኦል ወንድሞች ነበሩ። +3 መሪያቸው አሂዔዜር ሲሆን ከእሱ ጋር ዮአስ ነበር፤ ሁለቱም የጊብዓዊው+ የሸማህ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ ደግሞም የአዝማዌት ወንዶች ልጆች የዚኤል እና ጴሌጥ፣ ቤራካ፣ አናቶታዊው+ ኢዩ፣ +4 ከሠላሳዎቹ አለቆች+ መካከል ኃያል ተዋጊና የሠላሳዎቹ መሪ የሆነው ገባኦናዊው+ ይሽማያህ፤ በተጨማሪም ኤርምያስ፣ ያሃዚኤል፣ ዮሃናን፣ ገዴራዊው ዮዛባድ፣ +5 ኤልዑዛይ፣ የሪሞት፣ በአልያህ፣ ሸማርያህ፣ ሃሪፋዊው ሰፋጥያህ፣ +6 ቆሬያውያን+ የሆኑት ሕልቃና፣ ይሽሺያህ፣ አዛርዔል፣ ዮኤዘር፣ ያሾብአም፤ +7 የጌዶር ሰው የሆነው የየሮሃም ወንዶች ልጆች ዮኤላ እና ዘባድያህ ነበሩ። +8 አንዳንድ ጋዳውያን ዳዊት ወዳለበት በምድረ በዳ ወደሚገኘው ምሽግ+ መጥተው ከእሱ ጎን ተሰለፉ፤ እነሱም ኃያላን ተዋጊዎችና ለጦርነት የሠለጠኑ ወታደሮች ሲሆኑ ትልቅ ጋሻና ረጅም ጦር ታጥቀው የሚጠባበቁ ነበሩ፤ ፊታቸው እንደ አንበሳ ፊት ነበር፤ በተራሮችም ላይ እንደ ሜዳ ፍየል ፈጣኖች ነበሩ። +9 ኤጼር መሪ ነበር፤ ሁለተኛው አብድዩ፣ ሦስተኛው ኤልያብ፣ +10 አራተኛው ሚሽማና፣ አምስተኛው ኤርምያስ፣ +11 ስድስተኛው አታይ፣ ሰባተኛው ኤሊዔል፣ +12 ስምንተኛው ዮሃናን፣ ዘጠነኛው ኤልዛባድ፣ +13 አሥረኛው ኤርምያስ፣ አሥራ አንደኛው ማክባናይ ነበሩ። +"14 እነዚህ የሠራዊቱ መሪዎች የሆኑ ጋዳውያን+ ነበሩ። ታናሽ የሆነው 100 ወታደሮችን፣ ታላቅ የሆነውም 1,000 ወታደሮችን ይቋቋም ነበር።+" +15 በመጀመሪያው ወር ዮርዳኖስ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ እየፈሰሰ ሳለ፣ ወንዙን አቋርጠው በቆላው የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ያባረሩት እነዚህ ነበሩ። +16 በተጨማሪም ከቢንያምና ከይሁዳ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ዳዊት ወደሚኖርበት ወደ ምሽጉ መጡ።+ +17 ዳዊትም ወደ እነሱ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “የመጣችሁት በሰላም ከሆነና ��ኔን ለመርዳት ከሆነ ልቤ ከእናንተ ጋር አንድ ይሆናል። ሆኖም እጄ ከበደል ንጹሕ ሆኖ ሳለ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ የአባቶቻችን አምላክ ጉዳዩን አይቶ ይፍረድ።”+ +18 ከዚያም የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በአማሳይ ላይ መንፈስ ወረደበት፤+ እሱም እንዲህ አለ፦ “ዳዊት ሆይ፣ እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፣ እኛ ከአንተ ጋር ነን።+ ሰላም፣ አዎ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አንተን ለሚረዳም ሰላም ይሁን፤አምላክህ እየረዳህ ነውና።”+ ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤ በሠራዊቱም መሪ +19 ከምናሴ ነገድ የሆኑ አንዳንድ ሰዎችም ከድተው ወደ እሱ መጡ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት ከፍልስጤማውያን ጋር ሆኖ ሳኦልን ለመውጋት ወጥቶ ነበር፤ ሆኖም ፍልስጤማውያንን አልረዳቸውም፤ ምክንያቱም የፍልስጤም ገዢዎች+ ከተመካከሩ በኋላ “ከድቶ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል በመሄድ እኛን ያስጨርሰናል”+ ሲሉ መልሰውት ነበር +20 ዳዊት ወደ ጺቅላግ+ በሄደ ጊዜ ከምናሴ ነገድ ከድተው ወደ እሱ የመጡት አድናህ፣ ዮዛባድ፣ የዲአዔል፣ ሚካኤል፣ ዮዛባድ፣ ኤሊሁ እና ጺለታይ ሲሆኑ እነሱም ከምናሴ ነገድ የሆኑ የሺህ አለቆች ነበሩ።+ +21 ሁሉም ኃያልና ደፋር+ ስለነበሩ ዳዊት ከወራሪ ኃይሎች ጋር በሚያደርገው ውጊያ ረዱት። ከዚያም በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች ሆኑ። +22 ሠራዊቱም እንደ አምላክ ሠራዊት ታላቅ እስኪሆን ድረስ፣ ዳዊትን ለመርዳት በየዕለቱ ብዙ ሰዎች ይጎርፉ ነበር።+ +23 በይሖዋ ትእዛዝ መሠረት የሳኦልን ንግሥና ወደ ዳዊት ለማስተላለፍ በኬብሮን+ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት የመጡት ለውጊያ የታጠቁ መሪዎች ቁጥር ይህ ነው።+ +"24 ትልቅ ጋሻና ረጅም ጦር የያዙ ለውጊያ የታጠቁ የይሁዳ ሰዎች 6,800 ነበሩ።" +"25 ከስምዖናውያን መካከል ከሠራዊቱ ጋር የተቀላቀሉ 7,100 ኃያልና ደፋር ሰዎች ነበሩ። " +"26 ከሌዋውያን 4,600 ነበሩ።" +"27 ዮዳሄ+ የአሮን ልጆች+ መሪ የነበረ ሲሆን ከእሱም ጋር 3,700 ሰዎች ነበሩ፤" +28 በተጨማሪም ሳዶቅ+ የተባለው ኃያልና ደፋር ወጣት ከአባቶቹ ቤት ከተውጣጡ 22 አለቆች ጋር መጣ። +"29 የሳኦል ወንድሞች ከሆኑት ቢንያማውያን+ መካከል 3,000 ነበሩ፤ ቀደም ሲል ብዙዎቹ የሳኦልን ቤት በታማኝነት ይደግፉ ነበር።" +"30 ከኤፍሬማውያን መካከል ከአባቶቻቸው ቤት የተውጣጡ 20,800 ኃያል፣ ደፋርና ስመ ጥር ሰዎች ነበሩ። " +"31 ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዳዊትን ለማንገሥ የመጡ በስም የተጠቀሱ 18,000 ሰዎች ነበሩ።" +32 ከይሳኮር ነገድ መካከል ዘመኑን ያስተዋሉና እስራኤል ምን ማድረግ እንዳለበት የተገነዘቡ 200 መሪዎች ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ እነሱን ይታዘዙ ነበር። +"33 ከዛብሎን ነገድ በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የሚችሉ፣ ለውጊያ ዝግጁ የሆኑና ልዩ ልዩ ዓይነት መሣሪያዎች የታጠቁ 50,000 ሰዎች ነበሩ፤ ሁሉም ወደ ዳዊት የመጡት በፍጹም ታማኝነት ነበር።" +"34 ከንፍታሌም ነገድ 1,000 አለቆች ነበሩ፤ ከእነሱም ጋር ትልቅ ጋሻና ጦር የያዙ 37,000 ሰዎች ነበሩ።" +"35 ከዳናውያን ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ 28,600 ሰዎች ነበሩ።" +"36 ከአሴር ነገድ ደግሞ ለጦርነት ዝግጁ ሆነው በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የሚችሉ 40,000 ሰዎች ነበሩ። " +"37 ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ+ ካሉት ከሮቤላውያን፣ ከጋዳውያንና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለጦርነት የሚያስፈልጉ የተለያዩ መሣሪያዎችን የታጠቁ 120,000 ወታደሮች ነበሩ።" +38 እነዚህ ሁሉ በአንድነት ለውጊያ የተሰለፉና ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ወታደሮች ነበሩ፤ ዳዊትን በመላው እስራኤል ላይ ለማንገሥ በአንድ ልብ ሆነው ወደ ኬብሮን መጡ፤ በተጨማሪም የቀረው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በአንድ ልብ ሆኖ ዳዊትን ለማንገሥ ተነሳ።+ +39 ወንድሞቻቸው አዘጋጅተውላቸው ስለነበር በዚያ እየበሉና እየጠጡ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ቆዩ። +40 በተጨ��ሪም በአቅራቢያቸው ያሉትም ሆኑ እስከ ይሳኮር፣ ዛብሎንና ንፍታሌም ድረስ ርቀው የሚገኙት ሰዎች በአህያ፣ በግመል፣ በበቅሎና በከብት ምግብ ጭነው መጡ፤ ይኸውም ከፍተኛ መጠን ያለው ዱቄት፣ የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣ የወይን ጠጅ፣ ዘይት፣ ከብትና በግ ነበር፤ በእስራኤል ታላቅ ደስታ ሰፍኖ ነበርና። +1 አዳም፣ሴት፣+ሄኖስ፣ +2 ቃይናን፣መላልኤል፣ያሬድ፣+ +3 ሄኖክ፣+ማቱሳላ፣ላሜህ፣ +4 ኖኅ፣+ሴም፣+ ካምና ያፌት።+ +5 የያፌት ወንዶች ልጆች ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዳይ፣ ያዋን፣ ቱባል፣+ መሼቅ+ እና ቲራስ+ ነበሩ። +6 የጎሜር ወንዶች ልጆች አሽከናዝ፣ ሪፋት እና ቶጋርማ+ ነበሩ። +7 የያዋን ወንዶች ልጆች ኤሊሻ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም እና ሮዳኒም ነበሩ። +8 የካም ወንዶች ልጆች ኩሽ፣+ ሚጽራይም፣ ፑጥ እና ከነአን+ ነበሩ። +9 የኩሽ ወንዶች ልጆች ሴባ፣+ ሃዊላ፣ ሳብታ፣ ራአማ እና ሳብተካ ነበሩ። የራአማ+ ወንዶች ልጆች ሳባ እና ዴዳን+ ነበሩ። +10 ኩሽ ናምሩድን+ ወለደ። እሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኃያል ሰው ነበር። +11 ሚጽራይም ሉድን፣+ አናሚምን፣ ለሃቢምን፣ ናፊቱሂምን፣+ +12 ጳትሩሲምን፣+ ካስሉሂምን (ፍልስጤማውያን+ የተገኙት ከእሱ ነው) እንዲሁም ካፍቶሪምን+ ወለደ። +13 ከነአን የበኩር ልጁን ሲዶናን፣+ ሄትን+ +14 እንዲሁም ኢያቡሳዊውን፣+ አሞራዊውን፣+ ገርጌሻዊውን፣+ +15 ሂዋዊውን፣+ አርቃዊውን፣ ሲናዊውን፣ +16 አርዋዳዊውን፣+ ጸማራዊውን እና ሃማታዊውን ወለደ። +17 የሴም ወንዶች ልጆች ኤላም፣+ አሹር፣+ አርፋክስድ፣ ሉድ እና አራምእንዲሁም ዑጽ፣ ሁል፣ ጌተር እና ማሽ+ ነበሩ። +18 አርፋክስድ ሴሎምን+ ወለደ፤ ሴሎምም ኤቤርን ወለደ። +19 ኤቤር ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የአንደኛው ስም ፋሌቅ+ ነበር፤ ምክንያቱም በእሱ የሕይወት ዘመን ምድር ተከፋፍላ ነበር። የወንድሙ ስም ደግሞ ዮቅጣን ነበር። +20 ዮቅጣን አልሞዳድን፣ ሸሌፍን፣ ሃጻርማዌትን፣ ያራህን፣+ +21 ሃዶራምን፣ ዑዛልን፣ ዲቅላን፣ +22 ኦባልን፣ አቢማዔልን፣ ሳባን፣ +23 ኦፊርን፣+ ሃዊላን+ እና ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ነበሩ። +24 ሴም፣አርፋክስድ፣ሴሎም፣ +25 ኤቤር፣ፋሌቅ፣+ረኡ፣+ +26 ሴሮህ፣+ናኮር፣+ታራ፣+ +27 አብራም ማለትም አብርሃም።+ +28 የአብርሃም ወንዶች ልጆች ይስሐቅ+ እና እስማኤል+ ነበሩ። +29 የቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው የሚከተለው ነው፦ የእስማኤል የበኩር ልጅ ነባዮት+ ከዚያም ቄዳር፣+ አድበዔል፣ ሚብሳም፣+ +30 ሚሽማ፣ ዱማ፣ ማሳ፣ ሃዳድ፣ ቴማ፣ +31 የጡር፣ ናፊሽ እና ቄድማ። እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ነበሩ። +32 የአብርሃም ቁባት የነበረችው ኬጡራ+ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዚምራን፣ ዮቅሻን፣ ሚዳን፣ ምድያም፣+ ይሽባቅ እና ሹሃ+ ነበሩ። የዮቅሻን ወንዶች ልጆች ሳባ እና ዴዳን+ ነበሩ። +33 የምድያም ወንዶች ልጆች ኤፋ፣+ ኤፌር፣ ሃኖክ፣ አቢዳዕ እና ኤልዳዓ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ወንዶች ልጆች ነበሩ። +34 አብርሃም ይስሐቅን+ ወለደ። የይስሐቅ ወንዶች ልጆች ኤሳው+ እና እስራኤል+ ነበሩ። +35 የኤሳው ወንዶች ልጆች ኤሊፋዝ፣ ረኡዔል፣ የኡሽ፣ ያላም እና ቆሬ+ ነበሩ። +36 የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆች ቴማን፣+ ኦማር፣ ጸፎ፣ ጋታም፣ ቀናዝ፣ ቲምና እና አማሌቅ+ ነበሩ። +37 የረኡዔል ወንዶች ልጆች ናሃት፣ ዛራ፣ ሻማህ እና ሚዛህ+ ነበሩ። +38 የሴይር+ ወንዶች ልጆች ሎጣን፣ ሾባል፣ ጺብኦን፣ አና፣ ዲሾን፣ ኤጼር እና ዲሻን+ ነበሩ። +39 የሎጣን ወንዶች ልጆች ሆሪ እና ሆማም ነበሩ። የሎጣን እህት ቲምና+ ትባል ነበር። +40 የሾባል ወንዶች ልጆች አልዋን፣ ማናሃት፣ ኤባል፣ ሼፎ እና ኦናም ነበሩ። የጺብኦን ወንዶች ልጆች አያ እና አና+ ነበሩ። +41 የአና ልጅ ዲሾን ነ��ር። የዲሾን ወንዶች ልጆች ሄምዳን፣ ኤሽባን፣ ይትራን እና ኬራን+ ነበሩ። +42 የኤጼር+ ወንዶች ልጆች ቢልሃን፣ ዛአዋን እና አቃን ነበሩ። የዲሻን ወንዶች ልጆች ዑጽ እና አራን+ ነበሩ። +43 እነዚህ በእስራኤላውያን+ ላይ የትኛውም ንጉሥ መግዛት ከመጀመሩ በፊት በኤዶም+ ምድር ይገዙ የነበሩ ነገሥታት ናቸው፦ የቢዖር ልጅ ቤላ፣ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። +44 ቤላ ሲሞት የቦስራው+ የዛራ ልጅ ዮባብ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +45 ዮባብ ሲሞት ከቴማናውያን ምድር የመጣው ሁሻም በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +46 ሁሻም ሲሞት ምድያምን በሞዓብ ምድር ድል ያደረገው የቤዳድ ልጅ ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማው ስም አዊት ይባል ነበር። +47 ሃዳድ ሲሞት የማስረቃው ሳምላ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +48 ሳምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለው የረሆቦቱ ሻኡል በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +49 ሻኡል ሲሞት የአክቦር ልጅ ባአልሀናን በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። +50 ባአልሀናን ሲሞት ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማውም ስም ጳኡ ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣቤል ሲሆን እሷም የመዛሃብ ሴት ልጅ የማጥሬድ ልጅ ናት። +51 ከዚያም ሃዳድ ሞተ። የኤዶም አለቆች፣ አለቃ ቲምና፣ አለቃ አልዋህ፣ አለቃ የቴት፣+ +52 አለቃ ኦሆሊባማ፣ አለቃ ኤላህ፣ አለቃ ፒኖን፣ +53 አለቃ ቀናዝ፣ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ሚብጻር፣ +54 አለቃ ማግዲኤል እና አለቃ ኢራም ነበሩ። እነዚህ የኤዶም አለቆች ነበሩ። +29 ንጉሥ ዳዊትም ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፦ “አምላክ የመረጠው+ ልጄ ሰለሞን ገና ወጣት ነው፤ ተሞክሮም የለውም፤+ ሥራው ደግሞ ታላቅ ነው፤ ቤተ መቅደሱ የሚሠራው ለሰው ሳይሆን ለይሖዋ አምላክ ነውና።+ +2 እኔም አቅሜ በፈቀደው መጠን ለአምላኬ ቤት በወርቅ ለሚሠራው ወርቅ፣ በብር ለሚሠራው ብር፣ በመዳብ ለሚሠራው መዳብ፣ በብረት ለሚሠራው ብረትና+ በሳንቃ ለሚሠራው ሳንቃ+ እንዲሁም ኦኒክስ ድንጋዮች፣ በማያያዣ የሚጣበቁ ድንጋዮች፣ እንደ ጌጥ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ሕብር ያላቸው ድንጋዮች፣ ማንኛውንም ዓይነት +3 ከዚህም በላይ ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር+ የተነሳ ለቅዱሱ ቤት አስቀድሞ ካዘጋጀሁት በተጨማሪ የግል ሀብቴ+ የሆነውን ወርቅና ብርም ለአምላኬ ቤት እሰጣለሁ፤ +"4 ከዚህም ሌላ የቤቶቹን ግድግዳ ለመለበጥ 3,000 ታላንት የኦፊር ወርቅና+ 7,000 ታላንት የተጣራ ብር፣" +5 በወርቅ ለሚሠራው ወርቅ፣ በብር ለሚሠራው ብር፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ለሚሠሩትም ሥራ ሁሉ የሚያስፈልገውን እሰጣለሁ። ታዲያ ዛሬ ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ በእጁ ይዞ ለመቅረብ ፈቃደኛ የሆነ ማን ነው?”+ +6 በመሆኑም የአባቶች ቤቶች አለቆች፣ የእስራኤል ነገዶች አለቆች፣ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆችና+ የንጉሡን ጉዳይ የሚያስፈጽሙት አለቆች+ በፈቃደኝነት ቀረቡ። +"7 ደግሞም ለእውነተኛው አምላክ ቤት አገልግሎት የሚውል 5,000 ታላንት ወርቅ፣ 10,000 ዳሪክ፣ 10,000 ታላንት ብር፣ 18,000 ታላንት መዳብና 100,000 ታላንት ብረት ሰጡ።" +8 የከበሩ ድንጋዮች ያለው ሰው ሁሉ ጌድሶናዊው+ የሂኤል+ በኃላፊነት ለሚያስተዳድረው በይሖዋ ቤት ላለው ግምጃ ቤት ሰጠ። +9 ሕዝቡ በፈቃደኝነት መባ በመስጠታቸው እጅግ ተደሰቱ፤ በፈቃደኝነት ተነሳስተው ለይሖዋ መባ የሰጡት በሙሉ ልባቸው ነበርና፤+ ንጉሥ ዳዊትም እጅግ ደስ አለው። +10 ከዚያም ዳዊት በጉባኤው ሁሉ ፊት ይሖዋን አወደሰ። እንዲህም አለ፦ “የአባታችን የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ውዳሴ ይድረስህ። +11 ይሖዋ ሆይ፣ ታላቅነት፣+ ኃያልነት፣+ ውበት፣ ግርማና ሞገስ+ የአንተ ነው፤ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነው።+ ይሖዋ ሆይ፣ መንግሥት የአንተ ነው።+ ���ሁሉም በላይ ከፍ ከፍ ያልክ ራስ ነህ። +12 ሀብትና ክብር ከአንተ ነው፤+ አንተም ሁሉንም ነገር ትገዛለህ፤+ ኃይልና+ ብርታት+ በእጅህ ነው፤ እጅህ ሁሉንም ታላቅ ማድረግና+ ለሁሉም ብርታት መስጠት ይችላል።+ +13 አሁንም አምላካችን ሆይ፣ እናመሰግንሃለን፤ ውብ የሆነውን ስምህንም እናወድሳለን። +14 “ይሁንና በፈቃደኝነት ተነሳስተን እንዲህ ያለ መባ ማቅረብ እንችል ዘንድ እኔም ሆንኩ ሕዝቤ ማን ነን? ሁሉም ነገር የተገኘው ከአንተ ነውና፤ የሰጠንህም ከገዛ እጅህ የተቀበልነውን ነው። +15 እንደ አባቶቻችን ሁሉ እኛም በፊትህ የባዕድ አገር ሰዎችና ሰፋሪዎች ነንና።+ የሕይወት ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤+ ተስፋም የለውም። +16 አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ ለቅዱስ ስምህ ቤት ለመሥራት ያዘጋጀነው ይህ ሁሉ ሀብት የተገኘው ከገዛ እጅህ ነው፤ ሁሉም የአንተ ነው። +17 አምላኬ ሆይ፣ አንተ ልብን እንደምትመረምርና+ በንጹሕ አቋም ደስ እንደምትሰኝ+ በሚገባ አውቃለሁ። እኔ በልቤ ቅንነት፣ በፈቃደኝነት ተነሳስቼ ይህን ሁሉ ነገር ሰጥቻለሁ፤ ደግሞም እዚህ የተገኘው ሕዝብህ በፈቃደኝነት ተነሳስቶ ለአንተ መባ ሲያቀርብ በማየቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። +18 የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይስሐቅና የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሕዝብ እንዲህ ያለ የፈቃደኝነት መንፈስና ዝንባሌ ይዞ ለዘላለም እንዲኖርና በሙሉ ልቡ እንዲያገለግልህ እርዳው።+ +19 ልጄ ሰለሞንም ትእዛዛትህን፣ ማሳሰቢያዎችህንና ሥርዓቶችህን እንዲጠብቅ+ ሙሉ ልብ ስጠው፤+ እነዚህን ሁሉ ነገሮች እንዲያደርግና እኔ ባዘጋጀሁለት ነገሮች ቤተ መቅደስ እንዲገነባ እርዳው።”+ +20 ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ “አሁን፣ አምላካችሁን ይሖዋን አወድሱ” አለ። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን አወደሱ፤ ለይሖዋና ለንጉሡም በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ። +"21 በማግስቱም ለይሖዋ መሥዋዕት መሠዋታቸውንና ለይሖዋ የሚቃጠል መባ+ ማቅረባቸውን ቀጠሉ፤ 1,000 ወይፈኖች፣ 1,000 አውራ በጎች፣ 1,000 ተባዕት የበግ ጠቦቶችና የመጠጥ መባዎች+ አቀረቡ፤ ስለ እስራኤል ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።+" +22 በዚያ ዕለት በይሖዋ ፊት በታላቅ ደስታ ይበሉና ይጠጡ ነበር፤+ ደግሞም የዳዊትን ልጅ ሰለሞንን ለሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ በይሖዋም ፊት መሪ አድርገው ቀቡት፤+ ሳዶቅንም ካህን አድርገው ቀቡት።+ +23 ሰለሞንም በአባቱ በዳዊት ፋንታ በይሖዋ ዙፋን+ ላይ ንጉሥ ሆኖ ተቀመጠ፤ እሱም ተሳካለት፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ታዘዙለት። +24 መኳንንቱና+ ኃያላን ተዋጊዎቹ+ ሁሉ እንዲሁም የንጉሥ ዳዊት ወንዶች ልጆች+ ሁሉ ለንጉሥ ሰለሞን ተገዙለት። +25 ይሖዋም በእስራኤል ሁሉ ፊት ሰለሞንን እጅግ ታላቅ አደረገው፤ ደግሞም በእስራኤል ከእሱ በፊት የነበሩት ነገሥታት ያላገኙትን ንጉሣዊ ግርማ አጎናጸፈው።+ +26 በዚህ መንገድ የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ገዛ፤ +27 በእስራኤልም ላይ ንጉሥ ሆኖ የገዛበት ጊዜ ርዝመት 40 ዓመት ነበር። በኬብሮን ለ7 ዓመት፣+ በኢየሩሳሌም ደግሞ ለ33 ዓመት ነገሠ።+ +28 እሱም አስደሳች የሆነ ብዙ ዘመን ኖሮ፣+ ዕድሜ ጠግቦ እንዲሁም ብዙ ሀብትና ክብር አግኝቶ ሞተ፤ ልጁ ሰለሞንም በእሱ ፋንታ ነገሠ።+ +29 የንጉሥ ዳዊት ታሪክ ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ፣ ባለ ራእዩ ሳሙኤል፣ ነቢዩ ናታንና+ ባለ ራእዩ ጋድ+ ባዘጋጇቸው ጽሑፎች ውስጥ ሰፍሯል፤ +30 በተጨማሪም ስለ ንግሥናውና ስለ ኃያልነቱ ሁሉ እንዲሁም ከእሱ፣ ከእስራኤልና በዙሪያው ካሉ መንግሥታት ሁሉ ጋር በተያያዘ ስለተከናወኑት ነገሮች ተጽፏል። +28 ዳዊት የእስራኤልን መኳንንት ሁሉ ይኸውም የነገዶቹን አለቆች፣ ንጉሡን በሚያገለግሉት ምድቦች ላይ የተሾሙትን አለቆች፣+ የሺህ አለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን+ እንዲሁም በንጉሡና በልጆቹ ንብረትም ሆነ መንጋ ሁሉ ላይ የተሾሙትን አለቆች+ ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ፣ ከኃያላኑና ብቃት ካላቸው ሰዎች+ ሁሉ ጋ +2 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ተነስቶ እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼና ወገኖቼ ሆይ፣ ስሙኝ። እኔ ለይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ማረፊያና ለአምላካችን የእግር ማሳረፊያ የሚሆን ቤት ለመሥራት ከልቤ ተመኝቼ ነበር፤+ ደግሞም ይህን ቤት ለመሥራት ዝግጅት አድርጌ ነበር።+ +3 እውነተኛው አምላክ ግን ‘ብዙ ጦርነት ስላካሄድክና ደም ስላፈሰስክ ለስሜ የሚሆን ቤት አትሠራም’ አለኝ።+ +4 ይሁንና የእስራኤል አምላክ ይሖዋ በእስራኤል ላይ ለዘላለም ንጉሥ እንድሆን ከአባቴ ቤት ሁሉ መረጠኝ፤+ መሪ እንዲሆን የመረጠው ይሁዳን ነውና፤+ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት፣+ ከአባቴም ወንዶች ልጆች መካከል በመላው እስራኤል ላይ እንድነግሥ እኔን መረጠ።+ +5 ይሖዋ ከሰጠኝ ብዙ ወንዶች ልጆች+ መካከል ደግሞ በይሖዋ የንግሥና ዙፋን ላይ ተቀምጦ እስራኤልን እንዲገዛ ልጄን ሰለሞንን+ መርጦታል።+ +6 “እንዲህም አለኝ፦ ‘ቤቴንና ቅጥር ግቢዎቼን የሚሠራው ልጅህ ሰለሞን ነው፤ እሱን እንደ ልጄ አድርጌ መርጬዋለሁና፤ እኔም አባቱ እሆናለሁ።+ +7 አሁን እያደረገ እንዳለው ትእዛዛቴንና ድንጋጌዎቼን+ ሳያወላውል የሚፈጽም ከሆነ ንግሥናውን ለዘላለም አጸናለሁ።’+ +8 በመሆኑም የይሖዋ ጉባኤ በሆነው በእስራኤል ሁሉ ፊት፣ አምላካችን እየሰማ ይህን እነግራችኋለሁ፦ መልካሚቱን ምድር እንድትወርሱና+ ከእናንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆቻችሁ ቋሚ ርስት አድርጋችሁ እንድታወርሱ የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት በሙሉ በጥብቅ ተከተሉ፤ ደግሞም ፈልጉ። +9 “አንተም ልጄ ሰለሞን ሆይ፣ የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በሙሉ ልብና+ በደስተኛ ነፍስ አገልግለው፤ ይሖዋ ልብን ሁሉ ይመረምራልና፤+ ሐሳብንና ውስጣዊ ዝንባሌን ሁሉ ይረዳል።+ ብትፈልገው ይገኝልሃል፤+ ከተውከው ግን ለዘላለም ይተውሃል።+ +10 አሁንም ለመቅደስ የሚሆን ቤት እንድትሠራ ይሖዋ እንደመረጠህ ልብ በል። እንግዲህ ደፋር ሁን፤ ሥራህንም ጀምር።” +11 ከዚያም ዳዊት የበረንዳውን፣+ የመቅደሱን ክፍሎች፣ የግምጃ ቤቶቹን፣ ሰገነት ላይ ያሉትን ክፍሎች፣ የውስጠኛዎቹን ክፍሎችና የስርየት መክደኛው+ የሚቀመጥበትን ክፍል ንድፍ+ ለልጁ ለሰለሞን ሰጠው። +12 ዳዊት በመንፈስ የተገለጠለትን የይሖዋን ቤት ቅጥር ግቢዎች፣+ በዙሪያው ያሉትን የመመገቢያ ክፍሎች ሁሉ፣ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ግምጃ ቤቶችና የተቀደሱት ነገሮች+ የሚቀመጡባቸውን ግምጃ ቤቶች ንድፍ ሁሉ ለሰለሞን ሰጠው፤ +13 እንዲሁም የካህናቱንና+ የሌዋውያኑን ምድብ፣ በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ሁሉና በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ሁሉ በተመለከተ መመሪያ ሰጠው፤ +14 በተጨማሪም የወርቁን ይኸውም ለተለያዩ አገልግሎቶች ለሚውሉት ዕቃዎች ሁሉ የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠን፣ የብር ዕቃዎቹን ሁሉ መጠንና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉትን ዕቃዎች ሁሉ መጠን አሳወቀው፤ +15 ደግሞም እንደየመቅረዙ አገልግሎት ዓይነት፣ ለወርቅ መቅረዞቹና+ ለወርቅ መብራቶቻቸው ይኸውም ለተለያዩ ዓይነት መቅረዞችና መብራቶቻቸው የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠን እንዲሁም ለብር መቅረዞቹ ማለትም ለእያንዳንዱ መቅረዝና ለመብራቶቹ የሚያስፈልገውን ብር መጠን ገለጸለት፤ +16 በተጨማሪም የሚነባበረው ዳቦ+ ለሚቀመጥበት ለእያንዳንዱ ጠረጴዛ የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠንና ለብር ጠረጴዛዎቹ የሚያስፈልገውን ብር መጠን አሳወቀው፤ +17 ከንጹሕ ወርቅ ለሚሠሩት ሹካዎች�� ጎድጓዳ ሳህኖችና ማንቆርቆሪያዎች እንዲሁም ለእያንዳንዱ ትንሽ የወርቅ ጎድጓዳ ሳህን+ የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠንና ለእያንዳንዱ ትንሽ የብር ጎድጓዳ ሳህን የሚያስፈልገውን ብር መጠን ገለጸለት። +18 ደግሞም ለዕጣኑ መሠዊያ+ የሚያስፈልገውን እንዲሁም ለሠረገላው ምስል+ ይኸውም ክንፋቸውን ለሚዘረጉትና የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ለሚሸፍኑት የወርቅ ኪሩቦች+ የሚያስፈልገውን የጠራ ወርቅ መጠን አሳወቀው። +19 ዳዊትም “የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ የግንባታ ንድፉንም+ ዝርዝር በሙሉ በጽሑፍ እንዳሰፍር ማስተዋል ሰጠኝ” አለ።+ +20 ከዚያም ዳዊት ልጁን ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤ ሥራህንም ጀምር። አትፍራ ወይም አትሸበር፤ አምላኬ፣ ይሖዋ አምላክ ከአንተ ጋር ነውና።+ በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት አስፈላጊ የሆነው ሥራ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከአንተ ጋር ይሆናል እንጂ አይጥልህም ወይም አይተውህም።+ +21 እነሆ፣ በእውነተኛው አምላክ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ሁሉ የሚያስፈልጉት የካህናትና+ የሌዋውያን+ ምድቦች ተዘጋጅተዋል። ማንኛውንም ዓይነት አገልግሎት ለማከናወን ፈቃደኛ የሆኑና የተካኑ ሠራተኞች አሉልህ፤+ መኳንንቱና+ ሕዝቡም ሁሉ መመሪያህን በሙሉ ይፈጽማሉ።” +8 ቢንያም+ የበኩር ልጁን ቤላን፣+ ሁለተኛ ልጁን አሽቤልን፣+ ሦስተኛ ልጁን አሃራሕን፣ +2 አራተኛ ልጁን ኖሃንና አምስተኛ ልጁን ራፋን ወለደ። +3 የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ አዳር፣ ጌራ፣+ አቢሁድ፣ +4 አቢሹዓ፣ ንዕማን፣ አሆዓሕ፣ +5 ጌራ፣ ሼፉፋን እና ሁራም። +6 እነዚህ የኤሁድ ወንዶች ልጆች ይኸውም ወደ ማናሃት በግዞት የተወሰዱ በጌባ+ ይኖሩ የነበሩ ቤተሰቦች መሪዎች ናቸው፦ +7 ንዕማን፣ አኪያህ እና ጌራ፤ ሰዎቹን በዋነኝነት እየመራ ወደ ግዞት የወሰዳቸው ጌራ ነበር፤ እሱም ዑዛን እና አሂሑድን ወለደ። +8 ሻሃራይም ሰዎቹን ከሰደዳቸው በኋላ በሞዓብ ምድር ልጆች ወለደ። ሁሺም እና ባዓራ ሚስቶቹ ነበሩ። +9 ከሚስቱ ከሆዴሽ ዮባብን፣ ጺብያን፣ ሜሻን፣ ማልካምን፣ +10 የኡጽን፣ ሳክያህን እና ሚርማን ወለደ። እነዚህ ወንዶች ልጆቹ ሲሆኑ የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ነበሩ። +11 ከሁሺም አቢጡብን እና ኤልጳዓልን ወለደ። +12 የኤልጳዓል ወንዶች ልጆች ኤቤር፣ ሚሻም፣ ኦኖን+ እንዲሁም ሎድንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች የቆረቆረው ሻሜድ፣ +13 በሪአ እና ሼማ ነበሩ። እነዚህ በአይሎን+ ይኖሩ የነበሩ የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ናቸው። የጌትን ነዋሪዎች ያሳደዱት እነሱ ነበሩ። +14 ደግሞም አሂዮ፣ ሻሻቅ፣ የሬሞት፣ +15 ዘባድያህ፣ አራድ፣ ኤዴር፣ +16 ሚካኤል፣ ይሽጳ እና ዮሃ የበሪአ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ +17 ዘባድያህ፣ መሹላም፣ ሂዝቂ፣ ሄቤር፣ +18 ይሽመራይ፣ ይዝሊያ እና ዮባብ የኤልጳዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ +19 ያቂም፣ ዚክሪ፣ ዛብዲ፣ +20 ኤሊዔናይ፣ ጺለታይ፣ ኤሊዔል፣ +21 አዳያህ፣ ቤራያህ እና ሺምራት የሺምአይ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ +22 ይሽጳን፣ ኤቤር፣ ኤሊዔል፣ +23 አብዶን፣ ዚክሪ፣ ሃናን፣ +24 ሃናንያህ፣ ኤላም፣ አንቶቲያህ፣ +25 ይፍደያህ እና ጰኑኤል የሻሻቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ +26 ሻምሸራይ፣ ሸሃሪያህ፣ ጎቶልያ፣ +27 ያአሬሽያህ፣ ኤልያስ እና ዚክሪ የየሮሃም ወንዶች ልጆች ነበሩ። +28 እነዚህ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ተጽፎ በሚገኘው መሠረት የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ነበሩ። የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበር። +29 የገባኦን አባት የኢዔል በገባኦን+ ይኖር ነበር። የሚስቱ ስም ማአካ ይባል ነበር።+ +30 የበኩር ልጁ አብዶን ሲሆን ሌሎቹ ልጆቹ ደግሞ ጹር፣ ቂስ፣ ባአል፣ ናዳብ፣ +31 ጌዶር፣ አሂዮ እና ዛከር ነበሩ። +32 ሚቅሎት ሺምአህን ወለደ። እነዚህ ሁሉ ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር ሆነው በወንድሞቻቸው አቅራቢያ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። +33 ኔር+ ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን+ ወለደ፤ ሳኦል ዮናታንን፣+ ሜልኪሳን፣+ አቢናዳብን+ እና ኤሽባዓልን+ ወለደ። +34 የዮናታን ልጅ መሪበኣል+ ነበር። መሪበኣል ሚክያስን ወለደ።+ +35 የሚክያስ ወንዶች ልጆች ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬአ እና አካዝ ነበሩ። +36 አካዝ የሆአዳን ወለደ፤ የሆአዳ አለሜትን፣ አዝማዌትን እና ዚምሪን ወለደ፤ ዚምሪ ሞጻን ወለደ። +37 ሞጻ ቢንአን ወለደ፤ ቢንአ ራፋህን ወለደ፤ ራፋህ ኤልዓሳን ወለደ፤ ኤልዓሳ አዜልን ወለደ። +38 አዜል ስድስት ወንዶች ልጆች የነበሩት ሲሆን ስማቸውም አዝሪቃም፣ ቦከሩ፣ እስማኤል፣ ሸአርያህ፣ አብድዩ እና ሃናን ነበር። እነዚህ ሁሉ የአዜል ወንዶች ልጆች ነበሩ። +39 የወንድሙ የኤሼቅ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ዑላም፣ ሁለተኛው ልጁ የኡሽ፣ ሦስተኛው ልጁ ኤሊፌሌት ነበሩ። +40 የዑላም ወንዶች ልጆች ቀስተኞችና ኃያላን ተዋጊዎች የነበሩ ሲሆን 150 ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሯቸው። እነዚህ ሁሉ የቢንያም ዘሮች ነበሩ። +11 ከጊዜ በኋላ እስራኤላውያን በሙሉ በኬብሮን+ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት ተሰብስበው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ፣ የሥጋህም ቁራጭ ነን።+ +2 ባለፉት ዘመናት ሳኦል ንጉሥ በነበረበት ጊዜ እስራኤል ወደ ጦርነት ሲወጣ የምትመራው አንተ ነበርክ።+ አምላክህ ይሖዋም ‘ሕዝቤን እስራኤልን እረኛ ሆነህ ትጠብቃለህ፤ በሕዝቤ በእስራኤልም ላይ መሪ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”+ +3 በመሆኑም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ንጉሡ ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን ከእነሱ ጋር በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ገባ። ከዚያም በሳሙኤል አማካኝነት በተነገረው የይሖዋ ቃል መሠረት+ ዳዊትን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ቀቡት።+ +4 በኋላም ዳዊትና መላው እስራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ኢያቡሳውያን+ ይኖሩበት ወደነበረው ምድር ወደ ኢያቡስ+ ሄዱ። +5 የኢያቡስ ነዋሪዎችም ዳዊትን “ፈጽሞ ወደዚህ አትገባም!” በማለት ተሳለቁበት።+ ይሁን እንጂ ዳዊት በአሁኑ ጊዜ የዳዊት ከተማ+ ተብላ የምትጠራውን የጽዮንን+ ምሽግ ያዘ። +6 ስለሆነም ዳዊት “ኢያቡሳውያንን በመጀመሪያ የሚመታ ሰው አለቃና መኮንን ይሆናል” አለ። የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ+ በመጀመሪያ ወደዚያ ወጣ፤ እሱም አለቃ ሆነ። +7 ከዚያም ዳዊት በምሽጉ ውስጥ መኖር ጀመረ። ከዚህም የተነሳ ስፍራውን የዳዊት ከተማ አሉት። +8 እሱም ከጉብታው አንስቶ በዙሪያው እስካሉት ቦታዎች ድረስ ከተማዋን ዙሪያዋን ገነባ፤ ኢዮዓብ ደግሞ ቀሪውን የከተማዋን ክፍል መልሶ ሠራ። +9 በዚህ ሁኔታ ዳዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ ሄደ፤+ የሠራዊት ጌታ ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር። +10 የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ እነሱም ከመላው የእስራኤል ሕዝብ ጋር ሆነው ይሖዋ ለእስራኤል ቃል በገባው መሠረት ንጉሥ+ እንዲሆን ብርቱ ድጋፍ አድርገውለታል። +11 የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች ስም ዝርዝር ይህ ነው፦ የሦስቱ መሪ+ የሆነው የሃክሞናዊው ልጅ ያሾብአም።+ እሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ጊዜ 300 ሰው ገደለ።+ +12 ከእሱ ቀጥሎ የአሆሐያዊው+ የዶዶ ልጅ አልዓዛር ነበር።+ እሱም ከሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች መካከል አንዱ ነው። +13 ፍልስጤማውያን ለጦርነት ተሰብስበው በነበረበት ጊዜ በጳስዳሚም+ ከዳዊት ጋር አብሮ ነበር። በዚያም የገብስ ሰብል የሞላበት መሬት ነበር፤ ሕዝቡም ከፍልስጤማውያን የተነሳ ከአካባቢው ሸሹ። +14 እሱ ግን በእርሻው መካከል ካለበት ንቅንቅ ሳይል መሬቱ እንዳይያዝ አደረገ፤ ፍልስጤማውያንንም መታቸው፤ በመሆኑም ይሖዋ ታላቅ ድል አጎናጸፈ።+ +15 የ���ልስጤም ሠራዊት በረፋይም ሸለቆ+ ሰፍሮ በነበረበት ጊዜ፣ ከ30ዎቹ መሪዎች መካከል ሦስቱ ዓለታማ ወደሆነውና ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ አዱላም ዋሻ ወረዱ።+ +16 በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበር፤ የፍልስጤማውያንም ሠራዊት በቤተልሔም ነበር። +17 ከዚያም ዳዊት “በቤተልሔም+ በር አቅራቢያ ካለው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ የምጠጣው ውኃ ባገኝ ምንኛ ደስ ባለኝ!” በማለት ምኞቱን ገለጸ። +18 በዚህ ጊዜ ሦስቱ ወደ ፍልስጤማውያን ሰፈር ጥሰው በመግባት በቤተልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውኃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ ዳዊት ግን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ውኃውን ለይሖዋ አፈሰሰው። +19 እንዲህም አለ፦ “ለአምላኬ ካለኝ አክብሮት የተነሳ ይህን ማድረግ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው! ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም ልጠጣ ይገባል?+ ውኃውን ያመጡት በሕይወታቸው ቆርጠው ነውና።” በመሆኑም ውኃውን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም። ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎቹ ያደረጓቸው +20 የኢዮዓብ+ ወንድም አቢሳ+ የሌሎች ሦስት ሰዎች መሪ ነበር፤ እሱም ጦሩን ሰብቆ 300 ሰው ገደለ፤ እንደ ሦስቱም ሰዎች ዝነኛ ነበር።+ +21 ከሌሎቹ ሦስት ሰዎች መካከል እሱ ከሁለቱ የበለጠ ታዋቂ ነበር፤ የእነሱም አለቃ ነበር፤ ይሁን እንጂ የመጀመሪያዎቹን ሦስት ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም። +22 የዮዳሄ ልጅ በናያህ+ በቃብጽኤል+ ብዙ ጀብዱ የፈጸመ ደፋር ሰው ነበር። እሱም የሞዓቡን የአርዔልን ሁለት ወንዶች ልጆች ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በሚጥልበት ዕለት ወደ አንድ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።+ +23 ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ እጅግ ግዙፍ+ ግብፃዊ ገደለ። ግብፃዊው የሸማኔ መጠቅለያ+ የሚመስል ጦር በእጁ ይዞ የነበረ ቢሆንም በትር ብቻ ይዞ በመግጠም የግብፃዊውን ጦር ከእጁ ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደለው።+ +24 የዮዳሄ ልጅ በናያህ ያደረጋቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ፤ እሱም እንደ ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች ዝነኛ ነበር። +25 ከሠላሳዎቹም ይበልጥ ታዋቂ የነበረ ቢሆንም የሦስቱን ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም።+ ይሁን እንጂ ዳዊት የራሱ የክብር ዘብ አለቃ አድርጎ ሾመው። +26 በሠራዊቱ ውስጥ የነበሩት ኃያላን ተዋጊዎች የሚከተሉት ናቸው፦ የኢዮዓብ ወንድም አሳሄል፣+ የቤተልሔሙ የዶዶ ልጅ ኤልሃናን፣+ +27 ሃሮራዊው ሻሞት፣ ጴሎናዊው ሄሌጽ፣ +28 የተቆአዊው የኢቄሽ ልጅ ኢራ፣+ አናቶታዊው አቢዔዜር፣+ +29 ሁሻዊው ሲበካይ፣+ አሆሐያዊው ኢላይ፣ +30 ነጦፋዊው ማህራይ፣+ የነጦፋዊው የባአናህ ልጅ ሄሌድ፣+ +31 ከቢንያማውያን+ ወገን የሆነው የጊብዓው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣ ጲራቶናዊው በናያህ፣ +32 የጋአሽ+ ደረቅ ወንዞች ሰው የሆነው ሁራይ፣ አርባዊው አቢዔል፣ +33 ባሁሪማዊው አዝማዌት፣ ሻአልቢማዊው ኤሊያህባ፣ +34 የጊዞናዊው የሃሼም ወንዶች ልጆች፣ የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣ +35 የሃራራዊው የሳካር ልጅ አሂዓም፣ የዑር ልጅ ኤሊፋል፣ +36 መከራታዊው ሄፌር፣ ጴሎናዊው አኪያህ፣ +37 ቀርሜሎሳዊው ሄጽሮ፣ የኤዝባይ ልጅ ናአራይ፣ +38 የናታን ወንድም ኢዩኤል፣ የሃግሪ ልጅ ሚብሃር፣ +39 አሞናዊው ጼሌቅ፣ የጽሩያ ልጅ የኢዮዓብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮታዊው ናሃራይ፤ +40 ይትራዊው ኢራ፣ ይትራዊው ጋሬብ፣ +41 ሂታዊው ኦርዮ፣+ የአህላይ ልጅ ዛባድ፣ +42 የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ አዲና የሮቤላውያን መሪ ነበር፤ ከእሱም ጋር 30 ሰዎች ነበሩ፤ +43 የማአካ ልጅ ሃናን፣ ሚትናዊው ዮሳፍጥ፣ +44 አስታሮታዊው ዑዚያ፣ የአሮዔራዊው የሆታም ልጆች ሻማ እና የኢዔል፤ +45 የሺምሪ ልጅ የዲአዔል፣ ቲጺያዊው ወንድሙ ዮሃ፤ +46 ማሃዋዊው ኤሊዔል፣ የኤልናዓም ልጆች የሪባ��� እና ዮሻውያህ፣ ሞዓባዊው ይትማ፤ +47 ኤሊዔል፣ ኢዮቤድ እና መጾባዊው ያአሲዔል። +2 የእስራኤል+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ሮቤል፣+ ስምዖን፣+ ሌዊ፣+ ይሁዳ፣+ ይሳኮር፣+ ዛብሎን፣+ +2 ዳን፣+ ዮሴፍ፣+ ቢንያም፣+ ንፍታሌም፣+ ጋድ+ እና አሴር።+ +3 የይሁዳ ወንዶች ልጆች ኤር፣ ኦናን እና ሴሎም ነበሩ። እነዚህ ሦስቱ ከከነአናዊቷ ከሹአ ሴት ልጅ የተወለዱለት ናቸው።+ የይሁዳ የበኩር ልጅ የሆነው ኤር ግን ይሖዋን አሳዘነ፤ እሱም ቀሰፈው።+ +4 የይሁዳ ምራት ትዕማር+ ፋሬስን+ እና ዛራን ወለደችለት። የይሁዳ ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ አምስት ነበሩ። +5 የፋሬስ ወንዶች ልጆች ኤስሮን እና ሃሙል+ ነበሩ። +6 የዛራ ወንዶች ልጆች ዚምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ካልኮል እና ዳራ ነበሩ። በአጠቃላይ አምስት ነበሩ። +7 የካርሚ ልጅ አካር ነበር፤ እሱም ለጥፋት ከተለየው ነገር ጋር በተያያዘ እምነት በማጉደሉ በእስራኤል ላይ መዓት አምጥቷል።+ +8 የኤታን ልጅ አዛርያስ ነበር። +9 ለኤስሮን የተወለዱለት ወንዶች ልጆች የራህምኤል፣+ ራም+ እና ከሉባይ ነበሩ። +10 ራም አሚናዳብን+ ወለደ፤ አሚናዳብ የይሁዳ ዘሮች አለቃ የሆነውን ነአሶንን+ ወለደ። +11 ነአሶን ሳልማን+ ወለደ። ሳልማ ቦዔዝን+ ወለደ። +12 ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ። ኢዮቤድ እሴይን+ ወለደ። +13 እሴይ የበኩር ልጁን ኤልያብን፣ ሁለተኛውን ልጁን አቢናዳብን፣+ ሦስተኛውን ልጁን ሺምአን፣+ +14 አራተኛውን ልጁን ናትናኤልን፣ አምስተኛውን ልጁን ራዳይን፣ +15 ስድስተኛውን ልጁን ኦጼምን እና ሰባተኛውን ልጁን ዳዊትን+ ወለደ። +16 እህቶቻቸው ጽሩያ እና አቢጋኤል+ ነበሩ። የጽሩያ ወንዶች ልጆች ሦስት ሲሆኑ እነሱም አቢሳ፣+ ኢዮዓብ+ እና አሳሄል+ ነበሩ። +17 አቢጋኤልም አሜሳይን+ ወለደች፤ የአሜሳይ አባት እስማኤላዊው የቴር ነበር። +18 የኤስሮን ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከአዙባ እና ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ የእሷም ወንዶች ልጆች የሼር፣ ሾባብ እና አርዶን ነበሩ። +19 አዙባ ስትሞት ካሌብ ኤፍራታን+ አገባ፤ እሷም ሁርን+ ወለደችለት። +20 ሁር ዖሪን ወለደ። ዖሪ ባስልኤልን+ ወለደ። +21 ከዚያም ኤስሮን የጊልያድ+ አባት ከሆነው ከማኪር+ ሴት ልጅ ጋር ግንኙነት ፈጸመ። እሷን ያገባት በ60 ዓመቱ ነበር፤ እሷም ሰጉብን ወለደችለት። +22 ሰጉብ ያኢርን+ ወለደ፤ እሱም በጊልያድ+ ምድር 23 ከተሞች ነበሩት። +23 በኋላም ገሹር+ እና ሶርያ+ ቄናትንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች ጨምሮ ሃዎትያኢርን+ ይኸውም 60 ከተሞችን ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የጊልያድ አባት የሆነው የማኪር ዘሮች ነበሩ። +24 ኤስሮን+ በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮን ሚስት የሆነችው አቢያህ፣ የተቆአ+ አባት የሆነውን አሽሁርን+ ወለደችለት። +25 የኤስሮን የበኩር ልጅ የራህምኤል የወለዳቸው ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼም እና አኪያህ ነበሩ። +26 የራህምኤል፣ አታራ የተባለች ሌላ ሚስት አገባ። እሷም የኦናም እናት ነበረች። +27 የየራህምኤል የበኩር ልጅ የራም ወንዶች ልጆች ማአጽ፣ ያሚን እና ኤቄር ነበሩ። +28 የኦናም ወንዶች ልጆች ሻማይ እና ያዳ ነበሩ። የሻማይ ወንዶች ልጆች ናዳብ እና አቢሹር ነበሩ። +29 የአቢሹር ሚስት አቢሃይል ትባል ነበር፤ እሷም አህባንን እና ሞሊድን ወለደችለት። +30 የናዳብ ወንዶች ልጆች ሰሌድ እና አፋይም ነበሩ። ሆኖም ሰሌድ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ። +31 የአፋይም ልጅ ይሽኢ ነበር። የይሽኢ ልጅ ሸሻን ነበር፤ የሸሻን ልጅ አህላይ ነበር። +32 የሻማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች የቴር እና ዮናታን ነበሩ። የቴር ግን ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ። +33 የዮናታን ወንዶች ልጆች ፐሌት እና ዛዛ ነበሩ። እነዚህ የየራህምኤል ዘሮች ነበሩ�� +34 ሸሻን ሴቶች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። ሸሻን፣ ያርሃ የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበረው። +35 ሸሻን ለአገልጋዩ ለያርሃ ሴት ልጁን ዳረለት፤ እሷም አታይን ወለደችለት። +36 አታይ ናታንን ወለደ። ናታን ዛባድን ወለደ። +37 ዛባድ ኤፍላልን ወለደ። ኤፍላል ኢዮቤድን ወለደ። +38 ኢዮቤድ ኢዩን ወለደ። ኢዩ አዛርያስን ወለደ። +39 አዛርያስ ሄሌጽን ወለደ። ሄሌጽ ኤልዓሳን ወለደ። +40 ኤልዓሳ ሲስማይን ወለደ። ሲስማይ ሻሉምን ወለደ። +41 ሻሉም የቃምያህን ወለደ። የቃምያህ ኤሊሻማን ወለደ። +42 የየራህምኤል ወንድም የካሌብ+ ወንዶች ልጆች፣ የዚፍ አባት የሆነው የበኩር ልጁ ሜሻ እንዲሁም የኬብሮን አባት የማሬሻህ ወንዶች ልጆች ነበሩ። +43 የኬብሮን ወንዶች ልጆች ቆሬ፣ ታጱአ፣ ራቄም እና ሼማ ነበሩ። +44 ሼማ የዮርቀአምን አባት ራሃምን ወለደ። ራቄም ሻማይን ወለደ። +45 የሻማይ ልጅ ማኦን ነበር። ማኦን ቤትጹርን+ ወለደ። +46 የካሌብ ቁባት ኤፋ ካራንን፣ ሞጻንና ጋዜዝን ወለደች። ካራን ጋዜዝን ወለደ። +47 የያህዳይ ወንዶች ልጆች ረጌም፣ ኢዮዓታም፣ ጌሻን፣ ጴሌጥ፣ ኤፋ እና ሻአፍ ነበሩ። +48 የካሌብ ቁባት ማአካ ሸበርን እና ቲርሃናን ወለደች። +49 ከጊዜ በኋላም የማድማናን+ አባት ሻአፍን እንዲሁም የማክበናን እና የጊባዓን+ አባት ሻዌን ወለደች። የካሌብ+ ሴት ልጅ አክሳ+ ትባል ነበር። +50 የካሌብ ዘሮች እነዚህ ነበሩ። የኤፍራታ+ የበኩር ልጅ የሆነው የሁር+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የቂርያትየአሪም+ አባት ሾባል፣ +51 የቤተልሔም+ አባት ሳልማ እና የቤትጋዴር አባት ሃሬፍ። +52 የቂርያትየአሪም አባት የሾባል ልጆች ሃሮኤ እና የመኑሆት ሰዎች እኩሌታ ነበሩ። +53 የቂርያትየአሪም ወገኖች ይትራውያን፣+ ፑታውያን፣ ሹማታውያን እና ሚሽራውያን ነበሩ። ጾራውያን+ እና ኤሽታዖላውያን+ የተገኙት ከእነዚህ ወገኖች ነው። +54 የሳልማ ልጆች ቤተልሔም፣+ ነጦፋውያን፣ አትሮት ቤት ዮአብ፣ የማናሃታውያን ሰዎች እኩሌታና ጾራውያን ነበሩ። +55 በያቤጽ የሚኖሩት የጸሐፍት ወገኖች ቲራታውያን፣ ሺመአታውያን እና ሱካታውያን ነበሩ። እነዚህ የሬካብ+ ቤት አባት ከሆነው ከሃማት የተገኙት ቄናውያን+ ናቸው። +26 የበር ጠባቂዎቹ+ ምድብ እንደሚከተለው ነው፦ ከቆሬያውያን መካከል ከአሳፍ ልጆች አንዱ የሆነው የቆረ ልጅ መሺሌሚያህ።+ +2 መሺሌሚያህም ወንዶች ልጆች ነበሩት፦ የበኩር ልጁ ዘካርያስ፣ ሁለተኛው የዲአዔል፣ ሦስተኛው ዘባድያህ፣ አራተኛው ያትንኤል፣ +3 አምስተኛው ኤላም፣ ስድስተኛው የሆሃናን እና ሰባተኛው ኤሊየሆዔናይ። +4 ኦቤድዔዶምም ወንዶች ልጆች ነበሩት፦ የበኩር ልጁ ሸማያህ፣ ሁለተኛው የሆዛባድ፣ ሦስተኛው ዮአስ፣ አራተኛው ሳካር፣ አምስተኛው ናትናኤል፣ +5 ስድስተኛው አሚዔል፣ ሰባተኛው ይሳኮር እና ስምንተኛው ፐኡልታይ፤ አምላክ እነዚህን ልጆች በመስጠት ኦቤድዔዶምን ባረከው። +6 ልጁም ሸማያህ ልጆች ወለደ፤ እነሱም ብቃት ያላቸውና ኃያላን ነበሩ፤ የየቤተሰባቸውም መሪ ሆኑ። +7 የሸማያህ ወንዶች ልጆች ኦትኒ፣ ረፋኤል፣ ኢዮቤድ እና ኤልዛባድ ነበሩ፤ የኤልዛባድ ወንድሞች የሆኑት ኤሊሁ እና ሰማክያህም ብቃት ያላቸው ሰዎች ነበሩ። +8 እነዚህ ሁሉ የኦቤድዔዶም ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ እነሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው አገልግሎቱን ለማከናወን ችሎታና ብቃት ያላቸው ሰዎች ነበሩ፤ ከኦቤድዔዶም ወገን 62 ነበሩ። +9 መሺሌሚያህም+ ብቃት ያላቸው ወንዶች ልጆችና ወንድሞች ነበሩት፤ እነሱም 18 ነበሩ። +10 የሜራሪ ልጅ የሆነው ሆሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት። ሺምሪ የበኩር ልጅ ባይሆንም እንኳ አባቱ የቤተሰቡ መሪ አድርጎ ሾመው፤ +11 ሁለተኛው ኬልቅያስ��� ሦስተኛው ተባልያህ እና አራተኛው ዘካርያስ ነበሩ። የሆሳ ወንዶች ልጆችና ወንድሞች በአጠቃላይ 13 ነበሩ። +12 የበር ጠባቂዎቹ ምድብ መሪዎች ልክ እንደ ወንድሞቻቸው በይሖዋ ቤት በሚቀርበው አገልግሎት የሚያከናውኑት ሥራ ነበራቸው። +13 በመሆኑም ለእያንዳንዱ በር፣ ትንሽ ትልቅ ሳይባል ለሁሉም በየአባቶቻቸው ቤት ዕጣ+ ተጣለ። +14 ከዚያም የምሥራቁ በር ዕጣ ለሸሌምያህ ወጣ። አስተዋይ መካሪ ለሆነው ለልጁ ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ በዕጣውም መሠረት የሰሜን በር ደረሰው። +15 ኦቤድዔዶም በደቡብ በኩል ያለው በር ደረሰው፤ ወንዶች ልጆቹ+ ደግሞ ግምጃ ቤቶቹ ደረሷቸው። +16 ሹፒም እና ሆሳ+ በአቀበቱ መንገድ ባለው በሻለከት በር አቅራቢያ የሚገኘው የምዕራብ በር ደረሳቸው፤ የዘብ ጠባቂ ቡድኖቹ ጎን ለጎን ቆመው ይጠብቁ ነበር፤ +17 በምሥራቅ በኩል ስድስት ሌዋውያን ነበሩ፤ በሰሜን በኩል በየቀኑ አራት፣ በደቡብ በኩል በየቀኑ አራት እንዲሁም ግምጃ ቤቶቹን+ ሁለት ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር፤ +18 በምዕራብ በኩል ባለው መተላለፊያ በጎዳናው+ ላይ አራት፣ በመተላለፊያው ላይ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር። +19 የቆሬያውያንና የሜራራውያን ወንዶች ልጆች የበር ጥበቃ ምድብ ይህ ነበር። +20 ከሌዋውያን መካከል አኪያህ በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚገኙት ግምጃ ቤቶችና ቅዱስ የሆኑ ነገሮች ያሉባቸው ግምጃ ቤቶች ኃላፊ ነበር።+ +21 የላዳን ወንዶች ልጆች፦ የላዳን ወገን ከሆኑት ከጌድሶናውያን ወንዶች ልጆች ማለትም የጌድሶናዊው የላዳን ወገን ከሆኑት የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች መካከል የሂኤሊ+ +22 እንዲሁም የየሂኤሊ ወንዶች ልጆች ዜታምና ወንድሙ ኢዩኤል ነበሩ። እነሱም በይሖዋ ቤት የሚገኙት ግምጃ ቤቶች+ ኃላፊዎች ነበሩ። +23 ከአምራማውያን፣ ከይጽሃራውያን፣ ከኬብሮናውያን እና ከዑዚኤላውያን+ መካከል፣ +24 የሙሴ ልጅ፣ የጌርሳም ልጅ ሸቡኤል የግምጃ ቤቶቹ ኃላፊ ነበር። +25 የኤሊዔዘር+ ዘሮች የሆኑት ወንድሞቹ ረሃቢያህ፣+ የሻያህ፣ ዮራም፣ ዚክሪ እና ሸሎሞት ነበሩ። +26 ሸሎሞትና ወንድሞቹ ንጉሥ ዳዊት፣+ የአባቶች ቤት መሪዎች፣+ የሺህ አለቆቹ፣ የመቶ አለቆቹና የሠራዊቱ አለቆች የቀደሷቸው ቅዱስ ነገሮች+ የሚገኙባቸው ግምጃ ቤቶች ሁሉ ኃላፊዎች ነበሩ። +27 የይሖዋን ቤት ለማደስ በጦርነት+ ከተገኘው ምርኮ+ ውስጥ የተወሰነውን ቀደሱ፤ +28 በተጨማሪም ባለ ራእዩ+ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አበኔር+ እና የጽሩያ+ ልጅ ኢዮዓብ+ የቀደሷቸውን ነገሮች ሁሉ በኃላፊነት ይይዙ ነበር። ማንኛውም ሰው የቀደሰው ነገር በሸሎሚት እና በወንድሞቹ እጅ ይሆን ነበር። +29 ከይጽሃራውያን+ መካከል ኬናንያ እና ወንዶች ልጆቹ ከአምላክ ቤት ውጭ ባለው የአስተዳደር ሥራ ላይ በእስራኤል አለቆችና ዳኞች+ ሆነው ተመደቡ። +"30 ከኬብሮናውያን+ መካከል ብቁ የሆኑት ሃሻብያህ እና ወንድሞቹ 1,700 ነበሩ፤ እነሱም ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ባለው የእስራኤል ምድር ከይሖዋ ሥራ ሁሉና ከንጉሡ አገልግሎት ጋር በተያያዘ የማስተዳደር ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።" +31 የሪያህ+ የኬብሮናውያን አባቶች ቤቶችና ቤተሰቦች መሪ ነበር። በዳዊት ዘመነ መንግሥት 40ኛ ዓመት+ ምርመራ ተካሄደ፤ በእነሱም መካከል በጊልያድ፣ ያዜር+ በተባለ ቦታ ኃያላን የሆኑና ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ። +"32 የአባቶች ቤቶች መሪዎች የሆኑ ብቃት ያላቸው ወንድሞቹ 2,700 ነበሩ። በመሆኑም ንጉሥ ዳዊት ከእውነተኛው አምላክና ከንጉሡ ጉዳዮች ሁሉ ጋር በተያያዘ በሮቤላውያን፣ በጋዳውያንና በምናሴያውያን ነገድ እኩሌታ ላይ ሾማቸው።" +4 የይሁዳ ወንዶች ልጆች ፋሬስ፣+ ኤስሮን፣+ ካርሚ፣ ሁር+ እና ሾባል+ ነበሩ። +2 የሾባል ልጅ ረአያህ ያ���ትን ወለደ፤ ያሃት አሁማይን እና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾራውያን+ ቤተሰቦች ናቸው። +3 የኤጣም+ አባት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይድባሽ (የእህታቸውም ስም ሃጽሌልጶኒ ይባል ነበር)፤ +4 ጰኑኤል የጌዶር አባት ነው፤ ኤጼር ደግሞ የሁሻ አባት ነው። እነዚህ የኤፍራታ የበኩር ልጅና የቤተልሔም+ አባት የሆነው የሁር+ ወንዶች ልጆች ነበሩ። +5 የተቆአ+ አባት አሽሁር፣+ ሄላ እና ናዕራ የሚባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት። +6 ናዕራ አሁዛምን፣ ሄፌርን፣ ተመናይን እና ሃሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ የናዕራ ወንዶች ልጆች ናቸው። +7 የሄላ ወንዶች ልጆች ደግሞ ጸረት፣ ይጽሃር እና ኤትናን ናቸው። +8 ቆጽ አኑብን እና ጾበባን ወለደ፤ ደግሞም የሃሩም ልጅ የሆነው የአሃርሔል ቤተሰቦች የተገኙት ከእሱ ነው። +9 ያቤጽ ከወንድሞቹ ይበልጥ የተከበረ ሰው ነበር፤ እናቱም “በሥቃይ ወለድኩት” ስትል ያቤጽ የሚል ስም አወጣችለት። +10 ያቤጽ እንዲህ ሲል የእስራኤልን አምላክ ተማጸነ፦ “እንድትባርከኝና ግዛቴን እንድታሰፋልኝ እንዲሁም ጉዳት እንዳይደርስብኝ እጅህ ከእኔ ጋር እንድትሆንና ከጥፋት እንድትጠብቀኝ እለምንሃለሁ!” አምላክም የለመነውን ሰጠው። +11 የሹሃ ወንድም ከሉብ መሂርን ወለደ፤ መሂርም ኤሽቶንን ወለደ። +12 ኤሽቶን ቤትራፋን፣ ፓሰአህን እና የኢርናሃሽ አባት የሆነውን ተሂናን ወለደ። እነዚህ የረካ ሰዎች ነበሩ። +13 የቀናዝ ወንዶች ልጆች ኦትኒኤል+ እና ሰራያህ ነበሩ፤ የኦትኒኤል ልጅ ደግሞ ሃታት ነበር። +14 መኦኖታይ ኦፍራን ወለደ። ሰራያህ የገሃራሺም አባት የሆነውን ኢዮዓብን ወለደ፤ እንዲህ ተብለው የተጠሩት የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ስለነበሩ ነው። +15 የየፎኒ ልጅ የካሌብ+ ወንዶች ልጆች ኢሩ፣ ኤላህ እና ናአም ነበሩ፤ የኤላህ ልጅ ቀናዝ ነበር። +16 የይሃሌልዔል ወንዶች ልጆች ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲሪያ እና አሳርኤል ነበሩ። +17 የኤዝራ ወንዶች ልጆች የቴር፣ መሬድ፣ ኤፌር እና ያሎን ነበሩ፤ እሷ ሚርያምን፣ ሻማይን እና የኤሽተሞዓ አባት የሆነውን ይሽባን ወለደች። +18 (አይሁዳዊት ሚስቱ ደግሞ የጌዶርን አባት የሬድን፣ የሶኮን አባት ሄቤርን እና የዛኖሃን አባት የቁቲኤልን ወለደች።) እነዚህ የመሬድ ሚስት የሆነችው የፈርዖን ልጅ የቢትያ ወንዶች ልጆች ናቸው። +19 የናሃም እህት የሆነችው የሆዲያህ ሚስት ወንዶች ልጆች የጋርሚያዊው የቀኢላና የማአካታዊው የኤሽተሞዓ አባቶች ነበሩ። +20 የሺሞን ወንዶች ልጆች አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሃናን እና ቲሎን ነበሩ። የይሽኢ ወንዶች ልጆች ዞሄት እና ቤንዞሄት ነበሩ። +21 የይሁዳ ልጅ የሆነው የሴሎም+ ወንዶች ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ የለቃ አባት ኤር፣ የማሬሻህ አባት ላአዳ እንዲሁም (ጥራት ያለው ጨርቅ የሚያመርቱት ሠራተኞች ወገን የሆኑት) የአሽቤዓ ቤት ሰዎች፣ +22 ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ሞዓባውያን ሴቶችን ያገቡት ዮአስ እና ሳራፍ እንዲሁም ያሹቢላሔም። እነዚህ መዛግብት ጥንታዊ ናቸው። +23 እነሱም በነጣኢም እና በገዴራ የሚኖሩ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ። ለንጉሡ እየሠሩ በዚያ ይኖሩ ነበር። +24 የስምዖን+ ወንዶች ልጆች ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪብ፣ ዛራ እና ሻኡል+ ናቸው። +25 የሻኡል ልጅ ሻሉም፣ የሻሉም ልጅ ሚብሳም እና የሚብሳም ልጅ ሚሽማ ነበሩ። +26 ሃሙኤል የሚሽማ ልጅ ነበር፤ የሃሙኤል ልጅ ዛኩር፣ የዛኩር ልጅ ሺምአይ ነበር። +27 ሺምአይ 16 ወንዶችና 6 ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ከቤተሰቦቻቸውም መካከል እንደ ይሁዳ ሰዎች ብዙ ልጆች ያለው አልነበረም።+ +28 እነሱ የኖሩባቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ቤርሳቤህ፣+ ሞላዳ፣+ ሃጻርሹአል፣+ +29 ባላ፣ ኤጼም፣+ ቶላድ�� +30 ባቱኤል፣+ ሆርማ፣+ ጺቅላግ፣+ +31 ቤትማርካቦት፣ ሃጻርሱሲም፣+ ቤትቢርኢ እና ሻአራይም። ዳዊት እስከ ነገሠበት ጊዜ ድረስ በእነዚህ ከተሞች ይኖሩ ነበር። +32 ሰፈሮቻቸው ኤጣም፣ አይን፣ ሪሞን፣ ቶከን እና አሻን+ ሲሆኑ በአጠቃላይ አምስት ከተሞች ነበሩ፤ +33 በእነዚህም ከተሞች ዙሪያ ያሉት ሰፈሮቻቸው እስከ ባአል ድረስ ይደርሱ ነበር። የትውልድ መዝገባቸውና የመኖሪያ ቦታዎቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። +34 በተጨማሪም መሾባብ፣ ያምሌክ፣ የአሜስያስ ልጅ ዮሻ፣ +35 ኢዩኤል፣ የአሲዔል ልጅ፣ የሰራያህ ልጅ፣ የዮሽቢያህ ልጅ ኢዩ፣ +36 ኤሊዮዔናይ፣ ያዕቆባ፣ የሾሃያህ፣ አሳያህ፣ አዲዔል፣ የሲሚኤል፣ በናያህ፣ +37 የሸማያህ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፣ የየዳያህ ልጅ፣ የአሎን ልጅ፣ የሺፊ ልጅ ዚዛ፤ +38 እነዚህ በስም የተዘረዘሩት ሰዎች የየቤተሰቦቻቸው አለቆች ናቸው፤ የወገኖቻቸውም ቁጥር እየበዛ ሄደ። +39 እነሱም ለመንጎቻቸው የግጦሽ መሬት ለማግኘት እስከ ጌዶር መግቢያ፣ በሸለቆው በስተ ምሥራቅ በኩል እስካለው ስፍራ ድረስ ሄዱ። +40 በመጨረሻም ለም የሆነ ጥሩ የግጦሽ መሬት አገኙ፤ ምድሪቱም እጅግ ሰፊ እንዲሁም ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት ነበረች። በቀድሞ ዘመን በዚያ የሚኖሩት የካም+ ዝርያዎች ነበሩ። +41 እነዚህ በስም የተዘረዘሩት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ+ ዘመን መጥተው የካም ዝርያዎችን ድንኳንና በዚያ ይኖሩ የነበሩትን መኡኒማውያንን መቱ። ፈጽመውም አጠፏቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ ደብዛቸው የለም፤ በዚያ ለመንጎቻቸው የሚሆን የግጦሽ መሬት ስለነበር በእነሱ ቦታ ላይ ሰፈሩ። +42 ከስምዖናውያን መካከል የተወሰኑት ይኸውም 500 ወንዶች በይሽኢ ወንዶች ልጆች በጰላጥያህ፣ በነአርያህ፣ በረፋያህ እና በዑዚኤል መሪነት ወደ ሴይር+ ተራራ ወጡ። +43 እነሱም ከአማሌቃውያን+ መካከል አምልጠው የቀሩትን ሰዎች መቱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይኖራሉ። +16 የእውነተኛውን አምላክ ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አስቀመጡት፤+ ከዚያም የሚቃጠሉ መባዎችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን በእውነተኛው አምላክ ፊት አቀረቡ።+ +2 ዳዊት የሚቃጠሉትን መባዎችና+ የኅብረት መሥዋዕቶቹን+ አቅርቦ ሲጨርስ ሕዝቡን በይሖዋ ስም ባረከ። +3 በተጨማሪም ለእስራኤላውያን ሁሉ፣ ለእያንዳንዱ ወንድና ሴት አንድ ዳቦ፣ አንድ የቴምር ጥፍጥፍና አንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ አከፋፈለ። +4 ከዚያም የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ያከብሩ፣ ያመሰግኑና ያወድሱ ዘንድ የተወሰኑ ሌዋውያንን በይሖዋ ታቦት ፊት እንዲያገለግሉ ሾመ።+ +5 መሪው አሳፍ+ ነበር፤ ከእሱ ቀጥሎ ዘካርያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ የኢዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ማቲትያህ፣ ኤልያብ፣ በናያህ፣ ኦቤድዔዶም እና የኢዔል+ ባለ አውታር መሣሪያዎችና በገና ይጫወቱ ነበር፤+ አሳፍ ደግሞ ሲምባል ይጫወት ነበር፤+ +6 ካህናቱ በናያህ እና ያሃዚኤል በእውነተኛው አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ዘወትር መለከት ይነፉ ነበር። +7 በዚያ ቀን ዳዊት ለመጀመሪያ ጊዜ ለይሖዋ የምስጋና መዝሙር በማቀናበር አሳፍና+ ወንድሞቹ እንዲዘምሩት ሰጣቸው፦ +8 “ይሖዋን አመስግኑ፤+ ስሙን ጥሩ፤ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+ +9 ለእሱ ዘምሩ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩለት፤+አስደናቂ በሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ላይ አሰላስሉ።+ +10 በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ።+ ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።+ +11 ይሖዋንና ብርታቱን ፈልጉ።+ ፊቱን ሁልጊዜ እሹ።+ +12 ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣ተአምራቱንና የተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤+ +13 እናንተ የአገልጋዩ የእስራኤል ዘሮች፣+እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣+ ይህን አስታውሱ። +14 እሱ ይሖዋ አምላካችን ነው።+ ፍርዱ በመላው ምድር ላይ ነው።+ +15 ቃል ኪዳኑን ለዘላለም አስቡ፤የገባውን ቃል እስከ ሺህ ትውልድ አስታውሱ፤+ +16 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣+ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አስቡ።+ +17 ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤+ +18 ‘የከነአንን ምድርርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ’ አለ።+ +19 ይህን የተናገረው በቁጥር ጥቂት፣አዎ፣ በጣም ጥቂት በነበራችሁ ጊዜ ነው፤ በምድሪቱም ላይ የባዕድ አገር ሰዎች ነበራችሁ።+ +20 እነሱም ከአንዱ ብሔር ወደ ሌላው ብሔር፣ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ሕዝብ ተንከራተቱ።+ +21 ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቀደም፤+ይልቁንም ለእነሱ ሲል ነገሥታትን ገሠጸ፤+ +22 ‘የቀባኋቸውን አገልጋዮቼን አትንኩ፤በነቢያቴም ላይ አንዳች ክፉ ነገር አታድርጉ’ አላቸው።+ +23 መላዋ ምድር ለይሖዋ ትዘምር! ማዳኑን በየቀኑ አሳውቁ!+ +24 ክብሩን በብሔራት፣አስደናቂ ሥራዎቹንም በሕዝቦች ሁሉ መካከል አስታውቁ። +25 ይሖዋ ታላቅ ነውና፤ ደግሞም እጅግ ሊወደስ ይገባዋል። ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ የሚፈራ ነው።+ +26 የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ሁሉ ከንቱ ናቸው፤+ይሖዋ ግን ሰማያትን የሠራ አምላክ ነው።+ +27 ሞገስና ግርማ በፊቱ ናቸው፤+ብርታትና ደስታ እሱ በሚኖርበት ስፍራ ይገኛሉ።+ +28 እናንተ የሕዝብ ነገዶች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+ +29 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ፤+ስጦታ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ።+ ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ ለይሖዋ ስገዱ።+ +30 ምድር ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጪ! ምድር በጽኑ ተመሥርታለች፤ ከቦታዋ ልትንቀሳቀስ አትችልም።+ +31 ሰማያት ሐሴት ያድርጉ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤+በብሔራት መካከል ‘ይሖዋ ነገሠ!’ ብላችሁ አስታውቁ።+ +32 ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማ፤መስኩና በላዩ ላይ ያለው ሁሉ ሐሴት ያድርግ። +33 የዱር ዛፎችም በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ፤እሱ በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነውና። +34 ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ +35 እንዲህም በሉ፦ ‘አዳኝ አምላካችን ሆይ፣ አድነን፤+ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣+አንተንም በማወደስ ሐሴት እንድናደርግ፣+ከብሔራት ሰብስበን፤ ከእነሱም ታደገን። +36 የእስራኤል አምላክ ይሖዋከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ።’” ሕዝቡም ሁሉ “አሜን!” አሉ፤ ይሖዋንም አወደሱ። +37 ከዚያም ዳዊት በዕለታዊው ልማድ መሠረት+ በታቦቱ ፊት ዘወትር እንዲያገለግሉ+ አሳፍንና+ ወንድሞቹን በዚያ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው። +38 ኦቤድዔዶምና 68 ወንድሞቹ እንዲሁም የየዱቱን ልጅ ኦቤድዔዶምና ሆሳ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤ +39 ካህኑ ሳዶቅና+ አብረውት የሚያገለግሉት ካህናት ደግሞ በገባኦን በሚገኘው ከፍ ያለ ቦታ፣+ በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊት ነበሩ፤ +40 ይህም የሆነው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ዘወትር ጠዋትና ማታ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ እንዲያቀርቡና ይሖዋ ለእስራኤል በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በሕጉ ላይ የሰፈረውን ሁሉ እንዲፈጽሙ ነው።+ +41 ይሖዋን ያመሰግኑ ዘንድ ሄማን እና የዱቱን+ እንዲሁም በስም ተጠቅሰው የተመረጡት የቀሩት ሰዎች ከእነሱ ጋር ነበሩ፤+ ምክንያቱም “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል”፤+ +42 ደግሞም መለከት፣ ሲምባልና እውነተኛውን አምላክ ለማወደስ የሚያገለግሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ይጫወቱ ዘንድ ሄማን+ እና የዱቱን ከእነሱ ጋር ነበሩ፤ የየዱቱን+ ወንዶች ልጆች ደግሞ በር ላይ ተመድበው ነበር። +43 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ዳዊትም ቤተሰቡን ለ��ባረክ ወደ ቤቱ ሄደ። +6 የሌዊ+ ወንዶች ልጆች ጌድሶን፣ ቀአት+ እና ሜራሪ+ ነበሩ። +2 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣+ ኬብሮን እና ዑዚኤል+ ነበሩ። +3 የአምራም+ልጆች አሮን፣+ ሙሴ+ እና ሚርያም+ ነበሩ። የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብ፣ አቢሁ፣+ አልዓዛር+ እና ኢታምር+ ነበሩ። +4 አልዓዛር ፊንሃስን+ ወለደ፤ ፊንሃስ አቢሹዓን ወለደ። +5 አቢሹዓ ቡቂን ወለደ፤ ቡቂ ዑዚን ወለደ። +6 ዑዚ ዘራህያህን ወለደ፤ ዘራህያህ መራዮትን ወለደ። +7 መራዮት አማርያህን ወለደ፤ አማርያህ አኪጡብን+ ወለደ። +8 አኪጡብ ሳዶቅን+ ወለደ፤ ሳዶቅ አኪማዓስን+ ወለደ። +9 አኪማዓስ አዛርያስን ወለደ፤ አዛርያስ ዮሃናንን ወለደ። +10 ዮሃናን አዛርያስን ወለደ። እሱም ሰለሞን በኢየሩሳሌም በገነባው ቤት ውስጥ ካህን ሆኖ ያገለግል ነበር። +11 አዛርያስ አማርያህን ወለደ፤ አማርያህ አኪጡብን ወለደ። +12 አኪጡብ ሳዶቅን+ ወለደ፤ ሳዶቅ ሻሉምን ወለደ። +13 ሻሉም ኬልቅያስን+ ወለደ፤ ኬልቅያስ አዛርያስን ወለደ። +14 አዛርያስ ሰራያህን+ ወለደ፤ ሰራያህ የሆጼዴቅን+ ወለደ። +15 ይሖዋ፣ ይሁዳና ኢየሩሳሌም በናቡከደነጾር እጅ በግዞት እንዲወሰዱ ሲያደርግ የሆጼዴቅም በግዞት ተወሰደ። +16 የሌዊ ወንዶች ልጆች ጌርሳም፣ ቀአት እና ሜራሪ ነበሩ። +17 የጌርሳም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ሊብኒ እና ሺምአይ።+ +18 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣ ኬብሮን እና ዑዚኤል+ ነበሩ። +19 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ። የሌዋውያን ቤተሰቦች በየአባቶቻቸው ስም ሲዘረዘሩ እነዚህ ናቸው፦+ +20 ጌርሳም፣+ የጌርሳም ልጅ ሊብኒ፣ የሊብኒ ልጅ ያሃት፣ የያሃት ልጅ ዚማ፣ +21 የዚማ ልጅ ዮአህ፣ የዮአህ ልጅ ኢዶ፣ የኢዶ ልጅ ዛራ፣ የዛራ ልጅ የአትራይ። +22 የቀአት ወንዶች ልጆች፦ አሚናዳብ፣ የአሚናዳብ ልጅ ቆሬ፣+ የቆሬ ልጅ አሲር፣ +23 የአሲር ልጅ ሕልቃና፣ የሕልቃና ልጅ ኤቢያሳፍ፣+ የኤቢያሳፍ ልጅ አሲር፤ +24 የአሲር ልጅ ታሃት፣ የታሃት ልጅ ዑሪኤል፣ የዑሪኤል ልጅ ዖዝያ፣ የዖዝያ ልጅ ሻኡል። +25 የሕልቃና ወንዶች ልጆች አማሳይ እና አሂሞት ነበሩ። +26 ጾፋይ የሕልቃና ልጅ ነበር፤ የጾፋይ ልጅ ናሃት፣ +27 የናሃት ልጅ ኤልያብ፣ የኤልያብ ልጅ የሮሃም እና የየሮሃም ልጅ ሕልቃና+ ነበር። +28 የሳሙኤል+ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ኢዩኤልና ሁለተኛው አቢያህ+ ነበሩ። +29 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፦ ማህሊ፣+ የማህሊ ልጅ ሊብኒ፣ የሊብኒ ልጅ ሺምአይ፣ የሺምአይ ልጅ ዖዛ፣ +30 የዖዛ ልጅ ሺምአ፣ የሺምአ ልጅ ሃጊያህ፣ የሃጊያህ ልጅ አሳያህ። +31 ዳዊት፣ ታቦቱ በይሖዋ ቤት ከተቀመጠ በኋላ በዚያ የሚዘመረውን መዝሙር እንዲመሩ የሾማቸው እነዚህ ነበሩ።+ +32 እነሱ ሰለሞን የይሖዋን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪገነባ+ ድረስ በማደሪያ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ከመዝሙር ጋር የተያያዘ ኃላፊነት ተሰጣቸው፤ በተሰጣቸውም ኃላፊነት መሠረት አገልግሎታቸውን ያከናውኑ ነበር።+ +33 ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር አብረው የሚያገለግሉት ሰዎች እነዚህ ነበሩ፦ ከቀአታውያን መካከል ዘማሪው ሄማን፣+ የኢዩኤል+ ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣ +34 የሕልቃና+ ልጅ፣ የየሮሃም ልጅ፣ የኤሊዔል ልጅ፣ የቶአ ልጅ፣ +35 የጹፍ ልጅ፣ የሕልቃና ልጅ፣ የማሃት ልጅ፣ የአማሳይ ልጅ፣ +36 የሕልቃና ልጅ፣ የኢዩኤል ልጅ፣ የአዛርያስ ልጅ፣ የሶፎንያስ ልጅ፣ +37 የታሃት ልጅ፣ የአሲር ልጅ፣ የኤቢያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ፣ +38 የይጽሃር ልጅ፣ የቀአት ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣ የእስራኤል ልጅ ነበር። +39 ወንድሙ አሳፍ+ በቀኙ በኩል ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የቤራክያህ ልጅ፣ የሺምአ ልጅ፣ +40 የሚካኤል ልጅ፣ የባአሴያህ ልጅ፣ የማልኪያህ ልጅ፣ +41 የኤትኒ ልጅ፣ የዛ�� ልጅ፣ የአዳያህ ልጅ፣ +42 የኤታን ልጅ፣ የዚማ ልጅ፣ የሺምአይ ልጅ፣ +43 የያሃት ልጅ፣ የጌርሳም ልጅ፣ የሌዊ ልጅ ነበር። +44 ወንድሞቻቸው የሆኑት የሜራሪ+ ዘሮች በስተ ግራ የነበሩ ሲሆን ኤታን+ በዚያ ነበር፤ እሱም የቂሺ ልጅ፣ የአብዲ ልጅ፣ የማሉክ ልጅ፣ +45 የሃሻብያህ ልጅ፣ የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣ +46 የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣ የሼሜር ልጅ፣ +47 የማህሊ ልጅ፣ የሙሺ ልጅ፣ የሜራሪ ልጅ፣ የሌዊ ልጅ ነበር። +48 ሌዋውያን ወንድሞቻቸው በእውነተኛው አምላክ ቤት፣ በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ ሁሉንም አገልግሎት እንዲያከናውኑ ተሹመው ነበር።+ +49 አሮንና ወንዶች ልጆቹ+ የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች ጋር የተያያዙትን ሥራዎች በማከናወን ለእስራኤል ቤት ለማስተሰረይ፣+ የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያና+ በዕጣን መሠዊያው+ ላይ የሚጨስ መሥዋዕት አቀረቡ። +50 የአሮን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፦+ የአሮን ልጅ አልዓዛር፣+ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ፣ የፊንሃስ ልጅ አቢሹዓ፣ +51 የአቢሹዓ ልጅ ቡቂ፣ የቡቂ ልጅ ዑዚ፣ የዑዚ ልጅ ዘራህያህ፣ +52 የዘራህያህ ልጅ መራዮት፣ የመራዮት ልጅ አማርያህ፣ የአማርያህ ልጅ አኪጡብ፣+ +53 የአኪጡብ ልጅ ሳዶቅ፣+ የሳዶቅ ልጅ አኪማዓስ። +54 በክልላቸው ውስጥ በሰፈሮቻቸው የሚገኙት የመኖሪያ ቦታዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፦ የቀአታውያን ቤተሰብ የሆኑት የአሮን ዘሮች የመጀመሪያው ዕጣ ደረሳቸው፤ +55 በይሁዳ ምድር የምትገኘውን ኬብሮንን+ በዙሪያዋ ካሉት የግጦሽ መሬቶች ጋር ሰጧቸው። +56 ይሁንና የከተማዋን እርሻና ሰፈሮቿን ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ+ ሰጡ። +57 ለአሮንም ዘሮች የመማጸኛ ከተሞችን፣+ ኬብሮንን+ እንዲሁም ሊብናንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ ያቲርን፣+ ኤሽተሞዓንና የግጦሽ መሬቶቿን ሰጡ፤+ +58 ሂሌንንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ደቢርንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ +59 አሻንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ ቤትሼሜሽንና+ የግጦሽ መሬቶቿን ሰጡ፤ +60 ከቢንያም ነገድም ጌባና+ የግጦሽ መሬቶቿ፣ አለሜትና የግጦሽ መሬቶቿ እንዲሁም አናቶትና+ የግጦሽ መሬቶቿ ተሰጣቸው። ለወገኖቻቸው የተሰጡት ከተሞቻቸው በአጠቃላይ 13 ከተሞች ነበሩ።+ +61 ለቀሩት ቀአታውያን ከሌላው ነገድ ቤተሰብና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ+ ላይ አሥር ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው። +62 ለጌርሳማውያን በየቤተሰቦቻቸው ከይሳኮር ነገድ፣ ከአሴር ነገድ፣ ከንፍታሌም ነገድና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ 13 ከተሞች መደቡላቸው።+ +63 ለሜራራውያን በየቤተሰቦቻቸው ከሮቤል ነገድ፣ ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድ 12 ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው።+ +64 በዚህ መንገድ እስራኤላውያን ለሌዋውያኑ እነዚህን ከተሞች ከነግጦሽ መሬታቸው ሰጧቸው።+ +65 በተጨማሪም ከይሁዳ ነገድ፣ ከስምዖን ነገድና ከቢንያም ነገድ በስማቸው የተጠቀሱትን እነዚህን ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው። +66 ከቀአታውያን ቤተሰቦች መካከል የተወሰኑት ከኤፍሬም ነገድ ያገኟቸው የራሳቸው የሆኑ ከተሞች ነበሯቸው።+ +67 እነሱም የመማጸኛ ከተሞቹን፣ ተራራማ በሆነው የኤፍሬም ምድር ያለችውን ሴኬምንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ጌዜርንና+ የግጦሽ መሬቶቿን ሰጧቸው፤ +68 ዮቅመአምንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ቤትሆሮንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ +69 አይሎንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ጋትሪሞንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን ሰጧቸው፤ +70 ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ ደግሞ አኔርንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ቢልአምንና የግጦሽ መሬቶቿን ለቀሩት የቀአታውያን ቤተሰቦች ሰጧቸው። +71 ለጌርሳማውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ በባሳን የምትገኘውን ጎላንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም አስታሮትንና የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤+ +72 ከይሳኮር ነገድም ቃዴሽንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ዳብራትንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣+ +73 ራሞትንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም አኔምንና የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤ +74 ከአሴር ነገድም ማሻልንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ አብዶንንና የግጦሽ መሬቶቿን፣+ +75 ሁቆቅንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ሬሆብንና+ የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤ +76 ከንፍታሌም ነገድም በገሊላ+ የምትገኘውን ቃዴሽንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ ሃሞንንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ቂርያታይምንና የግጦሽ መሬቶቿን ሰጧቸው። +77 ለቀሩት ሜራራውያን ከዛብሎን+ ነገድ ላይ ሪሞኖንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ታቦርንና የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤ +78 ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፣ በኢያሪኮ ካለው የዮርዳኖስ አካባቢ ከሮቤል ነገድ ላይ በምድረ በዳ የምትገኘው ቤጼርና የግጦሽ መሬቶቿ፣ ያሃጽና+ የግጦሽ መሬቶቿ ተሰጧቸው፤ +79 ደግሞም ቀደሞትና+ የግጦሽ መሬቶቿ እንዲሁም መፋአትና የግጦሽ መሬቶቿ ተሰጧቸው፤ +80 ከጋድ ነገድ ላይ ደግሞ በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ማሃናይምንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ +81 ሃሽቦንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ያዜርንና+ የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው። +25 በተጨማሪም ዳዊትና የአገልግሎት ቡድኖቹ አለቆች በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና+ በሲምባል+ ትንቢት በመናገር እንዲያገለግሉ ከአሳፍ፣ ከሄማን እና ከየዱቱን+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዳንዶቹን ለዩ። ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑት ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ +2 ከአሳፍ ወንዶች ልጆች መካከል ዛኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያህ እና አሼርዔላ፤ እነዚህ በአሳፍ አመራር ሥር ያሉ የአሳፍ ወንዶች ልጆች ሲሆኑ በንጉሡ አመራር ሥር ሆነው ትንቢት ይናገሩ ነበር። +3 ከየዱቱን፣+ የየዱቱን ወንዶች ልጆች፦ ጎዶልያስ፣ ጸሪ፣ የሻያህ፣ ሺምአይ፣ ሃሻብያህ እና ማቲትያህ፤+ እነዚህ ስድስቱ በአባታቸው በየዱቱን አመራር ሥር ሲሆኑ ይሖዋን እያመሰገኑና እያወደሱ+ በበገና ትንቢት ይናገሩ ነበር። +4 ከሄማን፣+ የሄማን ወንዶች ልጆች፦ ቡቂያ፣ ማታንያህ፣ ዑዚኤል፣ ሸቡኤል፣ የሪሞት፣ ሃናንያህ፣ ሃናኒ፣ ኤሊዓታህ፣ ጊዳልቲ፣ ሮማምቲኤዘር፣ ዮሽበቃሻ፣ ማሎቲ፣ ሆቲር እና ማሃዚዮት። +5 እነዚህ ሁሉ የሄማን ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ እሱም ለአምላክ ክብር ያመጣ ዘንድ የእውነተኛውን አምላክ ቃል የሚገልጽ የንጉሡ ባለ ራእይ ነበር፤ እውነተኛውም አምላክ ለሄማን 14 ወንዶች ልጆችና 3 ሴቶች ልጆች ሰጠው። +6 እነዚህ ሁሉ በእውነተኛው አምላክ ቤት ለሚቀርበው አገልግሎት በአባታቸው አመራር ሥር ሆነው በሲምባል፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና በበገና+ በይሖዋ ቤት ይዘምሩ ነበር። አሳፍ፣ የዱቱን እና ሄማን በንጉሡ አመራር ሥር ነበሩ። +7 የእነሱና ለይሖዋ በሚቀርበው መዝሙር የሠለጠኑት ወንድሞቻቸው ይኸውም በዚህ የተካኑት ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 288 ነበር። +8 በመሆኑም ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ታናሽም ሆነ ታላቅ፣ በሙያው የተካነም ሆነ ተማሪ ሳይባል ሁሉም ዕጣ+ ተጣጣሉ። +9 የመጀመሪያው ዕጣ ለአሳፍ ልጅ ለዮሴፍ+ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎዶልያስ+ ወጣ (እሱና ወንድሞቹ እንዲሁም ወንዶች ልጆቹ 12 ነበሩ)፤ +10 ሦስተኛው ለዛኩር፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +11 አራተኛው ለይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +12 አምስተኛው ለነታንያህ፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +13 ስድስተኛው ለቡቂያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +14 ሰባተኛው ለየሳርኤላ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ��ጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +15 ስምንተኛው ለየሻያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +16 ዘጠነኛው ለማታንያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +17 አሥረኛው ለሺምአይ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +18 አሥራ አንደኛው ለአዛርዔል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +19 አሥራ ሁለተኛው ለሃሻብያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +20 አሥራ ሦስተኛው ለሹባኤል፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +21 አሥራ አራተኛው ለማቲትያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +22 አሥራ አምስተኛው ለየሬሞት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +23 አሥራ ስድስተኛው ለሃናንያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +24 አሥራ ሰባተኛው ለዮሽበቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +25 አሥራ ስምንተኛው ለሃናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +26 አሥራ ዘጠነኛው ለማሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +27 ሃያኛው ለኤሊዓታህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +28 ሃያ አንደኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +29 ሃያ ሁለተኛው ለጊዳልቲ፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +30 ሃያ ሦስተኛው ለማሃዚዮት፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ +31 ሃያ አራተኛው ለሮማምቲኤዘር፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር። +10 ፍልስጤማውያንም ከእስራኤል ጋር እየተዋጉ ነበር። የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦአ ተራራ ላይ ተገደሉ።+ +2 ፍልስጤማውያን ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን እግር በእግር ተከታተሏቸው፤ ፍልስጤማውያንም የሳኦልን ወንዶች ልጆች ዮናታንን፣ አቢናዳብንና ሜልኪሳን+ መተው ገደሏቸው። +3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታ፤ ቀስተኞቹም አገኙት፤ ደግሞም አቆሰሉት።+ +4 ከዚያም ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች መጥተው በጭካኔ እንዳያሠቃዩኝ+ ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበር ፈቃደኛ አልሆነም። በመሆኑም ሳኦል ሰይፉን ወስዶ በላዩ ላይ ወድቆ ሞተ።+ +5 ጋሻ ጃግሬው ሳኦል መሞቱን ሲያይ እሱም በራሱ ሰይፍ ላይ ወድቆ ሞተ። +6 ስለዚህ ሳኦልም ሆነ ሦስት ወንዶች ልጆቹ ሞቱ፤ የቤቱም ሰዎች ሁሉ አብረው ሞቱ።+ +7 በሸለቆው ውስጥ የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ሠራዊቱ መሸሹን እንዲሁም ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ጥለው ሸሹ፤ ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው ከተሞቹን ያዙ። +8 በማግስቱ ፍልስጤማውያን የሞቱትን ሰዎች ልብስና ትጥቅ ለመግፈፍ ሲመጡ ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን በጊልቦአ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።+ +9 ስለሆነም ሳኦልን ገፈፉት፤ ራሱን ከቆረጡና የጦር ትጥቁን ከወሰዱ በኋላ ወሬው ለጣዖቶቻቸውና+ ለሕዝቡ እንዲዳረስ ወደ ፍልስጤም ምድር ሁሉ መልእክት ላኩ። +10 ከዚያም የጦር ትጥቁን በአምላካቸው ቤት አስቀመጡት፤ ራሱን ደግሞ በዳጎን ቤት+ ላይ ቸነከሩት። +11 በጊልያድ በምትገኘው በኢያቢስ+ የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ ፍልስጤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን ሁሉ ሲሰሙ+ +12 ተዋጊዎቹ ሁሉ ተነሱ፤ የሳኦልንና የልጆቹንም አስከሬን ተሸክመው ወደ ኢያቢስ አመጡ። ከዚያም አፅማቸውን በኢያቢስ በሚገኝ ትልቅ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤+ ለሰባት ቀንም ጾሙ። +13 ስለዚህ ሳኦል ለይሖዋ ታማኝ ሳይሆን በመቅረቱ ሞተ፤ ምክንያቱም የይሖዋን ቃል አልታዘዘም፤+ ደግሞም መናፍስት ጠሪን አማከረ፤+ +14 ይሖዋንም አልጠየቀም። ስለሆነም ለሞት አሳልፎ ሰጠው፤ ንግሥናውም ለእሴይ ልጅ ለዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።+ +14 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም+ ለዳዊት ቤት እንዲሠሩለት መልእክተኞችን እንዲሁም የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎችን፣ ድንጋይ ጠራቢዎችንና አናጺዎችን ላከ።+ +2 ዳዊትም ይሖዋ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናው አወቀ፤+ ምክንያቱም አምላክ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤል ሲል ንግሥናውን ከፍ ከፍ አድርጎለት ነበር።+ +3 ዳዊት በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤+ ደግሞም ተጨማሪ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።+ +4 በኢየሩሳሌም ሳለ የተወለዱለት ልጆች ስም ይህ ነው፦+ ሻሙአ፣ ሾባብ፣ ናታን፣+ ሰለሞን፣+ +5 ይብሃር፣ ኤሊሹዓ፣ ኤልፔሌት፣ +6 ኖጋ፣ ኔፌግ፣ ያፊአ፣ +7 ኤሊሻማ፣ ቤኤልያዳ እና ኤሊፌሌት። +8 ፍልስጤማውያንም በሙሉ ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን+ ሲሰሙ እሱን ፍለጋ ወጡ።+ ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ ሊገጥማቸው ወጣ። +9 ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው በረፋይም ሸለቆ ወረራ አካሄዱ።+ +10 ዳዊትም “ወጥቼ ፍልስጤማውያንን ልግጠም? በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ?” ሲል አምላክን ጠየቀ። ይሖዋም “አዎ ውጣ፤ እኔም በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ” አለው።+ +11 በመሆኑም ዳዊት ወደ በዓልጰራጺም+ ወጥቶ በዚያ መታቸው። ከዚያም ዳዊት “እውነተኛው አምላክ፣ ውኃ እንደጣሰው ግድብ ጠላቶቼን በእጄ ደረማመሳቸው” አለ። ከዚህም የተነሳ ያን ቦታ በዓልጰራጺም ብለው ጠሩት። +12 ፍልስጤማውያንም አማልክታቸውን በዚያ ጥለው ሸሹ፤ ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረትም በእሳት አቃጠሏቸው።+ +13 ከጊዜ በኋላ ፍልስጤማውያን ሸለቆውን እንደገና ወረሩ።+ +14 ዳዊት ዳግመኛ አምላክን ጠየቀ፤ ሆኖም እውነተኛው አምላክ እንዲህ አለው፦ “እነሱን ለመግጠም በቀጥታ አትውጣ። ይልቁንም ከኋላቸው ዙርና በባካ ቁጥቋጦዎቹ ፊት መጥተህ ግጠማቸው።+ +15 ደግሞም በባካ ቁጥቋጦዎቹ አናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ጥቃት ሰንዝር፤ ምክንያቱም ይህ በሚሆንበት ጊዜ እውነተኛው አምላክ የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመምታት በፊትህ ወጥቷል ማለት ነው።”+ +16 ስለዚህ ዳዊት ልክ እውነተኛው አምላክ እንዳዘዘው አደረገ፤+ የፍልስጤማውያንንም ሠራዊት ከገባኦን አንስቶ እስከ ጌዜር+ ድረስ መቷቸው። +17 የዳዊትም ዝና በአገሩ ሁሉ ተሰማ፤ ይሖዋም ብሔራት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ።+ +9 እስራኤላውያን በሙሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተመዘገቡ፤ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍም ላይ ተጻፉ። ይሁዳም ታማኝ ሆኖ ስላልተገኘ ወደ ባቢሎን በግዞት ተወሰደ።+ +2 በከተሞቻቸው ወደሚገኙት ርስቶቻቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች አንዳንድ እስራኤላውያን፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ነበሩ።+ +3 የተወሰኑ የይሁዳ፣+ የቢንያም፣+ የኤፍሬምና የምናሴ ዘሮች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፦ +4 ከይሁዳ ልጅ፣ ከፋሬስ+ ዘሮች መካከል የባኒ ልጅ፣ የኢምሪ ልጅ፣ የኦምሪ ልጅ፣ የአሚሁድ ልጅ ዑታይ። +5 ከሴሎናውያንም የበኩር ልጅ የሆነው አሳያህ እና ወንዶች ልጆቹ። +6 ከዛራ ልጆች+ መካከል ደግሞ፣ የኡዔል እና 690 ወንድሞቻቸው ነበሩ። +7 በዚያ የተቀመጡት የቢንያም ዘሮችም የሚከተሉት ናቸው፦ የሃስኑአ ልጅ፣ የሆዳውያህ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ ሳሉ፤ +8 የየሮሃም ልጅ ይብኔያህ፣ የሚክሪ ልጅ፣ የዑዚ ልጅ ኤላህ፣ የይብኒያህ ልጅ፣ የረኡዔል ልጅ፣ የሰፋጥያህ ልጅ መሹላም። +9 በዘር ሐረጉ መዝገብ ላይ የሰፈሩት ወንድሞቻቸውም 956 ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ወንዶች በየአባቶቻቸ�� ቤት መሪዎች ነበሩ። +10 ከካህናቱም የዳያህ፣ የሆያሪብ፣ ያኪን፣+ +11 የእውነተኛው አምላክ ቤት መሪ የሆነው የአኪጡብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ አዛርያስ፣ +12 የማልኪያህ ልጅ፣ የጳስኮር ልጅ፣ የየሮሃም ልጅ አዳያህ፣ የኢሜር ልጅ፣ የመሺሌሚት ልጅ፣ የመሹላም ልጅ፣ የያህዜራ ልጅ፣ የአዲዔል ልጅ ማአሳይ፣ +"13 እንዲሁም የየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች የሆኑት ወንድሞቻቸው ነበሩ፤ እነሱም 1,760 ሲሆኑ ለእውነተኛው አምላክ ቤት አገልግሎት ዝግጁ የሆኑ ኃያላንና ብቁ ሰዎች ነበሩ። " +14 ከሌዋውያኑም ከሜራሪ ዘሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የሃሻብያህ ልጅ፣ የአዝሪቃም ልጅ፣ የሃሹብ ልጅ ሸማያህ፣+ +15 ባቅባቃር፣ ሄሬሽ፣ ጋላል፣ የአሳፍ ልጅ፣ የዚክሪ ልጅ፣ የሚካ ልጅ ማታንያህ፣ +16 የየዱቱን ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሸማያህ ልጅ አብድዩ እንዲሁም የሕልቃና ልጅ፣ የአሳ ልጅ ቤራክያህ። እሱም በነጦፋውያን+ ሰፈር ይኖር ነበር። +17 በር ጠባቂዎቹ+ ሻሉም፣ አቁብ፣ ታልሞን እና አሂማን ነበሩ፤ ወንድማቸው ሻሉምም መሪ ነበር፤ +18 እሱም እስከዚያን ጊዜ ድረስ በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በንጉሡ በር ላይ ነበር።+ እነዚህ የሌዋውያንን ሰፈሮች የሚጠብቁ በር ጠባቂዎች ነበሩ። +19 የቆሬ ልጅ፣ የኤቢያሳፍ ልጅ፣ የቆረ ልጅ ሻሉም እና የአባቱ ቤት ወገን የሆኑት ወንድሞቹ ቆሬያውያን የድንኳኑ በር ጠባቂዎች በመሆን በዚያ የሚከናወነውን አገልግሎት በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር፤ አባቶቻቸው ደግሞ የመግቢያው ጠባቂዎች በመሆን የይሖዋን ሰፈር በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር። +20 ከዚህ በፊት የእነሱ መሪ የነበረው የአልዓዛር+ ልጅ ፊንሃስ+ ሲሆን ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር። +21 የመሺሌሚያህ ልጅ ዘካርያስ+ የመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በር ጠባቂ ነበር። +22 በደጆቹ ላይ ቆመው እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ 212 ነበሩ። እነሱም በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ተጽፎ በሚገኘው መሠረት+ በሰፈሮቻቸው ውስጥ ይኖሩ ነበር። ዳዊትና ባለ ራእዩ+ ሳሙኤል እነዚህን ሰዎች ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ ሾሟቸው። +23 እነሱና ወንዶች ልጆቻቸው የይሖዋን ቤት ይኸውም የማደሪያ ድንኳኑን በሮች የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።+ +24 በር ጠባቂዎቹ በአራቱም አቅጣጫዎች ማለትም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ በኩል ነበሩ።+ +25 በየሰፈሮቻቸው የሚኖሩት ወንድሞቻቸው ለሰባት ቀናት አብረዋቸው ለማገልገል አልፎ አልፎ ይመጡ ነበር። +26 ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ የሚያገለግሉ አራት የበር ጠባቂ አለቆች ነበሩ። እነሱም ሌዋውያን ሲሆኑ በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።+ +27 በእውነተኛው አምላክ ቤት ዙሪያ በተመደቡበት ቦታ ላይ ሆነው ያድሩ ነበር፤ የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እንዲሁም ቁልፉ የተሰጣቸውና ቤቱን በየጠዋቱ የሚከፍቱት እነሱ ነበሩ። +28 ከእነሱ መካከል የተወሰኑት ለአገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች የመቆጣጠር ኃላፊነት ነበረባቸው፤+ እነሱም ዕቃዎቹን በሚያስገቡበትም ሆነ በሚያወጡበት ጊዜ ይቆጥሯቸው ነበር። +29 የተወሰኑት ደግሞ ሌሎቹን ዕቃዎች፣ ቅዱስ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ፣+ የላመውን ዱቄት፣+ የወይን ጠጁን፣+ ዘይቱን፣+ ነጭ ዕጣኑንና+ የበለሳን ዘይቱን+ እንዲቆጣጠሩ ተሹመው ነበር። +30 ከካህናቱ ልጆች መካከል አንዳንዶቹ የበለሳን ዘይት የተቀላቀለበት ቅባት ያዘጋጁ ነበር። +31 የቆሬያዊው የሻሉም የበኩር ልጅ የሆነው ሌዋዊው ማቲትያህ በምጣድ ላይ ከሚጋገሩት ነገሮች+ ጋር በተያያዘ ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ ተመድቦ ነበር። +32 ወንድሞቻቸው ከሆኑት ከቀዓታውያን አንዳንዶቹ የሚነባበረውን ዳቦ+ በየሰንበቱ የማዘጋጀት+ ኃላፊነት ነበራቸው። +33 እነዚህ የሌዋውያን አባቶች ቤት መሪዎች የሆኑ ዘማሪዎች ነበሩ፤ ከሌሎች ሥራዎች ነፃ እንዲሆኑ የተደረጉት እነዚህ ሰዎች በክፍሎቹ ውስጥ ይቀመጡ ነበር። ምክንያቱም ቀንም ሆነ ሌሊት በሥራቸው ላይ የመገኘት ኃላፊነት ነበረባቸው። +34 እነዚህ በትውልድ ሐረጉ መዝገብ ላይ እንደሰፈረው የሌዋውያን ቤተሰቦች መሪዎች ነበሩ። የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበር። +35 የገባኦን አባት የኢዔል በገባኦን+ ይኖር ነበር። የሚስቱ ስም ማአካ ይባል ነበር። +36 የበኩር ልጁ አብዶን ሲሆን ሌሎቹ ልጆቹ ደግሞ ጹር፣ ቂስ፣ ባአል፣ ኔር፣ ናዳብ፣ +37 ጌዶር፣ አሂዮ፣ ዘካርያስ እና ሚቅሎት ነበሩ። +38 ሚቅሎት ሺምአምን ወለደ። እነዚህ ሁሉ ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር ሆነው በወንድሞቻቸው አቅራቢያ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። +39 ኔር+ ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን+ ወለደ፤ ሳኦል ዮናታንን፣+ ሜልኪሳን፣+ አቢናዳብን+ እና ኤሽባዓልን ወለደ። +40 የዮናታን ልጅ መሪበኣል+ ነበር። መሪበኣል ሚክያስን ወለደ።+ +41 የሚክያስ ወንዶች ልጆች ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታህሬአ እና አካዝ ነበሩ። +42 አካዝ ያራን ወለደ፤ ያራ አለሜትን፣ አዝማዌትንና ዚምሪን ወለደ። ዚምሪ ሞጻን ወለደ። +43 ሞጻ ቢንአን ወለደ፤ ቢንአ ረፋያህን ወለደ፤ ረፋያህ ኤልዓሳን ወለደ፤ ኤልዓሳ አዜልን ወለደ። +44 አዜል ስድስት ወንዶች ልጆች የነበሩት ሲሆን ስማቸውም አዝሪቃም፣ ቦከሩ፣ እስማኤል፣ ሸአርያህ፣ አብድዩ እና ሃናን ነበር። እነዚህ የአዜል ወንዶች ልጆች ነበሩ። +"27 የእስራኤላውያን ቁጥር ይኸውም የአባቶች ቤቶች መሪዎች፣ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆችና+ ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚገቡትንም ሆነ የሚወጡትን ምድቦች በመምራት ንጉሡን የሚያገለግሉት+ አለቆቻቸው ቁጥር ይህ ነው፤ በእያንዳንዱ ምድብ 24,000 ነበሩ። " +"2 በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ምድብ አዛዥ የዛብድኤል ልጅ ያሾብአም+ ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +3 እሱ ከፋሬስ+ ወንዶች ልጆች መካከል በመጀመሪያው ወር እንዲያገለግሉ የተመደቡት የቡድኖቹ አለቆች ሁሉ መሪ ነበር። +"4 አሆሐያዊው+ ዶዳይ+ የሁለተኛው ወር ምድብ አዛዥ ነበር። መሪው ሚቅሎት ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +"5 በሦስተኛው ወር እንዲያገለግል የተመደበው የሦስተኛው ቡድን አዛዥ የካህናት አለቃው የዮዳሄ+ ልጅ በናያህ+ ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +6 በናያህ ከሠላሳዎቹ ኃያላን ተዋጊዎች አንዱ የነበረ ሲሆን የሠላሳዎቹ አለቃ ነበር፤ ልጁ አሚዛባድም በእሱ ምድብ ውስጥ የበላይ ነበር። +"7 በአራተኛው ወር፣ አራተኛው አዛዥ የኢዮዓብ ወንድም+ አሳሄል+ ሲሆን ልጁ ዘባድያህ የእሱ ተተኪ ነበር፤ በምድቡም ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +"8 በአምስተኛው ወር፣ አምስተኛው አዛዥ ይዝራሃዊው ሻምሁት ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +"9 በስድስተኛው ወር፣ ስድስተኛው አዛዥ የተቆአዊው+ የኢቄሽ ልጅ ኢራ+ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +"10 በሰባተኛው ወር፣ ሰባተኛው አዛዥ ከኤፍሬማውያን ወገን የሆነው ጴሎናዊው ሄሌጽ+ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +"11 በስምንተኛው ወር፣ ስምንተኛው አዛዥ ከዛራውያን+ ወገን የሆነው ሁሻዊው ሲበካይ+ ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +"12 በዘጠነኛው ወር፣ ዘጠነኛው አዛዥ ከቢንያማውያን ወገን የሆነው አናቶታዊው+ አቢዔዜር+ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +"13 በአሥረኛው ወር፣ አሥረኛው አዛዥ ከዛራውያን+ ወገን የሆነው ነጦፋዊው ማህራይ+ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ��በሩ።" +"14 በ11ኛው ወር፣ 11ኛው አዛዥ ከኤፍሬም ልጆች ወገን የሆነው ጲራቶናዊው በናያህ+ ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።" +"15 በ12ኛው ወር፣ 12ኛው አዛዥ ከኦትኒኤል ቤተሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሄልዳይ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። " +16 የእስራኤል ነገዶች መሪዎች እነዚህ ናቸው፦ ከሮቤላውያን የዚክሪ ልጅ ኤሊዔዘር መሪ ነበር፤ ከስምዖናውያን የማአካ ልጅ ሰፋጥያህ፤ +17 ከሌዊ የቀሙኤል ልጅ ሃሻብያህ፤ ከአሮን ቤተሰብ ሳዶቅ፤ +18 ከይሁዳ ከዳዊት ወንድሞች አንዱ የሆነው ኤሊሁ፤+ ከይሳኮር የሚካኤል ልጅ ኦምሪ፤ +19 ከዛብሎን የአብድዩ ልጅ ይሽማያህ፤ ከንፍታሌም የአዝርዔል ልጅ የሪሞት፤ +20 ከኤፍሬማውያን መካከል የአዛዝያ ልጅ ሆሺአ፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ የፐዳያህ ልጅ ኢዩኤል፤ +21 በጊልያድ ካለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ የዘካርያስ ልጅ ኢዶ፤ ከቢንያም የአበኔር+ ልጅ ያአሲዔል፤ +22 ከዳን የየሮሃም ልጅ አዛርዔል። እነዚህ የእስራኤል ነገዶች አለቆች ነበሩ። +23 ይሖዋ እስራኤልን በሰማያት እንዳሉ ከዋክብት እንደሚያበዛ ቃል ገብቶ ስለነበር ዳዊት 20 ዓመትና ከዚያ በታች የሆናቸውን አልቆጠረም።+ +24 የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ ቆጠራውን ጀምሮ የነበረ ቢሆንም አልፈጸመውም። የአምላክ ቁጣ በእስራኤል ላይ ስለነደደ+ በንጉሥ ዳዊት ዘመን ስለተከናወኑት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ ዘገባ ላይ ቁጥሩ አልሰፈረም። +25 የአዲዔል ልጅ አዝማዌት በንጉሡ ግምጃ ቤቶች+ ላይ ተሹሞ ነበር። የዖዝያ ልጅ ዮናታን ደግሞ በገጠሩ፣ በከተሞቹ፣ በመንደሮቹና በማማዎቹ ውስጥ በሚገኙት ግምጃ ቤቶች ላይ ተሹሞ ነበር። +26 የከሉብ ልጅ ኤዝሪ መሬቱን ለማልማት በመስክ በሚሠሩት ሠራተኞች ላይ ተሹሞ ነበር። +27 ራማዊው ሺምአይ በወይን እርሻዎቹ ላይ ተሹሞ ነበር፤ ሲፍሞታዊው ዛብዲ ለወይን ጠጅ አቅርቦት በሚውለው የወይን እርሻዎቹ ምርት ላይ ተሹሞ ነበር። +28 ጌዴራዊው ባአልሀናን በሸፌላ+ በነበሩት የወይራ ዛፎችና የሾላ ዛፎች+ ላይ ተሹሞ ነበር፤ ዮአስ ደግሞ በዘይት ማከማቻዎቹ ላይ ተሹሞ ነበር። +29 ሳሮናዊው ሺጥራይ በሳሮን+ የግጦሽ መሬት በሚሰማሩት ከብቶች ላይ ተሹሞ ነበር፤ የአድላይ ልጅ ሻፋጥ ደግሞ በሸለቋማ ሜዳዎቹ ላይ በሚሰማሩት ከብቶች ላይ ተሹሞ ነበር። +30 እስማኤላዊው ኦቢል በግመሎቹ ላይ ተሹሞ ነበር፤ መሮኖታዊው የህድያ በአህዮቹ ላይ ተሹሞ ነበር። +31 አጋራዊው ያዚዝ በመንጎቹ ላይ ተሹሞ ነበር። እነዚህ ሁሉ በንጉሥ ዳዊት ንብረት ላይ የተሾሙ አለቆች ነበሩ። +32 የዳዊት የወንድሙ ልጅ ዮናታን+ አስተዋይ የሆነ አማካሪና ጸሐፊ ነበር፤ የሃክሞኒ ልጅ የሂኤል የንጉሡ ልጆች ተንከባካቢ ነበር።+ +33 አኪጦፌል+ የንጉሡ አማካሪ ነበር፤ አርካዊው ኩሲ+ ደግሞ የንጉሡ ወዳጅ ነበር። +34 ከአኪጦፌል በኋላ አማካሪ ሆነው የተሾሙት የበናያህ+ ልጅ ዮዳሄ እና አብያታር+ ነበሩ፤ ኢዮዓብ+ ደግሞ የንጉሡ ሠራዊት ዋና አዛዥ ነበር። +13 ዳዊት ከሺህ አለቆቹና ከመቶ አለቆቹ እንዲሁም ከመሪዎቹ ሁሉ ጋር ተማከረ።+ +2 ከዚያም ዳዊት ለመላው የእስራኤል ጉባኤ እንዲህ አለ፦ “ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁና በአምላካችን በይሖዋ ፊት ተቀባይነት ያለው ከሆነ፣ በእስራኤል ምድር ሁሉ ያሉት የቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም የግጦሽ መሬቶች ባሏቸው ከተሞቻቸው የሚኖሩት ካህናትና ሌዋውያን+ ወደ እኛ እንዲሰበሰቡ መልእክት እንላክባቸ +3 የአምላካችንንም ታቦት መልሰን እናምጣ።”+ በሳኦል ዘመን ታቦቱን ችላ ብለውት ነበርና።+ +4 ነገሩ በሕዝቡ ሁሉ ፊት መልካም ሆኖ ስለተገኘ መላው ጉባኤ ይህን ለማድረግ ተስማማ። +5 በመሆኑም ዳዊት የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ከቂርያትየአሪም ለማምጣት ��ግብፅ ወንዝ አንስቶ እስከ ሌቦሃማት+ ድረስ ያለውን የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰበሰበ።+ +6 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ ከኪሩቤል በላይ በዙፋን የሚቀመጠውን+ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ይኸውም ሰዎች የይሖዋን ስም የሚጠሩበትን ታቦት ለማምጣት በይሁዳ ምድር ወደምትገኘው ቂርያትየአሪም ወደምትባለው ወደ ባዓላ+ ወጡ። +7 ይሁን እንጂ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጭነው+ ከአቢናዳብ ቤት አመጡት፤ ደግሞም ዖዛና አሂዮ ሠረገላውን እየነዱ ነበር።+ +8 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ በመዝሙር፣ በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በአታሞ፣+ በሲምባልና+ በመለከት+ ታጅበው በሙሉ ኃይላቸው በእውነተኛው አምላክ ፊት በደስታ ይጨፍሩ ነበር። +9 ወደ ኪዶን አውድማ ሲደርሱ ግን ከብቶቹ ታቦቱን ሊጥሉት ተቃርበው ስለነበር ዖዛ እጁን ዘርግቶ ታቦቱን ያዘ። +10 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ ታቦቱን ለመያዝ እጁን በመዘርጋቱም ቀሰፈው፤+ እሱም በአምላክ ፊት እዚያው ሞተ።+ +11 ሆኖም የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ስለነደደ ዳዊት ተበሳጨ፤ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ጴሬዝዖዛ ተብሎ ይጠራል። +12 ዳዊትም በዚያን ዕለት እውነተኛውን አምላክ ፈርቶ “ታዲያ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት እንዴት ወደ እኔ ማምጣት እችላለሁ?” አለ።+ +13 ዳዊት ታቦቱን እሱ ወዳለበት ወደ ዳዊት ከተማ አላመጣውም፤ ይልቁንም የጌት ሰው ወደሆነው ወደ ኦቤድዔዶም ቤት እንዲወሰድ አደረገ። +14 የእውነተኛው አምላክ ታቦት ከኦቤድዔዶም ቤተሰብ ጋር በቤቱ ለሦስት ወራት ያህል ተቀመጠ፤ ይሖዋም የኦቤድዔዶምን ቤተሰብና ያለውን ሁሉ ባረከ።+ +5 የእስራኤል የበኩር ልጅ የሆነው የሮቤል+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሱ በኩር ቢሆንም እንኳ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ+ የብኩርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ+ ወንዶች ልጆች ተሰጠ፤ ከዚህም የተነሳ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የብኩርና መብት እንዳለው ተደርጎ አልተመዘገበም። +2 ይሁዳ+ ከወንድሞቹ የሚበልጥ ከመሆኑም ሌላ መሪ+ የሚሆነው የተገኘው ከእሱ ነው፤ ሆኖም የብኩርና መብቱን ያገኘው ዮሴፍ ነበር። +3 የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች ሃኖክ፣ ፓሉ፣ ኤስሮን እና ካርሚ+ ነበሩ። +4 ሸማያህ የኢዩኤል ልጅ ነበር፤ የሸማያህ ልጅ ጎግ፣ የጎግ ልጅ ሺምአይ፣ +5 የሺምአይ ልጅ ሚክያስ፣ የሚክያስ ልጅ ረአያህ፣ የረአያህ ልጅ ባአል፣ +6 የባአል ልጅ ቤኤራህ ነበር፤ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ የሮቤላውያን አለቃ የሆነውን ቤኤራህን በግዞት ወሰደው። +7 ወንድሞቹ በየቤተሰቦቻቸውና በየዘር ሐረጋቸው ሲዘረዘሩ እንደሚከተለው ነው፦ መሪ የሆነው የኢዔል፣ ዘካርያስ፣ +8 የኢዩኤል ልጅ፣ የሼማ ልጅ፣ የአዛዝ ልጅ ቤላ፤ እሱ ከአሮዔር+ አንስቶ እስከ ነቦ እንዲሁም እስከ በዓልመዖን+ ድረስ ይኖር ነበር። +9 መንጎቻቸው በጊልያድ ምድር+ እጅግ በዝተው ስለነበር በስተ ምሥራቅ በኤፍራጥስ ወንዝ+ በኩል እስካለው፣ ምድረ በዳው እስከሚጀምርበት ቦታ ድረስ ሰፈረ። +10 በሳኦል ዘመን በአጋራውያን ላይ ጦርነት ከፍተው ድል መቷቸው፤ በመሆኑም ከጊልያድ በስተ ምሥራቅ ባለው ክልል ሁሉ በድንኳኖቻቸው ውስጥ ኖሩ። +11 ከእነሱ ጋር የሚዋሰኑት የጋድ ዘሮች ደግሞ ከባሳን አንስቶ እስከ ሳልካ+ ባለው ምድር ላይ ኖሩ። +12 ኢዩኤል መሪ ነበር፤ ሁለተኛው ሻፋም ሲሆን ያናይ እና ሻፋጥ ደግሞ በባሳን መሪዎች ነበሩ። +13 ከአባቶቻቸው ቤት የሆኑት ወንድሞቻቸውም ሚካኤል፣ መሹላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዚአ እና ኤቤር ሲሆኑ በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ። +14 እነዚህ የቡዝ ልጅ፣ የያህዶ ልጅ፣ የየሺሻይ ልጅ፣ የሚካኤል ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የያሮሃ ልጅ፣ የ��ሪ ልጅ፣ የአቢሃይል ወንዶች ልጆች ነበሩ። +15 የአባቶቻቸው ቤት መሪ የጉኒ ልጅ፣ የአብዲዔል ልጅ አሂ ነበር። +16 እነሱም በጊልያድ፣+ በባሳን፣+ በእነሱ ሥር ባሉት ከተሞች እንዲሁም በሳሮን የግጦሽ መሬቶች ሁሉ እስከ ዳርቻዎቻቸው ድረስ ተቀመጡ። +17 እነዚህ ሁሉ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓታም+ እና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም+ ዘመን በትውልድ መዝገቡ ላይ ሰፈሩ። +"18 ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ 44,760 ኃያላን ተዋጊዎችን ያቀፈ ሠራዊት ነበራቸው፤ እነሱም ጋሻና ሰይፍ የታጠቁ፣ ደጋን ያነገቡና ለውጊያ የሠለጠኑ ነበሩ።" +19 እነዚህ ተዋጊዎች በአጋራውያን፣+ በየጡር፣ በናፊሽ+ እና በኖዳብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። +20 በጦርነቱ ወቅት አምላክ እንዲረዳቸው ስለጠየቁ እንዲሁም በእሱ ስለታመኑና+ እሱም ልመናቸውን ስለሰማ ከእነሱ ጋር በሚዋጉበት ጊዜ እርዳታ አገኙ፤ በመሆኑም አጋራውያንና ከእነሱ ጋር የነበሩት ሁሉ እጃቸው ላይ ወደቁ። +"21 እነሱም መንጎቻቸውን ይኸውም 50,000 ግመሎች፣ 250,000 በጎችና 2,000 አህዮች እንዲሁም 100,000 ሰዎች ማረኩ።" +22 የተዋጋላቸው እውነተኛው አምላክ ስለነበር+ ተገድለው የወደቁት ብዙ ነበሩ። በግዞት+ እስከተወሰዱበትም ጊዜ ድረስ በእነሱ ቦታ ላይ ኖሩ። +23 የምናሴ ነገድ እኩሌታ+ ዘሮች ከባሳን እስከ በዓልሄርሞን፣ እስከ ሰኒር እንዲሁም እስከ ሄርሞን ተራራ+ ድረስ ባለው ምድር ላይ ኖሩ። ቁጥራቸውም እጅግ ብዙ ነበር። +24 የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች እነዚህ ነበሩ፦ ኤፌር፣ ይሽኢ፣ ኤሊዔል፣ አዝርዔል፣ ኤርምያስ፣ ሆዳውያህ እና ያህዲኤል፤ እነዚህ ሰዎች ኃያላን ተዋጊዎችና ስመ ገናና ሲሆኑ የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ነበሩ። +25 ሆኖም ለአባቶቻቸው አምላክ ታማኞች ሳይሆኑ ቀሩ፤ ደግሞም አምላክ ከፊታቸው ካጠፋቸው ከምድሪቱ ሕዝቦች አማልክት ጋር አመነዘሩ።+ +26 በመሆኑም የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፑልን መንፈስ አነሳሳ+ (የአሦርን ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን+ መንፈስ ማለት ነው)፤ እሱም ሮቤላውያንን፣ ጋዳውያንንና የምናሴ ነገድ እኩሌታን በግዞት ወደ ሃላህ፣ ወደ ሃቦር፣ ወደ ሃራ እና ወደ ጎዛን+ ወንዝ ወሰዳቸው፤ እስከ ዛሬም በዚያ ይገኛሉ። +21 ከዚያም ሰይጣን እስራኤልን ለማጥቃት ቆርጦ ተነሳ፤ ደግሞም እስራኤልን እንዲቆጥር ዳዊትን አነሳሳው።+ +2 በመሆኑም ዳዊት ኢዮዓብንና+ የሕዝቡን አለቆች “ሂዱና ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ዳን+ ድረስ ያሉትን እስራኤላውያን ቁጠሩ፤ ከዚያም ቁጥራቸውን አውቅ ዘንድ ንገሩኝ” አላቸው። +3 ኢዮዓብ ግን እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ሕዝቡን 100 እጥፍ ያብዛው! ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ሁሉም የጌታዬ አገልጋዮች አይደሉም? ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን ፈለገ? በእስራኤልስ ላይ ለምን በደል ያመጣል?” +4 ይሁን እንጂ የንጉሡ ቃል በኢዮዓብ ላይ አየለ። በመሆኑም ኢዮዓብ ወጥቶ በመላው እስራኤል ተጓዘ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።+ +"5 ኢዮዓብም የተመዘገበውን የሕዝቡን ቁጥር ለዳዊት ሰጠው። በመላው እስራኤል ሰይፍ የታጠቁ 1,100,000 ወንዶች ነበሩ፤ በይሁዳ ደግሞ ሰይፍ የታጠቁ 470,000 ወንዶች ነበሩ።+" +6 ይሁንና ኢዮዓብ የንጉሡን ቃል ተጸይፎ ስለነበር ሌዊንና ቢንያምን በቆጠራው ውስጥ አላካተተም።+ +7 ይህ ነገር እውነተኛውን አምላክ በጣም አስቆጣው፤ በመሆኑም እስራኤልን መታ። +8 በዚህ ጊዜ ዳዊት እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለ፦ “ይህን በማድረጌ ከባድ ኃጢአት ፈጽሜአለሁ።+ አሁንም እባክህ የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤+ ታላቅ የሞኝነት ድርጊት ፈጽሜአለሁና።”+ +9 ይሖዋም የዳዊት ባለ ራእይ የሆነውን ጋድን+ እንዲህ አለው፦ +10 “ሂድና ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሦስት ምርጫዎችን ሰጥቼሃለሁ። በአንተ ላይ አመጣብህ ዘንድ አንዱን ምረጥ።”’” +11 ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ገብቶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ምረጥ፤ +12 ለሦስት ዓመት ረሃብ+ ይሁን ወይስ የጠላቶችህ ሰይፍ አሸንፎህ ለሦስት ወራት ጠላቶችህ ጥፋት ያድርሱብህ+ ወይስ ለሦስት ቀናት የይሖዋ ሰይፍ ይኸውም ቸነፈር+ በምድሪቱ ላይ መጥቶ የይሖዋ መልአክ በመላው የእስራኤል ግዛት ጥፋት+ ያምጣ?’ እንግዲህ አሁን ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስብበት።” +13 ስለዚህ ዳዊት ጋድን እንዲህ አለው፦ “ሁኔታው በጣም አስጨንቆኛል። ምሕረቱ እጅግ ታላቅ ስለሆነ+ እባክህ በይሖዋ እጅ ልውደቅ፤ ሰው እጅ ላይ ግን አትጣለኝ።”+ +"14 ከዚያም ይሖዋ በእስራኤል ላይ ቸነፈር ላከ፤+ በዚህም የተነሳ ከእስራኤል 70,000 ሰዎች ሞቱ።+" +15 በተጨማሪም እውነተኛው አምላክ ኢየሩሳሌምን እንዲያጠፋ መልአክ ላከ፤ ሆኖም መልአኩ ሊያጠፋት ሲል ይሖዋ ሁኔታውን አይቶ በደረሰው ጥፋት ተጸጸተ፤+ ስለሆነም የሚያጠፋውን መልአክ “ይብቃ!+ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የይሖዋ መልአክ በኢያቡሳዊው+ በኦርናን+ አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር። +16 ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት የይሖዋ መልአክ በምድርና በሰማያት መካከል ቆሞ አየ፤ እሱም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ነበር።+ ዳዊትና ሽማግሌዎቹ ማቅ+ እንደለበሱ ወዲያውኑ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።+ +17 ዳዊትም እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለ፦ “ሕዝቡ እንዲቆጠር ያዘዝኩት እኔ አይደለሁም? ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ፤ በደል የፈጸምኩትም እኔ ነኝ፤+ ታዲያ እነዚህ በጎች ምን አደረጉ? አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን፤ በሕዝብህ ላይ ግን ይህን መቅሰፍት አታውርድ።”+ +18 በዚህ ጊዜ የይሖዋ መልአክ፣ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርናን አውድማ ላይ ለይሖዋ መሠዊያ እንዲሠራ ለዳዊት እንዲነግረው ጋድን+ አዘዘው።+ +19 ዳዊትም ጋድ በይሖዋ ስም በነገረው ቃል መሠረት ወጣ። +20 ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦርናን ዞር ሲል መልአኩን አየው፤ ከእሱ ጋር የነበሩት አራት ወንዶች ልጆቹም ተሸሸጉ። በዚህ ጊዜ ኦርናን ስንዴ እየወቃ ነበር። +21 ኦርናን ቀና ብሎ ሲመለከት ዳዊት ወደ እሱ ሲመጣ አየ፤ ወዲያውኑም ከአውድማው ወጥቶ በግንባሩ መሬት ላይ በመደፋት ለዳዊት ሰገደ። +22 ዳዊትም ኦርናንን እንዲህ አለው፦ “ለይሖዋ መሠዊያ እንድሠራበት አውድማውን ሽጥልኝ። በሕዝቡ ላይ የሚወርደው መቅሰፍት እንዲቆም+ ሙሉውን ዋጋ ከፍዬ ልግዛው።” +23 ኦርናን ግን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “በነፃ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሡ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ። እነሆ ከብቶቹን ለሚቃጠል መባ፣ ማሄጃውን+ ለማገዶ፣ ስንዴውን ደግሞ ለእህል መባ አቀርባለሁ። ሁሉንም ነገር እኔ እሰጣለሁ።” +24 ይሁን እንጂ ንጉሥ ዳዊት ኦርናንን እንዲህ አለው፦ “በፍጹም አይሆንም! ሙሉውን ዋጋ ሰጥቼ እገዛዋለሁ፤ ምክንያቱም የአንተ የሆነውን ነገር ወስጄ ለይሖዋ አልሰጥም ወይም ምንም ያልከፈልኩበትን ነገር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም።”+ +25 በመሆኑም ዳዊት የቦታውን ዋጋ 600 የወርቅ ሰቅል መዝኖ ለኦርናን ሰጠው። +26 ዳዊትም በዚያ ለይሖዋ መሠዊያ+ ሠርቶ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችና የኅብረት መሥዋዕቶች አቀረበ፤ የይሖዋንም ስም ጠራ፤ እሱም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማያት በእሳት+ መለሰለት። +27 ከዚያም ይሖዋ መልአኩን+ ሰይፉን ወደ ሰገባው እንዲመልስ አዘዘው። +28 በዚህ ጊዜ ዳዊት፣ ይሖዋ በኢያቡሳዊው በኦርናን አውድማ መልስ እንደሰጠው ባየ ጊዜ በዚያ ቦታ ላይ መሥዋዕት ማቅረቡን ቀጠለ። +29 ሆኖም ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የይሖዋ የማደሪያ ድንኳንና የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያ በዚያን ጊዜ በገባኦን ባለው ከፍ ያለ ቦታ ላይ ይገኝ ነበር።+ +30 ይሁንና ዳዊት ከይሖዋ መልአክ ሰይፍ የተነሳ እጅግ ፈርቶ ስለነበር አምላክን ለመጠየቅ ወደዚያ መሄድ አልቻለም። +15 ዳዊትም፣ በገዛ ከተማው ለራሱ ቤቶችን መገንባት ቀጠለ፤ ደግሞም የእውነተኛው አምላክ ታቦት የሚቀመጥበትን ስፍራ አዘጋጀ፤ ድንኳንም ተከለ።+ +2 በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “ከሌዋውያን በስተቀር ማንም ሰው የእውነተኛውን አምላክ ታቦት መሸከም የለበትም፤ የይሖዋን ታቦት እንዲሸከሙና ምንጊዜም እንዲያገለግሉት ይሖዋ የመረጠው እነሱን ነውና።”+ +3 ከዚያም ዳዊት የይሖዋን ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያመጡ መላውን የእስራኤል ሕዝብ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።+ +4 ዳዊት የአሮንን ዘሮችና+ ሌዋውያኑን+ ሰበሰበ፦ +5 ከቀአታውያን መካከል አለቃውን ዑሪኤልንና 120 ወንድሞቹን፣ +6 ከሜራራውያን መካከል አለቃውን አሳያህንና+ 220 ወንድሞቹን፣ +7 ከጌርሳማውያን መካከል አለቃውን ኢዩኤልንና+ 130 ወንድሞቹን፣ +8 ከኤሊጻፋን+ ዘሮች መካከል አለቃውን ሸማያህንና 200 ወንድሞቹን፣ +9 ከኬብሮን ዘሮች መካከል አለቃውን ኤሊዔልንና 80 ወንድሞቹን፣ +10 ከዑዚኤል+ ዘሮች መካከል አለቃውን አሚናዳብንና 112 ወንድሞቹን ሰበሰበ። +11 በተጨማሪም ዳዊት ካህናቱን ሳዶቅንና+ አብያታርን+ እንዲሁም ሌዋውያኑን ዑሪኤልን፣ አሳያህን፣ ኢዩኤልን፣ ሸማያህን፣ ኤሊዔልን እና አሚናዳብን ጠራ፤ +12 እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤት መሪዎች ናችሁ። እናንተና ወንድሞቻችሁ ራሳችሁን ቀድሱ፤ የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ታቦትም ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ አምጡ። +13 በመጀመሪያው ጊዜ ታቦቱን ሳትሸከሙ በመቅረታችሁ+ የአምላካችን የይሖዋ ቁጣ በእኛ ላይ ነድዶ ነበር፤+ ይህ የሆነው ትክክለኛውን መመሪያ ባለመከተላችን ነው።”+ +14 ስለዚህ ካህናቱና ሌዋውያኑ የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ታቦት ለማምጣት ራሳቸውን ቀደሱ። +15 ከዚያም ሌዋውያኑ ሙሴ በይሖዋ ቃል መሠረት እንዳዘዘው የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በመሎጊያዎቹ አድርገው በትከሻቸው ላይ ተሸከሙ።+ +16 ከዚያም ዳዊት በሙዚቃ መሣሪያዎች ይኸውም በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በበገና+ እና በሲምባል+ ታጅበው በደስታ ይዘምሩ ዘንድ ዘማሪ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን እንዲሾሙ ለሌዋውያኑ አለቆች ነገራቸው። +17 በመሆኑም ሌዋውያኑ የኢዩኤልን ልጅ ሄማንን፣+ ከወንድሞቹም መካከል የቤራክያህን ልጅ አሳፍን፣+ እንዲሁም ወንድሞቻቸው ከሆኑት ከሜራራውያን መካከል የቁሻያህን ልጅ ኤታንን+ ሾሙ። +18 ከእነሱ ጋር በሁለተኛው ምድብ ያሉት ወንድሞቻቸው ይገኙ ነበር፤+ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦ ዘካርያስ፣ ቤን፣ ያአዚዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ዑኒ፣ ኤልያብ፣ በናያህ፣ ማአሴያህ፣ ማቲትያህ፣ ኤሊፌሌሁ፣ ሚቅኔያህ፣ በር ጠባቂዎቹ ኦቤድዔዶም እና የኢዔል። +19 ዘማሪዎቹ ሄማን፣+ አሳፍ+ እና ኤታን ከመዳብ በተሠራ ሲምባል+ እንዲጫወቱ ተመደቡ፤ +20 ዘካርያስ፣ አዚዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ዑኒ፣ ኤልያብ፣ ማአሴያህ እና በናያህ ደግሞ በአላሞት ቅኝት+ በባለ አውታር መሣሪያዎች ይጫወቱ ነበር፤ +21 ማቲትያህ፣+ ኤሊፌሌሁ፣ ሚቅኔያህ፣ ኦቤድዔዶም፣ የኢዔል እና አዛዝያ ደግሞ በሸሚኒት ቅኝት+ በገና ይጫወቱና የሙዚቀኞች ቡድን መሪ ሆነው ያገለግሉ ነበር። +22 የሌዋውያን አለቃ የሆነው ኬናንያ+ ሥራውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ታቦቱን የማጓጓዙን ሥራ በበላይነት ይከታተል ነበር፤ +23 ቤራክያህ እና ሕልቃና ታቦቱ የተቀመጠበትን ቦታ በር ይጠብቁ ነበር። +24 ካህናቱ ሸባንያህ፣ ዮሳፍጥ፣ ና���ናኤል፣ አማሳይ፣ ዘካርያስ፣ በናያህ እና ኤሊዔዘር በእውነተኛው አምላክ ታቦት ፊት ከፍ ባለ ድምፅ መለከት ይነፉ ነበር፤+ ኦቤድዔዶም እና የሂያህ ታቦቱ የተቀመጠበትን ቦታ በር በመጠበቅም ያገለግሉ ነበር። +25 ከዚያም ዳዊትና የእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲሁም የሺህ አለቆቹ የይሖዋን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከኦቤድዔዶም+ ቤት በታላቅ ደስታ ለማምጣት ሄዱ።+ +26 የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያን፣ እውነተኛው አምላክ ስለረዳቸው ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ሠዉ።+ +27 ዳዊት፣ ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣ ዘማሪዎቹ እንዲሁም ታቦቱን የማጓጓዙ ሥራ ኃላፊና የዘማሪዎቹ አለቃ የሆነው ኬናንያ እጅጌ የሌለው ምርጥ ልብስ ለብሰው ነበር፤ በተጨማሪም ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ ነበር።+ +28 መላው የእስራኤል ሕዝብ በቀንደ መለከት፣ በመለከትና+ በሲምባል ድምፅ ታጅቦ ባለ አውታር መሣሪያዎችንና በገናን+ ከፍ ባለ ድምፅ እየተጫወተ በእልልታ+ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት አመጣ። +29 ይሁንና የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በመጣ ጊዜ+ የሳኦል ልጅ ሜልኮል+ በመስኮት ሆና ወደ ታች ተመለከተች፤ ንጉሥ ዳዊት ሲዘልና በደስታ ሲጨፍር አይታ በልቧ ናቀችው።+ +22 ከዚያም ዳዊት “የእውነተኛው አምላክ የይሖዋ ቤት በዚህ ይሆናል፤ ለእስራኤል የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያም በዚሁ ይቆማል” አለ።+ +2 ዳዊት በእስራኤል ምድር የሚኖሩትን የባዕድ አገር ሰዎች+ እንዲሰበስቡ አዘዘ፤ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ለመገንባት የሚያስፈልጉትንም ድንጋዮች እንዲጠርቡ ድንጋይ ጠራቢዎች አድርጎ መደባቸው።+ +3 በተጨማሪም ዳዊት ለመግቢያዎቹ በሮች የሚያስፈልጉ ምስማሮችንና ማጠፊያዎችን ለመሥራት የሚያገለግል ከፍተኛ መጠን ያለው ብረት አዘጋጀ፤ ደግሞም ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የማይችል መዳብ አከማቸ፤+ +4 ከዚህም ሌላ ስፍር ቁጥር የሌለው ከአርዘ ሊባኖስ የተሠራ ሳንቃ+ አዘጋጀ፤ ሲዶናውያንና+ ጢሮሳውያን+ ከአርዘ ሊባኖስ የተዘጋጀ ብዛት ያለው ሳንቃ ለዳዊት አምጥተውለት ነበርና። +5 ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “ልጄ ሰለሞን ገና ወጣት ነው፤ ተሞክሮም የለውም፤+ ለይሖዋ የሚሠራው ቤት ደግሞ እጅግ የሚያምር+ ከመሆኑ የተነሳ ዝናውም ሆነ ውበቱ+ በመላው ምድር የታወቀ ይሆናል።+ ስለዚህ የሚያስፈልገውን ነገር አዘጋጅለታለሁ።” በመሆኑም ዳዊት ከመሞቱ በፊት ለሥራው የሚያስፈልጉትን ነገሮች በብ +6 በተጨማሪም ልጁን ሰለሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ፣ ቤት እንዲሠራ አዘዘው። +7 ዳዊት ልጁን ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “እኔ በበኩሌ ለአምላኬ ለይሖዋ ስም፣ ቤት ለመሥራት ከልብ ተመኝቼ ነበር።+ +8 ሆኖም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ ‘አንተ እጅግ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ታላላቅ ጦርነቶችንም አድርገሃል። በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ስላፈሰስክ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም።+ +9 እነሆ፣ የሰላም ሰው የሚሆን ወንድ ልጅ ትወልዳለህ፤+ በዙሪያውም ካሉት ጠላቶቹ በሙሉ እረፍት እሰጠዋለሁ፤+ ስሙ ሰለሞን+ ይባላልና፤ በእሱም ዘመን ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታ እሰጣለሁ።+ +10 ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው።+ እሱ ልጄ ይሆናል፤ እኔም አባቱ እሆናለሁ።+ የንግሥናውን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’+ +11 “አሁንም ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ ከአንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አንተም በተናገረው መሠረት ተሳክቶልህ የአምላክህን የይሖዋን ቤት ለመሥራት ያብቃህ።+ +12 ብቻ ይሖዋ በእስራኤል ላይ ሲሾምህ የአምላክህን የይሖዋን ሕግ እንድትጠብቅ+ የማመዛዘንና የማስተዋል ችሎታ ይስጥህ።+ +13 ደግሞም ይሖዋ እስራኤልን በተመለከተ ሙሴን ያዘዘውን ሥርዓትና+ ድንጋጌ በጥንቃቄ ብትጠብቅ ይሳካልሃል።+ ደፋርና ብርቱ ሁን። አትፍራ ወይም አትሸበር።+ +"14 እነሆ፣ እኔ ለይሖዋ ቤት 100,000 ታላንት ወርቅና 1,000,000 ታላንት ብር እንዲሁም ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የማይችል መዳብና ብረት+ ለማዘጋጀት ብዙ ደክሜአለሁ፤ ደግሞም ሳንቃና ድንጋይ አዘጋጅቻለሁ፤+ አንተም በዚያ ላይ ትጨምርበታለህ።" +15 ከአንተም ጋር ብዙ ሠራተኞች፣ ድንጋይ ጠራቢዎች፣ ግንበኞች፣+ አናጺዎችና በተለያዩ ሙያዎች የተካኑ ሠራተኞች አሉ።+ +16 ወርቁ፣ ብሩ፣ መዳቡና ብረቱ ስፍር ቁጥር የለውም።+ በል ሥራውን ጀምር፤ ይሖዋም ከአንተ ጋር ይሁን።”+ +17 ከዚያም ዳዊት የእስራኤል መኳንንት ሁሉ ልጁን ሰለሞንን እንዲረዱት እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ +18 “አምላካችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር አይደለም? በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉስ እረፍት አልሰጣችሁም? የምድሪቱን ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና፤ ምድሪቱም በይሖዋና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለች። +19 አሁንም በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ጠይቁ፤+ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦትና የእውነተኛውን አምላክ የተቀደሱ ዕቃዎች+ ለይሖዋ ስም+ ወደሚሠራው ቤት እንድታመጡ የእውነተኛውን አምላክ የይሖዋን መቅደስ መሥራት ጀምሩ።”+ +17 ልጁ ኢዮሳፍጥም+ በምትኩ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ሥልጣኑን አጠናከረ። +2 በይሁዳ ባሉት የተመሸጉ ከተሞች ሁሉ የጦር ሠራዊት አሰፈረ፤ በይሁዳ ምድርና አባቱ አሳ በያዛቸው በኤፍሬም ከተሞችም የጦር ሰፈሮች አቋቋመ።+ +3 ኢዮሳፍጥ፣ በቀድሞዎቹ ዘመናት አባቱ ዳዊት የሄደበትን መንገድ በመከተሉና+ ባአልን ባለመፈለጉ ይሖዋ ከእሱ ጋር ነበር። +4 የእስራኤልን ልማድ ከመከተል ይልቅ+ የአባቱን አምላክ ፈልጓል፤+ ትእዛዙንም ተከትሏል።* +5 ይሖዋ መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤+ የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ለኢዮሳፍጥ ስጦታ ያመጡለት ነበር፤ እሱም ብዙ ሀብትና ታላቅ ክብር አገኘ።+ +6 ልቡም የይሖዋን መንገዶች በድፍረት ተከተለ፤ ደግሞም ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎችና የማምለኪያ ግንዶቹን* ከይሁዳ አስወገደ።+ +7 በነገሠ በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች እንዲያስተምሩ መኳንንቱን ይኸውም ቤንሃይልን፣ አብድዩን፣ ዘካርያስን፣ ናትናኤልንና ሚካያህን አስጠራቸው። +8 ከእነሱ ጋር ሌዋውያኑ ሸማያህ፣ ነታንያህ፣ ዘባድያህ፣ አሳሄል፣ ሸሚራሞት፣ የሆናታን፣ አዶንያስ፣ ጦቢያህ እና ቶብአዶኒያህ ይገኙ ነበር፤ ካህናቱ ኤሊሻማ እና ኢዮራምም አብረዋቸው ነበሩ።+ +9 እነሱም በይሁዳ ማስተማር ጀመሩ፤ የይሖዋን ሕግ መጽሐፍም ይዘው ነበር፤+ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር። +10 ይሖዋም በይሁዳ ዙሪያ በሚገኙ አገሮች ባሉት መንግሥታት ሁሉ ላይ ፍርሃት ለቆባቸው ስለነበር ከኢዮሳፍጥ ጋር አልተዋጉም። +"11 ፍልስጤማውያንም ለኢዮሳፍጥ ስጦታ አመጡለት፤ ገንዘብም ገበሩለት። ዓረቦች ከመንጎቻቸው መካከል 7,700 አውራ በጎችንና 7,700 አውራ ፍየሎችን አመጡለት። " +12 ኢዮሳፍጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ ሄደ፤+ በይሁዳም ምሽጎችንና+ የማከማቻ ከተሞችን+ መገንባቱን ተያያዘው። +13 በይሁዳ ከተሞች መጠነ ሰፊ የሆነ ሥራ አከናወነ፤ በኢየሩሳሌምም ኃያላን ተዋጊዎች የሆኑ ወታደሮች ነበሩት። +"14 እነዚህ ሰዎች በየአባቶቻቸው ቤት ተመድበው ነበር፦ ከይሁዳ የሺህ አለቆች መካከል አለቃው አድናህ የነበረ ሲሆን ከእሱ ጋር 300,000 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ።+" +"15 ከእሱ ሥር ደግሞ የሆሃናን የተባለ አለቃ የነበረ ሲሆን ከእሱም ጋር 280,000 ሰዎች ነበሩ።" +"16 ደግሞም ከእሱ ሥር ለይሖዋ አገልግሎት ራሱን በፈቃደኝነት ያቀረበው የዚክሪ ልጅ አማስያህ የነበረ ሲሆን ከእሱም ጋር 200,000 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ።" +"17 ከቢንያምም+ ወገን ኃያል ተዋጊ የሆነው ኤሊያዳ የነበረ ሲሆን ከእሱም ጋር ቀስትና ጋሻ የታጠቁ 200,000 ሰዎች ነበሩ።+" +"18 ከእሱም ሥር የሆዛባድ የነበረ ሲሆን ከእሱም ጋር ለውጊያ የታጠቁ 180,000 ሰዎች ነበሩ።" +19 እነዚህ ንጉሡ በመላው ይሁዳ በተመሸጉ ከተሞች+ ውስጥ ካስቀመጣቸው ሌላ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው። +30 ሕዝቅያስ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ፋሲካን*+ ለማክበር በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ይሖዋ ቤት እንዲመጡ ለእስራኤልና ለይሁዳ ሁሉ መልእክት ላከ፤+ ለኤፍሬምና ለምናሴም እንኳ ሳይቀር ደብዳቤ ጻፈ።+ +2 ይሁን እንጂ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያለው መላው ጉባኤ ፋሲካን በሁለተኛው ወር ለማክበር ወሰኑ፤+ +3 በቂ ካህናት ራሳቸውን ስላልቀደሱና+ ሕዝቡ ገና በኢየሩሳሌም ስላልተሰበሰበ ፋሲካውን በመደበኛው ጊዜ ማክበር አልቻሉም ነበር።+ +4 ይህ ዝግጅት በንጉሡና በመላው ጉባኤ ፊት ተቀባይነት አገኘ። +5 ስለዚህ ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ፋሲካን እንዲያከብር በመላው እስራኤል፣ ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ዳን+ ድረስ አዋጅ እንዲነገር ወሰኑ፤ በተጻፈው መሠረት በዓሉን በጋራ አክብረው አያውቁም ነበር።+ +6 ከዚያም መልእክተኞቹ* የንጉሡንና የመኳንንቱን ደብዳቤዎች ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ፤ ንጉሡም እንዲህ የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የእስራኤል አምላክ ወደሆነው ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤ እሱም ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጡት ቀሪዎች ይመለሳ +7 አሁን እንደምታዩት፣ መቀጣጫ እስኪያደርጋቸው ድረስ በአባቶቻቸው አምላክ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት እንደፈጸሙት እንደ አባቶቻችሁና እንደ ወንድሞቻችሁ አትሁኑ።+ +8 አሁንም እንደ አባቶቻችሁ አንገታችሁን አታደንድኑ።+ የሚነድ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ ለይሖዋ ተገዙ፤+ ለዘላለም ወደቀደሰው መቅደሱ ኑ፤+ አምላካችሁን ይሖዋን አገልግሉ። +9 ወደ ይሖዋ ስትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ በማረኳቸው ዘንድ ምሕረት ያገኛሉ፤+ ወደዚህች ምድር እንዲመለሱም ይለቋቸዋል፤+ አምላካችሁ ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ ነውና፤+ ወደ እሱም ከተመለሳችሁ ፊቱን አያዞርባችሁም።”+ +10 ስለዚህ መልእክተኞቹ* ከከተማ ወደ ከተማ እየተዘዋወሩ የኤፍሬምንና የምናሴን+ እንዲሁም የዛብሎንን አገር ሁሉ አዳረሱ፤ ሕዝቡ ግን ያፌዝባቸውና ይሳለቅባቸው ነበር።+ +11 ይሁን እንጂ ከአሴር፣ ከምናሴና ከዛብሎን ምድር የተወሰኑ ሰዎች ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።+ +12 በተጨማሪም የእውነተኛው አምላክ እጅ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ስለነበር ንጉሡና መኳንንቱ በይሖዋ ቃል መሠረት ያስተላለፉትን ትእዛዝ እንዲፈጽሙ አንድ ልብ ሰጣቸው። +13 በሁለተኛው ወር+ የቂጣን በዓል+ ለማክበር እጅግ ብዙ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ተሰበሰበ፤ ጉባኤው እጅግ ታላቅ ነበር። +14 እነሱም ተነስተው በኢየሩሳሌም የነበሩትን መሠዊያዎችና የዕጣን መሠዊያዎች ከነቃቀሉ+ በኋላ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ ጣሏቸው። +15 ከዚያም በሁለተኛው ወር በ14ኛው ቀን የፋሲካን መሥዋዕት አረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ አፍረው ስለነበር ራሳቸውን ቀደሱ፤ ወደ ይሖዋም ቤት የሚቃጠል መባ አመጡ። +16 በእውነተኛው አምላክ ሰው በሙሴ ሕግ መሠረት የተሰጣቸውን መመሪያ ተከትለው መደበኛ ቦታቸውን ያዙ፤ ከዚያም ካህናቱ ከሌዋውያኑ እጅ የተቀበሉትን ደም ረጩ።+ +17 በጉባኤው መካከል ራሳቸውን ያልቀደሱ ብዙ ሰዎች ስለነበሩ ሌዋውያኑ ያልነጹትን ሰዎች+ ለይሖዋ ለመቀደስ የፋሲካን መሥዋዕት የማረድ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበ���። +18 እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በተለይም ከኤፍሬም፣ ከምናሴ፣+ ከይሳኮርና ከዛብሎን የመጡ ሰዎች ራሳቸውን ያላነጹ ቢሆንም የተጻፈውን መመሪያ ተላልፈው ፋሲካውን በሉ። ይሁንና ሕዝቅያስ እንዲህ ሲል ጸለየላቸው፦ “ጥሩ የሆነው+ ይሖዋ ይቅር ይበል፤ +19 የቅድስናውን መሥፈርት አሟልተው ራሳቸውን ባያነጹም+ እንኳ እውነተኛ አምላክ የሆነውን የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ለመፈለግ ልባቸውን ያዘጋጁትን+ ሁሉ ይቅር ይበላቸው።” +20 ይሖዋም ሕዝቅያስን ሰምቶ ሕዝቡን ይቅር አለ።* +21 በመሆኑም በኢየሩሳሌም የተገኙት እስራኤላውያን የቂጣን በዓል+ ለሰባት ቀናት በታላቅ ደስታ አከበሩ፤+ ሌዋውያኑና ካህናቱም ከፍ ባለ ድምፅ ለይሖዋ የሙዚቃ መሣሪያዎቻቸውን በመጫወት በየዕለቱ ይሖዋን ያወድሱ ነበር።+ +22 በተጨማሪም ሕዝቅያስ ይሖዋን በማስተዋል ያገለግሉ የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ በማነጋገር አበረታታቸው።* እነሱም የኅብረት መሥዋዕቶች+ በማቅረብና ለአባቶቻቸው አምላክ ለይሖዋ ምስጋና በማቅረብ በዓሉ ተጀምሮ እስኪያበቃ ድረስ ለሰባት ቀናት በሉ።+ +23 ከዚያም መላው ጉባኤ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት በዓሉን ለማክበር ወሰነ፤ በመሆኑም እንደገና ለሰባት ቀናት በዓሉን በታላቅ ደስታ አከበሩ።+ +"24 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስም 1,000 በሬዎችና 7,000 በጎች ለጉባኤው ሰጥቶ ነበር፤ መኳንንቱ ደግሞ 1,000 በሬዎችና 10,000 በጎች ለጉባኤው አበረከቱ፤+ እጅግ ብዙ ካህናትም ራሳቸውን ቀደሱ።+" +25 መላው የይሁዳ ጉባኤ፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ ከእስራኤል የመጣው መላው ጉባኤ+ እንዲሁም ከእስራኤል ምድር የመጡትና በይሁዳ የሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች+ እጅግ ተደሰቱ። +26 ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰለሞን ዘመን አንስቶ በኢየሩሳሌም እንዲህ ያለ ነገር ሆኖ ስለማያውቅ በኢየሩሳሌም ታላቅ ደስታ ሆነ።+ +27 በመጨረሻም ሌዋውያኑ ካህናት ተነስተው ሕዝቡን ባረኩ፤+ አምላክም ድምፃቸውን ሰማ፤ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱሱ መኖሪያው ወደ ሰማያት ደረሰ። +35 ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለይሖዋ ፋሲካ አደረገ፤+ በመጀመሪያው ወር በ14ኛው ቀን+ የፋሲካን መሥዋዕት አረዱ።+ +2 ካህናቱን በየሥራቸው ላይ መደባቸው፤ የይሖዋንም ቤት አገልግሎት እንዲያከናውኑ አበረታታቸው።+ +3 ከዚያም የመላው እስራኤል አስተማሪዎች+ የሆኑትንና ለይሖዋ የተቀደሱትን ሌዋውያን እንዲህ አላቸው፦ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰለሞን በሠራው ቤት ውስጥ አስቀምጡት፤+ ከዚህ በኋላ ታቦቱን በትከሻችሁ መሸከም አያስፈልጋችሁም።+ አሁን አምላካችሁን ይሖዋንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ። +4 የእስራኤል ንጉሥ ዳዊትና+ ልጁ ሰለሞን+ በጻፉት ትእዛዝ መሠረት በየአባቶቻችሁ ቤት እንደየምድባችሁ ራሳችሁን አዘጋጁ። +5 ወንድሞቻችሁ የሆኑትን የቀሩትን ሰዎች* ለማገልገል በየአባቶች ቤት ምድብ በተቀደሰው ስፍራ ቁሙ፤ እያንዳንዱም የሌዋውያን ቡድን ከሕዝቡ መካከል የሚደርሰውን የአባቶች ቤት ምድብ ያገልግል። +6 የፋሲካውን መሥዋዕት እረዱ፤+ ራሳችሁንም ቀድሱ፤ ይሖዋ በሙሴ በኩል የሰጠውን ትእዛዝ መፈጸም እንድትችሉ ለወንድሞቻችሁ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጉ።” +"7 ኢዮስያስም ለሕዝቡ ይኸውም በዚያ ለተገኙት ሁሉ ለፋሲካ መሥዋዕት እንዲሆኑ ከመንጋው መካከል በድምሩ 30,000 ተባዕት የበግና የፍየል ጠቦቶች እንዲሁም 3,000 ከብቶች ሰጠ። እነዚህ የተሰጡት ከንጉሡ ሀብት ላይ ነበር።+" +"8 መኳንንቱም ለሕዝቡ፣ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ በፈቃደኝነት የሚቀርብ መባ ሰጡ። የእውነተኛው አምላክ ቤት መሪዎች የሆኑት ኬልቅያስ፣+ ዘካርያስና የሂኤል ለፋሲካ መሥዋዕት የሚሆኑ 2,600 በጎችና ፍየሎች እንዲሁም 300 ከብቶች ለካ���ናቱ ሰጡ።" +"9 ኮናንያ፣ ወንድሞቹ ሸማያህ እና ናትናኤል እንዲሁም የሌዋውያኑ አለቆች ሃሻብያህ፣ የኢዔል እና ዮዛባድ ለፋሲካ መሥዋዕት የሚሆኑ 5,000 በጎችና ፍየሎች እንዲሁም 500 ከብቶች ለሌዋውያኑ ሰጡ። " +10 የአገልግሎቱ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ ንጉሡ ባዘዘው መሠረት ካህናቱ በየቦታቸው፣ ሌዋውያኑም በየምድባቸው+ ቆሙ። +11 የፋሲካውንም መሥዋዕት አረዱ፤+ ሌዋውያኑ ቆዳውን ሲገፉ+ ካህናቱ ደግሞ ከእነሱ የተቀበሉትን ደም መሠዊያው ላይ ረጩ።+ +12 ከዚያም በየአባቶች ቤት ለተመደቡት ለቀሩት ሰዎች ለማከፋፈል የሚቃጠለውን መባ አዘጋጁ፤ ይህም የሆነው በሙሴ መጽሐፍ ላይ በተጻፈው መሠረት መባው ለይሖዋ እንዲቀርብ ነው፤ ከብቶቹንም በዚሁ መንገድ አዘጋጁ። +13 በልማዱም መሠረት የፋሲካን መባ በእሳት አበሰሉ፤*+ የተቀደሱትንም መባዎች በድስት፣ በሰታቴና በመጥበሻ አብስለው ወዲያውኑ ለቀሩት ሰዎች ሁሉ አቀረቡ። +14 ከዚያም ለራሳቸውና ለካህናቱ አዘጋጁ፤ ምክንያቱም የአሮን ዘሮች የሆኑት ካህናቱ እስኪመሽ ድረስ፣ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶችና ስቡን ያቀርቡ ነበር፤ በመሆኑም ሌዋውያኑ ለራሳቸውና የአሮን ዘሮች ለሆኑት ለካህናቱ አዘጋጁ። +15 ዳዊት፣+ አሳፍ፣+ ሄማንና የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው የዱቱን+ በሰጡት ትእዛዝ መሠረት የአሳፍ+ ልጆች የሆኑት ዘማሪዎቹ በየቦታቸው ላይ ነበሩ፤ በር ጠባቂዎቹም በየበሩ ላይ ነበሩ።+ ወንድሞቻቸው የሆኑት ሌዋውያን አዘጋጅተውላቸው ስለነበር ሥራቸውን ትተው መሄድ አላስፈለጋቸውም። +16 በመሆኑም ንጉሥ ኢዮስያስ ባዘዘው መሠረት+ ፋሲካን ለማክበርና+ በይሖዋ መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መባ ለማቅረብ፣ ለይሖዋ አገልግሎት የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ በዚያን ቀን ተዘጋጅቶ ነበር። +17 በስፍራው የተገኙት እስራኤላውያን በዚያ ጊዜ ፋሲካን አከበሩ፤ የቂጣንም በዓል ለሰባት ቀን አከበሩ።+ +18 ከነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ወዲህ እንደዚህ ያለ የፋሲካ በዓል በእስራኤል ተከብሮ አያውቅም፤ ኢዮስያስ፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በዚያ የተገኙት የይሁዳና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንዲሁም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ያከበሩት ዓይነት ፋሲካ ያከበረ አንድም የእስራኤል ንጉሥ የለም።+ +19 ይህ ፋሲካ የተከበረው ኢዮስያስ በነገሠ በ18ኛው ዓመት ነበር። +20 ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢዮስያስ ቤተ መቅደሱን* አዘጋጅቶ ባጠናቀቀ ጊዜ የግብፁ ንጉሥ ኒካዑ+ በኤፍራጥስ አጠገብ ባለው በካርከሚሽ ለመዋጋት መጣ። በዚህ ጊዜ ኢዮስያስ ሊገጥመው ወጣ።+ +21 ኒካዑም እንዲህ ሲል መልእክተኞችን ላከበት፦ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፣ እኔን ልትወጋ የመጣኸው ለምንድን ነው? አሁን የመጣሁት ከሌላ ብሔር ጋር ልዋጋ እንጂ አንተን ልወጋ አይደለም፤ አምላክም እንድፈጥን አዞኛል። ከእኔ ጋር የሆነውን አምላክ መቃወም ቢቀርብህ ይሻላል፤ አለዚያ ያጠፋሃል።” +22 ኢዮስያስ ግን ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም፤ ይልቁንም ማንነቱ እንዳይታወቅ ራሱን ለውጦ+ ከእሱ ጋር ለመዋጋት ወጣ፤ በኒካዑ በኩል የተነገረውን የአምላክ ቃል አልሰማም። በመሆኑም ለመዋጋት ወደ መጊዶ+ ሜዳ መጣ። +23 ቀስተኞችም ንጉሥ ኢዮስያስን ወጉት፤ ንጉሡም አገልጋዮቹን “ክፉኛ ስለቆሰልኩ ከዚህ አውጡኝ” አላቸው። +24 በመሆኑም አገልጋዮቹ ከሠረገላው አውርደው በሁለተኛው የጦር ሠረገላው ላይ ካስቀመጡት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት። እሱም በዚህ ሁኔታ ሞተ፤ በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ፤+ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱ። +25 ኤርምያስም+ ለኢዮስያስ የሐዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፤ ወንዶችና ሴቶች ዘማሪዎችም+ ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ በሙሿቸው* ላይ ስለ ኢዮስያስ ይዘምራሉ፤ ደግሞም በእስራኤል እንዲዘመርና ሌ��ች ሙሾዎች በተጻፉበት መጽሐፍ ላይ እንዲሰፍር ተወሰነ። +26 የቀረው የኢዮስያስ ታሪክና በይሖዋ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ያከናወናቸው ታማኝ ፍቅር የተንጸባረቀባቸው ተግባራት +27 እንዲሁም ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያደረጋቸው ነገሮች በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።+ +31 ከዚህ በኋላ በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው በመላው ይሁዳና ቢንያም እንዲሁም በኤፍሬምና በምናሴ+ የነበሩትን የማምለኪያ ዓምዶች+ ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ግንዶቹን*+ ቆረጡ፤ ከፍ ያሉትንም የማምለኪያ ቦታዎችና+ መሠዊያዎቹን+ አፈራረሱ፤ ምንም ያስቀሩት ነገር አልነበረም፤ ከ +2 ከዚያም ሕዝቅያስ ካህናቱን በየምድባቸው፣+ ሌዋውያኑንም በየምድባቸው+ ሾማቸው፤ እያንዳንዱን ካህንና ሌዋዊ በተሰጠው ሥራ መሠረት ደለደለ።+ እነሱም የሚቃጠለውን መባና የኅብረት መሥዋዕቶቹን ያቀርባሉ፣ ያገለግላሉ እንዲሁም በይሖዋ ቤተ መቅደስ ዙሪያ ባሉት የግቢዎቹ* በሮች ለእሱ ምስጋናና ውዳሴ ያቀርባሉ። +3 በይሖዋ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ጠዋትና ማታ የሚቀርበውን መባ+ እንዲሁም በየሰንበቱ፣+ በየወር መባቻውና+ በበዓላት ወቅት+ የሚቀርቡትን የሚቃጠሉ መባዎች ጨምሮ ለሚቃጠሉት መባዎች+ እንዲውል ከንጉሡ ንብረት ላይ የተወሰነ ድርሻ ይሰጥ ነበር። +4 በተጨማሪም ሕዝቅያስ የይሖዋን ሕግ በጥብቅ መከተል* እንዲችሉ በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ተገቢውን ድርሻ እንዲሰጥ አዘዘ።+ +5 ትእዛዙ እንደወጣ እስራኤላውያን የእህሉን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅ፣ የዘይቱን፣+ የማሩንና የእርሻውን ፍሬ+ ሁሉ በኩራት በብዛት ሰጡ፤ ከእያንዳንዱም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን አትረፍርፈው አመጡ።+ +6 በይሁዳ ከተሞች ይኖሩ የነበሩት የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብም ከከብቶቻቸውና ከበጎቻቸው አንድ አሥረኛውን እንዲሁም ለአምላካቸው ለይሖዋ ከተለዩት ቅዱስ የሆኑ ነገሮች ላይ አንድ አሥረኛውን አመጡ።+ ያመጡትንም ብዙ ቦታ ላይ ቆለሉት። +7 በሦስተኛው ወር+ ያመጡትን መዋጮ መከመር የጀመሩ ሲሆን በሰባተኛው ወር+ አጠናቀቁ። +8 ሕዝቅያስና መኳንንቱ መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ ይሖዋን አወደሱ፤ ሕዝቡን እስራኤልንም ባረኩ። +9 ሕዝቅያስ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ሲጠይቃቸው +10 ከሳዶቅ ቤት የሆነው የካህናት አለቃው አዛርያስ እንዲህ አለው፦ “መዋጮውን ወደ ይሖዋ ቤት ማምጣት+ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ሕዝቡ እስኪጠግብ ድረስ ሲበላ ቆይቷል፤ ገና ያልተነካ ብዙ ነገር አለ፤ ይሖዋ ሕዝቡን ስለባረከ ይህን ያህል ብዛት ያለው ነገር ሊተርፍ ችሏል።”+ +11 በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ በይሖዋ ቤት ማከማቻ ክፍሎች*+ እንዲያዘጋጁ አዘዘ፤ እነሱም አዘጋጁ። +12 ከዚያም መዋጮውን፣ አንድ አሥረኛውንና*+ ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች በታማኝነት ማምጣታቸውን ቀጠሉ፤ ሌዋዊው ኮናንያ የእነዚህ ሁሉ ነገሮች ተቆጣጣሪ ሆኖ ተሹሞ የነበረ ሲሆን ወንድሙ ሺምአይ ደግሞ የእሱ ምክትል ነበር። +13 የሂኤል፣ አዛዝያ፣ ናሃት፣ አሳሄል፣ የሪሞት፣ ዮዛባድ፣ ኤሊዔል፣ ይስማክያ፣ ማሃት እና በናያህ በንጉሥ ሕዝቅያስ ትእዛዝ ኮናንያን እና ወንድሙን ሺምአይን የሚረዱ ሹሞች ነበሩ፤ አዛርያስም የእውነተኛው አምላክ ቤት ተቆጣጣሪ ነበር። +14 የምሥራቁ በር ጠባቂ የሆነው ሌዋዊው+ የይምናህ ልጅ ቆረ ለእውነተኛው አምላክ በበጎ ፈቃድ የሚቀርቡትን መባዎች+ ይቆጣጠር ነበር፤ ደግሞም ለይሖዋ የተሰጠውን መዋጮና+ እጅግ ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች+ ያከፋፍል ነበር። +15 በእሱም አመራር ሥር ኤደን፣ ሚንያሚን፣ የሹዋ፣ ሸማያህ፣ አማርያህ እና ሸካንያህ የነበሩ ሲሆን በየምድቦቹ ውስጥ ላ��ት ወንድሞቻቸው፣+ ለትልቁም ሆነ ለትንሹ ድርሻቸውን እኩል ለማከፋፈል በካህናቱ ከተሞች+ ታማኝነት በሚጠይቅ ቦታ ላይ ተሹመው ነበር። +16 ይህም ስማቸው በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ለሰፈሩት ሦስት ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ወንዶች የሚከፋፈለውን ሳይጨምር ነው፤ እነሱም በይሖዋ ቤት ለማገልገል በየዕለቱ ይመጡና እንደየምድባቸው ያሉባቸውን ኃላፊነቶች ይፈጽሙ ነበር። +17 ካህናቱ፣ 20 ዓመትና ከዚያ በላይ+ እንደሆናቸው ሌዋውያን ሁሉ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የሰፈሩት በየአባቶቻቸው ቤት+ እንደየምድብ ሥራቸው ነበር።+ +18 የትውልድ ሐረግ መዝገቡ ልጆቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በሙሉ፣ መላውን የሌዋውያን ማኅበረሰብ ይጨምራል፤ እነሱ በተሾሙበት ታማኝነት የሚጠይቅ ቦታ የተነሳ ቅዱስ ለሆነው ነገር ራሳቸውን ቀድሰዋል፤ +19 በተጨማሪም መዝገቡ ላይ በከተሞቻቸው ዙሪያ ባሉ የግጦሽ መሬቶች ላይ የሚኖሩት የአሮን ዘሮች የሆኑት ካህናትም ይገኛሉ።+ በሁሉም ከተሞች ውስጥ በካህናት ቤተሰብ ውስጥ ላሉት ወንዶች ሁሉና በሌዋውያን የትውልድ ሐረግ መዝገብ ላይ ለተጻፉት በሙሉ እንዲያከፋፍሉ በስም ተጠቅሰው ኃላፊነት የተሰጣቸው ወንዶች +20 ሕዝቅያስ በመላው ይሁዳ ይህን አደረገ፤ በአምላኩ በይሖዋም ፊት ጥሩና ትክክል የሆነውን አደረገ፤ ለእሱም ታማኝ ነበር። +21 ከእውነተኛው አምላክ ቤት+ አገልግሎት ጋርም ሆነ ከሕጉና ከትእዛዙ ጋር በተያያዘ አምላኩን ይፈልግ ዘንድ የጀመረውን ሥራ ሁሉ፣ በሙሉ ልቡ አከናወነ፤ ደግሞም ተሳካለት። +18 ኢዮሳፍጥ ብዙ ሀብትና ታላቅ ክብር አገኘ፤+ ይሁንና ከአክዓብ+ ጋር በጋብቻ ተዛመደ። +2 ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም በሰማርያ ወደሚገኘው ወደ አክዓብ ወረደ፤+ አክዓብም ለኢዮሳፍጥና አብረውት ለነበሩት ሰዎች እጅግ ብዙ በግና ከብት መሥዋዕት አደረገ። ደግሞም በራሞትጊልያድ+ ላይ እንዲዘምት ገፋፋው።* +3 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “ወደ ራሞትጊልያድ ከእኔ ጋር አብረህ ትሄዳለህ?” አለው። እሱም “እኔ ማለት እኮ አንተ ማለት ነህ፤ ሕዝቤም ሕዝብህ ነው፤ በጦርነቱም አብረንህ እንሰለፋለን” አለው። +4 ሆኖም ኢዮሳፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ “እባክህ፣ በመጀመሪያ ይሖዋ ምን እንደሚል ጠይቅ” አለው።+ +5 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ 400 የሚሆኑ ነቢያትን አንድ ላይ ሰብስቦ “ራሞትጊልያድን ለመውጋት ልዝመት ወይስ ይቅርብኝ?” አላቸው። እነሱም “ዝመት፤ እውነተኛው አምላክ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” አሉት። +6 ከዚያም ኢዮሳፍጥ “በዚህ ቦታ የይሖዋ ነቢይ የለም?+ ካለ በእሱም አማካኝነት እንጠይቅ” አለ።+ +7 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “በእሱ አማካኝነት ይሖዋን ልንጠይቅ የምንችልበት አንድ ሰው ይቀራል፤+ ሆኖም ሁልጊዜ ስለ እኔ መጥፎ ነገር እንጂ መልካም ነገር ፈጽሞ ስለማይተነብይ በጣም እጠላዋለሁ።+ እሱም የይምላ ልጅ ሚካያህ ነው” አለው። ኢዮሳፍጥ ግን “ንጉሡ እንዲህ ሊል አይገባም” አለ። +8 ስለሆነም የእስራኤል ንጉሥ አንድ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን ጠርቶ “የይምላን ልጅ ሚካያህን በአስቸኳይ ይዘኸው ና” አለው።+ +9 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ የንግሥና ልብሳቸውን ለብሰው በየዙፋናቸው ተቀምጠው ነበር፤ የተቀመጡትም በሰማርያ መግቢያ በር በሚገኘው አውድማ ላይ ሲሆን ነቢያቱ ሁሉ በፊታቸው ትንቢት ይናገሩ ነበር። +10 ከዚያም የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስ የብረት ቀንዶች ሠርቶ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’”* አለ። +11 ሌሎቹ ነቢያትም ሁሉ “ወደ ራሞትጊልያድ ውጣ�� ይሳካልሃል፤+ ይሖዋም እሷን በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” በማለት ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር። +12 ሚካያህን ለመጥራት የሄደው መልእክተኛም “እነሆ፣ ነቢያቱ ሁሉ በአንድ ድምፅ ለንጉሡ የተናገሩት ነገር ጥሩ ነው። እባክህ፣ የአንተም ቃል እንደ እነሱ ይሁን፤+ አንተም ጥሩ ነገር ተናገር” አለው።+ +13 ሚካያህ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፤ የምናገረው አምላኬ የሚለውን ብቻ ነው” አለ።+ +14 ከዚያም ወደ ንጉሡ ገባ፤ ንጉሡም “ሚካያህ፣ ራሞትጊልያድን ለመውጋት እንዝመት ወይስ ይቅርብኝ?” ሲል ጠየቀው። እሱም ወዲያውኑ “ውጡ፤ ይቀናችኋል፤ በእጃችሁም አልፈው ይሰጣሉ” በማለት መለሰለት። +15 በዚህ ጊዜ ንጉሡ “በይሖዋ ስም ከእውነት በስተቀር ሌላ አንዳች ነገር እንዳትነግረኝ የማስምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው። +16 በመሆኑም ሚካያህ እንዲህ በማለት ተናገረ፦ “እስራኤላውያን ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበታትነው አያለሁ።+ ይሖዋም ‘እነዚህ ጌታ የላቸውም። እያንዳንዳቸው በሰላም ወደየቤታቸው ይመለሱ’ ብሏል።” +17 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “‘ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ ጥሩ ነገር አይተነብይም’ ብዬህ አልነበረም?” አለው።+ +18 በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣+ የሰማያት ሠራዊትም+ ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።+ +19 ከዚያም ይሖዋ ‘በራሞትጊልያድ ላይ ዘምቶ እዚያው እንዲሞት የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ማን ያሞኘዋል?’ አለ። በዚህ ጊዜ አንዱ አንድ ነገር፣ ሌላው ደግሞ ሌላ ነገር ተናገረ። +20 ከዚያም አንድ መንፈስ*+ ወደ ፊት ወጥቶ ይሖዋ ፊት በመቆም ‘እኔ አሞኘዋለሁ’ አለ። ይሖዋም ‘እንዴት አድርገህ?’ አለው። +21 ‘እኔ እወጣና በነቢያቱ ሁሉ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ እሆናለሁ’ አለ። እሱም ‘እንግዲያው ታሞኘዋለህ፤ ደግሞም ይሳካልሃል። ውጣና እንዳልከው አድርግ’ አለው። +22 ይሖዋም በእነዚህ ነቢያትህ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ አኑሯል፤+ ሆኖም ይሖዋ ጥፋት እንደሚመጣብህ ተናግሯል።” +23 የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስም+ ወደ ሚካያህ+ ቀርቦ በጥፊ መታውና+ “ለመሆኑ የይሖዋ መንፈስ እኔን በየት በኩል አልፎ ነው አንተን ያናገረህ?” አለው።+ +24 ሚካያህም “በየት በኩል እንዳለፈማ፣ ለመደበቅ ወደ ውስጠኛው ክፍል በምትገባበት ቀን ታውቀዋለህ” አለው። +25 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ እንዲህ አለ፦ “ሚካያህን ወስዳችሁ ለከተማው አለቃ ለአምዖን እና የንጉሡ ልጅ ለሆነው ለዮአስ አስረክቡት። +26 እንዲህም በሏቸው፦ ‘ንጉሡ “በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ይህን ሰው እስር ቤት አቆዩት፤+ ጥቂት ምግብና ውኃ ብቻ ስጡት” ብሏል።’” +27 ሚካያህ ግን “እውነት አንተ በሰላም ከተመለስክ ይሖዋ በእኔ አልተናገረም ማለት ነው!” አለ።+ ከዚያም “እናንተ ሰዎች፣ ሁላችሁም ልብ በሉ” አለ። +28 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ወደ ራሞትጊልያድ+ ወጡ። +29 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “እኔ ማንነቴ እንዳይታወቅ ራሴን ለውጬ ወደ ውጊያው እገባለሁ፤ አንተ ግን ንጉሣዊ ልብስህን ልበስ” አለው። ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ማንነቱ እንዳይታወቅ ራሱን ለወጠ፤ ከዚያም ወደ ውጊያው ገቡ። +30 በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ የሠረገሎቹን አዛዦች “ከእስራኤል ንጉሥ በስተቀር ከትንሹም ሆነ ከትልቁ፣ ከማንም ጋር እንዳትዋጉ” በማለት አዟቸው ነበር። +31 የሠረገሎቹ አዛዦችም ኢዮሳፍጥን ባዩት ጊዜ “ይህ የእስራኤል ንጉሥ ነው” ብለው አሰቡ። በመሆኑም ሊወጉት ወደ እሱ ዞሩ፤ በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ እርዳታ ለማግኘት ጮኸ፤+ ይሖዋም ረዳው፤ አምላክ��� ወዲያውኑ ከእሱ እንዲርቁ አደረገ። +32 የሠረገሎቹ አዛዦችም የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን ሲያዩ ወዲያውኑ እሱን ማሳደዳቸውን ትተው ተመለሱ። +33 ይሁንና አንድ ሰው በነሲብ* ቀስቱን ሲያስወነጭፍ የእስራኤልን ንጉሥ የጥሩሩ መጋጠሚያ ላይ ወጋው። ስለሆነም ንጉሡ ሠረገላ ነጂውን “ክፉኛ ስለቆሰልኩ ሠረገላውን አዙረህ ከጦርነቱ* ይዘኸኝ ውጣ” አለው።+ +34 ያን ቀን ሙሉ የተፋፋመ ውጊያ ተካሄደ፤ የእስራኤልንም ንጉሥ ሠረገላው ውስጥ እንዳለ ፊቱን ወደ ሶርያውያን አዙረው እስከ ምሽት ድረስ ደግፈው አቆሙት፤ ፀሐይ ስትጠልቅም ሞተ።+ +23 በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ድፍረት የተሞላበት እርምጃ በመውሰድ ከመቶ አለቆቹ+ ይኸውም ከየሮሃም ልጅ ከአዛርያስ፣ ከየሆሃናን ልጅ ከእስማኤል፣ ከኢዮቤድ ልጅ ከአዛርያስ፣ ከአዳያህ ልጅ ከማአሴያህ እና ከዚክሪ ልጅ ከኤሊሻፋጥ ጋር ስምምነት* አደረገ። +2 ከዚያም በይሁዳ ሁሉ በመዘዋወር ከመላው የይሁዳ ከተሞች ሌዋውያንንና+ የእስራኤልን የአባቶች ቤት መሪዎች ሰበሰቡ። ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ +3 መላው ጉባኤ በእውነተኛው አምላክ ቤት ከንጉሡ ጋር ቃል ኪዳን ገባ፤+ ከዚያም ዮዳሄ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፣ ይሖዋ የዳዊትን ወንዶች ልጆች አስመልክቶ ቃል በገባው መሠረት የንጉሡ ልጅ ይገዛል።+ +4 እናንተም እንዲህ ታደርጋላችሁ፦ በሰንበት ቀን ተረኛ ከሚሆኑት ካህናትና ሌዋውያን+ መካከል አንድ ሦስተኛዎቹ በር ጠባቂዎች ይሆናሉ፤+ +5 አንድ ሦስተኛዎቹ ደግሞ በንጉሡ ቤት*+ ይሆናሉ፤ ሌላው አንድ ሦስተኛ በመሠረት በር ላይ ይሆናል፤ ሕዝቡ ሁሉ ደግሞ በይሖዋ ቤት ግቢዎች+ ውስጥ ይሆናል። +6 ከሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን በስተቀር ማንንም ወደ ይሖዋ ቤት እንዳታስገቡ።+ እነሱ የተቀደሱ ስለሆኑ ይግቡ፤ የቀረውም ሕዝብ ሁሉ ለይሖዋ ያለበትን ግዴታ ይፈጽማል። +7 ሌዋውያኑም እያንዳንዳቸው የጦር መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው ንጉሡን ዙሪያውን ይክበቡት። ወደ ቤቱም ውስጥ የሚገባ ማንኛውም ሰው ይገደላል። ንጉሡ በሚሄድበት ሁሉ* አብራችሁት ሁኑ።” +8 ሌዋውያኑና የይሁዳ ሰዎች በሙሉ ልክ ካህኑ ዮዳሄ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እያንዳንዳቸውም በሰንበት ቀን ተረኛ የሚሆኑትንና በሰንበት ቀን ከሥራ ነፃ የሚሆኑትን የራሳቸውን ሰዎች ወሰዱ፤+ ካህኑ ዮዳሄ ተራቸው ባይሆንም እንኳ በየምድቡ+ ያሉትን ከሥራ አላሰናበተም ነበርና። +9 ካህኑ ዮዳሄም በእውነተኛው አምላክ ቤት+ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊት ጦሮች፣ ትናንሽ ጋሻዎችና* ክብ ጋሻዎች+ ለመቶ አለቆቹ+ ሰጣቸው። +10 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዳቸው የጦር መሣሪያቸውን* ይዘው በስተ ቀኝ በኩል ካለው የቤቱ ጎን አንስቶ በስተ ግራ በኩል እስካለው የቤቱ ጎን ድረስ በመሠዊያውና በቤቱ አጠገብ በንጉሡ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ። +11 የንጉሡንም ልጅ+ አውጥተው አክሊሉን* ጫኑበት፤ ምሥክሩንም*+ ሰጡት፤ በዚህም መንገድ አነገሡት፤ ዮዳሄና ወንዶች ልጆቹም ቀቡት። ከዚያም “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” አሉ።+ +12 ጎቶልያ ሕዝቡ ሲሯሯጥና ንጉሡን ሲያወድስ ስትሰማ ወዲያውኑ በይሖዋ ቤት ወዳለው ሕዝብ መጣች።+ +13 ከዚያም ንጉሡ በመግቢያው ላይ ባለው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ አየች። መኳንንቱና+ መለከት ነፊዎቹ ከንጉሡ ጋር ነበሩ፤ የምድሪቱም ሕዝብ ሁሉ እጅግ እየተደሰተና+ መለከት እየነፋ ነበር፤ የሙዚቃ መሣሪያ የያዙት ዘማሪዎችም ውዳሴውን ይመሩ* ነበር። በዚህ ጊዜ ጎቶልያ ልብሷን ቀዳ “ይህ ሴራ ነው! ሴራ ነው!” +14 ካህኑ ዮዳሄ ግን በሠራዊቱ ላይ የተሾሙትን መቶ አለቆች ይዟቸው በመውጣት “ከረድፉ መካከል አውጧት፤ እሷን ተከትሎ የሚመጣ ሰው ካለ በሰይፍ ግደሉት!” አላቸው። ካህኑ “በይሖዋ ቤት ውስጥ እ���ዳትገድሏት” ብሎ ነበር። +15 በመሆኑም ያዟት፤ በንጉሡም ቤት* ወዳለው የፈረስ በር መግቢያ እንደደረሰች ገደሏት። +16 ከዚያም ዮዳሄ የይሖዋ ሕዝብ ሆነው እንዲቀጥሉ እሱ፣ ሕዝቡ ሁሉና ንጉሡ ቃል ኪዳን እንዲጋቡ አደረገ።+ +17 የምድሪቱም ሕዝብ ሁሉ ወደ ባአል ቤት* መጥቶ አፈራረሰው፤+ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹንም ሰባበረ፤+ የባአል ካህን የነበረውን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ገደሉት።+ +18 ከዚያም ዮዳሄ በይሖዋ ቤት የሚከናወኑትን ሥራዎች እንዲቆጣጠሩ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሾመ፤ እነሱም በሙሴ ሕግ ላይ በተጻፈው+ እንዲሁም ዳዊት ባዘዘው መሠረት* በደስታና በመዝሙር ለይሖዋ የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት በይሖዋ ቤት በየምድቡ የመደባቸው ናቸው።+ +19 በተጨማሪም በማንኛውም ነገር የረከሰ ሰው እንዳይገባ በር ጠባቂዎቹን+ በይሖዋ ቤት በሮች ላይ አቆመ። +20 ከዚያም መቶ አለቆቹን፣+ መኳንንቱን፣ የሕዝቡን ገዢዎችና የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ ሰበሰበ፤ ንጉሡንም አጅበው ከይሖዋ ቤት ወደ ታች አመጡት። በላይኛውም በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት* ገቡ፤ ንጉሡንም በመንግሥቱ+ ዙፋን+ ላይ አስቀመጡት። +21 በመሆኑም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እጅግ ተደሰተ፤ ጎቶልያንም በሰይፍ ስለገደሏት ከተማዋ ጸጥታ ሰፈነባት። +34 ኢዮስያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ31 ዓመት ገዛ።+ +2 ኢዮስያስም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አላለም። +3 በነገሠ በ8ኛው ዓመት፣ ገና ልጅ ሳለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ መፈለግ ጀመረ፤+ በ12ኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከፍ ካሉ የማምለኪያ ቦታዎች፣+ ከማምለኪያ ግንዶች፣* ከተቀረጹ ምስሎችና+ ከብረት ከተሠሩ ሐውልቶች* አነጻ።+ +4 በተጨማሪም እሱ በተገኘበት የባአልን መሠዊያዎች አፈራረሱ፤ በላያቸው ላይ የነበሩትንም የዕጣን ማጨሻዎች ሰባበራቸው። ደግሞም የማምለኪያ ግንዶቹን፣* የተቀረጹትን ምስሎችና ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች* ሰባብሮ አደቀቃቸው፤ ከዚያም ለእነሱ ይሠዉ በነበሩት ሰዎች መቃብር ላይ በተነው።+ +5 የካህናቱንም አጥንቶች በመሠዊያዎቻቸው ላይ አቃጠለ።+ በዚህ መንገድ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አነጻ። +6 በተጨማሪም ከምናሴ፣ ከኤፍሬምና+ ከስምዖን አንስቶ እስከ ንፍታሌም ባሉት ከተሞች እንዲሁም በዙሪያቸው ባሉ የወደሙ ስፍራዎች ሁሉ፣ +7 መሠዊያዎችን አፈራረሰ፤ የማምለኪያ ግንዶችንና* የተቀረጹትን ምስሎች+ ሰባብሮ አደቀቃቸው፤ በመላው የእስራኤል ምድር የሚገኙትንም የዕጣን ማጨሻዎች ሰባበረ፤+ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። +8 እሱም በነገሠ በ18ኛው ዓመት ምድሪቱንና ቤተ መቅደሱን* ካነጻ በኋላ የአዜልያን ልጅ ሳፋንን፣+ የከተማዋን አለቃ ማአሴያህንና ታሪክ ጸሐፊውን የዮአሃዝን ልጅ ዮአህን የአምላኩን የይሖዋን ቤት እንዲጠግኑ ላካቸው።+ +9 እነሱም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኬልቅያስ መጥተው ወደ አምላክ ቤት የመጣውን ገንዘብ አስረከቡት፤ ገንዘቡም በር ጠባቂዎች ሆነው የሚያገለግሉት ሌዋውያን ከምናሴ፣ ከኤፍሬም፣ ከቀረው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ+ እንዲሁም ከይሁዳ፣ ከቢንያምና ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የሰበሰቡት ነበር። +10 ከዚያም በይሖዋ ቤት የሚከናወነውን ሥራ እንዲቆጣጠሩ ለተሾሙት ሠራተኞች ገንዘቡን ሰጧቸው። በይሖዋ ቤት የሚሠሩት ሠራተኞች ደግሞ ቤቱን ለመጠገንና ለማደስ አዋሉት። +11 በመሆኑም ጥርብ ድንጋዮችንና ለማጠናከሪያ የሚያገለግሉ ሳንቃዎችን እንዲሁም የይሁዳ ነገሥታት ትተዋቸው የፈራረሱትን ቤቶች ለመጠገን የሚያስፈልጉ ወራጆችን እንዲገዙ ገንዘቡን ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ለግንበኞቹ ሰጧቸው።+ +12 ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት አከናወኑ።+ በእነሱም ላይ ከሜራራውያን+ ሌዋውያኑ ያሃት እና አብድዩ፣ ከቀአታውያን+ ደግሞ ዘካርያስ እና መሹላም የበላይ ተመልካቾች ሆነው እንዲያገለግሉ ተሹመው ነበር። የሙዚቃ መሣሪያዎችን በመጫወት የተካኑት ሌዋውያንም ሁሉ፣+ +13 በጉልበት ሠራተኞቹ* ላይ ተሹመው ነበር፤ እንዲሁም በሁሉም ዓይነት አገልግሎት ላይ ተመድበው በሚሠሩት ሠራተኞች ላይ የበላይ ተመልካቾች ሆነው ያገለግሉ ነበር፤ ከሌዋውያኑም መካከል አንዳንዶቹ ጸሐፊዎች፣ አለቆችና በር ጠባቂዎች ነበሩ።+ +14 ወደ ይሖዋ ቤት የመጣውን ገንዘብ በሚያወጡበት+ ጊዜ ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ በኩል* የተሰጠውን+ የይሖዋን ሕግ መጽሐፍ+ አገኘ። +15 በመሆኑም ኬልቅያስ ጸሐፊውን ሳፋንን “የሕጉን መጽሐፍ በይሖዋ ቤት ውስጥ አገኘሁት” አለው። ከዚያም ኬልቅያስ መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው። +16 ሳፋንም መጽሐፉን ወደ ንጉሡ ወስዶ እንዲህ አለው፦ “አገልጋዮችህ የተመደበላቸውን ሥራ ሁሉ እያከናወኑ ነው። +17 በይሖዋ ቤት የተገኘውን ገንዘብ አውጥተው ለተሾሙት ሰዎችና ለሠራተኞቹ አስረክበዋል።” +18 በተጨማሪም ጸሐፊው ሳፋን ንጉሡን “ካህኑ ኬልቅያስ የሰጠኝ አንድ መጽሐፍ አለ” አለው።+ ከዚያም ሳፋን መጽሐፉን በንጉሡ ፊት ማንበብ ጀመረ።+ +19 ንጉሡ የሕጉን ቃል ሲሰማ ልብሱን ቀደደ።+ +20 ከዚያም ንጉሡ ኬልቅያስን፣ የሳፋንን ልጅ አኪቃምን፣+ የሚክያስን ልጅ አብዶንን፣ ጸሐፊውን ሳፋንን እና የንጉሡን አገልጋይ አሳያህን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ +21 “ሄዳችሁ በተገኘው መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን ቃል በተመለከተ እኔን እንዲሁም በእስራኤልና በይሁዳ የቀረውን ሕዝብ ወክላችሁ ይሖዋን ጠይቁ፤ አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን ነገሮች ሁሉ ስላልፈጸሙና የይሖዋን ቃል ስላልጠበቁ በእኛ ላይ የሚወርደው የይሖዋ ቁጣ ታላቅ ነው።”+ +22 በመሆኑም ኬልቅያስና ንጉሡ የላካቸው ሰዎች ወደ ነቢዪቱ+ ሕልዳና ሄዱ። ሕልዳና የሃርሐስ ልጅ፣ የቲቅዋ ልጅ፣ የአልባሳት ጠባቂው የሻሉም ሚስት ስትሆን ኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው ክፍል ትኖር ነበር፤ እነሱም በዚያ አነጋገሯት።+ +23 እሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ እኔ የላካችሁን ሰው እንዲህ በሉት፦ +24 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ መከራ አመጣለሁ፤+ በይሁዳ ንጉሥ ፊት ባነበቡት መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን እርግማን ሁሉ አመጣለሁ።+ +25 እኔን በመተው+ በእጆቻቸው ሥራ ሁሉ ያስቆጡኝ ዘንድ ለሌሎች አማልክት የሚጨስ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡ+ በዚህ ቦታ ላይ ቁጣዬ ይፈስሳል፤ ደግሞም አይጠፋም።’”+ +26 ይሖዋን እንድትጠይቁ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ ግን እንዲህ በሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማኸውን ቃል በተመለከተ፣+ +27 ስለዚህ ቦታና ስለ ነዋሪዎቹ የተናገረውን ቃል ስትሰማ ልብህ ስለተነካና* በአምላክ ፊት ራስህን ስላዋረድክ እንዲሁም ራስህን በፊቴ ዝቅ ስላደረግክ፣ ልብስህን ስለቀደድክና በፊቴ ስላለቀስክ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል ይሖዋ።+ +28 ወደ አባቶችህ የምሰበስብህ* በዚህ የተነሳ ነው፤ አንተም በሰላም በመቃብርህ ታርፋለህ፤ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ የማመጣውን መከራ ሁሉ ዓይኖችህ አያዩም።’”’”+ ከዚያም ሰዎቹ መልሱን ለንጉሡ አመጡለት። +29 ንጉሡም መልእክት ልኮ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠራ።+ +30 ከዚያ በኋላ ንጉሡ ከይሁዳ ሰዎች፣ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣ ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ እንዲሁም ትልቅ ትንሽ ሳይባል ከሕዝቡ ሁሉ ጋር ወደ ይሖዋ ቤት ወጣ። እሱም በይሖዋ ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ���ሉ የተሰበሰቡት ሰዎች እየሰሙ አነበበላቸው።+ +31 ንጉሡ ባለበት ስፍራ ቆሞ፣ በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈሩትን የቃል ኪዳኑን ቃላት በመፈጸም+ በሙሉ ልቡና በሙሉ ነፍሱ*+ ይሖዋን ለመከተል እንዲሁም ትእዛዛቱን፣ ማሳሰቢያዎቹንና ሥርዓቶቹን ለመጠበቅ በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ገባ።*+ +32 በተጨማሪም በኢየሩሳሌምና በቢንያም ያሉት ሁሉ በቃል ኪዳኑ እንዲስማሙ አደረገ። የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች በአምላክ ይኸውም በአባቶቻቸው አምላክ ቃል ኪዳን መሠረት እርምጃ ወሰዱ።+ +33 ከዚያም ኢዮስያስ ከመላው የእስራኤላውያን ምድር አስጸያፊዎቹን ነገሮች* በሙሉ አስወገደ፤+ እንዲሁም በእስራኤል ያሉ ሁሉ አምላካቸውን ይሖዋን እንዲያገለግሉ አደረገ። በሕይወት ዘመኑ* ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ከመከተል ፈቀቅ አላሉም። +19 ከዚያም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤቱ* በደህና ተመለሰ።+ +2 ባለ ራእዩ የሃናኒ+ ልጅ ኢዩ+ ከንጉሥ ኢዮሳፍጥ ጋር ለመገናኘት ሄደ፤ እንዲህም አለው፦ “ለክፉ ሰው እርዳታ መስጠት ይገባሃል?+ ይሖዋን የሚጠሉትንስ መውደድ ይገባሃል?+ በዚህ ምክንያት ይሖዋ በአንተ ላይ ተቆጥቷል። +3 ይሁንና የማምለኪያ ግንዶቹን* ከምድሪቱ ስላስወገድክና እውነተኛውን አምላክ ለመፈለግ ልብህን ስላዘጋጀህ*+ መልካም ነገር ተገኝቶብሃል።”+ +4 ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም መኖሩን ቀጠለ፤ ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ ይሖዋ ይመልሳቸውም ዘንድ ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ተራራማው የኤፍሬም ምድር+ ድረስ ወዳለው ሕዝብ ዳግመኛ ወጣ።+ +5 በተጨማሪም በመላ ምድሪቱ ይኸውም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ፣ በእያንዳንዱ ከተማ ፈራጆችን መደበ።+ +6 ፈራጆቹንም እንዲህ አላቸው፦ “የምትፈርዱት ለሰው ሳይሆን ለይሖዋ ስለሆነ የምታደርጉትን ነገር በጥንቃቄ አከናውኑ፤ እሱም በምትፈርዱበት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነው።+ +7 አሁንም ይሖዋን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን።+ በአምላካችን በይሖዋ ዘንድ ፍትሕ ማዛባት፣+ አድልዎ+ ወይም ጉቦ መቀበል+ ስለሌለ የምታደርጉትን ነገር በጥንቃቄ አከናውኑ።” +8 ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌምም የተወሰኑ ሌዋውያንንና ካህናትን እንዲሁም ከእስራኤል የአባቶች ቤት መሪዎች መካከል አንዳንዶቹን ፈራጆች ሆነው ይሖዋን እንዲያገለግሉና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ሙግት እንዲቋጩ መደበ።+ +9 እንዲህም ሲል አዘዛቸው፦ “ይሖዋን በመፍራት በታማኝነትና በሙሉ ልብ* ይህን ልታደርጉ ይገባል፦ +10 በየከተሞቻቸው የሚኖሩት ወንድሞቻችሁ ከደም መፋሰስ ጋር የተያያዘ ክስ+ አሊያም ከሕግ፣ ከትእዛዝ፣ ከሥርዓት ወይም ከድንጋጌዎች ጋር የተያያዘ ጥያቄ ይዘው በሚመጡበት ጊዜ ሁሉ በይሖዋ ፊት በደለኛ እንዳይሆኑ ልታስጠነቅቋቸው ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ግን በእናንተም ሆነ በወንድሞቻችሁ ላይ ቁጣው ይመጣል። በ +11 እነሆ፣ የይሖዋ በሆነው ነገር ሁሉ ላይ በእናንተ ላይ የተሾመው የካህናቱ አለቃ አማርያህ አለ።+ የእስማኤል ልጅ ዘባድያህ ከንጉሡ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ሁሉ የይሁዳ ቤት መሪ ነው። ሌዋውያኑ ደግሞ አለቆች ሆነው ያገለግሏችኋል። በርቱ፤ ሥራችሁንም በትጋት አከናውኑ፤ ይሖዋም መልካም የሆነውን ነገር ከሚያ +20 ከጊዜ በኋላ ሞዓባውያንና+ አሞናውያን+ ከተወሰኑ የአሞኒም ሰዎች* ጋር ሆነው ከኢዮሳፍጥ ጋር ለመዋጋት መጡ። +2 በመሆኑም ኢዮሳፍጥ እንዲህ የሚል ወሬ ሰማ፦ “በባሕሩ* አካባቢ ካለው ክልል፣ ከኤዶም+ ታላቅ ሠራዊት አንተን ሊወጋ መጥቷል፤ ሠራዊቱም በሃጻጾንታማር ማለትም በኤንገዲ+ ይገኛል።” +3 ኢዮሳፍጥ ይህን ሲሰማ ፈራ፤ ይሖዋንም ለመፈለግ ቆርጦ ተነሳ።*+ በመሆኑም በመላው ይሁዳ ጾም አወጀ። +4 ከዚያም የይሁዳ ሰዎች ይሖዋን ለመጠየቅ ተሰበሰቡ፤+ የይሖዋን መመሪያ ለማግኘት ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ መጡ። +5 ከዚያም ኢዮሳፍጥ በይሖዋ ቤት ከአዲሱ ግቢ ፊት ለፊት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ጉባኤ መካከል ቆመ፤ +6 እንዲህም አለ፦ “የአባቶቻችን አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በሰማያት ያለህ አምላክ አይደለህም?+ የብሔራትን መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህም?+ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ አንተን ሊቋቋም የሚችል ማንም የለም።+ +7 አምላካችን ሆይ፣ የዚህችን ምድር ነዋሪዎች ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት አሳደህ ምድሪቱን ለወዳጅህ ለአብርሃም ዘሮች ለዘለቄታው ርስት አድርገህ የሰጠኸው አንተ አይደለህም?+ +8 እነሱም በምድሪቱ መኖር ጀመሩ፤ በዚያም ለስምህ መቅደስ ሠሩ፤+ እንዲህም አሉ፦ +9 ‘ሰይፍ፣ የቅጣት ፍርድ፣ ቸነፈር ወይም ረሃብ በእኛ ላይ ጥፋት ቢያደርስብን በዚህ ቤትና በአንተ ፊት እንቆማለን (ይህን ቤት ለስምህ መርጠኸዋልና)፤+ ከጭንቀታችንም እንድትገላግለን ወደ አንተ እንጮኻለን፤ አንተም ሰምተህ አድነን።’+ +10 አሁንም የአሞንና የሞዓብ ሰዎች እንዲሁም በሴይር ተራራማ ክልል+ የሚኖሩ ሰዎች የሚያደርጉትን ተመልከት። እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡበት ጊዜ እነሱን እንዲወሩ አልፈቀድክም ነበር። እነሱም አልነኳቸውም፤ ደግሞም አላጠፏቸውም።+ +11 እነሱ ግን ርስት አድርገህ ካወረስከን ምድር እኛን በማባረር ብድራት ሊመልሱልን መጥተዋል።+ +12 አምላካችን ሆይ፣ በእነሱ ላይ አትፈርድባቸውም?+ እኛ የመጣብንን ይህን ታላቅ ሠራዊት ለመቋቋም የሚያስችል ኃይል የለንም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም አናውቅም፤+ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ይመለከታሉ።”+ +13 በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሰዎች በሙሉ ከሕፃኖቻቸው፣ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው* ጋር በይሖዋ ፊት ቆመው ነበር። +14 ከዚያም በጉባኤው መካከል የይሖዋ መንፈስ ከአሳፍ ልጆች ወገን በሆነው በሌዋዊው በማታንያህ ልጅ፣ በየኢዔል ልጅ፣ በበናያህ ልጅ፣ በዘካርያስ ልጅ በያሃዚኤል ላይ መጣ። +15 እሱም እንዲህ አለ፦ “የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ እናንተም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና ንጉሥ ኢዮሳፍጥ፣ አዳምጡ! ይሖዋ እንዲህ ይላችኋል፦ ‘ከዚህ ታላቅ ሠራዊት የተነሳ አትፍሩ፤ አትሸበሩ፤ ውጊያው የአምላክ እንጂ የእናንተ አይደለምና።+ +16 ነገ በእነሱ ላይ ውረዱ። እነሱ በጺጽ መተላለፊያ ሽቅብ ይወጣሉ፤ እናንተም የሩኤል ምድረ በዳ ከመድረሳችሁ በፊት በሸለቆው መጨረሻ* ላይ ታገኟቸዋላችሁ። +17 እናንተ ይህን ጦርነት መዋጋት አያስፈልጋችሁም። ቦታ ቦታችሁን ይዛችሁ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤+ ይሖዋ ለእናንተ ሲል የሚወስደውን የማዳን እርምጃ ተመልከቱ።*+ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አትፍሩ ወይም አትሸበሩ።+ ነገ በእነሱ ላይ ውጡ፤ ይሖዋም ከእናንተ ጋር ይሆናል።’”+ +18 ኢዮሳፍጥ ወዲያውኑ በግንባሩ ወደ መሬት ተደፋ፤ የይሁዳ ሰዎች ሁሉና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም በይሖዋ ፊት ተደፍተው ይሖዋን አመለኩ። +19 ከዚያም የቀአታውያንና+ የቆሬያውያን ዘሮች የሆኑት ሌዋውያን የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን እጅግ ከፍ ባለ ድምፅ ለማወደስ ተነሱ።+ +20 በማግስቱም በማለዳ ተነስተው በተቆአ+ ወደሚገኘው ምድረ በዳ ሄዱ። እየሄዱ ሳሉ ኢዮሳፍጥ ቆሞ እንዲህ አለ፦ “ይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ፣ ስሙኝ! ጸንታችሁ መቆም እንድትችሉ በአምላካችሁ በይሖዋ እመኑ። በነቢያቱም እመኑ፤+ እንዲህ ካደረጋችሁ ይሳካላችኋል።” +21 ከሕዝቡ ጋር ከተማከረ በኋላም ከታጠቁት ሰዎች ፊት ፊት እየሄዱ “ለይሖዋ ምስጋና አቅርቡ፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና”+ እያሉ ለይሖዋ የሚዘምሩ እንዲሁም ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሰው ውዳሴ የሚያቀርቡ ሰዎችን መደበ።+ +22 በደስ��� የውዳሴ መዝሙር መዘመር በጀመሩ ጊዜ ይሖዋ ይሁዳን በወረሩት በአሞን፣ በሞዓብና በሴይር ተራራማ ክልል በሚኖሩት ሰዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ሰነዘረባቸው፤ እነሱም እርስ በርስ ተፋጁ።+ +23 አሞናውያኑና ሞዓባውያኑ በሴይር ተራራማ ክልል+ በሚኖሩት ሰዎች ላይ ተነስተው አጠፏቸው፤ ደመሰሷቸውም፤ የሴይርን ነዋሪዎች ካጠፉም በኋላ እርስ በርስ ተላለቁ።+ +24 የይሁዳ ሰዎች በምድረ በዳ+ ወዳለው መጠበቂያ ግንብ መጥተው ሠራዊቱን ሲመለከቱ መሬቱ ሬሳ በሬሳ ሆኖ አዩ፤+ በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም። +25 በመሆኑም ኢዮሳፍጥና ሕዝቡ ከእነሱ ላይ ምርኮ ለመውሰድ መጡ፤ በእነሱም መካከል እጅግ ብዙ ዕቃ፣ ልብስና ውድ ነገሮች አገኙ፤ መሸከም እስኪያቅታቸው ድረስ ብዙ ነገር ገፈፏቸው።+ ከብዛቱ የተነሳ ለሦስት ቀን ያህል ምርኮ ሲሰበስቡ ቆዩ። +26 በአራተኛውም ቀን በቤራካ ሸለቆ* ተሰበሰቡ፤ በዚያም ይሖዋን አወደሱ።* ይህን ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የቤራካ* ሸለቆ ብለው የሚጠሩት ከዚህ የተነሳ ነው።+ +27 ከዚያም የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ ይሖዋ በጠላቶቻቸው ላይ ድል ስላቀዳጃቸው በኢዮሳፍጥ እየተመሩ በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።+ +28 በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በበገናና+ በመለከት+ ድምፅ ታጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ከዚያም ወደ ይሖዋ ቤት ሄዱ።+ +29 ይሖዋ የእስራኤልን ጠላቶች እንደተዋጋ በሰሙ ጊዜ በምድሪቱ ያሉ መንግሥታት ሁሉ አምላክን ፈሩ።+ +30 በመሆኑም የኢዮሳፍጥ መንግሥት ከሁከት ነፃ ሆነ፤ አምላኩም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ እረፍት ሰጠው።+ +31 ኢዮሳፍጥም በይሁዳ መግዛቱን ቀጠለ። በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 35 ዓመት የነበረ ሲሆን በኢየሩሳሌም 25 ዓመት ገዛ። እናቱ የሺልሂ ልጅ አዙባ ነበረች።+ +32 እሱም በአባቱ በአሳ መንገድ ሄደ።+ ከዚያ ፈቀቅ አላለም፤ በይሖዋም ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ +33 ይሁን እንጂ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር፤+ ሕዝቡም ልቡን ለአባቶቹ አምላክ ገና አላዘጋጀም ነበር።+ +34 ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለው የቀረው የኢዮሳፍጥ ታሪክ የሃናኒ+ ልጅ ኢዩ+ በጻፈው ዘገባ ላይ ሰፍሯል፤ ይህም በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ውስጥ ተካቷል። +35 ከዚህ በኋላ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ፣ ክፉ ድርጊት ከፈጸመው ከእስራኤል ንጉሥ ከአካዝያስ ጋር ግንባር ፈጠረ።+ +36 ወደ ተርሴስ+ የሚሄዱ መርከቦችን ለመሥራትም ተሻረኩ፤ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር+ ሠሩ። +37 ይሁን እንጂ የማሬሻ ሰው የሆነው የዶዳዋ ልጅ ኤሊዔዘር “ከአካዝያስ ጋር ግንባር በመፍጠርህ ይሖዋ ሥራህን ያፈርሰዋል” ሲል በኢዮሳፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረ።+ በመሆኑም መርከቦቹ ተሰባበሩ፤+ ወደ ተርሴስም መሄድ ሳይችሉ ቀሩ። +3 ከዚያም ሰለሞን በኢየሩሳሌም፣ ይሖዋ ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት+ በሞሪያ ተራራ+ ይኸውም ዳዊት በኢያቡሳዊው በኦርናን+ አውድማ ላይ ባዘጋጀው ቦታ የይሖዋን ቤት መሥራት ጀመረ።+ +2 በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በሁለተኛው ቀን የግንባታውን ሥራ ጀመረ። +3 ሰለሞን የእውነተኛውን አምላክ ቤት ለመሥራት የጣለው መሠረት በቀድሞው መለኪያ* ርዝመቱ 60 ክንድ፣ ወርዱም 20 ክንድ ነበር።+ +4 ከቤቱ ፊት ያለው በረንዳ ርዝመቱ 20 ክንድ ሲሆን ይህም ከቤቱ ወርድ ጋር እኩል ነው፤ ከፍታው ደግሞ 120* ነው፤ ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።+ +5 ዋናውን ክፍል* በጥድ እንጨት አልብሶ በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤+ ከዚያም በዘንባባ ዛፍ ምስሎችና+ በሰንሰለቶች+ አስጌጠው። +6 በተጨማሪም ቤቱን ባማሩና በከበሩ ድንጋዮች ለበጠው፤+ የተጠቀመበትም ወርቅ+ ከፓርዋይም የመጣ ነበር። +7 እሱም ቤቱን፣ ወራጆቹን፣ ደ���ቹን፣ ግድግዳዎቹንና በሮቹን በወርቅ ለበጣቸው፤+ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቦችን ምስል ቀረጸ።+ +8 ከዚያም የቅድስተ ቅዱሳኑን ክፍል* ሠራ፤+ ርዝመቱ ከቤቱ ወርድ ጋር እኩል የነበረ ሲሆን 20 ክንድ ነበር፤ ወርዱም 20 ክንድ ነበር። ከዚያም 600 ታላንት* በሚሆን ጥሩ ወርቅ ለበጠው።+ +9 ለምስማሮቹ የዋለው ወርቅ 50 ሰቅል* ይመዝን ነበር፤ ሰገነት ላይ ያሉትንም ክፍሎች በወርቅ ለበጣቸው። +10 ከዚያም በቅድስተ ቅዱሳኑ ክፍል* ውስጥ ሁለት የኪሩቦች ቅርጽ ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።+ +11 የኪሩቦቹ ክንፎች+ አጠቃላይ ርዝመት 20 ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን የቤቱን ግድግዳ ይነካ ነበር፤ ሌላኛው ክንፉም አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። +12 የሁለተኛውም ኪሩብ አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን በአንጻሩ ያለውን የቤቱን ግድግዳ ይነካ ነበር፤ ሌላኛው ክንፉም አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። +13 የተዘረጉት የእነዚህ ኪሩቦች ክንፎች 20 ክንድ ነበሩ፤ ኪሩቦቹም ፊታቸውን ወደ ውስጥ* አዙረው በእግራቸው ቆመው ነበር። +14 በተጨማሪም ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ክርና ጥራት ካለው ጨርቅ መጋረጃ+ ሠርቶ የኪሩቦችን ምስል ጠለፈበት።+ +15 ከቤቱ ፊት ለፊትም 35 ክንድ ርዝመት ያላቸው ሁለት ዓምዶችን+ ሠራ፤ በእያንዳንዱ ዓምድ ላይ ያለው የዓምድ ራስ አምስት ክንድ ነበር።+ +16 እንደ ሐብል ያሉ ሰንሰለቶች ሠርቶም በዓምዶቹ አናት ላይ አደረጋቸው፤ እንዲሁም 100 የሮማን ፍሬዎችን ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋር አያያዛቸው። +17 ዓምዶቹንም አንዱን በቀኝ* ሌላውን በግራ* አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በስተ ቀኝ ያለውን ያኪን፣* በስተ ግራ ያለውን ደግሞ ቦዔዝ* ብሎ ሰየማቸው። +24 ኢዮዓስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር፤+ በኢየሩሳሌም ሆኖ 40 ዓመት ገዛ። እናቱ ጺብያ የተባለች የቤርሳቤህ+ ተወላጅ ነበረች። +2 ኢዮዓስ ካህኑ ዮዳሄ በነበረበት ዘመን ሁሉ በይሖዋ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አደረገ።+ +3 ዮዳሄ ሁለት ሚስቶች መረጠለት፤ እሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ። +4 ከጊዜ በኋላ ኢዮዓስ የይሖዋን ቤት ለማደስ ልባዊ ፍላጎት አደረበት።+ +5 በመሆኑም ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ይሁዳ ከተሞች ሄዳችሁ የአምላካችሁን ቤት በየዓመቱ ለማደስ ከእስራኤል ሁሉ ገንዘብ ሰብስቡ፤+ እናንተም በአስቸኳይ ይህንኑ አድርጉ።” ሌዋውያኑ ግን አፋጣኝ እርምጃ አልወሰዱም።+ +6 ስለዚህ ንጉሡ የካህናቱን አለቃ ዮዳሄን ጠርቶ እንዲህ አለው፦+ “የይሖዋ አገልጋይ የሆነው ሙሴ ያዘዘውንና+ ለምሥክሩ ድንኳን+ የሚውለውን የተቀደሰ ግብር ይኸውም የእስራኤልን ጉባኤ የተቀደሰ ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲያመጡ ሌዋውያኑን ያላዘዝካቸው ለምንድን ነው? +7 የዚያች ክፉ ሴት የጎቶልያ+ ወንዶች ልጆች ወደ እውነተኛው አምላክ ቤት ሰብረው በመግባት+ በይሖዋ ቤት የነበሩትን የተቀደሱ ዕቃዎች በሙሉ ለባአል አገልግሎት እንዳዋሉ ታውቃለህ።” +8 ከዚያም በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ሣጥን+ ተሠርቶ በይሖዋ ቤት በር አጠገብ በውጭ በኩል ተቀመጠ።+ +9 ከዚህ በኋላ የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ ሳሉ በእስራኤል ላይ የጣለው የተቀደሰ ግብር+ ለይሖዋ እንዲሰጥ በመላው ይሁዳና ኢየሩሳሌም አዋጅ ተነገረ። +10 መኳንንቱ ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሐሴት አደረጉ፤+ ሣጥኑ እስኪሞላም* ድረስ መዋጮ እያመጡ ይጨምሩ ነበር። +11 ሌዋውያኑ ሣጥኑን ወደ ንጉሡ በሚያመጡበትና በውስጡ ብዙ ገንዘብ መኖሩን በሚያዩበት ጊዜ ��ሉ የንጉሡ ጸሐፊና የካህናቱ አለቃ ሹም መጥተው ሣጥኑን ካጋቡ+ በኋላ ወደ ቦታው ይመልሱት ነበር። በየዕለቱ እንዲህ ያደርጉ ነበር፤ እጅግ ብዙ ገንዘብም ሰበሰቡ። +12 ከዚያም ንጉሡና ዮዳሄ ገንዘቡን በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ለሚቆጣጠሩት ሰዎች ይሰጧቸው ነበር፤ እነሱ ደግሞ የይሖዋን ቤት ለማደስ+ ድንጋይ ጠራቢዎችንና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን እንዲሁም የይሖዋን ቤት ለመጠገን የብረትና የመዳብ ሠራተኞችን ይቀጥሩ ነበር። +13 ሥራውን የሚቆጣጠሩት ሰዎችም ሥራው እንዲጀመር አደረጉ፤ የጥገናውም ሥራ በእነሱ አመራር ሥር ተፋጠነ፤ የእውነተኛውን አምላክ ቤት በማደስ ወደ ቀድሞው ሁኔታ መለሱት፤ ቤቱንም አጠናከሩት። +14 ሥራውን እንደጨረሱም የተረፈውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ወደ ዮዳሄ አመጡ፤ እነሱም ለይሖዋ ቤት የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን፣ ለአገልግሎትና መባ ለማቅረብ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን፣ ጽዋዎችን እንዲሁም የወርቅና የብር ዕቃዎችን ለመሥራት ተጠቀሙበት።+ ዮዳሄ በነበረበት ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን+ +15 ዮዳሄ ሸምግሎና ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ በሞተ ጊዜ ዕድሜው 130 ዓመት ነበር። +16 ከእውነተኛው አምላክና ከአምላክ ቤት ጋር በተያያዘ በእስራኤል መልካም ነገር ስላደረገ+ በዳዊት ከተማ ከነገሥታት ጋር ቀበሩት።+ +17 ከዮዳሄ ሞት በኋላ የይሁዳ መኳንንት መጥተው ንጉሡን እጅ ነሱ፤ ንጉሡም እነሱ ያሉትን ሰማ። +18 እነሱም የአባቶቻቸውን አምላክ የይሖዋን ቤት ትተው የማምለኪያ ግንዶችንና* ጣዖቶችን ማገልገል ጀመሩ፤ ከፈጸሙት በደል የተነሳ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ የአምላክ ቁጣ መጣ።* +19 ይሖዋ ወደ እሱ እንዲመልሷቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ እነሱም ያስጠነቅቋቸው* ነበር፤ ሕዝቡ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልነበረም።+ +20 የአምላክ መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ+ ልጅ በዘካርያስ ላይ ወረደ፤ እሱም በሕዝቡ ፊት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ቆሞ እንዲህ አላቸው፦ “እውነተኛው አምላክ እንዲህ ይላል፦ ‘የይሖዋን ትእዛዛት የምትተላለፉት ለምንድን ነው? አይሳካላችሁም! ይሖዋን ስለተዋችሁ እሱም ይተዋችኋል።’”+ +21 እነሱ ግን በእሱ ላይ አሴሩ፤+ ንጉሡም በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በይሖዋ ቤት ግቢ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት።+ +22 ንጉሥ ኢዮዓስ፣ አባቱ* ዮዳሄ ያሳየውን ታማኝ ፍቅር አላሰበም፤ ልጁንም ገደለው፤ እሱም ሊሞት ሲል “ይሖዋ ይየው፤ የእጅህንም ይስጥህ” አለ።+ +23 በዓመቱ መጀመሪያ ላይ የሶርያ ሠራዊት በኢዮዓስ ላይ ዘመተ፤ እነሱም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ወረሩ።+ ከዚያም የሕዝቡን መኳንንት ሁሉ አጠፉ፤+ የማረኩትንም ሁሉ ወደ ደማስቆ ንጉሥ ላኩ። +24 ወራሪው የሶርያ ሠራዊት አነስተኛ ቁጥር የነበረው ቢሆንም ይሖዋ እጅግ ብዙ የሆነውን ሠራዊት በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤+ ይህም የሆነው የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን በመተዋቸው ነው፤ እነሱም* በኢዮዓስ ላይ የተላለፈውን ፍርድ ፈጸሙ። +25 እነሱም ጥለውት በሄዱ ጊዜ (ክፉኛ አቁስለውት* ነበርና) የገዛ አገልጋዮቹ የካህኑን የዮዳሄን ልጆች* ደም በማፍሰሱ አሴሩበት።+ አልጋው ላይ እንዳለ ገደሉት።+ ከሞተም በኋላ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤+ በነገሥታቱ የመቃብር ስፍራ ግን አልቀበሩትም።+ +26 በእሱ ላይ ያሴሩት+ የአሞናዊቷ የሺምዓት ልጅ ዛባድና የሞዓባዊቷ የሺምሪት ልጅ የሆዛባድ ነበሩ። +27 ስለ ወንዶች ልጆቹ፣ በእሱ ላይ ስለተላለፉት በርካታ የፍርድ መልእክቶችና+ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ስለማደሱ*+ የሚገልጸው ታሪክ ሁሉ በነገሥታቱ መጽሐፍ ዘገባዎች* ላይ ሰፍሯል። በእሱም ምትክ ልጁ አሜስያስ ነገሠ። +32 እነዚህ ነገሮች ከተከናወኑና ሕዝቅያስ በታማኝነት ሲመላለስ+ ከቆየ በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ይሁዳን ወረረ። ቅጥራቸውን አፍርሶ ለመያዝ ስላሰበ የተመሸጉትን ከተሞች ከበበ።+ +2 ሕዝቅያስ ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን ለመውጋት አስቦ እንደመጣ ባየ ጊዜ፣ +3 ከመኳንንቱና ከተዋጊዎቹ ጋር ተማክሮ ከከተማዋ ውጭ ያሉትን የውኃ ምንጮች ለመድፈን ወሰነ፤+ እነሱም ረዱት። +4 ብዙ ሰዎች ተሰብስበው “የአሦር ነገሥታት መጥተው ለምን ብዙ ውኃ ያግኙ?” በማለት ምንጮቹንና በምድሪቱ መካከል የሚፈሰውን ጅረት በሙሉ ደፈኑ። +5 በተጨማሪም ሕዝቅያስ በትጋት በመሥራት የፈረሰውን ቅጥር በሙሉ ገነባ፤ በላዩም ላይ ማማዎችን ሠራ፤ ከውጭ በኩልም ሌላ ቅጥር ገነባ። ደግሞም የዳዊትን ከተማ ጉብታ*+ ጠገነ፤ እንዲሁም ብዙ የጦር መሣሪያዎችና* ጋሻዎች ሠራ። +6 ከዚያም በሕዝቡ ላይ የጦር አለቆችን ሾሞ በከተማዋ በር በሚገኘው አደባባይ ሰበሰባቸው፤ እንዲህም በማለት አበረታታቸው፦* +7 “ደፋርና ብርቱዎች ሁኑ። ከአሦር ንጉሥና ከእሱ ጋር ካለው ብዙ ሠራዊት የተነሳ አትፍሩ ወይም አትሸበሩ፤+ ከእሱ ጋር ካሉት ይልቅ ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ።+ +8 ከእሱ ጋር ያለው የሥጋ ክንድ* ሲሆን ከእኛ ጋር ያለው ግን አምላካችን ይሖዋ ነው፤ እሱ ይረዳናል፤ ደግሞም ይዋጋልናል።”+ ሕዝቡም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ በተናገረው ቃል ተበረታታ።+ +9 ከዚህ በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከሠራዊቱ ሁሉ* ጋር በለኪሶ+ ሳለ አገልጋዮቹን ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስና በኢየሩሳሌም ወደሚኖሩት አይሁዳውያን+ ሁሉ እንዲህ ሲል ላከ፦ +10 “የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም እንዲህ ይላል፦ ‘ኢየሩሳሌም ተከባ ሳለ ከከተማዋ ሳትወጡ የቀራችሁት በምን ተማምናችሁ ነው?+ +11 ሕዝቅያስ “አምላካችን ይሖዋ ከአሦር ንጉሥ እጅ ይታደገናል” እያለ እናንተን በማታለል በረሃብና በጥም እንድትሞቱ አሳልፎ ሊሰጣችሁ አይደለም?+ +12 የአምላካችሁን* ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችና+ መሠዊያዎች+ ካስወገደ በኋላ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን “በአንድ መሠዊያ ፊት ስገዱ፤ በዚያም ላይ የሚጨስ መሥዋዕት አቅርቡ” ያለው ሕዝቅያስ ራሱ አይደለም?+ +13 እኔም ሆንኩ አባቶቼ በተለያዩ አገሮች ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደረግነውን አታውቁም?+ የእነዚህ አገሮች ሕዝቦች አማልክት ምድራቸውን ከእጄ መታደግ ችለዋል?+ +14 አባቶቼ ፈጽመው ካጠፏቸው ከእነዚህ ብሔራት አማልክት ሁሉ መካከል ሕዝቡን ከእጄ መታደግ የቻለ የትኛው ነው? ታዲያ የእናንተስ አምላክ ቢሆን ከእጄ ሊታደጋችሁ ይችላል?+ +15 አሁንም ሕዝቅያስ በዚህ መንገድ አያታላችሁ ወይም አያሳስታችሁ!+ አትመኑት፤ የየትኛውም ብሔርም ሆነ መንግሥት አምላክ ከእኔና ከአባቶቼ እጅ ሕዝቡን መታደግ አልቻለም። የእናንተ አምላክማ ከእጄ ይታደጋችሁ ዘንድ ምንኛ ያንስ!’”+ +16 የሰናክሬም አገልጋዮች በእውነተኛው አምላክ በይሖዋና በአገልጋዩ በሕዝቅያስ ላይ ሌላ ብዙ ነገር ተናገሩ። +17 በተጨማሪም ንጉሡ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ለመስደብና+ እሱን ለማቃለል እንዲህ ሲል ደብዳቤ ጻፈ፦+ “የሌሎች ብሔራት አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ መታደግ እንዳልቻሉ ሁሉ+ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊታደግ አይችልም።” +18 በቅጥሩ ላይ ያሉትን የኢየሩሳሌም ሰዎች በማስፈራራትና በማሸበር ከተማዋን ለመያዝ ሲሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በአይሁዳውያን ቋንቋ ለሰዎቹ መናገራቸውን ቀጠሉ።+ +19 የሰው እጅ ሥራ በሆኑት በሌሎች የምድር ሕዝቦች አማልክት ላይ እንደተናገሩ ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም አምላክ ላይም ተናገሩ። +20 ንጉሥ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ+ ግን ይህን ጉዳይ በተመለከተ አጥብቀው ጸለዩ፤ እርዳታ ለማግኘትም ወደ ሰማይ ጮኹ።+ +21 ከዚያም ይሖዋ አንድ መልአ�� ልኮ በአሦር ንጉሥ ሰፈር የነበሩትን ኃያላን ተዋጊዎች+ እንዲሁም መሪዎችና አለቆች ሁሉ ጠራርጎ አጠፋ፤ ንጉሡም ኀፍረት ተከናንቦ ወደ ገዛ አገሩ ተመለሰ። በኋላም ወደ አምላኩ ቤት ገባ፤* በዚያም ሳለ የገዛ ወንዶች ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት።+ +22 በዚህ መንገድ ይሖዋ ሕዝቅያስንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅና ከሌሎች ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካሉ ጠላቶቻቸው ሁሉ እረፍት ሰጣቸው። +23 ብዙዎችም ለይሖዋ ስጦታ፣ ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስም ምርጥ የሆኑ ነገሮች ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤+ እሱም ከዚያ በኋላ በብሔራት ሁሉ ዘንድ ታላቅ አክብሮት አተረፈ። +24 በዚያን ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ሞት አፋፍ ደርሶ ነበር፤ ወደ ይሖዋም ጸለየ፤+ እሱም መለሰለት፤ ምልክትም* ሰጠው።+ +25 ይሁንና ሕዝቅያስ ልቡ ታብዮ ስለነበር ለተደረገለት መልካም ነገር አድናቆት ሳያሳይ ቀረ፤ የአምላክም ቁጣ በእሱ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ መጣ። +26 ይሁን እንጂ ሕዝቅያስ ስለ ልቡ ትዕቢት ራሱን ዝቅ አደረገ፤+ እሱና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ትሕትና አሳዩ፤ የይሖዋም ቁጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።+ +27 ሕዝቅያስም እጅግ ብዙ ሀብት አገኘ፤ ታላቅ ክብርም ተጎናጸፈ፤+ ብሩን፣ ወርቁን፣ የከበሩ ድንጋዮቹን፣ የበለሳን ዘይቱን፣ ጋሻዎቹንና ውድ የሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ የሚያስቀምጥባቸው ግምጃ ቤቶች ሠራ።+ +28 በተጨማሪም ለእህሉ፣ ለአዲሱ የወይን ጠጅና ለዘይቱ የማከማቻ ቦታዎች አዘጋጀ፤ እንዲሁም ለተለያዩ እንስሳት በረት፣ ለበጎችና ለፍየሎች ደግሞ ጉረኖ ሠራ። +29 ለራሱም ከተሞችን ገነባ፤ እጅግ ብዙ ከብቶች፣ መንጎችና እንስሳት ነበሩት፤ አምላክ ብዙ ንብረት ሰጥቶት ነበር። +30 የግዮንን+ ውኃ የላይኛውን መውጫ ደፍኖ+ ውኃው በምዕራብ በኩል በቀጥታ ወደ ዳዊት ከተማ+ እንዲወርድ ያደረገው ሕዝቅያስ ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ተሳካለት። +31 ይሁንና የባቢሎን መኳንንት ቃል አቀባዮች በምድሪቱ ላይ ስለተከሰተው+ ምልክት* እንዲጠይቁት+ ወደ እሱ በተላኩ ጊዜ እውነተኛው አምላክ እሱን ለመፈተንና+ በልቡ ያለውን ሁሉ ለማወቅ+ ሲል ተወው። +32 የቀረው የሕዝቅያስ ታሪክና ያሳየው ታማኝ ፍቅር+ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ባየው ራእይ ላይ፣+ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል።+ +33 በመጨረሻም ሕዝቅያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ወደ ዳዊት ልጆች የመቃብር ስፍራ በሚወስድ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ቀበሩት፤+ በሞተበት ጊዜም መላው ይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አከበሩት። በእሱም ምትክ ልጁ ምናሴ ነገሠ። +7 ሰለሞንም ጸሎቱን እንደጨረሰ+ እሳት ከሰማያት ወርዶ+ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕቶቹን በላ፤ የይሖዋም ክብር ቤቱን ሞላው።+ +2 የይሖዋ ክብር የይሖዋን ቤት ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ወደ ይሖዋ ቤት መግባት አልቻሉም።+ +3 የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ እሳቱ ሲወርድና የይሖዋ ክብር ከቤቱ በላይ ሲሆን ይመለከቱ ነበር፤ ወደ መሬት አጎንብሰው ድንጋይ በተነጠፈበት ወለል ላይ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፤ ደግሞም “እሱ ጥሩ ነውና፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል” እያሉ ይሖዋን አመሰገኑ። +4 ከዚያም ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ በይሖዋ ፊት መሥዋዕት አቀረቡ።+ +"5 ንጉሥ ሰለሞን 22,000 ከብቶችና 120,000 በጎች መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። በዚህ መንገድ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእውነተኛውን አምላክ ቤት መረቁ።+" +6 ካህናቱም ሆኑ የይሖዋን መዝሙር ለማጀብ የሚያገለግሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን የያዙት ሌዋውያን እንዲያገለግሉ በተመደቡበት ስፍራ ቆመው ነበር።+ (ንጉሥ ዳዊት እነዚህን መሣሪያዎች የሠራው ከእነሱ ጋር* ሆኖ ውዳሴ በሚያቀርብበት ጊዜ “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” በማለት ይሖዋን ለማመስገን ነው።) +7 ከዚያም ሰለሞን በይሖዋ ቤት ፊት የሚገኘውን የግቢውን መሃል ቀደሰው፤ ምክንያቱም ሰለሞን የሚቃጠለውን መባና+ የኅብረት መሥዋዕቱን ስብ በዚያ ማቅረብ ነበረበት፤ ይህም የሆነው ሰለሞን የሠራው የመዳብ መሠዊያ+ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ የእህሉን መባና+ ስቡን+ መያዝ ስላልቻለ ነው። +8 በዚያን ጊዜ ሰለሞን ከመላው እስራኤል ጋር ይኸውም ከሌቦሃማት* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ* ድረስ+ ካለው ምድር ከመጣው ታላቅ ጉባኤ ጋር በመሆን ለሰባት ቀን በዓሉን* አከበረ።+ +9 ይሁንና የመሠዊያውን የምረቃ ሥነ ሥርዓት ለሰባት ቀን ስላከናወኑና በዓሉን ለሰባት ቀን ስላከበሩ በስምንተኛው ቀን* የተቀደሰ ጉባኤ አደረጉ።+ +10 ከዚያም በሰባተኛው ወር፣ በ23ኛው ቀን ሕዝቡን ወደየቤታቸው አሰናበተ፤ እነሱም ይሖዋ ለዳዊት፣ ለሰለሞንና ለሕዝቡ ለእስራኤል ባሳየው ጥሩነት እየተደሰቱና+ ከልባቸው እየፈነደቁ ሄዱ።+ +11 ሰለሞንም የይሖዋን ቤትና የንጉሡን ቤት*+ ሠርቶ ጨረሰ፤ ከይሖዋ ቤትና ከራሱ ቤት ጋር በተያያዘ በልቡ ያሰበውን ሁሉ በተሳካ ሁኔታ አከናወነ።+ +12 ከዚያም ይሖዋ በሌሊት ለሰለሞን ተገልጦለት+ እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህን ቦታ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቤት እንዲሆን ለራሴ መርጬዋለሁ።+ +13 ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን ብዘጋ፣ ምድሪቱን እንዲበሉ አንበጦችን ብልክ፣ በሕዝቤ መካከል ቸነፈር ብሰድ፣ +14 በስሜ የተጠሩትም ሕዝቤ+ ራሳቸውን ዝቅ ቢያደርጉ፣+ ቢጸልዩ፣ ፊቴን ቢሹና ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ፣+ ከሰማያት ሆኜ እሰማለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።+ +15 በዚህም ስፍራ ለሚቀርበው ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ፤ ጆሮዎቼም ይከፈታሉ።+ +16 አሁንም ስሜ ለዘለቄታው በዚያ እንዲጠራ ይህን ቤት መርጬዋለሁ፤+ ደግሞም ቀድሼዋለሁ፤ ዓይኔም ሆነ ልቤ ሁልጊዜ በዚያ ይሆናል።+ +17 “አንተም አባትህ ዳዊት እንዳደረገው ያዘዝኩህን ሁሉ በመፈጸም በፊቴ ብትሄድ እንዲሁም ሥርዓቶቼንና ድንጋጌዎቼን ብትጠብቅ፣+ +18 ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘር ሐረግህ በእስራኤል ላይ ገዢ የሚሆን አይታጣም’+ በማለት በገባሁለት ቃል ኪዳን መሠረት+ የንግሥና ዙፋንህን አጸናለሁ።+ +19 ሆኖም ጀርባችሁን ብትሰጡ፣ በፊታችሁ ያስቀመጥኳቸውን ደንቦቼንና ትእዛዛቴን ብትተዉ፣ ሄዳችሁም ሌሎች አማልክትን ብታገለግሉና ለእነሱ ብትሰግዱ፣+ +20 እስራኤልን ከሰጠሁት ምድሬ ላይ እነቅለዋለሁ፤+ ለስሜ የቀደስኩትንም ይህን ቤት ከፊቴ አስወግደዋለሁ፤ በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መቀለጃና* መሳለቂያ አደርገዋለሁ።+ +21 ይህም ቤት የፍርስራሽ ክምር ይሆናል። በዚያም የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ በመገረም ትኩር ብለው እየተመለከቱ+ ‘ይሖዋ በዚህች ምድርና በዚህ ቤት ላይ እንዲህ ያለ ነገር ያደረገው ለምንድን ነው?’ በማለት ይጠይቃሉ።+ +22 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን+ የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ትተው+ ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ለእነሱ ስለሰገዱ እንዲሁም እነሱን ስላገለገሉ ነው።+ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣባቸው ለዚህ ነው።’”+ +12 ሮብዓም በበረታና ንግሥናው በጸና ጊዜ+ እሱም ሆነ አብረውት ያሉት እስራኤላውያን ሁሉ የይሖዋን ሕግ ተዉ።+ +2 ለይሖዋ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ንጉሥ ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ+ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ። +"3 እሱም 1,200 ሠረገሎችና 60,000 ፈረሰኞች አስከትሎ ነበር፤ ከእሱም ጋር ከግብፅ የመጡት ሊቢያውያን፣ ሱኪማውያንና ኢትዮጵያውያን+ ወታደሮች ስፍር ቁጥር አልነበራቸውም።" +4 እሱም የይሁዳን የተመሸጉ ከተሞች ያዘ፤ በመጨረሻ�� ኢየሩሳሌም ደረሰ። +5 ነቢዩ ሸማያህ+ ወደ ሮብዓምና ሺሻቅን ፈርተው በኢየሩሳሌም ወደተሰበሰቡት የይሁዳ መኳንንት መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ ትታችሁኛል፤+ ስለዚህ እኔም በሺሻቅ እጅ ትቻችኋለሁ።’” +6 በዚህ ጊዜ የእስራኤል መኳንንትና ንጉሡ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ+ “ይሖዋ ጻድቅ ነው” አሉ። +7 ይሖዋ ራሳቸውን ዝቅ እንዳደረጉ ባየ ጊዜ፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሸማያህ መጣ፦ “ራሳቸውን ዝቅ ስላደረጉ አላጠፋቸውም፤+ በቅርቡም እታደጋቸዋለሁ። ቁጣዬንም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አላፈስም። +8 ይሁን እንጂ እኔን በማገልገልና የሌሎች አገሮች ነገሥታትን* በማገልገል መካከል ያለውን ልዩነት እንዲያውቁ የእሱ አገልጋዮች ይሆናሉ።” +9 በመሆኑም የግብፁ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት መጣ። እሱም በይሖዋ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶችና በንጉሡ ቤት* የነበሩትን ውድ ንብረቶች ወሰደ።+ ሰለሞን የሠራቸውን የወርቅ ጋሻዎች ጨምሮ ሁሉንም ነገር ወሰደ።+ +10 በመሆኑም ንጉሥ ሮብዓም በእነሱ ምትክ የመዳብ ጋሻዎችን ሠርቶ የንጉሡን ቤት በር ለሚጠብቁት የዘብ* አለቆች ሰጣቸው። +11 ዘቦቹም ንጉሡ ወደ ይሖዋ ቤት በመጣ ቁጥር ገብተው ጋሻዎቹን ያነግቡ ነበር፤ ከዚያም ወደ ዘቦቹ ክፍል ይመልሷቸው ነበር። +12 ንጉሡ ራሱን ስላዋረደ የይሖዋ ቁጣ ከእሱ ተመለሰ፤+ ሙሉ በሙሉም አላጠፋቸውም።+ በተጨማሪም በይሁዳ አንዳንድ መልካም ነገሮች ተገኝተው ነበር።+ +13 ንጉሥ ሮብዓም በኢየሩሳሌም ሥልጣኑን አጠናክሮ መግዛቱን ቀጠለ፤ ሮብዓም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 41 ዓመት ነበር፤ እሱም ይሖዋ ስሙ እንዲኖርባት ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም ሆኖ 17 ዓመት ገዛ። የንጉሡም እናት ናዕማ የተባለች አሞናዊት ነበረች።+ +14 ሆኖም ይሖዋን ለመፈለግ ከልቡ ቆርጦ ስላልተነሳ ክፉ ነገር አደረገ።+ +15 ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለው የሮብዓም ታሪክ ነቢዩ ሸማያህና+ ባለ ራእዩ ኢዶ+ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ውስጥ ይገኝ የለም? በሮብዓምና በኢዮርብዓም+ መካከል ምንጊዜም ጦርነት ይካሄድ ነበር። +16 በመጨረሻም ሮብዓም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም+ ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ አቢያህ+ ነገሠ። +1 የዳዊት ልጅ ሰለሞን ንግሥናውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከረ ሄደ፤ አምላኩ ይሖዋም ከእሱ ጋር ስለነበር እጅግ ገናና አደረገው።+ +2 ሰለሞን ለእስራኤል ሁሉ፣ ለሺህ አለቆች፣ ለመቶ አለቆች፣ ለፈራጆችና የአባቶች ቤቶች መሪዎች ለሆኑት በመላው እስራኤል ለሚገኙት አለቆች ሁሉ መልእክት ላከ። +3 ከዚያም ሰለሞንና መላው ጉባኤ በገባኦን+ ወደሚገኘው ኮረብታ ሄዱ፤ ምክንያቱም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእውነተኛው አምላክ የመገናኛ ድንኳን የሚገኘው በዚያ ነበር። +4 ይሁን እንጂ ዳዊት የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ከቂርያትየአሪም+ እሱ ወዳዘጋጀለት ስፍራ አምጥቶት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ድንኳን ተክሎለት ነበር።+ +5 የሁር ልጅ የዖሪ ልጅ ባስልኤል+ የሠራው የመዳብ መሠዊያ+ በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊት ይገኝ ነበር፤ ሰለሞንና ጉባኤውም በመሠዊያው ፊት ይጸልዩ ነበር።* +"6 ሰለሞንም በዚያ በይሖዋ ፊት መባ አቀረበ፤ በመገናኛው ድንኳን በሚገኘው የመዳብ መሠዊያ ላይ 1,000 የሚቃጠሉ መባዎችን አቀረበ።+ " +7 በዚያ ሌሊት አምላክ ለሰለሞን ተገልጦ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ጠይቅ” አለው።+ +8 በዚህ ጊዜ ሰለሞን አምላክን እንዲህ አለው፦ “ለአባቴ ለዳዊት ጥልቅ የሆነ ታማኝ ፍቅር አሳይተኸዋል፤+ በእሱም ምትክ አንግሠኸኛል።+ +9 አሁንም ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸው ቃል ይፈጸም፤+ እንደ ምድር አፈር እጅግ ብዙ በሆነ ሕዝብ+ ላይ አንግሠኸኛልና። +10 ይህን ሕዝብ መምራት* እንድችል ጥበብና እውቀት ስጠኝ፤+ አለዚያማ ይህን ታላቅ ሕዝብህን ማን ሊዳኝ ይችላል?”+ +11 ከዚያም አምላክ ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “የልብህ መሻት ይህ ስለሆነ ደግሞም ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር ወይም የሚጠሉህን ሰዎች ሞት* አሊያም ረጅም ዕድሜ* ስላልተመኘህ፣ ይልቁንም አንተን ንጉሥ አድርጌ የሾምኩበትን ሕዝቤን ማስተዳደር እንድትችል ጥበብና እውቀት ስለጠየቅክ፣+ +12 ጥበብና እውቀት ይሰጥሃል፤ ከዚህም ሌላ ከአንተ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ያላገኘውን፣ ከአንተም በኋላ የሚነሳ የትኛውም ንጉሥ የማያገኘውን ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር እሰጥሃለሁ።”+ +13 ሰለሞንም በገባኦን+ ኮረብታ ከሚገኘው ከመገናኛው ድንኳን ፊት ወጥቶ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ። +"14 ሰለሞን ሠረገሎችንና ፈረሶችን* መሰብሰቡን ቀጠለ፤ እሱም 1,400 ሠረገሎችና 12,000 ፈረሶች* ነበሩት፤+ እነሱንም በሠረገላ ከተሞችና+ በኢየሩሳሌም በንጉሡ አቅራቢያ አኖራቸው።+" +15 ንጉሡ ብርና ወርቅ በየቦታው እንደሚገኝ ድንጋይ እስኪሆን ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲበዛ አደረገ፤+ አርዘ ሊባኖሱንም ከብዛቱ የተነሳ በሸፌላ እንደሚገኘው የሾላ ዛፍ አደረገው።+ +16 የሰለሞን ፈረሶች ከግብፅ ያስመጣቸው ነበሩ፤+ የንጉሡ ነጋዴዎችም የፈረሶቹን መንጋ አንዴ በተተመነው ዋጋ ይገዙ ነበር።*+ +17 ከግብፅ የሚመጣው እያንዳንዱ ሠረገላ 600 የብር ሰቅል ያወጣ ነበር፤ አንድ ፈረስ ደግሞ 150 ሰቅል ያወጣል፤ እነሱ ደግሞ በተራቸው ለሂታውያን ነገሥታትና ለሶርያ ነገሥታት ሁሉ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይሸጡ ነበር። +36 ከዚያም የምድሪቱ ሕዝብ የኢዮስያስን ልጅ ኢዮዓካዝን+ በአባቱ ምትክ በኢየሩሳሌም አነገሡት።+ +2 ኢዮዓካዝ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 23 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ገዛ። +3 ይሁን እንጂ የግብፅ ንጉሥ በኢየሩሳሌም ካለው ዙፋኑ አወረደው፤ በምድሪቱም ላይ 100 የብር ታላንትና* አንድ የወርቅ ታላንት ቅጣት ጣለ።+ +4 በተጨማሪም የግብፁ ንጉሥ ኒካዑ+ የኢዮዓካዝን ወንድም ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው፤ ስሙንም ቀይሮ ኢዮዓቄም አለው፤ ወንድሙን ኢዮዓካዝን ግን ወደ ግብፅ ወሰደው።+ +5 ኢዮዓቄም+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ። እሱም በአምላኩ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ ከመዳብ በተሠሩ ሁለት የእግር ብረቶች አስሮ ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በእሱ ላይ ዘመተ።+ +7 ናቡከደነጾርም በይሖዋ ቤት ያሉ የተወሰኑ ዕቃዎችን ወደ ባቢሎን ወስዶ በባቢሎን በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ አስቀመጣቸው።+ +8 የቀረው የኢዮአቄም ታሪክ፣ የፈጸማቸው አስጸያፊ ነገሮችና በእሱ ላይ የተገኘበት መጥፎ ነገር በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል፤ በእሱም ምትክ ልጁ ዮአኪን ነገሠ።+ +9 ዮአኪን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 18 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ከአሥር ቀን ገዛ፤ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +10 በዓመቱ መጀመሪያ* ላይ ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹን ልኮ በይሖዋ ቤት ካሉት ውድ ዕቃዎች+ ጋር ወደ ባቢሎን አመጣው።+ የአባቱን ወንድም ሴዴቅያስንም በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።+ +11 ሴዴቅያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 21 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ።+ +12 በአምላኩ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። በይሖዋ ትእዛዝ በተናገረው በነቢዩ ኤርምያስ ፊት ራሱን ዝቅ አላደረገም።+ +13 ደግሞም በአምላክ ስም ባስማለ��� በንጉሥ ናቡከደነጾር ላይ ዓመፀ፤+ ግትር ሆነ፤* ልቡንም አጠነከረ፤ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ ይሖዋ ለመመለስ አሻፈረኝ አለ። +14 ዋነኞቹ ካህናት ሁሉና ሕዝቡ፣ ብሔራት የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ነገሮች በማድረግ እጅግ ከፍተኛ ክህደት ፈጸሙ፤ ይሖዋ በኢየሩሳሌም የቀደሰውንም ቤት አረከሱ።+ +15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። +16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር። +17 ስለዚህ የከለዳውያንን+ ንጉሥ አመጣባቸው፤ እሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሳቸው+ ውስጥ በሰይፍ ገደለ፤+ ለወጣቱም ሆነ ለድንግሊቱ፣ ለሽማግሌውም ሆነ ለአቅመ ደካማው አልራራም።+ አምላክ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።+ +18 በእውነተኛው አምላክ ቤት የነበሩትን ትላልቅም ሆኑ ትናንሽ ዕቃዎች በሙሉ፣ የይሖዋን ቤት ውድ ሀብት እንዲሁም የንጉሡንና የመኳንንቱን ውድ ሀብት ሁሉ ወደ ባቢሎን አጋዘ።+ +19 የእውነተኛውን አምላክ ቤት አቃጠለ፤+ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ፤+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤ እንዲሁም ውድ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ አወደመ።+ +20 ከሰይፍ የተረፉትንም ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤+ እነሱም የፋርስ መንግሥት* መግዛት እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ+ የእሱና የወንዶች ልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ፤+ +21 ይህም የሆነው ይሖዋ በኤርምያስ በኩል የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣+ ምድሪቱ የሰንበት ዕዳዋን እስክትከፍል ድረስ ነው።+ ፈራርሳ በቆየችባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ 70 ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ሰንበትን አከበረች።+ +22 በኤርምያስ በኩል የተነገረው የይሖዋ ቃል ይፈጸም ዘንድ+ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ+ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት የሚከተለውን አዋጅ በመላ ግዛቱ እንዲያውጅ ይሖዋ የፋርሱን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሳሳ፤ እሱም ይህ በጽሑፍ እንዲሰፍር አደረገ፦+ +23 “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማይ አምላክ ይሖዋ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤+ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌምም ቤት እንድሠራለት አዞኛል።+ ከእሱ ሕዝብ መካከል የሆነ አብሯችሁ የሚኖር ማንኛውም ሰው አምላኩ ይሖዋ ከእሱ ጋር ይሁን፤ እሱም ወደዚያ ይውጣ።’”+ +29 ሕዝቅያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ አቢያህ ትባል ነበር፤ እሷም የዘካርያስ ልጅ ነበረች።+ +2 አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ+ እሱም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ +3 መግዛት በጀመረ በመጀመሪያው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር የይሖዋን ቤት በሮች ከፈተ፤ አደሳቸውም።+ +4 ከዚያም ካህናቱንና ሌዋውያኑን አስጠርቶ በምሥራቅ በኩል በሚገኘው አደባባይ ሰበሰባቸው። +5 እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ሌዋውያን፣ ስሙኝ። ራሳችሁንም ሆነ የአባቶቻችሁን አምላክ የይሖዋን ቤት ቀድሱ፤+ ርኩስ የሆነውንም ነገር ከቅዱሱ ስፍራ አስወግዱ።+ +6 አባቶቻችን ታማኞች አልነበሩም፤ በአምላካችን በይሖዋም ፊት ክፉ ነገር አድርገዋል።+ እሱን የተዉት ከመሆኑም ሌላ ከይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊታቸውን መልሰዋል፤ ጀርባቸውንም ሰጥተውታል።+ +7 በተጨማሪም የበረንዳውን በሮች ዘጉ፤+ መብራቶቹንም አጠፉ።+ ዕጣን ማጠንና+ በተቀደሰው ስፍራ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ+ አቆሙ። +8 ስለዚህ የይሖዋ ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ነደደ፤+ በመሆኑም በገዛ ዓይናችሁ እንደምታዩት መቀጣጫ፣ የሰዎች መደነቂያና ማፏጫ* አደረጋቸው።+ +9 በዚህም የተነ�� አባቶቻችን በሰይፍ ወደቁ፤+ እንዲሁም ወንዶች ልጆቻችን፣ ሴቶች ልጆቻችንና ሚስቶቻችን ተማርከው ተወሰዱ።+ +10 አሁንም የሚነድ ቁጣው ከእኛ እንዲመለስ ከእስራኤል አምላክ ከይሖዋ ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ከልቤ ተመኝቻለሁ።+ +11 እንግዲህ ልጆቼ በፊቱ እንድትቆሙ፣ እንድታገለግሉትና+ የሚጨስ መሥዋዕቱን እንድታቀርቡ+ ይሖዋ የመረጠው እናንተን ስለሆነ አሁን ቸልተኛ የምትሆኑበት* ጊዜ አይደለም።” +12 በዚህ ጊዜ ሌዋውያኑ ለሥራ ተነሱ፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦ ከቀአታውያን+ መካከል የአማሳይ ልጅ ማሃት እና የአዛርያስ ልጅ ኢዩኤል፤ ከሜራራውያን+ መካከል የአብዲ ልጅ ቂስ እና የይሃሌልዔል ልጅ አዛርያስ፤ ከጌድሶናውያን+ መካከል የዚማ ልጅ ዮአህ እና የዮአህ ልጅ ኤደን፤ +13 ከኤሊጻፋን ልጆች መካከል ሺምሪ እና የኡዔል፤ ከአሳፍ+ ልጆች መካከል ዘካርያስ እና ማታንያህ፤ +14 ከሄማን+ ልጆች መካከል የሂኤል እና ሺምአይ እንዲሁም ከየዱቱን+ ልጆች መካከል ሸማያህ እና ዑዚኤል። +15 እነሱም ወንድሞቻቸውን ከሰበሰቡና ራሳቸውን ከቀደሱ በኋላ ንጉሡ በይሖዋ ቃል ባዘዛቸው መሠረት የይሖዋን ቤት ለማንጻት መጡ።+ +16 ከዚያም ካህናቱ የይሖዋን ቤት ለማንጻት ወደ ውስጥ ገቡ፤ በይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ ያገኙትን ርኩስ የሆነ ነገር ሁሉ አውጥተው ወደ ይሖዋ ቤት ግቢ+ ወሰዱት። ሌዋውያኑ ደግሞ ከዚያ አውጥተው በቄድሮን ሸለቆ+ ውስጥ ጣሉት። +17 እነሱም በዚህ መንገድ በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የማንጻት ሥራውን ጀመሩ፤ በወሩም በስምንተኛ ቀን ወደ ይሖዋ ቤት በረንዳ+ ደረሱ። የይሖዋንም ቤት ለስምንት ቀን ቀደሱ፤ በመጀመሪያውም ወር በ16ኛው ቀን ሥራውን አጠናቀቁ። +18 ከዚያም ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የይሖዋን ቤት በሙሉ፣ የሚቃጠለው መባ የሚቀርብበትን መሠዊያና+ ዕቃዎቹን በሙሉ+ እንዲሁም የሚነባበረው ዳቦ*+ የሚቀመጥበትን ጠረጴዛና ዕቃዎቹን በሙሉ አንጽተናል። +19 ንጉሥ አካዝ በንግሥና ዘመኑ ታማኝነቱን ባጎደለ ጊዜ+ ከቦታቸው ያስወገዳቸውን ዕቃዎች ሁሉ አዘጋጅተን ቀድሰናቸዋል፤+ ዕቃዎቹም በይሖዋ መሠዊያ ፊት ይገኛሉ።” +20 ንጉሥ ሕዝቅያስም በማለዳ ተነስቶ የከተማዋን መኳንንት ሰበሰበ፤ ከዚያም ወደ ይሖዋ ቤት ወጡ። +21 እነሱም ለመንግሥቱ፣ ለመቅደሱና ለይሁዳ የኃጢአት መባ ሆነው የሚቀርቡ ሰባት በሬዎች፣ ሰባት አውራ በጎች፣ ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና ሰባት ተባዕት ፍየሎች አመጡ።+ እሱም በይሖዋ መሠዊያ ላይ እንዲያቀርቧቸው የአሮን ዘሮች ለሆኑት ካህናት ነገራቸው። +22 ከዚያም ከብቶቹን አረዱ፤+ ካህናቱም ደሙን ወስደው በመሠዊያው ላይ ረጩት፤+ ቀጥሎም አውራ በጎቹን አርደው ደሙን መሠዊያው ላይ ረጩ፤ ተባዕት የበግ ጠቦቶቹንም አርደው ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩ። +23 ከዚያ በኋላ ለኃጢአት መባ የሚሆኑትን ተባዕት ፍየሎች በንጉሡና በጉባኤው ፊት አቀረቧቸው፤ እጆቻቸውንም ጫኑባቸው። +24 ካህናቱም ፍየሎቹን አርደው ለእስራኤል ሁሉ ማስተሰረያ እንዲሆን ደማቸውን በመሠዊያው ላይ የኃጢአት መባ አድርገው አቀረቡ፤ ምክንያቱም ንጉሡ የሚቃጠለው መባና ለኃጢአት የሚሆነው መባ ለመላው እስራኤል እንዲቀርብ አዝዞ ነበር። +25 እሱም በዳዊት፣+ የንጉሡ ባለ ራእይ በሆነው በጋድና+ በነቢዩ ናታን+ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሌዋውያኑን ሲምባል፣ ባለ አውታር መሣሪያዎችና በገና+ አስይዞ በይሖዋ ቤት እንዲቆሙ አደረገ፤ ይህም ይሖዋ በነቢያቱ አማካኝነት የሰጠው ትእዛዝ ነበር። +26 በመሆኑም ሌዋውያኑ የዳዊትን የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ ካህናቱ ደግሞ መለከቶችን+ ይዘው ቆሙ። +27 ከዚያም ሕዝቅያስ የሚቃጠለው መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እን��ቀርብ አዘዘ።+ የሚቃጠለው መባ መቅረብ በጀመረበት ጊዜ የይሖዋ መዝሙር ተሰማ፤ ደግሞም የእስራኤልን ንጉሥ የዳዊትን የሙዚቃ መሣሪያዎች ተከትለው መለከቶቹ ተነፉ። +28 መዝሙሩ በሚዘመርበትና መለከቶቹ በሚነፉበት ጊዜም መላው ጉባኤ ተደፍቶ ሰገደ፤ የሚቃጠለው መባ እስኪጠናቀቅ ድረስ ይህ ሁሉ መከናወኑን ቀጠለ። +29 መባውን አቅርበው እንደጨረሱም ንጉሡና አብረውት ያሉት ሁሉ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ። +30 ንጉሥ ሕዝቅያስና መኳንንቱ በዳዊትና+ በባለ ራእዩ በአሳፍ+ መዝሙራት ይሖዋን እንዲያወድሱ ሌዋውያኑን አዘዙ። እነሱም በታላቅ ደስታ ውዳሴ አቀረቡ፤ ተደፍተውም ሰገዱ። +31 ከዚያም ሕዝቅያስ እንዲህ አለ፦ “አሁን እናንተ ለይሖዋ ስለተለያችሁ* ቅረቡ፤ ለይሖዋም ቤት መሥዋዕቶችና የምስጋና መባዎች አምጡ።” በመሆኑም ጉባኤው መሥዋዕቶችንና የምስጋና መባዎችን ማምጣት ጀመረ፤ ልቡ ያነሳሳውም ሁሉ የሚቃጠል መባ አመጣ።+ +32 ጉባኤው ያመጣቸው የሚቃጠሉ መባዎች ብዛት 70 ከብቶች፣ 100 አውራ በጎችና 200 ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ+ ሆነው የሚቀርቡ ነበሩ፤ +"33 ሌሎቹ ቅዱስ መባዎች ደግሞ 600 ከብቶችና 3,000 በጎች ነበሩ።" +34 ይሁንና የሚቃጠል መባ ሆነው የሚቀርቡትን እንስሳት ሁሉ ለመግፈፍ በቂ ካህናት ስላልነበሩ ሥራው እስኪጠናቀቅና ካህናቱ ራሳቸውን እስኪቀድሱ+ ድረስ ወንድሞቻቸው የሆኑት ሌዋውያን ረዷቸው፤+ ሌዋውያኑ ራሳቸውን በመቀደስ ረገድ ከካህናቱ ይበልጥ ጠንቃቆች* ነበሩና። +35 በተጨማሪም የሚቃጠሉት መባዎችና+ የኅብረት መሥዋዕቶቹ+ ስብ እንዲሁም ከሚቃጠሉት መባዎች ጋር የሚቀርቡት የመጠጥ መባዎች+ ብዙ ነበሩ። በዚህ መንገድ የይሖዋ ቤት አገልግሎት እንደገና ተደራጀ።* +36 ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ እውነተኛው አምላክ ለሕዝቡ ይህን በማቋቋሙና ይህ ሁሉ ነገር በአጭር ጊዜ ውስጥ በመከናወኑ እጅግ ተደሰቱ።+ +28 አካዝ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 20 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አላደረገም።+ +2 ከዚህ ይልቅ የእስራኤልን ነገሥታት መንገድ ተከተለ፤+ አልፎ ተርፎም ከብረት የተሠሩ የባአል ሐውልቶችን* ሠራ።+ +3 በተጨማሪም በሂኖም ልጅ ሸለቆ* የሚጨስ መሥዋዕት ያቀረበ ከመሆኑም ሌላ ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሙ የነበረውን አስጸያፊ ድርጊት በመከተል+ ወንዶች ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።+ +4 ደግሞም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች፣ በኮረብቶቹና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ ሥር+ ይሠዋ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።+ +5 ስለዚህ አምላኩ ይሖዋ በሶርያ ንጉሥ+ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እነሱም ድል አደረጉት፤ ከሕዝቡም መካከል ብዙዎቹን ማርከው ወደ ደማስቆ+ ወሰዱ። ደግሞም አምላክ በእስራኤል ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም ከባድ እልቂት አደረሰበት። +"6 የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ+ በይሁዳ 120,000 ሰዎችን በአንድ ቀን የገደለ ሲሆን ሁሉም ደፋር ተዋጊዎች ነበሩ፤ ይህም የሆነው የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን በመተዋቸው ነው።+" +7 ዚክሪ የተባለው ኤፍሬማዊ ተዋጊም የንጉሡን ልጅ ማአሴያህን፣ የቤተ መንግሥቱን* አዛዥ አዝሪቃምንና የንጉሡ ምክትል የሆነውን ሕልቃናን ገደለ። +"8 በተጨማሪም እስራኤላውያን ከአይሁዳውያን ወገኖቻቸው መካከል 200,000 ሴቶችን፣ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችን ማረኩ፤ እጅግ ብዙ ምርኮም ወሰዱ፤ የበዘበዙትንም ወደ ሰማርያ+ ይዘው ሄዱ። " +9 ይሁንና በዚያ ኦዴድ የተባለ የይሖዋ ነቢይ ነበር። እሱም ወደ ሰማርያ እየመጣ የነበረውን ሠራዊት ለመገናኘት ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፣ የአባቶቻችሁ ��ምላክ ይሖዋ የይሁዳ ሰዎችን በእጃችሁ አሳልፎ የሰጣችሁ በእነሱ ላይ ስለተቆጣ ነው፤+ እናንተም እስከ ሰማይ በሚደርስ ታላቅ ቁጣ ፈጃችኋቸው። +10 አሁንም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለራሳችሁ ወንድ አገልጋዮችና ሴት አገልጋዮች ልታደርጓቸው ታስባላችሁ።+ እናንተስ ብትሆኑ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ተጠያቂ አይደላችሁም? +11 እንግዲህ ስሙኝ፤ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ስለነደደ ከወንድሞቻችሁ መካከል የማረካችኋቸውን ሰዎች መልሱ።” +12 በዚህ ጊዜ ከኤፍሬማውያን አለቆች መካከል አንዳንድ ሰዎች ይኸውም የየሆሃናን ልጅ አዛርያስ፣ የመሺሌሞት ልጅ ቤራክያህ፣ የሻሉም ልጅ የሂዝቂያ እና የሃድላይ ልጅ አሜሳይ ከጦርነቱ የተመለሱትን ሰዎች በመቃወም +13 እንዲህ አሏቸው፦ “ምርኮኞቹን ወደዚህ አታምጧቸው፤ በይሖዋ ፊት በደለኞች ታደርጉናላችሁ። በደላችን ብዙ ሆኖ ሳለ፣ በኃጢአታችንና በበደላችን ላይ ልትጨምሩብን ታስባላችሁ? በእስራኤል ላይ ቁጣ ነዷልና።” +14 ስለዚህ የታጠቁት ወታደሮች ምርኮኞቹንና የበዘበዙትን ነገር+ ለመኳንንቱና ለመላው ጉባኤ አስረከቡ። +15 ከዚያም በስም ተጠቅሰው ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ተነስተው ምርኮኞቹን ተረከቡ፤ ራቁታቸውን ለነበሩት ሁሉ ከምርኮው ልብስ ሰጧቸው። ልብስ አለበሷቸው፤ እንዲሁም ጫማ ሰጧቸው፤ የሚበሉትና የሚጠጡት ነገር አቀረቡላቸው፤ ለገላቸውም ዘይት ሰጧቸው። ከዚህም ሌላ የደከሙትን በአህያ ላይ አስቀምጠው ወንድሞቻቸው +16 በዚህ ጊዜ ንጉሥ አካዝ፣ የአሦር ነገሥታት እንዲረዱት ጠየቀ።+ +17 ኤዶማውያንም በድጋሚ መጥተው ይሁዳን በመውረር ጥቃት ሰነዘሩ፤ ምርኮኞችንም ወሰዱ። +18 ፍልስጤማውያን+ ደግሞ በይሁዳ የሚገኙትን የሸፌላንና+ የኔጌብን ከተሞች ወረሩ፤ ቤትሼሜሽን፣+ አይሎንን፣+ ገዴሮትን፣ ሶኮንና በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ ቲምናንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ጊምዞንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች ያዙ፤ በዚያም ተቀመጡ። +19 ይሖዋ በእስራኤል ንጉሥ በአካዝ የተነሳ ይሁዳን አዋረደ፤ ምክንያቱም አካዝ የይሁዳን ሰዎች መረን ለቆ ነበር፤ ይህም ንጉሡ ለይሖዋ የነበረውን ታማኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያጓድል አደረገው። +20 በመጨረሻም የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ እሱን ከመርዳት ይልቅ በእሱ ላይ ዘምቶ አስጨነቀው።+ +21 አካዝ የይሖዋን ቤት እንዲሁም የንጉሡን ቤትና*+ የመኳንንቱን ቤቶች አራቁቶ ለአሦር ንጉሥ ስጦታ አበረከተ፤ ይህ ግን ምንም የፈየደለት ነገር የለም። +22 ንጉሥ አካዝ በተጨነቀ ጊዜ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት መፈጸሙን ይበልጥ ገፋበት። +23 እሱም “የሶርያ ነገሥታት አማልክት እነሱን ስለሚረዷቸው፣ እኔንም እንዲረዱኝ መሥዋዕት አቀርብላቸዋለሁ”+ በማለት ላሸነፉት+ የደማስቆ አማልክት+ መሥዋዕት ያቀርብ ጀመር። ይሁንና እነሱ፣ ለእሱም ሆነ ለመላው እስራኤል እንቅፋት ሆኑ። +24 በተጨማሪም አካዝ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ዕቃዎች ሰበሰበ፤ ከዚያም የእውነተኛውን አምላክ ቤት ዕቃዎች ሰባበረ፤+ የይሖዋን ቤት በሮች ዘጋ፤+ በኢየሩሳሌምም በየመንገዱ ማዕዘን ላይ መሠዊያዎችን ለራሱ ሠራ። +25 በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት የሚጨስ መሥዋዕት የሚቀርቡባቸው ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን ሠራ፤+ በዚህም የአባቶቹን አምላክ ይሖዋን አስቆጣ። +26 የቀረው ታሪክ፣ ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያከናወነው ነገር ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል።+ +27 በመጨረሻም አካዝ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ እነሱም በኢየሩሳሌም ከተማ ቀበሩት፤ ሆኖም የቀበሩት በእስራኤል ነገሥታት የመቃብር ስፍራ አልነበረም።+ በእሱም ምትክ ልጁ ሕ��ቅያስ ነገሠ። +8 ሰለሞን የይሖዋን ቤትና የራሱን ቤት* ገንብቶ በጨረሰበት በ20ኛው ዓመት ማብቂያ ላይ+ +2 ኪራም+ የሰጠውን ከተሞች መልሶ ገነባቸው፤ እስራኤላውያንንም በዚያ አሰፈረ። +3 በተጨማሪም ሰለሞን በሃማትጾባ ላይ ዘምቶ ያዛት። +4 ከዚያም በምድረ በዳ የምትገኘውን ታድሞርንና በሃማት+ የሠራቸውን የማከማቻ ከተሞች ሁሉ ገነባ።*+ +5 ደግሞም ቅጥሮች፣ በሮችና መቀርቀሪያዎች ያሏቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ይኸውም ላይኛውን ቤትሆሮንንና+ ታችኛውን ቤትሆሮንን+ ገነባ፤ +6 በተጨማሪም ባዓላትን፣+ የሰለሞንን የእህልና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች በሙሉ፣ የሠረገላ ከተሞቹን በሙሉ፣+ የፈረሰኞቹን ከተሞች እንዲሁም ሰለሞን በኢየሩሳሌም፣ በሊባኖስና በእሱ ግዛት ውስጥ ባለው ምድር ሁሉ መገንባት የፈለጋቸውን ነገሮች በሙሉ ሠራ። +7 ከእስራኤል ወገን ያልሆኑትን+ ከሂታውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፈሪዛውያን፣ ከሂዋውያንና ከኢያቡሳውያን+ የተረፉትን ሕዝቦች በሙሉ፣ +8 ይኸውም እስራኤላውያን ፈጽመው ያላጠፏቸውን+ በምድሪቱ ላይ የቀሩትን ዘሮቻቸውን ሰለሞን የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ መለመላቸው፤+ እስከ ዛሬም ድረስ ይሠራሉ። +9 ሆኖም ሰለሞን ለሚያከናውነው ሥራ ከእስራኤላውያን መካከል አንዳቸውንም ባሪያ አላደረገም፤+ ምክንያቱም እነሱ ተዋጊዎቹ፣ የጦር መኮንኖቹ፣ የሠረገለኞቹና የፈረሰኞቹ አለቆች ነበሩ።+ +10 በሠራተኞቹ ላይ የተሾሙት ይኸውም የንጉሥ ሰለሞን የበታች ተቆጣጣሪዎቹ አለቆች+ 250 ነበሩ። +11 በተጨማሪም ሰለሞን የፈርዖንን ሴት ልጅ+ ከዳዊት ከተማ አውጥቶ ወደሠራላት ቤት አመጣት፤+ ይህን ያደረገው “እሷ ሚስቴ ብትሆንም የይሖዋ ታቦት የገባባቸው ቦታዎች ቅዱስ ስለሆኑ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት ልትኖር አይገባም” በማለት ነበር።+ +12 ከዚያም ሰለሞን ከበረንዳው+ ፊት ለፊት በሠራው የይሖዋ መሠዊያ+ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለይሖዋ አቀረበ።+ +13 ለሙሴ ከተሰጠው ትእዛዝ ጋር በሚስማማ ሁኔታ በሥርዓቱ መሠረት በየዕለቱ ሊቀርቡ የሚገባቸውን መባዎች ማለትም የየሰንበቱን፣+ የየወሩን መባቻና+ በዓመት ሦስት ጊዜ የሚደረጉትን የተወሰኑትን በዓላት+ ይኸውም የቂጣን* በዓል፣+ የሳምንታትን በዓልና+ የዳስን* በዓል+ መባዎች አቀረበ። +14 በተጨማሪም አባቱ ዳዊት ባወጣው ደንብ መሠረት ካህናቱን በየአገልግሎት ምድባቸው፣+ ሌዋውያኑንም በየዕለቱ ሊከናወን በሚገባው ሥርዓት መሠረት ካህናቱ ባሉበት አምላክን እንዲያወድሱና+ እንዲያገለግሉ በተመደቡበት ስፍራ ላይ ሾማቸው፤ በር ጠባቂዎቹንም በተለያዩ በሮች ላይ በየቡድናቸው መደባቸው፤+ የእውነተኛ +15 እነሱም ንጉሡ ማንኛውንም ጉዳይ ወይም ግምጃ ቤቶቹን በተመለከተ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ከሰጠው ትእዛዝ ፈቀቅ አላሉም። +16 በመሆኑም የይሖዋ ቤት መሠረቱ ከተጣለበት ጊዜ+ አንስቶ ሥራው እስካበቃበት ጊዜ ድረስ ሰለሞን የሠራው ሥራ ሁሉ በሚገባ የተደራጀ* ነበር። የይሖዋም ቤት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ።+ +17 ከዚያም ሰለሞን በኤዶም ምድር+ በባሕሩ ዳርቻ ወደሚገኙት ወደ ዔጽዮንጋብርና+ ወደ ኤሎት+ ሄደ። +18 ኪራም+ በአገልጋዮቹ አማካኝነት መርከቦችንና ልምድ ያላቸው ባሕረኞችን ላከለት። እነሱም ከሰለሞን አገልጋዮች ጋር ወደ ኦፊር+ በመሄድ 450 ታላንት* ወርቅ+ አምጥተው ለንጉሥ ሰለሞን ሰጡት።+ +"11 ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከእስራኤል ጋር ተዋግተው መንግሥቱን ለሮብዓም እንዲያስመልሱ ከይሁዳ ቤትና ከቢንያም ነገድ+ የተውጣጡ 180,000 የሠለጠኑ ተዋጊዎች* ወዲያውኑ ሰበሰበ።+" +2 ከዚያም የይሖዋ ቃል የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደሆነው ወደ ሸማያህ+ እንዲህ ሲል መጣ፦ +3 “ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም ��ንዲሁም በይሁዳና በቢንያም ላሉት እስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ +4 ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከወንድሞቻችሁ ጋር ለመዋጋት አትውጡ። ይህ እንዲሆን ያደረግኩት እኔ ስለሆንኩ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ።”’”+ ስለዚህ የይሖዋን ቃል ሰምተው ተመለሱ፤ በኢዮርብዓምም ላይ አልዘመቱም። +5 ሮብዓም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ገነባ። +6 ቤተልሔምን፣+ ኤጣምን፣ ተቆአን፣+ +7 ቤትጹርን፣ ሶኮን፣+ አዱላምን፣+ +8 ጌትን፣+ ማሬሻህን፣ ዚፍን፣+ +9 አዶራይምን፣ ለኪሶን፣+ አዜቃን፣+ +10 ጾራን፣ አይሎንንና+ ኬብሮንን+ ገነባ፤* እነዚህ በይሁዳና በቢንያም የነበሩ የተመሸጉ ከተሞች ናቸው። +11 በተጨማሪም የተመሸጉትን ከተሞች አጠናከረ፤ በከተሞቹም ላይ አዛዦችን ሾመ፤ በእነዚህ ከተሞች ምግብ፣ ዘይትና የወይን ጠጅ አከማቸ፤ +12 በከተሞቹም ሁሉ ትላልቅ ጋሻዎችና ጦር አስቀመጠ፤ ከተሞቹንም እጅግ አጠናከራቸው። ይሁዳንና ቢንያምንም መግዛቱን ቀጠለ። +13 በመላው እስራኤል ያሉት ካህናትና ሌዋውያንም የነበሩበትን ክልል በሙሉ ለቀው በመሄድ ከእሱ ጎን ቆሙ። +14 ሌዋውያኑ የይሖዋ ካህናት ሆነው እንዳያገለግሉ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አባረዋቸው ስለነበር+ የግጦሽ መሬታቸውንና ርስታቸውን+ ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ነበር። +15 በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች፣ ፍየል ለሚመስሉት አጋንንትና*+ ለሠራቸው የጥጃ ምስሎች+ የራሱን ካህናት ሾመ።+ +16 የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ለመፈለግ ከልባቸው ቆርጠው የተነሱ ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ሰዎች ለአባቶቻቸው አምላክ ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።+ +17 ለሦስት ዓመት በዳዊትና በሰለሞን መንገድ ይመላለሱ ስለነበር በእነዚህ ሦስት ዓመታት የይሁዳን መንግሥት አጠናከሩ፤ ደግሞም ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም ድጋፍ ሰጡ። +18 ከዚያም ሮብዓም የዳዊት ልጅ የሆነውን የየሪሞትን ሴት ልጅ ማሃላትን አገባ። ማሃላት የእሴይ ልጅ፣ የኤልያብ+ ሴት ልጅ የሆነችው የአቢሃይል ልጅ ነበረች። +19 ከጊዜ በኋላም የኡሽ፣ ሸማርያህ እና ዛሃም የተባሉ ወንዶች ልጆች ወለደችለት። +20 ከእሷ በኋላ የአቢሴሎም+ የልጅ ልጅ የሆነችውን ማአካን አገባ። እሷም አቢያህን፣+ አታይን፣ ዚዛን እና ሸሎሚትን ወለደችለት። +21 ሮብዓም የአቢሴሎም የልጅ ልጅ የሆነችውን ማአካን ከሌሎቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ሁሉ+ አስበልጦ ይወዳት ነበር፤ እሱም 18 ሚስቶችና 60 ቁባቶች ነበሩት፤ ደግሞም 28 ወንዶች ልጆችና 60 ሴቶች ልጆች ወለደ። +22 ሮብዓምም የማአካን ልጅ አቢያህን ሊያነግሠው ስለፈለገ በወንድሞቹ ላይ ራስና መሪ አድርጎ ሾመው። +23 ይሁን እንጂ ማስተዋል የታከለበት እርምጃ በመውሰድ ከወንዶች ልጆቹ መካከል አንዳንዶቹን በይሁዳና በቢንያም ምድር ሁሉ ወደሚገኙት ወደተመሸጉት ከተሞች+ ሁሉ ላካቸው፤* የሚያስፈልጓቸውንም ነገሮች በብዛት ሰጣቸው፤ ብዙ ሚስቶችም አጋባቸው። +2 ሰለሞን ለይሖዋ ስም ቤት፣+ ለመንግሥቱም ቤት*+ እንዲሠራ አዘዘ። +"2 ሰለሞን 70,000 ተራ የጉልበት ሠራተኞችና* በተራሮቹ ላይ ድንጋይ የሚጠርቡ 80,000 ሰዎች መረጠ፤+ በእነሱም ላይ 3,600 ሰዎችን የበላይ ተመልካቾች አድርጎ ሾመ።+" +3 ደግሞም ሰለሞን እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም+ ላከ፦ “አባቴ ዳዊት የሚኖርበትን ቤት* ሲሠራ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት እንደላክለት ሁሉ ለእኔም እንዲሁ አድርግልኝ።+ +4 እነሆ፣ በፊቱ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ለማጠን፣ የሚነባበረውን ዳቦ*+ ዘወትር በዚያ ለማስቀመጥ እንዲሁም በየጠዋቱና በየማታው፣+ በየሰንበቱ፣+ በየ��ር መባቻውና+ በአምላካችን በይሖዋ የበዓላት ወቅቶች+ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ ለአምላኬ ለይሖዋ ስም ቤት ልሠራና ለእሱ ልቀድሰው አስቤአለሁ። ይህም እስራኤ +5 አምላካችን ከሌሎች አማልክት ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ስለሆነ የምሠራውም ቤት ታላቅ ይሆናል። +6 ለእሱ ቤት መሥራት የሚችል ማነው? ሰማያትና የሰማያት ሰማይ ሊይዙት አይችሉምና፤+ በፊቱ የሚጨስ መሥዋዕት የሚቀርብበት ስፍራ ካልሆነ በስተቀር ለእሱ ቤት እሠራለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ? +7 አሁንም በወርቅ፣ በብር፣ በመዳብ፣+ በብረት፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ በደማቅ ቀይ ክርና በሰማያዊ ክር ሥራ የተካነ እንዲሁም ቅርጻ ቅርጽ የመሥራት ችሎታ ያለው የእጅ ጥበብ ባለሙያ ላክልኝ። እሱም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው የተካኑ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቼ ጋር በይሁዳና በኢየሩሳሌም አብሮ ይሠራል።+ +8 የአርዘ ሊባኖስ፣ የጥድና+ የሰንደል ዛፍ+ ሳንቃ ከሊባኖስ ላክልኝ፤ አገልጋዮችህ የሊባኖስን+ ዛፎች በመቁረጥ ረገድ የተካኑ መሆናቸውን በሚገባ አውቃለሁ። አገልጋዮቼ ከአገልጋዮችህ ጋር አብረው በመሥራት+ +9 በርካታ ሳንቃዎችን ያዘጋጁልኛል፤ የምሠራው ቤት እጅግ ታላቅ ነውና። +"10 እነሆ፣ ዛፍ ቆራጭና እንጨት ፈላጭ ለሆኑት አገልጋዮችህ ቀለብ እንዲሆናቸው 20,000 የቆሮስ መስፈሪያ* ስንዴ፣ 20,000 የቆሮስ መስፈሪያ* ገብስ፣ 20,000 የባዶስ መስፈሪያ* የወይን ጠጅና 20,000 የባዶስ መስፈሪያ ዘይት እሰጣቸዋለሁ።”+ " +11 በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም የሚከተለውን መልእክት በጽሑፍ ለሰለሞን ላከለት፦ “ይሖዋ ሕዝቡን ስለሚወድ አንተን በእነሱ ላይ ንጉሥ አድርጎ ሾመህ።” +12 ከዚያም ኪራም እንዲህ አለ፦ “ሰማያትንና ምድርን የሠራው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ውዳሴ ይድረሰው፤ ምክንያቱም ለይሖዋ ቤት፣ ለመንግሥቱም ቤት የሚሠራ ልባምና አስተዋይ+ የሆነ ጥበበኛ ልጅ ለንጉሥ ዳዊት ሰጥቷል።+ +13 አሁንም አስተዋይ የሆነውን ኪራምአቢ+ የተባለውን የእጅ ጥበብ ባለሙያ ልኬልሃለሁ፤ +14 እናቱ ከዳን ወገን ስትሆን አባቱ ግን የጢሮስ ሰው ነው፤ እሱም በወርቅ፣ በብር፣ በመዳብ፣ በብረት፣ በድንጋይ፣ በሳንቃ፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ በሰማያዊ ክር፣ ጥራት ባለው ጨርቅና በደማቅ ቀይ ክር ሥራ ልምድ ያካበተ ነው።+ ማንኛውንም ቅርጻ ቅርጽ መቅረጽ እንዲሁም የተሰጠውን ማንኛውንም ንድፍ መሥራት ይችላል +15 አሁንም ጌታዬ ቃል በገባው መሠረት ስንዴውን፣ ገብሱን፣ ዘይቱንና የወይን ጠጁን ለአገልጋዮቹ ይላክ።+ +16 እኛም የምትፈልገውን ያህል ከሊባኖስ+ ዛፎች ቆርጠን አንድ ላይ በማሰር በባሕር ላይ እያንሳፈፍን ወደ ኢዮጴ+ እናመጣልሃለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ልትወስደው ትችላለህ።”+ +"17 በዚህ ጊዜ ሰለሞን አባቱ ዳዊት ካደረገው ቆጠራ+ በኋላ በእስራኤል ምድር የሚኖሩትን የባዕድ አገር ወንዶች ሁሉ ቆጠረ፤+ ቁጥራቸውም 153,600 ሆነ።" +"18 ከእነሱም መካከል 70,000ዎቹን ተራ የጉልበት ሠራተኞች፣* 80,000ዎቹን በተራሮቹ ላይ ድንጋይ ጠራቢዎች፣+ 3,600ዎቹን ደግሞ ሰዎቹን የሚያሠሩ የበላይ ተመልካቾች አድርጎ ሾማቸው።+" +26 ከዚያም የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ የ16 ዓመት ልጅ የነበረውን ዖዝያን*+ ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ምትክ አነገሡት።+ +2 እሱም፣ ንጉሡ* ከአባቶቹ ጋር ካንቀላፋ በኋላ ኤሎትን+ መልሶ በመገንባት ወደ ይሁዳ መለሳት።+ +3 ዖዝያ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 16 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ52 ዓመት ገዛ። እናቱ ይኮልያ የተባለች የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች።+ +4 እሱም አባቱ አሜስያስ እንዳደረገው ሁሉ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ +5 እውነተኛውን አምላክ መፍራት ባስተማረው በዘካርያስ ዘመን አምላክን ይፈልግ ነበር። ይሖዋን ይፈልግ በነበረበት ዘመን እውነተኛው አምላክ አበለጸገው።+ +6 እሱም ወጥቶ ከፍልስጤማውያን+ ጋር በመዋጋት የጌትን+ ቅጥር፣ የያብነህን+ ቅጥርና የአሽዶድን ቅጥር አፈረሰ። ከዚያም በአሽዶድና+ በፍልስጤማውያን ክልል ከተሞችን ገነባ። +7 እውነተኛው አምላክ በፍልስጤማውያን ላይ፣ በጉርባዓል በሚኖሩት ዓረቦች+ ላይ እንዲሁም በመኡኒም ላይ ድል እንዲቀዳጅ ረዳው። +8 አሞናውያን+ ለዖዝያ ግብር ይገብሩለት ጀመር። እጅግ እየበረታ ስለሄደም ዝናው እስከ ግብፅ ድረስ ናኘ። +9 በተጨማሪም ዖዝያ በኢየሩሳሌም በማዕዘን በር፣+ በሸለቆ በርና+ የቅጥሩ ማጠናከሪያ በሚገኝበት ስፍራ ጠንካራ ማማዎችን+ ሠራ። +10 ከዚህም ሌላ በምድረ በዳው ማማዎችን ገነባ፤+ ብዙ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶችንም ቆፈረ* (ብዙ ከብቶች ነበሩትና)፤ በሸፌላና በሜዳውም* ላይ እንዲሁ አደረገ። ግብርና ይወድ ስለነበር በተራሮቹ ላይና በቀርሜሎስ፣ ገበሬዎችና የወይን አትክልት ሠራተኞች ነበሩት። +11 በተጨማሪም ዖዝያ ለውጊያ ዝግጁ የሆነ ሠራዊት ነበረው። በቡድን በቡድን ተደራጅተው ለጦርነት ይወጡ ነበር። እነዚህ ሰዎች ከንጉሡ መኳንንት አንዱ በሆነው በሃናንያህ አመራር ሥር ሆነው በሚያገለግሉት በጸሐፊው የኢዔል+ እና በአለቃው ማአሴያህ አማካኝነት ተቆጥረው ተመዘገቡ።+ +"12 በእነዚህ ኃያላን ተዋጊዎች ላይ የተሾሙት የአባቶች ቤት መሪዎች አጠቃላይ ቁጥር 2,600 ነበር።" +"13 በእነሱ አመራር ሥር 307,500 ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት ነበር፤ ይህም ንጉሡ በጠላት ላይ በሚያደርገው ዘመቻ ድጋፍ የሚሰጡ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ሰዎችን የያዘ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ነው።+" +14 ዖዝያ መላው ሠራዊት ጋሻ፣ ጦር፣+ የራስ ቁር፣ ጥሩር፣+ ቀስትና የወንጭፍ ድንጋይ+ እንዲታጠቅ አደረገ። +15 በተጨማሪም ባለሙያዎች ባወጡት ንድፍ የተሠሩ የጦር መሣሪያዎችን በኢየሩሳሌም አዘጋጀ፤ መሣሪያዎቹ በየማማውና+ በቅጥሩ ማዕዘናት ላይ የተተከሉ ሲሆን ቀስትና ትላልቅ ድንጋዮች ለማስወንጨፍ ያገለግሉ ነበር። ዖዝያ ከፍተኛ እርዳታ በማግኘቱና እየበረታ በመሄዱ ዝናው በሩቅ ቦታ ሁሉ ተሰማ። +16 ይሁን እንጂ ዖዝያ በበረታ ጊዜ ለጥፋት እስኪዳረግ ድረስ ልቡ ታበየ፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ይሖዋ ቤተ መቅደስ በመግባት በአምላኩ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጸመ።+ +17 ወዲያውኑም ካህኑ አዛርያስና ደፋር የሆኑ ሌሎች 80 የይሖዋ ካህናት ተከትለውት ገቡ። +18 ከዚያም ንጉሥ ዖዝያን ፊት ለፊት በመጋፈጥ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ፣ አንተ ለይሖዋ ዕጣን ማጠንህ ተገቢ አይደለም!+ ዕጣን ማጠን ያለባቸው ካህናቱ ብቻ ናቸው፤ እነሱ የተቀደሱ የአሮን ዘሮች ናቸውና።+ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ስለፈጸምክ ከመቅደሱ ውጣ፤ እንዲህ ማድረግህ በይሖዋ አምላክ ዘንድ ምን +19 ዕጣን ለማጠን በእጁ ጥና ይዞ የነበረው ዖዝያ ግን እጅግ ተቆጣ፤+ ካህናቱን እየተቆጣ ሳለም በይሖዋ ቤት በዕጣን መሠዊያው አጠገብ ካህናቱ ባሉበት ግንባሩ ላይ የሥጋ ደዌ+ ወጣበት። +20 የካህናቱ አለቃ አዛርያስና ካህናቱ ሁሉ ባዩት ጊዜ ግንባሩ በሥጋ ደዌ ተመቶ ነበር! በመሆኑም ከዚያ አጣድፈው አስወጡት፤ እሱ ራሱም ይሖዋ ስለመታው ለመውጣት ቸኩሎ ነበር። +21 ንጉሥ ዖዝያ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ የሥጋ ደዌ በሽተኛ ሆኖ ኖረ፤ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በመሆኑ በአንድ የተለየ ቤት ውስጥ ተገልሎ ተቀመጠ፤+ ወደ ይሖዋ ቤት እንዳይገባ ታግዶ ነበር። ልጁ ኢዮዓታም በንጉሡ ቤት* ላይ ተሹሞ በምድሪቱ በሚኖረው ሕዝብ ላይ ይፈርድ ነበር።+ +22 ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለውን የቀረውን የዖዝያ ታሪክ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ+ ጽፎታል። +23 በመጨረሻም ዖዝያ ከአባቶቹ ጋር አንቀ��ፋ፤ ከአባቶቹም ጋር ቀበሩት፤ ሆኖም “የሥጋ ደዌ አለበት” ብለው ስላሰቡ የቀበሩት ከነገሥታቱ የመቃብር ቦታ ውጭ ባለ መሬት ላይ ነበር። በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮዓታም+ ነገሠ። +4 ከዚያም ርዝመቱ 20 ክንድ፣ ወርዱ 20 ክንድ፣ ከፍታውም 10 ክንድ የሆነ የመዳብ መሠዊያ ሠራ።+ +2 ባሕሩን*+ በቀለጠ ብረት ሠራ። ባሕሩ ክብ ቅርጽ የነበረው ሲሆን ከአንዱ ጠርዝ እስከ ሌላኛው ጠርዝ 10 ክንድ፣ ከፍታው ደግሞ 5 ክንድ ነበር፤ መጠነ ዙሪያውም በመለኪያ ገመድ ሲለካ 30 ክንድ ሆነ።+ +3 በባሕሩም ዙሪያ ከሥሩ በእያንዳንዱ ክንድ ላይ በቅል+ ቅርጽ የተሠሩ አሥር ጌጦች ነበሩ። ቅሎቹም ከባሕሩ ጋር አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር። +4 ባሕሩ 3ቱ ወደ ሰሜን፣ 3ቱ ወደ ምዕራብ፣ 3ቱ ወደ ደቡብ እንዲሁም 3ቱ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ፊታቸውን ባዞሩ 12 በሬዎች+ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ባሕሩም ላያቸው ላይ ነበር፤ የሁሉም ሽንጥ ወደ መሃል ገባ ያለ ነበር። +"5 የውኃ ማጠራቀሚያው ውፍረት አንድ ጋት* ነበር፤ ጠርዙ የጽዋ ከንፈር ይመስል የነበረ ሲሆን በአበባ ቅርጽ የተሠራ ነበር። የውኃ ማጠራቀሚያው 3,000 የባዶስ መስፈሪያ* መያዝ ይችላል። " +6 በተጨማሪም ለመታጠቢያ የሚሆኑ አሥር የውኃ ገንዳዎች ሠርቶ አምስቱን በስተ ቀኝ፣ አምስቱን ደግሞ በስተ ግራ አስቀመጣቸው።+ ገንዳዎቹን የሚቃጠለውን መባ+ ለማቅረብ የሚያገለግሉትን ነገሮች ለማጠብ ይጠቀሙባቸው ነበር። ባሕሩ ግን የካህናቱ መታጠቢያ ነበር።+ +7 ከዚያም በተሰጠው መመሪያ መሠረት+ አሥር የወርቅ መቅረዞችን+ ሠርቶ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተ ቀኝ፣ አምስቱን ደግሞ በስተ ግራ አስቀመጣቸው።+ +8 በተጨማሪም አሥር ጠረጴዛዎችን ሠርቶ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተ ቀኝ፣ አምስቱን በስተ ግራ አስቀመጣቸው፤+ ከዚያም 100 ጎድጓዳ የወርቅ ሳህኖችን ሠራ። +9 ከዚያም የካህናቱን+ ግቢ+ እንዲሁም ትልቁን ግቢና+ የግቢውን በሮች ሠራ፤ የግቢዎቹንም በሮች በመዳብ ለበጣቸው። +10 ባሕሩንም በስተ ቀኝ በኩል፣ በስተ ደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ አስቀመጠው።+ +11 በተጨማሪም ኪራም አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹንና ጎድጓዳ ሳህኖቹን ሠራ።+ ኪራምም በእውነተኛው አምላክ ቤት ለንጉሥ ሰለሞን ያከናውን የነበረውን ሥራ ጨረሰ፤+ +12 ሁለቱን ዓምዶች፣+ በሁለቱ ዓምዶች አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸው የዓምድ ራሶች፣ በዓምዶቹ አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸውን ሁለቱን ክብ የዓምድ ራሶች የሚያስጌጡትን ሁለት መረቦች፣+ +13 ለሁለቱ መረቦች የተሠሩትን 400 ሮማኖች+ ማለትም በዓምዶቹ አናት ላይ የነበሩትን የጎድጓዳ ሳህን ቅርጽ ያላቸውን ሁለት የዓምድ ራሶች ለማስጌጥ የተሠሩትን በእያንዳንዱ መረብ ላይ በሁለት ረድፍ የተደረደሩትን ሮማኖች፣+ +14 አሥሩን ጋሪዎችና* በጋሪዎቹ ላይ የነበሩትን አሥር የውኃ ገንዳዎች፣+ +15 ባሕሩንና ከሥሩ የነበሩትን 12 በሬዎች፣+ +16 አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ ሹካዎቹንና+ ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ዕቃዎች ሁሉ ኪራምአቢቭ+ ለይሖዋ ቤት መገልገያ እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰለሞን ከተወለወለ መዳብ ሠራ። +17 ንጉሡ እነዚህ ነገሮች በዮርዳኖስ አውራጃ፣ በሱኮትና+ በጸሬዳህ መካከል በሚገኝ ስፍራ በሸክላ ጭቃ ውስጥ ቀልጠው እንዲሠሩ አደረገ። +18 ሰለሞን የሠራቸው ዕቃዎች እጅግ ብዙ ነበሩ፤ የመዳቡም ክብደት ምን ያህል እንደሆነ አልታወቀም።+ +19 ሰለሞን ለእውነተኛው አምላክ ቤት መገልገያ የሚሆኑትን የሚከተሉትን ነገሮች+ ሠራ፦ የወርቅ መሠዊያውን፣+ ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥባቸውን+ ጠረጴዛዎች፣+ +20 በመመሪያው መሠረት በውስጠኛው ክፍል ፊት የሚበሩትን ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞችና መብራቶቻቸውን፣+ +21 ከወርቅ ይኸውም እጅግ ከጠራ ወርቅ የተሠሩትን የፈኩ አበቦች፣ መብራቶችና መቆንጠጫዎች፣ +22 ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩትን የእሳት ማጥፊያዎች፣ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ ጽዋዎችና መኮስተሪያዎች እንዲሁም ከወርቅ የተሠሩትን የቤቱን መግቢያ፣ የቅድስተ ቅዱሳኑን+ የውስጥ በሮችና የቤተ መቅደሱን ቤት በሮች።+ +16 አሳ በነገሠ በ36ኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ+ በይሁዳ ላይ ዘመተ፤ እሱም ማንም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ እንዳይገባና እንዳይወጣ*+ ለማድረግ ራማን+ መገንባት* ጀመረ። +2 በዚህ ጊዜ አሳ ከይሖዋ ቤትና ከንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች ብርና ወርቅ አውጥቶ+ በደማስቆ ወደሚገኘው የሶርያ ንጉሥ ወደ ቤንሃዳድ+ እንዲህ ሲል ላከ፦ +3 “በእኔና በአንተ እንዲሁም በአባቴና በአባትህ መካከል ውል* አለ። እኔ ብርና ወርቅ ልኬልሃለሁ። ስለዚህ ና፣ የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ከእኔ እንዲርቅ ከእሱ ጋር የገባኸውን ውል* አፍርስ።” +4 ቤንሃዳድ የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀብሎ የጦር ሠራዊቱን አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ፤ እነሱም ኢዮንን፣+ ዳንን፣+ አቤልማይምን እና በንፍታሌም+ ከተሞች ውስጥ ያሉትን የማከማቻ ስፍራዎች ሁሉ መቱ። +5 ባኦስም ይህን ሲሰማ ወዲያውኑ ራማን መገንባቱን* አቆመ፤ ሥራውንም አቋረጠ። +6 ከዚያም ንጉሡ አሳ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ይዞ ሄደ፤ እነሱም ባኦስ እየገነባባቸው የነበሩትን+ የራማን+ ድንጋዮችና ሳንቃዎች አጋዙ፤ እሱም በድንጋዮቹና በሳንቃዎቹ ጌባንና+ ምጽጳን+ ገነባ።* +7 በዚህ ጊዜ ባለ ራእዩ ሃናኒ+ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “በአምላክህ በይሖዋ ከመታመን* ይልቅ በሶርያ ንጉሥ ስለታመንክ* የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት ከእጅህ አምልጧል።+ +8 ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ብዙ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ያሏቸው ታላቅ ሠራዊት አልነበሩም? ይሁንና በይሖዋ በመታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው።+ +9 አዎ፣ በሙሉ ልባቸው ወደ እሱ ላዘነበሉት ሰዎች*+ ብርታቱን ያሳይ ዘንድ* የይሖዋ ዓይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይመላለሳሉ።+ በዚህ ረገድ የሞኝነት ድርጊት ፈጽመሃል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ጦርነት አይለይህም።”+ +10 ሆኖም አሳ በባለ ራእዩ ተቆጣ፤ በዚህ ጉዳይ በጣም ስለተናደደበትም እስር ቤት* አስገባው። በዚያ ወቅት አሳ በሌሎች ሰዎችም ላይ በደል መፈጸም ጀመረ። +11 ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለው የአሳ ታሪክ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል።+ +12 አሳ በ39ኛው የግዛት ዘመኑ እግሩን ታመመ፤ ሕመሙም ጠናበት፤ ታሞ ሳለም እንኳ የባለ መድኃኒቶችን እንጂ የይሖዋን እርዳታ አልፈለገም። +13 በመጨረሻም አሳ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤+ በ41ኛው የግዛት ዘመኑም ሞተ። +14 እነሱም በዳዊት ከተማ+ ለራሱ ባስቆፈረው ታላቅ የመቃብር ቦታ ቀበሩት፤ የበለሳን ዘይት እንዲሁም ከተለያዩ ቅመሞች የተዘጋጀ ልዩ ቅባት በሞላበት ቃሬዛ ላይ አኖሩት።+ በተጨማሪም ለክብሩ ታላቅ እሳት አነደዱለት።* +6 በዚህ ጊዜ ሰለሞን እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደሚኖር ተናግሯል።+ +2 አሁን እኔ እጅግ ከፍ ያለ ቤት፣ ለዘላለም የምትኖርበት ጸንቶ የተመሠረተ ቦታ ገንብቼልሃለሁ።”+ +3 ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ ቆሞ ሳለ ንጉሡ ዞሮ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ መባረክ ጀመረ።+ +4 እንዲህም አለ፦ “ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ እንዲህ ብሎ ቃል የገባውና ይህን በራሱ እጆች የፈጸመው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ፦ +5 ‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ዕለት አንስቶ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ስሜ የሚጠራበት ቤት እንዲሠራበት አንድም ከተማ አልመረጥኩም፤+ ደግሞም የሕዝቤ የእስራኤል መሪ እንዲሆን ማንንም አልመረጥኩም። +6 ሆኖም ስሜ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን፣+ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ገዢ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ።’+ +7 አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ለመሥራት ከልቡ ተመኝቶ ነበር።+ +8 ሆኖም ይሖዋ አባቴን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ ‘ለስሜ ቤት ለመሥራት ከልብህ ተመኝተህ ነበር፤ ይህን በልብህ መመኘትህም መልካም ነው። +9 ይሁንና ቤቱን የምትሠራው አንተ አይደለህም፤ ሆኖም ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ የሚወለድልህ የገዛ ልጅህ* ይሆናል።’+ +10 ይሖዋ የገባውን ቃል ፈጽሟል፤ ልክ ይሖዋ ቃል በገባው መሠረት+ አባቴን ዳዊትን ተክቼ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀምጫለሁና።+ በተጨማሪም ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ስም ቤት ሠርቻለሁ፤ +11 በዚያም ይሖዋ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦት+ አስቀምጫለሁ።” +12 ከዚያም ሰለሞን በይሖዋ መሠዊያ ፊት፣ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ለፊት ቆመ፤ እጆቹንም ዘረጋ።+ +13 (ሰለሞን የመዳብ መድረክ ሠርቶ በግቢው መካከል አስቀምጦ ነበር።+ የመድረኩ ርዝመት አምስት ክንድ፣* ወርዱ አምስት ክንድ፣ ከፍታውም ሦስት ክንድ ነበር፤ እሱም በመድረኩ ላይ ቆሞ ነበር።) በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ተንበርክኮም እጆቹን ወደ ሰማያት ዘረጋ፤+ +14 እንዲህም አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ በፊቱ በሙሉ ልባቸው ለሚመላለሱ አገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ እንደ አንተ ያለ አምላክ በሰማያትም ሆነ በምድር የለም።+ +15 ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቀሃል።+ በገዛ አፍህ ቃል ገባህ፤ ዛሬ ደግሞ በራስህ እጅ ፈጸምከው።+ +16 አሁንም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ ‘አንተ በፊቴ እንደተመላለስከው ሁሉ+ ልጆችህም በጥንቃቄ ሕጌን ጠብቀው ከተመላለሱ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከፊቴ አይታጣም’+ በማለት ለአገልጋይህ ለአባቴ ለዳዊት የገባኸውን ቃል ጠብቅ። +17 አሁንም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ለአገልጋይህ ለዳዊት የገባኸው ቃል ይፈጸም። +18 “በእርግጥ አምላክ ከሰው ልጆች ጋር በምድር ላይ ይኖራል?+ እነሆ ሰማያት፣ አዎ ሰማየ ሰማያት እንኳ ሊይዙህ አይችሉም፤+ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤትማ ምንኛ ያንስ!+ +19 እንግዲህ አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመና በትኩረት ስማ፤ አገልጋይህ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰማውን ጩኸትና በፊትህ የሚያቀርበውን ጸሎት አዳምጥ። +20 አገልጋይህ ወደዚህ ስፍራ የሚያቀርበውን ጸሎት ለመስማት ስምህ እንደሚጠራበት+ ወደተናገርከው ወደዚህ ቤት ዓይኖችህ ሌሊትና ቀን ይመልከቱ። +21 አገልጋይህ እርዳታ ለማግኘት የሚያቀርበውን ልመናና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ በሚጸልይበት ጊዜ+ የሚያቀርበውን ልመና አዳምጥ፤ በማደሪያህም በሰማያት ሆነህ ስማ፤+ ሰምተህም ይቅር በል።+ +22 “አንድ ሰው ባልንጀራውን በድሎ እንዲምል ቢደረግ፣* በመሐላውም* ተጠያቂ ቢሆን፣ በዳዩም በዚህ መሐላ* ሥር ሆኖ እዚህ ቤት ውስጥ ባለው መሠዊያህ ፊት ቢቀርብ፣+ +23 አንተ በሰማያት ሆነህ ስማ፤ ለክፉው እንደ ሥራው በመመለስና+ የእጁን እንዲያገኝ በማድረግ፣ ጻድቁንም ንጹሕ* መሆኑን በማሳወቅና እንደ ጽድቁ ወሮታውን በመክፈል+ እርምጃ ውሰድ፤ አገልጋዮችህንም ዳኝ። +24 “ሕዝብህ እስራኤላውያን አንተን ከመበደላቸው የተነሳ በጠላት ድል ቢነሱና+ ተመልሰው ስምህን ቢያወድሱ+ እንዲሁም በዚህ ቤት በፊትህ ቢጸልዩና+ ሞገስ ለማግኘት ልመና ቢያቀርቡ+ +25 ከሰማያት ሆነህ ስማ፤+ የሕዝብህንም የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ለእነሱና ለአባቶቻቸው ወደሰጠኸው ምድርም መልሳቸው።+ +26 “ሕዝቡ አንተን በመበደሉ የተነሳ+ ሰማያት ተዘግተው ዝናብ ቢጠፋ፣+ እነሱም አንተ ስላዋረድካቸው* ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩና ስምህን ቢያወድሱ እንዲሁም ከኃጢአታቸው ቢመለሱ+ +27 ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የአገልጋዮችህን፣ የሕዝብህን የእስራኤላውያንን ኃጢአት ይቅር በል፤ ስለሚሄዱበት ቀና መንገድ ታስተምራቸዋለህና፤+ ለሕዝብህ ርስት አድርገህ ባወረስከው ምድርህም ላይ ዝናብ አዝንብ።+ +28 “በምድሪቱ ላይ ረሃብ+ ወይም ቸነፈር፣+ የሚለበልብና የሚያደርቅ ነፋስ ወይም ዋግ+ ቢከሰት፣ የአንበጣ መንጋ ወይም የማይጠግብ አንበጣ*+ ቢመጣ አሊያም ጠላቶቻቸው በምድሪቱ ላይ ባለ በየትኛውም ከተማ* ውስጥ ሳሉ ቢከቧቸው+ ወይም ደግሞ ማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት አሊያም ማንኛውም ዓይነት በሽታ ቢከሰት +29 ማንኛውም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል በሙሉ (እያንዳንዱ የገዛ ጭንቀቱንና ሥቃዩን ያውቃልና)+ ወደ አንተ ለመጸለይ+ ወይም ሞገስ እንድታሳየው ልመና ለማቅረብ+ እጁን ወደዚህ ቤት ቢዘረጋ+ +30 አንተ ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤+ ደግሞም ይቅር በል፤+ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው ብድራቱን ክፈለው፤ ምክንያቱም አንተ ልቡን ታውቃለህ (የሰውን ልብ በሚገባ የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ)፤+ +31 ይህም ለአባቶቻችን በሰጠኸው ምድር ላይ በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ በመንገዶችህ በመመላለስ አንተን እንዲፈሩ ነው። +32 “በተጨማሪም ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ የባዕድ አገር ሰው ከታላቁ ስምህ፣* ከኃያሉ እጅህና ከተዘረጋው ክንድህ የተነሳ ከሩቅ አገር ቢመጣ፣+ ወደዚህም ቤት መጥቶ ቢጸልይ፣+ +33 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና+ እንዲፈሩህ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት። +34 “ሕዝብህ ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትልካቸው መንገድ ለጦርነት ቢወጡና+ አንተ ወደመረጥከው ወደዚህ ከተማ እንዲሁም ለስምህ ወደሠራሁት ቤት አቅጣጫ+ ቢጸልዩ+ +35 ከሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡትን ልመና ስማ፤ ፍረድላቸውም።+ +36 “በአንተ ላይ ኃጢአት ቢሠሩ (መቼም ኃጢአት የማይሠራ ሰው የለም)፣+ አንተም በእነሱ እጅግ ተቆጥተህ ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው፣ ጠላቶቻቸውም ራቅ ወዳለ ወይም ቅርብ ወደሆነ ምድር ምርኮኛ አድርገው ቢወስዷቸው፣+ +37 እነሱም በምርኮ በተወሰዱበት ምድር ወደ ልቦናቸው ቢመለሱና ወደ አንተ ዞር በማለት ‘ኃጢአት ሠርተናል፤ አጥፍተናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል’ በማለት በተማረኩበት ምድር ሆነው ሞገስ ለማግኘት ወደ አንተ ልመና ቢያቀርቡ፣+ +38 ደግሞም ተማርከው በተወሰዱበት፣ ምርኮኛ ሆነው በሚኖሩበት ምድር፣+ በሙሉ ልባቸውና+ በሙሉ ነፍሳቸው* ወደ አንተ ቢመለሱ እንዲሁም ለአባቶቻቸው በሰጠሃቸው ምድር፣ አንተ በመረጥካት ከተማና ለስምህ በሠራሁት ቤት አቅጣጫ ቢጸልዩ፣+ +39 ጸሎታቸውንና ሞገስ ለማግኘት ያቀረቡትን ልመና ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ ፍረድላቸውም፤+ በአንተ ላይ ኃጢአት የሠራውን ሕዝብህን ይቅር በል። +40 “አሁንም አምላኬ ሆይ፣ እባክህ በዚህ ቦታ* ወደቀረበው ጸሎት ዓይኖችህ ይመልከቱ፤ ጆሮዎችህም በትኩረት ያዳምጡ።+ +41 አሁንም ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ከብርታትህ ታቦት ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ+ ውጣ። ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ካህናትህ መዳንን ይልበሱ፤ ታማኞችህም በጥሩነትህ ሐሴት ያድርጉ።+ +42 ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ የቀባኸውን ሰው ገሸሽ አታድርግ።*+ ለአገልጋይህ ለዳዊት ያሳየኸውን ታማኝ ፍቅር አስብ።”+ +25 አሜስያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ��በር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ29 ዓመት ገዛ። እናቱ ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች።+ +2 እሱም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፤ ሆኖም በሙሉ ልቡ አልነበረም። +3 መንግሥቱ በእጁ እንደጸናለትም ንጉሥ የነበረውን አባቱን የገደሉትን አገልጋዮቹን ገደላቸው።+ +4 ይሁንና “አባቶች በልጆቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም በአባቶቻቸው ኃጢአት መገደል የለባቸውም፤ ይልቁንም እያንዳንዱ ሰው በገዛ ኃጢአቱ ይገደል” በሚለው በሙሴ የሕግ መጽሐፍ ላይ በተጻፈው የይሖዋ ትእዛዝ መሠረት የገዳዮቹን ልጆች አልገደላቸውም።+ +"5 አሜስያስም የይሁዳን ሰዎች ሰብስቦ በየአባቶቻቸው ቤት፣ በሺህ አለቆችና በመቶ አለቆች በመደልደል መላውን ይሁዳና ቢንያም ወክለው እንዲቆሙ አደረገ።+ ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን መዘገበ፤+ በጦርና በትልቅ ጋሻ መጠቀምና በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የሚችሉ 300,000 የሠለጠኑ* ተዋጊዎች" +"6 በተጨማሪም በ100 የብር ታላንት፣* 100,000 ኃያላን ተዋጊዎችን ከእስራኤል ቀጠረ።" +7 ይሁንና አንድ የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደ እሱ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ንጉሥ ሆይ፣ ይሖዋ ከእስራኤል፣ ከኤፍሬማውያን ሁሉ ጋር ስላልሆነ+ የእስራኤል ሠራዊት ከአንተ ጋር እንዲዘምት አታድርግ። +8 ይልቁንም ብቻህን ዝመት፤ ወደኋላ አትበል፤ በቆራጥነትም ተዋጋ። እንዲህ ባታደርግ ግን እውነተኛው አምላክ በጠላቶችህ ፊት ሊጥልህ ይችላል፤ አምላክ ለመርዳትም ሆነ ለመጣል ኃይል አለውና።”+ +9 በዚህ ጊዜ አሜስያስ የእውነተኛውን አምላክ ሰው “ታዲያ ለእስራኤል ወታደሮች የሰጠሁት 100 ታላንት ምን ይሁን?” አለው። የእውነተኛውም አምላክ ሰው “ይሖዋ ከዚህ እጅግ የሚበልጥ ሊሰጥህ ይችላል” ሲል መለሰለት።+ +10 በመሆኑም አሜስያስ ከኤፍሬም ወደ እሱ የመጡትን ወታደሮች ወደ ስፍራቸው እንዲመለሱ አሰናበታቸው። እነሱ ግን በይሁዳ እጅግ ተበሳጭተው በታላቅ ቁጣ ወደ ገዛ አገራቸው ተመለሱ። +"11 ከዚያም አሜስያስ ተበረታታ፤ የራሱንም ወታደሮች እየመራ ወደ ጨው ሸለቆ+ ሄደ፤ ደግሞም 10,000 የሚሆኑ የሴይር ሰዎችን ገደለ።+" +"12 የይሁዳም ሰዎች 10,000 የሚሆኑ ሰዎችን ማረኩ። ከዚያም ወደ ገደል አፋፍ ወስደው፣ ከአፋፉ ላይ ቁልቁል ወረወሯቸው፤ ሁሉም ተፈጥፍጠው ብትንትናቸው ወጣ።" +"13 ይሁንና አሜስያስ ከእሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄዱ ያሰናበታቸው ወታደሮች+ ከሰማርያ+ አንስቶ እስከ ቤትሆሮን+ ድረስ ያሉትን የይሁዳ ከተሞች ወረሩ፤ 3,000 ሰዎችም ገደሉ፤ ብዙ ምርኮም ወሰዱ። " +14 አሜስያስ ኤዶማውያንን መትቶ ከተመለሰ በኋላ የሴይርን ሰዎች አማልክት ይዞ በመምጣት ለራሱ አማልክት አድርጎ አቆማቸው፤+ በእነሱም ፊት ይሰግድ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብላቸው ጀመር። +15 ስለሆነም የይሖዋ ቁጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ፤ ነቢይም ልኮ “የገዛ ሕዝባቸውን ከእጅህ መታደግ ያልቻሉትን የሕዝቡን አማልክት የምትከተለው ለምንድን ነው?” አለው።+ +16 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ነቢዩን “የንጉሡ አማካሪ አድርገን ሾመንሃል?+ ዝም በል!+ መሞት ትፈልጋለህ?” አለው። ነቢዩም ዝም አለ፤ ሆኖም “ይህን በማድረግህና ምክሬን ባለመስማትህ አምላክ ሊያጠፋህ እንደወሰነ ተረዳሁ” አለ።+ +17 የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ ከአማካሪዎቹ ጋር ከተማከረ በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ወደሆነው ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮዓካዝ ልጅ ወደ ኢዮዓስ “ና፣ ውጊያ እንግጠም”* የሚል መልእክት ላከበት።+ +18 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ደግሞ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ይህን መልእክት ላከ፦ “በሊባኖስ የሚገኘው ኩርንችት በሊባኖስ ወደሚገኘው አርዘ ሊባኖስ ‘ሴት ልጅህን ለወንድ ልጄ ዳርለት’ የሚል መልእክት ላከ። ይሁን እንጂ በሊባኖስ የነበረ አንድ የዱር አውሬ በዚያ ሲያልፍ ያን ኩርንችት ረገጠው። +19 አንተ ‘እኔ ኤዶምን መትቻለሁ’ ብለሃል።+ በመሆኑም ልብህ ክብር በመሻት ታብዮአል። አሁን ግን አርፈህ ቤትህ* ተቀመጥ። በራስህ ላይ ለምን ጥፋት ትጋብዛለህ? ደግሞስ ራስህንም ሆነ ይሁዳን ለምን ለውድቀት ትዳርጋለህ?” +20 አሜስያስ ግን አልሰማም፤+ የኤዶምን አማልክት በመከተላቸው+ እውነተኛው አምላክ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሊሰጣቸው ወስኗልና።+ +21 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ወጣ፤ እሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ በምትገኘው በቤትሼሜሽ+ ተጋጠሙ። +22 ይሁዳ በእስራኤል ድል ተመታ፤ እያንዳንዳቸውም ወደየቤታቸው* ሸሹ። +23 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ የኢዮአካዝ* ልጅ፣ የኢዮዓስ ልጅ የሆነውን የይሁዳን ንጉሥ አሜስያስን ቤትሼሜሽ ላይ ያዘው። ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ ከኤፍሬም በር+ አንስቶ እስከ ማዕዘን በር+ ድረስ አፈረሰ፤ ርዝመቱም 400 ክንድ* ያህል ነበር። +24 በእውነተኛው አምላክ ቤት በኦቤድዔዶም እጅና* በንጉሡ ቤት* ግምጃ ቤቶች+ የተገኘውን ወርቅ፣ ብርና ዕቃ ሁሉ እንዲሁም የታገቱትን ሰዎች ወሰደ። ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ። +25 የእስራኤል ንጉሥ የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ+ ከሞተ በኋላ፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ+ 15 ዓመት ኖረ።+ +26 ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለው የቀረው የአሜስያስ ታሪክ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ የለም? +27 አሜስያስ ይሖዋን መከተል ከተወበት ጊዜ ጀምሮ በኢየሩሳሌም በእሱ ላይ ሲያሴሩ ቆዩ፤+ እሱም ወደ ለኪሶ ሸሸ፤ እነሱ ግን ተከታትለው እንዲይዙት ሰዎችን ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት። +28 ከዚያም በፈረሶች ላይ ጭነው አመጡት፤ ከአባቶቹም ጋር በይሁዳ ከተማ ቀበሩት። +33 ምናሴ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 12 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ 55 ዓመት ገዛ።+ +2 እሱም ይሖዋ ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሟቸው የነበሩትን አስጸያፊ ልማዶች በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +3 አባቱ ሕዝቅያስ አፍርሷቸው የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች መልሶ ገነባ፣+ ለባአል አማልክት መሠዊያዎችን አቆመ፣ የማምለኪያ ግንዶች* ሠራ እንዲሁም ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ሰገደ፤ እነሱንም አገለገለ።+ +4 በተጨማሪም ይሖዋ “ኢየሩሳሌም ለዘላለም በስሜ ትጠራለች”+ ብሎ በተናገረለት በይሖዋ ቤት ውስጥ መሠዊያዎችን ሠራ።+ +5 ደግሞም በይሖዋ ቤት በሚገኙት በሁለቱ ግቢዎች ውስጥ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ።+ +6 በሂኖም ልጅ ሸለቆም+ የገዛ ልጆቹን ለእሳት አሳልፎ ሰጠ፤+ አስማተኛ፣+ ሟርተኛና መተተኛ ሆነ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ቀጠረ።+ ይሖዋን ያስቆጣው ዘንድ በእሱ ፊት በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሠራ። +7 ምናሴም የሠራውን የተቀረጸ ምስል አምላክ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን እንዲህ ብሎ በተናገረለት በእውነተኛው አምላክ ቤት ውስጥ አስቀመጠው፦+ “በዚህ ቤትና ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በመረጥኳት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለቄታው አኖራለሁ።+ +8 እነሱ በሙሴ በኩል የሰጠኋቸውን ሕግ ሁሉ እንዲሁም ሥርዓቶቹንና ድንጋጌዎቹን በጥንቃቄ ይጠብቁ እንጂ የእስራኤላውያን እግር ለአባቶቻቸው ከሰጠሁት ምድር ዳግመኛ እንዲወጣ አላደርግም።” +9 ምናሴም ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው ብሔራት የባሰ ክፉ ነገር እንዲሠሩ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች አሳተ።+ +10 ይሖዋ ለምናሴና ለሕዝቡ በተደጋጋሚ ቢናገርም እነሱ ለመስማት ፈቃደኛ አልሆኑም።+ +11 ስለዚህ ይሖዋ የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አለቆች አመጣባቸው፤ እነሱም ምናሴን በመንጠቆ ያዙት፤* ከመዳብ በተሠሩ ሁለት የእግር ብረቶች አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት። +12 በተጨነቀም ጊዜ ሞገስ እንዲያሳየው አምላኩን ይሖዋን ለመነ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ራሱን እጅግ አዋረደ። +13 ወደ እሱ አጥብቆ ጸለየ፤ እሱም ተለመነው፤ በእሱ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያቀረበውንም ልመና ሰማው፤ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ ንግሥናው መለሰው።+ ከዚያም ምናሴ፣ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አወቀ።+ +14 ከዚህ በኋላ በሸለቆው ውስጥ ከሚገኘው* ከግዮን+ በስተ ምዕራብ አንስቶ እስከ ዓሣ በር+ ድረስ ለዳዊት ከተማ+ በውጭ በኩል ቅጥር ሠራ። ቅጥሩ ከዚያ ተነስቶ ከተማዋን በመዞር እስከ ኦፌል+ የሚደርስ ሲሆን እጅግ ከፍ አድርጎ ሠራው። በተጨማሪም በተመሸጉ የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ የጦር አለቆች ሾመ። +15 ከዚያም ባዕዳን አማልክቱንና የጣዖቱን ምስል ከይሖዋ ቤት አስወገደ፤+ ደግሞም በይሖዋ ቤት ተራራ ላይና በኢየሩሳሌም የሠራቸውን መሠዊያዎች ሁሉ አፍርሶ ከከተማዋ ውጭ እንዲጣሉ አደረገ።+ +16 በተጨማሪም የይሖዋን መሠዊያ አድሶ+ በላዩ ላይ የኅብረት መሥዋዕቶችና+ የምስጋና መሥዋዕቶች+ ያቀርብ ጀመር፤ የይሁዳም ሰዎች የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን እንዲያገለግሉ አዘዘ። +17 ያም ሆኖ ሕዝቡ ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎቹ ላይ መሠዋታቸውን አልተዉም፤ የሚሠዉት ግን ለአምላካቸው ለይሖዋ ነበር። +18 የቀረው የምናሴ ታሪክ፣ ለአምላኩ ያቀረበው ጸሎትና በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ስም ያናገሩት ባለ ራእዮች ቃል ስለ እስራኤል ነገሥታት በተጻፈው ታሪክ ውስጥ ተመዝግበዋል። +19 በተጨማሪም ያቀረበው ጸሎት፣+ ልመናው እንዴት እንደተሰማለት፣ የሠራው ኃጢአት ሁሉና ታማኝነት በማጉደል የፈጸመው ድርጊት+ በባለ ራእዮቹ ዘገባዎች ውስጥ ተካተዋል፤ ደግሞም ራሱን ከማዋረዱ በፊት ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች የሠራባቸው እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶችና*+ የተቀረጹ ምስሎች ያቆመባቸው ስፍራዎ +20 በመጨረሻም ምናሴ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ እነሱም በቤቱ ቀበሩት፤ ልጁም አምዖን በእሱ ምትክ ነገሠ።+ +21 አምዖን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሁለት ዓመት ገዛ።+ +22 እሱም አባቱ ምናሴ እንዳደረገው በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረገ፤+ አምዖን አባቱ ምናሴ ለሠራቸው የተቀረጹ ምስሎች ሁሉ ሠዋ፤+ ያገለግላቸውም ነበር። +23 ይሁንና አባቱ ምናሴ ራሱን እንዳዋረደ፣+ በይሖዋ ፊት ራሱን አላዋረደም፤+ ይልቁንም በበደል ላይ በደል እየጨመረ ሄደ። +24 ከጊዜ በኋላም አገልጋዮቹ በእሱ ላይ አሲረው+ በገዛ ቤቱ ውስጥ ገደሉት። +25 ሆኖም የምድሪቱ ሕዝብ በንጉሥ አምዖን ላይ ያሴሩትን ሁሉ ገደላቸው፤+ በእሱም ምትክ ልጁን ኢዮስያስን አነገሠው።+ +10 እስራኤላውያን በሙሉ ሮብዓምን ለማንገሥ ወደ ሴኬም+ መጥተው ስለነበር እሱም ወደ ሴኬም ሄደ።+ +2 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ ይህን እንደሰማ (ምክንያቱም በወቅቱ ኢዮርብዓም ከንጉሥ ሰለሞን ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ነበር)፣+ ከግብፅ ተመልሶ መጣ። +3 ከዚያም ሰዎች ልከው አስጠሩት፤ ኢዮርብዓምና መላው እስራኤልም መጥተው ሮብዓምን እንዲህ አሉት፦ +5 በዚህ ጊዜ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” አላቸው። በመሆኑም ሕዝቡ ሄደ።+ +7 እነሱም “ለዚህ ሕዝብ ጥሩ ብትሆንና ደስ ብታሰኛቸው እንዲሁም መልካም ምላሽ ብትሰጣቸው ምንጊዜም አገልጋዮችህ ይሆናሉ” በማለት መለሱለት። +10 አብሮ አደጎቹ የሆኑት ወጣቶችም እንዲህ አሉት፦ “‘አባትህ ቀንበራችንን አክብዶብን ነበር፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚልህ ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች። +11 አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ግን ቀንበራችሁን የባሰ አከብደዋለሁ። አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ።’” +13 ይሁንና ንጉሡ መጥፎ ምላሽ ሰጣቸው። በዚህ መንገድ ንጉሥ ሮብዓም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ሳይቀበል ቀረ። +14 ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት “ቀንበራችሁን አከብደዋለሁ፤ ከቀድሞውም የከፋ አደርገዋለሁ። አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ እኔ ግን በእሾህ አለንጋ እገርፋችኋለሁ” አላቸው። +15 በመሆኑም ንጉሡ ሕዝቡን ሳይሰማ ቀረ፤ ይህም የሆነው ይሖዋ በሴሎናዊው በአኪያህ+ አማካኝነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ እውነተኛው አምላክ እነዚህ ነገሮች በዚህ መንገድ እንዲከናወኑ ስላደረገ ነው።+ +16 እስራኤላውያን ሁሉ ንጉሡ ሊሰማቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን ሲያዩ ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ምንም ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንድህ ወደ አማልክትህ ተመለስ! ዳዊት ሆይ፣ እንግዲህ የገዛ ቤትህን ጠብቅ!”+ ከዚያም እስራኤላውያን ሁሉ ወደየቤታቸው* ተመለሱ።+ +18 ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ የተመለመሉት ሰዎች አለቃ የነበረውን ሃዶራምን+ ላከው፤ ሆኖም እስራኤላውያን በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሥ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ።+ +19 እስራኤላውያንም እስከዚህ ቀን ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንዳመፁ ናቸው። +14 በመጨረሻም አቢያህ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም+ ቀበሩት፤ በምትኩም ልጁ አሳ ነገሠ። በእሱም ዘመን ምድሪቱ ለአሥር ዓመት አረፈች። +2 አሳ በአምላኩ በይሖዋ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ። +3 የባዕድ አማልክቱን መሠዊያዎችና+ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎች አስወገደ፤ የማምለኪያ ዓምዶቹንም ሰባበረ፤+ እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶቹን* ቆራረጠ።+ +4 በተጨማሪም የይሁዳ ሰዎች የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን እንዲፈልጉ እንዲሁም ሕጉንና ትእዛዙን እንዲያከብሩ አዘዘ። +5 ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎችና የዕጣን ማጨሻዎቹን አስወገደ፤+ መንግሥቱም በእሱ አገዛዝ ሥር ሰላም አገኘ። +6 ምድሪቱ እረፍት አግኝታ ስለነበር በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ገነባ፤+ ይሖዋ እረፍት ሰጥቶት ስለነበር በእነዚያ ዓመታት በእሱ ላይ ጦርነት የከፈተ አልነበረም።+ +7 የይሁዳንም ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “እነዚህን ከተሞች እንገንባ፤ በዙሪያቸውም ቅጥርና ማማዎች+ እንዲሁም በሮችና* መቀርቀሪያዎች እንሥራ። አምላካችንን ይሖዋን ስለፈለግነው ምድሪቱ አሁንም በእጃችን ናት። እኛ ፈልገነዋል፤ እሱም በዙሪያችን ካሉት ጠላቶቻችን ሁሉ እረፍት ሰጥቶናል።” በመሆኑም የግንባታ ሥራ +"8 አሳ ትልቅ ጋሻና ጦር የታጠቁ 300,000 የይሁዳ ሰዎችን ያቀፈ ሠራዊት ነበረው። ከቢንያምም ነገድ ትንሽ ጋሻ* የሚያነግቡና ደጋን የሚይዙ* 280,000 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ።+ " +"9 ከጊዜ በኋላ ኢትዮጵያዊው ዛራ 1,000,000 ሰዎችንና 300 ሠረገሎችን ያቀፈ ሠራዊት አስከትሎ ዘመተባቸው።+ ማሬሻህ+ በደረሰ ጊዜ" +10 አሳ ሊገጥመው ወጣ፤ በማሬሻህ በሚገኘው በጸፋታ ሸለቆም ለውጊያ ተሰለፉ። +11 በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ ይሖዋ እንዲህ ሲል ጮኸ፦+ “ይሖዋ ሆይ፣ የምትረዳው ሕዝብ ብዛት ያለውም ይሁን ደካማ ለአንተ የሚያመጣው ለውጥ የለም።+ ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ እርዳን፤ በአንተ ታምነናልና፤*+ በስምህ ይህን ታላቅ ሠራዊት ለመግጠም ወጥተናል።+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህ። ሟች +12 በመሆኑም ይሖዋ ኢትዮጵያውያንን በአሳና በይሁዳ ፊት ድል አደረጋቸው፤ ኢትዮጵያውያ���ም ሸሹ።+ +13 አሳና ከእሱ ጋር ያለው ሕዝብም እስከ ጌራራ+ ድረስ አሳደዷቸው፤ ኢትዮጵያውያኑም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ተመተው ወደቁ፤ በይሖዋና በሠራዊቱ ተደምስሰው ነበርና። በኋላም የይሁዳ ሰዎች እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ። +14 በተጨማሪም ይሖዋ በከተሞቹ ላይ ታላቅ ፍርሃት ለቆባቸው ስለነበር በጌራራ ዙሪያ ያሉትን ከተሞች ሁሉ መቱ፤ እነሱም በከተሞቹ ውስጥ ብዙ የሚበዘበዝ ነገር ስለነበር ከተሞቹን ሁሉ በዘበዙ። +15 በተጨማሪም የእረኞችን ድንኳኖች በመምታት እጅግ ብዙ በጎችንና ግመሎችን ማረኩ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። +9 የሳባ ንግሥት+ ስለ ሰለሞን ዝና በሰማች ጊዜ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች* ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። እሷም እጅግ ታላቅ አጀብ አስከትላ እንዲሁም የበለሳን ዘይት፣ በጣም ብዙ ወርቅና+ የከበሩ ድንጋዮች በግመል አስጭና ነበር። ወደ ሰለሞንም ገብታ በልቧ ያለውን ሁሉ ነገረችው።+ +2 ሰለሞንም ጥያቄዎቿን ሁሉ መለሰላት። ሰለሞን ሊያብራራላት ያልቻለው* ምንም ነገር አልነበረም። +3 የሳባ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብና+ የሠራውን ቤት+ ስትመለከት፣ +4 በገበታው ላይ የሚቀርበውን ምግብ፣+ የአገልጋዮቹን አቀማመጥ፣ አስተናጋጆቹ በማዕድ ላይ የሚያስተናግዱበትን መንገድና አለባበሳቸውን፣ መጠጥ አሳላፊዎቹንና አለባበሳቸውን እንዲሁም በይሖዋ ቤት ዘወትር የሚያቀርባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች+ ስታይ በመገረም ፈዛ ቀረች።* +5 በመሆኑም ንጉሡን እንዲህ አለችው፦ “ስላከናወንካቸው ነገሮችና* ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ነገር እውነት ነው። +6 ይሁንና እኔ ራሴ መጥቼ በገዛ ዓይኔ እስከማይ ድረስ የተነገረኝን ነገር አላመንኩም ነበር።+ እንደዚያም ሆኖ ታላቅ ከሆነው ጥበብህ ግማሹ እንኳ አልተነገረኝም!+ እኔ ስለ አንተ ከሰማሁት እጅግ የላቅክ ነህ።+ +7 አብረውህ ያሉ ሰዎች ደስተኞች ናቸው፤ ዘወትር በፊትህ ቆመው ጥበብህን የሚሰሙት አገልጋዮችህም እጅግ ደስተኞች ናቸው! +8 ለአምላክህ ለይሖዋ ንጉሥ ሆነህ እንድትገዛ አንተን በዙፋኑ ላይ በማስቀመጥ በአንተ ደስ የተሰኘው አምላክህ ይሖዋ ይወደስ። አምላክህ እስራኤልን ስለወደደውና+ ለዘላለም ያጸናው ዘንድ ስለፈለገ፣ ፍትሕንና ጽድቅን እንድታሰፍን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ ሾሞሃል።” +9 ከዚያም ለንጉሡ 120 ታላንት* ወርቅ+ እንዲሁም እጅግ ብዙ የበለሳን ዘይትና የከበሩ ድንጋዮችን ሰጠችው። የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰለሞን የሰጠችውን ያህል የበለሳን ዘይት ከዚያ በኋላ መጥቶ አያውቅም።+ +10 ከዚህ በተጨማሪ ከኦፊር ወርቅ+ ጭነው የመጡት የኪራም አገልጋዮችና የሰለሞን አገልጋዮች የሰንደል ዛፍ ሳንቃዎችና የከበሩ ድንጋዮች አመጡ።+ +11 ንጉሡም ከሰንደል ዛፍ ሳንቃዎቹ ለይሖዋ ቤትና ለንጉሡ ቤት*+ ደረጃዎችን+ እንዲሁም ለዘማሪዎቹ የሚሆኑ በገናዎችንና ሌሎች ባለ አውታር መሣሪያዎችን ሠራ።+ ከዚያ በፊት እንዲህ ያለ ነገር በይሁዳ ምድር ታይቶ አያውቅም። +12 ንጉሥ ሰለሞን ደግሞ የሳባ ንግሥት የፈለገችውንና የጠየቀችውን ነገር ሁሉ፣ ካመጣችለት ስጦታ የሚበልጥ ነገር ሰጣት።* ከዚያም ተነስታ አገልጋዮቿን በማስከተል ወደ አገሯ ተመለሰች።+ +13 ሰለሞን በየዓመቱ 666 ታላንት ወርቅ ይመጣለት ነበር፤+ +14 ይህም ነጋዴዎችና ሻጮች የሚያስገቡትን ገቢ እንዲሁም የዓረብ ነገሥታት ሁሉና አገረ ገዢዎች ለሰለሞን የሚያመጡትን ወርቅና ብር ሳይጨምር ነው።+ +15 ንጉሥ ሰለሞን ከቅይጥ ወርቅ 200 ትላልቅ ጋሻዎችን ሠራ፤+ (እያንዳንዱ ጋሻ በ600 ሰቅል* ቅይጥ ወርቅ ተለብጦ ነበር)፤+ +16 እንዲሁም ከቅይጥ ወርቅ 300 ትናንሽ ጋሻዎችን* ሠራ፤ (እያንዳንዱ ትንሽ ጋሻ በሦስት ምናን* ወርቅ ተለብጦ ነ��ር)። ከዚያም ንጉሡ የሊባኖስ ደን በተባለው ቤት አስቀመጣቸው።+ +17 በተጨማሪም ንጉሡ ከዝሆን ጥርስ ትልቅ ዙፋን ሠርቶ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።+ +18 ወደ ዙፋኑ የሚያስወጡ ስድስት ደረጃዎች ነበሩ፤ ከዙፋኑም ጋር የተያያዘ ከወርቅ የተሠራ የእግር ማሳረፊያ ነበር፤ መቀመጫውም በጎንና በጎኑ የእጅ መደገፊያዎች ያሉት ሲሆን ከእጅ መደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች+ ቆመው ነበር። +19 በስድስቱ ደረጃዎች ዳርና ዳር አንድ አንድ አንበሳ፣ በአጠቃላይ 12 አንበሶች+ ቆመው ነበር። እንዲህ ያለ ዙፋን የሠራ አንድም ሌላ መንግሥት አልነበረም። +20 የንጉሥ ሰለሞን የመጠጫ ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ የሊባኖስ ደን በተባለው ቤት የነበሩት ዕቃዎችም በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ። ከብር የተሠራ ምንም ነገር አልነበረም፤ በሰለሞን ዘመን ብር እንደ ተራ ነገር ይቆጠር ነበር።+ +21 የኪራም+ አገልጋዮች የሰለሞንን መርከቦች እየነዱ ወደ ተርሴስ+ ይጓዙ ነበር። እነዚህ የተርሴስ መርከቦች በሦስት ዓመት አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብር፣ የዝሆን ጥርስ፣+ ጦጣና ጣዎስ* ጭነው ይመጡ ነበር። +22 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን በብልጽግናና በጥበብ ምድር ላይ ካሉ ሌሎች ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ ነበር።+ +23 የምድር ነገሥታትም ሁሉ እውነተኛው አምላክ በሰለሞን ልብ ውስጥ ያኖረውን ጥበብ ይሰሙ ዘንድ ከእሱ ጋር ለመገናኘት ይጓጉ ነበር።*+ +24 ወደ እሱ የሚመጡትም ሰዎች በየዓመቱ የብር ዕቃዎች፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ ልብሶች፣+ የጦር ትጥቆች፣ የበለሳን ዘይት፣ ፈረሶችና በቅሎዎች ስጦታ አድርገው ያመጡ ነበር። +"25 ሰለሞንም ለፈረሶቹ የሚሆኑ 4,000 ጋጣዎች፣ ሠረገሎችና 12,000 ፈረሶች* ነበሩት፤+ እነሱንም በሠረገላ ከተሞችና በኢየሩሳሌም በንጉሡ አቅራቢያ አኖራቸው።+" +26 እሱም ከወንዙ* አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ምድርና እስከ ግብፅ ወሰን ድረስ ባሉት ነገሥታት ሁሉ ላይ ገዛ።+ +27 ንጉሡ በኢየሩሳሌም ያለውን ብር ከብዛቱ የተነሳ በየቦታው እንደሚገኝ ድንጋይ አደረገው፤ የአርዘ ሊባኖሱንም ብዛት በሸፌላ እንደሚገኘው የሾላ ዛፍ አደረገው።+ +28 ደግሞም ለሰለሞን ከግብፅና ከሌሎች አገሮች ሁሉ ፈረሶችን ያመጡለት ነበር።+ +29 ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ ያለው የቀረው የሰለሞን ታሪክ+ ነቢዩ ናታን+ ባዘጋጀው ጽሑፍ፣ የሴሎ ሰው የሆነው አኪያህ+ በተናገረው ትንቢትና ባለ ራእዩ ኢዶ+ ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም+ያየው ራእይ በሰፈረበት ዘገባ ላይ ተጽፎ የለም? +30 ሰለሞን በኢየሩሳሌም ሆኖ በመላው እስራኤል ላይ ለ40 ዓመት ገዛ። +31 በመጨረሻም ሰለሞን ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ። በአባቱም በዳዊት ከተማ+ ቀበሩት፤ በእሱም ምትክ ልጁ ሮብዓም ነገሠ።+ +27 ኢዮዓታም+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። እናቱም የሩሻህ ትባል ነበር፤ እሷም የሳዶቅ ልጅ ነበረች።+ +2 ኢዮዓታም አባቱ ዖዝያ እንዳደረገው ሁሉ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፤+ ይሁንና ሥርዓቱን ጥሶ ወደ ይሖዋ ቤተ መቅደስ አልገባም።+ ሕዝቡ ግን ክፉ ድርጊት መፈጸሙን አልተወም ነበር። +3 እሱም የይሖዋን ቤት+ የላይኛውን በር ሠራ፤ በኦፌልም+ ቅጥር ላይ መጠነ ሰፊ የግንባታ ሥራ አከናወነ። +4 በተጨማሪም በተራራማው የይሁዳ ክልል+ ከተሞችን ሠራ፤+ በደን በተሸፈኑት ስፍራዎችም ምሽጎችንና+ ማማዎችን+ ገነባ። +"5 ከአሞናውያንም ንጉሥ ጋር ተዋጋ፤+ በመጨረሻም አሸነፋቸው፤ በመሆኑም አሞናውያን በዚያ ዓመት 100 የብር ታላንት፣* 10,000 የቆሮስ መስፈሪያ* ስንዴና 10,000 የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። በተጨማሪም አሞናውያን በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ይህንኑ ግብር አመጡለት።+" +6 ኢዮዓታም በአምላኩ በይሖዋ ፊት መንገዱን ስላጸና* ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ ሄደ። +7 የቀረው የኢዮዓታም ታሪክ፣ ያካሄዳቸው ጦርነቶችና የተከተለው መንገድ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈዋል።+ +8 እሱ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ።+ +9 በመጨረሻም ኢዮዓታም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም+ ቀበሩት። በእሱም ምትክ ልጁ አካዝ ነገሠ።+ +13 ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በ18ኛው ዓመት አቢያህ በይሁዳ ላይ ነገሠ።+ +2 እሱም በኢየሩሳሌም ለሦስት ዓመት ገዛ። የእናቱ ስም ሚካያህ*+ ነበር፤ እሷም የጊብዓዊው+ የዑሪኤል ልጅ ነበረች። በአቢያህና በኢዮርብዓም መካከልም ጦርነት ነበር።+ +"3 በመሆኑም አቢያህ 400,000 የሠለጠኑ* ኃያላን ተዋጊዎችን ያቀፈ ሠራዊት ይዞ ዘመተ።+ ኢዮርብዓምም 800,000 የሠለጠኑ* ኃያላን ተዋጊዎችን አስከትሎ እሱን ለመግጠም ተሰለፈ።" +4 አቢያህ በኤፍሬም ተራራማ ክልል በሚገኘው በጸማራይም ተራራ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፦ “ኢዮርብዓምና እስራኤላውያን ሁሉ፣ ስሙኝ። +5 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ፣ ዳዊትና ልጆቹ+ በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንዲነግሡ በጨው ቃል ኪዳን*+ መንግሥት እንደሰጣቸው አታውቁም?+ +6 የዳዊት ልጅ የሰለሞን አገልጋይ የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ ግን ተነስቶ በጌታው ላይ ዓመፀ።+ +7 ሥራ ፈት የሆኑ የማይረቡ ሰዎችም ወደ እሱ ተሰበሰቡ። የሰለሞን ልጅ ሮብዓም ለጋ ወጣት በነበረበትና ልቡ በቀላሉ ይሸበር በነበረበት ጊዜም በእሱ ላይ በረቱበት፤ ሊቋቋማቸውም አልቻለም። +8 “አሁንም እናንተ እጅግ ብዙ ስለሆናችሁና ኢዮርብዓም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁን የወርቅ ጥጃዎች+ ስለያዛችሁ በዳዊት ልጆች እጅ ያለውን የይሖዋን መንግሥት መቋቋም እንደምትችሉ ተሰምቷችኋል። +9 የአሮን ዘሮች የሆኑትን የይሖዋን ካህናትና ሌዋውያንን አላባረራችሁም?+ ደግሞስ እንደ ሌሎቹ አገሮች ሕዝቦች የራሳችሁን ካህናት አልሾማችሁም?+ አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ የሚመጣ ማንኛውም ሰው አማልክት ላልሆኑት ጣዖቶች ካህን መሆን ይችላል። +10 እኛ ግን አምላካችን ይሖዋ ነው፤+ እሱንም አልተውነውም፤ የአሮን ዘሮች የሆኑት ካህናት ይሖዋን እያገለገሉ ሲሆን ሌዋውያንም በሥራው ይረዷቸዋል። +11 በየጠዋቱና በየማታው+ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ እንዲሁም ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ያቀርባሉ፤ የሚነባበረውም ዳቦ*+ ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ ላይ ይቀመጣል፤ የወርቁን መቅረዝና+ መብራቶቹን በየማታው ያበራሉ፤+ ምክንያቱም እኛ በአምላካችን በይሖዋ ፊት ያለብንን ኃላፊነት እየተወጣን ነው፤ እናንተ ግን +12 እነሆ፣ እውነተኛው አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ እሱም በእናንተ ላይ ጦርነት መታወጁን የሚያመለክት ድምፅ ለማሰማት መለከት ከያዙ ካህናቱ ጋር ሆኖ እየመራን ነው። የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ስለማይሳካላችሁ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከይሖዋ ጋር አትዋጉ።”+ +13 ኢዮርብዓም ግን ከበስተ ጀርባቸው አድፍጠው ጥቃት የሚሰነዝሩ ተዋጊዎችን ላከ፤ ዋናው ሠራዊት ከፊት፣ ያደፈጡትም ተዋጊዎች ከበስተ ጀርባ ይሁዳን እንዲገጥሙ አደረገ። +14 የይሁዳ ሰዎች ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከፊትና ከኋላ መከበባቸውን አዩ። በዚህ ጊዜ ወደ ይሖዋ ጮኹ፤+ ካህናቱም መለከቶቹን በኃይል ነፉ። +15 የይሁዳ ሰዎች ቀረርቶ አሰሙ፤ የይሁዳ ሰዎች ቀረርቶ ባሰሙ ጊዜም እውነተኛው አምላክ ኢዮርብዓምንና እስራኤላውያንን ሁሉ በአቢያህና በይሁዳ ፊት ድል አደረጋቸው። +16 እስራኤላውያን ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ አምላክም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። +"17 አቢያህና ሕዝቡም ፈጇቸው፤ ከእስራኤላውያንም መካከል 500,000 የሠለጠኑ ተዋጊዎች* ተገ��ሉ።" +18 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሰዎች ተዋረዱ፤ የይሁዳ ሰዎች ግን በአባቶቻቸው አምላክ በይሖዋ በመታመናቸው* ድል ነሱ።+ +19 አቢያህ ኢዮርብዓምን አሳደደው፤ ከተሞቹን ይኸውም ቤቴልንና+ በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ የሻናንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ኤፍራይንንና+ በሥሯ ያሉትን ከተሞች ወሰደበት። +20 ኢዮርብዓምም በአቢያህ ዘመን እንደገና ሊያንሰራራ አልቻለም፤ ከዚያም ይሖዋ ስለቀሰፈው ሞተ።+ +21 አቢያህ ግን እየበረታ ሄደ። ከጊዜ በኋላም 14 ሚስቶችን+ አግብቶ 22 ወንዶች ልጆችና 16 ሴቶች ልጆች ወለደ። +22 የቀረው የአቢያህ ታሪክ፣ የሠራውና የተናገረው ነገር ሁሉ በነቢዩ ኢዶ ጽሑፎች* ላይ ሰፍሯል።+ +5 በዚህ ሁኔታ ሰለሞን ከይሖዋ ቤት ጋር በተያያዘ መሥራት የሚገባውን ሥራ በሙሉ ሠርቶ አጠናቀቀ።+ ከዚያም ሰለሞን አባቱ ዳዊት የቀደሳቸውን ነገሮች ወደዚያ አስገባ፤+ ብሩን፣ ወርቁንና ዕቃዎቹን በሙሉ በእውነተኛው አምላክ ቤት ግምጃ ቤቶች ውስጥ አስቀመጠ።+ +2 በዚህ ጊዜ ሰለሞን የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የነገዶቹን መሪዎች ሁሉና የእስራኤልን የአባቶች ቤት አለቆች ሰበሰበ። እነሱም የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ማለትም ከጽዮን+ ለማምጣት ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።+ +3 የእስራኤል ሰዎች በሙሉ በሰባተኛው ወር በሚከበረው በዓል* ላይ በንጉሡ ፊት ተሰበሰቡ።+ +4 የእስራኤል ሽማግሌዎችም በሙሉ መጡ፤ ሌዋውያኑም ታቦቱን አነሱ።+ +5 ታቦቱን፣ የመገናኛ ድንኳኑንና+ በድንኳኑ ውስጥ የነበሩትን ቅዱስ ዕቃዎች በሙሉ አመጡ። እነዚህንም ያመጡት ካህናቱና ሌዋውያኑ* ናቸው። +6 ንጉሥ ሰለሞንና ወደ እሱ እንዲመጣ የተጠራው መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ታቦቱ ፊት ነበሩ። ከብዛታቸው የተነሳ ሊቆጠሩ የማይችሉ ብዙ በጎችና ከብቶች መሥዋዕት ሆነው ቀረቡ።+ +7 ከዚያም ካህናቱ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት አምጥተው ቦታው ላይ ማለትም በቤቱ ውስጠኛ ክፍል ይኸውም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ከኪሩቦቹ ክንፎች በታች አስቀመጡት።+ +8 የኪሩቦቹ ክንፎች ታቦቱ ባለበት ቦታ ላይ ተዘርግተው ስለነበር ኪሩቦቹ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን+ ከላይ ሸፍነዋቸው ነበር። +9 መሎጊያዎቹ ረጅም ስለነበሩ የመሎጊያዎቹን ጫፎች ከውስጠኛው ክፍል ፊት ለፊት ባለው በቅድስቱ ውስጥ ሆኖ ማየት ይቻል ነበር፤ ከውጭ ግን አይታዩም ነበር። እስከ ዛሬም ድረስ እዚያው ይገኛሉ። +10 የእስራኤል ሰዎች ከግብፅ ምድር ሲወጡ+ ይሖዋ ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን+ በገባበት ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ታቦቱ ውስጥ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች+ በስተቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም አልነበረም። +11 ካህናቱ ከቅዱሱ ስፍራ በወጡ ጊዜ (በዚያ የተገኙት ካህናት ሁሉ ከየትኛውም ምድብ+ ይሁኑ ራሳቸውን ቀድሰው ነበር)፣+ +12 ከአሳፍ፣+ ከሄማን፣+ ከየዱቱን+ እንዲሁም ከወንዶች ልጆቻቸውና ከወንድሞቻቸው ወገን የሆኑት ሌዋውያን ዘማሪዎች+ ሁሉ ጥራት ያለው ልብስ ለብሰውና ሲምባል፣* ባለ አውታር መሣሪያዎችና በገና ይዘው ነበር፤ ከመሠዊያው በስተ ምሥራቅ ቆመው የነበረ ሲሆን ከእነሱም ጋር መለከት የሚነፉ 120 ካህናት ነበሩ።+ +13 መለከት ነፊዎቹና ዘማሪዎቹ በኅብረት ይሖዋን ባወደሱና ባመሰገኑ ጊዜ እንዲሁም “እሱ ጥሩ ነውና፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል”+ እያሉ ይሖዋን በማወደስ የመለከቱን፣ የሲምባሉንና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ድምፅ ባሰሙ ጊዜ ቤቱ ይኸውም የይሖዋ ቤት በደመና ተሞልቶ ነበር።+ +14 የይሖዋ ክብር የእውነተኛውን አምላክ ቤት ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ከደመናው የተነሳ በዚያ ቆመው ማገልገል አልቻሉም።+ +21 በመጨረሻም ኢዮሳፍጥ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮራም ነገሠ።+ +2 የኢዮሳፍጥ ልጆች የሆኑት ወንድሞቹ አዛርያስ፣ የሂኤል፣ ዘካርያስ፣ አዛርያስ፣ ሚካኤል እና ሰፋጥያህ ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ወንዶች ልጆች ናቸው። +3 አባታቸውም ብዙ ብር፣ ወርቅና ውድ የሆኑ ነገሮች ስጦታ አድርጎ የሰጣቸው ከመሆኑም በላይ በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ሰጣቸው፤+ መንግሥቱን ግን የበኩር ልጁ ለነበረው ለኢዮራም+ ሰጠው። +4 ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ ተደላድሎ በተቀመጠ ጊዜ ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም ከእስራኤል መኳንንት መካከል የተወሰኑትን በሰይፍ በመግደል ሥልጣኑን አጠናከረ።+ +5 ኢዮራም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 32 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ስምንት ዓመት ገዛ።+ +6 የአክዓብን ልጅ አግብቶ+ ስለነበር ከአክዓብ ቤት የሆኑት እንዳደረጉት ሁሉ እሱም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤+ በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። +7 ሆኖም ይሖዋ ከዳዊት ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ሲል የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤+ ምክንያቱም ለእሱና ለልጆቹ ለሁልጊዜ የሚኖር መብራት* እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር።+ +8 በእሱ ዘመን ኤዶም በይሁዳ ላይ ዓምፆ+ የራሱን ንጉሥ አነገሠ።+ +9 በመሆኑም ኢዮራም ከአዛዦቹ ጋር ሠረገሎቹን ሁሉ ይዞ ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እሱንና የሠረገሎቹን አዛዦች ከበው የነበሩትን ኤዶማውያን ድል አደረገ። +10 ሆኖም ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው። ሊብናም+ በዚሁ ጊዜ በእሱ ላይ ዓመፀ፤ ምክንያቱም ኢዮራም የአባቶቹን አምላክ ይሖዋን ትቶ ነበር።+ +11 ደግሞም በይሁዳ ተራሮች ላይ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን ሠርቶ+ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መንፈሳዊ ምንዝር እንዲፈጽሙ አደረገ፤ ይሁዳንም አሳተ። +12 በመጨረሻም ነቢዩ ኤልያስ እንዲህ የሚል መልእክት በጽሑፍ ላከለት፦+ “የአባትህ የዳዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በአባትህ በኢዮሳፍጥ+ ወይም በይሁዳ ንጉሥ በአሳ+ መንገድ አልሄድክም። +13 ይልቁንም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ በመሄድ፣+ ይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የአክዓብ ቤት የፈጸመውን ምንዝር+ የሚመስል መንፈሳዊ ምንዝር እንዲፈጽሙ አድርገሃል፤+ ከዚህም በላይ ከአንተ ይሻሉ የነበሩትን የአባትህ ቤት ልጆች የሆኑትን የገዛ ወንድሞችህን ገድለሃል።+ +14 ስለዚህ ይሖዋ ሕዝብህን፣ ልጆችህን፣ ሚስቶችህንና ንብረትህን ሁሉ በታላቅ መቅሰፍት ይመታል። +15 አንተም የአንጀት በሽታን ጨምሮ በብዙ ሕመም ትሠቃያለህ፤ ከበሽታው የተነሳ አንጀትህ እስኪወጣ ድረስ ሕመሙ ዕለት ተዕለት እየጠናብህ ይሄዳል።’” +16 ከዚያም ይሖዋ ፍልስጤማውያንና+ በኢትዮጵያውያን አቅራቢያ የሚኖሩት ዓረቦች+ በኢዮራም ላይ እንዲነሱ አደረገ።*+ +17 እነሱም ይሁዳን ወረሩ፤ በኃይል ጥሰው በመግባትም በንጉሡ ቤት* ያገኙትን ንብረት ሁሉ+ እንዲሁም ልጆቹንና ሚስቶቹን ማርከው ወሰዱ፤ ከመጨረሻው ልጁ ከኢዮዓካዝ*+ በቀር አንድም ልጅ አልቀረለትም። +18 ከዚህ ሁሉ በኋላ ይሖዋ በማይድን የአንጀት በሽታ ቀሰፈው።+ +19 ድፍን ሁለት ዓመት ከታመመ በኋላም ሕመሙ ጠንቶበት አንጀቱ ወጣ፤ በበሽታውም እጅግ ሲሠቃይ ቆይቶ በመጨረሻ ሞተ፤ ሕዝቡም ለአባቶቹ ያደርጉት እንደነበረው ለእሱ ክብር እሳት አላነደዱም።+ +20 በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 32 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ለስምንት ዓመት ገዛ። ሲሞት ማንም አላዘነለትም። በመሆኑም በነገሥታቱ የመቃብር ስፍራ ሳይሆን+ በዳዊት ከተማ+ ቀበሩት። +15 የአምላክ መንፈስ በኦዴድ ልጅ በአዛርያስ ላይ ወረደ። +2 እሱም ከአሳ ጋር ለመገናኘት ወጥቶ እንዲህ አለው፦ “አሳ ሆይ፣ ይሁዳና ቢንያም ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእሱ ጋር እስከሆናችሁ ድረስ ይሖዋ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤+ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤+ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።+ +3 እስራኤል ያለእውነተኛው አምላክ፣ ያለአስተማሪ ካህንና ያለሕግ ብዙ ዘመን* አሳልፏል።+ +4 በተጨነቁ ጊዜ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ ይሖዋ ተመልሰው ፈለጉት፤ እሱም ተገኘላቸው።+ +5 በዚያ ዘመን በሰላም መጓዝ የሚችል ሰው አልነበረም፤* ምክንያቱም በየክልሉ በሚኖሩት ሰዎች ሁሉ መካከል ከፍተኛ ሁከት ነበር። +6 አምላክ በተለያየ ችግር ያውካቸው ስለነበር አንዱ ብሔር ሌላውን ብሔር፣ አንዱ ከተማም ሌላውን ከተማ ያደቅ ነበር።+ +7 እናንተ ግን የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ ተስፋም አትቁረጡ።”*+ +8 አሳ ይህን ቃልና ነቢዩ ኦዴድ የተናገረውን ትንቢት ሲሰማ ተበረታታ፤ አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶችም ከይሁዳና ከቢንያም ምድር ሁሉ እንዲሁም በተራራማው የኤፍሬም ክልል ከያዛቸው ከተሞች አስወገደ፤+ ከይሖዋ ቤት በረንዳ ፊት ለፊት የነበረውን የይሖዋን መሠዊያም አደሰ።+ +9 እሱም ይሁዳንና ቢንያምን ሁሉ እንዲሁም ከኤፍሬም፣ ከምናሴና ከስምዖን መጥተው ከእነሱ ጋር የተቀመጡትን የባዕድ አገር ሰዎች ሰበሰበ፤+ አምላኩ ይሖዋ ከእሱ ጋር እንደሆነ ባዩ ጊዜ በርካታ የባዕድ አገር ሰዎች እስራኤልን ትተው ወደ እሱ መጥተው ነበር። +10 በመሆኑም አሳ በነገሠ በ15ኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። +"11 በዚያም ቀን፣ ካመጡት ምርኮ ላይ 700 ከብቶችንና 7,000 በጎችን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።" +12 በተጨማሪም የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው* ለመፈለግ ቃል ኪዳን ገቡ።+ +13 የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን የማይፈልግ ማንኛውም ሰው ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንድም ሆነ ሴት እንዲገደል ተስማሙ።+ +14 በታላቅ ድምፅ፣ በእልልታ፣ በመለከትና በቀንደ መለከት ለይሖዋ ማሉ። +15 የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በሙሉ ልባቸው ስለማሉ በመሐላው ሐሴት አደረጉ፤ አምላክንም ከልባቸው ፈለጉት፤ እሱም ተገኘላቸው፤+ ይሖዋም በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው እረፍት ሰጣቸው።+ +16 ሌላው ቀርቶ ንጉሥ አሳ አያቱ ማአካ+ ለማምለኪያ ግንዱ* አምልኮ ጸያፍ ጣዖት ሠርታ ስለነበር ከእመቤትነቷ* ሻራት።+ ከዚያም አሳ፣ አያቱ የሠራችውን ጸያፍ ጣዖት ቆርጦ በማድቀቅ በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው።+ +17 ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች ግን ከእስራኤል አልተወገዱም ነበር።+ ይሁንና አሳ በሕይወት ዘመኑ* ሁሉ በሙሉ ልቡ ተመላልሷል።*+ +18 እሱና አባቱ የቀደሷቸውን ነገሮች ይኸውም ብሩን፣ ወርቁንና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ወደ እውነተኛው አምላክ ቤት አስገባ።+ +19 እስከ 35ኛው የአሳ ዘመነ መንግሥት ድረስ ጦርነት አልነበረም።+ +22 ከዚያም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የመጨረሻ ልጁን አካዝያስን* በእሱ ምትክ አነገሡት፤ ከዓረቦቹ ጋር ወደ ሰፈሩ የመጡት ወራሪዎች ታላላቆቹን በሙሉ ገድለዋቸው ነበር።+ በመሆኑም የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ።+ +2 አካዝያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም ጎቶልያ+ የተባለች የኦምሪ+ የልጅ ልጅ* ነበረች። +3 እናቱ ክፉ ነገር እንዲያደርግ ትመክረው ስለነበር እሱም የአክዓብን+ ቤት መንገድ ተከተለ። +4 ከአባቱ ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት ሰዎች አማካሪዎቹ በመሆን ወደ ጥፋት ስለመሩት ልክ እንደ አክዓብ ቤት እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ቀጠለ። +5 እሱም የእነሱን ምክር ተከትሎ ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል+ ጋር በራሞትጊልያድ+ ለመዋጋት ከእስራኤል ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሄደ፤ በዚያም ቀስተኞች ኢዮራምን አቆሰሉት። +6 እሱም ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል ጋር በተዋጋ��ት ጊዜ+ በራማ ካቆሰሉት ቁስል ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል+ ተመለሰ። የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም+ ልጅ አካዝያስ* የአክዓብ ልጅ ኢዮራም+ ቆስሎ*+ ስለነበር እሱን ለማየት ወደ ኢይዝራኤል ወረደ። +7 ይሁንና አካዝያስ ወደ ኢዮራም በመምጣቱ አምላክ ለውድቀት ዳረገው፤ እዚያ ከደረሰ በኋላም ከኢዮራም ጋር የኒምሺን የልጅ ልጅ* ኢዩን+ ለማግኘት ሄዱ፤ ኢዩ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ ይሖዋ የቀባው ሰው ነበር።+ +8 ኢዩም በአክዓብ ቤት ላይ የተላለፈውን ፍርድ ማስፈጸም ሲጀምር የአካዝያስ አገልጋዮች የነበሩትን የይሁዳን መኳንንትና የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው።+ +9 ከዚያም አካዝያስን ለመፈለግ ሄደ፤ እነሱም በሰማርያ ተደብቆ ሳለ ያዙት፤ ወደ ኢዩም አመጡት። ከዚያም ገደሉት፤ ይሁንና “ይሖዋን በሙሉ ልቡ የፈለገው የኢዮሳፍጥ የልጅ ልጅ ነው” በማለት ቀበሩት።+ ከአካዝያስ ቤት የመንግሥቱን ሥልጣን የመያዝ ብቃት ያለው ሰው አልነበረም። +10 የአካዝያስ እናት ጎቶልያ+ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ ተነስታ የይሁዳን ንጉሣውያን ቤተሰብ* በሙሉ አጠፋች።+ +11 ይሁንና የንጉሡ ልጅ የሆነችው ዮሳቤት ሊገደሉ ከነበሩት የንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮዓስን+ ሰርቃ በመውሰድ እሱንና ሞግዚቱን በውስጠኛው መኝታ ክፍል አስቀመጠቻቸው። የንጉሥ ኢዮራም+ ልጅ የሆነችው ዮሳቤት (የካህኑ ዮዳሄ+ ሚስትና የአካዝያስ እህት ነበረች) ከጎቶልያ ደብቃ አቆየችው፤ በመ +12 እሱም ከእነሱ ጋር ለስድስት ዓመት በእውነተኛው አምላክ ቤት ተደብቆ ቆየ፤ በዚህ ጊዜ ጎቶልያ በምድሪቱ ላይ ትገዛ ነበር። +3 በሰባተኛው ወር+ እስራኤላውያን* በከተሞቻቸው ውስጥ ነበሩ፤ እነሱም ልክ እንደ አንድ ሰው ሆነው በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። +2 የየሆጼዴቅ ልጅ የሹዋና+ አብረውት የሚያገለግሉት ካህናት እንዲሁም የሰላትያል+ ልጅ ዘሩባቤልና+ ወንድሞቹ በእውነተኛው አምላክ ሰው በሙሴ ሕግ+ ውስጥ በተጻፈው መሠረት በላዩ ላይ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን ለማቅረብ የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ። +3 በዙሪያቸው ባሉት አገሮች በሚኖሩት ሕዝቦች የተነሳ ፍርሃት አድሮባቸው+ የነበረ ቢሆንም መሠዊያውን በቀድሞ ቦታው ላይ ሠሩት፤ በላዩም ላይ ለይሖዋ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን ይኸውም ጠዋትና ማታ የሚቀርቡትን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ማቅረብ ጀመሩ።+ +4 ከዚያም በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት የዳስ* በዓልን አከበሩ፤+ እንዲሁም በእያንዳንዱ ቀን እንዲቀርብ በታዘዘው መጠን መሠረት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን አቀረቡ።+ +5 ከዚያም የተለመደውን የሚቃጠል መባ፣+ ለአዲስ ጨረቃና+ ለተቀደሱት የይሖዋ በዓላት+ የሚቀርቡትን መባዎች እንዲሁም እያንዳንዱ ሰው ለይሖዋ የሚያቀርበውን የፈቃደኝነት መባ+ አቀረቡ። +6 የይሖዋ ቤተ መቅደስ መሠረት ገና ያልተጣለ ቢሆንም ከሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን+ አንስቶ ለይሖዋ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን ማቅረብ ጀመሩ። +7 ለድንጋይ ጠራቢዎቹና+ ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹም+ ገንዘብ ሰጡ፤ በተጨማሪም የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ+ በሰጣቸው ፈቃድ መሠረት የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎችን ከሊባኖስ ወደ ኢዮጴ+ ወደብ ለሚያመጡ ለሲዶና እና ለጢሮስ ሰዎች የሚበላና የሚጠጣ ነገር እንዲሁም ዘይት ሰጡ። +8 በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እውነተኛው አምላክ ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የየሆጼዴቅ ልጅ የሹዋ እንዲሁም ካህናቱን፣ ሌዋውያኑንና ከምርኮ ወጥተው ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱትን+ በሙሉ ጨምሮ የቀሩት ወንድሞቻቸው ሥራውን ጀመሩ፤ የይሖዋን ቤት ሥራ በበላይነት እንዲ +9 በመሆኑም የሹዋ፣ ወንዶች ልጆቹና ወንድሞቹ፣ ቃድሚኤልና ወንዶች ልጆቹ እንዲሁም የይሁዳ ወንዶ�� ልጆች ሌዋውያን ከሆኑት የሄናዳድ+ ወንዶች ልጆች፣ ከእነሱ ወንዶች ልጆችና ከወንድሞቻቸው ጋር ሆነው በእውነተኛው አምላክ ቤት ውስጥ ሥራውን የሚሠሩትን ሰዎች በበላይነት ለመቆጣጠር ተባበሩ። +10 የይሖዋን ቤተ መቅደስ የሚገነቡት ሰዎች መሠረቱን ሲጥሉ+ የክህነት ልብሳቸውን የለበሱት ካህናት በመለከት፣+ ሌዋውያኑ የአሳፍ ወንዶች ልጆች ደግሞ በሲምባል* የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት ይሖዋን ለማወደስ ተነሱ።+ +11 “እሱ ጥሩ ነውና፤ ለእስራኤል የሚያሳየውም ታማኝ ፍቅር ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና”+ በማለት እየተቀባበሉ+ ይሖዋን ማወደስና ማመስገን ጀመሩ። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ የይሖዋ ቤት መሠረት በመጣሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይሖዋን አወደሰ። +12 የቀድሞውን ቤት ያዩ ሽማግሌዎች ይኸውም ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑና ከአባቶች ቤት መሪዎች መካከል አብዛኞቹ የዚህ ቤት መሠረት ሲጣል ሲያዩ+ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ብዙዎቹ ግን በደስታ እልልታቸውን አቀለጡት።+ +13 ሕዝቡ ድምፁ ከሩቅ እስኪሰማ ድረስ ከፍ ባለ ድምፅ ይጮኽ ስለነበር ሰዎቹ የደስታውን እልልታ ከለቅሶው ጩኸት መለየት አልቻሉም ነበር። +7 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ በፋርሱ ንጉሥ በአርጤክስስ+ የግዛት ዘመን ዕዝራ*+ ከባቢሎን ተመለሰ። ዕዝራ የሰራያህ+ ልጅ፣ ሰራያህ የአዛርያስ ልጅ፣ አዛርያስ የኬልቅያስ+ ልጅ፣ +2 ኬልቅያስ የሻሉም ልጅ፣ ሻሉም የሳዶቅ ልጅ፣ ሳዶቅ የአኪጡብ ልጅ፣ +3 አኪጡብ የአማርያህ ልጅ፣ አማርያህ የአዛርያስ+ ልጅ፣ አዛርያስ የመራዮት ልጅ፣ +4 መራዮት የዘራህያህ ልጅ፣ ዘራህያህ የዑዚ ልጅ፣ ዑዚ የቡቂ ልጅ፣ +5 ቡቂ የአቢሹዓ ልጅ፣ አቢሹዓ የፊንሃስ+ ልጅ፣ ፊንሃስ የአልዓዛር+ ልጅ፣ አልዓዛር የካህናት አለቃ የሆነው የአሮን+ ልጅ ነበር። +6 ይህ ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ። እሱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ የሰጠውን የሙሴን ሕግ ጠንቅቆ የሚያውቅ ገልባጭ* ነበር።*+ የአምላኩ የይሖዋ እጅ በእሱ ላይ ስለነበር ንጉሡ የጠየቀውን ሁሉ ሰጠው። +7 ንጉሥ አርጤክስስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ከእስራኤላውያን፣ ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ፣+ ከዘማሪዎቹ፣+ ከበር ጠባቂዎቹና+ ከቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ*+ መካከል የተወሰኑት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ። +8 ዕዝራም ንጉሡ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ኢየሩሳሌም ደረሰ። +9 በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከባቢሎን ተነስቶ ጉዞ ጀመረ፤ መልካም የሆነው የአምላኩ እጅ በእሱ ላይ ስለነበር+ በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ኢየሩሳሌም ደረሰ። +10 ዕዝራ የይሖዋን ሕግ ለመመርመርና ተግባራዊ ለማድረግ+ እንዲሁም ሥርዓቱንና ፍርዱን በእስራኤል ውስጥ ለማስተማር+ ልቡን አዘጋጅቶ* ነበር። +11 ንጉሥ አርጤክስስ የይሖዋን ትእዛዛትና ለእስራኤላውያን ያወጣቸውን ሥርዓቶች በማጥናት ለተካነውና* ገልባጭ* ለሆነው ለካህኑ ዕዝራ የሰጠው ደብዳቤ ቅጂ ይህ ነው፦ +12 * “ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ፣+ የሰማይ አምላክ ሕግ ገልባጭ* ለሆነው ለካህኑ ዕዝራ፦ ሰላም ለአንተ ይሁን። እንግዲህ +13 በግዛቴ ውስጥ ካሉ የእስራኤል ሕዝቦች እንዲሁም ከእነሱ ካህናትና ሌዋውያን መካከል ከአንተ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ እንዲሄድ ትእዛዝ ሰጥቻለሁ።+ +14 ንጉሡና ሰባቱ አማካሪዎቹ በእጅህ የሚገኘው የአምላክህ ሕግ በይሁዳና በኢየሩሳሌም በተግባር ላይ እየዋለ እንደሆነና እንዳልሆነ እንድትመረምር ልከውሃል፤ +15 እንዲሁም ንጉሡና አማካሪዎቹ በኢየሩሳሌም ለሚኖረው ለእስራኤል አምላክ በፈቃደኝነት የሰጡትን ብርና ወርቅ፣ +16 ከመላው የባቢሎን አውራጃ ከተቀበልከው* ብርና ወርቅ እንዲሁም ሕዝቡና ካህናቱ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው ለአምላካቸው ቤት በፈቃደኝነት ከሰጡት ስጦታ ጋር ይዘህ እንድትሄድ አዘዋል።+ +17 በዚህም ገንዘብ ሳትዘገይ በሬዎችን፣+ አውራ በጎችንና+ የበግ ጠቦቶችን+ ከእህል መባዎቻቸውና+ ከመጠጥ መባዎቻቸው+ ጋር ግዛ፤ እነዚህንም በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላካችሁ ቤት መሠዊያ ላይ አቅርባቸው። +18 “በተረፈው ብርና ወርቅ እንደ አምላካችሁ ፈቃድ አንተም ሆንክ ወንድሞችህ መልካም መስሎ የታያችሁን አድርጉበት። +19 በአምላክህ ቤት ለሚቀርበው አገልግሎት እንዲሆኑ የተሰጡህን ዕቃዎች በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ወስደህ በአምላክ ፊት ታስቀምጣቸዋለህ።+ +20 ለአምላክህ ቤት መስጠት የሚጠበቅብህን ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ከንጉሡ ግምጃ ቤት አውጥተህ ትሰጣለህ።+ +21 “እኔ ንጉሥ አርጤክስስ ከወንዙ ባሻገር* ባለው ክልል የምትገኙትን የግምጃ ቤት ኃላፊዎች በሙሉ የሰማይ አምላክ ሕግ ገልባጭ* የሆነው ካህኑ ዕዝራ+ የጠየቃችሁን ነገር ሁሉ በአስቸኳይ እንድትፈጽሙለት ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤ +22 እንዲሁም እስከ 100 ታላንት* ብር፣ እስከ 100 የቆሮስ* መስፈሪያ ስንዴ፣ እስከ 100 የባዶስ* መስፈሪያ የወይን ጠጅና+ እስከ 100 የባዶስ መስፈሪያ ዘይት+ ድረስ ስጡት፤ እንዲሁም የፈለገውን ያህል ጨው+ ስጡት። +23 በንጉሡ ግዛትና በልጆቹ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ+ የሰማይ አምላክ፣ የሰማይን አምላክ ቤት አስመልክቶ ያዘዘው ሁሉ በትጋት ይፈጸም።+ +24 በተጨማሪም ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ፣ ከሙዚቀኞቹ፣+ ከበር ጠባቂዎቹ፣ ከቤተ መቅደስ አገልጋዮቹም*+ ሆነ ይህን የአምላክ ቤት ከሚሠሩት ሰዎች መካከል በአንዳቸውም ላይ ምንም ዓይነት ቀረጥ፣ ግብር+ ወይም የኬላ ቀረጥ መጣል እንደማትችሉ እወቁ። +25 “አንተም ዕዝራ፣ አምላክህ የሰጠህን ጥበብ* ተጠቅመህ ከወንዙ ባሻገር ባለው ክልል ለሚኖሩት ሕዝቦች በሙሉ፣ የአምላክህን ሕጎች ለሚያውቁ ሁሉ ፍርድ የሚሰጡ ሕግ አስከባሪዎችንና ዳኞችን ሹም፤ ሕጎቹን የማያውቅ ሰው ካለም አስተምሩት።+ +26 እንዲሁም የአምላክህን ሕግና የንጉሡን ሕግ የማያከብር ማንኛውም ሰው ቅጣቱ ሞትም ይሁን ከአገር መባረር ወይም ገንዘብ አሊያም እስራት አፋጣኝ የፍርድ እርምጃ ይወሰድበት።” +27 እንዲህ ያለውን ነገር ይኸውም በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የይሖዋን ቤት የማስዋቡን ሐሳብ በንጉሡ ልብ ውስጥ ያኖረው የአባቶቻችን አምላክ ይሖዋ ይወደስ!+ +28 በንጉሡና+ በአማካሪዎቹ+ እንዲሁም ኃያላን በሆኑት የንጉሡ መኳንንት ሁሉ ፊት ታማኝ ፍቅር አሳይቶኛል። በመሆኑም የአምላኬ የይሖዋ እጅ በላዬ ስለነበር ድፍረት አገኘሁ፤* ከእኔም ጋር አብረው እንዲሄዱ ከእስራኤል መካከል መሪ* የሆኑትን ሰበሰብኩ። +1 በኤርምያስ በኩል የተነገረው የይሖዋ ቃል ይፈጸም ዘንድ+ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ+ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት የሚከተለውን አዋጅ በመላ ግዛቱ እንዲያውጅ ይሖዋ የፋርሱን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሳሳ፤ እሱም ይህ በጽሑፍ እንዲሰፍር አደረገ፦+ +2 “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማይ አምላክ ይሖዋ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤+ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌምም ቤት እንድሠራለት አዞኛል።+ +3 ከእሱ ሕዝብ መካከል የሆነ አብሯችሁ የሚኖር ማንኛውም ሰው አምላኩ ከእሱ ጋር ይሁን፤ እሱም በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፤ ቤቱ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን* የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ቤትም መልሶ ይገንባ፤ እሱ እውነተኛ አምላክ ነው። +4 በየትኛውም ስፍራ የባዕድ አገር ሰው ሆኖ የሚኖረውን+ ማንኛውንም ሰው፣ ጎረቤቶቹ* በኢየሩሳሌም ለነበረው ለእውነተኛው አምላክ ቤት ከሚቀርበው የፈቃደኝነት መባ+ በተጨማሪ ብር፣ ወርቅ፣ የተለያዩ ዕቃዎችና የቤት እንስሳት በመስጠት ይርዱት።’” +5 ከዚያም የይሁዳና የቢንያም የአባቶች ቤት መሪዎች፣ ካህናቱና ሌዋውያኑ፣ እውነተኛው አምላክ መንፈሳቸውን ያነሳሳው ሰዎች ሁሉ ወጥተው በኢየሩሳሌም የነበረውን የይሖዋን ቤት መልሰው ለመገንባት ተዘጋጁ። +6 በዙሪያቸው ያሉትም ሁሉ በፈቃደኝነት ከተሰጠው መባ በተጨማሪ የብርና የወርቅ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ ዕቃዎችን፣ የቤት እንስሳትን እንዲሁም ውድ የሆኑ ነገሮችን በመስጠት ረዷቸው።* +7 በተጨማሪም ንጉሥ ቂሮስ፣ ናቡከደነጾር ከኢየሩሳሌም ወስዶ በአምላኩ ቤት ያስቀመጣቸውን የይሖዋን ቤት ዕቃዎች አወጣ።+ +8 የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ በግምጃ ቤቱ ኃላፊ በሚትረዳት ተቆጣጣሪነት ዕቃዎቹ እንዲወጡ አደረገ፤ ሚትረዳትም ለይሁዳው አለቃ ለሸሽባጻር*+ ቆጥሮ አስረከበው። +"9 የተቆጠሩት ዕቃዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ በቅርጫት ቅርጽ የተሠሩ 30 የወርቅ ዕቃዎች፣ በቅርጫት ቅርጽ የተሠሩ 1,000 የብር ዕቃዎችና 29 ምትክ ዕቃዎች" +"10 እንዲሁም 30 ትናንሽ ጎድጓዳ የወርቅ ሳህኖች፣ 410 አነስተኛ ጎድጓዳ የብር ሳህኖችና 1,000 ሌሎች ዕቃዎች።" +"11 የወርቅና የብር ዕቃዎቹ በአጠቃላይ 5,400 ነበሩ። ሸሽባጻርም ግዞተኞቹ+ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ይዞ ወጣ።" +8 በንጉሥ አርጤክስስ+ የግዛት ዘመን ከባቢሎን አብረውኝ የወጡት የአባቶች ቤት መሪዎች የዘር ሐረግ ዝርዝር ይህ ነው፦ +2 ከፊንሃስ+ ልጆች ጌርሳም፣ ከኢታምር+ ልጆች ዳንኤል፣ ከዳዊት ልጆች ሃጡሽ፣ +3 ከሸካንያህ ልጆች፣ ከፓሮሽ ልጆች ዘካርያስ እንዲሁም ከእሱ ጋር የተመዘገቡ 150 ወንዶች ነበሩ፤ +4 ከፓሃትሞአብ+ ልጆች የዘራህያህ ልጅ የሆነው ኤሊየሆዔናይ እንዲሁም ከእሱ ጋር 200 ወንዶች፣ +5 ከዛቱ+ ልጆች የያሃዚኤል ልጅ የሆነው ሸካንያህ እንዲሁም ከእሱ ጋር 300 ወንዶች፣ +6 ከአዲን+ ልጆች የዮናታን ልጅ የሆነው ኤቤድ እንዲሁም ከእሱ ጋር 50 ወንዶች፣ +7 ከኤላም+ ልጆች የጎቶልያ ልጅ የሆነው የሻያህ እንዲሁም ከእሱ ጋር 70 ወንዶች፣ +8 ከሰፋጥያህ+ ልጆች የሚካኤል ልጅ የሆነው ዘባድያህ እንዲሁም ከእሱ ጋር 80 ወንዶች፣ +9 ከኢዮዓብ ልጆች የየሂኤል ልጅ የሆነው አብድዩ እንዲሁም ከእሱ ጋር 218 ወንዶች፣ +10 ከባኒ ልጆች የዮሲፍያህ ልጅ የሆነው ሸሎሚት እንዲሁም ከእሱ ጋር 160 ወንዶች፣ +11 ከቤባይ+ ልጆች የቤባይ ልጅ የሆነው ዘካርያስ እንዲሁም ከእሱ ጋር 28 ወንዶች፣ +12 ከአዝጋድ+ ልጆች የሃቃጣን ልጅ የሆነው ዮሃናን እንዲሁም ከእሱ ጋር 110 ወንዶች፣ +13 ከአዶኒቃም+ ልጆች የመጨረሻዎቹ የሆኑት ስማቸው ኤሊፌሌት፣ የኢዔልና ሸማያህ ሲሆን ከእነሱም ጋር 60 ወንዶች፤ +14 ከቢግዋይ+ ልጆች ዑታይና ዛቡድ እንዲሁም ከእነሱ ጋር 70 ወንዶች። +15 እኔም ወደ አሃዋ+ በሚፈሰው ወንዝ አጠገብ ሰበሰብኳቸው፤ በዚያም ለሦስት ቀን ሰፈርን። ሆኖም ሕዝቡንና ካህናቱን ልብ ብዬ ስመለከት ከሌዋውያን መካከል ማንንም በዚያ አላገኘሁም። +16 በመሆኑም መሪዎች ለሆኑት ለኤሊዔዘር፣ ለአርዔል፣ ለሸማያህ፣ ለኤልናታን፣ ለያሪብ፣ ለኤልናታን፣ ለናታን፣ ለዘካርያስና ለመሹላም እንዲሁም ለአስተማሪዎቹ ለዮያሪብና ለኤልናታን መልእክት ላክሁባቸው። +17 ከዚያም ካሲፍያ በተባለው ቦታ መሪ ወደሆነው ወደ ኢዶ እንዲሄዱ አዘዝኳቸው። ኢዶንና በካሲፍያ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች* የሆኑትን ወንድሞቹን በአምላካችን ቤት የሚያገለግሉ ሰዎችን ያመጡልን ዘንድ እንዲጠይቋቸው ነገርኳቸው። +18 መልካም የሆነው የአምላካችን እጅ በእኛ ላይ ስለነበር የእስራኤል ልጅ የሌዊ የልጅ ልጅ ከሆነው ከማህሊ+ ልጆች መካከል አስተዋይ የሆነውን ሸረበያህን፣+ ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን በአጠቃላይ 18 ሰዎችን አመጡልን፤ +19 እንዲሁም ሃሻብያህንና ከእሱም ጋር ከሜራራውያን+ መካከል የሻያህን፣ ወንድሞቹንና ወንዶች ልጆቻቸውን በአጠቃላይ 20 ሰዎችን አመጡልን። +20 በተጨማሪም ከቤተ መቅደሱ አገልጋዮች* መካከል ዳዊትና መኳንንቱ ሌዋውያኑ ለሚያቀርቡት አገልግሎት የሰጧቸው 220 ሰዎች ነበሩ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዝግበው ነበር። +21 ከዚያም ራሳችንን በአምላካችን ፊት ለማዋረድ እንዲሁም በጉዟችን ወቅት ለእኛም ሆነ ለልጆቻችንና ለንብረቶቻችን በሙሉ የሚሆን መመሪያ ከእሱ ለማግኘት እዚያው በአሃዋ ወንዝ ጾም አወጅኩ። +22 “መልካም የሆነው የአምላካችን እጅ እሱን በሚሹት ሁሉ ላይ ነው፤+ እሱን በሚተዉት ሁሉ ላይ ግን ኃይሉንና ቁጣውን ይገልጣል”+ በማለት ለንጉሡ ነግረነው ስለነበር በጉዟችን ላይ ከሚያጋጥሙን ጠላቶች የሚጠብቁን ወታደሮችና ፈረሰኞች እንዲሰጠን ንጉሡን መጠየቅ አፈርኩ። +23 ስለሆነም ጾምን፤ ይህን በተመለከተም ለአምላካችን ልመና አቀረብን፤ እሱም ልመናችንን ሰማ።+ +24 እኔም ከዋነኞቹ ካህናት መካከል 12ቱን ይኸውም ሸረበያህንና ሃሻብያህን+ እንዲሁም አሥር ወንድሞቻቸውን ለየሁ። +25 ከዚያም ንጉሡ፣ አማካሪዎቹና መኳንንቱ እንዲሁም በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን በሙሉ ለአምላካችን ቤት የሰጡትን መዋጮ ማለትም ብሩን፣ ወርቁንና ዕቃዎቹን መዘንኩላቸው።+ +26 የሚከተሉትንም ዕቃዎች መዝኜ ሰጠኋቸው፦ 650 ታላንት* ብር፣ 2 ታላንት የሚመዝኑ 100 የብር ዕቃዎች፣ 100 ታላንት ወርቅ +"27 እንዲሁም 1,000 ዳሪክ* የሚመዝኑ 20 ትናንሽ ጎድጓዳ የወርቅ ሳህኖችና የወርቅ ያህል ተፈላጊ የሆኑ ከሚያብረቀርቅ ጥሩ መዳብ የተሠሩ 2 ዕቃዎች። " +28 ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ “እናንተ ለይሖዋ የተቀደሳችሁ ናችሁ፤+ ዕቃዎቹም የተቀደሱ ናቸው፤ ብሩና ወርቁ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለይሖዋ የቀረበ የፈቃደኝነት መባ ነው። +29 በኢየሩሳሌም በሚገኙት በይሖዋ ቤት ክፍሎች* ውስጥ በዋነኞቹ ካህናትና ሌዋውያን እንዲሁም በእስራኤል የአባቶች ቤት መኳንንት ፊት እስክትመዝኗቸው ድረስ በጥንቃቄ ጠብቋቸው።”+ +30 ካህናቱና ሌዋውያኑም የተመዘነላቸውን ብር፣ ወርቅና ዕቃ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ አምላካችን ቤት ለመውሰድ ተረከቡ። +31 በኋላም በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ12ኛው ቀን+ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ከአሃዋ+ ወንዝ ተነሳን፤ የአምላካችንም እጅ በላያችን ነበር፤ እሱም በመንገድ ላይ ከጠላት እጅና ከሽምቅ ጥቃት ታደገን። +32 ወደ ኢየሩሳሌም+ መጥተን በዚያ ለሦስት ቀን ተቀመጥን። +33 በአራተኛውም ቀን ብሩን፣ ወርቁንና ዕቃዎቹን በአምላካችን ቤት+ መዝነን ለዑሪያህ ልጅ ለካህኑ ለመሬሞት+ አስረከብነው፤ ከእሱም ጋር የፊንሃስ ልጅ አልዓዛር እንዲሁም ሌዋውያን የሆኑት የየሹዋ ልጅ ዮዛባድና+ የቢኑይ+ ልጅ ኖአድያህ ነበሩ። +34 እያንዳንዱም ነገር ተቆጥሮ ተመዘነ፤ ክብደቱም ሁሉ ተመዘገበ። +35 በግዞት ተወስደው የነበሩት ከምርኮ ነፃ የወጡ ሰዎች ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን አቀረቡ፤ ለመላው እስራኤል 12 በሬዎችን፣+ 96 አውራ በጎችን፣+ 77 ተባዕት የበግ ጠቦቶችንና 12 ተባዕት ፍየሎችን+ የኃጢአት መባ አድርገው አቀረቡ፤ ይህ ሁሉ ለይሖዋ የቀረበ የሚቃጠል መባ ነበር።+ +36 ከዚያም ንጉሡ ያወጣቸውን ድንጋጌዎች+ ለንጉሡ የአውራጃ ገዢዎችና* ከወንዙ+ ባሻገር* ባለው ክልል ለሚገኙት ገዢዎች ሰጠናቸው፤ እነሱም ለሕዝቡና ለእውነተኛው አምላክ ቤት ድጋፍ ሰጡ።+ +2 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ወደ ባቢሎን በግዞት ወስዷቸው+ የነበሩትና ተማርከው በግዞት ከተወሰዱት+ መካከል ወጥተው በኋላ ላይ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ይኸውም ወደየከተሞቻቸው የተመለሱት የአውራጃው ነዋሪዎች እነዚህ ና��ው፤+ +2 ከዘሩባቤል፣+ ከየሆሹዋ፣+ ከነህምያ፣ ከሰራያህ፣ ከረኤላያህ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከቢልሻን፣ ከሚስጳር፣ ከቢግዋይ፣ ከረሁምና ከባአናህ ጋር የመጡት እነዚህ ናቸው። የእስራኤላውያን ወንዶች ቁጥር የሚከተሉትንም ይጨምራል፦+ +"3 የፓሮሽ ወንዶች ልጆች 2,172፣" +4 የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች 372፣ +5 የኤራ+ ወንዶች ልጆች 775፣ +"6 የየሹዋና የኢዮዓብ ወንዶች ልጆች የሆኑት የፓሃትሞአብ+ ወንዶች ልጆች 2,812፣" +"7 የኤላም ወንዶች ልጆች+ 1,254፣" +8 የዛቱ ወንዶች ልጆች+ 945፣ +9 የዛካይ ወንዶች ልጆች 760፣ +10 የባኒ ወንዶች ልጆች 642፣ +11 የቤባይ ወንዶች ልጆች 623፣ +"12 የአዝጋድ ወንዶች ልጆች 1,222፣" +13 የአዶኒቃም ወንዶች ልጆች 666፣ +"14 የቢግዋይ ወንዶች ልጆች 2,056፣" +15 የአዲን ወንዶች ልጆች 454፣ +16 የሕዝቅያስ ልጅ የአጤር ወንዶች ልጆች 98፣ +17 የቤጻይ ወንዶች ልጆች 323፣ +18 የዮራ ወንዶች ልጆች 112፣ +19 የሃሹም ወንዶች ልጆች+ 223፣ +20 የጊባር ወንዶች ልጆች 95፣ +21 የቤተልሔም ወንዶች ልጆች 123፣ +22 የነጦፋ ወንዶች ልጆች 56፣ +23 የአናቶት+ ሰዎች 128፣ +24 የአዝማዌት ወንዶች ልጆች 42፣ +25 የቂርያትየአሪም፣ የከፊራና የበኤሮት ወንዶች ልጆች 743፣ +26 የራማና+ የጌባ+ ወንዶች ልጆች 621፣ +27 የሚክማስ ሰዎች 122፣ +28 የቤቴልና የጋይ+ ሰዎች 223፣ +29 የነቦ ወንዶች ልጆች+ 52፣ +30 የማግቢሽ ወንዶች ልጆች 156፣ +"31 የሌላኛው ኤላም ወንዶች ልጆች 1,254፣" +32 የሃሪም ወንዶች ልጆች 320፣ +33 የሎድ፣ የሃዲድና የኦኖ ወንዶች ልጆች 725፣ +34 የኢያሪኮ ወንዶች ልጆች 345፣ +"35 የሰናአ ወንዶች ልጆች 3,630። " +36 ካህናቱ+ የሚከተሉት ናቸው፦ ከየሹዋ+ ቤተሰብ የሆነው የየዳያህ+ ወንዶች ልጆች 973፣ +"37 የኢሜር+ ወንዶች ልጆች 1,052፣" +"38 የጳስኮር+ ወንዶች ልጆች 1,247፣" +"39 የሃሪም+ ወንዶች ልጆች 1,017። " +40 ሌዋውያኑ+ የሚከተሉት ናቸው፦ የሆዳውያህ ወንዶች ልጆች የሆኑት የየሹዋና የቃድሚኤል+ ወንዶች ልጆች 74። +41 ዘማሪዎቹ+ የአሳፍ+ ወንዶች ልጆች 128። +42 የበር ጠባቂዎቹ+ ወንዶች ልጆች የሆኑት የሻሉም ወንዶች ልጆች፣ የአጤር ወንዶች ልጆች፣ የታልሞን+ ወንዶች ልጆች፣ የአቁብ+ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢጣ ወንዶች ልጆችና የሾባይ ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 139። +43 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች*+ የሚከተሉት ናቸው፦ የጺሃ ወንዶች ልጆች፣ የሃሱፋ ወንዶች ልጆች፣ የታባኦት ወንዶች ልጆች፣ +44 የቀሮስ ወንዶች ልጆች፣ የሲአ ወንዶች ልጆች፣ የፓዶን ወንዶች ልጆች፣ +45 የለባና ወንዶች ልጆች፣ የሃጋባ ወንዶች ልጆች፣ የአቁብ ወንዶች ልጆች፣ +46 የሃጋብ ወንዶች ልጆች፣ የሳልማይ ወንዶች ልጆች፣ የሃናን ወንዶች ልጆች፣ +47 የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ የጋሃር ወንዶች ልጆች፣ የረአያህ ወንዶች ልጆች፣ +48 የረጺን ወንዶች ልጆች፣ የነቆዳ ወንዶች ልጆች፣ የጋዛም ወንዶች ልጆች፣ +49 የዑዛ ወንዶች ልጆች፣ የፓሰአህ ወንዶች ልጆች፣ የቤሳይ ወንዶች ልጆች፣ +50 የአስና ወንዶች ልጆች፣ የመኡኒም ወንዶች ልጆች፣ የነፉሲም ወንዶች ልጆች፣ +51 የባቅቡቅ ወንዶች ልጆች፣ የሃቁፋ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሑር ወንዶች ልጆች፣ +52 የባጽሉት ወንዶች ልጆች፣ የመሂዳ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሻ ወንዶች ልጆች፣ +53 የባርቆስ ወንዶች ልጆች፣ የሲሳራ ወንዶች ልጆች፣ የተማ ወንዶች ልጆች፣ +54 የነጺሃ ወንዶች ልጆችና የሃጢፋ ወንዶች ልጆች። +55 የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ የሶጣይ ወንዶች ልጆች፣ የሶፈረት ወንዶች ልጆች፣ የፐሩዳ+ ወንዶች ልጆች፣ +56 የያላ ወንዶች ልጆች፣ የዳርቆን ወንዶች ልጆች፣ የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ +57 የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢል ወንዶች ልጆች፣ የፖክሄሬትሃጸባይም ወንዶች ልጆችና የአሚ ወንዶች ልጆች። +58 የቤተ ���ቅደሱ አገልጋዮችና* የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 392 ነበሩ። +59 ከቴልመላ፣ ከቴልሃርሻ፣ ከከሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የወጡት ሆኖም ከየትኛው የአባቶች ቤትና የዘር ሐረግ እንደመጡ በውል መለየትም ሆነ እስራኤላዊ መሆን አለመሆናቸውን በትክክል ማረጋገጥ ያልቻሉት የሚከተሉት ናቸው፦+ +60 የደላያህ ወንዶች ልጆች፣ የጦብያ ወንዶች ልጆችና የነቆዳ ወንዶች ልጆች 652። +61 ከካህናቱ ወንዶች ልጆች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የሃባያ ወንዶች ልጆች፣ የሃቆጽ+ ወንዶች ልጆች እንዲሁም ከጊልያዳዊው ከቤርዜሊ ሴቶች ልጆች መካከል አንዷን ያገባውና በስማቸው የተጠራው የቤርዜሊ+ ወንዶች ልጆች። +62 እነዚህ የዘር ሐረጋቸውን ለማረጋገጥ በመዝገቡ ላይ የቤተሰባቸውን ስም ለማግኘት ቢጥሩም ሊያገኙት አልቻሉም፤ በመሆኑም ከክህነት አገልግሎቱ ታገዱ።*+ +63 ገዢውም* በኡሪምና ቱሚም+ አማካኝነት ምክር የሚጠይቅ ካህን እስኪገኝ ድረስ እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት እንደማይችሉ ነገራቸው።+ +"64 መላው ጉባኤ በአጠቃላይ 42,360 ነበር፤+" +"65 ይህ 7,337 ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን አይጨምርም፤ በተጨማሪም 200 ወንድና ሴት ዘማሪዎች ነበሯቸው።" +66 ከዚህም ሌላ 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች +"67 እንዲሁም 435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው። " +68 ከአባቶች ቤት መሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ኢየሩሳሌም ወደነበረው ወደ ይሖዋ ቤት ሲደርሱ ቤቱን በቀድሞ ቦታው ላይ መልሶ ለመገንባት+ ለእውነተኛው አምላክ ቤት የፈቃደኝነት መባዎችን አቀረቡ።+ +"69 እነሱም ለሥራው ማስኬጃ እንዲሆን እንደየአቅማቸው 61,000 የወርቅ ድራክማ፣* 5,000 የብር ምናን*+ እና 100 የካህናት ቀሚስ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።" +70 ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ፣ ዘማሪዎቹ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ* በየከተሞቻቸው ሰፈሩ፤ የቀሩትም እስራኤላውያን በሙሉ በየከተሞቻቸው መኖር ጀመሩ።+ +4 የይሁዳና የቢንያም ጠላቶች፣+ ከግዞት የተመለሱት ሰዎች+ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ቤተ መቅደስ እየገነቡ መሆናቸውን ሲሰሙ +2 ወዲያውኑ ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች ቤት መሪዎች ቀርበው እንዲህ አሏቸው፦ “ከእናንተ ጋር እንገንባ፤ ልክ እንደ እናንተ እኛም አምላካችሁን እናመልካለን፤*+ ደግሞም ወደዚህ ካመጣን ከአሦር ንጉሥ ከኤሳርሃደን+ ዘመን ጀምሮ ለእሱ መሥዋዕት ስናቀርብ ኖረናል።”+ +3 ይሁንና ዘሩባቤል፣ የሆሹዋና የቀሩት የእስራኤል አባቶች ቤት መሪዎች እንዲህ አሏቸው፦ “የአምላካችንን ቤት በመገንባቱ ሥራ ከእኛ ጋር ተካፋይ መሆን አትችሉም፤+ ምክንያቱም የፋርሱ ንጉሥ፣ ንጉሥ ቂሮስ ባዘዘን መሠረት እኛው ራሳችን የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ቤት እንገነባለን።”+ +4 የምድሪቱም ነዋሪዎች የይሁዳን ሕዝቦች ተስፋ ለማስቆረጥና* ወኔ ከድቷቸው የግንባታ ሥራውን እንዲያቆሙ ለማድረግ ዘወትር ይጥሩ ነበር።+ +5 ከፋርሱ ንጉሥ ከቂሮስ ዘመን አንስቶ እስከ ፋርሱ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ+ የግዛት ዘመን ድረስ እቅዶቻቸውን ለማጨናገፍ አማካሪዎችን ቀጠሩባቸው።+ +6 በተጨማሪም በአሐሽዌሮስ የግዛት ዘመን መጀመሪያ ላይ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ በጽሑፍ ክስ መሠረቱባቸው። +7 ከዚህም ሌላ በፋርስ ንጉሥ በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፣ ሚትረዳት፣ ታብኤልና የቀሩት ግብረ አበሮቹ ለንጉሥ አርጤክስስ ደብዳቤ ጻፉ፤ ደብዳቤውንም ወደ አረማይክ ቋንቋ+ ተርጉመው በአረማይክ ፊደል ጻፉት።* +8 * ዋናው የመንግሥት ባለሥልጣን ረሁም እና ጸሐፊው ሺምሻይ ኢየሩሳሌምን በመክሰስ ለንጉሥ አርጤክስስ የሚከተለውን ደብዳቤ ጻፉ፦ +9 (ደብዳቤውን የላኩት ዋናው የመንግሥት ባለሥልጣን ረሁም፣ ጸሐፊው ሺ���ሻይና የቀሩት ግብረ አበሮቻቸው እንዲሁም ዳኞቹ፣ የበታች ገዢዎቹ፣ ጸሐፊዎቹ፣ የኤሬክ+ ሕዝቦች፣ ባቢሎናውያን፣ የሱሳ+ ነዋሪዎች ማለትም ኤላማውያን፣+ +10 ታላቁና የተከበረው አስናፈር በግዞት ወስዶ በሰማርያ ከተሞች ያሰፈራቸው+ የቀሩት ብሔራትና ከወንዙ ባሻገር* ባለው ክልል የሚኖሩት የቀሩት ሰዎች ነበሩ፤ እንግዲህ +11 የላኩለት ደብዳቤ ቅጂ ይህ ነው።) “ለንጉሥ አርጤክስስ፣ ከወንዙ ባሻገር ባለው ክልል ከሚኖሩት አገልጋዮችህ፦ እንግዲህ +12 ከአንተ ዘንድ ወደዚህ ወደ እኛ የመጡት አይሁዳውያን ኢየሩሳሌም መድረሳቸውን ንጉሡ ይወቅ። እነዚህ ሰዎች ዓመፀኛና ክፉ የሆነችውን ከተማ መልሰው እየገነቡ ነው፤ ቅጥሮቿን ሠርተው እየጨረሱ+ ሲሆን መሠረቶቿንም እየጠገኑ ነው። +13 ከተማዋ ተመልሳ ከተገነባችና ቅጥሮቿም ተሠርተው ከተጠናቀቁ እነዚህ ሰዎች ቀረጥም ሆነ ግብር+ ወይም የኬላ ቀረጥ እንደማይከፍሉ፣ በዚህም የተነሳ ወደ ነገሥታቱ ግምጃ ቤት የሚገባው ገቢ እንደሚቀንስ ንጉሡ ይወቅ። +14 እኛ ደግሞ የቤተ መንግሥቱን ጨው እየበላን* የንጉሡ ጥቅም ሲነካ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ መስሎ አልታየንም፤ በመሆኑም ንጉሡ ጉዳዩን እንዲያውቀው ለማድረግ ይህን ደብዳቤ ልከናል፤ +15 ስለዚህ የቀድሞ አባቶችህ መዝገብ ይመርመር።+ ይህች ከተማ ዓመፀኛና ነገሥታትንም ሆነ አውራጃዎችን ጉዳት ላይ የምትጥል፣ ከጥንት ጀምሮም ዓመፅ ቆስቋሾችን ሸሽጋ የምታኖር መሆኗን ከእነዚህ መዛግብት መረዳት ትችላለህ። ከተማዋም የተደመሰሰችው በዚህ የተነሳ ነው።+ +16 ይህች ከተማ ተመልሳ ከተገነባችና ቅጥሮቿም ተሠርተው ከተጠናቀቁ ከወንዙ+ ባሻገር ያለውን ክልል መቆጣጠር እንደማትችል* ልናሳውቅህ እንፈልጋለን።” +17 ንጉሡም ለዋናው የመንግሥት ባለሥልጣን ለረሁም፣ ለጸሐፊው ለሺምሻይ፣ በሰማርያ ለሚኖሩት ለቀሩት ግብረ አበሮቻቸውና ከወንዙ ባሻገር ላለው ለቀረው ክልል እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “ሰላምታዬ ይድረሳችሁ! እንግዲህ +18 የላካችሁልን ደብዳቤ በፊቴ ግልጽ ሆኖ ተነቧል።* +19 በሰጠሁትም ትእዛዝ መሠረት ምርመራ ተደርጎ ከተማዋ ከጥንት ጀምሮ በነገሥታት ላይ ረብሻ የምትቀሰቅስ እንዲሁም የዓመፅና የወንጀል መፍለቂያ እንደነበረች ተረጋግጧል።+ +20 ኢየሩሳሌም ከወንዙ ባሻገር ያሉትን አካባቢዎች በሙሉ የሚገዙ ኃያላን ነገሥታት ነበሯት፤ እነሱም ቀረጥ፣ ግብርና የኬላ ቀረጥ ይቀበሉ ነበር። +21 እንግዲህ እኔ ትእዛዝ እስከምሰጥ ድረስ ከተማዋ ተመልሳ እንዳትገነባ እነዚህ ሰዎች ሥራውን እንዲያቆሙ ትእዛዝ አስተላልፉ። +22 የነገሥታቱን ጥቅም ይበልጥ የሚጎዳ ነገር እንዳይከሰት ይህን ጉዳይ በተመለከተ እርምጃ ከመውሰድ ቸል እንዳትሉ ተጠንቀቁ።”+ +23 ንጉሥ አርጤክስስ የላከው ደብዳቤ በረሁም፣ በጸሐፊው በሺምሻይና በተባባሪዎቻቸው ፊት ከተነበበ በኋላ ወዲያውኑ በኢየሩሳሌም ወዳሉት አይሁዳውያን በመሄድ አስገድደው ሥራውን አስቆሟቸው። +24 በኢየሩሳሌም የነበረውን የአምላክን ቤት የመገንባቱ ሥራ የተቋረጠው በዚህ ጊዜ ነበር፤ እስከ ፋርሱ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ የንግሥና ዘመን ሁለተኛ ዓመት ድረስም ሥራው ባለበት ቆመ።+ +6 በዚያን ጊዜ ንጉሥ ዳርዮስ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነሱም በባቢሎን የሚገኘውን ውድ ነገሮች የሚቀመጡበትን ግምጃ ቤት* መረመሩ። +2 በሜዶን አውራጃ፣ በኤክባታና* ውስጥ በሚገኘው የተመሸገ ስፍራ አንድ ጥቅልል ተገኘ፤ በላዩም ላይ የሚከተለው መልእክት ተጽፎ ነበር፦ +3 “ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት፣ ንጉሥ ቂሮስ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የአምላክ ቤት አስመልክቶ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጠ፦+ ‘መሥዋዕቶችን በዚያ ማቅረብ እንዲችሉ ቤቱ ተመል��� ይገንባ፤ መሠረቶቹም ይጣሉ፤ ቁመቱ 60 ክንድ፣* ወርዱ 60 ክንድ+ ሆኖ +4 ትላልቅ ድንጋዮችን በሦስት ዙር በመደራረብና በላዩ ላይ አንድ ዙር ሳንቃ በማድረግ ይሠራ፤+ ወጪውም ከንጉሡ ቤት ይከፈል።+ +5 በተጨማሪም ናቡከደነጾር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ አውጥቶ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸው የወርቅና የብር ዕቃዎች ይመለሱ፤+ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ተወስደው በቀድሞ ቦታቸው ላይ ይደረጉ፤ በአምላክም ቤት ውስጥ ይቀመጡ።’+ +6 “አሁንም ከወንዙ ባሻገር* ያለው ክልል ገዢ የሆንከው ታተናይ፣ ሸታርቦዘናይና ከወንዙ ባሻገር የሚገኙ የበታች ገዢዎች የሆኑት ግብረ አበሮቻችሁ ከዚያ ራቁ።+ +7 በአምላክ ቤት ሥራ ጣልቃ አትግቡ። የአይሁዳውያን ገዢዎችና የአይሁዳውያን ሽማግሌዎች ያንን የአምላክ ቤት በቀድሞ ቦታው ላይ መልሰው ይገንቡት። +8 በተጨማሪም እነዚህ የአይሁዳውያን ሽማግሌዎች ያን የአምላክ ቤት መልሰው ሲገነቡ ልታደርጉላቸው የሚገባውን ነገር በተመለከተ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፦ ሥራው እንዳይስተጓጎል ከንጉሡ ግምጃ ቤት+ ይኸውም ከወንዙ ባሻገር ካለው ክልል ከተሰበሰበው ቀረጥ ላይ ተወስዶ የእነዚህ ሰዎች ወጪ በአፋጣኝ ይሸፈንላቸው።+ +9 ለሰማይ አምላክ ለሚቀርቡት የሚቃጠሉ መባዎች የሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ ይኸውም ወይፈኖች፣+ አውራ በጎች፣+ የበግ ጠቦቶች፣+ ስንዴ፣+ ጨው፣+ የወይን ጠጅና+ ዘይት+ በኢየሩሳሌም የሚገኙት ካህናት በሚጠይቁት መሠረት በየቀኑ ያለማቋረጥ ይሰጣቸው፤ +10 ይህም የሚደረገው የሰማይ አምላክን ደስ የሚያሰኙ መባዎችን ዘወትር እንዲያቀርቡ እንዲሁም ለንጉሡና ለልጆቹ ደህንነት እንዲጸልዩ ነው።+ +11 ከዚህ በተጨማሪ ይህን አዋጅ የጣሰ ማንኛውም ሰው ለዚህ ጥፋቱ ከቤቱ ምሰሶ እንዲነቀልና ወደ ላይ ከፍ ተደርጎ ላዩ ላይ እንዲቸነከር* እንዲሁም ቤቱ የሕዝብ መጸዳጃ ቤት* እንዲሆን አዝዣለሁ። +12 ስሙ በዚያ እንዲኖር ያደረገው አምላክ+ ይህን ትእዛዝ ለመቃወምና በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ያንን የአምላክ ቤት ለማጥፋት እጁን የሚያነሳን ማንኛውንም ንጉሥም ሆነ ሕዝብ ያጥፋው። እኔ ዳርዮስ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ። ይህም በአስቸኳይ ተግባራዊ ይደረግ።” +13 ከዚያም ከወንዙ ባሻገር ያለው ክልል ገዢ የሆነው ታተናይ፣ ሸታርቦዘናይና+ ግብረ አበሮቻቸው ንጉሥ ዳርዮስ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ወዲያውኑ ተግባራዊ አደረጉ። +14 የአይሁዳውያን ሽማግሌዎችም ነቢዩ ሐጌና+ የኢዶ የልጅ ልጅ ዘካርያስ+ በተናገሩት ትንቢት ተበረታተው ግንባታውን ማከናወናቸውንና ሥራውን ማፋጠናቸውን ቀጠሉ፤+ በእስራኤል አምላክ ትእዛዝ መሠረት+ እንዲሁም በቂሮስ፣+ በዳርዮስና+ በፋርሱ ንጉሥ በአርጤክስስ+ ትእዛዝ መሠረት ቤቱን ገንብተው አጠናቀቁ። +15 ቤቱንም በአዳር* ወር በሦስተኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት ሠርተው አጠናቀቁ። +16 ከዚያም እስራኤላውያን፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና+ በግዞት ተወስደው የነበሩት የቀሩት ሰዎች የአምላክን ቤት ምርቃት* በደስታ አከበሩ። +17 ለአምላክ ቤት ምርቃትም 100 በሬዎችን፣ 200 አውራ በጎችንና 400 የበግ ጠቦቶችን እንዲሁም ለመላው እስራኤል የኃጢአት መባ እንዲሆኑ በእስራኤል ነገዶች ቁጥር ልክ 12 አውራ ፍየሎችን አቀረቡ።+ +18 እንዲሁም በሙሴ መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው መሠረት+ በኢየሩሳሌም ለሚቀርበው የአምላክ አገልግሎት ካህናቱን በየክፍላቸው፣ ሌዋውያኑንም በየምድባቸው ሾሙ።+ +19 በግዞት ተወስደው የነበሩት ሰዎች በመጀመሪያው ወር በ14ኛው ቀን ላይ ፋሲካን* አከበሩ።+ +20 ካህናቱና ሌዋውያኑ በሙሉ ራሳቸውን ስላነጹ+ ሁሉም ንጹሕ ሆነው ነበር፤ እነሱም በግዞት ተወስደው ለነበሩት ሰዎች በሙሉ��� አብረዋቸው ለሚያገለግሉት ካህናትና ለራሳቸው የፋሲካውን እርድ አረዱ። +21 ከዚያም ከግዞት የተመለሱት እስራኤላውያን በምድሪቱ ከነበሩት ብሔራት ርኩሰት ራሳቸውን በመለየት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ለማምለክ* ከእነሱ ጋር ከተቀላቀሉት ሁሉ ጋር ሆነው በሉት።+ +22 በተጨማሪም ይሖዋ እንዲደሰቱ ስላደረጋቸውና የእስራኤል አምላክ የሆነውን የእውነተኛውን አምላክ ቤት ይሠሩ ዘንድ እንዲረዳቸው* የአሦርን ንጉሥ ልብ ስላራራላቸው+ የቂጣን* በዓል+ ለሰባት ቀን በደስታ አከበሩ። +10 ዕዝራ በእውነተኛው አምላክ ቤት ፊት ተደፍቶ እያለቀሰ፣ እየጸለየና+ እየተናዘዘ ሳለ በርካታ ቁጥር ያላቸው እስራኤላውያን ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ ሕዝቡም ምርር ብሎ ያለቅስ ነበር። +2 ከዚያም ከኤላም+ ልጆች መካከል የየሂኤል+ ልጅ ሸካንያህ ዕዝራን እንዲህ አለው፦ “በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦች መካከል ባዕዳን ሴቶችን በማግባት* በአምላካችን ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጽመናል።+ ያም ሆኖ እስራኤል አሁንም ተስፋ አለው። +3 እንግዲህ ይሖዋም ሆነ ለአምላካችን ትእዛዝ አክብሮት ያላቸው* ሰዎች+ በሰጡት መመሪያ መሠረት ሚስቶቻችንን በሙሉና ከእነሱ የተወለዱትን ልጆች ለማሰናበት ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እንጋባ።+ ሕጉንም ተግባራዊ እናድርግ። +4 ይህ የአንተ ኃላፊነት ስለሆነ ተነስ፤ እኛም ከጎንህ ነን። አይዞህ፣ እርምጃ ውሰድ።” +5 በዚህ ጊዜ ዕዝራ ተነስቶ የቀረበውን ሐሳብ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የካህናቱን፣ የሌዋውያኑንና የመላው እስራኤልን አለቆች አስማላቸው፤+ እነሱም ማሉ። +6 ከዚያም ዕዝራ ከእውነተኛው አምላክ ቤት ፊት ተነስቶ የኤልያሺብ ልጅ ወደሆነው ወደ የሆሃናን ክፍል* ሄደ። ሆኖም በግዞት የተወሰደው ሕዝብ በፈጸመው ታማኝነት የጎደለው ድርጊት+ አዝኖ ስለነበር ወደዚያ ቢሄድም እንኳ እህል አልቀመሰም፤ ውኃም አልጠጣም። +7 ከዚያም በግዞት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ የሚያዝዝ አዋጅ በይሁዳና በኢየሩሳሌም አወጁ፤ +8 መኳንንቱና ሽማግሌዎቹ ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ማንኛውም ሰው ንብረቱ በሙሉ እንዲወረስና* በግዞት ከተወሰደው ሕዝብ ጉባኤ እንዲባረር ይደረጋል።+ +9 በመሆኑም ከይሁዳና ከቢንያም ነገድ የሆኑ ወንዶች ሁሉ በሦስት ቀን ውስጥ ማለትም በዘጠነኛው ወር ከወሩም በ20ኛው ቀን በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ በእውነተኛው አምላክ ቤት ግቢ ውስጥ ተቀምጠው ነበር፤ ከጉዳዩ ክብደትና ከሚዘንበው ኃይለኛ ዝናብ የተነሳም ይንቀጠቀጡ ነበር። +10 ከዚያም ካህኑ ዕዝራ ተነስቶ እንዲህ አላቸው፦ “ባዕዳን ሚስቶችን በማግባት ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጽማችኋል፤+ በዚህም የተነሳ የእስራኤል በደል እንዲበዛ አድርጋችኋል። +11 እንግዲህ አሁን ለአባቶቻችሁ አምላክ ለይሖዋ ተናዘዙ፤ ፈቃዱንም ፈጽሙ። በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦችና ከባዕዳን ሚስቶቻችሁ ራሳችሁን ለዩ።”+ +12 በዚህ ጊዜ መላው ጉባኤ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ልክ እንደተናገርከው ማድረግ ግዴታችን ነው። +13 ይሁንና ሕዝቡ ብዙ ነው፤ የዝናብ ወቅት ስለሆነ ውጭ መቆም አስቸጋሪ ነው። ደግሞም ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የፈጸምነው ዓመፅ እጅግ ከባድ በመሆኑ ጉዳዩ በአንድ ወይም በሁለት ቀን የሚቋጭ አይደለም። +14 ስለዚህ እባክህ መኳንንታችን ለመላው ጉባኤ ተወካይ ሆነው ያገልግሉ፤+ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ በከተሞቻችን በሙሉ የሚገኙ ሰዎችም ከእያንዳንዱ ከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ጋር በተወሰነው ጊዜ ይምጡ፤ በዚህ ጉዳይ የተነሳ የመጣብን የአምላካችን የሚነድ ቁጣ እስኪመለስ ድረስ እንዲህ ብና���ርግ የተሻለ ነው።” +15 ይሁን እንጂ የአሳሄል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ያህዘያህ ይህን ሐሳብ ተቃወሙ፤ ሌዋውያኑ መሹላምና ሻበታይም+ ተባበሯቸው። +16 ሆኖም በግዞት የነበሩት ሰዎች በስምምነቱ መሠረት እርምጃ ወሰዱ፤ ከዚያም በአሥረኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ካህኑ ዕዝራና በየስማቸው የተመዘገቡት የአባቶቻቸው ቤት የቤተሰብ መሪዎች ሁሉ ጉዳዩን ለመመርመር ብቻቸውን ተሰበሰቡ። +17 እነሱም ባዕዳን ሴቶችን ያገቡትን ሰዎች ጉዳይ በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ መርምረው ጨረሱ። +18 ባዕዳን ሴቶችን ካገቡት ሰዎችም መካከል አንዳንድ የካህናት ልጆች መኖራቸው ታወቀ፤+ እነሱም የየሆጼዴቅ ልጅ የየሆሹዋ+ ወንዶች ልጆችና ወንድሞች የሆኑት ማአሴያህ፣ ኤሊዔዘር፣ ያሪብ እና ጎዶልያስ ናቸው። +19 እነዚህ ሰዎች ሚስቶቻቸውን ለማሰናበት ቃል ገቡ፤* በደለኞች ስለሆኑም ለበደላቸው ከመንጋው መካከል አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ።+ +20 ከኢሜር+ ወንዶች ልጆች ሃናኒ እና ዘባድያህ፤ +21 ከሃሪም+ ወንዶች ልጆች ማአሴያህ፣ ኤልያስ፣ ሸማያህ፣ የሂኤል እና ዖዝያ፤ +22 ከጳስኮር+ ወንዶች ልጆች ኤሊዮዔናይ፣ ማአሴያህ፣ እስማኤል፣ ናትናኤል፣ ዮዛባድ እና ኤልዓሳ። +23 ከሌዋውያኑ መካከል ዮዛባድ፣ ሺምአይ፣ ቄላያህ (ማለትም ቀሊጣ)፣ ፐታያህ፣ ይሁዳ እና ኤሊዔዘር፤ +24 ከዘማሪዎቹ መካከል ኤልያሺብ፤ ከበር ጠባቂዎቹ መካከል ሻሉም፣ ተሌም እና ዖሪ። +25 ከእስራኤል መካከል የፓሮሽ+ ወንዶች ልጆች የሆኑት ራምያህ፣ ይዝዚያህ፣ ማልኪያህ፣ ሚያሚን፣ አልዓዛር፣ ማልኪያህ እና በናያህ ነበሩ፤ +26 ከኤላም+ ወንዶች ልጆች ማታንያህ፣ ዘካርያስ፣ የሂኤል፣+ አብዲ፣ የሬሞት እና ኤልያስ፤ +27 ከዛቱ+ ወንዶች ልጆች ኤሊዮዔናይ፣ ኤልያሺብ፣ ማታንያህ፣ የሬሞት፣ ዛባድ እና አዚዛ፤ +28 ከቤባይ+ ወንዶች ልጆች የሆሃናን፣ ሃናንያህ፣ ዛባይ እና አትላይ፤ +29 ከባኒ ወንዶች ልጆች መሹላም፣ ማሉክ፣ አዳያህ፣ ያሹብ፣ ሸአል እና የሬሞት፤ +30 ከፓሃትሞአብ+ ወንዶች ልጆች አድና፣ ከላል፣ በናያህ፣ ማአሴያህ፣ ማታንያህ፣ ባስልኤል፣ ቢኑይ እና ምናሴ፤ +31 ከሃሪም+ ወንዶች ልጆች ኤሊዔዘር፣ ይሽሺያህ፣ ማልኪያህ፣+ ሸማያህ፣ ሺምኦን፣ +32 ቢንያም፣ ማሉክ እና ሸማርያህ፤ +33 ከሃሹም+ ወንዶች ልጆች ማቴናይ፣ ማታታ፣ ዛባድ፣ ኤሊፌሌት፣ የሬማይ፣ ምናሴ እና ሺምአይ፤ +34 ከባኒ ወንዶች ልጆች ማአዳይ፣ አምራም፣ ዑኤል፣ +35 በናያህ፣ ቤድያህ፣ ከሉሂ፣ +36 ዋንያህ፣ መሬሞት፣ ኤልያሺብ፣ +37 ማታንያህ፣ ማቴናይ እና ያአሱ፤ +38 ከቢኑይ ወንዶች ልጆች ሺምአይ፣ +39 ሸሌምያህ፣ ናታን፣ አዳያህ፣ +40 ማክናደባይ፣ ሻሻይ፣ ሻራይ፣ +41 አዛርዔል፣ ሸሌምያህ፣ ሸማርያህ፣ +42 ሻሉም፣ አማርያህ እና ዮሴፍ፤ +43 ከነቦ ወንዶች ልጆች የኢዔል፣ ማቲትያህ፣ ዛባድ፣ ዘቢና፣ ያዳይ፣ ኢዩኤል እና በናያህ። +44 እነዚህ ሁሉ ባዕዳን ሚስቶችን ያገቡ ናቸው፤+ እነሱም ሚስቶቻቸውን ከነልጆቻቸው አሰናበቱ።+ +9 እነዚህ ነገሮች እንደተጠናቀቁ መኳንንቱ ወደ እኔ መጥተው እንዲህ አሉኝ፦ “የእስራኤል ሕዝብ፣ ካህናቱና ሌዋውያኑ በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦች ይኸውም ከከነአናውያን፣ ከሂታውያን፣ ከፈሪዛውያን፣ ከኢያቡሳውያን፣ ከአሞናውያን፣ ከሞዓባውያን፣ ከግብፃውያንና+ ከአሞራውያን+ እንዲሁም አስጸያፊ ከሆኑት ልማዶቻቸው+ +2 ከእነሱም ሴቶች ልጆች መካከል ለራሳቸውና ለወንዶች ልጆቻቸው ሚስቶች ወስደዋል።+ በመሆኑም ቅዱስ ዘር+ የሆኑት እነዚህ ሰዎች በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦች ጋር ተቀላቅለዋል።+ ይህን ታማኝነት የጎደለው ድርጊት በመፈጸም ግንባር ቀደም የሆኑት መኳንንቱና የበታች ገዢዎቹ ናቸው።” +3 እኔም ይህን ስሰማ እጀ ���ባቤንና መደረቢያዬን ቀደድኩ፤ ፀጉሬንና ጺሜን ነጨሁ፤ በጣም ከመደንገጤም የተነሳ በተቀመጥኩበት ደርቄ ቀረሁ። +4 ምሽት ላይ እስከሚቀርበው የእህል መባ+ ድረስ እንደደነገጥኩ በዚያ ተቀምጬ ሳለሁ ለእስራኤል አምላክ ቃል አክብሮታዊ ፍርሃት ያላቸው* ሰዎች ሁሉ፣ በግዞት ተወስደው የነበሩት ሰዎች በፈጸሙት ታማኝነት የጎደለው ድርጊት የተነሳ በዙሪያዬ ተሰበሰቡ። +5 ከዚያም ምሽት ላይ የእህል መባው+ በሚቀርብበት ጊዜ እጀ ጠባቤና መደረቢያዬ እንደተቀደደ ራሴን አዋርጄ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ፤ በጉልበቴም ተንበርክኬ እጆቼን ወደ አምላኬ ወደ ይሖዋ ዘረጋሁ። +6 እንዲህም አልኩ፦ “አቤቱ አምላኬ ሆይ፣ ፊቴን ወደ አንተ ቀና ማድረግ አሳፈረኝ፤ አሸማቀቀኝ፤ ምክንያቱም አምላኬ ሆይ፣ የፈጸምናቸው ስህተቶች በአናታችን ላይ ተቆልለዋል፤ በደላችንም ከመብዛቱ የተነሳ እስከ ሰማይ ደርሷል።+ +7 ከአባቶቻችን ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ የፈጸምነው በደል ታላቅ ነው፤+ በሠራናቸውም ስህተቶች የተነሳ ይኸው ዛሬ እንደሚታየው እኛም ሆንን ነገሥታታችንና ካህናታችን በሌሎች አገሮች ነገሥታት እጅ ወድቀን ለሰይፍ፣+ ለምርኮ፣+ ለብዝበዛና+ ለውርደት ተዳርገናል።+ +8 አሁን ግን አምላካችን ይሖዋ ቀሪዎች እንዲተርፉና በቅዱስ ስፍራው አስተማማኝ ቦታ* እንድናገኝ በማድረግ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ሞገስ አሳይቶናል፤+ አምላካችን ሆይ፣ ይህን ያደረግከው ዓይኖቻችን እንዲበሩና ከተጫነብን የባርነት ቀንበር ትንሽ እንድናገግም ነው። +9 ባሪያዎች+ ብንሆንም እንኳ አምላካችን ባሪያዎች ሆነን እንድንቀር አልተወንም፤ ከዚህ ይልቅ በፋርስ ነገሥታት ፊት ታማኝ ፍቅሩን አሳየን፤+ ይህን ያደረገውም ዳግም አገግመን የአምላካችንን ቤት ከወደቀበት እንድናነሳና የፈራረሱትን ቦታዎች መልሰን እንድንገነባ+ እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የድንጋይ ቅጥር +10 “አሁን ግን አምላካችን ሆይ፣ ከዚህ በኋላ ምን ማለት እንችላለን? ምክንያቱም ትእዛዛትህን ተላልፈናል፤ +11 በአገልጋዮችህ በነቢያት አማካኝነት የሰጠኸንን የሚከተለውን ትእዛዝ አላከበርንም፦ ‘ትወርሷት ዘንድ የምትገቡባት ምድር በነዋሪዎቿ ርኩሰት የተነሳ የረከሰች ናት፤ ምክንያቱም በምድሪቱ የሚኖሩት ሰዎች በአስጸያፊ ድርጊቶቻቸው ምድሪቱን ከዳር እሰከ ዳር በርኩሰታቸው ሞልተዋታል።+ +12 ስለሆነም ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ፤+ እንዲሁም ይበልጥ እየበረታችሁ እንድትሄዱ፣ የምድሪቱን መልካም ነገር እንድትበሉና ምድሪቱን የልጆቻችሁ ዘላለማዊ ርስት ማድረግ እንድትችሉ ፈጽሞ የእነሱን ሰላምና ብልጽግና አትፈልጉ።’+ +13 በተጨማሪም በመጥፎ ሥራዎቻችንና በፈጸምነው ታላቅ በደል ምክንያት ይህ ሁሉ ደረሰብን፤ አንተ ግን አምላካችን ሆይ፣ እንደ ጥፋታችን መጠን አልቀጣኸንም፤+ ከዚህ ይልቅ እኛ እዚህ ያለነው እንድንተርፍ ፈቀድክ።+ +14 ታዲያ ትእዛዛትህን እንደገና መተላለፍና እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ከሚፈጽሙ ሕዝቦች ጋር በጋብቻ መዛመድ ይገባናል?+ አንተስ አንድም ሰው ሳታስቀር ወይም ሳታስተርፍ ፈጽሞ እስክታጠፋን ድረስ ልትቆጣ አይገባህም? +15 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ ነህ፤+ ምክንያቱም እኛ ከጥፋት ተርፈን እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በሕይወት አለን። እንዲህ ያለ ነገር አድርጎ በፊትህ መቆም የማይቻል ቢሆንም ይኸው ከነበደላችን በፊትህ ቀርበናል።”+ +5 ከዚያም ነቢዩ ሐጌና+ የኢዶ+ የልጅ ልጅ የሆነው ነቢዩ ዘካርያስ+ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁዳውያን፣ ይመራቸው በነበረው በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ���ናገሩ። +2 በዚህ ጊዜ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና+ የየሆጼዴቅ ልጅ የሆሹዋ+ በኢየሩሳሌም የነበረውን የአምላክን ቤት መልሰው መገንባት ጀመሩ፤+ አብረዋቸው የነበሩት የአምላክ ነቢያትም ያግዟቸው ነበር።+ +3 በወቅቱ፣ ከወንዙ ባሻገር* የነበረው ክልል ገዢ የሆነው ታተናይ እና ሸታርቦዘናይ እንዲሁም ግብረ አበሮቻቸው ወደ እነሱ መጥተው “ይህን ቤት እንድትገነቡና እንድታዋቅሩ ማን ትእዛዝ ሰጣችሁ?” ሲሉ ጠየቋቸው። +4 ከዚያም “ይህን ሕንፃ እየገነቡ ያሉት ሰዎች ስም ማን ነው?” አሏቸው። +5 ሆኖም አምላክ ለአይሁዳውያን ሽማግሌዎች+ ጥበቃ ያደርግላቸው* ስለነበር መልእክቱ ለዳርዮስ ተልኮ ጉዳዩን የሚመለከት ደብዳቤ ከዚያ እስኪመጣ ድረስ ሥራውን ሊያስቆሟቸው አልቻሉም። +6 ከወንዙ ባሻገር ያለው ክልል ገዢ የሆነው ታተናይ፣ ሸታርቦዘናይና ከወንዙ ባሻገር ያለው ክልል የበታች ገዢዎች የሆኑት ግብረ አበሮቹ ለንጉሥ ዳርዮስ የላኩት ደብዳቤ ቅጂ ይህ ነው፤ +7 እንዲህ የሚል መልእክት ጽፈው ላኩለት፦ “ለንጉሥ ዳርዮስ፦ “ሰላም ለአንተ ይሁን! +8 በይሁዳ አውራጃ ወደሚገኘው ወደ ታላቁ አምላክ ቤት እንደሄድንና ቤቱ በትላልቅ ድንጋዮች እየተገነባ፣ በግንቡም ላይ ሳንቃዎች እየተነጠፉ መሆናቸውን ንጉሡ ይወቅ። ሕዝቡ ሥራውን በትጋት እያከናወነ ሲሆን ሥራውም በእነሱ ጥረት እየተፋጠነ ነው። +9 ሽማግሌዎቹንም ‘ይህን ቤት እንድትገነቡና እንድታዋቅሩ ማን ትእዛዝ ሰጣችሁ?’ አልናቸው።+ +10 በተጨማሪም ግንባር ቀደም ሆነው የሚመሩትን ሰዎች ስም ጽፈን ለአንተ ለማሳወቅ የሰዎቹን ስም እንዲነግሩን ጠየቅናቸው። +11 “እነሱም የሚከተለውን ምላሽ ሰጡን፦ ‘እኛ የሰማይና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፤ አሁን መልሰን የምንገነባው ከበርካታ ዓመታት በፊት ተገንብቶ የነበረውን ይኸውም ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ ገንብቶ ያጠናቀቀውን ቤት ነው።+ +12 ሆኖም አባቶቻችን የሰማይን አምላክ ስላስቆጡት+ ለከለዳዊው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር+ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እሱም ይህን ቤት አፈራርሶ+ ሕዝቡን በግዞት ወደ ባቢሎን ወሰደ።+ +13 ይሁንና በባቢሎን ንጉሥ በቂሮስ የግዛት ዘመን የመጀመሪያ ዓመት ንጉሥ ቂሮስ ይህ የአምላክ ቤት ተመልሶ እንዲገነባ ትእዛዝ ሰጠ።+ +14 በተጨማሪም ንጉሥ ቂሮስ፣ ናቡከደነጾር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ አውጥቶ ወደ ባቢሎን ቤተ መቅደስ የወሰዳቸውን የአምላክን ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች ከባቢሎን ቤተ መቅደስ አወጣ።+ እነዚህም ዕቃዎች ቂሮስ ገዢ አድርጎ+ ለሾመው ሸሽባጻር*+ ለተባለ ሰው ተሰጡ። +15 ቂሮስም እንዲህ አለው፦ “እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ። ሄደህም በኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ ውስጥ አስቀምጣቸው፤ የአምላክም ቤት ቀድሞ በነበረበት ቦታ ላይ ተመልሶ ይገንባ።”+ +16 ከዚያም ሸሽባጻር መጥቶ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የአምላክን ቤት መሠረት ጣለ፤+ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ቤቱ በመገንባት ላይ ነው፤ ሆኖም ገና አላለቀም።’+ +17 “እንግዲህ አሁን፣ ንጉሡ መልካም መስሎ ከታየው ንጉሥ ቂሮስ በኢየሩሳሌም የነበረው ያ የአምላክ ቤት ተመልሶ እንዲገነባ ትእዛዝ ሰጥቶ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማረጋገጥ በባቢሎን በሚገኘው የንጉሡ ግምጃ ቤት ምርመራ ይካሄድ፤+ ይህን በተመለከተም ንጉሡ ያስተላለፈው ውሳኔ ይላክልን።” +3 ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብና+ ካህናት የሆኑት ወንድሞቹ የበግ በርን+ ለመገንባት ተነሱ። እነሱም ቀደሱት፤*+ መዝጊያዎቹንም ገጠሙለት፤ እስከ መአህ ማማና+ እስከ ሃናንኤል ማማ+ ድረስ ቀደሱት። +2 ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የኢያሪኮ+ ሰዎች እየገነቡ ነበር፤ ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን የኢምሪ ልጅ ዛኩር እየገነባ ነበር። +3 የሃስናአ ልጆች የዓሣ በርን+ ገነቡ፤ የጣውላ መቃኑንም ሠሩ፤+ ከዚያም መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠሙለት። +4 ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የሃቆጽ ልጅ የሆነው የዑሪያህ ልጅ መሬሞት+ ጠገነ፤ ቀጥሎ ያለውን የመሺዛቤል ልጅ የሆነው የቤራክያህ ልጅ መሹላም+ ጠገነ፤ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን የባአና ልጅ ሳዶቅ ጠገነ። +5 ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የተቆአ+ ሰዎች ጠገኑ፤ ሆኖም ከእነሱ መካከል ታዋቂ የሆኑት ሰዎች ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ* አለቆቻቸው በሚያሠሩት ሥራ መካፈል አልፈለጉም። +6 የፓሰአህ ልጅ ዮያዳ እና የቤሶድያህ ልጅ መሹላም የአሮጌ ከተማ በርን+ ጠገኑ፤ የጣውላ መቃኑንም ሠሩ፤ ከዚያም መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠሙለት። +7 ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ ከወንዙ+ ባሻገር* ባለው ክልል ገዢ ሥልጣን* ሥር የሚገኙት የገባኦንና የምጽጳ+ ሰዎች የሆኑት ገባኦናዊው+ መላጥያህና መሮኖታዊው ያዶን ጠገኑ። +8 ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ከወርቅ አንጥረኞቹ አንዱ የሆነው የሃርሐያህ ልጅ ዑዚኤል ጠገነ፤ ከእሱ ቀጥሎ ያለውን ከቅባት ቀማሚዎች* አንዱ የሆነው ሃናንያህ ጠገነ፤ ኢየሩሳሌምንም እስከ ሰፊ ቅጥር+ ድረስ ድንጋይ አነጠፉባት። +9 ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሁር ልጅ ረፋያህ ጠገነ። +10 የሃሩማፍ ልጅ የዳያህ ከእነሱ ቀጥሎ የሚገኘውን ከራሱ ቤት ፊት ለፊት ያለውን ጠገነ፤ ከእሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የሃሻበንያህ ልጅ ሃጡሽ ጠገነ። +11 የሃሪም+ ልጅ ማልኪያህና የፓሃትሞአብ+ ልጅ ሃሹብ ሌላኛውን ክፍል* ጠገኑ፤ እንዲሁም የምድጃዎች ማማን+ ጠገኑ። +12 ከእነሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሃሎሔሽ ልጅ ሻሉም እና ሴቶች ልጆቹ ጠገኑ። +"13 ሃኑን እና የዛኖሃ+ ነዋሪዎች የሸለቆ በርን+ ጠገኑ፤ እነሱም ከሠሩት በኋላ መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠሙለት፤ በተጨማሪም እስከ አመድ ቁልል በር+ ድረስ ያለውን 1,000 ክንድ* ቅጥር ጠገኑ።" +14 የቤትሃኬሬም+ አውራጃ ገዢ የሆነው የሬካብ ልጅ ማልኪያህ የአመድ ቁልል በርን ጠገነ፤ እሱም ከሠራው በኋላ መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠመለት። +15 የምጽጳ+ አውራጃ ገዢ የሆነው የኮልሆዜ ልጅ ሻሉን የምንጭ በርን+ ጠገነ፤ እሱም ከሠራው በኋላ ጣሪያ አበጀለት፤ ከዚያም መዝጊያዎቹን፣ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን ገጠመ፤ በተጨማሪም በንጉሡ የአትክልት ስፍራ+ ያለውን የሼላ የውኃ ገንዳ* ግንብ+ ከዳዊት ከተማ+ ተነስቶ ቁልቁል እስከሚወርደው ደረጃ +16 ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የቤትጹር+ አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የአዝቡቅ ልጅ ነህምያ ከዳዊት የመቃብር ስፍራ+ ፊት ለፊት አንስቶ እስከ ሰው ሠራሹ ኩሬና+ እስከ ኃያላኑ ቤት ድረስ ገነባ። +17 ከእሱ ቀጥሎ ያለውን በባኒ ልጅ በረሁም ሥር ያሉት ሌዋውያን ጠገኑት፤ ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የቀኢላ+ አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሃሻብያህ የራሱን አውራጃ ጠገነ። +18 ከእሱ ቀጥሎ ያለውን የቀኢላ አውራጃ እኩሌታ ገዢ በሆነው በሄናዳድ ልጅ በባዋይ ሥር ያሉት ወንድሞቻቸው ጠገኑ። +19 ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የምጽጳ ገዢ የሆነው የኤጼር ልጅ የሹዋ+ በቅጥሩ ቅስት+ አጠገብ ወደሚገኘው የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ከሚያስወጣው አቀበት ፊት ለፊት ያለውን ሌላኛውን ክፍል ጠገነ። +20 ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የዛባይ+ ልጅ ባሮክ የቅጥሩ ቅስት ከሚገኝበት አንስቶ እስከ ሊቀ ካህናቱ ኤልያሺብ+ ቤት መግቢያ ድረስ ያለውን ሌላኛውን ክፍል በቅንዓት ጠገነ። +21 ከእሱ ቀጥሎ የሃቆጽ ልጅ የሆነው የዑሪያህ ልጅ መሬሞት+ ከኤልያሺብ ቤት መግቢያ አንስቶ እስከ ኤልያሺብ ቤት መጨረሻ ድረስ ያለውን ሌላኛውን ክፍል ጠገነ። +22 ከእሱ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ ካህናቱ ይኸውም የዮርዳኖስ አውራጃ*+ ሰዎች ጠገኑት። +23 ከእነሱ ቀጥሎ ቢንያምና ሃሹብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን ጠገኑ። ከእነሱ ቀጥሎ ደግሞ የአናንያ ልጅ የሆነው የማአሴያህ ልጅ አዛርያስ ከራሱ ቤት አጠገብ ያለውን ጠገነ። +24 ከእሱ ቀጥሎ የሄናዳድ ልጅ ቢኑይ ከአዛርያስ ቤት አንስቶ እስከ ቅጥሩ ቅስትና+ እስከ ማዕዘኑ ድረስ ያለውን ሌላኛውን ክፍል ጠገነ። +25 ከእሱ ቀጥሎ የዑዛይ ልጅ ፓላል ከቅስቱ ፊት ለፊት ያለውን ቅጥርና በንጉሡ ቤት*+ አጠገብ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ውስጥ የሚገኘውን የላይኛውን ማማ ጠገነ። ከእሱ ቀጥሎ የፓሮሽ+ ልጅ ፐዳያህ ነበር። +26 እንዲሁም በኦፌል+ የሚኖሩት የቤተ መቅደስ አገልጋዮች*+ በስተ ምሥራቅ እስከ ውኃ በር+ ፊት ለፊት ድረስ ያለውን ቅጥርና ወጣ ያለውን ማማ ጠገኑ። +27 ከእነሱ ቀጥሎ የተቆአ+ ሰዎች ወጣ ካለው ትልቅ ማማ ፊት ለፊት አንስቶ እስከ ኦፌል ቅጥር ድረስ ያለውን ሌላኛውን ክፍል ጠገኑ። +28 ካህናቱ ከፈረስ በር+ በላይ ያለውን ጠገኑ፤ እያንዳንዳቸውም ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን ጠገኑ። +29 ከእነሱ ቀጥሎ የኢሜር ልጅ ሳዶቅ+ ከራሱ ቤት ፊት ለፊት ያለውን ጠገነ። ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የምሥራቅ በር+ ጠባቂ የሆነው የሸካንያህ ልጅ ሸማያህ ጠገነ። +30 ከእሱ ቀጥሎ የሸሌምያህ ልጅ ሃናንያህና የጻላፍ ስድስተኛ ልጅ ሃኑን ሌላኛውን ክፍል ጠገኑ። ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ የቤራክያህ ልጅ መሹላም+ ከራሱ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለውን ጠገነ። +31 ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ የወርቅ አንጥረኞች ማኅበር አባል የሆነው ማልኪያህ በመቆጣጠሪያ በር አጠገብ እስከሚገኘው እስከ ቤተ መቅደስ አገልጋዮቹና*+ እስከ ነጋዴዎቹ ቤት እንዲሁም በማዕዘኑ ላይ እስካለው ሰገነት ድረስ ያለውን ጠገነ። +32 የወርቅ አንጥረኞቹና ነጋዴዎቹም በሰገነቱ ማዕዘን ላይ በሚገኘው ክፍልና በበግ በር+ መካከል ያለውን ጠገኑ። +7 እኔም ቅጥሩ እንደገና ተገንብቶ እንዳለቀ+ መዝጊያዎቹን+ ገጠምኩ፤ ከዚያም በር ጠባቂዎቹ፣+ ዘማሪዎቹና+ ሌዋውያኑ+ ተሾሙ። +2 በኋላም ወንድሜን ሃናኒን፣+ የምሽጉ+ አለቃ ከሆነው ከሃናንያህ ጋር በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኩት፤ ምክንያቱም ሃናንያህ እምነት የሚጣልበትና ከሌሎቹ ሁሉ ይበልጥ እውነተኛውን አምላክ የሚፈራ ሰው ነበር።+ +3 እንዲህም አልኳቸው፦ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሐይ ሞቅ እስከሚል ድረስ መከፈት የለባቸውም፤ ጠባቂዎቹ በጥበቃ ሥራቸው ላይ እያሉ በሮቹን መዝጋትና መቀርቀር ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ጠባቂዎች አድርጋችሁ መድቡ፤ የተወሰኑት ሰዎች በተመደቡበት የጥበቃ ቦታ፣ ሌሎቹ ደግሞ ከቤታቸው ፊት ለፊ +4 ከተማዋ ሰፊና ትልቅ ነበረች፤ በውስጧ የነበሩት ሰዎች ጥቂት ሲሆኑ+ ቤቶቹም እንደገና አልተገነቡም ነበር። +5 ሆኖም አምላኬ የተከበሩትን ሰዎች፣ የበታች ገዢዎቹንና ሕዝቡን በአንድነት እንድሰበስብና በየዘር ሐረጋቸው እንዲመዘገቡ+ እንዳደርግ ይህን ሐሳብ በልቤ ውስጥ አኖረ። ከዚያም መጀመሪያ ላይ የመጡትን ሰዎች የዘር ሐረግ ዝርዝር የያዘ መጽሐፍ አገኘሁ፤ በውስጡም ተጽፎ ያገኘሁት ይህ ነው፦ +6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ በግዞት ወስዷቸው+ የነበሩትና ከምርኮ ነፃ ወጥተው፣ በኋላ ላይ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ይኸውም ወደየከተሞቻቸው የተመለሱት የአውራጃው ነዋሪዎች እነዚህ ናቸው፤+ +7 ከዘሩባቤል፣+ ከየሆሹዋ፣+ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከራሚያህ፣ ከናሃማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከቢልሻን፣ ከሚስጴሬት፣ ከቢግዋይ፣ ከነሁም እና ከባአናህ ጋር የመጡት እነዚህ ናቸው። የእስራኤላውያን ወንዶች ቁጥር የሚ��ተሉትን ይጨምራል፦+ +"8 የፓሮሽ ወንዶች ልጆች 2,172፣" +9 የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች 372፣ +10 የኤራ+ ወንዶች ልጆች 652፣ +"11 የየሹዋና የኢዮዓብ+ ወንዶች ልጆች የሆኑት የፓሃትሞአብ+ ወንዶች ልጆች 2,818፣" +"12 የኤላም+ ወንዶች ልጆች 1,254፣" +13 የዛቱ ወንዶች ልጆች 845፣ +14 የዛካይ ወንዶች ልጆች 760፣ +15 የቢኑይ ወንዶች ልጆች 648፣ +16 የቤባይ ወንዶች ልጆች 628፣ +"17 የአዝጋድ ወንዶች ልጆች 2,322፣" +18 የአዶኒቃም ወንዶች ልጆች 667፣ +"19 የቢግዋይ ወንዶች ልጆች 2,067፣" +20 የአዲን ወንዶች ልጆች 655፣ +21 የሕዝቅያስ ልጅ የአጤር ወንዶች ልጆች 98፣ +22 የሃሹም ወንዶች ልጆች 328፣ +23 የቤጻይ ወንዶች ልጆች 324፣ +24 የሃሪፍ ወንዶች ልጆች 112፣ +25 የገባኦን+ ወንዶች ልጆች 95፣ +26 የቤተልሔምና የነጦፋ ሰዎች 188፣ +27 የአናቶት+ ሰዎች 128፣ +28 የቤትአዝማዌት ሰዎች 42፣ +29 የቂርያትየአሪም፣+ የከፊራና የበኤሮት+ ሰዎች 743፣ +30 የራማና የጌባ+ ሰዎች 621፣ +31 የሚክማስ+ ሰዎች 122፣ +32 የቤቴልና+ የጋይ+ ሰዎች 123፣ +33 የሌላኛው ነቦ ሰዎች 52፣ +"34 የሌላኛው ኤላም ወንዶች ልጆች 1,254፣" +35 የሃሪም ወንዶች ልጆች 320፣ +36 የኢያሪኮ ወንዶች ልጆች 345፣ +37 የሎድ፣ የሃዲድና የኦኖ+ ወንዶች ልጆች 721፣ +"38 የሰናአ ወንዶች ልጆች 3,930። " +39 ካህናቱ+ የሚከተሉት ናቸው፦ ከየሹዋ ወገን የሆነው የየዳያህ ወንዶች ልጆች 973፣ +"40 የኢሜር ወንዶች ልጆች 1,052፣" +"41 የጳስኮር+ ወንዶች ልጆች 1,247፣" +"42 የሃሪም+ ወንዶች ልጆች 1,017። " +43 ሌዋውያኑ+ የሚከተሉት ናቸው፦ የሆዳውያህ ወንዶች ልጆች የሆኑት የየሹዋና የቃድሚኤል+ ወንዶች ልጆች 74። +44 ዘማሪዎቹ+ የአሳፍ+ ወንዶች ልጆች 148። +45 በር ጠባቂዎቹ+ የሻሉም ወንዶች ልጆች፣ የአጤር ወንዶች ልጆች፣ የታልሞን ወንዶች ልጆች፣ የአቁብ+ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢጣ ወንዶች ልጆችና የሾባይ ወንዶች ልጆች 138። +46 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች*+ የሚከተሉት ናቸው፦ የጺሃ ወንዶች ልጆች፣ የሃሱፋ ወንዶች ልጆች፣ የታባኦት ወንዶች ልጆች፣ +47 የቀሮስ ወንዶች ልጆች፣ የሲአ ወንዶች ልጆች፣ የፓዶን ወንዶች ልጆች፣ +48 የለባና ወንዶች ልጆች፣ የሃጋባ ወንዶች ልጆች፣ የሳልማይ ወንዶች ልጆች፣ +49 የሃናን ወንዶች ልጆች፣ የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ የጋሃር ወንዶች ልጆች፣ +50 የረአያህ ወንዶች ልጆች፣ የረጺን ወንዶች ልጆች፣ የነቆዳ ወንዶች ልጆች፣ +51 የጋዛም ወንዶች ልጆች፣ የዑዛ ወንዶች ልጆች፣ የፓሰአህ ወንዶች ልጆች፣ +52 የቤሳይ ወንዶች ልጆች፣ የመኡኒም ወንዶች ልጆች፣ የነፉሸሲም ወንዶች ልጆች፣ +53 የባቅቡቅ ወንዶች ልጆች፣ የሃቁፋ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሑር ወንዶች ልጆች፣ +54 የባጽሊት ወንዶች ልጆች፣ የመሂዳ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሻ ወንዶች ልጆች፣ +55 የባርቆስ ወንዶች ልጆች፣ የሲሳራ ወንዶች ልጆች፣ የተማ ወንዶች ልጆች፣ +56 የነጺሃ ወንዶች ልጆችና የሃጢፋ ወንዶች ልጆች። +57 የሰለሞን አገልጋዮች+ ወንዶች ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ የሶጣይ ወንዶች ልጆች፣ የሶፈረት ወንዶች ልጆች፣ የፐሪዳ ወንዶች ልጆች፣ +58 የያአላ ወንዶች ልጆች፣ የዳርቆን ወንዶች ልጆች፣ የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ +59 የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢል ወንዶች ልጆች፣ የፖክሄሬትሃጸባይም ወንዶች ልጆችና የአምዖን ወንዶች ልጆች። +60 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና*+ የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 392 ነበሩ። +61 ከቴልመላ፣ ከቴልሃርሻ፣ ከከሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የወጡት ሆኖም ከየትኛው የአባቶች ቤትና የዘር ሐረግ እንደመጡ በውል መለየትም ሆነ እስራኤላዊ መሆን አለመሆናቸውን በትክክል ማረጋገጥ ያልቻሉት የሚከተሉት ናቸው፦+ +62 የደላያህ ወንዶች ልጆች፣ የጦብያ ወንዶች ልጆችና የነቆዳ ወንዶች ልጆች 642። +63 ከካህናቱም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የሃባያ ወንዶች ልጆች፣ የሃቆጽ+ ወንዶች ልጆች እንዲሁም ከጊልያዳዊው ከቤርዜሊ ሴቶች ልጆች መካከል አንዷን ያገባውና በስማቸው የተጠራው የቤርዜሊ+ ወንዶች ልጆች። +64 እነዚህ የዘር ሐረጋቸውን ለማረጋገጥ በመዝገቡ ላይ የቤተሰባቸውን ስም ለማግኘት ቢጥሩም ሊገኙ አልቻሉም፤ በመሆኑም ከክህነት አገልግሎቱ ታገዱ።*+ +65 ገዢውም*+ በኡሪምና በቱሚም+ አማካኝነት ምክር የሚጠይቅ ካህን እስኪገኝ ድረስ እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት እንደማይኖርባቸው ነገራቸው።+ +"66 መላው ጉባኤ በአጠቃላይ 42,360 ነበር፤+" +"67 ይህ 7,337 ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን አይጨምርም፤+ በተጨማሪም 245 ወንድና ሴት ዘማሪዎች+ ነበሯቸው።" +68 ከዚህም ሌላ 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች +"69 እንዲሁም 435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው። " +"70 ከአባቶች ቤት መሪዎች መካከል ለሥራው መዋጮ ያደረጉ ነበሩ።+ ገዢው* 1,000 የወርቅ ድራክማ፣* 50 ጎድጓዳ ሳህኖችና 530 የካህናት ቀሚሶች ለግምጃ ቤቱ ሰጠ።+" +"71 ከአባቶች ቤት መሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ለሥራው ማስኬጃ የሚሆን 20,000 የወርቅ ድራክማና 2,200 የብር ምናን* ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።" +"72 የቀረው ሕዝብ ደግሞ 20,000 የወርቅ ድራክማ፣ 2,000 የብር ምናን እና 67 የካህናት ቀሚሶች ሰጠ። " +73 ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ ዘማሪዎቹ፣+ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ፣ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹና* የቀሩት እስራኤላውያን በሙሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ።+ በሰባተኛውም ወር+ እስራኤላውያን በየከተሞቻቸው ይኖሩ ነበር።+ +12 ከሰላትያል+ ልጅ ከዘሩባቤልና+ ከየሆሹዋ+ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን የሚከተሉት ነበሩ፦ ሰራያህ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣ +2 አማርያህ፣ ማሉክ፣ ሃጡሽ፣ +3 ሸካንያህ፣ ረሁም፣ መሬሞት፣ +4 ኢዶ፣ ጊነቶአይ፣ አቢያህ፣ +5 ሚያሚን፣ ማአድያህ፣ ቢልጋ፣ +6 ሸማያህ፣ ዮያሪብ፣ የዳያህ፣ +7 ሳሉ፣ አሞቅ፣ ኬልቅያስ እና የዳያህ። እነዚህ በየሆሹዋ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው መሪዎች ነበሩ። +8 ሌዋውያኑ ደግሞ የሹዋ፣ ቢኑይ፣ ቃድሚኤል፣+ ሸረበያህ፣ ይሁዳ እና ከወንድሞቹ ጋር ሆኖ የምስጋና መዝሙሮቹን የሚመራው ማታንያህ+ ነበሩ። +9 ወንድሞቻቸው ባቅቡቅያ እና ዑኒ ከእነሱ ትይዩ ለጥበቃ ቆመው ነበር።* +10 የሹዋ ዮአቂምን ወለደ፤ ዮአቂምም ኤልያሺብን+ ወለደ፤ ኤልያሺብም ዮያዳን+ ወለደ። +11 ዮያዳም ዮናታንን ወለደ፤ ዮናታንም ያዱአን ወለደ። +12 በዮአቂም ዘመን የአባቶች ቤት መሪዎች የሆኑት ካህናት የሚከተሉት ነበሩ፦ ከሰራያህ+ መራያህ፣ ከኤርምያስ ሃናንያህ፣ +13 ከዕዝራ+ መሹላም፣ ከአማርያህ የሆሃናን፣ +14 ከማሉኪ ዮናታን፣ ከሸባንያህ ዮሴፍ፣ +15 ከሃሪም+ አድና፣ ከመራዮት ሄልቃይ፣ +16 ከኢዶ ዘካርያስ፣ ከጊነቶን መሹላም፣ +17 ከአቢያህ+ ዚክሪ፣ ከሚንያሚን . . . ፣* ከሞአድያህ ፒልጣይ፣ +18 ከቢልጋ+ ሻሙአ፣ ከሸማያህ የሆናታን፣ +19 ከዮያሪብ ማቴናይ፣ ከየዳያህ+ ዑዚ፣ +20 ከሳላይ ቃላይ፣ ከአሞቅ ኤቤር፣ +21 ከኬልቅያስ ሃሻብያህ፣ ከየዳያህ ናትናኤል ተወክለው ነበር። +22 በኤልያሺብ፣ በዮያዳ፣ በዮሃናን እና በያዱአ+ ዘመን የነበሩት የሌዋውያኑ የአባቶች ቤት መሪዎች ልክ እንደ ካህናቱ ሁሉ እስከ ፋርሳዊው ዳርዮስ የንግሥና ዘመን ድረስ ተመዘገቡ። +23 የአባቶች ቤት መሪዎች የነበሩት ሌዋውያን የኤልያሺብ ልጅ እስከሆነው እስከ ዮሃናን ዘመን ድረስ በዘመኑ በነበረው የታሪክ መጽሐፍ ላይ ተመዝግበው ነበር። +24 የሌዋውያኑ መሪዎች ሃሻብያህ፣ ሸረበያህና የቃድሚኤል+ ልጅ የሹዋ+ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ከእነሱ ትይዩ ቆመው ይኸውም አንዱ የጥበቃ ቡድን ከሌላው የጥበቃ ቡድን ጎን ለጎን ሆኖ የእውነተኛው አምላ��� ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት+ ለአምላክ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር። +25 ማታንያህ፣+ ባቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ መሹላም፣ ታልሞን እና አቁብ+ እንደ በር ጠባቂዎች+ ዘብ በመቆም በበሮቹ አጠገብ ያሉትን ግምጃ ቤቶች ይጠብቁ ነበር። +26 እነዚህም በዮጻዴቅ ልጅ፣ በየሆሹዋ+ ልጅ በዮአቂም ዘመን እንዲሁም በገዢው በነህምያና የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* በሆነው በካህኑ ዕዝራ+ ዘመን አገለገሉ። +27 የኢየሩሳሌም ቅጥሮች በሚመረቁበት ጊዜ የምረቃውን በዓል በምስጋና መዝሙር፣+ በሲምባል፣* በባለ አውታር መሣሪያዎችና በበገና በደስታ እንዲያከብሩ ሌዋውያኑን ከሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም አመጧቸው። +28 የዘማሪዎቹ ወንዶች ልጆችም* ከአውራጃው፣* በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉት ቦታዎች ሁሉና ነጦፋውያን+ ከሰፈሩባቸው መንደሮች ተሰበሰቡ፤ +29 እንዲሁም ከቤትጊልጋል፣+ ከጌባ+ የእርሻ ቦታዎችና ከአዝማዌት+ ተሰበሰቡ፤ ምክንያቱም ዘማሪዎቹ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ለራሳቸው የሰፈራ መንደሮችን መሥርተው ነበር። +30 ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤+ ሕዝቡን፣ በሮቹንና+ ቅጥሩንም+ አነጹ። +31 ከዚያም የይሁዳን መኳንንት አምጥቼ በቅጥሩ አናት ላይ እንዲቆሙ አደረግኩ። በተጨማሪም ምስጋና የሚያቀርቡ ሁለት ትላልቅ የዘማሪ ቡድኖችን እንዲሁም እነሱን የሚያጅቡ ቡድኖችን መደብኩ፤ አንደኛው ቡድን በስተ ቀኝ በኩል በቅጥሩ አናት ላይ ወደ አመድ ቁልል በር+ ሄደ። +32 ሆሻያህ እና ከይሁዳ መኳንንት ግማሾቹ ከኋላ ተከተሏቸው፤ +33 ከእነሱም ጋር አዛርያስ፣ ዕዝራ፣ መሹላም፣ +34 ይሁዳ፣ ቢንያም፣ ሸማያህ እና ኤርምያስ ነበሩ። +35 መለከት ከሚነፉት+ ካህናት ወንዶች ልጆች መካከል የተወሰኑት አብረዋቸው ነበሩ፤ እነሱም የአሳፍ+ ልጅ፣ የዛኩር ልጅ፣ የሚካያህ ልጅ፣ የማታንያህ ልጅ፣ የሸማያህ ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ +36 እንዲሁም ወንድሞቹ ሸማያህ፣ አዛርዔል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ ማአይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳ እና ሃናኒ ናቸው፤ እነሱም የእውነተኛውን አምላክ ሰው የዳዊትን የሙዚቃ መሣሪያዎች+ ይዘው ነበር፤ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* የሆነው ዕዝራም+ ከፊታቸው ይሄድ ነበር። +37 ከዚያም፣ ምንጭ በር+ ጋ ሲደርሱ ሽቅብ የሚወጣውን ቅጥር ይዘው ፊት ለፊት ቀጥ ብለው በመሄድ በዳዊት ከተማ+ ደረጃ+ ላይ አልፈው ከዳዊት ቤት በላይ ወዳለው ስፍራና በስተ ምሥራቅ ወዳለው ወደ ውኃ በር+ አቀኑ። +38 ምስጋና የሚያቀርበው ሌላኛው የዘማሪዎች ቡድን ደግሞ በተቃራኒ አቅጣጫ ሄደ፤ እኔም ከግማሹ ሕዝብ ጋር በመሆን ቡድኑን ተከትዬ በቅጥሩ አናት ላይ በመሄድ የመጋገሪያ ምድጃ ማማን+ አልፌ ወደ ሰፊ ቅጥር+ ተጓዝኩ፤ +39 ከዚያም በኤፍሬም በርና+ በአሮጌው ከተማ በር+ አድርጌ ወደ ዓሣ በር፣+ ወደ ሃናንኤል ማማና+ ወደ መአህ ማማ፣ በኋላም ወደ በግ በር+ ሄድኩ፤ እነሱም የጠባቂው በር ጋ ሲደርሱ ቆሙ። +40 በመጨረሻም ምስጋና የሚያቀርቡት ሁለቱም የዘማሪ ቡድኖች በእውነተኛው አምላክ ቤት ፊት ለፊት ቆሙ፤ እኔም እንዲሁ አደረግኩ፤ በተጨማሪም ከእኔ ጋር የነበሩት ግማሾቹ የበታች ገዢዎች፣ +41 ካህናት የሆኑት ኤልያቄም፣ ማአሴያህ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያህ፣ ኤሊዮዔናይ፣ ዘካርያስና ሃናንያህ ከነመለከታቸው +42 እንዲሁም ማአሴያህ፣ ሸማያህ፣ አልዓዛር፣ ዑዚ፣ የሆሃናን፣ ማልኪያህ፣ ኤላም እና ኤጼር አብረውኝ ቆሙ። ዘማሪዎቹም በይዝራህያህ መሪነት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ዘመሩ። +43 እውነተኛው አምላክ እጅግ እንዲደሰቱ ስላደረጋቸው በዚያን ቀን ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሐሴትም አደረጉ።+ ሴቶችና ልጆችም ጭምር በጣም ተደሰቱ፤+ ስለዚህ የኢየሩሳሌም ደስታ ከሩቅ ይሰማ ነበር።+ +44 በዚያን ��ን መዋጮዎች፣+ የእህል በኩራትና+ አሥራት+ በሚቀመጡባቸው ግምጃ ቤቶች+ ላይ ሰዎች ተሾሙ። እነሱም በሕጉ ላይ በታዘዘው መሠረት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚሰጠውን ድርሻ ከየከተሞቹ እርሻዎች እየሰበሰቡ ወደዚያ ማስገባት ነበረባቸው፤+ ምክንያቱም በሚያገለግሉት ካህናትና ሌዋውያን+ የተነሳ በይሁዳ +45 ዘማሪዎቹና በር ጠባቂዎቹ እንዳደረጉት ሁሉ ካህናቱና ሌዋውያኑም አምላካቸው የሚጠብቅባቸውን ግዴታም ሆነ ከመንጻት ጋር በተያያዘ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ዳዊትና ልጁ ሰለሞን በሰጡት መመሪያ መሠረት መወጣት ጀመሩ። +46 ጥንት በዳዊትና በአሳፍ ዘመን ዘማሪዎቹን እንዲሁም ለአምላክ የሚቀርቡትን የውዳሴና የምስጋና መዝሙሮች የሚመሩ ሰዎች ነበሩ።+ +47 እንዲሁም በዘሩባቤል+ ዘመንና በነህምያ ዘመን እስራኤላውያን በሙሉ ለዘማሪዎቹና+ ለበር ጠባቂዎቹ+ በየዕለቱ የሚያስፈልጋቸውን ያህል ድርሻ ይሰጧቸው ነበር። በተጨማሪም ለሌዋውያኑ የሚገባውን ድርሻ+ ለይተው ያስቀምጡ የነበረ ሲሆን ሌዋውያኑ ደግሞ ለአሮን ዘሮች የሚገባውን ድርሻ ለይተው ያስቀምጡ ነበር። +1 የሃካልያህ ልጅ የነህምያ*+ ቃል ይህ ነው፦ በ20ኛው ዓመት በኪስሌው* ወር በሹሻን*+ ግንብ* ነበርኩ። +2 በዚህ ጊዜ ከወንድሞቼ አንዱ የሆነው ሃናኒ+ በይሁዳ ከነበሩ ሌሎች ሰዎች ጋር መጣ፤ እኔም ከምርኮ ስለተረፉት አይሁዳውያን ቀሪዎችና+ ስለ ኢየሩሳሌም ጠየቅኳቸው። +3 እነሱም እንዲህ አሉኝ፦ “ከምርኮ ተመልሰው በአውራጃው ውስጥ የሚገኙት ቀሪዎች በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ፤ መሳለቂያም ሆነዋል።+ የኢየሩሳሌም ቅጥሮች ፈራርሰዋል፤+ በሮቿም በእሳት ተቃጥለዋል።”+ +4 እኔም ይህን ስሰማ ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ፤ ለቀናትም በሰማይ አምላክ ፊት ሳዝን፣ ስጾምና+ ስጸልይ ቆየሁ። +5 ከዚያም እንዲህ አልኩ፦ “የሰማይ አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ለሚወዱህ፣ ትእዛዛትህንም ለሚያከብሩ ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅና ታማኝ ፍቅር የምታሳይ ታላቅና የምትፈራ አምላክ ነህ፤+ +6 እባክህ ዛሬ ወደ አንተ የማቀርበውን የአገልጋይህን ጸሎት ለመስማት ጆሮህ ወደ እኔ ያዘንብል፤ ዓይኖችህም ይከፈቱ፤ እኛ እስራኤላውያን በአንተ ላይ የፈጸምነውን ኃጢአት እየተናዘዝኩ ስለ አገልጋዮችህ ስለ እስራኤላውያን ቀን ከሌት እየጸለይኩ ነው።+ እኔም ሆንኩ የአባቴ ቤት ኃጢአት ሠርተናል።+ +7 ለአገልጋይህ ለሙሴ የሰጠሃቸውን ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ባለማክበር+ በአንተ ላይ መጥፎ ድርጊት እንደፈጸምን ምንም ጥርጥር የለውም።+ +8 “እባክህ አገልጋይህን ሙሴን እንዲህ በማለት ያዘዝከውን ቃል* አስታውስ፦ ‘ታማኝነት የጎደለው ድርጊት የምትፈጽሙ ከሆነ በሕዝቦች መካከል እበትናችኋለሁ።+ +9 ወደ እኔ ተመልሳችሁ ትእዛዛቴን ብትጠብቁና ብትፈጽሙ ግን ሕዝቦቻችሁ እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ቢበተኑ እንኳ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤+ እንዲሁም ስሜ እንዲኖርበት ወደመረጥኩት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።’+ +10 እነሱ በታላቅ ኃይልህና በብርቱ እጅህ የዋጀሃቸው አገልጋዮችህና ሕዝቦችህ ናቸው።+ +11 ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ የአገልጋይህን ጸሎትና ስምህን በመፍራት ደስ የሚሰኙ አገልጋዮችህን ጸሎት ለመስማት ጆሮህን አዘንብል፤ እባክህ ዛሬ አገልጋይህ እንዲሳካለት አድርግ፤ ይህም ሰው ይራራልኝ።”+ እኔም የንጉሡ መጠጥ አሳላፊ ነበርኩ።+ +8 ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ከውኃ በር+ ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ተሰበሰቡ፤ ከዚያም የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* የሆነው ዕዝራ+ ይሖዋ ለእስራኤል የሰጠውን ትእዛዝ+ የያዘውን የሙሴን ሕግ+ መጽሐፍ እንዲያመጣላቸው ጠየቁት። +2 በመሆኑም ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር+ የመጀመሪያ ቀን ላይ ወንዶችን፣ ሴቶችንና የሚነገረውን ነገር ሰምተው ማስተዋል የሚችሉትን ሁሉ ወዳቀፈው ጉባኤ ሕጉን አመጣ።+ +3 እሱም ከውኃ በር ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ በተሰበሰቡት ወንዶች፣ ሴቶችና ሰምተው ማስተዋል በሚችሉ ሁሉ ፊት ድምፁን ከፍ አድርጎ ከማለዳ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ሕጉን አነበበ፤+ ሕዝቡም የሕጉ መጽሐፍ ሲነበብ በትኩረት አዳመጡ።+ +4 የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* የሆነው ዕዝራ ለዝግጅቱ ተብሎ በተሠራው የእንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ ከጎኑም በስተ ቀኝ በኩል ማቲትያህ፣ ሼማ፣ አናያ፣ ኦርዮ፣ ኬልቅያስ እና ማአሴያህ ቆመው ነበር፤ በስተ ግራው ደግሞ ፐዳያህ፣ ሚሳኤል፣ ማልኪያህ፣+ ሃሹም፣ ሃሽባዳናህ፣ ዘካርያስ እና መሹላም ቆመው ነበ +5 ዕዝራ ከሕዝቡ ሁሉ ከፍ ብሎ ቆሞ ስለነበር ሁሉም እያዩት በፊታቸው መጽሐፉን ከፈተ። መጽሐፉንም ሲከፍት ሕዝቡ ሁሉ ተነስቶ ቆመ። +6 ከዚያም ዕዝራ ታላቁንና እውነተኛውን አምላክ ይሖዋን አመሰገነ፤ በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “አሜን!* አሜን!”+ በማለት መለሰ፤ ሁሉም እጃቸውን ወደ ላይ ዘረጉ፤ መሬት ላይ በግንባራቸው ተደፍተውም ለይሖዋ ሰገዱ። +7 ሌዋውያን የሆኑት የሹዋ፣ ባኒ፣ ሸረበያህ፣+ ያሚን፣ አቁብ፣ ሻበታይ፣ ሆዲያህ፣ ማአሴያህ፣ ቀሊጣ፣ አዛርያስ፣ ዮዛባድ፣+ ሃናን እና ፐላያህ ደግሞ ሕዝቡ እዚያው ቆሞ ሳለ ሕጉን ለሕዝቡ ያብራሩ ነበር።+ +8 እነሱም ከመጽሐፉ ይኸውም ከእውነተኛው አምላክ ሕግ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በማንበብ ሕጉን በግልጽ ያብራሩና ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይናገሩ ነበር፤ በዚህ መንገድ የተነበበውን ነገር ማስተዋል እንዲችል ሕዝቡን ይረዱት ነበር።+ +9 በወቅቱ ገዢ* የነበረው ነህምያ፣ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* የሆነው ካህኑ ዕዝራና+ ሕዝቡን ያስተምሩ የነበሩት ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ “ይህ ቀን ለአምላካችሁ ለይሖዋ ቅዱስ ቀን ነው።+ አትዘኑ ወይም አታልቅሱ” አሉ። ይህን ያሉት ሕዝቡ ሁሉ የሕጉ ቃል ሲነበብ በሚሰማበት ጊዜ ያለቅስ ስለነበር ነው። +10 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሂዱ፤ ምርጥ የሆኑትን* ነገሮች ብሉ፤ ጣፋጩንም ጠጡ፤ ምንም የተዘጋጀ ነገር ለሌላቸውም ምግብ ላኩላቸው፤+ ይህ ቀን ለጌታችን ቅዱስ ነውና፤ የይሖዋ ደስታ ምሽጋችሁ* ስለሆነ አትዘኑ።” +11 ሌዋውያኑም “ይህ ቀን ቅዱስ ስለሆነ ዝም በሉ! አትዘኑ” በማለት ሕዝቡን ያረጋጉ ነበር። +12 በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ ሊበላ፣ ሊጠጣ፣ ምግቡን ለሌሎች ሊያካፍልና ሊደሰት ሄደ፤+ ምክንያቱም የተነገራቸውን ቃል ተረድተውት ነበር።+ +13 በሁለተኛውም ቀን የሕዝቡ ሁሉ የአባቶች ቤት መሪዎች፣ ካህናቱና ሌዋውያኑ የሕጉን ቃል ይበልጥ በጥልቀት ለማስተዋል የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* በሆነው በዕዝራ ዙሪያ ተሰበሰቡ። +14 ከዚያም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ባዘዘው ሕግ ውስጥ እስራኤላውያን በሰባተኛው ወር በሚከበረው በዓል ወቅት ዳስ*+ ውስጥ መቀመጥ እንዳለባቸው የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ፤ +15 እንዲሁም “ወደ ተራራማው አካባቢ ውጡና በተጻፈው መሠረት ዳሶችን ለመሥራት ከወይራ ዛፍ፣ ከዘይት ዛፍ፣ ከአደስ ዛፍ፣ ከዘንባባና ከሌሎች ዛፎች ቅጠል ያላቸውን ቅርንጫፎች አምጡ” የሚል አዋጅ በከተሞቻቸው በሙሉና በመላው ኢየሩሳሌም ማወጅ እንዳለባቸው+ የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ። +16 ስለዚህ ሕዝቡ ወጥቶ እነዚህን ቅጠሎች በማምጣት እያንዳንዱ ሰው በቤቱ ጣሪያ ላይ እንዲሁም በግቢውና በእውነተኛው አምላክ ቤት ግቢ ውስጥ፣+ በውኃ በር+ አደባባይና በኤፍሬም በር+ አደባባይ ለራሱ ዳሶች ሠራ። +17 በዚህም መንገድ ከምርኮ የተመለሱትን ሰዎች ያቀፈው መላው ጉባኤ ዳሶችን ሠራ፤ በዳሶቹም ውስጥ ተቀመጠ፤ እስራኤላውያን ከነዌ ልጅ ከኢያሱ+ ዘመን ጀምሮ እስከዚያ ቀን ድረስ በዓሉን በዚህ መንገድ አክብረው አያውቁም ነበር፤ ስለሆነም ደስታቸው ታላቅ ሆነ።+ +18 የእውነተኛው አምላክ ሕግ+ መጽሐፍም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ በየዕለቱ ይነበብ ነበር። እነሱም በዓሉን ለሰባት ቀን አከበሩ፤ በደንቡ መሠረትም በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ተደረገ።+ +11 በዚህ ጊዜ የሕዝቡ መኳንንት የሚኖሩት በኢየሩሳሌም ነበር፤+ የቀሩት ሰዎች ግን ከአሥር ሰው አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም እንዲኖርና የቀሩት ዘጠኙ ደግሞ በሌሎች ከተሞች እንዲኖሩ ዕጣ+ ጣሉ። +2 በተጨማሪም ሕዝቡ በኢየሩሳሌም ለመኖር ፈቃደኛ የሆኑትን ሰዎች በሙሉ ባረኳቸው። +3 በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት የአውራጃው መሪዎች እነዚህ ናቸው። (የቀሩት እስራኤላውያን፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹና*+ የሰለሞን አገልጋዮች+ ወንዶች ልጆች በሌሎቹ የይሁዳ ከተሞች ማለትም እያንዳንዳቸው በየከተሞቻቸው ባለው በየራሳቸው ርስት ይኖሩ ነበር።+ +4 በተጨማሪም ከይሁዳና ከቢንያም ሰዎች መካከል የተወሰኑት በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር።) ከይሁዳ ሰዎች መካከል ከፋሬስ+ ቤተሰብ የሆነው የመላልኤል ልጅ፣ የሰፋጥያህ ልጅ፣ የአማርያህ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የዖዝያ ልጅ አታያህ +5 እንዲሁም ከሴሎማውያን ቤተሰብ የሆነው የዘካርያስ ልጅ፣ የዮያሪብ ልጅ፣ የአዳያህ ልጅ፣ የሃዛያህ ልጅ፣ የኮልሆዜ ልጅ፣ የባሮክ ልጅ ማአሴያህ ነበሩ። +6 በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት የፋሬስ ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 468 ብቃት ያላቸው ወንዶች ነበሩ። +7 የቢንያም ሰዎች የሚከተሉት ነበሩ፦ የየሻያህ ልጅ፣ የኢቲኤል ልጅ፣ የማአሴያህ ልጅ፣ የቆላያህ ልጅ፣ የፐዳያህ ልጅ፣ የዮኤድ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ ሳሉ፣+ +8 ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ ጋባይ እና ሳላይ ሲሆኑ በአጠቃላይ 928 ነበሩ፤ +9 የዚክሪ ልጅ ኢዩኤል የእነሱ የበላይ ተመልካች ነበር፤ የሃስኑአ ልጅ ይሁዳ ደግሞ በከተማዋ ላይ ሁለተኛ አዛዥ ነበር። +10 ከካህናቱ መካከል ደግሞ የሚከተሉት ነበሩ፦ የዮያሪብ ልጅ የዳያህ፣ ያኪን፣+ +11 የእውነተኛው አምላክ ቤት* መሪ የሆነው የአኪጡብ+ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ ሰራያህ፤ +12 እንዲሁም የቤቱን ሥራ የሠሩት ወንድሞቻቸው 822፤ የማልኪያህ ልጅ፣ የጳስኮር+ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የአማሲ ልጅ፣ የፐላልያህ ልጅ፣ የየሮሃም ልጅ አዳያህ፣ +13 የአባቶች ቤት መሪዎች የሆኑት ወንድሞቹ 242፤ እንዲሁም የኢሜር ልጅ፣ የመሺሌሞት ልጅ፣ የአህዛይ ልጅ፣ የአዛርዔል ልጅ አማሽሳይ +14 እንዲሁም ኃያላንና ጀግኖች የሆኑት ወንድሞቻቸው 128፤ የእነሱ የበላይ ተመልካች የአንድ ታዋቂ ቤተሰብ አባል የሆነው ዛብድኤል ነበር። +15 ከሌዋውያኑ መካከል ደግሞ የሚከተሉት ነበሩ፦ የቡኒ ልጅ፣ የሃሻብያህ ልጅ፣ የአዝሪቃም ልጅ፣ የሃሹብ ልጅ ሸማያህ፣+ +16 ከእውነተኛው አምላክ ቤት ጋር በተያያዘ በውጭ ያሉትን ጉዳዮች በበላይነት ከሚከታተሉት የሌዋውያን መሪዎች መካከል ሻበታይ+ እና ዮዛባድ፤+ +17 የውዳሴ መዝሙሩንና በጸሎት ጊዜ+ የሚቀርበውን ውዳሴ የሚመራው የአሳፍ+ ልጅ፣ የዛብዲ ልጅ፣ የሚክያስ ልጅ ማታንያህ፣+ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የሆነው ባቅቡቅያ እንዲሁም የየዱቱን+ ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሻሙአ ልጅ አብዳ። +18 በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩት ሌዋውያን በአጠቃላይ 284 ነበሩ። +19 በር ጠባቂዎቹ አቁብ፣ ታልሞን+ እና በየበሮቹ ላይ የሚጠብቁት ወንድሞቻቸው ደግሞ 172 ነበሩ። +20 ከእስራኤላውያን፣ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ የቀሩት ደግሞ በሌሎቹ የይሁዳ ከተሞች ሁሉ እያንዳንዳቸው በውርስ ባገኙት ርስት ላይ ይኖሩ ነበር። +21 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች*+ በኦፌል+ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ጺሃ እና ጊሽፓ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች* ኃላፊዎች ነበሩ። +22 በኢየሩሳሌም የነበሩት ሌዋውያን የበላይ ተመልካች ከዘማሪዎቹ ከአሳፍ ልጆች መካከል የሚካ ልጅ፣ የማታንያህ+ ልጅ፣ የሃሻብያህ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ዑዚ ነበር፤ እሱም በእውነተኛው አምላክ ቤት ሥራ ላይ ኃላፊ ነበር። +23 እነሱን በተመለከተ የወጣ ንጉሣዊ ትእዛዝ ነበር፤+ ለዘማሪዎቹ በየዕለቱ የሚያስፈልገውን ነገር በማቅረብ ረገድም ቋሚ የሆነ ዝግጅት ነበር። +24 የይሁዳ ልጅ ከሆነው ከዛራ ልጆች መካከል የመሺዛቤል ልጅ ፐታያህ ከሕዝቡ ጋር የተያያዘውን ማንኛውንም ጉዳይ በተመለከተ የንጉሡ አማካሪ* ነበር። +25 የሰፈራ መንደሮቹ ከነእርሻ ቦታዎቻቸው የሚከተሉት ናቸው፦ ከይሁዳ ወንዶች ልጆች መካከል የተወሰኑት በቂርያትአርባና+ በሥሯ* ባሉት ከተሞች፣ በዲቦንና በሥሯ ባሉት ከተሞች፣ በየቃብጸኤል+ እና በሥሯ ባሉት የሰፈራ መንደሮች፣ +26 በየሹዋ፣ በሞላዳ፣+ በቤትጳሌጥ፣+ +27 በሃጻርሹአል፣+ በቤርሳቤህና በሥሯ* ባሉት ከተሞች፣ +28 በጺቅላግ፣+ በመኮና እና በሥሯ* ባሉት ከተሞች፣ +29 በኤንሪሞን፣+ በጾራ፣+ በያርሙት፣ +30 በዛኖሃ፣+ በአዱላምና በሥሯ ባሉት የሰፈራ መንደሮች፣ በለኪሶና+ በእርሻ ቦታዎቿ እንዲሁም በአዜቃና+ በሥሯ* ባሉት ከተሞች ይኖሩ ነበር። እነሱም ከቤርሳቤህ እስከ ሂኖም ሸለቆ+ ባለው አካባቢ ሰፈሩ። +31 የቢንያም ሰዎች ደግሞ ከጌባ+ ጀምሮ በሚክማሽ፣ በጋያ፣ በቤቴል+ እና በሥሯ* ባሉት ከተሞች፣ +32 በአናቶት፣+ በኖብ፣+ በአናንያ፣ +33 በሃጾር፣ በራማ፣+ በጊታይም፣ +34 በሃዲድ፣ በጸቦይም፣ በነባላጥ፣ +35 በሎድ እና በኦኖ+ እንዲሁም በእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ሸለቆ ተቀመጡ። +36 በይሁዳ ከነበሩት ሌዋውያን መካከል የተወሰኑት ቡድኖች በቢንያም ተመደቡ። +2 ንጉሥ አርጤክስስ+ በነገሠ በ20ኛው ዓመት+ በኒሳን* ወር በንጉሡ ፊት የወይን ጠጅ ቀርቦ ነበር፤ እኔም እንደተለመደው የወይን ጠጁን አንስቼ ለንጉሡ ሰጠሁት።+ ሆኖም ከዚህ ቀደም እሱ ጋ ስቀርብ በፊቴ ላይ ሐዘን ታይቶ አያውቅም ነበር። +2 በመሆኑም ንጉሡ “ሳትታመም ፊትህ እንዲህ በሐዘን የጠቆረው ለምንድን ነው? ይህ መቼም የልብ ሐዘን እንጂ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም” አለኝ። በዚህ ጊዜ በጣም ፈራሁ። +3 ከዚያም ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር! አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፈራርሳ፣ በሮቿም በእሳት ተቃጥለው እያለ ለምን ፊቴ በሐዘን አይጠቁር?”+ +4 ንጉሡም መልሶ “ታዲያ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለኝ። እኔም ወዲያውኑ ወደ ሰማይ አምላክ ጸለይኩ።+ +5 ከዚያም ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነና አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ ካገኘ ከተማዋን መልሼ እንድገነባ አባቶቼ ወደተቀበሩባት ከተማ፣ ወደ ይሁዳ እንድሄድ ፍቀድልኝ።”+ +6 ንጉሡም ንግሥቲቱ አጠገቡ ተቀምጣ ሳለ “ጉዞህ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል? መቼ ትመለሳለህ?” አለኝ። ንጉሡም ደስ ብሎት እንድሄድ ፈቀደልኝ፤+ እኔም ጊዜውን ቆርጬ ነገርኩት።+ +7 ከዚያም ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ ከወንዙ+ ባሻገር* ያለው ክልል ገዢዎች ይሁዳ እስክደርስ ድረስ በሰላም ምድራቸውን አቋርጬ እንዳልፍ እንዲፈቅዱልኝ ደብዳቤ ይሰጠኝ፤ +8 በተጨማሪም የንጉሡ መናፈሻ ቦታ* ጠባቂ የሆነው አሳፍ ለቤቱ* የግንብ አጥር+ በሮች፣ ለከተማዋ ቅጥሮችና+ ለምሄድበት ቤት የሚያገለግሉ ሳንቃዎች እንዲሰጠኝ ደብዳቤ ይጻፍልኝ።” በዚህ ጊዜ መልካም የሆነው የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ ስለነበር+ ንጉሡ እነዚህን ሰጠኝ።+ +9 በመጨረሻም ከወንዙ ባሻገር ወዳለው ክልል ገዢዎች ሄጄ የንጉሡን ደብዳቤዎች ሰጠኋቸው። ��ተጨማሪም ንጉሡ የጦር አለቆችና ፈረሰኞች አብረውኝ እንዲሄዱ አድርጎ ነበር። +10 ሆሮናዊው ሳንባላጥና+ አሞናዊው+ ባለሥልጣን* ጦብያ+ ይህን ነገር ሲሰሙ ለእስራኤላውያን መልካም ነገር የሚያደርግ ሰው በመምጣቱ በጣም ተበሳጩ። +11 በመጨረሻም ኢየሩሳሌም ደረስኩ፤ እዚያም ሦስት ቀን ቆየሁ። +12 ከዚያም በሌሊት ተነሳሁ፤ ከእኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ አምላኬ ለኢየሩሳሌም እንዳደርግ በልቤ ያኖረውን ነገር ለማንም ሰው አልተናገርኩም፤ ከተቀመጥኩበት እንስሳም በስተቀር ሌላ እንስሳ ከእኔ ጋር አልነበረም። +13 በሌሊትም በሸለቆ በር+ ከወጣሁ በኋላ በትልቁ እባብ ምንጭ ፊት ለፊት በማለፍ ወደ አመድ ቁልል በር+ ሄድኩ፤ የፈራረሱትን የኢየሩሳሌም ቅጥሮችና በእሳት የተቃጠሉትን በሮቿንም አንድ በአንድ መረመርኩ።+ +14 ከዚያም አልፌ ወደ ምንጭ በርና+ ወደ ንጉሡ ኩሬ ሄድኩ፤ በዚያም የተቀመጥኩበትን እንስሳ ማሳለፍ የሚያስችል በቂ ቦታ አልነበረም። +15 ሆኖም ሌሊቱን ሸለቆውን*+ ይዤ ሽቅብ ወጣሁ፤ ቅጥሩንም መመርመሬን ቀጠልኩ፤ ከዚያም ተመልሼ በሸለቆ በር ገባሁ፤ በኋላም ወደመጣሁበት ተመለስኩ። +16 ለአይሁዳውያኑ፣ ለካህናቱ፣ ለተከበሩት ሰዎች፣ ለበታች ገዢዎቹና+ ለቀሩት ሠራተኞች ገና ምንም የነገርኳቸው ነገር ስላልነበር የበታች ገዢዎቹ የት እንደሄድኩና ምን እያደረግኩ እንደነበር አላወቁም። +17 በመጨረሻም እንዲህ አልኳቸው፦ “መቼም ያለንበት ሁኔታ ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆነ ሳትመለከቱ አትቀሩም፤ ኢየሩሳሌም ፈራርሳለች፣ በሮቿም በእሳት ተቃጥለዋል። እንግዲህ ተዋርደን እንዳንቀር ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች መልሰን እንገንባ።” +18 ከዚያም የአምላኬ መልካም እጅ ምን ያህል በእኔ ላይ እንደነበርና+ ንጉሡም ምን እንዳለኝ ነገርኳቸው።+ እነሱም “እንነሳና እንገንባ” አሉ። በመሆኑም መልካሙን ሥራ ለመሥራት ራሳቸውን* አበረቱ።+ +19 ሆሮናዊው ሳንባላጥና አሞናዊው+ ባለሥልጣን* ጦብያ+ እንዲሁም የዓረብ+ ተወላጅ የሆነው ጌሼም ይህን ሲሰሙ ያፌዙብንና+ በንቀት ዓይን ይመለከቱን ጀመር፤ እንዲህም አሉን፦ “ምን እያደረጋችሁ ነው? በንጉሡ ላይ ልታምፁ ነው?”+ +20 እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩላቸው፦ “ሥራችንን የሚያሳካልን የሰማይ አምላክ ነው፤+ እኛ አገልጋዮቹም ተነስተን እንገነባለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ምንም ዓይነት ድርሻም ሆነ መብት ወይም መታሰቢያ የላችሁም።”+ +4 ሳንባላጥ+ ቅጥሩን መልሰን እየገነባን መሆናችንን ሲሰማ በጣም ተናደደ፤ እጅግም ተበሳጨ፤ በአይሁዳውያንም ላይ ያፌዝ ነበር። +2 በወንድሞቹና በሰማርያ ጦር ሠራዊት ፊትም እንዲህ ይል ጀመር፦ “እነዚህ አቅመ ቢስ አይሁዳውያን ምን እያደረጉ ነው? ለመሆኑ ይህን ሥራ ራሳቸው ሊሠሩት ነው? መሥዋዕትስ ሊያቀርቡ ነው? ደግሞስ በአንድ ቀን ሠርተው ሊጨርሱ ያስባሉ? በእሳት ተቃጥለው የአመድ ቁልል የሆኑትን ድንጋዮች ሕይወት ሊዘሩባቸው ነው +3 በዚህ ጊዜ አጠገቡ ቆሞ የነበረው አሞናዊው+ ጦብያ+ “የሚገነቡት የድንጋይ ቅጥር እኮ ቀበሮ እንኳ ቢወጣበት ይፈርሳል” አለ። +4 አምላካችን ሆይ፣ መሳለቂያ ሆነናልና+ ስማ፤ ስድባቸውን በራሳቸው ላይ መልስባቸው፤+ እንዲበዘበዙና ተማርከው ወደ ሌላ አገር እንዲወሰዱ አድርጋቸው። +5 የግንባታውን ሥራ የሚሠሩትን ሰዎች ስለተሳደቡ በደላቸውን አትሸፍን፤+ ኃጢአታቸውም ከፊትህ እንዲደመሰስ አታድርግ። +6 እኛም ቅጥሩን መገንባታችንን ቀጠልን፤ ዙሪያውን ያለው ቅጥርም ክፍተቱ እየተደፈነ እስከ ቁመቱ እኩሌታ ድረስ ተጠገነ፤ ሕዝቡም ሥራውን ከልቡ መሥራቱን ቀጠለ። +7 ሳንባላጥ፣ ጦብያ፣+ ዓረቦች፣+ አሞናውያንና አሽዶዳውያን+ የኢየሩሳሌምን ቅጥ���ች የመጠገኑ ሥራ እየተፋጠነና ክፍተቶቹም እየተደፈኑ መሆናቸውን ሲሰሙ እጅግ ተናደዱ። +8 እነሱም መጥተው ኢየሩሳሌምን ለመውጋትና በውስጧ ሁከት ለመፍጠር በአንድነት አሴሩ። +9 እኛ ግን ወደ አምላካችን ጸለይን፤ ከእነሱ ጥቃት ሌት ተቀን የሚጠብቁን ጠባቂዎችም አቆምን። +10 የይሁዳ ሰዎች ግን እንዲህ ይሉ ነበር፦ “የሠራተኞቹ* አቅም እየተሟጠጠ ነው፤ ፍርስራሹ ደግሞ በጣም ብዙ ነው፤ ፈጽሞ ቅጥሩን መገንባት አንችልም።” +11 ጠላቶቻችንም “ምንም ሳያውቁ ወይም ሳያዩን መካከላቸው ገብተን እንገድላቸዋለን፤ ሥራውንም እናስቆማለን” ይሉ ነበር። +12 በእነሱ አቅራቢያ የሚኖሩት አይሁዳውያንም በመጡ ቁጥር “በሁሉም አቅጣጫ ይዘምቱብናል” እያሉ ደጋግመው* ይነግሩን ነበር። +13 ስለዚህ ከቅጥሩ ጀርባ በሚገኘው ገላጣ በሆነው ዝቅተኛ ቦታ ላይ ሰዎችን አቆምኩ፤ እነሱም ሰይፋቸውን፣ ጦራቸውንና ቀስታቸውን ይዘው በየቤተሰቦቻቸው እንዲቆሙ አደረግኩ። +14 ሰዎቹ መፍራታቸውን ሳይም ወዲያውኑ ተነስቼ የተከበሩትን ሰዎች፣+ የበታች ገዢዎቹንና የቀረውን ሕዝብ እንዲህ አልኳቸው፦ “አትፍሯቸው።+ ታላቁንና የተፈራውን ይሖዋን አስቡ፤+ ለወንድሞቻችሁ፣ ለወንዶች ልጆቻችሁ፣ ለሴቶች ልጆቻችሁ፣ ለሚስቶቻችሁና ለቤታችሁ ተዋጉ።” +15 ጠላቶቻችንም ሴራቸውን እንዳወቅንባቸውና እውነተኛው አምላክ ዕቅዳቸውን እንዳከሸፈባቸው ሰሙ፤ ከዚያም ሁላችንም ቅጥሩን ወደ መገንባቱ ሥራችን ተመለስን። +16 ከዚያን ቀን ጀምሮ አብረውኝ ካሉት ሰዎች መካከል ግማሾቹ ሥራውን ሲሠሩ+ ግማሾቹ ደግሞ ጦር፣ ጋሻና ቀስት ይዘው እንዲሁም ጥሩር ለብሰው ይቆሙ ነበር። መኳንንቱ+ ከአይሁዳውያኑ ኋላ ቆመው ድጋፍ ሲሰጧቸው +17 እነሱ ደግሞ ቅጥሩን ይገነቡ ነበር። ሸክም የሚሸከሙት ሰዎች እያንዳንዳቸው በአንድ እጃቸው ሥራውን ሲሠሩ በሌላ እጃቸው ደግሞ የጦር መሣሪያ* ይይዙ ነበር። +18 የግንባታውን ሥራ የሚሠራ እያንዳንዱ ሰው ግንባታውን የሚያከናውነው ሰይፉን በወገቡ ታጥቆ ነበር፤ ቀንደ መለከት የሚነፋውም+ ሰው አጠገቤ ይቆም ነበር። +19 ከዚያም የተከበሩትን ሰዎች፣ የበታች ገዢዎቹንና የቀረውን ሕዝብ እንዲህ አልኳቸው፦ “ሥራው እንደምታዩት ብዙና ሰፊ ነው፤ ቅጥሩንም የምንገነባው አንዳችን ከሌላው ተራርቀን ነው። +20 በመሆኑም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ እኛ ወዳለንበት ቦታ ተሰብሰቡ። አምላካችን ራሱ ይዋጋልናል።”+ +21 ስለዚህ ግማሾቻችን ሥራውን ስናከናውን ግማሾቹ ደግሞ ጎህ ከሚቀድበት አንስቶ ከዋክብት እስከሚወጡበት ጊዜ ድረስ ጦር ይዘው ይቆሙ ነበር። +22 በዚህ ጊዜ ሕዝቡን እንዲህ አልኳቸው፦ “እያንዳንዱ ሰው ከአገልጋዩ ጋር ሆኖ ሌሊቱን በኢየሩሳሌም ውስጥ ያሳልፍ፤ እነሱም ሌሊቱን ይጠብቁናል፤ ቀን ላይ ደግሞ ይሠራሉ።” +23 እኔም ሆንኩ ወንድሞቼና አገልጋዮቼ+ እንዲሁም ይከተሉኝ የነበሩት ጠባቂዎች ፈጽሞ ልብሳችንን አናወልቅም ነበር፤ የጦር መሣሪያችንም ከቀኝ እጃችን አይለይም ነበር። +6 ሳንባላጥ፣ ጦብያ፣+ የዓረብ+ ተወላጅ የሆነው ጌሼምና የቀሩት ጠላቶቻችን ቅጥሩን መልሼ እንደገነባሁና+ ክፍተቶቹ ሁሉ እንደተደፈኑ ሲነገራቸው (ምንም እንኳ ገና መዝጊያዎቹን በበሮቹ ላይ ባልገጥማቸውም)፣+ +2 ሳንባላጥና ጌሼም “እስቲ መጥተህ በኦኖ+ ሸለቋማ ሜዳ ከሚገኙት መንደሮች በአንዱ ለመገናኘት ቀጠሮ እንያዝ” የሚል መልእክት ወዲያውኑ ላኩብኝ። ሆኖም እኔን ለመጉዳት አሲረው ነበር። +3 በመሆኑም “ትልቅ ሥራ እየሠራሁ ስለሆነ ወደዚያ መውረድ አልችልም። ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ምክንያት ለምን ሥራው ይስተጓጎል?” ብለው እንዲነግሯቸው መልእክተኞችን ��ክሁባቸው። +4 እነሱም ያንኑ መልእክት አራት ጊዜ ላኩብኝ፤ እኔም በላኩብኝ ቁጥር ይህንኑ መልስ መለስኩላቸው። +5 ከዚያም ሳንባላጥ አገልጋዩን ያልታሸገ ደብዳቤ በእጁ አስይዞ ለአምስተኛ ጊዜ ያንኑ መልእክት ላከብኝ። +6 ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፦ “አንተም ሆንክ አይሁዳውያኑ ለማመፅ እያሴራችሁ+ መሆኑን ብሔራት ሁሉ ሰምተዋል፤ ጌሼምም+ ይህንኑ እየተናገረ ነው። ቅጥሩንም እየገነባህ ያለኸው ለዚሁ ነው፤ እንደተባለው ከሆነ ደግሞ ንጉሣቸው ልትሆን ነው። +7 በተጨማሪም በመላው ኢየሩሳሌም ‘በይሁዳ ንጉሥ አለ!’ ብለው ስለ አንተ እንዲያውጁ ነቢያትን ሾመሃል። እነዚህ ነገሮች ደግሞ ንጉሡ ጆሮ መድረሳቸው አይቀርም። ስለሆነም መጥተህ በጉዳዩ ላይ ብንነጋገር ይሻላል።” +8 እኔ ግን እንዲህ ስል መለስኩለት፦ “ከተናገርከው ነገር መካከል አንዱም አልተፈጸመም፤ ሁሉም ነገር አንተ ራስህ በአእምሮህ* የፈጠርከው ነው።” +9 ምክንያቱም ሁሉም “እጃቸው ስለሚዝል ሥራው እንደሆነ አይጠናቀቅም” በማለት ሊያስፈራሩን ይሞክሩ ነበር።+ በዚህ ጊዜ እጆቼን አበርታልኝ ብዬ ጸለይኩ።+ +10 ከዚያም የመሄጣቤል ልጅ ወደሆነው ወደ ደላያህ ልጅ ወደ ሸማያህ ቤት ሄድኩ፤ እሱም ቤቱ ውስጥ ነበር። እንዲህም አለኝ፦ “ሊገድሉህ ስለሚመጡ በእውነተኛው አምላክ ቤት ይኸውም ቤተ መቅደሱ ውስጥ መቼ እንደምንገናኝ እንቀጣጠር፤ የቤተ መቅደሱንም በሮች እንዝጋ። አንተን ለመግደል በሌሊት ይመጣሉ።” +11 እኔ ግን “እንደ እኔ ያለ ሰው መሸሽ ይገባዋል? ደግሞስ እንደ እኔ ያለ ሰው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ገብቶ በሕይወት ሊኖር ይችላል?+ በፍጹም አልገባም!” አልኩት። +12 ከዚያም ይህን ሰው አምላክ እንዳላከው ከዚህ ይልቅ ጦብያና ሳንባላጥ+ በእኔ ላይ ይህን ትንቢት እንዲናገር እንደቀጠሩት ተገነዘብኩ። +13 ይህን ሰው የቀጠሩት አስፈራርቶ ኃጢአት እንድሠራ እንዲያደርገኝና በዚህም የተነሳ ስሜን የሚያጠፉበት ምክንያት በማግኘት ሊሳለቁብኝ ፈልገው ነው። +14 አምላኬ ሆይ፣ ጦብያና+ ሳንባላጥ የሚያደርጉትን ይህን ነገር እንዲሁም እኔን ለማስፈራራት ተደጋጋሚ ሙከራ የሚያደርጉትን ነቢዪቱ ኖአድያህንና ሌሎቹን ነቢያት አስብ። +15 ቅጥሩም በኤሉል* ወር በ25ኛው ቀን በ52 ቀናት ውስጥ ተሠርቶ ተጠናቀቀ። +16 ጠላቶቻችን በሙሉ ይህን ሲሰሙና በዙሪያችን ያሉት ብሔራትም ይህን ሲያዩ በኀፍረት ተዋጡ፤*+ ይህ ሥራ የተከናወነው በአምላካችን እርዳታ እንደሆነም ተገነዘቡ። +17 በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ የተከበሩ ሰዎች+ ለጦብያ ብዙ ደብዳቤዎችን ይልኩለት የነበረ ሲሆን እሱም መልስ ይጽፍላቸው ነበር። +18 ጦብያ የኤራ+ ልጅ የሸካንያህ አማች ስለነበርና ልጁ የሆሃናን ደግሞ የቤራክያህን ልጅ የመሹላምን+ ሴት ልጅ ስላገባ በይሁዳ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በታማኝነት ከጎኑ እንደሚቆሙ ምለውለት ነበር። +19 በተጨማሪም ዘወትር ስለ እሱ መልካም ነገሮችን ይነግሩኝ የነበረ ከመሆኑም ሌላ እኔ የምለውንም ለእሱ ያወሩለት ነበር። ጦብያም እኔን ለማስፈራራት ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር።+ +10 በስምምነቱ ላይ ማኅተማቸውን በማተም ያጸደቁት+ እነዚህ ናቸው፦ የሃካልያህ ልጅ የሆነው ገዢው* ነህምያ፣ ሴዴቅያስ፣ +2 ሰራያህ፣ አዛርያስ፣ ኤርምያስ፣ +3 ጳስኮር፣ አማርያህ፣ ማልኪያህ፣ +4 ሃጡሽ፣ ሸባንያህ፣ ማሉክ፣ +5 ሃሪም፣+ መሬሞት፣ አብድዩ፣ +6 ዳንኤል፣+ ጊነቶን፣ ባሮክ፣ +7 መሹላም፣ አቢያህ፣ ሚያሚን፣ +8 ማአዝያህ፣ ቢልጋይ እና ሸማያህ፤ ካህናቱ እነዚህ ናቸው። +9 ሌዋውያኑ ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦ የአዛንያህ ልጅ የሹዋ፣ ከሄናዳድ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው ቢኑይ፣ ቃድሚኤል፣+ +10 እንዲሁም ወንድሞቻቸው የሆኑት ሸባንያህ፣ ሆዲያህ፣ ቀሊጣ፣ ፐላያህ፣ ሃናን፣ +11 ሚካ፣ ሬሆብ፣ ሃሻብያህ፣ +12 ዛኩር፣ ሸረበያህ፣+ ሸባንያህ፣ +13 ሆዲያህ፣ ባኒ እና ቤኒኑ። +14 የሕዝቡ መሪዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ፓሮሽ፣ ፓሃትሞአብ፣+ ኤላም፣ ዛቱ፣ ባኒ፣ +15 ቡኒ፣ አዝጋድ፣ ቤባይ፣ +16 አዶንያስ፣ ቢግዋይ፣ አዲን፣ +17 አጤር፣ ሕዝቅያስ፣ አዙር፣ +18 ሆዲያህ፣ ሃሹም፣ ቤጻይ፣ +19 ሃሪፍ፣ አናቶት፣ ነባይ፣ +20 ማግፒአሽ፣ መሹላም፣ ሄዚር፣ +21 መሺዛቤል፣ ሳዶቅ፣ ያዱአ፣ +22 ጰላጥያህ፣ ሃናን፣ አናያ፣ +23 ሆሺአ፣ ሃናንያህ፣ ሃሹብ፣ +24 ሃሎሔሽ፣ ፒልሃ፣ ሾቤቅ፣ +25 ረሁም፣ ሃሻብናህ፣ ማአሴያህ፣ +26 አኪያህ፣ ሃናን፣ አናን፣ +27 ማሉክ፣ ሃሪም እና ባአናህ። +28 የቀረው ሕዝብ ማለትም ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ ዘማሪዎቹ፣ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ* እንዲሁም የእውነተኛውን አምላክ ሕግ ለመጠበቅ በምድሪቱ ካሉት ሕዝቦች ራሳቸውን የለዩ ሁሉ+ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ጨምሮ እውቀትና ማስተዋል ያለው* ማንኛውም ሰው +29 ከወንድሞቻቸውና ታዋቂ ከሆኑት ሰዎቻቸው ጋር በመሆን የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ በሆነው በሙሴ እጅ በተሰጠው የእውነተኛው አምላክ ሕግ መሠረት ለመሄድ እንዲሁም የጌታችንን የይሖዋን ትእዛዛት፣ ፍርዶችና ሥርዓቶች ሁሉ በጥንቃቄ ለመጠበቅ በእርግማንና በመሐላ ራሳቸውን ግዴታ ውስጥ አስገቡ። +30 ሴቶች ልጆቻችንን በምድሪቱ ለሚኖሩ ሰዎች አንሰጥም፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም።+ +31 በምድሪቱ የሚኖሩት ሕዝቦች በሰንበት ቀን ሸቀጣ ሸቀጦቻቸውንና የተለያዩ ጥራጥሬዎችን ለመሸጥ ቢያመጡ በሰንበት+ ወይም ቅዱስ በሆነ ቀን+ ከእነሱ ላይ ምንም ነገር አንገዛም። በተጨማሪም በሰባተኛው ዓመት+ ምርት ከማምረት እንቆጠባለን፤ ያልተከፈለን ዕዳም ሁሉ እንሰርዛለን።+ +32 በተጨማሪም እያንዳንዳችን በአምላካችን ቤት* ለሚከናወነው አገልግሎት በየዓመቱ አንድ ሦስተኛ ሰቅል* ለመስጠት ራሳችንን ግዴታ ውስጥ እናስገባለን፤+ +33 ይህም በሰንበት ቀናትና+ በአዲስ ጨረቃ ወቅት+ ለሚቀርበው የሚነባበር ዳቦ*+ እንዲሁም በእነዚህ ጊዜያት ዘወትር ለሚቀርበው የእህል መባና+ የሚቃጠል መባ፣ በተጨማሪም በተወሰኑ ጊዜያት ለሚከበሩት በዓላት፣+ ቅዱስ ለሆኑት ነገሮች፣ እስራኤልን ለማስተሰረይ ለሚቀርቡት የኃጢአት መባዎችና+ በአምላካችን ቤት +34 ከዚህም ሌላ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና ሕዝቡ በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት በየዓመቱ በተወሰነው ጊዜ በአምላካችን በይሖዋ መሠዊያ ላይ እንዲቃጠል በየአባቶቻችን ቤት በየተራ ወደ አምላካችን ቤት ሊያመጡ የሚገባውን እንጨት በተመለከተ ዕጣ ጣልን።+ +35 እንዲሁም መሬታችን የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬና ማንኛውም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፍ የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ ሁሉ በየዓመቱ ወደ ይሖዋ ቤት እናመጣለን፤+ +36 በተጨማሪም በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት ከወንዶች ልጆቻችንና ከእንስሶቻችን በኩሩን+ እንዲሁም ከከብቶቻችንና ከመንጎቻችን በኩሩን እናመጣለን። ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት እናመጣለን።+ +37 ከዚህም በተጨማሪ የተፈጨውን የእህላችንን በኩር፣+ መዋጮዎቻችንን፣ ማንኛውም ዛፍ የሚያፈራውን ፍሬ፣+ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት+ ወደ አምላካችን ቤት ግምጃ ቤቶች*+ ወደ ካህናቱ እናመጣለን፤ እንዲሁም ከእርሻ ከተሞቻችን ሁሉ አንድ አሥረኛውን* የሚቀበሉት ሌዋውያኑ ስለሆኑ የመሬታችንን አንድ አሥረኛ ለ +38 ሌዋውያኑ አንድ አሥረኛውን በሚቀበሉበት ጊዜ ካህኑ የአሮን ልጅ ከሌዋውያኑ ጋር አብሮ መሆን አለበት፤ ሌዋውያኑም የአንድ አሥ��ኛውን አንድ አሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በግምጃ ቤቱ ውስጥ ወደሚገኙት ክፍሎች* መውሰድ ይኖርባቸዋል።+ +39 ምክንያቱም እስራኤላውያንም ሆኑ የሌዋውያኑ ልጆች የእህሉን፣ የአዲሱን ወይን ጠጅና የዘይቱን+ መዋጮ ማምጣት ያለባቸው ወደ ግምጃ ቤቶቹ* ነው፤+ ደግሞም የመቅደሱ ዕቃዎች የሚቀመጡትም ሆነ የሚያገለግሉት ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና ዘማሪዎቹ የሚገኙት በዚያ ነው። እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።+ +9 በዚህ ወር በ24ኛው ቀን እስራኤላውያን ተሰበሰቡ፤ ማቅ ለብሰውና በላያቸው ላይ አቧራ ነስንሰው ጾሙ።+ +2 ከዚያም የእስራኤል ዘሮች ከባዕዳን ሁሉ ራሳቸውን ለዩ፤+ ቆመውም ኃጢአታቸውንና አባቶቻቸው የፈጸሙትን ስህተት ሁሉ ተናዘዙ።+ +3 ከዚያም ባሉበት ስፍራ ቆሙ፤ በቀኑ አንድ አራተኛም* ከአምላካቸው ከይሖዋ የሕግ መጽሐፍ+ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያነብቡ፣ በቀኑ አንድ አራተኛ ደግሞ ለአምላካቸው ለይሖዋ ይናዘዙና ይሰግዱ ነበር። +4 የሹዋ፣ ባኒ፣ ቃድሚኤል፣ ሸባንያህ፣ ቡኒ፣ ሸረበያህ፣+ ባኒ እና ኬናኒ ለሌዋውያኑ በተሠራው ከፍ ያለ መድረክ ላይ ቆመው+ ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ ጮኹ። +5 እንዲሁም ሌዋውያኑ የሹዋ፣ ቃድሚኤል፣ ባኒ፣ ሃሻበንያህ፣ ሸረበያህ፣ ሆዲያህ፣ ሸባንያህ እና ፐታያህ እንዲህ አሉ፦ “ተነሱ፤ አምላካችሁን ይሖዋን ከዘላለም እስከ ዘላለም አመስግኑ።+ ከምስጋናና ከውዳሴ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለውን ክብራማ ስምህን ያመስግኑ። +6 “አንተ ብቻ ይሖዋ ነህ፤+ አንተ ሰማያትን፣ አዎ ሰማየ ሰማያትንና ሠራዊታቸውን ሁሉ፣ ምድርንና በላይዋ ያሉትን ሁሉ፣ ባሕርንና በውስጡ ያሉትን ሁሉ ሠርተሃል። ሁሉንም ሕያው አድርገህ ታኖራቸዋለህ፤ የሰማይ ሠራዊትም ለአንተ ይሰግዳል። +7 አብራምን+ መርጠህ ከከለዳውያን ዑር+ ያወጣኸውና አብርሃም+ ብለህ የጠራኸው እውነተኛው አምላክ ይሖዋ አንተ ነህ። +8 ልቡ በፊትህ ታማኝ ሆኖ ስላገኘኸው+ የከነአናውያንን፣ የሂታውያንን፣ የአሞራውያንን፣ የፈሪዛውያንን፣ የኢያቡሳውያንንና የገርጌሻውያንን ምድር ለእሱ ይኸውም ለዘሩ ለመስጠት ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን ተጋባህ፤+ ጻድቅ ስለሆንክም ቃልህን ጠበቅክ። +9 “በመሆኑም አባቶቻችን በግብፅ ሳሉ የደረሰባቸውን ሥቃይ አየህ፤+ በቀይ ባሕር ያሰሙትንም ጩኸት ሰማህ። +10 ከዚያም በፈርዖን፣ በአገልጋዮቹ ሁሉና በምድሩ በሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ፊት ምልክቶችንና ተአምራትን አሳየህ፤+ ይህን ያደረግከው በእነሱ ላይ የእብሪት ድርጊት+ እንደፈጸሙ ስላወቅክ ነው። ለራስህም እስከ ዛሬ ጸንቶ የኖረ ስም አተረፍክ።+ +11 በባሕሩ መሃል በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልክ፤+ አሳዳጆቻቸውንም የሚናወጥ ባሕር ውስጥ እንደተጣለ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ወረወርካቸው።+ +12 ቀን በደመና ዓምድ፣ ሌሊት ደግሞ የሚሄዱበት መንገድ ብርሃን እንዲሆንላቸው ለማድረግ ስትል በእሳት ዓምድ መራሃቸው።+ +13 በሲና ተራራ ላይ ወርደህ+ ከሰማይ አነጋገርካቸው፤+ እንዲሁም የጽድቅ ፍርዶችን፣ የእውነት ሕጎችን፣* መልካም ሥርዓቶችንና ትእዛዛትን ሰጠሃቸው።+ +14 ቅዱስ ሰንበትህን አሳወቅካቸው፤+ እንዲሁም በአገልጋይህ በሙሴ አማካኝነት ትእዛዛትህን፣ ሥርዓቶችህንና ሕግህን ሰጠሃቸው። +15 በተራቡ ጊዜ ከሰማይ ምግብ ሰጠሃቸው፤+ በተጠሙም ጊዜ ከዓለቱ ውኃ አፈለቅክላቸው፤+ ልትሰጣቸው የማልክላቸውን* ምድር ገብተው እንዲወርሱም ነገርካቸው። +16 “ይሁንና እነሱ ማለትም አባቶቻችን የእብሪት ድርጊት ፈጸሙ፤+ ግትሮችም ሆኑ፤*+ ትእዛዛትህንም አልሰሙም። +17 ለመስማትም አሻፈረኝ አሉ፤+ በመካከላቸው የፈጸምካቸውን እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች ረሱ፤ ከዚህ ይልቅ ግትሮች ሆኑ���* በግብፅ ወደነበሩበት የባርነት ሕይወት ለመመለስም መሪ ሾሙ።+ አንተ ግን ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆንክ፣* ሩኅሩኅ፣* መሐሪ፣ ለቁጣ የዘገየህና ታማኝ ፍቅርህ የበዛ* አምላክ ነህ፤+ እ +18 ሌላው ቀርቶ ለራሳቸው የብረት* ጥጃ ሐውልት ሠርተው ‘ከግብፅ መርቶ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው’+ በማለት ከፍተኛ የንቀት ተግባር በፈጸሙ ጊዜም +19 አንተ ምሕረትህ ታላቅ ስለሆነ በምድረ በዳ አልተውካቸውም።+ ቀን ቀን በመንገዳቸው ይመራቸው የነበረው የደመና ዓምድም ሆነ የሚሄዱበትን መንገድ የሚያበራላቸው ሌሊት ሌሊት ይታይ የነበረው የእሳት ዓምድ ከላያቸው አልተነሳም ነበር።+ +20 ጥልቅ ማስተዋል እንዲያገኙ መልካም መንፈስህን ሰጠሃቸው፤+ መናህንም ከአፋቸው አልከለከልክም፤+ በተጠሙም ጊዜ ውኃ ሰጠሃቸው።+ +21 በምድረ በዳም ለ40 ዓመት መገብካቸው።+ ምንም ያጡት ነገር አልነበረም። ልብሶቻቸው አላለቁም፤+ እግሮቻቸውም አላበጡም። +22 “መንግሥታትንና ሕዝቦችን እየከፋፈልክ ሰጠሃቸው፤+ በመሆኑም የሲሖንን+ ምድር ይኸውም የሃሽቦንን+ ንጉሥ ምድር እንዲሁም የባሳንን ንጉሥ የኦግን+ ምድር ወረሱ። +23 ወንዶች ልጆቻቸውንም በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት አበዛሃቸው።+ ከዚያም ገብተው እንዲወርሷት ለአባቶቻቸው ቃል ወደገባህላቸው ምድር አመጣሃቸው።+ +24 በመሆኑም ወንዶች ልጆቻቸው ገብተው ምድሪቱን ወረሱ፤+ አንተም የምድሪቱ ነዋሪዎች የሆኑትን ከነአናውያን በፊታቸው እንዲንበረከኩ አደረግክ፤+ በነገሥታታቸውና በምድሪቱ ሕዝቦች ላይም ያሻቸውን እንዲያደርጉ በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው። +25 የተመሸጉ ከተሞችንና+ ለም የሆነውን* መሬት ያዙ፤+ መልካም ነገሮች ሁሉ የሞሉባቸውን ቤቶች፣ የተቆፈሩ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶችን፣ የወይን እርሻዎችን፣ የወይራ ዛፎችንና+ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የፍራፍሬ ዛፎች ወረሱ። በመሆኑም እስኪጠግቡ ድረስ በሉ፤ ሰቡም፤ ታላቅ በሆነው ጥሩነትህም ተንደላቀቁ። +26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+ +27 በዚህም የተነሳ መከራ ለሚያሳዩአቸው ጠላቶቻቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።+ በተጨነቁ ጊዜ ግን ወደ አንተ ጮኹ፤+ አንተም ከሰማያት ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከታላቅ ምሕረትህ የተነሳም ከጠላቶቻቸው እጅ የሚታደጓቸውን አዳኞች ሰጠሃቸው።+ +28 “ሆኖም ፋታ ሲያገኙ እንደገና በፊትህ መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ አንተም በሚጨቁኗቸው* ጠላቶቻቸው እጅ ጣልካቸው።+ ከዚያም ተመልሰው ለእርዳታ ወደ አንተ ጮኹ፤+ አንተም በሰማያት ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከታላቅ ምሕረትህም የተነሳ በተደጋጋሚ አዳንካቸው።+ +29 ወደ ሕግህ እንዲመለሱ ለማድረግ ብታስጠነቅቃቸውም እነሱ ግን እብሪተኞች በመሆን ትእዛዛትህን ለመስማት አሻፈረኝ አሉ፤+ ለሚጠብቃቸው ሰው ሁሉ ሕይወት በሚያስገኙት ድንጋጌዎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ።+ ደግሞም በግትርነት ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውን አደነደኑ፤ ለመስማትም አሻፈረኝ አሉ። +30 አንተ ግን ለብዙ ዓመታት ታገሥካቸው፤+ በነቢያትህም አማካኝነት በመንፈስህ አስጠነቀቅካቸው፤ እነሱ ግን ለመስማት አሻፈረኝ አሉ። በመጨረሻም በምድሪቱ ለሚኖሩት ሕዝቦች አሳልፈህ ሰጠሃቸው።+ +31 ከታላቅ ምሕረትህ የተነሳ ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም+ ወይም አልተውካቸውም፤ ምክንያቱም አንተ ሩኅሩኅና* መሐሪ አምላክ ነህ።+ +32 “አምላካችን ሆይ፣ አንተ ታላቅ፣ ኃያል፣ የተፈራህ፣ ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅና ታማኝ ፍቅር የምታሳይ አምላክ ነህ፤+ ከአሦር ነገሥታት+ ዘመን አንስቶ እስካሁን ድረስ በእኛ፣ በነገሥታታችን፣ በመኳንንታችን፣+ በካህናታችን፣+ በነቢያታችን፣+ በአባቶቻችንና በመላው ሕዝብህ ላይ እየደረሰ ያለውን ይህን ሁሉ +33 በእኛ ላይ በደረሰው ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ምክንያቱም አንተ ማንኛውንም ነገር ያደረግከው በታማኝነት ነው፤ ክፉ ነገር የፈጸምነው እኛ ነን።+ +34 ነገሥታታችን፣ መኳንንታችን፣ ካህናታችንም ሆኑ አባቶቻችን ሕግህን አልጠበቁም፤ ደግሞም እነሱን ለማስጠንቀቅ ብለህ ለሰጠሃቸው ትእዛዛትም ሆነ ማሳሰቢያዎች ትኩረት አልሰጡም።* +35 ሌላው ቀርቶ በራሳቸው መንግሥት ሥር በሚተዳደሩበት፣ አትረፍርፈህ በሰጠሃቸው መልካም ነገሮች በሚደሰቱበት እንዲሁም ባዘጋጀህላቸው ሰፊና ለም* ምድር በሚኖሩበት ጊዜም እንኳ አንተን አላገለገሉም፤+ ከመጥፎ ተግባራቸውም አልተቆጠቡም። +36 በመሆኑም ይኸው ዛሬ እኛ ባሪያዎች ሆነናል፤+ አዎ፣ አባቶቻችን ፍሬዋንና በረከቷን እንዲበሉ በሰጠሃቸው ምድር ላይ ባሪያዎች ሆነናል። +37 በምድሪቱ የተትረፈረፈ ምርት እየተጠቀሙ ያሉት በኃጢአታችን የተነሳ በላያችን እንዲነግሡ ያደረግካቸው ነገሥታት ናቸው።+ እነሱም በሰውነታችንና በቤት እንስሶቻችን ላይ እንዳሻቸው እየገዙ ነው፤ እኛም በከባድ መከራ ውስጥ እንገኛለን። +38 “በዚህም ሁሉ የተነሳ በጽሑፍ የሰፈረ ጽኑ ስምምነት እናደርጋለን፤+ ስምምነቱም በመኳንንታችን፣ በሌዋውያናችንና በካህናታችን ማኅተም የጸደቀ ይሆናል።”+ +13 በዚያን ቀን ሕዝቡ እየሰማ የሙሴ መጽሐፍ ይነበብ ነበር፤+ በዚህ ጊዜ አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ+ የሆነ ማንኛውም ሰው ወደ እውነተኛው አምላክ ጉባኤ ፈጽሞ መግባት እንደሌለበት የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ ተገኘ፤+ +2 ይህም የሆነው ለእስራኤላውያን ምግብና ውኃ በመስጠት ፋንታ እነሱን እንዲረግምላቸው በለዓምን ቀጥረው ስለነበር ነው።+ ይሁንና አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።+ +3 እነሱም ይህን ሕግ እንደሰሙ የባዕድ አገር ሰዎችን ሁሉ* ከእስራኤላውያን መለየት ጀመሩ።+ +4 ይህ ከመሆኑ ቀደም ብሎ የአምላካችን ቤት* ግምጃ ቤቶች*+ ኃላፊ፣ የጦብያ+ ዘመድ የሆነው ካህኑ ኤልያሺብ+ ነበር። +5 እሱም ቀደም ሲል የእህል መባውን፣ ነጩን ዕጣን፣ ዕቃዎቹን እንዲሁም ለሌዋውያኑ፣+ ለዘማሪዎቹና ለበር ጠባቂዎቹ እንዲሰጥ የታዘዘውን የእህሉን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅና የዘይቱን+ አንድ አሥረኛ* እንዲሁም ለካህናቱ የሚዋጣውን መዋጮ+ ያስቀምጡበት የነበረውን ቦታ ትልቅ ግምጃ ቤት* አድርጎ አዘጋጀለት። +6 ይህ ሁሉ ሲሆን እኔ በኢየሩሳሌም አልነበርኩም፤ ምክንያቱም የባቢሎን ንጉሥ አርጤክስስ+ በነገሠ በ32ኛው ዓመት+ ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበር፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላም ንጉሡን ፈቃድ እንዲሰጠኝ ጠየቅኩ። +7 ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ስመጣ ኤልያሺብ+ በእውነተኛው አምላክ ቤት ግቢ ውስጥ ለጦብያ+ ግምጃ ቤት በማዘጋጀት የፈጸመውን መጥፎ ድርጊት አስተዋልኩ። +8 እኔም በዚህ በጣም አዘንኩ፤ በመሆኑም የጦብያን የቤት ዕቃዎች በሙሉ ከግምጃ ቤቱ* አውጥቼ ወረወርኳቸው። +9 ከዚያም ትእዛዝ ሰጠሁ፤ እነሱም ግምጃ ቤቶቹን አጸዱ፤* እኔም የእውነተኛውን አምላክ ቤት+ ዕቃዎች ከእህሉ መባና ከነጩ ዕጣን+ ጋር እዚያው መልሼ አስቀመጥኩ። +10 በተጨማሪም ሌዋውያኑ የሚገባቸው ድርሻ+ ስለማይሰጣቸው+ ሥራውን ያከናውኑ የነበሩት ሌዋውያንም ሆኑ ዘማሪዎች እያንዳንዳቸው ወደየእርሻቸው መሄዳቸውን ተረዳሁ።+ +11 እኔም የበታች ገዢዎቹን+ “ለመሆኑ የእውነተኛው አምላክ ቤት እንዲህ ቸል የተባለው ለምንድን ነው?” በማለት ገሠጽኳቸው።+ ከዚያም ሁሉንም አንድ ላይ ከሰበሰብኳቸው በኋላ ወደየሥራ ምድባቸው እንዲመለሱ አደረግኩ። +12 የይሁዳ ሰዎችም ��ሉ የእህሉን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅና የዘይቱን አንድ አሥረኛ+ ወደ ግምጃ ቤቶቹ አስገቡ።+ +13 ከዚያም ካህኑን ሸሌምያህን፣ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* የሆነውን ሳዶቅን እንዲሁም ከሌዋውያን መካከል ፐዳያህን በግምጃ ቤቶቹ ላይ ኃላፊዎች አደረግኳቸው፤ የማታንያህ ልጅ፣ የዛኩር ልጅ ሃናን ደግሞ የእነሱ ረዳት ነበር፤ እነዚህ ሰዎች እምነት የሚጣልባቸው ነበሩ። ለወንድሞቻቸው የማከፋፈሉ ኃላፊነት የእ +14 አምላኬ ሆይ፣ ስለዚህ ነገር አስበኝ፤+ ለአምላኬ ቤትና በዚያ ለሚከናወነው አገልግሎት* ስል የፈጸምኩትን ታማኝ ፍቅር የተንጸባረቀበት ተግባር አትርሳ።+ +15 በእነዚያ ቀናት በይሁዳ በሰንበት ቀን በመጭመቂያ ውስጥ ወይን የሚረግጡና+ እህል አምጥተው በአህያ ላይ የሚጭኑ እንዲሁም የወይን ጠጅ፣ የወይን ዘለላ፣ በለስና የተለያዩ ነገሮችን ጭነው በሰንበት ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያመጡ ሰዎችን አየሁ።+ በመሆኑም በዚያን ቀን ሸቀጣ ሸቀጦችን እንዳይሸጡ አስጠነቀቅኳ +16 በከተማዋ የሚኖሩ የጢሮስ ሰዎችም ዓሣና የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦችን እያመጡ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ የይሁዳ ሰዎች በሰንበት ቀን ይሸጡ ነበር።+ +17 ስለሆነም በይሁዳ ያሉትን የተከበሩ ሰዎች እንዲህ በማለት ገሠጽኳቸው፦ “ሰንበትን በማርከስ የምትፈጽሙት ይህ መጥፎ ድርጊት ምንድን ነው? +18 አምላካችን በእኛም ሆነ በዚህች ከተማ ላይ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣው አባቶቻችሁ እንዲህ ዓይነት ድርጊት በመፈጸማቸው አይደለም? አሁንም እናንተ ሰንበትን በማርከስ በእስራኤል ላይ የሚነደውን ቁጣ እያባባሳችሁ ነው።”+ +19 በመሆኑም በሰንበት ዋዜማ የምሽቱ ጥላ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ ማረፍ ሲጀምር በሮቹ እንዲዘጉ ትእዛዝ ሰጠሁ። ሰንበት እስኪያልፍም ድረስ እንዳይከፍቷቸው ነገርኳቸው፤ በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ጭነት እንዳይገባም ከአገልጋዮቼ የተወሰኑትን በበሮቹ ላይ አቆምኩ። +20 ስለዚህ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦችን የሚነግዱትና የሚሸጡት ሰዎች ከአንዴም ሁለቴ ከኢየሩሳሌም ውጭ አደሩ። +21 ከዚያም እኔ “ቅጥሩ አጠገብ የምታድሩት ለምንድን ነው? ዳግመኛ እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ የኃይል እርምጃ እወስድባችኋለሁ” በማለት አስጠነቀቅኳቸው። ከዚያን ጊዜ ወዲህ በሰንበት መጥተው አያውቁም። +22 ለሌዋውያኑም የሰንበት ቀን ምንጊዜም የተቀደሰ እንዲሆን ዘወትር ራሳቸውን እንዲያነጹና መጥተው በሮቹን እንዲጠብቁ ነገርኳቸው።+ አምላኬ ሆይ፣ ይህንም አስብልኝ፤ ማለቂያ ከሌለው ታማኝ ፍቅርህም የተነሳ እዘንልኝ።+ +23 በተጨማሪም በእነዚያ ቀናት አሽዶዳውያን፣+ አሞናውያንና ሞዓባውያን+ ሴቶችን ያገቡ* አይሁዳውያን መኖራቸውን አወቅኩ።+ +24 ከልጆቻቸው መካከል ግማሾቹ የአሽዶድን ቋንቋ ግማሾቹ ደግሞ ከተለያየ አገር የመጡትን ሰዎች ቋንቋ ይናገሩ የነበረ ቢሆንም ማንኛቸውም የአይሁዳውያንን ቋንቋ መናገር አይችሉም ነበር። +25 ስለሆነም ገሠጽኳቸው፤ እርግማንም አወረድኩባቸው፤ አንዳንዶቹንም መታኋቸው፤+ ፀጉራቸውንም ነጨሁ፤ እንዲሁም እንደሚከተለው በማለት በአምላክ አስማልኳቸው፦ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው መስጠት የለባችሁም፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁም ሆነ ለራሳችሁ መውሰድ የለባችሁም።+ +26 የእስራኤል ንጉሥ ሰለሞን ኃጢአት የሠራው በእነሱ ምክንያት አይደለም? በብዙ ብሔራት መካከል እንደ እሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፤+ ደግሞም በአምላኩ ዘንድ የተወደደ+ ስለነበር አምላክ በመላው እስራኤል ላይ ንጉሥ አደረገው። ይሁንና ባዕዳን ሚስቶች እሱን እንኳ ኃጢአት እንዲሠራ አደረጉት።+ +27 እናንተም ባዕዳን ሴቶችን በማግባት በአምላካችን ላይ ታማኝነት የጎደለው ተግባር ፈጸማችሁ፤ ታዲያ እንዲህ ያለውን ተሰምቶ የማያውቅ እጅግ መጥፎ ድርጊት እንዴት ትፈጽማላችሁ?”+ +28 ከሊቀ ካህናቱ ከኤልያሺብ+ ልጅ ከዮያዳ+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዱ የሆሮናዊው የሳንባላጥ+ አማች ሆኖ ነበር። በመሆኑም ከአጠገቤ አባረርኩት። +29 አምላኬ ሆይ፣ ክህነቱን+ እንዲሁም ከካህናቱና ከሌዋውያኑ+ ጋር የተገባውን ቃል ኪዳን ስላረከሱ አትርሳቸው። +30 እኔም ርኩስ ከሆነ ከማንኛውም ባዕድ ነገር አነጻኋቸው፤ ለካህናቱና ለሌዋውያኑም ለእያንዳንዳቸው በየምድባቸው መሠረት ሥራ ሰጠኋቸው፤+ +31 እንዲሁም በተወሰነው ጊዜ መቅረብ ያለበትን እንጨትና+ መጀመሪያ የሚደርሰውን ፍሬ በተመለከተ ዝግጅት አደረግኩ። አምላኬ ሆይ፣ በመልካም አስበኝ።+ +5 ሆኖም ወንዶቹም ሆኑ ሚስቶቻቸው በአይሁዳውያን ወንድሞቻቸው ላይ ታላቅ ጩኸት አሰሙ።+ +2 አንዳንዶቹ “የእኛም ሆነ የወንዶች ልጆቻችንና የሴቶች ልጆቻችን ቁጥር ብዙ ነው። በሕይወት ለመቆየት የምንበላው እህል ማግኘት ይኖርብናል” ይሉ ነበር። +3 ሌሎቹም “የምግብ እጥረት በተከሰተበት ወቅት እህል ለማግኘት ስንል ማሳችንን፣ የወይን እርሻችንንና ቤታችንን መያዣ አድርገን ሰጥተናል” አሉ። +4 የተቀሩት ደግሞ እንዲህ ይሉ ነበር፦ “የንጉሡን ግብር ለመክፈል ስንል ማሳችንንና የወይን እርሻችንን አስይዘን ገንዘብ ተበድረናል።+ +5 እንግዲህ ወንድሞቻችን የአጥንታችን ፍላጭ፣ የሥጋችን ቁራጭ ናቸው፤* ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው፤ ሆኖም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን ለባርነት አሳልፈን ለመስጠት ተገደናል፤ እንዲያውም ከሴቶች ልጆቻችን መካከል አንዳንዶቹ አሁንም በባርነት ላይ ናቸው።+ ያም ሆኖ ማሳችንና የወይን እርሻችን በሌሎች እጅ +6 እኔም ጩኸታቸውንና ይህን አቤቱታቸውን ስሰማ በጣም ተናደድኩ። +7 ስለዚህ ነገሩን በልቤ ካጤንኩ በኋላ የተከበሩትን ሰዎችና የበታች ገዢዎቹን “እያንዳንዳችሁ ከገዛ ወንድማችሁ ላይ ወለድ እየተቀበላችሁ* ነው” በማለት ወቀስኳቸው።+ በተጨማሪም በእነሱ የተነሳ ታላቅ ስብሰባ ጠራሁ። +8 እንዲህም አልኳቸው፦ “ለብሔራት ተሸጠው የነበሩትን አይሁዳውያን ወንድሞቻችንን በተቻለን መጠን መልሰን ገዝተናቸው ነበር፤ ታዲያ እናንተ አሁን የገዛ ወንድሞቻችሁን መልሳችሁ ትሸጣላችሁ?+ ደግሞስ እንደገና ለእኛ መሸጥ ይኖርባቸዋል?” በዚህ ጊዜ የሚመልሱት ስለጠፋቸው ዝም አሉ። +9 ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ “የምትሠሩት ሥራ ጥሩ አይደለም። ጠላቶቻችን የሆኑት ብሔራት መሳለቂያ እንዳያደርጉን አምላካችንን በመፍራት መመላለስ አልነበረባችሁም?+ +10 ከዚህም በላይ እኔም ሆንኩ ወንድሞቼና አገልጋዮቼ ገንዘብና እህል አበድረናቸዋል። እባካችሁ ይህን በወለድ ማበደር የሚባል ነገር እንተው።+ +11 ደግሞም እባካችሁ ማሳዎቻቸውን፣ የወይን እርሻዎቻቸውን፣ የወይራ ዛፎቻቸውንና ቤቶቻቸውን እንዲሁም ከገንዘብ፣ ከእህል፣ ከአዲስ የወይን ጠጅና ከዘይት ወለድ አድርጋችሁ የተቀበላችሁትን ከመቶ አንድ እጅ* ዛሬውኑ መልሱላቸው።”+ +12 እነሱም “እነዚህን ነገሮች እንመልስላቸዋለን፤ በምላሹም ምንም ነገር እንዲያደርጉልን አንጠይቅም። ልክ እንዳልከው እናደርጋለን” አሉ። እኔም ካህናቱን ጠርቼ ሰዎቹን ይህን ቃል እንዲጠብቁ አስማልኳቸው። +13 በተጨማሪም የልብሴን እጥፋት* አራግፌ እንዲህ አልኳቸው፦ “ይህን ቃል የማይፈጽመውን ማንኛውንም ሰው እውነተኛው አምላክ ከቤቱና ከንብረቱ እንዲህ አራግፎ ያስወጣው፤ ልክ እንደዚህ ተራግፎም ባዶውን ይቅር።” በዚህ ጊዜ መላው ጉባኤ “አሜን!”* አለ። ይሖዋንም አመሰገኑ፤ ሕዝቡም ቃል እንደገቡት አደረጉ። +14 ከዚህም በላይ ንጉሡ በይሁዳ ምድ�� ገዢያቸው አድርጎ ከሾመኝ+ ጊዜ አንስቶ ማለትም ንጉሥ አርጤክስስ+ ከነገሠ ከ20ኛው ዓመት+ አንስቶ እስከ 32ኛው ዓመት+ ድረስ ይኸውም ለ12 ዓመት ያህል እኔም ሆንኩ ወንድሞቼ ለገዢው የሚገባውን ቀለብ አልበላንም።+ +15 ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ ገዢዎች ግን በሕዝቡ ላይ ሸክም ጭነውበት የነበረ ከመሆኑም ሌላ ከሕዝቡ ላይ ለምግብና ለወይን ጠጅ በየቀኑ 40 የብር ሰቅል* ይወስዱ ነበር። በተጨማሪም አገልጋዮቻቸው ሕዝቡን ይጨቁኑ ነበር። እኔ ግን አምላክን ስለምፈራ+ እንዲህ አላደረግኩም።+ +16 ከዚህም በላይ ይህን ቅጥር በመገንባቱ ሥራ ተሳትፌያለሁ፤ አገልጋዮቼም በሙሉ ሥራውን ለመሥራት እዚያ ተሰባስበው ነበር፤ የራሳችንም መሬት አልነበረንም።+ +17 በተጨማሪም 150 አይሁዳውያንና የበታች ገዢዎች እንዲሁም ከሌሎች ብሔራት ወደ እኛ የመጡ ሰዎች ከማዕዴ ይበሉ ነበር። +18 በየቀኑ አንድ በሬ፣ ስድስት ምርጥ በጎች እንዲሁም ወፎች ይዘጋጁልኝ* ነበር፤ በየአሥር ቀኑ ደግሞ የተለያየ ዓይነት የወይን ጠጅ በብዛት ይቀርብልን ነበር። እንደዚያም ሆኖ ሕዝቡ የራሱ የአገልግሎት ቀንበር ከብዶት ስለነበር ለገዢው የሚገባው ቀለብ እንዲሰጠኝ ጠይቄ አላውቅም። +19 አምላኬ ሆይ፣ ለዚህ ሕዝብ ስላደረግኩት ነገር ሁሉ በመልካም አስበኝ።+ +3 ከዚህ በኋላ ንጉሥ አሐሽዌሮስ የአጋጋዊውን+ የሃመዳታን ልጅ የሃማን+ ዙፋን አብረውት ካሉት ከሌሎቹ መኳንንት ሁሉ በላይ በማድረግ ላቅ ያለ ሹመት ሰጠው፤ ደግሞም ከፍ ከፍ አደረገው።+ +2 በንጉሡ በር የነበሩት የንጉሡ አገልጋዮች በሙሉ ሃማን እጅ ይነሱትና ለእሱ ይሰግዱለት ነበር፤ ንጉሡ እንዲህ እንዲደረግለት አዝዞ ነበርና። መርዶክዮስ ግን እጅ ለመንሳትም ሆነ ለመስገድ ፈቃደኛ አልሆነም። +3 በመሆኑም በንጉሡ በር የነበሩት የንጉሡ አገልጋዮች መርዶክዮስን “የንጉሡን ትእዛዝ የማታከብረው ለምንድን ነው?” አሉት። +4 በየቀኑ ይህን ጉዳይ ቢያነሱበትም እሱ ግን ሊሰማቸው ፈቃደኛ አልሆነም። ከዚያም የመርዶክዮስ አድራጎት በቸልታ የሚታለፍ እንደሆነና+ እንዳልሆነ ለማየት ጉዳዩን ለሃማ ነገሩት፤ መርዶክዮስ አይሁዳዊ መሆኑን ነግሯቸው ነበርና።+ +5 ሃማም መርዶክዮስ እሱን እጅ ለመንሳትና ለእሱ ለመስገድ ፈቃደኛ አለመሆኑን ባስተዋለ ጊዜ እጅግ ተቆጣ።+ +6 ሆኖም ስለ መርዶክዮስ ወገኖች ነግረውት ስለነበር መርዶክዮስን ብቻ ማስገደሉ* ተራ ነገር እንደሆነ ተሰማው። ስለዚህ ሃማ በመላው የአሐሽዌሮስ ግዛት የሚገኙትን አይሁዳውያን በሙሉ ማለትም የመርዶክዮስን ወገኖች በአጠቃላይ ለማጥፋት ዘዴ ይፈልግ ጀመር። +7 ንጉሥ አሐሽዌሮስ በነገሠ በ12ኛው ዓመት+ ኒሳን* በተባለው የመጀመሪያ ወር ላይ፣ ቀኑንና ወሩን ለመወሰን በሃማ ፊት ፑር+ (ዕጣ ማለት ነው) ጣሉ፤ ዕጣውም በ12ኛው ወር ማለትም በአዳር*+ ወር ላይ ወደቀ። +8 ከዚያም ሃማ ንጉሥ አሐሽዌሮስን እንዲህ አለው፦ “በግዛትህ ውስጥ ባሉት አውራጃዎች ሁሉ+ ተበታትኖና ተሰራጭቶ የሚገኝ፣+ የሚመራበትም ሕግ ከሌሎቹ ሕዝቦች ሁሉ የተለየ አንድ ሕዝብ አለ፤ የንጉሡንም ሕጎች አያከብርም፤ ንጉሡም ይህን ሕዝብ ዝም ብሎ መመልከቱ ይጎዳዋል። +"9 ለንጉሡ መልካም መስሎ ከታየው እነዚህ ሰዎች እንዲጠፉ የሚያዝዝ ድንጋጌ በጽሑፍ ይውጣ። እኔም ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት እንዲያስገቡ ለባለሥልጣናቱ 10,000 የብር ታላንት* እከፍላለሁ።”* " +10 በዚህ ጊዜ ንጉሡ የማኅተም ቀለበቱን ከእጁ አውልቆ+ የአይሁዳውያን ጠላት ለነበረው ለአጋጋዊው+ ለሃመዳታ ልጅ ለሃማ ሰጠው።+ +11 ንጉሡም ሃማን “ተገቢ መስሎ የታየህን እንድታደርግበት ብሩም ሆነ ሕዝቡ ለአንተ ተሰጥቷል” አለው። +12 ከዚያም በመጀመሪያው ወር 13ኛ ቀን የንጉሡ ጸ��ፊዎች+ ተጠሩ። የሃማን ትእዛዝ ሁሉ በተለያዩ አውራጃዎች ላይ ለተሾሙት የንጉሡ አስተዳዳሪዎችና ገዢዎች እንዲሁም ለተለያዩ ሕዝቦች መኳንንት ጻፉ፤+ ለእያንዳንዱ አውራጃ በራሱ ጽሑፍ፣* ለእያንዳንዱም ሕዝብ በራሱ ቋንቋ ተጻፈ። ደብዳቤው የተጻፈው በንጉሥ አ +13 ወጣት ሽማግሌ፣ ሕፃንም ሆነ ሴት ሳይባል አይሁዳውያን በጠቅላላ በአንድ ቀን ይኸውም አዳር+ በተባለው በ12ኛው ወር 13ኛ ቀን ላይ እንዲጠፉ፣ እንዲገደሉ፣ እንዲደመሰሱና ንብረታቸው እንዲወረስ+ የሚያዝዙ ደብዳቤዎች በመልእክተኞች አማካኝነት ወደ ንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ ተላኩ። +14 ሕዝቡም ሁሉ ለዚያ ቀን ዝግጁ እንዲሆን ሲባል በደብዳቤዎቹ ላይ የሰፈረው ሐሳብ በሁሉም አውራጃዎች ውስጥ ሕግ ሆኖ እንዲደነገግና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲታወጅ መመሪያ ተላለፈ። +15 መልእክተኞቹም ከንጉሡ ትእዛዝ የተነሳ ተጣድፈው ወጡ፤+ ሕጉም በሹሻን* ግንብ*+ ታወጀ። ከዚያም ንጉሡና ሃማ ሊጠጡ ተቀመጡ፤ የሹሻን* ከተማ ግን ግራ ተጋባች። +7 ንጉሡና ሃማም+ ንግሥት አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ መጡ። +2 በሁለተኛው ቀን በወይን ጠጅ ግብዣው ላይ ንጉሡ አስቴርን በድጋሚ እንዲህ አላት፦ “ንግሥት አስቴር ሆይ፣ የምትጠይቂው ምንድን ነው? የጠየቅሽው ይሰጥሻል። የምትፈልጊውስ ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ብትጠይቂ ይሰጥሻል!”+ +3 ንግሥት አስቴርም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “ንጉሥ ሆይ፣ በፊትህ ሞገስ ካገኘሁና ንጉሡን የሚያስደስተው ከሆነ ሕይወቴን* እንድትታደግልኝ እማጸንሃለሁ፤ ሕዝቤንም+ እንድታድንልኝ እጠይቅሃለሁ። +4 እኔና ሕዝቤ ለጥፋት፣ ለመገደልና ለመደምሰስ+ ተሸጠናልና።+ የተሸጥነው ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች እንድንሆን ብቻ ቢሆን ኖሮ ዝም ባልኩ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ጥፋት በንጉሡም ላይ ጉዳት ስለሚያስከትል በቸልታ መታለፍ የለበትም።” +5 ንጉሥ አሐሽዌሮስም ንግሥት አስቴርን “ለመሆኑ ይህ ሰው ማን ነው? እንዲህ ያለውን ነገር ለማድረግ የደፈረውስ ሰው የታለ?” አላት። +6 አስቴርም “ባላጋራና ጠላት የሆነው ሰው ይህ ክፉው ሃማ ነው” አለች። ሃማም በንጉሡና በንግሥቲቱ ፊት በፍርሃት ተንቀጠቀጠ። +7 ንጉሡም ከወይን ጠጅ ግብዣው ላይ ተቆጥቶ ተነሳ፤ ወደ ቤተ መንግሥቱም የአትክልት ስፍራ ሄደ፤ ይሁንና ሃማ ንጉሡ ሊቀጣው ቆርጦ እንደተነሳ ስለተገነዘበ ንግሥት አስቴር ሕይወቱን* እንድታድንለት ለመማጸን ቆመ። +8 ንጉሡ ከቤተ መንግሥቱ የአትክልት ስፍራ ወደ ወይን ጠጅ ግብዣው ተመልሶ ሲመጣ ሃማ አስቴር ባለችበት ድንክ አልጋ ላይ ተደፍቶ ተመለከተ። ንጉሡም “ብሎ ብሎ በገዛ ቤቴ ንግሥቲቱን ሊደፍራት ያስባል?” ብሎ ጮኸ። ይህ ቃል ከንጉሡ አፍ እንደወጣ የሃማን ፊት ሸፈኑት። +9 ከንጉሡ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት አንዱ የሆነው ሃርቦና+ እንዲህ አለ፦ “ሃማ፣ የንጉሡ ሕይወት እንዲተርፍ ሴራውን ላጋለጠው+ ለመርዶክዮስ የመሰቀያ እንጨትም አዘጋጅቷል።+ እንጨቱ 50 ክንድ* ቁመት ያለው ሲሆን በሃማ ቤት ቆሟል።” በዚህ ጊዜ ንጉሡ “በዚያው እንጨት ላይ ስቀሉት” አለ። +10 በመሆኑም ሃማን ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው እንጨት ላይ ሰቀሉት፤ የንጉሡም ቁጣ በረደ። +1 ከሕንድ አንስቶ እስከ ኢትዮጵያ* ድረስ ባሉ 127 አውራጃዎች+ ይገዛ በነበረው በአሐሽዌሮስ* ዘመን +2 ይኸውም ንጉሥ አሐሽዌሮስ በሹሻን*+ ግንብ* በሚገኘው ንጉሣዊ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛ በነበረበት ጊዜ፣ +3 በግዛት ዘመኑ ሦስተኛ ዓመት ላይ ለመኳንንቱና ለአገልጋዮቹ በሙሉ ግብዣ አደረገ። የፋርስና+ የሜዶን+ ሠራዊት፣ ታላላቆቹ ሰዎችና የየአውራጃዎቹ መኳንንት በፊቱ ነበሩ፤ +4 እሱም የክብራማ መንግሥቱን ብልጽግና እንዲሁም የግርማውን ታላቅነትና ውበት ለብዙ ቀናት ይኸውም ለ180 ቀናት ሲያሳያቸው ቆየ። +5 እነዚህ ቀናት ሲያበቁ ንጉሡ ትልቅ ትንሽ ሳይባል በሹሻን* ግንብ* ለተገኘው ሕዝብ ሁሉ በንጉሡ ቤተ መንግሥት የአትክልት ስፍራ ባለው ግቢ ለሰባት ቀን ታላቅ ግብዣ አደረገ። +6 በዚያም ከበፍታ፣ ከጥሩ ጥጥና ከሰማያዊ ጨርቅ የተሠሩ መጋረጃዎች፣ ከፍተኛ ጥራት ካለው ክርና ከሐምራዊ ሱፍ በተሠሩ ገመዶች፣ በእብነ በረድ ዓምዶቹ ላይ በነበሩት የብር ቀለበቶች ላይ ታስረው ነበር፤ ነጭ ነጠብጣብ ያለው ቀይ ድንጋይ፣ ነጭ እብነ በረድ፣ ዕንቁና ጥቁር እብነ በረድ በተነጠፈበት መሬት ላይ +7 የወይን ጠጅ በወርቅ ጽዋዎች* ቀርቦ ነበር፤ ጽዋዎቹም አንዳቸው ከሌላው የተለዩ ናቸው፤ ከንጉሡም ብልጽግና የተነሳ የቤተ መንግሥቱ የወይን ጠጅ በገፍ ቀርቦ ነበር። +8 የመጠጡ ዝግጅት የተደረገው ማንም ጫና* እንዳይደረግበት ከሚያዘው ደንብ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ነበር፤ ንጉሡ እያንዳንዱ ሰው ደስ ያሰኘውን ማድረግ እንዲችል ለቤተ መንግሥቱ ባለሥልጣናት መመሪያ አስተላልፎ ነበርና። +9 ንግሥት አስጢንም+ በንጉሥ አሐሽዌሮስ ንጉሣዊ ቤት* ውስጥ ለሴቶቹ ታላቅ ግብዣ አድርጋ ነበር። +10 በሰባተኛው ቀን ንጉሥ አሐሽዌሮስ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ደስ በተሰኘ ጊዜ የቅርብ አገልጋዮቹ ለነበሩት ሰባት የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ማለትም ለሜሁማን፣ ለቢዝታ፣ ለሃርቦና፣+ ለቢግታ፣ ለአባግታ፣ ለዜታር እና ለካርካስ +11 ንግሥት አስጢንን የንግሥትነት አክሊሏን* እንዳደረገች ወደ ንጉሡ ፊት እንዲያመጧት ነገራቸው፤ ይህን ያደረገው በጣም ቆንጆ ስለነበረች ሕዝቡና መኳንንቱ ውበቷን እንዲያዩ ነበር። +12 ንግሥት አስጢን ግን ንጉሡ በቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ በኩል ያስተላለፈውን ትእዛዝ ባለመቀበል ፈጽሞ ለመምጣት ፈቃደኛ ሳትሆን ቀረች። በዚህ ጊዜ ንጉሡ በኃይል ተቆጣ፤ በጣም ተናደደ። +13 ከዚያም ንጉሡ ስለ ቀድሞው ዘመን* ጥልቅ ማስተዋል ያላቸውን ጥበበኛ ሰዎች አማከረ (ንጉሡ የሚያጋጥሙት ነገሮች ሕግንና የፍርድ ጉዳዮችን ጠንቅቀው በሚያውቁ ሰዎች ሁሉ ፊት የሚቀርቡት በዚህ መንገድ ነበርና፤ +14 የቅርብ ሰዎቹም ካርሼና፣ ሼታር፣ አድማታ፣ ተርሴስ፣ ሜሬስ፣ ማርሴና እና ሜሙካን ነበሩ፤ እነዚህ ንጉሡ ፊት መቅረብ የሚችሉና በመንግሥቱ ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ የያዙ ሰባቱ የፋርስና የሜዶን መኳንንት+ ናቸው)። +15 ንጉሡም እንዲህ ሲል ጠየቀ፦ “ንጉሥ አሐሽዌሮስ በቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ በኩል ያስተላለፈውን ትእዛዝ ባለማክበሯ በሕጉ መሠረት በንግሥት አስጢን ላይ ምን ቢደረግ ይሻላል?” +16 በዚህ ጊዜ ሜሙካን በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት እንዲህ አለ፦ “ንግሥት አስጢን የበደለችው ንጉሡን ብቻ አይደለም፤+ ከዚህ ይልቅ መኳንንቱን ሁሉና በመላው የንጉሥ አሐሽዌሮስ አውራጃዎች የሚኖሩትን ሕዝቦች ሁሉ ነው። +17 ሌሎች ሚስቶች ሁሉ ንግሥቲቱ ያደረገችውን ነገር ማወቃቸው ስለማይቀር ባሎቻቸውን ይንቃሉ፤ ደግሞም ‘ንጉሥ አሐሽዌሮስ ንግሥት አስጢንን በፊቱ እንዲያቀርቧት አዝዞ ነበር፤ እሷ ግን አልቀረበችም’ ይላሉ። +18 በዚህ ቀን ንግሥቲቱ ያደረገችውን ነገር የሰሙ የፋርስና የሜዶን ልዕልቶች ለንጉሡ መኳንንት ሁሉ ተመሳሳይ መልስ ሊሰጡ ነው፤ ይህም ከፍተኛ ንቀትና ቁጣ ያስከትላል። +19 በመሆኑም ንጉሡ መልካም መስሎ ከታየው አስጢን፣ ንጉሥ አሐሽዌሮስ ፊት ዳግመኛ እንዳትቀርብ የሚያዝዝ ንጉሣዊ አዋጅ ያውጣ፤ ይህም የማይሻር ሆኖ+ በፋርስና በሜዶን ሕጎች ውስጥ ይካተት፤ ንጉሡም የእቴጌነት ክብሯን ከእሷ ለተሻለች ሴት ይስጥ። +20 ንጉሡም የሚያወጣው አዋጅ ሰፊ በሆነው ግዛቱ ሁሉ ሲነገር ትልቅ ትንሽ ሳይል ሁሉም ሚስቶች ባሎቻቸውን ያከብራሉ።” +21 ይህ ሐሳብ ንጉሡንና መኳንንቱን ደስ አሰኛቸው፤ ንጉሡም ሜሙካን እንዳለው አደረገ። +22 በመሆኑም እያንዳንዱ ባል በቤቱ ውስጥ ጌታ እንዲሆንና* በራሱ ሕዝብ ቋንቋ እንዲናገር የሚያዝዝ ደብዳቤ ለመላው የንጉሡ አውራጃዎች+ ላከ፤ ደብዳቤውም ለእያንዳንዱ አውራጃ በየራሱ ጽሑፍ፣* ለእያንዳንዱም ሕዝብ በገዛ ቋንቋው የተዘጋጀ ነበር። +8 በዚያው ቀን ንጉሥ አሐሽዌሮስ የአይሁዳውያን ጠላት+ የነበረውን የሃማን ቤት ለንግሥት አስቴር ሰጣት፤+ አስቴር ከመርዶክዮስ ጋር ምን ዝምድና እንዳላቸው+ ለንጉሡ ነግራው ስለነበር መርዶክዮስ ንጉሡ ፊት ቀረበ። +2 ከዚያም ንጉሡ ከሃማ ላይ የወሰደውን የማኅተም ቀለበቱን አውልቆ+ ለመርዶክዮስ ሰጠው። አስቴርም መርዶክዮስን በሃማ ቤት ላይ ሾመችው።+ +3 በተጨማሪም አስቴር ንጉሡን እንደገና አናገረችው። እግሩ ላይ ወድቃ እያለቀሰች አጋጋዊው ሃማ ያደረሰውን ጉዳትና በአይሁዳውያን ላይ የጠነሰሰውን ሴራ እንዲያስወግድ ለመነችው።+ +4 ንጉሡም የወርቅ በትረ መንግሥቱን ለአስቴር ዘረጋላት፤+ አስቴርም ተነስታ በንጉሡ ፊት ቆመች። +5 እሷም እንዲህ አለች፦ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነና እኔም በፊቱ ሞገስ ካገኘሁ፣ ነገሩም በንጉሡ ፊት ተገቢ ሆኖ ከተገኘና በእኔ ደስ ከተሰኘ፣ ያ ሴረኛ አጋጋዊው+ የሃመዳታ ልጅ ሃማ+ በመላው የንጉሡ አውራጃዎች የሚገኙትን አይሁዳውያን ለማጥፋት ያዘጋጀውን ሰነድ የሚሽር ትእዛዝ ይጻፍ። +6 በሕዝቤ ላይ መዓት ሲወርድ ዓይኔ እያየ እንዴት አስችሎኝ ዝም እላለሁ? ዘመዶቼ ሲጠፉስ እያየሁ እንዴት አስችሎኝ ዝም እላለሁ?” +7 በመሆኑም ንጉሥ አሐሽዌሮስ ንግሥት አስቴርንና አይሁዳዊውን መርዶክዮስን እንዲህ አላቸው፦ “የሃማን ቤት ለአስቴር ሰጥቻለሁ፤+ አይሁዳውያንን ለማጥቃት በጠነሰሰው ሴራ የተነሳም* በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አድርጌአለሁ።+ +8 በንጉሡ ስም የተጻፈንና በንጉሡ የማኅተም ቀለበት የታተመን ድንጋጌ መሻር ስለማይቻል አይሁዳውያንን በተመለከተ ተገቢ መስሎ የታያችሁን ማንኛውንም ነገር በንጉሡ ስም ጻፉ፤ በንጉሡም የማኅተም ቀለበት አትሙት።”+ +9 ስለሆነም ሲዋን* በተባለው በሦስተኛው ወር፣ በ23ኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠሩ፤ እነሱም መርዶክዮስ ያዘዘውን ሁሉ ለአይሁዳውያኑ፣ ለአስተዳዳሪዎቹ፣+ ለገዢዎቹና ከሕንድ አንስቶ እስከ ኢትዮጵያ ላሉት 127 አውራጃዎች መኳንንት+ ጻፉ፤ ለእያንዳንዱ አውራጃ በራሱ ጽሑፍ፣* ለእያንዳንዱም ሕዝብ በራሱ ቋን +10 እሱም ደብዳቤውን በንጉሥ አሐሽዌሮስ ስም ጽፎ በንጉሡ የማኅተም ቀለበት+ አተመው፤ ደብዳቤውንም ፈረስ በሚጋልቡ መልእክተኞች እጅ ላከው፤ እነዚህ መልእክተኞች ለንጉሡ አገልግሎት የሚያሳድጓቸውን፣ ደብዳቤ ለማድረስ የሚያገለግሉ ፈጣን ፈረሶች የሚጋልቡ ነበሩ። +11 በእነዚህም ደብዳቤዎች ላይ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ አይሁዳውያን በሙሉ ተሰብስበው ሕይወታቸውን* ከጥቃት እንዲከላከሉ እንዲሁም ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ በእነሱ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩትን የየትኛውም ሕዝብ ወይም አውራጃ ኃይሎች በሙሉ እንዲያጠፉ፣ እንዲገድሉና እንዲደመስሱ ብሎም ንብረታቸውን እንዲዘርፉ ንጉ +12 ይህም በመላው የንጉሥ አሐሽዌሮስ አውራጃዎች በተመሳሳይ ቀን ይኸውም አዳር* በተባለው በ12ኛው ወር 13ኛ ቀን ላይ እንዲፈጸም ተወሰነ።+ +13 በደብዳቤው ላይ የሰፈረው ጽሑፍ* በሁሉም አውራጃዎች ውስጥ ሕግ ሆኖ እንዲወጣ ተወስኖ ነበር። በተጨማሪም አይሁዳውያኑ በዚያ ቀን ጠላቶቻቸውን ለመበቀል ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ ሲባል ለሕዝቦቹ ሁሉ እንዲታወጅ ተደንግጎ ነበር።+ +14 ለንጉሡ አገልግሎት የተመደቡትን ደብዳቤ ለማድረስ የሚያገለግሉ ፈረሶች የሚ��ልቡት መልእክተኞች በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት እየተቻኮሉና እየተጣደፉ ወጡ። ሕጉ በሹሻን* ግንብም *+ ታውጆ ነበር። +15 መርዶክዮስም ሰማያዊና ነጭ ልብሰ መንግሥት ለብሶ፣ ትልቅ የወርቅ አክሊል ደፍቶ እንዲሁም ከፍተኛ ጥራት ካለው ክርና ከሐምራዊ ሱፍ የተሠራ መጎናጸፊያ ደርቦ ከንጉሡ ፊት ወጣ።+ የሹሻን* ከተማም እልል አለች። +16 ለአይሁዳውያኑም እፎይታ፣* ደስታ፣ ሐሴትና ክብር ሆነላቸው። +17 የንጉሡ ድንጋጌና ሕግ በተሰማባቸው በሁሉም አውራጃዎችና ከተሞች የሚኖሩ አይሁዳውያን ተደሰቱ፤ ሐሴትም አደረጉ፤ የግብዣና የፈንጠዝያ ቀን ሆነ። ብዙዎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች አይሁዳውያንን ከመፍራታቸው የተነሳ አይሁዳዊ ሆኑ።+ +2 ከዚህ በኋላ ንጉሥ አሐሽዌሮስ+ ቁጣው ሲበርድለት አስጢን ያደረገችውን ነገርና+ በእሷ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ+ አስታወሰ። +2 ከዚያም የንጉሡ የቅርብ አገልጋዮች እንዲህ አሉ፦ “ለንጉሡ ቆንጆ የሆኑ ወጣት ደናግል ይፈለጉለት። +3 ንጉሡም ቆንጆ የሆኑትን ወጣት ደናግል ሁሉ ሰብስበው በሹሻን* ግንብ* ወደሚገኘው፣ ሴቶች ወደሚኖሩበት ቤት* እንዲያመጧቸው በግዛቱ ውስጥ በሚገኙት አውራጃዎች ሁሉ+ ሰዎችን ይሹም። እነሱም የንጉሡ ጃንደረባና የሴቶቹ ጠባቂ በሆነው በሄጌ+ ኃላፊነት ሥር ይሁኑ፤ የውበት እንክብካቤም ይደረግላቸው።* +4 ንጉሡ እጅግ ደስ የተሰኘባት ወጣትም በአስጢን ምትክ ንግሥት ትሆናለች።”+ ንጉሡም በሐሳቡ ደስ ተሰኘ፤ እንደተባለውም አደረገ። +5 በዚህ ጊዜ መርዶክዮስ+ የተባለ አንድ አይሁዳዊ በሹሻን*+ ግንብ* ይኖር ነበር፤ እሱም የቢንያማዊው+ የቂስ ልጅ፣ የሺምአይ ልጅ የሆነው የያኢር ልጅ ነው፤ +6 ይህ ሰው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በግዞት ከወሰደው ከይሁዳ ንጉሥ ከኢኮንያን*+ ጋር ከኢየሩሳሌም በግዞት ከተወሰዱት ሰዎች አንዱ ነበር። +7 እሱም የአባቱ ወንድም ልጅ የሆነችው የሃዳሳ* ማለትም የአስቴር አሳዳጊ* ነበር፤+ አስቴር አባትም ሆነ እናት አልነበራትም። ወጣቷ ቁመናዋ ያማረ፣ መልኳም ቆንጆ ነበር፤ መርዶክዮስም አባትና እናቷ ሲሞቱ እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ ወሰዳት። +8 የንጉሡ ቃልና ያወጣው ሕግ ታውጆ በርካታ ወጣት ሴቶች በሄጌ+ ኃላፊነት ሥር እንዲሆኑ በሹሻን* ግንብ* ሲሰበሰቡ አስቴርም ወደ ንጉሡ ቤት* ተወስዳ የሴቶች ጠባቂ በሆነው በሄጌ ኃላፊነት ሥር እንድትሆን ተደረገ። +9 እሱም በወጣቷ ደስ ተሰኘባት፤ እንዲሁም በእሱ ዘንድ ሞገስ አገኘች፤* በመሆኑም የውበት እንክብካቤ እንዲደረግላትና*+ የተለየ ምግብ እንዲሰጣት ወዲያውኑ ዝግጅት አደረገ፤ ከንጉሡም ቤት የተመረጡ ሰባት ወጣት ሴቶች መደበላት። በተጨማሪም እሷንና የተመደቡላትን ሴቶች በሴቶቹ ቤት* ውስጥ ወደሚገኘው ምርጥ ወ +10 መርዶክዮስ+ ለማንም እንዳትናገር አዟት ስለነበር+ አስቴር ስለ ሕዝቦቿም+ ሆነ ስለ ዘመዶቿ ምንም አልተናገረችም። +11 መርዶክዮስ ስለ አስቴር ደህንነትና ስላለችበት ሁኔታ ለማወቅ በሴቶቹ ቤት* ግቢ ፊት ለፊት በየዕለቱ ይመላለስ ነበር። +12 እያንዳንዷ ወጣት ለሴቶቹ በታዘዘው መሠረት 12 ወር የሚፈጅ እንክብካቤ ከተደረገላት በኋላ ተራዋ ደርሶ ወደ ንጉሥ አሐሽዌሮስ ትገባ ነበር፤ የውበት እንክብካቤው* በተሟላ ሁኔታ የሚከናወንላቸው በዚህ መንገድ ነበርና፤ ስድስት ወር በከርቤ+ ዘይት፣ ስድስት ወር ደግሞ በበለሳን ዘይት+ እንዲሁም በተለያዩ +13 ከዚያም ወጣቷ ወደ ንጉሡ ለመግባት ዝግጁ ትሆናለች፤ ከሴቶቹ ቤት* ወደ ንጉሡ ቤት በምትሄድበት ጊዜም የምትጠይቀው ነገር ሁሉ ይሰጣት ነበር። +14 ምሽት ላይ ትገባለች፤ ጠዋት ላይ ደግሞ የቁባቶች ጠባቂ በሆነው በንጉሡ ጃንደረባ+ በሻአሽጋዝ ኃላፊነት ሥር ወዳለው ወደ ሁለተኛው የሴቶች ቤት* ትመለሳለች። ንጉሡ በጣም ካልተደሰተባትና በስም ጠቅሶ ካላስጠራት በስተቀር ዳግመኛ ወደ ንጉሡ አትገባም።+ +15 መርዶክዮስ እንደ ልጁ አድርጎ የወሰዳት+ የአጎቱ የአቢሃይል ልጅ አስቴር ወደ ንጉሡ የምትገባበት ተራ ሲደርስ የሴቶች ጠባቂ የሆነው የንጉሡ ጃንደረባ ሄጌ እንድትጠይቅ ከነገራት ነገር በስተቀር ምንም አልጠየቀችም። (በዚህ ሁሉ ጊዜ አስቴር ባዩአት ሁሉ ዘንድ ሞገስ አግኝታ ነበር።) +16 አስቴር ንጉሥ አሐሽዌሮስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት+ ቴቤት* ተብሎ በሚጠራው አሥረኛ ወር ወደ ንጉሡ ቤት ተወሰደች። +17 ንጉሡም ከሌሎቹ ሴቶች ሁሉ ይበልጥ አስቴርን ወደዳት፤ ከሌሎቹም ደናግል ሁሉ ይበልጥ በእሱ ዘንድ ሞገስና ተቀባይነት አገኘች።* በመሆኑም በራሷ ላይ የንግሥትነት አክሊል* አደረገላት፤ በአስጢንም+ ፋንታ ንግሥት አደረጋት።+ +18 ንጉሡም ለመኳንንቱ ሁሉና ለአገልጋዮቹ በሙሉ እጅግ ታላቅ ግብዣ አዘጋጀ፤ ይህን ታላቅ ግብዣ ያዘጋጀው ለአስቴር ክብር ሲል ነው። ከዚያም በአውራጃዎቹ ውስጥ ለሚኖሩ ምሕረት አደረገ፤ ንጉሡም ካለው ብልጽግና የተነሳ ስጦታዎችን ይሰጥ ነበር። +19 ደናግሉ*+ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሰበሰቡ መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ ነበር። +20 መርዶክዮስ ባዘዛት መሠረት አስቴር ስለ ዘመዶቿም ሆነ ስለ ሕዝቦቿ ምንም አልተናገረችም፤+ አስቴር ከመርዶክዮስ ጋር በነበረችበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁንም እሱ የሚለውን ትታዘዝ ነበር።+ +21 በዚያን ጊዜ መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ ሳለ በር ጠባቂዎች የሆኑት ቢግታን እና ቴሬሽ የተባሉ የንጉሡ ሁለት የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ተቆጡ፤ ንጉሥ አሐሽዌሮስንም ለመግደል* አሴሩ። +22 ሆኖም መርዶክዮስ ይህን ጉዳይ አወቀ፤ ወዲያውኑም ለንግሥት አስቴር ነገራት። ከዚያም አስቴር ጉዳዩን በመርዶክዮስ ስም* ለንጉሡ ነገረችው። +23 በመሆኑም ሁኔታው ሲጣራ እውነት ሆኖ ተገኘ፤ ከዚያም ሁለቱ ሰዎች እንጨት ላይ ተሰቀሉ፤ ይህ ሁኔታም በዘመኑ በነበረው የታሪክ መጽሐፍ ላይ በንጉሡ ፊት ተጻፈ።+ +4 መርዶክዮስ+ የተደረገውን ነገር ሁሉ ባወቀ ጊዜ+ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለበሰ፤ በራሱም ላይ አመድ ነሰነሰ። ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጮኸና ምርር ብሎ እያለቀሰ ወደ ከተማዋ መሃል ወጣ። +2 ማንም ሰው ማቅ ለብሶ በንጉሡ በር እንዲገባ ስለማይፈቀድለት እስከ ንጉሡ በር ድረስ መጣ። +3 የንጉሡ ቃልና ድንጋጌ በተሰማባቸው አውራጃዎች በሙሉ+ በሚገኙ አይሁዳውያን መካከል ታላቅ ሐዘን ሆነ፤ እነሱም ጾሙ፤+ አለቀሱ፤ እንዲሁም ዋይታ አሰሙ። ብዙዎቹ ማቅ አንጥፈው፣ አመድ ነስንሰው ተኙ።+ +4 የአስቴር ሴት አገልጋዮችና ጃንደረቦችም ወደ እሷ ገብተው በነገሯት ጊዜ ንግሥቲቱ እጅግ ተጨነቀች። ከዚያም መርዶክዮስ ማቁን አውልቆ የሚለብሰው ልብስ ላከችለት፤ እሱ ግን አልተቀበለም። +5 በዚህ ጊዜ አስቴር ከንጉሡ ጃንደረቦች አንዱ የሆነውንና ንጉሡ እሷን እንዲያገለግል የመደበውን ሃታክን ጠርታ ወደ መርዶክዮስ ሄዶ ምን ችግር እንደተፈጠረና ምን እንደተከሰተ እንዲያጣራ አዘዘችው። +6 ስለዚህ ሃታክ በንጉሡ በር ፊት ለፊት ባለው የከተማዋ አደባባይ ወደሚገኘው ወደ መርዶክዮስ ወጣ። +7 መርዶክዮስም ያጋጠመውን ነገር ሁሉ ነገረው፤ እንዲሁም ሃማ አይሁዳውያንን ለማጥፋት+ ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ለማስገባት ቃል ስለገባው ገንዘብ መጠን ነገረው።+ +8 በተጨማሪም እነሱን ለማጥፋት በሹሻን*+ በጽሑፍ የወጣውን ድንጋጌ ቅጂ ሰጠው። ቅጂውን ለአስቴር እንዲያሳያትና እንዲያስረዳት እንዲሁም ወደ ንጉሡ ገብታ ሞገስ እንዲያሳያት እንድትለምነውና ስለ ሕዝቧ በግንባር ቀርባ እንድትማጸነው ይነግራት ዘንድ+ አሳሰበው። +9 ሃታክ ተ���ልሶ መርዶክዮስ ያለውን ለአስቴር ነገራት። +10 አስቴርም ለመርዶክዮስ+ እንዲህ ብሎ እንዲነግረው ሃታክን አዘዘችው፦ +11 “የንጉሡ አገልጋዮች ሁሉና በንጉሡ አውራጃዎች ውስጥ የሚኖሩት ሕዝቦች፣ ሳይጠራ ወደ ንጉሡ ውስጠኛ ግቢ+ የሚገባን ማንኛውንም ወንድ ወይም ሴት በተመለከተ ንጉሡ አንድ ሕግ እንዳለው ያውቃሉ፦ እንዲህ ያደረገ ሰው ይገደላል፤ ሰውየው በሕይወት ሊተርፍ የሚችለው ንጉሡ የወርቅ በትረ መንግሥቱን ከዘረጋለት ብ +12 መርዶክዮስ፣ የአስቴር ቃል በተነገረው ጊዜ +13 ለአስቴር ይህን መልስ ላከ፦ “በንጉሡ ቤት ስላለሽ ብቻ ከሌሎቹ አይሁዳውያን ተለይቼ እኔ እተርፋለሁ ብለሽ እንዳታስቢ። +14 በዚህ ጊዜ አንቺ ዝም ብትዪ አይሁዳውያን እፎይታና መዳን ከሌላ ቦታ ያገኛሉ፤+ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ። ደግሞስ ንግሥት ለመሆን የበቃሽው እንዲህ ላለው ጊዜ እንደሆነ ማን ያውቃል?”+ +15 ከዚያም አስቴር በምላሹ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ መርዶክዮስ ላከች፦ +16 “ሂድ፤ በሹሻን* ያሉትን አይሁዳውያን ሁሉ ሰብስብ፤ ስለ እኔም ጹሙ።+ ቀንም ሆነ ሌሊት ለሦስት ቀን እንዳትበሉ እንዲሁም እንዳትጠጡ።+ እኔም ከሴት አገልጋዮቼ ጋር እጾማለሁ። ከዚያም ሕጉ ባይፈቅድም እንኳ ወደ ንጉሡ እገባለሁ፤ ከጠፋሁም ልጥፋ።” +17 በመሆኑም መርዶክዮስ ሄደ፤ አስቴር ያዘዘችውንም ነገር ሁሉ አደረገ። +6 በዚያ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ እንቢ አለው።* በመሆኑም በዘመኑ የነበረውን የታሪክ መጽሐፍ+ እንዲያመጡለት አዘዘ። መጽሐፉም በንጉሡ ፊት ተነበበ። +2 በዚህ ጊዜ ንጉሥ አሐሽዌሮስን ለመግደል* አሲረው የነበሩትን የንጉሡን ሁለት የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ማለትም በር ጠባቂዎቹን ቢግታናን እና ቴሬሽን አስመልክቶ መርዶክዮስ የተናገረው ነገር ተጽፎ ተገኘ።+ +3 ንጉሡም “ታዲያ መርዶክዮስ ይህን በማድረጉ ምን ክብርና እውቅና አገኘ?” ሲል ጠየቀ። በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ አገልጋዮች “ምንም አልተደረገለትም” አሉ። +4 ንጉሡም “በግቢው ውስጥ ያለው ማን ነው?” አለ። ሃማም ባዘጋጀው እንጨት ላይ መርዶክዮስ እንዲሰቀል ለንጉሡ ለመናገር+ ወደ ንጉሡ ቤት* ውጨኛ ግቢ+ ገብቶ ነበር። +5 የንጉሡ አገልጋዮችም “ሃማ+ ግቢው ውስጥ ቆሟል” አሉት። ንጉሡም “ግባ በሉት” አለ። +6 ንጉሡም ሃማ በገባ ጊዜ “ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው ምን ሊደረግለት ይገባል?” አለው። ሃማም በልቡ “ንጉሡ ከእኔ በላይ ሊያከብረው የሚወደው ሰው ማን አለ?” ሲል አሰበ።+ +7 በመሆኑም ሃማ ንጉሡን እንዲህ አለው፦ “ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው፣ +8 ንጉሡ የሚጎናጸፈውን ልብሰ መንግሥት+ እንዲሁም ንጉሡ የሚቀመጥበትንና በራሱ ላይ አክሊል የተደረገለትን ፈረስ ያምጡለት። +9 ከዚያም ልብሱና ፈረሱ ከንጉሡ ታላላቅ መኳንንት መካከል ለአንዱ በኃላፊነት ይሰጥ፤ እነሱም ንጉሡ ሊያከብረው የወደደውን ሰው ያልብሱት፤ እንዲሁም በፈረሱ ላይ አስቀምጠው በከተማው አደባባይ እንዲያልፍ ያድርጉ። በፊቱም ‘ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል!’ ይበሉ።”+ +10 ንጉሡም ወዲያውኑ ሃማን እንዲህ አለው፦ “ፈጠን በል! ልብሱንና ፈረሱን ውሰድ፤ በንጉሡ በር ላይ ለሚቀመጠው ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስም ልክ እንዳልከው አድርግለት። ከተናገርከው ውስጥ አንዱም ሳይፈጸም እንዳይቀር።” +11 ስለዚህ ሃማ ልብሱንና ፈረሱን ወሰደ፤ መርዶክዮስንም+ አለበሰው፤ በፈረሱም ላይ አስቀምጦ በከተማው አደባባይ እንዲያልፍ አደረገ፤ “ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል!” እያለ በፊቱ ያውጅ ነበር። +12 ከዚያም መርዶክዮስ ወደ ንጉሡ በር ተመለሰ፤ ሃማ ግን ራሱን ተከናንቦ እያዘነ በጥ��ፊያ ወደ ቤቱ ሄደ። +13 ሃማ ያጋጠመውን ነገር ሁሉ ለሚስቱ ለዜሬሽና+ ለጓደኞቹ በሙሉ ሲነግራቸው ጥበበኛ አማካሪዎቹና ሚስቱ ዜሬሽ “በፊቱ መውደቅ የጀመርክለት መርዶክዮስ የአይሁዳውያን ዘር ከሆነ ልታሸንፈው አትችልም፤ ያለምንም ጥርጥር በፊቱ ትወድቃለህ” አሉት። +14 እነሱም ገና ከእሱ ጋር እየተነጋገሩ ሳሉ የንጉሡ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ደርሰው ሃማን አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ እያጣደፉ ወሰዱት።+ +10 ንጉሥ አሐሽዌሮስ በምድሪቱና በባሕር ደሴቶች ላይ የሚኖሩ ሰዎች የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ አደረገ። +2 ንጉሡ ያከናወናቸው ታላላቅና አስደናቂ ሥራዎች በሙሉ እንዲሁም መርዶክዮስን+ ከፍ ከፍ እንዲያደርገው+ ስላነሳሳው ስለ መርዶክዮስ ታላቅነት የሚገልጸው ዘገባ በሜዶንና በፋርስ ነገሥታት+ ዘመን ስለተከናወኑ ነገሮች በሚተርከው መጽሐፍ+ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? +3 አይሁዳዊው መርዶክዮስ ከንጉሥ አሐሽዌሮስ ቀጥሎ ያለ ሁለተኛ ሰው ነበር። በአይሁዳውያን መካከል ትልቅ ቦታ የነበረው፣* በብዙ ወንድሞቹ ዘንድ የተከበረ፣ ለወገኖቹ ጥቅም የቆመ እንዲሁም ለዘሮቻቸው ሁሉ ደህንነት የሚቆረቆር* ሰው ነበር። +9 አዳር* በተባለው በ12ኛው ወር፣ 13ኛ ቀን፣+ የንጉሡ ቃልና ሕግ በሚፈጸምበት+ እንዲሁም የአይሁዳውያን ጠላቶች በአይሁዳውያን ላይ ድል እንደሚቀዳጁ ተስፋ አድርገው በነበረበት ቀን ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነ፤ አይሁዳውያኑ የሚጠሏቸውን ሰዎች ድል አደረጉ።+ +2 አይሁዳውያኑ እነሱን ለመጉዳት በሚሹ ሰዎች ላይ እጃቸውን ለማንሳት በንጉሥ አሐሽዌሮስ+ አውራጃዎች በሙሉ በሚገኙ ከተሞቻቸው ውስጥ ተሰባሰቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ ፈርቷቸው ስለነበር ሊቃወማቸው የቻለ አንድም ሰው አልነበረም።+ +3 የአውራጃዎቹ መኳንንት በሙሉ፣ አስተዳዳሪዎቹ፣+ ገዢዎቹና የንጉሡን ጉዳይ የሚያስፈጽሙ ሰዎችም መርዶክዮስን ፈርተውት ስለነበር አይሁዳውያኑን ይረዷቸው ነበር። +4 መርዶክዮስ በንጉሡ ቤት* ውስጥ ገናና ሆኖ ነበር፤+ ገናናነቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ስለመጣ ዝናው በየአውራጃው ተዳረሰ። +5 አይሁዳውያኑ ጠላቶቻቸውን በሙሉ በሰይፍ ጨፈጨፏቸው፤ ገደሏቸው፤ እንዲሁም ደመሰሷቸው፤ በሚጠሏቸውም ሰዎች ላይ የፈለጉትን አደረጉባቸው።+ +6 አይሁዳውያኑ በሹሻን* ግንብ*+ 500 ሰዎችን ገደሉ፤ ደግሞም አጠፉ። +7 በተጨማሪም ፓርሻንዳታ፣ ዳልፎን፣ አስፋታ፣ +8 ፖራታ፣ አዳሊያ፣ አሪዳታ፣ +9 ፓርማሽታ፣ አሪሳይ፣ አሪዳይ እና ዋይዛታ የተባሉትን፣ +10 የአይሁዳውያን ጠላት+ የነበረውን የሃመዳታን ልጅ የሃማን አሥር ወንዶች ልጆች ገደሉ። ከገደሏቸው በኋላ ግን አንድም ምርኮ አልወሰዱም።+ +11 በዚያ ቀን በሹሻን* ግንብ* የተገደሉት ሰዎች ብዛት ለንጉሡ ተነገረው። +12 ንጉሡ ንግሥት አስቴርን እንዲህ አላት፦ “አይሁዳውያኑ በሹሻን* ግንብ* 500 ሰዎችንና አሥሩን የሃማ ወንዶች ልጆች ገድለዋል፤ ደግሞም አጥፍተዋል። በቀሩት የንጉሡ አውራጃዎችስ+ ምን አድርገው ይሆን? አሁንስ የምትጠይቂው ምንድን ነው? የጠየቅሽው ይሰጥሻል። ሌላስ የምትፈልጊው ነገር አለ? ይደረግልሻል። +13 አስቴርም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ+ በሹሻን* የሚኖሩት አይሁዳውያን ዛሬ ተግባራዊ ያደረጉትን ሕግ+ ነገም እንዲደግሙት ይፈቀድላቸው፤ አሥሩ የሃማ ልጆችም በእንጨት ላይ ይሰቀሉ።”+ +14 ንጉሡም እንዲሁ እንዲደረግ አዘዘ። ከዚያም በሹሻን* ሕግ ወጣ፤ አሥሩ የሃማ ልጆችም ተሰቀሉ። +15 በሹሻን* የሚኖሩት አይሁዳውያን አዳር+ በተባለው ወር 14ኛ ቀን ላይ በድጋሚ ተሰበሰቡ፤ በሹሻንም* 300 ሰዎችን ገደሉ፤ ይሁንና አንድም ምርኮ አልወሰዱም። +"16 በንጉሡ አውራጃዎች የሚኖሩት የቀሩት አይሁዳውያንም ተሰብስበው ሕይወታቸውን ከጥቃት ተከላከሉ።*+ እነሱን ይጠሏቸው ከነበሩት ሰዎች መካከል 75,000 ሰዎችን በመግደል ጠላቶቻቸውን አጠፉ፤+ ይሁንና አንድም ምርኮ አልወሰዱም።" +17 ይህ የሆነው አዳር በተባለው ወር 13ኛ ቀን ላይ ነበር፤ እነሱም በ14ኛው ቀን አረፉ፤ ዕለቱንም የግብዣና የሐሴት ቀን አደረጉት። +18 በሹሻን* የነበሩት አይሁዳውያን በ13ኛው ቀንና+ በ14ኛው ቀን+ ላይ ተሰበሰቡ፤ በ15ኛው ቀን ደግሞ አረፉ፤ ቀኑንም የግብዣና የሐሴት ቀን አደረጉት። +19 ከዋና ከተማዋ ውጭ በሚገኙ የገጠር ከተሞች የሚኖሩት አይሁዳውያን አዳር የተባለውን ወር 14ኛ ቀን የሐሴትና የግብዣ ቀን፣ የፈንጠዝያ ቀንና+ አንዳቸው ለሌላው ምግብ የሚልኩበት ጊዜ+ እንዲሆን ያደረጉት በዚህ የተነሳ ነው። +20 መርዶክዮስ+ እነዚህን ክንውኖች ከመዘገበ በኋላ በቅርብም ይሁን በሩቅ ስፍራ ላሉ፣ በመላው የንጉሥ አሐሽዌሮስ አውራጃዎች ለሚኖሩ አይሁዳውያን በሙሉ ሕጋዊ እውቅና ያላቸው ደብዳቤዎች ላከ። +21 በየዓመቱ የአዳርን ወር 14ኛና 15ኛ ቀን እንዲያከብሩ አዘዛቸው፤ +22 ምክንያቱም እነዚህ ቀናት አይሁዳውያኑ ከጠላቶቻቸው ያረፉባቸውና ሐዘናቸው ወደ ሐሴት፣ ለቅሷቸውም ወደ ፈንጠዝያ የተለወጠባቸው ቀናት ናቸው።+ እነዚህን ቀናት የግብዣና የደስታ እንዲሁም አንዳቸው ለሌላው ምግብ የሚልኩባቸውና ለድሆች ምጽዋት የሚሰጡባቸው ቀናት አድርገው እንዲያከብሩ ታዘው ነበር። +23 አይሁዳውያንም ማክበር የጀመሩትን ይህን በዓል ማክበራቸውን ለመቀጠልና መርዶክዮስ የጻፈላቸውን ነገር ለመፈጸም ተስማሙ። +24 የአይሁዳውያን ሁሉ ጠላት የነበረው የአጋጋዊው+ የሃመዳታ ልጅ ሃማ+ አይሁዳውያንን ለማጥፋት ሴራ ሸርቦ ነበርና፤+ እንዲሁም እነሱን ለማሸበርና ለመደምሰስ ፑር+ ወይም ዕጣ ጥሎ ነበር። +25 ሆኖም አስቴር ወደ ንጉሡ በገባች ጊዜ ንጉሡ “በአይሁዳውያን ላይ የሸረበው መጥፎ ሴራ+ በራሱ ላይ ይድረስበት” የሚል የጽሑፍ ትእዛዝ አስተላለፈ፤+ እነሱም እሱንና ልጆቹን በእንጨት ላይ ሰቀሏቸው።+ +26 በዚህም የተነሳ እነዚህን ቀናት ፑሪም አሏቸው፤ ይህ ስም የተወሰደው ፑር*+ ከተባለው ቃል ነው። በመሆኑም በዚህ ደብዳቤ ላይ ከሰፈረው ሐሳብ እንዲሁም ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ካዩአቸውና ካጋጠሟቸው ነገሮች የተነሳ +27 አይሁዳውያኑ ራሳቸውም ሆኑ ዘሮቻቸው እንዲሁም ከእነሱ ጋር የተባበሩ ሁሉ+ በየዓመቱ እነዚህን ሁለት ቀናት በተወሰነላቸው ጊዜ ላይ ለማክበርና እነዚህን ቀናት አስመልክቶ የተሰጣቸውን ትእዛዝ ለመፈጸም ቁርጥ ውሳኔ አደረጉ። +28 እያንዳንዱ ትውልድ፣ እያንዳንዱ ቤተሰብ፣ እያንዳንዱ አውራጃና እያንዳንዱ ከተማ እነዚህን ቀናት ማሰብና ማክበር ይጠበቅበት ነበር፤ እነዚህን የፑሪም ቀናት አይሁዳውያኑ ማክበራቸውን መተው የለባቸውም፤ መታሰቢያቸውም ከዘሮቻቸው መካከል መጥፋት የለበትም። +29 ከዚያም የአቢሃይል ልጅ ንግሥት አስቴርና አይሁዳዊው መርዶክዮስ ፑሪምን በተመለከተ የተጻፈውን ሁለተኛ ደብዳቤ በሙሉ ሥልጣናቸው አጸኑት። +30 እሱም የሰላምና የእውነት ቃል የያዙ ሕጋዊ እውቅና ያላቸው ደብዳቤዎችን በአሐሽዌሮስ+ ግዛት ውስጥ በሚገኙት 127 አውራጃዎች+ ለሚኖሩት አይሁዳውያን በሙሉ ላከ፤ +31 ይህም አይሁዳዊው መርዶክዮስና ንግሥት አስቴር ባዘዟቸው መሠረት+ እንዲሁም እነሱ ራሳቸው መጾምንና+ ምልጃ+ ማቅረብን ጨምሮ የሚጠበቅባቸውን ነገር ለመፈጸም ራሳቸውንና* ዘሮቻቸውን ግዴታ ውስጥ ባስገቡት መሠረት+ የፑሪምን ቀናት በተወሰነው ጊዜ እንዲያከብሩ ለማድረግ ነው። +32 አስቴር ያስተላለፈችውም ትእዛዝ ከፑሪም+ ጋር የተያያዙትን እነዚህን ነገሮች አጸና፤ ደግሞም መጽሐፍ ላይ ሰፈ��። +5 በሦስተኛው ቀን+ አስቴር ልብሰ መንግሥቷን ለብሳ ከንጉሡ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው በንጉሡ ቤት* ውስጠኛ ግቢ ቆመች፤ ንጉሡም በመግቢያው ፊት ለፊት በሚገኘው በንጉሡ ቤት ውስጥ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ነበር። +2 ንጉሡ፣ ንግሥት አስቴርን ግቢ ውስጥ ቆማ ሲያያት በፊቱ ሞገስ አገኘች፤ ንጉሡም እጁ ላይ የነበረውን የወርቅ በትረ መንግሥት ለአስቴር ዘረጋላት።+ በዚህ ጊዜ አስቴር ቀርባ የበትሩን ጫፍ ነካች። +3 ንጉሡም “ንግሥት አስቴር ሆይ፣ ምን ችግር አጋጠመሽ? የምትፈልጊው ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ብትጠይቂ ይሰጥሻል!” አላት። +4 አስቴርም መልሳ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ ንጉሡ ለእሱ ባዘጋጀሁት ግብዣ ላይ ዛሬ ከሃማ+ ጋር ይገኝልኝ” አለች። +5 በመሆኑም ንጉሡ አገልጋዮቹን “አስቴር ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት በአስቸኳይ እንዲመጣ ለሃማ ንገሩት” አለ። ስለዚህ ንጉሡና ሃማ አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ መጡ። +6 በወይን ጠጅ ግብዣው ላይ ንጉሡ አስቴርን እንዲህ አላት፦ “የምትጠይቂው ምንድን ነው? የጠየቅሽው ይሰጥሻል! የምትፈልጊውስ ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ብትጠይቂ ይሰጥሻል!”+ +7 አስቴርም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “የምጠይቀውም ሆነ የምፈልገው ነገር ይህ ነው፦ +8 በንጉሡ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ እንዲሁም ንጉሡ የምጠይቀውን ነገር መስጠትና የምፈልገውን መፈጸም ደስ ካሰኘው ነገ ንጉሡና ሃማ ለእነሱ በማዘጋጅላቸው ግብዣ ላይ ይገኙ፤ እኔም በነገው ዕለት ንጉሡ ያለውን አደርጋለሁ።” +9 በዚያ ቀን ሃማ ተደስቶ ልቡም ሐሴት አድርጎ ወጣ። ሆኖም ሃማ፣ መርዶክዮስን በንጉሡ በር ላይ ሲያየው እንዲሁም እንዳልተነሳለትና በፊቱ እንዳልተንቀጠቀጠ ሲመለከት በመርዶክዮስ ላይ ቁጣው ነደደ።+ +10 ይሁንና ሃማ ራሱን ተቆጣጥሮ ወደ ቤቱ ሄደ። ከዚያም ጓደኞቹንና ሚስቱን ዜሬሽን+ አስጠራቸው። +11 ሃማም ስለ ሀብቱ ታላቅነትና ስለ ወንዶች ልጆቹ ብዛት+ እንዲሁም ንጉሡ ላቅ ያለ ሹመት እንደሰጠውና ከመኳንንቱም ሆነ ከንጉሡ አገልጋዮች በላይ ከፍ ከፍ እንዳደረገው+ በጉራ ይነግራቸው ጀመር። +12 ሃማ በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “ምን ይሄ ብቻ፣ ንግሥት አስቴር አዘጋጅታ በነበረው ግብዣ+ ላይ ከንጉሡ ጋር እንድገኝ የጋበዘችው እኔን ብቻ ነው። በተጨማሪም ነገ ከንጉሡና ከእሷ ጋር እንድገኝ ጋብዛኛለች።+ +13 ይሁን እንጂ አይሁዳዊውን መርዶክዮስን በንጉሡ በር ላይ ተቀምጦ የማየው ከሆነ ይህ ሁሉ ምንም አያስደስተኝም።” +14 በዚህ ጊዜ ሚስቱ ዜሬሽና ጓደኞቹ በሙሉ እንዲህ አሉት፦ “ቁመቱ 50 ክንድ* የሆነ እንጨት አስተክል። ከዚያም ነገ ጠዋት በላዩ ላይ መርዶክዮስ እንዲሰቀል ለንጉሡ ንገረው።+ አንተም ከንጉሡ ጋር በግብዣው ላይ ተገኝተህ ሐሴት አድርግ።” ይህ ሐሳብ ሃማን አስደሰተው፤ እንጨቱንም አስተከለ። +17 “መንፈሴ ተሰብሯል፤ ዘመኔ አብቅቷል፤መቃብር ይጠብቀኛል።+ + 2 ፌዘኞች ከበውኛል፤+ዓይኔም የዓመፅ ተግባራቸውን በትኩረት ትመለከታለች።* + 3 እባክህ፣ መያዣዬን ተቀብለህ አንተ ዘንድ አስቀምጥልኝ። እጄን የሚመታና ተያዥ የሚሆነኝ ሌላ ማን ይኖራል?+ + 4 ማስተዋልን ከልባቸው ሰውረሃልና፤+ከዚህም የተነሳ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም። + 5 የልጆቹ ዓይን ደክሞ እያለ፣ያለውን ለወዳጆቹ ሊያካፍል ይችላል። + 6 አምላክ የሰዎች መቀለጃ* አደረገኝ፤+በመሆኑም ፊቱ ላይ እንደሚተፉበት ሰው ሆንኩ።+ + 7 ከሐዘን የተነሳ ዓይኔ ፈዘዘ፤+እጆቼና እግሮቼም እንደ ጥላ ሆኑ። + 8 ቅን የሆኑ ሰዎች በዚህ ነገር በመገረም ትኩር ብለው ይመለከታሉ፤ንጹሕ የሆነውም፣ አምላክ የለሽ* በሆነው ሰው ይረበሻል። + 9 ጻድቅ መንገዱን በጥብቅ ይከተላል፤+እጁ ንጹ��� የሆነ ሰውም እየበረታ ይሄዳል።+ +10 ይሁን እንጂ ሁላችሁም ተመልሳችሁ መከራከራችሁን መቀጠል ትችላላችሁ፤ከእናንተ መካከል አንድም ጥበበኛ አላገኘሁምና።+ +11 የሕይወት ዘመኔ አበቃ፤+ዕቅዴና የልቤ ምኞት ተንኮታኮተ።+ +12 ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤‘ጨለማ ስለሆነ ብርሃን የሚፈነጥቅበት ጊዜ ቀርቧል’ ይላሉ። +13 ዝም ብዬ ብጠብቅ ያን ጊዜ መቃብር፣* ቤቴ ይሆናል፤+በጨለማ መኝታዬን እዘረጋለሁ።+ +14 ጉድጓዱን*+ ‘አንተ አባቴ ነህ!’ እለዋለሁ፤ ትሏን ‘አንቺ እናቴና እህቴ ነሽ!’ እላታለሁ። +15 እንግዲህ የእኔ ተስፋ የት አለ?+ ተስፋ እንዳለኝ አድርጎ የሚያስብስ ማን ነው? +16 ሁላችንም ተያይዘን ወደ አፈር ስንገባ፣ተስፋዬ ወደተቀረቀሩ የመቃብር* በሮች ይወርዳል።”+ +30 “አሁን ግን ከእኔ በዕድሜ የሚያንሱ፣በእኔ ላይ ይስቃሉ፤+አባቶቻቸው መንጋዬን ከሚጠብቁ ውሾች ጋር እንዲሆኑፈቃደኛ አልነበርኩም። + 2 የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምን ይፈይድልኝ ነበር? እነሱ ጉልበት ከድቷቸዋል። + 3 ከችጋርና ከረሃብ የተነሳ ዝለዋል፤በወደመ እና ወና በሆነ ደረቅ ምድርያገኟትን ነገር ያላምጣሉ። + 4 በቁጥቋጦዎች አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚል ተክል ይሰበስባሉ፤ምግባቸው የክትክታ ዛፍ ሥር ነው። + 5 ከማኅበረሰቡ ተባረዋል፤+ሰዎችም ሌባ ላይ እንደሚጮኹ ይጮኹባቸዋል። + 6 በሸለቆዎች* ተዳፋት ላይ፣መሬት ላይ ባሉ ጉድጓዶች ውስጥና በዓለቶች መካከል ይኖራሉ። + 7 ከቁጥቋጦዎች ውስጥ ይጮኻሉ፤በሳማዎችም መካከል ይከማቻሉ። + 8 ማመዛዘን የጎደላቸውና የአልባሌ ሰዎች ልጆች ናቸው፤ከምድሪቱ ላይ ተባረዋል።* + 9 አሁን ግን በዘፈኖቻቸው ሳይቀር ይሳለቁብኛል፤+የእነሱ መሳለቂያ* ሆኛለሁ።+ +10 ይጸየፉኛል፤ ከእኔም ርቀዋል፤+በፊቴ ከመትፋት ወደኋላ አይሉም።+ +11 ምክንያቱም አምላክ ትጥቅ አስፈትቶኛል፤* ደግሞም አዋርዶኛል፤እነሱ በፊቴ እንዳሻቸው ይሆናሉ።* +12 በቀኜ በኩል እንደ አድመኛ ተነስተውብኛል፤እንድሸሽ አድርገውኛል፤በመንገዴም ላይ ለጥፋት የሚዳርግ መሰናክል አስቀምጠዋል። +13 መንገዶቼን ያፈርሳሉ፤መከራዬንም ያባብሳሉ፤+የሚገታቸውም የለም።* +14 ሰፊ ክፍተት ባለው ቅጥር እንደሚመጣ ሰው መጡ፤በፍርስራሹ መካከል እየገሰገሱ ገቡ። +15 በሽብር ተዋጥኩ፤ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዷል፤የመዳን ተስፋዬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቷል። +16 አሁን ሕይወቴ* ከውስጤ ተሟጠጠች፤+የጉስቁልና ዘመን+ ያዘኝ። +17 ከባድ ሕመም በሌሊት አጥንቶቼን ይበሳል፤*+የሚመዘምዘኝ ሥቃይ እረፍት አይሰጠኝም።+ +18 ልብሴ በታላቅ ኃይል ተበላሸ፤*እንደ ልብሴ አንገትጌ አንቆ ያዘኝ። +19 አምላክ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤አፈርና አመድ ሆንኩ። +20 እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትመልስልኝም፤+በፊትህ ቆምኩ፤ አንተ ግን ዝም ብለህ ታየኛለህ። +21 በጭካኔ በእኔ ላይ ተነሳህ፤+በእጅህ ብርታት አጠቃኸኝ። +22 ወደ ላይ አንስተህ በነፋስ ወሰድከኝ፤ከዚያም በአውሎ ነፋስ አንገላታኸኝ።* +23 በሕይወት ያለ ሁሉ ወደሚሰበሰብበት ቤት፣ወደ ሞት እንደምታወርደኝ አውቃለሁና። +24 ይሁንና የተሰበረ ሰው አደጋ ደርሶበት ለእርዳታ ሲጮኽ፣እጁን የሚያነሳበት ሰው አይኖርም።*+ +25 መከራ ላይ ለወደቁ ሰዎች* አላለቀስኩም? ለድሃውስ አላዘንኩም?*+ +26 መልካም ነገር በተስፋ ብጠባበቅም ክፉ ነገር ደረሰ፤ብርሃን ብጠባበቅም ጨለማ መጣ። +27 ውስጤ ያለማቋረጥ ተናወጠ፤የጉስቁልናም ዘመን መጣብኝ። +28 በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ፤+ የፀሐይ ብርሃንም የለም። በጉባኤ መካከል ቆሜ እርዳታ ለማግኘት እጮኻለሁ። +29 የቀበሮዎች ወንድም፣የሰጎንም ሴቶች ልጆች ባልንጀራ ሆንኩ።+ +30 ቆዳዬ ጠቁሮ ተቀረፈ፤+ከሙቀቱ* የተነሳ አጥንቶቼ ነደዱ። +31 በገናዬ ለሐዘን ብቻ ዋለ፤ዋሽንቴም* ለለቅሶ ሆነ። +35 ኤሊሁ እንዲህ ሲል መልስ መስጠቱን ቀጠለ፦ + 2 “ትክክል እንደሆንክ በጣም እርግጠኛ ከመሆንህ የተነሳ‘እኔ ከአምላክ ይበልጥ ጻድቅ ነኝ’ ትላለህ?+ + 3 ደግሞም ‘ይህ ለአንተ* ምን ለውጥ ያመጣል? ኃጢአት ብሠራ ኖሮ ከዚህ የከፋ ነገር ይደርስብኝ ነበር?’ ብለሃልና።+ + 4 ለአንተና አብረውህ ላሉት ወዳጆችህ፣+መልስ እሰጣለሁ። + 5 ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤ከአንተ ከፍ ያሉትን ደመናት በጥሞና ተመልከት።+ + 6 ኃጢአት ብትሠራ እሱን ምን ትጎዳዋለህ?+ በደልህ ቢበዛ እሱን ምን ታደርገዋለህ?+ + 7 ጻድቅ ብትሆን ለእሱ ምን ትጨምርለታለህ?ከአንተ እጅ ምን ይቀበላል?+ + 8 ክፋት ብትሠራ የምትጎዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጅ ነው። + 9 ሰዎች ከባድ ጭቆና ሲደርስባቸው ይጮኻሉ፤ከኃያል ሰው የሥልጣን ቀንበር* ለመገላገል ይጮኻሉ።+ +10 ይሁንና ‘በሌሊት መዝሙር እንዲዘመር የሚያደርገው፣+ታላቅ ፈጣሪዬ የሆነው አምላክ የት አለ?’ የሚል የለም።+ +11 ከምድር እንስሳት+ ይበልጥ እኛን ያስተምረናል፤+በሰማይ ከሚበርሩ ወፎችም በላይ ጥበበኞች አድርጎናል። +12 በክፉዎች ኩራት የተነሳ ሰዎች ይጮኻሉ፤ሆኖም እሱ አይመልስላቸውም።+ +13 በእርግጥ አምላክ ከንቱ ጩኸት* አይሰማም፤+ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ትኩረት አይሰጠውም። +14 አላየሁትም ብለህ ቅሬታ እያሰማህ፣ አንተንማ እንዴት ይስማህ!+ ጉዳይህ በእሱ ፊት ነው፤ ስለዚህ እሱን በትዕግሥት ተጠባበቅ።+ +15 ተቆጥቶ ተጠያቂ አላደረገህምና፤በችኮላ ያደረግከውንም አልያዘብህም።+ +16 ኢዮብ አፉን የሚከፍተው በከንቱ ነው፤እውቀት ሳይኖረው ብዙ ይናገራል።”+ +31 “ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።+ ታዲያ ለድንግሊቱ ተገቢ ያልሆነ ትኩረት እንዴት እሰጣለሁ?+ + 2 ለመሆኑ ከላይ ከአምላክ የማገኘው ድርሻ ምንድን ነው?ከፍ ባለ ስፍራ ከሚኖረው ሁሉን ቻይ አምላክ የማገኘውስ ውርሻ ምንድን ነው? + 3 በደለኛ ሰው ጥፋት፣ክፉ ነገር የሚያደርጉስ መቅሰፍት አይደርስባቸውም?+ + 4 እሱ መንገዴን ሁሉ አያይም?+እርምጃዬንስ ሁሉ አይቆጥርም? + 5 በውሸት ጎዳና ተመላልሼ* አውቃለሁ? እግሬ ለማታለል ተጣድፎ ያውቃል?+ + 6 አምላክ በትክክለኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤+ያን ጊዜ ንጹሕ አቋም* እንዳለኝ ይገነዘባል።+ + 7 እርምጃዬ ከመንገዱ ወጣ ብሎ፣+ወይም ልቤ ዓይኔን ተከትሎ፣+አሊያም እጄ ረክሶ ከሆነ፣ + 8 የዘራሁትን ዘር ሌላ ይብላው፤+የተከልኩትም ይነቀል።* + 9 ልቤ ሌላ ሴት ከጅሎ፣+በባልንጀራዬም ደጃፍ ላይ አድብቼ ከሆነ፣+ +10 ሚስቴ ለሌላ ሰው እህል ትፍጭ፤ሌሎች ወንዶችም ከእሷ ጋር ይተኙ።*+ +11 ይህ አሳፋሪ ምግባር፣ደግሞም በዳኞች ሊያስቀጣ የሚገባ በደል በሆነ ነበርና።+ +12 ይህ የሚያጠፋና የሚደመስስ፣*የፍሬዬንም ሥር ሁሉ የሚፈጅ* እሳት በሆነ ነበር።+ +13 ወንድ ባሪያዬ ወይም ሴት ባሪያዬ በእኔ ላይ አቤቱታ* ባቀረቡ ጊዜፍትሕ ነፍጌ ከሆነ፣ +14 አምላክ ሲከራከረኝ* ምን ማድረግ እችላለሁ? ሲጠይቀኝስ ምን መልስ እሰጣለሁ?+ +15 እኔን በማህፀን ውስጥ የሠራኝ እነሱንስ አልሠራም?+ ከመወለዳችን በፊት* የሠራን እሱ ራሱ አይደለም?+ +16 ድሃ የሆኑ ሰዎች የፈለጉትን ነገር ነፍጌ፣+ወይም የመበለቲቱ ዓይን እንዲያዝን* አድርጌ ከሆነ፣+ +17 ወላጅ አልባ ለሆኑ ልጆች ሳላካፍል፣የራሴን ምግብ ብቻዬን በልቼ ከሆነ፣+ +18 (ወላጅ አልባ የሆነውን ልጅ* ከወጣትነቴ ጀምሮ እንደ አባት ሆኜ አሳድጌዋለሁና፤ከልጅነቴም* አንስቶ መበለቲቱን* ስመራት ቆይቻለሁ።) +19 ሰው የሚለብሰው አጥቶ በብርድ ሲያልቅ፣ወይም ድሃው ሲታ���ዝ አይቼ ከሆነ፣+ +20 ከጠቦቶቼ የተሸለተውን ፀጉር ለብሶ በሞቀው ጊዜ፣ሳይባርከኝ ቀርቶ ከሆነ፣+ +21 በከተማዋ በር+ ላይ የእኔን እርዳታ በሚፈልግ ወላጅ አልባ ልጅ ላይ*እጄን በዛቻ አወዛውዤ ከሆነ፣+ +22 ክንዴ* ከትከሻዬ ይውለቅ፤ክንዴም ከክርኔ* ይሰበር። +23 ከአምላክ የሚመጣ ጥፋት ያስፈራኛልና፤በግርማውም ፊት መቆም አልችልም። +24 ወርቅን መታመኛዬ አድርጌ፣ወይም ምርጥ የሆነውን ወርቅ ‘አንተ መመኪያዬ ነህ!’ ብዬ ከሆነ፣+ +25 ታላቅ ሀብት በማፍራቴ፣እንዲሁም ብዙ ንብረት በማግኘቴ ደስ ብሎኝ ከሆነ፣+ +26 ፀሐይ ስትፈነጥቅ፣*ወይም ጨረቃ ግርማ ተላብሳ ስትሄድ አይቼ ከሆነ፣+ +27 ልቤ በስውር ተታሎ፣አፌም ለእነሱ አምልኮ ለማቅረብ እጄን ስሞ ከሆነ፣+ +28 ይህ በዳኞች ሊያስቀጣ የሚገባ በደል በሆነ ነበር፤በላይ ያለውን እውነተኛውን አምላክ መካድ ይሆንብኝ ነበርና። +29 ጠላቴ በደረሰበት ጥፋት ደስ ብሎኝ ያውቃል?+ወይስ ክፉ ነገር ስለደረሰበት ሐሴት አድርጌ አውቃለሁ? +30 በእርግማን ሕይወቱን* በመሻት፣አንደበቴ ኃጢአት እንዲሠራ አልፈቀድኩም።+ +31 በድንኳኔ የሚኖሩ ሰዎች‘እሱ ካቀረበው ምግብ* በልቶ ያልጠገበ ሰው ማግኘት የሚችል ማን አለ?’ አላሉም?+ +32 አንድም እንግዳ* ደጅ አያድርም ነበር፤+ቤቴን ለመንገደኛ እከፍት ነበር። +33 በደሌን በልብሴ ኪስ በመሸሸግ፣እንደ ሌሎች ሰዎች ጥፋቴን ለመሸፋፈን ሞክሬ አውቃለሁ?+ +34 የብዙ ሰዎችን ምላሽ በመፍራት፣ወይም በሌሎች ቤተሰቦች ንቀት በመሸበር፣ዝም ብያለሁ? ደግሞስ ወደ ውጭ መውጣት ፈርቻለሁ? +35 ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ!+ በተናገርኩት ነገር ላይ ስሜን አሰፍር ነበር።* ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ መልስ ይስጠኝ!+ ምነው ከሳሼ ክሱን በሰነድ ላይ ባሰፈረ ኖሮ! +36 በትከሻዬ እሸከመው ነበር፤እንደ አክሊልም በራሴ ላይ አስረው ነበር። +37 የወሰድኩትን እያንዳንዱን እርምጃ ባሳወቅኩት ነበር፤እንደ አለቃ በልበ ሙሉነት ወደ እሱ እቀርብ ነበር። +38 እርሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ፣ትልሞቿም በአንድ ላይ አልቅሰው ከሆነ፣ +39 ፍሬዋን ያለዋጋ በልቼ፣+ባለቤቶቿንም* አሳዝኜ ከሆነ፣+ +40 በስንዴ ፋንታ እሾህ፣በገብስም ምትክ የሚገማ አረም ይብቀልብኝ።” የኢዮብ ቃል እዚህ ላይ ተፈጸመ። +18 ሹሃዊው በልዳዶስ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “እንዲህ ያለ ንግግር መናገራችሁን* የምትቀጥሉት እስከ መቼ ነው? በተወሰነ መጠን ልታስተውሉ ይገባል፤ ያን ጊዜ እኛ እንናገራለን። + 3 ለምን እንደ እንስሳ እንቆጠራለን?+በፊታችሁስ ለምን እንደ ደነዝ* እንታያለን? + 4 አንተ በቁጣ ራስህን* ብትቦጫጭቅ፣ለአንተ ሲባል ምድር ባዶ ትቀራለች?ወይስ ዓለት ከስፍራው ተነቅሎ ይወሰዳል? + 5 አዎ፣ የክፉዎች ብርሃን ይጠፋል፤የእሳቱም ነበልባል አይበራም።+ + 6 በድንኳኑ ውስጥ ያለው ብርሃን በእርግጥ ይጨልማል፤በላዩ ያለው መብራትም ይጠፋል። + 7 ብርታት የተሞላበት እርምጃው ያጥራል፤የገዛ ዕቅዱም ይጥለዋል።+ + 8 እግሩ ወደ መረብ ይመራዋልና፤በመረቡም ገመድ ይተበተባል። + 9 ወጥመድ ተረከዙን ይይዘዋል፤ወስፈንጥርም ያጠምደዋል።+ +10 በመሬት ላይ ሸምቀቆ በስውር ይቀመጥለታል፤ወጥመድም በመንገዱ ላይ ይጠብቀዋል። +11 ሽብር ከሁሉም አቅጣጫ ፍርሃት ይለቅበታል፤+እግር በእግርም ያሳድደዋል። +12 ጉልበቱ ይከዳዋል፤አደጋም+ያንገዳግደዋል።* +13 ቆዳው ተበልቷል፤እጅግ ቀሳፊ የሆነ በሽታ* እጆቹንና እግሮቹን ይበላል። +14 ተማምኖ ከሚኖርበት ድንኳኑ ይወገዳል፤+ወደ ሽብር ንጉሥም* ይወሰዳል። +15 እንግዶች በድንኳኑ ውስጥ ይኖራሉ፤*በቤቱም ላይ ድኝ ይበተናል።+ +16 ሥሮቹ ከእሱ በታች ይደርቃሉ፤ቅርንጫፎቹ ደግሞ ከእሱ በላይ ይጠወልጋሉ። +17 መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፤በጎዳናም ላይ ስሙ አይታወቅም።* +18 ከብርሃን ወደ ጨለማ ይወሰዳል፤ፍሬያማ ከሆነችውም ምድር ይባረራል። +19 በሕዝቡ መካከል ልጆችም ሆኑ ዘሮች አይኖሩትም፤በሚኖርበት ስፍራም* የሚተርፍ ሰው አይኖረውም። +20 የሚጠፋበት ቀን ሲደርስ በምዕራብ ያሉ ሰዎች ይደነግጣሉ፤በምሥራቅ ያሉ ሰዎችም በፍርሃት ይዋጣሉ። +21 የክፉ አድራጊ ድንኳኖች፣አምላክን የማያውቁ ሰዎች ስፍራም እንዲህ ያለ ነገር ይደርስባቸዋል።” +23 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “ዛሬም እንኳ ብሶት ማሰማቴን አላቆምም፤*+ከመቃተቴ የተነሳ ኃይሌ ተሟጠጠ። + 3 አምላክን የት እንደማገኘው ባወቅኩ!+ ወደሚኖርበት ስፍራ እሄድ ነበር።+ + 4 ጉዳዬን በፊቱ አቀርብ፣አፌንም በሙግት እሞላ ነበር፤ + 5 እሱ እንዴት እንደሚመልስልኝ ባወቅኩ፣የሚለኝንም ባስተዋልኩ ነበር። + 6 ታላቅ ኃይሉን ተጠቅሞ ከእኔ ጋር ይሟገት ይሆን? በፍጹም! ይልቁንም ያዳምጠኛል።+ + 7 ያን ጊዜ ቅን የሆነው ሰው ከአምላክ ጋር ስምምነት መፍጠር ይችላል፤ፈራጄም እኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በነፃ ይለቀኛል። + 8 ይሁንና ወደ ምሥራቅ ብሄድ እሱ በዚያ የለም፤ተመልሼ ብመጣም ላገኘው አልችልም። + 9 በስተ ግራ ሆኖ ሲሠራ ላየው አልችልም፤ከዚያም ወደ ቀኝ ይዞራል፤ በዚህ ጊዜም ቢሆን አላየውም። +10 እሱ ግን የሄድኩበትን መንገድ ያውቃል።+ ከፈተነኝ በኋላ እንደጠራ ወርቅ እሆናለሁ።+ +11 እግሬ የእሱን ዱካ በጥብቅ ተከትሏል፤ምንም ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ።+ +12 ከከንፈሩ ትእዛዝ አልራቅኩም። የተናገረውን ቃል ከሚጠበቅብኝ* በላይ ከፍ አድርጌ ተመልክቻለሁ።+ +13 ቆርጦ ከተነሳ ማን ሊቃወመው ይችላል?+ እሱ አንድ ነገር ማድረግ ከፈለገ* ከማድረግ ወደኋላ አይልም።+ +14 በእኔ ላይ የተወሰነውን* ሙሉ በሙሉ ይፈጽማልና፤እንደዚህ ያሉ ብዙ ነገሮችም በእሱ ዘንድ አሉ። +15 በእሱ የተነሳ የተጨነቅኩት ለዚህ ነው፤ስለ እሱ ሳስብ ይበልጥ ፍርሃት ያድርብኛል። +16 አምላክ ራሱ ፈሪ አድርጎኛል፤ሁሉን ቻይ የሆነውም አምላክ አስደንግጦኛል። +17 ይሁን እንጂ ጨለማውም ሆነፊቴን የሸፈነው ድቅድቅ ጨለማ ዝም አላሰኘኝም። +34 ኤሊሁም መልስ መስጠቱን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ + 2 “እናንተ ጥበበኞች፣ ቃሌን አዳምጡ፤እናንተ ብዙ እውቀት ያላችሁ ስሙኝ። + 3 ምላስ* የምግብን ጣዕም እንደሚለይ ሁሉ፣ጆሮም ቃላትን ያመዛዝናል። + 4 ትክክለኛ የሆነውን ነገር እናመዛዝን፤መልካም የሆነውን ነገር በመካከላችን እንወስን። + 5 ኢዮብ እንዲህ ብሏልና፦ ‘እኔ ትክክል ነኝ፤+አምላክ ግን ፍትሕ ነፍጎኛል።+ + 6 ሊበየንብኝ የሚገባውን ፍርድ በተመለከተ እዋሻለሁ? በደል ባልሠራም እንኳ በላዬ ላይ ያለው ቁስል የማይሽር ነው።’+ + 7 ፌዝን እንደ ውኃ የሚጠጣ፣እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው? + 8 ክፉ ድርጊት ከሚፈጽሙ ጋር ተወዳጅቷል፤ከክፉዎችም ጋር ገጥሟል።+ + 9 ኢዮብ ‘ሰው አምላክን ለማስደሰት መሞከሩምንም ፋይዳ የለውም’ ብሏልና።+ +10 ስለዚህ እናንተ አስተዋዮች* ስሙኝ፦ ‘እውነተኛው አምላክ ክፉ ነገር ያደርጋል፤ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በደል ይፈጽማል’ ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው!+ +11 ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋልና፤+መንገዱም ያስከተለበትን መዘዝ እንዲቀበል ያደርገዋል። +12 በእርግጥም አምላክ ክፋት አይሠራም፤+ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ፍትሕን አያዛባም።+ +13 ምድርን እንዲገዛ ያደረገው ማን ነው?በመላው ዓለም* ላይ የሾመውስ ማን ነው? +14 እሱ ትኩረቱን* በእነሱ ላይ ቢያደርግ፣መንፈሳቸውንና እስትንፋሳቸውን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፣+ +15 ሰዎች* ሁሉ በአንድነት በጠፉ፣የሰውም ዘር ወደ አፈር በተመለሰ ነበር።+ +16 ስለ��ህ ማስተዋል ካለህ ለዚህ ነገር ትኩረት ስጥ፤የምናገረውንም በጥሞና አዳምጥ። +17 ፍትሕን የሚጠላ ሰው፣ ገዢ ሊሆን ይገባል?ወይስ ጻድቅ የሆነውን ኃያል ሰው ትኮንነዋለህ? +18 ንጉሥን ‘የማትረባ ነህ፣’ ታላላቅ የሆኑ ሰዎችንስ ‘ክፉዎች ናችሁ’ ትላለህ?+ +19 አምላክ ለመኳንንት አያዳላም፤ሀብታሙንም ከድሃው* አስበልጦ አይመለከትም፤+ሁሉም የእጁ ሥራዎች ናቸውና።+ +20 እነሱ በእኩለ ሌሊት ድንገት ሊሞቱ ይችላሉ፤+በኃይል ተንቀጥቅጠው ሕይወታቸው ያልፋል፤ኃያላን የሆኑትም እንኳ ይወገዳሉ፤ ይሁንና ይህ የሚሆነው በሰው እጅ አይደለም።+ +21 የአምላክ ዓይኖች የሰውን መንገድ ይመለከታሉና፤+ደግሞም እርምጃውን ሁሉ ያያል። +22 ክፉ ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች የሚደበቁበትጨለማም ሆነ ፅልማሞት የለም።+ +23 አምላክ፣ ማንኛውም ሰው በፊቱ ለፍርድ እንዲቀርብ፣የተወሰነ ጊዜ አልቀጠረምና። +24 ምርመራ ማድረግ ሳያስፈልገው ኃያላንን ይሰባብራል፤በእነሱም ቦታ ሌሎችን ይተካል።+ +25 እያደረጉ ያሉትን ያውቃልና፤+በሌሊት ይገለብጣቸዋል፤ እነሱም ይደቅቃሉ።+ +26 በክፋታቸው የተነሳ፣ሁሉም ማየት በሚችልበት ቦታ ይመታቸዋል፤+ +27 ምክንያቱም እሱን ከመከተል ወደኋላ ብለዋል፤+መንገዶቹንም ሁሉ ችላ ብለዋል፤+ +28 ድሃው ወደ እሱ እንዲጮኽ ያደርጋሉ፤እሱም የምስኪኖችን ጩኸት ይሰማል።+ +29 አምላክ ዝም ሲል ማን ሊወቅሰው ይችላል? ፊቱን በሚሰውርበት ጊዜ ማን ሊያየው ይችላል? ይህን ያደረገው በአንድ ብሔር ላይም ሆነ በአንድ ሰው ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም፤ +30 ይህም አምላክ የለሽ የሆነ* ሰው እንዳይገዛ፣+ወይም በሕዝቡ ላይ ወጥመድ እንዳይዘረጋ ነው። +31 አምላክን እንዲህ የሚል ሰው ይኖራል?‘የሠራሁት ጥፋት ባይኖርም ተቀጥቻለሁ፤+ +32 ማየት የተሳነኝን ነገር አስተምረኝ፤የሠራሁት ጥፋት ካለ ዳግመኛ አልሠራም።’ +33 ፍርዱን አልቀበልም ስትል አንተ በምትፈልገው መንገድ ሊክስህ ይገባል? መወሰን ያለብህ አንተ እንጂ እኔ አይደለሁም። ስለዚህ አንተ በደንብ የምታውቀውን ነገር ንገረኝ። +34 አስተዋይ የሆኑ* ሰዎች፣ደግሞም እኔን የሚሰሙ ጥበበኛ ሰዎች ሁሉ እንዲህ ይሉኛል፦ +35 ‘ኢዮብ ያለእውቀት ይናገራል፤+ቃሉም ማስተዋል የጎደለው ነው።’ +36 ኢዮብ እስከ መጨረሻው ድረስ ይፈተን!*እንደ ክፉ ሰዎች መልስ ሰጥቷልና። +37 በኃጢአቱ ላይ ዓመፅ ጨምሯል፤+በፊታችን በንቀት አጨብጭቧል፤በእውነተኛውም አምላክ ላይ ብዙ ነገር ተናግሯል!”+ +19 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “እናንተ ሰዎች ነፍሴን የምታበሳጯት፣*+በቃላት የምትደቁሱኝስ+ እስከ መቼ ነው? + 3 ይኸው አሥር ጊዜ ገሠጻችሁኝ፤*ከባድ በደል ስትፈጽሙብኝ አላፈራችሁም።+ + 4 ስህተት ብፈጽምም እንኳ፣የሠራሁት ስህተት ከእኔ ጋር ይኖራል። + 5 በእኔ ላይ የደረሰው ነቀፋ ተገቢ እንደሆነ አድርጋችሁ በመከራከር፣በእኔ ላይ ራሳችሁን ከፍ ከፍ ብታደርጉ፣ + 6 ያሳተኝ አምላክ እንደሆነ እወቁ፤በማጥመጃ መረቡም ይዞኛል። + 7 እነሆ ‘ግፍ ተፈጸመብኝ!’ ብዬ ብጮኽም መልስ አላገኘሁም፤+እርዳታ ለማግኘት ብጣራም ፍትሕ የለም።+ + 8 መንገዴን በድንጋይ ግንብ ዘጋ፤ እኔም ማለፍ አልቻልኩም፤ጎዳናዬንም በጨለማ ጋረደ።+ + 9 ክብሬን ገፎኛል፤አክሊሉንም ከራሴ ላይ አንስቷል። +10 እስክጠፋ ድረስ በሁሉም አቅጣጫ አፈራረሰኝ፤ተስፋዬን እንደ ዛፍ ነቀለው። +11 ቁጣው በእኔ ላይ ነደደ፤እንደ ጠላቱም ቆጠረኝ።+ +12 ሠራዊቱ በአንድነት መጥተው ከበቡኝ፤በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ። +13 የገዛ ወንድሞቼን ከእኔ አራቀ፤የሚያውቁኝም ሰዎች ጥለውኝ ሄዱ።+ +14 የቅርብ ወዳጆቼ ትተውኛል፤*በደንብ የማውቃቸውም ሰዎች ረሱኝ።+ +15 በቤቴ ያሉ እንግዶችና+ ሴቶች ባሪያዎቼ እንደ መጤ ቆጠሩኝ፤እንደ ባዕድ አገር ሰው ተመለከቱኝ። +16 አገልጋዬን ጠራሁት፤ እሱ ግን አልመለሰልኝም፤እንዲራራልኝ በአንደበቴ ለመንኩት። +17 ሚስቴ ትንፋሼን እንኳ ተጸየፈችው፤+ለገዛ ወንድሞቼም* መጥፎ ጠረን ሆንኩባቸው። +18 ትናንሽ ልጆች እንኳ ናቁኝ፤ስነሳ በእኔ ላይ ያላግጣሉ። +19 የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤+የምወዳቸውም ሰዎች በእኔ ላይ ተነሱ።+ +20 አጥንቶቼ ከቆዳዬና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ፤+ከሞት ለጥቂት* ተረፍኩ። +21 ወዳጆቼ ሆይ፣ ማሩኝ፤ እባካችሁ ማሩኝ፤የአምላክ እጅ መታኛለችና።+ +22 አምላክ እንዳሳደደኝ የምታሳድዱኝ ለምንድን ነው?+ያለፋታ የምታጠቁኝስ* ለምንድን ነው?+ +23 ምነው ቃሌ በተጻፈ!ምነው በመጽሐፍ ላይ በሰፈረ! +24 ምነው በብረት ብዕርና በእርሳስ፣በዓለቱ ላይ ለዘላለም በተቀረጸ! +25 የሚዋጀኝ*+ ሕያው እንደሆነ በሚገባ አውቃለሁና፤ከጊዜ በኋላ መጥቶ በምድር ላይ ይቆማል። +26 ቆዳዬ በዚህ መንገድ ቢጠፋም፣ገና በሥጋ እያለሁ አምላክን አየዋለሁ፤ +27 እኔ ራሴ እሱን እመለከተዋለሁ፤የሌላ ሰው ዓይን ሳይሆን የገዛ ዓይኖቼ ያዩታል።+ ይሁንና በውስጤ እንደዛልኩ ይሰማኛል!* +28 የችግሩ መንስኤ እኔ ጋ እያለ፣ ‘የምናሳድደው እንዴት ነው?’ ትላላችሁና።+ +29 እናንተ ራሳችሁ ሰይፉን ፍሩ፤+ሰይፉ በበደል ላይ ቅጣት ያመጣልና፤ፈራጅ መኖሩን ልታውቁ ይገባል።”+ +20 ናአማታዊው ሶፋር+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “ስሜቴ ስለታወከ፣የሚረብሸኝ ሐሳብ መልስ እንድሰጥ ይገፋፋኛል። + 3 እኔን የሚዘልፍ ወቀሳ ሰምቻለሁ፤ያለኝ ማስተዋል* መልስ እንድሰጥ ይገፋፋኛል። + 4 ከድሮ ጀምሮ ይህን ታውቅ ነበር ማለት ነው፤ሰው* በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እንዲህ ነበርና፤+ + 5 የክፉዎች እልልታ ለአጭር ጊዜ፣አምላክ የለሽ የሆነ* ሰው ደስታም ለቅጽበት ነው።+ + 6 ታላቅነቱ ወደ ሰማይ ከፍ ቢል፣ራሱም እስከ ደመናት ቢደርስ፣ + 7 እንደ ራሱ እዳሪ ለዘላለም ይጠፋል፤ያዩት የነበሩ ሰዎችም ‘የት ገባ?’ ይላሉ። + 8 እንደ ሕልም በሮ ይጠፋል፤ እነሱም አያገኙትም፤እንደ ሌሊት ራእይ ይሰደዳል። + 9 ቀድሞ ያየው ዓይን ዳግመኛ አያየውም፤የነበረበት ስፍራም ከእንግዲህ አይመለከተውም።+ +10 የገዛ ልጆቹ የድሆችን ሞገስ ለማግኘት ይሻሉ፤የገዛ እጆቹም ሀብቱን መልሰው ይሰጣሉ።+ +11 አጥንቶቹ በወጣትነት ጉልበት የተሞሉ ነበሩ፤ሆኖም ጉልበቱ ከእሱ ጋር አፈር ውስጥ ይተኛል። +12 መጥፎ የሆነ ነገር በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፣ከምላሱም በታች ቢደብቀው፣ +13 እንዳያልቅበት ሳስቶ ቢያላምጠው፣በአፉም ውስጥ ቢያቆየው፣ +14 ምግቡ በውስጡ ይጎመዝዛል፤በውስጡም እንደ ጉበና* መርዝ* ይሆናል። +15 የዋጠውን ሀብት መልሶ ይተፋዋል፤አምላክ ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል። +16 የጉበናዎችን መርዝ ይጠባል፤የእፉኝት ጥርስ* ይገድለዋል። +17 የውኃ ፈሳሾችን፣የማርና የቅቤ ጅረቶችን ፈጽሞ አያይም። +18 ንብረቱን ሳይጠቀምበት ይመልሳል፤ነግዶ ባገኘው ሀብት አይደሰትም።+ +19 ድሆችን አድቅቋልና፤ ደግሞም ትቷቸዋል፤ያልገነባውን ቤት ቀምቷል። +20 ሆኖም በውስጡ ሰላም አይኖረውም፤ያካበተው ሀብት አያድነውም። +21 ሊበላው የሚችል የተረፈ ነገር አይኖርም፤ከዚህም የተነሳ ብልጽግናው ዘላቂ አይሆንም። +22 ሀብቱ ሲትረፈረፍ በጭንቀት ይዋጣል፤የመከራ ዓይነት ይፈራረቅበታል። +23 ሆዱ በሞላ ጊዜ፣አምላክ* የሚነድ ቁጣውን በእሱ ላይ በመላክ፣ወደ አንጀቱ እስኪገባ ያዘንብበታል። +24 ከብረት የጦር መሣሪያ ሲሸሽ፣ከመዳብ የተሠራ ቀስት ይወጋዋል። +25 ቀስት ከጀርባው፣የሚያብረቀርቅ መሣሪያ ከሐሞቱ መዝዞ ያወጣል፤በሽብርም ይዋጣል።+ +26 ውድ ሀብቱ ለድቅድቅ ��ለማ ይዳረጋል፤ማንም ያላርገበገበው እሳት እሱን ይበላዋል፤በድንኳኑ ውስጥ የቀረ ማንኛውም ሰው ጥፋት ይደርስበታል። +27 ሰማይ በደሉን ይገልጥበታል፤ምድር በእሱ ላይ ትነሳለች። +28 ጎርፍ ቤቱን ጠርጎ ይወስደዋል፤በአምላክ የቁጣ ቀን* የውኃ መጥለቅለቅ ይከሰታል። +29 ክፉ ሰው ከአምላክ የሚቀበለው ድርሻ፣አምላክም የወሰነለት ርስት ይህ ነው።” +3 ከዚህ በኋላ ኢዮብ መናገርና የተወለደበትን ቀን መርገም ጀመረ።+ +2 ኢዮብም እንዲህ አለ፦ + 3 “የተወለድኩበት ቀን፣‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ!’ የተባለበትም ሌሊት ይጥፋ።+ + 4 ያ ቀን ጨለማ ይሁን። በላይ ያለው አምላክ አያስበው፤ብርሃንም አይፈንጥቅበት። + 5 ድቅድቅ ጨለማ* ይውረሰው። ጥቁር ደመና ይረፍበት። ቀንን የሚያጨልም ነገር ያሸብረው። + 6 ያን ሌሊት ጨለማ ይውረሰው፤+ከዓመቱ ቀኖች መካከል ያ ሌሊት ደስ አይበለው፤ከወራቱም ቁጥር መካከል አይደመር። + 7 አዎ፣ ያ ሌሊት መሃን ይሁን!እልልታም አይሰማበት። + 8 ቀንን የሚረግሙ፣ሌዋታንንም*+ መቀስቀስ የሚችሉ ቀኑን ይርገሙት። + 9 አጥቢያ ኮከቦቹ ይጨልሙ፤የቀን ብርሃንን ቢጠብቅም አያግኝ፤የንጋትንም ጮራ አይመልከት። +10 የእናቴን ማህፀን በሮች አልዘጋምና፤+ችግርንም ከዓይኔ አልሰወረም። +11 ምነው ስወለድ በሞትኩ! ምነው ከማህፀን ስወጣ በተቀጨሁ!+ +12 የሚቀበሉኝ ጉልበቶች፣የሚያጠቡኝም ጡቶች ለምን ተገኙ? +13 ይህን ጊዜ ሳልረበሽ በተጋደምኩ ነበርና፤+በተኛሁና እረፍት ባገኘሁ ነበር፤+ +14 በአሁኑ ጊዜ ፈራርሰው ያሉ ቦታዎችን ለራሳቸው ከገነቡ*የምድር ነገሥታትና አማካሪዎቻቸው ጋር፣ +15 ወይም ቤታቸውን በብር ከሞሉወርቅ ካላቸው መኳንንት ጋር ባረፍኩ ነበር። +16 እንደተሰወረ ጭንጋፍ፣ፈጽሞ ብርሃን እንዳላዩ ልጆች ለምን አልሆንኩም? +17 በዚያ ክፉዎች እንኳ ከሚረብሽ ነገር ተገላግለዋል፤የዛሉ ሰዎች በዚያ አርፈዋል።+ +18 በዚያ እስረኞች በአንድነት ተረጋግተው ይኖራሉ፤አስገድዶ የሚያሠራቸውን ሰው ድምፅ አይሰሙም። +19 በዚያ ትንሹም ሆነ ትልቁ አንድ ናቸው፤+ባሪያውም ከጌታው ነፃ ወጥቷል። +20 እሱ መከራ ላይ ላለ ሰው ብርሃን፣ለተመረሩ ሰዎችስ* ሕይወት ለምን ይሰጣል?+ +21 ሞትን ቢመኙም የማያገኙት ለምንድን ነው?+ ከተሰወረ ሀብት ይበልጥ ይሹታል፤ +22 መቃብር ሲያገኙ ሐሴት ያደርጋሉ፤እጅግም ደስ ይላቸዋል። +23 መንገዱ ለጠፋበት፣አምላክም ዙሪያውን ላጠረበት ሰው+ ለምን ብርሃን ይሰጣል? +24 በምግቤ ፋንታ ሲቃ ተናንቆኛልና፤+የሥቃይ ጩኸቴ+ እንደ ውኃ ይፈስሳል። +25 የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፤ያሸበረኝም ነገር ደርሶብኛል። +26 ሰላምም ሆነ እርጋታ አላገኘሁም፤ እረፍትም አልነበረኝም፤ይልቁንም መከራ አልተለየኝም።” +24 “ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ለምን ጊዜ አልወሰነም?+ እሱን የሚያውቁትስ ቀኑን* ለምን አያዩም? + 2 ሰዎች የወሰን ምልክቶችን ይገፋሉ፤+ነጥቀው የወሰዱትን መንጋ በራሳቸው መስክ ላይ ያሰማራሉ። + 3 አባት የሌላቸውን ልጆች አህያ እየነዱ ይወስዳሉ፤የመበለቲቱንም በሬ መያዣ አድርገው ይወስዳሉ።+ + 4 ድሃውን ከመንገድ ያስወጣሉ፤በዚህ ጊዜ የምድሪቱ ምስኪኖች ከእነሱ ለመሸሸግ ይገደዳሉ።+ + 5 ድሆች በምድረ በዳ እንዳሉ የዱር አህዮች፣+ ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤በበረሃ ለልጆቻቸው ምግብ ይፈልጋሉ። + 6 ከሌላው ሰው እርሻ እህል* ለመሰብሰብ ይገደዳሉ፤ከክፉውም ሰው የወይን እርሻ ይቃርማሉ። + 7 ያለልብስ ራቁታቸውን ያድራሉ፤+ብርድ የሚከላከሉበት ልብስ የላቸውም። + 8 ከተራሮች በሚወርደው ዝናብ ይበሰብሳሉ፤መጠለያ ስለማያገኙ ዓለት ያቅፋሉ። + 9 አባት የሌለው ልጅ ከእናቱ ጡት ላይ ተነጥቋል፤+የድሃውም ልብስ በመያዣነት ተወስዷል፤+ +10 ያለልብስ ራቁታቸውን ለመሄድ ይገደዳሉ፤ተርበው እያሉም ነዶ ተሸክመው ይሄዳሉ። +11 በቀትር ሐሩር በእርከኖቹ መካከል ይለፋሉ፤*የወይን መጭመቂያውን እየረገጡ እነሱ ግን ይጠማሉ።+ +12 በሞት አፋፍ ላይ ያሉት በከተማዋ ውስጥ ያጣጥራሉ፤ክፉኛም የቆሰሉት ሰዎች* እርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤+አምላክ ግን ይህን በቸልታ ያልፋል።* +13 በብርሃን ላይ የሚያምፁ አሉ፤+የብርሃኑን መንገድ አላወቁም፤ጎዳናውንም አልተከተሉም። +14 ነፍሰ ገዳዩ ጎህ ሲቀድ ይነሳል፤ምስኪኑንና ድሃውን ይገድላል፤+በሌሊትም ይሰርቃል። +15 የአመንዝራ ዓይን ድንግዝግዝታን ይጠባበቃል፤+‘ማንም አያየኝም!’ ይላል፤+ ፊቱንም ይሸፍናል። +16 በጨለማ ቤት ሰብረው* ይገባሉ፤ቀን ላይ ተሸሽገው ይውላሉ። ለብርሃን እንግዳ ናቸው።+ +17 ለእነሱ ንጋት እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነውና፤ድቅድቅ ጨለማ የሚያስከትለውን ሽብር ያውቁታል። +18 ይሁንና ውኃ በፍጥነት ጠርጎ ይወስዳቸዋል።* ርስታቸውም የተረገመ ይሆናል።+ ወደ ወይን እርሻቸው አይመለሱም። +19 ድርቁና ሐሩሩ የቀለጠውን በረዶ እንደሚያስወግደው፣መቃብር* ኃጢአተኞችን ይነጥቃል!+ +20 እናቱ* ትረሳዋለች፤ ትልም ትመጠምጠዋለች። ዳግመኛ አይታወስም።+ ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል። +21 በመሃኒቱ ላይ ያደባል፤መበለቲቱንም ይበድላል። +22 አምላክ* ኃይሉን ተጠቅሞ ብርቱ ሰዎችን ያጠፋል፤ከፍ ከፍ ቢሉም ሕይወታቸው ዋስትና የለውም። +23 አምላክ* የመተማመን ስሜት እንዲያድርባቸውና ደህንነት እንዲሰማቸው ይፈቅዳል፤+ይሁንና ዓይኑ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ* ላይ ነው።+ +24 ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ከዚያም ደብዛቸው ይጠፋል።+ ዝቅ ዝቅ ይደረጋሉ፤+ ደግሞም እንደ ማንኛውም ሰው ይሰበሰባሉ፤እንደ እህል ዛላ ይቆረጣሉ። +25 እንግዲህ አሁን እኔን ውሸታም ሊያደርገኝ፣ወይም ቃሌን ሊያስተባብል የሚችል ማን ነው?” +32 ኢዮብ ጻድቅ ነኝ የሚል ጽኑ እምነት ስለነበረው፣*+ እነዚህ ሦስት ሰዎች ለእሱ መልስ መስጠታቸውን አቆሙ። +2 ይሁን እንጂ ከራም ወገን የሆነው የቡዛዊው+ የባራክኤል ልጅ ኤሊሁ እጅግ ተቆጣ። ከአምላክ ይልቅ ራሱን* ጻድቅ ለማድረግ ስለሞከረ+ በኢዮብ ላይ ቁጣው ነደደ። +3 በተጨማሪም ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች መልስ መስጠት ባለመቻላቸው፣ ይልቁንም አምላክን ክፉ በማድረጋቸው+ በእነሱም ላይ እጅግ ተቆጣ። +4 ኤሊሁ በዕድሜ ይበልጡት ስለነበር፣ ተናግረው እስኪጨርሱ ድረስ ለኢዮብ ምንም መልስ ሳይሰጥ ሲጠብቅ ቆየ።+ +5 ኤሊሁ ሦስቱ ሰዎች መልስ መስጠት እንደተሳናቸው ባየ ጊዜ ቁጣው ነደደ። +6 በመሆኑም የቡዛዊው የባራክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፦ “እኔ በዕድሜ ትንሽ ነኝ፤*እናንተ ግን ትላልቆች ናችሁ።+ ለእናንተ ካለኝ አክብሮት የተነሳ ከመናገር ዝም አልኩ፤+ደግሞም የማውቀውን ለመናገር አልደፈርኩም። + 7 እኔም ‘ዕድሜ ይናገር፤*ረጅም ዘመንም ጥበብን ያሳውቅ’ ብዬ አስቤ ነበር። + 8 ሆኖም ለሰዎች ማስተዋል የሚሰጠው በውስጣቸው ያለው መንፈስ፣ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እስትንፋስ ነው።+ + 9 ዕድሜ* በራሱ ሰውን ጥበበኛ አያደርገውም፤ትክክለኛውን ነገር የሚያስተውሉትም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ብቻ አይደሉም።+ +10 ስለዚህ ‘እኔን ስማኝ፤እኔም የማውቀውን እነግርሃለሁ’ አልኩ። +11 እነሆ፣ እናንተ የተናገራችሁትን በትዕግሥት ሳዳምጥ ቆይቻለሁ፤የምትናገሩትን ነገር አውጥታችሁ አውርዳችሁ፣+ሐሳባችሁን በምትገልጹበት ጊዜ በትኩረት ስሰማ ነበር።+ +12 ልብ ብዬ አዳመጥኳችሁ፤ሆኖም አንዳችሁም ኢዮብ መሳሳቱን ማስረዳት፣*ወይም ላቀረበው የመከራከሪያ ሐሳብ መልስ መስጠት አልቻላችሁም። +13 ስለሆነም ‘እኛ ጥበብ ��ለን፤እሱ መሳሳቱን የሚነግረው አምላክ እንጂ ሰው አይደለም’ አትበሉ። +14 እሱ በእኔ ላይ የተናገረው ነገር የለም፤በመሆኑም እንደ እናንተ አልመልስለትም። +15 እነሱ ተሸብረዋል፤ መልስ መስጠትም ተስኗቸዋል፤የሚናገሩትም ጠፍቷቸዋል። +16 እኔ ጠበቅኳቸው፤ እነሱ ግን ንግግራቸውን መቀጠል አልቻሉም፤ከዚህ በላይ መልስ መስጠት አቅቷቸው ዝም ብለው ቆመዋል። +17 ስለዚህ እኔም መልስ እሰጣለሁ፤የማውቀውንም እናገራለሁ፤ +18 ብዙ የምናገረው ነገር አለኝና፤በውስጤ ያለው መንፈስ ገፋፍቶኛል። +19 ውስጤ መተንፈሻ እንዳጣ የወይን ጠጅ፣ሊፈነዳ እንደተቃረበ አዲስ አቁማዳ ሆኗል።+ +20 እፎይታ እንዳገኝ እስቲ ልናገር! አፌንም ከፍቼ መልስ እሰጣለሁ። +21 ለማንም ፈጽሞ አላዳላም፤+ማንንም ሰው አልሸነግልም፤* +22 ሰውን መሸንገል አላውቅበትምና፤እንደዛ ባደርግ ፈጣሪዬ ወዲያውኑ ባስወገደኝ ነበር። +7 “በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ሕይወት፣ እንደ ግዳጅ አገልግሎት አይደለም?የሕይወት ዘመኑስ እንደ ቅጥር ሠራተኛ ዘመን አይደለም?+ + 2 እንደ ባሪያ፣ ጥላ ለማግኘት ይመኛል፤እንደ ቅጥር ሠራተኛም ደሞዙን ለመቀበል በጉጉት ይጠባበቃል።+ + 3 እኔም ከንቱ የሆኑ ወራት ተመድበውልኛል፤በሥቃይ የተሞሉ ሌሊቶችም ተወስነውልኛል።+ + 4 በተኛሁ ጊዜ ‘የምነሳው መቼ ነው?’ እላለሁ።+ ሌሊቱም ሲረዝም ጎህ እስኪቀድ* ድረስ ያለእረፍት እገላበጣለሁ። + 5 ሥጋዬ ትልና የአፈር ጓል ለብሷል፤+ቆዳዬ በሙሉ አፈክፍኳል፤ ደግሞም መግል ይዟል።+ + 6 ዘመኔ ከሸማኔ መወርወሪያ ይበልጥ በፍጥነት ያልፋል፤+ያላንዳች ተስፋም ወደ ፍጻሜ ይደርሳል።+ + 7 ሕይወቴ ነፋስ እንደሆነ፣+ዓይኔም ዳግመኛ ደስታ* እንደማያይ አስታውስ። + 8 አሁን የሚያየኝ ዓይን ከእንግዲህ አያየኝም፤ዓይኖችህ እኔን ይፈልጋሉ፤ እኔ ግን አልኖርም።+ + 9 እንደሚበተንና እንደሚጠፋ ደመና፣ወደ መቃብር* የሚወርድም ተመልሶ አይወጣም።+ +10 ዳግመኛ ወደ ቤቱ አይመለስም፤ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አያውቀውም።+ +11 ስለዚህ እኔ ከመናገር ወደኋላ አልልም። ከመንፈሴ ጭንቀት የተነሳ እናገራለሁ፤በከባድ ምሬት* እሮሮ አሰማለሁ!+ +12 በእኔ ላይ ጠባቂ የምታቆመው፣እኔ ባሕር ነኝ ወይስ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት? +13 ‘መኝታዬ ያጽናናኛል፣አልጋዬ ሥቃዬን ያቀልልኛል’ ባልኩ ጊዜ፣ +14 አንተ በሕልም ታሸብረኛለህ፤በራእይም ታስፈራራኛለህ፤ +15 ስለዚህ እኔ* መታፈንን፣አዎ፣ ከሰውነቴም* ይልቅ ሞትን መረጥኩ።+ +16 ሕይወቴን ተጸየፍኳት፤+ በሕይወት መቀጠል አልፈልግም። ዘመኔ እንደ እስትንፋስ+ ስለሆነ ተወት አድርገኝ። +17 ታስበው ዘንድ፣ትኩረት ትሰጠውም* ዘንድ ሟች የሆነ ሰው ምንድን ነው?+ +18 በየማለዳው የምትመረምረው፣በየጊዜውም የምትፈትነው ለምንድን ነው?+ +19 ዓይንህን ከእኔ ላይ አታነሳም?ምራቄን እስክውጥስ ድረስ ፋታ አትሰጠኝም?*+ +20 የሰውን ልጅ የምትከታተል ሆይ፣+ ኃጢአት ብሠራ እንኳ አንተን እንዴት ልጎዳህ እችላለሁ? ዒላማህ ያደረግከኝ ለምንድን ነው? ሸክም ሆኜብሃለሁ? +21 መተላለፌን ይቅር የማትለው፣በደሌንም በምሕረት የማታልፈው ለምንድን ነው? ከጥቂት ጊዜ በኋላ አፈር ውስጥ እጋደማለሁና፤+አንተም ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን አልገኝም።” +12 ከዚያም ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “በእርግጥ አዋቂዎች እናንተ ናችኋ!*ጥበብም ከእናንተ ጋር ትሞታለቻ! + 3 እኔም እኮ ማስተዋል* አለኝ። ከእናንተ አላንስም። እነዚህን ነገሮች የማያውቅ ማን ነው? + 4 ወደ አምላክ ተጣርቼ መልስ የምጠብቅ፣+የባልንጀሮቼ መሳለቂያ ሆኛለሁ።+ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት ሰው፣ የሰዎች መሳለቂያ ነው። + 5 የደላው ሰው ‘መከራ የሚደርሰውእግ���ቸው በሚብረከረክ* ሰዎች ላይ ብቻ ነው’ ብሎ በማሰብ መከራን ይንቃል። + 6 የዘራፊዎች ድንኳን ሰላም አለው፤+አምላክን የሚያስቆጡ ሰዎችም፣አምላካቸውን* በእጃቸው እንደያዙ ሰዎች የደህንነት ስሜት ይሰማቸዋል።+ + 7 ይሁን እንጂ እስቲ እንስሳትን ጠይቅ፤ እነሱም ያስተምሩሃል፤በሰማያት የሚበርሩ ወፎችንም ጠይቅ፤ እነሱም ይነግሩሃል። + 8 ወይም በምድር ላይ ትኩረትህን አድርግ፤* እሷም ታስተምርሃለች፤የባሕር ዓሣም ያሳውቅሃል። + 9 የይሖዋ እጅ ይህን ማድረጉን፣ከእነዚህ ሁሉ መካከል የማያውቅ ማን ነው? +10 የሕያው ነገር ሁሉ ሕይወት፣*የሰውም ሁሉ መንፈስ* በእሱ እጅ ነው።+ +11 ምላስ* የምግብን ጣዕም እንደሚለይ ሁሉ፣ጆሮስ ቃላትን አያመዛዝንም?+ +12 በዕድሜ በገፉት መካከል ጥበብ፣ከረጅም ዕድሜስ ጋር ማስተዋል አይገኝም?+ +13 በእሱ ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ፤+ምክርና ማስተዋልም አለው።+ +14 እሱ ያፈረሰውን ነገር መልሶ መገንባት አይቻልም፤+እሱ የዘጋውን ማንም ሰው ሊከፍት አይችልም። +15 ውኃዎችን ሲከለክል ሁሉም ነገር ይደርቃል፤+ሲልካቸውም ምድርን ያጥለቀልቃሉ።+ +16 ብርታትና ጥበብ* በእሱ ዘንድ ናቸው፤+መንገድ የሚስተውም ሆነ የሚያስተው የእሱ ናቸው፤ +17 አማካሪዎችን ባዶ እግራቸውን ያስኬዳቸዋል፤*ፈራጆችንም ያሞኛቸዋል።+ +18 ነገሥታት ያሰሩትን ይፈታል፤+በወገባቸውም ዙሪያ መታጠቂያ ያስራል። +19 ካህናትን ባዶ እግራቸውን ያስኬዳቸዋል፤+በሥልጣን ላይ ተደላድለው የተቀመጡትንም ይገለብጣል፤+ +20 የታመኑ አማካሪዎችን የሚሉትን ነገር ያሳጣቸዋል፤ሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይነሳል፤ +21 በታላላቅ ሰዎች ላይ የውርደት መዓት ያዘንባል፤+ብርቱዎችንም ደካማ ያደርጋል፤* +22 ጥልቅ የሆኑ ነገሮችን ከጨለማ ውስጥ ይገልጣል፤+በድቅድቅ ጨለማ ላይ ብርሃን ይፈነጥቃል፤ +23 ያጠፋቸው ዘንድ ብሔራትን ታላቅ ያደርጋል፤ወደ ግዞት ይወስዳቸውም ዘንድ ብሔራትን እንዲስፋፉ ያደርጋቸዋል። +24 የሕዝቡን መሪዎች ማስተዋል* ይነሳል፤መንገድ በሌለበት ጠፍ መሬትም እንዲቅበዘበዙ ያደርጋል።+ +25 ብርሃን በሌለበት ጨለማ፣ በዳበሳ ይሄዳሉ፤+እንደሰከሩ ሰዎች እንዲዳክሩ ያደርጋቸዋል።+ +1 በዖጽ ምድር የሚኖር ኢዮብ*+ የሚባል ሰው ነበር። እሱም በንጹሕ አቋም የሚመላለስ ቅን ሰው*+ እንዲሁም አምላክን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ነበር።+ +2 ኢዮብ ሰባት ወንዶች ልጆችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት። +"3 የከብቶቹም ብዛት 7,000 በጎች፣ 3,000 ግመሎች፣ 1,000 ከብቶች፣* 500 አህዮች* ነበር፤ በተጨማሪም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ስለነበሩት በምሥራቅ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ሰው ሆነ። " +4 ወንዶች ልጆቹ ሁሉ በተመደበላቸው ተራ መሠረት በየቤታቸው* ግብዣ ያደርጉ ነበር። እነሱም ሦስቱ እህቶቻቸው አብረዋቸው እንዲበሉና እንዲጠጡ ይጋብዟቸው ነበር። +5 ሁሉም ተራው ደርሷቸው የግብዣዎቹ ቀናት ከተጠናቀቁ በኋላ ኢዮብ ልጆቹ ይቀደሱ ዘንድ መልእክት ይልክባቸው ነበር። ከዚያም “ልጆቼ ኃጢአት ሠርተውና አምላክን በልባቸው ረግመው ይሆናል” ብሎ በማሰብ በማለዳ ተነስቶ ለእያንዳንዳቸው የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።+ ኢዮብ ሁልጊዜ እንዲህ የማድረግ ልማድ ነ +6 የእውነተኛው አምላክ ልጆች*+ በይሖዋ ፊት ለመቆም+ የሚገቡበት ቀን በደረሰ ጊዜ ሰይጣንም+ መጥቶ በመካከላቸው ቆመ።+ +7 ከዚያም ይሖዋ ሰይጣንን “ከየት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም “በምድር ሁሉ ላይ ስዞርና በእሷ ላይ ስመላለስ ቆይቼ መጣሁ”+ ሲል ለይሖዋ መለሰ። +8 ይሖዋም ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትከው?* በምድር ላይ እንደ እሱ ያለ ሰው የለም። በንጹሕ አቋም* የሚመላለስ ቅን ሰው+ እንዲሁም አ���ላክን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ነው።” +9 ሰይጣንም ለይሖዋ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ኢዮብ አምላክን የሚፈራው እንዲያው በከንቱ ነው?+ +10 እሱን፣ ቤቱንና ያለውን ነገር ሁሉ በአጥር ከልለህ የለም?+ የእጁን ሥራ ባርከህለታል፤+ ከብቱም በምድሪቱ ላይ በዝቷል። +11 ሆኖም እስቲ እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ አጥፋ፤ በእርግጥ ፊት ለፊት ይረግምሃል።” +12 ከዚያም ይሖዋ ሰይጣንን “እነሆ፣ ያለው ነገር ሁሉ በእጅህ* ነው። እሱን ራሱን ግን እንዳትነካው!” አለው። ሰይጣንም ከይሖዋ ፊት ወጥቶ ሄደ።+ +13 የኢዮብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በታላቅ ወንድማቸው ቤት እየበሉና የወይን ጠጅ እየጠጡ በነበረበት ቀን፣+ +14 አንድ መልእክተኛ ወደ ኢዮብ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ከብቶቹ እያረሱ፣ አህዮቹም በአጠገባቸው እየጋጡ ሳለ +15 ሳባውያን ጥቃት ሰንዝረው ወሰዷቸው፤ አገልጋዮቹንም በሰይፍ ገደሉ። እኔም ብቻዬን አምልጬ ልነግርህ መጣሁ።” +16 እሱ ገና እየተናገረ ሳለ ሌላው መጥቶ እንዲህ አለ፦ “ከአምላክ ዘንድ ከሰማያት እሳት ወረደች፤* በበጎቹና በአገልጋዮቹ መካከልም ነድዳ በላቻቸው! እኔም ብቻዬን አምልጬ ልነግርህ መጣሁ።” +17 እሱ ገና እየተናገረ ሳለ ሌላው መጥቶ እንዲህ አለ፦ “ከለዳውያን+ በሦስት ቡድን መጥተው በድንገት ጥቃት በመሰንዘር ግመሎቹን ወሰዱ፤ አገልጋዮቹንም በሰይፍ ገደሉ። እኔም ብቻዬን አምልጬ ልነግርህ መጣሁ።” +18 እሱ ገና እየተናገረ ሳለ ሌላው ደግሞ መጥቶ እንዲህ አለ፦ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት እየበሉና የወይን ጠጅ እየጠጡ ነበር። +19 በድንገት ከምድረ በዳው ኃይለኛ ነፋስ መጥቶ የቤቱን አራት ማዕዘናት መታ፤ ቤቱም በልጆችህ ላይ ወድቆ ገደላቸው። እኔም ብቻዬን አምልጬ ልነግርህ መጣሁ።” +20 በዚህ ጊዜ ኢዮብ ተነስቶ ልብሱን ቀደደ፤ ፀጉሩንም ተላጨ፤ ከዚያም መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ፤ +21 እንዲህም አለ፦ “ከእናቴ ማህፀን ራቁቴን ወጣሁ፤ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ።+ ይሖዋ ሰጠ፤+ ይሖዋ ነሳ። የይሖዋ ስም ምንጊዜም ይወደስ።” +22 ኢዮብ ይህ ሁሉ ቢደርስበትም ኃጢአት አልሠራም ወይም አምላክን በደል ሠርቷል ብሎ አልወነጀለም።* +36 ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፦ + 2 “አምላክን ወክዬ ገና የምናገረው ነገር ስላለጉዳዩን በማብራራበት ጊዜ ትንሽ ታገሠኝ። + 3 ስለማውቀው ነገር በሰፊው እናገራለሁ፤ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደሆነም አስታውቃለሁ።+ + 4 በእርግጥ የምናገረው ቃል ውሸት አይደለም፤እውቀቱ ፍጹም የሆነው አምላክ+ በፊትህ ነው። + 5 በእርግጥ አምላክ ኃያል ነው፤+ ደግሞም ማንንም ገሸሽ አያደርግም፤የማስተዋል ችሎታው* ታላቅ ነው። + 6 የክፉዎችን ሕይወት አይጠብቅም፤+ጎስቋላው ግን ፍትሕ እንዲያገኝ ያደርጋል።+ + 7 ዓይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሳም፤+ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤*+ እነሱም ለዘላለም ከፍ ከፍ ይላሉ። + 8 ይሁንና ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣ + 9 ከመታበያቸው የተነሳ ስለፈጸሙት ድርጊትይኸውም ስለ በደላቸው ይነግራቸዋል። +10 እርማት እንዲቀበሉ ጆሯቸውን ይከፍታል፤ከክፋትም እንዲመለሱ ይነግራቸዋል።+ +11 ቢታዘዙትና ቢያገለግሉት፣የሕይወት ዘመናቸውን በብልጽግና ይፈጽማሉ፤ሕይወታቸውም አስደሳች ይሆናል።+ +12 ባይታዘዙ ግን በሰይፍ* ይጠፋሉ፤+ያለእውቀትም ይሞታሉ። +13 በልባቸው አምላክ የለሽ* የሆኑ ቂም ይይዛሉ። እሱ በሚያስራቸው ጊዜም እንኳ እርዳታ ለማግኘት አይጮኹም። +14 ገና ወጣት እያሉ ይሞታሉ፤*+በቤተ መቅደስ ቀላጮች* መካከል ሕይወታቸውን ያሳልፋሉ።*+ +15 ሆኖም አምላክ* የተጎሳቆሉ ሰዎችን ከጉስቁልናቸው ይታደጋቸዋል፤ጭቆና በሚደርስባቸው ጊ��� ጆሯቸውን ይከፍታል። +16 እሱ ከመከራ መንጋጋ አስጥሎ+የሚያጨናንቅ ነገር ወደሌለበት ሰፊ ስፍራ ያመጣሃል፤+ማዕድህ ምርጥ በሆነ ምግብ የተሞላ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ ያጽናናሃል።+ +17 ፍርድ ሲበየንና ፍትሕ ሲሰፍን፣በክፉዎች ላይ በሚፈጸመው ፍርድ ትረካለህ።+ +18 ይሁንና ቁጣ ወደ ክፋት* እንዳይመራህ ተጠንቀቅ፤+ጠቀም ያለ ጉቦም አያስትህ። +19 እርዳታ ለማግኘት መጮኽህ፣ወይም የምታደርገው ማንኛውም ብርቱ ጥረት ከጭንቀት ነፃ ያደርግሃል?+ +20 ሰዎች ካሉበት ስፍራ የሚጠፉበትንየሌሊቱን ጊዜ አትናፍቅ። +21 ከጉስቁልና ይልቅ ይህን መርጠህ፣+ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ። +22 እነሆ፣ አምላክ በኃይሉ ከፍ ከፍ ብሏል፤እንደ እሱ ያለ አስተማሪ ማን ነው? +23 እሱን መንገድ የመራው፣*ወይም ‘የሠራኸው ነገር ትክክል አይደለም’ ያለው ማን ነው?+ +24 ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣+የእሱን ሥራ ከፍ ከፍ ማድረግ አትዘንጋ።+ +25 የሰው ልጆች ሁሉ አይተውታል፤ሟች የሆነ ሰው ከሩቅ ያያል። +26 አዎ፣ አምላክ እኛ ልናውቀው ከምንችለው በላይ ታላቅ ነው፤+የዘመኑም ቁጥር ከመረዳት ችሎታ በላይ ነው።*+ +27 እሱ የውኃ ጠብታዎችን ወደ ላይ ይስባል፤+ጭጋጉም ወደ ዝናብነት ይለወጣል፤ +28 ከዚያም ደመናት ያዘንባሉ፤+በሰው ልጆችም ላይ ዶፍ ያወርዳሉ። +29 የደመናትን ንብርብር፣ከድንኳኑም የሚሰማውን ነጎድጓድ+ ማን ሊያስተውል ይችላል? +30 መብረቁን*+ በላዩ ላይ እንዴት እንደሚዘረጋ፣የባሕሩንም ወለል* እንዴት እንደሚሸፍን ተመልከት። +31 በእነዚህም ሕዝቦችን ያኖራል፤*ምግብ አትረፍርፎ ይሰጣቸዋል።+ +32 በእጆቹ መብረቁን ይሸፍናል፤ወደ ዒላማውም ይሰደዋል።+ +33 ነጎድጓዱ ስለ እሱ ይናገራል፤ከብቶች እንኳ ሳይቀሩ ማን* እየመጣ እንዳለ ይጠቁማሉ። +29 ኢዮብ ንግግሩን* በመቀጠል እንዲህ አለ፦ + 2 “የቀድሞዎቹን ወራት፣አምላክ ለእኔ ጥበቃ ያደርግ የነበረበትን ዘመን ተመኘሁ! + 3 ያን ጊዜ መብራቱን በራሴ ላይ ያበራ፣በእሱም ብርሃን፣ በጨለማ ውስጥ እሄድ ነበር፤+ + 4 ያኔ የወጣትነት ብርታት ነበረኝ፤አምላክ የቅርብ ወዳጄ ሆኖ በድንኳኔ ይገኝ ነበር፤+ + 5 ሁሉን ቻይ አምላክ ከእኔ ጋር ነበር፤ልጆቼም* በዙሪያዬ ነበሩ፤ + 6 መንገዴ በቅቤ የራሰ ነበር፤ዓለቱም ዘይት ያንዶለዱልልኝ ነበር።+ + 7 ወደ ከተማዋ በር እሄድ፣+በአደባባይዋም እቀመጥ ነበር፤+ + 8 ወጣቶች ሲያዩኝ መንገድ ይለቁልኝ፣*ሽማግሌዎችም እንኳ ተነስተው ይቆሙ ነበር።+ + 9 መኳንንት ከመናገር ይቆጠቡ፣እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር። +10 የታላላቆቹ ሰዎች ድምፅ አይሰማም ነበር፤ምላሳቸውም ከላንቃቸው ጋር ይጣበቅ ነበር። +11 ስናገር የሰማ ሁሉ ያሞግሰኝ፣ያዩኝ ሰዎችም ይመሠክሩልኝ ነበር። +12 ለእርዳታ የሚጮኸውን ድሃ፣አባት የሌለውን ልጅና ረዳት የሌለውን ሁሉ እታደግ ነበርና።+ +13 ሊጠፋ ተቃርቦ የነበረው ይባርከኝ ነበር፤+የመበለቲቱንም ልብ ደስ አሰኝ ነበር።+ +14 ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስኩ፤የፍትሕ አቋሜ እንደ ቀሚስና* እንደ ጥምጥም ሆነልኝ። +15 ለዓይነ ስውሩ ዓይን፣ለአንካሳውም እግር ነበርኩ። +16 ለድሃው አባት ነበርኩ፤+የማላውቃቸውን ሰዎች ሙግት እመረምር ነበር።+ +17 የክፉ አድራጊውን መንጋጋ እሰብር፣+አድኖ የያዘውንም ከጥርሱ አስጥል ነበር። +18 እንዲህ እል ነበር፦ ‘በገዛ ቤቴ* እሞታለሁ፤+የሕይወት ዘመኔም እንደ አሸዋ ይበዛል። +19 ሥሮቼ ወደ ውኃ ይዘረጋሉ፤ጠልም ሌሊቱን ሙሉ በቅርንጫፎቼ ላይ ያድራል። +20 ክብሬ ሁልጊዜ ይታደሳል፤በእጄም ያለው ደጋን ደጋግሞ ይወነጭፋል።’ +21 ሰዎች በጉጉት ያዳምጡኝ፣ምክሬንም ጸጥ ብለው ይጠባበቁ ነበር።+ +22 እኔ ከተናገርኩ በኋላ የሚጨምሩት ነ��ር አልነበረም፤ቃሌም በጆሯቸው ይንቆረቆር* ነበር። +23 ዝናብ እንደሚጠባበቁ ሰዎች እኔን ተጠባበቁ፤ቃሌንም እንደ በልግ ዝናብ+ ጠጡ። +24 በፈገግታ ባየኋቸው ጊዜ ማመን አቃታቸው፤የፊቴ ብርሃን ያጽናናቸው ነበር።* +25 እንደ መሪያቸው ሆኜ አመራር ሰጠኋቸው፤በወታደሮቹ መካከል እንዳለ ንጉሥ፣+ሐዘንተኞችንም እንደሚያጽናና ሰው ሆኜ ኖርኩ።+ +28 “ብር የሚወጣበት ቦታ፣ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ፤+ + 2 ብረት ከመሬት ውስጥ ይገኛል፤መዳብም ከዓለት ቀልጦ ይወጣል።*+ + 3 ሰው ጨለማን ያሸንፋል፤ማዕድን* ለማግኘትበጨለማና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እስከ ወሰኑ ድረስ ፍለጋ ያካሂዳል። + 4 ሰዎች ከሚኖሩበት ክልል ርቆ በሚገኝ ስፍራ፣ሰዎች ከሚመላለሱበት አካባቢ ርቀው በሚገኙ የተረሱ ቦታዎች ጥልቅ ጉድጓድ ይቆፍራል፤አንዳንድ ሰዎች በገመድ ወደዚያ ይወርዳሉ፤ ተንጠልጥለውም ይሠራሉ። + 5 በምድር ላይ እህል ይበቅላል፤ከታች ግን ምድር በእሳት የሆነ ያህል ትታመሳለች።* + 6 በዚያ በድንጋዮቹ ውስጥ ሰንፔር ይገኛል፤በአፈሩም ውስጥ ወርቅ አለ። + 7 ወደዚያ የሚወስደውን መንገድ የትኛውም አዳኝ አሞራ አያውቀውም፤የጥቁር ጭልፊትም ዓይን አላየውም። + 8 ግርማ የተላበሱ አራዊት አልረገጡትም፤ብርቱ አንበሳም በዚያ አላደባም። + 9 ሰው የባልጩት ድንጋይ በእጁ ይመታል፤ተራሮችንም ከሥር መሠረታቸው ይገለብጣል። +10 በዓለት ውስጥ የውኃ ቦዮች ይሠራል፤+ዓይኑም ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ያያል። +11 ወንዞች የሚፈልቁባቸውን ቦታዎች ይገድባል፤የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል። +12 ይሁንና ጥበብ የት ልትገኝ ትችላለች?+ማስተዋል የሚገኘውስ ከየት ነው?+ +13 ማንም ሰው ዋጋዋን አይገነዘብም፤+በሕያዋንም ምድር ልትገኝ አትችልም። +14 ጥልቁ ውኃ ‘እኔ ውስጥ የለችም!’ ይላል፤ ባሕሩም ‘በእኔ ዘንድ አይደለችም!’ ይላል።+ +15 እሷን በንጹሕ ወርቅ መግዛት አይቻልም፤በብርም ልትለወጥ አትችልም።+ +16 በኦፊር ወርቅም+ ሆነብርቅ በሆነው ኦኒክስና በሰንፔር ልትገዛ አትችልም። +17 ወርቅና መስተዋት* ከእሷ ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም፤ምርጥ ከሆነ* ወርቅ በተሠራ ዕቃም እሷን መለወጥ አይቻልም።+ +18 ዛጎልና ክሪስታል ጨርሶ አይወዳደሯትም፤+ጥበብ በከረጢት ሙሉ ካለ ዕንቁ ትበልጣለችና። +19 የኢትዮጵያ* ቶጳዝዮን+ ከእሷ ጋር ሊወዳደር አይችልም፤በንጹሕ ወርቅ እንኳ እሷን መግዛት አይቻልም። +20 ታዲያ ጥበብ ከየት ትመጣለች?ማስተዋል የሚገኘውስ ከየት ነው?+ +21 ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ዓይን ተሰውራለች፤+በሰማያት ከሚበርሩ ወፎችም ተሸሽጋለች። +22 ጥፋትና ሞት፣‘ወሬዋን ብቻ በጆሯችን ሰምተናል’ ይላሉ። +23 ወደ እሷ የሚወስደውን መንገድ የሚረዳው አምላክ ነው፤መኖሪያዋን የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው፤+ +24 እሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይመለከታልና፤ከሰማያትም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።+ +25 የነፋስን ኃይል* በወሰነ ጊዜ፣+ውኃዎችንም በለካ ጊዜ፣+ +26 ለዝናብ ሥርዓትን ባወጣ ጊዜ፣+ነጎድጓድ ለቀላቀለ ጥቁር ደመና መንገድን ባዘጋጀ ጊዜ፣+ +27 ያኔ ጥበብን አያት፤ ደግሞም ገለጻት፤መሠረታት፤ እንዲሁም መረመራት። +28 ሰውንም እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ ይሖዋን መፍራት ጥበብ ነው፤+ከክፉም መራቅ ማስተዋል ነው።’”+ +38 ከዚያም ይሖዋ ከአውሎ ነፋስ ውስጥ ለኢዮብ መለሰለት፦+ + 2 “ሐሳቤን የሚሰውርናያለእውቀት የሚናገር ይህ ማን ነው?+ + 3 እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም ንገረኝ። + 4 ምድርን በመሠረትኩ ጊዜ አንተ የት ነበርክ?+ ማስተዋል አለኝ የምትል ከሆነ ንገረኝ። + 5 የምታውቅ ከሆነ፣ መለኪያዎቿን የወሰነ፣ወይስ መለኪያ ገመድ በላይዋ ላይ የዘ���ጋ ማን ነው? + 6 የምድር ምሰሶዎች የተተከሉት ምን ላይ ነው?የማዕዘኗን ድንጋይ ያኖረስ ማን ነው?+ + 7 አጥቢያ ከዋክብት+ በአንድነት እልል ሲሉ፣የአምላክም ልጆች ሁሉ*+ በደስታ ሲጮኹ አንተ የት ነበርክ? + 8 ባሕሩ ከማህፀን አፈትልኮ በወጣ ጊዜ፣በር የዘጋበት ማን ነው?+ + 9 ደመና ባለበስኩት ጊዜ፣በድቅድቅ ጨለማም በጠቀለልኩት ጊዜ፣ +10 በላዩም ድንበሬን በወሰንኩ ጊዜ፣መቀርቀሪያዎችና በሮች ባደረግኩለት ጊዜ፣+ +11 ደግሞም ‘እስከዚህ ድረስ መምጣት ትችላለህ፤ ከዚህ ግን አታልፍም፤የኩሩው ማዕበልህም ገደብ ይህ ነው’ ባልኩ ጊዜ+ አንተ የት ነበርክ? +12 ለመሆኑ ንጋትን አዘህ ታውቃለህ?ወይስ ጎህ ስፍራውን እንዲያውቅ አድርገሃል?+ +13 የማለዳ ብርሃን ወደ ምድር ዳርቻዎች እንዲሄድ፣ክፉዎችንም ከላይዋ እንዲያራግፍ ያዘዝከው አንተ ነህ?+ +14 ምድር ከማኅተም በታች እንዳለ የሸክላ ጭቃ ትለወጣለች፤ገጽታዎቿም እንደሚያምር ልብስ ጎልተው ይታያሉ። +15 የክፉዎች ብርሃን ግን ከእነሱ ተወስዷል፤ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሯል። +16 ወደ ባሕሩ ምንጮች ወርደሃል?ወይስ ጥልቁን ውኃ መርምረሃል?+ +17 የሞት በሮች+ ተገልጠውልሃል?የድቅድቅ ጨለማንስ* በሮች አይተሃል?+ +18 ምድር ምን ያህል ሰፊ እንደሆነች አስተውለሃል?+ ይህን ሁሉ የምታውቅ ከሆነ ተናገር። +19 ብርሃን የሚኖረው በየት አቅጣጫ ነው?+ የጨለማ ስፍራስ የት ነው? +20 ወደ ክልሉ ልትወስደው ትችላለህ?ወደ ቤቱስ የሚወስደውን ጎዳና ታውቃለህ? +21 በዚያን ጊዜ ተወልደህ ስለነበር፣ዕድሜህም ትልቅ ስለሆነ* ይህን ሳታውቅ አትቀርም! +22 አመዳዩ ወደተከማቸበት መጋዘን ገብተሃል?+የበረዶውንስ ግምጃ ቤት አይተሃል?+ +23 ይህም ለመከራ ጊዜ፣ለውጊያና ለጦርነት ቀን ያስቀመጥኩት ነው።+ +24 ብርሃን* የሚሰራጨው ከየት አቅጣጫ ነው?የምሥራቅስ ነፋስ በምድር ላይ የሚነፍሰው ከየት ነው?+ +25 ለዶፍ መውረጃን፣ነጎድጓድ ለቀላቀለ ጥቁር ደመናም መንገድን ያዘጋጀ ማን ነው?+ +26 አንድም ሰው በሌለበት ቦታ፣ሰውም በማይኖርበት ምድረ በዳ የሚያዘንበው፣+ +27 የወደመውን ጠፍ መሬት የሚያረካው፣ሣርንም የሚያበቅለው ማን ነው?+ +28 ዝናብ አባት አለው?+ጠልንስ የወለደው ማን ነው?+ +29 በረዶ የሚወጣው ከማን ማህፀን ነው?የሰማዩንስ አመዳይ የወለደው ማን ነው?+ +30 ውኃዎች በድንጋይ የተሸፈኑ ያህል እንዲሆኑ፣የጥልቁ ውኃም ገጽ ግግር በረዶ እንዲሆን የሚያደርገው ማን ነው?+ +31 የኪማ ኅብረ ከዋክብትን* ገመድ ልታስር፣ወይስ የከሲል ኅብረ ከዋክብትን* ገመድ ልትፈታ ትችላለህ?+ +32 ኅብረ ከዋክብትን* በወቅቱ ልታወጣ፣ወይስ የአሽ ኅብረ ከዋክብትን* ከነልጆቹ ልትመራ ትችላለህ? +33 ሰማያት የሚመሩባቸውን ሕጎች ታውቃለህ?+ወይስ የሰማያትን* ሕጎች በምድር ላይ ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ? +34 ጎርፍ ይሸፍንህ ዘንድ፣ድምፅህን ወደ ደመናት ማንሳት ትችላለህ?+ +35 የመብረቅ ብልጭታዎችን መላክ ትችላለህ? እነሱስ አንተ ጋ ቀርበው ‘ይኸው መጥተናል!’ ይሉሃል? +36 በደመናት ውስጥ* ጥበብ ያኖረው፣+በሰማይ ለሚከናወነውስ ክስተት* ማስተዋልን የሰጠው ማን ነው?+ +37 ደመናትን ለመቁጠር የሚያስችል ጥበብ ያለው ማን ነው?ወይስ የሰማይን የውኃ ማሰሮዎች ሊደፋ የሚችል ማን ነው?+ +38 አፈሩ ቦክቶ እንዲጋገር፣የምድር ጓሎችም እንዲጣበቁ ሊያደርግ የሚችል ማን ነው? +39 ለአንበሳ አድነህ ግዳይ ልታመጣለት፣ወይስ የተራቡ የአንበሳ ግልገሎችን ልታጠግብ ትችላለህ?+ +40 እነሱ በዋሻቸው ውስጥ አድፍጠው፣ወይም በጎሬአቸው አድብተው ሳለ ይህን ልታደርግ ትችላለህ? +41 ጫጩቶቿ ወደ አምላክ ሲጮኹ፣የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ፣ለቁራ መብል የሚያዘጋጅ ማን ነው?+ +8 ከዚያም ሹሃ��ው+ በልዳዶስ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “እንዲህ የምትናገረው እስከ መቼ ነው?+ ከአፍህ የሚወጣው ቃል ብርቱ ነፋስ ነው! + 3 አምላክ ፍትሕን ያዛባል?ወይስ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ጽድቅን ያጣምማል? + 4 ልጆችህ በእሱ ላይ ኃጢአት ሠርተው ከሆነ፣ለፈጸሙት ዓመፅ እንዲቀጡ አድርጓል፤* + 5 አንተ ግን ወደ አምላክ ዞር ብትል፣+ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሞገስ እንዲያሳይህ ብትማጸን፣ + 6 በእርግጥ ንጹሕና ቅን ብትሆን፣+እሱ ትኩረት ይሰጥሃል፤*ወደ ትክክለኛ ቦታህም ይመልስሃል። + 7 ጅማሬህ አነስተኛ ቢሆንም፣የወደፊት ሕይወትህ ታላቅ ይሆናል።+ + 8 እስቲ የቀድሞውን ትውልድ ጠይቅ፤አባቶቻቸው ለተገነዘቧቸው ነገሮችም ትኩረት ስጥ።+ + 9 እኛ የተወለድነው ገና ትናንት ስለሆነ የምናውቀው ነገር የለም፤ምክንያቱም በምድር ላይ ዘመናችን እንደ ጥላ ነው። +10 እነሱ አያስተምሩህም?ደግሞስ የሚያውቁትን ነገር* አይነግሩህም? +11 ደንገል ረግረጋማ ባልሆነ ስፍራ ያድጋል? ሸምበቆስ ውኃ በሌለበት ቦታ ያድጋል? +12 ገና ሳያብብና ሳይቆረጥ፣ከሌላው ተክል ሁሉ በፊት ይደርቃል። +13 አምላክን የሚረሱ ሰዎች ሁሉ መጨረሻቸው እንደዚህ ነው፤*አምላክ የለሽ የሆነ* ሰው ተስፋ ይጨልማልና፤ +14 የሚመካበት ነገር ከንቱ ነው፤የሚታመንበትም ነገር ከሸረሪት ድር* የማይሻል ነው። +15 እሱ ቤቱን ይደገፈዋል፤ ሆኖም ቤቱ ጸንቶ አይቆምም፤አጥብቆ ሊይዘው ይሞክራል፤ ሆኖም አይጸናም። +16 እሱ በፀሐይ ብርሃን እንደሚያድግ እርጥበት ያለው ተክል ነው፤ቅርንጫፎቹም በአትክልት ስፍራው ውስጥ ይንሰራፋሉ።+ +17 ሥሩም በድንጋይ ክምር ውስጥ ይጠላለፋል፤በድንጋዮቹ መካከል ቤት ይፈልጋል።* +18 ሆኖም ከስፍራው በሚነቀልበት* ጊዜ፣ያ ስፍራ ‘ፈጽሞ አይቼህ አላውቅም’ ብሎ ይክደዋል።+ +19 አዎ፣ በዚህ ሁኔታ ይጠፋል፤*+ከዚያም ሌሎች ከአፈሩ ውስጥ ይበቅላሉ። +20 በእርግጥም አምላክ ንጹሕ አቋማቸውን* የሚጠብቁትን አይጥልም፤ክፉ ሰዎችንም አይረዳም፤* +21 በመጨረሻም አፍህን በሳቅ፣ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላል። +22 የሚጠሉህ ኀፍረት ይከናነባሉ፤የክፉዎችም ድንኳን ይጠፋል።” +11 ናአማታዊው ሶፋር+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “ይህ ሁሉ ቃል መልስ ሳይሰጠው ሊታለፍ ይገባል?ወይስ ብዙ ማውራት አንድን ሰው ትክክለኛ ያደርገዋል?* + 3 ከንቱ ንግግርህ ሰዎችን ዝም ያሰኛል? ስታፌዝስ የሚገሥጽህ የለም?+ + 4 ‘ትምህርቴ የጠራ ነው፤+በፊትህም ንጹሕ ነኝ’ ትላለህና።+ + 5 ምነው አምላክ በተናገረህ!ከንፈሩንም በአንተ ላይ በከፈተ!+ + 6 በዚያን ጊዜ የጥበብን ሚስጥር ይገልጥልሃል፤ጥበብ* ፈርጀ ብዙ ናትና። ያን ጊዜ፣ የሠራሃቸውን አንዳንድ በደሎች አምላክ እንደረሳልህ ትገነዘባለህ። + 7 የአምላክን ጥልቅ ነገሮች መርምረህ ልትደርስባቸው ትችላለህ?ወይስ ሁሉን ቻይ ስለሆነው አምላክ ሁሉንም ነገር መርምረህ ልትደርስበት* ትችላለህ? + 8 ጥበብ ከሰማይ ይልቅ ከፍ ትላለች። አንተ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከመቃብርም* ይልቅ ጥልቅ ነች። አንተ ምን ልታውቅ ትችላለህ? + 9 ከምድር ይልቅ ትረዝማለች፤ከባሕርም ይልቅ ትሰፋለች። +10 እሱ በሚያልፍበት ጊዜ አንድን ሰው ይዞ ለፍርድ ካቀረበ፣ማን ሊቃወመው ይችላል? +11 አታላይ ሰዎችን ያውቃልና። እሱ ክፉ ነገር ሲያይ ትኩረት አይሰጥም? +12 የዱር አህያ ሰው መውለድ ቢችል፣*ያን ጊዜ አእምሮ የሌለው ሰው ማስተዋል ያገኛል። +13 ምነው ልብህን ብታዘጋጅ፣እጆችህንም ወደ እሱ ብትዘረጋ! +14 እጅህ መጥፎ ነገር የሚሠራ ከሆነ አርቀው፤በድንኳኖችህም ውስጥ ክፋት አይኑር። +15 በዚያን ጊዜ ያለኀፍረት ፊትህን ቀና ታደርጋለህ፤ምንም ሳትፈራ ጸንተህ ትቆማለህ። +16 ያን ጊዜ ችግር���ን ትረሳለህና፤አልፎህ እንደሄደ ውኃ አድርገህ ታስበዋለህ። +17 ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ብሩህ ይሆናል፤ጨለማውም እንኳ እንደ ንጋት ይሆናል። +18 ተስፋ ስላለ ልበ ሙሉ ትሆናለህ፤ዙሪያህንም ትመለከታለህ፤ ያለስጋትም ትተኛለህ። +19 የሚያስፈራህ ሳይኖር ትተኛለህ፤ብዙ ሰዎችም የአንተን ሞገስ ለማግኘት ይሻሉ። +20 የክፉዎች ዓይን ግን ይደክማል፤የሚሸሹበት ቦታም አያገኙም፤ያላቸው ብቸኛ ተስፋ ሞት* ነው።”+ +2 የእውነተኛው አምላክ ልጆች፣*+ በይሖዋ ፊት ለመቆም+ የሚገቡበት ቀን በደረሰ ጊዜ ሰይጣንም በይሖዋ ፊት ለመቆም እነሱ መካከል ገባ።+ +2 ከዚያም ይሖዋ ሰይጣንን “ከየት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም “በምድር ሁሉ ላይ ስዞርና በእሷ ላይ ስመላለስ ቆይቼ መጣሁ”+ ሲል ለይሖዋ መለሰ። +3 ይሖዋም ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትከው?* በምድር ላይ እንደ እሱ ያለ ሰው የለም። በንጹሕ አቋም የሚመላለስ ቅን ሰው*+ እንዲሁም አምላክን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ነው። ያለምንም ምክንያት እንዳጠፋው* እኔን ለማነሳሳት ብትሞክርም+ እንኳ አሁንም በንጹሕ አቋሙ እንደጸና ነው። +4 ሆኖም ሰይጣን እንዲህ ሲል ለይሖዋ መለሰ፦ “ቁርበት ስለ ቁርበት ነው። ሰውም ለሕይወቱ* ሲል ያለውን ነገር ሁሉ ይሰጣል። +5 ሆኖም እስቲ እጅህን ዘርግተህ በአጥንቱና በሥጋው ላይ ጉዳት አድርስበት፤ በእርግጥ ፊት ለፊት ይረግምሃል።”+ +6 ከዚያም ይሖዋ ሰይጣንን “እነሆ፣ እሱ በእጅህ* ነው! ብቻ ሕይወቱን* እንዳታጠፋ!” አለው። +7 ሰይጣንም ከይሖዋ ፊት ወጥቶ በመሄድ ኢዮብን ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ ድረስ ክፉኛ በሚያሠቃይ እባጭ መታው።*+ +8 ኢዮብም ገላውን የሚያክበት ገል ወሰደ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ።+ +9 በመጨረሻም ሚስቱ “አሁንም በንጹሕ አቋምህ* እንደጸናህ ነው? አምላክን እርገምና ሙት!” አለችው። +10 እሱ ግን እንዲህ አላት፦ “የምትናገሪው ማመዛዘን እንደጎደላት ሴት ነው። ከእውነተኛው አምላክ መቀበል ያለብን መልካም ነገር ብቻ ነው? ክፉውንስ መቀበል የለብንም?”+ ኢዮብ ይህ ሁሉ ቢደርስበትም በከንፈሩ አልበደለም።+ +11 የኢዮብ ሦስት ጓደኞች* በእሱ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ ሰምተው እያንዳንዳቸው ከሚኖሩበት ቦታ መጡ፤ ጓደኞቹም ቴማናዊው ኤሊፋዝ፣+ ሹሃዊው+ በልዳዶስ+ እና ናአማታዊው ሶፋር+ ነበሩ። እነሱም አንድ ላይ ተገናኝተው ወደ ኢዮብ በመሄድ እሱን ለማስተዛዘንና ለማጽናናት ተስማሙ። +12 ከሩቅ ሲመለከቱት እሱ መሆኑን መለየት አቃታቸው። እነሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ማልቀስ ጀመሩ፤ ልብሳቸውንም ቀደዱ፤ እንዲሁም አቧራ ወደ ላይ በተኑ፤ ራሳቸውም ላይ ነሰነሱ።+ +13 ከዚያም ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት መሬት ላይ ከእሱ ጋር ተቀመጡ። ሥቃዩ በጣም ከባድ+ መሆኑን ስለተረዱ ከመካከላቸው አንድም ቃል የተናገረው አልነበረም። +26 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው! ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንከው!+ + 3 ጥበብ ለሌለው እንዴት ያለ ታላቅ ምክር ሰጠኸው!+ የጥበብህን* ብዛት* ምንኛ ገለጥክ! + 4 ለማን ለመናገር እየሞከርክ ነው?እንዲህ ያለ ነገር እንድትናገር የገፋፋህስ ማን ነው?* + 5 በሞት የተረቱት ይንቀጠቀጣሉ፤ከውኃዎችና በውስጣቸው ከሚኖሩት እንኳ በታች ናቸው። + 6 መቃብር* በአምላክ* ፊት የተራቆተ ነው፤+የጥፋትም ስፍራ* አይሸፈንም። + 7 የሰሜኑን ሰማይ* በባዶ ስፍራ* ላይ ዘርግቷል፤+ምድርንም ያለምንም ነገር አንጠልጥሏል፤ + 8 ውኃዎችን በደመናቱ ውስጥ ይጠቀልላል፤+ከክብደታቸውም የተነሳ ደመናቱ አይቀደዱም፤ + 9 ደመናውን በላዩ ላይ በመዘርጋት፣ዙፋኑን ይጋርዳል።+ +10 በውኃዎቹ ገጽ ላይ አድማሱን* ያበጃል፤+በብርሃንና በጨለማ መካከል ወሰን ያደርጋል። +11 የሰማይ ዓምዶች ተናጉ፤ከተግሣጹም የተነሳ ደነገጡ። +12 ባሕሩን በኃይሉ ያናውጣል፤+በማስተዋሉም ግዙፉን የባሕር ፍጥረት* ይቆራርጣል።+ +13 በእስትንፋሱ* ሰማያትን ያጠራል፤እጁ የማይጨበጠውን* እባብ ትወጋለች። +14 እነሆ፣ እነዚህ የመንገዱ ዳር ዳር ናቸው፤+ስለ እሱ የሰማነው የሹክሹክታ ያህል ብቻ ነው! ታዲያ ኃይለኛ የሆነውን ነጎድጓዱን ማን ሊያስተውል ይችላል?”+ +4 ከዚያም ቴማናዊው ኤሊፋዝ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “አንድ ሰው ሊያናግርህ ቢሞክር ትዕግሥት ታጣለህ? ደግሞስ ማን ከመናገር ሊቆጠብ ይችላል? + 3 እርግጥ ነው፣ አንተ ብዙዎችን ታርም ነበር፤የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር። + 4 ቃልህ የተሰናከለውን ሁሉ ያነሳ ነበር፤አንተም የሚብረከረኩትን ጉልበቶች ታጸና ነበር። + 5 አሁን ግን በአንተ ላይ ሲደርስ ዛልክ፤በአንተ ላይ ሲመጣ ተደናገጥክ። + 6 ለአምላክ ያለህ አክብሮት* መተማመኛህ አይደለም? ንጹሕ አቋምህን* ጠብቀህ መመላለስህ+ ተስፋ አልሰጠህም? + 7 እስቲ ለማስታወስ ሞክር፦ ንጹሕ ከሆኑ ሰዎች መካከል የጠፋ ማን አለ? ቅኖችስ መቼ ተደምስሰው ያውቃሉ? + 8 እኔ እንዳየሁት ክፉ ነገርን የሚያርሱ፣*መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ። + 9 በአምላክ እስትንፋስ ይጠፋሉ፤በቁጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ። +10 አንበሳ ሊያገሳ፣ የአንበሳም ግልገል ሊያጉረመርም ይችላል፤ይሁን እንጂ የብርቱ አንበሶች* ጥርስም እንኳ ይሰበራል። +11 አንበሳ የሚታደን ሲያጣ ይጠፋል፤የአንበሳም ግልገሎች ይበተናሉ። +12 ቃል በስውር መጣልኝ፤ሹክሹክታውም ወደ ጆሮዬ ደረሰ። +13 ይህም የሆነው ሌሊት ያየሁት ራእይ ባስጨነቀኝ ወቅት፣ሰዎችም ጭልጥ ያለ እንቅልፍ በወሰዳቸው ጊዜ ነበር፤ +14 በጣም ተንቀጠቀጥኩ፤አጥንቶቼም ሁሉ በፍርሃት ተዋጡ። +15 መንፈስም በፊቴ አለፈ፤የገላዬም ፀጉር ቆመ። +16 እሱም ባለበት ቆመ፤ሆኖም መልኩን መለየት አልቻልኩም። አንድ ቅርጽ በዓይኔ ፊት ነበር፤ጸጥታም ሰፍኖ ነበር፤ ከዚያም አንድ ድምፅ ሰማሁ፦ +17 ‘ሟች የሆነ ሰው ከአምላክ ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላል? ሰውስ ከገዛ ሠሪው ይበልጥ ንጹሕ ሊሆን ይችላል?’ +18 እነሆ፣ በአገልጋዮቹ ላይ እምነት የለውም፤በመላእክቱም* ላይ ስህተት ያገኛል። +19 በጭቃ ቤቶች የሚኖሩ፣መሠረታቸው አፈር ውስጥ የሆነ፣+እንደ ብል በቀላሉ የሚጨፈለቁማ ሁኔታቸው ምንኛ የከፋ ይሆን! +20 ከጠዋት እስከ ማታ ባለው ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይደቅቃሉ፤ለዘላለም ይጠፋሉ፤ ደግሞም ማንም ልብ አይላቸውም። +21 ገመዱ እንደተፈታበት ድንኳን አይደሉም? ያለጥበብ ይሞታሉ። +41 “ሌዋታንን*+ በመንጠቆ ልትይዘው፣ወይስ ምላሱን በገመድ ልታስረው ትችላለህ? + 2 በአፍንጫው ገመድ* ልታስገባ፣ወይስ መንጋጋዎቹን በሜንጦ* ልትበሳ ትችላለህ? + 3 እሱ እንድትምረው ይለማመጥሃል?ወይስ በለሰለሰ አንደበት ያናግርሃል? + 4 ዕድሜ ልኩን ባሪያህ ታደርገው ዘንድ፣ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን ይገባል? + 5 ከወፍ ጋር እንደምትጫወተው ከእሱ ጋር ትጫወታለህ?ወይስ ለትናንሽ ሴት ልጆችህ መጫወቻ እንዲሆን በውሻ ማሰሪያ ታስረዋለህ? + 6 ነጋዴዎች ይገበያዩበታል? ለቸርቻሪዎችስ ያከፋፍሉታል? + 7 ቆዳውን ለአደን በሚያገለግል ጦር፣+ራሱንስ በዓሣ መውጊያ ጭሬ ልትጠቀጥቅ ትችላለህ? + 8 እስቲ እጅህን አሳርፍበት፤ግብግቡን መቼም አትረሳውም፤ ዳግመኛም እንዲህ ለማድረግ አይቃጣህም! + 9 እሱን በቁጥጥር ሥር አውላለሁ ማለት ከንቱ ልፋት ነው። እሱን በማየትህ ብቻ እንኳ ብርክ ይይዝሃል።* +10 እሱን ለመተንኮስ የሚደፍር የለም። ታዲያ እኔን ሊቋቋም የሚችል ማን ነው?+ +11 ብድራት እመልስለት ዘንድ በመጀ���ሪያ አንዳች ነገር የሰጠኝ ማን ነው?+ ከሰማያት በታች ያለው ሁሉ የእኔ ነው።+ +12 ስለ እግሮቹ፣ ደግሞም ስለ ኃይሉናግሩም በሆነ መንገድ ስለተሠራው አካሉ ከመናገር አልቆጠብም። +13 የላይኛውን ሽፋኑን የገፈፈ ማን ነው? ወደተከፈቱ መንጋጋዎቹስ ማን ይገባል? +14 የአፉን* በሮች በኃይል ሊከፍት የሚችል ማን ነው? በዙሪያው ያሉት ጥርሶቹ አስፈሪ ናቸው። +15 ጀርባው ላይ እርስ በርስ የተጣበቁ፣በረድፍ የተቀመጡ ቅርፊቶች አሉ።* +16 ቅርፊቶቹ ግጥግጥ ያሉ ከመሆናቸው የተነሳ፣በመካከላቸው አየር እንኳ ሊገባ አይችልም። +17 አንዳቸው ከሌላው ጋር የተጣበቁ ናቸው፤እርስ በርስ የተያያዙ ናቸው፤ ሊለያዩም አይችሉም። +18 ፉርፉርታው የብርሃን ብልጭታ ያወጣል፤ዓይኖቹም እንደ ማለዳ ጨረር ናቸው። +19 ከአፉ የመብረቅ ብልጭታዎች ይወጣሉ፤የእሳት ፍንጣሪዎችም ይረጫሉ። +20 በእንግጫ እንደተቀጣጠለ ምድጃ፣ከአፍንጫው ጭስ ይወጣል። +21 እስትንፋሱ ከሰል ያቀጣጥላል፤ከአፉም ነበልባል ይወረወራል። +22 በአንገቱ ውስጥ ታላቅ ብርታት አለ፤ሽብርም በፊቱ ይሮጣል። +23 የሥጋው ንብርብር እርስ በርስ የተጣበቀ ነው፤ከቦታው እንደማይነቃነቅ ብረት ጠንካራ ነው። +24 ልቡ እንደ ድንጋይ የጠጠረ፣አዎ፣ እንደ ወፍጮ ድንጋይ የጠነከረ ነው። +25 በሚነሳበት ጊዜ ኃያላን እንኳ ይርዳሉ፤ውኃውን እየመታ ሲሄድ ያስደነብራል። +26 ሰይፍ፣ ጦር፣ መውጊያም ሆነ ፍላጻ ቢያገኙትሊያሸንፉት አይችሉም።+ +27 ብረትን እንደ ገለባ፣መዳብንም እንደበሰበሰ እንጨት ይቆጥራል። +28 ፍላጻ አያባርረውም፤የወንጭፍ ድንጋይም ለእሱ እንደ ገለባ ነው። +29 ቆመጥን እንደ ገለባ ይቆጥረዋል፤ጦር ሲሰበቅም ይስቃል። +30 ሆዱ እንደሾሉ የሸክላ ስብርባሪዎች ነው፤እንደ ማሄጃ*+ በጭቃ ላይ ምልክት ትቶ ያልፋል። +31 ጥልቁን ውኃ እንደ ድስት ያፈላዋል፤ባሕሩንም እንደ ቅባት መያዣ ይበጠብጠዋል። +32 በመንገዱ ላይ የሚያብረቀርቅ ፈለግ እየተወ ያልፋል። ተመልካችም ጥልቁ ውኃ ሽበት ያለው ይመስለዋል። +33 በምድር ላይ ያለፍርሃት የተፈጠረ፣እንደ እሱ ያለ ፍጡር የለም። +34 ትዕቢተኛ በሆነው ሁሉ ላይ በቁጣ ያፈጣል። ግርማ በተላበሱ የዱር እንስሳት ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።” +37 “ከዚህም የተነሳ ልቤ ይመታል፤ከስፍራውም ይዘላል። + 2 የድምፁን ጉምጉምታ፣ከአፉም የሚወጣውን ነጎድጓድ በጥሞና ስሙ። + 3 ከሰማያት በታች ይልከዋል፤መብረቁንም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይሰደዋል።+ + 4 ከዚያም በኋላ ድምፅ ያስተጋባል፤ግርማ በተላበሰ ድምፅ ያንጎደጉዳል፤+ድምፁም በሚሰማበት ጊዜ አይከለክለውም። + 5 አምላክ በሚያስደንቅ ሁኔታ በድምፁ ያንጎደጉዳል፤+እኛ መረዳት የማንችላቸውን ታላላቅ ነገሮች ያደርጋል።+ + 6 በረዶውን ‘ወደ መሬት ውረድ፣’+ ዶፉን ዝናብም ‘በኃይል ውረድ’ ይለዋልና።+ + 7 ሟች የሆነ ሰው ሁሉ ሥራውን እንዲያውቅ፣አምላክ የእያንዳንዱን ሰው ሥራ ያስቆማል።* + 8 የዱር አራዊት ወደ ጎሬአቸው ይገባሉ፤በዋሻዎቻቸውም ውስጥ ይቀመጣሉ። + 9 አውሎ ነፋስ ከማደሪያው ይነፍሳል፤+ቅዝቃዜም ከሰሜን ነፋሳት ይመጣል።+ +10 በአምላክ እስትንፋስ በረዶ ይገኛል፤+የተንጣለሉትም ውኃዎች ግግር በረዶ ይሆናሉ።+ +11 አዎ፣ ደመናትን እርጥበት ያሸክማቸዋል፤በደመናት መካከል መብረቁን ይበትናል፤+ +12 እሱ በመራቸው አቅጣጫ ይሽከረከራሉ፤ሰዎች በሚኖሩበት* የምድር ገጽ ላይ እሱ ያዘዘውን ሁሉ ይፈጽማሉ።+ +13 ለቅጣትም+ ሆነ* ለምድሩ ሲልአሊያም ታማኝ ፍቅር ለማሳየት ይህ እንዲሆን ያደርጋል።+ +14 ኢዮብ ሆይ፣ ይህን ስማ፤ቆም ብለህ የአምላክን ድንቅ ሥራዎች በጥሞና አስብ።+ +15 አምላክ ደመናትን እንዴት እንደሚቆጣ��ር፣*ከደመናውም እንዴት መብረቅ እንደሚያበርቅ ታውቃለህ? +16 ደመናት እንዴት እንደሚንሳፈፉ ታውቃለህ?+ እነዚህ፣ እውቀቱ ፍጹም የሆነው አምላክ ድንቅ ሥራዎች ናቸው።+ +17 ምድር በደቡብ ነፋስ ጸጥ ስትል፣ልብስህ የሚሞቀው ለምንድን ነው?+ +18 እንደ ብረት መስተዋት ጠንካራ የሆኑትን ሰማያት፣ከእሱ ጋር ልትዘረጋ* ትችላለህ?+ +19 ለእሱ የምንለውን ንገረን፤ጨለማ ውስጥ ስለሆን መልስ መስጠት አንችልም። +20 እኔ መናገር እንደምፈልግ ለእሱ ማሳወቅ ያስፈልጋል? ወይስ እሱ ሊያውቀው የሚገባ ነገር የተናገረ ሰው አለ?+ +21 በሰማይ ላይ ብርሃን ቢኖርም፣ነፋስ ነፍሶ ደመናቱን ካልበተነ፣ሰዎች ብርሃኑን* ማየት አይችሉም። +22 ከሰሜን ወርቃማ ጨረር ይወጣል፤የአምላክ ግርማ+ አስፈሪ ነው። +23 ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ከመረዳት ችሎታችን በላይ ነው፤+ኃይሉ ታላቅ ነው፤+ደግሞም ፍትሑንና ታላቅ ጽድቁን አይጥስም።+ +24 ስለዚህ ሰዎች ሊፈሩት ይገባል።+ ጠቢብ ነን ብለው ለሚያስቡ* ሁሉ ሞገስ አያሳይምና።”+ +40 ይሖዋ በመቀጠል ኢዮብን እንዲህ አለው፦ + 2 “ስህተት የሚፈላልግ ሰው፣ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ጋር ሊሟገት ይገባል?+ አምላክን መውቀስ የሚፈልግ እሱ መልስ ይስጥ።”+ + 3 ኢዮብ ለይሖዋ እንዲህ በማለት መለሰ፦ + 4 “እነሆ፣ እኔ የማልረባ ሰው ነኝ።+ ምን ልመልስልህ እችላለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።+ + 5 አንዴ ተናግሬአለሁ፤ ከአሁን በኋላ ግን የምሰጠው መልስ የለም፤ሁለተኛ ጊዜም ተናገርኩ፤ ከዚህ በኋላ ግን አልናገርም።” + 6 ከዚያም ይሖዋ ከአውሎ ነፋስ ውስጥ ለኢዮብ መለሰለት፦+ + 7 “እባክህ፣ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም ንገረኝ።+ + 8 የእኔን ፍትሕ ትጠራጠራለህ?* አንተ ትክክል ሆነህ ትገኝ ዘንድ እኔን ትኮንናለህ?+ + 9 ክንድህ የእውነተኛውን አምላክ ክንድ ያህል ኃያል ነው?+ወይስ ድምፅህ እንደ እሱ ድምፅ ሊያንጎደጉድ ይችላል?+ +10 እስቲ ራስህን በክብርና በግርማ አስጊጥ፤ደግሞም ታላቅነትና ሞገስ ተላበስ። +11 ቁጣህ ገንፍሎ ይፍሰስ፤ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልክተህ ዝቅ አድርገው። +12 ትዕቢተኛውን ሰው ሁሉ አይተህ አዋርደው፤ክፉዎችንም በቆሙበት ስፍራ ጨፍልቃቸው። +13 ሁሉንም በአፈር ውስጥ ደብቃቸው፤እነሱንም* በሰዋራ ቦታ እሰራቸው፤ +14 ያን ጊዜ ቀኝ እጅህ ልታድንህ እንደምትችል፣እኔ ራሴ አምኜ እቀበላለሁ።* +15 አንተን እንደፈጠርኩ፣ የፈጠርኩትን ብሄሞትን* ተመልከት። እንደ በሬ ሣር ይበላል። +16 በወገቡ ውስጥ ያለውን ጉልበት፣በሆዱም ጡንቻዎች ውስጥ ያለውን ኃይል ተመልከት! +17 ጅራቱን እንደ አርዘ ሊባኖስ ያጠነክረዋል፤የወርቹም ጅማቶች እርስ በርስ የተጠላለፉ ናቸው። +18 አጥንቶቹ የመዳብ ቱቦዎች ናቸው፤እግሮቹ እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው። +19 እሱ ከአምላክ የፍጥረት ሥራዎች መካከል አውራ ነው፤በሰይፍ ሊቀርበው የሚችለው ሠሪው ብቻ ነው። +20 የዱር እንስሳት ሁሉ የሚፈነጩባቸው ተራሮችመብሉን ያበቅሉለታልና። +21 በውኃ ላይ በሚያድጉ ዕፀዋት ጥላ ሥር፣ረግረጋማ በሆነ ቦታ በሚገኙ ቄጠማዎችም ሥር ይተኛል። +22 በውኃ ላይ የሚያድጉ ዕፀዋት በጥላቸው ይጋርዱታል፤በሸለቆ* ውስጥ የሚገኙ የአኻያ ዛፎችም ይከቡታል። +23 ወንዙ ቢናወጥ አይፈራም። ዮርዳኖስ+ ወደ እሱ ቢጎርፍ አይሸበርም። +24 ዓይኖቹ እያዩ ሊይዘው የሚችል አለ?ወይስ በአፍንጫው መንጠቆ* ሊያስገባ የሚችል ይኖራል? +16 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “ከዚህ በፊት እንዲህ ያሉ ብዙ ነገሮች ሰምቻለሁ። ሁላችሁም የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ!+ + 3 ከንቱ* ቃላት ማብቂያ የላቸውም? እንዲህ ብለህ እንድትመልስ ያነሳሳህ ምንድን ነው? + 4 እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር። እናንተ በእኔ ቦታ ብትሆኑ ኖሮ፣*አሳማኝ በሆነ መንገድ ልናገራችሁ እችል ነበር፤በእናንተም ላይ ራሴን መነቅነቅ እችል ነበር።+ + 5 እንዲህ ከማድረግ ይልቅ በአፌ ቃል አበረታችሁ ነበር፤የከንፈሮቼም ማጽናኛ ባሳረፋችሁ ነበር።+ + 6 ብናገር ከሥቃዬ አልገላገልም፤+ዝም ብልስ ሥቃዬ ምን ያህል ይቀንስልኛል? + 7 አሁን ግን አምላክ እንድዝል አድርጎኛል፤+መላ ቤተሰቤን* አጥፍቷል። + 8 ደግሞም ያዝከኝ፤ ይህም ምሥክር ሆኖብኛል፤በመሆኑም ክሳቴ ተነስቶ በፊቴ ይመሠክራል። + 9 ቁጣው ቦጫጨቀኝ፤ በጥላቻ ተመለከተኝ።+ ጥርሱን አፋጨብኝ። ባላጋራዬ በዓይኑ ወጋኝ።+ +10 እነሱ አፋቸውን በሰፊው ከፈቱብኝ፤+በንቀትም ጉንጬን አጮሉኝ፤ብዙ ሆነው በእኔ ላይ ተሰበሰቡ።+ +11 አምላክ ለልጆች አሳልፎ ሰጠኝ፤በክፉዎችም እጅ ላይ ገፍትሮ ጣለኝ።+ +12 ያለምንም ችግር እኖር ነበር፤ እሱ ግን ሰባበረኝ፤+ማጅራቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ከዚያም ዒላማው አደረገኝ። +13 ቀስተኞቹ ከበቡኝ፤+ኩላሊቴን ወጋ፤+ ምንም ርኅራኄ አላሳየኝም፤ሐሞቴን መሬት ላይ አፈሰሰ። +14 እንደ ግንብ ሰንጥቆ ሰነጣጥቆ አፈራረሰኝ፤እንደ ተዋጊ ተንደርድሮ መጣብኝ። +15 ቆዳዬን ለመሸፈን ማቅ ሰፍቻለሁ፤+ክብሬንም* አፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።+ +16 ከለቅሶ የተነሳ ፊቴ ቀልቷል፤+ድቅድቅ ጨለማም* በዓይኖቼ ቆብ ላይ አጥልቷል፤ +17 ይሁንና እጆቼ ምንም ዓመፅ አልሠሩም፤ጸሎቴም ንጹሕ ነው። +18 ምድር ሆይ፣ ደሜን አትሸፍኚ!+ ጩኸቴም ማረፊያ ስፍራ አያግኝ! +19 አሁንም እንኳ ምሥክሬ በሰማያት አለ፤ስለ እኔ መመሥከር የሚችል በከፍታ ቦታዎች ላይ ይገኛል። +20 ጓደኞቼ በእኔ ላይ ያፌዛሉ፤+ዓይኔም ወደ አምላክ ያነባል።*+ +21 በሰውና በባልንጀራው መካከል የሚዳኝ እንደሚኖር፣በሰውና በአምላክ መካከልም የሚዳኝ ይኑር።+ +22 የሚቀሩት ዓመታት ጥቂት ናቸውና፤እኔም በማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።+ +6 ከዚያም ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “ምነው ሥቃዬ ሁሉ+ በተመዘነ ኖሮ!ከመከራዬም ጋር ሚዛን ላይ በተቀመጠ ኖሮ! + 3 ከባሕር አሸዋ ይልቅ ከባድ ሆኖብኛልና። ከዚህም የተነሳ እንዳመጣልኝ* እናገራለሁ።+ + 4 ሁሉን የሚችለው አምላክ ፍላጻዎች ወግተውኛልና፤መንፈሴም መርዛቸውን እየጠጣ ነው፤+ከአምላክ የመጣ ሽብር በእኔ ላይ ተሰልፏል። + 5 የዱር አህያ+ ሣር እያለው ያናፋል?በሬስ ገፈራ እያለው ይጮኻል? + 6 ጣዕም የሌለው ምግብ ያለጨው ይበላል?ወይስ የልት* ፈሳሽ ጣዕም ይኖረዋል? + 7 እንዲህ ያሉ ነገሮችን መንካት ተጸይፌአለሁ።* በምግቤ ውስጥ እንዳሉ የሚበክሉ ነገሮች ናቸው።* + 8 ምነው ጥያቄዬ መልስ ባገኘ!አምላክም ፍላጎቴን በፈጸመልኝ! + 9 ምነው አምላክ እኔን ለማድቀቅ በፈቀደ!እጁንም ዘርግቶ ባጠፋኝ!+ +10 ይህም እንኳ ባጽናናኝ ነበርና፤ፋታ የማይሰጥ ሥቃይ ቢኖርብኝም በደስታ እዘላለሁ፤የቅዱሱን አምላክ ቃል አልካድኩምና።+ +11 ከዚህ በላይ መታገሥ የምችልበት ምን አቅም አለኝ?+ በሕይወት መኖሬን ብቀጥልስ* ምን አገኛለሁ? +12 እኔ የዓለት ዓይነት ጥንካሬ አለኝ? ወይስ ሥጋዬ ከመዳብ የተሠራ ነው? +13 ራሴን የምደግፍበት ነገር ሁሉ ከእኔ ርቆ ሳለ፣ራሴን መርዳት የምችልበት መንገድ ይኖራል? +14 ለገዛ ወዳጁ ታማኝ ፍቅር የማያሳይ ሰው፣+ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ መፍራት ይተዋል።+ +15 የገዛ ወንድሞቼ እንደ ክረምት ጅረት፣እንደሚደርቅ የክረምት የጅረት ውኃ ከዳተኞች ሆኑብኝ።+ +16 ከበረዶ የተነሳ ደፈረሱ፤የሚቀልጥ አመዳይም በእነሱ ውስጥ ተሰውሯል። +17 ሆኖም ወቅቱ ሲደርስ ውኃ አልባ ይሆናሉ፤ ደግሞም ደብዛቸው ይጠፋል፤በሙቀትም ጊዜ ይደርቃሉ። +18 የሚሄዱበት መንገድ ይቀየራል፤ወደ በረሃ ፈስሰው ይጠፋሉ። +19 የቴማ+ ነጋዴዎች ይፈልጓቸዋል፤የሳባም+ መንገደኞች* እነሱን ይጠባበቃሉ። +20 የተሳሳተ እምነት አድሮባቸው ስለነበር ለኀፍረት ተዳረጉ፤ወደዚያ ቢሄዱም የጠበቁትን ባለማግኘታቸው አዘኑ። +21 እናንተም እንደዚሁ ሆናችሁብኛል፤+መከራዬ ያስከተለውን ሽብር አይታችሁ በፍርሃት ተዋጣችሁ።+ +22 ለመሆኑ እኔ ‘አንድ ነገር ስጡኝ’ ብያለሁ? ወይስ ካፈራችሁት ሀብት ላይ ስጦታ እንድትሰጡኝ ጠይቄአለሁ? +23 ከጠላት እጅ እንድትታደጉኝ፣ወይም ከጨቋኞች እንድታድኑኝ* ጠይቄአለሁ? +24 አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤+የሠራሁትን ስህተት እንዳስተውል እርዱኝ። +25 በሐቀኝነት የተነገረ ቃል አያቆስልም!+ የእናንተ ወቀሳ ግን ጥቅሙ ምንድን ነው?+ +26 እኔ የምናገረውን ቃል፣ነፋስ ጠራርጎ የሚወስደውን፣ ተስፋ የቆረጠ ሰው ንግግር+ ለማረም ታስባላችሁ? +27 ወላጅ አልባ በሆነውም ልጅ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፤+ወዳጃችሁንም ትሸጣላችሁ!*+ +28 እስቲ አሁን ዞር ብላችሁ ተመልከቱኝ፤በፊታችሁ አልዋሽም። +29 እባካችሁ፣ ቆም ብላችሁ አስቡበት፤ በተሳሳተ መንገድ አትረዱኝ፤አዎ፣ ቆም ብላችሁ አስቡበት፤ ጽድቄ እንዳለ ነውና። +30 ምላሴ አግባብ ያልሆነ ነገር ይናገራል? ላንቃዬስ የሆነ ችግር እንዳለ መለየት አይችልም? +25 ሹሃዊው በልዳዶስ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “የመግዛት ሥልጣንና አስፈሪ ኃይል የእሱ ነው፤በሰማይ* ሰላምን ያሰፍናል። + 3 የሠራዊቱ ብዛት ሊቆጠር ይችላል? የእሱ ብርሃን የማያበራበት ማን አለ? + 4 ታዲያ ሟች የሆነ ሰው በአምላክ ፊት እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል?+ወይስ ከሴት የተወለደ ሰው እንዴት ንጹሕ* ሊሆን ይችላል?+ + 5 ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለችም፤ከዋክብትም በእሱ ፊት ንጹሕ አይደሉም፤ + 6 እጭ የሆነው ሟች የሰው ልጅ፣ትል የሆነው ሰውማ ምንኛ የባሰ ይሆን!” +33 “አሁን ግን ኢዮብ፣ እባክህ ቃሌን ስማ፤የምናገረውንም ሁሉ አዳምጥ። + 2 እባክህ ልብ በል! አፌን እከፍታለሁ፤አንደበቴም* ይናገራል። + 3 ቃሌ የልቤን ቅንነት ይገልጻል፤+ከንፈሮቼም የማውቀውን ነገር በቅንነት ይናገራሉ። + 4 የአምላክ መንፈስ ሠራኝ፤+ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እስትንፋስም ሕይወት ሰጠኝ።+ + 5 የምትችል ከሆነ መልስልኝ፤የመከራከሪያ ሐሳብህን በፊቴ አቅርብ፤ ቦታህንም ያዝ። + 6 እነሆ፣ በእውነተኛው አምላክ ፊት እኔም እንደ አንተው ነኝ፤እኔም የተሠራሁት ከሸክላ ነው።+ + 7 ስለዚህ እኔን ፈርተህ ልትሸበር አይገባም፤የማሳድርብህ ጫናም ሊደቁስህ አይገባም። + 8 ይሁንና የተናገርከውን ሰምቻለሁ፤አዎ፣ እነዚህን ቃላት ስሰማ ቆይቻለሁ፦ + 9 ‘ከበደል ነፃ ነኝ፤+ንጹሕ ነኝ፤ ጥፋትም የለብኝም።+ +10 አምላክ ግን እኔን ለመቃወም ምክንያት ይፈልጋል፤እንደ ጠላቱ ይቆጥረኛል።+ +11 እግሬን በእግር ግንድ ያስራል፤መንገዴንም ሁሉ ይመረምራል።’+ +12 ሆኖም እንዲህ ማለትህ ትክክል ስላልሆነ እመልስልሃለሁ፦ አምላክ ሟች ከሆነው ሰው እጅግ ይበልጣል።+ +13 በአምላክ ላይ የምታጉረመርመው ለምንድን ነው?+ ለተናገርከው ሁሉ መልስ ስላልሰጠህ ነው?+ +14 አምላክ ከአንዴም ሁለቴ ይናገራል፤ይሁንና ማንም አያስተውለውም፤ +15 ሰዎች ከባድ እንቅልፍ ሲይዛቸው፣በአልጋቸውም ላይ ሆነው ሲያሸልቡ፣በሕልም፣ በሌሊትም ራእይ ይናገራል።+ +16 በዚያን ጊዜ ጆሯቸውን ይከፍታል፤+መመሪያውንም እንዲገነዘቡ ያደርጋል፤* +17 ይህም ሰውን ከስህተት ይመልስ ዘንድ፣+ደግሞም ሰውን ከኩራት ይጠብቅ ዘንድ ነው።+ +18 አምላክ ነፍሱን* ከጉድጓድ* ያድናል፤+ሕይወቱ በሰይፍ* እንዳይጠፋ ይታደገዋል። +19 ደግሞም ሰው በአልጋው ላይ ሳለ በሕመም፣እንዲሁም አጥንቶቹ በሚያስከትሉበት ፋታ የሌለው ሥቃይ ተግሣጽ ይቀበላል፤ +20 በመሆኑም ሁለመናው* መብል ይጸየፋል፤ምርጥ የሆነ ምግብም ይጠላል።*+ +21 ሥጋውም መንምኖ ይጠፋል፤ተሸፍነው የነበሩት አጥንቶቹም ያገጣሉ።* +22 ነፍሱ* ወደ ጉድጓድ፣*ሕይወቱም ሊያጠፏት ወደሚሹ ትቀርባለች። +23 ለሰው ትክክል የሆነውን ነገር የሚነግረውአንድ መልእክተኛ፣*ከሺዎች መካከል አንድ ጠበቃ ቢገኝለት፣ +24 ያን ጊዜ አምላክ ሞገስ ያሳየዋል፤ እንዲህም ይላል፦‘ወደ ጉድጓድ* ከመውረድ አድነው!+ ቤዛ አግኝቻለሁ!+ +25 በወጣትነቱ ጊዜ ከነበረው የበለጠ ሥጋው ይለምልም፤*+ብርቱ ወደነበረበት የወጣትነት ዘመኑም ይመለስ።’+ +26 አምላክን ይለምናል፤+ እሱም ይቀበለዋል፤በእልልታም የአምላክን ፊት ያያል፤ደግሞም አምላክ የራሱን ጽድቅ፣ ሟች ለሆነው ሰው ይመልስለታል። +27 ግለሰቡም ለሰዎች እንዲህ ይላል፦*‘ኃጢአት ሠርቻለሁ፤+ ትክክል የሆነውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ሆኖም የእጄን አላገኘሁም።* +28 እሱ ነፍሴን* ወደ ጉድጓድ* ከመውረድ ታድጓታል፤+ሕይወቴም ብርሃን ታያለች።’ +29 በእርግጥም አምላክ እነዚህን ነገሮች ሁሉ፣ከሁለቴም ሦስቴ ለሰው ያደርጋል፤ +30 ይኸውም የሕይወት ብርሃን ይበራለት ዘንድ፣እሱን ከጉድጓድ* ለመመለስ ነው።+ +31 ኢዮብ፣ ልብ ብለህ ስማ! ደግሞም አዳምጠኝ! ዝም በል፤ እኔም መናገሬን እቀጥላለሁ። +32 የምትለው ካለ መልስልኝ። ትክክለኛነትህ እንዲረጋገጥ ማድረግ ስለምፈልግ ተናገር። +33 የምትለው ነገር ከሌለ ግን ስማኝ፤ዝም በል፤ እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ።” +10 “ሕይወቴን ተጸየፍኳት።*+ አንዳች ሳላስቀር ብሶቴን አሰማለሁ። በታላቅ ምሬት* እናገራለሁ! + 2 አምላክን እንዲህ እለዋለሁ፦ ‘በደለኛ ነህ አትበለኝ። ከእኔ ጋር የምትሟገተው ለምን እንደሆነ ንገረኝ። + 3 በክፉዎች ዕቅድ ደስ እየተሰኘህ፣የእጆችህን ሥራ መጨቆንህና መናቅህምን ይጠቅምሃል?+ + 4 ዓይንህ የሥጋ ለባሽ ዓይን ነው?ወይስ የምታየው ሟች የሆነ ሰው በሚያይበት መንገድ ነው? + 5 ዘመንህ እንደ ሟች ሰዎች ዘመን ነው?ወይስ ዕድሜህ እንደ ሰው ዘመን ነው?+ + 6 ታዲያ በደልን የምትፈላልግብኝ፣ኃጢአቴንስ የምትከታተለው ለምንድን ነው?+ + 7 በደለኛ እንዳልሆንኩ ታውቃለህ፤+ደግሞም ማንም ከእጅህ ሊያስጥለኝ አይችልም።+ + 8 የገዛ እጆችህ ቀረጹኝ፤ ደግሞም ሠሩኝ፤+አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ልታጠፋኝ ነው። + 9 ከሸክላ እንደሠራኸኝ እባክህ አስታውስ፤+አሁን ግን ወደ አፈር ትመልሰኛለህ።+ +10 እንደ ወተት አላፈሰስከኝም?እንደ እርጎስ አላረጋኸኝም? +11 ቆዳና ሥጋ አለበስከኝ፤በአጥንትና በጅማት አያይዘህ ሠራኸኝ።+ +12 ሕይወት ሰጠኸኝ፤ ታማኝ ፍቅርም አሳየኸኝ፤መንፈሴን* በእንክብካቤ ጠበቅክ።+ +13 ሆኖም እነዚህን ነገሮች በስውር ለማድረግ አሰብክ።* እነዚህ ነገሮች ከአንተ እንደመጡ አውቃለሁ። +14 ኃጢአት ብሠራ ትመለከተኛለህ፤+ከበደሌም ነፃ አታደርገኝም። +15 በደለኛ ከሆንኩ ወዮልኝ! ንጹሕ ብሆንም እንኳ ራሴን ቀና ማድረግ አልችልም፤+ውርደትና ጉስቁልና በዝቶብኛልና።+ +16 ራሴን ቀና ባደርግ እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፤+ዳግመኛም በእኔ ላይ ኃይልህን ታሳያለህ። +17 አዳዲስ ምሥክሮችን በእኔ ላይ ታቆማለህ፤ቁጣህንም በእኔ ላይ ታበዛለህ፤በመከራ ላይ መከራ ተደራርቦብኛል። +18 ታዲያ ከማህፀን ለምን አወጣኸኝ?+ ምነው የሰው ዓይን ሳያየኝ በሞትኩ ኖሮ! +19 እንዳልተፈጠርኩ በሆንኩ ነበር!በቀጥታ ከማህፀን ወደ መቃብር በተወሰድኩ ነበር!’ +20 የሕይወት ዘመኔ ጥቂት አይደለም?+ እስቲ ተወት ያድርገኝ፤ትንሽ ፋታ እንዳገኝ* ዓይኑን ከእኔ ላይ ያንሳ፤+ +21 ወደማልመለስበት ስፍራ፣+ወደ ድቅድቅ ጨለማ* ምድር በቅርቡ እሄዳለሁ፤+ +22 በጨለማ ወደተዋጠ፣ ፅልማሞት ወዳጠላበትናዝብርቅ ወደሰፈነበት፣ብርሃኑ እንኳ እንደ ጨለማ ወደሆነበት ምድር እሄዳለሁ።” +14 “ከሴት የተወለደ ሰው፣የሕይወት ዘመኑ አጭርና+ በመከራ የተሞላ* ነው።+ + 2 እንደ አበባ ይፈካል፤ ከዚያም ይጠወልጋል፤*+እንደ ጥላም ወዲያው ያልፋል፤ ደብዛውም ይጠፋል።+ + 3 አዎ፣ ዓይንህን በዚህ ሰው ላይ አሳርፈሃል፤እሱንም ከአንተ ጋር ፍርድ ፊት ታቀርበዋለህ።*+ + 4 ንጹሕ ካልሆነ ሰው፣ ንጹሕ የሆነ ሰው መውለድ የሚችል ማን ነው?+ ማንም የለም! + 5 የሰው የሕይወት ዘመን አጭር እንዲሆን የተወሰነ ከሆነ፣የወራቱ ቁጥር በአንተ ቁጥጥር ሥር ነው፤ከዚያ እንዳያልፍ ገደብ አበጅተህለታል።+ + 6 እንደ ቅጥር ሠራተኛ ጊዜውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ፣እረፍት ያገኝ ዘንድ ዓይንህን ከእሱ ላይ መልስ።+ + 7 ዛፍ እንኳ ተስፋ አለውና። ቢቆረጥ መልሶ ያቆጠቁጣል፤ቅርንጫፎቹም ማደጋቸውን ይቀጥላሉ። + 8 ሥሩ መሬት ውስጥ ቢያረጅ፣ጉቶውም አፈር ውስጥ ቢበሰብስ፣ + 9 የውኃ ሽታ ሲያገኝ ያቆጠቁጣል፤እንደ አዲስ ተክልም ቅርንጫፎች ያወጣል። +10 ሰው ግን ይሞታል፤ አቅም አጥቶም ይጋደማል፤ሰው ሲሞት የት ይገኛል?+ +11 ውኃ ከባሕር ውስጥ ይጠፋል፤ወንዝም ፈስሶ ይደርቃል። +12 ሰውም ያንቀላፋል፤ ደግሞም አይነሳም።+ ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቁም፤ከእንቅልፋቸውም አይነሱም።+ +13 ምነው በመቃብር* ውስጥ በሰወርከኝ!+ቁጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግከኝ!ቀጠሮም ሰጥተህ ባስታወስከኝ!+ +14 ሰው ከሞተ በኋላ ዳግመኛ በሕይወት ሊኖር ይችላል?+ እፎይታ የማገኝበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ፣የግዳጅ አገልግሎት በምፈጽምበት ዘመን ሁሉ በትዕግሥት እጠብቃለሁ።+ +15 አንተ ትጣራለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ።+ የእጅህን ሥራ ትናፍቃለህ።* +16 አሁን ግን እርምጃዬን ሁሉ ትቆጥራለህ፤ኃጢአቴን ብቻ ትመለከታለህ። +17 መተላለፌ በከረጢት ውስጥ ታሽጓል፤በደሌንም በሙጫ ታሽጋለህ። +18 ተራራ እንደሚወድቅና ተፈረካክሶ እንደሚጠፋ፣ቋጥኝም ከስፍራው እንደሚወገድ፣ +19 ውኃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ጎርፍም የምድርን አፈር አጥቦ እንደሚወስድ፣አንተም ሟች የሆነውን ሰው ተስፋ አጥፍተሃል። +20 እስኪጠፋ ድረስ በእሱ ላይ ታይልበታለህ፤+ገጽታውን ለውጠህ ታሰናብተዋለህ። +21 ልጆቹ ክብር ቢያገኙም እሱ ይህን አያውቅም፤ውርደት ሲደርስባቸውም ልብ አይልም።+ +22 ሕመም የሚሰማው በሥጋ ሳለ ብቻ ነው፤የሚያዝነው* በሕይወት ሳለ ብቻ ነው።” +9 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “እርግጥ ነገሩ እንዲህ መሆኑን አውቃለሁ። ሆኖም ሟች የሆነ ሰው ከአምላክ ጋር ተሟግቶ እንዴት ትክክል ሊሆን ይችላል?+ + 3 ሰው ከእሱ ጋር መሟገት ቢፈልግ፣*+አምላክ ከሚያቀርብለት አንድ ሺህ ጥያቄዎች መካከል ለአንዱ እንኳ መልስ መስጠት አይችልም። + 4 እሱ ጥበበኛ ልብ አለው፤ ኃይሉም ታላቅ ነው።+ እሱን ተገዳድሮ ከጉዳት ማምለጥ የሚችል ማን ነው?+ + 5 ማንም ሳያውቅ ተራሮችን ከስፍራቸው ይወስዳል፤*በቁጣውም ይገለብጣቸዋል። + 6 ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፤በመሆኑም ምሰሶዎቿ ይንቀጠቀጣሉ።+ + 7 ብርሃን እንዳትፈነጥቅ ፀሐይን ያዛታል፤የከዋክብትን ብርሃን ያሽጋል፤+ + 8 ሰማያትንም ብቻውን ይዘረጋል፤+ከፍ ባለው የባሕር ማዕበልም ላይ ይራመዳል።+ + 9 የአሽ፣* የከሲልና* የኪማ ኅብረ ከዋክብትን*+እንዲሁም የደቡቡን ሰማይ ኅብረ ከዋክብት* ሠርቷል፤ +10 ታላላቅና የማይመረመሩ ነገሮችን፣ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ድንቅ ነገሮች ያደርጋል።+ +11 በአጠገቤ ያልፋል፤ እኔ ግን ላየው አልችልም፤አልፎኝ ይሄዳል፤ እኔ ግን አለየውም። +12 አንዳች ነገር ነጥቆ ሲወስድ ማን ሊከለክለው ይችላል? ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ሊ���ው የሚችልስ ማን ነው?+ +13 አምላክ ቁጣውን አይገታም፤+የረዓብ*+ ረዳቶች እንኳ እግሩ ሥር ይወድቃሉ። +14 በመሆኑም ለእሱ መልስ ስሰጥ፣ይልቁንም ከእሱ ጋር ስከራከር አስቤ መናገር ይጠበቅብኛል። +15 ትክክል ብሆን እንኳ መልስ አልሰጠውም።+ ዳኛዬን* ምሕረት ከመለመን ሌላ ምንም ማድረግ አልችልም። +16 ብጠራው ይመልስልኛል? እኔ እንደሆነ፣ ስናገር ይሰማኛል የሚል እምነት የለኝም፤ +17 በአውሎ ነፋስ ያደቀኛልና፤ያለምክንያትም ቁስሌን ያበዛል።+ +18 ለመተንፈስ እንኳ ፋታ አይሰጠኝም፤መራራ ነገሮችን ያጠግበኛል። +19 የኃይል ጉዳይ ከሆነ እሱ ኃያል ነው።+ የፍትሕ ጉዳይ ከተነሳ ‘ማን ሊጠይቀኝ* ይችላል?’ ይላል። +20 ትክክል ብሆን እንኳ የገዛ አፌ ይፈርድብኛል፤ንጹሕ አቋሜን ብጠብቅ እንኳ* እሱ ጥፋተኛ* ነህ ይለኛል። +21 ንጹሕ አቋሜን ብጠብቅ እንኳ* ስለ ራሴ እርግጠኛ አይደለሁም፤*ይህን ሕይወቴን እጠላዋለሁ።* +22 ምንም ለውጥ የለውም። ‘እሱ ንጹሑንም* ሆነ ክፉውን ያጠፋል’የምለው ለዚህ ነው። +23 ደራሽ ውኃ በድንገት ሰዎችን ቢያጠፋ፣እሱ ንጹሐን ሰዎች በሚደርስባቸው ሥቃይ ያፌዛል። +24 ምድር ለክፉዎች ተሰጥታለች፤+እሱ የዳኞቿን ዓይኖች* ይሸፍናል። ይህን የሚያደርገው እሱ ካልሆነ ታዲያ ማን ነው? +25 ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፤+መልካም ነገር ሳያይ ፈጥኖ ይነጉዳል። +26 ከደንገል እንደተሠሩ ጀልባዎች፣የሚያድኑትንም ነገር ለመያዝ ወደ ታች እንደሚወረወሩ ንስሮች ይከንፋል። +27 ‘ብሶቴን እረሳለሁ፤የፊቴን ገጽታ ቀይሬ ደስተኛ እሆናለሁ’ ብል እንኳ፣ +28 ከሥቃዬ ሁሉ የተነሳ አሁንም ፍርሃት ይሰማኛል፤+ንጹሕ ሆኜ እንደማታገኘኝ አውቃለሁ። +29 በደለኛ* ሆኜ መገኘቴ አይቀርም። ታዲያ ለምን በከንቱ እደክማለሁ?+ +30 ከቀለጠ በረዶ በተገኘ ውኃ ብታጠብ፣እጆቼንም በእንዶድ* ባነጻ፣+ +31 አንተ አዘቅት ውስጥ ትነክረኛለህ፤ከዚህም የተነሳ የገዛ ልብሶቼ እንኳ ይጸየፉኛል። +32 መልስ እሰጠው ዘንድ፣ችሎት ፊትም አብረን እንቀርብ ዘንድ እሱ እንደ እኔ ሰው አይደለምና።+ +33 በመካከላችን የሚበይን፣*ሊዳኘንም የሚችል* ሰው የለም። +34 እኔን መምታቱን ቢያቆም፣*ሽብርም ባይለቅብኝ፣+ +35 ያን ጊዜ ያለፍርሃት አናግረዋለሁ፤በፍርሃት የምናገር ሰው አይደለሁምና። +27 ኢዮብ ንግግሩን* በመቀጠል እንዲህ አለ፦ + 2 “ፍትሕ በነፈገኝ ሕያው በሆነው አምላክ፣+እንድመረር ባደረገኝ*+ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ እምላለሁ፤ + 3 እስትንፋሴ በውስጤ፣ከአምላክ ያገኘሁትም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ እስካለ ድረስ፣+ + 4 ከንፈሮቼ ክፋት አይናገሩም፤ምላሴም ፈጽሞ የማታለያ ቃል አይወጣውም! + 5 በእኔ በኩል እናንተን ጻድቅ አድርጎ መቁጠር የማይታሰብ ነገር ነው! እስክሞት ድረስ ንጹሕ አቋሜን* አላጎድፍም!*+ + 6 ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ፤ ደግሞም ፈጽሞ አለቀውም፤+በሕይወት ዘመኔም ሁሉ* ልቤ አይኮንነኝም።* + 7 ጠላቴ እንደ ክፉ ሰው ይሁን፤እኔን የሚያጠቁኝ ሰዎች እንደ ዓመፀኛ ይሁኑ። + 8 አምላክ የለሽ የሆነ* ሰው ሲጠፋ፣አምላክ ሕይወቱን* ሲቀጨው ምን ተስፋ ይኖረዋል?+ + 9 መከራ ሲደርስበትአምላክ ጩኸቱን ይሰማዋል?+ +10 ወይስ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ደስ ይሰኛል? ሁልጊዜስ ወደ አምላክ ይጣራል? +11 እኔ ስለ አምላክ ኃይል* አስተምራችኋለሁ፤ሁሉን ቻይ ስለሆነው አምላክ ምንም የምደብቀው ነገር የለም። +12 ሁላችሁም ራእይ ካያችሁ፣ንግግራችሁ ጨርሶ ባዶ የሆነው ለምንድን ነው? +13 ክፉ ሰው ከአምላክ የሚያገኘው ድርሻ፣+ጨቋኞችም ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ የሚወርሱት ውርሻ ይህ ነው። +14 ልጆቹ ቢበዙ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+ዘሮቹም በቂ ምግብ አያገኙም። +15 ከእሱ በኋላ የተረፉት ወገኖቹ በመቅሰፍት ይቀበራሉ፤መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም። +16 ብርን እንደ አፈር ቢቆልል፣ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች እንኳ፣ +17 እሱ የሰበሰበውንጻድቁ ሰው ይለብሰዋል፤+ብሩንም ንጹሐን ይከፋፈሉታል። +18 የሚሠራው ቤት ብል እንደሠራው ሽፋን፣ጠባቂም እንደቀለሰው መጠለያ+ በቀላሉ የሚፈርስ ነው። +19 ባለጸጋ ሆኖ ይተኛል፤ ሆኖም ምንም የሚሰበስበው ነገር የለም፤ዓይኑን ሲገልጥ በዚያ ምንም ነገር አይኖርም። +20 ሽብር እንደ ጎርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤አውሎ ነፋስ በሌሊት ይዞት ይሄዳል።+ +21 የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፤ እሱም አይገኝም፤ከቦታው ጠርጎ ይወስደዋል።+ +22 ከነፋሱ ኃይል ለማምለጥ ሲፍጨረጨር፣+ያለርኅራኄ ተወርውሮ ይመጣበታል።+ +23 እጁን ያጨበጭብበታል፤ደግሞም ካለበት ቦታ ሆኖ ያፏጭበታል።*+ +13 “አዎ፣ ዓይኔ ይህን ሁሉ አይታለች፤ጆሮዬም ሰምታ አስተውላለች። + 2 እናንተ የምታውቁትን እኔም አውቃለሁ፤ከእናንተ አላንስም። + 3 እኔ በበኩሌ ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራሱን ባነጋግር እመርጣለሁ፤ከአምላክ ጋር መሟገት እፈልጋለሁ።+ + 4 እናንተ ግን በውሸት ስሜን እያጠፋችሁ ነው፤ሁላችሁም የማትረቡ ሐኪሞች ናችሁ።+ + 5 ምነው ዝም ብትሉ!ጥበበኛ መሆናችሁ በዚህ ይታወቅ ነበር።+ + 6 እስቲ የመከራከሪያ ሐሳቤን ስሙ፤የከንፈሬንም አቤቱታ አዳምጡ። + 7 ከአምላክ ጎን ቆማችሁ አግባብ ያልሆነ ነገር ታወራላችሁ?ለእሱ ብላችሁስ የማታለያ ቃል ትናገራላችሁ? + 8 ከእሱ ጎን ትቆማላችሁ?*ወይስ ለእውነተኛው አምላክ ትሟገታላችሁ? + 9 እሱ ቢመረምራችሁ መልካም ይሆንላችኋል?+ ሟች የሆነውን ሰው እንደምታሞኙ እሱን ታሞኛላችሁ? +10 በስውር አድልዎ ለማድረግ ብትሞክሩ፣እሱ በእርግጥ ይገሥጻችኋል።+ +11 ክብሩ ሽብር አይለቅባችሁም?የእሱ ፍርሃትስ አይወድቅባችሁም? +12 ጥበብ የተንጸባረቀባቸው* አባባሎቻችሁ ከንቱ ምሳሌዎች* ናቸው፤መከላከያዎቻችሁ* ከሸክላ እንደተሠሩ ጋሻዎች ተሰባሪ ናቸው። +13 እኔ እንድናገር በፊቴ ዝም በሉ። ከዚያ በኋላ የመጣው ይምጣብኝ! +14 ራሴን ለምን ለአደጋ አጋልጣለሁ?*ሕይወቴንስ* ለምን በእጄ እይዛለሁ? +15 ቢገድለኝ እንኳ እሱን በተስፋ እጠባበቃለሁ፤+በፊቱ ጉዳዬን አቅርቤ እከራከራለሁ።* +16 በዚህ ጊዜ እሱ አዳኜ ይሆናል፤+አምላክ የለሽ* ሰው ፈጽሞ ፊቱ አይቀርብምና።+ +17 ቃሌን በጥሞና ስሙ፤የምናገረውንም ነገር ልብ ብላችሁ አድምጡ። +18 እንግዲህ ሙግቴን አዘጋጅቻለሁ፤ትክክል እንደሆንኩ አውቃለሁ። +19 ከእኔ ጋር የሚሟገት ማን ነው? ዝም ብል እሞታለሁ!* +20 አምላክ ሆይ፣ ከአንተ ሁለት ነገሮች ብቻ እሻለሁ፤*በዚያን ጊዜ ራሴን ከፊትህ አልሰውርም፦ +21 ከባዱን እጅህን ከእኔ አርቅ፤አስፈሪነትህም አያስደንግጠኝ።+ +22 ጥራኝና ልመልስልህ፤አለዚያ እኔ ልናገር፤ አንተም መልስ ስጠኝ። +23 የሠራሁት በደልና ኃጢአት ምንድን ነው? መተላለፌንና ኃጢአቴን አሳውቀኝ። +24 ፊትህን የምትሰውረውና+እንደ ጠላትህ የምትቆጥረኝ ለምንድን ነው?+ +25 ነፋስ የወሰደውን ቅጠል ለማስፈራራት ትሞክራለህ?ወይስ የደረቀውን ገለባ ታሳድዳለህ? +26 ከባድ ክሶችን ትመዘግብብኛለህ፤በወጣትነቴ ለሠራኋቸው ኃጢአቶች መልስ እንድሰጥ ታደርገኛለህ። +27 እግሮቼን በእግር ግንድ አስረሃል፤መንገዴን ሁሉ ትመረምራለህ፤ዱካዬንም ሁሉ በዓይነ ቁራኛ ትከታተላለህ። +28 በመሆኑም ሰው* እንደበሰበሰ ነገር፣ብልም እንደበላው ልብስ እያለቀ ይሄዳል። +5 “እስቲ ተጣራ! የሚመልስልህ ይኖራል? ከቅዱሳንስ* መካከል ወደ የትኛው ዞር ትላለህ? + 2 ሞኝን ሰው ብስጭት ይገድለዋልና፤ማስተዋል የጎደለውንም ቅናት ይገድለዋል። + 3 ሞኝ ሰ�� ሥር ሰዶ አየሁት፤ይሁንና የመኖሪያ ስፍራው በድንገት ተረገመ። + 4 ወንዶች ልጆቹ ደህንነት ርቋቸዋል፤በከተማው በር ተረግጠዋል፤+ የሚያድናቸውም የለም። + 5 እሱ የሰበሰበውን፣ የራበው ሰው ይበላዋል፤ከእሾህም መካከል ይወስድበታል፤ደግሞም ንብረታቸው በወጥመድ ተይዟል። + 6 ጎጂ የሆነ ነገር ከአፈር አይበቅልምና፤ችግርም ከመሬት አይፈልቅም። + 7 የእሳት ፍንጣሪ ወደ ላይ እንደሚወረወር፣ሰው የሚወለደው ለችግር ነው። + 8 እኔ ብሆን ኖሮ አምላክን እለምን ነበር፤ጉዳዬንም ለአምላክ አቀርብ ነበር፤ + 9 እሱ ታላላቅና የማይመረመሩ ነገሮችን ያደርጋል፤ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ድንቅ ነገሮች ይሠራል። +10 በምድር ላይ ዝናብ ያዘንባል፤በሜዳዎችም ላይ ውኃ ይልካል። +11 ችግረኞችን ከፍ ያደርጋል፤እንዲሁም ያዘነውን ሰው መዳን እንዲያገኝ ከፍ ከፍ ያደርገዋል። +12 የብልጣ ብልጦችን ዕቅድ ያከሽፋል፤ስለዚህ የእጃቸው ሥራ አይሰምርም። +13 ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኮል ይይዛቸዋል፤+ስለሆነም የጮሌዎች ዕቅድ ይከሽፋል። +14 ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ሌሊት የሆነ ይመስል እኩለ ቀን ላይ በዳበሳ ይሄዳሉ። +15 ከአፋቸው ሰይፍ ያድናል፤ድሃውንም ከብርቱው እጅ ይታደጋል፤ +16 በመሆኑም ችግረኛው ተስፋ ይኖረዋል፤የክፋት አፍ ግን ይዘጋል። +17 እነሆ፣ አምላክ የሚወቅሰው ሰው ደስተኛ ነው፤ስለዚህ ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ተግሣጽ አትናቅ! +18 እሱ ሥቃይ ያመጣልና፤ ሆኖም ቁስሉን ይጠግናል፤እሱ ይሰብራል፤ ይሁንና በገዛ እጆቹ ይፈውሳል። +19 ከስድስት መቅሰፍቶች ያድንሃል፤ሰባተኛውም አይጎዳህም። +20 በረሃብ ወቅት ከሞት ይዋጅሃል፤በጦርነትም ጊዜ ከሰይፍ ኃይል ይታደግሃል። +21 ከምላስ ጅራፍ ትጠበቃለህ፤+ጥፋት ሲመጣም አትፈራም። +22 በጥፋትና በረሃብ ላይ ትስቃለህ፤የምድርንም አራዊት አትፈራም። +23 በሜዳ ያሉ ድንጋዮች አይጎዱህም፤*የዱር አራዊትም ከአንተ ጋር ሰላም ይኖራቸዋል። +24 በድንኳንህ ውስጥ አስተማማኝ ሁኔታ* እንደሚሰፍን ታውቃለህ፤የግጦሽ መሬትህን ስትቃኝም አንዳች ነገር አይጎድልብህም። +25 ብዙ ልጆች ይኖሩሃል፤ዘሮችህም በምድር ላይ እንደሚበቅል ሣር ይበዛሉ። +26 በወቅቱ እንደተሰበሰበ የእህል ነዶ፣ብርቱ እንደሆንክ ወደ መቃብር ትወርዳለህ። +27 እነሆ፣ ይህን መርምረናል፤ እውነት መሆኑንም አረጋግጠናል። ይህን ስማ፤ ደግሞም ተቀበል።” +21 ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “የምናገረውን በጥሞና አዳምጡ፤የምታጽናኑኝ በዚህ ይሁን። + 3 በምናገርበት ጊዜ በትዕግሥት አዳምጡኝ፤ከተናገርኩ በኋላ ልትሳለቁብኝ ትችላላችሁ።+ + 4 ቅሬታዬ በሰው ላይ ነው? ቢሆንማ ኖሮ የእኔ* ትዕግሥት አያልቅም ነበር? + 5 እዩኝ፤ በመገረምም ተመልከቱኝ፤እጃችሁን በአፋችሁ ላይ አድርጉ። + 6 ስለዚህ ነገር ሳስብ እረበሻለሁ፤መላ ሰውነቴም ይንቀጠቀጣል። + 7 ክፉዎች በሕይወት የሚኖሩት፣+ለእርጅና የሚበቁትና ባለጸጋ* የሚሆኑት ለምንድን ነው?+ + 8 ልጆቻቸው ሁልጊዜ አብረዋቸው ይኖራሉ፤ዘሮቻቸውንም ያያሉ። + 9 ቤታቸው ሰላም የሰፈነበት ነው፤ የሚያሰጋቸውም ነገር የለም፤+አምላክም በበትሩ አይቀጣቸውም። +10 ኮርማዎቻቸው ዘር ያፈራሉ፤ላሞቻቸው ይወልዳሉ፤ ደግሞም አይጨነግፉም። +11 ወንዶች ልጆቻቸው እንደ መንጋ በደጅ ይሯሯጣሉ፤ልጆቻቸውም ይቦርቃሉ። +12 በአታሞና በበገና ታጅበው ይዘፍናሉ፤በዋሽንትም ድምፅ* ደስ ይሰኛሉ።+ +13 ዕድሜያቸውን በደስታ ያሳልፋሉ፤በሰላምም* ወደ መቃብር* ይወርዳሉ። +14 ይሁንና እውነተኛውን አምላክ እንዲህ ይሉታል፦ ‘አትድረስብን! መንገዶችህን ማወቅ አንፈልግም።+ +15 እናገለግለው ዘንድ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው?+ ከእሱ ጋር መተዋወቃችን ምን ይጠቅመናል?’+ +16 ሆኖም ብልጽግናቸው በእነሱ ቁጥጥር ሥር እንዳልሆነ አውቃለሁ።+ የክፉዎች ሐሳብ* ከእኔ የራቀች ናት።+ +17 የክፉዎች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው?+ መዓት የደረሰባቸውስ ስንት ጊዜ ነው? አምላክ ተቆጥቶ ጥፋት የላከባቸው ስንት ጊዜ ነው? +18 ለመሆኑ በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣አውሎ ነፋስም እንደሚወስደው እብቅ ሆነው ያውቃሉ? +19 አምላክ አንድ ሰው የሚደርስበትን ቅጣት ለገዛ ልጆቹ ያከማቻል። ይሁንና ሰውየው ያውቀው ዘንድ አምላክ ብድራቱን ይክፈለው።+ +20 የገዛ ዓይኖቹ የሚደርስበትን ጥፋት ይዩ፤ደግሞም ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ቁጣ ይጠጣ።+ +21 የወራቱ ቁጥር ቢያጥር፣*+እሱ ከሄደ በኋላ በቤቱ ላይ ስለሚደርሰው ነገር ምን ግድ ይሰጠዋል? +22 ከፍ ባሉት ላይ እንኳ የሚፈርደው አምላክ ሆኖ ሳለ፣+ለእሱ እውቀት ሊሰጠው* የሚችል ይኖራል?+ +23 አንድ ሰው ሙሉ ብርታት እያለው፣ተረጋግቶና ያላንዳች ጭንቀት እየኖረ ሳለ ይሞታል፤+ +24 ጭኑ በስብ ተሞልቶ፣አጥንቶቹም ጠንካራ ሆነው* እያለ በሞት ይለያል። +25 ሌላው ሰው ግን አንዳች ጥሩ ነገር ሳይቀምስ፣በጭንቀት እንደተዋጠ* ይሞታል። +26 ሁለቱም በአንድነት አፈር ውስጥ ይጋደማሉ፤+ትሎችም ይሸፍኗቸዋል።+ +27 እነሆ፣ እናንተ የምታስቡትን፣እኔንም ለመጉዳት* የጠነሰሳችሁትን ሴራ በሚገባ አውቃለሁ።+ +28 እናንተ ‘የተከበረው ሰው ቤት የት አለ?ክፉው ሰው የኖረበት ድንኳንስ የት አለ?’ ትላላችሁና።+ +29 መንገደኞችን አልጠየቃችሁም? እነሱ የሰጧቸውን አስተያየቶችስ* በሚገባ አልመረመራችሁም? +30 ክፉ ሰው በጥፋት ቀን ይተርፍ የለ?በቁጣስ ቀን ይድን የለ? +31 ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው?ለሠራውስ ነገር ብድራቱን የሚከፍለው ማን ነው? +32 እሱ ወደ መቃብር ቦታ ሲወሰድ፣መቃብሩ ጥበቃ ይደረግለታል። +33 የሸለቆ* ጓል ይጣፍጠዋል፤+ደግሞም ከእሱ በፊት እንደነበሩት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች ሁሉ፣የሰው ዘር በሙሉ ይከተለዋል።*+ +34 ታዲያ ትርጉም የለሽ ማጽናኛ የምትሰጡኝ ለምንድን ነው?+ የምትሰጡት መልስ ሁሉ ማታለያ ነው!” +15 ቴማናዊው ኤሊፋዝ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “ጥበበኛ ሰው ከንቱ በሆነ ንግግር* ይመልሳል?ወይስ በምሥራቅ ነፋስ ሆዱን ይሞላል? + 3 በማይረባ ቃል መውቀስ ምንም ዋጋ የለውም፤ደግሞም ወሬ ብቻውን ምንም ጥቅም የለውም። + 4 አንተ ፈሪሃ አምላክን ታጣጥላለህና፤ስለ አምላክ ማሰብም ዋጋ የለውም ትላለህ። + 5 በደልህ በምትናገረው ነገር ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል፤*ተንኮል ያዘለ ንግግር መናገርም ትመርጣለህ። + 6 እኔ ሳልሆን የገዛ አፍህ ይፈርድብሃል፤የገዛ ከንፈሮችህ ይመሠክሩብሃል።+ + 7 ለመሆኑ ከሰው ሁሉ በፊት የተወለድከው አንተ ነህ?ወይስ የተወለድከው ከኮረብቶች በፊት ነው? + 8 የአምላክን ሚስጥር ትሰማለህ?ወይስ ጥበብ ያለህ አንተ ብቻ ነህ? + 9 እኛ የማናውቀው አንተ ግን የምታውቀው ምን ነገር አለ?+ ደግሞስ እኛ የማናስተውለው አንተ ግን የምታስተውለው ምን ነገር አለ? +10 የሸበቱም ሆኑ በዕድሜ የገፉ፣እንዲሁም ከአባትህ በዕድሜ እጅግ የሚበልጡ ከእኛ ጋር አሉ።+ +11 የአምላክ ማጽናኛ፣ወይም በለሰለሰ አንደበት የተነገረህ ቃል አነሰህ? +12 ልብህ ለምን ይታበያል?ዓይኖችህስ ለምን በቁጣ ይጉረጠረጣሉ? +13 በአምላክ ላይ ተቆጥተሃልና፤እንዲህ ያሉ ቃላትም ከገዛ አፍህ ወጥተዋል። +14 ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች የሆነ ሰው ምንድን ነው?ወይስ ጻድቅ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ሰው ምንድን ነው?+ +15 እነሆ፣ በቅዱሳኑ* ላይ እምነት የለውም፤ሰማያትም እንኳ በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።+ +16 ታዲያ ክፋትን እንደ ውኃ የሚጠጣ፣አስጸያፊና ብልሹ የሆነ ሰውማ እንዴት ሊታመን ይችላል?+ +17 አዳምጠኝ! እኔ አሳውቅሃለሁ። ያየሁትን እናገራለሁ፤ +18 ጥበበኛ ሰዎች ከአባቶቻቸው ሰምተው የተናገሩትን፣+ደግሞም ከሌሎች ያልሸሸጉትን ነገር እነግርሃለሁ። +19 ምድሪቱ የተሰጠችው ለእነሱ ብቻ ነበር፤በመካከላቸውም ባዕድ ሰው አላለፈም። +20 ክፉ ሰው ዕድሜውን ሁሉ፣ለጨቋኙ በተመደቡት ዓመታት በሙሉ ይሠቃያል። +21 አስፈሪ ድምፆችን ይሰማል፤+በሰላም ጊዜ ወራሪዎች ጥቃት ይሰነዝሩበታል። +22 ከጨለማ እንደሚያመልጥ አያምንም፤+ሰይፍም ይጠብቀዋል። +23 ‘ወዴት ነው?’ እያለ ምግብ* ፍለጋ ይቅበዘበዛል፤ የጨለማ ቀን እንደደረሰ በሚገባ ያውቃል። +24 ጭንቀትና ሥቃይ ያሸብሩታል፤ጥቃት ለመሰንዘር እንደተዘጋጀ ንጉሥ ያይሉበታል። +25 በአምላክ ላይ እጁን ያነሳልና፤ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ለመገዳደርም* ይሞክራል፤ +26 ወፍራምና ጠንካራ ጋሻ* አንግቦ፣በእልኸኝነት እየገሰገሰ ይመጣበታል፤ +27 ፊቱ በስብ ተሸፍኗል፤ወገቡም በስብ ተወጥሯል፤ +28 በሚፈራርሱ ከተሞች፣ደግሞም ማንም በማይኖርባቸውናየድንጋይ ክምር በሚሆኑ ቤቶች ውስጥ ይኖራል። +29 ባለጸጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይከማችም፤ንብረቱም በምድሪቱ ላይ አይበረክትም። +30 ከጨለማ አያመልጥም፤ነበልባል ቅርንጫፉን ያደርቀዋል፤*ከአምላክም* አፍ በሚወጣ እስትንፋስ ይጠፋል።+ +31 መንገድ መሳትና ከንቱ በሆነ ነገር መታመን የለበትም፤በአጸፋው የሚያገኘው ነገር ዋጋ አይኖረውምና፤ +32 ቀኑ ከመድረሱ በፊት ይፈጸማል፤ቅርንጫፎቹም አይለመልሙም።+ +33 ያልበሰሉ ፍሬዎቹን እንደሚጥል የወይን ተክል፣አበቦቹን እንደሚያረግፍ የወይራ ዛፍም ይሆናል። +34 አምላክ የለሽ የሆኑ ሰዎች* ጉባኤ ይመክናልና፤+የጉቦ ድንኳኖችም እሳት ይበላቸዋል። +35 ችግር ይፀንሳሉ፤ ክፉ ነገርም ይወልዳሉ፤ማህፀናቸውም ተንኮል ያፈራል።” +22 ቴማናዊው ኤሊፋዝ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “ሰው አምላክን ሊጠቅመው ይችላል? ማስተዋል ያለውስ ሰው ምን ይፈይድለታል?+ + 3 ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ አንተ ጻድቅ መሆንህ ግድ ይሰጠዋል?*ወይስ በንጹሕ አቋም* መመላለስህ እሱን ይጠቅመዋል?+ + 4 አክብሮት* ስላሳየህ ይቀጣሃል?ደግሞስ ፍርድ ቤት ያቀርብሃል? + 5 ይህን የሚያደርገው የሠራኸው ክፋት ታላቅ ስለሆነ፣በደልህም ማብቂያ ስለሌለው አይደለም?+ + 6 ያላንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ ላይ መያዣ ትወስዳለህና፤ሰዎችንም ልብሳቸውን ገፈህ ራቁታቸውን ታስቀራለህ።*+ + 7 ለደከመው ሰው የሚጠጣ ውኃ አልሰጠህም፤የራበውንም ሰው ምግብ ነፍገሃል።+ + 8 ምድሪቱ የኃያል ሰው ንብረት ነች፤+የታደለም ሰው ይኖርባታል። + 9 አንተ ግን መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰደሃል፤አባት የሌላቸውንም ልጆች* ክንድ ሰብረሃል። +10 ከዚህም የተነሳ በወጥመድ ተከበሃል፤+ድንገተኛ ሽብርም ያስደነግጥሃል፤ +11 በመሆኑም ማየት እንዳትችል ጨለማ ውጦሃል፤ጎርፍም አጥለቅልቆሃል። +12 አምላክ የሚኖረው ከፍ ባለው ሰማይ አይደለም? በሰማያት ያሉ ከዋክብትም ሁሉ ምን ያህል ከፍ ያሉ እንደሆኑ ተመልከት። +13 አንተ ግን እንዲህ ብለሃል፦ ‘አምላክ ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሊፈርድ ይችላል? +14 በሰማይ ክበብ ላይ ሲራመድ፣ማየት እንዳይችል ደመናት ይጋርዱታል።’ +15 ክፉ ሰዎች የሄዱበትን፣የጥንቱን መንገድ ተከትለህ ትሄዳለህ? +16 እነሱ ጊዜያቸው ሳይደርስ ሞት ነጥቋቸዋል፤*መሠረታቸው በጎርፍ* ተጠራርጎ ሄዷል።+ +17 እውነተኛውን አምላክ ‘አትድረስብን!’ ደግሞም ‘ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በእኛ ላይ ምን ሊያደርግ ይችላል?’ ይላሉ። +18 ሆኖም ቤቶቻቸውን በመልካም ነገሮች የሞላው እሱ ነው። (እንዲህ ዓይነቱ ክፉ ሐሳብ ከእኔ ��ራቀ ነው።) +19 ጻድቅ ይህን አይቶ ይደሰታል፤ንጹሕ የሆነውም ሰው ይሳለቅባቸዋል፤ እንዲህም ይላቸዋል፦ +20 ‘ተቃዋሚዎቻችን ጠፍተዋል፤ከእነሱ የቀረውንም እሳት ይበላዋል።’ +21 እሱን እወቅ፤ ከእሱም ጋር ሰላም ይኖርሃል፤እንዲህ ካደረግክ መልካም ነገሮች ታገኛለህ። +22 ሕጉን ከአፉ ተቀበል፤ቃሉንም በልብህ አኑር።+ +23 ሁሉን ቻይ ወደሆነው አምላክ ብትመለስ ትታደሳለህ፤+ክፋትን ከድንኳንህ ብታርቅ፣ +24 ወርቅህን* አፈር ውስጥ፣የኦፊርንም ወርቅ+ ዓለታማ ሸለቆ* ውስጥ ብትጥል፣ +25 ያን ጊዜ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ወርቅና*ጥራት ያለው ብር ይሆንልሃል። +26 በዚህ ጊዜ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ደስ ትሰኛለህና፤ፊትህንም ወደ አምላክ ቀና ታደርጋለህ። +27 ትለምነዋለህ፤ እሱም ይሰማሃል፤ስእለትህንም ትፈጽማለህ። +28 ለማድረግ ያሰብከው ነገር ሁሉ ይሳካልሃል፤በመንገድህም ላይ ብርሃን ይበራል። +29 በእብሪት ስትናገር ትዋረዳለህና፤ትሑት የሆነውን* ግን ያድነዋል። +30 እሱ ንጹሕ የሆኑትን ያድናል፤ስለዚህ እጅህ ንጹሕ ከሆነ በእርግጥ ትድናለህ።” +42 ከዚያም ኢዮብ ለይሖዋ እንዲህ ሲል መለሰ፦ + 2 “አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል፣ደግሞም ያሰብከውን ነገር ሁሉ ማድረግ እንደማይሳንህ አሁን አወቅኩ።+ + 3 አንተ ‘ያለእውቀት ሐሳቤን የሚሰውር ይህ ማን ነው?’ አልክ።+ በመሆኑም ስለማላውቃቸው እጅግ ድንቅ የሆኑ ነገሮች+ማስተዋል በጎደለው መንገድ ተናግሬአለሁ። + 4 ‘እባክህ ስማኝ፤ እኔም እናገራለሁ። እጠይቅሃለሁ፤ አንተም ትነግረኛለህ’ አልከኝ።+ + 5 ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤አሁን ግን በገዛ ዓይኔ አየሁህ። + 6 ስለዚህ በተናገርኩት ነገር እጸጸታለሁ፤*+በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬም ንስሐ እገባለሁ።”+ +7 ይሖዋ ከኢዮብ ጋር ተነጋግሮ ካበቃ በኋላ፣ ቴማናዊውን ኤሊፋዝን ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ እውነቱን ስላልተናገራችሁ+ በአንተና በሁለቱ ጓደኞችህ+ ላይ ቁጣዬ ነዷል። +8 አሁን ሰባት ኮርማዎችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ ለራሳችሁም የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ። አገልጋዬ ኢዮብም ለእናንተ ይጸልያል።+ እንደ ሞኝነታችሁ እንዳላደርግባችሁ የእሱን ልመና እቀበላለሁ፤* አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ እውነቱን አልተናገራችሁምና።” +9 በመሆኑም ቴማናዊው ኤሊፋዝ፣ ሹሃዊው በልዳዶስና ናአማታዊው ሶፋር ሄደው ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ። ይሖዋም የኢዮብን ጸሎት ሰማ። +10 ኢዮብ ለጓደኞቹ ከጸለየ+ በኋላ ይሖዋ በኢዮብ ላይ የደረሰው መከራ+ እንዲያበቃ አደረገ፤ ደግሞም ብልጽግናውን መለሰለት።* ይሖዋ ለኢዮብ ቀድሞ የነበረውን እጥፍ አድርጎ ሰጠው።+ +11 ወንድሞቹና እህቶቹ ሁሉ እንዲሁም የቀድሞ ወዳጆቹ ሁሉ+ ወደ እሱ መጡ፤ በቤቱም ከእሱ ጋር ምግብ በሉ። ሐዘናቸውን ገለጹለት፤ እንዲሁም ይሖዋ በእሱ ላይ እንዲደርስበት ከፈቀደው መከራ ሁሉ አጽናኑት። እያንዳንዳቸውም የገንዘብ ስጦታና የወርቅ ጌጥ ሰጡት። +"12 በመሆኑም ይሖዋ ከፊተኛው የኢዮብ ሕይወት ይልቅ የኋለኛውን አብዝቶ ባረከ፤+ ኢዮብም 14,000 በጎች፣ 6,000 ግመሎች፣ 1,000 ጥማድ ከብቶችና 1,000 እንስት አህዮች አገኘ።+" +13 ደግሞም ሌሎች ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ወለደ።+ +14 የመጀመሪያዋን ሴት ልጁን ይሚማ፣ ሁለተኛዋን ቃስያ፣ ሦስተኛዋን ደግሞ ቄሬንሃጱክ ብሎ ስም አወጣላቸው። +15 በምድሪቱ ሁሉ የኢዮብን ሴቶች ልጆች ያህል የተዋቡ ሴቶች አልነበሩም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው። +16 ከዚህ በኋላ ኢዮብ 140 ዓመት ኖረ፤ እስከ አራት ትውልድም ድረስ ልጆችንና የልጅ ልጆችን አ���። +17 በመጨረሻም ኢዮብ ሸምግሎና ዕድሜ ጠግቦ ሞተ። +39 “የተራራ ፍየሎች የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህ?+ ርኤሞች* ግልገሎቻቸውን ሲወልዱ ተመልክተሃል?+ + 2 የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደሆነ መቁጠር ትችላለህ? የሚወልዱበትን ጊዜስ ታውቃለህ? + 3 ግልገሎቻቸውን ተንበርክከው ይወልዳሉ፤ከምጣቸውም ይገላገላሉ። + 4 ግልገሎቻቸው ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ይሄዳሉ፤ ወደ እነሱም አይመለሱም። + 5 የዱር አህያውን ነፃ የለቀቀው፣+የዱር አህያውን ከእስራቱ የፈታውስ ማን ነው? + 6 በረሃማው ሜዳ ቤቱ፣ጨዋማውም ምድር መኖሪያው እንዲሆን አደረግኩ። + 7 በከተማ ሁካታ ያፌዛል፤የነጂውንም ጩኸት አይሰማም። + 8 መሰማሪያ ለማግኘት በኮረብቶች ላይ ይቅበዘበዛል፤ማንኛውንም አረንጓዴ ተክል ይፈልጋል። + 9 የዱር በሬ አንተን ለማገልገል ፈቃደኛ ነው?+ በጋጣህ ውስጥ ያድራል? +10 የዱር በሬ ትልም እንዲያወጣልህ ልትጠምደው ትችላለህ?ወይስ እየተከተለህ ሸለቆውን ያርሳል?* +11 በብርቱ ጉልበቱ ትታመናለህ?ደግሞስ ከባዱን ሥራህን እንዲሠራልህ ታደርጋለህ? +12 እህልህን እንዲሰበስብልህ፣በአውድማህም ላይ እንዲያከማችልህ በእሱ ትታመናለህ? +13 የሰጎን ክንፍ በደስታ ይርገበገባል፤ይሁንና የራዛ*+ ዓይነት ክንፍና ላባ አላት? +14 እንቁላሎቿን መሬት ላይ ትጥላለች፤በአፈርም ውስጥ ታሞቃቸዋለች። +15 እግር ሊሰብራቸው፣የዱር አውሬም ሊረግጣቸው እንደሚችል አታስብም። +16 ልጆቿ የራሷ ያልሆኑ ይመስል ትጨክንባቸዋለች፤+ድካሜ ሁሉ ከንቱ ይሆናል የሚል ስጋት አያድርባትም። +17 አምላክ ጥበብ ነስቷታልና፤*ማስተዋልንም አልሰጣትም። +18 ተነስታ ክንፎቿን በምታርገበግብበት ጊዜ ግን፣በፈረሱና በፈረሰኛው ላይ ትስቃለች። +19 ለፈረስ ጉልበት የምትሰጠው አንተ ነህ?+ አንገቱንስ የሚርገፈገፍ ጋማ ታለብሰዋለህ? +20 እንደ አንበጣ እንዲዘል ልታደርገው ትችላለህ? የፉርፉርታው ግርማ አስፈሪ ነው።+ +21 የሸለቆውን መሬት ይጎደፍራል፤ ደግሞም በኃይል ይዘላል፤+ወደ ውጊያ ይገሰግሳል።*+ +22 በፍርሃት ላይ ይስቃል፤ የሚያስፈራውም ነገር የለም።+ ሰይፍ አይቶም ወደኋላ አይልም። +23 ኮሮጆው በጎኑ ይንኳኳል፤ጭሬውና ጦሩ ያብረቀርቃል። +24 በደስታ እየተርገፈገፈ ወደ ፊት ይሸመጥጣል፤*የቀንደ መለከት ድምፅ ሲሰማ ያቅበጠብጠዋል።* +25 ቀንደ መለከቱ ሲነፋ ‘እሰይ!’ ይላል፤ ጦርነቱን ከሩቅ ያሸታል፤ደግሞም የጦር አዛዦችን ጩኸትና ቀረርቶውን ይሰማል።+ +26 ሲላ ክንፎቹን ወደ ደቡብ ዘርግቶወደ ላይ የሚወነጨፈው በአንተ ማስተዋል ነው? +27 ወይስ ንስር ወደ ላይ የሚመጥቀው፣+ጎጆውንም ከፍ ባለ ቦታ ላይ የሚሠራው+ አንተ አዘኸው ነው? +28 በገደል ላይ ያድራል፤በገደሉ አፋፍ ላይ በሚገኝ ዓለታማ ምሽግ ውስጥ* ይኖራል። +29 በዚያም ሆኖ የሚበላውን ነገር ይፈልጋል፤+ዓይኖቹም እጅግ ሩቅ ወደሆነ ቦታ ይመለከታሉ። +30 ጫጩቶቹም ደም ይጠጣሉ፤በድን ባለበት ስፍራም ሁሉ ይገኛል።”+ +113 ያህን አወድሱ!* እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች፣ ውዳሴ አቅርቡ፤የይሖዋን ስም አወድሱ። + 2 ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣የይሖዋ ስም ይወደስ።+ + 3 ከፀሐይ መውጫ አንስቶ እስከ መግቢያው ድረስየይሖዋ ስም ይወደስ።+ + 4 ይሖዋ ከብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤+ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።+ + 5 ከፍ ባለ ቦታ እንደሚኖረው*እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው?+ + 6 ሰማይንና ምድርን ለማየት ወደ ታች ያጎነብሳል፤+ + 7 ችግረኛውን ከአፈር ያነሳል። ድሃውን ከአመድ ቁልል* ላይ ብድግ ያደርገዋል፤+ + 8 ይህም ከታላላቅ ሰዎች፣ይኸውም በሕዝቡ መካከል ካሉ ታላላቅ ሰዎች ጋር ያስቀምጠው ዘንድ ነው። + 9 መሃኒቱ ሴት��� ደስተኛ የልጆች* እናት+ ሆና እንድትኖርቤት ይሰጣታል። ያህን አወድሱ!* +81 ብርታታችን ለሆነው አምላክ+ እልል በሉ። ለያዕቆብ አምላክ በድል አድራጊነት ስሜት ጩኹ። + 2 ሙዚቃውን መጫወት ጀምሩ፤ አታሞም ምቱ፤ደስ የሚያሰኘውን በገና ከባለ አውታር መሣሪያ ጋር ተጫወቱ። + 3 አዲስ ጨረቃ በምትታይበት፣ሙሉ ጨረቃም ወጥታ በዓል በምናከብርበት ዕለት+ ቀንደ መለከት ንፉ።+ + 4 ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ድንጋጌ፣የያዕቆብም አምላክ ያስተላለፈው ውሳኔ ነውና።+ + 5 በግብፅ ምድር ላይ ባለፈ ጊዜ፣+ይህን ለዮሴፍ ማሳሰቢያ አድርጎ ሰጠው።+ እኔም የማላውቀውን ድምፅ* ሰማሁ፦ + 6 “ሸክሙን ከትከሻው ላይ አነሳሁለት፤+እጆቹ ቅርጫት ከመያዝ አረፉ። + 7 በጨነቀህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግኩህ፤+ከነጎድጓዳማው ደመና* መለስኩልህ።+ የመሪባ* ውኃዎች ባሉበት ስፍራ ፈተንኩህ።+ (ሴላ) + 8 ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ፤ እኔም እመሠክርብሃለሁ። እስራኤል ሆይ፣ ምነው ብታዳምጠኝ!+ + 9 በመካከልህ እንግዳ አምላክ አይኖርም፤ለባዕድ አምላክም አትሰግድም።+ +10 ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+ አፍህን በሰፊው ክፈት፤ እኔም በምግብ እሞላዋለሁ።+ +11 ሕዝቤ ግን ድምፄን አልሰማም፤እስራኤል ለእኔ አይገዛም።+ +12 በመሆኑም እልኸኛ ልባቸውን እንዲከተሉ ተውኳቸው፤ትክክል መስሎ የታያቸውን አደረጉ።*+ +13 ምነው ሕዝቤ ቢያዳምጠኝ ኖሮ!+ምነው እስራኤል በመንገዴ ቢመላለስ ኖሮ!+ +14 ጠላቶቻቸውን ወዲያውኑ ባንበረከክኋቸው፣እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ በሰነዘርኩ ነበር።+ +15 ይሖዋን የሚጠሉ በፊቱ ይሸማቀቃሉ፤የሚደርስባቸውም ነገር* ዘላለማዊ ነው። +16 እሱ ግን ምርጡን ስንዴ* ይመግባችኋል፤*+ከዓለት በሚገኝ ማርም ያጠግባችኋል።”+ +17 ይሖዋ ሆይ፣ ፍትሕ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ፤እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት በጥሞና አዳምጥ፤ያለምንም ማታለል ያቀረብኩትን ጸሎት ስማ።+ + 2 ለእኔ ስትል ፍትሐዊ ውሳኔ አድርግ፤+ዓይኖችህ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ይዩ። + 3 ልቤን መረመርክ፤ በሌሊት በሚገባ አጤንከኝ፤+ደግሞም አጠራኸኝ፤+አንዳች መጥፎ ነገር እንዳላሰብኩ ታውቃለህ፤አንደበቴም አልበደለም። + 4 የሰዎችን ሥራ በተመለከተ ደግሞ፣የከንፈርህን ቃል በማክበር ከዘራፊዎች መንገድ ርቄአለሁ።+ + 5 እግሮቼ እንዳይደነቃቀፉ፣አረማመዴ በመንገድህ ላይ ይጽና።+ + 6 አምላክ ሆይ፣ መልስ ስለምትሰጠኝ አንተን እጣራለሁ።+ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል።* ቃሌን ስማ።+ + 7 በቀኝ እጅህ እንድትጠብቃቸው የሚሹትን፣በአንተ ላይ ከሚያምፁ ሰዎች የምታድን ሆይ፣ታማኝ ፍቅርህን ድንቅ በሆነ መንገድ አሳይ።+ + 8 እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤+በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ።+ + 9 ጥቃት ከሚሰነዝሩብኝ ክፉዎች፣ከሚከቡኝና ሊገድሉኝ ከሚፈልጉ ጠላቶቼ* ጠብቀኝ።+ +10 ደንታ ቢሶች ሆነዋል፤*በአፋቸው በእብሪት ይናገራሉ፤ +11 መፈናፈኛ አሳጡን፤+እኛን መጣል* የሚችሉበትን አጋጣሚ ነቅተው ይጠባበቃሉ። +12 እያንዳንዳቸው ያደነውን ለመዘነጣጠል እንደሚጓጓ አንበሳ፣በስውር እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው። +13 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስተህ ፊት ለፊት ግጠመው፤+ ደግሞም ጣለው፤በሰይፍህ ከክፉው ሰው ታደገኝ፤* +14 ይሖዋ ሆይ፣ ከዚህ ዓለም* ሰዎች በእጅህ ታደገኝ፤እነዚህ ሰዎች ድርሻቸው አሁን ያለው ሕይወት ነው፤+አንተ በሰጠሃቸው መልካም ነገሮች አጥግበሃቸዋል፤+ደግሞም ለብዙ ወንዶች ልጆቻቸው ርስት ያስተላልፋሉ። +15 እኔ ግን ፊትህን በጽድቅ አያለሁ፤በምነቃበት ጊዜ አንተን በማየት እደሰታለሁ።+ +60 አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ አድርገኸናል፤ መከላከያዎቻችንን ጥሰህ አልፈሃል።+ ተቆጥተኸናል፤ አሁን ግን መልሰህ ተቀበለን! + 2 ምድርን አናወጥካት፤ ሰነጣጠቅካት። እየፈራረሰች ነውና ስንጥቆቿን ጠግን። + 3 ሕዝብህ መከራ እንዲደርስበት አደረግክ። የወይን ጠጅ እንድንጠጣና እንድንንገዳገድ አደረግከን።+ + 4 አንተን የሚፈሩ ከቀስት መሸሽና ማምለጥ እንዲችሉምልክት አቁምላቸው።* (ሴላ) + 5 የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑበቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠን።+ + 6 አምላክ በቅድስናው* እንዲህ ብሏል፦ “ሐሴት አደርጋለሁ፤ ሴኬምን ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤+የሱኮትንም ሸለቆ* አከፋፍላለሁ።+ + 7 ጊልያድም ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤+ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤*ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው።+ + 8 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው።+ በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ።+ በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”+ + 9 ወደተከበበችው* ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል?+ +10 አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም።+ +11 ከጭንቅ እንድንገላገል እርዳን፤የሰው ማዳን ከንቱ ነውና።+ +12 አምላክ ኃይል ይሰጠናል፤+ጠላቶቻችንንም ይረጋግጣቸዋል።+ +30 ይሖዋ ሆይ፣ ወደ ላይ ስላነሳኸኝ* ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ጠላቶቼ በእኔ ሥቃይ እንዲደሰቱ አልፈቀድክም።+ + 2 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ፈወስከኝ።+ + 3 ይሖዋ ሆይ፣ ከመቃብር* አውጥተኸኛል።*+ በሕይወት አቆይተኸኛል፤ ወደ ጉድጓድ* ከመውረድ አድነኸኛል።+ + 4 እናንተ የእሱ ታማኝ አገልጋዮች፣ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤+ለቅዱስ ስሙ*+ ምስጋና አቅርቡ፤ + 5 ምክንያቱም የሚቆጣው ለአጭር ጊዜ ነው፤+ሞገስ የሚያሳየው* ግን ለዕድሜ ልክ ነው።+ ማታ ለቅሶ ቢሆንም ጠዋት ግን እልልታ ይሆናል።+ + 6 በተረጋጋሁ ጊዜ “ፈጽሞ አልናወጥም”* አልኩ። + 7 ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ ባሳየኸኝ ጊዜ እንደ ተራራ አጠነከርከኝ።+ ፊትህን በሰወርክ ጊዜ ግን ተሸበርኩ።+ + 8 ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ ደጋግሜ ተጣራሁ፤+ሞገስ ለማግኘትም ይሖዋን አብዝቼ ተማጸንኩ። + 9 መሞቴና* ወደ ጉድጓድ* መውረዴ+ ምን የሚያስገኘው ጥቅም አለ? አፈር ያወድስሃል?+ የአንተንስ ታማኝነት ይናገራል?+ +10 ይሖዋ ሆይ፣ ስማኝ፤ ሞገስም አሳየኝ።+ ይሖዋ ሆይ፣ ረዳቴ ሁን።+ +11 ሐዘኔን ወደ ጭፈራ ለወጥክ፤ማቄን አውልቀህ ደስታን አለበስከኝ፤ +12 ይህም እኔ* ዝም ከማለት ይልቅ ለአንተ የውዳሴ መዝሙር እዘምር ዘንድ ነው። ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ለዘላለም አወድስሃለሁ። +35 ይሖዋ ሆይ፣ ባላጋራዎቼን በመቃወም ተሟገትልኝ፤+የሚዋጉኝን ተዋጋቸው።+ + 2 ትንሹንና* ትልቁን ጋሻህን ያዝ፤+ለእኔ ለመከላከልም ተነስ።+ + 3 በሚያሳድዱኝ ላይ ጦርና መጥረቢያ* አንሳ።+ “የማድንህ እኔ ነኝ” በለኝ።*+ + 4 ሕይወቴን* የሚሹ ይፈሩ፤ ይዋረዱም።+ እኔን ለማጥፋት የሚያሴሩ ተዋርደው ያፈግፍጉ። + 5 በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ ይሁኑ፤የይሖዋ መልአክም ያባርራቸው።+ + 6 የይሖዋ መልአክ ሲያሳድዳቸውመንገዳቸው በጨለማ የተዋጠና የሚያዳልጥ ይሁን። + 7 ያላንዳች ምክንያት እኔን ለማጥመድ በስውር መረብ ዘርግተዋልና፤ያላንዳች ምክንያት ጉድጓድ ቆፍረውልኛል።* + 8 ሳያስቡት ጥፋት ይምጣባቸው፤በስውር ያስቀመጡት መረብም እነሱኑ ይያዛቸው፤እዚያም ውስጥ ወድቀው ይጥፉ።+ + 9 እኔ ግን በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ፤*በማዳን ሥራውም እጅግ ደስ ይለኛል። +10 አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይላሉ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? ምስኪኑን ብርቱ ከሆኑት፣ምስኪኑንና ድሃውን ከሚዘርፏቸው ሰዎች ትታደጋለህ።”+ +11 ክፉ ምሥክሮች ቀረቡ፤+ምንም ስለማላውቀው ነገር ጠየቁኝ። +12 ለመልካም ነገር ��ፉ መለሱልኝ፤+ደግሞም ሐዘን ላይ ጣሉኝ።* +13 እኔ ግን እነሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኩ፤ራሴን* በጾም አጎሳቆልኩ፤ጸሎቴም መልስ ሳያገኝ በተመለሰ ጊዜ፣* +14 ለጓደኛዬ ወይም ለወንድሜ እንደማደርገው እየተንቆራጠጥኩ አለቀስኩ፤እናቱ ሞታበት እንደሚያለቅስ ሰው አንገቴን በሐዘን ደፋሁ። +15 እኔ ስደናቀፍ ግን እነሱ ደስ ብሏቸው ተሰበሰቡ፤አድብተው እኔን ለመምታት ተሰበሰቡ፤ዘነጣጠሉኝ፤ በነገር መጎንተላቸውንም አልተዉም። +16 ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች በንቀት ያፌዙብኛል፤*በእኔ ላይ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ።+ +17 ይሖዋ ሆይ፣ ዝም ብለህ የምታየው እስከ መቼ ነው?+ ከሚሰነዝሩብኝ ጥቃት ታደገኝ፤*+ውድ ሕይወቴን* ከደቦል አንበሶች አድናት።+ +18 ያን ጊዜ በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ፤+በብዙ ሕዝብ መካከል አወድስሃለሁ። +19 ያላንዳች ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ እኔን አይተው እንዲፈነድቁ፣ያለምክንያት የሚጠሉኝ+ በተንኮል እንዲጠቃቀሱብኝ አትፍቀድ።+ +20 የሰላም ቃል ከአፋቸው አይወጣምና፤ከዚህ ይልቅ በምድሪቱ በሰላም በሚኖሩት ላይ ተንኮል ይሸርባሉ።+ +21 እኔን ለመወንጀል አፋቸውን ይከፍታሉ፤“እሰይ! እሰይ! ዓይናችን ይህን አየ” ይላሉ። +22 ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ተመልክተሃል። ዝም አትበል።+ ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+ +23 ለእኔ ጥብቅና ለመቆም ንቃ፤ ተነሳም፤ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ተሟገትልኝ። +24 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፤+በእኔ እንዲፈነድቁ አትፍቀድ። +25 በልባቸው “እሰይ! የተመኘነውን አገኘን”* አይበሉ። ደግሞም “ዋጥነው” አይበሉ።+ +26 እኔ ላይ በደረሰው ጉዳት የሚፈነድቁ ሁሉይፈሩ፣ ይዋረዱም። በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ። +27 በእኔ ጽድቅ የሚደሰቱ ግን እልል ይበሉ፤ሁልጊዜም እንዲህ ይበሉ፦ “በአገልጋዩ ሰላም የሚደሰተው ይሖዋ ከፍ ከፍ ይበል።”+ +28 በዚህ ጊዜ ምላሴ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤*+ቀኑን ሙሉም ያወድስሃል።+ +95 ኑ፣ ለይሖዋ እልል እንበል! አዳኛችን ለሆነው ዓለት በድል አድራጊነት ስሜት እልል እንበል።+ + 2 ምስጋና ይዘን በፊቱ እንቅረብ፤+በድል አድራጊነት ስሜት ለእሱ እንዘምር፤ ደግሞም እልል እንበል። + 3 ይሖዋ ታላቅ አምላክ ነውና፤በሌሎች አማልክት ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።+ + 4 ጥልቅ የሆኑት የምድር ክፍሎች በእጁ ናቸው፤የተራሮችም ጫፍ የእሱ ነው።+ + 5 እሱ የሠራው ባሕር የራሱ ነው፤+የብሱንም የሠሩት እጆቹ ናቸው።+ + 6 ኑ፣ እናምልክ፤ እንስገድም፤ሠሪያችን በሆነው በይሖዋ ፊት እንንበርከክ።+ + 7 እሱ አምላካችን ነውና፤እኛ ደግሞ በመስኩ የተሰማራን ሕዝቦች፣በእሱ እንክብካቤ* ሥር ያለን በጎች ነን።+ ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ፣+ + 8 አባቶቻችሁ በምድረ በዳ ሳሉ በመሪባ፣*በማሳህ* ቀን እንዳደረጉት ልባችሁን አታደንድኑ፤+ + 9 በዚያን ጊዜ እነሱ ፈተኑኝ፤+ሥራዬን ቢያዩም ተገዳደሩኝ።+ +10 ያን ትውልድ ለ40 ዓመት ተጸየፍኩት፤እኔም “ይህ ሕዝብ ሁልጊዜ ልቡ ይስታል፤መንገዴን ሊያውቅ አልቻለም” አልኩ። +11 በመሆኑም “ወደ እረፍቴ አይገቡም” ብዬ በቁጣዬ ማልኩ።+ +31 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።+ ፈጽሞ አልፈር።+ ከጽድቅህ የተነሳ ታደገኝ።+ + 2 ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል።* ፈጥነህ ታደገኝ።+ እኔን ለማዳን በተራራ ላይ ያለ ምሽግ፣የተመሸገ ስፍራም ሁንልኝ።+ + 3 አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ነህና፤+ለስምህ ስትል+ ትመራኛለህ፤ የምሄድበትንም መንገድ ታሳየኛለህ።+ + 4 አንተ መሸሸጊያዬ ስለሆንክ፣+እነሱ በስውር ከዘረጉብኝ ወጥመድ ታስጥለኛለህ።+ + 5 መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ።+ የእውነት* አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+ ዋጅተኸኛል። + 6 የማይረቡና ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችን የሚያመልኩ ሰዎችን እጠላለሁ፤እኔ ግን በይሖዋ እታመናለሁ። + 7 በታማኝ ፍቅርህ እጅግ ሐሴት አደርጋለሁ፤ጉስቁልናዬን አይተሃልና፤+በጭንቀት መዋጤን* ታውቃለህ። + 8 ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ይልቁንም ደህንነት በማገኝበት ስፍራ አቆምከኝ።* + 9 ይሖዋ ሆይ፣ በጭንቀት ስለተዋጥኩ ሞገስ አሳየኝ። መከራ ዓይኔንም ሆነ መላ ሰውነቴን አድክሞታል።*+ +10 ሕይወቴ በሐዘን፣ዕድሜዬም በመቃተት አልቋል።+ ከፈጸምኩት ኃጢአት የተነሳ ጉልበቴ ተሟጠጠ፤አጥንቶቼ ደከሙ።+ +11 ባላጋራዎቼ ሁሉ፣በተለይ ደግሞ ጎረቤቶቼ ተሳለቁብኝ።+ የሚያውቁኝ ሰዎችም እጅግ ፈሩኝ፤በአደባባይ ሲያዩኝ ከእኔ ይሸሻሉ።+ +12 የሞትኩ ያህል ከልባቸው ወጣሁ፤* ደግሞም ተረሳሁ፤እንደተሰበረ ማሰሮ ነኝ። +13 ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁ፤ሽብር ከቦኛል።+ ግንባር ፈጥረው በእኔ ላይ በተነሱ ጊዜሕይወቴን* ለማጥፋት ያሴራሉ።+ +14 ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።+ “አንተ አምላኬ ነህ” እላለሁ።+ +15 የሕይወት ዘመኔ በእጅህ ነው። ከጠላቶቼና ከሚያሳድዱኝ እጅ ታደገኝ።+ +16 ፊትህ በአገልጋይህ ላይ እንዲበራ አድርግ።+ በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ። +17 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በጠራሁ ጊዜ አልፈር።+ ክፉዎች ግን ይፈሩ፤+በመቃብር* ውስጥ ዝም ይበሉ።+ +18 በትዕቢትና በንቀት በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩሐሰተኛ ከንፈሮች ዱዳ ይሁኑ።+ +19 ጥሩነትህ ምንኛ ብዙ ነው!+ አንተን ለሚፈሩ ጠብቀህ አቆይተኸዋል፤+እንዲሁም አንተን መጠጊያ ለሚያደርጉ ስትል በሰዎች ሁሉ ፊት አሳይተኸዋል።+ +20 አንተ ባለህበት ሚስጥራዊ ቦታ፣ከሰዎች ሴራ ትሸሽጋቸዋለህ፤+በመጠለያህ ውስጥከክፉ ጥቃት* ትሰውራቸዋለህ።+ +21 በተከበበ ከተማ ውስጥ+ ታማኝ ፍቅሩን በአስደናቂ ሁኔታ ስላሳየኝ+ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን። +22 እኔ በድንጋጤ ተውጬ “ከፊትህ መጥፋቴ ነው” አልኩ።+ አንተ ግን እርዳታ ለማግኘት በጮኽኩ ጊዜ ልመናዬን ሰማህ።+ +23 እናንተ ለእሱ ታማኝ የሆናችሁ ሁሉ፣ ይሖዋን ውደዱ!+ ይሖዋ ታማኞችን ይጠብቃል፤+ትዕቢተኛ የሆነን ሰው ግን ክፉኛ ይቀጣል።+ +24 እናንተ ይሖዋን የምትጠባበቁ ሁሉ፣+ደፋር ሁኑ፤ ልባችሁም ይጽና።+ +18 ብርታቴ ይሖዋ ሆይ፣+ እወድሃለሁ። + 2 ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው።+ አምላኬ የምሸሸግበት ዓለቴ ነው፤+ጋሻዬ፣ የመዳኔ ቀንድና* አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው።+ + 3 ውዳሴ የሚገባውን ይሖዋን እጠራለሁ፤ከጠላቶቼም እድናለሁ።+ + 4 የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤+የማይረቡ ሰዎች የለቀቁት ድንገተኛ ጎርፍ አሸበረኝ።+ + 5 የመቃብር* ገመድ ተጠመጠመብኝ፤የሞት ወጥመድ ተጋረጠብኝ።+ + 6 በጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ይሖዋን ጠራሁት፤እርዳታ ለማግኘት አምላኬን አጥብቄ ተማጸንኩት። በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፤+እርዳታ ለማግኘት የማሰማውም ጩኸት ወደ ጆሮው ደረሰ።+ + 7 ምድርም ትንቀጠቀጥና ትናወጥ ጀመር፤+የተራሮች መሠረቶች ተንቀጠቀጡ፤እሱ ስለተቆጣም ራዱ።+ + 8 ከአፍንጫው ጭስ ወጣ፤የሚባላም እሳት ከአፉ ወጣ፤+ፍምም ከእሱ ፈለቀ። + 9 ወደ ታች ሲወርድ ሰማያት እንዲያጎነብሱ አደረገ፤+ከእግሮቹም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር።+ +10 በኪሩብ ላይ ተቀምጦ እየበረረ መጣ።+ በመንፈስ* ክንፎች በፍጥነት ወረደ።+ +11 ከዚያም በጨለማ ራሱን ሸፈነ፤+ጥቁር ውኃና ጥቅጥቅ ያለ ደመና+እንደ መጠለያ በዙሪያው ነበር። +12 በፊቱ ካለው ብርሃን፣ከደመናቱ መካከል በረዶና ፍም ወጣ። +13 ከዚያም ይሖዋ በሰማያት ያንጎደጉድ ጀመር፤+ልዑሉ አምላክ ድምፁን አሰማ፤+ደግሞም በረዶና ፍም ነበር። +14 ፍላጻዎቹን አስፈንጥሮ በታተናቸው፤+መብረቁን አዥጎድጉዶ ግራ አጋባቸው።+ +15 ይሖዋ ሆይ፣ ከተግሣጽህ፣ ከአፍንጫህም ከሚወጣው ኃይለኛ እስትንፋስ የተነሳ+የጅረቶች ወለል ታየ፤*+የምድር መሠረቶችም ተገለጡ። +16 ከላይ ሆኖ እጁን ሰደደ፤ከጥልቅ ውኃ ውስጥም አወጣኝ።+ +17 ከብርቱ ጠላቴ አዳነኝ፤+ከእኔ ይበልጥ ብርቱዎች ከሆኑት፣ ከሚጠሉኝ ሰዎች ታደገኝ።+ +18 ችግር ላይ በወደቅኩበት ቀን ተነሱብኝ፤+ይሖዋ ግን ድጋፍ ሆነልኝ። +19 ከዚያም ደህንነት ወደማገኝበት ስፍራ* አመጣኝ፤በእኔ ስለተደሰተ ታደገኝ።+ +20 ይሖዋ እንደ ጽድቄ ወሮታ ይከፍለኛል፤+እንደ እጄ ንጽሕና ብድራት ይመልስልኛል።+ +21 የይሖዋን መንገድ ጠብቄአለሁና፤አምላኬን በመተው ክፉ ድርጊት አልፈጸምኩም። +22 ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነው፤ደንቦቹን ቸል አልልም። +23 በፊቱ እንከን የለሽ ሆኜ እኖራለሁ፤+ራሴንም ከስህተት እጠብቃለሁ።+ +24 ይሖዋ እንደ ጽድቄ፣+በፊቱ ንጹሕ እንደሆኑት እጆቼ ብድራት ይመልስልኝ።+ +25 ታማኝ ለሆነ ሰው ታማኝ ትሆናለህ፤+እንከን የለሽ ለሆነ ሰው እንከን የለሽ ትሆናለህ፤+ +26 ከንጹሕ ሰው ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤+ጠማማ ለሆነ ሰው ግን ብልህ መሆንህን ታሳያለህ።+ +27 ችግረኞችን* ታድናለህና፤+ትዕቢተኛውን* ግን ታዋርዳለህ።+ +28 ይሖዋ ሆይ፣ መብራቴን የምታበራው አንተ ነህና፤አምላኬ ሆይ፣ ጨለማዬን ብርሃን የምታደርገው አንተ ነህ።+ +29 በአንተ እርዳታ ወራሪውን ቡድን መጋፈጥ እችላለሁ፤+በአምላክ ኃይል ቅጥር መውጣት እችላለሁ።+ +30 የእውነተኛው አምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤+የይሖዋ ቃል የነጠረ ነው።+ እሱ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው።+ +31 ደግሞስ ከይሖዋ ሌላ አምላክ ማን ነው?+ ከአምላካችንስ ሌላ ዓለት ማን ነው?+ +32 ብርታትን የሚያስታጥቀኝ እውነተኛው አምላክ ነው፤+መንገዴንም ፍጹም ያደርግልኛል።+ +33 እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤በከፍታ ቦታዎች ላይ ያቆመኛል።+ +34 እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ክንዶቼ የመዳብ ደጋን ማጠፍ ይችላሉ። +35 የመዳን ጋሻህን ትሰጠኛለህ፤+ቀኝ እጅህ ይደግፈኛል፤ትሕትናህም ታላቅ ያደርገኛል።+ +36 ለእርምጃዬ መንገዱን ታሰፋልኛለህ፤እግሮቼ* አያዳልጣቸውም።+ +37 ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ተጠራርገው እስኪጠፉ ድረስ ወደ ኋላ አልመለስም። +38 እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቃቸዋለሁ፤+እግሬ ሥር ይወድቃሉ። +39 ለውጊያው ብርታት ታስታጥቀኛለህ፤ጠላቶቼ ሥሬ እንዲወድቁ ታደርጋለህ።+ +40 ጠላቶቼ ከእኔ እንዲሸሹ ታደርጋለህ፤*እኔም የሚጠሉኝን አጠፋቸዋለሁ።*+ +41 እርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ ሆኖም የሚያድናቸው የለም፤ወደ ይሖዋም ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስላቸውም። +42 በነፋስ ፊት እንዳለ አቧራ ፈጽሜ አደቃቸዋለሁ፤በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ አውጥቼ እጥላቸዋለሁ። +43 ስህተት ከሚለቃቅሙ ሰዎች ታድነኛለህ።+ የብሔራት መሪ አድርገህ ትሾመኛለህ።+ የማላውቀው ሕዝብ ያገለግለኛል።+ +44 ስለ እኔ በሰሙት ነገር ብቻ ይታዘዙኛል፤የባዕድ አገር ሰዎችም አንገታቸውን ደፍተው ወደ ፊቴ ይቀርባሉ።+ +45 የባዕድ አገር ሰዎች ወኔ ይከዳቸዋል፤*ከምሽጎቻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ። +46 ይሖዋ ሕያው ነው! ዓለቴ+ ይወደስ! የመዳኔ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።+ +47 እውነተኛው አምላክ ይበቀልልኛል፤+ሕዝቦችንም ከበታቼ ያስገዛልኛል። +48 በቁጣ ከተሞሉ ጠላቶቼ ይታደገኛል፤ከሚያጠቁኝ ሰዎች በላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤+ከዓመፀኛ ሰው ታድነኛለህ። +49 ይሖዋ ሆይ፣ በብሔራት መካከል የማከብርህ ለዚህ ነው፤+ለስምህም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+ +50 እሱ ለንጉሡ ታላላቅ የማዳን ሥራዎች ያከናውናል፤*+ለቀባውም ታማኝ ፍቅር ያሳያል፤+ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይህን ያደርጋል።+ +100 ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለይሖዋ እልል በሉ።+ + 2 ይሖዋን በደስታ አገልግሉት።+ በእልልታ ወደ ፊቱ ቅረቡ። + 3 ይሖዋ፣ አምላክ መሆኑን እወቁ።*+ የሠራን እሱ ነው፤ እኛም የእሱ ንብረት ነን።*+ እኛ ሕዝቡና የማሰማሪያው በጎች ነን።+ + 4 በምስጋና ወደ በሮቹ፣በውዳሴም ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ።+ ምስጋና አቅርቡለት፤ ስሙንም አወድሱ።+ + 5 ይሖዋ ጥሩ ነውና፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም፣ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።+ +23 ይሖዋ እረኛዬ ነው።+ የሚጎድልብኝ ነገር የለም።+ + 2 በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤ውኃ ወዳለበት የእረፍት ቦታም* ይመራኛል።+ + 3 ኃይሌን* ያድሳል።+ ለስሙ ሲል በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።+ + 4 ድቅድቅ ጨለማ በዋጠው ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ+አንተ ከእኔ ጋር ስለሆንክ፣+ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፤+በትርህና ምርኩዝህ ያበረታቱኛል።* + 5 በጠላቶቼ ፊት ማዕድ አዘጋጀህልኝ።+ ራሴን በዘይት ቀባህ፤+ጽዋዬ ጢም ብሎ ሞልቷል።+ + 6 ጥሩነትህና ታማኝ ፍቅርህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፤+ዕድሜዬንም በሙሉ በይሖዋ ቤት እኖራለሁ።+ +34 ይሖዋን ሁልጊዜ አወድሰዋለሁ፤ውዳሴው ምንጊዜም ከአፌ አይለይም። + 2 በይሖዋ እኩራራለሁ፤*+የዋሆች ሰምተው ሐሴት ያደርጋሉ። + 3 ይሖዋን ከእኔ ጋር አወድሱት፤+በኅብረት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ። + 4 ይሖዋን ጠየቅኩት፤ እሱም መለሰልኝ።+ ከምፈራው ነገር ሁሉ ታደገኝ።+ + 5 እሱን ተስፋ ያደረጉ በደስታ ፈኩ፤ፊታቸው ፈጽሞ ለኀፍረት አይዳረግም። + 6 ይህ ችግረኛ ተጣራ፤ ይሖዋም ሰማው። ከጭንቀቱ ሁሉ ገላገለው።+ + 7 የይሖዋ መልአክ አምላክን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፤+ደግሞም ይታደጋቸዋል።+ + 8 ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም፤+እሱን መጠጊያ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው። + 9 ቅዱሳን አገልጋዮቹ ሁሉ፣ ይሖዋን ፍሩ፤እሱን የሚፈሩ የሚያጡት ነገር የለምና።+ +10 ብርቱ ደቦል አንበሶች እንኳ የሚበሉት አጥተው ይራባሉ፤ይሖዋን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጎድልባቸውም።+ +11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፣ አዳምጡኝ፤ይሖዋን መፍራት አስተምራችኋለሁ።+ +12 ከእናንተ መካከል በሕይወት የሚደሰት፣ብዙ መልካም ዘመን ማየት የሚወድስ ማን ነው?+ +13 እንግዲያው ምላስህን ከክፉ ነገር ጠብቅ፤+በከንፈሮችህም ከማታለል ተቆጠብ።+ +14 ክፉ ከሆነ ነገር ራቅ፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤+ሰላምን ፈልግ፤ ተከተለውም።+ +15 የይሖዋ ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉ፤+ጆሮዎቹም እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትን ጩኸት ይሰማሉ።+ +16 ሆኖም የክፉዎችን መታሰቢያ ሁሉ ከምድር ለማጥፋት፣የይሖዋ ፊት በእነሱ ላይ ነው።+ +17 ጻድቃን ጮኹ፤ ይሖዋም ሰማቸው፤+ከጭንቀታቸውም ሁሉ ገላገላቸው።+ +18 ይሖዋ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤+መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውንም* ያድናል።+ +19 የጻድቅ ሰው መከራ* ብዙ ነው፤+ይሖዋ ግን ከመከራው ሁሉ ይታደገዋል።+ +20 አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።+ +21 ክፉ ሰው በአደጋ ይሞታል፤ጻድቁን የሚጠሉ ሰዎችም ይፈረድባቸዋል። +22 ይሖዋ የአገልጋዮቹን ሕይወት* ይዋጃል፤እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ አይፈረድባቸውም።+ +19 ሰማያት የአምላክን ክብር ይናገራሉ፤+ጠፈርም የእጆቹን ሥራ ያውጃል።+ + 2 በየዕለቱ ንግግራቸው ይሰማል፤በእያንዳንዱም ሌሊት እውቀትን ይገልጣሉ። + 3 ንግግር የለም፤ ቃልም የለም፤ድምፃቸው አይሰማም። + 4 ይሁንና ጩኸታቸው* ወደ መላው ምድር ወጣ፤መልእክታቸውም እስከ ዓለም* ዳርቻዎች ተሰማ።+ እሱ በሰማያት ለፀሐይ ድንኳን ተክሏል፤ + 5 ፀሐይም ከጫጉላ ቤት እንደሚወጣ ሙሽራ ነው፤በጎዳናው ላይ እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል። + 6 ከአንደኛው የሰማያት ዳር�� ይወጣል፤ዞሮም ወደ ሌላኛው ዳርቻ ይሄዳል፤+ከሙቀቱም የሚሰወር አንዳች ነገር የለም። + 7 የይሖዋ ሕግ ፍጹም ነው፤+ ኃይልን ያድሳል።*+ የይሖዋ ማሳሰቢያ አስተማማኝ ነው፤+ ተሞክሮ የሌለውን ጥበበኛ ያደርጋል።+ + 8 የይሖዋ መመሪያዎች ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ፤+የይሖዋ ትእዛዝ ንጹሕ ነው፤ ዓይንን ያበራል።+ + 9 ይሖዋን መፍራት+ ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል። የይሖዋ ፍርዶች እውነት ናቸው፤ ሙሉ በሙሉ ትክክል ናቸው።+ +10 ከወርቅ እንዲያውም ብዛት ካለው ምርጥ ወርቅ*የበለጠ የሚወደዱ ናቸው፤+ደግሞም ከማርና ከማር እንጀራ ከሚንጠባጠብ ወለላ ይበልጥ ይጣፍጣሉ።+ +11 ለአገልጋይህ ማስጠንቀቂያ ሆነውለታል፤+እነሱን መጠበቅ ትልቅ ወሮታ አለው።+ +12 የራሱን ስህተት ማን ሊያስተውል ይችላል?+ ሳላውቅ የሠራኋቸውን ኃጢአቶች አትቁጠርብኝ። +13 አገልጋይህንም ከእብሪት ድርጊቶች ጠብቀው፤+እንዲቆጣጠሩኝም አትፍቀድ።+ ያን ጊዜ እንከን የሌለብኝ እሆናለሁ፤+ዓይን ካወጣ ኃጢአትም* ነፃ እሆናለሁ። +14 ዓለቴና+ አዳኜ+ ይሖዋ ሆይ፣ የአፌ ቃልና በልቤ የማሰላስለው ነገርአንተን ደስ የሚያሰኝ ይሁን።+ +118 ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። + 2 እስራኤል እንዲህ ይበል፦ “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” + 3 ከአሮን ቤት የሆኑ እንዲህ ይበሉ፦ “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” + 4 ይሖዋን የሚፈሩ እንዲህ ይበሉ፦ “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” + 5 በተጨነቅኩ ጊዜ ያህን* ተጣራሁ፤ያህም መለሰልኝ፤ ደህንነት ወደማገኝበት ስፍራም* አመጣኝ።+ + 6 ይሖዋ ከጎኔ ነው፤ አልፈራም።+ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+ + 7 ይሖዋ ረዳቴ ሆኖ* ከጎኔ አለ፤+የሚጠሉኝን ሰዎች በድል አድራጊነት እመለከታለሁ።+ + 8 በሰው ከመታመን ይልቅ፣ይሖዋን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል።+ + 9 በመኳንንት ከመታመን ይልቅ፣ይሖዋን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል።+ +10 ብሔራት ሁሉ ከበቡኝ፤እኔ ግን በይሖዋ ስምመከትኳቸው።+ +11 ከበቡኝ፤ አዎ፣ ዙሪያዬን ከበቡኝ፤እኔ ግን በይሖዋ ስምመከትኳቸው። +12 እንደ ንብ ከበቡኝ፤ሆኖም በእሳት እንደተያያዘ ቁጥቋጦ ወዲያውኑ ጠፉ። እኔም በይሖዋ ስምመከትኳቸው።+ +13 እወድቅ ዘንድ በኃይል ተገፋሁ፤*ይሖዋ ግን ረዳኝ። +14 ያህ መጠለያዬና ብርታቴ ነው፤አዳኝም ሆኖልኛል።+ +15 በጻድቃን ድንኳኖች ውስጥ፣የሐሴትና የመዳን* ድምፅ ይሰማል። የይሖዋ ቀኝ እጅ ኃይሉን ያሳያል።+ +16 የይሖዋ ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለ፤የይሖዋ ቀኝ እጅ ኃይሉን ያሳያል።+ +17 የያህን ሥራዎች አስታውቅ ዘንድበሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም።+ +18 ያህ ጠንከር ያለ ተግሣጽ ሰጥቶኛል፤+ሆኖም ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።+ +19 የጽድቅን በሮች ክፈቱልኝ፤+በዚያ ገብቼ ያህን አወድሳለሁ። +20 ይህ የይሖዋ በር ነው። ጻድቃን በዚያ በኩል ይገባሉ።+ +21 መልስ ስለሰጠኸኝናአዳኝ ስለሆንከኝ አወድስሃለሁ።+ +22 ግንበኞች የናቁት ድንጋይየማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ።+ +23 ይህ የይሖዋ ሥራ ነው፤+ለዓይናችንም ድንቅ ነው።+ +24 ይህ ይሖዋ የሠራው ቀን ነው፤በዚህ ቀን እንደሰታለን፤ ሐሴትም እናደርጋለን። +25 ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ እንድታድነን እንለምንሃለን! ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ድል አቀዳጀን! +26 በይሖዋ ስም የሚመጣው የተባረከ ነው፤+በይሖዋ ቤት ሆነን እንባርካችኋለን። +27 ይሖዋ አምላክ ነው፤ብርሃን ይሰጠናል።+ ቅርንጫፎች በመያዝ ወደ በዓሉ ከሚጓዙት ጋር ተቀላቅላችሁ+እስከ መሠዊያው ቀንዶች+ ድረስ ሂዱ። +28 አንተ አምላኬ ነህ፤ እኔም አወድስሃለሁ፤አምላኬ ሆይ፣ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።+ +29 ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ +58 እናንተ የሰው ልጆች፣ ዝም ብላችሁ እያለ ስለ ጽድቅ ልትናገሩ ትችላላችሁ?+ በቅንነትስ መፍረድ ትችላላችሁ?+ + 2 ይልቁንም በልባችሁ ክፋት ትጠነስሳላችሁ፤+እጆቻችሁም በምድሪቱ ላይ ዓመፅ ያስፋፋሉ።+ + 3 ክፉዎች፣ ከተወለዱበት ጊዜ* ጀምሮ መንገድ ስተዋል፤*ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ ሥርዓት የሌላቸውና ውሸታሞች ናቸው። + 4 መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤+ጆሮውን እንደ ደፈነ ጉበና* ደንቆሮ ናቸው። + 5 ድግምተኞቹ ምንም ያህል ችሎታ ቢኖራቸውጉበናው ድምፃቸውን አይሰማም። + 6 አምላክ ሆይ፣ ጥርሳቸውን ከአፋቸው አርግፍ! ይሖዋ ሆይ፣ የእነዚህን አንበሶች* መንጋጋ ሰባብር! + 7 ፈስሶ እንደሚያልቅ ውኃ ይጥፉ። አምላክ ደጋኑን ወጥሮ በቀስቶቹ ይጣላቸው። + 8 ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤ፀሐይን ፈጽሞ እንደማያይ ከሴት የተወለደ ጭንጋፍ ይሁኑ። + 9 በእሳት የተቀጣጠለው እሾህ ድስታችሁን ሳያሞቀው፣አምላክ እርጥቡንም ሆነ የሚነደውን ቅርንጫፍ እንደ አውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደዋል።+ +10 ጻድቅ ሰው በክፉዎች ላይ የተወሰደውን የበቀል እርምጃ በማየቱ ደስ ይለዋል፤+እግሮቹ በእነሱ ደም ይርሳሉ።+ +11 በዚህ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦ “በእርግጥ ጻድቁ ብድራት ይቀበላል።+ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ።”+ +83 አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበል፤+አምላክ ሆይ፣ ጸጥ አትበል፤* ደግሞም ጭጭ አትበል። + 2 እነሆ፣ ጠላቶችህ እየደነፉ ነውና፤+አንተን የሚጠሉ በእብሪት ይመላለሳሉ።* + 3 በስውር በሕዝቦችህ ላይ የተንኮል ሴራ ይሸርባሉ፤በውድ አገልጋዮችህ* ላይ ይዶልታሉ። + 4 “የእስራኤል ስም ተረስቶ እንዲቀር፣ኑ፣ ሕዝቡን እንደምስስ” ይላሉ።+ + 5 የጋራ ዕቅድ ይነድፋሉ፤*በአንተ ላይ ግንባር ፈጥረዋል፤*+ + 6 የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣ ሞዓብና+ አጋራውያን፣+ + 7 ጌባል፣ አሞንና+ አማሌቅ፣እንዲሁም ፍልስጤም+ ከጢሮስ ነዋሪዎች+ ጋር አበሩ። + 8 አሦርም+ ከእነሱ ጋር ተባብሯል፤ለሎጥ ልጆችም+ድጋፍ ይሰጣሉ።* (ሴላ) + 9 በምድያም እንዳደረግከው፣በቂሾንም ጅረት* በሲሳራና በያቢን ላይ እንዳደረግከው አድርግባቸው።+ +10 እነሱ በኤንዶር+ ተደመሰሱ፤ለምድርም ፍግ ሆኑ። +11 በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎች እንደ ኦሬብና ዜብ፣+አለቆቻቸውንም* እንደ ዘባህና ጻልሙና አድርጋቸው፤+ +12 እነሱ “አምላክ የሚኖርባቸውን ቦታዎች እንውረስ” ብለዋልና። +13 አምላኬ ሆይ፣ ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ፣*+ነፋስ እንደሚጠርገው ገለባ አድርጋቸው። +14 ጫካን እንደሚያቃጥል እሳት፣ተራሮችን እንደሚያነድ ነበልባል፣+ +15 አንተም እንዲሁ በሞገድህ አሳዳቸው፤+በአውሎ ነፋስህም አሸብራቸው።+ +16 ይሖዋ ሆይ፣ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ፊታቸውን በኀፍረት ሸፍን።* +17 ለዘላለም ይፈሩ፣ ይሸበሩም፤ውርደት ይከናነቡ፤ ደግሞም ይጥፉ፤ +18 ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣+አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል እንደሆንክ+ ሰዎች ይወቁ። +144 እጆቼን ለውጊያ፣ጣቶቼንም ለጦርነት የሚያሠለጥነው፣+ዓለቴ የሆነው ይሖዋ+ ይወደስ። + 2 እሱ ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላኬና ምሽጌ፣አስተማማኝ መጠጊያዬና ታዳጊዬ፣ጋሻዬና መጠለያዬ፣+ሕዝቦችን ከበታቼ የሚያስገዛልኝ አምላኬ ነው።+ + 3 ይሖዋ ሆይ፣ ታስተውለው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ቦታ ትሰጠውስ ዘንድ ሟች የሆነው የሰው ልጅ ምንድን ነው?+ + 4 ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤+ዘመኑ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።+ + 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያትህን ወደ ታች ዝቅ አድርገህ* ውረድ፤+ተራሮችን ዳስሰህ እንዲጨሱ አድርግ።+ + 6 መብረቅ ልከህ ጠላትን በትን፤+ፍላጻዎችህን ወርውረህ ግራ አ��ባቸው።+ + 7 እጆችህን ከላይ ዘርጋ፤ከሚያጥለቀልቅ ውኃ ታደገኝ፤ ደግሞም አድነኝ፤ከባዕድ አገር ሰዎች እጅ* አስጥለኝ፤+ + 8 እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ።* + 9 አምላክ ሆይ፣ አዲስ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።+ አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የታጀበ የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ፤ +10 እሱ ነገሥታትን ድል* ያጎናጽፋል፤+አገልጋዩን ዳዊትን ከገዳይ ሰይፍ ይታደጋል።+ +11 ከባዕድ አገር ሰዎች እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም፤እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ። +12 ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻችን በፍጥነት እንደሚያድጉ ችግኞች፣ሴቶች ልጆቻችን ደግሞ ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደተቀረጹ የማዕዘን ዓምዶች ይሆናሉ። +13 ጎተራዎቻችን በልዩ ልዩ የእህል ዓይነቶች ጢም ብለው ይሞላሉ፤በመስክ ያሉት መንጎቻችን ተራብተው ሺዎች ደግሞም አሥር ሺዎች ይሆናሉ። +14 የከበዱት ከብቶቻችን ጉዳት አይደርስባቸውም ወይም አይጨነግፉም፤በአደባባዮቻችን ላይ የጭንቅ ዋይታ አይሰማም። +15 ይህ የሚሆንለት ሕዝብ ደስተኛ ነው! አምላኩ ይሖዋ የሆነለት ሕዝብ ደስተኛ ነው!+ +75 ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ አምላክ ሆይ፣ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ስምህ ከእኛ ጋር ነው፤+ሰዎችም ድንቅ ሥራዎችህን ያውጃሉ። + 2 አንተ እንዲህ ትላለህ፦ “ጊዜ ስወስንበትክክል እፈርዳለሁ። + 3 ምድርና በላይዋ የሚኖሩ ሁሉ ሲቀልጡ፣ምሰሶዎቿን አጽንቼ ያቆምኩት እኔ ነኝ።” (ሴላ) + 4 ጉራቸውን ለሚነዙት “ጉራ አትንዙ” እላለሁ፤ ክፉዎቹንም እንዲህ እላለሁ፦ “ኃይላችሁን* ከፍ ከፍ አታድርጉ። + 5 ኃይላችሁን* ወደ ላይ ከፍ አታድርጉ፤ወይም በትዕቢት አትናገሩ። + 6 ክብር ከምሥራቅም ሆነ ከምዕራብወይም ከደቡብ አይመጣምና። + 7 አምላክ ፈራጅ ነውና።+ አንዱን ያዋርዳል፤ ሌላውን ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርጋል።+ + 8 በይሖዋ እጅ ጽዋ አለና፤+የወይን ጠጁ አረፋ ያወጣል፤ ደግሞም ሙሉ በሙሉ የተደባለቀ ነው። እሱ በእርግጥ ያፈሰዋል፤በምድርም ላይ ያሉ ክፉዎች ሁሉ ከነአተላው ይጨልጡታል።”+ + 9 እኔ ግን ይህን ለዘላለም አውጃለሁ፤ለያዕቆብ አምላክ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። +10 እሱ እንዲህ ይላልና፦ “የክፉዎችን ኃይል* በሙሉ እቆርጣለሁ፤የጻድቅ ሰው ኃይል ግን ከፍ ከፍ ይላል።” +20 በጭንቀት ቀን ይሖዋ ይስማህ። የያዕቆብ አምላክ ስም ይጠብቅህ።+ + 2 ከቅዱሱ ስፍራ እርዳታ ይላክልህ፤+ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።+ + 3 በስጦታ የምታቀርበውን መባ ሁሉ ያስብልህ፤የሚቃጠል መባህን በሞገስ ዓይን* ይቀበልህ። (ሴላ) + 4 የልብህን ፍላጎት ያሟላልህ፤+ዕቅድህንም* ሁሉ ያሳካልህ። + 5 በማዳን ሥራህ በደስታ እልል እንላለን፤+በአምላካችን ስም ዓርማችንን ወደ ላይ ከፍ እናደርጋለን።+ ይሖዋ የለመንከውን ሁሉ ይፈጽምልህ። + 6 ይሖዋ የቀባውን እንደሚያድን አሁን አወቅኩ።+ በቀኝ እጁ በሚያከናውነው ታላቅ የማዳን ሥራ፣*+ቅዱስ ከሆኑት ሰማያቱ ይመልስለታል። + 7 አንዳንዶች በሠረገሎች፣ ሌሎች ደግሞ በፈረሶች ይታመናሉ፤+እኛ ግን የአምላካችንን የይሖዋን ስም እንጠራለን።+ + 8 እነሱ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤እኛ ግን ተነስተን ቀጥ ብለን ቆመናል።+ + 9 ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡን አድን!+ እርዳታ ለማግኘት በተጣራን ቀን ይመልስልናል።+ +94 የበቀል አምላክ፣ ይሖዋ ሆይ፣+የበቀል አምላክ ሆይ፣ ብርሃንህን አብራ! + 2 የምድር ፈራጅ ሆይ፣ ተነስ።+ ለትዕቢተኞች የሚገባቸውን ብድራት ክፈላቸው።+ + 3 ክፉዎች እስከ መቼ፣ ይሖዋ ሆይ፣ክፉዎች እስከ መቼ ድረስ ይፈነጥዛሉ?+ + 4 ይለፈልፋሉ፤ በእብሪት ይናገራሉ፤ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ስለ ራሳቸው ���ራ ይነዛሉ። + 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን ያደቃሉ፤+ርስትህንም ይጨቁናሉ። + 6 መበለቲቱንና ባዕዱን ሰው ይገድላሉ፤አባት የሌላቸውንም ልጆች ሕይወት ያጠፋሉ። + 7 “ያህ አያይም፤+የያዕቆብ አምላክ አያስተውለውም” ይላሉ።+ + 8 እናንተ ማመዛዘን የጎደላችሁ ሰዎች፣ ይህን ልብ በሉ፤እናንተ ሞኞች፣ አስተዋዮች የምትሆኑት መቼ ነው?+ + 9 ጆሮን ያበጀው* እሱ መስማት አይችልም? ወይስ ዓይንን የሠራው እሱ ማየት አይችልም?+ +10 ብሔራትን የሚያርመው እሱ መውቀስ አይችልም?+ ለሰዎች እውቀት የሚሰጠው እሱ ነው!+ +11 ይሖዋ የሰዎችን ሐሳብ ያውቃል፤ከንቱ እንደሆነም ይረዳል።+ +12 ያህ ሆይ፣ አንተ የምታርመው፣+ከሕግህ ላይ የምታስተምረው ሰው ደስተኛ ነው፤+ +13 ይህም ለክፉዎች ጉድጓድ እስኪቆፈር ድረስ፣+በመከራ ወቅት ለእሱ ሰላም ትሰጠው ዘንድ ነው። +14 ይሖዋ ሕዝቡን አይጥልምና፤+ርስቱንም አይተውም።+ +15 ፍርድ፣ ዳግመኛ ጽድቅ የሚንጸባረቅበት ይሆናልና፤ልበ ቅን የሆኑ ሰዎችም ሁሉ ይከተሉታል። +16 ከክፉዎች ጋር የሚሟገትልኝ ማን ነው? ክፉ አድራጊዎችን በመቃወም ከጎኔ የሚቆም ማን ነው? +17 ይሖዋ ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣በአጭር ጊዜ ውስጥ በጠፋሁ ነበር።*+ +18 “እግሬ አዳለጠኝ” ባልኩ ጊዜ፣ ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ደገፈኝ።+ +19 በጭንቀት በተዋጥኩ ጊዜ፣*አጽናናኸኝ፤ ደግሞም አረጋጋኸኝ።*+ +20 ምግባረ ብልሹ ገዢዎች* በሕግ ስም* ችግር ለመፍጠር እያሴሩ፣+የአንተ ተባባሪ ሊሆኑ ይችላሉ? +21 በጻድቁ ላይ* ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ይሰነዝራሉ፤+በንጹሕ ሰው ላይ ሞት ይፈርዳሉ።*+ +22 ለእኔ ግን ይሖዋ አስተማማኝ መጠጊያ ይሆንልኛል፤አምላኬ መጠጊያ ዓለቴ ነው።+ +23 ክፉ ሥራቸውን በላያቸው ይመልሳል፤+ በገዛ ክፋታቸው ያጠፋቸዋል።* ይሖዋ አምላካችን ያጠፋቸዋል።+ +88 የመዳኔ አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+በቀን እጮኻለሁ፤በሌሊትም በፊትህ እቀርባለሁ።+ + 2 ጸሎቴ ወደ አንተ ይድረስ፤+እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ለማዳመጥ ጆሮህን አዘንብል።*+ + 3 ነፍሴ* በመከራ ተሞልታለችና፤+ሕይወቴም በመቃብር* አፋፍ ላይ ነች።+ + 4 አሁንም እንኳ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱ ሰዎች ጋር ተቆጥሬአለሁ፤+ምስኪን ሰው* ሆንኩ፤+ + 5 ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደተጋደሙ፣ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውናየአንተ እንክብካቤ* እንደተቋረጠባቸው ሰዎች፣በሙታን መካከል ተተውኩ። + 6 አዘቅት ውስጥ ከተትከኝ፤በጨለማ በተዋጠ ስፍራ፣ ጥልቅ በሆነ ጉድጓድ ውስጥ አኖርከኝ። + 7 በላዬ ላይ ያረፈው ቁጣህ እጅግ ከብዶኛል፤+በኃይለኛ ማዕበልህም አጥለቀለቅከኝ። (ሴላ) + 8 የሚያውቁኝን ሰዎች ከእኔ አራቅክ፤+በእነሱ ፊት አስጸያፊ ነገር አደረግከኝ። ወጥመድ ውስጥ ገብቻለሁ፤ ማምለጥም አልቻልኩም። + 9 ከደረሰብኝ ጉስቁልና የተነሳ ዓይኔ ፈዘዘ።+ ይሖዋ ሆይ፣ ቀኑን ሙሉ አንተን እጣራለሁ፤+እጆቼንም ወደ አንተ እዘረጋለሁ። +10 ለሙታን ድንቅ ሥራዎች ታከናውናለህ? በሞት የተረቱትስ ተነስተው ሊያወድሱህ ይችላሉ?+ (ሴላ) +11 ታማኝ ፍቅርህ በመቃብር፣ታማኝነትህስ በጥፋት ቦታ* ይታወጃል? +12 ያከናወንከው ድንቅ ሥራ በጨለማ፣ጽድቅህስ በተረሱ ሰዎች ምድር ይታወቃል?+ +13 ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን እርዳታ ለማግኘት አሁንም ወደ አንተ እጮኻለሁ፤+ጸሎቴም በየማለዳው ወደ አንተ ትደርሳለች።+ +14 ይሖዋ ሆይ፣ ፊት የምትነሳኝ ለምንድን ነው?*+ ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው ለምንድን ነው?+ +15 እኔ ከልጅነቴ ጀምሮየተጎሳቆልኩና ለመጥፋት የተቃረብኩ ነኝ፤+እንዲደርሱብኝ ከፈቀድካቸው አስከፊ ነገሮች የተነሳ ደንዝዣለሁ። +16 የሚነደው ቁጣህ በላዬ ላይ ወረደ፤+አንተ ያመጣህብኝ ሽብር አጠፋኝ። +17 ቀኑን ሙሉ ��ንደ ውኃ ከበበኝ፤በሁሉም አቅጣጫ* ከቦ መውጫ አሳጣኝ። +18 ወዳጆቼንና ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅክ፤+ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ። +114 እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ፣+የያዕቆብ ቤት ባዕድ ቋንቋ ከሚናገር ሕዝብ ተለይቶ ሲሄድ፣ + 2 ይሁዳ መቅደሱ፣*እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።+ + 3 ባሕሩ ይህን አይቶ ሸሸ፤+ዮርዳኖስ ወደ ኋላ ተመለሰ።+ + 4 ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ኮረብቶች እንደ ጠቦት ፈነጩ።+ + 5 አንተ ባሕር ሆይ፣ የሸሸኸው ምን ሆነህ ነው?+ ዮርዳኖስ ሆይ፣ ወደ ኋላ የተመለስከው ለምንድን ነው?+ + 6 ተራሮች ሆይ፣ እንደ አውራ በግ የዘለላችሁት፣እናንተ ኮረብቶች፣ እንደ ጠቦት የፈነጫችሁት ለምንድን ነው? + 7 ምድር ሆይ፣ ከጌታ የተነሳ፣ከያዕቆብም አምላክ የተነሳ ተንቀጥቀጪ፤+ + 8 እሱ ዓለቱን ቄጠማ ወደሞላበት ኩሬ፣ጠንካራውንም ዓለት ወደ ውኃ ምንጮች ይለውጣል።+ +67 አምላክ ሞገስ ያሳየናል፤ ደግሞም ይባርከናል፤ፊቱን በእኛ ላይ ያበራል፤+ (ሴላ) + 2 ይህም መንገድህ በምድር ሁሉ ላይ፣+የማዳን ሥራህም በብሔራት ሁሉ መካከል እንዲታወቅ ነው።+ + 3 አምላክ ሆይ፣ ሕዝቦች ያወድሱህ፤አዎ፣ ሕዝቦች ሁሉ ያወድሱህ። + 4 ብሔራት ሐሴት ያድርጉ፤ እልልም ይበሉ፤+በሕዝቦች ላይ በትክክል ትፈርዳለህና።+ የምድርን ብሔራት ትመራቸዋለህ። (ሴላ) + 5 አምላክ ሆይ፣ ሕዝቦች ያወድሱህ፤ሕዝቦች ሁሉ ያወድሱህ። + 6 ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች፤+አምላክ፣ አዎ፣ አምላካችን ይባርከናል።+ + 7 አምላክ ይባርከናል፤የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ ይፈሩታል።*+ +92 ለይሖዋ ምስጋና ማቅረብ ጥሩ ነው፤+ልዑሉ አምላክ ሆይ፣ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር መዘመር መልካም ነው፤ + 2 ታማኝ ፍቅርህን በማለዳ፣ታማኝነትህንም በሌሊት ማሳወቅ+ መልካም ነው፤ + 3 አሥር አውታር ባለው መሣሪያና በክራር፣ደስ በሚል የበገና ድምፅ+ ታጅቦ ማሳወቅ ጥሩ ነው። + 4 ይሖዋ ሆይ፣ ባከናወንካቸው ነገሮች እንድደሰት አድርገኸኛልና፤ከእጅህ ሥራዎች የተነሳ እልል እላለሁ። + 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ታላቅ ነው!+ ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!+ + 6 ማመዛዘን የጎደለው ሰው ይህን ሊያውቅ አይችልም፤ሞኝ የሆነም ሰው ይህን ሊረዳ አይችልም፦+ + 7 ክፉዎች እንደ አረም* ቢበቅሉ፣ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ቢያብቡ እንኳ፣ለዘላለም መጥፋታቸው የማይቀር ነው።+ + 8 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም ከሁሉ በላይ ነህ። + 9 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህን በድል አድራጊነት ስሜት ተመልከት፤ጠላቶችህ እንዴት እንደሚጠፉ እይ፤ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ይበተናሉ።+ +10 አንተ ግን ኃይሌን* እንደ ዱር በሬ ኃይል ታደርጋለህ፤እኔም ገላዬን ጥሩ ዘይት እቀባለሁ።+ +11 ዓይኔ ጠላቶቼን በድል አድራጊነት ስሜት ያያል፤+ጆሮዬም የሚያጠቁኝን ክፉ ሰዎች ውድቀት ይሰማል። +12 ጻድቅ ግን እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማል፤እንደ አርዘ ሊባኖስም ትልቅ ይሆናል።+ +13 በይሖዋ ቤት፣ ተተክለዋል፤በአምላካችን ቅጥር ግቢዎች ያብባሉ።+ +14 ባረጁ* ጊዜም እንኳ ማበባቸውን ይቀጥላሉ፤+እንደበረቱና* እንደጠነከሩ ይኖራሉ፤+ +15 ይሖዋ ትክክለኛ እንደሆነ እያወጁ ይኖራሉ። እሱ ዓለቴ ነው፤+ በእሱም ዘንድ ክፋት የለም። +3 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ እንዲህ የበዙት ለምንድን ነው?+ ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ የተነሱትስ ለምንድን ነው?+ + 2 ብዙዎች “አምላክ አያድነውም” እያሉ ስለ እኔ* ይናገራሉ።+ (ሴላ)* + 3 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን በዙሪያዬ ያለህ ጋሻ ነህ፤+አንተ ክብሬና+ ራሴን ቀና የምታደርግ ነህ።+ + 4 ድምፄን ከፍ አድርጌ ይሖዋን እጣራለሁ፤እሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል።+ (ሴላ) + 5 እተኛለሁ፣ አንቀላፋለሁም፤ይሖዋም ዘወትር ስለሚደግፈኝበሰላም እነቃለሁ።+ + 6 በየአቅጣጫው የተሰለፉብኝንበአሥ�� ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልፈራም።+ + 7 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! አምላኬ ሆይ፣ አድነኝ!+ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህና፤የክፉዎችን ጥርስ ትሰባብራለህ።+ + 8 ማዳን የይሖዋ ነው።+ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ነው። (ሴላ) +52 አንተ ኃያል፣ መጥፎ በሆነው ተግባርህ የምትኩራራው ለምንድን ነው?+ የአምላክ ታማኝ ፍቅር ዘላቂ እንደሆነ አታውቅም?+ + 2 ምላስህ እንደ ምላጭ የተሳለ ነው፤+ጥፋትን ይሸርባል፤ ተንኮልንም ያቀነባብራል።+ + 3 መልካም ከሆነው ነገር ይልቅ ክፋትን፣ትክክል የሆነውን ነገር ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ትወዳለህ። (ሴላ) + 4 አንተ አታላይ ምላስ!ጎጂ ቃልን ሁሉ ትወዳለህ። + 5 በመሆኑም አምላክ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያንኮታኩትሃል፤+መንጭቆ ይወስድሃል፤ ከድንኳንህም ጎትቶ ያወጣሃል፤+ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል።+ (ሴላ) + 6 ጻድቃንም ይህን አይተው በፍርሃት* ይዋጣሉ፤+በእሱም ላይ ይስቃሉ።+ + 7 “እንዲህ ያለ ሰው አምላክን መጠጊያው* አያደርግም፤+ይልቁንም በታላቅ ሀብቱ ይታመናል፤+ራሱ በሚጠነስሰውም ሴራ* ይመካል።”* + 8 እኔ ግን በአምላክ ቤት እንዳለ የለመለመ የወይራ ዛፍ እሆናለሁ፤ለዘላለም በአምላክ ታማኝ ፍቅር እታመናለሁ።+ + 9 እርምጃ ስለወሰድክ ለዘላለም አወድስሃለሁ፤+መልካም ነውና፣ በታማኝ አገልጋዮችህ ፊትበስምህ ተስፋ አደርጋለሁ።+ +24 ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ፣ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በእሷ ላይ የሚኖር ሁሉ የይሖዋ ነው።+ + 2 እሱ በባሕሮች ላይ መሥርቷታልና፤+በወንዞችም ላይ አጽንቶ አስቀምጧታል። + 3 ወደ ይሖዋ ተራራ መውጣት የሚችል ማን ነው?+በቅዱስ ስፍራውስ ሊቆም የሚችል ማን ነው? + 4 ከክፋት የጸዱ እጆችና ንጹሕ ልብ ያለው፣+በእኔ ሕይወት* በሐሰት ያልማለ፣በማታለልም መሐላ ያልፈጸመ።+ + 5 እሱ በረከትን ከይሖዋ ያገኛል፤+ጽድቅንም* አዳኝ ከሆነው አምላኩ ይቀበላል።+ + 6 እሱን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ ይህ ነው፤የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ፊትህን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ እንዲህ ያለ ነው። (ሴላ) + 7 እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤+እናንተ ጥንታዊ በሮች፣ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ!*+ + 8 ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው? ብርቱና ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው፤+በውጊያ ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው።+ + 9 እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤+እናንተ ጥንታዊ በሮች፣ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ! +10 ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው? የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው፤ ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ እሱ ነው።+ (ሴላ) +99 ይሖዋ ነገሠ።+ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ። እሱ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን ተቀምጧል።+ ምድር ትናወጥ። + 2 ይሖዋ በጽዮን ታላቅ ነው፤ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው።+ + 3 ሕዝቦች ታላቅ ስምህን ያወድሱ፤+ስምህ እጅግ የሚፈራና ቅዱስ ነውና። + 4 እሱ ፍትሕን የሚወድ ኃያል ንጉሥ ነው።+ አንተ ቅን የሆነውን ነገር በጽኑ መሥርተሃል። ፍትሕንና ጽድቅን ለያዕቆብ አስፍነሃል።+ + 5 ይሖዋ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፤+ በእግሩ ማሳረፊያ ፊት ስገዱ፤*+እሱ ቅዱስ ነው።+ + 6 ከካህናቱ መካከል ሙሴና አሮን ይገኙበታል፤+ስሙን ከሚጠሩ መካከልም ሳሙኤል አንዱ ነው።+ እነሱ ወደ ይሖዋ ይጣሩ ነበር፤እሱም ይመልስላቸው ነበር።+ + 7 በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ያነጋግራቸው ነበር።+ ማሳሰቢያዎቹንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠብቀዋል።+ + 8 አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ መልስ ሰጠሃቸው።+ ይቅር ባይ አምላክ ሆንክላቸው፤+ሆኖም ለሠሯቸው ኃጢአቶች ቀጣሃቸው።*+ + 9 አምላካችንን ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርጉት፤+በቅዱስ ተራራውም+ ፊት ስገዱ፤*አምላካችን ይሖዋ ቅዱስ ነውና።+ +32 በደሉ ይቅር የተባለ���ት፣ ኃጢአቱ የተሸፈነለት* ሰው+ ደስተኛ ነው። + 2 ይሖዋ በጥፋተኝነት የማይጠይቀው፣በመንፈሱ ሽንገላ የሌለበት ሰው ደስተኛ ነው።+ + 3 ዝም ባልኩ ጊዜ፣ ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሳ አጥንቶቼ መነመኑ።+ + 4 ቀንና ሌሊት እጅህ* በእኔ ላይ ከብዳለችና።+ በበጋ ንዳድ እንደሚተን ውኃ ኃይሌ ተነነ።* (ሴላ) + 5 በመጨረሻ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ስህተቴን አልሸፋፈንኩም።+ “የፈጸምኳቸውን በደሎች ለይሖዋ እናዘዛለሁ” አልኩ።+ አንተም ስህተቴንና ኃጢአቴን ይቅር አልክ።+ (ሴላ) + 6 ታማኝ የሆነ ሁሉአንተ በምትገኝበት ጊዜ ወደ አንተ የሚጸልየው ለዚህ ነው።+ በዚህ ጊዜ ኃይለኛ ጎርፍ እንኳ አይነካውም። + 7 አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ከጭንቀት ትሰውረኛለህ።+ በድል* እልልታ ትከበኛለህ።+ (ሴላ) + 8 አንተ እንዲህ ብለሃል፦ “ጥልቅ ማስተዋል እሰጥሃለሁ፤ ልትሄድበት የሚገባውንም መንገድ አስተምርሃለሁ።+ ዓይኔን በአንተ ላይ አድርጌ እመክርሃለሁ።+ + 9 በልጓም ወይም በልባብ ካልተገራ በስተቀር አልገዛም ብሎወደ እናንተ እንደማይቀርብ፣ማስተዋል እንደሌለው ፈረስ ወይም በቅሎ አትሁኑ።”+ +10 የክፉ ሰው ሥቃይ ብዙ ነው፤በይሖዋ የሚታመን ሰው ግን ታማኝ ፍቅሩ ይከበዋል።+ +11 ጻድቃን ሆይ፣ በይሖዋ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ፤ልበ ቀና የሆናችሁ ሁሉ፣ እልል በሉ። +149 ያህን አወድሱ!* ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+በታማኝ አገልጋዮች ጉባኤ መካከል አወድሱት።+ + 2 እስራኤል በታላቅ ሠሪው+ ሐሴት ያድርግ፤የጽዮን ልጆች በንጉሣቸው ደስ ይበላቸው። + 3 ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፤+በአታሞና በበገና የውዳሴ መዝሙር ይዘምሩለት።+ + 4 ይሖዋ በሕዝቡ ደስ ይሰኛልና።+ እሱ የዋሆችን በማዳን ውበት ያጎናጽፋቸዋል።+ + 5 ታማኝ አገልጋዮቹ በክብር ሐሴት ያድርጉ፤በመኝታቸው ላይ ሆነው እልል ይበሉ።+ + 6 አንደበታቸው አምላክን የሚያወድስ መዝሙር ይዘምር፤እጃቸውም በሁለቱም በኩል የተሳለ ሰይፍ ይያዝ፤ + 7 ይህም በብሔራት ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ፣ሕዝቦችንም እንዲቀጡ፣ + 8 ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎችም በእግር ብረት እንዲያስሩ፣ + 9 ደግሞም በእነሱ ላይ የተላለፈውን በጽሑፍ የሰፈረ ፍርድ እንዲፈጽሙ ነው።+ ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ ይህ ክብር ይገባቸዋል። ያህን አወድሱ!* +116 ይሖዋ ድምፄን፣እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስለሚሰማ እወደዋለሁ።*+ + 2 ጆሮውን ወደ እኔ ያዘነብላልና፣*+በሕይወት እስካለሁ ድረስ* እሱን እጣራለሁ። + 3 የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤መቃብር ያዘኝ።*+ በጭንቀትና በሐዘን ተዋጥኩ።+ + 4 እኔ ግን የይሖዋን ስም ጠራሁ፦+ “ይሖዋ ሆይ፣ ታደገኝ!”* + 5 ይሖዋ ሩኅሩኅና* ጻድቅ ነው፤+አምላካችን መሐሪ ነው።+ + 6 ይሖዋ ተሞክሮ የሌላቸውን ይጠብቃል።+ ተስፋ ቆርጬ ነበር፤ እሱ ግን አዳነኝ። + 7 ነፍሴ* ዳግመኛ እረፍት ታግኝ፤ይሖዋ ደግነት አሳይቶኛልና። + 8 እኔን* ከሞት፣ ዓይኔን ከእንባ፣እግሬንም ከእንቅፋት ታድገሃል።+ + 9 በሕያዋን ምድር በይሖዋ ፊት እሄዳለሁ። +10 አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ፤+እጅግ ተጎሳቁዬ ነበር። +11 በጣም ደንግጬ “ሰው ሁሉ ውሸታም ነው”+ አልኩ። +12 ላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ? +13 የማዳንን ጽዋ አነሳለሁ፤የይሖዋንም ስም እጠራለሁ። +14 በሕዝቡ ሁሉ ፊትስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ።+ +15 የታማኝ አገልጋዮቹ ሞትበይሖዋ ዓይን ከባድ ነገር* ነው።+ +16 ይሖዋ ሆይ፣እኔ አገልጋይህ ስለሆንኩ እለምንሃለሁ። እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ አገልጋይህ ነኝ። አንተ ከእስራቴ ነፃ አውጥተኸኛል።+ +17 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤+የይሖዋን ስም እጠራለሁ��� +18 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ፤+ +19 በይሖዋ ቤት ቅጥር ግቢዎች፣+በኢየሩሳሌም መካከል ስእለቴን አቀርባለሁ። ያህን አወድሱ!*+ +7 አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።+ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም።+ + 2 አለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤*+የሚታደገኝ በሌለበት ነጥቀው ይወስዱኛል። + 3 አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ የሠራሁት አንዳች ጥፋት ካለ፣አግባብ ያልሆነ ድርጊት ፈጽሜ ከሆነ፣ + 4 መልካም ያደረገልኝን ሰው በድዬ ከሆነ፣+ወይም ያላንዳች ምክንያት ጠላቴን ዘርፌ ከሆነ፣* + 5 ጠላት አሳዶ ይያዘኝ፤*ሕይወቴን መሬት ላይ ይጨፍልቃት፤ክብሬንም ከአፈር ይደባልቀው። (ሴላ) + 6 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ ተነስ፤በእኔ ላይ በቁጣ በሚገነፍሉት ጠላቶቼ ላይ ተነስ፤+ለእኔ ስትል ንቃ፤ ፍትሕ እንዲሰፍንም እዘዝ።+ + 7 ብሔራት ይክበቡህ፤አንተም ከላይ ሆነህ በእነሱ ላይ እርምጃ ትወስዳለህ። + 8 ይሖዋ በሕዝቦች ላይ ፍርድ ያስተላልፋል።+ ይሖዋ ሆይ፣ እንደ ጽድቄ፣እንደ ንጹሕ አቋሜም* ፍረድልኝ።+ + 9 እባክህ፣ የክፉ ሰዎች ክፋት እንዲያከትም አድርግ። ጻድቁን ሰው ግን አጽና፤+ልብንና+ ጥልቅ ስሜትን የምትመረምር*+ ጻድቅ አምላክ ነህና።+ +10 ቀና ልብ ያላቸውን ሰዎች የሚያድነው+ አምላክ ጋሻዬ ነው።+ +11 አምላክ ጻድቅ ፈራጅ ነው፤+በየቀኑም ፍርዱን ያውጃል።* +12 ማንም ሰው ንስሐ የማይገባ ከሆነ፣+ አምላክ ሰይፉን ይስላል፤+ደጋኑን ወጥሮ ያነጣጥራል።+ +13 ገዳይ የሆኑ መሣሪያዎቹን ያሰናዳል፤የሚንበለበሉ ፍላጻዎቹን ያዘጋጃል።+ +14 ክፋትን ያረገዘውን ሰው ተመልከት፤ችግርን ይፀንሳል፤ ሐሰትንም ይወልዳል።+ +15 ጉድጓድ ይምሳል፤ ጥልቅ አድርጎም ይቆፍረዋል፤ሆኖም በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ራሱ ይወድቃል።+ +16 የሚያመጣው ችግር በራሱ ላይ ይመለሳል፤+የዓመፅ ድርጊቱ በገዛ አናቱ ላይ ይወርዳል። +17 ይሖዋን ለፍትሑ አወድሰዋለሁ፤+ለልዑሉ አምላክ+ ለይሖዋ ስም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+ +133 እነሆ፣ ወንድሞች በአንድነት አብረው ቢኖሩምንኛ መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!+ + 2 በራስ ላይ ፈስሶ እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣በአሮን ጢም+ ላይ እንደሚወርድ፣እስከ ልብሱ ኮሌታ ድረስ እንደሚፈስጥሩ ዘይት ነው።+ + 3 በጽዮን ተራሮች+ ላይ እንደሚወርድ፣እንደ ሄርሞን+ ጤዛ ነው። በዚያ ይሖዋ በረከቱን ይኸውምየዘላለም ሕይወትን አዟል። +74 አምላክ ሆይ፣ ለዘላለም የጣልከን ለምንድን ነው?+ በመስክህ በተሰማራው መንጋ ላይ ቁጣህ የነደደው* ለምንድን ነው?+ + 2 ከረጅም ዘመን በፊት የራስህ ያደረግከውን ሕዝብ፣*+ርስትህ አድርገህ የዋጀኸውን ነገድ አስታውስ።+ የኖርክበትን የጽዮን ተራራ+ አስብ። + 3 ለዘለቄታው ወደፈራረሰው ቦታ አቅና።+ ጠላት በቅዱሱ ስፍራ ያለውን ነገር ሁሉ አጥፍቷል።+ + 4 ጠላቶችህ በመሰብሰቢያ ቦታህ* ውስጥ በድል አድራጊነት ጮኹ።+ በዚያም የራሳቸውን ዓርማ ምልክት አድርገው አቆሙ። + 5 መጥረቢያቸውን ይዘው ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችን እንደሚጨፈጭፉ ሰዎች ናቸው። + 6 በቅርጻ ቅርጾች ያጌጡትን+ ግድግዳዎች በጠቅላላ በመጥረቢያና በብረት ዘንግ አፈራረሱ። + 7 መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ።+ ስምህ የተጠራበትን የማደሪያ ድንኳን መሬት ላይ ጥለው አረከሱት። + 8 እነሱም ሆኑ ዘሮቻቸው በልባቸው “በምድሪቱ ላይ ያሉት የአምላክ መሰብሰቢያ* ቦታዎች በሙሉ ይቃጠሉ” ብለዋል። + 9 የምናያቸው ምልክቶች የሉም፤አንድም የቀረ ነቢይ የለም፤ደግሞም ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል ከእኛ መካከል የሚያውቅ የለም። +10 አምላክ ሆይ፣ ባላጋራ የሚሳለቀው እስከ መቼ ነው?+ ጠላት ስምህን ለዘላለም እያቃለለ ይኖራል?+ +11 እጅህን ይኸውም ቀኝ እጅህን የሰበሰብከው ለምንድን ነው?+ እጅህን ከጉያህ* አውጥተህ አጥፋቸው። +12 ይሁንና በምድር ላይ ታላቅ የማዳን ሥራ የሚፈጽመው አምላክከጥንት ጀምሮ ንጉሤ ነው።+ +13 በብርታትህ ባሕሩን አናወጥክ፤+በውኃ ውስጥ ያሉትን ግዙፍ የባሕር ፍጥረታት ራስ ሰባበርክ። +14 የሌዋታንን* ራሶች አደቀቅክ፤በበረሃ ለሚኖሩት ሰዎች ምግብ አድርገህ ሰጠሃቸው። +15 ለምንጮችና ለጅረቶች መውጫ ያበጀኸው አንተ ነህ፤+ሳያቋርጡ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅክ።+ +16 ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው። ብርሃንንና ፀሐይን* ሠራህ።+ +17 የምድርን ወሰኖች ሁሉ ደነገግክ፤+በጋና ክረምት እንዲፈራረቁ አደረግክ።+ +18 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላት እንደተሳለቀ፣ሞኝ ሕዝብ ስምህን እንዴት እንዳቃለለ አስብ።+ +19 የዋኖስህን ሕይወት* ለዱር አራዊት አትስጥ። የተጎሳቆለውን ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለም አትርሳ። +20 ቃል ኪዳንህን አስብ፤በምድሪቱ ላይ ያሉት ጨለማ ቦታዎች የዓመፅ መናኸሪያ ሆነዋልና። +21 የተደቆሰው ሰው አዝኖ አይመለስ፤+ችግረኛውና ድሃው ስምህን ያወድስ።+ +22 አምላክ ሆይ፣ ተነስ፤ ደግሞም ለራስህ ተሟገት። ሞኝ ሰው ቀኑን ሙሉ እንዴት እንደሚሳለቅብህ አስብ።+ +23 ጠላቶችህ የሚሉትን አትርሳ። አንተን የሚዳፈሩ ሰዎች የሚያሰሙት ሁካታ ያለማቋረጥ ወደ ላይ እየወጣ ነው። +48 ይሖዋ ታላቅ ነው፤በአምላካችን ከተማ፣ በቅዱስ ተራራው እጅግ ሊወደስ ይገባዋል። + 2 በከፍታ ቦታ ላይ ተውባ የምትታየው፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣+በስተ ሰሜን ርቃ የምትገኘው የጽዮን ተራራ ነች፤ደግሞም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች።+ + 3 አምላክ በማይደፈሩ ማማዎቿ ውስጥአስተማማኝ መጠጊያ መሆኑን አስመሥክሯል።+ + 4 እነሆ፣ ነገሥታት ተሰብስበዋልና፤*አንድ ላይ ሆነው ገሰገሱ። + 5 ከተማዋን ባዩአት ጊዜ ተገረሙ። ደንግጠውም ፈረጠጡ። + 6 በዚያም በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤እንደምትወልድ ሴት ጭንቅ ያዛቸው። + 7 የተርሴስን መርከቦች በምሥራቅ ነፋስ ሰባበርክ። + 8 የሰማነውን ነገር፣ በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ከተማይኸውም በአምላካችን ከተማ አሁን በገዛ ዓይናችን አይተናል። አምላክ ለዘላለም ያጸናታል።+ (ሴላ) + 9 አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነንስለ ታማኝ ፍቅርህ እናሰላስላለን።+ +10 አምላክ ሆይ፣ እንደ ስምህ ሁሉ ውዳሴህምእስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል።+ ቀኝ እጅህ በጽድቅ ተሞልቷል።+ +11 ከፍርድህ የተነሳ የጽዮን ተራራ+ ደስ ይበላት፤የይሁዳ ከተሞችም* ሐሴት ያድርጉ።+ +12 በጽዮን ዙሪያ ሂዱ፤ በዙሪያዋም ተጓዙ፤ማማዎቿን ቁጠሩ።+ +13 የመከላከያ ግንቦቿን*+ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። ለመጪዎቹ ትውልዶች መናገር ትችሉ ዘንድ፣የማይደፈሩ ማማዎቿን በሚገባ አጢኑ። +14 ይህ አምላክ፣ ለዘላለም አምላካችን ነውና።+ እስከ ወዲያኛው* ይመራናል።+ +90 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መኖሪያችን* ሆነሃል።+ + 2 ተራሮች ሳይወለዱ፣ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ*+ በፊት፣ከዘላለም እስከ ዘላለም አንተ አምላክ ነህ።+ + 3 ሟች የሆነ ሰው ወደ አፈር እንዲመለስ ታደርጋለህ፤“የሰው ልጆች ሆይ፣ ወደ አፈር ተመለሱ”+ ትላለህ። + 4 በአንተ ዘንድ ሺህ ዓመት፣ እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣+እንደ አንድ ክፍለ ሌሊትም* ነው። + 5 ጠራርገህ ታስወግዳቸዋለህ፤+ እንደ ሕልም ይጠፋሉ፤በማለዳ ሲታዩ እንደሚለመልም ሣር ናቸው።+ + 6 ጠዋት ላይ ሣሩ ያቆጠቁጣል፤ ደግሞም ይለመልማል፤ምሽት ላይ ግን ጠውልጎ ይደርቃል።+ + 7 በቁጣህ አልቀናልና፤+ከታላቅ ቁጣህም የተነሳ ተሸብረናል። + 8 በደላችንን በፊትህ ታኖራለህ፤*+የደበቅናቸው ነገሮች በፊትህ ብርሃን ተጋልጠዋል።+ + 9 ከኃይለኛ ቁጣህ የተነሳ ዘመናችን* ይመናመናል፤���ድሜያችንም ሽው ብሎ ያልፋል።* +10 የዕድሜያችን ርዝማኔ 70 ዓመት ነው፤ለየት ያለ ጥንካሬ ካለን* ደግሞ 80+ ዓመት ቢሆን ነው። ይህም በችግርና በሐዘን የተሞላ ነው፤ፈጥኖ ይነጉዳል፤ እኛም እናልፋለን።+ +11 የቁጣህን ኃይል መረዳት የሚችል ማን ነው? ቁጣህ፣ አንተ መፈራት የሚገባህን ያህል ታላቅ ነው።+ +12 ጥበበኛ ልብ ማግኘት እንችል ዘንድ፣ዕድሜያችንን እንዴት መቁጠር እንዳለብን አስተምረን።+ +13 ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ!+ ይህ ሁኔታ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው?+ ለአገልጋዮችህ ራራላቸው።+ +14 በሕይወት ዘመናችን ሁሉ እልል እንድንልና ሐሴት እንድናደርግ፣+በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን አጥግበን።+ +15 ባጎሳቆልከን ዘመን ልክ፣መከራም ባየንባቸው ዓመታት መጠን+ ሐሴት እንዲሰማን አድርገን።+ +16 አገልጋዮችህ ሥራህን ይዩ፤ልጆቻቸውም ግርማህን ይመልከቱ።+ +17 የአምላካችን የይሖዋ ሞገስ በእኛ ላይ ይሁን፤የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።* አዎ፣ የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።+ +61 አምላክ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ስማ። ጸሎቴን በትኩረት አዳምጥ።+ + 2 ልቤ ተስፋ በቆረጠ* ጊዜከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ።+ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለ ዓለት ምራኝ።+ + 3 አንተ መጠጊያዬ ነህና፤ከጠላት የምትጠብቀኝ ጽኑ ግንብ ነህ።+ + 4 በድንኳንህ ለዘላለም በእንግድነት እቀመጣለሁ፤+በክንፎችህ ጥላ ሥር እጠለላለሁ።+ (ሴላ) + 5 አምላክ ሆይ፣ ስእለቴን ሰምተሃልና። ስምህን የሚፈሩትን ሰዎች ርስት ሰጥተኸኛል።+ + 6 የንጉሡን ሕይወት* ታረዝምለታለህ፤+ዕድሜውም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ይሆናል። + 7 በአምላክ ፊት ለዘላለም ይነግሣል፤*+ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት እንዲጠብቁት እዘዝ።*+ + 8 እኔም ስእለቴን በየቀኑ ስፈጽም፣+ለስምህ ለዘላለም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+ +84 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ምንኛ ያማረ* ነው!+ + 2 ሁለንተናዬ* የይሖዋን ቅጥር ግቢዎችእጅግ ናፈቀ፤አዎ፣ በጣም ከመጓጓቴ የተነሳ ዛልኩ።+ ልቤም ሆነ ሥጋዬ ሕያው ለሆነው አምላክ እልል ይላል። + 3 ንጉሤና አምላኬ የሆንከው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ታላቁ መሠዊያህ ባለበት አቅራቢያ፣ወፍ እንኳ በዚያ ቤት ታገኛለች፤ወንጭፊትም ጫጩቶቿን የምታሳድግበት ጎጆለራሷ ትሠራለች። + 4 በቤትህ የሚኖሩ ደስተኞች ናቸው!+ እነሱ ሁልጊዜ ያወድሱሃል።+ (ሴላ) + 5 አንተን የብርታታቸው ምንጭ ያደረጉ፣ወደ ቤትህ የሚወስዱትን መንገዶች የሚናፍቅ ልብ ያላቸው ሰዎች ደስተኞች ናቸው።+ + 6 በባካ* ሸለቆ* በሚያልፉበት ጊዜ፣ስፍራውን ምንጮች የሚፈልቁበት ቦታ ያደርጉታል፤የመጀመሪያውም ዝናብ በረከት ያለብሰዋል።* + 7 በብርታት ላይ ብርታት እያገኙ ይሄዳሉ፤+እያንዳንዳቸውም በጽዮን፣ በአምላክ ፊት ይቀርባሉ። + 8 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ አዳምጠኝ። (ሴላ) + 9 ጋሻችንና+ አምላካችን ሆይ፣ ተመልከት፤*የተቀባውን የአገልጋይህን ፊት እይ።+ +10 በሌላ ቦታ አንድ ሺህ ቀን ከመኖር በቅጥር ግቢዎችህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላልና!+ በክፉዎች ድንኳን ከመኖር፣በአምላኬ ቤት ደጃፍ ላይ መቆም እመርጣለሁ። +11 ይሖዋ አምላክ ፀሐይና+ ጋሻ+ ነውና፤እሱ ሞገስና ክብር ይሰጣል። ንጹሕ አቋም ይዘው የሚመላለሱትንይሖዋ አንዳች መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።+ +12 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣በአንተ የሚታመን ሰው ደስተኛ ነው።+ +45 መልካም የሆነ ነገር ልቤን አነሳስቶታል። “መዝሙሬ* ስለ አንድ ንጉሥ ነው”+ እላለሁ። አንደበቴ የተዋጣለት ገልባጭ *+ እንደሚጠቀምበት ብዕር+ ይሁን። + 2 አንተ ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ። ከከንፈሮችህ ጸጋ የተላበሱ ቃ���ት ይፈስሳሉ።+ አምላክ ለዘላለም የባረከህ ለዚህ ነው።+ + 3 ኃያል ሆይ፣+ ሰይፍህን+ በጎንህ ታጠቅ፤ክብርህንና ግርማህንም+ ተጎናጸፍ። + 4 በግርማህም ድል ለመቀዳጀት* ገስግስ፤+ፈረስህን እየጋለብክ ለእውነት፣ ለትሕትናና ለጽድቅ ተዋጋ፤+ቀኝ እጅህም የሚያስፈሩ ተግባሮችን ያከናውናል።* + 5 ፍላጻዎችህ የሾሉ ናቸው፤ ሰዎችን በፊትህ ይረፈርፋሉ፤+የንጉሡን ጠላቶች ልብ ይወጋሉ።+ + 6 አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው፤+የመንግሥትህ በትር የቅንነት* በትረ መንግሥት ነው።+ + 7 ጽድቅን ወደድክ፤+ ክፋትን ጠላህ።+ ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይበልጥ በደስታ ዘይት+ ቀባህ።+ + 8 ልብሶችህ ሁሉ የከርቤ፣ የእሬትና* የብርጉድ መዓዛ አላቸው፤በዝሆን ጥርስ ካጌጠው ታላቅ ቤተ መንግሥት የሚወጣው የባለ አውታር መሣሪያዎች* ድምፅ ያስደስትሃል። + 9 ከተከበሩት እመቤቶችህ መካከል የነገሥታት ልጆች ይገኛሉ። እቴጌይቱ* በኦፊር ወርቅ+ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች። +10 ልጄ ሆይ፣ አዳምጪ፣ ልብ በዪ፣ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ። +11 ንጉሡም በውበትሽ ተማርኳል፤እሱ ጌታሽ ነውና፣እጅ ንሺው። +12 የጢሮስ ሴት ልጅ ስጦታ ይዛ ትመጣለች፤እጅግ ባለጸጋ የሆኑትም በአንቺ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ። +13 የንጉሡ ሴት ልጅ እጅግ ተውባ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ተቀምጣለች፤*ልብሷ በወርቅ ያጌጠ* ነው። +14 ያጌጠ ልብሷን* ለብሳ ወደ ንጉሡ ትወሰዳለች። ወዳጆቿ የሆኑ ደናግል አጃቢዎቿን ወደ ፊትህ ያቀርቧቸዋል። +15 በደስታና በሐሴት ይመሯቸዋል፤ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት ይገባሉ። +16 በአባቶችህ ፋንታ ወንዶች ልጆችህ ይተካሉ። በምድር ሁሉ ላይ መኳንንት አድርገህ ትሾማቸዋለህ።+ +17 ለሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ስምህን አሳውቃለሁ።+ በመሆኑም ሕዝቦች ለዘላለም ያወድሱሃል። +56 አምላክ ሆይ፣ ሟች የሆነ ሰው ጥቃት እየሰነዘረብኝ* ስለሆነ ሞገስ አሳየኝ። ቀኑን ሙሉ ይዋጉኛል፤ ደግሞም ያስጨንቁኛል። + 2 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ እኔን ለመንከስ ይሞክራሉ፤ብዙዎች በእብሪት ተነሳስተው ይዋጉኛል። + 3 ፍርሃት በሚሰማኝ ጊዜ+ በአንተ እታመናለሁ።+ + 4 ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+ + 5 ቀኑን ሙሉ የእኔን ጉዳይ ለማበላሸት ይጥራሉ፤ሐሳባቸው እኔን መጉዳት ብቻ ነው።+ + 6 እኔን ለማጥቃት ራሳቸውን ይሰውራሉ፤ሕይወቴን* ለማጥፋት በመሻት+እርምጃዬን አንድ በአንድ ይከታተላሉ።+ + 7 ከክፋታቸው የተነሳ አስወግዳቸው። አምላክ ሆይ፣ ብሔራትን በቁጣህ አጥፋቸው።+ + 8 ከቦታ ቦታ ስንከራተት አንድ በአንድ ትከታተላለህ።+ እንባዬን በአቁማዳህ አጠራቅም።+ ደግሞስ በመጽሐፍህ ውስጥ ሰፍሮ የለም?+ + 9 እርዳታ ለማግኘት በምጣራበት ቀን ጠላቶቼ ያፈገፍጋሉ።+ አምላክ ከጎኔ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።+ +10 ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣ቃሉን በማወድሰው በይሖዋ፣ +11 አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም።+ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+ +12 አምላክ ሆይ፣ ለአንተ በተሳልኳቸው ስእለቶች የተነሳ ግዴታ ውስጥ ገብቻለሁ፤+ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ።+ +13 አንተ ከሞት ታድገኸኛልና፤*+እግሮቼንም ከእንቅፋት አድነሃል፤+ይህም በሕያዋን ብርሃን በአምላክ ፊት እመላለስ ዘንድ ነው።+ +117 ብሔራት ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱት፤+ሕዝቦች* ሁሉ፣ ከፍ ከፍ አድርጉት።+ + 2 ለእኛ ያሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና፤+የይሖዋ ታማኝነት+ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ ያህን አወድሱ!*+ +135 ያህን አወድሱ!* የይሖዋን ስም አወድሱ፤እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች፣ ውዳሴ አቅርቡ፤+ + 2 በይሖዋ ቤት፣በአምላካችን ቤት ��ጥር ግቢዎች የቆማችሁ ሁሉ አወድሱት።+ + 3 ይሖዋ ጥሩ ነውና፣+ ያህን አወድሱ። ደስ የሚያሰኝ ነውና፣ ለስሙ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። + 4 ያህ ያዕቆብን የራሱ፣እስራኤልን ልዩ ንብረቱ* አድርጎ መርጧልና።+ + 5 ይሖዋ ታላቅ መሆኑን በሚገባ አውቃለሁና፤ጌታችን ከሌሎች አማልክት ሁሉ የላቀ ነው።+ + 6 በሰማይና በምድር፣ በባሕሮችና በጥልቆች ውስጥይሖዋ ደስ ያሰኘውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።+ + 7 ደመና* ከምድር ዳርቻዎች ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርጋል፤በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያበርቃል፤*ነፋሱን ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።+ + 8 በግብፅ የተወለደውንየሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ገደለ።+ + 9 ግብፅ ሆይ፣ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣+በመካከልሽ ምልክቶችንና ተአምራትን አደረገ።+ +10 ብዙ ብሔራትን መታ፤+ኃያላን ነገሥታትንም ገደለ፤+ +11 የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን፣+የባሳንን ንጉሥ ኦግን፣+የከነአንንም መንግሥታት ሁሉ ድል አደረገ። +12 ምድራቸውን ርስት አድርጎ፣አዎ፣ ርስት አድርጎ ለሕዝቡ ለእስራኤል ሰጠ።+ +13 ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። ይሖዋ ሆይ፣ ዝናህ* ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዘልቃል።+ +14 ይሖዋ ለሕዝቡ ይሟገታልና፤*+ለአገልጋዮቹም ይራራል።*+ +15 የብሔራት ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+ +16 አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤ +17 ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም። በአፋቸው ውስጥ እስትንፋስ የለም።+ +18 የሚሠሯቸውም ሆኑ የሚታመኑባቸው ሁሉ፣+እንደ እነሱ ይሆናሉ።+ +19 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይሖዋን አወድሱ። የአሮን ቤት ሆይ፣ ይሖዋን አወድሱ። +20 የሌዊ ቤት ሆይ፣ ይሖዋን አወድሱ።+ እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ ይሖዋን አወድሱ። +21 በኢየሩሳሌም የሚኖረው ይሖዋ፣+ከጽዮን ይወደስ።+ ያህን አወድሱ!+ +132 ይሖዋ ሆይ፣ ዳዊትን፣የደረሰበትንም መከራ ሁሉ አስታውስ፤+ + 2 ለይሖዋ እንዴት እንደማለ፣ኃያል ለሆነው ለያዕቆብ አምላክ እንዴት እንደተሳለ አስብ፦+ + 3 “ወደ ድንኳኔ፣ ወደ ቤቴ አልገባም።+ ወደ መኝታዬ፣ ወደ አልጋዬ አልወጣም፤ + 4 ዓይኖቼ እንዲያንቀላፉ፣ሽፋሽፍቶቼም እንዲያሸልቡ አልፈቅድም፤ + 5 ይህም ለይሖዋ ስፍራ፣ኃያል ለሆነው የያዕቆብ አምላክም ያማረ መኖሪያ እስከማገኝ ድረስ ነው።”+ + 6 እነሆ፣ በኤፍራታ+ ስለ እሷ ሰማን፤በጫካ በተሞላው ምድር አገኘናት።+ + 7 ወደ መኖሪያው እንግባ፤+በእግሩ ማሳረፊያ ፊት እንስገድ።+ + 8 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ፤አንተና የብርታትህ ታቦት፣+ ወደ ማረፊያ ስፍራህ ሂዱ።+ + 9 ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ታማኝ አገልጋዮችህም እልል ይበሉ። +10 ለአገልጋይህ ለዳዊት ስትል፣የቀባኸውን ሰው ገሸሽ አታድርግ።+ +11 ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦ “ከዘሮችህ መካከል አንዱን*በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።+ +12 ወንዶች ልጆችህ ቃል ኪዳኔንናየማስተምራቸውን ማሳሰቢያዎች ቢጠብቁ፣+የእነሱም ልጆችለዘላለም በዙፋንህ ላይ ይቀመጣሉ።”+ +13 ይሖዋ ጽዮንን መርጧታልና፤+የራሱ መኖሪያ እንድትሆን ፈልጓል፤+ እንዲህም ብሏል፦ +14 “ይህች ለዘላለም ማረፊያ ስፍራዬ ነች፤በእሷ እኖራለሁ፤+ ይህ ምኞቴ ነውና። +15 የተትረፈረፈ የምግብ አቅርቦት እንዲኖራት በማድረግ እባርካታለሁ፤ድሆቿን እህል አጠግባለሁ።+ +16 ካህናቷ መዳንን እንዲለብሱ አደርጋለሁ፤+ታማኝ ሕዝቦቿም እልል ይላሉ።+ +17 በዚያ የዳዊትን ብርታት እጨምራለሁ።* ለቀባሁት አገልጋዬ መብራት አዘጋጅቻለሁ።+ +18 ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባለሁ፤በራሱ ላይ ያለው አክሊል* ግን ያብባል።”+ +12 ይሖዋ ሆይ፣ አንድም ታማኝ ሰው ስለሌለ አድነኝ፤ከሰው ልጆች መካከል ታማኞች ጠፍተዋል። + 2 እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤በከንፈራቸው ይሸነግላሉ፤* አታላይ በሆነ ልብም* ይናገራሉ።+ + 3 ይሖዋ የሚሸነግልን ከንፈር ሁሉ፣ጉራ የሚነዛውንም ምላስ ይቆርጣል፤+ + 4 እነሱ “በምላሳችን እንረታለን። አንደበታችንን እንዳሻን እንጠቀምበታለን፤በእኛ ላይ ጌታ ሊሆን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።+ + 5 “የተጎሳቆሉት ሰዎች በመጨቆናቸው፣ድሆችም በመቃተታቸው፣+እርምጃ ለመውሰድ እነሳለሁ” ይላል ይሖዋ። “በንቀት ዓይን ከሚመለከቷቸው* ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።” + 6 የይሖዋ ቃል የጠራ ነው፤+ከሸክላ በተሠራ ምድጃ* እንደተጣራ ብር ሰባት ጊዜ የነጠረ ነው። + 7 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ትጋርዳቸዋለህ፤+እያንዳንዳቸውን ከዚህ ትውልድ ለዘላለም ትጠብቃቸዋለህ። + 8 የሰው ልጆች ብልሹ ምግባርን ስለሚያስፋፉ፣ክፉዎች እንዳሻቸው ይፈነጫሉ።+ +134 በሌሊት በይሖዋ ቤት የምታገለግሉ፣+እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች ሁሉ፣ይሖዋን አወድሱ።+ + 2 እጆቻችሁን በቅድስና* ወደ ላይ አንሱ፤+ይሖዋንም አወድሱ። + 3 ሰማይንና ምድርን የሠራው ይሖዋ፣ከጽዮን ይባርክህ። +1 በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣በኃጢአተኞች መንገድ+ የማይቆም፣በፌዘኞችም+ ወንበር የማይቀመጥ ሰው ደስተኛ ነው። + 2 ይልቁንም በይሖዋ ሕግ ደስ ይለዋል፤+ሕጉንም በቀንና በሌሊት በለሆሳስ ያነበዋል።*+ + 3 በጅረቶች ዳር እንደተተከለ፣ፍሬውን በወቅቱ እንደሚሰጥ፣ቅጠሉም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል። የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል።+ + 4 ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፤ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው። + 5 ከዚህም የተነሳ ክፉዎች በፍርድ ፊት ለዘለቄታው አይቆሙም፤+ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ ጸንተው አይቆሙም።+ + 6 ይሖዋ የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፤+የክፉዎች መንገድ ግን ይጠፋል።+ +49 እናንተ ሕዝቦች ሁሉ፣ ይህን ስሙ። በዓለም ላይ* የምትኖሩ ሁሉ፣ ልብ በሉ፤ + 2 ታናናሾችም ሆናችሁ ታላላቆች፣*ባለጸጎችና ድሆች፣ ሁላችሁም ስሙ። + 3 አፌ ጥበብን ይናገራል፤በልቤም የማሰላስለው ነገር+ ማስተዋልን ይገልጣል። + 4 ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ። + 5 በአስቸጋሪ ወቅት፣እኔን ለመጣል የሚፈልጉ ሰዎች ክፋት* በከበበኝ ጊዜ ለምን እፈራለሁ?+ + 6 በሀብታቸው የሚመኩትን፣+በታላቅ ብልጽግናቸው የሚኩራሩትንም+ ለምን እፈራለሁ? + 7 አንዳቸውም ቢሆኑ ሌላውን ሰው መዋጀት፣ወይም ለእሱ ቤዛ የሚሆን ነገር ለአምላክ መክፈል ጨርሶ አይችሉም፤+ + 8 (ለሕይወታቸው* የሚከፈለው የቤዛ* ዋጋ እጅግ ውድ ስለሆነመቼም ቢሆን ከአቅማቸው በላይ ነው)፤ + 9 ለዘላለም እንዲኖርና ወደ ጉድጓድ* እንዳይወርድ ቤዛ ሊከፍሉ አይችሉም።+ +10 ጥበበኞች እንኳ ሲሞቱ ያያል፤ሞኞችና ማመዛዘን የሚጎድላቸው ሰዎች አብረው ይጠፋሉ፤+ሀብታቸውንም ለሌሎች ትተውት ያልፋሉ።+ +11 ምኞታቸው ቤቶቻቸው ለዘላለም እንዲኖሩ፣ድንኳናቸውም ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ነው። ርስታቸውን በራሳቸው ስም ሰይመዋል። +12 ይሁንና የሰው ልጅ የተከበረ ቢሆንም እንኳ በሕይወት አይዘልቅም፤+ከሚጠፉ እንስሳት ምንም አይሻልም።+ +13 የሞኞች መንገድ ይህ ነው፤+እነሱ በሚናገሩት ከንቱ ቃል ተደስተው የሚከተሏቸው ሰዎች መንገድም ይኸው ነው። (ሴላ) +14 ለእርድ እንደሚነዱ በጎች ወደ መቃብር* እንዲወርዱ ተፈርዶባቸዋል። ሞት እረኛቸው ይሆናል፤በማለዳ ቅኖች ይገዟቸዋል።+ ደብዛቸው ይጠፋል፤+በቤተ መንግሥት ፋንታ መቃብር* መኖሪያቸው ይሆናል።+ +15 ሆኖም አምላክ ከመቃብር* እጅ ይዋጀኛል፤*+እሱ ይይዘኛልና። (ሴላ) +16 ሰው ሀብታም ሲሆንናየቤቱ ክብር ሲጨምር አትፍራው፤ +17 በሚሞትበት ጊዜ ከእሱ ጋር አንዳ�� ነገር ሊወስድ አይችልምና፤+ክብሩም አብሮት አይወርድም።+ +18 በሕይወት ዘመኑ ራሱን* ሲያወድስ ይኖራልና።+ (ስትበለጽግ ሰዎች ያወድሱሃል።)+ +19 መጨረሻ ላይ ግን ከአባቶቹ ትውልድ ጋር ይቀላቀላል። ከዚያ በኋላ ፈጽሞ ብርሃን አያዩም። +20 የተከበረ ቢሆንም እንኳ ይህን የማይረዳ ሰውከሚጠፉ እንስሳት ምንም አይሻልም።+ +128 ይሖዋን የሚፈሩ፣በመንገዱም የሚሄዱ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።+ + 2 በእጅህ ደክመህ ያፈራኸውን ትበላለህ። ደስተኛ ትሆናለህ፤ ደግሞም ትበለጽጋለህ።+ + 3 ሚስትህ በቤትህ ውስጥ፣ ፍሬ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤+ወንዶች ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ዛፍ ቡቃያዎች ይሆናሉ። + 4 እነሆ፣ ይሖዋን የሚፈራ ሰውእንደዚህ የተባረከ ይሆናል።+ + 5 ይሖዋ ከጽዮን ይባርክሃል። በሕይወት ዘመንህ ሁሉ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ለማየት ያብቃህ፤+ + 6 ደግሞም የልጅ ልጅ ለማየት ያብቃህ። በእስራኤል ሰላም ይስፈን። +77 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤ እሱም ይሰማኛል።+ + 2 በጭንቀት በተዋጥኩ ቀን ይሖዋን እፈልጋለሁ።+ በሌሊት እጆቼ ያለምንም ፋታ ወደ እሱ እንደተዘረጉ ናቸው፤ ልጽናና አልቻልኩም።* + 3 አምላክን ሳስታውስ እቃትታለሁ፤+ተጨንቄአለሁ፤ ኃይሌም ከዳኝ።*+ (ሴላ) + 4 የዓይኔ ቆብ እንዳይከደን ያዝከው፤በጣም ተረብሻለሁ፤ መናገርም አልችልም። + 5 የድሮውን ጊዜ መለስ ብዬ አሰብኩ፤+የጥንቶቹን ዓመታት አስታወስኩ። + 6 መዝሙሬን* በሌሊት አስታውሳለሁ፤+በልቤ አወጣለሁ አወርዳለሁ፤+በጥሞና እመረምራለሁ።* + 7 ይሖዋ ለዘላለም ይጥለናል?+ ዳግመኛስ ሞገስ አያሳየንም?+ + 8 ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ተቋርጧል? የተስፋ ቃሉስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ከንቱ ሆኖ ይቀራል? + 9 አምላክ ሞገሱን ማሳየት ረስቷል?+ወይስ ቁጣው ምሕረት ከማሳየት እንዲቆጠብ አድርጎታል? (ሴላ) +10 “እኔን የሚያስጨንቀኝ* ይህ ነው፦+ ልዑሉ አምላክ ለእኛ ያለውን አመለካከት* ለውጧል” እያልኩ ልኖር ነው? +11 ያህ ያከናወናቸውን ሥራዎች አስታውሳለሁ፤ጥንት የፈጸምካቸውን ድንቅ ተግባሮች አስታውሳለሁ። +12 በሥራዎችህም ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤ያከናወንካቸውንም ነገሮች አውጠነጥናለሁ።+ +13 አምላክ ሆይ፣ መንገዶችህ ቅዱስ ናቸው። አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?+ +14 አንተ ድንቅ ነገሮችን የምታከናውን እውነተኛ አምላክ ነህ።+ ብርታትህን ለሕዝቦች ገልጠሃል።+ +15 በኃይልህ* ሕዝብህን ይኸውምየያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች ታድገሃል።*+ (ሴላ) +16 አምላክ ሆይ፣ ውኃዎቹ አዩህ፤ውኃዎቹ ሲያዩህ ተረበሹ።+ ጥልቅ ውኃዎቹም ተናወጡ። +17 ደመናት ውኃ አዘነቡ። በደመና የተሸፈኑት ሰማያት አንጎደጎዱ፤ፍላጻዎችህም እዚህም እዚያም ተወነጨፉ።+ +18 የነጎድጓድህ ድምፅ+ እንደ ሠረገላ ድምፅ ነበር፤የመብረቅ ብልጭታዎች በዓለም* ላይ አበሩ፤+ምድር ተናወጠች፤ ደግሞም ተንቀጠቀጠች።+ +19 መንገድህ በባሕር ውስጥ ነበር፤+ጎዳናህም በብዙ ውኃዎች ውስጥ ነበር፤ይሁንና የእግርህ ዱካ ሊገኝ አልቻለም። +20 ሕዝብህን በሙሴና በአሮን እጅ+እንደ መንጋ መራህ።+ +36 ኃጢአት፣ ክፉውን ሰው በልቡ ውስጥ ሆኖ ያናግረዋል፤በዓይኖቹ ፊት አምላክን መፍራት የሚባል ነገር የለም።+ + 2 ስህተቱ ምን እንደሆነ ተረድቶ የሠራውን ነገር እንዳይጠላው፣ለራሱ ባለው አመለካከት ራሱን እጅግ ይሸነግላልና።+ + 3 ከአፉ የሚወጣው የክፋትና የሽንገላ ቃል ነው፤መልካም ነገር ለማድረግ ማስተዋል የለውም። + 4 በአልጋው ላይ ሆኖ እንኳ ክፋትን ያውጠነጥናል። ጥሩ ባልሆነ መንገድ ላይ ይቆማል፤መጥፎ የሆነውን ነገር ገሸሽ አያደርግም። + 5 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅ���ህ እስከ ሰማያት፣+ታማኝነትህ እስከ ደመናት ይደርሳል። + 6 ጽድቅህ ግርማ እንደተላበሱ ተራሮች* ነው፤+ፍርዶችህ እንደ ጥልቅ ባሕር ናቸው።+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰውንና እንስሳን ትጠብቃለህ።*+ + 7 አምላክ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው!+ የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ሥር ይሸሸጋሉ።+ + 8 በቤትህ ውስጥ ተትረፍርፎ የሚገኘውን ነገር* እስኪረኩ ድረስ ይጠጣሉ፤+መልካም ነገሮች ከሚፈስሱበት ወንዝህ ታጠጣቸዋለህ።+ + 9 የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነው፤+በብርሃንህ፣ ብርሃን ማየት እንችላለን።+ +10 ለሚያውቁህ ታማኝ ፍቅርህን፣ቀና ልብ ላላቸው ደግሞ ጽድቅህን ዘወትር አሳያቸው።+ +11 የትዕቢተኛ እግር እንዲረግጠኝ፣ወይም የክፉዎች እጅ እንዲያፈናቅለኝ አትፍቀድ። +12 ክፉ አድራጊዎች የት እንደወደቁ ተመልከት፤ተመተው ወድቀዋል፤ መነሳትም አይችሉም።+ +70 አምላክ ሆይ፣ አድነኝ፤ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+ + 2 ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚሹኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ። በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙአፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ። + 3 “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ። + 4 አንተን የሚፈልጉ ግንበአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ።+ የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣ ምንጊዜም “አምላክ ታላቅ ይሁን!” ይበሉ። + 5 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤+አምላክ ሆይ፣ ለእኔ ስትል ፈጥነህ እርምጃ ውሰድ።+ አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+ይሖዋ ሆይ፣ አትዘግይ።+ +29 እናንተ የኃያላን ልጆች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+ + 2 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ። ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ።* + 3 የይሖዋ ድምፅ ከውኃዎች በላይ ተሰማ፤ክብር የተጎናጸፈው አምላክ አንጎደጎደ።+ ይሖዋ ከብዙ ውኃዎች በላይ ነው።+ + 4 የይሖዋ ድምፅ ኃይለኛ ነው፤+የይሖዋ ድምፅ ክብራማ ነው። + 5 የይሖዋ ድምፅ አርዘ ሊባኖስን ይሰብራል፤አዎ፣ ይሖዋ አርዘ ሊባኖስን ይሰባብራል።+ + 6 ሊባኖስን* እንደ ጥጃ፣ሲሪዮንንም+ እንደ ዱር በሬ እንቦሳ እንዲዘሉ ያደርጋል። + 7 የይሖዋ ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል፤+ + 8 የይሖዋ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤+ይሖዋ የቃዴስን+ ምድረ በዳ ያናውጣል። + 9 የይሖዋ ድምፅ ርኤሞች* እንዲርበተበቱና እንዲወልዱ ያደርጋል፤ደኖችንም ያራቁታል።+ በቤተ መቅደሱም ውስጥ ያሉ ሁሉ “ክብር ለአምላክ!” ይላሉ። +10 ይሖዋ ከሚያጥለቀልቁት ውኃዎች*+ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ በዙፋን ላይ ይቀመጣል።+ +11 ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል።+ ይሖዋ ሰላም በመስጠት ሕዝቡን ይባርካል።+ +28 ዓለቴ ይሖዋ ሆይ፣ ሁልጊዜ ወደ አንተ እጣራለሁ፤+አንተም ጆሮ አትንፈገኝ። ዝም ካልከኝ፣ወደ ጉድጓድ* እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ።+ + 2 ወደ መቅደስህ ውስጠኛ ክፍል እጆቼን አንስቼ፣እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ በምጮኽበት ጊዜ ልመናዬን ስማ።+ + 3 ከክፉዎችና መጥፎ ነገር ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ጎትተህ አትውሰደኝ፤+እነሱ በልባቸው ክፋት እያለ ከባልንጀሮቻቸው ጋር የሰላም ቃል የሚያወሩ ናቸው።+ + 4 ለሠሩት ሥራ፣እንደ ክፉ ልማዳቸው ክፈላቸው።+ ለእጃቸው ሥራ መልሰህ ክፈላቸው፤እንዳደረጉትም መልስላቸው።+ + 5 ይሖዋ ላከናወናቸው ነገሮች፣ለእጆቹም ሥራ ትኩረት አይሰጡምና።+ እሱ ያፈርሳቸዋል፤ ደግሞም አይገነባቸውም። + 6 እርዳታ ለማግኘት ያቀረብኩትን ልመና ስለሰማይሖዋ የተመሰገነ ይሁን። + 7 ይሖዋ ብርታቴና+ ጋሻዬ ነው፤+ልቤ በእሱ ይተማመናል።+ ከእሱ እርዳታ ስላገኘሁ ልቤ ሐሴት ያደርጋል፤በመዝሙሬም አወድሰዋለሁ። + 8 ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ነው፤ለቀባው ታ��ቅ መዳን የሚያስገኝ መሸሸጊያ ነው።+ + 9 ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ።+ ለዘላለም እረኛ ሁናቸው፤ በክንድህም ተሸከማቸው።+ +71 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ። ፈጽሞ ለኀፍረት አልዳረግ።+ + 2 በጽድቅህ አድነኝ፤ ታደገኝም። ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤* አድነኝም።+ + 3 ምንጊዜም የምገባበትመሸሸጊያ ዓለት ሁንልኝ። አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ስለሆንክእኔን ለማዳን ትእዛዝ ስጥ።+ + 4 አምላኬ ሆይ፣ ከክፉው እጅ፣ግፈኛ ከሆነው ጨቋኝ ሰው መዳፍ ታደገኝ።+ + 5 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ተስፋዬ ነህ፤ከልጅነቴ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ።*+ + 6 ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ፤ከእናቴ ማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ።+ ሁልጊዜ አወድስሃለሁ። + 7 ለብዙዎች መደነቂያ ሆንኩ፤አንተ ግን ጽኑ መጠጊያዬ ነህ። + 8 አፌ በውዳሴህ ተሞልቷል፤+ቀኑን ሙሉ ስለ ግርማህ እናገራለሁ። + 9 በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤+ጉልበቴ በሚያልቅበት ጊዜም አትተወኝ።+ +10 ጠላቶቼ በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይናገራሉ፤ሕይወቴን* የሚሹ ሰዎችም በእኔ ላይ ሴራ ይጠነስሳሉ፤+ +11 እንዲህም ይላሉ፦ “አምላክ ትቶታል። የሚያድነው ስለሌለ አሳዳችሁ ያዙት።”+ +12 አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ። አምላኬ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+ +13 የሚቃወሙኝ* ሰዎችይፈሩ፤ ይጥፉም።+ የእኔን ጥፋት የሚሹውርደትና ኀፍረት ይከናነቡ።+ +14 እኔ ግን አንተን መጠባበቄን እቀጥላለሁ፤በውዳሴ ላይ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ። +15 አፌ ስለ ጽድቅህ ያወራል፤+ከብዛታቸው የተነሳ ላውቃቸው* ባልችልም እንኳአንደበቴ ስለ ማዳን ሥራዎችህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።+ +16 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣መጥቼ ስለ ብርቱ ሥራዎችህ እናገራለሁ፤ስለ አንተ ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ። +17 አምላክ ሆይ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ አስተምረኸኛል፤+እኔም እስካሁን ድረስ ድንቅ ሥራዎችህን አስታውቃለሁ።+ +18 አምላክ ሆይ፣ ሳረጅና ስሸብትም እንኳ አትጣለኝ።+ ለቀጣዩ ትውልድ ስለ ብርታትህ፣*ገና ለሚመጡትም ሁሉ ስለ ኃያልነትህ ልናገር።+ +19 አምላክ ሆይ፣ ጽድቅህ እጅግ ታላቅ ነው፤+ታላላቅ ነገሮችን አከናውነሃል፤አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ +20 ብዙ ጭንቅና መከራ ብታሳየኝም እንኳ+እንደገና እንዳንሰራራ አድርገኝ፤ጥልቅ ከሆነው ምድር* አውጣኝ።+ +21 ታላቅነቴ ገናና እንዲሆን አድርግ፤ዙሪያዬንም ከበህ አጽናናኝ። +22 እኔም አምላኬ ሆይ፣ ከታማኝነትህ+ የተነሳበባለ አውታር መሣሪያ አወድስሃለሁ። የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፣በበገና የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ። +23 ለአንተ የውዳሴ መዝሙር በምዘምርበት ጊዜ ከንፈሮቼ እልል ይላሉ፤+ሕይወቴን አድነሃታልና።*+ +24 ምላሴ ቀኑን ሙሉ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤*+የእኔን መጥፋት የሚሹ ሰዎች ያፍራሉና፤ ደግሞም ይዋረዳሉ።+ +38 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤ተናደህም አታርመኝ።+ + 2 ፍላጻዎችህ እስከ ውስጥ ድረስ ወግተውኛልና፤እጅህም ተጭኖኛል።+ + 3 ከቁጣህ የተነሳ መላ ሰውነቴ ታመመ።* ከኃጢአቴም የተነሳ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።+ + 4 የፈጸምኳቸው ስህተቶች በራሴ ላይ ያንዣብባሉና፤+እንደ ከባድ ሸክም በጣም ከብደውኛል። + 5 ከሞኝነቴ የተነሳቁስሌ ሸተተ፤ ደግሞም አመረቀዘ። + 6 በጭንቀት ተዋጥኩ፤ አንገቴንም ደፋሁ፤ቀኑን ሙሉ በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ። + 7 ውስጤ ተቃጠለ፤*መላ ሰውነቴ ታመመ።+ + 8 ደነዘዝኩ፤ ፈጽሞም ደቀቅኩ፤በጭንቀት ከተዋጠው ልቤ የተነሳ እጅግ እቃትታለሁ።* + 9 ይሖዋ ሆይ፣ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ነው፤የማሰማው ሲቃም ከአንተ የተሰወረ አይደለም። +10 ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበቴ ከድቶኛል፤የዓይኔም ብርሃን ጠፍቷል።+ +11 ከቁስሌ የተነሳ ወዳጆ��ና ጓደኞቼ ሸሹኝ፤በቅርብ የሚያውቁኝ ሰዎችም ከእኔ ራቁ። +12 ሕይወቴን* የሚሹ ሰዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤እኔን መጉዳት የሚፈልጉም ስለ ጥፋት ያወራሉ፤+ቀኑን ሙሉ ተንኮል ሲሸርቡ ይውላሉ። +13 እኔ ግን እንደ ደንቆሮ አልሰማቸውም፤+እንደ ዱዳም አፌን አልከፍትም።+ +14 መስማት እንደማይችል፣በአፉም የመከላከያ መልስ እንደማይሰጥ ሰው ሆንኩ። +15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በተስፋ ተጠባብቄአለሁና፤+ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተም መልስ ሰጥተኸኛል።+ +16 “በእኔ ውድቀት አይፈንድቁ፤ወይም እግሬ ቢንሸራተት በእኔ ላይ አይኩራሩ” ብያለሁና። +17 ልወድቅ ምንም አልቀረኝም ነበርና፤ሥቃዬም ከእኔ አልተለየም።+ +18 በደሌን ተናዘዝኩ፤+ኃጢአቴም አስጨንቆኝ ነበር።+ +19 ይሁንና ጠላቶቼ ብርቱዎችና* ኃያላን ናቸው፤*ያላንዳች ምክንያት የሚጠሉኝ ተበራከቱ። +20 ላደረግኩት መልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤መልካም የሆነውን ነገር በመከተሌ ይቃወሙኝ ነበር። +21 ይሖዋ ሆይ፣ አትተወኝ። አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+ +22 አዳኜ ይሖዋ ሆይ፣እኔን ለመርዳት ፍጠን።+ +86 ይሖዋ ሆይ፣ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤* ደግሞም መልስልኝ፤ጎስቋላና ድሃ ነኝና።+ + 2 እኔ ታማኝ ስለሆንኩ ሕይወቴን* ጠብቃት።+ በአንተ የሚታመነውን አገልጋይህን አድነው፤አንተ አምላኬ ነህና።+ + 3 ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ፤+ቀኑን ሙሉ አንተን እጣራለሁና።+ + 4 አገልጋይህን ደስ አሰኘው፤*ይሖዋ ሆይ፣ የአንተን እርዳታ እሻለሁና።* + 5 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጥሩ ነህና፤+ ይቅር ለማለትም ዝግጁ ነህ፤+አንተን ለሚጠሩ ሁሉ የምታሳየው ታማኝ ፍቅር ወሰን የለውም።+ + 6 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን አዳምጥ፤እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውንም ልመና በትኩረት ስማ።+ + 7 አንተ መልስ ስለምትሰጠኝ፣+በተጨነቅኩ ቀን አንተን እጣራለሁ።+ + 8 ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤+ከአንተ ሥራ ጋር የሚወዳደር አንድም ሥራ የለም።+ + 9 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ የሠራሃቸው ብሔራት ሁሉ ይመጣሉ፤በፊትህም ይሰግዳሉ፤+ለስምህም ክብር ይሰጣሉ።+ +10 አንተ ታላቅ ነህና፤ ድንቅ ነገሮችም ትሠራለህ፤+አንተ አምላክ ነህ፤ ከአንተ ሌላ የለም።+ +11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ።+ በእውነትህ እሄዳለሁ።+ ስምህን እፈራ ዘንድ ልቤን አንድ አድርግልኝ።*+ +12 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ፤+ስምህንም ለዘላለም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ +13 ለእኔ የምታሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና፤ሕይወቴንም* ጥልቅ ከሆነው መቃብር* አድነሃል።+ +14 አምላክ ሆይ፣ እብሪተኛ ሰዎች በእኔ ላይ ተነስተዋል፤+የጨካኞች ቡድን ሕይወቴን* ይሻታል፤አንተንም ከምንም አልቆጠሩም።*+ +15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን መሐሪና ሩኅሩኅ፣*ለቁጣ የዘገየህ እንዲሁም ታማኝ ፍቅርህና ታማኝነትህ* የበዛ አምላክ ነህ።+ +16 ወደ እኔ ተመልከት፤ ሞገስም አሳየኝ።+ ለአገልጋይህ ብርታትህን ስጠው፤+የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን። +17 እኔን የሚጠሉ አይተው እንዲያፍሩ፣የጥሩነትህን ምልክት* አሳየኝ። ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ረዳቴና አጽናኜ ነህና። +8 ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው፤ግርማህ ከሰማያትም በላይ ከፍ ከፍ እንዲል አድርገሃል!*+ + 2 ከባላጋራዎችህ የተነሳ፣ከልጆችና ከሕፃናት አፍ በሚወጡ ቃላት+ ብርታትህን አሳየህ፤ይህም ጠላትንና ተበቃይን ዝም ለማሰኘት ነው። + 3 የጣቶችህን ሥራ ሰማያትን፣አንተ የሠራሃቸውን ጨረቃንና ከዋክብትን ስመለከት፣+ + 4 ታስበው ዘንድ ሟች ሰው ምንድን ነው?ትንከባከበውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?+ + 5 ከመላእክት* በጥቂቱ አሳነስከው፤የክብርና የግርማ ዘውድም ደፋህለት። + 6 በእጆችህ ሥራዎች ላይ ሥልጣን ሰጠኸው፤+ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አደረግክለት፦ + 7 መንጎቹንና ከብቶቹን ሁሉ፣እንዲሁም የዱር አራዊትን፣+ + 8 የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣዎችን፣በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትን ሁሉ ከእግሩ በታች አደረግክለት። + 9 ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው! +11 ይሖዋን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ።+ ታዲያ እንዴት እንዲህ ትሉኛላችሁ?* “እንደ ወፍ ወደ ተራራህ ብረር!* + 2 ክፉዎች ደጋናቸውን እንዴት እንደወጠሩ ተመልከት፤በጨለማ፣ ልበ ቀና የሆኑትን ለመውጋት፣ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል። + 3 መሠረቶቹ* ከተናዱ፣ጻድቁ ሰው ምን ማድረግ ይችላል?” + 4 ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው።+ የይሖዋ ዙፋን በሰማያት ነው።+ የገዛ ዓይኖቹ ይመለከታሉ፤ ንቁ የሆኑት* ዓይኖቹ የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።+ + 5 ይሖዋ ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ይመረምራል፤+ዓመፅን* የሚወድን ማንኛውንም ሰው ይጠላል።*+ + 6 በክፉዎች ላይ ወጥመድ* ያዘንባል፤እሳትና ድኝ+ እንዲሁም የሚለበልብ ነፋስ ጽዋቸው ይሆናል። + 7 ይሖዋ ጻድቅ ነውና፤+ የጽድቅ ሥራዎችን ይወዳል።+ ቅን የሆኑ ሰዎች ፊቱን ያያሉ።*+ +2 ብሔራት የታወኩት ለምንድን ነው?ሕዝቦችስ ከንቱ ነገር የሚያጉተመትሙት* ለምንድን ነው?+ + 2 የምድር ነገሥታት ተሰለፉ፤ከፍተኛ ባለሥልጣናትም በአንድነት ተሰብስበው*+በይሖዋና እሱ በቀባው ላይ*+ ተነሱ። + 3 “ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፤ገመዳቸውንም እናስወግድ!” ይላሉ። + 4 በሰማያት በዙፋን ላይ የተቀመጠው ይስቃል፤ይሖዋ ይሳለቅባቸዋል። + 5 በዚያን ጊዜ በቁጣ ይናገራቸዋል፤በሚነድ ቁጣውም ያሸብራቸዋል፤ + 6 እንዲህም ይላቸዋል፦ “እኔ ራሴ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን+ ላይንጉሤን ሾምኩ።”+ + 7 የይሖዋን ድንጋጌ ልናገር፤እንዲህ ብሎኛል፦ “አንተ ልጄ ነህ፤+እኔ ዛሬ ወለድኩህ።+ + 8 ጠይቀኝ፤ ብሔራትን ርስትህ፣የምድርንም ዳርቻዎች ግዛትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ።+ + 9 በብረት በትረ መንግሥት ትሰብራቸዋለህ፤+እንደ ሸክላ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።”+ +10 እንግዲህ እናንተ ነገሥታት አስተውሉ፤እናንተ የምድር ፈራጆች እርማት ተቀበሉ።* +11 ይሖዋን በፍርሃት አገልግሉ፤ለእሱ በመንቀጥቀጥም ሐሴት አድርጉ። +12 ልጁን አክብሩ፤*+ አለዚያ አምላክ* ይቆጣል፤ከመንገዱም ትጠፋላችሁ፤+ቁጣው ፈጥኖ ይነድዳልና። እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ደስተኞች ናቸው። +147 ያህን አወድሱ!* ለአምላካችን የውዳሴ መዝሙር መዘመር ጥሩ ነው፤እሱን ማወደስ ደስ ያሰኛል፤ ደግሞም ተገቢ ነው።+ + 2 ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ይገነባል፤+የተበተኑትን የእስራኤል ነዋሪዎች ይሰበስባል።+ + 3 የተሰበረ ልብ ያላቸውን ይጠግናል፤ቁስላቸውን ይፈውሳል። + 4 የከዋክብትን ብዛት ይቆጥራል፤ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።+ + 5 ጌታችን ታላቅ ነው፤ ደግሞም እጅግ ኃያል ነው፤+ማስተዋሉም ወሰን የለውም።+ + 6 ይሖዋ የዋሆችን ያነሳል፤+ክፉዎችን ግን መሬት ላይ ይጥላል። + 7 ለይሖዋ በምስጋና ዘምሩ፤ለአምላካችን በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ + 8 እሱ ሰማያትን በደመናት ይሸፍናል፤ለምድር ዝናብ ይሰጣል፤+በተራሮች ላይ ሣር እንዲበቅል ያደርጋል።+ + 9 ለእንስሳት እንዲሁም የሚበሉትን ለማግኘት ለሚጮኹ የቁራ ጫጩቶችምግብ ይሰጣል።+ +10 በፈረስ ጉልበት አይደሰትም፤+የሰው እግር ጥንካሬም አያስደንቀውም።+ +11 ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እሱን በሚፈሩ፣ታማኝ ፍቅሩን በሚጠባበቁ ሰዎች ይደሰታል።+ +12 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርጊ። ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽን አወድሺ። +13 እሱ የከተማሽን በሮች መወርወሪያዎች ያጠናክራል፤በውስጥሽ ያሉትን ወንዶች ልጆች ይባርካል። +14 በክልል�� ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤+ምርጥ በሆነ ስንዴ* ያጠግብሻል።+ +15 ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ቃሉም በፍጥነት ይሮጣል። +16 በረዶን እንደ ሱፍ ይልካል፤+አመዳዩን እንደ አመድ ይበትናል።+ +17 የበረዶውን ድንጋይ እንደ ዳቦ ፍርፋሪ ይወረውራል።+ እሱ የሚልከውን ቅዝቃዜ ማን ሊቋቋም ይችላል?+ +18 ቃሉን ይልካል፤ እነሱም ይቀልጣሉ። ነፋሱ እንዲነፍስ ያደርጋል፤+ ውኃውም ይፈስሳል። +19 ቃሉን ለያዕቆብ፣ሥርዓቱንና ፍርዶቹን ለእስራኤል ያስታውቃል።+ +20 ይህን ለሌላ ለማንም ብሔር አላደረገም፤+እነሱ ስለ ፍርዶቹ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም። ያህን አወድሱ!*+ +26 ይሖዋ ሆይ፣ በንጹሕ አቋም* ተመላልሻለሁና ፍረድልኝ፤+ያለምንም ማወላወል በይሖዋ ታምኛለሁ።+ + 2 ይሖዋ ሆይ፣ መርምረኝ፤ ፈትነኝም፤በውስጤ ያለውን ሐሳብና* ልቤን አጥራልኝ።+ + 3 ታማኝ ፍቅርህ ምንጊዜም በፊቴ ነውና፤በእውነትህም እመላለሳለሁ።+ + 4 አታላይ ከሆኑ ሰዎች ጋር አልቀራረብም፤*+ማንነታቸውን ከሚደብቁም እርቃለሁ።* + 5 ከክፉ ሰዎች ጋር መሆን እጠላለሁ፤+ከክፉዎችም ጋር መቀራረብ* አልፈልግም።+ + 6 ንጹሕ መሆኔን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤ይሖዋ ሆይ፣ መሠዊያህን እዞራለሁ፤ + 7 ይህም የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣+ድንቅ ሥራዎችህንም ሁሉ አውጅ ዘንድ ነው። + 8 ይሖዋ ሆይ፣ የምትኖርበትን ቤት፣+የክብርህንም ማደሪያ ቦታ እወዳለሁ።+ + 9 ከኃጢአተኞች ጋር አታጥፋኝ፤*+ሕይወቴንም ከዓመፀኞች* ጋር አታስወግድ፤ +10 እጆቻቸው አሳፋሪ ድርጊት ይፈጽማሉ፤ቀኝ እጃቸውም በጉቦ የተሞላ ነው። +11 እኔ ግን ንጹሕ አቋሜን ጠብቄ እመላለሳለሁ። ታደገኝ፤* ሞገስም አሳየኝ። +12 እግሬ በደልዳላ ስፍራ ቆሟል፤+በታላቅ ጉባኤ መካከል* ይሖዋን አወድሳለሁ።+ +44 አምላክ ሆይ፣ በገዛ ጆሯችን ሰምተናል፤ከረጅም ጊዜ በፊት፣በእነሱ ዘመን ያከናወንካቸውን ተግባሮች፣አባቶቻችን ተርከውልናል።+ + 2 በእጅህ ብሔራትን አባረርክ፤+በዚያም አባቶቻችንን አሰፈርክ።+ ብሔራትን ድል አድርገህ አባረርካቸው።+ + 3 ምድሪቱን የወረሱት በገዛ ሰይፋቸው አይደለም፤+ድል ያጎናጸፋቸውም የገዛ ክንዳቸው አይደለም።+ ከዚህ ይልቅ በእነሱ ደስ ስለተሰኘህ+ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አድርጓል።+ + 4 አምላክ ሆይ፣ አንተ ንጉሤ ነህ፤+ለያዕቆብ ፍጹም ድል* እዘዝ።* + 5 በአንተ ኃይል ጠላቶቻችንን እንመክታለን፤+በእኛ ላይ የተነሱትን በስምህ እንረግጣለን።+ + 6 በቀስቴ አልታመንምና፤ሰይፌም ሊያድነኝ አይችልም።+ + 7 ከጠላቶቻችን ያዳንከን፣የሚጠሉንን ሰዎች ያዋረድካቸው አንተ ነህ።+ + 8 ቀኑን ሙሉ ለአምላክ ውዳሴ እናቀርባለን፤ስምህንም ለዘላለም እናመሰግናለን። (ሴላ) + 9 አሁን ግን ትተኸናል፤ ደግሞም አዋርደኸናል፤ከሠራዊታችንም ጋር አብረህ አትወጣም። +10 ከጠላታችን ፊት እንድንሸሽ ታደርገናለህ፤+የሚጠሉን ሰዎች የፈለጉትን ሁሉ ይወስዱብናል። +11 እንደ በግ እንዲበሉን ለጠላቶቻችን አሳልፈህ ሰጠኸን፤በብሔራት መካከል በተንከን።+ +12 ሕዝብህን በማይረባ ዋጋ ሸጥክ፤+ከሽያጩ ያገኘኸው ትርፍ የለም። +13 በጎረቤቶቻችን ዘንድ መሳለቂያ አደረግከን፤በዙሪያችን ያሉት ሁሉ እንዲያላግጡብንና እንዲዘብቱብን አደረግክ። +14 በብሔራት መካከል መቀለጃ እንድንሆን፣*ሕዝቦችም ራሳቸውን እንዲነቀንቁብን አደረግክ።+ +15 ቀኑን ሙሉ በኀፍረት ተውጫለሁ፤ውርደትም ተከናንቤአለሁ፤ +16 ይህም ከሚሳለቁና ከሚሳደቡ ሰዎች ድምፅ፣እንዲሁም ከሚበቀለን ጠላታችን የተነሳ ነው። +17 ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደርሷል፤ እኛ ግን አልረሳንህም፤ቃል ኪዳንህንም አላፈረስንም።+ +18 ልባችን አልሸፈተም፤እግራችንም ከመንገ���ህ አልወጣም። +19 ይሁንና ቀበሮዎች በሚኖሩበት ቦታ ሰባብረኸናል፤በድቅድቅ ጨለማም ሸፍነኸናል። +20 የአምላካችንን ስም ረስተን፣ወይም ወደ ባዕድ አምላክ ለመጸለይ እጃችንን ዘርግተን ከሆነ፣ +21 አምላክ ይህን አይደርስበትም? እሱ በልብ ውስጥ ያለውን ሚስጥር ያውቃል።+ +22 ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ሞትን እንጋፈጣለን፤እንደ እርድ በጎችም ተቆጠርን።+ +23 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ። ለምንስ ትተኛለህ?+ ንቃ! ለዘላለም አትጣለን።+ +24 ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? የደረሰብንን ጉስቁልናና ጭቆና የምትረሳው ለምንድን ነው? +25 ወደ አፈር ተጥለናልና፤*ሰውነታችን ከመሬት ጋር ተጣብቋል።+ +26 እኛን ለመርዳት ተነስ!+ ስለ ታማኝ ፍቅርህ ስትል ታደገን።*+ +80 ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራየእስራኤል እረኛ ሆይ፣+ አዳምጥ። ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፣+ብርሃን አብራ።* + 2 በኤፍሬም፣ በቢንያምና በምናሴ ፊትኃያልነትህን አሳይ፤+መጥተህም አድነን።+ + 3 አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤+እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+ + 4 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝቦችህ የሚያቀርቡትን ጸሎት የምትጠላው* እስከ መቼ ነው?+ + 5 እንባን እንደ ምግብ ትመግባቸዋለህ፤ደግሞም እንባ ትግታቸዋለህ። + 6 ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግከን፤ጠላቶቻችን እንዳሻቸው ያላግጡብናል።+ + 7 የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+ + 8 የወይን ተክል+ ከግብፅ እንድትወጣ አደረግክ። ብሔራትን አባረህ እሷን ተከልክ።+ + 9 መሬቱን መነጠርክላት፤እሷም ሥር ሰዳ በምድሪቱ ላይ ተንሰራፋች።+ +10 ተራሮች በጥላዋ፣የአምላክ አርዘ ሊባኖሶችም በቅርንጫፎቿ ተሸፈኑ። +11 ቅርንጫፎቿ እስከ ባሕሩ፣ቀንበጦቿም እስከ ወንዙ* ድረስ ተዘረጉ።+ +12 በዚያ የሚያልፉ ሁሉ ፍሬዋን እንዲቀጥፉ፣+የወይን እርሻዋን የድንጋይ ቅጥሮች ያፈረስከው ለምንድን ነው?+ +13 ከጫካ የወጡ የዱር አሳማዎች ያወድሟታል፤በሜዳ ያሉ የዱር አራዊትም ይበሏታል።+ +14 የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ እባክህ ተመለስ። ከሰማይ ወደ ታች እይ፤ ተመልከትም! ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤+ +15 ቀኝ እጅህ የተከላትን ግንድ*+ በእንክብካቤ ያዛት፤ለራስህ ስትል ያጠነከርከውንም ልጅ* ተመልከት።+ +16 እሷ ተቆርጣ በእሳት ተቃጥላለች።+ ሕዝቡ ከተግሣጽህ* የተነሳ ይጠፋል። +17 እጅህ በቀኝህ ላለው ሰው፣ለራስህም ስትል ብርቱ ላደረግከው የሰው ልጅ ድጋፍ ትስጥ።+ +18 እኛም ከአንተ አንርቅም። ስምህን መጥራት እንድንችል በሕይወት አኑረን። +19 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+ +137 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣+ በዚያ ተቀምጠን ነበር። ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።+ + 2 በመካከሏ* በሚገኙ የአኻያ ዛፎች ላይበገናዎቻችንን ሰቀልን።+ + 3 የማረኩን ሰዎች በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤+የሚያፌዙብን ሰዎች በመዝሙር እንድናዝናናቸው “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን። + 4 የይሖዋን መዝሙርበባዕድ ምድር እንዴት ልንዘምር እንችላለን? + 5 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺን ብረሳ፣ቀኝ እጄ ትክዳኝ።*+ + 6 ሳላስታውስሽ ብቀር፣ኢየሩሳሌምን ለደስታዬ ምክንያትከሆኑት ነገሮች በላይ ባላደርግ፣+ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ትጣበቅ። + 7 ይሖዋ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀንኤዶማውያን ያሉትን አስታውስ፤ “አፍርሷት! ከሥረ መሠረቷ አፍርሷት!”+ ብለው ነበር። + 8 በቅርቡ የምትጠፊው አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣+በእኛ ላይ በፈጸምሽው በዚያው ድርጊትብድራትሽን የሚመልስ ደስተኛ ይሆ���ል።+ + 9 ልጆችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጥ+ደስተኛ ይሆናል። +139 ይሖዋ ሆይ፣ በሚገባ መርምረኸኛል፤ ደግሞም ታውቀኛለህ።+ + 2 አንተ ስቀመጥም ሆነ ስነሳ ታውቃለህ።+ ሐሳቤን ከሩቅ ታስተውላለህ።+ + 3 ስጓዝም ሆነ ስተኛ በሚገባ ታየኛለህ፤መንገዶቼን ሁሉ ታውቃለህ።+ + 4 ይሖዋ ሆይ፣ ገና ቃል ከአፌ ሳይወጣ፣እነሆ፣ አንተ ሁሉን ነገር አስቀድመህ በሚገባ ታውቃለህ።+ + 5 ከኋላም ከፊትም ከበብከኝ፤እጅህንም በላዬ ላይ ታደርጋለህ። + 6 እንዲህ ያለው እውቀት እኔ ልረዳው ከምችለው በላይ ነው።* በጣም ከፍ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ልደርስበት አልችልም።*+ + 7 ከመንፈስህ ወዴት ላመልጥ እችላለሁ?ከፊትህስ ወዴት ልሸሽ እችላለሁ?+ + 8 ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ፤በመቃብር* አልጋዬን ባነጥፍም እነሆ፣ አንተ በዚያ ትኖራለህ።+ + 9 እጅግ ርቆ በሚገኝ ባሕር አቅራቢያ ለመኖር፣በንጋት ክንፍ ብበር፣ +10 በዚያም እንኳ እጅህ ትመራኛለች፤ቀኝ እጅህም ትይዘኛለች።+ +11 “በእርግጥ ጨለማ ይሰውረኛል!” ብል፣ በዚያን ጊዜ በዙሪያዬ ያለው ሌሊት ብርሃን ይሆናል። +12 ጨለማው ለአንተ አይጨልምብህም፤ይልቁንም ሌሊቱ እንደ ቀን ብሩህ ይሆናል፤+ጨለማ ለአንተ እንደ ብርሃን ነው።+ +13 አንተ ኩላሊቴን ሠርተሃልና፤በእናቴ ማህፀን ውስጥ ጋርደህ አስቀመጥከኝ።*+ +14 በሚያስደምም ሁኔታ ግሩምና ድንቅ ሆኜ ስለተፈጠርኩ+ አወድስሃለሁ። ሥራዎችህ አስደናቂ ናቸው፤+ይህን በሚገባ አውቃለሁ።* +15 በስውር በተሠራሁ ጊዜ፣በማህፀን ውስጥ እያደግኩ በነበረበት ወቅት፣*አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም ነበር።+ +16 ፅንስ እያለሁ እንኳ ዓይኖችህ አዩኝ፤የአካሌ ክፍሎች በሙሉ በመጽሐፍህ ተጻፉ፤አንዳቸውም ወደ ሕልውና ከመምጣታቸው በፊት፣የተሠሩባቸውን ቀኖች በተመለከተ በዝርዝር ተጻፈ። +17 ሐሳቦችህ ለእኔ ምንኛ ውድ ናቸው!+ አምላክ ሆይ፣ ቁጥራቸው ምንኛ ብዙ ነው!+ +18 ልቆጥራቸው ብሞክር ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ።+ ከእንቅልፌ ስነቃም ገና ከአንተው ጋር ነኝ።*+ +19 አምላክ ሆይ፣ ምነው ክፉውን በገደልከው!+ በዚያን ጊዜ ጨካኞች* ከእኔ ይርቁ ነበር፤ +20 እነሱ በተንኮል ተነሳስተው በአንተ ላይ ክፉ ነገር* ይናገራሉ፤ስምህን በከንቱ የሚያነሱ ጠላቶችህ ናቸው።+ +21 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን የሚጠሉትን እጠላ የለም?+በአንተ ላይ የሚያምፁትንስ እጸየፍ የለም?+ +22 እጅግ ጠላኋቸው፤+ለእኔ የለየላቸው ጠላቶች ሆነዋል። +23 አምላክ ሆይ፣ በሚገባ ፈትሸኝ፤ ልቤንም እወቅ።+ መርምረኝ፤ የሚያስጨንቁኝንም* ሐሳቦች እወቅ።+ +24 በውስጤ ጎጂ የሆነ ዝንባሌ ካለ እይ፤+በዘላለምም መንገድ ምራኝ።+ +68 አምላክ ይነሳ፤ ጠላቶቹ ይበታተኑ፤የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።+ + 2 ጭስ በኖ እንደሚጠፋ ሁሉ እነሱንም አጥፋቸው፤ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣ክፉዎችም ከአምላክ ፊት ይጥፉ።+ + 3 ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤+በአምላክ ፊት ሐሴት ያድርጉ፤በደስታም ይፈንጥዙ። + 4 ለአምላክ ዘምሩ፤ ለስሙም የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።+ በበረሃማ ሜዳዎች* እየጋለበ ለሚያቋርጠው ለእሱ ዘምሩ። ስሙ ያህ* ነው!+ በፊቱ እጅግ ደስ ይበላችሁ! + 5 በተቀደሰ መኖሪያው ያለው አምላክ+አባት ለሌላቸው ልጆች አባት፣ ለመበለቶች ደግሞ ጠባቂ* ነው።+ + 6 አምላክ ብቸኛ ለሆኑ ሰዎች መኖሪያ ቤት ይሰጣቸዋል፤+እስረኞችን ነፃ አውጥቶ ብልጽግና ያጎናጽፋቸዋል።+ ግትር የሆኑ ሰዎች* ግን ውኃ በተጠማ ምድር ይኖራሉ።+ + 7 አምላክ ሆይ፣ ሕዝብህን በመራህ ጊዜ፣*+በረሃውንም አቋርጠህ በተጓዝክ ጊዜ (ሴላ) + 8 ምድር ተናወጠች፤+በአምላክ ፊት ሰማይ ዝናብ አወረደ፤*ይህ የሲና ተራራ በአምላክ ይኸውም በእስራኤል አምላክ ፊት ተናወጠ።+ + 9 አምላክ ሆይ፣ ብዙ ���ናብ እንዲዘንብ አደረግክ፤ለዛለው ሕዝብህ* ብርታት ሰጠኸው። +10 ድንኳኖችህ በተተከሉበት ሰፈር ሕዝብህ ተቀመጠ፤+አምላክ ሆይ፣ በጥሩነትህ ለድሃው የሚያስፈልገውን ሰጠኸው። +11 ይሖዋ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ምሥራቹን የሚያውጁ ሴቶች ታላቅ ሠራዊት ናቸው።+ +12 የብዙ ሠራዊት ነገሥታት እግሬ አውጭኝ ብለው ይሸሻሉ!+ በቤት የምትቀር ሴትም ምርኮ ትካፈላለች።+ +13 እናንተ በሰፈሩ ውስጥ በሚነድ እሳት* መካከል ብትተኙ እንኳ፣በብር የተለበጡ ክንፎችናበጠራ* ወርቅ የተለበጡ ላባዎች ያሏት ርግብ ትኖራለች። +14 ሁሉን ቻይ የሆነው ነገሥታቷን በበታተነ ጊዜ፣+በጻልሞን በረዶ ወረደ።* +15 በባሳን የሚገኘው ተራራ+ የአምላክ ተራራ ነው፤*በባሳን የሚገኘው ተራራ ባለ ብዙ ጫፍ ተራራ ነው። +16 እናንተ ባለ ብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፣አምላክ መኖሪያው አድርጎ የመረጠውን ተራራ+ በምቀኝነት ዓይን የምታዩት ለምንድን ነው? አዎ፣ ይሖዋ በዚያ ለዘላለም ይኖራል።+ +17 የአምላክ የጦር ሠረገሎች እልፍ አእላፋት፣ ሺህ ጊዜ ሺህ ናቸው።+ ይሖዋ ከሲና ወደ ቅዱሱ ስፍራ መጥቷል።+ +18 ወደ ላይ ወጣህ፤+ምርኮኞችን ወሰድክ፤አምላካችን ያህ ሆይ፣ በመካከላቸው ትኖር ዘንድሰዎችን፣ አዎ እልኸኛ የሆኑትን ጭምር+ እንደ ስጦታ አድርገህ ወሰድክ።+ +19 ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣+የሚያድነን እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ይወደስ። (ሴላ) +20 እውነተኛው አምላክ፣ አዳኝ አምላካችን ነው፤+ደግሞም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ከሞት ይታደጋል።+ +21 አዎ፣ አምላክ የጠላቶቹን ራስ፣ኃጢአት መሥራታቸውን የማይተዉ ሰዎችንም ፀጉራም አናት ይፈረካክሳል።+ +22 ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “ከባሳን+ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ከጥልቅ ባሕር አውጥቼ አመጣቸዋለሁ፤ +23 ይህም እግርህ በደም እንዲታጠብ፣+ውሾችህም የጠላቶችህን ደም እንዲልሱ ነው።” +24 አምላክ ሆይ፣ እነሱ የድል ሰልፍህን ያያሉ፤ይህም አምላኬና ንጉሤ ወደ ቅዱሱ ስፍራ የሚያደርገው የድል ጉዞ ነው።+ +25 ዘማሪዎቹ ከፊት ሆነው ሲጓዙ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚጫወቱት ሙዚቀኞች ደግሞ ከኋላ ይከተሏቸው ነበር፤+አታሞ የሚመቱ ወጣት ሴቶችም በመካከላቸው ነበሩ።+ +26 ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት* አምላክን አወድሱ፤እናንተ ከእስራኤል ምንጭ የተገኛችሁ ሰዎች፣ ይሖዋን አወድሱ።+ +27 የሁሉም ታናሽ የሆነው ቢንያም+ በዚያ ሰዎችን ይገዛል፤የይሁዳ መኳንንትም ከሚንጫጩ ጭፍሮቻቸው ጋር፣እንዲሁም የዛብሎን መኳንንትና የንፍታሌም መኳንንት በዚያ አሉ። +28 አምላካችሁ ብርቱዎች እንድትሆኑ አዟል። ለእኛ ስትል እርምጃ የወሰድከው አምላክ ሆይ፣ ብርታትህን አሳይ።+ +29 በኢየሩሳሌም ካለው ቤተ መቅደስህ+ የተነሳ፣ነገሥታት ለአንተ ስጦታ ያመጣሉ።+ +30 ሕዝቦቹ ከብር የተሠሩ ነገሮችን አምጥተው እስኪሰግዱ* ድረስበሸምበቆዎች መካከል የሚኖሩትን አራዊት፣የኮርማዎችን ጉባኤና+ ጥጆቻቸውን ገሥጽ። ይሁንና ጦርነት የሚያስደስታቸውን ሕዝቦች ይበታትናል። +31 ከነሐስ የተሠሩ ዕቃዎች* ከግብፅ ይመጣሉ፤+ኢትዮጵያ* ለአምላክ ስጦታ ለመስጠት ትጣደፋለች። +32 እናንተ የምድር መንግሥታት ሆይ፣ ለአምላክ ዘምሩ፤+ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ (ሴላ) +33 ከጥንት ጀምሮ በነበሩት ሰማየ ሰማያት ላይ ለሚጋልበው ዘምሩ።+ እነሆ፣ እሱ በኃያል ድምፁ ያስገመግማል። +34 ለአምላክ ብርታት እውቅና ስጡ።+ ግርማዊነቱ በእስራኤል ላይ ነው፤ብርታቱም በሰማያት* ውስጥ ነው። +35 አምላክ ከታላቅ መቅደሱ ሲወጣ፣* ፍርሃት* ያሳድራል።+ እሱ ለሕዝቡ ብርታትና ኃይል የሚሰጥየእስራኤል አምላክ ነው።+ አምላክ ይወደስ። +4 ጻድቅ አምላኬ ሆይ፣+ ስጣራ መልስልኝ። በምጨነቅበት ጊዜ ማምለጫ መንገድ* አዘጋጅልኝ። ቸርነት አሳየኝ፤ ጸሎቴንም ስማ። + 2 እናንተ የሰው ልጆች፣ ክብሬን ወደ ውርደት የምትለውጡት እስከ መቼ ነው? ከንቱ ነገሮችን የምትወዱት እስከ መቼ ነው? ሐሰትንስ የምትሹት እስከ መቼ ነው? (ሴላ) + 3 ይሖዋ ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ልዩ በሆነ መንገድ እንደሚይዘው እወቁ፤*ይሖዋ በጠራሁት ጊዜ ይሰማኛል። + 4 ተቆጡ፤ ሆኖም ኃጢአት አትሥሩ።+ የምትናገሩትን በመኝታችሁ ላይ ሳላችሁ በልባችሁ ተናገሩ፤ ጸጥም በሉ። (ሴላ) + 5 የጽድቅ መሥዋዕቶች አቅርቡ፤በይሖዋም ታመኑ።+ + 6 “መልካም ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች አሉ። ይሖዋ ሆይ፣ የፊትህን ብርሃን በላያችን አብራ።+ + 7 የተትረፈረፈ እህል ከሰበሰቡና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ካመረቱ ሰዎች ይበልጥልቤ በሐሴት እንዲሞላ አደረግክ። + 8 በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤+ይሖዋ ሆይ፣ ተረጋግቼ እንድኖር የምታደርገኝ አንተ ብቻ ነህና።+ +41 ለተቸገረ ሰው የሚያስብ ደስተኛ ነው፤+በመከራ ቀን ይሖዋ ይታደገዋል። + 2 ይሖዋ ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል። በምድር ላይ ደስተኛ ይባላል፤+ለጠላቶቹ ምኞት* አሳልፈህ አትሰጠውም።+ + 3 ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ይሖዋ ይደግፈዋል፤+በታመመበት ወቅት መኝታውን ሙሉ በሙሉ ትቀይርለታለህ። + 4 እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ።+ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና+ ፈውሰኝ”*+ አልኩ። + 5 ጠላቶቼ ግን “የሚሞተውና ስሙ ከናካቴው የሚረሳው መቼ ነው?” እያሉ ስለ እኔ ክፉ ወሬ ያወራሉ። + 6 ከእነሱ አንዱ እኔን ለማየት ቢመጣ ልቡ ውሸት ይናገራል። እኔን የሚጎዳ ወሬ ይቃርማል፤ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ በየቦታው ያወራዋል። + 7 የሚጠሉኝ ሁሉ እርስ በርስ ይንሾካሾካሉ፤በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይሸርባሉ፤ + 8 “ክፉ ነገር ደርሶበታል፤ከእንግዲህ ከወደቀበት አይነሳም” ይላሉ።+ + 9 ሌላው ቀርቶ ከእኔ ጋር ሰላም የነበረው፣ እምነት የጣልኩበትና+ከማዕዴ ይበላ የነበረ ሰው ተረከዙን በእኔ ላይ አነሳ።*+ +10 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ብድራታቸውን እከፍል ዘንድሞገስ አሳየኝ፤ ደግሞም አንሳኝ። +11 ጠላቴ በእኔ ላይ በድል አድራጊነት እልል ሳይል ሲቀር፣ አንተ በእኔ ደስ እንደተሰኘህ በዚህ አውቃለሁ።+ +12 እኔ በበኩሌ ንጹሕ አቋሜን* በመጠበቄ ትደግፈኛለህ፤+በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።+ +13 የእስራኤል አምላክ ይሖዋከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ።+ አሜን፣ አሜን። +63 አምላክ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ዘወትር እጠባበቃለሁ።+ አንተን ተጠማሁ።*+ ውኃ በሌለበት ደረቅና የተጠማ ምድርአንተን ከመናፈቄ የተነሳ እጅግ ዝያለሁ።*+ + 2 ስለዚህ በቅዱሱ ስፍራ አንተን ተመለከትኩ፤ብርታትህንና ክብርህን አየሁ።+ + 3 ታማኝ ፍቅርህ ከሕይወት ስለሚሻል+የገዛ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።+ + 4 በመሆኑም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አወድስሃለሁ፤በአንተም ስም እጆቼን ወደ ላይ አነሳለሁ። + 5 ምርጥ የሆነውንና ስቡን በልቼ ጠገብኩ፤*ስለዚህ በከንፈሬ እልልታ አፌ ያወድስሃል።+ + 6 መኝታዬ ላይ ሆኜ አንተን አስታውሳለሁ፤ሌሊት* ስለ አንተ አሰላስላለሁ።+ + 7 አንተ ረዳቴ ነህና፤+በክንፎችህም ጥላ ሥር ሆኜ እልል እላለሁ።+ + 8 አንተን የሙጥኝ እላለሁ፤*ቀኝ እጅህ አጥብቆ ይይዘኛል።+ + 9 ሕይወቴን ለማጥፋት* የሚሹ ሰዎች ግንወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ። +10 ለሰይፍ ስለት አልፈው ይሰጣሉ፤የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ። +11 ንጉሡ ግን በአምላክ ሐሴት ያደርጋል። በእሱ የሚምል ሰው ሁሉ ይደሰታል፤*ሐሰትን የሚናገሩ ሰዎች አፍ ይዘጋልና። +124 “ይሖዋ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣”+ እስራኤል እንዲህ ይበል፦ + 2 “ይሖዋ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣+ሰዎች እኛን ለማጥቃት በተነሱ ጊዜ፣+ + 3 ቁጣቸው በእኛ ላይ በነደደ ጊዜ፣+በሕይወት ሳለን በዋጡን ነበር።+ + 4 በዚያን ጊዜ ውኃ ጠራርጎ በወሰደን፣ጎርፍም ባጥለቀለቀን ነበር።*+ + 5 ኃይለኛ ውኃ በዋጠን ነበር።* + 6 ለጥርሳቸው ሲሳይ እንድንሆን አሳልፎ ስላልሰጠንይሖዋ ይወደስ። + 7 ከአዳኝ ወጥመድእንዳመለጠች ወፍ ነን፤*+ወጥመዱ ተሰበረ፤እኛም አመለጥን።+ + 8 ሰማይንና ምድርን የሠራውየይሖዋ ስም ረዳታችን ነው።”+ +97 ይሖዋ ነገሠ!+ ምድር ደስ ይበላት።+ ብዙ ደሴቶችም ሐሴት ያድርጉ።+ + 2 ደመናና ድቅድቅ ጨለማ በዙሪያው አለ፤+ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።+ + 3 እሳት በፊቱ ይሄዳል፤+ጠላቶቹንም በሁሉም አቅጣጫ ይፈጃል።+ + 4 የመብረቅ ብልጭታዎቹ በመሬት ላይ አበሩ፤ምድር ይህን አይታ ተንቀጠቀጠች።+ + 5 ተራሮች በይሖዋ ፊት፣በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።+ + 6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ።+ + 7 ማንኛውንም የተቀረጸ ምስል የሚያመልኩ ሁሉ፣ከንቱ በሆኑ አማልክታቸው የሚኩራሩ ይፈሩ።+ እናንተ አማልክት ሁሉ፣ ለእሱ ስገዱ።*+ + 8 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ስላስተላለፍካቸው የፍርድ ውሳኔዎች፣ጽዮን ሰምታ ሐሴት አደረገች፤የይሁዳ ከተሞች* ደስ አላቸው።+ + 9 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በመላው ምድር ላይ ልዑል ነህና፤ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃል።+ +10 እናንተ ይሖዋን የምትወዱ፣ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ።+ እሱ የታማኝ አገልጋዮቹን ሕይወት* ይጠብቃል፤+ከክፉዎች እጅ* ይታደጋቸዋል።+ +11 ብርሃን ለጻድቃን ወጣ፤ደስታም ለልበ ቅኖች ተዳረሰ።+ +12 እናንተ ጻድቃን፣ በይሖዋ ሐሴት አድርጉ፤ለቅዱስ ስሙም* ምስጋና አቅርቡ። +115 ከታማኝ ፍቅርህና ከታማኝነትህ የተነሳ+ለእኛ ሳይሆን፣ ይሖዋ ሆይ፣ ለእኛ ሳይሆን፣*ለስምህ ክብር ስጥ።+ + 2 ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?+ + 3 አምላካችን ያለው በሰማያት ነው፤እሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል። + 4 የእነሱ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+ + 5 አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤ + 6 ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም፤አፍንጫ አላቸው፤ ማሽተት ግን አይችሉም፤ + 7 እጅ አላቸው፤ መዳሰስ ግን አይችሉም፤እግር አላቸው፤ መራመድ ግን አይችሉም፤+በጉሮሯቸው የሚያሰሙት ድምፅ የለም።+ + 8 የሚሠሯቸውም ሆኑ የሚታመኑባቸው ሁሉ፣እንደ እነሱ ይሆናሉ።+ + 9 እስራኤል ሆይ፣ በይሖዋ ታመኑ፤+እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።+ +10 የአሮን ቤት ሆይ፣+ በይሖዋ ታመኑ፤እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው። +11 እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ በይሖዋ ታመኑ፤+እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።+ +12 ይሖዋ ያስታውሰናል፤ ደግሞም ይባርከናል፤የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤+የአሮንን ቤት ይባርካል። +13 ይሖዋ እሱን የሚፈሩትን፣ታናናሾችንም ሆነ ታላላቆችን ይባርካል። +14 ይሖዋ እናንተን፣አዎ፣ እናንተንና ልጆቻችሁን* ያበዛል።+ +15 ሰማይንና ምድርን የሠራው+ይሖዋ ይባርካችሁ።+ +16 ሰማያት የይሖዋ ናቸው፤+ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።+ +17 ሙታንም ሆኑ ወደ ዝምታው ዓለም* የሚወርዱ ሁሉ፣+ያህን አያወድሱም።+ +18 እኛ ግን ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ያህን እናወድሳለን። ያህን አወድሱ!* +46 አምላክ መጠጊያችንና ብርታታችን፣+በጭንቅ ጊዜ ፈጥኖ የሚደርስልን ረዳታችን ነው።+ + 2 በመሆኑም በምድር ላይ ነውጥ ቢከሰት፣ተራሮች ተንደው ወደ ጥልቁ ባሕር ቢሰምጡ አንፈራም፤+ + 3 ውኃዎቹ ቢያስገመግሙና አረፋ ቢደፍቁ፣+ተራሮችም ከውኃዎቹ ነውጥ የተነሳ ቢንቀጠቀጡ አንሸበርም። (ሴላ) + 4 የአምላክን ከተማ+ ደስ የሚያሰኙ ጅረቶች ያሉት ወንዝ አለ፤ከተማዋም የልዑሉ አምላክ የተቀደሰ ታላቅ ማደሪያ ነች። + 5 አምላክ በከተማዋ ውስጥ ነው፤+ እሷም አትንኮታኮትም። ጎህ ሲቀድ አምላክ ይደርስላታል።+ + 6 ብሔራት ሁከት ፈጠሩ፤ መንግሥታት ተገለበጡ፤እሱ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች።+ + 7 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው፤+የያዕቆብ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያችን ነው። (ሴላ) + 8 ኑና የይሖዋን ሥራዎች እዩ፤በምድርም ላይ አስደናቂ ነገሮችን እንዴት እንዳከናወነ ተመልከቱ። + 9 ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።+ ቀስትን ይሰባብራል፤ ጦርንም ያነክታል፤የጦር ሠረገሎችን* በእሳት ያቃጥላል። +10 “አርፋችሁ ተቀመጡ፤ እኔ አምላክ እንደሆንኩም እወቁ። በብሔራት መካከል ከፍ ከፍ እላለሁ፤+በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”+ +11 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው፤+የያዕቆብ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያችን ነው።+ (ሴላ) +146 ያህን አወድሱ!*+ ሁለንተናዬ* ይሖዋን ያወድስ።+ + 2 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይሖዋን አወድሳለሁ። በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። + 3 በመኳንንትም* ሆነማዳን በማይችሉ ሰዎች አትታመኑ።+ + 4 መንፈሱ* ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤+በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።+ + 5 የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ፣+በአምላኩ በይሖዋ ተስፋ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው፤+ + 6 እሱ የሰማይ፣ የምድር፣የባሕርና በውስጣቸው ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ነው፤+ደግሞም ለዘላለም ታማኝ ነው፤+ + 7 ግፍ ለተፈጸመባቸው ፍትሕ ያሰፍናል፤ለተራቡት ምግብ ይሰጣል።+ ይሖዋ እስረኞችን ነፃ ያወጣል።*+ + 8 ይሖዋ የዓይነ ስውራንን ዓይን ያበራል፤+ይሖዋ ያጎነበሱትን ቀና ያደርጋል፤+ይሖዋ ጻድቃንን ይወዳል። + 9 ይሖዋ የባዕድ አገር ሰዎችን ይጠብቃል፤አባት የሌለውን ልጅና መበለቲቱን ይደግፋል፤+የክፉዎችን ዕቅድ ግን ያጨናግፋል።*+ +10 ይሖዋ ለዘላለም ይነግሣል፤+ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይገዛል። ያህን አወድሱ!* +53 ሞኝ* ሰው በልቡ “ይሖዋ የለም” ይላል።+ የዓመፅ ድርጊታቸው ብልሹና አስጸያፊ ነው፤መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+ + 2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት+አምላክ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+ + 3 ሁሉም ወደ ሌላ ዞር ብለዋል፤ሁሉም ብልሹ ናቸው። መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤አንድ እንኳ የለም።+ + 4 ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም? ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ። ይሖዋን አይጠሩም።+ + 5 ይሁንና በታላቅ ሽብር፣ከዚህ በፊት ተሰምቷቸው በማያውቅ ታላቅ ፍርሃት ይዋጣሉ፤*በአንተ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩትን* ሰዎች አጥንት አምላክ ይበታትነዋልና። ይሖዋ ስላልተቀበላቸው አንተ ታዋርዳቸዋለህ። + 6 የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+ ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ። +37 በክፉዎች አትበሳጭ፤*ወይም በክፉ አድራጊዎች አትቅና።+ + 2 እንደ ሣር በፍጥነት ይደርቃሉ፤+እንደለመለመ ተክልም ይጠወልጋሉ። + 3 በይሖዋ ታመን፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤+በምድር ላይ ኑር፤ ለሰዎችም ታማኝ ሁን።+ + 4 በይሖዋ ሐሴት አድርግ፤*እሱም የልብህን መሻት ይሰጥሃል። + 5 መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ፤*+በእሱ ታመን፤ እሱም ለአንተ ሲል እርምጃ ይወስዳል።+ + 6 ጽድቅህን እንደ ንጋት ብርሃን፣የአንተንም ፍትሕ እንደ ቀትር ፀሐይ ያበራዋል። + 7 በይሖዋ ፊት ዝም በል፤+እሱንም በተስፋ* ተጠባበቅ። የጠነሰሰውን ሴራበተሳካ ሁኔታ እየፈጸመ ባለ ሰው አትበሳጭ።+ + 8 ከቁጣ ተቆጠብ፤ ንዴትንም ተው፤+ተበሳጭተህ ክፉ ነገር አትሥራ።* + 9 ክፉ አድራጊዎ��� ይጠፋሉና፤+ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ።+ +10 ለጥቂት ጊዜ ነው እንጂ ክፉዎች አይኖሩም፤+በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤እነሱ ግን በዚያ አይገኙም።+ +11 የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤+በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል።+ +12 ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ያሴራል፤+በእሱ ላይ ጥርሱን ያፋጫል። +13 ይሖዋ ግን ይስቅበታል፤የሚጠፋበት ቀን እንደሚደርስ ያውቃልና።+ +14 ክፉዎች የተጨቆነውንና ድሃውን ለመጣል፣እንዲሁም ቀና የሆነውን መንገድ የሚከተሉትን ለማረድሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ደጋናቸውንም ይወጥራሉ። +15 ሆኖም ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤+ደጋኖቻቸው ይሰበራሉ። +16 ብዙ ክፉ ሰዎች ካላቸው የተትረፈረፈ ሀብት ይልቅጻድቅ ሰው ያለው ጥቂት ነገር ይሻላል።+ +17 የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፤ይሖዋ ግን ጻድቃንን ይደግፋል። +18 ይሖዋ ነቀፋ የሌለባቸውን ሰዎች የሕይወት ጎዳና* ያውቃል፤ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል።+ +19 በአደጋ ወቅት ለኀፍረት አይዳረጉም፤በረሃብ ዘመን የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራቸዋል። +20 ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤+የይሖዋ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይከስማሉ፤እንደ ጭስ ይበናሉ። +21 ክፉ ሰው ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ጻድቅ ሰው ግን ለጋስ ነው፤* ደግሞም ይሰጣል።+ +22 አምላክ የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤እሱ የረገማቸው ግን ይጠፋሉ።+ +23 ይሖዋ በሰው መንገድ ደስ ሲሰኝ፣+አካሄዱን ይመራለታል።*+ +24 ቢወድቅም እንኳ አይዘረርም፤+ይሖዋ እጁን ይዞ* ይደግፈዋልና።+ +25 በአንድ ወቅት ወጣት ነበርኩ፤ አሁን ግን አርጅቻለሁ፤ይሁንና ጻድቅ ሰው ሲጣል፣+ልጆቹም ምግብ* ሲለምኑ አላየሁም።+ +26 ሁልጊዜ ሳይሰስት ያበድራል፤+ልጆቹም በረከት ያገኛሉ። +27 ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፤+ለዘላለምም ትኖራለህ። +28 ይሖዋ ፍትሕን ይወዳልና፤ታማኝ አገልጋዮቹንም አይተዋቸውም።+ ע [አይን] ምንጊዜም ጥበቃ ያገኛሉ፤+የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።+ +29 ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤+በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።+ +30 የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤*ምላሱም ስለ ፍትሕ ያወራል።+ +31 የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤+በሚሄድበት ጊዜም እግሮቹ አይብረከረኩም።+ +32 ክፉ ሰው ጻድቁን ለመግደልበዓይነ ቁራኛ ይከታተለዋል። +33 ይሖዋ ግን በክፉው እጅ አይጥለውም፤+ወይም ለፍርድ በሚቀርብበት ጊዜ ጥፋት አያገኝበትም።+ +34 ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤ መንገዱንም ተከተል፤እሱም ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ምድርንም ትወርሳለህ። ክፉዎች ሲጠፉ+ ታያለህ።+ +35 ጨካኝ የሆነውን ክፉ ሰው፣በበቀለበት መሬት ላይ እንደለመለመ ዛፍ ተንሰራፍቶ አየሁት።+ +36 ይሁንና ሕይወቱ በድንገት አለፈ፤ በቦታውም አልነበረም፤+አጥብቄ ፈለግኩት፤ ላገኘው ግን አልቻልኩም።+ +37 ነቀፋ የሌለበትን* ሰው ልብ በል፤ቀና የሆነውንም ሰው+ በትኩረት ተመልከት፤የዚህ ሰው የወደፊት ሕይወት ሰላማዊ ይሆናልና።+ +38 ኃጢአተኞች ሁሉ ግን ይጠፋሉ፤ክፉዎች ምንም ተስፋ አይኖራቸውም።+ +39 ጻድቃን መዳን የሚያገኙት ከይሖዋ ነው፤+በጭንቅ ጊዜ መሸሸጊያቸው እሱ ነው።+ +40 ይሖዋ ይረዳቸዋል፤ ይታደጋቸዋልም።+ እሱን መጠጊያ ስላደረጉ፣ከክፉዎች ይታደጋቸዋል፤ ደግሞም ያድናቸዋል።+ +64 አምላክ ሆይ፣ የማቀርበውን ልመና ስማ።+ ጠላት ከሚሰነዝርብኝ አስፈሪ ጥቃት ሕይወቴን ታደግ። + 2 ከክፉ ሰዎች ስውር ሴራ፣ከክፉ አድራጊዎች ሸንጎ ጠብቀኝ፤+ + 3 እነሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤መርዘኛ ቃላቸውን እንደ ቀስት ያነጣጥራሉ፤ + 4 ይህን የሚያደርጉት ከተደበቁበት ቦታ ሆነው ንጹሑን ሰው ለመምታት ነው፤ያላንዳች ፍርሃት በድንገት ይመቱታል። + 5 ክፉ ዓላማቸውን ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፤*በስውር እንዴት ወጥመድ እንደሚዘረጉ ይነጋገራሉ። “ማን ያየዋል?” ይላሉ።+ + 6 ክፉ ነገር ለመሥራት አዳዲስ መንገዶች ይቀይሳሉ፤የረቀቀ ሴራቸውን በስውር ይሸርባሉ፤+በእያንዳንዳቸው ልብ ውስጥ ያለው ሐሳብ አይደረስበትም። + 7 ሆኖም አምላክ ይመታቸዋል፤+እነሱም በድንገት በቀስት ይቆስላሉ። + 8 የገዛ ምላሳቸው ለውድቀት ይዳርጋቸዋል፤+ይህን የሚመለከቱ ሁሉ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ። + 9 በዚህ ጊዜ ሰዎች ሁሉ ይፈራሉ፤አምላክ ያደረገውንም ነገር ያውጃሉ፤ሥራውንም በሚገባ ያስተውላሉ።+ +10 ጻድቅ ሰው በይሖዋ ሐሴት ያደርጋል፤ እሱንም መጠጊያው ያደርጋል፤+ቀና ልብ ያላቸውም ሁሉ ይደሰታሉ።* +107 ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ + 2 ይሖዋ የዋጃቸው፣*አዎ፣ ከጠላት እጅ* የዋጃቸው+ ይህን ይበሉ፤ + 3 ከምሥራቅና ከምዕራብ፣*ከሰሜንና ከደቡብ፣ከየአገሩ አንድ ላይ የሰበሰባቸው+ ይህን ይናገሩ። + 4 በምድረ በዳ፣ በበረሃም ተቅበዘበዙ፤ሊኖሩ ወደሚችሉበት ከተማ የሚወስድ መንገድ አላገኙም። + 5 ተርበውና ተጠምተው ነበር፤ኃይላቸው ከመሟጠጡ የተነሳ ተዝለፈለፉ።* + 6 በተጨነቁ ጊዜ ወደ ይሖዋ ይጮኹ ነበር፤+እሱም ከደረሰባቸው መከራ ታደጋቸው።+ + 7 መኖር ወደሚችሉበት ከተማ እንዲደርሱ+በትክክለኛው መንገድ መራቸው።+ + 8 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩናለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች+ ይሖዋን ያመስግኑት።+ + 9 እሱ የተጠማውን* አርክቷልና፤የተራበውንም* በመልካም ነገሮች አጥግቧል።+ +10 አንዳንዶች በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚኖሩ፣በመከራ ውስጥ ያሉና በሰንሰለት የተጠፈሩ እስረኞች ነበሩ። +11 በአምላክ ቃል ላይ ዓምፀዋልና፤የልዑሉን አምላክ ምክር ንቀዋል።+ +12 ስለዚህ በደረሰባቸው መከራ ልባቸው እንዲለሰልስ አደረገ፤+ተሰናከሉ፤ የሚረዳቸውም አንዳች ሰው አልነበረም። +13 በተጨነቁ ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ተጣሩ፤እሱም ከደረሰባቸው መከራ አዳናቸው። +14 ከድቅድቅ ጨለማ አወጣቸው፤የታሰሩበትንም ሰንሰለት በጠሰ።+ +15 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩናለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።+ +16 እሱ የመዳብ በሮችን ሰብሯልና፤የብረት መወርወሪያዎችንም ቆርጧል።+ +17 ከጥፋታቸውና ከበደላቸው የተነሳ+ሞኝ ሆኑ፤ ለመከራም ተዳረጉ።+ +18 የምግብ ፍላጎታቸው ሙሉ በሙሉ ጠፋ፤*ወደ ሞት ደጆች ቀረቡ። +19 በተጨነቁ ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጣሩ ነበር፤እሱም ከደረሰባቸው መከራ ያድናቸው ነበር። +20 ቃሉን ልኮ ይፈውሳቸው፣+ከተያዙበትም ጉድጓድ ይታደጋቸው ነበር። +21 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩናለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት። +22 የምስጋና መሥዋዕት ያቅርቡ፤+በእልልታም ሥራዎቹን ያስታውቁ። +23 በባሕር ላይ በመርከቦች የሚጓዙ፣በሰፋፊ ውኃዎች ላይ ንግድ የሚያካሂዱ፣+ +24 እነሱ የይሖዋን ሥራዎች፣በጥልቁም ውስጥ ያከናወናቸውን አስደናቂ ነገሮች+ ተመልክተዋል፤ +25 እሱ በቃሉ አውሎ ነፋስ ሲያስነሳ፣+የባሕሩንም ማዕበል ሲያናውጥ አይተዋል። +26 ወደ ሰማይ ይወጣሉ፣ወደ ጥልቆችም ይወርዳሉ። እየመጣባቸው ካለው መከራ የተነሳ ሐሞታቸው ፈሰሰ።* +27 እንደሰከረ ሰው ይንገዳገዳሉ፤ ደግሞም ይወላገዳሉ፤ችሎታቸውም ሁሉ የፈየደላቸው ነገር የለም።+ +28 በዚህ ጊዜ ከጭንቀታቸው የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤+እሱም ከደረሰባቸው መከራ ይታደጋቸዋል። +29 አውሎ ነፋሱ እንዲቆም ያደርጋል፤የባሕሩም ሞገዶች ጸጥ ይላሉ።+ +30 ሞገዶቹ ጸጥ ሲሉ ሰዎቹ ሐሴት ያደርጋሉ፤እሱም ወዳሰቡት ወደብ ይመራቸዋል። +31 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩናለሰው ልጆ�� ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።+ +32 በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤+በሽማግሌዎችም ሸንጎ* ያወድሱት። +33 እሱ ወንዞችን ወደ በረሃ፣የውኃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ መሬት ይለውጣል፤+ +34 ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሳፍሬያማዋን አገር ጨዋማ የሆነ ጠፍ ምድር ያደርጋታል።+ +35 በረሃውን ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣ደረቁንም ምድር የውኃ ምንጭ ያደርጋል።+ +36 ሊኖሩ የሚችሉበትን ከተማ እንዲመሠርቱ፣+የተራቡ ሰዎችን በዚያ ያኖራል።+ +37 መሬት ላይ ዘሩ፤ ወይንም ተከሉ፤+መሬቱም ብዙ ምርት ሰጠ።+ +38 እሱ ይባርካቸዋል፤ እነሱም እጅግ ይበዛሉ፤የከብቶቻቸው ብዛት እንዲያንስ አያደርግም።+ +39 ሆኖም ከደረሰባቸው ጭቆና፣ መከራና ሐዘን የተነሳዳግመኛ ቁጥራቸው ተመናመነ፤ ተዋረዱም። +40 በታላላቅ ሰዎች ላይ የውርደት መዓት ያዘንባል፤መንገድ በሌለበት ጠፍ መሬትም እንዲቅበዘበዙ ያደርጋል።+ +41 ድሆችን ግን ከጭቆና ይጠብቃል፤*+ቤተሰባቸውንም እንደ መንጋ ያበዛል። +42 ቅኖች ይህን አይተው ሐሴት ያደርጋሉ፤+ዓመፀኞች ሁሉ ግን አፋቸውን ይዘጋሉ።+ +43 ጥበበኛ የሆነ ሁሉ እነዚህን ነገሮች ልብ ይላል፤+ደግሞም ይሖዋ በታማኝ ፍቅር ያከናወናቸውን ነገሮች በትኩረት ይመለከታል።+ +119 በመንገዳቸው ነቀፋ የሌለባቸው፣*በይሖዋ ሕግ የሚመላለሱ ሰዎች ደስተኞች ናቸው።+ + 2 ማሳሰቢያዎቹን የሚጠብቁ፣+እሱን በሙሉ ልባቸው የሚፈልጉ ደስተኞች ናቸው።+ + 3 ክፉ ነገር አያደርጉም፤በመንገዶቹ ይሄዳሉ።+ + 4 አንተ መመሪያዎችህንበጥብቅ እንድንከተል አዘኸናል።+ + 5 ሥርዓትህን እጠብቅ ዘንድምነው በአቋሜ በጸናሁ!*+ + 6 ይህ ቢሆንልኝ፣ትእዛዛትህን ሁሉ በትኩረት ስመለከት አላፍርም።+ + 7 የጽድቅ ፍርዶችህን በተማርኩ ጊዜበቀና ልብ አወድስሃለሁ። + 8 ሥርዓትህን አከብራለሁ። አቤቱ እርግፍ አድርገህ አትተወኝ። + 9 ወጣቶች በንጽሕና መመላለስ የሚችሉት እንዴት ነው? በቃልህ መሠረት ራሳቸውን በመጠበቅ ነው።+ +10 በሙሉ ልቤ አንተን እሻለሁ። ከትእዛዛትህ እንድርቅ አትፍቀድ።+ +11 በአንተ ላይ ኃጢአት እንዳልሠራ፣+አንተ የተናገርከውን በልቤ ውስጥ እንደ ውድ ሀብት እሸሽጋለሁ።+ +12 ይሖዋ ሆይ፣ ውዳሴ ይድረስህ፤ሥርዓትህን አስተምረኝ። +13 የተናገርካቸውን ፍርዶች ሁሉበከንፈሮቼ አስታውቃለሁ። +14 ውድ ከሆኑ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ይበልጥ፣+በማሳሰቢያዎችህ ሐሴት አደርጋለሁ።+ +15 በመመሪያዎችህ ላይ አሰላስላለሁ፤*+ዓይኖቼንም በመንገዶችህ ላይ እተክላለሁ።+ +16 ያወጣሃቸውን ደንቦች እወዳቸዋለሁ። ቃልህን አልረሳም።+ +17 በሕይወት መኖርና ቃልህን መጠበቅ እችል ዘንድ፣ለአገልጋይህ ደግነት አሳይ።+ +18 በሕግህ ውስጥ ያሉትን አስደናቂ ነገሮችአጥርቼ እንዳይ ዓይኖቼን ክፈት። +19 በምድሪቱ ላይ የባዕድ አገር ሰው ነኝ።+ ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር። +20 እኔ* ፍርዶችህንዘወትር ከመናፈቄ የተነሳ ዛልኩ። +21 እብሪተኛ የሆኑትን፣ከትእዛዛትህ የራቁትን የተረገሙ ሰዎች ትገሥጻለህ።+ +22 ማሳሰቢያዎችህን ጠብቄአለሁና፣ዘለፋንና ንቀትን ከእኔ አስወግድ።* +23 መኳንንትም እንኳ አንድ ላይ ተቀምጠው ስለ እኔ መጥፎ ነገር ሲያወሩ፣አገልጋይህ በሥርዓትህ ላይ ያሰላስላል።* +24 ማሳሰቢያዎችህን እወዳቸዋለሁ፤+መካሪዎቼ ናቸው።+ +25 አፈር ላይ ተደፍቻለሁ።*+ በቃልህ መሠረት በሕይወት አቆየኝ።+ +26 መንገዶቼን ለአንተ ተናገርኩ፤ አንተም መለስክልኝ፤ሥርዓትህን አስተምረኝ።+ +27 አስደናቂ በሆኑት ሥራዎችህ ላይ አሰላስል ዘንድ፣*+የመመሪያዎችህን ትርጉም እንዳስተውል አድርገኝ። +28 ከሐዘን የተነሳ እንቅልፍ አጣሁ።* በቃልህ መሠረት አበርታኝ። +29 የአታላይነትን መንገድ ከእኔ አርቅ፤+ሕግህንም በማሳወቅ ሞገስ አሳየኝ። +30 የታማኝነትን ጎዳና መርጫለሁ።+ ፍርዶችህ ትክክል እንደሆኑ እገነዘባለሁ። +31 ማሳሰቢያዎችህን የሙጥኝ እላለሁ።+ ይሖዋ ሆይ፣ ለሐዘን* እንድዳረግ አትፍቀድ።+ +32 በልቤ ውስጥ ቦታ ስለሰጠኸው፣*የትእዛዛትህን መንገድ በጉጉት እከተላለሁ።* +33 ይሖዋ ሆይ፣ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፤+እኔም እስከ መጨረሻው እከተለዋለሁ።+ +34 ሕግህን እንዳከብርናበሙሉ ልቤ እንድጠብቅማስተዋል ስጠኝ። +35 በትእዛዛትህ መንገድ ምራኝ፤*+በእሱ ደስ እሰኛለሁና። +36 ልቤ የግል ጥቅም* ከማሳደድ+ ይልቅወደ ማሳሰቢያዎችህ እንዲያዘነብል አድርግ። +37 ከንቱ ነገር እንዳያዩ ዓይኖቼን መልስ፤+በመንገድህ ላይ በሕይወት እንድቀጥል አድርገኝ። +38 አንተ በሌሎች ትፈራ ዘንድ፣ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል* ፈጽም።* +39 በጣም የምፈራውን ውርደት ከእኔ አርቅ፤ፍርዶችህ ጥሩ ናቸውና።+ +40 መመሪያዎችህን ምን ያህል እንደናፈቅኩ ተመልከት። በጽድቅህ ሕያው ሆኜ እንድኖር አድርገኝ። +41 ይሖዋ ሆይ፣ ቃል በገባኸው* መሠረትታማኝ ፍቅርህንና ማዳንህን ልቅመስ፤+ +42 በዚህ ጊዜ ለሚሳለቅብኝ መልስ መስጠት እችላለሁ፤በቃልህ እታመናለሁና። +43 የእውነትን ቃል ከአፌ አታርቅ፤በፍርድህ ተስፋ አድርጌአለሁና።* +44 እኔ ሕግህን ዘወትር፣አዎ፣ ለዘላለም እጠብቃለሁ።+ +45 ደህንነት በማገኝበት ስፍራ* እንደ ልቤ እመላለሳለሁ፤+መመሪያዎችህን ከልቤ እፈልጋለሁና። +46 ስለ ማሳሰቢያዎችህ በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤ደግሞም አላፍርም።+ +47 ትእዛዛትህ ደስ ያሰኙኛል፤አዎ፣ እወዳቸዋለሁ።+ +48 ትእዛዛትህን ስለምወዳቸው+ እጆቼን ከፍ አድርጌ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤በሥርዓትህም ላይ አሰላስላለሁ።*+ +49 ለአገልጋይህ የተናገርከውን ቃል* አስታውስ፤በዚህ ቃል ተስፋ ሰጥተኸኛል።* +50 በመከራዬ ወቅት መጽናኛ የማገኘው በዚህ ነው፤+የተናገርከው ቃል በሕይወት አቆይቶኛልና። +51 እብሪተኞች እጅግ ይሳለቁብኛል፤እኔ ግን ከሕግህ ንቅንቅ አልልም።+ +52 ይሖዋ ሆይ፣ ከጥንት ጀምሮ የነበሩትን ፍርዶችህን አስታውሳለሁ፤+በእነዚህም መጽናኛ አገኛለሁ።+ +53 ሕግህን ከተዉ ክፉ ሰዎች የተነሳበቁጣ በገንኩ።+ +54 በምኖርበት ቦታ* ሁሉሥርዓትህ መዝሙር ሆነልኝ። +55 ይሖዋ ሆይ፣ ሕግህን እጠብቅ ዘንድበሌሊት ስምህን አስታውሳለሁ።+ +56 ይህን ልማድ አድርጌዋለሁ፤ምክንያቱም መመሪያዎችህን ጠብቄአለሁ። +57 ይሖዋ ድርሻዬ ነው፤+ሕግህን ለመጠበቅ ቃል ገብቻለሁ።+ +58 በሙሉ ልቤ አንተን እማጸናለሁ፤+በገባኸው ቃል* መሠረት ሞገስ አሳየኝ።+ +59 እግሮቼን ወደ ማሳሰቢያዎችህ እመልስ ዘንድመንገዴን መረመርኩ።+ +60 ትእዛዛትህን ለመጠበቅ ፈጠንኩ፤ፈጽሞ አልዘገየሁም።+ +61 የክፉዎች ገመድ ተተበተበብኝ፤ሆኖም ሕግህን አልረሳሁም።+ +62 ስለ ጽድቅ ፍርዶችህ አንተን ለማመስገንእኩለ ሌሊት ላይ እነሳለሁ።+ +63 አንተን ለሚፈሩ ሁሉ፣መመሪያዎችህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።+ +64 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምድርን ይሞላል፤+ሥርዓትህን አስተምረኝ። +65 ይሖዋ ሆይ፣ በቃልህ መሠረትለአገልጋይህ መልካም ነገር አድርገህለታል። +66 ማስተዋልንና እውቀትን አስተምረኝ፤+በትእዛዛትህ ታምኛለሁና። +67 መከራ ላይ ከመውደቄ በፊት፣ መንገድ ስቼ እሄድ ነበር፤*አሁን ግን የተናገርከውን እጠብቃለሁ።+ +68 አንተ ጥሩ ነህ፤+ ሥራህም ጥሩ ነው። ሥርዓትህን አስተምረኝ።+ +69 እብሪተኞች በውሸት ስሜን ያጎድፋሉ፤እኔ ግን በሙሉ ልቤ መመሪያዎችህን እጠብቃለሁ። +70 ልባቸው ደንዝዟል፤*+እኔ ግን ሕግህን እወዳለሁ።+ +71 ሥርዓትህን እማር ዘንድበመከራ ውስ��� ማለፌ ጥሩ ሆነልኝ።+ +72 አንተ ያወጅከው ሕግ ጠቅሞኛል፤+ለእኔ ከብዙ ወርቅና ብር እጅግ የተሻለ ነው።+ +73 እጆችህ ሠሩኝ፤ ደግሞም አበጁኝ። ትእዛዛትህን እማር ዘንድማስተዋል ስጠኝ።+ +74 አንተን የሚፈሩ ሰዎች እኔን አይተው ሐሴት ያደርጋሉ፤ቃልህ ተስፋዬ ነውና።*+ +75 ይሖዋ ሆይ፣ ፍርዶችህ በጽድቅ ላይ የተመሠረቱ እንደሆኑና+ከታማኝነትህ የተነሳ እንደቀጣኸኝ አውቃለሁ።+ +76 ለአገልጋይህ በገባኸው ቃል* መሠረት፣እባክህ፣ ታማኝ ፍቅርህ+ ያጽናናኝ። +77 በሕይወት መኖሬን እንድቀጥል ምሕረት አሳየኝ፤+ሕግህን እወዳለሁና።+ +78 እብሪተኞች ኀፍረት ይከናነቡ፤ያላንዳች ምክንያት* በድለውኛልና። እኔ ግን በመመሪያዎችህ ላይ አሰላስላለሁ።*+ +79 አንተን የሚፈሩ፣ ማሳሰቢያዎችህንም የሚያውቁ፣ወደ እኔ ይመለሱ። +80 ለኀፍረት እንዳልዳረግ፣ልቤ ነቀፋ በሌለበት መንገድ ሥርዓትህን ይከተል።+ +81 ማዳንህን እናፍቃለሁ፤*+ቃልህ ተስፋዬ ነውና።* +82 አንተ የተናገርከው ቃል ሲፈጸም ለማየት ዓይኖቼ ይጓጓሉ፤+“የምታጽናናኝ መቼ ነው?”+ እያልኩ እጠይቃለሁ። +83 ጭስ እንዳደረቀው አቁማዳ ሆኛለሁና፤ሆኖም ሥርዓትህን አልረሳም።+ +84 ባሪያህ በሕይወት የሚቆየው እስከ መቼ ነው? ስደት በሚያደርሱብኝ ላይ የምትፈርደው መቼ ነው?+ +85 ሕግህን የሚጥሱእብሪተኛ ሰዎች እኔን ለማጥመድ ጉድጓድ ይቆፍራሉ። +86 ትእዛዛትህ ሁሉ አስተማማኝ ናቸው። ሰዎች ያለምክንያት ያሳድዱኛል፤ አቤቱ እርዳኝ!+ +87 ከምድር ገጽ ሊያጠፉኝ ምንም ያህል አልቀራቸውም ነበር፤እኔ ግን መመሪያዎችህን አልተውኩም። +88 የተናገርካቸውን ማሳሰቢያዎች እጠብቅ ዘንድ፣ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ በሕይወት አቆየኝ። +89 ይሖዋ ሆይ፣ ቃልህ በሰማያት፣ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ +90 ታማኝነትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።+ ምድር ለዘለቄታው እንድትኖር በጽኑ መሠረትካት።+ +91 በፍርዶችህ መሠረት እስከ ዛሬ ጸንተው ኖረዋል፤*ሁሉም አገልጋዮችህ ናቸውና። +92 ሕግህን ባልወድ ኖሮ፣በደረሰብኝ ጉስቁልና በጠፋሁ ነበር።+ +93 መመሪያዎችህን ፈጽሞ አልረሳም፤ምክንያቱም በእነሱ አማካኝነት በሕይወት አቆይተኸኛል።+ +94 እኔ የአንተ ነኝ፤መመሪያዎችህን ፈልጌአለሁና+ አድነኝ።+ +95 ክፉዎች እኔን ለማጥፋት ያደባሉ፤እኔ ግን ለማሳሰቢያዎችህ ትኩረት እሰጣለሁ። +96 ፍጽምና ሁሉ ገደብ እንዳለው አይቻለሁ።ትእዛዝህ ግን ገደብ የለውም።* +97 ሕግህን ምንኛ ወደድኩ!+ ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ።*+ +98 ትእዛዝህ ለዘላለም ስለማይለየኝ፣ከጠላቶቼ ይበልጥ ጥበበኛ ያደርገኛል።+ +99 በማሳሰቢያዎችህ ላይ ስለማሰላስል፣*ከአስተማሪዎቼ ሁሉ የበለጠ ጥልቅ ማስተዋል አለኝ።+ +100 መመሪያዎችህን ስለማከብር፣ከሽማግሌዎች ይበልጥ በማስተዋል እመላለሳለሁ። +101 ቃልህን እጠብቅ ዘንድ፣በየትኛውም ክፉ መንገድ ከመሄድ እቆጠባለሁ።+ +102 አንተ አስተምረኸኛልና፣ከፍርዶችህ ፈቀቅ አልልም። +103 የተናገርከው ነገር ለምላሴ እጅግ ጣፋጭ ነው፤ለአፌም ከማር የበለጠ ይጥማል!+ +104 ከመመሪያዎችህ የተነሳ በማስተዋል እመላለሳለሁ።+ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ እጠላለሁ።+ +105 ቃልህ ለእግሬ መብራት፣ለመንገዴም ብርሃን ነው።+ +106 የጽድቅ ፍርዶችህን ለመጠበቅ ምያለሁ፤ደግሞም እፈጽመዋለሁ። +107 ከፍተኛ ጉስቁልና ደርሶብኛል።+ ይሖዋ ሆይ፣ በቃልህ መሠረት በሕይወት አቆየኝ።+ +108 ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ በፈቃደኝነት የማቀርበውን የውዳሴ መባ* በደስታ ተቀበል፤+ፍርዶችህንም አስተምረኝ።+ +109 ሕይወቴ ሁልጊዜ አደጋ ላይ ናት፤*እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም።+ +110 ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤እኔ ግን ከመመሪያዎችህ ዝንፍ አላልኩም��+ +111 ማሳሰቢያዎችህ ልቤን ደስ ስለሚያሰኙ፣+ቋሚ ንብረቴ* አደርጋቸዋለሁ። +112 ሥርዓትህን በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣እስከ መጨረሻው ለመጠበቅ ቆርጫለሁ።* +113 በግማሽ ልብ የሚመላለሱትን* እጠላለሁ፤+ሕግህን ግን እወዳለሁ።+ +114 አንተ መጠለያዬና ጋሻዬ ነህ፤+ቃልህ ተስፋዬ ነውና።*+ +115 እናንተ ክፉዎች፣የአምላኬን ትእዛዛት መጠበቅ እንድችል ከእኔ ራቁ።+ +116 በሕይወት እንድቀጥልቃል በገባኸው* መሠረት ደግፈኝ፤+ተስፋዬ ሳይፈጸም ቀርቶ እንዳዝን አትፍቀድ።*+ +117 እድን ዘንድ ደግፈኝ፤+ያን ጊዜ ለሥርዓትህ ዘወትር ትኩረት እሰጣለሁ።+ +118 ከሥርዓትህ የሚርቁትን ሁሉ ገሸሽ ታደርጋቸዋለህ፤+ውሸታሞችና አታላዮች ናቸውና። +119 በምድር ላይ ያሉ ክፉዎችን ሁሉ ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ታስወግዳቸዋለህ።+ ስለዚህ ማሳሰቢያዎችህን እወዳለሁ። +120 አንተን እጅግ ከመፍራቴ የተነሳ ሰውነቴ* ይንቀጠቀጣል፤ፍርዶችህን እፈራለሁ። +121 ትክክልና ጽድቅ የሆነውን አድርጌአለሁ። ለሚጨቁኑኝ አሳልፈህ አትስጠኝ! +122 ለአገልጋይህ ደህንነት ዋስትና ስጥ፤እብሪተኞች እንዲጨቁኑኝ አትፍቀድ። +123 ዓይኖቼ ማዳንህንናየገባኸውን* የጽድቅ ቃል በመጠባበቅ ደከሙ።+ +124 ለአገልጋይህ ታማኝ ፍቅርህን አሳየው፤+ሥርዓትህንም አስተምረኝ።+ +125 እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ማሳሰቢያዎችህን እንዳውቅ ማስተዋል ስጠኝ።+ +126 ይሖዋ ሆይ፣ እርምጃ የምትወስድበት ጊዜ ደርሷል፤+ሰዎች ሕግህን ጥሰዋልና። +127 ስለዚህ እኔ ትእዛዛትህን ከወርቅ፣ምርጥ ከሆነ* ወርቅ ይበልጥ እወዳለሁ።+ +128 በመሆኑም የምታስተምረው ትምህርት* በሙሉ ትክክል እንደሆነ አምናለሁ፤+የሐሰትን መንገድ ሁሉ እጠላለሁ።+ +129 ማሳሰቢያዎችህ ድንቅ ናቸው። ስለዚህ እጠብቃቸዋለሁ።* +130 አንተ የምትገልጣቸው ቃላት ብርሃን ይፈነጥቃሉ፤+ተሞክሮ የሌላቸውን አስተዋዮች ያደርጋሉ።+ +131 ትእዛዛትህን ለመስማት ከመጓጓቴ የተነሳ+አፌን ከፍቼ በረጅሙ እተነፍሳለሁ።* +132 ስምህን ለሚወዱ ሰዎች+ ከምትሰጠው ፍርድ ጋር በሚስማማ መንገድ፣ወደ እኔ ተመለስ፤ ሞገስም አሳየኝ።+ +133 በቃልህ መሠረት አካሄዴን በሰላም ምራ፤*ማንኛውም ክፉ ነገር በእኔ ላይ አይሠልጥን።+ +134 ጨቋኝ ከሆኑ ሰዎች ታደገኝ፤*እኔም መመሪያዎችህን እጠብቃለሁ። +135 በአገልጋይህ ላይ ፊትህን አብራ፤*+ሥርዓትህንም አስተምረኝ። +136 ሰዎች ሕግህን ስለማያከብሩእንባ ከዓይኖቼ እንደ ውኃ ፈሰሰ።+ +137 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ ነህ፤+ፍርዶችህም ትክክል ናቸው።+ +138 የምትሰጣቸው ማሳሰቢያዎች በጽድቅ ላይ የተመሠረቱናሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ናቸው። +139 ጠላቶቼ ቃልህን ስለረሱቅንዓቴ ይበላኛል።+ +140 ቃልህ እጅግ የጠራ ነው፤+አገልጋይህም ይወደዋል።+ +141 እኔ በሌሎች ዘንድ የተናቅኩና የማልረባ ነኝ፤+ሆኖም መመሪያዎችህን አልረሳሁም። +142 ጽድቅህ የዘላለም ጽድቅ ነው፤+ሕግህም እውነት ነው።+ +143 ጭንቀትና ችግር ቢደርስብኝምትእዛዛትህን ምንጊዜም እወዳለሁ። +144 ማሳሰቢያህ ለዘላለም ጽድቅ ነው። በሕይወት መኖሬን እንድቀጥል ማስተዋል ስጠኝ።+ +145 በሙሉ ልቤ እጣራለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ መልስልኝ። ሥርዓትህን እጠብቃለሁ። +146 አንተን እጣራለሁ፤ አቤቱ አድነኝ! ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ። +147 ጎህ ሳይቀድ* ተነስቼ እርዳታ ለማግኘት እጮኻለሁ፤+ቃልህ ተስፋዬ ነውና።* +148 በተናገርከው ቃል ላይ ማሰላሰል* እንድችል፣ክፍለ ሌሊቶቹ ከማብቃታቸው በፊት እነቃለሁ።+ +149 ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ ድምፄን ስማ።+ ይሖዋ ሆይ፣ ከአንተ ፍትሕ ጋር በሚስማማ መንገድ በሕይወት አቆየኝ። +150 አሳፋሪ በሆነ ድርጊት* የተጠመዱ ሰዎች ወደ እኔ ቀርበዋል፤ከሕግህም ርቀዋል። +151 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ቅርብ ነህ፤+ትእዛዛትህም ሁሉ እውነት ናቸው።+ +152 በቀድሞው ዘመን ስለ ማሳሰቢያዎችህ ተምሬአለሁ፤ለዘላለም ይጸኑ ዘንድ እንደመሠረትካቸው ተረድቻለሁ።+ +153 የደረሰብኝን ጉስቁልና ተመልከት፤ ደግሞም ታደገኝ፤+ሕግህን አልረሳሁምና። +154 ተሟገትልኝ፤* ደግሞም ታደገኝ፤+በገባኸው * ቃል መሠረት በሕይወት አቆየኝ። +155 ክፉዎች ሥርዓትህን ስላልፈለጉመዳን ከእነሱ ርቋል።+ +156 ይሖዋ ሆይ፣ ምሕረትህ ታላቅ ነው።+ ከአንተ ፍትሕ ጋር በሚስማማ መንገድ በሕይወት አቆየኝ። +157 አሳዳጆቼና ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤+እኔ ግን ከማሳሰቢያዎችህ ፈቀቅ አላልኩም። +158 ከዳተኛ የሆኑ ሰዎችን ተጸየፍኩ፤ምክንያቱም አንተ የተናገርከውን አይጠብቁም።+ +159 መመሪያዎችህን ምን ያህል እንደምወድ ተመልከት! ይሖዋ ሆይ፣ ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ በሕይወት አቆየኝ።+ +160 የቃልህ ፍሬ ነገር እውነት ነው፤+በጽድቅ ላይ የተመሠረተው ፍርድህ ሁሉ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። +161 መኳንንት ያለምክንያት ያሳድዱኛል፤+ልቤ ግን ለቃልህ ጥልቅ አክብሮት አለው።+ +162 ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፣እኔም አንተ በተናገርከው ነገር ሐሴት አደርጋለሁ።+ +163 ውሸትን እጠላለሁ፤ ደግሞም እጸየፈዋለሁ፤+ሕግህን ግን እወዳለሁ።+ +164 በጽድቅ ላይ ከተመሠረቱት ፍርዶችህ የተነሳበቀን ሰባት ጊዜ አወድስሃለሁ። +165 ሕግህን የሚወዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤+ሊያደናቅፋቸው የሚችል ምንም ነገር የለም።* +166 ይሖዋ ሆይ፣ የማዳን ሥራህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ትእዛዛትህንም እፈጽማለሁ። +167 ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ፤*ደግሞም እጅግ እወዳቸዋለሁ።+ +168 መመሪያዎችህንና ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ፤የማደርገውን ነገር ሁሉ ታውቃለህና።+ +169 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማሰማው ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ።+ እንደ ቃልህ ማስተዋል ስጠኝ።+ +170 ሞገስ ለማግኘት የማቀርበው ልመና ወደ አንተ ይድረስ። ቃል በገባኸው* መሠረት አድነኝ። +171 ሥርዓትህን ስለምታስተምረኝከንፈሮቼ ውዳሴን ያፍልቁ።+ +172 አንደበቴ ስለተናገርከው ቃል ይዘምር፤+ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸውና። +173 መመሪያዎችህን ለመታዘዝ ስለምመርጥ፣+እጅህ እኔን ለመርዳት ዝግጁ ይሁን።+ +174 ይሖዋ ሆይ፣ ማዳንህን እናፍቃለሁ፤ሕግህንም እወዳለሁ።+ +175 አወድስህ ዘንድ በሕይወት ልኑር፤*+አንተ ያወጣሃቸው ፍርዶች ይርዱኝ። +176 እንደጠፋ በግ ተቅበዘበዝኩ።+ አገልጋይህን ፈልገው፤ትእዛዛትህን አልረሳሁምና።+ +57 ሞገስ አሳየኝ፤ አምላክ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ፤አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና፤*+መከራው እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ ሥር እጠለላለሁ።+ + 2 ወደ ልዑሉ አምላክ፣ለእኔ ሲል መከራውን ወደሚያስቆመው ወደ እውነተኛው አምላክ እጣራለሁ። + 3 ከሰማይ እርዳታ ልኮ ያድነኛል።+ ሊነክሰኝ የሚሞክረውን ሰው እንዳይሳካለት ያደርጋል። (ሴላ) አምላክ ታማኝ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ያሳያል።+ + 4 አንበሶች ከበውኛል፤*+ሊውጡኝ በሚፈልጉ ሰዎች መካከል ለመተኛት ተገድጃለሁ፤ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ ነው፤ምላሳቸውም የተሳለ ሰይፍ ነው።+ + 5 አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+ + 6 እግሮቼን ለመያዝ ወጥመድ አዘጋጅተዋል፤+ከጭንቅ የተነሳ ጎብጫለሁ።*+ በፊቴ ጉድጓድ ቆፈሩ፤ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት።+ (ሴላ) + 7 ልቤ ጽኑ ነው፤አምላክ ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው።+ እዘምራለሁ፤ ደግሞም አዜማለሁ። + 8 ልቤ* ሆይ፣ ተነሳ። ባለ አውታር መሣሪያ ሆይ፣ አንተም በገና ሆይ፣ ተነሱ። እኔም በማለዳ እነሳለሁ።+ + 9 ይሖዋ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አወድስሃለሁ፤+በብሔራት መካከል የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።+ +10 ታማኝ ፍቅርህ ታላቅ ነውና፤ እንደ ሰማያት ከፍ ያለ ነው፤+ታማኝነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነው። +11 አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህ በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።+ +40 ተስፋዬን ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ላይ ጣልኩ፤*እሱም ጆሮውን ወደ እኔ አዘነበለ፤* ለእርዳታ ያሰማሁትንም ጩኸት ሰማ።+ + 2 የሚያስገመግም ድምፅ ካለበት ጉድጓድ፣ከሚያዘቅጥ ማጥም አወጣኝ። እግሮቼንም በዓለት ላይ አቆመ፤አረማመዴንም አጸና። + 3 ከዚያም በአፌ ላይ አዲስ መዝሙር፣+ለአምላካችን የሚቀርብ ውዳሴ አኖረ። ብዙዎች በፍርሃት* ተውጠው ይመለከታሉ፤በይሖዋም ይታመናሉ። + 4 በይሖዋ የሚታመን፣ እንቢተኛ ወደሆኑት ወይምሐሰት* ወደሆኑት ፊቱን ያላዞረ ሰው ደስተኛ ነው። + 5 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ያደረግካቸው ድንቅ ሥራዎች፣ለእኛ ያሰብካቸው ነገሮችም ብዙ ናቸው።+ ከአንተ ጋር ሊወዳደር የሚችል ማንም የለም፤+ስለ እነዚህ ነገሮች ላውራ፣ ልናገር ብል፣ዘርዝሬ ልጨርሳቸው አልችልም!+ + 6 መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤*+ከዚህ ይልቅ እንድሰማ ጆሮዎቼን ከፈትክልኝ።*+ የሚቃጠል መባና የኃጢአት መባ እንዲቀርብልህ አልጠየቅክም።+ + 7 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “እነሆ፣ መጥቻለሁ። ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል ተጽፏል።+ + 8 አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል፤*+ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።+ + 9 በታላቅ ጉባኤ መካከል የጽድቅን ምሥራች አውጃለሁ።+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው፣እነሆ፣ ከንፈሮቼን አልከለክልም።+ +10 ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሸሽግም። ታማኝነትህንና ማዳንህን አውጃለሁ። በታላቅ ጉባኤ መካከል ታማኝ ፍቅርህንና እውነትህን አልደብቅም።”+ +11 ይሖዋ ሆይ፣ ምሕረትህን አትንፈገኝ። ታማኝ ፍቅርህና እውነትህ ምንጊዜም ይጠብቁኝ።+ +12 ለመቁጠር እንኳ የሚያታክት መከራ ከቦኛል።+ የፈጸምኳቸው በርካታ ስህተቶች ስለዋጡኝ መንገዴን ማየት ተስኖኛል፤+በራሴ ላይ ካሉት ፀጉሮች እጅግ ይበዛሉ፤ደግሞም ተስፋ ቆረጥኩ። +13 ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለማዳን እባክህ ፈቃደኛ ሁን።+ ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+ +14 ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚሹ ሁሉ፣ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ። በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙአፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ። +15 “እሰይ! እሰይ!” የሚሉኝ በሚደርስባቸው ኀፍረት የተነሳ ክው ይበሉ። +16 አንተን የሚፈልጉ+ ግንበአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ።+ የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣ ምንጊዜም “ይሖዋ ታላቅ ይሁን” ይበሉ።+ +17 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤ይሖዋ ትኩረት ይስጠኝ። አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+አምላኬ ሆይ፣ አትዘግይ።+ +93 ይሖዋ ነገሠ!+ ግርማ ተጎናጽፏል፤ይሖዋ ብርታት ለብሷል፤እንደ ቀበቶ ታጥቆታል። ምድር* በጽኑ ተመሥርታለች፤ልትናወጥ አትችልም። + 2 ዙፋንህ ከብዙ ዘመናት በፊት ጸንቶ የተመሠረተ ነው፤+አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።+ + 3 ይሖዋ ሆይ፣ ወንዞቹ ጎረፉ፤ወንዞቹ ጎረፉ፤ አስገመገሙም፤ወንዞቹ ይጎርፋሉ፤ ደግሞም በኃይል ይላተማሉ። + 4 ከብዙ ውኃዎች ድምፅ፣ኃይለኛ ከሆነው የባሕር ማዕበልም በላይ፣+ይሖዋ ከፍ ባለ ቦታ ግርማ ተጎናጽፏል።+ + 5 ማሳሰቢያዎችህ እጅግ አስተማማኝ ናቸው።+ ይሖዋ ሆይ፣ ቤትህ ለዘላለሙ በቅድስና ያጌጠ ነው።*+ +16 አምላክ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና ጠብቀኝ።+ + 2 ይሖዋን እንዲህ አልኩት፦ “አንተ ይሖዋ ነህ፤ ለእኔ የጥሩ ነገሮች ምንጭ አንተ ነህ። + 3 ደግሞም በምድር ላይ ያሉት ቅዱሳን፣ክብር የተላበሱት አገልጋዮች እጅግ ደስ ያሰኙኛል።”+ + 4 ሌሎች አማልክትን የሚከተሉ ሐዘናቸውን ያበዛሉ።+ እንደ እነሱ ደምን የመጠጥ መባ አድርጌ አላቀርብም፤በከንፈሬም ስማቸውን አላነሳም።+ + 5 ይሖዋ ድርሻዬ፣ ዕጣ ፋንታዬና+ ጽዋዬ+ ነው። ርስቴን ትጠብቅልኛለህ። + 6 ለእኔ ርስት አድርገህ ለመስጠት የለካኸው ቦታ ያማረ ነው። አዎ፣ ባገኘሁት ርስት ረክቻለሁ።+ + 7 ምክር የሰጠኝን ይሖዋን አወድሳለሁ።+ በሌሊትም እንኳ በውስጤ ያለው ሐሳብ* ያርመኛል።+ + 8 ይሖዋን ሁልጊዜ በፊቴ አደርገዋለሁ።+ እሱ በቀኜ ስላለ ፈጽሞ አልናወጥም።*+ + 9 ስለዚህ ልቤ ሐሴት ያደርጋል፤ ሁለንተናዬ* ደስ ይለዋል። ያለስጋትም እኖራለሁ።* +10 መቃብር* ውስጥ አትተወኝምና።*+ ታማኝ አገልጋይህ ጉድጓድ እንዲያይ* አትፈቅድም።+ +11 የሕይወትን መንገድ አሳወቅከኝ።+ በፊትህ* ብዙ ደስታ አለ፤+በቀኝህ ለዘላለም ደስታ* አለ። +59 አምላኬ ሆይ፣ ከጠላቶቼ ታደገኝ፤+በእኔ ላይ ከተነሱት ሰዎች ጠብቀኝ።+ + 2 ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤ከጨካኝ* ሰዎችም አድነኝ። + 3 እነሆ፣ እኔን* ለማጥቃት አድፍጠው ይጠብቃሉ፤+ይሖዋ ሆይ፣ ምንም ዓይነት ዓመፅም ሆነ ኃጢአት ሳይገኝብኝብርቱ የሆኑ ሰዎች ያጠቁኛል።+ + 4 የሠራሁት ጥፋት ባይኖርም እኔን ለማጥቃት ተጣደፉ፤ ደግሞም ተዘጋጁ። ወደ አንተ ስጣራ ተነስ፤ ተመልከተኝም። + 5 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ ነህና።+ ብሔራትን ሁሉ ለመመርመር ተነስ። ተንኮለኛ ለሆኑ ከሃዲዎች ሁሉ ምሕረት አታድርግ።+ (ሴላ) + 6 በየምሽቱ ተመልሰው ይመጣሉ፤+እንደ ውሾች እያጉረመረሙ* በከተማዋ ዙሪያ ያደባሉ።+ + 7 ከአፋቸው የሚዥጎደጎደውን* ተመልከት፤ከንፈሮቻቸው እንደ ሰይፍ ናቸው፤+“ማን ይሰማል?” ይላሉና።+ + 8 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ትስቅባቸዋለህ፤+ብሔራትን ሁሉ ታላግጥባቸዋለህ።+ + 9 ብርታቴ ሆይ፣ አንተን እጠባበቃለሁ፤+አምላክ አስተማማኝ መጠጊያዬ ነውና።+ +10 ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላክ ይረዳኛል፤+አምላክ ጠላቶቼን በድል አድራጊነት ስሜት እንዳያቸው ያደርገኛል።+ +11 ሕዝቤ ይህን እንዳይረሳ አትግደላቸው። በኃይልህ እንዲቅበዘበዙ አድርጋቸው፤ጋሻችን ይሖዋ ሆይ፣ ለውድቀት ዳርጋቸው።+ +12 ከአፋቸው ኃጢአትና ከከንፈራቸው ቃል፣ከሚናገሩት እርግማንና የማታለያ ቃል የተነሳበኩራታቸው ይጠመዱ።+ +13 በቁጣህ አጥፋቸው፤+ከሕልውና ውጭ እንዲሆኑ ደምስሳቸው፤አምላክ ያዕቆብንና መላውን ምድር በመግዛት ላይ እንደሆነ አሳውቃቸው።+ (ሴላ) +14 ምሽት ላይ ተመልሰው ይምጡ፤እንደ ውሾች እያጉረመረሙ* በከተማዋ ዙሪያ ያድቡ።+ +15 ምግብ ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ይንከራተቱ፤+በልተውም አይጥገቡ፤ የሚያርፉበት ቦታም ይጡ። +16 እኔ ግን ስለ ብርታትህ እዘምራለሁ፤+በማለዳ ስለ ታማኝ ፍቅርህ በደስታ እናገራለሁ። አንተ አስተማማኝ መጠጊያዬ፣ደግሞም በጭንቀቴ ቀን መሸሸጊያዬ ነህና።+ +17 ብርታቴ ሆይ፣ ለአንተ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤+ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያዬ ነውና።+ +96 ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ።+ መላዋ ምድር ለይሖዋ ትዘምር!+ + 2 ለይሖዋ ዘምሩ፤ ስሙንም አወድሱ። የማዳኑን ምሥራች በየቀኑ አውጁ።+ + 3 ክብሩን በብሔራት፣አስደናቂ ሥራዎቹንም በሕዝቦች ሁሉ መካከል አስታውቁ።+ + 4 ይሖዋ ታላቅ ነው፤ ደግሞም እጅግ ሊወደስ ይገባዋል። ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ የሚፈራ ነው። + 5 የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ሁሉ ከንቱ ናቸው፤+ይሖዋ ግን ሰማያትን የሠራ አምላክ ነው።+ + 6 ሞገስና* ግርማ በፊቱ ናቸው፤+ብርታትና ውበት በመቅደሱ ውስጥ አሉ።+ + 7 እናንተ የሕዝብ ነገዶች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+ + 8 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ፤+ስጦታ ይዛችሁ ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ። + 9 ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ፤*ምድር ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጪ! +10 በብሔራት መካከል እንዲህ ብላችሁ አስታውቁ፦ “ይሖዋ ነገሠ!+ ምድር* በጽኑ ተመሥርታለች፤ ከቦታዋ ልትንቀሳቀስ አትችልም።* እሱ ለሕዝቦች በትክክል ይፈርዳል።”*+ +11 ሰማያት ሐሴት ያድርጉ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማ፤+ +12 መስኩና በላዩ ላይ ያለው ሁሉ ሐሴት ያድርግ።+ የዱር ዛፎችም ሁሉ በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ።+ +13 እሱ እየመጣ ነውና፤*በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነው። በዓለም* ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በታማኝነት ይፈርዳል።+ +51 አምላክ ሆይ፣ እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን ሞገስ አሳየኝ።+ እንደ ታላቅ ምሕረትህ መተላለፌን ደምስስ።+ + 2 ከበደሌ ሙሉ በሙሉ እጠበኝ፤+ከኃጢአቴም አንጻኝ።+ + 3 መተላለፌን በሚገባ አውቃለሁና፤ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነው።*+ + 4 አንተን፣ አዎ ከማንም በላይ አንተን* በደልኩ፤+በአንተ ዓይን ክፉ የሆነውን ነገር ፈጸምኩ።+ ስለዚህ አንተ በምትናገርበት ጊዜ ጻድቅ ነህ፤በምትፈርድበት ጊዜም ትክክል ነህ።+ + 5 እነሆ፣ በደለኛ ሆኜ ተወለድኩ፤እናቴም በኃጢአት ፀነሰችኝ።*+ + 6 ከልብ የመነጨ እውነት ደስ ያሰኝሃል፤+ልቤን* እውነተኛ ጥበብ አስተምረው። + 7 ንጹሕ እሆን ዘንድ በሂሶጵ ከኃጢአቴ አንጻኝ፤+ከበረዶም የበለጠ እነጣ ዘንድ እጠበኝ።+ + 8 ያደቀቅካቸው አጥንቶች ደስ እንዲላቸው፣+የደስታንና የሐሴትን ድምፅ አሰማኝ። + 9 ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፤*+የፈጸምኳቸውንም ስህተቶች ሁሉ አስወግድ።*+ +10 አምላክ ሆይ፣ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤+በውስጤም ጽኑ የሆነ አዲስ መንፈስ አኑር።+ +11 ከፊትህ አትጣለኝ፤ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድ። +12 የአንተ ማዳን የሚያስገኘውን ደስታ መልስልኝ፤+አንተን የመታዘዝ ፍላጎት በውስጤ እንዲቀሰቀስ አድርግ።* +13 ኃጢአተኞች ወደ አንተ እንዲመለሱ፣ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ።+ +14 አምላክ ሆይ፣ የመዳኔ አምላክ፣+ አንደበቴ ጽድቅህን በደስታ ያስታውቅ ዘንድ+የደም ባለዕዳ ከመሆን አድነኝ።+ +15 ይሖዋ ሆይ፣ አፌ ምስጋናህን እንዲያውጅከንፈሮቼን ክፈት።+ +16 መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትፈልግምና፤ ቢሆንማ ኖሮ ባቀረብኩልህ ነበር፤+ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አያስደስትህም።+ +17 አምላክን የሚያስደስተው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤አምላክ ሆይ፣ የተሰበረንና የተደቆሰን ልብ ችላ አትልም።*+ +18 በበጎ ፈቃድህ ለጽዮን መልካም ነገር አድርግላት፤የኢየሩሳሌምን ግንቦች ገንባ። +19 በዚያን ጊዜ የጽድቅ መሥዋዕቶች፣የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችና ሙሉ በሙሉ የሚቀርቡ መባዎች ደስ ያሰኙሃል፤በዚያን ጊዜ ኮርማዎች በመሠዊያህ ላይ ይቀርባሉ።+ +120 በተጨነቅኩ ጊዜ ይሖዋን ተጣራሁ፤+እሱም መለሰልኝ።+ + 2 ይሖዋ ሆይ፣ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ደግሞም ከአታላይ አንደበት ታደገኝ።* + 3 አንተ አታላይ አንደበት፣አምላክ ምን ያደርግህ ይሆን? እንዴትስ ይቀጣህ ይሆን?*+ + 4 ሹል በሆኑ የተዋጊ ፍላጻዎችና+በክትክታ እንጨት ፍም+ ይቀጣሃል። + 5 በመሼቅ+ የባዕድ አገር ሰው ሆኜ ስለኖርኩ ወዮልኝ! በቄዳር+ ድንኳኖች መካከል ኖሬአለሁ። + 6 ሰላም ከሚጠሉ ሰዎች ጋርለረጅም ጊዜ ኖሬአለሁ።*+ + 7 እኔ ለሰላም ቆሜአለሁ፤እነሱ ግን በተናገርኩ ቁጥር ለጦርነት ይነሳሉ። +150 ያህን አወድሱ!*+ አምላክን በተቀደሰ ስፍራው አወድሱት።+ ብርታቱን በሚያሳየው ጠፈር* አወድሱት።+ + 2 ስለ ብርቱ ሥራዎቹ አወድሱት።+ ወደር የለሽ ስለሆነው ታላቅነቱ አወድሱት።+ + 3 በቀንደ መለከት+ ድምፅ አወድሱት። በባለ አውታር መሣሪያና በበገና አወድሱት።+ + 4 በአታሞና+ በሽብሸባ አወድሱት። በባ��� አውታር መሣሪያና+ በዋሽንት+ አወድሱት። + 5 በሚያስተጋባ ሲምባል* አወድሱት። ኃይለኛ ድምፅ በሚያወጣ ሲምባል+ አወድሱት። + 6 እስትንፋስ ያለው ሁሉ ያህን ያወድስ። ያህን አወድሱ!*+ +6 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤በታላቅ ቁጣህም አታርመኝ።+ + 2 ይሖዋ ሆይ፣ ዝያለሁና ሞገስ አሳየኝ።* ይሖዋ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተንቀጥቅጠዋልና ፈውሰኝ።+ + 3 አዎ፣ እጅግ ተረብሻለሁ፤*+ይሖዋ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ድረስ ነው? ብዬ እጠይቅሃለሁ።+ + 4 ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ፤ ደግሞም ታደገኝ፤*+ለታማኝ ፍቅርህ ስትል አድነኝ።+ + 5 ሙታን አንተን አያነሱም፤*በመቃብር* ማን ያወድስሃል?+ + 6 ከመቃተቴ የተነሳ ዝያለሁ፤+ሌሊቱን ሙሉ መኝታዬን በእንባ አርሳለሁ፤*በለቅሶ አልጋዬን አጥለቀልቃለሁ።+ + 7 በሐዘኔ ምክንያት ዓይኔ ደክሟል፤+ከሚያጠቁኝ ሰዎች ሁሉ የተነሳ ዓይኔ ፈዟል።* + 8 እናንተ መጥፎ ምግባር ያላችሁ ሁሉ ከእኔ ራቁ፤ይሖዋ የለቅሶዬን ድምፅ ይሰማልና።+ + 9 ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳየኝ የማቀርበውን ልመና ይሰማል፤+ይሖዋ ጸሎቴን ይቀበላል። +10 ጠላቶቼ በሙሉ ያፍራሉ፤ ደግሞም እጅግ ይደነግጣሉ፤በድንገት ውርደት ተከናንበው ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።+ +25 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እማጸናለሁ።* + 2 አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፤+ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ።+ ጠላቶቼ በደረሰብኝ መከራ አይፈንድቁ።+ + 3 አንተን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ በፍጹም አያፍርም፤+ያላንዳች ምክንያት ክህደት የሚፈጽሙ ግን ለኀፍረት ይዳረጋሉ።+ + 4 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አሳውቀኝ፤+ጎዳናህንም አስተምረኝ።+ + 5 አንተ አዳኝ አምላኬ ስለሆንክበእውነትህ እንድመላለስ አድርገኝ፤ አስተምረኝም።+ ז [ዋው] ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አደርጋለሁ። + 6 ይሖዋ ሆይ፣ ምንጊዜም ታሳያቸው የነበሩትን*+ምሕረትህንና ታማኝ ፍቅርህን አስታውስ።+ + 7 በወጣትነቴ የሠራኋቸውን ኃጢአቶችና በደሎች አታስብብኝ። ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩነትህ ስትል+እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን አስበኝ።+ + 8 ይሖዋ ጥሩና ቀና ነው።+ ኃጢአተኞችን ሊኖሩበት የሚገባውን መንገድ የሚያስተምራቸው ለዚህ ነው።+ + 9 የዋሆችን በትክክለኛ መንገድ* ይመራቸዋል፤+እንዲሁም ለየዋሆች መንገዱን ያስተምራል።+ +10 የይሖዋ መንገዶች ሁሉ፣ ቃል ኪዳኑንና+ ማሳሰቢያዎቹን+ ለሚጠብቁ፣ታማኝ ፍቅር የሚንጸባረቅባቸውና እምነት የሚጣልባቸው ናቸው። +11 ይሖዋ ሆይ፣ ኃጢአቴ ታላቅ ቢሆንም እንኳለስምህ ስትል ይቅር በለኝ።+ +12 ይሖዋን የሚፈራ ሰው ማን ነው?+ መምረጥ ስላለበት መንገድ ያስተምረዋል።+ +13 እሱ ጥሩ የሆነውን ነገር ያገኛል፤*+ዘሮቹም ምድርን ይወርሳሉ።+ +14 ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት የሚኖራቸው እሱን የሚፈሩ ሰዎች ናቸው፤+ቃል ኪዳኑንም ያሳውቃቸዋል።+ +15 ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ ይሖዋ ያያሉ፤+እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና።+ +16 ብቸኛና ምስኪን ስለሆንኩፊትህን ወደ እኔ መልስ፤ ቸርነትም አሳየኝ። +17 የልቤ ጭንቀት በዝቷል፤+ከሥቃዬ ገላግለኝ። +18 ጉስቁልናዬንና መከራዬን ተመልከት፤+ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በል።+ +19 ጠላቶቼ ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ተመልከት፤ምን ያህል አምርረው እንደሚጠሉኝም እይ። +20 ሕይወቴን* ጠብቅ፤ አድነኝም።+ አንተን መጠጊያ ስላደረግኩ ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ። +21 ንጹሕ አቋሜና* ቅንነቴ ይጠብቁኝ፤+አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና።+ +22 አምላክ ሆይ፣ እስራኤልን ከጭንቀቱ ሁሉ ታደገው።* +140 ይሖዋ ሆይ፣ ከክፉ ሰዎች ታደገኝ፤ከጨካኞችም ጠብቀኝ፤+ + 2 እነሱ በልባቸው ክፉ ነገር ይጠነስሳሉ፤+ደግሞም ቀኑን ሙሉ ጠብ ይጭራሉ። + 3 እንደ እባብ ምላሳቸውን ያሾላሉ፤+ከከንፈራቸው ኋላ የእፉኝት መርዝ አለ።+ (ሴላ) + 4 ይሖዋ ሆይ፣ ከክፉዎች እጅ አድነኝ፤+እኔን ጠልፈው ለመጣል ከሚያሴሩጨካኝ ሰዎች ጠብቀኝ። + 5 ትዕቢተኞች በስውር ወጥመድ አስቀመጡብኝ፤ከመንገዱ አጠገብ የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ።+ አሽክላም አስቀመጡብኝ።+ (ሴላ) + 6 ይሖዋን እንዲህ እለዋለሁ፦ “አንተ አምላኬ ነህ። ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ።”+ + 7 ኃያል አዳኜ የሆንከው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣በጦርነት ቀን ራሴን ትከልላለህ።+ + 8 ይሖዋ ሆይ፣ የክፉዎች ምኞት እንዲሳካ አታድርግ። ራሳቸውን ከፍ ከፍ እንዳያደርጉ፣ ሴራቸው እንዲሰምር አትፍቀድ።+ (ሴላ) + 9 ዙሪያዬን የከበቡኝን ሰዎች ራስ፣የገዛ ከንፈራቸው የተናገረው ክፋት ይሸፍነው።+ +10 የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ።+ መነሳት እንዳይችሉ ወደ እሳት፣ወደ ጥልቅ ጉድጓዶች* ይወርወሩ።+ +11 ስም አጥፊ በምድር* ላይ አንዳች ቦታ አያግኝ።+ ጨካኞችን ክፋት አሳዶ ይምታቸው። +12 ይሖዋ ለችግረኛው እንደሚሟገትናለድሃው ፍትሕ እንደሚያሰፍን አውቃለሁ።+ +13 በእርግጥ ጻድቃን ለስምህ ምስጋና ያቀርባሉ፤ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ።+ +33 እናንተ ጻድቃን ሆይ፣ ይሖዋ ባደረጋቸው ነገሮች የተነሳ እልል በሉ።+ ቅኖች እሱን ማወደሳቸው የተገባ ነው። + 2 ይሖዋን በበገና አመስግኑት፤አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩለት። + 3 አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤+በባለ አውታር መሣሪያ ጥሩ አድርጋችሁ ተጫወቱ፤ እልልም በሉ። + 4 የይሖዋ ቃል ትክክል ነውና፤+ሥራውም ሁሉ እምነት የሚጣልበት ነው። + 5 ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል።+ ምድር በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ተሞልታለች።+ + 6 ሰማያት በይሖዋ ቃል፣በውስጣቸው ያሉትም ሁሉ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ* ተሠሩ።+ + 7 የባሕርን ውኃዎች እንደ ግድብ ያከማቻል፤+የሚናወጠውንም ውኃ በማከማቻ ቦታ ይሰበስባል። + 8 መላዋ ምድር ይሖዋን ትፍራ።+ የምድር ነዋሪዎች እሱን ይፍሩ።* + 9 እሱ ተናግሯልና፣ ሆኗል፤+እሱ አዟል፤ ደግሞም ተፈጽሟል።+ +10 ይሖዋ የብሔራትን ሴራ* አክሽፏል፤+የሕዝቦችን ዕቅድ* አጨናግፏል።+ +11 ይሁንና የይሖዋ ውሳኔዎች ለዘላለም ይጸናሉ፤*+የልቡ ሐሳብ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል። +12 ይሖዋ አምላኩ የሆነ ብሔር፣የራሱ ንብረት አድርጎ የመረጠው ሕዝብ ደስተኛ ነው።+ +13 ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ይመለከታል፤የሰው ልጆችን ሁሉ ያያል።+ +14 ከመኖሪያ ቦታው ሆኖበምድር የሚኖሩትን በትኩረት ይመለከታል። +15 የሁሉንም ልብ የሚሠራው እሱ ነው፤ሥራቸውን ሁሉ ይመረምራል።+ +16 በሠራዊት ብዛት የዳነ ንጉሥ የለም፤+ኃያል ሰው በታላቅ ኃይሉ አይድንም።+ +17 ፈረስ ያድነኛል* ብሎ መታመን ከንቱ ተስፋ ነው፤+ታላቅ ኃይሉ ለመዳን ዋስትና አይሆንም። +18 እነሆ፣ የይሖዋ ዓይን የሚፈሩትን፣ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን የሚጠባበቁትን በትኩረት ይመለከታል፤+ +19 ይህም እነሱን* ከሞት ለመታደግ፣በረሃብ ወቅትም እነሱን በሕይወት ለማኖር ነው።+ +20 ይሖዋን በተስፋ እንጠባበቃለን።* እሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው።+ +21 ልባችን በእሱ ሐሴት ያደርጋል፤በቅዱስ ስሙ እንታመናለንና።+ +22 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን ስንጠባበቅ፣+ታማኝ ፍቅርህ በእኛ ላይ ይሁን።+ +54 አምላክ ሆይ፣ በስምህ አድነኝ፤+በኃይልህም ደግፈኝ።*+ + 2 አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+ለአፌም ቃል ትኩረት ስጥ። + 3 ባዕዳን በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤ጨካኝ ሰዎችም ሕይወቴን* ይሻሉ።+ ስለ አምላክ ምንም ግድ የላቸውም።*+ (ሴላ) + 4 እነሆ፣ አምላክ ረዳቴ ነው፤+ይሖዋ እኔን* ከሚደግፉ ጋር ነው። + 5 የገዛ ክፋታቸውን በጠላቶቼ ላይ ይመልስባቸዋል፤+በታማኝነትህ አስወግዳቸው።*+ + 6 ለአንተ በፈቃደኝነት መሥዋዕት አቀርባለሁ።+ ይሖዋ ሆይ፣ መ��ካም ነውና፣ ስምህን አወድሳለሁ።+ + 7 ከጭንቅ ሁሉ ያድነኛልና፤+ጠላቶቼንም በድል አድራጊነት እመለከታለሁ።+ +10 ይሖዋ ሆይ፣ ርቀህ የምትቆመው ለምንድን ነው? በመከራ ጊዜ ራስህን የምትሰውረው ለምንድን ነው?+ + 2 ክፉ ሰው በእብሪት ተነሳስቶ ምስኪኑን ያሳድዳል፤+ይሁንና በወጠነው ሴራ ይያዛል።+ + 3 ክፉው ሰው በራስ ወዳድነት ምኞቱ ይኩራራልና፤*+ስግብግብ የሆነውንም ሰው ይባርካል፤*נ [ኑን] ይሖዋንም ያቃልላል። + 4 ክፉው ሰው ከትዕቢቱ የተነሳ ምንም ምርምር አያደርግም፤“አምላክ የለም” ብሎ ያስባል።+ + 5 መንገዱ ሁልጊዜ የተሳካ ነው፤+ሆኖም ፍርድህ እሱ ሊገነዘበው ከሚችለው በላይ ነው፤+በጠላቶቹ ሁሉ ላይ ያፌዛል።* + 6 በልቡ እንዲህ ይላል፦ “ፈጽሞ አልናወጥም፤*ከትውልድ እስከ ትውልድምንም መከራ አይደርስብኝም።”+ + 7 አፉ በእርግማን፣ በውሸትና በዛቻ የተሞላ ነው፤+ከምላሱ ሥር ችግርና ጉዳት የሚያስከትል ነገር አለ።+ + 8 በመንደሮቹ አጠገብ አድብቶ ይጠብቃል፤ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ንጹሑን ሰው ይገድላል።+ ע [አይን] ዓይኖቹ ያልታደለውን ሰለባ ይጠባበቃሉ።+ + 9 በጎሬው ውስጥ እንዳለ* አንበሳ በተደበቀበት ቦታ አድፍጦ ይጠብቃል።+ ምስኪኑን ሰው ለመያዝ ይጠባበቃል። ምስኪኑን ሰው መረቡ ውስጥ አስገብቶ ይይዘዋል።+ +10 ሰለባው ይደቅቃል፤ ደግሞም ይወድቃል፤ያልታደሉ ሰዎች መዳፉ ውስጥ ይወድቃሉ። +11 በልቡ እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ረስቷል።+ ፊቱን አዙሯል። ፈጽሞ ልብ አይልም።”+ +12 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ።+ አምላክ ሆይ፣ እጅህን አንሳ።+ ምስኪኖችን አትርሳ።+ +13 ክፉው ሰው አምላክን ያቃለለው ለምንድን ነው? በልቡ “ተጠያቂ አታደርገኝም” ይላል። +14 አንተ ግን ችግርንና መከራን ትመለከታለህ። ደግሞም አይተህ እርምጃ ትወስዳለህ።+ ያልታደለው ሰለባ ወደ አንተ ይጮኻል፤+አንተ አባት ለሌለው ልጅ* ረዳቱ ነህ።+ +15 ክፉና መጥፎ የሆነውን ሰው ክንድ ስበር፤+ከዚያ በኋላ ክፋቱን በምትፈልግበት ጊዜጨርሶ አታገኘውም። +16 ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ነው።+ ብሔራት ከምድር ጠፍተዋል።+ +17 ይሖዋ ሆይ፣ የዋሆች የሚያቀርቡትን ልመና ግን ትሰማለህ።+ ልባቸውን ታጸናለህ፤+ ደግሞም ትኩረት ትሰጣቸዋለህ።+ +18 በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ከእንግዲህ እንዳያሸብራቸው፣+አባት ለሌለው ልጅና ለተደቆሱ ሰዎች ፍትሕ ታሰፍናለህ።+ +76 አምላክ በይሁዳ የታወቀ ነው፤+ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።+ + 2 መጠለያው በሳሌም+ ነው፤መኖሪያውም በጽዮን ነው።+ + 3 በዚያም የሚንበለበሉትን ፍላጻዎች፣ጋሻን፣ ሰይፍንና የጦር መሣሪያዎችን ሰባበረ።+ (ሴላ) + 4 አንተ ደምቀህ ታበራለህ፤*አዳኝ አራዊት ከሚኖሩባቸው ተራሮች ይልቅ ታላቅ ግርማ ተጎናጽፈሃል። + 5 ልበ ሙሉ የሆኑት ሰዎች ተዘርፈዋል።+ እንቅልፍ ጥሏቸዋል፤ተዋጊዎቹ በሙሉ መከላከል የሚችሉበት ኃይል አልነበራቸውም።+ + 6 የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ከተግሣጽህ የተነሳባለ ሠረገላውም ሆነ ፈረሱ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል።+ + 7 አንተ ብቻ እጅግ የምትፈራ ነህ።+ ኃይለኛ ቁጣህን ማን ሊቋቋም ይችላል?+ + 8 አንተ ከሰማይ ፍርድ ተናገርክ፤+ምድር ፈርታ ዝም አለች፤+ + 9 ይህም የሆነው አምላክ በምድር ላይ የሚኖሩትን የዋሆች ሁሉ ለማዳን+ፍርድ ሊያስፈጽም በተነሳበት ጊዜ ነው። (ሴላ) +10 የሰው ቁጣ ለአንተ ውዳሴ ያመጣልና፤+በቀረው ቁጣቸው ራስህን ታስጌጣለህ። +11 ለአምላካችሁ ለይሖዋ ተሳሉ፤ ስእለታችሁንም ፈጽሙ፤+በዙሪያው ያሉ ሁሉ በፍርሃት ስጦታቸውን ያምጡ።+ +12 እሱ የመሪዎችን ኩራት* ያስወግዳል፤በምድር ነገሥታት ላይ ፍርሃት ያሳድራል። +121 ዓይኖቼን ወደ ተራሮች አነሳለሁ።+ እርዳታ የማገኘው ከየት ነው? + 2 እ���ን የሚረዳኝሰማይንና ምድርን የሠራው ይሖዋ ነው።+ + 3 እሱ እግርህ እንዲንሸራተት* ፈጽሞ አይፈቅድም።+ ጠባቂህ በጭራሽ አያንቀላፋም። + 4 እነሆ፣ እስራኤልን የሚጠብቀው፣ፈጽሞ አያንቀላፋም፤ ደግሞም አይተኛም።+ + 5 ይሖዋ ይጠብቅሃል። ይሖዋ በቀኝህ ሆኖ+ ይጋርድሃል።+ + 6 ቀን ፀሐይ አይመታህም፤+ሌሊትም ጨረቃ አይጎዳህም።+ + 7 ይሖዋ ከማንኛውም ጉዳት ይጠብቅሃል።+ እሱ ሕይወትህን* ይጠብቃል።+ + 8 ይሖዋ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣በምታደርገው ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል።* +14 ሞኝ* ሰው በልቡ “ይሖዋ የለም” ይላል።+ ሥራቸው ብልሹ ነው፤ ተግባራቸውም አስጸያፊ ነው፤መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+ + 2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት፣ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+ + 3 ሁሉም መንገድ ስተዋል፤+ሁሉም ብልሹ ናቸው። መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤አንድ እንኳ የለም። + 4 ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም? ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ። ይሖዋን አይጠሩም። + 5 ይሁንና በታላቅ ሽብር ይዋጣሉ፤+ይሖዋ ከጻድቅ ትውልድ ጋር ነውና። + 6 እናንተ ክፉ አድራጊዎች የችግረኛውን ሰው ዕቅድ ለማጨናገፍ ትሞክራላችሁ፤ይሖዋ ግን መጠጊያው ነው።+ + 7 የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+ ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ። +65 አምላክ ሆይ፣ በጽዮን+ ውዳሴ ይቀርብልሃል፤የተሳልነውን ለአንተ እንሰጣለን።+ + 2 ጸሎት ሰሚ የሆንከው አምላክ ሆይ፣ ሁሉም ዓይነት ሰው* ወደ አንተ ይመጣል።+ + 3 የፈጸምኳቸው በደሎች አሸንፈውኛል፤+አንተ ግን መተላለፋችንን ይቅር አልክ።+ + 4 በቅጥር ግቢዎችህ ይኖር ዘንድየመረጥከውና ያቀረብከው ሰው ደስተኛ ነው።+ እኛም በቤትህ፣ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደስህ+ ውስጥ ባሉ ጥሩ ነገሮች እንረካለን።+ + 5 የመዳናችን አምላክ ሆይ፣ፍርሃት* በሚያሳድሩ የጽድቅ ተግባሮች ትመልስልናለህ፤+በምድር ዳርቻዎች ሁሉናከባሕሩ ማዶ ርቀው ላሉት መታመኛቸው ነህ።+ + 6 አንተ* በኃይልህ ተራሮችን አጽንተህ መሥርተሃል፤ኃይልንም ለብሰሃል።+ + 7 አንተ* የሚናወጡትን ባሕሮች፣ የሞገዶቻቸውን ድምፅ፣የብሔራትንም ነውጥ ጸጥ ታሰኛለህ።+ + 8 ርቀው በሚገኙ ስፍራዎች የሚኖሩ ሰዎች ምልክቶችህን አይተው በታላቅ አድናቆት ይዋጣሉ፤+ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ያሉ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋለህ። + 9 ምድርን እጅግ ፍሬያማ* በማድረግናበማበልጸግ ትንከባከባታለህ።+ የአምላክ ጅረት በውኃ የተሞላ ነው፤ለሰዎች እህል ትሰጣለህ፤+ምድርን ያዘጋጀኸው በዚህ መንገድ ነውና። +10 ትልሞቿን በውኃ ታረሰርሳለህ፤ የታረሰውንም መሬት* ትደለድላለህ፤በካፊያ ታለሰልሳታለህ፤ ቡቃያዋንም ትባርካለህ።+ +11 ዘመኑ ጥሩነትህን እንደ ዘውድ እንዲጎናጸፍ ታደርጋለህ፤በጎዳናዎችህም ላይ የተትረፈረፉ ነገሮች ይፈስሳሉ።*+ +12 የምድረ በዳው የግጦሽ መሬቶች ሁልጊዜ እንደረሰረሱ ናቸው፤*+ኮረብቶቹም ደስታን ተጎናጽፈዋል።+ +13 የግጦሽ መሬቶቹ በመንጎች ተሞሉ፤ሸለቆዎቹም* በእህል ተሸፈኑ።+ በድል አድራጊነት እልል ይላሉ፤ አዎ፣ ይዘምራሉ።+ +145 ንጉሡ አምላኬ ሆይ፣+ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ለዘላለም ስምህን አወድሳለሁ።+ + 2 ቀኑን ሙሉ አወድስሃለሁ፤+ለዘላለም ስምህን አወድሳለሁ።+ + 3 ይሖዋ ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊወደስም ይገባዋል፤+ታላቅነቱ አይመረመርም።*+ + 4 ትውልዶች ሁሉ ሥራህን ያወድሳሉ፤ስላከናወንካቸው ታላላቅ ነገሮች ይናገራሉ።+ + 5 ታላቅ ውበት ስለተጎናጸፈው ግርማህ ይናገራሉ፤+እኔም ስለ ድንቅ ሥራዎችህ አሰላስላለሁ። + 6 እጅግ አስደናቂ ስለሆነው ሥራህ* ይናገራሉ፤እኔም ስለ ታላቅነትህ አውጃለሁ። + 7 የጥሩነትህን ብዛት ሲያስታውሱ በስሜት ያወራሉ፤+ከጽድቅህም የተነሳ እልል ይላሉ።+ + 8 ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ፣+እንዲሁም ለቁጣ የዘገየ ነው፤ ታማኝ ፍቅሩም ታላቅ ነው።+ + 9 ይሖዋ ለሁሉም ጥሩ ነው፤+ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ይታያል። +10 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራዎችህ ሁሉ ከፍ ከፍ ያደርጉሃል፤+ታማኝ አገልጋዮችህም ያወድሱሃል።+ +11 የንግሥናህን ክብር ያውጃሉ፤+ስለ ኃያልነትህም ይናገራሉ፤+ +12 ይህም ለሰዎች ታላላቅ ሥራዎችህንና+የንግሥናህን ታላቅ ክብር+ ያስታውቁ ዘንድ ነው። +13 ንግሥናህ ዘላለማዊ ነው፤ግዛትህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።+ +14 ይሖዋ ሊወድቁ የተቃረቡትን ሁሉ ይደግፋል፤+ያጎነበሱትንም ሁሉ ቀና ያደርጋል።+ +15 ዓይን ሁሉ አንተን በተስፋ ይመለከታል፤አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።+ +16 አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታሟላለህ።+ +17 ይሖዋ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣+በሥራውም ሁሉ ታማኝ ነው።+ +18 ይሖዋ ለሚጠሩት ሁሉ፣በእውነት* ለሚጠሩት+ ሁሉ ቅርብ ነው።+ +19 የሚፈሩትን ሰዎች ፍላጎት ያረካል፤+እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማል፤ ደግሞም ይታደጋቸዋል።+ +20 ይሖዋ የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤+ክፉዎችን ሁሉ ግን ይደመስሳል።+ +21 አፌ የይሖዋን ውዳሴ ያስታውቃል፤+ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ ቅዱስ ስሙን* ለዘላለም ያወድሱ።+ +66 ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለአምላክ እልል ትበል።+ + 2 ለክብራማ ስሙ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። ውዳሴውን አድምቁ።+ + 3 አምላክን እንዲህ በሉት፦ “ሥራዎችህ አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ ናቸው።+ ከኃይልህ ታላቅነት የተነሳጠላቶችህ በፊትህ ይሽቆጠቆጣሉ።+ + 4 በምድር ያሉ ሁሉ ይሰግዱልሃል፤+ለአንተ የውዳሴ መዝሙር ይዘምራሉ፤ለስምህም የውዳሴ መዝሙር ይዘምራሉ።”+ (ሴላ) + 5 ኑና የአምላክን ሥራዎች ተመልከቱ። ለሰው ልጆች ያከናወናቸው ተግባሮች አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ ናቸው።+ + 6 እሱ ባሕሩን ደረቅ ምድር አደረገው፤+ወንዙን በእግራቸው ተሻገሩ።+ በዚያ በእሱ እጅግ ደስ አለን።+ + 7 በኃይሉ ለዘላለም ይገዛል።+ ዓይኖቹ ብሔራትን አተኩረው ያያሉ።+ ግትር የሆኑ ሰዎች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ።+ (ሴላ) + 8 እናንተ ሕዝቦች ሆይ፣ አምላካችንን አወድሱ፤+ለእሱ የሚቀርበውም የውዳሴ ድምፅ ይሰማ። + 9 እሱ በሕይወት ያኖረናል፤*+እግራችን እንዲደናቀፍ* አይፈቅድም።+ +10 አምላክ ሆይ፣ አንተ መርምረኸናልና፤+ብር በእሳት እንደሚጠራ ሁሉ አንተም እኛን አጥርተኸናል። +11 ማጥመጃ መረብ ውስጥ አስገባኸን፤በላያችንም* ከባድ ሸክም ጫንክብን። +12 ሟች ሰው ላያችን* ላይ እንዲጋልብ አደረግክ፤በእሳት መካከልና በውኃ መካከል አለፍን፤ከዚያም እረፍት ወደምናገኝበት ስፍራ አመጣኸን። +13 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ይዤ ወደ ቤትህ እመጣለሁ፤+ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤+ +14 ይህም በጭንቅ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ ከንፈሮቼ ቃል የገቡት፣አፌም የተናገረው ነው።+ +15 የሰቡ እንስሳትን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጌከሚጨስ የአውራ በጎች መሥዋዕት ጋር አቀርብልሃለሁ። ከአውራ ፍየሎችም ጋር ኮርማዎችን አቀርባለሁ። (ሴላ) +16 እናንተ አምላክን የምትፈሩ ሁሉ፣ ኑና አዳምጡ፤ለእኔ ያደረገልኝንም* ነገር እነግራችኋለሁ።+ +17 በአፌ ወደ እሱ ተጣራሁ፤በአንደበቴም ከፍ ከፍ አደረግኩት። +18 በልቤ አንዳች መጥፎ ነገር ይዤ ቢሆን ኖሮ፣ይሖዋ ባልሰማኝ ነበር።+ +19 ሆኖም አምላክ ሰምቷል፤+ጸሎቴን በትኩረት አዳምጧል።+ +20 ጸሎቴን ከመስማት ጆሮውን ያልመለሰ፣ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን ያልነፈገኝ አምላክ ውዳሴ ይድረሰው። +43 አምላክ ሆይ፣ ፍረድልኝ፤+ከከዳተኛ ብሔር ጋር ያለብኝን ሙግት አንተ ተሟገትልኝ።+ አታላይና ዓመፀኛ ከሆነ ሰው ታደገኝ። + 2 አንተ አምላኬና ምሽጌ ነህና።+ ለምን ተውከኝ? ጠላቴ ከሚያደርስብኝ ጭቆና የተነሳ ለምን አዝኜ ልመላለስ?+ + 3 ብርሃንህንና እውነትህን ላክ።+ እነሱ ይምሩኝ፤+ወደተቀደሰው ተራራህና ወደ ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ይውሰዱኝ።+ + 4 ከዚያም ወደ አምላክ መሠዊያ፣+እጅግ ሐሴት ወደማደርግበት አምላክ እመጣለሁ። ደግሞም አምላክ ሆይ፣ አምላኬ፣ በበገና አወድስሃለሁ።+ + 5 ተስፋ የምቆርጠው* ለምንድን ነው? ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው? አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤+እሱን እንደ ታላቅ አዳኜና አምላኬ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና።+ +126 ይሖዋ የጽዮንን ምርኮኞች መልሶ በሰበሰበ ጊዜ፣+ሕልም የምናይ መስሎን ነበር። + 2 በዚያን ጊዜ አፋችን በሳቅ፣አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ።+ ያን ጊዜ ብሔራት እንዲህ አሉ፦ “ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች አደረገላቸው።”+ + 3 ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች አደረገልን፤+እኛም እጅግ ተደሰትን። + 4 ይሖዋ ሆይ፣ በኔጌብ እንዳሉ ጅረቶች፣*የተማረኩብንን ሰዎች መልሰህ ሰብስብ።* + 5 በእንባ የሚዘሩ፣በእልልታ ያጭዳሉ። + 6 ዘር ቋጥሮ የወጣው ሰው፣የሄደው እያለቀሰ ቢሆንም እንኳነዶውን ተሸክሞእልል እያለ ይመለሳል።+ +82 አምላክ በመለኮታዊ ጉባኤ መካከል ይሰየማል፤*+በአማልክት* መካከል ይፈርዳል፦+ + 2 “ፍትሕ የምታዛቡት እስከ መቼ ነው?+ለክፉዎችስ የምታዳሉት እስከ መቼ ነው?+ (ሴላ) + 3 ለችግረኛውና አባት ለሌለው ተሟገቱ።*+ ረዳት የሌለውና ምስኪኑ ፍትሕ እንዲያገኝ አድርጉ።+ + 4 ችግረኛውንና ድሃውን ታደጉ፤ከክፉዎችም እጅ አድኗቸው።” + 5 ፈራጆቹ ምንም አያውቁም፤ ደግሞም አያስተውሉም፤+በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፤የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናግተዋል።+ + 6 “እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘እናንተ አማልክት* ናችሁ፤+ሁላችሁም የልዑሉ አምላክ ልጆች ናችሁ። + 7 ይሁንና እናንተም ሰው እንደሚሞተው ትሞታላችሁ፤+ደግሞም እንደ ማንኛውም ገዢ ትወድቃላችሁ!’”+ + 8 አምላክ ሆይ፣ ተነስ፤ በምድርም ላይ ፍረድ፤+ብሔራት ሁሉ የአንተ ናቸውና። +104 ይሖዋን ላወድስ።*+ ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ።+ ሞገስንና* ግርማን ለብሰሃል።+ + 2 ብርሃንን እንደ ልብስ ተጎናጽፈሃል፤+ሰማያትን እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘርግተሃል።+ + 3 የላይኛዎቹን ክፍሎች ተሸካሚዎች ከላይ ባሉት ውኃዎች ላይ* ያኖራል፤+ደመናትን ሠረገላው ያደርጋል፤+በነፋስ ክንፎችም ይሄዳል።+ + 4 መላእክቱን መናፍስት፣አገልጋዮቹን የሚባላ እሳት ያደርጋል።+ + 5 ምድርን በመሠረቶቿ ላይ መሠረታት፤+እሷም ለዘላለም ከቦታዋ አትናወጥም።+ + 6 ጥልቅ ውኃን እንደ ልብስ አለበስካት።+ ውኃዎቹ ከተራሮቹ በላይ ቆሙ። + 7 በገሠጽካቸው ጊዜ ሸሹ፤+የነጎድጓድህን ድምፅ ሲሰሙ በድንጋጤ ፈረጠጡ፤ + 8 ተራሮች ወደ ላይ ወጡ፤+ ሸለቆዎችም ወደ ታች ወረዱ፤ሁሉም ወዳዘጋጀህላቸው ቦታ ሄዱ። + 9 ውኃዎቹ አልፈው እንዳይሄዱ፣እንደገናም ምድርን እንዳይሸፍኑ ወሰን አበጀህላቸው።+ +10 ምንጮችን ወደ ሸለቆዎች* ይልካል፤በተራሮች መካከል ይፈስሳሉ። +11 የዱር አራዊት ሁሉ ከዚያ ይጠጣሉ፤የዱር አህዮችም ጥማቸውን ይቆርጣሉ። +12 የሰማይ ወፎች ከእነሱ በላይ ይሰፍራሉ፤በለመለሙ የዛፍ ቅርንጫፎች መካከል ሆነው ይዘምራሉ። +13 ከላይ ካሉት ክፍሎቹ ሆኖ ተራሮችን ያጠጣል።+ በሥራህ ፍሬ ምድር ረካች።+ +14 ሣርን ለከብት፣አትክልትንም ለሰው ልጆች ጥቅም ያበቅላል፤+ይህን የሚያደርገው ምድር እህል እንድታስገኝ ነው፤ +15 እንዲሁም የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፣+ፊትን የሚያበራ ዘይትናየሰውን ልብ የሚያበረታ እህል እንዲገኝ ነው።+ +16 የይሖዋ ዛፎች፣ እሱ የተከላቸው አርዘ ሊባኖሶች፣ውኃ ጠጥተው ይረካሉ፤ +17 በዚያ ወፎች ጎጇቸውን ይሠራሉ። ራዛ*+ በጥድ ዛፎች ላይ ትኖራለች። +18 ረጃጅሞቹ ተራሮች፣ የተራራ ፍየሎች+ መኖሪያ ናቸው፤ቋጥኞቹ የሽኮኮዎች+ መሸሸጊያ ናቸው። +19 ጊዜያትን ለመለየት ጨረቃን ሠራ፤ፀሐይ የምትጠልቅበትን ጊዜ በሚገባ ታውቃለች።+ +20 ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤+በዚህ ጊዜ በጫካ የሚኖሩ አራዊት ሁሉ ወጥተው ይንቀሳቀሳሉ። +21 ደቦል አንበሶች አደን ለማግኘት ያገሳሉ፤+ምግባቸውንም ከአምላክ ይሻሉ።+ +22 ፀሐይ ስትወጣ፣ተመልሰው በየጎሬአቸው ይተኛሉ። +23 ሰውም ወደ ሥራው ተሰማርቶእስኪመሽ ድረስ ሲሠራ ይውላል። +24 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ብዙ ነው!+ ሁሉንም በጥበብ ሠራህ።+ ምድር በፈጠርካቸው ነገሮች ተሞልታለች። +25 ባሕሩ እጅግ ትልቅና ሰፊ ነው፤በዚያ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ትናንሽም ሆኑ ትላልቅ ሕያዋን ነገሮች ይርመሰመሳሉ።+ +26 በዚያም መርከቦች ይጓዛሉ፤በዚያ እንዲጫወት የፈጠርከው ሌዋታንም*+ በውስጡ ይሄዳል። +27 በወቅቱ ምግባቸውን እንድትሰጣቸው፣ሁሉም አንተን ይጠባበቃሉ።+ +28 አንተ የምትሰጣቸውን ይሰበስባሉ።+ እጅህን ስትከፍት መልካም ነገሮችን ይጠግባሉ።+ +29 ፊትህን ስትሰውር ይታወካሉ። መንፈሳቸውን ከወሰድክ ይሞታሉ፤ ወደ አፈርም ይመለሳሉ።+ +30 መንፈስህን ከላክ ይፈጠራሉ፤+የምድርንም ገጽ ታድሳለህ። +31 የይሖዋ ክብር ለዘላለም ይኖራል። ይሖዋ በሥራው ሐሴት ያደርጋል።+ +32 ምድርን ሲመለከት ትንቀጠቀጣለች፤ተራሮችን ሲነካ ይጨሳሉ።+ +33 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለይሖዋ እዘምራለሁ፤+በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+ +34 ሐሳቤ እሱን የሚያስደስት ይሁን።* እኔም በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ። +35 ኃጢአተኞች ከምድር ይጠፋሉ፤ክፉዎችም ከእንግዲህ አይገኙም።+ ይሖዋን ላወድስ።* ያህን አወድሱ!* +9 ይሖዋ ሆይ፣ በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ፤ስለ ድንቅ ሥራዎችህ ሁሉ እናገራለሁ።+ + 2 በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ልዑል አምላክ ሆይ፣ ለስምህ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።+ + 3 ጠላቶቼ ወደ ኋላ ሲያፈገፍጉ+ተሰናክለው ከፊትህ ይጠፋሉ። + 4 ለማቀርበው ትክክለኛ ክስ ትሟገትልኛለህና፤በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ በጽድቅ ትፈርዳለህ።+ + 5 ብሔራትን ገሠጽክ፤+ ክፉውንም አጠፋህ፤ስማቸውን ለዘላለም ደመሰስክ። + 6 ጠላቶች ለዘላለም ጠፍተዋል፤ከተሞቻቸውን አፈራርሰሃል፤መታሰቢያቸውም ሁሉ ይደመሰሳል።+ + 7 ይሖዋ ግን በዙፋኑ ላይ ለዘላለም ተቀምጧል፤+ዙፋኑንም ለፍትሕ ሲል አጽንቷል።+ + 8 ዓለምን* በጽድቅ ይዳኛል፤+ለብሔራት ትክክለኛ የፍርድ ውሳኔዎች ያስተላልፋል።+ + 9 ይሖዋ ለተጨቆኑ አስተማማኝ መጠጊያ ይሆናል፤+በመከራ ጊዜ አስተማማኝ መጠጊያ ነው።+ +10 ስምህን የሚያውቁ በአንተ ይታመናሉ፤+ይሖዋ ሆይ፣ አንተን የሚሹትን ፈጽሞ አትተዋቸውም።+ +11 በጽዮን ለሚኖረው ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አስታውቁ።+ +12 ደማቸውን የሚበቀለው እሱ ያስታውሳቸዋልና፤+የተጎሳቆሉ ሰዎች የሚያሰሙትን ጩኸት አይረሳም።+ +13 ይሖዋ ሆይ፣ ቸርነት አሳየኝ፤ከሞት ደጆች የምታነሳኝ አምላክ ሆይ፣+ የሚጠሉኝ ሰዎች የሚያደርሱብኝን እንግልት ተመልከት፤ +14 ያን ጊዜ የሚያስመሰግኑ ተግባሮችህን በጽዮን ሴት ልጅ ደጆች አውጃለሁ፤+በማዳን ሥራህም ሐሴት አደርጋለሁ።+ +15 ብሔራት፣ ራሳቸው በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ገቡ፤የገዛ እግራቸው በስውር ባስቀመጡት መረብ ተያዘ።+ +16 ይሖዋ በሚወስደው የፍርድ እርምጃ ይታወቃል።+ ክፉ ሰው በገዛ እጁ በሠራው ነገር ተጠመደ።+ ሂጋዮን።* (ሴላ) +17 ክፉ ሰው፣ አምላክን የሚረሱ ብሔራትም ሁሉወደ መቃብር* ይሄዳሉ። +18 ድሃ ግን ለዘላለም ተረስቶ አይቀርም፤+የየዋሆችም ተስፋ ፈጽሞ ከንቱ ሆኖ አይቀርም።+ +19 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! ሟች የሆነ ሰው እንዲያይል አትፍቀድ። ብሔራት በፊትህ ይፈረድባቸው።+ +20 ይሖዋ ሆይ፣ ፍርሃት ልቀቅባቸው፤+ሕዝቦች ሟች መሆናቸውን ይወቁ። (ሴላ) +138 በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ።+ በሌሎች አማልክት ፊትየውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።* + 2 ከታማኝ ፍቅርህና ከታማኝነትህ የተነሳወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤+ስምህንም አወድሳለሁ።+ ቃልህና ስምህ ከሁሉም ነገር በላይ ጎልቶ እንዲታይ አድርገሃልና።* + 3 በተጣራሁ ቀን መለስክልኝ፤+ደፋርና* ብርቱ አደረግከኝ።+ + 4 ይሖዋ ሆይ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያወድሱሃል፤+የተናገርካቸውን የተስፋ ቃሎች ይሰማሉና። + 5 ስለ ይሖዋ መንገዶች ይዘምራሉ፤የይሖዋ ክብር ታላቅ ነውና።+ + 6 ይሖዋ ከፍ ያለ ቢሆንም ትሑት የሆነውን ሰው ይመለከታል፤+ትዕቢተኛውን ግን ወደ እሱ እንዲቀርብ አይፈቅድም።+ + 7 አደገኛ በሆነ አካባቢ ባልፍም እንኳ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃለህ።+ በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤ቀኝ እጅህ ያድነኛል። + 8 ይሖዋ ለእኔ ሲል ሁሉንም ነገር ይፈጽማል። ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤+የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።+ +27 ይሖዋ ብርሃኔና+ አዳኜ ነው። ማንን እፈራለሁ?+ ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው።+ ማን ያሸብረኛል? + 2 ክፉዎች ሥጋዬን ለመብላት ባጠቁኝ ጊዜ፣+ተሰናክለው የወደቁት ባላጋራዎቼና ጠላቶቼ ናቸው። + 3 ሠራዊት በዙሪያዬ ቢሰፍርም፣ልቤ በፍርሃት አይዋጥም።+ ጦርነት ቢከፈትብኝም እንኳበልበ ሙሉነት እመላለሳለሁ። + 4 ይሖዋን አንድ ነገር ለመንኩት፤ምኞቴም ይኸው ነው፦በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት እኖር ዘንድ፣+ይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን በትኩረት እመለከት ዘንድ፣ቤተ መቅደሱንም በአድናቆት አይ* ዘንድ ነው።+ + 5 በመዓት ቀን በመጠለያው ይሸሽገኛል፤+ሚስጥራዊ ቦታ በሆነው ድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛል፤+ከፍ ባለ ዓለት ላይ ያስቀምጠኛል።+ + 6 በመሆኑም ራሴ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ በላይ ከፍ ብሏል፤በድንኳኑ ውስጥ በእልልታ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። + 7 ይሖዋ ሆይ፣ በምጮኽበት ጊዜ ስማኝ፤+ሞገስ አሳየኝ፤ መልስም ስጠኝ።+ + 8 ልቤ በአንተ ቦታ ሆኖ ሲናገር “ፊቴን ፈልጉ” ብሏል። ይሖዋ ሆይ፣ ፊትህን እሻለሁ።+ + 9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+ አገልጋይህን ተቆጥተህ ፊት አትንሳው። አንተ ረዳቴ ነህ፤+አዳኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም። +10 የገዛ አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ+ይሖዋ ራሱ ይቀበለኛል።+ +11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ፤+ከጠላቶቼ ጥበቃ እንዳገኝ ቀና በሆነ መንገድ ምራኝ። +12 ለጠላቶቼ* አሳልፈህ አትስጠኝ፤+ሐሰተኛ ምሥክሮች በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤+ደግሞም እኔን ለማጥቃት ይዝቱብኛል። +13 በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝ ኖሮምን ይውጠኝ ነበር!*+ +14 ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤+ደፋር ሁን፤ ልብህም ይጽና።+ አዎ፣ ይሖዋን ተስፋ አድርግ። +105 ይሖዋን አመስግኑ፤+ ስሙን ጥሩ፤ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+ + 2 ለእሱ ዘምሩ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩለት፤አስደናቂ በሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ላይ አሰላስሉ።*+ + 3 በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ።+ ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።+ + 4 ይሖዋንና ብርታቱን ፈልጉ።+ ፊቱን ሁልጊዜ እሹ። + 5 ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣ተአምራቱንና ��ተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤+ + 6 እናንተ የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች፣+እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣+ ይህን አስታውሱ። + 7 እሱ ይሖዋ አምላካችን ነው።+ ፍርዱ በመላው ምድር ላይ ነው።+ + 8 ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፣የገባውን ቃል* እስከ ሺህ ትውልድ ያስታውሳል፤+ + 9 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣+ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አይረሳም፤+ +10 ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤ +11 “የከነአንን ምድርርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ” አለ።+ +12 ይህን የተናገረው በቁጥር ጥቂት፣አዎ፣ በጣም ጥቂት በነበሩ ጊዜ ነው፤+ በምድሪቱም ላይ የባዕድ አገር ሰዎች ነበሩ።+ +13 እነሱም ከአንዱ ብሔር ወደ ሌላው ብሔር፣ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ሕዝብ ተንከራተቱ።+ +14 ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቀደም፤+ይልቁንም ለእነሱ ሲል ነገሥታትን ገሠጸ፤+ +15 “የቀባኋቸውን አገልጋዮቼን አትንኩ፤በነቢያቴም ላይ አንዳች ክፉ ነገር አታድርጉ” አላቸው።+ +16 በምድሪቱ ላይ ረሃብን ጠራ፤+የምግብ አቅርቦታቸው እንዲቋረጥ አደረገ።* +17 ባሪያ እንዲሆን የተሸጠውን ሰው፣ ዮሴፍንከእነሱ አስቀድሞ ላከው።+ +18 እግሮቹን በእግር ብረት አሰሩ፤*+አንገቱም ብረት ውስጥ ገባ፤* +19 የይሖዋ ቃል አጠራው፤ይህም የሆነው የተናገረው ቃል እስኪፈጸም ድረስ ነው።+ +20 ንጉሡ ልኮ አስፈታው፤+የሕዝቦቹም ገዢ ነፃ አወጣው። +21 የቤቱ ጌታ አድርጎ ሾመው፤የንብረቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፤+ +22 ይህም ደስ ባሰኘው* መንገድ በመኳንንቱ ላይ እንዲሠለጥን፣*ሽማግሌዎቹንም ጥበብ እንዲያስተምር ነው።+ +23 ከዚያም እስራኤል ወደ ግብፅ መጣ፤+ያዕቆብም በካም ምድር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ ኖረ። +24 አምላክ ሕዝቡ እየተባዛ እንዲሄድ አደረገ፤+ከጠላቶቻቸው ይበልጥ ኃያላን አደረጋቸው፤+ +25 ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ፣በአገልጋዮቹም ላይ ያሴሩ ዘንድ የጠላቶቻቸው ልብ እንዲለወጥ ፈቀደ።+ +26 አገልጋዩን ሙሴን፣+የመረጠውንም አሮንን ላከ።+ +27 እነሱም ምልክቶቹን በመካከላቸው፣ተአምራቱን በካም ምድር አደረጉ።+ +28 ጨለማን ላከ፤ ምድሪቱም ጨለመች፤+እነሱ በቃሉ ላይ አላመፁም። +29 ውኃዎቻቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ዓሣዎቻቸውንም ገደለ።+ +30 ምድራቸው፣ የነገሥታታቸውም እልፍኞች እንኳ* ሳይቀሩበእንቁራሪቶች ተጥለቀለቁ።+ +31 ተናካሽ ዝንቦች እንዲወሯቸው፣ትንኞችም በግዛቶቻቸው ሁሉ እንዲርመሰመሱ አዘዘ።+ +32 በዝናባቸው ፋንታ በረዶ አወረደባቸው፤በምድራቸውም ላይ መብረቅ* ላከ።+ +33 ወይናቸውንና የበለስ ዛፋቸውን መታ፤በግዛታቸው ውስጥ ያሉትንም ዛፎች አወደመ። +34 አንበጦች፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኩብኩባዎችምእንዲወሯቸው አዘዘ።+ +35 እነሱ በአገሪቱ የሚገኘውን አትክልት ሁሉ በሉ፤የምድሪቱንም ምርት ፈጁ። +36 ከዚያም በአገራቸው ያሉትን በኩራት ሁሉ፣የፍሬያቸው* መጀመሪያ የሆኑትን መታ።+ +37 ሕዝቡ ብርና ወርቅ ይዞ እንዲወጣ አደረገ፤+ከነገዶቹም መካከል የተሰናከለ አልነበረም። +38 በወጡ ጊዜ ግብፅ ሐሴት አደረገ፤እስራኤላውያንን* እጅግ ፈርተዋቸው ነበርና።+ +39 እነሱን ለመሸፈን ደመናን ዘረጋ፤+ በሌሊትም ብርሃን እንዲሰጥ እሳትን ላከ።+ +40 ሥጋ እንዲሰጣቸው በጠየቁት ጊዜ ድርጭት ላከላቸው፤+ከሰማይም ምግብ እያወረደ ያጠግባቸው ነበር።+ +41 ዓለትን ሰነጠቀ፤ ውኃም ተንዶለዶለ፤+በበረሃ እንደ ወንዝ ፈሰሰ።+ +42 ለአገልጋዩ ለአብርሃም የገባውን ቅዱስ ቃል አስታውሷልና።+ +43 ስለዚህ ሕዝቡን በታላቅ ደስታ፣የተመረጡ አገልጋዮቹንም በእልልታ አወጣቸው።+ +44 የሌሎችን ብሔራት ምድር ሰጣቸው፤+እነሱም ሌሎች ሕዝቦች ለፍተው ያፈሩትን ወረሱ፤+ +45 ይህን ያደ���ገው ድንጋጌዎቹን እንዲጠብቁ፣+ሕጎቹንም እንዲያከብሩ ነው። ያህን አወድሱ!* +47 እናንተ ሕዝቦች ሁሉ፣ እጆቻችሁን አጨብጭቡ። በድል አድራጊነት ለአምላክ እልል በሉ። + 2 ልዑሉ ይሖዋ እጅግ የሚያስፈራ ነውና፤+በመላው ምድር ላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።+ + 3 ሕዝቦችን ለእኛ ያስገዛል፤ብሔራትም ከእግራችን በታች እንዲሆኑ ያደርጋል።+ + 4 የሚወደውን የያዕቆብን+ መመኪያርስታችን አድርጎ ይመርጥልናል።+ (ሴላ) + 5 አምላክ በእልልታ አረገ፤ይሖዋ በቀንደ መለከት* ድምፅ ወደ ላይ ወጣ። + 6 ለአምላክ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። ለንጉሣችን የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። + 7 አምላክ የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤+የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ ማስተዋልም ይኑራችሁ። + 8 አምላክ በብሔራት ላይ ነግሦአል።+ በቅዱስ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል። + 9 የሕዝቡ መሪዎች ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋርአንድ ላይ ተሰብስበዋል። የምድር ገዢዎች* የአምላክ ናቸውና። እሱ እጅግ ከፍ ከፍ ብሏል።+ +127 ይሖዋ ቤትን ካልገነባ፣ግንበኞቹ የሚደክሙት በከንቱ ነው።+ ይሖዋ ከተማን ካልጠበቀ፣+ጠባቂው ንቁ ሆኖ መጠበቁ ከንቱ ድካም ነው። + 2 በማለዳ መነሳታችሁ፣እስከ ምሽት ድረስ መሥራታችሁ፣እንዲሁም የዕለት ጉርሳችሁን ለማግኘት መልፋታችሁ ከንቱ ነው፤ምክንያቱም አምላክ የሚወዳቸውን ሰዎች ይንከባከባቸዋል፤ እንቅልፍም ይሰጣቸዋል።+ + 3 እነሆ፣ ልጆች* ከይሖዋ የተገኙ ውርሻ ናቸው፤+የማህፀንም ፍሬ ከእሱ የሚገኝ ስጦታ ነው።+ + 4 አንድ ሰው በወጣትነቱ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች፣በኃያል ሰው እጅ እንዳሉ ፍላጻዎች ናቸው።+ + 5 ኮሮጆውን በእነዚህ የሞላ ሰው ደስተኛ ነው።+ እነሱ ፈጽሞ አያፍሩም፤በከተማዋ በር ከጠላቶቻቸው ጋር ይነጋገራሉና። +106 ያህን አወድሱ!* ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ + 2 የይሖዋን ታላላቅ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ሊያስታውቅ የሚችለው ማን ነው?ወይስ የሚያስመሰግኑ ተግባሮቹን ሁሉ ሊያውጅ የሚችለው ማን ነው?+ + 3 ፍትሐዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ምንጊዜም ትክክል የሆነውን የሚያደርጉ+ ደስተኞች ናቸው። + 4 ይሖዋ ሆይ፣ ለሕዝብህ ሞገስ* በምታሳይበት ጊዜ እኔንም አስታውሰኝ።+ ተንከባከበኝ፤ ደግሞም አድነኝ፤ + 5 ይህም ለተመረጡ አገልጋዮችህ+ የምታሳየውን ጥሩነት እንድቀምስ፣ከሕዝብህ ጋር ሐሴት እንዳደርግ፣ከርስትህም ጋር አንተን በኩራት እንዳወድስ* ነው። + 6 እኛም እንደ አባቶቻችን ኃጢአት ሠርተናል፤+በድለናል፤ ክፉ ነገርም አድርገናል።+ + 7 አባቶቻችን በግብፅ በነበሩበት ጊዜ፣ ድንቅ ሥራዎችህን በአድናቆት አልተመለከቱም።* የታማኝ ፍቅርህን ብዛት አላስታወሱም፤ከዚህ ይልቅ በባሕሩ አጠገብ ይኸውም ቀይ ባሕር አጠገብ ዓመፁ።+ + 8 ይሁንና ኃያልነቱ እንዲታወቅ ሲል፣+ለስሙ ብሎ አዳናቸው።+ + 9 ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ ባሕሩም ደረቀ፤በበረሃ* የሚሄዱ ያህል በጥልቅ ውኃው መካከል መራቸው፤+ +10 ከባላጋራዎቻቸው እጅ አዳናቸው፤+ከጠላቶቻቸውም እጅ ታደጋቸው።+ +11 ውኃው ጠላቶቻቸውን ዋጠ፤ከእነሱ አንድ ሰው እንኳ አልዳነም።+ +12 በዚያን ጊዜ በገባው ቃል አመኑ፤+የውዳሴ መዝሙር ይዘምሩለት ጀመር።+ +13 ይሁን እንጂ ያደረገውን ነገር ወዲያውኑ ረሱ፤+እሱ የሚሰጣቸውን ምክር በትዕግሥት አልጠበቁም። +14 በምድረ በዳ በራስ ወዳድነት ምኞት ተሸነፉ፤+በበረሃ አምላክን ተፈታተኑት።+ +15 እሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ነገር ግን በሚያመነምን* በሽታ መታቸው።+ +16 በሰፈር ውስጥ በሙሴ፣ደግሞም የይሖዋ ቅዱስ አገልጋይ+ በሆነው በአሮን ቀኑ።+ +17 በዚህ ጊዜ ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ከአቤሮንም ጋር ያበሩትን ���ለቀጠች።+ +18 እሳትም በማኅበራቸው መካከል ነደደች፤ነበልባልም ክፉዎችን በላች።+ +19 በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ከብረት ለተሠራም ሐውልት* ሰገዱ፤+ +20 ሣር በሚበላ ኮርማ ምስልክብሬን ለወጡ።+ +21 በግብፅ ታላላቅ ነገሮች ያደረገውን፣+አዳኛቸው የሆነውን አምላክ ረሱ፤+ +22 በካም ምድር አስደናቂ ሥራዎች፣+በቀይ ባሕር የሚያስፈሩ* ነገሮች ያከናወነውን+ አምላክ ዘነጉ። +23 እንዲጠፉ ሊያዝዝ ምንም አልቀረውም ነበር፤ሆኖም እሱ የመረጠው አገልጋዩ ሙሴ፣አጥፊ ቁጣውን እንዲመልስ አምላክን ተማጸነ።*+ +24 ከዚያም የተወደደችውን ምድር ናቁ፤+በገባው ቃል ላይ እምነት አልነበራቸውም።+ +25 በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ማጉረምረማቸውን ቀጠሉ፤+የይሖዋን ድምፅ አልሰሙም።+ +26 በመሆኑም በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣ስለ እነሱ እጁን አንስቶ ማለ፤+ +27 ዘራቸውን በብሔራት መካከል እንደሚጥል፣በየአገሩ እንደሚበትናቸውም ማለ።+ +28 ከዚያም በፌጎር የነበረውን ባአል አመለኩ፤*+ለሙታን የቀረቡትን መሥዋዕቶችም* በሉ። +29 በሥራቸው አምላክን አስቆጡት፤+በመካከላቸውም መቅሰፍት ተነሳ።+ +30 ሆኖም ፊንሃስ ተነስቶ እርምጃ በወሰደ ጊዜ፣መቅሰፍቱ ተገታ።+ +31 ይህም በትውልዶች ሁሉ፣ ለዘላለምጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።+ +32 በመሪባ* ውኃ አጠገብ አምላክን አስቆጡት፤በእነሱም የተነሳ ሙሴ ችግር ላይ ወደቀ።+ +33 መንፈሱን አስመረሩት፤እሱም በከንፈሮቹ በችኮላ ተናገረ።+ +34 ይሖዋ ባዘዛቸው መሠረት፣+ሕዝቦቹን ከማጥፋት ወደኋላ አሉ።+ +35 ይልቁንም በዚያ ከነበሩት ብሔራት ጋር ተቀላቀሉ፤+የእነሱንም መንገድ ተከተሉ።*+ +36 ጣዖቶቻቸውን አመለኩ፤+እነሱም ወጥመድ ሆኑባቸው።+ +37 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንለአጋንንት መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡ ነበር።+ +38 ንጹሕ ደም፣ይኸውም ለከነአን ጣዖቶች የሠዉአቸውን+የገዛ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ደም አፈሰሱ፤+ምድሪቱም በደም ተበከለች። +39 በሥራቸው ረከሱ፤በድርጊታቸውም መንፈሳዊ ምንዝር ፈጸሙ።+ +40 በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ርስቱንም ተጸየፈ። +41 በተደጋጋሚ ጊዜያት በብሔራት እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤+ይህም የሚጠሏቸው ሰዎች እንዲገዟቸው ነው።+ +42 ጠላቶቻቸው ጨቆኗቸው፤ለእነሱም ሥልጣን* ተገዢ ሆኑ። +43 ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤+እነሱ ግን ያምፁና ለመታዘዝ አሻፈረኝ ይሉ ነበር፤+ከሠሩት ጥፋት የተነሳም ተዋረዱ።+ +44 እሱ ግን ጭንቀታቸውን ይመለከት፣+እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማ ነበር።+ +45 ለእነሱ ሲል ቃል ኪዳኑን ያስታውስ ነበር፤ታላቅ በሆነው* ታማኝ ፍቅሩ ተገፋፍቶ ያዝንላቸው* ነበር።+ +46 የማረኳቸው ሰዎች ሁሉበሐዘኔታ እንዲይዟቸው ያደርግ ነበር።+ +47 ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ አድነን፤+ደግሞም ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣አንተንም በማወደስ ሐሴት እንድናደርግ፣*+ከብሔራት ሰብስበን።+ +48 የእስራኤል አምላክ ይሖዋከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ፤+ ሕዝቦችም ሁሉ “አሜን!”* ይበሉ። ያህን አወድሱ!* +69 አምላክ ሆይ፣ ውኃ ሕይወቴን አደጋ ላይ ስለጣላት* አድነኝ።+ + 2 መቆሚያ ስፍራ በሌለበት ጥልቅ ማጥ ውስጥ ሰምጫለሁ።+ ጥልቅ ውኃዎች ውስጥ ገባሁ፤ኃይለኛ ጅረትም ጠርጎ ወሰደኝ።+ + 3 ከመጮኼ ብዛት የተነሳ ደከምኩ፤+ድምፄም ጎረነነ። አምላኬን በመጠባበቅ ዓይኖቼ ፈዘዙ።+ + 4 ያለምክንያት የሚጠሉኝ+ከራሴ ፀጉር ይልቅ በዙ። ሊያጠፉኝ የሚፈልጉ፣ተንኮለኛ የሆኑ ጠላቶቼ እጅግ በዝተዋል። ያልሰረቅኩትን ነገር እንድመልስ ተገደድኩ። + 5 አምላክ ሆይ፣ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤ጥፋቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም። + 6 ሉዓላዊ ጌታ የሆንከው የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣አንተን ተስፋ የሚያደርጉ ��እኔ የተነሳ አይፈሩ። የእስራኤል አምላክ ሆይ፣አንተን የሚሹ በእኔ የተነሳ አይዋረዱ። + 7 በአንተ የተነሳ ነቀፋ ይደርስብኛል፤+ኀፍረት ፊቴን ይሸፍነዋል።+ + 8 ለወንድሞቼ እንደ እንግዳ፣ለእናቴ ልጆች እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆንኩ።+ + 9 ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት በልቶኛል፤+ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋም በእኔ ላይ ደረሰ።+ +10 በጾም ራሴን* ባዋረድኩ ጊዜ፣*ነቀፋ ደረሰብኝ። +11 ማቅ በለበስኩ ጊዜ፣መቀለጃ* አደረጉኝ። +12 በከተማዋ መግቢያ የሚቀመጡት የመወያያ ርዕስ አደረጉኝ፤ሰካራሞችም ስለ እኔ ይዘፍናሉ። +13 ይሁንና ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴ ተሰሚነት ሊያገኝ በሚችልበት ጊዜወደ አንተ ይድረስ።+ አምላክ ሆይ፣ በታማኝ ፍቅርህ ብዛት፣አስተማማኝ በሆነው የማዳን ሥራህም መልስልኝ።+ +14 ከማጡ አውጣኝ፤እንድሰምጥ አትፍቀድ። ከሚጠሉኝ ሰዎችናከጥልቁ ውኃ ታደገኝ።+ +15 ደራሽ ውኃ ጠርጎ እንዲወስደኝ አትፍቀድ፤+ጥልቁም አይዋጠኝ፤የጉድጓዱም አፍ በእኔ ላይ አይዘጋ።+ +16 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ መልስልኝ።+ እንደ ምሕረትህ ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፤+ +17 ፊትህንም ከአገልጋይህ አትሰውር።+ ጭንቅ ውስጥ ነኝና በፍጥነት መልስልኝ።+ +18 ወደ እኔ ቀርበህ ታደገኝ፤*ከጠላቶቼ የተነሳ ዋጀኝ። +19 የደረሰብኝን ነቀፋ፣ ኀፍረትና ውርደት ታውቃለህ።+ ጠላቶቼን በሙሉ ታያለህ። +20 የተሰነዘረብኝ ነቀፋ ልቤን ሰብሮታል፤ ቁስሉም የሚድን ዓይነት አይደለም።* የሚያዝንልኝ ሰው ለማግኘት ተመኝቼ ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አልነበረም፤+የሚያጽናናኝ ሰውም ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አላገኘሁም።+ +21 ይልቁንም መርዝ* እንድበላ ሰጡኝ፤+በጠማኝ ጊዜም ኮምጣጤ እንድጠጣ ሰጡኝ።+ +22 ማዕዳቸው ወጥመድ፣ብልጽግናቸውም አሽክላ* ይሁንባቸው።+ +23 ዓይኖቻቸው ማየት እንዳይችሉ ይጨልሙ፤ሰውነታቸውም* ምንጊዜም እንዲንቀጠቀጥ አድርግ። +24 ቁጣህን አውርድባቸው፤የሚነደው ቁጣህም ድንገት ይምጣባቸው።+ +25 ሰፈራቸው* ወና ይሁን፤በድንኳኖቻቸው የሚኖር ሰው አይገኝ።+ +26 አንተ የመታኸውን አሳደዋልና፤ደግሞም አንተ ያቆሰልካቸውን ሰዎች ሥቃይ ሁልጊዜ ያወራሉ። +27 በበደላቸው ላይ በደል ጨምርባቸው፤ከአንተም ጽድቅ ምንም ድርሻ አይኑራቸው። +28 ከሕያዋን መጽሐፍ* ይደምሰሱ፤+በጻድቃንም መካከል አይመዝገቡ።+ +29 እኔ ግን በጭንቅና በሥቃይ ላይ ነኝ።+ አምላክ ሆይ፣ የማዳን ኃይልህ ይጠብቀኝ። +30 ለአምላክ ስም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤እሱንም በምስጋና ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። +31 ይህ ከበሬ ይበልጥ ይሖዋን ያስደስተዋል፤ቀንድና ሰኮና ካለው ወይፈን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል።+ +32 የዋሆች ይህን ያያሉ፤ ሐሴትም ያደርጋሉ። እናንተ አምላክን የምትፈልጉ፣ ልባችሁ ይነቃቃ። +33 ይሖዋ ድሆችን ይሰማልና፤+በምርኮ ላይ ያለውን ሕዝቡንም አይንቅም።+ +34 ሰማይና ምድር፣ባሕርና በውስጡ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያወድሱት።+ +35 አምላክ ጽዮንን ያድናታልና፤+የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይገነባል፤እነሱም በዚያ ይኖራሉ፤ ደግሞም ይወርሷታል።* +36 የአገልጋዮቹ ዘሮች ይወርሷታል፤+ስሙን የሚወዱም+ በእሷ ላይ ይኖራሉ። +89 የይሖዋ ታማኝ ፍቅር ስለተገለጠባቸው መንገዶች ለዘላለም እዘምራለሁ። ታማኝነትህን ለትውልዶች በሙሉ በአፌ አስታውቃለሁ። + 2 እንዲህ በማለት ተናግሬአለሁና፦ “ታማኝ ፍቅር ለዘላለም ይገነባል፤*+ታማኝነትህንም በሰማያት አጽንተህ መሥርተሃል።” + 3 አንተም እንዲህ ብለሃል፦ “ከመረጥኩት ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፤+ለአገልጋዬ ለዳዊት ምያለሁ፦+ + 4 ‘ዘርህ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ፤+ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’”+ (ሴላ) + 5 ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣አዎ፣ በቅዱሳን ጉባኤ ታማኝነትህን ያወድሳሉ። + 6 በሰማያት ከይሖዋ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል?+ ከአምላክ ልጆች*+ መካከል እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው? + 7 አምላክ በቅዱሳን ጉባኤ መካከል እጅግ የተፈራ ነው፤+በዙሪያው ባሉት ሁሉ መካከል ታላቅና እጅግ የሚከበር ነው።+ + 8 የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ኃያል ነህ፤ያህ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ አንተ በሁሉም ነገር ታማኝ መሆንህን ታሳያለህ።+ + 9 የባሕሩን ሞገድ ትቆጣጠራለህ፤+ማዕበሉም ሲነሳ አንተ ራስህ ጸጥ ታሰኘዋለህ።+ +10 አንተ ረዓብን*+ እንደተገደለ ሰው አደቀቅከው።+ በብርቱ ክንድህ ጠላቶችህን በታተንካቸው።+ +11 ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤+ፍሬያማ የሆነችውን ምድርና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ የሠራኸው አንተ ነህ።+ +12 ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርክ አንተ ነህ፤ታቦርና+ ሄርሞን+ ስምህን በደስታ ያወድሳሉ። +13 ክንድህ ኃያል ነው፤+እጅህ ብርቱ ነው፤+ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለ ነው።+ +14 ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረት ናቸው፤+ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት በፊትህ ናቸው።+ +15 እልልታ የሚያውቁ ሰዎች ደስተኞች ናቸው።+ ይሖዋ ሆይ፣ እንዲህ ያሉ ሰዎች በፊትህ ብርሃን ይመላለሳሉ። +16 በስምህ ቀኑን ሙሉ ሐሴት ያደርጋሉ፤በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ። +17 አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤+በሞገስህም ብርታታችን* ከፍ ከፍ ብሏል።+ +18 ጋሻችን ከይሖዋ ነውና፤ንጉሣችን ከእስራኤል ቅዱስ ነው።+ +19 በዚያን ጊዜ ለታማኝ አገልጋዮችህ በራእይ ተናገርክ፤ እንዲህም አልክ፦ “ለኃያል ሰው ብርታት ሰጠሁ፤+ከሕዝቡም መካከል የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግኩ።+ +20 አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤+በተቀደሰ ዘይቴም ቀባሁት።+ +21 እጄ ይደግፈዋል፤+ክንዴም ያበረታዋል። +22 ማንኛውም ጠላት አያስገብረውም፤የትኛውም ክፉ ሰው አይጨቁነውም።+ +23 ባላጋራዎቹን ከፊቱ አደቃቸዋለሁ፤+የሚጠሉትንም እመታቸዋለሁ።+ +24 ታማኝነቴና ታማኝ ፍቅሬ ከእሱ ጋር ናቸው፤+በስሜም ኃይሉ* ከፍ ከፍ ይላል። +25 እጁን* በባሕሩ ላይ፣ቀኝ እጁንም በወንዞቹ ላይ አደርጋለሁ።+ +26 እሱም ‘አንተ አባቴ ነህ፤አምላኬና አዳኝ ዓለቴ ነህ’+ ብሎ ይጠራኛል። +27 እኔም በኩር እንዲሆን አደርገዋለሁ፤+ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ አስቀምጠዋለሁ።+ +28 ታማኝ ፍቅሬን ለዘላለም አሳየዋለሁ፤+ከእሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።+ +29 ዘሩን ለዘላለም አጸናለሁ፤ዙፋኑም የሰማያትን ዕድሜ ያህል ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ።+ +30 ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣ድንጋጌዎቼንም* አክብረው ባይመላለሱ፣ +31 ደንቦቼን ቢጥሱናትእዛዛቴን ባይጠብቁ፣ +32 ባለመታዘዛቸው* በበትር እቀጣቸዋለሁ፤+በደል በመፈጸማቸውም እገርፋቸዋለሁ። +33 ሆኖም ለእሱ ታማኝ ፍቅር ማሳየቴን አልተውም፤+የገባሁትንም ቃል አላጥፍም።* +34 ቃል ኪዳኔን አላፈርስም፤+ከአንደበቴ የወጣውንም ቃል አለውጥም።+ +35 ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁ፤ዳዊትን አልዋሸውም።+ +36 ዘሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤+ዙፋኑ በፊቴ እንዳለችው ፀሐይ ይጸናል።+ +37 በሰማያት ታማኝ ምሥክር ሆና እንደምትኖረው እንደ ጨረቃ፣ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” (ሴላ) +38 ሆኖም አንተ ራስህ ጣልከው፤ ደግሞም ገሸሽ አደረግከው፤+በተቀባው አገልጋይህ ላይ እጅግ ተቆጣህ። +39 ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ወደ ጎን ገሸሽ አደረግክ፤አክሊሉን* መሬት ላይ በመጣል አረከስከው። +40 በድንጋይ የተገነቡትን ቅጥሮቹን* ሁሉ አፈረስክ፤ምሽጎቹን የፍርስራሽ ክምር አደረግክ። +41 በዚያ የሚያልፉ ሁሉ ዘረፉት፤የጎረቤቶቹም መሳለቂያ ሆነ።+ +42 ባላጋራዎቹ ድል እንዲጎናጸፉ አድርገሃል፤*+ጠላቶቹ ሁሉ ደስ እንዲላቸው አደረግክ። +43 በተጨማሪም ሰይፉን መልሰህበታል፤በጦርነትም እንዲሸነፍ አደረግክ። +44 ግርማ ሞገሱ እንዲጠፋ አደረግክ፤ዙፋኑንም መሬት ላይ ጣልከው። +45 የወጣትነት ዕድሜውን አሳጠርክበት፤ኀፍረትም አከናነብከው። (ሴላ) +46 ይሖዋ ሆይ፣ ራስህን የምትሰውረው እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?+ ቁጣህስ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራል? +47 ዕድሜዬ ምን ያህል አጭር እንደሆነ አስብ!+ ሰዎችን ሁሉ የፈጠርከው እንዲያው ለከንቱ ነው? +48 ሞትን ጨርሶ ሳያይ በሕይወት ሊኖር የሚችል ሰው ማን ነው?+ ራሱን* ከመቃብር* እጅ ማዳን ይችላል? (ሴላ) +49 ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትህ ለዳዊት የማልክለት፣በቀደሙት ዘመናት ያሳየኸው ታማኝ ፍቅር የት አለ?*+ +50 ይሖዋ ሆይ፣ በአገልጋዮችህ ላይ የተሰነዘረውን ዘለፋ አስታውስ፤ሰዎች ሁሉ የሰነዘሩብኝን ዘለፋ እንዴት እንደተሸከምኩ* አስብ፤ +51 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህ ምን ያህል እንደተሳደቡ አስታውስ፤የቀባኸውን ሰው እርምጃ ሁሉ እንዴት እንደነቀፉ አስብ። +52 ይሖዋ ለዘላለም ይወደስ። አሜን፣ አሜን።+ +103 ይሖዋን ላወድስ፤*ሁለንተናዬ ቅዱስ ስሙን ያወድስ። + 2 ይሖዋን ላወድስ፤*ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ፈጽሞ አልርሳ።+ + 3 እሱ በደልሽን ሁሉ ይቅር ይላል፤+ሕመምሽንም ሁሉ ይፈውሳል፤+ + 4 ሕይወትሽን ከጉድጓድ* ያወጣል፤+ታማኝ ፍቅሩንና ምሕረቱን ያጎናጽፍሻል፤+ + 5 የወጣትነት ዕድሜሽ እንደ ንስር እንዲታደስ፣+በሕይወት ዘመንሽ ሁሉ መልካም ነገሮች ያጠግብሻል።+ + 6 ይሖዋ ለተጨቆኑ ሁሉበጽድቅና በፍትሕ እርምጃ ይወስዳል።+ + 7 መንገዶቹን ለሙሴ፣ያከናወናቸውንም ነገሮች ለእስራኤል ልጆች አሳወቀ።+ + 8 ይሖዋ መሐሪና ሩኅሩኅ፣*+ለቁጣ የዘገየ እንዲሁም ታማኝ ፍቅሩ* የበዛ ነው።+ + 9 እሱ ሁልጊዜ ስህተት አይፈላልግም፤+ለዘላለምም ቂም አይዝም።+ +10 እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፤+ለበደላችን የሚገባውንም ብድራት አልከፈለንም።+ +11 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣እሱ ለሚፈሩት የሚያሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና።+ +12 ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣በደላችንን ከእኛ አራቀ።+ +13 አባት ለልጆቹ ምሕረት እንደሚያሳይ፣ይሖዋም ለሚፈሩት ምሕረት አሳይቷል።+ +14 እሱ እንዴት እንደተሠራን በሚገባ ያውቃልና፤+አፈር መሆናችንን ያስታውሳል።+ +15 ሟች የሆነ የሰው ልጅ የሕይወት ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤+እንደ ሜዳ አበባ ያብባል።+ +16 ይሁንና ነፋስ ሲነፍስበት ደብዛው ይጠፋል፤በዚያ ስፍራ ያልነበረ ያህል ይሆናል።* +17 ይሖዋ ግን እሱን ለሚፈሩትታማኝ ፍቅሩን ከዘላለም እስከ ዘላለም ያሳያል፤+ጽድቁንም ለልጅ ልጆቻቸው ይገልጣል፤+ +18 ይህን የሚያደርገው ቃል ኪዳኑን ለሚጠብቁ፣+መመሪያዎቹን ለመፈጸም ለሚተጉ ነው። +19 ይሖዋ ዙፋኑን በሰማያት አጽንቶ መሥርቷል፤+በሁሉም ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።+ +20 ትእዛዛቱን በማክበር ቃሉን የምትፈጽሙ፣*+እናንተ ብርቱዎችና ኃያላን መላእክቱ ሁሉ፣+ ይሖዋን አወድሱ። +21 ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፣+ሠራዊቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ።+ +22 በግዛቱ* ሁሉ ያላችሁ፣ፍጥረታቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ። ሁለንተናዬ ይሖዋን ያወድስ።* +101 ስለ ታማኝ ፍቅርና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ ለአንተ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። + 2 በማስተዋልና ነቀፋ በሌለበት መንገድ* እመላለሳለሁ። ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? በቤቴ ውስጥ በንጹሕ ልብ* እመላለሳለሁ።+ + 3 በዓይኖቼ ፊት የማይረባ* ነገር አላኖርም። ከትክክለኛው መንገድ የሚወጡ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች እጠላለሁ፤+ከእነሱ ጋር የሚያገናኘኝ ምንም ጉዳይ የለም���* + 4 ጠማማ ልብ ከእኔ የራቀ ነው፤ምንም ዓይነት ክፉ ነገር አልቀበልም።* + 5 የባልንጀራውን ስም በስውር የሚያጠፋን ሰው፣+ጸጥ አሰኘዋለሁ።* ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብ ያለውን ሰው፣አልታገሠውም። + 6 ከእኔ ጋር እንዲኖሩበምድሪቱ ወዳሉ ታማኞች እመለከታለሁ። ነቀፋ በሌለበት መንገድ* የሚመላለስ ሰው እኔን ያገለግለኛል። + 7 አታላይ የሆነ ሰው በቤቴ አይኖርም፤ውሸት የሚናገር ሰው በፊቴ* አይቆምም። + 8 በምድሪቱ ላይ የሚገኙትን ክፉ ሰዎች ሁሉ በየማለዳው ጸጥ አሰኛለሁ፤*ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ከይሖዋ ከተማ አስወግዳለሁ።+ +87 የአምላክ ከተማ የተመሠረተችው በተቀደሱት ተራሮች ላይ ነው።+ + 2 ይሖዋ ከያዕቆብ ድንኳኖች ሁሉ ይበልጥየጽዮንን በሮች ይወዳል።+ + 3 የእውነተኛው አምላክ ከተማ ሆይ፣ ስለ አንቺ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች እየተነገሩ ነው።+ (ሴላ) + 4 እኔን ከሚያውቁኝ* መካከል ረዓብንና*+ ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤ኢትዮጵያን* ጨምሮ ፍልስጤምና ጢሮስም ይገኙበታል። እንዲህም ይባላል፦ “ይህ በዚያ የተወለደ ነው።” + 5 ስለ ጽዮን ደግሞ እንዲህ ይባላል፦ “ይሄኛውም ሆነ ያኛው የተወለደው በእሷ ውስጥ ነው።” ልዑሉ አምላክም አጽንቶ ይመሠርታታል። + 6 ይሖዋ ሕዝቡን ሲመዘግብ “ይህ በዚያ የተወለደ ነው” ብሎ ያስታውቃል። (ሴላ) + 7 ዘማሪዎችና+ ጨፋሪዎች*+ “ምንጮቼ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛሉ”*+ ይላሉ። +73 አምላክ ለእስራኤል፣ ልባቸው ንጹሕ ለሆነ ሁሉ በእርግጥ ጥሩ ነው።+ + 2 እኔ ግን እግሮቼ ከመንገድ ሊወጡ ተቃርበው ነበር፤አዳልጦኝ ልወድቅ ምንም አልቀረኝም።+ + 3 ክፉ ሰዎች ያላቸውን ሰላም በተመለከትኩ ጊዜ፣እብሪተኛ በሆኑ ሰዎች* ቀንቼ ነበርና።+ + 4 ሳይሠቃዩ ይሞታሉና፤ሰውነታቸው ጤናማ* ነው።+ + 5 እንደ ሌሎች ሰዎች ችግር አያጋጥማቸውም፤+እንደ ሌሎች ሰዎችም መከራ አይደርስባቸውም።+ + 6 ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ጌጣቸው ነው፤+ዓመፅም እንደ ልብስ ይሸፍናቸዋል። + 7 ከብልጽግናቸው* የተነሳ ዓይናቸው ፈጧል፤ልባቸው ካሰበው በላይ አግኝተዋል። + 8 በሌሎች ላይ ያፌዛሉ፤ ክፉ ነገርም ይናገራሉ፤+ ሌሎችን ለመጨቆን በእብሪት ይዝታሉ።+ + 9 የሰማይን ያህል ከፍ ያሉ ይመስል በእብሪት ይናገራሉ፤በአንደበታቸው እንዳሻቸው እየተናገሩ በምድር ላይ ይንጎራደዳሉ። +10 በመሆኑም ሕዝቡ ወደ እነሱ ይሄዳል፤ከእነሱ የተትረፈረፈ ውኃም ይጠጣል። +11 እነሱም “አምላክ እንዴት ያውቃል?+ ልዑሉ አምላክ በእርግጥ እውቀት አለው?” ይላሉ። +12 አዎ፣ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ ሳይጨናነቁ ይኖራሉ።+ የሀብታቸውንም መጠን ያሳድጋሉ።+ +13 በእርግጥም ልቤን ያነጻሁት፣ንጹሕ መሆኔንም ለማሳየት እጄን የታጠብኩት በከንቱ ነው።+ +14 ቀኑን ሙሉም ተጨነቅኩ፤+በየማለዳውም ተቀጣሁ።+ +15 እነዚህን ነገሮች ተናግሬ ቢሆን ኖሮ፣ሕዝብህን* መክዳት ይሆንብኝ ነበር። +16 ይህን ለመረዳት በሞከርኩ ጊዜ፣የሚያስጨንቅ ሆነብኝ፤ +17 ይኸውም ወደ ታላቁ የአምላክ መቅደስ እስክገባናየወደፊት ዕጣቸውን እስክረዳ ድረስ ነበር። +18 በእርግጥም በሚያዳልጥ መሬት ላይ ታስቀምጣቸዋለህ።+ ለጥፋት እንዲዳረጉም ትጥላቸዋለህ።+ +19 እንዴት በቅጽበት ጠፉ!+ በአስደንጋጭ ሁኔታ ተደመሰሱ! የደረሰባቸው ጥፋት ቅጽበታዊ ነው! +20 ይሖዋ ሆይ፣ ሰው ከእንቅልፉ ሲነሳ እንደሚረሳው ሕልም፣አንተም በምትነሳበት ጊዜ ምስላቸውን ታስወግዳለህ።* +21 ሆኖም ልቤ ተመሯል፤+ውስጤንም* ውጋት ቀስፎ ይዞታል። +22 እኔም ማመዛዘን የማልችልና ማስተዋል የጎደለኝ ሆኜ ነበር፤በአንተ ፊት ማሰብ እንደማይችል እንስሳ ሆንኩ። +23 አሁን ግን ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነኝ፤አንተም ቀኝ እጄን ይዘሃል።+ +24 ��ምክርህ ትመራኛለህ፤+በኋላም ክብር ታጎናጽፈኛለህ።+ +25 በሰማይ ማን አለኝ? በምድርም ላይ ከአንተ ሌላ የምሻው የለም።+ +26 ሰውነቴም ሆነ ልቤ ሊዝል ይችላል፤አምላክ ግን ለዘላለም የልቤ ዓለትና ድርሻዬ ነው።+ +27 ከአንተ የሚርቁ በእርግጥ ይጠፋሉ። አንተን በመተው ብልሹ ምግባር የሚፈጽሙትን* ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ።*+ +28 እኔ ግን ወደ አምላክ መቅረብ ይበጀኛል።+ ሥራዎቹን ሁሉ እንዳውጅ+ሉዓላዊውን ጌታ ይሖዋን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ። +62 ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ።* መዳን የማገኘው ከእሱ ዘንድ ነው።+ + 2 በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤+ከልክ በላይ አልናወጥም።+ + 3 አንድን ሰው ለመግደል ጥቃት የምትሰነዝሩበት እስከ መቼ ነው?+ ሁላችሁም እንዳዘመመ ግንብ፣ ሊወድቅ እንደተቃረበም የድንጋይ ቅጥር አደገኛ ናችሁ።* + 4 ካለበት ከፍ ያለ ቦታ ሊጥሉት* እርስ በርሳቸው ይማከራሉና፤በመዋሸት ደስ ይሰኛሉ። በአፋቸው ይባርካሉ፤ በልባቸው ግን ይራገማሉ።+ (ሴላ) + 5 ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ፤*+ምክንያቱም ተስፋዬ የሚመጣው ከእሱ ዘንድ ነው።+ + 6 በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤በምንም ዓይነት አልናወጥም።+ + 7 የእኔ መዳንና ክብር የተመካው በአምላክ ላይ ነው። እሱ ጠንካራ ዓለቴና መጠጊያዬ ነው።+ + 8 ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእሱ ታመኑ። ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ።+ አምላክ መጠጊያችን ነው።+ (ሴላ) + 9 የሰው ልጆች እስትንፋስ ናቸው፤ሰዎች ከንቱ መመኪያ ናቸው።+ አንድ ላይ ሆነው በሚዛን ሲመዘኑ ከአየር እንኳ ይቀልላሉ።+ +10 በዝርፊያ አትታመኑ፤ወይም በስርቆት እጠቀማለሁ ብላችሁ በከንቱ ተስፋ አታድርጉ። ሀብታችሁ ቢበዛ ልባችሁን በእሱ ላይ አትጣሉ።+ +11 አምላክ አንድ ጊዜ ተናገረ፤ እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፦ ብርታት የአምላክ ነው።+ +12 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርም የአንተ ነው፤+ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍላለህና።+ +142 ድምፄን አውጥቼ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ እጣራለሁ፤+ሞገስ እንዲያሳየኝ ይሖዋን እማጸናለሁ። + 2 የሚያሳስበኝን ነገር በፊቱ አፈስሳለሁ፤የውስጤን ጭንቀት በፊቱ እናገራለሁ፤+ + 3 መንፈሴ* በውስጤ ሲዝል፣ እሱን እማጸናለሁ። በዚህ ጊዜ ጎዳናዬን ትመለከታለህ።+ በምሄድበት መንገድ ላይበስውር ወጥመድ ዘረጉብኝ። + 4 ቀኝ እጄን ተመልከት፤ስለ እኔ ግድ የሚሰጠው* ሰው እንደሌለ እይ።+ ሸሽቼ ማምለጥ የምችልበት ቦታ የለም፤+ስለ እኔ* የሚያስብ ማንም የለም። + 5 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጣራለሁ። ደግሞም “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤+በሕያዋን ምድር ያለኸኝ አንተ ብቻ* ነህ” እላለሁ። + 6 መንፈሴ እጅግ ተደቁሷልና፣እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ። ከእኔ ይልቅ ብርቱ ስለሆኑከሚያሳድዱኝ ሰዎች ታደገኝ።+ + 7 ስምህን አወድስ ዘንድከእስር ቤት አውጣኝ።* ደግነት ስለምታሳየኝጻድቃን በዙሪያዬ ይሰብሰቡ። +50 የአማልክት አምላክ የሆነው ይሖዋ+ ተናግሯል፤ከፀሐይ መውጫ አንስቶ እስከ መግቢያው* ድረስምድርን ይጠራል። + 2 በውበቷ ፍጹም ከሆነችው ከጽዮን፣+ አምላክ ያበራል። + 3 አምላካችን ይመጣል፤ ፈጽሞም ዝም ሊል አይችልም።+ በፊቱ የሚባላ እሳት አለ፤+በዙሪያውም ሁሉ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ይነፍሳል።+ + 4 በሕዝቡ ላይ ለመፍረድ፣+በላይ ያሉትን ሰማያትና ምድርን ይጠራል፤+ + 5 “በመሥዋዕት አማካኝነት ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን የሚያደርጉትን፣+ታማኝ አገልጋዮቼን ወደ እኔ ሰብስቡ” ይላል። + 6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤አምላክ ራሱ ፈራጅ ነውና።+ (ሴላ) + 7 “ሕዝቤ ሆይ፣ ስማ፤ እኔም እናገራለሁ፤እስራኤል ሆይ፣ በአንተ ላይ እመሠክር��ሃለሁ።+ እኔ አምላክ፣ አዎ አምላክህ ነኝ።+ + 8 በመሥዋዕቶችህም ሆነዘወትር በፊቴ ባሉት የሚቃጠሉ መባዎችህ የተነሳ አልወቅስህም።+ + 9 ከቤትህ ኮርማ፣ከጉረኖህም ፍየሎች* መውሰድ አያስፈልገኝም።+ +10 በጫካ ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳት ሁሉ፣በሺህ ተራሮች ላይ ያሉ አራዊትም እንኳ የእኔ ናቸውና።+ +11 በተራሮች ላይ የሚኖሩትን ወፎች ሁሉ አውቃለሁ፤+በመስክ ያሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እንስሳት የእኔ ናቸው። +12 ብራብ እንኳ ለአንተ አልነግርህም፤ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የእኔ ነውና።+ +13 የኮርማዎችን ሥጋ እበላለሁ?የፍየሎችንስ ደም እጠጣለሁ?+ +14 ምስጋናን ለአምላክ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤+ስእለትህንም ለልዑሉ አምላክ ስጥ፤+ +15 በጭንቅ ቀን ጥራኝ።+ እኔ እታደግሃለሁ፤ አንተም ታወድሰኛለህ።”+ +16 ክፉውን ግን አምላክ እንዲህ ይለዋል፦ “ስለ ሥርዓቴ ለማውራት፣ወይም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳኔ ለመናገር ምን መብት አለህ?+ +17 ተግሣጼን* ትጠላለህና፤ለቃሌም ጀርባህን ትሰጣለህ።*+ +18 ሌባ ስታይ ትደግፈዋለህ፤*+ከአመንዝሮችም ጋር ትወዳጃለህ። +19 አንደበትህን ክፉ ወሬ ለመንዛት ትጠቀምበታለህ፤ማታለያም ከምላስህ አይጠፋም።+ +20 ከሌሎች ጋር ተቀምጠህ ወንድምህን ታማለህ፤+የገዛ እናትህን ልጅ ድክመት ታወራለህ።* +21 እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስታደርግ፣ ዝም አልኩ፤በመሆኑም እንደ አንተ የምሆን መስሎህ ነበር። አሁን ግን እወቅስሃለሁ፤ከአንተ ጋር ያለኝንም ሙግት አሳውቃለሁ።+ +22 እናንተ አምላክን የምትረሱ፣ እባካችሁ ይህን ልብ በሉ፤+አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚታደጋችሁም አይኖርም። +23 ምስጋናን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤+ደግሞም ትክክለኛውን መንገድ በጥብቅ የሚከተልን ሰው፣የአምላክን ማዳን እንዲያይ አደርገዋለሁ።”+ +13 ይሖዋ ሆይ፣ የምትረሳኝ እስከ መቼ ነው? ለዘላለም? ፊትህን ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ነው?+ + 2 ልቤ በየዕለቱ በሐዘን እየተደቆሰ፣በጭንቀት ተውጬ የምኖረው* እስከ መቼ ነው? ጠላቴ በእኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ነው?+ + 3 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስም ስጠኝ። በሞት እንዳላንቀላፋ ዓይኖቼን አብራልኝ፤ + 4 እንዲህ ከሆነ ጠላቴ “አሸነፍኩት!” አይልም፤ ባላጋራዎቼ በእኔ ውድቀት ሐሴት እንዲያደርጉ አትፍቀድ።+ + 5 እኔ በበኩሌ በታማኝ ፍቅርህ እታመናለሁ፤+ልቤ በማዳን ሥራህ ሐሴት ያደርጋል።+ + 6 በእጅጉ ስለካሰኝ+ ለይሖዋ እዘምራለሁ። +91 በልዑል አምላክ ሚስጥራዊ ቦታ የሚኖር ሰው+ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ጥላ ሥር ይቀመጣል።+ + 2 ይሖዋን “አንተ መጠጊያዬና ምሽጌ፣+የምታመንብህም አምላኬ ነህ”+ እለዋለሁ። + 3 እሱ ከወፍ አዳኙ ወጥመድ፣ከአውዳሚ ቸነፈርም ይታደግሃልና። + 4 በላባዎቹ ይከልልሃል፤*በክንፎቹም ሥር መጠጊያ ታገኛለህ።+ ታማኝነቱ+ ትልቅ ጋሻና+ መከላከያ ቅጥር* ይሆንልሃል። + 5 በሌሊት የሚያሸብሩ ነገሮችን፣በቀንም የሚወነጨፍ ፍላጻን አትፈራም፤+ + 6 በጨለማ የሚያደባ ቸነፈርም ሆነበቀትር የሚረፈርፍ ጥፋት አያስፈራህም። + 7 በአጠገብህ ሺህ፣በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ወደ አንተ ግን አይደርስም።+ + 8 በክፉዎች ላይ የሚደርሰውን ቅጣት* ትመለከታለህ፤በዓይንህ ብቻ ታየዋለህ። + 9 ምክንያቱም “ይሖዋ መጠጊያዬ ነው” ብለሃል፤ ልዑሉን አምላክ መኖሪያህ* አድርገኸዋል፤+ +10 ምንም ዓይነት አደጋ አይደርስብህም፤+አንዳችም መቅሰፍት ወደ ድንኳንህ አይጠጋም። +11 በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ+መላእክቱን ስለ አንተ ያዛልና።+ +12 እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው+በእጃቸው ያነሱሃል።+ +13 የአንበሳውን ግልገልና ጉበናውን* ት��ግጣለህ፤ደቦል አንበሳውንና ትልቁን እባብ ከእግርህ ሥር ትጨፈልቃለህ።+ +14 አምላክ እንዲህ ብሏል፦ “ስለወደደኝ፣* እታደገዋለሁ።+ ስሜን ስለሚያውቅ* እጠብቀዋለሁ።+ +15 ይጠራኛል፤ እኔም እመልስለታለሁ።+ በተጨነቀ ጊዜ ከእሱ ጋር እሆናለሁ።+ እታደገዋለሁ እንዲሁም አከብረዋለሁ። +16 ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤+የማዳን ሥራዎቼንም እንዲያይ* አደርገዋለሁ።”+ +123 በሰማያት ዙፋን ላይ የተቀመጥክ ሆይ፣ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሳለሁ።+ + 2 የአገልጋዮች ዓይን ወደ ጌታቸው እጅ፣የሴት አገልጋይም ዓይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት ሁሉ፣የእኛም ዓይኖች ሞገስ እስኪያሳየን ድረስ+ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለከታሉ።+ + 3 ንቀት እጅግ በዝቶብናልና፣+ሞገስ አሳየን፤ ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየን። + 4 ከልክ በላይ በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎችን ፌዝ፣የእብሪተኞችንም ንቀት ጠግበናል።* +5 ይሖዋ ሆይ፣ ቃሌን አዳምጥ፤+መቃተቴን ልብ በል። + 2 ንጉሤና አምላኬ ሆይ፣ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ለእርዳታ የማሰማውን ጩኸት በትኩረት አዳምጥ። + 3 ይሖዋ ሆይ፣ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤+ያሳሰበኝን ነገር በማለዳ ለአንተ እናገራለሁ፤+ በተስፋም እጠባበቃለሁ። + 4 አንተ በክፋት የምትደሰት አምላክ አይደለህምና፤+ክፉ ሰው ከአንተ ጋር አይቀመጥም።+ + 5 እብሪተኛ ሰው በፊትህ አይቆምም። መጥፎ ምግባር ያላቸውን ሁሉ ትጠላለህ፤+ + 6 ውሸት የሚናገሩትን ታጠፋለህ።+ ይሖዋ ዓመፀኞችንና አታላዮችን* ይጸየፋል።+ + 7 እኔ ግን ታላቅ ከሆነው ታማኝ ፍቅርህ የተነሳ+ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤+አንተን በመፍራት* ቅዱስ ወደሆነው ቤተ መቅደስህ እሰግዳለሁ።+ + 8 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ በዙሪያዬ ስላሉ በጽድቅህ ምራኝ፤ከመንገድህ ላይ እንቅፋቶችን አስወግድልኝ።+ + 9 የሚሉት ነገር ሁሉ ሊታመን አይችልም፤ውስጣቸው በተንኮል የተሞላ ነው።ጉሮሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤በምላሳቸው ይሸነግላሉ።*+ +10 አምላክ ግን ይፈርድባቸዋል፤የገዛ ራሳቸው ዕቅድ ለጥፋት ይዳርጋቸዋል።+ ከበደላቸው ብዛት የተነሳ ይባረሩ፤በአንተ ላይ ዓምፀዋልና። +11 አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ሐሴት ያደርጋሉ፤+ምንጊዜም በደስታ እልል ይላሉ። ሊጎዷቸው ከሚፈልጉ ሰዎች ትጠብቃቸዋለህ፤ስምህን የሚወዱም በአንተ ሐሴት ያደርጋሉ። +12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ የሆነውን ሁሉ ትባርካለህና፤ሞገስህ እንደ ትልቅ ጋሻ ይሆንላቸዋል።+ +141 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እጣራለሁ።+ እኔን ለመርዳት ፈጥነህ ድረስልኝ።+ አንተን ስጣራ በትኩረት ስማኝ።+ + 2 ጸሎቴ በአንተ ፊት እንደተዘጋጀ ዕጣን ይሁን፤+የተዘረጉት እጆቼ ምሽት ላይ እንደሚቀርብ የእህል መባ ይሁኑ።+ + 3 ይሖዋ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።+ + 4 ከክፉ ሰዎች ጋር መጥፎ ድርጊት እንዳልፈጽም፣ልቤ ወደ ክፉ ነገር እንዲያዘነብል አትፍቀድ፤+ጣፋጭ ከሆነው ምግባቸው አልቋደስ። + 5 ጻድቅ ቢመታኝ፣ የታማኝ ፍቅር መግለጫ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፤+ቢወቅሰኝ በራስ ላይ እንደሚፈስ ዘይት አድርጌ አየዋለሁ፤+ራሴም ይህን ፈጽሞ እንቢ አይልም።+ መከራ በገጠማቸው ወቅትም እንኳ መጸለዬን እቀጥላለሁ። + 6 ፈራጆቻቸው ከገደል አፋፍ ቢጣሉም፣ሕዝቡ ለምናገራቸው ቃላት ትኩረት ይሰጣል፤ ደስ የሚያሰኙ ናቸውና። + 7 ሰው ሲያርስና ጓል ሲከሰክስ አፈሩ እንደሚበታተን ሁሉ፣አጥንቶቻችንም በመቃብር* አፍ ላይ ተበታተኑ። + 8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ።+ አንተን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ። ሕይወቴን አትውሰድ።* + 9 ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣ክፉ አድራጊዎች ካስቀመጡብኝ አሽክላም ጠብቀኝ። +10 ክፉዎች አንድ ላይ የ��ዛ ወጥመዳቸው ውስጥ ይወድቃሉ፤+እኔ ግን አንድም ነገር ሳይነካኝ አልፋለሁ። +125 በይሖዋ የሚታመኑ፣+ፈጽሞ ሳይናወጥ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖረውእንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።+ + 2 ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንዳሉ ሁሉ፣+ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበሕዝቡ ዙሪያ ይሆናል።+ + 3 ጻድቃን ትክክል ያልሆነ ነገር መሥራት እንዳይጀምሩ፣*+የክፋት በትር ለጻድቃን በተሰጠ ምድር ላይ አይኖርም።+ + 4 ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩ ሰዎች፣ለልበ ቅኖች+ መልካም ነገር አድርግ።+ + 5 ወደ ጠማማ መንገዳቸው ዞር የሚሉትን፣ይሖዋ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ያስወግዳቸዋል።+ በእስራኤል ሰላም ይስፈን። +130 ይሖዋ ሆይ፣ ከጥልቅ ውስጥ አንተን እጣራለሁ።+ + 2 ይሖዋ ሆይ፣ ድምፄን ስማ። ጆሮዎችህ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና በትኩረት ያዳምጡ። + 3 ያህ* ሆይ፣ አንተ ስህተትን የምትከታተል* ቢሆን ኖሮ፣ይሖዋ ሆይ፣ ማን ሊቆም ይችል ነበር?+ + 4 በአንተ ዘንድ በእርግጥ ይቅርታ አለና፤+ይህም ሰዎች አንተን እንዲፈሩ* ያደርጋል።+ + 5 ይሖዋን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ሁለንተናዬ በእሱ ተስፋ ያደርጋል፤*ቃሉን በትዕግሥት እጠብቃለሁ። + 6 ንጋትን ከሚጠባበቁ፣አዎ፣ ንጋትን ከሚጠባበቁ ጠባቂዎች ይበልጥይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።*+ + 7 እስራኤል ይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ፤ይሖዋ በፍቅሩ ታማኝ ነውና፤+ሕዝቡንም ለመዋጀት ታላቅ ኃይል አለው። + 8 እስራኤልን ከበደላቸው ሁሉ ይዋጃል። +21 ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡ በአንተ ብርታት ደስ ይለዋል፤+በማዳን ሥራህ እጅግ ሐሴት ያደርጋል!+ + 2 የልቡን ፍላጎት አሟልተህለታል፤+የከንፈሩንም ልመና አልከለከልከውም። (ሴላ) + 3 የተትረፈረፉ በረከቶች ይዘህ ተቀበልከው፤ምርጥ ከሆነ* ወርቅ የተሠራ አክሊልም በራሱ ላይ ደፋህለት።+ + 4 ሕይወትን ለመነህ፤አንተም ረጅም ዕድሜ* ብሎም የዘላለም ሕይወት ሰጠኸው።+ + 5 የማዳን ሥራህ ታላቅ ክብር ያስገኝለታል።+ ሞገስና ግርማ አጎናጸፍከው። + 6 ለዘላለም እንዲባረክ አደረግከው፤+ከእሱ ጋር እንዳለህ ሲያውቅ* በጣም ደስ ይለዋል።+ + 7 ንጉሡ በይሖዋ ይተማመናልና፤+በልዑሉ አምላክ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ፈጽሞ አይናወጥም።*+ + 8 እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ይይዛቸዋል፤ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ይይዛቸዋል። + 9 በተወሰነው ጊዜ ትኩረትህን በእነሱ ላይ ስታደርግ እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ። ይሖዋ በቁጣው ይውጣቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል።+ +10 የሆዳቸውን ፍሬ ከምድር ገጽ፣ዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ። +11 በአንተ ላይ ክፉ ለመሥራት አስበዋልና፤+ሊሳካ የማይችል ሴራ ጠንስሰዋል።+ +12 ቀስትህን* በእነሱ ላይ* በማነጣጠርእንዲያፈገፍጉ ታደርጋለህና።+ +13 ይሖዋ ሆይ፣ በብርታትህ ተነስ። ለኃያልነትህ የውዳሴ መዝሙር እንዘምራለን። +15 ይሖዋ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ በእንግድነት የሚስተናገድ ማን ነው? በተቀደሰ ተራራህ የሚኖር ማን ነው?+ + 2 ያለነቀፋ* የሚመላለስ፣+ትክክል የሆነውን የሚያደርግ፣+በልቡም እውነትን የሚናገር ሰው ነው።+ + 3 በአንደበቱ ስም አያጠፋም፤+በባልንጀራው ላይ መጥፎ ነገር አይሠራም፤+የወዳጆቹንም ስም አያጎድፍም።*+ + 4 ነውረኛ የሆነን ሰው ሁሉ ይንቃል፤+ይሖዋን የሚፈሩትን ግን ያከብራል። ጉዳት ላይ ሊጥለው ቢችልም እንኳ ቃሉን* አያጥፍም።+ + 5 ገንዘቡን በወለድ አያበድርም፤+ንጹሕ የሆነውን ሰው ለመወንጀልም ጉቦ አይቀበልም።+ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ ፈጽሞ አይናወጥም።*+ +136 ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ + 2 ለአማልክት አምላክ+ ምስጋና አቅርቡ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። + 3 ለጌቶች ��ታ ምስጋና አቅርቡ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። + 4 እሱ ብቻ አስደናቂ የሆኑ ታላላቅ ነገሮች ይሠራል፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።+ + 5 ሰማያትን በጥበብ ሠራ፤*+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። + 6 ምድርን በውኃዎች ላይ ዘረጋ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። + 7 ታላላቅ ብርሃናትን ሠራ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ + 8 ፀሐይ በቀን እንዲያይል* አደረገ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ + 9 ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲያይሉ* አደረገ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +10 የግብፅን በኩር ቀሰፈ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +11 እስራኤልን ከመካከላቸው አወጣ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ +12 በኃያል እጅና በተዘረጋ ክንድ ይህን አድርጓል፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +13 ቀይ ባሕርን ለሁለት ከፈለ፤*+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +14 እስራኤል በመካከሉ እንዲያልፍ አደረገ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +15 ፈርዖንንና ሠራዊቱን ቀይ ባሕር ውስጥ ወረወረ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +16 ሕዝቡን በምድረ በዳ መራ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +17 ታላላቅ ነገሥታትን መታ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +18 ኃያላን ነገሥታትን ገደለ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ +19 የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን+ ገደለ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ +20 የባሳንንም ንጉሥ ኦግን+ ገደለ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +21 ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሰጠ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ +22 ለአገልጋዩ ለእስራኤል ርስት አድርጎ አወረሰ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +23 መንፈሳችን ተደቁሶ በነበረበት ጊዜ አስታወሰን፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።+ +24 ከጠላቶቻችን እጅ ይታደገን ነበር፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +25 ሕይወት ላለው* ሁሉ ምግብ ይሰጣል፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +26 ለሰማያት አምላክ ምስጋና አቅርቡ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። +72 አምላክ ሆይ፣ ፍርዶችህን ለንጉሡ ስጥ፤ጽድቅህንም ለንጉሡ ልጅ አጎናጽፍ።+ + 2 ስለ ሕዝብህ በጽድቅ ይሟገት፤ለተቸገሩ አገልጋዮችህም ፍትሕ ያስፍን።+ + 3 ተራሮች ለሕዝቡ ሰላም ያምጡ፤ኮረብቶችም ጽድቅን ያስገኙ። + 4 በሕዝቡ መካከል ላሉት ችግረኞች ጥብቅና ይቁም፤*የድሃውን ልጆች ያድን፤ቀማኛውንም ይደምስሰው።+ + 5 ፀሐይ ብርሃኗን እስከሰጠች፣ጨረቃም በሰማይ ላይ እስካለች ድረስ፣ከትውልድ እስከ ትውልድ+ አንተን ይፈሩሃል። + 6 እሱ በታጨደ ሣር ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ፣ምድርንም እንደሚያጠጣ ካፊያ ይወርዳል።+ + 7 በእሱ ዘመን ጻድቅ ይለመልማል፤*+ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ሰላም ይበዛል።+ + 8 ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ከወንዙም* እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተገዢዎች ይኖሩታል።*+ + 9 በበረሃ የሚኖሩ ሰዎች በፊቱ ይሰግዳሉ፤ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።+ +10 የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ ግብር ያመጣሉ።+ የሳባና የሴባ ነገሥታት፣ ስጦታ ይሰጣሉ።+ +11 ነገሥታትም ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ፤ብሔራትም ሁሉ ያገለግሉታል። +12 እርዳታ ለማግኘት የሚጮኸውን ድሃ፣እንዲሁም ችግረኛውንና ረዳት የሌለውን ሁሉ ይታደጋልና። +13 ለችግረኛውና ለድሃው ያዝናል፤የድሆችንም ሕይወት* ያድናል። +14 ከጭቆናና ከግፍ ይታደጋቸዋል፤*ደማቸውም በዓይኖቹ ፊት ክቡር ነው። +15 ረጅም ዘመን ይኑር፤ የሳባም ወርቅ ይሰጠው።+ ስለ እሱም ሁልጊዜ ጸሎት ይቅረብ፤ቀኑንም ሙሉ ይባረክ። +16 በ���ድር ላይ እህል ይትረፈረፋል፤+በተራሮችም አናት ላይ በብዛት ይኖራል። የንጉሡም ፍሬ እንደ ሊባኖስ ዛፎች ይንዠረገጋል፤+በከተሞቹም ውስጥ ሰዎች በምድር ላይ እንዳሉ ዕፀዋት ያብባሉ።+ +17 ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤+ፀሐይም እስካለች ድረስ ስሙ ይግነን። ሰዎች በእሱ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያግኙ፤+ብሔራት ሁሉ ደስተኛ ብለው ይጥሩት። +18 እሱ ብቻ አስደናቂ ነገሮችን የሚያደርገው፣+የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ።+ +19 ክብራማ ስሙ ለዘላለም ይወደስ፤+ምድርም ሁሉ በክብሩ ትሞላ።+ አሜን፣ አሜን። +20 የእሴይ ልጅ+ የዳዊት ጸሎቶች እዚህ ላይ አበቁ። +22 አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?+ እኔን ከማዳን፣ ከደረሰብኝም ሥቃይ የተነሳ የማሰማውን ጩኸት+ ከመስማትየራቅከው ለምንድን ነው? + 2 አምላኬ ሆይ፣ በቀን ደጋግሜ እጣራለሁ፤ አንተ ግን አትመልስልኝም፤+በሌሊትም ዝም ማለት አልቻልኩም። + 3 አንተ ግን ቅዱስ ነህ፤+እስራኤል በሚያቀርበው ውዳሴ ተከበሃል።* + 4 አባቶቻችን እምነታቸውን በአንተ ላይ ጣሉ፤+በአንተ ተማመኑ፤ አንተም ሁልጊዜ ትታደጋቸው ነበር።+ + 5 ወደ አንተ ጮኹ፤ ደግሞም ዳኑ፤በአንተ ተማመኑ፤ የጠበቁት ሳይፈጸም ቀርቶም አላዘኑም።*+ + 6 እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤ሰው ያፌዘብኝ፣* ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።+ + 7 የሚያዩኝ ሁሉ ያላግጡብኛል፤+በንቀትና በፌዝ ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ እንዲህ ይሉኛል፦+ + 8 “ራሱን ለይሖዋ በአደራ ሰጥቷል። እስቲ እሱ ይታደገው! በእሱ እጅግ የተወደደ ስለሆነ እሱ ያድነው!”+ + 9 ከማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤+በእናቴ ጡት ተማምኜ እንድኖር ያደረግከኝ አንተ ነህ። +10 ስወለድ ጀምሮ ለአንተ በአደራ ተሰጠሁ፤*ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ። +11 ችግር ሊደርስብኝ ስለሆነ ከእኔ አትራቅ፤+ደግሞም ሌላ ረዳት የለኝም።+ +12 ብዙ ወይፈኖች ከበውኛል፤+የባሳን ኃይለኛ ኮርማዎችም በዙሪያዬ ናቸው።+ +13 ያደነውን እንደሚቦጫጭቅ የሚያገሳ አንበሳ+አፋቸውን በእኔ ላይ ከፈቱ።+ +14 እንደ ውኃ ፈሰስኩ፤አጥንቶቼ ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ። ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤+በውስጤም ቀለጠ።+ +15 ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፤+ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤+እንድሞትም ወደ ጉድጓድ አወረድከኝ።+ +16 ውሾች ከበውኛልና፤+እንደ ክፉ አድራጊዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ሰፍረዋል፤+እንደ አንበሳ ሆነው እጆቼና እግሮቼ ላይ ተረባረቡ።*+ +17 አጥንቶቼን ሁሉ መቁጠር እችላለሁ።+ እነሱም አዩኝ፤ ትኩር ብለውም ተመለከቱኝ። +18 መደረቢያዎቼን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።+ +19 አንተ ግን ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+ አንተ ብርታቴ ነህ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+ +20 ከሰይፍ አድነኝ፤*ውድ ሕይወቴን* ከውሾች መዳፍ* ታደጋት፤+ +21 ከአንበሳ አፍና ከዱር በሬዎች ቀንድ አድነኝ፤+መልስ ስጠኝ፤ ታደገኝም። +22 ስምህን ለወንድሞቼ አሳውቃለሁ፤+በጉባኤ መካከልም አወድስሃለሁ።+ +23 እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ አወድሱት! እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁሉ፣ ከፍ ከፍ አድርጉት!+ እናንተ የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ ለእሱ ታላቅ አክብሮት አሳዩ። +24 እሱ የተጨቆነውን ሰው መከራ አልናቀምና፤+ ደግሞም አልተጸየፈም፤ፊቱን ከእሱ አልሰወረም።+ ለእርዳታ ወደ እሱ በጮኸ ጊዜ ሰምቶታል።+ +25 በታላቅ ጉባኤ መካከል አወድስሃለሁ፤+እሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ። +26 የዋሆች በልተው ይጠግባሉ፤+ይሖዋን የሚፈልጉት እሱን ያወድሱታል።+ ለዘላለም ተደስታችሁ ኑሩ።* +27 የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ይሖዋን አስታውሰው ወደ እሱ ይዞራሉ። የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ በፊትህ ይሰግዳሉ።+ +28 ንግሥና የይሖዋ ነውና፤+ብሔራትን ይገዛል። +29 በምድር ���ሉ ባለጸጎች ሁሉ* ይበላሉ፤ ይሰግዳሉም፤ወደ አፈር የሚወርዱ ሁሉ በእሱ ፊት ይንበረከካሉ፤ከእነሱ መካከል አንዳቸውም ሕይወታቸውን* ማቆየት አይችሉም። +30 ዘሮቻቸው ያገለግሉታል፤መጪው ትውልድ ስለ ይሖዋ ይነገረዋል። +31 መጥተው ጽድቁን ያወራሉ። ገና ለሚወለድ ሕዝብ ያደረገውን ነገር ይናገራሉ። +122 “ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ” ባሉኝ ጊዜ እጅግ ደስ አለኝ።+ + 2 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አሁን በበሮችሽ ገብተንከውስጥ ቆመናል።+ + 3 ኢየሩሳሌም አንድ ወጥ ሆናእንደተገነባች ከተማ ናት።+ + 4 ለእስራኤል በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት፣ነገዶቹ ይኸውም የያህ* ነገዶች፣ለይሖዋ ስም ምስጋና ለማቅረብወደዚያ ወጥተዋል።+ + 5 በዚያ የፍርድ ዙፋኖች፣የዳዊት ቤት ዙፋኖች+ ተቀምጠዋልና።+ + 6 ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ።+ አንቺ ከተማ ሆይ፣ አንቺን የሚወዱ ከስጋት ነፃ ይሆናሉ። + 7 በመከላከያ ግንቦችሽ* ውስጥ ሰላም ለዘለቄታው ይኑር፤በማይደፈሩ ማማዎችሽ ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታ ይስፈን። + 8 እንግዲህ ለወንድሞቼና ለወዳጆቼ ስል “በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ። + 9 ለአምላካችን ለይሖዋ ቤት ስል+ለአንቺ መልካም ነገር እሻለሁ። +79 አምላክ ሆይ፣ ብሔራት ርስትህን+ ወረውታል፤ቅዱስ መቅደስህንም አርክሰዋል፤+ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አድርገዋታል።+ + 2 የአገልጋዮችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣የታማኝ አገልጋዮችህንም ሥጋ ለምድር አራዊት ምግብ አድርገው ሰጥተዋል።+ + 3 ደማቸውን በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፤እነሱንም የሚቀብር አንድም ሰው አልተረፈም።+ + 4 በጎረቤቶቻችን ዘንድ መሳለቂያ ሆንን፤+በዙሪያችን ያሉትም ያፌዙብናል፤ ደግሞም ይዘብቱብናል። + 5 ይሖዋ ሆይ፣ የምትቆጣው እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?+ ቁጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?+ + 6 አንተን በማያውቁ ብሔራት፣ስምህንም በማይጠሩ መንግሥታት ላይ ቁጣህን አፍስስ።+ + 7 ያዕቆብን በልተውታልና፤የትውልድ አገሩንም አውድመዋል።+ + 8 አባቶቻችን በሠሩት ስህተት እኛን ተጠያቂ አታድርገን።+ ፈጥነህ ምሕረት አድርግልን፤+በጭንቀት ተውጠናልና። + 9 አዳኛችን የሆንክ አምላክ ሆይ፣ለታላቁ ስምህ ስትል እርዳን፤+ለስምህም ስትል ታደገን፤ ኃጢአታችንንም ይቅር በለን።*+ +10 ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?+ በፈሰሰው የአገልጋዮችህ ደም የተነሳ የሚወሰድባቸውን የበቀል እርምጃ፣ዓይናችን እያየ ብሔራት ይወቁት።+ +11 እስረኛው የሚያሰማውን ሲቃ ስማ።+ ሞት የተፈረደባቸውን* በታላቅ ኃይልህ* አድናቸው።*+ +12 ይሖዋ ሆይ፣ ጎረቤቶቻችን በአንተ ላይ በመሳለቃቸው+ሰባት እጥፍ አድርገህ ብድራታቸውን ክፈላቸው።+ +13 በዚህ ጊዜ እኛ ሕዝቦችህ፣ በመስክህ ያሰማራኸን መንጋ፣+ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ከትውልድ እስከ ትውልድም ውዳሴህን እናሰማለን።+ +109 የማወድስህ አምላክ ሆይ፣+ ዝም አትበል። + 2 ክፉዎችና አታላዮች በእኔ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉና። ስለ እኔ በሐሰተኛ አንደበት ይናገራሉ፤+ + 3 በዙሪያዬም ሆነው የጥላቻ ቃላት ይሰነዝሩብኛል፤ያለምክንያት ያጠቁኛል።+ + 4 ፍቅር ሳሳያቸው በምላሹ ይቃወሙኛል፤+እኔ ግን መጸለዬን እቀጥላለሁ። + 5 ለመልካም ነገር ክፋትን፣ላሳየኋቸው ፍቅር ጥላቻን ይመልሱልኛል።+ + 6 በእሱ ላይ ክፉ ሰው እዘዝበት፤በቀኙም ተቃዋሚ* ይቁም። + 7 ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ* ሆኖ ይገኝ፤ጸሎቱም እንኳ እንደ ኃጢአት ይቆጠርበት።+ + 8 የሕይወት ዘመኑ አጭር ይሁን፤+የበላይ ተመልካችነት ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው።+ + 9 ልጆቹ* ያለአባት ይቅሩ፤ሚስቱም መበለት ትሁን። +10 ልጆቹ* በየቦታው የሚቅበዘበዙ ለማኞች ይሁኑ፤ከፈራረሰው መኖሪያቸው ወጥተው ምግብ ፍለጋ ይንከራተቱ። +11 ያበደረው ሰው ያለውን ነገር ሁሉ ይውሰድበት፤*ባዕድ ሰዎችም ንብረቱን ይዝረፉት። +12 ደግነት* የሚያሳየው ሰው ከቶ አይኑር፤ያለአባት ለቀሩት ልጆቹ የሚራራ አንድም ሰው አይገኝ። +13 ዘሩ* ይጥፋ፤+ስማቸው በአንድ ትውልድ ውስጥ ይደምሰስ። +14 አባቶቹ የሠሩትን በደል ይሖዋ አይርሳ፤+የእናቱም ኃጢአት አይደምሰስ። +15 ይሖዋ የሠሩትን ነገር ምንጊዜም ያስብ፤መታሰቢያቸውንም ከምድር ገጽ ያጥፋ።+ +16 ክፉው ሰው ደግነት* ለማሳየት አላሰበምና፤+ይልቁንም የተጨቆነውን፣ ድሃውንና ልቡ በሐዘን የተደቆሰውን ሰውለመግደል ሲያሳድድ ነበር።+ +17 ሌሎችን መርገም ወደደ፤ በመሆኑም እርግማኑ በእሱ ላይ ደረሰበት፤ሌሎችን ለመባረክ ፍላጎት አልነበረውም፤ ስለዚህ ምንም በረከት አላገኘም። +18 እርግማንን እንደ ልብስ ለበሰ። እንደ ውኃም ሰውነቱ ውስጥ ፈሰሰ፤እንደ ዘይት ወደ አጥንቶቹ ዘለቀ። +19 እርግማኑ እንደሚከናነበው ልብስ፣ሁልጊዜ እንደሚታጠቀውም ቀበቶ ይሁንለት።+ +20 እኔን የሚቃወመኝ ሰው፣በእኔም* ላይ ክፉ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ከይሖዋ የሚያገኙት ዋጋ ይህ ነው።+ +21 አንተ ግን ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ለስምህ ስትል እርዳኝ።+ ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ ታደገኝ።+ +22 እኔ ምስኪንና ድሃ ነኝና፤+ልቤም በውስጤ ተወግቷል።+ +23 ፀሐይ ስትጠልቅ እንደሚጠፋ ጥላ አልፋለሁ፤እንደ አንበጣ አራግፈው ጣሉኝ። +24 ከመጾሜ የተነሳ ጉልበቶቼ ከዱኝ፤ሰውነቴ ከሳ፤ እኔም እየመነመንኩ ሄድኩ።* +25 የእነሱ መሳለቂያ ሆንኩ።+ ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።+ +26 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እርዳኝ፤በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ። +27 ይህ የአንተ እጅ መሆኑን ይወቁ፤ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ያደረግከው አንተ እንደሆንክ ይገንዘቡ። +28 እነሱ ይራገሙ፤ አንተ ግን ባርክ። እነሱ በእኔ ላይ ሲነሱ ለኀፍረት ይዳረጉ፤አገልጋይህ ግን ሐሴት ያድርግ። +29 እኔን የሚቃወሙኝ ውርደት ይከናነቡ፤ኀፍረታቸውንም እንደ ልብስ* ይጎናጸፉ።+ +30 አንደበቴ ይሖዋን ከልብ ታወድሰዋለች፤በብዙ ሕዝቦች ፊት አወድሰዋለሁ።+ +31 በእሱ* ላይ ከሚፈርዱት ሊያድነውበድሃው ቀኝ ይቆማልና። +42 ርኤም* ጅረቶችን እንደምትናፍቅ፣አምላክ ሆይ፣ አንተን እናፍቃለሁ።* + 2 አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማሁ።*+ ወደ አምላክ የምሄደውና በፊቱ የምቀርበው መቼ ይሆን?+ + 3 እንባዬ ቀን ከሌት ምግብ ሆነኝ፤ሰዎች ቀኑን ሙሉ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ይሳለቁብኛል።+ + 4 እነዚህን ነገሮች አስታውሳለሁ፤ ነፍሴንም* አፈሳለሁ፤በአንድ ወቅት ከብዙ ሰዎች ጋር እጓዝ ነበር፤በእልልታና በምስጋና ድምፅ፣በዓል በሚያከብር ሕዝብ ድምፅ፣ከፊታቸው ሆኜ ወደ አምላክ ቤት በኩራት* እሄድ ነበር።+ + 5 ተስፋ የምቆርጠው* ለምንድን ነው?+ ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው? አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤+እሱን እንደ ታላቅ አዳኜ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና።+ + 6 አምላኬ ሆይ፣ ተስፋ ቆርጫለሁ።*+ ከዮርዳኖስ ምድርና ከሄርሞን አናት፣ከሚዛር ተራራ*የማስብህ ለዚህ ነው።+ + 7 በፏፏቴህ ድምፅ አማካኝነትጥልቁ ውኃ፣ ጥልቁን ውኃ ይጣራል። ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ ዋጠኝ።+ + 8 ይሖዋ በቀን ታማኝ ፍቅሩን ያሳየኛል፤እኔ ደግሞ በሌሊት ስለ እሱ እዘምራለሁ፤ ሕይወት ለሰጠኝ አምላክ ጸሎት አቀርባለሁ።+ + 9 ዓለቴ የሆነውን አምላክ እንዲህ እለዋለሁ፦ “ለምን ረሳኸኝ?+ ጠላት ከሚያደርስብኝ ግፍ የተነሳ በሐዘን ተውጬ ለምን እሄዳለሁ?”+ +10 ለእኔ ካላቸው ጥላቻ የተነሳ ሊገድሉኝ የሚሹ* ጠላቶቼ ይሳለቁብኛል፤ቀኑን ሙሉ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ይሳለቁብኛል።+ +11 ተስፋ የምቆርጠው* ለምንድን ነው? ውስጤ የሚረበሸው ለምንድን ነው? አምላክን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤+እሱን እንደ ታላቅ አዳኜና አምላኬ አድርጌ ገና አወድሰዋለሁና።+ +102 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+እርዳታ ለማግኘት የማሰማው ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ።+ + 2 የሚያስጨንቅ ሁኔታ ባጋጠመኝ ጊዜ ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤*ስጣራ ፈጥነህ መልስልኝ።+ + 3 የሕይወት ዘመኔ እንደ ጭስ እየበነነ ነው፤አጥንቶቼም እንደ ምድጃ ከስለዋል።+ + 4 እህል መብላት ረስቻለሁና፤ልቤ እንደ ሣር ጠውልጓል፤ ደርቋልም።+ + 5 እጅግ ከመቃተቴ የተነሳ+አጥንቶቼ ከቆዳዬ ጋር ተጣበቁ።+ + 6 የምድረ በዳ ሻላ* መሰልኩ፤በፍርስራሽ ክምር መካከል እንዳለች ጉጉት ሆንኩ። + 7 እንቅልፍ አጥቼ አድራለሁ፤*በጣሪያ ላይ እንዳለች ብቸኛ ወፍ ሆንኩ።+ + 8 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይሳለቁብኛል።+ የሚያፌዙብኝ ሰዎች ስሜን ለእርግማን ይጠቀሙበታል። + 9 አመድን እንደ ምግብ እበላለሁና፤+የምጠጣውም ነገር ከእንባ ጋር ተቀላቅሏል፤+ +10 ይህም የሆነው ከቁጣህና ከንዴትህ የተነሳ ነው፤እኔን ለመጣል ወደ ላይ አንስተኸኛልና። +11 የሕይወቴ ዘመን ፀሐይ ስትጠልቅ እንደሚጠፋ* ጥላ ነው፤+እኔም እንደ ሣር ጠወለግኩ።+ +12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም ትኖራለህ፤+ዝናህም* ከትውልድ እስከ ትውልድ ይጸናል።+ +13 በእርግጥ ትነሳለህ፤ ለጽዮንም ምሕረት ታሳያለህ፤+ለእሷ ሞገስህን የምታሳይበት ጊዜ ነውና፤+የተወሰነው ጊዜ ደርሷል።+ +14 አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይላቸዋልና፤+ለአፈሯም እንኳ ልዩ ፍቅር አላቸው።+ +15 ብሔራት የይሖዋን ስም፣የምድር ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።+ +16 ይሖዋ ጽዮንን ዳግመኛ ይገነባልና፤+በክብሩም ይገለጣል።+ +17 የድሆችን ጸሎት በትኩረት ያዳምጣል፤+ጸሎታቸውን አይንቅም።+ +18 ይህ የተጻፈው ለመጪው ትውልድ ነው፤+በመሆኑም ወደፊት የሚመጣው* ሕዝብ ያህን ያወድሳል። +19 ይሖዋ ከፍ ካለው ቅዱስ ስፍራው ወደ ታች ይመለከታልና፤+ከሰማይ ሆኖ ወደ ታች ምድርን ያያል፤ +20 ይህም የእስረኛውን ሲቃ ለመስማት፣+ሞት የተፈረደባቸውንም ነፃ ለማውጣት ነው፤+ +21 በመሆኑም የይሖዋ ስም በጽዮን፣ውዳሴውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤+ +22 ይህም የሚሆነው ሕዝቦችና መንግሥታትይሖዋን ለማገልገል አንድ ላይ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ነው።+ +23 ያለጊዜዬ ኃይል አሳጣኝ፤የሕይወት ዘመኔን አሳጠረ። +24 እኔም እንዲህ አልኩ፦“ከትውልድ እስከ ትውልድ የምትኖረው አምላኬ ሆይ፣+በሕይወት ዘመኔ እኩሌታ አታጥፋኝ። +25 አንተ ከብዙ ዘመናት በፊት የምድርን መሠረት ጣልክ፤ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።+ +26 እነሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ። እንደ ልብስ ትቀይራቸዋለህ፤ እነሱም ያልፋሉ። +27 አንተ ግን ያው ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።+ +28 የአገልጋዮችህ ልጆች ያለስጋት ይኖራሉ፤ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”+ +148 ያህን አወድሱ!* ይሖዋን ከሰማያት አወድሱት፤+በከፍታ ቦታዎች አወድሱት። + 2 መላእክቱ ሁሉ፣ አወድሱት።+ ሠራዊቱ ሁሉ፣+ አወድሱት። + 3 ፀሐይና ጨረቃ፣ አወድሱት። የምታብረቀርቁ ከዋክብት ሁሉ፣ አወድሱት።+ + 4 ሰማየ ሰማያት፣ አወድሱት፤ከሰማያት በላይ ያላችሁ ውኃዎች፣ አወድሱት። + 5 የይሖዋን ስም ያወድሱ፤እሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና።+ + 6 ለዘላለም አጸናቸው፤+ጊዜ የማይሽረው ድንጋጌ አውጥቷል።+ + 7 ይሖዋን ከምድር አወድሱት፤እናንተ ግዙፍ የባሕር ፍጥረታትና ጥልቅ ውኃዎች ሁሉ፣ + 8 መብረቅና በረዶ፣ አመዳይና ጥቅጥቅ ያለ ደመና፣አንተም ቃሉን የምትፈጽም አውሎ ነፋስ፣+ + 9 እናንተ ተራሮችና ኮረብቶች ሁሉ፣+እናንተ ፍሬ የምታፈሩ ዛፎችና አርዘ ሊባኖሶች ሁሉ፣+ +10 እና���ተ የዱር እንስሳትና+ የቤት እንስሳት ሁሉ፣እናንተ መሬት ለመሬት የምትሳቡ ፍጥረታትና ክንፍ ያላችሁ ወፎች፣ +11 እናንተ የምድር ነገሥታትና ብሔራት ሁሉ፣እናንተ መኳንንትና የምድር ፈራጆች ሁሉ፣+ +12 እናንተ ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች፣*ሽማግሌዎችና ልጆች በኅብረት አወድሱት። +13 የይሖዋን ስም ያወድሱ፤ስሙ ብቻውን ከሌሎች ሁሉ በላይ ነውና።+ ግርማው ከምድርና ከሰማይ በላይ ነው።+ +14 ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ፣ማለትም ለእሱ ቅርብ የሆኑት የሕዝቡ የእስራኤል ልጆች ይወደሱ ዘንድየሕዝቡን ብርታት* ከፍ ያደርጋል። ያህን አወድሱ!* +112 ያህን አወድሱ!*+ א [አሌፍ] ይሖዋን የሚፈራና+ב [ቤት] ትእዛዛቱን እጅግ የሚወድ ሰው ደስተኛ ነው።+ + 2 ዘሮቹ በምድር ላይ ኃያላን ይሆናሉ።ד [ዳሌት] ደግሞም የቅኖች ትውልድ ይባረካል።+ + 3 በቤቱ ሀብትና ንብረት አለ፤ו [ዋው] ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል። + 4 ለቅኖች በጨለማ ውስጥ እንደ ብርሃን ያበራል።+ ח [ኼት] ሩኅሩኅና* መሐሪ+ እንዲሁም ጻድቅ ነው። + 5 በልግስና የሚያበድር ሰው ይሳካለታል።+ י [ዮድ] ጉዳዩን በፍትሕ ያከናውናል። + 6 እሱ ፈጽሞ አይናወጥም።+ ל [ላሜድ] ጻድቅ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል።+ + 7 ክፉ ወሬ አያስፈራውም።+ נ [ኑን] በይሖዋ ስለሚተማመን ልቡ ጽኑ ነው።+ + 8 ልቡ አይናወጥም፤* አይፈራምም፤+ע [አይን] በመጨረሻም ጠላቶቹን በድል አድራጊነት ይመለከታል።+ + 9 በብዛት* አከፋፈለ፤ ለድሆችም ሰጠ።+ צ [ጻዴ] ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል።+ ק [ኮፍ] የገዛ ብርታቱ* በክብር ከፍ ከፍ ይላል። +10 ክፉ ሰው አይቶ ይበሳጫል። ש [ሺን] ጥርሱን ያፋጫል፤ ቀልጦም ይጠፋል። ת [ታው] የክፉዎች ምኞት ይከስማል።+ +78 ሕዝቤ ሆይ፣ ሕጌን* አዳምጥ፤ከአፌ ወደሚወጣው ቃል ጆሮህን አዘንብል። + 2 አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ። በጥንት ዘመን የተነገሩትን እንቆቅልሾች አቀርባለሁ።+ + 3 የሰማናቸውንና ያወቅናቸውን ነገሮች፣አባቶቻችን ለእኛ የተረኩልንን፣+ + 4 ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ይሖዋ ያከናወናቸውን የሚያስመሰግኑ ሥራዎችና ብርታቱን፣+ደግሞም የሠራቸውን አስደናቂ ነገሮች+ለመጪው ትውልድ እንተርካለን።+ + 5 እሱ ለያዕቆብ ማሳሰቢያ ሰጠ፤በእስራኤልም ሕግ ደነገገ፤እነዚህን ነገሮች ለልጆቻቸው እንዲያሳውቁአባቶቻችንን አዘዛቸው፤+ + 6 ይህም ቀጣዩ ትውልድ፣ገና የሚወለዱት ልጆች እነዚህን ነገሮች እንዲያውቁ ነው።+ እነሱም በተራቸው ለልጆቻቸው ይተርካሉ።+ + 7 በዚህ ጊዜ እነሱ ትምክህታቸውን በአምላክ ላይ ይጥላሉ። የአምላክን ሥራዎች አይረሱም፤+ይልቁንም ትእዛዛቱን ይጠብቃሉ።+ + 8 ያን ጊዜ እንደ አባቶቻቸውእልኸኛና ዓመፀኛ ትውልድ፣+ደግሞም ልቡ የሚወላውልና*+መንፈሱ ለአምላክ ታማኝ ያልሆነ ትውልድ አይሆኑም። + 9 ኤፍሬማውያን ቀስት የታጠቁ ነበሩ፤ይሁንና በጦርነት ቀን ወደ ኋላ አፈገፈጉ። +10 የአምላክን ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤+በሕጉም ለመመላለስ ፈቃደኛ አልሆኑም።+ +11 በተጨማሪም ያደረጋቸውን ነገሮች፣ያሳያቸውን ድንቅ ሥራዎች ረሱ።+ +12 በአባቶቻቸው ፊት በግብፅ አገር፣በጾዓን+ ምድር አስደናቂ ነገሮች አከናውኖ ነበር።+ +13 በዚያ አቋርጠው እንዲሄዱ ባሕሩን ከፈለው፤ውኃዎቹንም እንደ ግድብ አቆመ።*+ +14 ቀን በደመና፣ ሌሊቱን ሙሉ ደግሞበእሳት ብርሃን መራቸው።+ +15 በምድረ በዳ ዓለቶችን ሰነጠቀ፤ከጥልቅ ውኃ የሚጠጡ ያህል እስኪረኩ ድረስ አጠጣቸው።+ +16 ከቋጥኝ ውስጥ ወራጅ ውኃ አወጣ፤ውኃዎችም እንደ ወንዝ እንዲፈስሱ አደረገ።+ +17 እነሱ ግን በበረሃ፣ በልዑሉ አምላክ ላይ በማመፅበእሱ ላይ ኃጢአት መሥራታቸውን ቀጠሉ፤+ +18 እንዲሁም የተመኙትን* ምግብ እንዲሰጣቸው በመጠየቅአምላክን በልባቸው ተገዳደሩት።*+ +19 “አምላክ በምድረ በዳ ማዕድ ማዘጋጀት ይችላል?” በማለትበአምላክ ላይ አጉረመረሙ።+ +20 እነሆ፣ ውኃ እንዲፈስና ጅረቶች እንዲንዶለዶሉዓለትን መታ።+ ይሁንና “ዳቦስ ሊሰጠን ይችላል?ወይስ ለሕዝቡ ሥጋ ሊያቀርብ ይችላል?” አሉ።+ +21 ይሖዋ በሰማቸው ጊዜ እጅግ ተቆጣ፤+በያዕቆብ ላይ እሳት+ ተቀጣጠለ፤በእስራኤልም ላይ ቁጣው ነደደ፤+ +22 ምክንያቱም በአምላክ ላይ እምነት አልጣሉም፤+እነሱን የማዳን ችሎታ እንዳለው አላመኑም። +23 ስለዚህ በላይ ያሉትን በደመና የተሸፈኑ ሰማያት አዘዘ፤የሰማይንም በሮች ከፈተ። +24 የሚበሉት መና አዘነበላቸው፤የሰማይንም እህል ሰጣቸው።+ +25 ሰዎች የኃያላንን*+ ምግብ በሉ፤እስኪጠግቡ ድረስ እንዲበሉ በቂ ምግብ አቀረበላቸው።+ +26 የምሥራቁን ነፋስ በሰማይ አስነሳ፤በኃይሉም የደቡብ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ።+ +27 ሥጋንም እንደ አፈር፣ወፎችንም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አዘነበላቸው። +28 በሰፈሩ መካከል፣በድንኳኖቹም ሁሉ ዙሪያ እንዲወድቁ አደረገ። +29 እነሱም በሉ፤ ከልክ በላይም ጠገቡ፤የተመኙትን ነገር ሰጣቸው።+ +30 ሆኖም ምኞታቸውን ሙሉ በሙሉ ከማርካታቸው በፊት፣ምግባቸው ገና በአፋቸው ውስጥ እያለ +31 የአምላክ ቁጣ በእነሱ ላይ ነደደ።+ ኃያላን ሰዎቻቸውን ገደለ፤+የእስራኤልን ወጣቶች ጣለ። +32 ይህም ሆኖ በኃጢአታቸው ገፉበት፤+አስደናቂ በሆኑ ሥራዎቹም አላመኑም።+ +33 ስለዚህ ዘመናቸው እንደ እስትንፋስ እንዲያበቃ፣+ዕድሜያቸውም በድንገተኛ ሽብር እንዲያከትም አደረገ። +34 ሆኖም በገደላቸው ቁጥር እሱን ይሹ ነበር፤+ተመልሰው አምላክን ይፈልጉ ነበር፤ +35 ይህን የሚያደርጉት አምላክ ዓለታቸው እንደሆነ፣+ልዑሉ አምላክም እንደሚዋጃቸው* በማስታወስ ነበር።+ +36 እነሱ ግን በአፋቸው ሊያታልሉት ሞከሩ፤በምላሳቸውም ዋሹት። +37 ልባቸው ለእሱ የጸና አልነበረም፤+ለቃል ኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም።+ +38 እሱ ግን መሐሪ ነው፤+በደላቸውን ይቅር ይል* ነበር፤ ደግሞም አላጠፋቸውም።+ ቁጣውን ሁሉ ከመቀስቀስ ይልቅብዙ ጊዜ ስሜቱን ይገታ ነበር።+ +39 ነፍሶ ዳግመኛ የማይመለስ ነፋስ፣*ሥጋ መሆናቸውንም አስታውሷልና።+ +40 በምድረ በዳ ስንት ጊዜ በእሱ ላይ ዓመፁ!+በበረሃ ሳሉም ብዙ ጊዜ ስሜቱን ጎዱት!+ +41 ደግመው ደጋግመው አምላክን ተፈታተኑት፤+የእስራኤልንም ቅዱስ እጅግ አሳዘኑት።* +42 እነሱን ከጠላት የታደገበትን* ቀን፣ኃይሉንም* አላስታወሱም፤+ +43 በግብፅ አስደናቂ ምልክቶችን፣በጾዓን ምድርም ተአምራቱን እንዴት እንዳሳየ አላሰቡም፤+ +44 እንዲሁም ከጅረቶቻቸው መጠጣት እንዳይችሉየአባይን የመስኖ ቦዮች እንዴት ወደ ደም እንደለወጠ ዘነጉ።+ +45 ይበሏቸው ዘንድ የተናካሽ ዝንቦችን መንጋ ሰደደባቸው፤+ያጠፏቸውም ዘንድ እንቁራሪቶችን ላከባቸው።+ +46 ሰብላቸውን ለማይጠግብ አንበጣ፣የድካማቸውን ፍሬ ለአንበጣ መንጋ ሰጠ።+ +47 የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣የሾላ ዛፎቻቸውንም በበረዶ ድንጋይ አጠፋ።+ +48 የጋማ ከብቶቻቸውን ለበረዶ፣+መንጎቻቸውንም ለመብረቅ ብልጭታ* ዳረገ። +49 የሚነድ ቁጣውን፣ንዴቱን፣ መዓቱንና መቅሰፍቱንእንዲሁም ጥፋት የሚያመጡ የመላእክት ሠራዊትን ላከባቸው። +50 ለቁጣው መንገድ ጠረገ። ከሞት አላተረፋቸውም፤*ለቸነፈርም አሳልፎ ሰጣቸው። +51 በመጨረሻም የግብፅን በኩሮች በሙሉ፣በካም ድንኳኖች ውስጥ ከሚገኙትም መካከል የፍሬያቸው መጀመሪያ የሆኑትን መታ።+ +52 ከዚያም ሕዝቡን እንደ በጎች እንዲወጡ አደረገ፤በምድረ በዳም እንደ መንጋ መራቸው።+ +53 በአስተማማኝ ሁኔታ መራቸው፤አንዳች ፍርሃትም አልተሰማቸውም፤+ባሕሩም ጠላቶቻቸውን ዋጠ።+ +54 ደግሞም ቅዱስ ወደሆነው ም��ሩ፣ቀኝ እጁ የራሱ ወዳደረገው ወደዚህ ተራራማ ክልል አመጣቸው።+ +55 ብሔራቱን ከፊታቸው አባረረ፤+በመለኪያ ገመድም ርስት አከፋፈላቸው፤+የእስራኤልን ነገዶች በቤቶቻቸው እንዲኖሩ አደረገ።+ +56 እነሱ ግን ልዑሉን አምላክ ተገዳደሩት፤* በእሱም ላይ ዓመፁ፤+ማሳሰቢያዎቹን ችላ አሉ።+ +57 በተጨማሪም ጀርባቸውን ሰጡ፤ እንደ አባቶቻቸውም ከሃዲዎች ሆኑ።+ ጅማቱ እንደረገበ ደጋን እምነት የማይጣልባቸው ነበሩ።+ +58 ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎቻቸው ብዙ ጊዜ አሳዘኑት፤+በተቀረጹ ምስሎቻቸውም ለቁጣ* አነሳሱት።+ +59 አምላክ ሰምቶ በጣም ተቆጣ፤+በመሆኑም እስራኤልን እርግፍ አድርጎ ተወው። +60 በመጨረሻም በሴሎ የሚገኘውን የማደሪያ ድንኳን፣በሰው ልጆች መካከል ይኖርበት የነበረውን ድንኳን ተወው።+ +61 የብርታቱ ምልክት ተማርኮ እንዲወሰድ ፈቀደ፤ግርማ ሞገሱን በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ።+ +62 ሕዝቡን ለሰይፍ አሳልፎ ሰጠ፤+በርስቱም ላይ እጅግ ተቆጣ። +63 ወጣቶቹን እሳት በላቸው፤ለደናግሎቹም የሠርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም።* +64 ካህናቱ በሰይፍ ወደቁ፤+የገዛ መበለቶቻቸውም አላለቀሱላቸውም።+ +65 ከዚያም ይሖዋ፣ የወይን ጠጅ ስካሩ እንደለቀቀው ኃያል ሰውከእንቅልፍ እንደነቃ ሆኖ ተነሳ።+ +66 ጠላቶቹንም አሳዶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤+ለዘለቄታው ውርደት አከናነባቸው። +67 የዮሴፍን ድንኳን ናቀ፤የኤፍሬምን ነገድ አልመረጠም። +68 ከዚህ ይልቅ የይሁዳን ነገድ፣የሚወደውን የጽዮንን ተራራ+ መረጠ።+ +69 መቅደሱን እንደ ሰማያት ጽኑ አድርጎ ሠራው፤*+ለዘላለምም እንደመሠረታት ምድር አድርጎ ገነባው።+ +70 አገልጋዩን ዳዊትን መረጠ፤+ከበጎች ጉረኖ ወስዶ፣+ +71 የሚያጠቡ በጎችን ከመጠበቅም አንስቶበሕዝቡ በያዕቆብ፣ በርስቱም በእስራኤል ላይእረኛ እንዲሆን ሾመው።+ +72 እሱም በንጹሕ ልብ* ጠበቃቸው፤+በተካኑ እጆቹም መራቸው።+ +131 ይሖዋ ሆይ፣ ልቤ አይኩራራም፤ዓይኖቼም አይታበዩም፤+እጅግ ታላላቅ ነገሮችን ወይምከአቅሜ በላይ የሆኑ ነገሮችን አልመኝም።+ + 2 ይልቁንም እናቱ ላይ እንደተቀመጠ ጡት የጣለ ሕፃንነፍሴን አረጋጋኋት፤* ደግሞም ጸጥ አሰኘኋት።+ጡት እንደጣለ ሕፃን ረካሁ።* + 3 እስራኤል ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ።+ +111 ያህን አወድሱ!*+ א [አሌፍ] ቅኖች በተሰበሰቡበት ማኅበርና በጉባኤב [ቤት] ይሖዋን በሙሉ ልቤ አወድሰዋለሁ።+ + 2 የይሖዋ ሥራ ታላቅ ነው፤+ד [ዳሌት] በሥራው የሚደሰቱ ሰዎች ሁሉ ያጠኑታል።+ + 3 ሥራው ግርማና ውበት የተላበሰ ነው፤ו [ዋው] ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+ + 4 አስደናቂ ሥራዎቹ እንዲታወሱ ያደርጋል።+ ח [ኼት] ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ ነው።+ + 5 ለሚፈሩት ምግብ ይሰጣል።+ י [ዮድ] ቃል ኪዳኑን ለዘላለም ያስታውሳል።+ + 6 የብሔራትን ርስት በመስጠት፣+ל [ላሜድ] ኃያል ሥራዎቹን ለሕዝቡ ገልጧል። + 7 የእጆቹ ሥራዎች እውነትና ፍትሕ ናቸው፤+נ [ኑን] መመሪያዎቹ ሁሉ እምነት የሚጣልባቸው ናቸው።+ + 8 አሁንም ሆነ ለዘላለም፣ ምንጊዜም አስተማማኝ* ናቸው፤ע [አይን] በእውነትና በጽድቅ ላይ የተመሠረቱ ናቸው።+ + 9 ሕዝቡን ዋጀ።+ צ [ጻዴ] ቃል ኪዳኑ ለዘላለም እንዲጸና አዘዘ። ק [ኮፍ] ስሙ ቅዱስና እጅግ የሚፈራ ነው።+ +10 ይሖዋን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው።+ ש [ሺን] መመሪያዎቹን የሚጠብቁ* ሁሉ ጥሩ ማስተዋል አላቸው።+ ת [ታው] ውዳሴው ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። +143 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና አዳምጥ። እንደ ታማኝነትህና እንደ ጽድቅህ መጠን መልስልኝ። + 2 ሕያው የሆነ ማንኛውም ሰው በፊትህ ጻድቅ ሊሆን ስለማይችል፣+አገልጋይህን ለፍርድ አታቅርበው። + 3 ጠላት ያሳ���ደኛልና፤*ሕይወቴንም አድቆ ከአፈር ደባልቋታል። ከረጅም ጊዜ በፊት እንደሞቱ ሰዎች በጨለማ ቦታ እንድኖር አድርጎኛል። + 4 መንፈሴ* በውስጤ ዛለ፤+ልቤ በውስጤ ደነዘዘ።+ + 5 የጥንቱን ዘመን አስታውሳለሁ፤ባከናወንካቸው ነገሮች ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤+የእጆችህን ሥራ በታላቅ ጉጉት አውጠነጥናለሁ።* + 6 እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤እንደ ደረቅ ምድር አንተን ተጠማሁ።*+ (ሴላ) + 7 ይሖዋ ሆይ፣ ፈጥነህ መልስልኝ።+ጉልበቴ* ተሟጠጠ።+ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤+አለዚያ ወደ ጉድጓድ* እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ።+ + 8 በአንተ ታምኛለሁና፣በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን ልስማ። ፊቴን ወደ አንተ አዞራለሁና፣*ልሄድበት የሚገባውን መንገድ አሳውቀኝ።+ + 9 ይሖዋ ሆይ፣ ከጠላቶቼ ታደገኝ። የአንተን ጥበቃ እሻለሁ።+ +10 አንተ አምላኬ ስለሆንክ፣ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ።+ መንፈስህ ጥሩ ነው፤በደልዳላ መሬት* ይምራኝ። +11 ይሖዋ ሆይ፣ ለስምህ ስትል በሕይወት አቆየኝ። በጽድቅህ ከጭንቅ ታደገኝ።*+ +12 በታማኝ ፍቅርህ ጠላቶቼን አስወግዳቸው፤*+አገልጋይህ ነኝና፣+የሚያጎሳቁሉኝን* ሰዎች ሁሉ አጥፋቸው።+ +39 እኔ “በምላሴ ኃጢአት እንዳልፈጽም+አካሄዴን እጠብቃለሁ። ክፉ ሰው ከእኔ ጋር እስካለ ድረስአፌን ለመጠበቅ ልጓም አስገባለሁ”*+ አልኩ። + 2 ዱዳ ሆንኩ፤ ደግሞም ዝም አልኩ፤+መልካም ነገር ከመናገር እንኳ ታቀብኩ፤ይሁንና ሥቃዬ ከባድ ነበር።* + 3 ልቤ በውስጤ ነደደ።* ሳወጣ ሳወርድ* እንደ እሳት ነደድኩ። በዚህ ጊዜ በአንደበቴ እንዲህ አልኩ፦ + 4 “ይሖዋ ሆይ፣ መጨረሻዬ ምን እንደሚሆን፣የዕድሜዬም ርዝማኔ ምን ያህል እንደሆነ እንዳውቅ እርዳኝ፤+ይህም ሕይወቴ ምን ያህል አጭር እንደሆነ* አውቅ ዘንድ ነው። + 5 በእርግጥም ቀኖቼን ጥቂት* አደረግካቸው፤+የሕይወት ዘመኔም በፊትህ ከምንም አይቆጠርም።+ አዎ፣ ሰው ሁሉ ምንም ነገር የማይነካው ቢመስልም እንኳ እንደ እስትንፋስ ነው።+ (ሴላ) + 6 በእርግጥም ሰው ሁሉ የሚመላለሰው እንደ ጥላ ነው። ላይ ታች የሚለው* በከንቱ ነው። ማን እንደሚጠቀምበት ሳያውቅ ንብረት ያከማቻል።+ + 7 ይሖዋ ሆይ፣ ታዲያ ተስፋዬ ምንድን ነው? ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ። + 8 ከፈጸምኩት በደል ሁሉ አድነኝ።+ ሞኝ ሰው እንዲሳለቅብኝ አትፍቀድ። + 9 ዱዳ ሆንኩ፤ይህን ያደረግከው አንተ ስለሆንክ+አፌን መክፈት አልቻልኩም።+ +10 በእኔ ላይ ያመጣኸውን መቅሰፍት ከእኔ አርቅ። እጅህ ስለመታኝ ዛልኩ። +11 ሰውን በሠራው ስህተት የተነሳ በመቅጣት ታርመዋለህ፤+እንደ ውድ ሀብት የሚመለከታቸውን ነገሮች እንደ ብል ትበላበታለህ። በእርግጥም ሰው ሁሉ እንደ እስትንፋስ ነው።+ (ሴላ) +12 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ለእርዳታ የማሰማውን ጩኸት አዳምጥ።+ እንባዬን ችላ አትበል። እኔ በአንተ ዘንድ የባዕድ አገር ሰው ነኝና፤+እንደ አባቶቼ አልፌ የምሄድ ተጓዥ* ነኝ።+ +13 ከመሞቴና ከሕልውና ውጭ ከመሆኔ በፊት፣ፊቴ እንዲፈካ በክፉ ዓይን አትየኝ።” +110 ይሖዋ ጌታዬን “ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ+በቀኜ ተቀመጥ”+ አለው። + 2 ይሖዋ የኃይልህን በትር ከጽዮን ይዘረጋል፤ “በጠላቶችህ መካከል በድል አድራጊነት ግዛ”*+ ይላል። + 3 ወደ ጦርነት በምትዘምትበት ቀን* ሕዝብህ በገዛ ፈቃዱ ራሱን ያቀርባል።በቅድስና ተውበህ ሳለ፣ ከንጋት ማህፀን እንደወጣ ጤዛ ያለ የወጣቶች ሠራዊት ከጎንህ ይሰለፋል። + 4 ይሖዋ “እንደ መልከጼዴቅ፣+ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ!” ሲል ምሏል፤+ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም።* + 5 ይሖዋ በቀኝህ ይሆናል፤+በቁጣው ቀን ነገሥታትን ያደቃል።+ + 6 በብሔራት ላይ* የፍርድ እርምጃ ይወስዳል፤+ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል።+ ሰፊ የሆነውን አገር* የሚገዛውን መሪ* ያደቀዋል። + 7 እሱ* በመንገድ ዳር ካለው ጅረት ይጠጣል። በመሆኑም ራሱን ቀና ያደርጋል። +85 ይሖዋ ሆይ፣ ለምድርህ ሞገስ አሳይተሃል፤+የተማረኩትን የያዕቆብ ልጆች መልሰሃል።+ + 2 የሕዝብህን በደል ተውክ፤ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይቅር አልክ።*+ (ሴላ) + 3 ንዴትህን ሁሉ ገታህ፤ከብርቱ ቁጣህም ተመለስክ።+ + 4 የመዳናችን አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞ ሁኔታችን መልሰን፤*በእኛ የተነሳ ያደረብህን ቁጣም መልስ።+ + 5 በእኛ ላይ የምትቆጣው ለዘላለም ነው?+ ቁጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ይዘልቃል? + 6 ሕዝቦችህ በአንተ ሐሴት እንዲያደርጉ፣ዳግመኛ እንድናንሰራራ አታደርገንም?+ + 7 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህን አሳየን፤+ማዳንህንም ለግሰን። + 8 እውነተኛው አምላክ ይሖዋ የሚናገረውን እሰማለሁ፤እሱ ለሕዝቡና ለታማኝ አገልጋዮቹ ስለ ሰላም ይናገራልና፤+ብቻ እንደቀድሞው በራሳቸው ከልክ በላይ አይተማመኑ።+ + 9 ክብሩ በምድራችን እንዲኖር፣እሱን ለሚፈሩት ማዳኑ በእርግጥ ቅርብ ነው።+ +10 ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ይገናኛሉ፤ጽድቅና ሰላም ይሳሳማሉ።+ +11 ታማኝነት ከምድር ትበቅላለች፤ጽድቅም ከሰማያት ወደ ታች ይመለከታል።+ +12 አዎ፣ ይሖዋ መልካም ነገር* ይሰጣል፤+ምድራችንም ምርቷን ትሰጣለች።+ +13 ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤+ለእርምጃውም መንገድ ያዘጋጃል። +108 አምላክ ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው። በሁለንተናዬ እዘምራለሁ፤ ደግሞም አዜማለሁ።+ + 2 ባለ አውታር መሣሪያ ሆይ፣ አንተም በገና ሆይ፣+ ተነሱ። እኔም በማለዳ እነሳለሁ። + 3 ይሖዋ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አወድስሃለሁ፤በብሔራትም መካከል የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ። + 4 ታማኝ ፍቅርህ ታላቅ ነውና፤ እንደ ሰማያት ከፍ ያለ ነው፤+ታማኝነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነው። + 6 የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑበቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠኝ።+ + 7 አምላክ በቅድስናው* እንዲህ ብሏል፦ “ሐሴት አደርጋለሁ፤ ሴኬምን ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤+የሱኮትንም ሸለቆ* አከፋፍላለሁ።+ + 8 ጊልያድም+ ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤*+ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው።+ + 9 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው።+ በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ።+ በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”+ +10 ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል?+ +11 አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም።+ +12 ከጭንቅ እንድንገላገል እርዳን፤+የሰው ማዳን ከንቱ ነውና።+ +13 አምላክ ኃይል ይሰጠናል፤+ጠላቶቻችንንም ይረጋግጣቸዋል።+ +129 “ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር”፤+ እስራኤል እንዲህ ይበል፦ + 2 “ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር፤+ሆኖም ሊያሸንፉኝ አልቻሉም።+ + 3 አራሾች ጀርባዬን አረሱት፤+ትልማቸውንም አስረዘሙት።”* + 4 ይሖዋ ግን ጻድቅ ነው፤+የክፉዎችን ገመድ በጣጥሷል።+ + 5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ኀፍረት ይከናነባሉ፤ ተዋርደውም ወደኋላቸው ይመለሳሉ።+ + 6 ከመነቀሉ በፊት እንደሚጠወልግ፣በጣሪያ ላይ እንደበቀለ ሣር ይሆናሉ፤ + 7 እንዲህ ዓይነቱ ሣር የአጫጁን እጅ፣ነዶ የሚሰበስበውንም ሰው ክንዶች ሊሞላ አይችልም። + 8 በዚያ የሚያልፉ ሰዎች “የይሖዋ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤በይሖዋ ስም እንባርካችኋለን” አይሉም። +55 አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+ምሕረት እንድታደርግልኝ የማቀርበውንም ልመና ቸል አትበል።*+ + 2 ትኩረት ስጠኝ፤ መልስልኝም።+ ያሳሰበኝ ጉዳይ እረፍት ነስቶኛል፤+ደግሞም በጣም ተጨንቄአለሁ፤ + 3 ይህም ጠላት ከሚናገረው ቃል፣ክፉውም ��ው ከሚያሳድረው ጫና የተነሳ ነው። እነሱ በእኔ ላይ መከራ ይከምራሉና፤በቁጣም ተሞልተው በጥላቻ ዓይን ያዩኛል።+ + 4 ልቤ በውስጤ በጣም ተጨነቀ፤+የሞት ፍርሃትም ዋጠኝ።+ + 5 ፍርሃት አደረብኝ፤ ደግሞም ተንቀጠቀጥኩ፤ብርክም ያዘኝ። + 6 እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “ምነው እንደ ርግብ ክንፍ በኖረኝ! በርሬ ሄጄ ያለስጋት በኖርኩ ነበር። + 7 እነሆ፣ ወደ ሩቅ ቦታ በበረርኩ፣+ በምድረ በዳም በቆየሁ ነበር።+ (ሴላ) + 8 ከአውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼመጠለያ ወደማገኝበት ቦታ ፈጥኜ በሄድኩ ነበር።” + 9 ይሖዋ ሆይ፣ ግራ አጋባቸው፤ ዕቅዳቸውንም አጨናግፍ፤+በከተማዋ ውስጥ ዓመፅና ብጥብጥ አይቻለሁና። +10 ቅጥሮቿ ላይ ወጥተው ቀንና ሌሊት ይዞራሉ፤በውስጧም ተንኮልና መከራ አለ።+ +11 ጥፋት በመካከሏ አለ፤ጭቆናና ማታለል ከአደባባይዋ ፈጽሞ አይጠፉም።+ +12 የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤+ቢሆንማ ኖሮ በቻልኩት ነበር። በእኔ ላይ የተነሳው ባላጋራ አይደለም፤ቢሆንማ ኖሮ ከእሱ በተሸሸግኩ ነበር። +13 ነገር ግን ይህን ያደረግከው እንደ እኔው ሰው* የሆንከው አንተ ነህ፤+በሚገባ የማውቅህ የገዛ ጓደኛዬ ነህ።+ +14 በመካከላችን የጠበቀ ወዳጅነት ነበር፤ከብዙ ሕዝብ ጋር ወደ አምላክ ቤት አብረን እንሄድ ነበር። +15 ጥፋት በድንገት ይምጣባቸው!+ በሕይወት ሳሉ ወደ መቃብር* ይውረዱ፤ክፋት በመካከላቸውና በውስጣቸው ያድራልና። +16 እኔ በበኩሌ አምላክን እጣራለሁ፤ይሖዋም ያድነኛል።+ +17 በማታ፣ በጠዋትና በቀትር እጨነቃለሁ፤ ደግሞም እቃትታለሁ፤*+እሱም ድምፄን ይሰማል።+ +18 በእኔ ላይ ጦርነት ከከፈቱ ሰዎች ይታደገኛል፤* ሰላም እንዳገኝም ያደርጋል፤እጅግ ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ ተነስተዋልና።+ +19 ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው አምላክ+ ይሰማል፤ምላሽም ይሰጣቸዋል።+ (ሴላ) አምላክን የማይፈሩት እነዚህ ሰዎች+ለመለወጥ ፈቃደኞች አይደሉም። +20 ከእሱ* ጋር ሰላም በነበራቸው ሰዎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል፤+የገባውን ቃል ኪዳን አፍርሷል።+ +21 የሚናገራቸው ቃላት ከቅቤ ይልቅ የለሰለሱ ናቸው፤+በልቡ ውስጥ ግን ጠብ አለ። ቃሎቹ ከዘይት ይልቅ የለሰለሱ ቢሆኑምእንደተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።+ +22 ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል፤+እሱም ይደግፍሃል።+ ጻድቁ እንዲወድቅ* ፈጽሞ አይፈቅድም።+ +23 አምላክ ሆይ፣ አንተ ግን ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ታወርዳቸዋለህ።+ የደም ዕዳ ያለባቸውና አታላይ የሆኑ ሰዎች የዕድሜያቸውን ግማሽ እንኳ አይኖሩም።+ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ። +98 ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+እሱ አስደናቂ ነገሮች አድርጓልና።+ ቀኝ እጁ፣ አዎ ቅዱስ ክንዱ መዳን አስገኝቷል።*+ + 2 ይሖዋ ማዳኑ እንዲታወቅ አድርጓል፤+በብሔራት ፊት ጽድቁን ገልጧል።+ + 3 ለእስራኤል ቤት ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ለማሳየት የገባውን ቃል አስታውሷል።+ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን* አይተዋል።+ + 4 ምድር ሁሉ፣ ለይሖዋ በድል አድራጊነት እልል በሉ። ደስ ይበላችሁ፤ ደግሞም እልል በሉ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩ።+ + 5 ለይሖዋ በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤በበገናና ደስ በሚል ዜማ ዘምሩለት። + 6 በእምቢልታና በቀንደ መለከት ድምፅ+በንጉሡ በይሖዋ ፊት በድል አድራጊነት እልል በሉ። + 7 ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ፣መሬትና* በላይዋ የሚኖር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰሙ። + 8 ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፤ተራሮችም በአንድነት በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ፤+ + 9 እሱ በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነውና።* በዓለም* ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በትክክል ይፈርዳል።+ +17 ጠብ እያለ ትልቅ ድግስ ከተደገሰበት* ቤት ይልቅሰላም* ባለበት ደረቅ የዳቦ ቁራሽ መብላት ይሻላል።+ + 2 ጥልቅ ��ስተዋል ያለው አገልጋይ አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ከወንድማማቾቹ እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል። + 3 ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤+ልብን የሚመረምር ግን ይሖዋ ነው።+ + 4 ክፉ ሰው ጎጂ የሆነን ንግግር በትኩረት ያዳምጣል፤አታላይ ሰውም ተንኮለኛ የሆነን አንደበት ያዳምጣል።+ + 5 በድሃ የሚያፌዝ ሁሉ ፈጣሪውን ይሳደባል፤+በሌላው ሰው ላይ በደረሰው መከራ የሚደሰትም ሁሉ ከቅጣት አያመልጥም።+ + 6 የልጅ ልጆች* የሽማግሌዎች ዘውድ ናቸው፤አባቶችም * ለወንዶች ልጆቻቸው* ክብር ናቸው። + 7 ለሞኝ ሰው ቀና* ንግግር አይስማማውም።+ ለገዢ* ደግሞ ሐሰተኛ ንግግር ጨርሶ አይሆነውም!+ + 8 ስጦታ ለባለቤቱ እንደከበረ ድንጋይ* ነው፤+በሄደበት ሁሉ ስኬት ያስገኝለታል።+ + 9 በደልን ይቅር የሚል* ሁሉ ፍቅርን ይሻል፤+አንድን ጉዳይ ደጋግሞ የሚያወራ ግን የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል።+ +10 ሞኝን ሰው መቶ ጊዜ ከመግረፍ ይልቅ+ማስተዋል ያለውን ሰው አንድ ጊዜ መገሠጽ የተሻለ ውጤት ያስገኛል።+ +11 ክፉ ሰው የሚሻው ዓመፅን ብቻ ነው፤ሆኖም እሱን እንዲቀጣ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።+ +12 የቂል ሥራ እየሠራ ካለ ሞኝ ሰው ጋር ከመገናኘት ይልቅግልገሎቿን ካጣች ድብ ጋር መገናኘት ይሻላል።+ +13 ማንኛውም ሰው ለመልካም ነገር ክፉ የሚመልስ ከሆነክፉ ነገር ከቤቱ አይጠፋም።+ +14 ጠብ መጫር ግድብን ከመሸንቆር* ተለይቶ አይታይም፤ስለዚህ ጥል ከመነሳቱ በፊት ከአካባቢው ራቅ።+ +15 ክፉውን ነፃ የሚያደርግ፣ በጻድቁም ላይ የሚፈርድ፣+ሁለቱም በይሖዋ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው። +16 ሞኝ ሰው ጥበብን የራሱ የሚያደርግበት ልብ* ከሌለውጥበብ የሚያገኝበት መንገድ ቢኖር ምን ይጠቅማል?+ +17 እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤+ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።+ +18 ማስተዋል የጎደለው ሰውበባልንጀራው ፊት እጅ በመጨበጥ ዋስ* ለመሆን ይስማማል።+ +19 ጠብ የሚወድ ሁሉ በደልን ይወዳል።+ በሩን ወደ ላይ አስረዝሞ የሚሠራ ጥፋትን ይጋብዛል።+ +20 ልቡ ጠማማ የሆነ አይሳካለትም፤*+በምላሱም የሚያታልል ጥፋት ይደርስበታል። +21 የሞኝ ልጅ አባት ሐዘን ላይ ይወድቃል፤የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ልጅ የወለደም ደስታ አይኖረውም።+ +22 ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው፤*+የተደቆሰ መንፈስ ግን ኃይል ያሟጥጣል።*+ +23 ክፉ ሰው ፍትሕን ለማዛባትበስውር* ጉቦ ይቀበላል።+ +24 ጥልቅ ግንዛቤ ባለው ሰው ፊት ጥበብ ትገኛለች፤የሞኝ ሰው ዓይን ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታል።+ +25 ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤እናቱም እንድትመረር ያደርጋል።+ +26 ጻድቁን መቅጣት* መልካም አይደለም። የተከበሩ ሰዎችንም መግረፍ ትክክል አይደለም። +27 አዋቂ ሰው ንግግሩ ቁጥብ ነው፤+ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰውም የተረጋጋ ነው።*+ +28 ሞኝ ሰው እንኳ ዝም ሲል እንደ ጥበበኛ ይቆጠራል፤ከንፈሮቹንም የሚዘጋ ማስተዋል እንዳለው ተደርጎ ይታያል። +30 የያቄ ልጅ አጉር ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለዑካል የተናገራቸው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘሉ ቃላት። + 2 እኔ ከማንም የባሰ አላዋቂ ነኝ፤+ሰው ሊኖረው የሚገባው ማስተዋልም የለኝም። + 3 ጥበብን አልተማርኩም፤እጅግ ቅዱስ የሆነው አምላክ እውቀትም የለኝም። + 4 ወደ ሰማይ የወጣ፣ ከዚያም የወረደ ማን ነው?+ ነፋስን በእፍኙ ሰብስቦ የያዘ ማን ነው? ውኃን በልብሱ የጠቀለለ ማን ነው?+ የምድርን ዳርቻዎች ሁሉ የወሰነ* ማን ነው?+ ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው? ታውቅ እንደሆነ ንገረኝ። + 5 የአምላክ ቃል ሁሉ የነጠረ ነው።+ እሱ፣ መጠጊያቸው ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው።+ + 6 በቃሉ ላይ ምንም አትጨምር፤+አለዚያ ይወቅስሃል፤ሐሰተኛም ሆነህ ��ገኛለህ። + 7 ሁለት ነገር እንድታደርግልኝ እለምንሃለሁ። እነሱንም ከመሞቴ በፊት አትንፈገኝ። + 8 ውሸትንና ሐሰትን ከእኔ አርቅ።+ ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ። ብቻ የሚያስፈልገኝን ቀለብ አታሳጣኝ፤+ + 9 አለዚያ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ከዚያም “ይሖዋ ማን ነው?” እላለሁ፤+ ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ* አትፍቀድ። +10 እንዳይረግምህና በደለኛ ሆነህ እንዳትገኝበጌታው ፊት የአገልጋዩን ስም አታጥፋ።+ +11 አባቱን የሚረግም፣እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ።+ +12 በገዛ ዓይኑ ፊት ንጹሕ የሆነ፣+ሆኖም ከቆሻሻው* ያልነጻ ትውልድ አለ። +13 እጅግ ትዕቢተኛ ዓይን ያለው ትውልድ አለ፤ዓይኖቹም በታላቅ እብሪት ይመለከታሉ!+ +14 ጥርሱ ሰይፍ፣መንገጭላው ደግሞ ቢላ የሆነ ትውልድ አለ፤በምድር ላይ ያሉ ምስኪኖችን፣በሰው ዘር መካከል ያሉ ድሆችንም ይውጣል።+ +15 አልቅቶች “ስጡን! ስጡን!” እያሉ የሚጮኹ ሁለት ሴቶች ልጆች አሏቸው። ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፤ደግሞም “በቃኝ!” የማያውቁ አራት ነገሮች አሉ። +16 እነሱም መቃብር፣*+ መሃን የሆነ ማህፀን፣ውኃ የተጠማ መሬትእንዲሁም “በቃኝ!” የማይል እሳት ናቸው። +17 በአባቷ ላይ የምታፌዝን፣ የእናቷንም ትእዛዝ የምትንቅን+ ዓይንየሸለቆ* ቁራዎች ይጎጠጉጧታል፤የንስር ጫጩቶችም ይበሏታል።+ +18 ከመረዳት አቅሜ በላይ የሆኑ* ሦስት ነገሮች አሉ፤የማልገነዘባቸውም አራት ነገሮች አሉ፦ +19 ንስር በሰማያት የሚበርበት መንገድ፣እባብ በዓለት ላይ የሚሄድበት መንገድ፣መርከብ በባሕር ላይ የሚጓዝበት መንገድ፣ሰውም ከሴት ልጅ ጋር የሚሄድበት መንገድ ናቸው። +20 የአመንዝራ ሴት መንገድ ይህ ነው፦ በልታ አፏን ከጠራረገች በኋላ“ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም” ትላለች።+ +21 ምድርን የሚያናውጡ ሦስት ነገሮች አሉ፤መታገሥ የማትችላቸውም አራት ነገሮች አሉ፦ +22 ባሪያ ንጉሥ ሆኖ ሲገዛ፣+ሞኝ በልቶ ሲጠግብ፣ +23 የተጠላች* ሴት ባል ስታገኝ፣ሴት አገልጋይም የእመቤቷን ቦታ ስትወስድ* የሚከሰቱ ሁኔታዎች ናቸው።+ +24 በምድር ላይ በጣም ትናንሽ የሆኑ አራት ፍጥረታት አሉ፤ሆኖም በደመ ነፍስ ጥበበኞች* ናቸው፦+ +25 ጉንዳኖች ኃይል የሌላቸው ፍጥረታት* ናቸው፤ይሁንና ምግባቸውን በበጋ ያዘጋጃሉ።+ +26 ሽኮኮዎች+ ኃያላን ፍጥረታት* አይደሉም፤ነገር ግን መኖሪያቸውን በቋጥኞች ውስጥ ያደርጋሉ።+ +27 አንበጦች+ ንጉሥ የላቸውም፤ሆኖም ሁሉም በሰልፍ ወደ ፊት* ይጓዛሉ።+ +28 እንሽላሊት*+ በእግሮቿ ቆንጥጣ ትይዛለች፤ወደ ንጉሥ ቤተ መንግሥትም ትገባለች። +29 ግርማ የተላበሰ አረማመድ ያላቸው ሦስት ፍጥረታት አሉ፤አዎ፣ እየተጎማለሉ የሚሄዱ አራት ፍጥረታት አሉ፦ +30 ከአራዊት ሁሉ ኃያል የሆነውናማንንም አይቶ ወደ ኋላ የማይመለሰው አንበሳ፣+ +31 አዳኝ ውሻ፣ አውራ ፍየል፣እንዲሁም በሠራዊቱ የታጀበ ንጉሥ ናቸው። +32 በሞኝነት ራስህን ከፍ ከፍ ካደረግክ፣+ወይም እንዲህ ለማድረግ ካሰብክእጅህን በአፍህ ላይ አድርግ።+ +33 ወተት ሲናጥ ቅቤ እንደሚወጣው፣አፍንጫም ሲጨመቅ እንደሚደማ ሁሉቁጣን ማነሳሳትም ጠብ ያስከትላል።+ +31 የንጉሥ ልሙኤል ቃል፤ እናቱ እሱን ለማስተማር የተናገረችው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘለ መልእክት፦+ + 2 ልጄ ሆይ፣ ምን ልበልህ?የማህፀኔ ልጅ ሆይ፣ ምን ልበልህ?የስእለቴ ልጅ ሆይ፣ ምን ልበልህ?+ + 3 ጉልበትህን ለሴቶች አትስጥ፤+ነገሥታትንም ለጥፋት የሚዳርግ መንገድ አትከተል።+ + 4 ልሙኤል ሆይ፣ ነገሥታት የወይን ጠጅ መጠጣት የለባቸውም፤አዎ፣ ነገሥታት ይህን ማድረግ አይገባቸውም፤ገዢዎችም “መጠጤ የት አለ?” ሊሉ አይገባም።+ + 5 አለዚያ ጠጥተው የተደነገገውን ሕ�� ይረሳሉ፤የችግረኞችንም መብት ይጥሳሉ። + 6 ሊጠፉ ለተቃረቡ ሰዎች መጠጥ፣+ከባድ ጭንቀት ለደረሰባቸውም* የወይን ጠጅ ስጧቸው።+ + 7 ጠጥተው ድህነታቸውን ይርሱ፤ችግራቸውንም ዳግመኛ አያስታውሱ። + 8 ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት አንተ ተናገርላቸው፤ሊጠፉ ለተቃረቡት ሰዎች ሁሉ መብት ተሟገት።+ + 9 ተናገር፤ በጽድቅም ፍረድ፤ለችግረኛውና ለድሃው መብት ጥብቅና ቁም።*+ +10 ባለሙያ ሚስትን* ማን ሊያገኛት ይችላል?+ ዋጋዋ ከዛጎል* እጅግ ይበልጣል። +11 ባሏ ከልቡ ይታመንባታል፤አንዳችም ጠቃሚ ነገር አይጎድልበትም። +12 በሕይወቷ ዘመን ሁሉመልካም ነገር ታደርግለታለች እንጂ ክፉ ነገር አታደርግበትም። +13 ሱፍና በፍታ ታመጣለች፤በእጆቿ መሥራት ያስደስታታል።+ +14 እሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤+ምግቧን ከሩቅ ቦታ ታመጣለች። +15 ገና ሳይነጋም ትነሳለች፤ለቤተሰቦቿም ምግባቸውን፣ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች።+ +16 በጥሞና ካሰበችበት በኋላ መሬት ትገዛለች፤በራሷ ጥረት* ወይን ትተክላለች። +17 ወገቧን ታጥቃ ለሥራ ትነሳለች፤*+ክንዶቿንም ታበረታለች። +18 ንግዷ ትርፋማ እንደሆነ ታስተውላለች፤መብራቷ በሌሊት አይጠፋም። +19 እጆቿ አመልማሎ የያዘ ዘንግ ይጨብጣሉ፤ጣቶቿም እንዝርት ይይዛሉ።*+ +20 እጆቿን ለተቸገረ ሰው ትዘረጋለች፤ለድሃውም እጇን ትከፍታለች።+ +21 ቤተሰቦቿ ሁሉ የሚያሞቅ* ልብስ ስለሚለብሱበበረዶ ወቅት እንኳ አትሰጋም። +22 ለራሷ የአልጋ ልብስ ትሠራለች። ልብሷ ከበፍታና ከሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው። +23 ባሏ ከአገሩ ሽማግሌዎች ጋር በሚቀመጥበት በከተማዋ በሮች+በሰዎች ዘንድ በሰፊው የታወቀ ነው። +24 የበፍታ ልብሶች እየሠራች* ትሸጣለች፤ለነጋዴዎችም ቀበቶ ታስረክባለች። +25 ብርታትንና ግርማን ትጎናጸፋለች፤የወደፊቱንም ጊዜ በልበ ሙሉነት ትጠባበቃለች።* +26 አፏን በጥበብ ትከፍታለች፤+የደግነት ሕግም* በአንደበቷ አለ። +27 የቤተሰቧን እንቅስቃሴ በደንብ ትከታተላለች፤የስንፍናንም ምግብ አትበላም።+ +28 ልጆቿ ተነስተው ደስተኛ ይሏታል፤ባሏ ተነስቶ ያወድሳታል። +29 ባለሙያ* የሆኑ ብዙ ሴቶች አሉ፤አንቺ ግን፣ አዎ አንቺ ከሁሉም ትበልጫለሽ። +30 ውበት ሐሰት፣ ቁንጅናም አላፊ* ነው፤+ይሖዋን የምትፈራ ሴት ግን ትመሰገናለች።+ +31 ላከናወነችው ነገር ሽልማት ስጧት፤*+ሥራዎቿም በከተማዋ በሮች ያስመስግኗት።+ +18 ራሱን የሚያገል ሰው ሁሉ የራስ ወዳድነት ምኞቱን ያሳድዳል፤ጥበብንም* ሁሉ ይቃወማል።* + 2 ሞኝ ሰው ማስተዋል አያስደስተውም፤ይልቁንም በልቡ ያለውን ሐሳብ ይገልጣል።+ + 3 ክፉ ሰው ሲመጣ ንቀትም ይመጣል፤ከውርደትም ጋር ኀፍረት ይመጣል።+ + 4 ከሰው አፍ የሚወጣ ቃል ጥልቅ ውኃ ነው።+ የጥበብ ምንጭ የሚንዶለዶል ጅረት ነው። + 5 ለክፉ ሰው ማድላት፣ጻድቁንም ፍትሕ መንፈግ+ መልካም አይደለም።+ + 6 የሞኝ ሰው ንግግር ጠብ ያስነሳል፤+አፉም ዱላ ይጋብዛል።+ + 7 የሞኝ አንደበት መጥፊያው ነው፤+ከንፈሮቹም ለሕይወቱ* ወጥመድ ናቸው። + 8 ስም አጥፊ የሚናገረው ቃል ጣፋጭ እንደሆነ ቁራሽ ምግብ ነው፤*+በፍጥነት ተውጦ በቀጥታ ወደ ሆድ ይገባል።+ + 9 በሥራው ታካች የሆነ ሰው ሁሉ፣የአጥፊ ወንድም ነው።+ +10 የይሖዋ ስም ጽኑ ግንብ ነው።+ ጻድቅ ወደዚያ በመሮጥ ጥበቃ ያገኛል።*+ +11 የባለጸጋ ሰው ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው፤በሐሳቡም ጥበቃ እንደሚያስገኝ ግንብ አድርጎ ይመለከተዋል።+ +12 ሰው ለውድቀት ከመዳረጉ በፊት ልቡ ይታበያል፤+ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።+ +13 እውነታውን ከመስማቱ በፊት መልስ የሚሰጥ ሰው፣ሞኝነት ይሆንበታል፤ ውርደትም ይከናነባል።+ +14 ጠንካራ መንፈስ ያለው ሰው ሕመሙን መቋቋም ይችላል፤+የተደቆሰን መንፈስ* ግን ማን ሊቋቋም ይችላል?+ +15 የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፤+የጥበበኛም ጆሮ እውቀትን ለማግኘት ይጥራል። +16 ስጦታ ለሰጪው መንገዱን ይከፍትለታል፤+በታላላቅ ሰዎችም ፊት መቅረብ ያስችለዋል። +17 ክሱን አስቀድሞ ያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤+ይህም ሌላው ወገን መጥቶ እስኪመረምረው ድረስ ነው።+ +18 ዕጣ መጣል ጭቅጭቅ እንዲያበቃ ያደርጋል፤+ኃይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል። +19 የተበደለ ወንድም ከተመሸገች ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤+እንደ ግንብ በሮች መቀርቀሪያም የጠነከረ ጠብ አለ።+ +20 ሰው በአፉ ፍሬ ሆዱ ይሞላል፤+ከንፈሩም በሚያስገኘው ምርት ይረካል። +21 አንደበት የሞትና የሕይወት ኃይል አላት፤+ሊጠቀምባት የሚወድ ፍሬዋን ይበላል።+ +22 ጥሩ ሚስት ያገኘ ጥሩ ነገር አግኝቷል፤+የይሖዋንም ሞገስ* ያገኛል።+ +23 ድሃ እየተለማመጠ ይናገራል፤ሀብታም ግን በኃይለ ቃል ይመልሳል። +24 እርስ በርስ ከመጠፋፋት ወደኋላ የማይሉ ጓደኛሞች አሉ፤+ነገር ግን ከወንድም ይበልጥ የሚቀርብ ጓደኛ አለ።+ +23 ከንጉሥ ጋር ለመመገብ ስትቀመጥ፣በፊትህ ያለውን በሚገባ አስተውል፤ + 2 ለመብላት ብትቋምጥ* እንኳበጉሮሮህ ላይ ቢላ አስቀምጥ።* + 3 የእሱ ጣፋጭ ምግብ አያስጎምጅህ፤ምግቡ አታላይ ነውና። + 4 ሀብት ለማግኘት አትልፋ።+ ይህን ትተህ በማስተዋል ተመላለስ።* + 5 ዓይንህን ስትጥልበት በዚያ አታገኘውም፤+የንስር ዓይነት ክንፎች አውጥቶ ወደ ሰማይ ይበርራልና።+ + 6 የስስታምን* ምግብ አትብላ፤ጣፋጭ ምግቡ አያስጎምጅህ፤ + 7 እሱ ሒሳብ እንደሚይዝ* ሰው ነውና። “ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ የሚናገረው ግን ከልቡ አይደለም።* + 8 የበላሃትን ቁራሽ ምግብ ታስመልሳለህ፤የተናገርካቸው የምስጋና ቃላትም ከንቱ ይሆናሉ። + 9 የምትናገራቸውን ጥበብ ያዘሉ ቃላት ስለሚንቅ+ለሞኝ ሰው ምንም አትናገር።+ +10 የጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ፤+ደግሞም አባት የሌላቸውን ልጆች መሬት አትያዝ። +11 የሚከራከርላቸው* ብርቱ ነውና፤እሱ ራሱ ከአንተ ጋር ይሟገትላቸዋል።+ +12 ልብህን ለተግሣጽ፣ጆሮህንም ለእውቀት ቃል ስጥ። +13 ልጅን* ከመገሠጽ ወደኋላ አትበል።+ በበትር ብትመታው አይሞትም። +14 ከመቃብር* ታድነው ዘንድ*በበትር ምታው። +15 ልጄ ሆይ፣ ልብህ ጥበበኛ ቢሆን፣የእኔ ልብ ሐሴት ያደርጋል።+ +16 ከንፈሮችህ ትክክል የሆነውን ሲናገሩውስጤ ደስ ይለዋል።* +17 ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤+ከዚህ ይልቅ ቀኑን ሙሉ ይሖዋን በመፍራት ተመላለስ፤+ +18 እንዲህ ብታደርግ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤+ተስፋህም ከንቱ አይሆንም። +19 ልጄ ሆይ፣ አዳምጥ፤ ጥበበኛም ሁን፤ልብህንም በትክክለኛው መንገድ ምራ። +20 ብዙ የወይን ጠጅ እንደሚጠጡ፣+ሥጋም ያለልክ እንደሚሰለቅጡ ሰዎች አትሁን፤+ +21 ሰካራምና ሆዳም ይደኸያሉና፤+ድብታ ሰውን የተቦጫጨቀ ልብስ ያስለብሰዋል። +22 የወለደህን አባትህን ስማ፤እናትህንም ስላረጀች አትናቃት።+ +23 እውነትንና ጥበብን፣ ተግሣጽንና ማስተዋልን ግዛ፤*+ፈጽሞም አትሽጣቸው።+ +24 የጻድቅ አባት ደስ ይለዋል፤ጥበበኛ ልጅ የወለደ ሁሉ በልጁ ሐሴት ያደርጋል። +25 አባትህና እናትህ ሐሴት ያደርጋሉ፤አንተን የወለደችም ደስ ይላታል። +26 ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ፤ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።+ +27 ዝሙት አዳሪ ጥልቅ ጉድጓድ፣ባለጌ* ሴትም ጠባብ ጉድጓድ ናትና።+ +28 እንደ ዘራፊ ታደባለች፤+ታማኝ ያልሆኑ ወንዶችን ቁጥር ታበዛለች። +29 ዋይታ የማን ነው? ጭንቀት የማን ነው? ጠብ የማን ነው? እሮሮ የማን ነው? ያለምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን ቅላት* የማን ነው? +30 ይህ ሁሉ የሚደርሰው የወ���ን ጠጅ በመጠጣት ረጅም ጊዜ በሚያሳልፉ፣+የተደባለቀም ወይን ጠጅ ፍለጋ በሚዞሩ* ሰዎች ላይ ነው። +31 በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣እየጣፈጠም ሲወርድ በወይን ጠጅ ቅላት ዓይንህ አይማረክ፤ +32 በመጨረሻ እንደ እባብ ይናደፋልና፤እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል። +33 ዓይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤ልብህም ጠማማ ነገር ይናገራል።+ +34 በባሕር መካከል እንደተኛ፣በመርከብ ምሰሶም ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ። +35 እንዲህ ትላለህ፦ “መቱኝ፤ ሆኖም አልተሰማኝም።* ደበደቡኝ፤ ሆኖም አልታወቀኝም። ተጨማሪ መጠጥ እጠጣ ዘንድ* የምነቃው መቼ ነው?”+ +19 ሞኝ ከመሆንና ውሸት ከመናገርድሃ ሆኖ ንጹሕ አቋምን* ጠብቆ መመላለስ ይሻላል።+ + 2 እውቀት የሌለው ሰው* ጥሩ አይደለም፤+ችኩል* ሰውም ኃጢአት ይሠራል። + 3 የሰውን መንገድ የሚያጣምምበት የገዛ ሞኝነቱ ነው፤ልቡም በይሖዋ ላይ ይቆጣል። + 4 ሀብት ብዙ ወዳጆችን ይስባል፤ድሃን ግን ጓደኛው እንኳ ይተወዋል።+ + 5 ሐሰተኛ ምሥክር መቀጣቱ አይቀርም፤+ባወራ ቁጥር የሚዋሽም ከቅጣት አያመልጥም።+ + 6 ብዙዎች በተከበረ ሰው* ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ይጥራሉ፤ስጦታ ከሚሰጥ ሰው ጋር ደግሞ ሁሉም ይወዳጃል። + 7 ድሃን ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፤+ጓደኞቹማ ምን ያህል ይርቁት!+ እየተከታተለ ሊለማመጣቸው ይሞክራል፤ ምላሽ የሚሰጠው ግን የለም። + 8 ማስተዋል* የሚያገኝ ሰው ሁሉ ራሱን* ይወዳል።+ ጥልቅ ግንዛቤን እንደ ውድ ሀብት አድርጎ የሚመለከት ሁሉ ይሳካለታል።*+ + 9 ሐሰተኛ ምሥክር መቀጣቱ አይቀርም፤ባወራ ቁጥር የሚዋሽም ይጠፋል።+ +10 ሞኝ ሰው ተንደላቆ መኖር አይገባውም፤አገልጋይ መኳንንትን ቢገዛማ ምንኛ የከፋ ነው!+ +11 ጥልቅ ማስተዋል ሰውን ቶሎ እንዳይቆጣ ያደርገዋል፤+በደልንም መተዉ* ውበት ያጎናጽፈዋል።+ +12 የንጉሥ ቁጣ እንደ አንበሳ* ግሳት ነው፤+ሞገሱ ግን በሣር ላይ እንዳለ ጤዛ ነው። +13 ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ መከራ ያመጣል፤+ጨቅጫቃ ሚስትም * ያለማቋረጥ እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት።+ +14 ቤትና ሀብት ከአባቶች ይወረሳል፤ልባም ሚስት ግን የምትገኘው ከይሖዋ ነው።+ +15 ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ታካች ሰውም ይራባል።*+ +16 ትእዛዝን የሚጠብቅ ሕይወቱን* ይጠብቃል፤+መንገዱን ቸል የሚል ይሞታል።+ +17 ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤+ላደረገውም ነገር ብድራት* ይከፍለዋል።+ +18 ገና ተስፋ ሳለ ልጅህን ገሥጽ፤+ለእሱም ሞት ተጠያቂ አትሁን።*+ +19 ግልፍተኛ ሰው ይቀጣል፤ልታድነው ብትሞክር እንኳ በተደጋጋሚ እንዲህ ለማድረግ ትገደዳለህ።+ +20 የኋላ ኋላ ጥበበኛ እንድትሆንምክርን ስማ፤ ተግሣጽንም ተቀበል።+ +21 ሰው በልቡ ብዙ ነገር ያቅዳል፤የሚፈጸመው ግን የይሖዋ ፈቃድ* ነው።+ +22 የሰው ተወዳጅ ባሕርይ ታማኝ ፍቅሩ ነው፤+ውሸታም ከመሆን ድሃ መሆን ይሻላል። +23 ይሖዋን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤+እንዲህ የሚያደርግ ሰው ጥሩ እረፍት ያገኛል፤ ጉዳትም አይደርስበትም።+ +24 ሰነፍ እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፤ሆኖም ወደ አፉ እንኳ መመለስ ይሳነዋል።+ +25 ተሞክሮ የሌለው ብልህ+ እንዲሆን ፌዘኛን ምታው፤+ተጨማሪ እውቀት እንዲያገኝም አስተዋይ የሆነን ሰው ውቀሰው።+ +26 አባቱን የሚበድልና እናቱን የሚያባርር ልጅኀፍረትና ውርደት ያመጣል።+ +27 ልጄ ሆይ፣ ተግሣጽን መስማት ከተውክእውቀት ከሚገኝበት ቃል ትርቃለህ። +28 የማይረባ ምሥክር በፍትሕ ላይ ያፌዛል፤+የክፉዎችም አፍ ክፋትን ይሰለቅጣል።+ +29 ፌዘኞች ፍርድ ይጠብቃቸዋል፤+ለሞኞች ጀርባ ደግሞ ዱላ ተዘጋጅቷል።+ +20 የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣+ የሚያሰክር መጠጥም ሥርዓት አልበኛ ያደርጋል፤+በዚህ ምክንያት ከትክክለኛው መንገድ የሚወጣ ሁሉ ጥበበኛ አይደለም።+ + 2 ንጉሥ የሚፈጥረው ሽብር* እንደ አንበሳ* ግሳት ነው፤+የእሱን ቁጣ የሚያነሳሳ ሁሉ ሕይወቱን ለአደጋ ያጋልጣል።+ + 3 ሰው ከጠብ መራቁ ያስከብረዋል፤+ሞኝ የሆነ ሁሉ ግን ጥል ውስጥ ይዘፈቃል።+ + 4 ሰነፍ ሰው በክረምት አያርስም፤በመሆኑም በመከር ወራት ባዶውን ሲቀር ይለምናል።*+ + 5 በሰው ልብ ውስጥ ያለ ሐሳብ* እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤አስተዋይ ሰው ግን ቀድቶ ያወጣዋል። + 6 ብዙ ሰዎች ስለ ራሳቸው ታማኝ ፍቅር ያወራሉ፤ይሁንና ታማኝ የሆነን ሰው ማን ሊያገኘው ይችላል? + 7 ጻድቅ ንጹሕ አቋሙን* ጠብቆ ይመላለሳል።+ ከእሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቹ ደስተኞች ናቸው።+ + 8 ንጉሥ ለመፍረድ በዙፋን ላይ ሲቀመጥ፣+ክፋትን ሁሉ በዓይኖቹ ያበጥራል።+ + 9 “ልቤን አንጽቻለሁ፤+ከኃጢአቴም ነጽቻለሁ” ሊል የሚችል ማን ነው?+ +10 አባይ ሚዛንና የሐሰት መለኪያ፣*ሁለቱም በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ናቸው።+ +11 ሕፃን እንኳ ባሕርይው ንጹሕና ትክክል መሆኑበአድራጎቱ ይታወቃል።+ +12 የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዓይንን፣ሁለቱንም የሠራው ይሖዋ ነው።+ +13 እንቅልፍ አትውደድ፤ አለዚያ ድሃ ትሆናለህ።+ ዓይንህን ግለጥ፤ የተትረፈረፈ ምግብም ታገኛለህ።+ +14 ዕቃ የሚገዛ ሰው “የማይረባ ነው፣ የማይረባ ነው!” ይላል፤ከሄደ በኋላ ግን በራሱ ይኩራራል።+ +15 ወርቅ አለ፤ ዛጎልም* ተትረፍርፏል፤እውቀትን የሚናገሩ ከንፈሮች ግን ውድ ናቸው።+ +16 አንድ ሰው ለማያውቀው ሰው ዋስ ከሆነ ልብሱን ውሰድበት፤+ይህን ያደረገው ለባዕድ ሴት* ብሎ ከሆነ መያዣውን ውሰድ።+ +17 ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ያስደስተዋል፤በኋላ ግን አፉን ኮረት ይሞላዋል።+ +18 መመካከር* ሲኖር የታቀደው ነገር ይሳካል፤*+ለውጊያም ስትወጣ ጥበብ ያለበት አመራር ተቀበል።+ +19 ስም የሚያጠፋ ሰው እየዞረ የሌሎችን ሚስጥር ይገልጣል፤+ማማት ከሚወድ ሰው* ጋር አትወዳጅ። +20 አባቱንና እናቱን የሚረግም ሁሉጨለማ ሲሆን መብራቱ ይጠፋበታል።+ +21 በመጀመሪያ በስግብግብነት የተገኘ ውርስ፣የኋላ ኋላ በረከት አይሆንም።+ +22 “ቆይ፣ ብድሬን ባልመልስ!” አትበል።+ ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤+ እሱም ያድንሃል።+ +23 አባይ ሚዛን* በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤ለማጭበርበር የሚያገለግሉ መለኪያዎችንም መጠቀም ጥሩ አይደለም። +24 ይሖዋ የሰውን አካሄድ ይመራል፤+ሰው የገዛ መንገዱን* እንዴት ማስተዋል ይችላል? +25 ሰው ቸኩሎ “የተቀደሰ ነው!”+ ቢልና ከተሳለ በኋላ ስእለቱን መልሶ ማጤን ቢጀምር ወጥመድ ይሆንበታል።+ +26 ጥበበኛ ንጉሥ ክፉ ሰዎችን ያበጥራል፤+የመውቂያ መንኮራኩርም* በላያቸው ያስኬዳል።+ +27 የሰው እስትንፋስ የይሖዋ መብራት ነው፤ውስጣዊ ማንነቱን በሚገባ ይመረምራል። +28 ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቃሉ፤+በታማኝ ፍቅርም ዙፋኑን ያጸናል።+ +29 የወጣቶች ክብር ጉልበታቸው ነው፤+የአረጋውያንም ግርማ ሽበታቸው ነው።+ +30 ሰንበርና ቁስል ክፋትን ያስወግዳል፤*+ግርፋትም የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት ያጠራል። +3 ልጄ ሆይ፣ ትምህርቴን* አትርሳ፤ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ፤ + 2 ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመንእንዲሁም ሰላም ያስገኙልሃልና።+ + 3 ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት* አይለዩህ።+ በአንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፋቸው፤+ + 4 ያን ጊዜ በአምላክና በሰው ፊት ሞገስ ታገኛለህ፤+እንዲሁም ጥሩ ማስተዋል እንዳለህ ታስመሠክራለህ። + 5 በሙሉ ልብህ በይሖዋ ታመን፤+ደግሞም በገዛ ራስህ ማስተዋል አትመካ።*+ + 6 በመንገድህ ሁሉ እሱን ግምት ውስጥ አስገባ፤+እሱም ጎዳናህን ቀና ያደርገዋል።+ + 7 በራስህ አመለካከት ጥበበኛ አትሁን።+ ይሖዋን ፍራ፤ ከክፉም ራቅ። + 8 ለሰውነትህ* ፈውስ፣ለአጥንትህም ብርታት ይሆንልሃል። + 9 ባሉህ ውድ ነገሮች፣+ከምርትህ* ሁሉ በኩራት* ይሖዋን አክብር፤+ +10 ይህን ካደረግክ ጎተራዎችህ ጢም ብለው ይሞላሉ፤+በወይን መጭመቂያዎችህም አዲስ የወይን ጠጅ ሞልቶ ይፈስሳል። +11 ልጄ ሆይ፣ የይሖዋን ተግሣጽ ለመቀበል እንቢተኛ አትሁን፤+ወቀሳውም አያስመርርህ፤+ +12 አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚወቅስ ሁሉይሖዋም የሚወዳቸውን ይወቅሳልና።+ +13 ጥበብን የሚያገኝ፣+ጥልቅ ግንዛቤንም የራሱ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው፤ +14 ጥበብን ማግኘት ብርን ከማግኘት የተሻለ ነው፤እሷንም ማትረፍ ወርቅ ከማግኘት የተሻለ ነው።+ +15 ከዛጎል* ይበልጥ ውድ ናት፤አንተ የምትመኘው ማንኛውም ነገር ሊተካከላት አይችልም። +16 በቀኟ ረጅም ዕድሜ አለ፤በግራዋም ሀብትና ክብር ይገኛል። +17 መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም የሰፈነበት ነው።+ +18 ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት፤አጥብቀው የሚይዟትም ደስተኞች ይባላሉ።+ +19 ይሖዋ በጥበብ ምድርን መሠረተ።+ በማስተዋል ሰማያትን አጸና።+ +20 በእውቀቱ ጥልቅ ውኃዎች ተከፈሉ፤ደመና ያዘሉ ሰማያትም ጠል አንጠባጠቡ።+ +21 ልጄ ሆይ፣ እነዚህ ባሕርያት ከእይታህ አይራቁ።* ጥበብንና* የማመዛዘን ችሎታን ጠብቅ፤ +22 ሕይወት ያስገኙልሃል፤*ለአንገትህም ጌጥ ይሆናሉ፤ +23 በዚያን ጊዜ በመንገድህ ላይ ተማምነህ ትሄዳለህ፤እግርህም ፈጽሞ አይሰናከልም።*+ +24 በምትተኛበት ጊዜ አትፈራም፤+ትተኛለህ፤ እንቅልፍህም ጣፋጭ ይሆናል።+ +25 ድንገት የሚከሰት የሚያሸብር ነገርም+ ሆነበክፉ ሰዎች ላይ የሚመጣ መዓት አያስፈራህም።+ +26 ይሖዋ መታመኛህ ይሆናልና፤+እግርህን በወጥመድ እንዳይያዝ ይጠብቃል።+ +27 ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል አቅም ካለህ*+ለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትበል።+ +28 ለባልንጀራህ አሁኑኑ መስጠት እየቻልክ “ሂድና በኋላ ተመልሰህ ና! ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው። +29 ከአንተ ጋር ተማምኖ እየኖረ ሳለባልንጀራህን ለመጉዳት አታሲር።+ +30 መጥፎ ነገር ካላደረገብህከሰው ጋር ያለምክንያት አትጣላ።+ +31 በዓመፀኛ ሰው አትቅና፤+የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ፤ +32 ይሖዋ ተንኮለኛን ሰው ይጸየፋልና፤+ከቅኖች ጋር ግን የጠበቀ ወዳጅነት አለው።+ +33 ይሖዋ የክፉውን ቤት ይረግማል፤+የጻድቁን መኖሪያ ግን ይባርካል።+ +34 በፌዘኞች ላይ ይሳለቃል፤+ለየዋሆች ግን ሞገስ ያሳያል።+ +35 ጥበበኞች ክብርን ይወርሳሉ፤ሞኞች ግን ለውርደት የሚዳርግን ነገር ከፍ አድርገው ይመለከታሉ።+ +24 በክፉ ሰዎች አትቅና፤ከእነሱም ጋር ለመሆን አትጓጓ፤+ + 2 ልባቸው ዓመፅን ያውጠነጥናልና፤ከንፈራቸውም ተንኮልን ያወራል። + 3 ቤት በጥበብ ይገነባል፤*+በማስተዋልም ይጸናል። + 4 በእውቀት አማካኝነት ክፍሎቹበተለያዩ ውድ የሆኑና ያማሩ ነገሮች ተሞልተዋል።+ + 5 ጥበበኛ ሰው ኃያል ነው፤+ሰውም በእውቀት ኃይሉን ይጨምራል። + 6 ጥበብ ያለበት አመራር ተቀብለህ ለውጊያ ትወጣለህ፤+በብዙ አማካሪዎችም ድል* ይገኛል።+ + 7 ለሞኝ ሰው እውነተኛ ጥበብ ሊገኝ የማይችል ነገር ነው፤+በከተማው በር ላይ አንዳች የሚናገረው ነገር የለውም። + 8 መጥፎ ነገር ለማድረግ የሚያሴር ሁሉሴራ በመጠንሰስ የተካነ ተብሎ ይጠራል።+ + 9 በሞኝነት የሚጠነሰስ ሴራ* ኃጢአት ነው፤ሰዎችም ፌዘኛን ይጸየፋሉ።+ +10 በመከራ ቀን* ተስፋ የምትቆርጥ ከሆነጉልበትህ እጅግ ይዳከማል። +11 ወደ ሞት እየተወሰዱ ያሉትን ታደግ፤ለእርድ እየተውተረተሩ የሚሄዱትንም አስጥል።+ +12 “እኛ ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም አናውቅም” ብትል፣ ልብን* የሚመረምረው እሱ ይህን አያስተውልም?+ አዎ፣ አንተን* የሚመለከተ�� አምላክ ያውቃል፤ለእያንዳንዱም ሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል።+ +13 ልጄ ሆይ፣ መልካም ስለሆነ ማር ብላ፤ከማር እንጀራ የሚገኝ ማር ጣፋጭ ጣዕም አለው። +14 በተመሳሳይም ጥበብ ለአንተ መልካም* እንደሆነ እወቅ።+ ጥበብን ብታገኝ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።+ +15 በጻድቁ ቤት ላይ በክፋት አትሸምቅ፤ማረፊያ ቦታውንም አታፍርስበት። +16 ጻድቅ ሰባት ጊዜ ቢወድቅ እንኳ መልሶ ይነሳልና፤+ክፉ ሰው ግን በሚደርስበት መከራ ይሰናከላል።+ +17 ጠላትህ ሲወድቅ ሐሴት አታድርግ፤ሲሰናከልም ልብህ ደስ አይበለው፤+ +18 አለዚያ ይሖዋ ይህን አይቶ ያዝናል፤ቁጣውንም ከእሱ* ይመልሳል።+ +19 መጥፎ በሆኑ ሰዎች አትበሳጭ፤በክፉዎች አትቅና፤ +20 መጥፎ ሰው ሁሉ ምንም ተስፋ የለውምና፤+የክፉዎች መብራት ይጠፋል።+ +21 ልጄ ሆይ፣ ይሖዋንና ንጉሥን ፍራ።+ ከተቃዋሚዎች* ጋር አትተባበር፤+ +22 ጥፋታቸው ድንገት ይመጣልና።+ ሁለቱም* በእነሱ ላይ የሚያመጡትን ጥፋት ማን ያውቃል?+ +23 እነዚህም አባባሎች የጥበበኞች ናቸው፦ በፍርድ ማዳላት ጥሩ አይደለም።+ +24 ክፉውን “አንተ ጻድቅ ነህ”+ የሚለውን ሰው ሁሉ ሕዝቦች ይረግሙታል፤ ብሔራትም ያወግዙታል። +25 እሱን የሚወቅሱት ግን መልካም ይሆንላቸዋል፤+በመልካም ነገሮችም ይባረካሉ።+ +26 ሰዎች በሐቀኝነት መልስ የሚሰጥን ሰው ከንፈር ይስማሉ።*+ +27 በደጅ ያለህን ሥራ አሰናዳ፤ በእርሻም ላይ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አዘጋጅ፤ከዚያ በኋላ ቤትህን ሥራ።* +28 ምንም መሠረት ሳይኖርህ በባልንጀራህ ላይ አትመሥክር።+ በከንፈሮችህ ሌሎችን አታታል።+ +29 “እሱ እንዳደረገብኝ እንዲሁ አደርግበታለሁ፤እንደ ሥራው እከፍለዋለሁ”* አትበል።+ +30 በሰነፍ ሰው እርሻ፣+ማስተዋል* በጎደለው ሰው የወይን ቦታ አለፍኩ። +31 እርሻው አረም ወርሶት አየሁ፤መሬቱን ሳማ ሸፍኖት፣የድንጋዩም አጥር ፈራርሶ ነበር።+ +32 ይህን ተመልክቼ በጥሞና አሰብኩበት፤ካየሁትም ነገር ይህን ትምህርት አገኘሁ፦* +33 ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣ +34 ድህነት እንደ ወንበዴ፣ችጋርም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።+ +7 ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ጠብቅ፤ትእዛዛቴንም እንደ ውድ ሀብት ያዝ።+ + 2 ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ፤+መመሪያዬን* እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ። + 3 በጣቶችህ ላይ እሰራቸው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፋቸው።+ + 4 ጥበብን “እህቴ ነሽ” በላት፤ ማስተዋልንም “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፤ + 5 ጋጠወጥና*+ ባለጌ* ከሆነች ሴት፣እንዲሁም ከምትናገረው የሚያባብል* ቃል ይጠብቁሃል።+ + 6 በቤቴ መስኮት በፍርግርጉ በኩልአጮልቄ ወደ ታች ተመለከትኩ፤ + 7 ደግሞም ሞኞችን* ትክ ብዬ በማይበት ጊዜ፣በዚያ ከነበሩት ወንዶች ልጆች መካከል ማስተዋል* የጎደለውን አንድ ወጣት አየሁ።+ + 8 በቤቷ አቅራቢያ በሚገኝ መታጠፊያ አልፎወደ ቤቷ አቅጣጫ አመራ፤ + 9 ቀኑ መሸትሸት ብሎ ለዓይን ያዝ አድርጓል፤+የሌሊቱ ጨለማ እየተቃረበ ነበር። +10 ከዚያም እንደ ዝሙት አዳሪ* የለበሰችና+በልቧ አታላይ የሆነች ሴት ከእሱ ጋር ስትገናኝ አየሁ። +11 ሴትየዋ ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ነች።+ ፈጽሞ ቤቷ አትቀመጥም።* +12 አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ ትታያለች፤በየመንገዱ መታጠፊያም ታደባለች።+ +13 አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ያላንዳች ኀፍረትም እንዲህ አለችው፦ +14 “የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ።+ ዛሬ ስእለቴን ፈጽሜአለሁ። +15 አንተን ለማግኘት የወጣሁት ለዚህ ነው፤አንተን ፍለጋ ወጣሁ፤ ደግሞም አገኘሁህ! +16 መኝታዬን ባማረ የአልጋ ልብስ፣ከግብፅ በመጣ በቀለማት ያሸበረቀ ���ፍታ አስጊጬዋለሁ።+ +17 አልጋዬ ላይ ከርቤ፣ እሬትና* ቀረፋ አርከፍክፌአለሁ።+ +18 ና፣ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፤እርስ በርሳችን ፍቅራችንን በመግለጽ እንደሰት፤ +19 ባሌ ቤት የለምና፤ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል። +20 በከረጢት ገንዘብ ይዟል፤ደግሞም ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን ድረስ ወደ ቤት አይመለስም።” +21 እንደ ምንም ብላ አግባብታ ታሳስተዋለች።+ በለሰለሰ አንደበቷ ታታልለዋለች። +22 ለእርድ እንደሚነዳ በሬ፣ለቅጣትም በእግር ግንድ* እንደታሰረ ሞኝ ሰው በድንገት ይከተላታል፤+ +23 ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ፣በወጥመድ ለመያዝ እንደምትቸኩል ወፍ ተከትሏት ይሄዳል፤ ሕይወቱን* ሊያሳጣው እንደሚችል አላወቀም።+ +24 እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤የምናገረውንም ቃል በትኩረት ስሙ። +25 ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ። መንገድ ስታችሁ ወደ ጎዳናዋ አትግቡ፤+ +26 ተሰይፈው እንዲወድቁ ያደረገቻቸው ብዙ ናቸውና፤+እሷ የገደለቻቸውም እጅግ ብዙ ናቸው።+ +27 ቤቷ ወደ መቃብር* ይወስዳል፤ሙታን ወዳሉበት ስፍራም* ይወርዳል። +12 ተግሣጽን የሚወድ እውቀትን ይወዳል፤+ወቀሳን የሚጠላ ግን የማመዛዘን ችሎታ* ይጎድለዋል።+ + 2 ጥሩ ሰው የይሖዋን ሞገስ ያገኛል፤ክፋት የሚያሴርን ሰው ግን እሱ ይፈርድበታል።+ + 3 በክፋት ጸንቶ መቆም የሚችል ሰው የለም፤+ጻድቅ ግን ፈጽሞ አይነቀልም። + 4 ጥሩ ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት፤+አሳፋሪ* ሚስት ግን አጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት።+ + 5 የጻድቃን ሐሳብ ፍትሐዊ ነው፤የክፉዎች ምክር ግን አሳሳች ነው። + 6 የክፉዎች ቃል ገዳይ ወጥመድ ነው፤*+የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል።+ + 7 ክፉዎች ሲገለበጡ ደብዛቸው ይጠፋል፤የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።+ + 8 ሰው አስተዋይ በሆነ አንደበቱ ይመሰገናል፤+ልቡ ጠማማ የሆነ ግን ይናቃል።+ + 9 የሚበላው* ሳይኖረው ራሱን ከፍ ከፍ ከሚያደርግ ሰው ይልቅአገልጋይ ኖሮት ራሱን ዝቅ አድርጎ የሚኖር ሰው ይሻላል።+ +10 ጻድቅ የቤት እንስሳቱን* ይንከባከባል፤+ክፉዎች ግን ርኅራኄያቸው እንኳ ጭካኔ ነው። +11 መሬቱን የሚያርስ ሰው የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤+ከንቱ ነገሮችን የሚያሳድድ ግን ማስተዋል* ይጎድለዋል። +12 ክፉ ሰው፣ ሌሎች መጥፎ ሰዎች ባጠመዱት ነገር ይቀናል፤የጻድቃን ሥር ግን ፍሬ ያፈራል። +13 መጥፎ ሰው በክፉ ንግግሩ ይጠመዳል፤+ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል። +14 ሰው ከአፉ ፍሬ መልካም ነገር ይጠግባል፤+የእጁ ሥራም ብድራት ይከፍለዋል። +15 የሞኝ መንገድ በራሱ ዓይን ትክክል ነው፤+ጥበበኛ ግን ምክር ይቀበላል።+ +16 ሞኝ ሰው ቁጣውን ወዲያውኑ* ይገልጻል፤+ብልህ ሰው ግን ስድብን ችላ ብሎ ያልፋል።* +17 ታማኝ ምሥክር እውነቱን* ይናገራል፤ውሸታም ምሥክር ግን ያታልላል። +18 ሳይታሰብበት የሚነገር ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤የጥበበኞች ምላስ ግን ፈውስ ነው።+ +19 እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤+ሐሰተኛ ምላስ ግን የሚቆየው ለቅጽበት ብቻ ነው።+ +20 ተንኮል በሚሸርቡ ሰዎች ልብ ውስጥ ማታለያ አለ፤ሰላምን የሚያራምዱ* ግን ደስተኞች ናቸው።+ +21 ጻድቅ ምንም ዓይነት ጉዳት አያገኘውም፤+የክፉዎች ሕይወት ግን በመከራ የተሞላ ይሆናል።+ +22 ይሖዋ ውሸታም ከንፈሮችን ይጸየፋል፤+በታማኝነት የሚመላለሱ ግን ደስ ያሰኙታል። +23 ብልህ ሰው እውቀቱን ይሰውራል፤የሞኝ ልብ ግን ሞኝነቱን ይዘከዝካል።+ +24 የትጉ ሰዎች እጅ ገዢ ትሆናለች፤+ሥራ ፈት እጆች ግን ለባርነት ይዳረጋሉ።+ +25 በሰው ልብ ውስጥ ያለ ጭንቀት ልቡ እንዲዝል ያደርገዋል፤*+መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።+ +26 ጻድቅ የግጦሽ መሬቱን በሚገባ ይቃኛል፤የክፉዎች መንገድ ግን እንዲባዝኑ ያደ��ጋቸዋል። +27 ሰነፍ ሰው አደኑን አሳድዶ አይዝም፤+ትጋት ግን የሰው ውድ ሀብት ነው። +28 የጽድቅ ጎዳና ወደ ሕይወት ይመራል፤+በጎዳናው ላይ ሞት የለም። +1 የእስራኤል ንጉሥ፣+ የዳዊት ልጅ+ የሰለሞን ምሳሌዎች፦+ + 2 ጥበብንና+ ተግሣጽን ለመማር፣*ጥበብ ያዘሉ አባባሎችን ለመረዳት፣ + 3 ጥልቅ ማስተዋል፣ ጽድቅ፣+ ጥሩ ፍርድና*+ቅንነት* የሚያስገኝ ተግሣጽ ለመቀበል፣+ + 4 ተሞክሮ ለሌላቸው ብልሃትን፣+ለወጣቶች እውቀትንና የማመዛዘን ችሎታን ለመስጠት።+ + 5 ጥበበኛ ሰው ያዳምጣል፤ ደግሞም ተጨማሪ ትምህርት ይቀስማል፤+ማስተዋል ያለው ሰውም ጥበብ ያለበትን መመሪያ ይቀበላል፤+ + 6 ይህም ምሳሌንና ስውር የሆነ አባባልንእንዲሁም የጥበበኞችን ቃላትና የሚናገሩትን እንቆቅልሽ ይረዳ ዘንድ ነው።+ + 7 ይሖዋን መፍራት* የእውቀት መጀመሪያ ነው።+ ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁት ሞኞች ብቻ ናቸው።+ + 8 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ተግሣጽ አዳምጥ፤+የእናትህንም መመሪያ* አትተው።+ + 9 ለራስህ የሚያምር የአበባ ጉንጉን፣+ለአንገትህም ውብ ጌጥ ይሆንልሃል።+ +10 ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች ሊያግባቡህ ቢሞክሩ እሺ አትበላቸው።+ +11 እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ና አብረን እንሂድ። ደም ለማፍሰስ እናድባ። ንጹሐን ሰዎችን ያለምክንያት ለማጥቃት እናደፍጣለን። +12 እንደ መቃብር፣* በሕይወት እንዳሉ እንውጣቸዋለን፤ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንሰለቅጣቸዋለን። +13 ውድ ሀብታቸውን ሁሉ እንውሰድባቸው፤ቤቶቻችንን በዘረፍናቸው ነገሮች እንሞላለን። +14 ከእኛ ጋር ልትተባበር ይገባል፤*ሁላችንም የሰረቅነውን እኩል እንካፈላለን።”* +15 ልጄ ሆይ፣ አትከተላቸው። እግርህን ከመንገዳቸው አርቅ፤+ +16 እግሮቻቸው ክፉ ነገር ለመሥራት ይሮጣሉና፤ደም ለማፍሰስ ይጣደፋሉ።+ +17 ወፎች ዓይናቸው እያየ እነሱን ለማጥመድ መረብ መዘርጋት ከንቱ ነው። +18 እነዚህ ሰዎች ደም ለማፍሰስ የሚያደቡት ለዚህ ነው፤የሰዎችን ሕይወት* ለማጥፋት ያደፍጣሉ። +19 በማጭበርበር ትርፍ ለማግኘት የሚሹ መንገዳቸው ይህ ነው፤እንዲህ ያለው ትርፍ የተጠቃሚዎቹን ሕይወት* ያጠፋል።+ +20 እውነተኛ ጥበብ+ በጎዳና ላይ ትጮኻለች።+ በአደባባይ ላይ ያለማቋረጥ ድምፅዋን ታሰማለች።+ +21 ሰው በሚበዛባቸው ጎዳናዎች ማዕዘን* ላይ ሆና ትጣራለች። በከተማው መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ ትላለች፦+ +22 “እናንተ አላዋቂዎች እስከ መቼ አላዋቂነትን ትወዳላችሁ? እናንተ ፌዘኞች እስከ መቼ በሌሎች ላይ በማፌዝ ትደሰታላችሁ? እናንተ ሞኞች እስከ መቼ እውቀትን ትጠላላችሁ?+ +23 ለወቀሳዬ ምላሽ ስጡ።*+ እንዲህ ብታደርጉ መንፈሴን አፈስላችኋለሁ፤ቃሌን አሳውቃችኋለሁ።+ +24 በተጣራሁ ጊዜ በእንቢተኝነታችሁ ጸንታችኋል፤እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ትኩረት አልሰጠም፤+ +25 ምክሬን ሁሉ ችላ ብላችኋል፤ወቀሳዬንም አልተቀበላችሁም፤ +26 እኔም ጥፋት ሲደርስባችሁ እስቃለሁ፤የፈራችሁት ነገር ሲደርስ አላግጥባችኋለሁ፤+ +27 የፈራችሁት ነገር እንደ ማዕበል ሲደርስባችሁ፣ጥፋታችሁም እንደ አውሎ ነፋስ ከተፍ ሲልባችሁ፣ጭንቀትና መከራ ሲመጣባችሁ አፌዝባችኋለሁ። +28 በዚያን ጊዜ ደጋግመው ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ሆኖም አያገኙኝም፤+ +29 ምክንያቱም እውቀትን ጠልተዋል፤+ይሖዋን መፍራትንም አልወደዱም።+ +30 ምክሬን አልተቀበሉም፤ወቀሳዬን ሁሉ አቃለዋል። +31 ስለዚህ መንገዳቸው የሚያስከትለውን መዘዝ ይቀበላሉ፤*+በገዛ ራሳቸውም ምክር* ከልክ በላይ ይጠግባሉ። +32 ተሞክሮ የሌላቸውን ሰዎች ጋጠወጥነታቸው ይገድላቸዋልና፤ሞኞችን ደግሞ ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል። +33 እኔን የሚሰማ ሰው ���ን ተረጋግቶ ይኖራል፤+መከራ ይደርስብኛል የሚል ስጋትም አያድርበትም።”+ +29 ብዙ ጊዜ ተወቅሶ አንገቱን ያደነደነ* ሰው፣+ሊፈወስ በማይችል ሁኔታ በድንገት ይሰበራል።+ + 2 ጻድቃን ሲበዙ ሕዝብ ሐሴት ያደርጋል፤ክፉ ሰው ሲገዛ ግን ሕዝብ ይቃትታል።+ + 3 ጥበብን የሚወድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤+ከዝሙት አዳሪዎች ጋር የሚወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል።+ + 4 ንጉሥ ፍትሕ በማስፈን አገርን ያረጋጋል፤+ጉቦ የሚፈልግ ሰው ግን ያወድማታል። + 5 ባልንጀራውን የሚሸነግል ሰው፣ለእግሩ ወጥመድ ይዘረጋበታል።+ + 6 መጥፎ ሰው በደሉ ወጥመድ ይሆንበታል፤+ጻድቅ ግን እልል ይላል፤ ሐሴትም ያደርጋል።+ + 7 ጻድቅ ለድሆች መብት ይቆረቆራል፤+ክፉ ሰው ግን ለእንዲህ ዓይነት ጉዳይ ደንታ የለውም።+ + 8 ጉራ የሚነዙ ሰዎች ከተማን ያቃጥላሉ፤+ጥበበኞች ግን ቁጣን ያበርዳሉ።+ + 9 ጥበበኛ ሰው ከሞኝ ጋር ቢሟገት፣ሁከትና ፌዝ ይነግሣል፤ ደስታ ግን አይኖርም።+ +10 ደም የተጠሙ ሰዎች ንጹሕ የሆነን* ሰው ሁሉ ይጠላሉ፤+ቅን የሆነውን ሰው ሕይወት* ለማጥፋት ይሻሉ።* +11 ሞኝ ስሜቱን* ሁሉ እንዳሻው ይገልጻል፤+ጥበበኛ ግን ስሜቱን ይቆጣጠራል።+ +12 ገዢ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣አገልጋዮቹ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።+ +13 ድሃንና ጨቋኝን የሚያመሳስላቸው* ነገር አለ፦ ይሖዋ ለሁለቱም የዓይን ብርሃን ይሰጣል።* +14 ንጉሥ ለድሆች በትክክል ሲፈርድ፣+ዙፋኑ ምንጊዜም ጸንቶ ይኖራል።+ +15 በትርና* ወቀሳ ጥበብ ያስገኛሉ፤+መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል። +16 ክፉዎች ሲበዙ ክፋት ይበዛል፤ጻድቃን ግን የእነሱን ውድቀት ያያሉ።+ +17 ልጅህን ገሥጸው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤ደግሞም እጅግ ደስ ያሰኝሃል።*+ +18 ራእይ* ከሌለ ሕዝብ እንዳሻው ይሆናል፤+ሕግን የሚጠብቁ ግን ደስተኞች ናቸው።+ +19 አገልጋይ በቃል ብቻ ለመታረም ፈቃደኛ አይሆንም፤የሚነገረውን ነገር ቢረዳውም እንኳ እሺ ብሎ አይታዘዝምና።+ +20 ለመናገር የሚቸኩል ሰው አይተህ ታውቃለህ?+ ከእሱ ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው።+ +21 አገልጋይ ከልጅነቱ ጀምሮ ከተሞላቀቀ፣የኋላ ኋላ ምስጋና ቢስ ይሆናል። +22 በቀላሉ የሚቆጣ ሰው ጠብ ያስነሳል፤+ግልፍተኛ የሆነም ብዙ በደል ይፈጽማል።+ +23 ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤+ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብር ይጎናጸፋል።+ +24 የሌባ ግብረ አበር ራሱን* ይጠላል። እንዲመሠክር የቀረበለትን ጥሪ* ቢሰማም ምንም አይናገርም።+ +25 ሰውን መፍራት* ወጥመድ ነው፤+በይሖዋ የሚታመን ግን ጥበቃ ያገኛል።+ +26 ብዙዎች ከገዢ ጋር ተገናኝተው መነጋገር* ይሻሉ፤ሰው ግን ፍትሕ የሚያገኘው ከይሖዋ ነው።+ +27 ጻድቅ ፍትሐዊ ያልሆነን ሰው ይጸየፋል፤+ክፉ ሰው ግን በቀና መንገድ የሚሄደውን ይጸየፋል።+ +28 ክፉዎች ማንም ሳያሳድዳቸው ይሸሻሉ፤ጻድቃን ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ናቸው።+ + 2 በአንድ አገር ውስጥ ሕግ ተላላፊነት* ሲነግሥ ብዙ ገዢዎች ይፈራረቁበታል፤+ይሁንና ጥልቅ ግንዛቤና እውቀት ያለው ሰው በሚያበረክተው እርዳታ ገዢ* ለረጅም ዘመን ይቆያል።+ + 3 ችግረኞችን የሚበዘብዝ ድሃ፣+እህሉን ሁሉ ጠራርጎ እንደሚወስድ ዝናብ ነው። + 4 ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ሕግን የሚጠብቁ ሰዎች ግን በእነሱ ላይ ይቆጣሉ።+ + 5 ክፉዎች ፍትሕን መረዳት አይችሉም፤ይሖዋን የሚፈልጉ ግን ሁሉን ነገር መረዳት ይችላሉ።+ + 6 መንገዱ ብልሹ ከሆነ ሀብታም ይልቅንጹሕ አቋም* ይዞ የሚመላለስ ድሃ ይሻላል።+ + 7 አስተዋይ ልጅ ሕግን ይጠብቃል፤ከሆዳሞች ጋር የሚወዳጅ ግን አባቱን ያዋርዳል።+ + 8 ወለድና+ አራጣ በማስከፈል ሀብት የሚያካብት፣ለድሆች ሞገስ ለሚያሳይ ሰው ያከማችለታል።+ + 9 ሕግን ለመስማት አሻፈረኝ የሚ��� ሰው፣ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።+ +10 ቅኖችን አሳስቶ ወደ መጥፎ መንገድ የሚመራ፣ እሱ ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ይገባል፤+ነቀፋ የሌለባቸው ሰዎች ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ።+ +11 ሀብታም ሰው በገዛ ዓይኖቹ ፊት ጥበበኛ ነው፤+ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ድሃ ግን ማንነቱን ይደርስበታል።+ +12 ጻድቃን ድል ሲያደርጉ ታላቅ ክብር ይሆናል፤ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሰዎች ይሸሸጋሉ።+ +13 የሠራውን በደል የሚሸፋፍን አይሳካለትም፤+የሚናዘዝና የሚተወው ሁሉ ግን ምሕረት ያገኛል።+ +14 ምንጊዜም ተጠንቅቆ የሚኖር* ሰው ደስተኛ ነው፤ልቡን የሚያደነድን ሁሉ ግን ለጥፋት ይዳረጋል።+ +15 ምስኪን በሆነ ሕዝብ ላይ የተሾመ ክፉ ገዢ፣እንደሚያገሳ አንበሳና ተንደርድሮ እንደሚመጣ ድብ ነው።+ +16 ጥልቅ ግንዛቤ የሌለው መሪ ሥልጣኑን አላግባብ ይጠቀማል፤+በማጭበርበር የሚገኝን ትርፍ የሚጠላ ግን ዕድሜውን ያራዝማል።+ +17 የሰው ሕይወት በማጥፋቱ የደም* ባለ ዕዳ የሆነ ሰው መቃብር* እስኪገባ ድረስ ሲሸሽ ይኖራል።+ እንዲህ ያለውን ሰው ማንም አይርዳው። +18 እንከን የለሽ በሆነ መንገድ የሚመላለስ ሰው ይድናል፤+መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ድንገት ይወድቃል።+ +19 መሬቱን የሚያርስ ሰው የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ የሆኑ ነገሮችን የሚያሳድድ ግን እጅግ ይደኸያል።+ +20 ታማኝ ሰው ብዙ በረከት ያገኛል፤+ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ንጽሕናውን ማጉደፉ አይቀርም።+ +21 አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፤+ሆኖም ሰው ለቁራሽ ዳቦ ብሎ ስህተት ሊፈጽም ይችላል። +22 ቀናተኛ* ሰው ሀብት ለማግኘት ይጓጓል፤ድህነት ላይ እንደሚወድቅ አያውቅም። +23 በምላሱ ከሚሸነግል ይልቅሰውን የሚወቅስ+ የኋላ ኋላ ይበልጥ ሞገስ ያገኛል።+ +24 አባቱንና እናቱን እየዘረፈ “ምንም ጥፋት የለበትም” የሚል ሁሉ+ የአጥፊ ተባባሪ ነው።+ +25 ስግብግብ ሰው* ጠብ ያነሳሳል፤በይሖዋ የሚታመን ግን ይበለጽጋል።*+ +26 በገዛ ልቡ የሚታመን ሁሉ ሞኝ ነው፤+በጥበብ የሚመላለስ ግን ክፉ አያገኘውም።+ +27 ለድሃ የሚሰጥ ሁሉ አይቸገርም፤+እነሱን ላለማየት ዓይኖቹን የሚከድን ግን ብዙ እርግማን ይደርስበታል። +28 ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ሰው ራሱን ይሸሽጋል፤ክፉዎች ሲጠፉ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።+ +8 ጥበብ እየተጣራች አይደለም? ማስተዋልስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እያሰማች አይደለም?+ + 2 በጎዳና አጠገብ በሚገኙ ከፍታ ቦታዎች፣+መንገዶች በሚገናኙበት ቦታ ላይ ቆማለች። + 3 ወደ ከተማዋ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣በደጆቹ መግቢያዎች ላይድምፅዋን ከፍ አድርጋ ትጮኻለች፦+ + 4 “ሰዎች ሆይ፣ የምጣራው እናንተን ነው፤ድምፄን ከፍ አድርጌ የማሰማው ለሁሉም* ነው። + 5 እናንተ ተሞክሮ የሌላችሁ፣ ብልሃትን ተማሩ፤+እናንተ ሞኞች፣ አስተዋይ ልብ ይኑራችሁ። + 6 የምናገረው ነገር በጣም አስፈላጊ ስለሆነ አዳምጡኝ፤ከንፈሮቼ ትክክል የሆነውን ይናገራሉ፤ + 7 አንደበቴ በለሰለሰ ድምፅ እውነትን ይናገራልና፤ከንፈሮቼም ክፋትን ይጸየፋሉ። + 8 ከአፌ የሚወጡት ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው። የተጣመመ ወይም የተወላገደ ነገር አይገኝባቸውም። + 9 ጥልቅ ግንዛቤ ላለው፣ ሁሉም ቀና ናቸው፤እውቀት ላላቸውም ትክክል ናቸው። +10 ከብር ይልቅ ተግሣጼን፣ጥራት ካለውም ወርቅ ይልቅ እውቀትን ተቀበሉ፤+ +11 ጥበብ ከዛጎል* ትበልጣለችና፤ተፈላጊ የሆኑ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ከእሷ ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም። +12 እኔ ጥበብ፣ ከብልሃት ጋር አብሬ እኖራለሁ፤እውቀትና የማመዛዘን ችሎታ አግኝቻለሁ።+ +13 ይሖዋን መፍራት ማለት ክፉ ነገርን መጥላት ነው።+ ትዕቢትን፣ ኩራትን፣+ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።+ +14 ጥሩ ምክር መስጠት እችላለሁ፤ ማስተዋል የታከለበት ጥበብም አለኝ፤+ማስተዋልና+ ኃይል+ የእኔ ናቸው። +15 ነገሥታት የሚገዙት በእኔ ነው፤ከፍተኛ ባለሥልጣናትም የጽድቅ ድንጋጌ የሚያወጡት በእኔ ነው።+ +16 መኳንንት የሚገዙት በእኔ ነው፤ታላላቅ ሰዎችም በጽድቅ የሚፈርዱት በእኔ ነው። +17 የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፤የሚፈልጉኝም ያገኙኛል።+ +18 ሀብትና ክብር፣ዘላቂ ብልጽግናና* ጽድቅ በእኔ ዘንድ አሉ። +19 ፍሬዬ ከወርቅ፣ አልፎ ተርፎም ከጠራ ወርቅ ይሻላል፤ከእኔ የምታገኙት ስጦታም ጥራት ካለው ብር ይበልጣል።+ +20 በጽድቅ መንገድ፣በፍትሕ ጎዳና መካከል እጓዛለሁ፤ +21 ለሚወዱኝ ውድ የሆኑ ነገሮችን አወርሳለሁ፤ግምጃ ቤቶቻቸውንም እሞላለሁ። +22 ይሖዋ የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፤+ከብዙ ዘመን በፊት ካከናወናቸው ሥራዎች ቀዳሚው አደረገኝ።+ +23 ከጥንት፣* ከመጀመሪያው አንስቶ፣ምድርም ከመፈጠሯ አስቀድሞ+ ከፍ ያለ ቦታ ተሰጠኝ።+ +24 ጥልቅ ውኃዎች ባልነበሩበት ጊዜ፣+ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድኩ።* +25 ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፣ከኮረብቶች በፊት ተወለድኩ፤ +26 ምድርንም ሆነ ሜዳዎቹን እንዲሁምየመጀመሪያዎቹን የአፈር ጓሎች ከመሥራቱ በፊት ተወለድኩ። +27 ሰማያትን ባዘጋጀ ጊዜ+ በዚያ ነበርኩ፤በውኃዎች ላይ የአድማስን ምልክት* ባደረገ ጊዜ፣+ +28 ደመናትን በላይ ባዘጋጀ* ጊዜ፣የጥልቅ ውኃ ምንጮችን በመሠረተ ጊዜ፣ +29 የባሕሩ ውኃከትእዛዙ አልፎ እንዳይሄድ በደነገገ ጊዜ፣+የምድርን መሠረቶች ባቆመ* ጊዜ፣ +30 በዚያን ወቅት የተዋጣለት ሠራተኛ ሆኜ ከጎኑ ነበርኩ።+ በየዕለቱ በእኔ የተነሳ ልዩ ደስታ ይሰማው ነበር፤+እኔም በፊቱ ሁልጊዜ ሐሴት አደርግ ነበር፤+ +31 እሱ በፈጠረው፣ ሰው በሚኖርበት ምድር ሐሴት አደረግኩ፤በተለይ ደግሞ በሰው ልጆች እጅግ እደሰት ነበር። +32 እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤አዎ፣ መንገዴን የሚጠብቁ ደስተኞች ናቸው። +33 ተግሣጽን ስሙ፤+ ጥበበኞችም ሁኑ፤ፈጽሞም ቸል አትበሉት። +34 በየዕለቱ በማለዳ በራፌ ላይ መጥቶ፣*በበሬ መቃን አጠገብ ቆሞ በመጠባበቅየሚያዳምጠኝ ሰው ደስተኛ ነው፤ +35 እኔን የሚያገኝ ሕይወትን ያገኛልና፤+በይሖዋም ዘንድ ሞገስ ያገኛል። +36 እኔን ችላ የሚል ግን ራሱን* ይጎዳል፤የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወዳሉ።”+ +11 አባይ* ሚዛን በይሖዋ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ትክክለኛ መለኪያ* ግን ደስ ያሰኘዋል።+ + 2 እብሪት ከመጣ ውርደት ይከተላል፤+ልካቸውን በሚያውቁ ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።+ + 3 ቅኖችን ንጹሕ አቋማቸው* ይመራቸዋል፤+ከዳተኞችን ግን ተንኮላቸው ያጠፋቸዋል።+ + 4 በቁጣ ቀን ሀብት ፋይዳ አይኖረውም፤*+ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።+ + 5 ነቀፋ የሌለበት ሰው የሚሠራው ጽድቅ መንገዱን ቀና ያደርግለታል፤ክፉ ሰው ግን በገዛ ክፋቱ ይወድቃል።+ + 6 ቅኖችን ጽድቃቸው ያድናቸዋል፤+ከዳተኞች ግን በገዛ ምኞታቸው ይጠመዳሉ።+ + 7 ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው መና ይቀራል፤በኃይሉ ተመክቶ ተስፋ የሚያደርገው ነገርም ይጠፋል።+ + 8 ጻድቅ ከመከራ ይድናል፤ክፉ ሰው ደግሞ በእሱ ቦታ ይተካል።+ + 9 ከሃዲ ሰው* በአፉ ባልንጀራውን ያጠፋል፤ጻድቃን ግን በእውቀት ይድናሉ።+ +10 በጻድቃን ጥሩነት ከተማ ሐሴት ታደርጋለች፤ክፉዎች ሲጠፉም እልልታ ይሆናል።+ +11 በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤+የክፉዎች አፍ ግን ያፈራርሳታል።+ +12 ማስተዋል* የጎደለው ሰው ባልንጀራውን ይንቃል፤*ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ዝም ይላል።+ +13 ስም የሚያጠፋ ሰው እየዞረ የሌሎችን ሚስጥር ይገልጣል፤+እምነት የሚጣልበት ሰው* ግን ሚስጥር ይጠብቃል።* +14 ጥበብ ያለበት አመራር ሲጓደል ሕዝብ ይጎዳል፤ብዙ አማካሪዎች ባሉበት ግን ስኬት* ይገኛል።+ +15 የ��ያውቀው ሰው ለወሰደው ብድር ዋስ የሚሆን* ጉዳት ላይ መውደቁ አይቀርም፤+እጅ በመምታት* ቃል ከመግባት የሚቆጠብ* ግን ምንም አይደርስበትም። +16 ሞገስ ያላት* ሴት ክብር ታገኛለች፤+ጨካኞች ግን ሀብት ያካብታሉ። +17 ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፤*+ጨካኝ ሰው ግን በራሱ ላይ መከራ* ያመጣል።+ +18 ክፉ ሰው የሚያገኘው ደሞዝ እርባና የለውም፤+ጽድቅን የሚዘራ ግን እውነተኛ ብድራት ያገኛል።+ +19 ለጽድቅ ጽኑ አቋም ያለው ሰው ሕይወት የማግኘት ተስፋ አለው፤+ክፋትን የሚያሳድድ ግን ለሞት መዳረጉ አይቀርም። +20 ይሖዋ ጠማማ ልብ ያላቸውን ሰዎች ይጸየፋል፤+ነቀፋ በሌለበት ጎዳና የሚመላለሱ ግን ደስ ያሰኙታል።+ +21 ይህን አትጠራጠር፦ ክፉ ሰው ከቅጣት አያመልጥም፤+የጻድቃን ልጆች ግን ይድናሉ። +22 ማስተዋልን የምትንቅ ቆንጆ ሴት፣በአሳማ አፍንጫ ላይ እንዳለ የወርቅ ቀለበት ናት። +23 የጻድቅ ምኞት መልካም ነገር ያስገኛል፤+የክፉ ሰው ተስፋ ግን ወደ ቁጣ ይመራል። +24 አንዱ በልግስና ይሰጣል፤* ሆኖም ተጨማሪ ያገኛል፤+ሌላው ደግሞ ለመስጠት ይሰስታል፤ ነገር ግን ለድህነት ይዳረጋል።+ +25 ለጋስ ሰው* ይበለጽጋል፤*+ሌሎችን የሚያረካም* እሱ ራሱ ይረካል።+ +26 እህል ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆነውን ሕዝቡ ይረግመዋል፤የሚሸጠውን ግን ይባርከዋል። +27 መልካም ነገር ለማድረግ የሚተጋ ሞገስ ለማግኘት ይጥራል፤+መጥፎ ነገር ለማድረግ የሚፈልግ ግን ክፋቱ በራሱ ላይ እንደሚመጣ የተረጋገጠ ነው።+ +28 በሀብቱ የሚታመን ሰው ይወድቃል፤+ጻድቅ ግን እንዳማረ ቅጠል ይለመልማል።+ +29 ቤተሰቡ ላይ ችግር* የሚያመጣ ሰው ሁሉ ነፋስን ይወርሳል፤+ሞኝ ሰውም ጥበበኛ ልብ ላለው ሰው አገልጋይ ይሆናል። +30 የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ነው፤+ነፍሳትንም* የሚማርክ ጥበበኛ ነው።+ +31 በእርግጥ ጻድቅ በምድር ላይ የሚገባውን ብድራት የሚቀበል ከሆነክፉውና ኃጢአተኛው የሚቀበሉት ብድራትማ ምንኛ የከፋ ይሆን!+ +2 ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ብትቀበልናትእዛዛቴን እንደ ውድ ሀብት ብታስቀምጥ፣+ + 2 ይህን ለማድረግ ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣+ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ልብህን ብታዘነብል፣+ + 3 ደግሞም ማስተዋልን ብትጣራና+ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ድምፅህን ብታሰማ፣+ + 4 እንደ ብር ተግተህ ብትፈልጋት፣+እንዲሁም እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣+ + 5 ያን ጊዜ ይሖዋን መፍራት ምን ማለት እንደሆነ ትረዳለህ፤+ደግሞም ስለ አምላክ እውቀት ትቀስማለህ።+ + 6 ይሖዋ ራሱ ጥበብ ይሰጣልና፤+ከአፉ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ ይወጣል። + 7 ለቅኖች ጥበብን* እንደ ውድ ሀብት ያከማቻል፤ንጹሕ አቋማቸውን* ጠብቀው ለሚመላለሱት ጋሻ ነው።+ + 8 የፍትሕን ጎዳና ይከታተላል፤የታማኞቹንም መንገድ ይጠብቃል።+ + 9 በዚህ ጊዜ ጽድቅ፣ ፍትሕና ትክክል የሆነውን ነገርይኸውም የጥሩነትን ጎዳና በሙሉ ትረዳለህ።+ +10 ጥበብ ወደ ልብህ ስትገባና+እውቀት ነፍስህን* ደስ ስታሰኝ፣+ +11 የማመዛዘን ችሎታ ምንጊዜም ይጠብቅሃል፤+ጥልቅ ግንዛቤም ይጋርድሃል፤ +12 ይህም አንተን ከክፉ መንገድ ለማዳንእንዲሁም ጠማማ ነገር ከሚናገር ሰው፣+ +13 በጨለማ መንገድ ለመጓዝቀናውን ጎዳና ከሚተዉ፣+ +14 መጥፎ ድርጊት በመፈጸም ሐሴት ከሚያደርጉ፣ጠማማ በሆኑ ክፉ ነገሮች ከሚደሰቱ፣ +15 መንገዳቸው ጠማማ ከሆነናአካሄዳቸው በተንኮል ከተሞላ ሰዎች አንተን ለመታደግ ነው። +16 ጋጠወጥ* ከሆነች ሴት፣ባለጌ* ሴት ከምትናገረው የሚያባብል* ቃል ያድንሃል፤+ +17 ይህች ሴት በወጣትነቷ የነበራትን የቅርብ ወዳጇን*+ የምትተውእንዲሁም ከአምላኳ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን የምትረሳ ናት፤ +18 ቤቷ ሰውን ይዞ ወደ ሞት ይወርዳልና፤አካሄዷም* በሞት ወደተረቱት ይወስዳል።+ +19 ከእሷ ጋር ግንኙነት ያላቸው* ሁሉ አይመለሱም፤የሕይወትንም መንገድ ዳግመኛ አያገኙም።+ +20 በመሆኑም የጥሩ ሰዎችን መንገድ ተከተል፤እንዲሁም ከጻድቃን ጎዳና አትውጣ፤+ +21 በምድር ላይ የሚኖሩት ቅኖች ብቻ ናቸውና፤በእሷም ላይ የሚቀሩት ነቀፋ የሌለባቸው* ናቸው።+ +22 ክፉዎች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፤+ከዳተኞችም ከእሷ ይወገዳሉ።+ +26 በረዶ በበጋ፣ ዝናብም በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም።+ + 2 ወፍ ቱር የምትልበት፣ ወንጭፊትም የምትበርበት ምክንያት እንዳላት ሁሉእርግማንም ያለበቂ ምክንያት አይመጣም።* + 3 አለንጋ ለፈረስ፣ ልጓም ለአህያ፣+በትርም ለሞኞች ጀርባ ነው።+ + 4 ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ አትመልስለት፤አለዚያ አንተም የእሱ ቢጤ ትሆናለህ።* + 5 ጥበበኛ የሆነ እንዳይመስለውለሞኝ እንደ ሞኝነቱ መልስለት።+ + 6 አንድን ጉዳይ ለሞኝ በአደራ የሚሰጥእግሩን ከሚያሽመደምድና ራሱን ከሚጎዳ* ሰው ተለይቶ አይታይም። + 7 በሞኞች አፍ የሚነገር ምሳሌ፣እንደ አንካሳ ሰው እግር* ነው።+ + 8 ለሞኝ ክብር መስጠት፣በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።+ + 9 በሞኞች አፍ የሚነገር ምሳሌበሰካራም እጅ እንዳለ እሾህ ነው። +10 ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን የሚቀጥር፣በነሲብ ያገኘውን ሁሉ* እንደሚያቆስል ቀስተኛ ነው። +11 ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ፣ሞኝ ሰውም ሞኝነቱን ይደጋግማል።+ +12 ጥበበኛ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው አይተህ ታውቃለህ?+ ከእሱ ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው። +13 ሰነፍ “በመንገድ ላይ ደቦል አንበሳ፣በአደባባይም አንበሳ አለ!” ይላል።+ +14 በር በማጠፊያው* ላይ እንደሚዞር፣ሰነፍም በአልጋው ላይ ይገላበጣል።+ +15 ሰነፍ እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፤ወደ አፉ ለመመለስ ግን እጅግ ይታክታል።+ +16 ሰነፍ ሰው በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ሰባት ሰዎች ይበልጥጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል። +17 በሌሎች ጠብ የሚቆጣ* መንገደኛየውሻ ጆሮ እንደሚይዝ ሰው ነው።+ +18 የሚንበለበሉ ተወንጫፊ መሣሪያዎችን፣ ፍላጻዎችንና ሞትን* እንደሚወረውር እብድ፣ +19 ባልንጀራውን አታሎ ሲያበቃ “ቀልዴን እኮ ነው!” የሚል ሰውም እንዲሁ ነው።+ +20 እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤ስም አጥፊ ከሌለ ደግሞ ጭቅጭቅ ይበርዳል።+ +21 ከሰል ፍምን፣ እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥልጨቅጫቃ ሰውም ጠብ ይጭራል።+ +22 ስም አጥፊ የሚናገረው ቃል ጣፋጭ እንደሆነ ቁራሽ ምግብ ነው፤*በፍጥነት ተውጦ በቀጥታ ወደ ሆድ ይገባል።+ +23 ከክፉ ልብ የሚወጡ የፍቅር ቃላት፣*በቀለጠ ብር እንደተለበጠ የሸክላ ዕቃ ስባሪ ናቸው።+ +24 ሌሎችን የሚጠላ ሰው ጥላቻውን በከንፈሩ ይደብቃል፤በውስጡ ግን ተንኮል ይቋጥራል። +25 አነጋገሩን ቢያሳምርም እንኳ አትመነው፤በልቡ ውስጥ ሰባት አስጸያፊ ነገሮች አሉና።* +26 ጥላቻው በተንኮል ቢሸፈንምክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል። +27 ጉድጓድ የሚቆፍር እሱ ራሱ እዚያ ውስጥ ይወድቃል፤ድንጋይ የሚያንከባልልም ወደ እሱ ተመልሶ ይመጣበታል።+ +28 ውሸታም ምላስ የጎዳቻቸውን ሰዎች ትጠላለች፤የሚሸነግል አንደበትም ጥፋት ያስከትላል።+ +4 ልጆቼ ሆይ፣ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፤+ማስተዋል እንድታገኙ በትኩረት አዳምጡ፤ + 2 ጥሩ መመሪያ እሰጣችኋለሁና፤ትምህርቴን* አትተዉ።+ + 3 እኔ ለአባቴ ጥሩ ልጅ ነበርኩ፤+እናቴም ለእኔ ልዩ ፍቅር ነበራት።+ + 4 አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፦ “ልብህ ቃሌን አጥብቆ ይያዝ።+ ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ።+ + 5 ጥበብን አግኝ፤ ማስተዋልንም አዳብር።+ የምናገረውን ነገር አትርሳ፤ ከእሱም ፈቀቅ አትበል። + 6 ጥበብን አትተዋት፤ እሷም ትጠብቅሃለች። ውደዳት፤ እሷም ትከልልሃለች። + 7 ጥበብ በጣም አስፈላጊ* ነገር ናት፤+ ስለዚህ ጥበብን አግኝ፤ደግሞም ባለህ ነገር ሁሉ ማስተዋልን ለማግኘት ጥረት አድርግ።+ + 8 ለጥበብ የላቀ ዋጋ ስጥ፤ እሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች።+ ብታቅፋት ታከብርሃለች።+ + 9 በራስህ ላይ የሚያምር የአበባ ጉንጉን ትደፋልሃለች፤በውበት አክሊልም ታስጌጥሃለች።” +10 ልጄ ሆይ፣ አዳምጥ፤ የምናገረውንም ተቀበል፤የሕይወትህም ዘመን ይረዝማል።+ +11 በጥበብ መንገድ እንድትሄድ አስተምርሃለሁ፤+ቀና በሆነ ጎዳና እመራሃለሁ።+ +12 በምትጓዝበት ጊዜ እርምጃህ አይስተጓጎልም፤ብትሮጥም አትሰናከልም። +13 ተግሣጽን ያዛት፤ አትልቀቃትም።+ ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።+ +14 ወደ ክፉዎች መንገድ አትግባ፤በመጥፎ ሰዎች ጎዳናም አትሂድ።+ +15 ከእሱ ራቅ፤ በዚያም አትሂድ፤+ከዚያ ጎዳና ፈቀቅ በል፤ ደግሞም አልፈኸው ሂድ።+ +16 እነሱ ክፋት ካልሠሩ አይተኙምና። ሰውን ለውድቀት ካልዳረጉ እንቅልፍ በዓይናቸው አይዞርም። +17 የክፋት ምግብ ይበላሉ፤የዓመፅም ወይን ጠጅ ይጠጣሉ። +18 የጻድቃን መንገድ ግን ፍንትው ብሎ እንደሚወጣ የማለዳ ብርሃን ነው፤እንደ ቀትር ብርሃን ቦግ ብሎ እስኪበራም ድረስ እየደመቀ ይሄዳል።+ +19 የክፉዎች መንገድ እንደ ጨለማ ነው፤ምን እንደሚያሰናክላቸው አያውቁም። +20 ልጄ ሆይ፣ ቃሌን በትኩረት ተከታተል፤ንግግሬን በጥሞና አዳምጥ።* +21 ከእይታህ አይራቅ፤በልብህ ውስጥ አስቀምጠው፤+ +22 ለሚያገኙት ሕይወት ነውና፤+ለመላ አካላቸውም* ጤና ነው። +23 ከምንም ነገር በላይ ልብህን ጠብቅ፤+የሕይወት ምንጭ ከእሱ ዘንድ ነውና። +24 ጠማማ አንደበትን ከአንተ አስወግድ፤+አታላይ የሆነን ንግግርም ከአንተ አርቅ። +25 ዓይኖችህ በቀጥታ ይዩ፤አዎ፣ ፊት ለፊት በትኩረት ተመልከት።*+ +26 የእግርህን መንገድ ደልዳላ አድርግ፤*+መንገድህም ሁሉ አስተማማኝ ይሆናል። +27 ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል።+ እግርህን ከክፉ ነገር መልስ። +16 ሰው የልቡን ሐሳብ ያዘጋጃል፤*የሚሰጠው መልስ* ግን ከይሖዋ ዘንድ ነው።+ + 2 ሰው መንገዱ ሁሉ ትክክል* መስሎ ይታየዋል፤+ይሖዋ ግን ውስጣዊ ዓላማን* ይመረምራል።+ + 3 የምታደርገውን ሁሉ ለይሖዋ አደራ ስጥ፤*+ዕቅድህም ሁሉ ይሳካል። + 4 ይሖዋ ማንኛውንም ነገር ያዘጋጀው ለራሱ ዓላማ ነው፤ክፉውም ሰው እንኳ በመዓት ቀን እንዲጠፋ ያደርጋል።+ + 5 ይሖዋ ኩሩ ልብ ያለውን ሁሉ ይጸየፋል።+ እንዲህ ያለው ሰው ሳይቀጣ እንደማይቀር እርግጠኛ ሁን። + 6 በታማኝ ፍቅርና በታማኝነት በደል ይሰረያል፤+ሰውም ይሖዋን በመፍራት ከክፋት ይርቃል።+ + 7 ይሖዋ በሰው አካሄድ ደስ በሚሰኝበት ጊዜጠላቶቹ እንኳ ሳይቀሩ ከሰውየው ጋር ሰላም እንዲኖራቸው ያደርጋል።+ + 8 አግባብ ባልሆነ መንገድ ከሚገኝ ብዙ ገቢ ይልቅበጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።+ + 9 ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፤ይሖዋ ግን አካሄዱን ይመራለታል።+ +10 የንጉሥ ከንፈር በመንፈስ ተመርቶ ውሳኔ* መስጠት ይገባዋል፤+ፍትሕን ፈጽሞ ማዛባት የለበትም።+ +11 ትክክለኛ መለኪያና ሚዛን ከይሖዋ ናቸው፤በከረጢት ውስጥ ያሉት መለኪያዎች ሁሉ የእሱ ሥራ ናቸው።+ +12 ክፉ ድርጊት በነገሥታት ዘንድ አስጸያፊ ነው፤+ዙፋን የሚጸናው በጽድቅ ነውና።+ +13 ነገሥታት የጽድቅ ንግግር ደስ ያሰኛቸዋል። ሐቁን የሚናገር ሰው ይወዳሉ።+ +14 የንጉሥ ቁጣ እንደ ሞት መልእክተኛ ነው፤+ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ያበርደዋል።*+ +15 የንጉሥ ፊት ሲፈካ ሰው በደስታ ይኖራል፤ሞገሱም ዝናብ እንዳዘለ የበልግ ደመና ነው።+ +16 ጥበብን ማግኘት ወርቅ ከማግኘት ምንኛ የተሻለ ነው!+ ማስተዋልን ማግኘትም ብር ከማግኘት ይመረጣል።+ +17 ቅኖች ከክፋት ጎዳና ይርቃሉ። መንገዱን የሚ��ብቅ ሁሉ በሕይወት ይኖራል።*+ +18 ኩራት ጥፋትን፣የትዕቢት መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።+ +19 የትዕቢተኞችን ምርኮ ከመካፈል ይልቅከየዋሆች ጋር የትሕትና መንፈስ* ማሳየት ይሻላል።+ +20 አንድን ነገር ጠለቅ ብሎ የሚያስተውል ሰው ስኬታማ ይሆናል፤*በይሖዋ የሚታመንም ደስተኛ ነው። +21 ልቡ ጥበበኛ የሆነ ሰው አስተዋይ ይባላል፤+በደግነት የሚናገርም* የማሳመን ችሎታ አለው።+ +22 ጥልቅ ማስተዋል ለባለቤቱ የሕይወት ምንጭ ነው፤ሞኞች ግን በገዛ ሞኝነታቸው ይቀጣሉ። +23 የጥበበኛ ሰው ልብ፣ አንደበቱ ጥልቅ ማስተዋል እንዲኖረው ያደርጋል፤+ለንግግሩም የማሳመን ችሎታ ይጨምርለታል። +24 ደስ የሚያሰኝ ቃል እንደ ማር እንጀራ ነው፤ለነፍስ* ጣፋጭ፣ ለአጥንትም ፈውስ ነው።+ +25 ለሰው ትክክለኛ መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል።+ +26 ሠራተኛን የምግብ ፍላጎቱ* ተግቶ እንዲሠራ ያደርገዋል፤ረሃቡ* እንዲህ እንዲያደርግ ያስገድደዋልና።+ +27 የማይረባ ሰው ክፋትን ይምሳል፤+ንግግሩ እንደሚለበልብ እሳት ነው።+ +28 ነገረኛ ሰው* ጭቅጭቅ ያስነሳል፤+ስም አጥፊም የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል።+ +29 ዓመፀኛ ሰው ባልንጀራውን ክፉ ነገር እንዲሠራ ያግባባዋል፤ወደተሳሳተ መንገድም ይመራዋል። +30 በዓይኑ እየጠቀሰ ተንኮል ይሸርባል። ከንፈሮቹን ነክሶ ሸር ይሠራል። +31 ሽበት በጽድቅ መንገድ ሲገኝ+የውበት* ዘውድ ነው።+ +32 ቶሎ የማይቆጣ ሰው+ ከኃያል ሰው፣ስሜቱን የሚቆጣጠርም* ከተማን ድል ከሚያደርግ ሰው ይሻላል።+ +33 ዕጣ ጭን ላይ ይጣላል፤+ውሳኔውን በሙሉ የሚያስተላልፈው ግን ይሖዋ ነው።+ +6 ልጄ ሆይ፣ ለባልንጀራህ ዋስ* ብትሆን፣+የማታውቀውን ሰው እጅ ብትመታ፣*+ + 2 በገባኸው ቃል ብትጠመድ፣ከአፍህ በወጣው ቃል ብትያዝ፣+ + 3 ልጄ ሆይ፣ በባልንጀራህ እጅ ወድቀሃልና፣ይህን በማድረግ ራስህን ነፃ አውጣ፦ ሂድና ባልንጀራህን በትሕትና አጥብቀህ ለምነው።+ + 4 ይህን ሳታደርግ አትተኛ፤በዓይንህም እንቅልፍ አይዙር። + 5 እንደ ሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ፣እንደ ወፍም ከወፍ አዳኝ እጅ ራስህን አድን። + 6 አንተ ሰነፍ፣ ወደ ጉንዳን ሂድ፤+መንገዷንም በጥሞና ተመልክተህ ጥበበኛ ሁን። + 7 አዛዥ፣ አለቃ ወይም ገዢ ባይኖራትም እንኳ፣ + 8 ምግቧን በበጋ ታዘጋጃለች፤+ቀለቧንም በመከር ወቅት ትሰበስባለች። + 9 አንተ ሰነፍ፣ የምትጋደመው እስከ መቼ ነው? ከእንቅልፍህ የምትነሳውስ መቼ ነው? +10 ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣+ +11 ድህነት እንደ ወንበዴ፣እጦትም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።+ +12 የማይረባና ክፉ ሰው ንግግሩ ጠማማ ነው፤+ +13 በዓይኑ ይጣቀሳል፤+ በእግሩ ምልክት ይሰጣል፤ በጣቶቹም ይጠቁማል። +14 ጠማማ በሆነው ልቡ፣ነጋ ጠባ ሴራ ይጠነስሳል፤+ ጠብም ይዘራል።+ +15 በመሆኑም ጥፋት በድንገት ይመጣበታል፤እንደማይጠገን ሆኖ በቅጽበት ይሰበራል።+ +16 ይሖዋ የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤እንዲያውም እሱ የሚጸየፋቸው* ነገሮች ሰባት ናቸው፦ +17 ትዕቢተኛ ዓይን፣+ ውሸታም ምላስ፣+ ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች፣+ +18 ክፉ ሐሳብ የሚያውጠነጥን ልብና+ ወደ ክፋት በፍጥነት የሚሮጡ እግሮች፣ +19 ባወራ ቁጥር ውሸት የሚናገር ሐሰተኛ ምሥክርና+በወንድማማቾች መካከል ጠብ የሚዘራ ሰው።+ +20 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፤የእናትህንም መመሪያ* ቸል አትበል።+ +21 ምንጊዜም በልብህ አኑራቸው፤በአንገትህም ዙሪያ እሰራቸው። +22 በምትሄድበት ሁሉ ይመራሃል፤ስትተኛም ይጠብቅሃል፤ስትነቃም ያነጋግርሃል።* +23 ትእዛዙ መብራት ነውና፤+ሕጉም ብርሃን ነው፤+የተግሣጽ ወቀሳም ወደ ሕይወት ይመራል።+ +24 ከክፉ ሴት፣+ ከባለጌ* ሴትምየሚያባብል አንደበት ይጠብቁሃል።+ +25 ውበቷን በልብህ አትመኝ፤+የሚያማምሩ ዓይኖቿም አይማርኩህ፤ +26 አንድ ሰው በዝሙት አዳሪ የተነሳ ለድህነት ይዳረጋልና፤*+አመንዝራ ሴት ደግሞ የሰውን ውድ ሕይወት* ታጠምዳለች። +27 በጉያው እሳት ታቅፎ ልብሱ የማይቃጠልበት ሰው አለ?+ +28 ወይስ በፍም ላይ ተራምዶ እግሮቹ የማይቃጠሉበት ሰው ይኖራል? +29 ከባልንጀራው ሚስት ጋር የሚተኛ ሰውም እንደዚሁ ነው፤የሚነካት ሁሉ መቀጣቱ አይቀርም።+ +30 ሌባ በተራበ ጊዜ ራሱን* ሊያጠግብ ቢሰርቅ፣ሰዎች በንቀት አያዩትም። +31 በተያዘ ጊዜ ግን ሰባት እጥፍ ይከፍላል፤በቤቱ ያለውን ውድ ነገር ሁሉ ያስረክባል።+ +32 ከሴት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሁሉ ማስተዋል* ይጎድለዋል፤እንዲህ የሚያደርግ ሰው በራሱ* ላይ ጥፋት ያመጣል።+ +33 የሚያተርፈው ነገር ቢኖር ቁስልና ውርደት ነው፤+ኀፍረቱም መቼም አይወገድም።+ +34 ቅናት ባልን እጅግ ያስቆጣዋልና፤ለበቀል በሚነሳበት ጊዜም ፈጽሞ ርኅራኄ አያሳይም።+ +35 ማንኛውንም ዓይነት ካሳ* አይቀበልም፤ምንም ያህል ስጦታ ብታቀርብለት ቁጣው አይበርድም። +25 እነዚህም የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ+ ሰዎች የጻፏቸው* የሰለሞን ምሳሌዎች ናቸው፦+ + 2 አንድን ጉዳይ መሰወር ለአምላክ ክብሩ ነው፤+ጉዳይን በሚገባ መመርመር ደግሞ ለነገሥታት ክብራቸው ነው። + 3 ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉየንጉሥም ልብ አይመረመርም። + 4 የብርን ቆሻሻ አስወግድ፤ሙሉ በሙሉም የጠራ ይሆናል።+ + 5 ክፉን ሰው ከንጉሥ ፊት አስወግድ፤ዙፋኑም በጽድቅ ይጸናል።+ + 6 በንጉሥ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤+ታላላቅ ሰዎችም ባሉበት ስፍራ አትቀመጥ፤+ + 7 በተከበረ ሰው ፊት ከሚያዋርድህ እሱ ራሱ “ወደዚህ ከፍ በል” ቢልህ ይሻላልና።+ + 8 ክስ ለመመሥረት አትቸኩል፤የኋላ ኋላ ባልንጀራህ ቢያዋርድህ ምን ይውጥሃል?+ + 9 ከባልንጀራህ ጋር ስለ ራስህ ጉዳይ ተሟገት፤+ሆኖም በሚስጥር የተነገረህን ጉዳይ* አትግለጥ፤+ +10 አለዚያ የሚሰማህ ሰው ያዋርድሃል፤ያናፈስከውንም መጥፎ ወሬ* መመለስ አትችልም። +11 በተገቢው ጊዜ የተነገረ ቃልከብር በተሠራ ዕቃ ላይ* እንዳለ የወርቅ ፖም ነው።+ +12 በጥበብ ወቀሳ የሚሰጥ ሰው፣ የሚሰማ ጆሮ ላለውእንደ ወርቅ ጉትቻና ከጥሩ ወርቅ እንደተሠራ ጌጥ ነው።+ +13 ታማኝ መልእክተኛ ለላኩት ሰዎችበመከር ወቅት እንደሚገኝ የበረዶ ቅዝቃዜ ነው፤የጌታውን መንፈስ* ያድሳልና።+ +14 የማይሰጠውን ስጦታ* እሰጣለሁ እያለ ጉራውን የሚነዛ ሰውዝናብ እንደማያመጣ ደመናና ነፋስ ነው።+ +15 በትዕግሥት አዛዥን ማሸነፍ ይቻላል፤ለስላሳም አንደበት* አጥንትን ይሰብራል።+ +16 ማር ካገኘህ የሚበቃህን ያህል ብቻ ብላ፤ከልክ በላይ ከበላህ ሊያስመልስህ ይችላልና።+ +17 እንዳይሰለችህና እንዳይጠላህወደ ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ። +18 በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሠክርእንደ ቆመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ሹል ፍላጻ ነው።+ +19 በችግር ወቅት እምነት በማይጣልበት* ሰው መተማመን፣እንደተሰበረ ጥርስና እንደሰለለ እግር ነው። +20 ላዘነ ልብ የሚዘምር ሰው፣በብርድ ቀን ልብሱን እንደሚያወልቅ፣በሶዳም ላይ እንደተጨመረ ኮምጣጤ ነው።+ +21 ጠላትህ* ቢራብ ምግብ ስጠው፤ቢጠማ ውኃ ስጠው፤+ +22 ይህን ብታደርግ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህና፤*+ይሖዋም ወሮታ ይከፍልሃል። +23 የሰሜን ነፋስ ኃይለኛ ዝናብ ያመጣል፤ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቆጣል።+ +24 ከጨቅጫቃ* ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖርበጣሪያ ማዕዘን ላይ መኖር ይሻላል።+ +25 ቀዝቃዛ ውኃ የዛለችን ነፍስ* እንደሚያረካ ሁሉከሩቅ አገር የመጣ መልካም ወሬም እንዲሁ ነው።+ +26 ለክፉ ሰው የሚንበረከክ* ጻድቅ፣እንደጨቀየ ምንጭና እንደተበከለ የውኃ ጉድጓድ ነው። +27 ብዙ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤+የራስንም ክብር መሻት አያስከብርም።+ +28 ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ሰው*ቅጥር እንደሌላት የፈረሰች ከተማ ነው።+ +10 የሰለሞን ምሳሌዎች።+ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤+ሞኝ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናል። + 2 በክፋት የተገኘ ሀብት ምንም ፋይዳ የለውም፤ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።+ + 3 ይሖዋ ጻድቅ ሰው እንዲራብ* አያደርግም፤+የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል። + 4 ሥራ የፈቱ እጆች ያደኸያሉ፤+ትጉ እጆች ግን ብልጽግና ያስገኛሉ።+ + 5 ጥልቅ ማስተዋል ያለው ልጅ እህሉን በበጋ ይሰበስባል፤አሳፋሪ ልጅ ግን በመከር ወቅት ለጥ ብሎ ይተኛል።+ + 6 በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፤+የክፉዎች አፍ ግን የዓመፅ ዕቅዳቸውን ይሰውራል። + 7 የጻድቅ መታሰቢያ* በረከት ያስገኛል፤+የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል።*+ + 8 ጥበበኛ ልብ ያለው ሰው መመሪያዎችን* ይቀበላል፤+በሞኝነት የሚናገር ሰው ግን ጥፋት ይደርስበታል።+ + 9 ንጹሕ አቋሙን* ጠብቆ የሚሄድ ያለስጋት ይመላለሳል፤+መንገዱን ጠማማ የሚያደርግ ግን ይጋለጣል።+ +10 በተንኮል የሚጣቀስ ሐዘን ያመጣል፤+በሞኝነት የሚናገር ሰውም ጥፋት ይደርስበታል።+ +11 የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ነው፤+የክፉዎች አፍ ግን የዓመፅ ዕቅዳቸውን ይሰውራል።+ +12 ጥላቻ ጭቅጭቅ ያስነሳል፤ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ይሸፍናል።+ +13 አስተዋይ በሆነ ሰው ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፤+በትር ግን ማስተዋል* ለጎደለው ሰው ጀርባ ነው።+ +14 ጥበበኞች እውቀትን እንደ ውድ ሀብት ያከማቻሉ፤+የሞኝ ሰው አፍ ግን ጥፋት ይጋብዛል።+ +15 የባለጸጋ ሀብት* የተመሸገ ከተማው ነው። ድሆችን የሚያጠፋቸው ድህነታቸው ነው።+ +16 የጻድቅ ሰው ሥራ ወደ ሕይወት ይመራል፤የክፉ ሰው ፍሬ ግን ወደ ኃጢአት ይመራል።+ +17 ተግሣጽን የሚቀበል ለሌሎች የሕይወት መንገድ ይሆናል፤*ወቀሳን ችላ የሚል ግን ሌሎች መንገድ እንዲስቱ ያደርጋል። +18 ጥላቻውን የሚሸፋፍን ሰው ሐሰት ይናገራል፤+ተንኮል ያዘለ ወሬ* የሚያስፋፋ ሰውም ሞኝ ነው። +19 ከቃላት ብዛት ስህተት አይታጣም፤+ከንፈሩን የሚገታ ግን ልባም ሰው ነው።+ +20 የጻድቅ አንደበት ጥራት ያለው ብር ነው፤+የክፉ ሰው ልብ ግን እርባና የለውም። +21 የጻድቅ ከንፈሮች ብዙዎችን ይመግባሉ፤*+ሞኞች ግን ማስተዋል ስለሚጎድላቸው ይሞታሉ።+ +22 የይሖዋ በረከት ባለጸጋ ታደርጋለች፤+እሱም ከበረከቱ ጋር ሥቃይን* አይጨምርም። +23 አሳፋሪ ምግባር መፈጸም ለሞኝ ሰው እንደ ጨዋታ ነው፤ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ጥበበኛ ነው።+ +24 ክፉ ሰው የፈራው ነገር ይደርስበታል፤ጻድቅ ግን የተመኘውን ያገኛል።+ +25 አውሎ ነፋስ ሲያልፍ ክፉ ሰው ተጠርጎ ይወሰዳል፤+ጻድቅ ግን ለዘላለም እንደሚኖር መሠረት ነው።+ +26 ኮምጣጤ ጥርስን፣ ጭስም ዓይንን እንደሚጎዳ፣ሰነፍም ለሚልከው ሰው* እንዲሁ ነው። +27 ይሖዋን መፍራት ዕድሜን ያስረዝማል፤+የክፉዎች ዕድሜ ግን በአጭሩ ይቀጫል።+ +28 የጻድቃን ተስፋ ደስታ ያስገኛል፤+የክፉዎች ተስፋ ግን መና ይቀራል።+ +29 የይሖዋ መንገድ፣ ያለነቀፋ ለሚመላለስ ሰው መሸሸጊያ ነው፤+ለክፉ አድራጊዎች ግን መጥፊያቸው ነው።+ +30 ጻድቅ ሰው ምንም ነገር አይጥለውም፤+ክፉዎች ግን በምድር ላይ መኖራቸውን አይቀጥሉም።+ +31 የጻድቅ አፍ ጥበብን ያፈልቃል፤*ጠማማ ምላስ ግን ትቆረጣለች። +32 የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ደስ የሚያሰኘው ነገር ምን እንደሆነ ያውቃሉ፤የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነው። +14 ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትገነባለች፤+ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች። + 2 አካሄዱ ቅን የሆነ ሰው ይሖዋን ይፈራል፤መንገዱ መሠሪ* የሆነ ግን ይንቀዋል። + 3 በሞኝ ሰው አፍ የትዕቢት በትር አለ፤የጥበበኞች ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። + 4 ከብት በሌለበት ግርግሙ ንጹሕ ይሆናል፤የበሬ ጉልበት ግን ብዙ ምርት ያስገኛል። + 5 ሐቀኛ ምሥክር አይዋሽም፤ሐሰተኛ ምሥክር ግን ባወራ ቁጥር ይዋሻል።+ + 6 ፌዘኛ ጥበብን ይፈልጋል፤ ሆኖም አያገኛትም፤አስተዋይ ሰው ግን እውቀትን በቀላሉ ያገኛል።+ + 7 ከሞኝ ሰው ራቅ፤ከከንፈሮቹ ምንም ዓይነት እውቀት አታገኝምና።+ + 8 ብልህ ሰው የሚሄድበትን መንገድ በጥበብ ያስተውላል፤ሞኞች ግን በቂልነታቸው ይታለላሉ።*+ + 9 ሞኞች በደል ፈጽመው* ያፌዛሉ፤+ቅኖች ግን እርቅ ለመፍጠር ፈቃደኞች ናቸው።* +10 ልብ የራሱን* ምሬት ያውቃል፤ደስታውንም ሌላ ሰው ሊጋራው አይችልም። +11 የክፉዎች ቤት ይወድማል፤+የቅኖች ድንኳን ግን ይበለጽጋል። +12 ለሰው ትክክለኛ መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤+በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል።+ +13 አንድ ሰው እየሳቀ እንኳ ልቡ ሊያዝን ይችላል፤ደስታም በሐዘን ሊቋጭ ይችላል። +14 በልቡ ጋጠወጥ የሆነ ሰው አካሄዱ የሚያስከትለውን መዘዝ ይቀበላል፤+ጥሩ ሰው ግን የሥራውን ውጤት ያገኛል።+ +15 ተላላ* ቃልን ሁሉ ያምናል፤ብልህ ግን አካሄዱን አንድ በአንድ ያጤናል።+ +16 ጥበበኛ ሰው ጠንቃቃ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤ሞኝ ግን ደንታ ቢስ ነው፤* ደግሞም ከልክ በላይ በራሱ ይመካል። +17 ለቁጣ የሚቸኩል ሰው የሞኝነት ተግባር ይፈጽማል፤+በጥሞና የሚያስብ ሰው* አይወደድም። +18 ተላሎች* ሞኝነትን ይወርሳሉ፤ብልሆች ግን እውቀትን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+ +19 መጥፎ ሰዎች በጥሩ ሰዎች ፊት፣ክፉዎችም በጻድቅ ደጃፍ ይሰግዳሉ። +20 ድሃ በባልንጀሮቹ ዘንድ እንኳ የተጠላ ነው፤+የባለጸጋ ወዳጆች ግን ብዙ ናቸው።+ +21 ባልንጀራውን የሚንቅ ኃጢአት ይሆንበታል፤ለችግረኞች የሚራራ ግን ደስተኛ ነው።+ +22 ተንኮል የሚሸርቡ ሰዎች መንገድ ይስቱ የለም? መልካም ነገር ለመሥራት የሚያስቡ ሰዎች ግን ታማኝ ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ።+ +23 በትጋት ያከናወኑት ነገር ሁሉ ጥቅም ያስገኛል፤እንዲሁ ማውራት ግን ችግር ላይ ይጥላል።+ +24 የጥበበኞች ዘውድ ሀብታቸው ነው፤የሞኞች ቂልነት ግን ለከፋ ሞኝነት ይዳርጋል።+ +25 እውነተኛ ምሥክር ሕይወትን* ይታደጋል፤አታላይ ግን ባወራ ቁጥር ይዋሻል። +26 ይሖዋን የሚፈራ ሁሉ በማንኛውም ነገር በእሱ ይታመናል፤+ልጆቹም መጠጊያ ያገኛሉ።+ +27 ይሖዋን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል። +28 የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ግርማ ነው፤+ተገዢዎች የሌሉት ገዢ ግን ይጠፋል። +29 ቶሎ የማይቆጣ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤+ትዕግሥት የሌለው ሰው ግን ሞኝነቱን ይገልጣል።+ +30 የሰከነ ልብ ለሰውነት ሕይወት* ይሰጣል፤ቅናት ግን አጥንትን ያነቅዛል።+ +31 ችግረኛን የሚያጭበረብር ፈጣሪውን ይሰድባል፤+ለድሃ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል።+ +32 ክፉ ሰው በገዛ ክፋቱ ይወድቃል፤ጻድቅ ግን ንጹሕ አቋሙ* መጠጊያ ያስገኝለታል።+ +33 ጥበብ በአስተዋይ ልብ ውስጥ በጸጥታ ታርፋለች፤+በሞኞች መካከል ግን ራሷን ትገልጣለች። +34 ጽድቅ አንድን ብሔር ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤+ኃጢአት ግን ሕዝብን ታዋርዳለች። +35 ንጉሥ አስተውሎ በሚሠራ አገልጋይ ደስ ይሰኛል፤+አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም አገልጋይ ላይ ግን ይቆጣል።+ +9 እውነተኛ ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አዘጋጀች። + 2 ሥጋዋን በሚገባ አዘጋጀች፤*የወይን ጠጇንም ደባለቀች፤ደግሞም ገበታዋን አሰናዳች። + 3 ከከተማዋ በላይ ባሉ ከፍታ ቦታዎች ላይ ሆነውእንዲህ ብለው እንዲጣሩ ሴት አገልጋዮቿን ላከች፦+ + 4 “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።” ማስተዋል* ለጎደለው እንዲህ ትላለች፦ + 5 “ኑ፣ ያዘጋጀሁትን ምግብ ብሉ፤የደባለቅኩትንም የወይን ጠጅ ጠጡ። + 6 አላዋቂነታችሁን ተዉ፤* በሕይወትም ኑሩ፤+በማስተዋል መንገድ ወደ ፊት ሂዱ።”+ + 7 ፌዘኛን የሚያርም በራሱ ላይ ውርደት ያመጣል፤+ክፉን ሰው የሚወቅስም ሁሉ ጉዳት ይደርስበታል። + 8 ፌዘኛን አትውቀስ፤ አለዚያ ይጠላሃል።+ ጥበበኛን ሰው ውቀሰው፤ እሱም ይወድሃል።+ + 9 ጥበበኛን ሰው አስተምረው፤ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል።+ ጻድቅን ሰው አስተምረው፤ ተጨማሪ እውቀት ያገኛል። +10 የጥበብ መጀመሪያ ይሖዋን መፍራት ነው፤+እጅግ ቅዱስ ስለሆነው አምላክ ማወቅም+ ማስተዋል ነው። +11 በእኔ ምክንያት ዘመንህ ይረዝማል፤+በሕይወትህም ላይ ዕድሜ ይጨመርልሃል። +12 ጥበበኛ ብትሆን፣ ጥበበኛነትህ የሚጠቅመው ራስህን ነው፤ፌዘኛ ብትሆን ግን መዘዙን የምትቀበለው አንተው ነህ። +13 ማስተዋል የጎደላት ሴት ጯኺ ናት።+ እሷ ጨርሶ ማመዛዘን አትችልም፤ ደግሞም አንዳች ነገር አታውቅም። +14 በከተማዋ ከፍ ያሉ ቦታዎች ላይ፣በቤቷ ደጃፍ ወንበር ላይ ትቀመጣለች፤+ +15 በጎዳናው የሚያልፉትን፣ቀጥ ብለው በመንገዳቸው የሚሄዱትን ትጣራለች፦ +16 “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።” ማስተዋል* ለጎደላቸው ሁሉ እንዲህ ትላለች፦+ +17 “የተሰረቀ ውኃ ይጣፍጣል፤ተደብቀው የበሉት ምግብም ይጥማል።”+ +18 እሱ ግን በሞት የተረቱት በዚያ እንዳሉ፣እንግዶቿም በመቃብር* ጥልቅ ውስጥ እንደሚገኙ አያውቅም።+ +27 ነገ በሚሆነው ነገር አትመካ፤ቀን የሚያመጣውን* አታውቅምና።+ + 2 የገዛ አፍህ ሳይሆን ሌላ ሰው ያመስግንህ፤*የገዛ ከንፈርህ ሳይሆን ሌሎች* ያወድሱህ።+ + 3 ድንጋይ ከባድ ነው፤ አሸዋም ሸክም ነው፤የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።+ + 4 ንዴት ጨካኝ ነው፤ ቁጣም ጎርፍ ነው፤ይሁንና ቅናትን ማን ሊቋቋም ይችላል?+ + 5 ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ወቀሳ ይሻላል።+ + 6 የወዳጅ ማቁሰል ከታማኝነት የሚመነጭ ነው፤+የጠላት መሳም ግን የበዛ* ነው። + 7 የጠገበ ሰው* ከማር እንጀራ የሚገኝን ማር አይፈልግም፤*የተራበ* ግን የሚመር ነገር እንኳ ይጣፍጠዋል። + 8 ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን* ሰውከጎጆዋ ወጥታ እንደምትባዝን ወፍ ነው። + 9 ዘይትና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤በቀና ምክር ላይ* የተመሠረተ ጥሩ ወዳጅነትም እንዲሁ ነው።+ +10 መከራ ባጋጠመህ ቀን የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ ትተህወደ ገዛ ወንድምህ ቤት አትግባ፤ሩቅ ቦታ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።+ +11 ልጄ ሆይ፣ ለሚነቅፈኝ መልስ መስጠት እችል ዘንድጥበበኛ ሁን፤+ ልቤንም ደስ አሰኘው።+ +12 ብልህ ሰው አደጋ አይቶ ይሸሸጋል፤+ተሞክሮ የሌለው ሰው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም ይቀበላል።* +13 አንድ ሰው ለማያውቀው ሰው ዋስ ከሆነ ልብሱን ውሰድበት፤ይህን ያደረገው ለባዕድ ሴት* ብሎ ከሆነ መያዣውን ውሰድ።+ +14 ሰው በማለዳ ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን ቢባርክእንደ እርግማን ይቆጠርበታል። +15 ጨቅጫቃ* ሚስት በዝናባማ ቀን ያለማቋረጥ እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት።+ +16 እሷን መግታት የሚችል ሁሉ ነፋስን መግታት፣ዘይትንም በቀኝ እጁ መጨበጥ ይችላል። +17 ብረት ብረትን እንደሚስል ሁሉሰውም ጓደኛውን ይስለዋል።*+ +18 የበለስን ዛፍ የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤+ጌታውንም የሚንከባከብ ክብር ይጎናጸፋል።+ +19 ውኃ የሰውን ፊት እንደሚያንጸባርቅ ሁሉ፣የሰውም ልብ የሌላ ሰው ልብ ነጸብራቅ ነው። +20 መቃብርና የጥፋት ቦታ* አይጠግቡም፤+ልክ እንደዚሁም የሰው ዓይን ፈጽሞ አይጠግብም። +21 ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤+ሰው��� በሚቀበለው ውዳሴ ይፈተናል።* +22 ሞኝን ሙቀጫ ውስጥ ከተህ በዘነዘና ብትወቅጠውናእንደ እህል ብታደቀው እንኳሞኝነቱ ከእሱ አይወገድም። +23 የመንጋህን ሁኔታ በሚገባ እወቅ። በጎችህን በደንብ ተንከባከብ፤*+ +24 ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤+አክሊልም* ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም። +25 ሣሩ በቦታው የለም፤ አዲስ ሣርም በቅሏል፤በተራሮች ላይ ያለው ተክልም ተሰብስቧል። +26 የበግ ጠቦቶች ለልብስ፣አውራ ፍየሎችም ለመሬት መግዣ ይሆኑልሃል። +27 ደግሞም አንተንና ቤተሰብህን ለመመገብ፣ልጃገረዶችህንም በሕይወት ለማኖር የሚያስችል በቂ የፍየል ወተት ይኖርሃል። +13 ጥበበኛ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይቀበላል፤+ፌዘኛ ግን ተግሣጽን* አይሰማም።+ + 2 ሰው ከአፉ ፍሬ መልካም ነገር ይበላል፤+ከዳተኞች* ግን ዓመፅን ይመኛሉ። + 3 አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል።*+ አፉን የሚከፍት ግን ይጠፋል።+ + 4 ሰነፍ ሰው ይመኛል፤ ነገር ግን ምንም አያገኝም፤*+ትጉ ሰው* ግን በሚገባ ይጠግባል።*+ + 5 ጻድቅ ውሸትን ይጠላል፤+የክፉ ሰው ድርጊት ግን ኀፍረትና ውርደት ያመጣበታል። + 6 በመንገዱ ነቀፋ የሌለበትን ሰው ጽድቅ ትጠብቀዋለች፤+ክፋት ግን ኃጢአተኛውን ትጥለዋለች። + 7 ምንም ሳይኖረው ባለጸጋ መስሎ ለመታየት የሚሞክር ሰው አለ፤+ሌላው ደግሞ ብዙ ሀብት እያለው ድሃ መስሎ ይኖራል። + 8 የሰው ሀብት ለሕይወቱ* ቤዛ ነው፤+ድሃ ግን ምንም ዓይነት ስጋት የለበትም።+ + 9 የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤*+የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል።+ +10 እብሪተኝነት ጠብ ከመፍጠር ውጭ የሚያመጣው ነገር የለም፤+ምክር በሚሹ* ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።+ +11 በፍጥነት የተገኘ ሀብት* ይመናመናል፤+ጥቂት በጥቂት የሚያጠራቅም* ሰው ግን ሀብቱ ይጨምራል። +12 የዘገየ ተስፋ ልብን ያሳምማል፤+የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው።+ +13 መመሪያን የሚንቅ* ሁሉ ይቀጣል፤+ትእዛዝን የሚያከብር ግን ብድራት ያገኛል።+ +14 የጥበበኛ ሰው ትምህርት* የሕይወት ምንጭ ነው፤+ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል። +15 ጥልቅ ማስተዋል ሞገስ ያስገኛል፤የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው። +16 ብልህ ሰው ተግባሩን በእውቀት ያከናውናል፤+ሞኝ ሰው ግን የገዛ ራሱን ሞኝነት ይገልጣል።+ +17 ክፉ መልእክተኛ ችግር ውስጥ ይወድቃል፤+ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስ ያመጣል።+ +18 ተግሣጽን ችላ የሚል ሁሉ ይደኸያል፤ ይዋረዳልም፤እርማትን የሚቀበል* ግን ይከበራል።+ +19 ሰው* የተመኘው ነገር ሲፈጸም ደስ ይለዋል፤+ሞኞች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ።+ +20 ከጥበበኞች ጋር የሚሄድ ጥበበኛ ይሆናል፤+ከሞኞች ጋር የሚገጥም ግን ጉዳት ይደርስበታል።+ +21 ኃጢአተኞችን ጥፋት ያሳድዳቸዋል፤+ጻድቃንን ግን ብልጽግና ይክሳቸዋል።+ +22 ጥሩ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ይተዋል፤የኃጢአተኛ ሀብት ግን ለጻድቅ ይከማቻል።+ +23 የድሃ እርሻ ብዙ እህል ያስገኛል፤ሆኖም ከፍትሕ መጓደል የተነሳ ተጠራርጎ ይጠፋል።* +24 ልጁን በበትር ከመምታት* ወደኋላ የሚል ይጠላዋል፤+የሚወደው ግን ተግቶ* ይገሥጸዋል።+ +25 ጻድቅ ይበላል፤ የምግብ ፍላጎቱንም * ያረካል፤+የክፉ ሰው ሆድ ግን ባዶ ነው።+ +5 ልጄ ሆይ፣ ጥበቤን ልብ በል። ማስተዋልን በተመለከተ የምሰጠውን ትምህርት በጥሞና አዳምጥ፤*+ + 2 ይህም የማመዛዘን ችሎታህን እንድትጠብቅ፣በከንፈሮችህም እውቀትን በጥንቃቄ እንድትይዝ ነው።+ + 3 የጋጠወጥ* ሴት ከንፈር እንደ ማር እንጀራ ያንጠባጥባልና፤+አፏም ከዘይት ይለሰልሳል።+ + 4 በመጨረሻ ግን እንደ ጭቁኝ ትመርራለች፤+ደግሞም በሁለት በኩል እንደተሳለ ሰይፍ ትሆናለች።+ + 5 እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ። እርምጃዎቿ በቀጥታ ወደ መቃብር* ይመራሉ። + 6 ስለ ሕይወት መንገድ ግድ የላትም። በጎዳናዎቿ ላይ ትባዝናለች፤ ወዴት እንደሚወስዱም አታውቅም። + 7 እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤ከምናገረውም ቃል አትራቁ። + 8 ከእሷ ራቅ፤ወደ ቤቷም ደጃፍ አትቅረብ፤+ + 9 ይህም ክብርህን ለሌሎች አሳልፈህ እንዳትሰጥ ነው፤+ቀሪ የሕይወት ዘመንህም በመከራ የተሞላ እንዳይሆን ነው፤+ +10 ደግሞም እንግዳ የሆኑ ሰዎች ጥሪትህን* እንዳያሟጥጡ፣+የለፋህበትንም ነገር የባዕድ አገር ሰው እንዳይወርሰው ነው። +11 አለዚያ በሕይወትህ ማብቂያሥጋህና መላ ሰውነትህ እየመነመነ ሲሄድ ትቃትታለህ፤+ +12 ደግሞም እንዲህ ትላለህ፦ “ምነው ተግሣጽን ጠላሁ! ልቤስ ምነው ወቀሳን ናቀ! +13 የአስተማሪዎቼን ቃል አላዳመጥኩም፤መምህሮቼንም በጥሞና አልሰማሁም። +14 በመላው ጉባኤ መካከል*ሙሉ በሙሉ ልጠፋ ምንም አልቀረኝም ነበር።”+ +15 ከራስህ ጉድጓድ እንዲሁምከገዛ ምንጭህ የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ።*+ +16 ምንጮችህ ወደ ውጭ፣ጅረቶችህም በአደባባይ ሊፈሱ ይገባል?+ +17 ለአንተ ብቻ ይሁኑ፤ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ።+ +18 ምንጭህ የተባረከ ይሁን፤ከወጣትነት ሚስትህም ጋር ደስ ይበልህ፤+ +19 እሷ እንደምትወደድ ሚዳቋና እንደምታምር የተራራ ፍየል* ናት።+ ጡቶቿ ምንጊዜም ያርኩህ።* ፍቅሯ ምንጊዜም ይማርክህ።+ +20 ልጄ ሆይ፣ ጋጠወጥ* ሴት ለምን ትማርክሃለች?ባለጌ* ሴትንስ ለምን ታቅፋለህ?+ +21 የሰው መንገድ በይሖዋ ዓይኖች ፊት ነውና፤እሱ መንገዱን ሁሉ ይመረምራል።+ +22 ክፉ ሰው የገዛ ጥፋቱ ወጥመድ ይሆንበታል፤ኃጢአቱም እንደ ገመድ ተብትቦ ይይዘዋል።+ +23 ተግሣጽ ከማጣቱ የተነሳ ይሞታል፤በጣም ሞኝ ከመሆኑም የተነሳ መንገድ ይስታል። +21 የንጉሥ ልብ በይሖዋ እጅ እንዳለ ጅረት ነው።+ እሱ ደስ ወዳሰኘው አቅጣጫ ሁሉ ይመራዋል።+ + 2 ሰው መንገዱ ሁሉ ትክክል መስሎ ይታየዋል፤+ይሖዋ ግን ልብን ይመረምራል።*+ + 3 መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅትክክልና ፍትሐዊ የሆነ ነገር ማድረግ ይሖዋን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል።+ + 4 ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብየክፉዎች መብራት ናቸው፤ ደግሞም ኃጢአት ናቸው።+ + 5 የትጉ ሰው ዕቅድ ለስኬት ያበቃዋል፤*+ችኩሎች ሁሉ ግን ለድህነት ይዳረጋሉ።+ + 6 በሐሰተኛ ምላስ የሚገኝ ውድ ሀብትወዲያው እንደሚጠፋ ጉም ነው፤ ገዳይ ወጥመድም ነው።*+ + 7 ክፉዎች ፍትሕን ማስፈን ስለማይፈልጉየሚፈጽሙት ግፍ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።+ + 8 የበደለኛ ሰው መንገድ ጠማማ ነው፤የንጹሕ ሰው ሥራ ግን ቀና ነው።+ + 9 ከጨቅጫቃ* ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖርበጣሪያ ማዕዘን ላይ መኖር ይሻላል።+ +10 ክፉ ሰው* መጥፎ ነገር ይመኛል፤+ለባልንጀራው ሞገስ አያሳይም።+ +11 ፌዘኛ ሲቀጣ ተሞክሮ የሌለው ሰው ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ጥበበኛ ሰው ጥልቅ ማስተዋል ሲያገኝም እውቀት ይቀስማል።*+ +12 ጻድቅ የሆነው አምላክ፣ የክፉውን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ክፉዎችንም ይጠፉ ዘንድ ይገለብጣቸዋል።+ +13 ችግረኛው የሚያሰማውን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን ሁሉ፣እሱ ራሱ ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።+ +14 በድብቅ የተሰጠ ስጦታ ቁጣን ያበርዳል፤+በስውር የተሰጠ ጉቦም* ኃይለኛ ቁጣ እንዲከስም ያደርጋል። +15 ጻድቅ ፍትሐዊ ነገር ማድረግ ያስደስተዋል፤+ክፉ ድርጊት ለሚፈጽሙ ግን አስከፊ ነገር ነው። +16 ከማስተዋል መንገድ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣በሞት ከተረቱት ጋር ያርፋል።+ +17 ፈንጠዝያ* የሚወድ ሰው ይደኸያል፤+የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድ ባለጸጋ አይሆንም። +18 ክፉ ሰው ለጻድቅ ቤዛ ነው፤ከዳተኛ የሆነ ሰውም በቅን ሰው ፋንታ ይወሰዳል።+ +19 ጨቅጫቃና* ቁጡ ከሆነች ሚስት ጋር ከመኖርበምድረ በዳ መኖር ይሻላል።+ +20 ውድ ሀብትና ምርጥ ዘይት በጥበበኛ ሰው ቤት ይገኛል፤+ሞኝ ሰው ግን ያለውን ያባክናል።*+ +21 ጽድቅንና ታማኝ ፍቅርን የሚከታተል ሰው ሁሉሕይወትን፣ ጽድቅንና ክብርን ያገኛል።+ +22 ጥበበኛ ሰው የኃያላን ሰዎች ከተማ ላይ ይወጣል፤*የሚታመኑበትንም ብርታት ያዳክማል።+ +23 አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ፣ራሱን ከችግር ይጠብቃል።*+ +24 በእብሪት የመሰለውን የሚያደርግ ሰውእብሪተኛና ጉረኛ ይባላል።+ +25 ሰነፍ ሰው ምኞቱ ይገድለዋል፤እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።+ +26 ቀኑን ሙሉ በስግብግብነት ሲመኝ ይውላል፤ጻድቅ ግን ምንም ሳይሰስት ይሰጣል።+ +27 የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው።+ በክፉ ዓላማ ተነሳስቶ* ሲያቀርብማ ምንኛ የከፋ ይሆናል! +28 ውሸታም ምሥክር ይጠፋል፤+በጥሞና የሚያዳምጥ ሰው ግን የምሥክርነት ቃሉ ተቀባይነት ያገኛል።* +29 ክፉ ሰው ኀፍረት የሚባል ነገር አያውቅም፤+የቅን ሰው አካሄድ ግን አስተማማኝ ነው።*+ +30 ይሖዋን የሚጻረር ጥበብ፣ ማስተዋልም ሆነ ምክር ከንቱ ነው።+ +31 ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤+መዳን ግን ከይሖዋ ዘንድ ነው።+ +15 የለዘበ* መልስ ቁጣን ያበርዳል፤+ክፉ* ቃል ግን ቁጣን ያነሳሳል።+ + 2 የጥበበኞች ምላስ እውቀትን በሚገባ ይጠቀማል፤+የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ይገልጣል። + 3 የይሖዋ ዓይኖች በሁሉም ቦታ ናቸው፤ክፉዎችንም ሆነ ጥሩ ሰዎችን ይመለከታሉ።+ + 4 የረጋ አንደበት* የሕይወት ዛፍ ነው፤+ጠማማ ንግግር ግን ተስፋ ያስቆርጣል።* + 5 ሞኝ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል፤+ብልህ ግን እርማትን ይቀበላል።+ + 6 በጻድቅ ሰው ቤት ብዙ ሀብት አለ፤የክፉ ሰው ምርት* ግን ችግር ያስከትልበታል።+ + 7 የጥበበኞች ከንፈር እውቀትን ታስፋፋለች፤+የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።+ + 8 ይሖዋ የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤+የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል።+ + 9 ይሖዋ የክፉውን መንገድ ይጸየፋል፤+ጽድቅን የሚከታተለውን ግን ይወደዋል።+ +10 ከመንገድ የሚወጣ ሰው፣ ተግሣጽ መጥፎ* ነገር ይመስለዋል፤+ወቀሳን የሚጠላ ሁሉ ግን ይሞታል።+ +11 መቃብርና* የጥፋት ቦታ* በይሖዋ ፊት ወለል ብለው ይታያሉ።+ የሰዎች ልብማ በፊቱ ምንኛ የተገለጠ ነው!+ +12 ፌዘኛ የሚያርመውን* ሰው አይወድም።+ ጥበበኞችን አያማክርም።+ +13 ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፤የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይደቁሳል።+ +14 አስተዋይ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፤+የሞኞች አፍ ግን ቂልነትን ይመገባል።*+ +15 ጎስቋላ ሰው ዘመኑ ሁሉ አስከፊ ነው፤+ደስተኛ* ልብ ያለው ሰው ግን ሁልጊዜ ግብዣ ላይ ያለ ያህል ነው።+ +16 ከጭንቀት* ጋር ከሚገኝ ብዙ ሀብት ይልቅይሖዋን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።+ +17 ጥላቻ ባለበት የሰባ* ፍሪዳ ከመብላት ይልቅፍቅር ባለበት አትክልት መብላት ይሻላል።+ +18 ግልፍተኛ ሰው ጭቅጭቅ ይፈጥራል፤+ቶሎ የማይቆጣ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።+ +19 የሰነፍ መንገድ እንደ እሾህ አጥር ነው፤+የቅኖች መንገድ ግን እንደተስተካከለ አውራ ጎዳና ነው።+ +20 ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤+ሞኝ ግን እናቱን ያቃልላል።+ +21 ማስተዋል* የጎደለው ሰው ሞኝነት ያስደስተዋል፤+ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ቀጥተኛውን መንገድ ተከትሎ ይሄዳል።+ +22 መመካከር* ከሌለ የታቀደው ነገር ሳይሳካ ይቀራል፤በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል።+ +23 ሰው ትክክለኛውን መልስ በመስጠት* ሐሴት ያደርጋል፤+በትክክለኛው ጊዜ የተነገረ ቃልም ምንኛ መልካም ነው!+ +24 ጥልቅ ማስተዋል ያለው ሰው ወደ መቃብር* ከመውረድ ይድን ዘንድየሕይወት መንገድ ወደ ላይ ይመራዋል።+ +25 ይሖዋ የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤+የመበለቲቱን ወሰን ግን ያስከብራል።+ +26 ይሖዋ የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤+���ማረ ቃል ግን በፊቱ ንጹሕ ነው።+ +27 በማጭበርበር የተገኘ ትርፍ የሚያጋብስ ሰው በቤተሰቡ ላይ ችግር* ያመጣል፤+ጉቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።+ +28 የጻድቅ ልብ፣ መልስ ከመስጠቱ በፊት ያሰላስላል፤*+የክፉዎች አፍ ግን መጥፎ ነገር ይዘከዝካል። +29 ይሖዋ ከክፉዎች እጅግ የራቀ ነው፤የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።+ +30 ብሩህ ዓይን* ልብን ደስ ያሰኛል፤መልካም ዜናም አጥንትን ያበረታል።*+ +31 ሕይወት የሚያስገኝ ወቀሳን የሚሰማ፣በጥበበኛ ሰዎች መካከል ይኖራል።+ +32 ተግሣጽን ገሸሽ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ሕይወቱን* ያቃልላል፤+ወቀሳን የሚሰማ ሁሉ ግን ማስተዋል* ያገኛል።+ +33 ይሖዋን መፍራት ጥበብን ያስተምራል፤+ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።+ +22 መልካም ስም* ከብዙ ሀብት ይመረጣል፤+መከበር* ከብርና ከወርቅ ይሻላል። + 2 ሀብታምንና ድሃን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፦* ሁለቱንም የፈጠረው ይሖዋ ነው።+ + 3 ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል፤ተሞክሮ የሌለው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም* ይቀበላል። + 4 ትሕትናና ይሖዋን መፍራትሀብት፣ ክብርና ሕይወት ያስገኛል።+ + 5 በጠማማ ሰው መንገድ ላይ እሾህና ወጥመድ አለ፤ለሕይወቱ* ትልቅ ግምት የሚሰጥ ሁሉ ግን ከእነዚህ ይርቃል።+ + 6 ልጅን* ሊሄድበት በሚገባው መንገድ አሠልጥነው፤+በሚያረጅበት ጊዜም እንኳ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።+ + 7 ሀብታም ድሃን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪው ባሪያ ነው።+ + 8 ክፋትን የሚዘራ ሁሉ ጥፋትን ያጭዳል፤+የቁጣውም በትር ያከትማል።+ + 9 ለጋስ ሰው* ይባረካል፤ምግቡን ለድሃ ያካፍላልና።+ +10 ንቀት የሚያሳይን ሰው አባረው፤ጭቅጭቅም ይቀራል፤ጥልና* ስድብ ያከትማል። +11 ንጹሕ ልብ የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፣የንጉሥ ወዳጅ ይሆናል።+ +12 የይሖዋ ዓይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፤የከዳተኛን ቃል ግን ይሽራል።+ +13 ሰነፍ “ውጭ አንበሳ አለ! አደባባይ ላይ እገደላለሁ!” ይላል።+ +14 የጋጠወጥ* ሴት አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው።+ ይሖዋ ያወገዘው ሰው እዚያ ውስጥ ይወድቃል። +15 ሞኝነት በልጅ* ልብ ውስጥ ታስሯል፤+የተግሣጽ በትር ግን ከእሱ ያርቀዋል።+ +16 ሀብቱን ለመጨመር ድሃውን የሚያጭበረብር+እንዲሁም ለባለጸጋ ስጦታ የሚሰጥ ሰውየኋላ ኋላ ይደኸያል። +17 እውቀቴን በሙሉ ልብ እንድትቀበል+ጆሮህን አዘንብል፤ የጥበበኞችንም ቃል አዳምጥ፤+ +18 ምንጊዜም ይህ ቃል ሙሉ በሙሉ በከንፈሮችህ ላይ እንዲሆን+ቃሉን በውስጥህ መያዝህ መልካም ነውና።+ +19 በይሖዋ እንድትተማመን፣ዛሬ እውቀት እሰጥሃለሁ። +20 ከዚህ ቀደም ምክርናእውቀት የያዙ ሐሳቦች አልጻፍኩልህም? +21 ይህን ያደረግኩት ለላከህ ትክክለኛ ወሬ ይዘህ እንድትመለስ፣እውነት የሆነውንና እምነት የሚጣልበትን ቃል ላስተምርህ አይደለም? +22 ድሃውን ድሃ ስለሆነ ብቻ አትዝረፈው፤+ችግረኛውንም በከተማው በር ላይ ግፍ አትፈጽምበት፤+ +23 ይሖዋ ራሱ ይሟገትላቸዋልና፤+የሚያጭበረብሯቸውንም ሰዎች ሕይወት ያጠፋል።* +24 ከግልፍተኛ ሰው ጋር አትግጠም፤በቀላሉ ቱግ ከሚል ሰውም ጋር አትቀራረብ፤ +25 አለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤ለራስህም* ወጥመድ ይሆናል።+ +26 ዋስ ለመሆን እጅ እንደሚመቱ፣*ለብድር ተያዥ እንደሚሆኑ ሰዎች አትሁን።+ +27 የምትከፍለው ካጣህየተኛህበት አልጋ ከሥርህ ይወሰድብሃል! +28 አባቶችህ ያደረጉትንየጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ።+ +29 በሥራው የተካነን ሰው አይተሃል? በነገሥታት ፊት ይቆማል፤+ተራ በሆኑ ሰዎች ፊት አይቆምም። +3 ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ከሰማይ በታች ለሚከናወን ነገር ሁሉ ጊዜ አለው፦ + 2 ለመወለድ ጊዜ አለው፤* ለመሞትም ጊዜ አለው፤ለመትከል ጊዜ አለው፤ የተተከለውን ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ + 3 ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ + 4 ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ለዋይታ ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም* ጊዜ አለው፤ + 5 ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ለማቀፍ ጊዜ አለው፤ ከማቀፍ ለመቆጠብም ጊዜ አለው፤ + 6 ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ጠፍቷል ብሎ ለመተውም ጊዜ አለው፤ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ + 7 ለመቅደድ ጊዜ አለው፤+ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ዝም ለማለት ጊዜ አለው፤+ ለመናገርም ጊዜ አለው፤+ + 8 ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤+ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው። +9 ሠራተኛ ከልፋቱ ሁሉ የሚያገኘው ጥቅም ምንድን ነው?+ +10 አምላክ የሰው ልጆች እንዲጠመዱበት የሰጣቸውን ሥራ ተመለከትኩ። +11 አምላክ ሁሉንም ነገር በወቅቱ ውብ* አድርጎ ሠርቶታል።+ ደግሞም ዘላለማዊነትን በልባቸው ውስጥ አኑሯል፤ ይሁንና የሰው ልጆች እውነተኛው አምላክ ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ ያከናወነውን ሥራ በምንም ዓይነት መርምረው ሊደርሱበት አይችሉም። +12 ለሰው በሕይወት ዘመኑ ከመደሰትና መልካም ከማድረግ የተሻለ ነገር የለም ብዬ ደመደምኩ፤+ +13 ደግሞም ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በሚሠራው ሥራ ሁሉ ደስታ ከማግኘት የተሻለ ነገር የለም። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።+ +14 እውነተኛው አምላክ የሚሠራው ነገር ሁሉ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖር ተረድቻለሁ። በእሱ ላይ የሚጨመር ምንም ነገር የለም፤ ከእሱም ላይ የሚቀነስ ምንም ነገር የለም። እውነተኛው አምላክ በዚህ መንገድ የሠራው ሰዎች ይፈሩት ዘንድ ነው።+ +15 አሁን የሚሆነው ነገር ሁሉ ከዚህ በፊት የሆነ ነው፤ ወደፊት የሚመጣው ነገር ከዚህ በፊት የነበረ ነው፤+ ሆኖም እውነተኛው አምላክ፣ ሲያሳድዱት የነበረውን* አጥብቆ ይሻዋል። +16 ደግሞም ከፀሐይ በታች ይህን አየሁ፦ በፍትሕ ቦታ ክፋት፣ በጽድቅም ቦታ ክፋት ነበር።+ +17 እኔም በልቤ እንዲህ አልኩ፦ “እውነተኛው አምላክ በጻድቁም ሆነ በኃጢአተኛው ላይ ይፈርዳል፤+ ማንኛውም ድርጊትና ማንኛውም ተግባር ጊዜ አለውና።” +18 እኔም በልቤ፣ እውነተኛው አምላክ የሰው ልጆችን ይፈትናቸዋል፤ እንደ እንስሳት መሆናቸውንም ያሳያቸዋል አልኩ፤ +19 የሰው ልጆች ፍጻሜና* የእንስሳት ፍጻሜ ተመሳሳይ ነውና፤ የሁሉም ፍጻሜ አንድ ነው።+ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት ነው።+ በመሆኑም ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነውና። +20 ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ።+ ሁሉም የተገኙት ከአፈር ነው፤+ ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳሉ።+ +21 የሰው ልጆች መንፈስ ወደ ላይ ይወጣ እንደሆነ፣ የእንስሳት መንፈስ ደግሞ ወደ ታች ወደ ምድር ይወርድ እንደሆነ በእርግጠኝነት የሚያውቅ ማን ነው?+ +22 ሰው በሥራው ደስ ከመሰኘት የተሻለ ነገር እንደሌለው አስተዋልኩ፤+ ምክንያቱም ይህ ወሮታው* ነው፤ እሱ ካለፈ በኋላ የሚከናወነውን ነገር ተመልሶ እንዲያይ ሊያደርገው የሚችል ማን ነው?+ +7 ጥሩ ስም* ከጥሩ ዘይት፣+ የሞትም ቀን ከልደት ቀን ይሻላል። +2 ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ይልቅ ወደ ሐዘን ቤት መሄድ ይሻላል፤+ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ሞት ነውና፤ በሕይወት ያለ ሰውም ይህን ልብ ማለት ይገባዋል። +3 ከሳቅ ትካዜ ይሻላል፤+ የፊት ሐዘን ለልብ መልካም ነውና።+ +4 የጥበበኞች ልብ በሐዘን ቤት ነው፤ የሞኞች ልብ ግን በደስታ* ቤት ነው።+ +5 የሞኞችን መዝሙር ከመስማት ይልቅ የጥበበኛን ወቀሳ መስማት ይሻላል።+ +6 የሞኝ ሳቅ ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ የእሾህ ማገዶ ነው፤+ ይህም ቢሆን ከንቱ ነው��� +7 ግፍ ጥበበኛውን ሊያሳብደው ይችላል፤ ጉቦም ልብን ያበላሻል።+ +8 የአንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል። ትዕቢተኛ ከመሆን ይልቅ ታጋሽ መሆን ይሻላል።+ +9 የሞኞች ቁጣ በጉያቸው ውስጥ ስለሆነ*+ ለቁጣ አትቸኩል።*+ +10 “የቀድሞው ዘመን ከአሁኑ ዘመን ለምን ተሻለ?” አትበል፤ እንዲህ ብሎ መጠየቅ ጥበብ አይደለምና።+ +11 ጥበብ ከውርስ ጋር መልካም ነገር ናት፤ የቀን ብርሃን ለሚያዩ ሰዎችም* ጠቃሚ ነች። +12 ገንዘብ ጥበቃ እንደሚያስገኝ+ ሁሉ ጥበብም ጥበቃ ታስገኛለችና፤+ የእውቀት ብልጫ ግን፣ ጥበብ የባለቤቷን ሕይወት ጠብቃ ማቆየት መቻሏ ነው።+ +13 እውነተኛው አምላክ ያከናወነውን ሥራ ልብ በል፤ እሱ ያጣመመውን ማን ሊያቃና ይችላል?+ +14 በጥሩ ቀን አንተም ይህን ጥሩነት መልሰህ አንጸባርቅ፤+ በአስቸጋሪ* ቀን ግን ይሄኛውንም ሆነ ያኛውን ያደረገው አምላክ እንደሆነ አስተውል፤+ ይህም የሆነው ሰዎች ወደፊት የሚደርስባቸውን ማንኛውንም ነገር በተመለከተ እርግጠኞች መሆን* እንዳይችሉ ነው።+ +15 ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመኔ+ ሁሉንም ነገር አይቻለሁ፤ ጻድቁ ሰው በጽድቁ ሲጠፋ፣+ ክፉው ሰው ደግሞ ክፉ ቢሆንም ረጅም ዘመን ሲኖር ተመልክቻለሁ።+ +16 ከልክ በላይ ጻድቅ አትሁን፤+ እጅግም ጥበበኛ መስለህ ለመታየት አትሞክር።+ በራስህ ላይ ለምን ጥፋት ታመጣለህ?+ +17 እጅግ ክፉ አትሁን፤ ሞኝም አትሁን።+ ያለጊዜህ ለምን በሞት ትቀጫለህ?+ +18 አንደኛውን ማስጠንቀቂያ ሳትተው ሌላኛውንም አጥብቀህ መያዝህ የተሻለ ነው፤+ አምላክን የሚፈራ ሰው ሁለቱንም ይሰማልና። +19 ጥበብ ጥበበኛውን ሰው፣ በአንድ ከተማ ካሉ አሥር ብርቱ ሰዎች ይበልጥ ኃያል ታደርገዋለች።+ +20 ሁልጊዜ ጥሩ ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኃጢአት የማይሠራ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለምና።+ +21 በተጨማሪም ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ሁሉ ትኩረት ሰጥተህ አትከታተል፤+ አለዚያ አገልጋይህ ስለ አንተ መጥፎ ነገር ሲናገር* ልትሰማ ትችላለህ፤ +22 አንተ ራስህ ስለ ሌሎች ብዙ ጊዜ መጥፎ ነገር እንደተናገርክ ልብህ በሚገባ ያውቃልና።+ +23 ይህን ሁሉ በጥበብ ፈተንኩ፤ እኔም “ጥበበኛ እሆናለሁ” አልኩ። ይህ ግን ከአቅሜ በላይ ነበር። +24 የተከናወነው ነገር ሁሉ ሊደረስበት የማይቻል ከመሆኑም ሌላ እጅግ ጥልቅ ነው። ማንስ ሊረዳው ይችላል?+ +25 እኔም ጥበብንና የነገሮችን መንስኤ ለመረዳት፣ ለመመርመርና ለማጥናት እንዲሁም የሞኝነትን ክፋትና የእብደትን ቂልነት ለመገንዘብ ልቤን አዘነበልኩ።+ +26 ከዚያም የሚከተለውን ነገር ተገነዘብኩ፦ እንደ አዳኝ ወጥመድ የሆነች ደግሞም እንደ መረብ ያለ ልብ፣ እንደ እስር ቤት ሰንሰለትም ያሉ እጆች ያሏት ሴት ከሞት እጅግ የመረረች ናት። እውነተኛውን አምላክ የሚያስደስት ሰው ከእሷ ያመልጣል፤+ ኃጢአተኛ ግን በእሷ ይያዛል።+ +27 ሰብሳቢው+ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ መርምሬ ያገኘሁት ነገር ይህ ነው። አንድ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ እያንዳንዱን ነገር በሚገባ አጠናሁ፤ +28 ሆኖም ስፈልገው* የነበረውን ነገር ላገኘው አልቻልኩም። ከሺህ መካከል አንድ ወንድ* አገኘሁ፤ ከእነዚህ ሁሉ መካከል ግን አንዲትም ሴት አላገኘሁም። +29 ይህን አንድ ነገር ብቻ አገኘሁ፦ እውነተኛው አምላክ የሰውን ልጆች ቅን አድርጎ ሠራቸው፤+ እነሱ ግን ሌላ ብዙ ዕቅድ አወጡ።”+ +12 እንግዲያው አስጨናቂ የሆኑት ዘመናት*+ ከመምጣታቸው እንዲሁም “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመታት ከመድረሳቸው በፊት በወጣትነትህ ጊዜ ታላቁን ፈጣሪህን አስብ፤+ +2 ፀሐይ፣ ብርሃን፣ ጨረቃና ከዋክብት ከመጨለማቸው በፊት+ እንዲሁም ዶፍ ከጣለ በኋላ ደመናት ተመልሰው* ከመምጣታቸው በፊት ፈጣሪህን አስብ፤ +3 በዚያን ጊዜ ቤ�� ጠባቂዎች* ይንቀጠቀጣሉ፤* ጠንካራ የነበሩ ሰዎች ይጎብጣሉ፤ የሚፈጩ ሴቶች ጥቂት በመሆናቸው ሥራቸውን ያቆማሉ፤ በመስኮት የሚያዩ ወይዛዝርትም ይጨልምባቸዋል፤+ +4 ወደ መንገድ የሚያወጡ በሮች ይዘጋሉ፤ የወፍጮ ድምፅ ይቀንሳል፤ ሰውም የወፍ ድምፅ ይቀሰቅሰዋል፤ ሴቶች ልጆችም ሁሉ ዝግ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ።+ +5 በተጨማሪም ሰው ከፍታ ያስፈራዋል፤ በመንገድ ሲሄድም ይሸበራል። የአልሞንድ ዛፍ ያብባል፤+ ፌንጣም እየተጎተተ ይሄዳል፤ የምግብ ፍላጎት* ይጠፋል፤ ምክንያቱም ሰው ለረጅም ጊዜ ወደሚኖርበት ቤት ይሄዳል፤+ አልቃሾችም በጎዳና ይዞራሉ፤+ +6 የብር ገመድ ሳይበጠስ፣ የወርቅ ሳህን ሳይሰበር፣ እንስራ በምንጭ አጠገብ ሳይከሰከስ፣ ከጉድጓድ ውኃ ለማውጣት የሚያገለግለው መንኮራኩር* ሳይሰበር ፈጣሪህን አስብ። +7 አፈር ቀድሞ ወደነበረበት መሬት ይመለሳል፤+ መንፈስም* ወደ ሰጪው፣ ወደ እውነተኛው አምላክ ይመለሳል።+ +8 ሰብሳቢው+ “የከንቱ ከንቱ* ነው! ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” ይላል።+ +9 ሰብሳቢው ጥበበኛ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሕዝቡ የሚያውቀውን ነገር ሁልጊዜ ያስተምር ነበር፤+ ብዙ ምሳሌዎችንም ማጠናቀር* ይችል ዘንድ አሰላሰለ እንዲሁም ሰፊ ምርምር አደረገ።+ +10 ሰብሳቢው ደስ የሚያሰኙ ቃላትን+ ለማግኘትና የእውነትን ቃል በትክክል ለመመዝገብ ጥረት አደረገ። +11 የጥበበኞች ቃላት እንደ በሬ መውጊያ ናቸው፤+ የሰበሰቧቸው አባባሎችም በሚገባ እንደተቸነከሩ ምስማሮች ናቸው፤ እነዚህ ቃላት ከአንድ እረኛ የተሰጡ ናቸው። +12 ልጄ ሆይ፣ ከዚህም ሌላ ይህን ማስጠንቀቂያ ልብ በል፦ ብዙ መጻሕፍት መጻፍ ማብቂያ የለውም፤ በእነሱ ዙሪያ ምርምር ማብዛትም ሰውነትን ያደክማል።+ +13 ሁሉ ነገር ከተሰማ በኋላ መደምደሚያው ይህ ነው፦ እውነተኛውን አምላክ ፍራ፤+ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤+ ይህ የሰው አጠቃላይ ግዴታ ነውና።+ +14 እውነተኛው አምላክ እያንዳንዱን የተሰወረ ነገር ጨምሮ ማንኛውንም ሥራ፣ ጥሩም ይሁን መጥፎ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።+ +1 በኢየሩሳሌም የነገሠው+ የሰብሳቢው*+ የዳዊት ልጅ ቃል። + 2 ሰብሳቢው “የከንቱ ከንቱ* ነው!የከንቱ ከንቱ ነው! ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” አለ።+ + 3 ሰው ከፀሐይ በታች በትጋት ከሚያከናውነውና ከሚለፋበት ሥራ ሁሉየሚያገኘው ጥቅም ምንድን ነው?+ + 4 ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።*+ + 5 ፀሐይ ትወጣለች፤* ደግሞም ትጠልቃለች፤ከዚያም ዳግመኛ ወደምትወጣበት ቦታ ለመመለስ ትጣደፋለች።*+ + 6 ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፤ ወደ ሰሜንም ዞሮ ይሄዳል፤ክብ እየሠራ ያለማቋረጥ ይሽከረከራል፤ ደግሞም ነፋሱ ዑደቱን ይቀጥላል። + 7 ጅረቶች* ሁሉ ወደ ባሕር ይፈስሳሉ፤ ሆኖም ባሕሩ አይሞላም።+ ጅረቶቹ እንደገና ይፈስሱ ዘንድ ወደሚነሱበት ወደዚያው ቦታ ተመልሰው ይሄዳሉ።+ + 8 ሁሉ ነገር አሰልቺ ነው፤ሁሉንም ነገር ሊገልጽ የሚችል ሰው የለም። ዓይን አይቶ አይጠግብም፤ጆሮም ሰምቶ አይሞላም። + 9 ከዚህ በፊት የነበረው ነገር ወደፊትም ይሆናል፤ከዚህ በፊት የተደረገውም ነገር እንደገና ይደረጋል፤ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።+ +10 አንድ ሰው “ተመልከት፣ ይህ አዲስ ነገር ነው” ሊል የሚችለው ነገር ይኖራል? ከጥንት ጀምሮ የነበረ ነው፤ከእኛ ዘመን በፊት የነበረ ነው። +11 በቀድሞ ዘመን የነበሩትን ሰዎች ማንም አያስታውሳቸውም፤ከጊዜ በኋላ የሚመጡትንም የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ከእነሱ በኋላ የሚነሱት ሰዎችም እንኳ አያስታውሷቸውም።+ +12 እኔ ሰብሳቢው በኢየሩሳሌም፣ የእስራኤል ንጉሥ ነበርኩ።+ +13 ከሰማይ በታች የተሠራውን ነገር ሁሉ ይኸውም አምላክ የሰው ልጆች እንዲጠመዱበ�� የሰጣቸውን አሰልቺ ሥራ በጥበብ+ ለማጥናትና ለመመርመር ከልቤ ጥረት አደረግኩ።+ +14 ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ ተመለከትኩ፤እነሆ፣ ሁሉም ከንቱ ነፋስንም እንደማሳደድ ነው።+ +15 የተጣመመ ነገር ሊቃና አይችልም፤የሌለም ነገር በምንም መንገድ ሊቆጠር አይችልም። +16 እኔም በልቤ እንዲህ አልኩ፦ “እነሆ፣ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ እጅግ የላቀ ጥበብ አገኘሁ፤+ ልቤም ከፍተኛ ጥበብና እውቀት አገኘ።”+ +17 እኔም ጥበብንና እብደትን* እንዲሁም ሞኝነትን ለመረዳት ከልቤ ጥረት አደረግኩ፤+ ይህም ቢሆን ነፋስን እንደማሳደድ ነው። +18 ጥበብ ሲበዛ ብስጭትም ይበዛልና፤በመሆኑም እውቀትን የሚጨምር ሁሉ ሥቃይንም ይጨምራል።+ +8 እንደ ጥበበኛው ሰው ያለ ማን ነው? የአንድን ችግር መፍትሔ* የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበብ ፊቱ እንዲበራ እንዲሁም ኮስታራ ፊቱ እንዲፈታ ታደርጋለች። +2 እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “በአምላክ ፊት በገባኸው መሐላ+ የተነሳ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር።+ +3 ከንጉሡ ፊት ለመውጣት አትቸኩል።+ መጥፎ የሆነውን ነገር ሁሉ አትደግፍ፤+ እሱ ደስ ያሰኘውን ሁሉ ማድረግ ይችላልና፤ +4 ምክንያቱም የንጉሥ ቃል የማይሻር ነው፤+ ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ሊለው የሚችል ማን ነው?” +5 ትእዛዛትን የሚጠብቅ ሰው ጉዳት አይደርስበትም፤+ ጥበበኛ ልብም ትክክለኛውን ጊዜና አሠራር* ያውቃል።+ +6 የሰው ልጆች ብዙ መከራ ቢኖርባቸውም ማንኛውም ጉዳይ ትክክለኛ ጊዜና አሠራር* አለው።+ +7 ወደፊት የሚሆነውን ነገር የሚያውቅ ሰው ስለሌለ ይህ እንዴት እንደሚሆን ሊነግረው የሚችል ማን ነው? +8 በመንፈስ* ላይ ሥልጣን ያለው ወይም መንፈስን መግታት የሚችል ሰው እንደሌለ ሁሉ በሞት ቀን ላይም ሥልጣን ያለው የለም።+ በጦርነት ጊዜ ከግዳጅ የሚሰናበት እንደሌለ ሁሉ ክፋትም ክፋት የመሥራት ልማድ ያላቸውን ሰዎች እንዲያመልጡ ዕድል አይሰጣቸውም።* +9 ይህን ሁሉ የተገነዘብኩት ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ በልቤ ከመረመርኩ በኋላ ነው። በዚህ ሁሉ ወቅት ሰው ሰውን የገዛው ለጉዳቱ* ነው።+ +10 ደግሞም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይገቡና ይወጡ የነበሩት ክፉዎች ሲቀበሩ አይቻለሁ፤ ይሁንና ይህን ባደረጉበት ከተማ ወዲያው ተረሱ።+ ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። +11 በክፉ ሥራ ላይ በአፋጣኝ ፍርድ ስለማይሰጥ+ የሰው ልጆች ልብ ክፉ ነገር ለማድረግ ተደፋፈረ።+ +12 ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ መጥፎ ነገር እየሠራ ረጅም ዘመን ቢኖር እንኳ እውነተኛውን አምላክ የሚፈሩ ሰዎች አምላክን በመፍራታቸው የኋላ ኋላ መልካም እንደሚሆንላቸው ተረድቻለሁ።+ +13 ክፉ ሰው ግን አምላክን ስለማይፈራ የኋላ ኋላ መልካም አይሆንለትም፤+ እንደ ጥላ የሆነውን የሕይወት ዘመኑንም ማራዘም አይችልም።+ +14 በምድር ላይ የሚፈጸም አንድ ከንቱ* ነገር አለ፦ ክፉ እንደሠሩ ተደርገው የሚታዩ ጻድቃን አሉ፤+ ጽድቅ እንደሠሩ ተደርገው የሚታዩ ክፉ ሰዎችም አሉ።+ ይህም ቢሆን ከንቱ ነው እላለሁ። +15 በመሆኑም ደስታ መልካም ነው አልኩ፤+ ምክንያቱም ለሰው ከፀሐይ በታች ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ከመደሰት የተሻለ ነገር የለም፤ ከፀሐይ በታች እውነተኛው አምላክ በሚሰጠው የሕይወት ዘመን በትጋት ሲሠራ ይህ ደስታ ሊርቀው አይገባም።+ +16 ቀንም ሆነ ሌሊት እንቅልፍ በዓይኔ ሳይዞር* ጥበብን ለማግኘትና በምድር ላይ ያለውን እንቅስቃሴ* ለማየት ከፍተኛ ጥረት አደረግኩ።+ +17 ከዚያም የእውነተኛውን አምላክ ሥራ ሁሉ አጤንኩ፤ የሰው ልጆች ከፀሐይ በታች የሚሆነውን ነገር ሁሉ መረዳት እንደማይችሉም ተገነዘብኩ።+ ሰዎች የቱንም ያህል ጥረት ቢያደርጉ ሊረዱት አይችሉም። ይህን ለማወቅ የሚያስችል ጥበብ አለን ቢሉም እንኳ ሊረ��ት አይችሉም።+ +11 ቂጣህን በውኃ ላይ ጣል፤*+ ከብዙ ቀናት በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።+ +2 ካለህ ነገር ላይ ለሰባት፣ እንዲያውም ለስምንት አካፍለህ ስጥ፤+ በምድር ላይ የሚመጣውን አደጋ* አታውቅምና። +3 ደመናት ውኃ ካዘሉ በምድር ላይ ዶፍ ያወርዳሉ፤ እንዲሁም ዛፍ በስተ ደቡብ ወይም በስተ ሰሜን ከወደቀ በዚያው በወደቀበት ይቀራል። +4 ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚመለከት አያጭድም።+ +5 መንፈስ፣ በእርጉዝ ሴት ውስጥ በሚገኝ ሕፃን አጥንቶች* ላይ እንዴት እንደሚሠራ እንደማታውቅ ሁሉ፣+ ሁሉንም ነገር የሚያከናውነውን የእውነተኛውን አምላክ ሥራም አታውቅም።+ +6 በማለዳ ዘርህን ዝራ፤ እስከ ምሽትም ድረስ እጅህ ሥራ አይፍታ፤+ ይህ ወይም ያ የትኛው እንደሚያድግ ወይም ደግሞ ሁለቱም ይጸድቁ እንደሆነ አታውቅምና። +7 ብርሃን ደስ ያሰኛል፤ ፀሐይንም ማየት ለዓይን መልካም ነው። +8 ሰው የቱንም ያህል ብዙ ዓመት ቢኖር በእያንዳንዱ ቀን ደስ ይበለው።+ ሆኖም በጨለማ የተዋጡት ቀናት ብዙ ሊሆኑ እንደሚችሉ መዘንጋት አይኖርበትም፤ የሚመጣው ሁሉ ከንቱ ነው።+ +9 አንተ ወጣት፣ በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ይበለው። የልብህን መንገድ ተከተል፤ ዓይንህ በሚመራህም መንገድ ሂድ፤ ሆኖም ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እውነተኛው አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ* እወቅ።+ +10 ስለዚህ የሚያስጨንቁ ነገሮችን ከልብህ አስወግድ፤ ጎጂ ነገሮችንም ከሰውነትህ አርቅ፤* ወጣትነትና የለጋነት ዕድሜ ከንቱ ናቸውና።+ +2 እኔም በልቤ “እስቲ ደስታን ልፈትንና ምን መልካም ነገር እንደሚገኝ ልይ” አልኩ። ይሁንና ይህም ከንቱ ነበር። + 2 ሳቅ “እብደት ነው!” ደስታም “ምን ይጠቅማል?” አልኩ። +3 በገዛ ጥበቤ እየተመራሁና ራሴን በወይን ጠጅ እያስደሰትኩ+ በጥልቀት መረመርኩ፤ ሰዎች አጭር በሆነው የሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ሊያደርጉት የሚችሉት ከሁሉ የተሻለ ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ በሞኝነት እንኳ ሳይቀር ተመላለስኩ። +4 ታላላቅ ሥራዎችን አከናወንኩ።+ ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፤+ ወይንም ተከልኩ።+ +5 ለራሴ የአትክልት ስፍራዎችንና መናፈሻዎችን አዘጋጀሁ፤ በእነዚህም ቦታዎች ሁሉንም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፎች ተከልኩ። +6 በእርሻው መሬት ላይ እያደጉ ያሉትን ዛፎች* ለማጠጣት የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ሠራሁ። +7 ወንድና ሴት አገልጋዮች አስመጣሁ፤+ በቤቴ የተወለዱ አገልጋዮችም* ነበሩኝ። በተጨማሪም ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ብዛት ያላቸው እንስሶች፣ ከብቶችና መንጎች ነበሩኝ።+ +8 ለራሴም ብርና ወርቅ፣+ የነገሥታትንና የአውራጃዎችን ውድ ሀብት* አከማቸሁ።+ ወንድና ሴት ዘፋኞችን እንዲሁም የሰው ልጆች እጅግ የሚደሰቱባቸውን ብዙ ሴቶች* ሰበሰብኩ። +9 በመሆኑም ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ሰው ሆንኩ።+ ደግሞም ጥበቤ ከእኔ አልተለየችም። +10 የተመኘሁትን ነገር ሁሉ ራሴን አልነፈግኩም።*+ ልቤንም ደስ የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ አልከለከልኩትም፤ ልቤ በትጋት በማከናውነው ሥራ ሁሉ ደስ ይሰኝ ነበርና፤ ብዙ ለደከምኩበት ሥራ ሁሉ ያገኘሁት ወሮታ* ይህ ነበር።+ +11 ሆኖም እጆቼ የሠሩትን ሥራ ሁሉና ዳር ለማድረስ የደከምኩበትን ሥራ+ ሁሉ መለስ ብዬ ሳስብ፣ ሁሉ ነገር ከንቱ፣ ነፋስንም እንደማሳደድ መሆኑን አስተዋልኩ፤+ ከፀሐይም በታች እውነተኛ ፋይዳ* ያለው አንዳች ነገር አልነበረም።+ +12 ከዚያም ትኩረቴን ወደ ጥበብ፣ እብደትና ሞኝነት አዞርኩ።+ (ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል? ሊያደርግ የሚችለው ቀደም ሲል የተደረገውን ነገር ብቻ ነው።) +13 እኔም ብርሃን ከጨለማ የተሻለ ጥቅም እንዳለው ሁሉ ጥበብም ከሞኝነት የተሻለ ጥቅም እንዳለው ተገነዘብኩ።+ +14 የጥበበኛ ሰው ዓይኖች ያሉት በራሱ ላይ ነው፤*+ ሞኝ ሰው ግን በጨለማ ውስጥ ይሄዳል።+ ደግሞም የሁለቱም ፍጻሜ* አንድ እንደሆነ ተገነዘብኩ።+ +15 እኔም በልቤ “በሞኙ ላይ የሚደርሰው በእኔም ላይ ይደርሳል” አልኩ።+ ታዲያ እጅግ ጥበበኛ በመሆኔ ምን አተርፋለሁ? በልቤም “ይህም ከንቱ ነው” አልኩ። +16 ጥበበኛውም ሆነ ሞኙ ለዘለቄታው አይታወሱምና።+ ሁሉም በሚመጡት ዘመናት ይረሳሉ። ለመሆኑ ጥበበኛው የሚሞተው እንዴት ነው? ልክ እንደ ሞኙ ሰው ይሞታል።+ +17 እኔም ከፀሐይ በታች የሚሠራው ሥራ ሁሉ አስጨናቂ ሆኖ ስለታየኝ ሕይወትን ጠላሁ፤+ ሁሉም ከንቱ፣+ ነፋስንም እንደማሳደድ ነውና።+ +18 ከኋላዬ ለሚመጣው ሰው ትቼው ስለምሄድ+ ከፀሐይ በታች እጅግ የደከምኩበትን ሥራ ሁሉ+ ጠላሁ። +19 ጥበበኛ ወይም ሞኝ እንደሚሆን የሚያውቅ ማን ነው?+ ሆኖም ከፀሐይ በታች በድካሜና በጥበቤ ያፈራሁትን ነገር ሁሉ ይወርሰዋል። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። +20 በመሆኑም ከፀሐይ በታች በለፋሁበት አድካሚ ሥራ ሁሉ ልቤ ተስፋ መቁረጥ ጀመረ። +21 ሰው በጥበብ፣ በእውቀትና በብልሃት እየተመራ ሥራውን በትጋት ሊያከናውን ይችላል፤ ይሁንና ድርሻውን* ምንም ላልደከመበት ሰው ያስረክባል።+ ይህም ከንቱና እጅግ አሳዛኝ* ነው። +22 ሰው ከፀሐይ በታች ከደከመበት ሁሉና ተግቶ እንዲሠራ ከሚገፋፋው ብርቱ ፍላጎት* የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው?+ +23 በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሥራው የሚያስገኝለት ነገር ቢኖር ሥቃይና ብስጭት ነው፤+ በሌሊትም እንኳ ልቡ አያርፍም።+ ይህም ከንቱ ነው። +24 ሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በመሥራት እርካታ ከማግኘት* የሚሻለው ነገር የለም።+ ይህም ቢሆን ከእውነተኛው አምላክ እጅ የተገኘ መሆኑን ተገንዝቤአለሁ፤+ +25 ደግሞስ ከእኔ የተሻለ የሚበላና የሚጠጣ ማን ነው?+ +26 አምላክ እሱን ለሚያስደስት ሰው ጥበብ፣ እውቀትና ደስታ ይሰጣል፤+ ኃጢአተኛ ለሆነው ግን እውነተኛውን አምላክ ለሚያስደስት ሰው ይሰጥ ዘንድ የመሰብሰብና የማከማቸት ሥራ ሰጥቶታል።+ ይህም ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። +4 ከፀሐይ በታች የሚፈጸመውን ግፍ ሁሉ በድጋሚ ተመለከትኩ። ግፍ የተፈጸመባቸውን ሰዎች እንባ ተመለከትኩ፤ የሚያጽናናቸውም ሰው አልነበረም።+ ግፍ የሚፈጽሙባቸውም ሰዎች ኃይል ነበራቸው፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም። +2 እኔም ‘ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱ ሙታን ይሻላሉ’ አልኩ።+ +3 ደግሞም ከሁለቱ ይልቅ ገና ያልተወለደው፣+ ከፀሐይ በታች የሚፈጸሙትንም አስጨናቂ ድርጊቶች ያላየው ይሻላል።+ +4 እኔም በሰዎች መካከል ያለው ፉክክር፣ ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉና* የተዋጣለት ሥራ እንዲያከናውኑ እንደሚያነሳሳቸው ተመለከትኩ፤+ ይህም ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። +5 ሞኝ ሰው ሥጋው እየመነመነ ሲሄድ፣* እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል።+ +6 ብዙ በመልፋትና ነፋስን በማሳደድ ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ ጥቂት እረፍት በማድረግ የሚገኝ አንድ እፍኝ ይሻላል።+ +7 እኔም ከፀሐይ በታች ያለውን ሌላ ከንቱ ነገር እንደገና ተመለከትኩ፦ +8 ብቸኛ የሆነና ጓደኛ የሌለው ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁንና የሚሠራው ሥራ ማብቂያ የለውም። ዓይኖቹ ሀብትን አይጠግቡም።+ ሆኖም ‘እንዲህ በትጋት የምሠራውና ራሴን* መልካም ነገር የምነፍገው ለማን ብዬ ነው?’ ብሎ ራሱን ይጠይቃል?+ ይህም ቢሆን ከንቱና አሰልቺ ሥራ ነው።+ +9 አንድ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል፤+ ምክንያቱም ሁለት ሆነው የሚያከናውኑት ሥራ ጥሩ ውጤት* ያስገኝላቸዋል። +10 አንዱ ቢወድቅ ሁለተኛው ���ልንጀራውን ደግፎ ሊያነሳው ይችላልና። ይሁንና ደግፎ የሚያነሳው ሰው በሌለበት አንዱ ቢወድቅ እንዴት ይሆናል? +11 በተጨማሪም ሁለት ሰዎች አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ ሆኖም አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ እንዴት ሊሞቀው ይችላል? +12 ደግሞም አንድ ሰው ብቻውን ያለን ሰው ሊያሸንፈው ይችል ይሆናል፤ ሁለት ከሆኑ ግን ሊቋቋሙት ይችላሉ። በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም።* +13 የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ እንዳያደርግ ማስተዋል ከጎደለው በዕድሜ የገፋ ሞኝ ንጉሥ+ ይልቅ ድሃ የሆነ ጥበበኛ ልጅ ይሻላል።+ +14 በእሱ ግዛት ውስጥ ድሃ ሆኖ የተወለደ ቢሆንም* ከእስር ቤት ወጥቶ ንጉሥ ይሆናል።+ +15 እኔም ከፀሐይ በታች የሚመላለሱት ሕያዋን ሁሉ እንዲሁም በንጉሡ ቦታ የሚተካው ልጅ ምን እንደሚገጥማቸው አጤንኩ። +16 ስፍር ቁጥር የሌላቸው ደጋፊዎች ቢኖሩትም በኋላ የሚመጡት ሰዎች በእሱ አይደሰቱም።+ ይህም ቢሆን ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። +6 ከፀሐይ በታች ያየሁት ሌላ አሳዛኝ ነገር* አለ፤ ይህም በሰው ልጆች ላይ በተደጋጋሚ ሲከሰት ይታያል፦ +2 እውነተኛው አምላክ፣ ሰው የሚፈልገውን ነገር* ሁሉ እንዳያጣ ሀብትን፣ ቁሳዊ ንብረትንና ክብርን ይሰጠዋል፤ ሆኖም እውነተኛው አምላክ በእነዚህ ነገሮች እንዲደሰት አያስችለውም፤ ከዚህ ይልቅ እንግዳ ሰው ይደሰትባቸዋል። ይህም ከንቱና እጅግ አስከፊ ነገር ነው። +3 አንድ ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፣ ብዙ ዓመት ቢኖርና ለእርጅና ቢበቃ፣ ወደ መቃብር ከመውረዱ በፊት ባሉት መልካም ነገሮች መደሰት ካልቻለ* ከእሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ።+ +4 ከማህፀን የወጣው በከንቱ ነውና፤ በጨለማም ሄዷል፤ ስሙም በጨለማ ተሸፍኗል። +5 ፀሐይን ባያይና ምንም ነገር ባያውቅም እንኳ ከዚያኛው ይልቅ ይሄኛው ይሻላል።*+ +6 ሰው ደስታ ካላገኘ ሁለት ጊዜ ሺህ ዓመት ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? ሁሉም የሚሄደው ወደ አንድ ቦታ አይደለም?+ +7 የሰው ልጅ በትጋት የሚሠራው ሆዱን ለመሙላት ነው፤+ የምግብ ፍላጎቱ* ግን ፈጽሞ አይረካም። +8 ታዲያ ጥበበኛው ከሞኙ ሰው የሚሻለው በምንድን ነው?+ ድሃስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዴት መኖር እንደሚችል* ማወቁ የሚያስገኝለት ጥቅም ምንድን ነው? +9 በምኞት ከመቅበዝበዝ* ይልቅ ዓይን በሚያየው መደሰት ይሻላል። ይህም ቢሆን ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። +10 አሁን ያለው ነገር ሁሉ አስቀድሞ ስያሜ የተሰጠው ነው፤ ደግሞም የሰው ምንነት የታወቀ ነው፤ ከእሱ ከሚበረታም ጋር ሊከራከር* አይችልም። +11 ቃል ሲበዛ* ከንቱነት ይበዛል፤ ታዲያ ይህ ለሰው ምን ጥቅም ያስገኛል? +12 ሰው በሕይወት ሳለ ይኸውም ከንቱ በሆነውና እንደ ጥላ በሚያልፈው አጭር የሕይወት ዘመኑ ሊያደርገው የሚችለው የተሻለ ነገር ምን እንደሆነ የሚያውቅ ማን ነው?+ እሱ ካለፈስ በኋላ ከፀሐይ በታች የሚሆነውን ነገር ማን ሊነግረው ይችላል? +10 የሞቱ ዝንቦች በጥሩ ቀማሚ የተዘጋጀውን ሽቶ እንዲበላሽና እንዲገማ እንደሚያደርጉት ሁሉ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብንና ክብርን ዋጋ ያሳጣል።+ + 2 የጥበበኛ ሰው ልብ በትክክለኛ መንገድ ይመራዋል፤* የሞኝ ልብ ግን በተሳሳተ መንገድ ይመራዋል።*+ +3 ሞኝ ሰው በየትኛውም መንገድ ቢመላለስ ማስተዋል* ይጎድለዋል፤+ ሞኝ መሆኑንም ሰው ሁሉ እንዲያውቅ ያደርጋል።+ +4 የገዢ ቁጣ* በአንተ ላይ ቢነድ ስፍራህን አትልቀቅ፤+ የረጋ መንፈስ ታላቅ ኃጢአትን ጸጥ ያደርጋልና።+ +5 ከፀሐይ በታች ያየሁት አንድ የሚያስጨንቅ ነገር አለ፤ ይህም በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች እንደሚሠሩት ያለ ስህተት ነው፦+ +6 ሞኞች በከፍተኛ የሥልጣን ቦታዎች ላይ ሲቀመጡ የናጠጡ ሀብታሞች* ግን በዝቅተኛ ቦታዎች ላይ ይገኛሉ። +7 አገልጋዮች በፈረስ ተቀምጠው ሲጓዙ፣ መኳንንት ግን እንደ አገልጋዮች በእግራቸው ሲሄዱ አይቻለሁ።+ +8 ጉድጓድ የሚቆፍር ራሱ ሊገባበት ይችላል፤+ ግንብን የሚያፈርስም በእባብ ሊነደፍ ይችላል። +9 ድንጋይ የሚፈነቅል ሰው በፈነቀለው ድንጋይ ሊጎዳ ይችላል፤ ግንድንም የሚፈልጥ አደጋ ሊያደርስበት ይችላል።* +10 ከብረት የተሠራ መሣሪያ ቢደንዝ፣ ሰውም ባይስለው ብዙ ጉልበት መጠቀም ያስፈልገዋል። ጥበብ ግን ስኬታማ ለመሆን ይረዳል። +11 እባብ በድግምት ከመፍዘዙ በፊት ቢነድፍ፣ በድግምት የተካነው ሰው* ምንም ጥቅም አያገኝም። +12 ጥበበኛ ሰው ከአፉ የሚወጡት ቃላት ሞገስ ያስገኙለታል፤+ የሞኝ ሰው ከንፈር ግን ለጥፋት ይዳርገዋል።+ +13 ከአፉ የሚወጡት የመጀመሪያ ቃላት ሞኝነት ይንጸባረቅባቸዋል፤+ የንግግሩ ማሳረጊያም የከፋ እብደት ነው። +14 ይሁንና ሞኙ ማውራቱን ይቀጥላል።+ ሰው ወደፊት የሚሆነውን ነገር አያውቅም፤ ከእሱ በኋላ የሚመጣውን ነገር ማን ሊነግረው ይችላል?+ +15 ሞኝ ሰው የሚሠራው አድካሚ ሥራ እንዲዝል ያደርገዋል፤ ወደ ከተማ የሚወስደውን መንገድ ማግኘት እንኳ አይችልምና። +16 አንዲት አገር ንጉሧ ልጅ ቢሆን፣+ መኳንንቷ ደግሞ በጠዋት ግብዣ ላይ የሚገኙ ቢሆኑ ምንኛ አሳዛኝ ነው! +17 ከትልቅ ቤተሰብ የተወለደ ንጉሥ ያላት እንዲሁም ለስካር ሳይሆን ብርታት ለማግኘት በተገቢው ጊዜ የሚመገቡ መኳንንት ያሏት አገር ምንኛ ደስተኛ ናት!+ +18 ስንፍና ሲበዛ ጣሪያ ይዘብጣል፤ እጆችም ካልሠሩ ቤት ያፈሳል።+ +19 ምግብ* ለሳቅ ይዘጋጃል፤ የወይን ጠጅም ሕይወትን አስደሳች ያደርጋል፤+ ይሁን እንጂ ገንዘብ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያሟላል።+ +20 በሐሳብህ* እንኳ ንጉሡን አትርገም፤*+ በመኝታ ቤትህም ሆነህ ባለጸጋውን አትርገም፤ ቃሉን* ወፍ* ልትወስደው አሊያም ክንፍ ያላት ፍጥረት የተወራውን ደግማ ልትናገር ትችላለችና። +9 ስለዚህ ይህን ሁሉ በጥሞና ተመልክቼ ጻድቃንም ሆኑ ጥበበኞች እንዲሁም የሚያከናውኗቸው ሥራዎች በእውነተኛው አምላክ እጅ ናቸው ብዬ ደመደምኩ።+ ሰዎች ከእነሱ በፊት በነበረው ዘመን የታየውን ፍቅርና ጥላቻ አያውቁም። +2 ጻድቁና ክፉው ሰው፣+ ጥሩው ሰውም ሆነ ንጹሕ የሆነውና ንጹሕ ያልሆነው ሰው፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡትም ሆኑ የማያቀርቡት ፍጻሜያቸው* ተመሳሳይ ነው።+ ጥሩው ሰው ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ነው፤ የሚምለውም ሰው፣ ላለመማል ከሚጠነቀቀው ሰው ጋር አንድ ነው። +3 ከፀሐይ በታች የሚፈጸመው አስጨናቂ ነገር ይህ ነው፦ የሁሉም ፍጻሜ* አንድ ስለሆነ+ የሰዎችም ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወታቸው ዘመን በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ ከዚያም ይሞታሉ!* + 4 በሕያዋን መካከል ያለ ማንኛውም ሰው ተስፋ አለው፤ ምክንያቱም በሕይወት ያለ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላል።+ +5 ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤+ ሙታን ግን ምንም አያውቁም፤+ ከእንግዲህም የሚያገኙት ብድራት* የለም፤ ምክንያቱም የሚታወሱበት ነገር ሁሉ ተረስቷል።+ +6 በተጨማሪም ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸውና ቅናታቸው ጠፍቷል፤ ከዚህም በኋላ ከፀሐይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ ፈጽሞ ድርሻ አይኖራቸውም።+ +7 ሂድ፣ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ልብህም ደስ ብሎት የወይን ጠጅህን ጠጣ፤+ እውነተኛው አምላክ በሥራህ ደስ ተሰኝቷልና።+ +8 ልብስህ ምንጊዜም ነጭ* ይሁን፤ ራስህንም ዘይት መቀባት አትዘንጋ።+ +9 አምላክ ከፀሐይ በታች በሰጠህ ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመንህ ሁሉ፣ ከንቱ በሆነውም ዕድሜህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ተደስተህ ኑር፤+ በሕይወትህ እንዲሁም ከፀሐይ በታች በምትደክምበትና በትጋት በምታከናውነው ሥራ ዕጣ ፋንታህ* ይህ ነውና።+ +10 እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኃይልህ አከናውን፤ አንተ በምትሄድበት በመቃብር* ሥራም ሆነ ዕቅድ፣ እውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።+ +11 እኔም ከፀሐይ በታች ሌላ ነገር ተመለከትኩ፤ ፈጣኖች በውድድር ሁልጊዜ አያሸንፉም፤ ኃያላን በውጊያ ሁልጊዜ ድል አይቀናቸውም፤+ ጥበበኞች ሁልጊዜ ምግብ አያገኙም፤ አስተዋዮች ሁልጊዜ ሀብት አያገኙም፤+ እውቀት ያላቸው ሰዎችም ሁልጊዜ ስኬታማ አይሆኑም፤+ ምክንያቱም ሁሉም መጥፎ ጊዜና ያልተጠበቁ ክስተቶች +12 ሰው የራሱን ጊዜ አያውቅምና።+ ዓሣዎች በአደገኛ መረብ እንደሚጠመዱና ወፎች በወጥመድ እንደሚያዙ፣ የሰው ልጆችም ድንገት በሚያጋጥማቸው ክፉ ጊዜ* ይጠመዳሉ። +13 ደግሞም ከፀሐይ በታች ስላለች ጥበብ ይህን አስተዋልኩ፤ በእሷም እጅግ ተገረምኩ፦ +14 ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኃያል ንጉሥም መጥቶ ከበባት፤ በዙሪያዋም ትልቅ ቅጥር ገነባ። +15 በከተማዋ ውስጥ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድሃ ሰው ነበር፤ እሱም በጥበቡ ከተማዋን አዳናት። ሆኖም ይህን ድሃ ማንም ሰው አላስታወሰውም።+ +16 እኔም ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ ‘ጥበብ ከኃይል ትበልጣለች፤+ ይሁንና የድሃው ጥበብ ተናቀ፤ የተናገረውም ነገር ሰሚ አላገኘም።’+ +17 ሞኞችን የሚገዛ ሰው ከሚያሰማው ጩኸት ይልቅ ጥበበኞች በዝግታ የሚናገሩትን ቃል መስማት ይሻላል። +18 ከጦር መሣሪያ ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ አንድ ኃጢአተኛ ግን ብዙ መልካም ነገርን ሊያጠፋ ይችላል።+ +5 ወደ እውነተኛው አምላክ ቤት በምትሄድበት ጊዜ ሁሉ አካሄድህን ጠብቅ፤+ ሞኞች እንደሚያደርጉት መሥዋዕት ለማቅረብ ከመሄድ+ ይልቅ ለመስማት መሄድ ይሻላል፤+ እነሱ እየሠሩ ያሉት ነገር መጥፎ መሆኑን አያውቁምና። +2 በአፍህ ለመናገር አትጣደፍ፤ ልብህም በእውነተኛው አምላክ ፊት ለመናገር አይቸኩል፤+ እውነተኛው አምላክ በሰማያት፣ አንተ ግን በምድር ላይ ነህና። ስለዚህ የምትናገራቸው ቃላት ጥቂት ሊሆኑ ይገባል።+ +3 ሐሳብ ሲበዛ* ለቅዠት ይዳርጋል፤+ የቃላት ብዛትም ሞኝን ሰው ለፍላፊ ያደርገዋል።+ +4 ለአምላክ ስእለት በምትሳልበት ጊዜ ሁሉ ስእለትህን ለመፈጸም አትዘግይ፤+ እሱ በሞኞች አይደሰትምና።+ ስእለትህን ፈጽም።+ +5 ስእለት ተስለህ ሳትፈጽም ከምትቀር ባትሳል ይሻላል።+ +6 አፍህ ወደ ኃጢአት እንዲመራህ* አትፍቀድ፤+ በመልአክም* ፊት “ተሳስቼ ነው” አትበል።+ እውነተኛው አምላክ በተናገርከው ነገር ተቆጥቶ የእጅህን ሥራ ለምን ያጥፋ?+ +7 ሐሳብ ሲበዛ ቅዠት እንደሚያስከትል፣+ የቃላት ብዛት ደግሞ ከንቱነትን ያስከትላልና። አንተ ግን እውነተኛውን አምላክ ፍራ።+ +8 በምትኖርበት ግዛት ውስጥ በድሃ ላይ ግፍ ሲፈጸም፣ ፍትሕ ሲጓደልና ጽድቅ ወደ ጎን ገሸሽ ሲደረግ ብታይ በዚህ ጉዳይ አትገረም።+ ይህን ባለሥልጣን፣ ከእሱ ከፍ ያለ ቦታ ያለው ይመለከተዋልና፤ ከእነሱም በላይ የሆኑ ሌሎች አሉ። +9 ከምድሩ የሚገኘውን ትርፍ ሁሉም ይከፋፈሉታል፤ ንጉሡ እንኳ የሚያስፈልገውን ነገር የሚያገኘው ከእርሻው ነው።+ +10 ብርን የሚወድ ብርን አይጠግብም፤ ሀብትንም የሚወድ በሚያገኘው ገቢ አይረካም።+ ይህም ቢሆን ከንቱ ነው።+ +11 መልካም ነገሮች ሲበዙ፣ በላተኛውም ይበዛል።+ ታዲያ በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ይህ ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል?+ +12 የሚበላው ጥቂትም ሆነ ብዙ፣ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው፤ ባለጸጋ ሰው ያለው ብዙ ሀብት ግን እንቅልፍ ይነሳዋል። +13 ከፀሐይ በታች ያየሁት እጅግ አሳዛኝ የሆነ ነገር* አለ፦ ይህም ባለቤቱ በገዛ ራሱ ላይ ጉዳት ለማምጣት ያከማቸው ሀብት ነው። +14 ይህ ሰው አደገኛ ነገር* ውስጥ በመግባቱ ሀብቱን አጥቷል፤ ልጅ በሚወልድበት ጊዜም ለልጁ የሚያወርሰው ምንም ነገር አይኖረውም።+ +15 ሰው ከእ���ቱ ማህፀን ራቁቱን እንደወጣ ሁሉ፣ ልክ እንደዚያው ተመልሶ ይሄዳል።+ ደግሞም ከደከመበት ነገር ሁሉ ሊወስደው የሚችል አንዳች ነገር የለም።+ +16 ይህም ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነገር* ነው፦ ሰው በዚያው በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይሄዳል፤ ለነፋስ የሚደክም ሰው የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው?+ +17 ደግሞም በየቀኑ ጨለማ ውስጥ በከፍተኛ ብስጭት፣ በሕመምና በንዴት ይበላል።+ +18 እኔ ያየሁት መልካምና ተገቢ የሆነ ነገር፣ ሰው እውነተኛው አምላክ በሰጠው አጭር የሕይወት ዘመን ሁሉ መብላቱና መጠጣቱ እንዲሁም ከፀሐይ በታች በደከመበትና በትጋት ባከናወነው ሥራ ሁሉ ደስታ ማግኘቱ ነው፤+ ይህ ብድራቱ* ነውና።+ +19 ደግሞም እውነተኛው አምላክ ለሰው ሀብትና ቁሳዊ ንብረት+ ብሎም በእነዚህ ነገሮች የመደሰት ችሎታ ሲሰጠው ብድራቱን* ተቀብሎ በትጋት በሚያከናውነው ሥራ መደሰት ይገባዋል። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።+ +20 እውነተኛው አምላክ ልቡን ደስ በሚያሰኙ ነገሮች እንዲጠመድ ስለሚያደርገው የሚያልፈውን የሕይወት ዘመኑን ፈጽሞ ልብ አይለውም።*+ +3 “ሌሊት በአልጋዬ ላይ ሆኜየምወደውን* ሰው ለማግኘት ተመኘሁ።+ ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም።+ + 2 ተነስቼ በከተማዋ ውስጥ እዘዋወራለሁ፤የምወደውን* ሰውእስቲ በጎዳናዎቹና በአደባባዮቹ ልፈልገው። ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም። + 3 በከተማዋ ውስጥ የሚዘዋወሩት ጠባቂዎች አገኙኝ።+ እኔም ‘የምወደውን* ሰው አይታችሁታል?’ ብዬ ጠየቅኳቸው። + 4 ከእነሱ ገና እልፍ እንዳልኩየምወደውን* ሰው አገኘሁት። አጥብቄም ያዝኩት፤ወደ እናቴ ቤት፣ ወደ ፀነሰችኝም ሴት እልፍኝእስካስገባው ድረስ አለቀኩትም።+ + 5 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ በሜዳ ፍየሎችና በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ።”+ + 6 “በከርቤና በነጭ ዕጣን፣ጥሩ መዓዛ ባላቸውም የነጋዴ ቅመማ ቅመሞች ታውዶ፣+እንደ ጭስ ዓምድ ከምድረ በዳ እየመጣ ያለው ይህ ነገር ምንድን ነው?” + 7 “እነሆ፣ ይህ የሰለሞን ድንክ አልጋ ነው። ከእስራኤል ኃያላን የተውጣጡስልሳ ኃያላን አጅበውታል፤+ + 8 ሁሉም ሰይፍ የታጠቁናበውጊያ የሠለጠኑ ናቸው፤እያንዳንዳቸውም በሌሊት የሚያጋጥሙ አስፈሪ ነገሮችን ለመከላከልሰይፋቸውን ወገባቸው ላይ ታጥቀዋል።” + 9 “ይህ፣ ንጉሥ ሰለሞን ከሊባኖስ እንጨት+ለራሱ ያሠራው የንጉሥ ድንክ አልጋ* ነው። +10 ዓምዶቹን የሠራው ከብር፣መደገፊያዎቹን ደግሞ ከወርቅ ነው። መቀመጫው በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው፤ውስጡንም የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆችበፍቅር ተነሳስተው ለብጠውታል።” +11 “እናንተ የጽዮን ሴቶች ልጆች ሆይ፣ወጥታችሁ ንጉሥ ሰለሞንን ተመልከቱ፤በሠርጉ ዕለት፣ልቡ ሐሴት ባደረገበት በዚያ ቀን፣እናቱ+ የሠራችለትን የሠርግ አክሊል* ደፍቷል።” +7 “አንቺ የተከበርሽ ልጃገረድ ሆይ፣እግሮችሽ በነጠላ ጫማሽ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ! የዳሌዎችሽ ቅርጽየእጅ ባለሙያ የተጠበበባቸው ጌጦች ይመስላሉ። + 2 እምብርትሽ እንደ ክብ ሳህን ነው። የተደባለቀ ወይን ጠጅ ከእሱ አይታጣ። ሆድሽ ዙሪያውን በአበቦች እንደታጠረየስንዴ ክምር ነው። + 3 ሁለቱ ጡቶችሽ ሁለት ግልገሎችን፣የሜዳ ፍየል መንታዎችን ይመስላሉ።+ + 4 አንገትሽ+ በዝሆን ጥርስ የተሠራ ማማ ይመስላል።+ ዓይኖችሽ+ በባትራቢም በር አጠገብ እንዳሉትየሃሽቦን+ ኩሬዎች ናቸው። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ እንደሚመለከትየሊባኖስ ማማ ነው። + 5 ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ+ አክሊል ሆኖልሻል፤ፀጉርሽ*+ ሐምራዊ ሱፍ+ ይመስላል። ንጉሡ በዘንፋላው ፀጉርሽ ተማርኳል።* + 6 አንቺ የተወደድሽ ልጃገረድ ሆይ፣ ምንኛ ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!በጣም ከሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ በላይ ትማርኪያለሽ! + 7 ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፤ጡቶችሽ ደግሞ የቴምር ዘለላ ይመስላሉ።+ + 8 እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘የቴምር ዘለላዎቹን መያዝ እንድችልዛፉ ላይ እወጣለሁ።’ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ይሁኑ፤የትንፋሽሽ መዓዛ እንደ ፖም ሽታ ይሁን፤ + 9 አፍሽም* እንደ ምርጥ ወይን ጠጅ ይሁን።” “ይህ የወይን ጠጅ ለውዴ እየተንቆረቆረ ይውረድ፤በተኙ ሰዎች ከንፈር በቀስታ ይፍሰስ። +10 እኔ የውዴ ነኝ፤+እሱም የሚመኘው እኔን ነው። +11 ውዴ ሆይ፣ ና፤ወደ መስክ እንሂድ፤በሂና ተክሎች+ መካከል እንቀመጥ። +12 ወይኑ ለምልሞ፣*አበባው ፈክቶ፣+የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለማየት+በማለዳ ተነስተን ወደ ወይን እርሻዎቹ እንሂድ። እኔም በዚያ ለአንተ ያለኝን ፍቅር እገልጽልሃለሁ።+ +13 የዱዳይም* ፍሬዎቹ+ መዓዛቸውን ሰጥተዋል፤በደጆቻችንም ሁሉም ዓይነት ምርጥ ፍሬዎች አሉ።+ ውዴ ሆይ፣ አዲሶቹንም ሆነ በፊት የተቀጠፉትን ፍሬዎችለአንተ አስቀምጬልሃለሁ። +1 ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጠው የሰለሞን+ መዝሙር፦* + 2 “በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ፤የፍቅር መግለጫዎችህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛሉና።+ + 3 የዘይትህ መዓዛ ደስ ይላል።+ ስምህ ጥሩ መዓዛ እንዳለው የሚፈስ ዘይት ነው።+ ቆነጃጅት የሚወዱህ ለዚህ ነው። + 4 ይዘኸኝ ሂድ፤* አብረን እንሩጥ። ንጉሡ ወደ እልፍኞቹ አስገብቶኛል! በአንተ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ። ከወይን ጠጅ ይልቅ የፍቅር መግለጫዎችህን እናወድስ።* አንተን መውደዳቸው* ተገቢ ነው። + 5 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ እኔ ጥቁር ብሆንም ውብ ነኝ፤እንደ ቄዳር+ ድንኳኖች፣ እንደ ሰለሞን ድንኳኖችም+ ነኝ። + 6 ጥቁር ስለሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትዩኝ፤ፀሐይ ፊቴን አክስሎታልና። ወንድሞቼ በጣም ተቆጡኝ፤የወይን እርሻዎች ጠባቂ አደረጉኝ፤የገዛ ራሴን የወይን እርሻ ግን መጠበቅ አልቻልኩም። + 7 “እጅግ የምወድህ* ፍቅረኛዬ፣መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣+እኩለ ቀንም ላይ የት እንደምታሳርፍ ንገረኝ። በጓደኞችህ መንጎች መካከልበመሸፈኛ* ፊቷን ተሸፋፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?” + 8 “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ የማታውቂ ከሆነየመንጋውን ዱካ ተከትለሽ ሂጂ፤የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።” + 9 “ፍቅሬ ሆይ፣ የፈርዖንን ሠረገሎች በሚጎትቱ ፈረሶች መካከል እንዳለች ባዝራ* ውብ ነሽ።+ +10 ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፤*አንገትሽም በጨሌ ሐብል አጊጧል። +11 በብር ፈርጥ የተንቆጠቆጡየወርቅ ጌጦች* እንሠራልሻለን።” +12 “ንጉሡ ክብ ጠረጴዛው ጋ ተቀምጦ ሳለየሽቶዬ*+ መዓዛ አካባቢውን አወደው። +13 ውዴ ለእኔ ጥሩ መዓዛ እንዳለው በከረጢት ያለ ከርቤ+ ነው፤በጡቶቼ መካከል ያድራል። +14 ውዴ በኤንገዲ+ የወይን እርሻዎች መካከልእጅብ ብሎ እንደበቀለ የሂና ተክል+ ነው።” +15 “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ እንደ ርግብ+ ዓይኖች ናቸው።” +16 “ውዴ ሆይ፣ እነሆ፣ አንተ ውብ* ነህ፤ ደግሞም ደስ ትላለህ።+ አልጋችን በለምለም ቅጠል መካከል ነው። +17 የቤታችን* ተሸካሚዎች አርዘ ሊባኖሶች፣ጣሪያችንም የጥድ ዛፎች ናቸው። +8 “ምነው አንተ፣ የእናቴን ጡት እንደጠባ፣እንደ ወንድሜ በሆንክ! እንዲህ ቢሆን ኖሮ ውጭ ሳገኝህ በሳምኩህ ነበር፤+ማንም ባልናቀኝ ነበር። + 2 እኔም ወዳስተማረችኝወደ እናቴ ቤት በወሰድኩህናወደዚያ ባስገባሁህ ነበር።+ ትጠጣው ዘንድ ቅመም የተጨመረበት ወይን ጠጅናየሮማን ጭማቂ በሰጠሁህ ነበር። + 3 ግራ እጁን በተንተራስኩ፣ቀኝ እጁም ባቀፈኝ ነበር።+ + 4 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስ ፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ አምላችኋለሁ።”+ + 5 “ውዷን ደገፍ ብላከምድረ በዳ የምትመጣው ይህች ማን ናት?” “ከፖም ዛፍ ሥር ቀሰቀስኩህ። በዚያ እናትህ አንተን ለመውለድ አማጠች። በዚያም ወላጅ እናትህ ምጥ ይዟት ነበር። + 6 እንደ ማኅተም በልብህ፣እንደ ማኅተም በክንድህ አስቀምጠኝ፤ፍቅር እንደ ሞት የበረታ ነውና፤+ታማኝነትም* እንደ መቃብር* ጽኑ ነው፤ የፍቅር ወላፈን የእሳት ወላፈን ነው፤ የያህም* ነበልባል ነው።+ + 7 ጎርፍ ፍቅርን ሊያጠፋው አይችልም፤+ወንዞችም ጠራርገው ሊወስዱት አይችሉም።+ አንድ ሰው ለፍቅር ሲል የቤቱን ሀብት ሁሉ ለመስጠት ቢያቀርብሰዎች በጣም ይንቁበታል።”* + 8 “ገና ጡት ያላወጣችትንሽ እህት አለችን።+ እሷን በሚጠይቁን ቀንለእህታችን ምን ብናደርግ ይሻላል?” + 9 “እሷ ቅጥር ብትሆንበላይዋ ላይ የብር ጉልላት እንሠራለን፤በር ብትሆን ግንከአርዘ ሊባኖስ በተሠራ ሳንቃ እናሽጋታለን።” +10 “እኔ ቅጥር ነኝ፤ጡቶቼም እንደ ማማ ናቸው። በእሱም ፊትሰላም እንዳገኘች ሴት ሆንኩ። +11 ሰለሞን በበዓልሃሞን የወይን እርሻ ነበረው።+ እሱም የወይን እርሻውን ለጠባቂዎች በአደራ ሰጠ። እያንዳንዳቸውም ለሚያገኙት ፍሬ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ያመጡ ነበር። +12 የራሴ የሆነ የወይን እርሻ አለኝ። ሰለሞን ሆይ፣ አንድ ሺው የብር ሰቅል* የአንተ ነው፤ሁለት መቶው ደግሞ ፍሬውን ለሚጠብቁት ነው።” +13 “አንቺ በአትክልት ቦታዎቹ የምትኖሪ ሆይ፣+ጓደኞቼ* ድምፅሽን ያዳምጣሉ። እስቲ እኔም ልስማው።”+ +14 “ውዴ ሆይ፣ ቶሎ ና፤እንደ ሜዳ ፍየልወይም የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራሮች ላይ እንዳለየአጋዘን ግልገል ፍጠን።”+ +2 “እኔ ግን በባሕር ዳርቻ ላይ የሚበቅል የሳሮን አበባ* ነኝ፤የሸለቆም አበባ ነኝ።”+ + 2 “ፍቅሬ በሴቶች መካከል ስትታይበእሾህ መካከል እንዳለ አበባ ናት።” + 3 “ውዴ በወንዶች መካከል ሲታይበዱር ዛፎች መካከል እንዳለ የፖም ዛፍ ነው። በጥላው ሥር ለመቀመጥ እጅግ እጓጓለሁ፤ፍሬውም ለአፌ ጣፋጭ ነው። + 4 ወደ ግብዣ ቤት* ወሰደኝ፤የፍቅር ዓርማውንም በእኔ ላይ አውለበለበ። + 5 በዘቢብ ቂጣ ኃይሌን አድሱልኝ፤+በፖም አበረታቱኝ፤በፍቅሩ ተይዤ ታምሜአለሁና። + 6 ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤ቀኝ እጁም አቅፎኛል።+ + 7 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ፣ በሜዳ ፍየሎችና+ በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ።+ + 8 እነሆ፣ ውዴ ተራሮቹን እየወጣና በኮረብቶቹ ላይ እየዘለለ ሲመጣድምፁ ይሰማኛል! + 9 ውዴ፣ የሜዳ ፍየል ወይም የአጋዘን ግልገል+ ይመስላል። በመስኮት በኩል ትኩር ብሎ እየተመለከተ፣በፍርግርጉ በኩል አጮልቆ እያየከግድግዳችን ጀርባ ቆሟል። +10 ውዴ እንዲህ አለኝ፦ ‘ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽ፤የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ። +11 እነሆ፣ ክረምቱ አልፏል። ዝናቡ ቆሟል፤ ደግሞም ጠፍቷል። +12 በምድሩ ላይ አበቦች አብበዋል፤+ተክሎች የሚገረዙበት ጊዜ ደርሷል፤+በምድራችንም ላይ የዋኖስ ዝማሬ ተሰምቷል።+ +13 የበለስ ዛፏ መጀመሪያ ላይ ያፈራቻቸው ፍሬዎች በስለዋል፤+የወይን ተክሎቹም አብበው መዓዛቸውን ሰጥተዋል። ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽና ነይ፤የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ። +14 በዓለቶች መሃል በሚገኝ መሸሸጊያ፣በገደላማ ስፍራ ባለ ሰዋራ ቦታ ያለሽ ርግቤ ሆይ፣+እስቲ ልይሽ፤ ድምፅሽንም ልስማው፤+ድምፅሽ ማራኪ፣ ቁመናሽም ያማረ ነውና።’”+ +15 “ቀበሮዎቹን ይኸውም የወይን እርሻዎቹን የሚያበላሹትንትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን፤የወይን እርሻችን አብቧልና።” +16 “ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእሱ ነኝ።+ መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።+ +17 የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊትውዴ ሆይ፣ እንደ ሜዳ ፍየልወይም በመካከላችን ባሉት ተራሮች* ላይ እንደሚገኝ የአጋዘን ግልገል በፍጥነት ተመለስ።+ +4 “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ዓይኖች ናቸው። ፀጉርሽ ከጊልያድ+ ተራሮችእየተግተለተለ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው። + 2 ጥርሶችሽ ገና ተሸልተውናታጥበው እንደወጡ፣ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱ የበግ መንጋ ናቸው፤ደግሞም ከመካከላቸው ግልገሉን ያጣ የለም። + 3 ከንፈሮችሽ እንደ ደማቅ ቀይ ፈትል ናቸው፤ንግግርሽም አስደሳች ነው። በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ*የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። + 4 አንገትሽ+ አንድ ሺህ ጋሻዎች፣ይኸውም ኃያላን ሰዎች የሚይዟቸው ክብ ጋሻዎች+ ሁሉ የተንጠለጠሉበትንናበንብርብር ድንጋዮች የተገነባውንየዳዊት ማማ+ ይመስላል። + 5 ሁለቱ ጡቶችሽበአበቦች መካከል የተሰማሩ፣መንታ የሆኑ ሁለት የሜዳ ፍየል ግልገሎችን ይመስላሉ።”+ + 6 “የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊትወደ ከርቤው ተራራናወደ ነጭ ዕጣኑ ኮረብታ እሄዳለሁ።”+ + 7 “ፍቅሬ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤+እንከንም የለብሽም። + 8 ሙሽራዬ ሆይ፣ ተያይዘን ከሊባኖስ እንሂድ፤አዎ፣ ከሊባኖስ+ አብረን እንሂድ። ከአማና አናት፣ከሰኒር ጫፍ፣ ከሄርሞን+ አናት፣ከአንበሳ ዋሻዎች፣ ከነብር ተራሮች ውረጂ። + 9 እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ ልቤን ማርከሽዋል፤+በአንድ አፍታ እይታሽ፣ከሐብልሽ ዶቃዎች በአንዱ ልቤን ማርከሽዋል። +10 እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ የፍቅር መግለጫዎችሽ እንዴት ደስ ያሰኛሉ!+ የፍቅር መግለጫሽ ከወይን ጠጅ፣የሽቶሽም መዓዛ ከየትኛውም ዓይነት ቅመም+ እጅግ ይበልጣል!+ +11 ሙሽራዬ ሆይ፣ ከንፈሮችሽ የማር እንጀራ ወለላ ያንጠባጥባሉ።+ ከምላስሽ ሥር ማርና ወተት ይፈልቃል፤+የልብሶችሽም ጠረን እንደ ሊባኖስ መዓዛ ነው። +12 እህቴ፣ ሙሽራዬ፣ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣አዎ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣ የታሸገም ምንጭ ናት። +13 ቡቃያሽ* ሮማንና ምርጥ ፍራፍሬዎችደግሞም የሂና እና የናርዶስ ተክሎች የበቀሉበት ገነት* ነው፤ +14 በተጨማሪም ናርዶስ፣+ ሳፍሮን፣* ጠጅ ሣር፣+ ቀረፋ፣+ነጭ ዕጣን የሚገኝባቸው የተለያዩ ዛፎች፣ ከርቤ፣ እሬትና*+ሁሉም ዓይነት ምርጥ ሽቶዎች+ ያሉበት ገነት ነው። +15 አንቺ በአትክልት ቦታ ያለ ምንጭ፣ ንጹሕ ውኃ የሚገኝበት ጉድጓድናከሊባኖስ የሚፈስሱ ጅረቶች ነሽ።+ +16 የሰሜን ነፋስ ሆይ፣ ንቃ፤የደቡብ ነፋስ ሆይ፣ ና። በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ።* መዓዛውም አካባቢውን ያውደው።” “ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባናምርጥ የሆኑትን ፍራፍሬዎች ይብላ።” +6 “ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ውድሽ የት ሄደ? ለመሆኑ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው? አብረንሽ እንፈልገው።” + 2 “ውዴ መንጋውን በአትክልት ቦታዎቹ መካከል ለማሰማራትናአበቦችን ለመቅጠፍየቅመማ ቅመም ተክሎች መደብ ወዳለበትወደ አትክልት ቦታው ወርዷል።+ + 3 እኔ የውዴ ነኝ፤ውዴም የእኔ ነው።+ እሱ መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።”+ + 4 “ፍቅሬ ሆይ፣ አንቺ እንደ ቲርጻ*+ ቆንጆ ነሽ፤+እንደ ኢየሩሳሌምም ውብ ነሽ፤+በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ ታምሪያለሽ።+ + 5 ስሜቴን አውከውታልና፣ዓይኖችሽን+ ከእኔ ላይ አንሺ። ፀጉርሽ ከጊልያድ እየተግተለተለ እንደሚወርድየፍየል መንጋ ነው።+ + 6 ጥርሶችሽ ታጥበው እንደወጡ፣ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱየበግ መንጋ ናቸው፤ከመካከላቸውም ግልገሉን ያጣ የለም። + 7 በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽ*የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። + 8 እርግጥ 60 ንግሥቶች፣80 ቁባቶችናቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ቆነጃጅት ሊኖሩ ይችላሉ።+ + 9 እንከን የሌለባት ርግቤ+ ግን አንድ ብቻ ናት። እሷ ለእናቷ ብርቅዬ ልጅ ናት። በወለደቻት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ* ናት። ሴቶች ልጆች አይተዋት ‘የታደልሽ ነሽ’ ይሏታል፤ንግሥቶችና ቁባቶችም ያወድሷታል። +10 ‘እንደ ማለዳ ወጋገን የምታበራ፣*እንደ ሙሉ ጨረቃ ውብ የሆነች፣እንደ ፀሐይ ብርሃን የጠራች፣በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ የምታምረው ይህች ሴት ማን ናት?’”+ +11 “በሸለቆው* ውስጥ ያቆጠቆጡትን ተክሎች ለማየት፣ደግሞም ወይኑ ለምልሞ፣*የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለመመልከትየገውዝ ዛፎች ወዳሉበት ወደ አትክልት ቦታው ወረድኩ።+ +12 ምንም ሳይታወቀኝምኞቴ* የተከበሩ* ወገኖቼየያዟቸው ሠረገሎች ወዳሉበት ወሰደኝ።” +13 “አንቺ ሱላማዊት፣ ተመለሺ፤ ተመለሺ! እናይሽ ዘንድተመለሺ፤ ተመለሺ!” “በሱላማዊቷ ላይ የምታፈጡት ለምንድን ነው?”+ “እሷ የመሃናይምን ጭፈራ* ትመስላለች!” +5 “እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ወደ አትክልት ቦታዬ ገብቻለሁ።+ ከርቤዬንና ቅመሜን+ ወስጃለሁ። የማር እንጀራዬንና ወለላውን በልቻለሁ፤የወይን ጠጄንና ወተቴን ጠጥቻለሁ።”+ “ውድ ጓደኞቼ፣ ብሉ! ጠጥታችሁም በፍቅር መግለጫዎች ስከሩ!”+ + 2 “እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል።+ ውዴ በሩን ሲያንኳኳ ይሰማኛል! ‘እህቴ ሆይ፣ የእኔ ፍቅር፣እንከን የለሽ ርግቤ ሆይ፣ ክፈቺልኝ! ራሴ በጤዛ፣ፀጉሬም በሌሊቱ እርጥበት ርሷል።’+ + 3 ልብሴን አውልቄአለሁ። መልሼ መልበስ ሊኖርብኝ ነው? እግሬን ታጥቤአለሁ። እንደገና ላቆሽሸው ነው? + 4 ውዴ እጁን ከበሩ ቀዳዳ መለሰ፤ለእሱ ያለኝ ስሜትም ተነሳሳ። + 5 እኔም ለውዴ በሩን ለመክፈት ተነሳሁ፤የመዝጊያው እጀታ ላይእጆቼ ከርቤ፣ጣቶቼም የከርቤ ፈሳሽ አንጠባጠቡ። + 6 ለውዴ በሩን ከፈትኩለት፤ውዴ ግን በዚያ አልነበረም፤ ሄዶ ነበር። በመሄዱም ተስፋ ቆረጥኩ።* ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም።+ ጠራሁት፤ እሱ ግን አልመለሰልኝም። + 7 ከተማዋን እየተዘዋወሩ የሚጠብቁት ሰዎች አገኙኝ። መቱኝ፤ አቆሰሉኝ። የቅጥሩ ጠባቂዎች ነጠላዬን* ገፈፉኝ። + 8 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ውዴን ካገኛችሁት በፍቅሩ ተይዤ መታመሜንእንድትነግሩት አምላችኋለሁ።” + 9 “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው? እንዲህ ያለ መሐላ ያስገባሽን፣ለመሆኑ ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው?” +10 “ውዴ በጣም ቆንጆና ቀይ ነው፤በአሥር ሺህ ሰዎች መካከል እንኳ ጎልቶ ይታያል። +11 ራሱ እንደ ወርቅ፣ አዎ እንደጠራ ወርቅ ነው። ፀጉሩ እንደሚወዛወዝ የዘንባባ ዝንጣፊ* ነው፤እንደ ቁራም ጥቁር ነው። +12 ዓይኖቹ በውኃ ጅረት አጠገብ እንዳሉ፣ጢም ብሎ በሞላ ኩሬ ዳርቻ* ሆነውበወተት እንደሚታጠቡ ርግቦች ናቸው። +13 ጉንጮቹ የቅመማ ቅመም መደብ፣+ጥሩ መዓዛ ያላቸው ዕፀዋት ክምር ይመስላሉ። ከንፈሮቹ ፈሳሽ ከርቤ የሚያንጠባጥቡ አበቦች ናቸው።+ +14 የእጆቹ ጣቶች ወርቅ፣ የጣቶቹም ጫፎች ክርስቲሎቤ ናቸው። ሆዱ በሰንፔር የተሸፈነ የተወለወለ የዝሆን ጥርስ ነው። +15 እግሮቹ ከምርጥ ወርቅ በተሠሩ መሰኪያዎች ላይ የቆሙ የእብነ በረድ ዓምዶች ናቸው። መልኩ እንደ ሊባኖስ ያማረ ነው፤ እንደ አርዘ ሊባኖስም አቻ የለውም።+ +16 አፉ* እጅግ ጣፋጭ ነው፤ሁለመናውም ደስ ያሰኛል።+ የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ውዴ ይህ ነው፤ ፍቅሬ እንዲህ ያ�� ነው።” +17 በደማስቆ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ “እነሆ፣ ደማስቆ ከተማ መሆኗ ይቀራል፤የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች።+ + 2 የአሮዔር+ ከተሞች ወና ይሆናሉ፤የመንጎች ማረፊያ ይሆናሉ፤የሚያስፈራቸውም አይኖርም። + 3 የተመሸጉ ከተሞች ከኤፍሬም፣+መንግሥትም ከደማስቆ ይወገዳል፤+የተረፉት የሶርያ ሰዎች ክብርምልክ እንደ እስራኤላውያን ክብር ይጠፋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። + 4 “በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይከስማል፤ጤናማ የሆነው ሰውነቱም* ይከሳል። + 5 አጫጁ በማሳ ውስጥ ያለውን እህል በሚሰበስብበትናበእጁ ዛላውን በሚቆርጥበት ጊዜ እንደሚሆነው፣ደግሞም ሰው በረፋይም ሸለቆ*+ እህል በሚቃርምበት ጊዜ እንደሚሆነው እንዲሁ ይሆናል። + 6 የወይራ ዛፍ ሲመታከፍ ባለው ቅርንጫፍ ላይ ሁለት ወይም ሦስት የወይራ ፍሬዎች ብቻ፣ ፍሬ በሚይዙት ቅርንጫፎችም ላይ አራት ወይም አምስት ፍሬዎች ብቻ እንደሚቀሩ፣በእሱም ላይ ቃርሚያ ብቻ ይቀራል”+ ይላል የእስራኤል አምላክ ይሖዋ። +7 በዚያም ቀን ሰው ወደ ሠሪው ይመለከታል፤ ዓይኖቹም የእስራኤልን ቅዱስ ትኩር ብለው ያያሉ። +8 የእጁ ሥራ+ ወደሆኑት መሠዊያዎች አይመለከትም፤+ ጣቶቹ የሠሯቸውን የማምለኪያ ግንዶችም* ሆነ የዕጣን ማጨሻዎች አተኩሮ አያይም። + 9 በዚያም ቀን፣ የተመሸጉ ከተሞቹ በጫካ እንዳለ የተተወ ቦታ፣+በእስራኤላውያን ዘንድ እንደተተወ ቅርንጫፍ ይሆናሉ፤ቦታው ጠፍ መሬት ይሆናል። +10 አንቺ፣* አዳኝ አምላክሽን ረስተሻልና፤+መሸሸጊያ ዓለትሽንም+ አላስታወስሽም። ያማሩ ተክሎችን ያለማሽውናበመካከሉም የባዕድ* ቡቃያ የተከልሽው ለዚህ ነው። +11 በቀን በተክሎችሽ ዙሪያ አጥር ትሠሪያለሽ፤በማለዳም ዘርሽ እንዲበቅል ታደርጊያለሽ፤ይሁን እንጂ በበሽታና በማይሽር ሕመም ቀን አዝመራው ይጠፋል።+ +12 አዳምጡ! እንደሚናወጥ ባሕር ያለየብዙ ሕዝቦች ትርምስ ይሰማል! እንደ ኃይለኛ ውኃዎች ድምፅ ያለየሚያስገመግም የብሔራት ጫጫታ ይሰማል! +13 ብሔራት እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ያለ የሚያስገመግም ድምፅ ያሰማሉ። እሱ ይገሥጻቸዋል፤ እነሱም ወደ ሩቅ ቦታ ይሸሻሉ፤በተራራ ላይ እንዳለ በነፋስ እንደሚበን ገለባናአውሎ ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ ይሆናሉ። +14 ሲመሽ ሽብር ይነግሣል። ከመንጋቱም በፊት በዚያ አንዳቸውም አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች ድርሻ፣የበዘበዙንም ሰዎች ዕጣ ይህ ነው። +60 “አንቺ ሴት ሆይ፣ ተነሺ፣+ ብርሃን አብሪ፤ ብርሃንሽ መጥቷልና። የይሖዋ ክብር በአንቺ ላይ ያበራል።+ + 2 እነሆ፣ ጨለማ ምድርን፣ድቅድቅ ጨለማም ብሔራትን ይሸፍናል፤በአንቺ ላይ ግን ይሖዋ ያበራል፤ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል። + 3 ብሔራት ወደ ብርሃንሽ፣+ነገሥታትም+ አንጸባራቂ ወደሆነው ውበትሽ* ይመጣሉ።+ + 4 ዓይንሽን አንስተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ! ሁሉም አንድ ላይ ተሰብስበዋል፤ ወደ አንቺም እየመጡ ነው። ከሩቅ ቦታ ወንዶች ልጆችሽ በመምጣት ላይ ናቸው፤+ሴቶች ልጆችሽም ታዝለው እየመጡ ነው።+ + 5 በዚያን ጊዜ ታያለሽ፤ ፊትሽም ይፈካል፤+ልብሽ በኃይል ይመታል፤ በደስታም ይሞላል፤ምክንያቱም የባሕር ብልጽግና ወደ አንቺ ይጎርፋል፤የብሔራትም ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል።+ + 6 የግመል መንጋ ምድርሽን ይሸፍናል፤*የምድያምና የኤፋ+ ግልገል ግመሎች ያጥለቀልቁሻል። ሁሉም ወርቅና ነጭ ዕጣን ይዘውከሳባ ይመጣሉ። የይሖዋንም ውዳሴ ያውጃሉ።+ + 7 የቄዳር+ መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ። የነባዮት+ አውራ በጎች ያገለግሉሻል። እነሱም በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ይሆናሉ፤+ክብራማ የሆነውንም ቤቴን* አሳምረዋለሁ።+ + 8 እንደ ደመና፣ ወደ ቤታቸውም* እንደሚተሙ ርግቦችእየበረሩ ���ሚመጡት እነዚህ እነማን ናቸው? + 9 ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉና፤+የተርሴስ መርከቦችም ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽንከነብራቸውና ከነወርቃቸውለአምላክሽ ለይሖዋ ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ለማምጣት+ቀዳሚ ሆነው* ይወጣሉ፤እሱ ክብር* ያጎናጽፍሻልና።+ +10 የባዕድ አገር ሰዎች ቅጥሮችሽን ይገነባሉ፤ነገሥታታቸውም ያገለግሉሻል፤+በቁጣዬ መትቼሻለሁና፤በሞገሴ* ግን ምሕረት አሳይሻለሁ።+ +11 በሮችሽ ሁልጊዜ ክፍት ይሆናሉ፤+የብሔራትን ሀብት ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድበሮችሽ ቀንም ሆነ ሌሊት አይዘጉም፤ነገሥታታቸውም ቀዳሚ ይሆናሉ።+ +12 አንቺን የማያገለግል ማንኛውም ብሔርም ሆነ ማንኛውም መንግሥት ይጠፋልና፤ብሔራትም ፈጽመው ይደመሰሳሉ።+ +13 የመቅደሴን ስፍራ አስውብ ዘንድየሊባኖስ ክብር፣+ ጥዱ፣ የአሽ ዛፉና* የፈረንጅ ጥዱበአንድነት ወደ አንቺ ይመጣሉ፤+እግሬ የሚያርፍበትንም ስፍራ አከብራለሁ።+ +14 የጨቋኞችሽ ወንዶች ልጆች መጥተው በፊትሽ ይሰግዳሉ፤የሚያዋርዱሽ ሁሉ እግርሽ ሥር ይደፋሉ፤ደግሞም የይሖዋ ከተማ፣የእስራኤልም ቅዱስ አምላክ ንብረት የሆንሽ ጽዮን ብለው ይጠሩሻል።+ +15 የተተውሽና የተጠላሽ፣ ማንም ሰው የማያልፍብሽ መሆንሽ ቀርቶ+የዘላለም መኩሪያ፣ከትውልድ እስከ ትውልድም የደስታ ምንጭ እንድትሆኚ አደርግሻለሁ።+ +16 አንቺም የብሔራትን ወተት ትጠጫለሽ፤+የነገሥታትን ጡት ትጠቢያለሽ፤+እኔ ይሖዋ አዳኝሽ እንደሆንኩ፣ደግሞም የያዕቆብ ኃያል አምላክ የሆንኩት እኔ እንደምቤዥሽ በእርግጥ ታውቂያለሽ።+ +17 በመዳብ ፋንታ ወርቅ፣በብረት ፋንታ ብር፣በእንጨት ፋንታ መዳብ፣በድንጋዮችም ፋንታ ብረት አመጣለሁ፤ሰላምንም የበላይ ተመልካቾችሽ፣ጽድቅንም አሠሪዎችሽ አድርጌ እሾማለሁ።+ +18 ከዚህ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ዓመፅ፣ወይም በክልልሽ ውስጥ ጥፋትና ውድመት አይሰማም።+ ቅጥሮችሽን መዳን፣+ በሮችሽንም ውዳሴ ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ። +19 ከእንግዲህ ፀሐይ በቀን ብርሃን አትሆንልሽም፤የጨረቃም ብርሃን ከእንግዲህ አያበራልሽም፤ይሖዋ የዘላለም ብርሃን፣+አምላክሽም ውበት ይሆንልሻልና።+ +20 ፀሐይሽ ከእንግዲህ አትጠልቅም፤ጨረቃሽም አትደበዝዝም፤ይሖዋ የዘላለም ብርሃን ይሆንልሻልና፤+የሐዘንሽም ጊዜ ያበቃል።+ +21 ሕዝቦችሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ምድሪቱን ለዘላለም ይወርሳሉ። እነሱ፣ ውበት እጎናጸፍ ዘንድ የተከልኳቸው ችግኞች፣የእጆቼም ሥራ ናቸው።+ +22 ጥቂት የሆነው ሺህ፣ትንሽ የሆነውም ኃያል ብሔር ይሆናል። እኔ ይሖዋ፣ ይህን በራሱ ጊዜ አፋጥነዋለሁ።” +30 “ግትር ለሆኑ ልጆች ወዮላቸው”+ ይላል ይሖዋ፤“በኃጢአት ላይ ኃጢአት ለመጨመርየእኔን ሳይሆን የራሳቸውን ዕቅድ ይፈጽማሉ፤+ደግሞም ኅብረት ይፈጥራሉ፤* ይህን የሚያደርጉት ግን በመንፈሴ አይደለም። + 2 በፈርዖን ጥበቃ ሥር* ለመሸሸግናበግብፅ ጥላ ሥር ለመጠለልእኔን ሳያማክሩ*+ ወደ ግብፅ ይወርዳሉ!+ + 3 ይሁንና ፈርዖን የሚያደርግላችሁ ጥበቃ ለኀፍረት፣በግብፅ ጥላ ሥር መጠለልም ለውርደት ይዳርጋችኋል።+ + 4 መኳንንቱ በጾዓን+ ናቸውና፤መልእክተኞቹም ሃኔስ ደርሰዋል። + 5 ምንም ሊጠቅማቸው በማይችል፣እርዳታ በማይሰጥና ጥቅም በማያስገኝ፣ይልቁንም ለውርደትና ለነቀፋ በሚዳርግ ሕዝብሁሉም ኀፍረት ይከናነባሉ።”+ +6 በደቡብ እንስሳት ላይ የተላለፈ ፍርድ፦ አንበሳ፣ አዎ የሚያገሳ አንበሳ ባለበት፣እፉኝት እንዲሁም የሚበርና የሚያቃጥል እባብ* በሚገኙበት፣አስጨናቂና አስቸጋሪ ሁኔታዎች በሞሉበት ምድርሀብታቸውን በአህያ ላይ፣ቁሳቁሳቸውንም በግመል ሻኛ ላይ ጭነው ይሄዳሉ። ሆኖም እነዚህ ነገሮች ለሕዝቡ ምንም ጥቅም አያስገኙ + 7 ግብፅ የምትሰጠው እርዳ�� ምንም እርባና የለውምና።+ ስለዚህ እሷን “ረዓብ፣+ ሥራ ፈታ የምትጎለት” ብዬ ጠርቻታለሁ። + 8 “በል ሂድ፤ ለመጪዎቹ ዘመናት፣ቋሚ ምሥክር እንዲሆንእነሱ ባሉበት በጽላት ላይ ጻፈው፤በመጽሐፍም ላይ ክተበው።+ + 9 እነሱ ዓመፀኛ ሕዝብ፣+ አታላይ ልጆችና+የይሖዋን ሕግ* ለመስማት እንቢተኛ የሆኑ ልጆች ናቸውና።+ +10 ባለ ራእዮችን ‘ከእንግዲህ ራእይ አትዩ’ ይላሉ፤ ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እውነተኛ ራእይ አትንገሩን።+ የሚጥም* ነገር ንገሩን፤ አሳሳች የሆነ ሕልም አልሙልን።+ +11 ከመንገዱ ዞር በሉ፤ ጎዳናውንም ልቀቁ። የእስራኤልን ቅዱስ በፊታችን አታድርጉ።’”+ +12 ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ይህን ቃል ስለናቃችሁ፣+በማጭበርበርና በማታለል ስለታመናችሁ፣በዚያም ላይ ስለተደገፋችሁ፣+ +13 ይህ በደል እንደተሰነጠቀ ቅጥር፣ሊወድቅ እንደተቃረበ ያዘመመ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል። ሳይታሰብ በድንገት ይፈርሳል። +14 ሸክላ ሠሪ እንደሠራው ትልቅ እንስራ ይሰባበራል፤እንክትክቱ ከመውጣቱ የተነሳ ከምድጃ ፍም ለመውሰድወይም ከረግረጋማ ቦታ* ውኃ ለመጨለፍ የሚያስችልአንድም ገል አይገኝም።” +15 የእስራኤል ቅዱስ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ወደ እኔ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ሳትረበሹ፣ ተማምናችሁ በመኖር ብርቱ መሆናችሁን ታሳያላችሁ።”+ እናንተ ግን ፈቃደኞች አልሆናችሁም።+ +16 ይልቁንም “አይሆንም፣ በፈረሶች እንሸሻለን!” አላችሁ። ደግሞም ትሸሻላችሁ። “በፈጣን ፈረሶችም እንጋልባለን!” አላችሁ።+ ስለሆነም የሚያሳድዷችሁ ሰዎች ፈጣኖች ይሆናሉ።+ +17 አንድ ሰው ከሚሰነዝረው ዛቻ የተነሳ ሺዎች ይሸበራሉ፤+በተራራ አናት ላይ እንደተተከለ ምሰሶናበኮረብታ ላይ እንደቆመ ለምልክት የሚያገለግል ግንድ ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፣አምስት ሰዎች ከሚሰነዝሩት ዛቻ የተነሳ ትሸሻላችሁ።+ +18 ይሁንና ይሖዋ ሞገስ ሊያሳያችሁ በትዕግሥት* ይጠባበቃል፤+ምሕረት ሊያሳያችሁም ይነሳል።+ ይሖዋ የፍትሕ አምላክ ነውና።+ እሱን በተስፋ* የሚጠባበቁ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።+ +19 ሕዝቡ በጽዮን ይኸውም በኢየሩሳሌም በሚኖርበት ጊዜ+ ፈጽሞ አታለቅሱም።+ እርዳታ ለማግኘት በምትጮኹበት ጊዜ በእርግጥ ሞገስ ያሳያችኋል፤ ጩኸታችሁን እንደሰማም ይመልስላችኋል።+ +20 ይሖዋ የጭንቀትን ምግብና የጭቆናን ውኃ ቢሰጥህም+ እንኳ ታላቁ አስተማሪህ ከእንግዲህ ራሱን አይሰውርም፤ በገዛ ዓይኖችህም ታላቁን አስተማሪህን+ ታያለህ። +21 ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ዞር ብትል ጆሮህ ከኋላህ “መንገዱ ይህ ነው።+ በእሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል።+ +22 የተቀረጹ ምስሎችህ የተለበጡበትን ብርና ከብረት የተሠሩ ሐውልቶችህ*+ የተለበጡበትን ወርቅ ታረክሳለህ። እንደ ወር አበባ ጨርቅ “ከዚህ ጥፉ!”* በማለት አሽቀንጥረህ ትጥላቸዋለህ።+ +23 እሱም መሬት ላይ ለምትዘራው ዘር ዝናብ ይሰጥሃል፤+ ምድሪቱም የምታፈራው እህል የተትረፈረፈና ምርጥ* ይሆናል።+ በዚያም ቀን ከብቶችህ ሰፊ በሆነ የግጦሽ መስክ ይሰማራሉ።+ +24 መሬቱንም የሚያርሱ ከብቶችና አህዮች በእንቧጮ* የተቀመመ እንዲሁም በላይዳና በመንሽ የተለየ ገፈራ ይበላሉ። +25 ብዙ እልቂት በሚደርስበትና ግንቦች በሚፈርሱበት ቀን፣ በረጅም ተራራና ከፍ ባለ ኮረብታ ሁሉ ላይ ጅረቶች ይፈስሳሉ፤+ የውኃ መውረጃ ቦዮችም ይኖራሉ። +26 የሙሉ ጨረቃ ብርሃንም እንደ ፀሐይ ብርሃን ይሆናል፤ ይሖዋ የሕዝቡን ስብራት* በሚጠግንበትና+ በእሱ ምት የተነሳ የደረሰባቸውን ከባድ ቁስል በሚፈውስበት ቀን+ የፀሐይ ብርሃን፣ እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይደምቃል።+ +27 እነሆ፣ የይሖዋ ስም በቁጣው እየነደደጥቅጥቅ ካለ ደመና ጋር ከሩቅ ይመጣል። ከንፈሮቹ በቁጣ ተሞልተዋል፤ምላሱም እንደሚባላ እሳት ነው።+ +28 መንፈሱ* እስከ አንገት ድረስ እንደሚደርስ የሚያጥለቀልቅ ወንዝ ነው፤ብሔራትን በጥፋት ወንፊት* ይነፋቸዋል፤በሕዝቦች መንጋጋም መንገድ እንዲስቱ የሚያደርግ ልጓም ይገባል።+ +29 እናንተ ግን፣ ለበዓል በምትዘጋጁበት* ጊዜ+በሌሊት እንደሚዘመረው ያለ መዝሙር ትዘምራላችሁ፤ደግሞም ወደ እስራኤል ዓለት፣+ ወደ ይሖዋ ተራራ ሲጓዝዋሽንት ይዞ* እንደሚሄድ ሰውልባችሁ ሐሴት ያደርጋል። +30 ይሖዋ ግርማ የተላበሰ ድምፁ+ እንዲሰማ ያደርጋል፤የክንዱንም ብርታት ይገልጣል፤+ይህን የሚያደርገው በሚነድ ቁጣ፣+ በሚባላ የእሳት ነበልባል፣+ሳይታሰብ በሚወርድ ዶፍ፣+ ነጎድጓድ በቀላቀለ ውሽንፍርና በበረዶ ድንጋይ+ ታጅቦ ክንዱ ጥቃት ለመሰንዘር ወደ ታች በሚወርድበት ጊዜ ነው። +31 ከይሖዋ ድምፅ የተነሳ አሦር በሽብር ይናጣልና፤+በበትርም ይመታዋል።+ +32 ይሖዋ በጦርነት ክንዱን በእነሱ ላይ በሚያነሳበት ጊዜ+በአሦር ላይ የሚያወርደውየቅጣት በትር ሁሉበአታሞና በበገና የታጀበ ይሆናል።+ +33 ቶፌቱ*+ ከወዲሁ ተዘጋጅቷልና፤ለንጉሡም ተዘጋጅቶለታል።+ የእንጨት ክምሩ ጥልቀትና ስፋት ያለው እንዲሆን አድርጓል፤ብዙ እሳትና እንጨትም አለ። የይሖዋ እስትንፋስ ልክ እንደ ድኝ ጅረትበእሳት ያያይዘዋል። +35 ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ሐሴት ያደርጋል፤+በረሃማው ቦታም ደስ ይለዋል፤ እንደ ሳሮን አበባም * ያብባል።+ + 2 በእርግጥ ያብባል፤+ሐሴት ያደርጋል፤ በደስታም እልል ይላል። የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤+የቀርሜሎስንና+ የሳሮንን+ ግርማ ይለብሳል። የይሖዋን ክብር፣ የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ። + 3 የደከሙትን እጆች አበርቱ፤የሚብረከረኩትንም ጉልበቶች አጽኑ።+ + 4 በጭንቀት የተዋጠ ልብ ላላቸው እንዲህ በሏቸው፦ “በርቱ፤ አትፍሩ። እነሆ፣ አምላካችሁ ሊበቀል ይመጣል፤አምላክ ብድራት ሊከፍል ይመጣል።+ እሱ መጥቶ ያድናችኋል።”+ + 5 በዚያን ጊዜ የዓይነ ስውራን ዓይን ይገለጣል፤+መስማት የተሳናቸው ሰዎች ጆሮም ይከፈታል።+ + 6 በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፤+የዱዳም ምላስ በደስታ እልል ይላል።+ በምድረ በዳ ውኃ ይፈልቃልና፤በበረሃማ ሜዳም ጅረት ይፈስሳል። + 7 በሐሩር የተቃጠለው ምድር ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣የተጠማውም ምድር የውኃ ምንጭ ይሆናል።+ ቀበሮዎች ይኖሩበት የነበረው ጎሬ+ለምለም ሣር፣ ሸምበቆና ደንገል ይበቅልበታል። + 8 በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፤+ደግሞም “የቅድስና ጎዳና” ተብሎ ይጠራል። ንጹሕ ያልሆነ ሰው አይጓዝበትም።+ ጎዳናው፣ በመንገዱ ላይ ለሚሄዱት ብቻ ይሆናል፤ሞኞችም አይሄዱበትም። + 9 በዚያ አንበሳ አይኖርም፤አዳኝ አራዊትም ወደዚያ አይወጡም። አንዳቸውም በዚያ አይገኙም፤+የተቤዡት ብቻ በዚያ ይሄዳሉ።+ +10 ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ፤+ ወደ ጽዮንም በእልልታ ይመጣሉ።+ ፍጻሜ የሌለው ደስታን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+ ደስታንና ሐሴትን ያገኛሉ፤ሐዘንና ሲቃም ከዚያ ይርቃሉ።+ +31 እርዳታ ለማግኘት ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣+በፈረሶች ለሚመኩ፣+ብዛት ባላቸው የጦር ሠረገሎችናብርቱ በሆኑ የጦር ፈረሶች* ለሚታመኑ ወዮላቸው! ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ ተስፋ አያደርጉም፤ይሖዋንም አይሹም። + 2 ይሁንና እሱም ጥበበኛ ነው፤ ጥፋትም ያመጣል፤ቃሉንም አያጥፍም። በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣እንዲሁም መጥፎ ነገር የሚሠሩ ሰዎችን በሚረዱ ላይ ይነሳል።+ + 3 ግብፃውያን ግን ተራ ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ፈረሶቻቸው ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም።+ ይሖዋ እጁን ሲዘረጋ፣እርዳታ የሚሰጥ ሁሉ ይሰናከላል፤እርዳታ ተቀባዩም ሁሉ ��ወድቃል፤ሁሉም አንድ ላይ ይጠፋሉ። + 4 ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “አንበሳ ይኸውም ደቦል አንበሳ ባደነው እንስሳ ላይ ቆሞ እንደሚያገሳ፣ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበትምጩኸታቸው እንደማያሸብረው፣የሚያሰሙትም ሁካታ እንደማያስፈራው ሁሉየሠራዊት ጌታ ይሖዋም ለጽዮን ተራራና ለኮረብታዋ ሲልለመዋጋት ይወርዳል። + 5 ተወርውረው እንደሚወርዱ ወፎች፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋም እንዲሁ ኢየሩሳሌምን ይከልላታል።+ ይከልላታል፤ ደግሞም ያድናታል። ከአደጋ ያስጥላታል፤ እንዲሁም ይታደጋታል።” +6 “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እጅግ ወዳመፃችሁበት አምላክ ተመለሱ።+ +7 በዚያ ቀን እያንዳንዱ ሰው በገዛ እጆቻችሁ በኃጢአት የሠራችኋቸውን የማይረቡ የብር አማልክቱንና ከንቱ የሆኑ የወርቅ አማልክቱን ያስወግዳልና። + 8 አሦራዊውም የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤የሰው ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል።+ እሱም ሰይፉን ፈርቶ ይሸሻል፤ወጣቶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ። + 9 ቋጥኙ እጅግ ከመፍራቱ የተነሳ ደብዛው ይጠፋል፤መኳንንቱም ምልክት ሆኖ የሚያገለግለውን ምሰሶ ሲያዩ ይሸበራሉ” ይላልብርሃኑ* በጽዮን፣ እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነው ይሖዋ። +18 በክንፋቸው ጥዝ የሚል ድምፅ የሚያሰሙ ጥቃቅን ነፍሳት ላሉባትበኢትዮጵያ ወንዞች አካባቢ ለምትገኝ ምድር ወዮላት!+ + 2 ይህች ምድር በባሕር ላይ፣በደንገል ጀልባ ውኃዎችን አቋርጠው የሚሄዱ መልእክተኞችን እንዲህ በማለት ትልካለች፦ “እናንተ ፈጣን መልእክተኞች፣ረጃጅም የሆኑና ለስላሳ ቆዳ ያላቸው ሰዎች ወደሚገኙበት ብሔር፣*ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ወደሚፈራ ሕዝብ፣+ጥንካሬ ወዳለውና ድል አድራጊ ወደሆነው*እንዲሁም መሬቱ በወንዞ + 3 እናንተ በአገሪቱ የምትኖሩ ሁሉና እናንተ የምድር ነዋሪዎች ሁሉ፣በተራሮች ላይ እንደሚቆም ምልክት* ያለ ነገር ትመለከታላችሁ፤እንዲሁም ቀንደ መለከት ሲነፋ የሚሰማው ዓይነት ድምፅ ትሰማላችሁ። + 4 ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “በቀን ብርሃን እንዳለ የሚያጥበረብር ሐሩር፣በመከርም ሙቀት እንዳለ የደመና ጠል፣ጸጥ ብዬ ተቀምጬ ጽኑ ሆኖ የተመሠረተውን ስፍራዬን* እመለከታለሁ። + 5 ከመከር በፊት፣አበባው በሚረግፍበትና የወይን ፍሬው በሚበስልበት ጊዜቀንበጦቹ በማጭድ ይቆረጣሉና፤ሐረጎቹም ተቆርጠው ይወገዳሉ። + 6 ሁሉም በተራሮች ላይ ላሉ አዳኝ አሞሮችናለምድር አራዊት ይተዋሉ። አዳኝ አሞሮቹም እነሱን በመመገብ በጋውን ያሳልፋሉ፤በምድር ላይ ያሉ አራዊትም ሁሉ እነሱን በመመገብ የመከሩን ወቅት ያሳልፋሉ። + 7 በዚያን ጊዜ ረጃጅም የሆኑና ለስላሳ ቆዳ ያላቸው ሰዎች የሚገኙበት ብሔር፣*ከቅርብም ሆነ ከሩቅ የሚፈራው ሕዝብ፣ጥንካሬ ያለው፣ ድል አድራጊ የሆነውና*መሬቱ በወንዞች ተጠርጎ የተወሰደበት ብሔርለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ስጦታ ያመጣል፤ስጦታውንም የሚያመጣው የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ +23 ስለ ጢሮስ የተነገረ የፍርድ መልእክት፦+ እናንተ የተርሴስ መርከቦች+ ዋይ ዋይ በሉ! ወደቧ ወድሟልና፤ ወደ እሷ መግባት አይቻልም። ከኪቲም+ አገር ወሬው ደርሷቸዋል። + 2 እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ ሰዎች፣ ጸጥ በሉ። ባሕሩን አቋርጠው የሚመጡት የሲዶና+ ነጋዴዎች ሀብት በሀብት አድርገዋችኋል። + 3 የገቢ ምንጮቿ የሆኑት የሺሆር*+ እህልና*የአባይ መከር በብዙ ውኃዎች ላይ ተጓጉዘውየብሔራትን ትርፍ ያመጡላት ነበር።+ + 4 አንቺ የባሕር ምሽግ ሲዶና ሆይ፣ እፈሪ፤ምክንያቱም ባሕሩ እንዲህ ብሏል፦ “አላማጥኩም፤ አልወለድኩምም፤ወጣት ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን* አላሳደግኩም።”+ + 5 ስለ ግብፅ በተነገረው ወሬ እንደሆነው ሁሉ+ስለ ጢሮስም በሚነገረው ወሬ ሰዎች ጭንቅ ይይ��ቸዋል።+ + 6 ባሕሩን አቋርጣችሁ ወደ ተርሴስ ተሻገሩ! እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ ሰዎች ዋይ ዋይ በሉ! + 7 ከጥንት ዘመን፣ ከድሮ ጀምሮ ሐሴት ታደርግ የነበረችው ከተማችሁ ይህች ናት? በዚያ ትኖር ዘንድ እግሮቿ ወደ ሩቅ ቦታዎች ይወስዷት ነበር። + 8 ዘውድ በምታጎናጽፈው፣እንዲሁም መኳንንት የሆኑ ነጋዴዎች፣በመላውም ምድር ላይ የተከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯትበጢሮስ ላይ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው ማን ነው?+ + 9 በውበቷ ሁሉ የተነሳ የሚሰማትን ኩራት ለማርከስእንዲሁም በመላው ምድር ላይ የተከበሩትን ሁሉ ለማዋረድይህን ውሳኔ ያስተላለፈው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ራሱ ነው።+ +10 የተርሴስ ሴት ልጅ ሆይ፣ እንደ አባይ ወንዝ ምድርሽን አጥለቅልቂ። ከእንግዲህ ወዲያ መርከብ የሚሠራበት ቦታ* አይኖርም።+ +11 አምላክ እጁን በባሕሩ ላይ ዘርግቷል፤መንግሥታትን አንቀጥቅጧል። ይሖዋ የፊንቄ ምሽጎች እንዲወድሙ ትእዛዝ አስተላልፏል።+ +12 እሱም እንዲህ ይላል፦ “አንቺ የተጨቆንሽ የሲዶና ድንግል ሆይ፣ዳግመኛ ሐሴት አታደርጊም።+ ተነሽ፣ ወደ ኪቲም+ ተሻገሪ። እዚያም ቢሆን እረፍት አታገኚም።” +13 የከለዳውያንን+ ምድር ተመልከቱ! በበረሃ የሚኖሩ እንስሳት መፈንጫ ያደረጓትአሦራውያን+ ሳይሆኑ እነዚህ ሰዎች ናቸው። ጥቃት ለመሰንዘር የሚያስችል ማማ አቁመዋል፤የማይደፈሩ ማማዎቿን በማፈራረስ+የፍርስራሽ ክምር አድርገዋታል። +14 እናንተ የተርሴስ መርከቦች፣ምሽጋችሁ ስለወደመ ዋይ ዋይ በሉ።+ +15 በዚያም ቀን ጢሮስ እንደ አንድ ንጉሥ ዕድሜ* ለ70 ዓመት የተረሳች ትሆናለች።+ በ70ኛው ዓመት ማብቂያ ላይ ጢሮስ እንዲህ ተብሎ እንደሚዘመርላት ዝሙት አዳሪ ትሆናለች፦ +16 “አንቺ የተረሳሽ ዝሙት አዳሪ፣ በገና ይዘሽ በከተማው ውስጥ ተዘዋወሪ። በገናሽንም ጥሩ አድርገሽ ተጫወቺ፤እነሱም እንዲያስታውሱሽብዙ ዘፈን ዝፈኚ።” +17 በሰባው ዓመት መጨረሻ ላይ ይሖዋ ትኩረቱን በጢሮስ ላይ ያደርጋል፤ እሷም ዳግመኛ ክፍያ መቀበሏን ትቀጥላለች፤ በመላው ምድር ላይ ካሉ የዓለም መንግሥታትም ጋር ታመነዝራለች። +18 ሆኖም ትርፏና የምትቀበለው ክፍያ ለይሖዋ የተቀደሰ ይሆናል። አይከማችም ወይም አይጠራቀምም፤ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት የሚኖሩ ሰዎች እስኪጠግቡ ድረስ እንዲበሉና የሚያምር ልብስ እንዲለብሱ እሷ የምትቀበለው ክፍያ ለእነሱ ይሰጣል።+ +34 እናንተ ብሔራት፣ ለመስማት ወደዚህ ቅረቡ፤እናንተ ሕዝቦች፣ በትኩረት አዳምጡ። ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ፣ምድርና ከእሷ የሚገኘው ምርት ሁሉ ይስሙ። + 2 ይሖዋ በሁሉም ብሔራት ላይ ተቆጥቷልና፤+በሠራዊታቸውም ሁሉ ላይ ተቆጥቷል።+ ፈጽሞ ያጠፋቸዋል፤ለእርድም አሳልፎ ይሰጣቸዋል።+ + 3 የተገደሉባቸው ሰዎች ይጣላሉ፤የአስከሬኖቻቸውም ግማት ወደ ላይ ይወጣል፤+ከደማቸውም የተነሳ ተራሮቹ ይሸረሸራሉ።*+ + 4 የሰማያት ሠራዊት ሁሉ ይበሰብሳሉ፤ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ። ደርቆ እንደረገፈ የወይን ቅጠልናደርቆ እንደወደቀ በለስሠራዊታቸውም ሁሉ ደርቀው ይረግፋሉ። + 5 “ሰይፌ በሰማያት በደም ትርሳለችና።+ በኤዶም ይኸውም እንዲጠፋፍርድ ባስተላለፍኩበት ሕዝብ ላይ ትወርዳለች።+ + 6 ይሖዋ ሰይፍ አለው፤ ሰይፉም በደም ትሸፈናለች። በስብ፣+ በበግ ጠቦቶችና በፍየሎች ደምእንዲሁም በአውራ በጎች ኩላሊት ስብ ትለወሳለች።ይሖዋ በቦስራ መሥዋዕት፣ በኤዶምም ምድርታላቅ እርድ ያዘጋጃልና።+ + 7 የዱር በሬዎች ከእነሱ ጋር ይወድቃሉ፤ወይፈኖችም ከብርቱ ኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ። ምድራቸውም በደም ይሸፈናል፤አፈራቸውም በስብ ይርሳል።” + 8 ይሖዋ የሚበቀልበት ቀን፣+በጽዮን ላይ ለተፈጸመው በደል ቅጣት የ���ያስፈጽምበት ዓመት አለውና።+ + 9 በእሷ* የሚገኙት ጅረቶች ወደ ዝፍት ይለወጣሉ፤አፈሯም ወደ ድኝ ይቀየራል፤ምድሪቱም እንደሚቃጠል ዝፍት ትሆናለች። +10 እሳቱ በሌሊትም ሆነ በቀን አይጠፋም፤ጭሷም ለዘላለም ይወጣል። ከትውልድ እስከ ትውልድም እንደወደመች ትቀራለች፤ለዘላለም ማንም በእሷ አያልፍም።+ +11 ሻላና* ጃርት ይወርሷታል፤ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉቶችና ቁራዎችም በእሷ ውስጥ ይኖራሉ። አምላክ፣ ምድሪቱ ባዶ እንደምትሆንና እንደምትጠፋ ለማሳየትበመለኪያ ገመድና በቱንቢ* ይለካታል። +12 ከታላላቅ ሰዎቿ መካከል ለንግሥና የሚበቃ አንድም ሰው አይኖርም፤መኳንንቷም ሁሉ ይጠፋሉ። +13 በማይደፈሩ ማማዎቿ ላይ እሾህ፣በምሽጎቿም ላይ ሳማና ኩርንችት ይበቅላል። የቀበሮዎች ማደሪያ፣+የሰጎኖችም መኖሪያ ትሆናለች። +14 የበረሃ ፍጥረታት ከሚያላዝኑ እንስሶች ጋር ይገናኛሉ፤የዱር ፍየልም* ባልንጀራውን ይጠራል። የሌሊት ወፍ በዚያ ታርፋለች፤ ማረፊያ ስፍራም ታገኛለች። +15 ተወንጫፊ እባብ በዚያ ጎጆዋን ትሠራለች፤ እንቁላልም ትጥላለች፤ከዚያም ትቀፈቅፋለች፤ በጥላዋም ሥር ትሰበስባቸዋለች። ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው በዚያ ይሰበሰባሉ። +16 በይሖዋ መጽሐፍ ውስጥ ፈልጉ፤ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ አንብቡ፤ ከእነሱ መካከል አንዳቸውም አይጎድሉም፤ሁሉም ተጓዳኝ አያጡም፤ይህ ትእዛዝ የወጣው ከይሖዋ አፍ ነውና፤አንድ ላይ የሰበሰባቸውም የእሱ መንፈስ ነው። +17 ዕጣ የጣለላቸው እሱ ነው፤የተመደበላቸውን ቦታ የለካው የገዛ እጁ ነው።* እነሱም ለዘለቄታው ይወርሱታል፤ከትውልድ እስከ ትውልድም በዚያ ይኖራሉ። +19 በግብፅ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ እነሆ፣ ይሖዋ በፈጣን ደመና እየጋለበ ወደ ግብፅ እየመጣ ነው። የግብፅ ከንቱ አማልክት በእሱ ፊት ይንቀጠቀጣሉ፤+የግብፅም ልብ በውስጧ ይቀልጣል። + 2 “ግብፃውያንን በግብፃውያን ላይ አስነሳለሁ፤እርስ በርሳቸውም ይጨራረሳሉ፤እያንዳንዱ ወንድሙን፣ እያንዳንዱም ባልንጀራውን፣ከተማም ከተማን፣ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል። + 3 የግብፅም መንፈስ በውስጧ ይረበሻል፤ዕቅዷንም አፋልሳለሁ።+ እነሱም እርዳታ ለማግኘት ከንቱ ወደሆኑት አማልክት፣ወደ ድግምተኞች፣ ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች ይዞራሉ።+ + 4 ግብፅ በኃይለኛ ገዢ እጅ እንድትወድቅ አደርጋለሁ፤ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል”+ ይላል እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። + 5 የባሕሩ ውኃ ይደርቃል፤ወንዙም ይተናል፤ ጨርሶም ይደርቃል።+ + 6 ወንዞቹም ይገማሉ፤በግብፅ የሚገኙት የአባይ የመስኖ ቦዮች ይጎድላሉ፤ ይደርቃሉም። ቄጠማውና እንግጫው ይበሰብሳል።+ + 7 በአባይ ወንዝ መዳረሻ አካባቢ፣ በአባይ ዳር ያለው ተክልእንዲሁም በአባይ ወንዝ አጠገብ ዘር የተዘራበት መሬት+ ሁሉ ይደርቃል።+ በነፋስ ተጠርጎ ይወሰዳል፤ ደብዛውም ይጠፋል። + 8 ዓሣ አጥማጆቹም ያዝናሉ፤ወደ አባይ ወንዝ የዓሣ መንጠቆ የሚወረውሩም ሁሉ ያለቅሳሉ፤በውኃው ላይ የዓሣ ማጥመጃ መረቦችን የሚጥሉም ይመናመናሉ። + 9 በተነደፈ የተልባ እግር+ የሚሠሩም ሆኑነጭ ሸማ የሚሠሩ ሸማኔዎች ለኀፍረት ይዳረጋሉ። +10 የሽመና ባለሙያዎቿ ይደቆሳሉ፤ቅጥር ሠራተኞቹ ሁሉ ያዝናሉ።* +11 የጾዓን+ መኳንንት ሞኞች ናቸው። ጥበበኞች የሆኑ የፈርዖን አማካሪዎች የሚሰጡት ምክር ማስተዋል የጎደለው ነው።+ ፈርዖንን “እኔ የጥበበኞች ልጅ፣ የጥንት ነገሥታትም ዘር ነኝ”እንዴት ትሉታላችሁ? +12 ጥበበኞችህ ታዲያ የት አሉ?+ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ግብፅ የወሰነውን የሚያውቁ ከሆነ ይንገሩህ። +13 የጾዓን መኳንንት የሞኝ ሥራ ሠርተዋል፤የኖፍ*+ መኳንንት ተታለዋል፤የነገዶቿ አለቆች ግብፅ እንድትባዝን አድርገዋል። +14 ይሖዋ በእሷ ላይ ግራ የመጋባት መንፈስ አፍስሷል፤+የሰከረ ሰው በትፋቱ ላይ እንደሚንገዳገድ ሁሉእነሱም ግብፅ በሥራዋ ሁሉ እንድትባዝን አድርገዋል። +15 ግብፅ ለራስም ሆነ ለጅራት፣ ለቀንበጥም ሆነ ለእንግጫ*ልታደርገው የምትችለው ምንም ነገር የለም። +16 በዚያ ቀን ግብፃውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በእነሱ ላይ እጁን በዛቻ ስለሚያወዛውዝ ይንቀጠቀጣሉ፤ ይሸበራሉም።+ +17 የይሁዳም ምድር ግብፅን ታሸብራለች። ስለ ምድሪቱ ሲወራ የሚሰሙ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በግብፃውያን ላይ ከወሰነው ውሳኔ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ።+ +18 በዚያ ቀን በግብፅ ምድር የከነአንን ቋንቋ የሚናገሩና+ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ታማኝ እንደሚሆኑ በመሐላ የሚያረጋግጡ አምስት ከተሞች ይኖራሉ። ከእነዚህም መካከል አንዷ ‘የማፍረስ ከተማ’ ተብላ ትጠራለች። +19 በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል ለይሖዋ መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ላይ ለይሖዋ ዓምድ ይቆማል። +20 ይህም በግብፅ ምድር ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ምልክትና ምሥክር ይሆናል፤ እነሱ ከጨቋኞቻቸው የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻሉና፤ እሱም የሚታደጋቸው አዳኝ፣ አዎ ታላቅ አዳኝ ይልክላቸዋል። +21 ይሖዋም በግብፃውያን ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ በዚያም ቀን ግብፃውያን ይሖዋን ያውቁታል፤ መሥዋዕትና ስጦታ ያቀርባሉ፤ ለይሖዋም ይሳላሉ፤ የተሳሉትንም ይፈጽማሉ። +22 ይሖዋ ግብፅን ይመታታል፤+ መትቶ ይፈውሳታል፤ እነሱም ወደ ይሖዋ ይመለሳሉ፤ እሱም ልመናቸውን ሰምቶ ይፈውሳቸዋል። +23 በዚያ ቀን ከግብፅ ወደ አሦር የሚወስድ አውራ ጎዳና ይኖራል።+ ከዚያም አሦር ወደ ግብፅ፣ ግብፅም ወደ አሦር ይመጣል፤ ግብፅና አሦርም በአንድነት አምላክን ያገለግላሉ። +24 በዚያ ቀን እስራኤል ሦስተኛ ወገን ሆና ከግብፅና ከአሦር ጋር ትተባበራለች፤+ በምድርም መካከል በረከት ትሆናለች፤ +25 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ “ሕዝቤ ግብፅ፣ የእጄም ሥራ አሦር፣ ርስቴም እስራኤል የተባረኩ ይሁኑ”+ ብሎ ይባርካቸዋልና። +58 “ጉሮሮህ እስኪሰነጠቅ ጩኽ፤ ምንም አትቆጥብ! ድምፅህን እንደ ቀንደ መለከት አሰማ። ለሕዝቤ ዓመፃቸውን፣ለያዕቆብ ቤት ኃጢአታቸውን አውጅ።+ + 2 እነሱ በየዕለቱ እኔን ይፈልጉኛል፤ጽድቅ ይሠራ የነበረ፣የአምላኩንም ፍትሕ ያልተወ ብሔር የሆኑ ይመስል+መንገዶቼን ማወቅ ደስ እንደሚያሰኛቸው ይገልጻሉ። በጽድቅ እንድፈርድላቸው ይጠይቃሉ፤ወደ አምላክ መቅረብ ደስ ያሰኛቸዋል፦+ + 3 ‘ስንጾም የማታየው ለምንድን ነው?+ ራሳችንን* ስናጎሳቁል የማታስተውለውስ ለምንድን ነው?’+ በምትጾሙበት ቀን የራሳችሁን ጥቅም* ስለምታሳድዱናሠራተኞቻችሁን ስለምትጨቁኑ ነው።+ + 4 ጾማችሁ በጭቅጭቅና በጥል ያበቃል፤እንዲሁም ያለርኅራኄ በቡጢ ትማታላችሁ። ዛሬ እንደምትጾሙት እየጾማችሁ ድምፃችሁ በሰማይ ሊሰማ አይችልም። + 5 እኔ የመረጥኩት ጾም እንዲህ ሊሆን ይገባል?ሰው ራሱን* የሚያጎሳቁልበት፣እንደ እንግጫ ራሱን የሚደፋበት፣መኝታውን በማቅና በአመድ ላይ የሚያነጥፍበት ቀን መሆን አለበት? እናንተ ጾም የምትሉት፣ ይሖዋንም ደስ የሚያሰኝ ቀን ብላችሁ የምትጠሩት ይህን ነው? + 6 አይደለም፤ እኔ የመረጥኩት ጾም ይህ ነው፦ የክፋትን የእግር ብረት እንድታስወግዱ፣የቀንበርን ማሰሪያ እንድትፈቱ፣+የተጨቆኑትን በነፃ እንድትለቁ፣+ቀንበርንም ሁሉ እንድትሰብሩ ነው፤ + 7 ምግብህን ለተራበው እንድታካፍል፣+ድሆችንና ቤት የሌላቸውን ወደ ቤትህ እንድታስገባ፣የተራቆተ ሰው ስታይ እንድታለብስ፣+ለሥጋ ዘመድህም ጀርባህን እንዳትሰጥ ነው። + 8 በዚህ ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ጮራ ይፈነጥቃል፤+ፈውስህም ���ጥኖ ይመጣል። ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፤የይሖዋም ክብር ደጀን ይሆንልሃል።+ + 9 የዚያን ጊዜ ትጣራለህ፤ ይሖዋም ይመልስልሃል፤እርዳታ ለማግኘት ትጮኻለህ፤ እሱም ‘አለሁልህ!’ ይልሃል። ከመካከልህ ቀንበሩን ብታስወግድእንዲሁም ጣትህን መቀሰርና ተንኮል ያዘለ ንግግር መናገር ብትተው፣+ +10 ለተራበው ሰው አንተ ራስህ* የምትፈልገውን ነገር ብታደርግለት፣+የተጎሳቆሉትንም ብታረካ፣*ያን ጊዜ ብርሃንህ በጨለማ እንኳ ቦግ ብሎ ይበራል፤ጨለማህም እንደ ቀትር ብርሃን ይሆናል።+ +11 ይሖዋ ምንጊዜም ይመራሃል፤ደረቅ በሆነ ምድርም እንኳ ፍላጎትህን ያረካል፤*+አጥንቶችህን ያበረታል፤አንተም ውኃ እንደሚጠግብ የአትክልት ቦታናውኃው እንደማይቋረጥ ምንጭ ትሆናለህ።+ +12 ከአንተም የተነሳ የጥንቶቹን ፍርስራሾች መልሰው ይገነባሉ፤+ያለፉትን ትውልዶች መሠረቶች ታድሳለህ።+ አንተም የፈረሱትን* ግንቦች የሚያድስ፣በመኖሪያ ቦታዎች አካባቢ የሚገኙ ጎዳናዎችን የሚጠግን ተብለህ ትጠራለህ።+ +13 ሰንበትን በማክበር በተቀደሰው ቀኔ የራስህን ጥቅም* ከማሳደድ ብትቆጠብ፣*+ሰንበትንም ሐሴት፣ የተቀደሰ የይሖዋ ቀንና ሊከበር የሚገባው ቀን ብለህ ብትጠራው+እንዲሁም የራስህን ጥቅም ከማሳደድና ከንቱ ቃል ከመናገር ይልቅ ብታከብረው፣ +14 ያን ጊዜ በይሖዋ ሐሴት ታደርጋለህ፤ደግሞም በምድር ከፍ ያሉ ቦታዎች ላይ እንድትጋልብ አደርግሃለሁ።+ ከአባትህ ከያዕቆብ ርስት አበላሃለሁ፤*+የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።” +20 የአሦር ንጉሥ ሳርጎን የላከው ታርታን* ወደ አሽዶድ+ በመጣበት ዓመት አሽዶድን ወግቶ ያዛት።+ +2 በዚያን ጊዜ ይሖዋ የአሞጽ ልጅ በሆነው በኢሳይያስ በኩል እንዲህ ሲል ተናገረ፦+ “ሂድ፣ ማቁን ከወገብህ ላይ አስወግድ፤ ጫማህንም ከእግርህ ላይ አውልቅ።” እሱም እንደተባለው አደረገ፤ ራቁቱንና* ባዶ እግሩንም ተመላለሰ። +3 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ በግብፅና+ በኢትዮጵያ+ ላይ ለሚደርሰው ነገር ምልክትና+ ማስጠንቀቂያ እንዲሆን ለሦስት ዓመት ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደተመላለሰ ሁሉ፣ +4 የአሦር ንጉሥም የግብፅን ምርኮኞችና+ የኢትዮጵያን ግዞተኞች፣ ልጆችንና ሽማግሌዎችን ሳይቀር መቀመጫቸውን ገልቦ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን እየነዳ ይወስዳቸዋል፤ የግብፅንም እርቃን ያጋልጣል።* +5 ተስፋቸውን በጣሉባት በኢትዮጵያና በሚኮሩባት* በግብፅ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ፤ ብሎም ያፍራሉ። +6 በዚያም ቀን በዚህ የባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ ‘ተስፋ የጣልንበትን ይኸውም እርዳታ ለማግኘትና ከአሦር ንጉሥ ለመዳን የሸሸንበትን አገር ተመልከቱ! በዚህ ዓይነት እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ማለቱ አይቀርም።” +3 እነሆ፣ እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋኢየሩሳሌምና ይሁዳ ማንኛውም ዓይነት ድጋፍና አቅርቦትይኸውም የምግብና የውኃ አቅርቦት ሁሉ እንዲቋረጥባቸው ያደርጋል፤+ + 2 ኃያሉን ሰውና ተዋጊውን፣ዳኛውንና ነቢዩን፣+ ሟርተኛውንና ሽማግሌውን፣ + 3 የሃምሳ አለቃውን፣+ ባለሥልጣኑንና አማካሪውን፣በአስማት የተካነውንና በድግምት የላቀ ችሎታ ያለውን ያስወግዳል።+ + 4 በእነሱ ላይ ልጆችን መኳንንት አድርጌ እሾማለሁ፤ያልሰከነ* ሰውም ይገዛቸዋል። + 5 ሕዝቡ አንዱ ሌላውን፣እያንዳንዱም ባልንጀራውን ይጨቁናል።+ ልጅ በሽማግሌ ላይ ጥቃት ይሰነዝራል፤ተራው ሰውም የተከበረውን ይዳፈራል።+ + 6 እያንዳንዱ ሰው በአባቱ ቤት የሚኖረውን ወንድሙን ይዞ “አንተ ካባ አለህ፤ ስለዚህ በእኛ ላይ አዛዥ ሁን። ይህን የፍርስራሽ ክምር ግዛ” ይለዋል። + 7 እሱ ግን በዚያ ቀን እንዲህ ሲል ይቃወማል፦ “እኔ ቁስላችሁን አላክምም፤*በቤቴ ምግብም ሆነ ልብስ የለም። በሕዝቡ ላይ አዛዥ አድርጋችሁ አትሹሙኝ።” + 8 ኢየሩሳሌም ተሰናክላለችና፤ይሁዳም ወድቃለች፤ምክንያቱም እነሱ በአንደበታቸውም ሆነ በሥራቸው ይሖዋን ይቃወማሉ፤በክብራማው አምላክ ፊት* አሻፈረን ይላሉ።+ + 9 የፊታቸው ገጽታ ይመሠክርባቸዋል፤ደግሞም እንደ ሰዶም+ ኃጢአታቸውን በይፋ ይናገራሉ፤ኃጢአታቸውን ለመደበቅ አይሞክሩም። በራሳቸው ላይ ጥፋት ስለሚያመጡ ወዮላቸው!* +10 ለጻድቃን መልካም እንደሚሆንላቸው ንገሯቸው፤ለሥራቸው ወሮታ ይከፈላቸዋል።*+ +11 ለክፉ ሰው ወዮለት! ጥፋት ይደርስበታል፤በሌሎች ላይ ሲያደርግ የነበረው በራሱ ላይ ይደርሳልና! +12 የሕዝቤ አሠሪዎች ጨቋኞች ናቸው፤ሴቶችም ይገዟቸዋል። ሕዝቤ ሆይ፣ የሚመሯችሁ ሰዎች እንድትባዝኑናበየትኛው መንገድ እንደምትሄዱ ግራ እንድትጋቡ እያደረጓችሁ ነው።+ +13 ይሖዋ ለመክሰስ ተሰይሟል፤በሕዝቦች ላይ ብያኔውን ለማሰማት ተነስቷል። +14 ይሖዋ የሕዝቡን ሽማግሌዎችና አለቆች ይፋረዳል። “የወይኑን እርሻ አቃጥላችኋል፤ከድሃው የዘረፋችሁት ንብረትም በቤታችሁ ይገኛል።+ +15 ሕዝቤን የምታደቁት፣ የድሆችንም ፊት መሬት ላይ የምትፈጩትእንዴት ብትዳፈሩ ነው?”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +16 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የጽዮን ሴቶች ልጆች ትዕቢተኛ ስለሆኑ፣ራሳቸውን ቀና አድርገው* ስለሚራመዱ፣በዓይናቸው እየተጣቀሱና እየተውረገረጉ በመሄድእግራቸው ላይ ያደረጉትን አልቦ ስለሚያቃጭሉ፣ +17 ይሖዋ የጽዮንን ሴቶች አናት በቁስል ይመታል፤ደግሞም ይሖዋ ግንባራቸውን ይገልጣል።+ +18 በዚያ ቀን ይሖዋ ጌጦቻቸውን ሁሉ ይነጥቃል፦አልቦውን፣ የፀጉር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን ጌጥ፣+ +19 የጆሮ ጉትቻውን፣* አምባሩን፣ መከናነቢያውን፣ +20 የራስ መሸፈኛውን፣ የሰንሰለት አልቦውን፣ ጌጠኛውን መቀነት፣*የሽቶ ዕቃውን፣* ክታቡን፣ +21 የጣት ቀለበቱን፣ የአፍንጫ ቀለበቱን፣ +22 የክት ልብሱን፣ መደረቢያውን፣ ካባውን፣ የእጅ ቦርሳውን፣ +23 የእጅ መስተዋቱን፣+ የበፍታ ልብሶቹን፣*ጥምጥሙንና መከናነቢያውን ይወስድባቸዋል። +24 በበለሳን ዘይት+ መዓዛ ፋንታ የጠነባ ሽታ፣በመታጠቂያ ፋንታ ገመድ፣አምሮ በተሠራ ፀጉር ፋንታ መላጣነት፣+ባማረ ልብስ ፋንታ ማቅ፣+በውበትም ፋንታ ጠባሳ* ይሆናል። +25 ወንዶችሽ በሰይፍ፣ኃያላኖችሽም በውጊያ ይወድቃሉ።+ +26 የከተማዋም መግቢያዎች ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉም፤+እሷም ባዶዋን ቀርታ በሐዘን መሬት ላይ ትቀመጣለች።”+ +52 ጽዮን ሆይ፣+ ተነሺ! ተነሺ! ብርታትን ልበሺ!+ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ የሚያምሩ ልብሶችሽን ልበሺ!+ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዘና ርኩስ የሆነ ወደ አንቺ አይገባምና።+ + 2 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አቧራሽን አራግፊ፤ ተነስተሽ ቦታሽን ያዢ። ምርኮኛ የሆንሽው የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ አንገትሽ ላይ ያለውን ማሰሪያ ፍቺ።+ + 3 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ያለዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤+ያለገንዘብም ትቤዣላችሁ።”+ + 4 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “በመጀመሪያ ሕዝቤ ባዕድ ሆኖ ለመኖር ወደ ግብፅ ወረደ፤+ከዚያም አሦር ያላንዳች ምክንያት በጭቆና ገዛው።” + 5 “ታዲያ እዚህ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” ይላል ይሖዋ። “ሕዝቤ የተወሰደው ያለዋጋ ነውና። የሚገዟቸው በድል አድራጊነት ጉራ ይነዛሉ”+ ይላል ይሖዋ፤“ስሜንም ቀኑን ሙሉ ያለማቋረጥ ያቃልላሉ።+ + 6 በዚህ ምክንያት ሕዝቤ ስሜን ያውቃል፤+በዚህም የተነሳ የተናገርኩት እኔ እንደሆንኩ በዚያ ቀን ያውቃሉ። እነሆ፣ እኔ ነኝ!” + 7 ምሥራች ይዞ የሚመጣ፣+ሰላምን የሚያውጅ፣+የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ምሥራች የሚያበስር፣መዳንን የሚያውጅ፣ጽዮንንም “���ምላክሽ ነግሦአል!”+ የሚል በተራሮች ላይ እግሮቹ እንዴት ያማሩ ናቸው! + 8 ስሚ! ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ ያደርጋሉ። በአንድነት ሆነው እልል ይላሉ፤ይሖዋ ጽዮንን መልሶ ሲሰበስብ በግልጽ* ያያሉና። + 9 እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ ደስ ይበላችሁ፤ በአንድነትም እልል በሉ፤+ይሖዋ ሕዝቡን አጽናንቷልና፤+ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷል።+ +10 ይሖዋ በብሔራት ሁሉ ፊት ቅዱስ ክንዱን ገልጧል፤+የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ የአምላካችንን የማዳን ሥራዎች* ያያሉ።+ +11 እናንተ የይሖዋን ዕቃ የምትሸከሙ፣+ ገለል በሉ፣ ገለል በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤+ ማንኛውንም ርኩስ ነገር አትንኩ!+ከመካከሏ ውጡ፤+ ንጽሕናችሁን ጠብቁ። +12 ተደናግጣችሁ አትወጡም፤ሸሽታችሁም አትሄዱም፤ይሖዋ በፊታችሁ ይሄዳልና፤+የእስራኤል አምላክም ደጀን ይሆናችኋል።+ +13 እነሆ፣ አገልጋዬ+ ማንኛውንም ነገር የሚያከናውነው በጥልቅ ማስተዋል ነው። ላቅ ያለ ቦታ ይሰጠዋል፤ከፍ ከፍ ይላል፤ እጅግም ይከበራል።+ +14 ብዙዎች በመገረም ትኩር ብለው እንዳዩት ሁሉ፣(መልኩ ከማንኛውም ሰው የባሰ፣ግርማ የተላበሰ ቁመናውም ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ተጎሳቁሎ ነበር) +15 እሱም ብዙ ብሔራትን+ ያስደንቃል። ነገሥታት በእሱ ፊት አፋቸውን ይዘጋሉ፤*+ምክንያቱም ያልተነገራቸውን ያያሉ፤ወዳልሰሙትም ነገር ትኩረታቸውን ያዞራሉ።+ +24 እነሆ፣ ይሖዋ ምድሪቱን ወና እና ባድማ ያደርጋታል።+ ይገለብጣታል፤*+ ነዋሪዎቿንም ይበትናቸዋል።+ + 2 በሁሉም ላይ ተመሳሳይ ነገር ይደርሳል፦ በሕዝቡ ላይ የሚሆነው በካህኑ፣በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው በጌታው፣በአገልጋይዋ ላይ የሚሆነው በእመቤቷ፣በገዢው ላይ የሚሆነው በሻጩ፣በአበዳሪው ላይ የሚሆነው በተበዳሪው፣በወለድ ተቀባዩ ላይ የሚሆነው በወለድ ከፋዩ ላይ ይደርሳል።+ + 3 ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ወና ትሆናለች፤ፈጽሞ ትበዘበዛለች፤+ይሖዋ ይህን ቃል ተናግሯልና። + 4 ምድሪቱ ታዝናለች፤*+ ትከስማለች። ፍሬያማዋ ምድር ትራቆታለች፤ ትጠፋለች። የምድሪቱ ታላላቅ ሰዎች ይዝላሉ። + 5 ሕጎቹን ስለተላለፉ፣+ሥርዓቱን ስለለወጡና+ዘላቂውን* ቃል ኪዳን ስላፈረሱ+ምድሪቱ በገዛ ነዋሪዎቿ ተበክላለች።+ + 6 ስለዚህ እርግማኑ ምድሪቱን በላት፤+በላይዋም የሚኖሩ ሰዎች በደለኞች ሆነው ተገኝተዋል። የምድሪቱ ነዋሪዎች ቁጥር የመነመነው በዚህ ምክንያት ነው፤የቀሩት ሰዎችም በጣም ጥቂት ናቸው።+ + 7 አዲሱ የወይን ጠጅ ያለቅሳል፤* የወይን ተክሉም ይጠወልጋል፤+በልባቸውም ሐሴት አድርገው የነበሩ ሁሉ ያዝናሉ።+ + 8 አስደሳች የሆነው የአታሞ ድምፅ መሰማት አቁሟል፤ይፈነጥዙ የነበሩት ሰዎች ድምፅ ጠፍቷል፤ደስ የሚያሰኘው የበገና ድምፅ መሰማቱ ቀርቷል።+ + 9 ዘፈን በሌለበት የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፤መጠጡም ለሚጠጡት ሰዎች መራራ ይሆናል። +10 የተተወችው ከተማ ፈራርሳለች፤+እያንዳንዱ ቤት ማንም እንዳይገባበት ተዘግቷል። +11 በየጎዳናው ላይ የወይን ጠጅ ፍለጋ ይጮኻሉ። ሐሴት ጨርሶ ጠፍቷል፤ምድሪቱም ደስታ ርቋታል።+ +12 ከተማዋ ፈራርሳለች፤በሩም ተሰባብሮ የፍርስራሽ ክምር ሆኗል።+ +13 የወይራ ዛፍ ሲራገፍ+ እንደሚቀር ፍሬ፣ ወይንም ተሰብስቦ ካበቃ በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ፣+ሕዝቤም በምድሪቱና በሌሎች ሕዝቦች መካከል እንዲሁ ይሆናል። +14 ድምፃቸውን ከፍ ያደርጋሉ፤በደስታ እልል ይላሉ። ከባሕሩ* የይሖዋን ግርማ ያውጃሉ።+ +15 ከዚህም የተነሳ በብርሃን ምድር*+ ለይሖዋ ክብር ይሰጣሉ፤በባሕር ደሴቶችም የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ስም ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።+ +16 ከምድር ዳርቻ “ለጻድቁ ክብር* ይሁን!”+ የሚል ዝማሬ እንሰማለን። እኔ ግን እንዲህ አልኩ፦ “አቅም አጣሁ፤ አቅም አጣሁ! ወዮልኝ! ���ሃዲዎች ክህደት ፈጽመዋል፤ከሃዲዎች በማታለል ክህደት ፈጽመዋል።”+ +17 አንተ የምድሪቱ ነዋሪ ሆይ፣ ሽብር፣ ጉድጓድና ወጥመድ ይጠብቅሃል።+ +18 ከሚያሸብረው ድምፅ የሚሸሽ ሁሉ ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፤ከጉድጓዱም የሚወጣ ሁሉ በወጥመዱ ይያዛል።+ የሰማይ የውኃ በሮች ይከፈታሉና፤የምድርም መሠረቶች ይናወጣሉ። +19 ምድሪቱ ተሰነጣጥቃለች፤ምድሪቱ ተንቀጥቅጣለች፤ምድሪቱ በኃይል ትናወጣለች።+ +20 ምድሪቱ እንደሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ነፋስ እንደሚወዘውዘው ጎጆም በነፋስ ወዲያና ወዲህ ትወዛወዛለች። በደሏም በላይዋ ላይ እጅግ ከብዷል፤+ዳግመኛም እንደማትነሳ ሆና ትወድቃለች። +21 በዚያን ቀን ይሖዋ በላይ፣ በከፍታ ቦታ ባለው ሠራዊት ላይ፣እንዲሁም በታች፣ በምድር ባሉት ነገሥታት ላይ ትኩረቱን ያደርጋል። +22 እነሱም እንደ እስረኞች ጉድጓድ ውስጥአንድ ላይ ይታጎራሉ፤በእስር ቤት ውስጥም ይዘጋባቸዋል፤ከብዙ ቀናት በኋላ ጉዳያቸው ይታያል። +23 ሙሉ ጨረቃ ትዋረዳለች፤የምታበራው ፀሐይም ታፍራለች፤+የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በጽዮን ተራራና+ በኢየሩሳሌም ነግሦአልና፤+በሕዝቡ ሽማግሌዎች ፊት* ክብር ተጎናጽፏል።+ +32 እነሆ፣ ንጉሥ+ ለጽድቅ ይነግሣል፤+መኳንንትም ፍትሕ ለማስፈን ይገዛሉ። + 2 እያንዳንዱም ከነፋስ እንደ መከለያ፣*ከውሽንፍር እንደ መሸሸጊያ፣*ውኃ በሌለበት ምድር እንደ ጅረት፣+በደረቅ ምድርም እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል። + 3 በዚያ ጊዜ፣ የሚያዩ ሰዎች ዓይኖች አይጨፈኑም፤የሚሰሙ ሰዎችም ጆሮዎች በትኩረት ያዳምጣሉ። + 4 የችኩሎች ልብ እውቀትን ያሰላስላል፤የሚንተባተብ ምላስም አቀላጥፎና አጥርቶ ይናገራል።+ + 5 የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው ከእንግዲህ ለጋስ አይባልም፤ሥርዓት የሌለው ሰውም ትልቅ ሰው አይባልም፤ + 6 የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው የማይረባ ነገር ይናገራልና፤ደግሞም በይሖዋ ላይ ክህደት ለመፈጸምና* የውሸት ቃል ለመናገር፣እንዲሁም የተራበ ሰው የሚበላ ነገር እንዳያገኝና*የተጠማ ሰው የሚጠጣ ነገር እንዳያገኝ ለማድረግልቡ ክፋትን ያውጠነጥናል።+ + 7 ሥርዓት የሌለው ሰው የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች መጥፎ ናቸው፤+ድሃው ትክክል የሆነውን ነገር በሚናገርበት ጊዜም እንኳየተጎሳቆለውን ሰው በውሸት ቃል ለማጥፋትአሳፋሪ ለሆነ ምግባር ድጋፍ ይሰጣል።+ + 8 ለጋስ ሰው ግን ስለ ልግስና ያስባል፤ዘወትር የልግስና* ተግባር ለመፈጸም ይተጋል። + 9 “እናንተ ደንታ ቢስ ሴቶች፣ ተነሱ፤ ድምፄንም ስሙ! እናንተ ግድየለሽ ሴቶች ልጆች፣+ የምናገረውን ነገር በትኩረት አዳምጡ! +10 እናንተ ግድየለሾች፣ ከአንድ ዓመት ብዙም ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ትሸበራላችሁ፤ምክንያቱም የወይን ፍሬ የምትለቅሙበት ጊዜ ሲያልፍ የተሰበሰበ ፍሬ አይኖርም።+ +11 እናንተ ደንታ ቢስ ሴቶች፣ ተንቀጥቀጡ! እናንተ ግድየለሾች፣ ተሸበሩ! ልብሳችሁን በሙሉ አውልቁ፤በወገባችሁም ላይ ማቅ ታጠቁ።+ +12 ስለ መልካሙ እርሻና ፍሬያማ ስለሆነው ወይንበሐዘን ደረታችሁን ምቱ። +13 የሕዝቤን ምድር እሾህና አሜኬላ ይወርሱታልና፤በደስታ ተሞልተው የነበሩትን ቤቶች ሁሉ፣አዎ፣ በሐሴት ተሞልታ የነበረችውን ከተማ ይሸፍናሉ።+ +14 የማይደፈረው ማማ ባዶ ሆኗልና፤ሁካታ የነበረበት ከተማ ወና ቀርቷል።+ ኦፌልና+ መጠበቂያ ግንቡ ለዘለቄታው ጠፍ ሆነዋል፤የዱር አህዮች መፈንጫናየመንጎች መሰማሪያ ሆነዋል፤+ +15 ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስብን፣+ምድረ በዳውም የፍራፍሬ እርሻ እስከሚሆን፣የፍራፍሬ እርሻውም እንደ ጫካ እስከሚቆጠር ድረስ ነው።+ +16 ከዚያም በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤በፍራፍሬ እርሻም ጽድቅ ይኖራል።+ +17 የእውነተኛ ጽድቅ ውጤት ሰላም፣+የእውነተኛ ጽድቅ ፍሬም ዘላቂ ጸጥታና ደህንነት ይሆናል።+ +18 ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ የመኖሪያ ስፍራ፣አስተማማኝ በሆነ መኖሪያና ጸጥታ በሰፈነበት የማረፊያ ቦታ ይኖራል።+ +19 ሆኖም በረዶው ጫካውን ያወድማል፤ከተማዋም ሙሉ በሙሉ ትፈራርሳለች። +20 እናንተ በውኃዎች ሁሉ ዳር ዘር የምትዘሩ፣በሬውንና አህያውንም የምትለቁ* ደስተኞች ናችሁ።”+ +7 በዖዝያ+ ልጅ፣ በኢዮዓታም ልጅ በይሁዳ ንጉሥ በአካዝ ዘመን፣ የሶርያው ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የሆነው የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ+ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ እሱ ግን ድል ሊያደርጋት አልቻለም።*+ +2 የዳዊት ቤት፣ “ሶርያ ከኤፍሬም ጋር ግንባር ፈጥራለች” የሚል ወሬ ደረሰው። በዚህ ጊዜ የአካዝም ሆነ የሕዝቡ ልብ በነፋስ እንደሚናወጥ የዱር ዛፍ መናወጥ ጀመረ። +3 ከዚያም ይሖዋ ኢሳይያስን እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ አንተና ልጅህ ሸአርያሹብ*+ ከአካዝ ጋር ለመገናኘት ወደ አጣቢው እርሻ በሚወስደው መንገድ አጠገብ ወዳለው ወደ ላይኛው ኩሬ የውኃ መውረጃ ቦይ ጫፍ ውጡ።+ +4 እንዲህም በለው፦ ‘አይዞህ፣ ተረጋጋ። በእነዚህ ከእሳት ተርፈው በሚጤሱ ሁለት የግንድ ጉማጆች ማለትም በሶርያ ንጉሥ በረጺንና በረማልያህ+ ልጅ ኃይለኛ ቁጣ የተነሳ አትፍራ፤ ልብህም አይደንግጥ። +5 ሶርያ ከኤፍሬምና ከረማልያህ ልጅ ጋር እንዲህ ብላ አሲራብሃለች፦ +6 “በይሁዳ ላይ እንዝመትና እንበታትነው፤* በቁጥጥራችንም ሥር እናውለው፤* የታብኤልንም ልጅ እናንግሥበት።”+ +7 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሴራ አይሳካም፤ደግሞም አይፈጸምም። + 8 የሶርያ ራስ ደማስቆ፣የደማስቆ ራስ ደግሞ ረጺን ነውና። ኤፍሬም በ65 ዓመት ውስጥብትንትኑ ወጥቶ ሕዝብ መሆኑ ይቀራል።+ + 9 የኤፍሬም ራስ ሰማርያ+ ነው፤የሰማርያም ራስ የረማልያህ ልጅ ነው።+ ጠንካራ እምነት ከሌላችሁጸንታችሁ መቆም አትችሉም።”’” +10 ከዚያም ይሖዋ አካዝን እንዲህ አለው፦ +11 “አምላክህ ይሖዋ ምልክት እንዲያሳይህ ጠይቅ፤+ ምልክቱም እንደ መቃብር* ጥልቅ የሆነ ወይም እንደ ሰማይ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል።” +12 አካዝ ግን “አልጠይቅም፤ ይሖዋንም አልፈትንም” አለ። +13 ከዚያም ኢሳይያስ እንዲህ አለ፦ “የዳዊት ቤት ሆይ፣ እባካችሁ ስሙ። የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላክንም ትዕግሥት ልትፈታተኑ ትፈልጋላችሁ?+ +14 በመሆኑም ይሖዋ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፦ እነሆ፣ ወጣቷ* ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤+ አማኑኤል* ብላም ትጠራዋለች።+ +15 ክፉውን መጥላትና መልካሙን መምረጥ በሚችልበት ጊዜ ቅቤና ማር ይበላል። +16 ልጁ ክፉውን መጥላትና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት በጣም የምትፈራቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ጨርሶ የተተወ ይሆናል።+ +17 ይሖዋ፣ ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት+ ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፣ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የአሦርን ንጉሥ ያመጣልና።+ +18 “በዚያ ቀን ይሖዋ በግብፅ፣ ርቀው በሚገኙት የአባይ ጅረቶች ያሉትን ዝንቦች፣ በአሦርም ምድር ያሉትን ንቦች በፉጨት ይጠራል፤ +19 ሁሉም መጥተው ጥልቅ በሆኑ ሸለቆዎች፣* በየዓለቱ ንቃቃት፣ በቁጥቋጦዎች ሁሉና ውኃ ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ። +20 “በዚያም ቀን ይሖዋ በወንዙ* አካባቢ ከሚገኘው ቦታ በተከራየው ምላጭ ይኸውም በአሦር ንጉሥ+ አማካኝነት ራሱንና የእግሩን ፀጉር ይላጨዋል፤ ጢሙንም ሙልጭ አድርጎ ያስወግደዋል። +21 “በዚያም ቀን አንድ ሰው ከመንጋው መካከል አንዲት ጊደርና ሁለት በጎች በሕይወት ያተርፋል። +22 በብዛት ከሚገኘው ወተት የተነሳም ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱ መካከል የቀረው ሰው ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል። +"23 “በዚያ ቀን 1,000 የብር ሰቅል የሚያወጣ 1,000 የወይን ተክል ይገኝበት የነበረው ቦታ ሁሉ ቁጥቋጦና አረም ይወርሰዋል።" +24 ምድሪቱ በቁጥቋጦና በአረም ስለምትሸፈን ሰዎች ወደዚያ የሚሄዱት ቀስትና ደጋን ይዘው ነው። +25 በአንድ ወቅት በመቆፈሪያ ተመንጥረውና ከአረም ጸድተው የነበሩ ተራሮች ሁሉ ቁጥቋጦና አረም ስለሚወርሳቸው ወደዚያ መሄድ ትፈራለህ፤ እነዚህ ቦታዎች በሬዎች የሚሰማሩባቸውና በጎች የሚፈነጩባቸው ይሆናሉ።” +48 እናንተ ራሳችሁን በእስራኤል ስም የምትጠሩ፣+ከይሁዳ ምንጭ የፈለቃችሁ፣*በእውነትና በጽድቅ ባይሆንምበይሖዋ ስም የምትምሉና+የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩየያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ይህን ስሙ።+ + 2 እነሱ የቅድስቲቱ ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ ይናገራሉና፤+ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነውንየእስራኤልን አምላክ ድጋፍ ለማግኘት ይጥራሉ።+ + 3 “ከብዙ ዘመን በፊት የቀድሞዎቹን* ነገሮች ነግሬአችኋለሁ። ከአፌም ወጥተዋል፤እንዲታወቁም አድርጌአለሁ።+ በድንገት እርምጃ ወሰድኩ፤ እነሱም ተፈጸሙ።+ + 4 ምን ያህል ልበ ደንዳና እንደሆንክ፣ይኸውም የአንገትህ ጅማት ብረት፣ ግንባርህም መዳብ መሆኑን ስለማውቅ፣+ + 5 ከረጅም ጊዜ በፊት ነግሬሃለሁ። ‘ይህን ያደረገው የራሴ ጣዖት ነው፤ይህን ያዘዘው የተቀረጸው ምስሌና ከብረት የተሠራው ምስሌ* ነው’ እንዳትልገና ከመፈጸሙ በፊት አሳውቄሃለሁ። + 6 አንተም ሰምተሃል፤ ደግሞም ይህን ሁሉ አይተሃል። ይህን አታሳውቅም?*+ ከአሁን ጀምሮ አዳዲስ ነገሮችን፣የማታውቃቸውን ጥብቅ ሚስጥሮች እነግርሃለሁ።+ + 7 እነዚህ ነገሮች የተፈጠሩት ጥንት ሳይሆን ገና አሁን ነው፤‘እነዚህንማ ከዚህ በፊት አውቃቸዋለሁ!’ እንዳትል፣ከዛሬ በፊት ሰምተሃቸው አታውቅም። + 8 አዎ፣ አንተ አልሰማህም፤+ አላወቅክምም፤ከዚህ በፊት ጆሮህ ክፍት አልነበረም። በጣም አታላይ እንደሆንክና+ከተወለድክበት ጊዜ ጀምሮ ዓመፀኛ ተብለህ እንደተጠራህ አውቃለሁና።+ + 9 ይሁንና ስለ ስሜ ስል ቁጣዬን እቆጣጠራለሁ፤+ስለ ውዳሴዬም ስል ራሴን እገታለሁ፤ደግሞም አላጠፋህም።+ +10 እነሆ፣ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ።+ እንደ ማቅለጫ ምድጃ ባለ መከራ ፈትኜሃለሁ።*+ +11 ለራሴ ስል፣ አዎ ለራሴ ስል እርምጃ እወስዳለሁ፤+ስሜ እንዲረክስ እንዴት እፈቅዳለሁ?+ ክብሬን ለማንም አልሰጥም።* +12 ያዕቆብ ሆይ፣ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማኝ። እኔ ምንጊዜም ያው ነኝ።+ የመጀመሪያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻውም እኔ ነኝ።+ +13 የገዛ እጄ የምድርን መሠረት ጣለ፤+ቀኝ እጄም ሰማያትን ዘረጋ።+ እነሱን ስጠራቸው በአንድነት ይቆማሉ። +14 ሁላችሁም አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ስሙ። ከመካከላቸው እነዚህን ነገሮች ያሳወቀ ማን ነው? ይሖዋ ወዶታል።+ እሱ ደስ የሚያሰኘውን በባቢሎን ላይ ይፈጽማል፤+ክንዱም በከለዳውያን ላይ ያርፋል።+ +15 እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እሱንም ጠርቼዋለሁ።+ አምጥቼዋለሁ፤ መንገዱም የተቃና ይሆናል።+ +16 ወደ እኔ ቅረቡ፤ ደግሞም ይህን ስሙ። ከመጀመሪያው አንስቶ በሚስጥር አልተናገርኩም።+ ከተፈጸመበት ጊዜ አንስቶ እኔ በዚያ ነበርኩ።” አሁንም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ መንፈሱም * ልኮኛል። +17 የሚቤዥህ፣ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦+ “የሚጠቅምህን ነገር* የማስተምርህ፣+ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህእኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+ +18 ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው!+ እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣+ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል።+ +19 ዘርህ እንደ አሸዋ፣የአብራክህም ክፋዮች እንደ አሸዋ ቅንጣቶች ብዙ ይሆናሉ።+ ስማቸው ከፊቴ አይጠፋም ወይም አይደመሰስም።” +20 ከባቢሎን ውጡ!+ ከከለዳው��ን ሽሹ! ይህን በእልልታ አስታውቁ! አውጁትም!+ እስከ ምድር ዳርቻ እንዲሰማ አድርጉ።+ እንዲህም በሉ፦ “ይሖዋ አገልጋዩን ያዕቆብን ተቤዥቶታል።+ +21 ባድማ በሆኑ ቦታዎች በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም።+ ከዓለት ውስጥ ውኃ አፈለቀላቸው፤ዓለቱን ሰንጥቆ ውኃ አንዶለዶለላቸው።”+ +22 “ክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል ይሖዋ።+ +61 የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤+ምክንያቱም ይሖዋ የዋህ ለሆኑ ሰዎች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል።+ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ለተማረኩት ነፃነትን እንዳውጅእንዲሁም ‘የእስረኞች ዓይን ይከፈታል’ ብዬ እንድናገር ልኮኛል፤+ + 2 ይሖዋ በጎ ፈቃድ* የሚያሳይበትን ዓመት፣አምላካችን የሚበቀልበትንም ቀን እንዳውጅ፣+የሚያለቅሱትንም ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል፤+ + 3 በጽዮን የተነሳ ላዘኑትበአመድ ፋንታ የራስ መሸፈኛ፣በሐዘን ፋንታ የደስታ ዘይት፣በተደቆሰም መንፈስ ፋንታ የውዳሴ ልብስ እንድሰጥ ልኮኛል። እነሱም ይሖዋ ራሱን ክብር ለማጎናጸፍ*የተከላቸው ትላልቅ የጽድቅ ዛፎች ተብለው ይጠራሉ።+ + 4 የጥንቶቹን ፍርስራሾች መልሰው ይገነባሉ፤በቀድሞዎቹ ጊዜያት ባድማ የሆኑትን ቦታዎች ይሠራሉ፤+የወደሙትን ከተሞች፣ከትውልድ እስከ ትውልድም ፈራርሰው የቆዩትን ቦታዎች መልሰው ይገነባሉ።+ + 5 “እንግዳ ሰዎች መጥተው መንጎቻችሁን ይጠብቃሉ፤የባዕድ አገር ሰዎችም+ ገበሬዎቻችሁና የወይን አትክልት ሠራተኞቻችሁ ይሆናሉ።+ + 6 እናንተም የይሖዋ ካህናት ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤+የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሯችኋል። የብሔራትን ሀብት ትበላላችሁ፤+በእነሱም ክብር* ትኮራላችሁ። + 7 በኀፍረት ፋንታ እጥፍ ድርሻ ይኖራችኋል፤በውርደትም ፋንታ በሚያገኙት ድርሻ በደስታ እልል ይላሉ። አዎ፣ በምድራቸው እጥፍ ድርሻ ይወርሳሉ።+ የዘላለም ሐሴት የእነሱ ይሆናል።+ + 8 እኔ ይሖዋ ፍትሕን እወዳለሁና፤+ዝርፊያንና ክፋትን እጠላለሁ።+ ደሞዛቸውን በታማኝነት እሰጣቸዋለሁ፤ከእነሱም ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።+ + 9 ዘሮቻቸው በብሔራት፣ልጆቻቸውም በሕዝቦች መካከል የታወቁ ይሆናሉ።+ የሚያዩአቸው ሁሉይሖዋ የባረካቸው ዘሮች እንደሆኑ ይገነዘባሉ።”+ +10 እኔ በይሖዋ እጅግ ደስ ይለኛል። ሁለንተናዬ በአምላኬ ሐሴት ያደርጋል።*+ የመዳንን መጎናጸፊያ አልብሶኛልና፤+የካህን ዓይነት ጥምጥም+ እንደሚያደርግ ሙሽራ፣በጌጣጌጧም ራሷን እንዳስዋበች ሙሽሪትየጽድቅ ቀሚስ አልብሶኛል። +11 ምድር ቡቃያዋን እንደምታበቅል፣የአትክልት ቦታም በላዩ ላይ የተዘሩትን ዘሮች እንደሚያበቅልሉዓላዊው ጌታ ይሖዋምበብሔራት ሁሉ ፊት ጽድቅንና+ ውዳሴን ያበቅላል።+ +45 ይሖዋ ለቀባው ለቂሮስ+ እንዲህ ይላል፦ብሔራትን በፊቱ ለማስገዛት፣+ነገሥታትን ትጥቅ ለማስፈታት*እንዲሁም የከተማው በሮች እንዳይዘጉመዝጊያዎቹን በፊቱ ለመክፈት ስልቀኝ እጁን ለያዝኩት+ ለቂሮስ፦ + 2 “እኔ በፊትህ እሄዳለሁ፤+ኮረብቶቹንም ደልዳላ አደርጋለሁ። የመዳብ በሮቹን እሰባብራለሁ፤የብረት መቀርቀሪያዎቹንም እቆርጣለሁ።+ + 3 በስምህ የምጠራህ+እኔ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ መሆኔን እንድታውቅ፣በጨለማ ያለውን ውድ ሀብትናስውር በሆኑ ቦታዎች የተደበቀውን ውድ ሀብት እሰጥሃለሁ።+ + 4 ለአገልጋዬ ለያዕቆብ፣ ለመረጥኩትም ለእስራኤል ስልበስምህ እጠራሃለሁ። አንተ ባታውቀኝም እንኳ የክብር ስም እሰጥሃለሁ። + 5 እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም ሌላ ማንም የለም። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።+ አንተ ባታውቀኝም እንኳ አበረታሃለሁ፤* + 6 ይኸውም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ* ያሉ ሕዝቦችከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው።+እኔ ይሖዋ ���ኝ፤ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።+ + 7 ብርሃንን እሠራለሁ፤+ ጨለማንም እፈጥራለሁ፤+ሰላምን አሰፍናለሁ፤+ ጥፋትንም እፈጥራለሁ፤+እኔ ይሖዋ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አደርጋለሁ። + 8 እናንተ ሰማያት፣ ከላይ አዝንቡ፤+ደመናት ጽድቅን እንደ ዶፍ ያውርዱ። ምድር ትከፈት፤ መዳንንም ታፍራ፤ጽድቅንም በአንድነት ታብቅል።+ እኔ ይሖዋ ፈጥሬዋለሁ።” + 9 ከሠሪው ጋር ሙግት ለሚገጥም* ወዮለት!እሱ መሬት ላይ በተጣሉሌሎች ገሎች መካከል ያለ ተራ ገል ነውና። ሸክላ፣ ሠሪውን* “የምትሠራው ምንድን ነው?” ይለዋል?+ የሠራኸውስ ነገር “እሱ እጅ የለውም” ይላል?* +10 አንድን አባት “ምን ልትወልድ ነው?” ብሎ ለሚጠይቅ፣ ሴትንም “ምን ልትወልጂ ነው?”* ለሚል ወዮለት! +11 የእስራኤል ቅዱስ፣+ ሠሪው የሆነው ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደፊት ስለሚሆኑት ነገሮች ልትጠይቁኝ፣ደግሞስ ልጆቼንና+ የእጆቼን ሥራ በተመለከተ ልታዙኝ ትፈልጋላችሁ? +12 እኔ ምድርን ሠርቻለሁ፤+ በላይዋም ላይ ሰውን ፈጥሬአለሁ።+ በገዛ እጆቼ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፤+ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዛለሁ።”+ +13 “እኔ አንድን ሰው በጽድቅ አስነስቻለሁ፤+መንገዱንም ሁሉ ቀና አደርጋለሁ። እሱ ከተማዬን ይገነባል፤+በግዞት ያለውንም ሕዝቤን ያለዋጋ ወይም ያለጉቦ ነፃ ያወጣል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +14 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የግብፅ ትርፍ፣* የኢትዮጵያ ሸቀጦችና* ቁመተ ረጃጅሞቹ የሳባ ሰዎችወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የአንቺም ይሆናሉ። በሰንሰለት ታስረው ከኋላሽ ይሄዳሉ። መጥተው ይሰግዱልሻል።+ ደግሞም በጸሎት ‘አምላክ በእርግጥ ከአንቺ ጋር ነው፤+ከእሱም በቀር ሌላ የለም፤ ሌላም አምላክ የለም’ ይሉሻል። +15 አዳኝ የሆንከው የእስራኤል አምላክ ሆይ፣+በእርግጥ አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ። +16 ሁሉም ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤ጣዖቶችን የሚሠሩ ሁሉ ውርደት ተከናንበው ይሄዳሉ።+ +17 እስራኤል ግን በይሖዋ ዘላለማዊ መዳን ያገኛል።+ እናንተም ለዘላለም አታፍሩም ወይም አትዋረዱም።+ +18 ሰማያትን የፈጠረው፣+ እውነተኛው አምላክ፣ምድርን የሠራትና ያበጃት፣ አጽንቶም የመሠረታት፣+መኖሪያ እንድትሆን እንጂ ለከንቱ* ያልፈጠራት+ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም። +19 ስውር በሆነ ቦታ፣ ጨለማ በዋጠው ምድር አልተናገርኩም፤+ለያዕቆብ ዘር‘በከንቱ ፈልጉኝ’ አላልኩም። እኔ ይሖዋ ጽድቅ የሆነውን እናገራለሁ፤ ቅን የሆነውንም አወራለሁ።+ +20 ተሰብስባችሁ ኑ። እናንተ ከብሔራት ያመለጣችሁ፣ በአንድነት ቅረቡ።+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ተሸክመው የሚዞሩም ሆኑሊያድናቸው ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ+ ምንም እውቀት የላቸውም። +21 ጉዳያችሁን ተናገሩ፤ እንዲሁም ሙግታችሁን አቅርቡ። ተሰብስበው በአንድነት ይማከሩ። ከረጅም ጊዜ በፊት ይህን አስቀድሞ የተናገረ ማን ነው?ከጥንትስ ጀምሮ ይህን ያወጀ ማን ነው? ይህን ያደረግኩት እኔ ይሖዋ አይደለሁም? ከእኔ ሌላ አምላክ የለም፤ከእኔ በቀር ጻድቅ አምላክና አዳኝ+ የሆነ ማንም የለም።+ +22 የምድር ዳርቻዎች ሁሉ፣ ወደ እኔ ተመለሱ፤ ትድናላችሁ፤+እኔ አምላክ ነኝና፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።+ +23 በራሴ ምያለሁ፤ቃል ከአፌ በጽድቅ ወጥቷል፤ደግሞም አይመለስም፦+ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ምላስም ሁሉ ታማኝ ለመሆን ይምላል፤+ +24 እንዲህም ይላል፦ ‘በእርግጥም በይሖዋ ዘንድ እውነተኛ ጽድቅና ብርታት አለ። በእሱ ላይ የተቆጡ ሁሉ ኀፍረት ተከናንበው ወደ እሱ ይመጣሉ። +25 የእስራኤል ዘር ሁሉ በይሖዋ ትክክለኛ ሆኖ ይገኛል፤+በእሱም ይኮራል።’” +56 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ፍትሕን ጠብቁ፤+ ጽድቅ የሆነውንም አድርጉ፤ማዳኔ ��ቅርቡ ይመጣልና፤ጽድቄም ይገለጣል።+ + 2 ይህን የሚያደርግ ሰው፣ደግሞም ይህን አጥብቆ የሚይዝ፣ሰንበትን የሚጠብቅና የማያረክስ፣+እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት ክፋት እጁን የሚመልስ የሰው ልጅ ደስተኛ ነው። + 3 ከይሖዋ ጋር የሚቆራኝ የባዕድ አገር ሰው+‘ይሖዋ ከሕዝቡ እንደሚለየኝ ጥርጥር የለውም’ አይበል። ጃንደረባም ‘እነሆ፣ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ’ አይበል።” +4 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ሰንበቶቼን ለሚጠብቁ፣ ደስ የሚያሰኘኝን ነገር ለሚመርጡና ቃል ኪዳኔን አጥብቀው ለሚይዙ ጃንደረቦች፣ + 5 በቤቴና በቅጥሮቼ ውስጥከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የሚሻል ነገር፣ ይኸውም የመታሰቢያ ሐውልትና ስም እሰጣቸዋለሁ።ለዘላለም የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ። + 6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣ + 7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+ +8 የተበተኑትን የእስራኤል ሰዎች የሚሰበስበው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦ “አስቀድሞ ከተሰበሰቡት በተጨማሪ ሌሎችን ወደ እሱ እሰበስባለሁ።”+ + 9 እናንተ በሜዳ ያላችሁ አራዊት ሁሉ፣እናንተ በጫካ የምትኖሩ አራዊት ሁሉ፣ ኑና ብሉ።+ +10 ጠባቂዎቹ ዕውሮች ናቸው፤+ አንዳቸውም አላስተዋሉም።+ ሁሉም መናገር የማይችሉ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም።+ ተጋድመው ያለከልካሉ፤ እንቅልፍም ይወዳሉ። +11 በቀላሉ የማይጠግቡ* ውሾች ናቸው፤ጠገብኩ ማለትን አያውቁም። ማስተዋል የሌላቸው እረኞች ናቸው።+ ሁሉም በገዛ ራሳቸው መንገድ ሄደዋል፤እያንዳንዳቸው አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሻሉ፤ እንዲህም ይላሉ፦ +12 “ኑ! የወይን ጠጅ ላምጣናእስኪወጣልን ድረስ እንጠጣ።+ ነገም እንደ ዛሬ ይሆናል፤ እንዲያውም በጣም የተሻለ ይሆናል።” +12 በዚያ ቀን በእርግጥ እንዲህ ትላለህ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ተቆጥተኸኝ የነበረ ቢሆንምቁጣህ ቀስ በቀስ ስለበረደደግሞም ስላጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ።+ + 2 እነሆ፣ አምላክ አዳኜ ነው!+ በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤+ያህ* ይሖዋ ብርታቴና ኃይሌ ነው፤ለእኔም አዳኝ ሆኖልኛል።”+ + 3 ከመዳን ምንጮችበደስታ ውኃ ትቀዳላችሁ።+ + 4 በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “ይሖዋን አመስግኑ! ስሙን ጥሩ፤ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+ ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱን አውጁ።+ + 5 አስደናቂ ነገሮችን+ ስላከናወነ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።+ ይህም በመላው ምድር ይታወጅ። + 6 እናንተ የጽዮን ነዋሪዎች* ሆይ፣ ጩኹ፤ በደስታም እልል በሉ፤የእስራኤል ቅዱስ በመካከላችሁ ታላቅ ነውና።” +1 የይሁዳ ነገሥታት+ በሆኑት በዖዝያ፣+ በኢዮዓታም፣+ በአካዝና+ በሕዝቅያስ+ ዘመን የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ* ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ፦+ + 2 ሰማያት ሆይ፣ ስሙ፤ ምድር ሆይ፣ አድምጪ፤+ይሖዋ እንዲህ ሲል ተናግሯልና፦ “ወንዶች ልጆችን ተንከባክቤ አሳደግኩ፤+እነሱ ግን በእኔ ላይ ዓመፁ።+ + 3 በሬ ጌታውን፣አህያም የባለቤቱን ጋጣ በሚገባ ያውቃል፤እስራኤል ግን እኔን* አላወቀም፤+የገዛ ሕዝቤም አላስተዋለም።” + 4 ኃጢአተኛ የሆነው ብሔር፣+ከባድ በደል የተጫነው ሕዝብ፣የክፉዎች ዘር፣ ብልሹ የሆኑ ልጆች ወዮላቸው! እነሱ ይሖዋን ትተዋል፤+የእስራኤልን ቅዱስ አቃለዋል፤ጀርባቸውን ሰጥተውታል። + 5 በዓመፅ ላይ ዓመፅ የምትጨምሩት፣ አሁን ደግሞ ምናችሁ ላይ መመታት ፈልጋችሁ ነው?+ መላው ራስ ታሟል፤መላው ልብም በበሽታ ተይዟል።+ + 6 ከእግር ጥፍር አንስቶ እስከ ራስ ፀጉር ድረስ አንድም ጤነኛ የአካል ክፍል የለም። በቁስልና በሰምበር ተሞልቷል፤ እንዲሁም ተተልትሏል፤ቁስሉ አልታከመም* ወይም አልታሰረም አሊያም በዘይት አለዘበም።+ + 7 ምድራችሁ ባድማ ሆኗል። ከተሞቻችሁ በእሳት ጋይተዋል። የባዕድ አገር ሰዎች ዓይናችሁ እያየ ምድራችሁን ይውጣሉ።+ ባዕዳን እንዳወደሙት ጠፍ መሬት ሆኗል።+ + 8 የጽዮን ሴት ልጅ በወይን እርሻ ውስጥ እንዳለ መጠለያ፣*በኪያር የእርሻ ቦታ እንዳለ ጎጆ፣እንደተከበበችም ከተማ ተትታለች።+ + 9 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ጥቂት ሰዎች ከጥፋት እንዲተርፉልን ባያደርግ ኖሮእንደ ሰዶም በሆንን፣ገሞራንም በመሰልን ነበር።+ +10 እናንተ የሰዶም+ አምባገነኖች፣* የይሖዋን ቃል ስሙ። እናንተ የገሞራ+ ሰዎች፣ የአምላካችንን ሕግ* አዳምጡ። +11 “የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?”+ ይላል ይሖዋ። “የሚቃጠሉ የአውራ በግ መባዎችና+ የደለቡ እንስሳት ስብ+ በቅቶኛል፤በወይፈኖች፣+ በበግ ጠቦቶችና በፍየሎች+ ደም+ደስ አልሰኝም። +12 በፊቴ ለመቅረብ የምትመጡት፣+ይህን እንድታደርጉ፣የቤተ መቅደሴን ግቢ እንድትረግጡ ማን ጠይቋችሁ ነው?+ +13 ከንቱ የሆኑትን የእህል መባዎች ከዚህ በኋላ አታምጡ። ዕጣናችሁ በፊቴ አስጸያፊ ነው።+ የአዲስ ጨረቃ+ በዓልንና ሰንበትን+ ታከብራላችሁ፤ ስብሰባም+ ትጠራላችሁ። በአንድ በኩል የተቀደሱ ጉባኤዎችን እያከበራችሁ በሌላ በኩል የምትፈጽሙትን አስማታዊ ድርጊት+ መታገሥ አልችልም። +14 የአዲስ ጨረቃ በዓሎቻችሁንና ሌሎች በዓሎቻችሁን ጠልቻለሁ።* ለእኔ ሸክም ሆነውብኛል፤እነሱንም ከመሸከሜ የተነሳ ዝያለሁ። +15 እጆቻችሁን ስትዘረጉዓይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ።+ ጸሎት ብታበዙም እንኳ+አልሰማችሁም፤+እጆቻችሁ በደም ተሞልተዋል።+ +16 ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤+ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አስወግዱ፤መጥፎ ድርጊት መፈጸማችሁን አቁሙ።+ +17 መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን ፈልጉ፤+ጨቋኙ እንዲታረም አድርጉ፤አባት የሌለውን ልጅ* መብት አስከብሩ፤ለመበለቲቱም ተሟገቱ።”+ +18 “ኑና በመካከላችን የተፈጠረውን ችግር ተወያይተን እንፍታ” ይላል ይሖዋ።+ “ኃጢአታችሁ እንደ ደም ቢቀላእንደ በረዶ ይነጣል፤+እንደ ደማቅ ቀይ ጨርቅ ቢቀላምእንደ ነጭ የሱፍ ጨርቅ ይሆናል። +19 እሺ ብትሉና ብትታዘዙየምድሪቱን መልካም ፍሬ ትበላላችሁ።+ +20 እንቢ ብትሉና ብታምፁ ግንሰይፍ ይበላችኋል፤+የይሖዋ አፍ ይህን ተናግሯልና።” +21 ታማኝ የነበረችው ከተማ+ እንዴት ዝሙት አዳሪ ሆነች!+ ፍትሕ የሞላባትና+ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤+አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ጎሬ ሆናለች።+ +22 ብርሽ እንደ ዝቃጭ ሆኗል፤+መጠጥሽ* በውኃ ተበርዟል። +23 አለቆችሽ ግትሮችና የሌባ ግብረ አበሮች ናቸው።+ ሁሉም ጉቦ የሚወዱና እጅ መንሻ የሚያሳድዱ ናቸው።+ አባት የሌለው ልጅ ፍትሕ እንዲያገኝ* አያደርጉም፤የመበለቲቱም አቤቱታ ወደ እነሱ አይደርስም።+ +24 ስለዚህ እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣የእስራኤል ኃያል አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እንግዲያው ስሙ! ባላጋራዎቼን አጠፋለሁ፤ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።+ +25 እጄን በአንቺ ላይ አነሳለሁ፤በመርዝ የማጥራት ያህል ቆሻሻሽን አቅልጬ አወጣለሁ፤ዝቃጭሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።+ +26 መጀመሪያ ላይ እንደነበረው ፈራጆችሽን፣እንደቀድሞውም አማካሪዎችሽን መልሼ አመጣለሁ።+ ከዚያ በኋላ የጽድቅ መዲና፣ የታመነች ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።+ +27 ጽዮን በፍትሕ፣የሚመለሱት ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይቤዣሉ።+ +28 ዓመፀኞችና ኃጢአተኞች በአንድ ላይ ይደቅቃሉ፤+ይሖዋን የሚተዉም ያከትምላቸዋል።+ +29 እናንተ በተመኛችኋቸው ግዙፍ ዛፎች ያፍራሉና፤+በመረጣችኋቸው የአትክልት ቦታዎች* የተነሳም ትዋረዳላችሁ።+ +30 ቅጠሉ እንደጠወለገ ትልቅ ዛፍ፣+ውኃም እንደሌለው የአትክልት ቦታ ትሆናላችሁና። +31 ብርቱውም ሰው እንደ ተልባ እግር* ይሆናል፤የሥራውም ውጤት እንደ እሳት ብልጭታ ይሆናል፤ሁለቱም አብረው ይቃጠላሉ፤እሳቱንም ማጥፋት የሚችል ማንም የለም።” +49 እናንተ ደሴቶች ስሙኝ፤እናንተም በሩቅ ያላችሁ ብሔራት+ በጥሞና አዳምጡ። ይሖዋ ከመወለዴ በፊት* ጠርቶኛል።+ በእናቴ ማህፀን ከነበርኩበት ጊዜ አንስቶ ስሜን ጠርቷል። + 2 አፌን እንደተሳለ ሰይፍ አደረገው፤በእጁ ጥላ ሥር ሰወረኝ።+ የሾለ ፍላጻ አደረገኝ፤በኮሮጆው ውስጥ ሸሸገኝ። + 3 እሱም “እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግርማዬን የምገልጥብህ+አገልጋዬ ነህ”+ አለኝ። + 4 እኔ ግን “የደከምኩት በከንቱ ነው። ጉልበቴንም ያፈሰስኩት ከንቱ ለሆነና ምንም ፋይዳ ለሌለው ነገር ነው። ሆኖም የሚዳኘኝ ይሖዋ ነው፤*ደሞዜንም* የሚከፍለኝ አምላኬ ነው”+ አልኩ። + 5 የእሱ አገልጋይ እንድሆን ከማህፀን ጀምሮ የሠራኝ ይሖዋ፣እስራኤል ወደ እሱ ይሰበሰብ ዘንድያዕቆብን ወደ እሱ እንድመልስ አዞኛል።+ በይሖዋ ፊት እከብራለሁ፤አምላኬም ብርታቴ ይሆናል። + 6 እንዲህም አለ፦ “የያዕቆብን ነገዶች ዳግመኛ ለማቋቋምናጥበቃ ያገኙትን እስራኤላውያን መልሰህ ለማምጣትአገልጋዬ መሆንህ በቂ አይደለም። የማዳን ሥራዬ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ+ለብሔራት ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ።”+ +7 እስራኤልን የሚቤዠው፣ የእስራኤል ቅዱስ የሆነው ይሖዋ፣+ እጅግ ለተናቀውና*+ በሕዝብ ለተጠላው የገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦ “ታማኝ በሆነው በይሖዋ፣+አንተንም በመረጠህ+ በእስራኤል ቅዱስ የተነሳነገሥታት አይተው ይነሳሉ፤መኳንንትም ይሰግዳሉ።” + 8 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሞገስ* በማሳይበት ዘመን መልስ ሰጥቼሃለሁ፤+በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤+ለሰዎች ቃል ኪዳን አድርጌ እሰጥህ ዘንድ ጠብቄሃለሁ፤+ይህም ምድሪቱን ዳግመኛ እንድታቋቁም፣የወደመውን ርስታቸውን መልሰህ እንድታወርሳቸው፣+ + 9 እስረኞቹን ‘ኑ ውጡ!’+ በጨለማ ያሉትንም+ ‘ራሳችሁን ግለጡ!’ እንድትል ነው። በየመንገዱ ዳር ይመገባሉ፤በተበላሹ መንገዶችም* ሁሉ አጠገብ መሰማሪያ ያገኛሉ። +10 አይራቡም፤ አይጠሙም፤+ሐሩርም ሆነ ፀሐይ አያቃጥላቸውም።+ ምሕረት የሚያደርግላቸው ይመራቸዋልና፤+የውኃ ምንጮች ወዳሉበትም ይወስዳቸዋል።+ +11 ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤አውራ ጎዳናዎቼም ከፍ ያሉ ይሆናሉ።+ +12 እነሆ፣ እነዚህ ከሩቅ ይመጣሉ፤+እነሆም፣ እነዚህ ከሰሜንና ከምዕራብ፣እነዚህ ደግሞ ከሲኒም ምድር ይመጣሉ።”+ +13 እናንተ ሰማያት፣ እልል በሉ፤ አንቺም ምድር፣ ሐሴት አድርጊ።+ ተራሮች በደስታ እልል ይበሉ።+ ይሖዋ ሕዝቡን አጽናንቷልና፤+ለተጎሳቆሉት ሕዝቦቹም ምሕረት ያሳያል።+ +14 ጽዮን ግን “ይሖዋ ትቶኛል፤+ ይሖዋም ረስቶኛል”+ ትላለች። +15 እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለች?ከማህፀኗ ለወጣውስ ልጅ አትራራም? እነዚህ ሴቶች ቢረሱ እንኳ እኔ ፈጽሞ አልረሳሽም።+ +16 እነሆ፣ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ። ግንቦችሽ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው። +17 ወንዶች ልጆችሽ ፈጥነው ይመለሳሉ። ያፈራረሱሽና ያወደሙሽ አንቺን ለቀው ይሄዳሉ። +18 ዓይንሽን አንስተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ። ሁሉም በአንድነት እየተሰበሰቡ ነው።+ ወደ አንቺም እየመጡ ነው። “በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፣“አንቺም ሁሉንም እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፤እንደ ሙሽራም ትጎ���ጸፊያቸዋለሽ። +19 ስፍራዎችሽ ባድማና ወና፣ ምድርሽም የወደመ ቢሆንም+አሁን በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ቦታው በጣም ይጠባቸዋል፤+የዋጡሽም+ ከአንቺ ይርቃሉ።+ +20 የወላድ መሃን ከሆንሽ በኋላ የተወለዱት ወንዶች ልጆች፣ጆሮሽ እየሰማ ‘ይህ ቦታ በጣም ጠቦናል። የምንኖርበት በቂ ስፍራ ስጪን’ ይላሉ።+ +21 አንቺም በልብሽ እንዲህ ትያለሽ፦‘እኔ ልጆቼን በሞት ያጣሁና መሃንእንዲሁም በምርኮ የተወሰድኩና እስረኛ የሆንኩ ሴት ሆኜ ሳለእነዚህን ልጆች የወለደልኝ ማን ነው? ያሳደጋቸውስ ማን ነው?+ እነሆ፣ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤+ታዲያ እነዚህ ከየት መጡ?’”+ +22 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እጄን ለብሔራት አነሳለሁ፤ምልክቴንም * ለሕዝቦች ከፍ አደርጋለሁ።+ ወንዶች ልጆችሽን በክንዳቸው* ይዘው ያመጧቸዋል፤ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ይሸከሟቸዋል።+ +23 ነገሥታት ይንከባከቡሻል፤+ልዕልቶቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ። በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዱልሻል፤+የእግርሽንም አቧራ ይልሳሉ፤+አንቺም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤እኔን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም።”+ +24 በምርኮ የተያዙ ሰዎች ከኃያል ሰው እጅ ሊወሰዱ ይችላሉ?ወይስ በጨቋኝ እጅ የወደቁ ምርኮኞችን የሚታደጋቸው ይኖራል? +25 ይሖዋ ግን እንዲህ ይላል፦ “በኃያል ሰው የተማረኩ ሰዎችም እንኳ ከእጁ ላይ ይወሰዳሉ፤+በጨቋኝ እጅ የወደቁ ሰዎችንም የሚታደጋቸው ይኖራል።+ አንቺን የሚቃወሙትን እቃወማለሁ፤+ወንዶች ልጆችሽንም አድናቸዋለሁ። +26 በደል የሚፈጽሙብሽን የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤ልክ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ። ሰውም* ሁሉ እኔ ይሖዋአዳኝሽና+ የምቤዥሽ፣+የያዕቆብም ኃያል አምላክ እንደሆንኩ ያውቃል።”+ +36 ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ+ ሰናክሬም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ዘምቶ ያዛቸው።+ +2 ከዚያም የአሦር ንጉሥ፣ ራብሻቁን*+ ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ፣+ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ላከው። እነሱም ወደ ልብስ አጣቢው እርሻ+ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ በሚገኘው በላይኛው ኩሬ የውኃ መውረጃ ቦይ አጠገብ ቆሙ።+ +3 ከዚያም የቤቱ* ኃላፊ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣+ ጸሐፊው ሸብና+ እንዲሁም ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአህ ወደ እሱ መጡ። +4 ራብሻቁም እንዲህ አላቸው፦ “እስቲ ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፦ ‘ታላቁ ንጉሥ፣ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “ለመሆኑ እንዲህ እንድትተማመን ያደረገህ ምንድን ነው?+ +5 ‘የጦር ስልትና ለመዋጋት የሚያስችል ኃይል አለኝ’ ትላለህ፤ ይሁንና ይህ ከንቱ ወሬ ነው። ለመሆኑ በእኔ ላይ ለማመፅ የደፈርከው በማን ተማምነህ ነው?+ +6 እነሆ፣ ሰው ቢመረኮዘው እጁ ላይ ሊሰነቀርና ሊወጋው ከሚችለው ከዚህ ከተቀጠቀጠ ሸምበቆ፣ ከግብፅ ድጋፍ አገኛለሁ ብለህ ተማምነሃል። የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው።+ +7 ‘እኛ የምንታመነው በአምላካችን በይሖዋ ነው’ የምትለኝ ከሆነ ደግሞ፣ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ‘መስገድ ያለባችሁ በዚህ መሠዊያ ፊት ነው’+ ብሎ የእሱን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችና መሠዊያዎች አስወግዶ የለም?”’+ +"8 በል እስቲ፣ አሁን ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ+ ጋር ተወራረድ፦ ጋላቢዎች ማግኘት የምትችል ከሆነ 2,000 ፈረሶች እሰጥሃለሁ።" +9 አንተ የምትታመነው በግብፅ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ነው፤ ታዲያ ከጌታዬ አገልጋዮች መካከል ዝቅተኛ ደረጃ ያለውን አንዱን አለቃ እንኳ እንዴት መመከት ትችላለህ? +10 ለመሆኑ ይህን ምድር ለማጥፋት የመጣሁት ይሖዋ ሳይፈቅድልኝ ይመስልሃል? ይሖዋ ራሱ ‘በዚህ ምድር ላይ ዘ���ተህ አጥፋው’ ብሎኛል።” +11 በዚህ ጊዜ ኤልያቄም፣ ሸብና+ እና ዮአህ ራብሻቁን+ እንዲህ አሉት፦ “እባክህ፣ እኛ አገልጋዮችህ ቋንቋውን ስለምናውቅ በአረማይክ* ቋንቋ+ አናግረን፤ በቅጥሩ ላይ ያለው ሕዝብ በሚሰማው በአይሁዳውያን ቋንቋ አታነጋግረን።”+ +12 ራብሻቁ ግን እንዲህ አለ፦ “ጌታዬ ይህን ቃል እንድናገር የላከኝ ለጌታህና ለአንተ ብቻ ነው? ከእናንተ ጋር የገዛ ራሳቸውን እዳሪ ለሚበሉትና የገዛ ራሳቸውን ሽንት ለሚጠጡት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎች ጭምር አይደለም?” +13 ከዚያም ራብሻቁ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ በአይሁዳውያን ቋንቋ+ እንዲህ አለ፦ “የታላቁን ንጉሥ፣ የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ።+ +14 ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ ‘ሕዝቅያስ አያታላችሁ፤ እሱ ሊታደጋችሁ አይችልምና።+ +15 ደግሞም ሕዝቅያስ “ይሖዋ በእርግጥ ይታደገናል፤ ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትወድቅም” እያለ በይሖዋ እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።+ +16 ሕዝቅያስን አትስሙት፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፦ “ከእኔ ጋር ሰላም ፍጠሩ፤ እጃችሁንም ስጡ፤* እያንዳንዳችሁም ከራሳችሁ ወይንና ከራሳችሁ በለስ ትበላላችሁ፤ ከራሳችሁም የውኃ ጉድጓድ ትጠጣላችሁ፤ +17 ይህም የሚሆነው መጥቼ የእናንተን ምድር ወደምትመስለው፣ እህልና አዲስ የወይን ጠጅ፣ ዳቦና የወይን እርሻ ወደሚገኝባት ምድር እስክወስዳችሁ ድረስ ነው።+ +18 ሕዝቅያስ ‘ይሖዋ ይታደገናል’ በማለት አያታላችሁ። ከብሔራት አማልክት መካከል ምድሩን ከአሦር ንጉሥ እጅ ያስጣለ አለ?+ +19 የሃማትና የአርጳድ+ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዊም+ አማልክትስ የት አሉ? ሰማርያን ከእጄ ማስጣል ችለዋል?+ +20 ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ ምድሩን ከእጄ ማስጣል የቻለ የትኛው ነው? ታዲያ ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ከእጄ ሊያስጥላት ይችላል?”’”+ +21 እነሱ ግን ንጉሡ “ምንም መልስ አትስጡት” ብሎ አዝዞ ስለነበር ዝም አሉ፤ አንድም ቃል አልመለሱለትም።+ +22 ይሁንና የቤቱ* አስተዳዳሪ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሐፊው ሸብና+ እንዲሁም ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአህ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ ራብሻቁ ያለውንም ነገሩት። +29 “ለአርዔል፣* ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ+ ለአርዔል ወዮላት! በዓመት ላይ ዓመት ጨምሩ፤ዓመታዊ በዓሎቻችሁን+ ማክበራችሁን ቀጥሉ። + 2 እኔ ግን በአርዔል ላይ የሚያስጨንቅ ነገር አመጣለሁ፤+ለቅሶና ዋይታም ይሆናል፤+እሷም ለእኔ፣ እንደ አምላክ የመሠዊያ ምድጃ ትሆናለች።+ + 3 አንቺን ለማጥቃት በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤በሹል እንጨት አጥርሻለሁ፤በአንቺም ዙሪያ ቅጥር እገነባለሁ።+ + 4 ትወድቂያለሽ፤ ትዋረጃለሽም፤መሬት ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፤የምትናገሪው ነገር በአፈር ይታፈናል። ድምፅሽ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅከመሬት ይመጣል፤+ቃልሽም ከአፈር ይጮኻል። + 5 የጠላቶችሽ* ሠራዊት እንደላመ ዱቄት ይሆናል፤+የጨቋኞች መንጋ ተጠርጎ እንደሚሄድ ገለባ ይሆናል።+ ይህም ሳይታሰብ፣ በቅጽበት ይፈጸማል።+ + 6 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ትኩረቱን ወደ አንቺ በማዞርበነጎድጓድ፣ በምድር መናወጥ፣ በታላቅ ድምፅ፣በውሽንፍር፣ በአውሎ ነፋስና በሚባላ የእሳት ነበልባል ያድንሻል።”+ + 7 በዚያን ጊዜ አርዔልን የሚወጉ የብሔራት ሠራዊት ሁሉ፣+ይኸውም ጦርነት የሚከፍቱባት ሁሉ፣በእሷ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ማማዎችን የሚሠሩናጭንቀት ላይ የሚጥሏት ሁሉእንደ ሕልም፣ በሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናሉ። + 8 አዎ፣ የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ቆይቶሲነቃ ግን ረሃቡ እንደማይለቀው* ሁሉ፣ደግሞም የተጠማ ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ቆይቶሲነቃ ግን ዝሎና ተጠምቶ እንደሚነሳ* ሁሉ እንዲሁ ይሆናል። በጽዮን ተራራ ላይ ጦርነት የሚከፍቱ የብሔራት ሠራዊትም ሁሉተመሳሳይ ነገር ይደርስባቸዋል።+ + 9 ክው በሉ፤ ተደነቁም፤+ዓይናችሁን ጨፍኑ፤ ዕውሮችም ሁኑ።+ በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ሰክረዋል፤በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገዳግደዋል። +10 ይሖዋ ኃይለኛ የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋልና፤+ዓይኖቻችሁን ይኸውም ነቢያትን ጨፍኖባችኋል፤+ራሶቻችሁን ይኸውም ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል።+ +11 የሁሉ ነገር ራእይ እንደታሸገ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል።+ መጽሐፉን ማንበብ ለሚችል ሰው “እባክህ፣ ጮክ ብለህ አንብበው” ብለው ሲሰጡት “ታሽጓልና አልችልም” ይላል። +12 መጽሐፉንም ማንበብ ለማይችል ሰው “እባክህ፣ ይህን አንብበው” ብለው ሲሰጡት “ፈጽሞ ማንበብ አልችልም” ይላል። +13 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ ወደ እኔ የሚቀርበው በአፉ ብቻ ነው፤በከንፈሩም ያከብረኛል፤+ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው፤እኔንም የሚፈራው፣ ሰዎች ያስተማሩትን ትእዛዛት በማክበር ነው።+ +14 ስለዚህ እኔ በእነዚህ ሰዎች ላይ ዳግመኛ የሚያስደንቁ ነገሮች አደርጋለሁ፤+በድንቅ ላይ ድንቅ ነገር እፈጽማለሁ፤የጥበበኞቻቸውም ጥበብ ይጠፋል፤የአስተዋዮቻቸውም ማስተዋል ይሰወራል።”+ +15 ዕቅዳቸውን ከይሖዋ ለመሰወር* ከፍተኛ ጥረት ለሚያደርጉ ወዮላቸው!+ “ማን ያየናል?ማንስ ያውቅብናል?” በማለት ተግባራቸውን በጨለማ ቦታ ያከናውናሉ።+ +16 እናንተ ሰዎች፣ ነገር ታጣምማላችሁ!* ሸክላ ሠሪው እንደ ሸክላው ሊቆጠር ይገባል?+ የተሠራው ነገር ስለ ሠሪው “እሱ አልሠራኝም” ማለቱ ተገቢ ነው?+ ደግሞስ ዕቃው ሠሪውን “ማስተዋል የለውም” ይላል?+ +17 በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊባኖስ ወደ ፍራፍሬ እርሻነት ይለወጣል፤+የፍራፍሬ እርሻውም እንደ ጫካ ይቆጠራል።+ +18 በዚያ ቀን፣ መስማት የተሳናቸው ሰዎች የመጽሐፉን ቃል ይሰማሉ፤የዓይነ ስውራኑም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ።+ +19 የዋሆች በይሖዋ እጅግ ሐሴት ያደርጋሉ፤በሰዎች መካከል ያሉ ድሆችም በእስራኤል ቅዱስ ደስ ይላቸዋል።+ +20 ጨቋኙ ያከትምለታልና፤ጉረኛውም ያበቃለታል፤ሌሎችን ለመጉዳት አሰፍስፈው የሚጠባበቁ ሁሉ ይጠፋሉ፤+ +21 ሌሎችን በውሸት ቃል በደለኛ የሚያደርጉ፣በከተማዋ በር፣+ በተሟጋቹ* ላይ ወጥመድ የሚዘረጉናመሠረተ ቢስ በሆነ ክስ ጻድቁን ሰው ፍትሕ የሚነፍጉ ይጠፋሉ።+ +22 ስለዚህ አብርሃምን+ የተቤዠው ይሖዋ ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፦ “ያዕቆብ ከእንግዲህ አያፍርም፤ፊቱም ከእንግዲህ አይገረጣም።*+ +23 የእጆቼ ሥራ የሆኑትን ልጆቹንበመካከሉ በሚያይበት ጊዜ፣+ስሜን ይቀድሳሉና፤አዎ፣ የያዕቆብን ቅዱስ ይቀድሳሉ፤የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።*+ +24 በመንፈስ የባዘኑ ማስተዋል ያገኛሉ፤የሚያጉረመርሙም የሚሰጣቸውን ትምህርት ይቀበላሉ።” +28 ጎልታ ለምትታየው* ለኤፍሬም+ ሰካራሞች አክሊል* ወዮላት!ይህች የምታምር ጌጥ በወይን ጠጅ የተሸነፉ ሰዎች በሚኖሩበትለም ሸለቆ አናት ላይ የምትገኝ የምትጠወልግ አበባ ናት። + 2 እነሆ፣ ይሖዋ ጠንካራና ብርቱ የሆነውን ይልካል። እሱም እንደ ነጎድጓዳማ የበረዶ ውሽንፍር፣ እንደ አጥፊ አውሎ ነፋስ፣ኃይለኛ ጎርፍ እንደሚያስከትል ነጎድጓዳማ ውሽንፍርበኃይል አሽቀንጥሮ ወደ ምድር ይጥላታል። + 3 ጎልተው የሚታዩት* የኤፍሬም ሰካራሞች ያደረጓቸው አክሊሎችበእግር ይረገጣሉ።+ + 4 ለም በሆነው ሸለቆ አናት ላይ የምትገኘውናየምታምር ጌጥ የሆነችው የምትጠወልግ አበባከበጋ በፊት፣ በመጀመሪያው ወቅት እንደምትበስል በለስ ትሆናለች። ሰውም ባያት ጊዜ ቀጥፎ ወዲያውኑ ይውጣታል። +5 በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከሕዝቡ መካከል ለተረፉት ሰዎች የሚያምር አክሊልና ውብ የአበባ ጉንጉን ይሆናል።+ +6 በፍርድ ወንበር ለተቀመጠውም የፍትሕ መንፈስ፣ የከተማዋ በር ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ለሚመክቱም የብርታት ምንጭ ይሆናል።+ + 7 እነዚህም ከወይን ጠጅ የተነሳ መንገድ ይስታሉ፤ከሚያሰክር መጠጥ የተነሳም ይንገዳገዳሉ። ካህኑና ነቢዩ ከጠጡት መጠጥ የተነሳ መንገድ ይስታሉ፤ከወይን ጠጅ የተነሳ ግራ ይጋባሉ፤ከሚያሰክር መጠጥ የተነሳም ይንገዳገዳሉ፤የሚያዩት ራእይ መንገድ ያስታቸዋል፤ፍርድ ሲሰጡም ይሳሳታሉ።+ + 8 ገበታቸው ሁሉ በሚያስጸይፍ ትውከት ተሞልቷል፤ያልተበላሸ ቦታም የለም። + 9 እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ “እውቀትን የሚያካፍለው ለማን ነው?መልእክቱንስ የሚያስረዳው ለማን ነው? ገና ወተት ለተዉ፣ጡትም ለጣሉ ሕፃናት ነው? +10 ‘በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣ በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣*+እዚህ ጥቂት፣ እዚያ ጥቂት’ ነውና።” +11 ስለዚህ በሚንተባተቡ ሰዎች አንደበትና በባዕድ ቋንቋ ለዚህ ሕዝብ ይናገራል።+ +12 በአንድ ወቅት “ይህ የእረፍት ቦታ ነው። የዛለው እንዲያርፍ አድርጉ፤ ይህ የእፎይታ ቦታ ነው” ብሏቸው ነበር፤ እነሱ ግን ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም።+ +13 የይሖዋም ቃል ለእነሱ “በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣ በሥርዓት ላይ ሥርዓት፣*+እዚህ ጥቂት፣ እዚያ ጥቂት” ይሆንባቸዋል፤ በመሆኑም ሲሄዱ፣ተሰናክለው ወደ ኋላ ይወድቃሉ፤ደግሞም ይሰበራሉ፣ ይጠመዳሉ እንዲሁም ይያዛሉ።+ +14 ስለዚህ እናንተ ጉረኞች፣በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ገዢዎች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ +15 እናንተ እንዲህ ብላችኋልና፦ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል፤+ከመቃብርም * ጋር ስምምነት አድርገናል።* በድንገት የሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ሲያልፍእኛን አይነካንም፤ውሸትን መጠጊያችን አድርገናልና፤በሐሰትም ውስጥ ተደብቀናል።”+ +16 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በጽዮን የመሠረት ድንጋይ ይኸውም የተፈተነ ድንጋይ፣+አስተማማኝ መሠረት+ ሆኖ የተጣለ ክቡር የማዕዘን ድንጋይ+ አኖራለሁ። በእሱ የሚያምን አይደናገጥም።+ +17 እኔም ፍትሕን የመለኪያ ገመድ፣+ጽድቅንም ውኃ ልክ* አደርጋለሁ።+ የውሸት መጠጊያውን፣ በረዶ ጠራርጎ ይወስደዋል፤ውኃዎቹም መደበቂያ ቦታውን ያጥለቀልቁታል። +18 ከሞት ጋር የገባችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፤ከመቃብርም * ጋር ያደረጋችሁት ስምምነት አይጸናም።+ በድንገት የሚያጥለቀልቀው ጎርፍ ሲያልፍድምጥማጣችሁን ያጠፋል። +19 ጎርፉ ባለፈ ቁጥርጠራርጎ ይወስዳችኋል፤+በየማለዳው እንዲሁምበቀንና በሌሊት ያልፋልና። የተነገረውን ነገር እንዲረዱ የሚያደርገው ሽብር ብቻ ነው።”* +20 እግር ተዘርግቶ እንዳይተኛ አልጋው አጭር ነውና፤ተሸፋፍኖም እንዳይተኛ ጨርቁ በጣም ጠባብ ነው። +21 ይሖዋ ተግባሩን ይኸውም እንግዳ የሆነ ተግባሩን ያከናውን ዘንድእንዲሁም ሥራውን ይኸውም ያልተለመደ ሥራውን ይሠራ ዘንድ+በጰራጺም ተራራ እንዳደረገው ይነሳልና፤በገባኦን አቅራቢያ ባለው ሸለቆ* እንዳደረገውም ራሱን ያነሳሳል።+ +22 እንግዲህ ፌዘኞች አትሁኑ፤+አለዚያ እስራቱ ይበልጥ ይጠብቅባችኋል፤ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋአገሪቱን በሙሉ* ለማጥፋት ያስተላለፈውን ፍርድ ሰምቻለሁና።+ +23 ጆሯችሁን አዘንብሉ፤ ድምፄንም ስሙ፤ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጡ፤ በጥሞናም አዳምጡ። +24 ገበሬ ዘር ከመዝራቱ በፊት ቀኑን ሙሉ ሲያርስ ይውላል? ደግሞስ ጓሉን ሲከሰክስና መሬቱን ሲያለሰልስ ይከርማል?+ +25 ከዚህ ይልቅ መሬቱን ከደለደለ በኋላጥቁር አዝሙድና ከሙን አይዘራም?ስንዴውን፣ ማሽላውንና ገብሱንስ በቦታ በቦታቸው አይዘራም?ደግሞስ አጃውን+ ዳር ላይ አይዘራም? +26 አምላክ ሰውን በትክክለኛው መንገድ ያስተምረዋል፤*ደግሞም ይመራዋል።+ +27 ጥቁር አዝሙድ በማሄጃ*+ አይወቃም፤በከሙንም ላይ የመውቂያ መንኮራኩር* እንዲሄድ አይደረግም። ጥቁር አዝሙድ በበትር፣ከሙንም በዘንግ ይወቃል። +28 ሰው የዳቦ እህል እንዲደቅ ያደርጋል? በጭራሽ፤ እስኪደቅ ድረስ አይወቃውም፤+በፈረሶቹ የሚጎተተውን የመውቂያ መንኮራኩር በሚያስኬድበት ጊዜ፣እህሉን አያደቀውም።+ +29 ይህም የተገኘው፣ አስደናቂ ምክር* ካለውናታላላቅ ሥራዎችን ካከናወነው*ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ነው።+ +38 በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ሞት አፋፍ ደርሶ ነበር።+ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ+ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህ ስለማይቀር ለቤተሰብህ መመሪያ ስጥ።’”+ +2 በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ ፊቱን ወደ ግድግዳው አዙሮ ወደ ይሖዋ መጸለይ ጀመረ፦ +3 “እባክህ ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትና በሙሉ ልብ+ በፊትህ እንዴት እንደተመላለስኩ እንዲሁም በዓይኖችህ ፊት መልካም የሆነውን ነገር እንዳደረግኩ እንድታስታውስ አጥብቄ እለምንሃለሁ።”+ ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ። +4 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኢሳይያስ መጣ፦ +5 “ተመልሰህ ሄደህ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦+ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ።+ እንባህንም አይቻለሁ።+ እነሆ በዕድሜህ* ላይ 15 ዓመት እጨምርልሃለሁ፤+ +6 አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ከተማዋንም እጠብቃታለሁ።+ +7 ይሖዋ የተናገረውን ቃል እንደሚፈጽም የሚያሳየው ይሖዋ የሰጠህ ምልክት ይህ ነው፦+ +8 በአካዝ ደረጃ* ላይ ወደ ታች የወረደውን የፀሐይ ጥላ ወደ ኋላ አሥር ደረጃ እንዲመለስ አደርገዋለሁ።”’”+ በመሆኑም ወደ ታች ወርዶ የነበረው የፀሐይ ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ። +9 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ከሕመሙ ከዳነ በኋላ የጻፈው* ጽሑፍ፦ +10 እኔ “በዕድሜዬ አጋማሽ ላይወደ መቃብር* በሮች እገባለሁ። ቀሪውን የሕይወት ዘመኔን እነፈጋለሁ” አልኩ። +11 እንዲህም አልኩ፦ “በሕያዋን ምድር ያህን፣* አዎ ያህን አላይም። ሁሉም ነገር ከሕልውና ውጭ በሆነበት ስፍራ ከሚኖሩት ጋር በምሆንበት ጊዜየሰው ልጆችን አልመለከትም።+ +12 መኖሪያዬ ልክ እንደ እረኛ ድንኳንተነቅሎ ተወስዶብኛል።+ ሕይወቴን እንደ ሸማኔ ጠቀለልኩ፤ተሠርቶ ያለቀ ጨርቅ ከሽመና መሣሪያው ላይ እንደሚቆረጥ እኔንም ይቆርጠኛል። ከማለዳ አንስቶ እስከ ምሽት ድረስ ትጨርሰኛለህ።+ +13 እስከ ጠዋት ድረስ ራሴን አረጋጋለሁ። አጥንቶቼን ሁሉ እንደ አንበሳ ይሰባብራል፤ከማለዳ አንስቶ እስከ ምሽት ድረስ ትጨርሰኛለህ።+ +14 እንደ ወንጭፊት ወይም እንደ ጭሪ* እጮኻለሁ፤+እንደ ርግብ አልጎመጉማለሁ።+ ወደ ላይ ከመመልከቴ የተነሳ ዓይኖቼ ፈዘዙ፦+ ‘ይሖዋ ሆይ፣ እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ድጋፍ ሁነኝ!’*+ +15 እንግዲህ ምን ማለት እችላለሁ? እሱ አናግሮኛል፤ ምላሽም ሰጥቷል። ከደረሰብኝ አስከፊ ጭንቀት* የተነሳበሕይወት ዘመኔ ሁሉ በትሕትና* እመላለሳለሁ። +16 ‘ይሖዋ ሆይ፣ ሁሉም ሰው በእነዚህ ነገሮች* በሕይወት ይኖራል፤በእነሱም የእኔ መንፈስ በሕይወት ይኖራል። አንተ ጤናዬን ትመልስልኛለህ፤ በሕይወትም ታኖረኛለህ።+ +17 እነሆ፣ ሰላም ከማግኘት ይልቅ በጣም ተመርሬ ነበር፤አንተ ግን ለእኔ* ካለህ ፍቅር የተነሳ፣ከጥፋት ጉድጓድ ጠበቅከኝ።+ ኃጢአቴን ሁሉ ወደ ኋላህ ጣልክ።*+ +18 መቃብር* ከፍ ከፍ ሊያደርግህ አይችልምና፤+ሞትም ሊያወድስህ አይችልም።+ ወደ ጉድጓድ የሚወርዱ በታማኝነትህ ተስፋ ሊያደርጉ አይችሉም።+ +19 እኔ ዛሬ እንደማደር���ው፣አንተን ሊያወድስ የሚችለው ሕያው፣ አዎ ሕያው የሆነ ሰው ነው። አባት ለልጆቹ ስለ አንተ ታማኝነት እውቀት ሊያካፍላቸው ይችላል።+ +20 ይሖዋ ሆይ፣ አድነኝ፤በሕይወታችን ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት፣+በባለ አውታር መሣሪያዎች መዝሙሮቼን እንዘምራለን።’”+ +21 ከዚያም ኢሳይያስ “ሕመሙ እንዲሻለው የደረቀ የበለስ ጥፍጥፍ አምጡና እባጩ ላይ አድርጉለት” አለ።+ +22 ሕዝቅያስ “ወደ ይሖዋ ቤት እንደምወጣ ማወቅ የምችልበት ምልክት ምንድን ነው?” ብሎ ነበር።+ +8 ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “አንድ ትልቅ ጽላት+ ወስደህ በብዕር* ‘ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ’* ብለህ ጻፍ። +2 ታማኝ ምሥክሮች የሆኑት ካህኑ ኦርዮና+ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደግሞ የጽሑፍ ማረጋገጫ ይስጡኝ።”* +3 እኔም ከነቢዪቱ* ጋር ተገናኘሁ፤* እሷም ፀነሰች፤ በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች።+ ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው፤ +4 ልጁ ‘አባዬ!’ እና ‘እማዬ!’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወሰዳል።”+ +5 ይሖዋ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፦ + 6 “ይህ ሕዝብ ቀስ ብለው የሚወርዱትን የሺሎአ* ውኃዎች ንቆ+በረጺንና በረማልያህ+ ልጅ ሐሴት ስላደረገ + 7 እነሆ፣ ይሖዋ ብርቱ የሆኑትንና ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የወንዙን* ውኃዎች ይኸውምየአሦርን ንጉሥና+ ክብሩን ሁሉበእነሱ ላይ ያመጣባቸዋል። እሱም የውኃ መውረጃዎቹን ሁሉ ሞልቶ ይፈስሳል፤ዳርቻዎቹንም ሁሉ ያጥለቀልቃል፤ + 8 ይሁዳንም ጠራርጎ ይሄዳል። አካባቢውን እያጥለቀለቀ በማለፍ እስከ አንገት ይደርሳል፤+አማኑኤል*+ ሆይ፣ የተዘረጉት ክንፎቹምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ!” + 9 እናንተ ሕዝቦች፣ ጉዳት አድርሱባቸው፤ ሆኖም ድምጥማጣችሁ ይጠፋል። ራቅ ባሉ የምድር ክፍሎች የምትኖሩ ሁሉ አዳምጡ! ለውጊያ ተዘጋጁ፤* ነገር ግን ድምጥማጣችሁ ይጠፋል!+ ለውጊያ ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ድምጥማጣችሁ ይጠፋል! +10 ዕቅድ አውጡ፤ ይሁንና ይጨናገፋል! የፈለጋችሁትን ተናገሩ፤ ሆኖም አይሳካም፤አምላክ ከእኛ ጋር ነውና!*+ +11 ይሖዋ ብርቱ እጁን በእኔ ላይ አድርጎ የዚህን ሕዝብ መንገድ እንዳልከተል ለማስጠንቀቅ እንዲህ አለኝ፦ +12 “ይህ ሕዝብ ‘ሴራ እንጠንስስ!’ ሲል እናንተ ‘በሴራው ተባበሩ!’ አትበሉ፤ እነሱ የሚያስፈራቸውን ነገር አትፍሩ፤አትንቀጥቀጡለትም። +13 ቅዱስ አድርጋችሁ ልትመለከቱ የሚገባው የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ነው፤+ልትፈሩ የሚገባው እሱን ነው፤እንዲሁም ልትንቀጠቀጡ የሚገባው ለእሱ ነው።”+ +14 እሱ እንደ መቅደስ ይሆናል፤ለሁለቱ የእስራኤል ቤቶች ግንእንደሚያሰናክል ድንጋይናእንደሚያደናቅፍ ዓለት፣+ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎችምእንደ ወጥመድና እንደ አሽክላ ይሆንባቸዋል። +15 ከእነሱ መካከል ብዙዎቹ ይደናቀፋሉ፣ ይወድቃሉ፣ ይሰበራሉ፤ወጥመድ ውስጥ ገብተው ይያዛሉ። +16 በጽሑፍ የሰፈረውን ማረጋገጫ* ጠቅልለው፤ሕጉን* በደቀ መዛሙርቴ መካከል አሽገው! +17 እኔም ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሰወረውን+ ይሖዋን እጠባበቃለሁ፤*+ በእሱም ተስፋ አደርጋለሁ። +18 እነሆ፣ እኔና ይሖዋ የሰጠኝ ልጆች+ በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ለእስራኤል እንደተሰጡ ምልክቶችና+ ተአምራት ነን። +19 እነሱም “የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ጠይቁ” ቢሏችሁ፣ አንድ ሕዝብ መጠየቅ ያለበት የራሱን አምላክ አይደለም? ስለ ሕያዋንስ ሙታንን መጠየቁ ተገቢ ነው?+ +20 ከዚህ ይልቅ ሕጉንና የማረጋገጫ ሰነዱን* መመርመር ይገባቸዋል! ከዚህ ቃል ጋር የሚስማማ ነገር ሳይናገሩ ሲቀሩ ብርሃን አይበራላቸውም።*+ +21 እያንዳንዱም ተጎሳቁሎና ተርቦ ��ምድሪቱ ላይ ይንከራተታል፤+ ከመራቡና ከመበሳጨቱ የተነሳ ወደ ላይ እያየ ንጉሡንና አምላኩን ይረግማል። +22 ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታል፤ የሚያየውም ነገር ጭንቀትና ጨለማ፣ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ፣ አስቸጋሪ ወቅትና ብርሃን የሌለበት ፅልማሞት ብቻ ይሆናል። +11 ከእሴይ+ ጉቶ፣ ቅርንጫፍ ይወጣል፤ከሥሮቹም የሚወጣው ቀንበጥ ፍሬ ያፈራል።+ + 2 በእሱም ላይ የይሖዋ መንፈስ፣+የጥበብና+ የማስተዋል መንፈስ፣የምክርና የኃይል+ መንፈስ፣የእውቀትና ይሖዋን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። + 3 ይሖዋን በመፍራትም ደስ ይሰኛል።+ ዓይኑ እንዳየ አይፈርድምወይም ጆሮው በሰማው ነገር ላይ ብቻ ተመሥርቶ አይወቅስም።+ + 4 ለችግረኞች በትክክል* ይፈርዳል፤በምድር ላሉ የዋሆች ጥቅም ሲል ሌሎችን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ይወቅሳል። በአፉም በትር ምድርን ይመታል፤+በከንፈሩም እስትንፋስ* ክፉዎችን ይገድላል።+ + 5 ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣ታማኝነትም የጎኑ መታጠቂያ ይሆናል።+ + 6 ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር የሚቀመጥበት ጊዜ ይኖራል፤+ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤ጥጃ፣ አንበሳና* የሰባ ከብት አብረው ይሆናሉ፤*+ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል። + 7 ላምና ድብ አብረው ይበላሉ፤ልጆቻቸውም አብረው ይተኛሉ። አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል።+ + 8 ጡት የሚጠባ ሕፃንም በእባብ* ጉድጓድ ላይ ይጫወታል፤ጡት የጣለውም ሕፃን እጁን በመርዘኛ እባብ ጎሬ ላይ ያደርጋል። + 9 በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይምንም ዓይነት ጉዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤+ምክንያቱም ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍንምድርም በይሖዋ እውቀት ትሞላለች።+ +10 በዚያን ቀን የእሴይ ሥር+ ለሕዝቦች ምልክት* ሆኖ ይቆማል።+ ብሔራት ከእሱ መመሪያ ይሻሉ፤*+ማረፊያ ስፍራውም እጅግ የከበረ ይሆናል። +11 በዚያን ቀን ይሖዋ ዳግመኛ እጁን ዘርግቶ የተረፉትን የሕዝቡን ቀሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ ከአሦር፣+ ከግብፅ፣+ ከጳትሮስ፣+ ከኢትዮጵያ፣*+ ከኤላም፣+ ከሰናኦር፣* ከሃማትና ከባሕር ደሴቶች+ መልሶ ይሰበስባል። +12 ለብሔራት ምልክት* ያቆማል፤ በየቦታው የተሰራጩትን እስራኤላውያንም መልሶ ያመጣቸዋል፤+ እንዲሁም የተበታተኑትን የይሁዳ ሰዎች ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች ይሰበስባል።+ +13 የኤፍሬም ቅናት ይወገዳል፤+ይሁዳንም የሚጠሉ ይጠፋሉ። ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላውም።+ +14 በምዕራብ በኩል በፍልስጤም ተረተር* ላይ በድንገት ይወርዳሉ፤ግንባር ፈጥረው በምሥራቅ የሚኖሩ ሕዝቦችን ይዘርፋሉ። በኤዶምና+ በሞዓብ+ ላይ እጃቸውን* ይዘረጋሉ፤አሞናውያንም ተገዢዎቻቸው ይሆናሉ።+ +15 ይሖዋ የግብፅን ባሕረ ሰላጤ* ይከፍላል፤*+በወንዙም*+ ላይ እጁን በዛቻ ያወዛውዛል። በሚያቃጥል እስትንፋሱ* የወንዙን ሰባት ጅረቶች ይመታል፤*ሰዎችም ከነጫማቸው እንዲሻገሩ ያደርጋል። +16 እስራኤል ከግብፅ ምድር በወጣበት ጊዜ እንደሆነው ሁሉ፣ከሕዝቡ የተረፉት ቀሪዎችም+ ከአሦር የሚወጡበት ጎዳና+ ይኖራል። +2 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፦+ + 2 በዘመኑ መጨረሻ*የይሖዋ ቤት ተራራከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤+ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ብሔራትም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።+ + 3 ብዙ ሕዝቦችም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+ እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”+ ሕግ* ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።+ + 4 እሱ በብሔራት መካከል ይፈርዳል፤ከብዙ ሕዝቦች ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል።* እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+ አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+ + 5 እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ፤በይሖዋ ብርሃን እንሂድ።+ + 6 አንተ ሕዝብህን ይኸውም የያዕቆብን ቤት ትተሃል፤+ምክንያቱም እነሱ ከምሥራቅ በመጡ ነገሮች ተሞልተዋል፤እንደ ፍልስጤማውያን የአስማት ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፤+በባዕድ አገር ሰዎች ልጆችም ተጥለቅልቀዋል። + 7 ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ሀብታቸውም ገደብ የለውም። ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤ሠረገሎቻቸውም ስፍር ቁጥር የላቸውም።+ + 8 ምድራቸውም ከንቱ በሆኑ አማልክት ተጥለቅልቃለች።+ የገዛ እጃቸው ለሠራው፣የገዛ ጣታቸውም ላበጀው ነገር ይሰግዳሉ። + 9 በመሆኑም ሰው አንገቱን ይደፋል፤ ኀፍረትም ይከናነባል፤አንተም ይቅር ልትላቸው አትችልም። +10 ይሖዋ አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳናከታላቅ ግርማው የተነሳበዓለት ውስጥ ተደበቅ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።+ +11 ትዕቢተኛ ዓይኖች ይዋረዳሉ፤እብሪተኛ ሰዎችም አንገታቸውን ይደፋሉ።* በዚያም ቀን ይሖዋ ብቻ ከፍ ከፍ ይደረጋል። +12 ይህ ቀን የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ነውና።+ ቀኑ ትዕቢተኛና ኩሩ በሆነው ሁሉ ላይ፣ከፍ ባለውም ሆነ ዝቅ ባለው ሁሉ ላይ ይመጣል፤+ +13 ታላላቅ በሆኑትና ከፍ ከፍ ባሉት አርዘ ሊባኖሶች ሁሉ ላይእንዲሁም በባሳን የባሉጥ ዛፎች ሁሉ ላይ፣ +14 ታላላቅ በሆኑት ተራሮች ሁሉናበረጃጅም ኮረብቶች ሁሉ ላይ፣ +15 ረጅም በሆነ ማማ ሁሉና ጠንካራ በሆነ ግንብ ሁሉ ላይ፣ +16 በተርሴስ መርከቦች+ ሁሉናበሚያማምሩ ጀልባዎች ሁሉ ላይ ይደርሳል። +17 ትዕቢተኛ ሰው ይዋረዳል፤እብሪተኞችም አንገታቸውን ይደፋሉ።* በዚያም ቀን ይሖዋ ብቻ ከፍ ከፍ ይደረጋል። +18 ከንቱ የሆኑት አማልክት ሙሉ በሙሉ ይወገዳሉ።+ +19 ይሖዋ ምድርን በሽብር ለማንቀጥቀጥ በሚነሳበት ጊዜ፣አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳናከታላቅ ግርማው የተነሳ+ሰዎች በዓለት ዋሻዎችናበጉድጓዶች ውስጥ* ይደበቃሉ።+ +20 በዚያ ቀን፣ ሰዎች በፊታቸው ይሰግዱ ዘንድለራሳቸው የሠሯቸውን ከንቱ የሆኑ የብርና የወርቅ አማልክትለአይጦችና* ለሌሊት ወፎች ይወረውራሉ፤+ +21 ይሖዋ ምድርን በሽብር ለማንቀጥቀጥ በሚነሳበት ጊዜ፣አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳናከታላቅ ግርማው የተነሳበዓለት ዋሻዎችናበቋጥኝ ስንጥቆች ውስጥ ይደበቃሉ። +22 ለራሳችሁ ስትሉ፣ከአፍንጫው እንደሚወጣ እስትንፋስ በሆነ ሰው* አትታመኑ። ለመሆኑ እሱ ያን ያህል ቦታ እንዲሰጠው የሚያደርግ ምን ነገር አለ? +26 በዚያ ቀን በይሁዳ ምድር ይህ መዝሙር ይዘመራል፦+ “ጠንካራ ከተማ አለችን።+ እሱ መዳንን፣ ቅጥሯና መከላከያ ግንቧ ያደርጋል።+ + 2 ጻድቅ ብሔር ይኸውም በታማኝነት የሚመላለሰው ብሔርእንዲገባ በሮቹን ክፈቱ።+ + 3 ሙሉ በሙሉ በአንተ የሚመኩትን* ትጠብቃለህ፤በአንተ ስለሚታመኑ+ዘላቂ ሰላም ትሰጣቸዋለህ።+ + 4 በይሖዋ ለዘላለም ታመኑ፤+ያህ* ይሖዋ የዘላለም ዓለት ነውና።+ + 5 ከፍ ባለ ቦታ የሚኖሩትን፣ ከፍ ያለችውንም ከተማ ዝቅ አድርጓልና።ያዋርዳታል፤ ወደ ምድር ይጥላታል፤ከአፈርም ይደባልቃታል። + 6 የጎስቋላ ሰው እግር፣የችግረኞችም ኮቴ ይረግጣታል።” + 7 የጻድቅ ሰው መንገድ ቀና* ነው። አንተ ቅን ስለሆንክየጻድቁን መንገድ ደልዳላ ታደርጋለህ። + 8 ይሖዋ ሆይ፣ የፍትሕ ጎዳናህን ስንከተል፣ተስፋ የምናደርገው አንተን ነው። ስምህና መታሰቢያህ የልባችን* ምኞት ነው።* + 9 ሁለንተናዬ* በሌሊት አንተን ለማግኘት ይጓጓል፤አዎ፣ መንፈሴ አንተን በጥብቅ ትፈልጋለች፤+በምድር ላይ በምትፈርድበት ጊዜየምድሪቱ ነዋሪዎች ስለ ጽድቅ+ ይማራሉና። +10 ክፉ ሰው ቸርነት ቢደረግለት እንኳፈጽሞ ጽድቅን አይማርም።+ በቅንነት* ምድር እንኳ ክፋት ይሠራል፤+���ይሖዋንም ግርማ አያይም።+ +11 ይሖዋ ሆይ፣ እጅህ ከፍ ብሏል፤ እነሱ ግን አላዩትም።+ ለሕዝብህ ያለህን ቅንዓት በምታሳይበት ጊዜ ያያሉ፤ ለኀፍረትም ይዳረጋሉ። አዎ፣ ለጠላቶችህ የተዘጋጀው እሳት ይበላቸዋል። +12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰላም ትሰጠናለህ፤+ምክንያቱም የሠራነውን ነገር ሁሉያከናወንክልን አንተ ነህ። +13 ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ ከአንተ ሌላ፣ ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤+እኛ ግን የአንተን ስም ብቻ እንጠራለን።+ +14 እነሱ ሞተዋል፤ በሕይወትም አይኖሩም። በሞት ተረተዋል፤ አይነሱም።+ ታጠፋቸውና ስማቸው ጨርሶ እንዳይነሳ ታደርግ ዘንድትኩረትህን ወደ እነሱ አዙረሃልና። +15 ሕዝቡን አበዛህ፤ ይሖዋ ሆይ፣ሕዝቡን አበዛህ፤ራስህን አስከበርክ።+ የምድሪቱን ወሰን ሁሉ እጅግ አሰፋህ።+ +16 ይሖዋ ሆይ፣ በተጨነቁ ጊዜ አንተን ፈለጉ፤በገሠጽካቸው ጊዜ በሹክሹክታ ድምፅ በመጸለይ ልባቸውን አፈሰሱ።+ +17 ይሖዋ ሆይ፣ ነፍሰ ጡር ሴት ልትወልድ ስትልምጥ እንደሚይዛትና በምጥ ጣር እንደምትጮኽ ሁሉእኛም በአንተ የተነሳ እንዲሁ ሆነናል። +18 እኛ አርግዘናል፤ ደግሞም አምጠናል፤ይሁንና ነፋስ የወለድን ያህል ሆነናል። ለምድሪቱ መዳን አላስገኘንምእንዲሁም በምድሪቱ ላይ እንዲኖር የተወለደ አንድም ልጅ የለም። +19 “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ። የእኔ አስከሬኖች ይነሳሉ።+ እናንተ በአፈር ውስጥ የምትኖሩ፣+ተነሱ፤ በደስታም እልል በሉ! ጠልህ እንደ ማለዳ ጠል ነውና፤*ምድርም በሞት የተረቱት ዳግም ሕይወት እንዲያገኙ ታደርጋለች።* +20 ሕዝቤ ሆይ፣ ሂድ ወደ ውስጠኛው ክፍልህ ግባ፤በርህንም ከኋላህ ዝጋ።+ ቁጣው* እስኪያልፍ ድረስለጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።+ +21 እነሆ፣ ይሖዋ የምድሪቱ ነዋሪ የፈጸመውን በደል ለመፋረድከመኖሪያ ቦታው ይመጣልና፤ምድሪቱም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤በላይዋም የተገደሉትን ከዚህ በኋላ አትደብቅም።” +44 “አሁን ግን፣ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣የመረጥኩህም እስራኤል ሆይ፣+ ስማ። + 2 የሠራህና ያበጀህ፣+ከማህፀን* ጀምሮ የረዳህይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አገልጋዬ ያዕቆብ፣የመረጥኩህም የሹሩን*+ ሆይ፣ አትፍራ።+ + 3 ለተጠማው* ውኃ አፈሳለሁና፤+በደረቁ ምድርም ላይ ጅረቶች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ። መንፈሴን በዘርህ ላይ፣በረከቴንም በልጅ ልጆችህ ላይ አፈሳለሁ።+ + 4 እነሱም በለምለም ሣር መካከል፣በጅረቶችም ዳር እንዳሉ የአኻያ ዛፎች ይበቅላሉ።+ + 5 አንዱ “እኔ የይሖዋ ነኝ” ይላል።+ ሌላውም ራሱን በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ሌላው ደግሞ በእጁ ላይ “የይሖዋ ነኝ” ብሎ ይጽፋል። ደግሞም ራሱን በእስራኤል ስም ይጠራል።’ + 6 የእስራኤል ንጉሥ+ የሆነውና እስራኤልን የተቤዠው+ ይሖዋ፣የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የመጀመሪያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻውም እኔ ነኝ።+ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።+ + 7 እንደ እኔ ያለ ማን ነው?+ በድፍረት ይናገር፤ ያሳውቅም፤ ማስረጃውንም ለእኔ ያቅርብ!+ የጥንቱን ሕዝብ ካቋቋምኩበት ጊዜ ጀምሮ፣በቅርቡ የሚከሰቱትንናወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይናገሩ። + 8 ስጋት አይደርባችሁ፤በፍርሃትም አትሽመድመዱ።+ አስቀድሜ ለእያንዳንዳችሁ አልነገርኳችሁም? ደግሞስ አላሳወቅኳችሁም? እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ።+ ከእኔ ሌላ አምላክ አለ? በፍጹም፣ ሌላ ዓለት የለም፤+ እኔ የማውቀው አንድም የለም።’” + 9 የተቀረጹ ምስሎችን የሚሠሩ ሁሉ ከንቱ ናቸው፤የሚወዷቸውም ጣዖቶች ምንም ጥቅም የላቸውም።+ እንደ ምሥክሮቻቸው እነሱም* ምንም አያዩም፤ ምንም አያውቁም፤+በመሆኑም ሠሪዎቻቸው ለኀፍረት ይዳረጋሉ።+ +10 ለምንም የማይጠቅም አምላክ የሚሠራወይም የብረት ምስል* የሚያበጅ ማን ነው?+ +11 እነሆ፣ ባ��ደረቦቹ ሁሉ ያፍራሉ!+ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹ ተራ ሰዎች ናቸው። ሁሉም ተሰብስበው ይቁሙ። በፍርሃት ይዋጣሉ፤ ሁሉም ያፍራሉ። +12 አንጥረኛ በመሣሪያው* ተጠቅሞ ብረቱን በከሰል ፍም ላይ ይሠራዋል። ብርቱ በሆነው ክንዱበመዶሻ ቅርጽ ይሰጠዋል።+ ከዚያም ይርበዋል፤ ጉልበትም ያጣል፤ውኃ ስለማይጠጣ ይደክማል። +13 እንጨት ጠራቢው በገመድ ይለካል፤ በቀይ ጠመኔም ንድፍ ያወጣል። በመሮም ይጠርበዋል፤ በማክበቢያም ምልክት ያደርግበታል። በሰው አምሳል ይቀርጸዋል፤+የሰውንም ውበት ያላብሰዋል፤ከዚያም ቤት ውስጥ* ያስቀምጠዋል።+ +14 አርዘ ሊባኖስ የሚቆርጥ ሰው አለ። እሱም አንድ የዛፍ ዝርያ ይኸውም የባሉጥ ዛፍ ይመርጣል፤እስኪጠነክርለት ድረስ በጫካው ውስጥ ባሉት ዛፎች መካከል ይተወዋል።+ የላውሮ ዛፍ ይተክላል፤ ዝናብም ያሳድገዋል። +15 ከዚያም ሰው ለማገዶ ይጠቀምበታል። የተወሰነውን እንጨት ወስዶ በማንደድ እሳት ይሞቃል፤እሳት አያይዞም ዳቦ ይጋግራል። ይሁንና አምላክ ሠርቶም ያመልከዋል። የተቀረጸ ምስል ሠርቶበት በፊቱ ይደፋል።+ +16 ግማሹን በእሳት ያነደዋል፤በዚያም ላይ የሚበላውን ሥጋ ይጠብሳል፤ በልቶም ይጠግባል። እሳቱንም እየሞቀ “እሰይ! እሳቱን እያየሁ ሞቅኩ” ይላል። +17 የቀረውን ግን ምስል ይቀርጽበታል፤ አምላክ አድርጎም ይሠራዋል። በፊቱም ተደፍቶ ይሰግድለታል። “አንተ አምላኬ ነህና አድነኝ” ብሎ ወደ እሱ ይጸልያል።+ +18 ምንም አያውቁም እንዲሁም አያስተውሉም፤+ምክንያቱም ዓይኖቻቸው ተጨፍነዋል፤ ማየትም አይችሉም፤ልባቸውም ማስተዋል ጎድሎታል። +19 ቆም ብሎ በልቡ ያሰበወይም እውቀትም ሆነ ማስተዋል ኖሮት እንዲህ ብሎ የተናገረ የለም፦ “ግማሹን እሳት አንድጄበታለሁ፤በፍሙም ላይ ዳቦ ጋግሬአለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ። ታዲያ በቀረው እንጨት አስጸያፊ ነገር መሥራቴ ተገቢ ነው?+ ከዛፍ ለተቆረጠ እንጨት* መስገድ ይገባኛል?” +20 እሱ አመድ ይበላል። የተታለለው የገዛ ልቡ አስቶታል። ራሱን* ሊያድን አይችልም፤ ደግሞም “በቀኝ እጄ ያለው ውሸት አይደለም?” አይልም። +21 “ያዕቆብ ሆይ፣ አንተም እስራኤል ሆይ፣አገልጋዬ ስለሆንክ እነዚህን ነገሮች አስታውስ። እኔ ሠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ አገልጋይ ነህ።+ እስራኤል ሆይ፣ አልረሳህም።+ +22 በደልህን በደመና፣ኃጢአትህንም ጥቅጥቅ ባለ ደመና እሸፍነዋለሁ።+ ወደ እኔ ተመለስ፤ እኔም እቤዥሃለሁ።+ +23 እናንተ ሰማያት በደስታ እልል በሉ!ይሖዋ እርምጃ ወስዷልና። እናንተ ጥልቅ የምድር ክፍሎች በድል አድራጊነት ጩኹ! እናንተ ተራሮች፣ አንተም ደን ሆይ፣በውስጡም ያላችሁ ዛፎች ሁሉ በደስታ እልል በሉ!+ ይሖዋ ያዕቆብን ተቤዥቷልና፤በእስራኤልም ላይ ግርማውን ገልጧል።”+ +24 የተቤዠህና+ ከማህፀን ጀምሮ የሠራህይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሁሉንም ነገር የሠራሁ እኔ ይሖዋ ነኝ። ብቻዬን ሰማያትን ዘረጋሁ፤+ምድርንም ሠራሁ።+ ያኔ ከእኔ ጋር ማን ነበር? +25 የሆነ ያልሆነውን የሚቀባጥሩ ሰዎችን* ምልክቶች አከሽፋለሁ፤ሟርተኞችንም ነፈዝ አደርጋለሁ፤+ጥበበኞቹንም ግራ አጋባለሁ፤እውቀታቸውንም ሞኝነት አደርጋለሁ፤+ +26 የአገልጋዬን ቃል እውን አደርጋለሁ፤የመልእክተኞቼንም ትንቢት ሙሉ በሙሉ እፈጽማለሁ፤+ስለ ኢየሩሳሌም ‘የሰው መኖሪያ ትሆናለች’፤+ ስለ ይሁዳ ከተሞችም ‘ዳግም ይገነባሉ፤+ፍርስራሾቿንም መልሼ እሠራለሁ’+ እላለሁ፤ +27 ጥልቁን ውኃ ‘ደረቅ ሁን፤ወንዞችህንም ሁሉ አደርቃለሁ’+ እላለሁ፤ +28 ስለ ቂሮስ+ ‘እሱ እረኛዬ ነው፤ፈቃዴንም ሁሉ ሙሉ በሙሉ ይፈጽማል’+ እላለሁ፤ስለ ኢየሩሳሌም ‘ዳግም ትገነባለች’፤ ስለ ቤተ መቅደሱም ‘መሠረትህ ይጣላል’+ እላለሁ።” +4 ��ዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንድን ወንድ ይዘው እንዲህ ይሉታል፦+ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ብቻ በእኛ ላይ የደረሰው ውርደት* እንዲወገድ+በአንተ ስም እንድንጠራ ፍቀድልን።” +2 በዚያን ቀን፣ ይሖዋ እንዲያቆጠቁጥ ያደረገው ተክል ያማረና ክብር የተላበሰ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፉት እስራኤላውያን የኩራት ምንጭና ውበት ይሆንላቸዋል።+ +3 በጽዮን የቀሩትና በኢየሩሳሌም የተረፉት ሁሉ ይኸውም በኢየሩሳሌም እንዲኖሩ የተመዘገቡት በጠቅላላ ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።+ +4 ይሖዋ በፍርድ መንፈስና በሚነድ* መንፈስ+ የጽዮንን ሴቶች ልጆች ቆሻሻ* አጥቦ ያስወግዳል፤+ የኢየሩሳሌምንም የደም ዕዳ ከመካከሏ አጥቦ ያነጻል፤ +5 ያን ጊዜ ይሖዋ በመላው የጽዮን ተራራ ላይና በመሰብሰቢያ ቦታዋ ላይ በቀን ደመናና ጭስ፣ በሌሊት ደግሞ የሚንበለበል የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤+ እንዲሁም ክብራማ በሆነው ቦታ ሁሉ ላይ መጠለያ ይኖራል። +6 ደግሞም በቀን ካለው ንዳድ ጥላ+ እንዲሁም ከውሽንፍርና ከዝናብ መጠጊያና መሸሸጊያ+ የሚሆን ዳስ ይኖራል። +41 “እናንተ ደሴቶች፣ ዝም ብላችሁ አዳምጡኝ፤*ብሔራትም ኃይላቸውን ያድሱ። በመጀመሪያ ይቅረቡ፤ ከዚያም ይናገሩ።+ ለፍርድ አንድ ላይ እንሰብሰብ። + 2 ብሔራትን አሳልፎ ይሰጠውናነገሥታትን ድል ይነሳ ዘንድ+ከፀሐይ መውጫ* አንዱን ያስነሳው፣+በጽድቅ ወደ እግሩ የጠራው* ማን ነው? በሰይፉ ፊት አቧራ የሚያደርጋቸው፣በቀስቱ ፊት በነፋስ እንደተወሰደ ገለባ የሚያደርጋቸው ማን ነው? + 3 እግሩ ባልረገጠው መንገድ በመጓዝምንም ነገር ሳያግደው እነሱን ያሳድዳል። + 4 ይህን የሠራና ያደረገ፣ትውልዶቹንም ከመጀመሪያ አንስቶ የጠራ ማን ነው? እኔ ይሖዋ የመጀመሪያው ነኝ፤+ከመጨረሻዎቹም ጋር እኔ ያው ነኝ።”+ + 5 ደሴቶች አይተው ፈሩ። የምድር ዳርቻዎች ተንቀጠቀጡ። ቀረቡ፤ ወደ ፊትም መጡ። + 6 እያንዳንዱም ባልንጀራውን ይረዳል፤ወንድሙንም “አይዞህ፣ በርታ” ይለዋል። + 7 የእጅ ጥበብ ባለሙያውም አንጥረኛውን ያበረታታል፤+በመዶሻ ብረቱን የሚያሳሳውበመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያበረታታዋል። ብየዳውን በተመለከተ “ጥሩ ነው” ይላል። ከዚያም ጣዖቱ እንዳይወድቅ አንድ ሰው በምስማር ይቸነክረዋል። + 8 “እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግን አገልጋዬ ነህ፤+ያዕቆብ ሆይ፣ አንተን መርጬሃለሁ፤+የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ፤+ + 9 አንተን ከምድር ዳርቻዎች ወሰድኩህ፤+እጅግ ርቀው ከሚገኙ ቦታዎችም ጠራሁህ። እንዲህ ብዬሃለሁ፦ ‘አንተ አገልጋዬ ነህ፤+እኔ መርጬሃለሁ፤ ገሸሽ አላደረግኩህም።+ +10 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።+ እኔ አምላክህ ነኝና አትጨነቅ።+ አበረታሃለሁ፤ አዎ እረዳሃለሁ፤+በጽድቅ ቀኝ እጄ አጥብቄ እይዝሃለሁ።’ +11 እነሆ፣ በአንተ ላይ የተቆጡ ሁሉ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም።+ ከአንተ ጋር የሚጣሉ ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።+ +12 ከአንተ ጋር የሚፋለሙትን ሰዎች ትፈልጋቸዋለህ፤ ሆኖም አታገኛቸውም፤ከአንተ ጋር የሚዋጉ ሰዎች እንደሌሉና ፈጽሞ እንዳልነበሩ ያህል ይሆናሉ።+ +13 ‘አትፍራ። እረዳሃለሁ’ የምልህእኔ፣ አምላክህ ይሖዋ ቀኝ እጅህን ይዣለሁና።+ +14 ትል* የሆንከው አንተ ያዕቆብ አትፍራ፤+እናንተ የእስራኤል ሰዎች፣ እረዳችኋለሁ” ይላል የሚቤዥህ+ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ። +15 “እነሆ፣ ማሄጃ፣ በሁለቱም በኩል የተሳሉ ጥርሶች ያሉትአዲስ የመውቂያ መሣሪያ አድርጌሃለሁ።+ አንተም ተራሮቹን ረግጠህ ታደቃቸዋለህ፤ኮረብቶቹንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ። +16 ወደ ላይ ትበትናቸዋለህ፤ነፋስም ይወስዳቸዋል፤አውሎ ነፋስ ይበትናቸዋል። በይሖዋ ደስ ይልሃ���፤+በእስራኤልም ቅዱስ ትኮራለህ።”+ +17 “ችግረኞችና ድሆች ውኃ ይፈልጋሉ፤ ሆኖም አያገኙም። ከመጠማታቸው የተነሳ ምላሳቸው ደርቋል።+ እኔ ይሖዋ እመልስላቸዋለሁ።+ እኔ የእስራኤል አምላክ አልተዋቸውም።+ +18 በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ወንዞች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤+በሸለቋማ ሜዳዎች መካከል ምንጮችን አፈልቃለሁ።+ ምድረ በዳውን ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣ውኃ የሌለበትንም ምድር የውኃ ምንጭ አደርጋለሁ።+ +19 በበረሃ አርዘ ሊባኖስ፣ግራር፣ አደስና ዘይት የሚሰጥ ዛፍ እተክላለሁ።+ በበረሃማ ሜዳ የጥድ ዛፍ፣የአሽ ዛፍና* የፈረንጅ ጥድ በአንድነት እተክላለሁ፤+ +20 ይህም የሚሆነው የይሖዋ እጅ ይህን እንዳደረገናየእስራኤል ቅዱስ ይህን እንደፈጠረሰዎች ሁሉ እንዲያዩና እንዲያውቁ፣ልብ እንዲሉና በጥልቅ እንዲያስተውሉ ነው።”+ +21 “ሙግታችሁን አቅርቡ” ይላል ይሖዋ። “የመከራከሪያ ሐሳባችሁን አሰሙ” ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። +22 “ማስረጃ አቅርቡ፤ እንዲሁም ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ንገሩን። በጥሞና እንድናስብባቸውና* ፍጻሜያቸውን እንድናውቅስለቀድሞዎቹ* ነገሮች ንገሩን። ወይም የሚመጡትን ነገሮች አሳውቁን።+ +23 አማልክት መሆናችሁን እንድናውቅወደፊት የሚሆነውን ነገር ንገሩን።+ አዎ፣ አይተን በአድናቆት እንድንዋጥመልካምም ሆነ ክፉ፣ የሆነ ነገር አድርጉ።+ +24 እነሆ፣ እናንተ ጨርሶ ሕልውና የሌላችሁ ናችሁ፤ምንም የምታከናውኑት ነገር የለም።+ እናንተን የሚመርጥ ሁሉ አስጸያፊ ነው።+ +25 አንዱን ከሰሜን አስነስቻለሁ፤ እሱም ይመጣል፤+የሚመጣው ከፀሐይ መውጫ*+ ሲሆን ስሜንም ይጠራል። ጭቃውን እንደሚረግጥ ሸክላ ሠሪገዢዎችን* እንደ ሸክላ አፈር ይረግጣቸዋል።+ +26 እኛ እናውቅ ዘንድ ስለዚህ ነገር ከመጀመሪያው የተናገረወይም ‘እሱ ትክክል ነው’ እንድንል ከጥንት ጀምሮ የተናገረ ማን ነው?+ በእርግጥ የተናገረ የለም! ያሳወቀም የለም! ከእናንተ አንዳች ነገር የሰማ የለም!”+ +27 ከማንም በፊት ጽዮንን “ወደፊት የሚሆነውን ነገር ተመልከቺ!” ያልኩት እኔ ነኝ፤+ ለኢየሩሳሌምም ምሥራች ነጋሪ እልካለሁ።+ +28 ሆኖም እኔ መመልከቴን ቀጠልኩ፤ አንድም ሰው አልነበረም፤ከእነሱ መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም። እኔም መልስ እንዲሰጡ መጠየቄን ቀጠልኩ። +29 እነሆ፣ ሁሉም ቅዠት* ናቸው። ሥራቸው ከንቱ ነው። ከብረት የተሠሩት ምስሎቻቸው* ነፋስና መና ናቸው።+ +63 ይህ ከኤዶም የሚመጣው፣+ደማቅ ቀለም ያለው* ልብስ ለብሶ ከቦስራ+ የሚገሰግሰው ማን ነው?ይህ እጅግ ያማረ ልብስ ለብሶናበታላቅ ኃይል ተሞልቶ የሚራመደው ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር፣ለማዳን የሚያስችል ታላቅ ኃይል ያለኝ እኔ ነኝ።” + 2 መጎናጸፊያህ የቀላውናልብሶችህ በመጭመቂያ ውስጥ ወይን እንደሚረግጥ ሰው ልብስ የሆኑት ለምንድን ነው?+ + 3 “በወይን መጭመቂያው ውስጥ ወይኑን ብቻዬን ረገጥኩ። ከሕዝቦች መካከል ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም። በቁጣዬም ረጋገጥኳቸው፤በታላቅ ቁጣዬም ጨፈላለቅኳቸው።+ ደማቸውም ልብሶቼ ላይ ተረጨ፤ልብሴንም ሁሉ በከልኩ። + 4 የምበቀልበት ቀን በልቤ ውስጥ ነውና፤+የምቤዥበትም ዓመት ደርሷል። + 5 ተመለከትኩ፤ ሆኖም እርዳታ የሚሰጥ አልነበረም፤ማንም ድጋፍ ባለመስጠቱ ደነገጥኩ። ስለዚህ ክንዴ መዳን* አስገኘልኝ፤+የገዛ ቁጣዬም ድጋፍ ሆነልኝ። + 6 ሕዝቦችን በቁጣዬ ረጋገጥኩ፤በታላቅ ቁጣዬም አሰከርኳቸው፤+ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስኩ።” + 7 ይሖዋ በምሕረቱና ታላቅ በሆነው ታማኝ ፍቅሩለእኛ ባደረገልን ነገሮች ሁሉ+ይኸውም ለእስራኤል ቤት ባደረጋቸው በርካታ መልካም ነገሮች የተነሳየይሖዋን የታማኝ ፍቅር መግለጫዎች፣ደግሞም ሊወደሱ የሚ��ባቸውን የይሖዋን ሥራዎች እናገራለሁ። + 8 እሱ እንዲህ ብሏልና፦ “እነሱ በእርግጥ ሕዝቤ፣ የማይከዱ* ወንዶች ልጆች ናቸው።”+ ስለዚህ አዳኝ ሆነላቸው።+ + 9 በጭንቃቸው ሁሉ እሱ ተጨነቀ።+ የግል መልእክተኛውም* አዳናቸው።+ እሱ በፍቅሩና በርኅራኄው ተቤዣቸው፤+በቀድሞውም ዘመን ሁሉ አነሳቸው እንዲሁም ተሸከማቸው።+ +10 እነሱ ግን ዓመፁ፤+ ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ።+ በዚህ ጊዜ ጠላት ሆነባቸው፤+ደግሞም ተዋጋቸው።+ +11 እነሱም የጥንቱን ዘመን፣አገልጋዩ ሙሴ የኖረበትን ጊዜ አስታወሱ፦ “ከመንጋው እረኞች+ ጋር ከባሕሩ ያወጣቸው የት አለ?+ በእሱ ውስጥ ቅዱስ መንፈሱን ያኖረው፣+ +12 የከበረ ክንዱ ከሙሴ ቀኝ እጅ ጋር እንዲሄድ ያደረገው፣+ለራሱ ዘላለማዊ ስም ለማትረፍ+ውኃዎቹን በፊታቸው የከፈለው፣+ +13 አውላላ ሜዳ* ላይ እንዳለ ፈረስ፣በሚናወጡ ውኃዎች* መካከልሳይደናቀፉ እንዲሄዱ ያደረገው የት አለ? +14 የከብት መንጋ ወደ ሸለቋማ ሜዳ ሲወርድ እንደሚሆነው፣የይሖዋ መንፈስ አሳረፋቸው።”+ ለራስህ የከበረ* ስም ለማትረፍ ስትል+ሕዝብህን የመራኸው በዚህ መንገድ ነው። +15 ከሰማይ ተመልከት፤ከፍ ካለው የቅድስናና የክብር* መኖሪያህም ሆነህ እይ። ቅንዓትህና ታላቅ ኃይልህ፣የሚንሰፈሰፈው አንጀትህና+ ምሕረትህ የት አለ?+ እነዚህን ነገሮች ነፍገኸኛል። +16 አንተ አባታችን ነህና፤+አብርሃም ባያውቀን፣እስራኤልም ባያስታውሰን እንኳይሖዋ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ። ስምህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ “እኛን የተቤዠ” የሚል ነው።+ +17 ይሖዋ ሆይ፣ ከመንገዶችህ ወጥተን እንድንቅበዘበዝ የፈቀድከው* ለምንድን ነው? አንተን እንዳንፈራ ልባችን እንዲደነድን የፈቀድከው* ለምንድን ነው?+ ስለ አገልጋዮችህ፣ርስትህ ስለሆኑትም ነገዶች ስትል ተመለስ።+ +18 ቅዱስ ሕዝብህ ለጥቂት ጊዜ ወርሶት ነበር። ጠላቶቻችን መቅደስህን ረግጠዋል።+ +19 እኛ ለረጅም ጊዜ፣ ፈጽሞ እንዳልገዛኻቸው፣ጨርሶ በስምህ እንዳልተጠሩ ሰዎች ሆነናል። +46 ቤል ያጎነብሳል፤+ ነቦ አንገቱን ይደፋል። ጣዖቶቻቸው በደከሙ እንስሳት ላይ እንደሚጫን ከባድ ጭነትበእንስሳት ይኸውም በጋማ ከብቶች ላይ ተጭነዋል።+ + 2 አንገታቸውን ይደፋሉ፤ በአንድነት ያጎነብሳሉ፤ጭነቱን* ማዳን አይችሉም፤እነሱ ራሳቸውም ተማርከው ይወሰዳሉ።* + 3 “የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ከእስራኤልም ቤት የቀራችሁት ሁሉ፣+ከተወለዳችሁበት ጊዜ አንስቶ የረዳኋችሁ፣ በማህፀን ከነበራችሁበት ጊዜም አንስቶ የተሸከምኳችሁ+ ስሙኝ። + 4 እስከ እርጅናችሁ ዘመን ድረስ እኔ ያው ነኝ፤+ፀጉራችሁ እስኪሸብትም ድረስ እሸከማችኋለሁ። ከዚህ ቀደም እንዳደረግኩት እሸከማችኋለሁ፣ እደግፋችኋለሁ እንዲሁም እታደጋችኋለሁ።+ + 5 ከማን ጋር ታመሳስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር እኩል ታደርጉኛላችሁ?+ወይስ እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታነጻጽሩኛላችሁ?+ + 6 ከኮሮጇቸው ወርቅ የሚዘረግፉ ሰዎች አሉ፤ብሩን በሚዛን ይመዝናሉ። አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ እሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል።+ እነሱም በፊቱ ይደፋሉ፤ ደግሞም ያመልኩታል።*+ + 7 አንስተው ትከሻቸው ላይ ያደርጉታል፤+ተሸክመው ወስደው ቦታው ላይ ያኖሩታል፤ በዚያም ዝም ብሎ ይቆማል። ካለበት ቦታ አይንቀሳቀስም።+ ወደ እሱ ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስም፤ማንንም ከጭንቀት ሊታደግ አይችልም።+ + 8 ይህን አስታውሱ፤ ደግሞም አይዟችሁ። እናንተ ሕግ ተላላፊዎች ይህን ልብ በሉ። + 9 ጥንት የተከናወኑትን የቀድሞዎቹን* ነገሮች፣እኔ አምላክ* መሆኔንና ከእኔ ሌላ አምላክ እንደሌለ አስታውሱ። እኔ አምላክ ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።+ +10 ከመጀመሪያ መጨረሻውን፣ገና ያልተከናወኑትንም ነገሮች ከረጅም ጊ��� በፊት አስቀድሜ እናገራለሁ።+ እኔ ‘ውሳኔዬ* ይጸናል፤+ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ሁሉ አደርጋለሁ’+ እላለሁ። +11 ከፀሐይ መውጫ* አዳኝ አሞራን፣+ከሩቅ ምድርም ውሳኔዬን* የሚፈጽመውን ሰው እጠራለሁ።+ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም እፈጽመዋለሁ። ይህን ለማድረግ አስቤአለሁ፤ አደርገዋለሁም።+ +12 እናንተ ልበ ደንዳኖች፣*እናንተ ከጽድቅ የራቃችሁ ሰዎች ስሙኝ። +13 ጽድቄን አምጥቻለሁ፤ሩቅም አይደለም፤ማዳኔም አይዘገይም።+ በጽዮን መዳን አስገኛለሁ፤ ለእስራኤልም ግርማዬን አጎናጽፋለሁ።”+ +53 ከእኛ የሰማውን* ነገር ያመነ ማን ነው?+ የይሖዋስ ክንድ+ ለማን ተገለጠ?+ + 2 እሱ በፊቱ* እንደ ቅርንጫፍ፣+ በደረቅ ምድር እንዳለ ሥር ይበቅላል። የሚያምር ቁመናም ሆነ ግርማ ሞገስ የለውም፤+ባየነውም ጊዜ መልኩ አልሳበንም።* + 3 ሰዎች የናቁትና ያገለሉት፣+ሥቃይን ያየ፣* ሕመምንም የሚያውቅ ሰው ነበር። ፊቱ የተሰወረብን ያህል ነበር።* ሰዎች ናቁት፤ እኛም ከቁብ አልቆጠርነውም።+ + 4 በእርግጥም እሱ ራሱ ሕመማችንን ተሸከመ፤+ሥቃያችንንም ተቀበለ።+ እኛ ግን እንደተቀሰፈ፣ በአምላክ እንደተመታና እንደተጎሳቆለ አድርገን ቆጠርነው። + 5 እሱ ግን ስለ መተላለፋችን+ ተወጋ፤+ስለ በደላችን ደቀቀ።+ በእሱ ላይ የደረሰው ቅጣት ለእኛ ሰላም አስገኘልን፤+በእሱም ቁስል የተነሳ እኛ ተፈወስን።+ + 6 ሁላችንም እንደ በጎች ተቅበዘበዝን፤+እያንዳንዳችን በየራሳችን መንገድ ሄድን፤ይሖዋም የሁላችንንም በደል እሱ እንዲሸከም አደረገ።+ + 7 ግፍ ተፈጸመበት፤+ መከራም ለመቀበል ፈቃደኛ ሆነ፤+ነገር ግን አፉን አልከፈተም። እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤+በሸላቾቿ ፊት ዝም እንደምትል በግ፣እሱም አፉን አልከፈተም።+ + 8 ፍትሕ ተነፈገ፤* በአግባቡም ሳይዳኝ ተወሰደ፤ትኩረት ሰጥቶ ትውልዱን በዝርዝር ለማወቅ* የሚሞክር ማን ነው? ከሕያዋን ምድር ተወግዷልና፤+በሕዝቤ መተላለፍ የተነሳ ተመታ።*+ + 9 ምንም ዓይነት በደል* አልፈጸመም፤እንዲሁም ከአንደበቱ የማታለያ ቃል አልወጣም፤+ሆኖም በሚሞትበት ጊዜ የመቃብር ቦታውከክፉዎችና+ ከሀብታሞች*+ ጋር ይሆናል።* +10 ይሁንና እሱን ማድቀቅ የይሖዋ ፈቃድ ነበር፤* ለሕመም እንዲዳረግም ፈቅዷል። ሕይወቱን* የበደል መባ አድርገህ የምታቀርበው ከሆነ+ዘሩን ያያል፤ ዘመኑን ያስረዝማል፤+እንዲሁም በእሱ አማካኝነት ይሖዋ ደስ የሚሰኝበት ነገር* ይከናወናል።+ +11 በእሱ ላይ ከደረሰው ሥቃይ* የተነሳ፣ በሚያየው መልካም ነገር ይደሰታል። ጻድቅ አገልጋዬ+ በእውቀቱ አማካኝነትብዙ ሰዎች ጻድቅ ሆነው እንዲቆጠሩ ይረዳል፤+በደላቸውንም ይሸከማል።+ +12 ስለዚህ ከብዙዎች ጋር ድርሻውን እሰጠዋለሁ፤ምርኮውን ከኃያላን ጋር ይካፈላል፤ሕይወቱን* እስከ ሞት ድረስ አፍስሷልና፤+ከሕግ ተላላፊዎችም ጋር ተቆጥሯል፤+የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸክሟል፤+ስለ ሕግ ተላላፊዎችም ማልዷል።+ +37 ንጉሥ ሕዝቅያስ ይህን እንደሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶም ወደ ይሖዋ ቤት ገባ።+ +2 ከዚያም የቤቱ* አስተዳዳሪ የሆነውን ኤልያቄምን፣ ጸሐፊውን ሸብናን እንዲሁም የካህናቱን ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ+ እንዲሄዱ ላካቸው። +4 ምናልባት አምላክህ ይሖዋ፣ ሕያው የሆነውን አምላክ እንዲያቃልል+ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራብሻቁን ቃል ይሰማ ይሆናል፤ ደግሞም አምላክህ ይሖዋ፣ የተናገረውን ቃል ሰምቶ ተጠያቂ ያደርገው ይሆናል። ስለዚህ በሕይወት ለተረፉት ቀሪዎች+ ጸልይ።’”+ +6 ኢሳይያስም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታችሁን እንዲህ በሉት፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች+ እኔን በመሳደብ የተናገሩትን ቃል በመስማትህ አትፍራ���+ +7 እነሆ፣ በአእምሮው አንድ ሐሳብ አስገባለሁ፤* እሱም ወሬ ሰምቶ ወደ አገሩ ይመለሳል፤+ በገዛ አገሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።”’”+ +8 ራብሻቁም የአሦር ንጉሥ ለኪሶን ለቆ እንደሄደ ሲሰማ ወደ ንጉሡ ተመለሰ፤ ከሊብናም ጋር ሲዋጋ አገኘው።+ +9 በዚህ ጊዜ ንጉሡ የኢትዮጵያው ንጉሥ ቲርሃቅ “ከአንተ ጋር ሊዋጋ ወጥቷል” የሚል ወሬ ሰምቶ ነበር። እሱም ይህን በሰማ ጊዜ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት በድጋሚ መልእክተኞች ላከ፦+ +12 አባቶቼ ያጠፏቸውን ብሔራት አማልክታቸው ታድገዋቸዋል?+ ጎዛን፣ ካራን፣+ ረጼፍና በቴልአሳር የነበሩት የኤደን ሕዝቦች የት አሉ? +13 የሃማት ንጉሥ፣ የአርጳድ ንጉሥ፣ የሰፋርዊም+ ከተሞች ንጉሥ እንዲሁም የሄና እና የኢዋ ነገሥታት የት አሉ?’” +15 ሕዝቅያስም ወደ ይሖዋ እንዲህ ሲል ጸለየ፦+ +16 “ከኪሩቤል በላይ* የምትቀመጥ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣+ የምድር መንግሥታት ሁሉ እውነተኛ አምላክ አንተ ብቻ ነህ። ሰማያትንና ምድርን ሠርተሃል። +17 ይሖዋ ሆይ፣ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ!+ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይንህን ገልጠህ እይ!+ ሰናክሬም ሕያው የሆነውን አምላክ ለማቃለል የላከውን ቃል ሁሉ ስማ።+ +18 ይሖዋ ሆይ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን አገሮች ሁሉና የገዛ ራሳቸውን ምድር እንዳጠፉ አይካድም።+ +19 አማልክታቸውንም እሳት ውስጥ ጨምረዋል፤+ ምክንያቱም የሰው እጅ ሥራ፣ እንጨትና ድንጋይ እንጂ አማልክት አይደሉም።+ ሊያጠፏቸው የቻሉት በዚህ ምክንያት ነው። +20 አሁን ግን አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ፣ አንተ ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ይሖዋ ሆይ፣ ከእጁ አድነን።”+ +21 ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ሕዝቅያስ ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የአሦርን ንጉሥ ሰናክሬምን በተመለከተ ወደ እኔ ስለጸለይክ፣+ +22 ይሖዋ በእሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ “ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ትንቅሃለች፤ ደግሞም ታፌዝብሃለች። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ራሷን ትነቀንቅብሃለች። +23 ያቃለልከውና+ የሰደብከው ማንን ነው? ድምፅህን ከፍ ያደረግከው፣+እብሪተኛ ዓይንህንም ያነሳኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ እኮ ነው!+ +24 በአገልጋዮችህ በኩል ይሖዋን አቃለሃል፤+ እንዲህም ብለሃል፦‘ብዛት ባላቸው የጦር ሠረገሎቼ፣ወደ ተራሮች ከፍታ፣ርቀው ወደሚገኙትም የሊባኖስ ስፍራዎች እወጣለሁ።+ ረጃጅሞቹን አርዘ ሊባኖሶች፣ ምርጥ የሆኑትንም የጥድ ዛፎች እቆርጣለሁ። እጅግ ከፍ ወዳለው ማረፊያ ቦታ፣ በጣም ጥቅጥቅ ወዳለው ጫካ እገባለሁ። +25 ጉድጓድ ቆፍሬ ውኃ እጠጣለሁ፤የግብፅን ጅረቶች* በእግሬ ረግጬ አደርቃለሁ።’ +26 አልሰማህም? ይህ ከጥንት ዘመን ጀምሮ የተወሰነ* ነው። ከድሮ ጀምሮ ይህን አስቤአለሁ።*+ አሁን እንዲፈጸም አደርጋለሁ።+ አንተም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር ታደርጋለህ።+ +27 ነዋሪዎቻቸው አቅመ ቢስ ይሆናሉ፤ይሸበራሉ፤ ደግሞም ያፍራሉ። እንደ ሜዳ ተክል፣ እንደ ለምለም ሣር፣እንዲሁም የምሥራቅ ነፋስ እንዳቃጠለው በጣሪያ ላይ የበቀለ ሣር ይሆናሉ። +28 ይሁንና መቼ እንደምትቀመጥ፣ መቼ እንደምትወጣና መቼ እንደምትገባ፣እንዲሁም መቼ በእኔ ላይ እንደተቆጣህ በሚገባ አውቃለሁ፤+ +29 ምክንያቱም በእኔ ላይ የተቆጣኸው ቁጣና+ ጩኸትህ ወደ ጆሮዬ ደርሷል።+ ስለዚህ ስናጌን በአፍንጫህ፣ ልጓሜንም+ በአፍህ አስገባለሁ፤በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።” +30 “‘ይህም ምልክት ይሆንሃል፦* በዚህ ዓመት የገቦውን እህል* ትበላላችሁ፤ በሁለተኛውም ዓመት ከዚያው ላይ የበቀለውን እህል ትበላ���ችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን ዘር ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁም፤ እንዲሁም ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።+ +31 ከይሁዳ ቤት ያመለጡትና በሕይወት የቀሩት ሰዎች+ ወደ ታች ሥር ይሰዳሉ፤ ወደ ላይም ያፈራሉ። +32 ከኢየሩሳሌም ቀሪዎች፣ ከጽዮን ተራራም በሕይወት የተረፉ ሰዎች ይወጣሉና።+ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።+ +33 “‘ስለዚህ ይሖዋ ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦+ “ወደዚህች ከተማ አይመጣም፤+ፍላጻም አይወረውርባትም፤ጋሻም ይዞ አይመጣባትም፤ከበባ ለማድረግም በዙሪያዋ የአፈር ቁልል አይደለድልም።”’+ +34 ‘በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤ወደዚህች ከተማ አይገባም’ ይላል ይሖዋ። +35 ‘ስለ እኔና+ ስለ አገልጋዬ ስለ ዳዊት ስል+ይህችን ከተማ እጠብቃታለሁ፤+ ደግሞም አድናታለሁ።’” +"36 የይሖዋም መልአክ ወጥቶ በአሦራውያን ሰፈር የነበሩትን 185,000 ሰዎች ገደለ። ሰዎችም በማለዳ ሲነሱ ሬሳውን አዩ።+" +37 በመሆኑም የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከዚያ ተነስቶ ወደ ነነዌ+ ተመለሰ፤ በዚያም ተቀመጠ።+ +38 ሰናክሬም በአምላኩ በኒስሮክ ቤት* እየሰገደ ሳለ አድራሜሌክና ሳሬጸር የተባሉት የገዛ ልጆቹ በሰይፍ መትተው ገደሉት፤+ ከዚያም ወደ አራራት+ ምድር ሸሽተው ሄዱ። ልጁም ኤሳርሃደን+ በእሱ ምትክ ነገሠ። +64 በአንተ የተነሳ ተራሮች ይናወጡ ዘንድምነው ሰማያትን ቀደህ በወረድክ! + 2 እሳት ጭራሮን አቀጣጥሎውኃን እንደሚያፈላ ሁሉ፣ያን ጊዜ ጠላቶችህ ስምህን ያውቃሉ፤ብሔራትም በፊትህ ይሸበራሉ! + 3 እኛ ፈጽሞ ያልጠበቅናቸውን እጅግ አስደናቂ ነገሮች ባደረግክ ጊዜ፣+አንተ ወረድክ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።+ + 4 ከጥንት ዘመን ጀምሮ፣ እሱን በተስፋ ለሚጠባበቁት* ሲል እርምጃ የወሰደከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ የሰማም ሆነ በጆሮው ያዳመጠወይም በዓይኑ ያየ ማንም የለም።+ + 5 ትክክል የሆነውን ነገር በደስታ ከሚያደርጉ፣+አንተን ከሚያስቡና መንገዶችህን ከሚከተሉ ሰዎች ጋር ተገናኝተሃል። እነሆ፣ ኃጢአት መሥራታችንን በቀጠልን ጊዜ ተቆጣህ፤+ይህን ያደረግነውም ለረጅም ጊዜ ነው። ታዲያ አሁን መዳን ይገባናል? + 6 ሁላችንም እንደረከሰ ሰው ሆነናል፤የጽድቅ ሥራችንም ሁሉ እንደ ወር አበባ ጨርቅ ነው።+ ሁላችንም እንደ ቅጠል እንጠወልጋለን፤በደላችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደናል። + 7 ስምህን የሚጠራ የለም፤አንተን የሙጥኝ ብሎ ለመያዝ የሚነሳሳ የለም፤ፊትህን ከእኛ ሰውረሃልና፤+በበደላችን የተነሳ እንድንመነምን* አድርገኸናል። + 8 አሁን ግን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ።+ እኛ ሸክላ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ፤*+ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን። + 9 ይሖዋ ሆይ፣ እጅግ አትቆጣ፤+በደላችንንም ለዘላለም አታስታውስ። እባክህ ተመልከተን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነንና። +10 የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል። ጽዮን ምድረ በዳ፣ኢየሩሳሌምም ጠፍ ምድር ሆናለች።+ +11 አባቶቻችን አንተን ያወደሱበትየቅድስናና የክብር ቤታችን*በእሳት ተቃጥሏል፤+ከፍ አድርገን እንመለከታቸው የነበሩት ነገሮች በሙሉ ፈራርሰዋል። +12 ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሁሉ ሆኖ እያለ እርምጃ ከመውሰድ ትታቀባለህ? ዝም ብለህስ ታያለህ? ደግሞስ ከልክ በላይ እንድንጎሳቆል ትፈቅዳለህ?+ +57 ጻድቁ ሞቷል፤ይህን ግን ማንም ልብ አይልም። ታማኝ ሰዎች ተወስደዋል፤*+ሆኖም ጻድቁ የተወሰደውከመከራ የተነሳ እንደሆነ* የሚያስተውል የለም። + 2 እሱ ሰላም ያገኛል። በቅንነት የሚሄዱ ሁሉ አልጋቸው* ላይ ያርፋሉ። + 3 “ይሁንና እናንተ የአስማተኛዋ ወንዶች ልጆች፣የአመንዝራና የዝሙት አዳሪ ልጆች፣ኑ ወደዚህ ቅረቡ፦ + 4 የምታሾፉት በማን ላይ ነው? አፋችሁን የምትከፍቱትና ምላሳችሁን የምታወጡትስ በማን ላይ ነው? እናንተ የዓመፅ ልጆች፣የሐሰትም* ልጆች አይደላችሁም?+ + 5 በትላልቅ ዛፎች መካከል፣ቅጠሉ በተንዠረገገም ዛፍ ሥር ሁሉ በስሜት የተቃጠላችሁ፣+በሸለቆዎች* ውስጥ፣ በቋጥኞች መካከልልጆችን የምታርዱ አይደላችሁም?+ + 6 በሸለቆው* ውስጥ ያሉት ለስላሳ ድንጋዮች ድርሻዎችሽ ናቸው።+ አዎ፣ እነዚህ ዕጣ ፋንታዎችሽ ናቸው። ለእነሱም ጭምር የመጠጥ መባ አፍስሰሻል፤ ስጦታም አቅርበሻል።+ ታዲያ እኔ በእነዚህ ነገሮች ደስ ልሰኝ ይገባል?* + 7 በረጅሙና ከፍ ባለው ተራራ ላይ አልጋሽን አነጠፍሽ፤+መሥዋዕት ለማቅረብም ወደዚያ ወጣሽ።+ + 8 ከበሩና ከመቃኑ ጀርባ የመታሰቢያ ምልክትሽን አደረግሽ። እኔን ተውሽኝ፤ እርቃንሽንም ገለጥሽ፤ወደ ላይ ወጣሽ፤ መኝታሽንም አሰፋሽ። ከእነሱም ጋር ቃል ኪዳን ገባሽ። በአልጋቸው ላይ አብረሽ መተኛት ወደድሽ፤+የወንድ ብልትም* አፍጥጠሽ አየሽ። + 9 ዘይትና ብዛት ያለው ሽቶ ይዘሽወደ ሜሌክ* ወረድሽ። መልእክተኞችሽን ወደ ሩቅ ቦታ ላክሽ፤በመሆኑም ወደ መቃብር* ወረድሽ። +10 ብዛት ያላቸውን መንገዶችሽን በመከተል ደከምሽ፤ሆኖም ‘ተስፋ የለውም!’ አላልሽም። ጉልበትሽ ታደሰ። ተስፋ ያልቆረጥሽው* ለዚህ ነው። +11 መዋሸት የጀመርሽው+ ማን አስፈርቶሽ፣ማንስ ስጋት አሳድሮብሽ ነው? እኔን አላስታወስሽም።+ ልብ ያልሽውም ነገር የለም።+ እኔ ዝም አላልኩም? ደግሞስ ከመናገር አልተቆጠብኩም?*+ በመሆኑም እኔን አልፈራሽም። +12 ‘ጽድቅሽን’+ እና ሥራሽን+ እናገራለሁ፤እነሱም አይጠቅሙሽም።+ +13 እርዳታ ለማግኘት በምትጮኺበት ጊዜየሰበሰብሻቸው ጣዖቶች አይታደጉሽም።+ ነፋስ ሁሉንም ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤እስትንፋስ ይዟቸው ይሄዳል፤እኔን መጠጊያ የሚያደርግ ግን ምድሪቱን ይወርሳል፤ቅዱስ ተራራዬም ርስቱ ይሆናል።+ +14 እንዲህ ይባላል፦ ‘መንገድ ሥሩ! መንገድ ሥሩ! መንገዱን አዘጋጁ!+ ሕዝቤ ከሚሄድበት መንገድ ላይ ማንኛውንም እንቅፋት አስወግዱ።’” +15 ለዘላለም የሚኖረውና+ ስሙ ቅዱስ የሆነው፣+ከፍ ከፍ ያለውና እጅግ የከበረው እንዲህ ይላልና፦ “ከፍ ባለውና ቅዱስ በሆነው ስፍራ እኖራለሁ፤+ደግሞም የተሰበረ ልብ ካለውና መንፈሱ ከተደቆሰው ጋር እሆናለሁ፤ይህም የችግረኞችን መንፈስ አነሳሳ ዘንድ፣የተሰበረ ልብ ያላቸውንም አነቃቃ ዘንድ ነው።+ +16 ለዘላለም አልቃወማቸውም፤ወይም ለዘለቄታው አልቆጣም፤+በእኔ የተነሳ የሰው መንፈስ፣እኔ የሠራኋቸው እስትንፋስ ያላቸው ፍጥረታትም እንኳ ይዝላሉና።+ +17 በማጭበርበር ጥቅም ለማግኘት ሲል በፈጸመው ኃጢአት እጅግ ተቆጣሁ፤+በመሆኑም መታሁት፤ ፊቴን ሰወርኩ፤ ተቆጣሁም። እሱ ግን እንደ ከዳተኛ የልቡን መንገድ ተከትሎ መሄዱን ገፋበት።+ +18 መንገዶቹን አይቻለሁ፤ሆኖም እፈውሰዋለሁ፤+ እንዲሁም እመራዋለሁ፤+ለእሱም ሆነ ላዘኑ ወገኖቹ መጽናኛን እመልሳለሁ።”*+ +19 “የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ። በሩቅም ሆነ በቅርብ ያለው ዘላቂ ሰላም ያገኛል፤+እኔም እፈውሰዋለሁ” ይላል ይሖዋ። +20 “ክፉዎች ግን ጸጥ ማለት እንደማይችል የሚናወጥ ባሕር ናቸው፤ውኃውም የባሕር ውስጥ ዕፀዋትንና ጭቃን ያወጣል። +21 ክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል አምላኬ።+ +40 “አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ” ይላል አምላካችሁ።+ + 2 “ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤*የግዳጅ አገልግሎቷ እንዳበቃናየበደሏ ዋጋ እንደተከፈለ ንገሯት።+ ለሠራችው ኃጢአት ሁሉ ከይሖዋ እጅ ሙሉ* ዋጋ ተቀብላለች።”+ + 3 አንድ ሰው በምድረ በዳ እንዲህ ብሎ ይጮኻል፦ “የይሖዋን መንገድ ጥረጉ!*+ በበረሃ ለአምላካችን አውራ ጎዳናውን+ አቅኑ።+ + 4 ሸለቆው ሁሉ ይሞላ፤ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝ��� ይበል። ወጣ ገባውም መሬት ይስተካከል፤ጎርበጥባጣውም ምድር ሸለቋማ ሜዳ ይሁን።+ + 5 የይሖዋ ክብር ይገለጣል፤+ሥጋም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፤*+የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።” + 6 አዳምጥ! አንድ ሰው “ጮክ ብለህ ተናገር!” አለ። ሌላውም “ምን ብዬ ልናገር?” አለ። “ሥጋ ሁሉ* ለምለም ሣር ነው። ታማኝ ፍቅሩ ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው።+ + 7 ለምለሙ ሣር ይደርቃል፤አበባው ይጠወልጋል፤+ምክንያቱም የይሖዋ እስትንፋስ* ይነፍስበታል።+ ሕዝቡ በእርግጥ ለምለም ሣር ነው። + 8 ለምለሙ ሣር ይደርቃል፤አበባው ይጠወልጋል፤የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”+ + 9 አንቺ ለጽዮን ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣+ከፍ ወዳለ ተራራ ውጪ። አንቺ ለኢየሩሳሌም ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣ድምፅሽን በኃይል ከፍ አድርጊ። ድምፅሽን ከፍ አድርጊ፤ አትፍሪ። ለይሁዳ ከተሞች “እነሆ፣ አምላካችሁ” በማለት አስታውቂ።+ +10 እነሆ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በኃይል ይመጣል፤ክንዱም ስለ እሱ ይገዛል።+ እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ።+ +11 መንጋውን እንደ እረኛ ይንከባከባል።+ ግልገሎቹን በክንዱ ይሰበስባል፤በእቅፉም ይሸከማቸዋል። ግልገሎቻቸውን የሚያጠቡትን በቀስታ ይመራል።+ +12 ውኃዎችን በእፍኙ የሰፈረ፣+ሰማያትን በስንዝሩ* የለካ፣ የምድርን አፈር ሰብስቦ በመስፈሪያ የያዘ+ወይም ተራሮችን በመለኪያ፣ኮረብቶችንም በሚዛን የመዘነ ማን ነው? +13 የይሖዋን መንፈስ የለካ*እንዲሁም አማካሪው ሆኖ ሊያስተምረው የሚችል ማን ነው?+ +14 ማስተዋል ለማግኘት ከማን ጋር ተማከረ?የፍትሕን መንገድ ያስተማረውአሊያም እውቀትን ያካፈለው ማን ነው?ደግሞስ የእውነተኛ ማስተዋልን ጎዳና ያሳየው ማን ነው?+ +15 እነሆ፣ ብሔራት በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው፤በሚዛንም ላይ እንዳለ አቧራ ይቆጠራሉ።+ እነሆ፣ ደሴቶችን እንደ ደቃቅ አፈር ያነሳቸዋል። +16 እሳት መንደዱን እንዲቀጥል ለማድረግ የሊባኖስ ዛፎች እንኳ አይበቁም፤*በውስጡም ያሉት የዱር እንስሳት የሚቃጠል መባ ለማቅረብ በቂ አይደሉም። +17 ብሔራት ሁሉ በፊቱ የሌሉ ያህል ናቸው፤+በእሱም ዘንድ ከምንም የማይቆጠሩና ዋጋ ቢስ ናቸው።+ +18 አምላክን ከማን ጋር ታወዳድሩታላችሁ?+ ከየትኛውስ ምስል ጋር ታነጻጽሩታላችሁ?+ +19 የእጅ ጥበብ ባለሙያ ብረት አቅልጦ ጣዖት* ይሠራል፤አንጥረኛውም በወርቅ ይለብጠዋል፤+የብር ሰንሰለትም ይሠራለታል። +20 አንድ ሰው መዋጮ አድርጎ ለመስጠትየማይበሰብስ ዛፍ ይመርጣል።+ የማይወድቅ ምስል ቀርጾ እንዲያዘጋጅለትበእጅ ጥበብ ሥራ የተካነ ባለሙያ ይፈልጋል።+ +21 ይህን አታውቁም? ደግሞስ አልሰማችሁም? ከመጀመሪያ አንስቶስ አልተነገራችሁም? የምድር መሠረት ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን ማስረጃስ አላስተዋላችሁም?+ +22 እሱ ክብ* ከሆነችው ምድር በላይ ይኖራል፤+በእሷም ላይ የሚኖሩት እንደ ፌንጣ ናቸው። እሱ ሰማያትን እንደ ስስ ጨርቅ ይዘረጋል፤እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይወጥራቸዋል።+ +23 ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ያስወግዳል፤የምድር ፈራጆችንም* እንዳልነበሩ ያደርጋል። +24 ገና እንደተተከለ፣ገና እንደተዘራ፣ግንዱም በአፈር ውስጥ ሥር እንዳልሰደደ ተክል ናቸው፤ሲነፍስባቸውም ይደርቃሉ፤ነፋስም እንደ ገለባ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።+ +25 “እኩያው እሆን ዘንድ ከማን ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱሱ። +26 “ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንስታችሁ ተመልከቱ። እነዚህን ነገሮች የፈጠረ ማን ነው?+ እንደ ሠራዊት በቁጥር የሚመራቸው እሱ ነው፤ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።+ ገደብ ከሌለው ብርቱ ጉልበቱና ከሚያስደምመው ኃይሉ+ የተነሳአንዳቸውም ��ይጎድሉም። +27 ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ፣‘መንገዴ ከይሖዋ ተሰውሯል፤ከአምላክ ፍትሕ አላገኝም’ ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?+ +28 ይህን አታውቅም? ደግሞስ አልሰማህም? የምድር ዳርቻዎች ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነው።+ እሱ ፈጽሞ አይደክምም ወይም አይዝልም።+ ማስተዋሉ አይመረመርም።*+ +29 ለደከመው ኃይል፣ጉልበት ለሌላቸውም የተሟላ ብርታት* ይሰጣል።+ +30 ወንዶች ልጆች ይደክማሉ፤ ደግሞም ይዝላሉ፤ወጣቶችም ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤ +31 ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ኃይላቸው ይታደሳል። እንደ ንስር በክንፍ ወደ ላይ ይወጣሉ።+ ይሮጣሉ፣ አይዝሉም፤ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።”+ +16 ከሴላ በምድረ በዳው በኩል አድርጋችሁበጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ለሚገኘውለምድሪቱ ገዢ አውራ በግ ላኩ። + 2 የሞዓብ ሴቶች ልጆች በአርኖን+ መልካ*ከጎጆው እንደተባረረ ወፍ ይሆናሉ።+ + 3 “ምክር ለግሱ፤ ውሳኔውን ተግባራዊ አድርጉ። እኩለ ቀን ላይ እንደ ምሽት ጨለማ ያለ ጥላ አጥሉ። የተበተኑትን ሸሽጉ፤ የሚሸሹትንም አሳልፋችሁ አትስጡ። + 4 ሞዓብ ሆይ፣ የተበተኑት ሕዝቦቼ በአንተ ውስጥ ይኑሩ። ከአጥፊው+ የተነሳ መሸሸጊያ ቦታ ሁንላቸው። ጨቋኙ ፍጻሜው ይመጣል፤ጥፋቱም ያበቃል፤ሌሎችን የሚረግጡትም ከምድር ገጽ ይጠፋሉ። + 5 ከዚያም ዙፋን በታማኝ ፍቅር ጸንቶ ይመሠረታል። በዳዊት ድንኳን ላይ በዙፋኑ የሚቀመጠው ታማኝ ይሆናል፤+በትክክል ይፈርዳል፤ ጽድቅንም በቶሎ ያስፈጽማል።”+ + 6 ስለ ሞዓብ ኩራት ይኸውም በጣም ኩሩ እንደሆነ ሰምተናል፤+ስለ ትዕቢቱ፣ ስለ ኩራቱና ስለ ታላቅ ቁጣው ሰምተናል፤+ይሁንና ድንፋታው ሁሉ ከንቱ ይሆናል። + 7 በመሆኑም ሞዓብ፣ ስለ ሞዓብ ዋይ ዋይ ይላል፤አዎ፣ ሁሉም ዋይ ዋይ ይላሉ።+ የተመቱት ሰዎች ስለ ቂርሃረሰት+ የዘቢብ ቂጣ ያለቅሳሉ። + 8 በሃሽቦን+ እርከኖች ላይ የሚገኙት ተክሎች ጠውልገዋልና፤የሲብማ+ የወይን ተክሎች ረግፈዋል፤የብሔራት ገዢዎች ቀያይ ቅርንጫፎቹን* ረጋግጠዋል፤እስከ ያዜር+ ደርሰዋል፤በምድረ በዳውም ተንሰራፍተዋል። ቀንበጦቹም ተዘርግተው እስከ ባሕሩ ድረስ ዘልቀዋል። + 9 ስለዚህ ስለ ያዜር እንዳለቀስኩት ለሲብማ የወይን ተክልም አለቅሳለሁ። ሃሽቦንና ኤልዓሌ+ ሆይ፣ በእንባዬ አርሳችኋለሁ፤ምክንያቱም የበጋ ፍሬና መከር በምትሰበስቡበት ወቅት የሚሰማው ጩኸት አብቅቷል።* +10 ሐሴትና ደስታ ከፍራፍሬ እርሻው ተወስዷል፤በወይን እርሻዎቹም የደስታ ዝማሬ ወይም ጩኸት አይሰማም።+ ወይን የሚረግጥ ሰው ከእንግዲህ በወይን መጭመቂያው ውስጥ ወይን አይረግጥም፤ጩኸቱን ሁሉ ጸጥ አሰኝቻለሁና።+ +11 ከዚህም የተነሳ እንደሚርገበገብ የበገና ክርውስጤ ስለ ሞዓብ፣አንጀቴም ስለ ቂርሃረሰት ይታወካል።+ +12 ሞዓብ በከፍታ ስፍራው ላይ ራሱን ቢያደክምም እንኳ ዋጋ የለውም፤ ለመጸለይ ወደ መቅደሱ ቢመጣም ምንም ማድረግ አይችልም።+ +13 ይሖዋ አስቀድሞ ስለ ሞዓብ የተናገረው ቃል ይህ ነው። +14 ደግሞም ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልክ እንደ ቅጥር ሠራተኛ የሥራ ዘመን፣* በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሞዓብ ክብር በብዙ ብጥብጥ ይዋረዳል፤ የሚተርፉትም በጣም ጥቂትና እዚህ ግቡ የማይባሉ ይሆናሉ።”+ +59 እነሆ፣ የይሖዋ እጅ ማዳን ይሳናት ዘንድ አላጠረችም፤+ጆሮውም መስማት ይሳናት ዘንድ አልደነዘዘችም።*+ + 2 ከዚህ ይልቅ ከአምላካችሁ ያለያያችሁ የገዛ በደላችሁ ነው።+ የፈጸማችሁት ኃጢአት ፊቱን እንዲሰውርባችሁ አድርጎታል፤እናንተን ለመስማትም ፈቃደኛ አይደለም።+ + 3 እጆቻችሁ በደም፣ጣቶቻችሁም በበደል ተበክለዋልና።+ ከንፈሮቻችሁ ውሸት ይናገራሉ፤+ አንደበታችሁም ክፋትን ያጉተመትማ��። + 4 ጽድቅን የሚጣራ ማንም የለም፤+እውነትን ይዞ ፍርድ ቤት የሚቀርብ የለም። በማይጨበጥ* ነገር ይታመናሉ፤+ ፍሬ ቢስ ነገሮችን ይናገራሉ። ችግርን ይፀንሳሉ፤ የሚጎዳ ነገርም ይወልዳሉ።+ + 5 የመርዘኛ እባብን እንቁላሎች ይቀፈቅፋሉ፤የሸረሪት ድርም ያደራሉ።+ እንቁላሎቻቸውንም የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤እንቁላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል። + 6 የሸረሪት ድራቸው ልብስ ሆኖ አያገለግልም፤በሚሠሩትም ነገር ራሳቸውን መሸፈን አይችሉም።+ ሥራቸው ጉዳት የሚያስከትል ነው፤በእጃቸውም የዓመፅ ሥራ አለ።+ + 7 እግሮቻቸው ክፋት ለመፈጸም ይሮጣሉ፤ንጹሕ ደም ለማፍሰስም ይጣደፋሉ።+ የሚያስቡት ጎጂ ሐሳብ ነው፤በመንገዳቸው ላይ ጥፋትና መከራ አለ።+ + 8 የሰላምን መንገድ አያውቁም፤በጎዳናቸውም ፍትሕ የለም።+ መንገዳቸውን ጠማማ ያደርጋሉ፤በዚያም የሚሄድ ሁሉ ሰላምን አያውቅም።+ + 9 ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ከእኛ ራቀ፤ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም። ብርሃን ይሆናል ብለን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ሆኖም ጨለማ ሆነ፤ጸዳልን ተጠባበቅን፤ ሆኖም በጨለማ እንመላለሳለን።+ +10 ልክ እንደ ዓይነ ስውራን ቅጥሩን እየዳበስን እንሄዳለን፤ዓይን እንደሌላቸው ሰዎች እንደናበራለን።+ በምሽት ጨለማ እንደሚሆነው በቀትር ብርሃን እንሰናከላለን፤በብርቱ ሰዎች መካከል እንደ ሙታን ነን። +11 ሁላችንም እንደ ድቦች እናጉረመርማለን፤እንደ ርግቦችም በሐዘን እናልጎመጉማለን። ፍትሕን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ነገር ግን አላገኘንም፤መዳንን ተጠባበቅን፤ ነገር ግን ከእኛ ርቋል። +12 ዓመፃችን በፊትህ በዝቷልና፤+የሠራነው ኃጢአት ሁሉ ይመሠክርብናል።+ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፤በደላችንን በሚገባ እናውቃለን።+ +13 ሕግ ተላልፈናል፤ ይሖዋንም ክደናል፤ለአምላካችን ጀርባችንን ሰጥተናል። ግፍንና ዓመፅን ተናግረናል፤+በልባችን ውሸትን ፀንሰናል፤ እንዲሁም የሐሰት ቃላትን አጉተምትመናል።+ +14 ፍትሕ ወደ ኋላ ተመልሷል፤+ጽድቅም በሩቅ ቆሟል፤+እውነት* በአደባባይ ተሰናክሏልና፤ቀና የሆነውም ነገር ወደዚያ መግባት አልቻለም። +15 እውነት* ጠፍቷል፤+ከክፋት የራቀ ሁሉ ለጥፋት ተዳርጓል። ይሖዋ ይህን አየ፤ ደስም አልተሰኘም፤*ፍትሕ አልነበረምና።+ +16 እርዳታ የሚሰጥ ሰው እንደሌለ አየ፤ጣልቃ የሚገባ ባለመኖሩም ተገረመ፤በመሆኑም የገዛ ክንዱ መዳን አስገኘ፤*የገዛ ጽድቁም ድጋፍ ሆነለት። +17 ከዚያም ጽድቅን እንደ ጥሩር ለበሰ፤በራሱም ላይ የመዳንን* ቁር አደረገ።+ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤+ቅንዓትንም እንደ ካባ* ተጎናጸፈ። +18 ላደረጉት ነገር ብድራት ይከፍላቸዋል፦+ ቁጣን ለባላጋራዎቹ፣ በቀልን ለጠላቶቹ ይከፍላል።+ ለደሴቶችም የሚገባቸውን ዋጋ ይከፍላቸዋል። +19 በፀሐይ መግቢያ ያሉ የይሖዋን ስም ይፈራሉ፤በፀሐይ መውጫም ያሉ ክብሩን ይፈራሉ፤እሱ የይሖዋ መንፈስ እንደሚነዳውኃይለኛ ወንዝ ሆኖ ይመጣልና። +20 “ጽዮንን፣ በደል መፈጸም ያቆሙትንምየያዕቆብ ቤት ሰዎች የሚቤዥ+ ይመጣል”+ ይላል ይሖዋ።+ +21 “በእኔ በኩል ከእነሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ይህ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “በአንተ ላይ ያለው መንፈሴና በአፍህ ያኖርኩት ቃሌ፣ ከአንተ አፍ ወይም ከልጆችህ* አፍ ወይም ከልጅ ልጆችህ* አፍ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም አይወሰዱም” ይላል ይሖዋ። +51 “እናንተ ጽድቅን የምትከታተሉ፣ይሖዋንም የምትፈልጉ ስሙኝ። ተፈልፍላችሁ የወጣችሁበትን ዓለት፣ተቆፍራችሁ የወጣችሁበትንም ካባ ተመልከቱ። + 2 አባታችሁን አብርሃምን፣የወለደቻችሁንም* ሣራን+ ተመልከቱ። እሱ በጠራሁት ጊዜ ብቻውን ነበርና፤+እኔም ባረክሁት፤ ደግሞም አበዛሁት።+ + 3 ይሖዋ ጽዮንን ያጽናናታልና።+ ፍርስራሾቿ�� ሁሉ ያጽናናል፤+ምድረ በዳዋንም እንደ ኤደን፣+በረሃማ ሜዳዋንም እንደ ይሖዋ የአትክልት ስፍራ ያደርጋል።+ በእሷም ውስጥ ሐሴትና ታላቅ ደስታእንዲሁም ምስጋናና ደስ የሚያሰኝ መዝሙር ይገኛሉ።+ + 4 ሕዝቤ ሆይ፣ በጥሞና አዳምጡኝ፤አንተም የእኔ ብሔር፣ ጆሮህን ስጠኝ።+ ሕግ ከእኔ ይወጣልና፤+የፍትሕ እርምጃዬም ለሕዝቦች እንደ ብርሃን ጸንቶ እንዲቆም አደርጋለሁ።+ + 5 ጽድቄ ቀርቧል።+ ማዳኔ ወደ እናንተ ይመጣል፤+ክንዴም በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል።+ ደሴቶች በእኔ ተስፋ ያደርጋሉ፤+ክንዴንም* ይጠባበቃሉ። + 6 ዓይኖቻችሁን ወደ ሰማያት አንሱ፤ወደታችም ወደ ምድር ተመልከቱ። ሰማያት እንደ ጭስ በነው ይጠፋሉና፤ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፤ነዋሪዎቿም እንደ ትንኝ ይረግፋሉ። ማዳኔ ግን ለዘላለም ይኖራል፤+ጽድቄም ፈጽሞ አይከስምም።*+ + 7 እናንተ ጽድቅን የምታውቁ፣ሕጌንም* በልባችሁ ያኖራችሁ ሰዎች፣+ ስሙኝ። ሟች የሆኑ ሰዎች የሚሰነዝሩትን ትችት አትፍሩ፤ስድባቸውም አያሸብራችሁ። + 8 ብል እንደ ልብስ ይበላቸዋልና፤የልብስ ብል* እንደ ሱፍ ጨርቅ ይበላቸዋል።+ ሆኖም ጽድቄ ለዘላለም፣ማዳኔም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።”+ + 9 የይሖዋ ክንድ ሆይ፣+ተነስ! ተነስ! ብርታትንም ልበስ! ከረጅም ጊዜ በፊት፣ በጥንቶቹ ትውልዶች ዘመን እንደሆነው ተነስ። ረዓብን*+ ያደቀከው፣ግዙፉንም የባሕር ፍጥረት የወጋኸው አንተ አይደለህም?+ +10 ባሕሩን፣ የተንጣለለውን የጥልቁን ውኃ ያደረቅከው አንተ አይደለህም?+ የተቤዠሃቸው ሰዎች እንዲሻገሩ ጥልቁን ባሕር መንገድ ያደረግከው አንተ አይደለህም?+ +11 ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ።+ በእልልታ ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤+ማብቂያ የሌለውንም ደስታ እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+ ሐሴት ያደርጋሉ፤ ታላቅ ደስታም ያገኛሉ፤ሐዘንና ሲቃም ከእነሱ ይሸሻሉ።+ +12 “የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ።+ ሟች የሆነውን ሰው፣እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ የምትፈሪው ለምንድን ነው?+ +13 ሰማያትን የዘረጋውንና+ የምድርን መሠረት የጣለውንሠሪህን ይሖዋን+ የምትረሳው ለምንድን ነው? ደግሞም ጨቋኙ* ሊያጠፋህ የተዘጋጀ ይመስልከእሱ ቁጣ የተነሳ ቀኑን ሙሉ በፍርሃት ተውጠህ ነበር። ታዲያ አሁን የጨቋኙ ቁጣ የት አለ? +14 በሰንሰለት ታስሮ ያጎነበሰው እስረኛ ቶሎ ይፈታል፤+ሞትን አያይም፤ ወደ ጉድጓድም አይወርድም፤የሚበላውም ነገር አያጣም። +15 ባሕሩን የማናውጥና ኃይለኛ ማዕበል የማስነሳ፣+እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ፤ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።+ +16 ሰማያትን እዘረጋና የምድርን መሠረት እጥል ዘንድ፣+ጽዮንንም ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’+ እል ዘንድቃሌን በአፍህ አኖራለሁ፤በእጄም ጥላ እጋርድሃለሁ።+ +17 ከይሖዋ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽኢየሩሳሌም ሆይ፣ ተነሺ! ተነሺ! ቁሚ።+ ዋንጫውን ጠጥተሻል፤የሚያንገዳግደውን ጽዋ ጨልጠሻል።+ +18 ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል አንድም የሚመራት የለም፤ካሳደገቻቸውም ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል እጇን ይዞ የወሰዳት ማንም የለም። +19 እነዚህ ሁለት ነገሮች ደርሰውብሻል። ማን ያስተዛዝንሻል? ጥፋትና ውድመት እንዲሁም ረሃብና ሰይፍ መጥቶብሻል!+ ማንስ ያጽናናሻል?+ +20 ወንዶች ልጆችሽ ራሳቸውን ስተዋል።+ በመረብ እንደተያዘ የዱር በግበየመንገዱ ማዕዘን ላይ* ይተኛሉ። የይሖዋ ቁጣ፣ የአምላክሽም ተግሣጽ ሙሉ በሙሉ ወርዶባቸዋል።” +21 ስለዚህ አንቺ የተጎሳቆልሽና ያለወይን ጠጅ የሰከርሽ ሴት ሆይ፣እባክሽ ይህን ስሚ። +22 ለሕዝቡ የሚሟገተው ጌታሽና አምላክሽ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የሚያንገዳግደውን ጽዋ፣+ ይኸውም ዋንጫውን፣የቁጣዬን ጽዋ ከእጅሽ እወስዳለሁ፤ከእንግዲህ ዳግመኛ አት��ጪም።+ +23 ጽዋውን ‘በላይሽ ላይ እንድንሻገር አጎንብሺልን!’ ባሉሽ፣*አንቺን በሚያሠቃዩት እጅ ላይ አደርገዋለሁ፤+ አንቺም ጀርባሽን እንደ መሬት፣እንደሚሄዱበትም መንገድ አደረግሽላቸው።” +6 ንጉሥ ዖዝያ በሞተበት ዓመት+ ይሖዋን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤+ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። +2 ሱራፌልም ከእሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፎች ነበሯቸው። እያንዳንዱ* በሁለቱ ክንፍ ፊቱን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ እግሩን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ ደግሞ ይበር ነበር። + 3 አንዳቸውም ሌላውን እንዲህ ይሉ ነበር፦ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው።+ መላዋ ምድር በክብሩ ተሞልታለች።” +4 ከድምፁ ጩኸት* የተነሳ የበሩ መቃኖች ተናወጡ፤ ቤቱም በጭስ ተሞላ።+ + 5 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ወዮልኝ! ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ስለሆንኩናየምኖረውም ከንፈራቸው በረከሰ ሕዝብ+ መካከል ስለሆነበቃ መሞቴ ነው፤*ዓይኖቼ ንጉሡን፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ራሱን አይተዋልና!” +6 በዚህ ጊዜ ከሱራፌል አንዱ ወደ እኔ እየበረረ መጣ፤ እሱም ከመሠዊያው ላይ በጉጠት ያነሳውን ፍም+ በእጁ ይዞ ነበር።+ +7 አፌንም ነክቶ እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ ይህ ከንፈሮችህን ነክቷል። በደልህ ተወግዶልሃል፤ኃጢአትህም ተሰርዮልሃል።” +8 ከዚያም የይሖዋ ድምፅ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?”+ ሲል ሰማሁ። እኔም “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!” አልኩ።+ + 9 እሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፦ “ሄደህ ይህን ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ደጋግማችሁ ትሰማላችሁ፣ነገር ግን አታስተውሉም፤ደጋግማችሁ ታያላችሁ፣ነገር ግን ምንም እውቀት አታገኙም።’+ +10 በዓይናቸው እንዳያዩ፣በጆሯቸውም እንዳይሰሙ፣ልባቸውም እንዳያስተውል፣ተመልሰውም እንዳይፈወሱየዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤+ጆሯቸውንም ድፈን፤+ዓይናቸውንም ሸፍን።”+ +11 በዚህ ጊዜ “ይሖዋ ሆይ፣ እስከ መቼ ነው?” አልኩ። እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ከተሞች እስኪፈራርሱና የሚኖርባቸው እስኪያጡ፣ቤቶችም ሰው አልባ እስኪሆኑ፣ምድሪቱም እስክትጠፋና ባድማ እስክትሆን ድረስ ነው፤+ +12 ይሖዋም ሰዎችን ወደ ሩቅ ቦታ እስከሚሰድ፣+የምድሪቱም በረሃነት በእጅጉ እስኪስፋፋ ድረስ ነው። +13 “ይሁንና በእሷ ውስጥ አንድ አሥረኛ ይቀራል፤ እሱም በድጋሚ ይቃጠላል፤ ከተቆረጡ በኋላ ጉቷቸው እንደሚቀር እንደ ትልቅ ዛፍና እንደ ባሉጥ ዛፍ ይሆናል፤ በምድሪቱ ላይ የቀረው ጉቶ የተቀደሰ ዘር ይሆናል።” +25 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ። ድንቅ ነገሮችን ስላደረግክና+ከጥንት ዘመን ጀምሮ ያሰብካቸውን ነገሮች*+በታማኝነትና+ እምነት በሚጣልበት መንገድ ስለፈጸምክከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ። + 2 ከተማዋን የድንጋይ ቁልል፣የተመሸገችውንም ከተማ የፍርስራሽ ክምር አድርገሃልና። የባዕዳኑ ማማ፣ ከተማ መሆኑ አብቅቶለታል፤ከተማዋ በምንም ዓይነት ዳግመኛ አትገነባም። + 3 ከዚህም የተነሳ ኃያል የሆነ ሕዝብ ያከብርሃል፤የጨቋኝ ብሔራት ከተማም ትፈራሃለች።+ + 4 ለችግረኛው ምሽግ ሆነሃልና፤ለድሃውም ከደረሰበት ጭንቀት መሸሸጊያ፣+ከውሽንፍርም መጠለያ፣ከፀሐይ ንዳድም ጥላ ሆነሃል።+ የጨቋኞች ቁጣ ከግንብ ጋር እንደሚላተም ውሽንፍር በሚሆንበት ጊዜ ጥበቃ ታደርጋለህ፤ + 5 ውኃ በተጠማ ምድር እንዳለ ሙቀትየባዕዳንን ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ። ሙቀት በደመና ጥላ እንደሚበርድ ሁሉየጨቋኞችም ዝማሬ ጸጥ ረጭ ይላል። + 6 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በዚህ ተራራ+ ላይ ለሕዝቦች ሁሉምርጥ ምግቦች* የሚገኙበት ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤+ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ፣መቅኒ የሞላባቸው ምርጥ ምግቦችእ���ዲሁም የተጣራና ጥሩ የወይን ጠጅ የሚቀርቡበት ታላቅ ግብዣ ያደርጋል። + 7 በዚህ ተራራ ላይ ሕዝቦችን ሁሉ የሸፈነውን ከፈንእንዲሁም ብሔራትን ሁሉ ተብትቦ የያዘውን መሸፈኛ ያስወግዳል።* + 8 ሞትን ለዘላለም ይውጣል፤*+ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል።*+ በሕዝቡ ላይ የደረሰውን ነቀፋ ከመላው ምድር ያስወግዳል፤ይሖዋ ራሱ ይህን ተናግሯልና። + 9 በዚያም ቀን እንዲህ ይላሉ፦ “እነሆ፣ አምላካችን ይህ ነው!+ እሱን ተስፋ አድርገናል፤+እሱም ያድነናል።+ ይሖዋ ይህ ነው! እሱን ተስፋ አድርገናል። በእሱ ማዳን ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ።”+ +10 የይሖዋ እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋልና፤+ጭድ በፍግ ክምር ላይ እንደሚረገጥሞዓብም በስፍራው እንዲሁ ይረገጣል።+ +11 አንድ ዋናተኛ በሚዋኝበት ጊዜ በእጆቹ ውኃውን እንደሚመታእሱም እጁን ዘርግቶ ሞዓብን ይመታዋል፤በእጆቹ በጥበብ በመምታትትዕቢቱን ያበርድለታል።+ +12 የተመሸገውን ከተማከረጃጅም የመከላከያ ግንቦችህ ጋር ያፈርሳል፤ምድር ላይ ጥሎ ከአፈር ይደባልቀዋል። +33 አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣+ክህደት ሳይፈጸምብህ ክህደት የምትፈጽም ወዮልህ! ማጥፋትህን እንዳጠናቀክ አንተም ትጠፋለህ።+ ክህደት መፈጸምህን እንዳበቃህ ትካዳለህ። + 2 ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየን።+ በአንተ ተስፋ አድርገናል። በየማለዳው በክንድህ ደግፈን፤*+አዎ፣ በጭንቅ ጊዜ አዳኛችን ሁን።+ + 3 የድምፅህን ነጎድጓድ ሲሰሙ ሕዝቦች ይሸሻሉ። በምትነሳበት ጊዜ ብሔራት ይበታተናሉ።+ + 4 የማይጠግቡ አንበጦች በሚሰበሰቡበት ጊዜ እንደሚሆነው ከእናንተም የሚወሰደው ምርኮ እንዲሁ ይሰበሰባል፤ሰዎች እንደ አንበጣ መንጋ ምርኮውን ይቀራመቱታል። + 5 ይሖዋ ከፍ ከፍ ይላል፤በከፍታ ቦታ ይኖራልና። ጽዮንን በፍትሕና በጽድቅ ይሞላል። + 6 እሱ የዘመንህ መተማመኛ ነው፤የመዳን፣+ የጥበብና የእውቀት ብዛት እንዲሁም ይሖዋን መፍራት፣+ይህ የእሱ ውድ ሀብት ነው። + 7 እነሆ፣ ጀግኖቻቸው በጎዳና ላይ ይጮኻሉ፤የሰላም መልእክተኞቹም አምርረው ያለቅሳሉ። + 8 አውራ ጎዳናዎቹ ጭር ብለዋል፤በመንገድ ላይ የሚጓዝ ሰው የለም። እሱ* ቃል ኪዳኑን አፍርሷል፤ከተሞቹን ንቋል፤ሟች ለሆነው ሰው ደንታ የለውም።+ + 9 ምድሪቱ አዘነች፤* ጠወለገችም። ሊባኖስ ተዋረደ፤+ እንዲሁም በሰበሰ። ሳሮን እንደ በረሃ ሆነች፤ባሳንና ቀርሜሎስም ቅጠላቸውን አረገፉ።+ +10 “አሁን እነሳለሁ” ይላል ይሖዋ፤“አሁን ራሴን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤+አሁን ራሴን አከብራለሁ። +11 ደረቅ ሣር ትፀንሳላችሁ፤ ገለባንም ትወልዳላችሁ። የገዛ መንፈሳችሁም እንደ እሳት ይበላችኋል።+ +12 ሕዝቦችም እንደተቃጠለ ኖራ ይሆናሉ። እንደተቆረጠ እሾህ በእሳት ይጋያሉ።+ +13 እናንተ በሩቅ ያላችሁ፣ የማደርገውን ስሙ! እናንተም በቅርብ ያላችሁ፣ ለኃይሌ እውቅና ስጡ! +14 በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች እጅግ ፈሩ፤+ከሃዲዎቹም ብርክ ያዛቸው፦ ‘ከእኛ መካከል የሚባላ እሳት ባለበት ቦታ መኖር የሚችል ማን ነው?+ ከእኛስ መካከል ከማይጠፋ የእሳት ነበልባል ጋር መኖር የሚችል ማን ነው?’ +15 ዘወትር በጽድቅ የሚመላለስ፣+ቅን+ የሆነውን ነገር የሚናገር፣በማታለልና በማጭበርበር የሚገኝን ጥቅም የሚጠላ፣ጉቦ ከመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣+ደም ለማፍሰስ የሚጠነሰስን ሴራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍንእንዲሁም ክፉ የሆነውን ላለማየት ዓይኑን የሚጨፍን ሰው፣ +16 በከፍታ ቦታዎች ይኖራል፤ዓለታማ ምሽጎች አስተማማኝ መጠጊያው ይሆናሉ፤ምግቡም ይቀርብለታል፤የውኃ አቅርቦትም ፈጽሞ አይቋረጥበትም።”+ +17 ዓይኖችህ ንጉሡን ግርማ ተላብሶ ያዩታል፤በሩቅ ያለችውን ምድር ያያሉ። +18 ሽብር የነበረበትን ��ቅት በልብህ ታስታውሳለህ፦* “ጸሐፊው የት አለ? ግብር የመዘነው የት አለ?+ ማማዎቹንስ የቆጠረው የት አለ?” +19 የማይገባ ቋንቋ የሚናገረውንና*ለመረዳት የሚያስቸግር ተብታባ አንደበት ያለውን+ጋጠወጥ ሕዝብ ከእንግዲህ አታይም። +20 በዓሎቻችንን+ የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት! ጸጥታ የሰፈነባት መኖሪያ፣የማትነቃነቅ ድንኳን+ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን ዓይኖችህ ያያሉ። የድንኳን ካስማዎቿ ፈጽሞ አይነቀሉም፤ከገመዶቿም አንዱ እንኳ አይበጠስም። +21 ይልቁንም ግርማ ሞገስ የተላበሰው ይሖዋበዚያ ስፍራ እንደ ወንዞችና እንደ ሰፋፊ ቦዮች ሆኖ ይጠብቀናል፤በእነሱም ላይ ጠላት የሚያሰልፋቸው ባለ መቅዘፊያ ጀልባዎችም ሆኑትላልቅ መርከቦች አያልፉም። +22 ይሖዋ ዳኛችን ነው፤+ይሖዋ ሕግ ሰጪያችን ነው፤+ይሖዋ ንጉሣችን ነው፤+የሚያድነን እሱ ነው።+ +23 ገመዶችህ ይላላሉ፤የመርከቡን ምሰሶ አጽንተው ማቆምም ሆነ ሸራውን ወጥረው መያዝ አይችሉም። በዚያን ጊዜ ብዛት ያለው ምርኮ ይከፋፈላል፤አንካሶችም እንኳ ብዙ የሚበዘበዝ ነገር ያገኛሉ።+ +24 በዚያም የሚቀመጥ* ማንኛውም ሰው “ታምሜአለሁ” አይልም።+ በምድሪቱ ላይ የሚቀመጡ በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።+ +54 “አንቺ ያልወለድሽ መሃን ሴት፣ እልል በይ!+ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ ሴት፣+ ደስ ይበልሽ፤ በደስታም ጩኺ፤+የተተወችው ሴት ወንዶች ልጆች፣*ባል ካላት ሴት* ወንዶች ልጆች ይልቅ በዝተዋልና”+ ይላል ይሖዋ። + 2 “የድንኳንሽን ቦታ አስፊ።+ ታላቅ የሆነውን የማደሪያ ድንኳንሽን ሸራዎች ዘርጊ። ፈጽሞ አትቆጥቢ፤ የድንኳንሽን ገመዶች አስረዝሚ፤ካስማዎችሽንም አጠንክሪ።+ + 3 በቀኝም ሆነ በግራ ትስፋፊያለሽና። ዘሮችሽ ብሔራትን ይወርሳሉ፤ባድማ በሆኑትም ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ።+ + 4 ኀፍረት ስለማይደርስብሽ+ አትፍሪ፤+ለሐዘን ስለማትዳረጊም አትሸማቀቂ። በልጅነትሽ ዘመን የደረሰብሽን ኀፍረት ትረሺዋለሽና፤መበለትነትሽ ያስከተለብሽን ውርደትም ከእንግዲህ አታስታውሽም።” + 5 “ታላቁ ሠሪሽ+ ባልሽ* ነውና፤+ስሙም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው፤የሚቤዥሽም+ የእስራኤል ቅዱስ ነው። እሱም የምድር ሁሉ አምላክ ተብሎ ይጠራል።+ + 6 ይሖዋ የተተወችና በሐዘን የተደቆሰች* ሚስት፣+ደግሞም በልጅነቷ አግብታ፣ ከጊዜ በኋላ የተጠላች ሚስት እንደሆንሽ ቆጥሮ ጠርቶሻልና” ይላል አምላክሽ። + 7 “ለአጭር ጊዜ ተውኩሽ፤ሆኖም በታላቅ ምሕረት መልሼ እሰበስብሻለሁ።+ + 8 በቁጣ ጎርፍ ለጥቂት ጊዜ ፊቴን ከአንቺ ሰውሬ ነበር፤+ሆኖም በዘላለማዊ ታማኝ ፍቅር ምሕረት አሳይሻለሁ”+ ይላል የሚቤዥሽ+ ይሖዋ። + 9 “ይህ ለእኔ እንደ ኖኅ ዘመን ነው።+ የኖኅ ውኃ ምድርን ዳግመኛ አያጥለቀልቅም ብዬ እንደማልኩ ሁሉ+አንቺንም ከእንግዲህ ላለመቆጣትም ሆነ ላለመገሠጽ እምላለሁ።+ +10 ተራሮች ከቦታቸው ሊወገዱ፣ኮረብቶችም ሊናወጡ ይችላሉ፤ይሁንና ታማኝ ፍቅሬ ከአንቺ አይለይም፤+የሰላም ቃል ኪዳኔም አይናጋም”+ ይላል ምሕረት የሚያሳይሽ ይሖዋ።+ +11 “አንቺ የተጎሳቆልሽ፣+ በአውሎ ነፋስ የተናወጥሽና ማጽናኛ ያላገኘሽ ሴት ሆይ፣+እነሆ ድንጋዮችሽን በኃይለኛ ማጣበቂያ እገነባለሁ፤መሠረትሽንም በሰንፔር እሠራለሁ።+ +12 መጠበቂያ ማማዎችሽን በሩቢ ድንጋዮች፣የከተማሽንም በሮች በሚያብረቀርቁ ድንጋዮች፣*ወሰኖችሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ። +13 ልጆችሽም* ሁሉ ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ፤+የልጆችሽም* ሰላም ብዙ ይሆናል።+ +14 በጽድቅ ጽኑ ሆነሽ ትመሠረቺያለሽ።+ ጭቆና ከአንቺ ይርቃል፤+ምንም ነገር አትፈሪም፤ የሚያሸብርሽም ነገር አይኖርም፤ወደ አንቺ አይቀርብምና።+ +15 ማንም ጥቃት ቢሰነዝርብሽእኔ አዝዤው አ��ደለም። ጥቃት የሚሰነዝርብሽ ሁሉ ከአንቺ የተነሳ ይወድቃል።”+ +16 “እነሆ፣ የከሰል እሳቱን በወናፍ የሚያናፋውንየእጅ ጥበብ ባለሙያ የፈጠርኩት እኔ ነኝ፤የሚያከናውነውም ሥራ የጦር መሣሪያ ያስገኛል። ደግሞም ጥፋት እንዲያደርስ አጥፊውን ሰው የፈጠርኩት እኔ ራሴ ነኝ።+ +17 አንቺን ለማጥቃት የተሠራ ማንኛውም መሣሪያ ይከሽፋል፤+አንቺን ለመክሰስ የሚነሳን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የይሖዋ አገልጋዮች ውርሻ* ይህ ነው፤ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው” ይላል ይሖዋ።+ +10 ጉዳት የሚያስከትሉ ሥርዓቶችን የሚያወጡ፣+ሁልጊዜ ጨቋኝ ድንጋጌዎችን የሚያረቁ ወዮላቸው! + 2 የድሆችን አቤቱታ ላለመስማት፣በሕዝቤም መካከል የሚገኙትን ምስኪኖች ፍትሕ ለመንፈግ ሕግ የሚያወጡ ወዮላቸው!+መበለቶችን ይበዘብዛሉ፤አባት የሌላቸውንም ልጆች* ይዘርፋሉ።+ + 3 በምትመረመሩበት* ቀን፣+ጥፋትም ከሩቅ በሚመጣበት ጊዜ ምን ይውጣችሁ ይሆን?+ እርዳታ ለማግኘት ወደ ማን ትሸሻላችሁ?+ሀብታችሁንስ* የት ትተዉት ይሆን? + 4 በእስረኞች መካከል ተኮራምታችሁ ከመቀመጥናበሞቱ ሰዎች መካከል ከመውደቅ በስተቀር የምታተርፉት ነገር የለም። ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+ + 5 “የቁጣዬ በትር የሆነውንና+ውግዘቴን የምገልጽበትን ዱላ በእጁ የያዘውንአሦራዊ+ ተመልከት! + 6 ከሃዲ በሆነው ብሔር ላይ፣እጅግ ባስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤+ብዙ ምርኮ እንዲወስድ፣ ብዙ ሀብት እንዲዘርፍናሕዝቡን በጎዳናዎች ላይ እንዳለ ጭቃ እንዲረጋግጥ አዘዋለሁ።+ + 7 እሱ ግን እንዲህ ያለ ዝንባሌ አይኖረውም፤ልቡም እንዲህ ለማድረግ አያቅድም፤የልቡ ፍላጎት መደምሰስናጥቂት ሳይሆን ብዙ ብሔራትን ማጥፋት ነውና። + 8 እሱ እንዲህ ይላል፦‘አለቆች ሆነው የሚያገለግሉኝ ሁሉ ነገሥታት አይደሉም?+ + 9 ካልኖ+ እንደ ካርከሚሽ+ አይደለችም? ሃማት+ እንደ አርጳድ+ አይደለችም? ሰማርያስ+ እንደ ደማስቆ+ አይደለችም? +10 እጄ በኢየሩሳሌምና በሰማርያ ካሉት ይበልጥ በርካታ የተቀረጹ ምስሎች ያሏቸውንናከንቱ አማልክት የሚያመልኩትን መንግሥታት ይዟል!+ +11 በሰማርያና ከንቱ በሆኑት አማልክቷ ላይ እንዳደረግኩት ሁሉ፣በኢየሩሳሌምና በጣዖቶቿስ ላይ እንዲሁ አላደርግም?’+ +12 “ይሖዋ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚያከናውነውን ሥራ ሁሉ ሲያጠናቅቅ በእብሪተኛ ልቡ፣ በኩራቱና በትዕቢተኛ ዓይኑ የተነሳ የአሦርን ንጉሥ ይቀጣዋል።*+ +13 እሱ እንዲህ ይላልና፦‘በእጄ ብርታትና በጥበቤይህን አደርጋለሁ፤ እኔ ጥበበኛ ነኝና። የሕዝቦችን ድንበር አስወግዳለሁ፤+ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፤+እንደ ኃያል ሰውም ነዋሪዎቹን በቁጥጥር ሥር አውላለሁ።+ +14 ሰው እጁን ወደ ወፍ ጎጆ እንደሚሰድ፣እጄ የሕዝቦችን ሀብት ይይዛል፤አንድ ሰው የተተዉ እንቁላሎችን እንደሚሰበስብእኔም መላውን ምድር እሰበስባለሁ! ክንፎቹን የሚያራግብ ወይም አፉን የሚከፍት አሊያም የሚጮኽ አይኖርም።’” +15 መጥረቢያ፣ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራል? መጋዝ፣ በሚገዘግዝበት ሰው ላይ ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል? በትር፣+ የሚያነሳውን ሰው ወዲያና ወዲህ ማንቀሳቀስ ይችላል? ወይስ ዱላ፣ ከእንጨት ያልተሠራውን ሰው ወደ ላይ ከፍ ማድረግ ይችላል? +16 ስለዚህ እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋበወፈሩት ሰዎች ላይ ክሳትን ይሰዳል፤+ከክብሩም በታች እንደ እሳት ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ያነዳል።+ +17 የእስራኤል ብርሃን+ እንደ እሳት፣+ቅዱስ አምላኩም እንደ ነበልባል ይሆናል፤አረሙንና ቁጥቋጦውን በአንድ ቀን ያጋየዋል፤ ደግሞም ይበላዋል። +18 አምላክ የደኑንና የፍራፍሬ እርሻውን ክብር ፈጽሞ* ያጠፋል፤ክብሩም እንደታመመ ሰው እየመነመነ ይሄዳል።+ +19 በደኑ ውስጥ የሚተርፉት ዛፎችጥቂት ከመሆናቸው የተነሳ አንድ ትንሽ ልጅ ቆጥሮ ሊመዘግባቸው ይችላል። +20 በዚያ ቀን ከእስራኤላውያን መካከል የሚቀሩት፣ከያዕቆብም ቤት የሚተርፉት ሰዎችከእንግዲህ ወዲህ፣ በመታቸው ላይ ፈጽሞ አይታመኑም፤+ከዚህ ይልቅ የእስራኤል ቅዱስ በሆነው በይሖዋ ላይበታማኝነት ይደገፋሉ። +21 ጥቂት ቀሪዎች ይኸውም ከያዕቆብ ቤት የሚተርፉት ሰዎችወደ ኃያሉ አምላክ ይመለሳሉ።+ +22 እስራኤል ሆይ፣ሕዝብህ እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንምከእነሱ መካከል ጥቂት ቀሪዎች ይመለሳሉ።+ ጥፋት ተወስኗል፤+ፍትሕም* ይውጣቸዋል።+ +23 አዎ፣ ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የወሰነው ጥፋት፣በመላ ምድሪቱ ላይ ይፈጸማል።+ +24 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፣ በበትር+ ይመታህና ግብፅ እንዳደረገብህ+ ዱላውን በአንተ ላይ ያነሳ የነበረውን አሦርን አትፍራ። +25 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ውግዘቱ ያበቃልና፤ ቁጣዬም እስኪጠፉ ድረስ በእነሱ ላይ ይነድዳል።+ +26 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በኦሬብ ዓለት ምድያምን ድል እንዳደረገ+ ሁሉ ጅራፉን በእሱ ላይ ያወዛውዛል።+ በትሩም በባሕሩ ላይ ይሆናል፤ በግብፅ ላይ እንዳደረገውም በትሩን ያነሳዋል።+ +27 “በዚያ ቀን ሸክሙ ከትከሻህ ላይ፣+ቀንበሩም ከአንገትህ ላይ ይወርዳል፤+ከዘይቱም የተነሳ ቀንበሩ ይሰበራል።”+ +28 በአያት+ ላይ መጥቷል፤ሚግሮንን አቋርጦ አልፏል፤በሚክማሽ+ ጓዙን ያስቀምጣል። +29 መልካውን* ተሻግረዋል፤በጌባ+ ያድራሉ፤ራማ ራደች፤ የሳኦል ከተማ ጊብዓ+ ሸሽታለች።+ +30 የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፣ እሪታሽን አቅልጪው! ላይሻ ሆይ፣ አዳምጪ! ምስኪኗ አናቶት+ ሆይ፣ ጩኺ! +31 ማድመና ሸሽታለች። የጌቢም ነዋሪዎች መሸሸጊያ ፈለጉ። +32 በዚሁ ቀን በኖብ+ ያርፋል። በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ፣በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ እጁን በዛቻ ያወዛውዛል። +33 እነሆ፣ እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋቅርንጫፎችን በታላቅ ኃይል እየቆራረጠ ይጥላል፤+ረጃጅሞቹ ዛፎች ይገነደሳሉ፤ከፍ ያሉትም ይዋረዳሉ። +34 በደን ውስጥ ያለውን ጥሻ በብረት መሣሪያ* ይቆራርጣል፤ሊባኖስም በኃያሉ እጅ ይወድቃል። +14 ይሖዋ ለያዕቆብ ምሕረት ያሳያልና፤+ እስራኤልንም እንደገና ይመርጠዋል።+ በምድራቸው ላይ ያሰፍራቸዋል፤*+ የባዕድ አገር ሰዎችም ከእነሱ ጋር ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃሉ።+ +2 ሕዝቦችም ይወስዷቸዋል፤ ወደ ገዛ ስፍራቸውም ይመልሷቸዋል፤ የእስራኤልም ቤት በይሖዋ ምድር ላይ ወንድና ሴት አገልጋዮቻቸው ያደርጓቸዋል፤+ ማርከው የወሰዷቸውንም ይማርካሉ፤ አስገድደው ያሠሯቸው የነበሩትንም* ይገዟቸዋል። +3 ይሖዋ ከሥቃይህ፣ ከጭንቀትህና በላይህ ተጭኖ ከነበረው ከባድ የባርነት ቀንበር ባሳረፈህ ቀን፣+ +4 በባቢሎን ንጉሥ ላይ እንዲህ ብለህ ትተርታለህ፦* “ሌሎችን አስገድዶ ሲያሠራ የነበረው* እንዴት አበቃለት! ጭቆናውስ እንዴት አከተመ!+ + 5 ይሖዋ የክፉዎችን ዘንግ፣የገዢዎችን በትር ሰብሯል፤+ + 6 ሕዝቦችን ያለማቋረጥ በቁጣ ሲመታ የነበረውን፣+ብሔራትን በማያባራ ስደት በቁጣ ሲገዛቸው የቆየውን ሰብሯል።+ + 7 መላዋ ምድር አርፋለች፤ ከረብሻም ነፃ ሆናለች። ሕዝቦች በደስታ እልል ብለዋል።+ + 8 የጥድ ዛፎችና አርዘ ሊባኖሶች እንኳ ሳይቀሩበአንተ ላይ በደረሰው ነገር ሐሴት ያደርጋሉ። ‘አንተ ከወደቅክ ጀምሮማንም ዛፍ ቆራጭ በእኛ ላይ አልተነሳም’ ይላሉ። + 9 “ከታች ያለው መቃብር* እንኳወደዚያ በወረድክ ጊዜ አንተን ለመቀበል ሲል ተረበሸ። በሞት የተረቱትን፣ ጨቋኝ የምድር መሪዎች* ሁሉበአንተ የተነሳ ቀሰቀሳቸው። የብሔራትን ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ላይ አስነሳቸው። +10 ሁሉም እንዲህ በማለት ይናገራሉ፤ እንዲህም ይሉሃል፦‘አንተም እንደ እኛው ደከምክ ማለት ነው? አንተም እንደ እኛው ሆንክ? +11 ኩራትህና ባለ አውታር መሣሪያዎችህ የሚያሰሙት ድምፅወደ መቃብር* ወረዱ።+ እጮች ከበታችህ እንደ አልጋ ተነጥፈውልሃል፤የአልጋ ልብስህም ትሎች ናቸው።’ +12 አንተ የምታበራ ኮከብ፣ የንጋት ልጅ ሆይ፣እንዴት ከሰማይ ወደቅክ! አንተ ብሔራትን ድል ያደረግክ፣እንዴት ተቆርጠህ ወደ ምድር ወደቅክ!+ +13 በልብህ እንዲህ ብለህ ነበር፦ ‘ወደ ሰማያት እወጣለሁ።+ ዙፋኔን ከአምላክ ከዋክብት በላይ ከፍ አደርጋለሁ፤+በስተ ሰሜን ርቆ በሚገኘውየመሰብሰቢያ ተራራም ላይ እቀመጣለሁ።+ +14 ከደመናዎች ከፍታ በላይ እወጣለሁ፤ራሴንም እንደ ልዑል አምላክ አደርጋለሁ።’ +15 ከዚህ ይልቅ ወደ መቃብር፣*ወደ ጥልቁም ጉድጓድ ትወርዳለህ። +16 የሚያዩህ አተኩረው ይመለከቱሃል፤በሚገባም ይመረምሩሃል፤ እንዲህም ይላሉ፦‘ምድርን ሲያንቀጠቅጥ፣መንግሥታትንም ሲያናውጥ የነበረው ይህ ሰው አይደለም?+ +17 ሰው የሚኖርበትን ምድር፣ ምድረ በዳ ያደረገው፣ከተሞቹንም የገለበጠው፣+እስረኞቹንም ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ የከለከለው እሱ አይደለም?’+ +18 ሌሎቹ የብሔራት ነገሥታት ሁሉ፣አንዳቸውም እንኳ ሳይቀሩ በክብር አንቀላፍተዋል፤እያንዳንዳቸው በየመቃብራቸው* አርፈዋል። +19 አንተ ግን እንደተጠላ ቀንበጥ*መቀበሪያ ሳታገኝ ተጥለሃል፤በሰይፍ ተወግተውወደ ዓለታማ ጉድጓድ በወረዱ አስከሬኖች ተሸፍነሃል፤እንደተረገጠም ሬሳ ሆነሃል። +20 ከእነሱ ጋር አብረህ በመቃብር አትቀበርም፤የገዛ ምድርህን አጥፍተሃልና፤የገዛ ሕዝብህንም ፈጅተሃል። የክፉ አድራጊዎች ዘር ስም ዳግመኛ አይጠራም። +21 ተነስተው ምድሪቱን እንዳይወርሱናምድሪቱን በከተሞች እንዳይሞሏትበአባቶቻቸው በደል የተነሳልጆቹ የሚታረዱበትን ስፍራ አዘጋጁ።” +22 “በእነሱ ላይ እነሳለሁ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “ከባቢሎን ስምን፣ ቀሪዎችን፣ ልጆችንና ዘርማንዘርን አጠፋለሁ”+ ይላል ይሖዋ። +23 “የጃርት መኖሪያና ረግረጋማ ቦታ አደርጋታለሁ፤ በጥፋት መጥረጊያም እጠርጋታለሁ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +24 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ሲል ምሏል፦ “ልክ እንዳሰብኩት ይሆናል፤በወሰንኩትም መሠረት ይፈጸማል። +25 አሦራዊውን በምድሬ ላይ አደቀዋለሁ፤በተራሮቼም ላይ እረግጠዋለሁ።+ ቀንበሩ ከላያቸው ላይ ይነሳል፤ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።”+ +26 በመላው ምድር ላይ የተላለፈው ውሳኔ* ይህ ነው፤በብሔራትም ሁሉ ላይ የተዘረጋው* እጅ ይህ ነው። +27 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ወስኗልና፤ውሳኔውን ማን ሊያጨናግፍ ይችላል?+ እጁ ተዘርግቷል፤ማንስ ሊያጥፈው ይችላል?+ +28 ንጉሥ አካዝ በሞተበት+ ዓመት የሚከተለው ፍርድ ተላለፈ፦ +29 “ፍልስጤማውያን ሆይ፣ የመቺያችሁ በትር ስለተሰበረአንዳችሁም ብትሆኑ ደስ አይበላችሁ። ከእባቡ ሥር+ መርዘኛ እባብ ይወጣልና፤+ዘሩም የሚበርና የሚያቃጥል እባብ* ይሆናል። +30 የችግረኞቹ የበኩር ልጆች ሲመገቡ፣ድሆቹም ያለስጋት ሲተኙ፣የአንተን ሥር ግን በረሃብ እገድላለሁ፤ከአንተ የሚተርፈውም ይገደላል።+ +31 አንተ በር ሆይ፣ አላዝን! አንቺ ከተማ ሆይ፣ ጩኺ! ፍልስጤማውያን ሆይ፣ ሁላችሁም ተስፋ ትቆርጣላችሁ! ከሰሜን ጭስ እየመጣ ነውና፤አንዳቸውም ቢሆኑ ከሰልፉ ተነጥለው ወደ ኋላ አይቀሩም።” +32 ለብሔሩ መልእክተኞች ምን ብለው መመለስ ይገባቸዋል? ‘የጽዮንን መሠረት የጣለው ይሖዋ ነው፤+በሕዝቡም መካከል ያሉት ችግረኛ ሰዎች እሷን መጠጊያ ያደርጋሉ’ ብለው ይመልሱላቸዋል። +65 “እኔን ላልጠየቁ ሰዎች ተገለጥኩ፤ላልፈለጉኝ ሰዎች ተገኘሁ።+ ስሜን ላልጠራ ብሔር ‘እነሆኝ፤ እነሆኝ!’ አልኩ።+ + 2 የራሳቸውን ሐሳብ እየተከተሉ፣+መልካም ባልሆነ መንገድ ወደሚሄዱ+ግትር ሰዎች ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ፤+ + 3 እነሱ ዘወትር በፊቴ እኔን የሚያስከፋ ነገር ይፈጽማሉ፤+በአትክልት ቦታዎች ይሠዋሉ፤+ በጡቦችም ላይ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርባሉ። + 4 በመቃብር መካከል ይቀመጣሉ፤+በተሰወሩ ቦታዎችም* ውስጥ ያድራሉ፤የአሳማ ሥጋ ይበላሉ፤+ዕቃዎቻቸው ጸያፍ* በሆኑ ነገሮች መረቅ የተሞሉ ናቸው።+ + 5 ‘እዚያው ባለህበት ሁን፤ አትጠጋኝ፤እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና’* ይላሉ። እነዚህ ሰዎች በአፍንጫዬ እንዳለ ጭስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድ እሳት ናቸው። + 6 እነሆ፣ በፊቴ ተጽፏል፤እኔ ዝም አልልም፤ከዚህ ይልቅ እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ፤+ብድራቱን ሙሉ በሙሉ እመልስባቸዋለሁ፤* + 7 ይህን የማደርገው እነሱ በሠሩት በደልና አባቶቻቸው በሠሩት በደል የተነሳ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “ምክንያቱም በተራሮች ላይ የሚጨስ መሥዋዕት አቅርበዋል፤በኮረብቶችም ላይ አዋርደውኛል፤+እኔም በመጀመሪያ፣ ዋጋቸውን ሙሉ በሙሉ እከፍላቸዋለሁ።”* + 8 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አዲስ ወይን፣ በወይን ዘለላ ውስጥ ሲገኝአንድ ሰው ‘በውስጡ ጥሩ ነገር* ስላለ አታጥፋው’ እንደሚል፣ እኔም ለአገልጋዮቼ ስል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ሁሉንም አላጠፋቸውም።+ + 9 ከያዕቆብ ዘርን፣ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፤+የመረጥኳቸው ምድሪቱን ይወርሳሉ፤አገልጋዮቼም በዚያ ይኖራሉ።+ +10 እኔን ለሚፈልገኝ ሕዝቤ፣ሳሮን+ የበጎች መሰማሪያ፣የአኮርም ሸለቆ*+ የከብቶች ማረፊያ ይሆናል። +11 እናንተ ግን ይሖዋን ከተዉት፣+ቅዱስ ተራራዬን ከረሱት፣+መልካም ዕድል ለተባለ አምላክ ማዕድ ካሰናዱት፣ዕጣ ለተባለም አምላክ የተደባለቀ ወይን ጠጅ በዋንጫ ከሞሉት ሰዎች መካከል ናችሁ። +12 በመሆኑም ዕጣችሁ በሰይፍ መውደቅ ይሆናል፤+ሁላችሁም ለመታረድ ታጎነብሳላችሁ፤+ምክንያቱም ስጣራ አልመለሳችሁም፤ስናገር አልሰማችሁም፤+በዓይኔ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ማድረጋችሁን ቀጠላችሁ፤እኔ የማልደሰትበትንም ነገር መረጣችሁ።”+ +13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ አገልጋዮቼ ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ።+ እነሆ፣ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ፤+ እናንተ ግን ትጠማላችሁ። እነሆ፣ አገልጋዮቼ ሐሴት ያደርጋሉ፤+ እናንተ ግን ኀፍረት ትከናነባላችሁ።+ +14 እነሆ፣ አገልጋዮቼ ከልባቸው ደስታ የተነሳ እልል ይላሉ፤እናንተ ግን ከልባችሁ ሐዘን የተነሳ ትጮኻላችሁ፤መንፈሳችሁ ስለተሰበረም ዋይ ዋይ ትላላችሁ። +15 የተመረጡት አገልጋዮቼ ለእርግማን የሚጠቀሙበት ስም ትታችሁ ታልፋላችሁ፤ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋም እያንዳንዳችሁን ይገድላችኋል፤የራሱን አገልጋዮች ግን በሌላ ስም ይጠራቸዋል፤+ +16 ስለዚህ በምድር ላይ በረከትን የሚሻ ሁሉበእውነት አምላክ* ይባረካል፤በምድር ላይ መሐላ የሚምልም ሁሉበእውነት አምላክ* ይምላል።+ ቀደም ሲል የነበሩት የሚያስጨንቁ ነገሮች* ይረሳሉና፤ከዓይኔ ይሰወራሉ።+ +17 እነሆ፣ አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር እየፈጠርኩ ነውና፤+የቀድሞዎቹ ነገሮች አይታሰቡም፤*ወደ ልብም አይገቡም።+ +18 በመሆኑም በምፈጥረው ነገር ለዘላለም ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ። እነሆ፣ ኢየሩሳሌምን ለደስታ፣ሕዝቧንም ለሐሴት እፈጥራለሁና።+ +19 እኔም በኢየሩሳሌም ደስ እሰኛለሁ፤ በሕዝቤም ሐሴት አደርጋለሁ፤+ከዚህ በኋላ በውስጧ የለቅሶ ድምፅም ሆነ የጭንቅ ጩኸት አይሰማም።”+ +20 “ከእንግዲህ በዚያ፣ ለጥቂት ቀን ብቻ የሚኖ�� ሕፃንም ሆነዕድሜ የማይጠግብ አረጋዊ አይኖርም። መቶ ዓመት ሞልቶት የሚሞት ማንኛውም ሰው ገና በልጅነቱ እንደተቀጨ ይቆጠራል፤ኃጢአተኛው መቶ ዓመት ቢሞላውም እንኳ ይረገማል።* +21 ቤቶችን ይሠራሉ፤ በዚያም ይኖራሉ፤+ወይንንም ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።+ +22 እነሱ በሠሩት ቤት ሌላ ሰው አይኖርም፤እነሱ የተከሉትንም ሌላ ሰው አይበላውም። የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፤+የመረጥኳቸው አገልጋዮቼም በእጃቸው ሥራ የተሟላ እርካታ ያገኛሉ። +23 በከንቱ አይለፉም፤+ወይም ለመከራ የሚዳረጉ ልጆች አይወልዱም፤ምክንያቱም እነሱም ሆኑ ልጆቻቸው+ይሖዋ የባረከው ዘር ናቸው።+ +24 ገና ሳይጣሩ እመልስላቸዋለሁ፤እየተናገሩ ሳሉ እሰማቸዋለሁ። +25 ተኩላና የበግ ግልገል በአንድነት ይበላሉ፤አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤+የእባብም መብል አፈር ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳትም ሆነ ጥፋት አያደርሱም”+ ይላል ይሖዋ። +66 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድር ደግሞ የእግሬ ማሳረፊያ ናት።+ ታዲያ እናንተ ምን ዓይነት ቤት ልትሠሩልኝ ትችላላችሁ?+ ደግሞስ የማርፍበት ቦታ የት ነው?”+ + 2 “እነዚህን ነገሮች ሁሉ የሠራው እጄ ነው፤ሁሉም ወደ ሕልውና የመጡት በዚህ መንገድ ነው” ይላል ይሖዋ።+ “እኔ የማየው ትሑት የሆነውን፣መንፈሱ የተሰበረውንና በቃሌ የሚንቀጠቀጠውን* ሰው ነው።+ + 3 በሬን የሚያርድ፣ ሰውን እንደሚገድል ነው።+ በግን የሚሠዋ፣ የውሻን አንገት እንደሚሰብር ነው።+ ስጦታ የሚሰጥ ሰው፣ የአሳማ ደም እንደሚያቀርብ ነው!+ ነጭ ዕጣንን የመታሰቢያ መባ አድርጎ የሚያቀርብ፣+ በአስማታዊ ቃላት እንደሚባርክ* ሰው ነው።+ እነሱ የራሳቸውን መንገድ መርጠዋል፤በአስጸያፊ ነገሮችም + 4 ስለዚህ እነሱን የምቀጣበትን መንገድ እፈልጋለሁ፤+የፈሩትንም ያንኑ ነገር አመጣባቸዋለሁ። ምክንያቱም ስጣራ መልስ የሰጠ ማንም አልነበረም፤ስናገር የሰማ አንድም ሰው አልነበረም።+ በዓይኔ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ማድረጋቸውን ቀጠሉ፤እኔ የማልደሰትበትንም ነገር መረጡ።”+ + 5 እናንተ በቃሉ የምትንቀጠቀጡ* ሰዎች ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ “በስሜ የተነሳ የሚጠሏችሁና የሚያገሏችሁ ወንድሞቻችሁ፣ ‘ይሖዋ የተከበረ ይሁን!’ ብለዋል።+ ሆኖም አምላክ ይገለጣል፤ ደስታንም ያጎናጽፋችኋል፤እነሱም ለኀፍረት ይዳረጋሉ።”+ + 6 ከከተማዋ ሁካታ፣ ከቤተ መቅደሱም ድምፅ ይሰማል! ይህም ይሖዋ ለጠላቶቹ የሚገባቸውን ብድራት በሚከፍላቸው ጊዜ የሚሰማ ድምፅ ነው። + 7 እሷ ገና ምጥ ሳይጀምራት ወለደች።+ ምጥ ሳይዛት በፊት ወንድ ልጅ ተገላገለች። + 8 እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶ ያውቃል? እንዲህ ያሉ ነገሮችስ ማን አይቶ ያውቃል? አገር በአንድ ቀን ይወለዳል? ወይስ ብሔር በአንድ ጊዜ ይወለዳል? ሆኖም ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ወንዶች ልጆቿን ወልዳለች። + 9 “ማህፀኑን ከከፈትኩ በኋላ ልጁ እንዳይወለድ አደርጋለሁ?” ይላል ይሖዋ። “ወይስ ምጡ እንዲፋፋም ካደረግኩ በኋላ ማህፀኑን እዘጋለሁ?” ይላል አምላክሽ። +10 እናንተ የምትወዷት ሁሉ፣+ ከኢየሩሳሌም ጋር ሐሴት አድርጉ፤ ከእሷም ጋር ደስ ይበላችሁ።+ ለእሷ የምታዝኑ ሁሉ ከእሷ ጋር እጅግ ደስ ይበላችሁ፤ +11 የሚያጽናኑ ጡቶቿን ትጠባላችሁና፤ ሙሉ በሙሉም ትረካላችሁ፤እስኪበቃችሁም ድረስ ትጠጣላችሁ፤ በክብሯም ብዛት ሐሴት ታደርጋላችሁ። +12 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፣ ሰላምን እንደ ወንዝ፣+የብሔራትንም ክብር እንደሚያጥለቀልቅ ጅረት አፈስላታለሁ።+ እናንተም ትጠባላችሁ፤ ጀርባዋም ላይ ታዝላችኋለች፣ጭኗም ላይ ሆናችሁ ትዘላላችሁ። +13 እናት ልጇን እንደምታጽናና፣���ኔም እናንተን ሁልጊዜ አጽናናችኋለሁ፤+በኢየሩሳሌምም ትጽናናላችሁ።+ +14 እናንተ ይህን ታያላችሁ፤ ልባችሁም ሐሴት ያደርጋል፤አጥንቶቻችሁ እንደ ሣር ይለመልማሉ። የይሖዋም እጅ* በአገልጋዮቹ ዘንድ ትታወቃለች፤ጠላቶቹን ግን ያወግዛቸዋል።”+ +15 “ይሖዋ፣ ብድራቱን በታላቅ ቁጣ ለመመለስ፣በእሳት ነበልባልም ለመገሠጽ+እንደ እሳት ሆኖ ይመጣልና፤+ሠረገሎቹም እንደ አውሎ ነፋስ ይመጣሉ።+ +16 ይሖዋ በእሳት ፍርዱን ይፈጽማልና፤አዎ፣ በሥጋ ለባሽ* ሁሉ ላይ በሰይፍ ፍርዱን ይፈጽማል፤በይሖዋ እጅ የሚገደሉትም ብዙ ይሆናሉ። +17 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መሃል ላይ ያለውን ተከትለው ወደ አትክልት ቦታዎቹ*+ ለመግባት ሲሉ ራሳቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የአሳማ ሥጋና አስጸያፊ ነገር እንዲሁም አይጥ የሚበሉ ሁሉ+ በአንድነት ይጠፋሉ። +18 እኔ ሥራቸውንና ሐሳባቸውን ስለማውቅ፣ ከሁሉም ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጡ ሰዎችን ለመሰብሰብ እመጣለሁ፤ እነሱም መጥተው ክብሬን ያያሉ።” +19 “በመካከላቸው ምልክት አቆማለሁ፤ ከተረፉት መካከል አንዳንዶቹን ወደ ብሔራት ይኸውም ወደ ተርሴስ፣+ ወደ ፑል እና ወደ ሉድ+ እልካለሁ። በቱባልና በያዋን+ ወዳሉት ቀስተኞች እልካቸዋለሁ። ስለ እኔ ወዳልሰሙ ወይም ክብሬን ወዳላዩ፣ ርቀው በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ ወደሚኖሩ ሕዝቦችም እልካቸዋለሁ፤ እነሱም በ +20 የእስራኤል ልጆች በንጹሕ ዕቃ ስጦታ ይዘው ወደ ይሖዋ ቤት እንደሚያመጡ፣ ወንድሞቻችሁን ሁሉ ለይሖዋ ስጦታ እንዲሆኑ ከየብሔራቱ በፈረሶች፣ በሠረገሎች፣ ጥላ ባላቸው ጋሪዎች፣ በበቅሎዎችና በፈጣን ግመሎች ጭነው ወደተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጧቸዋል”+ ይላል ይሖዋ። +21 “በተጨማሪም አንዳንዶቹን ካህናት፣ ሌሎቹን ደግሞ ሌዋውያን እንዲሆኑ እወስዳለሁ” ይላል ይሖዋ። +22 “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር+ በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ ሁሉ የእናንተም ዘርና ስማችሁ እንዲሁ ጸንቶ ይኖራል”+ ይላል ይሖዋ። +23 “ከአንዱ ወር መባቻ እስከ ሌላው ወር መባቻ እንዲሁም ከአንዱ ሰንበት እስከ ሌላው ሰንበት፣ሰው* ሁሉ በፊቴ ለመስገድ* ይመጣል”+ ይላል ይሖዋ። +24 “እነሱም ሄደው በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤በእነሱ ላይ ያሉት ትሎች አይሞቱምና፤እሳታቸውም አይጠፋም፤+ለሰዎችም* ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።” +43 አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ ፈጣሪህ፣እስራኤልም ሆይ የሠራህ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ተቤዥቼሃለሁና+ አትፍራ። በስምህ ጠርቼሃለሁ። አንተ የእኔ ነህ። + 2 በውኃዎች መካከል ስታልፍ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤+በወንዞችም መካከል ስትሻገር አያሰምጡህም።+ በእሳት መካከል ስትሄድ አትቃጠልም፤ነበልባሉም አይፈጅህም። + 3 እኔ ይሖዋ አምላክህ፣የእስራኤል ቅዱስ፣ አዳኝህ ነኝና። ግብፅን ለአንተ ቤዛ አድርጌ ሰጥቻለሁ፤ኢትዮጵያንና ሴባን በአንተ ምትክ ሰጥቻለሁ። + 4 አንተ በዓይኔ ፊት ውድ ሆነሃልና፤+የተከበርክም ነህ፤ እኔም ወድጄሃለሁ።+ ስለዚህ በአንተ ምትክ ሰዎችን፣በሕይወትህም* ምትክ ብሔራትን እሰጣለሁ። + 5 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።+ ዘርህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።+ + 6 ሰሜንን ‘ልቀቃቸው!’ እለዋለሁ፤+ ደቡብንም እንዲህ እለዋለሁ፦ ‘አታግታቸው። ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ አምጣ፤+ + 7 በስሜ የተጠራውን፣+ለክብሬም የፈጠርኩትን፣የሠራሁትንና ያበጀሁትን ሁሉ አምጣ።’+ + 8 ዓይን ቢኖራቸውም ዕውር የሆኑትን፣ጆሮ ቢኖራቸውም ደንቆሮ የሆኑትን ሰዎች አውጣ።+ + 9 ብሔራት ሁሉ አንድ ቦታ ይሰብሰቡ፤ሕዝቦችም በአንድነት ይሰብሰቡ።+ ከመካከላቸው ይህን ሊናገር የሚችል ማን አለ? ወይስ የመጀመሪያዎቹን ነገሮች ሊነግሩን ይችላሉ?*+ ትክክል መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ምሥክሮቻቸውን ያቅርቡ፤ወይም ሰምተው ‘ይህ እውነት ነው!’ ይበሉ።”+ +10 “እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ”+ ይላል ይሖዋ፤“አዎ፣ የመረጥኩት አገልጋዬ ናችሁ፤+ይህም ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ*ደግሞም እኔ ምንጊዜም ያው እንደሆንኩ ታስተውሉ ዘንድ ነው።+ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ከእኔም በኋላ የለም።+ +11 እኔ፣ አዎ እኔ ይሖዋ ነኝ፤+ ከእኔ በቀር አዳኝ የለም።”+ +12 “በመካከላችሁ ባዕድ አምላክ ባልነበረበት ጊዜየተናገርኩት፣ ያዳንኩትና ያሳወቅኩት እኔ ነኝ።+ ስለዚህ እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ” ይላል ይሖዋ፤ “እኔም አምላክ ነኝ።+ +13 ደግሞም እኔ ምንጊዜም ያው ነኝ፤+ከእጄም አንዳች ነገር ሊነጥቅ የሚችል የለም።+ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ሊያግድ የሚችል ማን ነው?”+ +14 እናንተን የሚቤዠው+ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦ “ለእናንተ ስል ወደ ባቢሎን እሰዳለሁ፤ የበሮቹንም መቀርቀርያዎች ሁሉ እጥላለሁ፤+በመርከቦቻቸው ላይ ያሉት ከለዳውያንም በጭንቀት ይጮኻሉ።+ +15 እኔ ይሖዋ የእናንተ ቅዱስ፣+ የእስራኤል ፈጣሪ፣+ ንጉሣችሁ ነኝ።”+ +16 ይሖዋ ይኸውምበባሕር መካከል መንገድ የሚያበጀው፣በሚናወጡ ውኃዎችም መካከል ጎዳና የሚዘረጋው፣+ +17 የጦር ሠረገላውንና ፈረሱን፣+ሠራዊቱንና ኃያላን ተዋጊዎቹን በአንድነት የሚያወጣው አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ይተኛሉ፤ አይነሱምም።+ እንደሚነድ የጧፍ ክር ተዳፍነው ይጠፋሉ።” +18 “የቀድሞዎቹን ነገሮች አታስታውሱ፤ያለፈውንም ነገር አታውጠንጥኑ። +19 እነሆ፣ አዲስ ነገር አደርጋለሁ፤+አሁንም እንኳ መከናወን ጀምሯል። ይህን አታስተውሉም? በምድረ በዳ መንገድ አዘጋጃለሁ፤+በበረሃም ወንዞችን አፈልቃለሁ።+ +20 የዱር አውሬ፣ ቀበሮዎችናሰጎኖች ያከብሩኛል፤በምድረ በዳ ውኃ፣በበረሃም ወንዞችን እሰጣለሁና፤+ይህን የማደርገው የመረጥኩት ሕዝቤ+ እንዲጠጣ፣ +21 ለራሴ የሠራሁትም ሕዝብ እንዲጎነጭ ነው፤ሕዝቤ ውዳሴዬን እንዲያውጅ ይህን አደርጋለሁ።+ +22 እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግን የእኔ ነገር ስለታከተህ፣+ያዕቆብ ሆይ፣ አልጠራኸኝም።+ +23 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ በግ አላመጣህልኝም፤ወይም መሥዋዕቶች በማቅረብ አላከበርከኝም። ስጦታ እንድታመጣልኝ አላስገደድኩህም፤ነጭ ዕጣን አቅርብልኝ ብዬም አላሰለቸሁህም።+ +24 በገንዘብህ ጠጅ ሣር* አልገዛህልኝም፤በመሥዋዕቶችህም ስብ አላጠገብከኝም።+ ከዚህ ይልቅ ኃጢአትህን አሸክመኸኛል፤በምትፈጽማቸውም በደሎች አሰልችተኸኛል።+ +25 ስለ ራሴ ስል+ በደልህን* እኔ ራሴ እደመስሰዋለሁ፤+ኃጢአትህንም አላስታውስም።+ +26 እስቲ አስታውሰኝ፤ ጉዳያችንን አቅርበን እንሟገት፤ትክክለኛ መሆንህን ለማረጋገጥ በበኩልህ ጉዳይህን ተናገር። +27 የመጀመሪያው አባትህ ኃጢአት ሠርቷል፤የገዛ ቃል አቀባዮችህም* በእኔ ላይ ዓምፀዋል።+ +28 ስለዚህ በቅዱሱ ስፍራ የሚገኙትን መኳንንት አረክሳለሁ፤ያዕቆብንም ለጥፋት አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤እስራኤልንም ለስድብ እዳርገዋለሁ።+ +9 ይሁን እንጂ ፅልማሞቱ ምድሪቱ በተጨነቀችበት ጊዜ እንደነበረው ይኸውም የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር በተዋረዱበት ወቅት እንደነበረው እንደቀድሞው ዘመን አይሆንም።+ በኋለኛው ዘመን ግን ምድሩ ማለትም በባሕሩ አጠገብ የሚያልፈው መንገድ፣ በዮርዳኖስ ክልል የሚገኘው የአሕዛብ ገሊላ እንዲከበር ያደርጋል። + 2 በጨለማ ውስጥ ይሄዱ የነበሩ ሰዎችታላቅ ብርሃን አዩ። ድቅድቅ ጨለማ ባጠላበት ምድር የሚኖሩ ሰዎችምብርሃን ወጣላቸው።+ + 3 ሕዝቡን አብዝተሃል፤ታላቅ ደስታ እ���ዲያገኝ አድርገሃል። መከር በሚሰበሰብበት ጊዜ ሐሴት እንደሚያደርጉ፣ምርኮንም ሲከፋፈሉ እንደሚደሰቱ ሰዎችበፊትህ ደስ ይሰኛሉ። + 4 ምድያም ድል በተደረገበት ጊዜ እንደሆነው ሁሉ+የሸክማቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ ያለውን በትር፣የተቆጣጣሪያቸውንም ዘንግ ሰባብረሃልና። + 5 መሬቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ በኃይል የሚረግጡ ሰልፈኞች ጫማ ሁሉእንዲሁም በደም የተጨማለቀ ልብስ በሙሉለእሳት ማገዶ ይሆናል። + 6 ልጅ ተወልዶልናልና፤+ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ገዢነትም* በጫንቃው ላይ ይሆናል።+ ስሙ ድንቅ መካሪ፣+ ኃያል አምላክ፣+ የዘላለም አባትና የሰላም መስፍን ይባላል። + 7 በዳዊት ዙፋንና+ በመንግሥቱ ላይ ይቀመጣል፤እየተጠናከረ የሚሄደው አገዛዙም* ሆነሰላሙ ፍጻሜ አይኖረውም።+ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበማይናወጥ ሁኔታ ይመሠረታል፤+በፍትሕና+ በጽድቅም+ ጸንቶ ይኖራል። የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል። + 8 ይሖዋ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤ቃሉም በእስራኤል ላይ ደረሰ።+ + 9 ሕዝቡም ሁሉ ይኸውም የኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎችይህን ያውቃሉ፤በትዕቢታቸውና በልባቸው እብሪት የተነሳ እንዲህ ይላሉ፦ +10 “ጡቦቹ ወድቀዋል፤እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ እንገነባለን።+ የሾላ ዛፎቹ ተቆርጠዋል፤እኛ ግን በአርዘ ሊባኖስ እንተካቸዋለን።” +11 ይሖዋ የረጺንን ባላጋራዎች በእሱ ላይ ያስነሳል፤ጠላቶቹንም እርምጃ እንዲወስዱ ይቀሰቅሳቸዋል፤ +12 ሶርያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጤማውያንን ደግሞ ከምዕራብ* ያመጣበታል፤+እነሱም አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይውጡታል።+ ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+ +13 ሕዝቡ ወደመታቸው አልተመለሱምና፤የሠራዊት ጌታ ይሖዋን አልፈለጉም።+ +14 ይሖዋ ራስንና ጅራትን፣ ቀንበጥንና እንግጫን*ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቆርጣል።+ +15 ሽማግሌውና የተከበረው ሰው ራስ ነው፤የሐሰት መመሪያ የሚሰጠው ነቢይ ደግሞ ጅራት ነው።+ +16 ይህን ሕዝብ የሚመሩት ሰዎች እንዲባዝን ያደርጉታል፤በእነሱ የሚመራውም ሕዝብ ግራ ይጋባል። +17 ይሖዋ በወጣቶቻቸው የማይደሰተው ለዚህ ነው፤በመካከላቸው ላሉት አባት የሌላቸው ልጆችና* መበለቶች ምሕረት አያሳይም፤ምክንያቱም ሁሉም ከሃዲዎችና ክፉ አድራጊዎች ናቸው፤+የሁሉም አፍ የማይረባ ነገር ይናገራል። ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+ +18 ክፋት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ቁጥቋጦውንና አረሙንም ይበላል። በደን ውስጥ ያለውን ጥሻ ያነደዋል፤ጥሻው በሚቃጠልበት ጊዜም ጭሱ እየተትጎለጎለ ይወጣል። +19 ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ቁጣ የተነሳምድሪቷ በእሳት ተያያዘች፤ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው ማገዶ ይሆናል። ማንም ሰው ወንድሙን እንኳ አይምርም። +20 አንዱ በቀኝ በኩል ይቆርጣል፤ሆኖም ይራባል፤ሌላው ደግሞ በግራ በኩል ይበላል፤ሆኖም አይጠግብም። እያንዳንዳቸው የገዛ ክንዳቸውን ሥጋ ይበላሉ፤ +21 ምናሴ ኤፍሬምን፣ኤፍሬም ደግሞ ምናሴን ይበላል። በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሳሉ።+ ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+ +27 በዚያን ቀን ይሖዋ፣ በፍጥነት እየተሳበ የሚሄደውን እባብ ሌዋታንን፣*ደግሞም እየተጥመለመለ የሚጓዘውን እባብ ሌዋታንንትልቅ፣ ኃይለኛና ምሕረት የለሽ በሆነው ሰይፉ ይቀጣዋል፤+በባሕር ውስጥ ያለውንም ግዙፍ ፍጥረት ይገድለዋል። + 2 በዚያ ቀን ለእሷ* እንዲህ ብላችሁ ዘምሩ፦ “የሚፈላ የወይን ጠጅ የሚመረትባት የወይን እርሻ!+ + 3 እኔ ይሖዋ እጠብቃታለሁ።+ በየጊዜው ውኃ አጠጣታለሁ።+ ማንም ጉዳት እንዳያደርስባትሌት ተቀን እጠብቃታለሁ።+ + 4 ከእንግዲህ አልቆጣትም።+ በውጊያው ላይ ቁጥቋጦና አረም ይዞ የሚገጥመኝ ማን ነው? ሁሉንም በአንድ ላይ እረግጣቸዋለሁ፤ በእሳትም አቃጥላቸዋለሁ። + 5 አለዚያ ምሽጌን የሙጥኝ ይበል። ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠር፤አዎ፣ ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠር።” + 6 በመጪዎቹ ቀናት ያዕቆብ ሥር ይሰዳል፤እስራኤል ያብባል እንዲሁም ይለመልማል፤+ምድሩንም በምርት ይሞሉታል።+ + 7 እሱ አሁን በተመታበት ሁኔታ መመታቱ ተገቢ ነው? ወይስ የተገደሉበት ሰዎች በተፈጁበት መንገድ መገደሉ አስፈላጊ ነው? + 8 እሷን በምትልካት ጊዜ በአስደንጋጭ ጩኸት ትፋለማታለህ። የምሥራቅ ነፋስ በሚነፍስበት ቀን በኃይለኛ አውሎ ነፋሱ ያስወግዳታል።+ + 9 በመሆኑም የያዕቆብ በደል በዚህ መንገድ ይሰረይለታል፤+ኃጢአቱ በሚወገድበት ጊዜ ፍሬው በሙሉ ይህ ይሆናል፦ የመሠዊያ ድንጋዮቹን ሁሉእንደደቀቀ የኖራ ድንጋይ ያደርጋል፤የማምለኪያ ግንዶቹም* ሆኑ የዕጣን ማጨሻዎቹ አይተርፉም።+ +10 የተመሸገችው ከተማ ትተዋለችና፤የግጦሽ መሬቱም ወና ይሆናል፤ እንደ ምድረ በዳም የተተወ ይሆናል።+ በዚያ ጥጃ ይግጣል፤ ይተኛልም፤ቅርንጫፎቿንም ይበላል።+ +11 ቀንበጦቿ በሚደርቁበት ጊዜሴቶች መጥተው ይሰብሯቸዋል፤ከዚያም ማገዶ ያደርጓቸዋል። ይህ ሕዝብ ማስተዋል ይጎድለዋልና።+ በዚህም ምክንያት ፈጣሪያቸው ምንም ምሕረት አያደርግላቸውም፤ሠሪያቸውም ምንም ዓይነት ሞገስ አያሳያቸውም።+ +12 በዚያም ቀን የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ሰው ዛፍ ላይ ያሉ ፍሬዎችን አርግፎ አንድ በአንድ እንደሚለቅም ሁሉ፣ ይሖዋም ከታላቁ ወንዝ* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ ድረስ ባለው ቦታ ሁሉ የተበተናችሁትን ይሰበስባችኋል።+ +13 በዚያም ቀን ትልቅ ቀንደ መለከት ይነፋል፤+ በአሦር ምድር+ የጠፉትና በግብፅ ምድር+ የተበተኑት መጥተው በኢየሩሳሌም በሚገኘው ቅዱስ ተራራ ላይ ለይሖዋ ይሰግዳሉ።+ +47 አንቺ ድንግል የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣+ወርደሽ አፈር ላይ ተቀመጪ። አንቺ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፣ዙፋን በሌለበት መሬት ላይ ተቀመጪ፤+ከእንግዲህ ሰዎች ቅምጥልና ሞልቃቃ ብለው አይጠሩሽምና። + 2 ወፍጮ ወስደሽ እህል ፍጪ። መሸፋፈኛሽን አንሺ። ቀሚስሽን አውልቂ፤ ባትሽን ግለጪ። ወንዞቹን ተሻገሪ። + 3 እርቃንሽ ይገለጣል። ኀፍረትሽም ይታያል። እኔ የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ፤+ ማንም ሰው ሊያግደኝ አይችልም።* + 4 “እኛን የሚቤዠንየእስራኤል ቅዱስ ነው፤+ስሙም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።” + 5 አንቺ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፣በዚያ ዝም ብለሽ ተቀመጪ፤ ወደ ጨለማም ግቢ፤+ከእንግዲህ የመንግሥታት እመቤት* ብለው አይጠሩሽም።+ + 6 ሕዝቤን ተቆጣሁ።+ ርስቴን አረከስኩ፤+አሳልፌም በእጅሽ ሰጠኋቸው።+ አንቺ ግን ምሕረት አላሳየሻቸውም።+ በሽማግሌው ላይ እንኳ ሳይቀር ከባድ ቀንበር ጫንሽ።+ + 7 አንቺም “ሁልጊዜ ብሎም ለዘላለም እመቤት* እሆናለሁ” አልሽ።+ እነዚህን ነገሮች ልብ አላልሽም፤ነገሩ ምን ፍጻሜ እንደሚኖረው አላሰብሽም። + 8 በመሆኑም አንቺ ለሥጋዊ ደስታ ያደርሽ፣+ተማምነሽ የተቀመጥሽና በልብሽ “እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።+ መበለት አልሆንም። በምንም ዓይነት የወላድ መሃን አልሆንም” የምትዪ ሴት ሆይ፣+ ይህን ስሚ። + 9 ሆኖም እነዚህ ሁለት ነገሮች ይኸውም የወላድ መሃንነትና መበለትነት በአንድ ቀን በድንገት ይደርሱብሻል።+ በመተት ስለተሞላሽና ታላቅ ኃይል ባለው ድግምት ስለተዘፈቅሽ*+እነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንቺ ላይ ይደርሳሉ።+ +10 አንቺ በክፋትሽ ታምነሻል። “ማንም አያየኝም” ብለሻል። ያሳቱሽ ጥበብሽና እውቀትሽ ናቸው፤በልብሽም “እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ትያለሽ። +11 ሆኖም ጥፋት ይመጣብሻል፤ደግሞም ከዚህ ሊያስጥልሽ የሚችል ድግምት የለሽም።* መከራ ይደርስብሻል፤ ልታስወግጂውም አትችዪም። አይተሽው የማታውቂው ጥፋት በድንገት ይደርስብሻል።+ +12 እንግዲያው ከልጅነትሽ ጀምሮ ስትደክሚበት የነበረውንድግምት ሁሉና ብዛት ያለው የጥንቆላ ድርጊት+ መፈጸምሽን ቀጥዪ። ምናልባት ይጠቅምሽ ይሆናል፤ሰዎችን ለማሸበር ይረዳሽ ይሆናል። +13 በመካሪዎችሽ ብዛት እጅግ ተዳክመሻል። በሰማያት ያሉ ነገሮችን የሚያመልኩ፣* ከዋክብትን በትኩረት የሚመለከቱ፣+አዲስ ጨረቃም ስትወጣበአንቺ ላይ ስለሚመጣው ነገር የሚተነብዩ ሰዎች፣እስቲ አሁን ተነስተው ያድኑሽ። +14 እነሆ፣ እነሱ እንደ ገለባ ናቸው። እሳት ያቃጥላቸዋል። ራሳቸውን* ከነበልባሉ ኃይል ማዳን አይችሉም። ይህ ሰዎች የሚሞቁት ፍምም ሆነበፊቱ ተቀምጠው የሚሞቁት እሳት አይደለም። +15 ከልጅነትሽ ጀምሮ አብረሻቸው ስትደክሚ የነበሩትድግምተኞች እንዲሁ ይሆኑብሻል። እያንዳንዳቸው የመረጡትን አቅጣጫ ተከትለው ይባዝናሉ።* አንቺን የሚያድን አይኖርም።+ +62 ጽድቋ እንደ ደማቅ ብርሃን እስኪፈነጥቅ፣+መዳኗም እንደ ችቦ እስኪቀጣጠል ድረስለጽዮን ስል ጸጥ አልልም፤+ለኢየሩሳሌምም ስል ዝም ብዬ አልቀመጥም።+ + 2 “አንቺ ሴት ሆይ፣+ ብሔራት ጽድቅሽን፣ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ።+ አንቺም የይሖዋ አፍ በሚያወጣልሽአዲስ ስም ትጠሪያለሽ።+ + 3 በይሖዋ እጅ የውበት ዘውድ፣በአምላክሽ መዳፍ የንጉሥ ጥምጥም ትሆኛለሽ። + 4 ከእንግዲህ የተተወች ሴት አትባዪም፤+ምድርሽም ከእንግዲህ ባድማ ተብላ አትጠራም።+ ከዚህ ይልቅ “ደስታዬ በእሷ ነው” ተብለሽ ትጠሪያለሽ፤+ምድርሽም “ያገባች ሴት” ትባላለች። ይሖዋ በአንቺ ደስ ይለዋልና፤ምድርሽም እንዳገባች ሴት ትሆናለች። + 5 አንድ ወጣት ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ወንዶች ልጆችሽ አንቺን ያገባሉ። አንድ ሙሽራ በሙሽራይቱ ሐሴት እንደሚያደርግ፣አምላክሽም በአንቺ ሐሴት ያደርጋል።+ + 6 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ በቅጥሮችሽ ላይ ጠባቂዎች አቁሜአለሁ። ቀኑንም ሆነ ሌሊቱን በሙሉ፣ መቼም ቢሆን ዝም ሊሉ አይገባም። እናንተ ስለ ይሖዋ የምትናገሩ፣ፈጽሞ አትረፉ፤ + 7 ደግሞም ኢየሩሳሌምን አጽንቶ እስኪመሠርታት፣አዎ፣ የምድር ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ ምንም እረፍት አትስጡት።”+ + 8 ይሖዋ በቀኝ እጁ፣ ብርቱ በሆነውም ክንዱ እንዲህ ሲል ምሏል፦ “ከእንግዲህ እህልሽን ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤የደከምሽበትንም አዲስ የወይን ጠጅ የባዕድ አገር ሰዎች አይጠጡትም።+ + 9 ሆኖም እህሉን፣ የሚሰበስቡት ሰዎች ይበሉታል፤ ይሖዋንም ያወድሳሉ፤ወይኑንም፣ የሚለቅሙት ሰዎች ቅዱስ በሆኑት ቅጥር ግቢዎቼ ውስጥ ይጠጡታል።”+ +10 በበሮቹ በኩል እለፉ፤ እለፉ። ለሕዝቡ መንገዱን ጥረጉ።+ ሥሩ፤ አውራ ጎዳናውን ሥሩ። ድንጋዮቹን አስወግዱ።+ ለሕዝቦችም ምልክት* አቁሙ።+ +11 እነሆ፣ ይሖዋ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ አውጇል፦ “ለጽዮን ሴት ልጅ‘እነሆ፣ መዳንሽ ቀርቧል።+ እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ’ በሏት።”+ +12 ቅዱስ ሕዝብ፣ ይሖዋ የተቤዣቸው+ ተብለው ይጠራሉ፤አንቺም “እጅግ የምትፈለግ፣” “ያልተተወች ከተማ” ተብለሽ ትጠሪያለሽ።+ +50 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እናታችሁን በሰደድኳት ጊዜ የፍቺ የምሥክር ወረቀት+ ሰጥቻታለሁ? እናንተንስ የሸጥኳችሁ ለየትኛው አበዳሪዬ ነው? እነሆ፣ የተሸጣችሁት በገዛ ጥፋታችሁ+ ነው፤እናታችሁም እንድትሄድ የተደረገው በገዛ በደላችሁ ነው።+ + 2 ታዲያ በመጣሁ ጊዜ እዚህ ማንም ያልነበረው ለምንድን ነው? በተጣራሁስ ጊ��� የሚመልስ ሰው የጠፋው ለምንድን ነው?+ እጄ አጭር ሆና እናንተን መዋጀት ተስኗታል?ወይስ እናንተን ለመታደግ የሚያስችል ኃይል የለኝም?+ እነሆ፣ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤+ወንዞችን በረሃ አደርጋለሁ።+ ዓሣዎቻቸው ውኃ ባለማግ + 3 ሰማያትን ጨለማ አለብሳለሁ፤+ማቅንም መሸፈኛቸው አደርጋለሁ።” + 4 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ለደከመው ትክክለኛውን ቃል በመናገርእንዴት መልስ* መስጠት እንደምችል አውቅ ዘንድ+ የተማሩ ሰዎችን አንደበት* ሰጥቶኛል።+ በየማለዳው ያነቃኛል፤እንደ ተማሪ አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃል።+ + 5 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ጆሮዬን ከፍቷል፤እኔም ዓመፀኛ አልነበርኩም።+ ጀርባዬን አልሰጠሁም።+ + 6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ። ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+ + 7 ሆኖም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይረዳኛል።+ ስለዚህ አልዋረድም። ከዚህም የተነሳ ፊቴን እንደ ባልጩት አደረግኩ፤+ለኀፍረት እንደማልዳረግም አውቃለሁ። + 8 ጻድቅ መሆኔን የሚመሠክርልኝ ቀርቧል። ታዲያ ማን ሊከሰኝ* ይችላል?+ በአንድነት እንቁም።* ከእኔ ጋር ሙግት ያለው ማን ነው? እስቲ ወደ እኔ ይቅረብ። + 9 እነሆ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይረዳኛል። ታዲያ ጥፋተኛ ነህ ሊለኝ የሚችል ማን ነው? እነሆ፣ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ። ብል ይበላቸዋል። +10 ከመካከላችሁ ይሖዋን የሚፈራ፣የአገልጋዩንም ድምፅ የሚሰማ ማን ነው?+ ብርሃን በሌለበት በድቅድቅ ጨለማ የሄደ ማን ነው? በይሖዋ ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።* +11 “እነሆ፣ እናንተ እሳት የምታያይዙ፣የእሳት ፍንጣሪ የምታበሩ ሁሉ፣በእሳታችሁ ብርሃን፣ባያያዛችሁትም እሳት ብልጭታዎች መካከል ሂዱ። ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፦ በከባድ ሥቃይ ትጋደማላችሁ። +13 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ+ በራእይ ያየው በባቢሎን ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ + 2 “በተራቆተ ዓለታማ ተራራ ላይ ምልክት* አቁሙ።+ ታላላቅ ሰዎች ወደሚገቡባቸው በሮች እንዲመጡድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጥሯቸው፤ እጃችሁንም አውለብልቡ። + 3 እኔ ለሾምኳቸው* ትእዛዝ ሰጥቻለሁ።+ ቁጣዬን ለመግለጥበኩራት ሐሴት የሚያደርጉትን ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ። + 4 ስሙ! በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ ያለየብዙ ሰዎች ድምፅ ይሰማል! አዳምጡ! አንድ ላይ የተሰበሰቡ መንግሥታትናብሔራት+ ሁካታ ይሰማል! የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፏል።+ + 5 ይሖዋና የቁጣው መሣሪያዎችመላ ምድሪቱን ለመደምሰስ+ከሩቅ አገር፣+ከሰማያትም ዳርቻ እየመጡ ነው። + 6 የይሖዋ ቀን ቀርቧልና ዋይ ዋይ በሉ! በዚያ ቀን ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣል።+ + 7 ከዚህም የተነሳ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፤የሰዎችም ልብ ሁሉ በፍርሃት ይቀልጣል።+ + 8 ሰዎቹ እጅግ ተሸብረዋል።+ ምጥ እንደያዛት ሴትብርክና ሥቃይ ይዟቸዋል። እርስ በርሳቸው በታላቅ ድንጋጤ ይተያያሉ፤ፊታቸው በጭንቀት ቀልቷል። + 9 እነሆ፣ የይሖዋ ቀን ምድሪቱን አስፈሪ ቦታ ለማድረግናበምድሪቱ ላይ ያሉትን ኃጢአተኞች ለማጥፋትበንዴትና በታላቅ ቁጣጨካኝ ሆኖ እየመጣ ነው።+ +10 የሰማያት ከዋክብትና የኅብረ ከዋክብት ስብስቦቻቸው*+ብርሃን አይሰጡም፤ፀሐይ ስትወጣ ትጨልማለች፤ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም። +11 ምድሪቱን ስለ ክፋቷ፣+ክፉዎችንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ። የእብሪተኞችን ኩራት አጠፋለሁ፤የጨቋኞችንም ትዕቢት አዋርዳለሁ።+ +12 ሟች የሆነውን ሰው ከጠራ ወርቅ፣ሰዎችንም ከኦፊር ወርቅ+ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ።+ +13 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቁጣ በሚነድበት ቀን፣በታላቅ ቁጣ ሰማይን አናውጣለሁ፤ምድርንም ከቦታዋ አናጋለሁ።+ +14 እንደሚታደን የሜዳ ፍየል፣ እረ���ም እንደሌለው መንጋእያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።+ +15 የተገኘ ሁሉ ይወጋል፤የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።+ +16 ልጆቻቸው ዓይናቸው እያየ ይጨፈጨፋሉ፤+ቤታቸው ይዘረፋል፤ሚስቶቻቸውም ተገደው ይደፈራሉ። +17 እነሆ፣ ለብር ደንታ የሌላቸውን፣በወርቅም ደስ የማይሰኙትንሜዶናውያንን አስነሳባቸዋለሁ።+ +18 ቀስታቸው ወጣቶችን ይፈጃል፤+ለማህፀን ፍሬ አያዝኑም፤ለልጆችም አይራሩም። +19 ከመንግሥታትም ሁሉ እጅግ የከበረችው፣*+የከለዳውያን ውበትና ኩራት የሆነችው ባቢሎን፣+አምላክ እንደገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች።+ +20 ከዚያ በኋላ የሚቀመጥባት አይኖርም፤እንዲሁም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ የመኖሪያ ቦታ አትሆንም።+ በዚያም ዓረብ ድንኳኑን አይተክልም፤እረኞችም መንጎቻቸውን በዚያ አያሳርፉም። +21 የበረሃ ፍጥረታት በዚያ ይተኛሉ፤ቤቶቻቸው በጉጉቶች ይሞላሉ። ሰጎኖች በዚያ ይኖራሉ፤+የዱር ፍየሎችም* በዚያ ይፈነጫሉ። +22 የሚያላዝኑ ፍጥረታት በማማዎቿ፣ቀበሮዎችም በሚያማምሩ ቤተ መንግሥቶቿ ውስጥ ሆነው ይጮኻሉ። ጊዜዋ ቀርቧል፤ ቀኖቿም አይራዘሙም።”+ +5 እስቲ ለወዳጄ መዝሙር ልዘምር።መዝሙሩ ስለ ወዳጄና ስለ ወይን እርሻው+ የሚገልጽ ነው። ወዳጄ ለም በሆነ ኮረብታ ላይ የወይን እርሻ ነበረው። + 2 እሱም መሬቱን ቆፈረ፤ ድንጋዮቹንም አስወገደ። ምርጥ የሆነ ቀይ ወይን ተከለ፤በመካከሉ ማማ ገነባ፤ድንጋይ ፈልፍሎም የወይን መጭመቂያ ጉድጓድ ሠራ።+ ከዚያም ‘ወይኑ ጥሩ ፍሬ ያፈራል’ ብሎ ይጠብቅ ጀመር፤ይሁንና መጥፎ ፍሬ ብቻ አፈራ።+ + 3 “እናንተ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፣በእኔና በወይን እርሻዬ መካከል እስቲ ፍረዱ።+ + 4 ለወይን እርሻዬ ከዚህ በላይ ላደርግለት የሚገባምን ነገር አለ?+ ‘ጥሩ ወይን ያፈራል’ ብዬ ስጠብቅመጥፎ ወይን ብቻ ያፈራው ለምንድን ነው? + 5 እንግዲህ በወይን እርሻዬ ላይምን እንደማደርግ ልንገራችሁ፦ በዙሪያው ያለውን የቁጥቋጦ አጥር እነቅላለሁ፤ለእሳትም ይማገዳል።+ የድንጋይ ቅጥሩን አፈርሳለሁ፤በእግርም ይረጋገጣል። + 6 ቦታውን ጠፍ መሬት አደርገዋለሁ፤+የወይን ተክሉ አይገረዝም እንዲሁም አይኮተኮትም። ቁጥቋጦና አረም ይወርሰዋል፤+ደመናቱም ዝናብ እንዳያዘንቡበት ትእዛዝ እሰጣለሁ።+ + 7 የሠራዊት ጌታ የይሖዋ የወይን እርሻ የእስራኤል ቤት ነውና፤+የይሁዳ ሰዎች እሱ ይወደው የነበረው የአትክልት ቦታ ናቸው።* ፍትሕን ሲጠብቅ+እነሆ፣ ግፍ ይፈጸማል፤‘ጽድቅ ይሰፍናል’ ብሎ ሲጠብቅእነሆ፣ የጭንቅ ጩኸት ይሰማል።”+ + 8 ቦታ እስኪጠፋ ድረስበቤት ላይ ቤት ለሚጨምሩና+በመሬት ላይ መሬት ለሚይዙ ወዮላቸው!+እናንተም በምድሪቱ ላይ ብቻችሁን ትቀመጣላችሁ። + 9 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ማለ፦ብዙ ቤቶች ታላላቅና ያማሩ ቢሆኑም እንኳአንድም ነዋሪ የማይገኝባቸውአስፈሪ ቦታዎች ይሆናሉ።+ +10 ከአራት ሄክታር* የወይን እርሻ አንድ የባዶስ* መስፈሪያ ብቻ ይገኛል፤ከአንድ የሆሜር* መስፈሪያ ዘርም አንድ የኢፍ* መስፈሪያ ብቻ ይገኛል።+ +11 የሚያሰክር መጠጥ ለመጠጣት በማለዳ ለሚነሱ፣+የወይን ጠጅ እስከሚያቃጥላቸው ድረስ እስከ ሌሊት ለሚያመሹ ወዮላቸው! +12 በግብዣቸው ላይ በገና፣ ባለ አውታር መሣሪያ፣አታሞና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤እነሱ ግን ይሖዋ ያከናወነውን ተግባር አያስቡም፤የእጁንም ሥራ አይመለከቱም። +13 ስለዚህ ሕዝቤ እውቀት በማጣቱ+ተማርኮ ይወሰዳል፤በመካከላቸው የሚገኙ የተከበሩ ሰዎች ይራባሉ፤+ሕዝባቸውም እንዳለ በውኃ ጥም ይቃጠላል። +14 በመሆኑም መቃብር* ራሷን* አሰፋች፤አፏንም ያለልክ ከፈተች፤+የከተማዋ ውበት፣* የሚንጫጫው ሕዝቧና በውስጧ የሚፈነጥዙት ሰዎችወደዚያ ይወርዳሉ። +15 ሰውም አንገቱን ይደፋል፤የሰው ልጅ ኀፍረት ይከናነባል፤የትዕቢተኞችም ዓይን ይዋረዳል። +16 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በሚሰጠው ፍርድ* ከፍ ከፍ ይላል፤ቅዱስ+ የሆነው እውነተኛው አምላክ በጽድቅ ራሱን ይቀድሳል።+ +17 የበግ ጠቦቶችም በገዛ መሰማሪያቸው እንደተሰማሩ ሆነው ይግጣሉ፤የባዕድ አገር ሰዎች፣ የሰቡ እንስሳት ይኖሩባቸው በነበሩ ወና የሆኑ ቦታዎች ይበላሉ። +18 በደላቸውን በአታላይ ገመድ የሚስቡ፣ኃጢአታቸውንም በሠረገላ ገመድ የሚጎትቱ ወዮላቸው፤ +19 “ሥራውን ያፋጥን፤እናየውም ዘንድ ቶሎ ይምጣ። እናውቀውም ዘንድየእስራኤል ቅዱስ አምላክ ዓላማ* ይፈጸም” የሚሉ ወዮላቸው!+ +20 ጥሩውን መጥፎ፣ መጥፎውንም ጥሩ የሚሉ፣+ጨለማውን በብርሃን፣ ብርሃኑን በጨለማ የሚተኩጣፋጩን መራራ፣ መራራውን ጣፋጭ አድርገው የሚያቀርቡ ወዮላቸው! +21 በገዛ ዓይናቸው ጥበበኛ የሆኑናበራሳቸው አመለካከት ልባም የሆኑ ወዮላቸው!+ +22 የወይን ጠጅ በመጠጣት ረገድ ብርቱዎች የሆኑ፣መጠጥ በመደባለቅም የተካኑ ወዮላቸው፤+ +23 ጉቦ በመቀበል ክፉውን ከበደል ነፃ የሚያደርጉ፣+ጻድቁንም ፍትሕ የሚነፍጉ ወዮላቸው!+ +24 የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፣የደረቀም ሣር በነበልባል በንኖ እንደሚጠፋየእነሱም ሥር ይበሰብሳል፤አበባቸውም ልክ እንደ ዱቄት በየቦታው ይበናል፤ምክንያቱም እነሱ የሠራዊት ጌታ የሆነውን የይሖዋን ሕግ* ለመቀበል አሻፈረን ብለዋል፣የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል ንቀዋል።+ +25 የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ የነደደው በዚህ ምክንያት ነው፤እሱም እጁን በእነሱ ላይ ይዘረጋል፤ ይመታቸዋልም።+ ተራሮችም ይናወጣሉ፤አስከሬናቸውም በጎዳናዎች ላይ እንዳለ ቆሻሻ ይሆናል።+ ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው። +26 በሩቅ ላለ ታላቅ ሕዝብም ምልክት* አቁሟል፤+ከምድር ዳርቻ እንዲመጡ በፉጨት ጠርቷቸዋል፤+እነሆም፣ ሕዝቡ በከፍተኛ ፍጥነት እየመጣ ነው።+ +27 ከእነሱ መካከል የደከመም ሆነ የሚደናቀፍ አንድም ሰው የለም። የሚያንጎላጅም ሆነ የሚተኛ የለም። በወገባቸውም ላይ ያለው ቀበቶ አልተፈታም፤እንዲሁም የጫማቸው ማሠሪያ አልተበጠሰም። +28 ፍላጻዎቻቸው ሁሉ የሾሉ፣ደጋኖቻቸውም በሙሉ የተወጠሩ* ናቸው። የፈረሶቻቸው ኮቴ እንደ ባልጩት ድንጋይ ነው፤የሠረገሎቻቸውም መንኮራኩሮች* እንደ አውሎ ነፋስ ናቸው።+ +29 ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤እንደ ደቦል አንበሳ ያገሳሉ።+ የጉርምርምታ ድምፅ እያሰሙ አድብተው ይይዛሉ፤ከእጃቸውም የሚያስጥል ስለሌለ ተሸክመውት ይሄዳሉ። +30 በዚያም ቀን እንደ ባሕር ሞገድያጉረመርሙበታል።+ ምድሪቷን ትኩር ብሎ የሚመለከት ማንኛውም ሰው የሚያስጨንቅ ጨለማ ያያል፤ብርሃኑም እንኳ ከደመናው የተነሳ ጨልሟል።+ +21 በምድረ በዳው ባሕር* ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ ከደቡብ አቅጣጫ አውሎ ነፋሳት እየጠራረጉ እንደሚመጡ፣ከምድረ በዳ ይኸውም አስፈሪ ከሆነው ምድር የሆነ ነገር እየመጣ ነው።+ + 2 አንድ የሚያስጨንቅ ራእይ ተነገረኝ፦ ከሃዲው ክህደት ይፈጽማል፤አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፣ ተነሺ! ሜዶን ሆይ፣ ክበቢ!+ እሷ ያስከተለችው ሲቃ ሁሉ እንዲያከትም አደርጋለሁ።+ + 3 ከዚህም የተነሳ በጣም ተሠቃየሁ።*+ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት፣ምጥ ያዘኝ። እጅግ ከመጨነቄ የተነሳ መስማት ተሳነኝ፤እጅግ ከመረበሼም የተነሳ ማየት አቃተኝ። + 4 ልቤ ደከመ፤ በፍርሃት ተንቀጠቀጥኩ። የምናፍቀው የምሽት ድንግዝግዝታ ሽብር ለቀቀብኝ። + 5 ማዕዱን አሰናዱ፤ መቀመጫ ቦታዎ���ን አዘጋጁ! ብሉ፣ ጠጡ!+ እናንተ መኳንንት፣ ተነሱ፤ ጋሻውን ዘይት ቀቡ! + 6 ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “ሂድ፣ ጠባቂ አቁም፤ የሚያየውንም ነገር እንዲናገር አድርግ።” + 7 እሱም በፈረሶች የሚጎተቱ የጦር ሠረገሎች፣በአህዮች የሚጎተቱ የጦር ሠረገሎች፣በግመሎች የሚጎተቱ የጦር ሠረገሎች አየ። ዓይኑን ተክሎ በከፍተኛ ትኩረት ተመለከተ። + 8 ከዚያም እንደ አንበሳ ጮኾ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በየቀኑ በመጠበቂያው ግንብ ላይ ቆሜአለሁ፤በየሌሊቱም በጥበቃ ቦታዬ ላይ ተሰይሜአለሁ።+ + 9 እየመጣ ያለውን ነገር ተመልከት፦ ሰዎች በፈረሶች በሚጎተት የጦር ሠረገላ እየመጡ ነው!”+ ከዚያም ጮክ ብሎ እንዲህ አለ፦ “ወደቀች! ባቢሎን ወደቀች!+ የተቀረጹትን የአማልክቷን ምስሎች በሙሉ መሬት ላይ ጥሎ ሰባበረ!”+ +10 እንደ እህል የተወቃኸው ሕዝቤ፣የአውድማዬ ውጤት* ሆይ፣+ከእስራኤል አምላክ፣ ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ የሰማሁትን ነግሬሃለሁ። +11 በዱማ* ላይ የተላለፈ ፍርድ፦ አንዱ ከሴይር ጠርቶኝ እንዲህ አለኝ፦+ “ጠባቂ ሆይ፣ ስለ ሌሊቱ ምን ትላለህ? ጠባቂ ሆይ፣ ስለ ሌሊቱ ምን ትላለህ?” +12 ጠባቂውም እንዲህ አለ፦ “ሊነጋ ነው፤ ሆኖም ተመልሶ ይመሻል። መጠየቅ ከፈለጋችሁ ጠይቁ። ተመልሳችሁ ኑ!” +13 በበረሃማው ሜዳ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦ እናንተ የዴዳን+ ተጓዥ ነጋዴዎች ሆይ፣በበረሃማው ሜዳ በሚገኘው ዱር ሌሊቱን ታሳልፋላችሁ። +14 የተጠማውን ለመገናኘት ውኃ ይዛችሁ ኑ፤እናንተ የቴማ+ ነዋሪዎች ሆይ፣ለሚሸሸውም ሰው ምግብ አምጡ። +15 እነሱ ከሰይፍ፣ ከተመዘዘ ሰይፍ፣ከተደገነ ቀስትና ከተፋፋመ ጦርነት ሸሽተዋልና። +16 ይሖዋ እንዲህ ብሎኛል፦ “እንደ ቅጥር ሠራተኛ የሥራ ዘመን፣* በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የቄዳር+ ክብር ሙሉ በሙሉ ይጠፋል። +17 ከቄዳር ተዋጊዎች የሚተርፉት ቀስተኞች ጥቂት ይሆናሉ፤ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይህን ተናግሯልና።” +15 በሞዓብ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ የሞዓብ ኤር+ በሌሊት ስለወደመችጸጥ ረጭ ብላለች። የሞዓብ ቂር+ በሌሊት ስለወደመችጸጥ ረጭ ብላለች። + 2 ወደ ቤቱ፣* ወደ ዲቦን፣+ወደ ከፍታ ቦታዎቹም ለማልቀስ ወጥቷል። ሞዓብ ስለ ነቦና+ ስለ መደባ+ ዋይ ዋይ ይላል። ራስ ሁሉ ተመልጧል፤+ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።+ + 3 በጎዳናዎቹ ላይ ማቅ ለብሰው ይታያሉ። ሁሉም በጣሪያዎቻቸውና በአደባባዮቻቸው ላይ ዋይ ዋይ ይላሉ፤እያለቀሱም ይወርዳሉ።+ + 4 ሃሽቦንና ኤልዓሌ+ ያለቅሳሉ፤ድምፃቸው እስከ ያሃጽ+ ድረስ ተሰምቷል። ከዚህም የተነሳ የሞዓብ ተዋጊዎች ይጮኻሉ። እሱም* ይንቀጠቀጣል። + 5 ልቤ ስለ ሞዓብ ያለቅሳል። የሚሸሹት የሞዓብ ሰዎች እስከ ዞአርና+ እስከ ኤግላት ሸሊሺያ+ ድረስ ተሰደዱ። እያለቀሱ የሉሂትን ዳገት ይወጣሉ፤በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥፋት የተነሳ ወደ ሆሮናይም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሄዱ ይጮኻሉ።+ + 6 የኒምሪም ውኃዎች ደርቀዋልና፤ለምለሙ የግጦሽ መስክ ደርቋል፤ሣሩ ጠፍቷል፤ አንድም የለመለመ ነገር አይታይም። + 7 በመሆኑም ካከማቹት ንብረት ውስጥ የተረፈውን እንዲሁም ሀብታቸውን ተሸክመውየአኻያ ዛፎች የሚገኙበትን ሸለቆ* ይሻገራሉ። + 8 ጩኸታቸው እስከ ሞዓብ ወሰን ድረስ አስተጋብቷል።+ ዋይታቸው እስከ ኤግላይም፣እስከ በኤርዔሊም ድረስም ተሰምቷል። + 9 የዲሞን ውኃዎች በደም ተሞልተዋልና፤በዲሞንም ላይ ተጨማሪ ነገሮች አመጣለሁ፦ በሚሸሹት ሞዓባውያንናበምድሪቱ ላይ በሚቀሩት ሰዎች ላይ አንበሶች እሰዳለሁ።+ +22 ስለ ራእይ ሸለቆ* የተነገረ የፍርድ መልእክት፦+ ሁላችሁም ጣሪያ ላይ የወጣችሁት ምን ሆናችሁ ነው? + 2 አንቺ ሁከት የነገሠብሽ መዲና፣ የፈንጠዝያም ከተማ፣በትርምስ ተሞልተሻል። ነዋሪዎችሽ ያለቁት በሰይፍወይም በጦርነት ተገድለው አይደለም።+ + 3 አምባገነን መሪዎችሽ ሁሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል።+ ሆኖም ቀስት መጠቀም ሳያስፈልግ ተማርከዋል። ወደ ሩቅ ቦታ ሸሽተው ቢሄዱምየተገኙት ሁሉ ተማርከዋል።+ + 4 ስለዚህ እንዲህ አልኩ፦ “ዓይናችሁን ከእኔ ላይ አንሱ፤እኔም አምርሬ አለቅሳለሁ።+ የሕዝቤ ሴት ልጅ* ከደረሰባት ጥፋት የተነሳእኔን ለማጽናናት አትድከሙ።+ + 5 ከሉዓላዊው ጌታ፣ ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ዘንድበራእይ ሸለቆግራ የመጋባት፣ የሽንፈትና የመደናገጥ ቀን ሆኗልና።+ ቅጥሩ ይፈርሳል፤+ወደ ተራራውም ይጮኻሉ።* + 6 ኤላም+ ሰዎችን ባሳፈሩ ሠረገሎችና በፈረሶች* ላይየፍላጻ ኮሮጆዋን ይዛለች፤ቂርም+ የጋሻውን ልባስ አወለቀች።* + 7 ምርጥ የሆኑት ሸለቆዎችሽ*በጦር ሠረገሎች ይሞላሉ፤ፈረሶቹም* የከተማዋ በር ላይ ይቆማሉ፤ + 8 የይሁዳም መከለያ*+ ይወገዳል። “አንተም በዚያ ቀን የደኑን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ትመለከታለህ፤ +9 እናንተም በዳዊት ከተማ ቅጥር ላይ ያሉትን በርካታ ክፍተቶች ትመለከታላችሁ።+ በታችኛውም ኩሬ ውኃ ታጠራቅማላችሁ።+ +10 የኢየሩሳሌምን ቤቶች ትቆጥራላችሁ፤ ቅጥሩንም ለማጠናከር ቤቶቹን ታፈርሳላችሁ። +11 በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በድሮው ኩሬ ላለው ውኃ የሚሆን ማጠራቀሚያ ትሠራላችሁ፤ ይሁንና ይህን ወዳደረገው ታላቅ አምላክ አትመለከቱም፤ ከዘመናት በፊት ወደሠራውም አምላክ አታዩም። +12 በዚያም ቀን ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋእንድታለቅሱና እንድታዝኑ፣+ፀጉራችሁን እንድትላጩና ማቅ እንድትለብሱ ይጠራችኋል። +13 ይሁን እንጂ ድግስና ፈንጠዝያ፣ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት ሆኗል።+ ‘ነገ ስለምንሞት እንብላ፣ እንጠጣ’ ትላላችሁ።”+ +14 ከዚያም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በጆሮዬ ይህን ገለጠልኝ፦ “‘እናንተ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል አይሰረይላችሁም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።” +15 ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በቤቱ* ላይ ወደተሾመው ወደ መጋቢው ወደ ሸብና+ ሄደህ እንዲህ በለው፦ +16 ‘በዚህ ለራስህ የመቃብር ቦታ የወቀርከው፣ የአንተ የሆነ ምን ነገር ቢኖርህ ነው? በዚህስ የአንተ የሆነ ማን አለ? በከፍታ ቦታ የራሱን መቃብር ወቅሯል፤ ቋጥኝ ጠርቦ ለራሱ ማረፊያ ስፍራ* አዘጋጅቷል። +17 ‘አንተ ሰው፣ እነሆ፣ ይሖዋ በኃይል አሽቀንጥሮ ይጥልሃል፤ ጨምድዶም ይይዝሃል። +18 ጠቅልሎና አጡዞ እንደ ኳስ ወደ ሰፊ ምድር ይወረውርሃል። በዚያ ትሞታለህ፤ ያማሩ ሠረገሎችህም በዚያ ለጌታህ ቤት ውርደት ይሆናሉ። +19 እኔም ከሹመትህ እሽርሃለሁ፤ ከኃላፊነትህም አባርርሃለሁ። +20 “‘በዚያም ቀን አገልጋዬን የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን+ እጠራለሁ፤ +21 ቀሚስህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህንም በደንብ አስታጥቀዋለሁ፤+ ሥልጣንህንም* በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። እሱም ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና ለይሁዳ ቤት አባት ይሆናል። +22 የዳዊትንም ቤት ቁልፍ+ በትከሻው ላይ አደርጋለሁ። እሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ እሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም። +23 በአስተማማኝ ቦታ ላይ እንደ ማንጠልጠያ እተክለዋለሁ፤ ለአባቱም ቤት እንደ ክብር ዙፋን ይሆናል። +24 በእሱም ላይ የአባቱን ቤት ክብር* በሙሉ፣ ልጆቹንና ዘሮቹን* ይኸውም ትናንሾቹን ዕቃዎች በሙሉ፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹንና ትላልቆቹን እንስራዎች ሁሉ ይሰቅሉበታል። +25 “‘በዚያም ቀን’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘በአስተማማኝ ቦታ ላይ የተተከለው ማንጠልጠያ ይነቀላል፤+ ተቆርጦም ይወድቃል፤ በላዩ ላይ የተንጠለጠለው ሸክምም ወድቆ ይከሰከሳል፤ ይሖዋ ራሱ ተናግሯልና።’” +42 እነሆ፣ ደግፌ የያዝኩት፣ ደስ የምሰኝበትና*+ የመረጥኩት+ አገልጋዬ!+ መንፈሴን በእሱ ላይ አድርጌአለሁ፤+እሱ ለብሔራት ፍትሕን ያመጣል።+ + 2 አይጮኽም ወይም ድምፁን ከፍ አያደርግም፤ድምፁንም በጎዳና ላይ አያሰማም።+ + 3 የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፤የሚጨስንም የጧፍ ክር አያጠፋም።+ ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።+ + 4 እሱ ፍትሕን በምድር ላይ እስኪያሰፍን ድረስ አይሰበርም ወይም ብርሃኑ አይደክምም፤+ደሴቶችም ሕጉን* በተስፋ ይጠባበቃሉ። + 5 ሰማያትን የፈጠረውና የዘረጋው፣+ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች ሁሉ የሠራው፣+በላይዋም ለሚኖሩ ሰዎች እስትንፋስን፣+በእሷም ላይ ለሚመላለሱ መንፈስን የሰጠው+እውነተኛው አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ + 6 “እኔ ይሖዋ በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤እጅህን ይዣለሁ። እጠብቅሃለሁ፤ እንዲሁም ለሰዎች ቃል ኪዳን፣ለብሔራትም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ፤+ + 7 አንተም የዓይነ ስውራንን ዓይን ታበራለህ፤+እስረኛውን ከወህኒ ቤት፣በጨለማ ውስጥ የተቀመጡትንም ከእስር ቤት ታወጣለህ።+ + 8 እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው፤ክብሬን ለሌላ፣*ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።+ + 9 እነሆ፣ የቀደሙት ነገሮች ተፈጽመዋል፤አሁን ደግሞ አዳዲስ ነገሮችን እናገራለሁ። ገና ከመከሰታቸው በፊት ስለ እነሱ እነግራችኋለሁ።”+ +10 እናንተ በባሕር ላይና በውስጡ ባሉት ፍጥረታት መካከል የምትጓዙ፣እናንተ ደሴቶችና በእነሱ ላይ የምትኖሩ ሁሉ፣+ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+ከምድር ዳርቻም ውዳሴውን አሰሙ።+ +11 ምድረ በዳውና በዚያ ያሉ ከተሞች፣ቄዳር+ ያለችባቸውም ሰፈሮች ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ።+ ዓለታማ በሆኑ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች በደስታ እልል ይበሉ፤በተራሮችም አናት ላይ ሆነው ይጩኹ። +12 ለይሖዋ ክብር ይስጡ፤በደሴቶችም ላይ ውዳሴውን ያውጁ።+ +13 ይሖዋ እንደ ኃያል ሰው ይወጣል።+ እንደ ተዋጊ ቅንዓቱን ይቀሰቅሳል።+ ይጮኻል፤ አዎ፣ ቀረርቶ ያሰማል፤ከጠላቶቹ ይበልጥ ኃያል መሆኑን ያሳያል።+ +14 “ለረጅም ጊዜ ዝም አልኩ። ጸጥ ብዬ ቆየሁ፤ ራሴንም ገታሁ። ምጥ እንደያዛት ሴትእቃትታለሁ፣ አለከልካለሁ እንዲሁም ቁና ቁና እተነፍሳለሁ። +15 ተራሮችንና ኮረብቶችን አወድማለሁ፤ደግሞም በላያቸው ላይ ያለውን ተክል ሁሉ አደርቃለሁ። ወንዞችን ደሴቶች* አደርጋለሁ፤ቄጠማ የሞላባቸውንም ኩሬዎች አደርቃለሁ።+ +16 ዓይነ ስውራንን በማያውቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤+ባልለመዱት ጎዳናም እንዲሄዱ አደርጋቸዋለሁ።+ ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን፣+ወጣ ገባ የሆነውንም ምድር ደልዳላ ሜዳ አደርጋለሁ።+ ይህን አደርግላቸዋለሁ፤ ደግሞም አልተዋቸውም።” +17 በተቀረጸ ምስል የሚታመኑ፣ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች* “እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ” የሚሉወደ ኋላ ይመለሳሉ፤ እጅግም ያፍራሉ።+ +18 እናንተ ደንቆሮዎች፣ ስሙ፤እናንተ ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።+ +19 ከአገልጋዬ በቀር የታወረ፣እንደምልከው መልእክተኛዬም ደንቆሮ የሆነ ማን አለ? ብድራት እንደተከፈለው ሰው ዕውር የሆነወይም እንደ ይሖዋ አገልጋይ የታወረ ማን ነው?+ +20 ብዙ ነገሮች ብታዩም ልብ የምትሉት ነገር የለም። ጆሮዎቻችሁን ብትከፍቱም ምንም አትሰሙም።+ +21 ይሖዋ ለጽድቁ ሲልሕጉን* ታላቅና ክብራማ በማድረግ ደስ ተሰኝቷል። +22 ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ነው፤+ሁሉም ጉድጓድ ውስጥ ተይዘዋል፤ በእስር ቤትም ተሰውረዋል።+ የሚታደጋቸው በሌለበት ተበዝብዘዋል፤+“መልሷቸው!” የሚል በሌለበትም ተዘርፈዋል። +23 ከእናንተ መካከል ይህን የሚሰማ ማን ነው? በትኩረት የሚያዳምጥና ለወደፊቱ ጊዜ ትምህርት የሚወስድ ማን ነው? +24 ያዕቆብን ለዘረፋ፣እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው? በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም? እነሱ በመንገዱ ለመሄድ አልፈለጉም፤ሕጉንም* አይታዘዙም።+ +25 ስለዚህ ንዴቱን፣ ቁጣውንና የጦርነቱን መዓትበእስራኤል ላይ አፈሰሰ።+ የጦርነቱም እሳት በዙሪያው ያለውን ሁሉ በላው፤ እሱ ግን አላስተዋለም።+ አቃጠለው፤ እሱ ግን ጨርሶ ልብ አላለም።+ +39 በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባላዳን ልጅ ሜሮዳክባላዳን ሕዝቅያስ ታሞ እንደነበረና ከሕመሙ እንዳገገመ በመስማቱ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።+ +2 ሕዝቅያስም መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበላቸው፤ ከዚያም ግምጃ ቤቱን ይኸውም ብሩን፣ ወርቁን፣ የበለሳን ዘይቱን፣ ሌላውን ምርጥ ዘይት፣ የጦር መሣሪያውን ሁሉና በግምጃ ቤቶቹ+ ውስጥ ያለውን ንብረት በሙሉ አሳያቸው። ሕዝቅያስ በቤቱም* ሆነ በግዛቱ ሁሉ ያላሳያቸው ምንም ነገር አልነበረም። +3 ከዚያ በኋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ መጥቶ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? የመጡትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “የመጡት ከሩቅ አገር፣ ከባቢሎን ነው” አለው።+ +4 ቀጥሎም “በቤትህ* ያዩት ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “በቤቴ* ያለውን ነገር ሁሉ አይተዋል። በግምጃ ቤቶቼ ውስጥ ካለው ንብረት ሁሉ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” ሲል መለሰለት። +5 በዚህ ጊዜ ኢሳይያስ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፦ “የሠራዊት ጌታ የይሖዋን ቃል ስማ፤ +6 ‘እነሆ፣ በቤትህ* ያለው ሁሉና አባቶችህ እስካሁን ድረስ ያከማቹት ነገር ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚጋዝበት ቀን ይመጣል። አንድም የሚቀር ነገር አይኖርም’+ ይላል ይሖዋ።+ +7 ‘ከአንተ ከሚወለዱት ከገዛ ልጆችህ መካከልም አንዳንዶቹ ይወሰዳሉ፤ በባቢሎን ንጉሥ ቤተ መንግሥትም ባለሥልጣናት ይሆናሉ።’”+ +8 በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ ኢሳይያስን “የተናገርከው የይሖዋ ቃል መልካም ነው” አለው። አክሎም እንዲህ አለ፦ “ምክንያቱም በእኔ የሕይወት ዘመን* ሰላምና መረጋጋት* ይኖራል።”+ +55 እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ+ ኑ፤ ወደ ውኃው ኑ!+ እናንተ ገንዘብ የሌላችሁ ኑና ገዝታችሁ ብሉ! አዎ፣ ኑና ያለገንዘብ፣ ያለዋጋም የወይን ጠጅና ወተት+ ግዙ።+ + 2 ምግብ ላልሆነ ነገር ለምን ገንዘባችሁን ታወጣላችሁ?እርካታ ለማያስገኝ ነገርስ ለምን ገቢያችሁን* ታባክናላችሁ? እኔን በጥሞና አዳምጡ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤+ምርጥ ምግብ በመብላትም* ሐሴት ታደርጋላችሁ።*+ + 3 ጆሯችሁን አዘንብሉ፤ ወደ እኔም ኑ።+ አዳምጡ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤*ለዳዊት ካሳየሁት የማይከስም * ታማኝ ፍቅር+ ጋር በሚስማማ ሁኔታከእናንተ ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።+ + 4 እነሆ፣ ለብሔራት ምሥክር፣+መሪና+ አዛዥ+ አድርጌዋለሁ። + 5 እነሆ፣ የማታውቀውን ብሔር ትጠራለህ፤የማያውቅህ ብሔርም ለአምላክህ ለይሖዋና ለእስራኤል ቅዱስ ሲልወደ አንተ ሮጦ ይመጣል፤+ምክንያቱም እሱ ክብር ያጎናጽፍሃል።+ + 6 ይሖዋን በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት።+ በቅርብም ሳለ ጥሩት።+ + 7 ክፉ ሰው መንገዱን፣መጥፎ ሰውም ሐሳቡን ይተው፤+ምሕረት ወደሚያሳየው አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለስ፤+ይቅርታው ብዙ ነውና።*+ + 8 “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና”+ ይላል ይሖዋ። + 9 “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉመንገዴ ከመንገዳችሁ፣ሐሳቤም ከሐሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።+ +10 ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፣ምድርን በማራስ እንድታበቅልና እንድታፈራ፣ለዘሪው ዘርን፣ ለበላተኛውም ምግብን እንድትሰጥ ሳያደርግ ወደመጣበት እንደማይመለስ ሁሉ፣ +11 ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ እንዲሁ ይሆናል።+ ደስ የሚያሰኘኝን ነገር* ያደርጋል፣+የተላከበትንም ዓላማ በእርግጥ ይፈ���ማል እንጂያላንዳች ውጤት ወደ እኔ አይመለስም።+ +12 በታላቅ ደስታ ትወጣላችሁና፤+በሰላምም ትመለሳላችሁ።+ ተራሮቹና ኮረብቶቹ በደስታ በፊታችሁ እልል ይላሉ፤+የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ።+ +13 በቁጥቋጦ ፋንታ የጥድ ዛፍ ይበቅላል፤+በሳማም ፋንታ የአደስ ዛፍ ይበቅላል። የይሖዋ ስም እንዲገን ያደርጋል፤*+እንዲሁም ፈጽሞ የማይጠፋ የዘላለም ምልክት ይሆናል።” +17 “የይሁዳ ኃጢአት በብረት ብዕር ተጽፏል። በሾለ የአልማዝ ጫፍ በልባቸው ጽላትናበመሠዊያዎቻቸው ቀንዶች ላይ ተቀርጿል፤ + 2 ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻቸው ከፍ ባሉ ኮረብቶች ላይ ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ አጠገብ ያሉትን+መሠዊያዎቻቸውንና የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ያስታውሳሉ፤+ + 3 በአውላላ ሜዳ ላይ ባሉት ተራሮች ላይ ያሉትንም ያስባሉ። ንብረትህን ይኸውም ውድ ሀብትህን ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ፤+አዎ፣ በመላው ክልልህ ካለው ኃጢአት የተነሳ ከፍ ያሉ ቦታዎችህ እንዲበዘበዙ አደርጋለሁ።+ + 4 የሰጠሁህን ርስት በገዛ ፈቃድህ አሳልፈህ ትሰጣለህ።+ በማታውቀውም ምድር ጠላቶችህን እንድታገለግል አደርግሃለሁ፤+ቁጣዬን እንደ እሳት አቀጣጥለሃልና።*+ እሳቱም ለዘላለም ይነዳል።” + 5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሰዎች የሚታመን፣+በሰብዓዊ ኃይል የሚመካና*+ልቡ ከይሖዋ የራቀ ሰው* የተረገመ ነው። + 6 በበረሃ ብቻውን እንዳለ ዛፍ ይሆናል። መልካም ነገር ሲመጣ አያይም፤ይልቁንም በምድረ በዳ ደረቅ በሆኑ ስፍራዎች፣ማንም መኖር በማይችልበት የጨው ምድር ይኖራል። + 7 በይሖዋ የሚታመን፣መመኪያውም ይሖዋ የሆነ ሰው* የተባረከ ነው።+ + 8 በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣ሥሮቹን ወደ ጅረት እንደሚሰድ ዛፍ ይሆናል። ሙቀት ሲመጣ አያስተውልም፤ከዚህ ይልቅ ቅጠሉ ሁልጊዜ ይለመልማል።+ ድርቅ በሚከሰትበት ዓመትም ምንም አይጨነቅም፤ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም። + 9 ልብ ከምንም ነገር በላይ ከዳተኛ* ነው፤ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ አይመለስም።*+ ማንስ ሊያውቀው ይችላል? +10 እኔ ይሖዋ፣ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱ፣እንደ ሥራውም ፍሬ ለመስጠትልብን እመረምራለሁ፤+የውስጥ ሐሳብንም* እፈትናለሁ።+ +11 በማጭበርበር* ሀብት የሚያከማች ሰው፣ያልጣለችውን እንቁላል እንደምትሰበስብ ቆቅ ነው።+ በዕድሜው አጋማሽ ላይ ሀብቱ ትቶት ይሄዳል፤በመጨረሻም የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው መሆኑ ይረጋገጣል።” +12 ከመጀመሪያ አንስቶ ክብራማ የሆነ ዙፋን ከፍ ከፍ ብሏል፤እሱም መቅደሳችን ነው።+ +13 የእስራኤል ተስፋ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ። አንተን* የሚክዱ ስማቸው በአፈር ላይ ይጻፋል፤+ምክንያቱም የሕያው ውኃ ምንጭ የሆነውን ይሖዋን ትተዋል።+ +14 ይሖዋ ሆይ፣ ፈውሰኝ፤ እኔም እፈወሳለሁ። አድነኝ፤ እኔም እድናለሁ፤+የማወድሰው አንተን ነውና። +15 እነሆ፣ “የይሖዋ ቃል የት አለ?+ እስቲ ይፈጸም!” የሚሉኝ ሰዎች አሉ። +16 እኔ ግን እረኛ ሆኜ አንተን ከመከተል ወደኋላ አላልኩም፤የጥፋትንም ቀን ፈጽሞ አልተመኘሁም። አንተ ከንፈሮቼ የተናገሩትን ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ፤ሁሉም የተፈጸመው በፊትህ ነው! +17 ሽብር ላይ አትጣለኝ። አንተ በጥፋት ቀን መጠጊያዬ ነህ። +18 አሳዳጆቼ ኀፍረት ይከናነቡ፤+እኔ ግን ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ። እነሱ በሽብር ይዋጡ፤እኔ ግን አልሸበር። የጥፋት ቀን አምጣባቸው፤+አድቅቃቸው፤ ሙሉ በሙሉም አጥፋቸው።* +19 ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሂድና የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር እንዲሁም በኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም።+ +20 እንዲህም በላቸው፦ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ፣ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፣ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሙሉ የይሖዋን ቃል ስሙ። +21 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለራሳችሁ* ተጠንቀቁ፤ በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም አትሸከሙ ወይም በኢየሩሳሌም በሮች አታስገቡ።+ +22 በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም ከቤታችሁ ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ።+ አባቶቻችሁን እንዳዘዝኳቸው ሁሉ እናንተም የሰንበትን ቀን ቀድሱ።+ +23 ሆኖም እነሱ አልሰሙም፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም፤ ላለመታዘዝና ተግሣጽ ላለመቀበል በእንቢተኝነታቸው ጸኑ።”’*+ +24 “‘“ይሁን እንጂ በሚገባ ብትታዘዙኝ” ይላል ይሖዋ፣ “በሰንበትም ቀን በከተማዋ በሮች ሸክም ይዛችሁ ባትገቡና በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሥራ ባለመሥራት ቀኑን ብትቀድሱት፣+ +25 በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መኳንንት+ ይኸውም እነሱና መኳንንታቸው እንዲሁም የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤+ ይህችም ከተማ ለዘለቄታው የሰው መኖሪያ ትሆናለች። +26 ሰዎችም ከይሁዳ ከተሞች፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ ቦታዎች፣ ከቢንያም አገር፣+ ከቆላው፣+ ከተራራማው አካባቢና ከኔጌብ* ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎች፣+ መሥዋዕቶች፣+ የእህል መባዎች፣+ ነጭ ዕጣንና የምስጋና መሥዋዕቶች ይዘው ወደ ይሖዋ ቤት ይመጣሉ።+ +27 “‘“የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በሮቿን በእሳት አነዳለሁ፤ እሳቱም የኢየሩሳሌምን የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤+ ፈጽሞም አይጠፋም።”’”+ +30 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ +2 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የምነግርህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው። +3 “እነሆ፣ ተማርከው የተወሰዱትን ሕዝቤን፣ እስራኤልንና ይሁዳን የምሰበስብበት ጊዜ ይመጣል”+ ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ለአባቶቻቸው ወደሰጠኋት ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ዳግመኛ ይወርሷታል” ይላል ይሖዋ።’”+ +4 ይሖዋ ለእስራኤልና ለይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው። + 5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሚንቀጠቀጡ ሰዎችን ድምፅ ሰምተናል፤ሽብር ነግሦአል፤ ሰላምም የለም። + 6 ወንድ፣ መውለድ ይችል እንደሆነ እስቲ ጠይቁ። ታዲያ ብርቱ የሆነ ወንድ ሁሉ፣ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት+ እጁን ሆዱ* ላይ አድርጎ የማየው ለምንድን ነው? የሰዉ ሁሉ ፊት የገረጣው ለምንድን ነው? + 7 ወዮ! ያ ቀን አስፈሪ* ነውና።+ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ቀን ነው፤ለያዕቆብ የጭንቅ ጊዜ ይሆናል። ሆኖም ከዚያ ቀን ይተርፋል።” +8 “በዚያም ቀን፣” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “ቀንበሩን ከአንገትህ ላይ እሰብራለሁ፤ ማሰሪያህንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህ እንግዶች* ባሪያቸው አያደርጉትም።* +9 እነሱም አምላካቸውን ይሖዋንና የማስነሳላቸውን ንጉሣቸውን ዳዊትን ያገለግላሉ።”+ +10 “አንተም አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ” ይላል ይሖዋ፤“እስራኤል ሆይ፣ አትሸበር።+ አንተን ከሩቅ አገር፣ዘርህንም ተማርኮ ከተወሰደበት ምድር እታደጋለሁና።+ ያዕቆብ ይመለሳል፤ ሳይረበሽም ተረጋግቶ ይቀመጣል፤የሚያስፈራቸው አይኖርም።”+ +11 “እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ። “አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ግን ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤+ይሁን እንጂ አንተን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም።+ በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ* እንጂበምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።”+ +12 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ስብራትሽ ፈውስ የለውም።+ ቁስልሽ የማይድን ነው። +13 የሚሟገትልሽ የለም፤ቁስልሽ በምንም መንገድ ሊድን አይችልም። ለአንቺ የሚሆን ፈውስ የለም። +14 አጥብቀው የሚወዱሽ ��ሉ ረስተውሻል።+ ከእንግዲህ አይፈልጉሽም። ከባድ በደል ስለፈጸምሽና ብዙ ኃጢአት ስለሠራሽጠላት በሚማታበት መንገድ መትቼሻለሁና፤+እንደ ጨካኝ ቀጥቼሻለሁ።+ +15 ከስብራትሽ የተነሳ የምትጮኺው ለምንድን ነው? ሕመምሽ የማይፈወስ ሆኗል! ከባድ በደል ስለፈጸምሽና ብዙ ኃጢአት ስለሠራሽ+ይህን አድርጌብሻለሁ። +16 በእርግጥ የሚውጡሽ ሁሉ ይዋጣሉ፤+ጠላቶችሽም ሁሉ በምርኮ ይወሰዳሉ።+ የሚዘርፉሽ ሁሉ ይዘረፋሉ፤የሚበዘብዙሽንም ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።”+ +17 “ይሁንና ጤንነትሽን እመልስልሻለሁ፤ ቁስሎችሽንም እፈውሳለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤“እነሱ ግን የተገለለች፣ ‘ማንም የማይፈልጋት ጽዮን’ ብለውሻል።”+ +18 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ከያዕቆብ ድንኳኖች የተማረኩትን እሰበስባለሁ፤+ለማደሪያ ድንኳኖቹም እራራለሁ። ከተማዋ በጉብታዋ ላይ ዳግም ትገነባለች፤+የማይደፈረውም ማማ በተገቢው ቦታ ላይ ይቆማል። +19 ከእነሱም የምስጋናና የሳቅ ድምፅ ይሰማል።+ እኔ አበዛቸዋለሁ፤ እነሱም ጥቂት አይሆኑም፤+ቁጥራቸው እንዲጨምር* አደርጋለሁ፤የተናቁም አይሆኑም።+ +20 ወንዶች ልጆቹ እንደቀድሞው ጊዜ ይሆናሉ፤ጉባኤውም በፊቴ ጸንቶ ይመሠረታል።+ እሱን በሚጨቁኑት ሁሉ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ።+ +21 ታላቅ ግርማ የተላበሰው መሪ ከራሱ ወገን ይገኛል፤ገዢውም ከመካከሉ ይወጣል። ወደ እኔ እንዲቀርብ እፈቅድለታለሁ፤ እሱም ወደ እኔ ይቀርባል።” “አለዚያ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር* ማን ነው?” ይላል ይሖዋ። +22 “እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤+ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።”+ +23 እነሆ፣ የይሖዋ አውሎ ነፋስ በታላቅ ቁጣ ይነሳል፤+በክፉዎች ራስ ላይ እየተሽከረከረ የሚወርድ ኃይለኛ ነፋስ ይነፍሳል። +24 ይሖዋ የልቡን ሐሳብ ሳያከናውንና ሳይፈጽም፣የሚነደው ቁጣው አይመለስም።+ በዘመኑ መጨረሻ ይህን ትረዳላችሁ።+ +35 በኢዮስያስ ልጅ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም+ የግዛት ዘመን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +2 “ወደ ሬካባውያን+ ቤት ሄደህ አነጋግራቸው፤ ወደ ይሖዋም ቤት አምጥተህ ወደ አንዱ መመገቢያ ክፍል አስገባቸው፤ ከዚያም የሚጠጡትን የወይን ጠጅ አቅርብላቸው።” +3 ስለዚህ የሃባጺንያን ልጅ፣ የኤርምያስን ልጅ፣ ያአዛንያህን፣ ወንድሞቹን፣ ወንዶች ልጆቹን ሁሉና የሬካባውያንን ወገን ሁሉ ወሰድኩ፤ +4 ወደ ይሖዋ ቤትም አመጣኋቸው። የእውነተኛው አምላክ ሰው፣ የይግዳልያ ልጅ፣ የሃናን ልጆች መመገቢያ ወደሆነው ክፍል አስገባኋቸው፤ ክፍሉም የሚገኘው ከበር ጠባቂው ከሻሉም ልጅ፣ ከማአሴያህ መመገቢያ ክፍል በላይ ካለው ከመኳንንቱ መመገቢያ ክፍል አጠገብ ነው። +5 ከዚያም ከሬካባውያን ወገን በሆኑት ሰዎች ፊት በወይን ጠጅ የተሞሉ ጽዋዎችንና ዋንጫዎችን አቅርቤ “የወይን ጠጅ ጠጡ” አልኳቸው። +6 እነሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ ምክንያቱም አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ*+ እንዲህ ሲል አዞናል፦ ‘እናንተም ሆናችሁ ወንዶች ልጆቻችሁ መቼም ቢሆን የወይን ጠጅ አትጠጡ። +7 ቤት አትሥሩ፤ ዘር አትዝሩ፤ ወይን አትትከሉ ወይም የወይን እርሻ አይኑራችሁ። ይልቁንም የባዕድ አገር ሰዎች ሆናችሁ በተቀመጣችሁበት ምድር ረጅም ዘመን እንድትኖሩ ምንጊዜም በድንኳን ውስጥ ተቀመጡ።’ +8 ስለዚህ እኛም ሆንን ሚስቶቻችን እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን የአባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዘንን ቃል ሁሉ በማክበር የወይን ጠጅ የሚባል ነገር መቼም ቢሆን አንጠጣም። +9 መኖሪያ ቤትም አንሠራም፤ የወይን እርሻ፣ መሬትም ሆነ የእህል ዘር የለንም። +10 በድንኳን ውስጥ መኖራችንንና አባታችን ኢዮናዳብ* የሰጠንን ትእዛዝ ማክበራችንን እንቀጥላለን። +11 ሆኖም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ምድሪቱን ሊወጋ በመጣ ጊዜ+ እንዲህ አልን፦ ‘ኑ፣ ከከለዳውያንና ከሶርያውያን ሠራዊት ለማምለጥ ወደ ኢየሩሳሌም እንግባ’፤ በመሆኑም አሁን በኢየሩሳሌም እየኖርን ነው።” +12 የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +13 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሂድና ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ በል፦ “ቃሌን እንድትታዘዙ በተደጋጋሚ ጊዜ ማሳሰቢያ አልተሰጣችሁም?”+ ይላል ይሖዋ። +14 “የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ፣ ዘሮቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ አዝዞ ነበር፤ እነሱም እስከ ዛሬ ድረስ የወይን ጠጅ ባለመጠጣት ቃሉን ጠብቀዋል፤ በዚህም መንገድ የአባታቸውን ትእዛዝ አክብረዋል።+ ይሁንና እኔ ደግሜ ደጋግሜ ብነግራችሁም አልታዘዛችሁኝም።+ +15 እኔም አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ እንዲህ በማለት ደግሜ ደጋግሜ ወደ እናንተ ላክኋቸው፦+ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤+ ትክክል የሆነውንም ነገር አድርጉ! ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፤ ደግሞም አታገልግሏቸው። እንዲህ ካደረጋችሁ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ። +16 የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ዘሮች አባታቸው የሰጣቸውን ትእዛዝ ፈጽመዋል፤+ እነዚህ ሰዎች ግን እኔን አልሰሙም።”’” +17 “ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አደርሳለሁ ያልኩትን ጥፋት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ፤+ ብነግራቸውም እንኳ አይሰሙኝምና፤ ደጋግሜ ብጠራቸውም አይመልሱልኝም።’”+ +18 ኤርምያስም ለሬካባውያን ወገኖች እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የአባታችሁን የኢዮናዳብን ትእዛዝ ስላከበራችሁ እንዲሁም ትእዛዙን ሁሉ ስለጠበቃችሁና ያዘዛችሁን በትክክል ስለፈጸማችሁ፣ +19 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ* ዘር በፊቴ የሚያገለግል ሰው ፈጽሞ አይታጣም።”’” +31 “በዚያን ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+ + 2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወደ ማረፊያ ቦታው በሄደ ጊዜ፣ከሰይፍ የተረፉት ሰዎች በምድረ በዳ የአምላክን ሞገስ አገኙ።” + 3 ይሖዋ ከሩቅ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፦ “በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ። ከዚህም የተነሳ በታማኝ ፍቅር ወደ እኔ ሳብኩሽ።*+ + 4 አሁንም መልሼ እገነባሻለሁ፤ አንቺም ዳግመኛ ትገነቢያለሽ።+ የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ አታሞዎችሽን እንደገና አንስተሽበደስታ እየጨፈርሽ* ትወጫለሽ።+ + 5 በሰማርያ ተራሮች ላይ እንደገና የወይን ተክሎችን ትተክያለሽ፤+አትክልተኞቹ ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።+ + 6 በኤፍሬም ተራሮች የሚገኙ ጠባቂዎች ‘ተነሱ፤ ወደ ጽዮን፣ ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ እንውጣ’ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና።”+ + 7 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “በታላቅ ደስታ ወደ ያዕቆብ ጩኹ። ከብሔራት በላይ ስለሆናችሁ እልል በሉ።+ ይህን አውጁ፤ ውዳሴ አቅርቡ፤ደግሞም ‘ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን፣ የእስራኤልን ቀሪዎች አድን’ በሉ።+ + 8 ከሰሜን ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ።+ ከምድር ዳርቻዎች እሰበስባቸዋለሁ።+ በመካከላቸው ዓይነ ስውርና አንካሳ፣+ነፍሰ ጡርና ልትወልድ የተቃረበች ሴት በአንድነት ይገኛሉ። ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።+ + 9 እያለቀሱ ይመጣሉ።+ ሞገስ ለማግኘት ሲለምኑ እየመራሁ አመጣቸዋለሁ። ወደ ውኃ ጅረቶች* እመራቸዋለሁ፤+በማይሰናከሉበት ደልዳላ መንገድ እወስዳቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፤ ኤፍሬምም የበኩር ልጄ ነው።”+ +10 እናንተ ብሔራት፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፤ርቀው በሚገኙ ደሴቶችም ቃሉን አውጁ፦+ “እስራኤልን የበተነው እሱ ይሰበስበዋል። መንጋውን እንደሚጠብቅ እረኛ ይጠብቀዋል።+ +11 ይሖዋ ያዕቆብን ይዋጀዋልና፤+ከእሱም ከሚበረታው እጅ ይታደገዋል።*+ +12 እነሱም መጥተው በጽዮን ከፍ ያለ ቦታ በደስታ እልል ይላሉ፤+ደግሞም በይሖዋ ጥሩነት፣*በእህሉ፣ በአዲሱ የወይን ጠጅ፣+ በዘይቱእንዲሁም በመንጎቹ ግልገሎችና በከብቶቹ ጥጆች የተነሳ ፊታቸው ይፈካል።+ ውኃ እንደጠገበ የአትክልት ቦታ ይሆናሉ፤*+ከእንግዲህም ወዲህ አይደክሙም።”+ +13 “በዚያን ጊዜ ድንግሊቱ በደስታ ትጨፍራለች፤ወጣቶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድነት በደስታ ይጨፍራሉ።+ ሐዘናቸውን ወደ ሐሴት እለውጠዋለሁ።+ ከሐዘናቸው ተላቀው እንዲጽናኑና ደስ እንዲሰኙ አደርጋለሁ።+ +14 ካህናቱን* በተትረፈረፈ ምግብ* አጠግባለሁ፤ሕዝቤም በጥሩነቴ ይረካል”+ ይላል ይሖዋ። +15 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ+ ተሰማ፦ ራሔል ስለ ወንዶች ልጆቿ* አለቀሰች።+ ወንዶች ልጆቿ ስለሌሉከደረሰባት ሐዘን ለመጽናናት እንቢ አለች።’”+ +16 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘አታልቅሺ፤ ዓይኖችሽም እንባ አያፍስሱ፤ሥራሽ ወሮታ አለውና’ ይላል ይሖዋ። ‘ከጠላት ምድር ይመለሳሉ።’+ +17 ‘አንቺም ብሩህ ተስፋ ይጠብቅሻል’+ ይላል ይሖዋ። ‘ወንዶች ልጆችሽ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመለሳሉ።’”+ +18 “የኤፍሬምን ሲቃ በእርግጥ ሰምቻለሁ፤‘እንዳልተገራ ጥጃ አረምከኝ፤እኔም ታረምኩ። መልሰኝ፤ እኔም ወዲያውኑ እመለሳለሁ፤አንተ አምላኬ ይሖዋ ነህና። +19 ከተመለስኩ በኋላ ተጸጽቻለሁና፤+እንዳስተውል ከተደረግኩ በኋላ በሐዘን ጭኔን መታሁ። አፈርኩ፤ ተዋረድኩም፤+በወጣትነቴ የደረሰብኝን ነቀፋ ተሸክሜአለሁና።’” +20 “ኤፍሬም ከፍ አድርጌ የምመለከተው ውድ ልጄ አይደለም?+ ብዙ ጊዜ እሱን ተቃውሜ የምናገረውን ያህል፣ አሁንም አስበዋለሁና። አንጀቴ ለእሱ የሚንሰፈሰፈው ለዚህ ነው።+ ደግሞም እራራለታለሁ” ይላል ይሖዋ።+ +21 “የጎዳና ምልክቶችን ለራስሽ አቁሚ፤መንገድ የሚጠቁሙ ዓምዶችን ትከዪ።+ የምትሄጂበትን አውራ ጎዳና ልብ ብለሽ ተመልከቺ።+ የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ ተመለሽ፤ የራስሽ ወደሆኑት ወደነዚህ ከተሞች ተመለሽ። +22 ከዳተኛዪቱ ሴት ልጅ ሆይ፣ የምትወላውዪው እስከ መቼ ድረስ ነው? ይሖዋ በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሯልና፦ ሴት ወንድን አጥብቃ ታሳድዳለች።” +23 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የተማረኩባቸውን ሰዎች በምሰበስብበት ጊዜ በይሁዳ ምድርና በከተሞቹ ‘አንተ ጻድቅ መኖሪያ፣+ አንተ ቅዱስ ተራራ፣+ ይሖዋ ይባርክህ’ የሚል ቃል እንደገና ይናገራሉ። +24 በእሷም ውስጥ ይሁዳና ከተሞቹ ሁሉ እንዲሁም ገበሬዎችና የመንጋ እረኞች በአንድነት ይኖራሉ።+ +25 የዛለውን* አድሳለሁና፤ የደከመውንም* ሁሉ አበረታለሁ።”+ +26 በዚህ ጊዜ ነቃሁ፤ ዓይኔንም ገለጥኩ፤ እንቅልፌም ጣፋጭ ሆኖልኝ ነበር። +27 “እነሆ፣ በእስራኤል ቤትና በይሁዳ ቤት የሰውን ዘርና የከብትን ዘር የምዘራበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ።+ +28 “እነሱን ለመንቀል፣ ለማፍረስ፣ ለማውደም፣ ለማጥፋትና ለመደምሰስ እከታተላቸው እንደነበረ ሁሉ፣+ እነሱን ለመገንባትና ለመትከልም እከታተላቸዋለሁ”+ ይላል ይሖዋ። +29 “በዚያም ዘመን ‘የሚጎመዝዝ ወይን የበሉት አባቶች ሆነው ሳለ የልጆቹ ጥርስ ጠረሰ’*+ ብለው ዳግመኛ አይናገሩም። +30 ከዚህ ይልቅ በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው በገዛ በደሉ ይሞታል። የሚጎመዝዝ ወይን የሚበላ ሰው ሁሉ፣ የገዛ ራሱ ጥርስ ይጠርሳል።” +31 “እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ።+ +32 “ይህም ቃል ኪዳን አባቶቻቸውን እጃቸውን ይዤ ከግብፅ ምድር እየመራሁ ባወጣኋቸው ቀን ከእነሱ ጋር እንደገባሁት ዓይነት ቃል ኪዳን አይሆንም፤+ ‘እኔ እውነተኛ ጌታቸው* ብሆንም እንኳ እነሱ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል’ ይላል ይሖዋ።”+ +33 “ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና” ይላል ይሖዋ። “ሕጌን በውስጣቸው አኖራለሁ፤+ በልባቸውም እጽፈዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+ +34 “እነሱም እያንዳንዳቸው ባልንጀራቸውን፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን ‘ይሖዋን እወቅ!’ ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም፤+ ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና”+ ይላል ይሖዋ። “በደላቸውን ይቅር እላለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስታውስም።”+ +35 ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነው፣በቀን እንድታበራ ፀሐይን የሰጠው፣በሌሊትም እንዲያበሩ የጨረቃንና የከዋክብትን ሕጎች ያወጣው፣*ባሕሩን የሚያናውጠውና ኃይለኛ ማዕበል የሚያስነሳውይሖዋ እንዲህ ይላል፦+ +36 “‘የእስራኤል ዘር ምንጊዜም በፊቴ የሚኖር ብሔር መሆኑ የሚያከትመው’ ይላል ይሖዋ፣‘ይህ ሥርዓት ከተሻረ ብቻ ነው።’”+ +37 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘መላውን የእስራኤል ዘር፣ በሠሩት ነገር ሁሉ የተነሳ ልተዋቸው የምችለው፣ በላይ ያሉትን ሰማያት መለካት፣ በታች ያሉትንም የምድር መሠረቶች መመርመር የሚቻል ከሆነ ብቻ ነው’ ይላል ይሖዋ።”+ +38 “እነሆ፣ ከተማዋ ከሃናንኤል ማማ+ እስከ ማዕዘን በር+ ድረስ ለይሖዋ የምትገነባበት ጊዜ ይመጣል”+ ይላል ይሖዋ። +39 “የመለኪያ ገመዱም+ በቀጥታ ወደ ጋሬብ ኮረብታ ይዘረጋል፤ ደግሞም ወደ ጎዓ ይዞራል። +40 ሬሳና አመድ* ያለበት ሸለቆ* ሁሉ እንዲሁም የቄድሮንን ሸለቆ+ ይዞ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረስ በር+ ማዕዘን ድረስ ያለው ደልዳላ ቦታ ሁሉ ለይሖዋ የተቀደሰ ይሆናል።+ ከእንግዲህ ወዲህ አይነቀልም ወይም አይወድምም።” +18 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ +2 “ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፤+ እኔም በዚያ ቃሌን አሰማሃለሁ።” +3 ስለዚህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ወረድኩ፤ እሱም በሸክላ መዘውሮቹ ላይ እየሠራ ነበር። +4 ሆኖም ሸክላ ሠሪው በጭቃ እየሠራ የነበረው ዕቃ እጁ ላይ ተበላሸ። በመሆኑም ሸክላ ሠሪው ተስማሚ ሆኖ ባገኘው መንገድ* መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው። +5 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +6 “‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይህ ሸክላ ሠሪ እንዳደረገው እኔም በእናንተ ላይ ማድረግ አልችልም?’ ይላል ይሖዋ። ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ ጭቃ፣ እናንተም በእኔ እጅ እንዲሁ ናችሁ።+ +7 አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምነቅል፣ እንደማፈርስና እንደማጠፋ በተናገርኩ ጊዜ፣+ +8 ያ ብሔር እኔ ያወገዝኩትን ክፉ ነገር ቢተው፣ ሐሳቤን ለውጬ በእሱ ላይ ላመጣው ያሰብኩትን ጥፋት እተወዋለሁ።*+ +9 ሆኖም አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምገነባውና እንደምተክለው በተናገርኩ ጊዜ፣ +10 በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ቢያደርግና ድምፄን ባይሰማ እኔም ሐሳቤን ለውጬ ለእሱ አደርገዋለሁ ብዬ ያሰብኩትን መልካም ነገር እተወዋለሁ።’* +11 “አሁንም ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እባክህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣት እየተዘጋጀሁ ነው፤* በእናንተም ላይ ክፉ ነገር እየጠነሰስኩ ነው። እባካችሁ፣ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ�� መንገዳችሁንና ተግባራችሁንም አስተካክሉ።”’”+ +12 እነሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “ይህ ያበቃለት ጉዳይ ነው!+ እኛ እንደሆነ በራሳችን ሐሳብ እንሄዳለን፤ እያንዳንዳችንም ግትር የሆነውን ክፉ ልባችንን እንከተላለን።”+ +13 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስቲ ራሳችሁ ብሔራትን ጠይቁ። እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቷል? የእስራኤል ድንግል እጅግ የሚሰቀጥጥ ነገር አድርጋለች።+ +14 የሊባኖስ ዓለታማ ተረተር በረዶ ተለይቶት ያውቃል? ወይስ ከሩቅ ስፍራ የሚፈስሱት ቀዝቃዛ ውኃዎች ይደርቃሉ? +15 ሕዝቤ ግን እኔን ረስቶኛል።+ ለማይረባ ነገር መሥዋዕት ያቀርባሉና፤+ሰዎችም በመንገዳቸው፣ በጥንቶቹ ጎዳናዎች እንዲሰናከሉ+ደግሞም ባልተስተካከሉና ባልተደለደሉ* ተለዋጭ መንገዶች እንዲሄዱ ያደርጋሉ፤ +16 ስለዚህ ምድራቸው አስፈሪ ቦታ፣+ለዘላለምም ማፏጫ ትሆናለች።+ በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።+ +17 እንደ ምሥራቅ ነፋስ በጠላት ፊት እበትናቸዋለሁ። በሚጠፉበት ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”+ +18 እነሱም እንዲህ አሉ፦ “ኑ፣ በኤርምያስ ላይ እናሲር፤+ ሕጉ* ከካህናት፣ ምክር ከጠቢባን ወይም ቃሉ ከነቢያት አይጠፋምና። ኑና በአንደበታችን እናጥቃው፤* የሚናገረውንም ቃል አንስማ።” +19 ይሖዋ ሆይ፣ ትኩረትህን ወደ እኔ አድርግ፤ተቃዋሚዎቼ የሚናገሩትንም ስማ። +20 ስለ መልካም ነገር ክፉ መመለስ አግባብ ነው? እነሱ ጉድጓድ ቆፍረውልኛልና።*+ ቁጣህ ከእነሱ እንዲመለስ፣ ስለ እነሱ መልካም ነገር ለመናገር ምን ያህል ጊዜ በፊትህ እንደቆምኩ አስብ። +21 ስለዚህ ወንዶች ልጆቻቸውን ለረሃብ ዳርጋቸው፤ለሰይፍ ኃይል አሳልፈህ ስጣቸው።+ ሚስቶቻቸው የወላድ መሃንና መበለት ይሁኑ።+ ወንዶቻቸው በገዳይ መቅሰፍት ይሙቱ፤ወጣቶቻቸው በጦር ሜዳ በሰይፍ ተመተው ይውደቁ።+ +22 በድንገት ወራሪዎችን ስታመጣባቸውከየቤታቸው ጩኸት ይሰማ። እኔን ለመያዝ ጉድጓድ ቆፍረዋልና፤ለእግሮቼም ወጥመድ ዘርግተዋል።+ +23 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግንእኔን ለመግደል የጠነሰሱትን ሴራ ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ።+ በደላቸውን አትሸፍን፤ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ። በቁጣ ተነሳስተህ እርምጃ ስትወስድባቸው+በፊትህ ይሰናከሉ።+ +23 “በማሰማሪያዬ ያሉትን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል ይሖዋ።+ +2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሕዝቡን በሚጠብቁት እረኞች ላይ እንዲህ ይላል፦ “በጎቼን በትናችኋል፤ አባራችኋቸዋል፤ ትኩረትም አልሰጣችኋቸውም።”+ “ስለዚህ ከክፉ ድርጊታችሁ የተነሳ ትኩረቴን በእናንተ ላይ አደርጋለሁ” ይላል ይሖዋ። +3 “ከዚያም የቀሩትን በጎቼን ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደ መሰማሪያቸውም መልሼ አመጣቸዋለሁ፤+ እነሱም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ደግሞም ይበዛሉ።+ +4 እኔም በሚገባ የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሳላቸዋለሁ።+ ከእንግዲህ አይፈሩም፣ አይሸበሩም እንዲሁም አንዳቸውም አይጎድሉም” ይላል ይሖዋ። +5 “እነሆ፣ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቀንበጥ* የማስነሳበት ጊዜ እየደረሰ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “ንጉሥም ይገዛል፤+ በማስተዋል ይመላለሳል እንዲሁም በምድሪቱ ላይ ለፍትሕና ለጽድቅ ይቆማል።+ +6 በእሱ ዘመን ይሁዳ ይድናል፤+ እስራኤልም ያለስጋት ይኖራል።+ የሚጠራበትም ስም ‘ይሖዋ ጽድቃችን ነው’ የሚል ይሆናል።”+ +7 “ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ ‘የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ባወጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!’ የማይሉበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ፤+ +8 “ከዚህ ይልቅ ‘የእስራኤልን ቤት ዘሮች ከሰሜን ምድርና እነሱን ከበተነባቸው አገሮች ሁሉ ባወጣውና መልሶ ��መጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ’ ይላሉ፤ እነሱም በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።”+ +9 ነቢያቱን በተመለከተ፣ ልቤ በውስጤ ተሰብሯል። አጥንቶቼ ሁሉ እየተንቀጠቀጡ ነው። ከይሖዋና ከቅዱስ ቃሉ የተነሳእንደሰከረ ሰውናየወይን ጠጅ እንዳሸነፈው ሰው ሆንኩ። +10 ምድሪቱ በአመንዝሮች ተሞልታለችና፤+ከእርግማኑ የተነሳ ምድሪቱ አዝናለች፤+በምድረ በዳ ያሉት ማሰማሪያዎችም ደርቀዋል።+ መንገዳቸው መጥፎ ነው፤ ሥልጣናቸውንም አላግባብ ይጠቀሙበታል። +11 “ነቢዩም ሆነ ካህኑ ተበክለዋል።*+ በገዛ ቤቴ እንኳ ሳይቀር የሠሩትን ክፋት አግኝቻለሁ”+ ይላል ይሖዋ። +12 “ስለሆነም መንገዳቸው የሚያዳልጥና ጨለማ ይሆናል፤+ይገፋሉ እንዲሁም ይወድቃሉ። በሚመረመሩበት ዓመት፣ጥፋት አመጣባቸዋለሁና” ይላል ይሖዋ። +13 “በሰማርያ+ ነቢያት ላይ ደግሞ አስጸያፊ ነገር አይቻለሁ። ትንቢት የሚናገሩት በባአል አነሳሽነት ነው፤ሕዝቤ እስራኤልም እንዲባዝን አድርገዋል። +14 በኢየሩሳሌም ነቢያትም ላይ የሚዘገንኑ ነገሮች አይቻለሁ። ያመነዝራሉ፤+ በሐሰትም ይመላለሳሉ፤+ክፉ አድራጊዎችን ያደፋፍራሉ፤*ከክፋታቸውም አይመለሱም። ለእኔ ሁሉም እንደ ሰዶም፣+ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ+ ናቸው።” +15 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በነቢያቱ ላይ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እኔ ጭቁኝ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤የተመረዘም ውኃ እንዲጠጡ እሰጣቸዋለሁ።+ የኢየሩሳሌም ነቢያት በምድሪቱ ሁሉ ላይ ክህደት አሰራጭተዋልና።” +16 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ትንቢት የሚተነብዩላችሁ ነቢያት የሚናገሩትን ቃል አትስሙ።+ እነሱ እያሞኟችሁ ነው።* የሚናገሩት ራእይ ከይሖዋ አፍ የወጣ ሳይሆን+ከገዛ ልባቸው የመነጨ ነው።+ +17 እነሱ እኔን ለሚንቁ ሰዎች ደግመው ደጋግመው‘ይሖዋ “ሰላም ታገኛላችሁ” ብሏል’ ይላሉ።+ ግትር የሆነ ልባቸውን የሚከተሉትን ሁሉ‘ጥፋት አይደርስባችሁም’ ይሏቸዋል።+ +18 ቃሉን ለማየትና ለመስማትከይሖዋ የቅርብ ወዳጆች ጋር የቆመ ማን ነው? ይሰማስ ዘንድ ለቃሉ ትኩረት የሰጠ ማን ነው? +19 እነሆ፣ የይሖዋ አውሎ ነፋስ በታላቅ ቁጣ ይነሳል፤እንደሚሽከረከር ኃይለኛ ነፋስ በክፉዎች ራስ ላይ እየተሽከረከረ ይወርዳል።+ +20 ይሖዋ የልቡን ሐሳብ ሳያከናውንና ሳይፈጽምቁጣው አይመለስም። በዘመኑ መጨረሻ ይህን በግልጽ ትረዳላችሁ። +21 ነቢያቱን እኔ አልላክኋቸውም፤ እነሱ ግን ሮጡ። እኔ የነገርኳቸው ነገር የለም፤ እነሱ ግን ትንቢት ተናገሩ።+ +22 ከእኔ የቅርብ ወዳጆች ጋር ቢቆሙ ኖሮሕዝቤ ቃሌን እንዲሰማ ባደረጉ ነበር፤ደግሞም ከክፉ መንገዱና ከመጥፎ ድርጊቱ እንዲመለስ ባደረጉ ነበር።”+ +23 “እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝ? የሩቅስ አምላክ አይደለሁም?” ይላል ይሖዋ። +24 “እኔ እንዳላየው በስውር ቦታ መሸሸግ የሚችል ሰው ይኖራል?”+ ይላል ይሖዋ። “ሰማያትንና ምድርን የሞላሁት እኔ አይደለሁም?”+ ይላል ይሖዋ። +25 “‘ሕልም አይቻለሁ! ሕልም አይቻለሁ!’+ እያሉ በስሜ የሐሰት ትንቢት የሚናገሩ ነቢያትን ቃል ሰምቻለሁ። +26 የሐሰት ትንቢት ይናገሩ ዘንድ ይህ ነገር በነቢያት ልብ ውስጥ የሚኖረው እስከ መቼ ነው? እነሱ ከገዛ ልባቸው ያመነጩትን ማታለያ የሚናገሩ ነቢያት ናቸው።+ +27 አባቶቻቸው በባአል የተነሳ ስሜን እንደረሱ ሁሉ፣+ እነሱም አንዳቸው ለሌላው በሚናገሩት ሕልም አማካኝነት ሕዝቤ ስሜን እንዲረሳ ማድረግ ይፈልጋሉ። +28 ሕልም ያየ ነቢይ ሕልሙን ይናገር፤ ይሁንና ቃሌ ያለው ቃሌን በእውነት ይናገር።” “ገለባና እህል አንድ የሚያደርጋቸው ምን ነገር አለ?” ይላል ይሖዋ። +29 “ቃሌ እንደ እሳት አይደለም?”+ ይላል ይሖዋ፤ “ቋጥኝንስ እንደሚያደቅ መዶ�� አይደለም?”+ +30 “ስለዚህ እርስ በርስ ቃሌን በሚሰራረቁ ነቢያት ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ።+ +31 “እነሆ፣ በምላሳቸው እየቀባጠሩ ‘እሱ እንዲህ ይላል!’ ብለው በሚናገሩ ነቢያት ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ።+ +32 “እነሆ፣ ሐሰትን በሚያልሙና በሚናገሩ እንዲሁም የሐሰት ወሬ እያናፈሱና ጉራ እየነዙ ሕዝቤን በሚያስቱ ነቢያት ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ሆኖም እኔ አልላክኋቸውም ወይም አላዘዝኳቸውም። ስለዚህ ይህን ሕዝብ ምንም አይጠቅሙትም”+ ይላል ይሖዋ። +33 “ይህ ሕዝብ ወይም አንድ ነቢይ አሊያም አንድ ካህን ‘የይሖዋ ሸክም* ምንድን ነው?’ ብለው በሚጠይቁህ ጊዜ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘“ሸክሙ እናንተ ናችሁ! እኔም እጥላችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።’ +34 ነቢይ ወይም ካህን አሊያም ማንኛውም ሰው ‘ይህ የይሖዋ ሸክም* ነው!’ እያለ ቢናገር በእሱም ሆነ በቤተሰቡ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ። +35 እያንዳንዳችሁ ባልንጀራችሁንና ወንድማችሁን ‘ይሖዋ የሰጠው መልስ ምንድን ነው? ይሖዋ የተናገረውስ ምንድን ነው?’ ትላላችሁ። +36 ሆኖም ከእንግዲህ የይሖዋ ሸክም* ብላችሁ አትናገሩ፤ ሸክሙ* የእያንዳንዱ ሰው የገዛ ራሱ ቃል ነውና፤ እናንተም ሕያው አምላክ የሆነውን የአምላካችንን የሠራዊት ጌታ የይሖዋን ቃል ለውጣችኋል። +37 “ነቢዩን እንዲህ ትለዋለህ፦ ‘ይሖዋ የሰጠህ መልስ ምንድን ነው? ይሖዋ የተናገረውስ ምንድን ነው? +38 “የይሖዋ ሸክም!”* ማለታችሁን የማታቆሙ ከሆነ፣ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘“የይሖዋ ሸክም!”* አትበሉ’ ብዬ ከነገርኳችሁ በኋላ እናንተ ‘ይህ ቃል የይሖዋ ሸክም* ነው’ በማለታችሁ፣ +39 እነሆ፣ እናንተንም ሆነ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ የሰጠኋትን ከተማ አንስቼ ከፊቴ እወረውራችኋለሁ። +40 የማይረሳ የዘላለም ኀፍረትና የዘላለም ውርደት በእናንተ ላይ አመጣለሁ።”’”+ +34 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር፣* ሠራዊቱ ሁሉ፣ በእሱ ግዛት ሥር ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ ሁሉ ኢየሩሳሌምንና በዙሪያዋ ያሉትን ከተሞች በሙሉ እየወጉ ሳሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+ +2 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሂድና የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን+ አናግረው፤ እንዲህም በለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እሱም በእሳት ያቃጥላታል።+ +3 አንተም ከእጁ አታመልጥም፤ ያለጥርጥር ትያዛለህና፤ በእጁም አልፈህ ትሰጣለህ።+ የባቢሎንንም ንጉሥ በዓይኖችህ ታየዋለህ፤ ፊት ለፊትም ያነጋግርሃል፤ ወደ ባቢሎንም ትወሰዳለህ።’+ +4 ይሁንና የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስማ፤ ‘ይሖዋ ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ “በሰይፍ አትሞትም። +5 በሰላም ትሞታለህ፤+ ለአባቶችህ ይኸውም ከአንተ ቀድሞ ለነበሩት ነገሥታት እንዳደረጉት ለክብርህ እሳት ያነዱልሃል፤ ‘ወዮ፣ ጌታችን!’ እያሉም ያለቅሱልሃል፤ ‘እኔ ይህን ቃል ተናግሬአለሁና’ ይላል ይሖዋ።”’”’” +6 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ በኢየሩሳሌም ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ ይህን ሁሉ ቃል ነገረው፤ +7 በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ይኸውም ለኪሶንና+ አዜቃን+ እየወጋ ነበር፤+ ከይሁዳ ከተሞች መካከል ድል ሳይደረጉ የቀሩት እነዚህ የተመሸጉ ከተሞች ብቻ ነበሩና። +8 ንጉሥ ሴዴቅያስ ነፃነት ለማወጅ+ በኢየሩሳሌም ከነበረው ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ከገባ በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ +9 ቃል ኪዳኑ፣ እያንዳንዱ ሰው ዕብራውያን የሆኑ ወንድና ሴት ባሪያዎቹን በነፃ እንዲለቅ፣ ደግሞም ማንኛውም ሰው ወገኑ የሆነውን አይሁዳዊ፣ ባሪያው አድርጎ እ��ዳያሠራ የሚያዝዝ ነበር። +10 በመሆኑም መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ እንደተባሉት አደረጉ። እያንዳንዳቸው ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን በነፃ ለመልቀቅና ከዚያ በኋላ ባሪያ አድርገው ላለማሠራት ቃል ኪዳን ገቡ። እንደተባሉት በማድረግ ባሪያዎቻቸውን አሰናበቷቸው። +11 በኋላ ግን ነፃ ለቀዋቸው የነበሩትን ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን መለሷቸው፤ እንደገናም አስገድደው በባርነት ገዟቸው። +12 ስለዚህ የይሖዋ ቃል ከይሖዋ ዘንድ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +13 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ቤት ባወጣኋቸው ጊዜ+ እንዲህ ስል ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፦+ +14 “እያንዳንዳችሁ የተሸጠላችሁንና ስድስት ዓመት ሲያገለግላችሁ የቆየውን ዕብራዊ የሆነውን ወንድማችሁን በሰባተኛው ዓመት ማብቂያ ላይ ልቀቁት፤ በነፃ ልታሰናብቱት ይገባል።”+ አባቶቻችሁ ግን አልሰሙኝም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡኝም። +15 እናንተም በቅርቡ* ተመልሳችሁ ለወገኖቻችሁ ነፃነት በማወጅ በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር አደረጋችሁ፤ ስሜ በተጠራበትም ቤት በፊቴ ቃል ኪዳን ገባችሁ። +16 በኋላ ግን ሐሳባችሁን ቀይራችሁ፣ እንደ ፍላጎታቸው* በነፃ የለቀቃችኋቸውን ወንድና ሴት ባሪያዎቻችሁን መልሳችሁ በማምጣት ስሜን አረከሳችሁ፤+ አስገድዳችሁም ወደ ባርነት መለሳችኋቸው።’ +17 “ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ለወንድማችሁና ለወገናችሁ ነፃነት በማወጅ አልታዘዛችሁኝም።+ በመሆኑም እኔ ለእናንተ ያወጅኩት ነፃነት ይህ ነው’ ይላል ይሖዋ፤ ‘በሰይፍ፣ በቸነፈርና* በረሃብ ታልቃላችሁ፤+ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መቀጣጫ አደርጋችኋለሁ።+ +18 ጥጃውን ሁለት ቦታ ከፍለው በመካከሉ ባለፉ ጊዜ በፊቴ የገቡትን ቃል ኪዳን+ ባለማክበር ቃል ኪዳኔን የጣሱት ሰዎች የሚደርስባቸው ነገር ይህ ነው፤ +19 ይኸውም የይሁዳ መኳንንት፣ የኢየሩሳሌም መኳንንት፣ የቤተ መንግሥቱ ባለሥልጣናት፣ ካህናቱና ለሁለት በተከፈለው ጥጃ መካከል ያለፈው የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ይህ ነገር ይደርስባቸዋል፦ +20 ለጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎች አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።+ +21 የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን ሁሉ ለጠላቶቻቸው፣ ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎችና እናንተን መውጋት ትቶ ለተመለሰው+ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ።’+ +22 “‘እነሆ፣ እኔ ይህን ትእዛዝ አስተላልፋለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱንም ወደዚህች ከተማ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ይወጓታል፣ ይይዟታል፣ በእሳትም ያቃጥሏታል፤+ የይሁዳንም ከተሞች ማንም የማይኖርበት ጠፍ መሬት አደርጋቸዋለሁ።’”+ +19 ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “ሄደህ፣ ከሸክላ ሠሪ ገንቦ ግዛ።+ ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከካህናቱ ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑትን ይዘህ +2 በገል በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሂኖም ልጅ ሸለቆ+ ውጣ። የምነግርህንም ቃል በዚያ አውጅ። +3 እንዲህ ትላለህ፦ ‘እናንተ የይሁዳ ነገሥታትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የይሖዋን ቃል ስሙ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘“በዚህ ስፍራ ላይ ጥፋት ላመጣ ነው፤ ስለሚመጣው ጥፋት የሚሰማ ሰው ሁሉ ጆሮውን ይነዝረዋል። +4 ምክንያቱም እኔን ትተውኛል፤+ ይህን ስፍራም የማይታወቅ ቦታ አድርገውታል።+ በዚህ ስፍራ እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው እንዲሁም የይሁዳ ነገሥታት ለማያውቋቸው ሌሎች አማልክት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ይህን ስፍራም በንጹሐን ደም ሞልተውታል።+ +5 እኔ ያላዘዝኩትን ወይም ያልተናገርኩትን፣ በልቤም እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን* ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶች ልጆቻቸውን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገው ለባአል በእሳት ለማቃጠል ከፍ ያሉትን የባአል የማምለኪያ ቦታዎች ሠሩ።”’+ +6 “‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ስለዚህ፣ እነሆ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ እንጂ ቶፌት ወይም የሂኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል።+ +7 በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ዕቅድ አጨናግፋለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት በሰይፍ እንዲወድቁ፣ ሕይወታቸውንም* በሚሹ ሰዎች እጅ እንዲጠፉ አደርጋለሁ። አስከሬናቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል እንዲሆን እሰጣለሁ።+ +8 ይህችንም ከተማ አስፈሪ ቦታና ማፏጫ አደርጋታለሁ። በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በደረሰባት መቅሰፍት የተነሳ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ ደግሞም ያፏጫል።+ +9 ጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚሹ* ሰዎች ሲከቧቸውና መፈናፈኛ አሳጥተው ሲያስጨንቋቸው የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸው የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።”’+ +10 “ከዚያም ገንቦውን ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ስበረው፤ +11 እንዲህም በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንድ ሰው የሸክላ ሠሪን ዕቃ ሊጠገን በማይችል መንገድ እንደሚሰብረው፣ እኔም ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እንዲሁ እሰባብራለሁ፤ እነሱም የመቃብር ቦታ እስኪታጣ ድረስ የሞቱትን በቶፌት ይቀብራሉ።”’+ +12 “‘ይህችን ከተማ እንደ ቶፌት አደርጋት ዘንድ በዚህ ስፍራና በነዋሪዎቹ ላይ ይህን እፈጽማለሁ’ ይላል ይሖዋ። +13 ‘የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፣ አዎ በጣሪያዎቻቸው ላይ ለሰማያት ሠራዊት መሥዋዕቶች ያቀረቡባቸውና+ ለሌሎች አማልክት የመጠጥ መባዎች ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ+ እንደዚህ ስፍራ፣ እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።’”+ +14 ኤርምያስ፣ ይሖዋ ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ከቶፌት ሲመለስ በይሖዋ ቤት ግቢ ቆሞ ለመላው ሕዝብ እንዲህ አለ፦ +15 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ሁሉ ላይ አመጣዋለሁ ብዬ የተናገርኩትን ጥፋት ሁሉ አወርድባቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ቃሌን ለመታዘዝ በግትርነት አሻፈረን ብለዋል።’”*+ +20 በይሖዋ ቤት ዋና ሹም የነበረው የኢሜር ልጅ ካህኑ ጳስኮር፣ ኤርምያስ እነዚህን ነገሮች ሲተነብይ ሰማ። +2 ጳስኮርም ነቢዩ ኤርምያስን መታው፤ ከዚያም በይሖዋ ቤት ባለው በላይኛው የቢንያም በር በእግር ግንድ ጠረቀው።+ +3 ይሁንና በማግስቱ ጳስኮር ኤርምያስን ከእግር ግንዱ ውስጥ ፈታው፤ በዚህ ጊዜ ኤርምያስ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ፣ ማጎርሚሳቢብ*+ ብሎ ይጠራሃል እንጂ ጳስኮር አይልህም። +4 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘አንተም ሆንክ ወዳጆችህ እንድትሸበሩ አደርጋለሁ፤ እነሱም ዓይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ፤+ ይሁዳንም ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እሱም በግዞት ወደ ባቢሎን ይወስዳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።+ +5 የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን ሁሉ፣ ውድ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ እንዲሁም የይሁዳን ነገሥታት ውድ ሀብት ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።+ እነሱም ይበዘብዟቸዋል፤ ወደ ባቢሎንም ያግዟቸዋል።+ +6 ጳስኮር ሆይ፣ አንተና በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ በግዞት ትወሰዳላችሁ። ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ፤ በዚያም ትሞታለህ፤ ከወዳጆችህም ሁሉ ጋር በዚያ ትቀበራለህ፤ ምክንያቱም ለእነሱ የሐሰት ትንቢት ተናግረሃል።’”+ + 7 ይሖዋ ሆይ፣ አሞኘኸኝ፤ እኔም ተሞኘሁ። አንተ በእኔ ላይ በረታህ፤ አሸነፍክም።+ እኔም ቀኑን ሙሉ መሳለቂያ ሆንኩ፤ሁሉም ያፌዙብኛል።+ + 8 በተናገር�� ቁጥር እጮኻለሁና፤“ዓመፅና ጥፋት!” ብዬ አውጃለሁ። የይሖዋ ቃል ቀኑን ሙሉ ስድብና ፌዝ አስከትሎብኛል።+ + 9 ስለዚህ “እሱን አላነሳም፤ከእንግዲህም በስሙ አልናገርም” አልኩ።+ ይሁንና ቃሉ በልቤ ውስጥ እንዳለ፣ በአጥንቶቼም ውስጥ እንደገባ የሚነድ እሳት ሆነብኝ፤አፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ከዚህ በላይ መቋቋም አልቻልኩም።+ +10 ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁና፤በዙሪያዬ ያለው ሁኔታ አሸብሮኛል።+ “አውግዙት፤ እናውግዘው!” ሰላም የሚመኝልኝ ሰው ሁሉ የእኔን ውድቀት ይጠባበቃል፦+ “ምናልባት ይታለል ይሆናል፤እኛም እናሸንፈዋለን፤ ደግሞም እንበቀለዋለን።” +11 ይሖዋ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነበር።+ ከዚህም የተነሳ የሚያሳድዱኝ ሰዎች ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም።+ ስለማይሳካላቸውም ለከፍተኛ ኀፍረት ይዳረጋሉ። የሚደርስባቸው ዘላለማዊ ውርደት ፈጽሞ አይረሳም።+ +12 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ጻድቁን ትመረምራለህ፤የውስጥ ሐሳብንና* ልብን ታያለህ።+ በእነሱ ላይ የምትወስደውን የበቀል እርምጃ እንዳይ አድርገኝ፤+ጉዳዬን ለአንተ አቅርቤአለሁና።+ +13 ለይሖዋ ዘምሩ! ይሖዋን አወድሱ! እሱ ድሃውን* ከክፉ አድራጊዎች እጅ ታድጓልና። +14 የተወለድኩበት ቀን የተረገመ ይሁን! እናቴ እኔን የወለደችበት ቀን አይባረክ!+ +15 ለአባቴ “ልጅ፣ አዎ ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል!” የሚል ምሥራች አብስሮ እጅግ ደስ ያሰኘው ሰው የተረገመ ይሁን። +16 ያ ሰው፣ ይሖዋ ያላንዳች ጸጸት እንደገለበጣቸው ከተሞች ይሁን። በማለዳ ዋይታ፣ በቀትርም የጦርነት ሁካታ ይስማ። +17 እናቴ የመቃብሬ ቦታ እንድትሆን፣ማህፀኗም ዘወትር እርጉዝ እንደሆነ ይኖር ዘንድ፣ገና በማህፀን ሳለሁ ለምን አልገደለኝም?+ +18 ችግርንና ሐዘንን እንዳይ፣ዕድሜዬም በኀፍረት እንዲያከትምለምን ከማህፀን ወጣሁ?+ +3 ሰዎች እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፦ “አንድ ሰው ሚስቱን ቢያሰናብታት፣ እሷም ተለይታው ብትሄድና የሌላ ሰው ሚስት ብትሆን፣ ዳግመኛ ወደ እሷ መመለስ ይኖርበታል?” ይህች ምድር ጨርሶ ተበክላ የለም?+ “አንቺ ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመነዘርሽ፤+ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ይገባሻል?” ይላል ይሖዋ። + 2 “ዓይንሽን አንስተሽ የተራቆቱትን ኮረብቶች ተመልከቺ። አንቺ ያልተደፈርሽበት ቦታ ይገኛል? በምድረ በዳ እንዳለ ዘላን*አንቺም በመንገዶቹ ዳር ተቀምጠሽ ጠበቅሻቸው። በዝሙትሽና በክፋትሽምድሪቱን በከልሽ።+ + 3 ስለዚህ ዝናብ እንዳይዘንብ ተከልክሏል፤+የኋለኛው ዝናብም አልዘነበም። አንቺ ዝሙት አዳሪ እንደሆነች ሚስት፣ ዓይን አውጣ ነሽ፤*ኀፍረት የሚባል ነገር አታውቂም።+ + 4 አሁን ግን ወደ እኔ ተጣርተሽ እንዲህ ትያለሽ፦‘አባቴ፣ አንተ ከልጅነቴ ጀምሮ ወዳጄ ነህ!+ + 5 ለዘላለም ቅር ትሰኛለህ?ወይስ ቂም እንደያዝክ ትኖራለህ?’ አንቺ እንዲህ ትያለሽ፤ይሁንና የቻልሽውን ያህል ክፉ ነገር መሥራትሽን ቀጥለሻል።”+ +6 በንጉሥ ኢዮስያስ+ ዘመን ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል ያደረገችውን አይተሃል? ከፍ ባለው ተራራ ሁሉ ላይና ቅጠሉ ከተንዠረገገው ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ሄዳለች።+ +7 ይህን ሁሉ ነገር ካደረገች በኋላ እንኳ ወደ እኔ እንድትመለስ መወትወቴን ቀጠልኩ፤+ እሷ ግን አልተመለሰችም፤ ይሁዳም ከሃዲ የሆነችውን እህቷን ተመለከተች።+ +8 ይህን ባየሁ ጊዜ፣ በማመንዘሯ የተነሳ+ ታማኝነቷን ላጎደለችው ለእስራኤል የፍችዋን የምሥክር ወረቀት ሰጥቼ አሰናበትኳት።+ ያም ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ አልፈራችም፤ እሷም ሄዳ አመነዘረች።+ +9 አመንዝራነቷን አቅልላ ተመለከተችው፤ ምድሪቱን መበከሏን እንዲሁም ከድንጋዮችና ከዛፎች ጋር ማመ���ዘሯን ቀጠለች።+ +10 ይህም ሁሉ ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ ለይስሙላ እንጂ በሙሉ ልቧ ወደ እኔ አልተመለሰችም’ ይላል ይሖዋ።” +11 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል፣ ከሃዲ ከሆነችው ይሁዳ ይልቅ ጻድቅ ሆና* ተገኝታለች።+ +12 ሂድና እነዚህን ቃላት ወደ ሰሜን+ አውጅ፦ “‘“ከዳተኛይቱ እስራኤል ሆይ፣ ተመለሽ” ይላል ይሖዋ።’+ ‘“እኔ ታማኝ ስለሆንኩ እናንተን በቁጣ አልመለከትም”*+ ይላል ይሖዋ።’ ‘“ለዘላለም ቅር አልሰኝም። +13 ብቻ የሠራሽውን በደል አምነሽ ተቀበይ፤ በአምላክሽ በይሖዋ ላይ ዓምፀሻልና። ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር ከእንግዶች* ጋር አመነዘርሽ፤* ቃሌንም አትታዘዢም” ይላል ይሖዋ።’” +14 “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ” ይላል ይሖዋ። “እኔ እውነተኛ ጌታችሁ* ሆኛለሁና፤ ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድም ሁለት እያደረግኩ እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ።+ +15 እንደ ልቤ የሆኑ እረኞችም እሰጣችኋለሁ፤+ እነሱም በእውቀትና በጥልቅ ማስተዋል ይመግቧችኋል። +16 በዚያ ዘመን በምድሪቱ ላይ ትበዛላችሁ፤ ፍሬያማም ትሆናላችሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ከእንግዲህ ‘የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት!’ አይሉም፤ ስለ እሱ አያስቡም፤ ጨርሶ አያስታውሱትም ወይም እንዳጎደላቸው ሆኖ አይሰማቸውም፤ ታቦቱም ዳግመኛ አይሠራም። +17 በዚያን ጊዜ ኢየሩሳሌምን የይሖዋ ዙፋን ብለው ይጠሯታል፤+ ብሔራትም ሁሉ በአንድነት የይሖዋን ስም ለማወደስ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ፤+ ከዚያ በኋላ ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን አይከተሉም።” +18 “በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት አብረው ይሄዳሉ፤+ በአንድነት ከሰሜን ምድር ተነስተው ለአባቶቻችሁ ርስት አድርጌ ወደሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።+ +19 እኔም እንዲህ ብዬ አሰብኩ፦ ‘በወንዶች ልጆች መካከል ባስቀምጥሽ፣ የተወደደችውንም ምድር፣ በብሔራት መካከል የምትገኘውን እጅግ ያማረች ርስት ብሰጥሽ ምንኛ ደስ ባለኝ!’+ በተጨማሪም እናንተ ‘አባቴ!’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሱም ብዬ አስቤ ነበር። +20 ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እናንተ ግን ባሏን* ክዳ እንደምትሄድ ሚስት በእኔ ላይ ክህደት ፈጽማችኋል’+ ይላል ይሖዋ።” +21 በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ድምፅ ተሰምቷል፤አዎ፣ የእስራኤል ልጆች ለቅሶና ልመና ተሰምቷል፤እነሱ መንገዳቸውን አጣመዋልና፤አምላካቸውን ይሖዋን ረስተዋል።+ +22 “እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ። ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።”+ “እነሆ፣ እኛ ወደ አንተ መጥተናል!ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህና።+ +23 ኮረብቶቹና በተራሮቹ ላይ የሚሰማው ሁካታ የሐሰት ናቸው።+ በእርግጥ የእስራኤል መዳን በአምላካችን በይሖዋ ነው።+ +24 ይሁንና አሳፋሪው ነገር* ከልጅነታችን ጀምሮ አባቶቻችን የደከሙበትን ሁሉ፣+መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በልቷል። +25 ኀፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ውርደታችንም ይሸፍነን፤እኛና አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ እስካሁን ድረስበአምላካችን በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፤+ የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅም አልታዘዝንም።” +52 ሴዴቅያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 21 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ። እናቱ ሀሙጣል+ ትባል ነበር፤ እሷም የሊብና ሰው የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። +2 ሴዴቅያስም ኢዮዓቄም እንዳደረገው ሁሉ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ +3 እነዚህ ነገሮች በኢየሩሳሌምና በይሁዳ የተፈጸሙት ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ ነው፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው።+ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዓመፀ።+ +4 ሴዴቅያስ በነገሠ በ���ጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ሠራዊቱን ሁሉ አስከትሎ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ። በዙሪያዋም ሰፈሩ፤ ደግሞም በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ቆለሉ።+ +5 ከተማዋም እስከ ንጉሥ ሴዴቅያስ 11ኛ ዓመት ድረስ ተከበበች። +6 በአራተኛው ወር፣ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን+ በከተማዋ ውስጥ ረሃቡ እጅግ ከፋ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትም ሰዎች የሚላስ የሚቀመስ አጡ።+ +7 በመጨረሻም የከተማዋ ቅጥር ተነደለ፤ ከለዳውያን ከተማዋን ከበው ሳለም ወታደሮቹ ሁሉ በንጉሡ የአትክልት ቦታ አቅራቢያ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ከከተማዋ ወጥተው ሸሹ፤ ወደ አረባ የሚወስደውንም አቅጣጫ ይዘው ሄዱ።+ +8 ይሁንና የከለዳውያን ሠራዊት ንጉሡን አሳደደ፤ ሴዴቅያስንም+ በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት፤ ወታደሮቹም ሁሉ ጥለውት ተበታተኑ። +9 ከዚያም ንጉሡን ይዘው በሃማት ምድር በምትገኘው በሪብላ ወደነበረው የባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ እሱም ፈረደበት። +10 የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አረዳቸው፤ በተጨማሪም የይሁዳን መኳንንት ሁሉ በዚያው በሪብላ አረዳቸው። +11 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ፣ የሴዴቅያስን ዓይን አሳወረ፤+ በመዳብ የእግር ብረት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ እስከ ዕለተ ሞቱም ድረስ በእስር ቤት አቆየው። +12 በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ናቡከደነጾር* በነገሠ በ19ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃና የባቢሎን ንጉሥ አገልጋይ የሆነው ናቡዛራዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።+ +13 እሱም የይሖዋን ቤት፣ የንጉሡን ቤትና* በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ ትላልቅ ቤቶችንም ሁሉ በእሳት አጋየ። +14 ከዘቦቹ አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር በሙሉ አፈረሰ።+ +15 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ችግረኛ ከሆኑት ሰዎች መካከል የተወሰኑትንና በከተማዋ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎች አጋዘ። በተጨማሪም ከድተው ለባቢሎን ንጉሥ እጃቸውን የሰጡትን ሰዎችና የቀሩትን የተካኑ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ወሰደ።+ +16 ሆኖም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን፣ በምድሪቱ ከነበሩት ያጡ የነጡ ድሆች መካከል አንዳንዶቹ የወይን አትክልት ሠራተኞች ሆነው እንዲያገለግሉና የግዳጅ አገልግሎት እንዲሰጡ በዚያው ተዋቸው።+ +17 ከለዳውያን የይሖዋን ቤት የመዳብ ዓምዶች+ እንዲሁም በይሖዋ ቤት ውስጥ የነበሩትን የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችና+ የመዳብ ባሕር+ ሰባብረው መዳቡን በሙሉ ወደ ባቢሎን አጋዙ።+ +18 በተጨማሪም አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ አካፋዎቹን፣ የእሳት ማጥፊያዎቹን፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹን፣+ ጽዋዎቹንና+ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉትን የመዳብ ዕቃዎች ሁሉ ወሰዱ። +19 የዘቦቹ አለቃ ከንጹሕ ወርቅና ብር የተሠሩትን ዕቃዎች+ ይኸውም ሳህኖቹን፣+ መኮስተሪያዎቹን፣ ጎድጓዳ ሳህኖቹን፣ አመድ ማጠራቀሚያዎቹን፣ መቅረዞቹን፣+ ጽዋዎቹንና ሌሎቹን ጎድጓዳ ሳህኖች ወሰደ። +20 ንጉሥ ሰለሞን ለይሖዋ ቤት ያሠራቸው ሁለቱ ዓምዶች፣ ባሕሩ፣ ከባሕሩ ሥር ያሉት 12 የመዳብ በሬዎችና+ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎቹ የተሠሩበት መዳብ ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የሚችል አልነበረም። +21 ዓምዶቹ እያንዳንዳቸው 18 ክንድ* ቁመት ነበራቸው፤ የዙሪያቸው መጠን በመለኪያ ገመድ 12 ክንድ፣+ ውፍረታቸውም አራት ጣት* ሲሆን ውስጣቸው ክፍት ነበር። +22 በዓምዱም አናት ላይ ያለው ጌጥ ከመዳብ የተሠራ ነበር፤ የአንዱ ጌጥ ርዝማኔ አምስት ክንድ+ ሲሆን በዙሪያው ያሉት ሮማኖችና መረቡ በሙሉ ከመዳብ የተሠሩ ነበሩ። ሁለተኛው ዓምድ፣ ሮማኖቹን ጨምሮ ከዚህ ጋ�� ተመሳሳይ ነበር። +23 በጎኖቹ ላይ* 96 ሮማኖች የነበሩ ሲሆን በመረቡ ዙሪያ ያሉት ሮማኖች በጠቅላላ 100 ነበሩ።+ +24 በተጨማሪም የዘቦቹ አለቃ የካህናት አለቃ የሆነውን ሰራያህን፣+ ሁለተኛውን ካህን ሶፎንያስንና+ ሦስቱን የበር ጠባቂዎች ወሰዳቸው።+ +25 ደግሞም ከከተማዋ የወታደሮቹ ኃላፊ የሆነን አንድ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን፣ በከተማዋ ውስጥ የነበሩትን ሰባቱን የንጉሡ የቅርብ ሰዎች፣ የምድሪቱን ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ እንዲሁም ከተማዋ ውስጥ የተገኙትን በምድሪቱ የሚኖሩ 60 ተራ ሰዎች ወሰደ። +26 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን እነዚህን ሰዎች ይዞ፣ በሪብላ ወዳለው ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጣቸው። +27 የባቢሎን ንጉሥ በሃማት ምድር ባለችው በሪብላ+ ሰዎቹን መትቶ ገደላቸው። በዚህ መንገድ ይሁዳ ከምድሩ በግዞት ተወሰደ።+ +"28 ናቡከደነጾር* በግዞት የወሰዳቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፦ በሰባተኛው ዓመት 3,023 አይሁዳውያንን ወሰደ።+ " +29 በናቡከደነጾር* 18ኛ ዓመት+ ከኢየሩሳሌም 832 ሰዎች* ተጋዙ። +"30 ናቡከደነጾር* በነገሠ በ23ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ከአይሁዳውያን መካከል 745 ሰዎችን* በግዞት ወሰደ።+ በአጠቃላይ 4,600 ሰዎች* በግዞት ተወሰዱ። " +31 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ኤዊልሜሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን+ ፈታው፤* ከእስር ቤትም አወጣው፤+ ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በግዞት በተወሰደ በ37ኛው ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በ25ኛው ቀን ነበር። +32 በርኅራኄም አናገረው፤ ዙፋኑንም በባቢሎን ከእሱ ጋር ከነበሩት ከሌሎች ነገሥታት ዙፋን ይበልጥ ከፍ ከፍ አደረገለት። +33 በመሆኑም ዮአኪን የእስር ቤት ልብሱን አወለቀ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ በቋሚነት ከንጉሡ ማዕድ ይመገብ ነበር። +34 የባቢሎን ንጉሥ፣ ዮአኪን እስከሞተበት ጊዜ ድረስ፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሳያቋርጥ ቀለቡን በየዕለቱ ይሰጠው ነበር። +24 ከዚያም ይሖዋ በለስ የያዙ ሁለት ቅርጫቶችን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የይሁዳን ንጉሥ የኢዮዓቄምን ልጅ+ ኢኮንያንን፣*+ ከይሁዳ መኳንንት፣ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ከአንጥረኞቹ* ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ከወሰዳቸው በኋ +2 በአንደኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች በመጀመሪያው ወቅት ላይ እንደሚደርሱ በለሶች ጥሩ ዓይነት ነበሩ፤ በሌላኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች ደግሞ መጥፎ ዓይነት ነበሩ፤ በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳም ሊበሉ የሚችሉ አልነበሩም። +3 ከዚያም ይሖዋ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ አልኩ፦ “የበለስ ፍሬዎችን አያለሁ፤ ጥሩዎቹ በለሶች በጣም ጥሩ ዓይነት ናቸው፤ መጥፎዎቹ ደግሞ በጣም መጥፎ ዓይነት ናቸው፤ ከመጥፎነታቸውም የተነሳ ሊበሉ አይችሉም።”+ +4 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +5 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድኳቸውን የይሁዳ ግዞተኞች እንደነዚህ ጥሩ ዓይነት በለሶች በጥሩ ዓይን እመለከታቸዋለሁ። +6 መልካም ነገር አደርግላቸው ዘንድ ዓይኔን በእነሱ ላይ አኖራለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እንዲመለሱ አደርጋለሁ።+ እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።+ +7 እኔ ይሖዋ መሆኔን እንዲያውቁም ልብ እሰጣቸዋለሁ።+ በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ+ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።+ +8 “‘ይሁንና ከመጥፎነታቸው የተነሳ ሊበሉ የማይችሉትን መጥፎ በለሶች+ በተመለከተ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣+ መኳንንቱን፣ በዚህች ምድር ላይ የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቀሪዎችና በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በዚሁ ዓይን እመለከታቸዋለሁ።+ +9 ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤+ በምበትናቸው ቦታም ሁሉ+ ነቀፋ እንዲደርስባቸው፣ መተረቻ እንዲሆኑ፣ እንዲፌዝባቸውና እንዲረገሙ አደርጋለሁ።+ +10 ለእነሱና ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር ላይ እስኪጠፉ ድረስ በእነሱ ላይ ሰይፍ፣+ ረሃብና ቸነፈር* እሰዳለሁ።”’”+ +32 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በ10ኛው ዓመት ይኸውም ናቡከደነጾር* በነገሠ በ18ኛው ዓመት ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው።+ +2 በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤርምያስም በይሁዳ ንጉሥ ቤት፣* በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ታስሮ ነበር። +3 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ በማለት አስሮት ነበርና፦+ “እንዲህ ብለህ ትንቢት የምትናገረው ለምንድን ነው? አንተ እንዲህ ትላለህ፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እሱም ይይዛታል፤+ +4 የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፤ ያላንዳች ጥርጥር በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፤ ከንጉሡም ጋር ፊት ለፊት ይነጋገራል፤ በዓይኖቹም ያየዋል።”’+ +5 ‘ሴዴቅያስን ወደ ባቢሎን ይወስደዋል፤ ትኩረቴን ወደ እሱ እስካዞር ድረስም በዚያ ይቆያል’ ይላል ይሖዋ። ‘ከከለዳውያን ጋር መዋጋታችሁን ብትቀጥሉም እንኳ አይሳካላችሁም።’”+ +6 ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ “የይሖዋ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ +7 ‘እነሆ፣ የአጎትህ* የሻሉም ልጅ ሃናምኤል ወደ አንተ መጥቶ “የመቤዠት መብት ያለህ የመጀመሪያው ሰው አንተ ስለሆንክ+ በአናቶት+ የሚገኘውን መሬቴን ለራስህ ግዛው” ይልሃል።’” +8 ይሖዋ በተናገረው መሠረት የአጎቴ ልጅ ሃናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ክብር ዘቦቹ ግቢ መጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “በቢንያም አገር፣ በአናቶት የሚገኘውን መሬቴን እባክህ ግዛኝ፤ የመውረስና የመቤዠት መብት ያለህ አንተ ነህና። ስለዚህ መሬቱን ለራስህ ግዛው።” ይህ የሆነው ይሖዋ በተናገረው ቃል መሠረት እንደሆነ +9 በመሆኑም በአናቶት ያለውን መሬት ከአጎቴ ልጅ ከሃናምኤል ላይ ገዛሁ። እኔም ሰባት ሰቅልና* አሥር የብር ሰቅል ገንዘብ መዝኜ ሰጠሁት።+ +10 ከዚያም የውል ሰነድ+ ካዘጋጀሁ በኋላ በማኅተም አሸግኩት፤ ምሥክሮችንም ጠርቼ+ ገንዘቡን በሚዛን መዘንኩ። +11 በመመሪያውና በሕጉ መሠረት የታሸገውን እንዲሁም ያልታሸገውን የግዢውን የውል ሰነድ ወሰድኩ፤ +12 ከዚያም የግዢውን የውል ሰነድ በአጎቴ ልጅ በሃናምኤል፣ በግዢው ውል ላይ በፈረሙት ምሥክሮች እንዲሁም በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተቀምጠው በነበሩት አይሁዳውያን ሁሉ ፊት ለማህሴያህ ልጅ፣ ለነሪያህ+ ልጅ ለባሮክ+ ሰጠሁት። +13 ባሮክንም በእነሱ ፊት እንዲህ ብዬ አዘዝኩት፦ +14 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነዚህን የውል ሰነዶች፣ የታሸገውንም ሆነ ያልታሸገውን የግዢ የውል ሰነድ ወስደህ ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አስቀምጣቸው።’ +15 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህች ምድር፣ ቤቶችና የእርሻ ቦታዎች እንዲሁም የወይን እርሻዎች እንደገና ይገዛሉ።’”+ +16 የግዢውን የውል ሰነድ ለነሪያህ ልጅ ለባሮክ ከሰጠሁት በኋላ እንዲህ ብዬ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ፦ +17 “አቤቱ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ! እነሆ፣ አንተ ሰማያትንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ሠርተሃል።+ አንተ ምንም የሚሳንህ ነገር የለም፤ +18 ለሺዎች ታማኝ ፍቅር ታሳያለህ፤ ይሁንና የአባቶችን በደል ከእነሱ ���ኋላ በሚመጡት ልጆቻቸው ላይ* ትመልሳለህ፤+ አንተ እውነተኛ፣ ታላቅና ኃያል አምላክ ነህ፤ ስምህም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው። +19 በምክር ታላቅ፣* በሥራም ኃያል ነህ፤+ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ለመክፈል+ ዓይኖችህ የሰው ልጆችን መንገዶች ሁሉ ያያሉ።+ +20 እስከ ዛሬ ድረስ የሚነገርላቸውን ምልክቶችና ተአምራት በግብፅ ምድር አደረግክ፤ በዚህም መንገድ አሁን እየሆነ እንዳለው ሁሉ በእስራኤልና በሰው ልጆች መካከል ለራስህ ስም አተረፍክ።+ +21 ሕዝብህን እስራኤልን በምልክቶች፣ በተአምራት፣ በኃያል እጅ፣ በተዘረጋች ክንድና አስፈሪ በሆኑ ክንውኖች ከግብፅ ምድር አወጣህ።+ +22 “ከጊዜ በኋላም ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማልክላቸውን+ ወተትና ማር የምታፈሰውን ይህችን ምድር ሰጠሃቸው።+ +23 እነሱም ገብተው ምድሪቱን ወረሷት፤ ሆኖም ቃልህን አልታዘዙም ወይም በሕግህ አልተመላለሱም። እንዲያደርጉ ያዘዝካቸውን ነገር ሁሉ አላደረጉም፤ ከዚህም የተነሳ ይህን ሁሉ ጥፋት በላያቸው አመጣህ።+ +24 እነሆ፣ ከተማዋን ለመያዝ ሰዎች በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ደልድለዋል፤+ ከሰይፉ፣+ ከረሃቡና ከቸነፈሩ*+ የተነሳ ከተማዋ እየወጓት ባሉት ከለዳውያን እጅ መውደቋ አይቀርም፤ አሁን እንደምታየው አንተ ያልከው ሁሉ ተፈጽሟል። +25 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ከተማዋ በከለዳውያን እጅ መውደቋ የማይቀር ቢሆንም ‘መሬቱን ለራስህ በምሥክሮች ፊት በገንዘብ ግዛ’ አልከኝ።” +26 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +27 “እነሆ፣ እኔ የሰው ዘር* ሁሉ አምላክ፣ ይሖዋ ነኝ። ለመሆኑ እኔ የሚሳነኝ ነገር አለ? +28 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህችን ከተማ ለከለዳውያንና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* እሰጣታለሁ፤ እሱም ይይዛታል።+ +29 ይህችን ከተማ የሚወጓት ከለዳውያንም ይገባሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤+ ደግሞም ከተማዋን እንዲሁም ሕዝቡ እኔን ለማስቆጣት ሲሉ በጣሪያዎቻቸው ላይ ለባአል መሥዋዕቶች ያቀረቡባቸውንና ለሌሎች አማልክት የመጠጥ መባ ያፈሰሱባቸውን ቤቶች+ በእሳት ያቃጥሏቸዋል።’ +30 “‘የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ከልጅነታቸው ጀምሮ በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ብቻ አድርገዋልና፤+ የእስራኤል ሕዝብ በእጃቸው ሥራ እኔን ማስቆጣታቸውን አልተዉም’ ይላል ይሖዋ። +31 ‘ይህች ከተማ ከገነቧት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ቁጣዬንና ንዴቴን ከማነሳሳት በስተቀር ምንም የፈየደችው ነገር የለም፤+ በመሆኑም ከፊቴ አስወግዳታለሁ፤+ +32 ይህም የሆነው የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ይኸውም እነሱ፣ ነገሥታታቸው፣+ መኳንንታቸው፣+ ካህናታቸው፣ ነቢያታቸው፣+ የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እኔን ለማስቆጣት በሠሩት ክፉ ነገር ሁሉ የተነሳ ነው። +33 ለእኔ ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡ፤+ ደግሜ ደጋግሜ ላስተምራቸው ብሞክርም፣ አንዳቸውም ተግሣጼን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉም።+ +34 ስሜ የተጠራበትንም ቤት ለማርከስ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን በዚያ አስቀመጡ።+ +35 በተጨማሪም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት አሳልፈው ለመስጠት በሂኖም ልጅ ሸለቆ*+ ያሉትን የባአልን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ሠርተዋል፤+ ይሁዳን ኃጢአት ለማሠራት ይህን አስጸያፊ ነገር እንዲፈጽሙ እኔ አላዘዝኩም፤+ ፈጽሞም በልቤ አላሰብኩም።’* +36 “ስለዚህ እናንተ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ለባቢሎን ንጉሥ አልፋ ትሰጣለች ስለምትሏት ስለዚህች ከተማ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ +37 ‘እነሆ፣ እነሱን በመዓቴና በታላቅ ቁጣዬ ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደዚህም ቦታ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ ያለስጋት እንዲኖሩም አደርጋለሁ።+ +38 እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።+ +39 ለእነሱም ሆነ ከእነሱ በኋላ ለሚመጡት ልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ዘወትር እኔን እንዲፈሩ+ አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።+ +40 ደግሞም ለእነሱ መልካም ነገር ከማድረግ እንዳልቆጠብ+ ከእነሱ ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ ከእኔም እንዳይርቁ በልባቸው ውስጥ እኔን የመፍራት መንፈስ አሳድራለሁ።+ +41 ለእነሱ መልካም በማድረግ እጅግ ደስ እሰኛለሁ፤+ በሙሉ ልቤና በሙሉ ነፍሴም* በዚህች ምድር ላይ አጽንቼ እተክላቸዋለሁ።’”+ +42 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህ ሕዝብ ላይ ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት እንዳመጣሁ፣ ልክ እንዲሁ ቃል የገባሁላቸውን መልካም ነገር ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።+ +43 እናንተ “ሰውም ሆነ እንስሳ የማይኖርባት ጠፍ መሬት ናት፤ ለከለዳውያንም ተሰጥታለች” ብትሉም በዚህች ምድር ላይ እንደገና መሬት ይገዛል።’+ +44 “‘ተማርከው የተወሰዱባቸውን ሰዎች መልሼ ስለማመጣቸው፣+ በቢንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ ቦታዎች፣ በይሁዳ ከተሞች፣+ በተራራማው ምድር ባሉ ከተሞች፣ በዝቅተኛው ስፍራ ባሉ ከተሞችና+ በደቡብ በሚገኙ ከተሞች መሬት በገንዘብ ይገዛል፤ የግዢ ውል ተዘጋጅቶ በማኅተም ይታሸጋል፤ ምሥክሮችም ይጠራሉ’ +7 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ +2 “በይሖዋ ቤት በር ላይ ቆመህ በዚያ ይህን መልእክት አውጅ፦ ‘ለይሖዋ ለመስገድ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። +3 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መንገዳችሁንና ተግባራችሁን አስተካክሉ፤ እኔም በዚህ ስፍራ እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።+ +4 ‘ይህ* የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ ነው!’ እያላችሁ በአሳሳች ቃል አትታመኑ።+ +5 በእርግጥ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን ብታስተካክሉ፣ በሰውና በባልንጀራው መካከል ፍትሕ ብታሰፍኑ፣+ +6 ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና* መበለቶችን ባትጨቁኑ፣+ በዚህ ቦታ የንጹሕ ሰው ደም ባታፈሱ እንዲሁም ጉዳት ላይ የሚጥሏችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣+ +7 በዚህች ስፍራ፣ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው በዚህ ምድር ለዘለቄታው እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።”’” +8 “እናንተ ግን አሳሳች በሆነ ቃል ታምናችኋል፤+ ይህ ደግሞ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም። +9 እየሰረቃችሁ፣+ እየገደላችሁ፣ እያመነዘራችሁ፣ በሐሰት እየማላችሁ፣+ ለባአል መሥዋዕት* እያቀረባችሁና+ የማታውቋቸውን አማልክት እየተከተላችሁ፣ +10 በስሜ ወደሚጠራው ወደዚህ ቤት መጥታችሁ በፊቴ መቆምና እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች እያደረጋችሁ ‘ምንም ችግር አይደርስብንም’ ማለት ትችላላችሁ? +11 ስሜ የሚጠራበት ይህ ቤት በእናንተ ዓይን የዘራፊዎች ዋሻ ሆኗል ማለት ነው?+ እነሆ፣ እኔ ራሴ ይህን አይቻለሁ” ይላል ይሖዋ። +12 “‘አሁን ግን መጀመሪያ የስሜ ማደሪያ+ አድርጌው ወደነበረው በሴሎ+ ወዳለው ስፍራዬ ሂዱ፤ ከሕዝቤ ከእስራኤል ክፋት የተነሳም ምን እንዳደረግኩት እዩ።+ +13 እናንተ ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች መሥራታችሁን ቀጠላችሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ ደግሜ ደጋግሜ ብናገርም እንኳ አልሰማችሁም።+ ደጋግሜ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን መልስ አትሰጡም።+ +14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግኩት ሁሉ በስሜ በተጠራው፣+ እናንተም በምትታመኑበት በዚህ ቤት+ ላይ እንዲሁም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠሁት በዚህ ቦታ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ +15 ወንድሞቻችሁን ሁሉ ይኸውም መላውን የኤፍሬም ዘር እንዳስወገድኩ እናንተንም ከፊቴ አስወግዳችኋለሁ።’+ +16 “አ���ተም ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ። እኔ ስለማልሰማህ+ ስለ እነሱ የልመና ጩኸትም ሆነ ጸሎት አታሰማ ወይም እኔን አትማጸን።+ +17 በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የሚያደርጉትን አታይም? +18 እኔን ያሳዝኑ ዘንድ ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት የሚሆን ቂጣ ለመጋገር ወንዶች ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፣ አባቶች እሳት ያቀጣጥላሉ፣ ሚስቶች ደግሞ ሊጥ ያቦካሉ፤+ ለሌሎች አማልክትም የመጠጥ መባ ያፈሳሉ።+ +19 ‘ለመሆኑ የሚጎዱት* እኔን ነው?’ ይላል ይሖዋ። ‘በራሳቸው ላይ ውርደት በማምጣት የሚጎዱት ራሳቸውን አይደለም?’+ +20 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ንዴቴና ቁጣዬ በዚህ ቦታ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በዱር ዛፎችና በምድሪቱ ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤+ ቁጣዬ ይነድዳል፤ ፈጽሞም አይጠፋም።’+ +21 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የጀመራችሁትን ግፉበት፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን በሌሎች መሥዋዕቶቻችሁ ላይ ጨምሩ፤ ሥጋውንም ራሳችሁ ብሉ።+ +22 አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ሙሉ በሙሉ ስለሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች አልነገርኳቸውም ወይም አላዘዝኳቸውም።+ +23 ከዚህ ይልቅ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻቸው ነበር፦ “ድምፄን ስሙ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ።+ መልካም እንዲሆንላችሁ በማዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”’+ +24 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤+ ይልቁንም ግትር ሆነው ክፉ ልባቸውን በመከተል በገዛ ራሳቸው ዕቅድ* ሄዱ፤+ ወደ ፊት በመሄድ ፋንታ ወደ ኋላ ተመለሱ፤ +25 አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህ ቀን ድረስ ይህን አደረጉ።+ በመሆኑም አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያት ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ ደግሜ ደጋግሜ በየዕለቱ ላክኋቸው።+ +26 እነሱ ግን እኔን ለመስማት እንቢተኛ ሆኑ፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም።+ ይልቁንም ግትር ሆኑ፤* አባቶቻቸው ከሠሩት የከፋ ነገር አደረጉ! +27 “ይህን ሁሉ ቃል ትነግራቸዋለህ፤+ እነሱ ግን አይሰሙህም፤ ትጠራቸዋለህ፤ እነሱ ግን አይመልሱልህም። +28 እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ‘ይህ ብሔር የአምላኩን የይሖዋን ድምፅ አልሰማም፤ ተግሣጽ ለመቀበልም እንቢተኛ ሆኗል። ታማኝነት ጠፍቷል፤ በመካከላቸውም ጨርሶ አይነሳም።’*+ +29 “ያልተቆረጠውን* ፀጉርሽን ሸልተሽ ጣይው፤ በተራቆቱት ኮረብቶችም ላይ ሙሾ አውርጂ፤* ይሖዋ እጅግ ያስቆጣውን ይህን ትውልድ ጥሎታልና፤ እርግፍ አድርጎም ይተወዋል። +30 ‘የይሁዳ ሰዎች በፊቴ መጥፎ ነገር ሠርተዋልና’ ይላል ይሖዋ። ‘አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን በስሜ በተጠራው ቤት ውስጥ በማስቀመጥ አርክሰውታል።+ +31 ያላዘዝኩትንና በልቤ እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን* ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል+ በሂኖም ልጅ ሸለቆ*+ የሚገኘውን የቶፌትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ሠርተዋል።’+ +32 “‘ከዚህ የተነሳ፣’ ይላል ይሖዋ፣ ‘የእርድ ሸለቆ እንጂ ቶፌት ወይም የሂኖም ልጅ ሸለቆ* ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። እነሱም ቦታ እስኪታጣ ድረስ በቶፌት ይቀብራሉ።+ +33 የዚህ ሕዝብ አስከሬንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ ፈርተው እንዲሸሹ የሚያደርጋቸውም የለም።+ +34 የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ፣ ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አጠፋለሁ፤+ ምድሪቱ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለችና።’”+ +48 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ሞዓብ+ እንዲህ ይላል፦ “ወዮ፣ ነቦ+ ጠፍታለችና! ቂርያታይም+ ኀፍረት ተከናንባለች፤ ደግሞም ተይዛለች። አስተማማኝ የሆነው መጠጊያ ተዋርዷል፤ ���ራርሷልም።+ + 2 ከእንግዲህ ሞዓብን አያወድሷትም። ለውድቀት ትዳረግ ዘንድ፣ ‘ኑ ብሔር መሆኗ እንዲያከትም እንደምስሳት’ ብለው በሃሽቦን+ ይዶልቱባታል። አንቺም ማድመን ሆይ፣ ዝም በይ፤ከኋላሽ ሰይፍ ይከተልሻልና። + 3 ከሆሮናይም+ የጩኸት ድምፅእንዲሁም የጥፋትና የታላቅ ውድቀት ድምፅ ይሰማል። + 4 ሞዓብ ጠፍታለች። ልጆቿ ይጮኻሉ። + 5 ወደ ሉሂት በሚወስደው አቀበት እያለቀሱ ይወጣሉ። በደረሰው ጥፋት የተነሳ፣ ከሆሮናይም ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ሲወርዱም የጭንቅ ጩኸት ይሰማሉ።+ + 6 ሽሹ፤ ሕይወታችሁን አትርፉ!* በምድረ በዳ እንዳለ የጥድ ዛፍ ሁኑ። + 7 ምክንያቱም አንቺ በሥራሽና ውድ በሆነ ሀብትሽ ትታመኛለሽ፤ደግሞም ትያዣለሽ። ከሞሽ+ ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋርበአንድነት በግዞት ይወሰዳል። + 8 አጥፊው በእያንዳንዱ ከተማ ላይ ይመጣል፤አንድም ከተማ አያመልጥም።+ ይሖዋ በተናገረው መሠረትሸለቆው* ይጠፋል፤ ደልዳላውም መሬት* እንዳልነበረ ይሆናል። + 9 ለሞዓብ ምልክት አቁሙ፤ስትፈራርስ ትሸሻለችና፤ከተሞቿም አስፈሪ ቦታ ይሆናሉ፤የሚቀመጥባቸውም ሰው አይኖርም።+ +10 ይሖዋ የሰጠውን ተልእኮ በግድየለሽነት የሚያከናውን የተረገመ ነው! ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚመልስ ሰው የተረገመ ነው! +11 ሞዓባውያን ከልጅነታቸው ጀምሮበአምቡላው ላይ እንደረጋ ወይን ጠጅ ተረጋግተው ተቀምጠዋል። ከአንዱ ዕቃ ወደ ሌላው ዕቃ አልተገላበጡም፤በግዞትም ተወስደው አያውቁም። በዚህም ምክንያት ቃናቸው እንዳለ ነው፤መዓዛቸውም አልተለወጠም። +12 “‘ስለዚህ፣ እነሆ እነሱን እንዲገለብጡ ሰዎችን የምልክበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። ‘እነሱም ይገለብጧቸዋል፤ ዕቃዎቻቸውንም ባዶ ያስቀራሉ፤ ትላልቅ እንስራዎቻቸውንም ይሰባብራሉ። +13 የእስራኤል ቤት ይተማመንበት በነበረው በቤቴል እንዳፈረ ሁሉ ሞዓባውያንም በከሞሽ ያፍራሉ።+ +14 “እኛ ለውጊያ የተዘጋጀን ኃያላን ተዋጊዎች ነን” በማለት እንዴት በድፍረት ትናገራላችሁ?’+ +15 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ተብሎ የሚጠራው ንጉሥ+ እንዲህ ይላል፦‘ሞዓብ ጠፍታለች፤ከተሞቿ ተወረዋል፤+ ምርጥ የሆኑት ወጣቶቻቸውም ታርደዋል።’+ +16 በሞዓባውያን ላይ የሚደርሰው ጥፋት ቀርቧል፤ውድቀታቸውም በፍጥነት እየቀረበ ነው።+ +17 በዙሪያቸው ያሉ ሁሉ፣ስማቸውን የሚያውቁ ሁሉ አብረዋቸው ያዝናሉ። ‘ኃያሉ በትር፣ የውበትም ዘንግ እንዴት ተሰበረ!’ በሏቸው። +18 አንቺ በዲቦን+ የምትኖሪ ሴት ልጅ ሆይ፣ከክብርሽ ውረጂ፤ ተጠምተሽም* ተቀመጪ፤የሞዓብ አጥፊ በአንቺ ላይ መጥቶብሻልና፤የተመሸጉ ቦታዎችሽንም ያፈራርሳል።+ +19 አንቺ በአሮዔር+ የምትኖሪ፣ መንገዱ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ። የሚሸሸውን ወንድና የምታመልጠውን ሴት ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ። +20 ሞዓብ ኀፍረት ተከናነበች፤ በሽብርም ተውጣለች። ዋይ ዋይ በሉ፤ እንዲሁም ጩኹ። ሞዓብ መጥፋቷን በአርኖን+ አውጁ። +21 “ፍርድ ወደ ደልዳላው መሬት* መጥቷል፤+ በሆሎን፣ በያሃጽና+ በመፋአት፣+ +22 በዲቦን፣+ በነቦና+ በቤትዲብላታይም፣ +23 በቂርያታይም፣+ በቤትጋሙልና በቤትምዖን፣+ +24 በቀሪዮትና+ በቦስራ እንዲሁም በሩቅና በቅርብ ባሉ የሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል። +25 ‘የሞዓብ ብርታት* ተቆርጧል፤ክንዱም ተሰብሯል’ ይላል ይሖዋ። +26 ‘በይሖዋ ላይ ስለ ታበየ+ አስክሩት።+ ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለላል፤መሳለቂያም ሆኗል። +27 እስራኤል የአንተ መሳለቂያ ሆኖ አልነበረም?+ ራስህን የምትነቀንቀውና እሱን የምትቃወመውእስራኤል ከሌቦች ጋር ተገኝቶ ነው? +28 እናንተ የሞዓብ ነዋሪዎች፣ ከከተሞቹ ወጥታችሁ በቋጥኝ ላይ ኑሩ፤በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ ���ግብም ሁኑ።’” +29 “ስለ ሞዓብ ኩራት ሰምተናል፤ እሱ በጣም ትዕቢተኛ ነው፤ስለ እብሪቱ፣ ስለ ኩራቱ፣ ስለ ትዕቢቱና ስለ ልቡ ማበጥ ሰምተናል።”+ +30 “‘ቁጣውን አውቃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤‘ሆኖም ጉራው ከንቱ ይሆናል። አንዳች ነገር አያደርጉም። +31 ከዚህ የተነሳ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤ለሞዓብ ምድር ሁሉ እጮኻለሁ፤ለቂርሄረስ+ ነዋሪዎችም እቃትታለሁ። +32 የሲብማ+ ወይን ሆይ፣ ለያዜር+ ከተለቀሰው በበለጠለአንቺ አለቅሳለሁ። የተንዠረገጉት ቅርንጫፎችሽ ባሕሩን ተሻግረዋል። እስከ ባሕሩ፣ እስከ ያዜርም ደርሰዋል። አጥፊው በበጋ ፍሬሽና*ለመከር በደረሰው ወይንሽ ላይ መጥቷል።+ +33 ከፍራፍሬ እርሻውና ከሞዓብ ምድርሐሴትና ደስታ ጠፍቷል።+ ከወይን መጭመቂያዎቹ የወይን ጠጅ መፍሰሱን እንዲያቆም አድርጌአለሁ። በእልልታ ወይን የሚረግጥ ሰው አይኖርም። ጩኸቱ ለየት ያለ ጩኸት ይሆናል።’”+ +34 “‘በሃሽቦን+ የሚያስተጋባው ጩኸት እስከ ኤልዓሌ+ ድረስ ይሰማል። እስከ ያሃጽ+ ድረስ ድምፃቸውን ያሰማሉ፤በዞአር የሚያስተጋባው ጩኸት እስከ ሆሮናይምና+ እስከ ኤግላት ሸሊሺያ ድረስ ይሰማል። የኒምሪም ውኃዎች እንኳ ይደርቃሉ።+ +35 ከፍ ባለ የማምለኪያ ቦታ ላይ መባ የሚያቀርበውንናለአምላኩ መሥዋዕት የሚያቀርበውን ሰውከሞዓብ አጠፋለሁ’ ይላል ይሖዋ። +36 ‘ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት* በሐዘን ያንጎራጉራል፤*+ለቂርሄረስ ሰዎችም ልቤ እንደ ዋሽንት* በሐዘን ያንጎራጉራል።* ያከማቸው ሀብት ይጠፋልና። +37 ራስ ሁሉ ተመልጧል፤+ጢምም ሁሉ ተላጭቷል። እጅ ሁሉ ተሸንትሯል፤+በወገባቸውም ላይ ማቅ ታጥቀዋል!’”+ +38 “‘በሞዓብ ጣሪያዎች ሁሉናበአደባባዮቿ ሁሉ ላይከዋይታ ሌላ የሚሰማ ነገር የለም። ሞዓብን እንደተጣለ እንስራሰባብሬአታለሁና’ ይላል ይሖዋ። +39 ‘እጅግ ተሸብራለች! ዋይ ዋይ በሉ! ሞዓብ ኀፍረት ተከናንቦ ጀርባውን አዙሯል! ሞዓብ መሳለቂያ ሆኗል፤በዙሪያው ያሉት ሁሉ ከእሱ የተነሳ ይደነግጣሉ።’” +40 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ ተወንጭፎ እንደሚወርድ ንስር፣+እሱም በሞዓብ ላይ ክንፎቹን ይዘረጋል።+ +41 ከተሞቹ ይወረራሉ፤ምሽጎቿም ይያዛሉ። በዚያ ቀን የሞዓብ ተዋጊዎች ልብምጥ እንደያዛት ሴት ልብ ይሆናል።’” +42 “‘ሞዓብም ሕዝብ መሆኑ ያከትማል፤+በይሖዋ ላይ ታብዮአልና።+ +43 የሞዓብ ነዋሪ ሆይ፣ሽብር፣ ጉድጓድና ወጥመድ ይጠብቅሃል’ ይላል ይሖዋ። +44 ‘ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ ጉድጓዱ ውስጥ ይወድቃል፤ከጉድጓዱም የሚወጣ ሁሉ በወጥመዱ ይያዛል።’ ‘የሚቀጡበትን ዓመት በሞዓብ ላይ አመጣለሁና’ ይላል ይሖዋ። +45 ‘የሚሸሹት ሰዎች ኃይላቸው ተሟጦ በሃሽቦን ጥላ ሥር ይቆማሉ። ከሃሽቦን እሳት፣ከሲሖን መካከልም ነበልባል ይወጣልና።+ የሞዓብን ግንባርናየሁከት ልጆችን ራስ ቅል ይበላል።’+ +46 ‘ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! የከሞሽ+ ሰዎች ጠፍተዋል። ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፤ሴቶች ልጆችህም በግዞት ተወስደዋል።+ +47 በዘመኑ መጨረሻ ግን፣ ከሞዓብ የተማረኩትን እሰበስባለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘በሞዓብ ላይ የተላለፈው የፍርድ መልእክት እዚህ ላይ ይደመደማል።’”+ +45 የኢዮስያስ ልጅ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣+ የነሪያህ ልጅ ባሮክ+ ይህን ቃል ከኤርምያስ አፍ እየሰማ በመጽሐፍ በጻፈበት ጊዜ፣+ ነቢዩ ኤርምያስ ለባሮክ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ +2 “ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ አንተን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ +3 ‘አንተ “ወዮልኝ፣ ይሖዋ በሥቃዬ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና! ከማሰማው ሲቃ የተነሳ ዝያለሁ፤ ማረፊያ ቦታም አላገኘሁም” ብለሃል።’ +4 “እሱን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “���ነሆ፣ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልኩትንም እነቅላለሁ፤ ምድሪቱን በሙሉ አወድማለሁ።+ +5 አንተ ግን ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህ።* እንዲህ ያሉ ነገሮችን ፈጽሞ አትፈልግ።”’* “‘በሥጋ ለባሽ* ሁሉ ላይ ጥፋት ላመጣ ነውና’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘በምትሄድበትም ቦታ ሁሉ ሕይወትህን* እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።’”*+ +12 ይሖዋ ሆይ፣ አቤቱታዬን ለአንተ ሳቀርብ፣ከፍትሕ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ሳናግርህ እነሆ፣ አንተ ጻድቅ ነህ።+ ታዲያ የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል?+ደግሞስ ከዳተኞች ሳይጨነቁ የሚኖሩት ለምንድን ነው? + 2 አንተ ተክለሃቸዋል፤ እነሱም ሥር ሰደዋል። አድገዋል፤ ፍሬም አፍርተዋል። ከከንፈራቸው አይለዩህም፤ የውስጥ ሐሳባቸው* ግን ከአንተ የራቀ ነው።+ + 3 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን በሚገባ ታውቀኛለህ፤+ ታየኛለህም፤ልቤን መረመርክ፤ ከአንተም ጋር የሚስማማ ሆኖ አገኘኸው።+ ለእርድ እንደተዘጋጁ በጎች ለያቸው፤ለሚገደሉበትም ቀን ለይተህ አቆያቸው። + 4 ምድሪቱ ተራቁታ፣የሜዳውም ተክል ሁሉ ደርቆ የሚቆየው እስከ መቼ ድረስ ነው?+ በምድሪቱ በሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሳአራዊቱና ወፎቹ ተጠራርገው ጠፉ። እነሱ፣ “ወደፊት ምን እንደሚገጥመን አያውቅም” ብለዋልና። + 5 ከእግረኞች ጋር ሮጠህ ከደከምክ፣ከፈረሶች ጋር እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ?+ በሰላም ምድር ተማምነህ ብትቀመጥ እንኳጥቅጥቅ ባለው የዮርዳኖስ ጥሻ ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው? + 6 የገዛ ወንድሞችህ፣የገዛ አባትህ ቤተሰቦች እንኳ አታለውሃልና።+ እነሱ በአንተ ላይ ጮኸዋል። መልካም ነገር ቢናገሩህ እንኳፈጽሞ አትመናቸው። + 7 “ቤቴን ትቻለሁ፤+ ርስቴን ጥዬ ሄጃለሁ።+ እጅግ የምወዳትን* በጠላቶቿ እጅ አሳልፌ ሰጥቻታለሁ።+ + 8 ርስቴ በጫካ ውስጥ እንዳለ አንበሳ ሆነችብኝ። በእኔ ላይ ጮኻብኛለች። በዚህም የተነሳ ጠላኋት። + 9 ርስቴ ለእኔ ብዙ ቀለማት እንዳለው* አዳኝ አሞራ ነች፤ሌሎች አዳኝ አሞሮች ይከቧታል፤ ደግሞም ያጠቋታል።+ እናንተ የዱር አራዊት ሁሉ ኑ፤ በአንድነት ተሰብሰቡ፤ትቀራመቷት ዘንድ ኑ።+ +10 ብዙ እረኞች የወይን እርሻዬን አጥፍተውታል፤+ይዞታዬንም ረግጠውታል።+ የተወደደውን ይዞታዬን ጠፍ ምድረ በዳ አድርገውታል። +11 ባድማ ሆኗል። ደግሞም ተራቁቷል፤*በፊቴ ወና ሆኗል።+ ምድሪቱ በሙሉ ባድማ ሆናለች፤ይሁንና ይህን ልብ ያለ አንድም ሰው የለም።+ +12 በምድረ በዳ ባሉት፣ በተበላሹ መንገዶች ሁሉ አጥፊዎች መጥተዋል፤የይሖዋ ሰይፍ ከአንዱ ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ ምድሪቱን ትበላለችና።+ ማንም ሰው* ሰላም የለውም። +13 ስንዴ ዘሩ፤ ሆኖም እሾህን አጨዱ።+ እስኪዝሉ ድረስ ሠሩ፤ ነገር ግን ምንም ጥቅም አላገኙም። ከሚነደው የይሖዋ ቁጣ የተነሳበሚያገኙት ምርት ያፍራሉ።” +14 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እስራኤል እንዲወርሰው ያደረግኩትን ርስት የሚነኩ ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ+ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤+ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ። +15 ከነቀልኳቸው በኋላ ግን ዳግመኛ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸውን ወደየርስታቸው፣ እያንዳንዳቸውንም ወደየምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።” +16 “ሕዝቤን በባአል እንዲምሉ እንዳስተማሩ ሁሉ እነሱም የሕዝቤን መንገድ በእርግጥ ቢማሩና ‘ሕያው ይሖዋን!’ ብለው በስሜ ቢምሉ በሕዝቤ መካከል ጸንተው ይኖራሉ። +17 ይሁንና ከእነዚህ ብሔራት መካከል የማይታዘዝ ቢኖር ያን ብሔር እነቅለዋለሁ፤ ነቅዬም አጠፋዋለሁ” ይላል ይሖዋ።+ +1 በቢንያም አገር በአናቶት+ ከነበሩት ካህናት አንዱ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ* ቃል ይህ ነው። +2 የይሁዳ ንጉሥ የአምዖን+ ልጅ ኢዮስያስ+ በነገሠ ���13ኛው ዓመት የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። +3 ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮዓቄም+ ዘመን፣ እንዲሁም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ የሴዴቅያስ+ 11ኛው ዓመት የግዛት ዘመን እስካበቃበት ጊዜ ድረስ ይኸውም ኢየሩሳሌም ወደ ግዞት እስከተወሰደችበት እስከ አምስተኛው ወር+ ድረስ ቃሉ ወደ እሱ መጣ። + 4 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ + 5 “በማህፀን ውስጥ ሳልሠራህ በፊት አውቄሃለሁ፤*+ከመወለድህም* በፊት ቀድሼሃለሁ።*+ ለብሔራት ነቢይ አድርጌሃለሁ።” + 6 እኔ ግን “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮልኝ! እኔ ገና ልጅ* ስለሆንኩ+ ምን ብዬ እንደምናገር አላውቅም”+ አልኩ። + 7 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘እኔ ገና ልጅ ነኝ’ አትበል። ወደምልክህ ሁሉ ትሄዳለህና፤የማዝህንም ሁሉ ትናገራለህ።+ + 8 ከቁመናቸው የተነሳ አትፍራ፤+‘አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና’+ ይላል ይሖዋ።” +9 ከዚያም ይሖዋ እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ።+ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ።+ +10 እንግዲህ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድታወድም፣ እንድትገነባና እንድትተክል ዛሬ በብሔራትና በመንግሥታት ላይ ሾሜሃለሁ።”+ +11 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” እኔም “የአልሞንድ ዛፍ* ቅርንጫፍ አያለሁ” አልኩ። +12 ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “በትክክል አይተሃል፤ እኔ ቃሌን ለመፈጸም በከፍተኛ ንቃት እየተጠባበቅኩ ነውና።” +13 የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጥቶ “ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የተጣደ* ድስት* አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደ ደቡብ ያዘነበለ ነው” አልኩ። +14 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “በምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ ላይከሰሜን ጥፋት ይመጣል።+ +15 ‘በሰሜን ያሉትን መንግሥታት ነገዶች ሁሉ እጠራለሁና’ ይላል ይሖዋ፤+‘እነሱም ይመጣሉ፤ እያንዳንዱም ዙፋኑንበኢየሩሳሌም በሮች መግቢያ፣+በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉናበይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያደርጋል።+ +16 ደግሞም እኔን ስለተዉ፣+ለሌሎች አማልክትም የሚጨስ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡና+በገዛ እጃቸው ለሠሯቸው ነገሮች ስለሚሰግዱ+በክፋታቸው ሁሉ ላይ ፍርዴን አውጃለሁ።’ +17 አንተ ግን ለሥራ ተዘጋጅ፤*ደግሞም ተነስ፤ እኔ የማዝህንም ሁሉ ንገራቸው። እኔ ራሴ በፊታቸው እንዳላሸብርህ፣እነሱን አትፍራቸው።+ +18 ምድሪቱን ሁሉ፣ የይሁዳን ነገሥታትና መኳንንቷን፣ካህናቷንና የምድሪቱን ሕዝብ እንድትቋቋም፣+ዛሬ አንተን የተመሸገ ከተማ፣የብረት ዓምድና የመዳብ ቅጥር አድርጌሃለሁ።+ +19 እነሱም በእርግጥ ይዋጉሃል፤ሆኖም አያሸንፉህም፤*‘አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና’+ ይላል ይሖዋ።” +49 ይሖዋ፣ ስለ አሞናውያን+ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትም? ወራሽስ የለውም? ታዲያ ማልካም፣+ ጋድን የወረሰው ለምንድን ነው?+ ሕዝቦቹስ በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩት ለምንድን ነው?” + 2 “‘ስለዚህ እነሆ፣ አሞናውያን በሚኖሩባት በራባ+ ላይየጦርነት ማስጠንቀቂያ ድምፅ* የማሰማበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። ‘የፍርስራሽ ቁልል ትሆናለች፤በእሷም ሥር* ያሉት ከተሞች በእሳት ይቃጠላሉ።’ ‘እስራኤልም የቀሙትን መልሶ በእጁ ያስገባል’+ ይላል ይሖዋ። + 3 ‘ሃሽቦን ሆይ፣ ጋይ ስለወደመች ዋይ ዋይ በዪ! በራባ ሥር ያላችሁ ከተሞች ሆይ፣ ጩኹ። ማቅ ልበሱ። ማልካም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋርበግዞት ስለሚወሰድ+ከድንጋይ በተሠራ የእንስሳት ማጎሪያ* ውስጥ ወዲያ ወዲህ እያላችሁ አልቅሱ። + 4 አንቺ በውድ ሀብቶችሽ የምትታመኚ፣“ማን ይነካኛል?” የምትዪከዳተኛ የሆንሽ ሴት ልጅ ሆይ፣በሸለቆዎችሽ* ይኸውም ውኃ በሚንዶለዶልበት ሜዳሽ የምትኩራሪው ለምንድን ነው?’” + 5 “‘እነሆ፣ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ፣በአንቺ ላይ የሚያስፈራ ነገር አመጣለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ። ‘እናንተም በየአቅጣጫው ትበታተናላችሁ፤የሚሸሹትንም የሚሰበስብ አይኖርም።’” + 6 “‘ከዚያ በኋላ ግን ተማርከው የተወሰዱትን አሞናውያንን እሰበስባለሁ’ ይላል ይሖዋ።” +7 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦ “ጥበብ ከቴማን+ ጠፍቷል? ጥሩ ምክርስ ከአስተዋዮች ጠፍቷል? ጥበባቸውስ ተበላሽቷል? + 8 የዴዳን+ ነዋሪዎች ሆይ፣ ሽሹ! ወደ ኋላ ተመለሱ! ወደ ጥልቁ ወርዳችሁ ተደበቁ! ትኩረቴን ወደ እሱ በማዞርበት ጊዜበኤሳው ላይ ጥፋት አመጣለሁና። + 9 ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡጥቂት ቃርሚያ አያስቀሩም? ሌቦች በሌሊት ቢመጡ፣የሚዘርፉት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ ነው።+ +10 እኔ ግን ኤሳውን እርቃኑን አስቀረዋለሁ። መደበቅ እንዳይችልመሸሸጊያ ቦታዎቹን እገልጣለሁ። ልጆቹ፣ ወንድሞቹና ጎረቤቶቹ በሙሉ ይጠፋሉ፤+እሱም ከሕልውና ውጭ ይሆናል።+ +11 አባት የሌላቸው ልጆችህን ተዋቸው፤እኔ በሕይወት አኖራቸዋለሁ፤መበለቶችህም በእኔ ይታመናሉ።” +12 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፣ ጽዋውን እንዲጠጡ ያልተፈረደባቸውም እንኳ ለመጠጣት የሚገደዱ ከሆነ አንተ እንዴት ከቅጣት ታመልጣለህ? ከቅጣት አታመልጥም፤ ጽዋውን ትጠጣለህና።”+ +13 “በራሴ ምያለሁና” ይላል ይሖዋ፤ “ቦስራ አስፈሪ ቦታ ትሆናለች፤+ ለነቀፋ፣ ለጥፋትና ለእርግማንም ትዳረጋለች፤ ከተሞቿም ሁሉ ለዘለቄታው ባድማ ይሆናሉ።”+ +14 ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦ “በአንድነት ተሰብሰቡ፤ በእሷም ላይ ውጡ፤ለጦርነት ተዘጋጁ።”+ +15 “እነሆ፣ በብሔራት መካከል ከቁብ የማትቆጠር፣በሰዎችም መካከል የተናቅክ አድርጌሃለሁና።+ +16 አንተ በቋጥኝ መሸሸጊያ ውስጥ የምትኖር፣በጣም ረጅሙን ኮረብታ የያዝክ ሆይ፣የነዛኸው ሽብርናየልብህ እብሪት አታሎሃል። ጎጆህን እንደ ንስር በከፍታ ቦታ ላይ ብትሠራም፣እኔ ከዚያ አወርድሃለሁ” ይላል ይሖዋ። +17 “ኤዶምም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች።+ በእሷ አጠገብ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ በደረሱባት መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳም ያፏጫል። +18 ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉት ከተሞች በተደመሰሱ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ”+ ይላል ይሖዋ፤ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።+ +19 “እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ+ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርረዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ። እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው? +20 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በኤዶም ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና* በቴማን+ ነዋሪዎች ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፦ ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም። ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።+ +21 እነሱ ሲወድቁ ከሚሰማው ታላቅ ድምፅ የተነሳ ምድር ተናወጠች። ጩኸት ይሰማል! ድምፁም እስከ ቀይ ባሕር+ ድረስ አስተጋብቷል። +22 እነሆ፣ ልክ እንደ ንስር ወደ ላይ ይወጣና ተወንጭፎ ይወርዳል፤+በቦስራም ላይ ክንፎቹን ይዘረጋል።+ በዚያ ቀን የኤዶም ተዋጊዎች ልብ፣ምጥ እንደያዛት ሴት ልብ ይሆናል።” +23 ስለ ደማስቆ+ የተነገረ መልእክት፦ “ሃማትና+ አርጳድክፉ ወሬ በመስማታቸው አፍረዋል። በፍርሃት ይቀልጣሉ። ባሕሩ ታውኳል፤ ጸጥ ሊል አይችልም። +24 ደማስቆ ወኔ ከዳት። ለመሸሽ ወደ ኋላ ዞረች፤ ይሁንና ብርክ ያዛት። ልትወልድ እንደተቃረበች ሴትጭንቅና ሥቃይ ያዛት። +25 የምትወደሰው ከተማ፣ በሐሴትም የተሞላችው መዲናእንዴት ሳትተው ቀረች? +26 ወጣቶቿ በአደባባዮቿ ይወድቃሉና፤በዚያም ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይጠፋሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +27 “የደማስቆን ቅጥር በእሳት አነዳለሁ፤እሳቱም የቤንሃዳድን የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።”+ +28 ይሖዋ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ስለመታቸው ስለ ቄዳርና+ ስለ ሃጾር መንግሥታት እንዲህ ይላል፦ “ተነሱ፤ ወደ ቄዳር ውጡ፤የምሥራቅንም ሰዎች አጥፉ። +29 ድንኳኖቻቸውና መንጎቻቸው፣የድንኳን ሸራዎቻቸውና ዕቃዎቻቸው ሁሉ ይወሰዳሉ። ግመሎቻቸውን ይነጠቃሉ፤‘ሽብር በየቦታው ነግሦአል!’ ብለው ወደ እነሱ ይጮኻሉ።” +30 “እናንተ የሃጾር ነዋሪዎች፣ ሽሹ፤ ወደ ሩቅ ቦታም ተሰደዱ! ወደ ጥልቁ ወርዳችሁ ተደበቁ” ይላል ይሖዋ። “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* በእናንተ ላይ የጦር ስልት ነድፏልና፤በእናንተም ላይ አንድ ዕቅድ አቅዷል።” +31 “በሰላም፣ ተረጋግቶ በተቀመጠው ብሔር ላይተነሱ፣ ውጡ!” ይላል ይሖዋ። “በሮችም ሆነ መቀርቀሪያዎች የሉትም፤ ብቻቸውንም ይኖራሉ። +32 ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ፤ብዛት ያላቸው ከብቶቻቸውም በምርኮ ይወሰዳሉ። በሰሪሳራቸው* ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩትን ሰዎች+ነፋስ ወደሚነፍስበት አቅጣጫ ሁሉ* እበትናቸዋለሁ፤ከሁሉም አቅጣጫ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ” ይላል ይሖዋ። +33 “ሃጾርም የቀበሮዎች ጎሬ፣ለዘለቄታውም ባድማ ትሆናለች። በዚያ ማንም ሰው አይኖርም፤አንድም ሰው በእሷ ውስጥ አይቀመጥም።” +34 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ኤላምን+ አስመልክቶ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ +35 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ የብርታታቸው ምንጭ* የሆነውን የኤላምን+ ቀስት እሰብራለሁ። +36 ከአራቱ የሰማያት ዳርቻዎች፣ አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፤ እኔም እነዚህ ነፋሳት በሚነፍሱበት አቅጣጫ ሁሉ እበትናቸዋለሁ። ከኤላም የተበተኑት ሰዎችም የማይሄዱበት ብሔር አይኖርም።’” +37 “ኤላማውያንን በጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ማጥፋት በሚሹ* ሰዎች ፊት አሸብራለሁ፤ በእነሱም ላይ ጥፋትን ይኸውም የሚነድ ቁጣዬን አመጣለሁ” ይላል ይሖዋ። “ፈጽሞ እስካጠፋቸውም ድረስ ከኋላቸው ሰይፍ እሰዳለሁ።” +38 “እኔም ዙፋኔን በኤላም+ አደርጋለሁ፤ ከዚያም ስፍራ ንጉሡንና መኳንንቱን አስወግዳለሁ” ይላል ይሖዋ። +39 “በዘመኑ መጨረሻ ግን ከኤላም ተማርከው የተወሰዱትን እሰበስባለሁ” ይላል ይሖዋ። +36 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +2 “አንድ ጥቅልል* ውሰድና በኢዮስያስ ዘመን ለአንተ መናገር ከጀመርኩበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ+ በእስራኤል፣ በይሁዳና በብሔራት ሁሉ+ ላይ አመጣዋለሁ ብዬ የነገርኩህን ቃል በሙሉ ጻፍበት።+ +3 ምናልባት የይሁዳ ቤት ሰዎች በእነሱ ላይ ላመጣ ያሰብኩትን ጥፋት ሁሉ ሲሰሙ ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”+ +4 ከዚያም ኤርምያስ የነሪያህን ልጅ ባሮክን+ ጠራው፤ ይሖዋ የነገረውንም ቃል ሁሉ በቃሉ አስጻፈው፤ ባሮክም በጥቅልሉ* ላይ ጻፈው።+ +5 ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “እኔ ታግጃለሁ፤ ወደ ይሖዋ ቤትም መግባት አልችልም። +6 ስለዚህ ገብተህ እኔ ያስጻፍኩህን የይሖዋን ቃል ከጥቅልሉ ላይ ጮክ ብለህ ማንበብ ያለብህ አንተ ነህ። በጾም ቀን በይሖዋ ቤት የተሰበሰቡ ሰዎች እየሰ��� አንብበው፤ በዚህ መንገድ፣ ከየከተሞቻቸው ለመጡት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ታነብላቸዋለህ። +7 ምናልባት ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡት ልመና ወደ ይሖዋ ሊደርስና እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ሊመለሱ ይችላሉ፤ ይሖዋ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣና መዓት ታላቅ ነውና።” +8 በመሆኑም የነሪያህ ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፤ በይሖዋ ቤት የይሖዋን ቃል ከጥቅልሉ* ላይ ጮክ ብሎ አነበበ።+ +9 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአምስተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም ያለው ሕዝብ ሁሉና ከይሁዳ ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጣው ሕዝብ ሁሉ በይሖዋ ፊት ጾም አወጀ።+ +10 ከዚያም ባሮክ በይሖዋ ቤት በላይኛው ግቢ ይኸውም በይሖዋ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ+ አጠገብ ባለው፣ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ* በሆነው በሳፋን+ ልጅ በገማርያህ+ ክፍል* ሕዝቡ ሁሉ እየሰማ የኤርምያስን ቃል ከጥቅልሉ* ላይ አነበበ። +11 የሳፋን ልጅ፣ የገማርያህ ልጅ ሚካያህ ከጥቅልሉ* ላይ የተነበበውን የይሖዋን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ +12 ወደ ንጉሡ ቤት፣* ወደ ጸሐፊው ክፍል ወረደ። መኳንንቱ* ሁሉ ይኸውም ጸሐፊው ኤሊሻማ፣+ የሸማያህ ልጅ ደላያህ፣ የአክቦር+ ልጅ ኤልናታን፣+ የሳፋን ልጅ ገማርያህ፣ የሃናንያህ ልጅ ሴዴቅያስና ሌሎቹ መኳንንት ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር። +13 ሚካያህ፣ ባሮክ ሕዝቡ እየሰማ ከጥቅልሉ* ላይ ሲያነብ ያዳመጠውን ቃል ሁሉ ነገራቸው። +14 በዚህ ጊዜ መኳንንቱ ሁሉ የኩሺ ልጅ፣ የሸሌምያህ ልጅ፣ የነታንያህ ልጅ የሆነውን የሁዲን “ሕዝቡ እየሰማህ ያነበብከውን ጥቅልል ይዘህ ና” ብሎ እንዲነግረው ወደ ባሮክ ላኩት። የነሪያህ ልጅ ባሮክም ጥቅልሉን ይዞ ወደ እነሱ ሄደ። +15 እነሱም “እባክህ ተቀመጥና ጥቅልሉን ጮክ ብለህ አንብብልን” አሉት። ባሮክም አነበበላቸው። +16 እነሱም ቃሉን ሁሉ እንደሰሙ በፍርሃት ተውጠው እርስ በርስ ተያዩ፤ ከዚያም ባሮክን “ይህን ቃል ሁሉ ለንጉሡ ልንነግረው ይገባል” አሉት። +17 ደግሞም ባሮክን “ይህን ሁሉ ቃል የጻፍከው እንዴት እንደሆነ እስቲ ንገረን። በቃሉ ነው ያስጻፈህ?” ብለው ጠየቁት። +18 ባሮክም “ይህን ሁሉ በቃሉ አስጻፈኝ፤ እኔም በጥቅልሉ* ላይ በቀለም ጻፍኩት” ብሎ መለሰላቸው። +19 መኳንንቱ ባሮክን “ሂድ፣ አንተና ኤርምያስ ተደበቁ፤ ያላችሁበትንም ማንም ሰው አይወቅ” አሉት።+ +20 ከዚያም ንጉሡ ወደሚገኝበት ግቢ ሄዱ፤ ጥቅልሉንም በጸሐፊው በኤሊሻማ ክፍል አስቀመጡት፤ የሰሙትንም ነገር ሁሉ ለንጉሡ ነገሩት። +21 ንጉሡም ጥቅልሉን እንዲያመጣ የሁዲን+ ላከው፤ እሱም ጥቅልሉን ከጸሐፊው ከኤሊሻማ ክፍል ይዞት መጣ። የሁዲም ንጉሡና በንጉሡ አጠገብ ቆመው የነበሩት መኳንንት ሁሉ እየሰሙ ያነበው ጀመር። +22 ንጉሡ በዘጠነኛው ወር* የክረምቱን ወቅት በሚያሳልፍበት ቤት ተቀምጦ ነበር፤ በፊቱም በምድጃ የሚነድ እሳት ነበር። +23 የሁዲ ሦስት ወይም አራት ዓምድ ካነበበ በኋላ ንጉሡ የተነበበውን ክፍል በጸሐፊ ቢላ እየቀደደ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ይወረውረው ነበር፤ ጥቅልሉ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ እስኪያልቅ ድረስ እንዲሁ አደረገ። +24 ይህን ሁሉ ቃል ሲሰሙ የነበሩት ንጉሡም ሆነ አገልጋዮቹ በሙሉ ምንም ፍርሃት አልተሰማቸውም፤ ልብሳቸውንም አልቀደዱም። +25 ኤልናታን፣+ ደላያህና+ ገማርያህ+ ንጉሡ ጥቅልሉን እንዳያቃጥለው ቢለምኑትም እንኳ አልሰማቸውም። +26 በተጨማሪም ንጉሡ ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን እንዲይዟቸው የንጉሡን ልጅ የራህምኤልን፣ የአዝርዔልን ልጅ ሰራያህንና የአብድዔልን ልጅ ሸሌምያህን አዘዘ፤ ይሖዋ ግን ሰውሯቸው ነበር።+ +27 ንጉሡ፣ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ ��የሰማ የጻፈውን ቃል የያዘውን ጥቅልል+ ካቃጠለው በኋላ የይሖዋ ቃል እንደገና እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +28 “ሌላ ጥቅልል ውሰድና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም ባቃጠለው በመጀመሪያው ጥቅልል+ ላይ የነበረውን ያንኑ ቃል ሁሉ ጻፍበት። +29 የይሁዳን ንጉሥ ኢዮዓቄምንም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህን ጥቅልል አቃጥለሃል፤ ደግሞም ‘“የባቢሎን ንጉሥ ያላንዳች ጥርጥር መጥቶ ይህችን ምድር ያወድማል፤ ሰውንና እንስሳንም ከምድሪቱ ላይ ያጠፋል” ብለህ በጥቅልሉ ላይ የጻፍከው ለምንድን ነው?’ ብለሃል።+ +30 ስለዚህ ይሖዋ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም ላይ እንዲህ ይላል፦ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይኖረውም፤+ ሬሳውም የቀን ሐሩርና የሌሊት ቁር ይፈራረቅበታል።+ +31 እሱን፣ ልጆቹንና* አገልጋዮቹን ለፈጸሙት በደል ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤ ደግሞም በእነሱ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና በይሁዳ ሰዎች ላይ አመጣባቸዋለሁ ብዬ የተናገርኩትን ጥፋት ሁሉ አወርድባቸዋለሁ፤+ እነሱ ግን አልሰሙም።’”’”+ +32 ከዚያም ኤርምያስ ሌላ ጥቅልል ወስዶ ለነሪያህ ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፤+ እሱም ኤርምያስ በቃል እያስጻፈው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በእሳት ባቃጠለው ጥቅልል*+ ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ጻፈበት። ደግሞም ከዚያ ጋር የሚመሳሰል ብዙ ቃል ተጨመረበት። +29 ነቢዩ ኤርምያስ፣ በግዞት ከተወሰዱት ሰዎች መካከል በሕይወት ለቀሩት ሽማግሌዎች፣ ለካህናቱ፣ ለነቢያቱና ናቡከደነጾር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ለወሰደው ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው ደብዳቤ ቃል ይህ ነው፦ +2 ይህም የሆነው ንጉሥ ኢኮንያን፣+ የንጉሡ እናት፣*+ ባለሥልጣናቱ፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መኳንንት፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና አንጥረኞቹ* ከኢየሩሳሌም ከሄዱ በኋላ ነው።+ +3 ደብዳቤውን የላከው፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ+ ወደ ባቢሎን ይኸውም የባቢሎን ንጉሥ ወደሆነው ወደ ናቡከደነጾር በላካቸው በሳፋን+ ልጅ በኤልዓሳና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያህ እጅ ነው። ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፦ +4 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት እንዲወሰዱ ላደረጋቸው ለተማረኩት ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ይላል፦ +5 ‘ቤት ሠርታችሁ በዚያ ኑሩ። አትክልት ተክላችሁ ፍሬውን ብሉ። +6 ሚስት አግብታችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ውለዱ፤ እነሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲወልዱ፣ ወንዶች ልጆቻችሁንና ሴቶች ልጆቻችሁን ዳሩ። በዚያም ቁጥራችሁ ይብዛ እንጂ አይነስ። +7 በግዞት ተወስዳችሁ እንድትኖሩባት ላደረግኳት ከተማም ሰላምን ፈልጉ፤ ስለ እሷም ወደ ይሖዋ ጸልዩ፤ እሷ ሰላም ከሰፈነባት እናንተም በሰላም ትኖራላችሁና።+ +8 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “በመካከላችሁ ያሉት ነቢያትና ሟርተኞች አያታሏችሁ፤+ የሚያልሙትንም ሕልም አትስሙ። +9 ‘በስሜ የሚተነብዩላችሁ ሐሰት ነውና። እኔ አልላክኋቸውም’+ ይላል ይሖዋ።”’” +10 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በባቢሎን የምትኖሩበት 70 ዓመት ሲፈጸም ትኩረቴን ወደ እናንተ አዞራለሁ፤+ ወደዚህም ስፍራ መልሼ በማምጣት፣ የገባሁትን ቃል እፈጽማለሁ።’+ +11 “‘ለእናንተ የማስበውን ሐሳብ በሚገባ አውቀዋለሁና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ የማስበው ጥፋትን ሳይሆን ሰላምን+ እንዲሁም የተሻለ ሕይወትንና ተስፋን ነው።+ +12 እናንተም ትጠሩኛላችሁ፤ ወደ እኔም ቀርባችሁ ትጸልያላችሁ፤ እኔም እሰማችኋለሁ።’+ +13 “‘እኔን ትሻላችሁ፤ በሙሉ ልባችሁ ስለምትፈልጉኝ ታገኙኛላችሁ።+ +14 እኔም እገኝላችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በምርኮ የተወሰዱትን ወገኖቻችሁን እሰበስባለሁ፤ እናንተን ���በተንኩባቸው ብሔራትና ቦታዎች ሁሉ እሰበስባችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በግዞት እንድትወሰዱ ባደረግኩ ጊዜ ትታችሁት ወደሄዳችሁት ቦታ መልሼ አመጣችኋለሁ።’+ +15 “እናንተ ግን ‘ይሖዋ በባቢሎን ነቢያት አስነስቶልናል’ ብላችኋል። +16 “ይሖዋ በዳዊት ዙፋን ላይ ለተቀመጠው ንጉሥና+ በዚህች ከተማ ውስጥ ለሚኖረው ሕዝብ ሁሉ ይኸውም ከእናንተ ጋር በግዞት ላልተወሰዱት ወንድሞቻችሁ እንዲህ ይላልና፦ +17 ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በእነሱ ላይ ሰይፍን፣ ረሃብንና ቸነፈርን* እሰዳለሁ፤+ በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳ ሊበሉ እንደማይችሉ የበሰበሱ* በለሶች አደርጋቸዋለሁ።”’+ +18 “‘በሰይፍ፣+ በረሃብና በቸነፈር አሳድዳቸዋለሁ፤ በምድር ላይ ላሉ መንግሥታትም ሁሉ መቀጣጫ አደርጋቸዋለሁ፤+ እነሱን በምበትንባቸው ብሔራት ሁሉ መካከልም ለእርግማን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ደግሞም መደነቂያ፣ ማፏጫና+ መሳለቂያ አደርጋቸዋለሁ፤+ +19 ምክንያቱም ደግሜ ደጋግሜ በላክኋቸው አገልጋዮቼ ይኸውም በነቢያት አማካኝነት ያስተላለፍኩትን ቃል አልሰሙም’+ ይላል ይሖዋ። “‘ይሁንና እናንተም አልሰማችሁም’+ ይላል ይሖዋ። +20 “ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኳችሁ እናንተ ግዞተኞች ሁሉ የይሖዋን ቃል ስሙ። +21 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚተነብዩላችሁ+ ስለ ቆላያህ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ ማአሴያህ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እሱም በፊታችሁ ይገድላቸዋል። +22 በእነሱ ላይ የሚደርሰውንም ነገር በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ግዞተኞች ሁሉ እንደ እርግማን ይጠቀሙበታል፤ “ይሖዋ፣ የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ ያድርግህ!” ይላሉ፤ +23 ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋር በማመንዘርና እኔ ያላዘዝኳቸውን ቃል በስሜ በሐሰት በመናገር+ በእስራኤል የሚያሳፍር ድርጊት ፈጽመዋልና።+ “‘“እኔ ይህን አውቃለሁ፤ ለዚህም ነገር ምሥክር ነኝ”+ ይላል ይሖዋ።’” +24 “ኔሄላማዊውን ሸማያህን+ እንዲህ ትለዋለህ፦ +25 ‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በኢየሩሳሌም ላሉት ሰዎች ሁሉና ለማአሴያህ ልጅ ለካህኑ ሶፎንያስ+ እንዲሁም ለካህናቱ ሁሉ፣ በገዛ ስምህ እንዲህ ብለህ ደብዳቤዎችን ልከሃልና፦ +26 ‘በይሖዋ ቤት የበላይ ተመልካች እንድትሆን፣ እንደ ነቢይ የሚያደርገውን ማንኛውንም ያበደ ሰው እንድትይዝ እንዲሁም በእግር ግንድ ብሎም በአንገትና በእጅ መጠረቂያ* እንድታስር ይሖዋ በካህኑ በዮዳሄ ምትክ ካህን አድርጎሃል፤+ +27 ታዲያ ነቢይ ነኝ የሚላችሁን የአናቶቱን+ ኤርምያስን ለምን አልገሠጽከውም?+ +28 በባቢሎን ላለነው ሰዎችም እንኳ ሳይቀር እንዲህ የሚል መልእክት ልኮብናል፦ “በግዞት የምትቆዩበት ጊዜ ረጅም ነው! ቤት ሠርታችሁ በዚያ ኑሩ። አትክልት ተክላችሁ ፍሬውን ብሉ፤+ . . .”’”’” +29 ካህኑ ሶፎንያስ+ ይህን ደብዳቤ ነቢዩ ኤርምያስ እየሰማ ባነበበ ጊዜ +30 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +31 “በግዞት ወዳሉት ሁሉ እንዲህ የሚል መልእክት ላክ፦ ‘ይሖዋ ስለ ኔሄላማዊው ሸማያህ እንዲህ ይላል፦ “ሸማያህ እኔ ሳልከው ስለተነበየላችሁና በሐሰት እንድትታመኑ ለማድረግ ስለሞከረ፣+ +32 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ትኩረቴን በኔሄላማዊው ሸማያህና በዘሮቹ ላይ አደርጋለሁ።’ በዚህ ሕዝብ መካከል የእሱ ዘር የሆነ አንድም ሰው አይተርፍም፤ ለሕዝቤ የማደርገውንም መልካም ነገር አያይም’ ይላል ይሖዋ፤ ‘በይሖዋ ላይ ዓመፅ አነሳስቷልና።’”’” +28 በዚያው ዓመት፣ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ፣ በአራተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ የገባኦን+ ሰው የሆነው የአዙር ልጅ ነቢዩ ሃናንያህ፣ በይሖዋ ቤት ውስጥ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦ +2 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁ።+ +3 በሁለት ዓመት* ጊዜ ውስጥ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ከዚህ ስፍራ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን የይሖዋን ቤት ዕቃዎች ሁሉ ወደዚህ ቦታ መልሼ አመጣለሁ።’”+ +4 “‘የኢዮዓቄምን+ ልጅ፣ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን+ እንዲሁም ወደ ባቢሎን በግዞት የተወሰዱትን የይሁዳ ሰዎች ሁሉ+ ወደዚህ ቦታ መልሼ አመጣለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።’” +5 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ በካህናቱ ፊትና በይሖዋ ቤት ቆመው በነበሩት ሕዝብ ሁሉ ፊት ነቢዩ ሃናንያህን አናገረው። +6 ነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ “አሜን! ይሖዋ ይህን ያድርግ! የይሖዋን ቤት ዕቃዎችና በግዞት የተወሰዱትን ሰዎች ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ እንዲመለሱ በማድረግ ይሖዋ የተነበይከውን ቃል ይፈጽም! +7 ይሁንና እባክህ፣ በጆሮህና በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ የምናገረውን ይህን መልእክት ስማ። +8 በጥንት ዘመን ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩት ነቢያት፣ ብዙ አገሮችና ታላላቅ መንግሥታት ስለሚያጋጥማቸው ጦርነት እንዲሁም ስለሚደርስባቸው ጥፋትና ቸነፈር* ይተነብዩ ነበር። +9 አንድ ነቢይ ስለ ሰላም ትንቢት ከተናገረና ነቢዩ የተናገረው ቃል ከተፈጸመ ይሖዋ ይህን ነቢይ በእርግጥ እንደላከው ይታወቃል።” +10 በዚህ ጊዜ ነቢዩ ሃናንያህ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ አንገት ላይ ወስዶ ሰበረው።+ +11 ከዚያም ሃናንያህ በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ልክ እንዲሁ እኔም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነጾርን ቀንበር ከብሔራት ሁሉ አንገት ላይ እሰብራለሁ።’”+ ነቢዩ ኤርምያስም ትቶት ሄደ። +12 ነቢዩ ሃናንያህ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ አንገት ላይ ወስዶ ከሰበረው በኋላ ይህ የይሖዋ መልእክት ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +13 “ሄደህ ሃናንያህን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተ የእንጨት ቀንበር ሰብረሃል፤+ ይሁንና በእሱ ምትክ የብረት ቀንበር ትሠራለህ።” +14 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን እንዲያገለግሉ በእነዚህ ሁሉ ብሔራት አንገት ላይ የብረት ቀንበር አደርጋለሁ፤ እነሱም ያገለግሉታል።+ የዱር አራዊትንም እንኳ እሰጠዋለሁ።”’”+ +15 ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ ነቢዩ ሃናንያህን+ እንዲህ አለው፦ “ሃናንያህ ሆይ፣ እባክህ ስማ! ይሖዋ ሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።+ +16 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ። በይሖዋ ላይ ዓመፅ ስላነሳሳህ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።’”+ +17 በመሆኑም ነቢዩ ሃናንያህ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ። +38 የማታን ልጅ ሰፋጥያህ፣ የጳስኮር ልጅ ጎዶልያስ፣ የሸሌምያህ ልጅ ዩካልና+ የማልኪያህ ልጅ ጳስኮር፣+ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን የሚከተለውን ቃል ሰሙ፦ +2 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህች ከተማ የሚቀር በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* ይሞታል።+ ለከለዳውያን እጁን የሚሰጥ* ግን ይተርፋል፤ ሕይወቱ * እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፤* በሕይወትም ይኖራል።’+ +3 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህች ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት መሰጠቷ አይቀርም፤ እሱም ይይዛታል።’”+ +4 መኳንንቱ ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው እንዲህ ያለ ቃል በመናገር በዚህች ከተማ ውስጥ የ���ሩትን ወታደሮችና የሕዝቡን ሁሉ ወኔ* እያዳከመ ስለሆነ እባክህ አስገድለው።+ ይህ ሰው ለዚህ ሕዝብ ጥፋትን እንጂ ሰላምን አይመኝምና።” +5 ንጉሥ ሴዴቅያስም “እነሆ፣ እሱ በእጃችሁ ነው፤ ንጉሡ እናንተን ለማስቆም ምንም ነገር ሊያደርግ አይችልምና” ሲል መለሰላቸው። +6 እነሱም ኤርምያስን ወስደው በክብር ዘቦቹ ግቢ+ በሚገኘው በንጉሡ ልጅ በማልኪያህ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት። ኤርምያስን በገመድ ወደ ጉድጓዱ አወረዱት። በጉድጓዱ ውስጥም ጭቃ ብቻ እንጂ ውኃ አልነበረም፤ ኤርምያስም ጭቃው ውስጥ መስመጥ ጀመረ። +7 በንጉሡ ቤት* የነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ* ኤቤድሜሌክ+ ኤርምያስን በውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ እንደጣሉት ሰማ። በዚህ ጊዜ ንጉሡ በቢንያም በር ተቀምጦ ነበር፤+ +8 በመሆኑም ኤቤድሜሌክ ከንጉሡ ቤት* ወጥቶ ንጉሡን እንዲህ አለው፦ +9 “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች በነቢዩ ኤርምያስ ላይ ክፉ ነገር ፈጽመዋል! በውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጥለውታል፤ ከረሃቡም የተነሳ እዚያው ይሞታል፤ በከተማዋ ውስጥ ዳቦ የሚባል ነገር የለምና።”+ +10 ከዚያም ንጉሡ ኢትዮጵያዊውን ኤቤድሜሌክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ከዚህ 30 ሰዎች ይዘህ ሂድ፤ ነቢዩ ኤርምያስንም ከመሞቱ በፊት ከውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ ጎትተህ አውጣው።” +11 በመሆኑም ኤቤድሜሌክ ሰዎቹን ይዞ በንጉሡ ቤት* ከግምጃ ቤቱ+ ሥር ወዳለው ቦታ ሄደ፤ ከዚያም የተቦጫጨቀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ ከዚያ ወስደው በውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ ላለው ለኤርምያስ በገመድ አወረዱለት። +12 ኢትዮጵያዊው ኤቤድሜሌክ ኤርምያስን “ይህን የተቦጫጨቀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ በብብትህና በገመዱ መካከል አድርገው” አለው። ኤርምያስም እንደተባለው አደረገ፤ +13 እነሱም ኤርምያስን በገመዱ ጎትተው ከውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ አወጡት። ኤርምያስም በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተቀመጠ። +14 ንጉሥ ሴዴቅያስ ሰው ልኮ ነቢዩ ኤርምያስን እሱ ወዳለበት፣ በይሖዋ ቤት ወደሚገኘው ወደ ሦስተኛው መግቢያ አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን “አንድ ነገር ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። ምንም ነገር እንዳትደብቀኝ” አለው። +15 በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ሴዴቅያስን “ብነግርህ ትገድለኛለህ። ብመክርህም አትሰማኝም” አለው። +16 ንጉሥ ሴዴቅያስም በሚስጥር ለኤርምያስ እንዲህ ሲል ማለለት፦ “ይህን ሕይወት በሰጠን* ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ አልገድልህም፤ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹት* ለእነዚህ ሰዎችም አሳልፌ አልሰጥህም።” +17 ከዚያም ኤርምያስ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን ብትሰጥ* ሕይወትህ ትተርፋለች፤* ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በሕይወት ትተርፋላችሁ።+ +18 ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን የማትሰጥ ከሆነ* ግን ይህች ከተማ ለከለዳውያን አልፋ ትሰጣለች፤ እነሱም በእሳት ያቃጥሏታል፤+ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም።’”+ +19 ከዚያም ንጉሥ ሴዴቅያስ ኤርምያስን “ወደ ከለዳውያን የኮበለሉትን አይሁዳውያን እፈራለሁ፤ ለእነሱ አሳልፈው የሰጡኝ እንደሆነ ሊያሠቃዩኝ ይችላሉ” አለው። +20 ኤርምያስ ግን እንዲህ አለው፦ “ለእነሱ አሳልፈው አይሰጡህም። እባክህ የምነግርህን የይሖዋን ቃል ታዘዝ፤ መልካምም ይሆንልሃል፤ በሕይወትም ትኖራለህ።* +21 እጅህን ለመስጠት* ፈቃደኛ ካልሆንክ ግን ይሖዋ የገለጠልኝ ነገር ይህ ነው፦ +22 እነሆ፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤት* የቀሩት ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ይወሰዳሉ፤+ እነሱም እንዲህ ይላሉ፦‘ተማምነህባቸው የነበሩት ሰዎች* አታለውሃል፤ ደግሞም አሸንፈውሃል።+ እግርህ ጭቃ ውስጥ እንዲሰምጥ አድርገዋል። አሁን አፈግፍገው ተመልሰዋል።’ +23 “ሚስቶችህንና ወንዶች ልጆችህን ሁሉ ለከለዳውያን ይሰጣሉ፤ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይልቁንም የባቢሎን ንጉሥ ይይዝሃል፤+ በአንተም ምክንያት ይህች ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”+ +24 ከዚያም ሴዴቅያስ ኤርምያስን እንዲህ አለው፦ “ስለዚህ ጉዳይ ማንም ሰው እንዳይሰማ፤ አለዚያ ትሞታለህ። +25 መኳንንቱ ከአንተ ጋር እንደተነጋገርኩ ሰምተው ወደ አንተ ቢመጡና ‘ለንጉሡ የነገርከውን ነገር እስቲ ንገረን። ምንም ነገር አትደብቀን፤ እኛም አንገድልህም።+ ንጉሡ የነገረህ ምንድን ነው?’ ቢሉህ፣ +26 ‘በዚያ እንዳልሞት ንጉሡ ወደ የሆናታን ቤት መልሶ እንዳይልከኝ ስለምነው ነበር’ በላቸው።”+ +27 በኋላም መኳንንቱ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት። እሱም ንጉሡ እንዲናገር ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው። እነሱም ከዚያ በኋላ ምንም አላሉትም፤ ያደረጉትን ውይይት የሰማ ሰው አልነበረምና። +28 ኤርምያስ ኢየሩሳሌም እስከተያዘችበት ጊዜ ድረስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተቀመጠ፤ ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ጊዜም እዚያው ነበር።+ +8 “በዚያን ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “የይሁዳ ነገሥታት አጥንቶች፣ የመኳንንቱ አጥንቶች፣ የካህናቱ አጥንቶች፣ የነቢያቱ አጥንቶችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አጥንቶች ከየመቃብራቸው ይወሰዳሉ። +2 በወደዷቸው፣ ባገለገሏቸው፣ በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና በሰገዱላቸው በፀሐይ፣ በጨረቃና በሰማያት ሠራዊት ሁሉ ፊት ይሰጣሉ።+ አይሰበሰቡም፤ እንዲሁም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።”+ +3 “ደግሞም ከዚህ ክፉ ወገን የሚተርፉት ቀሪዎች በሙሉ እኔ በምበትናቸው ቦታዎች ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +4 “አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሰዎች ከወደቁ በኋላ ዳግመኛ አይነሱም? አንዱ ከተመለሰ ሌላውስ አይመለስም? + 5 ታዲያ ይህ ሕዝብ፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪ በክህደት ሥራው የጸናው ለምንድን ነው? ተንኮልን የሙጥኝ ብለዋል፤ለመመለስ አሻፈረን ብለዋል።+ + 6 እኔም ትኩረት ሰጥቼ ማዳመጤን ቀጠልኩ፤ የሚናገሩበት መንገድ ግን ትክክል አልነበረም። ከክፋቱ ንስሐ የገባ ወይም ‘ምን መሥራቴ ነው?’ ብሎ የጠየቀ አንድም ሰው የለም።+ እያንዳንዱ ሰው ወደ ጦርነት እንደሚገሰግስ ፈረስ ብዙኃኑ ወደሚከተለው መንገድ ይመለሳል። + 7 በሰማይ የምትበረው ራዛ* እንኳ ወቅቷን* ታውቃለች፤ዋኖስ፣ ወንጭፊትና ጭሪ* የሚመለሱበትን* ጊዜ ያከብራሉ። የገዛ ሕዝቤ ግን የይሖዋን ፍርድ አይገነዘብም።”’+ + 8 ‘“ጥበበኞች ነን፤ የይሖዋም ሕግ* አለን” እንዴት ትላላችሁ? እንዲያውም የጸሐፊዎቹ ሐሰተኛ* ብዕር+ ያገለገለው ውሸት ለመጻፍ ብቻ ነው። + 9 ጥበበኞቹ ለኀፍረት ተዳርገዋል።+ ተሸብረዋል፤ ደግሞም ይያዛሉ። እነሆ፣ እነሱ የይሖዋን ቃል ንቀዋል፤ታዲያ ምን ዓይነት ጥበብ ይኖራቸዋል? +10 ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች ሰዎች፣እርሻዎቻቸውንም ለሌሎች እሰጣለሁ፤+ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣልና፤+ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+ +11 ሰላም ሳይኖር፣“ሰላም ነው! ሰላም ነው!” እያሉ የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት ላይ ላዩን* ለመጠገን ይሞክራሉ።+ +12 በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል? እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም! ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም!+ “‘ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ። እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ’+ ይላል ይሖዋ። +13 ‘በምሰበስባቸው ጊዜ አ��ፋቸዋለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘በወይን ተክሉ ላይ የቀረ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፉ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሉም ይጠወልጋል። የሰጠኋቸውም ነገር ይጠፋባቸዋል።’” +14 “እዚህ የምንቀመጠው ለምንድን ነው? በአንድነት እንሰብሰብ፤ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች ገብተን+ በዚያ እንጥፋ። አምላካችን ይሖዋ ያጠፋናልና፤የተመረዘ ውኃ እንድንጠጣ ይሰጠናል፤+ምክንያቱም በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል። +15 ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም መልካም ነገር አልመጣም፤የፈውስ ጊዜ ይመጣል ብለን ጠበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ነገሠ!+ +16 የፈረሶቹ ፉርፉርታ ከዳን ተሰማ። ድንጉላ ፈረሶቹ ሲያሽካኩምድሪቱ በሙሉ ትንቀጠቀጣለች። እነሱ መጥተው ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ይበላሉ።” +17 “እነሆ፣ ድግምት የማይገታቸው እባቦችንና እፉኝቶችንበመካከላችሁ እልካለሁ፤እነሱም ይነድፏችኋል” ይላል ይሖዋ። +18 ማጽናኛ የማይገኝለት ሐዘን ደርሶብኛል፤ልቤ ታሟል። +19 የሕዝቤ ሴት ልጅ “ይሖዋ በጽዮን የለም?ወይስ ንጉሧ በዚያ የለም?” የሚል የእርዳታ ጥሪ ከሩቅ አገር ታሰማለች። “በተቀረጹት ምስሎቻቸውናከንቱ በሆኑት ባዕዳን አማልክታቸው ያስከፉኝ ለምንድን ነው?” +20 “መከሩ አልፏል፤ በጋውም አብቅቷል፤እኛ ግን አልዳንም!” +21 በሕዝቤ ሴት ልጅ ውድቀት የተነሳ ደቅቄአለሁ፤+በጣም አዝኛለሁ፤ በፍርሃት ተውጫለሁ። +22 በጊልያድ የበለሳን ዘይት የለም?*+ ወይስ በዚያ ፈዋሽ* የለም?+ ታዲያ የሕዝቤ ሴት ልጅ ያላገገመችው ለምንድን ነው?+ +11 ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ +2 “እናንተ ሰዎች፣ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ! “ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ቃሉን ተናገር፤* +3 እንዲህም በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይታዘዝ ሰው የተረገመ ነው፤+ +4 ይህም አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር፣ ከብረት ማቅለጫ ምድጃው ባወጣኋቸው ጊዜ+ እንዲህ ብዬ ያዘዝኳቸው ቃል ነው፦+ ‘ድምፄን ስሙ፤ ያዘዝኳችሁንም ነገር ሁሉ አድርጉ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤+ +5 ይህም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ለመስጠት ለአባቶቻችሁ የገባሁትን መሐላ ለመፈጸም ነው።’”’”+ እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ አሜን”* ብዬ መለስኩ። +6 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህን ቃላት ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ አውጅ፦ ‘የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ፤ በሥራም ላይ አውሉት። +7 አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ “ድምፄን ስሙ” በማለት ደግሜ ደጋግሜ አጥብቄ ሳሳስባቸው ነበርና።+ +8 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤ ከዚህ ይልቅ እያንዳንዳቸው ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን ተከተሉ።+ ስለዚህ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ያዘዝኳቸውንና እነሱ ሥራ ላይ ያላዋሉትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ በእነሱ ላይ አመጣሁባቸው።’” +9 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሴራ ጠንስሰዋል። +10 ቃሌን ያልታዘዙት የቀድሞ አባቶቻቸው ይፈጽሙት ወደነበረው በደል ተመልሰዋል።+ እነሱም ሌሎች አማልክትን ተከትለዋል፤ ደግሞም አገልግለዋል።+ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል።+ +11 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ማምለጥ የማይችሉትን ጥፋት አመጣባቸዋለሁ።+ እርዳታ ለማግኘት ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውም።+ +12 ከዚያም የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መሥዋዕት* ወደሚያቀርቡላቸው አማልክት ሄደው እርዳታ ይጠይቃሉ፤+ ሆኖም ጥፋት በሚደርስባቸው ጊዜ ፈጽሞ አያድኗቸውም። +13 ይሁዳ ሆይ፣ አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋልና፤ ለአሳፋሪው ነገር* ይኸውም ለባአል መሥዋዕት ለማቅረብ የኢየሩሳሌምን ጎዳናዎች ያህል ብዛት ያላቸው መሠዊያዎች ሠርታችኋል።’+ +14 “አንተም* ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ። ስለ እነሱ የልመና ጩኸትም ሆነ ጸሎት አታሰማ፤+ ጥፋት ደርሶባቸው ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና። +15 ብዙዎቹ የሸረቡትን ክፉ ሐሳብ እየፈጸሙ ሳለ፣ውዴ በቤቴ ለመገኘት ምን መብት አላት? ጥፋት በአንቺ ላይ ሲመጣ በቅዱስ ሥጋ* ጥፋቱን ሊከላከሉልሽ ይችላሉ? በዚያን ጊዜ ሐሴት ታደርጊ ይሆን? +16 በአንድ ወቅት ይሖዋ በመልካም ፍሬ የተዋበ፣የለመለመ የወይራ ዛፍ ብሎ ጠርቶሽ ነበር። በሚያስገመግም ታላቅ ድምፅ፣ በእሳት አነደዳት፤እነሱም ቅርንጫፎቿን ሰባበሩ። +17 “የተከለሽ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣+ ለባአል መሥዋዕት በማቅረብ እኔን ያስከፉኝ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በሠሩት ክፉ ነገር የተነሳ በአንቺ ላይ ጥፋት እንደሚመጣ አስታውቋል።”+ +18 ይሖዋ ይህን እንዳውቅ ገለጠልኝ፤አምላክ ሆይ፣ በዚያን ጊዜ የፈጸሙትን ነገር እንዳይ አደረግከኝ። +19 እኔ ለመታረድ እንደሚነዳ የዋህ የበግ ጠቦት ነበርኩ። “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋው፤ ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ እንዳይታወስከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለውበእኔ ላይ ሴራ እንደጠነሰሱ አላወቅኩም ነበር።+ +20 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ግን በጽድቅ ይፈርዳል፤የውስጥ ሐሳብንና* ልብን ይመረምራል።+ አምላክ ሆይ፣ በእነሱ ላይ የምትወስደውን የበቀል እርምጃ እንዳይ አድርገኝ፤ጉዳዬን ለአንተ አቅርቤአለሁና። +21 ስለዚህ ይሖዋ ሕይወትህን ለማጥፋት በሚሹ* በአናቶት+ ሰዎች ላይ ይህን ቃል ተናግሯል፤ እነሱ “በይሖዋ ስም ትንቢት አትናገር፤+ አለዚያ በእጃችን ትጠፋለህ” ይላሉ፤ +22 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እነሱን ተጠያቂ አደርጋለሁ። ወጣት ወንዶቹ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በረሃብ ያልቃሉ።+ +23 እነሱን ተጠያቂ በማደርግበት ዓመት፣ በአናቶት+ ሰዎች ላይ ጥፋት ስለማመጣ ከእነሱ መካከል የሚተርፍ አንድም ሰው አይኖርም።” +2 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “ሂድና ኢየሩሳሌም ጆሮዋ እየሰማ ይህን አውጅ፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በወጣትነትሽ ጊዜ ለአምላክ ያደርሽ እንደነበርሽ፣*+ደግሞም ለጋብቻ በታጨሽበት ጊዜ ያሳየሽውን ፍቅር፣+ዘር በማይዘራበት ምድር፣ በምድረ በዳእንዴት እንደተከተልሽኝ በሚገባ አስታውሳለሁ።+ + 3 እስራኤል ለይሖዋ የተቀደሰ፣+ የመከሩ በኩር ነበር።”’ ‘እሱን የሚውጥ ሁሉ በደለኛ ይሆናል። በእነሱም ላይ ጥፋት ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።”+ + 4 የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ፣የይሖዋን ቃል ስሙ። + 5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አባቶቻችሁ ከእኔ እጅግ የራቁት፣ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችን የተከተሉትና+እነሱ ራሳቸው ከንቱ የሆኑት+ ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?+ + 6 እነሱ ‘ከግብፅ ምድር ያወጣን፣+በምድረ በዳ፣ በረሃማ በሆነና+ጉድጓድ ባለበት ምድር፣በድርቅ በተጠቃና+ ድቅድቅ ጨለማ በዋጠው ምድርእንዲሁም ማንም ሰው በማይጓዝበትናሰው በማይኖርበት ምድርየመራን ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም። + 7 በዚያን ጊዜ እኔ ፍሬዋንና በውስጧ ያሉትን ጥሩ ጥሩ ነገሮች እንድትበሉየፍራፍሬ ዛፎች ወዳሉባት ምድር አመጣኋችሁ።+ እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤ርስቴንም አስጸያፊ ነገር አደረጋችሁት።+ + 8 ካህናቱ ‘ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም፤+ ሕጉ በአደራ የተሰጣቸውም እኔን አላወቁም፤እረኞቹ በእኔ ላይ ዓመፁ፤+ነቢያቱ በባአል ስም ትንቢት ተናገሩ፤+ምንም ጥቅም የማያስገኙላቸውንም አማልክት ተከተሉ። + 9 ‘በመሆኑም ከእናንተ ጋር ገና እሟገታለሁ’+ ይላል ይሖዋ፤‘ከልጅ ልጆቻችሁም ጋር እሟገታለሁ።’ +10 ‘እስቲ ወደ ኪቲም+ የባሕር ዳርቻዎች* ተሻግራችሁ ተመልከቱ። አዎ፣ መልእክተኞችን ወደ ቄዳር+ ልካችሁ ጉዳዩን በጥሞና መርምሩ፤እንዲህ ያለ ነገር ተፈጽሞ እንደሆነ እዩ። +11 አማልክቱን፣ አማልክት ባልሆኑት ለውጦ የሚያውቅ ብሔር አለ? የገዛ ሕዝቤ ግን ክብሬን ምንም ጥቅም በሌለው ነገር ለውጧል።+ +12 እናንተ ሰማያት በዚህ ተደነቁ፤በታላቅ ድንጋጤም ተርበትበቱ’ ይላል ይሖዋ፤ +13 ‘ምክንያቱም ሕዝቤ ሁለት መጥፎ ነገሮች ፈጽመዋል፦ የሕያው ውኃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተው+የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ይኸውም ውኃ መያዝ የማይችሉና የሚያፈሱየውኃ ማጠራቀሚያዎችን ለራሳቸው ቆፍረዋል።’* +14 ‘እስራኤል፣ አገልጋይ ወይም የቤት ውልድ ባሪያ ነው? ታዲያ እንዲበዘበዝ የተደረገው ለምንድን ነው? +15 ደቦል አንበሶች በእሱ ላይ አገሡ፤+በኃይለኛ ድምፅ ጮኹበት። ምድሩን የሚያስፈራ ቦታ አደረጉት። ከተሞቹ ማንም እንዳይኖርባቸው በእሳት ተቃጠሉ። +16 የኖፍና*+ የጣፍነስ+ ሕዝቦች፣ መሃል አናትሽን ይበላሉ። +17 አምላክሽ ይሖዋ በመንገዱ በመራሽ ወቅትእሱን በመተው+ይህን በራስሽ ላይ አላመጣሽም? +18 ደግሞስ የሺሆርን ውኃዎች* ለመጠጣትወደ ግብፅ የሚወስደውን መንገድ የመረጥሽው ለምንድን ነው?+ የወንዙን* ውኃዎች ለመጠጣትወደ አሦር የሚወስደውን መንገድ የመረጥሽው ለምንድን ነው?+ +19 ከክፋትሽ ትምህርት ልታገኚ ይገባል፤ታማኝነት በማጉደል የፈጸምሻቸው ድርጊቶችም ወቀሳ ያስከትሉብሻል። አምላክሽን ይሖዋን መተውሽመጥፎና መራራ እንደሆነ ማወቅና መገንዘብ ይኖርብሻል፤+እኔን ፈጽሞ አልፈራሽም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ። +20 ‘ከረጅም ጊዜ በፊት ቀንበርሽን ሰባበርኩ፤+የታሰርሽበትንም ሰንሰለት በጣጠስኩ። አንቺ ግን “አንተን አላገለግልም” አልሽ፤ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይና ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር+ለማመንዘር ተንጋለሽ ተኝተሻልና።+ +21 እኔ፣ እንደ ምርጥ ቀይ የወይን ተክል፣ ሙሉ በሙሉ ንጹሕ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤+ታዲያ በፊቴ እንዲህ ተለውጠሽ የተበላሸ ባዕድ የወይን ተክል የሆንሽው እንዴት ነው?’+ +22 ‘በሶዳ* ብትታጠቢና ብዛት ያለው እንዶድ* ብትጠቀሚ እንኳከበደልሽ የተነሳ ዕድፍሽ በፊቴ ይኖራል’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +23 ‘ራሴን አላረከስኩም። ባአልንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆው ውስጥ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ። ያደረግሽውን ነገር ልብ በይ። በመንገዷ ላይ ወዲያና ወዲህ እንደምትፋንንየደረሰች ፈጣን ግመል ነሽ፤ +24 በምድረ በዳ መኖር እንደለመደች፣በፍትወቷ* ነፋሱን እንደምታነፈንፍ የዱር አህያ ነሽ። ስሜቷ ሲነሳሳ ማን ሊመልሳት ይችላል? የሚፈልጓት ሁሉ እሷን ለማግኘት ብዙ ድካም አይጠይቅባቸውም። በመራቢያዋ ወቅት* ያገኟታል። +25 እግርሽ እስኪነቃ አትዙሪ፤ጉሮሮሽም በውኃ ጥም አይቃጠል። አንቺ ግን ‘አይሆንም! ምንም ተስፋ የሌለው ነገር ነው!+ እኔ ከባዕዳን* ጋር ፍቅር ይዞኛል፤+እነሱንም እከተላለሁ’ አልሽ።+ +26 ሌባ ሲያዝ እንደሚያፍር፣የእስራኤል ቤት ሰዎችም እንዲሁ አፍረዋል፤እነሱም ሆኑ ነገሥታታቸው፣ መኳንንታቸው፣ካህናታቸውና ነቢያታቸው ውርደት ተከናንበዋል።+ +27 ዛፉን ‘አንተ አባቴ ነህ’፤+ ድንጋዩንም ‘የወለድከኝ አንተ ነህ’ ይላሉ። ለእኔ ግን ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጥተውኛል።+ ጥፋት ሲመጣባቸውም‘ተነስተህ አድነን!’ ይላሉ።+ +28 ለራስህ የሠራሃቸው አማ���ክት ታዲያ የት አሉ?+ ጥፋት ሲደርስብህ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ ይነሱ፤ይሁዳ ሆይ፣ አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋልና።+ +29 ‘አሁንም ከእኔ ጋር የምትሟገቱት ለምንድን ነው? ሁላችሁም በእኔ ላይ ያመፃችሁት ለምንድን ነው?’+ ይላል ይሖዋ። +30 ልጆቻችሁን የመታሁት በከንቱ ነው።+ ለመታረም ፈቃደኞች አይደሉም፤+የገዛ ራሳችሁ ሰይፍ እንደሚያደባ አንበሳነቢያታችሁን በልቷል።+ +31 የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ልብ በሉ። እኔ ለእስራኤል፣ እንደ ምድረ በዳወይም ድቅድቅ ጨለማ እንደዋጠው ምድር ሆኛለሁ? የእኔ ሕዝብ የሆኑት እነዚህ ሰዎች ‘እኛ ወደፈለግንበት እንሄዳለን። ከእንግዲህ ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላሉ?+ +32 ለመሆኑ አንዲት ድንግል ጌጣጌጧን፣ሙሽሪትስ ጌጠኛ መቀነቷን* ትረሳለች? የገዛ ሕዝቤ ግን ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ቀናት ረስቶኛል።+ +33 አንቺ ሴት፣ ፍቅረኛ ለማግኘት መንገድሽን ምንኛ በጥበብ አመቻቸሽ! የክፋትን መንገዶች ተምረሻል።+ +34 ልብሶችሽ በንጹሐን ድሆች* ደም ቆሽሸዋል፤+ይሁንና ይህን ያገኘሁት ቤት ሲዘረፍ አይደለም፤ይልቁንም በልብሶችሽ ሁሉ ላይ ነው።+ +35 አንቺ ግን ‘እኔ ንጹሕ ነኝ። በእርግጥ ቁጣው ከእኔ ተመልሷል’ ትያለሽ። ‘ኃጢአት አልሠራሁም’ ስለምትዪ፣በአንቺ ላይ ፍርድ አመጣለሁ። +36 መንገድሽን በመለዋወጥ የምትፈጽሚውን ድርጊት አቅልለሽ የምትመለከቺው ለምንድን ነው? በአሦር እንዳፈርሽ ሁሉ+በግብፅም ታፍሪያለሽ።+ +37 በዚህም የተነሳ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ትወጫለሽ፤+ይሖዋ የምትተማመኚባቸውን ነገሮች አስወግዷልና፤እነሱ ለስኬት አያበቁሽም።” +26 በኢዮስያስ ልጅ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ይህ ቃል ከይሖዋ ዘንድ መጣ፦ +2 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በይሖዋ ቤት ግቢ ውስጥ ቆመህ፣ ለአምልኮ* ወደ ይሖዋ ቤት ስለሚመጡት፣ በይሁዳ ከተሞች ስለሚኖሩት* ሰዎች ሁሉ ተናገር። የማዝህን ቃል ሁሉ ንገራቸው፤ አንዲትም ቃል አታስቀር። +3 ምናልባት ይሰሙና እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በክፉ ሥራቸው የተነሳ በእነሱ ላይ ላመጣ ያሰብኩትን ጥፋት እተወዋለሁ።*+ +4 እንዲህ በላቸው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የማትሰሙኝና የሰጠኋችሁን ሕግ* የማትከተሉ ከሆነ፣ +5 እንዲሁም ደግሜ ደጋግሜ ወደ እናንተ የላክኋቸውን፣ እናንተ ያልሰማችኋቸውን የአገልጋዮቼን የነቢያትን ቃል የማትቀበሉ ከሆነ፣+ +6 ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፤+ ይህችንም ከተማ ለምድር ብሔራት ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።’”’”+ +7 ካህናቱ፣ ነቢያቱና ሕዝቡ ሁሉ ኤርምያስ በይሖዋ ቤት ይህን ቃል ሲናገር ሰሙ።+ +8 በመሆኑም ኤርምያስ፣ ይሖዋ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲናገር ያዘዘውን ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ካህናቱ፣ ነቢያቱና ሕዝቡ ሁሉ ይዘው እንዲህ አሉት፦ “አንተ በእርግጥ ትሞታለህ። +9 ‘ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆናል፤ ይህችም ከተማ ወድማ ሰው አልባ ትሆናለች’ ብለህ በይሖዋ ስም የተነበይከው ለምንድን ነው?” ሕዝቡም ሁሉ በይሖዋ ቤት በኤርምያስ ዙሪያ ተሰበሰበ። +10 የይሁዳ መኳንንት ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ከንጉሡ ቤት* ወደ ይሖዋ ቤት መጥተው በይሖዋ ቤት ባለው በአዲሱ በር መግቢያ ተቀመጡ።+ +11 ካህናቱና ነቢያቱ፣ ለመኳንንቱና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በሞት ሊቀጣ ይገባዋል፤+ ምክንያቱም በገዛ ጆሯችሁ እንደሰማችሁት በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሯል።”+ +12 በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ለመኳንንቱ ሁሉና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “የሰማችሁትን ቃል ሁሉ በዚህ ቤትና በዚህች ከተማ ላይ እንድተነብይ የላከኝ ይሖዋ ነው።+ +13 እንግዲያው አሁን መንገዳችሁንና ድርጊ���ችሁን አስተካክሉ፤ የአምላካችሁንም የይሖዋን ቃል ስሙ፤ ይሖዋም በእናንተ ላይ አመጣዋለሁ ብሎ የተናገረውን ጥፋት ይተወዋል።*+ +14 እኔ ግን በእጃችሁ ነኝ። መልካምና ትክክል መስሎ የታያችሁን ነገር ሁሉ አድርጉብኝ። +15 ከገደላችሁኝ በራሳችሁ፣ በዚህች ከተማና በነዋሪዎቿ ላይ የንጹሕ ሰው ደም ዕዳ እንደምታመጡ በእርግጥ እወቁ፤ ይህን ሁሉ ቃል በጆሯችሁ እንድናገር የላከኝ በእርግጥ ይሖዋ ነውና።” +16 በዚህ ጊዜ መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ ካህናቱንና ነቢያቱን “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በይሖዋ ስም ስለሆነ በሞት ሊቀጣ አይገባውም” አሏቸው። +17 በተጨማሪም በምድሪቱ ከሚኖሩ ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ተነስተው ለተሰበሰበው ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አሉ፦ +18 “የሞረሸቱ ሚክያስ+ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ+ ዘመን ትንቢት ይናገር ነበር፤ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብሎ ነበር፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+የቤቱም* ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች* ይሆናል።”’+ +19 “ታዲያ በዚያ ጊዜ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ገደሉት? ይልቁንም ይሖዋን ፈርቶ፣ ይሖዋ እንዲራራለት አልተማጸነም? ከዚህስ የተነሳ ይሖዋ በእነሱ ላይ ሊያመጣ አስቦት የነበረውን ጥፋት አልተወውም?*+ እኛ ግን በራሳችን* ላይ ጥፋት እየጋበዝን ነው። +20 “ደግሞም በይሖዋ ስም ትንቢት የሚናገር ሌላ ሰው ነበር፤ እሱም የቂርያትየአሪም+ ሰው የሆነው የሸማያህ ልጅ ዑሪያህ ሲሆን ኤርምያስ የተናገረውን ዓይነት ቃል በመናገር በዚህች ከተማና በዚህች ምድር ላይ ተንብዮአል። +21 ንጉሥ ኢዮዓቄም፣+ ኃያል ተዋጊዎቹ ሁሉና መኳንንቱ ሁሉ እሱ የተናገረውን ቃል ሰሙ፤ ንጉሡም ሊገድለው ፈለገ።+ ዑሪያህ ይህን እንደሰማ በጣም ስለፈራ ሸሽቶ ወደ ግብፅ ሄደ። +22 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ኢዮዓቄም የአክቦርን ልጅ ኤልናታንን+ እንዲሁም ከእሱ ጋር ሌሎች ሰዎችን ወደ ግብፅ ላከ። +23 እነሱም ዑሪያህን ከግብፅ አምጥተው ወደ ንጉሥ ኢዮዓቄም ወሰዱት፤ እሱም በሰይፍ መትቶ ገደለው፤+ አስከሬኑንም ተራ ሰዎች በሚቀበሩበት ስፍራ ጣለው።” +24 ይሁንና የሳፋን+ ልጅ አኪቃም+ ኤርምያስን ረዳው፤ በመሆኑም ኤርምያስ እንዲገደል ለሕዝቡ አልተሰጠም።+ +44 በግብፅ ምድር+ ይኸውም በሚግዶል፣+ በጣፍነስ፣+ በኖፍ*+ እና በጳትሮስ+ ምድር ለሚኖሩ አይሁዳውያን ሁሉ እንዲነገር ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ +2 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች በሙሉ ያመጣሁትን ጥፋት ሁሉ አይታችኋል፤+ ዛሬ ማንም የማይኖርባቸው የፍርስራሽ ክምር ሆነዋል።+ +3 ይህም የሆነው እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቋቸው ሌሎች አማልክት+ ሄደው ለእነሱ መሥዋዕት በማቅረብና እነሱን በማገልገል እኔን ለማስቆጣት በፈጸሙት ክፉ ድርጊት የተነሳ ነው።+ +4 አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላክኋቸው፤ “እባካችሁ፣ እኔ የምጠላውን ይህን አስጸያፊ ነገር አታድርጉ” በማለት ደግሜ ደጋግሜ ላክኋቸው።+ +5 እነሱ ግን አልሰሙም፤ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት ከማቅረብ+ በመቆጠብም ከክፉ መንገዳቸው ለመመለስ ጆሯቸውን አልሰጡም። +6 በመሆኑም ቁጣዬና ንዴቴ ፈሰሰ፤ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎችም ላይ ነደደ፤ እነሱም ዛሬ እንደሚታዩት የፍርስራሽ ክምርና ጠፍ መሬት ሆነዋል።’+ +7 “አሁንም የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወንዶችና ሴቶች፣ ልጆችና ሕፃናት ሁሉ ከይሁዳ ጠፍተው ለራሳችሁ አንድም ቀሪ እንዳይተርፍ በራሳችሁ* ላይ ለምን ታላቅ ጥፋት ታመጣ���ችሁ? +8 ለመኖር በሄዳችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ በእጃችሁ ሥራ የምታስቆጡኝ ለምንድን ነው? ትጠፋላችሁ፤ በምድር ብሔራትም ሁሉ መካከል ለእርግማንና ለነቀፋ ትዳረጋላችሁ።+ +9 በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አባቶቻችሁ የሠሩትን ክፉ ሥራ፣ የይሁዳ ነገሥታት የሠሩትን ክፉ ሥራና+ ሚስቶቻቸው የሠሩትን ክፉ ሥራ+ እንዲሁም እናንተ ራሳችሁ የሠራችሁትን ክፉ ሥራና ሚስቶቻችሁ የሠሩትን ክፉ ሥራ ረሳችሁት?+ +10 እነሱ እስከ ዛሬ ድረስ ራሳቸውን ዝቅ አላደረጉም፤* የፍርሃትም ስሜት አላደረባቸውም፤+ በእናንተና በአባቶቻችሁ ፊት ያኖርኩትን ሕጌንና ሥርዓቴንም አልተከተሉም።’+ +11 “ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣትና ይሁዳን ሁሉ ለመደምሰስ ቆርጬ ተነስቻለሁ። +12 በግብፅ ምድር ለመኖር ወደዚያ ለመሄድ ቆርጠው የተነሱትንም የይሁዳ ቀሪዎች እወስዳለሁ፤ ሁሉም በግብፅ ምድር ይጠፋሉ።+ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ከትንሹ እስከ ትልቁ ድረስ በረሃብ ያልቃሉ፤ በሰይፍና በረሃብ ይሞታሉ። ለእርግማን፣ ለውርደትና ለነቀፋ ይዳረጋሉ፤ መቀጣጫም ይሆናሉ።+ +13 ኢየሩሳሌምን እንደቀጣሁ ሁሉ በግብፅ ምድር የሚኖሩትንም በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* እቀጣለሁ።+ +14 በግብፅ ምድር ለመኖር የሄዱት የይሁዳ ቀሪዎችም አምልጠው ወይም በሕይወት ተርፈው ወደ ይሁዳ ምድር አይመለሱም። ወደዚያ ለመመለስና በዚያ ለመኖር ቢመኙም እንኳ* ከጥቂት ሰዎች በስተቀር አምልጦ የሚመለስ አይኖርም።’” +15 ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት ያቀርቡ እንደነበረ የሚያውቁ ወንዶች ሁሉ፣ ብዙ ሆነው የተሰበሰቡት ሚስቶቻቸው ሁሉ እንዲሁም በግብፅ ምድር+ ይኸውም በጳትሮስ+ የሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ለኤርምያስ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ +16 “በይሖዋ ስም የነገርከንን ቃል አንሰማም። +17 ይልቁንም አፋችን የተናገረውን ቃል ሁሉ መፈጸማችን አይቀርም፤ እኛና አባቶቻችን እንዲሁም ነገሥታታችንና መኳንንታችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ እናደርግ እንደነበረው ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት እናቀርባለን፤ ለእሷም የመጠጥ መባ እናፈሳለን፤+ በዚያን ጊዜ እስክንጠግብ ድረስ እንበላና +18 ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት ማቅረብና የመጠጥ መባ ማፍሰስ ካቆምንበት ጊዜ ጀምሮ ግን ሁሉን ነገር አጥተናል፤ እንዲሁም በሰይፍና በረሃብ አልቀናል።” +19 ሴቶቹም አክለው እንዲህ አሉ፦ “ደግሞስ ‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት እናቀርብና የመጠጥ መባ እናፈስ በነበረበት ጊዜ፣ በእሷ ምስል የመሥዋዕት ቂጣ የምንጋግረውና ለእሷ የመጠጥ መባ የምናፈሰው ባሎቻችንን ሳናማክር ነበር?” +20 በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ ይኸውም ለወንዶቹ፣ ለሚስቶቻቸውና እያናገሩት ለነበሩት ሰዎች ሁሉ እንዲህ አለ፦ +21 “እናንተ፣ አባቶቻችሁ፣ ነገሥታታችሁ፣ መኳንንታችሁና በምድሪቱ የሚኖረው ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ያቀረባችኋቸውን መሥዋዕቶች+ ይሖዋ አልዘነጋም፤ በልቡም አኑሯቸዋል! +22 በመጨረሻም ይሖዋ የፈጸማችኋቸውን ክፉ ድርጊቶችና የሠራችኋቸውን አስጸያፊ ነገሮች ሊታገሥ አልቻለም፤ ምድራችሁም ዛሬ እንደምታዩት ባድማ ስፍራ፣ አስፈሪ ቦታና ሰው የማይኖርባት ቦታ ሆነች፤ ለእርግማንም ተዳረገች።+ +23 እነዚህን መሥዋዕቶች ስላቀረባችሁ፣ ደግሞም የይሖዋን ቃል ባለመታዘዝ እንዲሁም የእሱን ሕግ፣ ደንብና ማሳሰቢያ ባለመከተል በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁ ዛሬ እንደምታዩት ይህ ጥፋት ደርሶባችኋል።”+ +24 ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉና ለሴቶቹ ሁሉ እንዲህ ሲል አክሎ ተናገረ፦ “በግብፅ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። +25 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ የተናገራችሁትን በእጃችሁ ፈጽማችሁታል፤ እንዲህ ብላችኋልና፦ “‘ለሰማይ ንግሥት’* መሥዋዕት ለማቅረብና ለእሷ የመጠጥ መባ ለማፍሰስ የተሳልነውን ስእለት በእርግጥ እንፈጽማለን።”+ እናንተ ሴቶች የገባችሁትን ስእለት +26 “ስለዚህ በግብፅ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ‘“እነሆ፣ በገዛ ራሴ ታላቅ ስም እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “በመላው የግብፅ ምድር፣ የትኛውም የይሁዳ ሰው ‘ሕያው በሆነው በሉዓላዊው ጌታ በይሖዋ እምላለሁ’+ በማለት ከእንግዲህ ስሜን በመሐላ አይጠራም።+ +27 መልካም ነገር ሳይሆን ጥፋት ለማምጣት እከታተላቸዋለሁ፤+ በግብፅ ምድር የሚኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በረሃብ ያልቃሉ።+ +28 ጥቂት ሰዎች ብቻ ከሰይፍ አምልጠው ከግብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ።+ ከዚያም በግብፅ ምድር ለመኖር ወደዚያ የመጡት የይሁዳ ቀሪዎች ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነሱ፣ የማን ቃል እንደተፈጸመ ያውቃሉ!”’” +29 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣት የተናገርኩት ቃል መፈጸሙ እንደማይቀር ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሆናችኋል። +30 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነውና ሕይወቱን ሊያጠፋ ይፈልግ* ለነበረው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* አሳልፌ እንደሰጠሁ ሁሉ የግብፁን ንጉሥ፣ ፈርዖን ሆፍራንም ለጠላቶቹና ሕይወቱን ለማጥፋት ለሚፈልጉት* ሰዎች አሳልፌ እሰጣለሁ።”’”+ +4 “እስራኤል ሆይ፣ ብትመለስ” ይላል ይሖዋ፣“ወደ እኔ ብትመለስ፣አስጸያፊ ጣዖቶችህን ከፊቴ ብታስወግድተንከራታች አትሆንም።+ + 2 ‘በእውነት፣ በፍትሕና በጽድቅሕያው ይሖዋን!’ ብለህ ብትምል፣ብሔራት በእሱ አማካኝነት በረከት ያገኛሉ፤በእሱም ይኮራሉ።”+ +3 ይሖዋ ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይላልና፦ “ያልለማውን መሬት እረሱ፤በእሾህ መካከልም አትዝሩ።+ + 4 እናንተ የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣ለይሖዋ ተገረዙ፤የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤+አለዚያ በክፉ ሥራችሁ የተነሳቁጣዬ እንደ እሳት ይነድዳል፤ማንም ሊያጠፋው አይችልም።”+ + 5 ይህን በይሁዳ ተናገሩ፤ በኢየሩሳሌምም አውጁ። ጩኹ፤ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ቀንደ መለከት ንፉ።+ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ እንዲህ በሉ፦ “አንድ ላይ ተሰብሰቡ፤ወደተመሸጉት ከተሞችም እንሽሽ።+ + 6 ወደ ጽዮን የሚጠቁም ምልክት* አቁሙ። መጠለያ ፈልጉ፤ ዝም ብላችሁም አትቁሙ።” ከሰሜን ጥፋት ብሎም ታላቅ መዓት አመጣለሁና።+ + 7 ጠላት እንደ አንበሳ ከጥሻው ውስጥ ወጥቷል፤+ብሔራትንም የሚያጠፋው ተነስቷል።+ ምድርሽን አስፈሪ ቦታ ሊያደርግ ከቦታው ወጥቷል። ከተሞችሽ አንድም ሰው የማይኖርባቸው የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ።+ + 8 ስለዚህ ማቅ ልበሱ፤+እዘኑ፤* ዋይ ዋይም በሉ፤ምክንያቱም የሚነደው የይሖዋ ቁጣ ከእኛ አልተመለሰም። + 9 “በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣ “የንጉሡ ልብናየመኳንንቱ ልብ ይቀልጣል፤*+ካህናቱም ይሸበራሉ፤ ነቢያቱም ይገረማሉ።”+ +10 ከዚያም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! ሰይፍ አንገታችን ላይ ተጋድሞ* እያለ ‘ሰላም ታገኛላችሁ’+ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን ፈጽሞ አታለሃል።”+ +11 በዚያን ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይባላል፦ “የሚለበልብ ነፋስ በበረሃ ከሚገኙ ጠፍ ኮረብቶች ተነስቶወደ ሕዝቤ ሴት ልጅ* በፍጥነት ይነፍሳል፤ነፋሱ የሚነፍሰው እህል ለማዝራትም* ሆነ ለማጥራት አይደለም። +12 በእኔ ትእዛዝ ኃይለኛው ነፋስ ከእነዚህ ስፍራዎች ይመጣል። አሁን በእነሱ ላይ ፍርድ አስተላልፋለሁ። +13 እነሆ፣ እሱ ዝናብ እንዳዘሉ ደመናት ይመጣል፤ሠረገሎቹም እንደ አውሎ ነፋስ ናቸው።+ ፈረሶቹ ከንስር ይበልጥ ፈጣኖች ናቸው።+ ጠፍተናልና ወዮልን! +14 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ እንድትድኚ ልብሽን ከክፋት ሁሉ አጥሪ።+ እስከ መቼ በውስጥሽ ክፉ ሐሳብ ይዘሽ ትኖሪያለሽ? +15 አንድ ድምፅ ከዳን ዜናውን ይናገራልና፤+ከኤፍሬም ተራሮችም ጥፋትን ያውጃል። +16 ይህን አሳውቁ፤ አዎ ለብሔራት ተናገሩ፤በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ።” “ጠባቂዎች* ከሩቅ አገር እየመጡ ነው፤በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይጮኻሉ። +17 ማሳ እንደሚጠብቁ ሰዎች ከሁሉም አቅጣጫ ይመጡባታል፤+ምክንያቱም እሷ በእኔ ላይ ዓምፃለች”+ ይላል ይሖዋ። +18 “ለተከተልሽው መንገድና ለፈጸምሽው ተግባር ዋጋሽን ትቀበያለሽ።+ የሚደርስብሽ ጥፋት ምንኛ መራራ ነው፤ወደ ልብሽ ዘልቆ ይገባልና!” +19 ወይ አበሳዬ!* ወይ አበሳዬ! ልቤን ሥቃይ ቀስፎታል። ልቤ በውስጤ በኃይል ይመታል። ዝም ማለት አልችልም፤የቀንደ መለከት ድምፅ፣የጦርነት ማስጠንቀቂያ ድምፅ* ሰምቻለሁና።*+ +20 በጥፋት ላይ ጥፋት መድረሱ ተወርቷል፤ምድሪቱ በሙሉ ወድማለችና። የገዛ ድንኳኖቼ በድንገት፣የድንኳን ሸራዎቼም በቅጽበት ጠፍተዋል።+ +21 ምልክቱን* የማየውናየቀንደ መለከቱን ድምፅ የምሰማው እስከ መቼ ድረስ ነው?+ +22 “ሕዝቤ ሞኝ ነውና፤+እነሱ ለእኔ ትኩረት አይሰጡም። ማስተዋል የሌላቸው ቂል ልጆች ናቸው። ክፉ ነገር ለማድረግ ብልሃተኞች* ናቸው፤መልካም ነገር ማድረግ ግን አያውቁም።” +23 ምድሪቱን አየሁ፤ እነሆም፣ ባዶና ወና ነበረች።+ ወደ ሰማያት ተመለከትኩ፤ ብርሃናቸው ጠፍቶ ነበር።+ +24 ተራሮቹን አየሁ፤ እነሆ፣ ይናወጡ ነበር፤ኮረብቶቹም ይንቀጠቀጡ ነበር።+ +25 እኔም ተመለከትኩ፤ እነሆ፣ በዚያ አንድም ሰው አልነበረም፤የሰማይ ወፎችም ሁሉ ሸሽተው ነበር።+ +26 እኔም አየሁ፤ እነሆ፣ የፍራፍሬ እርሻው ምድረ በዳ ሆኖ ነበር፤ከተሞቹም ሁሉ ፈራርሰው ነበር።+ ይህም የሆነው በይሖዋ፣በሚነደውም ቁጣው የተነሳ ነው። +27 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ምድሪቱ በሙሉ ባድማ ትሆናለች፤+ሆኖም ፈጽሜ አላጠፋትም። +28 ከዚህ የተነሳ ምድሪቱ ታዝናለች፤+በላይ ያሉት ሰማያትም ይጨልማሉ።+ ምክንያቱም እኔ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም ወስኛለሁ፤ሐሳቤንም አለውጥም፤* ወደ ኋላም አልመለስም።+ +29 ከፈረሰኞቹና ከቀስተኞቹ ድምፅ የተነሳከተማዋ በሙሉ ትሸሻለች።+ ጥሻ ውስጥ ይገባሉ፤ዓለቶቹም ላይ ይወጣሉ።+ ከተሞቹ ሁሉ ተትተዋል፤የሚኖርባቸውም ሰው የለም።” +30 ለጥፋት ተዳርገሻል፤ ታዲያ ምን ታደርጊ ይሆን? ደማቅ ቀይ ልብስ ትጎናጸፊ፣በወርቅ ጌጣጌጦች ታጌጪናዓይኖችሽን ትኳዪ ነበር። ይሁንና ትዋቢ የነበረው እንዲያው በከንቱ ነው፤+በፍትወት ስሜት ይከተሉሽ የነበሩት ትተውሻልና፤አሁን ሕይወትሽን* ይሿታል።+ +31 እንደታመመች ሴት ድምፅ፣የመጀመሪያ ልጇንም ለመውለድ እንደምታምጥ ሴት ያለ የጭንቅ ድምፅ፣ደግሞም ትንፋሽ አጥሯት ቁና ቁና የምትተነፍሰውን የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ ሰምቻለሁና። እሷም እጆቿን ዘርግታ+ “ወዮልኝ! ከገዳዮች የተነሳ ዝያለሁና”* ትላለች። +41 በሰባተኛው ወር፣ ከንጉሣውያን ቤተሰብ* የሆነውና ከንጉሡ ባለሥልጣናት አንዱ የነበረው የኤሊሻማ ልጅ፣ የነታንያህ ልጅ እስማኤል+ ከሌሎች አሥር ሰዎች ጋር ሆኖ በምጽጳ+ ወዳለው ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ። በምጽጳ አንድ ላይ ምግብ እየበሉ ሳለ +2 የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት አሥሩ ሰዎች ተነስተው የሳፋንን ልጅ፣ የአኪቃምን ���ጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መተው ገደሉት። በዚህ መንገድ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ የሾመውን ሰው ገደለው። +3 በተጨማሪም እስማኤል በምጽጳ ከጎዶልያስ ጋር የነበሩትን አይሁዳውያን በሙሉ እንዲሁም በዚያ የነበሩትን ከለዳውያን ወታደሮች ገደላቸው። +4 ጎዶልያስ በተገደለ በሁለተኛው ቀን ስለ ሁኔታው ማንም ሰው ከማወቁ በፊት፣ +5 ከሴኬም፣+ ከሴሎና+ ከሰማርያ+ 80 ሰዎች መጡ። ጢማቸውን ላጭተው፣ ልብሳቸውን ቀደውና ሰውነታቸውን ተልትለው+ የነበረ ሲሆን በይሖዋ ቤት የሚያቀርቧቸውን የእህል መባዎችና ነጭ ዕጣን+ ይዘው ነበር። +6 የነታንያህ ልጅ እስማኤልም ከእነሱ ጋር ለመገናኘት ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሄደ። ባገኛቸው ጊዜ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ” አላቸው። +7 ሆኖም ወደ ከተማዋ ሲገቡ የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች አረዷቸው፤ ወደ ውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድም ጣሏቸው። +8 ይሁንና በመካከላቸው የነበሩ አሥር ሰዎች እስማኤልን “በእርሻ ውስጥ የደበቅነው የተከማቸ እህል ይኸውም ስንዴ፣ ገብስ፣ ዘይትና ማር ስላለን አትግደለን” አሉት። ስለዚህ ከወንድሞቻቸው ጋር አልገደላቸውም። +9 እስማኤል የገደላቸውን ሰዎች አስከሬን በሙሉ በአንድ ትልቅ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጣለ፤ ይህ ጉድጓድ ንጉሥ አሳ የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ባስፈራራው ጊዜ የሠራው ነበር።+ የነታንያህ ልጅ እስማኤል ይህን ጉድጓድ ባረዳቸው ሰዎች አስከሬን ሞላው። +10 እስማኤል በምጽጳ+ የቀረውን ሕዝብ በሙሉ ይኸውም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን+ በላያቸው ገዢ አድርጎ የሾመባቸውን፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና በምጽጳ የቀሩትን ሰዎች ሁሉ ማረከ። የነታንያህ ልጅ እስማኤል እነሱን ማርኮ ወደ አሞናውያን ለመሻገር ጉዞ ጀመረ።+ +11 የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን+ እና ከእሱ ጋር የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች የነታንያህ ልጅ እስማኤል ስላደረገው ክፉ ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ +12 ከእነሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች በሙሉ ይዘው ከነታንያህ ልጅ ከእስማኤል ጋር ለመዋጋት ሄዱ፤ እሱንም በገባኦን ባለው በታላቁ ውኃ* አጠገብ አገኙት። +13 ከእስማኤል ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን እና ከእሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ ባዩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው። +14 ከዚያም እስማኤል ከምጽጳ+ ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ሁሉ ዞረው ከቃሬሃ ልጅ ከዮሃናን ጋር ተመለሱ። +15 የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት ስምንት ሰዎች ግን ከዮሃናን ፊት ሸሽተው ወደ አሞናውያን ሄዱ። +16 የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና ከእሱ ጋር የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ ከምጽጳ የተወሰዱትን የቀሩትን ሰዎች ይዘዋቸው ሄዱ፤ እነዚህ ሰዎች የነታንያህ ልጅ እስማኤል፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለው በኋላ+ ዮሃናን እና የሠራዊቱ አለቆች ከእሱ የታደጓቸው ናቸው። ወንዶቹን፣ ወታደሮቹን፣ ሴቶቹንና ልጆቹን +17 ከዚያም ተነስተው ሄዱ፤ ወደ ግብፅ ለመሄድ+ ስላሰቡም በቤተልሔም+ አጠገብ በሚገኘው በኪምሃም ማረፊያ ቦታ ቆዩ፤ +18 ይህን ያደረጉት ከከለዳውያን የተነሳ ነው። የነታንያህ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ ሾሞት የነበረውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋቸው ነበር።+ +46 ብሔራትን አስመልክቶ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+ +2 የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአራተኛው ዓመት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውንና የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* በካርከሚሽ ድል ያደረገውን የግብፅን ንጉሥ የፈርዖን ኒካዑን+ ሠራዊት በተመለከተ ለግብፅ+ የተነገረ መልእ��ት፦ + 3 “ትንሹንና* ትልቁን ጋሻችሁን አዘጋጁ፤ለውጊያም ውጡ። + 4 እናንተ ፈረሰኞች፣ ፈረሶችን ጫኑ፤ በላያቸውም ተቀመጡ። ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ የራስ ቁራችሁንም አድርጉ። ጦሩን ወልውሉ፤ ጥሩራችሁንም ልበሱ። + 5 ‘እንዲህ ተሸብረው ያየኋቸው ለምንድን ነው? እያፈገፈጉ ነው፤ ተዋጊዎቻቸው ተፍረክርከዋል። በድንጋጤ እግሬ አውጪኝ ብለዋል፤ ተዋጊዎቻቸው ወደ ኋላ አልተመለከቱም። በየቦታው ሽብር ነግሦአል’ ይላል ይሖዋ። + 6 ‘ፈጣን የሆኑት መሸሽ አይችሉም፤ ተዋጊዎቹም ማምለጥ አይችሉም። በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ ዳርቻተሰናክለው ወድቀዋል።’+ + 7 እንደ አባይ ወንዝ፣እንደሚናወጥም የወንዝ ውኃ ሆኖ የሚመጣው ይህ ማን ነው? + 8 ግብፅ እንደ አባይ ወንዝና+እንደሚናወጥ የወንዝ ውኃ ሆኖ ይመጣል፤ደግሞም ‘እወጣለሁ፤ ምድርንም እሸፍናለሁ። ከተማዋንና ነዋሪዎቿን አጠፋለሁ’ ይላል። + 9 እናንተ ፈረሶች፣ ወደ ላይ ውጡ! እናንተ ሠረገሎች፣ በፍጥነት ገስግሱ! ተዋጊዎቹ ይውጡ፤ጋሻ የሚያነግቡት የኢትዮጵያ* እና የፑጥ ሰዎች+እንዲሁም ደጋን የመወጠርና*+ በጥበብ የመጠቀም ችሎታ ያላቸው የሉድ+ ሰዎች ይውጡ። +10 “ያ ቀን የሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው። ሰይፉ ይበላል፤ ይጠግባልም፤ ደማቸውንም እስኪረካ ድረስ ይጠጣል፤ ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ በኤፍራጥስ ወንዝ+ አጠገብ በሚገኘው የሰሜን ምድር መሥዋዕት* አዘጋጅቷልና። +11 ድንግሊቱ የግብፅ ሴት ልጅ ሆይ፣ወደ ጊልያድ ወጥተሽ በለሳን አምጪ።+ መድኃኒት የምታበዢው እንዲያው በከንቱ ነው፤ፈውስ አታገኚምና።+ +12 ብሔራት በአንቺ ላይ የደረሰውን ውርደት ሰምተዋል፤+ጩኸትሽም አገር ምድሩን አናውጧል። ተዋጊ በተዋጊው ይሰናከላልና፤ሁለቱም በአንድነት ተያይዘው ወድቀዋል።” +13 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የግብፅን ምድር ለመምታት ስለመምጣቱ ይሖዋ ለነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦+ +14 “ይህን በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶል+ አውጁት። በኖፍ* እና በጣፍነስ+ አውጁት። እንዲህም በሉ፦ ‘ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ተዘጋጁም፤ሰይፍ በዙሪያችሁ ያለውን ሁሉ ይበላልና። +15 ኃያላኖቻችሁ ተጠራርገው የጠፉት ለምንድን ነው? ጸንተው መቆም አልቻሉም፤ይሖዋ ገፍትሮ ጥሏቸዋልና። +16 ብዙዎቹ ይሰናከላሉ፤ ደግሞም ይወድቃሉ። እርስ በርሳቸውም “ተነሱ! ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ” ይባባላሉ።’ +17 በዚያም ‘ያገኘውን አጋጣሚ* ያልተጠቀመበትየግብፅ ንጉሥ ፈርዖንጉራውን የሚነዛው በከንቱ ነው’ ብለዋል።+ +18 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ተብሎ የተጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤እሱ* በተራሮች መካከል እንዳለው እንደ ታቦርና+በባሕር አጠገብ እንዳለው እንደ ቀርሜሎስ+ ሆኖ ይመጣል። +19 አንቺ በግብፅ የምትኖሪ ሴት ልጅ ሆይ፣በግዞት ለመሄድ ጓዝሽን አሰናጂ። ኖፍ* አስፈሪ ቦታ ትሆናለችና፤በእሳት ትጋያለች፤* ማንም ሰው የማይኖርባትም ምድር ትሆናለች።+ +20 ግብፅ እንደምታምር ጊደር ናት፤ሆኖም ከሰሜን ተናዳፊ ዝንቦች ይመጡባታል። +21 በመካከሏ ያሉት ቅጥረኛ ወታደሮችም እንኳ እንደሰቡ ጥጆች ናቸው፤ይሁንና እነሱም ጭምር ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ሸሽተዋል። ጸንተው መቆም አልቻሉም፤+የሚጠፉበት ቀን፣የሚመረመሩበትም ጊዜ ደርሶባቸዋልና።’ +22 ‘ድምፅዋ እየተጥመዘመዘ እንደሚሄድ እባብ ድምፅ ነው፤ዛፍ እንደሚቆርጡ* ሰዎችመጥረቢያ ይዘው በኃይል ይመጡባታልና። +23 በውስጡ ማለፍ የማይቻል ቢመስልም ጫካዋን ይመነጥራሉ’ ይላል ይሖዋ። ‘ቁጥራቸው ከአንበጣ ይበልጥ ይበዛልና፤ ስፍር ቁጥርም የላቸውም። +24 የግብፅ ሴት ልጅ ለኀፍረት ትዳረጋለች። ለሰሜን ሰዎች ትሰጣለች።’+ +25 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አሁን ትኩረቴን በኖእ*+ ከተማ ወደሚገኘው ወደ አምዖን፣+ ወደ ፈርዖን፣ ወደ ግብፅ፣ ወደ አማልክቷና+ ወደ ነገሥታቷ፣ አዎ በፈርዖንና በእሱ ወደሚታመኑት ሰዎች ሁሉ አደርጋለሁ።’+ +26 “‘ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ* ሰዎች፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾርና* ለአገልጋዮቹ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ ከዚያ በኋላ ግን እንደቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች’ ይላል ይሖዋ።+ +27 ‘አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፤እስራኤልም ሆይ፣ አትሸበር።+ አንተን ከሩቅ ቦታ፣ዘሮችህንም ተማርከው ከተወሰዱበት ምድር አድናለሁና።+ ያዕቆብ ይመለሳል፤ የሚያስፈራውም ሳይኖርተረጋግቶና ሰላም አግኝቶ ይቀመጣል።+ +28 ስለዚህ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እኔ ከአንተ ጋር ነኝና። አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤+አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም።+ በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ* እንጂ+በምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።’” +37 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የኢዮስያስን ልጅ ንጉሥ ሴዴቅያስን+ በይሁዳ ምድር ስላነገሠው በኢዮአቄም ልጅ በኮንያሁ*+ ፋንታ መግዛት ጀመረ።+ +2 ይሁንና እሱም ሆነ አገልጋዮቹ እንዲሁም የምድሪቱ ሕዝብ ይሖዋ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል የተናገረውን ቃል አልሰሙም። +3 ንጉሥ ሴዴቅያስም የሸሌምያህን ልጅ የሁካልንና+ የካህኑን የማአሴያህን ልጅ ሶፎንያስን+ “እባክህ፣ ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ጸልይ” ብለው እንዲነግሩት ወደ ነቢዩ ኤርምያስ ላካቸው። +4 በዚያ ወቅት ኤርምያስ ገና እስር ቤት ስላላስገቡት በሕዝቡ መካከል በነፃነት ይገባና ይወጣ ነበር።+ +5 በዚህ ጊዜ የፈርዖን ሠራዊት ከግብፅ ወጥቶ ነበር፤+ ኢየሩሳሌምን ከበው የነበሩት ከለዳውያንም ይህን ሰሙ። በመሆኑም ኢየሩሳሌምን ለቀው ሄዱ።+ +6 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ነቢዩ ኤርምያስ መጣ፦ +7 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔን እንድትጠይቁ ወደ እኔ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ “እነሆ፣ እናንተን ለመርዳት የመጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብፅ ይመለሳል።+ +8 ከለዳውያኑም ተመልሰው መጥተው ይህችን ከተማ ይወጓታል፤ ይይዟታልም፤ በእሳትም ያቃጥሏታል።”+ +9 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ከለዳውያን ያላንዳች ጥርጥር ትተውን ይሄዳሉ’ እያላችሁ ራሳችሁን አታታሉ፤* ምክንያቱም ትተዋችሁ አይሄዱም። +10 እናንተን የሚወጋችሁን መላውን የከለዳውያን ሠራዊት ብትመቱና ቁስለኞቻቸው ብቻ ቢቀሩ እንኳ ከድንኳናቸው ተነስተው ይህችን ከተማ በእሳት ያቃጥሏታል።”’”+ +11 የከለዳውያን ሠራዊት ከፈርዖን ሠራዊት የተነሳ ኢየሩሳሌምን ትቶ በተመለሰ ጊዜ፣+ +12 ኤርምያስ ወደ ቢንያም አገር+ ሄዶ በሕዝቡ መካከል ድርሻውን ለመውሰድ ከኢየሩሳሌም ተነሳ። +13 ይሁንና ወደ ቢንያም በር በደረሰ ጊዜ የሃናንያህ ልጅ፣ የሸሌምያህ ልጅ ይሪያህ የተባለ የጠባቂዎች አለቃ ነቢዩ ኤርምያስን ይዞ “ከድተህ ወደ ከለዳውያን ልትሄድ ነው!” አለው። +14 ኤርምያስ ግን “በፍጹም! ከድቼ ወደ ከለዳውያን ልሄድ አይደለም” አለ። እሱ ግን አልሰማውም። በመሆኑም ይሪያህ ኤርምያስን ይዞ ወደ መኳንንቱ ወሰደው። +15 መኳንንቱ ኤርምያስን እጅግ ተቆጥተው+ መቱት፤ ከዚያም በወቅቱ እስር ቤት አድርገውት በነበረው በጸሐፊው በየሆናታን ቤት አሰሩት።*+ +16 ኤርምያስ በምድር ቤት* ውስጥ ወደሚገኝ የእስረኞች ክፍል እንዲገባ ተደረገ፤ በዚያም ለብዙ ቀናት ቆየ። +17 ከዚያም ንጉሥ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፤ ንጉሡም በቤቱ* ውስጥ በሚስጥር ጠየቀው።+ “ከይሖዋ የመጣ ቃል አለ?” አለው። ኤርምያስም “አዎ፣ አለ!” ሲል መለሰለት፤ አክሎም “በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ!” አለው።+ +18 በተጨማሪም ኤርምያስ ንጉሥ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “እስር ቤት ያስገባችሁኝ በአንተ፣ በአገልጋዮችህና በዚህ ሕዝብ ላይ ምን የሠራሁት በደል ቢኖር ነው? +19 ‘የባቢሎን ንጉሥ እናንተንና ይህችን ምድር ለመውጋት አይመጣም’ ብለው የተነበዩላችሁ ነቢያታችሁ አሁን የት አሉ?+ +20 አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እባክህ ስማኝ። በፊትህ ሞገስ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና እባክህ ተቀበል። ወደ ጸሐፊው ወደ የሆናታን ቤት+ መልሰህ አትላከኝ፤ ካልሆነ ግን በዚያ እሞታለሁ።”+ +21 በመሆኑም ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ እንዲታሰር አዘዘ፤ ዳቦ ከከተማዋ እስኪጠፋ ድረስም+ ከዳቦ ጋጋሪዎች ጎዳና በየዕለቱ አንድ አንድ ዳቦ ይሰጠው ነበር።+ ኤርምያስም በክብር ዘቦቹ ግቢ ተቀመጠ። +40 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ ኤርምያስን ከራማ+ በነፃ ከለቀቀው በኋላ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው። ናቡዛራዳን ኤርምያስን ወደዚያ ሲወስደው እጆቹ በሰንሰለት ታስረው ነበር፤ ደግሞም ወደ ባቢሎን በግዞት እየተወሰዱ ከነበሩት የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ግዞተኞች ሁሉ መካከል ነበር። +2 ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ኤርምያስን ወስዶ እንዲህ አለው፦ “አምላክህ ይሖዋ በዚህ ስፍራ ላይ ይህ ጥፋት እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል፤ +3 በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁና ቃሉን ስላልታዘዛችሁ ይሖዋ በተናገረው መሠረት ይህን ጥፋት አመጣ። ይህ ነገር በእናንተ ላይ የደረሰው ለዚህ ነው።+ +4 እጆችህ የታሰሩበትን ሰንሰለት ዛሬ እፈታልሃለሁ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መሄድ መልካም መስሎ ከታየህ መሄድ ትችላለህ፤ እኔም እንከባከብሃለሁ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መሄድ ካልፈለግክ ግን መቅረት ትችላለህ። እነሆ፣ ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት። ወደመረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።”+ +5 ኤርምያስ ከመመለሱ በፊት ናቡዛራዳን እንዲህ አለው፦ “የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን+ ልጅ፣ ወደ አኪቃም+ ልጅ ወደ ጎዶልያስ+ ተመለስ፤ በሕዝቡም መካከል ከእሱ ጋር ተቀመጥ፤ ወይም ደግሞ ወደመረጥከው ቦታ ሂድ።” ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው። +6 በመሆኑም ኤርምያስ በምጽጳ+ ወደሚገኘው ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ሄዶ በምድሪቱ በቀሩት ሕዝብ መካከል ከእሱ ጋር መኖር ጀመረ። +7 በኋላም ከሰዎቻቸው ጋር በየቦታው የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ እንደሾመው እንዲሁም ወደ ባቢሎን በግዞት ባልተወሰዱትና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት ድሆች የሆኑ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ እንደሾመው ሰሙ።+ +8 ስለሆነም በምጽጳ+ ወደሚገኘው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም የነታንያህ ልጅ እስማኤል፣+ የቃሬሃ ልጆች የሆኑት ዮሃናን+ እና ዮናታን፣ የታንሁመት ልጅ ሰራያህ፣ የነጦፋዊው የኤፋይ ልጆችና የማአካታዊው ልጅ የዛንያህ+ እንዲሁም አብረዋቸው የነበሩት ሰዎች ናቸው። +9 የሳፋን ልጅ፣ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነሱና አብረዋቸው ለነበሩት ሰዎች እንዲህ ብሎ ማለላቸው፦ “ከለዳውያንን ማገልገል አያስፈራችሁ። በምድሪቱ ላይ ኑሩ፤ የባቢሎንንም ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካምም ይሆንላችኋል።+ +10 እኔም ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እናንተን ወክዬ ለመቅረብ* በምጽጳ እቀመጣለሁ። እናንተ ግን ወይን፣ የበጋ ፍሬዎችና* ዘይት አከማቹ፤ በማጠራቀሚያ ዕቃዎቻችሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸው ከተሞችም ውስጥ ኑሩ።”+ +11 በሞዓብ፣ በአሞንና በኤዶም እንዲሁም በሌሎች አገሮች ሁሉ የነበሩት አይሁዳውያንም በሙሉ የባቢሎን ንጉሥ የተወሰኑ ቀሪዎች በይሁዳ ምድር እንዲኖሩ እንደፈቀደላቸውና የሳፋንን ልጅ፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በእነሱ ላይ እንደሾመ ሰሙ። +12 በመሆኑም አይሁዳውያኑ በሙሉ ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ ይመለሱ ጀመር፤ በይሁዳ ምድር በምጽጳ ወዳለው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም ወይንና የበጋ ፍሬዎችን በብዛት አከማቹ። +13 የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና በየቦታው የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ በምጽጳ ወዳለው ወደ ጎዶልያስ መጡ። +14 እንዲህም አሉት፦ “የአሞናውያን+ ንጉሥ ባአሊስ አንተን ለመግደል* የነታንያህን ልጅ እስማኤልን እንደላከው አታውቅም?”+ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም። +15 ከዚያም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ ጎዶልያስን በምጽጳ በሚስጥር እንዲህ አለው፦ “ሄጄ የነታንያህን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ማንም አያውቅም። ለምን ይግደልህ?* ወደ አንተ የተሰበሰቡት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ለምን ይበተኑ? የይሁዳ ቀሪዎችስ ለምን ይጥፉ?” +16 የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ+ ግን የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን “ስለ እስማኤል የምትነግረኝ ነገር እውነት ስላልሆነ እንዲህ አታድርግ” አለው። +16 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አትውለድ። +3 ይሖዋ በዚህ ስለሚወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲሁም በዚህች ምድር ስለሚወልዷቸው እናቶችና አባቶች እንዲህ ይላልና፦ +4 ‘በገዳይ በሽታዎች ይሞታሉ፤+ ይሁንና ማንም አያለቅስላቸውም ወይም አይቀብራቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።+ በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ፤+ አስከሬናቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።’ + 5 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦‘ለለቀስተኞች ድግስ ወደተዘጋጀበት ቤት አትግባ፤እዚያም ሄደህ አታልቅስ ወይም አታስተዛዝን።’+ ‘ሰላሜን ከዚህ ሕዝብ ወስጄአለሁና’ ይላል ይሖዋ፤‘ታማኝ ፍቅሬና ምሕረቴ ከእነሱ እንዲርቅ አድርጌአለሁ።+ + 6 ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች በዚህች ምድር ላይ ይሞታሉ። ደግሞም አይቀበሩም፤ማንም ሰው አያዝንላቸውም፤ለእነሱ ሲል ሰውነቱን የሚተለትልም ሆነ ራሱን የሚላጭ አይኖርም።* + 7 ሰው የሞተባቸውንም ለማጽናናትየእዝን እንጀራ የሚወስድላቸው አይኖርም፤አባት ወይም እናት ለሞተባቸውምየመጽናኛ ጽዋ እንዲጠጡ የሚሰጣቸው አይኖርም። + 8 ከእነሱ ጋር ተቀምጠህ ለመብላትና ለመጠጣትግብዣ ወደተዘጋጀበት ቤት አትግባ።’ +9 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህ ስፍራ፣ በእናንተ ዘመን ዓይናችሁ እያየ የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ አስወግዳለሁ።’+ +10 “ይህን ሁሉ ቃል ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ እንዲህ ብለው ይጠይቁሃል፦ ‘ይሖዋ ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ የተናገረው ለምንድን ነው? በአምላካችን በይሖዋ ላይ የፈጸምነው በደልና ኃጢአት ምንድን ነው?’+ +11 አንተም እንዲህ ብለህ ትመልስላቸዋለህ፦ ‘“አባቶቻችሁ እኔን ስለተዉ ነው”+ ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ስላገለገሉ እንዲሁም ስለሰገዱላቸው ነው።+ እኔን ግን ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም።+ +12 እናንተ ደግሞ አባቶቻችሁ ከፈጸሙት የባሰ ነገር አድርጋችኋል፤+ እያንዳንዳችሁም እኔን ከመታዘዝ ይልቅ ግትር የሆነውን ክፉ ልባችሁን ተከተላችሁ።+ +13 ስለዚህ ከዚህች ምድር አስወጥቼ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቁት ምድር እጥላችኋለሁ፤+ በዚያም ሌሎች አማልክትን ቀን ከሌት ታገለግላላችሁ፤+ ምክንያቱም እኔ ምንም ምሕረት አላሳያችሁም።”’ +14 “‘ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ “የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ባወጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” የማይሉበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤+ +15 ‘ከዚህ ይልቅ “እስራኤላውያንን ከሰሜን ምድርና እነሱን ከበተነባቸው አገሮች ሁሉ ሰብስቦ ባመጣቸው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ” ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት፣ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።’+ +16 ‘እነሆ፣ እኔ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰዳለሁ’ ይላል ይሖዋ፤‘እነሱንም ያጠምዷቸዋል። ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰዳለሁ፤እነሱም ከየተራራው፣ ከየኮረብታውናከየቋጥኙ ስንጣቂ አድነው ይይዟቸዋል። +17 ዓይኖቼ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ* ላይ ነውና። ከፊቴ አልተሸሸጉም፤በደላቸውም ከዓይኔ አልተሰወረም። +18 በመጀመሪያ፣ ለሠሩት በደልና ኃጢአት የሚገባቸውን ሙሉ ዋጋ እከፍላቸዋለሁ፤+ምድሬን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው በድን ምስሎች* አርክሰዋልና፤ርስቴንም አስነዋሪ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋል።’”+ +19 ብርታቴና መጠጊያዬ፣በጭንቀት ጊዜ መሸሸጊያዬ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+ብሔራት ከምድር ዳርቻዎች ወደ አንተ ይመጣሉ፤እንዲህም ይላሉ፦ “አባቶቻችን ፍጹም ውሸትን፣ከንቱ የሆኑና ምንም ጥቅም የሌላቸውን የማይረቡ ነገሮች ወርሰዋል።”+ +20 ሰው ለራሱ አማልክት ሊሠራ ይችላል?የሚሠራቸው አማልክት እውነተኛ አማልክት አይደሉም።+ +21 “ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤በዚህ ጊዜ ኃይሌንና ብርታቴን እንዲያውቁ አደርጋለሁ፤እነሱም ስሜ ይሖዋ መሆኑን ያውቃሉ።” +51 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በባቢሎንና+ በሌብቃማይ* ነዋሪዎች ላይአጥፊ ነፋስ አስነሳለሁ። + 2 እህል የሚያዘሩ* ሰዎችን ወደ ባቢሎን እሰዳለሁ፤እነሱም ያዘሯታል፤ ምድሯንም ባዶ ያደርጋሉ፤በጥፋት ቀን ከሁሉም አቅጣጫ ይመጡባታል።+ + 3 ቀስተኛው ደጋኑን አይወጥር።* በተጨማሪም ማንም ሰው ጥሩሩን ለብሶ አይነሳ። ለወጣቶቿ ምንም ዓይነት ርኅራኄ አታሳዩ።+ ሠራዊቷን ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ። + 4 እነሱም በከለዳውያን ምድር ታርደው፣በጎዳናዎቿም ላይ ክፉኛ ቆስለው ይወድቃሉ።+ + 5 እስራኤልና ይሁዳ ከአምላካቸው፣ ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ተለይተው መበለት አልሆኑም።+ ምድራቸው* ግን በእስራኤል ቅዱስ ፊት በበደል ተሞልታለች። + 6 ከባቢሎን መካከል ሸሽታችሁ ውጡ፤ሕይወታችሁን* አድኑ።+ በእሷ በደል የተነሳ አትጥፉ። ይህ የይሖዋ የበቀል ጊዜ ነውና። ላደረገችው ነገር የእጇን ይከፍላታል።+ + 7 ባቢሎን በይሖዋ እጅ ያለች የወርቅ ጽዋ ነበረች፤ምድርን ሁሉ አሰከረች። ብሔራት ወይን ጠጇን ጠጥተው ሰከሩ፤+ብሔራት ያበዱት ለዚህ ነው።+ + 8 ባቢሎን በድንገት ወድቃ ተሰበረች።+ ዋይ ዋይ በሉላት!+ ለሕመሟ የሚሆን በለሳን ውሰዱላት፤ ምናልባት ትፈወስ ይሆናል።” + 9 “ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክረን ነበር፤ እሷ ግን ልትፈወስ አልቻለችም። ትታችኋት ሂዱ፤ እያንዳንዳችንም ወደ ገዛ ምድራችን እንሂድ።+ ፍርዷ እስከ ሰማያት ደርሷልና፤እስከ ደመናት ድረስ ከፍ ብሏል።+ +10 ይሖዋ ፍትሕ አስፍኖልናል።+ ኑ፣ የአምላካችንን የይሖዋን ሥራ በጽዮን እንናገር።”+ +11 “ፍላጻዎቻችሁን አሹሉ፤+ ክብ የሆኑትን ጋሻዎች አንሱ።* ይሖዋ የሜዶናውያንን ነገሥታት መንፈስ አነሳስቷል፤+ምክንያቱም ባቢሎንን ለማጥፋት አስቧል። ይህ የይሖዋ በቀል ይኸውም ስለ ቤተ መቅደሱ የሚወስደው የበቀል እርምጃ ነውና። +12 የባቢሎንን ቅጥሮች ለማጥቃት ምልክት* አቁሙ።+ ጥበቃውን አጠናክሩ፤ ጠባቂዎችን አቁሙ። ሽምቅ ተዋጊዎችን አዘጋጁ። ይሖዋ በባቢሎን ነዋሪዎች ላይ የጦር ስልት ነድፏልና፤በእነሱ ላይ የተናገረውንም ቃል ይፈጽ��ል።”+ +13 “አንቺ በብዙ ውኃዎች ላይ የምትኖሪ፣+በሀብትም የበለጸግሽ ሆይ፣+መጨረሻሽ ቀርቧል፤ አላግባብ የምታገኚው ትርፍ ገደቡ ላይ ደርሷል።+ +14 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ሲል በራሱ* ምሏል፦‘እንደ አንበጣ ብዛት ባላቸው ሰዎች እሞላሻለሁ፤እነሱም በአንቺ ላይ በድል አድራጊነት ይጮኻሉ።’+ +15 ምድርን በኃይሉ የሠራው፣ፍሬያማ የሆነችውን መሬት በጥበቡ የመሠረተውና+ሰማያትን በማስተዋሉ የዘረጋው እሱ ነው።+ +16 ድምፁን ሲያሰማበሰማያት ያሉ ውኃዎች ይናወጣሉ፤ደመና* ከምድር ዳርቻዎች ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርጋል። በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያበርቃል፤*ነፋሱንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።+ +17 እያንዳንዱ ሰው ማስተዋልና እውቀት የጎደለው ድርጊት ይፈጽማል። እያንዳንዱ አንጥረኛ፣ በተቀረጸው ምስል የተነሳ ኀፍረት ይከናነባል፤+ከብረት የተሠራው ምስሉ* ሐሰት ነውና፤በውስጣቸውም መንፈስ* የለም።+ +18 እነሱ ከንቱና*+ መሳለቂያ ናቸው። የሚመረመሩበት ቀን ሲመጣ ይጠፋሉ። +19 የያዕቆብ ድርሻ ግን እንደነዚህ ነገሮች አይደለም፤እሱ የርስቱን በትር ጨምሮየሁሉ ነገር ሠሪ ነውና።+ ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።”+ +20 “አንቺ ለእኔ እንደ ቆመጥ፣ እንደ ጦር መሣሪያም ነሽ፤በአንቺ ብሔራትን አደቃለሁ። በአንቺ መንግሥታትን አወድማለሁ። +21 በአንቺ ፈረሱንና ፈረሰኛውን አደቃለሁ። በአንቺ የጦር ሠረገላውንና ነጂውን አደቃለሁ። +22 በአንቺ ወንድንና ሴትን አደቃለሁ። በአንቺ ሽማግሌንና ልጅን አደቃለሁ። በአንቺ ወጣቱንና ወጣቷን አደቃለሁ። +23 በአንቺ እረኛንና መንጋውን አደቃለሁ። በአንቺ ገበሬንና ጥማድ ከብቶቹን አደቃለሁ። በአንቺ ገዢዎችንና የበታች ገዢዎችን አደቃለሁ። +24 ደግሞም በጽዮን፣ በፊታችሁ ለሠሩት ክፋት ሁሉባቢሎንንና የከለዳውያን ምድር ነዋሪዎችን በሙሉ ዋጋቸውን እከፍላቸዋለሁ”+ ይላል ይሖዋ። +25 “አንቺ ምድርን ሁሉ ያጠፋሽ፣+አጥፊ ተራራ ሆይ፣ እነሆ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ”+ ይላል ይሖዋ። “በአንቺ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ከቋጥኞችም ላይ አንከባልልሻለሁ፤የተቃጠለም ተራራ አደርግሻለሁ።” +26 “ሰዎች የማዕዘን ድንጋይም ሆነ የመሠረት ድንጋይ ከአንቺ አይወስዱም፤ምክንያቱም አንቺ ለዘላለም ባድማ ትሆኛለሽ”+ ይላል ይሖዋ። +27 “በምድሪቱ ላይ ምልክት* አቁሙ።+ በብሔራት መካከል ቀንደ መለከት ንፉ። በእሷ ላይ እንዲዘምቱ ብሔራትን መድቡ።* የአራራት፣+ የሚኒ እና የአሽከናዝ መንግሥታት+ እሷን እንዲወጉ ሰብስቧቸው። በላይዋም ወታደሮችን የሚመለምል መኮንን ሹሙባት። ፈረሶችንም እንደ ኩብኩባ ስደዱባት። +28 ብሔራትን፣ የሜዶንን+ ነገሥታት፣ ገዢዎቿን፣ የበታች ገዢዎቿን ሁሉናበእያንዳንዳቸው ግዛት ሥር ያለውን ምድር ሁሉበእሷ ላይ እንዲዘምቱ መድቧቸው።* +29 ምድርም ትናወጣለች፤ ትንቀጠቀጣለችም፤ይሖዋ የባቢሎንን ምድር አስፈሪ ቦታና ሰው አልባ ለማድረግበባቢሎን ላይ ያሰበው ሐሳብ ይፈጸማልና።+ +30 የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋት አቁመዋል። በምሽጎቻቸው ውስጥ ይቀመጣሉ። ጉልበት ከድቷቸዋል።+ እንደ ሴት ሆነዋል።+ መኖሪያዎቿ በእሳት ነደዋል። መቀርቀሪያዎቿ ተሰብረዋል።+ +31 ከተማው በየአቅጣጫው እንደተያዘች ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገርአንዱ መልእክተኛ ሲሮጥ ከሌላው መልእክተኛ ጋር፣አንዱም ወሬ ነጋሪ ሲሮጥ ከሌላው ወሬ ነጋሪ ጋር ይገናኛል፤+ +32 መልካዎቹ* እንደተያዙ፣+የደንገል ጀልባዎቹ በእሳት እንደተቃጠሉናወታደሮቹ እንደተሸበሩ ሊነግሩት ይሯሯጣሉ።” +33 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ እንደ አውድማ ናት። ይህ በኃይል የምትረገጥበት ጊዜ ነው። በአጭር ��ዜ ውስጥ የመከር ወቅት ይደርስባታል።” +34 “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ዋጠኝ፤+ጨርሶ ግራ አጋባኝ። እንደ ባዶ ዕቃ አደረገኝ። እንደ ትልቅ እባብ ዋጠኝ፤+የእኔን መልካም ነገሮች በልቶ ሆዱን ሞላ። በውኃም ጠራርጎ አስወገደኝ። +35 የጽዮን ነዋሪ ‘በእኔና በአካሌ ላይ የተፈጸመው ግፍ በባቢሎን ላይ ይድረስ!’ ትላለች።+ ኢየሩሳሌም ‘ደሜም በከለዳውያን ምድር ነዋሪዎች ላይ ይሁን!’ ትላለች።” +36 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እኔ እሟገትልሻለሁ፤+ደግሞም እበቀልልሻለሁ።+ ባሕሯን አደርቃለሁ፤ የውኃ ጉድጓዶቿንም ደረቅ አደርጋለሁ።+ +37 ባቢሎንም የድንጋይ ቁልል፣+የቀበሮዎች ጎሬ፣+አስፈሪ ቦታና ማፏጫ ትሆናለች፤የሚኖርባትም አይገኝም።+ +38 ሁሉም በአንድነት እንደ ደቦል አንበሳ ያገሳሉ። እንደ አንበሳ ግልገሎች ያጉረመርማሉ።” +39 “ፍላጎታቸው በኃይል ሲነሳሳ እጅግ ደስ እንዲሰኙድግሳቸውን አዘጋጅላቸዋለሁ፤ እንዲሰክሩም አደርጋለሁ፤+ከዚያም ጨርሶ ላይነቁእስከ ወዲያኛው ያንቀላፋሉ”+ ይላል ይሖዋ። +40 “እንደ ጠቦቶች፣እንደ አውራ በጎችም ከፍየሎች ጋር ወደሚታረዱበት ቦታ አወርዳቸዋለሁ።” +41 “ሼሻቅ* እንዴት ተማረከች!+የምድር ሁሉ ‘ውዳሴ’ እንዴት ተያዘች!+ ባቢሎን በብሔራት መካከል ምንኛ አስፈሪ ቦታ ሆነች! +42 ባሕሩ ባቢሎንን አጥለቅልቋታል። በማዕበሉ ብዛት ተሸፍናለች። +43 ከተሞቿ አስፈሪ ቦታ እንዲሁም ውኃ የሌለበት ምድርና በረሃ ሆነዋል። ማንም ሰው የማይኖርበትና አንድም ሰው የማያልፍበት ምድር ሆነዋል።+ +44 ትኩረቴን በባቢሎን በሚገኘው በቤል+ ላይ አደርጋለሁ፤የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ።+ ብሔራት ከእንግዲህ ወደ እሱ አይጎርፉም፤የባቢሎንም ቅጥር ይፈርሳል።+ +45 ሕዝቤ ሆይ፣ ከመካከሏ ውጡ!+ ከሚነደው የይሖዋ ቁጣ+ ሕይወታችሁን* ለማትረፍ ሽሹ!+ +46 በምድሪቱ ላይ በሚሰማው ወሬ ልባችሁ አይሸበር፤ በፍርሃትም አትዋጡ። በምድሪቱ ላይ ዓመፅ ስለመኖሩ፣ገዢም በገዢ ላይ ስለመነሳቱ፣ በአንደኛው ዓመት አንድ ወሬ ይሰማል፤በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሌላ ወሬ ይናፈሳል። +47 ስለዚህ፣ እነሆ ትኩረቴንበባቢሎን የተቀረጹ ምስሎች ላይ የማደርግበት ጊዜ ይመጣል። ምድሪቱ በሙሉ ኀፍረት ትከናነባለች፤የታረዱባትም ሰዎች ሁሉ በመካከሏ ይወድቃሉ።+ +48 ሰማያትና ምድር እንዲሁም በውስጣቸው ያሉት ሁሉበባቢሎን የተነሳ እልል ይላሉ፤+አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና”+ ይላል ይሖዋ። +49 “ባቢሎን ተጠያቂ የሆነችው ታርደው ለወደቁት እስራኤላውያን ብቻ አይደለም፤+ከዚህ ይልቅ ከመላው ምድር የመጡ ሰዎችም በባቢሎን ታርደው ወድቀዋል። +50 እናንተ ከሰይፍ ያመለጣችሁ፣ መንገዳችሁን ቀጥሉ፤ ፈጽሞ አትቁሙ!+ በሩቅ ቦታ ሆናችሁ ይሖዋን አስታውሱ፤ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።”+ +51 “ዘለፋውን ስለሰማን በኀፍረት ተውጠናል። ባዕድ ሰዎች* በይሖዋ ቤት ባሉት ቅዱስ ስፍራዎች ላይ ስለተነሱውርደት ፊታችንን ሸፍኖታል።”+ +52 “ስለዚህ፣ እነሆ ትኩረቴንበተቀረጹ ምስሎቿ ላይ የማደርግበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ፤“በምድሪቱም ሁሉ፣ የቆሰሉት ሰዎች ያቃስታሉ።”+ +53 “ባቢሎን ወደ ሰማያት ብትወጣ፣+ከፍ ያሉ ምሽጎቿንም ብታጠናክር እንኳ፣እሷን የሚያጠፉ ከእኔ ዘንድ ይመጡባታል”+ ይላል ይሖዋ። +54 “ስሙ! ከባቢሎን ጩኸት፣+ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል፤+ +55 ይሖዋ ባቢሎንን ያጠፋልና፤ታላቅ ድምፅዋን ጸጥ ያሰኛል፤ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኃዎች ያስተጋባል። የድምፃቸው ጩኸት ይሰማል። +56 በባቢሎን ላይ አጥፊ ይመጣልና፤+ተዋጊዎቿ ይያዛሉ፤+ቀስቶቻቸው ይሰባበራሉ፤ይሖዋ የሚበቀል አምላክ ነውና።+ በእርግጥ ብድራትን ይመልሳል።+ +57 መኳንንቷንና ጥበበኞቿን፣ገዢዎቿንና የበታች ገዢዎቿን እንዲሁም ተዋጊዎቿን አሰክራለሁ፤+እነሱም ጨርሶ ላይነቁእስከ ወዲያኛው ያንቀላፋሉ”+ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነው ንጉሥ። +58 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ቅጥር ሰፊ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ይፈርሳል፤+በሮቿ ረጃጅም ቢሆኑም በእሳት ይጋያሉ። ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤ብሔራትም እሳት ለሚበላው ነገር ራሳቸውን እንዲሁ ያደክማሉ።”+ +59 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የማህሴያህ ልጅ፣ የነሪያህ+ ልጅ ሰራያህ ከንጉሡ ጋር ወደ ባቢሎን በተጓዘ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ለእሱ የሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ሰራያህ የቤተ መንግሥት አስተዳዳሪ ነበር። +60 ኤርምያስ በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት ሁሉ፣ ደግሞም በባቢሎን ላይ ስለሚደርሰው ነገር የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ በአንድ መጽሐፍ ላይ ጻፈው። +61 በተጨማሪም ኤርምያስ ሰራያህን እንዲህ አለው፦ “ባቢሎን ስትደርስና ከተማዋን ስታይ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ይህን ቃል ሁሉ አንብብ። +62 ከዚያም እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ ሆይ፣ ይህች ስፍራ እንደምትጠፋና ሰውም ሆነ እንስሳ፣ አንድም የሚኖርባት እንደማይገኝ፣ እንዲሁም ለዘላለም ባድማ እንደምትሆን ተናግረሃል።’+ +63 ይህን መጽሐፍ አንብበህ ከጨረስክ በኋላም መጽሐፉን ከድንጋይ ጋር አስረህ ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ወርውረው። +64 ከዚያም እንዲህ በል፦ ‘ባቢሎን በእሷ ላይ ከማመጣው ጥፋት የተነሳ እንዲህ ትሰምጣለች፤ ዳግመኛም አትነሳም፤+ እነሱም ይዝላሉ።’”+ የኤርምያስ ቃል እዚህ ላይ ያበቃል። +6 እናንተ የቢንያም ልጆች፣ ተሸሸጉ፤ ከኢየሩሳሌም ወጥታችሁ ሽሹ። በተቆአ+ ቀንደ መለከት ንፉ፤+በቤትሃኬሬም እሳት በማንደድ ምልክት አሳዩ! ከሰሜን ጥፋት፣ ይኸውም ታላቅ መዓት እያንዣበበ ነውና።+ + 2 የጽዮን ሴት ልጅ ያማረችና ቅምጥል ሴት ትመስላለች።+ + 3 እረኞችና መንጎቻቸው ይመጣሉ። በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፤+እያንዳንዳቸውም የሚጠብቋቸውን መንጎች ያሰማራሉ።+ + 4 “በእሷ ላይ ጦርነት ለማወጅ ተዘጋጁ!* ተነሱ፣ እኩለ ቀን ላይ ጥቃት እንሰንዝርባት!” “ወዮልን፣ ቀኑ እየመሸ፣የምሽቱም ጥላ እየረዘመ ነውና!” + 5 “ተነሱ፣ በሌሊት ጥቃት እንሰንዝርባት፤የማይደፈሩትንም ማማዎቿን እንደምስስ።”+ + 6 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እንጨት ቁረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያም የአፈር ቁልል ደልድሉ።+ ይህች ከተማ ተጠያቂ ልትሆን ይገባል፤በውስጧ ከግፍ በቀር ምንም አይገኝም።+ + 7 የውኃ ጉድጓድ ውኃውን እንደቀዘቀዘ እንደሚያቆይ፣እሷም ክፋቷን እንዳለ ጠብቃ አቆይታለች። ዓመፅና ጥፋት በውስጧ ይሰማል፤+ሕመምና ደዌ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው። + 8 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ተጸይፌሽ ከአንቺ እንዳልርቅ* ተጠንቀቂ፤+ባድማና ሰው የማይኖርበት ምድር አደርግሻለሁ።”+ + 9 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ቀሪዎች በወይን ተክል ላይ እንደቀሩ የመጨረሻ የወይን ፍሬዎች ምንም ሳያስቀሩ ይቃርሟቸዋል። ከወይን ተክሎች ላይ የወይን ፍሬዎች እንደሚለቅም ሰው በድጋሚ እጅህን ዘርጋ።” +10 “ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው ስለተዘጉ* ማዳመጥ አይችሉም።+ እነሆ፣ የይሖዋን ቃል መሳለቂያ አድርገውታል፤+ቃሉም ደስ አያሰኛቸውም። +11 በመሆኑም በይሖዋ ቁጣ ተሞልቻለሁ፤በውስጤ አፍኜ ስለያዝኩት ዝያለሁ።”+ “በጎዳና ባለ ልጅ፣ተሰብስበው ባሉ ወጣቶች ላይ አፍስሰው።+ ባልም ሆነ ሚስቱ፣አረጋውያኑም ሆኑ ያረጁት* ይያዛሉ።+ +12 ቤቶቻቸው፣ እርሻዎቻቸውና ሚስቶቻቸውለሌሎች ይሰጣሉ።+ እጄን በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ እዘረጋለሁና” ይላል ይሖዋ። +13 “ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ እያንዳንዱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣል፤+ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+ +14 ሰላም ሳይኖር፣‘ሰላም ነው! ሰላም ነው!’ እያሉ የሕዝቤን ስብራት* ላይ ላዩን* ለመጠገን ይሞክራሉ።+ +15 በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል? እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም! ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም!+ ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ። እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ” ይላል ይሖዋ። +16 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መስቀለኛ መንገዶቹ ላይ ቁሙና ተመልከቱ። ስለ ጥንቶቹ ጎዳናዎች፣መልካም የሆነው መንገድ የትኛው እንደሆነ ጠይቁ፤ በዚያም ሂዱ፤+እረፍትም አግኙ።”* እነሱ ግን “በዚያ አንሄድም” ይላሉ።+ +17 “እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂዎችን ሾምኩ፤+ጠባቂዎቹም ‘የቀንደ መለከቱን ድምፅ በትኩረት አዳምጡ!’ አሉ”፤+ እነሱ ግን “አናዳምጥም” አሉ።+ +18 “ስለዚህ እናንተ ብሔራት፣ ስሙ! እናንተ ሰዎች ሆይ፣ምን እንደሚደርስባቸው እወቁ። +19 ምድር ሆይ፣ ስሚ! በእነዚህ ሰዎች ላይ የገዛ ውጥናቸውን ፍሬ፣ጥፋትን አመጣባቸዋለሁ፤+እነሱ ለቃሌ ምንም ትኩረት አልሰጡምና፤ሕጌንም* አልተቀበሉም።” +20 “ነጭ ዕጣን ከሳባ፣ጠጅ ሣር* ከሩቅ አገር ብታመጡልኝ ምን ይጠቅመኛል? ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባችሁን አልቀበልም፤መሥዋዕቶቻችሁም ደስ አያሰኙኝም።”+ +21 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በዚህ ሕዝብ ፊት መሰናክል አስቀምጣለሁ፤አባቶችም ሆኑ ልጆች፣ጎረቤትም ሆነ ባልንጀራውበአንድነት ይሰናከላሉ፤ሁሉም ይጠፋሉ።”+ +22 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ከሰሜን ምድር አንድ ሕዝብ እየመጣ ነው፤ከምድር ዳርቻም ታላቅ ብሔር ይነሳል።+ +23 ቀስትና ጦር ይይዛሉ። ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው። ድምፃቸው እንደ ባሕር ያስተጋባል፤ፈረሶችንም ይጋልባሉ።+ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልክ እንደ ተዋጊ በአንቺ ላይ ይሰለፋሉ።” +24 ወሬውን ሰምተናል። እጆቻችንም ዝለዋል፤+በጭንቀት ተውጠናል፤ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ሥቃይ ቀስፎናል።*+ +25 ወደ ውጭ አትውጡ፤በመንገዱም ላይ አትዘዋወሩ፤ጠላት ሰይፍ ታጥቋልና፤በየቦታውም ሽብር ነግሦአል። +26 የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣ማቅ ልበሺ፤+ በአመድም ላይ ተንከባለዪ። አንድ ልጁን እንዳጣ ሰው መራራ ለቅሶ አልቅሺ፤+አጥፊው በእኛ ላይ በድንገት ይመጣልና።+ +27 “አንተን* በሕዝቤ መካከል ብረትን እንደሚፈትን፣በጥንቃቄም እንደሚመረምር ሰው አድርጌሃለሁ፤አንተም ልብ በል፤ መንገዳቸውንም መርምር። +28 ሁሉም በጣም ግትር ናቸው፤+እየዞሩ ስም ያጠፋሉ።+ እንደ መዳብና ብረት ናቸው፤ሁሉም ምግባረ ብልሹዎች ናቸው። +29 ወናፎቹ በእሳት ተቃጠሉ። ከእሳቱም የሚወጣው እርሳስ ነው። አንጥረኛ በደንብ የሚያጣራው እንዲያው በከንቱ ነው፤+መጥፎዎቹም ተለይተው አልወጡም።+ +30 ሰዎች ‘የተጣለ ብር’ ብለው ይጠሯቸዋል፤ይሖዋ ጥሏቸዋልና።”+ +25 የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ይኸውም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት መላውን የይሁዳን ሕዝብ በተመለከተ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። +2 ነቢዩ ኤርምያስ የይሁዳን ሕዝብ ሁሉና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች በሙሉ አስመልክቶ* እንዲህ ሲል ተናገረ፦ +3 “ከይሁዳ ንጉሥ ከአምዖን ልጅ ከኢዮስያስ 13ኛ ዓመት የግዛት ዘመን+ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ላለፉት 23 ዓመታት የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ደግሜ ደጋግሜ ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን አትሰሙም።+ +4 ይሖዋም ደግሞ ደጋግሞ አገልጋዮቹን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላከ፤ እናንተ ግን አትሰሙም ወይም ጆሯችሁን አትሰጡም።+ +5 እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ድርጊታችሁ ተመለሱ፤+ ይህን ካደረጋችሁ ይሖዋ ለብዙ ዘመን እንድትኖሩባት ሲል ከረጅም ጊዜ በፊት ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ላይ ትኖራላችሁ። +6 በእጃችሁ ሥራ ታስቆጡኝ ዘንድ ሌሎች አማልክትን አትከተሉ፣ አታገልግሏቸው፣ አትስገዱላቸውም፤ አለዚያ ጥፋት አመጣባችኋለሁ።’ +7 “‘እናንተ ግን እኔን አትሰሙም’ ይላል ይሖዋ። ‘ይልቁንም በራሳችሁ ላይ ጥፋት ታመጡ ዘንድ አስቆጣችሁኝ።’+ +8 “ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“ቃሌን ስለማትታዘዙ፣ +9 የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤ “አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* እጠራለሁ፤+ በዚህች ምድር፣ በነዋሪዎቿና በዙሪያዋ ባሉ በእነዚህ ብሔራት ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ።+ ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤ እንዲሁም መቀጣጫና ማፏጫ እንዲሆኑ ብሎም ባድማ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋለሁ። +10 የሐሴትንና የደስታን ድምፅ፣ የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ፣ የወፍጮን ድምፅና የመብራትን ብርሃን ከመካከላቸው አስቀራለሁ።+ +11 መላ ምድሪቱ ትወድማለች፤ እንዲሁም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች፤ እነዚህም ብሔራት የባቢሎንን ንጉሥ 70 ዓመት ያገለግሉታል።”’+ +12 “‘ይሁንና ሰባው ዓመት ሲፈጸም+ በበደላቸው የተነሳ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ብሔር ተጠያቂ አደርጋለሁ’*+ ይላል ይሖዋ፤ ‘የከለዳውያንንም ምድር እስከ ወዲያኛው ባድማ አደርገዋለሁ።+ +13 በምድሪቱ ላይ የተናገርኩትን ቃል ሁሉ ይኸውም ኤርምያስ በሁሉም ብሔራት ላይ የተነበየውንና በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ነገር ሁሉ አመጣባታለሁ። +14 ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት+ ባሪያዎች ያደርጓቸዋልና፤+ እኔም እንደ ድርጊታቸውና እንደ ገዛ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።’”+ +15 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “የቁጣ ወይን ጠጅ ያለበትን ይህን ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ እኔም ወደምልክህ ብሔራት ሁሉ ሄደህ አጠጣቸው። +16 እነሱም በመካከላቸው ከምሰደው ሰይፍ የተነሳ ይጠጣሉ፣ ይንገዳገዳሉ፣ እንደ አበደ ሰውም ይሆናሉ።”+ +17 ስለዚህ ከይሖዋ እጅ ጽዋውን ወሰድኩ፤ ይሖዋ ወደላከኝም ብሔራት ሁሉ ሄጄ አጠጣኋቸው፦+ +18 ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ባድማ፣ መቀጣጫና ማፏጫ እንዲሆኑ እንዲሁም ለእርግማን እንዲዳረጉ+ በመጀመሪያ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣+ ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠጣኋቸው፤ +19 ከዚያም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንና አገልጋዮቹ፣ መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ፣+ +20 ድብልቅ የሆነው ሕዝባቸው ሁሉ፣ የዑጽ ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ የፍልስጤማውያን+ ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ አስቀሎን፣+ ጋዛ፣ ኤቅሮንና ከአሽዶድ የቀሩት ሰዎች፣ +21 ኤዶም፣+ ሞዓብና+ አሞናውያን፣+ +22 የጢሮስ ነገሥታት ሁሉ፣ የሲዶና+ ነገሥታት ሁሉና በባሕሩ ላይ ያለው ደሴት ነገሥታት፣ +23 ዴዳን፣+ ቴማ፣ ቡዝና በሰሪሳራቸው* ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩ ሁሉ፣+ +24 የዓረብ ነገሥታት ሁሉና+ በምድረ በዳ የሚኖሩት ድብልቅ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣ +25 የዚምሪ ነገሥታት ሁሉ፣ የኤላም+ ነገሥታት ሁሉና የሜዶናውያን ነገሥታት+ ሁሉ፣ +26 በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉ የሰሜን ነገሥታት ሁሉ አንድ በአንድ እንዲሁም በምድር ላይ ያሉ ሌሎች የዓለም መንግሥታት ሁሉ ጠጡ፤ ከእነሱም በኋላ የሼሻቅ*+ ንጉሥ ይጠጣል። +27 “አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በመካከላችሁ ከምሰደው ሰይፍ የተነሳ ጠጡ፣ ስከሩ፣ አስታውኩ፣ ዳግመኛም ላትነሱ ውደቁ።”’+ +28 ጽዋውን ከእጅህ ወስደው ���መጠጣት ፈቃደኛ ባይሆኑ እንዲህ በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በግድ ትጠጣላችሁ! +29 እነሆ፣ በመጀመሪያ የማጠፋው በስሜ የተጠራችውን ከተማ+ ከሆነ እናንተስ ከቅጣት ታመልጣላችሁ?”’+ “‘በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ ሰይፍን ስለምጠራ እናንተም ከቅጣት አታመልጡም’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +30 “አንተም ይህን ቃል ሁሉ ትተነብይላቸዋለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፦‘ይሖዋ ከላይ ሆኖ ይጮኻል፤ከቅዱስ ማደሪያውም ድምፁን ያሰማል። በመኖሪያ ስፍራውም ላይ በኃይል ይጮኻል። ወይን መጭመቂያውን እንደሚረግጡ ሰዎች፣በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ በድል አድራጊነት ይዘምራል።’ +31 ‘ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል፤ይሖዋ ከብሔራት ጋር ሙግት አለውና። እሱ ራሱ በሰዎች* ሁሉ ላይ ይፈርዳል።+ ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል’ ይላል ይሖዋ። +32 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ጥፋት ብሔራትን አንድ በአንድ ያዳርሳል፤+ታላቅ አውሎ ነፋስም ከምድር ዳርቻዎች ይነሳል።+ +33 “‘በዚያም ቀን፣ ይሖዋ የገደላቸው ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ። አይለቀስላቸውም፣ አይሰበሰቡም ወይም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።’ +34 እናንተ እረኞች፣ ዋይ ዋይ በሉ፤ ጩኹም! እናንተ በመንጋው መካከል ያላችሁ ታላላቆች፣ በአመድ ላይ ተንከባለሉ፤ምክንያቱም የምትታረዱበትና የምትበታተኑበት ጊዜ ደርሷል፤እንደ ውድ የሸክላ ዕቃ ትከሰከሳላችሁ! +35 እረኞቹ የሚሸሹበት ቦታ የለም፤በመንጋው መካከል ያሉት ታላላቆችም ማምለጫ የላቸውም። +36 አዳምጡ! የእረኞቹ ጩኸትናበመንጋው መካከል ያሉ ታላላቆች ዋይታ ይሰማል፤ይሖዋ ማሰማሪያቸውን እያወደመ ነውና። +37 ከሚነደው የይሖዋ ቁጣም የተነሳሰላማዊ የሆኑት የመኖሪያ ቦታዎች ሕይወት አልባ ሆነዋል። +38 እንደ ደቦል አንበሳ ከጎሬው ወጥቷል፤+ከጨካኙ ሰይፍናከሚነደው ቁጣው የተነሳምድራቸው የሚያስፈራ ቦታ ሆኗልና።” +33 ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ታስሮ ሳለ የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ +2 “ምድርን የሠራት ይሖዋ፣ አዎ፣ ያበጃትና አጽንቶ የመሠረታት ይሖዋ እንዲህ ይላል፤ ስሙ ይሖዋ ነው፤ +3 ‘ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተ የማታውቀውን ታላቅና ለመረዳት አዳጋች የሆነ ነገር ወዲያውኑ እነግርሃለሁ።’”+ +4 “እኔ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ፣ በዙሪያዋ በተደለደለው የአፈር ቁልልና በሰይፍ የተነሳ ስለፈረሱት የዚህች ከተማ ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንዲህ እላለሁ፤+ +5 ደግሞም ከከለዳውያን ጋር ሊዋጉ የሚመጡትን ሰዎች እንዲሁም ከክፋታቸው የተነሳ ፊቴን ከዚህች ከተማ እንድሰውር ባደረጉኝና በታላቅ ቁጣዬ በመታኋቸው ሰዎች ሬሳ የሚሞሉትን ቦታዎች በተመለከተ እንዲህ እላለሁ፦ +6 ‘እነሆ፣ ከተማዋ እንድታገግም አደርጋለሁ፤ ጤናም እሰጣታለሁ፤+ እኔም እፈውሳቸዋለሁ እንዲሁም የተትረፈረፈ ሰላምና እውነት እሰጣቸዋለሁ።+ +7 ከይሁዳ የተማረኩትንና ከእስራኤል የተማረኩትን እመልሳለሁ፤+ እንደቀድሞውም እገነባቸዋለሁ።+ +8 እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤+ በእኔ ላይ የሠሩትን ኃጢአትና በደል ሁሉ ይቅር እላለሁ።+ +9 እሷም የማደርግላቸውን መልካም ነገር በሙሉ በሚሰሙ የምድር ብሔራት ሁሉ ፊት የሐሴት ስም፣ ውዳሴና ውበት ትሆንልኛለች።+ በማደርግላት መልካም ነገር ሁሉና በምሰጣት ሰላም ሁሉ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።’”+ +10 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውም ሆነ ከብት የማይኖርበት ጠፍ መሬት በምትሉት በዚህ ቦታ እንዲሁም ሰው ወይም ነዋሪ ወይም ከብት በሌለባቸው ወና የሆኑ የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ጎዳናዎች እንደገና ድምፅ ይሰማል፤ +11 አዎ፣ የሐሴት ድምፅ፣ የደስታ ድምፅ፣+ የሙሽራና የሙሽሪት ድምፅ እንዲሁም “ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ+ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን አመስግኑ፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል!”+ የሚሉ ሰዎች ድምፅ ይሰማል።’ “‘ቀድሞ እንደነበረው ከምድሪቱ ተማርከው የተወሰዱትን ስለምመልስ ወደ ይሖዋ ቤት የምሥጋና መባዎች ይ +12 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰው ወይም ከብት በሌለበት በዚህ ጠፍ መሬት እንዲሁም በከተሞቹ ሁሉ እረኞች መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት የግጦሽ መሬት ዳግመኛ ያገኛሉ።’+ +13 “‘በተራራማው ምድር በሚገኙ ከተሞች፣ በዝቅተኛው ስፍራ በሚገኙ ከተሞች፣ በደቡብ ባሉ ከተሞች፣ በቢንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ ቦታዎችና+ በይሁዳ ከተሞች፣+ እረኞች በጎቻቸውን የሚቆጥሩበት ጊዜ ዳግመኛ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።” +14 “‘እነሆ፣ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የገባሁትን የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።+ +15 ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ ለዳዊት ቀንበጥ* ይኸውም ጻድቅ ቀንበጥ አበቅላለሁ፤+ እሱም በምድሪቱ ላይ ፍትሕንና ጽድቅን ያሰፍናል።+ +16 በዚያ ዘመን ይሁዳ ትድናለች፤+ ኢየሩሳሌምም ያለስጋት ትቀመጣለች።+ እሷም “ይሖዋ ጽድቃችን ነው” ተብላ ትጠራለች።’”+ +17 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከዳዊት ዘር፣ በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይታጣም፤+ +18 ከሌዋውያን ካህናትም መካከል ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችን ለማቅረብ፣ የእህል መባዎችን ለማቃጠልና መሥዋዕቶችን ለማቅረብ በፊቴ የሚቆም ሰው ጨርሶ አይታጣም።’” +19 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +20 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ፣ የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ የምትችሉ ከሆነ፣+ +21 ያን ጊዜ ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋር የገባሁት ቃል ኪዳኔ ሊፈርስ ይችላል፤+ ያን ጊዜ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ አይኖረውም፤+ አገልጋዮቼ ከሆኑት ከሌዋውያን ካህናት+ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ይፈርሳል። +22 የሰማያት ሠራዊት ሊቆጠር፣ የባሕርም አሸዋ ሊሰፈር እንደማይችል ሁሉ የአገልጋዬን የዳዊትን ዘርና አገልጋዮቼን ሌዋውያንን እንዲሁ አበዛቸዋለሁ።’” +23 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +24 “እነዚህ ሰዎች፣ ‘ይሖዋ የመረጣቸውን ሁለቱን ወገኖች ይተዋቸዋል’ እንደሚሉ አላስተዋልክም? የገዛ ሕዝቤንም ይንቃሉ፤ እነሱን እንደ ብሔር አድርገው መመልከት አቁመዋል። +25 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማቋቋሜ+ እንዲሁም የሰማይንና የምድርን ሕግ* መደንገጌ የተረጋገጠ እንደሆነ ሁሉ፣+ +26 በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ልጆች* ላይ የሚነግሡ ገዢዎች ከዘሩ እንዳይታጡ የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር ፈጽሞ አልጥልም። ተማርከው የተወሰዱባቸውን መልሼ እሰበስባለሁና፤+ ርኅራኄም አሳያቸዋለሁ።’”+ +10 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይሖዋ በእናንተ ላይ የተናገረውን ቃል ስሙ። +2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የብሔራትን መንገድ አትማሩ፤+በሰማያት ምልክቶችም አትሸበሩ፤ምክንያቱም ብሔራት በእነዚህ ነገሮች ተሸብረዋል።+ + 3 የእነዚህ ሕዝቦች ልማድ ከንቱ* ነውና፤ የእጅ ጥበብ ባለሙያ ዛፍ ከጫካ ይቆርጥናበመሣሪያው* ጠርቦ ጣዖት ይሠራል።+ + 4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፤+እንዳይወድቅም በመዶሻና በምስማር ይቸነክሩታል።+ + 5 እነሱ በኪያር እርሻ ውስጥ ለወፍ ማስፈራሪያነት እንደሚተከል ማስፈራርቾ መናገር አይችሉም፤+መራመድ ስለማይችሉ ተሸካሚ ያስፈልጋቸዋል።+ ጉዳት ማድ���ስም ሆነምንም ዓይነት መልካም ነገር መሥራት ስለማይችሉ አትፍሯቸው።”+ + 6 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+ አንተ ታላቅ ነህ፤ ስምህም ታላቅና ኃያል ነው። + 7 የብሔራት ንጉሥ ሆይ፣+ አንተን የማይፈራ ማን ነው? አንተ ልትፈራ ይገባሃልና፤ምክንያቱም ከብሔራት ጠቢባን ሁሉ እንዲሁም ከመንግሥቶቻቸው ሁሉ መካከልእንደ አንተ ያለ ማንም የለም።+ + 8 ሁሉም የማመዛዘን ችሎታ የጎደላቸውና ሞኞች ናቸው።+ ከእንጨት ምስል የሚመጣ መመሪያ ፈጽሞ ከንቱ* ነው።+ + 9 በእጅ ጥበብ ባለሙያና በአንጥረኛ የተሠራየተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣+ ወርቅም ከዑፋዝ ይመጣል። ልብሳቸው በሰማያዊ ክርና በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው። ሁሉም በባለሙያዎች የተሠሩ ናቸው። +10 ይሖዋ ግን እውነተኛ አምላክ ነው። እሱ ሕያው አምላክና+ ዘላለማዊ ንጉሥ ነው።+ ከቁጣው የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤+የእሱን ውግዘት ሊቋቋም የሚችል አንድም ብሔር የለም። +11 * እናንተ እንዲህ በሏቸው፦ “ሰማያትንና ምድርን ያልሠሩት አማልክትከምድር ገጽ፣ ከእነዚህም ሰማያት በታች ይጠፋሉ።”+ +12 ምድርን በኃይሉ የሠራው፣ፍሬያማ የሆነችውን መሬት በጥበቡ የመሠረተውና+ሰማያትን በማስተዋሉ የዘረጋው እሱ ነው።+ +13 ድምፁን ሲያሰማበሰማያት ያሉ ውኃዎች ይናወጣሉ፤+ደመና* ከምድር ዳርቻዎች ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርጋል።+ በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያበርቃል፤*ነፋሱንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።+ +14 እያንዳንዱ ሰው ማስተዋልና እውቀት የጎደለው ድርጊት ይፈጽማል። እያንዳንዱ አንጥረኛ፣ በተቀረጸው ምስል የተነሳ ኀፍረት ይከናነባል፤+ከብረት የተሠራው ምስሉ* ሐሰት ነውና፤በውስጣቸውም መንፈስ* የለም።+ +15 እነሱ ከንቱና* መሳለቂያ ናቸው።+ የሚመረመሩበት ቀን ሲመጣ ይጠፋሉ። +16 የያዕቆብ ድርሻ ግን እንደነዚህ ነገሮች አይደለም፤እሱ የሁሉ ነገር ሠሪ ነውና፤እስራኤልም የርስቱ በትር ነው።+ ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።+ +17 አንቺ የተከበብሽ ሴት፣ጓዝሽን ከመሬት ላይ ሰብስቢ። +18 ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፣ በዚህ ጊዜ ነዋሪዎቹን ከምድሪቱ ውጭ እወረውራቸዋለሁ፤*+ጭንቀት እንዲይዛቸውም አደርጋለሁ።” +19 ስብራት* ደርሶብኛልና ወዮልኝ!+ ቁስሌ የማይድን ነው። እኔም እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ ይህ የእኔ ሕመም ነው፤ ልሸከመውም ይገባል። +20 ድንኳኔ ፈርሷል፤ የድንኳኔም ገመዶች ሁሉ ተበጥሰዋል።+ ወንዶች ልጆቼ ጥለውኝ ሄደዋል፤ ከዚህ በኋላ አይኖሩም።+ ድንኳኔን የሚተክልልኝ ወይም የድንኳኔን ሸራዎች የሚዘረጋልኝ አንድም ሰው የለም። +21 እረኞቹ የሞኝነት ድርጊት ፈጽመዋልና፤+ይሖዋንም አልጠየቁም።+ ማስተዋል የጎደለው ድርጊት የፈጸሙት ለዚህ ነው፤መንጎቻቸውም ሁሉ ተበታትነዋል።”+ +22 አዳምጡ! አንድ ወሬ ስሙ! ወደዚህ እየመጣ ነው! የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮዎች ጎሬ ሊያደርግ+ከሰሜን ምድር ድም፣ ድም የሚል ኃይለኛ ድምፅ እየቀረበ ነው።+ +23 ይሖዋ ሆይ፣ የሰው መንገድ በራሱ እጅ እንዳልሆነ በሚገባ አውቃለሁ። አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም።+ +24 ይሖዋ ሆይ፣ አርመኝ፤ሆኖም ፈጽመህ እንዳታጠፋኝ+ በፍትሕ እንጂ በቁጣህ አይሁን።+ +25 አንተን ችላ በሚሉ ብሔራት+እንዲሁም ስምህን በማይጠሩ ነገዶች ላይ ቁጣህን አፍስስ። ያዕቆብን በልተውታልና፤+አዎ፣ ሙሉ በሙሉ እስኪጠፋ ድረስ በልተውታል፤+የትውልድ አገሩንም አውድመዋል።+ +14 ድርቅን አስመልክቶ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦+ + 2 ይሁዳ ታለቅሳለች፤+ በሮቿም ወላልቀዋል። በሐዘን ተውጠው መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ከኢየሩሳሌምም ጩኸት ይሰማል። + 3 ጌቶቻቸውም አገልጋዮቻቸውን* ውኃ እንዲፈልጉ ላኳቸው። እ��ሱም ወደ ውኃ ጉድጓዶቹ* ሄዱ፤ ውኃ ግን አላገኙም። ባዶ ዕቃ ይዘው ተመለሱ። በኀፍረት ተዋጡ፤ ተስፋም ቆረጡ፤ራሳቸውንም ተከናነቡ። + 4 በምድሪቱ ላይ ዝናብ ባለመዝነቡ የተነሳመሬቱ ስለተሰነጣጠቀ+ገበሬዎቹ እጅግ አዘኑ፤ ራሳቸውንም ተከናነቡ። + 5 በሜዳ ያለች እንስት ርኤም* እንኳምንም ሣር ባለመኖሩ እንደወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች። + 6 የዱር አህዮች በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ይቆማሉ። እንደ ቀበሮ አየር አጥሯቸው ያለከልካሉ፤ምንም ዓይነት ተክል ባለመኖሩ ዓይኖቻቸው ፈዘዙ።+ + 7 ይሖዋ ሆይ፣ የገዛ ራሳችን በደል በእኛ ላይ የሚመሠክርብን ቢሆንምለስምህ ስትል እርምጃ ውሰድ።+ የክህደት ሥራችን በዝቷልና፤+ኃጢአት የሠራነውም በአንተ ላይ ነው። + 8 አንተ የእስራኤል ተስፋ፣ በጭንቀትም ጊዜ አዳኙ+ የሆንክ ሆይ፣በምድሪቱ እንደ እንግዳ፣ሌሊቱን ለማሳለፍ ሲል ብቻ ጎራ እንዳለ መንገደኛ የሆንከው ለምንድን ነው? + 9 ክው ብሎ እንደቀረ ሰው፣ማዳን እንደማይችል ኃያል ሰው የሆንከው ለምንድን ነው? ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በመካከላችን ነህና፤+እኛም በስምህ ተጠርተናል።+ እባክህ አትተወን። +10 ይሖዋ ይህን ሕዝብ አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦ “መቅበዝበዝ ይወዳሉ፤+ እግራቸውን አልሰበሰቡም።+ ስለዚህ ይሖዋ በእነሱ ደስ አይሰኝም።+ አሁን በደላቸውን ያስባል፤ በኃጢአታቸውም የተነሳ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።”+ +11 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ሕዝብ መልካም ሁኔታ እንዲገጥመው አትጸልይ።+ +12 በሚጾሙበት ጊዜ የሚያቀርቡትን ልመና አልሰማም፤+ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የእህል መባዎች በሚያቀርቡበት ጊዜም በእነሱ ደስ አልሰኝም፤+ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* አጠፋቸዋለሁና።”+ +13 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሆ፣ ነቢያቱ ‘ሰይፍ አታዩም፤ ለረሃብም አትዳረጉም፤ ከዚህ ይልቅ በዚህ ስፍራ እውነተኛ ሰላም እሰጣችኋለሁ’ ይሏቸዋል።”+ +14 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ።+ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኳቸውም ወይም አላናገርኳቸውም።+ የሐሰት ራእይን፣ ከንቱ የሆነ ሟርትንና የገዛ ልባቸውን ማታለያ ይተነብዩላችኋል።+ +15 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ሳልካቸው በስሜ የሚተነብዩትና በዚህች ምድር ላይ ሰይፍም ሆነ ረሃብ አይከሰትም የሚሉት እነዚህ ነቢያት በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ።+ +16 የሚተነብዩለትም ሕዝብ ከረሃቡና ከሰይፉ የተነሳ አስከሬኑ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ይጣላል፤ እነሱን፣ አዎ እነሱን፣ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቀብራቸው አይኖርም፤+ የሚገባቸውን ጥፋት በላያቸው ላይ አመጣለሁና።’+ +17 “ይህን ቃል ንገራቸው፦‘ዓይኖቼ ሌት ተቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ፤+ድንግሊቱ የሕዝቤ ሴት ልጅ እጅግ አስከፊ በሆነ ቁስል ሙሉ በሙሉ ደቃለችና፤ደግሞም ተሰብራለች።+ +18 ወደ መስክ ብወጣ፣እነሆ፣ በሰይፍ የተገደሉትን አያለሁ!+ ወደ ከተማም ብገባ፣በረሃብ የተነሳ የታመሙ ሰዎችን አያለሁ!+ ነቢዩና ካህኑ በማያውቁት አገር ተቅበዝብዘዋልና።’”+ +19 ይሁዳን ጨርሶ ትተኸዋል? ወይስ ጽዮንን ተጸይፈሃታል?*+ ታዲያ ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ የመታኸን ለምንድን ነው?+ ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም መልካም ነገር አልመጣም፤የፈውስ ጊዜ ይመጣል ብለን ጠበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ነገሠ!+ +20 ይሖዋ ሆይ፣ ክፋት መሥራታችንን፣አባቶቻችንም በደል መፈጸማቸውን አምነን እንቀበላለን፤በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና።+ +21 ስለ ስምህ ስትል አትናቀን፤+ክብር የተላበሰውን ዙፋንህን አታቃልል። ከእኛ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አስ��ውስ፤ አታፍርሰውም።+ +22 ከንቱ ከሆኑት የአሕዛብ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለ?ሰማያትስ በራሳቸው ዝናብ ማውረድ ይችላሉ? አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ ይህን የምታደርገው አንተ ብቻ አይደለህም?+ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረግከው አንተ ብቻ ስለሆንክአንተን ተስፋ እናደርጋለን። +43 ኤርምያስ አምላካቸው ይሖዋ ለእነሱ እንዲነግራቸው የላከውን የአምላካቸውን የይሖዋን ቃል ሁሉ፣ አንድም ሳያስቀር ለሕዝቡ በሙሉ ተናግሮ ሲጨርስ +2 የሆሻያህ ልጅ አዛርያስ፣ የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን+ እና እብሪተኛ የሆኑት ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “የምትናገረው ነገር ውሸት ነው! አምላካችን ይሖዋ ‘በግብፅ ለመኖር ወደዚያ አትሂዱ’ ብሎ አላከህም። +3 ከዚህ ይልቅ ከለዳውያን እንዲገድሉን ወይም ወደ ባቢሎን በግዞት እንዲወስዱን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ በእኛ ላይ ያነሳሳህ የነሪያህ ልጅ ባሮክ+ ነው።”+ +4 በመሆኑም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ የሠራዊቱ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ በሙሉ በይሁዳ ምድር እንዲቀመጡ ያዘዛቸውን የይሖዋን ቃል አልሰሙም። +5 እንዲያውም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና የሠራዊቱ አለቆች በሙሉ፣ በይሁዳ ምድር ለመኖር ከተበተኑባቸው ብሔራት ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳ ቀሪዎች በሙሉ ይዘው ሄዱ።+ +6 ወንዶቹን፣ ሴቶቹን፣ ልጆቹን፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ ከሳፋን+ ልጅ፣ ከአኪቃም+ ልጅ ከጎዶልያስ+ ጋር የተዋቸውን ሁሉ* እንዲሁም ነቢዩን ኤርምያስንና የነሪያህን ልጅ ባሮክን ይዘው ሄዱ። +7 የይሖዋን ቃል ባለመታዘዝ ወደ ግብፅ ምድር ገቡ፤ እስከ ጣፍነስ+ ድረስም ሄዱ። +8 ከዚያም የይሖዋ ቃል በጣፍነስ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +9 “ትላልቅ ድንጋዮችን ውሰድና አይሁዳውያኑ እያዩ በጣፍነስ በሚገኘው በፈርዖን ቤት መግቢያ፣ ከጡብ ከተሠራው መደብ ሥር ሸሽገህ በቅጥራን ለስናቸው። +10 ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* እጠራዋለሁ፤+ ዙፋኑንም እኔ ከሸሸግኳቸው ከእነዚህ ድንጋዮች በላይ አስቀምጣለሁ፤ ንጉሣዊ ድንኳኑንም በእነሱ ላይ ይዘረጋል።+ +11 እሱም መጥቶ የግብፅን ምድር ይመታል።+ ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ ለገዳይ መቅሰፍት፣ በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ለምርኮ እንዲሁም ሰይፍ የሚገባው ሁሉ ለሰይፍ ይሰጣል።+ +12 የግብፅን አማልክት ቤቶችም* በእሳት አያይዛለሁ፤+ እሱም ያቃጥላቸዋል፤ ማርኮም ይወስዳቸዋል። እረኛ ልብሱን እንደሚጎናጸፍ የግብፅን ምድር ይጎናጸፋል፤ ከዚያም ቦታ በሰላም* ይሄዳል። +13 በግብፅም ምድር የሚገኙትን የቤትሼሜሽን* ዓምዶች* ይሰባብራል፤ የግብፅን አማልክት ቤቶችም* በእሳት ያቃጥላል።”’” +9 ምነው ራሴ በውኃ በተሞላ!ዓይኖቼ የእንባ ምንጭ በሆኑ!+ ለታረዱት ወገኖቼቀን ከሌት ባለቀስኩ ነበር። + 2 ምነው በምድረ በዳ ለተጓዦች የሚሆን ማረፊያ ቦታ ባገኘሁ ኖሮ! በዚያን ጊዜ ሕዝቤን ትቼና ከእነሱ ተለይቼ በሄድኩ ነበር፤ሁሉም አመንዝሮች፣+የከዳተኞች ጥርቅም ሆነዋልና። + 3 ምላሳቸውን እንደ ደጋን ወጠሩ፤በምድሪቱ ላይ ታማኝነት ሳይሆን ውሸት ሰፍኗል።+ “በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤እኔንም ጨርሶ አይሰሙም”+ ይላል ይሖዋ። + 4 “እያንዳንዳችሁ ራሳችሁን ከባልንጀራችሁ ጠብቁ፤ወንድማችሁን እንኳ ሳይቀር አትመኑ። እያንዳንዱ ወንድም ከሃዲ ነውና፤+እያንዳንዱ ባልንጀራም ስም አጥፊ ነው።+ + 5 እያንዳንዱ ባልንጀራውን ያታልላል፤አንድም ሰው እውነትን አይናገርም። ምላሳቸውን ውሸት መናገር አስተምረውታል።+ ትክክል ያልሆነ ነገር በማድረግ ራሳቸው�� ያደክማሉ። + 6 የምትኖረው አታላይ በሆኑ ሰዎች መካከል ነው። አታላይ ከመሆናቸውም የተነሳ እኔን ለማወቅ እንቢተኞች ሆነዋል” ይላል ይሖዋ። + 7 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እኔ አቀልጣቸዋለሁ፤ ደግሞም እፈትናቸዋለሁ፤+ከሕዝቤ ሴት ልጅ ጋር በተያያዘ ከዚህ ሌላ ምን ማድረግ እችላለሁ? + 8 ምላሳቸው ማታለያ የሚናገር፣ ገዳይ ፍላጻ ነው። ሰው በአፉ ለባልንጀራው ስለ ሰላም ይናገራል፤በውስጡ ግን ለማጥቃት ያደባል።” + 9 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ። “እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?+ +10 በተራሮቹ የተነሳ አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤በምድረ በዳ ባሉት ማሰማሪያዎችም የተነሳ ሙሾ አወርዳለሁ፤*ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና፤የከብቶችም ድምፅ አይሰማም። የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊት ሸሽተዋል፤ ከአካባቢው ጠፍተዋል።+ +11 ኢየሩሳሌምን የድንጋይ ክምር፣+ የቀበሮም ጎሬ አደርጋታለሁ፤+የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።+ +12 ይህን ይረዳ ዘንድ ጥበበኛ የሆነ ማን ነው? ይህን ያሳውቅ ዘንድ የይሖዋ አፍ የተናገረው ለማን ነው? ምድሪቱ የጠፋችው ለምንድን ነው? ማንም እንዳያልፍባትእንደ ምድረ በዳ የተለበለበችው ለምንድን ነው?” +13 ይሖዋ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “በፊታቸው ያኖርኩትን ሕጌን* ስለተዉና ስላልተከተሉ እንዲሁም ድምፄን ስላልሰሙ ነው። +14 ከዚህ ይልቅ ግትር ሆነው የገዛ ልባቸውን+ እንዲሁም አባቶቻቸው ባስተማሯቸው መሠረት የባአልን ምስሎች ተከተሉ።+ +15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህ ሕዝብ ጭቁኝ እንዲበላ አደርጋለሁ፤ የተመረዘም ውኃ እንዲጠጣ አደርጋለሁ።+ +16 እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው በማያውቋቸው ብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤+ ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ ከኋላቸው ሰይፍን እሰዳለሁ።’+ +17 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘በማስተዋል ተመላለሱ። ሙሾ የሚያወርዱትን* ሴቶች ጥሩ፤+የሠለጠኑ አልቃሽ ሴቶችንም ልካችሁ አስመጡ፤ +18 ዓይኖቻችን እንባ ያጎርፉ ዘንድ፣ሽፋሽፍቶቻችንም ውኃ ያንጠባጥቡ ዘንድፈጥነው እንዲመጡና የሐዘን እንጉርጉሮ እንዲያንጎራጉሩልን ጥሯቸው።+ +19 ከጽዮን የሐዘን እንጉርጉሮ ድምፅ ተሰምቷልና፦+ “ከባድ ጥፋት ደርሶብናል! ታላቅ ኀፍረት ተከናንበናል! ምድሪቱን ጥለን ሄደናልና፤ እነሱም ቤቶቻችንን አፈራርሰዋል።”+ +20 እናንተ ሴቶች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። ጆሯችሁ የአፉን ቃል ያዳምጥ። ሴቶች ልጆቻችሁን ይህን የሐዘን እንጉርጉሮ አስተምሯቸው፤አንዳችሁም ለሌላው ይህን ሙሾ አስተምሩ።+ +21 ሞት በመስኮቶቻችን በኩል ገብቷልና፤ልጆቹን ከጎዳናዎቹ፣ወጣቶቹንም ከአደባባዮቹ ለመውሰድወደማይደፈሩት ማማዎቻችን ገብቷል።’+ +22 እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ሲል አውጇል፦ “የሰዎች አስከሬን በምድር ላይ ልክ እንደ ፍግ ይወድቃል፤አጫጅ አጭዶ እንደተወውም እህል ይሆናል፤የሚሰበስበው አይኖርም።”’”+ +23 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጥበበኛው በጥበቡ አይኩራራ፤+ኃያሉ በኃያልነቱ አይኩራራ፤ባለጸጋውም በሀብቱ አይኩራራ።”+ +24 “ከዚህ ይልቅ የሚኩራራ በዚህ ነገር ይኩራራ፦ ስለ እኔ ጥልቅ ማስተዋልና እውቀት ያለው በመሆኑ+እንዲሁም በምድር ላይ ታማኝ ፍቅር የማሳየው፣ ደግሞም ፍትሕና ጽድቅ የማሰፍነው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ፤+በእነዚህ ነገሮች ደስ እሰኛለሁና”+ ይላል ይሖዋ። +25 “እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ቀን ይመጣል” ይላል ይሖዋ፣ “የተገረዘ ቢሆንም እንኳ ያልተገረዘውን ሁሉ ተጠያቂ አደርጋለሁ፤+ +26 ��ብፅን፣+ ይሁዳን፣+ ኤዶምን፣+ አሞናውያንን፣+ ሞዓብንና+ በሰሪሳራቸው* ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩትን በምድረ በዳ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ተጠያቂ አደርጋለሁ፤+ ብሔራት ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነው።”+ +27 በኢዮስያስ ልጅ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም* ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ይህ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ +2 “ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ለራስህ ማሰሪያና ቀንበር ሠርተህ አንገትህ ላይ አድርገው። +3 ከዚያም በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሴዴቅያስ በመጡት መልእክተኞች እጅ፣ ወደ ኤዶም+ ንጉሥ፣ ወደ ሞዓብ+ ንጉሥ፣ ወደ አሞናውያን+ ንጉሥ፣ ወደ ጢሮስ+ ንጉሥና ወደ ሲዶና+ ንጉሥ ላከው። +4 ለጌቶቻቸው ይህን ትእዛዝ እንዲያስተላልፉ ንገራቸው፦ “‘“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ለጌቶቻችሁ እንዲህ በሏቸው፦ +5 ‘ምድርን እንዲሁም በምድር ላይ ያሉትን ሰዎችና እንስሳት በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ የሠራሁት እኔ ነኝ፤ ለወደድኩትም ሰጥቼዋለሁ።+ +6 አሁንም እነዚህን ሁሉ አገሮች ለአገልጋዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤+ የዱር አራዊትም እንኳ እንዲገዙለት አድርጌአለሁ። +7 የእሱ መንግሥት የሚያበቃበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ+ ብሔራት ሁሉ እሱን፣ ልጁንና የልጅ ልጁን ያገለግላሉ፤ በዚያን ጊዜ ግን ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያቸው ያደርጉታል።’+ +8 “‘“‘የትኛውም ብሔር ወይም መንግሥት የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ለማገልገል ፈቃደኛ ባይሆን እንዲሁም አንገቱን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር ለማስገባት እንቢተኛ ቢሆን ያንን ብሔር በእሱ እጅ ፈጽሞ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍ፣+ በረሃብና በቸነፈር* እቀጣዋለሁ’ ይላል ይሖዋ። +9 “‘“‘ስለዚህ “የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም” የሚሏችሁን በመካከላችሁ ያሉትን ነቢያት፣ ሟርተኞች፣ ሕልም አላሚዎች፣ አስማተኞችና መተተኞች አትስሙ። +10 የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነውና፤ እነሱን የምትሰሙ ከሆነ ከምድራችሁ ተፈናቅላችሁ ወደ ሩቅ ቦታ ትወሰዳላችሁ፤ እኔም እበትናችኋለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ። +11 “‘“‘ሆኖም አንገቱን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር የሚያስገባንና እሱን የሚያገለግልን ብሔር ምድሪቱን እንዲያርስና በዚያ እንዲኖር በገዛ ምድሩ እንዲቀር* አደርገዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።”’” +12 ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም+ ተመሳሳይ ነገር ነገርኩት፤ እንዲህም አልኩት፦ “አንገታችሁን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር አስገቡ፤ እሱንና ሕዝቡንም አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።+ +13 ይሖዋ የባቢሎንን ንጉሥ የማያገለግልን ብሔር አስመልክቶ በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት፣ አንተም ሆንክ ሕዝብህ በሰይፍ፣+ በረሃብና+ በቸነፈር ለምን ታልቃላችሁ?+ +14 ‘የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሏችሁን ነቢያት ቃል አትስሙ፤+ ምክንያቱም የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነው።+ +15 “‘እኔ አልላክኋቸውምና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱ ግን በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እነሱን የምትሰሙ ከሆነ እናንተንና የሚተነብዩላችሁን ነቢያት እበትናለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።’”+ +16 ደግሞም ለካህናቱና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልኩ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“እነሆ፣ የይሖዋ ቤት ዕቃዎች ከባቢሎን በቅርቡ ይመለሳሉ!”+ እያሉ የሚተነብዩላችሁን የነቢያታችሁን ቃል አትስሙ፤ የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነውና።+ +17 እነሱን አትስሟቸው። የባቢሎንን ንጉሥ አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።+ ይህች ከተማ ለምን ትፈራርስ? +18 ሆኖም እነሱ ነቢያት ከሆኑና የይሖዋ ቃል እነሱ ጋር ካለ፣ በይሖዋ ቤ��፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤትና* በኢየሩሳሌም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይወሰዱ እስቲ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ይለምኑ።’ +19 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ዓምዶቹ፣+ ስለ ባሕሩ፣*+ ስለ ዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎቹና+ በዚህች ከተማ ስለቀሩት የተረፉ ዕቃዎች እንዲህ ይላልና፦ +20 እነዚህ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር የኢዮዓቄምን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ታላላቅ ሰዎች ሁሉ ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባጋዘበት ወቅት ሳይወስዳቸው የቀሩ ነገሮች ናቸው፤+ +21 አዎ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ በይሖዋ ቤት፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤትና* በኢየሩሳሌም ስለቀሩት ዕቃዎች እንዲህ ይላል፦ +22 ‘“ትኩረቴን ወደ እነሱ እስከማዞርበት ጊዜ ድረስ ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤+ በዚያም ይቆያሉ” ይላል ይሖዋ። “ከዚያ በኋላ አመጣቸዋለሁ፤ ወደዚህ ስፍራም እመልሳቸዋለሁ።”’”+ +47 ፈርዖን ጋዛን ከመውጋቱ በፊት ፍልስጤማውያንን+ በተመለከተ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው። +2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ከሰሜን ውኃ እየመጣ ነው። የሚያጥለቀልቅም ወንዝ ይሆናል። ምድሪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ፣ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ያጥለቀልቃል። ሰዎቹ ይጮኻሉ፤በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ። + 3 ከድንጉላ ፈረሶቹ ኃይለኛ የኮቴ ድምፅ፣ከሚንገጫገጩት የጦር ሠረገሎቹ ድምፅናከመንኮራኩሮቹ* የማያባራ ድምፅ የተነሳአባቶች እጃቸው ስለሚዝልልጆቻቸውን ለመርዳት እንኳ ወደ ኋላ አይዞሩም፤ + 4 ምክንያቱም የሚመጣው ቀን ፍልስጤማውያንን+ ሁሉ ያጠፋል፤በሕይወት ተርፈው ጢሮስንና+ ሲዶናን+ የሚረዱትን ሁሉ ያስወግዳል። ይሖዋ ፍልስጤማውያንንይኸውም ከካፍቶር*+ ደሴት የመጡ ቀሪዎችን ያጠፋልና። + 5 ጋዛ ትመለጣለች።* አስቀሎን ጸጥ ትላለች።+ ሸለቋሟ በሆነው ሜዳቸው* የምትኖሩ ቀሪዎች ሆይ፣ሰውነታችሁን የምትቆርጡት እስከ መቼ ነው?+ + 6 አንተ የይሖዋ ሰይፍ!+ የማታርፈው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ግባ። እረፍ፤ ጸጥ ብለህም ተቀመጥ። + 7 ይሖዋ ትእዛዝ ሰጥቶት እያለእንዴት አርፎ ሊቀመጥ ይችላል? ትእዛዝ የተሰጠው በአስቀሎንና በባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው፤+በዚያ መድቦታል።” +50 ይሖዋ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ስለ ባቢሎን+ ይኸውም ስለ ከለዳውያን ምድር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ + 2 “በብሔራት መካከል ይህን ተናገሩ፤ ደግሞም አውጁ። ምልክት* አቁሙ፤ ይህን አውጁ። ምንም ነገር አትደብቁ! እንዲህም በሉ፦ ‘ባቢሎን ተይዛለች።+ ቤል ኀፍረት ተከናንቧል።+ ሜሮዳክ በፍርሃት ርዷል። ምስሎቿ ተዋርደዋል። አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቿ* ተሸብረዋል።’ + 3 ከሰሜን አንድ ብሔር በእሷ ላይ ተነስቷልና።+ እሱም ምድሪቷን አስፈሪ ቦታ ያደርጋታል፤በእሷ ውስጥ የሚኖር ሰው የለም። ሰውም ሆነ እንስሳ ሸሽቷል፤አካባቢውን ለቀው ሄደዋል።” +4 “በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “የእስራኤል ሕዝብም ሆነ የይሁዳ ሕዝብ በአንድነት ይመጣሉ።+ እያለቀሱ ይሄዳሉ፤+ በአንድነትም አምላካቸውን ይሖዋን ይፈልጋሉ።+ +5 ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤+ ፊታቸውንም ወደዚያ አቅጣጫ አዙረው ‘ኑ፣ ከይሖዋ ጋር የማይረሳ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እንግባ’ ይላሉ።+ +6 ሕዝቤ የጠፉ በጎች መንጋ ሆኗል።+ የገዛ እረኞቻቸው እንዲባዝኑ አድርገዋቸዋል።+ ወደ ተራሮች ነዷቸው፤ እነሱም በየተራራውና በየኮረብታው ተቅበዘበዙ። ማረፊያ ቦታቸውን ረሱ። +7 ያገኟቸውም ሁሉ ዋጧቸው፤+ ጠላቶቻቸውም ‘በይሖዋ ይኸውም የጽድቅ መኖሪያና የአባቶቻቸው ተስፋ በሆነው በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠሩ እኛ በደለኞች አይደለንም’ ብለዋል።” + 8 “ከባቢሎን መካከል ወጥታችሁ ሽሹ፤ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፤+መንጋውንም እንደሚመሩ እንስሳት* ሁኑ። + 9 እነሆ፣ እኔ ከሰሜን ምድር የታላላቅ ብሔራትን ጉባኤ አስነስቼበባቢሎን ላይ አመጣባታለሁና።+ እነሱም እሷን ለመውጋት ይሰለፋሉ፤በዚያም በኩል ትያዛለች። ፍላጻዎቻቸው እንደ ተዋጊ ፍላጻዎች ናቸው፤ወላጆችን የወላድ መሃን ያደርጋሉ፤+ዓላማቸውን ሳይፈጽሙ አይመለሱም። +10 የከለዳውያን ምድር ትበዘበዛለች።+ የሚበዘብዟትም ሁሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይመዘብሯታል”+ ይላል ይሖዋ። +11 “እናንተ እጅግ ደስ ብሏችኋልና፤+የገዛ ርስቴን ስትመዘብሩ ሐሴት አድርጋችኋል።+ በለምለም ሣር ላይ እንዳለች ጊደር ፈንጭታችኋልና፤እንደ ድንጉላ ፈረሶችም አሽካክታችኋል። +12 እናታችሁ ለኀፍረት ተዳርጋለች።+ የወለደቻችሁም እጅግ አዝናለች። እነሆ፣ ከብሔራት ሁሉ ያነሰች፣ውኃ የሌለባት ምድረ በዳና በረሃ ሆናለች።+ +13 ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ ሰው የማይኖርባት ምድር ትሆናለች፤+ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናለች።+ በባቢሎን በኩል የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታታል፤ከደረሱባትም መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳ ያፏጫል።+ +14 እናንተ ደጋን የምትወጥሩ* ሁሉ፣ባቢሎንን ለመውጋት በዙሪያዋ ተሰለፉ። ፍላጻ ወርውሩባት፤ በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራች+አንድም ፍላጻ አታስቀሩ።+ +15 በዙሪያዋ ሁሉ ቀረርቶ አሰሙ። እጇን ሰጥታለች። ዓምዶቿ ወድቀዋል፤ ቅጥሮቿ ፈርሰዋል፤+ይህ የይሖዋ በቀል ነውና።+ እሷን ተበቀሏት። እንዳደረገችው አድርጉባት።+ +16 ዘር የሚዘራውንናበመከር ወቅት ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አስወግዱ።+ ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለሳል፤እያንዳንዱም ወደ ገዛ ምድሩ ይሸሻል።+ +17 “የእስራኤል ሕዝብ የባዘነ በግ ነው።+ እንዲባዝን ያደረጉት አንበሶች ናቸው።+ በመጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፤+ ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* አጥንቱን ቆረጣጠመው።+ +18 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በአሦር ንጉሥ ላይ እንዳደረግኩት ሁሉ በባቢሎን ንጉሥና በምድሩ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ +19 እስራኤልንም ወደ መሰማሪያው እመልሰዋለሁ፤+ እሱም በቀርሜሎስና በባሳን ይሰማራል፤+ በኤፍሬምና+ በጊልያድ+ ተራሮችም ላይ እስኪጠግብ ድረስ ይመገባል።’”* +20 “በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣“የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ሆኖም አይገኝም፤የይሁዳም ኃጢአት አይገኝም፤እንዲተርፉ ያደረግኳቸውን ይቅር እላቸዋለሁና።”+ +21 “በመረታይም ምድር ላይ ውጣ፤ በጰቆድ+ ነዋሪዎችም ላይ ተነሳ። ነዋሪዎቹ ይጨፍጨፉ፤ ሙሉ በሙሉም ይጥፉ”* ይላል ይሖዋ። “ያዘዝኩህንም ሁሉ አድርግ። +22 በምድሪቱ ላይ የጦርነትናየታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል። +23 የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ተቆረጠ! እንዴትስ ተሰበረ!+ ባቢሎን በብሔራት መካከል እንዴት መቀጣጫ ሆነች!+ +24 ባቢሎን ሆይ፣ በአንቺ ላይ ወጥመድ ዘርግቻለሁ፤ ደግሞም ተይዘሻል፤አንቺ ግን አልታወቀሽም። ተገኘሽ፤ እንዲሁም ተያዝሽ፤+የተቃወምሽው ይሖዋን ነውና። +25 ይሖዋ ግምጃ ቤቱን ከፍቷል፤የቁጣ የጦር መሣሪያዎቹንም ያወጣል።+ ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋበከለዳውያን ምድር የሚሠራው ሥራ አለና። +26 ከሩቅ ቦታ መጥታችሁ በእሷ ላይ ውጡ።+ ጎተራዎቿን ክፈቱ።+ እንደ እህል ክምር ከምሯት። ፈጽማችሁ አጥፏት።+ አንድም ሰው አታስቀሩላት። +27 ወይፈኖቿን ሁሉ እረዱ፤+ወደ እርድ ቦታ ይውረዱ። ቀናቸው ይኸውም የሚመረመሩበት ጊዜስለደረሰ ወዮላቸው! +28 የአምላካችንን የይሖዋን በቀል፣ስለ ቤተ መቅደሱ ሲል የወሰደውን የበቀል እርምጃ+ በጽዮን ለማወጅከባቢሎን ምድር የሚሸሹናአምልጠው የሚሄዱ ሰዎች ድምፅ ይሰማል። +29 ቀስተኞችን፣ ደጋን የሚወጥሩትንም* ሁሉበባቢሎን ላይ ጥሩ።+ በዙሪያዋም ስፈሩ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ። እንደ ሥራዋ መልሱላት።+ እሷ እንዳደረገችው ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉባት።+ በይሖዋ ላይ ይኸውም በእስራኤል ቅዱስ ላይየእብሪት ድርጊት ፈጽማለችና።+ +30 በመሆኑም ወጣቶቿ በአደባባዮቿ ይወድቃሉ፤+በዚያም ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይጠፋሉ”* ይላል ይሖዋ። +31 “አንቺ ዓመፀኛ፣+ እነሆ፣ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤“ቀንሽ ይኸውም አንቺን ተጠያቂ የማደርግበት ጊዜ ይመጣልና። +32 አንቺ ዓመፀኛ ተሰናክለሽ ትወድቂያለሽ፤የሚያነሳሽም አይኖርም።+ ከተሞችሽንም በእሳት አነዳለሁ፤በዙሪያሽም ያለውን ሁሉ ይበላል።” +33 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ ተጨቁነዋል፤ማርከው የወሰዷቸውም ሁሉ ጠፍረው ይዘዋቸዋል።+ እነሱን ለመልቀቅ ፈቃደኞች አልሆኑም።+ +34 ይሁንና የሚቤዣቸው ብርቱ ነው።+ ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።+ ለምድሪቱ እረፍት ለመስጠትና+የባቢሎንን ነዋሪዎች ለማሸበር+ያላንዳች ጥርጥር ይሟገትላቸዋል።”+ +35 “በከለዳውያን፣ በባቢሎን ነዋሪዎች፣ በመኳንንቷእንዲሁም በጥበበኞቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል” ይላል ይሖዋ።+ +36 “ከንቱ ነገር በሚናገሩ ሰዎች* ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም የሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ። በተዋጊዎቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም በሽብር ይዋጣሉ።+ +37 በፈረሶቻቸው፣ በጦር ሠረገሎቻቸውናበመካከሏ በሚኖሩ ድብልቅ ሕዝብ ሁሉ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤እነሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ።+ ውድ በሆኑ ሀብቶቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም ይዘረፋሉ።+ +38 ውኃዎቿ ይበከላሉ፤ ይደርቃሉም።+ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፤+አስፈሪ በሆኑት ራእዮቻቸው የተነሳ እንደ እብድ ያደርጋቸዋል። +39 ስለዚህ የበረሃ ፍጥረታት ከሚያላዝኑ እንስሳት ጋር ይኖራሉ፤በእሷም ውስጥ ሰጎኖች ይኖራሉ።+ ከዚህ በኋላ የሚኖርባት አይገኝም፤ከትውልድ እስከ ትውልድም ማንም አይቀመጥባትም።”+ +40 “አምላክ ሰዶምንና ገሞራን+ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉትን ከተሞች በደመሰሰ ጊዜ+ እንደሆነው ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።+ +41 እነሆ፣ አንድ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፤አንድ ታላቅ ብሔርና ታላላቅ ነገሥታት+ከምድር ዳርቻዎች ይነሳሉ።+ +42 ቀስትና ጦር ይይዛሉ።+ ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው።+ ፈረሶቻቸውን እየጋለቡ ሲመጡድምፃቸው እንደሚጮኽ ባሕር ነው።+ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣ አንቺን ለመውጋት በአንድ ልብ ሆነው ይሰለፉብሻል።+ +43 የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነሱ ወሬ ሰምቷል፤+እጆቹም ይዝለፈለፋሉ።+ ጭንቀት ይይዘዋል፤ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ይሠቃያል። +44 “እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርራቸዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ።+ እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው +45 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በባቢሎን ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና*+ በከለዳውያን ምድር ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ። ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም። ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።+ +46 ባቢሎን ስትያዝ ከሚሰማው ድምፅ የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤ከብሔራትም መካከል ጩኸት ይሰማል።”+ +13 ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሂድና ከተልባ እግር የተሠራ ቀበቶ ግዛ፤ በወገብህም ላይ ታጠ���ው፤ ሆኖም ፈጽሞ ውኃ አታስነካው።” +2 ስለዚህ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ቀበቶውን ገዝቼ ወገቤ ላይ ታጠቅኩት። +3 የይሖዋም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጣ፦ +4 “የገዛኸውንና የታጠቅከውን ቀበቶ ይዘህ ተነስ፤ ወደ ኤፍራጥስም ሄደህ በቋጥኝ ስንጥቅ ውስጥ ደብቀው።” +5 ስለዚህ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ሄጄ በኤፍራጥስ አጠገብ ደበቅኩት። +6 ሆኖም ከብዙ ቀናት በኋላ ይሖዋ “ተነስ፤ ወደ ኤፍራጥስ ሄደህ፣ በዚያ እንድትደብቀው ያዘዝኩህን ቀበቶ አምጣ” አለኝ። +7 እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፣ ቀበቶውን ከደበቅኩበት ቦታ ቆፍሬ አወጣሁ፤ ቀበቶው ተበላሽቶና ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ አገኘሁት። +8 ከዚያም የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፦ +9 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የይሁዳን ኩራትና የኢየሩሳሌምን እብሪት ልክ እንደዚሁ አጠፋዋለሁ።+ +10 ቃሌን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ያለው፣+ ግትር ሆኖ የገዛ ልቡን የሚከተለው+ እንዲሁም ሌሎች አማልክትን የሚከተለው፣ የሚያገለግለውና ለእነሱ የሚሰግደው ይህ ክፉ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ እንደሆነው እንደዚህ ቀበቶ ይሆናል።’ +11 ‘ቀበቶ በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፣ መላው የእስራኤል ቤትና መላው የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋር እንዲጣበቅ አደረግኩ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ይህም ሕዝቤ፣+ ስሜ፣+ ውዳሴዬና ውበቴ እንዲሆኑ ነው። እነሱ ግን አልታዘዙም።’+ +12 “አንተም ይህን መልእክት አክለህ ንገራቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ “እያንዳንዱ ትልቅ እንስራ በወይን ጠጅ ይሞላል” ይላል።’ እነሱም ‘እያንዳንዱ ትልቅ እንስራ በወይን ጠጅ እንደሚሞላ እኛ መች ጠፋን?’ ብለው ይመልሱልሃል። +13 በዚህ ጊዜ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ፣ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡትን ነገሥታት፣ ካህናቱንና ነቢያቱን እንዲሁም የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች በሙሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።+ +14 እነሱንም እርስ በርሳቸው፣ አባቶችንና ልጆችንም አጋጫለሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ምንም ዓይነት ርኅራኄም ሆነ አዘኔታ አላሳይም፤ ምሕረትም አላደርግላቸውም፤ እነሱን ከማጥፋት ምንም ነገር አያግደኝም።”’+ +15 ስሙ፤ ልብ በሉ። ትዕቢተኞች አትሁኑ፤ ይሖዋ ተናግሯልና። +16 ጨለማን ከማምጣቱ በፊትናጨለምለም ባሉት ተራሮች ላይ እግሮቻችሁ ከመደናቀፋቸው በፊትለአምላካችሁ ለይሖዋ ክብር ስጡ። እናንተ ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤እሱ ግን ፅልማሞትን ያመጣል፤ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይለውጠዋል።+ +17 ለመስማት አሻፈረን ካላችሁ፣በኩራታችሁ የተነሳ በስውር አለቅሳለሁ።* የይሖዋ መንጋ+ በምርኮ ስለተወሰደእንባዬ እንደ ጎርፍ ይወርዳል፤ ዓይኔም በእንባ ይታጠባል።+ +18 ንጉሡንና የንጉሡን እናት*+ እንዲህ በላቸው፦ ‘የሚያምረው አክሊላችሁ ከራሳችሁ ላይ ስለሚወድቅ፣ዝቅ ባለ ስፍራ ተቀመጡ።’ +19 የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፤* የሚከፍታቸውም የለም። መላው ይሁዳ በግዞት ተወስዷል፤ ሙሉ በሙሉም ተግዟል።+ +20 ዓይንሽን አንስተሽ ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቺ።+ ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣ ያማሩት በጎችሽ የት አሉ?+ +21 ከመጀመሪያው አንስቶ የተወዳጀሻቸው የቅርብ ጓደኞችሽአንቺን ለመቅጣት ሲነሱ ምን ትዪ ይሆን?+ ልክ እንደምትወልድ ሴት ምጥ አይዝሽም?+ +22 በልብሽም ‘እነዚህ ነገሮች የደረሱብኝ ለምንድን ነው?’ በምትይበት ጊዜ፣+ ቀሚስሽን የተገፈፍሽውና+ ተረከዝሽ ለሥቃይ የተዳረገው በፈጸምሽው ታላቅ በደል የተነሳ መሆኑን ልታውቂ ይገባል። +23 ኢትዮጵያዊ* መልኩን፣ ነብርስ ዥጉርጉርነቱን መለወጥ ይችላል?+ እንዲህ ማድረግ የሚችል ከሆነ፣ክፉ ነገር መሥራት የለመዳችሁት እናንተም መልካም ማድረግ ትችላላችሁ ማለት ነው። +24 ስለዚህ የበረሃ ���ፋስ ይዞት እንደሚሄድ ገለባ እበትናቸዋለሁ።+ +25 ይህ ዕጣሽ፣ ሰፍሬም የሰጠሁሽ ድርሻሽ ነው” ይላል ይሖዋ፤“ምክንያቱም እኔን ረስተሽኛል፤+ በሐሰትም ትታመኛለሽ።+ +26 በመሆኑም ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ እገልባለሁ፤ኀፍረትሽም ይታያል፤+ +27 የፈጸምሽው ምንዝር፣+ በፍትወት ማሽካካትሽ፣ጸያፍ* የሆነው ዝሙት አዳሪነትሽ ይገለጣል። አስጸያፊ ምግባርሽንበኮረብቶቹና በሜዳው ላይ አይቼአለሁ።+ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ወዮልሽ! ርኩስ ሆነሽ የምትኖሪው እስከ መቼ ድረስ ነው?”+ +5 በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ወዲያና ወዲህ ተመላለሱ። ዙሪያውን ተመልከቱ፤ ልብ በሉ። ፍትሕን የሚያደርግ፣+ታማኝ መሆን የሚሻ ሰውም ታገኙ እንደሆነበአደባባዮቿ ፈልጉ፤እኔም ይቅር እላታለሁ። + 2 “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!” ቢሉም የሚምሉት ሐሰት ለሆነ ነገር ነው።+ + 3 ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖችህ የሚመለከቱት ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት አይደለም?+ አንተ መተሃቸዋል፤ በእነሱ ላይ ግን ያመጣው ለውጥ የለም።* አንተ አድቅቀሃቸዋል፤ እነሱ ግን አልታረሙም።+ ፊታቸውን ከዓለት ይልቅ አጠነከሩ፤+ለመመለስም አሻፈረን አሉ።+ + 4 እኔ ግን ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ “በእርግጥ እነዚህ ምስኪኖች ናቸው። የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድ ባለማወቃቸውየሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ። + 5 ታዋቂ ወደሆኑት ሰዎች ሄጄ አነጋግራቸዋለሁ፤እነሱ የይሖዋን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ፍርድአስተውለው መሆን አለበትና።+ ነገር ግን ሁሉም ቀንበሩን ሰብረዋል፤ማሰሪያውንም በጥሰዋል።” + 6 ስለዚህ ከጫካ የወጣ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፤የበረሃ ተኩላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ነብር በከተሞቻቸው አቅራቢያ አድብቶ ይጠብቃል። ከዚያ የሚወጣውንም ሁሉ ይዘነጣጥላል። በደላቸው በዝቷልና፤የክህደት ሥራቸው ተበራክቷል።+ + 7 ታዲያ ይህን ነገር እንዴት ይቅር እልሻለሁ? ወንዶች ልጆችሽ ትተውኛል፤አምላክ ባልሆነውም ይምላሉ።+ እኔም የሚያስፈልጋቸውን ነገር አሟላሁላቸው፤እነሱ ግን ምንዝር መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤ወደ ዝሙት አዳሪ ቤትም እየተንጋጉ ሄዱ። + 8 እንደሚቅበጠበጡ፣ ብርቱ ፈረሶች ናቸው፤እያንዳንዱ የሌላውን ሰው ሚስት ተከትሎ ያሽካካል።+ + 9 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ። “እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም?”+ +10 “የወይን እርሻዋን እርከኖች ሄዳችሁ አበላሹ፤ሆኖም ሙሉ በሙሉ አታጥፉት።+ የተንሰራፉ ቅርንጫፎቿን አስወግዱ፤የይሖዋ አይደሉምና። +11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤትበእኔ ላይ ከፍተኛ ክህደት ፈጽመዋልና” ይላል ይሖዋ።+ +12 “እነሱ ይሖዋን ክደዋል፤‘እሱ ምንም ነገር አያደርግም።*+ በእኛ ላይ ምንም ጥፋት አይመጣም፤ሰይፍም ሆነ ረሃብ አናይም’ ይላሉ።+ +13 ነቢያቱ በነፋስ የተሞሉ ናቸው፤ቃሉም* በውስጣቸው የለም። ይህ በእነሱ ላይ ይድረስ!” +14 ስለዚህ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነዚህ ሰዎች እንዲህ ስለሚሉ፣ቃሌን በአፋችሁ ውስጥ እሳት አደርጋለሁ፤+እንጨቱ ደግሞ ይህ ሕዝብ ነው፤እሳቱም ይበላቸዋል።”+ +15 “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሩቅ ቦታ ያለን ብሔር አመጣባችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ። “እሱም ለረጅም ጊዜ የኖረ ብሔር ነው። ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረ፣ቋንቋውን የማታውቀውናንግግሩን የማትረዳው ብሔር ነው።+ +16 የፍላጻ ኮሮጇቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፤ሁሉም ተዋጊዎች ናቸው። +17 እነሱ አዝመራህንና ምግብህን ይበላሉ።+ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይበላሉ። መንጎችህንና ከብቶችህን ይበላሉ። የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ይበላሉ። የምትታመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችህን በሰይፍ ያወድማሉ።” +18 “ይሁንና በእነዚያ ቀናት እንኳ” ይላል ይሖዋ፣ “ሙሉ በሙሉ አላጠፋችሁም።+ +19 ‘አምላካችን ይሖዋ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገብን ለምንድን ነው?’ ብለው ሲጠይቁ ደግሞ ‘በምድራችሁ ላይ ባዕድ አምላክን ለማገልገል ስትሉ እኔን እንደተዋችሁኝ ሁሉ የራሳችሁ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።”+ +20 ይህን በያዕቆብ ቤት ተናገሩ፤በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ አውጁ፦ +21 “እናንተ ሞኞችና የማመዛዘን ችሎታ የጎደላችሁ ሰዎች* ይህን ስሙ፦+ ዓይን አላቸው ግን አያዩም፤+ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም።+ +22 ‘እኔን አትፈሩም?’ ይላል ይሖዋ፤‘በፊቴስ ልትሸበሩ አይገባም? ውኃው አልፎ እንዳይሄድ፣ በማይሻር ድንጋጌአሸዋውን የባሕሩ ወሰን አድርጌ የሠራሁት እኔ ነኝ። ሞገዶቹ ቢናወጡም ጥሰው መሄድ አይችሉም፤ቢያስገመግሙም ከዚያ አልፈው መሄድ አይችሉም።+ +23 ነገር ግን ይህ ሕዝብ ልቡ ግትርና ዓመፀኛ ነው፤ጀርባቸውን ሰጥተው በራሳቸው መንገድ ሄደዋል።+ +24 እነሱም በልባቸው “እንግዲያው፣ ዝናቡን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብበወቅቱ የሚሰጠንን፣የተወሰኑትን የአዝመራ ሳምንታት የሚጠብቅልንንአምላካችንን ይሖዋን እንፍራ” አላሉም።+ +25 የገዛ ራሳችሁ በደል እነዚህ ነገሮች እንዲቀሩ አድርጓል፤የገዛ ኃጢአታችሁ መልካም የሆነ ነገር አሳጥቷችኋል።+ +26 በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና። አድብተው እንደሚጠብቁ ወፍ አዳኞች፣ በዓይነ ቁራኛ ይመለከታሉ። ገዳይ ወጥመድ ይዘረጋሉ። ሰዎችን ያጠምዳሉ። +27 በወፎች እንደተሞላ የወፍ ጎጆ፣ቤቶቻቸው በማታለያ የተሞሉ ናቸው።+ ኃያላንና ሀብታም የሆኑት ለዚህ ነው። +28 ወፍረዋል፤ ቆዳቸውም ለስልሷል፤በክፋት ተሞልተዋል። ለራሳቸው ስኬት ሲያስቡአባት ለሌለው ልጅ አይሟገቱም፤+ድሆችንም ፍትሕ ይነፍጋሉ።’”+ +29 “ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ። “እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል* አይገባም? +30 በምድሪቱ ላይ የሚያስደነግጥና የሚያሰቅቅ ነገር ተከስቷል፦ +31 ነቢያቱ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤+ካህናቱም በራሳቸው ሥልጣን በኃይል ይገዛሉ። የገዛ ሕዝቤም ይህን ወዶታል።+ ይሁንና መጨረሻው ሲመጣ ምን ታደርጉ ይሆን?” +21 ንጉሥ ሴዴቅያስ+ የማልኪያህን ልጅ ጳስኮርንና+ የማአሴያህን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን+ ወደ ኤርምያስ በላካቸው ጊዜ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ እነሱም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ +2 “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ሊወጋን ስለሆነ+ እባክህ፣ ስለ እኛ ይሖዋን ጠይቅልን። ንጉሡ ከእኛ እንዲመለስ ይሖዋ እንደቀድሞው ሁሉ አሁንም ተአምር ይፈጽምልን ይሆናል።”+ +3 ኤርምያስ እንዲህ አላቸው፦ “ሴዴቅያስን እንዲህ በሉት፦ +4 ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎንን ንጉሥና ከቅጥሩ ውጭ የከበቧችሁን ከለዳውያንን ለመውጋት የምትጠቀሙባቸውን በገዛ እጃችሁ ላይ ያሉትን የጦር መሣሪያዎች በእናንተው ላይ አዞራለሁ።+ በዚህችም ከተማ መሃል እሰበስባቸዋለሁ። +5 እኔ ራሴ በተዘረጋች እጅና በኃያል ክንድ እንዲሁም በመዓትና በታላቅ ቁጣ እዋጋችኋለሁ።+ +6 የዚህችን ከተማ ነዋሪዎች፣ ሰውንም ሆነ እንስሳን እመታለሁ። እነሱም በታላቅ ቸነፈር* ይሞታሉ።”’+ +7 “‘“ከዚያም በኋላ” ይላል ይሖዋ፣ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣ አገልጋዮቹን እንዲሁም ከቸነፈር፣ ከሰይፍና ከረሃብ ተርፎ በከተማዋ ውስጥ የሚቀረውን ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ፣ በጠላቶቻቸው እጅና ሕይወታቸውን ለማጥፋት በሚሹ* ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ እሱም በሰይፍ ይመታቸዋል። +8 “ደግሞም ይህን ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አድርጌአለሁ። +9 በዚህች ከተማ የሚቀሩ ሰዎች በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ይሞታሉ። ይሁንና ከከተማዋ ወጥቶ፣ ለከበቧችሁ ከለዳውያን እጁን የሚሰጥ በሕይወት ይኖራል፤ ሕይወቱም* እንደ ምርኮ ትሆንለታለች።”’*+ +10 “‘“መልካም ነገር ሳይሆን ጥፋት ለማምጣት ፊቴን ወደዚህች ከተማ አዙሬአለሁና”+ ይላል ይሖዋ። “ለባቢሎን ንጉሥ ትሰጣለች፤+ እሱም በእሳት ያቃጥላታል።”+ +11 “‘የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ፦ የይሖዋን ቃል ስሙ። +12 የዳዊት ቤት ሆይ፣ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከክፉ ድርጊታችሁ የተነሳቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይቀጣጠልና+ማንም ሊያጠፋው እስከማይችል ድረስ እንዳይነድበየማለዳው ለፍትሕ ቁሙ፤የተዘረፈውንም ሰው ከአጭበርባሪው እጅ ታደጉ።”’+ +13 ‘አንቺ በሸለቆ ውስጥ* የምትኖሪ፣ በደልዳላው መሬት ላይ የተቀመጥሽ ዓለት ሆይ፣እነሆ፣ እኔ በአንቺ ላይ እነሳለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘“በእኛ ላይ ማን ይወርዳል? ደግሞስ መኖሪያዎቻችንን ማን ይወራል?” የምትሉ ይህን እወቁ፤ +14 እንደ ሥራችሁ መጠንተጠያቂ አደርጋችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘ጫካዋን በእሳት አነዳለሁ፤እሳቱም በዙሪያዋ ያለውን ነገር ሁሉ ይበላል።’”+ +15 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙ እንኳ+ ለዚህ ሕዝብ አልራራም።* ከፊቴ አስወጣቸው። ይሂዱ። +2 እነሱም ‘ወዴት እንሂድ?’ ቢሉህ፣ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ በመቅሰፍት እንዲሞት ይሂድ፤ ሰይፍ የሚገባው ሁሉ በሰይፍ ይሙት፤+ ረሃብ የሚገባው ሁሉ በረሃብ ይሙት፤ በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ደግሞ ተማርኮ ይወሰድ!”’+ +3 “‘እኔም አራት ዓይነት ጥፋት* አዝባቸዋለሁ’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱም፦ ለመግደል ሰይፍ፣ ጎትቶ ለመውሰድ ውሾች እንዲሁም ለመሰልቀጥና ለማጥፋት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ናቸው።+ +4 የይሁዳ ንጉሥ፣ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ከፈጸመው ድርጊት የተነሳ+ ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ።+ + 5 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ማን ይራራልሻል?ማንስ ያዝንልሻል?ደህንነትሽንስ ማን ጎራ ብሎ ይጠይቃል?’ + 6 ‘ትተሽኛል’ ይላል ይሖዋ።+ ‘አሁንም ጀርባሽን ሰጥተሽኛል።*+ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጠፋሻለሁ።+ ለአንቺ አዘኔታ ማሳየት* ታክቶኛል። + 7 በምድሪቱ በሮች፣ በመንሽ እበትናቸዋለሁ። የወላድ መሃን አደርጋቸዋለሁ።+ ሕዝቤን አጠፋዋለሁ፤ከመንገዱ ለመመለስ አሻፈረኝ ብሏልና።+ + 8 መበለቶቻቸው በፊቴ ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይበዛሉ። በእነሱ ይኸውም በእናቶችና በወጣት ወንዶች ላይ በቀትር አጥፊ አመጣለሁ። ከባድ ጭንቀትና ሽብር በድንገት አመጣባቸዋለሁ። + 9 ሰባት ልጆች የወለደችው ሴት ተዝለፍልፋለች፤ትንፋሽ አጥሯት* ታጣጥራለች። ገና ቀን ሳለ ፀሐይዋ ጠልቃለች፤ይህም ኀፍረትና ውርደት አስከትሎባታል።’* ‘ከእነሱ መካከል የተረፉትንም ጥቂት ሰዎችበጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።”+ +10 እናቴ ሆይ፣ ወዮልኝ!በምድሪቱ ሁሉ ላይ የጠብና የጭቅጭቅ መንስኤ የሆንኩትን እኔን ወልደሻልና።+ እኔ ለማንም አላበደርኩም፤ ከማንም አልተበደርኩም፤ይሁንና ሁሉም ይረግሙኛል። +11 ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “እኔ በእርግጥ ለአንተ መልካም ነገር አደርግልሃለሁ፤በጥፋትና በጭንቀት ጊዜበአንተና በጠላት መካከል ጣልቃ ገብቼ እረዳሃለሁ። +12 ሰው ብረትን ይኸውም ከሰሜን የመጣን ብረትናመዳብን መሰባበር ይችላል? +13 በመላው ክልልህ ከፈጸምከው ኃጢአት ሁሉ የተነሳንብረትህንና ውድ ሀብትህን፣ ያለዋጋ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።+ +14 እነዚህን ነገሮች ጠላቶችህ ወደማታውቀው አገር እንዲወስዷቸውአሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ ቁጣዬ እሳት አስነስቷልና፤በእናንተም ላይ እየነደደ ነው።”+ +15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ታውቃለህ፤አስበኝ፤ ትኩረትህንም ወደ እኔ አዙር። አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ።+ ቁጣህን በማዘግየት እንድጠፋ አታድርግ።* ይህን ነቀፋ የተሸከምኩት ለአንተ ስል እንደሆነ እወቅ።+ +16 ቃልህ ተገኝቷል፤ እኔም በልቼዋለሁ፤+የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ በስምህ ተጠርቻለሁና፣ቃልህ ሐሴት፣ ለልቤም ደስታ ሆነልኝ። +17 ፈንጠዝያ ከሚወዱ ሰዎች ጋር አልተቀመጥኩም፤ ከእነሱም ጋር ሐሴት አላደረግኩም።+ እጅህ በእኔ ላይ ስለሆነ ብቻዬን እቀመጣለሁ፤በቁጣ* ሞልተኸኛልና።+ +18 ሕመሜ ሥር የሰደደው፣ ቁስሌም የማይፈወስ የሆነው ለምንድን ነው? ጨርሶ አልድን ብሏል። እምነት ሊጣልበት እንደማይችልየሚያታልል የውኃ ምንጭ ትሆንብኛለህ? +19 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ብትመለስ፣ እኔም ወደ ቀድሞው ሁኔታህ እመልስሃለሁ፤በፊቴም ትቆማለህ። ውድ የሆነውን ነገር ከማይረባው ነገር ብትለይ፣እንደ አፌ* ትሆናለህ። እነሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂአንተ ወደ እነሱ አትመለስም።” +20 “ለዚህ ሕዝብ ጠንካራ የመዳብ ቅጥር አደርግሃለሁ።+ እነሱ በእርግጥ ይዋጉሃል፤ሆኖም በአንተ ላይ አያይሉም፤*+እኔ አንተን ለማዳንና ለመታደግ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ። +21 “ከክፉዎች እጅ እታደግሃለሁ፤ከጨካኞችም መዳፍ እቤዥሃለሁ።” +22 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት* ወርደህ ይህን መልእክት ተናገር። +2 እንዲህ በል፦ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የተቀመጥከው የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፣ አንተም ሆንክ አገልጋዮችህ እንዲሁም በእነዚህ በሮች የሚገባው ሕዝብህ የይሖዋን ቃል ስሙ። +3 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለፍትሕና ለጽድቅ ቁሙ። የተዘረፈውን ሰው ከአጭበርባሪው እጅ ታደጉ። ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አታንገላቱ፤ አባት የሌለውን ልጅ* ወይም መበለቲቱን አትበድሉ።+ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።+ +4 ይህን ቃል በሚገባ ብትጠብቁ፣ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታት+ በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው ከአገልጋዮቻቸውና ከሕዝቦቻቸው ጋር በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ።”’+ +5 “‘ይህን ቃል ባትታዘዙ ግን’ ይላል ይሖዋ፣ ‘ይህ ቤት እንደሚወድም በራሴ እምላለሁ።’+ +6 “ይሖዋ የይሁዳን ንጉሥ ቤት አስመልክቶ እንዲህ ይላልና፦‘አንተ ለእኔ እንደ ጊልያድናእንደ ሊባኖስ ተራራ አናት ነህ። ይሁንና ምድረ በዳ አደርግሃለሁ፤ከተሞችህን በሙሉ ሰው አልባ አደርጋቸዋለሁ።+ + 7 በአንተ ላይ ጥፋት የሚያደርሱ ሰዎችን፣እያንዳንዳቸውን ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር እሾማለሁ።*+ ምርጥ የሆኑ አርዘ ሊባኖሶችህን ይቆርጣሉ፤ለእሳትም ይማግዷቸዋል።+ +8 “‘ብዙ ብሔራትም በዚህች ከተማ በኩል ያልፋሉ፤ እርስ በርሳቸውም “ይሖዋ በዚህች ታላቅ ከተማ ላይ ይህን ያደረገው ለምንድን ነው?” ይባባላሉ።+ +9 እነሱም እንዲህ ብለው ይመልሳሉ፦ “የአምላካቸውን የይሖዋን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለሰገዱና እነሱን ስላገለገሉ ነው።”’+ +10 ለሞተው ሰው አታልቅሱ፤ደግሞም አትዘኑለት። ይልቁንም በግዞት ለተወሰደው አምርራችሁ አልቅሱ፤ከእንግዲህ የትውልድ አገሩን ለማየት አይመለስምና። +11 “በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለነገሠው፣ ከዚህም ቦታ ስለሄደው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ+ ስለ ሻሉም*+ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከእንግዲህ ወደዚያ አይመለስም። +12 በግዞት በተወሰደበት በዚያው ስፍራ ይሞታል እንጂ ይህን ምድር ዳግመኛ አያይም።’+ +13 ጽድቅን በሚጻረር መንገድ ቤቱን ለሚገነባ፣ፍትሕን በማዛባት ደርብ ለሚሠራ፣የወገኑን ጉልበት እንዲሁ ለሚበዘብዝናደሞዙን ለማይከፍለው ወዮለት፤+ +14 ‘ለራሴ ሰፊ ቤትናየተንጣለለ ደርብ እገነባለሁ። መስኮቶች እንዲኖረው አደርጋለሁ፤በአርዘ ሊባኖስም እለብጠዋለሁ፤ ቀይ ቀለምም እቀባዋለሁ’ ለሚል ወዮለት! +15 በአርዘ ሊባኖስ እንጨት ከሌሎች ስለምትበልጥ በንግሥና የምትቀጥል ይመስልሃል? አባትህም ቢሆን ይበላና ይጠጣ ነበር፤ሆኖም ለፍትሕና ለጽድቅ ቆሟል፤+እንዲህ በማድረጉም ተሳክቶለት ነበር። +16 ለተጎሳቆለው ሰውና ለድሃው ተሟግቷል፤ስለዚህ መልካም ሆኖለት ነበር። ‘እኔን ማወቅ ማለት ይህ አይደለም?’ ይላል ይሖዋ። +17 ‘አንተ ግን ዓይንህና ልብህ ያረፈው አላግባብ በምታገኘው ጥቅም፣ንጹሕ ደም በማፍሰስእንዲሁም በማጭበርበርና በቅሚያ ላይ ብቻ ነው።’ +18 “ስለዚህ ይሖዋ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮዓቄም+ እንዲህ ይላል፦‘“ወይኔ ወንድሜን! ወይኔ እህቴን!” ብለው አያለቅሱለትም። “ወይኔ ጌታዬን! ክብሩ ሁሉ እንዲህ ይጥፋ!” ብለው አያለቅሱለትም። +19 አህያ እንደሚቀበረው ይቀበራል፤+ከኢየሩሳሌም በሮች ውጭጎትተው ይጥሉታል።’+ +20 ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ፤በባሳን ድምፅሽን አሰሚ፤በአባሪም+ ሆነሽ ጩኺ፤አጥብቀው የሚወዱሽ ሁሉ ደቀዋልና።+ +21 ተማምነሽ በተቀመጥሽበት ጊዜ አነጋገርኩሽ። አንቺ ግን ‘አልታዘዝም’ አልሽ።+ ከልጅነትሽ ጀምሮ ይህን ጎዳና ተከተልሽ፤ቃሌን አልታዘዝሽምና።+ +22 ነፋስ እረኞችሽን በሙሉ ይነዳቸዋል፤+አጥብቀው የሚወዱሽም በግዞት ይወሰዳሉ። በዚያን ጊዜ ከሚደርስብሽ ጥፋት ሁሉ የተነሳ ታፍሪያለሽ፤ ውርደትም ትከናነቢያለሽ። +23 አንቺ በሊባኖስ የምትኖሪ፣+በአርዘ ሊባኖሶች መካከል ተደላድለሽ የተቀመጥሽ፣+ጣር ሲይዝሽ፣አዎ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ጭንቅ* ሲይዝሽ ምንኛ ታቃስቺ ይሆን!”+ +24 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ይሖዋ፣ ‘አንተ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮዓቄም+ ልጅ፣ ኮንያሁ*+ በቀኝ እጄ እንዳለ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ ከዚያ አውጥቼ እጥልሃለሁ! +25 ሕይወትህን ለማጥፋት በሚሹ* ሰዎች እጅ፣ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅና በከለዳውያን እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።+ +26 አንተንና የወለደችህን እናትህን ወዳልተወለዳችሁበት፣ ወደ ሌላ አገር እወረውራችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ። +27 ወደሚናፍቋትም ምድር* ፈጽሞ አይመለሱም።+ +28 ኮንያሁ የተባለው ይህ ሰው የተናቀና የተሰበረ ገንቦ፣ማንም የማይፈልገው የሸክላ ዕቃ ነው? እሱም ሆነ ዘሮቹ ወደማያውቋት ምድር የተወረወሩትናየተጣሉት ለምንድን ነው?’+ +29 ምድር፣* ምድር፣ አንቺ ምድር ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስሚ። +30 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ሰው፣ ልጅ እንደሌለውናበሕይወት ዘመኑ* ሁሉ ምንም እንደማይሳካለት አድርጋችሁ መዝግቡት፤ከዘሮቹ መካከል አንዱም እንኳ አይሳካለትምና፤በዳዊት ዙፋን ላይ አይቀመጥም እንዲሁም ይሁዳን ዳግመኛ አይገዛም።’”+ +42 ከዚያም የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ፣ የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣+ የሆሻያህ ልጅ የዛንያህ* እና ሕዝቡ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ቀርበው +2 ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “ሞገስ ለማግኘት የምናቀርበውን ልመና እባክህ ስማ፤ ስለ እኛና ስለ እነዚህ ቀሪዎች ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ጸልይ፤ ይኸው እንደምታየው ከብዙዎች መካከል የቀረነው ጥቂቶች ብቻ ነን።+ +3 አምላክህ ይሖዋ በየት መሄድ እንደሚገባንና ምን ማድረግ እንዳለብን ይንገረን።” +4 ነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እሺ፣ ሰምቻችኋለሁ፤ በጠየቃችሁኝ መሠረት ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ እጸልያለሁ��� ይሖዋ የሚመልስላችሁንም ቃል ሁሉ እነግራችኋለሁ። አንድም ቃል አላስቀርባችሁም።” +5 እነሱም ለኤርምያስ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “አምላክህ ይሖዋ በአንተ በኩል እንዳዘዘን ባናደርግ፣ ይሖዋ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምሥክር ይሁን። +6 የአምላካችንን የይሖዋን ቃል በመታዘዝ መልካም እንዲሆንልን፣ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ ወደ እሱ የምንልክህ አምላካችን ይሖዋ የሚለውን ሁሉ እንፈጽማለን።” +7 ከአሥር ቀን በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። +8 ስለዚህ የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን፣ ከእሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡን ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ድረስ ጠራ።+ +9 እንዲህም አላቸው፦ “ሞገስ ለማግኘት ያሰማችሁትን ልመና በፊቱ እንዳቀርብ ወደ እሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ +10 ‘በእርግጥ በዚህች ምድር ላይ የምትኖሩ ከሆነ፣ እገነባችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም፤ በእናንተ ላይ ባመጣሁት ጥፋት እጸጸታለሁና።*+ +11 ከምትፈሩት ከባቢሎን ንጉሥ የተነሳ አትሸበሩ።’+ “‘ከእሱ የተነሳ አትፍሩ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘አድናችሁና ከእጁ እታደጋችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና። +12 ምሕረት አደርግላችኋለሁ፤+ እሱም ምሕረት ያደርግላችኋል፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም ይመልሳችኋል። +13 “‘እናንተ ግን “አይሆንም፤ በዚህች ምድር ላይ አንኖርም!” ብትሉና የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ባትታዘዙ፣ +14 ደግሞም “አይሆንም፤ ጦርነት ወደማናይበት፣ የቀንደ መለከት ድምፅ ወደማንሰማበት ወይም ምግብ አጥተን ወደማንራብበት ወደ ግብፅ ምድር እንሄዳለን፤+ በዚያም እንኖራለን” ብትሉ፣ +15 እናንተ የይሁዳ ቀሪዎች ሆይ፣ እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስሙ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደ ግብፅ ለመግባት ቆርጣችሁ ከተነሳችሁና በዚያ ለመኖር* ከሄዳችሁ፣ +16 የፈራችሁት ሰይፍ ራሱ በግብፅ ምድር ያገኛችኋል፤ የፈራችሁትም ረሃብ ወደ ግብፅ ተከትሏችሁ ይሄዳል፤ በዚያም ትሞታላችሁ።+ +17 በዚያ ለመኖር ሲሉ ወደ ግብፅ ለመሄድ ቆርጠው የተነሱ ሰዎች ሁሉ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር* ይሞታሉ። በእነሱ ላይ ከማመጣው ጥፋት ከመካከላቸው የሚተርፍ ወይም የሚያመልጥ አይኖርም።”’ +18 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ወደ ግብፅ ከሄዳችሁ፣ ቁጣዬና ንዴቴ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ እንደወረደ ሁሉ+ በእናንተም ላይ ቁጣዬ ይወርዳል፤ እናንተም ለእርግማን፣ ለውርደትና ለነቀፋ ትዳረጋላችሁ፤ መቀጣጫም ትሆናላችሁ፤+ ይህን ቦታም ዳግመኛ አታዩትም።’ +19 “የይሁዳ ቀሪዎች ሆይ፣ ይሖዋ በእናንተ ላይ ተናግሯል። ወደ ግብፅ አትሂዱ። ዛሬ እንዳስጠነቀቅኳችሁ በእርግጥ እወቁ፤ +20 በደላችሁም ሕይወታችሁን* እንደሚያሳጣችሁ እወቁ። እንዲህ ስትሉ ወደ ይሖዋ አምላካችሁ ልካችሁኝ ነበርና፦ ‘ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ስለ እኛ ጸልይ፤ አምላካችን ይሖዋም የሚለውን ነገር ሁሉ ንገረን፤ እኛም የተባልነውን እናደርጋለን።’+ +21 እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ እናንተ ግን የአምላካችሁን የይሖዋን ቃልም ሆነ ወደ እናንተ ልኮኝ የነገርኳችሁን ሁሉ አትታዘዙም።+ +22 ስለዚህ ሄዳችሁ ልትኖሩበት በፈለጋችሁት ቦታ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር እንደምትሞቱ በእርግጥ እወቁ።”+ +39 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾርና* መላው ሠራዊቱ መጥተው ኢየሩሳሌምን ከበቧት።+ +2 በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በ11ኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን የከተማዋን ቅጥር ነደሉ።+ +3 የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ይኸውም ሳምጋሩ ኔርጋልሻሬጸር፣ ራብሳሪስ የሆነው ነቦሳርሰኪም፣* ራብማግ* የሆነው ኔርጋልሻሬጸርና የቀሩት የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ገብተው በመካከለኛው በር አጠገብ ተቀመጡ።+ +4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ፣ በንጉሡ የአትክልት ቦታ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ከከተማዋ ወጥተው ሸሹ፤+ ወደ አረባ የሚወስደውንም መንገድ ተከትለው ሄዱ።+ +5 የከለዳውያን ሠራዊት ግን አሳደዳቸው፤ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት።+ ከያዙት በኋላ በሃማት+ ምድር በሪብላ+ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነጾር* አመጡት፤ እሱም በዚያ ፈረደበት። +6 የባቢሎን ንጉሥ በሪብላ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አሳረዳቸው፤ በተጨማሪም የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ታላላቅ ሰዎች ሁሉ አሳረደ።+ +7 የሴዴቅያስንም ዓይን አሳወረ፤ ከዚያም ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በመዳብ የእግር ብረት አሰረው።+ +8 ከለዳውያንም የንጉሡን ቤትና* የሕዝቡን ቤቶች አቃጠሉ፤+ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች አፈረሱ።+ +9 የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን+ በከተማዋ ውስጥ የቀሩትን በሕይወት የተረፉ ሰዎችና ከድተው ለእሱ እጃቸውን የሰጡትን ሰዎች እንዲሁም የቀሩትን ሁሉ በግዞት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው። +10 ሆኖም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ምንም ነገር ያልነበራቸውን አንዳንድ ያጡ የነጡ ድሆች በይሁዳ ምድር እንዲኖሩ ተዋቸው። ደግሞም በዚያ ቀን የወይን እርሻዎችና የሚያርሱት የእርሻ መሬት* ሰጣቸው።+ +11 በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ኤርምያስን አስመልክቶ የዘቦች አለቃ ለሆነው ለናቡዛራዳን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦ +12 “ወስደህ የሚያስፈልገውን እንክብካቤ አድርግለት፤ ክፉ ነገር አታድርግበት፤ የሚጠይቅህንም ነገር ሁሉ አድርግለት።”+ +13 በመሆኑም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን፣ ራብሳሪስ* የሆነው ናቡሻዝባን፣ ራብማግ* የሆነው ኔርጋልሻሬጸር እንዲሁም የባቢሎን ንጉሥ ሹማምንት ሁሉ ልከው +14 ኤርምያስን ከክብር ዘቦቹ ግቢ+ አስወጡት፤ ደግሞም ወደ ቤቱ እንዲወስደው ለሳፋን+ ልጅ፣ ለአኪቃም+ ልጅ፣ ለጎዶልያስ+ ሰጡት። በመሆኑም ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ተቀመጠ። +15 ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ+ ተዘግቶበት በነበረ ጊዜ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ +16 “ሂድና ለኢትዮጵያዊው ለኤቤድሜሌክ+ እንዲህ በለው፦ ‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በዚህች ከተማ ላይ ለመልካም ሳይሆን ለጥፋት ቃሌን እፈጽማለሁ፤ በዚያም ቀን ይህ ሲፈጸም ታያለህ።”’ +17 “‘አንተን ግን በዚያ ቀን እታደግሃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለምትፈራቸውም ሰዎች አልፈህ አትሰጥም።’ +18 “‘የምታመልጥበትን መንገድ አዘጋጅልሃለሁ፤ በሰይፍም አትወድቅም። በእኔ ስለታመንክ+ ሕይወትህ* እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች’*+ ይላል ይሖዋ።” +3 እኔ ከቁጣው በትር የተነሳ መከራ ያየሁ ሰው ነኝ። + 2 ወደ ውጭ አስወጥቶኛል፤ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ ውስጥ እንድሄድ አድርጎኛል።+ + 3 ቀኑን ሙሉ በተደጋጋሚ እጁን በእኔ ላይ ሰነዘረ።+ + 4 ሥጋዬና ቆዳዬ እንዲያልቅ አደረገ፤አጥንቶቼን ሰባበረ። + 5 ቅጥር ሠራብኝ፤ በመራራ መርዝና+ በመከራ ዙሪያዬን ከበበኝ። + 6 ከሞቱ ብዙ ጊዜ እንደሆናቸው ሰዎች፣ በጨለማ ስፍራዎች እንድቀመጥ አስገደደኝ። + 7 ማምለጥ እንዳልችል በቅጥር ዘጋብኝ፤ከመዳብ በተሠራ ከባድ የእግር ብረት አሰረኝ።+ + 8 ደግሞም እርዳታ ለማግኘት አምርሬ ስጮኽ ጸሎቴን አይሰማም።*+ + 9 መንገዶቼን በተጠረቡ ድንጋዮች ዘጋ፤ጎዳናዎቼን አጣመመ።+ +10 እንደ ድብ፣ እንዳደፈጠ አንበሳም አድብቶ ይጠብቀኛል።+ +11 ከመንገድ ገፍትሮ አስወጣኝ፤ ገነጣጠለኝም፤*ወና አስቀረኝ።+ +12 ደጋኑን ወጠረ፤* የፍላጻውም ዒላማ አደረገኝ። +13 ኮሮጆው ውስጥ በያዛቸው ፍላጻዎች* ኩላሊቴን ወጋ። +14 የሕዝብ ሁሉ ማላገጫ ሆንኩ፤ ቀኑን ሙሉ በእኔ ላይ እየዘፈኑ ይሳለቁብኛል። +15 መራራ ነገሮችን እስኪበቃኝ ድረስ አበላኝ፤ ጭቁኝም አጠገበኝ።+ +16 ጥርሶቼን በጠጠር ይሰብራል፤አመድ ላይ ይጥለኛል።+ +17 ሰላም ነፈግከኝ፤* ጥሩ ነገር ምን እንደሆነ እንኳ ረሳሁ። +18 ስለዚህ “ግርማ ሞገሴ ተገፏል፤ ከይሖዋ የጠበቅኩት ነገርም ጠፍቷል” እላለሁ። +19 መጎሳቆሌንና ዱር አዳሪ* መሆኔን እንዲሁም ጭቁኝና መራራ መርዝ መብላቴን አስታውስ።+ +20 አንተ በእርግጥ ታስታውሳለህ፤* እኔን ለመርዳትም ታጎነብሳለህ።+ +21 ይህ ከልቤ አይጠፋም፤ ከዚህም የተነሳ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።+ +22 ከይሖዋ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ሙሉ በሙሉ አልጠፋንም፤+ምሕረቱ ፈጽሞ አያልቅምና።+ +23 በየማለዳው አዲስ ነው፤+ ታማኝነትህ እጅግ ብዙ ነው።+ +24 እኔ “ይሖዋ ድርሻዬ ነው”+ አልኩ፤* “እሱን በትዕግሥት የምጠባበቀው ለዚህ ነው።”+ +25 ይሖዋ በእሱ ተስፋ ለሚያደርግ፣+ እሱንም ዘወትር ለሚሻ ሰው* ጥሩ ነው።+ +26 የይሖዋን ማዳን+ ዝም ብሎ* መጠባበቅ ጥሩ ነው።+ +27 ሰው በልጅነቱ ቀንበር ቢሸከም ጥሩ ነው።+ +28 አምላክ ቀንበሩን በእሱ ላይ ሲጥልበት ዝም ብሎ ለብቻው ይቀመጥ።+ +29 ፊቱን አቧራ ውስጥ ይቅበር፤+ ገና ተስፋ ሊኖር ይችላል።+ +30 ጉንጩን፣ ለሚመታው ሰው ይስጥ፤ ስድብንም ይጥገብ። +31 ይሖዋ ለዘላለም አይጥለንምና።+ +32 ለሐዘን የዳረገን ቢሆንም እንኳ እንደ ታማኝ ፍቅሩ ብዛት ምሕረት ያሳያል።+ +33 የልቡ ፍላጎት የሰው ልጆች እንዲጎሳቆሉ ወይም እንዲያዝኑ ማድረግ አይደለምና።+ +34 የምድር እስረኞች ሁሉ በእግር ሲረገጡ፣+ +35 በልዑል አምላክ ፊት ሰው ፍትሕ ሲነፈግ፣+ +36 ሰው ከፍርድ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሲጭበረበር፣ይሖዋ እንዲህ ያለውን ነገር በቸልታ አያልፍም። +37 ይሖዋ ካላዘዘ በቀር አንድን ነገር ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማን ነው? +38 ከልዑሉ አምላክ አፍክፉ ነገርና መልካም ነገር በአንድነት አይወጣም። +39 ሕያው የሆነ ሰው ኃጢአቱ ባስከተለበት መዘዝ ለምን ያጉረመርማል?+ +40 መንገዳችንን እንመርምር፤ ደግሞም እንፈትን፤+ ከዚያም ወደ ይሖዋ እንመለስ።+ +41 በሰማያት ወዳለው አምላክ እጃችንን ዘርግተን ከልብ የመነጨ ልመና እናቅርብ፦+ +42 “እኛ በድለናል፤ ደግሞም ዓምፀናል፤+ አንተም ይቅር አላልክም።+ +43 ጨርሶ እንዳንቀርብ በቁጣ አገድከን፤+አሳደድከን፤ ያለርኅራኄም ገደልከን።+ +44 ጸሎታችን እንዳያልፍ ወደ አንተ መቅረብ የሚቻልበትን መንገድ በደመና ዘጋህ።+ +45 በሕዝቦች መካከል ጥራጊና ቆሻሻ አደረግከን።” +46 ጠላቶቻችን ሁሉ በእኛ ላይ አፋቸውን ከፈቱ።+ +47 ፍርሃትና ወጥመድ፣ ባድማነትና ጥፋት ዕጣ ፋንታችን ሆነ።+ +48 ከሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት የተነሳ ዓይኔ የእንባ ጎርፍ አፈሰሰ።+ +49 ዓይኖቼ ያለማቋረጥና ያለእረፍት ያነባሉ፤+ +50 ይሖዋ ከሰማይ ወደ ታች እስኪያይና እስኪመለከት ድረስ ያነባሉ።+ +51 በከተማዬ ሴቶች ልጆች* ሁሉ ላይ የደረሰውን በማየቴ አዘንኩ።*+ +52 ጠላቶቼ ያለምክንያት እንደ ወፍ አደኑኝ። +53 ሕይወቴን በጉድጓድ ውስጥ ጸጥ ሊያደርጓት ሞከሩ፤ በላዬም ላይ የድንጋይ ናዳ ያወርዱብኛል። +54 በራሴ ላይ ውኃ ጎረፈ፤ እኔም “አለቀልኝ!” አልኩ። +55 ይሖዋ ሆይ፣ ከጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ስምህን ጠራሁ።+ +56 ድምፄን ስማ፤ እርዳታና እፎይታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ላለመስማት ጆሮህን አትድፈን። +57 በጠራሁ�� ቀን ወደ እኔ ቀረብክ። “አትፍራ” አልከኝ። +58 ይሖዋ ሆይ፣ ተሟገትክልኝ፤* ሕይወቴን ዋጀህ።+ +59 ይሖዋ ሆይ፣ በእኔ ላይ የደረሰውን በደል አይተሃል፤ እባክህ ፍትሕ እንዳገኝ አድርግ።+ +60 በቀላቸውን ሁሉ፣ በእኔም ላይ ያሴሩትን ሁሉ ተመልክተሃል። +61 ይሖዋ ሆይ፣ ዘለፋቸውን፣ በእኔም ላይ ያሴሩትን ሁሉ ሰምተሃል፤+ +62 ከባላንጣዎቼ አፍ የሚወጣውን ቃልና ቀኑን ሙሉ በእኔ ላይ የሚያንሾካሹኩትን ነገር ሰምተሃል። +63 እያቸው፤ ተቀምጠውም ሆነ ቆመው በዘፈናቸው ይሳለቁብኛል! +64 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ ሥራቸው መልሰህ ትከፍላቸዋለህ። +65 እርግማንህን በእነሱ ላይ በማውረድ ደንዳና ልብ እንዲኖራቸው ታደርጋለህ። +66 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣ ታሳድዳቸዋለህ፤ ከሰማያትህም በታች ታጠፋቸዋለህ። +1 በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን እንዴት ብቻዋን ቀረች!+ ከሌሎች ብሔራት ይበልጥ ብዙ ሕዝብ የነበረባት ከተማ እንዴት እንደ መበለት ሆነች!+ በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው ከተማ እንዴት ለባርነት ተዳረገች!+ + 2 በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤+ እንባዋም በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል። ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል አንድም የሚያጽናናት የለም።+ ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤+ ጠላት ሆነውባታል። + 3 ይሁዳ ተጎሳቁላና ለአስከፊ ባርነት ተዳርጋ+ በግዞት ተወስዳለች።+ በብሔራት መካከል ትቀመጣለች፤+ ምንም ማረፊያ ስፍራ አታገኝም። በተጨነቀች ጊዜ አሳዳጆቿ ሁሉ ያዟት። + 4 በዓል ለማክበር የሚመጣ ስለሌለ ወደ ጽዮን የሚወስዱት መንገዶች አዝነዋል።+ በሮቿ ሁሉ ወና ሆነዋል፤+ ካህናቷም ሲቃ ይዟቸዋል። ደናግሏ* አዝነዋል፤ እሷም አስከፊ ሥቃይ ደርሶባታል። + 5 ባላጋራዎቿ አሁን ጌቶቿ* ሆነዋል፤ ጠላቶቿ ጭንቀት የለባቸውም።+ ከበደሏ ብዛት የተነሳ ይሖዋ ሐዘን አምጥቶባታልና።+ ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው ተወስደዋል።+ + 6 የጽዮን ሴት ልጅ፣ ግርማ ሞገሷ ሁሉ ተገፏል።+ መኳንንቷ መሰማሪያ ቦታ እንዳጡ አጋዘኖች ሆነዋል፤በሚያሳድዳቸውም ፊት አቅም አጥተው ይጓዛሉ። + 7 ኢየሩሳሌም በምትጎሳቆልበትና መኖሪያ በምታጣበት ጊዜ፣በጥንት ዘመን የነበሯትን ውድ ነገሮች ሁሉ ታስታውሳለች።+ ሕዝቧ በጠላት እጅ በወደቀበትና የሚረዳት ባልነበረበት ጊዜ+ጠላቶቿ አዩአት፤ በደረሰባትም ውድቀት ሳቁ።*+ ח[ኼት] + 8 ኢየሩሳሌም ከባድ ኃጢአት ፈጽማለች።+ አስጸያፊ ነገር የሆነችው ለዚህ ነው። ያከብሯት የነበሩ ሁሉ አሁን ናቋት፤ እርቃኗን አይተዋልና።+ እሷ ራሷም ትቃትታለች፤+ በኀፍረትም ፊቷን ታዞራለች። + 9 ርኩሰቷ ቀሚሷ ላይ አለ። ወደፊት የሚገጥማትን ቆም ብላ አላሰበችም።+ ውድቀቷ አስደንጋጭ ነበር፤ የሚያጽናናትም የለም። ይሖዋ ሆይ፣ ጉስቁልናዬን ተመልከት፤ ጠላት ራሱን ከፍ ከፍ አድርጓልና።+ +10 ጠላት በውድ ሀብቶቿ ሁሉ ላይ እጁን አሳርፏል።+ ወደ አንተ ጉባኤ እንዳይገቡ ያዘዝካቸው ብሔራትወደ መቅደሷ ሲገቡ አይታለችና።+ +11 ነዋሪዎቿ ሁሉ ሲቃ ይዟቸዋል፤ የሚበላ ነገር ይፈልጋሉ።+ ምግብ ለማግኘትና በሕይወት ለመቆየት* ብቻ ሲሉ ያሏቸውን ውድ ነገሮች ሰጥተዋል። ይሖዋ ሆይ፣ እይ ደግሞም ተመልከት፤ እንደማትረባ ሴት ሆኛለሁና።* +12 በዚህ መንገድ የምታልፉ ሁሉ፣ ይህ ለእናንተ ከምንም የማይቆጠር ነገር ነው? እዩ፤ ደግሞም ተመልከቱ! ይሖዋ በሚነድ ቁጣው ቀን እንድሠቃይ ያደረገበትን፣በእኔ ላይ የደረሰውን ሥቃይ የመሰለ ሥቃይ አለ?+ +13 ከከፍታ ቦታ ወደ አጥንቶቼ እሳት ላከ፤+ በእያንዳንዳቸውም ላይ አየለባቸው። ለእግሬ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላ እንድመለስ አስገደደኝ። የተጣለች ሴት አድርጎኛል። ቀኑን ሙሉ ታምሜአለሁ። +14 በደሎቼ እንደ ቀንበር ታስረዋል፤ በእጁም ተገምደዋል። አንገቴ ላይ ተደርገዋል፤ ጉልበቴም ተዳክሟል። ይሖዋ መቋቋም ለማልችላቸው ሰዎች አሳልፎ ሰጥቶኛል።+ +15 ይሖዋ በውስጤ ያሉትን ኃያላን በሙሉ አስወገደ።+ ወጣቶቼን ለማድቀቅ በእኔ ላይ ጉባኤ ጠርቷል።+ ይሖዋ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በወይን መጭመቂያ ውስጥ ረግጧል።+ +16 በእነዚህ ነገሮች የተነሳ አለቅሳለሁ፤+ ዓይኖቼ እንባ ያፈሳሉ። ሊያጽናናኝ ወይም መንፈሴን* ሊያድስ የሚችል ሰው ከእኔ ርቋልና። ወንዶች ልጆቼ ተጥለዋል፤ ጠላት አይሏልና። +17 ጽዮን እጆቿን ዘረጋች፤+ የሚያጽናናትም የለም። በያዕቆብ ዙሪያ ያሉት ሁሉ ጠላቶቹ እንዲሆኑ ይሖዋ ትእዛዝ አስተላልፏል።+ ኢየሩሳሌም ለእነሱ አስጸያፊ ነገር ሆናለች።+ +18 ይሖዋ ጻድቅ ነው፤+ ትእዛዙን ተላልፌአለሁና።*+ እናንተ ሰዎች ሁሉ፣ አዳምጡ፤ ሥቃዬንም ተመልከቱ። ደናግሌና* ወጣት ወንዶቼ በግዞት ተወስደዋል።+ +19 ወዳጆቼን ጠራኋቸው፤ እነሱ ግን ከዱኝ።+ ካህናቴና ሽማግሌዎቼ በሕይወት ለመቆየት* ብለውየሚበላ ነገር ሲፈልጉ በከተማዋ ውስጥ አለቁ።+ +20 ይሖዋ ሆይ፣ ተመልከት፤ በከባድ ጭንቀት ተውጫለሁና። አንጀቴም ተላወሰ። ልቤ በውስጤ እጅግ ተረብሿል፤ የለየለት ዓመፀኛ ሆኛለሁና።+ በውጭ ሰይፍ ይፈጃል፤+ በቤት ውስጥ ደግሞ ሞት አለ። +21 ሰዎች ሲቃዬን ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝም የለም። ጠላቶቼ ሁሉ ስለደረሰብኝ ጥፋት ሰምተዋል። ይህን ጥፋት ስላመጣህ ደስ ተሰኝተዋል።+ አንተ ግን የተናገርከውን ቀን በእነሱ ላይ ታመጣለህ፤+ በዚያን ጊዜ እነሱ እንደ እኔ ይሆናሉ።+ +22 ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ በሠራኋቸው በደሎች ሁሉ የተነሳእኔን እንደቀጣኸኝ፣ እነሱንም ቅጣቸው።+ ለቅሶዬ በዝቷልና፤ ልቤም ታሟል። +2 ይሖዋ የጽዮንን ሴት ልጅ በቁጣው ደመና እንዴት ሸፈናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጥሏል።+ በቁጣው ቀን የእግሩን ማሳረፊያ አላስታወሰም።+ + 2 ይሖዋ የያዕቆብን መኖሪያዎች በሙሉ ያላንዳች ርኅራኄ ውጧል። የይሁዳን ሴት ልጅ የተመሸጉ ቦታዎች በቁጣው አፈራርሷል።+ መንግሥቱንና መኳንንቷን ወደ መሬት ጥሏል፤ ደግሞም አርክሷል።+ + 3 የእስራኤልን ብርታት* ሁሉ በታላቅ ቁጣ ቆረጠ። ጠላት በቀረበ ጊዜ እሱ ቀኝ እጁን መለሰ፤+በዙሪያው ያለውን ሁሉ እንደሚበላ እሳትም ቁጣው በያዕቆብ ላይ ነደደ።+ + 4 እንደ ጠላት ደጋኑን ወጠረ፤* ቀኝ እጁም እንደ ባላጋራ ተዘጋጀች፤+ለዓይን የሚማርኩትን ሁሉ ገደለ።+ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳንም ላይ+ ቁጣውን እንደ እሳት አፈሰሰ።+ + 5 ይሖዋ እንደ ጠላት ሆነ፤+እስራኤልን ዋጠ። ማማዎቿን ሁሉ ዋጠ፤የተመሸጉ ስፍራዎቿን ሁሉ አወደመ። በይሁዳ ሴት ልጅ ዘንድ ለቅሶንና ዋይታን አበዛ። + 6 የራሱን ዳስ በአትክልት ቦታ እንዳለች ጎጆ አፈረሰ።+ በዓሉ እንዲያከትም* አደረገ።+ ይሖዋ በጽዮን፣ በዓልና ሰንበት እንዲረሳ አድርጓል፤በኃይለኛ ቁጣውም ንጉሡንና ካህኑን አቃሏል።+ + 7 ይሖዋ መሠዊያውን ናቀ፤መቅደሱን ተወ።+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ግንቦች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ።+ በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ በይሖዋ ቤት በታላቅ ድምፅ ጮኹ።+ + 8 ይሖዋ የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ለማፍረስ ቆርጧል።+ የመለኪያ ገመዱን ዘርግቷል።+ ከማጥፋትም እጁን አልመለሰም። የመከላከያ ግንቡና ቅጥሩ እንዲያዝኑ አደረገ። በአንድነትም ደከሙ። + 9 በሮቿ ወደ መሬት ሰጠሙ።+ መቀርቀሪያዎቿን አስወገደ፤ ደግሞም ሰባበረ። ንጉሥዋና መኳንንቷ በብሔራት መካከል ናቸው።+ ሕግ* የለም፤ ነቢያቷም እንኳ ከይሖዋ የተገለጠላቸው ራእይ የለም።+ +10 የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው መሬት ላይ ይቀመጣሉ።+ በራሳቸው ላይ አቧራ ይነሰንሳሉ፤ ማቅም ይለብሳሉ።+ የኢየሩሳሌም ደናግ�� ራሳቸውን ወደ መሬት ደፍተዋል። +11 ከማልቀሴ ብዛት ዓይኖቼ ፈዘዙ።+ አንጀቴ ተላወሰ። በሕዝቤ ሴት ልጅ* ላይ ከደረሰው ውድቀት+እንዲሁም በከተማዋ አደባባዮች ተዝለፍልፈው ከወደቁት ልጆችና ሕፃናት+ የተነሳ ጉበቴ መሬት ላይ ፈሰሰ። +12 ልክ እንደቆሰለ ሰው በከተማዋ አደባባዮች ተዝለፍልፈው ሲወድቁና በእናቶቻቸው ጉያ ሆነው ለመሞት ሲያጣጥሩ፣*እናቶቻቸውን “እህልና የወይን ጠጅ የት አለ?” ብለው ይጠይቃሉ።+ +13 የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ ምሥክር የሚሆን ምን ነገር ላቀርብልሽ እችላለሁ?ከምንስ ጋር ላመሳስልሽ እችላለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ አጽናናሽ ዘንድ ከማን ጋር ላወዳድርሽ እችላለሁ? የደረሰብሽ ጥፋት እንደ ባሕር ሰፊ ነውና።+ ማን ሊፈውስሽ ይችላል?+ +14 ነቢያትሽ ያዩልሽ ራእይ ሐሰትና ከንቱ ነው፤+ተማርከሽ እንዳትወሰጂ ለማድረግ በደልሽን አላጋለጡም፤+ይልቁንም ራእይ ተገለጠልን እያሉ ሐሰትና አሳሳች ቃል ይነግሩሻል።+ +15 በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በማሾፍ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል።+ “‘ፍጹም ውበት የተላበሰችና የምድር ሁሉ ደስታ’+ በማለት ይጠሯት የነበረችው ከተማ ይህች ናት?” እያሉ በመገረም በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፏጫሉ፤+ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ። +16 ጠላቶችሽ ሁሉ በአንቺ ላይ አፋቸውን ከፍተዋል። እነሱ ያፏጫሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ፤ ደግሞም “ዋጥናት።+ ስንጠብቀው የነበረው ቀን ይህ ነው!+ ጊዜው ደርሶ ለማየት በቃን!”+ ይላሉ። +17 ይሖዋ ያሰበውን አድርጓል፤+የተናገረውን፣ ከጥንትም ጀምሮ ያዘዘውን+ ፈጽሟል።+ ያላንዳች ርኅራኄ አፍርሷል።+ ጠላት በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ደስ እንዲሰኝ፣ የባላጋራዎችሽም ብርታት* ከፍ ከፍ እንዲል አድርጓል። +18 የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፣ ልባቸው ወደ ይሖዋ ይጮኻል። እንባሽ እንደ ጅረት ቀን ከሌት ይፍሰስ። ለራስሽ ፋታ አትስጪ፤ ዓይንሽ እንባ ማፍሰሱን አያቋርጥ።* +19 ተነሺ! ሌሊት፣ ክፍለ ሌሊቶቹ ሲጀምሩ ጩኺ። በይሖዋ ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ። በረሃብ ምክንያት በየመንገዱ ማዕዘን* ተዝለፍልፈው ለወደቁት+ ልጆችሽ ሕይወት* ስትዪ፣እጆችሽን ወደ እሱ ዘርጊ። +20 ይሖዋ ሆይ፣ ክፉኛ የቀጣኸውን እይ፤ ደግሞም ተመልከት። ሴቶች የሆዳቸውን ፍሬ፣ የገዛ ራሳቸውን ልጆች* ይብሉ?+ደግሞስ ካህናቱና ነቢያቱ በይሖዋ መቅደስ ውስጥ ይገደሉ?+ +21 ወንድ ልጅና ሽማግሌ ሞተው በየመንገዱ ተዘርረዋል።+ ደናግሌና* ወጣት ወንዶቼ በሰይፍ ወድቀዋል።+ በቁጣህ ቀን ገደልክ፤ ያላንዳች ርኅራኄ አረድክ።+ +22 በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ+ ሽብርን ከየአቅጣጫው ጠራህ። በይሖዋ የቁጣ ቀን ያመለጠም ሆነ በሕይወት የተረፈ የለም፤+የወለድኳቸውንና* ያሳደግኳቸውን ልጆች ጠላቴ ፈጃቸው።+ +4 ያንጸባርቅ የነበረው ጥሩው ወርቅ፣+ ምንኛ ደበዘዘ! የተቀደሱት ድንጋዮች*+ በየመንገዱ ማዕዘኖች* ላይ እንዴት ተበተኑ!+ + 2 በጠራ ወርቅ የተመዘኑት* የጽዮን ውድ ልጆች፣የሸክላ ሠሪ እጅ እንደሠራውየሸክላ ዕቃ እንዴት ተቆጠሩ! + 3 ቀበሮዎች እንኳ ግልገሎቻቸውን ለማጥባት ጡታቸውን ይሰጣሉ፤የሕዝቤ ሴት ልጅ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች ጨካኝ ሆነች።+ + 4 ከውኃ ጥም የተነሳ፣ የሚጠባው ሕፃን ምላስ ከላንቃው ጋር ይጣበቃል። ልጆች ምግብ ይለምናሉ፤+ አንዳች ነገር የሚሰጣቸው ግን የለም።+ + 5 ምርጥ ምግብ ይበሉ የነበሩ ሰዎች በየጎዳናው ላይ ጠኔ ይዟቸው ይተኛሉ።*+ ውድ ልብስ* ለብሰው ያደጉም+ የአመድ ቁልል ያቅፋሉ። + 6 የሕዝቤ ሴት ልጅ የደረሰባት ቅጣት፣*የማንም እጅ ሳይረዳት በድንገት የተገለበጠችው ሰዶም፣ በሠራችው ኃጢአት የተነሳ ከደረሰባት ቅጣት ይበልጥ ታላቅ ነው።+ + 7 ናዝራውያኗ+ ከበረዶ ይልቅ የጠሩ፣ ከወተትም ይልቅ የነጡ ነበሩ። ከዛጎል ይበልጥ የቀሉ ነበሩ፤ እንደተወለወለም ሰንፔር ነበሩ። + 8 መልካቸው ከጥላሸት ይልቅ ጠቁሯል፤በጎዳና ላይ ማንነታቸውን መለየት የቻለ የለም። ቆዳቸው ተሸብሽቦ አጥንታቸው ላይ ተጣብቋል፤+ እንደደረቀ እንጨት ሆኗል። + 9 በሰይፍ የሚወድቁት በረሃብ ከሚያልቁት ይሻላሉ፤+እነዚህ የምድርን ፍሬ በማጣታቸው መንምነው ያልቃሉ። +10 ሩኅሩኅ የሆኑ ሴቶች በገዛ እጃቸው ልጆቻቸውን ቀቅለዋል።+ የሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት በደረሰባት ጊዜ እንደ እዝን እንጀራ ሆነውላቸዋል።+ +11 ይሖዋ ቁጣውን ገልጿል፤የሚነድ ቁጣውንም አፍስሷል።+ በጽዮን መሠረቶቿን የሚበላ እሳት አንድዷል።+ +12 የምድር ነገሥታትና የምድር ነዋሪዎች ሁሉባላጋራም ሆነ ጠላት በኢየሩሳሌም በሮች ይገባል የሚል እምነት አልነበራቸውም።+ +13 ይህ የደረሰው ነቢያቷ በሠሩት ኃጢአትና ካህናቷ በፈጸሙት በደል የተነሳ ነው፤+እነሱ በመካከሏ የነበሩትን ጻድቃን ደም አፍስሰዋል።+ +14 ታውረው በየጎዳናው ተቅበዘበዙ።+ በደም ስለተበከሉ+ማንም ልብሳቸውን ለመንካት አይደፍርም። +15 “እናንተ ርኩሳን! ሂዱ!” ይሏቸዋል። “ሂዱ! ሂዱ! አትንኩን!” ብለው ይጮኹባቸዋል። መኖሪያ አጥተው ይቅበዘበዛሉና። በብሔራት መካከል ያሉ ሰዎች እንዲህ ብለዋል፦ “ከእንግዲህ ከእኛ ጋር እዚህ መኖር አይችሉም።*+ +16 ይሖዋ ራሱ በታትኗቸዋል፤+ዳግመኛም በሞገስ ዓይን አይመለከታቸውም። ሰዎች ለካህናቱ አክብሮት አይኖራቸውም፤+ ለሽማግሌዎቹም ሞገስ አያሳዩም።”+ +17 አሁንም እንኳ እርዳታ እናገኛለን ብለን በከንቱ ስንጠባበቅ ዓይኖቻችን ደከሙ።+ ሊያድነን ከማይችል ብሔር እርዳታ ለማግኘት ስንጠባበቅ ቆየን።+ +18 እግር በእግር ተከታተሉን፤+ በመሆኑም በአደባባዮቻችን መንቀሳቀስ አልቻልንም። መጨረሻችን ቀርቧል፤ የሕይወት ዘመናችን አብቅቷል፤ ፍጻሜያችን ደርሷልና። +19 አሳዳጆቻችን በሰማይ ከሚበርሩ ንስሮች ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ።+ በተራሮች ላይ አጥብቀው አሳደዱን፤ በምድረ በዳ አድፍጠው አጠቁን። +20 በይሖዋ የተቀባው፣+ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ ጥልቅ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ፤+“በእሱ ጥላ ሥር በብሔራት መካከል እንኖራለን” ብለን ነበር። +21 በዑጽ ምድር የምትኖሪ የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣+ ሐሴት አድርጊ፤ ደስም ይበልሽ። ይሁንና ጽዋው ለአንቺም ይደርስሻል፤+ ትሰክሪያለሽ፤ እርቃንሽንም ትገልጫለሽ።+ +22 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ በበደልሽ ምክንያት የደረሰብሽ ቅጣት አብቅቷል። ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ግዞት አይወስድሽም።+ ይሁንና የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣ ትኩረቱን በሠራሽው በደል ላይ ያደርጋል። ኃጢአትሽን ይገልጣል።+ +5 ይሖዋ ሆይ፣ የደረሰብንን ነገር አስታውስ። ውርደታችንን እይ፤ ደግሞም ተመልከት።+ + 2 ርስታችን ለእንግዶች፣ ቤቶቻችን ለባዕድ አገር ሰዎች ተሰጡ።+ + 3 አባት እንደሌላቸው ወላጅ አልባ ልጆች ሆንን፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።+ + 4 የገዛ ራሳችንን ውኃ ለመጠጣት መክፈል ነበረብን፤+ የገዛ እንጨታችንን የምናገኘውም በግዢ ነበር። + 5 አሳዳጆቻችን አንገታችንን ሊይዙ ተቃረቡ፤ዝለናል፤ እረፍት የሚባል ነገርም አላገኘንም።+ + 6 በቂ ምግብ ለማግኘት ወደ ግብፅና ወደ አሦር እጃችንን ዘረጋን።+ + 7 ኃጢአት የሠሩት አባቶቻችን አሁን በሕይወት የሉም፤ እኛ ግን የእነሱን በደል ለመሸከም ተገደድን። + 8 አሁን አገልጋዮች ይገዙናል፤ ከእጃቸው የሚያስጥለን ማንም የለም። + 9 በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሳ ምግባችንን የምናመጣው በሕይወታችን* ቆርጠን ነው።+ +10 ከከባድ ረሃብ የተነሳ ቆዳችን እንደ ምድጃ ጋለ።+ +11 በጽዮን ያሉ ሚስቶችና በይሁዳ ከተሞች ያሉ ደናግል ተዋረዱ።*+ +12 መኳንንቱ በእጃቸው ተንጠለጠሉ፤+ ሽማግሌዎችም አልተከበሩም።+ +13 ወጣቶች ወፍጮውን ይሸከማሉ፤ ልጆችም ከባድ እንጨት ሲሸከሙ ይደናቀፋሉ። +14 ሽማግሌዎች ከከተማዋ በር ሄደዋል፤+ ወጣቶችም ሙዚቃቸውን መጫወት አቁመዋል።+ +15 ደስታ ከልባችን ራቀ፤ ጭፈራችን በሐዘን ተተካ።+ +16 ራሳችን ላይ ያለው አክሊል ወድቋል። ኃጢአት ስለሠራን ወዮልን! +17 ከዚህ የተነሳ ልባችን ታመመ፤+ከእነዚህም ነገሮች የተነሳ ዓይኖቻችን ፈዘዙ፤+ +18 ባድማ የሆነችው የጽዮን ተራራ+ አሁን የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና። +19 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ላይ ትቀመጣለህ። ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።+ +20 ለዘላለም የረሳኸንና ለረጅም ዘመን የተውከን ለምንድን ነው?+ +21 ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም በፈቃደኝነት እንመለሳለን።+ ዘመናችንን እንደቀድሞው አድስልን።+ +22 አንተ ግን ፈጽሞ ጥለኸናል። አሁንም በእኛ ላይ እጅግ እንደተቆጣህ ነህ።+ +17 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ እስራኤል ቤት እንቆቅልሽና ምሳሌ ተናገር።+ +3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ትላልቅ ክንፎችና ረጃጅም ማርገብገቢያዎች ያሉት እንዲሁም መላ አካሉ ዥጉርጉር በሆኑ ላባዎች የተሸፈነው ታላቁ ንስር+ ወደ ሊባኖስ+ መጥቶ የአርዘ ሊባኖስን ጫፍ ያዘ።+ +4 አናቱ ላይ ያለውን ቀንበጥ ቀጥፎ ወደ ነጋዴዎች* ምድር አመጣው፤ በነጋዴዎችም ከተማ ተከለው።+ +5 ከዚያም ከምድሪቱ ዘር የተወሰነውን ወስዶ+ ለም በሆነ መሬት ላይ ዘራው። እንደ ሪጋ* ዛፍ ብዙ ውኃ ባለበት ቦታ አጠገብ ተከለው። +6 በመሆኑም ዘሩ በቀለ፤ አጭርና የተንሰራፋ እንዲሁም ወደ ራሱ አቅጣጫ የበቀሉ ቅጠሎች ያሉት የወይን ተክል ሆነ፤+ ሥሮቹም ከበታቹ አደጉ። በዚህ ሁኔታ የወይን ተክል ሆነ፤ ቀንበጦችና ቅርንጫፎችም አወጣ።+ +7 “‘“ደግሞም ትላልቅ ክንፎች ያሉትና የክንፎቹ ላባዎች ረጃጅም የሆኑ ሌላ ታላቅ ንስር መጣ።+ ከዚያም ይህ የወይን ተክል ሥሮቹን ከተተከለበት የአትክልት መደብ አሻግሮ በታላቅ ጉጉት ወደ እሱ ዘረጋ፤ ውኃ ያጠጣውም ዘንድ ቅርንጫፎቹን ወደ እሱ ሰደደ።+ +8 ቅርንጫፎችን እንዲያወጣና ፍሬ እንዲያፈራ እንዲሁም ያማረ የወይን ተክል እንዲሆን ብዙ ውኃ ባለበት አቅራቢያ መልካም መሬት ላይ ተተክሎ ነበር።”’+ +9 “እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ያድግ ይሆን? ሰው ሥሮቹን ነቅሎ አይጥልም?+ ፍሬው እንዲበሰብስ አያደርግም? ቀንበጦቹስ እንዲጠወልጉ አያደርግም?+ የወይኑ ተክል በጣም ስለሚደርቅ ከሥሩ ለመንቀል ብርቱ ክንድም ሆነ ብዙ ሰው አያስፈልግም። +10 ተነቅሎ በሌላ ቦታ ቢተከልስ ያድግ ይሆን? የምሥራቅ ነፋስ ሲነፍስበት ሙሉ በሙሉ አይደርቅም? በበቀለበት የአትክልት መደብ ላይ ይደርቃል።”’” +11 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +12 “እባክህ፣ ለዓመፀኛው ቤት ይህን ተናገር፦ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትገነዘቡም?’ እንዲህ በል፦ ‘እነሆ፣ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሥዋንና መኳንንቷን ማረከ፤ ወደ ባቢሎንም ይዟቸው ተመለሰ።+ +13 በተጨማሪም ከንጉሣውያን ዘር አንዱን ወስዶ+ ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ በመሐላም ቃል አስገባው።+ ከዚያም የምድሪቱን ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤+ +14 ይህም መንግሥቲቱ ዝቅ እንድትልና ማንሰራራት እንዳትችል እንዲሁም የእሱን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ብቻ እንድትኖር ለማድረግ ነው።+ +15 ንጉሡ ግን በመጨረሻ ፈረሶችና+ ብዙ ሠራዊት እንዲልኩለት መልእክተኞቹን ወደ ግብፅ በመስደድ+ በእሱ ላይ ዓመፀ።+ ታዲያ ���ሳካለት ይሆን? እነዚህን ነገሮች ያደረገው ከቅጣት ያመልጣል? ቃል ኪዳኑንስ አፍርሶ ማምለጥ ይችላል?’+ +16 “‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “እሱን ንጉሥ* አድርጎ የሾመው ንጉሥ* በሚኖርበት ቦታ ይኸውም በባቢሎን ይሞታል፤ ይህ ሰው መሐላውን አቃሎበታል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሶበታል።+ +17 ብዙ ሕይወት* ለማጥፋት የአፈር ቁልል በሚደለደልበትና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ በሚሠራበት ጊዜ የፈርዖን ታላቅ ሠራዊትና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወታደሮች ሊረዱት አይችሉም።+ +18 እሱ መሐላውን አቃሏል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሷል። ቃል ቢገባለትም* እንኳ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርጓል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አያመልጥም።”’ +19 “‘በመሆኑም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ መሐላዬን መናቁና ቃል ኪዳኔን ማፍረሱ የሚያስከትልበትን መዘዝ በራሱ ላይ አመጣበታለሁ።+ +20 መረቤን በላዩ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል።+ ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ በእኔ ላይ ክህደት ስለፈጸመ በዚያ እፋረደዋለሁ።+ +21 ከወታደሮቹ መካከል የሸሹት ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በሕይወት የተረፉትም በየአቅጣጫው* ይበታተናሉ።+ በዚህ ጊዜም እኔ ይሖዋ ራሴ እንደተናገርኩ ታውቃላችሁ።”’+ +22 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከረጅሙ አርዘ ሊባኖስ ጫፍ ላይ ቀንበጥ+ ቀጥፌ እተክለዋለሁ፤ ከቀንበጦቹም ጫፍ ላይ ለጋ የሆነውን ቀጥፌ+ ረጅምና ግዙፍ በሆነ ተራራ ላይ እኔ ራሴ እተክለዋለሁ።+ +23 ረጅም በሆነ የእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎቹም ያድጋሉ፤ ፍሬም ያፈራል፤ ደግሞም የሚያምር አርዘ ሊባኖስ ይሆናል። በሥሩም የወፍ ዓይነቶች ሁሉ ይኖራሉ፤ በቅጠሎቹም ጥላ ሥር ያርፋሉ። +24 የዱር ዛፎች ሁሉ፣ ከፍ ያለውን ዛፍ ዝቅ ዝቅ ያደረግኩት፣ ዝቅ ያለውን ዛፍ ደግሞ ከፍ ከፍ ያደረግኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤+ ለምለሙን ዛፍ አድርቄአለሁ፤ ደረቁም ዛፍ እንዲለመልም አድርጌአለሁ።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አድርጌአለሁ።”’” +30 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ዋይ ዋይ በሉ፤ ‘ቀኑ ስለቀረበ ወዮ!’ + 3 ቀኑ ቀርቧልና፤ አዎ፣ የይሖዋ ቀን ቀርቧል።+ የደመናት ቀን፣+ በብሔራትም ላይ የሚፈረድበት ቀን ይሆናል።+ + 4 ሰይፍ በግብፅ ላይ ይመጣል፤ የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣ሀብቷ ሲወሰድ እንዲሁም መሠረቶቿ ሲፈራርሱ ኢትዮጵያ በሽብር ትዋጣለች።+ + 5 ኢትዮጵያ፣+ ፑጥ፣+ ሉድና ድብልቅ ሕዝቦች ሁሉ*እንዲሁም ኩብ፣ ከቃል ኪዳኑ ምድር ልጆች* ጋርሁሉም በሰይፍ ይወድቃሉ።”’ + 6 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለግብፅ ድጋፍ የሚሰጡም ይወድቃሉ፤የምትታበይበት ኃይሏም ይወገዳል።’+ “‘ከሚግዶል+ እስከ ሰዌኔ+ በምድሪቱ ላይ በሰይፍ ይወድቃሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +7 ‘ከሌሎች አገሮች በከፋ ሁኔታ ባድማ ይሆናሉ፤ ከተሞቿም ከሌሎች ከተሞች በከፋ ሁኔታ ይወድማሉ።+ +8 በግብፅም ላይ እሳት በማነድበትና ተባባሪዎቿ ሁሉ በሚደቁበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። +9 በዚያን ቀን በራሷ የምትታመነውን ኢትዮጵያን ለማንቀጥቀጥ መልእክተኞችን በመርከብ እልካለሁ፤ ግብፅ በምትጠፋበት ቀን በሽብር ይዋጣሉ፤ ቀኑ በእርግጥ ይመጣልና።’ +10 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስፍር ቁጥር የሌለውን የግብፅ ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ አጠፋለሁ።+ +11 ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እሱና ሠራዊቱ+ ምድሪቱን ለማውደም ይመጣሉ። እነሱም በግብፅ ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ።+ +12 የአባይን የመስኖ ቦዮች አደርቃለሁ፤+ ምድሪቱንም ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ። ምድሪቱና በውስጧ ያለው ሁሉ በባዕዳን እጅ እንዲጠፉ አደርጋለሁ።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ።’ +13 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አስጸያፊ የሆኑትንም ጣዖቶች* አጠፋለሁ፤ ከንቱ የሆኑትንም የኖፍ*+ አማልክት አስወግዳለሁ። ከእንግዲህ ከግብፅ ምድር የሚወጣ ገዢ* አይኖርም፤ በግብፅም ምድር ፍርሃት እሰዳለሁ።+ +14 ጳትሮስን+ ባድማ አደርጋለሁ፤ በጾዓን እሳት አነዳለሁ፤ ደግሞም በኖእ*+ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ። +15 የግብፅ ምሽግ በሆነችው በሲን ላይ ቁጣዬን አፈስሳለሁ፤ የኖእንም ሕዝብ አጠፋለሁ። +16 በግብፅ ላይ እሳት አነዳለሁ፤ ሲን በሽብር ትዋጣለች፤ ኖእ ቅጥሯ ይፈርሳል፤ ኖፍ* ደግሞ በጠራራ ፀሐይ ጥቃት ይሰነዘርባታል! +17 የኦንና* የጲበሰት ወጣቶች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ የከተሞቹም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ። +18 በዚያ የግብፅን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ በጣፍነስ ቀኑ ይጨልማል።+ የምትታበይበት ኃይሏ ይጠፋል፤+ ደመናት ይሸፍኗታል፤ የከተሞቿም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ።+ +19 በግብፅ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’” +20 በ11ኛውም ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በሰባተኛው ቀን፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +21 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ እንዲድን አይታሰርም፤ ወይም ጠንክሮ ሰይፍ እንዲይዝ በጨርቅ አይጠቀለልም።” +22 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ እኔ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነስቻለሁ፤+ ብርቱውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤+ ሰይፉም ከእጁ ላይ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።+ +23 ከዚያም ግብፃውያንን በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።+ +24 የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤*+ ሰይፌንም አስጨብጠዋለሁ፤+ የፈርዖንን ክንዶች እሰብራለሁ፤ እሱም ሊሞት እያጣጣረ እንዳለ ሰው በፊቱ* እጅግ ያቃስታል። +25 የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንዶች ግን ይዝላሉ፤ ሰይፌንም ለባቢሎን ንጉሥ ሳስጨብጠውና በግብፅ ምድር ላይ ሲሰነዝረው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ +26 ግብፃውያንንም በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤+ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’” +35 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ተራራማ ወደሆነው የሴይር+ ምድር አዙረህ በእሱ ላይ ትንቢት ተናገር።+ +3 እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ እነሆ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ፤ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤ ባድማና ወና አደርግሃለሁ።+ +4 ከተሞችህን አፈራርሳለሁ፤ አንተም ባድማና ወና ትሆናለህ፤+ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ። +5 የእስራኤል ልጆች ጥፋት በደረሰባቸውና የመጨረሻውን ቅጣት በተቀበሉበት ጊዜ የማያባራ የጠላትነት ስሜት በማሳየት+ ለሰይፍ አሳልፈህ ሰጥተሃቸዋልና።”’+ +6 “‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለእርድ አዘጋጅሃለሁ፤ ደምህም ይፈስሳል።+ ደም ጠልተህ ስለነበር ደምህ ይፈስሳል።+ +7 የሴይርን ተራራማ ምድር ባድማና ወና አደርጋለሁ፤+ በዚያ የሚያልፈውንም ሆነ የሚመለሰውን ማንኛውንም ሰው አጠፋለሁ። +8 ተራሮቹን በታረዱ ሰዎች እሞላለሁ፤ በሰይፍ የታረዱት በኮረብቶችህ፣ በሸለቆዎችህና በጅረቶችህ ላይ ይወድቃሉ። +9 ለዘላለም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህም ሰው አልባ ይሆናሉ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’ +10 “ይሖዋ ራሱ በዚያ ቢኖርም እንኳ፣ አንተ ‘እነዚህ ሁለት ብሔራትና ሁለት አገሮች የእኔ ይሆናሉ፤ እኛም ሁለቱን አገሮች እንወርሳለን’+ ስላልክ፣ +11 ‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለእነሱ ካደረብህ የጥላቻ ስሜት የተነሳ በእነሱ ላይ በገለጥከው በዚያው ዓይነት ቁጣና ቅናት እኔም እርምጃ እወስድብሃለሁ፤+ በአንተም ላይ በምፈርድበት ጊዜ በእነሱ መካከል ማንነቴ እንዲታወቅ አደርጋለሁ። +12 አንተ “ወና ሆነዋል፤ ለእኛም እንደ መብል ተሰጥተዋል” ባልክ ጊዜ በእስራኤል ተራሮች ላይ በንቀት የተናገርከውን ነገር ሁሉ እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሰማሁ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ።” +13 እናንተ በእኔ ላይ በእብሪት ተናግራችኋል፤ ደግሞም በእኔ ላይ ብዙ ነገር ተናግራችኋል።+ የተናገራችሁትን ሁሉ ሰምቻለሁ።’ +14 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን ባድማና ወና በማደርግበት ጊዜ መላዋ ምድር ሐሴት ታደርጋለች። +15 የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነበት ጊዜ ስለተደሰትክ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ።+ የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ አንተም ሆንክ መላው የኤዶም ምድር ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናላችሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’” +31 በ11ኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖንና ስፍር ቁጥር ለሌለው ሕዝቡ እንዲህ በል፦+‘በታላቅነትህ ከማን ጋር ትመሳሰላለህ? + 3 አንድ አሦራዊ፣ በሊባኖስ ያደገ አርዘ ሊባኖስ ነበር፤አርዘ ሊባኖሱ ጥላ እንደሚሰጡ ችፍግ ብለው ያደጉ ዛፎች፣ የሚያማምሩ ቅርንጫፎች ያሉት እጅግ ረጅም ዛፍ ሲሆንጫፉም ደመናትን ይነካ ነበር። + 4 ውኃዎቹ ትልቅ ዛፍ እንዲሆን አደረጉት፤ ጥልቅ ከሆኑት ምንጮች የተነሳ ዛፉ በጣም ረጅም ሆነ። በተተከለበት ቦታ ዙሪያ ጅረቶች ነበሩ፤የውኃ መውረጃዎቻቸውም በሜዳ ያሉትን ዛፎች ሁሉ ያጠጡ ነበር። + 5 ከዚህም የተነሳ ቁመቱ በሜዳ ካሉት ከሌሎቹ ዛፎች ሁሉ ረዘመ። ብዙ ቅርንጫፎች አወጣ፤ ጅረቶቹ ብዙ ውኃ ስለነበራቸውቅርንጫፎቹ ረጃጅም ሆኑ። + 6 የሰማይ ወፎች ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ጎጇቸውን ሠሩ፤የዱር እንስሳትም ሁሉ ከቅርንጫፎቹ ሥር ግልገሎቻቸውን ወለዱ፤ከጥላውም ሥር ብዙ ሕዝብ ያላቸው ብሔራት ሁሉ ሰፈሩ። + 7 ከውበቱና ከቅርንጫፎቹ ርዝመት የተነሳ ግርማ ሞገስ ተላበሰ፤ሥሮቹን ብዙ ውኃ ወዳለበት ስፍራ ሰዶ ነበርና። + 8 በአምላክ የአትክልት ስፍራ+ ያሉ ሌሎች አርዘ ሊባኖሶች ሊተካከሉት አልቻሉም። ከጥድ ዛፎች መካከል የእሱ ዓይነት ቅርንጫፎች ያሉት አንድም ዛፍ የለም፤የአርሞን ዛፎችም* ከእሱ ቅርንጫፎች ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም። በአምላክ የአትክልት ስፍራ ያለ የትኛውም ዛፍ በውበቱ አይወዳደረውም። + 9 ብዙ ቅጠሎች ያሉት ውብ ዛፍ አድርጌ ሠራሁት፤በእውነተኛው አምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ያሉ ሌሎች ዛፎችም ሁሉ ቀኑበት።’ +10 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ቁመቱ* እጅግ ከመርዘሙ የተነሳ ጫፉን በደመናት መካከል ከፍ ስላደረገና በቁመቱ የተነሳ ልቡ ስለታበየ፣ +11 ኃያል ለሆነ የብሔራት ገዢ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።+ እሱም በእርግጥ ይነሳበታል፤ በክፋቱም የተነሳ እጥለዋለሁ። +12 ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑት ባዕዳን ቆርጠው ይጥሉታል፤ በተራሮችም ላይ ጥለውት ይሄዳሉ፤ ቅጠሎቹም በየሸለቆው ይረግፋሉ፤ ቅርንጫፎቹም በምድሪቱ ላይ ባሉ ጅረቶች ሁሉ ላይ ተሰባብረው ይወድቃሉ።+ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ሥር ወጥተው ትተውት ይሄዳሉ። +13 የሰማይ ��ፎች ሁሉ በወደቀው ግንዱ ላይ ይሰፍራሉ፤ የዱር እንስሳትም ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ይኖራሉ።+ +14 ይህም የሚሆነው በውኃዎች አጠገብ ካሉ ዛፎች መካከል አንዳቸውም ቁመታቸው በጣም እንዳይረዝም ወይም ጫፋቸውን በደመናት መካከል ከፍ እንዳያደርጉ እንዲሁም ውኃ የጠገበ አንድም ዛፍ ቁመቱ እነሱ ጋ እንዳይደርስ ነው። ሁሉም ለሞት ይዳረጋሉና፤ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት የሰው ልጆች ጋር በአንድነት ከምድር በ +15 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ መቃብር* በሚወርድበት ቀን ሰዎች እንዲያዝኑ አደርጋለሁ። ስለዚህ ጥልቅ የሆኑትን ውኃዎች እሸፍናለሁ፤ ጅረቶቹንም እገታለሁ፤ ይህም በገፍ የሚፈስሱት ውኃዎች ይቋረጡ ዘንድ ነው። ከእሱ የተነሳ ሊባኖስን አጨልማለሁ፤ በሜዳም ያሉ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ። +16 ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ሁሉ ጋር ወደ መቃብር* በማወርደው ጊዜ ሲወድቅ በሚሰማው ድምፅ ብሔራት እንዲናወጡ አደርጋለሁ፤ ከምድርም በታች የኤደን ዛፎች ሁሉ፣+ ምርጥና ግሩም የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እንዲሁም ውኃ የጠገቡት ዛፎች ሁሉ ይጽናናሉ። +17 ከእሱ ጋር እንዲሁም በብሔራት መካከል በጥላው ሥር ይኖሩ ከነበሩት ደጋፊዎቹ* ጋር በሰይፍ የታረዱት ወዳሉበት ወደ መቃብር* ወርደዋል።’+ +18 “‘በኤደን ካሉት ዛፎች መካከል የአንተ ዓይነት ክብርና ታላቅነት ያለው የትኛው ነው?+ ይሁንና ከኤደን ዛፎች ጋር ከምድር በታች ትወርዳለህ። ባልተገረዙት መካከል፣ በሰይፍ ከታረዱት ጋር ትጋደማለህ። ይህ በፈርዖንና ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቡ ላይ ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +18 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “በእስራኤል ምድር ‘ጎምዛዛ ወይን የበሉት አባቶች ሆነው ሳለ የልጆቹ ጥርስ ጠረሰ’ የሚለውን ምሳሌያዊ አባባል የምትጠቅሱት ምን ለማለት ነው?+ +3 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ከእንግዲህ በእስራኤል ይህን ምሳሌ አትጠቅሱም። +4 እነሆ፣ ነፍስ* ሁሉ የእኔ ነው። የአባት ነፍስ የእኔ እንደሆነች ሁሉ የልጅም ነፍስ የእኔ ናት። ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች።* +5 “‘አንድ ሰው ጻድቅ ነው እንበል፤ ይህ ሰው ፍትሐዊና ትክክል የሆነውን ነገር ያደርጋል። +6 በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን+ አይበላም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት የእስራኤል ቤት ጣዖቶች* አይመለከትም፤ የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም+ ወይም ከሴት ጋር በወር አበባዋ ጊዜ ግንኙነት አይፈጽምም፤+ +7 ማንንም ሰው አይበድልም፤+ ይልቁንም ተበዳሪ መያዣ አድርጎ የሰጠውን ይመልሳል፤+ ማንንም ሰው አይዘርፍም፤+ ይልቁንም ለተራበ ሰው የራሱን ምግብ ይሰጣል፤+ እንዲሁም የተራቆተውን ያለብሰዋል፤+ +8 ወለድ አይጠይቅም ወይም በአራጣ አያበድርም፤+ ይልቁንም ፍትሕ የጎደለው ድርጊት ከመፈጸም ይቆጠባል፤+ በሰዎች መካከል እውነተኛ ፍትሕ ያሰፍናል፤+ +9 ያወጣኋቸውን ደንቦች ይከተላል፤ እንዲሁም በታማኝነት ይመላለስ ዘንድ ድንጋጌዎቼን ይጠብቃል። እንዲህ ያለው ሰው ጻድቅ ነው፤ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +10 “‘ይሁንና ይህ ሰው ዘራፊ+ ወይም ነፍሰ ገዳይ*+ የሆነ ወይም ከእነዚህ ነገሮች አንዱን የሚያደርግ ልጅ አለው እንበል፤ +11 (አባቱ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱንም ባያደርግ እንኳ) ልጁ በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን ይበላል፤ የባልንጀራውን ሚስት ያባልጋል፤ +12 የተቸገረውንና ድሃውን ይበድላል፤+ ሰዎችን ይዘርፋል፤ መያዣ አድርጎ የወሰደውን አይመልስም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት ጣዖቶች ይመለከታል፤+ ጸያፍ የሆኑ ልማዶችን ይፈጽማል፤+ +13 በአራጣ ያበድራል፤ እንዲሁም ወለድ ይቀበላል፤+ በመሆኑም ይህ ል��� ፈጽሞ በሕይወት አይኖርም። እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች በመሥራቱ በእርግጥ ይሞታል። ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል። +14 “‘ይሁንና አንድ አባት የተለያዩ ኃጢአቶች ሲሠራ ልጁ ይመለከተዋል እንበል፤ ልጁ ይህን ቢመለከትም እንዲህ ያሉ ነገሮች አይሠራም። +15 በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን አይበላም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት የእስራኤል ቤት ጣዖቶች አይመለከትም፤ የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም፤ +16 ማንንም ሰው አይበድልም፤ መያዣ እንዲሆን የተሰጠውን አይወስድም፤ ከሰው ላይ ምንም ነገር አይዘርፍም፤ ለተራበ ሰው የራሱን ምግብ ይሰጣል፤ እንዲሁም የተራቆተውን ያለብሰዋል፤ +17 ድሃውን ሰው ከመጨቆን ይቆጠባል፤ በአራጣ አያበድርም ወይም ወለድ አይጠይቅም፤ ድንጋጌዎቼንም ያከብራል፤ እንዲሁም ያወጣኋቸውን ደንቦች ይከተላል። እንዲህ ያለ ሰው አባቱ በፈጸመው በደል የተነሳ አይሞትም። በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። +18 አባቱ ግን የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸሙ፣ ወንድሙን በመዝረፉና በሕዝቡ መካከል መጥፎ የሆነ ነገር በመሥራቱ በፈጸመው በደል የተነሳ ይሞታል። +19 “‘እናንተ ግን “ልጅ፣ አባቱ በሠራው በደል ተጠያቂ የማይሆነው ለምንድን ነው?” ትላላችሁ። ልጁ ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ስላደረገ፣ ያወጣኋቸውን ደንቦች ሁሉ ስለጠበቀና በሥራ ላይ ስላዋለ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።+ +20 ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች።*+ ልጅ፣ አባቱ በሠራው በደል ተጠያቂ አይሆንም፤ አባትም ልጁ በሠራው በደል ተጠያቂ አይሆንም። የጻድቁ ሰው ጽድቅ የሚታሰብለት ለራሱ ብቻ ነው፤ የክፉውም ሰው ክፋት የሚታሰበው በራሱ ላይ ብቻ ነው።+ +21 “‘ክፉ ሰው ከሠራው ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ፣ ያወጣኋቸውን ደንቦች ቢጠብቅ እንዲሁም ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም።+ +22 ከሠራው በደል ውስጥ አንዱም አይታሰብበትም።*+ በሠራው ጽድቅ የተነሳ በሕይወት ይኖራል።’+ +23 “‘እኔ በክፉ ሰው ሞት ደስ እሰኛለሁ?’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘እኔ ደስ የምሰኘው ከመንገዱ ቢመለስና በሕይወት ቢኖር አይደለም?’+ +24 “‘ይሁንና ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ* ነገር ቢፈጽም፣ ደግሞም ክፉው ሰው እንደሚያደርገው አስጸያፊ ነገሮችን ሁሉ ቢሠራ በሕይወት ይኖራል? ካከናወነው የጽድቅ ሥራ መካከል አንዱም አይታወስም።+ ታማኝነቱን በማጉደሉና ኃጢአት በመሥራቱ የተነሳ ይሞታል።+ +25 “‘ይሁንና እናንተ “የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም” ትላላችሁ።+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እባካችሁ ስሙ! በእርግጥ መንገዴ ፍትሐዊ አይደለም?+ ይልቁንስ ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ አይደለም?+ +26 “‘ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ በዚህም የተነሳ ቢሞት፣ የሚሞተው በገዛ ራሱ በደል ነው። +27 “‘ክፉ ሰው ከሠራው ክፉ ድርጊት ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ማድረግ ቢጀምር የራሱን ሕይወት* ያድናል።+ +28 የሠራውን በደል ሁሉ ተገንዝቦ ከዚያ ቢመለስ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም። +29 “‘ይሁንና የእስራኤል ቤት ሰዎች “የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም” ይላሉ። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእርግጥ መንገዴ ፍትሐዊ አይደለም?+ ይልቁንስ ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ አይደለም?’ +30 “‘ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደየመንገዳችሁ እፈርዳለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ተመለሱ፤ አዎ፣ ተጠያቂ እንድትሆኑ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ እንዳይሆንባችሁ ከሠራችሁት በደል ሁሉ ሙሉ በሙሉ ተመለሱ። +31 የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ ከራሳችሁ ላይ አስወግዱ፤+ ደግሞም አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ይኑራችሁ፤*+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለምን ትሞታላችሁ?’+ +32 “‘እኔ በማንም ሰው ሞት ደስ አልሰኝም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።’”+ +23 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ከአንድ እናት የተወለዱ ሁለት ሴቶች ነበሩ።+ +3 እነሱም በግብፅ ዝሙት አዳሪዎች ሆኑ፤+ ከወጣትነታቸው ጊዜ ጀምሮ አመነዘሩ። በዚያም ጡታቸው ተሻሸ፤ የድንግልናቸውም ጉያ ተዳበሰ። +4 የታላቂቱ ስም ኦሆላ፣* የእህቷም ስም ኦሆሊባ* ነበር። እነሱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውን በተመለከተ፣ ኦሆላ ሰማርያ+ ስትሆን ኦሆሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት። +5 “ኦሆላ የእኔ ሆና ሳለች ታመነዝር ጀመር።+ ጎረቤቶቿ የሆኑትን ፍቅረኞቿን+ አሦራውያንን በፍትወት ተመኘች።+ +6 እነሱ ሰማያዊ ልብስ የለበሱ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች ሲሆኑ ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች እንዲሁም ፈረሰኞች ነበሩ። +7 እሷ ምርጥ ከሆኑት የአሦር ልጆች ሁሉ ጋር ማመንዘሯን ቀጠለች፤ ደግሞም በፍትወት የምትመኛቸው ሰዎች በሚያመልኳቸው አስጸያፊ ጣዖቶች* ራሷን አረከሰች።+ +8 በግብፅ ትፈጽመው የነበረውን ምንዝር አልተወችም፤ እነሱ በወጣትነቷ ከእሷ ጋር ተኝተዋልና፤ የድንግልናዋን ጉያ ዳብሰዋል እንዲሁም ፍትወታቸውን በእሷ ላይ አፍስሰዋል።*+ +9 ስለዚህ በፍትወት ለተመኘቻቸው፣ ፍቅረኞቿ ለሆኑት አሦራውያን አሳልፌ ሰጠኋት።+ +10 እነሱ እርቃኗን ገለጡ፤+ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ማረኩ፤+ እሷንም በሰይፍ ገደሏት። በሴቶች መካከል መጥፎ ስም አተረፈች፤ እነሱም የፍርድ እርምጃ ወሰዱባት። +11 “እህቷ ኦሆሊባ ይህን ስትመለከት ፍትወቷ እጅግ የከፋ ሆነ፤ አመንዝራነቷም ከእህቷ የባሰ ሆነ።+ +12 ጎረቤቶቿ የሆኑትን የአሦርን ልጆች በፍትወት ተመኘች፤+ እነሱ ያማረ ልብስ የለበሱ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች እንዲሁም ፈረሰኞች ሲሆኑ ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች ነበሩ። +13 እሷ ራሷን ባረከሰች ጊዜ ሁለቱም በአንድ መንገድ እንደሄዱ ተገነዘብኩ።+ +14 ይሁን እንጂ እሷ በአመንዝራነቷ ገፋችበት። በግድግዳው ላይ የተቀረጹትን የወንድ ምስሎች ይኸውም ቀይ ቀለም የተቀቡትን የከለዳውያን የተቀረጹ ምስሎች አየች፤ +15 እነሱ ወገባቸው ላይ ቀበቶ ታጥቀዋል፤ በራሳቸውም ላይ የተንዘረፈፈ ጥምጥም አድርገዋል፤ ደግሞም ተዋጊዎች ይመስላሉ፤ ሁሉም በከለዳውያን ምድር የተወለዱትን ባቢሎናውያን ያመለክታሉ። +16 እሷም እነሱን እንዳየቻቸው በፍትወት ትመኛቸው ጀመር፤ ወደ ከለዳውያንም ምድር መልእክተኞች ላከችባቸው።+ +17 በመሆኑም የባቢሎን ልጆች ከእሷ ጋር ለመተኛት ወደ እሷ መምጣታቸውን ቀጠሉ፤ በፍትወታቸውም* አረከሷት። በእነሱ ከረከሰች በኋላ ተጸይፋቸው* ከእነሱ ራቀች። +18 “ዓይን አውጣ በመሆን ማመንዘሯንና እርቃኗን መግለጧን በቀጠለች ጊዜ+ እህቷን ተጸይፌ* እንደራቅኳት ሁሉ እሷንም ተጸይፌ ራቅኳት።+ +19 እሷ ግን በግብፅ ምድር ስታመነዝር+ የነበረበትን የወጣትነቷን ዘመን በማስታወስ በአመንዝራነቷ ይባስ ገፋችበት።+ +20 ብልታቸው እንደ አህያ ብልት፣ አባለዘራቸውም እንደ ፈረስ አባለዘር በሆኑ ወንዶች የተያዙ ቁባቶች እንደሚያደርጉት እሷም በፍትወት ተመኘቻቸው። +21 በግብፅ ምድር ጉያሽን በዳበሱበት፣ የወጣትነትሽንም ጡቶች ባሻሹበት ጊዜ በወጣትነትሽ ትፈጽሚው የነበረውን ጸያፍ ምግባር ተመኘሽ።+ +22 “ስለዚህ ኦሆሊባ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ተጸይፈሽ* የራቅሻቸውን ፍቅረኞችሽን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ፤+ እነሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤+ +23 እነሱም የባቢሎን ልጆችና+ ከለዳውያን+ ���ሉ እንዲሁም የአሦርን ልጆች ሁሉ ጨምሮ የጰቆድ፣+ የሾአ እና የቆአ ሰዎች ናቸው። ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች፣ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች፣ ተዋጊዎችና የተመረጡ አማካሪዎች እንዲሁም ፈረሰኞች ናቸው። +24 እነሱም የጦር ሠረገሎችንና መንኮራኩሮችን* ሁሉ እያንጋጉ፣ ትልቅና ትንሽ* ጋሻ የያዘ እንዲሁም የራስ ቁር የደፋ ብዙ ሠራዊት አስከትለው ጥቃት ይሰነዝሩብሻል። በዙሪያሽም ይሰለፋሉ፤ እኔም የመፍረድ ሥልጣን እሰጣቸዋለሁ፤ እነሱም ትክክል መስሎ በታያቸው መንገድ ይፈርዱብሻል።+ +25 እኔም ቁጣዬን በአንቺ ላይ እገልጣለሁ፤ እነሱም በታላቅ ቁጣ እርምጃ ይወስዱብሻል። አፍንጫሽንና ጆሮዎችሽን ይቆርጣሉ፤ ከአንቺም የቀሩት በሰይፍ ይወድቃሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዳሉ፤ ከአንቺም የቀሩት በእሳት ይበላሉ።+ +26 ልብሶችሽን ይገፉሻል፤+ ያማሩ ጌጣጌጦችሽንም ይነጥቁሻል።+ +27 በግብፅ ምድር የጀመርሽው+ ጸያፍ ምግባርና አመንዝራነትሽ እንዲያበቃ አደርጋለሁ።+ ከእንግዲህ ዓይንሽን ወደ እነሱ አታነሺም፤ ግብፅንም አታስታውሺም።’ +28 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ ለጠላሻቸው ሰዎች፣ ተጸይፈሽ* ለራቅሻቸው ሰዎች አሳልፌ ልሰጥሽ ነው።+ +29 እነሱ በጥላቻ እርምጃ ይወስዱብሻል፤ የደከምሽበትን ነገር ሁሉ ይወስዳሉ፤+ ራቁትሽንና እርቃንሽን ያስቀሩሻል። የፆታ ብልግና ስትፈጽሚ የተገለጠው አሳፋሪ የሆነው እርቃንሽ፣ ጸያፍ ምግባርሽና አመንዝራነትሽ ይፋ ይወጣል።+ +30 እንደ ዝሙት አዳሪ ብሔራትን ተከትለሽ ስለሄድሽና+ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ራስሽን ስላረከስሽ+ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይፈጸሙብሻል። +31 የእህትሽን መንገድ ተከትለሻል፤+ ስለዚህ የእሷን ጽዋ አስጨብጥሻለሁ።’+ +32 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጥልቅና ሰፊ የሆነውን የእህትሽን ጽዋ ትጠጫለሽ፤+ደግሞም መሳቂያና መሳለቂያ ትሆኛለሽ፤ ጽዋውም በዚህ የተሞላ ነው።+ +33 በስካርና በሐዘን፣በሽብርና በጥፋት ጽዋ ትዋጫለሽ፤*ይህም የእህትሽ የሰማርያ ጽዋ ነው። +34 ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽ፤+ የጽዋውንም ስብርባሪዎች ትቆረጣጥሚያለሽ፤ከዚያም ጡቶችሽን ትቆርጫለሽ። “እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’ +35 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለረሳሽኝና ጨርሶ ቸል ስላልሽኝ*+ ጸያፍ ምግባርሽና አመንዝራነትሽ የሚያስከትለውን መዘዝ ትቀበያለሽ።’” +36 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በኦሆላና በኦሆሊባ+ ላይ ትፈርዳለህ? አስጸያፊ ተግባራቸውንስ ፊት ለፊት ትነግራቸዋለህ? +37 እነሱ አመንዝረዋል፤*+ እጃቸውም በደም ተበክሏል። አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻቸው ጋር ከማመንዘራቸውም በተጨማሪ ለእኔ የወለዷቸውን ልጆች ለጣዖቶቻቸው መብል እንዲሆኑ ለእሳት አሳልፈው ሰጥተዋል።+ +38 በተጨማሪም በእኔ ላይ እንዲህ አድርገዋል፦ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል፤ ሰንበቶቼንም አቃለዋል። +39 ልጆቻቸውን አስጸያፊ ለሆኑት ጣዖቶቻቸው ከሠዉ+ በኋላ በዚያው ቀን ወደ መቅደሴ መጥተው አረከሱት።+ እንግዲህ በቤቴ ውስጥ ይህን አድርገዋል። +40 አልፎ ተርፎም ከሩቅ ቦታ ወንዶች እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ።+ እነሱ በመጡ ጊዜ ገላሽን ታጠብሽ፤ ዓይንሽን ተኳልሽ፤ በጌጣጌጥም ተዋብሽ።+ +41 እጅግ ባማረ ድንክ አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፤+ በፊቱም በተሰናዳ ማዕድ+ ላይ ዕጣኔንና+ ዘይቴን አኖርሽ።+ +42 በዚያም በፈንጠዝያ ላይ ያሉ ብዙ ወንዶች ሁካታ ይሰማ ነበር፤ በመካከላቸውም ከምድረ በዳ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ። እነሱም በሴቶቹ እጆች ላይ አምባር አጠለቁ፤ በራሳቸውም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉላቸው። +43 “ከዚያም እኔ ሰውነቷ በምንዝር ስላለቀው ሴት፣ ‘አሁንም ማመንዘሯን ትቀጥላለች’ አልኩ። +44 ሰው ወደ ዝሙት አዳሪ እንደሚሄድ ሁሉ እነሱም ወደ እሷ መሄዳቸውን ቀጠሉ። በዚህ መንገድ፣ ባለጌ ወደሆኑት ወደ ኦሆላና ወደ ኦሆሊባ ገቡ። +45 ጻድቃን ግን ለምንዝርና ለደም አፍሳሽነት የሚገባውን ፍርድ ይፈርዱባታል፤+ እነሱ አመንዝሮች ናቸውና፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል።+ +46 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘መቀጣጫ ያደርጋቸውና ለብዝበዛ ይዳርጋቸው ዘንድ በእነሱ ላይ ብዙ ሠራዊት ይሰበሰባል።+ +47 ሠራዊቱ ድንጋይ ይወረውርባቸዋል፤+ በሰይፉም ይቆራርጣቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ይገድላል፤+ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላል።+ +48 በምድሪቱ ላይ የሚፈጸመው ጸያፍ ምግባር እንዲወገድ አደርጋለሁ፤ ሴቶቹም ሁሉ ከዚህ ይማራሉ፤ የእናንተንም ጸያፍ ምግባር ከመከተል ይርቃሉ።+ +49 የፈጸማችሁት ጸያፍ ምግባር እንዲሁም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ የሠራችሁት ኃጢአት የሚያስከትለውን መዘዝ እንድትቀበሉ ያደርጋሉ፤ እኔም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”+ +34 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር። ትንቢት ተናገር፤ እረኞቹንም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ራሳቸውን ለሚመግቡ የእስራኤል እረኞች ወዮላቸው!+ እረኞቹ ሊመግቡ የሚገባው መንጋውን አይደለም?+ +3 ጮማውን ትበላላችሁ፤ ሱፉን ትለብሳላችሁ፤ የሰባውንም እንስሳ ታርዳላችሁ፤+ መንጋውን ግን አትመግቡም።+ +4 የደከመውን አላበረታችሁም፣ የታመመውን አልፈወሳችሁም፣ የተጎዳውን በጨርቅ አላሰራችሁትም፣ የባዘኑትን መልሳችሁ አላመጣችሁም ወይም የጠፋውን አልፈለጋችሁም፤+ ከዚህ ይልቅ በጭካኔና በግፍ ገዛችኋቸው።+ +5 በጎቹ እረኛ በማጣታቸው ተበታተኑ፤+ ተበታትነው ለዱር አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ። +6 በጎቼ በየተራራውና ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ባዘኑ፤ በምድር ሁሉ ላይ ተበተኑ፤ የፈለጋቸው ወይም እነሱን ለማግኘት የጣረ አንድም ሰው የለም። +7 “‘“ስለዚህ እናንተ እረኞች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ +8 ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “በጎቼ እረኛ ስላጡና እረኞቼ በጎቼን ስላልፈለጉ፣ ይልቁንም እረኞቹ ራሳቸውን ስለመገቡና በጎቼን ስላልመገቡ፣ በጎቼ ለአደን ተዳርገዋል፤ ለዱር አራዊትም ሁሉ መብል ሆነዋል፤”’ +9 ስለዚህ እናንተ እረኞች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። +10 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ በእረኞቹ ላይ ተነስቻለሁ፤ ስለ በጎቼ እጠይቃቸዋለሁ፤* በጎቼን እንዳያሰማሩም* እከለክላቸዋለሁ፤+ እረኞቹም ከእንግዲህ ራሳቸውን አይመግቡም። በጎቼን ከአፋቸው አስጥላለሁ፤ ከእንግዲህ ለእነሱ መብል አይሆኑም።’” +11 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆኝ፣ እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ ደግሞም እንከባከባቸዋለሁ።+ +12 የተበታተኑትን በጎቹን አግኝቶ እንደሚመግብ እረኛ በጎቼን እንከባከባለሁ።+ በደመናትና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።+ +13 ከሕዝቦች መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየአገሩም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች፣ በየጅረቱ ዳርና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት መኖሪያ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።+ +14 ጥሩ በሆነ መስክ ላይ አሰማራቸዋለሁ፤ ከፍ ያሉት የእስራኤል ተራሮችም የግጦሽ መሬት ይሆኗቸዋል።+ በዚያም ጥሩ በሆነ የግጦሽ መሬት ላይ ያርፋሉ፤+ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ መስክ ይሰማራሉ።” +15 “‘“በጎቼን እኔ ራሴ አሰማራለሁ፤+ እኔ ራሴም አሳርፋቸዋለሁ”+ ይላ�� ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +16 “የጠፋውን እፈልጋለሁ፤+ የባዘነውን መልሼ አመጣለሁ፤ የተጎዳውን በጨርቅ አስራለሁ፤ የደከመውን አበረታለሁ፤ የወፈረውንና ጠንካራ የሆነውን ግን አጠፋለሁ። እፈርድበታለሁ፤ ተገቢውንም ቅጣት እሰጠዋለሁ።” +17 “‘በጎቼ ስለሆናችሁት ስለ እናንተ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በበግና በበግ መካከል እንዲሁም በአውራ በጎችና በአውራ ፍየሎች መካከል ልፈርድ ነው።+ +18 እናንተ ምርጥ ከሆነው የግጦሽ ስፍራ መመገባችሁ አነሳችሁ? የቀሩትን የግጦሽ ስፍራዎች ደግሞ በእግራችሁ መረጋገጥ ይገባችኋል? እጅግ የጠራውን ውኃ ከጠጣችሁ በኋላስ ውኃውን በእግራችሁ እየመታችሁ ማደፍረሳችሁ ተገቢ ነው? +19 ታዲያ በጎቼ በእግራችሁ በረጋገጣችሁት የግጦሽ መስክ ላይ መሰማራትና በእግራችሁ እየመታችሁ ያደፈረሳችሁትን ውኃ መጠጣት ይኖርባቸዋል?” +20 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላቸዋል፦ “እነሆኝ፣ እኔ ራሴ በሰባው በግና ከሲታ በሆነው በግ መካከል እፈርዳለሁ፤ +21 እናንተ የታመሙት ሁሉ በየአቅጣጫው እስኪበታተኑ ድረስ በጎናችሁና በትከሻችሁ ገፍታችኋቸዋልና፤ በቀንዳችሁም ገፍትራችኋቸዋል። +22 በጎቼንም አድናለሁ፤ እነሱም ከእንግዲህ ለአደን አይዳረጉም፤+ እኔም በበግና በበግ መካከል እፈርዳለሁ። +23 በእነሱ ላይ አንድ እረኛ ይኸውም አገልጋዬን ዳዊትን* አስነሳለሁ፤+ እሱም ይመግባቸዋል። እሱ ራሱ ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል።+ +24 ደግሞም እኔ ይሖዋ አምላካቸው እሆናለሁ፤+ አገልጋዬ ዳዊት ደግሞ በመካከላቸው አለቃ ይሆናል።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁ። +25 “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ አደገኛ የሆኑ የዱር አራዊትንም ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ፤+ በመሆኑም በምድረ በዳ ያለስጋት ይኖራሉ፤ በጫካዎችም ውስጥ ይተኛሉ።+ +26 እነሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያለውን ቦታ በረከት አደርጋቸዋለሁ፤+ ዝናብም በወቅቱ እንዲዘንብ አደርጋለሁ። በረከት እንደ ዝናብ ይወርዳል።+ +27 የሜዳው ዛፎች ፍሬያቸውን ይሰጣሉ፤ መሬቱም ፍሬ ይሰጣል፤+ እነሱም በምድሪቱ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ። ቀንበራቸውን በምሰብርበትና ባሪያ አድርገው ከሚገዟቸው እጅ በማድናቸው ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ +28 ከእንግዲህ ወዲህ ብሔራት እነሱን ለማደን አይነሱም፤ የምድር አራዊትም አይበሏቸውም፤ ያለስጋትም ይኖራሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።+ +29 “‘“ዝና የሚያስገኝ* የእርሻ ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ በምድሪቱ ላይ በረሃብ አያልቁም፤+ ደግሞም ከእንግዲህ ወዲህ ብሔራት አያዋርዷቸውም።+ +30 ‘በዚህ ጊዜ እኔ አምላካቸው ይሖዋ ከእነሱ ጋር እንደሆንኩና እነሱ ይኸውም የእስራኤል ቤት ሕዝቤ እንደሆኑ ያውቃሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’ +31 “‘እናንተ በጎቼ፣+ የምንከባከባችሁ በጎች፣ ከአፈር የተሠራችሁ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +19 “ስለ እስራኤል አለቆች ሙሾ አውጣ፤* +2 እንዲህም በል፦‘እናትህ ምን ነበረች? በአንበሶች መካከል ያለች እንስት አንበሳ ነበረች። በብርቱ ደቦል አንበሶች መሃል ተኛች፤ ግልገሎቿንም በዚያ አሳደገች። + 3 ከግልገሎቿ መካከል አንዱን ተንከባክባ አሳደገችው፤ እሱም ብርቱ ደቦል አንበሳ ሆነ።+ አድኖ መብላት ተማረ፤ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ። + 4 ብሔራት ስለ እሱ ሰሙ፤ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶም ያዙት፤በስናግም እየጎተቱ ወደ ግብፅ ምድር አመጡት።+ + 5 እሷም በትዕግሥት ስትጠባበቅ ከቆየች በኋላ የመመለስ ተስፋ እንደሌለው ተገነዘበች። በመሆኑም ከግልገሎቿ መካከል ሌላውን ወስዳ እንደ ብርቱ ደቦል አንበሳ አድርጋ ላከችው። + 6 ��ሱም በአንበሶች መካከል ይጎማለል ጀመር፤ ብርቱ ደቦል አንበሳም ሆነ። አድኖ መብላት ተማረ፤ ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ።+ + 7 በማይደፈሩት ማማዎቻቸው መካከል አደባ፤ ከተሞቻቸውንም አወደመ፤ከዚህም የተነሳ ግሳቱ ወና በሆነችው ምድር ላይ አስተጋባ።+ + 8 በዙሪያው ባሉ ግዛቶች ያሉ ብሔራት መረባቸውን በእሱ ላይ ለመዘርጋት ተነሱበት፤እሱም ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ። + 9 በስናግ ጎትተው በእንስሳት ጎጆ ውስጥ በመክተት ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት። ከዚያ በኋላ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ እንዳይሰማ በዚያ አሰሩት። +10 እናትህ በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣ በደምህ ውስጥ ያለ የወይን ተክል* ነበረች።+ ከውኃው ብዛት የተነሳ ፍሬ አፈራች፤ ብዙ ቅርንጫፎችም ነበሯት። +11 ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆኑ ጠንካራ ቅርንጫፎች* አወጣች። አድጋ ከሌሎች ዛፎች ይበልጥ ረጅም ሆነች፤ደግሞም ከርዝመቷና ከቅጠሎቿ ብዛት የተነሳ ጎልታ ታየች። +12 ሆኖም በቁጣ ተነቀለች፤+ ወደ ምድርም ተጣለች፤የምሥራቅም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀው። ጠንካራ ቅርንጫፎቿ ተሰብረው ደረቁ፤+ እሳትም በላቸው።+ +13 በዚህ ጊዜ በምድረ በዳ፣ውኃ በሌለበት ደረቅ ምድር ተተከለች።+ +14 እሳት ከቅርንጫፎቿ* ወጥቶ ቀንበጦቿንና ፍሬዋን በላ፤በእሷም ላይ አንድም ጠንካራ ቅርንጫፍ፣ ለገዢዎችም የሚሆን በትረ መንግሥት አልተረፈም።+ “‘ይህ ሙሾ ነው፤ ሙሾ ሆኖም ያገለግላል።’” +20 በሰባተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ይሖዋን ለመጠየቅ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። +2 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +3 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመጣችሁት እኔን ለመጠየቅ ነው? ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ለጥያቄያችሁ ምላሽ አልሰጥም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’ +4 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነሱ ላይ ለመፍረድ* ተዘጋጅተሃል? በእነሱ ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅተሃል? አባቶቻቸው የሠሯቸውን አስጸያፊ ነገሮች አሳውቃቸው።+ +5 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤልን በመረጥኩበት ቀን፣+ ለያዕቆብ ቤት ዘሮች ማልኩላቸው፤* በግብፅም ምድር ራሴን አሳወቅኳቸው።+ አዎ፣ ማልኩላቸው፤ ደግሞም ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ’ አልኳቸው። +6 በዚያ ቀን፣ ከግብፅ ምድር አውጥቼ ለእነሱ ወደመረጥኳት* ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር እንደማስገባቸው ማልኩላቸው።+ እሷም ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ* ነበረች። +7 ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እያንዳንዳችሁ በዓይናችሁ ፊት ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አስወግዱ፤ አስጸያፊ በሆኑት የግብፅ ጣዖቶች* ራሳችሁን አታርክሱ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’+ +8 “‘“እነሱ ግን በእኔ ላይ ዓመፁ፤ እኔን ለመስማትም ፈቃደኞች አልነበሩም። በፊታቸው ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አላስወገዱም፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑትን የግብፅ ጣዖቶች አልተዉም።+ በመሆኑም በግብፅ ምድር ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል ገባሁ። +9 ይሁንና እነሱ በሚኖሩባቸው ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ።+ እነሱን* ከግብፅ ምድር ባወጣሁበት ጊዜ በእነዚህ ብሔራት ፊት ማንነቴን አሳውቄአቸዋለሁና።*+ +10 ስለሆነም ከግብፅ ምድር አውጥቼ ወደ ምድረ በዳ መራኋቸው።+ +11 “‘“ከዚያም ደንቦቼን ሰጠኋቸው፤ ድንጋጌዎቼንም አሳወቅኳቸው፤+ ይህን ያደረግኩት እነሱን የሚከተል ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት እንዲኖር ነው።+ +12 ደግሞም በእኔና በእነሱ መካከል ���ልክት እንዲሆን+ ሰንበቶቼን ሰጠኋቸው፤+ ይህን ያደረግኩት የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ እንዲያውቁ ነው። +13 “‘“ሆኖም የእስራኤል ቤት ሰዎች በምድረ በዳ በእኔ ላይ ዓመፁ።+ ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አቃለዋል። ሰንበቶቼንም ፈጽሞ አረከሱ። በመሆኑም ጨርሶ አጠፋቸው ዘንድ በምድረ በዳ በእነሱ ላይ ታላቅ ቁጣዬን ለማፍሰስ ቃል ገባሁ።+ +14 እነሱን* ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ።+ +15 ደግሞም ለእነሱ ወደሰጠኋት ወተትና ማር ወደምታፈሰው፣+ ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ* ወደሆነችው ምድር እንደማላስገባቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤+ +16 ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አቃለዋል፤ ደንቦቼንም አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰንበቶቼንም አርክሰዋል፤ ልባቸው አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻቸውን ተከትሏልና።+ +17 “‘“እኔ* ግን እንዳላጠፋቸው ራራሁላቸው፤ ደግሞም አላጠፋኋቸውም፤ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልፈጀኋቸውም። +18 በምድረ በዳ ልጆቻቸውን እንዲህ አልኳቸው፦+ ‘የአባቶቻችሁን ሥርዓት አትከተሉ፤+ ድንጋጌዎቻቸውንም አታክብሩ፤ ወይም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ራሳችሁን አታርክሱ። +19 እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። ደንቦቼን አክብራችሁ ተመላለሱ፤ ድንጋጌዎቼንም ጠብቁ፤ በሥራም አውሏቸው።+ +20 ደግሞም ሰንበቶቼን ቀድሱ፤+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ሆነው ያገለግላሉ።’+ +21 “‘“ሆኖም ልጆቹ በእኔ ላይ ያምፁ ጀመር።+ ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደግሞም በሥራ ላይ አላዋሉም። ሰንበቶቼን አረከሱ። በመሆኑም በምድረ በዳ ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል +22 ይሁንና እነሱን* ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል እጄን መለስኩ፤+ ስለ ስሜም ስል እርምጃ ወሰድኩ።+ +23 ደግሞም በብሔራት መካከል እንደምበታትናቸውና ወደተለያዩ አገሮች እንደምሰዳቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤+ +24 ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደንቦቼንም አቃለዋል፤+ ሰንበቶቼን አርክሰዋል፤ ደግሞም እነሱ* አስጸያፊ የሆኑትን የአባቶቻቸውን ጣዖቶች ተከትለዋል።+ +25 እኔም ጥሩ ባልሆነ ሥርዓት እንዲመላለሱና ሕይወት የማያስገኙላቸውን ድንጋጌዎች እንዲከተሉ ተውኳቸው።+ +26 አስከፊ ሁኔታ ይደርስባቸው ዘንድ እያንዳንዱን የበኩር ልጅ ለእሳት አሳልፈው ሲሰጡ+ በገዛ መሥዋዕታቸው እንዲረክሱ አደረግኩ፤ ይህም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቁ ዘንድ ነው።”’ +27 “ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በዚህም መንገድ አባቶቻችሁ ለእኔ ያላቸውን ታማኝነት በማጉደል ሰደቡኝ። +28 ለእነሱ ለመስጠት ወደማልኩላቸው ምድር አመጣኋቸው።+ ከፍ ያለ ኮረብታና የለመለመ ዛፍ ሁሉ ባዩ ጊዜ+ በዚያ መሥዋዕታቸውንና ቁጣ የሚያነሳሳ መባቸውን ያቀርቡ ጀመር። በዚያም ደስ የሚያሰኘውን* የመሥዋዕቶቻቸውን መዓዛ አቀረቡ፤ የመጠጥ መባቸውንም አፈሰሱ። +29 እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እናንተ የምትሄዱበት ይህ ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ ምንድን ነው? (ይህ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ባማ * ተብሎ ይጠራል።)’”’+ +30 “እንግዲህ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አባቶቻችሁ አስጸያፊ ከሆኑ ጣዖቶቻቸው ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ሲሉ እነሱን በመከተል ራሳቸውን እንዳረከሱ ���ሉ እናንተም ራሳችሁን ታረክሳላችሁ?+ +31 አስጸያፊ ለሆኑት ጣዖቶቻችሁ ሁሉ መሥዋዕት በማቅረብ ይኸውም ልጆቻችሁን ለእሳት አሳልፋችሁ በመስጠት እስከ ዛሬ ድረስ ራሳችሁን እያረከሳችሁ ነው?+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ታዲያ እንዲህ እያደረጋችሁ ለጥያቄያችሁ ምላሽ መስጠት ይኖርብኛል?”’+ “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለጥያ +32 “እንጨትና ድንጋይ እንደሚያመልኩት* ብሔራት፣ እንደ ሌሎቹም አገሮች ሕዝቦች እንሁን”+ በማለት የምታውጠነጥኑት ሐሳብ* ፈጽሞ አይሳካም።’” +33 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ በእናንተ ላይ ንጉሥ ሆኜ እገዛለሁ።+ +34 በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ ከሕዝቦች መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ።+ +35 ወደ ሕዝቦች ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ፤ በዚያም ፊት ለፊት እፋረዳችኋለሁ።+ +36 “‘አባቶቻችሁን በግብፅ ምድረ በዳ እንደተፋረድኳቸው ሁሉ እናንተንም እፋረዳችኋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +37 ‘ከእረኛ በትር በታች አሳልፋችኋለሁ፤+ ደግሞም በቃል ኪዳኑ ግዴታ ውስጥ* እንድትገቡ አደርጋለሁ። +38 ሆኖም በእኔ ላይ የሚያምፁትንና በደል የሚፈጽሙትን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ።+ የባዕድ አገር ሰው ሆነው ከሚኖሩበት ምድር አወጣቸዋለሁና፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’ +39 “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ እናንተን በተመለከተ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ሄዳችሁ አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻችሁን አገልግሉ።+ ከዚያ በኋላ ግን እኔን ባለመስማታችሁ መዘዙን ትቀበላላችሁ፤ በመሥዋዕቶቻችሁና አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ቅዱስ ስሜን አታረክሱም +40 “‘በቅዱሱ ተራራዬ፣ ከፍ ባለውም የእስራኤል ተራራ ላይ፣’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘መላው የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ አዎ ሁሉም በዚያ በምድሪቱ ላይ ያገለግሉኛልና።+ በዚያም በእነሱ ደስ እሰኛለሁ፤ ደግሞም ቅዱስ ከሆኑት ነገሮቻችሁ ሁሉ መዋጮዎቻችሁንና የመባችሁን የፍሬ በኩራት እሻለሁ።+ +41 ከሕዝቦች መካከል በማወጣችሁና ከተበተናችሁባቸው አገሮች በምሰበስባችሁ ጊዜ+ ደስ በሚያሰኘው* መዓዛ የተነሳ በእናንተ እረካለሁ፤ በብሔራትም ፊት በእናንተ መካከል እቀደሳለሁ።’+ +42 “‘ለአባቶቻችሁ ለመስጠት ወደማልኩላቸው አገር፣ ወደ እስራኤል ምድር ሳመጣችሁ+ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ +43 በዚያም ራሳችሁን ያረከሳችሁባቸውን ምግባራችሁንና ድርጊቶቻችሁን ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤+ በሠራችኋቸውም መጥፎ ነገሮች ሁሉ የተነሳ ራሳችሁን* ትጸየፋላችሁ።+ +44 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እንደ ክፉ ምግባራችሁ ወይም እንደ ብልሹ ተግባራችሁ ሳይሆን፣ ስለ ስሜ ስል እርምጃ በምወስድበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +45 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +46 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን በስተ ደቡብ አቅጣጫ አዙረህ ወደ ደቡብ ተናገር፤ በደቡብም ምድር ባለው ደን ላይ ትንቢት ተናገር። +47 በደቡብ ለሚገኘው ደን እንዲህ በል፦ ‘የይሖዋን ቃል ስማ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንተ ላይ እሳት አነዳለሁ፤+ እሳቱም በአንተ ውስጥ ያለውን የለመለመውንና ደረቁን ዛፍ ሁሉ ይበላል። የሚንቦገቦገው ነበልባል አይጠፋም፤+ እሱም ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለውን ፊት* ሁሉ ይለበልባል። +48 ሥጋ ለባሽም* ሁሉ እሳቱን ያነደድኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያያል፤ በመሆኑም እሳቱ አይጠፋም።”’”+ +49 እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሱ ስለ እኔ ‘ሁልጊዜ የሚናገረው እንቆቅልሽ* ነው’ ይላሉ።” +3 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ በፊትህ ያለውን ብላ።* ይህን ጥቅልል ብላ፤ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር” አለኝ።+ +2 ስለዚህ አፌን ከፈትኩ፤ እሱም ጥቅልሉን እንድበላው ሰጠኝ። +3 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን የሰጠሁህን ጥቅልል ብላ፤ ሆድህንም ሙላ” አለኝ። እኔም ጥቅልሉን መብላት ጀመርኩ፤ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠኝ።+ +4 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወደ እስራኤል ቤት ሂድ፤ ቃሌንም ንገራቸው። +5 የተላክኸው ወደ እስራኤል ቤት እንጂ ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገር ሕዝብ አይደለምና። +6 ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገሩና ቃላቸው ሊገባህ ወደማይችል ብዙ ሕዝቦች አልተላክህም። ወደ እነሱ ብልክህማ ኖሮ ይሰሙህ ነበር።+ +7 የእስራኤል ቤት ግን ሊሰሙህ አይፈልጉም፤ እኔን መስማት አይፈልጉምና።+ የእስራኤል ቤት ወገኖች ሁሉ ግትርና ልበ ደንዳና ናቸው።+ +8 እነሆ፣ ፊትህን ልክ እንደ እነሱ ፊት ጠንካራ አድርጌዋለሁ፤ ግንባርህንም ልክ እንደ እነሱ ግንባር አጠንክሬዋለሁ።+ +9 ግንባርህን እንደ አልማዝ፣ ከባልጩትም ይበልጥ ጠንካራ አድርጌዋለሁ።+ አትፍራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር፤+ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።” +10 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የምነግርህን ቃል ሁሉ በልብህ ያዝ፤ ደግሞም አዳምጥ። +11 በምርኮ ወደተወሰዱት ወገኖችህ*+ ሄደህ ንገራቸው። ቢሰሙም ባይሰሙም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው።”+ +12 ከዚያም መንፈስ ወደ ላይ አነሳኝ፤+ ከበስተ ኋላዬም ታላቅ የጉምጉምታ ድምፅ “የይሖዋ ክብር ከስፍራው ይወደስ” ሲል ሰማሁ። +13 በዚያም የሕያዋን ፍጥረታቱ ክንፎች እርስ በርስ ሲነካኩ የሚያሰሙት ድምፅ፣+ በአጠገባቸው ያሉት መንኮራኩሮች*+ የሚያሰሙት ድምፅና የታላቅ ጉምጉምታ ድምፅ ነበር። +14 መንፈስም ወደ ላይ አንስቶ ወሰደኝ፤ እኔም ተማርሬና መንፈሴ ተቆጥቶ ሄድኩ፤ የይሖዋም ብርቱ እጅ በእኔ ላይ አርፋ ነበር። +15 ስለሆነም በቴልአቢብ፣ በኬባር ወንዝ+ አቅራቢያ ይኖሩ ወደነበሩት በግዞት የተወሰዱ ሰዎች ሄድኩ፤ እነሱም በሚኖሩበት ስፍራ ተቀመጥኩ፤ በድንጋጤ ፈዝዤም+ በመካከላቸው ሰባት ቀን ቆየሁ። +16 ሰባቱ ቀናት ካለፉ በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፦ +17 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤+ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው።+ +18 ክፉውን ሰው ‘በእርግጥ ትሞታለህ’ ባልኩት ጊዜ ባታስጠነቅቀው፣ ደግሞም ክፉው ሰው በሕይወት ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ ማስጠንቀቂያ ባትሰጠው፣+ እሱ ክፉ በመሆኑ በሠራው በደል ይሞታል፤+ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ።*+ +19 ሆኖም ክፉውን ሰው አስጠንቅቀኸው ከክፋቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፣ እሱ በሠራው በደል ይሞታል፤ አንተ ግን የገዛ ሕይወትህን* በእርግጥ ታድናለህ።+ +20 ይሁንና ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣* እኔ በፊቱ መሰናክል አስቀምጣለሁ፤ እሱም ይሞታል።+ ሳታስጠነቅቀው ከቀረህ በሠራው ኃጢአት የተነሳ ይሞታል፤ ያከናወነውም የጽድቅ ሥራ አይታወስም፤ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ።*+ +21 ሆኖም ጻድቁን ሰው ኃጢአት እንዳይሠራ ብታስጠነቅቀውና ኃጢአት ባይሠራ፣ ማስጠንቀቂያውን በመስማቱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤+ አንተም የገዛ ሕይወትህን* ታድናለህ።” +22 በዚያም የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ሆነች፤ እሱም “ተነስተህ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሂድ፤ በዚያም አናግርሃለሁ” አለኝ። +23 ስለዚህ ተነስቼ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሄድኩ፤ እነሆም በኬባር ወንዝ+ አጠገብ ያየሁትን ክብር የሚመስል የይሖዋ ክብር በዚያ ነበር፤+ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ። +24 ከዚያም መንፈስ ወደ ውስጤ ገብቶ በእግሬ አቆመኝ፤+ አምላክም አናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፦ “ወደ ቤትህ ሄደህ በርህን ዘግተህ ተቀመጥ። +25 የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን በገመድ ይጠፍሩሃል፤ በመካከላቸውም እንዳትመላለስ ያስሩሃል። +26 እኔም ምላስህን ከላንቃህ ጋር አጣብቃለሁ፤ ዱዳም ትሆናለህ፤ ልትወቅሳቸውም አትችልም፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው። +27 በማናግርህ ጊዜ ግን አፍህን እከፍታለሁ፤ አንተም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው።+ የሚሰማ ይስማ፤+ የማይሰማም አይስማ፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው።+ +24 የይሖዋ ቃል በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ቀን፣* አዎ ይህንኑ ቀን መዝግብ። የባቢሎን ንጉሥ በዚሁ ቀን በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀምሯል።+ +3 ዓመፀኛውን ቤት አስመልክቶ ምሳሌ* ተናገር፤ ስለ እነሱም እንዲህ በል፦ “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ድስቱን* ጣደው፤ እሳት ላይ ጣደው፤ ውኃም ጨምርበት።+ + 4 ጭኑንና ወርቹን ጨምሮ ጥሩ ጥሩ የሆነውን ሙዳ ሥጋ ሁሉ ሰብስበህ ጨምርበት፤+ምርጥ የሆኑ አጥንቶችንም ሙላበት። + 5 ከመንጋው ምርጥ የሆነውን በግ ውሰድ፤+ በድስቱም ሥር ዙሪያውን ማገዶ ጨምር። ሥጋውን ቀቅለው፤ በውስጡ ያለውንም አጥንት አብስለው።”’ +6 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የዛገ ድስት ለሆነችውና ዝገቷ ላለቀቀው እንዲሁም ደም አፍሳሽ ለሆነችው ከተማ ወዮላት!+ ሥጋውን አንድ በአንድ አውጣ፤+ ዕጣ መጣል አያስፈልግህም። + 7 ያፈሰሰችው ደም በውስጧ ይገኛልና፤+ በገላጣ ዓለት ላይ አፍስሳዋለች። በአፈር እንዲሸፈን መሬት ላይ አላፈሰሰችውም።+ + 8 ቁጣዬ ተነሳስቶ እበቀላት ዘንድያፈሰሰችው ደም እንዳይሸፈንደሙን በሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለት ላይ አደረግኩት።’+ + 9 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ደም አፍሳሽ ለሆነችው ከተማ ወዮላት!+ ማገዶውን እቆልለዋለሁ። +10 እንጨቱን ከምር፤ እሳቱን አቀጣጥል፤ሥጋውን በደንብ ቀቅል፤ መረቁን አፍስ፤ አጥንቶቹም ይረሩ። +11 ባዶውን ድስት እንዲግል ፍሙ ላይ ጣደው፤መዳቡም በጣም ይግላል። ቆሻሻው በውስጡ ይቀልጣል፤+ ዝገቱንም እሳት ይበላዋል። +12 ድስቱ በጣም ከመዛጉ የተነሳ ስለማይለቅ ከንቱ ልፋት ነው፤ደግሞም እንዲሁ ድካም ብቻ ነው።+ ከነዝገቱ እሳት ውስጥ ጣለው!’ +13 “‘በጸያፍ ምግባርሽ የተነሳ ረክሰሻል።+ ላነጻሽ ሞክሬ ነበር፤ አንቺ ግን ከርኩሰትሽ ንጹሕ ልትሆኚ አትችዪም። በአንቺ ላይ ያደረብኝ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ንጹሕ አትሆኚም።+ +14 እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ። በእርግጥ ይፈጸማል። ምንም ሳላቅማማ፣ ያላንዳች ሐዘንና ጸጸት እርምጃ እወስዳለሁ።+ እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +15 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +16 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በፊትህ ተወዳጅ የሆነውን በአንድ ምት ልወስድብህ ነው።+ አንተም ዋይታ አታሰማ* ወይም አታልቅስ ወይም ደግሞ እንባህን አታፍስ። +17 ሐዘንህን በውስጥህ አምቀህ ያዝ፤ ለሞተው በወጉ መሠረት ሐዘንህን አትግለጽ።+ ጥምጥምህን እሰር፤+ ጫማህንም አድርግ።+ ሪዝህን* አትሸፍን፤+ ሰዎች የሚያመጡልህንም ምግብ* አትብላ።”+ +18 እኔም በጠዋት ለሕዝቡ ተናገርኩ፤ ሚስቴም ማታ ላይ ሞተች። ስለሆነም ጠዋት፣ ልክ እንደታዘዝኩት አደረግኩ። +19 ሕዝቡም “ይህ የምታደርገው ነገር ለእኛ ምን መልእክት እንዳለው አትነግረንም?” አሉኝ። +20 እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ “የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +21 ‘ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እጅግ የምትኮሩበትን፣ በፊታችሁ ተወዳጅ የሆነውንና የልባችሁ ምኞት የሆነውን* መቅደሴን ላረክስ ነው።+ ትታችኋቸው የሄዳችሁት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ +22 ከዚያም እኔ እንዳደረግኩት ታደርጋላችሁ። ሪዛችሁን አትሸፍኑም፤ ሰዎች የሚያመጡላችሁንም ምግብ አትበሉም።+ +23 ጥምጥማችሁ አይፈታም፤ ጫማችሁ ከእግራችሁ ላይ አይወልቅም። ዋይታ አታሰሙም ወይም አታለቅሱም። ይልቁንም በበደላችሁ ትመነምናላችሁ፤+ አንዳችሁ ለሌላው እሮሮ ታሰማላችሁ። +24 ሕዝቅኤል ምልክት ይሆንላችኋል።+ እሱ እንዳደረገው ሁሉ ታደርጋላችሁ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”’” +25 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ምሽጋቸውን ይኸውም ደስ የሚሰኙበትን ያማረ ነገር፣ በፊታቸው ተወዳጅ የሆነውን ነገርና የልባቸውን* ምኞት እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በምወስድባቸው ቀን፣+ +26 አምልጦ የመጣ ሰው ወሬውን ይነግርሃል።+ +27 በዚያን ቀን አፍህን ከፍተህ፣ ካመለጠው ሰው ጋር ትነጋገራለህ፤ ከዚያ በኋላ ዱዳ አትሆንም።+ ምልክት ትሆንላቸዋለህ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።” +32 በ12ኛውም ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፤* እንዲህም በለው፦‘በብሔራት መካከል እንደ ብርቱ ደቦል አንበሳ ነበርክ፤አሁን ግን አክትሞልሃል። አንተ እንደ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት ነበርክ፤+ በወንዞችህ ውስጥ ትንቦጫረቅ፣በእግርህም ውኃውን ታደፈርስ፣ ወንዞቹንም * ታቆሽሽ ነበር።’ + 3 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በብዙ ብሔራት ጉባኤ አማካኝነት መረቤን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤እነሱም በማጥመጃ መረቤ ጎትተው ያወጡሃል። + 4 በምድር ላይ እተውሃለሁ፤አውላላ ሜዳ ላይ እጥልሃለሁ። የሰማይ ወፎች ሁሉ በአንተ ላይ እንዲሰፍሩ አደርጋለሁ፤በመላው ምድር የሚገኙትን የዱር እንስሳትም በአንተ አጠግባለሁ።+ + 5 ሥጋህን በተራሮች ላይ እጥላለሁ፤ከሬሳህ በተረፉት ነገሮችም ሸለቆዎቹን እሞላለሁ።+ + 6 ምድሪቷ እስከ ተራሮች ድረስ በሚፈሰው ደምህ እንድትርስ አደርጋለሁ፤ጅረቶችም በደምህ ይሞላሉ።’* + 7 ‘አንተም በምትጠፋበት ጊዜ ሰማያትን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብታቸውንም አጨልማለሁ። ፀሐይን በደመና እሸፍናለሁ፤ጨረቃም ብርሃኗን አትፈነጥቅም።+ + 8 በሰማያት ያሉትን ብርሃን ሰጪ አካላት ሁሉ ከአንተ የተነሳ አጨልማቸዋለሁ፤ምድርህንም ጨለማ አለብሳለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። + 9 ‘ከአንተ የተማረኩትን ወደ ሌሎች ብሔራት ይኸውም ወደማታውቃቸው አገሮች በምወስድበት ጊዜ+የብዙ ሰዎችን ልብ አስጨንቃለሁ። +10 ብዙ ሕዝቦች እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤ሰይፌንም በፊታቸው ሳወዛውዝ ከአንተ የተነሳ ንጉሦቻቸው በፍርሃት ይርዳሉ። አንተ በምትወድቅበት ቀንእያንዳንዳቸው ለሕይወታቸው በመፍራት ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣሉ።’ +11 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል።+ +12 ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብህ በኃያላን ተዋጊዎች ሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ሁሉም ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኞች ናቸው።+ እነሱም የግብፅን ኩራት ያንኮታኩታሉ፤ ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቧም ሁሉ ይደመሰሳል።+ +13 ከብቶቿን ሁሉ ከብዙ ውኃዎቿ አጠገብ አጠፋለሁ፤+የሰው እግርም ሆነ የከብቶች ኮቴ ዳግመኛ አያደፈርሳቸውም።’+ +14 ‘በዚያን ጊዜ ውኃዎቻቸውን አጠራለሁ፤ወንዞቻቸውም እንደ ዘይት እንዲፈስሱ አደርጋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +15 ‘ግብፅን ባድማና ወና በማድረግ ምድሪቱን የሞላውን ነገር ሁሉ በማስወግድበት ጊዜ፣+ነዋሪዎቿንም ሁሉ በምመታበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ +16 ይህ ሙሾ ነው፤ ሰዎችም ያንጎራጉሩታል፤የብሔራት ሴቶች ልጆች ያንጎራጉሩታል። በግብፅና ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቧ ሁሉ የተነሳ ያንጎራጉሩታል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +17 ከዚያም በ12ኛው ዓመት፣ ከወሩም በ15ኛው ቀን፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +18 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስፍር ቁጥር ለሌለው የግብፅ ሕዝብ ዋይ ዋይ በል፤ እሷንና የኃያላን ብሔራትን ሴቶች ልጆች ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ጋር ከምድር በታች አውርዳቸው። +19 “‘በውበት ማንን ትበልጣለህ? ወደ ታች ውረድ፤ ካልተገረዙትም ጋር ተጋደም!’ +20 “‘በሰይፍ በታረዱት መካከል ይወድቃሉ።+ እሷ ለሰይፍ ተሰጥታለች፤ እሷንም ሆነ ስፍር ቁጥር የሌለውን ሕዝቧን ሁሉ ጎትቱ። +21 “‘ኃያላኑ ተዋጊዎች እሱንና ረዳቶቹን ከጥልቅ መቃብር* ውስጥ ያነጋግሯቸዋል። እነሱ በእርግጥ ወደ ታች ይወርዳሉ፤ ደግሞም በሰይፍ ታርደው፣ እንዳልተገረዙት ሰዎች ይጋደማሉ። +22 አሦር ከመላ ጉባኤዋ ጋር በዚያ ትገኛለች። መቃብሮቻቸው በእሱ ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀዋል።+ +23 መቃብሮቿ በጥልቅ ጉድጓድ* ውስጥ ይገኛሉ፤ ጉባኤዋም በመቃብሯ ዙሪያ አለ፤ ሁሉም በሰይፍ ተመትተው ወድቀዋል፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረው ነበር። +24 “‘ኤላም+ ስፍር ቁጥር ከሌለው ሕዝቧ ሁሉ ጋር በመቃብሯ ዙሪያ ትገኛለች፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀዋል። በሕያዋን ምድር ሽብር የፈጠሩት እነዚህ ሰዎች ሳይገረዙ ከምድር በታች ወርደዋል። ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። +25 በመቃብሯ ዙሪያ ከሚገኘው ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቧ ሁሉ ጋር፣ በታረዱት መካከል መኝታ አዘጋጅተውላታል። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የታረዱ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረው ነበር፤ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። እሱ በታረዱት መካከል እንዲቀመጥ ተደርጓል። +26 “‘መሼቅና ቱባል+ እንዲሁም ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝባቸው ሁሉ* በዚያ ይገኛሉ። መቃብሮቻቸው* በዙሪያው ናቸው። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተወጉ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረዋል። +27 እነሱ፣ ከወደቁትና ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር ወደ መቃብር* ከወረዱት ያልተገረዙ ኃያላን ተዋጊዎች ጋር ይጋደሙ የለም? ሰይፎቻቸውን ከራሳቸው በታች ያደርጋሉ፤* በኃጢአታቸውም የተነሳ የሚደርስባቸው ቅጣት በአጥንታቸው ላይ ይሆናል፤ ምክንያቱም እነዚህ ኃያላን ተዋጊዎች የሕያዋንን ምድር አሸብረዋል። +28 አንተ ግን ባልተገረዙት መካከል ትደቅቃለህ፤ በሰይፍ ከታረዱትም ጋር ትጋደማለህ። +29 “‘ኤዶም፣+ ነገሥታቷና አለቆቿ ሁሉ በዚያ ይገኛሉ፤ ኃያላን ሆነው ሳለ በሰይፍ በታረዱት መካከል ተጋድመዋል፤ እነሱም ካልተገረዙትና+ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱት ጋር ይጋደማሉ። +30 “‘የሰሜን ገዢዎች* በሙሉ ከሲዶናውያን+ ሁሉ ጋር በዚያ ይገኛሉ፤ ኃይላቸው ሽብር የፈጠረ ቢሆንም ከታረዱት ሰዎች ጋር ኀፍረት ተከናንበው ወርደዋል። በሰይፍ ከታረዱት ጋር ሳይገረዙ ይጋደማሉ፤ ወደ ጉድጓድ* ከሚወርዱትም ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። +31 “‘ፈርዖን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይመለከታል፤ ደግሞም ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቡ ላይ ከደረሰው ነገር ሁሉ ይጽናናል፤+ ፈርዖንና ሠራዊቱ ሁሉ በሰይፍ ይታረዳሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +32 “‘በሕያዋን ምድር ሽብር ስለፈጠረ ፈርዖንና ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቡ ሁሉ በሰይፍ ከታረዱት፣ ካልተገረዙት ሰዎች ጋር ለማረፍ ይጋደማሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +7 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “አንተ የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፦ ‘ፍጻሜ! በአራቱ የምድሪቱ ማዕዘናት ላይ ፍጻሜ መጥቷል። +3 አሁን ፍጻሜሽ ደርሷል፤ ቁጣዬንም በአንቺ ላይ አወርዳለሁ፤ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፤ ለፈጸምሻቸውም አስጸያፊ ድርጊቶች ሁሉ ተጠያቂ አደርግሻለሁ። +4 ዓይኔ አያዝንልሽም፤ ደግሞም አልራራልሽም፤+ የተከተልሽው መንገድ የሚያስከትለውን ውጤት አመጣብሻለሁና፤ የፈጸምሻቸው አስጸያፊ ድርጊቶች የሚያስከትሉትን መዘዝ ትቀምሻለሽ።+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’+ +5 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ ጥፋት፣ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥፋት እየመጣ ነው!+ +6 ፍጻሜ እየመጣ ነው፤ ፍጻሜው ይመጣል፤ በአንቺ ላይ ይነሳል።* እነሆ፣ ፍጻሜው እየመጣ ነው! +7 አንቺ በምድሪቱ የምትኖሪ፣ ተራሽ ደርሷል።* ጊዜው እየደረሰ ነው፤ ቀኑ ቀርቧል።+ በተራሮች ላይ የእልልታ ሳይሆን የሁከት ድምፅ ይሰማል። +8 “‘በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ አወርዳለሁ፤+ ንዴቴንም ሁሉ በአንቺ ላይ እወጣለሁ፤+ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፤ ለፈጸምሻቸውም አስጸያፊ ድርጊቶች ሁሉ ተጠያቂ አደርግሻለሁ። +9 ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም።+ የተከተልሽው መንገድ የሚያስከትለውን ውጤት አመጣብሻለሁ፤ የፈጸምሻቸው አስጸያፊ ድርጊቶች የሚያስከትሉብሽን መዘዝ ትቀምሻለሽ። እናንተም የምመታችሁ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ +10 “‘እነሆ ቀኑ! እነሆ ቀኑ እየመጣ ነው!+ ተራሽ ደርሷል፤* በትሩ አብቧል፤ እብሪትም አቆጥቁጧል። +11 ዓመፅ አድጎ የክፋት በትር ሆኗል።+ እነሱም ሆኑ ሀብታቸው ደግሞም ሕዝባቸውም ሆነ ታላቅነታቸው ይጠፋል። +12 ጊዜው ይደርሳል፤ ቀኑም ይመጣል። የሚገዛ አይደሰት፤ የሚሸጥም አይዘን፤ በሕዝባቸው ሁሉ ላይ ቁጣ ነዷልና።*+ +13 ሻጩ በሕይወት ቢተርፍ እንኳ ወደተሸጠው ነገር አይመለስም፤ ራእዩ በሕዝቡ ሁሉ ላይ ነውና። ማንም አይመለስም፤ ከፈጸመውም በደል የተነሳ* ማንም ሕይወቱን ማትረፍ አይችልም። +14 “‘መለከት ነፍተዋል፤+ ሁሉም ቢዘጋጁም ወደ ውጊያ የሚሄድ አንድም ሰው የለም፤ ምክንያቱም ቁጣዬ በሕዝቡ ሁሉ ላይ ነዷል።+ +15 በውጭ ሰይፍ፣+ በውስጥ ደግሞ ቸነፈርና ረሃብ አለ። በሜዳ ያለ ሁሉ በሰይፍ ይሞታል፤ በከተማዋ ውስጥ ያሉትን ደግሞ ረሃብና ቸነፈር ይፈጃቸዋል።+ +16 አምልጠው መትረፍ የቻሉት ሁሉ ወደ ተራሮች ይሄዳሉ፤ እያንዳንዳቸውም በሸለቆ ውስጥ እንዳሉ ርግቦች በበደላቸው ይቃትታሉ።+ +17 እጃቸው ሁሉ ይዝላል፤ ጉልበታቸውም ሁሉ በውኃ ይርሳል።*+ +18 ማቅ ለብሰዋል፤+ ብርክም ይዟቸዋል። ሁሉም ኀፍረት ይከናነባሉ፤ ራስም ሁሉ ይመለጣል።*+ +19 “‘ብራቸውን በየጎዳናው ይጥላሉ፤ ወርቃቸውም አስጸያፊ ነገር ይሆንባቸዋል። በይሖዋ የቁጣ ቀን ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም።+ በልተው አይጠግቡም፤* ሆዳቸውንም አይሞሉም፤ በኃጢአት እንዲወድቁ እንቅፋት ሆኖባቸዋልና።* +20 በጌጦቻቸው ውበት ታበዩ፤ በእነዚህም* ጸያፍ የሆኑ ምስሎቻቸውን ይኸውም አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን ሠሩ።+ በዚህም ምክንያት ብሩንና ወርቁን ርኩስ ነገር አደርግባቸዋለሁ። +21 ባዕዳን የሆኑ ሰዎች እንዲዘርፉት፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ክፉ ሰዎችም እንዲበዘብዙት አሳልፌ እሰ��ቸዋለሁ፤* እነሱም ያረክሱታል። +22 “‘ፊቴን ከእነሱ አዞራለሁ፤+ እነሱም የተሰወረውን ቦታዬን* ያረክሳሉ፤ ዘራፊዎችም ወደ እሷ ይገባሉ፤ ደግሞም ያረክሷታል።+ +23 “‘ምድሪቱ ነፍስ ግድያ በሚያስከትል የተዛባ ፍርድ ስለተሞላች፣+ ከተማዋም በዓመፅ ስለተሞላች+ ሰንሰለት*+ ሥራ። +24 ከብሔራት መካከል እጅግ የከፉትን አመጣለሁ፤+ እነሱም ቤቶቻቸውን ይወርሳሉ፤+ የብርቱዎቹንም ኩራት አጠፋለሁ፤ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ።+ +25 መከራ ሲመጣባቸው ሰላምን ይሻሉ፤ ሆኖም ሰላም አይኖርም።+ +26 በጥፋት ላይ ጥፋት ይመጣል፤ በወሬም ላይ ወሬ ይናፈሳል፤ ሰዎችም ከነቢይ ራእይ ይሻሉ፤+ ሆኖም ሕግ* ከካህን፣ ምክርም ከሽማግሌዎች ዘንድ ይጠፋል።+ +27 ንጉሡ ያለቅሳል፤+ አለቃውም በተስፋ መቁረጥ* ስሜት ይዋጣል፤ የምድሪቱም ሕዝብ ከመሸበሩ የተነሳ እጁ ይንቀጠቀጣል። እንደ መንገዳቸው አደርግባቸዋለሁ፤ ደግሞም እነሱ እንደፈረዱት እፈርድባቸዋለሁ። እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”+ +48 “ከሰሜናዊ ጫፍ አንስቶ የነገዶቹ ስም ይህ ነው፦ የዳን ድርሻ+ የሄትሎንን መንገድ ተከትሎ እስከ ሌቦሃማት*+ እንዲሁም በስተ ሰሜን በደማስቆ ድንበር በኩል፣ ከሃማት+ አጠገብ እስካለው እስከ ሃጻርኤናን ድረስ ይዘልቃል፤ ድርሻውም ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +2 የአሴር ድርሻ+ ከዳን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +3 የንፍታሌም ድርሻ+ ከአሴር ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +4 የምናሴ ድርሻ+ ከንፍታሌም ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +5 የኤፍሬም ድርሻ ከምናሴ ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +6 የሮቤል ድርሻ ከኤፍሬም ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +7 የይሁዳ ድርሻ ከሮቤል ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +"8 በይሁዳ ድንበር፣ ከምሥራቁ ወሰን አንስቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ መዋጮ አድርጋችሁ ለመስጠት የምትለዩት መሬት ወርዱ 25,000 ክንድ* ይሁን፤+ ደግሞም ይህ መሬት ከምሥራቁ ወሰን አንስቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ርዝመቱ ከሌሎቹ ነገዶች ድርሻ ጋር እኩል ይሁን። መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል። " +"9 “መዋጮ አድርጋችሁ በመስጠት ለይሖዋ የምትለዩት መሬት ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ ይሆናል።" +"10 ይህ ለካህናቱ መዋጮ ሆኖ የሚሰጥ ቅዱስ ስፍራ ይሆናል።+ በሰሜን በኩል 25,000 ክንድ፣ በምዕራብ በኩል 10,000፣ በምሥራቅ በኩል 10,000፣ በደቡብ በኩል ደግሞ 25,000 ይሆናል። የይሖዋ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል።" +11 ይህ የሳዶቅ ልጆች+ ለሆኑት የተቀደሱ ካህናት ይሆናል፤ እነሱ በእኔ ፊት ያለባቸውን ኃላፊነት ተወጥተዋል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንና ሌዋውያን በባዘኑ ጊዜ+ ከእነሱ ጋር አልባዘኑም። +12 በሌዋውያን ድንበር በኩል፣ እጅግ ቅዱስ ተደርጎ ከተለየውና መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው መሬት ላይ ድርሻ ያገኛሉ። +"13 ሌዋውያኑ ከካህናቱ መሬት አጠገብ ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ የሆነ ድርሻ ይኖራቸዋል። (አጠቃላይ ርዝመቱ 25,000፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ይሆናል።)" +14 ምርጥ ከሆነው ከዚህ የመሬቱ ድርሻ ላይ የትኛውንም ቦታ መሸጥ፣ መለወጥ ወይም ለሌሎች አሳልፈው መስጠት የለባቸውም፤ ለይሖዋ የተቀደሰ ነውና። +"15 “ደግሞም 25,000 ክንድ ከሆነው ወሰን አጠገብ የሚገኘው፣ ወርዱ 5,000 ክንድ የሆነው የቀረው ቦታ ለከተማዋ ቅዱስ ያልሆነ አገልግሎት+ ይኸውም ለመኖሪያ ቤትና ለግጦሽ መሬት ይውላል። ከተማዋ በመካከሉ ትሆናለች።+" +"16 የከተማዋም መጠን ይህ ነው፦ የሰሜኑ ወሰን 4,500፣ የደቡቡ ወሰን 4,500፣ የምሥራቁ ወሰን 4,500 እንዲሁም የምዕራቡ ወሰን 4,500 ክንድ ነው።" +17 የከተማዋ የግጦሽ መሬት በስተ ሰሜን 250፣ በስተ ደቡብ 250፣ በስተ ምሥራቅ 250 እና በስተ ምዕራብ 250 ክንድ ይሆናል። +"18 “የቀረው ድርሻ ርዝመቱ፣ መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራ+ ጋር እኩል ይሆናል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ 10,000፣ በስተ ምዕራብም 10,000 ክንድ ይሆናል። ርዝመቱ መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራ ጋር እኩል ይሆናል፤ በዚያም የሚመረተው ከተማዋን ለሚያገለግሉ ምግብ ይሆናል።" +19 ከተማዋን የሚያገለግሉ ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ሰዎች መሬቱን ያርሳሉ።+ +"20 “በመዋጮ የተሰጠው መሬት በአጠቃላይ አራቱም ማዕዘኑ እኩል ሲሆን እያንዳንዱ ማዕዘን 25,000 ክንድ ነው። መዋጮ ሆኖ የተሰጠ ቅዱስ ስፍራና የከተማዋ ይዞታ አድርጋችሁ ትለዩታላችሁ። " +"21 “መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከከተማዋ ይዞታ ግራና ቀኝ ያለው የቀረው ቦታ የአለቃው ይሆናል።+ ይህ ቦታ በመዋጮ ከተሰጠው መሬት በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ከሚገኙት 25,000 ክንድ ከሆኑት ወሰኖች አጠገብ ይሆናል። በአቅራቢያው ካሉት የነገዶቹ ድርሻዎች ጋር ይዋሰናል፤ ይህም ለአለቃው ይሆና" +22 “የሌዋውያኑ ይዞታና የከተማዋ ይዞታ በአለቃው ክልል መካከል ይሆናል። የአለቃው ክልል በይሁዳ ድንበርና+ በቢንያም ድንበር መካከል ይሆናል። +23 “የቀሩትን ነገዶች በተመለከተ፣ የቢንያም ድርሻ ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው።+ +24 የስምዖን ድርሻ ከቢንያም ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +25 የይሳኮር ድርሻ+ ከስምዖን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +26 የዛብሎን ድርሻ ከይሳኮር ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው።+ +27 የጋድ ድርሻ ከዛብሎን ምድር ጋር የሚዋሰን+ ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። +28 በጋድ ወሰን በኩል ያለው ደቡባዊ ድንበር ከትዕማር+ እስከ የመሪባትቃዴስ ውኃዎች፣+ እስከ ደረቁ ወንዝና*+ እስከ ታላቁ ባሕር* ይዘልቃል። +29 “ለእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ምድር ይህች ናት፤+ ይህም ድርሻቸው ይሆናል”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +"30 “የከተማዋ መውጫዎች እነዚህ ይሆናሉ፦ በሰሜን በኩል ያለው 4,500 ክንድ ነው።+ " +31 “የከተማዋ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይሰየማሉ። በስተ ሰሜን ሦስት በሮች ያሉ ሲሆን አንዱ በር ለሮቤል፣ አንዱ በር ለይሁዳ፣ አንዱ በር ደግሞ ለሌዊ ይሆናል። +"32 “ምሥራቃዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለዮሴፍ፣ አንዱ በር ለቢንያም፣ አንዱ በር ደግሞ ለዳን ይሆናል። " +"33 “ደቡባዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለስምዖን፣ አንዱ በር ለይሳኮር፣ አንዱ በር ደግሞ ለዛብሎን ይሆናል። " +"34 “ምዕራባዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለጋድ፣ አንዱ በር ለአሴር፣ አንዱ በር ደግሞ ለንፍታሌም ይሆናል። " +"35 “ዙሪያውን መጠኑ 18,000 ክንድ ይሆናል። ከዚያን ቀን ጀምሮ ከተማዋ ‘ይሖዋ በዚያ አለ’ ተብላ ትጠራለች።”+" +"45 “‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በምትከፋፈሉበት ጊዜ+ ከምድሪቱ ላይ ቅዱስ የሆነ ድርሻ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ስጡ።+ ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣* ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ ይሁን።+ ስፍራው በሙሉ* ቅዱስ ድርሻ ይሆናል።" +2 በዚህ ቦታ ውስጥ ለቅዱሱ ስፍራ የሚያገለግል 500 ክንድ በ500 ክንድ*+ የሆነ አራት ማዕዘን ቦታ ይኖራ���፤ በሁሉም በኩል 50 ክንድ የሆነ የግጦሽ መሬት ይኖረዋል።+ +"3 ከተለካው መሬት ላይ ርዝመቱ 25,000፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 የሆነ ስፍራ ለካ፤ እጅግ ቅዱስ የሆነውም መቅደስ በዚያ ውስጥ ይሆናል።" +4 ይሖዋን ለማገልገል ለሚቀርቡትና በመቅደሱ ለሚያገለግሉት ካህናት ቅዱስ ድርሻ ይሆናል።+ ለቤቶቻቸው እንዲሁም ለመቅደሱ የሚሆን ቅዱስ ስፍራ ይሆናል። +"5 “‘በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉት ሌዋውያን ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ የሆነ ድርሻ ይኖራቸዋል፤+ እነሱም 20 የመመገቢያ ክፍሎችን*+ ርስት አድርገው ይወስዳሉ። " +"6 “‘እናንተም ለከተማዋ እንደ ርስት እንዲሆን ርዝመቱ 25,000 ክንድ (መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራ ትይዩ የሆነ) ወርዱ ደግሞ 5,000 ክንድ የሆነ ቦታ ትሰጣላችሁ።+ ይህም ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል። " +7 “‘አለቃው መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ለከተማዋ ከተሰጠው ቦታ ግራና ቀኝ መሬት ይኖረዋል። መሬቱ መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከከተማዋ ይዞታ አጠገብ ይሆናል። ደግሞም በስተ ምዕራብና በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይሆናል። ከምዕራቡ ወሰን እስከ ምሥራቁ ወሰን ድረስ ያለው ርዝመት ለአንዱ ነገድ ከተ +8 ይህ መሬት በእስራኤል ምድር የእሱ ርስት ይሆናል። ከእንግዲህ አለቆቼ በሕዝቤ ላይ ግፍ አይፈጽሙም፤+ ምድሪቱንም ለእስራኤል ቤት ሰዎች በየነገዳቸው ይሰጧቸዋል።’+ +9 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ የእስራኤል አለቆች፣ በጣም አብዝታችሁታል!’ “‘ግፍና ጭቆና መፈጸማችሁን አቁሙ፤ ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ።+ የሕዝቤን ንብረት መቀማታችሁን ተዉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +10 ‘ትክክለኛ ሚዛን፣ ትክክለኛ የኢፍ መስፈሪያና* ትክክለኛ የባዶስ መስፈሪያ* ተጠቀሙ።+ +11 ለኢፍ መስፈሪያና ለባዶስ መስፈሪያ ቋሚ የሆነ መመዘኛ መኖር አለበት። የባዶስ መስፈሪያው አንድ አሥረኛ ሆሜር* የሚይዝ ይሁን፤ የኢፍ መስፈሪያውም አንድ አሥረኛ ሆሜር የሚይዝ ይሁን። ሆሜር መደበኛ መመዘኛ ይሆናል። +12 አንድ ሰቅል*+ 20 ጌራ* ይሁን። ደግሞም 20 ሰቅል፣ 25 ሰቅልና 15 ሰቅል አንድ ላይ ሲደመር አንድ ማኔህ* ይሁንላችሁ።’ +13 “‘የምትሰጡት መዋጮ ይህ ነው፦ ከእያንዳንዱ ሆሜር ስንዴ የኢፍ አንድ ስድስተኛ፣ ከእያንዳንዱ ሆሜር ገብስ ደግሞ የኢፍ አንድ ስድስተኛ መዋጮ ታደርጋላችሁ። +14 የሚሰጠው ዘይት የሚለካው በባዶስ መስፈሪያ ይሆናል። አንድ ባዶስ፣ የቆሮስ* አንድ አሥረኛ ነው፤ አሥር ባዶስ ደግሞ አንድ ሆሜር ነው፤ አሥር ባዶስ ከአንድ ሆሜር ጋር እኩል ነውና። +15 ደግሞም ከእስራኤል መንጎች መካከል ከየሁለት መቶው አንድ በግ ስጡ። እነዚህ ስጦታዎች ለሕዝቡ ማስተሰረያ እንዲሆኑ+ ለእህል መባ፣+ ሙሉ በሙሉ ለሚቃጠል መባና+ ለኅብረት መሥዋዕት+ ይውላሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +16 “‘የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ይህን መዋጮ ለእስራኤል አለቃ ይሰጣል።+ +17 አለቃውም በበዓላት፣ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ወቅት፣ በየሰንበቱና+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች በተወሰኑት በዓላት ወቅት ሁሉ+ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባ፣+ የእህሉን መባና+ የመጠጡን መባ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት።+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ማስተሰረያ እንዲሆን የኃጢአት መባ፣ የእህል መባ፣ ሙሉ በሙሉ የ +18 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከከብቶቹ መካከል ምንም እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን ወስደህ መቅደሱን ከኃጢአት አንጻው።+ +19 ካህኑ የኃጢአት መባ ሆኖ ከቀረበው ደም የተወሰነውን ወስዶ በቤተ መቅደሱ መቃን፣+ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን አራት ማዕዘኖችና በውስጠኛው ግቢ በር መቃን ላይ ያድርግ። +20 አንድ ሰው በ���ህተትና ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ+ ከወሩ በሰባተኛው ቀን እንዲሁ አድርግ፤ እናንተም ለቤተ መቅደሱ ማስተሰረያ ታቀርባላችሁ።+ +21 “‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በ14ኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ።+ ለሰባት ቀን ቂጣ* ትበላላችሁ።+ +22 በዚያም ቀን አለቃው ለራሱና ለምድሩ ነዋሪ ሁሉ የኃጢአት መባ እንዲሆን አንድ ወይፈን ያቀርባል።+ +23 በዓሉ በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀናት፣ በእያንዳንዱ ቀን፣ እንከን የሌለባቸውን ሰባት ወይፈኖችና እንከን የሌለባቸውን ሰባት አውራ በጎች ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል፤+ ደግሞም ለኃጢአት መባ በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቀርባል። +24 በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ወይፈን አንድ ኢፍ፣ ለእያንዳንዱም አውራ በግ አንድ ኢፍ የእህል መባ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን* ዘይት ያቅርብ። +25 “‘በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ15ኛው ቀን፣ በበዓሉ ወቅት ለሰባት ቀናት+ ይህንኑ የኃጢአት መባ፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ፣ የእህል መባና ዘይት ያቅርብ።’” +12 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የምትኖረው በዓመፀኛ ሕዝብ መካከል ነው። እነሱ የሚያዩበት ዓይን አላቸው፣ ግን አያዩም፤ የሚሰሙበት ጆሮ አላቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም፤+ እነሱ ዓመፀኛ ሕዝብ ናቸውና።+ +3 የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተ ግን በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ለመሄድ ጓዝህን አዘጋጅ። ከዚያም እነሱ እያዩህ በቀን ጉዞ ጀምር። እነሱ እያዩህ ከቤትህ ተነስተህ ወደ ሌላ ቦታ እንደ ግዞተኛ ሂድ። ዓመፀኛ ሕዝብ ቢሆኑም እንኳ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይገባቸው ይሆናል። +4 በቀን እነሱ እያዩህ በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ለመሄድ ጓዝህን አዘጋጅተህ አውጣ፤ ከዚያም ምሽት ላይ እነሱ እያዩህ በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ውጣ።+ +5 “እነሱ እያዩ ግንቡን ነድለህ በዚያ በኩል ጓዝህን ተሸክመህ ውጣ።+ +6 እነሱ እያዩ ጓዝህን በትከሻህ ተሸክመህ በጨለማ ይዘኸው ውጣ። መሬቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን፤ ለእስራኤል ቤት ምልክት አደርግሃለሁና።”+ +7 እኔም ልክ እንደታዘዝኩት አደረግኩ። ቀን ላይ በግዞት እንደሚሄድ ሰው ጓዝ፣ ጓዜን ጠቅልዬ አወጣሁ፤ ከዚያም ምሽት ላይ ግንቡን በእጄ ነደልኩት። ሲጨልምም ዓይናቸው እያየ ጓዜን በትከሻዬ ተሸክሜ ወጣሁ። +8 ጠዋት ላይ የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +9 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ዓመፀኛ ሕዝብ የሆኑት የእስራኤል ቤት ሰዎች ‘ምን እያደረግክ ነው?’ ብለው አልጠየቁህም? +10 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ቃል የተነገረው በኢየሩሳሌም ለሚኖረው አለቃና+ በከተማዋ ውስጥ ለሚኖረው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ነው።”’ +11 “እንዲህ በል፦ ‘እኔ ለእናንተ ምልክት ነኝ።+ ልክ እኔ እንዳደረግኩት በእነሱም ላይ እንዲሁ ይደረግባቸዋል። ተማርከው በግዞት ይወሰዳሉ።+ +12 በመካከላቸው ያለው አለቃ በጨለማ ጓዙን በትከሻው ተሸክሞ ይወጣል። ግንቡን ይነድልና ጓዙን ተሸክሞ በዚያ በኩል ይወጣል።+ መሬቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።’ +13 መረቤን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል።+ ከዚያም ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ምድሪቱን ግን አያይም፤ በዚያም ይሞታል።+ +14 በእሱም ዙሪያ ያሉትን ሁሉ ይኸውም ረዳቶቹንና ወታደሮቹን በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ፤+ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+ +15 በብሔራት መካከል ስበትናቸውና በአገሮችም መካከል ስዘራቸው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። +16 ይሁንና በሚሄዱባቸው ብሔራት መካከል አስጸያፊ ስለሆኑት ልማዶቻቸው ሁሉ እንዲናገሩ ከእነሱ መካከል ጥቂት ሰዎች ከሰይፍ፣ ከረሃብና ከቸ��ፈር እንዲተርፉ አደርጋለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።” +17 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +18 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ምግብህን እየተንቀጠቀጥክ ብላ፤ ውኃህንም በስጋትና በጭንቀት ጠጣ።+ +19 ለምድሪቱም ሕዝብ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእስራኤል ምድር ላሉት የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ ይላል፦ “ምግባቸውን በጭንቀት ይበላሉ፤ ውኃቸውንም በፍርሃት ይጠጣሉ፤ በምድሪቱ ላይ የሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ከሚፈጽሙት ዓመፅ የተነሳ ምድራቸው ፈጽማ ባድማ ትሆናለችና።+ +20 ሰው ይኖርባቸው የነበሩት ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም ወና ትሆናለች፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’”+ +21 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +22 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል ምድር ‘ዘመኑ አልፏል፤ ራእይም ሁሉ መና ቀርቷል’ የምትሉት ይህ አባባል ምንድን ነው?+ +23 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህን አባባል አስቀራለሁ፤ በእስራኤልም ምድር ይህን አባባል ዳግመኛ አይጠቀሙበትም።”’ ሆኖም እንዲህ በላቸው፦ ‘ዘመኑ ቀርቧል፤+ እያንዳንዱም ራእይ ይፈጸማል።’ +24 በእስራኤል ቤት መካከል ከእንግዲህ የሐሰት ራእይ ወይም አሳሳች* ሟርት አይኖርምና።+ +25 ‘“እኔ ይሖዋ እናገራለሁና። የተናገርኩት ቃል ሁሉ ከእንግዲህ ሳይዘገይ ይፈጸማል።+ ዓመፀኛው ቤት ሆይ፣ በእናንተ ዘመን+ እኔ እናገራለሁ፤ የተናገርኩትንም እፈጽማለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’” +26 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +27 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ሰዎች* ‘እሱ የሚያየው ራእይ የሚፈጸመው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፤ ትንቢት የሚናገረውም በጣም ሩቅ ስለሆነ ጊዜ ነው’ ይላሉ።+ +28 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ከተናገርኩት ቃል ውስጥ የሚዘገይ አይኖርም፤ የተናገርኩት ቃል ሁሉ ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’” +1 በ30ኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፣ በኬባር ወንዝ+ አጠገብ በግዞት በተወሰደው ሕዝብ+ መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው አምላክ የገለጠልኝን ራእዮች ማየት ጀመርኩ። +2 ከወሩ በአምስተኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ዮአኪን+ በግዞት በተወሰደ በአምስተኛው ዓመት፣ +3 በከለዳውያን+ ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የይሖዋ ቃል የካህኑ የቡዚ ልጅ ወደሆነው ወደ ሕዝቅኤል* መጣ። በዚያም የይሖዋ ኃይል* በእሱ ላይ ወረደ።+ +4 እኔም በማየት ላይ ሳለሁ ከሰሜን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ+ ሲመጣ ተመለከትኩ፤ በዚያም ታላቅ ደመናና በደማቅ ብርሃን የተከበበ የእሳት+ ብልጭታ* ነበር፤ ከእሳቱም መካከል የሚያብረቀርቅ ብረት*+ የሚመስል ነገር ይወጣ ነበር። +5 በመካከሉም የአራት ሕያዋን ፍጥረታት+ አምሳያ ነበር፤ የእያንዳንዳቸውም መልክ እንደ ሰው መልክ ነበር። +6 እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው።+ +7 እግሮቻቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእግራቸውም ኮቴ የጥጃ ኮቴ ይመስል ነበር፤ እግሮቻቸውም እንደተወለወለ መዳብ ያብረቀርቃሉ።+ +8 በአራቱም ጎኖቻቸው ከክንፎቻቸው ሥር የሰው እጆች ነበሯቸው፤ አራቱም ፊቶችና ክንፎች ነበሯቸው። +9 ክንፎቻቸውም እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር። በሚሄዱበት ጊዜ አይዞሩም፤ እያንዳንዳቸውም ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+ +10 የፊታቸው መልክ ይህን ይመስል ነበር፦ አራቱም የሰው ፊት ነበራቸው፤ በስተ ቀኝ የአንበሳ+ ፊት፣ በስተ ግራ የበሬ+ ፊት ነበራቸው፤ ደግሞም አራቱም የንስር+ ፊት ነበራቸው።+ +11 ፊታቸው ይህን ይመስላል። ክንፎቻቸው ከእነሱ በላይ ተዘርግተዋል። እያንዳንዳ��ው እርስ በርሳቸው የሚነካኩ ሁለት ክንፎች ነበሯቸው፤ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር።+ +12 እያንዳንዳቸው መንፈሱ ወደመራቸው አቅጣጫ ሁሉ ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+ በሚሄዱበት ጊዜ አይዞሩም። +13 የሕያዋን ፍጥረታቱ መልክ የሚነድ የከሰል ፍም ይመስላል፤ በሕያዋን ፍጥረታቱም መካከል እየነደደ ያለ ችቦ የሚመስል ነገር ወዲያና ወዲህ ይል ነበር፤ ከእሳቱም+ መካከል መብረቅ ይወጣ ነበር። +14 ሕያዋን ፍጥረታቱም ወዲያና ወዲህ ሲሄዱ እንቅስቃሴያቸው የመብረቅ ብልጭታ ይመስል ነበር። +15 እኔም ሕያዋን ፍጥረታቱን ስመለከት አራት ፊቶች ባሉት በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር አጠገብ በምድር ላይ አንድ አንድ መንኮራኩር* አየሁ።+ +16 መንኮራኩሮቹ በአጠቃላይ ሲታዩ እንደ ክርስቲሎቤ የሚያብረቀርቅ መልክ ነበራቸው፤ አራቱም ይመሳሰላሉ። መልካቸውና አሠራራቸው ሲታይ በአንድ መንኮራኩር ውስጥ በጎን በኩል ሌላ መንኮራኩር የተሰካ ይመስላል። +17 በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መዞር ሳያስፈልጋቸው በአራቱም ጎን በፈለጉበት አቅጣጫ መሄድ ይችላሉ። +18 የመንኮራኩሮቹም ጠርዝ እጅግ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ የሚያስፈራ ነበር፤ የአራቱም መንኮራኩሮች ጠርዝ ዙሪያውን በዓይኖች የተሞላ ነበር።+ +19 ሕያዋን ፍጥረታቱ በተንቀሳቀሱ ቁጥር፣ መንኮራኩሮቹም ከእነሱ ጋር አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ሕያዋን ፍጥረታቱ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከፍ ከፍ ይላሉ።+ +20 መንፈሱ ወደመራቸው አቅጣጫ፣ መንፈሱ ወደሚሄድበት ቦታ ሁሉ ይሄዳሉ። መንኮራኩሮቹ ከእነሱ ጋር አብረው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ* በመንኮራኩሮቹም ውስጥ ነበርና። +21 ሕያዋን ፍጥረታቱ ሲንቀሳቀሱ እነሱም ይንቀሳቀሳሉ፤ ሕያዋን ፍጥረታቱ ሲቆሙ እነሱም ይቆማሉ፤ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከእነሱ ጋር አብረው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ በመንኮራኩሮቹም ውስጥ ነበርና። +22 ከሕያዋን ፍጥረታቱ ራስ በላይ እጅግ አስደናቂ እንደሆነ በረዶ የሚያብረቀርቅ ጠፈር የሚመስል ነገር ነበር፤ ይህም ከራሳቸው በላይ ተዘርግቶ ነበር።+ +23 ከጠፈሩ በታች ክንፎቻቸው አንዳቸው ወደ ሌላው ቀጥ ብለው ነበር።* እያንዳንዳቸውም በዚህ ጎንና በዚያኛው ጎን ሰውነታቸውን የሚሸፍኑባቸው ሁለት ሁለት ክንፎች ነበሯቸው። +24 የክንፎቻቸውን ድምፅ ስሰማ እንደሚጎርፍ ውኃ ድምፅ፣ ደግሞም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ድምፅ ነበር።+ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ድምፁ እንደ ሠራዊት ድምፅ ነበር። በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻቸውን ወደ ታች ያደርጋሉ። +25 ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር በላይ አንድ ድምፅ ይሰማ ነበር። (በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻቸውን ወደ ታች ያደርጉ ነበር።) +26 ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ+ የመሰለ እንደ ዙፋን ያለ ነገር ነበር።+ ከላይ በኩል ባለው በዙፋኑ ላይ መልኩ የሰው መልክ የሚመስል ተቀምጦ ነበር።+ +27 ወገቡ ከሚመስለው ነገር ጀምሮ ወደ ላይ፣ እሳት የሚመስል እንደ ብረት የሚያብረቀርቅ ነገር+ ሲወጣ አየሁ፤ ደግሞም ከወገቡ ጀምሮ ወደ ታች፣ እሳት የሚመስል ነገር አየሁ።+ በዙሪያውም ደማቅ ብርሃን ነበር፤ +28 ይህም ዝናባማ በሆነ ቀን በደመና ውስጥ እንደሚታይ ቀስተ ደመና ነበር።+ በዙሪያው ያለው ደማቅ ብርሃን ይህን ይመስላል። ደግሞም የይሖዋን ክብር ይመስል ነበር።+ እኔም ባየሁት ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፤ ከዚያም አንዱ ሲናገር ድምፅ ሰማሁ። +36 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ እስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። +2 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል��� “ጠላት ስለ እናንተ ‘እሰይ! የጥንቶቹ ከፍ ያሉ ቦታዎች ሳይቀሩ የእኛ ርስት ሆነዋል!’ ብሏል።”’+ +3 “ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከብሔራት መካከል ለተረፉት* ርስት እንድትሆኑ ባድማ ስላደረጓችሁና ከየአቅጣጫው ጥቃት ስለሰነዘሩባችሁ እንዲሁም ሰው አፍ ውስጥ ስለገባችሁና ሰዎች ስማችሁን ስላጠፉ፣+ +4 የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ የተናገረውን ቃል ስሙ! ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለተራሮችና ለኮረብቶች፣ ለጅረቶችና ለሸለቆዎች፣ ፈራርሰው ባድማ ለሆኑት ቦታዎችና+ በዙሪያቸው ባሉት ከጥፋት የተረፉ ብሔራት ለተበዘበዙት እንዲሁም መሳለቂያ ለሆኑት የተተዉ ከተሞች ይህን ቃል ተናግሯል፤+ +5 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እነሱን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ ‘የግጦሽ ቦታዎቿን ለመውሰድና ምድሪቱን ለመበዝበዝ ሲሉ በታላቅ ደስታና በከፍተኛ ንቀት*+ ምድሬን የገዛ ርስታቸው እንደሆነ አድርገው በተናገሩት፣ ከጥፋት በተረፉት ብሔራትና በመላዋ ኤዶም ላይ በቅንዓቴ እሳት+ እናገራለሁ።’”’+ +6 “ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፤ ለተራሮችና ለኮረብቶች፣ ለጅረቶችና ለሸለቆዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ብሔራት ያደረሱባችሁን ውርደት ስለተሸከማችሁ በቅንዓቴና በቁጣዬ እናገራለሁ።”’+ +7 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዙሪያችሁ ያሉት ብሔራት የገዛ ራሳቸውን ኀፍረት ይሸከማሉ ብዬ እጄን አንስቼ ምያለሁ።+ +8 የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ እናንተ ግን ለሕዝቤ ለእስራኤል ቅርንጫፍ ታወጣላችሁ፤ ፍሬም ታፈራላችሁ፤+ እነሱ በቅርቡ ይመለሳሉና። +9 እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ፊቴንም ወደ እናንተ እመልሳለሁ፤ እናንተም ትታረሳላችሁ፤ ደግሞም ዘር ይዘራባችኋል። +10 ሕዝባችሁን ይኸውም መላውን የእስራኤል ቤት አበዛለሁ፤ ከተሞቹም የሰው መኖሪያ ይሆናሉ፤+ የፈራረሱትም ስፍራዎች ዳግመኛ ይገነባሉ።+ +11 አዎ፣ ሕዝባችሁንና ከብቶቻችሁን አበዛለሁ፤+ እነሱም ይበዛሉ፤ ፍሬያማም ይሆናሉ። እንደቀድሞው ዘመን ሰዎች እንዲኖሩባችሁ አደርጋለሁ፤+ ደግሞም ከበፊቱ የበለጠ አበለጽጋችኋለሁ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ +12 በእናንተ ላይ ሰዎች ይኸውም ሕዝቤ እስራኤል እንዲመላለሱ አደርጋለሁ፤ እነሱም ይወርሷችኋል።+ የእነሱ ርስት ትሆናላችሁ፤ ከእንግዲህ ልጅ አልባ አታደርጓቸውም።’”+ +13 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“ሰዎችን የምትበላና በላይዋ ያሉትን ብሔራት የወላድ መሃን የምታደርግ ምድር ናችሁ” ስለሚሏችሁ፣’ +14 ‘ከእንግዲህ ሰው አትበሉም ወይም በምድሪቱ ላይ ያሉትን ብሔራት ልጅ አልባ አታደርጉም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +15 ‘ከእንግዲህ ብሔራት እናንተን እንዲሰድቡ ወይም ሰዎች የሚሰነዝሩባችሁን ዘለፋ እንድትሸከሙ አልፈቅድም፤+ ደግሞም በምድሪቱ ላይ ላሉት ብሔራት መሰናክል አትሆኑም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +16 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +17 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች በምድራቸው ላይ ይኖሩ በነበረበት ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው ምድሪቱን አረከሷት።+ መንገዳቸው በፊቴ እንደ ወር አበባ ርኩሰት ነበር።+ +18 በምድሪቱ ላይ ደም ስላፈሰሱና ምድሪቱን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው* ስላረከሱ+ ቁጣዬን አፈሰስኩባቸው።+ +19 ደግሞም በብሔራት መካከል በተንኳቸው፤ በየአገሩም ዘራኋቸው።+ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው ፈረድኩባቸው። +20 ሆኖም ወደ እነዚህ ብሔራት በመጡ ጊዜ ሰዎች ስለ እነሱ ‘እነዚህ የይሖዋ ሕዝብ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ከእሱ ምድር ለመ��ናቀል ተገደዱ’ እያሉ ቅዱስ ስሜን አረከሱ።+ +21 በመሆኑም የእስራኤል ቤት በሄዱባቸው ብሔራት መካከል ያረከሱት ቅዱስ ስሜ ያሳስበኛል።”+ +22 “ስለዚህ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ እርምጃ የምወስደው ለእናንተ ብዬ ሳይሆን በሄዳችሁባቸው ብሔራት መካከል ላረከሳችሁት ቅዱስ ስሜ ስል ነው።”’+ +23 ‘በብሔራት መካከል የረከሰውን፣ ይኸውም በእነሱ መካከል ያረከሳችሁትን ታላቅ ስሜን በእርግጥ እቀድሰዋለሁ፤+ ዓይኖቻቸው እያዩ በመካከላችሁ በምቀደስበት ጊዜ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ብሔራት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ +24 ከብሔራት መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየአገሩም ሁሉ ሰብስቤ ወደ ምድራችሁ አመጣችኋለሁ።+ +25 ንጹሕ ውኃ እረጫችኋለሁ፤ እናንተም ንጹሕ ትሆናላችሁ፤+ ከርኩሰታችሁ ሁሉና አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻችሁ ሁሉ+ አነጻችኋለሁ።+ +26 አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤+ በውስጣችሁም አዲስ መንፈስ አሳድራለሁ።+ የድንጋይ ልባችሁን+ ከሰውነታችሁ አስወግጄ የሥጋ ልብ* እሰጣችኋለሁ። +27 መንፈሴን በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ በሥርዓቴም እንድትመላለሱ አደርጋለሁ፤+ ድንጋጌዎቼንም ትጠብቃላችሁ፣ በተግባርም ታውሏቸዋላችሁ። +28 በዚያን ጊዜ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ላይ ትኖራላችሁ፤ ሕዝቤም ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።’+ +29 “‘ከርኩሰታችሁ ሁሉ አድናችኋለሁ፤ እህሉን እጠራዋለሁ፤ ደግሞም አበዛዋለሁ፤ ረሃብም አላመጣባችሁም።+ +30 በረሃብ የተነሳ በብሔራት መካከል ዳግመኛ ውርደት እንዳይደርስባችሁ፣ የዛፉን ፍሬና የእርሻውን ምርት አበዛለሁ።+ +31 በዚያን ጊዜ ክፉ መንገዳችሁንና መጥፎ ሥራችሁን ታስታውሳላችሁ፤ በበደላችሁና በምትፈጽሟቸው አስጸያፊ ልማዶች የተነሳ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።+ +32 ይሁንና ይህን እወቁ፦ ይህን የማደርገው ለእናንተ ብዬ አይደለም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ይልቁንም የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ ከመንገዳችሁ የተነሳ እፈሩ፤ ደግሞም ተሸማቀቁ።’ +33 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከበደላችሁ ሁሉ በማነጻችሁ ቀን ከተሞቹ የሰው መኖሪያ እንዲሆኑ፣ የፈራረሱትም ቦታዎች እንደገና እንዲገነቡ አደርጋለሁ።+ +34 አላፊ አግዳሚው ሁሉ ጠፍ ሆኖ ሲያየው የነበረው ባድማ መሬት ይታረሳል። +35 ሰዎችም እንዲህ ይላሉ፦ “ባድማ የነበረው ምድር እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ+ ሆነ፤ ፈራርሰው ባድማና ወና ሆነው የነበሩት ከተሞችም አሁን የተመሸጉ ከተሞችና የሰው መኖሪያ ሆነዋል።”+ +36 ደግሞም ከጥፋት የተረፉት በዙሪያችሁ ያሉት ብሔራት፣ የፈረሰውን የገነባሁትና ባድማ የሆነውን ምድር ያለማሁት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። እኔ ይሖዋ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አድርጌዋለሁ።’+ +37 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የእስራኤል ቤት ሰዎችም ይህን እንዳደርግላቸው እንዲጠይቁኝ እፈቅድላቸዋለሁ፦ ሕዝባቸውን እንደ መንጋ አበዛዋለሁ። +38 እንደ ቅዱሳን መንጋና በበዓል ወቅት+ በኢየሩሳሌም ውስጥ እንደሚገኘው መንጋ፣* ፈራርሰው የነበሩት ከተሞችም በሰው መንጋ ይሞላሉ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’” +29 በአሥረኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በ12ኛው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈርዖን አዙረህ በእሱና በመላዋ ግብፅ ላይ ትንቢት ተናገር።+ +3 እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በአባይ* ጅረቶች መካከል የተጋደምክና+‘የአባይ ወንዝ የእኔ ነው።የሠራሁት ለገዛ ራሴ ነው’ የምትል+ አንተ ግዙፍ የባሕር ፍ���ረት፣ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን፣ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ።+ + 4 በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፤ በአባይ ወንዝህ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ከቅርፊትህ ጋር እንዲጣበቁ አደርጋለሁ። ቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁት የአባይ ዓሣዎች ሁሉ ጋር ከአባይ ወንዝህ መካከል አወጣሃለሁ። + 5 አንተንም ሆነ በአባይ ወንዝህ ውስጥ ያሉትን ዓሣዎች ሁሉ በረሃ ላይ እጥላለሁ። አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ የሚሰበስብህም ሆነ የሚያነሳህ አይኖርም።+ ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።+ + 6 በዚያን ጊዜ የግብፅ ነዋሪዎች ሁሉ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ለእስራኤል ቤት ከአገዳ* የተሻለ ድጋፍ መሆን አልቻሉምና።+ + 7 እጅህን ሲይዙህ ተሰበርክ፤ትከሻቸውንም ወጋህ። በተመረኮዙህ ጊዜ ተሰበርክ፤እግራቸውም እንዲብረከረክ* አደረግክ።”+ +8 “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ሰይፍ አመጣብሃለሁ፤+ በአንተ ዘንድ የሚገኘውን ሰውም ሆነ እንስሳ አጠፋለሁ። +9 የግብፅ ምድር ባድማና ወና ይሆናል፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ አንተ ‘የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ብለሃልና።*+ +10 ስለዚህ በአንተና በአባይ ወንዝህ ላይ ተነስቻለሁ፤ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል+ እስከ ሰዌኔ+ ብሎም እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ ባድማ፣ ደረቅና ወና አደርጋለሁ።+ +11 የሰው እግርም ሆነ የከብት ኮቴ አያልፍባትም፤+ ለ40 ዓመትም ማንም አይኖርባትም። +12 የግብፅን ምድር ከሌሎች አገሮች በከፋ ሁኔታ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከተሞቿም ከሌሎች ከተሞች በከፋ ሁኔታ ለ40 ዓመት ያህል ባድማ ይሆናሉ፤+ ግብፃውያንንም በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።”+ +13 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ከ40 ዓመት በኋላ ግብፃውያንን ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል እሰበስባቸዋለሁ፤+ +14 የተማረኩትን ግብፃውያን ወደ ትውልድ አገራቸው ወደ ጳትሮስ+ ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ በዚያም ደካማ መንግሥት ይሆናሉ። +15 ግብፅ ከሌሎቹ መንግሥታት ያነሰች ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ሌሎች ብሔራትን አትጨቁንም፤+ ደግሞም በጣም ትንሽ ስለማደርጋቸው ሌሎች ብሔራትን መግዛት አይችሉም።+ +16 ግብፅ ለእስራኤል ቤት ዳግመኛ መታመኛ አትሆንም፤+ ይልቁንም ከግብፃውያን እርዳታ በመሻት ለሠሩት ስህተት መታሰቢያ ትሆናለች። እነሱም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’” +17 በ27ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +18 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር*+ ሠራዊቱ በጢሮስ ላይ ታላቅ ግዳጅ እንዲፈጽም አደረገ።+ ራስ ሁሉ ተመልጧል፤ ትከሻም ሁሉ ተልጧል። ይሁን እንጂ እሱም ሆነ ሠራዊቱ በጢሮስ ላይ ላፈሰሱት ጉልበት ያገኙት ዋጋ የለም። +19 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ የግብፅን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር* እሰጣለሁ፤+ እሱም ሀብቷን ያግዛል፤ በእጅጉ ይበዘብዛል እንዲሁም ይመዘብራል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደሞዝ ይሆናል።’ +20 “‘በእሷ* ላይ ላፈሰሰው ጉልበት የግብፅን ምድር ካሳ አድርጌ እሰጠዋለሁ፤ ምክንያቱም ይህን ያደረጉት ለእኔ ነው’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +21 “በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድ እንዲበቅል አደርጋለሁ፤*+ ለአንተም በእነሱ መካከል መናገር የምትችልበት አጋጣሚ እከፍትልሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።” +28 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የጢሮስን ገዢ እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልብህ ከመታበዩ የተነሳ+ ‘እኔ አምላ�� ነኝ። በባሕሩ መካከል በአምላክ ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ’ ትላለህ።+ በልብህ አምላክ እንደሆንክ የምታስብ ቢሆንምአንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም። + 3 እነሆ፣ አንተ ከዳንኤል+ ይበልጥ ጥበበኛ እንደሆንክ ይሰማሃል። ከአንተ የተሰወረ ሚስጥር እንደሌለ አድርገህ ታስባለህ። + 4 በጥበብህና በማስተዋልህ ራስህን አበልጽገሃል፤በግምጃ ቤቶችህም ውስጥ ወርቅና ብር ማከማቸትህን ቀጥለሃል።+ + 5 በንግድህ ስኬታማ ከመሆንህ የተነሳ ብዙ ሀብት አፈራህ፤+ካካበትከውም ሀብት የተነሳ ልብህ ታበየ።”’ + 6 “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በልብህ አምላክ እንደሆንክ ስለተሰማህ፣ + 7 ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑትን ባዕዳን አመጣብሃለሁ፤+እነሱም በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ታላቅ ግርማህንም ያረክሳሉ።+ + 8 ወደ ጉድጓድ* ያወርዱሃል፤በተንጣለለውም ባሕር መካከል አስከፊ ሞት ትሞታለህ።+ + 9 ያም ሆኖ በገዳይህ ፊት ‘እኔ አምላክ ነኝ’ ትላለህ? በሚያረክሱህ ሰዎች እጅ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።”’ +10 ‘በባዕዳን እጅ፣ ያልተገረዙ ሰዎችን አሟሟት ትሞታለህ፤እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +12 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ጢሮስ ንጉሥ ሙሾ አውርድ፤* እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተ ጥበብ የተሞላህና+ ፍጹም ውበት የተላበስክ+የፍጽምና ተምሳሌት* ነበርክ። +13 በአምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ነበርክ። በከበሩ ድንጋዮች ሁሉይኸውም በሩቢ፣ በቶጳዝዮን፣ በኢያስጲድ፣ በክርስቲሎቤ፣ በኦኒክስ፣ በጄድ፣ በሰንፔር፣ በበሉርና+ በመረግድ አጊጠህ ነበር፤እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች የተሰኩባቸው ማቀፊያዎችም ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ። በተፈጠርክበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር። +14 የተቀባህ፣ የምትጋርድ ኪሩብ አድርጌ ሾምኩህ። በአምላክ ቅዱስ ተራራ ላይ ነበርክ፤+ በእሳታማ ድንጋዮችም መካከል ትመላለስ ነበር። +15 ከተፈጠርክበት ቀን አንስቶ ዓመፅ እስከተገኘብህ ጊዜ ድረስበመንገድህ ሁሉ ምንም እንከን አልነበረብህም።+ +16 ከንግድህ ብዛት የተነሳ+ውስጥህ በዓመፅ ተሞላ፤ ኃጢአትም መሥራት ጀመርክ።+ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፣ እንደ ርኩስ ቆጥሬ ከአምላክ ተራራ እጥልሃለሁ፤ከእሳታማዎቹ ድንጋዮች መካከልም አስወግድሃለሁ።+ +17 በውበትህ+ ምክንያት ልብህ ታበየ። ከታላቅ ግርማህ የተነሳ ጥበብህን አበላሸህ።+ ወደ ምድር እጥልሃለሁ።+ በነገሥታት ፊት ትዕይንት አደርግሃለሁ። +18 ታላቅ በደል በመፈጸምና በንግድ ሥራ በማጭበርበር መቅደሶችህን አረከስክ። እኔም ከመካከልህ እሳት እንዲወጣ አደርጋለሁ፤ እሳቱም ይበላሃል።+ በሚያዩህ ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አደርግሃለሁ። +19 ከሕዝቦች መካከል የሚያውቁህ ሁሉ በመገረም አተኩረው ያዩሃል።+ ፍጻሜህ ድንገተኛና አስከፊ ይሆናል፤ደግሞም ለዘላለም ከሕልውና ውጭ ትሆናለህ።”’”+ +20 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +21 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ሲዶና+ አዙረህ በእሷ ላይ ትንቢት ተናገር። +22 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሲዶና ሆይ፣ እነሆ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ በመካከልሽም እከበራለሁ፤ደግሞም በእሷ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበትና በእሷ አማካኝነት በምቀደስበት ጊዜ ሰዎች እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። +23 በእሷ ላይ ቸነፈር እሰዳለሁ፤ በጎዳናዎቿም ላይ ደም ይፈስሳል። ከየአቅጣጫው ሰይፍ በሚመጣባት ጊዜ የታረዱት ሰዎች በመካከሏ ይወድቃሉ፤እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ +24 “‘“ከዚያ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ አደገኛ በሆነ አሜኬላና በሚያሠቃይ እሾህ+ ይኸውም በሚንቁት ብሔራት ዳግመኛ አይከበብም፤ ሰዎችም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’ +25 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ቤት ሰዎች ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል ዳግመኛ በምሰበስባቸው ጊዜ+ በብሔራት ፊት በእነሱ መካከል እቀደሳለሁ።+ እነሱም ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት+ ምድራቸው ላይ ይኖራሉ።+ +26 በላይዋ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤+ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይንንም ይተክላሉ፤+ ደግሞም በዙሪያቸው ባሉት በሚንቋቸው ሁሉ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ያለስጋት ይኖራሉ፤+ እኔም አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’” +38 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን የመሼቅና የቱባል+ ዋና አለቃ* በሆነውና በማጎግ ምድር በሚገኘው በጎግ ላይ አድርገህ+ በእሱ ላይ ትንቢት ተናገር።+ +3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመሼቅና የቱባል ዋና አለቃ* የሆንከው ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። +4 እመልስሃለሁ፤ በመንጋጋህም መንጠቆ አስገባለሁ፤+ ከመላው ሠራዊትህ ይኸውም ከፈረሶች፣ ያማረ ልብስ ከለበሱ ፈረሰኞች፣ ትልቅ ጋሻና ትንሽ ጋሻ* ከያዘ እንዲሁም ሰይፍ ከሚመዝ ታላቅ ጉባኤ ጋር አወጣሃለሁ፤+ +5 ትንሽ ጋሻ የያዙና የራስ ቁር የደፉ የፋርስ፣ የኢትዮጵያና የፑጥ+ ሰዎች ከእነሱ ጋር አሉ፤ +6 ጎሜርንና ወታደሮቹን ሁሉ፣ ራቅ ባለው የሰሜን ምድር የሚገኙትን የቶጋርማ+ ቤት ሰዎችንና ወታደሮቻቸውን ሁሉ ጨምሮ ብዙ ሕዝቦች ከአንተ ጋር አሉ።+ +7 “‘“አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር የተሰበሰበው ሠራዊትህ ሁሉ ተነሡ፣ ተዘጋጁም፤ አንተም አዛዣቸው* ትሆናለህ። +8 “‘“ከብዙ ቀናት በኋላ በአንተ ላይ ትኩረት ይደረጋል።* በመጨረሻዎቹ ዓመታት ከሰይፍ ጥቃት የተረፈውንና ከብዙ ሕዝቦች መካከል ተሰብስቦ ለብዙ ጊዜ ባድማ ሆነው ወደቆዩት የእስራኤል ተራሮች የተመለሰውን ሕዝብ ምድር ትወራለህ። የምድሪቱ ነዋሪዎች ከተለያዩ ሕዝቦች መካከል ተመልሰው የመጡ ናቸው፤ ደግሞም ሁ +9 አንተም በእነሱ ላይ እንደ አውሎ ነፋስ ትመጣለህ፤ አንተና ወታደሮችህ ሁሉ እንዲሁም ከአንተ ጋር ያሉት ብዙ ሕዝቦች ምድሪቱን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።”’ +10 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያ ቀን ሐሳብ ወደ ልብህ ይገባል፤ ክፉ ዕቅድም ታወጣለህ፤ +11 እንዲህ ትላለህ፦ “ከለላ የሌላቸው ሰፈሮች* የሚገኙበትን ምድር እወራለሁ።+ ያለስጋት ተረጋግተው በሚኖሩት ላይ እመጣለሁ፤ ሁሉም የሚኖሩት ቅጥር፣ መቀርቀሪያና በር በሌላቸው ሰፈሮች ነው።” +12 ዓላማህ ብዙ ሀብት መበዝበዝና መዝረፍ፣ ደግሞም አሁን የሰው መኖሪያ የሆኑትን ባድማ የነበሩ ስፍራዎችና+ ከብሔራት ሁሉ መካከል ዳግመኛ የተሰበሰበውን ሕዝብ+ ማጥቃት ነው፤ ይህ ሕዝብ ሀብትና ንብረት አከማችቷል፤+ በምድርም እምብርት ላይ ይኖራል። +13 “‘ሳባ፣+ ዴዳን፣+ የተርሴስ+ ነጋዴዎችና ተዋጊዎቹ* ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “ወረራ የምታካሂደው ብዙ ሀብት ለመበዝበዝና ለመዝረፍ ነው? ሠራዊትህን የሰበሰብከው ብርና ወርቅ ለማጋበስ፣ ሀብትና ንብረት ለመውሰድ እንዲሁም ብዙ ምርኮ ለመንጠቅ ነው?”’ +14 “ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ ጎግንም እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እስራኤል ያለስጋት በሚቀመጥበት ጊዜ፣ አንተ በዚያን ቀን ይህን ማወቅህ ይቀራል?+ +15 አንተ ከስፍራህ ይኸውም ርቆ ከሚገኘው የሰሜን ምድር ትመጣለህ፤+ አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ብዙ ሕዝቦች ትመጣላችሁ፤ ሁሉም በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፣ ታላቅ ጉባኤና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ናቸው።+ +16 ምድርን እንደሚሸፍን ደመና ሆነህ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትመጣለህ። ጎግ ሆይ፣ በዘመኑ መጨረሻ በአንተ አማካኝነት በፊታቸው ራሴን በምቀድስበት ጊዜ ብሔራት ያውቁኝ ዘንድ በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።”’+ +17 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን በእነሱ ላይ እንደማመጣ ለብዙ ዓመታት ትንቢት በተናገሩትና አገልጋዮቼ በሆኑት የእስራኤል ነቢያት አማካኝነት በቀድሞ ዘመን የተናገርኩት ስለ አንተው አይደለም?’ +18 “‘በዚያ ቀን፣ ጎግ የእስራኤልን ምድር በሚወርበት ቀን’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ታላቅ ቁጣዬ ይነድዳል።+ +19 በቅንዓቴና በቁጣዬ እሳት እናገራለሁ፤ ደግሞም በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይከሰታል። +20 የባሕር ዓሣዎች፣ የሰማይ ወፎች፣ የዱር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ እንስሳት ሁሉና በምድር ላይ ያሉ ሰዎች በሙሉ ከእኔ የተነሳ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮችም ይናዳሉ፤+ ገደላማ ቦታዎችም ይደረመሳሉ፤ ቅጥሩም ሁሉ ይፈርሳል።’ +21 “‘በተራሮቼ ሁሉ፣ በጎግ ላይ ሰይፍ እጠራለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘የእያንዳንዱ ሰው ሰይፍ በገዛ ወንድሙ ላይ ይሆናል።+ +22 እኔም በቸነፈርና+ በደም መፋሰስ እፈርድበታለሁ፤* በእሱ፣ በወታደሮቹና ከእሱ ጋር ባሉ ብዙ ሕዝቦች ላይ ኃይለኛ ዶፍ፣ በረዶ፣+ እሳትና+ ድኝ+ አዘንባለሁ።+ +23 ደግሞም ራሴን ገናና አደርጋለሁ፤ እንዲሁም ራሴን እቀድሳለሁ፤ በብዙ ብሔራትም ፊት ማንነቴ እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’ +8 በስድስተኛውም ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ በዚያ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ እጅ ያዘኝ። +2 እነሆም እሳት የሚመስል ነገር ተመለከትኩ፤ ወገቡ ከሚመስለው ነገር በታች እሳት ነበር፤+ ደግሞም ከወገቡ በላይ መልኩ እንደሚያብረቀርቅ ብረት* ደማቅ ነበር።+ +3 ከዚያም እጅ የሚመስል ነገር ዘርግቶ የራስ ፀጉሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል ይዞ ወሰደኝ፤ አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ቅናት የሚቀሰቅሰው የቅናት ጣዖት ምልክት* ወደቆመበት+ በሰሜን ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው ግቢ በር+ አመጣኝ። +4 እነሆም፣ በሸለቋማው ሜዳ አይቼው የነበረውን የሚመስል የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበር።+ +5 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እባክህ ዓይንህን አንስተህ ወደ ሰሜን ተመልከት” አለኝ። ስለዚህ ወደ ሰሜን ተመለከትኩ፤ በዚያም ከመሠዊያው በር በስተ ሰሜን በኩል መግቢያው ላይ ይህ የቅናት ምልክት* ነበር። +6 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ከመቅደሴ እንድርቅ የሚያደርጉ ነገሮች+ ይኸውም የሚፈጽሟቸውን አስከፊና አስጸያፊ ነገሮች ትመለከታለህ?+ ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮችን ገና ታያለህ።” +7 ከዚያም ወደ ቅጥር ግቢው መግቢያ አመጣኝ፤ እኔም ስመለከት በግድግዳው ላይ አንድ ቀዳዳ አየሁ። +8 እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እስቲ ግድግዳውን ንደለው” አለኝ። እኔም ግድግዳውን ነደልኩት፤ አንድ መግቢያም ተመለከትኩ። +9 እሱም “ወደ ውስጥ ግባና በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት” አለኝ። +10 እኔም ገብቼ አየሁ፤ መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታትንና የሚያስጠሉ አራዊትን+ ሁሉ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ የእስራኤል ቤት ጣዖቶችን* ሁሉ ምስል+ ተመለከትኩ፤ ምስላቸውም በግድግዳው ዙሪያ ተቀርጾ ነበር። +11 ደግሞም 70 የሚሆኑ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በምስሎቹ ፊት ቆመው ነበር፤ የሳፋን+ ልጅ ያአዛንያህ በመካከላቸው ቆሞ ነበር። እያንዳንዳ��ውም በእጃቸው ጥና የያዙ ሲሆን መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጭስም እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር።+ +12 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዳቸው ጣዖቶቻቸው ባሉባቸው* እልፍኞች ውስጥ በጨለማ ምን እንደሚያደርጉ ታያለህ? እነሱ ‘ይሖዋ አያየንም። ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል’ ይላሉና።”+ +13 ደግሞም “እነሱ የሚሠሯቸውን ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ። +14 በመሆኑም በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ይሖዋ ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ በዚያም ሴቶች ተቀምጠው ታሙዝ ለተባለው አምላክ ሲያለቅሱ አየሁ። +15 እሱም በመቀጠል “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? ከእነዚህ የባሰ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ።+ +16 በመሆኑም ወደ ይሖዋ ቤት ውስጠኛው ግቢ+ አመጣኝ። በዚያም በይሖዋ ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ በበረንዳውና በመሠዊያው መካከል 25 ያህል ወንዶች ነበሩ፤ እነሱም ጀርባቸውን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ ሰጥተው ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ነበር፤ ደግሞም በምሥራቅ አቅጣጫ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።+ +17 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? የይሁዳ ቤት እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች መፈጸማቸው፣ ምድሪቱን በዓመፅ መሙላታቸውና+ እኔን ማስቆጣታቸው ቀላል ነገር ነው? እነሆ፣ ቅርንጫፉን* ወደ አፍንጫዬ አቅርበዋል። +18 በመሆኑም በቁጣ እርምጃ እወስዳለሁ። ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም።+ በታላቅ ድምፅ ወደ ጆሮዬ ቢጮኹም አልሰማቸውም።”+ +11 መንፈስም ወደ ላይ አንስቶ በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው የይሖዋ ቤት የምሥራቅ በር+ አመጣኝ። በዚያም በበሩ መግቢያ ላይ 25 ሰዎች አየሁ፤ ከእነሱም መካከል የሕዝቡ አለቆች+ የሆኑት የአዙር ልጅ ያአዛንያህና የበናያህ ልጅ ጰላጥያህ ነበሩ። +2 ከዚያም አምላክ እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች ክፋትን የሚያቅዱና በዚህች ከተማ* መጥፎ ምክር የሚመክሩ ናቸው። +3 እነሱ ‘አሁን ቤት የምንሠራበት ጊዜ አይደለም?+ ከተማዋ* ድስት ናት፤+ እኛ ደግሞ ሥጋ* ነን’ ይላሉ። +4 “ስለዚህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር።”+ +5 ከዚያም የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ መጣ፤+ እንዲህም አለኝ፦ “እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ የተናገራችሁት ነገር ትክክል ነው፤ የምታስቡትን ነገር* አውቃለሁ። +6 በዚህች ከተማ ብዙዎች እንዲሞቱ አድርጋችኋል፤ ጎዳናዎቿንም በሙታን ሞልታችኋል።”’”+ +7 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ በከተማዋ ዙሪያ የጣላችኋቸው ሬሳዎች፣ እነሱ ሥጋው ናቸው፤ ከተማዋ ደግሞ ድስቱ ናት።+ እናንተ ግን ከውስጧ ትወሰዳላችሁ።’” +8 “‘ሰይፍን ፈርታችኋል፤+ እኔም ሰይፍ አመጣባችኋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +9 ‘ከእሷ አውጥቼ ለባዕዳን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የፍርድ እርምጃም እወስድባችኋለሁ።+ +10 በሰይፍ ትወድቃላችሁ።+ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ +11 ከተማዋ ድስት አትሆንላችሁም፤ እናንተም በውስጧ እንዳለ ሥጋ አትሆኑም፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ +12 እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። በሥርዓቴ አልተመላለሳችሁምና፤ ድንጋጌዎቼንም አላከበራችሁም፤+ ይልቁንም በዙሪያችሁ ያሉትን ብሔራት ድንጋጌዎች ተከተላችሁ።’”+ +13 ትንቢት ተናግሬ እንደጨረስኩ የበናያህ ልጅ ጰላጥያህ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ተደፍቼ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! የእስራኤልን ቀሪዎች ፈጽመህ ልታጠፋ ነው?” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኽኩ።+ +14 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እ��ዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +15 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣ ወንድሞችህን ይኸውም የመቤዠት መብት ያላቸውን ወንድሞችህንና የእስራኤልን ቤት ሁሉ ‘ከይሖዋ ራቁ። ምድሪቱ የእኛ ናት፤ ለእኛ ርስት ሆና ተሰጥታለች’ ብለዋቸዋል። +16 ስለዚህ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሩቅ ወዳሉ ብሔራት በግዞት እንዲወሰዱና በብዙ አገሮች መካከል እንዲበተኑ ባደርግም+ በሄዱባቸው አገሮች ውስጥ ለጥቂት ጊዜ መቅደስ እሆናቸዋለሁ።”’+ +17 “ስለዚህ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ደግሞም ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች አመጣችኋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እሰጣችኋለሁ።+ +18 እነሱም ወደዚያ ይመለሳሉ፤ በላይዋም ላይ ያሉትን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉና ጸያፍ የሆኑ ልማዶች ሁሉ ያስወግዳሉ።+ +19 እኔም ያልተከፋፈለ ልብ* እሰጣቸዋለሁ፤+ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አኖራለሁ፤+ ድንጋይ የሆነውንም ልብ ከሰውነታቸው አውጥቼ+ የሥጋ ልብ* እሰጣቸዋለሁ፤+ +20 ይህም ደንቦቼን አክብረው እንዲመላለሱ እንዲሁም ድንጋጌዎቼን እንዲጠብቁና እንዲታዘዙ ነው። በዚህ ጊዜ እነሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”’ +21 “‘“ሆኖም አስጸያፊ ነገሮቻቸውንና ጸያፍ የሆኑ ልማዶቻቸውን አጥብቀው ለመከተል በልባቸው ቆርጠው የተነሱትን በተመለከተ፣ መንገዳቸው የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’” +22 በዚህ ጊዜ ኪሩቦቹ ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘረጉ፤ መንኮራኩሮቹም* በአጠገባቸው ነበሩ፤+ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ነበር።+ +23 ከዚያም የይሖዋ ክብር+ ከከተማዋ ተነስቶ ወደ ላይ ወጣ፤ ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ ባለው ተራራም ላይ ቆመ።+ +24 ከዚያም መንፈስ፣ በአምላክ ኃይል* አማካኝነት በተሰጠኝ ራእይ ወደ ላይ አነሳኝ፤ ደግሞም በከለዳውያን ምድር ወዳሉት ግዞተኞች አመጣኝ። ከዚያም ያየሁት ራእይ ከእኔ ተለየ። +25 እኔም ይሖዋ ያሳየኝን ነገር ሁሉ በግዞት ላሉት ሰዎች መናገር ጀመርኩ። +2 ከዚያም “የሰው ልጅ* ሆይ፣ ተነስተህ በእግርህ ቁም፤ እኔም አናግርሃለሁ” አለኝ።+ +2 እሱም ባናገረኝ ጊዜ መንፈስ ወደ ውስጤ ገባ፤ የሚያነጋግረኝንም እሰማ ዘንድ በእግሬ አቆመኝ።+ +3 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወደ እስራኤል ሕዝብ፣ በእኔ ላይ ወዳመፁት ወደ ዓመፀኞቹ ብሔራት+ እልክሃለሁ።+ እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው እስከዚህች ቀን ድረስ ሕጌን ተላልፈዋል።+ +4 ግትርና* ልበ ደንዳና+ ወደሆኑ ልጆች እልክሃለሁ፤ አንተም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው። +5 እነሱ ዓመፀኛ+ ቤት ስለሆኑ ቢሰሙም ባይሰሙም በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ በእርግጥ ያውቃሉ።+ +6 “አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፣ በአሜኬላና በእሾህ+ የተከበብክ* እንዲሁም በጊንጦች መካከል የምትኖር ቢሆንም እነሱንም ሆነ የሚናገሩትን ቃል አትፍራ።+ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ስለሆኑ የሚናገሩትን አትፍራ፤+ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር።+ +7 እነሱ ዓመፀኛ ስለሆኑ ቢሰሙም ባይሰሙም ቃሌን ንገራቸው።+ +8 “አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፣ የምነግርህን ስማ። እንደዚህ ዓመፀኛ ቤት፣ ዓመፀኛ አትሁን። አፍህን ክፈት፤ የምሰጥህንም ብላ።”+ +9 እኔም ባየሁ ጊዜ ወደ እኔ የተዘረጋ እጅ+ ተመለከትኩ፤ ደግሞም የተጻፈበት ጥቅልል*+ አየሁ። +10 እሱም በፊቴ ጥቅልሉን ሲተረትረው፣ ከፊትና ከኋላ ተጽፎበት ነበር።+ በላዩ ላይ የሙሾ፣* የሐዘንና የዋይታ ቃላት ተጽፈውበት ነበር።+ +26 በ11ኛው ዓመት፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ጢሮ�� ስለ ኢየሩሳሌም+ ‘እሰይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች!+ አሁን እሷ ስለጠፋች ሁሉም ነገር ይሳካልኛል፤ ደግሞም እበለጽጋለሁ’ ስላለች፣ +3 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ፣ እነሆ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ባሕር ሞገዱን እንደሚያስነሳ ብዙ ብሔራትን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ። +4 እነሱ የጢሮስን ቅጥሮች ያፈርሳሉ፤ ማማዎቿንም ያወድማሉ፤+ አፈሯን ከላይዋ ጠርጌ አስወግዳለሁ፤ የሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለትም አደርጋታለሁ። +5 በባሕር መካከል የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆናለች።’+ “‘እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና፣’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ብሔራትም ይበዘብዟታል። +6 በገጠር ያሉ ሰፈሮቿም* በሰይፍ ይመታሉ፤ ሰዎችም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’ +7 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ በጢሮስ ላይ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* ከሰሜን አመጣለሁ፤+ እሱ ፈረሶችን፣+ የጦር ሠረገሎችን፣+ ፈረሰኞችንና ብዙ ወታደሮችን* ያቀፈ ሠራዊት ያለው የነገሥታት ንጉሥ ነው።+ +8 በገጠር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማል፤ በአንቺም ላይ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ይገነባል፤ የአፈር ቁልልም ይደለድላል፤ በአንቺም ላይ ትልቅ ጋሻ ያነሳል። +9 ቅጥሮችሽን በግንብ መደርመሻ መሣሪያ* ይደበድባል፤ ማማዎችሽንም በመጥረቢያ* ያፈርሳል። +10 ፈረሶቹ እጅግ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ አቧራ ያለብሱሻል፤ ሰዎች ቅጥሮቿ ወደፈረሱባት ከተማ እንደሚገቡ ሁሉ እሱም በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ የፈረሰኞቹ፣ የመንኮራኩሮቹና* የሠረገሎቹ ድምፅ ቅጥሮችሽን ያናውጣል። +11 የፈረሶቹ ኮቴዎች ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረግጣሉ፤+ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ግዙፍ የሆኑት ዓምዶችሽ መሬት ላይ ይንኮታኮታሉ። +12 ሀብትሽን ይበዘብዛሉ፤ ሸቀጥሽን ይዘርፋሉ፤+ ቅጥሮችሽን ያፈርሳሉ፤ የሚያማምሩ ቤቶችሽንም ያወድማሉ፤ ከዚያም ድንጋዮችሽን፣ ሳንቃዎችሽንና አፈርሽን ወደ ባሕር ይጥላሉ።’ +13 “‘የዘፈንሽ ጩኸት ጸጥ እንዲል አደርጋለሁ፤ የበገናሽም ድምፅ ከእንግዲህ አይሰማም።+ +14 የሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለትም አደርግሻለሁ፤ የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆኛለሽ።+ ዳግመኛ አትገነቢም፤ እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +15 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ጢሮስን እንዲህ ይላል፦ ‘ሞት አፋፍ ላይ ያሉት* ሲያቃስቱና በመካከልሽ ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሳ ደሴቶች አይናወጡም?+ +16 የባሕርም ገዢዎች* ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ ልብሳቸውንም * ያወልቃሉ፤ የተጠለፉ ሸማዎቻቸውንም አውልቀው ይጥላሉ፤ ደግሞም በጣም ይንቀጠቀጣሉ።* መሬት ላይ ተቀምጠው ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣሉ፤ በመገረምም አተኩረው ይመለከቱሻል።+ +17 በአንቺም ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፤*+ እንዲህም ይሉሻል፦ “ባሕር አቋርጠው የመጡ ሰዎች የሰፈሩብሽ፣ የተወደስሽ ከተማ ሆይ፣ እንዴት ጠፋሽ!+አንቺም ሆንሽ ነዋሪዎችሽ በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይሽብር የምትነዙ የባሕር ላይ ኃያላን ነበራችሁ።+ +18 በምትወድቂበት ቀን ደሴቶች ይንቀጠቀጣሉ፤ጥፋት በሚደርስብሽ ጊዜ በባሕር ላይ ያሉ ደሴቶች ይሸበራሉ።”’+ +19 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ሳደርግሽ፣ የሚያጥለቀልቅ ውኃ ሳመጣብሽና ኃይለኛ ውኃ ሲሸፍንሽ፣+ +20 አንቺንም ሆነ ከአንቺ ጋር ወደ ጉድጓድ* የሚወርዱትን፣ የጥንት ዘመን ሰዎች ወዳሉበት አወርዳችኋለሁ፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር፣ ጥንት እንደወደሙት ቦታዎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ምድር እንድትኖሪ አደርጋለሁ፤+ ይህም የሚሆነው ሰው እንዳይኖርብሽ ነው። ከዚያ በኋላ የሕያዋንን ምድር ከፍ ከፍ አደርጋለሁ +21 “‘በአንቺ ላይ ድንገተኛ ሽብር አመጣለሁ፤ ከእንግዲህም አትኖሪም።+ ይፈልጉሻል ግን ፈጽሞ አትገኚም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +44 ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው ወደ ውጨኛው የመቅደሱ በር ወደሚወስደው መንገድ መልሶ አመጣኝ፤+ በሩም ዝግ ነበር።+ +2 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በር እንደተዘጋ ይኖራል። መከፈት የለበትም፤ ደግሞም ማንም ሰው አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ በዚያ በኩል ገብቷልና፤+ ስለዚህ እንደተዘጋ ይኖራል። +3 አለቃው ግን አለቃ ስለሆነ በይሖዋ ፊት ምግብ ለመብላት በዚያ ይቀመጣል።+ በበሩ መተላለፊያ በረንዳ በኩል ይገባል፤ በዚያም ይወጣል።”+ +4 ከዚያም በስተ ሰሜን በሚገኘው በር በኩል ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ወዳለው ቦታ አመጣኝ። እኔም ባየሁ ጊዜ የይሖዋ ክብር፣ የይሖዋን ቤተ መቅደስ ሞልቶት ተመለከትኩ።+ በዚህ ጊዜ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፋሁ።+ +5 ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ይሖዋ ቤተ መቅደስ ደንቦችና ሕጎች የምነግርህን ሁሉ በትኩረት ተከታተል፤ በዓይኖችህም ተመልከት እንዲሁም በጥሞና አዳምጥ። የቤተ መቅደሱን መግቢያና የመቅደሱን መውጫዎች ሁሉ ልብ በል።+ +6 ዓመፀኛ ለሆኑት የእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ አስጸያፊ ልማድ መፈጸማችሁ ከእንግዲህ ይብቃ! +7 ልባቸውንና ሥጋቸውን ያልተገረዙትን የባዕድ አገር ሰዎች ወደ መቅደሴ ስታመጧቸው ቤተ መቅደሴን ያረክሳሉ። በምትፈጽሟቸው አስጸያፊ ልማዶች ሁሉ የተነሳ ቃል ኪዳኔ እየፈረሰ ሳለ እናንተ ግን ምግቤን ይኸውም ስቡንና ደሙን ታቀርባላችሁ። +8 ቅዱስ ከሆኑት ነገሮቼ ጋር በተያያዘ ያለባችሁን ኃላፊነት አልተወጣችሁም።+ ይልቁንም በመቅደሴ ውስጥ ያሉትን ሥራዎች እንዲያከናውኑ ሌሎች ሰዎችን መደባችሁ።”’ +9 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልቡንና ሥጋውን ያልተገረዘ በእስራኤል የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ወደ መቅደሴ አይግባ።”’ +10 “‘ይሁንና እስራኤላውያን አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን* ለመከተል ሲሉ ከእኔ በራቁ ጊዜ ከእኔ የራቁት ሌዋውያን+ በደላቸው የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይቀበላሉ። +11 ከዚያም በመቅደሴ የቤተ መቅደሱን በሮች የሚቆጣጠሩ+ እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉ አገልጋዮች ይሆናሉ። ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕት ለሕዝቡ ያርዳሉ፤ ደግሞም ሕዝቡን ለማገልገል በፊታቸው ይቆማሉ። +12 አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ፊት ስላገለገሏቸውና የእስራኤል ቤት ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የማሰናከያ ድንጋይ ስለሆኑባቸው+ በመሐላ እጄን በእነሱ ላይ አንስቻለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ‘እነሱም የሠሩት በደል የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይሸከማሉ። +13 ካህናቴ ሆነው ለማገልገል ወደ እኔ አይቀርቡም፤ ደግሞም ቅዱስ ወይም እጅግ ቅዱስ ወደሆኑት ነገሮቼ አይቀርቡም፤ በሠሯቸውም አስጸያፊ ነገሮች የተነሳ የሚደርስባቸውን ኀፍረት ይሸከማሉ። +14 ይሁንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ በኃላፊነት እንዲሠሩ ይኸውም በውስጡ የሚካሄደውን አገልግሎትና መሠራት ያለበትን ሥራ ሁሉ እንዲያከናውኑ አደርጋለሁ።’+ +15 “‘እስራኤላውያን ከእኔ በራቁ ጊዜ+ የመቅደሴን አገልግሎት ያከናውኑ የነበሩት የሳዶቅ+ ልጆች የሆኑት ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ለእኔም ስቡንና+ ደሙን ለማቅረብ በፊቴ ይቆማሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +16 ‘ወደ መቅደሴ የሚገቡት እነሱ ናቸው፤ እኔን ለማገልገልም ወደ ገበታዬ* ይቀርባሉ፤+ በእኔ ፊት ያለባቸውንም ኃላፊነት ይወጣሉ።+ +17 “‘ወደ ውስጠኛው ግቢ በሚያስገቡት በሮች በሚገቡበት ጊዜ በፍ��� መልበስ ይኖርባቸዋል።+ በውስጠኛው ግቢ በሮች ወይም በውስጥ ባሉት ቦታዎች ሲያገለግሉ የሱፍ ልብስ መልበስ የለባቸውም። +18 በራሳቸው ላይ ከበፍታ የተሠራ ጥምጥም ያድርጉ፤ በወገባቸውም ላይ የበፍታ ቁምጣ ይታጠቁ።+ እንዲያልባቸው የሚያደርግ ማንኛውም ዓይነት ልብስ መልበስ የለባቸውም። +19 ወደ ውጨኛው ግቢ ይኸውም ሕዝቡ ወዳለበት ግቢ ከመውጣታቸው በፊት አገልግሎታቸውን ሲያከናውኑ ለብሰውት የነበረውን ልብስ አውልቀው+ ቅዱስ በሆኑት የመመገቢያ ክፍሎች*+ ውስጥ ማስቀመጥ አለባቸው። ከዚያም ቅድስናን ወደ ሕዝቡ እንዳያስተላልፉ* ሌላ ልብስ ይለብሳሉ። +20 ራሳቸውን አይላጩ፤+ ወይም ፀጉራቸውን አያስረዝሙ። ይልቁንም ፀጉራቸውን ይከርክሙ። +21 ካህናቱ ወደ ውስጠኛው ግቢ በሚገቡበት ጊዜ የወይን ጠጅ አይጠጡ።+ +22 መበለት የሆነች ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት አያግቡ፤+ ይሁንና የእስራኤል ዘር የሆነች ድንግል ወይም የካህን ሚስት የነበረች መበለት ማግባት ይችላሉ።’+ +23 “‘ቅዱስ በሆነና ተራ በሆነ ነገር መካከል ያለውን ልዩነት ለሕዝቤ ያስተምሩ፤ ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውንም ልዩነት ያሳውቋቸው።+ +24 ፍርድ ነክ ጉዳዮችን ይዳኙ፤+ በድንጋጌዎቼ መሠረት ይፍረዱ።+ ከሁሉም በዓሎቼ ጋር የተያያዙትን ሕጎቼንና ደንቦቼን ይጠብቁ፤+ እንዲሁም ሰንበቶቼን ይቀድሱ። +25 ወደ ሞተ ሰው አይቅረቡ፤ አለዚያ ይረክሳሉ። ሆኖም ለአባታቸው፣ ለእናታቸው፣ ለወንድ ወይም ለሴት ልጃቸው፣ ለወንድማቸው ወይም ላላገባች እህታቸው ሲሉ ራሳቸውን ሊያረክሱ ይችላሉ።+ +26 ደግሞም አንድ ካህን ከነጻ በኋላ ለሰባት ቀን ሊያቆዩት ይገባል። +27 በተቀደሰው ስፍራ ለማገልገል፣ በውስጠኛው ግቢ ወደሚገኘው ቅዱስ ስፍራ በሚገባበት ቀን የኃጢአት መባውን ያቅርብ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +28 “‘የእነሱም ውርሻ ይህ ይሆናል፦ ውርሻቸው እኔ ነኝ።+ በእስራኤል ምንም ዓይነት ርስት አትስጧቸው፤ ርስታቸው እኔ ነኝና። +29 የእህሉን መባ፣+ የኃጢአቱን መባና የበደሉን መባ ይበላሉ፤+ በእስራኤል ምድር ቅዱስ ለሆነ ነገር የተለየ ሁሉ የእነሱ ይሆናል።+ +30 መጀመሪያ ላይ ከደረሱት ፍሬዎች ሁሉና መዋጮ አድርጋችሁ ከምትሰጡት ነገር ሁሉ ምርጥ የሆነው ለካህናቱ ይሆናል።+ የተፈጨውንም የእህል በኩር ለካህኑ ስጡ።+ እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ ቤተሰቦቻችሁ ይባረካሉ።+ +31 ካህናቱ ሞቶ የተገኘውንም ሆነ በአራዊት የተዘነጠለውን ማንኛውም ወፍ ወይም እንስሳ መብላት የለባቸውም።’+ +4 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ ጡብ ወስደህ በፊትህ አስቀምጥ። በላዩም ላይ የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅረጽበት። +2 ከተማዋን ክበብ፤+ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ሥራባት፤+ የአፈር ቁልል ደልድልባት፤+ የጦር ሰፈሮችን ሥራባት እንዲሁም በዙሪያዋ የመደርመሻ መሣሪያዎችን ደግንባት።+ +3 የብረት ምጣድ ወስደህ በአንተና በከተማዋ መካከል እንደ ብረት ቅጥር አቁመው። ፊትህንም በእሷ ላይ አዙር፤ ከተማዋም ትከበባለች፤ አንተም ትከባታለህ። ይህ ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።+ +4 “ከዚያም በግራ ጎንህ ትተኛለህ፤ የእስራኤልንም ቤት በደል በላይህ ላይ* ታኖራለህ።+ በጎንህ በተኛህበት ቀን ቁጥር በደላቸውን ትሸከማለህ። +5 እኔም በደል በፈጸሙባቸው ዓመታት መጠን 390 ቀናት በአንተ ላይ እመድባለሁ፤+ አንተም የእስራኤልን ቤት በደል ትሸከማለህ። +6 እነዚህንም ቀናት ማጠናቀቅ ይኖርብሃል። “ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ በቀኝ ጎንህ ትተኛለህ፤ የይሁዳንም ቤት በደል+ ለ40 ቀናት ትሸከማለህ። ለአንድ ዓመት አንድ ቀን፣ ለአንድ ዓመት አንድ ቀን ሰጥቼሃለሁ። +7 ክንድህን ገልጠህ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም ከበ���+ ታዞራለህ፤ በእሷም ላይ ትንቢት ትናገራለህ። +8 “እነሆ፣ የከበባህን ጊዜ እስክታጠናቅቅ ድረስ ከአንዱ ጎንህ ወደ ሌላው መገላበጥ እንዳትችል በገመድ አስርሃለሁ። +9 “አንተም ስንዴ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ ምስር፣ ማሽላና አጃ ወስደህ በአንድ ዕቃ ውስጥ አስቀምጣቸው፤ ለራስህም ዳቦ ጋግር። በጎንህ በምትተኛባቸው 390 ቀናት ትበላዋለህ።+ +10 በየቀኑ 20 ሰቅል* እየመዘንክ ትበላለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትበላዋለህ። +11 “ደግሞም የሂን አንድ ስድስተኛ* ለክተህ ውኃ ትጠጣለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትጠጣዋለህ። +12 “የገብስ ሙልሙል እንደምትበላ ትበላዋለህ፤ የደረቀን የሰው ዓይነ ምድር እንደ ማገዶ ተጠቅመህ በፊታቸው ትጋግረዋለህ።” +13 ከዚያም ይሖዋ “ልክ እንደዚሁ እስራኤላውያንም እነሱን በምበትንባቸው ብሔራት መካከል የረከሰ ምግብ ይበላሉ” አለ።+ +14 ከዚያም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ይህስ አይሁን! እኔ* ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሞቶ የተገኘም ሆነ አውሬ የቦጫጨቀው እንስሳ ሥጋ በልቼ የረከስኩበት ጊዜ የለም፤+ የረከሰም * ሥጋ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም።”+ +15 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “መልካም፣ በሰው ዓይነ ምድር ፋንታ የከብት ኩበት እንድትጠቀም ፈቅጄልሃለሁ፤ የምትበላውንም ዳቦ በእሱ ትጋግራለህ።” +16 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በኢየሩሳሌም የምግብ አቅርቦቱ እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤*+ እነሱም እየተመጠነ የሚሰጣቸውን ዳቦ በሚዛን እየለኩ በከፍተኛ ጭንቀት ይበላሉ፤+ እየተመጠነ የሚሰጣቸውንም ውኃ እየለኩ በስጋት ይጠጣሉ።+ +17 ይህም የሚሆነው ምግብና ውኃ አጥተው እርስ በርስ በድንጋጤ እንዲተያዩ እንዲሁም ከበደላቸው የተነሳ እንዲመነምኑ ነው። +41 ከዚያም ወደ ውጨኛው መቅደስ* አስገባኝ፤ በጎንና በጎን ያሉትንም ዓምዶች ለካ፤ የዓምዶቹ ወርድ በአንደኛው ጎን ስድስት ክንድ፣* በሌላኛውም ጎን ስድስት ክንድ ሆነ። +2 የመግቢያው ወርድ አሥር ክንድ ነበር፤ በመግቢያው ግራና ቀኝ ያሉት ግንቦች* አምስት አምስት ክንድ ነበሩ። የውጨኛውን መቅደስ ርዝመት ሲለካ 40 ክንድ ሆነ፤ ወርዱ ደግሞ 20 ክንድ ሆነ። +3 ከዚያም ወደ ውስጥ* ገብቶ በመግቢያው ጎን ላይ ያለውን ዓምድ ውፍረት ሲለካ ሁለት ክንድ ሆነ፤ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበር። በመግቢያው ግራና ቀኝ ያሉት ግንቦች ሰባት ክንድ ነበሩ።* +4 ከዚያም ከውጨኛው መቅደስ ትይዩ ያለውን ክፍል ለካ፤ ርዝመቱም 20 ክንድ፣ ወርዱም 20 ክንድ ሆነ።+ እሱም “ይህ ቅድስተ ቅዱሳኑ+ ነው” አለኝ። +5 ከዚያም የቤተ መቅደሱን ግንብ ሲለካ ውፍረቱ ስድስት ክንድ ሆነ። በቤተ መቅደሱ ጎን ዙሪያውን ያሉት ክፍሎች ወርድ አራት ክንድ ነበር።+ +6 በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች ከበላያቸው ሁለት ፎቅ ነበራቸው፤ በእያንዳንዱ ፎቅ ላይ 30 ክፍሎች ነበሩ። በቤተ መቅደሱ ግንብ ዙሪያ፣ በጎን በኩል ያሉትን ክፍሎች ደግፈው የሚይዙ ተሸካሚዎች ነበሩ፤ በመሆኑም እነዚህ ተሸካሚዎች ወደ ቤተ መቅደሱ ግንብ ዘልቀው አልገቡም።+ +7 በቤተ መቅደሱ ግራና ቀኝ ጠመዝማዛ መተላለፊያ* ነበር፤ ላይ ወደሚገኙት ክፍሎች ሲወጣ የመወጣጫዎቹ ወርድ ይጨምር ነበር።+ አንድ ሰው ከታች ተነስቶ በመካከለኛው ፎቅ በኩል ወደ መጨረሻው ፎቅ ሲወጣ ፎቁ እየሰፋ ይሄድ ነበር። +8 በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ከፍ ያለ መሠረት መኖሩን አየሁ፤ በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች መሠረትም እስከ ማዕዘኑ ድረስ ሙሉ ዘንግ ይኸውም ስድስት ክንድ ነበር። +9 በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች የውጨኛው ግንብ ወርድ አምስት ክንድ ነበር። በጎን ካሉት ክፍሎች አጠገብ የቤተ መቅደሱ ክፍል የሆነ ክፍት ቦታ* ነበር። +10 በቤተ መቅደሱና በመመገቢያ ክፍሎቹ*+ መካከል በሁለቱም በኩል ወርዱ 20 ክንድ የሆነ ቦታ ነበር። +11 በሰሜን አቅጣጫ፣ በጎን በኩል ባሉት ክፍሎችና ክፍት በሆነው ቦታ መካከል መግቢያ ነበር፤ በደቡብ አቅጣጫም ሌላ መግቢያ ነበር። ክፍት የሆነው ቦታ በሁሉም አቅጣጫ ወርዱ አምስት ክንድ ነበር። +12 በምዕራብ በኩል ክፍት ከሆነው ስፍራ ትይዩ ያለው ሕንፃ ወርዱ 70 ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ 90 ክንድ ነበር፤ የሕንፃው ግንብ ውፍረት ዙሪያውን አምስት ክንድ ነበር። +13 ቤተ መቅደሱን ሲለካ ርዝመቱ 100 ክንድ ሆነ። ክፍት የሆነው ስፍራ፣ ሕንፃውና* ግንቦቹ ርዝመታቸው 100 ክንድ ነበር። +14 ከምሥራቅ ትይዩ የሆነው የቤተ መቅደሱ የፊተኛው ክፍልና ክፍት የሆነው ስፍራ ወርድ 100 ክንድ ነበር። +15 በሁለቱም ጎን ያሉትን መተላለፊያዎቹን ጨምሮ በጀርባ በኩል ክፍት ከሆነው ስፍራ ጋር ትይዩ የሆነውን ሕንፃ ርዝመት ሲለካ 100 ክንድ ሆነ። እንዲሁም ውጨኛውን መቅደስ፣ ውስጠኛውን መቅደስና+ የግቢውን በረንዳዎች ለካ፤ +16 ደግሞም በሦስቱም ቦታዎች ያሉትን ደፎች፣ እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶችና+ መተላለፊያዎች ለካ። ከደፉ አጠገብ ከወለሉ አንስቶ እስከ መስኮቶቹ ድረስ የእንጨት ማስጌጫዎች ነበሩ፤+ መስኮቶቹም ተሸፍነው ነበር። +17 ከመግቢያው በላይ ያለው፣ የቤተ መቅደሱ ውስጥና ውጭ እንዲሁም በዙሪያው ያለው ግንብ ሁሉ ተለካ። +18 ግንቡ ኪሩቤልና+ የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጸውበት ነበር፤+ በሁለት ኪሩቤል መካከል የዘንባባ ዛፍ ምስል ነበር፤ እያንዳንዱ ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው። +19 ሰው የሚመስለው ፊት በአንድ በኩል ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ምስል የዞረ ሲሆን፣ አንበሳ* የሚመስለው ፊት ደግሞ በሌላ በኩል ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ዞሮ ነበር።+ በዚህ መንገድ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ተቀርጸው ነበር። +20 በመቅደሱ ግድግዳ ላይ ከወለሉ አንስቶ ከመግቢያው በላይ እስካለው ስፍራ ድረስ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር። +21 የመቅደሱ መቃኖች አራት ማዕዘን ናቸው።*+ ከቅዱሱ ስፍራ* ፊት ለፊት +22 ቁመቱ ሦስት ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ ሁለት ክንድ የሆነ ከእንጨት የተሠራ መሠዊያ+ የሚመስል ነገር ነበር። የማዕዘን ቋሚዎች ነበሩት፤ መሠረቱና* ጎኖቹ ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ። እሱም “በይሖዋ ፊት ያለው ጠረጴዛ ይህ ነው”+ አለኝ። +23 የውጨኛው መቅደስና ቅዱሱ ስፍራ እያንዳንዳቸው ሁለት በሮች ነበሯቸው።+ +24 በሮቹ ታጣፊ የሆኑ ሁለት ሳንቃዎች ነበሯቸው፤ እያንዳንዱ በር ሁለት ሳንቃዎች ነበሩት። +25 በግድግዳው ላይ ያሉት ዓይነት ኪሩቦችና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች በመቅደሱ በሮች ላይ ተቀርጸው ነበር።+ በተጨማሪም በውጭ በኩል ከፊት ለፊት በረንዳው ላይ ከእንጨት የተሠራ ወጣ ያለ ነገር* ነበር። +26 እንዲሁም በበረንዳው ግራና ቀኝ፣ ከቤተ መቅደሱ ጎን ባሉት ክፍሎች ላይና በታዛው አካባቢ እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶችና+ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ነበሩ። +46 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከምሥራቅ ትይዩ የሆነው የውስጠኛው ግቢ በር+ በስድስቱ የሥራ ቀናት+ ዝግ እንደሆነ ይቆይ፤+ ሆኖም በሰንበት ቀንና አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን ይከፈት። +2 አለቃው ከውጭ በኩል በበሩ በረንዳ ገብቶ+ በበሩ መቃን አጠገብ ይቆማል። ካህናቱ የእሱን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ እሱም በበሩ ደፍ ላይ ይሰግዳል፤ ከዚያም ይወጣል። በሩ ግን እስከ ምሽት ድረስ አይዘጋ። +3 የምድሪቱም ነዋሪዎች በየሰንበቱና አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን+ በበሩ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት ይሰግዳሉ። +4 “‘አለቃው በሰንበት ቀን እንከን የሌለባቸው ስድስት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና እንከን የሌለበት አንድ አውራ በግ ለይሖዋ ���ሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል።+ +5 ለአውራ በጉ አንድ ኢፍ* የእህል መባ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹም መስጠት የሚችለውን ያህል የእህል መባ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን* ዘይት ያቀርባል።+ +6 አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን ከከብቶቹ መካከል እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን፣ ስድስት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና አንድ አውራ በግ ያቀርባል፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው ይሁኑ።+ +7 ለወይፈኑ አንድ ኢፍ፣ ለአውራ በጉም አንድ ኢፍ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ ደግሞ መስጠት የሚችለውን ያህል እንደ እህል መባ አድርጎ ያቅርብ። እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ። +8 “‘አለቃው ሲገባ፣ በበሩ በረንዳ በኩል ይግባ፤ ሲወጣም በዚያው በኩል ይውጣ።+ +9 የምድሪቱም ነዋሪዎች በበዓል ወቅቶች በይሖዋ ፊት በሚቀርቡበት ጊዜ፣+ የአምልኮ ሥርዓት ለመፈጸም በሰሜን በር+ የሚገቡ፣ በደቡብ በር ይውጡ፤ በደቡብ በር+ የሚገቡ ደግሞ በሰሜን በር ይውጡ። ማንም ሰው በገባበት በር ተመልሶ አይውጣ፤ ይልቁንም በተቃራኒ አቅጣጫ ባለው በር ይውጣ። +10 በመካከላቸው ያለው አለቃ እነሱ በሚገቡበት ጊዜ ይግባ፤ እነሱ በሚወጡበት ጊዜም ይውጣ። +11 በበዓላትና በተወሰኑት የበዓል ወቅቶች፣ ለወይፈኑ አንድ ኢፍ፣ ለአውራ በጉ አንድ ኢፍ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ ደግሞ መስጠት የሚችለውን ያህል የእህል መባ ያቅርብ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ።+ +12 “‘አለቃው ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባን+ ወይም የኅብረት መሥዋዕትን የፈቃደኝነት መባ አድርጎ ለይሖዋ የሚያቀርብ ከሆነ በምሥራቅ ትይዩ ያለው በር ይከፈትለታል፤ በሰንበት ቀን እንደሚያደርገው ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባውንና የኅብረት መሥዋዕቱን ያቀርባል።+ ከወጣ በኋላ በሩ ይዘጋ።+ +13 “‘በየዕለቱ፣ እንከን የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባዕት የበግ ጠቦት ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርብ።+ ይህን በየማለዳው አድርግ። +14 ከዚህም ጋር በየማለዳው የኢፍ አንድ ስድስተኛ የእህል መባ እንዲሁም በላመው ዱቄት ላይ የሚፈስ የሂን አንድ ሦስተኛ ዘይት የዘወትር የእህል መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርብ። ይህ የዘላለም ደንብ ነው። +15 ተባዕቱን የበግ ጠቦት፣ የእህል መባውንና ዘይቱን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል የዘወትር መባ አድርገው በየማለዳው ያቅርቡ።’ +16 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አለቃው ለወንዶች ልጆቹ፣ ለእያንዳንዳቸው ውርስ አድርጎ ስጦታ ቢሰጣቸው፣ ስጦታው የልጆቹ ንብረት ይሆናል። ይህ በውርስ ያገኙት ንብረታቸው ነው። +17 ሆኖም ከአገልጋዮቹ ለአንዱ ከርስቱ ላይ ስጦታ ቢሰጥ፣ ነፃ እስከሚወጣበት ዓመት+ ድረስ ስጦታው የእሱ ይሆናል፤ ከዚያም ለአለቃው ይመለስለታል። ርስቱን ለዘለቄታው የራሳቸው አድርገው መያዝ የሚችሉት ወንዶች ልጆቹ ብቻ ናቸው። +18 አለቃው ሕዝቡን ከይዞታቸው በማፈናቀል የትኛውንም ርስት ሊወስድባቸው አይገባም። ከሕዝቤ መካከል አንዳቸውም ከይዞታቸው እንዳይፈናቀሉ ለወንዶች ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ይዞታ ላይ ነው።’” +19 ከዚያም ከሰሜን ትይዩ ወደሚገኙት ቅዱስ ወደሆኑት የካህናቱ መመገቢያ ክፍሎች*+ ከሚወስደው በር አጠገብ ባለው መግቢያ+ በኩል አድርጎ አመጣኝ፤ በዚያም በምዕራብ በኩል ከበስተ ኋላ አንድ ቦታ አየሁ። +20 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ካህናቱ አንድም ነገር ወደ ውጨኛው ግቢ ይዘው በመውጣት ቅድስናን ወደ ሕዝቡ እንዳያስተላልፉ*+ ሲባል የበደል መባውንና የኃጢአት መባውን የሚቀቅሉት እንዲሁም የእህል መባውን የሚጋግሩት+ በዚህ ቦታ ነው።” +21 ከዚያም ወደ ውጨኛው ግቢ ከወሰደኝ በኋላ በአራቱ የግቢው ��ዕዘኖች በኩል አዞረኝ፤ በውጨኛው ግቢ በአራቱም ማዕዘኖች በኩል ግቢ አየሁ። +22 በአራቱም የግቢው ማዕዘኖች፣ ርዝመታቸው 40 ክንድ፣* ወርዳቸው 30 ክንድ የሆኑ ትናንሽ ግቢዎች ነበሩ። አራቱም መጠናቸው እኩል ነበር።* +23 በአራቱም ዙሪያ እርከን* የነበረ ሲሆን ከእርከኑ ሥር መባዎቹ የሚቀቀሉባቸው ቦታዎች ተሠርተው ነበር። +24 ከዚያም “እነዚህ፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው+ ቦታዎች ናቸው” አለኝ። +37 የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ ይሖዋም በመንፈሱ ወሰደኝ፤ በሸለቋማው ሜዳ መካከልም አኖረኝ፤+ ስፍራውም በአጥንቶች ተሞልቶ ነበር። +2 እሱም በዙሪያቸው እንዳልፍ አደረገኝ፤ በሸለቋማው ሜዳ ላይ በጣም ብዙ አጥንቶች ወድቀው አየሁ፤ አጥንቶቹም በጣም ደርቀው ነበር።+ +3 እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ አጥንቶች ሕያው ሊሆኑ ይችላሉ?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ የምታውቀው አንተ ነህ” አልኩ።+ +4 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ስለ እነዚህ አጥንቶች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እናንተ ደረቅ አጥንቶች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ +5 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል፦ “እስትንፋስ እንዲገባባችሁ አደርጋለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ።+ +6 ጅማት አደርግላችኋለሁ፤ ሥጋም አለብሳችኋለሁ፤ በቆዳም እሸፍናችኋለሁ፤ እስትንፋስም አስገባባችኋለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’” +7 ከዚያም በታዘዝኩት መሠረት ትንቢት ተናገርኩ። ትንቢቱን እንደተናገርኩ የሚንኮሻኮሽ ድምፅ ተሰማ፤ አጥንቶቹም እርስ በርስ መገጣጠም ጀመሩ። +8 ከዚያም አጥንቶቹ ጅማትና ሥጋ ሲለብሱ አየሁ፤ በቆዳም ተሸፈኑ። ሆኖም በውስጣቸው ገና እስትንፋስ አልነበረም። +9 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ለነፋሱ ትንቢት ተናገር። የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ ነፋሱንም እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ነፋስ* ሆይ፣ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፤ ሕያው እንዲሆኑም በእነዚህ በተገደሉት ሰዎች ላይ ንፈስ።”’” +10 ስለዚህ ባዘዘኝ መሠረት ትንቢት ተናገርኩ፤ እስትንፋስም* ገባባቸው፤ እነሱም ሕያው ሆነው በእግራቸው ቆሙ፤+ እጅግ ታላቅ ሠራዊትም ሆኑ። +11 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው።+ እነሱ ‘አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጨልሟል።+ ከሌሎች ጋር ሙሉ በሙሉ ተቆራርጠናል’ ይላሉ። +12 ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ሆይ፣ መቃብሮቻችሁን እከፍታለሁ፤+ ከመቃብሮቻችሁም ውስጥ አስነሳችኋለሁ፤ ወደ እስራኤልም ምድር አመጣችኋለሁ።+ +13 ሕዝቤ ሆይ፣ መቃብሮቻችሁን ስከፍትና ከመቃብሮቻችሁ ውስጥ ሳስነሳችሁ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’+ +14 ‘መንፈሴን በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ፤+ በምድራችሁም ላይ አሰፍራችኋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ ራሴ እንደተናገርኩና ይህን እንዳደረግኩ ታውቃላችሁ’ ይላል ይሖዋ።” +15 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +16 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በትር ወስደህ ‘ለይሁዳና ከእሱ ጋር ላሉት* የእስራኤል ሰዎች’+ ብለህ ጻፍበት። ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ ‘ለዮሴፍ ይኸውም ኤፍሬምን ለሚወክለው በትርና ከእሱ ጋር ላሉት* የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ’+ ብለህ ጻፍበት። +17 ከዚያም በእጅህ ውስጥ አንድ በትር ይሆኑ ዘንድ ሁለቱንም አንድ ላይ ያዛቸው።+ +18 ወገኖችህ* ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትነግረንም?’ ብለው ሲጠይቁህ፣ +19 እንዲህ በላቸ��፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በኤፍሬም እጅ ውስጥ ያለውን የዮሴፍንና ከእሱ ጋር ያሉትን የእስራኤልን ነገዶች በትር ወስጄ ከይሁዳ በትር ጋር አያይዘዋለሁ፤ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፤+ እነሱም በእጄ ላይ አንድ በትር ይሆናሉ።”’ +20 የጻፍክባቸውን በትሮች ማየት እንዲችሉ በእጅህ ያዝ። +21 “ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያንን ከሄዱባቸው ብሔራት መካከል አመጣቸዋለሁ፤ ከየአቅጣጫውም ሰብስቤ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።+ +22 በምድሪቱ፣ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ብሔር አደርጋቸዋለሁ፤+ በሁሉም ላይ አንድ ንጉሥ ይገዛል፤+ ከእንግዲህ ሁለት ብሔራት አይሆኑም፤ ደግሞም ተከፍለው ሁለት መንግሥታት አይሆኑም።+ +23 ከእንግዲህ ወዲህ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው፣* ጸያፍ በሆኑት ልማዶቻቸውና በሚፈጽሟቸው በደሎች ሁሉ ራሳቸውን አያረክሱም።+ ታማኝነት በማጉደል ከሠሩት ኃጢአት ሁሉ እታደጋቸዋለሁ፤ ደግሞም አነጻቸዋለሁ። እነሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔ ራሴም አምላካቸው እሆናለሁ።+ +24 “‘“አገልጋዬ ዳዊት ንጉሣቸው ይሆናል፤+ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል።+ ድንጋጌዎቼን አክብረው ይመላለሳሉ፤ ደንቦቼንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ።+ +25 አባቶቻችሁ በኖሩባት፣ ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይቀመጣሉ፤+ እነሱና ልጆቻቸው* እንዲሁም የልጅ ልጆቻቸው በእሷ ላይ ለዘላለም ይኖራሉ፤+ አገልጋዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃቸው* ይሆናል።+ +26 “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ዘላለማዊ ይሆናል። እነሱንም አጸናቸዋለሁ፤ አበዛቸዋለሁ+ እንዲሁም መቅደሴን በመካከላቸው ለዘላለም አኖራለሁ። +27 ድንኳኔ* ከእነሱ ጋር* ይሆናል፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።+ +28 መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሚሆንበት ጊዜ፣ ብሔራት እስራኤልን የቀደስኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”+ +40 በግዞት በተወሰድን+ በ25ኛው ዓመት፣ በዓመቱ መጀመሪያ፣ በወሩ አሥረኛ ቀን፣ ከተማዋ በወደቀች+ በ14ኛው ዓመት፣ በዚያው ዕለት የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ እሱም ወደ ከተማዋ ወሰደኝ።+ +2 አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ፤ በአንድ ትልቅ ተራራም+ ላይ አስቀመጠኝ፤ በዚያም በስተ ደቡብ በኩል ከተማ የሚመስል ሕንፃ ነበር። +3 ወደዚያ በወሰደኝ ጊዜ መዳብ የሚመስል መልክ ያለው አንድ ሰው አየሁ።+ በእጁም ከተልባ እግር የተሠራ ገመድና የመለኪያ ዘንግ* ይዞ+ መግቢያው ላይ ቆሞ ነበር። +4 ሰውየው እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በደንብ ተመልከት፤ በጥሞና አዳምጥ፤ የማሳይህንም ሁሉ በትኩረት ተመልከት፤* እዚህ የመጣኸው ለዚህ ነውና። የምታየውን ነገር ሁሉ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ተናገር።”+ +5 ከቤተ መቅደሱ* ውጭ በዙሪያው ያለውን ቅጥር አየሁ። ሰውየው ስድስት ክንድ ርዝመት ያለው የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበር፤ እያንዳንዱ ክንድ አንድ ጋት ተጨምሮበት ነበር።* እሱም ቅጥሩን መለካት ጀመረ፤ የቅጥሩ ውፍረት አንድ ዘንግ፣ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር። +6 ከዚያም በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው በር+ መጣ፤ በደረጃዎቹም ወጣ። የበሩን ደፍ ሲለካ ወርዱ አንድ ዘንግ ነበር፤ የሌላኛውም ደፍ ወርድ አንድ ዘንግ ነበር። +7 እያንዳንዱ የዘብ ጠባቂ ክፍል ርዝመቱ አንድ ዘንግ፣ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበር፤ በዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ+ መካከል ደግሞ አምስት ክንድ ስፋት ነበር። ከበሩ በረንዳ አጠገብ በውስጥ በኩል ያለው የበሩ ደፍ አንድ ዘንግ ነበር። +8 በውስጥ በኩል ያለውን የበሩን በረንዳ ለካ፤ አንድ ዘንግም ሆነ። +9 ከዚያም የበሩን በረንዳ ሲለካ ስምንት ክንድ ሆነ፤ በጎን በኩል ያሉትን ዓምዶችም ሲለካ ሁለት ክንድ ሆኑ፤ የበሩም በረንዳ በውስጥ በኩል ነበር። +10 በምሥራቁ በር ግራና ቀኝ ሦስት ሦስት የዘብ ጠባቂ ክፍሎች ነበሩ። ሦስቱም መጠናቸው እኩል ነበር፤ በሁለቱም በኩል ያሉት ዓምዶችም መጠናቸው እኩል ነበር። +11 ከዚያም የበሩን መግቢያ ወርድ ሲለካ 10 ክንድ ሆነ፤ የበሩ ስፋት ከውጭ በኩል 13 ክንድ ነበር። +12 ከዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ ፊት ለፊት ያለው የተከለለ ቦታ በሁለቱም በኩል አንድ አንድ ክንድ ነበር። የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ በሁለቱም በኩል ስድስት ስድስት ክንድ ነበሩ። +13 ከዚያም በሩን ከአንዱ የዘብ ጠባቂ ክፍል ጣሪያ* እስከ ሌላኛው የዘብ ጠባቂ ክፍል ጣሪያ ድረስ ለካ፤ ወርዱም 25 ክንድ ነበር፤ አንደኛው መግቢያ ከሌላኛው መግቢያ ትይዩ ነበር።+ +14 ከዚያም በጎንና በጎን በኩል ያሉትን ዓምዶች ቁመት ሲለካ 60 ክንድ ሆነ፤ በግቢው ዙሪያ በሚገኙት በሮች ላይ ያሉትንም ዓምዶች ለካ። +15 ከመግቢያው በር ፊት አንስቶ በበሩ ውስጠኛ ክፍል በኩል እስካለው በረንዳ ፊት ድረስ 50 ክንድ ነበር። +16 ከበሩ በውስጥ በኩል በግራና በቀኝ፣ የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹና በጎን ያሉት ዓምዶቻቸው እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶች* ነበሯቸው።+ በረንዳዎቹም በውስጥ በኩል፣ በግራም በቀኝም መስኮቶች ነበሯቸው፤ በጎን ያሉት ዓምዶች ደግሞ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸውባቸው ነበር።+ +17 ከዚያም ወደ ውጨኛው ግቢ አመጣኝ፤ በግቢውም ዙሪያ የመመገቢያ ክፍሎችና*+ መመላለሻ መንገድ አየሁ። በመንገዱ ላይ 30 የመመገቢያ ክፍሎች ነበሩ። +18 በበሮቹ ጎን ያለው መመላለሻ መንገድ ከበሮቹ ርዝመት ጋር እኩል ነበር፤ ይህም የታችኛው መመላለሻ መንገድ ነበር። +19 ከዚያም ከታችኛው በር አንስቶ ወደ ውስጠኛው ግቢ እስከሚያስገባው በር ድረስ ያለውን ርቀት* ለካ። በምሥራቅም ሆነ በሰሜን በኩል ያለው ርቀት 100 ክንድ ነበር። +20 የውጨኛው ግቢ ከሰሜን ጋር ትይዩ የሆነ በር ነበረው፤ እሱም ርዝመቱንና ወርዱን ለካ። +21 በሁለቱም ጎን ሦስት ሦስት የዘብ ጠባቂ ክፍሎች ነበሩ። በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከመጀመሪያው በር ጋር እኩል ነበር። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። +22 የመስኮቶቹ፣ የበረንዳውና የዘንባባ ዛፍ ምስሎቹ+ መጠን በምሥራቁ በር ካሉት ጋር እኩል ነበር። ሰዎች ሰባት ደረጃዎች ወጥተው ወደዚያ መግባት ይችላሉ፤ በረንዳውም ከፊት ለፊታቸው ነበር። +23 በውስጠኛው ግቢ፣ ከሰሜኑ በር ትይዩ አንድ በር፣ ከምሥራቁ በር ትይዩ ደግሞ ሌላ በር ነበር። እሱም ከአንደኛው በር እስከ ሌላኛው በር ሲለካ 100 ክንድ ሆነ። +24 ከዚያም ወደ ደቡብ አቅጣጫ አመጣኝ፤ በስተ ደቡብ በኩል አንድ በር አየሁ።+ እሱም በጎን ያሉትን ዓምዶቹንና በረንዳውን ለካ፤ መጠናቸውም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። +25 በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ እንደ ሌሎቹ ዓይነት መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። +26 ወደዚያ የሚወስዱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤+ በረንዳውም ከፊት ለፊታቸው ነበር። በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች ላይ አንድ አንድ የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጾ ነበር። +27 የውስጠኛው ግቢ ከደቡብ ጋር ትይዩ የሆነ በር ነበረው፤ እሱም ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከአንደኛው በር እስከ ሌላኛው በር ለካ፤ ርቀቱም 100 ክንድ ሆነ። +28 ከዚያም በደቡብ በር በኩል ወደ ውስጠኛው ግቢ ወሰደኝ፤ የደቡቡን በር ሲለካ መጠኑ ከሌሎቹ ጋር እኩል ሆነ። +29 የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክ���ድ ነበር።+ +30 ዙሪያውን በረንዳዎች ነበሩ፤ ርዝመታቸው 25 ክንድ፣ ወርዳቸው ደግሞ 5 ክንድ ነበር። +31 በረንዳው ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበር፤ በጎን ባሉት ዓምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ነበሩ፤+ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ።+ +32 በምሥራቅ በኩል ወደ ውስጠኛው ግቢ ሲወስደኝ በሩን ለካ፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። +33 የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር፤ በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። +34 በረንዳው ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ። +35 ከዚያም ወደ ሰሜን በር+ ወሰደኝና ለካው፤ መጠኑ ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። +36 የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። በግራና በቀኝ መስኮቶች ነበሩት። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። +37 በጎን ያሉት ዓምዶቹ ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበሩ፤ በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶቹ ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ። +38 በበሮቹ ጎንና ጎን ባሉት ዓምዶች አጠገብ የመመገቢያ ክፍል ነበር፤ መግቢያም ነበረው፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባ የሚያጥቡት በዚያ ነበር።+ +39 በበሩም በረንዳ ላይ በግራና በቀኝ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ፣+ የኃጢአት መባና+ የበደል መባ+ የሚታረድባቸው ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። +40 ወደ ሰሜን በር በሚወስደው መንገድ ላይ ከመግቢያው ውጭ ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። በተጨማሪም ከበሩ በረንዳ በሌላኛው በኩል ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። +41 በበሩ ግራና ቀኝ አራት አራት ጠረጴዛዎች፣ በድምሩ መሥዋዕት የታረደባቸው ስምንት ጠረጴዛዎች ነበሩ። +42 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ የሚያገለግሉት አራቱ ጠረጴዛዎች ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ ነበሩ። ርዝመታቸው አንድ ክንድ ተኩል፣ ወርዳቸው አንድ ክንድ ተኩል፣ ቁመታቸው ደግሞ አንድ ክንድ ነበር። በእነሱም ላይ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕቱን ለማረድ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ተቀምጠው ነበር። +43 ከውስጠኛው ግንብ ጋር ተያይዘው ዙሪያውን የተሠሩ መደርደሪያዎች የነበሩ ሲሆን ወርዳቸው አንድ ጋት ነበር፤ በጠረጴዛዎቹም ላይ የስጦታ መባው ሥጋ ይቀመጥ ነበር። +44 ከውስጠኛው በር ውጭ የዘማሪዎቹ መመገቢያ ክፍሎች ነበሩ፤+ ክፍሎቹ ከደቡብ ትይዩ ባለው የሰሜን በር አጠገብ በሚገኘው በውስጠኛው ግቢ ውስጥ ነበሩ። ከሰሜን ትይዩ ባለው የምሥራቅ በር አጠገብ ሌላ የመመገቢያ ክፍል ነበር። +45 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “በደቡብ ትይዩ ያለው ይህ የመመገቢያ ክፍል የቤተ መቅደሱን አገልግሎት እንዲያከናውኑ ኃላፊነት ለተጣለባቸው ካህናት የተመደበ ነው።+ +46 በሰሜን ትይዩ ያለው የመመገቢያ ክፍል ከመሠዊያው ጋር የተያያዘ አገልግሎት እንዲያከናውኑ ኃላፊነት ለተጣለባቸው ካህናት የተመደበ ነው።+ እነዚህ የሳዶቅ+ ልጆች ሲሆኑ ከሌዋውያን መካከል ይሖዋን ለማገልገል ወደ እሱ እንዲቀርቡ የተመደቡ ናቸው።”+ +47 ከዚያም የውስጠኛውን ግቢ ለካ። ርዝመቱ 100 ክንድ፣ ወርዱም 100 ክንድ የሆነ አራት ማዕዘን ነበር። መሠዊያው ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ነበር። +48 ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ በረንዳ+ አመጣኝ፤ በጎን በኩል ያለውንም የበረንዳውን ዓምድ ለካ፤ ዓምዱም በአንደኛው ጎን አምስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን አምስት ክንድ ነበር። የበሩ ወርድ በአንደኛው ጎን ሦስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን ሦስት ክንድ ነበ���። +49 የበረንዳው ርዝመት 20 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 11* ክንድ ነበር። ሰዎች ወደዚያ የሚወጡት በደረጃዎች ነበር። በጎንና በጎን ባሉት ምሰሶዎች አጠገብ በግራና በቀኝ አንድ አንድ ዓምድ ነበር።+ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለኢየሩሳሌም አስጸያፊ ልማዶቿን አሳውቃት።+ +3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይላል፦ “መገኛሽና ትውልድሽ በከነአናውያን ምድር ነው። አባትሽ አሞራዊ፣+ እናትሽም ሂታዊት ነበሩ።+ +4 አወላለድሽንም በተመለከተ፣ በተወለድሽበት ቀን እትብትሽ አልተቆረጠም፤ ንጹሕም እንድትሆኚ በውኃ አልታጠብሽም፤ በጨውም አልታሸሽም፤ ደግሞም በጨርቅ አልተጠቀለልሽም። +5 ለአንቺ አዝኖ ከእነዚህ ነገሮች አንዱንም እንኳ ያደረገልሽ የለም። የራራልሽም የለም። ይልቁንም በተወለድሽበት ቀን ስለተጠላሽ* አውላላ ሜዳ ላይ ተጣልሽ። +6 “‘“በአጠገብሽ ሳልፍ በደምሽ ላይ ስትንፈራገጪ አየሁሽ፤ ደግሞም በደምሽ ላይ ተኝተሽ ሳለ ‘በሕይወት ኑሪ!’ አልኩሽ። አዎ፣ በደምሽ ላይ ተኝተሽ ሳለ ‘በሕይወት ኑሪ!’ አልኩሽ። +7 በሜዳ ላይ እንደሚበቅሉ ዕፀዋት እጅግ እንድትበዢ አደረግኩ፤ አንቺም አደግሽ፤ ደግሞም ሙሉ ሰው ሆንሽ፤ እጅግ ያማረ ጌጥም አደረግሽ። ጡቶችሽ አጎጠጎጡ፤ ፀጉርሽም አደገ፤ ይሁንና በዚህ ጊዜም እርቃንሽንና ራቁትሽን ነበርሽ።”’ +8 “‘በአጠገብሽ ሳልፍ አየሁሽ፤ የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ዕድሜሽ እንደደረሰ አስተዋልኩ። ስለዚህ ልብሴን* በአንቺ ላይ ዘርግቼ+ እርቃንሽን ሸፈንኩ፤ ደግሞም ማልኩልሽ፤ ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን አደረግኩ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ‘አንቺም የእኔ ሆንሽ። +9 በተጨማሪም በውኃ አጠብኩሽ፤ ከደምሽም አነጻሁሽ፤ ዘይትም ቀባሁሽ።+ +10 ከዚያም የተጠለፈ ሸማ አለበስኩሽ፤ ከጥሩ ቆዳ* የተሠራ ጫማም ሰጠሁሽ፤ በጥሩ በፍታም ጠቀለልኩሽ፤ እጅግ ውድ የሆነ ልብስም አለበስኩሽ። +11 በጌጣጌጥ አንቆጠቆጥኩሽ፤ በእጆችሽ አምባር፣ በአንገትሽም ሐብል አጠለቅኩልሽ። +12 በተጨማሪም በአፍንጫሽ ቀለበት፣ በጆሮዎችሽ ጉትቻ፣ በራስሽም ላይ የሚያምር አክሊል አደረግኩልሽ። +13 ራስሽን በወርቅና በብር አስጌጥሽ፤ ልብስሽም ጥሩ በፍታ፣ እጅግ ውድ በሆነ ጨርቅ የተሠራና የተጠለፈ ሸማ ነበር። ምግብሽም የላመ ዱቄት፣ ማርና ዘይት ነበር፤ እጅግ ውብ ሆንሽ፤+ ንግሥት ለመሆንም* በቃሽ።’” +14 “‘ከውበትሽ የተነሳ ዝናሽ* በብሔራት መካከል ገነነ፤+ ውበትሽ በአንቺ ላይ ካኖርኩት ግርማዬ የተነሳ ፍጹም ሆኖ ነበርና’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +15 “‘ሆኖም አንቺ በውበትሽ መመካት ጀመርሽ፤+ ዝናሽንም ለዝሙት አዳሪነት ተጠቀምሽበት።+ ከአላፊ አግዳሚው ጋር ያለገደብ አመነዘርሽ፤+ ውበትሽንም ለማንም አሳልፈሽ ሰጠሽ። +16 የተለያዩ ቀለማት ካሏቸው ልብሶችሽ አንዳንዶቹን ወስደሽ የምታመነዝሪባቸውን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችሽን አስጌጥሽባቸው፤+ እነዚህ ነገሮች መሆን የለባቸውም፤ ጨርሶ ሊፈጸሙም አይገባም። +17 ደግሞም በሰጠሁሽ ወርቅና ብር የተሠሩትን ያማሩ ጌጣጌጦችሽን ወስደሽ ለራስሽ የወንድ ምስሎች ሠራሽ፤ ከእነሱም ጋር አመነዘርሽ።+ +18 የተጠለፉ ሸማዎችሽንም ወስደሽ አለበስሻቸው፤* ዘይቴንና ዕጣኔንም አቀረብሽላቸው።+ +19 ደግሞም እንድትበዪው የሰጠሁሽን ከላመ ዱቄት፣ ከዘይትና ከማር የተዘጋጀ ምግብ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ አድርገሽ አቀረብሽላቸው።+ የተፈጸመው ነገር ይኸው ነው’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +20 “‘ለእኔ የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን+ ወስደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ለጣዖቶቹ ሠዋሽላቸው፤+ የምትፈጽሚው ምንዝር እጅግ አልበዛም? +21 ወንዶች ልጆቼን አረድሽ፤ በእ���ትም አሳልፈሽ መሥዋዕት አድርገሽ አቀረብሻቸው።+ +22 አስጸያፊ ልማዶችሽንና ምንዝርሽን ሁሉ ስትፈጽሚ እርቃንሽንና ራቁትሽን ሆነሽ በገዛ ደምሽ ላይ ስትንፈራገጪ የነበርሽበትን የልጅነትሽን ጊዜ አላስታወስሽም። +23 ይህን ሁሉ ክፋት ከፈጸምሽ በኋላ ወዮ፣ ወዮልሽ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +24 ‘ለራስሽ ጉብታ አበጀሽ፤ በየአደባባዩም ከፍ ያለ ቦታ ሠራሽ። +25 በየመንገዱ ላይ በሚገኝ የታወቀ ስፍራ ሁሉ ከፍ ያለ ቦታ ሠራሽ፤ ለአላፊ አግዳሚው ሁሉ ራስሽን በመስጠት*+ ውበትሽን ወደ አስጸያፊ ነገር ለወጥሽ፤ የምትፈጽሚውንም ምንዝር አበዛሽ።+ +26 በፍትወት ከተቃጠሉ ጎረቤቶችሽ* ይኸውም ከግብፅ ወንዶች ልጆች ጋር አመነዘርሽ፤+ ገደብ በሌለው ምንዝርሽ አስቆጣሽኝ። +27 አሁን እጄን በአንቺ ላይ እዘረጋለሁ፤ ቀለብሽንም እቀንሳለሁ፤+ በጸያፍ ተግባርሽ የተነሳ የሚሸማቀቁትና የሚጠሉሽ ሴቶች ይኸውም የፍልስጤም ሴቶች ልጆች ያሻቸውን እንዲያደርጉብሽ አሳልፌ እሰጥሻለሁ።+ +28 “‘እርካታ ባለማግኘትሽ ከአሦር ወንዶች ልጆች ጋር ደግሞ አመነዘርሽ፤+ ሆኖም ከእነሱ ጋር ካመነዘርሽ በኋላም እንኳ አልረካሽም። +29 ስለዚህ ምንዝርሽን በነጋዴዎች* ምድርና በከለዳውያን ምድር አበዛሽ፤+ ያም ሆኖ እንኳ አልረካሽም። +30 ዓይን አውጣ እንደሆነች ዝሙት አዳሪ+ ይህን ሁሉ ነገር የፈጸምሽው ልብሽ ምንኛ ታማሚ* ቢሆን ነው!’* ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +31 ‘ይሁንና በየመንገዱ ላይ በሚገኝ የታወቀ ስፍራ ሁሉ ጉብታሽን ስታበጂና በየአደባባዩ ለራስሽ ከፍ ያለ ቦታ ስትሠሪ እንደ ዝሙት አዳሪ አልሆንሽም፤ ምክንያቱም ምንም ዓይነት ክፍያ አትቀበዪም። +32 አንቺ በባሏ ፋንታ እንግዳ የሆኑ ሰዎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ሚስት ነሽ!+ +33 ሰዎች ለዝሙት አዳሪዎች ሁሉ ስጦታ ይሰጣሉ፤+ በፍትወት ለሚመኙሽ ሁሉ ስጦታ የሰጠሽው ግን አንቺ ነሽ፤+ ደግሞም ከየቦታው መጥተው ከአንቺ ጋር እንዲያመነዝሩ ጉቦ ትሰጫቸዋለሽ።+ +34 አንቺ ከሌሎች ዝሙት አዳሪ ሴቶች ፈጽሞ የተለየሽ ነሽ። አንቺ የፈጸምሽው ዓይነት ምንዝር የፈጸመ ሰው ታይቶ አይታወቅም! አንቺ ትከፍያቸዋለሽ እንጂ እነሱ አይከፍሉሽም። የአንቺ አድራጎት ተቃራኒ ነው።’ +35 “በመሆኑም አንቺ ዝሙት አዳሪ፣+ የይሖዋን ቃል ስሚ። +36 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከፍቅረኞችሽና የወንዶች ልጆችሽን ደም መሥዋዕት አድርገሽ ካቀረብሽላቸው+ አስጸያፊና ቀፋፊ ጣዖቶችሽ*+ ሁሉ ጋር ባመነዘርሽ ጊዜ ከልክ በላይ በፍትወት ስለተቃጠልሽና እርቃንሽ ስለተገለጠ፣ +37 እኔ ደስ ያሰኘሻቸውን ፍቅረኞችሽን ሁሉ፣ የወደድሻቸውንም ሆነ የጠላሻቸውን ሁሉ አንድ ላይ እሰበስባለሁ። እነሱን ከየቦታው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ እርቃንሽን ለእነሱ እገልጣለሁ፤ እነሱም ሙሉ በሙሉ እርቃንሽን ሆነሽ ያዩሻል።+ +38 “‘አመንዝሮችና ደም የሚያፈሱ ሴቶች+ ሊፈረድባቸው በሚገባው ፍርድ እቀጣሻለሁ፤+ ደግሞም በቁጣና በቅናት ደምሽ ይፈስሳል።+ +39 በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነሱም ጉብታዎችሽን ያፈርሳሉ፤ ከፍ ያሉ ቦታዎችሽንም ያወድማሉ፤+ ልብሶችሽንም ይገፉሻል፤+ ያማሩ ጌጣጌጦችሽንም ይወስዳሉ፤+ እርቃንሽንና ራቁትሽንም ያስቀሩሻል። +40 ብዙ ሰዎችን ያነሳሱብሻል፤+ በድንጋይም ይወግሩሻል፤+ በሰይፋቸውም ያርዱሻል።+ +41 ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፤+ በብዙ ሴቶችም ፊት በአንቺ ላይ ፍርዴን ይፈጽማሉ፤ ምንዝርሽንም አስተውሻለሁ፤+ ከእንግዲህም ወዲህ ዋጋ አትከፍዪም። +42 በአንቺ ላይ የነበረው ቁጣዬ ይበርዳል፤+ ንዴቴም ከአንቺ ይርቃል።+ እኔም እረጋጋለሁ፤ ከእንግዲህም አልቆጣም።’ +43 “‘የልጅነት ጊዜሽን ስላላስታወስሽና+ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በማድረግ ስላስቆጣሽኝ እኔም የተከተልሽው መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራስሽ ላይ አመጣብሻለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ‘አንቺም ከእንግዲህ ወዲህ አስነዋሪ ምግባርሽንና አስጸያፊ የሆኑ ልማዶችሽን ሁሉ አትፈጽሚም። +44 “‘እነሆ፣ ምሳሌያዊ አባባል የሚጠቀም ሁሉ “ልጅቷም በእናቷ ወጣች!”+ እያለ ይተርትብሻል። +45 አንቺ የእናትሽ ልጅ ነሽ፤ እሷ ባሏንና ልጆቿን ትንቃለች። ደግሞም ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን የናቁት የእህቶችሽ እህት ነሽ። እናታችሁ ሂታዊት፣ አባታችሁ ደግሞ አሞራዊ ነበሩ።’”+ +46 “‘ታላቅ እህትሽ ከሴቶች ልጆቿ*+ ጋር ከአንቺ በስተ ሰሜን* የምትኖረው ሰማርያ ናት፤+ ታናሽ እህትሽም ከሴቶች ልጆቿ ጋር ከአንቺ በስተ ደቡብ* የምትኖረው ሰዶም ናት።+ +47 በእነሱ መንገድ መሄድና የእነሱን አስጸያፊ ልማዶች መከተል ብቻ ሳይሆን በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምግባርሽ ሁሉ ከእነሱ ይበልጥ ብልሹ ሆንሽ።+ +48 በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘አንቺና ሴቶች ልጆችሽ ያደረጋችሁትን እህትሽ ሰዶምና ሴቶች ልጆቿ አላደረጉትም። +49 እነሆ፣ የእህትሽ የሰዶም በደል ይህ ነበር፦ እሷና ሴቶች ልጆቿ+ ኩራተኞች ነበሩ፤+ የተትረፈረፈ ምግብ የነበራቸው+ ሲሆን ያለጭንቀት ተረጋግተው ይኖሩ ነበር፤+ ይሁንና ጎስቋላውንና ድሃውን አልደገፉም።+ +50 እነሱም ትዕቢታቸውን አላስወገዱም፤+ በፊቴም አስጸያፊ የሆኑ ልማዶችን መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤+ በመሆኑም እነሱን ማስወገድ ተገቢ ሆኖ አገኘሁት።+ +51 “‘ሰማርያም+ ብትሆን አንቺ የሠራሽውን ኃጢአት ግማሹን እንኳ አልሠራችም። አንቺ ከምትፈጽሚያቸው አስጸያፊ ልማዶች ሁሉ የተነሳ እህቶችሽ ጻድቃን መስለው እስኪታዩ ድረስ ከእነሱ ይበልጥ ብዙ አስጸያፊ ልማዶች መፈጸምሽን ቀጠልሽ።+ +52 የእህቶችሽ ምግባር ተገቢ መስሎ እንዲታይ ስላደረግሽ* አሁን ኀፍረትሽን ተከናነቢ። ከእነሱ ይበልጥ አስጸያፊ በሆነ መንገድ ከፈጸምሽው ኃጢአት የተነሳ እነሱ ከአንቺ ይልቅ ጻድቃን ሆነዋል። እንግዲህ እህቶችሽን ጻድቃን ስላስመሰልሻቸው ኀፍረት ተከናነቢ፤ ውርደትሽንም ተሸከሚ።’ +53 “‘በምርኮ የተወሰዱባቸውን ይኸውም ከሰዶምና ከሴቶች ልጆቿ የተማረኩትን እንዲሁም ከሰማርያና ከሴቶች ልጆቿ የተማረኩትን እሰበስባለሁ፤ በተጨማሪም ከአንቺ የተማረኩትን ከእነሱ ጋር እሰበስባለሁ፤+ +54 ይህም የሚሆነው ውርደትሽን እንድትሸከሚ ነው፤ ደግሞም እነሱን በማጽናናት ባደረግሽው ነገር የተነሳ ውርደት ትከናነቢያለሽ። +55 የገዛ እህቶችሽ፣ ሰዶምና ሴቶች ልጆቿ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ፤ እንዲሁም ሰማርያና ሴቶች ልጆቿ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ፤ አንቺና ሴቶች ልጆችሽም ቀድሞ ወደነበራችሁበት ሁኔታ ትመለሳላችሁ።+ +56 ኩሩ በነበርሽበት ቀን እህትሽ ሰዶም በአንደበትሽ ለመጠራት እንኳ የምትበቃ አልነበረችም፤ +57 ይህም የሆነው ክፋትሽ ከመጋለጡ በፊት ነበር።+ አሁን ግን የሶርያ ሴቶች ልጆችና ጎረቤቶቿ በአንቺ ላይ ነቀፋ ይሰነዝራሉ፤ እንዲሁም የፍልስጤማውያን+ ሴቶች ልጆች፣ በዙሪያሽም ያሉ ሁሉ በንቀት ያዩሻል። +58 አስነዋሪ ምግባርሽና አስጸያፊ ልማዶችሽ የሚያስከትሉብሽን መዘዝ ትቀበያለሽ’ ይላል ይሖዋ።” +59 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እንግዲህ ቃል ኪዳኔን በማፍረስ መሐላውን ስለናቅሽ+ እኔም እንዳደረግሽው አደርግብሻለሁ።+ +60 ይሁንና እኔ ራሴ በልጅነትሽ ጊዜ ከአንቺ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤ ደግሞም ከአንቺ ጋር ዘላቂ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።+ +61 ታላላቆችሽና ታናናሾችሽ የሆኑትን እህቶችሽን ስትቀበዪ ምግባርሽን ታስታውሻለሽ፤ ደግሞም ታፍ���ያለሽ፤+ እኔም እነሱን ሴቶች ልጆች አድርጌ እሰጥሻለሁ፤ ይህን የማደርገው ግን ከአንቺ ጋር በገባሁት ቃል ኪዳን የተነሳ አይደለም።’ +62 “‘እኔ ራሴም ከአንቺ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አጸናለሁ፤ አንቺም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ። +63 ከዚያም፣ ያን ሁሉ ነገር ብታደርጊም እንኳ ለአንቺ ባስተሰረይኩልሽ ጊዜ ሥራሽን ታስታውሻለሽ፤+ ከደረሰብሽም ውርደት የተነሳ አፍሽን ለመክፈት እጅግ ታፍሪያለሽ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +6 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። +3 እንዲህም በል፦ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለተራሮቹ፣ ለኮረብቶቹ፣ ለጅረቶቹና ለሸለቆዎቹ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እኔ በእናንተ ላይ ሰይፍ አመጣለሁ፤ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎቻችሁንም አጠፋለሁ። +4 መሠዊያዎቻችሁ ይፈርሳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ይሰባበራሉ፤+ የታረዱ ወገኖቻችሁንም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ* ፊት እጥላለሁ።+ +5 የእስራኤልን ሕዝብ ሬሳ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ፊት እጥላለሁ፤ አጥንቶቻችሁንም በመሠዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ።+ +6 በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ያሉት ከተሞች ይወድማሉ፤+ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎቹም ፈራርሰው ባድማ ይሆናሉ።+ መሠዊያዎቻችሁ ፈራርሰው እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ አስጸያፊ የሆኑት ጣዖቶቻችሁ ይወገዳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ተገንድሰው ይወድቃሉ፤ የሠራችኋቸው ሥራዎችም ተጠራርገው ይጠፋሉ። +7 የታረዱትም ሰዎች በመካከላችሁ ይወድቃሉ፤+ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ +8 “‘“ይሁንና የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ በየአገሩ በምትበተኑበት ጊዜ፣ ከእናንተ ውስጥ አንዳንዶቻችሁ በብሔራት መካከል ስትኖሩ ከሰይፍ ታመልጣላችሁና።+ +9 የተረፉትም ሰዎች በምርኮ በተወሰዱባቸው ብሔራት መካከል ሆነው እኔን ያስታውሳሉ።+ ከእኔ በራቀው ከሃዲ* ልባቸውና+ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን በፍትወት ስሜት በተመለከቱት* ዓይኖቻቸው የተነሳ+ ምን ያህል ልቤ እንዳዘነ ይገነዘባሉ። በሠሯቸው መጥፎና አስነዋሪ ነገሮች ሁሉ ያፍራሉ፤ እነዚህንም ነገሮች ይ +10 እኔ ይሖዋ እንደሆንኩና ይህን ጥፋት እንደማመጣባቸው የዛትኩት በከንቱ እንዳልሆነ ያውቃሉ።”’+ +11 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የእስራኤል ቤት ሰዎች በሠሯቸው ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ስለሚወድቁ በእጅህ እያጨበጨብክ፣ በእግርህም መሬቱን እየደበደብክ አልቅስ።+ +12 በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፤ በቅርብ ያለው በሰይፍ ይወድቃል፤ ከእነዚህ ነገሮች ያመለጠና በሕይወት የተረፈ ሁሉ በረሃብ ያልቃል፤ ቁጣዬንም ሁሉ በእነሱ ላይ አወርዳለሁ።+ +13 የታረዱት ወገኖቻቸው አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው መካከል፣ በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፣ ከፍ ባለ ኮረብታ ሁሉና በተራሮች አናት ሁሉ ላይ፣ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች እንዲሁም በትላልቅ ዛፎች ቅርንጫፎች ሥር ይኸውም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ሁሉ ቁጣ ለማብረድ፣ ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያላቸው መባዎች*+ ባቀረቡ +14 በእነሱ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱንም ባድማ አደርጋለሁ፤ መኖሪያ ቦታዎቻቸውም ሁሉ በዲብላ አቅራቢያ ካለው ምድረ በዳ የባሰ ባድማ ይሆናሉ። እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’” +25 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ አሞናውያን+ አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር።+ +3 አሞናውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መቅደሴ በረከሰ ጊዜና የእስራኤል ምድር ባድማ በሆነ ጊዜ እንዲሁም የይሁዳ ቤት ሰዎች በግዞት በተወሰዱ ጊዜ ‘እሰይ!’ ስላላችሁ +4 ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እነሱ በእናንተ ውስጥ ይሰፍራሉ፤* ድንኳኖቻቸውንም በመካከላችሁ ይተክላሉ። ፍሬያችሁን ይበላሉ፤ ወተታችሁንም ይጠጣሉ። +5 ራባን+ የግመሎች መሰማሪያ፣ የአሞናውያንን ምድርም መንጋ የሚያርፍበት ስፍራ አደርጋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’” +6 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በእጅህ ስላጨበጨብክና+ በእግርህ መሬቱን ስለመታህ እንዲሁም በእስራኤል ምድር ላይ የደረሰውን ሁኔታ ስታይ በንቀት ተሞልተህ* ሐሴት ስላደረግክ፣+ +7 ብሔራት እንዲበዘብዙህ ለእነሱ አሳልፌ እሰጥህ ዘንድ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ። ከሕዝቦች መካከል አስወግድሃለሁ፤ ከአገራትም መካከል ለይቼ አጠፋሃለሁ።+ እደመስስሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ።’ +8 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሞዓብና+ ሴይር+ “እነሆ፣ የይሁዳ ቤት ልክ እንደ ሌሎቹ ብሔራት ነው” ስላሉ፣ +9 በድንበሩ ላይ የሚገኙትና የምድሪቱ ውበት* የሆኑት ከተሞች ማለትም ከቤትየሺሞትና ከበዓልመዖን አንስቶ እስከ ቂርያታይም+ ድረስ ያለው የሞዓብ ክንፍ* ለጠላት እንዲጋለጥ አደርጋለሁ። +10 ከአሞናውያን ጋር ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጠዋለሁ፤+ ይህም አሞናውያን በብሔራት መካከል እንዳይታወሱ ለማድረግ ነው።+ +11 በሞዓብም ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’ +12 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ኤዶም በቂም በቀል ተነሳስቶ በይሁዳ ቤት ላይ እርምጃ ወስዷል፤ ደግሞም እነሱን በመበቀል ከፍተኛ በደል ፈጽሟል፤+ +13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ።+ ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ +14 ‘በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ።+ እነሱም፣ ኤዶም የምወስደውን የበቀል እርምጃ ይቀምስ ዘንድ ቁጣዬንና መዓቴን በኤዶም ላይ ያወርዳሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’ +15 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ፍልስጤማውያን በማይበርድ የጠላትነት ስሜት ተነሳስተው በክፋት* የበቀል እርምጃ ለመውሰድና ጥፋት ለማድረስ ጥረት አድርገዋል።+ +16 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በፍልስጤማውያን ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤+ ከሪታውያንንም አጠፋለሁ፤+ በባሕሩ ዳርቻ ላይ የቀሩትንም ነዋሪዎች እደመስሳለሁ።+ +17 ኃይለኛ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ የበቀል እርምጃ እወስድባቸዋለሁ፤ በምበቀላቸውም ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’” +33 የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለሕዝብህ ልጆች ተናገር፤+ እንዲህም በላቸው፦ “‘በአንድ አገር ላይ ሰይፍ አመጣሁ እንበል፤+ በዚህ ጊዜ የአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ አንድ ሰው በመምረጥ ጠባቂ አድርጎ ሾመው፤ +3 እሱም በአገሪቱ ላይ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ ቀንደ መለከት በመንፋት ሕዝቡን አስጠነቀቀ።+ +4 አንድ ሰው የቀንደ መለከቱን ድምፅ ሰምቶ ማስጠንቀቂያውን ተግባራዊ ሳያደርግ ቢቀር፣+ ሰይፍም መጥቶ ሕይወቱን ቢያጠፋ፣* ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል።+ +5 የቀንደ መለከቱን ድምፅ ቢሰማም ማስጠንቀቂያውን ተግባራዊ አላደረገም። ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል። ቢጠነቀቅ ኖሮ ሕይወቱ* በተረፈ ነበር። +6 “‘ነገር ግን ጠባቂው ሰይፍ ሲመጣ አይቶ ቀንደ መለከት ባይነፋና+ ሕዝቡን ባያስጠነቅቅ፣ ሰይፍም መጥቶ ከመካከላቸው የአንዱን ሰው ሕይወት* ቢያጠፋ፣ ይህ ሰው በገዛ በደሉ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከጠባቂው እጅ እሻለሁ።’*+ +7 “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው።+ +8 ክፉውን ሰው ‘አንተ ክፉ ሰው፣ በእርግጥ ትሞታለህ!’ ባልኩት ጊዜ፣+ ክፉውን ሰው አካሄዱን እንዲያስተካክል ባታስጠነቅቀው፣ እሱ ክፉ በመሆኑ ከሠራው በደል የተነሳ ይሞታል፤+ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ። +9 ሆኖም ክፉውን ሰው ከመንገዱ እንዲመለስ አስጠንቅቀኸው አካሄዱን ለማስተካከል ፈቃደኛ ባይሆን፣ እሱ በሠራው በደል ይሞታል፤+ አንተ ግን የገዛ ሕይወትህን* በእርግጥ ታድናለህ።+ +10 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ‘እናንተ እንዲህ ብላችኋል፦ “ዓመፃችንና ኃጢአታችን እጅግ ከብዶናል፤ በዚህም የተነሳ እየመነመንን ሄደናል፤+ ታዲያ እንዴት በሕይወት መቀጠል እንችላለን?”’+ +11 እንዲህ በላቸው፦ ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “በክፉው ሰው ሞት ደስ አልሰኝም፤+ ይልቁንም ክፉው ሰው አካሄዱን አስተካክሎ+ በሕይወት እንዲኖር እፈልጋለሁ።+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ተመለሱ፤ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤+ ለምን ትሞታላችሁ?”’+ +12 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ለሕዝብህ ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ‘ጻድቁ ሰው በሚያምፅበት ጊዜ ጽድቁ አያድነውም፤+ ክፉውም ሰው ከክፋቱ በሚመለስበት ጊዜ በክፋቱ አይሰናከልም፤+ ደግሞም ጻድቅ የሆነ ማንኛውም ሰው ኃጢአት በሚሠራበት ቀን በጽድቁ በሕይወት ሊኖር አይችልም።+ +13 ጻድቁን ሰው “በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ” ባልኩት ጊዜ በገዛ ጽድቁ ታምኖ መጥፎ* ነገር ቢፈጽም፣+ ከጽድቅ ሥራው መካከል አንዱም አይታሰብም፤ ይልቁንም መጥፎ ነገር በመፈጸሙ ይሞታል።+ +14 “‘እንዲሁም ክፉውን ሰው “በእርግጥ ትሞታለህ” ባልኩት ጊዜ ከኃጢአቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣+ +15 ደግሞም ክፉው ሰው መያዣ አድርጎ የወሰደውን ቢመልስ፣+ የሰረቀውን መልሶ ቢሰጥና+ መጥፎ ነገር ከመፈጸም ተቆጥቦ ሕይወት የሚያስገኙትን ደንቦች ቢከተል፣ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።+ ፈጽሞ አይሞትም። +16 ከሠራቸው ኃጢአቶች ውስጥ አንዱም አይታወስበትም።*+ ፍትሕና ጽድቅ የሆነውን ነገር ስላደረገ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።’+ +17 “ይሁንና ወገኖችህ ፍትሐዊ ያልሆነው የእነሱ መንገድ ሆኖ ሳለ ‘የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም’ ብለዋል። +18 “ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ በዚህ የተነሳ ይሞታል።+ +19 ሆኖም ክፉ ሰው ከክፋቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣ ይህን በማድረጉ በሕይወት ይኖራል።+ +20 “ይሁንና እናንተ ‘የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም’ ብላችኋል።+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።” +21 ከረጅም ጊዜ በኋላ ይኸውም በተማረክን በ12ኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ ሰው ወደ እኔ መጥቶ+ “ከተማዋ ተመታች!” አለኝ።+ +22 ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ ሰውየው ጠዋት ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት፣ አምላክ አፌን ከፈተልኝ። እኔም አፌ ተከፍቶ በድጋሚ መናገር ቻልኩ።+ +23 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +24 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነዚህ የፈራረሱ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች+ ስለ እስራኤል ምድር እንዲህ በማለት ይናገራሉ፦ ‘አብርሃም አንድ ራሱ ብቻ ነበር፤ ይሁንና ምድሪቱን ወረሰ።+ እኛ ግን ብዙ ነን፤ ���እርግጥ ምድሪቱ ርስት ሆና ተሰጥታናለች።’ +25 “ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤+ ዓይኖቻችሁን አስጸያፊ ወደሆኑት ጣዖቶቻችሁ* ታነሳላችሁ፤ ደምም ታፈሳላችሁ።+ ታዲያ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል? +26 በሰይፋችሁ ታምናችኋል፤+ አስጸያፊ ልማዶች ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የባልንጀራችሁን ሚስት አርክሳችኋል።+ ታዲያ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል?”’+ +27 “አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ በፈራረሱት ቦታዎች የሚኖሩት ሰዎች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ አውላላ ሜዳ ላይ ያሉትንም ለዱር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣቸዋለሁ፤ በምሽጎችና በዋሻዎች ውስጥ ያሉትም በበሽታ ይሞታሉ።+ +28 ምድሪቱን ፈጽሞ ባድማ አደርጋታለሁ፤+ ከልክ ያለፈ ኩራቷም ይጠፋል፤ የእስራኤልም ተራሮች ባድማ ይሆናሉ፤+ የሚያልፍባቸውም አይኖርም። +29 ደግሞም በፈጸሟቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ+ ምድሪቱን ፈጽሞ ባድማ በማደርግበት ጊዜ+ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’ +30 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወገኖችህ በየግድግዳው ሥርና በየቤቱ በራፍ ላይ ሆነው እርስ በርሳቸው ስለ አንተ ይነጋገራሉ።+ አንዱ ሌላውን፣ እያንዳንዱም ወንድሙን፣ ‘ና፣ ከይሖዋ የመጣውን ቃል እንስማ’ ይለዋል። +31 እንደ ሕዝቤ በፊትህ ለመቀመጥ ተሰብስበው ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ቃልህን ይሰማሉ፤ ሆኖም በተግባር አያውሉትም።+ በአፋቸው ይሸነግሉሃልና፤* ልባቸው ግን አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይስገበገባል። +32 እነሆ፣ አንተ ለእነሱ ባማረ ድምፅ እንደሚዘፈንና በባለ አውታር መሣሪያ አሳምረው እንደሚጫወቱት የፍቅር ዘፈን ሆነህላቸዋል። ቃልህን ይሰማሉ፤ ሆኖም አንዳቸውም አያደርጉትም። +33 ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ፣ ደግሞም ይፈጸማል፣ በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ ያውቃሉ።”+ +10 እኔም እያየሁ ሳለ ከኪሩቦቹ ራስ በላይ ካለው ጠፈር በላይ እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ ነገር ተገለጠ፤ መልኩም ዙፋን ይመስል ነበር።+ +2 ከዚያም አምላክ በፍታ የለበሰውን ሰው+ “በኪሩቦቹ ሥር ወደሚገኙት የሚሽከረከሩ መንኮራኩሮች*+ መሃል ግባና በኪሩቦቹ መካከል ካለው ፍም+ በእጆችህ ዘግነህ በከተማዋ ላይ በትነው”+ አለው። እሱም እኔ እያየሁት ገባ። +3 ሰውየው ወደዚያ ሲገባ ኪሩቦቹ ከቤተ መቅደሱ በስተ ቀኝ ቆመው ነበር፤ ደመናውም የውስጠኛውን ግቢ ሞላው። +4 የይሖዋም ክብር+ ከኪሩቦቹ ላይ ተነስቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ሄደ፤ ቤተ መቅደሱም ቀስ በቀስ በደመናው ተሞላ፤+ ግቢውም በይሖዋ ክብር ብርሃን ተሞላ። +5 የኪሩቦቹም ክንፎች ድምፅ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሲናገር እንደሚሰማው ድምፅ እስከ ውጨኛው ግቢ ድረስ ይሰማ ነበር።+ +6 ከዚያም አምላክ፣ በፍታ የለበሰውን ሰው “ከሚሽከረከሩት መንኮራኩሮች መካከልና ከኪሩቦቹ መሃል እሳት ውሰድ” ብሎ አዘዘው፤ ሰውየውም ገብቶ ከመንኮራኩሩ አጠገብ ቆመ። +7 ከዚያም አንዱ ኪሩብ፣ በኪሩቦቹ መካከል ወዳለው እሳት+ እጁን ዘረጋ። የተወሰነ እሳት ወስዶ በፍታ በለበሰው ሰው+ እጆች ላይ አደረገ፤ እሱም እሳቱን ይዞ ወጣ። +8 ኪሩቦቹ ከክንፎቻቸው ሥር የሰው እጅ የሚመስል ነገር ነበራቸው።+ +9 እኔም እያየሁ ሳለ በኪሩቦቹ አጠገብ አራት መንኮራኩሮች ተመለከትኩ፤ በእያንዳንዱ ኪሩብ አጠገብ አንድ መንኮራኩር ነበር፤ መንኮራኩሮቹም እንደ ክርስቲሎቤ ድንጋይ የሚያብረቀርቅ መልክ ነበራቸው።+ +10 የአራቱም መልክ ይመሳሰል ነበር፤ በአንድ መንኮራኩር ውስጥ በጎን በኩል ሌላ መንኮራኩር የተሰካ ይመስል ነበር። +11 በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መዞር ሳያስፈልጋቸው በአራቱም አቅጣጫ መሄድ ይችሉ ነበር፤ ምክንያቱም መዞር ሳያስፈልጋቸው ፊታቸው ወደሚያይበት* አቅጣጫ ሁሉ ይሄዱ ነበር። +12 ሰውነታቸው ሁሉ፣ ጀርባቸው፣ እጃቸው፣ ክንፋቸው እንዲሁም መንኮራኩሮቹ ይኸውም የአራቱም መንኮራኩሮች ሁለመና በዓይን የተሞላ ነበር።+ +13 አንድ ድምፅ መንኮራኩሮቹን “ተሽከርካሪ መንኮራኩሮች!” ብሎ ሲጠራቸው ሰማሁ። +14 እያንዳንዳቸው* አራት አራት ፊት ነበራቸው። የመጀመሪያው ፊት የኪሩብ ፊት፣ ሁለተኛው ፊት የሰው ፊት፣ ሦስተኛውም የአንበሳ ፊት፣ አራተኛው ደግሞ የንስር ፊት ነበር።+ +15 ኪሩቦቹም ወደ ላይ ተነሱ፤ በኬባር ወንዝ+ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት እነዚሁ ነበሩ፤* +16 ኪሩቦቹ ሲንቀሳቀሱ፣ መንኮራኩሮቹም አጠገባቸው ሆነው ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ኪሩቦቹ ከምድር በላይ ከፍ ከፍ ለማለት ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ሲዘረጉ መንኮራኩሮቹ ከአጠገባቸው አይለዩም ወይም አይርቁም ነበር።+ +17 እነሱ ሲቆሙ፣ መንኮራኩሮቹም ይቆማሉ፤ እነሱ ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም አብረዋቸው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ* በውስጣቸው ነበርና። +18 ከዚያም የይሖዋ ክብር+ ከቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ተነስቶ በመሄድ ከኪሩቦቹ በላይ ቆመ።+ +19 ኪሩቦቹ እኔ እያየኋቸው ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ከምድር ተነሱ። እነሱ ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም አብረዋቸው ነበሩ። በይሖዋ ቤት በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በር መግቢያም ላይ ቆሙ፤ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ነበር።+ +20 እነዚህ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት ናቸው፤+ በመሆኑም ኪሩቦች መሆናቸውን አወቅኩ። +21 አራቱም፣ አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው፤ ከክንፎቻቸውም ሥር የሰው እጆች የሚመስሉ ነገሮች ነበሯቸው።+ +22 የፊታቸውም መልክ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ እንዳየኋቸው ፊቶች ነበር።+ እያንዳንዳቸው ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+ +14 ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ።+ +3 “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን* ለመከተል ቆርጠው ተነስተዋል፤ ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጠዋል። ታዲያ እኔን እንዲጠይቁኝ ልፈቅድላቸው ይገባል?+ +4 እንግዲህ ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንድ እስራኤላዊ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ አንድን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ እኔ ይሖዋ፣ እንደ አስጸያፊ ጣዖቶቹ ብዛት በተገቢው መንገድ እ +5 የእስራኤልን ቤት ሰዎች ልብ አሸብራለሁና፤* ምክንያቱም ሁሉም ከእኔ ርቀዋል፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ተከትለዋል።”’+ +6 “ስለሆነም የእስራኤልን ቤት ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ተመለሱ፤ አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻችሁ ራቁ፤ ቀፋፊ ከሆኑት ልማዶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ።+ +7 ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ከእኔ በመለየት አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ የእኔን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ+ እኔ ይሖዋ፣ አዎ እኔ ራሴ እመልስለታለሁ። +8 ፊቴን ወደዚህ ሰው አዞራለሁ፤ መቀጣጫና መተረቻ አደርገዋለሁ፤ ከሕዝቤም መካከል አስወግደዋለሁ፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’ +9 “‘ይሁንና ነቢዩ ቢሞኝና ምላሽ ቢሰጥ፣ ያንን ነቢይ ያሞኘሁት እኔ ይሖዋ ነኝ።+ ከዚያም እጄን በእሱ ላይ ዘርግ��� ከሕዝቤ ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ። +10 የፈጸሙት በደል የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይሸከማሉ፤ ነቢዩን ሊጠይቅ የመጣው ሰው በደል ነቢዩ ከፈጸመው በደል ጋር አንድ ዓይነት ይሆናል፤ +11 ይህም የሚሆነው የእስራኤል ቤት ሰዎች ከእኔ ርቀው እንዳይባዝኑና በሚፈጽሙት በደል ሁሉ ራሳቸውን ከማርከስ እንዲቆጠቡ ነው። እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +12 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +13 “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ አገር ታማኝ ሳይሆን ቀርቶ በእኔ ላይ ኃጢአት ቢፈጽም እጄን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ የምግብ አቅርቦቱም እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤*+ ረሃብም እሰድበታለሁ+ እንዲሁም ሰውንም ሆነ እንስሳን ከዚያ አጠፋለሁ።”+ +14 “‘እነዚህ ሦስት ሰዎች ይኸውም ኖኅ፣+ ዳንኤልና+ ኢዮብ+ በዚያ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን* ብቻ ነው’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +15 “‘ወይም አደገኛ የዱር አራዊትን ወደዚያ አገር ብሰድ፣ በአገሩ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ቢፈጁና* አገሩ በዱር አራዊቱ የተነሳ ማንም ሰው የማያልፍበት ወና እንዲሆን ቢያደርጉ፣+ +16 በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው፤ አገሩም ባድማ ይሆናል።’” +17 “‘ወይም ደግሞ በአገሩ ላይ ሰይፍ ባመጣና+ “በአገሩ መካከል ሰይፍ ይለፍ” ብል፣ በአገሩም ላይ ያለውን ሰውም ሆነ እንስሳ ባጠፋ፣+ +18 እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው።’” +19 “‘ወይም በአገሩ ላይ ቸነፈር ብሰድና+ ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት ደም በማፍሰስ በአገሩ ላይ ቁጣዬን ባወርድ፣ +20 ኖኅ፣+ ዳንኤልና+ ኢዮብ+ በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን* ብቻ ነው።’”+ +21 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት+ በኢየሩሳሌም ላይ አራት ቅጣቶቼን*+ ይኸውም ሰይፍን፣ ረሃብን፣ አደገኛ የዱር አራዊትንና ቸነፈርን በምሰድበት ጊዜ+ ምንኛ የከፋ ይሆን! +22 ሆኖም በዚያ የሚቀሩ አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በሕይወት ይተርፋሉ፤ ደግሞም ከዚያ ይወሰዳሉ።+ ወደ እናንተ ይመጣሉ፤ መንገዳቸውንና ሥራቸውንም በምታዩበት ጊዜ በኢየሩሳሌም ላይ ካመጣሁት ጥፋት፣ በእሷም ላይ ካደረስኩት ነገር ሁሉ በእርግጥ ትጽናናላችሁ።’” +23 “‘መንገዳቸውንና ሥራቸውን ስታዩ ያጽናኗችኋል፤ በእሷም ላይ ላደርገው የሚገባኝን ነገር ያደረግኩት ያለምክንያት አለመሆኑን ትገነዘባላችሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +43 ከዚያም ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው በር ወሰደኝ።+ +2 በዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤+ ድምፁም እንደሚጎርፍ ውኃ ድምፅ ነበር፤+ ከክብሩም የተነሳ ምድር አበራች።+ +3 ያየሁት ነገር ከተማዋን ለማጥፋት* በመጣሁ* ጊዜ ያየሁትን ራእይ ይመስል ነበር፤ ደግሞም በኬባር ወንዝ+ አቅራቢያ አይቼው ከነበረው ነገር ጋር ይመሳሰል ነበር፤ እኔም መሬት ላይ በግንባሬ ተደፋሁ። +4 ከዚያም የይሖዋ ክብር ከምሥራቅ ትይዩ በሆነው በር በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ* ገባ።+ +5 መንፈስም አንስቶ ወደ ውስጠኛው ግቢ አመጣኝ፤ እኔም ቤተ መቅደሱ በይሖዋ ክብር ተሞልቶ አየሁ።+ +6 ከዚያም አንድ ሰው ከቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያናግረኝ ሰማሁ፤ ሰውየውም መጥቶ አጠገቤ ቆመ።+ +7 አምላክም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህ የዙፋኔ መቀመጫ፣+ የእግሬ ማሳረፊያና+ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምኖርበት ስፍራ ነው።+ የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ እነሱም ሆኑ ንጉሦቻቸው በሚፈጽሙት መንፈሳዊ ምንዝርና በሞቱት ንጉሦቻቸው* ሬሳ ከእንግዲህ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።+ +8 በእኔና በእነሱ መካከል ግንቡ ብቻ ሲቀር፣ ደፋቸውን ከቤቴ ደፍ አጠገብ፣ መቃናቸውንም ከቤቴ መቃን አጠገብ በማድረግ+ በሠሯቸው አስጸያፊ ነገሮች ቅዱስ ስሜን አርክሰዋል፤ ስለዚህ በቁጣዬ አጠፋኋቸው።+ +9 ከእንግዲህ የሚፈጽሙትን መንፈሳዊ ምንዝር ያስወግዱ፤ የንጉሦቻቸውንም ሬሳ ከእኔ ያርቁ፤ እኔም በመካከላቸው ለዘላለም እኖራለሁ።+ +10 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ከሠሩት በደል የተነሳ ኀፍረት እንዲሰማቸው+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ስለ ቤተ መቅደሱ ግለጽላቸው፤+ ንድፉንም ያጥኑ።* +11 በሠሩት ነገር ሁሉ ኀፍረት ከተሰማቸው የቤተ መቅደሱን ንድፍ፣ አቀማመጡን፣ መውጫዎቹንና መግቢያዎቹን አሳውቃቸው።+ አጠቃላይ ንድፉንና ደንቦቹን፣ ንድፉንና ሕጎቹን አሳያቸው፤ ደግሞም እነሱ እያዩ ጻፋቸው፤ ይህን የምታደርገው አጠቃላይ ንድፉንና ደንቦቹን አስተውለው በተግባር እንዲያውሉ ነው።+ +12 የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው። በተራራው አናት ዙሪያ ያለው ቦታ ሁሉ እጅግ ቅዱስ ነው።+ እነሆ፣ የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው። +13 “የመሠዊያው ልክ በክንድ* ሲለካ መጠኑ ይህ ነው፤+ እያንዳንዱ ክንድ አንድ ጋት ተጨምሮበት ነበር። የመሠዊያው መሠረት አንድ ክንድ ነው፤ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። በጠርዙ ዙሪያ፣ ወርዱ አንድ ስንዝር* የሆነ ክፈፍ አለው። ይህ የመሠዊያው መሠረት ነው። +14 መሬት ላይ ካረፈው መሠረት አንስቶ በዙሪያው እስካለው የታችኛው እርከን ድረስ ሁለት ክንድ ሲሆን ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ነው። በዙሪያው ካለው ከትንሹ እርከን እስከ ትልቁ እርከን ድረስ አራት ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ነው። +15 የመሠዊያው ምድጃ ከፍታ አራት ክንድ ሲሆን ከምድጃው በላይ ወጣ ወጣ ያሉ አራት ቀንዶች አሉ።+ +16 የመሠዊያው ምድጃ አራት ማዕዘን ሲሆን ርዝመቱ 12 ክንድ፣ ወርዱም 12 ክንድ ነው።+ +17 በዙሪያው ያለው እርከን አራቱም ጎኖች ርዝመታቸው 14 ክንድ፣ ወርዳቸውም 14 ክንድ ነው፤ በዙሪያውም ያለው ክፈፍ ግማሽ ክንድ ሲሆን መሠረቱም በሁሉም ጎኖች አንድ ክንድ ነው። “ደረጃዎቹም ከምሥራቅ ትይዩ ነበሩ።” +18 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመሠዊያው ላይ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ እንዲቀርብና በላዩ ላይ ደም እንዲረጭበት፣ መሠዊያው ሲሠራ ሊከተሏቸው የሚገቡት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው።’+ +19 “‘እኔን ለማገልገል በፊቴ ለሚቀርቡት የሳዶቅ ዘር ለሆኑት ሌዋውያን ካህናት፣+ ከመንጋው መካከል ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ ወይፈን ትሰጣቸዋለህ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +20 ‘ከደሙ ጥቂት ወስደህ በመሠዊያው አራት ቀንዶች፣ በዙሪያው ባለው እርከን አራት ጎኖችና በዙሪያው ባለው ጠርዝ ላይ አድርግ፤ ይህን የምታደርገው መሠዊያውን ከኃጢአት ለማንጻትና ለመሠዊያው ማስተሰረያ ለማቅረብ ነው።+ +21 ከዚያም ከመቅደሱ ውጭ፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተመደበው ቦታ ታቃጥለው ዘንድ የኃጢአት መባ የሆነውን ወይፈን ውሰድ።+ +22 በሁለተኛው ቀን የኃጢአት መባ የሚሆን እንከን የሌለበት ተባዕት ፍየል ታቀርባለህ፤ እነሱም በወይፈኑ መሠዊያውን ከኃጢአት እንዳነጹት ሁሉ በዚህም መሠዊያውን ከኃጢአት ያነጹታል።’ +23 “‘መሠዊያውን ከኃጢአት ካነጻህ በኋላ ከከብቶቹ መካከል እንከን የሌለበት አንድ ወይፈንና ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበት አንድ አውራ በግ ታቀርባለህ። +24 ለይሖዋ ታቀርባቸዋለህ፤ ካህናቱም ጨው ከነሰነሱባቸው+ በኋላ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገው ያቀርቧቸዋል። +25 በየዕለቱ፣ ለሰባት ቀናት አንድ አውራ ፍየል የኃጢአት መባ አድርገህ ታቀርባለህ፤+ እንዲሁም ከከብቶቹ መካከል አንድ ወይፈንና ከመንጋው መካከል አንድ አውራ በግ ታቀርባለህ፤ የምታቀርባቸው እንስሳት እንከን የሌለባቸው* ይሁኑ። +26 ለሰባት ቀናት ለመሠዊያው ማስተሰረያ ያቀርባሉ፤ መሠዊያውንም ያነጹታል እንዲሁም ለአገልግሎት ያዘጋጁታል። +27 እነዚህ ቀናት ከተፈጸሙ በኋላ ከስምንተኛው ቀን+ አንስቶ ካህናቱ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባችሁንና* የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በመሠዊያው ላይ ያቀርባሉ፤ እኔም በእናንተ ደስ እሰኛለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +9 ከዚያም በጆሮዬ እየሰማሁ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከተማዋን የሚቀጡት፣ እያንዳንዳቸው አጥፊ መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው እንዲመጡ ጥሯቸው!” አለ። +2 እኔም እያንዳንዳቸው በእጃቸው የማጥፊያ መሣሪያ የያዙ ስድስት ሰዎች በሰሜን ትይዩ ባለው በላይኛው በር+ በኩል ሲመጡ አየሁ፤ ከእነሱም ጋር በፍታ የለበሰ፣ በወገቡ ላይም የጸሐፊ የቀለም ቀንድ* የያዘ አንድ ሰው ነበር፤ እነሱም መጥተው ከመዳብ በተሠራው መሠዊያ+ አጠገብ ቆሙ። +3 ከዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር፣+ አርፎበት ከነበረው ከኪሩቦቹ በላይ ተነስቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ሄደ፤+ አምላክም በፍታ የለበሰውንና በወገቡ ላይ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራው። +4 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “በከተማዋ መካከል ይኸውም በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፤ በከተማዋ ውስጥ እየተፈጸሙ ባሉት አስጸያፊ ነገሮች+ ሁሉ እያዘኑና እየቃተቱ ባሉት ሰዎች+ ግንባር ላይም ምልክት አድርግ።” +5 ሌሎቹን ደግሞ እኔ እየሰማሁ እንዲህ አላቸው፦ “እሱን ተከትላችሁ በከተማዋ መካከል እለፉ፤ ሰዉንም ግደሉ። ዓይናችሁ አይዘን፤ ደግሞም አትራሩ።+ +6 ሽማግሌውን፣ ወጣቱን፣ ድንግሊቱን፣ ሕፃኑንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ።+ ምልክቱ ወዳለበት ወደ ማንኛውም ሰው ግን አትቅረቡ።+ ከመቅደሴም ጀምሩ።”+ ስለዚህ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት በነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።+ +7 ከዚያም “ቤተ መቅደሱን አርክሱ፤ ግቢዎቹንም ሬሳ በሬሳ አድርጓቸው።+ ሂዱ!” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የከተማዋን ሕዝብ ገደሉ። +8 እነሱ ሰዉን እየገደሉ ሳሉ ብቻዬን ቀረሁ፤ በግንባሬም ተደፍቼ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣህን በማፍሰስ የእስራኤልን ቀሪዎች ሁሉ ልታጠፋ ነው?” በማለት ጮኽኩ።+ +9 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት በደል እጅግ በጣም ታላቅ ነው።+ ምድሪቱ በደም ተጥለቅልቃለች፤+ ከተማዋም በክፋት ተሞልታለች።+ ‘ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል፤ ይሖዋም አያይም’ ይላሉና።+ +10 እኔ ግን ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም።+ የተከተሉት መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ።” +11 ከዚያም በፍታ የለበሰውና በወገቡ ላይ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው ተመልሶ መጥቶ “ልክ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ” አለ። +27 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጢሮስ ላይ ሙሾ አውርድ፤*+ +3 ጢሮስንም እንዲህ በላት፦‘አንቺ በባሕሩ መግቢያዎች ላይ የምትኖሪናበብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር የንግድ ልውውጥ የምታደርጊ፣ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጢሮስ ሆይ፣ አንቺ ራስሽ ‘ፍጹም ውብ ነኝ’ ብለሻል።+ + 4 ግዛትሽ በባሕሩ መካከል ነው፤የገነቡሽ ሰዎችም ውበትሽን ፍጹም አድርገ���ታል። + 5 ሳንቃዎችሽን ሁሉ ከሰኒር*+ በመጣ የጥድ እንጨት ሠሩ፤ለአንቺም የመርከብ ምሰሶ ለመሥራት ከሊባኖስ፣ አርዘ ሊባኖስ አመጡ። + 6 በባሳን የባሉጥ ዛፎች መቅዘፊያዎችሽን ሠሩ፤የፊተኛውን ክፍልሽንም ከኪቲም+ ደሴቶች በመጣ በዝሆን ጥርስ በተለበጠ የጥድ እንጨት ሠሩ። + 7 ከግብፅ የመጣው የተለያየ ቀለም ያለው በፍታ የመርከብ ሸራሽን ለመሥራት አገልግሏል፤የላይኛው መድረክ መሸፈኛዎችሽም ከኤሊሻ+ ደሴቶች በመጣ ሰማያዊ ክርና ሐምራዊ ሱፍ የተሠሩ ናቸው። + 8 ቀዛፊዎችሽ የሲዶና እና የአርዋድ+ ነዋሪዎች ነበሩ። ጢሮስ ሆይ፣ የገዛ ራስሽ ባለሙያዎች መርከበኞችሽ ነበሩ።+ + 9 ልምድ ያካበቱት* የጌባል+ ባለሙያዎች ስንጥቆችሽን ይደፍናሉ።+ በባሕር ላይ የሚጓዙ መርከቦችና ባሕረኞቻቸው ሁሉ ሸቀጣ ሸቀጦችን ለመገበያየት ወደ አንቺ ይመጡ ነበር። +10 የፋርስ፣ የሉድና የፑጥ+ ሰዎች ተዋጊዎች ሆነው በጦር ሠራዊትሽ ውስጥ ያገለግሉ ነበር። ጋሻቸውንና የራስ ቁራቸውን በአንቺ ውስጥ ሰቀሉ፤ ደግሞም ግርማ ሞገስ አጎናጸፉሽ። +11 በሠራዊትሽ ውስጥ ያሉት የአርዋድ ሰዎች በቅጥሮችሽ ላይ ዙሪያውን ቆመው ነበር፤ጀግኖችም በማማዎችሽ ላይ ነበሩ። ክብ የሆኑ ጋሻዎቻቸውን በቅጥሮችሽ ዙሪያ ሰቀሉ፤ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ። +12 “‘“ከተትረፈረፈው ውድ ሀብትሽ የተነሳ ተርሴስ+ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር።+ ሸቀጣ ሸቀጦችሽን በብር፣ በብረት፣ በቆርቆሮና በእርሳስ ይለውጡ ነበር።+ +13 ያዋን፣ ቱባልና+ መሼቅ+ ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በባሪያዎችና በመዳብ ዕቃዎች ይለውጡ ነበር።+ +14 የቶጋርማ+ ሰዎች ደግሞ ሸቀጦችሽን በጭነት ፈረሶች፣ በጦር ፈረሶችና በበቅሎዎች ይለውጡ ነበር። +15 የዴዳን+ ሰዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ በብዙ ደሴቶች ላይ ነጋዴዎች ቀጠርሽ፤ የዝሆን ጥርስና+ ዞጲ* በግብር መልክ ያመጡልሽ ነበር። +16 ከምታመርቻቸው ዕቃዎች ብዛት የተነሳ ኤዶም ከአንቺ ጋር ትነግድ ነበር። ሸቀጦችሽን በበሉር፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ የተለያዩ ቀለማት ባላቸው ጥልፎች፣ ጥራት ባለው ልብስ፣ በዛጎልና በሩቢ ይለውጡ ነበር። +17 “‘“ይሁዳና የእስራኤል ምድር ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በሚኒት+ ስንዴ፣ ምርጥ በሆኑ ምግቦች፣ በማር፣+ በዘይትና በበለሳን+ ይለውጡ ነበር።+ +18 “‘“ደማስቆ+ ከተትረፈረፈው ምርትሽና ከሀብትሽ የተነሳ ከአንቺ ጋር ትነግድ ነበር፤ የሄልቦን የወይን ጠጅና የዛሃር ሱፍ* ጨርቅ ትሸጥልሽ ነበር። +19 በዑዛል አቅራቢያ የሚገኙት ዌዳንና ያዋን ሸቀጦችሽን በሚተጣጠፍ ብረት፣ በብርጉድና* በጠጅ ሣር ይለውጡ ነበር። +20 ዴዳን፣+ በከብት ላይ ለመቀመጥ የሚያገለግል ግላስ* በማቅረብ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር። +21 የጠቦቶች፣ የአውራ በጎችና የፍየሎች+ ነጋዴ የሆኑ ዓረቦችንና የቄዳር+ አለቆችን ሁሉ ቀጠርሽ። +22 የሳባና የራአማ+ ነጋዴዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በሁሉም ዓይነት ምርጥ የሆኑ ሽቶዎች፣ የከበሩ ድንጋዮችና በወርቅ ይለውጡ ነበር።+ +23 ካራን፣+ ካኔህና ኤደን+ እንዲሁም የሳባ፣+ የአሹርና+ የኪልማድ ነጋዴዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር። +24 በገበያ ቦታሽ ያማሩ ልብሶችን፣ በሰማያዊ ጨርቅና የተለያዩ ቀለማት ባለው ጥልፍ የተሠራን ካባ እንዲሁም ብዙ ዓይነት ቀለም ያላቸውን ምንጣፎች ይነግዱ የነበረ ሲሆን ሁሉም በገመድ በጥብቅ የታሰሩ ነበሩ። +25 የተርሴስ መርከቦች+ ሸቀጦችሽን ያጓጉዙልሽ ነበር፤በመሆኑም በባሕሩ መካከል በሀብት ተሞልተሽና ጭነት በዝቶልሽ* ነበር። +26 ቀዛፊዎችሽ ወደ ታላቅ ባሕር አምጥተውሻል፤የምሥራቁ ነፋስ በተንጣለለው ባሕር መካከል ሰባብሮሻል። +27 ውድቀት በሚደርስብሽ ቀን ሀብትሽ፣ ሸቀጦችሽ፣ የምትነግጃቸው ዕቃዎች፣ ባሕረኞችሽ፣ መርከበኞችሽ፣ስንጥቆችሽን የሚደፍኑልሽ ሰዎች፣ ነጋዴዎችሽና+ ተዋጊዎችሽ ሁሉ+ይኸውም በአንቺ ውስጥ ያለው ሕዝብ* ሁሉበተንጣለለው ባሕር መካከል ይሰምጣል።+ +28 መርከበኞችሽ ሲጮኹ የባሕሩ ጠረፍ ይናወጣል። +29 ቀዛፊዎቹ፣ ባሕረኞቹና መርከበኞቹ ሁሉከመርከቦቻቸው ይወርዳሉ፤ መሬት ላይም ይቆማሉ። +30 በአንቺ የተነሳ በራሳቸው ላይ አቧራ እየነሰነሱና በአመድ ላይ እየተንከባለሉድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ምርር ብለውም ያለቅሳሉ።+ +31 በአንቺ የተነሳ ራሳቸውን ይላጫሉ፣ ማቅ ይለብሳሉእንዲሁም ዋይ ዋይ እያሉ አምርረው * ያለቅሳሉ። +32 ለአንቺም በሚያለቅሱበት ጊዜ ሙሾ ያወርዳሉ፤ የሐዘን እንጉርጉሮም ያንጎራጉራሉ፦ ‘በባሕር መካከል ጸጥ እንዳለችው እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው?+ +33 ሸቀጥሽ ከተንጣለለው ባሕር በመጣ ጊዜ ብዙ ሕዝቦችን አጥግበሻል።+ የተትረፈረፈው ሀብትሽና ሸቀጣ ሸቀጥሽ የምድርን ነገሥታት አበልጽጓል።+ +34 አሁን ግን በተንጣለለው ባሕር ላይ ተሰባብረሽ ጥልቁ ውኃ ውስጥ ሰምጠሻል፤+ሸቀጥሽና ሕዝብሽ ሁሉ አብረውሽ ሰምጠዋል።+ +35 የደሴቶቹም ነዋሪዎች ሁሉ በመገረም አተኩረው ይመለከቱሻል፤+ነገሥታታቸውም በታላቅ ፍርሃት ይርዳሉ፤+ ፊታቸውም ይለዋወጣል። +36 በብሔራት መካከል ያሉ ነጋዴዎች በአንቺ ላይ ከደረሰው ነገር የተነሳ ያፏጫሉ። ፍጻሜሽ ድንገተኛና አስከፊ ይሆናል፤ደግሞም ለዘላለም ከሕልውና ውጭ ትሆኛለሽ።’”’”+ +47 ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ+ መልሶ አመጣኝ፤ በዚያም ከቤተ መቅደሱ ደፍ ሥር ወደ ምሥራቅ የሚፈስ ውኃ ተመለከትኩ፤+ የቤተ መቅደሱ ፊት ከምሥራቅ ትይዩ ነበር። ውኃው ከቤተ መቅደሱ በስተ ቀኝ ከሥር ወጥቶ ከመሠዊያው በስተ ደቡብ ይወርድ ነበር። +2 ከዚያም ወደ ሰሜን በር+ በሚወስደው መንገድ በኩል አምጥቶ ወደ ውጭ ካወጣኝ በኋላ ከምሥራቅ ትይዩ ወዳለው የውጨኛው በር+ አዙሮ አመጣኝ፤ እኔም በስተ ቀኝ በኩል ቀስ እያለ የሚፈስ ውኃ አየሁ። +"3 ሰውየው መለኪያ ገመድ በእጁ ይዞ+ ወደ ምሥራቅ በመሄድ 1,000 ክንድ* ለካ፤ ከዚያም በውኃው መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃው እስከ ቁርጭምጭሚት ይደርስ ነበር። " +"4 ከዚያም 1,000 ክንድ ለካ፤ በውኃውም መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃውም እስከ ጉልበት ደረሰ። ደግሞም 1,000 ክንድ ለካ፤ በውኃውም መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ። " +"5 እንደገናም 1,000 ክንድ በለካ ጊዜ ውኃው ልሻገረው የማልችል ወንዝ ሆነ፤ እጅግ ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ በዋና ካልሆነ በስተቀር በእግር ሊሻገሩት የማይቻል ወንዝ ሆኖ ነበር። " +6 እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ?” ሲል ጠየቀኝ። ከዚያም መልሶ ወደ ጅረቱ ዳርቻ ወሰደኝ። +7 በተመለስኩ ጊዜ በጅረቱ ዳርቻ፣ በግራና በቀኝ በጣም ብዙ ዛፎች አየሁ።+ +8 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ውኃ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ምድር ይፈስሳል፤ አረባን*+ አቋርጦም ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም* ይገባል። ወደ ባሕሩ በሚገባበት ጊዜ+ በዚያ ያለው ውኃ ይፈወሳል። +9 ውኃዎቹ* በሚፈስሱበት ቦታ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕያዋን ፍጥረታት* በሕይወት መኖር ይችላሉ። ይህ ውኃ ወደዚያ ስለሚፈስ በዚያ እጅግ ብዙ ዓሣዎች ይኖራሉ። የባሕሩ ውኃ ይፈወሳል፤ ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል። +10 “ከኤንገዲ+ እስከ ኤንዔግላይም ድረስ ዓሣ አጥማጆች በዳርቻው ይቆማሉ፤ በዚያም መረባቸውን የሚያሰጡበት ቦታ ይኖራል። በታላቁ ባሕር*+ እንዳሉት ዓሣዎች በዚያም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ብዙ ዓይነት ዓሣዎች ይኖራሉ። +11 “ረግ���ጋማ የሆኑና ውኃ ያቆሩ ቦታዎች ይኖሩታል፤ እነዚህ ቦታዎች አይፈወሱም። ጨዋማ እንደሆኑ ይቀራሉ።+ +12 “በወንዙ ዳርና ዳር ለመብል የሚሆኑ ብዙ ዓይነት ዛፎች ይበቅላሉ። ቅጠላቸው አይጠወልግም፤ ፍሬ ማፍራትም አያቆሙም። ከመቅደሱ የሚወጣውን ውኃ+ ስለሚጠጡ በየወሩ አዲስ ፍሬ ይሰጣሉ። ፍሬያቸው ለመብል፣ ቅጠላቸውም ለመድኃኒት ይሆናል።”+ +13 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ክልል ይህች ናት፤ ዮሴፍ ሁለት ድርሻ ይኖረዋል።+ +14 እናንተ ትወርሷታላችሁ፤ እኩል ድርሻም ታገኛላችሁ።* ለአባቶቻችሁ ይህችን ምድር እንደምሰጣቸው ምዬላቸው ነበር፤+ አሁንም ይህች ምድር ርስት ሆና ተሰጥታችኋለች።* +15 “በስተ ሰሜን በኩል የምድሪቱ ወሰን ይህ ነው፦ ከታላቁ ባሕር ተነስቶ ወደ ሄትሎን+ በሚወስደው መንገድ በኩል እስከ ጼዳድ+ ይደርሳል፤ +16 ከዚያም እስከ ሃማት፣+ እስከ ቤሮታ+ እንዲሁም በደማስቆ ክልልና በሃማት ክልል መካከል እስካለው እስከ ሲብራይም ብሎም በሃውራን+ ወሰን እስከሚገኘው እስከ ሃጸርሃቲኮን ይዘልቃል። +17 ስለዚህ ወሰኑ ከባሕሩ በመነሳት በስተ ሰሜን በደማስቆ ድንበርና በሃማት+ ድንበር በኩል እስከ ሃጻርኤናን+ ድረስ ይዘልቃል። በሰሜን በኩል ወሰኑ ይህ ነው። +18 “በምሥራቅ በኩል ወሰኑ ከሃውራን እስከ ደማስቆ እንዲሁም በዮርዳኖስ አጠገብ ከጊልያድ+ እስከ እስራኤል ምድር ይዘልቃል። ከወሰኑ አንስቶ እስከ ምሥራቁ ባሕር* ድረስ ትለካላችሁ። በምሥራቅ በኩል ወሰኑ ይህ ነው። +19 “በደቡብ በኩል ያለው ወሰን* ከትዕማር ተነስቶ እስከ መሪባትቃዴስ+ ውኃዎች፣ ከዚያም እስከ ደረቁ ወንዝና* እስከ ታላቁ ባሕር+ ይደርሳል። በደቡብ በኩል ወሰኑ* ይህ ነው። +20 “በምዕራብ በኩል ታላቁ ባሕር የሚገኝ ሲሆን ይህም ከወሰኑ አንስቶ ከሌቦሃማት*+ ትይዩ እስካለው ቦታ ድረስ ይዘልቃል። በምዕራብ በኩል ወሰኑ ይህ ነው።” +21 “ይህችን ምድር ለእናንተ ይኸውም ለ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ታከፋፍላላችሁ። +22 ምድሪቱን ለእናንተ እንዲሁም በመካከላችሁ በመኖር ልጆች ለወለዱት፣ አብረዋችሁ ለሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች ርስት አድርጋችሁ አከፋፍሉ፤ እነሱም የአገሪቱ ተወላጆች እንደሆኑት እስራኤላውያን ይሆናሉ። እንደ እስራኤል ነገዶች ከእናንተ ጋር ርስት ያገኛሉ። +23 ከባዕድ አገር ለመጣው ሰው በሚኖርበት ነገድ ክልል ውስጥ ርስት ልትሰጡት ይገባል” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +13 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤+ የገዛ ራሳቸውን ትንቢት ፈጥረው የሚናገሩትንም*+ እንዲህ በላቸው፦ ‘የይሖዋን ቃል ስሙ። +3 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ምንም ያዩት ነገር ሳይኖር የገዛ መንፈሳቸውን ለሚከተሉት ሞኝ ነቢያት ወዮላቸው!+ +4 እስራኤል ሆይ፣ ነቢያትህ በፍርስራሽ መካከል እንደሚኖሩ ቀበሮዎች ሆነዋል። +5 እስራኤል፣ በይሖዋ ቀን በሚኖረው ውጊያ+ ጸንቶ ይቆም ዘንድ በድንጋይ ቅጥሩ ላይ የሚገኙትን የፈረሱ ቦታዎች ለእስራኤል ቤት መልሳችሁ ለመገንባት ወደዚያ አትሄዱም።”+ +6 “ይሖዋ ሳይልካቸው ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል’ የሚሉ ሰዎች ያዩአቸው ራእዮች ውሸት ናቸው፤ ትንቢታቸውም ሐሰት ነው፤ ይሁንና ቃላቸው እንዲፈጸም ይጠብቃሉ።+ +7 እኔ የተናገርኩት ነገር ሳይኖር ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል’ ስትሉ ያያችሁት ራእይ ውሸት፣ የተናገራችሁትም ትንቢት ሐሰት መሆኑ አይደለም?”’ +8 “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ውሸት ስለተናገራችሁና ያያችኋቸው ራእዮች ሐሰት ስለሆኑ እኔ በእናንተ ላይ ተነስቻለሁ’ ይላ�� ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”+ +9 እጄ የውሸት ራእዮች በሚያዩና የሐሰት ትንቢት በሚናገሩ ነቢያት ላይ ተነስታለች።+ ሚስጥሬን ከማካፍላቸው ሰዎች መካከል አይሆኑም፤ በእስራኤል ቤት መዝገብም ላይ አይጻፉም፤ ወደ እስራኤልም ምድር አይመለሱም፤ እናንተም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ +10 ይህ ሁሉ የሚሆነው ሰላም ሳይኖር “ሰላም አለ!” እያሉ ሕዝቤን በማሳታቸው ነው።+ ሕዝቡ ጥንካሬ የሌለው ግድግዳ ሲሠራ እነሱ በኖራ ይለስኑታል።’*+ +11 “በኖራ የሚለስኑትን ሰዎች ’ግድግዳው ይፈርሳል’ በላቸው። ከባድ ዶፍ ይጥላል፤ የበረዶ ድንጋይ ይወርዳል፤ ኃይለኛ አውሎ ነፋስም ግድግዳውን ያፈርሰዋል።+ +12 ግድግዳው በሚወድቅበት ጊዜም ‘የለሰናችሁት ልስን የት አለ?’ ብለው ይጠይቋችኋል።+ +13 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በታላቅ ቁጣዬ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ እንዲነሳ አደርጋለሁ፤ በቁጣዬም ከባድ ዶፍ አዘንባለሁ፤ ደግሞም ጥፋት በሚያስከትል ታላቅ ንዴት የበረዶ ድንጋይ አወርዳለሁ። +14 እናንተ በኖራ የለሰናችሁትን ግድግዳ አፍርሼ ከመሬት እደባልቀዋለሁ፤ መሠረቱም ይታያል። ከተማዋ ስትወድቅ በውስጧ ትጠፋላችሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’ +15 “‘ቁጣዬን ሁሉ በግድግዳውና ግድግዳውን በኖራ በለሰኑት ሰዎች ላይ በማወርድበት ጊዜ እንዲህ እላችኋለሁ፦ “ግድግዳው ፈርሷል፤ በኖራ የለሰኑት ሰዎችም የሉም።+ +16 ለኢየሩሳሌም ትንቢት የሚናገሩትና ሰላም ሳይኖር የሰላም ራእዮች የሚያዩላት የእስራኤል ነቢያት ጠፍተዋል”’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +17 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ የገዛ ራሳቸውን ትንቢት ፈጥረው ወደሚናገሩት የሕዝብህ ሴቶች ልጆች ፊትህን አዙር፤ በእነሱም ላይ ትንቢት ተናገር። +18 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሰዎችን ሕይወት* ለማደን፣ በክንድ* ሁሉ ላይ የሚታሰር ቀጭን ጨርቅ ለሚሰፉና ለሰው እንደየቁመቱ የራስ መሸፈኛ ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤን ሕይወት* እያደናችሁ የራሳችሁን ሕይወት* ለማዳን ትጥራላችሁ? +19 የእናንተን ውሸት ለሚያዳምጠው ሕዝቤ ውሸት እየተናገራችሁ+ መሞት የማይገባቸውን ሰዎች* በመግደልና መኖር የማይገባቸውን ሰዎች* በሕይወት በማቆየት፣ ለጥቂት እፍኝ ገብስና ለቁርስራሽ ዳቦ ብላችሁ+ በሕዝቤ መካከል ታረክሱኛላችሁ?”’ +20 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ ሴቶች፣ እነሆ ሰዎችን* እንደ ወፎች ለማደን በምትጠቀሙበት ጨርቅ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤ ከክንዳችሁም ላይ እቀደዋለሁ፤ እንደ ወፎች ያደናችኋቸውንም ሰዎች ነፃ አወጣለሁ። +21 የራስ መሸፈኛችሁን እቀዳለሁ፤ ሕዝቤንም ከእጃችሁ እታደጋለሁ፤ ከእንግዲህ አድናችሁ አትይዟቸውም፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ +22 እኔ እንዲያዝን* ያላደረግኩትን ጻድቅ ሰው ሐሰት በመናገር+ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጋችኋልና፤ ደግሞም ክፉው ሰው ከክፋት መንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዳይኖር+ እጁን አበርትታችኋል።+ +23 ስለዚህ እናንተ ሴቶች፣ ከእንግዲህ የውሸት ራእዮች አታዩም፤ ሟርትም አታሟርቱም፤+ ሕዝቤንም ከእጃችሁ እታደጋለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’” +5 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ እንደ ፀጉር አስተካካይ ምላጭ የምትጠቀምበት ስለታም ሰይፍ ውሰድ። የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ፤ ከዚያም ሚዛን ወስደህ ፀጉሩን መዝነውና ከፋፍለው። +2 የከበባው ጊዜ ሲፈጸም+ አንድ ሦስተኛውን በከተማዋ ውስጥ በእሳት ታቃጥለዋለህ። ከዚያም ሌላ አንድ ሦስተኛ ወስደህ በከተማዋ ዙሪያ በሰይፍ ትመታዋለህ፤+ የመጨረሻውንም አንድ ሦስተኛ ለነፋስ ትበትነዋለህ፤ እ���ም እነሱን ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+ +3 “ደግሞም ከፀጉሮቹ ላይ ጥቂት ወስደህ በልብስህ እጥፋት* ቋጥራቸው። +4 የተወሰነውን ደግሞ ወስደህ እሳት ውስጥ ጨምረው፤ ሙሉ በሙሉም በእሳት አቃጥለው። ይህ እሳት ወጥቶ በእስራኤል ቤት ሁሉ ይሰራጫል።+ +5 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህች ኢየሩሳሌም ናት። አገሮችን በዙሪያዋ አድርጌ፣ በብሔራት መካከል አስቀምጫታለሁ። +6 እሷ ግን ከብሔራትና በዙሪያዋ ካሉ አገሮች ሁሉ የባሰ ክፋት በመሥራት በድንጋጌዎቼና ባወጣኋቸው ደንቦች ላይ ዓምፃለች።+ ሕዝቡ ድንጋጌዎቼን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጓልና፤ ደንቦቼንም አክብሮ አልተመላለሰም።’ +7 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዙሪያችሁ ካሉት ብሔራት ይበልጥ አስቸጋሪ በመሆናችሁ፣ ደንቦቼን አክብራችሁ ባለመመላለሳችሁ ወይም ድንጋጌዎቼን ባለመጠበቃችሁ፣ ይልቁንም በዙሪያችሁ ያሉትን ብሔራት ድንጋጌዎች በመከተላችሁ፣+ +8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንቺ ከተማ ሆይ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤+ ደግሞም እኔ ራሴ በብሔራት ፊት በመካከልሽ ፍርዴን አስፈጽማለሁ።+ +9 በአስጸያፊ ድርጊቶችሽ ሁሉ የተነሳ ከዚህ በፊት ፈጽሞ ያላደረግኩትን፣ ከዚህም በኋላ የማልደግመውን በአንቺ ላይ አደርጋለሁ።+ +10 “‘“ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፤+ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ በመካከልሽ ፍርዴን አስፈጽማለሁ፤ ከአንቺ የቀሩትንም በሙሉ በየአቅጣጫው* እበትናቸዋለሁ።”’+ +11 “‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በአስጸያፊ ጣዖቶችሽ ሁሉና ጸያፍ በሆኑ ድርጊቶችሽ ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፣+ እኔ ራሴ እተውሻለሁ፤* ዓይኔ አያዝንም ደግሞም አልራራም።+ +12 ከአንቺም አንድ ሦስተኛው በቸነፈር* ይሞታል ወይም በመካከልሽ በረሃብ ያልቃል። ሌላ አንድ ሦስተኛ ደግሞ በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል።+ የመጨረሻውን አንድ ሦስተኛ ደግሞ በየአቅጣጫው* እበትነዋለሁ፤ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+ +13 ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፤ በእነሱም ላይ የነደደው ቁጣዬ ይበርዳል፤ እኔም እረካለሁ።+ በእነሱም ላይ ቁጣዬን ፈጽሜ ባወረድኩ ጊዜ፣ እኔ ብቻ መመለክ የምፈልገው፣+ እኔ ይሖዋ ይህን እንደተናገርኩ ያውቃሉ። +14 “‘በዙሪያሽ ባሉ ብሔራት መካከል እንዲሁም በአጠገብሽ በሚያልፉ ሁሉ ፊት ባድማና መሳለቂያ አደርግሻለሁ።+ +15 በቁጣ፣ በንዴትና በኃይለኛ ቅጣት የፍርድ እርምጃ ስወስድብሽ በዙሪያሽ ባሉ ብሔራት ዘንድ መሳለቂያና መዘባበቻ+ ደግሞም የማስጠንቀቂያ ምሳሌና ማስፈራሪያ ትሆኛለሽ። እኔ ይሖዋ ይህን ተናግሬአለሁ። +16 “‘እነሱን ለማጥፋት ገዳይ የሆኑ የረሃብ ፍላጻዎችን እሰድባቸዋለሁ። የምሰዳቸው የረሃብ ፍላጻዎች ያጠፏችኋል።+ የምግብ አቅርቦታችሁ እንዲቋረጥ በማድረግ* ረሃቡን አባብሳለሁ።+ +17 በእናንተ ላይ ረሃብንና አደገኛ የዱር አራዊትን እሰዳለሁ፤+ እነሱም የወላድ መሃን ያደርጓችኋል። ቸነፈርና ደም መፋሰስ ያጥለቀልቋችኋል፤ ሰይፍም አመጣባችኋለሁ።+ እኔ ይሖዋ ይህን ተናግሬአለሁ።’” +21 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አዙረህ ቅዱስ በሆኑት ስፍራዎች ላይ አውጅ፤ በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር። +3 ለእስራኤል ምድር እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ሰይፌንም ከሰገባው መዝዤ+ ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ከአንቺ አስወግዳለሁ። +4 ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ከአንቺ ስለማስወግድ ሰይፌ ከደቡብ እስከ ሰሜን ድረስ በሥጋ ለባሽ* ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል። +5 ሰዎች ሁሉ ሰይፌን ��ሰገባው የመዘዝኩት እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሆንኩ ያውቃሉ። ዳግመኛ ወደ ሰገባው አይመለስም።”’+ +6 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ እየተንቀጠቀጥክ* አቃስት፤ አዎ፣ በፊታቸው በምሬት አቃስት።+ +7 ‘የምታቃስተው ለምንድን ነው?’ ቢሉህ ‘ከሰማሁት ወሬ የተነሳ ነው’ ትላለህ። በእርግጥ ይመጣልና፤ ልብም ሁሉ በፍርሃት ይቀልጣል፤ እጅ ሁሉ ይዝላል፤ መንፈስ ሁሉ ያዝናል፤ ጉልበትም ሁሉ በውኃ ይርሳል።*+ ‘እነሆ፣ በእርግጥ ይመጣል! ደግሞም ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +8 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +9 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ሰይፍ! ሰይፍ+ ተስሏል፤ ደግሞም ተወልውሏል። +10 የተሳለው ታላቅ እልቂት ለማስከተል ነው፤ የተወለወለውም እንደ መብረቅ እንዲያበራ ነው’ በል።”’” “ታዲያ ደስ ሊለን አይገባም?” “‘ማንኛውንም ዛፍ እንደሚንቅ* ሁሉ የገዛ ልጄን በትረ መንግሥት+ ይንቃል? +11 “‘እንዲወለወልና በእጅ እንዲያዝ ተሰጥቷል። ገዳዩ በእጁ እንዲይዘው ይህ ሰይፍ ተስሏል፤ ደግሞም ተወልውሏል።+ +12 “‘የሰው ልጅ ሆይ፣ ሰይፍ በሕዝቤ ላይ ስለመጣ ጩኽ፤ ደግሞም ዋይ ዋይ በል፤+ በእስራኤል አለቆች ሁሉ ላይ ተነስቷል።+ እነዚህ ሰዎች ከሕዝቤ ጋር በአንድ ላይ የሰይፍ ሰለባ ይሆናሉ። ስለዚህ ጭንህን በሐዘን ምታ። +13 ሰይፉ ተፈትሿልና፤+ ደግሞስ በትረ መንግሥቱን ከናቀው ምን ይሆናል? ከሕልውና ውጭ ይሆናል’*+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +14 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ በእጅህም አጨብጭብ፤ ደግሞም ‘ሰይፍ!’ የሚለውን ቃል ሦስት ጊዜ ደጋግመህ ተናገር። ሰለባዎቹን የሚገድልና ታላቅ እልቂት የሚያስከትል፣ እነሱን የሚከብ ሰይፍ ነው።+ +15 ልባቸው በፍርሃት ይቀልጣል፤+ ብዙዎችም በከተሞቻቸው በር ላይ ይወድቃሉ፤ እኔም በሰይፉ እገድላለሁ። አዎ፣ ሰይፉ እንደ መብረቅ ያበራል፤ ለመግደልም ተወልውሏል! +16 በስተ ቀኝ በኩል በኃይል ቁረጥ! በስተ ግራ በኩል ተንቀሳቀስ! ስለትህ በዞረበት አቅጣጫ ሁሉ ሂድ! +17 እኔም በእጄ አጨበጭባለሁ፤ ቁጣዬንም አበርዳለሁ።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ።” +19 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ የሚመጣባቸውን ሁለት መንገዶች ንድፍ አውጣ። ሁለቱም መንገዶች የሚነሱት ከአንድ ምድር ነው፤ መንገዱ ወደ ሁለቱ ከተሞች የሚገነጠልበት ቦታ ላይ ምልክት አድርግ። +20 ሰይፍ በአሞናውያን ከተማ በራባ+ ላይ ይመጣ ዘንድ አንደኛውን መንገድ አመልክት፤ እንዲሁም በይሁዳ በምትገኘው በተመሸገችው ኢየሩሳሌም+ ላይ ይመጣ ዘንድ ሌላኛውን መንገድ አመልክት። +21 የባቢሎን ንጉሥ ያሟርት ዘንድ በመንታ መንገድ ይኸውም በሁለቱ መንገዶች መገንጠያ ላይ ይቆማልና። ፍላጾችን ይወዘውዛል። ጣዖቶቹን* ያማክራል፤ ጉበት ይመረምራል። +22 በቀኝ እጁ የወጣው ሟርት የመደርመሻ መሣሪያዎችን ለመደገን፣ የግድያ ትእዛዝ ለማስተላለፍ፣ የጦርነት ሁካታ ለማሰማት፣ በበሮቿ ላይ የመደርመሻ መሣሪያዎች ለመደገን፣ በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ለመደልደልና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ለመሥራት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ አመለከተው።+ +23 ቃለ መሐላዎች የገቡላቸው ሰዎች* ግን ይህ የሐሰት ሟርት ይመስላቸዋል።+ ይሁንና እሱ በደላቸውን በማስታወስ ማርኮ ይወስዳቸዋል።+ +24 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምትፈጽሙት ድርጊት ሁሉ መተላለፋችሁ እንዲገለጥና ኃጢአታችሁ እንዲታይ በማድረግ በደላችሁ እንዲታሰብ አድርጋችኋል። እናንተም አሁን ስለታሰባችሁ በኃይል* ትወሰዳላችሁ።’ +25 “አንተ ክፉኛ የቆሰልከው፣ መጥፎው የእስራኤል አለቃ፣+ ቀንህ ይኸውም የመጨረሻ ቅጣት የምትቀበልበት ጊዜ ደርሷል። +26 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጥምጥሙን ፍታ፤ አክሊሉንም አንሳ።+ ይህ እንደ በፊቱ አይሆንም።+ ዝቅ ያለውን ከፍ አድርግ፤+ ከፍ ያለውን ደግሞ ዝቅ አድርግ።+ +27 ባድማ፣ ባድማ፣ ባድማ አደርጋታለሁ። እሷም ሕጋዊ መብት ያለው እስኪመጣ ድረስ+ ለማንም አትሆንም፤ ለእሱም እሰጣታለሁ።’+ +28 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ አሞናውያንና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል።’ እንዲህ በል፦ ‘ሰይፍ! ሰይፍ ለግድያ ተመዟል፤ እንዲበላና እንደ መብረቅ እንዲያበራ ተወልውሏል። +29 ስለ ራስሽ የሐሰት ራእዮች ያየሽና የውሸት ሟርት ያሟረትሽ ቢሆንም ቀናቸው፣ የመጨረሻ ቅጣት የሚቀበሉበት ጊዜ በደረሰባቸው ክፉዎች ማለትም በሚገደሉት ሰዎች* ላይ ትከመሪያለሽ። +30 ሰይፉ ወደ ሰገባው ይመለስ። በተፈጠርሽበት ስፍራ፣ በተገኘሽበትም ምድር እፈርድብሻለሁ። +31 ቁጣዬን በአንቺ ላይ አወርዳለሁ። የታላቅ ቁጣዬን እሳት በላይሽ ላይ አነዳለሁ፤ በማጥፋትም ለተካኑ ጨካኝ ሰዎች አሳልፌ እሰጥሻለሁ።+ +32 ለእሳት ማገዶ ትሆኛለሽ፤+ የገዛ ደምሽ በምድሪቱ ላይ ይፈስሳል፤ ደግሞም ከእንግዲህ ወዲህ አትታወሺም፤ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁና።’” +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የወይን ተክል እንጨት በጫካ ዛፎች መካከል ካለ ከየትኛውም ዛፍ ወይም ቅርንጫፍ ከተወሰደ እንጨት ጋር እንዴት ሊወዳደር ይችላል? +3 ከወይን ተክል የሚገኝ ግንድ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? ወይስ ሰዎች ግንዱን ተጠቅመው ዕቃ ለማንጠልጠል የሚያገለግል ኩላብ ይሠራሉ? +4 እነሆ፣ ማገዶ እንዲሆን እሳት ውስጥ ይጣላል፤ እሳቱ ጫፍና ጫፉን ይበላዋል፤ መሃሉንም ይለበልበዋል። ከዚህ በኋላ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? +5 ምንም ነገር ሳይነካውም እንኳ ለምንም ነገር ሊያገለግል አይችልም። እሳት ሲበላውና ሲለበልበውማ ጨርሶ ከጥቅም ውጭ ይሆናል!” +6 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ማገዶ እንዲሆን ለእሳት አሳልፌ እንደሰጠሁት በጫካ ዛፎች መካከል እንዳለ የወይን ተክል እንጨት ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+ +7 ፊቴን በእነሱ ላይ አድርጌአለሁ። ከእሳቱ ቢያመልጡም እሳት ይበላቸዋል። ፊቴንም በእነሱ ላይ በማደርግበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”+ +8 “‘ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸውም+ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +22 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተስ የደም ዕዳ ባለባት ከተማ ላይ ፍርድ ለማወጅና+ አስጸያፊ ነገሮቿን ሁሉ+ ለማሳወቅ ተዘጋጅተሃል? +3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በመካከልሽ ደም የምታፈሺ፣+ ፍርድ የምትቀበዪበት ጊዜ የደረሰብሽ፣+ ትረክሺም ዘንድ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶች* የምትሠሪ ከተማ ሆይ፣+ +4 ያፈሰስሽው ደም በደለኛ አድርጎሻል፤+ ደግሞም አስጸያፊ ጣዖቶችሽ አርክሰውሻል።+ የቀኖችሽን መጨረሻ አፋጥነሻል፤ የዘመኖችሽም መጨረሻ ደርሷል። ስለዚህ ብሔራት ነቀፋ እንዲሰነዝሩብሽ፣ አገሩም ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ።+ +5 አንቺ ስምሽ ርኩስ የሆነና ሽብር የሞላብሽ ከተማ ሆይ፣ በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉት አገሮች ይሳለቁብሻል።+ +6 እነሆ፣ በመካከልሽ ያለ እያንዳንዱ የእስራኤል አለቃ ሥልጣኑን ደም ለማፍሰስ ይጠቀምበታል።+ +7 በአንቺ ውስጥ ያሉት ሰዎች አባቶቻቸውንና እናቶቻቸውን ያቃልላሉ።+ ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው ያጭበረብራሉ፤ ደግሞም አባት የሌለውን ልጅና* መበለቲቱን ይበድላሉ።”’”+ +8 “‘ቅዱስ ስፍራዎቼ��� ታቃልያለሽ፤ ሰንበቶቼንም ታረክሻለሽ።+ +9 በአንቺ ውስጥ ደም የማፍሰስ ዓላማ ያላቸው ስም አጥፊዎች አሉ።+ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ መሥዋዕቶችን ይበላሉ፤ በመካከልሽም ጸያፍ ምግባር ይፈጽማሉ።+ +10 በአንቺ ውስጥ የአባታቸውን መኝታ ያረክሳሉ፤*+ ደግሞም በወር አበባዋ የረከሰችን ሴት አስገድደው ይደፍራሉ።+ +11 በአንቺ ውስጥ አንዱ ከባልንጀራው ሚስት ጋር አስጸያፊ ነገር ይሠራል፤+ ሌላው ጸያፍ ምግባር በመፈጸም የገዛ ምራቱን ያረክሳታል፤+ ሌላው ደግሞ የገዛ አባቱ ልጅ የሆነችውን እህቱን አስገድዶ ይደፍራል።+ +12 በአንቺ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደም ለማፍሰስ ጉቦ ይቀበላሉ።+ ወለድና ትርፍ ለማግኘት* ታበድሪያለሽ፤+ የባልንጀሮችሽንም ገንዘብ ትቀሚያለሽ።+ አዎ፣ እኔን ጨርሶ ረስተሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +13 “‘እነሆ፣ ያገኘሽውን አግባብ ያልሆነ ጥቅምና በመካከልሽ ያፈሰስሽውን ደም በመጸየፍ አጨበጭባለሁ። +14 በአንቺ ላይ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ልብሽ ሊጸና፣ እጆችሽስ ብርቱ ሆነው ሊቀጥሉ ይችላሉ?+ እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አደርገዋለሁ። +15 በብሔራት መካከል እበትንሻለሁ፤ በየአገሩም እዘራሻለሁ፤+ ርኩሰትሽንም አስወግዳለሁ።+ +16 አንቺም በብሔራት ፊት ትዋረጃለሽ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ።’”+ +18 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ሆነውብኛል። ሁሉም ምድጃ ውስጥ ያለ መዳብ፣ ቆርቆሮ፣ ብረትና እርሳስ ናቸው። ብር ሲቀልጥ ከላይ እንደሚሰፍ ቆሻሻ ሆነዋል።+ +19 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሁላችሁም ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ+ ስለሆናችሁ በኢየሩሳሌም ውስጥ እሰበስባችኋለሁ። +20 እሳት በላያቸው ላይ እንዲነድባቸውና እንዲቀልጡ ብር፣ መዳብ፣ ብረት፣ እርሳስና ቆርቆሮ በምድጃ ውስጥ እንደሚሰበሰቡ ሁሉ እኔም እናንተን በንዴትና በታላቅ ቁጣ እሰበስባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ እሳት በማንደድ አቀልጣችኋለሁ።+ +21 አንድ ላይ እሰበስባችኋለሁ፤ በላያችሁም ላይ የቁጣዬን እሳት አነዳለሁ፤+ እናንተም በውስጧ ትቀልጣላችሁ።+ +22 ብር በምድጃ ውስጥ እንደሚቀልጥ ሁሉ እናንተም በውስጧ ትቀልጣላችሁ፤ በእናንተ ላይ ቁጣዬን ያፈሰስኩት እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’” +23 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ +24 “የሰው ልጅ ሆይ፣ እንዲህ በላት፦ ‘አንቺ በቁጣ ቀን የማትጸጂ ወይም ዝናብ የማይዘንብብሽ ምድር ነሽ። +25 ነቢያቷ ያደነውን እንስሳ እንደሚቦጫጭቅ የሚያገሳ አንበሳ+ በውስጧ ሴራ ጠንስሰዋል።+ ሰዎችን* ይውጣሉ። ውድ ሀብትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ። በውስጧ ያሉትን ብዙ ሴቶች መበለት አድርገዋል። +26 ካህናቷ ሕጌን ጥሰዋል፤+ ቅዱስ ስፍራዎቼንም ያረክሳሉ።+ ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው ነገር መካከል ምንም ልዩነት አያደርጉም፤+ ደግሞም ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውን ልዩነት አያስታውቁም፤+ ሰንበቶቼንም ለማክበር አሻፈረኝ ይላሉ፤ እኔም በመካከላቸው ረከስኩ። +27 በመካከሏ ያሉት አለቆቿ ያደኑትን እንስሳ እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው፤ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ደም ያፈሳሉ፤ የሰዎችንም ሕይወት* ያጠፋሉ።+ +28 ነቢያቷ ግን እነሱ የሚያደርጉትን ነገር በኖራ ይለስናሉ። የሐሰት ራእዮች ያያሉ፤ የውሸት ሟርትም ያሟርታሉ፤+ ደግሞም ይሖዋ ራሱ ምንም ሳይናገር “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል” ይላሉ። +29 የምድሪቱ ሰዎች የማጭበርበር ድርጊት ፈጽመዋል፤ ሌሎችን ዘርፈዋል፤+ ችግረኛውንና ድሃውን በድለዋል፤ ደግሞም ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አጭበርብረዋል፤ ፍትሕን��� ነፍገውታል።’ +30 “‘ከመካከላቸው የድንጋይ ቅጥሩን የሚጠግን ወይም ምድሪቱ እንዳትጠፋ በፈረሰው ቦታ ላይ በፊቴ የሚቆምላት ሰው ይኖር እንደሆነ ተመለከትኩ፤+ ሆኖም አንድም ሰው አላገኘሁም። +31 ስለዚህ ቁጣዬን በእነሱ ላይ አወርዳለሁ፤ በታላቅ ቁጣዬም እሳት ፈጽሜ አጠፋቸዋለሁ። የመረጡት መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +42 ከዚያም በስተ ሰሜን ወዳለው ወደ ውጨኛው ግቢ ወሰደኝ።+ ደግሞም በአቅራቢያው ከሚገኘው ሕንፃ+ በስተ ሰሜን፣ ክፍት ከሆነው ስፍራ አጠገብ ወዳሉት የመመገቢያ ክፍሎች ያሏቸው ሕንፃዎች+ አመጣኝ። +2 ሕንፃዎቹ በሰሜኑ መግቢያ በኩል ርዝመታቸው 100 ክንድ* ነበር፤ ወርዳቸው ደግሞ 50 ክንድ ነበር። +3 ሕንፃዎቹ የሚገኙት ወርዱ 20 ክንድ በሆነው በውስጠኛው ግቢና+ በውጨኛው ግቢ መመላለሻ መንገድ መካከል ነበር። ሕንፃዎቹ ባለ ሁለት ፎቅ ሲሆኑ ትይዩ ሆነው የተሠሩ ሰገነቶች ነበሯቸው። +4 በመመገቢያ ክፍሎቹ ፊት* ወርዱ 10 ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ 100 ክንድ የሆነ መተላለፊያ* በውስጥ በኩል ነበር፤+ የክፍሎቹም መግቢያዎች የሚገኙት በስተ ሰሜን በኩል ነበር። +5 ከላይ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ከታች ካሉትና መካከል ላይ ካሉት የሕንፃው ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያሉ ነበሩ፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ሰፋ ያለ ቦታ ይዘውባቸው ነበር። +6 የመመገቢያ ክፍሎቹ ባለ ሁለት ፎቅ ነበሩ፤ ይሁንና በግቢው ውስጥ እንዳሉት ዓይነት ዓምዶች አልነበሯቸውም። ከታች ካሉትና መካከል ላይ ካሉት ይበልጥ ከላይኛው ፎቅ ክፍሎች ሰፊ ቦታ የተወሰደው ለዚህ ነው። +7 ከሌሎቹ የመመገቢያ ክፍሎች ጋር ትይዩ ከሆኑትና በውጨኛው ግቢ በኩል ካሉት የመመገቢያ ክፍሎች አጠገብ የሚገኘው የውጨኛው የድንጋይ ቅጥር ርዝመት 50 ክንድ ነበር። +8 በውጨኛው ግቢ በኩል ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ርዝመት 50 ክንድ ሲሆን ከመቅደሱ ትይዩ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ርዝመት ግን 100 ክንድ ነበር። +9 የመመገቢያ ክፍሎቹ በስተ ምሥራቅ በኩል፣ ከውጨኛው ግቢ ወደ ክፍሎቹ የሚወስድ መግቢያ ነበራቸው። +10 በደቡብም በኩል ክፍት በሆነው ስፍራና በሕንፃው አቅራቢያ፣ በስተ ምሥራቅ ባለው የግቢው የድንጋይ ቅጥር ውስጥ* የመመገቢያ ክፍሎች ነበሩ።+ +11 በስተ ሰሜን እንዳሉት የመመገቢያ ክፍሎች ሁሉ በእነዚህ የመመገቢያ ክፍሎች ፊትም መተላለፊያ ነበር።+ ክፍሎቹ ተመሳሳይ ርዝመትና ወርድ ነበራቸው፤ መውጫዎቻቸውም ሆኑ ንድፎቻቸው ተመሳሳይ ነበሩ። መግቢያዎቻቸው +12 በደቡብ በኩል ከሚገኙት የመመገቢያ ክፍሎች መግቢያዎች ጋር ተመሳሳይ ነበሩ። በስተ ምሥራቅ በኩል በአቅራቢያው ካለው የድንጋይ ቅጥር ፊት፣ በመተላለፊያው መንገድ መነሻ ላይ ሰው ሊገባበት የሚችል መግቢያ ነበር።+ +13 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ክፍት ከሆነው ስፍራ አጠገብ የሚገኙት በስተ ሰሜን ያሉት የመመገቢያ ክፍሎችና በስተ ደቡብ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች፣+ ወደ ይሖዋ የሚቀርቡት ካህናት እጅግ ቅዱስ የሆኑትን መባዎች የሚበሉባቸው የተቀደሱ መመገቢያ ክፍሎች ናቸው።+ በዚያም እጅግ ቅዱስ የሆኑትን መባዎች፣ የእህል +14 ካህናቱ በሚገቡበት ጊዜ፣ ሲያገለግሉ የሚለብሱትን ልብስ ሳያወልቁ ከቅዱሱ ስፍራ ወደ ውጨኛው አደባባይ መውጣት አይችሉም፤+ ልብሶቹ ቅዱስ ናቸውና። ለሕዝቡ ወደተፈቀዱት ቦታዎች ከመሄዳቸው በፊት ልብሳቸውን ይቀይሩ ነበር።” +15 የቤተ መቅደሱን የውስጠኛውን ስፍራ ለክቶ* ሲጨርስ ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው በር+ በሚወስደው መተላለፊያ በኩል ይዞኝ ወጣ፤ ከዚያም ስፍራውን በጠቅላላ ለካ። +16 በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን በመለኪያ ዘንግ* ለካ። በመለኪያ ዘንጉ ከአንዱ ���ን እስከ ሌላው ጎን ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ። +17 በስተ ሰሜን በኩል ያለውን ለካ፤ በመለኪያ ዘንጉም ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ። +18 በስተ ደቡብ በኩል ያለውን ለካ፤ በመለኪያ ዘንጉም ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ። +19 ከዚያም ወደ ምዕራብ ዞረ። በመለኪያ ዘንጉ ሲለካ ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ። +20 ስፍራውን በአራቱም ጎን ለካ። ቅዱስ የሆነውንና ቅዱስ ያልሆነውን ስፍራ ለመለየት የሚያገለግል+ ርዝመቱ 500 ዘንግ፣ ወርዱም 500 ዘንግ+ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበር።+ +39 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጎግ ላይ ትንቢት ተናገር፤+ እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመሼቅና የቱባል+ ዋና አለቃ* የሆንከው ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። +2 እመልስሃለሁ፤ ደግሞም እነዳሃለሁ፤ ራቅ ካለውም የሰሜን ምድር አምጥቼ+ ወደ እስራኤል ተራሮች እወስድሃለሁ። +3 በግራ እጅህ ያለውን ደጋንህንም ሆነ በቀኝ እጅህ የያዝካቸውን ፍላጻዎችህን አስጥልሃለሁ። +4 አንተና ወታደሮችህ ሁሉ እንዲሁም ከአንተ ጋር የሚሆኑት ሕዝቦች በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ።+ ለተለያዩ አዳኝ አሞሮች ሁሉና ለዱር አራዊት መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።”’+ +5 “‘አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤+ እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +6 “‘በማጎግና ያለስጋት በደሴቶች በሚኖሩት ላይም እሳት እሰዳለሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። +7 ቅዱስ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ቅዱስ ስሜ እንዲረክስ አልፈቅድም፤ ብሔራትም እኔ ይሖዋ፣ የእስራኤል ቅዱስ+ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’+ +8 “‘አዎ፣ በትንቢት የተነገረው ነገር ይመጣል፤ ደግሞም ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ያ ያልኩት ቀን ይህ ነው። +9 በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ወጥተው፣ የጦር መሣሪያዎቹን ይኸውም ትናንሾቹንና* ትላልቆቹን ጋሻዎች፣ ደጋኖቹን፣ ፍላጻዎቹን፣ የጦር ቆመጦቹንና* ጦሮቹን እሳት ያነዱባቸዋል። ለሰባት ዓመታትም እሳት ለማንደድ ይጠቀሙባቸዋል።+ +10 የጦር መሣሪያዎቹን እሳት ለማንደድ ስለሚጠቀሙባቸው ከሜዳ እንጨት መልቀም ወይም ከጫካ ማገዶ መሰብሰብ አያስፈልጋቸውም።’ “‘የበዘበዟቸውን ይበዘብዛሉ፤ የመዘበሯቸውንም ይመዘብራሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +11 “‘በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር፣ ከባሕሩ በስተ ምሥራቅ በሚጓዙት ሰዎች ሸለቆ ለጎግ+ የመቃብር ቦታ እሰጠዋለሁ፤ በዚያ የሚያልፉትንም ሰዎች መንገድ ይዘጋል። ጎግንና ስፍር ቁጥር የሌለውን ሠራዊቱን ሁሉ በዚያ ይቀብራሉ፤ ሸለቆውንም የሃሞን ጎግ ሸለቆ*+ ብለው ይጠሩታል። +12 የእስራኤል ቤት ሰዎች እነሱን ቀብረው ምድሪቱን ለማንጻት ሰባት ወር ይፈጅባቸዋል።+ +13 የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እነሱን ይቀብራል፤ ይህም ራሴን በማስከብርበት ቀን ዝና ያስገኝላቸዋል’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +14 “‘ምድሪቱ ትነጻ ዘንድ፣ ሰዎች በየጊዜው በምድሪቱ ላይ እንዲያልፉና በምድሪቱ ላይ የቀሩትን አስከሬኖች እንዲቀብሩ ይመደባሉ። ለሰባት ወራትም ፍለጋቸውን ይቀጥላሉ። +15 በምድሪቱ ላይ የሚያልፉት ሰዎች የሰው አፅም ሲያዩ በአጠገቡ ምልክት ያደርጋሉ። ከዚያም እንዲቀብሩ የተመደቡት አፅሙን በሃሞን ጎግ ሸለቆ+ ይቀብሩታል። +16 በዚያም ሃሞና* ተብላ የምትጠራ ከተማ ትኖራለች። እነሱም ምድሪቱን ያነጻሉ።’+ +17 “አንተም፣ የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለተለያዩ ወፎችና ለዱር አራዊት ሁሉ እንዲህ በል፦ “አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ኑ። ለእናንተ በማዘጋጀው መሥዋዕቴ ዙሪያ ተሰብሰቡ፤ ይህም በእስራኤል ተራሮች ላይ የሚዘጋጅ ታላቅ መሥዋዕት ነው።+ ሥጋ ���በላላችሁ፤ ደምም ትጠጣላችሁ።+ +18 የኃያላንን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም አለቆች ደም ትጠጣላችሁ፤ እነሱ አውራ በጎች፣ ጠቦቶች፣ አውራ ፍየሎችና ወይፈኖች ሲሆኑ ሁሉም የሰቡ የባሳን ከብቶች ናቸው። +19 እናንተም እኔ ከማዘጋጅላችሁ መሥዋዕት፣ እስክትጠግቡ ድረስ ስብ ትሰለቅጣላችሁ፤ እስክትሰክሩም ደም ትጠጣላችሁ።”’ +20 “‘በማዕዴም ፈረሶችንና ሠረገለኞችን እንዲሁም ኃያላን ሰዎችንና ሁሉንም ዓይነት ተዋጊዎች እስክትጠግቡ ትበላላችሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +21 “‘በብሔራት መካከል ክብሬን እገልጣለሁ፤ ብሔራት ሁሉ የወሰድኩትን የፍርድ እርምጃና በእነሱ መካከል የገለጥኩትን ኃይል* ያያሉ።+ +22 ከዚያ ቀን አንስቶ የእስራኤል ቤት ሰዎች እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። +23 ብሔራትም የእስራኤል ቤት ሰዎች በግዞት የተወሰዱት በገዛ ራሳቸው በደል ይኸውም ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እንደሆነ ያውቃሉ።+ ስለዚህ ፊቴን ከእነሱ ሰወርኩ፤+ ለጠላቶቻቸውም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤+ ሁሉም በሰይፍ ወደቁ። +24 እንደ ርኩሰታቸውና እንደ በደላቸው መጠን አደረግኩባቸው፤ ፊቴንም ከእነሱ ሰወርኩ።’ +25 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምርኮ የተወሰዱትን የያዕቆብ ወገኖች እመልሳለሁ፤+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤+ የስሜንም ቅድስና አስከብራለሁ።*+ +26 ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ውርደት ከደረሰባቸው+ በኋላ የሚያስፈራቸው ሳይኖር በምድራቸው ላይ ያለስጋት ይኖራሉ።+ +27 ከሕዝቦች መካከል መልሼ ሳመጣቸውና ከጠላቶቻቸው አገሮች ስሰበስባቸው፣+ በብዙ ብሔራት ፊት፣ በመካከላቸው ራሴን እቀድሳለሁ።’+ +28 “‘በብሔራት መካከል በግዞት እንዲኖሩ ሳደርግና ከዚያም አንዳቸውንም ሳላስቀር ወደ ገዛ ምድራቸው መልሼ ሳመጣቸው፣ እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ +29 ከእንግዲህ ፊቴን ከእስራኤል ቤት ሰዎች አልሰውርም፤+ በእነሱ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁና’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” +3 ንጉሥ ናቡከደነጾር ቁመቱ 60 ክንድ፣* ወርዱ 6 ክንድ* የሆነ የወርቅ ምስል* ሠራ። ምስሉን በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው። +2 ከዚያም ንጉሥ ናቡከደነጾር የአውራጃ ገዢዎቹ፣ አስተዳዳሪዎቹ፣ አገረ ገዢዎቹ፣ አማካሪዎቹ፣ የግምጃ ቤት ኃላፊዎቹ፣ ዳኞቹ፣ ሕግ አስከባሪዎቹና የየአውራጃዎቹ አስተዳዳሪዎች በሙሉ ንጉሥ ናቡከደነጾር ላቆመው ምስል የምረቃ ሥነ ሥርዓት እንዲሰበሰቡ ጥሪ አስተላለፈ። +3 በመሆኑም የአውራጃ ገዢዎቹ፣ አስተዳዳሪዎቹ፣ አገረ ገዢዎቹ፣ አማካሪዎቹ፣ የግምጃ ቤት ኃላፊዎቹ፣ ዳኞቹ፣ ሕግ አስከባሪዎቹና የየአውራጃዎቹ አስተዳዳሪዎች በሙሉ ንጉሥ ናቡከደነጾር ላቆመው ምስል የምረቃ ሥነ ሥርዓት ተሰበሰቡ። ናቡከደነጾር ባቆመውም ምስል ፊት ቆሙ። +4 አዋጅ ነጋሪው ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጣችሁ ሕዝቦች ሆይ፣ እንዲህ እንድታደርጉ ታዛችኋል፦ +5 የቀንደ መለከት፣ የእምቢልታ፣ የተለያዩ ባለ አውታር መሣሪያዎች፣ የባለ ሦስት ማዕዘን በገና፣ የባለ ከረጢት ዋሽንትና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ በግንባራችሁ ተደፍታችሁ ንጉሥ ናቡከደነጾር ላቆመው የወርቅ ምስል ስገዱ። +6 ተደፍቶ የማይሰግድ ማንኛውም ሰው ወዲያውኑ ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት ይጣላል።”+ +7 ስለዚህ ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጡት ሕዝቦች በሙሉ የቀንደ መለከት፣ የእምቢልታ፣ የተለያዩ ባለ አውታር መሣሪያዎች፣ የባለ ሦስት ማዕዘን በገናና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ሁሉ ድምፅ ሲሰሙ ተደፍተው ንጉሥ ናቡከደነጾር ላቆመ��� የወርቅ ምስል ሰገዱ። +8 በዚህ ጊዜ አንዳንድ ከለዳውያን ወደ ፊት ቀርበው አይሁዳውያንን ከሰሱ።* +9 ንጉሥ ናቡከደነጾርን እንዲህ አሉት፦ “ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ኑር። +10 ንጉሥ ሆይ፣ ማንኛውም ሰው የቀንደ መለከት፣ የእምቢልታ፣ የተለያዩ ባለ አውታር መሣሪያዎች፣ የባለ ሦስት ማዕዘን በገና፣ የባለ ከረጢት ዋሽንትና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ሁሉ ድምፅ ሲሰማ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል እንዲሰግድ ትእዛዝ አስተላልፈሃል፤ +11 ተደፍቶ የማይሰግድ ሁሉ ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት እንደሚጣል ተናግረሃል።+ +12 ሆኖም በባቢሎን አውራጃ አስተዳዳሪዎች አድርገህ የሾምካቸው ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ የሚባሉ አይሁዳውያን አሉ።+ ንጉሥ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች ለአንተ አክብሮት የላቸውም። አማልክትህን አያገለግሉም እንዲሁም ላቆምከው የወርቅ ምስል ለመስገድ እንቢተኞች ሆነዋል።” +13 በዚህ ጊዜ ናቡከደነጾር እጅግ ተቆጥቶ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን እንዲያመጧቸው አዘዘ። እነሱንም በንጉሡ ፊት አቀረቧቸው። +14 ናቡከደነጾርም እንዲህ አላቸው፦ “ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ፣ አማልክቴን አለማገልገላችሁና+ ላቆምኩት የወርቅ ምስል አንሰግድም ማለታችሁ እውነት ነው? +15 አሁንም የቀንደ መለከት፣ የእምቢልታ፣ የተለያዩ ባለ አውታር መሣሪያዎች፣ የባለ ሦስት ማዕዘን በገና፣ የባለ ከረጢት ዋሽንትና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ ለሠራሁት ምስል ተደፍታችሁ ለመስገድ ፈቃደኞች ከሆናችሁ፣ መልካም! የማትሰግዱ ከሆነ ግን ወዲያውኑ ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት +16 ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ለንጉሡ መልሰው እንዲህ አሉ፦ “ናቡከደነጾር ሆይ፣ በዚህ ጉዳይ ለአንተ መልስ መስጠት አያስፈልገንም። +17 ወደ እሳቱ የምንጣል ከሆነ የምናገለግለው አምላካችን ከሚንበለበለው የእቶን እሳት ሊያስጥለን ይችላል፤ ንጉሥ ሆይ፣ ከእጅህም ያስጥለናል።+ +18 ሆኖም እሱ ባያስጥለንም እንኳ ንጉሥ ሆይ፣ የአንተን አማልክት እንደማናገለግልና ላቆምከው የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ እወቅ።”+ +19 በዚህ ጊዜ ናቡከደነጾር በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ እጅግ ተቆጣ፤ የፊቱም ገጽታ ተለወጠባቸው፤* የእቶኑም እሳት ከወትሮው ይበልጥ ሰባት እጥፍ እንዲነድ አዘዘ። +20 ከዚያም በሠራዊቱ መካከል ያሉ ኃያላን ሰዎች ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን አስረው ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት እንዲጥሏቸው አዘዘ። +21 በመሆኑም እነዚህ ሰዎች ልብሳቸውን እንደለበሱ ማለትም መጎናጸፊያቸውን፣ ከውስጥም ሆነ ከላይ ያደረጉትን ልብስና ጥምጥማቸውን በሙሉ እንደለበሱ ታስረው ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት ተጣሉ። +22 የንጉሡ ትእዛዝ እጅግ ጥብቅ ስለነበረና የእቶኑ እሳት በኃይል ስለተቀጣጠለ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን የወሰዷቸው ሰዎች በእሳቱ ወላፈን ተቃጥለው ሞቱ። +23 ይሁንና ሦስቱ ሰዎች ይኸውም ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ እንደታሰሩ በሚንበለበለው የእቶን እሳት ውስጥ ወደቁ። +24 ከዚያም ንጉሥ ናቡከደነጾር በድንጋጤ ከተቀመጠበት ዘሎ ተነሳ፤ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱንም “አስረን እሳት ውስጥ የጣልናቸው ሦስት ሰዎች አልነበሩም እንዴ?” ሲል ጠየቃቸው፤ እነሱም “አዎ፣ ንጉሥ ሆይ” ብለው መለሱ። +25 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፣ ያልታሰሩ አራት ሰዎች በእሳቱ መካከል ሲመላለሱ አያለሁ፤ ጉዳትም አልደረሰባቸውም፤ አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል።” +26 ናቡከደነጾር የሚንበለበል እሳት ወዳለበት እቶን በር ቀርቦ “እናንተ የልዑል አምላክ አገልጋዮች፣+ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ወጥታችሁ ወደዚህ ኑ!” አለ። ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎም ከ���ሳቱ ውስጥ ወጡ። +27 በዚያ ተሰብስበው የነበሩት የአውራጃ ገዢዎቹ፣ አስተዳዳሪዎቹ፣ አገረ ገዢዎቹና የንጉሡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣+ እሳቱ ሰውነታቸውን እንዳልጎዳው፣*+ ከራሳቸው ፀጉር አንዲቷ እንኳ እንዳልተቃጠለች፣ መጎናጸፊያቸው መልኩ እንዳልተለወጠና የእሳቱ ሽታ በላያቸው እንዳልነበረ ተመለከቱ። +28 ከዚያም ናቡከደነጾር እንዲህ አለ፦ “መልአኩን ልኮ አገልጋዮቹን የታደገው የሲድራቅ፣ የሚሳቅና የአብደናጎ አምላክ የተመሰገነ ይሁን።+ እነሱ በእሱ በመታመን የንጉሡን ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም፤ የራሳቸውን አምላክ ትተው ሌላ አምላክ ከማገልገል ወይም ከማምለክ ይልቅ ሞትን መርጠዋል።*+ +29 ስለዚህ በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ ማንኛውንም መጥፎ ነገር የሚናገር ከየትኛውም ብሔርና ቋንቋ የሆነ ሕዝብ ሁሉ እንዲቆራረጥ፣ ቤቱም የሕዝብ መጸዳጃ* እንዲሆን አዝዣለሁ፤ እንደ እሱ ማዳን የሚችል ሌላ አምላክ የለምና።”+ +30 ከዚያም ንጉሡ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ በባቢሎን አውራጃ ውስጥ የደረጃ እድገት እንዲያገኙ አደረገ።+ +7 የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዛር+ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልምና ራእዮች አየ።+ ከዚያም ያየውን ሕልም ጻፈ፤+ ጉዳዩንም በዝርዝር አሰፈረ። +2 ዳንኤልም እንዲህ ሲል ገለጸ፦ “በሌሊት ባየኋቸው ራእዮች ላይ አራቱ የሰማያት ነፋሳት የተንጣለለውን ባሕር ሲያናውጡት ተመለከትኩ።+ +3 አራት ግዙፍ አራዊትም+ ከባሕር ውስጥ ወጡ፤ እያንዳንዳቸውም አንዱ ከሌላው የተለዩ ነበሩ። +4 “የመጀመሪያው አንበሳ ይመስል ነበር፤+ የንስር ክንፎችም ነበሩት።+ እኔም እየተመለከትኩ ሳለ ክንፎቹ ተነቃቀሉ፤ ከምድር እንዲነሳና ልክ እንደ ሰው በሁለት እግሩ እንዲቆም ተደረገ፤ የሰውም ልብ ተሰጠው። +5 “እነሆ፣ ሁለተኛው አውሬ ድብ ይመስል ነበር።+ በአንድ ጎኑም ተነስቶ ነበር፤ በአፉም ውስጥ በጥርሶቹ መካከል ሦስት የጎድን አጥንቶች ይዞ ነበር፤ ‘ተነስተህ ብዙ ሥጋ ብላ’ ተባለ።+ +6 “ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ ነብር የሚመስል ሌላ አውሬ ነበር፤+ ሆኖም ጀርባው ላይ አራት የወፍ ክንፎች ነበሩት። አውሬውም አራት ራሶች ነበሩት፤+ የመግዛት ሥልጣንም ተሰጠው። +7 “ከዚህ በኋላ በሌሊት ባየኋቸው ራእዮች ላይ የሚያስፈራ፣ የሚያስደነግጥና ለየት ያለ ጥንካሬ ያለው አራተኛ አውሬ ተመለከትኩ፤ ትላልቅ የብረት ጥርሶችም ነበሩት። ይበላና ያደቅ እንዲሁም የቀረውን በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር።+ ከእሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን አሥር ቀንዶች ነበሩት። +8 ቀንዶቹን እየተመለከትኩ ሳለ፣ እነሆ ሌላ ትንሽ ቀንድ በመካከላቸው ወጣ፤+ ከመጀመሪያዎቹ ቀንዶች መካከል ሦስቱ በፊቱ ተነቃቀሉ። እነሆ፣ በዚህ ቀንድ ላይ የሰው ዓይኖች የሚመስሉ ዓይኖች ነበሩ፤ በእብሪት* የሚናገርም አፍ ነበረው።+ +9 “እኔም እየተመለከትኩ ሳለ ዙፋኖች ተዘጋጁ፤ ከዘመናት በፊት የነበረውም+ ተቀመጠ።+ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ፣+ የራሱም ፀጉር እንደጠራ ሱፍ ነበር። ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኮራኩሮቹም የሚነድ እሳት ነበሩ።+ +10 ከፊቱ የእሳት ጅረት ይፈልቅና ይፈስ ነበር።+ ሺህ ጊዜ ሺዎች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍም* በፊቱ ቆመው ነበር።+ ችሎቱ+ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ። +11 “በዚህ ጊዜ ቀንዱ ከሚናገረው የእብሪት* ቃል የተነሳ መመልከቴን ቀጠልኩ፤+ እኔም እየተመለከትኩ ሳለ አውሬው ተገደለ፤ አካሉም ወደሚንበለበል እሳት ተጥሎ እንዲጠፋ ተደረገ። +12 የቀሩት አራዊት+ ግን የገዢነት ሥልጣናቸውን ተቀሙ፤ ሆኖም ለተወሰነ ጊዜና ወቅት ዕድሜያቸው ተራዘመ። +13 “በሌሊት የተገለጡልኝን ራእዮች ማየቴን ቀጠልኩ፤ እነሆ የሰው ልጅ+ የሚመስል ከሰማያት ደመና ጋር መጣ፤ ከዘመናት በፊት ወደነበረውም+ እንዲገባ ተፈቀደለት፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። +14 ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጡ ሕዝቦች ሁሉ እንዲያገለግሉት የገዢነት ሥልጣን፣+ ክብርና+ መንግሥት ተሰጠው።+ የገዢነት ሥልጣኑ የማያልፍና ዘላለማዊ፣ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።+ +15 “እኔ ዳንኤል ያየኋቸው ራእዮች ፍርሃት ስላሳደሩብኝ በውስጤ መንፈሴ ታወከ።+ +16 ከቆሙት መካከል ወደ አንዱ ቀርቤ የዚህ ሁሉ ትክክለኛ ትርጉም ምን እንደሆነ ጠየቅኩት። እሱም መለሰልኝ፤ ደግሞም የእነዚህን ነገሮች ትርጉም ገለጸልኝ። +17 “‘እነዚህ አራት ግዙፍ አራዊት+ ከምድር የሚነሱ አራት ነገሥታት ናቸው።+ +18 ይሁንና ከሁሉ የላቀው አምላክ ቅዱሳን፣+ መንግሥቱን ይቀበላሉ፤+ መንግሥቱን ለዘላለም፣ አዎ ለዘላለም ዓለም ይወርሳሉ።’+ +19 “ከዚያም ከሌሎቹ ሁሉ የተለየ ስለሆነው ስለ አራተኛው አውሬ ይበልጥ ማወቅ ፈለግኩ፤ የብረት ጥርሶችና የመዳብ ጥፍሮች ያሉት እጅግ አስፈሪ አውሬ ነበር፤ ይበላና ያደቅ እንዲሁም የቀረውን በእግሩ ይረጋግጥ ነበር፤+ +20 ደግሞም በራሱ ላይ ስለነበሩት አሥር ቀንዶች+ እንዲሁም በኋላ ስለወጣውና ሦስቱ በፊቱ እንዲወድቁ ስላደረገው ስለ ሌላኛው ቀንድ+ ይኸውም ዓይኖችና በእብሪት* የሚናገር አፍ ስላሉት እንዲሁም ከሌሎቹ ስለበለጠው ቀንድ ማወቅ ፈለግኩ። +21 “እየተመለከትኩ ሳለ ይህ ቀንድ በቅዱሳኑ ላይ ጦርነት ከፈተ፤ በእነሱም ላይ አየለባቸው፤+ +22 ይህም የሆነው ከዘመናት በፊት የነበረው+ እስኪመጣና ከሁሉ የላቀው አምላክ ቅዱሳን አገልጋዮች+ እስኪፈረድላቸው ድረስ ነበር፤ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወርሱበት የተወሰነው ዘመን መጣ።+ +23 “እሱም እንዲህ አለ፦ ‘አራተኛው አውሬ በምድር ላይ የሚነሳ አራተኛ መንግሥት ነው። ከሌሎቹ መንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፤ መላዋን ምድር ያወድማል፣ ይረግጣል እንዲሁም ያደቃል።+ +24 አሥሩ ቀንዶች ከዚህ መንግሥት የሚነሱ አሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከእነሱም በኋላ ሌላ ይነሳል፤ እሱም ከመጀመሪያዎቹ የተለየ ይሆናል፤ ሦስት ነገሥታትንም ያዋርዳል።+ +25 በልዑሉ አምላክ ላይ የተቃውሞ ቃል ይናገራል፤+ ከሁሉ በላቀው አምላክ ቅዱሳንም ላይ ያለማቋረጥ ችግር ያደርስባቸዋል። ዘመናትንና ሕግን ለመለወጥ ያስባል፤ እነሱም ለዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመን እኩሌታ* በእጁ አልፈው ይሰጣሉ።+ +26 ይሁንና ችሎቱ ተሰየመ፤ የገዢነት ሥልጣኑንም ቀሙት፤ ከዚያም አስወገዱት፤ ፈጽሞም አጠፉት።+ +27 “‘ከሰማያት በታች ያለ መንግሥት፣ የገዢነት ሥልጣንና የመንግሥታት ግርማ በሙሉ ከሁሉ የላቀው አምላክ ቅዱሳን ለሆኑት ሰዎች ተሰጠ።+ መንግሥታቸው ዘላለማዊ መንግሥት ነው፤+ መንግሥታትም ሁሉ ያገለግሏቸዋል፤ ደግሞም ይታዘዟቸዋል።’ +28 “የነገሩ ፍጻሜ ይህ ነው። እኔም ዳንኤል ሳስበው የነበረው ነገር በጣም አስፈራኝ፤ ፊቴም ገረጣ፤* ነገሩን ግን በልቤ ያዝኩት።” +12 “በዚያ ዘመን ለሕዝብህ* የሚቆመው ታላቁ አለቃ+ ሚካኤል*+ ይነሳል።* ብሔራት ከተቋቋሙበት ጊዜ አንስቶ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ሆኖ የማያውቅ የጭንቀት ጊዜ ይመጣል። በዚያን ወቅት ሕዝብህ ይኸውም በመጽሐፍ ላይ ተጽፎ የተገኘ+ እያንዳንዱ ሰው ይተርፋል።+ +2 በምድር አፈር ውስጥ ካንቀላፉትም መካከል ብዙዎቹ ይነሳሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹ ደግሞ ለነቀፋና ለዘላለማዊ ውርደት ይነሳሉ። +3 “ደግሞም ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች እንደ ሰማይ ጸዳል ያበራሉ፤ የጽድቅን ጎዳና እንዲከተሉ ብዙ ሰዎችን የሚረዱም ለዘላለም እንደ ከዋክብት ያበራሉ። +4 “አንተም ዳንኤል ሆይ፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ ቃሉን በሚስጥር ያዝ፤ መጽሐፉንም አትመው።+ ብዙዎች መጽሐፉን በሚገባ ይመረምራሉ፤* እውነተኛው እውቀትም ይበዛል።”+ +5 ከዚያም እኔ ዳንኤል ስመለከት ሌሎች ሁለት በዚያ ቆመው አየሁ፤ አንደኛው ከወንዙ በዚህኛው ዳር ቆሞ የነበረ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከወንዙ በዚያኛው ዳር ቆሞ ነበር።+ +6 ከዚያም አንዱ፣ ከወንዙ ውኃ በላይ ያለውንና በፍታ የለበሰውን+ ሰው “እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ፍጻሜያቸውን የሚያገኙት ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ነው?” አለው። +7 ከዚያም ከወንዙ ውኃ በላይ ያለውና በፍታ የለበሰው ሰው መልስ ሲሰጥ ሰማሁ። እሱም ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማያት ዘርግቶ ለዘላለም ሕያው በሆነው+ በመማል እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “ከተወሰነ ዘመን፣ ዘመናትና የዘመን እኩሌታ* በኋላ ነው። የቅዱሱ ሕዝብ ኃይል ተደምስሶ እንዳበቃ+ እነዚህ ሁሉ ነገሮ +8 እኔም ሰማሁ፤ ሆኖም ሊገባኝ አልቻለም፤+ ስለዚህ “ጌታዬ ሆይ፣ የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ምን ይሆን?” አልኩት። +9 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ፣ ሂድ፤ ምክንያቱም የፍጻሜው ዘመን እስኪመጣ ድረስ ቃሉ በሚስጥር የተያዘና የታተመ ይሆናል።+ +10 ብዙዎች ራሳቸውን ያጸዳሉ፣ ያነጻሉ እንዲሁም ይጠራሉ።+ ክፉዎች ደግሞ ክፉ ድርጊት ይፈጽማሉ፤ ከክፉዎች መካከል አንዳቸውም አይረዱትም፤ ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ግን ይረዱታል።+ +"11 “የዘወትሩ መሥዋዕት+ ከተቋረጠበትና ጥፋት የሚያመጣው ርኩስ ነገር ከቆመበት+ ጊዜ አንስቶ 1,290 ቀን ይሆናል። " +"12 “ደግሞም 1,335ቱ ቀን እስከሚያልፍ ድረስ በትዕግሥት የሚጠባበቅ* ሰው ደስተኛ ነው! " +13 “አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ። ታርፋለህ፤ ሆኖም በዘመኑ ፍጻሜ ዕጣ ፋንታህን ለመቀበል* ትነሳለህ።”+ +1 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም+ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት።+ +2 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይሖዋ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮዓቄምንና በእውነተኛው አምላክ ቤት* ውስጥ ካሉት ዕቃዎች መካከል የተወሰኑትን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤+ እሱም በሰናኦር+ ምድር* ወደሚገኘው ወደ አምላኩ ቤት* አመጣቸው። ዕቃዎቹን በአምላኩ ግምጃ ቤት ውስጥ አስቀመጣቸው።+ +3 ከዚያም ንጉሡ የቤተ መንግሥቱ ዋና ባለሥልጣን የሆነውን አሽፈኔዝን ከንጉሡና ከመሳፍንቱ ዘር የሆኑትን ጨምሮ አንዳንድ እስራኤላውያንን* እንዲያመጣ አዘዘው።+ +4 እነሱም ምንም እንከን የሌለባቸው፣ መልከ መልካሞች፣ ጥበብ፣ እውቀትና ማስተዋል ያላቸው+ እንዲሁም በንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ማገልገል የሚችሉ ወጣቶች* መሆን ነበረባቸው። የከለዳውያንን ጽሑፍና ቋንቋም እንዲያስተምራቸው አዘዘው። +5 በተጨማሪም ንጉሡ ለእሱ ከሚቀርበው ምርጥ ምግብና ከሚጠጣው የወይን ጠጅ ላይ የዕለት ቀለብ እንዲሰጣቸው አደረገ። እነዚህ ወጣቶች ለሦስት ዓመት ከሠለጠኑ በኋላ* ንጉሡን ለማገልገል የሚሰማሩ ናቸው። +6 ከእነሱ መካከል ከይሁዳ ነገድ የሆኑት ዳንኤል፣*+ ሃናንያህ፣* ሚሳኤልና* አዛርያስ* ይገኙበታል።+ +7 ዋናው ባለሥልጣንም ስም* አወጣላቸው፤ ዳንኤልን ብልጣሶር፣+ ሃናንያህን ሲድራቅ፣ ሚሳኤልን ሚሳቅ፣ አዛርያስን ደግሞ አብደናጎ ብሎ ጠራቸው።+ +8 ዳንኤል ግን በንጉሡ ምርጥ ምግብ ወይም በሚጠጣው የወይን ጠጅ ላለመርከስ በልቡ ቁርጥ ውሳኔ አደረገ። በመሆኑም በዚህ መንገድ ራሱን እንዳያረክስ ዋናውን ባለሥልጣን ፈቃድ ጠየቀው። +9 እውነተኛው አምላክም ዋናው ባለሥልጣን ለዳንኤል ሞገስና* ምሕረት እንዲያሳየው አደረገ።+ +10 ሆኖም ዋናው ባለሥልጣን ዳንኤልን እንዲህ አለው፦ “የምትበሉትንና የምትጠጡትን የመደበላችሁን ጌታዬን ንጉሡን እፈራለሁ። እኩዮቻችሁ ከሆኑት ��ሌሎቹ ወጣቶች* ይልቅ ፊታችሁ ተጎሳቁሎ ቢያይስ? እኔን* በንጉሡ ፊት በደለኛ ታደርጉኛላችሁ።” +11 ዳንኤል ግን ዋናው ባለሥልጣን በዳንኤል፣ በሃናንያህ፣ በሚሳኤልና በአዛርያስ ላይ ጠባቂ አድርጎ የሾመውን ሰው እንዲህ አለው፦ +12 “እባክህ አገልጋዮችህን ለአሥር ቀን ያህል ፈትነን፤ የምንበላው አትክልትና የምንጠጣው ውኃ ይሰጠን፤ +13 ከዚያም የእኛን ቁመና የንጉሡን ምርጥ ምግብ ከሚበሉት ወጣቶች* ቁመና ጋር አወዳድር፤ በኋላም ባየኸው መሠረት በአገልጋዮችህ ላይ የፈለግከውን ነገር አድርግ።” +14 እሱም በሐሳባቸው ተስማማ፤ ለአሥር ቀንም ፈተናቸው። +15 ከአሥር ቀን በኋላም የንጉሡን ምርጥ ምግብ ከሚበሉት ወጣቶች* ሁሉ ይበልጥ ቁመናቸው የተሻለና ጤናማ ሆነው* ተገኙ። +16 ስለዚህ ጠባቂው ምርጥ በሆነው ምግባቸውና በወይን ጠጃቸው ምትክ አትክልት ይሰጣቸው ነበር። +17 እውነተኛው አምላክም ለእነዚህ አራት ወጣቶች* በሁሉም ዓይነት የጽሑፍና የጥበብ መስክ እውቀትና ጥልቅ ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤልም ሁሉንም ዓይነት ራእዮችና ሕልሞች የመረዳት ችሎታ ተሰጠው።+ +18 ንጉሡ በፊቱ እንዲያቀርቧቸው የቀጠረው ጊዜ ሲደርስ+ ዋናው ባለሥልጣን ናቡከደነጾር ፊት አቀረባቸው። +19 ንጉሡ ሲያነጋግራቸው ከወጣቶቹ መካከል እንደ ዳንኤል፣ ሃናንያህ፣ ሚሳኤልና አዛርያስ ያለ አልተገኘም፤+ እነሱም በንጉሡ ፊት ማገልገላቸውን ቀጠሉ። +20 ንጉሡ ጥበብና ማስተዋል የሚጠይቁ ጉዳዮችን ሁሉ አንስቶ በጠየቃቸው ጊዜ በመላ ግዛቱ ካሉት አስማተኛ ካህናትና ጠንቋዮች ሁሉ+ አሥር እጅ በልጠው አገኛቸው። +21 ዳንኤልም እስከ ንጉሥ ቂሮስ+ የመጀመሪያ ዓመት ድረስ በዚያ ቆየ። +8 ንጉሥ ቤልሻዛር+ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ ቀደም ሲል ከተገለጠልኝ ራእይ በኋላ ለእኔ፣ ለዳንኤል ሌላ ራእይ ተገለጠልኝ።+ +2 እኔም ራእዩን ተመለከትኩ፤ በራእዩም ላይ ራሴን፣ በኤላም+ አውራጃ በሚገኘው በሹሻን*+ ግንብ* አየሁት፤ ደግሞም ራእዩን ተመለከትኩ፤ እኔም በኡላይ የውኃ መውረጃ አጠገብ ነበርኩ። +3 ዓይኔን አንስቼ ስመለከት፣ እነሆ በውኃ መውረጃው አጠገብ ሁለት ቀንዶች ያሉት+ አንድ አውራ በግ+ ቆሞ ነበር። ሁለቱ ቀንዶች ረጃጅም ነበሩ፤ ይሁንና አንደኛው ከሌላው ይረዝማል፤ ይበልጥ ረጅም የሆነው ቀንድ የበቀለው በኋላ ነው።+ +4 አውራ በጉ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ በቀንዱ ሲወጋ ተመለከትኩ፤ አንድም አውሬ ሊቋቋመው አልቻለም፤ ከእጁም መታደግ የሚችል ማንም አልነበረም።+ የፈለገውን ያደርግ ነበር፤ ራሱንም ከፍ ከፍ አደረገ። +5 እየተመለከትኩ ሳለ፣ እነሆ አንድ አውራ ፍየል+ ከምዕራብ* ተነስቶ መሬት ሳይነካ መላዋን ምድር እያቋረጠ መጣ። አውራውም ፍየል በዓይኖቹ መካከል ጎልቶ የሚታይ ቀንድ ነበረው።+ +6 እሱም በውኃ መውረጃው አጠገብ ቆሞ ወዳየሁት ሁለት ቀንድ ወዳለው አውራ በግ አመራ፤ በታላቅ ቁጣም ተንደርድሮ መጣበት። +7 ወደ አውራው በግ ሲቀርብ አየሁት፤ በበጉም እጅግ ተመርሮ ነበር። በጉን መትቶ ሁለቱንም ቀንዶቹን ሰባበራቸው፤ አውራውም በግ ሊቋቋመው የሚችልበት አቅም አልነበረውም። በጉን መሬት ላይ ጥሎ ረጋገጠው፤ አውራ በጉንም ከእጁ የሚያስጥለው አልነበረም። +8 ከዚያም አውራው ፍየል እጅግ ታበየ፤ ሆኖም ኃያል በሆነ ጊዜ ትልቁ ቀንድ ተሰበረ፤ በምትኩም ጎልተው የሚታዩ አራት ቀንዶች ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በቀሉ።+ +9 ከእነሱ መካከል ከአንደኛው፣ አንድ ሌላ ትንሽ ቀንድ በቀለ፤ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና* ውብ ወደሆነችው ምድር*+ በጣም እያደገ ሄደ። +10 ወደ ሰማይ ሠራዊት እስከሚደርስ ድረስ እያደገ ሄደ፤ ከሠራዊቱና ከከዋክብቱ መካከልም የተወሰኑትን ወደ ምድር ጣለ፤ ��ጋገጣቸውም። +11 በሠራዊቱ አለቃ ላይ እንኳ ሳይቀር ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፤ የዘወትሩም መሥዋዕት ከአለቃው ተወሰደ፤ ጽኑ የሆነው የመቅደሱ ስፍራም ፈረሰ።+ +12 ከተፈጸመው በደል የተነሳ ሠራዊቱ ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋር ለቀንዱ አልፎ ተሰጠ፤ እውነትን ወደ ምድር ጣለ፤ እንደ ፈቃዱ አደረገ፤ ደግሞም ተሳካለት። +13 ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ፤ ሌላውም ቅዱስ እየተናገረ ለነበረው ቅዱስ እንዲህ አለው፦ “ስለ ዘወትሩ መሥዋዕትና ጥፋት ስለሚያመጣው በደል+ እንዲሁም ቅዱሱ ስፍራና ሠራዊቱ እንዲረገጡ ስለመተዋቸው በሚገልጸው ራእይ ላይ የታየው ነገር የሚቆየው እስከ መቼ ነው?” +"14 እሱም “2,300 ምሽቶችና ንጋቶች እስኪያልፉ ድረስ ነው፤ ቅዱሱም ስፍራ ወደ ትክክለኛው ሁኔታ በእርግጥ ይመለሳል” አለኝ። " +15 እኔ ዳንኤል ራእዩን እየተመለከትኩና ለመረዳት እየጣርኩ ሳለ፣ ሰው የሚመስል ድንገት ከፊት ለፊቴ ቆሞ አየሁ። +16 ከዚያም ከኡላይ+ መካከል የሰው ድምፅ ሰማሁ፤ እሱም ጮክ ብሎ “ገብርኤል፣+ ለዚህ ሰው ያየውን ነገር አስረዳው” አለ።+ +17 በመሆኑም እኔ ወደቆምኩበት ስፍራ ቀረበ፤ ሆኖም ወደ እኔ ሲመጣ፣ በጣም ከመደንገጤ የተነሳ በግንባሬ ተደፋሁ። እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ራእዩ የሚፈጸመው በዘመኑ ፍጻሜ መሆኑን ተረዳ” አለኝ።+ +18 እኔ ግን እያናገረኝ ሳለ መሬት ላይ በግንባሬ ተደፋሁ፤ ከባድ እንቅልፍም ወሰደኝ። ስለዚህ ዳሰሰኝና ቆሜበት በነበረው ቦታ እንድቆም አደረገኝ።+ +19 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ በቁጣው ዘመን ማብቂያ ላይ የሚሆነውን ነገር አሳውቅሃለሁ፤ ምክንያቱም ራእዩ በተወሰነው የፍጻሜ ዘመን ይፈጸማል።+ +20 “ያየኸው ሁለት ቀንዶች ያሉት አውራ በግ የሜዶንንና የፋርስን ነገሥታት ያመለክታል።+ +21 ፀጉራሙ አውራ ፍየል የግሪክን ንጉሥ ያመለክታል፤+ በዓይኖቹ መካከል ያለው ትልቁ ቀንድ የመጀመሪያውን ንጉሥ ያመለክታል።+ +22 ቀንዱ ተሰብሮ በምትኩ አራት ቀንዶች እንደወጡ ሁሉ+ ከእሱ ብሔር የሚነሱ አራት መንግሥታት ይኖራሉ፤ ሆኖም የእሱን ያህል ኃይል አይኖራቸውም። +23 “በዘመነ መንግሥታቸውም መገባደጃ ላይ በደለኞቹ እስከ መጨረሻ* በደል ሲፈጽሙ፣ ግራ የሚያጋቡ አባባሎችን የሚረዳ* አስፈሪ መልክ ያለው ንጉሥ ይነሳል። +24 ኃይሉ እጅግ ታላቅ ይሆናል፤ በገዛ ኃይሉ ግን አይደለም። ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጥፋት* ያደርሳል፤ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለታል። በኃያላን ሰዎችና በቅዱሳኑ ሕዝብ ላይ ጥፋት ያደርሳል።+ +25 መሠሪ ዘዴ ተጠቅሞ ብዙዎችን በማታለል ረገድ ይሳካለታል፤ በልቡም ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ሰዎች ተረጋግተው በሚኖሩበት ጊዜም* በብዙዎች ላይ ጥፋት ያደርሳል። አልፎ ተርፎም የልዑላን ልዑል በሆነው ላይ ይነሳል፤ ሆኖም የሰው እጅ ሳይነካው ይሰበራል። +26 “ምሽቶቹንና ንጋቶቹን በተመለከተ በራእይ የተነገረው ነገር እውነት ነው፤ አንተ ግን ራእዩን በሚስጥር ያዝ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ* የሚሆነውን ነገር የሚያመለክት ነውና።”+ +27 እኔም ዳንኤል ኃይሌ ተሟጠጠ፤ ለተወሰኑ ቀናትም ታመምኩ።+ ከዚያም ተነስቼ ለንጉሡ የማከናውነውን ሥራ መሥራት ጀመርኩ፤+ ሆኖም ባየሁት ነገር የተነሳ ደንዝዤ ነበር፤ ራእዩንም ማንም ሰው ሊረዳው አልቻለም።+ +11 “እኔም ሜዶናዊው ዳርዮስ+ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት፣ እሱን ለማበረታታትና ለማጠናከር* ቆሜ ነበር። +2 አሁን የምነግርህ ነገር እውነት ነው፦ “እነሆ፣ ሦስት ተጨማሪ ነገሥታት በፋርስ ምድር ይነሳሉ፤* አራተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይበልጥ ብዙ ሀብት ያከማቻል። በሀብቱም በበረታ ጊዜ፣ ሁሉንም ነገር በግሪክ መንግሥት ላይ ያስነሳል።+ +3 “አንድ ኃያል ንጉሥ ይነሳል፤ በታላቅ ኃ���ልም ይገዛል፤+ የፈለገውንም ያደርጋል። +4 ሆኖም በተነሳ ጊዜ መንግሥቱ ይፈራርሳል፤ ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት አቅጣጫ ይከፋፈላል፤+ ለልጆቹ* ግን አይተላለፍም፤ ግዛታቸው እንደ እሱ ግዛት አይሆንም፤ መንግሥቱ ይነቀላልና፤ ከእነሱም ለሌሎች ይተላለፋል። +5 “የደቡቡ ንጉሥ ይኸውም ከገዢዎቹ አንዱ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁንና አንዱ በእሱ ላይ ያይላል፤ ከዚያኛው የገዢነት ሥልጣንም በላቀ ኃይል ይገዛል። +6 “ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ኅብረት ይፈጥራሉ፤ የደቡቡ ንጉሥ ሴት ልጅ ስምምነት ለማድረግ ወደ ሰሜኑ ንጉሥ ትመጣለች። ሆኖም የክንዷ ኃይል አይጸናም፤ ደግሞም እሱም ሆነ ክንዱ አይጸናም፤ እሷም አልፋ ትሰጣለች፤ እሷና ያመጧት ሰዎች፣ የወለዳትና በዚያ ዘመን ብርቱ እንድትሆን ያደረጋት አልፈው ይሰጣሉ። +7 ከሥሮቿም ከሚበቅለው ቀንበጥ አንዱ በእሱ ቦታ ይነሳል፤ እሱም ወደ ሠራዊቱ ይመጣል፤ በሰሜኑ ንጉሥ ምሽግም ላይ ይዘምታል፤ በእነሱም ላይ እርምጃ ይወስዳል፤ ያሸንፋቸዋልም። +8 በተጨማሪም አማልክታቸውን፣ ከብረት የተሠሩ ምስሎቻቸውን፣* ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ጠቃሚ* ዕቃዎቻቸውንና ምርኮኞቹን ይዞ ወደ ግብፅ ይመጣል። ለተወሰኑ ዓመታት ከሰሜኑ ንጉሥ ርቆ ይቆማል፤ +9 የሰሜኑም ንጉሥ የደቡቡን ንጉሥ መንግሥት ይወርራል፤ ሆኖም ወደ ገዛ ምድሩ ይመለሳል። +10 “ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እጅግ ታላቅ ሠራዊትም ያሰባስባሉ። እሱ በእርግጥ ይገሰግሳል፤ እንደ ጎርፍም ምድሪቱን እያጥለቀለቀ ያልፋል። ሆኖም ይመለሳል፤ ወደ ምሽጉም እስከሚደርስ ድረስ ይዋጋል። +11 “የደቡቡም ንጉሥ በምሬት ተሞልቶ ይወጣል፤ ደግሞም ከእሱ ይኸውም ከሰሜኑ ንጉሥ ጋር ይዋጋል፤ ይሄኛውም ታላቅ ሠራዊት ያሰልፋል፤ ይሁንና ሠራዊቱ ለዚያኛው እጅ አልፎ ይሰጣል። +12 ሠራዊቱም ተጠራርጎ ይወሰዳል። ልቡም ይታበያል፤ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠፋል፤ ሆኖም ያገኘውን ጥሩ አጋጣሚ አይጠቀምበትም። +13 “የሰሜኑም ንጉሥ ይመለሳል፤ ከመጀመሪያውም የሚበልጥ ሠራዊት ያሰባስባል፤ ከተወሰነ ጊዜ ይኸውም ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ በሚገባ የታጠቀ ታላቅ ሠራዊት ይዞ ይመጣል። +14 በዚያ ዘመን ብዙዎች በደቡቡ ንጉሥ ላይ ይነሳሉ። “በሕዝብህ መካከል ያሉ ዓመፀኛ ሰዎች* ይነሳሉ፤ ደግሞም ራእይን ለመፈጸም ይጥራሉ፤ ሆኖም አይሳካላቸውም። +15 “የሰሜኑም ንጉሥ ይመጣል፤ የአፈር ቁልልም ይደለድላል፤ የተመሸገችንም ከተማ ይይዛል። የደቡቡ ክንዶችም ሆኑ* የተመረጡት ተዋጊዎቹ አይቋቋሙትም፤ ለመቋቋም የሚያስችል ኃይልም አይኖራቸውም። +16 በእሱ ላይ የሚመጣው እንደፈለገው ያደርጋል፤ በፊቱም የሚቆም አይኖርም። ውብ በሆነችው* ምድር+ ላይ ይቆማል፤ የማጥፋትም ኃይል ይኖረዋል። +17 የመንግሥቱን ወታደራዊ ኃይል በሙሉ አሰባስቦ ለመምጣት ፊቱን ያቀናል፤* ከእሱም ጋር ስምምነት ያደርጋል፤ እርምጃም ይወስዳል። የሴቶችንም ሴት ልጅ እንዲያጠፋ ይፈቀድለታል። እሷም አትጸናም፤ የእሱም ሆና አትቀጥልም። +18 እሱም ፊቱን ወደ ባሕር ዳርቻዎች በመመለስ ብዙ ቦታዎችን ይይዛል። አንድ አዛዥ ከእሱ የደረሰበትን ነቀፋ ያስቀራል፤ ከዚያ በኋላ የሚሰነዘርበት ነቀፋ ይቆማል። ነቀፋውንም በራሱ ላይ ይመልስበታል። +19 ከዚያም ፊቱን በገዛ ምድሩ ወደሚገኙት ምሽጎች ይመልሳል፤ ተሰናክሎም ይወድቃል፤ ደግሞም አይገኝም። +20 “በእሱም ቦታ የሚነሳው ዕፁብ ድንቅ በሆነው ግዛቱ የሚያልፍ አስገባሪ* ይልካል፤ ይሁንና በቁጣ ወይም በጦርነት ባይሆንም እንኳ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይሰበራል። +21 “በእሱም ቦታ የተናቀ* ሰው ይነሳል፤ እነሱም ንጉሣዊ ክብር አይሰጡትም፤ እሱም ሰዎች ተረጋግተው በሚኖሩበት ጊዜ* ይመጣል፤ መንግሥቱንም በብልጠት* ይይዛል። +22 የጎርፉም ክንዶች* በእሱ የተነሳ ተጠራርገው ይወሰዳሉ፤ ደግሞም ይሰበራሉ፤ የቃል ኪዳኑም+ መሪ+ ይሰበራል። +23 እነሱም ከእሱ ጋር በማበራቸው ማታለሉን ይቀጥላል፤ ደግሞም ይነሳል፤ በጥቂት ሕዝብ አማካኝነትም ኃያል ይሆናል። +24 ሰዎች ተረጋግተው በሚኖሩበት ጊዜ* ወደበለጸገው* የአውራጃው ክፍል ይገባል፤ አባቶቹና የአባቶቹ አባቶች ያላደረጉትን ነገር ያደርጋል። ብዝበዛን፣ ምርኮንና ንብረትን በሕዝቡ መካከል ያከፋፍላል፤ በተመሸጉት ቦታዎችም ላይ ሴራ ይጠነስሳል፤ ይህን የሚያደርገው ግን ለጊዜው ብቻ ነው። +25 “እሱም ታላቅ ሠራዊት አሰባስቦ ኃይሉንና ልቡን በደቡቡ ንጉሥ ላይ ያነሳሳል፤ የደቡቡም ንጉሥ እጅግ ታላቅና ኃያል የሆነ ሠራዊት አሰባስቦ ለጦርነቱ ይዘጋጃል። ሴራ ስለሚጠነስሱበትም መቋቋም አይችልም። +26 የእሱን ምርጥ ምግብ የሚበሉም ለውድቀት ይዳርጉታል። “ሠራዊቱ ተጠራርጎ* ይወሰዳል፤ ብዙዎችም ተገድለው ይወድቃሉ። +27 “እነዚህ ሁለት ነገሥታት ልባቸው መጥፎ ነገር ለመሥራት ይነሳሳል፤ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው እርስ በርስ ውሸት ይነጋገራሉ። ሆኖም ፍጻሜው እስከተወሰነው ጊዜ+ ድረስ ስለሚቆይ ምንም ነገር አይሳካላቸውም። +28 “እሱም በጣም ብዙ ንብረት ሰብስቦ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ ልቡም በቅዱሱ ቃል ኪዳን ላይ ይነሳል። እርምጃ ይወስዳል፤ ወደ አገሩም ይመለሳል። +29 “በተወሰነው ጊዜ ይመለሳል፤ በደቡቡ ላይም ይነሳል። በዚህ ጊዜ ግን ቀድሞ እንደነበረው አይሆንም፤ +30 የኪቲም+ መርከቦች በእሱ ላይ ይመጡበታልና፤ ይዋረዳልም። “ወደ ኋላ ይመለሳል፤ በቅዱሱ ቃል ኪዳንም ላይ የውግዘት ቃል* ይሰነዝራል፤+ እርምጃም ይወስዳል፤ ተመልሶም ትኩረቱን ቅዱስ ቃል ኪዳኑን በተዉት ላይ ያደርጋል። +31 ከእሱ የሚወጡ ክንዶች ይቆማሉ፤* እነሱም ምሽጉን ይኸውም መቅደሱን ያረክሳሉ፤+ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ።+ “ጥፋት የሚያመጣውንም ርኩስ ነገር በዚያ ያኖራሉ።+ +32 “ክፋት የሚሠሩትንና ቃል ኪዳኑን የሚያፈርሱትን በማታለል* ወደ ክህደት ጎዳና ይመራቸዋል። አምላካቸውን የሚያውቁት ሰዎች ግን ይበረታሉ፤ እርምጃም ይወስዳሉ። +33 በሕዝቡም መካከል ያሉ ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች+ ብዙዎች ማስተዋል እንዲኖራቸው ያደርጋሉ። እነሱም ለተወሰነ ጊዜ የሰይፍ፣ የእሳት፣ የምርኮና የብዝበዛ ሰለባ በመሆን ይወድቃሉ። +34 ሆኖም በሚወድቁበት ጊዜ መጠነኛ እርዳታ ያገኛሉ፤ ብዙዎችም አታላይ በሆነ አንደበት* ከእነሱ ጋር ይተባበራሉ። +35 እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ በእነሱ የተነሳ የማጥራት፣ የማጽዳትና የማንጻት ሥራ+ ይከናወን ዘንድ ጥልቅ ማስተዋል ካላቸው ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንዲወድቁ ይደረጋል፤ ምክንያቱም ይህ እስከተወሰነው ጊዜ ድረስ ይቆያል። +36 “ንጉሡ እንደፈለገው ያደርጋል፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ እጅግም ይኩራራል፤ በአማልክትም አምላክ+ ላይ አስደንጋጭ ነገር ይናገራል። ቁጣው እስኪፈጸም ድረስ ይሳካለታል፤ ምክንያቱም የተወሰነው ነገር መፈጸም አለበት። +37 ለአባቶቹ አምላክ ምንም ቦታ አይሰጥም፤ ደግሞም ለሴቶች ፍላጎትም ሆነ ለሌላ ለማንኛውም አምላክ ምንም ቦታ አይሰጥም፤ ራሱን ግን በሁሉም ላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል። +38 ይልቁንም* ለምሽጎች አምላክ ክብር ይሰጣል፤ አባቶቹም ለማያውቁት አምላክ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮችና ተፈላጊ* በሆኑ ነገሮች ክብር ይሰጣል። +39 ከባዕድ አምላክ ጋር ሆኖ* እጅግ ጠንካራ በሆኑት ምሽጎች ላይ እርምጃ ይወስዳል። ለእሱ እውቅና የሚሰጡትን ሁሉ* ከፍተኛ ክብር ያጎናጽፋቸዋል፤ ��ብዙዎችም መካከል እንዲገዙ ያደርጋል፤ ምድሩንም በዋጋ ያከፋፍላል።* +40 “በፍጻሜው ዘመን የደቡቡ ንጉሥ ከእሱ ጋር ይጋፋል፤* የሰሜኑም ንጉሥ ከሠረገሎች፣ ከፈረሰኞችና ከብዙ መርከቦች ጋር እንደ አውሎ ነፋስ ይመጣበታል፤ ወደ ብዙ አገሮችም ይገባል፤ እንደ ጎርፍም እያጥለቀለቀ ያልፋል። +41 ውብ* ወደሆነችውም ምድር+ ይገባል፤ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ። ሆኖም ኤዶም፣ ሞዓብና የአሞናውያን ዋነኛ ክፍል ከእጁ ያመልጣሉ። +42 እጁንም በብዙ አገሮች ላይ ይዘረጋል፤ የግብፅም ምድር አታመልጥም። +43 እሱም በተደበቁ ውድ ሀብቶች፣ በወርቅና በብር እንዲሁም በግብፅ የከበሩ* ነገሮች ሁሉ ላይ ይሠለጥናል። ሊቢያውያንና ኢትዮጵያውያንም ይከተሉታል። +44 “ሆኖም ከምሥራቅና* ከሰሜን የሚመጣ ወሬ ይረብሸዋል፤ እሱም ለማጥፋትና ብዙዎችን ለመደምሰስ በታላቅ ቁጣ ይወጣል። +45 ንጉሣዊ* ድንኳኖቹንም በታላቁ ባሕርና ቅዱስ በሆነው ውብ* ተራራ+ መካከል ይተክላል፤ እሱም ወደ ፍጻሜው ይመጣል፤ የሚረዳውም አይኖርም። +2 ናቡከደነጾር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልሞችን አለመ፤ መንፈሱም እጅግ ከመታወኩ የተነሳ+ እንቅልፍ ሊወስደው አልቻለም። +2 ስለዚህ ንጉሡ ሕልሞቹን እንዲነግሩት አስማተኞቹ ካህናት፣ ጠንቋዮቹ፣ መተተኞቹና ከለዳውያኑ* እንዲጠሩ አዘዘ። በዚህም መሠረት ገብተው በንጉሡ ፊት ቆሙ።+ +3 ከዚያም ንጉሡ “ሕልም አልሜ ነበር፤ ሕልሙ ምን እንደሆነ ማወቅ ስለፈለግኩ መንፈሴ ታውኳል” አላቸው። +4 ከለዳውያኑም በአረማይክ ቋንቋ*+ ለንጉሡ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ኑር። ያየኸውን ሕልም ለአገልጋዮችህ ንገረን፤ እኛም ትርጉሙን እናሳውቅሃለን።” +5 ንጉሡም ለከለዳውያኑ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የመጨረሻ ውሳኔዬ ይህ ነው፦ ሕልሙን ከነትርጉሙ የማታሳውቁኝ ከሆነ ሰውነታችሁ ይቆራረጣል፤ ቤቶቻችሁም የሕዝብ መጸዳጃ* ይሆናሉ። +6 ሕልሙንና ትርጉሙን ብታሳውቁኝ ግን ስጦታ፣ ሽልማትና ታላቅ ክብር እሰጣችኋለሁ።+ ስለዚህ ሕልሙንና ትርጉሙን አሳውቁኝ።” +7 እነሱም በድጋሚ መልሰው “ንጉሡ ሕልሙን ለአገልጋዮቹ ይንገረን፤ እኛም ትርጉሙን እንናገራለን” አሉት። +8 ንጉሡም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የመጨረሻ ውሳኔዬን ስላወቃችሁ ጊዜ ለማራዘም እየሞከራችሁ እንደሆነ በሚገባ ተረድቻለሁ። +9 ሕልሙን የማታሳውቁኝ ከሆነ ሁላችሁም የሚጠብቃችሁ ቅጣት አንድ ነው። እናንተ ግን ሁኔታው እስኪለወጥ ድረስ፣ የሆነ ውሸትና ማታለያ ልትነግሩኝ ተስማምታችኋል። ስለዚህ ሕልሙን ንገሩኝ፤ እኔም ትርጉሙን ልታብራሩ እንደምትችሉ በዚህ አውቃለሁ።” +10 ከለዳውያኑም ለንጉሡ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ንጉሡ የሚጠይቀውን ነገር መፈጸም የሚችል አንድም ሰው በምድር ላይ የለም፤ የትኛውም ታላቅ ንጉሥ ወይም ገዢ፣ ከማንኛውም አስማተኛ ካህን ወይም ጠንቋይ ወይም ከለዳዊ እንዲህ ዓይነት ነገር ጠይቆ አያውቅም። +11 ንጉሡ እየጠየቀ ያለው ነገር በጣም አስቸጋሪ ነው፤ በሰዎች መካከል* ከማይኖሩት አማልክት በስተቀር ይህን ለንጉሡ ሊገልጽለት የሚችል የለም።” +12 በዚህ ጊዜ ንጉሡ በቁጣ ቱግ አለ፤ በባቢሎን ያሉት ጥበበኛ ሰዎች ሁሉ እንዲገደሉም አዘዘ።+ +13 ትእዛዙ ሲወጣና ጠቢባኑ ሊገደሉ ሲሉ ዳንኤልንና ጓደኞቹንም ለመግደል ይፈልጓቸው ጀመር። +14 በዚህ ጊዜ ዳንኤል በባቢሎን የሚገኙትን ጥበበኛ ሰዎች ለመግደል የወጣውን የንጉሡን የክብር ዘብ አለቃ አርዮክን በጥበብና በዘዴ አናገረው። +15 የንጉሡ ባለሥልጣን የሆነውን አርዮክን “ንጉሡ እንዲህ ያለ ከባድ ትእዛዝ ያወጣው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። አርዮክም ጉዳዩን ለዳንኤል ገለጸለት።+ +16 ዳንኤልም ወደ ንጉሡ ገብቶ የሕልሙን ትርጉም ለእሱ የሚያስታውቅበት ጊዜ እንዲሰጠው ንጉሡን ጠየቀው። +17 ከዚያም ዳንኤል ወደ ቤቱ ሄደ፤ ጉዳዩንም ለጓደኞቹ ለሃናንያህ፣ ለሚሳኤልና ለአዛርያስ ነገራቸው። +18 ደግሞም ዳንኤልንና ጓደኞቹን ከቀሩት የባቢሎን ጠቢባን ጋር እንዳይገድሏቸው የሰማይ አምላክ ምሕረት እንዲያሳያቸውና ሚስጥሩን እንዲገልጥላቸው ይጸልዩ ዘንድ ነገራቸው። +19 ከዚያም ሚስጥሩ በሌሊት ለዳንኤል በራእይ ተገለጠለት።+ በመሆኑም ዳንኤል የሰማይን አምላክ አወደሰ። +20 ዳንኤልም እንዲህ አለ፦ “የአምላክ ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ፤ጥበብና ኃይል የእሱ ብቻ ነውና።+ +21 እሱ ጊዜያትንና ወቅቶችን ይለውጣል፤+ነገሥታትን ያስወግዳል፤ ደግሞም ያስቀምጣል፤+ለጥበበኞች ጥበብን፣ ለአስተዋዮችም እውቀትን ይሰጣል።+ +22 ጥልቅ የሆኑትንና የተሰወሩትን ነገሮች ይገልጣል፤+በጨለማ ውስጥ ያለውን ያውቃል፤+ብርሃንም ከእሱ ጋር ይኖራል።+ +23 የአባቶቼ አምላክ ሆይ፣ ለአንተ ምስጋናና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ምክንያቱም ጥበብንና ኃይልን ሰጥተኸኛል። አሁን ደግሞ ከአንተ የጠየቅነውን ነገር አሳውቀኸኛል፤ንጉሡ ያሳሰበውን ጉዳይ አሳውቀኸናል።”+ +24 ከዚያም ዳንኤል የባቢሎንን ጠቢባን እንዲያጠፋ ንጉሡ ወደ ሾመው ወደ አርዮክ ሄዶ+ “ከባቢሎን ጠቢባን መካከል አንዳቸውንም አትግደል። በንጉሡ ፊት አቅርበኝ፤ እኔም የሕልሙን ትርጉም ለንጉሡ አሳውቃለሁ” አለው። +25 አርዮክም ዳንኤልን ወዲያውኑ በንጉሡ ፊት አቅርቦ “ከይሁዳ ግዞተኞች መካከል የሕልሙን ትርጉም ለንጉሡ ማሳወቅ የሚችል ሰው አግኝቻለሁ”+ አለው። +26 ንጉሡም ብልጣሶር የተባለውን ዳንኤልን+ “ያየሁትን ሕልምና ትርጉሙን በእርግጥ ልትነግረኝ ትችላለህ?” አለው።+ +27 ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ከጠቢባኑ፣ ከጠንቋዮቹ፣ አስማተኛ ከሆኑት ካህናት ወይም ከኮከብ ቆጣሪዎቹ መካከል ንጉሡ የጠየቀውን ሚስጥር መግለጥ የሚችል የለም።+ +28 ይሁንና ሚስጥርን የሚገልጥ አምላክ በሰማያት አለ፤+ እሱም በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚሆነውን ነገር ለንጉሥ ናቡከደነጾር አሳውቆታል። በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለህ ያየኸው ሕልምና የተመለከትካቸው ራእዮች እነዚህ ናቸው፦ +29 “ንጉሥ ሆይ፣ በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለ ወደፊት የሚሆነውን ነገር ታስብ ነበር፤ ሚስጥርን የሚገልጠውም አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ነገር አሳውቆሃል። +30 ይህ ሚስጥር ለእኔ የተገለጠልኝ ከሰው ሁሉ የላቀ ጥበብ ስላለኝ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በልብህ ታስባቸው የነበሩትን ነገሮች ታውቅ ዘንድ የሕልሙ ትርጉም ለንጉሡ እንዲገለጥ ነው።+ +31 “ንጉሥ ሆይ፣ በትኩረት እየተመለከትክ ሳለ አንድ ግዙፍ ምስል* አየህ። ግዙፍ የሆነውና እጅግ የሚያብረቀርቀው ይህ ምስል በፊትህ ቆሞ ነበር፤ መልኩም በጣም የሚያስፈራ ነበር። +32 የምስሉ ራስ ከጥሩ ወርቅ፣+ ደረቱና ክንዶቹ ከብር፣+ ሆዱና ጭኖቹ ከመዳብ፣+ +33 ቅልጥሞቹ ከብረት የተሠሩ+ ሲሆን እግሮቹ ከፊሉ ብረት፣ ከፊሉ ደግሞ ሸክላ* ነበሩ።+ +34 አንተም አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትን የምስሉን እግሮች ሲመታቸውና ሲያደቅቃቸው አየህ።+ +35 በዚህ ጊዜ ብረቱ፣ ሸክላው፣ መዳቡ፣ ብሩና ወርቁ ሁሉም በአንድነት ተሰባበሩ፤ በበጋ ወቅት በአውድማ ላይ እንደሚቀር ገለባም ሆኑ፤ ነፋስም አንዳች ሳያስቀር ጠራርጎ ወሰዳቸው። ምስሉን የመታው ድንጋይ ግን ትልቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሁሉ ሞላ። +36 “ሕልሙ ይህ ነው፤ አሁን ደግሞ ትርጉሙን ለንጉሡ እናሳውቃለን። +37 ንጉሥ ሆይ፣ አንተ የነገሥታት ንጉሥ ነህ፤ የሰማይ አምላክ መንግሥትን፣ ኃይልን፣ ብርታትንና ክብርን ሰ���ቶሃል፤+ +38 ደግሞም በየትኛውም ቦታ የሚኖሩትን ሰዎችም ሆነ የዱር እንስሳትና የሰማይ ወፎች በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶሃል፤ በሁሉም ላይ ገዢ አድርጎሃል፤+ የወርቁ ራስ አንተ ራስህ ነህ።+ +39 “ይሁንና ከአንተ በኋላ፣ ከአንተ ያነሰ ሌላ መንግሥት ይነሳል፤+ ከዚያም መላውን ምድር የሚገዛ ሌላ ሦስተኛ የመዳብ መንግሥት ይነሳል።+ +40 “አራተኛው መንግሥት ደግሞ እንደ ብረት የጠነከረ ይሆናል።+ ብረት ሁሉንም ነገር እንደሚሰባብርና እንደሚፈጭ ሁሉ፣ እሱም እንደሚያደቅ ብረት እነዚህን መንግሥታት ሁሉ ይሰባብራቸዋል፤ ደግሞም ያደቅቃቸዋል።+ +41 “እግሮቹና ጣቶቹ ከፊሉ ሸክላ፣ ከፊሉ ደግሞ ብረት ሆነው እንዳየህ ሁሉ መንግሥቱም የተከፋፈለ ይሆናል፤ ሆኖም ብረቱና የሸክላ ጭቃው ተደባልቆ እንዳየህ ሁሉ በተወሰነ መጠን የብረት ጥንካሬ ይኖረዋል። +42 የእግሮቹ ጣቶች ከፊሉ ብረት፣ ከፊሉ ሸክላ እንደሆኑ ሁሉ ይህም መንግሥት በከፊል ብርቱ፣ በከፊል ደግሞ ደካማ ይሆናል። +43 ብረቱና የሸክላ ጭቃው ተደባልቀው እንዳየህ ሁሉ እነሱም ከሕዝቡ* ጋር ይደባለቃሉ፤ ሆኖም ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይዋሃድ ሁሉ እነሱም አንዱ ከሌላው ጋር አይጣበቁም። +44 “በእነዚያ ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋ+ መንግሥት ያቋቁማል።+ ይህም መንግሥት ለሌላ ሕዝብ አይሰጥም።+ እነዚህን መንግሥታት ሁሉ ያደቅቃል፤ ፈጽሞም ያጠፋቸዋል፤+ እሱም ብቻውን ለዘላለም ይቆማል፤+ +45 አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ብረቱን፣ መዳቡን፣ ሸክላውን፣ ብሩንና ወርቁን ሲያደቅ እንዳየህ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።+ ታላቁ አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ነገር ለንጉሡ አሳውቆታል።+ ሕልሙ እውነት፣ ትርጉሙም አስተማማኝ ነው።” +46 ከዚያም ንጉሥ ናቡከደነጾር በዳንኤል ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ዳንኤልንም እጅግ አከበረው። ደግሞም ስጦታና ዕጣን እንዲቀርብለት አዘዘ። +47 ንጉሡም ዳንኤልን እንዲህ አለው፦ “በእርግጥም አምላካችሁ የአማልክት አምላክና የነገሥታት ጌታ እንዲሁም ሚስጥርን የሚገልጥ ነው፤ ምክንያቱም አንተ ይህን ሚስጥር መግለጥ ችለሃል።”+ +48 ከዚያም ንጉሡ ዳንኤልን ከፍ ከፍ አደረገው፤ ብዙ የከበሩ ስጦታዎችም ሰጠው፤ የመላው ባቢሎን አውራጃ ገዢና የባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ዋና አስተዳዳሪ አደረገው።+ +49 ዳንኤልም ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ንጉሡ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን+ በባቢሎን አውራጃ አስተዳዳሪዎች አድርጎ ሾማቸው፤ ዳንኤል ግን በንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ያገለግል ነበር። +4 “ከንጉሥ ናቡከደነጾር፣ በመላው ምድር ለሚኖሩ ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች ለተውጣጡ ሕዝቦች፦ ሰላም ይብዛላችሁ! +2 ልዑሉ አምላክ ለእኔ ያደረጋቸውን ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ሥራዎች ስነግራችሁ ደስ ይለኛል። +3 ተአምራዊ ምልክቱ እንዴት ታላቅ ነው! ድንቅ ሥራውም በዓይነቱ ልዩ ነው! መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፤ የመግዛት ሥልጣኑም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዘልቃል።+ +4 “እኔ ናቡከደነጾር በቤቴ ዘና ብዬ፣ በቤተ መንግሥቴም ደልቶኝ እኖር ነበር። +5 አንድ አስፈሪ ሕልም አየሁ። በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ ወደ አእምሮዬ ይመጡ የነበሩት ምስሎችና ራእዮች አስፈሩኝ።+ +6 ስለዚህ ያየሁትን ሕልም ትርጉም እንዲያሳውቁኝ የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ በፊቴ እንዲያቀርቧቸው አዘዝኩ።+ +7 “በዚህ ጊዜ አስማተኞቹ ካህናት፣ ጠንቋዮቹ፣ ከለዳውያኑና* ኮከብ ቆጣሪዎቹ+ ገቡ። ያየሁትን ሕልም ስነግራቸው ትርጉሙን ሊያሳውቁኝ አልቻሉም።+ +8 በመጨረሻም በአምላኬ ስም+ ብልጣሶር ተብሎ የተጠራውና+ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ዳንኤል በፊቴ ቀረበ፤+ እኔም ያየሁትን ��ልም ነገርኩት፦ +9 “‘የአስማተኛ ካህናት አለቃ የሆንከው ብልጣሶር ሆይ፣+ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ውስጥ እንዳለና+ ለመግለጥ የሚያስቸግርህ ምንም ዓይነት ሚስጥር እንደሌለ በሚገባ አውቃለሁ።+ በመሆኑም በሕልሜ ያየኋቸውን ራእዮችና ትርጉማቸውን ግለጽልኝ። +10 “‘በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ ባየኋቸው ራእዮች ላይ፣ በምድር መካከል ቁመቱ እጅግ ረጅም የሆነ አንድ ዛፍ+ ቆሞ ተመለከትኩ።+ +11 ዛፉም አድጎ ጠንካራ ሆነ፤ ጫፉም እስከ ሰማያት ደረሰ፤ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ይታይ ነበር። +12 ቅጠሉ ያማረ፣ ፍሬውም በጣም ብዙ ሲሆን ዛፉ ላይ ለሁሉ የሚሆን መብል ነበር። የዱር እንስሳት በጥላው ሥር ያርፉ፣ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎቹ ላይ ይቀመጡ ነበር፤ ፍጥረታትም ሁሉ ከእሱ ይመገቡ ነበር።* +13 “‘በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ራእዮቹን ስመለከት ቅዱስ የሆነ አንድ ጠባቂ ከሰማያት ሲወርድ አየሁ።+ +14 እሱም ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “ዛፉን ቁረጡ፤+ ቅርንጫፎቹን ጨፍጭፉ፤ ቅጠሎቹን አራግፉ፤ ፍሬውንም በትኑ! የዱር እንስሳቱ ከሥሩ፣ ወፎቹም ከቅርንጫፎቹ ላይ ይሽሹ። +15 ጉቶው ግን በብረትና በመዳብ ታስሮ በሜዳ ሣር መካከል ከነሥሩ መሬት ውስጥ ይቆይ። በሰማያትም ጠል ይረስርስ፤ ዕጣ ፋንታውም በምድር ተክሎች መካከል ከአራዊት ጋር ይሁን።+ +16 ልቡ ከሰው ልብ ይለወጥ፤ የአውሬም ልብ ይሰጠው፤ ሰባት ዘመናትም+ ይለፉበት።+ +17 ይህ ነገር በጠባቂዎች ታውጇል፤+ የፍርድ ውሳኔውም በቅዱሳኑ ተነግሯል፤ ይህም ልዑሉ አምላክ በሰው ልጆች መንግሥት ላይ እንደሚገዛ+ እንዲሁም መንግሥቱን ለወደደው እንደሚሰጥና ከሰዎች ሁሉ የተናቀውን እንደሚሾምበት በሕይወት ያሉ ሁሉ ያውቁ ዘንድ ነው።” +18 “‘እኔ ንጉሥ ናቡከደነጾር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አሁንም ብልጣሶር ሆይ፣ በመንግሥቴ ውስጥ የሚኖሩት ሌሎቹ ጠቢባን ሁሉ ትርጉሙን ሊያሳውቁኝ ስላልቻሉ አንተ ትርጉሙን ንገረኝ።+ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ትርጉሙን ልታሳውቀኝ ትችላለህ።’ +19 “በዚህ ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል+ ለጥቂት ጊዜ በድንጋጤ ተዋጠ፤ ወደ አእምሮው የመጣው ሐሳብም በጣም አስፈራው። “ንጉሡም ‘ብልጣሶር ሆይ፣ ሕልሙና ትርጉሙ አያስፈራህ’ አለው። “ብልጣሶርም መልሶ እንዲህ አለው፦ ‘ጌታዬ ሆይ፣ ሕልሙ ለሚጠሉህ፣ ትርጉሙም ለጠላቶችህ ይሁን። +20 “‘አንተ ያየኸው ዛፍ ይኸውም በጣም ያደገውና የጠነከረው፣ ጫፉ እስከ ሰማያት የደረሰውና ከየትኛውም የምድር ክፍል የሚታየው፣+ +21 ቅጠሉ ያማረውና ፍሬው የበዛው፣ ለሁሉም የሚሆን መብል ያለበት፣ የዱር እንስሳት መጠለያ የሆነውና በቅርንጫፎቹ ላይ የሰማይ ወፎች የሚኖሩበት ዛፍ፣+ +22 ንጉሥ ሆይ፣ አንተ ነህ፤ ምክንያቱም አንተ ታላቅና ብርቱ ሆነሃል፤ ታላቅነትህ ገንኖ እስከ ሰማያት ደርሷል፤+ ግዛትህም እስከ ምድር ዳርቻ ተንሰራፍቷል።+ +23 “‘ንጉሡም አንድ ቅዱስ ጠባቂ+ “ዛፉን ቆርጣችሁ አጥፉት፤ ጉቶው ግን በብረትና በመዳብ ታስሮ በሜዳ ሣር መካከል ከነሥሩ መሬት ውስጥ ይቆይ። በሰማያትም ጠል ይረስርስ፤ ሰባት ዘመናትም እስኪያልፉበት ድረስ ዕጣ ፋንታው ከዱር አራዊት ጋር ይሁን” እያለ ከሰማያት ሲወርድ አይቷል።+ +24 ንጉሥ ሆይ፣ ትርጉሙ ይህ ነው፤ ልዑሉ አምላክ በጌታዬ በንጉሡ ላይ ይደርሳል ብሎ ያወጀው ነገር ይህ ነው። +25 ከሰዎች መካከል ትሰደዳለህ፤ ከዱር አራዊትም ጋር ትኖራለህ፤ እንደ በሬም ሣር ትበላለህ፤ በሰማያትም ጠል ትረሰርሳለህ፤+ ልዑሉ አምላክ በሰው ልጆች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና መንግሥቱንም ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ+ ሰባት ዘመናት+ ያልፉብሃል።+ +26 “‘ይሁንና የዛፉን ጉቶ ከነሥሩ እንዲተዉት+ ስለተነገራቸው፣ አምላክ በሰማያት እንደሚገዛ ካወቅክ በኋላ መንግሥትህ ይመለስልሃል። +27 ስለዚህ ንጉሥ ሆይ፣ ምክሬ በአንተ ዘንድ ተቀባይነት ያግኝ። ኃጢአት መሥራትህን ትተህ ትክክል የሆነውን አድርግ፤ ግፍ መፈጸምህን ትተህ ለድሆች ምሕረት አሳይ። ምናልባት የተደላደለ ሕይወት የምትኖርበት ዘመን ይራዘምልህ ይሆናል።’”+ +28 ይህ ሁሉ በንጉሥ ናቡከደነጾር ላይ ደረሰ። +29 ከ12 ወራት በኋላ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ሰገነት ላይ እየተመላለሰ ነበር። +30 ንጉሡም “ይህች፣ ንጉሣዊ መኖሪያ እንድትሆን ለግርማዬ ክብር፣ በገዛ ብርታቴና ኃይሌ የገነባኋት ታላቂቱ ባቢሎን አይደለችም?” አለ። +31 ንጉሡ ንግግሩን ገና ከአፉ ሳይጨርስ እንዲህ የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ፦ “ንጉሥ ናቡከደነጾር ሆይ፣ የተላከልህ መልእክት ይህ ነው፦ ‘መንግሥትህ ከአንተ ተወስዷል፤+ +32 ከሰዎች መካከል ትሰደዳለህ። ከዱር አራዊት ጋር ትኖራለህ፤ እንደ በሬም ሣር ትበላለህ፤ ልዑሉ አምላክ በሰው ልጆች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና መንግሥቱንም ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዘመናት ያልፉብሃል።’”+ +33 ወዲያውኑ ይህ ቃል በናቡከደነጾር ላይ ተፈጸመ። ከሰው ልጆች መካከል ተሰደደ፤ እንደ በሬም ሣር መብላት ጀመረ፤ ፀጉሩ እንደ ንስር ላባ እስኪረዝም፣ ጥፍሮቹም እንደ ወፍ ጥፍሮች እስኪያድጉ ድረስ ሰውነቱ በሰማያት ጠል ረሰረሰ።+ +34 “ዘመኑ በተፈጸመ ጊዜ+ እኔ ናቡከደነጾር ወደ ሰማያት ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑሉንም አምላክ አመሰገንኩ፤ ለዘላለም የሚኖረውንም አወደስኩ፤ አከበርኩትም፤ ምክንያቱም የመግዛት ሥልጣኑ ዘላለማዊ ነው፤ መንግሥቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።+ +35 የምድር ነዋሪዎች ሁሉ እንደ ኢምንት ይቆጠራሉ፤ በሰማያት ሠራዊትና በምድር ነዋሪዎች ላይ እንደ ፈቃዱ ያደርጋል። ሊያግደው* ወይም ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ብሎ ሊጠይቀው የሚችል ማንም የለም።+ +36 “በዚህ ጊዜ አእምሮዬ ተመለሰልኝ፤ ደግሞም የመንግሥቴ ክብር፣ ግርማዊነቴና ሞገሴ ተመለሰልኝ።+ ከፍተኛ ባለሥልጣናቴና መኳንንቴ አጥብቀው ፈለጉኝ፤ እኔም ወደ መንግሥቴ ተመለስኩ፤ ከቀድሞውም የበለጠ ታላቅ ሆንኩ። +37 “አሁንም እኔ ናቡከደነጾር የሰማያትን ንጉሥ አወድሰዋለሁ፣ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ እንዲሁም አከብረዋለሁ፤+ ምክንያቱም ሥራው ሁሉ እውነት፣ መንገዶቹም ትክክል ናቸው፤+ በኩራት የሚመላለሱትንም ማዋረድ ይችላል።”+ +6 ዳርዮስ በመላው ንጉሣዊ ግዛቱ ላይ 120 የአውራጃ ገዢዎችን ለመሾም ወሰነ።+ +2 በእነሱ ላይ ሦስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሾመ፤ ከእነዚህም አንዱ ዳንኤል ነበር፤+ ንጉሡ ለኪሳራ እንዳይዳረግ እነዚህ የአውራጃ ገዢዎች+ ተጠሪነታቸው ለባለሥልጣናቱ እንዲሆን ተደረገ። +3 ዳንኤልም በዓይነቱ ልዩ የሆነ መንፈስ ስለነበረው ከከፍተኛ ባለሥልጣናቱና ከአውራጃ ገዢዎቹ ይበልጥ ብቃት እንዳለው አስመሠከረ፤+ ንጉሡም በመላው ንጉሣዊ ግዛቱ ላይ ከፍ ያለ ቦታ ሊሰጠው አሰበ። +4 በዚህ ጊዜ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱና የአውራጃ ገዢዎቹ ከመንግሥት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ዳንኤልን ለመክሰስ የሚያስችል ሰበብ ለማግኘት ይከታተሉት ነበር፤ ሆኖም ዳንኤል እምነት የሚጣልበት ስለነበርና ምንም ዓይነት እንከንና ጉድለት ስላልነበረበት በእሱ ላይ አንዳች ሰበብ ወይም ጉድለት ሊያገኙ አልቻሉም። +5 በመሆኑም “ከአምላኩ ሕግ ጋር በተያያዘ ካልሆነ በቀር ዳንኤልን ለመክሰስ ምንም ዓይነት ሰበብ ልናገኝ አንችልም” አሉ።+ +6 ስለዚህ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱና የአውራጃ ገዢዎቹ ተሰብስበው ወደ ንጉሡ በመግባት እንዲህ አሉት፦ “ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ፣ ለዘላ��ም ኑር። +7 ንጉሥ ሆይ፣ ለ30 ቀናት ያህል ለአንተ ካልሆነ በስተቀር ለአምላክም ሆነ ለሰው ልመና የሚያቀርብ ማንኛውም ግለሰብ ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲወረወር+ የሚያዝዝ ንጉሣዊ ድንጋጌ እንዲወጣና እገዳ እንዲጣል የመንግሥት ባለሥልጣናቱ፣ አስተዳዳሪዎቹ፣ የአውራጃ ገዢዎቹ፣ የንጉሡ አማካሪዎችና አገረ ገዢዎቹ ሁሉ +8 አሁንም ንጉሥ ሆይ፣ ሊሻር በማይችለው የሜዶናውያንና የፋርሳውያን ሕግ+ መሠረት ድንጋጌው እንዳይለወጥ አጽናው፤ በጽሑፉም ላይ ፈርምበት።”+ +9 ስለዚህ ንጉሥ ዳርዮስ እገዳውን በያዘው ድንጋጌ ላይ ፈረመ። +10 ዳንኤል ግን ድንጋጌው በፊርማ መጽደቁን እንዳወቀ ወደ ቤቱ ገባ፤ በሰገነት ላይ ባለው ክፍሉ ውስጥ በኢየሩሳሌም አቅጣጫ ያሉት መስኮቶች ተከፍተው ነበር።+ ከዚህ በፊት አዘውትሮ ያደርግ እንደነበረውም በቀን ሦስት ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ ጸለየ፤ ለአምላኩም ውዳሴ አቀረበ። +11 ሰዎቹ በሩን በርግደው በገቡ ጊዜ ዳንኤል በአምላኩ ፊት ሞገስ ለማግኘት ልመና ሲያቀርብና ሲማጸን አገኙት። +12 በመሆኑም ወደ ንጉሡ ቀርበው “ንጉሥ ሆይ፣ ለ30 ቀናት ያህል ለአንተ ካልሆነ በስተቀር ለአምላክም ሆነ ለሰው ልመና የሚያቀርብ ማንኛውም ግለሰብ ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲወረወር የሚደነግገውን እገዳ በፊርማህ አጽድቀህ አልነበረም?” በማለት ንጉሡ የጣለውን እገዳ አስታወሱት። ንጉሡም “ጉዳዩ ሊሻር በማ +13 እነሱም ቀበል አድርገው ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ንጉሥ ሆይ፣ ከይሁዳ ግዞተኞች አንዱ የሆነው ዳንኤል፣+ ለአንተም ሆነ በፊርማህ ላጸደቅከው እገዳ አክብሮት የለውም፤ ይልቁንም በቀን ሦስት ጊዜ ይጸልያል።”+ +14 ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተጨነቀ፤ ዳንኤልንም መታደግ የሚችልበትን መንገድ ያወጣና ያወርድ ጀመር፤ ፀሐይ እስክትጠልቅም ድረስ እሱን ለማዳን የተቻለውን ሁሉ ጥረት ሲያደርግ ቆየ። +15 በመጨረሻም እነዚህ ሰዎች አንድ ላይ ሆነው ወደ ንጉሡ በመግባት ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ንጉሥ ሆይ፣ በሜዶናውያንና በፋርሳውያን ሕግ መሠረት ንጉሡ ያጸናው ማንኛውም እገዳ ወይም ድንጋጌ ሊለወጥ እንደማይችል አትርሳ።”+ +16 ስለዚህ ንጉሡ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ እነሱም ዳንኤልን አምጥተው አንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት።+ ንጉሡም ዳንኤልን “ሁልጊዜ የምታገለግለው አምላክህ ይታደግሃል” አለው። +17 ከዚያም ድንጋይ አምጥተው በጉድጓዱ አፍ* ላይ ገጠሙት፤ ንጉሡም በዳንኤል ላይ የተወሰደው እርምጃ እንዳይለወጥ፣ በራሱ የማኅተም ቀለበትና በመኳንንቱ የማኅተም ቀለበት በድንጋዩ ላይ አተመበት። +18 ከዚያም ንጉሡ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሄደ። ጾሙንም አደረ፤ በምንም ነገር መዝናናት አልፈለገም፤* እንቅልፍም በዓይኑ አልዞረም።* +19 በመጨረሻም ንጉሡ ገና ጎህ ሲቀድ ተነስቶ እየተጣደፈ ወደ አንበሶቹ ጉድጓድ ሄደ። +20 ወደ ጉድጓዱ በቀረበ ጊዜ ሐዘን በተቀላቀለበት ድምፅ ጮክ ብሎ ዳንኤልን ተጣራ። ንጉሡም ዳንኤልን “የሕያው አምላክ አገልጋይ ዳንኤል ሆይ፣ ሁልጊዜ የምታገለግለው አምላክህ ከአንበሶቹ ሊታደግህ ችሏል?” አለው። +21 ዳንኤልም ንጉሡን እንዲህ አለው፦ “ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ኑር። +22 አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤+ እነሱም አልጎዱኝም፤+ በፊቱ ንጹሕ ሆኜ ተገኝቻለሁና፤ ንጉሥ ሆይ፣ በአንተም ላይ የሠራሁት በደል የለም።” +23 ንጉሡ እጅግ ተደሰተ፤ ዳንኤልንም ከጉድጓዱ እንዲያወጡት አዘዘ። እነሱም ከጉድጓዱ አወጡት፤ ዳንኤል በአምላኩ ታምኖ ስለነበር ምንም ጉዳት አልደረሰበትም።+ +24 ከዚያም በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት፣ የዳንኤልን ከሳሾች* አምጥተው ከነልጆቻቸውና ከነሚስቶቻቸው ወደ አንበሶቹ ጉድጓድ ጣሏቸው። ገና ወደ ጉድጓዱ መጨረሻ ሳይደርሱ አንበሶቹ ተቀራመቷቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ አደቀቁ።+ +25 ከዚያም ንጉሥ ዳርዮስ በመላው ምድር ለሚኖሩ ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች ለተውጣጡ ሕዝቦች ሁሉ እንዲህ ሲል ጻፈ፦+ “ሰላም ይብዛላችሁ! +26 በየትኛውም የመንግሥቴ ግዛት የሚኖሩ ሰዎች የዳንኤልን አምላክ ፈርተው እንዲንቀጠቀጡ ትእዛዝ አስተላልፌአለሁ።+ እሱ ለዘላለም የሚኖር ሕያው አምላክ ነውና። መንግሥቱ ፈጽሞ አይጠፋም፤ የመግዛት ሥልጣኑም* ዘላለማዊ ነው።+ +27 እሱ ይታደጋል፤+ ደግሞም ያድናል፤ በሰማያትና በምድርም ተአምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን ያደርጋል፤+ ዳንኤልን ከአንበሶች መዳፍ ታድጎታልና።” +28 ስለዚህ ዳንኤል በዳርዮስ+ መንግሥት እንዲሁም በፋርሳዊው በቂሮስ+ መንግሥት ሁሉ ነገር ተሳካለት። +10 የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ+ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ተብሎ የተጠራው ዳንኤል+ አንድ ራእይ ተሰጠው፤ ይህም መልእክት እውነት ነው፤ መልእክቱም ስለ አንድ ታላቅ ውጊያ ይገልጻል። እሱም መልእክቱን ተረድቶት ነበር፤ ያየውንም ነገር ማስተዋል ችሎ ነበር። +2 በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ በሐዘን ላይ ነበርኩ።+ +3 ሦስቱ ሳምንታት እስኪያበቁ ድረስ ምርጥ ምግብ አልበላሁም፤ ሥጋም ሆነ የወይን ጠጅ አልቀመስኩም እንዲሁም ሰውነቴን ቅባት አልተቀባሁም። +4 በመጀመሪያው ወር በ24ኛው ቀን በታላቁ ወንዝ ይኸውም በጤግሮስ*+ ዳርቻ ሳለሁ፣ +5 ቀና ብዬ ስመለከት በፍታ የለበሰና+ ወገቡ ላይ በዑፋዝ ወርቅ የተሠራ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ። +6 ሰውነቱ እንደ ክርስቲሎቤ፣+ ፊቱ እንደ መብረቅ፣ ዓይኖቹ እንደሚንቦገቦግ ችቦ፣ ክንዶቹና እግሮቹ እንደሚያብረቀርቅ መዳብ፣+ ድምፁም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበር። +7 ራእዩን ያየሁት እኔ ዳንኤል ብቻ ነበርኩ፤ ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች ግን ራእዩን አላዩም።+ ነገር ግን እጅግ ስለተሸበሩ ሸሽተው ተደበቁ። +8 እኔም ብቻዬን ቀረሁ፤ ይህን ታላቅ ራእይ በተመለከትኩ ጊዜም በውስጤ ምንም ኃይል አልቀረም፤ ግርማ ሞገስ የተላበሰው ቁመናዬ ተለወጠ፤ ኃይሌም በሙሉ ተሟጠጠ።+ +9 ከዚያም ሲናገር ድምፁን ሰማሁ፤ ሆኖም ሲናገር እየሰማሁት ሳለ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፍቼ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ።+ +10 በዚህ ጊዜ አንድ እጅ ዳሰሰኝ፤+ ከቀሰቀሰኝ በኋላ በእጄና በጉልበቴ ተደግፌ እንድነሳ አደረገኝ። +11 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “እጅግ የተወደድክ*+ ዳንኤል ሆይ፣ የምነግርህን ቃል አስተውል። በነበርክበት ቦታ ላይ ቁም፤ ወደ አንተ ተልኬ መጥቼአለሁና።” ይህን ሲለኝ እየተንቀጠቀጥኩ ቆምኩ። +12 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ፣ አትፍራ።+ እነዚህን ነገሮች ለመረዳት ልባዊ ጥረት ማድረግና በአምላክህ ፊት ራስህን ዝቅ ማድረግ ከጀመርክበት ቀን አንስቶ ቃልህ ተሰምቷል፤ እኔም የመጣሁት ከቃልህ የተነሳ ነው።+ +13 ሆኖም የፋርስ ንጉሣዊ ግዛት አለቃ+ ለ21 ቀናት ተቋቋመኝ። በኋላ ግን ከዋነኞቹ አለቆች* አንዱ የሆነው ሚካኤል*+ ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም በዚያን ጊዜ ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ቆየሁ። +14 ራእዩ ከብዙ ዘመን በኋላ የሚፈጸም ስለሆነ+ በዘመኑ መጨረሻ በሕዝብህ ላይ የሚደርሰውን ነገር አስረዳህ ዘንድ መጥቻለሁ።”+ +15 ይህን ቃል በነገረኝ ጊዜ ወደ መሬት አቀረቀርኩ፤ መናገርም ተሳነኝ። +16 በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤+ እኔም አፌን ከፍቼ በፊቴ ቆሞ የነበረውን እንዲህ አልኩት፦ “ጌታዬ ሆይ፣ ከራእዩ የተነሳ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፤ ኃይሌም ተሟጥጧል።+ +17 ስለዚህ የጌታዬ አገልጋይ ከጌታዬ ጋር እንዴት መነጋገር ይችላል?+ አሁን ምንም ኃይል የለኝምና፤ በውስጤም የቀረ እስትንፋስ የለም።”+ +18 ሰው የሚመስለው እንደገና ዳሰሰኝ፤ አበረታኝም።+ +19 ከዚያም “አንተ እጅግ የተወደድክ* ሰው+ ሆይ፣ አትፍራ።+ ሰላም ለአንተ ይሁን።+ በርታ፣ አይዞህ በርታ” አለኝ። እንዲህ ባለኝ ጊዜ ተበረታትቼ “ጌታዬ ሆይ፣ ብርታት ሰጥተኸኛልና ተናገር” አልኩት። +20 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ወደ አንተ የመጣሁት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አሁን ከፋርስ አለቃ ጋር ለመዋጋት ተመልሼ እሄዳለሁ።+ እኔ ስሄድ የግሪክ አለቃ ይመጣል። +21 ሆኖም በእውነት መጽሐፍ ላይ የሠፈሩትን ነገሮች እነግርሃለሁ። ከእነዚህ ነገሮች ጋር በተያያዘ የሕዝብህ አለቃ+ ከሆነው ከሚካኤል+ በስተቀር በእጅጉ ሊረዳኝ የሚችል የለም። +9 በከለዳውያን መንግሥት ላይ ንጉሥ ሆኖ የተሾመውና የሜዶናውያን ተወላጅ የሆነው የአሐሽዌሮስ ልጅ ዳርዮስ+ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት፣+ +2 አዎ፣ በዘመነ መንግሥቱ የመጀመሪያ ዓመት እኔ ዳንኤል ለነቢዩ ኤርምያስ በተነገረው የይሖዋ ቃል ላይ በተጠቀሰው መሠረት ኢየሩሳሌም ፈራርሳ የምትቆየው+ ለ70 ዓመት+ እንደሆነ ከመጻሕፍቱ* አስተዋልኩ። +3 በመሆኑም ወደ እውነተኛው አምላክ ወደ ይሖዋ ፊቴን አዞርኩ፤ ማቅ ለብሼና በራሴ ላይ አመድ ነስንሼ በጸሎትና በጾም ተማጸንኩት።+ +4 ወደ አምላኬ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ፤ ደግሞም ተናዘዝኩ፤ እንዲህም አልኩ፦ “እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ለሚወዱህ፣ ትእዛዛትህንም ለሚያከብሩ ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅና ታማኝ ፍቅር የምታሳይ+ ታላቅና የምትፈራ አምላክ ነህ፤+ +5 እኛ ኃጢአት ሠርተናል፤ በደል ፈጽመናል፤ ክፋት ሠርተናል እንዲሁም ዓምፀናል፤+ ከትእዛዛትህና ከድንጋጌዎችህ ዞር ብለናል። +6 ለነገሥታታችን፣ ለመኳንንታችን፣ ለአባቶቻችንና ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በስምህ የተናገሩትን አገልጋዮችህን ነቢያትን አልሰማንም።+ +7 ይሖዋ ሆይ፣ ጽድቅ የአንተ ነው፤ እኛ ግን ይኸውም የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲሁም በቅርብም ይሁን በሩቅ ባሉ አገራት ሁሉ የበተንካቸው የእስራኤል ቤት ሰዎች በሙሉ ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ኀፍረት* ተከናንበናል፤ ምክንያቱም እነሱ ለአንተ ታማኝ ሳይሆኑ ቀርተዋል።+ +8 “ይሖዋ ሆይ፣ እኛ፣ ነገሥታታችን፣ መኳንንታችንና አባቶቻችን በአንተ ላይ ኃጢአት በመሥራታችን ኀፍረት* ተከናንበናል። +9 ምሕረትና ይቅር ባይነት የአምላካችን የይሖዋ ነው፤+ እኛ በእሱ ላይ ዓምፀናልና።+ +10 የአምላካችንን የይሖዋን ቃል አልታዘዝንም፤ አገልጋዮቹ በሆኑት በነቢያት አማካኝነት የሰጠንን ሕጎችም አላከበርንም።+ +11 የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ሕግህን ተላልፈዋል፤ ቃልህን ባለመታዘዝም ለአንተ ጀርባቸውን ሰጥተዋል፤ በዚህም የተነሳ የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ በሆነው በሙሴ ሕግ የተጻፈውን እርግማንና መሐላ በእኛ ላይ አወረድክ፤+ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና። +12 በእኛ ላይ ታላቅ ጥፋት በማምጣት በእኛ ላይና እኛን በገዙት ገዢዎቻችን ላይ* የተናገረውን ቃል ፈጸመብን፤+ በኢየሩሳሌም ላይ እንደተፈጸመው ያለ ነገር ከሰማይ በታች ታይቶ አያውቅም።+ +13 በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው ይህ ሁሉ ጥፋት ደረሰብን፤+ ያም ሆኖ ከበደላችን በመመለስና ለእውነትህ* ትኩረት በመስጠት የአምላካችንን የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት አልተማጸንም።+ +14 “በመሆኑም ይሖዋ በትኩረት ሲከታተል ቆይቶ ጥፋት አመጣብን፤ አምላካችን ይሖዋ በሥራው ሁሉ ጻድቅ ነውና፤ እኛ ግን ቃሉን አልታዘዝንም።+ +15 “አሁንም ሕዝብህን ከግብፅ ምድር በኃያል እጅ ያወጣህና+ እስከዚህ ቀን ድረስ ስምህ እንዲታወቅ ያደረግክ አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣+ እኛ ኃጢአት ሠርተናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል። +16 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ ጽድቅ ሥራህ መጠን፣+ እባክህ ቁጣህንና ንዴትህን ከከተማህ ከኢየሩሳሌም ይኸውም ከቅዱስ ተራራህ መልስ፤ ምክንያቱም በኃጢአታችንና አባቶቻችን በፈጸሙት በደል የተነሳ ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ባሉት ሁሉ ዘንድ መሳለቂያ ሆነዋል።+ +17 አሁንም አምላካችን ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ልመና ስማ፤ ይሖዋ ሆይ፣ ለራስህ ስትል ለፈረሰው+ መቅደስህ ሞገስ አሳይ።+ +18 አምላኬ ሆይ፣ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ! ዓይንህን ገልጠህ በስምህ በተጠራችው ከተማችን ላይ የደረሰውን ጥፋት ተመልከት፤ ልመናችንን በፊትህ የምናቀርበው ከእኛ ጽድቅ የተነሳ ሳይሆን ከታላቅ ምሕረትህ የተነሳ ነው።+ +19 ይሖዋ ሆይ፣ ስማ። ይሖዋ ሆይ፣ ይቅር በል።+ ይሖዋ ሆይ፣ ትኩረት ስጥ፤ እርምጃም ውሰድ! አምላኬ ሆይ፣ ለራስህ ስትል አትዘግይ፤ ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቷልና።”+ +20 እኔም ገና እየተናገርኩና እየጸለይኩ፣ የራሴንና የሕዝቤን የእስራኤልን ኃጢአት እየተናዘዝኩ እንዲሁም በአምላኬ ቅዱስ ተራራ+ ላይ ሞገሱን እንዲያደርግ አምላኬን ይሖዋን እየለመንኩ፣ +21 አዎ፣ እየጸለይኩ ሳለ፣ ቀደም ሲል በራእዩ+ ላይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል፣+ በጣም ተዳክሜ ሳለ የምሽቱ የስጦታ መባ በሚቀርብበት ጊዜ ወደ እኔ መጣ። +22 እሱም እንዲህ በማለት እንዳስተውል ረዳኝ፦ “ዳንኤል ሆይ፣ አሁን ጥልቅ ማስተዋልና የመረዳት ችሎታ ልሰጥህ መጥቻለሁ። +23 ልመናህን ገና ማቅረብ ስትጀምር ትእዛዝ ተሰጥቷል፤ እኔም ልነግርህ መጥቻለሁ፤ ምክንያቱም አንተ እጅግ የተወደድክ* ነህ።+ ስለዚህ ለጉዳዩ ትኩረት ስጥ፤ ራእዩንም አስተውል። +24 “መተላለፍን ለማስቆም፣ ኃጢአትን ለመደምሰስ፣+ በደልን ለማስተሰረይ፣+ የዘላለም ጽድቅ ለማምጣት፣+ ራእዩንና ትንቢቱን* ለማተም+ እንዲሁም ቅድስተ ቅዱሳኑን ለመቀባት ለሕዝብህና ለቅድስቲቱ ከተማህ+ 70 ሳምንታት* ተወስኗል። +25 ኢየሩሳሌምን ለማደስና መልሶ ለመገንባት+ ትእዛዝ ከሚወጣበት ጊዜ አንስቶ መሪ+ የሆነው መሲሕ*+ እስከሚገለጥበት ጊዜ ድረስ 7 ሳምንታትና 62 ሳምንታት እንደሚሆን እወቅ፤ አስተውልም።+ ኢየሩሳሌም ትታደሳለች፤ ዳግመኛም ትገነባለች፤ አደባባይዋና የመከላከያ ቦይዋ እንደገና ይሠራል፤ ይህ የሚሆነው ግን በ +26 “ከ62ቱ ሳምንታት በኋላ መሲሑ ይቆረጣል፤*+ ትቶት የሚያልፈው ምንም ነገር አይኖርም።+ “የሚመጣውም መሪ ሠራዊት፣ ከተማዋንና ቅዱሱን ስፍራ ያጠፋል።+ ፍጻሜው በጎርፍ ይሆናል። እስከ ፍጻሜውም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተወስኗል።+ +27 “እሱም ለብዙዎች ቃል ኪዳኑን ለአንድ ሳምንት ያጸናል፤ በሳምንቱም አጋማሽ ላይ መሥዋዕትንና የስጦታ መባን ያስቀራል።+ “ጥፋት የሚያመጣውም በአስጸያፊ ነገሮች ክንፍ ላይ ሆኖ ይመጣል፤+ ጥፋት እስኪመጣም ድረስ የተወሰነው ነገር በወደመው ነገር ላይ ይፈስሳል።” +5 ንጉሥ ቤልሻዛር+ ለሺህ መኳንንቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ በእነሱም ፊት የወይን ጠጅ እየጠጣ ነበር።+ +2 ቤልሻዛር የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሞቅ ሲለው አባቱ ናቡከደነጾር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ የወሰዳቸውን የወርቅና የብር ዕቃዎች፣+ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም ቁባቶቹና ቅምጦቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጧቸው አዘዘ። +3 በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም፣ በአምላክ ቤት ከነበረው ቤተ መቅደስ የወሰዷቸውን የወርቅ ዕቃዎች አመጡ፤ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም ቁባቶቹና ቅምጦቹ ጠጡባቸው። +4 እነሱም የወይን ጠጅ እየጠጡ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመዳብ፣ ከብረት፣ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክትን አወደሱ። +5 ወዲያውኑም የሰው እጅ ጣቶች ብቅ ብለው በንጉሡ ቤተ መንግሥት፣ በመቅረዙ ትይዩ ባለው ግድግዳ ልስን ላይ መጻፍ ጀመሩ��� ንጉሡም የሚጽፈውን እጅ አየ። +6 በዚህ ጊዜ ንጉሡ ፊቱ ገረጣ፤* ወደ አእምሮው የመጣው ሐሳብ አሸበረው፤ ወገቡም ተንቀጠቀጠ፤+ ጉልበቶቹም ይብረከረኩ ጀመር። +7 ንጉሡ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጠንቋዮቹን፣ ከለዳውያኑንና* ኮከብ ቆጣሪዎቹን እንዲያመጧቸው አዘዘ።+ ንጉሡም የባቢሎንን ጠቢባን እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ጽሑፍ የሚያነብና ትርጉሙን የሚነግረኝ ማንኛውም ሰው ሐምራዊ ልብስ ይለብሳል፤ አንገቱ ላይ የወርቅ ሐብል ይደረግለታል፤+ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዢ ይሆ +8 በዚህ ጊዜ የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፤ ሆኖም ጽሑፉን ማንበብም ሆነ ትርጉሙን ለንጉሡ ማሳወቅ አልቻሉም።+ +9 በመሆኑም ንጉሥ ቤልሻዛር እጅግ ፈራ፤ ፊቱም ገረጣ፤ መኳንንቱም ግራ ተጋቡ።+ +10 ንግሥቲቱም ንጉሡና መኳንንቱ የተናገሩትን በሰማች ጊዜ ወደ ግብዣው አዳራሽ ገባች። እንዲህም አለች፦ “ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ኑር። በፍርሃት አትዋጥ፤ ፊትህም አይለዋወጥ። +11 በመንግሥትህ ውስጥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ሰው* አለ። በአባትህ ዘመን እንደ አማልክት ጥበብ ያለ ጥበብ፣ የእውቀት ብርሃንና ጥልቅ ማስተዋል ተገኝቶበት ነበር።+ አባትህ ንጉሥ ናቡከደነጾር የአስማተኛ ካህናቱ፣ የጠንቋዮቹ፣ የከለዳውያኑና* የኮከብ ቆጣሪዎቹ አለቃ አድርጎ ሾመው፤+ ንጉሥ ሆይ፣ +12 ንጉሡ፣ ብልጣሶር ብሎ የሰየመው ዳንኤል+ ሕልምን በመተርጎም ረገድ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ችሎታ፣ እውቀትና ጥልቅ ማስተዋል እንዲሁም እንቆቅልሽንና የተወሳሰቡ ችግሮችን የመፍታት* ችሎታ ነበረው።+ እንግዲህ ዳንኤል ይጠራ፤ እሱም ትርጉሙን ይነግርሃል።” +13 በመሆኑም ዳንኤልን በንጉሡ ፊት አቀረቡት። ንጉሡም ዳንኤልን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ “ንጉሡ አባቴ ከይሁዳ ምድር ካመጣቸው+ የይሁዳ ግዞተኞች አንዱ የሆንከው ዳንኤል አንተ ነህ?+ +14 የአማልክት መንፈስ በውስጥህ እንዳለ+ እንዲሁም የእውቀት ብርሃን፣ ጥልቅ ማስተዋልና በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥበብ እንደተገኘብህ ስለ አንተ ሰምቻለሁ።+ +15 ይህን ጽሑፍ አንብበው ትርጉሙን እንዲያሳውቁኝ ጥበበኞችንና ጠንቋዮችን በፊቴ አቅርበዋቸው ነበር፤ እነሱ ግን የመልእክቱን ትርጉም መናገር አልቻሉም።+ +16 አንተ ግን የመተርጎምና የተወሳሰቡ ችግሮችን የመፍታት* ችሎታ እንዳለህ ሰምቻለሁ።+ አሁንም ይህን ጽሑፍ አንብበህ ትርጉሙን ልታሳውቀኝ ከቻልክ ሐምራዊ ልብስ ትለብሳለህ፤ አንገትህ ላይ የወርቅ ሐብል ይደረግልሃል፤ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዢ ትሆናለህ።”+ +17 በዚህ ጊዜ ዳንኤል ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ስጦታህ ለራስህ ይሁን፤ ገጸ በረከቶችህንም ለሌሎች ስጥ። ይሁንና ጽሑፉን ለንጉሡ አነባለሁ፤ ትርጉሙንም አሳውቀዋለሁ። +18 ንጉሥ ሆይ፣ ልዑሉ አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነጾር መንግሥት፣ ታላቅነት፣ ክብርና ግርማ ሰጠው።+ +19 ታላቅነትን ስላጎናጸፈው ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጡ ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር።+ የፈለገውን ይገድል ወይም በሕይወት እንዲኖር ይፈቅድ፣ የፈለገውን ከፍ ከፍ ያደርግ ወይም ያዋርድ ነበር።+ +20 ሆኖም ልቡ ታብዮና አንገተ ደንዳና ሆኖ የእብሪተኝነት መንፈስ ባሳየ ጊዜ+ ከመንግሥቱ ዙፋን እንዲወርድ ተደረገ፤ ክብሩንም ተገፈፈ። +21 ከሰው ልጆች መካከል ተሰደደ፤ ልቡም ወደ አውሬ ልብ ተለወጠ፤ መኖሪያውም ከዱር አህዮች ጋር ሆነ። ልዑሉ አምላክ በሰው ልጆች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና የፈለገውን በመንግሥቱ ላይ እንደሚያስቀምጥ እስኪያውቅ ድረስ እንደ በሬ ሣር በላ፤ ሰውነቱም በሰማያት ጠል ረሰረሰ።+ +22 “ቤልሻዛር ሆይ፣ አንተ ግን ልጁ እንደመሆንህ መጠን ይህን ሁሉ ብታውቅም ትሕትና አላሳየህም። +23 ��ልቁንም በሰማያት ጌታ ላይ ታበይክ፤+ የቤተ መቅደሱንም ዕቃ አስመጣህ።+ ከዚያም አንተና መኳንንትህ እንዲሁም ቁባቶችህና ቅምጦችህ በእነዚህ ዕቃዎች የወይን ጠጅ ጠጣችሁ፤ አንዳች ነገር ማየትም ሆነ መስማት ወይም ማወቅ የማይችሉትን ከብር፣ ከወርቅ፣ ከመዳብ፣ ከብረት፣ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማል +24 ስለዚህ ይህን እጅ የላከው እሱ ነው፤ ይህም ጽሑፍ ተጻፈ።+ +25 የተጻፈውም ጽሑፍ፣ ‘ሚኒ፣ ሚኒ፣ ቲቄል እና ፋርሲን’ ይላል። +26 “የቃላቱ ትርጉም ይህ ነው፦ ሚኒ ማለት አምላክ የመንግሥትህን ዘመን ቆጠረው፤ ወደ ፍጻሜም አመጣው ማለት ነው።+ +27 “ቲቄል ማለት በሚዛን ተመዘንክ፤ ጉድለትም ተገኘብህ ማለት ነው። +28 “ፊሬስ ማለት ደግሞ መንግሥትህ ተከፈለ፤ ለሜዶናውያንና ለፋርሳውያን ተሰጠ ማለት ነው።”+ +29 በዚህ ጊዜ ቤልሻዛር ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ዳንኤልንም ሐምራዊ ልብስ አለበሱት፤ በአንገቱም ላይ የወርቅ ሐብል አጠለቁለት፤ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዢ ሆኖ መሾሙን አወጁ።+ +30 በዚያኑ ሌሊት ከለዳዊው ንጉሥ ቤልሻዛር ተገደለ።+ +31 ሜዶናዊው ዳርዮስም+ መንግሥቱን ተረከበ፤ ዕድሜውም 62 ዓመት ገደማ ነበር። +3 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሌሎች አማልክትን የሚከተሉና+ የዘቢብ ቂጣ* የሚወዱ ሆነው ሳለ ይሖዋ እንደወደዳቸው ሁሉ፣+ አንተም ሄደህ በሌላ ሰው የተወደደችውንና ምንዝር የምትፈጽመውን ሴት ዳግመኛ ውደዳት።”+ +2 በመሆኑም በ15 የብር ሰቅልና በአንድ ተኩል የሆሜር* መስፈሪያ ገብስ ለራሴ ገዛኋት። +3 ከዚያም እንዲህ አልኳት፦ “ለብዙ ቀናት የእኔ ሆነሽ ትቀመጫለሽ። አታመንዝሪ፤* ከሌላ ሰውም ጋር ግንኙነት አታድርጊ፤ እኔም ከአንቺ ጋር ግንኙነት አልፈጽምም።” +4 ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ ለረጅም ጊዜ ያለንጉሥ፣+ ያለገዢ፣ ያለመሥዋዕት፣ ያለዓምድ፣ ያለኤፉድና+ ያለተራፊም ምስል*+ ይኖራሉ። +5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ተመልሰው አምላካቸውን ይሖዋንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤+ በዘመኑም መጨረሻ ወደ ይሖዋና ወደ ጥሩነቱ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።+ +7 “እስራኤልን ለመፈወስ በሞከርኩ ቁጥርየኤፍሬም በደል፣+የሰማርያም ክፋት ይገለጣል።+ እነሱ ያታልላሉና፤+ሌቦች ሰብረው ይገባሉ፤ የወራሪዎች ቡድን በውጭ ጥቃት ይሰነዝራል።+ + 2 እነሱ ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ ልብ አይሉም።+ የገዛ ድርጊታቸው ከቧቸዋል፤የሠሩት ሥራ ሁሉ በፊቴ ነው። + 3 ንጉሡን በክፋታቸው፣መኳንንቱንም አታላይ በሆነ ድርጊታቸው ያስደስታሉ። + 4 ሁሉም አመንዝሮች ናቸው፤አንድ ዳቦ ጋጋሪ እሳቱን አንዴ ካቀጣጠለው በኋላ፣ያቦካው ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ እሳቱን መቆስቆስ እንደማያስፈልገው የጋለ ምድጃ ናቸው። + 5 በንጉሣችን ክብረ በዓል ቀን፣ መኳንንቱ ታመሙ፤በወይን ጠጅ የተነሳ በቁጣ ተሞሉ።+ ንጉሡ ለፌዘኞች እጁን ዘረጋ። + 6 እንደ ምድጃ የሚነድ ልብ ይዘው ይቀርባሉና።* ዳቦ ጋጋሪው ሌሊቱን ሙሉ ይተኛል፤በማለዳ ምድጃው እንደሚንበለበል እሳት ይንቀለቀላል። + 7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ገዢዎቻቸውንም* ይውጣሉ። ነገሥታታቸው ሁሉ ወድቀዋል፤+ከእነሱ መካከል ወደ እኔ የሚጮኽ ማንም የለም።+ + 8 ኤፍሬም ከብሔራት ጋር ይቀላቀላል።+ እሱ እንዳልተገላበጠ ቂጣ ነው። + 9 እንግዶች ጉልበቱን በዘበዙ፤+ እሱ ግን ይህን አላወቀም። ራሱንም ሽበት ወረሰው፤ እሱ ግን ይህን ልብ አላለም። +10 የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ መሥክሮበታል፤+ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ አልተመለሱም፤+እሱንም አልፈለጉትም። +11 ኤፍሬም ማስተዋል እንደሌላት* ሞኝ ርግብ ነው።+ ግብፅን ተጣሩ፤+ ወደ አሦርም ሄዱ።+ +12 የትም ቢሄዱ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ። እንደ ሰማይ ወፎች ወደ ታች አወርዳቸዋለሁ። ለጉባኤያቸው በሰጠሁት ማስጠንቀቂያ መሠረት እገሥጻቸዋለሁ።+ +13 ከእኔ ስለሸሹ ወዮላቸው! በእኔ ላይ በደል ስለፈጸሙ ጥፋት ይምጣባቸው! እነሱን ለመዋጀት ዝግጁ ነበርኩ፤ እነሱ ግን በእኔ ላይ ውሸት ተናገሩ።+ +14 በአልጋቸው ላይ ሆነው ዋይ ዋይ ቢሉምእርዳታ ለማግኘት ከልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም።+ ለእህላቸውና ለአዲስ የወይን ጠጃቸው ሲሉ ሰውነታቸውን ይተለትላሉ፤በእኔም ላይ ዓመፁ። +15 ያሠለጠንኳቸውና ክንዳቸውን ያበረታሁ ቢሆንምክፉ ነገር በማሴር በእኔ ላይ ተነስተዋል። +16 አካሄዳቸውን ለወጡ፤ ከፍ ወዳለ ነገር ግን አይደለም፤*ጅማቱ እንደረገበ ደጋን እምነት የማይጣልባቸው ሆነዋል።+ አለቆቻቸው እብሪተኛ ከሆነው አንደበታቸው የተነሳ በሰይፍ ይወድቃሉ። በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር መሳለቂያ ይሆናሉ።”+ +12 “ኤፍሬም ነፋስን ይመገባል። ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል። ውሸትንና ዓመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ፤+ ወደ ግብፅም ዘይት ይወስዳሉ።+ + 2 ይሖዋ በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤+ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤እንደ ድርጊቱም ብድራት ይከፍለዋል።+ + 3 በማህፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤+ባለ በሌለ ኃይሉም ከአምላክ ጋር ታገለ።+ + 4 ከመልአክ ጋር መታገሉን ቀጠለ፤ ደግሞም አሸነፈ። ሞገስ እንዲያሳየው አልቅሶ ለመነው።”+ አምላክ በቤቴል አገኘው፤ በዚያም እኛን አነጋገረን፤+ + 5 እሱ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።+የመታሰቢያ ስሙ* ይሖዋ ነው።+ + 6 “ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤+ታማኝ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤+ምንጊዜም በአምላክህ ተስፋ አድርግ። + 7 ይሁንና በነጋዴው እጅ አታላይ ሚዛን አለ፤እሱ ማጭበርበር ይወዳል።+ + 8 ኤፍሬም ‘በእርግጥ እኔ ባለጸጋ ሆኛለሁ፤+ሀብት አካብቻለሁ።+ ደግሞም ከደከምኩበት ነገር ሁሉ ጋር በተያያዘ በደልም ሆነ ኃጢአት አያገኙብኝም’ ይላል። + 9 ይሁንና ከግብፅ ምድር አንስቶ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ።+ በተወሰነው ጊዜ* እንደነበረው ሁሉ፣እንደገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ። +10 ለነቢያቱ ተናገርኩ፤+ራእዮቻቸውን አበዛሁ፤በነቢያቱም በኩል ምሳሌዎችን ተናገርኩ። +11 በጊልያድ ማታለልና* ውሸት አለ።+ በጊልጋል በሬዎችን ሠውተዋል፤+በተጨማሪም መሠዊያዎቻቸው በእርሻ ትልም ላይ እንዳለ የድንጋይ ክምር ናቸው።+ +12 ያዕቆብ ወደ አራም* ምድር ሸሸ፤+እስራኤል+ ሚስት ለማግኘት ሲል በዚያ አገለገለ፤+ሚስት ለማግኘትም ሲል በግ ጠባቂ ሆነ።+ +13 ይሖዋ በነቢይ አማካኝነት እስራኤልን ከግብፅ አወጣው፤+በነቢይም አማካኝነት ጠበቀው።+ +14 ኤፍሬም ግን እጅግ በደለው፤+ደም በማፍሰስ የፈጸመው በደል በላዩ ላይ ይሆናል፤ላመጣበትም ነቀፋ ጌታው ብድራት ይከፍለዋል።”+ +1 በይሁዳ ነገሥታት+ በዖዝያ፣+ በኢዮዓታም፣+ በአካዝና+ በሕዝቅያስ+ እንዲሁም በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ+ ልጅ በኢዮርብዓም+ ዘመን ወደ ቤኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ* የመጣው የይሖዋ ቃል። +2 ይሖዋ በሆሴዕ አማካኝነት ቃሉን መናገር ሲጀምር ይሖዋ ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ሄደህ ዝሙት አዳሪ ሴት* አግባ፤ እሷ በምትፈጽመውም ምንዝር* ልጆች ይወለዱልሃል፤ ምክንያቱም በምንዝር የተነሳ* ምድሪቱ ይሖዋን ከመከተል ሙሉ በሙሉ ርቃለች።”+ +3 ስለዚህ ሄዶ የዲብላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት። +4 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ልጁን ኢይዝራኤል* ብለህ ጥራው፤ በኢይዝራኤል* ለፈሰሰው ደም የኢዩን ቤት በቅርቡ ተጠያቂ አደርጋለሁና፤+ የእስራኤል ቤት ንጉሣዊ አገዛዝም እንዲያከትም አደርጋለሁ።+ +5 በዚያ ቀን የእስራኤልን ቀስት በኢይዝራኤል ሸለቆ* እሰብራለሁ።” +6 እሷም ዳግመኛ ፀነሰች፤ ሴት ልጅም ወለደች። አምላክም እንዲህ አለው፦ “ልጅቷን ሎሩሃማ* ብለህ ጥራት፤ ምክንያቱም ከእንግዲህ ለእስራኤል ቤት ምሕረት አላሳይም፤+ በእርግጥ አስወግዳቸዋለሁ።+ +7 ለይሁዳ ቤት ግን ምሕረት አደርጋለሁ፤+ በቀስት፣ በሰይፍ፣ በጦርነት፣ በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በይሖዋ አድናቸዋለሁ።”+ +8 ጎሜር፣ ሎሩሃማን ጡት ካስጣለች በኋላ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። +9 ከዚያም አምላክ እንዲህ አለው፦ “ልጁን ሎአሚ* ብለህ ጥራው፤ ምክንያቱም እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም፤ እኔም አምላካችሁ አይደለሁም። +10 “የእስራኤልም ሕዝብ* ብዛት ሊሰፈር ወይም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል።+ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’+ ተብሎ በተነገራቸው ስፍራም ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ይባላሉ።+ +11 የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ተሰብስበው አንድ ይሆናሉ፤+ ለራሳቸውም አንድ መሪ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።+ +8 “ቀንደ መለከት ንፋ!+ ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና+ ሕጌን ስለጣሱ+በይሖዋ ቤት ላይ ጠላት እንደ ንስር ይመጣል።+ + 2 ‘አምላካችን ሆይ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች እናውቅሃለን!’ እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ።+ + 3 እስራኤል መልካም የሆነውን ነገር ገሸሽ አድርጓል።+ ጠላት ያሳደው። + 4 እኔ ሳልላቸው ነገሥታትን አነገሡ። መኳንንትን ሾሙ፤ እኔ ግን እውቅና አልሰጠኋቸውም። በገዛ ራሳቸው ላይ ጥፋት ለማምጣት+በብራቸውና በወርቃቸው ጣዖቶች ሠሩ።+ + 5 ሰማርያ ሆይ፣ የጥጃ ጣዖትሽ ተጥሏል።+ ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል።+ ንጹሕ መሆን* የሚሳናቸው እስከ መቼ ነው? + 6 ይህ ከእስራኤል ነውና። የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ አምላክ አይደለም፤የሰማርያ ጥጃ ተሰባብሮ እንዳልነበረ ይሆናል። + 7 ነፋስን ይዘራሉ፤አውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ።+ አገዳው፣ የደረሰ ፍሬ* የለውም፤+እህሉ፣ ዱቄት አላስገኘም። ፍሬ ቢያፈራ እንኳ ባዕዳን* ይበሉታል።+ + 8 የእስራኤል ሰዎች ይዋጣሉ።+ በብሔራት መካከልማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ይሆናሉ።+ + 9 ተገልሎ እንደሚኖር የዱር አህያ ወደ አሦር ሄደዋልና።+ ኤፍሬም በገንዘብ ፍቅረኞች አፍርቷል።+ +10 ፍቅረኞቻቸውን ያፈሩት ከብሔራት ቢሆንም፣እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ንጉሥና መኳንንት በጫኑባቸው ሸክም የተነሳ ሥቃይ ይደርስባቸዋል።+ +11 ኤፍሬም ኃጢአት ለመሥራት መሠዊያዎችን አብዝቷል።+ ኃጢአት የሚፈጽምባቸው መሠዊያዎች ሆነውለታል።+ +12 በሕጌ* ውስጥ ያለውን አብዛኛውን ነገር ጽፌለታለሁ፤እነሱ ግን እንግዳ ነገር አድርገው ቆጠሩት።+ +13 መሥዋዕቶችን ስጦታ አድርገው ለእኔ ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ይሖዋ ግን በእነሱ አልተደሰተም።+ በደላቸውን ያስታውሳል፤ ለሠሯቸውም ኃጢአቶች ይቀጣቸዋል።+ እነሱ ወደ ግብፅ ተመልሰዋል።*+ +14 እስራኤል ፈጣሪውን ረስቷል፤+ ቤተ መቅደሶችንም ገንብቷል፤+ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አብዝቷል።+ እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤እሳቱም የእያንዳንዳቸውን ማማዎች ይበላል።”+ +11 “እስራኤል ገና ልጅ ሳለ ወደድኩት፤+ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት።+ + 2 እነሱ* ደጋግመው በጠሯቸው መጠንበዚያው ልክ ከእነሱ ራቁ።+ ለባአል ምስሎች መሠዋታቸውን፣+ለተቀረጹት ምስሎችም መሥዋዕት ማቅረባቸውን ቀጠሉ።+ + 3 እኔ ግን ኤፍሬምን መራመድ አስተማርኩት፤+ በክንዶቼም ተሸከምኳቸው፤+የፈወስኳቸውም እኔ እንደሆንኩ አምነው አልተቀበሉም። + 4 በሰዎች ገመድ፣* በፍቅርም ማሰሪያ ሳብኳቸው፤+ደግሞም ከጫንቃቸው ላይ* ቀንበር እንደሚያነሳ ሰው ሆንኩላቸው፤ለእያንዳንዳቸውም በደግነት ምግብ አቀረብኩላቸው። + 5 እነሱ ወደ ግብፅ ምድር አይመለሱም፤ ሆኖም አሦር ንጉሣቸው ይሆናል፤+ምክንያቱም ወደ እኔ ለመመለስ አሻፈረን ብለዋል።+ + 6 በጠነሰሱት ሴራ የተነሳ በከተሞቹ ላይ ሰይፍ ያንዣብባል፤+መቀርቀሪያዎቹንም ይሰባብራል፤ ይበላቸዋልም።+ + 7 ሕዝቤ በእኔ ላይ ክህደት ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም።+ ወደ ላይ* ቢጠሯቸውም ማንም አይነሳም። + 8 ኤፍሬም ሆይ፣ እንዴት ልተውህ እችላለሁ?+ እስራኤል ሆይ፣ እንዴት አሳልፌ ልሰጥህ እችላለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? ደግሞስ እንዴት እንደ ጸቦይም ላደርግህ እችላለሁ?+ ስለ አንተ ያለኝ አመለካከት ተለወጠ፤የርኅራኄ ስሜቴም ተቀሰቀሰ።*+ + 9 የሚነድ ቁጣዬን አልገልጽም። ኤፍሬምን ዳግመኛ አላጠፋም፤+እኔ አምላክ እንጂ ሰው አይደለሁምና፤በመካከልህ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ፤በአንተም ላይ በቁጣ አልመጣም። +10 እነሱ ይሖዋን ተከትለው ይሄዳሉ፤ እሱም እንደ አንበሳ ያገሳል፤+እሱ ሲያገሳ ልጆቹ ከምዕራብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።+ +11 ከግብፅ ሲወጡ እንደ ወፍ፣ከአሦርም ምድር ሲወጡ እንደ ርግብ ይርገፈገፋሉ፤+እኔም በየቤታቸው እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ” ይላል ይሖዋ።+ +12 “ኤፍሬም በውሸት፣የእስራኤልም ቤት በማታለል ከበበኝ።+ ይሁዳ ግን አሁንም ከአምላክ ጋር ይሄዳል፤*እጅግ ቅዱስ ለሆነውም አምላክ ታማኝ ነው።”+ +2 “ወንድሞቻችሁን ‘ሕዝቤ!’*+ እህቶቻችሁን ደግሞ ‘ምሕረት የተደረገልሽ ሴት!’* በሏቸው።+ + 2 እናታችሁን ክሰሷት፤ እሷ ሚስቴ ስላልሆነች፣+እኔም ባሏ ስላልሆንኩ ክሰሷት። ከእሷ ዘንድ ዘማዊነቷን፣*ከጡቶቿም መካከል ምንዝሯን ታስወግድ፤ + 3 አለዚያ ራቁቷን አስቀራታለሁ፤ በተወለደችበት ቀን እንደነበረችውም አደርጋታለሁ፤እንደ ምድረ በዳ፣ውኃ እንደሌለበትም ምድር አደርጋታለሁ፤በውኃ ጥምም እገድላታለሁ። + 4 ወንዶች ልጆቿ የምንዝር* ልጆች ስለሆኑምሕረት አላደርግላቸውም። + 5 እናታቸው አመንዝራለችና።*+ እነሱን የፀነሰችው ሴት አሳፋሪ ድርጊት ፈጽማለች፤+‘አጥብቀው የሚወዱኝን፣ደግሞም ምግቤንና ውኃዬን፣የሱፍ ልብሴንና በፍታዬን እንዲሁም ዘይቴንና መጠጤን የሚሰጡኝን ተከትዬ እሄዳለሁ’ ብላለችና።+ + 6 ስለዚህ መንገዷን በእሾህ አጥር እዘጋለሁ፤መውጫ መንገድ እንዳታገኝምዙሪያዋን በድንጋይ አጥራለሁ። + 7 አጥብቀው የሚወዷትን ተከትላ ትሄዳለች፤ ሆኖም አትደርስባቸውም፤+ትፈልጋቸዋለች፤ ሆኖም አታገኛቸውም። ከዚያም ‘ተመልሼ ወደ መጀመሪያው ባሌ እሄዳለሁ፤+ከአሁኑ ኑሮዬ ይልቅ የበፊቱ ይሻለኛልና’ ትላለች።+ + 8 እህሉን፣ አዲሱን የወይን ጠጅና ዘይቱን የሰጠኋትእንዲሁም ለባአል አምልኮ የተጠቀሙበትን ብርና ወርቅ+በብዛት እንድታገኝ ያደረግኩት እኔ እንደሆንኩ አልተገነዘበችም።+ + 9 ‘ስለዚህ ሐሳቤን ቀይሬ፣ እህሌን በጊዜው፣አዲሱን የወይን ጠጄንም በወቅቱ እወስዳለሁ፤+እርቃኗን የምትሸፍንበትንም የሱፍ ልብሴንና በፍታዬን እነጥቃታለሁ። +10 አሁንም ኀፍረተ ሥጋዋን አጥብቀው በሚወዷት ፊት እገልጣለሁ፤ከእጄም የሚያስጥላት ሰው አይኖርም።+ +11 ደስታዋን፣ በዓሏን፣ የወር መባቻዋንና ሰንበቷን ሁሉእንዲሁም የተወሰኑትን የበዓል ወቅቶቿን ሁሉ አስቀራለሁ።+ +12 “አጥብቀው የሚወዱኝ ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ደሞዜ ናቸው” የምትላቸውን የወይን ተክሏንና የበለስ ዛፏን አወድማለሁ፤ጫካም አደርጋቸዋለሁ፤የዱር አራዊትም ይበሏቸዋል። +13 ለባአል ምስሎች መሥዋዕት ባቀረበችባቸው፣+ በጉትቻዋና በጌጦቿ በተንቆጠቆጠችባቸውእንዲሁም አጥብቀው የሚወዷትን በተከተለችባቸው ቀናት የተነሳ ተጠያቂ አደርጋታለሁ፤እኔንም ረስታኝ ነበር’+ ይላል ይሖዋ። +14 ‘ስለዚህ አግባብቼ አሳምናታለሁ፤ወደ ምድረ በዳ እመራታለሁ፤ልቧን በሚማርክ መንገድ አናግራታለሁ። +15 ከዚያን ጊዜ አንስቶ የወይን እርሻዎቿን መልሼ እሰጣታለሁ፤+የአኮርም ሸለቆ*+ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤በዚያም እንደ ልጅነቷ ጊዜናከግብፅ ምድር እንደወጣችበት ቀን መልስ ትሰጠኛለች።+ +16 በዚያም ቀን’ ይላል ይሖዋ፣‘ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ ከእንግዲህ ጌታዬ* ብለሽ አትጠሪኝም።’ +17 ‘የባአልን ምስሎች ስሞች ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤+ስማቸውም ከእንግዲህ አይታወስም።+ +18 በዚያም ቀን ለእነሱ ጥቅም ስል ከዱር አራዊት፣+ከሰማይ ወፎችና መሬት ለመሬት ከሚሳቡ ፍጥረታት ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤+ያለስጋት እንዲያርፉም* አደርጋለሁ።+ +19 ለዘላለም አጭሻለሁ፤በጽድቅ፣ በፍትሕ፣ በታማኝ ፍቅርናበምሕረት አጭሻለሁ።+ +20 በታማኝነት አጭሻለሁ፤አንቺም በእርግጥ ይሖዋን ታውቂያለሽ።’+ +21 ‘በዚያም ቀን መልስ እሰጣለሁ’ ይላል ይሖዋ፤‘ለሰማያት መልስ እሰጣለሁ፤እነሱ ደግሞ ለምድር መልስ ይሰጣሉ፤+ +22 ምድር ደግሞ ለእህሉ፣ ለአዲሱ የወይን ጠጅና ለዘይቱ መልስ ትሰጣለች፤እነሱም ለኢይዝራኤል* መልስ ይሰጣሉ።+ +23 በምድር ላይ ለራሴ እንደ ዘር እዘራታለሁ፤+ደግሞም ምሕረት ላልተደረገላት* ለእሷ ምሕረት አደርግላታለሁ፤ሕዝቤ ያልሆኑትን* “እናንተ ሕዝቤ ናችሁ” እላቸዋለሁ፤+ እነሱ ደግሞ “አንተ አምላኬ ነህ” ይላሉ።’”+ +4 የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ይሖዋ ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ስለሚፋረድ የይሖዋን ቃል ስሙ፤+ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ እውነት፣ ታማኝ ፍቅርና አምላክን ማወቅ የለም።+ + 2 የሐሰት መሐላ፣ ውሸት፣+ ነፍስ ግድያ፣+ስርቆትና ምንዝር+ ተስፋፍቷል፤ደም የማፍሰስ ወንጀልም በላይ በላዩ ይፈጸማል።+ + 3 ከዚህም የተነሳ ምድሪቱ ታዝናለች፤+በእሷም ላይ የሚኖሩ ሁሉ ይመነምናሉ፤የዱር እንስሳትና የሰማይ ወፎችየባሕር ዓሣዎችም እንኳ ሳይቀሩ ይጠፋሉ። + 4 “ይሁን እንጂ ማንም ሰው አይሟገት ወይም ሌላውን አይውቀስ፤+ሕዝብህ ከካህን ጋር እንደሚሟገት ሰው ነውና።+ + 5 ስለዚህ እናንተ በጠራራ ፀሐይ ትሰናከላላችሁ፤የጨለመ ይመስል ነቢዩም ከእናንተ ጋር ይሰናከላል። እናታችሁንም ጸጥ አሰኛታለሁ።* + 6 ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ይጠፋል። እናንተ እውቀትን ስለናቃችሁ+እኔም ካህናት ሆናችሁ እንዳታገለግሉኝ እንቃችኋለሁ፤የአምላካችሁን ሕግ* ስለረሳችሁ+እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ። + 7 እነሱ በበዙ ቁጥር በእኔ ላይ የሚሠሩት ኃጢአት በዝቷል።+ ክብራቸውን ወደ ውርደት እለውጣለሁ።* + 8 የሕዝቤ ኃጢአት መብል ሆኖላቸዋል፤ደግሞም እነሱ በደል እንዲሠሩ ይቋምጣሉ።* + 9 ሕዝቡንም ሆነ ካህኑንለተከተሉት መንገድ ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤አድራጎታቸው ያስከተለውንም መዘዝ በላያቸው አመጣለሁ።+ +10 ይበላሉ፤ ሆኖም አይጠግቡም።+ ሴሰኞች ይሆናሉ፤* ሆኖም ቁጥራቸው አይጨምርም፤+ምክንያቱም ይሖዋን ችላ ብለዋል። +11 ምንዝር፣* ያረጀ የወይን ጠጅና አዲስ የወይን ጠጅ፣ሰው ትክክል የሆነውን ነገር ለመፈጸም ያለውን ልባዊ ፍላጎት ያጠፋሉ።*+ +12 ሕዝቤ ከእንጨት የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን ያማክራሉ፤በትራቸው* የሚላቸውን ነገር ያደርጋሉ፤ምክንያቱም የአመንዝራነት* መንፈስ እንዲባዝኑ ያደርጋቸዋል፤በአመንዝራነታቸው* የተነሳም ለአምላካቸው ለመገዛት አሻፈረን ይላሉ። +13 በተራሮች አናት ላይ ይሠዋሉ፤+ደግሞም በኮረብቶች ላይእንዲሁም በባሉጥ ዛፎች፣ በሊብነህ ዛፎችና* በትልቅ ዛፍ ሁሉ ሥር የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርባሉ፤+ምክንያቱም የዛፎቹ ጥላ መልካም ነው። ከዚህም የተነሳ ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች* ይሆናሉ፤ምራቶቻችሁም ያመነዝራሉ። +14 ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች* በመሆናቸው፣ምራቶቻችሁም በማመንዘራቸው አልቀጣቸውም። ወንዶቹ ከጋለሞታዎች ጋር ተያይዘው ይሄዳሉና፤ከቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪዎችም ጋር መሥዋዕት ያቀርባሉ፤እንዲህ ያለ ማስተዋል የሌለው ሕዝብ+ ይጠፋል። +15 እስራኤል ሆይ፣ አንቺ ብታመነዝሪም*+ይሁዳ ግን ተመሳሳይ በደል አትፈጽም።+ ወደ ጊልጋል+ ወይም ወደ ቤትአዌን+ አትሂዱ፤‘ሕያው ይሖዋን!’ ብላችሁም አትማሉ።+ +16 እስራኤል እንደ እልኸኛ በሬ እልኸኛ ሆናለችና።+ ታዲያ ይሖዋ እንደ በግ ጠቦት በተንጣለለ የግጦሽ መስክ* ያሰማራቸዋል? +17 ኤፍሬም ከጣዖቶች ጋር ተቆራኝቷል።+ በቃ ተዉት! +18 መጠጣቸው* ሲያልቅሴሰኞች ይሆናሉ።* ገዢዎቿም* ነውርን አጥብቀው ይወዳሉ።+ +19 ነፋስ በክንፎቹ ይጠቀልላታል፤*እነሱም ባቀረቧቸው መሥዋዕቶች ያፍራሉ።” +6 “ኑ ወደ ይሖዋ እንመለስ፤እሱ ቦጫጭቆናል፤+ ሆኖም ይፈውሰናል። እሱ መቶናል፤ ሆኖም ቁስላችንን ይጠግናል። + 2 ከሁለት ቀናት በኋላ ያነቃናል። በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል፤እኛም በፊቱ እንኖራለን። + 3 ይሖዋን እናውቀዋለን፤ እሱን ለማወቅ ልባዊ ጥረት እናደርጋለን። የእሱ መውጣት እንደ ንጋት ብርሃን የተረጋገጠ ነው፤እንደ ዶፍ ዝናብ፣ ምድርንም እንደሚያጠግበው የኋለኛው ዝናብወደ እኛ ይመጣል።” + 4 “ኤፍሬም ሆይ፣ ምን ላድርግህ? ይሁዳ ሆይ፣ ምን ላድርግህ? ታማኝ ፍቅራችሁ እንደ ጠዋት ጉም፣ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ነውና። + 5 ከዚህም የተነሳ በነቢያቴ አማካኝነት እቆራርጣቸዋለሁ፤+በአፌም ቃል እገድላቸዋለሁ።+ በእናንተም ላይ የምፈርደው ፍርድ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል።+ + 6 ከመሥዋዕት ይልቅ ታማኝ ፍቅር፣*ሙሉ በሙሉ ከሚቃጠል መባም ይልቅ አምላክን ማወቅ ያስደስተኛልና።+ + 7 እነሱ ግን እንደ ተራ ሰዎች ቃል ኪዳኑን ተላለፉ።+ በዚያም እኔን ከዱኝ። + 8 ጊልያድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ናት፤+ከተማዋ በደም ጨቅይታለች።+ + 9 የካህናቱ ማኅበር ሰውን አድብቶ እንደሚጠብቅ የወራሪዎች ቡድን ነው። በሴኬም+ መንገድ ላይ ሰው ይገድላሉ፤ምግባራቸው አሳፋሪ ነውና። +10 በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ። በዚያ ኤፍሬም ያመነዝራል፤+እስራኤል ራሱን አርክሷል።+ +11 በአንጻሩ ግን ይሁዳ ሆይ፣ የሕዝቤን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜመከር ይጠብቅሃል።”+ +10 “እስራኤል ፍሬ የሚሰጥ እየተበላሸ* ያለ ወይን ነው።+ ፍሬው በበዛ መጠን መሠዊያዎቹንም በዚያው ልክ አበዛ፤+ምድሩ የተሻለ ምርት ባስገኘ መጠን ይበልጥ ያማሩ የማምለኪያ ዓምዶችን ሠራ።+ + 2 ልባቸው ግብዝ* ነው፤በመሆኑም በደለኞች ናቸው። መሠዊያዎቻቸውን የሚሰባብር፣ ዓምዶቻቸውንም የሚያፈራርስ አለ። + 3 እነሱም ‘ንጉሥ የለንም፤+ ይሖዋን አልፈራንምና። ንጉሥ ቢኖረንስ ምን ሊያደርግልን ይችላል?’ ይላሉ። + 4 ከንቱ ቃል ይናገራሉ፤ በሐሰት ይምላሉ፤+ ቃል ኪዳንም ይገባሉ፤ስለዚህ የሚፈረደው ፍርድ በእርሻ ትልም ውስጥ እንዳለ መርዛማ አረም ነው።+ + 5 የሰማርያ ነዋሪዎች በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ስጋት ያድርባቸዋል።+ ሕዝቡም ሆኑ በእሱና በክብሩ ሐሴት ያደረጉት የባዕድ አምላክ ካህናትለእሱ ያዝናሉ፤ከእነሱ ተለይቶ በግዞት ይወሰዳልና። + 6 ለአንድ ታላቅ ንጉሥ እንደሚቀርብ ስጦታ ወደ አሦር ይወሰዳል።+ ኤፍሬም ውርደት ይከናነባል፤እስራኤልም በተከተለው ምክር የተነሳ ያፍራል።+ + 7 ሰማርያና ንጉሧ ተቆርጦ ውኃ ላይ እንደወደቀ ቅርንጫፍተጠራርገው ይጠፋሉ።+ + 8 የእስራኤል ኃጢአት+ የሆኑት በቤትአዌን+ የሚገኙ ከፍ ያሉ ���ማምለኪያ ቦታዎች ይወድማሉ።+ መሠዊያዎቻቸውን እሾህና አሜኬላ ይወርሷቸዋል።+ ሰዎች ተራሮቹን ‘ሸሽጉን!’ ኮረብቶቹንም ‘በላያችን ውደቁ!’ ይሏቸዋል።+ + 9 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ከጊብዓ ዘመን ጀምሮ ኃጢአት ሠርታችኋል።+ እነሱ በዚያ ጸንተዋል። በጊብዓ የተካሄደው ጦርነት የዓመፅን ልጆች አልፈጃቸውም።* +10 በፈለግኩ ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ። ሁለቱ በደሎቻቸው በላያቸው በሚጫኑበት ጊዜ*ሕዝቦች በእነሱ ላይ ይሰበሰባሉ። +11 ኤፍሬም ማበራየት የምትወድ የተገራች ጊደር ነው፤በመሆኑም ያማረ አንገቷን አተረፍኩ። ሰውም ኤፍሬምን እንዲጋልብ አደርጋለሁ።*+ ይሁዳ ያርሳል፤ ያዕቆብም መሬቱን ለእሱ ያለሰልሳል። +12 ለራሳችሁ የጽድቅን ዘር ዝሩ፤ ታማኝ ፍቅርንም እጨዱ። ይሖዋን መፈለግ የምትችሉበት ጊዜ ከማለፉ በፊት፣+እሱም መጥቶ በጽድቅ መመሪያ እስኪሰጣችሁ ድረስ+ያልለማውን መሬት ለራሳችሁ እረሱ።+ +13 እናንተ ግን ክፋትን አረሳችሁ፤ዓመፅን አጨዳችሁ፤+የማታለልንም ፍሬ በላችሁ፤በገዛ ራሳችሁ መንገድ፣በተዋጊዎቻችሁም ብዛት ታምናችኋልና። +14 በሕዝባችሁ ላይ ሁከት ይነሳል፤እናቶች ከልጆቻቸው ጋር በተጨፈጨፉበት* የውጊያ ቀንሻልማን፣ ቤትአርቤልን እንዳወደመ ሁሉ፣የተመሸጉ ከተሞቻችሁ በሙሉ ይወድማሉ።+ +15 ቤቴል ሆይ፣ ክፋትሽ ታላቅ ስለሆነ እንዲሁ ይደረግብሻል።+ ጎህ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።”*+ +14 “እስራኤል ሆይ፣ በበደልህ ስለተሰናከልክወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ተመለስ።+ + 2 ይህን ቃል ይዛችሁ ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤እንዲህ በሉት፦ ‘በደላችንን ይቅር በለን፤+ መልካም የሆነውንም ነገር ተቀበለን፤እኛም ወይፈኖች እንደምናቀርብ፣ የከንፈራችንን ውዳሴ እናቀርብልሃለን።*+ + 3 አሦር አያድነንም።+ ፈረሶችን አንጋልብም፤+ከእንግዲህም ወዲህ የገዛ እጆቻችን የሠሩትን “አምላካችን ሆይ!” አንልም፤አባት የሌለው ልጅ ምሕረት ያገኘው በአንተ ነውና።’+ + 4 እኔም ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ።+ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ፤+ምክንያቱም ቁጣዬ ከእሱ ተመልሷል።+ + 5 እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤እሱም እንደ አበባ ያብባል፤እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥሮቹን ይሰዳል። + 6 ቀንበጦቹ ይንሰራፋሉ፤ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣መዓዛውም እንደ ሊባኖስ ዛፍ ይሆናል። + 7 እነሱም ዳግመኛ በጥላው ሥር ይኖራሉ። እህል ያበቅላሉ፤ እንደ ወይን ተክልም ያብባሉ።+ ዝናው* እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይሆናል። + 8 ኤፍሬም ‘ከእንግዲህ ከጣዖቶች ጋር ምን ጉዳይ አለኝ?’ ይላል።+ መልስ እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም እጠብቀዋለሁ።+ እኔ እንደለመለመ የጥድ ዛፍ እሆናለሁ። ከእኔም ፍሬ ታገኛላችሁ።” + 9 ጥበበኛ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ያስተውል። ልባም የሆነ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ይወቅ። የይሖዋ መንገዶች ቀና ናቸውና፤+ጻድቃንም በመንገዶቹ ላይ ይሄዳሉ፤በደለኞች ግን በእነሱ ይሰናከላሉ። +9 “እስራኤል ሆይ፣ ሐሴት አታድርግ፤+እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች ደስ አይበልህ። ምንዝር በመፈጸም* ከአምላክህ ርቀሃልና።+ በየእህል አውድማ ላይ ለዝሙት አዳሪ የሚከፈለውን ደሞዝ ወደኸዋል።+ + 2 ሆኖም የእህል አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፤አዲሱም የወይን ጠጅ ይቋረጥባቸዋል።+ + 3 በይሖዋ ምድር ላይ አይኖሩም፤+ይልቁንም ኤፍሬም ወደ ግብፅ ይመለሳል፤በአሦርም የረከሰ ነገር ይበላሉ።+ + 4 ከእንግዲህ ለይሖዋ የወይን ጠጅ መባ አያፈሱም፤+መሥዋዕታቸውም አያስደስተውም።+ እንደ እዝን እንጀራ ናቸው፤የሚበሉትም ሁሉ ራሳቸውን ያረክሳሉ። ምግባቸው ለራሳቸው ብቻ* ነውና፤ወደ ይሖዋ ቤት አይገባም። + 5 የምትሰበሰቡበትና* ለይሖዋ በዓል የምታከብሩበት ��ን ሲደርስምን ታደርጉ ይሆን? + 6 እነሆ፣ ምድሪቱ በመውደሟ ለመሸሽ ይገደዳሉ።+ ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤+ ሜምፊስ ደግሞ ትቀብራቸዋለች።+ ከብር የተሠሩ ውድ ንብረቶቻቸውን ሳማ ይወርሰዋል፤በድንኳኖቻቸውም ውስጥ እሾሃማ ቁጥቋጦ ይበቅላል። + 7 ምርመራ የሚካሄድበት ጊዜ ይመጣል፤+የበቀል ቀን ይመጣል፤እስራኤልም ይህን ይወቅ! የእነሱ ነቢይ ሞኝ፣ በመንፈስ የሚናገረውም ሰው እንደ እብድ ይሆናል፤ምክንያቱም በደልህ ብዙ ነው፤ በአንተም ላይ የሚደርሰው ጥላቻ በዝቷል።” + 8 የኤፍሬም ጠባቂ+ ከአምላኬ ጋር ነበር።+ አሁን ግን የነቢያቱ+ መንገዶች ሁሉ እንደ ወፍ አዳኝ ወጥመዶች ናቸው፤በአምላኩ ቤት ጠላትነት አለ። + 9 በጊብዓ ዘመን እንደነበረው፣ ጥፋት በሚያስከትሉ ነገሮች ተዘፍቀዋል።+ እሱ በደላቸውን ያስባል፤ በሠሩትም ኃጢአት የተነሳ ይቀጣቸዋል።+ +10 “እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ ወይን ሆኖ አገኘሁት።+ አባቶቻችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ባፈራ የበለስ ዛፍ ላይ እንደ ጎመራ የበለስ ፍሬ ሆነው አየኋቸው። ሆኖም ወደ ፌጎር ባአል ሄዱ፤+ለአሳፋሪውም ነገር* ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፤+እንደወደዱትም ነገር አስጸያፊዎች ሆኑ። +11 የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤መውለድ፣ ማርገዝም ሆነ መፀነስ የለም።+ +12 ልጆች ቢያሳድጉም እንኳአንድም ሰው እስከማይቀር ድረስ የወላድ መሃን አደርጋቸዋለሁ፤+አዎ፣ ከእነሱ በራቅኩ ጊዜ ወዮላቸው!+ +13 በግጦሽ ስፍራ የተተከለው ኤፍሬም ለእኔ እንደ ጢሮስ ነበር፤+አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለእርድ አሳልፎ ይሰጣል።” +14 ይሖዋ ሆይ፣ ልትሰጣቸው የሚገባውን ስጣቸው፤የሚጨነግፍ ማህፀንና የደረቁ* ጡቶች ስጣቸው። +15 “ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ በጊልጋል ፈጸሙ፤+ እኔም በዚያ ጠላኋቸው። በሠሩት ክፉ ድርጊት የተነሳ ከቤቴ አባርራቸዋለሁ።+ ከእንግዲህ ወዲያ ፍቅሬን እነፍጋቸዋለሁ፤+አለቆቻቸው ሁሉ እልኸኞች ናቸው። +16 ኤፍሬም ጉዳት ይደርስበታል።+ ሥራቸው ይደርቃል፤ አንዳችም ፍሬ አያፈሩም። ቢወልዱ እንኳ የሚወዷቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።” +17 እሱን ስላልሰሙት+አምላኬ ይተዋቸዋል፤በብሔራትም መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።+ +13 “ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤በእስራኤል ነገዶች መካከል ትልቅ ቦታ ነበረው።+ ሆኖም ባአልን በማምለክ በደል በመፈጸሙ+ ሞተ። + 2 አሁንም ተጨማሪ ኃጢአት ይሠራሉ፤በብራቸውም ለራሳቸው የብረት ምስሎች* ይሠራሉ፤+በጥበብ ጣዖቶችን ያበጃሉ፤ ሁሉም የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራቸው ናቸው። ‘መሥዋዕት የሚያቀርቡት ሰዎች ጥጃዎቹን ይሳሙ’+ በማለት ለእነሱ ይናገራሉ። + 3 ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ይሆናሉ፤አውሎ ነፋስ ከአውድማ ላይ ጠራርጎ እንደሚወስደው እብቅ፣በጭስ ማውጫም በኩል እንደሚወጣ ጭስ ይሆናሉ። + 4 ይሁንና ከግብፅ ምድር አንስቶ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ፤+ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም ነበር፤ከእኔም ሌላ አዳኝ የለም።+ + 5 እኔ በምድረ በዳ፣ ድርቅ ባለበትም ምድር ተንከባከብኩህ።+ + 6 በግጦሽ መሬታቸው ላይ ከበሉ በኋላ ጠገቡ፤+በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ። ከዚህም የተነሳ ረሱኝ።+ + 7 ስለዚህ እንደ አንበሳ፣+በመንገድም ዳር እንደሚያደባ ነብር እሆንባቸዋለሁ። + 8 ግልገሎቿን እንደተነጠቀች ድብ ሆኜ እመጣባቸዋለሁ፤ደረታቸውንም እዘነጥላለሁ። በዚያ እንደ አንበሳ እውጣቸዋለሁ፤የዱር አውሬ ይቦጫጭቃቸዋል። + 9 እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ላይ ስለተነሳህ፣ረዳትህንም ስለተቃወምክ ያጠፋሃል። +10 ‘ንጉሥና መኳንንት ስጠኝ’ ብለህ ነበር፤ታዲያ በከተሞችህ ሁሉ ያድንህ ዘንድ+ንጉሥህ የት አለ? ገዢዎችህስ* የት አሉ?+ +11 እኔም ተቆጥቼ ንጉሥ ሰጠሁህ፤+በታላቅ ቁጣዬም አስወግደዋለሁ።+ +12 የኤፍሬም በደል ታሽጎ ተቀምጧል፤*ኃጢአቱም ተከማችቷል። +13 ምጥ እንደያዛት ሴት ይሆናል። እሱ ግን ጥበበኛ ልጅ አይደለም፤የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ በቦታው ላይ አይገኝም። +14 ከመቃብር* እጅ እዋጃቸዋለሁ፤ከሞትም እታደጋቸዋለሁ።+ ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ?+ መቃብር ሆይ፣ አጥፊነትህ የት አለ?+ ርኅራኄ ከዓይኔ ፊት ይሰወራል። +15 በቄጠማዎች መካከል ተመችቶት ቢያድግ እንኳየምሥራቅ ነፋስ ይኸውም የይሖዋ ነፋስ ይመጣል፤የውኃ ጉድጓዱ እንዲደርቅ፣ ምንጩም እንዲነጥፍ ለማድረግ ከበረሃ ይመጣል። ውድ የሆኑ ንብረቶቹ ሁሉ የሚገኙበትን ግምጃ ቤቱን ይበዘብዛል።+ +16 ሰማርያ በአምላኳ ላይ ስላመፀች+ ተጠያቂ ትሆናለች።+ በሰይፍ ይወድቃሉ፤+ልጆቻቸው ይፈጠፈጣሉ፤የእርጉዝ ሴቶቻቸውም ሆድ ይቀደዳል።” +5 “እናንተ ካህናት፣ ይህን ስሙ፤+እናንተ የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ በትኩረት አዳምጡ፤እናንተም የንጉሡ ቤት ሰዎች፣ አዳምጡ፤ፍርዱ እናንተንም ይጨምራልና፤ምክንያቱም ለምጽጳ ወጥመድ፣በታቦርም+ ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል። + 2 ከትክክለኛው መንገድ የራቁት ሰዎች* ደም በማፍሰስ ወንጀል ተዘፍቀዋል፤*እኔም ለሁሉም ማስጠንቀቂያ እሰጣለሁ።* + 3 ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፤እስራኤልም ከእኔ የተሰወረ አይደለም። ኤፍሬም ሆይ፣ አሁን አንተ ሴሰኛ ሆነሃል፤*እስራኤል ራሱን አርክሷል።+ + 4 የሠሩት ሥራ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ምክንያቱም በመካከላቸው የአመንዝራነት* መንፈስ አለ፤+ለይሖዋም እውቅና አይሰጡም። + 5 የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ* መሥክሮበታል፤+እስራኤልና ኤፍሬም የሠሩት በደል አሰናክሏቸዋል፤ይሁዳም ከእነሱ ጋር ተሰናክሏል።+ + 6 መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ይዘው ይሖዋን ፍለጋ ሄዱ፤ሆኖም ሊያገኙት አልቻሉም። እሱ ከእነሱ ርቋል።+ + 7 እነሱ ይሖዋን ከድተዋል፤+ባዕድ ወንዶች ልጆች ወልደዋልና። አሁንም አንድ ወር፣ እነሱንና ድርሻቸውን* ይውጣል።* + 8 በጊብዓ ቀንደ መለከት፣ በራማም+ መለከት ንፉ!+ ‘ቢንያም ሆይ፣ ከኋላህ ነን!’ ብላችሁ በቤትአዌን+ ቀረርቶ አሰሙ። + 9 ኤፍሬም ሆይ፣ በምትቀጣበት ቀን መቀጣጫ ትሆናለህ።+ በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ምን እንደሚከሰት አሳውቄአለሁ። +10 የይሁዳ መኳንንት ወሰን እንደሚገፉ ሰዎች ናቸው።+ በእነሱ ላይ ቁጣዬን እንደ ውኃ አፈሳለሁ። +11 ኤፍሬም ተጨቁኗል፤ በፍርድ ተረግጧል፤ባላጋራውን ለመከተል ቆርጧልና።+ +12 በመሆኑም እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ለይሁዳ ቤት ደግሞ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ። +13 ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቁስሉን ሲመለከትኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤+ ወደ ታላቅ ንጉሥም መልእክተኞች ላከ። ይሁንና ንጉሡ እናንተን ሊፈውሳችሁ አልቻለም፤ቁስላችሁንም ሊያድን አልቻለም። +14 እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ለይሁዳም ቤት እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና። እኔ ራሴ ቦጫጭቄአቸው እሄዳለሁ፤+ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ የሚታደጋቸውም አይኖርም።+ +15 እሄዳለሁ፤ በደላቸው የሚያስከትልባቸውን መዘዝ እስኪሸከሙም ድረስ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤በዚህ ጊዜም ሞገሴን* ይሻሉ።+ በጭንቀት በሚዋጡበት ጊዜ እኔን ይሻሉ።”+ +3 “እነሆ፣ በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜየይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮኞች ስመልስ፣+ + 2 ብሔራትን ሁሉ ሰብስቤወደ ኢዮሳፍጥ* ሸለቆ* አወርዳቸዋለሁ። ለሕዝቤና ርስቴ ለሆነው ለእስራኤል ስልበዚያ ከእነሱ ጋር እፋረዳለሁ፤+በብሔራት መካከል በትነዋቸዋልና፤ደግሞም ምድሬን ተከፋፍለዋታል።+ + 3 በሕዝቤ ላይ ዕጣ ይጣጣላሉና፤+ዝሙት አዳሪ ለማግኘት ሲሉ ወንድ ልጅን አሳልፈው ይሰጣሉ፤የወይን ጠጅ ለመጠጣት ሲሉም ሴት ልጅን ይሸጣሉ። + 4 ጢሮስ፣ ሲዶና እና የፍልስጤም ግዛቶች ሁሉ፣ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አላችሁ? ላደረግኩባችሁ ነገር ብድራት ልትመልሱልኝ ነው? ብድራት የምትመልሱልኝ ከሆነብድራታችሁን ወዲያውኑ፣ በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።+ + 5 ምክንያቱም እናንተ ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፤+እጅግ ምርጥ የሆነውን ውድ ንብረቴንም ወደ ቤተ መቅደሶቻችሁ አስገብታችኋል፤ + 6 ደግሞም ከምድራቸው ርቀው እንዲሄዱ ለማድረግ ስትሉየይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለግሪኮች ሸጣችሁ፤+ + 7 እነሆ፣ እነሱን ከሸጣችሁባቸው ቦታዎች እንዲመለሱ አነሳሳቸዋለሁ፤+ብድራታችሁንም በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ። + 8 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ለይሁዳ ሕዝብ እሸጣለሁ፤+እነሱም በሩቅ ላለ ብሔር ይኸውም ለሳባ ሰዎች ይሸጧቸዋል፤ይሖዋ ራሱ ይህን ተናግሯልና። + 9 በብሔራት መካከል ይህን አውጁ፦+ ‘ለጦርነት ተዘጋጁ!* ኃያላን ሰዎችን አነሳሱ! ወታደሮቹ ሁሉ ቀርበው ጥቃት ይሰንዝሩ!+ +10 ማረሻችሁን ሰይፍ፣ ማጭዳችሁንም ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ። ደካማው ሰው “እኔ ብርቱ ነኝ” ይበል። +11 እናንተ ዙሪያውን ያላችሁ ብሔራት ሁሉ፣ ኑና ተረዳዱ፤ አንድ ላይም ተሰብሰቡ!’”+ ይሖዋ ሆይ፣ ኃያላንህን* ወደዚያ ቦታ አውርድ። +12 “ብሔራት ይነሱና ወደ ኢዮሳፍጥ ሸለቆ* ይምጡ፤ዙሪያውን ባሉት ብሔራት ሁሉ ላይ ለመፍረድ በዚያ እቀመጣለሁና።+ +13 መከሩ ስለደረሰ ማጭድ ስደዱ። የወይን መጭመቂያው ስለሞላ ኑ፣ ወርዳችሁ እርገጡ።+ ማጠራቀሚያዎቹ ሞልተው አፍስሰዋል፤ ክፋታቸው እጅግ በዝቷልና። +14 ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ የፍርድ ውሳኔ በሚሰጥበት ሸለቆ* ተሰብስቧል፤የፍርድ ውሳኔ በሚሰጥበት ሸለቆ* የይሖዋ ቀን ቀርቧልና።+ +15 ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ከዋክብትም ብርሃናቸውን አይሰጡም። +16 ይሖዋም ከጽዮን እንደ አንበሳ ያገሳል፤ከኢየሩሳሌም ድምፁን በኃይል ያሰማል። ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፤ይሖዋ ግን ለሕዝቡ መጠጊያ፣+ለእስራኤል ሕዝብ ምሽግ ይሆናል። +17 እናንተም እኔ በተቀደሰው ተራራዬ+ በጽዮን የምኖር አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። ኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራ ትሆናለች፤+እንግዶችም* ከእንግዲህ በእሷ አያልፉም።+ +18 በዚያ ቀን ተራሮቹ ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤+ኮረብቶቹ ወተት ያፈሳሉ፤የይሁዳ ጅረቶችም ሁሉ በውኃ ይሞላሉ። ከይሖዋም ቤት ምንጭ ይፈልቃል፤+የሺቲምንም* ሸለቆ* ያጠጣል። +19 ግብፅ ግን ባድማ ትሆናለች፤+ኤዶምም በምድራቸው ንጹሕ ደም በማፍሰስ+በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ስለፈጸመች+ጠፍ ምድረ በዳ ትሆናለች።+ +20 ይሁንና ይሁዳ ምንጊዜም፣ኢየሩሳሌምም ከትውልድ እስከ ትውልድ የሰው መኖሪያ ትሆናለች።+ +21 ንጹሕ አድርጌ ያልቆጠርኩትን ደማቸውን* ንጹሕ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፤+ይሖዋም በጽዮን ይኖራል።”+ +1 ወደ ፐቱኤል ልጅ፣ ወደ ኢዩኤል* የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ + 2 “እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ፤የአገሪቱም* ነዋሪዎች ሁሉ ልብ በሉ። በእናንተም ዘመን ይሁን በአባቶቻችሁ ዘመንእንዲህ ያለ ነገር ተከስቶ ያውቃል?+ + 3 ይህን ለልጆቻችሁ ተናገሩ፤ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው፣የእነሱ ልጆች ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ ይናገሩ። + 4 ከአውዳሚ አንበጣ የተረፈውን የአንበጣ መንጋ በላው፤+ከአንበጣ መንጋ የተረፈውንም ኩብኩባ በላው፤ከኩብኩባ የተረፈውን ደግሞ የማይጠግብ አንበጣ በላው።+ + 5 እናንተ ሰካራሞች ንቁ፤+ ደግሞም አልቅሱ! እናንተ የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉጣፋጩ የወይን ጠጅ ከአፋችሁ ላይ ስለተወሰደ ዋይ ዋይ በሉ።+ + 6 ኃያል የሆነና የሕዝቡ ብዛት ስፍር ቁጥር የሌለው ብሔር ምድሬን ወሮታልና።+ ጥርሶቹ የአንበሳ ጥርሶች ናቸ���፤+ መንገጭላውም የአንበሳ መንገጭላ ነው። + 7 የወይን ተክሌን አጠፋው፤ የበለስ ዛፌንም ጉቶ አደረገው፤ቅርፊታቸውን ሙልጭ አድርጎ ልጦ ወዲያ ጣላቸው፤በቅርንጫፎቻቸው ላይ አንድም ልጥ አልቀረም። + 8 ማቅ ለብሳ ለልጅነት ሙሽራዋ* እንደምታለቅስ ድንግል*ዋይ ዋይ በዪ። + 9 የእህል መባና+ የመጠጥ መባ+ ከይሖዋ ቤት ተቋርጧል፤የይሖዋ አገልጋዮች የሆኑት ካህናቱም ሐዘን ላይ ናቸው። +10 እርሻው ወድሟል፤ ምድሪቱ አዝናለች፤+እህሉ ወድሟልና፤ አዲሱ የወይን ጠጅ ደርቋል፤ ዘይቱም ተሟጧል።+ +11 ገበሬዎች አፍረዋል፤ የወይን አትክልት ሠራተኞች ዋይ ዋይ ይላሉ፤ይህም የሆነው ከስንዴውና ከገብሱ የተነሳ ነው፤የእርሻው መከር ጠፍቷልና። +12 ወይኑ ደርቋል፤የበለስ ዛፉም ጠውልጓል። ሮማኑ፣ ዘንባባው፣ ፖሙናበሜዳው ላይ ያለው ዛፍ ሁሉ ደርቋል፤+በሕዝቡ መካከል የነበረው ደስታ ወደ ኀፍረት ተለውጧልና። +13 እናንተ ካህናት ማቅ ልበሱ፤* ደግሞም ሐዘን ተቀመጡ፤*እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ+ ዋይ ዋይ በሉ። እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች ኑ፣ ማቅ ለብሳችሁ እደሩ፤ከአምላካችሁ ቤት የእህል መባና+ የመጠጥ መባ+ ተቋርጧልና። +14 ጾም አውጁ!* የተቀደሰ ጉባኤ ጥሩ።+ ሽማግሌዎቹንና የምድሪቱን ነዋሪዎች ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ ቤት ሰብስቡ፤+እርዳታም ለማግኘት ወደ ይሖዋ ጩኹ። +15 ከቀኑ የተነሳ ወዮላችሁ! የይሖዋ ቀን ቀርቧልና፤+ሁሉን ከሚችለው አምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል! +16 ምግብ ከዓይናችን ፊት፣ሐሴትና ደስታም ከአምላካችን ቤት ጠፍቶ የለም? +17 ዘሮቹ* ከአካፋዎቻቸው ሥር ጠውልገዋል። ጎተራዎቹም ተራቁተዋል። ጎታዎቹ* ፈራርሰዋል፤ እህሉ ደርቋልና። +18 መንጎቹ እንኳ ሳይቀሩ ያቃስታሉ! ከብቶቹ ግራ ተጋብተው ይቅበዘበዛሉ፤ መሰማሪያ የላቸውምና! የበጎቹም መንጋ ቅጣቱን ይቀበላል። +19 ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ፤+በምድረ በዳ ያለውን የግጦሽ መሬት እሳት በልቶታልና፤በሜዳ ያሉትንም ዛፎች ሁሉ ነበልባል አቃጥሏቸዋል። +20 የዱር አራዊትም እንኳ አንተን በጉጉት ይጠባበቃሉ፤ምክንያቱም የውኃ ጅረቶቹ ደርቀዋል፤በምድረ በዳ ያለውን የግጦሽ መሬትም እሳት በልቶታል።” +2 “በጽዮን ቀንደ መለከት ንፉ!+ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ ቀረርቶ አሰሙ። የአገሪቱ* ነዋሪዎች በሙሉ ይንቀጥቀጡ፤የይሖዋ ቀን ቀርቧልና!+ ቀኑ ደፍ ላይ ነው! + 2 የጨለማና የጭጋግ ቀን፣+የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤+በተራሮች ላይ እንደፈነጠቀ የማለዳ ወጋገን ነው። ስፍር ቁጥር የሌለውና ኃያል የሆነ ሕዝብ ይመጣል፤+ከዚህ በፊት እንደ እሱ ያለ ፈጽሞ ታይቶ አያውቅም፤ወደፊትም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስእንደ እሱ ያለ አይኖርም። + 3 ከፊቱ ያለውን እሳት ይበላዋል፤ከኋላው ያለውንም ነበልባል ያቃጥለዋል።+ ከፊቱ ያለው ምድር እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ ነው፤+ከኋላው ያለው ግን ወና ምድረ በዳ ነው፤ከእሱም የሚያመልጥ አይኖርም። + 4 መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤እንደ ጦር ፈረሶችም ይጋልባሉ።+ + 5 በተራሮች አናት ላይ ሲዘሉ የሚሰማው ድምፅ እንደ ሠረገሎች ድምፅ፣+ገለባንም እንደሚበላ የሚንጣጣ የእሳት ነበልባል ድምፅ ነው። ለጦርነት እንደተሰለፈ+ ኃያል ሕዝብ ናቸው። + 6 ከእነሱም የተነሳ ሕዝቦች ይጨነቃሉ። የሰውም ፊት ሁሉ ይቀላል። + 7 እንደ ተዋጊዎች በፍጥነት ጥቃት ይሰነዝራሉ፤እንደ ወታደሮች ቅጥር ላይ ይወጣሉ፤እያንዳንዱም የራሱን መንገድ ይዞ ይሄዳል፤አቅጣጫቸውንም አይቀይሩም። + 8 እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤እያንዳንዱ ሰው መንገዱን ይዞ ይገሰግሳል። አንዳንዶቹ በመሣሪያ* ተመተው ቢወድቁ እንኳሌሎቹ አይፍረከረኩም። + 9 ወደ ከተማዋ እየተ��ደፉ ይገባሉ፤ በቅጥርም ላይ ይሮጣሉ። ቤቶችም ላይ ይወጣሉ፤ እንደ ሌባ በመስኮት ይገባሉ። +10 ምድሪቱ በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፤ ሰማያትም ይናወጣሉ። ፀሐይና ጨረቃ ጨልመዋል፤+ከዋክብትም ብርሃናቸውን መስጠት አቁመዋል። +11 ይሖዋ በሠራዊቱ+ ፊት ድምፁን በኃይል ያሰማል፤ ሠራዊቱ ስፍር ቁጥር የለውም።+ ቃሉን የሚፈጽመው ኃያል ነውና፤የይሖዋ ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነው።+ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?”+ +12 “አሁንም ቢሆን” ይላል ይሖዋ፣“በጾም፣+ በለቅሶና በዋይታ በሙሉ ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ።+ +13 ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤+ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋም ተመለሱ፤እሱ ሩኅሩኅና* መሐሪ፣ ለቁጣ የዘገየና+ ታማኝ ፍቅሩ የበዛ ነውና፤+ሊያመጣ ያሰበውንም ጥፋት መለስ ብሎ ያጤናል።* +14 ደግሞም ተመልሶ ጉዳዩን እንደገና በማጤን፣*+ለአምላካችሁ ለይሖዋ የእህል መባና የመጠጥ መባ ማቅረብ ትችሉ ዘንድበረከት ያስቀርላችሁ እንደሆነ ማን ያውቃል? +15 በጽዮን ቀንደ መለከት ንፉ! ጾም አውጁ፤* የተቀደሰ ጉባኤ ጥሩ።+ +16 ሕዝቡን ሰብስቡ፤ ጉባኤውን ቀድሱ።+ ሽማግሌዎቹን ሰብስቡ፤ ልጆቹንና ጡት የሚጠቡትን ሕፃናት ሰብስቡ።+ ሙሽራው ከውስጠኛው ክፍል፣ ሙሽሪትም ከጫጉላ ቤት ይውጡ። +17 የይሖዋ አገልጋዮች የሆኑት ካህናቱበበረንዳውና በመሠዊያው መካከል+ ሆነው ያልቅሱ፤ እንዲህም ይበሉ፦ ‘ይሖዋ ሆይ፣ ለሕዝብህ እዘን፤ርስትህ መሳለቂያ እንዲሆን አታድርግ፤ብሔራትም አይግዟቸው። ሕዝቦች “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?’+ +18 ያን ጊዜ ይሖዋ ለምድሩ ይቀናል፤ለሕዝቡም ይራራል።+ +19 ይሖዋ ለሕዝቡ መልስ ይሰጣል፦ ‘እነሆ እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት እልክላችኋለሁ፤እናንተም በሚገባ ትጠግባላችሁ፤+ከእንግዲህ በብሔራት መካከል ለነቀፋ አልዳርጋችሁም።+ +20 የሰሜኑን ሠራዊት ከእናንተ አርቃለሁ፤ደረቅና ወና ወደሆነ ጠፍ መሬት እበትነዋለሁ፤ፊቱ ወደ ምሥራቁ ባሕር፣*ኋላውም ወደ ምዕራቡ ባሕር* ይሆናል። ግማቱ ወደ ላይ ይወጣል፤ክርፋቱም ወደ ላይ መውጣቱን ይቀጥላል፤+አምላክ ታላላቅ ነገሮች ያደርጋልና።’ +21 ምድር ሆይ፣ አትፍሪ። ደስ ይበልሽ፤ ሐሴትም አድርጊ፤ ይሖዋ ታላላቅ ነገሮች ያደርጋልና። +22 እናንተ የዱር እንስሳት፣ አትፍሩ፤በምድረ በዳ ያሉት መሰማሪያዎች ይለመልማሉና፤+ዛፎችም ፍሬ ያፈራሉ፤+የበለስ ዛፉና የወይን ተክሉ ጥሩ ምርት ይሰጣሉ።+ +23 እናንተ የጽዮን ልጆች ሆይ፣ በአምላካችሁ በይሖዋ ተደሰቱ፤ ሐሴትም አድርጉ፤+እሱ የፊተኛውን ዝናብ በተገቢው መጠን ይሰጣችኋልና፤በእናንተም ላይ ዝናቡን ያዘንባል፤እንደቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ ይሰጣችኋል።+ +24 አውድማዎቹ በእህል ይሞላሉ፤መጭመቂያዎቹም በአዲስ የወይን ጠጅና በዘይት ተሞልተው ያፈሳሉ።+ +25 ደግሞም በመካከላችሁ የሰደድኩት ታላቁ ሠራዊቴይኸውም የአንበጣ መንጋው፣ ኩብኩባው፣ የማይጠግበው አንበጣና አውዳሚው አንበጣሰብላችሁን ለበሉባቸው ዓመታት ማካካሻ እሰጣችኋለሁ።+ +26 እስክትጠግቡ ድረስ ትበላላችሁ፤+ደግሞም ድንቅ ነገሮችን ያደረገላችሁንየአምላካችሁን የይሖዋን ስም ታወድሳላችሁ፤+ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ አያፍርም።+ +27 እናንተም እኔ በእስራኤል መካከል እንደሆንኩ+እንዲሁም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ፣+ ከእኔም በቀር ሌላ እንደሌለ ታውቃላችሁ! ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ አያፍርም። +28 ከዚያ በኋላ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁ፤+ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፤ወጣቶቻችሁም ራእዮችን ያያሉ።+ +29 በዚያ ቀን በወንዶች ባሪያዎቼና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ሳይቀርመንፈሴን አፈሳለሁ። +30 በሰማያትና በምድር ድንቅ ነገሮች አሳያለሁ፤*ደም፣ እሳትና የጭስ ዓምድ ይታያል።+ +31 ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን+ ከመምጣቱ በፊትፀሐይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።+ +32 የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤+ይሖዋ እንደተናገረው በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚድኑ+ ይኸውምይሖዋ የሚጠራቸው ከጥፋት የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉ።” +3 “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ይሖዋ ስለ እናንተ ይኸውም ከግብፅ ምድር ስላወጣሁት ስለ መላው ብሔር የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦ + 2 ‘በምድር ላይ ካሉ ብሔራት ሁሉ እኔ የማውቀው እናንተን ብቻ ነው።+ ስለዚህ ለፈጸማችሁት በደል ሁሉ ተጠያቂ አደርጋችኋለሁ።+ + 3 ሁለት ሰዎች ለመገናኘት ሳይስማሙ* አብረው ይጓዛሉ? + 4 አንበሳ አድኖ ሳይዝ በጫካ ውስጥ ያገሳል? ደቦል አንበሳስ ምንም ነገር ሳይዝ በዋሻው ውስጥ ሆኖ ያጉረመርማል? + 5 ወጥመድ ሳይዘጋጅ* ወፍ መሬት ላይ ይጠመዳል? ወጥመድስ ምንም ነገር ሳይዝ ይፈነጠራል? + 6 በከተማ ውስጥ ቀንደ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይሸበርም? በከተማው ውስጥ ጥፋት ቢከሰት ይህን ያደረገው ይሖዋ አይደለም? + 7 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሚስጥሩን* ሳይገልጥምንም ነገር አያደርግምና።+ + 8 አንበሳ አገሳ!+ የማይፈራ ማን ነው? ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ተናገረ! ትንቢት የማይናገር ማን ነው?’+ + 9 ‘በአሽዶድ በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎችደግሞም በግብፅ ምድር በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎች ላይ አውጁት። እንዲህ በሉ፦ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤+በመካከሏ ያለውን ሁከትናበውስጧ የሚፈጸመውን ግፍ ተመልከቱ።+ +10 በማይደፈሩ ማማዎቻቸው ውስጥ ዓመፅንና ጥፋትን የሚያከማቹ ሰዎችትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ አያውቁምና” ይላል ይሖዋ።’ +11 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ጠላት ምድሪቱን ይከባል፤+ብርታትሽን ያሟጥጣል፤የማይደፈሩ ማማዎችሽም ይበዘበዛሉ።’+ +12 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት ቅልጥም ወይም የጆሮ ቁራጭ ነጥቆ እንደሚወስድ ሁሉበሰማርያ ባማረ አልጋና ምርጥ በሆነ ድንክ አልጋ* የሚቀመጡየእስራኤል ሰዎችም ተነጥቀው ይወሰዳሉ።’+ +13 ‘ስሙ፤ የያዕቆብንም ቤት አስጠንቅቁ’* ይላል የሠራዊት አምላክ የሆነው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። +14 ‘እስራኤልን ለፈጸመው የዓመፅ ድርጊት* ሁሉ ተጠያቂ በማደርገው ቀን+የቤቴልንም መሠዊያዎች ተጠያቂ አደርጋለሁና፤+የመሠዊያው ቀንዶች ተቆርጠው ወደ ምድር ይወድቃሉ።+ +15 የክረምቱን ቤትና የበጋውን ቤት አፈርሳለሁ።’ ‘በዝሆን ጥርስ የተሠሩት ቤቶች ይወድማሉ፤+ትላልቅ* ቤቶችም ይደመሰሳሉ’+ ይላል ይሖዋ።” +7 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ በኋለኛው ወቅት የተዘራው እህል* መብቀል በጀመረበት ጊዜ እሱ የአንበጣ መንጋ ሰደደ። ይህም የንጉሡ ድርሻ የሆነው ሣር ታጭዶ ሲያበቃ በኋለኛው ወቅት የበቀለ እህል ነበር። +2 የአንበጣው መንጋ በምድሪቱ ላይ የበቀለውን ተክል ሁሉ በልቶ በጨረሰ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ይቅር በል!+ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋም ይችላል? እሱ አቅመ ቢስ ነውና!”+ +3 በመሆኑም ይሖዋ ጉዳዩን በድጋሚ አጤነ።*+ ይሖዋም “ይህ አይፈጸምም” አለ። +4 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእሳት እንደሚቀጣ ተናገረ። እሳቱም የተንጣለለውን ጥልቅ ውኃ በላ፤ ደግሞም የተወሰነውን የምድሪቱን ክፍል በላ። +5 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ይህ ነገር እንዲደርስ አታድርግ።+ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋም ይችላል? እሱ አቅመ ቢስ ��ውና!”+ +6 በመሆኑም ይሖዋ ጉዳዩን በድጋሚ አጤነ።*+ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋም “ይህም ቢሆን አይፈጸምም” አለ። +7 እሱም ይህን አሳየኝ፦ እነሆ ይሖዋ በቱምቢ በተሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር፤ በእጁም ቱምቢ ይዞ ነበር። +8 ከዚያም ይሖዋ “አሞጽ፣ ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “ቱምቢ” አልኩ። ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ እዘረጋለሁ። ከእንግዲህ ወዲህ ይቅርታ አላደርግላቸውም።+ +9 የይስሐቅ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች+ ይወድማሉ፤ የእስራኤልም መቅደሶች ይፈራርሳሉ፤+ ደግሞም በኢዮርብዓም* ቤት ላይ ሰይፍ ይዤ እመጣለሁ።”+ +10 የቤቴል ካህን የሆነው አሜስያስ+ ለእስራኤል ንጉሥ ለኢዮርብዓም+ ይህን መልእክት ላከ፦ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሴረ ነው።+ ምድሪቱ የእሱን ቃል ሁሉ መታገሥ አትችልም።+ +11 አሞጽ እንዲህ ይላልና፦ ‘ኢዮርብዓም በሰይፍ ይገደላል፤ እስራኤልም ያላንዳች ጥርጥር ከምድሩ ተፈናቅሎ በግዞት ይወሰዳል።’”+ +12 ከዚያም አሜስያስ አሞጽን እንዲህ አለው፦ “አንተ ባለ ራእይ፣ ሂድ፤ ወደ ይሁዳም ምድር ሽሽ፤ ቀለብህን ከዚያ አግኝ፤ በዚያም ትንቢት ተናገር።+ +13 ከእንግዲህ ወዲያ ግን በቤቴል ትንቢት አትናገር፤+ ቤቴል የንጉሥ መቅደስና+ የመንግሥት መኖሪያ ናትና።” +14 በዚህ ጊዜ አሞጽ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ ከዚህ ይልቅ እረኛና+ የሾላ ዛፎች የምንከባከብ* ሰው ነኝ። +15 ይሖዋ ግን ከመንጋ ጠባቂነት ወሰደኝ፤ ይሖዋም ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ።+ +16 እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ‘አንተ “በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤+ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ”+ እያልክ ነው። +17 በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሚስትህ በከተማዋ ውስጥ ዝሙት አዳሪ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ደግሞ በሰይፍ ይወድቃሉ። ምድርህም በገመድ እየተለካ ይከፋፈላል፤ አንተ ራስህም በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ያላንዳች ጥርጥር ከምድሩ ተፈናቅሎ በግዞት ይወሰዳል።”’”+ +1 በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያና+ በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ+ ልጅ በኢዮርብዓም+ ዘመን፣ የመሬት መንቀጥቀጡ+ ከመከሰቱ ከሁለት ዓመት በፊት በተቆአ+ ከነበሩት በግ አርቢዎች መካከል አንዱ ለሆነው ለአሞጽ* ስለ እስራኤል በራእይ የተገለጠለት ቃል። +2 እሱ እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ ከጽዮን እንደ አንበሳ ያገሳል፤ከኢየሩሳሌምም ድምፁን በኃይል ያሰማል። የእረኞቹ ማሰማሪያዎች ያለቅሳሉ፤የቀርሜሎስም አናት ይደርቃል።”+ + 3 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘“ስለ ሦስቱ የደማስቆ ዓመፅ* ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም በብረት ማሄጃ ጊልያድን ወቅተዋል።+ + 4 በመሆኑም በሃዛኤል+ ቤት ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የቤንሃዳድንም የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።+ + 5 የደማስቆን በሮች መቀርቀሪያ እሰብራለሁ፤+የቢቃትአዌን ነዋሪዎችን አጠፋለሁ፤በቤትኤደን ተቀምጦ የሚገዛውን* አስወግዳለሁ፤የሶርያ ሰዎችም ወደ ቂር በግዞት ይሄዳሉ”+ ይላል ይሖዋ።’ + 6 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘“ስለ ሦስቱ የጋዛ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም ሕዝቡን ሁሉ ማርከው+ ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል። + 7 በመሆኑም በጋዛ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤+የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል። + 8 የአሽዶድን ነዋሪዎች አጠፋለሁ፤+በአስቀሎን ተቀምጦ የሚገዛውንም* አስወግዳለሁ፤+እጄን በኤቅሮን ላይ እዘረጋለሁ፤+የተረፉት ፍልስጤማውያንም ይጠፋሉ”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’ + 9 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የጢሮስ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስ��፤ምክንያቱም ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤ደግሞም የወንድማማቾችን ቃል ኪዳን አላስታወሱም።+ +10 በመሆኑም በጢሮስ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል።’+ +11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የኤዶም ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም የገዛ ወንድሙን በሰይፍ አሳዷል፤+ምሕረት ለማሳየትም እንቢተኛ ሆኗል፤በቁጣው ያላንዳች ፋታ ይዘነጣጥላቸዋል፤አሁንም ቢሆን በእነሱ ላይ ቁጣው አልበረደም።+ +12 በመሆኑም በቴማን+ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የቦስራንም የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።’+ +13 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘“ስለ ሦስቱ የአሞናውያን ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም ግዛታቸውን ለማስፋት ሲሉ የጊልያድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀደዋል።+ +14 በመሆኑም በራባ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤+የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል፤በውጊያው ቀን ቀረርቶ ይሰማል፤አውሎ ነፋስ በሚነሳበትም ቀን ነውጥ ይኖራል። +15 ንጉሣቸውም ከመኳንንቱ ጋር በግዞት ይወሰዳል”+ ይላል ይሖዋ።’ +8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ፣ የበጋ ፍሬ* የያዘ ቅርጫት ነበር። +2 ከዚያም “አሞጽ፣ ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የበጋ ፍሬ የያዘ ቅርጫት” ብዬ መለስኩ። ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሷል። ከእንግዲህ ወዲህ ይቅር አልላቸውም።+ +3 ‘በዚያን ቀን የቤተ መቅደሱ መዝሙሮች ወደ ዋይታ ይቀየራሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘በየቦታው የተጣሉ ብዙ አስከሬኖች ይኖራሉ፤+ ዝምታ ይስፈን!’ + 4 እናንተ ድሆችን የምትረጋግጡ፣በምድሪቱ ላይ ያሉትንም የዋሆች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤+ + 5 እንዲህም ትላላችሁ፦ ‘እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው የሚያልፈው መቼ ነው?+አዝመራችንንስ መሸጥ እንድንችል ሰንበት+ የሚያልፈው መቼ ነው? ያን ጊዜ በሐሰተኛ ሚዛን ለማጭበርበርየኢፍ* መስፈሪያውን ማሳነስ፣ሰቅሉንም* ከፍ ማድረግ እንችላለን፤+ + 6 ደግሞም ችግረኛውን በብር፣ድሃውንም በጥንድ ጫማ ዋጋ እንገዛለን፤+መናኛውንም እህል መሸጥ እንችላለን።’ + 7 የያዕቆብ ክብር+ የሆነው ይሖዋ በራሱ ምሏል፦‘ሥራቸውን ሁሉ ፈጽሞ አልረሳም።+ + 8 ከዚህ የተነሳ አገሪቱ* ትሸበራለች፤በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ለሐዘን ይዳረጋሉ።+ ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ አትነሳም?በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ወደ ላይ ከወጣች በኋላ ተመልሳ ወደ ታች አትወርድም?’+ + 9 ‘በዚያ ቀን’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣‘ፀሐይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ብሩህ በሆነ ቀንም ምድሪቱን አጨልማለሁ።+ +10 በዓሎቻችሁን ወደ ሐዘን፣መዝሙሮቻችሁንም ሁሉ ወደ ሙሾ* እለውጣለሁ።+ ወገብን ሁሉ ማቅ አስታጥቃለሁ፤ ራስንም ሁሉ እመልጣለሁ፤ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ያለቅሳሉ፤ፍጻሜውም እንደ መራራ ቀን ይሆናል።’ +11 ‘እነሆ፣ በምድሪቱ ላይ ረሃብ የምሰድበት ጊዜ ይመጣል’ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤‘ረሃቡ የይሖዋን ቃል የመስማት ረሃብ እንጂምግብን የመራብ ወይም ውኃን የመጠማት አይደለም።+ +12 እነሱ ከባሕር ወደ ባሕር፣ከሰሜንም ወደ ምሥራቅ* ይባዝናሉ። የይሖዋን ቃል ፍለጋ በየቦታው ይንከራተታሉ፤ ሆኖም አያገኙትም። +13 በዚያ ቀን፣ ውብ የሆኑት ደናግልናወጣት ወንዶች ከውኃ ጥም የተነሳ ራሳቸውን ይስታሉ፤ +14 በሰማርያ በደል+ የሚምሉደግሞም “ዳን ሆይ፣ ሕያው በሆነው በአምላክህ እምላለሁ!”+ እንዲሁም “ሕያው በሆነው በቤርሳቤህ መንገድ+ እምላለሁ!” የሚሉ ሰዎች፣ ይወድቃሉ፤ ዳግመኛም አይነሱም።’”+ +2 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘“ስለ ሦስቱ የሞዓብ ዓመፅ*+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም ኖራ ለማግኘት የኤዶምን ንጉሥ አጥንቶች አቃጥሏል። + 2 በመሆኑም በሞዓብ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤ የቀሪዮትንም+ የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤ ሞዓብ በትርምስ፣በቀረርቶና በቀንደ መለከት ድምፅ መካከል ይሞታል።+ + 3 ገዢውን* ከመካከሏ አስወግዳለሁ፤መኳንንቷንም ሁሉ ከእሱ ጋር እገድላለሁ”+ ይላል ይሖዋ።’ + 4 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የይሁዳ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም የይሖዋን ሕግ* ንቀዋል፤ሥርዓቱንም አልጠበቁም፤+ይልቁንም አባቶቻቸው በተከተሉት በዚያው ውሸት ስተዋል።+ + 5 በመሆኑም በይሁዳ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የኢየሩሳሌምንም የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።’+ + 6 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የእስራኤል ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም ጻድቁን ለብር፣*ድሃውንም ለጥንድ ጫማ ሲሉ ይሸጣሉ።+ + 7 የችግረኞችን ራስ በምድር አፈር ላይ ይረግጣሉ፤+የየዋሆችንም መንገድ ይዘጋሉ።+ አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ግንኙነት በመፈጸምቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ። + 8 የብድር መያዣ አድርገው በወሰዱት ልብስ+ ላይ በየመሠዊያው ሥር ይተኛሉ፤+መቀጫ በማስከፈል ያገኙትን የወይን ጠጅ በአማልክታቸው ቤት* ይጠጣሉ።’ + 9 ‘ይሁንና ቁመቱ እንደ አርዘ ሊባኖስ፣ ጥንካሬውም እንደ ባሉጥ ዛፍ የሆነውን አሞራዊበፊታቸው ያጠፋሁት እኔ ነኝ፤+ከላይ ያለውን ፍሬውንም ሆነ ከታች ያሉትን ሥሮቹን አጠፋሁ።+ +10 ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤+የአሞራዊውንም ምድር እንድትወርሱበምድረ በዳ ለ40 ዓመት መራኋችሁ።+ +11 ከልጆቻችሁ መካከል አንዳንዶቹን ነቢያት፣+ከወጣቶቻችሁም መካከል አንዳንዶቹን ናዝራውያን አድርጌ አስነሳሁ።+ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ይህን አላደረግኩም?’ ይላል ይሖዋ። +12 ‘እናንተ ግን ናዝራውያኑ የወይን ጠጅ እንዲጠጡ ሰጣችኋቸው፤+ነቢያቱንም “ትንቢት አትናገሩ” በማለት አዘዛችኋቸው።+ +13 ስለዚህ በታጨደ እህል የተሞላ ጋሪ ከሥሩ ያለውን እንደሚያደቅ፣ባላችሁበት ስፍራ አደቃችኋለሁ። +14 ፈጣኑ ሰው የሚሸሽበት ቦታ አያገኝም፤+ብርቱ የሆነው ሰው ኃይሉን ይዞ አይቀጥልም፤ተዋጊውም ሕይወቱን* አያድንም። +15 ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤ፈጣኑም ሮጦ አያመልጥም፤ፈረሰኛውም ሕይወቱን* አያድንም። +16 ከተዋጊዎቹ መካከል እጅግ ደፋር* የሆነው እንኳበዚያን ቀን ራቁቱን ይሸሻል’+ ይላል ይሖዋ።” +4 “እናንተ በሰማርያ ተራራ ላይ ያላችሁ፣+ችግረኛ በሆኑ ሰዎች ላይ ግፍ የምትፈጽሙና+ ድሆችን የምትጨቁኑ ሴቶች፣ባሎቻችሁንም* ‘የምንጠጣው ነገር አምጡልን!’የምትሉ የባሳን ላሞች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ። + 2 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በቅድስናው ምሏል፤‘“እነሆ፣ እናንተን በሜንጦ፣ከእናንተ የቀሩትንም በመንጠቆ የሚያነሳበት ቀን እየመጣባችሁ ነው። + 3 እያንዳንዳችሁ ከፊታችሁ በምታገኟቸው፣ በቅጥሩ ላይ ባሉት ክፍተቶች በኩል ትወጣላችሁ፤ወደ ሃርሞንም ትጣላላችሁ” ይላል ይሖዋ።’ + 4 ‘ወደ ቤቴል ኑና ኃጢአት ሥሩ፤*+ወደ ጊልጋልም ሄዳችሁ ብዙ ኃጢአት ፈጽሙ!+ በማለዳ መሥዋዕቶቻችሁን፣+በሦስተኛውም ቀን አሥራቶቻችሁን* አቅርቡ።+ + 5 እርሾ ያለበትን ዳቦ የሚቃጠል የምስጋና መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤+በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትንም መባ በአዋጅ አስነግሩ! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። + 6 ‘እኔም በከተሞቻችሁ ሁሉ አፋችሁን ባዶ አደረግኩት፤*በቤታችሁም ሁሉ የምትበሉት ነገር አሳጣኋችሁ፤+እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ። + 7 ‘በተጨማሪም መከር ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ ከለከልኳችሁ፤+በአንዱ ከተማ ዝናብ እንዲዘንብ ሳደርግ በሌላው ከተማ ግን እንዳይዘንብ አደረግኩ። አንዱ እርሻ ዝናብ ያገኛል፤ዝናብ ያላገኘው ሌላው እርሻ ግን ይደርቃል። + 8 በሁለት ወይም በሦስት ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ውኃ ለመጠጣት ወደ አንዲት ከተማ እያዘገሙ ሄዱ፤+ይሁንና ጥማቸውን ማርካት አልቻሉም፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ። + 9 ‘በሚያቃጥል ሙቀትና በዋግ መታኋችሁ።+ የአትክልት ስፍራዎቻችሁንና የወይን እርሻዎቻችሁን አበዛችሁ፤ይሁንና የበለስ ዛፎቻችሁንና የወይራ ዛፎቻችሁን አንበጣ ይበላቸዋል፤+ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ። +10 ‘በግብፅ ላይ የደረሰውን ዓይነት ቸነፈር ሰደድኩባችሁ።+ ወጣቶቻችሁን በሰይፍ ገደልኩ፤+ ፈረሶቻችሁንም ማረክሁ።+ የሰፈሮቻችሁ ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግኩ፤+እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። +11 ‘ሰዶምንና ገሞራን እንደገለበጥኳቸው ሁሉምድራችሁን ገለበጥኩ።+ እናንተም ከእሳት እንደተነጠቀ ጉማጅ ነበራችሁ፤ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ። +12 ስለዚህ እስራኤል ሆይ፣ እንዲሁ አደርግብሃለሁ። እስራኤል ሆይ፣ ይህን ነገር ስለማደርግብህአምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ። +13 እነሆ፣ ተራሮችን የሠራው፣+ ነፋስን የፈጠረው እሱ ነው፤+ሐሳቡ ምን እንደሆነ ለሰው ይነግረዋል፤የንጋት ብርሃንን ያጨልማል፤+በምድር ላይ ያሉ ከፍ ያሉ ስፍራዎችን ይረግጣል፤+ስሙ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።” +6 “በጽዮን በራሳቸው ተማምነው* የሚኖሩ፣በሰማርያም ተራራ ያለስጋት የተቀመጡ ወዮላቸው!+እነሱ ከብሔራት ሁሉ መካከል ዋነኛ በሆነው ብሔር ውስጥ የጎላ ስፍራ ያላቸው ናቸው፤ የእስራኤል ቤትም ወደ እነሱ ይመጣል። + 2 ወደ ካልኔ ተሻግራችሁ ተመልከቱ። ከዚያም ተነስታችሁ ወደ ታላቋ ሃማት+ ሂዱ፤የፍልስጤማውያን ከተማ ወደሆነችውም ወደ ጌት ውረዱ። እነሱ ከእነዚህ መንግሥታት* ይሻላሉ?የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣል? + 3 የጥፋትን ቀን ከአእምሯችሁ አውጥታችሁ+የዓመፅ አገዛዝ* እንዲሰፍን ታደርጋላችሁ?+ + 4 የመንጋውን ጠቦቶች እንዲሁም የሰቡ ጥጃዎችን* እየበሉ+ከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ ይተኛሉ፤+ በድንክ አልጋም ላይ ይንጋለላሉ፤+ + 5 በገና* እየተጫወቱ የመጣላቸውን ዘፈን ያቀናብራሉ፤+እንደ ዳዊትም የሙዚቃ መሣሪያዎች+ ይፈለስፋሉ፤ + 6 በትላልቅ ጽዋዎች የወይን ጠጅ ሞልተው ይጠጣሉ፤+ምርጥ የሆኑ ዘይቶችም ይቀባሉ። በዮሴፍ ላይ ስለደረሰው መቅሰፍት ግን ግድ የላቸውም።+ + 7 ስለዚህ እነሱ በግዞት ከሚወሰዱት መካከል የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ፤+ተንጋለው በመዝናናት የሚያሳልፉት ጊዜም ያበቃል። + 8 ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በራሱ* ምሏል’+ ይላል የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፤‘“የያዕቆብን ኩራት እጸየፋለሁ፤+የማይደፈሩ ማማዎቹን እጠላለሁ፤+ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ።+ +9 “‘“በአንድ ቤት ውስጥ አሥር ሰዎች ቢቀሩ እነሱም ይሞታሉ። +10 እነሱን አንድ በአንድ አውጥቶ ለማቃጠል አንድ ዘመድ* ይመጣል። አጥንቶቻቸውን ከቤት ውስጥ ያወጣል፤ ከዚያም በቤቱ ውስጠኛ ክፍል ላለ ሰው ‘ከአንተ ጋር የቀሩ ሌሎች ሰዎች አሉ?’ ይለዋል። ሰውየውም ‘ማንም የለም!’ ይላል። ከዚያም ‘ዝም በል! ይህ የይሖዋ ስም የሚጠራበት ጊዜ አይደለም’ ይላል።” +11 ትእዛዝ የሰጠው ይሖዋ ነውና፤+እሱም ትልቁን ቤት አመድ፣ትንሹንም ቤት የፍርስራሽ ክምር ያደርጋል።+ +12 ፈረሶች በቋጥኝ ላይ ይሮጣሉ?ሰውስ እዚያ ላይ በከብት ያርሳል? እናንተ ፍትሕን ወደ መርዛማ ተክል፣የጽድቅንም ፍሬ ወደ ጭቁኝ* ለውጣችኋልና።+ +13 እናንተ ከንቱ በሆነ ���ገር ሐሴት ታደርጋላችሁ፤ደግሞም “በራሳችን ብርታት ኃይለኞች ሆነን የለም?”* ትላላችሁ።+ +14 ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእናንተ ላይ አንድ ብሔር አመጣለሁ’+ ይላል የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፤‘እነሱም ከሌቦሃማት*+ አንስቶ እስከ አረባ ደረቅ ወንዝ* ድረስ ይጨቁኗችኋል።’” +9 ይሖዋን ከመሠዊያው በላይ ቆሞ አየሁት፤+ እሱም እንዲህ አለ፦ “የዓምዱን አናት ምታ፤ መሠረቶቹም ይናወጣሉ። አናታቸውን ቁረጥ፤ የቀሩትንም በሰይፍ እገድላቸዋለሁ። የሚሸሽ ሁሉ አያመልጥም፤ ለማምለጥ የሚሞክርም ሁሉ አይሳካለትም።+ + 2 በመቃብር* ለመደበቅ ወደ ታች ቢቆፍሩምእጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ወደ ሰማያት ቢወጡምከዚያ አወርዳቸዋለሁ። + 3 ቀርሜሎስ አናት ላይ ቢደበቁምፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ።+ ወደ ታችኛው የባሕር ወለል ወርደው ራሳቸውን ከዓይኔ ቢሰውሩምበዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ። + 4 ጠላቶቻቸው ማርከው ቢወስዷቸውበዚያ ሰይፍ አዛለሁ፤ ሰይፉም ይገድላቸዋል፤+ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ዓይኔን በእነሱ ላይ አደርጋለሁ።+ + 5 ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፣ አገሪቱን* ይነካልና፤እሷም ትቀልጣለች፤+ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ለሐዘን ይዳረጋሉ፤+ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ ትነሳለች፤በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ተመልሳ ወደ ታች ትወርዳለች።+ + 6 ‘ደረጃዎቹን በሰማያት የሚሠራው፣ከምድርም በላይ ሕንፃውን* የሚገነባው፣ወደ ምድር ያፈሰው ዘንድየባሕርን ውኃ ወደ እሱ የሚጠራው፣+ስሙ ይሖዋ ነው።’+ + 7 ‘የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች* አይደላችሁም?’ ይላል ይሖዋ። ‘እስራኤልን ከግብፅ ምድር፣+ ፍልስጤማውያንን ከቀርጤስ፣+ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁም?’+ + 8 ‘እነሆ፣ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ ዓይኖች በኃጢአተኛው መንግሥት ላይ ናቸው፤እሱም ከምድር ገጽ ያጠፋዋል።+ ይሁንና የያዕቆብን ቤት ሙሉ በሙሉ አልደመስስም’+ ይላል ይሖዋ። + 9 ‘እነሆ፣ እኔ ትእዛዝ እሰጣለሁና፤ሰው እህልን በወንፊት እንደሚነፋናአንዲትም ጠጠር ወደ ምድር እንደማትወድቅ ሁሉየእስራኤልንም ቤት በብሔራት ሁሉ መካከል እነፋለሁ።+ +10 “ጥፋት አይደርስብንም ወይም ወደ እኛ አይጠጋም” የሚሉበሕዝቤ መካከል ያሉ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።’ +11 ‘በዚያ ቀን የፈረሰውን የዳዊትን ዳስ አቆማለሁ፤+በግንቡ ላይ ያሉትን ክፍተቶች እጠግናለሁ፤*ፍርስራሾቹንም አድሳለሁ፤በጥንት ዘመን እንደነበረው ዳግም እገነባዋለሁ፤+ +12 በመሆኑም ከኤዶምና ስሜ ከተጠራባቸው ብሔራት ሁሉ የቀረውን ይወርሳሉ’+ይላል ይህን የሚያደርገው ይሖዋ። +13 ‘እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤‘አራሹ አጫጁ ላይ ይደርስበታል፤ዘሪውም ወይን ጨማቂው ላይ ይደርስበታል፤+ተራሮችም ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤+ኮረብቶችም ሁሉ በወይን ጠጅ ይጥለቀለቃሉ።*+ +14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+ +15 ‘በምድራቸው ላይ እተክላቸዋለሁ፤ከሰጠኋቸውም ምድር ላይዳግመኛ አይነቀሉም’+ ይላል አምላክህ ይሖዋ።” +5 “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእናንተ ላይ እንደ ሙሾ* አድርጌ የምናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦ + 2 ‘ድንግሊቱ እስራኤል ወድቃለች፤ዳግመኛም አትነሳም። በገዛ ምድሯ ተጥላለች፤የሚያነሳትም የለም።’ + 3 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘አንድ ሺህ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማ መቶ ሰዎች ብቻ ይቀሯታል፤መቶ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማም አሥር ሰ��ች ብቻ ይቀሯታል። ይህ በእስራኤል ቤት ላይ ይደርሳል።’+ + 4 “ይሖዋ ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ ‘እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።+ + 5 ቤቴልን አትፈልጉ፤+ወደ ጊልጋል አትሂዱ፤+ ወደ ቤርሳቤህም አትሻገሩ፤+ጊልጋል ያለጥርጥር በግዞት ትወሰዳለችና፤+ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለች።* + 6 ይሖዋን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤+አለዚያ በዮሴፍ ቤት ላይ ቁጣው እንደ እሳት ይነድዳል፤ቤቴልንም ይበላል፤ የሚያጠፋውም አይኖርም። + 7 እናንተ ፍትሕን ወደ ጭቁኝ* ትለውጣላችሁ፤ጽድቅንም ወደ ምድር ትጥላላችሁ።+ + 8 የኪማ ኅብረ ከዋክብትንና* የከሲል ኅብረ ከዋክብትን* የሠራው፣+ድቅድቅ ጨለማን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጠው፣ቀኑንም እንደ ሌሊት ጨለማ የሚያደርገው፣+ወደ ምድር ያፈሰው ዘንድየባሕርን ውኃ ወደ እሱ የሚጠራው፣+ስሙ ይሖዋ ነው። + 9 የተመሸጉትን ቦታዎች በማውደም፣ብርቱ በሆነው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣል። +10 እነሱ በከተማዋ በር ላይ ሆነው የሚወቅሱትን ይጠላሉ፤እውነት የሚናገሩትንም ይጸየፋሉ።+ +11 ድሃው ለእርሻ ቦታው ኪራይ* እንዲከፍል ስለምታደርጉ፣እህሉንም በግብር መልክ ስለምትወስዱ፣+በተጠረበ ድንጋይ በሠራችሁት ቤት ውስጥ አትኖሩም፤+ደግሞም ከተከላችኋቸው ምርጥ የወይን ተክሎች የሚገኘውን የወይን ጠጅ አትጠጡም።+ +12 ዓመፃችሁ* ምን ያህል እንደበዛናኃጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደሆነ አውቃለሁና፤ጻድቁን ትጨቁናላችሁ፤ጉቦ* ትቀበላላችሁ፤በከተማዋም በር ላይ የድሆችን መብት ትነፍጋላችሁ።+ +13 ስለሆነም ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች በዚያን ጊዜ ዝም ይላሉ፤የመከራ ጊዜ ይሆናልና።+ +14 በሕይወት እንድትኖሩ+መልካም የሆነውን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ።+ የሠራዊት አምላክ ይሖዋምእንደተናገራችሁት ከእናንተ ጋር ይሆናል።+ +15 ክፉ የሆነውን ጥሉ፤ መልካም የሆነውንም ውደዱ፤+በከተማዋም በር ላይ ፍትሕ እንዲሰፍን አድርጉ።+ የሠራዊት አምላክ ይሖዋከዮሴፍ ለቀሩት ሰዎች ሞገሱን ያሳያቸው ይሆናል።’+ +16 “ስለዚህ ይሖዋ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በየአደባባዩ ዋይታ ይሆናል፤በየመንገዱም ሰዎች “ወዮ! ወዮ!” ይላሉ። ገበሬዎችን ለለቅሶ፣አስለቃሾችንም ለዋይታ ይጠራሉ።’ +17 ‘በየወይን እርሻውም ዋይታ ይኖራል፤+እኔ በመካከልህ አልፋለሁና’ ይላል ይሖዋ። +18 ‘የይሖዋን ቀን ለሚናፍቁ ወዮላቸው!+ የይሖዋ ቀን ለእናንተ ምን ያመጣ ይሆን?+ ያ ቀን ጨለማ እንጂ ብርሃን አይሆንም።+ +19 ይህም ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፣ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳው ላይ ሲያስደግፍም እባብ እንደሚነድፈው ዓይነት ይሆናል። +20 የይሖዋ ቀን ብርሃን የሌለበት ድቅድቅ ጨለማ ይሆን የለም?ደግሞስ የብርሃን ጸዳል የሌለበት ጨለማ ይሆን የለም? +21 በዓሎቻችሁን እጠላለሁ፤ ደግሞም እንቃለሁ፤+የተቀደሱ ጉባኤዎቻችሁ መዓዛም ደስ አያሰኘኝም። +22 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የስጦታ መባዎች ብታቀርቡልኝ እንኳእነዚህ መባዎች አያስደስቱኝም፤+ለኅብረት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡ እንስሳትም በሞገስ ዓይን አልመለከትም።+ +23 የተደበላለቁ መዝሙሮችህን ከእኔ አርቅ፤በባለ አውታር መሣሪያዎች የምትጫወተውንም ዜማ መስማት አልፈልግም።+ +24 ፍትሕ እንደ ውኃ፣+ጽድቅም ያለማቋረጥ እንደሚወርድ ጅረት ይፍሰስ። +25 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ በቆያችሁበት ጊዜመሥዋዕትና የስጦታ መባ አቅርባችሁልኝ ነበር?+ +26 አሁንም ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን፣ ንጉሣችሁ የሆነውን የሳኩትን እንዲሁም የኪዋንን* ምስሎች፣ይኸውም የአምላካችሁን ኮከብ ተሸክማችሁ ትሄዳላችሁ። +27 እኔም ከደማስቆ ወዲያ ርቃችሁ በግዞት እንድትወሰዱ አደርጋለሁ’+ ይላል ስሙ ይሖዋ የሆነው የሠራዊት አምላክ።”+ +1 የአብድዩ* ራእይ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦+ “ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምተናል፤በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦ ‘ተነሱ፤ እሷን ለመውጋት እንዘጋጅ።’”+ + 2 “እነሆ፣ በብሔራት መካከል ከቁብ የማትቆጠር አድርጌሃለሁ፤አንተ እጅግ ተንቀሃል።+ + 3 አንተ በቋጥኝ መሸሸጊያ ውስጥ የምትኖር፣መኖሪያህን በከፍታ ቦታ ላይ ያደረግክ፣በልብህ ‘ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?’ የምትል፣የልብህ እብሪት አታሎሃል።+ + 4 መኖሪያህን እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ*ወይም ጎጆህን በከዋክብት መካከል ብትሠራ እንኳእኔ ከዚያ አወርድሃለሁ” ይላል ይሖዋ። + 5 “ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ዘራፊዎች በሌሊት ቢገቡ(ታላቅ ጥፋት በደረሰብህ ነበር!)* የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ አይደለም? ደግሞስ ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡጥቂት ቃርሚያ አያስቀሩም?+ + 6 ኤሳው ምንኛ ተበረበረ! የተደበቀው ውድ ሀብቱ ምንኛ ተፈለገ! + 7 እስከ ድንበሩ ድረስ እንድትሄድ አስገደዱህ። አጋሮችህ* ሁሉ አታለውሃል። ከአንተ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች አይለውብሃል። ከአንተ ጋር የሚበሉ ሰዎች ከሥርህ መረብ ይዘረጉብሃል፤አንተ ግን አታስተውለውም። + 8 በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ጥበበኞችን ከኤዶም አላጠፋም?+ማስተዋልንስ ከኤሳው ተራራማ ምድር አላስወግድም? + 9 ቴማን+ ሆይ፣ ተዋጊዎችሽ ይሸበራሉ፤+ምክንያቱም እያንዳንዳቸው ታርደው ከተራራማው የኤሳው ምድር ይወገዳሉ።+ +10 በወንድምህ በያዕቆብ ላይ በተፈጸመው ግፍ የተነሳ+ኀፍረት ትከናነባለህ፤+ለዘላለምም ትጠፋለህ።+ +11 ዳር ቆመህ ትመለከት በነበረበት ጊዜ፣እንግዶች ሠራዊቱን ማርከው በወሰዱበትና+የባዕድ አገር ሰዎች በበሩ ገብተው በኢየሩሳሌም ላይ ዕጣ በተጣጣሉበት ጊዜ፣+አንተም ልክ እንደ እነሱ አደረግክ። +12 በወንድምህ ቀን ይኸውም ወንድምህ ክፉ ነገር በደረሰበት ቀን መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤+የይሁዳ ሕዝብ በጠፋበት ቀን ሐሴት ማድረግ አልነበረብህም፤+ደግሞም በጭንቀታቸው ቀን በእብሪት መናገር አይገባህም ነበር። +13 በጥፋታቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር መምጣት አልነበረብህም፤+በጥፋቱ ቀን በደረሰበት መከራ መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤ደግሞም ጥፋት በደረሰበት ቀን ሀብቱን መውሰድ አልነበረብህም።+ +14 የሚሸሹትን የይሁዳ ሰዎች ለመግደል መንታ መንገድ ላይ መቆም አይገባህም ነበር፤+በጭንቀቱም ቀን በሕይወት የተረፉትን አሳልፈህ መስጠት አልነበረብህም።+ +15 ይሖዋ በብሔራት ሁሉ ላይ የሚነሳበት ቀን ቀርቧልና።+ አንተ በእሱ ላይ እንዳደረግከው በአንተም ላይ ይደረጋል።+ በሌሎች ላይ ያደረግከው ነገር በገዛ ራስህ ላይ ይመለሳል። +16 እናንተ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ እንደጠጣችሁ፣ልክ እንደዚሁ ብሔራት በሙሉ ዘወትር ይጠጣሉ።+ ይጠጣሉ፤ ደግሞም ይጨልጡታል፤ፈጽሞ እንዳልነበሩም ይሆናሉ። +17 ያመለጡት ግን በጽዮን ተራራ ላይ ይሆናሉ፤+እሱም የተቀደሰ ይሆናል፤+የያዕቆብ ቤት ሰዎችም የራሳቸው የሆኑትን ነገሮች ይወርሳሉ።+ +18 የያዕቆብ ቤት እሳት፣የዮሴፍም ቤት ነበልባል ይሆናል፤የኤሳው ቤት ደግሞ እንደ ገለባ ይሆናል፤እነሱም ያቃጥሏቸዋል፤ ይበሏቸዋልም፤ከኤሳውም ቤት የሚተርፍ አይኖርም፤+ይሖዋ ራሱ ተናግሯልና። +19 እነሱ ኔጌብንና የኤሳውን ተራራማ ምድር፣+ሸፌላንና የፍልስጤምን ምድር ይወርሳሉ።+ የኤፍሬምን መሬትና የሰማርያን መሬት ይወርሳሉ፤+ቢንያምም ጊልያድን ይወርሳል። +20 እስከ ሰራፕታ+ ድረስ ያለው የከነአናውያን ምድር፣ከዚህ የመከላከያ ግንብ* በግዞት የተወሰዱት ሰዎች+ ይኸውም የእስራኤል ሕዝብ ይዞታ ይሆናል። በሰፋራድ የነበሩት ከኢየሩሳሌም በግዞት የተወሰዱ ሰዎችም የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።+ +21 ሕዝቡን የሚታደጉ ሰዎችም በኤሳው ተራራማ ምድር ላይ ለመፍረድ+ወደ ጽዮን ተራራ ይወጣሉ፤ንግሥናውም የይሖዋ ይሆናል።”+ +3 ከዚያም የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ዮናስ መጣ፦+ +2 “ተነስተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ+ ሂድ፤ የምነግርህንም መልእክት በመካከሏ አውጅ።” +3 ዮናስም የይሖዋን ቃል በመታዘዝ ተነስቶ ወደ ነነዌ+ ሄደ።+ ነነዌ እጅግ ታላቅ ከተማ የነበረች ስትሆን* በእግር የሦስት ቀን ያህል መንገድ ታስኬድ ነበር። +4 ዮናስም ወደ ከተማዋ ገብቶ የአንድ ቀን መንገድ ከተጓዘ በኋላ “ነነዌ በ40 ቀን ውስጥ ትደመሰሳለች” ብሎ አወጀ። +5 የነነዌም ሰዎች በአምላክ አመኑ፤+ ከትልቁም አንስቶ እስከ ትንሹ ድረስ ጾም አወጁ፤ ማቅም ለበሱ። +6 የነነዌ ንጉሥ መልእክቱን በሰማ ጊዜ ከዙፋኑ ተነስቶ ልብሰ መንግሥቱን አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ አመድ ላይ ተቀመጠ። +7 በተጨማሪም በመላው ነነዌ አዋጅ አስነገረ፤“ንጉሡና መኳንንቱ ያወጡት ድንጋጌ፦ ሰውም ሆነ እንስሳ፣ ከብትም ሆነ መንጋ ምንም ነገር አይቅመስ። ምግብ አይብሉ፤ ውኃም አይጠጡ። +8 ሰውም ሆነ እንስሳ ማቅ ይልበስ፤ ሁሉም አጥብቆ ወደ አምላክ ይጩኽ፤ ክፉ መንገዳቸውንና የሚፈጽሙትን ግፍ ይተዉ። +9 እኛ እንዳንጠፋ፣ እውነተኛው አምላክ ሊያመጣው ያሰበውን ነገር እንደገና በማጤን* ከሚነደው ቁጣው ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?” +10 እውነተኛው አምላክ ያደረጉትን ነገር ይኸውም ከክፉ መንገዳቸው እንዴት እንደተመለሱ አየ፤+ በእነሱም ላይ አመጣዋለሁ ያለውን ነገር መልሶ በማጤን* ጥፋቱን ከማምጣት ተቆጠበ።+ +1 የይሖዋ ቃል ወደ አሚታይ ልጅ ወደ ዮናስ*+ እንዲህ ሲል መጣ፦ +2 “ተነስተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ+ ሂድና በእሷ ላይ የፍርድ መልእክት አውጅ፤ ክፋታቸውን አስተውያለሁና።” +3 ዮናስ ግን ከይሖዋ ፊት ኮብልሎ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሳ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፤ ከዚያም ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብ አገኘ። ከይሖዋም ፊት ሸሽቶ፣ በመርከቡ ውስጥ ከነበሩት ጋር ወደ ተርሴስ ለመሄድ የጉዞውን ዋጋ ከፍሎ ተሳፈረ። +4 ከዚያም ይሖዋ በባሕሩ ላይ ኃይለኛ ነፋስ አመጣ፤ ከባድ ማዕበል ስለተነሳ መርከቧ ልትሰበር ተቃረበች። +5 መርከበኞቹ እጅግ ከመፍራታቸው የተነሳ እርዳታ ለማግኘት እያንዳንዳቸው ወደየአምላካቸው ይጮኹ ጀመር። የመርከቧንም ክብደት ለመቀነስ በውስጧ የነበሩትን ዕቃዎች ወደ ባሕሩ መጣል ጀመሩ።+ ዮናስ ግን ወደ መርከቧ* ውስጠኛ ክፍል ወርዶ ተኝቶ ነበር፤ ጭልጥ ያለ እንቅልፍም ወስዶት ነበር። +6 የመርከቧ አዛዥ ወደ እሱ ቀርቦ እንዲህ አለው፦ “እንዴት ትተኛለህ? ተነስተህ ወደ አምላክህ ጩኽ! ምናልባት እውነተኛው አምላክ ለእኛ አስቦ ከጥፋት ያድነን ይሆናል።”+ +7 ከዚያም እርስ በርሳቸው “ይህ መከራ የደረሰብን በማን ምክንያት እንደሆነ ማወቅ እንድንችል፣ ኑ ዕጣ እንጣጣል”+ ተባባሉ። በመሆኑም ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።+ +8 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ይህ መከራ የደረሰብን በማን ምክንያት እንደሆነ እባክህ ንገረን። ሥራህ ምንድን ነው? የመጣኸው ከየት ነው? አገርህስ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ?” +9 እሱም መልሶ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማያትን አምላክ ይሖዋን የምፈራ* ሰው ነኝ” አላቸው። +10 በዚህ ጊዜ ሰዎቹ የባሰ ፈሩ፤ “ያደረግከው ነገር ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። (ሰዎቹ ዮናስ ነግሯቸው ስለነበር ከይሖዋ ፊት እየሸሸ እንዳለ አወቁ።) +11 የባሕሩ ማዕበል እያየ��� በመሄዱ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት። +12 እሱም “አንስታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል፤ ይህ ከባድ ማዕበል የመጣባችሁ በእኔ የተነሳ መሆኑን አውቃለሁና” በማለት መለሰላቸው። +13 ሰዎቹ ግን መርከቧን ወደ የብስ ለመመለስ በኃይል ቀዘፉ፤* ይሁንና ማዕበሉ ይበልጥ እያየለባቸው ስለሄደ ሊሳካላቸው አልቻለም። +14 ከዚያም ወደ ይሖዋ በመጮኽ እንዲህ አሉ፦ “እንግዲህ ይሖዋ ሆይ፣ በዚህ ሰው ምክንያት* እንዳንጠፋ እንለምንሃለን! ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ደስ እንዳሰኘህ ስላደረግክ ለንጹሕ ሰው ደም ተጠያቂ አታድርገን!” +15 ከዚያም ዮናስን አንስተው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም መናወጡን አቆመ። +16 በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ይሖዋን እጅግ ፈሩ፤+ ለይሖዋም መሥዋዕት አቀረቡ፤ ስእለትም ተሳሉ። +17 ይሖዋም ዮናስን እንዲውጠው አንድ ትልቅ ዓሣ ላከ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ቆየ።+ +2 ከዚያም ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ ይሖዋ ጸለየ፤+ +2 እንዲህም አለ፦ “ተጨንቄ ሳለሁ ወደ ይሖዋ ተጣራሁ፤ እሱም መለሰልኝ።+ በመቃብር* ጥልቅ* ውስጥ ሆኜ እርዳታ ለማግኘት ጮኽኩ።+ አንተም ድምፄን ሰማህ። + 3 ወደ ጥልቁ፣ ወደ ታችኛው የባሕሩ ወለል በጣልከኝ ጊዜፈሳሹ ውኃ ዋጠኝ።+ ማዕበሎችህና ሞገዶችህ ሁሉ በላዬ አለፉ።+ + 4 እኔም ‘ከፊትህ አባረርከኝ! ቅዱስ የሆነውን ቤተ መቅደስህን ዳግመኛ እንዴት መመልከት እችላለሁ?’ አልኩ። + 5 ውኃው ዋጠኝ፤ ሕይወቴንም አደጋ ላይ ጣለው፤*+ጥልቁ ውኃ ከበበኝ። የባሕር አረም ራሴ ላይ ተጠመጠመ። + 6 ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥኩ። የምድር መቀርቀሪያዎች ለዘላለም ተዘጉብኝ። ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተ ግን ሕይወቴን ከጉድጓዱ ውስጥ አወጣህ።+ + 7 ሕይወቴ* እየተዳከመች ስትሄድ ይሖዋን አስታወስኩ።+ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ቅዱስ ወደሆነው ቤተ መቅደስህ ገባ።+ + 8 ለማይረቡ ጣዖቶች ያደሩ ሰዎች ታማኝ ፍቅር የሚያሳያቸውን ይተዋሉ።* + 9 እኔ ግን በምስጋና ድምፅ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ። የተሳልኩትን እከፍላለሁ።+ መዳን ከይሖዋ ነው።”+ +10 በኋላም ይሖዋ ዓሣውን አዘዘው፤ ዓሣውም ዮናስን በደረቅ ምድር ላይ ተፋው። +4 ሆኖም ይህ ጉዳይ ዮናስን ፈጽሞ አላስደሰተውም፤ በመሆኑም እጅግ ተቆጣ። +2 ወደ ይሖዋም እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በገዛ አገሬ ሳለሁ ያሳሰበኝ ጉዳይ ይህ አልነበረም? መጀመሪያውኑም ወደ ተርሴስ ለመሸሽ የሞከርኩት ለዚህ ነበር፤+ አንተ ሩኅሩኅና* መሐሪ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየህና ታማኝ ፍቅርህ የበዛ፣+ አዝነህም ጥፋት ከማምጣት የምትቆጠብ እንደሆንክ አውቃለሁና። +3 አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ በሕይወት ከመኖር ይልቅ መሞት ስለሚሻለኝ እባክህ ግደለኝ።”*+ +4 ይሖዋም “እንዲህ መቆጣትህ ተገቢ ነው?” ብሎ ጠየቀው። +5 ከዚያም ዮናስ ከከተማዋ ወጥቶ በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ። በዚያም ለራሱ መጠለያ ሠርቶ በከተማዋ ላይ የሚደርሰውን ነገር ለማየት በጥላው ሥር ተቀመጠ።+ +6 በዚህ ጊዜ ይሖዋ አምላክ፣ ዮናስ ራሱን እንዲያስጠልልባትና ከሥቃዩ እንዲያርፍ ሲል አንዲት የቅል ተክል* ከበላዩ እንድታድግ አደረገ። ዮናስም በቅል ተክሏ እጅግ ተደሰተ። +7 ይሁን እንጂ እውነተኛው አምላክ በሚቀጥለው ቀን፣ ማለዳ ላይ አንድ ትል ላከ፤ ትሉም የቅል ተክሏን በላት፤ ተክሏም ደረቀች። +8 ፀሐይ መውጣት ስትጀምር አምላክ የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አመጣ፤ ፀሐይዋም የዮናስን አናት አቃጠለችው፤ እሱም ተዝለፈለፈ። እንዲሞትም* ለመነ፤ ደግሞ ደጋግሞም “በሕይወት ከምኖር ብሞት ይሻለኛል” አለ።+ +9 አምላክም ዮናስን “ስለ ቅል ተክሏ እንዲህ መቆጣትህ ተገቢ ነው?” ሲል ጠየቀው።+ እሱም “መቆጣት ሲያንሰኝ ነው፤ እንዲያውም ብሞት ይሻለኛል” አለ። +10 ይሖዋ ግን እንዲህ አለው፦ “አንተ በአንድ ሌሊት አድጋ በአንድ ሌሊት ለጠፋችው፣ ላልደከምክባት ወይም ላላሳደግካት የቅል ተክል አዝነሃል። +"11 ታዲያ እኔ ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር* ለይተው የማያውቁ ከ120,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎችና በርካታ እንስሶቻቸው ለሚኖሩባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ+ ላዝን አይገባም?”+" +3 እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎችናየእስራኤል ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ስሙ።+ ትክክል የሆነውን ነገር ማወቅ አይገባችሁም? + 2 ሆኖም እናንተ መልካም የሆነውን ትጠላላችሁ፤+ ክፉ የሆነውን ደግሞ ትወዳላችሁ፤+የሕዝቤን ቆዳ ትገፍፋላችሁ፤ ሥጋቸውንም ከአጥንቶቻቸው ትለያላችሁ።+ + 3 የሕዝቤንም ሥጋ ትበላላችሁ፤+ቆዳቸውንም ትገፍፋላችሁ፤አጥንቶቻቸውንም ትሰባብራላችሁ፤+በድስት ውስጥ እንዳለ አጥንትና በአፍላል* ውስጥ እንዳለ ሥጋ ትቆራርጧቸዋላችሁ። + 4 በዚያን ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤እሱ ግን አይመልስላቸውም። ክፉ ድርጊት በመፈጸማቸው፣+በዚያን ጊዜ ፊቱን ይሰውርባቸዋል።+ + 5 ሕዝቤ እንዲባዝን በሚያደርጉ፣+በጥርሳቸው ሲነክሱ*+ ‘ሰላም!’ እያሉ በሚያውጁ፣+አፋቸው ላይ የሚያደርጉት ነገር በማይሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ግን ጦርነት በሚያውጁ* ነቢያት ላይ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ + 6 ‘ሌሊት ይመጣባችኋል፤+ ራእይም አታዩም፤+ጨለማ ብቻ ይሆንባችኋል፤ ሟርትም አታሟርቱም። ፀሐይ በነቢያቱ ላይ ትጠልቅባቸዋለች፤ቀኑም ወደ ጨለማ ይለወጥባቸዋል።+ + 7 ባለ ራእዮች ኀፍረት ይከናነባሉ፤+ሟርተኞችም ይዋረዳሉ። ከአምላክ ዘንድ መልስ ስለማይኖርሁሉም አፋቸውን* ይሸፍናሉ።’” + 8 እኔ በበኩሌ ለያዕቆብ ዓመፁን፣ ለእስራኤልም ኃጢአቱን እንድነግርበይሖዋ መንፈስ ኃይልን፣ፍትሕንና ብርታትን ተሞልቻለሁ። + 9 ፍትሕን የምትጸየፉና ቀና የሆነውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፣+እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣የእስራኤልም ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ይህን ስሙ፤+ +10 ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምንም በዓመፅ የምትገነቡ፣ ስሙ።+ +11 መሪዎቿ* በጉቦ ይፈርዳሉ፤+ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፤+ነቢያቷም በገንዘብ* ያሟርታሉ።+ ያም ሆኖ “ይሖዋ ከእኛ ጋር አይደለም?+ ምንም ዓይነት ጥፋት አይደርስብንም”+ እያሉ በይሖዋ ይመካሉ።* +12 ስለዚህ በእናንተ የተነሳጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤+የቤቱም* ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች* ይሆናል።+ +7 ወዮልኝ! የበጋ ፍሬ* ከተሰበሰበናወይን የሚሰበሰብበት ጊዜ አብቅቶቃርሚያ ከተለቀመ በኋላየሚበላ የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ሆኛለሁ፤በጣም የምመኘውን፣* በመጀመሪያው ወቅት የሚደርሰውን በለስም አላገኘሁም። + 2 ታማኝ ሰው ከምድሪቱ ጠፍቷል፤*ከሰው ልጆችም መካከል ቅን የሆነ የለም።+ ሁሉም ደም ለማፍሰስ ያደባሉ።+ እያንዳንዱም የገዛ ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል። + 3 እጆቻቸው መጥፎ ነገር በማድረግ የተካኑ ናቸው፤+ገዢው የሆነ ነገር እንዲደረግለት ይጠይቃል፤ፈራጁ ክፍያ ይጠይቃል፤+ታዋቂ የሆነው ሰው የራሱን ፍላጎት ይገልጻል፤*+እነሱም አንድ ላይ ሆነው ያሴራሉ።* + 4 ከእነሱ መካከል የተሻለ የተባለው እንደ እሾህ ነው፤እጅግ ቅን የተባለው ደግሞ ከእሾህ ቁጥቋጦ የከፋ ነው። ጠባቂዎችህ የተናገሩለት፣ አንተ የምትጎበኝበት ቀን ይመጣል።+ እነሱ አሁን ይሸበራሉ።+ + 5 ባልንጀራህን አትመን፤ወይም በቅርብ ወዳጅህ አትታመን።+ በእቅፍህ ለምትተኛው ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ። + 6 ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፤ሴት ልጅ በእናቷ ላይ ትነሳ���ች፤+ምራት ደግሞ በአማቷ ላይ ትነሳለች፤+የሰው ጠላቶቹ ቤተሰቦቹ ናቸው።+ + 7 እኔ ግን ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።+ የሚያድነኝን አምላክ በትዕግሥት እጠብቃለሁ።*+ አምላኬ ይሰማኛል።+ + 8 ጠላቴ ሆይ፣ በእኔ ላይ በደረሰው ነገር ሐሴት አታድርጊ። ብወድቅም እንኳ እነሳለሁ፤በጨለማ ውስጥ ብቀመጥም ይሖዋ ብርሃን ይሆንልኛል። + 9 በእሱ ላይ ኃጢአት ስለሠራሁ+ለእኔ እስኪሟገትልኝና ፍትሕ እንዳገኝ እስከሚያደርግ ድረስየይሖዋን ቁጣ ችዬ እኖራለሁ። እሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤እኔም የእሱን ጽድቅ አያለሁ። +10 “አምላክህ ይሖዋ የት አለ?”ስትለኝ የነበረችው ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትም ትከናነባለች።+ ዓይኖቼም ያዩአታል። በዚያን ጊዜ በጎዳና ላይ እንዳለ ጭቃ የምትረገጥ ቦታ ትሆናለች። +11 የድንጋይ ቅጥሮችሽ የሚገነቡበት ቀን ይሆናል፤በዚያ ቀን ድንበሩ ይሰፋል።* +12 በዚያ ቀን ከአሦርና ከግብፅ ከተሞች፣ከግብፅ አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ፣ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከተራራም እስከ ተራራ ድረስ ያሉ ሰዎችወደ አንቺ ይመጣሉ።+ +13 ምድሪቱም ከነዋሪዎቿና ከሠሩት ነገር* የተነሳባድማ ትሆናለች። +14 ሕዝብህን ይኸውም በጫካ ውስጥ በፍራፍሬ እርሻ መካከል ብቻውን ያለውን፣የርስትህን መንጋ እንደ እረኛ በበትር ጠብቅ።+ እንደ ድሮው ዘመን በባሳንና በጊልያድ ይሰማሩ።+ +15 “ከግብፅ ምድር በወጣችሁበት ዘመን እንደነበረውድንቅ ሥራዎችን አሳያችኋለሁ።+ +16 ብሔራትም ያያሉ፤ ታላቅ ኃይል ቢኖራቸውም ያፍራሉ።+ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ይጭናሉ፤ጆሯቸው ይደነቁራል። +17 እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፤+በምድር ላይ እንደሚሳቡ እንስሳት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጎቻቸው ይወጣሉ። በፍርሃት ተውጠው ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመጣሉ፤አንተንም ይፈሩሃል።”+ +18 የርስቱን ቀሪዎች+ ኃጢአት ይቅር የሚል፣ በደላቸውንም የሚያልፍእንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው?+ እሱ ለዘላለም አይቆጣም፤ታማኝ ፍቅር በማሳየት ደስ ይሰኛልና።+ +19 ዳግመኛ ምሕረት ያሳየናል፤ በደላችንን በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል።* ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ ጥልቅ ባሕር ትጥላለህ።+ +20 በጥንት ዘመን ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረትለያዕቆብ ታማኝነትን፣ለአብርሃም ደግሞ ታማኝ ፍቅርን ታሳያለህ።+ +1 በይሁዳ ነገሥታት+ በኢዮዓታም፣+ በአካዝና+ በሕዝቅያስ+ ዘመን ወደ ሞረሸታዊው ወደ ሚክያስ*+ የመጣው እንዲሁም ሚክያስ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ ያየው የይሖዋ ቃል ይህ ነው።”+ + 2 “እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁም ስሙ! ምድርና በውስጧ ያሉ ሁሉ፣ በትኩረት ያዳምጡ፤ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ነው። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእናንተ ላይ ይመሥክርባችሁ።+ + 3 እነሆ፣ ይሖዋ ከስፍራው ይወጣል፤ወደ ታች ወርዶ የምድርን ከፍ ያሉ ቦታዎች ይረግጣል። + 4 በእሳት ፊት እንዳለ ሰምናበገደል ላይ እንደሚወርድ ውኃተራሮቹ ከሥሩ ይቀልጣሉ፤+ሸለቆዎቹም* ይሰነጠቃሉ። + 5 ይህ ሁሉ የሆነው በያዕቆብ ዓመፅ፣በእስራኤልም ቤት ኃጢአት የተነሳ ነው።+ ለያዕቆብ ዓመፅ ተጠያቂው ማን ነው? ሰማርያ አይደለችም?+ በይሁዳ ለሚገኙት ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችስ ተጠያቂው ማን ነው?+ ኢየሩሳሌም አይደለችም? + 6 ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የፍርስራሽ ክምር፣ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤ድንጋዮቿን ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፤*መሠረቶቿንም አራቁታለሁ። + 7 የተቀረጹ ምስሎቿ በሙሉ ይደቅቃሉ፤+ለዝሙት አዳሪነቷ የተሰጧት ስጦታዎች ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።*+ ጣዖቶቿን ሁሉ እደመስሳለሁ። እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሰበሰበችው ለዝሙት አዳሪነቷ በተከፈላት ደሞዝ ነው፤አሁን ደግሞ እነዚህ ነገሮች በሌላ ቦታ ላሉ ዝሙት ��ዳሪዎች ክፍያ እንዲሆኑ ይወሰዳሉ።” + 8 ከዚህ የተነሳ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ ደግሞም አላዝናለሁ፤+ባዶ እግሬንና ራቁቴን እሄዳለሁ።+ እንደ ቀበሮዎች አላዝናለሁ፤እንደ ሰጎኖችም አለቅሳለሁ። + 9 ቁስሏ ሊፈወስ አይችልም፤+እስከ ይሁዳ ድረስ ተሰራጭቷል።+ መቅሰፍቱ እስከ ሕዝቤ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ተዛምቷል።+ +10 “በጌት አታውሩት፤ከቶም አታልቅሱ። በቤትአፍራ* በአፈር ላይ ተንከባለሉ። +11 የሻፊር ነዋሪዎች ሆይ፣ እርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ተሻገሩ። የጻናን ነዋሪዎች አልወጡም። በቤትዔጼል ዋይታ ይኖራል፤ ለእናንተ ድጋፍ መስጠቱንም ያቆማል። +12 የማሮት ነዋሪዎች መልካም ነገርን ተጠባበቁ፤ይሁንና ከይሖዋ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም በር የወረደው ክፉ ነገር ነው። +13 የለኪሶ+ ነዋሪዎች ሆይ፣ ፈረሶቹን ከሠረገላው ጋር እሰሩ። ለጽዮን ሴት ልጅ የኃጢአት መጀመሪያ ነበራችሁ፤በእናንተ ውስጥ የእስራኤል ዓመፅ ተገኝቷልና።+ +14 ስለዚህ ለሞረሸትጋት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጫለሽ። የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት ማታለያ ነበሩ። +15 የማሬሻህ+ ነዋሪዎች ሆይ፣ ድል አድራጊውን* ገና አመጣባችኋለሁ።+ የእስራኤል ክብር እስከ አዱላም+ ድረስ ይመጣል። +16 ለምትወዷቸው ልጆቻችሁ ፀጉራችሁን ተቆረጡ፤ ራሳችሁንም ተላጩ። እንደ ንስር ተመለጡ፤ልጆቻችሁ በግዞት ተወስደውባችኋልና።”+ +2 “መጥፎ ነገር ለሚሸርቡናበአልጋቸው ላይ ሆነው ክፉ ነገር ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ጠዋት ሲነጋ ያሰቡትን ይፈጽማሉ፤ምክንያቱም ይህን የሚያደርጉበት ኃይል በእጃቸው ነው።+ + 2 እርሻን ይመኛሉ፤ ነጥቀውም ይይዙታል፤+ቤቶችንም ይመኛሉ፤ ደግሞም ይወስዳሉ፤የሰውን ቤት፣የሰውንም ርስት አታለው ይወስዳሉ።+ + 3 ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በዚህ ወገን ላይ ጥፋት ላመጣ አስቤአለሁ፤+ እናንተም ከዚህ ጥፋት አታመልጡም።*+ ከእንግዲህ ወዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤+ ይህ የጥፋት ጊዜ ነውና።+ + 4 በዚያም ቀን ሰዎች እናንተን አስመልክተው ምሳሌ ይናገራሉ፤በእናንተም የተነሳ አምርረው ያለቅሳሉ።+ እንዲህ ይላሉ፦ “እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል!+ የሕዝቤን ድርሻ ለሌሎች ሰጥቷል፤ ከእኔም ወስዶታል!+ እርሻዎቻችንን ለከዳተኛው ይሰጣል።” + 5 ስለዚህ በይሖዋ ጉባኤ ውስጥ፣ምድሪቷን ለማከፋፈል በገመድ የሚለካ ሰው አይኖርህም። + 6 “አትስበኩ!” ብለው ይሰብካሉ፤“እነዚህን ነገሮች መስበክ አይገባቸውም፤ውርደት አይደርስብንም!” + 7 የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ “የይሖዋ መንፈስ አይታገሥም? እነዚህንስ ነገሮች ያደረገው እሱ ነው?” ሲባል ሰምተሃል? ቀና በሆነ መንገድ ለሚሄዱ የገዛ ቃሌ መልካም ነገር አያስገኝም? + 8 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የገዛ ሕዝቤ ጠላት ሆኖ ተነስቷል። ከጦርነት እንደሚመለሱ ሰዎች በልበ ሙሉነት ከሚያልፉት ላይየሚያምረውን ጌጥ ከልብሱ ጋር* በይፋ ገፈፋችሁ። + 9 የሕዝቤን ሴቶች ከሚያምረው ቤታቸው አፈናቀላችኋቸው፤ክብሬን ከልጆቻቸው ለዘላለም ወሰዳችሁ። +10 ተነሱና ከዚህ ሂዱ፤ ይህ የማረፊያ ቦታ አይደለምና። ከርኩሰት የተነሳ+ ጥፋት ይመጣል፤ ጥፋቱም ከባድ ነው።+ +11 አንድ ሰው ነፋስንና ማታለያን ተከትሎ ቢሄድና “ስለ ወይን ጠጅና ስለ መጠጥ እሰብክላችኋለሁ” ብሎ ውሸት ቢናገር ይህ ሰው ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ሰባኪ ይሆናል!+ +12 ያዕቆብ ሆይ፣ ሁላችሁንም በእርግጥ እሰበስባለሁ፤ከእስራኤል የቀሩትን ያላንዳች ጥርጥር አንድ ላይ እሰበስባለሁ።+ በጉረኖ ውስጥ እንዳለ በግ፣በግጦሽ መስክ ላይ እንዳለም መንጋ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤+ቦታውም በሕዝብ ሁካታ ይሞላል።’+ +13 የሚሰብረውም ከፊታቸው ይሄዳል፤እነሱም ሰብረው በበሩ በኩ�� ያልፋሉ፤ በዚያም ወጥተው ይሄዳሉ።+ ንጉሣቸው በፊታቸው ያልፋል፤ይሖዋም ከፊታቸው ይሄዳል።”*+ +4 በዘመኑ መጨረሻ*የይሖዋ ቤት ተራራ+ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ወደዚያ ይጎርፋሉ።+ + 2 ብዙ ብሔራትም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራናወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+ እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።” ሕግ* ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። + 3 እሱ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤+በሩቅ ካሉ ኃያላን ብሔራት ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል።* እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+ አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+ + 4 እያንዳንዱም ከወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ይቀመጣል፤*+የሚያስፈራቸውም አይኖርም፤+የሠራዊት ጌታ የይሖዋ አፍ ተናግሯልና። + 5 ሕዝቦች ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው በአምላካቸው ስም ይሄዳሉ፤እኛ ግን በአምላካችን በይሖዋ ስም ለዘላለም እንሄዳለን።+ + 6 “በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣“የሚያነክሰውን* እሰበስባለሁ፤ደግሞም የተበተኑትንናያንገላታኋቸውን ሰዎች አንድ ላይ እሰበስባለሁ።+ + 7 የሚያነክሰው የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩት* አደርጋለሁ፤+ወደ ሩቅ ስፍራ የተወሰደውንም ኃያል ብሔር አደርገዋለሁ፤+ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበጽዮን ተራራ በእነሱ ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል። + 8 አንተም የመንጋው ማማ፣የጽዮን+ ሴት ልጅ ጉብታ ሆይ፣አንተ ወዳለህበት ይመለሳል፤ አዎ፣ የመጀመሪያው* ግዛትህ፣የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ይመለሳል።+ + 9 አሁንስ ድምፅሽን ከፍ አድርገሽ የምትጮኺው ለምንድን ነው? ንጉሥ የለሽም?ወይስ አማካሪሽ ጠፍቷል?ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት የምትሠቃዪው ለዚህ ነው?+ +10 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴትተንፈራገጪ፤ አቃስቺም፤አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትሰፍሪያለሽና። እስከ ባቢሎን ድረስ ትሄጃለሽ፤+በዚያም ይታደግሻል፤+በዚያ ይሖዋ ከጠላቶችሽ እጅ ይዋጅሻል።+ +11 አሁንም ብዙ ብሔራት በአንቺ ላይ ይሰበሰባሉ፤እነሱም ‘የረከሰች ትሁን፤ዓይኖቻችንም ይህ በጽዮን ላይ ሲደርስ ይመልከቱ’ ይላሉ። +12 ይሁንና የይሖዋን ሐሳብ አያውቁም፤ዓላማውንም አይረዱም፤እሱ ገና እንደታጨደ እህል ወደ አውድማ ይሰበስባቸዋልና። +13 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ተነስተሽ እህሉን ውቂ፤+ቀንድሽን ወደ ብረት፣ሰኮናሽንም ወደ መዳብ እለውጣለሁና፤አንቺም ብዙ ሕዝቦችን ታደቂያለሽ።+ በማጭበርበር ያገኙት ትርፍ ለይሖዋ የተወሰነ እንዲሆን፣ሀብታቸውም ለምድር ሁሉ ጌታ ብቻ እንዲውል ታደርጊያለሽ።”+ +6 ይሖዋ የሚለውን እባካችሁ ስሙ። ተነሱ፤ በተራሮች ፊት ሙግታችሁን አቅርቡ፤ኮረብቶችም ቃላችሁን ይስሙ።+ + 2 ተራሮች ሆይ፣ እናንተ ጽኑ የምድር መሠረቶች፣የይሖዋን ሙግት ስሙ፤+ይሖዋ ከሕዝቡ ጋር ሙግት አለውና፤ከእስራኤልም ጋር ይከራከራል፦+ + 3 “ሕዝቤ ሆይ፣ ምን ያደረግኩህ ነገር አለ? ያደከምኩህስ ምን አድርጌ ነው?+ እስቲ መሥክርብኝ። + 4 ከግብፅ ምድር አወጣሁህ፤+ከባርነትም ቤት ዋጀሁህ፤+ሙሴን፣ አሮንንና ሚርያምን+ በፊትህ ላክሁ። + 5 ሕዝቤ ሆይ፣ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያሴረብህን ነገር፣+የቢዖር ልጅ በለዓምም የሰጠውን መልስ+ እባክህ አስታውስ፤የይሖዋን የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድከሺቲም+ እስከ ጊልጋል+ ድረስ የሆነውን ነገር አስታውስ።” + 6 በይሖዋ ፊት ምን ይዤ ልቅረብ? ከፍ ባለ ስፍራ በሚኖረው አምላክ ፊት ምን ይዤ ልስገድ? ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችናየአንድ ዓመት ጥጃዎች ይዤ ልቅረብ?+ + 7 ይሖዋ በሺህ በሚቆጠሩ አውራ በጎችወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋል?+ ለሠራሁት በደል የበኩር ወንድ ልጄን፣ለሠራሁትም* ኃጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብ?+ + 8 ሰው ሆይ፣ መልካም የሆነውን ነግሮሃል። ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን እንድታደርግ፣*+ ታማኝነትን እንድትወድና*+ልክህን አውቀህ+ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ ብቻ ነው!+ + 9 የይሖዋ ድምፅ ከተማዋን ይጣራል፤ጥበበኞች* ስምህን ይፈራሉ። የበትሩን ድምፅና ቅጣቱን የወሰነውን ስሙ።+ +10 ክፉ በሆነ ሰው ቤት፣ በክፋት የተገኘ ሀብትእንዲሁም አስጸያፊ የሆነ ጎዶሎ የኢፍ መስፈሪያ* አሁንም አለ? +11 አባይ ሚዛንና* የተዛቡ* የድንጋይ መለኪያዎች የያዘ ከረጢት+ እየተጠቀምኩንጹሕ ሥነ ምግባር ሊኖረኝ ይችላል?* +12 ባለጸጎቿ በግፍ የተሞሉ ናቸው፤ነዋሪዎቿም ውሸት ይናገራሉ፤+ምላሳቸው በአፋቸው ውስጥ አታላይ ነው።+ +13 “ስለዚህ መትቼ አቆስልሃለሁ፤+ከኃጢአትህ የተነሳ አጠፋሃለሁ። +14 ትበላለህ፤ ግን አትጠግብም፤ሆድህም ባዶ ይሆናል።+ የምትወስዳቸውን ነገሮች ጠብቀህ ማቆየት አትችልም፤ጠብቀህ ያቆየኸውንም ነገር ሁሉ ለሰይፍ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። +15 ዘር ትዘራለህ፤ ሆኖም የምታጭደው ነገር አይኖርም። የወይራ ፍሬ ትጨምቃለህ፤ ሆኖም ዘይቱን አትጠቀምበትም፤ደግሞም አዲስ የወይን ጠጅ ትጨምቃለህ፤ ሆኖም የወይን ጠጅ አትጠጣም።+ +16 የኦምሪን ደንቦችና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ትከተላላችሁና፤+ምክራቸውንም ተከትላችሁ ትሄዳላችሁ። ስለዚህ አንተን መቀጣጫ፣ነዋሪዎቿንም ማፏጫ አደርጋለሁ፤+የሰዎችንም ፌዝ ትሸከማላችሁ።”+ +5 “አንቺ ጥቃት የተሰነዘረብሽ ሴት ልጅ ሆይ፣አሁን ሰውነትሽን ትተለትያለሽ፤ዙሪያችንን ተከበናል።+ የእስራኤልን ፈራጅ ጉንጩን በዱላ ይመቱታል።+ + 2 ከይሁዳ አእላፋት* መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽውቤተልሔም ኤፍራታ+ ሆይ፣ምንጩ ከጥንት፣ ከረጅም ዘመን በፊት የሆነ፣በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል።+ + 3 ስለዚህ ልትወልድ የተቃረበችው ሴት እስክትወልድ ድረስአሳልፎ ይሰጣቸዋል። የቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ። + 4 እሱ በይሖዋ ብርታትና በአምላኩ በይሖዋ ስም ታላቅነት ይነሳል፤መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል።+ እነሱም በዚያ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤+በዚያን ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳልና።+ + 5 እሱም ሰላም ያመጣል።+ አሦራዊው ምድራችንን ከወረረና የማይደፈሩ ማማዎቻችንን ከረገጠ+በእሱ ላይ ሰባት እረኞችን፣ አዎ ከሰው ልጆች መካከል ስምንት አለቆችን* እናስነሳበታለን። + 6 እነሱ የአሦርን ምድር በሰይፍ ይቀጣሉ፤+የናምሩድንም+ ምድር መግቢያዎች ይቆጣጠራሉ። አሦራዊው ምድራችንን ሲወርና ክልላችንን ሲረግጥእሱ ይታደገናል።+ + 7 የተረፉት የያዕቆብ ወገኖች በብዙ ሕዝቦች መካከል፣ከይሖዋ ዘንድ እንደሚወርድናሰውን ተስፋ እንደማያደርግወይም የሰው ልጆችን እንደማይጠባበቅ ጠል፣በአትክልትም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ። + 8 በዱር እንስሳት መካከል እንዳለ አንበሳ፣በሚያልፍበት ጊዜ እየረጋገጠና እየሰባበረ እንደሚሄድ፣በበግ መንጎች መካከል እንዳለ ደቦል አንበሳ፣የተረፉት የያዕቆብ ወገኖችም በብሔራት፣በብዙ ሕዝቦችም መካከል እንዲሁ ይሆናሉ፤ሊያስጥል የሚችልም አይኖርም። + 9 እጅህ ከባላጋራዎችህ በላይ ከፍ ከፍ ትላለች፤ጠላቶችህም ሁሉ ይወገዳሉ።” +10 “በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ፈረሶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ ሠረገሎችህንም አጠፋለሁ። +11 በምድርህ ላይ የሚገኙትን ከተሞች እደመስሳለሁ፤የተመሸጉ ስፍራዎችህንም ሁሉ አፈራርሳለሁ። +12 ጥንቆላህን አስወግዳለሁ፤*ከእንግዲህም ��ስማተኛ በመካከልህ አይኖርም።+ +13 የተቀረጹ ምስሎችህንና ዓምዶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ወዲህ ለእጆችህ ሥራ አትሰግድም።+ +14 የማምለኪያ ግንዶችህንም* ከመካከልህ እነቅላለሁ፤+ከተሞችህንም እደመስሳለሁ። +15 ታዛዥ ያልሆኑትን ብሔራት፣በቁጣና በንዴት እበቀላለሁ።” +3 ለደም አፍሳሿ ከተማ ወዮላት! በማታለልና በዝርፊያ የተሞላች ናት። ከማደን ቦዝና አታውቅም! + 2 የአለንጋ ድምፅና የመንኮራኩር* ኳኳቴ ይሰማል፤ፈረሶች ሲጋልቡና ሠረገሎች ሲፈተለኩ ይታያል። + 3 ፈረስ ጋላቢው ይጋልባል፤ ሰይፉ ያንጸባርቃል፤ ጦሩ ያብረቀርቃል፤የተገደሉት በጣም ብዙ ናቸው፤ የአስከሬን ክምር ይታያል፤ሬሳው ስፍር ቁጥር የለውም። አስከሬኖቹም ያደናቅፏቸዋል። + 4 ይህ የሆነው ዝሙት አዳሪዋ በምትፈጽመው በርካታ የአመንዝራነት ተግባር የተነሳ ነው፤እሷ ብሔራትን በምንዝሯ፣ ወገኖችንም በጥንቆላዋ የምታጠምድ፣የምታምርና የምትማርክ እንዲሁም በጥንቆላ የተካነች ናት። + 5 “እነሆ፣ በአንቺ* ላይ ተነስቻለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤+“ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ ድረስ እገልበዋለሁ፤ብሔራትም እርቃንሽን፣መንግሥታትም ነውርሽን እንዲያዩ አደርጋለሁ። + 6 ቆሻሻ እደፋብሻለሁ፤የተናቅሽ አደርግሻለሁ፤ማላገጫም እንድትሆኚ አደርጋለሁ።+ + 7 አንቺን የሚያይ ሁሉ ከአንቺ ይሸሻል፤+ደግሞም ‘ነነዌ ወድማለች! የሚያዝንላት ማን ነው?’ ይላል። አንቺን የሚያጽናና ከየት ማግኘት እችላለሁ? + 8 አንቺ በአባይ የመስኖ ቦዮች+ አጠገብ ከነበረችው ከኖአሞን*+ ትሻያለሽ? እሷ በውኃ የተከበበች ነበረች፤ባሕሩም ሀብት ያስገኝላት፣ እንደ ቅጥርም ሆኖ ያገለግላት ነበር። + 9 ኢትዮጵያና ግብፅ ገደብ የለሽ የኃይል ምንጮቿ ነበሩ። ፑጥና+ ሊቢያውያን ረዳቶቿ ነበሩ።+ +10 ይሁንና እሷም እንኳ በግዞት ተወሰደች፤ተማርካም ሄደች።+ ልጆቿም በየመንገዱ ማዕዘን* ተፈጠፈጡ። በተከበሩ ሰዎቿ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ታላላቅ ሰዎቿም ሁሉ በእግር ብረት ታሰሩ። +11 አንቺም ትሰክሪያለሽ፤+ደግሞም ትሰወሪያለሽ። ከጠላት የምትሸሸጊበት ቦታ ትፈልጊያለሽ። +12 ምሽጎችሽ ሁሉ የመጀመሪያዎቹን የበሰሉ ፍሬዎች እንደያዙ የበለስ ዛፎች ናቸው፤ዛፎቹ ከተነቀነቁ ፍሬዎቹ ረግፈው በበላተኛ አፍ ውስጥ ይወድቃሉ። +13 እነሆ፣ ወታደሮችሽ በመካከልሽ እንዳሉ ሴቶች ናቸው። የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ይከፈታሉ። የበሮችሽን መቀርቀሪያዎች እሳት ይበላቸዋል። +14 ለከበባው ውኃ ቅጂ!+ ምሽጎችሽን አጠናክሪ። ማጥ ውስጥ ግቢ፤ ጭቃውንም ርገጪ፤የጡብ ቅርጽ ማውጫውንም ያዢ። +15 ይህም ሆኖ እሳት ይበላሻል። ሰይፍ ይቆርጥሻል።+ እንደ ኩብኩባ ይበላሻል።+ እንደ ኩብኩባ ተባዢ! አዎ፣ እንደ አንበጣ ተራቢ! +16 ነጋዴዎችሽን ከሰማያት ከዋክብት ይበልጥ አብዝተሻል። ኩብኩባው ቅርፊቱን ከላዩ ላይ ጥሎ ይበርራል። +17 ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣መኮንኖችሽም እንደ አንበጣ መንጋ ናቸው። ቅዝቃዜ ባለበት ቀን በድንጋይ ቅጥሮች ውስጥ ይሰፍራሉ፤ፀሐይ ስትወጣ ግን በርረው ይሄዳሉ፤የት እንደደረሱም ማንም አያውቅም። +18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፣ እረኞችህ እንቅልፍ ተጫጭኗቸዋል፤ታላላቅ ሰዎችህ በመኖሪያቸው ይቀመጣሉ። ሕዝብህ በተራሮቹ ላይ ተበታትነዋል፤የሚሰበስባቸውም የለም።+ +19 የደረሰብህን መቅሰፍት የሚያቆም ነገር የለም። ቁስልህ ሊድን የሚችል አይደለም። ስለ አንተ ወሬ የሚሰሙ ሁሉ ያጨበጭባሉ፤+በማያባራው ጭካኔህ ያልተጎዳ ማን አለና?”+ +1 በነነዌ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ የኤልቆሻዊው የናሆም* የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፦ + 2 ይሖዋ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግና+ የሚበቀል አምላክ ነው፤ይሖዋ ይበቀላል፤ ቁጣውንም ለመግለጽ ዝግጁ ነው።+ ይሖዋ ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ለጠላቶቹም ቁጣ ያከማቻል። + 3 ይሖዋ ለቁጣ የዘገየ ነው፤+ ኃይሉም ታላቅ ነው፤+ይሁንና ይሖዋ ተገቢውን ቅጣት ከመስጠት ፈጽሞ ወደኋላ አይልም።+ መንገዱ በአደገኛ ነፋስና በወጀብ ውስጥ ነው፤ደመናት ከእግሩ በታች እንዳለ አቧራ ናቸው።+ + 4 ባሕሩን ይገሥጻል፤+ ያደርቀዋልም፤ወንዞቹንም በሙሉ ያደርቃቸዋል።+ ባሳንና ቀርሜሎስ ይጠወልጋሉ፤+የሊባኖስ አበባዎችም ይጠወልጋሉ። + 5 ከእሱ የተነሳ ተራሮች ይንቀጠቀጣሉ፤ኮረብቶችም ይቀልጣሉ።+ ከፊቱም የተነሳ ምድር፣የብስና በላዩ የሚኖሩት ሁሉ ይናወጣሉ።+ + 6 በቁጣው ፊት ማን ሊቆም ይችላል?+ የንዴቱን ትኩሳት ሊቋቋም የሚችልስ ማን ነው?+ ቁጣው እንደ እሳት ይፈስሳል፤ዓለቶችም ከእሱ የተነሳ ይፈረካከሳሉ። + 7 ይሖዋ ጥሩ ነው፤+ በጭንቀትም ቀን መሸሸጊያ ነው።+ እሱን መጠጊያ ማድረግ የሚፈልጉትን ያውቃል።*+ + 8 ጠራርጎ በሚወስድ ጎርፍ ስፍራዋን* ፈጽሞ ያጠፋል፤ጠላቶቹንም ጨለማ ያሳድዳቸዋል። + 9 በይሖዋ ላይ የምታሴሩት ምንድን ነው? እሱ ፈጽሞ ያጠፋል። ጭንቀት ዳግመኛ አይመጣም።+ +10 እርስ በርሳቸው እንደ እሾህ ተጠላልፈዋልና፤መጠጥ* ጠጥተው እንደሰከሩ ሰዎች ናቸው፤ሆኖም እንደደረቀ ገለባ እሳት ይበላቸዋል። +11 በይሖዋ ላይ ክፉ ነገር የሚያሴር፣ከንቱ ምክርም የሚሰጥ ከመካከልሽ ይወጣል። +12 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ምንም እንኳ የተሟላ ኃይል ያላቸውና ብዙዎች ቢሆኑምይቆረጣሉ፤ ደግሞም ይጠፋሉ።* መከራ አሳይቼሃለሁ፤* ከዚያ በኋላ ግን መከራ አላመጣብህም። +13 አሁንም ቀንበሩን ከአንተ ላይ እሰብራለሁ፤+እስራትህንም እበጥሳለሁ። +14 ይሖዋ አንተን* በተመለከተ እንዲህ ሲል አዟል፦‘ከእንግዲህ ስምህን የሚያስጠራ አይኖርም። የተቀረጹትን ምስሎችና ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች* ከአማልክትህ ቤት* አስወግዳለሁ። የተናቅክ ስለሆንክ መቃብር አዘጋጅልሃለሁ።’ +15 እነሆ ምሥራች ይዞ የሚመጣ፣ሰላምንም የሚያውጅ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው።+ ይሁዳ ሆይ፣ በዓሎችሽን አክብሪ፤+ ስእለትሽን ፈጽሚ፤ከእንግዲህ ወዲህ የማይረባ ሰው በመካከልሽ አያልፍምና። እንዲህ ያለው ሰው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል።” +2 የሚበትን መጥቶብሻል።*+ ምሽጎቹን ጠብቂ። መንገዱን በትኩረት ተመልከቺ። ወገብሽን ታጠቂ፤* ኃይልሽንም ሁሉ አሰባስቢ። + 2 ይሖዋ የያዕቆብን ክብርከእስራኤል ክብር ጋር ይመልሳልና፤አጥፊዎች አጥፍተዋቸዋልና፤+ቀንበጦቻቸውንም ከጥቅም ውጭ አድርገዋል። + 3 የኃያላኑ ጋሻዎች ቀይ ቀለም የተነከሩ ናቸው፤ተዋጊዎቹ ደማቅ ቀይ ልብስ ለብሰዋል። ለጦርነት ዝግጁ በሚሆንበት ቀን፣የጦር ሠረገላው ብረቶች እንደ እሳት ያብረቀርቃሉ፤ከጥድ የተሠሩት ረጃጅም ጦሮች ይወዛወዛሉ። + 4 የጦር ሠረገሎቹ በጎዳናዎቹ ላይ ይከንፋሉ። በአደባባዮቹም ላይ ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ። እንደሚነድ ችቦ ያበራሉ፤ እንደ መብረቅም ያንጸባርቃሉ። + 5 እሱ አለቆቹን ይጠራል። እነሱ ወደ ፊት ሲገሰግሱ ይሰናከላሉ። ወደ ቅጥሯ እየተጣደፉ ይሄዳሉ፤መከላከያም ያቆማሉ። + 6 የወንዞቹ በሮች ይከፈታሉ፤ቤተ መንግሥቱም ይቀልጣል።* + 7 ጉዳዩ ታውጇል፦* እሷ ተጋልጣለች፤ተማርካ ተወስዳለች፤ ሴቶች ባሪያዎቿም ያቃስታሉ፤ደረታቸውን* እየደቁ እንደ ርግብ ያላዝናሉ። + 8 ነነዌ ከተቆረቆረችበት+ ጊዜ አንስቶ እንደ ውኃ ኩሬ ነበረች፤አሁን ግን እነሱ ይሸሻሉ። አንዳንዶች “ቁሙ! ቁሙ!” ብለው ይጮኻሉ። ሆኖም ወደ ኋላ የሚዞር የለም።+ + 9 ብሩን ዝረፉ፤ ወርቁን ዝረፉ! የተከማቸው ሀብት ስፍር ቁጥር የለውም። በብዙ ዓይነት የከበሩ ዕቃዎች ተሞልቷል። +10 ከተማዋ ባዶና ወና እንዲሁም ባድማ ሆናለች!+ ልባቸው በፍርሃት ቀልጧል፤ ጉልበታቸው ተብረክርኳል፤ ወገባቸውም ተንቀጥቅጧል፤የሁሉም ፊት ቀልቷል። +11 ደቦል አንበሶቹ የሚመገቡበት፣ማንም ሳያስፈራቸው አንበሳው ግልገሎቹን እየመራ የሚወጣበትየአንበሶቹ ዋሻ የት አለ?+ +12 አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃቸውን ያህል አደነ፤ለእንስቶቹም አንቆ ገደለላቸው። ጎሬውን በታደኑ እንስሶች፣ዋሻውንም በተቦጫጨቁ እንስሶች ሞላ። +13 “እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤+“የጦር ሠረገላዋን በጭስ መካከል አቃጥላለሁ፤+ደቦል አንበሶችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል። አደንሽን ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ፤የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።”+ +3 ነቢዩ ዕንባቆም በሙሾ* ያቀረበው ጸሎት፦ + 2 ይሖዋ ሆይ፣ ስለ አንተ የተወራውን ሰምቻለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ፍርሃት* አሳደረብኝ። በዓመታት መካከል* ሥራህን ሕያው አድርግ! በዓመታትም መካከል* ሥራህን አሳውቅ። መዓት በሚወርድበት ጊዜ ምሕረትን አስታውስ።+ + 3 አምላክ ከቴማን፣ቅዱሱም ከፋራን ተራራ መጣ።+ (ሴላ)* ግርማው ሰማያትን ሸፈነ፤+ምድርም በውዳሴው ተሞላች። + 4 ጸዳሉ እንደ ፀሐይ ብርሃን ነው።+ ከእጁ ሁለት ጨረሮች ፈነጠቁ፤ብርታቱም በዚያ ተሰውሯል። + 5 ቸነፈር ከፊቱ ሄደ፤+የሚያቃጥል ትኩሳትም እግር በእግር ተከተለው። + 6 ቆመ፤ ምድርንም አንቀጠቀጠ።+ ባየም ጊዜ ብሔራትን አብረከረካቸው።+ ዘላለማዊ የሆኑት ተራሮች ተፈረካከሱ፤የጥንቶቹ ኮረብቶች ተደፉ።+ የጥንቶቹ መንገዶች የእሱ ናቸው። + 7 በኩሻን ድንኳኖች ውስጥ ችግር አየሁ። የምድያም የድንኳን ሸራዎች ተንቀጠቀጡ።+ + 8 ይሖዋ ሆይ፣ ቁጣህ የነደደው በወንዞች ላይ ነው?በእርግጥ በወንዞች ላይ ነው? ወይስ ታላቅ ቁጣህን የገለጽከው በባሕሩ ላይ ነው?+ በፈረሶችህ ላይ ተቀምጠህ ጋልበሃልና፤+ሠረገሎችህ ድል ተቀዳጅተዋል።*+ + 9 የቀስትህ ሽፋን ተነስቷል፤ ቀስትህም ተዘጋጅቷል። ዘንጎቹ* በመሐላ ተመድበዋል።* (ሴላ) ምድሪቱን በወንዞች ከፈልክ። +10 ተራሮች አንተን ሲያዩ በሥቃይ ተንፈራገጡ።+ ዶፍ ዝናብ ጠራርጎ ሄደ። ጥልቁ በኃይል ጮኸ።+ እጁን ወደ ላይ አነሳ። +11 ፀሐይና ጨረቃ ከፍ ባለው መኖሪያ ስፍራቸው ቆሙ።+ ፍላጾችህ እንደ ብርሃን ተወረወሩ።+ ጦርህ እንደ መብረቅ አብረቀረቀ። +12 በምድር ላይ በቁጣ ዘመትክ። ብሔራትን በቁጣ ረገጥካቸው።* +13 ሕዝብህን ለመታደግ፣ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ። የክፉውን ቤት መሪ* አደቀቅክ። ቤቱ ከመሠረቱ አንስቶ እስከ አናቱ* ድረስ ተጋለጠ። (ሴላ) +14 እኔን ለመበታተን በቁጣ በተነሱ ጊዜበገዛ ራሱ መሣሪያዎች* የተዋጊዎቹን ራስ ወጋህ። እነሱ ጎስቋላውን ሰው በስውር በመዋጥ ሐሴት አድርገዋል። +15 በባሕር ውስጥ፣ በሚናወጠው ብዙ ውኃ መካከልበፈረሶችህ እየጋለብክ አለፍክ። +16 እኔ ሰማሁ፤ ሆዴም ታወከ፤ከድምፁ የተነሳ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ። አጥንቶቼም ነቀዙ፤+ከታች ያሉት እግሮቼ ተብረከረኩ። ሆኖም የጭንቀትን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ፤+ይህ ቀን ጥቃት በሚሰነዝርብን ሕዝብ ላይ ይመጣልና። +17 የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣የወይን ተክልም ፍሬ ባይሰጥ፣የወይራ ዛፍም ባያፈራ፣እርሻዎቹም* እህል ባይሰጡ፣መንጋው ከጉረኖው ቢጠፋ፣ከብቶቹም ሁሉ በረት ውስጥ ባይገኙ፣ +18 እኔ ግን በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ፤አዳኜ በሆነውም አምላክ እደሰታለሁ።+ +19 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ብርታቴ ነው፤+እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤በከፍታ ስፍራዎችም ላይ ያስኬደኛል።+ +1 ነቢዩ ዕንባቆም* በራእይ የተቀበለው መልእክት፦ + 2 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው?+ ከግፍ እንድታስጥለኝ ስለምን ጣልቃ የማትገባው እስከ መቼ ነው?*+ + 3 ለምን በደል ሲፈጸም እንዳይ ታደርገኛለህ? ጭቆናንስ ለምን ዝም ብለህ ታያለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ የሚፈጸመው ለምንድን ነው? ጠብና ግጭትስ ለምን በዛ? + 4 ስለዚህ ሕግ ላልቷል፤ፍትሕም ጨርሶ የለም። ክፉው ጻድቁን ከቦታልና፤ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ተጣሟል።+ + 5 “ብሔራትን እዩ፣ ደግሞም ልብ በሉ! በመገረም ተመልከቱ፤ ተደነቁም፤እናንተ ቢነገራችሁም እንኳ የማታምኑት አንድ ነገርበዘመናችሁ ይከናወናልና።+ + 6 እነሆ፣ ጨካኝና ፈጣን የሆነውን ብሔር ይኸውምከለዳውያንን አስነሳለሁና።+ የእነሱ ያልሆኑ ቤቶችን ለመውረስ፣ሰፋፊ የምድር ክፍሎችን ይወራሉ።+ + 7 እነሱ አስደንጋጭና አስፈሪ ናቸው። የገዛ ራሳቸውን ፍትሕና ሥልጣን* ያቋቁማሉ።+ + 8 ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፤ከሌሊት ተኩላዎችም ይልቅ ጨካኞች ናቸው።+ የጦር ፈረሶቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ፈረሶቻቸው ከሩቅ ስፍራ ይመጣሉ። ለመብላት እንደሚጣደፍ ንስር ተምዘግዝገው ይወርዳሉ።+ + 9 ሁሉም ዓመፅ ለመፈጸም ቆርጠው ይመጣሉ።+ እንደ ምሥራቅ ነፋስ ፊታቸውን ያቀናሉ፤+ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ያፍሳሉ። +10 በነገሥታት ይሳለቃሉ፤በከፍተኛ ባለሥልጣናትም ላይ ይስቃሉ።+ በተመሸገ ስፍራ ሁሉ ላይ ይስቃሉ፤+የአፈር ቁልልም ሠርተው ይይዙታል። +11 ከዚያም እንደ ነፋስ ወደ ፊት እየገሰገሱ በምድሪቱ ላይ ያልፋሉ፤ይሁንና በደለኛ ይሆናሉ፤+ምክንያቱም የኃይላቸው ምንጭ አምላካቸው እንደሆነ* ይናገራሉ።”+ +12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከዘላለም አንስቶ ያለህ አይደለህም?+ ቅዱስ የሆንከው አምላኬ ሆይ፣ አንተ አትሞትም።*+ ይሖዋ ሆይ፣ እነሱን ፍርድ ለማስፈጸም ሾመሃቸዋል፤ዓለቴ+ ሆይ፣ ቅጣት ለማስፈጸም* አቋቁመሃቸዋል።+ +13 ዓይኖችህ ክፉ የሆነውን ነገር እንዳያዩ እጅግ ንጹሐን ናቸው፤ክፋትንም ዝም ብለህ ማየት አትችልም።+ ታዲያ ከዳተኛውን ዝም ብለህ የምትመለከተው ለምንድን ነው?+ደግሞስ ክፉ ሰው ከእሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጥ ለምን ዝም ትላለህ?+ +14 ሰው እንደ ባሕር ዓሣ፣ገዢም እንደሌላቸው መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታት እንዲሆን ለምን ትፈቅዳለህ? +15 እሱ* እነዚህን ሁሉ በመንጠቆ ጎትቶ ያወጣል። በመረቡ ይይዛቸዋል፤በዓሣ ማጥመጃ መረቡም ይሰበስባቸዋል። በዚህም እጅግ ሐሴት ያደርጋል።+ +16 በመሆኑም ለመረቡ መሥዋዕት ይሠዋል፤ለዓሣ ማጥመጃ መረቡም መሥዋዕት* ያቀርባል፤በእነሱ የተነሳ ድርሻው በቅባት ተሞልቷል፤ምግቡም ምርጥ ነው። +17 ታዲያ መረቡን ሁልጊዜ ያራግፋል?* ብሔራትንስ ያለርኅራኄ መፍጀቱን ይቀጥላል?+ +2 በጥበቃ ቦታዬ ላይ እሰየማለሁ፤+በመከላከያ ግንቧም ላይ እቆማለሁ። በእኔ አማካኝነት ምን መናገር እንደሚፈልግ ለማየትናበምወቀስበት ጊዜ ምን መልስ እንደምሰጥ ለማወቅ በንቃት እጠባበቃለሁ። + 2 ይሖዋም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነበው ሰው በቀላሉ* እንዲያነበው+ራእዩን ጻፈው፤ በጽላትም ላይ ግልጽ በሆነ መንገድ ቅረጸው።+ + 3 ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ገና ይጠብቃልና፤ወደ ፍጻሜውም ይቸኩላል፤ ደግሞም አይዋሽም። ቢዘገይ* እንኳ በተስፋ ጠብቀው!*+ ያላንዳች ጥርጥር ይፈጸማልና። ራእዩ አይዘገይም! + 4 ኩሩ የሆነውን ተመልከት፤*ውስጡ ቀና አይደለም። ጻድቅ ግን በታማኝነቱ* በሕይወት ይኖራል።+ + 5 በእርግጥም የወይን ጠጅ አታላይ ስለሆነእብሪተኛው ሰው ግቡን አይመታም። ፍላጎቱን* እንደ መቃብር* ያሰፋል፤እሱ እንደ ሞት ነው፤ ደግሞም ሊጠግብ አይችልም። ብሔራትን ሁሉ ወደ ራሱ መሰብሰቡን ይቀጥላል፤ሕዝቦችንም ሁሉ ለራሱ ያከማቻል።+ + 6 እነዚህ ሁሉ ሰዎች በእሱ ላይ አይተርቱም? ደግሞስ አሽሙርና ግራ የሚያጋባ ቃል አይሰነዝሩም?+ እንዲህ ይላሉ፦‘የራሱ ያልሆነውን የሚያጋብስ፣ዕዳውንም የሚያበዛ ወዮለት! ይህን የሚያደርገው እስከ መቼ ነው? + 7 አበዳሪዎችህ በድንገት አይነሱም? ተነስተው በኃይል ይነቀንቁሃል፤በእነሱም እጅ ለብዝበዛ ትዳረጋለህ።+ + 8 ብዙ ብሔራትን ስለዘረፍክከሕዝቦቹ መካከል የቀሩት ሁሉ ይዘርፉሃል፤+ምክንያቱም አንተ የሰው ልጆችን ደም አፍስሰሃል፤በምድሪቱ፣ በከተሞችናበዚያ በሚኖሩት ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።+ + 9 ከጥፋት እጅ ያመልጥ ዘንድጎጆውን ከፍ ባለ ቦታ ላይ ለመሥራትለቤቱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም የሚሰበስብ ወዮለት! +10 በቤትህ ላይ አሳፋሪ ነገር አሲረሃል። ብዙ ሕዝቦችን ጠራርገህ በማጥፋት በራስህ* ላይ ኃጢአት ሠርተሃል።+ +11 ድንጋይ ከግንቡ ውስጥ ይጮኻል፤ከጣሪያው እንጨቶችም መካከል አንድ ወራጅ ይመልስለታል። +12 ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚገነባናበዓመፅ ለሚመሠርታት ወዮለት! +13 እነሆ፣ ሰዎች እሳት ለሚበላው ነገር እንዲደክሙ፣ብሔራትም ከንቱ ለሆነ ነገር እንዲለፉ የሚያደርገው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አይደለም?+ +14 ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣ምድርም የይሖዋን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።+ +15 እርቃናቸውን ለማየት ሲልታላቅ ቁጣውንና ንዴቱን ቀላቅሎለባልንጀሮቹ መጠጥ በመስጠት እንዲሰክሩ ለሚያደርግ ሰው ወዮለት! +16 በክብር ፋንታ ውርደት ትሞላለህ። አንተ ራስህም ጠጣ፤ ያልተገረዝክ መሆንህንም አሳይ።* በይሖዋ ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ወደ አንተ ይዞራል፤+ክብርህም በውርደት ይሸፈናል፤ +17 በሊባኖስ ላይ የተፈጸመው ግፍ ይሸፍንሃል፤አራዊትንም ያሸበረው ጥፋት በአንተ ላይ ይደርሳል፤ምክንያቱም አንተ የሰዎችን ደም አፍስሰሃል፤በምድር፣ በከተሞቿናበውስጧ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።+ +18 የተቀረጸ ምስል፣ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳከብረት የተሠራ ሐውልትና* ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?+ +19 እንጨቱን “ንቃ!” መናገር የማይችለውንም ድንጋይ “ተነስ! አስተምረን!” ለሚል ወዮለት! እነሆ፣ በወርቅና በብር ተለብጧል፤+በውስጡም እስትንፋስ የለም።+ +20 ይሖዋ ግን በቅዱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው።+ ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ በይ!’”+ +3 ዓመፀኛ ለሆነችው፣ ለረከሰችውና ለጨቋኟ ከተማ ወዮላት!+ + 2 ማንንም ለመታዘዝ ፈቃደኛ አልሆነችም፤+ ምንም ዓይነት ተግሣጽ አልተቀበለችም።+ በይሖዋ አልታመነችም፤+ ወደ አምላኳም አልቀረበችም።+ + 3 በውስጧ ያሉት መኳንንቷ የሚያገሱ አንበሶች ናቸው።+ ፈራጆቿ የሌሊት ተኩላዎች ናቸው፤ለጠዋት ምንም ሳያስቀሩ አጥንቱን ሁሉ ይግጣሉ። + 4 ነቢያቷ እብሪተኞችና አታላዮች ናቸው።+ ካህናቷ ቅዱስ የሆነውን ነገር ያረክሳሉ፤+በሕጉ ላይ ያምፃሉ።+ + 5 በመካከሏ ያለው ይሖዋ ጻድቅ ነው፤+ እሱ ምንም ዓይነት ስህተት አይፈጽምም። ፍርዱን እንደማይነጥፍ የንጋት ብርሃን፣በየማለዳው ያሳውቃል።+ ክፉ ሰው ግን ኀፍረት የሚባል ነገር አያውቅም።+ + 6 “ብሔራትን አጥፍቻለሁ፤ በቅጥር ማዕዘኖች ላይ ያሉ ማማዎቻቸው ወድመዋል። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው መንገዶቻቸውን አፍርሻለሁ። ከተሞቻቸው ፈራርሰዋል፤ በዚያ አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም አይገኝባቸውም።+ + 7 እኔም ‘በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፤ ተግሣጽም* ትቀበያለሽ’ አልኩ፤+ ይህም መኖሪያዋ እንዳይጠፋ ነው፤+ለሠራችው ኃጢአት ሁሉ ተጠያቂ አደርጋታለሁ።* እነሱ ግን ብልሹ ነገር ለመፈጸም ይበልጥ ጓጉ።+ + 8 ‘ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሳበት ቀን* ድረስእኔን በተስፋ ተጠባበቁ’*+ ይላል ይሖዋ፤‘ብሔራት��� ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትን ለማከማቸት፣በእነሱም ላይ መዓቴንና የሚነደውን ቁጣዬን ሁሉ ለማውረድ የፍርድ ውሳኔ አስተላልፌአለሁና፤+መላዋ ምድር በቅንዓቴ እሳት ትበላለች።+ + 9 በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የይሖዋን ስም እንዲጠሩናእጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲያገለግሉት*ቋንቋቸውን ለውጬ ንጹሕ ቋንቋ እሰጣቸዋለሁ።’+ +10 የሚለምኑኝ ሰዎች ይኸውም የተበተኑት ሕዝቦቼየኢትዮጵያ ወንዞች ከሚገኙበት ስፍራ ስጦታ ያመጡልኛል።+ +11 በዚያን ቀን በእኔ ላይ በማመፅ በፈጸምሻቸው ሥራዎች ሁሉለኀፍረት አትዳረጊም፤+በዚያን ጊዜ በትዕቢት ጉራ የሚነዙትን ከመካከልሽ አስወግዳለሁና፤አንቺም ከእንግዲህ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ ፈጽሞ አትታበዪም።+ +12 እኔም ትሑት የሆነና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሕዝብ በመካከላችሁ እንዲቀር አደርጋለሁ፤+እነሱም የይሖዋን ስም መጠጊያቸው ያደርጉታል። +13 የእስራኤል ቀሪዎች+ ምንም ዓይነት ክፋት አይሠሩም፤+ውሸት አይናገሩም፤ በአፋቸውም ውስጥ አታላይ ምላስ አይገኝም፤ይልቁንም ይመገባሉ፤* ይተኛሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።”+ +14 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እልል በይ! እስራኤል ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ!+ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በሙሉ ልብሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሴትም አድርጊ!+ +15 ይሖዋ በአንቺ ላይ የተላለፈውን ፍርድ ሽሯል።+ ጠላትሽን ከአንቺ መልሷል።+ የእስራኤል ንጉሥ ይሖዋ በመካከልሽ ነው።+ ከእንግዲህ ወዲህ ጥፋት አያስፈራሽም።+ +16 በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይባላል፦ “ጽዮን ሆይ፣ አትፍሪ።+ እጆችሽ አይዛሉ። +17 አምላክሽ ይሖዋ በመካከልሽ ነው።+ እንደ ኃያል ተዋጊ ያድናል። በታላቅ ደስታ በአንቺ ሐሴት ያደርጋል።+ ለአንቺ ፍቅር በማሳየቱ ረክቶ ዝም ይላል።* በእልልታ በአንቺ ሐሴት ያደርጋል። +18 በበዓላትሽ ላይ ባለመገኘታቸው ያዘኑትን ሰዎች እሰበስባለሁ፤+ለእሷ ሲሉ በደረሰባቸው ነቀፋ የተነሳ ወደ አንቺ አልመጡም።+ +19 እነሆ፣ በዚያን ጊዜ በሚጨቁኑሽ ሁሉ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤+የምታነክሰውንም አድናታለሁ፤+የተበተነችውንም እሰበስባለሁ።+ ኀፍረት በተከናነቡበት ምድር ሁሉእንዲወደሱና ዝና* እንዲያተርፉ አደርጋቸዋለሁ። +20 በዚያን ጊዜ መልሼ አመጣችኋለሁ፤አዎ፣ በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ። ተማርከው የተወሰዱባችሁን ሰዎች በፊታችሁ መልሼ በምሰበስብበት ጊዜ+በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ዝና* እንድታተርፉና እንድትወደሱ አደርጋለሁና”+ ይላል ይሖዋ። +1 በይሁዳ ንጉሥ በአምዖን+ ልጅ በኢዮስያስ+ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያህ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኩሺ ልጅ፣ ወደ ሶፎንያስ* የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ + 2 “ማንኛውንም ነገር ሙሉ በሙሉ ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ” ይላል ይሖዋ።+ + 3 “ሰውንና እንስሳን ጠራርጌ አጠፋለሁ። የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣንእንዲሁም ማሰናከያዎቹንና*+ ክፉ ሰዎችን ጠራርጌ አጠፋለሁ፤+ደግሞም የሰውን ዘር ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ” ይላል ይሖዋ። + 4 “በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ላይእጄን እዘረጋለሁ፤የባአልን ቀሪዎች* ሁሉና የባዕድ አምላክ ካህናትን ስምከሌሎቹ ካህናት ጋር ከዚህ ስፍራ ፈጽሜ አስወግዳለሁ፤+ + 5 በቤት ጣሪያዎች ላይ ሆነው ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትን+እንዲሁም በአንድ በኩል ለይሖዋ እየሰገዱና ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል እየገቡ+በሌላ በኩል ግን ለማልካም ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል የሚገቡትን አጠፋለሁ፤+ + 6 ደግሞም ይሖዋን ከመከተል ወደኋላ የሚሉትን፣+ይሖዋን የማይፈልጉትን ወይም እሱን የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።”+ + 7 በሉዓላዊው ጌታ በይሖዋ ፊት ዝም በሉ፤ የይሖዋ ቀን ቀርቧልና።+ ይሖዋ መሥዋዕት አዘጋጅቷ��፤ የጠራቸውን ቀድሷል። + 8 “በይሖዋ የመሥዋዕት ቀን መኳንንቱን፣የንጉሡን ወንዶች ልጆችና+ የባዕዳንን ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ። + 9 በዚያም ቀን መድረኩ* ላይ የሚወጡትን ሁሉ፣የጌቶቻቸውንም ቤት በዓመፅና በማታለል የሚሞሉትን እቀጣለሁ። +10 በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ከዓሣ በር+ የጩኸት ድምፅ፣ከከተማዋም ሁለተኛ ክፍል+ ዋይታ፣ከኮረብቶቹም ታላቅ ሁከት ይሰማል። +11 እናንተ የማክተሽ* ነዋሪዎች፣ ዋይ በሉ፤ነጋዴዎቹ ሁሉ እንዳልነበሩ ሆነዋልና፤*ብር የሚመዝኑትም ሁሉ ጠፍተዋል። +12 በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ደግሞም ቸልተኛ የሆኑትንና*በልባቸው ‘ይሖዋ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።+ +13 ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይወድማሉ።+ ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሆኖም አይኖሩባቸውም፤ወይንም ይተክላሉ፤ ሆኖም የወይን ጠጁን አይጠጡም።+ +14 ታላቁ የይሖዋ ቀን ቅርብ ነው!+ ቅርብ ነው፤ ደግሞም በፍጥነት እየቀረበ ነው!*+ የይሖዋ ቀን ድምፅ አስፈሪ* ነው።+ በዚያ ተዋጊው ይጮኻል።+ +15 ያ ቀን የታላቅ ቁጣ ቀን፣+የጭንቀትና የሥቃይ ቀን፣+የአውሎ ነፋስና የጥፋት ቀን፣የጨለማና የጭጋግ ቀን፣+የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤+ +16 በተመሸጉ ከተሞችና በቅጥር ማዕዘኖች ላይ ባሉ ረጃጅም ማማዎች ላይ+የቀንደ መለከትና የጦርነት ሁካታ ድምፅ የሚሰማበት ቀን ይሆናል።+ +17 በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣለሁ፤እነሱም እንደ ዕውር ይሄዳሉ፤+ምክንያቱም በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተዋል።+ ደማቸው እንደ አቧራ፣አንጀታቸውም እንደ ፋንድያ ይፈስሳል።+ +18 በይሖዋ ታላቅ ቁጣ ቀን ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤+መላዋ ምድር በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፤+ምክንያቱም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሁሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋቸዋል።”+ +2 እናንተ ኀፍረት የማይሰማችሁ ሕዝቦች ሆይ፣+በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አዎ ተሰብሰቡ።+ + 2 የተላለፈው ውሳኔ ከመፈጸሙ በፊት፣ቀኑ እንደ ገለባ ከማለፉ በፊት፣የሚነደው የይሖዋ ቁጣ ሳይመጣባችሁ፣+የይሖዋ የቁጣ ቀን ሳይደርስባችሁ፣ + 3 እናንተ የጽድቅ ድንጋጌዎቹን* የምታከብሩ፣በምድር ላይ የምትኖሩ የዋሆች* ሁሉ ይሖዋን ፈልጉ።+ ጽድቅን ፈልጉ፤ የዋህነትን* ፈልጉ። ምናልባት በይሖዋ የቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።+ + 4 ጋዛ የተተወች ከተማ ትሆናለችና፤አስቀሎንም ባድማ ትሆናለች።+ አሽዶድ በጠራራ ፀሐይ* ትባረራለች፤ኤቅሮንም ከሥሯ ትመነገላለች።+ + 5 “በባሕሩ ዳርቻ ለሚኖረው ሕዝብ ይኸውም ለከሪታውያን ብሔር ወዮለት!+ የይሖዋ ቃል በአንተ ላይ ነው። የፍልስጤማውያን ምድር የሆንሽው ከነአን ሆይ፣ አጠፋሻለሁ፤አንድም ነዋሪ አይተርፍም። + 6 የባሕሩ ዳርቻም መሰማሪያ ይሆናል፤ለእረኞች የውኃ ጉድጓድና ለበጎች ከድንጋይ የተሠራ ጉረኖ ይኖረዋል። + 7 ከይሁዳ ቤት ለቀሩት ሰዎች መኖሪያ ስፍራ ይሆናል፤+በዚያም የግጦሽ ቦታ ያገኛሉ። በምሽት በአስቀሎን ቤቶች ውስጥ ይተኛሉ። አምላካቸው ይሖዋ ትኩረቱን በእነሱ ላይ ያደርጋልና፤*የተማረኩባቸውንም ሰዎች መልሶ ይሰበስባል።”+ + 8 “ሞዓብ የሰነዘረችውን ነቀፋና+ የአሞናውያንን ስድብ ሰምቻለሁ፤+እነሱ በሕዝቤ ላይ ተሳልቀዋል፤ ግዛታቸውንም ለመውሰድ በእብሪት ዝተዋል።+ + 9 ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣“ሞዓብ እንደ ሰዶም፣+አሞናውያንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤+ሳማ የወረሰው ምድርና የጨው ጉድጓድ ይሆናሉ፤ ለዘለቄታውም ባድማ ሆነው ይቀራሉ።+ የሕዝቤ ቀሪዎች ይዘርፏቸዋል፤ከገዛ ብሔሬ የቀሩት ሰዎችም ይወርሷቸዋል። +10 ከኩራታቸው የተነሳ ይህ ይደርስባቸዋል፤+ምክንያቱ�� በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ሕዝብ ላይ ተሳልቀዋል፤ ራሳቸውንም ከፍ ከፍ አድርገዋል። +11 ይሖዋ በእነሱ ዘንድ የተፈራ* ይሆናል፤በምድር ላይ ያሉትን አማልክት ሁሉ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋልና፤*የብሔራት ደሴቶች ሁሉ በያሉበት ሆነውለእሱ ይሰግዳሉ።*+ +12 እናንተም ኢትዮጵያውያን በሰይፌ ትገደላላችሁ።+ +13 እሱ እጁን ወደ ሰሜን ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ነነዌንም ባድማና እንደ በረሃ ደረቅ ያደርጋታል።+ +14 መንጎች ይኸውም ሁሉም ዓይነት የዱር እንስሳት* በውስጧ ይተኛሉ። ሻላ* እና ጃርት በፈራረሱት ዓምዶቿ መካከል ያድራሉ። የዝማሬ ድምፅ በመስኮት ይሰማል። ደጃፍ ላይ ፍርስራሽ ይኖራል፤የአርዘ ሊባኖስ እንጨቶቹ እንዲጋለጡ ያደርጋልና። +15 በልቧ ‘እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም’ ስትል የነበረችውያለስጋት የተቀመጠችው ኩሩዋ ከተማ ይህች ናት። ምንኛ አስፈሪ ቦታ ሆነች!የዱር እንስሳት የሚተኙባት ስፍራ ሆናለች። በእሷ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ያፏጫል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።”+ +1 ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል በነቢዩ ሐጌ*+ በኩል የይሁዳ ገዢ ወደሆነው ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና+ ሊቀ ካህናት ወደሆነው ወደ የሆጼዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦ +2 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነዚህ ሰዎች “የይሖዋ ቤት* የሚገነባበት* ጊዜ ገና አልደረሰም” ይላሉ።’”+ +3 የይሖዋም ቃል በነቢዩ ሐጌ+ በኩል እንዲህ ሲል በድጋሚ መጣ፦ +4 “ይህ ቤት ፈርሶ እያለ፣ እናንተ በሚያምር እንጨት በተለበጡ ቤቶቻችሁ ውስጥ የምትኖሩበት ጊዜ ነው?+ +5 አሁንም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘መንገዳችሁን ልብ በሉ።* +6 ብዙ ዘር ዘራችሁ፤ የምትሰበስቡት ግን ጥቂት ነው።+ ትበላላችሁ፤ ሆኖም አትጠግቡም። ትጠጣላችሁ፤ ሆኖም አትረኩም። ትለብሳላችሁ፤ የሚሞቀው ሰው ግን የለም። ተቀጥሮ የሚሠራው ደሞዙን ብዙ ቀዳዳዎች ባሉት ከረጢት ውስጥ ያስቀምጣል።’” +7 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘መንገዳችሁን ልብ በሉ።’* +8 “‘ወደ ተራራው ወጥታችሁ ጥርብ እንጨት አምጡ።+ እኔ ደስ እንድሰኝበትና እንድከበርበት+ ቤቱን ሥሩ’+ ይላል ይሖዋ።” +9 “‘ብዙ ነገር ጠበቃችሁ፤ ሆኖም ያገኛችሁት ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ባመጣችሁትም ጊዜ እፍ ብዬ በተንኩት።+ ይህ የሆነው ለምንድን ነው?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። ‘የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ እያንዳንዳችሁ የገዛ ቤታችሁን ለማሳመር ስለምትሯሯጡ ነው።+ +10 ስለዚህ ከእናንተ በላይ ያሉት ሰማያት ጠል ማዝነባቸውን አቆሙ፤ ምድርም ፍሬዋን አልሰጥ አለች። +11 እኔም በምድር ላይ፣ በተራሮች ላይ፣ በእህሉ ላይ፣ በአዲሱ የወይን ጠጅ ላይ፣ በዘይቱ ላይ፣ ምድሪቱ በምታበቅለው ነገር ላይ፣ በሰዎች ላይ፣ በመንጎች ላይ እንዲሁም እጆቻችሁ በደከሙበት ነገር ሁሉ ላይ ድርቅን ጠራሁ።’” +12 የሰላትያል+ ልጅ ዘሩባቤል፣+ የየሆጼዴቅ+ ልጅ ሊቀ ካህናቱ ኢያሱና የቀረው ሕዝብ በሙሉ የአምላካቸውን የይሖዋን ድምፅ እንዲሁም ነቢዩ ሐጌ የተናገረውን ቃል ሰሙ፤ አምላካቸው ይሖዋ ልኮታልና፤ ሕዝቡም ከይሖዋ የተነሳ ፈሩ። +13 ከዚያም የይሖዋ መልእክተኛ የሆነው ሐጌ ከይሖዋ በተሰጠው ተልእኮ መሠረት ለሕዝቡ “‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ’+ ይላል ይሖዋ” የሚል መልእክት ተናገረ። +14 ስለዚህ ይሖዋ የይሁዳን ገዢ+ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የየሆጼዴቅን ልጅ የኢያሱን+ መንፈስ እንዲሁም የቀረውን ሕዝብ መንፈስ በሙሉ አነሳሳ፤+ እነሱም መጥተው የአምላካቸውን የሠራዊት ጌታ የይሖዋን ቤት መሥራት ጀመሩ።+ +15 ይህ የሆነው ንጉሥ ዳር���ስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን ነበር።+ +2 በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ21ኛው ቀን የይሖዋ ቃል በነቢዩ ሐጌ+ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፦ +2 “የይሁዳን ገዢ+ የሰላትያልን ልጅ ዘሩባቤልንና+ ሊቀ ካህናቱን የየሆጼዴቅን+ ልጅ ኢያሱን+ እንዲሁም የቀረውን ሕዝብ እባክህ እንዲህ ብለህ ጠይቃቸው፦ +3 ‘የዚህ ቤት* የቀድሞ ክብሩ እንዴት እንደነበረ ያየ ሰው በመካከላችሁ አለ?+ አሁንስ እንዴት ሆኖ ይታያችኋል? ከቀድሞው ጋር ሲነጻጸር ከምንም የማይቆጠር አይደለም?’+ +4 “‘አሁን ግን ዘሩባቤል፣ በርታ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የየሆጼዴቅ ልጅ ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ፣ አንተም በርታ።’ “‘እናንተም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ፣ በርቱና ሥሩ’+ ይላል ይሖዋ። “‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና’+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +5 ‘ከግብፅ በወጣችሁበት ጊዜ የገባሁላችሁን ቃል አስታውሱ፤+ መንፈሴም በመካከላችሁ ይኖራል።*+ አትፍሩ።’”+ +6 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ሰማያትን፣ ምድርን፣ ባሕርንና የብስን አናውጣለሁ።’+ +7 “‘ብሔራትንም ሁሉ አናውጣለሁ፤ በብሔራትም ሁሉ መካከል ያሉ የከበሩ* ነገሮች ይመጣሉ፤+ ደግሞም ይህን ቤት በክብር እሞላዋለሁ’+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +8 “‘ብሩ የእኔ ነው፤ ወርቁም የእኔ ነው’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +9 “‘ይህ ቤት ወደፊት የሚጎናጸፈው ክብር ከቀድሞው የበለጠ ይሆናል’+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “‘በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ’+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።” +10 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ነቢዩ ሐጌ+ እንዲህ ሲል መጣ፦ +11 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እባክህ፣ ካህናቱን ስለ ሕጉ እንዲህ ብለህ ጠይቃቸው፦+ +12 “አንድ ሰው በልብሱ እጥፋት የተቀደሰ ሥጋ ቢይዝና ልብሱ ዳቦ፣ ወጥ፣ የወይን ጠጅ፣ ዘይት ወይም ሌላ ማንኛውም ዓይነት ምግብ ቢነካ፣ የነካው ነገር ቅዱስ ይሆናል?”’” ካህናቱ “አይሆንም!” ብለው መለሱ። +13 ከዚያም ሐጌ እንዲህ ሲል ጠየቀ፦ “አስከሬን በመንካቱ* የረከሰ ሰው ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱን ቢነካ የተነካው ነገር ይረክሳል?”+ ካህናቱ “አዎ፣ ይረክሳል” ብለው መለሱ። +14 ሐጌም እንዲህ አለ፦ “‘ይህም ሕዝብ እንዲሁ ነው፤ ይህም ብሔር በፊቴ እንዲሁ ነው’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የእጆቻቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፤ በዚያ የሚያቀርቡት ማንኛውም ነገር የረከሰ ነው።’ +15 “‘አሁን ግን እባካችሁ ከዚህ ቀን ጀምሮ፣ ይህን ልብ በሉ፦* በይሖዋ ቤተ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመነባበሩ በፊት፣+ +16 ያኔ ሁኔታው ምን ይመስል ነበር? አንድ ሰው 20 መስፈሪያ አገኛለሁ ብሎ እህል ወደተከመረበት ቦታ በመጣ ጊዜ 10 መስፈሪያ ብቻ አገኘ፤ ደግሞም አንድ ሰው 50 መለኪያ የወይን ጠጅ ለማግኘት ወደ ወይን መጭመቂያው በመጣ ጊዜ 20 መለኪያ ብቻ አገኘ፤+ +17 እናንተን ይኸውም የእጃችሁን ሥራ ሁሉ በሚለበልብና በሚያደርቅ ነፋስ፣ በዋግና+ በበረዶ መታሁ፤ ይሁንና አንዳችሁም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። +18 “‘በዛሬው ዕለት ይኸውም በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን የይሖዋ ቤተ መቅደስ መሠረት ተጥሏል።+ እባካችሁ ከዚህ ቀን ጀምሮ ይህን ልብ በሉ፦* +19 በጎተራ* ውስጥ የቀረ ዘር አሁንም አለ?+ የወይን ተክሉ፣ በለሱ፣ ሮማኑና የወይራ ዛፉ እስካሁን ድረስ ፍሬ አላፈሩም። ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ።’”+ +20 በወሩ 24ኛ ቀን የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ሐጌ መጣ፦+ +21 “ለይሁዳ ገዢ ለዘሩባቤል እንዲህ በለው፦ ‘ሰማያትንና ምድርን አናውጣለሁ።+ +22 የመንግ��ታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ የብሔራት መንግሥታትንም ብርታት አጠፋለሁ፤+ ሠረገላውንና የሚቀመጡበትን ሰዎች እገለብጣለሁ፤ ፈረሶቹና ጋላቢዎቻቸውም እያንዳንዳቸው በገዛ ወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።’”+ +23 “‘የሰላትያል+ ልጅ አገልጋዬ ዘሩባቤል+ ሆይ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘በዚያ ቀን እወስድሃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ደግሞም እንደ ማኅተም ቀለበት አደርግሃለሁ፤ ምክንያቱም የመረጥኩት አንተን ነው’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።” +3 እሱም ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን+ በይሖዋ መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፤ ሰይጣንም+ እሱን ለመቃወም በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር። +2 ከዚያም የይሖዋ መልአክ ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “ሰይጣን፣ ይሖዋ ይገሥጽህ፤+ አዎ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠው+ ይሖዋ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት መካከል የተነጠቀ የእንጨት ጉማጅ አይደለም?” +3 ኢያሱም ያደፈ ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር። +4 መልአኩ በፊቱ ቆመው የነበሩትን “ያደፈውን ልብሱን አውልቁለት” አላቸው። ከዚያም እሱን “እነሆ፣ ጥፋትህን* አስወግጄልሃለሁ፤ ደግሞም ጥሩ ልብስ ትለብሳለህ”*+ አለው። +5 እኔም “በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም ይደረግለት”+ አልኩ። እነሱም ንጹሑን ጥምጥም በራሱ ላይ አደረጉለት፤ ልብስም አለበሱት፤ የይሖዋም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር። +6 ከዚያም የይሖዋ መልአክ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ +7 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመንገዶቼ ብትመላለስና በፊቴ ኃላፊነቶችህን ብትወጣ፣ በቤቴ ፈራጅ ሆነህ ታገለግላለህ፤+ ቅጥር ግቢዎቼንም ትንከባከባለህ፤* እኔም እዚህ በቆሙት መካከል በነፃነት የመቅረብ መብት እሰጥሃለሁ።’ +8 “‘ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ ሆይ፣ አንተም ሆንክ በፊትህ የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ እባካችሁ ስሙ፤ እነዚህ ሰዎች ምልክት ሆነው ያገለግላሉና፤ እነሆ፣ ቀንበጥ+ የሚል ስም ያለውን አገልጋዬን አመጣለሁ!+ +9 በኢያሱ ፊት ያስቀመጥኩትን ድንጋይ እዩ! በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፤ እኔም በላዩ ላይ ጽሑፍ እቀርጻለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።’+ +10 “‘በዚያ ቀን’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘እያንዳንዳችሁ ጎረቤታችሁን ከወይናችሁና ከበለስ ዛፋችሁ ሥር እንዲቀመጥ ትጋብዛላችሁ።’”+ +7 ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ኪስሌው* በተባለው በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በአራተኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ።+ +2 የቤቴል ሰዎች ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳያቸው ለመለመን ሳሬጸርንና ረጌምሜሌክን ከሰዎቹ ጋር ላኩ፤ +3 እነሱም የሠራዊት ጌታን የይሖዋን ቤት* ካህናትና ነቢያቱን “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግኩት በአምስተኛው ወር ማልቀስና+ መጾም ይኖርብኛል?” ብለው ጠየቁ። +4 የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ +5 “ለምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ ‘ለ70 ዓመታት+ በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ዋይ ዋይ ስትሉ፣+ ትጾሙ የነበረው በእርግጥ ለእኔ ነበር? +6 ትበሉና ትጠጡ በነበረበት ጊዜስ ትበሉና ትጠጡ የነበረው ለራሳችሁ አልነበረም? +7 ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉት ከተሞቿ በሰዎች ተሞልተውና ሰላም ሰፍኖባቸው በነበረበት ጊዜ እንዲሁም ሰዎች በኔጌብና በሸፌላ ይኖሩ በነበረበት ወቅት ይሖዋ በቀድሞዎቹ ነቢያት አማካኝነት ያወጀውን ቃል መታዘዝ አልነበረባችሁም?’”+ +8 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ ዘካርያስ መጣ፦ +9 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነተኛ ፍትሕ ላይ ተመሥርታችሁ ፍረዱ፤+ አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ፍቅርና+ ምሕረት አሳዩ። +10 መበለቲቱንም ሆነ አባት የሌለውን ልጅ፣*+ ��ባዕድ አገር የመጣውን ሰውም+ ሆነ ድሃውን አታታሉ፤+ ደግሞም አንዳችሁ በሌላው ላይ ክፉ ለማድረግ በልባችሁ አታሲሩ።’+ +11 እነሱ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆኑም፤+ በግትርነትም ጀርባቸውን ሰጡ፤+ ላለመስማትም ሲሉ ጆሯቸውን ደፈኑ።+ +12 ልባቸውን እንደ አልማዝ* አጠነከሩ፤+ እንዲሁም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት፣ በቀድሞዎቹ ነቢያት በኩል የላከውን ሕግና* ቃል አልታዘዙም።+ ከዚህም የተነሳ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እጅግ ተቆጣ።”+ +13 “‘እኔ ስጠራቸው እንዳልሰሙኝ ሁሉ+ እነሱ ሲጣሩም አልሰማቸውም’+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +14 ‘ደግሞም ወደማያውቋቸው ብሔራት ሁሉ በአውሎ ነፋስ በተንኳቸው፤+ ምድሪቱም ትተዋት ከሄዱ በኋላ ባድማ ሆነች፤ በእሷ የሚያልፍ ወይም ወደ እሷ የሚመለስ ማንም የለም፤+ የተወደደችውን ምድር አስፈሪ ቦታ አድርገዋታልና።’” +12 የፍርድ መልእክት፦ “ስለ እስራኤል የተነገረው የይሖዋ ቃል።”ሰማያትን የዘረጋው፣+የምድርን መሠረት የጣለውና+የሰውን መንፈስ* በውስጡ የሠራው ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ +2 “እነሆ፣ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ የምታንገዳግድ ጽዋ* አደርጋታለሁ፤ ጠላት ይሁዳንም ሆነ ኢየሩሳሌምን ይከባል።+ +3 በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን ለሕዝቦች ሁሉ ከባድ* ድንጋይ አደርጋታለሁ። ድንጋዩን የሚያነሱት ሁሉ ክፉኛ መጎዳታቸው የማይቀር ነው፤+ የምድር ብሔራትም ሁሉ በእሷ ላይ ይሰበሰባሉ።+ +4 በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣ “እያንዳንዱን ፈረስ በድንጋጤ፣ ጋላቢውንም በእብደት እመታለሁ። ዓይኖቼን በይሁዳ ቤት ላይ አደርጋለሁ፤ የሕዝቦቹን ፈረሶች ሁሉ ግን አሳውራለሁ። +5 የይሁዳም አለቆች* በልባቸው ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አምላካቸው ስለሆነ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ብርታታችን ናቸው’ ይላሉ።+ +6 በዚያን ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ የሚነድ ምድጃና በታጨደ እህል መካከል እንዳለ የሚነድ ችቦ አደርጋቸዋለሁ፤+ እነሱም በስተ ቀኝም ሆነ በስተ ግራ፣ በዙሪያቸው ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ይበላሉ፤+ ኢየሩሳሌምም በገዛ ስፍራዋ* ይኸውም በኢየሩሳሌም ዳግመኛ የሰዎች መኖሪያ ትሆናለች።+ +7 “የዳዊት ቤት ውበትና* የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ውበት* ከይሁዳ እጅግ የበለጠ እንዳይሆን ይሖዋ በመጀመሪያ የይሁዳን ድንኳኖች ያድናል። +8 በዚያ ቀን ይሖዋ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ዙሪያ መከታ ይሆናል፤+ በዚያም ቀን ከእነሱ መካከል የሚሰናከለው* እንደ ዳዊት ይሆናል፤ የዳዊትም ቤት እንደ አምላክ፣ በፊታቸውም እንደሚሄደው የይሖዋ መልአክ ይሆናል።+ +9 ደግሞም በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን ብሔራት ሁሉ ለማጥፋት ቆርጬ እነሳለሁ።+ +10 “በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የሞገስንና የምልጃን መንፈስ አፈሳለሁ፤ እነሱም የወጉትን ያዩታል፤+ ለአንድያ ልጅም እንደሚለቀስ ያለቅሱለታል፤ ለበኩር ልጅ እንደሚለቀሰው ያለ መራራ ለቅሶም ያለቅሱለታል። +11 በዚያን ቀን በኢየሩሳሌም የሚለቀሰው ለቅሶ በመጊዶ ሜዳ፣ በሃዳድሪሞን እንደተለቀሰው ለቅሶ ታላቅ ይሆናል።+ +12 ምድሪቱም ታለቅሳለች፤ እያንዳንዱም ቤተሰብ ለየብቻው ያለቅሳል፤ የዳዊት ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የናታን+ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ +13 የሌዊ+ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የሺምአይ+ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ +14 የቀሩትም ቤተሰቦች በሙሉ፣ እያንዳንዱ ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው ያለቅሳሉ። +1 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣+ በስምንተኛው ወር የይሖዋ ቃል ወደ ኢዶ ልጅ፣ ወደ ቤራክያህ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ*+ እንዲህ ሲል መጣ፦ +2 “ይሖዋ በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቆጥቶ ነበር።+ +3 “እንዲህ በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ወደ እኔ ተመለሱ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ’+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።”’ +4 “‘የቀደሙት ነቢያት “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ‘እባካችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ራቁ’* ይላል በማለት የነገሯቸውን አባቶቻችሁን አትምሰሉ።”’+ “‘እነሱ ግን አልሰሙም፤ ለእኔም ትኩረት አልሰጡም’+ ይላል ይሖዋ። +5 “‘አባቶቻችሁ አሁን የት አሉ? ነቢያቱስ ለዘላለም መኖር ችለዋል? +6 ይሁን እንጂ አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያትን ያዘዝኳቸው ቃልና ድንጋጌ በአባቶቻችሁ ላይ ደርሶ የለም?’+ በመሆኑም ወደ እኔ ተመልሰው እንዲህ አሉ፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በወሰነው መሠረት እንደ መንገዳችንና እንደ ሥራችን አደረገብን።’”+ +7 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣+ ሺባት* በተባለው በ11ኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ኢዶ ልጅ፣ ወደ ቤራክያህ ልጅ፣ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ +8 “በሌሊት ራእይ አየሁ። አንድ ሰው ቀይ ፈረስ እየጋለበ ነበር፤ እሱም በሸለቆው ውስጥ በሚገኙት የአደስ ዛፎች መካከል ቆመ፤ ከበስተ ኋላውም ቀይ፣ ቀይ ቡኒና ነጭ ፈረሶች ነበሩ።” +9 እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ እነማን ናቸው?” አልኩ። ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ “እነዚህ እነማን እንደሆኑ አሳይሃለሁ” ሲል መለሰልኝ። +10 ከዚያም በአደስ ዛፎቹ መካከል ቆሞ የነበረው ሰው “እነዚህ በምድር ላይ እንዲመላለሱ ይሖዋ የላካቸው ናቸው” አለ። +11 እነሱም በአደስ ዛፎቹ መካከል ቆሞ ለነበረው የይሖዋ መልአክ “በምድር ላይ ተመላለስን፤ እነሆም መላዋ ምድር ጸጥታና እርጋታ ሰፍኖባታል”+ አሉት። +12 የይሖዋም መልአክ እንዲህ አለ፦ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ በእነዚህ 70 ዓመታት የተቆጣሃቸውን+ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ምሕረትህን የምትነፍጋቸው እስከ መቼ ነው?”+ +13 ይሖዋም ሲያነጋግረኝ ለነበረው መልአክ ደግነት በተሞላባቸውና በሚያጽናኑ ቃላት መለሰለት። +14 ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፦ “እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለኢየሩሳሌምና ለጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ።+ +15 ዘና ብለው በተቀመጡት ብሔራት ላይ እጅግ ተቆጥቻለሁ፤+ ምክንያቱም በመጠኑ ብቻ ተቆጥቼ+ እያለ እነሱ ግን ከልክ ያለፈ እርምጃ ወሰዱ።”’+ +16 “ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት እመለሳለሁ፤+ የገዛ ቤቴም በውስጧ ይገነባል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “በኢየሩሳሌምም ላይ የመለኪያ ገመድ ይዘረጋል።”’+ +17 “በድጋሚ እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከተሞቼ እንደገና መልካም ነገር ይትረፈረፍባቸዋል፤ ይሖዋም እንደገና ጽዮንን ያጽናናል፤+ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣል።”’”+ +18 ከዚያም ቀና ብዬ ስመለከት አራት ቀንዶች አየሁ።+ +19 በመሆኑም ሲያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልኩት። እሱም “እነዚህ ይሁዳን፣+ እስራኤልንና+ ኢየሩሳሌምን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው”+ ሲል መለሰልኝ። +20 ከዚያም ይሖዋ አራት የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች አሳየኝ። +21 እኔም “እነዚህ የመጡት ምን ሊያደርጉ ነው?” ስል ጠየቅኩ። እሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ፣ ማንም ራሱን ቀና ማድረግ እስኪሳነው ድረስ ይሁዳን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው። እነዚህ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ደግሞ እነሱን ለማሸበር፣ ይሁዳን ይበታትኗት ዘንድ በምድሯ ላይ ቀንዶቻቸውን ያነሱትን የብሔራቱን ቀን +8 የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲ�� ዳግመኛ መጣ፦ +2 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለጽዮን በታላቅ ቅንዓት እቀናለሁ፤+ ደግሞም በታላቅ ቁጣ ለእሷ እቀናለሁ።’” +3 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ ጽዮን እመለሳለሁ፤+ በኢየሩሳሌምም እኖራለሁ፤+ ኢየሩሳሌምም የእውነት* ከተማ ተብላ ትጠራለች፤+ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ተራራም ቅዱስ ተራራ ተብሎ ይጠራል።’”+ +4 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሽማግሌዎችና አሮጊቶች በኢየሩሳሌም አደባባዮች እንደገና ይቀመጣሉ፤ እያንዳንዳቸውም ከዕድሜያቸው ርዝመት የተነሳ* በእጃቸው ምርኩዝ ይይዛሉ።+ +5 የከተማዋም አደባባዮች በዚያ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።’”+ +6 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ይህ ነገር ለዚህ ሕዝብ ቀሪዎች የማይቻል ነገር መስሎ ቢታይ እንኳ ለእኔ የማይቻል ነገር ሊመስል ይገባል?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።” +7 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ሕዝቤን ከምሥራቅና ከምዕራብ አገሮች* አድናለሁ።+ +8 እኔም አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም በኢየሩሳሌም ይኖራሉ፤+ ሕዝቤም ይሆናሉ፤ እኔም በእውነትና* በጽድቅ አምላካቸው እሆናለሁ።’”+ +9 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእነዚህ ቀናት በነቢያት አፍ የተነገሩትን+ እነዚህን ቃላት የምትሰሙ ሁሉ እጃችሁን አበርቱ፤*+ እነዚህ ቃላት፣ ቤተ መቅደሱን ለመገንባት፣ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቤት መሠረት በተጣለበት ጊዜ ነቢያት የተናገሯቸው ናቸው። +10 ከእነዚያ ቀናት በፊት ለሰውም ሆነ ለእንስሳ የሚከፈል ደሞዝ አልነበረምና፤+ ደግሞም ከጠላት የተነሳ በሰላም መግባትና መውጣት አይቻልም ነበር፤ ሰው ሁሉ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ አድርጌ ነበርና።’ +11 “‘አሁን ግን በዚህ ሕዝብ ቀሪዎች ላይ እንደቀድሞው ዘመን አላደርግም’+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +12 ‘የሰላም ዘር ይዘራልና፤ የወይን ተክሉ ፍሬ ያፈራል፤ ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች፤+ ሰማያትም ጠል ያዘንባሉ፤ እኔም የዚህ ሕዝብ ቀሪዎች እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንዲወርሱ አደርጋለሁ።+ +13 የይሁዳና የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በብሔራት መካከል እርግማን ነበራችሁ፤+ አሁን ግን አድናችኋለሁ፤ እናንተም በረከት ትሆናላችሁ።+ አትፍሩ!+ እጃችሁን አበርቱ።’*+ +14 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘“አባቶቻችሁ ስላስቆጡኝ በእናንተ ላይ ጥፋት ላመጣባችሁ ቆርጬ እንደነበርና በዚያም እንዳልተጸጸትኩ ሁሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣+ +15 “አሁንም ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት መልካም ለማድረግ ቆርጫለሁ።+ አትፍሩ!”’+ +16 “‘እናንተ እነዚህን ነገሮች ልታደርጉ ይገባል፦ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤+ በከተማዋም በሮች የምትፈርዱት ፍርድ እውነትን የሚያጠናክርና ሰላምን የሚያሰፍን ይሁን።+ +17 አንዳችሁ በሌላው ላይ ክፉ ነገር ለማድረግ በልባችሁ አታሲሩ፤+ ማንኛውንም የሐሰት መሐላ አትውደዱ፤+ እነዚህን ነገሮች ሁሉ እጠላለሁና’+ ይላል ይሖዋ።” +18 የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ +19 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የአራተኛው ወር፣+ የአምስተኛው ወር፣+ የሰባተኛው ወርና+ የአሥረኛው ወር+ ጾም ለይሁዳ ቤት የፍስሐና የደስታ ይኸውም የሐሴት በዓል ይሆናል።+ በመሆኑም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።’ +20 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሕዝቦችና የብዙ ከተማ ነዋሪዎች በእርግጥ ይመጣሉ፤ +21 በአንዲት ከተማ የሚኖሩ ሰዎችም በሌላ ከተማ ወደሚኖሩ ሰዎች ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳየን ለመለመንና የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግ ተነሱ፤ እንሂድ። እኔም እሄዳለሁ።”+ +22 ደግሞም ብዙ ሕዝቦችና ኃያላን ብሔራት የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግና ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳያቸው ለመለመን ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ።’+ +23 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ+ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ* አጥብቀው በመያዝ “አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን”+ ይላሉ።’”+ +11 “ሊባኖስ ሆይ፣ እሳት አርዘ ሊባኖሶችህን እንድትበላበሮችህን ክፈት። + 2 የጥድ ዛፍ ሆይ፣ አርዘ ሊባኖሱ ስለወደቀ ዋይ ዋይ በል፤ታላላቆቹ ዛፎች ወድመዋል! እናንተ የባሳን የባሉጥ ዛፎች፣ጥቅጥቅ ያለው ጫካ ስለጠፋ ዋይ ዋይ በሉ! + 3 ስሙ! እረኞች ግርማ ሞገሳቸው ስለተገፈፈዋይ ዋይ ይላሉ። አዳምጡ! በዮርዳኖስ አጠገብ ያሉት ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ስለወደሙደቦል አንበሶች ያገሳሉ። +4 “አምላኬ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለእርድ የተዘጋጀውን መንጋ ጠብቅ፤+ +5 የገዟቸው ያርዷቸዋል፤+ ሆኖም ተጠያቂ አይሆኑም። የሚሸጧቸውም+ “ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን፤ ባለጸጋ እሆናለሁና” ይላሉ። እረኞቻቸውም ምንም ዓይነት ርኅራኄ አያሳዩአቸውም።’+ +6 “‘ከእንግዲህ ለምድሪቱ ነዋሪዎች አልራራላቸውም’ ይላል ይሖዋ። ‘በመሆኑም እያንዳንዱ ሰው በባልንጀራው እጅና በንጉሡ እጅ እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ እነሱም ምድሪቱን ያደቋታል፤ እኔም እነሱን ከእጃቸው አልታደግም።’” +7 እናንተ ጉስቁልና የደረሰባችሁ የመንጋው አባላት፣ ለመታረድ የተዘጋጀውን መንጋ መጠበቅ ጀምሬአለሁ፤+ ይህን ያደረግኩትም ለእናንተ ስል ነው። ስለዚህ ሁለት በትሮችን ወስጄ አንደኛውን በትር “ደስታ፣” ሌላኛውን ደግሞ “ኅብረት” ብዬ ጠራሁት፤+ እኔም መንጋውን መጠበቅ ጀመርኩ። +8 ደግሞም በአንድ ወር ውስጥ ሦስት እረኞችን አባረርኩ፤ ይህን ያደረግኩት እነሱን መታገሥ ስላልቻልኩና* እነሱም እኔን ስለተጸየፉኝ* ነው። +9 እንዲህም አልኩ፦ “ከእንግዲህ እረኛችሁ አልሆንም። የምትሞተው ትሙት፤ የምትጠፋውም ትጥፋ። የቀሩት ደግሞ አንዳቸው የሌላውን ሥጋ ይብሉ።” +10 ስለዚህ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን በማፍረስ “ደስታ” የተባለውን በትሬን+ ወስጄ ሰበርኩት። +11 በመሆኑም በዚያን ቀን ቃል ኪዳኑ ፈረሰ፤ ይመለከቱኝ የነበሩት የተጎሳቆሉት የመንጋው አባላትም ይህ የይሖዋ ቃል መሆኑን አወቁ። +12 ከዚያም “መልካም መስሎ ከታያችሁ ደሞዜን ስጡኝ፤ ካልሆነ ግን ተዉት” አልኳቸው። እነሱም ደሞዜን፣ 30 የብር ሰቅል ከፈሉኝ።*+ +13 ከዚያም ይሖዋ “እኔን የገመቱበትን የከበረ ዋጋ+ ይኸውም ብሩን ግምጃ ቤት ውስጥ ጣለው” አለኝ። እኔም 30ውን የብር ሰቅል ወስጄ በይሖዋ ቤት ግምጃ ቤት ውስጥ ጣልኩት።+ +14 ከዚያም በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውን ወንድማማችነት በማፍረስ “ኅብረት” የተባለውን ሁለተኛውን በትሬን+ ሰበርኩት።+ +15 ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “እንግዲህ የሰነፍ እረኛ መሣሪያዎችን ውሰድ።+ +16 በምድሪቱ ላይ እረኛ አስነሳለሁና። እያለቁ ያሉትን በጎች አይንከባከብም፤+ ግልገሎቹን አይፈልግም ወይም የተጎዳውን አይፈውስም+ አሊያም መቆም የሚችሉትን አይቀልብም። ከዚህ ይልቅ የሰባውን በግ ሥጋ ይበላል፤+ የበጎቹንም ሰኮና ቆርጦ ይጥላል።+ +17 መንጋውን ለሚተው+ የማይረባ እረኛዬ ወዮለት!+ ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዓይኑን ይመታዋል። ክንዱ ሙሉ በሙሉ ይሰልላል፤ቀኝ ዓይኑም ሙሉ በሙሉ ይታወራል።”* +2 እኔም ቀና ብዬ ስመለከት በእጁ የመለኪያ ገመድ+ የያዘ ሰው አየሁ። +2 ከዚያም “ወዴት እየሄድክ ነው?” ብዬ ጠየቅኩት። እሱም “ወርዷና ርዝመቷ ምን ያህል እንደሆነ አውቅ ዘንድ ኢየሩሳሌምን ለመለካት እየሄድኩ ነው”+ ሲል መለሰልኝ። +3 እነሆም፣ ከእኔ ጋር ሲነጋገር የነበረው መልአክ ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ። +4 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ወደዚያ ሮጠህ ሂድና ያንን ወጣት እንዲህ በለው፦ ‘“በመካከሏ ካሉት ሰዎችና መንጎች ሁሉ የተነሳ+ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች በነዋሪዎች ትሞላለች።+ +5 እኔም በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤ “ክብሬም በመካከሏ ይሆናል።”’”+ +6 “ኑ! ኑ! ከሰሜን ምድር ሽሹ”+ ይላል ይሖዋ። “ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና”+ ይላል ይሖዋ። +7 “ጽዮን ሆይ፣ ነይ! ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፣ አምልጪ።+ +8 ክብር ከተጎናጸፈ በኋላ፣* እናንተን ወደዘረፏችሁ ብሔራት የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦+ ‘እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን* ይነካል።+ +9 አሁን በእነሱ ላይ እጄን በዛቻ አወዛውዛለሁ፤ የገዛ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል።’+ እናንተም እኔን የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። +10 “የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እልል በይ፤+ እኔ እመጣለሁና፤+ በመካከልሽም እኖራለሁ”+ ይላል ይሖዋ። +11 “በዚያን ቀን ብዙ ብሔራት ከይሖዋ ጋር ይተባበራሉ፤+ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በመካከልሽ እኖራለሁ።” ደግሞም እኔን ወደ አንቺ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቂያለሽ። +12 ይሖዋ ይሁዳን በተቀደሰው ምድር ላይ ድርሻው አድርጎ ይወርሰዋል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣል።+ +13 የሰው ልጆች ሁሉ፣* በይሖዋ ፊት ጸጥ በሉ፤ በቅዱስ መኖሪያው ሆኖ እርምጃ እየወሰደ ነውና። +4 ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ተመልሶ መጥቶ አንድን ሰው ከእንቅልፉ እንደሚቀሰቅስ ቀሰቀሰኝ። +2 ከዚያም “የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም እንዲህ አልኩት፦ “እነሆ፣ ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተሠራና ላዩ ላይ ሳህን ያለበት መቅረዝ+ ይታየኛል። በላዩ ላይ ሰባት መብራቶች፣ አዎ ሰባት መብራቶች አሉበት፤+ አናቱ ላይ ያሉት ሰባት መብራቶችም ሰባት ቱቦዎች አሏቸው። +3 ከጎኑም አንዱ ከሳህኑ በስተ ቀኝ፣ አንዱ ደግሞ በስተ ግራ የቆሙ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”+ +4 ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “ጌታዬ ሆይ፣ የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምንድን ነው?” በማለት ጠየቅኩት። +5 ከእኔ ጋር ሲነጋገር የነበረውም መልአክ “የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አታውቅም?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” ብዬ መለስኩለት። +6 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለኝ፦ “ይሖዋ ለዘሩባቤል የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘“በመንፈሴ እንጂ፣+ በወታደራዊ ኃይል ወይም በጉልበት አይደለም”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +7 ታላቅ ተራራ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል+ ፊት ደልዳላ መሬት* ትሆናለህ።+ “እንዴት ያምራል! እንዴት ያምራል!” እያሉ በሚጮኹበት ጊዜ እሱ የመደምደሚያውን ድንጋይ* ያወጣል።’” +8 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ +9 “የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤት መሠረት ጥለዋል፤+ የገዛ እጆቹም ያጠናቅቁታል።+ እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። +10 ሥራው በትንሹ የተጀመረበትን ቀን* የናቀ ማን ነው?+ እነሱ ሐሴት ያደርጋሉና፤ በዘሩባቤልም እጅ ላይ ቱምቢውን* ያያሉ። እነዚህ ሰባቱ በመላው ምድር የሚዘዋወሩ የይሖዋ ዓይኖች ናቸው።”+ +11 ከዚያም “ከመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉት የእነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ትርጉም ምንድን ነው?” በማለት ጠየቅኩት።+ +12 ለሁለተኛም ጊዜ እንዲህ ስል ጠየቅኩት፦ “በሁለቱ የወርቅ ቱቦዎች አማካኝነት ወርቃማ ፈሳሽ የሚያፈሱት የሁለቱ የወይራ ዛፎች ቅርንጫፎች* ትርጉም ምንድን ነው?” +13 እሱም “የእ��ዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አታውቅም?” አለኝ። እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” ብዬ መለስኩለት። +14 እሱም “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት ሁለቱ ቅቡዓን ናቸው” አለ።+ +6 ዳግመኛም ቀና ብዬ ስመለከት አራት ሠረገሎች ከሁለት ተራሮች መካከል ሲመጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የመዳብ ተራሮች ነበሩ። +2 የመጀመሪያውን ሠረገላ የሚጎትቱት ቀይ ፈረሶች፣ ሁለተኛውን ሠረገላ የሚጎትቱት ደግሞ ጥቁር ፈረሶች ነበሩ።+ +3 ሦስተኛውን ሠረገላ የሚጎትቱት ነጭ ፈረሶች፣ አራተኛውን ሠረገላ የሚጎትቱት ደግሞ ነጠብጣብ ያለባቸውና ዥጉርጉር ፈረሶች ነበሩ።+ +4 ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” ብዬ ጠየቅኩት። +5 መልአኩ እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙ በኋላ፣+ ከዚያ የሚወጡት አራቱ የሰማያት መናፍስት ናቸው።+ +6 በጥቁር ፈረሶች የሚጎተተው ሠረገላ ወደ ሰሜን ምድር ይወጣል፤+ ነጮቹ ፈረሶች ከባሕሩ ባሻገር ወዳለው ምድር ይወጣሉ፤ ነጠብጣብ ያለባቸው ፈረሶች ደግሞ ወደ ደቡብ ምድር ይወጣሉ። +7 ዥጉርጉሮቹ ፈረሶችም ወጥተው በምድር መካከል ለመመላለስ አቆብቁበው* ነበር።” እሱም “ሂዱ፤ በምድር መካከል ተመላለሱ” አለ። እነሱም በምድር መካከል ይመላለሱ ጀመር። +8 ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ ወደ ሰሜን ምድር የሚወጡት፣ የይሖዋ መንፈስ በሰሜን ምድር እንዲያርፍ አድርገዋል።” +9 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ +10 “በግዞት ከተወሰደው ሕዝብ ያመጡትን ነገር ከሄልዳይ፣ ከጦቢያህና ከየዳያህ ውሰድ፤ በዚያም ቀን፣ ከባቢሎን ከመጡት ከእነዚህ ሰዎች ጋር ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ። +11 ብርና ወርቅ ወስደህ አክሊል* ሥራ፤ ከዚያም በየሆጼዴቅ ልጅ በሊቀ ካህናቱ በኢያሱ+ ራስ ላይ አድርገው። +12 እንዲህም በለው፦ “‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ቀንበጥ ተብሎ የሚጠራው ሰው ይህ ነው።+ እሱ በገዛ ቦታው ላይ ያቆጠቁጣል፤ የይሖዋንም ቤተ መቅደስ ይሠራል።+ +13 የይሖዋን ቤተ መቅደስ የሚገነባው እሱ ነው፤ ግርማ የሚጎናጸፈውም እሱ ነው። በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ ደግሞም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ካህን ሆኖ ያገለግላል፤+ በሁለቱም መካከል* ሰላማዊ ስምምነት ይኖራል። +14 አክሊሉም* ለሄሌም፣ ለጦቢያህ፣ ለየዳያህና+ ለሶፎንያስ ልጅ ለሄን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ መታሰቢያ* ሆኖ ያገለግላል። +15 በሩቅ ያሉትም ይመጣሉ፤ በይሖዋ ቤተ መቅደስ የግንባታ ሥራም ይካፈላሉ።” እኔን ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ብትሰሙ ይህ ይሆናል።’” +10 “በበልግ ዝናብ ወቅት ይሖዋ ዝናብ እንዲያዘንብላችሁ ጠይቁ። ነጎድጓድ የቀላቀለ ደመና የሚያመጣው፣ለሰዎች ዝናብ የሚያዘንበው፣+ለእያንዳንዱም በሜዳ ላይ የሚበቅለውን ተክል የሚሰጠው ይሖዋ ነው። + 2 የተራፊም ምስሎች* አታላይ ነገር* ተናግረዋልና፤ሟርተኞችም የሐሰት ራእይ አይተዋል። ከንቱ ስለሆኑ ሕልሞች ይናገራሉ፤በከንቱም ሊያጽናኑ ይሞክራሉ። ከዚህም የተነሳ ሕዝቡ እንደ በግ ይቅበዘበዛል። እረኛ ስለሌለ ይሠቃያል። + 3 በእረኞቹ ላይ ቁጣዬ ይነዳል፤ጨቋኞቹንም መሪዎች* ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ትኩረቱን ወደ መንጋው፣ ወደ ይሁዳ ቤት አዙሯልና፤+ግርማ ሞገስ እንደተላበሰው የጦር ፈረሱ እነሱንም ግርማ ሞገስ አላብሷቸዋል። + 4 ከእሱ ቁልፍ የሆነ ሰው፣*ድጋፍ የሚሰጥ ገዢና*የጦርነት ቀስት ይወጣል፤ተቆጣጣሪዎች* ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው ከእሱ ይወጣሉ። + 5 እነሱም በጦርነት ጊዜ፣በመንገድ ላይ ያለን ጭቃ እንደሚረግጡ ተዋጊዎች ይሆናሉ። ይሖዋ ከእነሱ ጋር ስለሆነ ይዋጋሉ፤+የጠላት ፈረሰኞችም ኀፍረት ይከናነባሉ።+ + 6 የይሁዳን ቤት ከሁሉ የላቀ አደርጋለሁ፤የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ።+ ምሕረት ስለማሳያቸው+ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ እመልሳቸዋለሁ፤እነሱም ፈጽሞ እንዳልጣልኳቸው ሰዎች ይሆናሉ፤+እኔ ይሖዋ አምላካቸው ነኝና፤ ደግሞም እመልስላቸዋለሁ። + 7 የኤፍሬም ሰዎች እንደ ኃያል ተዋጊ ይሆናሉ፤ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደጠጣ ሰው ሐሴት ያደርጋል።+ ልጆቻቸው ይህን አይተው ሐሴት ያደርጋሉ፤ልባቸውም በይሖዋ ደስ ይለዋል።+ + 8 ‘አፏጭቼ አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤እዋጃቸዋለሁና፣+ ብዙ ይሆናሉ፤መባዛታቸውንም ይቀጥላሉ። + 9 በሕዝቦች መካከል እንደ ዘር ብበትናቸውም፣በሩቅ ስፍራዎች ሆነው ያስታውሱኛል፤ከልጆቻቸው ጋር ሆነው ያንሰራራሉ፤ ደግሞም ይመለሳሉ። +10 ከግብፅ ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ከአሦርም አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤+ወደ ጊልያድ+ ምድርና ወደ ሊባኖስ አመጣቸዋለሁ፤በቂ ስፍራም አይገኝላቸውም።+ +11 እሱም ባሕሩን አስጨንቆ ያልፋል፤በባሕሩም ውስጥ ሞገዱን ይመታል፤+የአባይ ጥልቆች በሙሉ ይደርቃሉ። የአሦር ኩራት ይዋረዳል፤የግብፅም በትረ መንግሥት ይወገዳል።+ +12 በይሖዋ ብርቱ አደርጋቸዋለሁ፤+በስሙም ይሄዳሉ’+ ይላል ይሖዋ።” +14 “እነሆ፣ የይሖዋ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ከአንቺ* የተማረከው በመካከልሽ ይከፋፈላል። +2 ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ ብሔራትን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዋም ትያዛለች፤ ቤቶቹ ይዘረፋሉ፤ ሴቶቹም ይደፈራሉ። የከተማዋም እኩሌታ ለግዞት ይዳረጋል፤ ከሕዝቡ መካከል የሚቀሩት ሰዎች ግን ከከተማዋ አይወገዱም። +3 “ይሖዋ ይወጣል፤ በጦርነት ቀን እንደሚዋጋው እነዚያን ብሔራት ይዋጋል።+ +4 በዚያ ቀን እግሮቹ በስተ ምሥራቅ በኢየሩሳሌም ትይዩ በሚገኘው በደብረ ዘይት ተራራ+ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም ከምሥራቅ* አንስቶ እስከ ምዕራብ* ድረስ ለሁለት ይከፈላል፤ እጅግ ትልቅ ሸለቆም ይፈጠራል፤ የተራራው አንዱ ግማሽ ወደ ሰሜን፣ ሌላው ግማሽ ደግሞ ወደ ደቡብ ፈቀቅ ይላል። +5 እናንተ በተራሮቼ መካከል ወዳለው ሸለቆ ትሸሻላችሁ፤ በተራሮቹ መካከል ያለው ሸለቆ እስከ አዜል ድረስ ይደርሳልና። በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተነሳ+ ሸሽታችሁ እንደነበረ ሁሉ አሁንም ትሸሻላችሁ። አምላኬ ይሖዋም ይመጣል፤ ቅዱሳኑም ሁሉ ከእሱ ጋር ይሆናሉ።+ +6 “በዚያ ቀን ደማቅ ብርሃን አይኖርም፤+ ነገሮች ሁሉ ባሉበት ይረጋሉ።* +7 ያም ቀን የይሖዋ ቀን ተብሎ የሚታወቅ ልዩ ቀን ይሆናል።+ ቀንም ሆነ ሌሊት አይሆንም፤ በመሸም ጊዜ ብርሃን ይኖራል። +8 በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ሕያው ውኃዎች+ ይወጣሉ፤+ ግማሾቹ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ባሕር፣*+ ግማሾቹ ደግሞ በስተ ምዕራብ ወዳለው ባሕር* ይፈስሳሉ።+ ይህም በበጋና በክረምት ይሆናል። +9 ይሖዋም በመላው ምድር ላይ ይነግሣል።+ በዚያ ቀን ይሖዋ አንድ፣+ ስሙም አንድ ይሆናል።+ +10 “ከጌባ+ አንስቶ ከኢየሩሳሌም በስተ ደቡብ እስካለችው እስከ ሪሞን+ ድረስ መላው ምድር እንደ አረባ+ ይሆናል፤ ኢየሩሳሌም በቀድሞ ስፍራዋ ላይ ትነሳለች፤ የሰዎችም መኖሪያ ትሆናለች፤+ ደግሞም ከቢንያም በር+ አንስቶ እስከ መጀመሪያው በርና እስከ ማዕዘን በር ድረስ ያለው ስፍራ ሁሉ እንዲሁም ከሃናንኤል +11 በከተማዋም ውስጥ ሰዎች ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም ጥፋት እንዲደርስባት አትረገምም፤+ ደግሞም ኢየሩሳሌም ሰዎች ያለስጋት የሚኖሩባት ቦታ ትሆናለች።+ +12 “ይሖዋ ኢየሩሳሌምን የሚወጉ ሕዝቦችን ሁሉ የሚቀስፍበት መቅሰፍት ይህ ነው፦+ በእግራቸው ቆመው እያለ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዓይኖቻቸውም በጉድጓዶቻቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፤ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። +13 “በዚያ ቀን ከይሖዋ ዘንድ የመጣ ሽብር በመካከላቸው ይሰራጫል፤ እያንዳንዱም ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ እጁንም በባልንጀራው እጅ ላይ ያነሳል።*+ +14 ይሁዳም ራሱ በኢየሩሳሌም በሚደረገው ውጊያ ይካፈላል፤ በዙሪያዋም ያሉ ብሔራት ሁሉ ሀብት ይኸውም ወርቅ፣ ብርና ልብስ በብዛት ይሰበሰባል።+ +15 “በየሰፈሩ ባሉት ፈረሶች፣ በቅሎዎች፣ ግመሎች፣ አህዮችና መንጎች ሁሉ ላይ ተመሳሳይ መቅሰፍት ይወርዳል። +16 “በኢየሩሳሌም ላይ ከተነሱት ብሔራት ሁሉ የሚተርፉት ሰዎች በሙሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ለመስገድና*+ የዳስ* በዓልን ለማክበር+ በየዓመቱ ይወጣሉ።+ +17 ይሁንና ከምድር ብሔራት መካከል ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጡ ቢኖሩ ዝናብ አይዘንብላቸውም።+ +18 የግብፅ ሰዎች ባይወጡና ወደ ከተማዋ ባይገቡ ዝናብ አይዘንብላቸውም። እንዲያውም ይሖዋ የዳስ በዓልን ለማክበር ባልመጡት ብሔራት ላይ በሚያመጣቸው መቅሰፍቶች ይቀሰፋሉ። +19 ግብፅ ለፈጸመችው ኃጢአትና የዳስ በዓልን ለማክበር ያልወጡት ብሔራት ሁሉ ለሠሩት ኃጢአት ይህ ቅጣት ይደርስባቸዋል። +20 “በዚያ ቀን በፈረሶቹ ቃጭል ላይ ‘ቅድስና የይሖዋ ነው!’ ተብሎ ይጻፋል።+ በይሖዋ ቤት ያሉት ድስቶች+ በመሠዊያው ፊት እንዳሉት ሳህኖች+ ይሆናሉ። +21 በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ድስቶች በሙሉ ቅዱስና ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ የተወሰኑ ይሆናሉ፤ መሥዋዕት የሚያቀርቡትም ሁሉ ገብተው የተወሰኑትን ድስቶች ለመቀቀያ ይጠቀሙባቸዋል። በዚያ ቀን በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ቤት ዳግመኛ ከነአናዊ* አይገኝም።”+ +9 የፍርድ መልእክት፦ “የይሖዋ ቃል በሃድራክ ምድር ላይ ነው፤ደማስቆንም ዒላማው* አድርጓል፤+የይሖዋ ዓይን በሰው ዘርናበእስራኤል ነገዶች ሁሉ ላይ ነውና፤+ + 2 አዋሳኟ የሆነችውን ሃማትንም+ ዒላማው አድርጓል፤ደግሞም እጅግ ጥበበኛ ቢሆኑም+ እንኳ ጢሮስንና+ ሲዶናን+ ዒላማው አድርጓል። + 3 ጢሮስ የመከላከያ ግንብ* ገንብታለች። ብርን እንደ አቧራ፣ወርቅንም በመንገድ ላይ እንዳለ አፈር ቆልላለች።+ +4 እነሆ፣ ይሖዋ ንብረቷን ይወስዳል፤ሠራዊቷንም ባሕሩ ውስጥ* ይደመስሳል፤+እሷም በእሳት ትበላለች።+ + 5 አስቀሎን ይህን አይታ ትፈራለች፤ጋዛ በጣም ትጨነቃለች፤ኤቅሮንም እንዲሁ ትሆናለች፤ ምክንያቱም ተስፋ የምታደርግባት ለኀፍረት ትዳረጋለች። ከጋዛ ንጉሥ ይጠፋል፤አስቀሎንም ሰው አልባ ትሆናለች።+ + 6 ዲቃላም በአሽዶድ ይቀመጣል፤እኔም የፍልስጤምን ኩራት አስወግዳለሁ።+ + 7 በደም የተበከሉትን ነገሮች ከአፉ፣አስጸያፊ የሆኑትንም ነገሮች ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፤ከእሱም የሚተርፈው ማንኛውም ሰው የአምላካችን ይሆናል፤እሱም በይሁዳ እንደ አለቃ፣*+ኤቅሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።+ + 8 የሚገባም ሆነ የሚወጣ እንዳይኖር፣ቤቴን ለመጠበቅ በውጭ በኩል ድንኳን እተክላለሁ፤*+ከእንግዲህም ወዲህ በመካከላቸው የሚያልፍ አሠሪ* አይኖርም፤+አሁን በገዛ ዓይኔ አይቼዋለሁና።* + 9 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እጅግ ሐሴት አድርጊ። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ። እነሆ፣ ንጉሥሽ ወደ አንቺ ይመጣል።+ እሱ ጻድቅ ነው፤ መዳንንም ያመጣል፤*ትሑት ነው፤+ ደግሞም በአህያ፣በአህያዪቱ ልጅ፣ በውርንጭላ* ላይ ይቀመጣል።+ +10 የጦር ሠረገላውን ከኤፍሬም፣ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ። የጦርነቱ ቀስት ይወሰዳል። እሱም ለብሔራት ሰላምን ያውጃል፤+ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርእንዲሁም ከወንዙ* እስከ ምድር ዳርቻ ይሆናል።+ +11 አ���ቺ ሴት፣ በእኔና በአንቺ መካከል ካለው የደም ቃል ኪዳን የተነሳእስረኞችሽን ውኃ ከሌለበት ጉድጓድ አውጥቼ እልካቸዋለሁ።+ +12 እናንተ ተስፋ ያላችሁ እስረኞች ወደ ምሽጉ ተመለሱ።+ ዛሬ እንዲህ እልሻለሁ፦‘ድርሻሽን እጥፍ አድርጌ እከፍልሻለሁ።+ +13 ይሁዳን በእጄ እንዳለ ደጋን እወጥረዋለሁና።* ደጋኑን በኤፍሬም እሞላዋለሁ፤*ጽዮን ሆይ፣ ወንዶች ልጆችሽን እቀሰቅሳለሁ፤ግሪክ ሆይ፣ በወንዶች ልጆችሽ ላይ ይነሳሉ፤ጽዮን ሆይ፣ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።’ +14 ይሖዋ በእነሱ ላይ ይገለጣል፤ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወነጨፋል። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ቀንደ መለከት ይነፋል፤+እሱም ከደቡብ አውሎ ነፋሳት ጋር ይሄዳል። +15 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ይከላከልላቸዋል፤እነሱም የሚወነጨፍባቸውን ድንጋይ ውጠው ያስቀራሉ፤ ደግሞም ያመክናሉ።+ ይጠጣሉ፤ የወይን ጠጅ እንደጠጣም ሰው ይንጫጫሉ፤እንዲሁም እንደ ሳህኖቹናእንደ መሠዊያው ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ።+ +16 በዚያ ቀን አምላካቸው ይሖዋ፣እንደ ሕዝቡ መንጋ ያድናቸዋል፤+በአክሊል* ላይ እንዳሉ ፈርጦች በምድሩ ላይ ያብረቀርቃሉና።+ +17 ጥሩነቱ ምንኛ ታላቅ ነው!+ ውበቱስ እንዴት ያማረ ነው! እህል ወጣት ወንዶችን፣አዲስ የወይን ጠጅም ደናግሉን ያለመልማል።”+ +13 “በዚያ ቀን፣ ኃጢአታቸውንና ርኩሰታቸውን ለማንጻት ለዳዊት ቤትና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የውኃ ጉድጓድ ይቆፈራል።+ +2 “በዚያ ቀን” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “የጣዖቶቹን ስም ከምድሪቱ ላይ እደመስሳለሁ፤+ እነሱም ዳግመኛ አይታወሱም፤ ደግሞም ነቢያቱንና የርኩሰት መንፈሱን ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ።+ +3 አንድ ሰው ዳግመኛ ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባትና እናቱ ‘በይሖዋ ስም ሐሰት ስለተናገርክ በሕይወት አትኖርም’ ይሉታል። ደግሞም የወለዱት አባትና እናቱ ትንቢት በመናገሩ ይወጉታል።+ +4 “በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ትንቢት በሚናገርበት ጊዜ ሁሉ በገዛ ራእዩ ያፍራል፤ ሰዎችንም ለማታለል የነቢያት ዓይነት ፀጉራም ልብስ+ አይለብስም። +5 ደግሞም እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ነቢይ አይደለሁም። ይልቁንም አራሽ ነኝ፤ ምክንያቱም አንድ ሰው ልጅ ሳለሁ ባሪያ አድርጎ ገዝቶኛል።’ +6 አንድ ሰውም ‘በትከሻዎችህ መካከል* ያሉት ቁስሎች ምንድን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቀው ‘በወዳጆቼ ቤት ሳለሁ የቆሰልኩት ነው’ ይላል።” + 7 “ሰይፍ ሆይ፣ በእረኛዬ+ ይኸውምበወዳጄ ላይ ንቃ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “እረኛውን ምታ፤+ መንጋውም ይበተን፤*+እኔም እጄን ታናናሽ በሆኑት ላይ አዞራለሁ።” + 8 “በምድሪቱም ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣“በእሷ ላይ ካለው ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤*አንድ ሦስተኛው ግን በውስጧ ይቀራል። + 9 ደግሞም አንድ ሦስተኛው በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ብር እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ።+ እነሱ ስሜን ይጠራሉ፤እኔም እመልስላቸዋለሁ። ‘እነሱ ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤+ እነሱ ደግሞ ‘ይሖዋ አምላካችን ነው’ ይላሉ።” +5 ዳግመኛ ቀና ብዬ ስመለከት የሚበር ጥቅልል አየሁ። +2 እሱም “የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም “ርዝመቱ 20 ክንድ፣* ወርዱ ደግሞ 10 ክንድ የሆነ የሚበር ጥቅልል አያለሁ” ስል መለስኩለት። +3 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በመላው ምድር ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፤ ምክንያቱም የሚሰርቁ ሁሉ+ በአንደኛው በኩል በተጻፈው መሠረት አልተቀጡም፤ ደግሞም በሐሰት የሚምሉ ሁሉ+ በሌላኛው በኩል በተጻፈው መሠረት አልተቀጡም። +4 ‘እኔ ልኬዋለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘ወደ ሌባውም ቤት ይገባል፤ በስሜ በሐሰት ወደሚምለውም ሰው ቤት ይገባል፤ በዚያም ቤት ���ስጥ ይቀመጣል፤ እንጨቱንና ድንጋዩን ጨምሮ ቤቱን ይበላዋል።’” +5 ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረው መልአክ ወደ እኔ ቀርቦ “እባክህ ቀና ብለህ የምትወጣውን ነገር ተመልከት” አለኝ። +6 እኔም “ምንድን ነች?” አልኩ። እሱም መልሶ “ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ* ናት” አለ። አክሎም “በምድሪቱ ሁሉ የሰዎቹ መልክ ይህ ነው” አለ። +7 እኔም ከእርሳስ የተሠራው ክቡ መክደኛ ሲነሳ አየሁ፤ በመስፈሪያዋም ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። +8 እሱም “ይህች ሴት ክፋትን ታመለክታለች” አለኝ። ከዚያም የኢፍ መስፈሪያዋ ውስጥ መልሶ ጣላት፤ ቀጥሎም ከእርሳስ የተሠራውን ከባዱን መክደኛ መስፈሪያዋ አፍ ላይ ገጠመው። +9 ከዚያም ቀና ብዬ ስመለከት ሁለት ሴቶች ወደ ፊት ሲመጡ አየሁ፤ በነፋስም መካከል ወደ ላይ ተወነጨፉ። ክንፎቻቸው የራዛ* ዓይነት ክንፎች ነበሩ። እነሱም መስፈሪያዋን በምድርና በሰማይ መካከል አነሷት። +10 እኔም ያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “የኢፍ መስፈሪያዋን ወዴት እየወሰዷት ነው?” ስል ጠየቅኩት። +11 እሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ቤት ሊሠሩላት ወደ ሰናኦር*+ ምድር እየወሰዷት ነው፤ ቤቱም በተዘጋጀ ጊዜ በዚያ በተገቢው ቦታዋ ላይ ያስቀምጧታል።” +3 “እነሆ፣ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ እሱም በፊቴ መንገድ ይጠርጋል።*+ እናንተ የምትፈልጉት እውነተኛው ጌታ* በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤+ ደስ የምትሰኙበት የቃል ኪዳኑ መልእክተኛም ይመጣል። እነሆ፣ እሱ በእርግጥ ይመጣል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +2 “ይሁንና እሱ የሚመጣበትን ቀን ሊቋቋም የሚችል ማን ነው? እሱ በሚገለጥበት ጊዜስ ማን ሊቆም ይችላል? እሱ እንደ አንጥረኛ እሳት፣ እንደ ልብስ አጣቢም እንዶድ* ይሆናልና።+ +3 ደግሞም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤+ የሌዊንም ልጆች ያነጻል፤* እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያጠራቸዋል፤ ይሖዋም በጽድቅ መባ የሚያቀርብ ሕዝብ ይኖረዋል። +4 ይሁዳና ኢየሩሳሌም ስጦታ አድርገው የሚያቀርቡት መባ በቀድሞው ጊዜና በጥንት ዘመን እንደነበረው ይሖዋን ደስ ያሰኘዋል።*+ +5 “ለመፍረድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በመተተኞቹ፣+ በአመንዝሮቹ፣ በሐሰት በሚምሉት ሰዎች+ እንዲሁም ቅጥር ሠራተኛውን፣+ መበለቲቱንና አባት የሌለውን ልጅ* በሚያጭበረብሩትና+ ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ በማይሆኑት* ላይ ወዲያውኑ እመሠክርባቸዋለሁ።+ እነዚህ ሰዎች እኔን አልፈሩም” ይላ +6 “እኔ ይሖዋ ነኝና፤ አልለወጥም።*+ እናንተም የያዕቆብ ልጆች ናችሁ፤ ገና አልጠፋችሁም። +7 ከአባቶቻችሁ ዘመን አንስቶ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፤ ደግሞም ሥርዓቴን አልጠበቃችሁም።+ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። እናንተ ግን “የምንመለሰው እንዴት ነው?” ትላላችሁ። +8 “በውኑ ተራ ሰው አምላክን ይሰርቃል? እናንተ ግን እኔን ትሰርቁኛላችሁ።” እናንተም “የሰረቅንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ። “በምትሰጡት አሥራትና* መዋጮ ነው። +9 እናንተ በእርግጥ የተረገማችሁ ናችሁ፤* ትሰርቁኛላችሁና፤ አዎ፣ መላው ብሔር እንዲህ ያደርጋል። +10 በቤቴ ውስጥ እህል እንዲኖር አሥራቱን* ሁሉ ወደ ጎተራው አስገቡ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “የሰማያትን መስኮቶች ከፍቼ+ ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የተትረፈረፈ በረከት ባላፈስላችሁ፣*+ እስቲ በዚህ ፈትኑኝ።” +11 “ለእናንተም ስል፣ በላተኛውን* እገሥጻለሁ፤ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፤ በእርሻችሁ ላይ ያለው የወይን ተክልም ፍሬ አልባ አይሆንም”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +12 “እናንተ የደስታ ምድር ስለምትሆኑ ብሔራት ሁሉ ደስተኞች ብለው ይ���ሯችኋል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +13 “በእኔ ላይ ኃይለ ቃል ተናግራችኋል” ይላል ይሖዋ። እናንተም “በአንተ ላይ የተናገርነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ።+ +14 “እንዲህ ትላላችሁ፦ ‘አምላክን ማገልገል ዋጋ የለውም።+ ለእሱ ያለብንን ግዴታ በመጠበቃችንና በኃጢአታችን የተነሳ ማዘናችንን በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ፊት በማሳየታችን ምን ተጠቀምን? +15 አሁን እብሪተኛ የሆኑ ሰዎችን ደስተኞች እንደሆኑ አድርገን እንመለከታቸዋለን። ደግሞም ክፉ አድራጊዎች ስኬታማ ሆነዋል።+ እነሱ በድፍረት አምላክን ይፈታተናሉ፤ ከቅጣትም ያመልጣሉ።’” +16 በዚያ ጊዜ ይሖዋን የሚፈሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው፣ ከባልንጀሮቻቸው ጋር ተነጋገሩ፤ ይሖዋም በትኩረት አዳመጠ፤ ደግሞም ሰማ። ይሖዋንም ለሚፈሩና በስሙ ላይ ለሚያሰላስሉ*+ በፊቱ የመታሰቢያ መጽሐፍ ተጻፈ።+ +17 “የእኔ ልዩ ንብረት*+ በማደርጋቸውም ቀን እነሱ የእኔ ይሆናሉ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “አባት ለሚታዘዝለት ልጁ እንደሚራራ እኔም እራራላቸዋለሁ።+ +18 እናንተም በጻድቁና በክፉው እንዲሁም አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው ሰው መካከል ያለውን ልዩነት ዳግመኛ ታያላችሁ።”+ +1 የፍርድ መልእክት፦ በሚልክያስ* በኩል ለእስራኤል የተነገረው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ +2 “እኔ ፍቅር አሳይቻችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ። እናንተ ግን “ፍቅር ያሳየኸን እንዴት ነው?” አላችሁ። “ኤሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረም?”+ ይላል ይሖዋ። “እኔ ግን ያዕቆብን ወደድኩ፤ +3 ኤሳውንም ጠላሁ፤+ ተራሮቹን ባድማ አደረግኩ፤+ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮዎች ሰጠሁ።”+ +4 “ኤዶም* ‘ተደምስሰናል፤ ሆኖም ተመልሰን የፈራረሱትን ዳግመኛ እንገነባለን’ ቢልም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሱ ይገነባሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ቦታዎቹ “የክፋት ምድር፣” እነሱ ደግሞ “ይሖዋ ለዘላለም ያወገዘው ሕዝብ” ተብለው ይጠራሉ።+ +5 የገዛ ዓይናችሁ ይህን ያያል፤ እናንተም “ይሖዋ በእስራኤል ምድር ከፍ ከፍ ይበል” ትላላችሁ።’” +6 “እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፣+ ‘ልጅ አባቱን፣ አገልጋይም ጌታውን ያከብራል።+ እኔ አባት ከሆንኩ+ ለእኔ የሚገባው ክብር የት አለ?+ ጌታስ* ከሆንኩ መፈራቴ* የት አለ?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “‘እናንተ ግን “ስምህን ያቃለልነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ።’ +7 “‘በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ* በማቅረብ ነው።’ “‘ደግሞም “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ።’ “‘“የይሖዋ ገበታ+ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው። +8 ዕውሩን እንስሳ መሥዋዕት አድርጋችሁ ስታቀርቡ “ምንም ችግር የለውም” ትላላችሁ። ደግሞም አንካሳ ወይም የታመመ እንስሳ ስታቀርቡ “ምንም ችግር የለውም” ትላላችሁ።’”+ “እነዚህን እንስሳት እስቲ ለገዢህ ለማቅረብ ሞክር። በአንተ ደስ ይለዋል? ወይስ በሞገስ ዓይን ይቀበልሃል?” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ +9 “አሁንም እባካችሁ፣ ሞገስ እንዲያሳየን አምላክን ተማጸኑ። እንዲህ ያሉ መባዎች በገዛ እጃችሁ ስታቀርቡ ከእናንተ መካከል የእሱን ሞገስ የሚያገኝ ይኖራል?” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +10 “ከእናንተ መካከል በሮቹን ለመዝጋት ፈቃደኛ የሚሆን ማን ነው?*+ በመሠዊያዬ ላይ እሳት ለማንደድ እንኳ ክፍያ ትጠይቃላችሁና።+ በእናንተ ፈጽሞ ደስ አልሰኝም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ስጦታ አድርጋችሁ በምታቀርቡት በየትኛውም መባ አልደሰትም።”+ +11 “ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ* ድረስ ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል።+ በየቦታው ለስሜ የሚጨስ መሥዋዕትና መባ ተቀባይነት ያለው ስጦታ ሆኖ ይቀርባል፤ ምክንያቱም ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +12 “እናንተ ግን ‘የይሖዋ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬው ይኸውም ምግቡ የተናቀ ነው’ በማለት ታረክሱታላችሁ።*+ +13 በተጨማሪም እናንተ ‘እንዴት አድካሚ ነው!’ ትላላችሁ፤ ደግሞም ትጸየፉታላችሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “የተሰረቀን፣ አንካሳውንና የታመመውን እንስሳ ታመጣላችሁ። አዎ፣ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ስጦታ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ! ታዲያ ይህን ከእጃችሁ ልቀበል ይገባል?”+ ይላል ይሖዋ። +14 “በመንጎቹ መካከል ተባዕት እንስሳ እያለው፣ ስእለት ተስሎ እንከን ያለበትን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ የሚያታልል የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ስሜም በብሔራት መካከል የተፈራ ይሆናል።”+ +2 “አሁንም ካህናት ሆይ፣ ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።+ +2 ለመስማት አሻፈረኝ ብትሉና ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ በልባችሁ ባታኖሩት” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “በእናንተ ላይ እርግማን እሰዳለሁ፤+ በረከታችሁንም ወደ እርግማን እለውጣለሁ።+ አዎ፣ በልባችሁ ስላላኖራችሁት እያንዳንዱን በረከት ወደ እርግማን ለውጫለሁ።” +3 “እነሆ፣ በእናንተ የተነሳ የዘራችሁትን ዘር አጠፋለሁ፤*+ ፈርሱንም ይኸውም በበዓሎቻችሁ ላይ የምትሠዉአቸውን እንስሳት ፈርስ ፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ እናንተንም ወደዚያ* ወስደው ይጥሏችኋል። +4 ይህን ትእዛዝ የሰጠኋችሁ ከሌዊ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ጸንቶ እንዲኖር መሆኑን ታውቃላችሁ”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +5 “ከእሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነው፤ እነዚህን በረከቶች በማግኘቱ እኔን ለመፍራት* ተነሳሳ። አዎ፣ ለስሜ ታላቅ አክብሮት አሳየ። +6 የእውነት ሕግ* በአፉ ውስጥ ነበር፤+ በከንፈሮቹም ክፋት አልተገኘም። ከእኔ ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፤+ ብዙዎቹንም ከስህተት ጎዳና መለሰ። +7 ካህኑ ምንጊዜም በከንፈሮቹ ላይ እውቀት ሊኖረው ይገባል፤ ሰዎችም ሕጉን* ከአፉ ሊሹ ይገባል፤+ ምክንያቱም እሱ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ መልእክተኛ ነው። +8 “እናንተ ግን ከመንገዱ ፈቀቅ ብላችኋል። ብዙዎች ከሕጉ ጋር በተያያዘ* እንዲሰናከሉ አድርጋችኋል።+ የሌዊን ቃል ኪዳን አርክሳችኋል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +9 “ስለዚህ በሰዎች ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ እንድትሆኑ አደርጋለሁ፤ ምክንያቱም መንገዶቼን አልጠበቃችሁም፤ ከዚህ ይልቅ ሕጉን ተግባራዊ ስታደርጉ አድልዎ ፈጽማችኋል።”+ +10 “የሁላችንም አባት አንድ አይደለም?+ የፈጠረንስ አምላክ አንድ አይደለም? ታዲያ የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን በማርከስ አንዳችን በሌላው ላይ ክህደት የምንፈጽመው ለምንድን ነው?+ +11 ይሁዳ ክህደት ፈጽሟል፤ በእስራኤልና በኢየሩሳሌምም አስጸያፊ ነገር ተፈጽሟል፤ ይሁዳ፣ ይሖዋ የሚወደውን ቅድስናውን* አርክሷልና፤+ ደግሞም የባዕድ አምላክ ሴት ልጅን አግብቷል።+ +12 ይህን የሚያደርግ ማንኛውም ሰው ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ስጦታ አድርጎ መባ ቢያቀርብም እንኳ ይሖዋ ከያዕቆብ ድንኳኖች ያስወግደዋል።”+ +13 “ሌላም የምታደርጉት ነገር አለ፤ ይህም የይሖዋ መሠዊያ በእንባ፣ በለቅሶና በሐዘን እንዲሞላ ምክንያት ሆኗል፤ በመሆኑም ስጦታ አድርጋችሁ የምታቀርቧቸውን መባዎች ከእንግዲህ አይቀበልም፤ የምታቀርቡትንም ነገር ሁሉ በሞገስ ዓይን አይመለከትም።+ +14 እናንተም ‘ይህ የሆነው ለምንድን ነው?’ ብላችኋል። ይህ የሆነው ይሖዋ በአንተ ላይ ስለመሠከረብህ ነው፤ ምክንያቱም እሷ አጋርህና የቃል ኪዳን ሚስትህ* ሆና ሳለ በወጣትነት ሚስትህ ላይ ክህደት ፈጽመሃል።+ +15 ሆኖም እንዲህ ያላደረገ አለ፤ እሱ በተወሰነ መጠን የአምላክ መንፈስ ነበረው። ፍላጎቱስ ምን ነበር? የአምላክ ዘር ነበር። በመሆኑም መንፈሳችሁን ጠብቁ፤ በወጣትነት ሚስታችሁም ላይ ክህደት አትፈጽሙ። +16 እኔ ፍቺን እጠላለሁና”*+ ይላል የእስራኤል አምላክ ይሖዋ፤ “ልብሱን በግፍ ድርጊት የሚሸፍነውንም* እጠላለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “መንፈሳችሁን ጠብቁ፤ ክህደትም አትፈጽሙ።+ +17 “ይሖዋን በቃላችሁ አታክታችሁታል።+ እናንተ ግን ‘ያታከትነው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ። ‘ክፉ ድርጊት የሚፈጽም ሁሉ በይሖዋ ዓይን ጥሩ ነው፤ እሱ እንዲህ ባለ ሰው ደስ ይሰኛል’+ ወይም ‘የፍትሕ አምላክ የት አለ?’ በማለታችሁ ነው።” +4 “እነሆ፣ ያ ቀን እንደ ምድጃ እየነደደ ይመጣል፤+ በዚያ ጊዜ እብሪተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ እንደ ገለባ ይሆናሉ። የሚመጣው ቀን በእርግጥ ይበላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አይተውላቸውም። +2 ስሜን ለምታከብሩት* ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ በጨረሮቿ* ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም እንደሰቡ ጥጆች ትቦርቃላችሁ።” +3 “እኔም እርምጃ በምወስድበት ቀን ክፉዎችን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ሥር እንዳለ አቧራ ይሆናሉና” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። +4 “የአገልጋዬን የሙሴን ሕግ ይኸውም መላው እስራኤል እንዲያከብረው በኮሬብ ያዘዝኩትን ሥርዓትና ድንጋጌ አስታውሱ።+ +5 “እነሆ፣ ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን ከመምጣቱ በፊት+ ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ።+ +6 እሱም መጥቼ ምድርን እንዳልመታና ፈጽሜ እንዳላጠፋ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ፣+ የልጆችንም ልብ እንደ አባቶች ልብ ያደርጋል።”* +17 ኢየሱስ ከስድስት ቀን በኋላ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን ብቻ ይዞ ወደ አንድ ረጅም ተራራ ወጣ።+ +2 በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን አንጸባረቀ።*+ +3 ከዚያም ሙሴና ኤልያስ ከእሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። +4 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን “ጌታ ሆይ፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። ከፈለግክ በዚህ ስፍራ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴና አንድ ለኤልያስ ሦስት ድንኳኖች እተክላለሁ” አለው። +5 ገና እየተናገረ ሳለም ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም “በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ ተሰማ። +6 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲሰሙ በፍርሃት ተውጠው በግንባራቸው ተደፉ። +7 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ወደ እነሱ ቀርቦ ዳሰሳቸውና “ተነሱ። አትፍሩ” አላቸው። +8 ቀና ብለው ሲመለከቱ ከኢየሱስ በቀር ሌላ ማንንም አላዩም። +9 ከተራራው እየወረዱ ሳሉ ኢየሱስ “የሰው ልጅ ከሞት እስኪነሳ ድረስ ራእዩን ለማንም እንዳትናገሩ” ሲል አዘዛቸው።+ +10 ይሁን እንጂ ደቀ መዛሙርቱ “ታዲያ ጸሐፍት ኤልያስ በመጀመሪያ መምጣት አለበት የሚሉት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+ +11 እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “በእርግጥ ኤልያስ መጥቶ ሁሉንም ነገር ወደ ቀድሞ ሁኔታው ይመልሳል።+ +12 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ኤልያስ መምጣቱን መጥቷል፤ እነሱ ግን የፈለጉትን ነገር አደረጉበት+ እንጂ አላወቁትም። የሰው ልጅም እንደዚሁ በእነሱ እጅ ይሠቃያል።”+ +13 በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ የነገራቸው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንደሆነ ገባቸው። +14 ወደ ሕዝቡ በመጡ ጊዜ+ አንድ ሰው ወደ እሱ ቀረበና ተንበርክኮ እንዲህ አለው፦ +15 “ጌታ ሆይ፣ ለልጄ ምሕረት አድርግለት፤ የሚጥል በሽታ ስላለበት በጠና ታሟል። አንዴ እሳት ውስጥ አንዴ ደግሞ ውኃ ውስጥ ይወድቃል።+ +16 ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት፤ እነሱ ግን ሊፈውሱት አልቻሉም።” +17 ኢየሱስም መልሶ “እምነት የለሽና ጠማማ ትውልድ ሆይ፣+ ከእናንተ ጋር እስከ መቼ መቆየት ሊኖርብኝ ነው? እስከ መቼስ እናንተን መታገሥ ሊኖርብኝ ነው? ልጁን ወደ እኔ አምጡት” አለ። +18 ከዚያም ኢየሱስ ጋኔኑን ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከልጁ ወጣ፤ ልጁም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ።+ +19 ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ ኢየሱስ መጥተው “እኛ ልናስወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?” አሉት። +20 እሱም “እምነታችሁ ስላነሰ ነው። እውነት እላችኋለሁ፣ የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክል እምነት ካላችሁ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነስተህ ወደዚያ ሂድ’ ብትሉት ይሄዳል፤ የሚሳናችሁም ነገር አይኖርም”+ አላቸው። +21 *—— +22 በገሊላ ተሰብስበው ሳሉ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የሰውን ልጅ ለሰዎች አሳልፈው ይሰጡታል፤+ +23 እነሱም ይገድሉታል፤ እሱም በሦስተኛው ቀን ይነሳል።”+ ደቀ መዛሙርቱም በጣም አዘኑ። +24 ቅፍርናሆም ከደረሱ በኋላ የቤተ መቅደሱን ግብር* የሚሰበስቡት ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀርበው “መምህራችሁ የቤተ መቅደሱን ግብር አይከፍልም?”+ አሉት። +25 እሱም “ይከፍላል” አላቸው። ይሁን እንጂ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ኢየሱስ በቅድሚያ እንዲህ አለው፦ “ስምዖን ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥ ወይም ግብር የሚቀበሉት ከማን ነው? ከልጆቻቸው ወይስ ከሌሎች?” +26 እሱም “ከሌሎች” ብሎ ሲመልስለት ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “እንግዲያው ልጆቹ ግብር ከመክፈል ነፃ ናቸው። +27 ሆኖም እንቅፋት እንዳንሆንባቸው+ ወደ ባሕሩ ሄደህ መንጠቆ ጣል፤ ከዚያም መጀመሪያ የምትይዘውን ዓሣ አፉን ስትከፍት አንድ የብር ሳንቲም * ታገኛለህ። ሳንቲሙን ወስደህ ለእኔና ለአንተ ክፈል።” +18 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው ማን ነው?” አሉት።+ +2 ኢየሱስም አንድ ትንሽ ልጅ ጠርቶ በመካከላቸው በማቆም +3 እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ካልተመለሳችሁና* እንደ ልጆች ካልሆናችሁ+ በምንም ዓይነት ወደ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም።+ +4 ስለዚህ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው እንደዚህ ትንሽ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ነው፤+ +5 እንዲሁም እንደዚህ ያለውን ትንሽ ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል። +6 ሆኖም በእኔ ከሚያምኑት ከእነዚህ ከትናንሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ የወፍጮ ድንጋይ* በአንገቱ ታስሮ ጥልቅ ባሕር ውስጥ ቢሰጥም ይሻለዋል።+ +7 “ይህ ዓለም ሰዎችን የሚያሰናክል ነገር ስለሚያስቀምጥ ወዮለት! እርግጥ ማሰናከያ መምጣቱ የማይቀር ነው፤ ነገር ግን በእሱ ጠንቅ ሌሎች እንዲሰናከሉ ለሚያደርግ ሰው ወዮለት! +8 እንግዲያው እጅህ ወይም እግርህ ቢያሰናክልህ ቆርጠህ ጣለው።+ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለማዊ እሳት+ ከምትወረወር ጉንድሽ ወይም አንካሳ ሆነህ ሕይወት ብታገኝ ይሻልሃል። +9 እንዲሁም ዓይንህ ቢያሰናክልህ አውጥተህ ጣለው። ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ እሳታማ ገሃነም* ከምትወረወር አንድ ዓይን ኖሮህ ሕይወት ብታገኝ ይሻልሃል።+ +10 በሰማይ ያሉት መልአኮቻቸው በሰማይ ባለው አባቴ ፊት ዘወትር ስለሚቀርቡ ከእነዚህ ከትናንሾቹ መካከል አንዱንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ።+ +11 *—— +12 “ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው 100 በጎች ቢኖሩትና ከእነሱ አንዷ ብትጠፋ+ 99ኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋችውን ለመፈለግ አይሄድም?+ +13 እውነት እላችኋለሁ፣ የጠፋችውን በግ ካገኛት፣ ካልጠፉት ከ99ኙ ይልቅ በእሷ ይበልጥ ይደሰታል። +14 በተመሳሳይም በሰማይ ያለው አባቴ* ከእነዚህ ከትናንሾቹ መካከል አንዱም እንኳ እንዲጠፋ አይፈልግም።+ +15 “በተጨማሪም ወንድምህ ቢበድልህ አንተና እሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ጥፋቱን በግልጽ ንገረው።*+ ከሰማህ ወንድምህን ታተርፋለህ።+ +16 የማይሰማ��� ከሆነ ግን ማንኛውም ጉዳይ ሁለት ወይም ሦስት ምሥክሮች በሚሰጡት የምሥክርነት ቃል* ስለሚጸና አንድ ወይም ሁለት ሰው ይዘህ ሂድ።+ +17 እነሱንም ካልሰማ ለጉባኤ ተናገር። ጉባኤውንም እንኳ የማይሰማ ከሆነ እንደ አሕዛብና+ እንደ ቀረጥ ሰብሳቢ+ አድርገህ ቁጠረው። +18 “እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር የምታስሩት ነገር ሁሉ ቀድሞውኑ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ እንዲሁም በምድር የምትፈቱት ነገር ሁሉ ቀድሞውኑ በሰማያት የተፈታ ይሆናል። +19 ደግሞም እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር ላይ ከእናንተ መካከል ሁለታችሁ አንድ አስፈላጊ የሆነ ነገር ለመለመን ብትስማሙ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላችኋል።+ +20 ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት+ በዚያ በመካከላቸው እገኛለሁና።” +21 ከዚያም ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ “ጌታ ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ይቅር ልበለው?” አለው። +22 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እስከ 77 ጊዜ* እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም።+ +23 “ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ከባሪያዎቹ ጋር ሒሳብ መተሳሰብ ከፈለገ አንድ ንጉሥ ጋር ይመሳሰላል። +"24 ሒሳቡን መተሳሰብ በጀመረ ጊዜም 10,000 ታላንት* ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው አቀረቡለት።" +25 ሆኖም ሰውየው ዕዳውን የሚከፍልበት ምንም መንገድ ስላልነበረው ጌታው እሱም ሆነ ሚስቱ እንዲሁም ልጆቹና ያለው ንብረት ሁሉ ተሸጠው ዕዳው እንዲከፈል አዘዘ።+ +26 ባሪያውም ወድቆ በመስገድ* ‘ጌታዬ ሆይ፣ እባክህ ታገሠኝ፤ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ’ ሲል ለመነው። +27 ጌታውም እጅግ አዘነለትና ለቀቀው፤ ዕዳውንም ሰረዘለት።+ +28 ሆኖም ይህ ባሪያ ወጥቶ ከሄደ በኋላ 100 ዲናር* ያበደረውን እንደ እሱ ያለ ባሪያ አግኝቶ ያዘውና አንገቱን አንቆ ‘ያለብህን ዕዳ ክፈለኝ’ አለው። +29 ባልንጀራው የሆነው ያ ባሪያም እግሩ ላይ ወድቆ ‘ወንድሜ ሆይ፣ እባክህ ታገሠኝ፤ እከፍልሃለሁ’ ብሎ ይለምነው ጀመር። +30 እሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ሄዶ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍል ድረስ ወህኒ ቤት አሳሰረው። +31 ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሪያዎች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ አዘኑ፤ ሄደውም የሆነውን ነገር ሁሉ ለጌታቸው ነገሩት። +32 በዚህ ጊዜ ጌታው አስጠራውና እንዲህ አለው፦ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፣ ስለተማጸንከኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውኩልህ። +33 ታዲያ እኔ ምሕረት እንዳደረግኩልህ ሁሉ አንተስ ባልንጀራህ ለሆነው ባሪያ ምሕረት ልታደርግለት አይገባም ነበር?’+ +34 ጌታውም በዚህ እጅግ ተቆጥቶ ያለበትን ዕዳ ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ለወህኒ ቤት ጠባቂዎቹ አሳልፎ ሰጠው። +35 እናንተም እያንዳንዳችሁ ወንድማችሁን ከልባችሁ ይቅር ካላላችሁ+ በሰማይ ያለው አባቴ እንደዚሁ ያደርግባችኋል።”+ +23 ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡንና ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ +2 “ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በገዛ ሥልጣናቸው የሙሴን ቦታ ወስደዋል። +3 ስለዚህ የሚነግሯችሁን ነገር ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ሆኖም የሚናገሩትን በተግባር ስለማያውሉ እነሱ የሚያደርጉትን አታድርጉ።+ +4 ከባድ ሸክም አስረው በሰዎች ትከሻ ላይ ይጭናሉ፤+ እነሱ ግን በጣታቸው እንኳ ለመንካት* ፈቃደኞች አይደሉም።+ +5 ማንኛውንም ነገር የሚያደርጉት በሰዎች ለመታየት ብለው ነው፤+ ለምሳሌ ትልቅ ክታብ* ያስራሉ፤+ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ።+ +6 በራት ግብዣ ላይ የክብር ቦታ ማግኘት፣ በምኩራብ ደግሞ ከፊት መቀመጥ* ይወዳሉ፤+ +7 በገበያ ቦታም ሰዎች እጅ እንዲነሷቸው ይፈልጋሉ እንዲሁም ረቢ* ተብለው መጠራት ይሻሉ። +8 እናንተ ግን መምህራችሁ+ አንድ ስለሆነ ረቢ ተብላችሁ አትጠሩ፤ እናንተ ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ። +9 በተጨማሪም አባ��ችሁ+ አንድ እሱም በሰማይ ያለው ብቻ ስለሆነ በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ። +10 እንዲሁም መሪያችሁ አንድ እሱም ክርስቶስ ስለሆነ መሪ ተብላችሁ አትጠሩ። +11 ይልቁንም ከመካከላችሁ ታላቅ የሆነው የእናንተ አገልጋይ መሆን ይገባዋል።+ +12 ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይደረጋል፤+ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ደግሞ ከፍ ይደረጋል።+ +13 “እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ ሰዎች ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዳይገቡ በሩን ስለምትዘጉ ወዮላችሁ! እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ ለመግባት የሚመጡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።+ +14 *—— +15 “እናንተ ግብዞች+ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ አንድን ሰው ወደ ይሁዲነት ለመለወጥ በባሕርና በየብስ ስለምትጓዙና ሰውየው በተለወጠ ጊዜ ከእናንተ ይባስ ሁለት እጥፍ ለገሃነም* የተገባ እንዲሆን ስለምታደርጉት ወዮላችሁ! +16 “‘አንድ ሰው በቤተ መቅደሱ ቢምል ምንም አይደለም፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ባለው ወርቅ ቢምል ግን መሐላውን የመጠበቅ ግዴታ አለበት’+ የምትሉ እናንተ ዕውር መሪዎች+ ወዮላችሁ! +17 እናንተ ሞኞችና ዕውሮች! ለመሆኑ ከወርቁና ወርቁ እንዲቀደስ ካደረገው ቤተ መቅደስ የትኛው ይበልጣል? +18 ደግሞም ‘አንድ ሰው በመሠዊያው ቢምል ምንም አይደለም፤ በመሠዊያው ላይ ባለው መባ ቢምል ግን መሐላውን የመጠበቅ ግዴታ አለበት’ ትላላችሁ። +19 እናንተ ዕውሮች! ለመሆኑ ከመባውና መባው እንዲቀደስ ካደረገው መሠዊያ የትኛው ይበልጣል? +20 ስለዚህ በመሠዊያው የሚምል ሁሉ በመሠዊያውና በላዩ ላይ ባለው ነገር ሁሉ ይምላል፤ +21 እንዲሁም በቤተ መቅደሱ የሚምል ሁሉ በቤተ መቅደሱና በዚያ በሚኖረው+ ይምላል፤ +22 በሰማይ የሚምል ሁሉ ደግሞ በአምላክ ዙፋንና በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ይምላል። +23 “እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ከኮሰረት፣ ከእንስላልና ከከሙን አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን በሕጉ ውስጥ የሚገኙትን እንደ ፍትሕ፣+ ምሕረትና+ ታማኝነት ያሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ችላ ትላላችሁ። እነዚያን ችላ ማለት ባይኖርባችሁም እነዚህን ነገሮች ማድረጋችሁ አስፈላጊ ነ +24 እናንተ ዕውር መሪዎች!+ ትንኝን+ አጥልላችሁ ታወጣላችሁ፤ ግመልን+ ግን ትውጣላችሁ! +25 “እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ጽዋውንና ሳህኑን ከውጭ በኩል ታጸዳላችሁ፤+ ውስጡ ግን ስግብግብነትና*+ ራስ ወዳድነት የሞላበት ነው።+ +26 አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፣ በመጀመሪያ ጽዋውንና ሳህኑን ከውስጥ በኩል አጽዳ፤ ከዚያ በኋላ ከውጭ በኩልም ንጹሕ ይሆናል። +27 “እናንተ ግብዞች+ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ ከውጭ አምረው የሚታዩ ከውስጥ ግን በሙታን አፅምና በብዙ ዓይነት ርኩሰት የተሞሉ በኖራ የተቀቡ መቃብሮችን ስለምትመስሉ ወዮላችሁ!+ +28 እናንተም ከውጭ ስትታዩ ጻድቅ ትመስላላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን በግብዝነትና በዓመፅ የተሞላ ነው።+ +29 “እናንተ ግብዞች+ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ የነቢያትን መቃብር ስለምትገነቡና የጻድቃንን መቃብር ስለምታስጌጡ ወዮላችሁ!+ +30 ደግሞም ‘በአባቶቻችን ዘመን ኖረን ቢሆን ኖሮ የነቢያትን ደም በማፍሰስ አንተባበራቸውም ነበር’ ትላላችሁ። +31 በመሆኑም የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሠክራላችሁ።+ +32 እንግዲያው አባቶቻችሁ የጀመሩትን ተግባር ዳር አድርሱ። +33 “እናንተ እባቦች፣ የእፉኝት ልጆች፣+ ከገሃነም* ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?+ +34 ስለዚህ ነቢያትን፣+ ጥበበኞችንና የሕዝብ አስተማሪዎችን+ ወደ እናንተ እልካለሁ። ከእነሱም መካከል አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ+ እንዲሁም በእንጨት ላይ ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ በምኩራቦቻችሁ ትገርፋላች��፤+ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዷቸዋላችሁ፤+ +35 በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም+ ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ ተጠያቂ ትሆናላችሁ።+ +36 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳሉ። +37 “ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም፣ ነቢያትን የምትገድል! ወደ እሷ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግር!+ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግኩ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።+ +38 እነሆ፣ ቤታችሁ* ለእናንተ የተተወ ይሆናል።*+ +39 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ‘በይሖዋ* ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!’+ እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ አታዩኝም።” +19 ኢየሱስ ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ከገሊላ ወጥቶ ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳሉት የይሁዳ ድንበሮች መጣ።+ +2 እጅግ ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ እሱም በዚያ ፈወሳቸው። +3 ፈሪሳውያንም ወደ እሱ መጥተው ሊፈትኑት በማሰብ “አንድ ሰው በማንኛውም ምክንያት ሚስቱን እንዲፈታ ሕግ ይፈቅድለታል?” ሲሉ ጠየቁት።+ +4 እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “ፈጣሪ ከመጀመሪያውም ወንድና ሴት አድርጎ እንደፈጠራቸው አላነበባችሁም?+ +5 ‘ከዚህ የተነሳ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’ ብሎ እንደተናገረስ አላነበባችሁም?+ +6 በመሆኑም ከዚህ በኋላ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። ስለዚህ አምላክ ያጣመረውን* ማንም ሰው አይለያየው።”+ +7 እነሱም “ታዲያ ሙሴ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ሰጥቶ እንዲፈታት ያዘዘው ለምንድን ነው?” አሉት።+ +8 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሴ የልባችሁን ደንዳናነት አይቶ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ፈቀደላችሁ+ እንጂ ከመጀመሪያው እንዲህ አልነበረም።+ +9 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፆታ ብልግና* ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።”+ +10 ደቀ መዛሙርቱም “በባልና በሚስት መካከል ያለው ሁኔታ እንዲህ ከሆነስ አለማግባት ይመረጣል” አሉት። +11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ስጦታው ያላቸው ካልሆኑ በስተቀር ይህን ሁሉም ሰው ሊቀበለው አይችልም።+ +12 ምክንያቱም ጃንደረባ ሆነው የሚወለዱ አሉ፤ ሰው የሰለባቸው ጃንደረቦችም አሉ፤ እንዲሁም ለመንግሥተ ሰማያት ሲሉ ራሳቸውን ጃንደረባ ያደረጉ ጃንደረቦችም አሉ። ይህን ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው።”+ +13 ከዚያም ኢየሱስ እጁን እንዲጭንባቸውና* እንዲጸልይላቸው ትናንሽ ልጆችን ወደ እሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው።+ +14 ይሁን እንጂ ኢየሱስ “ልጆቹን ተዉአቸው፤ ወደ እኔ እንዳይመጡ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ነውና” አለ።+ +15 እጁንም ከጫነባቸው* በኋላ ከዚያ ስፍራ ተነስቶ ሄደ። +16 ከዚያም አንድ ወጣት ወደ እሱ መጥቶ “መምህር፣ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ጥሩ ነገር ማድረግ ይኖርብኛል?” አለው።+ +17 እሱም “ስለ ጥሩ ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? ጥሩ የሆነው አምላክ ብቻ ነው።+ ሆኖም ሕይወት ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ዘወትር ትእዛዛቱን ጠብቅ” አለው።+ +18 እሱም “የትኞቹን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “አትግደል፣+ አታመንዝር፣+ አትስረቅ፣+ በሐሰት አትመሥክር፣+ +19 አባትህንና እናትህን አክብር+ እንዲሁም ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ።”+ +20 ወጣቱም “እነዚህን ሁሉ ስጠብቅ ኖሬአለሁ፤ ታዲያ አሁን የሚጎድለኝ ነገር ምንድን ነው?” አለው። +21 ኢየሱስም “ፍጹም* መሆን ከፈለግክ ሂድና ንብረትህን ሸጠህ ገንዘቡን ለድሆች ስጥ፤ በሰማይም ውድ ሀብት ታገኛለህ፤+ ደግሞ��� መጥተህ ተከታዬ ሁን” አለው።+ +22 ወጣቱም ይህን ሲሰማ ብዙ ንብረት ስለነበረው እያዘነ ሄደ።+ +23 ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ሀብታም ሰው ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት እጅግ አስቸጋሪ ይሆንበታል።+ +24 ዳግመኛም እላችኋለሁ፣ ሀብታም ሰው ወደ አምላክ መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።”+ +25 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲሰሙ በጣም ተገርመው “በዚህ ዓይነትማ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።+ +26 ኢየሱስም ትኩር ብሎ እያያቸው “ይህ በሰዎች ዘንድ አይቻልም፤ በአምላክ ዘንድ ግን ሁሉ ነገር ይቻላል” አላቸው።+ +27 ከዚያም ጴጥሮስ መልሶ “እነሆ፣ እኛ ሁሉን ትተን ተከትለንሃል፤ ታዲያ የምናገኘው ምን ይሆን?” አለው።+ +28 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ሁሉም ነገር አዲስ በሚሆንበት ጊዜ* የሰው ልጅ፣ ክብራማ በሆነው ዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ እኔን የተከተላችሁኝ እናንተ በ12 ዙፋኖች ላይ ተቀምጣችሁ በ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።+ +29 እንዲሁም ስለ ስሜ ሲል ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እህቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘላለም ሕይወትም ይወርሳል።+ +30 “ሆኖም ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች፣ ኋለኞች የሆኑ ደግሞ ፊተኞች ይሆናሉ።+ +20 “መንግሥተ ሰማያት በወይን እርሻው ላይ የሚሠሩ ሠራተኞችን ለመቅጠር ማልዶ ከወጣ የእርሻ ባለቤት ጋር ይመሳሰላል።+ +2 በቀን አንድ ዲናር* ሊከፍላቸው ከተዋዋለ በኋላ ሠራተኞቹን ወደ ወይን እርሻው ላካቸው። +3 በሦስት ሰዓት ገደማም ወጥቶ በገበያ ቦታ ሥራ ፈተው የቆሙ ሌሎች ሰዎች አየ፤ +4 እነዚህንም ሰዎች ‘እናንተም ወደ ወይኑ እርሻ ሂዱ፤ ተገቢውንም ክፍያ እከፍላችኋለሁ’ አላቸው። +5 እነሱም ሄዱ። ዳግመኛም በስድስት ሰዓትና በዘጠኝ ሰዓት ገደማ ወጥቶ እንዲሁ አደረገ። +6 በመጨረሻም በ11 ሰዓት ገደማ ወጥቶ ቆመው የነበሩ ሌሎች ሰዎች አገኘና ‘ቀኑን ሙሉ ሥራ ፈታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው?’ አላቸው። +7 እነሱም ‘የሚቀጥረን ሰው ስላጣን ነው’ ሲሉ መለሱለት። እሱም ‘እናንተም ወደ ወይኑ እርሻ ሄዳችሁ ሥሩ’ አላቸው። +8 “በመሸም ጊዜ የወይኑ እርሻ ባለቤት የሠራተኞቹን ተቆጣጣሪ ‘ሠራተኞቹን ጠርተህ በመጨረሻ ከተቀጠሩት አንስቶ በመጀመሪያ እስከተቀጠሩት ድረስ ደሞዛቸውን ክፈላቸው’+ አለው። +9 በ11 ሰዓት የተቀጠሩት ሰዎች መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር* ተቀበሉ። +10 በመሆኑም በመጀመሪያ የተቀጠሩት ሲመጡ እነሱ የበለጠ የሚከፈላቸው መስሏቸው ነበር፤ ነገር ግን እነሱም የተከፈላቸው አንድ አንድ ዲናር* ነበር። +11 ክፍያውን ሲቀበሉ በእርሻው ባለቤት ላይ ማጉረምረም ጀመሩ፤ +12 እንዲህም አሉት፦ ‘እነዚህ በመጨረሻ የተቀጠሩት ሰዎች አንድ ሰዓት ብቻ ነው የሠሩት፤ ያም ሆኖ አንተ ቀኑን ሙሉ ስንደክምና በፀሐይ ስንቃጠል ከዋልነው ከእኛ ጋር እኩል አደረግካቸው!’ +13 እሱ ግን ከመካከላቸው ለአንዱ እንዲህ አለው፦ ‘የኔ ወንድም፣ ምንም የበደልኩህ ነገር የለም። የተስማማነው አንድ ዲናር* እንድከፍልህ ነው፣ አይደለም እንዴ?+ +14 ስለዚህ ድርሻህን ይዘህ ሂድ። በመጨረሻ ለተቀጠሩት ለእነዚህ ሰዎችም ለአንተ የሰጠሁትን ያህል መስጠት ፈለግኩ። +15 በገዛ ገንዘቤ የፈለግኩትን የማድረግ መብት የለኝም? ወይስ እኔ ደግ* በመሆኔ ዓይንህ ተመቀኘ?’*+ +16 ስለሆነም ኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞች ደግሞ ኋለኞች ይሆናሉ።”+ +17 ወደ ኢየሩሳሌም እየወጡ ሳሉ ኢየሱስ 12ቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ነጥሎ ወሰዳቸው፤ በመንገድ ላይ ሳሉም እንዲህ አላቸው፦+ +18 “እነሆ፣ ወደ ኢ��ሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት አልፎ ይሰጣል። እነሱም ሞት ይፈርዱበታል፤+ +19 እንዲሁም እንዲያፌዙበት፣ እንዲገርፉትና በእንጨት ላይ እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤+ እሱም በሦስተኛው ቀን ይነሳል።”+ +20 ከዚያም የዘብዴዎስ+ ሚስት ከልጆቿ ጋር ወደ እሱ ቀርባ እየሰገደች* አንድ ነገር እንዲያደርግላት ለመነችው።+ +21 እሱም “ምንድን ነው የፈለግሽው?” አላት። እሷም መልሳ “በመንግሥትህ እነዚህን ሁለቱን ልጆቼን፣ አንዱን በቀኝህ አንዱን ደግሞ በግራህ አስቀምጥልኝ” አለችው።+ +22 ኢየሱስም መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ በቅርቡ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ትችላላችሁ?” አላቸው።+ እነሱም “እንችላለን” አሉት። +23 እሱም “በእርግጥ የእኔን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤+ በቀኜ ወይም በግራዬ መቀመጥ ግን አባቴ ላዘጋጀላቸው የሚሰጥ እንጂ በእኔ ፈቃድ የሚሆን አይደለም” አላቸው።+ +24 የቀሩት አሥሩ ይህን ሲሰሙ በሁለቱ ወንድማማቾች ላይ ተቆጡ።+ +25 ሆኖም ኢየሱስ ወደ እሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “የዚህ ዓለም ገዢዎች በሕዝባቸው ላይ ሥልጣናቸውን እንደሚያሳዩ፣ ታላላቅ ሰዎችም በኃይል እንደሚገዟቸው ታውቃላችሁ።+ +26 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፤+ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል፤+ +27 እንዲሁም ከመካከላችሁ ፊተኛ መሆን የሚፈልግ ሁሉ ባሪያችሁ ሊሆን ይገባል።+ +28 የሰው ልጅም የመጣው ለማገልገልና+ በብዙ ሰዎች ምትክ ሕይወቱን* ቤዛ አድርጎ ለመስጠት+ እንጂ እንዲገለገል አይደለም።” +29 ከኢያሪኮ ወጥተው እየሄዱ ሳሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከተለው። +30 በዚህ ጊዜ መንገድ ዳር የተቀመጡ ሁለት ዓይነ ስውሮች ኢየሱስ በዚያ እያለፈ መሆኑን ሲሰሙ “ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልን!” እያሉ ጮኹ።+ +31 ሆኖም ሕዝቡ ዝም እንዲሉ ገሠጿቸው፤ እነሱ ግን “ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልን!” እያሉ ይበልጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጮኹ። +32 ኢየሱስም ቆም ብሎ ጠራቸውና “ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። +33 እነሱም “ጌታ ሆይ፣ ዓይናችንን አብራልን” አሉት። +34 ኢየሱስም በጣም አዘነላቸውና ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ፤+ ወዲያውኑም ማየት ቻሉ፤ ከዚያም ተከተሉት። +3 በዚያ ወቅት መጥምቁ ዮሐንስ+ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ፤+ +2 “መንግሥተ ሰማያት ስለቀረበ ንስሐ ግቡ” ይል ነበር።+ +3 “አንድ ሰው በምድረ በዳ ‘የይሖዋን* መንገድ አዘጋጁ፤ ጎዳናዎቹንም አቅኑ’+ በማለት ይጮኻል” ተብሎ በነቢዩ ኢሳይያስ የተነገረለት እሱ ነው።+ +4 ዮሐንስ ከግመል ፀጉር የተሠራ ልብስ ይለብስ፣ ወገቡም ላይ የቆዳ ቀበቶ ይታጠቅ ነበር።+ ምግቡ አንበጣና የዱር ማር ነበር።+ +5 በኢየሩሳሌምና በመላዋ ይሁዳ እንዲሁም በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ክልል ሁሉ የሚኖሩ ሰዎች ወደ እሱ ይመጡ ነበር፤+ +6 ደግሞም ኃጢአታቸውን በግልጽ እየተናዘዙ ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በእሱ ይጠመቁ* ነበር።+ +7 ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን+ ወደሚያጠምቅበት ቦታ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእፉኝት ልጆች፣+ ከሚመጣው ቁጣ+ እንድትሸሹ ያስጠነቀቃችሁ ማን ነው? +8 እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ። +9 ‘እኛ እኮ አባታችን አብርሃም ነው’ ብላችሁ አታስቡ።+ አምላክ ለአብርሃም ከእነዚህ ድንጋዮች ልጆች ሊያስነሳለት እንደሚችል ልነግራችሁ እወዳለሁ። +10 መጥረቢያው ዛፎቹ ሥር ተቀምጧል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ እሳት ውስጥ ይጣላል።+ +11 እኔ በበኩሌ ንስሐ በመግባታችሁ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤+ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይበረታል፤ እኔ ጫማውን ለማውለቅ እንኳ ብቁ አይደለሁም።+ እሱ በመንፈስ ቅዱስና+ በእሳት+ ያጠምቃችኋል። +12 ላይዳውን* በእጁ ይዟል፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጸዳል፤ ስንዴውንም ወደ ጎተራ ያስገባል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”+ +13 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።+ +14 ዮሐንስ ግን “በአንተ መጠመቅ የሚያስፈልገኝ እኔ ሆኜ ሳለ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህ?” ብሎ ሊከለክለው ሞከረ። +15 ኢየሱስም መልሶ “ግድ የለም እሺ በለኝ፤ በዚህ መንገድ ጽድቅ የሆነውን ሁሉ መፈጸማችን ተገቢ ነው” አለው። በዚህ ጊዜ ዮሐንስ ፈቀደለት። +16 ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃው ወጣ፤ እነሆ፣ ሰማያት ተከፈቱ፤+ የአምላክም መንፈስ በእሱ ላይ እንደ ርግብ ሲወርድ አየ።+ +17 ደግሞም “በጣም የምደሰትበት+ የምወደው ልጄ ይህ ነው”+ የሚል ድምፅ ከሰማያት ተሰማ።+ +24 ኢየሱስ ከቤተ መቅደሱ ወጥቶ እየሄደ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ወደ እሱ ቀረቡ። +2 እሱም መልሶ “ይህን ሁሉ ታያላችሁ? እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ሁሉ ሳይፈርስ እንዲህ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ ከቶ አይኖርም” አላቸው።+ +3 በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እሱ መጥተው “እስቲ ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የመገኘትህና*+ የዚህ ሥርዓት* መደምደሚያ+ ምልክትስ ምንድን ነው?” አሉት። +4 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ፤+ +5 ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ።+ +6 ጦርነትና የጦርነት ወሬ ትሰማላችሁ። በዚህ ጊዜ እንዳትደናገጡ ተጠንቀቁ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸው የግድ ነው፤ ሆኖም ፍጻሜው ገና ነው።+ +7 “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳልና፤+ በተለያየ ስፍራ የምግብ እጥረትና+ የምድር ነውጥ ይከሰታል።+ +8 እነዚህ ነገሮች ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። +9 “በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፣+ ይገድሏችኋል+ እንዲሁም በስሜ ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።+ +10 በተጨማሪም ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ እርስ በርሳቸውም ይጠላላሉ። +11 ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ፤+ +12 ክፋት* እየበዛ ስለሚሄድ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል። +13 እስከ መጨረሻው የጸና* ግን ይድናል።+ +14 ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤+ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል። +15 “ስለዚህ ነቢዩ ዳንኤል በተናገረው መሠረት ጥፋት የሚያመጣው ‘ርኩስ ነገር’ በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ስታዩ+ አንባቢው ያስተውል፤ +16 በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ።+ +17 በጣሪያ* ላይ ያለ ሰው ዕቃውን ከቤቱ ለመውሰድ አይውረድ፤ +18 በእርሻም ያለ መደረቢያውን ለመውሰድ አይመለስ። +19 በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! +20 ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት* ቀን እንዳይሆን ዘወትር ጸልዩ፤ +21 ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ የማያውቅ ዳግመኛም የማይሆን+ ታላቅ መከራ+ ይከሰታል። +22 እንዲያውም ቀኖቹ ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ ሁሉ ባልዳነ ነበር፤ ሆኖም ለተመረጡት ሲባል ቀኖቹ ያጥራሉ።+ +23 “በዚያን ጊዜ ማንም ‘እነሆ፣ ክርስቶስ ይኸውላችሁ’+ ወይም ‘ያውላችሁ’ ቢላችሁ አትመኑ።+ +24 ምክንያቱም ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤+ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችና አስደናቂ ነገሮች ያደርጋሉ።+ +25 እንግዲህ አስቀ��ሜ አስጠንቅቄያችኋለሁ። +26 ስለዚህ ሰዎች ‘እነሆ፣ በምድረ በዳ ነው’ ቢሏችሁ ወደዚያ አትውጡ፤ ‘እነሆ፣ ቤት ውስጥ በውስጠኛው ክፍል ይገኛል’ ቢሏችሁ አትመኑ።+ +27 መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚያበራ ሁሉ የሰው ልጅ መገኘትም* እንዲሁ ይሆናል።+ +28 በድን ባለበት ሁሉ ንስሮች ይሰበሰባሉ።+ +29 “በእነዚያ ቀናት ከሚኖረው መከራ በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤+ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይላትም ይናወጣሉ።+ +30 ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ የምድር ወገኖችም ሁሉ በሐዘን ደረታቸውን ይደቃሉ፤+ የሰው ልጅም+ በኃይልና በታላቅ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል።+ +31 እሱም መላእክቱን በታላቅ የመለከት ድምፅ ይልካል፤ እነሱም ከአራቱ ነፋሳት፣* ከአንዱ የሰማይ ዳርቻ እስከ ሌላው የሰማይ ዳርቻ ለእሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።+ +32 “እንግዲያው ይህን ምሳሌ ከበለስ ዛፍ ተማሩ፦ ቅርንጫፎቿ ሲለመልሙና ቅጠሎቿ ሲያቆጠቁጡ በጋ* እንደቀረበ ታውቃላችሁ።+ +33 በተመሳሳይ እናንተም እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስታዩ የሰው ልጅ ደጃፍ ላይ እንደደረሰ እርግጠኞች ሁኑ።+ +34 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ ፈጽሞ አያልፍም። +35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።+ +36 “ስለዚያ ቀንና ሰዓት ከአብ ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ሆኑ ወልድ፣+ ማንም አያውቅም።+ +37 በኖኅ ዘመን እንደነበረው ሁሉ+ የሰው ልጅ መገኘትም* እንደዚሁ ይሆናል።+ +38 ከጥፋት ውኃ በፊት በነበረው ዘመን ኖኅ ወደ መርከቡ እስከገባበት ቀን+ ድረስ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ወንዶች ያገቡ፣ ሴቶችም ይዳሩ ነበር፤ +39 የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉንም ጠራርጎ እስከወሰዳቸው ጊዜ ድረስ ምንም አላስተዋሉም፤+ የሰው ልጅ መገኘትም እንደዚሁ ይሆናል። +40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ቦታ ይሠራሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው እዚያው ይተዋል። +41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ እዚያው ትተዋለች።+ +42 ስለዚህ ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ ስለማታውቁ ምንጊዜም ነቅታችሁ ጠብቁ።+ +43 “ነገር ግን ይህን እወቁ፦ አንድ ሰው ሌባ+ በየትኛው ክፍለ ሌሊት* እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ ነቅቶ በጠበቀና ቤቱ እንዳይደፈር በተከላከለ ነበር።+ +44 ስለዚህ እናንተም የሰው ልጅ ባላሰባችሁት ሰዓት ስለሚመጣ ዝግጁ ሁኑ።+ +45 “በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው ጌታው በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው ታማኝና ልባም* ባሪያ በእርግጥ ማን ነው?+ +46 ጌታው በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ ካገኘው ያ ባሪያ ደስተኛ ነው!+ +47 እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታው በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል። +48 “ነገር ግን ያ ክፉ ባሪያ በልቡ ‘ጌታዬ ይዘገያል’ ብሎ ቢያስብ+ +49 ደግሞም ባልንጀሮቹ የሆኑትን ባሪያዎች መደብደብ ቢጀምር እንዲሁም ከሰካራሞች ጋር ቢበላና ቢጠጣ፣ +50 የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላሰበው ሰዓት ይመጣል፤+ +51 ከባድ ቅጣት ይቀጣዋል፤* ዕጣውንም ከግብዞች ጋር ያደርገዋል። በዚያም ያለቅሳል፤ ጥርሱንም ያፋጫል።+ +7 “እንዳይፈረድባችሁ በሌሎች ላይ አትፍረዱ፤*+ +2 በምትፈርዱት ፍርድ ይፈረድባችኋል፤+ በምትሰፍሩበት መስፈሪያም ይሰፍሩላችኋል።+ +3 ታዲያ በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ትተህ በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለምን ታያለህ?+ +4 ወይም በራስህ ዓይን ውስጥ ግንድ እያለ ወንድምህን ‘ዓይንህ ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? +5 አንተ ግብዝ! መጀመሪያ በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለ���ውጣት አጥርተህ ማየት ትችላለህ። +6 “ቅዱስ የሆነውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በአሳማ ፊት አትጣሉ።+ አለዚያ ዕንቁዎቹን በእግራቸው ይረጋግጧቸዋል፤ ተመልሰውም ይጎዷችኋል። +7 “ደጋግማችሁ ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤+ ሳታቋርጡ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ ደጋግማችሁ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።+ +8 የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋልና፤+ የሚፈልግ ሁሉ ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ሁሉ ይከፈትለታል። +9 ደግሞስ ከእናንተ መካከል ልጁ ዳቦ ቢለምነው ድንጋይ የሚሰጠው አለ? +10 ወይስ ዓሣ ቢለምነው እባብ ይሰጠዋል? +11 ታዲያ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት+ መልካም ነገር እንዴት አብልጦ አይሰጣቸው!+ +12 “እንግዲህ ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እናንተም አድርጉላቸው።+ ሕጉም ሆነ የነቢያት ቃል የሚሉት ይህንኑ ነው።+ +13 “በጠባቡ በር ግቡ፤+ ምክንያቱም ወደ ጥፋት የሚወስደው በር ትልቅ፣ መንገዱም ሰፊ ነው፤ በዚያ የሚሄዱም ብዙዎች ናቸው፤ +14 ወደ ሕይወት የሚወስደው በር ግን ጠባብ፣ መንገዱም ቀጭን ነው፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።+ +15 “በውስጣቸው ነጣቂ ተኩላዎች+ ሆነው ሳሉ የበግ ለምድ ለብሰው+ ወደ እናንተ ከሚመጡ ሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ።+ +16 ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ሰዎች ከእሾህ ወይን፣ ከአሜኬላስ በለስ ይለቅማሉ?+ +17 በተመሳሳይም ጥሩ ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፤ የበሰበሰ ዛፍ ሁሉ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል።+ +18 ጥሩ ዛፍ መጥፎ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፤ የበሰበሰም ዛፍ መልካም ፍሬ ሊያፈራ አይችልም።+ +19 መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ ወደ እሳት ይጣላል።+ +20 በመሆኑም እነዚህን ሰዎች ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።+ +21 “‘ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት አይገባም፤ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባው በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ብቻ ነው።+ +22 በዚያ ቀን ብዙዎች እንዲህ ይሉኛል፦ ‘ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣+ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም? በስምህ አጋንንትን አላወጣንም? በስምህስ ብዙ ተአምራት አላደረግንም?’+ +23 እኔም በዚያ ጊዜ ‘ቀድሞውንም አላውቃችሁም! እናንተ ዓመፀኞች፣ ከእኔ ራቁ!’ እላቸዋለሁ።+ +24 “ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራን አስተዋይ ሰው ይመስላል።+ +25 ዶፍ ወረደ፤ ጎርፍ ጎረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ቤቱንም በኃይል መታው፤ ሆኖም ቤቱ በዓለት ላይ ስለተመሠረተ አልተደረመሰም። +26 ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የማያውል ሁሉ ግን ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራን ሞኝ ሰው ይመስላል።+ +27 ዶፍ ወረደ፤ ጎርፍ ጎረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ቤቱንም በኃይል መታው፤+ ቤቱም ተደረመሰ፤ እንዳልነበረም ሆነ።” +28 ኢየሱስ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርት አሰጣጡ እጅግ ተደነቁ፤+ +29 የሚያስተምራቸው እንደ እነሱ ጸሐፍት ሳይሆን እንደ ባለሥልጣን ነበርና።+ +12 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት ቀን በእህል እርሻ መካከል አለፈ። ደቀ መዛሙርቱም ተርበው ስለነበር እሸት እየቀጠፉ መብላት ጀመሩ።+ +2 ፈሪሳውያን ይህን ባዩ ጊዜ “ተመልከት! ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ቀን በሕግ የተከለከለ ነገር እያደረጉ ነው” አሉት።+ +3 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ዳዊት እሱና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ምን እንዳደረገ አላነበባችሁም?+ +4 ወደ አምላክ ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር+ እሱም ሆነ ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች እንዲበሉ ያልተፈቀደውን በአምላክ ፊት የቀረበ ኅብስት+ አልበሉም? +5 ደግሞስ ካህናት የሰንበትን ሕግ እንደሚተላለፉና ይህም እንደ በደል እንደማይቆጠርባቸ��� በሕጉ ላይ አላነበባችሁም?+ +6 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ከቤተ መቅደሱ የሚበልጥ እዚህ አለ።+ +7 ይሁንና ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን+ እንጂ መሥዋዕትን+ አይደለም’ የሚለውን ቃል ትርጉም ተረድታችሁ ቢሆን ኖሮ ምንም በደል ባልሠሩት ላይ ባልፈረዳችሁ ነበር። +8 የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።”+ +9 ከዚያ ስፍራ ከሄደ በኋላ ወደ ምኩራባቸው ገባ፤ +10 በዚያም እጁ የሰለለ* አንድ ሰው ነበር።+ እነሱም ኢየሱስን መክሰስ ፈልገው “በሰንበት መፈወስ በሕግ ተፈቅዷል?” ሲሉ ጠየቁት።+ +11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ መካከል አንድ በግ ያለው ሰው ቢኖርና በሰንበት ቀን ጉድጓድ ውስጥ ቢገባበት በጉን ጎትቶ የማያወጣው ይኖራል?+ +12 ታዲያ ሰው ከበግ እጅግ አይበልጥም? ስለዚህ በሰንበት መልካም ነገር ማድረግ ተፈቅዷል።” +13 ከዚያም ሰውየውን “እጅህን ዘርጋ” አለው። ሰውየውም እጁን ዘረጋ፤ እጁም እንደ ሌላኛው እጁ ደህና ሆነለት። +14 ፈሪሳውያኑ ግን ወጥተው እሱን ለመግደል አሴሩ። +15 ኢየሱስም ይህን ሲያውቅ አካባቢውን ለቆ ሄደ። ብዙ ሰዎችም ተከትለውት ሄዱ፤+ እሱም የታመሙትን ሁሉ ፈወሳቸው፤ +16 ሆኖም የእሱን ማንነት ለሌሎች እንዳይገልጹ በጥብቅ አዘዛቸው፤+ +17 ይህን ያደረገው በነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፦ +18 “እነሆ፣ የምወደውና ደስ የምሰኝበት*+ የመረጥኩት አገልጋዬ!+ መንፈሴን በእሱ ላይ አደርጋለሁ፤+ ፍትሕ ምን ማለት እንደሆነም ለብሔራት ያሳውቃል። +19 አይጨቃጨቅም+ ወይም አይጮኽም፤ በአውራ ጎዳናዎችም ላይ ድምፁን የሚሰማ አይኖርም። +20 ፍትሕን በአስተማማኝ ሁኔታ እስኪያሰፍን ድረስ፣ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጨስንም የጧፍ ክር አያጠፋም።+ +21 በእርግጥም ብሔራት በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።”+ +22 ከጊዜ በኋላም፣ ጋኔን የያዘው ዓይነ ስውርና ዱዳ ሰው ወደ እሱ አመጡ፤ እሱም ፈወሰው፤ ዱዳውም መናገርና ማየት ቻለ። +23 ሕዝቡም ሁሉ በጣም ተደንቀው “ይህ የዳዊት ልጅ ይሆን እንዴ?” ይሉ ጀመር። +24 ፈሪሳውያን ይህን ሲሰሙ “ይህ ሰው በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል* ካልሆነ በስተቀር አጋንንትን ሊያስወጣ አይችልም” አሉ።+ +25 ኢየሱስም ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ እንዲሁም እርስ በርሱ የሚከፋፈል ከተማ ወይም ቤት ሁሉ ጸንቶ አይቆምም። +26 በተመሳሳይም ሰይጣን ሰይጣንን የሚያስወጣ ከሆነ እርስ በርሱ ተከፋፍሏል ማለት ነው፤ ይህ ከሆነ ታዲያ መንግሥቱ እንዴት ጸንቶ ሊቆም ይችላል? +27 በተጨማሪም እኔ አጋንንትን የማስወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ* የሚያስወጧቸው ታዲያ በማን ነው? ልጆቻችሁ ፈራጆች የሚሆኑባችሁ* ለዚህ ነው። +28 ሆኖም አጋንንትን የማስወጣው በአምላክ መንፈስ ከሆነ የአምላክ መንግሥት ሳታስቡት ደርሶባችኋል ማለት ነው።+ +29 ደግሞስ አንድ ሰው በቅድሚያ ሰውየውን ሳያስር ወደ አንድ ብርቱ ሰው ቤት ገብቶ እንዴት ንብረቱን ሊወስድ ይችላል? ቤቱን መዝረፍ የሚችለው እንዲህ ካደረገ ብቻ ነው። +30 ከእኔ ጎን ያልቆመ ሁሉ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ሁሉ ይበትናል።+ +31 “ስለሆነም እላችኋለሁ፣ ሰዎች የሚሠሩት ኃጢአትና የሚሳደቡት ስድብ ሁሉ ይቅር ይባልላቸዋል፤ መንፈስ ቅዱስን የሰደበ ግን ይቅር አይባልለትም።+ +32 ለምሳሌ በሰው ልጅ ላይ ክፉ ቃል የሚናገር ሁሉ ይቅርታ ይደረግለታል፤+ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ክፉ ቃል የሚናገር ሁሉ ግን በዚህም ሆነ በሚመጣው ሥርዓት* ይቅርታ አይደረግለትም።+ +33 “መልካም ዛፍ ካላችሁ መልካም ፍሬ ያፈራል፤ የበሰበሰ ዛፍ ካላችሁ ደግሞ የበሰበሰ ፍሬ ያፈራል፤ ዛፍ የሚታወቀው በፍሬው ነውና።+ +34 እናንተ የእፉኝት ልጆች፣+ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ እንዴት መልካም ነገር ልትናገሩ ትችላላችሁ? አንደበት የሚናገረው በልብ ውስጥ የሞላውን ነውና።+ +35 ጥሩ ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር ጥሩ ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰው ደግሞ በልቡ ካከማቸው መጥፎ ነገር ክፉ ነገር ያወጣል።+ +36 ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ሰዎች ለሚናገሩት ከንቱ ቃል ሁሉ በፍርድ ቀን ይጠየቁበታል፤+ +37 ከቃልህ የተነሳ ጻድቅ ትባላለህና፤ ከቃልህም የተነሳ ትኮነናለህ።” +38 ከዚያም ከጸሐፍትና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ “መምህር፣ ምልክት እንድታሳየን እንፈልጋለን” አሉት።+ +39 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ክፉና አመንዝራ* ትውልድ ሁልጊዜ ምልክት ማየት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከነቢዩ ዮናስ ምልክት በስተቀር ምንም ምልክት አይሰጠውም።+ +40 ዮናስ በትልቅ ዓሣ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረ+ ሁሉ የሰው ልጅም በምድር ልብ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይቆያል።+ +41 የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሐ ስለገቡ+ በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይኮንኑታል። ነገር ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።+ +42 የደቡብ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለመጣች+ በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስታ ትኮንነዋለች። ነገር ግን ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።+ +43 “ርኩስ መንፈስ ከሰው ሲወጣ የሚያርፍበት ቦታ ፍለጋ ውኃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ ሆኖም የሚያርፍበት ቦታ አያገኝም።+ +44 ከዚያም ‘ወደለቀቅኩት ቤቴ ተመልሼ እሄዳለሁ’ ይላል፤ ሲመለስም ቤቱ ባዶ ሆኖ፣ ጸድቶና አጊጦ ያገኘዋል። +45 ከዚያም ሄዶ ከእሱ የከፉ ሌሎች ሰባት መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውም ይኖሩበታል፤ የዚያም ሰው የኋለኛው ሁኔታ ከቀድሞው የከፋ ይሆንበታል።+ ይህ ክፉ ትውልድም ተመሳሳይ ነገር ይደርስበታል።” +46 ኢየሱስ ለሕዝቡ እየተናገረ ሳለ እናቱና ወንድሞቹ+ ሊያነጋግሩት ፈልገው ውጭ ቆመው ነበር።+ +47 ስለሆነም አንድ ሰው “እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ሊያነጋግሩህ ፈልገው ውጭ ቆመዋል” አለው። +48 ኢየሱስም መልሶ ሰውየውን “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አለው። +49 እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ እንዲህ አለ፦ “እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው!+ +50 በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ ለእኔ ወንድሜ፣ እህቴና እናቴ ነውና።”+ +1 የዳዊት ልጅ፣+ የአብርሃም ልጅ+ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን* ታሪክ* የያዘ መጽሐፍ፦ + 2 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤+ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤+ያዕቆብ ይሁዳንና+ ወንድሞቹን ወለደ፤ + 3 ይሁዳ ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን+ ወለደ፤ፋሬስ ኤስሮንን ወለደ፤+ኤስሮን ራምን ወለደ፤+ + 4 ራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤+ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ + 5 ሰልሞን ከረዓብ+ ቦዔዝን ወለደ፤ቦዔዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤+ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤+ + 6 እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።+ ዳዊት ከኦርዮ ሚስት ሰለሞንን ወለደ፤+ + 7 ሰለሞን ሮብዓምን ወለደ፤+ሮብዓም አቢያህን ወለደ፤አቢያህ አሳን ወለደ፤+ + 8 አሳ ኢዮሳፍጥን ወለደ፤+ኢዮሳፍጥ ኢዮራምን ወለደ፤+ኢዮራም ዖዝያን ወለደ፤ + 9 ዖዝያ ኢዮዓታምን ወለደ፤+ኢዮዓታም አካዝን ወለደ፤+አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤+ +10 ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤+ምናሴ አምዖንን ወለደ፤+አምዖን ኢዮስያስን ወለደ፤+ +11 ኢዮስያስ+ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን በተጋዙበት ዘመን+ ኢኮንያንን+ እና ወንድሞቹን ወለደ። +12 ወደ ባቢሎን ከተጋዙ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ሰላትያል ዘሩባቤልን ወለደ፤+ +13 ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤ኤልያቄም አዞርን ወለደ፤ +14 አዞር ሳዶቅን ወለደ፤ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤አኪም ኤልዩድን ወለደ፤ +15 ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤አልዓዛር ማታንን ወለደ፤ማታን ያዕቆብን ወለደ፤ +16 ያዕቆብ ዮሴፍን ወለደ፤ ዮሴፍም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደችው የማርያም ባል ነበር።+ +17 ስለዚህ ጠቅላላው ትውልድ፣ ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14 ትውልድ፣ ከዳዊት አንስቶ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን እስከተጋዙበት ጊዜ ድረስ 14 ትውልድ እንዲሁም ወደ ባቢሎን ከተጋዙበት ዘመን እስከ ክርስቶስ ድረስ 14 ትውልድ ነው። +18 ይሁንና ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ሁኔታ እንደሚከተለው ነው፦ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ በነበረበት ጊዜ፣ አብረው መኖር ከመጀመራቸው በፊት በመንፈስ ቅዱስ* ፀንሳ ተገኘች።+ +19 ይሁን እንጂ ባሏ* ዮሴፍ ጻድቅ ስለሆነና በይፋ ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊፈታት አሰበ።+ +20 ሆኖም ይህን ለማድረግ አስቦ ሳለ የይሖዋ* መልአክ በሕልም ተገልጦለት እንዲህ አለው፦ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፣ ሚስትህ ማርያም የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ+ እሷን ወደ ቤት ለመውሰድ አትፍራ። +21 ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ እሱንም ኢየሱስ* ብለህ ትጠራዋለህ፤+ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና።”+ +22 ይህ ሁሉ የሆነው ይሖዋ* በነቢዩ በኩል እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፦ +23 “እነሆ! ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል+ ይሉታል”፤ ትርጉሙም “አምላክ ከእኛ ጋር ነው”+ ማለት ነው። +24 ከዚያም ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቃ፤ የይሖዋ* መልአክ ባዘዘውም መሠረት ሚስቱን ወደ ቤቱ ወሰዳት። +25 ሆኖም ልጁን እስክትወልድ ድረስ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት አልፈጸመም፤+ ልጁንም ኢየሱስ ብሎ ጠራው።+ +28 ከሰንበት ቀን በኋላ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን* ጎህ ሲቀድ መግደላዊቷ ማርያምና ሌላዋ ማርያም መቃብሩን ለማየት መጡ።+ +2 እነሆም የይሖዋ* መልአክ ከሰማይ ስለወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ተከሰተ፤ መልአኩም መጥቶ ድንጋዩን አንከባለለውና በላዩ ተቀመጠ።+ +3 መልኩ እንደ መብረቅ ያበራ ነበር፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር።+ +4 ጠባቂዎቹ እሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተንቀጠቀጡ፤ እንደ በድንም ሆኑ። +5 ሆኖም መልአኩ ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፤ በእንጨት ላይ የተሰቀለውን ኢየሱስን እየፈለጋችሁ እንደሆነ አውቃለሁ።+ +6 አስቀድሞ እንደተናገረው ከሞት ስለተነሳ እዚህ የለም።+ ኑና አስከሬኑ አርፎበት የነበረውን ስፍራ እዩ። +7 ስለሆነም ፈጥናችሁ ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ ከሞት እንደተነሳ ንገሯቸው፤ ‘እነሆ፣ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል።+ እዚያም ታዩታላችሁ’ በሏቸው። እነሆ ነግሬአችኋለሁ።”+ +8 ስለዚህ ሴቶቹ በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ተውጠው ከመታሰቢያ መቃብሩ በፍጥነት በመውጣት ወሬውን ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር እየሮጡ ሄዱ።+ +9 ወዲያውም ኢየሱስ አገኛቸውና “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነሱም ወደ እሱ ቀረቡና እግሩን ይዘው ሰገዱለት።* +10 ከዚያም ኢየሱስ “አትፍሩ! ሂዱና ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሯቸው፤ እዚያም ያዩኛል” አላቸው። +11 ሴቶቹ በመንገድ ላይ ሳሉ ከጠባቂዎቹ አንዳንዶቹ+ ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ነገር ሁሉ ለካህናት አለቆቹ ነገሯቸው። +12 የካህናት አለቆቹም ከሽማግሌዎቹ ጋር ተሰብስበው ከተማከሩ በኋላ ለወታደሮቹ በርከት ያሉ የብር ሳንቲሞች* በመስጠት +13 እንዲህ አሏቸው፦ “‘ሌሊት ተኝተን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው አስከሬኑን ሰረቁት’ በሉ።+ +14 አትጨነቁ፤ ወሬው ወደ አገረ ገዢው ጆሮ ከደረሰ ሁኔታውን እናስረዳዋለን።”* +15 እነሱም የብር ሳንቲሞቹን ተቀብለው እንደታዘዙት አደረጉ፤ ይህም ታሪክ እስከ ዛሬ ��ረስ በአይሁዳውያን ዘንድ በስፋት ይወራል። +16 ይሁንና የኢየሱስ 11 ደቀ መዛሙርት ከእሱ ጋር ለመገናኘት በገሊላ ወደሚገኘው፣ እሱ ወደነገራቸው ተራራ ሄዱ።+ +17 ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤* አንዳንዶች ግን ተጠራጠሩ። +18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው፦ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።+ +19 ስለዚህ ሂዱና ከሁሉም ብሔራት ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ፤+ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣+ +20 ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።+ እነሆም እኔ እስከ ሥርዓቱ* መደምደሚያ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”+ +8 ከተራራው ከወረደ በኋላ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከተለው። +2 በዚህ ጊዜ በሥጋ ደዌ የተያዘ አንድ ሰው ወደ እሱ መጥቶ በመስገድ* “ጌታ ሆይ፣ ብትፈልግ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” አለው።+ +3 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው።+ ወዲያውኑ ከሥጋ ደዌው ነጻ።+ +4 ከዚያም ኢየሱስ “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤+ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤+ ሙሴ ያዘዘውንም መባ አቅርብ።+ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ” አለው። +5 ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም በገባ ጊዜ አንድ የጦር መኮንን ወደ እሱ ቀርቦ እንዲህ ሲል ተማጸነው፦+ +6 “ጌታዬ፣ አገልጋዬ ሽባ ሆኖ ቤት ተኝቷል፤ በጣም እየተሠቃየ ነው።” +7 እሱም “መጥቼ እፈውሰዋለሁ” አለው። +8 መኮንኑም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታዬ፣ አንተ ወደ ቤቴ ትገባ ዘንድ የሚገባኝ ሰው አይደለሁም፤ ነገር ግን እዚሁ ሆነህ አንድ ቃል ተናገር፣ አገልጋዬም ይፈወሳል። +9 እኔ ራሴ የምታዘዛቸው የበላይ አዛዦች አሉ፤ ለእኔም የሚታዘዙ የበታች ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም ‘ይህን አድርግ!’ ስለው ያደርጋል።” +10 ኢየሱስ ይህን ሲሰማ በጣም ተገርሞ ይከተሉት ለነበሩት እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ በእስራኤል ውስጥ እንዲህ ዓይነት ታላቅ እምነት+ ያለው አንድም ሰው አላገኘሁም። +11 ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ በመንግሥተ ሰማያትም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በማዕድ ይቀመጣሉ።+ +12 የመንግሥተ ሰማያት ልጆች ግን ውጭ ወዳለው ጨለማ ይጣላሉ። በዚያም ያለቅሳሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ።”+ +13 ከዚያም ኢየሱስ መኮንኑን “ሂድ። እንደ እምነትህ ይሁንልህ”+ አለው። አገልጋዩም በዚያች ቅጽበት ተፈወሰ።+ +14 ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት ሲመጣ የጴጥሮስ አማት+ ትኩሳት ይዟት ተኝታ አገኛት።+ +15 እጇንም ሲዳስሳት+ ትኩሳቱ ለቀቃት፤ ተነስታም ታገለግለው ጀመር። +16 ከመሸ በኋላ ሰዎች አጋንንት ያደሩባቸውን ብዙ ሰዎች ወደ እሱ አመጡ፤ መናፍስቱንም በአንድ ቃል አስወጣ፤ እየተሠቃዩ የነበሩትንም ሁሉ ፈወሰ፤ +17 ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ “እሱ ሕመማችንን ተቀበለ፤ ደዌያችንንም ተሸከመ” ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው።+ +18 ኢየሱስ በዙሪያው ብዙ ሰዎች እንደተሰበሰቡ ባየ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ባሕሩ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዛቸው።+ +19 ከጸሐፍትም አንዱ መጥቶ “መምህር፣ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው።+ +20 ኢየሱስ ግን “ቀበሮዎች ጉድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ቦታ የለውም” አለው።+ +21 ከዚያም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ “ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው።+ +22 ኢየሱስም “አንተ እኔን መከተልህን ቀጥል፤ ሙታን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው” አለው።+ +23 ከዚያም ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ጀልባ ላይ ተሳፈሩ።+ +24 እነሆ፣ ���ጉዞ ላይ ሳሉ በባሕሩ ላይ ኃይለኛ ማዕበል ስለተነሳ ጀልባዋ በውኃ ተሞልታ ልትሰጥም ተቃረበች፤ ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር።+ +25 እነሱም ወደ እሱ ቀርበው ቀሰቀሱትና “ጌታ ሆይ፣ ማለቃችን እኮ ነው፤ አድነን!” አሉት። +26 እሱ ግን “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ለምን ትሸበራላችሁ?”* አላቸው።+ ከዚያም ተነስቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሰፈነ።+ +27 ሰዎቹም ተደንቀው “ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? ነፋስና ባሕር እንኳ ይታዘዙለታል” አሉ። +28 ባሕሩን ተሻግሮ ገዳሬኖስ* ወደተባለው ክልል በደረሰ ጊዜ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ቦታ ወጥተው ከእሱ ጋር ተገናኙ።+ ሰዎቹ በጣም ኃይለኛ ከመሆናቸው የተነሳ ማንም ሰው በዚያ ለማለፍ አይደፍርም ነበር። +29 እነሱም “የአምላክ ልጅ ሆይ፣ እኛ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለን?+ የመጣኸው ጊዜው ሳይደርስ+ ልታሠቃየን ነው?”+ ብለው ጮኹ። +30 ከእነሱ ራቅ ብሎ ብዙ የአሳማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር።+ +31 አጋንንቱም “የምታስወጣን ከሆነ ወደ አሳማው መንጋ ስደደን” ብለው ይማጸኑት ጀመር።+ +32 እሱም “ሂዱ!” አላቸው። እነሱም ወጥተው ወደ አሳማዎቹ ሄዱ፤ የአሳማውም መንጋ በሙሉ ከገደሉ አፋፍ* እየተንደረደረ በመውረድ ባሕሩ ውስጥ ሰጥሞ አለቀ። +33 እረኞቹ ግን ሸሽተው ወደ ከተማው በመሄድ አጋንንት ባደሩባቸው ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጨምሮ የሆነውን ነገር ሁሉ አወሩ። +34 ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ለማግኘት ወጣ፤ ሰዎቹም ባዩት ጊዜ አካባቢያቸውን ለቆ እንዲሄድ ለመኑት።+ +11 ኢየሱስ ለ12 ደቀ መዛሙርቱ መመሪያ ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ በሌሎች ከተሞች ለማስተማርና ለመስበክ ሄደ።+ +2 ዮሐንስ በእስር ቤት ሆኖ+ ክርስቶስ ስላከናወናቸው ሥራዎች ሲሰማ ደቀ መዛሙርቱን በመላክ+ +3 “ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ሲል ጠየቀው።+ +4 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የምትሰሙትንና የምታዩትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፤+ +5 ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤+ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤+ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።+ +6 በእኔ ምክንያት የማይሰናከል ደስተኛ ነው።”+ +7 መልእክተኞቹ ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ ይናገር ጀመር፦ “ወደ ምድረ በዳ የሄዳችሁት ምን ለማየት ነበር?+ ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆ?+ +8 ታዲያ ምን ለማየት ነበር የሄዳችሁት? ምርጥ ልብስ* የለበሰ ሰው ለማየት? ምርጥ ልብስ የለበሱማ የሚገኙት በነገሥታት ቤት ነው። +9 ታዲያ ለምን ሄዳችሁ? ነቢይ ለማየት? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጥ ነው።+ +10 ‘እነሆ፣ ከፊትህ እየሄደ መንገድህን እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ!’+ ተብሎ የተጻፈው ስለ እሱ ነው። +11 እውነት እላችኋለሁ፣ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፤ ሆኖም በመንግሥተ ሰማያት ዝቅተኛ የሆነው እንኳ ይበልጠዋል።+ +12 መንግሥተ ሰማያት ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሰዎች የሚጋደሉለት ግብ ሆኗል፤ በተጋድሏቸው የሚጸኑም ያገኙታል።+ +13 ነቢያትና ሕጉ በሙሉ እስከ ዮሐንስ ዘመን ድረስ ተንብየዋልና፤+ +14 እንግዲህ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆናችሁ ‘ይመጣል የተባለው ኤልያስ’ እሱ ነው።+ +15 ጆሮ ያለው ይስማ። +16 “ይህን ትውልድ ከማን ጋር ላመሳስለው?+ በገበያ ስፍራ ተቀምጠው ጓደኞቻቸውን እየተጣሩ እንዲህ ከሚሉ ልጆች ጋር ይመሳሰላል፦ +17 ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ እናንተ ግን አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ እናንተ ግን በሐዘን ደረታችሁን አልደቃችሁም።’ +18 በተመሳሳይም ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ ሰዎች ግን ‘ጋኔን አለበት’ አሉ። +19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤+ ሰዎች ግን ‘እዩ፣ ይህን ሆዳምና ለወይን ጠጅ ያደረ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኃጢአተኞች ወዳጅ’ አሉ።+ የሆነ ሆኖ፣ ጥበብ ጻድቅ መሆኗ* በሥራዋ* ተረጋግጧል።”+ +20 ከዚያም ብዙ ተአምራት የፈጸመባቸውን ከተሞች ንስሐ ባለመግባታቸው የተነሳ እንዲህ ሲል ይነቅፋቸው ጀመር፦ +21 “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ ውስጥ የተደረጉት ተአምራት በጢሮስና በሲዶና* ተደርገው ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ማቅ ለብሰውና አመድ ላይ ተቀምጠው ንስሐ በገቡ ነበር።+ +22 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።+ +23 አንቺም ቅፍርናሆም+ ወደ ሰማይ ከፍ የምትዪ ይመስልሻል? በፍጹም! ወደ መቃብር* ትወርጃለሽ፤+ ምክንያቱም በአንቺ ውስጥ የተደረጉት ተአምራት በሰዶም ተደርገው ቢሆን ኖሮ እስከ ዛሬ በኖረች ነበር። +24 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም ምድር ይቀልላታል።”+ +25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ።+ +26 አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ የአንተ ፈቃድ ነውና። +27 አባቴ ሁሉንም ነገር ለእኔ ሰጥቶኛል፤+ ከአብ በስተቀር ወልድን በሚገባ የሚያውቅ የለም፤+ ከወልድና ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በስተቀር አብን በሚገባ የሚያውቅ ማንም የለም።+ +28 እናንተ የደከማችሁና ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እረፍት እሰጣችኋለሁ። +29 ቀንበሬን ተሸከሙ፤* ከእኔም ተማሩ፤* እኔ ገርና* በልቤ ትሑት ነኝ፤+ ለራሳችሁም* እረፍት ታገኛላችሁ። +30 ቀንበሬ ልዝብ፣* ሸክሜም ቀላል ነውና።” +2 በንጉሥ ሄሮድስ* ዘመን+ ኢየሱስ በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም+ ከተወለደ በኋላ ኮከብ ቆጣሪዎች* ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፣ +2 “የተወለደው የአይሁዳውያን ንጉሥ የሚገኘው የት ነው?+ በምሥራቅ ሳለን ኮከቡን በማየታችን ልንሰግድለት* መጥተናል” አሉ። +3 ንጉሥ ሄሮድስና መላው የኢየሩሳሌም ሕዝብ ይህን ሲሰሙ ተሸበሩ። +4 ንጉሡም የሕዝቡን የካህናት አለቆችና ጸሐፍት በሙሉ ሰብስቦ ክርስቶስ* የት እንደሚወለድ ጠየቃቸው። +5 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም+ ነው፤ ምክንያቱም ነቢዩ እንዲህ ብሎ ጽፏል፦ +6 ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተልሔም ሆይ፣ ለሕዝቤ ለእስራኤል እረኛ የሚሆን ገዢ ከአንቺ ስለሚወጣ በይሁዳ ገዢዎች ዘንድ ከሁሉ የተናቅሽ ከተማ አትሆኚም።’”+ +7 ከዚያም ሄሮድስ ኮከብ ቆጣሪዎቹን በድብቅ ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ጊዜ በትክክል አረጋገጠ። +8 ኮከብ ቆጣሪዎቹንም “ሄዳችሁ ሕፃኑን በደንብ ፈልጉ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔም ሄጄ እንድሰግድለት መጥታችሁ ንገሩኝ” ብሎ ወደ ቤተልሔም ላካቸው። +9 እነሱም ንጉሡ የነገራቸውን ከሰሙ በኋላ ጉዟቸውን ቀጠሉ፤ እነሆም፣ በምሥራቅ ሳሉ ያዩት ኮከብ+ ሕፃኑ ባለበት ቦታ እስከቆመበት ጊዜ ድረስ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር። +10 ኮከቡ መቆሙን ሲያዩ በጣም ተደሰቱ። +11 ወደ ቤት ሲገቡም ልጁን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት።* ዕቃ መያዣቸውንም ከፍተው ወርቅ፣ ነጭ ዕጣንና ከርቤ በስጦታ መልክ አቀረቡለት። +12 ይሁንና ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ በሕልም መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ስለተሰጣቸው+ በሌላ መንገድ አድርገው ወደ አገራቸው ሄዱ። +13 እነሱ ከሄዱ በኋላ የይሖዋ* መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ+ “ሄሮድስ ሕፃኑን አፈላልጎ ሊገድለው ስላሰበ ተነስ፣ ሕፃኑንና እ���ቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፤ እኔ እስካሳውቅህም ድረስ እዚያው ቆይ” አለው። +14 ስለዚህ ዮሴፍ ተነሳ፤ ሕፃኑንና የሕፃኑን እናት ይዞ በሌሊት ወደ ግብፅ ሄደ። +15 ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ እዚያው ቆየ። በመሆኑም ይሖዋ* “ልጄን ከግብፅ ጠራሁት”+ ብሎ በነቢዩ አማካኝነት የተናገረው ቃል ተፈጸመ። +16 ከዚያም ሄሮድስ ኮከብ ቆጣሪዎቹ እንዳታለሉት ሲያውቅ በጣም ተናደደ፤ ኮከቡ የታየበትን ጊዜ በተመለከተ ከኮከብ ቆጣሪዎቹ ባገኘው መረጃ መሠረት+ ሰዎች ልኮ በቤተልሔምና በአካባቢዋ ሁሉ የሚገኙትን ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑትን ወንዶች ልጆች በሙሉ አስገደለ። +17 በዚህ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው የሚከተለው ቃል ተፈጸመ፦ +18 “የለቅሶና የዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ። ራሔል+ ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ ልጆቿ ስለሌሉ ልትጽናና አልቻለችም።”+ +19 ሄሮድስ ከሞተ በኋላ የይሖዋ* መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ+ +20 “ተነስ፣ የሕፃኑን ሕይወት* ለማጥፋት የሚፈልጉት ሰዎች ስለሞቱ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ምድር ተመለስ” አለው። +21 ዮሴፍም ተነሳ፤ ሕፃኑንና የሕፃኑን እናት ይዞ ወደ እስራኤል ምድር ተመለሰ። +22 ሆኖም አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ፋንታ ይሁዳን እየገዛ እንዳለ በመስማቱ ወደዚያ መሄድ ፈራ። በተጨማሪም በሕልም መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ስለተሰጠው+ ወደ ገሊላ+ ምድር ሄደ። +23 ደግሞም “የናዝሬት ሰው* ይባላል” ተብሎ በነቢያት የተነገረው+ ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት+ ወደምትባል ከተማ መጥቶ መኖር ጀመረ። +26 ኢየሱስ ይህን ሁሉ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ +2 “እንደምታውቁት ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ* ይከበራል፤+ የሰው ልጅም በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አልፎ ይሰጣል።”+ +3 በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ቀያፋ+ ተብሎ በሚጠራው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተሰብስበው +4 የተንኮል ዘዴ በመጠቀም ኢየሱስን ለመያዝና* ለመግደል ሴራ ጠነሰሱ።+ +5 ይሁን እንጂ “በሕዝቡ መካከል ሁከት እንዳይፈጠር በበዓሉ ወቅት መሆን የለበትም” ይሉ ነበር። +6 ኢየሱስ በቢታንያ፣ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በነበረው በስምዖን+ ቤት ሳለ +7 አንዲት ሴት በጣም ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እሱ ቀረበች፤ እየበላ ሳለም ዘይቱን ራሱ ላይ ታፈስ ጀመር። +8 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲያዩ ተቆጥተው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሁሉ ብክነት ለምንድን ነው? +9 ይህ ዘይት እኮ በውድ ዋጋ ተሸጦ ለድሆች ሊሰጥ ይችል ነበር።” +10 ኢየሱስ ስለ ምን እየተነጋገሩ እንዳለ አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ይህችን ሴት ለምን ታስቸግሯታላችሁ? እሷ ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች። +11 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤+ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።+ +12 ይህች ሴት ዘይቱን በሰውነቴ ላይ ስታፈስ እኔን ለቀብር ማዘጋጀቷ ነው።+ +13 እውነት እላችኋለሁ፣ በመላው ዓለም ይህ ምሥራች በሚሰበክበት ቦታ ሁሉ ይህች ሴት ያደረገችውም መታሰቢያ ሆኖ ይነገርላታል።”+ +14 ከዚህ በኋላ፣ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ+ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ+ +15 “እሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ምን ትሰጡኛላችሁ?” አላቸው።+ እነሱም 30 የብር ሳንቲሞች* ሊሰጡት ተስማሙ።+ +16 ስለዚህ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት ምቹ አጋጣሚ ይፈልግ ነበር። +17 የቂጣ* በዓል+ በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው “ፋሲካን እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።+ +18 እሱም “ወደ ከተማ ሄዳችሁ እገሌ የተባለውን ሰው፣ ‘መምህሩ “የተወሰነው ጊዜዬ ደርሷል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በቤትህ አ���ብራለሁ” ብሏል’ በሉት” አላቸው። +19 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ። +20 በመሸም ጊዜ+ ከ12 ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።+ +21 እየበሉ ሳሉም “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።+ +22 እነሱም በዚህ እጅግ አዝነው ሁሉም ተራ በተራ “ጌታ ሆይ፣ እኔ እሆን?” ይሉት ጀመር። +23 እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር በሳህኑ ውስጥ የሚያጠቅሰው ነው።+ +24 እርግጥ፣ የሰው ልጅ ስለ እሱ በተጻፈው መሠረት ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው+ ለዚያ ሰው ግን ወዮለት!+ ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር።”+ +25 አሳልፎ ሊሰጠው የተዘጋጀው ይሁዳም “ረቢ፣ እኔ እሆን?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም “አንተው ራስህ ተናገርከው” አለው። +26 እየበሉም ሳሉ ኢየሱስ ቂጣ አንስቶ ከባረከ በኋላ ቆረሰው፤+ ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ በመስጠት “እንኩ፣ ብሉ። ይህ ሥጋዬን ያመለክታል” አለ።+ +27 ጽዋ አንስቶም አምላክን ካመሰገነ በኋላ ሰጣቸው፤ እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁም ከዚህ ጠጡ፤+ +28 ይህ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ+ የሚፈሰውን+ ‘የቃል ኪዳን+ ደሜን’+ ያመለክታል። +29 ነገር ግን እላችኋለሁ፦ በአባቴ መንግሥት አዲሱን ወይን ከእናንተ ጋር እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከአሁን በኋላ ከዚህ ወይን አልጠጣም።”+ +30 በመጨረሻ የውዳሴ መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዱ።+ +31 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’+ ተብሎ ስለተጻፈ በዚህች ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ላይ በሚደርሰው ነገር የተነሳ ትሰናከላላችሁ። +32 ከተነሳሁ በኋላ ግን ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ።”+ +33 ይሁንና ጴጥሮስ መልሶ “ሌሎቹ ሁሉ በአንተ ምክንያት ቢሰናከሉ እንኳ እኔ ፈጽሞ አልሰናከልም!” አለው።+ +34 ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፣ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ አንተ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው።+ +35 ጴጥሮስም “አብሬህ መሞት ቢያስፈልገኝ እንኳ በምንም ዓይነት አልክድህም” አለው።+ የቀሩት ደቀ መዛሙርትም ሁሉ እንደዚሁ አሉ። +36 ከዚያም ኢየሱስ ከእነሱ ጋር ጌትሴማኒ ወደተባለ ቦታ መጣ፤+ ደቀ መዛሙርቱንም “ወደዚያ ሄጄ በምጸልይበት ጊዜ እናንተ እዚህ ተቀመጡ” አላቸው።+ +37 ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዴዎስ ልጆች ይዞ ከሄደ በኋላ እጅግ ያዝንና ይረበሽ ጀመር።+ +38 ከዚያም “እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ።* እዚህ ሁኑና ከእኔ ጋር ነቅታችሁ ጠብቁ” አላቸው።+ +39 ትንሽ ወደ ፊት ራቅ በማለት በግንባሩ ተደፍቶ “አባቴ ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ+ ከእኔ ይለፍ። ሆኖም እንደ እኔ ፈቃድ ሳይሆን እንደ አንተ ፈቃድ ይሁን”+ ብሎ ጸለየ።+ +40 ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸውና ጴጥሮስን እንዲህ አለው፦ “ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት እንኳ ነቅታችሁ መጠበቅ አልቻላችሁም?+ +41 ወደ ፈተና እንዳትገቡ+ ነቅታችሁ ጠብቁ፤+ ሳታሰልሱም ጸልዩ።+ እርግጥ፣ መንፈስ ዝግጁ* ነው፤ ሥጋ* ግን ደካማ ነው።”+ +42 እንደገናም ሄዶ ለሁለተኛ ጊዜ “አባቴ ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ሳልጠጣው ይለፍ። ካልሆነ ግን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም”+ ሲል ጸለየ። +43 ዳግመኛም ተመልሶ ሲመጣ እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ስለነበር ተኝተው አገኛቸው። +44 እንደገናም ትቷቸው ሄደና ለሦስተኛ ጊዜ ስለዚያው ነገር ደግሞ ጸለየ። +45 ከዚያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ይህ የእንቅልፍና የእረፍት ሰዓት ነው? እነሆ፣ የሰው ልጅ ለኃጢአተኞች አልፎ የሚሰጥበት ሰዓት ደርሷል። +46 ተነሱ፣ እንሂድ። እነሆ፣ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል።” +47 ገና እየተናገረ ሳለ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፤ ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች የተላኩ ሰይፍና ቆመጥ የያዙ ብዙ ሰዎችም አብረውት ነበሩ።+ +48 አሳልፎ የሚሰጠውም “እኔ የምስመው ሰው እሱ ነው፤ ያዙት” በማለት ምልክት ሰጥቷቸው ነበር። +49 ይሁዳም በቀጥታ ወደ ኢየሱስ በመሄድ “ረቢ! ሰላም ለአንተ ይሁን” ብሎ ሳመው። +50 ኢየሱስ ግን “ወዳጄ፣ እዚህ የተገኘህበት ዓላማ ምንድን ነው?” አለው።+ በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ቀርበው ኢየሱስን ያዙት፤ አሰሩትም። +51 ሆኖም ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ሰዶ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቆረጠው።+ +52 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፤+ ሰይፍ የሚመዙ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ።+ +53 ለመሆኑ በዚህች ቅጽበት ከ12 ሌጌዎን* የሚበልጡ መላእክት እንዲልክልኝ አባቴን መጠየቅ የማልችል ይመስልሃል?+ +54 እንዲህ ከሆነ ታዲያ፣ እንደዚህ ሊሆን ይገባል የሚሉት ቅዱሳን መጻሕፍት እንዴት ይፈጸማሉ?” +55 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ የመጣችሁት እኔን ለመያዝ ነው? በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ አስተምር ነበር፤+ ሆኖም ያን ጊዜ አልያዛችሁኝም።+ +56 ይህ ሁሉ የሆነው ግን በነቢያት መጻሕፍት* የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።”+ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ።+ +57 ኢየሱስን ያሰሩት ሰዎች ጸሐፍትና ሽማግሌዎች ወደተሰበሰቡበት+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ+ ወሰዱት። +58 ይሁንና ጴጥሮስ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ በርቀት ይከተለው ነበር፤ ወደ ውስጥ ከገባ በኋላም መጨረሻውን ለማየት ከቤቱ አገልጋዮች ጋር ተቀመጠ።+ +59 በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና መላው የሳንሄድሪን ሸንጎ ኢየሱስን ለመግደል በእሱ ላይ የሐሰት የምሥክርነት ቃል እየፈለጉ ነበር።+ +60 ይሁንና ብዙ የሐሰት ምሥክሮች ቢቀርቡም ምንም ማስረጃ አላገኙም።+ በኋላ ሁለት ሰዎች ቀርበው +61 “ይህ ሰው ‘የአምላክን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ ልሠራው እችላለሁ’ ብሏል” አሉ።+ +62 በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ቆሞ “ምንም መልስ አትሰጥም? እነዚህ ሰዎች በአንተ ላይ ስለሰጡት ምሥክርነት ምን ትላለህ?” አለው።+ +63 ኢየሱስ ግን ዝም አለ።+ ሊቀ ካህናቱም “አንተ የአምላክ ልጅ ክርስቶስ መሆን አለመሆንህን እንድትነግረን በሕያው አምላክ አስምልሃለሁ!” አለው።+ +64 ኢየሱስም “አንተው ራስህ ተናገርከው። ነገር ግን እላችኋለሁ፦ ከዚህ በኋላ የሰው ልጅ+ በኃያሉ ቀኝ ተቀምጦ+ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ”+ አለው። +65 በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ እንዲህ አለ፦ “አምላክን ተሳድቧል! ከዚህ በላይ ምን ምሥክሮች ያስፈልጉናል? ስድቡን እንደሆነ እናንተም ሰምታችኋል። +66 እንግዲህ ምን ትላላችሁ?” እነሱም “ሞት ይገባዋል”+ ብለው መለሱ። +67 ከዚያም ፊቱ ላይ ተፉበት፤+ በቡጢም መቱት።+ ሌሎቹም በጥፊ እየመቱት+ +68 “ክርስቶስ ሆይ፣ ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደመታህ ንገረን?” አሉት። +69 ጴጥሮስ ከቤት ውጭ፣ ግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት አገልጋይ ወደ እሱ መጥታ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው።+ +70 እሱ ግን “ስለ ምን እየተናገርሽ እንዳለ አላውቅም” በማለት በሁሉም ፊት ካደ። +71 ወደ ግቢው መግቢያ አካባቢ ሲሄድ ሌላ ሴት አየችውና በዚያ ለነበሩት ሰዎች “ይህ ሰው ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበር” አለች።+ +72 እሱም “ሰውየውን አላውቀውም!” ብሎ በመማል ዳግመኛ ካደ። +73 ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካባቢው ቆመው የነበሩት መጥተው ጴጥሮስን “አነጋገርህ* ያስታውቃል፤ በእርግጥ አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” አሉት። +74 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “��ውየውን አላውቀውም!” በማለት ይምልና ራሱን ይረግም ጀመር። ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ። +75 ጴጥሮስም “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ”+ ሲል ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አስታወሰ። ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ። +4 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፣ ዲያብሎስ+ ይፈትነው+ ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ መራው። +2 እሱም 40 ቀንና 40 ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። +3 ፈታኙም+ ቀርቦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ እነዚህ ድንጋዮች ዳቦ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው። +4 እሱ ግን “‘ሰው ከይሖዋ* አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰ።+ +5 ከዚያም ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ+ ከወሰደው በኋላ በቤተ መቅደሱ አናት* ላይ አቁሞ+ +6 እንዲህ አለው፦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል።’ እንዲሁም ‘እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው በእጃቸው ያነሱሃል።’”+ +7 ኢየሱስም “‘አምላክህን ይሖዋን* አትፈታተነው’ ተብሎም ተጽፏል” አለው።+ +8 እንደገናም ዲያብሎስ በጣም ረጅም ወደሆነ ተራራ ወስዶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉና ክብራቸውን አሳየው።+ +9 ከዚያም “አንድ ጊዜ ተደፍተህ ብታመልከኝ እነዚህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው። +10 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “አንተ ሰይጣን፣ ከፊቴ ራቅ! ‘ይሖዋ* አምላክህን ብቻ አምልክ፤+ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’+ ተብሎ ተጽፏልና” አለው። +11 ከዚያም ዲያብሎስ ትቶት ሄደ፤+ እነሆም፣ መላእክት መጥተው ያገለግሉት ጀመር።+ +12 ኢየሱስ፣ ዮሐንስ እንደታሰረ+ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ሄደ።+ +13 ከዚያም ከናዝሬት ወጥቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አውራጃዎች፣ በባሕሩ* አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም+ መጥቶ መኖር ጀመረ፤ +14 ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ የተነገረው የሚከተለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፦ +15 “ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ወደ ባሕሩ* በሚወስደው መንገድ አጠገብ ያላችሁ የዛብሎን ምድር፣ የንፍታሌም ምድርና የአሕዛብ ገሊላ ሆይ! +16 በጨለማ ውስጥ ያሉ ሰዎች ታላቅ ብርሃን አዩ፤ ሞት በሰዎች ላይ ባጠላበት ምድር ላሉም ብርሃን+ ወጣላቸው።”+ +17 ከዚያን ጊዜ አንስቶ ኢየሱስ “መንግሥተ ሰማያት ስለቀረበ ንስሐ ግቡ” እያለ ይሰብክ ጀመር።+ +18 በገሊላ ባሕር* አጠገብ ሲሄድ ሁለቱን ወንድማማቾች ማለትም ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራውን ስምዖንን+ እና ወንድሙን እንድርያስን አያቸው፤ እነሱም ዓሣ አጥማጆች+ ስለነበሩ መረባቸውን ወደ ባሕሩ እየጣሉ ነበር። +19 እሱም “ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው።+ +20 እነሱም ወዲያውኑ መረቦቻቸውን ትተው ተከተሉት።+ +21 ከዚያ እልፍ እንዳለ ሌሎች ሁለት ወንድማማቾችን ማለትም የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን አያቸው።+ እነሱም ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ላይ ሆነው መረቦቻቸውን እየጠገኑ ነበር፤ ኢየሱስም ጠራቸው።+ +22 እነሱም ወዲያውኑ ጀልባዋንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት። +23 ከዚያም በምኩራቦቻቸው+ እያስተማረና የመንግሥቱን ምሥራች እየሰበከ እንዲሁም በሕዝቡ መካከል ያለውን ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እየፈወሰ+ በመላዋ ገሊላ ተዘዋወረ።+ +24 ስለ እሱም የተወራው ወሬ በመላዋ ሶርያ ተዳረሰ፤ ሰዎችም በተለያየ በሽታና ከባድ ሕመም የሚሠቃዩትን፣+ ጋኔን የያዛቸውን፣+ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና+ ሽባዎችን ሁሉ ወደ እሱ አመጡ፤ እሱም ፈወሳቸው። +25 ከዚህም የተነሳ ከገሊላ፣ ከዲካፖሊስ፣* ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ማዶ የመጡ እጅግ ብዙ ሰዎች ተከተሉት። +16 ከዚያም ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ እሱ መጡ፤ ሊፈትኑትም ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።+ +2 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ሲመሽ ‘ሰማዩ ስለ ቀላ ብራ ይሆናል’ ትላላችሁ፤ +3 ጠዋት ላይ ደግሞ ‘ሰማዩ ቢቀላም ደመና ስለሆነ ዛሬ ብርድ ይሆናል፣ ዝናብም ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን መልክ በማየት መተርጎም ትችላላችሁ፤ የዘመኑን ምልክት ግን መተርጎም አትችሉም። +4 ክፉና አመንዝራ* ትውልድ ሁልጊዜ ምልክት ማየት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከዮናስ ምልክት በስተቀር+ ምንም ምልክት አይሰጠውም።”+ ይህን ከተናገረ በኋላ ትቷቸው ሄደ። +5 ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕሩ ማዶ ተሻገሩ፤ በዚህ ጊዜ ዳቦ መያዝ ረስተው ነበር።+ +6 ኢየሱስ “ተጠንቀቁ፣ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠበቁ” አላቸው።+ +7 እነሱም እርስ በርሳቸው “ዳቦ ስላልያዝን ይሆናል” ይባባሉ ጀመር። +8 ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ዳቦ ስላልያዝን ነው ብላችሁ ለምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ? +"9 አሁንም ነጥቡ አልገባችሁም? ወይስ አምስቱ ዳቦ ለ5,000ዎቹ ሰዎች በቅቶ ከዚያ የተረፈውን ምን ያህል ቅርጫት እንደሰበሰባችሁ አታስታውሱም?+" +"10 ወይስ ሰባቱ ዳቦ ለ4,000ዎቹ ሰዎች በቅቶ ከዚያ የተረፈውን በትላልቅ ቅርጫት ምን ያህል እንደሰበሰባችሁ ትዝ አይላችሁም?+" +11 ታዲያ የነገርኳችሁ ስለ ዳቦ እንዳልሆነ እንዴት አታስተውሉም? እንግዲህ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ።”+ +12 በዚህ ጊዜ ተጠንቀቁ ያላቸው ከዳቦ እርሾ ሳይሆን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንደሆነ ገባቸው። +13 ኢየሱስ ወደ ቂሳርያ ፊልጵስዩስ አካባቢ በመጣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች፣ የሰውን ልጅ ማን ነው ይሉታል?” ሲል ጠየቃቸው።+ +14 እነሱም “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣+ ሌሎች ኤልያስ፣+ ሌሎች ደግሞ ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ” አሉት። +15 እሱም “እናንተስ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ?” አላቸው። +16 ስምዖን ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ፣+ የሕያው አምላክ ልጅ ነህ”+ ብሎ መለሰለት። +17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “የዮናስ ልጅ ስምዖን፣ ይህን የገለጠልህ ሥጋና ደም ሳይሆን* በሰማያት ያለው አባቴ ስለሆነ ደስ ይበልህ።+ +18 ደግሞም እልሃለሁ፦ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤+ በዚህች ዓለት+ ላይ ጉባኤዬን እገነባለሁ፤ የመቃብር* በሮችም አያሸንፏትም። +19 የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ ቀድሞውኑ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ እንዲሁም በምድር የምትፈታው ሁሉ ቀድሞውኑ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” +20 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እሱ ክርስቶስ መሆኑን ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አዘዛቸው።+ +21 ከዚያን ጊዜ አንስቶ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ እንዳለበት እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት እጅ ከባድ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ እንደሚገባው ብሎም በሦስተኛው ቀን እንደሚነሳ ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጽላቸው ጀመር።+ +22 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው በመውሰድ “ጌታ ሆይ፣ በራስህ ላይ እንዲህ አትጨክን፤ በምንም ዓይነት እንዲህ ያለ ነገር አይደርስብህም” እያለ ይገሥጸው ጀመር።+ +23 እሱ ግን ጀርባውን በመስጠት ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፣ ሰይጣን!* የሰውን እንጂ የአምላክን ሐሳብ ስለማታስብ እንቅፋት ሆነህብኛል” አለው።+ +24 ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ፤ የራሱን የመከራ እንጨት* ይሸከም፤ ያለማቋረጥም ይከተለኝ።+ +25 ሕይወቱን* ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔ ሲል ሕይወቱን* የሚያጣ ሁሉ ግን ያገኛታል።+ +26 ደግሞስ አንድ ሰው ዓለምን ሁሉ የራሱ ቢያደርግ፣ ሕይወቱን* ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል?+ ወይስ ሰው ለሕይወቱ* ምትክ የሚሆን ምን ነገር ሊሰጥ ይችላል?+ +27 የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣልና፤ ከዚያም ለእያንዳንዱ እንደ ምግባሩ ይከፍለዋል።+ +28 እውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆሙት መካከል አንዳንዶች የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ ፈጽሞ ሞትን አይቀምሱም።”+ +6 “ሰዎች እንዲያዩላችሁ ብላችሁ+ የጽድቅ ሥራችሁን በእነሱ ፊት እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ አለዚያ በሰማያት ካለው አባታችሁ ምንም ብድራት አታገኙም። +2 በመሆኑም ምጽዋት* በምትሰጡበት ጊዜ በሰዎች ዘንድ ለመከበር ብለው በምኩራቦችና በጎዳናዎች ላይ አስቀድመው መለከት እንደሚያስነፉ ግብዞች አትሁኑ። እውነት እላችኋለሁ፣ እነሱ ሙሉ ብድራታቸውን ተቀብለዋል። +3 አንተ ግን ምጽዋት ስትሰጥ ቀኝ እጅህ የሚያደርገውን ግራ እጅህ አይወቅ፤ +4 ይህም ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ያስችላል። በስውር የሚያይ አባትህም መልሶ ይከፍልሃል።+ +5 “በተጨማሪም በምትጸልዩበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤+ እነሱ ሰዎች እንዲያዩአቸው+ በምኩራቦችና በየአውራ ጎዳናው ማዕዘኖች ላይ ቆመው መጸለይ ይወዳሉና። እውነት እላችኋለሁ፣ እነሱ ሙሉ ብድራታቸውን ተቀብለዋል። +6 አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በርህንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ።+ በስውር የሚያይ አባትህም መልሶ ይከፍልሃል። +7 በምትጸልዩበት ጊዜ አሕዛብ እንደሚያደርጉት አንድ ዓይነት ነገር ደጋግማችሁ አታነብንቡ፤ እነሱ ቃላት በማብዛት ጸሎታቸው የሚሰማላቸው ይመስላቸዋል። +8 ስለዚህ እንደ እነሱ አትሁኑ፤ አባታችሁ ገና ሳትለምኑት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃልና።+ +9 “እንግዲያው እናንተ በዚህ መንገድ ጸልዩ፦+ “‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ+ ይቀደስ።*+ +10 መንግሥትህ+ ይምጣ። ፈቃድህ+ በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም።*+ +11 የዕለቱን ምግባችንን* ዛሬ ስጠን፤+ +12 የበደሉንን* ይቅር እንዳልን በደላችንን* ይቅር በለን።+ +13 ከክፉው+ አድነን* እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’+ +14 “የበደሏችሁን ሰዎች ይቅር ካላችሁ በሰማይ ያለው አባታችሁ ይቅር ይላችኋል፤+ +15 እናንተ ግን የበደሏችሁን ሰዎች ይቅር ካላላችሁ አባታችሁም በደላችሁን ይቅር አይላችሁም።+ +16 “በምትጾሙበት+ ጊዜ እንደ ግብዞች ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ እነሱ መጾማቸው በሰው ዘንድ እንዲታወቅላቸው ፊታቸውን ያጠወልጋሉ።*+ እውነት እላችኋለሁ፣ እነሱ ሙሉ ብድራታቸውን ተቀብለዋል። +17 አንተ ግን ስትጾም ራስህን ተቀባ፤ ፊትህንም ታጠብ፤ +18 እንዲህ ካደረግክ የምትጾመው በሰው ለመታየት ሳይሆን በስውር ላለው አባትህ ስትል ብቻ ይሆናል። በስውር የሚያይ አባትህም መልሶ ይከፍልሃል። +19 “ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸውና ሌባ ገብቶ ሊሰርቀው በሚችልበት በምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ።*+ +20 ከዚህ ይልቅ ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸውና+ ሌባ ገብቶ ሊሰርቀው በማይችልበት በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ።+ +21 ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይሆናልና። +22 “የሰውነት መብራት ዓይን ነው።+ ስለሆነም ዓይንህ በአንድ ነገር ላይ ያተኮረ* ከሆነ መላ ሰውነትህ ብሩህ* ይሆናል። +23 ይሁን እንጂ ዓይንህ ምቀኛ*+ ከሆነ መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን በእርግጥ ጨለማ ከሆነ ጨለማው እንዴት ድቅድቅ ይሆን! +24 “ለሁለት ጌቶች ባሪያ ሆኖ መገዛት የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል+ ወይም አንዱን ደግፎ ሌላውን ይንቃል። ለአምላክም ለሀብትም በአንድነት መገዛት አትችሉም።+ +25 “ስለዚህ እላችኋለ��፦ ስለ ሕይወታችሁ* ምን እንበላለን፣ ምንስ እንጠጣለን ወይም ደግሞ ስለ ሰውነታችሁ ምን እንለብሳለን ብላችሁ+ አትጨነቁ።*+ ሕይወት* ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥም?+ +26 የሰማይ ወፎችን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤+ እነሱ አይዘሩም፣ አያጭዱም ወይም በጎተራ አያከማቹም፤ ይሁንና በሰማይ ያለው አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከእነሱ አትበልጡም? +27 ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ርዝማኔ ላይ አንድ ክንድ* መጨመር የሚችል ይኖራል?+ +28 ስለ ልብስስ ቢሆን ለምን ትጨነቃላችሁ? እስቲ የሜዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ አይለፉም ወይም አይፈትሉም፤ +29 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ያን ያህል ክብር የነበረው ሰለሞን+ እንኳ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዷ አላጌጠም። +30 አምላክ ዛሬ ታይቶ ነገ ወደ ምድጃ የሚጣለውን የሜዳ ተክል እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም? +31 ስለዚህ ‘ምን እንበላለን?’ ወይም ‘ምን እንጠጣለን?’ አሊያም ‘ምን እንለብሳለን?’+ ብላችሁ ፈጽሞ አትጨነቁ።+ +32 እነዚህ ነገሮች ሁሉ አሕዛብ አጥብቀው የሚፈልጓቸው ናቸው። በሰማይ የሚኖረው አባታችሁ እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። +33 “እንግዲያው ከሁሉ አስቀድማችሁ የአምላክን መንግሥትና ጽድቅ ፈልጉ፤* እነዚህም ነገሮች ሁሉ ይሰጧችኋል።+ +34 ስለዚህ ስለ ነገ ፈጽሞ አትጨነቁ፤+ ምክንያቱም ነገ የራሱ የሆኑ የሚያስጨንቁ ነገሮች አሉት። እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ በቂ ችግር አለው። +25 “በተጨማሪም መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን+ ይዘው ሙሽራውን+ ሊቀበሉ ከወጡ አሥር ደናግል ጋር ሊመሳሰል ይችላል። +2 አምስቱ ሞኞች፣ አምስቱ ደግሞ ልባሞች* ነበሩ።+ +3 ሞኞቹ መብራታቸውን ቢይዙም መጠባበቂያ ዘይት አልያዙም ነበር፤ +4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በዕቃ ዘይት ይዘው ነበር። +5 ሙሽራው በዘገየ ጊዜ ሁሉም እንቅልፍ ተጫጫናቸውና ተኙ። +6 እኩለ ሌሊት ላይ ‘ሙሽራው እየመጣ ነው፤ ወጥታችሁ ተቀበሉት!’ የሚል ጫጫታ ተሰማ። +7 በዚህ ጊዜ ደናግሉ ሁሉ ተነስተው መብራቶቻቸውን አዘጋጁ።+ +8 ሞኞቹ ደናግል ልባሞቹን ‘መብራታችን ሊጠፋብን ስለሆነ ከያዛችሁት ዘይት ላይ ስጡን’ አሏቸው። +9 ልባሞቹም ‘ለእናንተ ከሰጠናችሁ ለእኛም ለእናንተም ላይበቃን ስለሚችል ወደ ሻጮች ሄዳችሁ ለራሳችሁ የተወሰነ ዘይት ብትገዙ ይሻላል’ ብለው መለሱላቸው። +10 ሊገዙ ሄደው ሳሉም ሙሽራው ደረሰ። ተዘጋጅተው የነበሩት ደናግልም ወደ ሠርጉ ድግስ ገቡ፤+ በሩም ተዘጋ። +11 በኋላም የቀሩት ደናግል መጥተው ‘ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣ ክፈትልን!’ አሉ።+ +12 እሱ ግን ‘እውነቴን ነው የምላችሁ፣ አላውቃችሁም’ አላቸው። +13 “እንግዲህ ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን ስለማታውቁ+ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ።+ +14 “ደግሞም መንግሥተ ሰማያት ባሪያዎቹን ጠርቶ ንብረቱን ለእነሱ በአደራ በመስጠት ወደ ሌላ አገር ለመሄድ ከተነሳ ሰው ጋር ይመሳሰላል።+ +15 ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው፣ ለአንዱ አምስት ታላንት፣* ለሌላው ሁለት፣ ለሌላው ደግሞ አንድ በመስጠት ወደ ሌላ አገር ሄደ። +16 አምስት ታላንት የተቀበለው ሰው ወዲያው ሄዶ ነገደበትና ሌላ አምስት ታላንት አተረፈ። +17 በተመሳሳይም ሁለት ታላንት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። +18 አንድ ታላንት ብቻ የተቀበለው ባሪያ ግን ሄዶ መሬት ቆፈረና ጌታው የሰጠውን ገንዘብ* ቀበረ። +19 “ከረጅም ጊዜ በኋላ የእነዚያ ባሪያዎች ጌታ መጥቶ ሒሳቡን ከባሪያዎቹ ጋር ተሳሰበ።+ +20 ስለዚህ አምስት ታላንት የተቀበለው ባሪያ ሌላ አምስት ተጨማሪ ታላንት ይዞ በመቅረብ ‘ጌታ ሆይ፣ አምስት ታላንት ሰጥተኸ�� ነበር፤ ይኸው ሌላ አምስት ታላንት አተረፍኩ’ አለ።+ +21 ጌታውም ‘ጎበዝ፣ አንተ ጥሩና ታማኝ ባሪያ! በጥቂት ነገሮች ታማኝ ሆነህ ተገኝተሃል። ስለዚህ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ።+ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።+ +22 ቀጥሎም ሁለት ታላንት የተቀበለው ባሪያ ቀርቦ ‘ጌታ ሆይ፣ ሁለት ታላንት ሰጥተኸኝ ነበር፤ ይኸው ሌላ ሁለት ታላንት አተረፍኩ’ አለ።+ +23 ጌታውም ‘ጎበዝ፣ አንተ ጥሩና ታማኝ ባሪያ! በጥቂት ነገሮች ታማኝ ሆነህ ተገኝተሃል። ስለዚህ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው። +24 “በመጨረሻም አንድ ታላንት የተቀበለው ባሪያ ቀርቦ እንዲህ አለው፦ ‘ጌታ ሆይ፣ አንተ ያልዘራኸውን የምታጭድ፣ ያልደከምክበትንም እህል የምትሰበስብ ኃይለኛ ሰው መሆንህን አውቃለሁ።+ +25 ስለዚህ ፈራሁ፤ ሄጄም ታላንትህን መሬት ውስጥ ቀበርኩት። ገንዘብህ ይኸውልህ።’ +26 ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፦ ‘አንተ ክፉና ሰነፍ ባሪያ፣ ያልዘራሁትን የማጭድ፣ ያልደከምኩበትንም እህል የምሰበስብ መሆኔን ታውቅ ኖሯል? +27 ይህን ካወቅክ ገንዘቤን፣* ገንዘብ ለዋጮች ጋ ማስቀመጥ ነበረብህ፤ እኔም ስመጣ ገንዘቤን ከነወለዱ እወስደው ነበር። +28 “‘ስለዚህ ታላንቱን ውሰዱበትና አሥር ታላንት ላለው ስጡት።+ +29 ምክንያቱም ላለው ሁሉ ይጨመርለታል፤ ደግሞም ይትረፈረፍለታል። የሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።+ +30 ይህን የማይረባ ባሪያ ውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት። በዚያም ያለቅሳል፤ ጥርሱንም ያፋጫል።’ +31 “የሰው ልጅ+ ከመላእክቱ ሁሉ ጋር+ በክብሩ ሲመጣ በክብራማ ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል። +32 ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ ሁሉ እሱም ሰዎችን አንዱን ከሌላው ይለያል። +33 በጎቹን+ በቀኙ፣ ፍየሎቹን ግን በግራው ያደርጋቸዋል።+ +34 “ከዚያም ንጉሡ በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከተመሠረተበት* ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። +35 ምክንያቱም ተርቤ አብልታችሁኛል፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል። እንግዳ ሆኜ አስተናግዳችሁኛል፤+ +36 ታርዤ* አልብሳችሁኛል።+ ታምሜ አስታማችሁኛል። ታስሬ ጠይቃችሁኛል።’+ +37 ከዚያም ጻድቃኑ መልሰው እንዲህ ይሉታል፦ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህ? ተጠምተህ አይተንስ መቼ አጠጣንህ?+ +38 እንግዳ ሆነህ አይተን መቼ አስተናገድንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? +39 ታመህ ወይም ታስረህ አይተን መቼ ጠየቅንህ?’ +40 ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ይቆጠራል’ ይላቸዋል።+ +41 “ከዚያም በግራው ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ የተረገማችሁ፣ ከእኔ ራቁ፤+ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀው+ ዘላለማዊ እሳት+ ሂዱ። +42 ምክንያቱም ተርቤ አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም። +43 እንግዳ ሆኜ አላስተናገዳችሁኝም፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ አልጠየቃችሁኝም።’ +44 እነሱም መልሰው ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን ሳናገለግልህ ቀረን?’ ይሉታል። +45 እሱም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ይህን ሳታደርጉ መቅረታችሁ ለእኔ እንዳላደረጋችሁት ይቆጠራል’ ይላቸዋል።+ +46 እነዚህ ወደ ዘላለም ጥፋት*+ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት+ ይሄዳሉ።” +10 ከዚያም ኢየሱስ 12ቱን ደቀ መዛሙርት ጠርቶ ርኩሳን መናፍስትን እንዲያዝዙ ሥልጣን ሰጣቸው፤+ ይህን ያደረገውም ርኩሳን መናፍስትን እንዲያስወጡ ��ንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እንዲፈውሱ ነው። +2 የ12ቱ ሐዋርያት ስም የሚከተለው ነው፦+ በመጀመሪያ፣ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና+ ወንድሙ እንድርያስ፣+ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣+ +3 ፊልጶስና በርቶሎሜዎስ፣+ ቶማስና+ ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ፣+ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ፣ +4 ቀነናዊው* ስምዖንና በኋላ ኢየሱስን የከዳው የአስቆሮቱ ይሁዳ።+ +5 ኢየሱስ እነዚህን 12ቱን የሚከተለውን መመሪያ በመስጠት ላካቸው፦+ “ወደ አሕዛብ አትሂዱ፤ ወደ ማንኛውም የሳምራውያን ከተማም+ አትግቡ፤ +6 ከዚህ ይልቅ ከእስራኤል ቤት ወደጠፉት በጎች ብቻ ሂዱ።+ +7 በምትሄዱበት ጊዜም ‘መንግሥተ ሰማያት ቀርቧል’ ብላችሁ ስበኩ።+ +8 የታመሙትን ፈውሱ፤+ የሞቱትን አስነሱ፤ የሥጋ ደዌ ያለባቸውን አንጹ፤ አጋንንትንም አስወጡ። በነፃ እንደተቀበላችሁ በነፃ ስጡ። +9 ወርቅ ወይም ብር አሊያም መዳብ በመቀነታችሁ አትያዙ፤+ +10 ወይም ለጉዞ የምግብ ከረጢት ወይም ሁለት ልብስ* ወይም ትርፍ ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤+ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።+ +11 “በምትገቡበት ማንኛውም ከተማ ወይም መንደር መልእክቱን መስማት የሚገባውን ሰው ፈልጉ፤ እስክትወጡም ድረስ እዚያው ቆዩ።+ +12 ወደ ቤትም ስትገቡ ቤተሰቡን ሰላም በሉ። +13 ቤቱ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ ሰላማችሁ ይድረሰው፤+ የማይገባው ከሆነ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለስ። +14 የሚቀበላችሁ ወይም ቃላችሁን የሚሰማ ሰው ካጣችሁ ከዚያ ቤት ወይም ከተማ ስትወጡ፣ የእግራችሁን አቧራ አራግፉ።*+ +15 እውነት እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ+ ይቀልላቸዋል። +16 “እነሆ፣ በተኩላዎች መካከል እንዳሉ በጎች እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ጠንቃቆች፣ እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ።+ +17 ሰዎች ለፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤+ በምኩራቦቻቸውም+ ይገርፏችኋል፤+ ስለዚህ ራሳችሁን ከእነሱ ጠብቁ። +18 ደግሞም በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ያቀርቧችኋል፤+ በዚያ ጊዜ ለእነሱም ሆነ ለአሕዛብ መመሥከር ትችላላችሁ።+ +19 ይሁን እንጂ አሳልፈው ሲሰጧችሁ እንዴት ወይም ምን ብለን እንመልሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ የምትናገሩት ነገር በዚያኑ ሰዓት ይሰጣችኋልና፤+ +20 በምትናገሩበት ጊዜ ብቻችሁን አይደላችሁም፤ ይልቁንም በእናንተ የሚናገረው የአባታችሁ መንፈስ ነው።+ +21 በተጨማሪም ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሳሉ፤ ደግሞም ያስገድሏቸዋል።+ +22 በስሜ የተነሳም ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል፤+ እስከ መጨረሻው የጸና* ግን ይድናል።+ +23 በአንድ ከተማ ስደት ሲያደርሱባችሁ ወደ ሌላ ከተማ ሽሹ፤+ እውነት እላችኋለሁ፣ የሰው ልጅ እስከሚመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተሞችና መንደሮች ፈጽሞ አታዳርሱም። +24 “ተማሪ* ከአስተማሪው፣ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም።+ +25 ተማሪ እንደ አስተማሪው፣ ባሪያም እንደ ጌታው ከሆነ በቂ ነው።+ ሰዎች የቤቱን ጌታ ብዔልዜቡል*+ ካሉት ቤተሰቦቹንማ እንዴት ከዚህ የከፋ አይሏቸው! +26 ስለዚህ አትፍሯቸው፤ የተሸፈነ ሁሉ መገለጡ፣ ሚስጥር የሆነም ሁሉ መታወቁ አይቀርም።+ +27 በጨለማ የነገርኳችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በሹክሹክታ የሰማችሁትንም በይፋ ስበኩ።+ +28 ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን* ግን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤+ ከዚህ ይልቅ ነፍስንም ሆነ ሥጋን በገሃነም* ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ።+ +29 ሁለት ድንቢጦች የሚሸጡት አነስተኛ ዋጋ ባላት ሳንቲም* አይደለም? ሆኖም ከእነሱ አንዷም እንኳ አባታችሁ ሳያውቅ መሬት ላይ አትወድቅም።+ +30 የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆ���ሯል። +31 ስለዚህ አትፍሩ፤ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።+ +32 “እንግዲያው በሰዎች ፊት ለሚመሠክርልኝ+ ሁሉ እኔም በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እመሠክርለታለሁ።+ +33 በሰዎች ፊት የሚክደኝን ሁሉ ግን እኔም በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እክደዋለሁ።+ +34 በምድር ላይ ሰላም ለማስፈን የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ የመጣሁት ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አይደለም።+ +35 እኔ የመጣሁት ወንድ ልጅን ከአባቱ፣ ሴት ልጅን ከእናቷ እንዲሁም ምራትን ከአማቷ ለመለያየት ነው።+ +36 በእርግጥም የሰው ጠላቶቹ የገዛ ቤተሰቦቹ ይሆናሉ። +37 ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ሁሉ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ሁሉ ለእኔ ሊሆን አይገባም።+ +38 የመከራውን እንጨት* የማይቀበልና የማይከተለኝ ሁሉ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።+ +39 ነፍሱን* ለማዳን የሚሞክር ሁሉ ያጣታል፤ ነፍሱን* ስለ እኔ አሳልፎ የሚሰጥ ሁሉ ግን ያገኛታል።+ +40 “እናንተን የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ እኔን የሚቀበል ሁሉ ደግሞ የላከኝን ይቀበላል።+ +41 ነቢይን ስለ ነቢይነቱ የሚቀበል ሁሉ የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤+ ጻድቅን ስለ ጻድቅነቱ የሚቀበል ሁሉ የጻድቅን ዋጋ ያገኛል። +42 እውነት እላችኋለሁ፣ የእኔ ደቀ መዝሙር በመሆኑ ምክንያት ከእነዚህ ከትናንሾቹ ለአንዱ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውኃ የሚሰጥ ሁሉ በምንም ዓይነት ዋጋውን አያጣም።”+ +14 በዚያን ጊዜ የአውራጃ ገዢ* የነበረው ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ሲሰማ+ +2 አገልጋዮቹን “ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው። ከሞት ተነስቷል ማለት ነው፤ እነዚህን ተአምራት መፈጸም የቻለውም ለዚህ ነው” አላቸው።+ +3 ሄሮድስ* የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት በሆነችው በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን ይዞ በሰንሰለት በማሰር ወህኒ አስገብቶት ነበር።+ +4 ዮሐንስ ሄሮድስን “እሷን እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር።+ +5 ሄሮድስ ሊገድለው ይፈልግ የነበረ ቢሆንም ሕዝቡ እንደ ነቢይ ይመለከተው ስለነበር ሕዝቡን ፈራ።+ +6 ሆኖም የሄሮድስ ልደት+ በተከበረበት ዕለት የሄሮድያዳ ልጅ በግብዣው ላይ በመጨፈር ሄሮድስን እጅግ ደስ አሰኘችው፤+ +7 በመሆኑም የጠየቀችውን ሁሉ ሊሰጣት በመሐላ ቃል ገባላት። +8 ከዚያም እናቷ በሰጠቻት ምክር መሠረት “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በዚህ ሳህን ስጠኝ” አለችው።+ +9 ንጉሡ ቢያዝንም ስለ መሐላውና አብረውት ይበሉ ስለነበሩት ሲል የዮሐንስ ራስ እንዲሰጣት አዘዘ። +10 ሰው ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ ቤት አስቆረጠ። +11 ራሱን በሳህን አምጥተው ለልጅቷ ሰጧት፤ እሷም ለእናቷ ሰጠቻት። +12 በኋላም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መጡና አስከሬኑን ወስደው ቀበሩት፤ ከዚያም መጥተው ለኢየሱስ ነገሩት። +13 ኢየሱስ ይህን ሲሰማ ብቻውን ለመሆን በጀልባ ተሳፍሮ ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ። ሕዝቡ ግን መሄዱን ሰምተው ከየከተማው እየወጡ በእግር ተከተሉት።+ +14 ኢየሱስ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሲመጣ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተመለከተና በጣም አዘነላቸው፤+ በመካከላቸው የነበሩትንም ሕመምተኞች ፈወሰ።+ +15 በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ ቀርበው “ቦታው ገለል ያለ ነው፤ ሰዓቱ ደግሞ ገፍቷል፤ ስለዚህ ሕዝቡ ወደ መንደሮቹ ሄደው ምግብ እንዲገዙ አሰናብታቸው” አሉት።+ +16 ይሁን እንጂ ኢየሱስ “መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው። +17 እነሱም “ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ በስተቀር እዚህ ምንም ነገር የለንም” አሉት። +18 እሱም “ያለውን ወደ እኔ አምጡት” አላቸው። +19 ሕዝቡንም ሣሩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ። ከዚያም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ፤+ ዳቦውን ከቆረሰ በኋ��ም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ እነሱ ደግሞ ለሕዝቡ ሰጡ። +20 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ +"21 የበሉትም ከሴቶችና ከትናንሽ ልጆች ሌላ 5,000 ወንዶች ነበሩ።+" +22 ወዲያውም፣ እሱ ሕዝቡን እያሰናበተ ሳለ ደቀ መዛሙርቱን ጀልባ ተሳፍረው ቀድመውት ወደ ማዶ እንዲሻገሩ ነገራቸው።+ +23 ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ለመጸለይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ።+ በመሸም ጊዜ በዚያ ብቻውን ነበር። +24 በዚህ ጊዜ ጀልባው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሜትሮች* ከየብስ ርቆ የነበረ ሲሆን ነፋሱ ወደ እነሱ ይነፍስ ስለነበር ማዕበሉ በጣም አስቸገራቸው። +25 ሆኖም ኢየሱስ በአራተኛው ክፍለ ሌሊት* በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነሱ መጣ። +26 ደቀ መዛሙርቱ በባሕሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ ደንግጠው “ምትሃት ነው!” አሉ። በፍርሃት ተውጠውም ጮኹ። +27 ሆኖም ኢየሱስ ወዲያውኑ “አይዟችሁ! እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው።+ +28 ጴጥሮስም መልሶ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ከሆንክ በውኃው ላይ እየተራመድኩ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” አለው። +29 እሱም “ና!” አለው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ከጀልባው ላይ ወርዶ በውኃው ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ አመራ። +30 ሆኖም አውሎ ነፋሱን ሲያይ ፈራ። መስጠም ሲጀምርም “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ። +31 ወዲያው ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ! ለምን ተጠራጠርክ?” አለው።+ +32 ጀልባው ላይ ከወጡ በኋላ አውሎ ነፋሱ ጸጥ አለ። +33 ከዚያም በጀልባው ውስጥ ያሉት “አንተ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።* +34 ባሕሩንም ተሻግረው ጌንሴሬጥ+ ወደተባለ ቦታ ደረሱ። +35 በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ኢየሱስ መሆኑን ሲያውቁ በዙሪያው ወዳለው አካባቢ ሁሉ መልእክት ላኩ፤ ሰዎችም የታመሙትን ሁሉ ወደ እሱ አመጡ። +36 የልብሱን ዘርፍ ብቻ እንኳ ለመንካት ይማጸኑት ነበር፤+ የነኩትም ሁሉ ሙሉ በሙሉ ተፈወሱ። +9 ከዚህ በኋላ ጀልባ በመሳፈር ባሕሩን ተሻግሮ ወደ ራሱ ከተማ* መጣ።+ +2 በዚያም ሰዎች ቃሬዛ ላይ የተኛ አንድ ሽባ ሰው ወደ እሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ፣ ሽባውን “ልጄ ሆይ አይዞህ! ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው።+ +3 በዚህ ጊዜ አንዳንድ ጸሐፍት በልባቸው “ይህ ሰው እኮ አምላክን እየተዳፈረ ነው” አሉ። +4 ኢየሱስ ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ “በልባችሁ ክፉ ነገር የምታስቡት ለምንድን ነው?+ +5 ለመሆኑ ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሏል’ ከማለትና ‘ተነስተህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀላል?+ +6 ይሁን እንጂ የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ . . .” አላቸውና ሽባውን “ተነስ፣ ቃሬዛህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።+ +7 እሱም ተነስቶ ወደ ቤቱ ሄደ። +8 ሕዝቡም ይህን ሲያዩ በፍርሃት ተዋጡ፤ እንዲህ ያለ ሥልጣን ለሰው የሰጠውንም አምላክ አከበሩ። +9 ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ እየሄደ ሳለ ማቴዎስ የሚባል ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያው ቦታ ተቀምጦ አየና “ተከታዬ ሁን” አለው። በዚህ ጊዜ ተነስቶ ተከተለው።+ +10 በኋላም በማቴዎስ ቤት እየበላ ሳለ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይበሉ ጀመር።+ +11 ፈሪሳውያን ግን ይህን ባዩ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላው ለምንድን ነው?” አሏቸው።+ +12 ኢየሱስም የተናገሩትን ሰምቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።+ +13 እንግዲያው ሄዳችሁ ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን እንጂ መሥዋዕትን አይደለም’+ የሚለውን ቃል ትርጉም አስተውሉ። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ልጠራ ነውና።” +14 ከዚያም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እሱ መጥተው “እኛና ፈሪሳውያን ዘወትር ስንጾም የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት።+ +15 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የሙሽራው ጓደኞች ሙሽራው ከእነሱ ጋር እስካለ ድረስ የሚያዝኑበት ምን ምክንያት አለ?+ ሆኖም ሙሽራው ከእነሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤+ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ። +16 በአሮጌ ልብስ ላይ ውኃ ያልነካው አዲስ ጨርቅ የሚጥፍ ሰው የለም፤ አዲሱ ጨርቅ ሲሸበሸብ ልብሱን ስለሚስበው ቀዳዳው የባሰ ይሰፋልና።+ +17 ደግሞም ሰዎች ባረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ አያስቀምጡም። እንዲህ ቢያደርጉ አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁ ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። ነገር ግን ሰዎች አዲስ የወይን ጠጅ የሚያስቀምጡት በአዲስ አቁማዳ ነው፤ በመሆኑም ሁለቱም ሳይበላሹ ይቆያሉ።” +18 ይህን እየነገራቸው ሳለ አንድ የምኩራብ አለቃ ወደ እሱ መጥቶ በመስገድ* “እስካሁን ልጄ ሳትሞት አትቀርም፤ ቢሆንም መጥተህ እጅህን ጫንባት፤ ዳግመኛም ሕያው ትሆናለች”+ አለው። +19 ኢየሱስም ተነስቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው። +20 እነሆም፣ ለ12 ዓመት ደም ይፈሳት የነበረች አንዲት ሴት+ ከኋላ መጥታ የልብሱን ዘርፍ ነካች፤+ +21 “ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ” ብላ ታስብ ነበርና። +22 ኢየሱስ ወደ ኋላ ዞር ብሎ አያትና “ልጄ ሆይ አይዞሽ! እምነትሽ አድኖሻል” አላት።+ ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ሴትየዋ ዳነች።+ +23 ኢየሱስ ወደ ምኩራብ አለቃው ቤት ሲደርስ ዋሽንት ነፊዎቹን እንዲሁም የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ+ +24 “እስቲ አንዴ ውጡ፤ ልጅቷ ተኝታለች+ እንጂ አልሞተችም” አለ። በዚህ ጊዜ በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። +25 ሕዝቡ ከወጣ በኋላ ወደ ውስጥ ገብቶ እጇን ያዛት፤+ ልጅቷም ተነሳች።+ +26 ይህም ነገር በዚያ አገር ሁሉ በሰፊው ተወራ። +27 ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ ሁለት ዓይነ ስውሮች+ “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልን” ብለው እየጮኹ ተከተሉት። +28 ወደ ቤት ከገባ በኋላ ዓይነ ስውሮቹ ወደ እሱ መጡ፤ ኢየሱስም “ዓይናችሁን ላበራላችሁ እንደምችል ታምናላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።+ እነሱም “አዎ ጌታ ሆይ” ብለው መለሱለት። +29 ከዚያም ዓይናቸውን ዳስሶ+ “እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ” አላቸው። +30 ዓይናቸውም በራ። ኢየሱስም “ማንም ሰው ስለዚህ ጉዳይ እንዳያውቅ ተጠንቀቁ” ሲል አጥብቆ አሳሰባቸው።+ +31 እነሱ ግን ከወጡ በኋላ በዚያ አካባቢ ሁሉ ስለ እሱ በይፋ አወሩ። +32 እነሱም ሲወጡ፣ ሰዎች ጋኔን ያደረበት ዱዳ ሰው ወደ እሱ አመጡ፤+ +33 ጋኔኑን ካስወጣለት በኋላ ዱዳው ተናገረ።+ ሕዝቡም እጅግ ተደንቀው “በእስራኤል ምድር እንዲህ ያለ ነገር ታይቶ አያውቅም” አሉ።+ +34 ፈሪሳውያን ግን “አጋንንትን የሚያስወጣው በአጋንንት አለቃ ነው” ይሉ ነበር።+ +35 ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፣ የመንግሥቱን ምሥራች እየሰበከ እንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እየፈወሰ በየከተማውና በየመንደሩ ይዞር ጀመር።+ +36 ሕዝቡንም ባየ ጊዜ እረኛ እንደሌላቸው በጎች+ ተገፈውና ተጥለው ስለነበር እጅግ አዘነላቸው።+ +37 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “አዎ፣ አዝመራው ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂት ናቸው።+ +38 ስለዚህ የመከሩ ሥራ ኃላፊ ወደ መከሩ፣ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።”+ +27 በነጋ ጊዜም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች በሙሉ ኢየሱስን ለመግደል አንድ ላይ ተማከሩ።+ +2 ካሰሩት በኋላ ወስደው ለአገረ ገዢው ለጲላጦስ አስረከቡት።+ +3 አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ኢየሱስ እንደተፈረደበት ባየ ጊዜ ጸጸት ተሰምቶት 30ዎቹን የብር ሳን���ሞች* ወደ ካህናት አለቆቹና ወደ ሽማግሌዎቹ ይዞ በመምጣት+ +4 “ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ” አለ። እነሱም “ታዲያ እኛ ምን አገባን? የራስህ ጉዳይ ነው!”* አሉት። +5 ስለዚህ የብር ሳንቲሞቹን ቤተ መቅደሱ ውስጥ በትኖ ወጣ። ከዚያም ሄደና ታንቆ ሞተ።+ +6 የካህናት አለቆቹ ግን የብር ሳንቲሞቹን ወስደው “ይህ ገንዘብ የደም ዋጋ ስለሆነ ግምጃ ቤት ውስጥ መግባት የለበትም” አሉ። +7 ከተመካከሩም በኋላ ለእንግዶች የመቃብር ቦታ እንዲሆን በገንዘቡ የሸክላ ሠሪውን መሬት ገዙበት። +8 በመሆኑም ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት”+ ተብሎ ይጠራል። +9 በዚህ ጊዜ በነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፦ “ከእስራኤል ልጆች አንዳንዶቹ የገመቱትን፣ ለሰውየው የወጣውን የዋጋ ተመን ይኸውም 30ዎቹን የብር ሳንቲሞች ወሰዱ፤ +10 ይሖዋ* ባዘዘኝም መሠረት ሳንቲሞቹን ለሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉ።”+ +11 ኢየሱስም አገረ ገዢው ፊት ቀረበ፤ አገረ ገዢውም “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም መልሶ “አንተው ራስህ ተናገርከው” አለው።+ +12 የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ በከሰሱት ጊዜ ግን ምንም መልስ አልሰጠም።+ +13 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “በስንት ነገር እየመሠከሩብህ እንዳሉ አትሰማም?” አለው። +14 እሱ ግን አገረ ገዢው እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል እንኳ አልመለሰለትም። +15 አገረ ገዢው ሁልጊዜ በዚህ በዓል ወቅት፣ ሕዝቡ እንዲፈታላቸው የሚፈልጉትን ማንኛውንም እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው።+ +16 በዚያን ጊዜ በዓመፀኝነቱ የታወቀ በርባን የተባለ እስረኛ ነበራቸው። +17 በመሆኑም ሕዝቡ በተሰበሰቡ ጊዜ ጲላጦስ “ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ? በርባንን ወይስ ክርስቶስ የሚባለውን ኢየሱስን?” አላቸው። +18 ጲላጦስ ይህን ያለው አሳልፈው የሰጡት በቅናት ተነሳስተው እንደሆነ ያውቅ ስለነበር ነው። +19 በተጨማሪም በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “በእሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ስለተሠቃየሁ በዚያ ጻድቅ ሰው ላይ ምንም ነገር እንዳታደርግ” የሚል መልእክት ላከችበት። +20 ይሁንና የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ በርባን እንዲፈታላቸው፣+ ኢየሱስ ግን እንዲገደል ይጠይቁ ዘንድ ሕዝቡን አግባቡ።+ +21 አገረ ገዢውም መልሶ “ከሁለቱ ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። እነሱም “በርባንን” አሉ። +22 ጲላጦስም “እንግዲያው ክርስቶስ የሚባለውን ኢየሱስን ምን ባደርገው ይሻላል?” አላቸው። ሁሉም “ይሰቀል!”* አሉ።+ +23 እሱም “ለምን? ምን ያጠፋው ነገር አለ?” አላቸው። እነሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ የባሰ መጮኻቸውን ቀጠሉ።+ +24 ጲላጦስ ያደረገው ጥረት ምንም የፈየደው ነገር እንደሌለ ከዚህ ይልቅ ሁከት እያስነሳ መሆኑን በመገንዘብ “ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ። ከዚህ በኋላ ተጠያቂ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ” በማለት ውኃ አምጥቶ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ። +25 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” አሉ።+ +26 ከዚያም በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ካስገረፈው በኋላ+ በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።+ +27 በዚህ ጊዜ የአገረ ገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ አገረ ገዢው መኖሪያ ቤት ወሰዱት፤ ሠራዊቱንም ሁሉ በዙሪያው አሰባሰቡ።+ +28 ልብሱንም ገፈው ቀይ መጎናጸፊያ አለበሱት፤+ +29 የእሾህ አክሊል ጎንጉነውም በራሱ ላይ ደፉበት፤ በቀኝ እጁም የመቃ ዘንግ አስያዙት። በፊቱ ተንበርክከውም “የአይሁዳውያን ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ አሾፉበት። +30 ደግሞም ተፉበት፤+ መቃውንም ወስደው ራሱን ይመቱት ጀመር። +31 ሲያፌዙበት ከቆዩ በኋላም መጎናጸፊያውን ገ���ው የራሱን መደረቢያዎች አለበሱት፤ ከዚያም በእንጨት ላይ እንዲቸነከር ይዘውት ሄዱ።+ +32 እየሄዱም ሳሉ ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው አገኙ። ሰውየውንም ኢየሱስ የሚሰቀልበትን የመከራ እንጨት* እንዲሸከም አስገደዱት።*+ +33 የራስ ቅል ቦታ የሚል ትርጉም ወዳለው ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ+ በደረሱ ጊዜ +34 ሐሞት* የተቀላቀለበት የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤+ እሱ ግን ከቀመሰው በኋላ ሊጠጣው አልፈለገም። +35 እንጨት ላይ ከቸነከሩት በኋላ ዕጣ ተጣጥለው መደረቢያዎቹን ተከፋፈሉ፤+ +36 በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር። +37 እንዲሁም “ይህ የአይሁዳውያን ንጉሥ ኢየሱስ ነው” የሚል የተከሰሰበትን ጉዳይ የሚገልጽ ጽሑፍ ከራሱ በላይ አንጠልጥለው ነበር።+ +38 በዚያን ጊዜ ሁለት ዘራፊዎች ከእሱ ጋር፣ አንዱ በቀኙ ሌላው ደግሞ በግራው በእንጨት ላይ ተሰቅለው ነበር።+ +39 በዚያ የሚያልፉም ይሰድቡት ነበር፤+ ራሳቸውንም እየነቀነቁ+ +40 “ቤተ መቅደሱን አፍርሼ በሦስት ቀን እሠራዋለሁ ባይ፣+ እስቲ ራስህን አድን! የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ከተሰቀልክበት እንጨት* ላይ ውረድ!” ይሉት ነበር።+ +41 የካህናት አለቆችም እንደዚሁ ከጸሐፍትና ከሽማግሌዎች ጋር ሆነው እንዲህ እያሉ ያፌዙበት ጀመር፦+ +42 “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አልቻለም! የእስራኤል ንጉሥ+ ከሆነ እስቲ አሁን ከተሰቀለበት እንጨት* ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን። +43 በአምላክ ታምኗል፤ ‘የአምላክ ልጅ ነኝ’+ ብሎ የለ፤ አምላክ ከወደደው እስቲ አሁን ያድነው።”+ +44 ከእሱ ጋር በእንጨት ላይ የተሰቀሉት ዘራፊዎችም እንኳ ሳይቀሩ ልክ እንደዚሁ ይነቅፉት ነበር።+ +45 ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ አገሩ በሙሉ በጨለማ ተሸፈነ።+ +46 በዘጠኝ ሰዓት ገደማ ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ “ኤሊ፣ ኤሊ፣ ላማ ሳባቅታኒ?” ብሎ ጮኸ፤ ይህም “አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው።+ +47 በዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ “ይህ ሰው ኤልያስን እየተጣራ ነው” ይሉ ጀመር።+ +48 ወዲያውኑም ከመካከላቸው አንዱ ሮጦ በመሄድ ሰፍነግ* ወስዶ የኮመጠጠ የወይን ጠጅ ውስጥ ከነከረ በኋላ በመቃ ላይ አድርጎ እንዲጠጣ ሰጠው።+ +49 የቀሩት ግን “ተወው! ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደሆነ እንይ” አሉ። +50 ኢየሱስ ዳግመኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን ሰጠ።*+ +51 በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ+ ከላይ እስከ ታች+ ለሁለት ተቀደደ፤+ ምድርም ተናወጠች፤ ዓለቶችም ተሰነጣጠቁ። +52 መቃብሮችም ተከፈቱ፤ በሞት ካንቀላፉት ቅዱሳን ሰዎች መካከልም የብዙዎቹ አስከሬኖች ወጡ፤ +53 ብዙ ሰዎችም አዩአቸው። (ኢየሱስ ከተነሳ በኋላ ሰዎች ከመቃብር ስፍራው ወጥተው ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ገቡ።)* +54 ሆኖም መኮንኑና አብረውት ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች የምድር ነውጡንና የተከሰቱትን ነገሮች ሲመለከቱ እጅግ ፈርተው “ይህ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር” አሉ።+ +55 ኢየሱስን ለማገልገል ከገሊላ ጀምሮ አብረውት የነበሩ ብዙ ሴቶችም+ እዚያ ሆነው ከሩቅ ይመለከቱ ነበር፤ +56 ከእነሱም መካከል መግደላዊቷ ማርያም፣ የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም እንዲሁም የዘብዴዎስ ልጆች እናት ይገኙ ነበር።+ +57 ቀኑ በመገባደድ ላይ ሳለ የአርማትያስ ሰው የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሀብታም መጣ፤ እሱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር።+ +58 ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጠየቀ።+ ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ።+ +59 ከዚያም ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ በንጹሕ በፍታ ገነዘው፤+ +60 ከዓለት ፈልፍሎ በሠራው በራሱ አዲስ መቃብር ውስጥም አኖረው።+ ከዚያም አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ የመቃብሩን ደጃፍ ዘጋውና ሄደ። +61 በዚ��� ጊዜ መግደላዊቷ ማርያምና ሌላዋ ማርያም ከመቃብሩ ፊት ለፊት እዚያው ተቀምጠው ነበር።+ +62 እነዚህ ነገሮች የተከናወኑት ለሰንበት ዝግጅት በሚደረግበት ቀን+ ነበር። በማግስቱም የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን አንድ ላይ ተሰብስበው ጲላጦስ ፊት ቀረቡና +63 እንዲህ አሉ፦ “ክቡር ሆይ፣ ያ አስመሳይ በሕይወት ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሳለሁ’ ብሎ የተናገረው ትዝ አለን።+ +64 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው እንዳይሰርቁትና+ ለሕዝቡ ‘ከሞት ተነስቷል!’ እንዳይሉ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ መቃብሩ እንዲጠበቅ ትእዛዝ ስጥልን። አለዚያ ይህ የኋለኛው ማታለያ ከፊተኛው የከፋ ይሆናል።” +65 ጲላጦስም “ጠባቂዎች መውሰድ ትችላላችሁ። ሄዳችሁ በምታውቁት መንገድ አስጠብቁ” አላቸው። +66 ስለዚህ ሄደው ድንጋዩ ላይ ማኅተም በማድረግ መቃብሩን አሸጉ፤ ጠባቂም አቆሙ። +13 በዚያን ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕሩ ዳር ተቀመጠ። +2 እጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እሱ መጥተው ተሰበሰቡ፤ በመሆኑም ጀልባ ላይ ወጥቶ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳር ቆመው ነበር።+ +3 ከዚያም ብዙ ነገሮችን እንዲህ እያለ በምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፦+ “እነሆ፣ አንድ ዘሪ ሊዘራ ወጣ።+ +4 በሚዘራበት ጊዜ አንዳንዶቹ ዘሮች መንገድ ዳር ወደቁ፤ ወፎችም መጥተው ለቀሟቸው።+ +5 ሌሎቹ ደግሞ ብዙ አፈር በሌለው ድንጋያማ መሬት ላይ ወደቁ፤ አፈሩም ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያውኑ በቀሉ።+ +6 ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን ተቃጠሉ፤ ሥር ስላልነበራቸውም ደረቁ። +7 ሌሎቹ በእሾህ መካከል ወደቁ፤ እሾሁም አድጎ አነቃቸው።+ +8 ሌሎቹ ደግሞ ጥሩ አፈር ላይ ወድቀው ፍሬ ማፍራት ጀመሩ፤ አንዱ 100፣ አንዱ 60፣ ሌላውም 30 እጥፍ አፈራ።+ +9 ጆሮ ያለው ይስማ።”+ +10 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ መጥተው “በምሳሌ የምትነግራቸው ለምንድን ነው?” አሉት።+ +11 እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ቅዱስ ሚስጥሮች የመረዳት ችሎታ ተሰጥቷችኋል፤+ ለእነሱ ግን አልተሰጣቸውም። +12 ላለው ሁሉ ይጨመርለታል፤ ደግሞም ይትረፈረፍለታል፤ የሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።+ +13 በምሳሌ የምነግራቸው ለዚህ ነው፤ ቢያዩም የሚያዩት እንዲያው በከንቱ ነውና፤ ቢሰሙም የሚሰሙት እንዲያው በከንቱ ነው፤ ትርጉሙንም አያስተውሉም።+ +14 ደግሞም የኢሳይያስ ትንቢት በእነሱ ላይ እየተፈጸመ ነው። ትንቢቱ እንዲህ ይላል፦ ‘መስማቱን ትሰማላችሁ ግን በፍጹም ትርጉሙን አታስተውሉም፤ ማየቱን ታያላችሁ ግን በፍጹም ልብ አትሉም።+ +15 ምክንያቱም በዓይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው እንዲሁም በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ እንዳይመለሱና እንዳልፈውሳቸው የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗል፤ በጆሯቸው ሰምተው ምላሽ አልሰጡም፤ ዓይናቸውንም ጨፍነዋል።’+ +16 “እናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ፣ ጆሮዎቻችሁም ስለሚሰሙ ደስተኞች ናችሁ።+ +17 እውነት እላችኋለሁ፣ ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ አሁን የምታዩትን ነገር ለማየት ተመኝተው ነበር፤ ግን አላዩም፤+ አሁን የምትሰሙትን ነገር ለመስማት ተመኝተው ነበር፤ ግን አልሰሙም። +18 “እንግዲህ እናንተ ዘር የዘራውን ሰው ምሳሌ ስሙ።+ +19 አንድ ሰው የመንግሥቱን ቃል ሰምቶ የማያስተውል ከሆነ ክፉው+ መጥቶ በልቡ ውስጥ የተዘራውን ዘር ይነጥቀዋል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ዘር ይህ ነው።+ +20 በድንጋያማ መሬት ላይ የተዘራው ደግሞ ቃሉን ሲሰማ ወዲያውኑ በደስታ የሚቀበል ሰው ነው።+ +21 ሆኖም ቃሉ በውስጡ ሥር ስለማይሰድ የሚቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ በቃሉ የተነሳም መከራ ወይም ስደት ሲደርስበት ወዲያው ይሰናከላል። +22 በእሾህ መካከል የተዘራው ደግሞ ቃሉን የሚሰማ ነው፤ ይሁንና የዚህ ሥርዓት* ጭንቀት+ እንዲሁም ሀብት ያለው የማታለል ኃይል ቃሉን ያንቀዋል፤ የማያፈራም ይሆናል።+ +23 በጥሩ አፈር ላይ የተዘራው ደግሞ ቃሉን የሚሰማና የሚያስተውል ነው፤ ፍሬም ያፈራል፤ አንዱ 100፣ አንዱም 60፣ ሌላውም 30 እጥፍ ይሰጣል።”+ +24 ደግሞም እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማያት በእርሻው ላይ ጥሩ ዘር ከዘራ ሰው ጋር ይመሳሰላል። +25 ነገር ግን ሰው ሁሉ ተኝቶ ሳለ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው ላይ እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ። +26 እህሉ አድጎ ፍሬ ባፈራ ጊዜ እንክርዳዱም አብሮ ታየ። +27 ስለሆነም የቤቱ ጌታ ባሪያዎች፣ ወደ እሱ ቀርበው ‘ጌታ ሆይ፣ በእርሻህ ላይ የዘራኸው ጥሩ ዘር አልነበረም እንዴ? ታዲያ እንክርዳዱ ከየት መጣ?’ አሉት። +28 እሱም ‘ይህን ያደረገው ጠላት ነው’ አላቸው።+ ባሪያዎቹም ‘ታዲያ ሄደን እንድንነቅለው ትፈልጋለህ?’ አሉት። +29 እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ‘እንክርዳዱን ስትነቅሉ ስንዴውንም አብራችሁ ልትነቅሉ ስለምትችሉ ተዉት። +30 እስከ መከር ጊዜ ድረስ አብረው ይደጉ፤ በመከር ወቅት አጫጆቹን፣ በመጀመሪያ እንክርዳዱን ሰብስቡና እንዲቃጠል በየነዶው እሰሩ፤ ከዚያም ስንዴውን ሰብስባችሁ ወደ ጎተራዬ አስገቡ እላቸዋለሁ።’”+ +31 ደግሞም እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማያት አንድ ሰው ወስዶ እርሻው ውስጥ ከተከላት አንዲት የሰናፍጭ ዘር ጋር ይመሳሰላል፤+ +32 የሰናፍጭ ዘር ከሌሎች ዘሮች ሁሉ ያነሰች ብትሆንም ስታድግ ግን ከተክሎች ሁሉ በልጣ ዛፍ ስለምትሆን የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎቿ ላይ መስፈሪያ ያገኛሉ።” +33 አሁንም እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማያት አንዲት ሴት ወስዳ ሊጡ በሙሉ እስኪቦካ ድረስ ከሦስት ትላልቅ መስፈሪያ* ዱቄት ጋር ከደባለቀችው እርሾ ጋር ይመሳሰላል።”+ +34 ኢየሱስ ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ። እንዲያውም ያለምሳሌ አይነግራቸውም ነበር፤+ +35 ይህም የሆነው “አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከምሥረታው* ጊዜ አንስቶ የተሰወሩትን ነገሮች አውጃለሁ” ተብሎ በነቢዩ የተነገረው እንዲፈጸም ነው።+ +36 ከዚያም ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ ቀርበው “በእርሻው ውስጥ ስላለው እንክርዳድ የተናገርከውን ምሳሌ አብራራልን” አሉት። +37 እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “ጥሩውን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ +38 እርሻው ዓለም ነው።+ ጥሩው ዘር ደግሞ የመንግሥቱ ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱ ግን የክፉው ልጆች ናቸው፤+ +39 እንክርዳዱን የዘራው ጠላት፣ ዲያብሎስ ነው። መከሩ የዚህ ሥርዓት* መደምደሚያ ሲሆን አጫጆቹ ደግሞ መላእክት ናቸው። +40 በመሆኑም እንክርዳዱ ተሰብስቦ በእሳት እንደሚቃጠል ሁሉ በዚህ ሥርዓት* መደምደሚያም እንዲሁ ይሆናል።+ +41 የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ እነሱም እንቅፋት የሚፈጥሩትን ነገሮች ሁሉና ዓመፅ የሚፈጽሙትን ሰዎች ከመንግሥቱ ይለቅማሉ፤ +42 ወደ እሳታማ እቶንም ይጥሏቸዋል።+ በዚያም ያለቅሳሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ። +43 በዚያ ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ።+ ጆሮ ያለው ሁሉ ይስማ። +44 “መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ ከተደበቀ ውድ ሀብት ጋር ይመሳሰላል፤ አንድ ሰው ባገኘው ጊዜ ሸሸገው፤ ከመደሰቱም የተነሳ ሄዶ ያለውን ሁሉ በመሸጥ እርሻውን ገዛው።+ +45 “በተጨማሪም መንግሥተ ሰማያት ጥሩ ዕንቁ ከሚፈልግ ተጓዥ ነጋዴ ጋር ይመሳሰላል። +46 ከፍተኛ ዋጋ ያለው አንድ ዕንቁ ባገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ወዲያውኑ በመሸጥ ዕንቁውን ገዛው።+ +47 “ደግሞም መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር ተጥሎ የተለያየ ዓይነት ዓሣ ከሰበሰበ መረብ ጋር ይመሳሰላል። +48 መረቡ በሞላ ጊዜ ወደ ባሕሩ ዳር ጎትተው አወጡት፤ ከዚያም ተቀምጠው ጥሩ ጥሩውን+ እየለዩ በዕቃ ውስጥ አስቀመጡ፤ መጥፎ መጥፎውን+ ግን ጣሉት። +49 በዚህ ሥርዓት* መደምደሚያም እንደዚሁ ይሆናል። መላእክት ተልከው ክፉዎችን ከጻድቃን ይለያሉ፤ +50 ወደ እሳታማ እቶንም ይጥሏቸዋል። በዚያም ያለቅሳሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ። +51 እሱም “የዚህ ሁሉ ትርጉም ገብቷችኋል?” አላቸው። እነሱም “አዎ” አሉት። +52 ከዚያም ኢየሱስ “እንደዚያ ከሆነ፣ ስለ መንግሥተ ሰማያት የተማረ ማንኛውም የሕዝብ አስተማሪ ከከበረ ሀብት ማከማቻው አዲስና አሮጌ ዕቃ ከሚያወጣ የቤት ጌታ ጋር ይመሳሰላል” አላቸው። +53 ኢየሱስ እነዚህን ምሳሌዎች ተናግሮ ሲጨርስ ከዚያ ስፍራ ተነስቶ ሄደ። +54 ወደ ትውልድ አገሩ+ ከመጣ በኋላ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ጀመር፤ ሰዎቹም ተገርመው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ይህን ጥበብና እነዚህን ተአምራት የማድረግ ችሎታ ከየት አገኘ?+ +55 ይህ የአናጺው ልጅ አይደለም?+ እናቱስ ማርያም አይደለችም? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉም?+ +56 እህቶቹስ ሁሉ የሚኖሩት ከእኛ ጋር አይደለም? ታዲያ ይህን ሁሉ ከየት አገኘው?”+ +57 ከዚህም የተነሳ ተሰናከሉበት።+ ኢየሱስ ግን “ነቢይ በገዛ አገሩና በገዛ ቤቱ ካልሆነ በስተቀር በሌላ ቦታ ሁሉ ይከበራል” አላቸው።+ +58 በእሱ ባለማመናቸው በዚያ ብዙ ተአምራት አልፈጸመም። +5 ሕዝቡንም ባየ ጊዜ ወደ ተራራ ወጣ፤ በዚያ ከተቀመጠ በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ መጡ። +2 ከዚያም ኢየሱስ መናገር ጀመረ፤ እንዲህም ሲል አስተማራቸው፦ +3 “መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ* ደስተኞች ናቸው፤+ መንግሥተ ሰማያት የእነሱ ነውና። +4 “የሚያዝኑ ደስተኞች ናቸው፤ መጽናኛ ያገኛሉና።+ +5 “ገሮች*+ ደስተኞች ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።+ +6 “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ደስተኞች ናቸው፤+ ይጠግባሉና።*+ +7 “መሐሪዎች ደስተኞች ናቸው፤+ ምሕረት ይደረግላቸዋልና። +8 “ልባቸው ንጹሕ የሆነ ደስተኞች ናቸው፤+ አምላክን ያያሉና። +9 “ሰላም ፈጣሪዎች* ደስተኞች ናቸው፤+ የአምላክ ልጆች ይባላሉና። +10 “ለጽድቅ ሲሉ ስደት የሚደርስባቸው ደስተኞች ናቸው፤+ መንግሥተ ሰማያት የእነሱ ነውና። +11 “በእኔ ምክንያት ሰዎች ሲነቅፏችሁ፣+ ስደት ሲያደርሱባችሁና+ ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲያስወሩባችሁ ደስተኞች ናችሁ።+ +12 በሰማያት የሚጠብቃችሁ ሽልማት ታላቅ ስለሆነ+ ሐሴት አድርጉ፤ በደስታም ፈንጥዙ፤+ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንደዚሁ ስደት አድርሰውባቸው ነበርና።+ +13 “እናንተ የምድር ጨው+ ናችሁ፤ ሆኖም ጨው የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን እንዴት መልሶ ሊያገኝ ይችላል? ከዚህ በኋላ ወደ ውጭ ተጥሎ+ በሰው ከመረገጥ በቀር ለምንም ነገር አያገለግልም። +14 “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።+ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አትችልም። +15 ሰዎች መብራት አብርተው እንቅብ* አይደፉበትም፤ ከዚህ ይልቅ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል፤ በቤት ውስጥ ላሉትም ሁሉ ያበራል።+ +16 በተመሳሳይም ሰዎች መልካም ሥራችሁን+ አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ+ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።+ +17 “ሕጉን ወይም የነቢያትን ቃል ልሽር እንደመጣሁ አድርጋችሁ አታስቡ። ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም።+ +18 እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማይና ምድር ቢያልፉ እንኳ እነዚህ ሁሉ ነገሮች እስኪከናወኑ ድረስ ከሕጉ አነስተኛዋ ፊደል ወይም የአንዷ ፊደል ጭረት ሳትፈጸም አትቀርም።+ +19 በመሆኑም አነስተኛ ከሆኑት ከእነዚህ ትእዛዛት አንዷን የሚጥስና ሌሎች ሰዎችም እንዲህ እንዲያደርጉ የሚያስተምር ሰው ሁሉ በመንግሥተ ሰማያት ታናሽ* ይባላል። እነዚህን ትእዛዛት የሚያከብርና የሚያስተምር ሰው ግን በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ* ይባላል። +20 ጽድቃችሁ ከጸሐፍትና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ+ በምንም ዓይነት ወደ መንግሥተ ሰማያት እንደማትገቡ+ ልነግራችሁ እወዳለሁ። +21 “በጥንት ዘመን ለነበሩት ‘አትግደል፤+ ሰው የገደለ ሁሉ ግን በፍርድ ቤት ይጠየቃል’+ እንደተባለ ሰምታችኋል። +22 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በወንድሙ ላይ ተቆጥቶ ቁጣው የማይበርድለት+ ሁሉ በፍርድ ቤት ይጠየቃል፤ ወንድሙንም ጸያፍ በሆነ ቃል የሚያጥላላ ሁሉ በከፍተኛ ፍርድ ቤት* ይጠየቃል፤ ‘አንተ የማትረባ ጅል’ የሚለው ደግሞ ለእሳታማ ገሃነም* ሊዳረግ ይችላል።+ +23 “እንግዲያው መባህን ወደ መሠዊያው ባመጣህ ጊዜ+ ወንድምህ በአንተ ቅር የተሰኘበት ነገር እንዳለ ትዝ ካለህ +24 መባህን በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ። በመጀመሪያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ፤ ከዚያም ተመልሰህ መባህን አቅርብ።+ +25 “ክስ ከመሠረተብህ ባላጋራ ጋር ወደ ፍርድ ቤት እየሄዳችሁ ሳለ ፈጥነህ ታረቅ፤ አለዚያ ባላጋራህ ለዳኛው፣ ዳኛው ደግሞ ለፍርድ ቤቱ ዘብ አሳልፎ ይሰጥህና እስር ቤት ልትገባ ትችላለህ።+ +26 እውነት እልሃለሁ፣ የመጨረሻዋን ሳንቲምህን* ከፍለህ እስክትጨርስ ድረስ ፈጽሞ ከዚያ አትወጣም። +27 “‘አታመንዝር’+ እንደተባለ ሰምታችኋል። +28 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ አንዲትን ሴት በፍትወት ስሜት የሚመለከት+ ሁሉ በዚያን ጊዜ በልቡ ከእሷ ጋር አመንዝሯል።+ +29 ስለዚህ ቀኝ ዓይንህ ቢያሰናክልህ አውጥተህ ጣለው።+ መላ ሰውነትህ ወደ ገሃነም* ከሚወረወር ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱን ብታጣ ይሻልሃል።+ +30 እንዲሁም ቀኝ እጅህ ቢያሰናክልህ ቆርጠህ ጣለው።+ መላ ሰውነትህ ወደ ገሃነም* ከሚጣል ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱን ብታጣ ይሻልሃል።+ +31 “በተጨማሪም ‘ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ይስጣት’+ ተብሏል። +32 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፆታ ብልግና* ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ ምንዝር ለመፈጸም እንድትጋለጥ ያደርጋታል፤ እንዲሁም በዚህ መንገድ የተፈታችን ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።+ +33 “ከዚህም ሌላ በጥንት ዘመን ለነበሩት ‘በከንቱ አትማል፤+ ይልቁንም ለይሖዋ* የተሳልከውን ፈጽም’+ እንደተባለ ሰምታችኋል። +34 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ፈጽሞ አትማሉ።+ በሰማይም ቢሆን አትማሉ፤ የአምላክ ዙፋን ነውና፤ +35 በምድርም ቢሆን አትማሉ፤ የእግሩ ማሳረፊያ ነችና፤+ በኢየሩሳሌምም ቢሆን አትማሉ፤ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነችና።+ +36 በራስህም ቢሆን አትማል፤ ከፀጉርህ አንዷን እንኳ ነጭ ወይም ጥቁር ማድረግ አትችልምና። +37 ቃላችሁ ‘አዎ’ ከሆነ አዎ ይሁን፤ ‘አይደለም’ ከሆነ አይደለም ይሁን፤+ ከዚህ ውጭ የሆነ ግን ከክፉው+ ነው። +38 “‘ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ’+ እንደተባለ ሰምታችኋል። +39 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ክፉን ሰው አትቃወሙት፤ ከዚህ ይልቅ ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሌላኛውን ደግሞ አዙርለት።+ +40 አንድ ሰው ፍርድ ቤት ሊያቀርብህና እጀ ጠባብህን ሊወስድ ቢፈልግ መደረቢያህንም ጨምረህ ስጠው፤+ +41 እንዲሁም አንድ ባለሥልጣን አንድ ኪሎ ሜትር* እንድትሄድ ቢያስገድድህ* ሁለት ኪሎ ሜትር አብረኸው ሂድ። +42 ለሚለምንህ ስጥ፤ ሊበደርህ የሚፈልገውንም ሰው* ፊት አትንሳው።+ +43 “‘ባልንጀራህን ውደድ፤+ ጠላትህን ጥላ’ እንደተባለ ሰምታችኋል። +44 እኔ ግን እላችኋለሁ፦ ጠላቶቻችሁን ውደዱ+ እንዲሁም ስደት ለሚያደርሱባችሁ ጸልዩ፤+ +45 ይህን ብታደርጉ በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ፤+ እሱ በክፉዎችም ሆነ በጥሩ ሰዎች ላይ ፀሐዩን ያወጣልና፤ በጻድቃንም ሆነ ጻድቃን ባልሆኑ ሰዎች ላይ ዝናብ ያዘንባል።+ +46 የሚወዷችሁን ብቻ ብትወዱ ምን ብድራት ታገኛላችሁ?+ ቀረጥ ሰብሳቢዎችስ የሚያደርጉት ይህንኑ አይደለም? +47 ደግሞስ ወንድሞቻችሁን ብቻ ሰላም ብትሉ ምን የተለየ ነገር ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ የሚያደርጉት ይህንኑ አይደለም? +48 በሰማይ ያለው አባታችሁ ፍጹም* እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።+ +21 ወደ ኢየሩሳሌም በተቃረቡና በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ወደምትገኘው ወደ ቤተፋጌ በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤+ +2 እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ እዚያ እንደደረሳችሁም አንዲት የታሰረች አህያ ከነውርንጭላዋ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደ እኔ አምጧቸው። +3 ማንም ሰው ቢጠይቃችሁ ‘ጌታ ይፈልጋቸዋል’ በሉት። በዚህ ጊዜ ወዲያውኑ ይልካቸዋል።” +4 ይህም የሆነው ነቢዩ እንዲህ ብሎ የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፦ +5 “ለጽዮን ልጅ እንዲህ በሏት፦ ‘እነሆ ንጉሥሽ+ ገር+ ሆኖ በአህያ፣ አዎ በአህያይቱ ግልገል በውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል።’”+ +6 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ።+ +7 አህያይቱንና ውርንጭላዋን አምጥተው መደረቢያዎቻቸውን በላያቸው ላይ አደረጉ፤ እሱም ተቀመጠባቸው።*+ +8 ከሕዝቡ መካከል አብዛኞቹ መደረቢያቸውን በመንገዱ ላይ አነጠፉ፤+ ሌሎች ደግሞ ከዛፎች ላይ ቅርንጫፎች እየቆረጡ በመንገዱ ላይ ያነጥፉ ነበር። +9 በተጨማሪም ከፊት ከፊቱ የሚሄደውና ከኋላው የሚከተለው ሕዝብ “የዳዊትን ልጅ እንድታድነው እንለምንሃለን!*+ በይሖዋ* ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!+ በሰማይ የምትኖረው ሆይ፣ እንድታድነው እንለምንሃለን!”+ ብሎ ይጮኽ ነበር። +10 ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜም “ይህ ሰው ማን ነው?” በማለት መላዋ ከተማ ታወከች። +11 ሕዝቡም “ይህ በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት የመጣው ነቢዩ ኢየሱስ ነው!”+ ይል ነበር። +12 ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ ገብቶ በቤተ መቅደሱ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችን መቀመጫዎችም ገለባበጠ።+ +13 እንዲህም አላቸው፦ “‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል፤+ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አድርጋችሁታል።”+ +14 ቤተ መቅደሱ ውስጥ እንዳለም ዓይነ ስውሮችና አንካሶች ወደ እሱ መጡ፤ እሱም ፈወሳቸው። +15 የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ያደረጋቸውን አስደናቂ ነገሮች እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ውስጥ “የዳዊትን ልጅ እንድታድነው እንለምንሃለን!”+ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ ተቆጥተው+ +16 “እነዚህ የሚሉትን ትሰማለህ?” አሉት። ኢየሱስም “አዎ እሰማለሁ። ‘ከልጆችና ከሕፃናት አፍ ምስጋና አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁም?” አላቸው።+ +17 ከዚያም ትቷቸው ከከተማዋ ከወጣ በኋላ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ እዚያም አደረ።+ +18 በማለዳም ወደ ከተማዋ እየተመለሰ ሳለ ተራበ።+ +19 በመንገድ ዳር አንድ የበለስ ዛፍ አየና ወደ እሷ ሄደ፤ ሆኖም ከቅጠል በቀር ምንም ስላላገኘባት+ “ከእንግዲህ ወዲህ ፍሬ አይገኝብሽ” አላት።+ የበለስ ዛፏም ወዲያውኑ ደረቀች። +20 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ባዩ ጊዜ ተገርመው “የበለስ ዛፏ እንዲህ በአንዴ ልትደርቅ የቻለችው እንዴት ነው?” አሉ።+ +21 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ እምነት ካላችሁና ካልተጠራጠራችሁ እኔ በበለስ ዛፏ ላይ ያደረግኩትን ማድረግ ብቻ ሳይሆን ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነስተህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት እንኳ ይሆንላችኋል።+ +22 እምነት ካላችሁ በጸሎት የምትጠይቁትን ነገር ሁሉ ታገኛላችሁ።”+ +23 ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ እያስተማረ ሳለ የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ወደ እሱ መጥተው “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥ���ጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” አሉት።+ +24 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ። መልሱን ከነገራችሁኝ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፦ +25 ዮሐንስ እንዲያጠምቅ ሥልጣን የሰጠው ማን ነው? አምላክ* ነው ወይስ ሰው?” እነሱ ግን እርስ በርሳቸው እንዲህ ይባባሉ ጀመር፦ “‘አምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤+ +26 ‘ሰው’ ብንል ደግሞ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ስለሚያየው ሕዝቡን እንፈራለን።” +27 ስለዚህ ለኢየሱስ “አናውቅም” ብለው መለሱለት። እሱ ደግሞ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም። +28 “ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት። ወደ መጀመሪያው ልጁ ሄዶ ‘ልጄ ሆይ፣ ዛሬ ወደ ወይኑ እርሻ ሄደህ ሥራ’ አለው። +29 ልጁም መልሶ ‘አልሄድም’ አለው፤ በኋላ ግን ጸጸተውና ሄደ። +30 ሁለተኛውንም ቀርቦ እንደዚሁ አለው። ልጁም መልሶ ‘እሺ አባዬ፣ እሄዳለሁ’ አለው፤ ግን አልሄደም። +31 ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው የትኛው ነው?” እነሱም “የመጀመሪያው” አሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ዝሙት አዳሪዎች ወደ አምላክ መንግሥት በመግባት ረገድ ይቀድሟችኋል። +32 ዮሐንስ የጽድቅን መንገድ ሊያሳያችሁ መጣ፤ እናንተ ግን አላመናችሁትም። ይሁን እንጂ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ዝሙት አዳሪዎች አመኑት፤+ እናንተ ይህን አይታችሁም እንኳ ጸጸት ተሰምቷችሁ እሱን ለማመን አልፈለጋችሁም። +33 “ሌላም ምሳሌ ስሙ፦ የወይን እርሻ+ ያለማ አንድ ባለ ርስት ነበር፤ ዙሪያውንም አጠረው፤ በዚያም የወይን መጭመቂያ ቆፈረ እንዲሁም ማማ ሠራ፤+ ከዚያም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።+ +34 ፍሬው የሚሰበሰብበት ወቅት ሲደርስ ድርሻውን እንዲያመጡለት ባሪያዎቹን ወደ ገበሬዎቹ ላከ። +35 ገበሬዎቹ ግን ባሪያዎቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት።+ +36 ከበፊቶቹ የሚበዙ ሌሎች ባሪያዎች በድጋሚ ላከ፤ ይሁንና በእነሱም ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙባቸው።+ +37 በመጨረሻም ‘መቼም ልጄን ያከብሩታል’ በማለት ልጁን ላከው። +38 ገበሬዎቹ ልጁን ሲያዩት እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው።+ ኑ እንግደለው፤ ርስቱንም እንውረስ!’ ተባባሉ። +39 ስለዚህ ያዙትና ከወይን እርሻው ጎትተው በማውጣት ገደሉት።+ +40 እንግዲህ የወይኑ እርሻ ባለቤት ሲመጣ እነዚህን ገበሬዎች ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል?” +41 የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎችም “ክፉዎች ስለሆኑ ከባድ ጥፋት ያደርስባቸዋል፤ ከዚያም የወይን እርሻውን፣ ፍሬውን በወቅቱ ለሚያስረክቡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት። +42 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እንዲህ የሚለውን የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል አላነበባችሁም? ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ የማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ።+ ይህ የይሖዋ* ሥራ ነው፤ ለዓይናችንም ድንቅ ነው።’+ +43 የአምላክ መንግሥት ከእናንተ ተወስዶ ፍሬውን ለሚያፈራ ሕዝብ ይሰጣል የምላችሁ ለዚህ ነው። +44 በተጨማሪም በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰባበራል።+ ድንጋዩ የሚወድቅበት ሰው ሁሉ ደግሞ ይደቅቃል።”+ +45 የካህናት አለቆቹና ፈሪሳውያኑ ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ ስለ እነሱ እንደተናገረ ገባቸው።+ +46 ሊይዙት* ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም ሕዝቡን ፈሩ፤ ምክንያቱም ሕዝቡ እንደ ነቢይ ያየው ነበር።+ +15 ከዚያም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት+ ወደ ኢየሱስ ቀርበው እንዲህ አሉት፦ +2 “ደቀ መዛሙርትህ የአባቶችን ወግ የሚጥሱት ለምንድን ነ���? ለምሳሌ፣ ሊበሉ ሲሉ እጃቸውን አይታጠቡም።”*+ +3 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ለወጋችሁ ስትሉ የአምላክን ትእዛዝ የምትጥሱት ለምንድን ነው?+ +4 ለምሳሌ አምላክ ‘አባትህንና እናትህን አክብር’+ እንዲሁም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ* ይገደል’ ብሏል።+ +5 እናንተ ግን እንዲህ ትላላችሁ፦ ‘ማንኛውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን “እናንተን መጦር የምችልበት፣ ያለኝ ነገር ሁሉ ለአምላክ የተወሰነ ስጦታ ነው”+ ካለ +6 አባቱን የማክበር ግዴታ የለበትም።’ በመሆኑም ለወጋችሁ ስትሉ የአምላክን ቃል ሽራችኋል።+ +7 እናንተ ግብዞች፣ ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ስለ እናንተ በትክክል ተንብዮአል፦+ +8 ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው። +9 የሚያስተምሩት የሰውን ሥርዓት ስለሆነ እኔን የሚያመልኩት በከንቱ ነው።’”+ +10 ከዚያም ሕዝቡን ወደ እሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ስሙ፤ ደግሞም ይህን ቃል አስተውሉ፦+ +11 ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፉ የሚገባው አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሚያረክሰው ከአፉ የሚወጣው ነው።”+ +12 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው “ፈሪሳውያን በተናገርከው ነገር ቅር እንደተሰኙ አውቀሃል?” አሉት።+ +13 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል። +14 ተዉአቸው፤ እነሱ ዕውር መሪዎች ናቸው። ስለዚህ ዕውር ዕውርን ቢመራ ሁለቱም ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ።”+ +15 ጴጥሮስም መልሶ “ምሳሌውን አብራራልን” አለው። +16 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተም እስካሁን ማስተዋል ተስኗችኋል?+ +17 ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ እንደሚዘልቅና ከዚያም ወጥቶ ወደ ጉድጓድ እንደሚገባ አታውቁም? +18 ይሁን እንጂ ከአፍ የሚወጣ ሁሉ ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ይህ ነው።+ +19 ለምሳሌ ከልብ ክፉ ሐሳብ ይወጣል፦+ ግድያ፣ ምንዝር፣ የፆታ ብልግና፣* ሌብነት፣ በሐሰት መመሥከርና ስድብ። +20 ሰውን የሚያረክሱት እነዚህ ነገሮች ናቸው፤ እጅን ሳይታጠቡ* መብላት ግን ሰውን አያረክስም።” +21 ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ሲዶና አካባቢ ሄደ።+ +22 በዚያ ክልል የምትኖር አንዲት ፊንቄያዊት* ሴት መጥታ “ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልኝ። ልጄን ጋኔን ስለያዛት ክፉኛ እየተሠቃየች ነው” ብላ ጮኸች።+ +23 እሱ ግን ምንም መልስ አልሰጣትም። ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው “ይህች ሴት ከኋላችን እየተከተለች ስለምትጮኽ እባክህ አሰናብታት” እያሉ ይለምኑት ጀመር። +24 እሱም መልሶ “እኔ የተላክሁት ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች እንጂ ለሌላ ለማንም አይደለም” አለ።+ +25 ሴትየዋ ግን ቀርባ “ጌታ ሆይ፣ እርዳኝ!” እያለች ሰገደችለት።* +26 እሱም መልሶ “የልጆችን ዳቦ ወስዶ ለቡችሎች መጣል ተገቢ አይደለም” አለ። +27 እሷም “አዎ ጌታ ሆይ፣ ግን እኮ ቡችሎችም ከጌቶቻቸው ማዕድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለች።+ +28 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ መልሶ “አንቺ ሴት፣ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ በይ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ” አላት። ልጇም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰች። +29 ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ ወደ ገሊላ ባሕር+ አቅራቢያ መጣ፤ ወደ ተራራ ወጥቶም ተቀመጠ። +30 በዚህ ጊዜ እጅግ ብዙ ሰዎች አንካሶችን፣ ሽባዎችን፣ ዓይነ ስውሮችን፣ ዱዳዎችንና ሌሎች በርካታ ሕመምተኞችን ይዘው ወደ እሱ በመምጣት እግሩ ሥር አስቀመጧቸው፤ እሱም ፈወሳቸው።+ +31 ሕዝቡም ዱዳዎች ሲናገሩ፣ ሽባዎች ሲፈወሱ፣ አንካሶች ሲራመዱና ዓይነ ስውሮች ሲያዩ ተመልክተው እጅግ ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ።+ +32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ እሱ ጠርቶ “እነዚህ ሰዎች ሦስት ቀን ሙሉ ከእኔ ጋር ስለቆዩና የሚበሉ��� ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ።+ እንዲሁ ጦማቸውን ልሰዳቸው አልፈልግም፤ መንገድ ላይ ዝለው ሊወድቁ ይችላሉ” አላቸው።+ +33 ደቀ መዛሙርቱ ግን “በዚህ ገለልተኛ ስፍራ ይህን ሁሉ ሕዝብ ሊያጠግብ የሚችል በቂ ዳቦ ከየት እናገኛለን?” አሉት።+ +34 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “ስንት ዳቦ አላችሁ?” አላቸው። እነሱም “ሰባት ዳቦና ጥቂት ትናንሽ ዓሣዎች” አሉት። +35 እሱም ሕዝቡ መሬት ላይ እንዲቀመጥ ካዘዘ በኋላ +36 ሰባቱን ዳቦና ዓሣዎቹን ወሰደ፤ ካመሰገነ በኋላም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ለሕዝቡ ሰጡ።+ +37 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ሰባት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ +"38 የበሉትም ከሴቶችና ከትናንሽ ልጆች ሌላ 4,000 ወንዶች ነበሩ።" +39 በመጨረሻም ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ጀልባ ተሳፍሮ ወደ መጌዶን ክልል መጣ።+ +22 በተጨማሪም ኢየሱስ እንዲህ ሲል በምሳሌ ነገራቸው፦ +2 “መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሠርግ ከደገሰ+ ንጉሥ ጋር ሊመሳሰል ይችላል። +3 ንጉሡም ወደ ሠርጉ የተጋበዙትን እንዲጠሩ ባሪያዎቹን ላከ፤ ተጋባዦቹ ግን ለመምጣት ፈቃደኛ አልሆኑም።+ +4 በድጋሚ ሌሎች ባሪያዎች ልኮ ‘ተጋባዦቹን “የምሳ ግብዣ አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ፍሪዳዎቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ነገር ዝግጁ ነው። ወደ ሠርጉ ኑ” በሏቸው’ አለ። +5 እነሱ ግን ግብዣውን ችላ በማለት አንዱ ወደ እርሻው፣ ሌላው ወደ ንግዱ ሄደ፤+ +6 ሌሎቹ ደግሞ ባሪያዎቹን ይዘው ካንገላቷቸው በኋላ ገደሏቸው። +7 “ንጉሡም እጅግ ተቆጣ፤ ወታደሮቹንም ልኮ እነዚያን ነፍሰ ገዳዮች ገደለ እንዲሁም ከተማቸውን አቃጠለ።+ +8 ከዚያም ባሪያዎቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ሠርጉ ተደግሷል፤ የተጋበዙት ግን የሚገባቸው ሆነው አልተገኙም።+ +9 ስለዚህ በየአውራ ጎዳናው ሂዱና ያገኛችሁትን ሰው ሁሉ ወደ ሠርጉ ጥሩ።’+ +10 በዚህ መሠረት ባሪያዎቹ ወደ አውራ ጎዳናዎች ሄደው ክፉውንም ጥሩውንም፣ ያገኙትን ሰው ሁሉ ሰበሰቡ፤ የሠርጉ አዳራሽም በተጋባዦች ተሞላ። +11 “ንጉሡ እንግዶቹን ለማየት ሲገባ የሠርግ ልብስ ያልለበሰ አንድ ሰው አየ። +12 በዚህ ጊዜ ‘ወዳጄ ሆይ፣ የሠርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት እዚህ ልትገባ ቻልክ?’ አለው። ሰውየውም የሚለው ጠፋው። +13 ከዚያም ንጉሡ አገልጋዮቹን ‘እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት። እዚያም ሆኖ ያለቅሳል፤ ጥርሱንም ያፋጫል’ አላቸው። +14 “የተጠሩት ብዙዎች፣ የተመረጡት ግን ጥቂቶች ናቸውና።” +15 ከዚያም ፈሪሳውያን ሄደው በንግግሩ ሊያጠምዱት ሴራ ጠነሰሱ።+ +16 ስለዚህ ደቀ መዝሙሮቻቸውን ከሄሮድስ ሥርወ መንግሥት ደጋፊዎች+ ጋር ወደ እሱ በመላክ እንዲህ አሉት፦ “መምህር፣ አንተ እውነተኛ እንደሆንክና የአምላክን መንገድ በትክክል እንደምታስተምር እንዲሁም ለመወደድ ብለህ ምንም ነገር እንደማታደርግ፣ የሰውንም ውጫዊ ማንነት አይተህ እንደማትፈርድ እናውቃለን። +17 እስቲ ንገረን፣ ምን ይመስልሃል? ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?”* +18 ኢየሱስ ግን ክፋታቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ግብዞች፣ ለምን ትፈትኑኛላችሁ? +19 እስቲ ለግብር የሚከፈለውን ሳንቲም አሳዩኝ።” እነሱም አንድ ዲናር* አመጡለት። +20 እሱም “ይህ ምስልና የተቀረጸው ጽሑፍ የማን ነው?” አላቸው። +21 እነሱም “የቄሳር” አሉ። እሱም “እንግዲያው የቄሳር የሆነውን ለቄሳር፣ የአምላክ የሆነውን ደግሞ ለአምላክ ስጡ” አላቸው።+ +22 ይህን ሲሰሙ ተደነቁ፤ ከዚያም ትተውት ሄዱ። +23 በዚያኑ ዕለት፣ በትንሣኤ የማያምኑት+ ሰዱቃውያን መጥተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦+ +24 “መምህር፣ ሙሴ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወ���ድ ቢሞት ወንድሙ የሟቹን ሚስት ማግባትና ለወንድሙ ዘር መተካት አለበት’ ብሏል።+ +25 በእኛ ዘንድ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ። የመጀመሪያው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ በመሞቱ ወንድሙ የሟቹን ሚስት አገባ። +26 ሁለተኛውም ሆነ ሦስተኛው እስከ ሰባተኛው ድረስ ልጅ ሳይወልዱ ሞቱ። +27 በመጨረሻም ሴትየዋ ሞተች። +28 እንግዲህ ሁሉም ስላገቧት በትንሣኤ ከሰባቱ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች?” +29 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ “እናንተ ቅዱሳን መጻሕፍትንም ሆነ የአምላክን ኃይል ስለማታውቁ ተሳስታችኋል፤+ +30 ምክንያቱም በትንሣኤ ጊዜ ወንዶችም አያገቡም ሴቶችም አይዳሩም፤ ከዚህ ይልቅ በሰማይ እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ።+ +31 የሙታንን ትንሣኤ በተመለከተ አምላክ እንዲህ ሲል ለእናንተ የተናገረውን አላነበባችሁም? +32 ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ነኝ’ ብሏል።+ እሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም።”+ +33 ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ በትምህርቱ ተደነቁ።+ +34 ፈሪሳውያን፣ ኢየሱስ ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው ሲሰሙ ተሰብስበው መጡ። +35 ከእነሱም መካከል አንድ ሕግ አዋቂ እሱን ለመፈተን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ +36 “መምህር፣ ከሕጉ ውስጥ ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው ነው?”+ +37 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና* በሙሉ አእምሮህ ውደድ።’+ +38 ይህ ከሁሉ የሚበልጠውና የመጀመሪያው ትእዛዝ ነው። +39 ሁለተኛውም ይህንኑ የሚመስል ሲሆን ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’ ይላል።+ +40 መላው ሕግም ሆነ የነቢያት ቃል በእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።”+ +41 ፈሪሳውያን አንድ ላይ ተሰብስበው እንዳሉ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦+ +42 “ስለ መሲሑ ምን ትላላችሁ? የማን ልጅ ነው?” እነሱም “የዳዊት” አሉት።+ +43 እሱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “ታዲያ ዳዊት በመንፈስ ተመርቶ+ እንዴት ጌታ ብሎ ይጠራዋል? +44 ምክንያቱም ዳዊት ‘ይሖዋ* ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው’ ሲል ተናግሯል።+ +45 ታዲያ ዳዊት ጌታ ብሎ ከጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል?”+ +46 ከዚህ በኋላ አንዲት ቃል ሊመልስለት የቻለም ሆነ ከዚያ ቀን ጀምሮ ሊጠይቀው የደፈረ አንድም ሰው አልነበረም። +3 ዳግመኛ ወደ ምኩራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለ* አንድ ሰው ነበር።+ +2 ኢየሱስን ሊከሱት ይፈልጉ ስለነበር ሰውየውን በሰንበት ይፈውሰው እንደሆነ ለማየት በትኩረት ይከታተሉት ነበር። +3 እሱም እጁ የሰለለበትን* ሰው “ተነሳና ወደ መሃል ና” አለው። +4 ከዚያም “በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ? ሕይወት* ማዳን ነው ወይስ ማጥፋት?” አላቸው።+ እነሱ ግን ዝም አሉ። +5 በልባቸው ደንዳናነት+ በጣም አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በብስጭት ከተመለከተ በኋላ ሰውየውን “እጅህን ዘርጋ” አለው። እሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት። +6 ፈሪሳውያኑ ወጥተው ከሄዱ በኋላ ወዲያው ከሄሮድስ ሥርወ መንግሥት ደጋፊዎች+ ጋር በመሰብሰብ እንዴት እንደሚገድሉት መመካከር ጀመሩ። +7 ኢየሱስ ግን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ባሕሩ ሄደ፤ ከገሊላና ከይሁዳ የመጣ ብዙ ሕዝብም ተከተለው።+ +8 ያከናወናቸውን በርካታ ነገሮች የሰሙ ብዙ ሰዎች ከኢየሩሳሌም፣ ከኤዶምያስና ከዮርዳኖስ ማዶ እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና አካባቢ እንኳ ሳይቀር ወደ እሱ መጡ። +9 ኢየሱስም ሕዝቡ እንዳያጨናንቀው አንዲት ትንሽ ጀልባ እንዲያዘጋጁለት ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው። +10 ብዙ ሰዎችን ፈውሶ ስለነበር ከባድ በሽታ የያዛቸው ሁሉ እሱን ለመንካት በዙሪያው ይጋፉ ነበር።+ +11 ርኩሳን መናፍስት+ እን�� ሳይቀሩ ባዩት ቁጥር በፊቱ ወድቀው “አንተ የአምላክ ልጅ ነህ” በማለት ይጮኹ ነበር።+ +12 ሆኖም የእሱን ማንነት ለሌሎች እንዳይገልጹ በተደጋጋሚ አጥብቆ አዘዛቸው።+ +13 ኢየሱስም ወደ ተራራ ወጥቶ የሚፈልጋቸውን ሰዎች ጠራ፤+ እነሱም ወደ እሱ መጡ።+ +14 ከዚያም 12 ሰዎች መርጦ ሐዋርያት ብሎ ሰየማቸው፤* እነዚህ አብረውት የሚሆኑ ከመሆኑም ሌላ ከጊዜ በኋላ ለስብከት ሥራ የሚልካቸውና +15 አጋንንትን የማስወጣት ሥልጣን የሚሰጣቸው ናቸው።+ +16 የመረጣቸውም* 12 ሐዋርያት+ እነዚህ ናቸው፦ ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው ስምዖን፣+ +17 የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና የያዕቆብ ወንድም ዮሐንስ (እነዚህን ቦአኔርጌስ ብሎ የሰየማቸው ሲሆን ትርጉሙም “የነጎድጓድ ልጆች” ማለት ነው)፣+ +18 እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ በርቶሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታዴዎስ፣ ቀነናዊው* ስምዖን +19 እንዲሁም በኋላ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ። ከዚያ በኋላ ወደ አንድ ቤት ሄደ፤ +20 ዳግመኛም ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ፤ ከዚህም የተነሳ እህል እንኳ መቅመስ አልቻሉም። +21 ዘመዶቹ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ “አእምሮውን ስቷል” በማለት ሊይዙት መጡ።+ +22 ከኢየሩሳሌም የመጡ ጸሐፍትም “ብዔልዜቡል* አለበት፤ አጋንንትን የሚያስወጣው በአጋንንት አለቃ ነው” ይሉ ነበር።+ +23 በመሆኑም ወደ እሱ ከጠራቸው በኋላ በምሳሌ እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣን እንዴት ሰይጣንን ሊያስወጣ ይችላል? +24 አንድ መንግሥት እርስ በርሱ ከተከፋፈለ ያ መንግሥት ጸንቶ ሊቆም አይችልም፤+ +25 አንድ ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤት ጸንቶ ሊቆም አይችልም። +26 በተመሳሳይም ሰይጣን በራሱ ላይ የሚነሳና የሚከፋፈል ከሆነ ያከትምለታል እንጂ ሊጸና አይችልም። +27 ደግሞም ወደ አንድ ብርቱ ሰው ቤት የገባ ሰው በቅድሚያ ብርቱውን ሰው ሳያስር ንብረቱን ሊሰርቅ አይችልም። ቤቱን መዝረፍ የሚችለው እንዲህ ካደረገ ብቻ ነው። +28 እውነት እላችኋለሁ፣ የሰው ልጆች ምንም ዓይነት ኃጢአት ቢሠሩ ወይም ምንም ዓይነት የስድብ ቃል ቢናገሩ ሁሉም ይቅር ይባልላቸዋል። +29 ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ለዘላለም ይቅር አይባልም፤+ ከዚህ ይልቅ ለዘላለም የሚጠየቅበት ኃጢአት ይሆንበታል።”+ +30 ይህን ያለው “ርኩስ መንፈስ አለበት” ይሉ ስለነበር ነው።+ +31 በዚህ ጊዜ እናቱና ወንድሞቹ+ መጡ፤ ውጭ ቆመውም ሰው ልከው አስጠሩት።+ +32 በዙሪያውም ብዙ ሰዎች ተቀምጠው ስለነበር “እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ውጭ ሆነው እየጠሩህ ነው” አሉት።+ +33 እሱ ግን መልሶ “እናቴና ወንድሞቼ እነማን ናቸው?” አላቸው። +34 ከዚያም ዙሪያውን ከበው ወደተቀመጡት ሰዎች ተመልክቶ እንዲህ አለ፦ “እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው!+ +35 የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ ለእኔ ወንድሜ፣ እህቴና እናቴ ነው።”+ +7 ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና አንዳንድ ጸሐፍት ወደ እሱ ተሰበሰቡ።+ +2 ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ በረከሰ ማለትም ባልታጠበ እጅ* ምግብ ሲበሉ አዩ። +3 (ፈሪሳውያንና አይሁዳውያን ሁሉ የአባቶችን ወግ አጥብቀው ስለሚከተሉ እጃቸውን እስከ ክርናቸው ድረስ ካልታጠቡ አይበሉም ነበር፤ +4 ከገበያ ሲመለሱም ካልታጠቡ በስተቀር አይበሉም። ጽዋዎችን፣ ገንቦዎችንና የነሐስ ዕቃዎችን ውኃ ውስጥ እንደመንከር* ያሉ ከአባቶቻቸው የወረሷቸውና አጥብቀው የሚከተሏቸው ሌሎች በርካታ ወጎችም አሉ።)+ +5 በመሆኑም እነዚህ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት “ደቀ መዛሙርትህ የአባቶችን ወግ ከመከተል ይልቅ በረከሰ እጅ የሚበሉት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+ +6 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ኢሳይያስ፣ ግብዞች ስለሆናችሁት ስለ እናንተ በትክክል ተንብዮአል፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው።+ +7 የሚያስተምሩት የሰውን ሥርዓት ስለሆነ እኔን የሚያመልኩት በከንቱ ነው።’+ +8 የአምላክን ትእዛዝ ትታችሁ የሰውን ወግ አጥብቃችሁ ትከተላላችሁ።”+ +9 ደግሞም እንዲህ አላቸው፦ “የራሳችሁን ወግ ለመጠበቅ ስትሉ የአምላክን ትእዛዝ በዘዴ ገሸሽ ታደርጋላችሁ።+ +10 ለምሳሌ ሙሴ ‘አባትህንና እናትህን አክብር’+ እንዲሁም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ* ይገደል’+ ብሏል። +11 እናንተ ግን እንዲህ ትላላችሁ፦ ‘አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን “እናንተን መጦር የምችልበት፣ ያለኝ ነገር ሁሉ ቁርባን (ማለትም ለአምላክ የተወሰነ ስጦታ) ነው” ቢል’ +12 ከዚያ በኋላ ለአባቱ ወይም ለእናቱ ምንም ነገር እንዲያደርግ አትፈቅዱለትም።+ +13 በመሆኑም ለሌሎች በምታስተላልፉት ወግ የአምላክን ቃል ትሽራላችሁ።+ እንዲህ ያለም ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።”+ +14 ከዚያም ሕዝቡን እንደገና ወደ እሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሁላችሁም ስሙኝ፤ የምናገረውንም አስተውሉ።+ +15 ከውጭ ወደ ውስጥ ገብቶ ሰውን ሊያረክስ የሚችል ምንም ነገር የለም፤ ከዚህ ይልቅ ሰውን የሚያረክሰው ከውስጡ የሚወጣው ነው።”+ +16 *—— +17 ከሕዝቡ ተለይቶ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ ምሳሌው ይጠይቁት ጀመር።+ +18 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተም እንደ እነሱ ማስተዋል ተሳናችሁ? ከውጭ ወደ ውስጥ ገብቶ ሰውን ሊያረክስ የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ አታውቁም? +19 ምክንያቱም የሚገባው ወደ ልቡ ሳይሆን ወደ ሆዱ ነው፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ ጉድጓድ ይገባል።” እንዲህ በማለት ምግብ ሁሉ ንጹሕ መሆኑን አመለከተ። +20 አክሎም እንዲህ አለ፦ “ሰውን የሚያረክሰው ከውስጡ የሚወጣው ነው።+ +21 ከውስጥ ይኸውም ከሰው ልብ+ ክፉ ሐሳብ ይወጣል፦ የፆታ ብልግና፣* ሌብነት፣ ግድያ፣ +22 ምንዝር፣ መጎምጀት፣ ክፋት፣ ማታለል፣ ዓይን ያወጣ ምግባር፣* ምቀኝነት፣* ስድብ፣ ትዕቢትና ሞኝነት። +23 እነዚህ ክፉ ነገሮች ሁሉ ከሰው ልብ ይወጣሉ፤ ሰውንም ያረክሳሉ።” +24 ከዚያም ተነስቶ ወደ ጢሮስና ሲዶና ክልል ሄደ።+ ወደ አንድ ቤትም ገባ፤ እዚያ መኖሩንም ማንም እንዲያውቅ አልፈለገም፤ ይሁንና ከሰዎች ሊሰወር አልቻለም። +25 ወዲያውም፣ ትንሽ ልጇ በርኩስ መንፈስ የተያዘችባት አንዲት ሴት ስለ እሱ ሰምታ መጣችና እግሩ ላይ ወደቀች።+ +26 ሴትየዋ ግሪካዊት፣ በዜግነት* ደግሞ ሲሮፊንቃዊት ነበረች፤ እሷም ጋኔኑን ከልጇ እንዲያስወጣላት ወተወተችው። +27 እሱ ግን “የልጆችን ዳቦ ወስዶ ለቡችሎች መጣል ተገቢ ስላልሆነ መጀመሪያ ልጆቹ ይጥገቡ” አላት።+ +28 ሆኖም ሴትየዋ መልሳ “አዎ ጌታዬ፣ ቡችሎችም እኮ ከገበታ በታች ሆነው ከልጆች የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለችው። +29 በዚህ ጊዜ “ሂጂ፤ እንዲህ ስላልሽ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቷል” አላት።+ +30 እሷም ወደ ቤቷ ስትመለስ ልጇ አልጋ ላይ ተኝታ፣ ጋኔኑም ወጥቶላት አገኘቻት።+ +31 ኢየሱስ ከጢሮስ ክልል ሲመለስ በሲዶና በኩል አድርጎ ዲካፖሊስ በተባለው ክልል* በማለፍ ወደ ገሊላ ባሕር ሄደ።+ +32 በዚያም* ሰዎች መስማት የተሳነውና የመናገር እክል ያለበት+ አንድ ሰው ወደ እሱ አምጥተው እጁን እንዲጭንበት ተማጸኑት። +33 እሱም ከሕዝቡ ለይቶ ለብቻው ወሰደው። ከዚያም ጣቶቹን በሰውየው ጆሮዎች ውስጥ አስገባ፤ እንትፍ ካለ በኋላም የሰውየውን ምላስ ዳሰሰ።+ +34 ወደ ሰማይ እየተመለከተም በረጅሙ ተንፍሶ “ኤፈታ” አለው፤ ይህም “ተከፈት” ማለት ነው። +35 በዚህ ጊዜ ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤+ ምላሱም ተፈቶ አጥርቶ መናገር ጀመረ። +36 ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤+ እነሱ ግን ይበል�� ባስጠነቀቃቸው መጠን የዚያኑ ያህል ነገሩን በስፋት ያወሩ ነበር።+ +37 እንዲያውም ከመጠን በላይ ከመደነቃቸው የተነሳ+ “ያደረገው ነገር ሁሉ መልካም ነው። ሌላው ቀርቶ መስማት የተሳናቸው ሰዎች እንዲሰሙ፣ ዱዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል” አሉ።+ +12 ከዚያም ምሳሌ በመጠቀም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ሰው የወይን እርሻ አለማ፤+ ዙሪያውንም አጠረው፤ ጉድጓድ ቆፍሮም የወይን መጭመቂያ አዘጋጀ፤ ማማም ሠራለት፤+ ከዚያም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።+ +2 ወቅቱ ሲደርስ ከወይኑ ፍሬ ድርሻውን ከገበሬዎቹ እንዲያመጣለት አንድ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ። +3 እነሱ ግን ይዘው ደበደቡት፤ ባዶ እጁንም ሰደዱት። +4 በድጋሚ ሌላ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ፤ እሱንም ራሱን ፈነከቱት፤ ደግሞም አዋረዱት።+ +5 ሌላም ባሪያ ላከ፤ እሱን ደግሞ ገደሉት፤ ሌሎች ብዙዎችንም ላከ፤ አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ ገደሉ። +6 አሁን የቀረው የሚወደው ልጁ ነበር።+ ‘መቼም ልጄን ያከብሩታል’ በማለት በመጨረሻ እሱን ላከው። +7 እነዚያ ገበሬዎች ግን እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው።+ ኑ እንግደለው፤ ርስቱም የእኛ ይሆናል’ ተባባሉ። +8 ስለዚህ ይዘው ገደሉት፤ ከወይን እርሻውም አውጥተው ጣሉት።+ +9 እንግዲህ የወይኑ እርሻ ባለቤት ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? ይመጣና ገበሬዎቹን ይገድላል፤ የወይን እርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል።+ +10 እንዲህ የሚለውን የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል አላነበባችሁም? ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ የማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ።+ +11 ይህ የይሖዋ* ሥራ ነው፤ ለዓይናችንም ድንቅ ነው።’”+ +12 በዚህ ጊዜ ምሳሌውን የተናገረው እነሱን አስቦ እንደሆነ ስለተረዱ ሊይዙት* ፈለጉ። ሆኖም ሕዝቡን ስለፈሩ ትተውት ሄዱ።+ +13 ከዚያም በንግግሩ ሊያጠምዱት ፈልገው አንዳንድ ፈሪሳውያንን እና የሄሮድስ ሥርወ መንግሥት ደጋፊዎችን ወደ እሱ ላኩ።+ +14 እነሱም መጥተው እንዲህ አሉት፦ “መምህር፣ አንተ እውነተኛ እንደሆንክና ለመወደድ ብለህ ምንም ነገር እንደማታደርግ፣ የሰውንም ውጫዊ ማንነት አይተህ እንደማትፈርድ፣ ከዚህ ይልቅ የአምላክን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን። ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?* +15 እንክፈል ወይስ አንክፈል?” እሱም ግብዝነታቸውን ተረድቶ “ለምን ትፈትኑኛላችሁ? እስቲ አንድ ዲናር* አምጡና አሳዩኝ” አላቸው። +16 እነሱም አመጡለት፤ እሱም “ይህ ምስልና የተቀረጸው ጽሑፍ የማን ነው?” አላቸው። እነሱም “የቄሳር” አሉት። +17 ከዚያም ኢየሱስ “የቄሳር የሆነውን ለቄሳር፣+ የአምላክ የሆነውን ደግሞ ለአምላክ+ ስጡ” አላቸው። እነሱም በእሱ ተደነቁ። +18 በትንሣኤ የማያምኑት+ ሰዱቃውያን ደግሞ መጥተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦+ +19 “መምህር፣ ሙሴ አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሚስቱ በሞት ቢለይ ወንድሙ ሚስትየዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር መተካት እንዳለበት ጽፎልናል።+ +20 ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ። የመጀመሪያው ሚስት አገባና ዘር ሳይተካ ሞተ። +21 ከዚያም ሁለተኛው አገባት፤ ሆኖም ዘር ሳይተካ ሞተ፤ ሦስተኛውም እንዲሁ፤ +22 ሰባቱም ዘር አልተኩም። በመጨረሻም ሴትየዋ ሞተች። +23 እንግዲህ ሰባቱም ስላገቧት በትንሣኤ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች?” +24 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የምትሳሳቱት ቅዱሳን መጻሕፍትንም ሆነ የአምላክን ኃይል ባለማወቃችሁ አይደለም?+ +25 ከሞት በሚነሱበት ጊዜ ወንዶችም አያገቡም ሴቶችም አይዳሩም፤ ከዚህ ይልቅ በሰማያት እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ።+ +26 ስለ ሙታን መነሳት ግን በሙሴ መጽሐፍ፣ ስለ ቁጥቋጦው በሚገልጸው ታሪክ ላይ አምላክ ሙሴን ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የ��ስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ነኝ’ እንዳለው አላነበባችሁም?+ +27 እሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም። እናንተ እጅግ ተሳስታችኋል።”+ +28 ከጸሐፍት ወገን የሆነ አንድ ሰው መጥቶ ሲከራከሩ ይሰማ ነበር፤ ኢየሱስ ጥሩ አድርጎ እንደመለሰላቸው አስተውሎ “ከትእዛዛት ሁሉ የመጀመሪያው* የትኛው ነው?” ሲል ጠየቀው።+ +29 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የመጀመሪያው ይህ ነው፦ ‘እስራኤል ሆይ ስማ፤ ይሖዋ* አምላካችን አንድ ይሖዋ* ነው፤ +30 አንተም አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ አእምሮህና በሙሉ ኃይልህ ውደድ።’+ +31 ሁለተኛው ደግሞ ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’ የሚል ነው።+ ከእነዚህ የሚበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለም።” +32 ጸሐፊውም እንዲህ አለው፦ “መምህር፣ የተናገርከው እውነት ነው፤ ‘እሱ አንድ ነው፤ ከእሱ ሌላ አምላክ የለም’፤+ +33 እሱን በሙሉ ልብ፣ በሙሉ አእምሮና* በሙሉ ኃይል መውደድ እንዲሁም ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ፣ ሙሉ በሙሉ ከሚቃጠል መባና ከመሥዋዕት ሁሉ እጅግ ይበልጣል።”+ +34 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ በማስተዋል እንደመለሰ ተረድቶ “አንተ ከአምላክ መንግሥት የራቅክ አይደለህም” አለው። ከዚህ በኋላ ግን ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም።+ +35 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ እያስተማረ ሳለ እንዲህ አለ፦ “ጸሐፍት ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ?+ +36 ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ+ ሲናገር ‘ይሖዋ* ጌታዬን “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው’ ብሏል።+ +37 ዳዊት ራሱ ጌታ ብሎ ከጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል?”+ ሕዝቡም በደስታ ያዳምጠው ነበር። +38 ማስተማሩንም በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ ዘርፋፋ ልብስ ለብሰው መዞር ይወዳሉ፤ በገበያ ቦታም ሰዎች እጅ እንዲነሷቸው ይፈልጋሉ፤+ +39 በምኩራብ ከፊት መቀመጥ፣* በራት ግብዣ ላይም የክብር ቦታ ይፈልጋሉ።+ +40 የመበለቶችን ቤት* ያራቁታሉ፤ ለታይታ ብለውም* ጸሎታቸውን ያስረዝማሉ። እነዚህ የከፋ ፍርድ ይጠብቃቸዋል።” +41 ኢየሱስ በመዋጮ ሣጥኖቹ*+ ትይዩ ተቀምጦ ሕዝቡ በመዋጮ ሣጥኖቹ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንደሚከቱ ይመለከት ጀመር፤ ብዙ ሀብታሞችም ብዙ ሳንቲሞች ይከቱ ነበር።+ +42 በዚህ ጊዜ አንዲት ድሃ መበለት መጥታ በጣም አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ትናንሽ ሳንቲሞች* ከተተች።+ +43 ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ በመዋጮ ሣጥኖቹ* ውስጥ ገንዘብ ከጨመሩት ሁሉ የበለጠ የሰጠችው ይህች ድሃ መበለት ነች።+ +44 ሁሉም የሰጡት ከትርፋቸው ነውና፤ እሷ ግን በድሃ አቅሟ ያላትን ሁሉ፣ መተዳደሪያዋን በጠቅላላ ሰጥታለች።”+ +1 የአምላክ ልጅ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገልጸው ምሥራች የሚጀምረው እንደሚከተለው ነው፦ +2 ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “(እነሆ፣ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ፤ እሱም መንገድህን ያዘጋጃል።)*+ +3 አንድ ሰው በምድረ በዳ ‘የይሖዋን* መንገድ አዘጋጁ፤ ጎዳናዎቹንም አቅኑ’ በማለት ይጮኻል።”+ +4 አጥማቂው ዮሐንስ ለኃጢአት ይቅርታ፣ የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት በምድረ በዳ እየሰበከ ነበር።+ +5 መላው የይሁዳ ምድር እንዲሁም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሙሉ ወደ እሱ ይመጡ ነበር፤ ደግሞም ኃጢአታቸውን በግልጽ እየተናዘዙ ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በእሱ ይጠመቁ* ነበር።+ +6 ዮሐንስ የግመል ፀጉር ይለብስ፣ ወገቡም ላይ የቆዳ ቀበቶ ይታጠቅ+ የነበረ ሲሆን አንበጣና የዱር ማር ይበላ ነበር።+ +7 እንዲህ እያለም ይሰብክ ነበር፦ “ከእኔ በኋላ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እኔ ጎንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ ���ንኳ ለመፍታት አልበቃም።+ +8 እኔ በውኃ አጠመቅኳችሁ፤ እሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል።”+ +9 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት መጥቶ ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ በዮሐንስ ተጠመቀ።+ +10 ወዲያው ከውኃው እንደወጣ ሰማያት ተከፍተው መንፈስ እንደ ርግብ በእሱ ላይ ሲወርድ አየ።+ +11 ከዚያም “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።+ +12 ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ገፋፋው። +13 በምድረ በዳም 40 ቀን ቆየ። በዚያ ሳለ ሰይጣን ፈተነው፤+ ከአራዊትም ጋር ነበረ። መላእክትም ያገለግሉት ነበር።+ +14 ዮሐንስ ከታሰረ በኋላ ኢየሱስ የአምላክን ምሥራች እየሰበከ+ ወደ ገሊላ ሄደ።+ +15 “የተወሰነው ጊዜ ደርሷል፤ የአምላክ መንግሥት ቀርቧል። ንስሐ ግቡ፤+ በምሥራቹም እመኑ” ይል ነበር። +16 በገሊላ ባሕር* አጠገብ እየሄደ ሳለ ዓሣ አጥማጆች የነበሩት+ ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ+ መረቦቻቸውን ወደ ባሕሩ ሲጥሉ አየ።+ +17 ኢየሱስም “ኑ ተከተሉኝ፤ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው።+ +18 እነሱም ወዲያውኑ መረቦቻቸውን ትተው ተከተሉት።+ +19 ትንሽ እልፍ እንዳለ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን ጀልባቸው ላይ ሆነው መረቦቻቸውን ሲጠግኑ+ አያቸውና +20 ወዲያውኑ ጠራቸው። እነሱም አባታቸውን ዘብዴዎስን ከቅጥር ሠራተኞቹ ጋር ጀልባው ላይ ትተው ተከተሉት። +21 ከዚያም ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ። የሰንበት ቀን እንደደረሰም ወደ ምኩራብ ገብቶ ማስተማር ጀመረ።+ +22 እንደ ጸሐፍት ሳይሆን እንደ ባለሥልጣን ያስተምራቸው ስለነበረ ሕዝቡ በትምህርት አሰጣጡ እጅግ ተደነቁ።+ +23 በዚሁ ጊዜ በምኩራባቸው ውስጥ የነበረ፣ ርኩስ መንፈስ የያዘው አንድ ሰው በኃይል ጮኾ እንዲህ አለ፦ +24 “የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ እኛ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለን?+ የመጣኸው ልታጠፋን ነው? ማን እንደሆንክ በሚገባ አውቃለሁ፤ አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ ነህ!”+ +25 ሆኖም ኢየሱስ “ዝም በል፤ ከእሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። +26 ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን ጥሎ ካንፈራገጠው በኋላ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእሱ ወጣ። +27 ሕዝቡ ሁሉ እጅግ በመገረም እርስ በርሳቸው “ይህ ምንድን ነው? ትምህርቱ ለየት ያለ ነው! ርኩሳን መናፍስትን እንኳ ሳይቀር በሥልጣን ያዛል፤ እነሱም ይታዘዙለታል” ተባባሉ። +28 ወዲያውኑም በመላው የገሊላ ግዛት በየአቅጣጫው ስለ እሱ በስፋት ተወራ። +29 በዚህ ጊዜ ከምኩራብ ወጥተው ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት ሄዱ።+ +30 የስምዖን አማት+ ትኩሳት ይዟት ተኝታ ነበር፤ ስለ እሷም ወዲያው ለኢየሱስ ነገሩት። +31 እሱም ወደተኛችበት በመሄድ እጇን ይዞ አስነሳት። በዚህ ጊዜ ትኩሳቱ ለቀቃትና ታገለግላቸው ጀመር። +32 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ፣ ምሽት ላይ ሰዎች የታመሙትንና በአጋንንት የተያዙትን ሁሉ ወደ እሱ ያመጡ ጀመር፤+ +33 የከተማዋም ሰው ሁሉ በደጅ ተሰብስቦ ነበር። +34 ኢየሱስም በተለያየ በሽታ የተያዙ በርካታ ሰዎችን ፈወሰ፤+ ብዙ አጋንንትንም አወጣ። ሆኖም አጋንንቱ ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ስለነበር* እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም። +35 ኢየሱስ በማለዳ ገና ጎህ ሳይቀድ ተነስቶ ከቤት ወጣና ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ፤ እዚያም መጸለይ ጀመረ።+ +36 ይሁን እንጂ ስምዖንና ከእሱ ጋር የነበሩት አጥብቀው ፈለጉት፤ +37 ባገኙትም ጊዜ “ሰው ሁሉ እየፈለገህ ነው” አሉት። +38 እሱ ግን “በዚያም እንድሰብክ በአቅራቢያ ወዳሉት ከተሞች እንሂድ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና” አላቸው።+ +39 እንዳለውም በምኩራቦቻቸው እየሰበከና አጋንንትን እያወጣ በመላዋ ገሊላ ተዘዋወረ።+ +40 በሥጋ ደዌ የተያዘ አንድ ሰውም ወ�� እሱ ቀርቦ “ብትፈልግ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ተንበርክኮ ተማጸነው።+ +41 በዚህ ጊዜ በጣም አዘነለትና እጁን ዘርግቶ ዳሰሰው፤ ከዚያም “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው።+ +42 ወዲያውኑ የሥጋ ደዌው ለቀቀውና ነጻ። +43 ከዚያም ኢየሱስ ሰውየውን በጥብቅ አስጠንቅቆ ቶሎ አሰናበተው፤ +44 እንዲህም አለው፦ “ለማንም አንዳች ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ሙሴ ያዘዛቸውንም ነገሮች አቅርብ፤+ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ።”+ +45 ሰውየው ግን ከሄደ በኋላ የሆነውን ነገር በሰፊው አወራ፤ ወሬውንም በየቦታው አሰራጨ፤ ስለሆነም ኢየሱስ ከዚህ በኋላ በግልጽ ወደ ከተማ መግባት ባለመቻሉ ከከተማ ውጭ ገለል ባሉ ቦታዎች ይኖር ጀመር። ይሁንና ሰዎች ከየአቅጣጫው ወደ እሱ መምጣታቸውን ቀጠሉ።+ +8 በዚያን ወቅት፣ እንደገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ የሚበሉትም አልነበራቸውም። ስለዚህ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ +2 “እነዚህ ሰዎች ሦስት ቀን ሙሉ ከእኔ ጋር ስለቆዩና የሚበሉት ስለሌላቸው+ አዝንላቸዋለሁ።+ +3 እንዲሁ ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ብሰዳቸው መንገድ ላይ ዝለው ይወድቃሉ፤ ደግሞም አንዳንዶቹ የመጡት ከሩቅ ነው።” +4 ደቀ መዛሙርቱ ግን “በዚህ ገለልተኛ ስፍራ እነዚህን ሰዎች የሚያጠግብ በቂ ዳቦ ከየት ማግኘት ይቻላል?” ሲሉ መለሱለት። +5 በዚህ ጊዜ “ስንት ዳቦ አላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነሱም “ሰባት” አሉት።+ +6 እሱም ሕዝቡ መሬት ላይ እንዲቀመጥ አዘዘ። ከዚያም ሰባቱን ዳቦ ይዞ አምላክን አመሰገነ፤ ቆርሶም እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነሱም ለሕዝቡ አደሉ።+ +7 ጥቂት ትናንሽ ዓሣዎችም ነበሯቸው፤ እነዚህንም ከባረከ በኋላ እንዲያድሉ ነገራቸው። +8 ሕዝቡም በልቶ ጠገበ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ሰባት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ +"9 በዚያም 4,000 ገደማ ወንዶች ነበሩ። በመጨረሻም አሰናበታቸው። " +10 ወዲያውኑ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በጀልባ ተሳፍሮ ዳልማኑታ ወደተባለ ክልል መጣ።+ +11 እዚያም ፈሪሳውያን መጥተው እሱን ለመፈተን ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው በመጠየቅ ይከራከሩት ጀመር።+ +12 እሱም እጅግ አዝኖ በረጅሙ ከተነፈሰ በኋላ “ይህ ትውልድ ምልክት የሚፈልገው ለምንድን ነው?+ እውነት እላችኋለሁ፣ ለዚህ ትውልድ ምንም ምልክት አይሰጠውም” አለ።+ +13 ከዚያም ትቷቸው ሄደ፤ እንደገና ጀልባ ተሳፍሮም ወደ ባሕሩ ማዶ ተሻገረ። +14 ይሁንና ዳቦ መያዝ ረስተው ስለነበር በጀልባው ውስጥ ከአንድ ዳቦ በስተቀር ምንም አልነበራቸውም።+ +15 ኢየሱስም “ተጠንቀቁ፣ ከፈሪሳውያን እርሾና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ” ሲል በግልጽ አስጠነቀቃቸው።+ +16 እነሱም ዳቦ ባለመያዛቸው እርስ በርሳቸው ይከራከሩ ጀመር። +17 ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ዳቦ ባለመያዛችሁ ለምን ትከራከራላችሁ? አሁንም አልገባችሁም? ደግሞስ አላስተዋላችሁም? ልባችሁ መረዳት እንደተሳነው ነው? +18 ‘ዓይን እያላችሁ አታዩም? ጆሮ እያላችሁ አትሰሙም?’ ደግሞስ አታስታውሱም? +"19 አምስቱን ዳቦ ለ5,000ዎቹ ወንዶች በቆረስኩ+ ጊዜ ስንት ቅርጫት ሙሉ ትርፍራፊ ሰበሰባችሁ?” እነሱም “አሥራ ሁለት”+ አሉት።" +"20 “ሰባቱን ዳቦ ለ4,000ዎቹ ወንዶች በቆረስኩ ጊዜ ስንት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ትርፍራፊ አነሳችሁ?” እነሱም “ሰባት” አሉት።+" +21 እሱም “ታዲያ አሁንም አልገባችሁም?” አላቸው። +22 ከዚያም ወደ ቤተሳይዳ መጡ። በዚያም ሰዎች አንድ ዓይነ ስውር ወደ ኢየሱስ አምጥተው እንዲዳስሰው ተማጸኑት።+ +23 እሱም ዓይነ ስውሩን፣ እጁን ይዞ ከመንደሩ ውጭ ወሰደው። በዓይኖቹ ላይ እንትፍ ካለ በኋላ+ እጆቹን ጫነበትና “የሚታይህ ነገር አለ?” ሲል ጠየቀው። +24 ሰውየውም ቀና ብሎ በማየት “ሰዎች ይታዩኛል፤ ሆኖም የሚራመዱ ዛፎች ይመስላሉ” አለ። +25 ኢየሱስ እንደገና እጆቹን ሰውየው ዓይኖች ላይ ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ሰውየው አጥርቶ አየ። ዓይኖቹም በሩ፤ ሁሉንም ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ቻለ። +26 በመጨረሻም “ወደ መንደሩ አትግባ” ብሎ ወደ ቤቱ ሰደደው። +27 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቂሳርያ ፊልጵስዩስ መንደሮች አመሩ፤ በመንገድም ላይ ሳሉ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል?” ሲል ጠየቃቸው።+ +28 እነሱም “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣+ ሌሎች ኤልያስ፣+ ሌሎች ደግሞ ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል” አሉት። +29 ከዚያም እነሱን “እናንተስ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ ነህ”+ ብሎ መለሰለት። +30 በዚህ ጊዜ ስለ እሱ ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አዘዛቸው።+ +31 በተጨማሪም የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበሉ እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት ተቀባይነት ማጣቱ ብሎም መገደሉና+ ከሦስት ቀን በኋላ መነሳቱ+ እንደማይቀር ያስተምራቸው ጀመር። +32 ደግሞም ይህን በግልጽ ነገራቸው። ጴጥሮስ ግን ኢየሱስን ለብቻው በመውሰድ ይገሥጸው ጀመር።+ +33 በዚህ ጊዜ ዞር ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ተመለከተና ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፣ ሰይጣን!* የሰውን እንጂ የአምላክን ሐሳብ አታስብም” ሲል ገሠጸው።+ +34 ከዚህ በኋላ ሕዝቡን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ እሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ፤ የራሱን የመከራ እንጨት* ይሸከም፤ ያለማቋረጥም ይከተለኝ።+ +35 ሕይወቱን* ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔና ለምሥራቹ ሲል ሕይወቱን* የሚያጣ ሁሉ ግን ያድናታል።+ +36 ደግሞስ አንድ ሰው ዓለምን ሁሉ የራሱ ቢያደርግና ሕይወቱን* ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል?+ +37 ሰው ለሕይወቱ* ምትክ የሚሆን ምን ነገር ሊሰጥ ይችላል?+ +38 በዚህ አመንዝራና* ኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅም ከቅዱሳን መላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ሲመጣ+ ያፍርበታል።”+ +11 ወደ ኢየሩሳሌም፣ በደብረ ዘይት ተራራ ወዳሉት ወደ ቤተፋጌ እና ወደ ቢታንያ+ በተቃረቡ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ላካቸው፤+ +2 እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ ወደ መንደሩም እንደገባችሁ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ ውርንጭላ ታስሮ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደዚህ አምጡት። +3 ማንም ሰው ‘ምን ማድረጋችሁ ነው?’ ቢላችሁ ‘ጌታ ይፈልገዋል፤ ደግሞም ወዲያውኑ ወደዚህ ይመልሰዋል’ በሉት።” +4 እነሱም ሄዱ፤ ውርንጭላውንም በአንድ ጠባብ መንገድ ዳር፣ ደጃፍ ላይ ታስሮ አገኙት።+ +5 በዚያ ከቆሙት ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ “ውርንጭላውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። +6 እነሱም ኢየሱስ ያለውን ነገሯቸው፤ ከዚያም ፈቀዱላቸው። +7 ውርንጭላውንም+ ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ መደረቢያቸውንም በውርንጭላው ጀርባ ላይ አደረጉ፤ እሱም ተቀመጠበት።+ +8 ብዙዎችም መደረቢያቸውን በመንገዱ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎች ደግሞ በመንገድ ዳር ካሉት ዛፎች ቅርንጫፎች እየቆረጡ አነጠፉ።+ +9 ከፊቱ የሚሄዱትና ከኋላው የሚከተሉት እንዲህ እያሉ ይጮኹ ነበር፦ “እንድታድነው እንለምንሃለን!*+ በይሖዋ* ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!+ +10 የሚመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከ ነው!+ በሰማይ የምትኖረው ሆይ፣ እንድታድነው እንለምንሃለን!” +11 ኢየሱስም ኢየሩሳሌም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያውም ያለውን ነገር ሁሉ ተመለከተ፤ ሆኖም ሰዓቱ ገፍቶ ስለነበር ከአሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ሄደ።+ +12 በማግስቱ ከቢታንያ እየወጡ ሳለ ተራበ።+ +13 ቅጠሏ የለመለመ አንዲት የበለስ ዛፍ ከሩቅ አየና ምናልባት ፍሬ ይገኝባት እንደሆነ ለማየት ሄደ። ወደ እሷ በቀረበ ጊዜ ግን በለስ የሚያፈራበት ወቅት ስላልነበረ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። +14 ስለዚህ ኢየሱስ ዛፏን “ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ” አላት።+ ይህን ሲናገርም ደቀ መዛሙርቱ ይሰሙት ነበር። +15 ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። በዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በቤተ መቅደሱ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያስወጣ ጀመር፤ የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችን መቀመጫዎችም ገለባበጠ፤+ +16 ማንም ሰው ዕቃ ተሸክሞ በቤተ መቅደሱ አቋርጦ እንዳያልፍም ከለከለ። +17 ሰዎቹንም ያስተምር ነበር፤ ደግሞም “‘ቤቴ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ አልተጻፈም?+ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት” አላቸው።+ +18 የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም ያደረገውን በሰሙ ጊዜ እሱን የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ጀመር፤+ ምክንያቱም ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ስለሚገረም ኢየሱስን ይፈሩት ነበር።+ +19 አመሻሽ ላይ ከከተማዋ ወጡ። +20 ማለዳም ላይ በመንገድ ሲያልፉ የበለስ ዛፏ ከነሥሯ ደርቃ አዩ።+ +21 ጴጥሮስም ትዝ አለውና “ረቢ፣ ተመልከት! የረገምካት የበለስ ዛፍ ደርቃለች” አለው።+ +22 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “በአምላክ ላይ እምነት ይኑራችሁ። +23 እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነስተህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ቢለውና በልቡ ሳይጠራጠር የተናገረው ነገር እንደሚፈጸም ቢያምን ይሆንለታል።+ +24 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ በጸሎት የምትጠይቁትንና የምትለምኑትን ነገር ሁሉ እንዳገኛችሁት አድርጋችሁ እመኑ፤ ደግሞም ታገኙታላችሁ።+ +25 በሰማያት ያለው አባታችሁ በደላችሁን ይቅር እንዲላችሁ እናንተም ለመጸለይ በምትቆሙበት ጊዜ በማንም ሰው ላይ ያላችሁን ቅሬታ ሁሉ ይቅር በሉ።”+ +26 *—— +27 እንደገናም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። በቤተ መቅደሱም ሲዘዋወር የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና ሽማግሌዎች መጥተው +28 “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? እነዚህን ነገሮች እንድታደርግስ ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” አሉት።+ +29 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ። እናንተም መልሱልኝ፤ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ። +30 ዮሐንስ የማጥመቅ ሥልጣን+ ያገኘው ከአምላክ* ነው ወይስ ከሰው? መልሱልኝ።”+ +31 እነሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ይባባሉ ጀመር፦ “‘ከአምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ +32 ደፍረን ‘ከሰው ነው’ ብንልስ?” ሰዎቹ ሁሉ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያዩት ስለነበር ሕዝቡን ፈሩ።+ +33 ስለዚህ ለኢየሱስ “አናውቅም” ብለው መለሱለት። ኢየሱስም “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው። +2 ይሁን እንጂ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ተመልሶ መጣ፤ ደግሞም ቤት ውስጥ እንዳለ ተወራ።+ +2 በመሆኑም ቤቱ ሞልቶ ደጅ ላይ እንኳ ቦታ እስኪታጣ ድረስ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ እሱም የአምላክን ቃል ይነግራቸው ጀመር።+ +3 ሰዎችም አንድ ሽባ በአራት ሰዎች አሸክመው ወደ እሱ አመጡ።+ +4 ሆኖም ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ሽባውን ወደ ኢየሱስ ማቅረብ ስላልቻሉ ከኢየሱስ በላይ ያለውን ጣሪያ ከነደሉ በኋላ ሽባው የተኛበትን ቃሬዛ ወደ ታች አወረዱት። +5 ኢየሱስም እምነታቸውን በማየት+ ሽባውን “ልጄ ሆይ፣ ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው።+ +6 በዚያ ተቀምጠው የነበሩ አንዳንድ ጸሐፍት ግን እንዲህ ሲሉ በልባቸው አሰቡ፦+ +7 “ይህ ሰው እንዲህ ብሎ የሚናገ��ው ለምንድን ነው? አምላክን እየተዳፈረ እኮ ነው። ከአንዱ ከአምላክ በቀር ኃጢአትን ማን ይቅር ሊል ይችላል?”+ +8 ሆኖም ኢየሱስ በልባቸው ይህን እያሰቡ እንዳሉ ወዲያው በመንፈሱ ተረድቶ “በልባችሁ እንዲህ እያላችሁ የምታስቡት ለምንድን ነው?+ +9 ሽባውን ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሏል’ ከማለትና ‘ተነሳና ቃሬዛህን ተሸክመህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀላል? +10 ይሁንና የሰው ልጅ+ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ . . .”+ ካለ በኋላ ሽባውን እንዲህ አለው፦ +11 “ተነስ፣ ቃሬዛህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ።” +12 በዚህ ጊዜ ሽባው ብድግ ብሎ ወዲያው ቃሬዛውን በማንሳት በሁሉ ፊት እየተራመደ ወጣ። ይህን ሲያዩ ሁሉም እጅግ ተደነቁ፤ ደግሞም “እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም”+ በማለት አምላክን አከበሩ። +13 ኢየሱስ እንደገና ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሄደ፤ ሕዝቡም ወደ እሱ ጎረፈ፤ እሱም ያስተምራቸው ጀመር። +14 በመንገድ እያለፈ ሳለም የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን በቀረጥ መሰብሰቢያው ቦታ ተቀምጦ አየውና “ተከታዬ ሁን” አለው። በዚህ ጊዜ ተነስቶ ተከተለው።+ +15 በኋላም በሌዊ ቤት ተቀምጦ እየበላ ነበር፤ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኃጢአተኞችም ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እየበሉ ነበር። ከእነሱም መካከል ብዙዎቹ እሱን መከተል ጀምረው ነበር።+ +16 ሆኖም ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ ጸሐፍት ከኃጢአተኞችና ከቀረጥ ሰብሳቢዎች ጋር ሲበላ ባዩ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “እንዴት ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር ይበላል?” አሏቸው። +17 ኢየሱስ ይህን ሲሰማ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ልጠራ ነው” አላቸው።+ +18 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን የመጾም ልማድ ነበራቸው። ስለዚህም ወደ እሱ መጥተው “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ዘወትር ሲጾሙ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?” አሉት።+ +19 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው+ ከእነሱ ጋር እያለ ጓደኞቹ የሚጾሙበት ምን ምክንያት አለ? ሙሽራው አብሯቸው እስካለ ድረስ ሊጾሙ አይችሉም። +20 ሆኖም ሙሽራው ከእነሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤+ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ። +21 በአሮጌ ልብስ ላይ ውኃ ያልነካው አዲስ ጨርቅ የሚጥፍ ሰው የለም። እንዲህ ቢያደርግ ግን አዲሱ ጨርቅ ሲሸበሸብ አሮጌውን ስለሚስበው ቀዳዳው የባሰ ይሰፋል።+ +22 እንዲሁም ባረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያስቀምጥ ሰው የለም። እንዲህ ቢያደርግ ግን የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁ ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። ይሁንና አዲስ የወይን ጠጅ የሚቀመጠው በአዲስ አቁማዳ ነው።” +23 በሰንበት ቀን በእህል እርሻ መካከል እያለፈ ሳለ አብረውት ይሄዱ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር።+ +24 በመሆኑም ፈሪሳውያን “ተመልከት! በሰንበት ቀን በሕግ የተከለከለ ነገር የሚያደርጉት ለምንድን ነው?” አሉት። +25 እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ዳዊት የሚበላው ባጣ ጊዜ እንዲሁም እሱና አብረውት የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ነገር ፈጽሞ አላነበባችሁም?+ +26 ሊቀ ካህናት ስለሆነው ስለ አብያታር+ በሚናገረው ታሪክ ላይ ዳዊት ወደ አምላክ ቤት ገብቶ ከካህናት በቀር ማንም እንዲበላ ያልተፈቀደውን በአምላክ ፊት የቀረበ ኅብስት+ እንደበላና ከእሱ ጋር ለነበሩትም እንደሰጣቸው አላነበባችሁም?” +27 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰንበት ለሰው ተሰጠ እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም።+ +28 በመሆኑም የሰው ልጅ የሰንበትም እንኳ ጌታ ነው።”+ +4 ዳግመኛም በባሕሩ አጠገብ ��ኖ ያስተምር ጀመር፤ እጅግ ብዙ ሕዝብም ወደ እሱ መጥቶ ተሰበሰበ። በመሆኑም ጀልባ ላይ ወጥቶ ከተቀመጠ በኋላ ከባሕሩ ዳርቻ ፈቀቅ አለ፤ ሕዝቡ ሁሉ ግን በባሕሩ ዳርቻ ነበር።+ +2 ከዚያም ብዙ ነገር በምሳሌ ያስተምራቸው ጀመር፤+ እንዲህም አላቸው፦+ +3 “ስሙ። እነሆ፣ ዘሪው ሊዘራ ወጣ።+ +4 በሚዘራበት ጊዜ አንዳንዶቹ ዘሮች መንገድ ዳር ወደቁ፤ ወፎችም መጥተው ለቀሟቸው። +7 ሌሎቹ ዘሮች ደግሞ በእሾህ መካከል ወደቁ፤ እሾሁም አድጎ አነቃቸው፤ ፍሬም አልሰጡም።+ +8 ሌሎቹ ግን ጥሩ አፈር ላይ ወድቀው ከበቀሉና ካደጉ በኋላ ፍሬ ማፍራት ጀመሩ፤ ደግሞም 30፣ 60 እና 100 እጥፍ አፈሩ።”+ +9 ከዚያም “የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ” አለ።+ +10 ብቻውን በሆነ ጊዜ አሥራ ሁለቱና በዙሪያው የነበሩት ሌሎች ሰዎች ስለ ምሳሌዎቹ ይጠይቁት ጀመር።+ +11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ለእናንተ የአምላክን መንግሥት ቅዱስ ሚስጥር+ የመረዳት ችሎታ ተሰጥቷችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን የሚሰሙት ነገር ሁሉ እንዲሁ ምሳሌ ብቻ ሆኖ ይቀርባቸዋል፤+ +12 በመሆኑም ማየቱን ያያሉ ግን ልብ አይሉም፤ መስማቱን ይሰማሉ ግን ትርጉሙን አይረዱም፤ ደግሞም ሙሉ በሙሉ ስለማይመለሱ ይቅርታ አያገኙም።”+ +13 በተጨማሪም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ምሳሌ ካልተረዳችሁ ታዲያ ሌሎቹን ምሳሌዎች ሁሉ እንዴት ትረዳላችሁ? +14 “ዘሪው ቃሉን ይዘራል።+ +15 ቃሉ ሲዘራ መንገድ ዳር እንደወደቁት ዘሮች የሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ቃሉን እንደሰሙ ግን ሰይጣን መጥቶ+ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስደዋል።+ +16 በተመሳሳይም በድንጋያማ መሬት እንደተዘሩት ዘሮች የሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ቃሉን እንደሰሙ በደስታ ይቀበሉታል።+ +17 ሆኖም ቃሉ በውስጣቸው ሥር ስለማይሰድ የሚቆዩት ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ከዚያም በቃሉ የተነሳ መከራ ወይም ስደት ሲደርስባቸው ወዲያውኑ ይሰናከላሉ። +18 በእሾህ መካከል እንደተዘሩት ዘሮች የሆኑ ሌሎች ደግሞ አሉ። እነዚህ ቃሉን የሰሙ ናቸው፤+ +19 ይሁንና የዚህ ሥርዓት* ጭንቀትና+ ሀብት ያለው የማታለል ኃይል+ እንዲሁም የሌሎች ነገሮች ሁሉ ምኞት+ ወደ ልባቸው ሰርጎ በመግባት ቃሉን ያንቀዋል፤ የማያፈራም ይሆናል። +20 በመጨረሻም፣ ጥሩ አፈር ላይ እንደተዘሩት ዘሮች የሆኑት ቃሉን የሚሰሙና በደስታ የሚቀበሉ እንዲሁም 30፣ 60 እና 100 እጥፍ የሚያፈሩ ናቸው።”+ +21 ደግሞም እንዲህ አላቸው፦ “መብራት አምጥቶ እንቅብ* የሚደፋበት ወይም አልጋ ሥር የሚያስቀምጠው ይኖራል? የሚቀመጠው በመቅረዝ ላይ አይደለም?+ +22 ስለዚህ የተሸሸገ መገለጡ፣ የተሰወረም ይፋ መውጣቱ አይቀርም።+ +23 የሚሰማ ጆሮ ያለው ሁሉ ይስማ።”+ +24 አክሎም እንዲህ አላቸው፦ “የምትሰሙትን ነገር ልብ በሉ።+ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም ከዚያ የበለጠ ይጨመርላችኋል። +25 ላለው ይጨመርለታልና፤+ የሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።”+ +26 ከዚያም እንዲህ አለ፦ “የአምላክ መንግሥት መሬት ላይ ዘር የሚዘራን ሰው ይመስላል። +27 ሰውየው ሌሊት ይተኛል፤ ማለዳም ይነሳል፤ እንዴት እንደሆነም ሳያውቅ ዘሩ ይበቅልና ያድጋል። +28 መሬቱም ራሱ ቀስ በቀስ ፍሬ ያፈራል፤ በመጀመሪያ ቡቃያውን፣ ከዚያም ዛላውን በመጨረሻም በዛላው ላይ የጎመራ ፍሬ ይሰጣል። +29 ሰብሉ እንደደረሰ ግን የመከር ወቅት በመሆኑ ሰውየው ማጭዱን ይዞ ያጭዳል።” +30 ደግሞም እንዲህ አለ፦ “የአምላክን መንግሥት ከምን ጋር ልናነጻጽረው እንችላለን? ወይስ በምን ምሳሌ ልንገልጸው እንችላለን? +31 መሬት ላይ በተዘራች ጊዜ በምድር ላይ ካሉ ዘሮች ሁሉ እጅግ የምታንስን የሰናፍጭ ዘር ይመስላል።+ +32 ከተዘራች በኋላ ግን አድጋ ከሌሎች ተክሎች ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች��� ትላልቅ ቅርንጫፎችም ታወጣለች፤ በመሆኑም የሰማይ ወፎች በጥላዋ ሥር መስፈሪያ ያገኛሉ።” +33 ኢየሱስ እንዲህ የመሳሰሉ በርካታ ምሳሌዎችን+ ተጠቅሞ መረዳት በሚችሉት መጠን ቃሉን ይነግራቸው ነበር። +34 እንዲያውም ያለምሳሌ አይነግራቸውም ነበር፤ ብቻቸውን በሚሆኑበት ጊዜ ግን ለደቀ መዛሙርቱ ሁሉንም ነገር ያብራራላቸው ነበር።+ +35 በዚያ ቀን፣ ምሽት ላይ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው።+ +36 በመሆኑም ሕዝቡን ካሰናበቱ በኋላ እዚያው ጀልባዋ ውስጥ እንዳለ ይዘውት ሄዱ፤ ሌሎች ጀልባዎችም አብረውት ነበሩ።+ +37 በዚህ ጊዜ እጅግ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተነሳ፤ ማዕበሉም ከጀልባዋ ጋር እየተላተመ ወደ ውስጥ ይገባ ጀመር፤ ከዚህም የተነሳ ጀልባዋ በውኃ ልትሞላ ተቃረበች።+ +38 ኢየሱስ ግን በጀልባዋ የኋለኛ ክፍል ትራስ* ተንተርሶ ተኝቶ ነበር። ስለዚህ ቀስቅሰውት “መምህር፣ ስናልቅ ዝም ብለህ ታያለህ?” አሉት። +39 በዚህ ጊዜ ተነስቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ጸጥ በል! ረጭ በል!” አለው።+ ነፋሱ ቆመ፤ ታላቅ ጸጥታም ሰፈነ። +40 ከዚያም “ለምን ትሸበራላችሁ?* አሁንም እምነት የላችሁም?” አላቸው። +41 እነሱ ግን በታላቅ ፍርሃት ተውጠው እርስ በርሳቸው “ለመሆኑ ይህ ማን ነው? ነፋስና ባሕር እንኳ ይታዘዙለታል” ተባባሉ።+ +16 ሰንበት+ ካለፈ በኋላም መግደላዊቷ ማርያም፣ የያዕቆብ እናት ማርያምና+ ሰሎሜ ሄደው አስከሬኑን ሊቀቡ ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞች ገዙ።+ +2 ከዚያም በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በማለዳ ፀሐይ ስትወጣ ወደ መቃብሩ መጡ።+ +3 እርስ በርሳቸውም “በመቃብሩ ደጃፍ ላይ ያለውን ድንጋይ ማን ያንከባልልልናል?” ይባባሉ ነበር። +4 ቀና ብለው ሲመለከቱ ግን በጣም ትልቅ የነበረው ድንጋይ ከቦታው ተንከባሎ አዩ።+ +5 ወደ መቃብሩ ሲገቡ ነጭ ልብስ የለበሰ አንድ ወጣት በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ። +6 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “አትደንግጡ።+ በእንጨት ላይ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን እየፈለጋችሁ እንደሆነ አውቃለሁ። እሱ ተነስቷል።+ እዚህ የለም። ተመልከቱ፣ እሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውና።+ +7 ይልቁንስ ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱና ለጴጥሮስ ‘ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል።+ እንደነገራችሁም እዚያ ታዩታላችሁ’ በሏቸው።”+ +8 እነሱም ከመቃብሩ ከወጡ በኋላ በአድናቆት ተውጠው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ሸሽተው ሄዱ። ከፍርሃታቸውም የተነሳ ለማንም ምንም ነገር አልተናገሩም።*+ +6 ከዚያ ተነስቶ ወደ ትውልድ አገሩ መጣ፤+ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት። +2 እሱም በሰንበት ቀን በምኩራብ ማስተማር ጀመረ፤ የሰሙትም አብዛኞቹ ሰዎች በመገረም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው እነዚህን ነገሮች የተማረው ከየት ነው?+ ይህን ጥበብ ያገኘውስ እንዴት ነው? ደግሞስ እንዲህ ያሉ ተአምራትን ማከናወን የቻለው እንዴት ነው?+ +3 ይህ አናጺው+ የማርያም ልጅ+ እንዲሁም የያዕቆብ፣+ የዮሴፍ፣ የይሁዳና የስምዖን ወንድም+ አይደለም? እህቶቹስ የሚኖሩት ከእኛው ጋር አይደለም?” ከዚህም የተነሳ ተሰናከሉበት። +4 ኢየሱስ ግን “ነቢይ በገዛ አገሩ፣ በዘመዶቹ ዘንድና በገዛ ቤቱ ካልሆነ በስተቀር በሌላ ቦታ ሁሉ ይከበራል” አላቸው።+ +5 ስለሆነም ጥቂት ሕመምተኞች ላይ እጁን በመጫን ከመፈወስ በቀር በዚያ ሌላ ተአምር መፈጸም አልቻለም። +6 እንዲያውም ባለማመናቸው እጅግ ተደነቀ። ከዚህ በኋላ በዙሪያው ባሉት መንደሮች እየተዘዋወረ አስተማረ።+ +7 አሥራ ሁለቱን ከጠራ በኋላ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው፤+ ርኩሳን መናፍስትን እንዲያዝዙም ሥልጣን ሰጣቸው።+ +8 ደግሞም ከበትር በስተቀር ለጉዟቸው ዳቦም ሆነ የምግብ ከረጢት እንዲሁም በመቀነታቸው ገንዘብ* እንዳይዙ አዘዛቸው፤+ +9 በተ��ማሪም ሁለት ልብስ* እንዳይዙ፣ ጫማ ግን እንዲያደርጉ ነገራቸው። +10 አክሎም እንዲህ አላቸው፦ “ወደ አንድ ቤት ስትገቡ አካባቢውን ለቃችሁ እስክትሄዱ ድረስ እዚያው ቆዩ።+ +11 ነገር ግን የሚቀበላችሁ ወይም የሚሰማችሁ ካጣችሁ ከዚያ ቦታ ስትወጡ ምሥክር እንዲሆንባቸው የእግራችሁን አቧራ አራግፉ።”*+ +12 እነሱም ከዚያ ወጥተው ሰዎች ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰበኩ፤+ +13 ብዙ አጋንንትም አስወጡ፤+ እንዲሁም ብዙ ሕመምተኞችን ዘይት እየቀቡ ፈወሱ። +14 የኢየሱስ ስም በሰፊው ታውቆ ስለነበር ንጉሥ ሄሮድስ ይህን ሰማ፤ ሰዎችም “አጥማቂው ዮሐንስ ከሞት ተነስቷል፤ እንዲህ ያሉ ተአምራት መፈጸም የቻለውም ለዚህ ነው” ይሉ ነበር።+ +15 ሌሎች ግን “ኤልያስ ነው” ይሉ ነበር። ሌሎች ደግሞ “እንደቀድሞዎቹ ነቢያት ያለ ነቢይ ነው” ይሉ ነበር።+ +16 ሄሮድስ ግን ይህን በሰማ ጊዜ “እኔ ራሱን የቆረጥኩት ዮሐንስ ከሞት ተነስቷል” አለ። +17 ሄሮድስ የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት በሆነችው በሄሮድያዳ ምክንያት ሰዎች ልኮ ዮሐንስን በማስያዝ በሰንሰለት አስሮ ወህኒ አስገብቶት ነበር፤ ይህም የሆነው ሄሮድስ እሷን አግብቶ ስለነበር ነው።+ +18 ዮሐንስ ሄሮድስን “የወንድምህን ሚስት እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር።+ +19 በመሆኑም ሄሮድያዳ በእሱ ላይ ቂም ይዛ ልትገድለው ትፈልግ ነበር፤ ሆኖም ይህን ማድረግ አልቻለችም። +20 ሄሮድስ፣ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው+ መሆኑን ስለሚያውቅ ይፈራውና ጉዳት እንዳያገኘው ይጠብቀው ነበር። ዮሐንስ የሚናገረውን ሲሰማ ምን እንደሚያደርገው ግራ ይገባው የነበረ ቢሆንም በደስታ ያዳምጠው ነበር። +21 ይሁንና ሄሮድስ በልደት ቀኑ+ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን፣ የጦር አዛዦቹንና በገሊላ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ራት በጋበዘ ጊዜ ሄሮድያዳ ምቹ አጋጣሚ ተፈጠረላት።+ +22 የሄሮድያዳ ልጅ ገብታ በመጨፈር ሄሮድስንና ከእሱ ጋር እየበሉ የነበሩትን አስደሰተቻቸው። ንጉሡም ልጅቷን “የፈለግሽውን ሁሉ ጠይቂኝ፣ እሰጥሻለሁ” አላት። +23 ደግሞም “እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ቢሆን የምትጠይቂኝን ሁሉ እሰጥሻለሁ” ሲል ማለላት። +24 እሷም ወደ እናቷ ሄዳ “ምን ብጠይቀው ይሻላል?” አለቻት። እናቷም “የአጥማቂው ዮሐንስን ራስ ጠይቂው” አለቻት። +25 ወዲያውም ወደ ንጉሡ ፈጥና በመግባት “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አሁኑኑ በሳህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” ስትል ጠየቀችው።+ +26 ንጉሡ በዚህ እጅግ ቢያዝንም ስለገባው መሐላና ስለ እንግዶቹ ሲል እንቢ ሊላት አልፈለገም። +27 ከዚያም ንጉሡ ጠባቂውን ወዲያው ልኮ የዮሐንስን ራስ እንዲያመጣ አዘዘው። ጠባቂውም ሄዶ ወህኒ ቤት ውስጥ ራሱን ቆረጠው፤ +28 ራሱንም በሳህን ይዞ መጣ። ከዚያም ለልጅቷ ሰጣት፤ ልጅቷም ለእናቷ ሰጠቻት። +29 ደቀ መዛሙርቱም ይህን በሰሙ ጊዜ መጥተው አስከሬኑን በመውሰድ በመቃብር አኖሩት። +30 ሐዋርያቱ በኢየሱስ ዙሪያ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ነገር ሁሉ ነገሩት።+ +31 እሱም “ለብቻችን ወደ አንድ ገለል ያለ ስፍራ እንሂድና በዚያ ትንሽ አረፍ በሉ” አላቸው።+ ብዙዎች ይመጡና ይሄዱ ስለነበር ምግብ ለመብላት እንኳ ፋታ አላገኙም። +32 ስለዚህ ብቻቸውን ለመሆን በጀልባ ተሳፍረው ገለል ወዳለ ስፍራ ሄዱ።+ +33 ይሁንና ሰዎች ሲሄዱ አዩአቸው፤ ብዙዎችም መሄዳቸውን አወቁ፤ ስለሆነም ከከተሞች ሁሉ አንድ ላይ በእግር በመሮጥ ቀድመዋቸው ደረሱ። +34 ኢየሱስም ከጀልባዋ ሲወርድ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተመለከተ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጎች+ ስለነበሩም በጣም አዘነላቸው።+ ብዙ ነገርም ያስተምራቸው ጀመር።+ +35 ሰዓቱ እየገፋ በመሄዱ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ ቀርበው እንዲህ አሉት፦ “ይህ ቦታ ራቅ ያለ ነው፤ ሰዓቱ ደግሞ ገፍቷል።+ +36 በአካባቢው ወዳሉት ገጠሮችና መንደሮች ሄደው ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ አሰናብታቸው።”+ +37 እሱም መልሶ “እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው። እነሱም “ሄደን በ200 ዲናር* ዳቦ ገዝተን እንዲበሉ እንስጣቸው?” አሉት።+ +38 እሱም “ስንት ዳቦ አላችሁ? እስቲ ሄዳችሁ እዩ!” አላቸው። ሄደው ካዩ በኋላ “አምስት ዳቦና ሁለት ዓሣ” አሉት።+ +39 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ በቡድን በቡድን ሆኖ በለመለመው መስክ ላይ እንዲቀመጥ አዘዘ።+ +40 በመሆኑም ሕዝቡ መቶ መቶና ሃምሳ ሃምሳ እየሆነ በቡድን ተቀመጠ። +41 እሱም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ።+ ከዚያም ዳቦውን ቆርሶ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ሁለቱን ዓሣም ለሁሉም አከፋፈለ። +42 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ +43 ከዚያም ቁርስራሹን ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ዓሣውን ሳይጨምር 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ +"44 ዳቦውን የበሉትም 5,000 ወንዶች ነበሩ። " +45 ወዲያውም፣ እሱ ሕዝቡን እያሰናበተ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ጀልባ ተሳፍረው በቤተሳይዳ አቅጣጫ ወዳለው የባሕር ዳርቻ ቀድመውት እንዲሻገሩ አደረገ።+ +46 ከተሰናበታቸው በኋላ ግን ለመጸለይ ወደ አንድ ተራራ ወጣ።+ +47 በመሸም ጊዜ ጀልባዋ በባሕሩ መካከል ነበረች፤ እሱ ግን ብቻውን የብስ ላይ ነበር።+ +48 ነፋሱ ከፊት ለፊታቸው ይነፍስ ስለነበር ለመቅዘፍ ሲታገሉ ባያቸው ጊዜ በአራተኛው ክፍለ ሌሊት* ገደማ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነሱ መጣ፤ ይሁንና አልፏቸው ሊሄድ ነበር።* +49 እነሱም በባሕሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ “ምትሃት ነው!” ብለው ስላሰቡ በኃይል ጮኹ። +50 ሁሉም እሱን ባዩት ጊዜ ተረበሹ። ሆኖም ወዲያውኑ አነጋገራቸው፤ ደግሞም “አይዟችሁ! እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው።+ +51 ከዚያም ጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሯቸው ሆነ፤ ነፋሱም ቆመ። በዚህ ጊዜ በከፍተኛ የአድናቆት ስሜት ተዋጡ፤ +52 ይህም የሆነው የዳቦውን ተአምር ትርጉም ባለማስተዋላቸው ነው፤ ልባቸው አሁንም መረዳት ተስኖት ነበር። +53 ወደ የብስ በተሻገሩ ጊዜ ጌንሴሬጥ ደረሱ፤ በአቅራቢያውም ጀልባዋን አቆሙ።+ +54 ሆኖም ከጀልባዋ እንደወረዱ ሰዎች አወቁት። +55 ወደ አካባቢው ሁሉ በመሮጥ ሕመምተኞችን በቃሬዛ እየተሸከሙ እሱ ይገኝበታል ወደተባለው ቦታ ያመጡ ጀመር። +56 በገባበት መንደር ወይም ከተማ ወይም ገጠር ሁሉ ሕመምተኞቹን በገበያ ስፍራ* ያስቀምጡ ነበር፤ የልብሱንም ዘርፍ እንኳ ለመንካት ይማጸኑት ነበር።+ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ። +10 ከዚያም ተነስቶ ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳሉት የይሁዳ ድንበሮች መጣ፤ ብዙ ሰዎችም እንደገና ወደ እሱ ተሰበሰቡ። አሁንም እንደ ልማዱ ያስተምራቸው ጀመር።+ +2 ፈሪሳውያንም ቀርበው እሱን ለመፈተን በማሰብ አንድ ሰው ሚስቱን እንዲፈታ ሕግ ይፈቅድለት እንደሆነ ጠየቁት።+ +3 እሱም መልሶ “ሙሴ ምን ብሎ ነው ያዘዛችሁ?” አላቸው። +4 እነሱም “ሙሴ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ እንዲፈታት ፈቅዷል” አሉት።+ +5 ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ሙሴ ይህን ትእዛዝ የጻፈላችሁ ልባችሁ ደንዳና+ መሆኑን አይቶ ነው።+ +6 ይሁን እንጂ በፍጥረት መጀመሪያ ‘አምላክ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።+ +7 ከዚህ የተነሳ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤+ +8 ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’፤+ በመሆኑም ከዚህ በኋላ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። +9 ስለዚህ አምላክ ያጣመረውን* ማንም ሰው አይለያየው።”+ +10 እንደገና ወደ ቤት በገቡ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ጉዳይ ይጠይቁት ጀመር። +11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በማመንዘር+ ሚስቱን ይበድላል፤ +12 አንዲት ሴትም ብትሆን ባሏን ፈታ ሌላ ብታገባ ታመነዝ���ለች።”+ +13 ሰዎችም ኢየሱስ እጁን እንዲጭንባቸው ትናንሽ ልጆችን ወደ እሱ ያመጡ ጀመር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው።+ +14 ኢየሱስ ይህን ሲያይ ተቆጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ልጆቹ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ የአምላክ መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ነውና።+ +15 እውነት እላችኋለሁ፣ የአምላክን መንግሥት እንደ አንድ ትንሽ ልጅ ሆኖ የማይቀበል ሁሉ ፈጽሞ ወደዚህ መንግሥት አይገባም።”+ +16 ልጆቹንም አቀፋቸው፤ እጁንም ጭኖ ባረካቸው።+ +17 ከዚያ ወጥቶ በመሄድ ላይ ሳለ አንድ ሰው እየሮጠ መጣ፤ በፊቱም በጉልበቱ ተንበርክኮ “ጥሩ መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” ሲል ጠየቀው።+ +18 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ለምን ጥሩ ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከአምላክ በቀር ጥሩ የለም።+ +19 ‘አትግደል፣+ አታመንዝር፣+ አትስረቅ፣+ በሐሰት አትመሥክር፣+ አታታል፣+ አባትህንና እናትህን አክብር’+ የሚሉትን ትእዛዛት ታውቃለህ።” +20 ሰውየውም “መምህር፣ እነዚህን ሁሉ ከልጅነቴ ጀምሮ ስጠብቅ ኖሬአለሁ” አለው። +21 ኢየሱስም ተመለከተውና ወደደው፤ ከዚያም “አንድ ነገር ይጎድልሃል፤ ሂድና ያለህን ነገር ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድሆች ስጥ፤ በሰማይም ውድ ሀብት ታገኛለህ፤ ደግሞም መጥተህ ተከታዬ ሁን” አለው።+ +22 ሰውየው ግን ይህን ሲሰማ አዘነ፤ ብዙ ንብረት ስለነበረውም እያዘነ ሄደ።+ +23 ኢየሱስ ዙሪያውን ከተመለከተ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “ገንዘብ ላላቸው ሰዎች ወደ አምላክ መንግሥት መግባት ምንኛ አስቸጋሪ ነው!” አላቸው።+ +24 ደቀ መዛሙርቱ ግን በንግግሩ ተገረሙ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ልጆቼ ሆይ፣ ወደ አምላክ መንግሥት መግባት እንዴት አስቸጋሪ ነው! +25 ሀብታም ሰው ወደ አምላክ መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።”+ +26 ደቀ መዛሙርቱ ይበልጥ በመገረም “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” አሉት።*+ +27 ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ትኩር ብሎ በመመልከት “ይህ በሰዎች ዘንድ አይቻልም፤ በአምላክ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፤ በአምላክ ዘንድ ሁሉ ነገር ይቻላል” አለ።+ +28 ጴጥሮስም “እነሆ፣ እኛ ሁሉን ትተን ተከትለንሃል” አለው።+ +29 ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ስለ እኔና ስለ ምሥራቹ ሲል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እህቶችን ወይም እናትን ወይም አባትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ፣+ +30 አሁን በዚህ ዘመን ከስደት+ ጋር ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እህቶችን፣ እናቶችን፣ ልጆችንና እርሻን 100 እጥፍ፣ በሚመጣው ሥርዓት* ደግሞ የዘላለም ሕይወት ያገኛል። +31 ሆኖም ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች፣ ኋለኞች የሆኑ ደግሞ ፊተኞች ይሆናሉ።”+ +32 ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ እያቀኑ ሳሉ ኢየሱስ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፤ እነሱም ተደነቁ፤ ይከተሉት የነበሩት ሰዎች ግን ፍርሃት አደረባቸው። እሱም እንደገና አሥራ ሁለቱን ገለል አድርጎ በመውሰድ የሚደርስበትን ነገር ይነግራቸው ጀመር፦+ +33 “እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት አልፎ ይሰጣል። እነሱም ሞት ይፈርዱበታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፤ +34 ያፌዙበታል፤ ይተፉበታል፤ ይገርፉታል፤ ከዚያም ይገድሉታል፤ ሆኖም ከሦስት ቀን በኋላ ይነሳል።”+ +35 ሁለቱ የዘብዴዎስ ልጆች+ ያዕቆብና ዮሐንስ ወደ እሱ ቀርበው “መምህር፣ የምንለምንህን ማንኛውንም ነገር እንድታደርግልን እንፈልጋለን” አሉት።+ +36 እሱም “ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። +37 እነሱም “በክብር ቦታህ ላይ ስትቀመጥ አንዳችን በቀኝህ፣ አንዳችን ደግሞ በግራህ እንድንቀመጥ ፍቀድልን” ሲ��� መለሱለት።+ +38 ኢየሱስ ግን “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ወይም እኔ የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁ?” አላቸው።+ +39 እነሱም “እንችላለን” አሉት። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ።+ +40 በቀኜ ወይም በግራዬ መቀመጥ ግን ለተዘጋጀላቸው የሚሰጥ እንጂ በእኔ ፈቃድ የሚሆን አይደለም።” +41 የቀሩት አሥሩ ይህን ሲሰሙ በያዕቆብና በዮሐንስ ላይ ተቆጡ።+ +42 ሆኖም ኢየሱስ ወደ እሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ብሔራትን የሚገዙ* ነገሥታት በሕዝባቸው ላይ ሥልጣናቸውን እንደሚያሳዩ፣ ታላላቆቻቸውም በኃይል እንደሚገዟቸው ታውቃላችሁ።+ +43 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፤ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል፤+ +44 እንዲሁም ከመካከላችሁ ፊተኛ መሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የሁሉ ባሪያ ሊሆን ይገባል። +45 ምክንያቱም የሰው ልጅ እንኳ የመጣው ለማገልገልና+ በብዙ ሰዎች ምትክ ሕይወቱን* ቤዛ አድርጎ ለመስጠት+ እንጂ እንዲገለገል አይደለም።” +46 ከዚያም ወደ ኢያሪኮ መጡ። እሱና ደቀ መዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዓይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።+ +47 እሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን ሲሰማ “የዳዊት ልጅ፣+ ኢየሱስ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!”+ እያለ ይጮኽ ጀመር። +48 በዚህ ጊዜ ብዙዎች ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” እያለ ይበልጥ መጮኹን ቀጠለ። +49 ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት” አለ። እነሱም ዓይነ ስውሩን “አይዞህ! ተነስ፤ እየጠራህ ነው” አሉት። +50 እሱም መደረቢያውን ጥሎ ዘሎ በመነሳት ወደ ኢየሱስ ሄደ። +51 ኢየሱስም “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው። ዓይነ ስውሩም “ራቦኒ፣* የዓይኔን ብርሃን መልስልኝ” አለው። +52 ኢየሱስም “ሂድ፣ እምነትህ አድኖሃል” አለው።+ ወዲያውም የዓይኑ ብርሃን ተመለሰለት፤+ እሱም ከሕዝቡ ጋር አብሮ ይከተለው ጀመር። +14 ፋሲካና*+ የቂጣ* በዓል+ ሁለት ቀን ቀርቶት ነበር።+ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት የተንኮል ዘዴ ተጠቅመው እሱን የሚይዙበትንና* የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፤+ +2 ደግሞም “ሕዝቡ ሁከት ሊያስነሳ ስለሚችል በበዓሉ ወቅት መሆን የለበትም” ይሉ ነበር። +3 በቢታንያ፣ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በነበረው በስምዖን ቤት እየበላ ሳለ አንዲት ሴት እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ይኸውም ንጹሕ ናርዶስ የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች። ብልቃጡንም ሰብራ በመክፈት ዘይቱን ራሱ ላይ ታፈስ ጀመር።+ +4 በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ተቆጥተው እንዲህ ተባባሉ፦ “ይህ ዘይት እንዲህ የሚባክነው ለምንድን ነው? +5 ከ300 ዲናር* በላይ ተሸጦ ገንዘቡ ለድሆች ሊሰጥ ይችል ነበር!” በሴትየዋም እጅግ ተበሳጩ።* +6 ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ “ተዉአት። ለምን ታስቸግሯታላችሁ? እሷ ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች።+ +7 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤+ በፈለጋችሁ ጊዜ ሁሉ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።+ +8 እሷ የምትችለውን አድርጋለች፤ ሰውነቴን ለቀብሬ ለማዘጋጀት ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት አስቀድማ ቀብታዋለች።+ +9 እውነት እላችኋለሁ፣ በመላው ዓለም ምሥራቹ በሚሰበክበት+ ቦታ ሁሉ ይህች ሴት ያደረገችውም መታሰቢያ ሆኖ ይነገርላታል።”+ +10 ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።+ +11 እነሱም ይህን ሲሰሙ ደስ አላቸውና የብር ገንዘብ* ሊሰጡት ቃል ገቡለት።+ ስለዚህ እሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር። +12 የቂጣ በዓል+ በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣ እንደተለመደው የፋሲካን መሥዋዕት+ በሚያቀርቡበት ዕለት ደቀ መዛሙርቱ “ፋሲካን እንድትበላ የት ሄደን እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።+ +13 እሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦ “ወደ ከተማው ሂዱ፤ በዚያም የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ። እሱንም ተከተሉት፤+ +14 ወደሚገባበት ቤት ሄዳችሁ የቤቱን ጌታ ‘መምህሩ “ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሏል’ በሉት። +15 እሱም የተነጠፈና የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል። እዚያ አዘጋጁልን።” +16 ደቀ መዛሙርቱም ሄዱ፤ ወደ ከተማውም ገቡ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ። +17 እሱም ከመሸ በኋላ ከአሥራ ሁለቱ ጋር መጣ።+ +18 በማዕድ ተቀምጠው እየበሉ ሳለም ኢየሱስ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ፣ ከእኔ ጋር እየበላ ያለ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።+ +19 እነሱም አዝነው በየተራ “እኔ እሆን?” ይሉት ጀመር። +20 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይኸውም ከእኔ ጋር በሳህኑ ውስጥ የሚያጠቅሰው ነው።+ +21 የሰው ልጅ ስለ እሱ በተጻፈው መሠረት ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት!+ ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር።”+ +22 እየበሉም ሳሉ ቂጣ አንስቶ ባረከ፤ ከቆረሰውም በኋላ ሰጣቸውና “እንኩ፣ ይህ ሥጋዬን ያመለክታል” አለ።+ +23 ጽዋ አንስቶም አምላክን ካመሰገነ በኋላ ሰጣቸው፤ ሁሉም ከእሱ ጠጡ።+ +24 እንዲህም አላቸው፦ “ይህ ለብዙዎች የሚፈሰውን+ ‘የቃል ኪዳን+ ደሜን’+ ያመለክታል። +25 እውነት እላችኋለሁ፣ በአምላክ መንግሥት አዲሱን ወይን እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከእንግዲህ በኋላ ከዚህ ወይን አልጠጣም።” +26 በመጨረሻ የውዳሴ መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዱ።+ +27 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “‘እረኛውን እመታለሁ፤+ በጎቹም ይበተናሉ’+ ተብሎ ስለተጻፈ ሁላችሁም ትሰናከላላችሁ። +28 ከተነሳሁ በኋላ ግን ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ።”+ +29 ይሁንና ጴጥሮስ “ሌሎቹ ሁሉ ቢሰናከሉ እንኳ እኔ አልሰናከልም” አለው።+ +30 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “እውነት እልሃለሁ፦ ዛሬ፣ አዎ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ አንተ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው።+ +31 እሱ ግን “አብሬህ መሞት ቢኖርብኝ እንኳ በምንም ዓይነት አልክድህም” በማለት አጥብቆ ይናገር ጀመር። የቀሩትም ሁሉ እንደዚሁ አሉ።+ +32 ከዚያም ጌትሴማኒ ወደተባለ ቦታ መጡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም “እኔ በምጸልይበት ጊዜ እናንተ እዚህ ተቀመጡ” አላቸው።+ +33 ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ከእሱ ጋር ይዟቸው ሄደ፤+ ከዚያም እጅግ ይጨነቅና* ይረበሽ ጀመር። +34 ኢየሱስም “እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ።*+ እዚህ ሁኑና ነቅታችሁ ጠብቁ”+ አላቸው። +35 ትንሽ ወደ ፊት ራቅ በማለት መሬት ላይ ተደፍቶ ቢቻል ሰዓቱ ከእሱ እንዲያልፍ ይጸልይ ጀመር። +36 እንዲህም አለ፦ “አባ፣* አባት ሆይ፣+ አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ ትችላለህ፤ ይህን ጽዋ ከእኔ አርቅ። ሆኖም እኔ የምፈልገው ሳይሆን አንተ የምትፈልገው ይሁን።”+ +37 ተመልሶ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸውና ጴጥሮስን እንዲህ አለው፦ “ስምዖን፣ ተኝተሃል? አንድ ሰዓት እንኳ ነቅተህ መጠበቅ አልቻልክም?+ +38 ወደ ፈተና እንዳትገቡ+ ነቅታችሁ ጠብቁ፤ ሳታሰልሱም ጸልዩ። እርግጥ፣ መንፈስ ዝግጁ* ነው፤ ሥጋ* ግን ደካማ ነው።”+ +39 እንደገናም ሄዶ ስለዚያው ነገር ጸለየ።+ +40 ዳግመኛም ተመልሶ ሲመጣ እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ስለነበር ተኝተው አገኛቸው፤ በመሆኑም የሚሉት ነገር ጠፋቸው። +41 ለሦስተኛ ጊዜም ተመልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ይህ የእንቅልፍና የእረፍት ሰዓት ነው? በቃ! ሰዓቱ ደርሷል!+ እነሆ፣ የሰው ልጅ ለኃጢአተኞች አልፎ ሊሰጥ ነው። +42 ተነሱ፣ እንሂድ። እነሆ፣ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል።”+ +43 ወዲያውም ገና እየተናገረ ሳለ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፤ ከካህናት አለቆች፣ ከጸሐፍትና ከሽማግሌዎች የተላኩ ሰይፍና ቆመጥ የያዙ ብዙ ሰዎችም አብረውት ነበሩ።+ +44 አሳልፎ የሚሰጠውም “እኔ የምስመው ሰው እሱ ነው፤ ያዙትና እንዳያመልጥ ተጠንቅቃችሁ ውሰዱት” በማለት አስቀድሞ ምልክት ሰጥቷቸው ነበር። +45 ይሁዳም በቀጥታ መጥቶ ወደ እሱ በመቅረብ “ረቢ!” ብሎ ሳመው። +46 ሰዎቹም ያዙት፤ ደግሞም አሰሩት። +47 ይሁን እንጂ አጠገቡ ቆመው ከነበሩት አንዱ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቆረጠው።+ +48 ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ የመጣችሁት እኔን ለመያዝ ነው?+ +49 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ እያስተማርኩ+ ከእናንተ ጋር ነበርኩ፤ ሆኖም ያን ጊዜ አልያዛችሁኝም። ይሁንና ይህ የሆነው ቅዱሳን መጻሕፍት እንዲፈጸሙ ነው።”+ +50 በዚህ ጊዜ ሁሉም ጥለውት ሸሹ።+ +51 ሆኖም እርቃኑን ለመሸፈን በፍታ ብቻ የለበሰ አንድ ወጣት በቅርብ ርቀት ይከተለው ጀመር፤ ሊይዙትም ሞከሩ፤ +52 እሱ ግን በፍታውን ትቶ ራቁቱን* አመለጠ። +53 ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዱት፤+ የካህናት አለቆች፣ ሽማግሌዎችና ጸሐፍትም በሙሉ ተሰበሰቡ።+ +54 ይሁንና ጴጥሮስ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ በርቀት ተከተለው፤ ከዚያም ከቤቱ አገልጋዮች ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ጀመር።+ +55 በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና መላው የሳንሄድሪን ሸንጎ ኢየሱስን ለመግደል በእሱ ላይ የምሥክሮች ቃል እየፈለጉ ነበር፤ ነገር ግን ምንም አላገኙም።+ +56 እርግጥ ብዙዎች በእሱ ላይ የሐሰት ምሥክርነት ይሰጡ ነበር፤+ ሆኖም ቃላቸው ሊስማማ አልቻለም። +57 አንዳንዶችም ተነስተው እንዲህ ሲሉ በሐሰት ይመሠክሩበት ነበር፦ +58 “‘ይህን በእጅ የተሠራ ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ በእጅ ያልተሠራ ሌላ እገነባለሁ’ ሲል ሰምተነዋል።”+ +59 በዚህ ጉዳይም ቢሆን የምሥክርነት ቃላቸው ሊስማማ አልቻለም። +60 ከዚያም ሊቀ ካህናቱ በመካከላቸው ቆሞ ኢየሱስን “ምንም መልስ አትሰጥም? እነዚህ ሰዎች በአንተ ላይ ስለሰጡት ምሥክርነት ምን ትላለህ?” ሲል ጠየቀው።+ +61 እሱ ግን ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም።+ ሊቀ ካህናቱም እንደገና “አንተ ብሩክ የሆነው አምላክ ልጅ ክርስቶስ ነህ?” እያለ ይጠይቀው ጀመር። +62 ኢየሱስም “አዎ ነኝ፤ እናንተም የሰው ልጅ+ በኃያሉ ቀኝ ተቀምጦ+ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ”+ አለ። +63 በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ እንዲህ አለ፦ “ከዚህ በላይ ምን ምሥክሮች ያስፈልጉናል?+ +64 አምላክን ሲሳደብ ሰምታችኋል። ታዲያ ውሳኔያችሁ ምንድን ነው?”* ሁሉም ሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት።+ +65 አንዳንዶች ይተፉበት ጀመር፤+ ፊቱንም ሸፍነው በቡጢ እየመቱት “ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደመታህ ንገረን!” ይሉት ነበር። የሸንጎው አገልጋዮችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።+ +66 ጴጥሮስ ግቢው ውስጥ በታች በኩል ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ሴት አገልጋዮች አንዷ መጣች።+ +67 እሳት ሲሞቅ አይታ ትኩር ብላ ተመለከተችውና “አንተም ከዚህ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበርክ” አለችው። +68 እሱ ግን “ሰውየውን አላውቀውም፤ ምን እንደምታወሪም አላውቅም” ሲል ካደ፤ ከዚያም ወደ መግቢያው* ሄደ። +69 አገልጋይዋም እዚያ አየችውና በአጠገቡ ለቆሙት “ይህ ከእነሱ አንዱ ነው” ብላ እንደገና ትናገር ጀመር። +70 አሁንም ካደ። ከጥቂት ��ዜ በኋላ ደግሞ በዚያ ቆመው የነበሩት ጴጥሮስን እንደገና “የገሊላ ሰው ስለሆንክ፣ በእርግጥ አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” ይሉት ጀመር። +71 እሱ ግን “ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም!” ሲል ይምልና ራሱን ይረግም ጀመር። +72 ወዲያውኑ ዶሮ ለሁለተኛ ጊዜ ጮኸ፤+ ጴጥሮስም “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ሲል ኢየሱስ የተናገረው ቃል ትዝ አለው።+ ከዚያም እጅግ አዝኖ ያለቅስ ጀመር። +9 ቀጥሎም “እውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆሙት መካከል አንዳንዶች የአምላክ መንግሥት በታላቅ ኃይል መምጣቱን እስኪያዩ ድረስ ፈጽሞ ሞትን አይቀምሱም” አላቸው።+ +2 ኢየሱስ ከስድስት ቀን በኋላ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ብቻ ይዞ ወደ አንድ ረጅም ተራራ ወጣ። በፊታቸውም ተለወጠ፤+ +3 ልብሱ በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ልብስ አጣቢ አጥቦ ሊያነጣው ከሚችለው በላይ እጅግ ነጭ ሆኖ ያንጸባርቅ ጀመር። +4 ደግሞም ኤልያስና ሙሴ ታዩአቸው፤ ከኢየሱስም ጋር እየተነጋገሩ ነበር። +5 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን “ረቢ፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። ስለዚህ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴና አንድ ለኤልያስ ሦስት ድንኳኖች እንትከል” አለው። +6 እርግጥ፣ በጣም ስለፈሩ ምን ማለት እንዳለበት አላወቀም ነበር። +7 ከዚያም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ከደመናውም “የምወደው ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ መጣ።+ +8 ከዚያም ድንገት ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከኢየሱስ በቀር ማንም አብሯቸው አልነበረም። +9 ከተራራው እየወረዱ ሳሉ የሰው ልጅ ከሞት እስኪነሳ ድረስ+ ያዩትን ለማንም እንዳይናገሩ በጥብቅ አዘዛቸው።+ +10 እነሱም ቃሉን በልባቸው አኖሩ፤* ነገር ግን ከሞት መነሳት ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። +11 ከዚያም “ጸሐፍት፣ ኤልያስ+ በመጀመሪያ መምጣት አለበት የሚሉት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+ +12 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “በእርግጥ ኤልያስ መጀመሪያ መጥቶ ሁሉንም ነገር ወደ ቀድሞ ሁኔታው ይመልሳል፤+ ይሁንና የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበልና+ መናቅ+ እንዳለበት የተጻፈው ለምን ይመስላችኋል? +13 ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ኤልያስ+ ስለ እሱ በተጻፈው መሠረት በእርግጥ መጥቷል፤ እነሱም የፈለጉትን ሁሉ አድርገውበታል።”+ +14 ወደቀሩት ደቀ መዛሙርት በመጡም ጊዜ ብዙ ሕዝብ ከቧቸው አዩ፤ ጸሐፍትም ከእነሱ ጋር እየተከራከሩ ነበር።+ +15 ሆኖም የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ኢየሱስን እንዳዩት በጣም ተገረሙ፤ ከዚያም ሰላም ሊሉት ወደ እሱ ሮጡ። +16 እሱም “ከእነሱ ጋር የምትከራከሩት ስለ ምን ጉዳይ ነው?” ሲል ጠየቃቸው። +17 ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “መምህር፣ ልጄ ዱዳ የሚያደርግ መንፈስ ስላደረበት ወደ አንተ አመጣሁት።+ +18 በያዘው ስፍራ ሁሉ መሬት ላይ ይጥለዋል፤ ከዚያም አፉ አረፋ ይደፍቃል፤ ጥርሱን ያፋጫል እንዲሁም ይዝለፈለፋል። ደቀ መዛሙርትህ እንዲያስወጡት ጠየቅኳቸው፤ እነሱ ግን ሊያስወጡት አልቻሉም።” +19 እሱም መልሶ “እምነት የለሽ ትውልድ ሆይ፣+ ከእናንተ ጋር እስከ መቼ መቆየት ሊኖርብኝ ነው? እስከ መቼስ እናንተን መታገሥ ሊኖርብኝ ነው? ልጁን ወደ እኔ አምጡት” አላቸው።+ +20 ልጁንም ወደ እሱ አመጡት፤ ልጁን የያዘው መንፈስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ ወዲያውኑ ልጁን አንዘፈዘፈው። ልጁም መሬት ላይ ከወደቀ በኋላ አፉ አረፋ እየደፈቀ ይንከባለል ጀመር። +21 ከዚያም ኢየሱስ አባትየውን “እንዲህ ማድረግ ከጀመረው ምን ያህል ጊዜ ሆነው?” ሲል ጠየቀው። አባትየውም እንዲህ አለው፦ “ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው፤ +22 ሊገድለው ፈልጎ ብዙ ጊዜ እሳት ውስጥና ውኃ ውስጥ ይጥለዋል። ማድረግ የምትችለው ነገር ካለ እዘንልንና ��ርዳን።” +23 ኢየሱስም “‘የምትችለው ነገር ካለ’ አልክ? እምነት ላለው ሰው፣ ሁሉ ነገር ይቻላል” አለው።+ +24 ወዲያውም የልጁ አባት “እምነት አለኝ! እምነቴ እንዲጠነክር ደግሞ አንተ እርዳኝ!”+ በማለት ጮክ ብሎ ተናገረ። +25 ኢየሱስ ሕዝቡ ወደ እነሱ ግር ብሎ እየሮጠ በመምጣት ላይ መሆኑን ሲያይ ርኩሱን መንፈስ “አንተ ዱዳና ደንቆሮ የምታደርግ መንፈስ ከእሱ ውጣ፤ ዳግመኛም ወደ እሱ እንዳትገባ አዝሃለሁ!” ሲል ገሠጸው።+ +26 ርኩሱ መንፈስ በኃይል ከጮኸና ብዙ ካንዘፈዘፈው በኋላ ወጣ፤ ልጁም የሞተ ያህል ሆነ፤ በዚህ ጊዜ አብዛኞቹ ሰዎች “ሞቷል!” ይሉ ጀመር። +27 ይሁን እንጂ ኢየሱስ እጁን ይዞ አስነሳው፤ ልጁም ተነስቶ ቆመ። +28 ከዚያም ወደ ቤት ከገባ በኋላ ብቻውን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ “እኛ ልናስወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+ +29 እሱም “እንዲህ ዓይነቱ በጸሎት ካልሆነ በቀር ሊወጣ አይችልም” አላቸው። +30 ከዚያ ተነስተው በገሊላ በኩል አለፉ፤ ሆኖም ይህን ማንም እንዲያውቅ አልፈለገም። +31 ምክንያቱም ደቀ መዛሙርቱን እያስተማራቸው የነበረ ከመሆኑም ሌላ “የሰውን ልጅ ለሰዎች አሳልፈው ይሰጡታል፤ እነሱም ይገድሉታል፤+ ይሁንና ቢገደልም ከሦስት ቀን በኋላ ይነሳል”+ በማለት እየነገራቸው ነበር። +32 ይሁን እንጂ የተናገረው ነገር አልገባቸውም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። +33 ከዚህ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። ወደ ቤት ከገባም በኋላ “በመንገድ ላይ ስትከራከሩ የነበረው ስለ ምን ጉዳይ ነው?”+ ሲል ጠየቃቸው። +34 በመንገድ ላይ እርስ በርስ የተከራከሩት “ከሁላችን የሚበልጠው ማን ነው?” በሚል ስለነበረ ዝም አሉ። +35 ስለዚህ ከተቀመጠ በኋላ አሥራ ሁለቱን ጠርቶ “መጀመሪያ መሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የሁሉም መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ መሆን አለበት” አላቸው።+ +36 ከዚያም አንድ ትንሽ ልጅ አምጥቶ በመካከላቸው አቆመ፤ አቅፎትም እንዲህ አላቸው፦ +37 “እንዲህ ካሉት ልጆች+ አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ እኔን ብቻ ሳይሆን የላከኝንም ይቀበላል።”+ +38 ዮሐንስ እንዲህ አለው፦ “መምህር፣ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያስወጣ አየን፤ ሆኖም እኛን ስለማይከተል ልንከለክለው ሞከርን።”+ +39 ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ “በስሜ ተአምር ሠርቶ ወዲያውኑ ስለ እኔ ክፉ ነገር ሊናገር የሚችል ስለሌለ አትከልክሉት። +40 እኛን የማይቃወም ሁሉ ከእኛ ጋር ነውና።+ +41 ደግሞም የክርስቶስ በመሆናችሁ ምክንያት አንድ ጽዋ የሚጠጣ ውኃ የሚሰጣችሁ ሁሉ፣+ እውነት እላችኋለሁ፣ በምንም መንገድ ብድራቱን አያጣም።+ +42 ሆኖም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ የወፍጮ ድንጋይ* በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል።+ +43 “እጅህ ቢያሰናክልህ ቁረጠው። ሁለት እጅ ኖሮህ እሳቱ ሊጠፋ ወደማይችልበት ወደ ገሃነም* ከምትሄድ ጉንድሽ ሆነህ ሕይወት ብታገኝ ይሻልሃል።+ +44 *—— +45 እግርህም ቢያሰናክልህ ቁረጠው። ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ገሃነም* ከምትጣል አንካሳ ሆነህ ሕይወት ብታገኝ ይሻልሃል።+ +46 *—— +47 ዓይንህም ቢያሰናክልህ አውጥተህ ጣለው።+ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነም* ከምትጣል አንድ ዓይን ኖሮህ ወደ አምላክ መንግሥት ብትገባ ይሻልሃል፤+ +48 በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱም አይጠፋም።+ +49 “ሰው ጨው እንደሚነሰንስ ሁሉ እንዲህ ዓይነት ሰዎችም እሳት ሊወርድባቸው ይገባል።+ +50 ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን በምን መመለስ ትችላላችሁ?+ በሕይወታችሁ ውስጥ ጨው ይኑራችሁ፤+ እርስ በርሳችሁም ሰላም ይኑራችሁ።”+ +13 ከቤተ መቅደስ እየወጣ ሳለ ከደቀ መዛሙ���ቱ አንዱ “መምህር፣ እንዴት ያሉ ግሩም ድንጋዮችና ሕንጻዎች እንደሆኑ ተመልከት!” አለው።+ +2 ኢየሱስ ግን “እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህ? ይህ ሁሉ ሳይፈርስ እንዲህ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ ከቶ አይኖርም” አለው።+ +3 በቤተ መቅደሱ ትይዩ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና እንድርያስ ብቻቸውን ሆነው እንዲህ በማለት ጠየቁት፦ +4 “እስቲ ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የእነዚህ ነገሮች ሁሉ መደምደሚያ መቅረቡን የሚያሳየው ምልክትስ ምንድን ነው?”+ +5 ኢየሱስም እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ “ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ።+ +6 ብዙዎች ‘እኔ እሱ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ። +7 ከዚህም ሌላ ጦርነትና የጦርነት ወሬ ስትሰሙ አትደናገጡ፤ እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸው የግድ ነው፤ ሆኖም ፍጻሜው ገና ነው።+ +8 “ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳልና፤+ በተለያየ ስፍራ የምድር ነውጥ ይከሰታል፤ በተጨማሪም የምግብ እጥረት ይኖራል።+ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።+ +9 “እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ሰዎች ለፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤+ በምኩራብም ትገረፋላችሁ፤+ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ያቀርቧችኋል፤ በዚያ ጊዜ ለእነሱ መመሥከር ትችላላችሁ።+ +10 አስቀድሞም ምሥራቹ ለብሔራት ሁሉ መሰበክ አለበት።+ +11 አሳልፈው ለመስጠት በሚወስዷችሁ ጊዜም ምን እንላለን በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ ከዚህ ይልቅ በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።+ +12 በተጨማሪም ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሳሉ፤ ደግሞም ያስገድሏቸዋል።+ +13 በስሜ የተነሳም ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል።+ እስከ መጨረሻው የጸና+ ግን* ይድናል።+ +14 “ይሁንና ጥፋት የሚያመጣው ‘ርኩስ ነገር’+ በማይገባው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል፤ በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ።+ +15 በጣሪያ* ላይ ያለ ሰው አይውረድ፤ አንዳችም ነገር ለመውሰድ ወደ ቤቱ አይግባ፤ +16 በእርሻም ያለ መደረቢያውን ለመውሰድ ወደ ኋላ አይመለስ። +17 በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!+ +18 ይህ በክረምት እንዳይሆን ዘወትር ጸልዩ፤ +19 ምክንያቱም በእነዚያ ቀናት ከአምላክ የፍጥረት ሥራ መጀመሪያ አንስቶ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ሆኖ የማያውቅ ዳግመኛም የማይሆን+ መከራ+ ይከሰታል። +20 እንዲያውም ይሖዋ* ቀኖቹን ባያሳጥራቸው ኖሮ ሥጋ ሁሉ ባልዳነ ነበር። ሆኖም እሱ ለመረጣቸው ምርጦች ሲል ቀኖቹን አሳጥሯል።+ +21 “በዚያን ጊዜም ማንም ‘እነሆ፣ ክርስቶስ ይኸውላችሁ’ ወይም ‘እነሆ፣ ያውላችሁ’ ቢላችሁ አትመኑ።+ +22 ምክንያቱም ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤+ ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ምልክቶችና አስደናቂ ነገሮች ያደርጋሉ። +23 ስለዚህ ተጠንቀቁ።+ ሁሉን ነገር አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ። +24 “ሆኖም በእነዚያ ቀናት፣ ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤+ +25 ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ በሰማያት ያሉ ኃይላትም ይናወጣሉ። +26 ከዚያም የሰው ልጅ+ በታላቅ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።+ +27 እሱም መላእክቱን ልኮ ከአራቱ ነፋሳት፣ ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ ለእሱ የተመረጡትን ይሰበስባል።+ +28 “እንግዲያው ይህን ምሳሌ ከበለስ ዛፍ ተማሩ፦ ቅርንጫፎቿ ሲለመልሙና ቅጠሎቿ ሲያቆጠቁጡ በጋ* እንደቀረበ ታውቃላችሁ።+ +29 በተመሳሳይ እናንተም እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ ስታዩ ��ሰው ልጅ ደጃፍ ላይ እንደደረሰ እርግጠኞች ሁኑ።+ +30 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ ፈጽሞ አያልፍም።+ +31 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤+ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።+ +32 “ስለዚያ ቀን ወይም ሰዓት ከአብ በቀር በሰማይ ያሉ መላእክትም ሆኑ ወልድ፣ ማንም አያውቅም።+ +33 ስለዚህ የተወሰነው ጊዜ መቼ እንደሆነ ስለማታውቁ+ ምንጊዜም በንቃት ተከታተሉ፤ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ።+ +34 ይህም ለባሪያዎቹ ሥልጣን ከሰጠና ለእያንዳንዱ የሥራ ድርሻውን ከመደበ በኋላ በር ጠባቂውን ነቅቶ እንዲጠብቅ በማዘዝ+ ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደሄደ ሰው ነው።+ +35 ስለዚህ የቤቱ ጌታ፣ በምሽት* ይሁን በእኩለ ሌሊት* ወይም ዶሮ ሲጮኽ* ይሁን ከመንጋቱ* በፊት፣ መቼ እንደሚመጣ ስለማታውቁ ምንጊዜም ነቅታችሁ ጠብቁ፤+ +36 አለዚያ ድንገት ሲመጣ ተኝታችሁ ያገኛችኋል።+ +37 ይሁንና ለእናንተ የምነግራችሁን ለሁሉም እናገራለሁ፤ ምንጊዜም ነቅታችሁ ጠብቁ።”+ +5 ከዚያም ወደ ባሕሩ ማዶ ተሻግረው ጌርጌሴኖን+ ወደተባለው ክልል ደረሱ። +2 ኢየሱስ ከጀልባ እንደወረደ፣ ርኩስ መንፈስ ያደረበት አንድ ሰው ከመቃብር ቦታ ወጥቶ ከእሱ ጋር ተገናኘ። +3 ይህ ሰው በመቃብር ቦታ ይኖር የነበረ ሲሆን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በሰንሰለት እንኳ አጥብቆ ሊያስረው የቻለ አንድም ሰው አልነበረም። +4 ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር የነበረ ቢሆንም ሰንሰለቱን ይበጣጥስ፣ እግር ብረቱንም ይሰባብር ነበር፤ እሱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያስችል ጉልበት ያለው አንድም ሰው አልነበረም። +5 ዘወትር ሌሊትና ቀን በመቃብር ቦታና በተራሮች ላይ ይጮኽ እንዲሁም ሰውነቱን በድንጋይ ይተለትል ነበር። +6 ኢየሱስን ከሩቅ ባየው ጊዜ ግን ወደ እሱ ሮጦ በመሄድ ሰገደለት።+ +7 ከዚያም በታላቅ ድምፅ እየጮኸ “የልዑል አምላክ ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በአምላክ ስም አስምልሃለሁ” አለው።+ +8 ይህን ያለው ኢየሱስ “አንተ ርኩስ መንፈስ ከዚህ ሰው ውጣ”+ ብሎት ስለነበር ነው። +9 ኢየሱስም “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እሱም “ብዙ ስለሆንን ስሜ ሌጌዎን* ነው” ብሎ መለሰለት። +10 መናፍስቱን ከአገሪቱ እንዳያስወጣቸውም ኢየሱስን ተማጸነው።+ +11 በዚያም በተራራው ላይ ብዙ የአሳማ+ መንጋ ተሰማርቶ ነበር።+ +12 ርኩሳን መናፍስቱም “አሳማዎቹ ውስጥ እንድንገባ ወደ እነሱ ስደደን” ብለው ተማጸኑት። +"13 እሱም ፈቀደላቸው። በዚህ ጊዜ ርኩሳን መናፍስቱ ወጥተው አሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ ወደ 2,000 የሚጠጉ አሳማዎችም ከገደሉ አፋፍ* እየተንደረደሩ በመውረድ ባሕሩ ውስጥ ሰጠሙ።" +14 የአሳማዎቹ እረኞች ግን ሸሽተው በመሄድ ወሬውን በከተማውና በገጠሩ አዳረሱ፤ ሰዎችም የሆነውን ነገር ለማየት መጡ።+ +15 ወደ ኢየሱስም መጥተው ጋኔን ያደረበትን ይኸውም ቀደም ሲል ሌጌዎን የነበረበትን ሰው ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ተቀምጦ አዩት፤ በዚህ ጊዜ ፍርሃት አደረባቸው። +16 የተፈጸመውንም ነገር ያዩ ሰዎች አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው እንዴት እንዲህ ሊሆን እንደቻለና በአሳማዎቹ ላይ የሆነውን ነገር አወሩላቸው። +17 በመሆኑም አካባቢያቸውን ለቆ እንዲሄድ ኢየሱስን ይማጸኑት ጀመር።+ +18 ኢየሱስ ወደ ጀልባው በመውጣት ላይ ሳለ ጋኔን አድሮበት የነበረው ሰው አብሮት ይሄድ ዘንድ ተማጸነው።+ +19 ኢየሱስ ግን አልፈቀደለትም፤ ከዚህ ይልቅ “ወደ ቤት ሄደህ ይሖዋ * ያደረገልህን ነገር ሁሉና ያሳየህን ምሕረት ለዘመዶችህ ንገራቸው” አለው። +20 ሰውየውም ሄዶ ኢየሱስ ያደረገለትን ነገር በሙሉ በዲካፖሊስ* ያውጅ ጀመር፤ ሕዝቡም ሁሉ ተደነቁ። +21 ኢየሱ��� በጀልባ ዳግመኛ ወደ ባሕሩ ማዶ ከተሻገረ በኋላ እጅግ ብዙ ሕዝብ ወደ እሱ ተሰበሰበ፤ እሱም በባሕሩ አጠገብ ነበር።+ +22 በዚህ ጊዜ ከምኩራብ አለቆች አንዱ የሆነ ኢያኢሮስ የሚባል ሰው ወደዚያ መጣ፤ ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እግሩ ላይ ወደቀ።+ +23 ከዚያም “ትንሿ ልጄ በጠና ታምማለች።* እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር፣ እባክህ መጥተህ እጅህን ጫንባት”+ በማለት ደጋግሞ ተማጸነው። +24 ኢየሱስም አብሮት ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሕዝብም ተከትሎት እየተጋፋው ይሄድ ነበር። +25 በዚያም፣ ለ12 ዓመት ደም ሲፈሳት+ የኖረች አንዲት ሴት ነበረች።+ +26 ይህች ሴት በርካታ ሐኪሞች ጋር የሄደች ሲሆን ሕክምናው ለብዙ ሥቃይ ዳርጓት ነበር፤ ያላትን ጥሪት ሁሉ ብትጨርስም ሕመሙ ባሰባት እንጂ አልተሻላትም። +27 ስለ ኢየሱስ የተወራውን በሰማች ጊዜ በሰዎች መካከል ከኋላው መጥታ ልብሱን ነካች፤+ +28 ምክንያቱም “ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ” ብላ ታስብ ነበር።+ +29 ወዲያውም ይፈሳት የነበረው ደም ቆመ፤ ያሠቃያት ከነበረው ሕመም እንደተፈወሰችም ታወቃት። +30 ወዲያውኑ ኢየሱስ ኃይል ከእሱ እንደወጣ ታወቀው፤+ በመሆኑም ወደ ሕዝቡ በመዞር “ልብሴን የነካው ማን ነው?” ሲል ጠየቀ።+ +31 ደቀ መዛሙርቱ ግን “ሕዝቡ እንዲህ ሲጋፋህ እያየህ ‘የነካኝ ማን ነው?’ እንዴት ትላለህ?” አሉት። +32 ይሁንና ኢየሱስ ይህን ያደረገው ማን እንደሆነ ለማየት ዙሪያውን ተመለከተ። +33 ሴትየዋ በእሷ ላይ የተፈጸመውን ነገር ስላወቀች በፍርሃት እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ ከዚያም ምንም ሳታስቀር እውነቱን ነገረችው። +34 እሱም “ልጄ ሆይ፣ እምነትሽ አድኖሻል። በሰላም ሂጂ፤+ ከሚያሠቃይ ሕመምሽም ተፈወሽ” አላት።+ +35 ገና እየተናገረ ሳለ ከምኩራብ አለቃው ቤት የመጡ ሰዎች “ልጅህ ሞታለች! ከዚህ በኋላ መምህሩን ለምን ታስቸግረዋለህ?” አሉት።+ +36 ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ሰምቶ የምኩራብ አለቃውን “አትፍራ፤ ብቻ እመን” አለው።+ +37 ከዚህ በኋላ ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብና ከያዕቆብ ወንድም ከዮሐንስ በስተቀር ማንም እንዲከተለው አልፈቀደም።+ +38 ወደ ምኩራብ አለቃው ቤት በደረሱም ጊዜ ትርምሱን እንዲሁም የሚያለቅሱትንና ዋይ ዋይ የሚሉትን ሰዎች ተመለከተ።+ +39 ወደ ውስጥ ከገባም በኋላ “የምታለቅሱትና የምትንጫጩት ለምንድን ነው? ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።+ +40 በዚህ ጊዜ በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። እሱ ግን ሁሉንም ወደ ውጭ ካስወጣ በኋላ የልጅቷን አባትና እናት እንዲሁም ከእሱ ጋር የነበሩትን አስከትሎ ልጅቷ ወዳለችበት ገባ። +41 ከዚያም የልጅቷን እጅ ይዞ “ጣሊታ ቁሚ” አላት፤ ትርጉሙም “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” ማለት ነው።+ +42 ልጅቷም ወዲያው ተነስታ መራመድ ጀመረች። (ዕድሜዋ 12 ዓመት ነበር።) ወዲያውም እጅግ ከመደሰታቸው የተነሳ የሚሆኑት ጠፋቸው። +43 እሱ ግን ይህን ለማንም እንዳይናገሩ ደጋግሞ አስጠነቀቃቸው፤*+ ለልጅቷም የሚበላ ነገር እንዲሰጧት ነገራቸው። +15 ወዲያውኑ በማለዳ የካህናት አለቆች፣ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ማለትም መላው የሳንሄድሪን ሸንጎ አባላት ተሰብስበው ተማከሩ፤ ኢየሱስንም አስረው በመውሰድ ለጲላጦስ አስረከቡት።+ +2 ጲላጦስም “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው።+ እሱም መልሶ “አንተው ራስህ ተናገርከው” አለው።+ +3 የካህናት አለቆቹ ግን በእሱ ላይ በርካታ ክስ መደርደራቸውን ቀጠሉ። +4 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “ምንም መልስ አትሰጥም?+ በስንት ነገር እየከሰሱህ እንዳሉ ተመልከት” ሲል እንደገና ጠየቀው።+ +5 ሆኖም ኢየሱስ ምንም ተጨማሪ መልስ አልሰጠም፤ በመሆኑም ጲላጦስ ተገረመ።+ +6 ጲላጦስ ሁልጊዜ በዚህ በዓል ወቅት፣ ሕዝቡ ይፈታልን ብለው የጠየቁትን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው።+ +7 በወቅቱ፣ በመንግሥት ላይ ዓመፅ በማነሳሳት ሰው ገድለው ከታሰሩ ዓመፀኞች መካከል በርባን የሚባል ሰው ይገኝ ነበር። +8 ሕዝቡም መጥተው ጲላጦስ እንደ ልማዱ ያደርግላቸው ዘንድ ይጠይቁት ጀመር። +9 እሱም መልሶ “የአይሁዳውያንን ንጉሥ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው።+ +10 ጲላጦስ ይህን ያለው የካህናት አለቆች አሳልፈው የሰጡት በቅናት ተነሳስተው እንደሆነ ያውቅ ስለነበር ነው።+ +11 ይሁንና የካህናት አለቆቹ በኢየሱስ ምትክ በርባንን ይፈታላቸው ዘንድ እንዲጠይቁ ሕዝቡን አነሳሱ።+ +12 ጲላጦስም እንደገና መልሶ “እንግዲያው የአይሁዳውያን ንጉሥ የምትሉትን ምን ባደርገው ይሻላል?” አላቸው።+ +13 እነሱም “ይሰቀል!”* ብለው እንደገና ጮኹ።+ +14 ሆኖም ጲላጦስ “ለምን? ምን ያጠፋው ነገር አለ?” አላቸው። እነሱ ግን “ይሰቀል!”* እያሉ የባሰ ጮኹ።+ +15 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ ሕዝቡን ለማስደሰት ስለፈለገ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስንም ካስገረፈው+ በኋላ በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።+ +16 ወታደሮቹ ወደ ግቢው ይኸውም ወደ አገረ ገዢው መኖሪያ ቤት ወሰዱት፤ ሠራዊቱንም ሁሉ አንድ ላይ ሰበሰቡ።+ +17 ሐምራዊ ልብስም አለበሱት፤ የእሾህ አክሊል ጎንጉነውም በራሱ ላይ ደፉበት፤ +18 ደግሞም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “የአይሁዳውያን ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” ይሉት ጀመር።+ +19 ከዚህም ሌላ ራሱን በመቃ ይመቱትና ይተፉበት ነበር፤ ተንበርክከውም እጅ ነሱት።* +20 ሲያፌዙበት ከቆዩ በኋላም ሐምራዊውን ልብስ ገፈው የራሱን መደረቢያዎች አለበሱት። ከዚያም በእንጨት ላይ ሊቸነክሩት ይዘውት ሄዱ።+ +21 ስምዖን የተባለ አንድ የቀሬና ሰው ከገጠር መጥቶ በዚያ ሲያልፍ አግኝተው ኢየሱስ የሚሰቀልበትን የመከራ እንጨት* እንዲሸከም አስገደዱት፤* ይህ ሰው የእስክንድርና የሩፎስ አባት ነበር።+ +22 በኋላም ኢየሱስን ጎልጎታ ወደተባለ ቦታ አመጡት፤ ትርጉሙም “የራስ ቅል ቦታ” ማለት ነው።+ +23 እዚያም ከርቤ* የተቀላቀለበት የወይን ጠጅ ሰጡት፤+ እሱ ግን አልተቀበለም። +24 ከዚያም እንጨት ላይ ቸነከሩት፤ ማን ምን እንደሚወስድ ለመወሰንም ዕጣ ተጣጥለው መደረቢያዎቹን ተከፋፈሉ።+ +25 እንጨት ላይ ሲቸነክሩትም ጊዜው ሦስት ሰዓት ነበር። +26 የተከሰሰበትን ጉዳይ የሚገልጽ “የአይሁዳውያን ንጉሥ” የሚል ጽሑፍ ተጽፎ ነበር።+ +27 ከእሱም ጋር ሁለት ዘራፊዎችን፣ አንዱን በቀኙ ሌላውን ደግሞ በግራው በእንጨት ላይ ሰቀሉ።+ +28 *—— +29 በዚያ የሚያልፉም ይሰድቡትና ራሳቸውን እየነቀነቁ+ እንዲህ ይሉት ነበር፦ “ቤተ መቅደሱን አፍርሼ በሦስት ቀን እሠራዋለሁ ባይ!+ +30 እስቲ ከተሰቀልክበት እንጨት* ላይ ወርደህ ራስህን አድን።” +31 የካህናት አለቆችም እንደዚሁ ከጸሐፍት ጋር ሆነው እርስ በርሳቸው እንዲህ እያሉ ያፌዙበት ነበር፦ “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አልቻለም!+ +32 አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ እስቲ አሁን ከተሰቀለበት እንጨት* ይውረድ።”+ ከእሱ ጋር በእንጨት ላይ የተሰቀሉትም እንኳ ሳይቀሩ ይነቅፉት ነበር።+ +33 ስድስት ሰዓት በሆነ ጊዜም አገሩ በሙሉ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በጨለማ ተሸፈነ።+ +34 በዘጠነኛውም ሰዓት ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ “ኤሊ፣ ኤሊ፣ ላማ ሳባቅታኒ?” ብሎ ጮኸ፤ ትርጉሙም “አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው።+ +35 በአቅራቢያው ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ “አያችሁ! ኤልያስን እየተጣራ ነው” ይሉ ጀመር። +36 ከዚያም አንድ ሰው ሮጦ በመሄድ የኮመጠጠ የወይን ጠጅ ውስጥ ሰፍነግ* ከነከረ በኋላ በመቃ ላይ አድርጎ እንዲጠጣ ሰጠውና+ “ተዉት! እስቲ ኤልያስ መጥቶ ያወርደው እንደሆነ እንይ” አለ። +37 ሆኖም ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ሞተ።*+ +38 የቤተ መቅደሱ መጋረጃም+ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ።+ +39 ከፊት ለፊቱ ቆሞ የነበረው መኮንንም በዚህ ሁኔታ መሞቱን ሲያይ “ይህ ሰው በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር” አለ።+ +40 በተጨማሪም ከሩቅ ሆነው የሚያዩ ሴቶች የነበሩ ሲሆን ከእነሱም መካከል መግደላዊቷ ማርያም እንዲሁም የትንሹ* ያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያምና ሰሎሜ ነበሩ፤+ +41 እነዚህም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ ናቸው፤+ ከእሱ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሌሎች በርካታ ሴቶችም ነበሩ። +42 ቀኑ በመገባደዱና የዝግጅት ቀን ማለትም የሰንበት ዋዜማ በመሆኑ +43 የተከበረ የሸንጎ* አባል የሆነውና የአምላክን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ መጣ። ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ።+ +44 ጲላጦስ ግን ኢየሱስ ሞቶ እንደሆነ ለማወቅ የመቶ አለቃውን ጠርቶ በእርግጥ ሞቶ እንደሆነ ጠየቀው። +45 መሞቱን ከመቶ አለቃው ካረጋገጠ በኋላም አስከሬኑን እንዲወስድ ለዮሴፍ ፈቀደለት። +46 እሱም በፍታ ገዝቶ አስከሬኑን ካወረደ በኋላ በበፍታው ገነዘው፤ ከዚያም ከዓለት ተፈልፍሎ በተሠራ መቃብር ውስጥ አኖረው፤+ ድንጋይ አንከባሎም የመቃብሩን ደጃፍ ዘጋው።+ +47 በዚህ ጊዜ መግደላዊቷ ማርያምና የዮሳ እናት ማርያም አስከሬኑ የተቀመጠበትን ቦታ ይመለከቱ ነበር።+ +17 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ሰዎችን የሚያሰናክሉ ነገሮች መከሰታቸው የማይቀር ነው። ሆኖም ለመሰናክሉ ምክንያት ለሚሆነው ለዚያ ሰው ወዮለት! +2 ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል።+ +3 ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤+ ከተጸጸተም ይቅር በለው።+ +4 በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህ እንኳ ‘ተጸጽቻለሁ’ እያለ ሰባት ጊዜ ወደ አንተ ከመጣ ይቅር ልትለው ይገባል።”+ +5 በዚህ ጊዜ ሐዋርያቱ ጌታን “እምነት ጨምርልን” አሉት።+ +6 ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰናፍጭ ዘር የሚያህል እምነት ካላችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ ባሕሩ ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዛችኋል።+ +7 “ከእናንተ መካከል አራሽ ወይም እረኛ የሆነ ባሪያ ያለው ሰው ቢኖር፣ ባሪያው ከእርሻ ሲመለስ ‘ቶሎ ናና ወደ ማዕድ ቅረብ’ ይለዋል? +8 ከዚህ ይልቅ ‘ራቴን አዘጋጅልኝ፤ በልቼና ጠጥቼ እስክጨርስም ድረስ አሸርጠህ አገልግለኝ፤ ከዚያ በኋላ መብላትና መጠጣት ትችላለህ’ አይለውም? +9 ባሪያው የተሰጠውን ሥራ በማከናወኑ ጌታው የሚያመሰግነው ይመስላችኋል? +10 በተመሳሳይ እናንተም የተሰጣችሁን ሥራ ሁሉ ባከናወናችሁ ጊዜ ‘ምንም የማንጠቅም ባሪያዎች ነን። ያደረግነው ልናደርገው የሚገባንን ነገር ነው’ በሉ።”+ +11 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄደ ሳለ በሰማርያና በገሊላ መካከል አለፈ። +12 ወደ አንድ መንደር እየገባም ሳለ የሥጋ ደዌ የያዛቸው አሥር ሰዎች አዩት፤ እነሱም በርቀት ቆሙ።+ +13 ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ “ኢየሱስ፣ መምህር፣ ምሕረት አድርግልን!” አሉ። +14 እሱም ባያቸው ጊዜ “ሄዳችሁ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ” አላቸው።+ ከዚያም እየሄዱ ሳሉ ነጹ።+ +15 ከእነሱ አንዱ እንደተፈወሰ ባየ ጊዜ አምላክን በታላቅ ድምፅ እያመሰገነ ተመለሰ። +16 ኢየሱስ እግር ላይ ተደፍቶም አመሰገነው። ሰውየውም ሳምራዊ+ ነበር። +17 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “የነጹት አሥሩም አይደሉም እንዴ? ታዲያ ዘጠኙ የት አሉ? +18 ከዚህ ከባዕድ አገር ሰው በስተቀር አምላክን ለማመስገን የተመለሰ ሌላ አንድም ሰው የለም?” +19 ከ���ያም ሰውየውን “ተነስና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።+ +20 ፈሪሳውያን የአምላክ መንግሥት መቼ እንደሚመጣ ሲጠይቁት+ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የአምላክ መንግሥት በግልጽ በሚታይ ሁኔታ አይመጣም፤ +21 ሰዎችም ‘እነሆ እዚህ ነው!’ ወይም ‘እዚያ ነው!’ አይሉም። እነሆ፣ የአምላክ መንግሥት በመካከላችሁ ነውና።”+ +22 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትመኙበት ጊዜ ይመጣል፤ ግን አታዩትም። +23 ሰዎችም ‘እዚያ ነው!’ ወይም ‘እዚህ ነው!’ ይሏችኋል። ነገር ግን አትሂዱ ወይም አትከተሏቸው።+ +24 ምክንያቱም መብረቅ ከአንዱ የሰማይ ክፍል እስከ ሌላኛው የሰማይ ክፍል እንደሚያበራ ሁሉ የሰው ልጅ+ በሚገለጥበትም ቀን እንዲሁ ይሆናል።+ +25 በመጀመሪያ ግን ብዙ መከራ መቀበሉና በዚህ ትውልድ ተቀባይነት ማጣቱ የግድ ነው።+ +26 በተጨማሪም በኖኅ ዘመን+ እንደተከሰተው ሁሉ በሰው ልጅ ዘመንም እንዲሁ ይሆናል፦+ +27 ኖኅ ወደ መርከቡ እስከገባበትና+ የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉንም እስካጠፋበት ቀን+ ድረስ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ወንዶች ያገቡ፣ ሴቶችም ይዳሩ ነበር። +28 በተመሳሳይም በሎጥ ዘመን እንደተከሰተው ሁሉ እንዲሁ ይሆናል፦+ ሰዎች ይበሉ፣ ይጠጡ፣ ይገዙ፣ ይሸጡ፣ ይተክሉና ቤቶችን ይገነቡ ነበር። +29 ሆኖም ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ከሰማይ እሳትና ድኝ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋቸው።+ +30 የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን+ እንዲሁ ይሆናል። +31 “በዚያን ቀን በጣሪያ* ላይ ያለ ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ ለመውሰድ አይውረድ፤ እርሻም ላይ ያለ ሰው በኋላው ያለውን ነገር ለመውሰድ አይመለስ። +32 የሎጥን ሚስት አስታውሱ።+ +33 ሕይወቱን* ጠብቆ ለማቆየት የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ሕይወቱን የሚያጣት ሁሉ ግን በሕይወት ጠብቆ ያቆያታል።+ +34 እላችኋለሁ፣ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ላይ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላኛው ግን ይተዋል።+ +35 ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላኛዋ ግን ትተዋለች።” +36 *—— +37 እነሱም መልሰው “ጌታ ሆይ፣ የት?” አሉት። እሱም “በድን ባለበት ንስሮች ይሰበሰባሉ” አላቸው።+ +18 ከዚያም ምንጊዜም ተስፋ ሳይቆርጡ የመጸለይን+ አስፈላጊነት በተመለከተ ለደቀ መዛሙርቱ አንድ ምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፤ +2 እንዲህም አላቸው፦ “በአንዲት ከተማ አምላክን የማይፈራና ሰውን የማያከብር አንድ ዳኛ ነበር። +3 በዚያች ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ በየጊዜው ወደ እሱ እየሄደች ‘ከባላጋራዬ ጋር ለምከራከርበት ጉዳይ ፍረድልኝ’ ትለው ነበር። +4 ይሁንና ዳኛው ለተወሰነ ጊዜ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ፤ በኋላ ግን በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፦ ‘ምንም እንኳ አምላክን የማልፈራ፣ ሰውንም የማላከብር ብሆን +5 ይህች መበለት ሁልጊዜ እየመጣች ስለምታስቸግረኝ ፍትሕ እንድታገኝ አደርጋለሁ፤ አለዚያ በየጊዜው እየመጣች ትነዘንዘኛለች።’”*+ +6 ከዚያም ጌታ እንዲህ አለ፦ “ምንም እንኳ ዳኛው ዓመፀኛ ቢሆንም ምን እንዳለ ልብ በሉ! +7 ታዲያ አምላክ በትዕግሥት የሚይዛቸውና+ ቀን ከሌት ወደ እሱ የሚጮኹት ምርጦቹ+ ፍትሕ እንዲያገኙ አያደርግም? +8 እላችኋለሁ፣ በቶሎ ፍትሕ እንዲያገኙ ያደርጋል። ሆኖም የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር ላይ በእርግጥ እምነት* ያገኝ ይሆን?” +9 በራሳቸው ጽድቅ ለሚታመኑና ሌሎችን በንቀት ዓይን ለሚመለከቱ ደግሞ የሚከተለውን ምሳሌ ተናገረ፦ +10 “ሁለት ሰዎች ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፤ አንደኛው ፈሪሳዊ፣ ሌላኛው ደግሞ ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር። +11 ፈሪሳዊው ቆሞ በልቡ እንዲህ ሲል ይጸልይ ጀመር፦ ‘አምላክ ሆይ፣ እንደ ሌላው ሰው ቀማኛ፣ ዓመፀኛ፣ ��መንዝራ፣ በተለይ ደግሞ እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ። +12 በሳምንት ሁለቴ እጾማለሁ፤ ከማገኘውም ነገር ሁሉ አሥራት እሰጣለሁ።’+ +13 ቀረጥ ሰብሳቢው ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ለማየትም እንኳ አልደፈረም፤ እንዲያውም ‘አምላክ ሆይ፣ ኃጢአተኛ ለሆንኩት ለእኔ ቸርነት አድርግልኝ’* እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።+ +14 እላችኋለሁ፣ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይሄኛው ሰው ይበልጥ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ።+ ምክንያቱም ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ግን ከፍ ይደረጋል።”+ +15 ሰዎችም ኢየሱስ እጁን እንዲጭንባቸው ሕፃናትን ወደ እሱ ያመጡ ጀመር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ይህን ሲያዩ ገሠጿቸው።+ +16 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ሕፃናቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አለ፦ “ልጆቹ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ የአምላክ መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ነውና።+ +17 እውነት እላችኋለሁ፣ የአምላክን መንግሥት እንደ አንድ ትንሽ ልጅ ሆኖ የማይቀበል ሁሉ ፈጽሞ ወደዚህ መንግሥት አይገባም።”+ +18 ከአይሁዳውያን አለቆችም አንዱ “ጥሩ መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” ሲል ጠየቀው።+ +19 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ለምን ጥሩ ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከአምላክ በቀር ጥሩ የለም።+ +20 ‘አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ በሐሰት አትመሥክር፣+ አባትህንና እናትህን አክብር’+ የሚሉትን ትእዛዛት ታውቃለህ።” +21 ሰውየውም “እነዚህን ሁሉ ከልጅነቴ ጀምሮ ስጠብቅ ኖሬአለሁ” አለ። +22 ኢየሱስ ይህን ከሰማ በኋላ “አሁንም አንድ የሚቀርህ ነገር አለ፤ ያለህን ነገር ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድሆች አከፋፍል፤ በሰማያትም ውድ ሀብት ታገኛለህ፤ ደግሞም መጥተህ ተከታዬ ሁን” አለው።+ +23 ሰውየው በጣም ሀብታም ስለነበረ ይህን ሲሰማ እጅግ አዘነ።+ +24 ኢየሱስም ሰውየውን ተመልክቶ እንዲህ አለ፦ “ገንዘብ ላላቸው ሰዎች ወደ አምላክ መንግሥት መግባት ምንኛ አስቸጋሪ ነው!+ +25 እንዲያውም ሀብታም ሰው ወደ አምላክ መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።”+ +26 ይህን የሰሙ ሰዎች “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።+ +27 እሱም “በሰዎች ዘንድ የማይቻል፣ በአምላክ ዘንድ ይቻላል” አለ።+ +28 ጴጥሮስ ግን “እነሆ፣ እኛ ያለንን ነገር ትተን ተከትለንሃል” አለ።+ +29 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ለአምላክ መንግሥት ሲል ቤትን ወይም ሚስትን ወይም ወንድሞችን ወይም ወላጆችን ወይም ልጆችን የተወ ሁሉ፣+ +30 አሁን በዚህ ዘመን ብዙ እጥፍ፣ በሚመጣው ሥርዓት* ደግሞ የዘላለም ሕይወት ያገኛል።”+ +31 ከዚያም አሥራ ሁለቱን ገለል አድርጎ በመውሰድ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ! ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰውን ልጅ በተመለከተም በነቢያት የተጻፉት ነገሮች ሁሉ ይፈጸማሉ።+ +32 ለምሳሌ ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤+ ያፌዙበታል፤+ ያንገላቱታል እንዲሁም ይተፉበታል።+ +33 ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤+ በሦስተኛው ቀን ግን ይነሳል።”+ +34 ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ መካከል አንዱንም አልተረዱም፤ የተናገረው ቃል ተሰውሮባቸው ነበርና፤ የተባለውም ነገር አልገባቸውም። +35 ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ እየተቃረበ ሳለ አንድ ዓይነ ስውር መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።+ +36 ዓይነ ስውሩም ብዙ ሕዝብ በዚያ ሲያልፍ ሰምቶ ስለ ሁኔታው ይጠይቅ ጀመር። +37 ሰዎቹም “የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ እያለፈ ነው!” ብለው ነገሩት። +38 በዚህ ጊዜ “ኢየሱስ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” ሲል ጮኸ። +39 ከፊት ከፊት የሚሄዱትም ሰዎች ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት ��ድርግልኝ!” እያለ ይበልጥ መጮኹን ቀጠለ። +40 ኢየሱስም ቆመና ሰውየውን ወደ እሱ እንዲያመጡት አዘዘ። ሰውየው ወደ እሱ በቀረበ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ +41 “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” እሱም “ጌታ ሆይ፣ የዓይኔን ብርሃን መልስልኝ” አለው። +42 ስለዚህ ኢየሱስ “የዓይንህ ብርሃን ይመለስልህ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።+ +43 ወዲያውም የዓይኑ ብርሃን ተመለሰለት፤ አምላክን እያመሰገነም ይከተለው ጀመር።+ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ አምላክን አወደሱ።+ +23 ስለዚህ በዚያ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች በሙሉ ተነስተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱት።+ +2 ከዚያም እንዲህ እያሉ ይከሱት ጀመር፦+ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያሳምፅ፣ ለቄሳር ግብር እንዳይከፈል ሲከለክልና+ ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ’+ ሲል አግኝተነዋል።” +3 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም መልሶ “አንተው ራስህ እኮ እየተናገርከው ነው” አለው።+ +4 ከዚያም ጲላጦስ ለካህናት አለቆቹና ለሕዝቡ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም” አለ።+ +5 እነሱ ግን “በመላው ይሁዳ፣ ከገሊላ አንስቶ እስከዚህ ድረስ እያስተማረ ሕዝቡን ይቀሰቅሳል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ። +6 ጲላጦስ ይህን ሲሰማ ሰውየው የገሊላ ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ጠየቀ። +7 ከሄሮድስ+ ግዛት የመጣ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ወደነበረው ወደ ሄሮድስ ላከው። +8 ሄሮድስ ኢየሱስን ሲያየው በጣም ደስ አለው። ስለ እሱ ብዙ ነገር ሰምቶ ስለነበር+ ለረጅም ጊዜ እሱን ለማየት ይፈልግ ነበር፤ አንዳንድ ተአምራት ሲፈጽም ለማየትም ተስፋ ያደርግ ነበር። +9 በመሆኑም ብዙ ጥያቄ ይጠይቀው ጀመር፤ እሱ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም።+ +10 ይሁን እንጂ የካህናት አለቆቹና ጸሐፍት በተደጋጋሚ እየተነሱ አጥብቀው ይከሱት ነበር። +11 ከዚያም ሄሮድስ ከወታደሮቹ ጋር ሆኖ አቃለለው፤+ እንዲሁም ያማረ ልብስ አልብሶ ካፌዘበት+ በኋላ መልሶ ወደ ጲላጦስ ላከው። +12 በዚያን ዕለት ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ፤ ከዚያ በፊት በመካከላቸው ጠላትነት ነበር። +13 ከዚያም ጲላጦስ የካህናት አለቆቹን፣ ገዢዎቹንና ሕዝቡን በአንድነት ጠርቶ +14 እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁት ሕዝቡን ለዓመፅ ያነሳሳል ብላችሁ ነበር። ይኸው በፊታችሁ መረመርኩት፤ ሆኖም በእሱ ላይ ያቀረባችሁትን ክስ የሚደግፍ ምንም ነገር አላገኘሁም።+ +15 ሄሮድስም ቢሆን ምንም ጥፋት ስላላገኘበት ወደ እኛ መልሶ ልኮታል፤ በመሆኑም ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር አልፈጸመም። +16 ስለዚህ ቀጥቼ+ እፈታዋለሁ።” +17 *—— +18 ሕዝቡ ሁሉ ግን “ይህን ሰው ግደለው፤* በርባንን ግን ፍታልን!” እያሉ ጮኹ።+ +19 (ይህ ሰው በከተማው ውስጥ በተከሰተ የሕዝብ ዓመፅና በነፍስ ግድያ የታሰረ ነበር።) +20 ጲላጦስ ኢየሱስን ሊፈታው ስለፈለገ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደገና ለሕዝቡ ተናገረ።+ +21 እነሱ ግን “ይሰቀል! ይሰቀል!”* እያሉ ይጮኹ ጀመር።+ +22 እሱም ለሦስተኛ ጊዜ “ለምን? ይህ ሰው ምን ያጠፋው ነገር አለ? ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ” አላቸው። +23 በዚህ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ኢየሱስ እንዲገደል* አጥብቀው ወተወቱት፤ ድምፃቸውም አየለ።+ +24 ስለዚህ ጲላጦስ የጠየቁት እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላለፈ። +25 ሕዝብ በማሳመፅና በነፍስ ግድያ ታስሮ የነበረውንና እንዲፈታላቸው የጠየቁትን ሰው ለቀቀው፤ ኢየሱስን ግን የፈለጉትን እንዲያደርጉበት አሳልፎ ሰጣቸው። +26 ይዘውትም እየሄዱ ሳሉ ከገጠር እየመጣ የነበረውን ስምዖን የተባለ አንድ የቀሬና ሰው ያዙትና የመከራውን እንጨት* ���ሸክመው ከኢየሱስ ኋላ እንዲሄድ አደረጉት።+ +27 ብዙ ሕዝብም ይከተለው ነበር፤ ከእነሱም መካከል በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ የሚያለቅሱለት ሴቶች ነበሩ። +28 ኢየሱስም ወደ ሴቶቹ ዞር ብሎ እንዲህ አለ፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፣ ለእኔ አታልቅሱ። ይልቁንስ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ፤+ +29 ሰዎች ‘መሃን የሆኑ ሴቶች፣ ያልወለዱ ማህፀኖችና ያላጠቡ ጡቶች ደስተኞች ናቸው!’+ የሚሉበት ቀን ይመጣልና። +30 በዚያን ጊዜ ተራሮችን ‘በላያችን ውደቁ!’ ኮረብቶችንም ‘ሸሽጉን!’ ይላሉ።+ +31 ዛፉ እርጥብ ሆኖ ሳለ እንዲህ ካደረጉ በደረቀ ጊዜማ ምን ይከሰት ይሆን?” +32 ወንጀለኞች የሆኑ ሌሎች ሁለት ሰዎችም ከእሱ ጋር ሊገደሉ እየተወሰዱ ነበር።+ +33 የራስ ቅል+ ወደተባለ ቦታ በደረሱ ጊዜ ኢየሱስን በዚያ ከወንጀለኞቹ ጋር በእንጨት ላይ ቸነከሩት፤ ወንጀለኞቹም አንዱ በቀኙ ሌላው ደግሞ በግራው ተሰቅለው ነበር።+ +34 ኢየሱስም “አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው” ይል ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ልብሶቹን ለመከፋፈል ዕጣ ተጣጣሉ።+ +35 ሕዝቡም ቆሞ ይመለከት ነበር። የሃይማኖት መሪዎቹ ግን* “ሌሎችን አዳነ፤ የተመረጠው የአምላክ ክርስቶስ እሱ ከሆነ እስቲ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌዙበት ነበር።+ +36 ወታደሮቹ እንኳ ሳይቀሩ ወደ እሱ ቀርበው የኮመጠጠ የወይን ጠጅ በመስጠት+ አፌዙበት፤ +37 እንዲሁም “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ከሆንክ ራስህን አድን” ይሉት ነበር። +38 በተጨማሪም ከበላዩ “ይህ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነው” የሚል ጽሑፍ ነበር።+ +39 ከዚያም በዚያ ከተሰቀሉት ወንጀለኞች አንዱ “አንተ ክርስቶስ አይደለህም እንዴ? እስቲ ራስህንም እኛንም አድን!” እያለ ይዘልፈው+ ጀመር። +40 ሌላኛው ግን መልሶ እንዲህ ሲል ገሠጸው፦ “አንተ ራስህ ተመሳሳይ ፍርድ ተቀብለህ እያለ ትንሽ እንኳ አምላክን አትፈራም? +41 እኛስ ላደረግነው ነገር የሚገባንን ቅጣት በሙሉ እየተቀበልን ስለሆነ በእኛ ላይ የተፈጸመው ፍርድ ተገቢ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም የሠራው ጥፋት የለም።” +42 ቀጥሎም “ኢየሱስ ሆይ፣ ወደ መንግሥትህ ስትመጣ አስበኝ” አለው።+ +43 እሱም “እውነት እልሃለሁ ዛሬ፣ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” አለው።+ +44 ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ የነበረ ቢሆንም ምድሪቱ በሙሉ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በጨለማ ተሸፈነች፤+ +45 ይህም የሆነው የፀሐይ ብርሃን በመጥፋቱ ነው፤ ከዚያም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ+ መሃል ለመሃል ተቀደደ።+ +46 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ “አባት ሆይ፣ መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ”+ አለ። ይህን ካለ በኋላ ሞተ።*+ +47 መኮንኑም የተፈጸመውን ነገር በማየቱ “ይህ ሰው በእርግጥ ጻድቅ ነበር”+ በማለት ለአምላክ ክብር ይሰጥ ጀመር። +48 ይህን ለማየት በቦታው ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች ሁሉ የተከሰቱትን ነገሮች ሲመለከቱ በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ ወደ ቤታቸው ተመለሱ። +49 በቅርብ የሚያውቁትም ሁሉ በርቀት ቆመው ነበር። እንዲሁም ከገሊላ አንስቶ አብረውት የተጓዙት ሴቶች በዚያ ተገኝተው እነዚህን ነገሮች ይመለከቱ ነበር።+ +50 እነሆም፣ የሸንጎ* አባል የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ጥሩና ጻድቅ ሰው ነበረ።+ +51 (ይህ ሰው ሴራቸውንና ድርጊታቸውን በመደገፍ ድምፅ አልሰጠም ነበር።) እሱም የአይሁዳውያን ከተማ የሆነችው የአርማትያስ ሰው ሲሆን የአምላክን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር። +52 ይህም ሰው ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ። +53 አስከሬኑንም አውርዶ+ በበፍታ ገነዘው፤ ከዚያም ማንም ሰው ተቀብሮበት በማያውቅ ከዓለት ተፈልፍሎ በተሠራ መቃብር ውስጥ አኖረው።+ +54 ዕለቱ የዝግጅት ቀን ነበር፤+ ሰንበት+ የሚጀምርበ�� ጊዜም ተቃርቦ ነበር። +55 ከገሊላ ከኢየሱስ ጋር አብረው የመጡት ሴቶች ግን ተከትለው በመሄድ መቃብሩን አዩ፤ አስከሬኑም እንዴት እንዳረፈ ተመለከቱ።+ +56 ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞችና ዘይቶች ለማዘጋጀትም ተመልሰው ሄዱ። ሆኖም ሕጉ በሚያዘው መሠረት በሰንበት አረፉ።+ +19 ከዚያም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ እያለፈ ነበር። +2 በዚያም ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሀብታም ሰው የነበረ ሲሆን ይህ ሰው የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ ነበር። +3 እሱም ኢየሱስ የሚባለው ማን እንደሆነ ለማየት ይፈልግ ነበር፤ ሆኖም አጭር በመሆኑ ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ማየት አልቻለም። +4 ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለነበር ዘኬዎስ ሮጦ ወደ ፊት በመሄድ እሱን ለማየት አንድ የሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። +5 ኢየሱስ እዚያ ቦታ በደረሰ ጊዜ ቀና ብሎ ተመለከተውና “ዘኬዎስ፣ ዛሬ ወደ አንተ ቤት ስለምመጣ ቶሎ ውረድ” አለው። +6 በዚህ ጊዜ በፍጥነት ወርዶ ደስ እያለው በእንግድነት ተቀበለው። +7 ሰዎቹ ይህን ባዩ ጊዜ “ኃጢአተኛ ሰው ቤት ሊስተናገድ ገባ” ብለው ሁሉም አጉተመተሙ።+ +8 ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን “ጌታ ሆይ፣ ካለኝ ሀብት ግማሹን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ከሰው የቀማሁትንም* ሁሉ አራት እጥፍ እመልሳለሁ” አለው።+ +9 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ይህም ሰው የአብርሃም ልጅ ስለሆነ ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን መጥቷል። +10 ምክንያቱም የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ለመፈለግና ለማዳን ነው።”+ +11 እነሱም እነዚህን ነገሮች እየሰሙ ሳሉ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ ይህን የተናገረው ኢየሩሳሌም ሲደርሱ የአምላክ መንግሥት ወዲያውኑ የሚገለጥ ስለመሰላቸው ነው።+ +12 ስለዚህ እንዲህ አለ፦ “አንድ መስፍን ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተረክቦ ለመመለስ ወደ ሩቅ አገር ሊሄድ ተነሳ።+ +13 ከባሪያዎቹ መካከል አሥሩን ጠርቶ አሥር ምናን* ሰጣቸውና ‘እስክመጣ ድረስ ነግዱበት’ አላቸው።+ +14 የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ስለነበር እሱ ከሄደ በኋላ ‘ይህ ሰው በእኛ ላይ እንዲነግሥ አንፈልግም’ ብለው እንዲነግሩላቸው መልእክተኞች ላኩ። +15 “ከጊዜ በኋላ ንጉሣዊ ሥልጣኑን* ተረክቦ ሲመጣ ገንዘብ* የሰጣቸው ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ለማወቅ አስጠራቸው።+ +16 በመሆኑም የመጀመሪያው ቀርቦ ‘ጌታዬ፣ ምናንህ አሥር ምናን ትርፍ አስገኝቷል’ አለው።+ +17 ጌታው ‘ጎበዝ፣ አንተ ጥሩ ባሪያ! በጣም አነስተኛ በሆነው ነገር ታማኝ ሆነህ ስለተገኘህ በአሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ተሰጥቶሃል’ አለው።+ +18 ሁለተኛው ደግሞ ቀርቦ ‘ጌታዬ፣ ምናንህ አምስት ምናን አስገኝቷል’ አለ።+ +19 ይሄኛውንም ‘አንተም በአምስት ከተሞች ላይ ተሹመሃል’ አለው። +20 ሆኖም ሌላኛው መጥቶ እንዲህ አለ፦ ‘ጌታዬ፣ በጨርቅ ጠቅልዬ የደበቅኩት ምናንህ ይኸውልህ። +21 ይህን ያደረግኩት ጨካኝ ሰው ስለሆንክ ፈርቼህ ነው፤ አንተ ያላስቀመጥከውን የምትወስድ፣ ያልዘራኸውንም የምታጭድ ሰው ነህ።’+ +22 ጌታውም እንዲህ አለው፦ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፣ በራስህ ቃል እፈርድብሃለሁ። ያላስቀመጥኩትን የምወስድ፣ ያልዘራሁትንም የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደሆንኩ ታውቅ ኖሯል ማለት ነው?+ +23 ታዲያ ገንዘቤን* ለምን ለገንዘብ ለዋጮች* አልሰጠህም? እንደዚህ አድርገህ ቢሆን ኖሮ ስመጣ ከነወለዱ እወስደው ነበር።’ +24 “ከዚያም በዚያ ቆመው የነበሩትን ሰዎች ‘ምናኑን ውሰዱበትና አሥር ምናን ላለው ስጡት’ አላቸው።+ +25 እነሱ ግን ‘ጌታ ሆይ፣ እሱ እኮ አሥር ምናን አለው’ አሉት። እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ +26 ‘እላችኋለሁ፣ ላለው ሁሉ ተጨማሪ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ሰው ላይ ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።+ +27 በተጨማሪም በእነሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶ���ን ወደዚህ አምጡና በፊቴ ግደሏቸው።’” +28 ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ጉዞውን በመቀጠል ወደ ኢየሩሳሌም አቀና። +29 ደብረ ዘይት በተባለው ተራራ+ ወደሚገኙት ወደ ቤተፋጌ እና ወደ ቢታንያ በተቃረበ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ላካቸው፤+ +30 እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ ወደ መንደሩ ከገባችሁም በኋላ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ ውርንጭላ ታስሮ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደዚህ አምጡት። +31 ይሁን እንጂ ማንም ሰው ‘የምትፈቱት ለምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ ‘ጌታ ይፈልገዋል’ ብላችሁ ንገሩት።” +32 የተላኩትም ሄደው ልክ እንዳላቸው ሆኖ አገኙት።+ +33 ውርንጭላውን እየፈቱ ሳሉ ግን ባለቤቶቹ “ውርንጭላውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። +34 እነሱም “ጌታ ይፈልገዋል” አሉ። +35 ከዚያም ውርንጭላውን ወደ ኢየሱስ ወሰዱት፤ መደረቢያቸውንም በውርንጭላው ላይ ጣል አድርገው ኢየሱስን በላዩ አስቀመጡት።+ +36 እየተጓዘም ሳለ መደረቢያቸውን በመንገዱ ላይ ያነጥፉ ነበር።+ +37 ከደብረ ዘይት ተራራ ቁልቁል ወደሚወስደው መንገድ እንደተቃረበ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደቀ መዛሙርቱ ባዩአቸው ተአምራት መደሰትና አምላክን በታላቅ ድምፅ ማወደስ ጀመሩ፤ +38 እንዲህም ይሉ ነበር፦ “በይሖዋ* ስም ንጉሥ ሆኖ የሚመጣ የተባረከ ነው! በሰማይ ሰላም፣ በአርያም ላለውም ክብር ይሁን!”+ +39 በሕዝቡ መካከል የነበሩ አንዳንድ ፈሪሳውያን ግን “መምህር፣ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው እንጂ” አሉት።+ +40 እሱ ግን መልሶ “እላችኋለሁ፣ እነዚህ ዝም ቢሉ እንኳ ድንጋዮች ይጮኻሉ” አላቸው። +41 ወደ ኢየሩሳሌም በተቃረበ ጊዜም ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት፤+ +42 እንዲህም አለ፦ “አንቺ፣ አዎ አንቺ ራስሽ፣ ሰላም የሚያስገኙልሽን ነገሮች ምነው ዛሬ በተረዳሽ ኖሮ፤ አሁን ግን ከዓይኖችሽ ተሰውረዋል።+ +43 ምክንያቱም ጠላቶችሽ በሾለ እንጨት በዙሪያሽ ቅጥር ቀጥረው አንቺን የሚከቡበትና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣል።+ +44 አንቺንና በውስጥሽ የሚኖሩትን ልጆችሽን ፈጥፍጠው ከአፈር ይደባልቃሉ፤+ በአንቺ ውስጥም ሳያፈርሱ እንደተነባበረ የሚተዉት ድንጋይ አይኖርም፤+ ምክንያቱም በአንቺ ላይ ምርመራ የተካሄደበትን ጊዜ አልተገነዘብሽም።” +45 ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ ገብቶ በዚያ የሚሸጡትን ያስወጣ ጀመር፤+ +46 እንዲህም አላቸው፦ “‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል’+ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት።”+ +47 እሱም በየዕለቱ በቤተ መቅደሱ ማስተማሩን ቀጠለ። ሆኖም የካህናት አለቆችና ጸሐፍት እንዲሁም የሕዝቡ መሪዎች ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፤+ +48 ይሁንና ሕዝቡ ሁሉ እሱን ለመስማት ከአጠገቡ ስለማይለይ ምን እንደሚያደርጉ ግራ ገባቸው።+ +20 አንድ ቀን ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሕዝቡን እያስተማረና ምሥራቹን እያወጀ ሳለ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር መጡ፤ +2 ከዚያም “እስቲ ንገረን፤ እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” አሉት።+ +3 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም መልሱልኝ፦ +4 ዮሐንስ የማጥመቅ ሥልጣን ያገኘው ከአምላክ* ነው ወይስ ከሰው?” +5 እነሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “‘ከአምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ +6 ‘ከሰው’ ብንል ደግሞ ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ ነው ብለው ስለሚያምኑ+ በድንጋይ ይወግሩናል።” +7 ስለዚህ ‘ከየት እንደሆነ አናውቅም’ ብለው መለሱለት። +8 ኢየሱስም “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው። +9 ከዚያም ለሕዝቡ የሚከተለውን ምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፦ “አንድ ሰው የወይን እርሻ+ አለማና ለገበሬዎች አከራየ፤ ወደ ሌላ አገር ሄዶም ረዘም ላለ ጊዜ ቆየ።+ +10 ወቅቱ ሲደርስ ከወይኑ ፍሬ ድርሻውን እንዲልኩለት አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ። ይሁንና ገበሬዎቹ ባሪያውን ከደበደቡት በኋላ ባዶ እጁን ሰደዱት።+ +11 እሱ ግን በድጋሚ ሌላ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ። ይሄኛውንም ደብድበውና አዋርደው* ባዶ እጁን ሰደዱት። +12 አሁንም ሦስተኛ ባሪያ ላከ፤ እሱንም ካቆሰሉት በኋላ አውጥተው ጣሉት። +13 በዚህ ጊዜ የወይን እርሻው ባለቤት ‘ምን ባደርግ ይሻላል? የምወደውን ልጄን+ እልካለሁ። መቼም እሱን ያከብሩታል’ አለ። +14 ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው። ርስቱ የእኛ እንዲሆን እንግደለው’ ተባባሉ። +15 ከዚያም ከወይን እርሻው ጎትተው በማውጣት ገደሉት።+ ታዲያ የወይኑ እርሻ ባለቤት ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል? +16 ይመጣና እነዚህን ገበሬዎች ይገድላል፤ የወይን እርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል።” ሕዝቡም ይህን ሲሰሙ “ይህስ ከቶ አይሁን!” አሉ። +17 ኢየሱስም እነሱን ትኩር ብሎ በመመልከት እንዲህ አለ፦ “ታዲያ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እሱ የማዕዘን ራስ ድንጋይ* ሆነ’+ ተብሎ የተጻፈው ትርጉሙ ምንድን ነው? +18 በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይሰባበራል።+ ድንጋዩ የሚወድቅበት ሰው ሁሉ ደግሞ ይደቅቃል።” +19 በዚህ ጊዜ ጸሐፍትና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ የተናገረው እነሱን አስቦ እንደሆነ ስለተረዱ በዚያኑ ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፤ ሆኖም ሕዝቡን ፈሩ።+ +20 በቅርብ ሲከታተሉት ከቆዩ በኋላ በንግግሩ እንዲያጠምዱት ጻድቅ መስለው የሚቀርቡ ሰዎችን በድብቅ ቀጥረው ላኩ፤+ ይህን ያደረጉት ለመንግሥትና ለአገረ ገዢው* አሳልፈው ለመስጠት ነው። +21 የተላኩትም ሰዎች እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ “መምህር፣ አንተ ትክክለኛውን ነገር እንደምትናገርና እንደምታስተምር እንዲሁም እንደማታዳላ፣ ከዚህ ይልቅ የአምላክን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፦ +22 ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባናል ወይስ አይገባንም?”* +23 እሱ ግን ተንኮላቸው ገብቶት እንዲህ አላቸው፦ +24 “እስቲ አንድ ዲናር* አሳዩኝ። በላዩ ላይ ያለው ምስልና የተቀረጸው ጽሑፍ የማን ነው?” እነሱም “የቄሳር” አሉ። +25 እሱም “እንግዲያው የቄሳር የሆነውን ለቄሳር፣+ የአምላክ የሆነውን ደግሞ ለአምላክ+ ስጡ” አላቸው። +26 እነሱም በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ ከዚህ ይልቅ በመልሱ በመገረም ዝም አሉ። +27 ሆኖም በትንሣኤ ከማያምኑት+ ሰዱቃውያን መካከል አንዳንዶቹ መጥተው ጥያቄ አቀረቡለት፦+ +28 “መምህር፣ ሙሴ ‘አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ ሚስትየዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር መተካት አለበት’ ብሎ ጽፎልናል።+ +29 እንግዲህ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ። የመጀመሪያው ሚስት አገባ፤ ሆኖም ልጅ ሳይወልድ ሞተ። +30 ሁለተኛውም እንደዚሁ፤ +31 ሦስተኛውም አገባት። በዚሁ አኳኋን ሰባቱም አግብተዋት ልጆች ሳይወልዱ ሞቱ። +32 በመጨረሻም ሴትየዋ ሞተች። +33 እንግዲህ ሰባቱም ስላገቧት በትንሣኤ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች?” +34 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የዚህ ሥርዓት* ልጆች ያገባሉ እንዲሁም ይዳራሉ፤ +35 ሆኖም የሚመጣውን ሥርዓት መውረስና የሙታን ትንሣኤን ማግኘት የሚገባቸው አያገቡም እንዲሁም አይዳሩም።+ +36 እንዲያውም እንደ መላእክት ስለሆኑ ከዚያ በኋላ ሊሞቱ አይችሉም፤ የትንሣኤ ልጆች ስለሆኑም የአምላክ ልጆች ናቸው። +37 ይሁንና ሙሴም እንኳ ስለ ቁጥቋጦው በሚገልጸው ታሪክ ላይ ይሖዋን* ‘የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ ��ምላክና የያዕቆብ አምላክ’+ ብሎ በጠራው ጊዜ ሙታን እንደሚነሡ አስታውቋል። +38 እሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፤ በእሱ ፊት* ሁሉም ሕያዋን ናቸውና።”+ +39 በዚህ ጊዜ አንዳንድ ጸሐፍት “መምህር፣ ጥሩ ብለሃል” አሉ። +40 ከዚያ በኋላ አንድም ጥያቄ ሊጠይቁት አልደፈሩም። +41 እሱ ደግሞ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “ሰዎች ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ?+ +42 ምክንያቱም ዳዊት ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ ላይ እንዲህ ብሏል፦ ‘ይሖዋ* ጌታዬን እንዲህ ብሎታል፦ “በቀኜ ተቀመጥ፤ +43 ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ሁን።”’+ +44 ስለዚህ ዳዊት ‘ጌታ’ ብሎ ጠርቶታል፤ ታዲያ እንዴት ልጁ ይሆናል?” +45 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ +46 “ዘርፋፋ ልብስ ለብሰው መዞር ከሚወዱ፣ በገበያ ቦታ ሰዎች እጅ እንዲነሷቸው ከሚሹ እንዲሁም በምኩራብ ከፊት መቀመጥ፣* በራት ግብዣ ላይም የክብር ቦታ መያዝ ከሚፈልጉ+ ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ +47 እነሱ የመበለቶችን ቤት* ያራቁታሉ፤ ለታይታ ብለውም* ጸሎታቸውን ያስረዝማሉ። እነዚህ የከፋ* ፍርድ ይጠብቃቸዋል።” +3 ጢባርዮስ ቄሳር በነገሠ በ15ኛው ዓመት፣ ጳንጥዮስ ጲላጦስ የይሁዳ አገረ ገዢ፣ ሄሮድስ*+ የገሊላ አውራጃ ገዢ፣* ወንድሙ ፊልጶስ ደግሞ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ አውራጃ ገዢ፣ ሊሳኒዮስ የአቢላኒስ አውራጃ ገዢ በነበሩበት ጊዜ +2 እንዲሁም ቀያፋና የካህናት አለቃው ሐና በነበሩበት ዘመን+ የአምላክ ቃል በምድረ በዳ+ ወደነበረው ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ+ መጣ። +3 ዮሐንስም ለኃጢአት ይቅርታ፣ የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለው አገር ሁሉ ሄደ፤+ +4 ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ላይ እንዲህ ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት ነው፦ “አንድ ሰው በምድረ በዳ ‘የይሖዋን* መንገድ አዘጋጁ! ጎዳናዎቹንም አቅኑ’ በማለት ይጮኻል።+ +5 ‘ሸለቆው ሁሉ ይሞላ፤ ተራራውና ኮረብታው ሁሉ ይደልደል፤ ጠማማው መንገድ ቀጥ ያለ፣ ጎርበጥባጣውም መንገድ ለጥ ያለ ይሁን፤ +6 ሥጋም* ሁሉ የአምላክን ማዳን* ያያል።’”+ +7 በመሆኑም ዮሐንስ በእሱ እጅ ለመጠመቅ የሚመጡትን ሰዎች እንዲህ ይላቸው ነበር፦ “እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ያስጠነቀቃችሁ ማን ነው?+ +8 እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ። ‘እኛ እኮ አባታችን አብርሃም ነው’ እያላችሁ ራሳችሁን አታጽናኑ። አምላክ ለአብርሃም ከእነዚህ ድንጋዮች ልጆች ማስነሳት እንደማይሳነው ልነግራችሁ እወዳለሁ። +9 እንዲያውም መጥረቢያው ዛፎቹ ሥር ተቀምጧል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ እሳት ውስጥ ይጣላል።”+ +10 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ “ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” ብለው ይጠይቁት ነበር። +11 እሱም መልሶ “ሁለት ልብስ* ያለው አንዱን ምንም ለሌለው ይስጥ፤ ምግብ ያለውም እንዲሁ ያድርግ” አላቸው።+ +12 ቀረጥ ሰብሳቢዎች እንኳ ሳይቀሩ ለመጠመቅ+ ወደ እሱ መጥተው “መምህር፣ ምን እናድርግ?” አሉት። +13 እሱም “ከተተመነው ቀረጥ በላይ አትጠይቁ”* አላቸው።+ +14 ወታደሮች ደግሞ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እሱም “በማንም ላይ ግፍ አትሥሩ* ወይም ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፤+ ከዚህ ይልቅ ባላችሁ መተዳደሪያ* ረክታችሁ ኑሩ” አላቸው። +15 ሕዝቡ ክርስቶስን ይጠባበቁ ስለነበር “ይህ ሰው ክርስቶስ ይሆን?” እያሉ ሁሉም በልባቸው ስለ ዮሐንስ ያስቡ ነበር።+ +16 ዮሐንስ ለሁሉም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ሆኖም ከእኔ የሚበረታ የሚመጣ ሲሆን እኔ የጫማውን ማሰሪያ እንኳ ለመፍታት አልበቃም።+ እሱ በመን���ስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።+ +17 አውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን ወደ ጎተራ ለማስገባት ላይዳውን* በእጁ ይዟል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።” +18 በተጨማሪም ዮሐንስ በተለያዩ መንገዶች ምክር በመስጠት ለሕዝቡ ምሥራች ማብሰሩን ቀጠለ። +19 ሆኖም የአውራጃ ገዢ የሆነው ሄሮድስ የወንድሙ ሚስት በሆነችው በሄሮድያዳ ምክንያትና በሠራቸው ሌሎች ክፉ ድርጊቶች የተነሳ ዮሐንስ ስለወቀሰው +20 በክፋት ላይ ክፋት በመጨመር ዮሐንስን ወህኒ ቤት አስገባው።+ +21 ሕዝቡም ሁሉ እየተጠመቁ በነበረ ጊዜ ኢየሱስም ተጠመቀ።+ እየጸለየም ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤+ +22 መንፈስ ቅዱስም አካላዊ ቅርጽ ይዞ በርግብ መልክ በእሱ ላይ ወረደ፤ ከዚያም “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።+ +23 ኢየሱስ+ ሥራውን ሲጀምር 30 ዓመት ገደማ ሆኖት ነበር፤+ ሕዝቡም የዮሴፍ ልጅ+ እንደሆነ አድርገው ያስቡ ነበር፤ዮሴፍ የሄሊ ልጅ፣ +24 ሄሊ የማታት ልጅ፣ማታት የሌዊ ልጅ፣ሌዊ የሚልኪ ልጅ፣ሚልኪ የያና ልጅ፣ያና የዮሴፍ ልጅ፣ +25 ዮሴፍ የማታትዩ ልጅ፣ማታትዩ የአሞጽ ልጅ፣አሞጽ የናሆም ልጅ፣ናሆም የኤስሊ ልጅ፣ኤስሊ የናጌ ልጅ፣ +26 ናጌ የማአት ልጅ፣ማአት የማታትዩ ልጅ፣ማታትዩ የሴሜይ ልጅ፣ሴሜይ የዮሴክ ልጅ፣ዮሴክ የዮዳ ልጅ፣ +27 ዮዳ የዮናን ልጅ፣ዮናን የሬስ ልጅ፣ሬስ የዘሩባቤል ልጅ፣+ዘሩባቤል የሰላትያል ልጅ፣+ሰላትያል የኔሪ ልጅ፣ +28 ኔሪ የሚልኪ ልጅ፣ሚልኪ የሐዲ ልጅ፣ሐዲ የቆሳም ልጅ፣ቆሳም የኤልሞዳም ልጅ፣ኤልሞዳም የኤር ልጅ፣ +29 ኤር የኢየሱስ* ልጅ፣ኢየሱስ የኤሊዔዘር ልጅ፣ኤሊዔዘር የዮሪም ልጅ፣ዮሪም የማታት ልጅ፣ማታት የሌዊ ልጅ፣ +30 ሌዊ የሲምዖን ልጅ፣ሲምዖን የይሁዳ ልጅ፣ይሁዳ የዮሴፍ ልጅ፣ዮሴፍ የዮናም ልጅ፣ዮናም የኤልያቄም ልጅ፣ +31 ኤልያቄም የሜልያ ልጅ፣ሜልያ የሜና ልጅ፣ሜና የማጣታ ልጅ፣ማጣታ የናታን ልጅ፣+ናታን የዳዊት ልጅ፣+ +32 ዳዊት የእሴይ ልጅ፣+እሴይ የኢዮቤድ ልጅ፣+ኢዮቤድ የቦዔዝ ልጅ፣+ቦዔዝ የሰልሞን ልጅ፣+ሰልሞን የነአሶን ልጅ፣+ +33 ነአሶን የአሚናዳብ ልጅ፣አሚናዳብ የአርናይ ልጅ፣አርናይ የኤስሮን ልጅ፣ኤስሮን የፋሬስ ልጅ፣+ፋሬስ የይሁዳ ልጅ፣+ +34 ይሁዳ የያዕቆብ ልጅ፣+ያዕቆብ የይስሐቅ ልጅ፣+ይስሐቅ የአብርሃም ልጅ፣+አብርሃም የታራ ልጅ፣+ታራ የናኮር ልጅ፣+ +35 ናኮር የሴሮህ ልጅ፣+ሴሮህ የረኡ ልጅ፣+ረኡ የፋሌቅ ልጅ፣+ፋሌቅ የኤቤር ልጅ፣+ኤቤር የሴሎም ልጅ፣+ +36 ሴሎም የቃይናን ልጅ፣ቃይናን የአርፋክስድ ልጅ፣+አርፋክስድ የሴም ልጅ፣+ሴም የኖኅ ልጅ፣+ኖኅ የላሜህ ልጅ፣+ +37 ላሜህ የማቱሳላ ልጅ፣+ማቱሳላ የሄኖክ ልጅ፣ሄኖክ የያሬድ ልጅ፣+ያሬድ የመላልኤል ልጅ፣+መላልኤል የቃይናን ልጅ፣+ +38 ቃይናን የሄኖስ ልጅ፣+ሄኖስ የሴት ልጅ፣+ሴት የአዳም ልጅ፣+አዳም የአምላክ ልጅ። +24 ይሁን እንጂ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣ ያዘጋጇቸውን ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞች ይዘው ጠዋት በማለዳ ወደ መቃብሩ ሄዱ።+ +2 ሆኖም ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፤+ +3 ወደ ውስጥ ሲገቡም የጌታ ኢየሱስን አስከሬን አላገኙም።+ +4 በሁኔታው ግራ ተጋብተው እያሉ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ። +5 ሴቶቹ ፈርተው ወደ መሬት አቀርቅረው ሳሉ ሰዎቹ እንዲህ አሏቸው፦ “ሕያው የሆነውን ለምን ከሙታን መካከል ትፈልጉታላችሁ?+ +6 እሱ እዚህ የለም፤ ከሞት ተነስቷል። ገና በገሊላ በነበረበት ጊዜ ምን እንዳላችሁ አስታውሱ፤ +7 ‘የሰውን ልጅ ለኃጢአተኞች አሳልፈው ሊሰጡት፣ በእንጨት ላይ ሊሰቀልና በሦስተኛው ቀን ሊነሳ ይገባል’ ብሎ ነበር።”+ +8 በዚህ ጊዜ ሴቶቹ የተናገረው�� ቃል አስታወሱ፤+ +9 ከዚያም መቃብሩ ካለበት ስፍራ ተመልሰው እነዚህን ነገሮች በሙሉ ለአሥራ አንዱና ለቀሩት ሁሉ ነገሯቸው።+ +10 እነሱም መግደላዊቷ ማርያም፣ ዮሐናና የያዕቆብ እናት ማርያም ነበሩ። ከእነሱ ጋር የነበሩት ሌሎቹ ሴቶችም እነዚህን ነገሮች ለሐዋርያት ነገሯቸው። +11 ይሁን እንጂ እንዲሁ የሚቀባጥሩ ስለመሰላቸው ሴቶቹ የሚናገሩትን አላመኗቸውም። +12 ጴጥሮስ ግን ተነስቶ ወደ መቃብሩ ሮጠ፤ ጎንበስ ብሎም ወደ ውስጥ ሲመለከት በፍታውን ብቻ አየ። በሆነውም ነገር እየተገረመ ከዚያ ሄደ። +13 ይሁንና በዚያው ቀን ከመካከላቸው ሁለቱ ከኢየሩሳሌም አሥራ አንድ ኪሎ ሜትር* ያህል ርቃ ወደምትገኝ ኤማሁስ ወደምትባል መንደር እየተጓዙ ነበር፤ +14 እነሱም ስለሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው እየተነጋገሩ ነበር። +15 ስለዚህ ጉዳይ እየተነጋገሩና እየተወያዩ ሳሉም ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ አብሯቸው መሄድ ጀመረ፤ +16 ሆኖም ማንነቱን እንዳይለዩ ዓይናቸው ተጋርዶ ነበር።+ +17 እሱም “እየተጓዛችሁ እንዲህ እርስ በርስ የምትወያዩበት ጉዳይ ምንድን ነው?” አላቸው። በዚህ ጊዜ በሐዘን እንደተዋጡ ባሉበት ቆሙ። +18 ቀለዮጳ የተባለውም መልሶ “በኢየሩሳሌም ውስጥ ለብቻህ የምትኖር እንግዳ ሰው ነህ እንዴ? ሰሞኑን በዚያ የተፈጸመውን ነገር አታውቅም ማለት ነው?”* አለው። +19 እሱም “ምን ተፈጸመ?” አላቸው። እነሱም እንዲህ አሉት፦ “በአምላክና በሰው ሁሉ ፊት በሥራም ሆነ በቃል ኃያል ነቢይ ከሆነው ከናዝሬቱ ኢየሱስ+ ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ነገር ነዋ!+ +20 የካህናት አለቆቻችንና ገዢዎቻችን ለሞት ፍርድ አሳልፈው ሰጡት፤+ እንዲሁም በእንጨት ላይ ቸነከሩት። +21 እኛ ግን ይህ ሰው እስራኤልን ነፃ ያወጣል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር።+ ከዚህም በላይ ይህ ነገር ከተፈጸመ እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑ ነው። +22 ደግሞም ከእኛው መካከል አንዳንድ ሴቶች በማለዳ ወደ መቃብሩ ሄደው ስለነበር+ የሚያስገርም ነገር ነገሩን፤ +23 አስከሬኑንም ባጡ ጊዜ ተመልሰው መጥተው በተአምር የተገለጡላቸውንና እሱ ሕያው እንደሆነ የነገሯቸውን መላእክት እንዳዩ ነገሩን። +24 ከዚያም ከእኛ መካከል አንዳንዶች ወደ መቃብሩ ሄደው ነበር፤+ እነሱም ሴቶቹ እንደተናገሩት ሆኖ አገኙት፤ እሱን ግን አላዩትም።” +25 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁና ነቢያት የተናገሩትን ሁሉ ከማመን ልባችሁ የዘገየ! +26 ክርስቶስ እነዚህን መከራዎች መቀበልና+ ክብር ማግኘት አይገባውም?”+ +27 ከዚያም ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ+ ጀምሮ ስለ እሱ በቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን በሚገባ አብራራላቸው። +28 በመጨረሻም ወደሚሄዱበት መንደር ተቃረቡ፤ ይሁንና እሱ አልፎ የሚሄድ ይመስል ነበር። +29 እነሱ ግን “ቀኑ እየተገባደደና ምሽቱ እየተቃረበ ስለሆነ እኛ ጋ እደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት። እሱም እነሱ ጋ ለማደር ገባ። +30 ከእነሱ ጋር እየበላ ሳለም ዳቦውን አንስቶ ባረከ፤ ቆርሶም ይሰጣቸው ጀመር።+ +31 በዚህ ጊዜ ዓይናቸው ሙሉ በሙሉ ተከፈተና ማን መሆኑን በሚገባ አወቁ፤ እሱ ግን ከአጠገባቸው ተሰወረ።+ +32 እነሱም እርስ በርሳቸው “በመንገድ ላይ ሲያነጋግረንና ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ ሲገልጥልን* ልባችን እንደ እሳት ይቃጠልብን አልነበረም?” ተባባሉ። +33 በዚያኑም ሰዓት ተነስተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ አሥራ አንዱንና ከእነሱ ጋር የነበሩትንም አንድ ላይ ተሰብስበው አገኟቸው፤ +34 እነሱም “ጌታ በእርግጥ ተነስቷል፤ ለስምዖንም ተገልጦለታል!” ይሉ ነበር።+ +35 ሁለቱ ደግሞ በመንገድ ላይ ያጋጠማቸውን ነገርና ዳቦውን በቆረሰበት+ ጊዜ እንዴት እንዳወቁት ተረኩላቸው። +36 እነዚህን ነገሮች እየተነጋገሩ ሳለ እሱ ራሱ በመካከላቸው ቆመ፤ ከዚያም “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።+ +37 እነሱ ግን ከመደንገጣቸውና ከመፍራታቸው የተነሳ መንፈስ ያዩ መሰላቸው። +38 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ለምን ትረበሻላችሁ? ለምንስ በልባችሁ ውስጥ ጥርጣሬ ያድራል? +39 እኔ ራሴ መሆኔን እንድታውቁ እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ ደግሞም ዳስሳችሁኝ እዩ፤ መንፈስ በእኔ ላይ እንደምታዩት ሥጋና አጥንት የለውምና።” +40 ይህን እያለም እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። +41 እነሱ ግን በጣም ከመደሰታቸው የተነሳ ለማመን ተቸግረው በነገሩ እየተገረሙ ሳሉ “የሚበላ ነገር አላችሁ?” አላቸው። +42 እነሱም የተጠበሰ ቁራሽ ዓሣ ሰጡት፤ +43 እሱም ተቀብሎ በፊታቸው በላ። +44 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ‘በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙራት ስለ እኔ የተጻፉት ነገሮች ሁሉ+ መፈጸም አለባቸው’ ብዬ የነገርኳችሁ ቃሌ ይህ ነው።”+ +45 ከዚያም የቅዱሳን መጻሕፍትን ትርጉም መረዳት እንዲችሉ አእምሯቸውን ከፈተላቸው፤+ +46 እንዲህም አላቸው፦ “እንደሚከተለው ተብሎ ተጽፏል፤ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሳል፤+ +47 በስሙም የኃጢአት ይቅርታ የሚያስገኝ+ ንስሐ ከኢየሩሳሌም አንስቶ+ ለብሔራት ሁሉ ይሰበካል።+ +48 እናንተም ለእነዚህ ነገሮች ምሥክር ትሆናላችሁ።+ +49 እኔም አባቴ ቃል የገባውን ነገር እልክላችኋለሁ። እናንተ ግን ከላይ የሚመጣውን ኃይል እስክትለብሱ+ ድረስ በከተማዋ ውስጥ ቆዩ።” +50 ከዚያም እስከ ቢታንያ ይዟቸው ሄደ፤ እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው። +51 እየባረካቸውም ሳለ ከእነሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ተወሰደ።+ +52 እነሱም ሰገዱለት፤* ከዚያም በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።+ +53 ዘወትር በቤተ መቅደስ እየተገኙም አምላክን ያወድሱ ነበር።+ +7 ኢየሱስ ለሕዝቡ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ገባ። +2 በዚያም አንድ የጦር መኮንን* ነበር፤ በጣም የሚወደው ባሪያውም በጠና ታሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር።+ +3 እሱም ስለ ኢየሱስ ሲሰማ መጥቶ ባሪያውን እንዲፈውስለት ይለምኑለት ዘንድ የተወሰኑ አይሁዳውያን ሽማግሌዎችን ላከ። +4 እነሱም ወደ ኢየሱስ መጥተው እንዲህ በማለት ተማጸኑት፦ “ይህን ሰው ልትረዳው ይገባል፤ +5 ምክንያቱም ሕዝባችንን ይወዳል፤ ምኩራባችንንም ያሠራልን እሱ ነው።” +6 ስለዚህ ኢየሱስ አብሯቸው ሄደ። ሆኖም ወደ ቤቱ በተቃረበ ጊዜ መኮንኑ ወዳጆቹን እንዲህ ሲል ወደ ኢየሱስ ላከ፦ “ጌታዬ፣ በቤቴ ጣሪያ ሥር ልትገባ የሚገባኝ ሰው ስላልሆንኩ አትድከም።+ +7 ከዚህም የተነሳ አንተ ፊት መቅረብ የሚገባኝ ሰው እንደሆንኩ አልተሰማኝም። ስለዚህ አንተ አንድ ቃል ተናገርና አገልጋዬ ይፈወስ። +8 እኔ ራሴ የምታዘዛቸው የበላይ አዛዦች አሉ፤ ለእኔም የሚታዘዙ የበታች ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም ‘ይህን አድርግ!’ ስለው ያደርጋል።” +9 ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ በሰውየው በጣም ተደንቆ ይከተለው ወደነበረው ሕዝብ ዞር በማለት “እላችኋለሁ፣ በእስራኤል ውስጥ እንኳ እንዲህ ዓይነት ታላቅ እምነት አላገኘሁም” አለ።+ +10 የተላኩትም ሰዎች ወደ ቤት ሲመለሱ ባሪያው ድኖ አገኙት።+ +11 ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ናይን ወደምትባል ከተማ ተጓዘ፤ ደቀ መዛሙርቱና ሌሎች ብዙ ሰዎችም አብረውት ይጓዙ ነበር። +12 ወደ ከተማዋ መግቢያ ሲቃረብ ሰዎች የአንድ ሰው አስከሬን ተሸክመው በመውጣት ላይ ነበሩ፤ ሟቹ ለእናቱ አንድ ልጇ ነበር።+ በተጨማሪም እናቱ መበለት ነበረች። ብዙ የከተማዋ ሕዝብም ከእሷ ጋር ነበር። +13 ጌታ ባያት ጊዜ በጣም አዘነላትና+ ��በቃ፣ አታልቅሺ”+ አላት። +14 ከዚያም ቀረብ ብሎ ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙት ሰዎችም ባሉበት ቆሙ፤ ኢየሱስም “አንተ ወጣት፣ ተነስ እልሃለሁ!” አለ።+ +15 የሞተውም ሰው ቀና ብሎ ተቀመጠና መናገር ጀመረ፤ ኢየሱስም ለእናቱ ሰጣት።+ +16 በዚህ ጊዜ ሁሉም በፍርሃት ተውጠው “ታላቅ ነቢይ በመካከላችን ተነስቷል፤”+ እንዲሁም “አምላክ ሕዝቡን አሰበ” እያሉ አምላክን ያወድሱ ጀመር።+ +17 ኢየሱስ ያከናወነውም ነገር በይሁዳ ሁሉና በአካባቢው ባለ አገር ሁሉ ተሰማ። +18 በዚህ ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ይህን ሁሉ አወሩለት።+ +19 ዮሐንስም ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ጠርቶ “ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ+ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ብለው እንዲጠይቁት ወደ ጌታ ላካቸው። +20 ሰዎቹም ወደ ኢየሱስ መጥተው “መጥምቁ ዮሐንስ፣ ‘ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?’ ብለን እንድንጠይቅህ ወደ አንተ ልኮናል” አሉት። +21 ኢየሱስ በዚያኑ ሰዓት ብዙዎችን ከሕመምና ከከባድ በሽታ ፈወሳቸው፤+ እንዲሁም ያደሩባቸውን ክፉ መናፍስት አወጣ፤ የብዙ ዓይነ ስውራንንም ዓይን አበራ። +22 እሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፦ ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤+ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤+ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።+ +23 በእኔ ምክንያት የማይሰናከል ደስተኛ ነው።”+ +24 የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ ይናገር ጀመር፦ “ወደ ምድረ በዳ የሄዳችሁት ምን ለማየት ነበር? ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆ?+ +25 ታዲያ ምን ለማየት ነበር የሄዳችሁት? ምርጥ ልብስ* የለበሰ ሰው ለማየት?+ የተንቆጠቆጠ ልብስ የሚለብሱና በቅንጦት የሚኖሩማ የሚገኙት በቤተ መንግሥት ነው። +26 ታዲያ ምን ለማየት ሄዳችሁ? ነቢይ? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጥ ነው።+ +27 ‘እነሆ፣ ከፊትህ እየሄደ መንገድህን እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ’ ተብሎ የተጻፈው ስለ እሱ ነው።+ +28 እላችኋለሁ፣ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ የለም፤ ሆኖም በአምላክ መንግሥት ዝቅተኛ የሆነው እንኳ ይበልጠዋል።”+ +29 (ሕዝቡ ሁሉ እንዲሁም ቀራጮች ይህን በሰሙ ጊዜ በዮሐንስ ጥምቀት ተጠምቀው ስለነበር አምላክ ጻድቅ መሆኑን አምነው ተቀበሉ።+ +30 ሆኖም ፈሪሳውያንና የሕጉ አዋቂዎች በዮሐንስ ባለመጠመቃቸው የአምላክን ምክር* አቃለሉ።)+ +31 ኢየሱስ በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የዚህን ትውልድ ሰዎች ከማን ጋር ላነጻጽራቸው? ማንንስ ይመስላሉ?+ +32 በገበያ ስፍራ ተቀምጠው እርስ በርሳቸው እየተጠራሩ ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ እናንተ ግን አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ እናንተ ግን አላለቀሳችሁም’ ከሚባባሉ ልጆች ጋር ይመሳሰላሉ። +33 በተመሳሳይም መጥምቁ ዮሐንስ እህል ሳይበላና ወይን ጠጅ ሳይጠጣ መጣ፤+ እናንተ ግን ‘ጋኔን አለበት’ አላችሁ። +34 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እናንተ ግን ‘እዩ፣ ይህን ሆዳምና ለወይን ጠጅ ያደረ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኃጢአተኞች ወዳጅ!’ አላችሁ።+ +35 የሆነ ሆኖ፣ ጥበብ ጻድቅ* መሆኗ በልጆቿ* ሁሉ ተረጋግጧል።”+ +36 ከዚህ በኋላ ከፈሪሳውያን አንዱ አብሮት እንዲበላ ኢየሱስን ደጋግሞ ለመነው። ስለሆነም ኢየሱስ ወደ ፈሪሳዊው ቤት ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። +37 እነሆም፣ በከተማው ውስጥ በኃጢአተኝነቷ የምትታወቅ አንዲት ሴት ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት እየበላ መሆኑን በሰማች ጊዜ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይ�� መጣች።+ +38 እሷም ከበስተ ኋላ እግሩ አጠገብ ሆና እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመር፤ ከዚያም በፀጉሯ አበሰችው። በተጨማሪም እግሩን እየሳመች ዘይቱን ቀባችው። +39 የጋበዘው ፈሪሳዊም ይህን ሲያይ “ይህ ሰው በእርግጥ ነቢይ ቢሆን ኖሮ የምትነካው ማን መሆኗንና ምን ዓይነት ሴት እንደሆነች ይኸውም ኃጢአተኛ መሆኗን ባወቀ ነበር” ብሎ በልቡ አሰበ።+ +40 ኢየሱስ ግን መልሶ “ስምዖን፣ አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። እሱም “መምህር፣ እሺ ንገረኝ” አለው። +41 “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንዱ 500 ሌላው ደግሞ 50 ዲናር* ተበድረው ነበር። +42 ሁለቱም የተበደሩትን መክፈል ባቃታቸው ጊዜ አበዳሪው ዕዳቸውን ሙሉ በሙሉ ተወላቸው። እንግዲህ ከሁለቱ ሰዎች አበዳሪውን አብልጦ የሚወደው የትኛው ነው?” +43 ስምዖንም መልሶ “ብዙ ዕዳ የተተወለት ይመስለኛል” አለው። እሱም “በትክክል ፈርደሃል” አለው። +44 ከዚያም ወደ ሴቲቱ ዞር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያታለህ? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ይሁንና አንተ ለእግሬ ውኃ አልሰጠኸኝም። ይህች ሴት ግን እግሬን በእንባዋ እያራሰች በፀጉሯ አበሰች። +45 አንተ አልሳምከኝም፤ ይህች ሴት ግን ከገባሁበት ሰዓት አንስቶ እግሬን መሳሟን አላቋረጠችም። +46 አንተ ራሴን ዘይት አልቀባህም፤ ይህች ሴት ግን እግሬን ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ቀባች። +47 ስለዚህ እልሃለሁ፣ ኃጢአቷ ብዙ* ቢሆንም ይቅር ተብሎላታል፤+ ምክንያቱም ታላቅ ፍቅር አሳይታለች። በትንሹ ይቅር የተባለ ግን የሚያሳየውም ፍቅር አነስተኛ ነው።” +48 ከዚያም ሴትየዋን “ኃጢአትሽ ይቅር ተብሎልሻል” አላት።+ +49 በማዕድ አብረውት የተቀመጡት በልባቸው “ኃጢአትን እንኳ ይቅር የሚል ይህ ሰው ማን ነው?” ይሉ ጀመር።+ +50 ኢየሱስ ግን ሴትየዋን “እምነትሽ አድኖሻል፤+ በሰላም ሂጂ” አላት። +12 በዚያን ጊዜ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ እርስ በርስ እየተጋፋ እስኪረጋገጥ ድረስ ተሰብስቦ ሳለ ኢየሱስ በቅድሚያ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ከፈሪሳውያን እርሾ ይኸውም ከግብዝነት ተጠንቀቁ።+ +2 ይሁንና የተሰወረ መገለጡ፣ ሚስጥር የሆነም መታወቁ አይቀርም።+ +3 ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በጓዳ የምታንሾካሹኩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። +4 በተጨማሪም ወዳጆቼ+ ሆይ፣ እላችኋለሁ፣ ሥጋን የሚገድሉትን ከዚያ በላይ ግን ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ።+ +5 ይልቁንስ ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ አሳያችኋለሁ፦ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም* የመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ።+ አዎ፣ እላችኋለሁ እሱን ፍሩ።+ +6 አምስት ድንቢጦች አነስተኛ ዋጋ ባላቸው ሁለት ሳንቲሞች* ይሸጡ የለም? ሆኖም አንዷም እንኳ በአምላክ ዘንድ አትረሳም።*+ +7 የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል።+ አትፍሩ፤ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።+ +8 “እላችኋለሁ፣ በሰዎች ፊት የሚመሠክርልኝን+ ሁሉ የሰው ልጅም በአምላክ መላእክት ፊት ይመሠክርለታል።+ +9 በሰዎች ፊት የሚክደኝ ሁሉ ግን በአምላክ መላእክት ፊት ይካዳል።+ +10 በሰው ልጅ ላይ ክፉ ቃል የሚናገር ሁሉ ይቅር ይባልለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን ይቅር አይባልም።+ +11 በሕዝባዊ ሸንጎዎች* እንዲሁም በመንግሥት ሹማምንትና ባለሥልጣናት ፊት ሲያቀርቧችሁ እንዴት ብለን ወይም ምን ብለን የመከላከያ መልስ እንሰጣለን ወይም ደግሞ ምን እንላለን ብላችሁ አትጨነቁ፤+ +12 ምን መናገር እንዳለባችሁ መንፈስ ቅዱስ በዚያኑ ሰዓት ያስተምራችኋልና።”+ +13 ከዚያም ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው “መምህር፣ ወንድሜ ውርሳችንን እንዲያካፍለኝ ንገረው” አለ���። +14 ኢየሱስም “አንተ ሰው፣ በእናንተ መካከል ፈራጅና ዳኛ እንድሆን ማን ሾመኝ?” አለው። +15 ከዚያም “አንድ ሰው ሀብታም ቢሆንም እንኳ ንብረቱ ሕይወት ሊያስገኝለት አይችልም፤+ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም* ሁሉ ተጠበቁ”+ አላቸው። +16 ይህን ካለ በኋላ እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “አንድ ሀብታም ሰው መሬቱ ብዙ ምርት አስገኘለት። +17 በመሆኑም ‘ምርቴን የማከማችበት ቦታ ስለሌለኝ ምን ባደርግ ይሻላል?’ ብሎ በልቡ ማሰብ ጀመረ። +18 ከዚያም እንዲህ አለ፦ ‘እንዲህ አደርጋለሁ፦+ ያሉኝን ጎተራዎች አፈርስና ትላልቅ ጎተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም እህሌንና ንብረቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ +19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ +20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+ +21 ለራሱ ሀብት የሚያከማች በአምላክ ዘንድ ግን ሀብታም ያልሆነ ሰው መጨረሻው ይኸው ነው።”+ +22 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ስለ ሕይወታችሁ* ምን እንበላለን ወይም ደግሞ ስለ ሰውነታችሁ ምን እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ።*+ +23 ሕይወት* ከምግብ ሰውነትም ከልብስ የላቀ ዋጋ አለውና። +24 ቁራዎችን ተመልከቱ፦ አይዘሩም፣ አያጭዱም እንዲሁም የእህል ማከማቻ ወይም ጎተራ የላቸውም፤ ሆኖም አምላክ ይመግባቸዋል።+ ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ የላቀ ዋጋ የላችሁም?+ +25 ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ርዝማኔ ላይ አንድ ክንድ* መጨመር የሚችል ይኖራል? +26 ታዲያ እንዲህ ያለውን ትንሽ ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ ስለ ሌሎች ነገሮች ለምን ትጨነቃላችሁ?+ +27 እስቲ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ፦ አይለፉም ወይም አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ያን ያህል ክብር የነበረው ሰለሞን እንኳ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዷ አላጌጠም።+ +28 አምላክ ዛሬ ያለውንና ነገ ወደ ምድጃ የሚጣለውን በሜዳ ያለ ተክል እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁ! +29 ስለዚህ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት ነገር ከልክ በላይ አታስቡ፤ እንዲሁም አትጨነቁ፤*+ +30 እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዓለም ያሉ ሰዎች አጥብቀው የሚፈልጓቸው ናቸው፤ ይሁንና አባታችሁ እነዚህ ነገሮች እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል።+ +31 ይልቁንስ ዘወትር መንግሥቱን ፈልጉ፤ እነዚህም ነገሮች ይሰጧችኋል።+ +32 “አንተ ትንሽ መንጋ+ አትፍራ፤ አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗልና።+ +33 ያላችሁን ንብረት ሸጣችሁ ምጽዋት* ስጡ።+ የማያረጁ የገንዘብ ኮሮጆዎች አዘጋጁ፤ አዎ፣ ሌባ በማይደርስበት፣ ብልም ሊበላው በማይችልበት በሰማያት ለራሳችሁ የማያልቅ ውድ ሀብት አከማቹ።+ +34 ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም በዚያ ይሆናልና። +35 “ወገባችሁን ታጠቁ፤*+ መብራታችሁንም አብሩ፤+ +36 ጌታቸው ከሠርግ+ እስኪመለስ እንደሚጠባበቁና+ መጥቶ በሩን ሲያንኳኳ ወዲያው ለመክፈት እንደተዘጋጁ ዓይነት ሰዎች ሁኑ። +37 ጌታቸው በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው ሲጠባበቁ የሚያገኛቸው ባሪያዎች ደስተኞች ናቸው! እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታቸው ለሥራ ካሸረጠና* በማዕድ እንዲቀመጡ ካደረገ በኋላ ቆሞ ያስተናግዳቸዋል። +38 በሁለተኛው ክፍለ ሌሊትም* ይምጣ በሦስተኛው፣* ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ካገኛቸው ደስተኞች ናቸው! +39 ነገር ግን ይህን እወቁ፤ አንድ ሰው ሌባ በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ ቤቱ እንዳይደፈር በተከላከለ ነበር።+ +40 እናንተም የሰው ልጅ ይመጣል ብላችሁ ባላ���ባችሁት ሰዓት ስለሚመጣ ዝግጁ ሆናችሁ ጠብቁ።”+ +41 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ፣ ይህን ምሳሌ እየተናገርክ ያለኸው ለእኛ ብቻ ነው ወይስ ለሁሉም?” አለው። +42 ጌታም እንዲህ አለ፦ “ጌታው ምንጊዜም የሚያስፈልጋቸውን ምግብ በተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው በአገልጋዮቹ* ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም* መጋቢ* በእርግጥ ማን ነው?+ +43 ጌታው ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ ካገኘው ያ ባሪያ ደስተኛ ነው! +44 እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታው በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል። +45 ነገር ግን ያ ባሪያ በልቡ ‘ጌታዬ የሚመጣው ዘግይቶ ነው’ ብሎ ቢያስብና ወንድና ሴት አገልጋዮችን መደብደብ እንዲሁም መብላት፣ መጠጣትና መስከር ቢጀምር+ +46 የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላሰበው ሰዓት ይመጣል፤ ከባድ ቅጣት ይቀጣዋል፤* ዕጣውንም ታማኝ ካልሆኑ ሰዎች ጋር ያደርገዋል። +47 ደግሞም የጌታውን ፈቃድ እያወቀ ተዘጋጅቶ ያልጠበቀው ወይም ጌታው የጠየቀውን ነገር ያላደረገው * ያ ባሪያ ብዙ ግርፋት ይገረፋል።+ +48 ነገር ግን ሳያውቅ፣ ግርፋት የሚገባው ድርጊት የፈጸመ ጥቂት ይገረፋል። በእርግጥም ብዙ ከተሰጠው ሁሉ ብዙ ይጠበቅበታል፤ ብዙ ኃላፊነት የተሰጠውም ብዙ ይጠበቅበታል።+ +49 “እኔ የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኮስ ነው፤ ታዲያ እሳቱ ከተቀጣጠለ ከዚህ በላይ ምን እፈልጋለሁ? +50 እርግጥ እኔ የምጠመቀው አንድ ጥምቀት አለኝ፤ ይህ እስኪፈጸም ድረስ በጣም ተጨንቄአለሁ!+ +51 የመጣሁት በምድር ላይ ሰላም ለማስፈን ይመስላችኋል? በፍጹም አይደለም፤ እላችኋለሁ፣ የመጣሁት ሰላም ለማስፈን ሳይሆን ለመከፋፈል ነው።+ +52 ከአሁን ጀምሮ በአንድ ቤት ውስጥ እርስ በርስ የተከፋፈሉ አምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሦስቱ በሁለቱ ላይ ሁለቱ ደግሞ በሦስቱ ላይ ይነሳሉ። +53 አባት በልጁ፣ ልጅ በአባቱ፣ እናት በልጇ፣ ልጅ በእናቷ፣ አማት በምራቷ፣ ምራት በአማቷ ላይ በመነሳት እርስ በርስ ይከፋፈላሉ።”+ +54 ከዚያም ለሕዝቡ ደግሞ እንዲህ አለ፦ “ከምዕራብ በኩል ደመና ሲመጣ ስታዩ ወዲያውኑ ‘ዶፍ ዝናብ ሊጥል ነው’ ትላላችሁ፤ እንዳላችሁትም ይሆናል። +55 የደቡብ ነፋስ ሲነፍስ ስታዩ ደግሞ ‘ኃይለኛ ሙቀት ይሆናል’ ትላላችሁ፤ በእርግጥም ይሆናል። +56 እናንተ ግብዞች፣ የምድሩንና የሰማዩን መልክ አይታችሁ መረዳት ትችላላችሁ፤ ታዲያ ይህን የአሁኑን ዘመን መርምራችሁ መረዳት እንዴት ተሳናችሁ?+ +57 ደግሞስ ጽድቅ የሆነውን ነገር ለራሳችሁ ለምን አትፈርዱም? +58 ለምሳሌ ከከሳሽህ ጋር ወደ አንድ ባለሥልጣን እየሄድክ ሳለ፣ ከእሱ ጋር ያለህን ቅራኔ እዚያው በመንገድ ላይ ለመፍታት ጥረት አድርግ፤ አለዚያ ዳኛ ፊት ያቀርብሃል፤ ዳኛውም ለፍርድ ቤቱ መኮንን አሳልፎ ይሰጥሃል፤ መኮንኑ ደግሞ እስር ቤት ያስገባሃል።+ +59 እልሃለሁ፣ የመጨረሻዋን ትንሽ ሳንቲም* ከፍለህ እስክትጨርስ ድረስ ከዚያ ፈጽሞ አትወጣም።” +1 ብዙዎች እኛ ሙሉ እምነት የጣልንባቸውን መረጃዎች ለማጠናቀር የተቻላቸውን ጥረት አድርገዋል፤+ +2 ደግሞም ከመጀመሪያው አንስቶ የዓይን ምሥክሮች የነበሩ ሰዎችና+ መልእክቱን የሚያውጁ አገልጋዮች+ እነዚህን መረጃዎች ለእኛ አስተላልፈዋል። +3 ክቡር ቴዎፍሎስ ሆይ፣+ እኔም በበኩሌ ሁሉንም ነገር ከመጀመሪያው አንስቶ በጥንቃቄ ስለመረመርኩ ታሪኩን በቅደም ተከተል ልጽፍልህ ወሰንኩ። +4 ይህን ያደረግኩት በቃል የተማርካቸው ነገሮች እርግጠኛ መሆናቸውን በሚገባ እንድታውቅ ነው።+ +5 በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ* ዘመን፣+ በአቢያህ+ የክህነት ምድብ ውስጥ የሚያገለግል ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበር። ሚስቱ የአሮን ዘር ስትሆን ስሟም ኤልሳቤጥ ነበር። +6 ሁለቱም በአምላክ ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ የይሖዋን* ትእዛዛትና ሕግጋት ሁሉ እየጠበቁ ያለነቀፋ ይኖሩ ነበር። +7 ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መሃን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፤ እንዲሁም ሁለቱም በዕድሜ የገፉ ነበሩ። +8 አንድ ቀን ዘካርያስ እሱ ያለበት ምድብ+ ተራው ደርሶ በአምላክ ፊት በክህነት እያገለገለ ሳለ +9 በክህነት ሥርዓቱ* መሠረት ወደ ይሖዋ* ቤተ መቅደስ+ ገብቶ ዕጣን+ የሚያጥንበት ተራ ደረሰው። +10 ዕጣን በሚቀርብበትም ሰዓት ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ሆነው ይጸልዩ ነበር። +11 የይሖዋም* መልአክ ከዕጣን መሠዊያው በስተ ቀኝ ቆሞ ታየው። +12 ዘካርያስም መልአኩን ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሃትም ተዋጠ። +13 መልአኩ ግን እንዲህ አለው፦ “ዘካርያስ፣ አትፍራ፤ ምክንያቱም አምላክ ያቀረብከውን ምልጃ ሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።+ +14 አንተም ደስ ይልሃል፤ ሐሴትም ታደርጋለህ፤ ብዙዎችም በእሱ መወለድ ደስ ይላቸዋል፤+ +15 በይሖዋ* ፊት ታላቅ ይሆናልና።+ ይሁንና የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ ፈጽሞ መጠጣት የለበትም፤+ ከመወለዱ በፊት እንኳ* በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፤+ +16 ከእስራኤል ልጆች መካከልም ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ* ይመልሳል።+ +17 በተጨማሪም ሰዎችን ለይሖዋ * ያዘጋጅ ዘንድ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ ለማድረግ፣*+ የማይታዘዙትንም ሰዎች ወደ ጻድቃን ጥበብ ለመመለስ በኤልያስ መንፈስና ኃይል+ በአምላክ ፊት ይሄዳል።”+ +18 ዘካርያስ መልአኩን “ይህ እንደሚሆን እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለሁ? እኔ እንደሆነ አርጅቻለሁ፤ ሚስቴም ዕድሜዋ ገፍቷል” አለው። +19 መልአኩም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እኔ በአምላክ አጠገብ በፊቱ የምቆመው+ ገብርኤል+ ነኝ፤ አንተን እንዳነጋግርህና ይህን ምሥራች እንዳበስርህ ተልኬአለሁ። +20 ሆኖም የተወሰነለትን ጊዜ ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንክ ይህ ነገር እስኪፈጸም ድረስ ዱዳ ትሆናለህ! መናገርም አትችልም።” +21 ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕዝቡ ዘካርያስን በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፤ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ብዙ በመቆየቱም ግራ ተጋቡ። +22 በወጣ ጊዜም ሊያናግራቸው አልቻለም፤ እነሱም በቤተ መቅደሱ ውስጥ አንድ ራእይ እንዳየ ተገነዘቡ። ከዚያ በኋላ ዱዳ ስለሆነ በምልክት ብቻ ያናግራቸው ነበር። +23 በቤተ መቅደሱ ውስጥ ቅዱስ አገልግሎት* የሚያቀርብባቸው ቀናት ሲያበቁ ወደ ቤቱ ሄደ። +24 ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፤ ለአምስት ወርም ከቤት ሳትወጣ ቆየች፤ እንዲህም አለች፦ +25 “ይሖዋ* በዚህ ወቅት ይህን አደረገልኝ። በሰዎች መካከል ይደርስብኝ የነበረውን ነቀፋ ለማስወገድ ፊቱን ወደ እኔ መለሰ።”+ +26 ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድስተኛ ወሯ አምላክ መልአኩ ገብርኤልን+ በገሊላ ወደምትገኝ ናዝሬት ወደተባለች ከተማ ላከው፤ +27 የተላከውም ከዳዊት ቤት ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች አንዲት ድንግል+ ሲሆን የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር።+ +28 መልአኩም ገብቶ “እጅግ የተባረክሽ ሆይ፣ ሰላም ለአንቺ ይሁን፤ ይሖዋ* ከአንቺ ጋር ነው” አላት። +29 እሷ ግን በንግግሩ በጣም ደንግጣ ይህ ሰላምታ ምን ትርጉም እንዳለው ለመረዳት በውስጧ ታስብ ጀመር። +30 ስለዚህ መልአኩ እንዲህ አላት፦ “ማርያም ሆይ፣ በአምላክ ፊት ሞገስ ስላገኘሽ አትፍሪ። +31 እነሆም፣ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤+ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።+ +32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ +33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”+ +34 ማርያም ግን መልአኩን “እኔ ከወንድ ጋር ግንኙነት ፈጽሜ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለችው።+ +35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤+ የልዑሉም ኃይል በአንቺ ላይ ያርፋል። ስለሆነም የሚወለደው ልጅ ቅዱስና+ የአምላክ ልጅ+ ይባላል። +36 እነሆ፣ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም በስተርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መሃን ትባል የነበረ ቢሆንም ይኸው ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤ +37 አምላክ የተናገረው ቃል ሳይፈጸም አይቀርምና።”*+ +38 በዚህ ጊዜ ማርያም “እነሆ፣ እኔ የይሖዋ* ባሪያ ነኝ! እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” አለች። ከዚያም መልአኩ ተለይቷት ሄደ። +39 ማርያምም በዚያው ሰሞን ተነስታ በተራራማው አገር ወደምትገኝ አንዲት የይሁዳ ከተማ በፍጥነት ሄደች፤ +40 ወደ ዘካርያስ ቤት ገብታም ኤልሳቤጥን ሰላም አለቻት። +41 ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማህፀኗ ውስጥ ያለው ፅንስ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፤ +42 ድምፅዋንም ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፦ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማህፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው! +43 የጌታዬ እናት ወደ እኔ መምጣቷ ለእኔ እንዴት ያለ ታላቅ ክብር ነው! +44 እነሆ፣ የሰላምታሽን ድምፅ እንደሰማሁ በማህፀኔ ያለው ፅንስ በደስታ ዘሏልና። +45 ይሖዋ* የነገራት ነገር ሙሉ በሙሉ የሚፈጸም በመሆኑ ይህን ያመነች ደስተኛ ነች።” +46 ማርያምም እንዲህ አለች፦ “ነፍሴ ይሖዋን* ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፤*+ +47 መንፈሴም አዳኜ በሆነው አምላክ እጅግ ደስ ይሰኛል፤+ +48 ምክንያቱም የባሪያውን መዋረድ* ተመልክቷል።+ እነሆ፣ ከአሁን ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ደስተኛ ይሉኛል፤+ +49 ምክንያቱም ኃያል የሆነው አምላክ ታላላቅ ነገሮች አድርጎልኛል፤ ስሙም ቅዱስ ነው፤+ +50 ምሕረቱም በሚፈሩት ሁሉ ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።+ +51 በክንዱም ታላላቅ ሥራዎች አከናውኗል፤ በልባቸው ሐሳብ ትዕቢተኛ የሆኑትንም በትኗቸዋል።+ +52 ኃያላን ሰዎችን ከዙፋናቸው አውርዷል፤+ ዝቅ ያሉትንም ከፍ አድርጓል፤+ +53 የተራቡትን በመልካም ነገሮች አጥግቧል፤+ ሀብታሞችንም ባዶ እጃቸውን ሰዷቸዋል። +54 ምሕረቱን በማስታወስ አገልጋዩን እስራኤልን ረድቷል፤+ +55 ይህን ያደረገው ለአባቶቻችን በገባው ቃል መሠረት ለአብርሃምና ለዘሩ+ ለዘላለም ምሕረት ለማሳየት ነው።” +56 ማርያምም ከኤልሳቤጥ ጋር ሦስት ወር ያህል ከቆየች በኋላ ወደ ቤቷ ተመለሰች። +57 ኤልሳቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰና ወንድ ልጅ ወለደች። +58 ጎረቤቶቿና ዘመዶቿም ይሖዋ* ታላቅ ምሕረት እንዳደረገላት ሰምተው የደስታዋ ተካፋዮች ሆኑ።+ +59 በስምንተኛው ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤+ በአባቱም ስም ዘካርያስ ብለው ሊጠሩት ፈልገው ነበር። +60 እናትየው ግን መልሳ “አይሆንም! ዮሐንስ ይባል” አለች። +61 በዚህ ጊዜ “ከዘመዶችሽ መካከል በዚህ ስም የተጠራ ማንም የለም” አሏት። +62 ከዚያም አባቱን ማን ተብሎ እንዲጠራ እንደሚፈልግ በምልክት ጠየቁት። +63 እሱም የእንጨት ጽላት እንዲያመጡለት ጠየቀና “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ።+ በዚህ ጊዜ ሁሉም ተደነቁ። +64 ወዲያውም አፉ ተከፈተ፤ ምላሱም ተፈቶ መናገር ጀመረ፤+ አምላክንም አወደሰ። +65 ጎረቤቶቻቸውም ሁሉ በፍርሃት ተዋጡ፤ የሆነውም ነገር ሁሉ በተራራማው የይሁዳ አገር በሙሉ ይወራ ጀመር። +66 ይህን የሰሙም ሁሉ “የዚህ ሕፃን መጨረሻ ምን ይሆን?” በማለት ነገሩን በልባቸው ያዙ። የይሖዋ* እጅ ከእሱ ጋር እንደሆነ በግልጽ ይታይ ነበርና። +67 ከዚያም አባቱ ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፦ +68 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ* ፊቱን ወደ ሕዝቡ ስለመለሰና ሕዝቡን ስላዳነ+ ውዳሴ ይድረሰው።+ +69 ደግሞም በአገ���ጋዩ በዳዊት ቤት+ የመዳን ቀንድ* አስነስቶልናል፤+ +70 ይህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ በነበሩት ቅዱሳን ነቢያቱ አፍ በተናገረው መሠረት ነው።+ +71 ከባላጋራዎቻችንና ከሚጠሉን ሰዎች ሁሉ እጅ እንደሚያድነን ቃል ገብቷል።+ +72 ለአባቶቻችን በሰጠው ተስፋ መሠረት ምሕረት ያሳየናል፤ ቅዱስ ቃል ኪዳኑንም ያስታውሳል።+ +73 ይህም ቃል ኪዳን ለአባታችን ለአብርሃም የማለው መሐላ ነው፤+ +74 በመሐላው መሠረትም ከጠላቶቻችን እጅ ነፃ ካወጣን በኋላ ለእሱ ያለፍርሃት ቅዱስ አገልግሎት የማቅረብ መብት ይሰጠናል፤ +75 ይህም ታማኝ እንድንሆንና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ጽድቅ የሆነውን ነገር እንድናደርግ ነው። +76 ደግሞም አንተ ሕፃን፣ መንገዱን ለማዘጋጀት ቀድመህ በይሖዋ* ፊት ስለምትሄድ የልዑሉ ነቢይ ትባላለህ፤+ +77 ለሕዝቡም ኃጢአታቸው ይቅር ተብሎላቸው መዳን እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን እውቀት ትሰጣቸዋለህ፤+ +78 ይህም የሆነው አምላካችን ከአንጀት ስለራራልን ነው። ከዚህ ርኅራኄም የተነሳ እንደ ንጋት ፀሐይ የሚያበራ ብርሃን ከላይ ይወጣልናል፤ +79 ይኸውም በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ+ ለተቀመጡት ብርሃን ለመስጠት እንዲሁም እግሮቻችንን በሰላም መንገድ ለመምራት ነው።” +80 ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤልም በይፋ እስከታየበት ቀን ድረስ በበረሃ ኖረ። +8 ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የአምላክን መንግሥት ምሥራች እየሰበከና እያወጀ ከከተማ ወደ ከተማ እንዲሁም ከመንደር ወደ መንደር ተጓዘ።+ አሥራ ሁለቱም ከእሱ ጋር ነበሩ፤ +2 በተጨማሪም ከክፉ መናፍስትና ከበሽታ የተፈወሱ አንዳንድ ሴቶች አብረውት ነበሩ፦ ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የተባለችው ማርያም፣ +3 የሄሮድስ ቤት አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐና፣+ ሶስና እንዲሁም ሌሎች ብዙ ሴቶች የነበሩ ሲሆን በንብረታቸው ያገለግሏቸው ነበር።+ +4 ኢየሱስም የየከተማው ሕዝብ ተከትሎት በመጣ ጊዜና እጅግ ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት ወቅት እንዲህ ሲል በምሳሌ ተናገረ፦+ +5 “አንድ ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ። በሚዘራበት ጊዜ አንዳንዶቹ ዘሮች መንገድ ዳር ወድቀው ተረጋገጡ፤ የሰማይ ወፎችም መጥተው ለቀሟቸው።+ +6 አንዳንዶቹ ዓለት ላይ ወደቁ፤ ከበቀሉም በኋላ እርጥበት ስላላገኙ ደረቁ።+ +7 ሌሎቹ ደግሞ በእሾህ መካከል ወደቁ፤ አብሯቸው ያደገውም እሾህ አነቃቸው።+ +8 ሌሎቹ ግን ጥሩ አፈር ላይ ወደቁ፤ ከበቀሉም በኋላ 100 እጥፍ አፈሩ።”+ ይህን ከተናገረ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ “የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ” አለ።+ +9 ደቀ መዛሙርቱ ግን የዚህን ምሳሌ ትርጉም ጠየቁት።+ +10 እሱም እንዲህ አለ፦ “ለእናንተ የአምላክን መንግሥት ቅዱስ ሚስጥሮች የመረዳት ችሎታ ተሰጥቷችኋል፤ ለቀሩት ግን በምሳሌ እነግራቸዋለሁ፤+ ይኸውም እያዩ እንዳያስተውሉ እንዲሁም እየሰሙ ትርጉሙን እንዳይረዱ ነው።+ +11 እንግዲህ የምሳሌው ትርጉም ይህ ነው፦ ዘሩ የአምላክ ቃል ነው።+ +12 በመንገድ ዳር የወደቁት ቃሉን የሰሙ ናቸው፤ ከዚያ በኋላ ግን አምነው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል።+ +13 በዓለት ላይ የወደቁት ቃሉን ሲሰሙ በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ ነገር ግን ሥር የላቸውም። ለጊዜው አምነው ቢቀበሉም በፈተና ወቅት ይወድቃሉ።+ +14 በእሾህ መካከል የወደቁት ቃሉን የሰሙ ናቸው፤ ሆኖም በዚህ ዓለም የኑሮ ጭንቀት፣ ሀብትና+ ሥጋዊ ደስታ+ ትኩረታቸው ተከፋፍሎ ሙሉ በሙሉ ይታነቃሉ፤ ለፍሬም አይበቁም።+ +15 በጥሩ አፈር ላይ የወደቁት ደግሞ ቃሉን በመልካምና በጥሩ ልብ+ ሰምተው በውስጣቸው በማኖር በጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።+ +16 “መብራት አብርቶ ዕቃ የሚከድንበት ወይም አልጋ ሥር የሚያስቀምጥ ሰው የለም፤ ከዚህ ይልቅ ��ደ ቤት የሚገቡ ሁሉ ብርሃን እንዲያገኙ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል።+ +17 በመሆኑም ተሸሽጎ የማይገለጥ፣ በሚገባ ቢሰወርም የማይታወቅና ይፋ የማይወጣ ነገር የለም።+ +18 ስለዚህ እንዴት እንደምታዳምጡ በጥሞና አስቡ፤ ላለው ተጨማሪ ይሰጠዋልና፤+ የሌለው ግን እንዳለው አድርጎ የሚያስበው ነገር እንኳ ይወሰድበታል።”+ +19 ከዚህ በኋላ እናቱና ወንድሞቹ+ እሱ ወዳለበት መጡ፤ ሆኖም ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ወደ እሱ ሊቀርቡ አልቻሉም።+ +20 ስለዚህ “እናትህና ወንድሞችህ ሊያገኙህ ፈልገው ውጭ ቆመዋል” ተብሎ ተነገረው። +21 እሱም መልሶ “እናቴና ወንድሞቼ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው” አላቸው።+ +22 አንድ ቀን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጀልባ ከተሳፈረ በኋላ “ወደ ሐይቁ ማዶ እንሻገር” አላቸው። በመሆኑም ጉዞ ጀመሩ።+ +23 እየተጓዙም ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደው። በዚህ ጊዜ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በሐይቁ ላይ ተነሳ፤ ጀልባቸውም በውኃ መሞላት ስለጀመረች አደጋ ላይ ወደቁ።+ +24 ስለዚህ ሄደው ቀሰቀሱትና “መምህር፣ መምህር ማለቃችን እኮ ነው!” አሉት። እሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ ነፋሱንና የሚናወጠውን ውኃ ገሠጸ፤ በዚህ ጊዜ ነፋሱ ቆመ፤ ጸጥታም ሰፈነ።+ +25 ከዚያም “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነሱ ግን በፍርሃት ተውጠውና በጣም ተደንቀው እርስ በርሳቸው “ለመሆኑ ይህ ማን ነው? ነፋስና ውኃ እንኳ ይታዘዙለታል” ተባባሉ።+ +26 ከዚያም በገሊላ ማዶ ወደሚገኘው ጌርጌሴኖን+ ወደተባለው ክልል የባሕር ዳርቻ ደረሱ። +27 ኢየሱስ ከጀልባዋ ወደ የብስ በወረደ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት በአቅራቢያው በሚገኝ ከተማ የሚኖር አንድ ሰው አገኘው። ይህ ሰው ልብስ መልበስ ከተወ ብዙ ጊዜ ሆኖት ነበር፤ የሚኖረውም በቤት ውስጥ ሳይሆን በመቃብር ስፍራ ነበር።+ +28 ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እየጮኸ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም “የልዑል አምላክ ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለ።+ +29 (ይህን ያለውም ኢየሱስ ርኩሱ መንፈስ ከሰውየው እንዲወጣ እያዘዘው ስለነበረ ነው። ርኩሱ መንፈስ ሰውየውን ብዙ ጊዜ ይይዘው ነበር፤*+ ሰውየው በተደጋጋሚ በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም የታሰረበትን ሰንሰለት ይበጣጥስ ነበር፤ ጋኔኑም ጭር ወዳሉ ቦታዎች ይነዳው ነበር።) +30 ኢየሱስ “ስምህ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው። እሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ስለነበር “ሌጌዎን” አለው። +31 አጋንንቱም ወደ ጥልቁ እንዲሄዱ እንዳያዛቸው ተማጸኑት።+ +32 በዚያም በተራራው ላይ ብዛት ያለው የአሳማ+ መንጋ ተሰማርቶ ነበር፤ ስለዚህ ወደ አሳማዎቹ ይገቡ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ተማጸኑት፤ እሱም ፈቀደላቸው።+ +33 በዚህ ጊዜ አጋንንቱ ከሰውየው ወጥተው አሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ የአሳማውም መንጋ ከገደሉ አፋፍ* እየተንደረደረ በመውረድ ሐይቁ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። +34 እረኞቹ ግን የሆነውን ነገር ሲያዩ ሸሽተው በመሄድ ወሬውን በከተማውና በገጠሩ አዳረሱ። +35 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ የሆነውን ነገር ለማየት ወጡ። ወደ ኢየሱስ ሲመጡም አጋንንት የወጡለት ሰው ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጦ አገኙት፤ በዚህ ጊዜ ፍርሃት አደረባቸው። +36 የተፈጸመውን ነገር ያዩ ሰዎች አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው እንዴት ጤናማ ሊሆን እንደቻለ አወሩላቸው። +37 በዚህ ጊዜ ከጌርጌሴኖን ክልል የመጡት ሰዎች በሙሉ ታላቅ ፍርሃት ስላደረባቸው ኢየሱስን ከዚያ እንዲሄድላቸው ለመኑት። እሱም ከዚያ ለመሄድ ጀልባዋ ላይ ተሳፈረ። +38 አጋንንት የወጡለት ሰው ግን አብሮት ይሆን ዘንድ ደጋግሞ ለመነው፤ ሆኖም ኢየሱስ ��ውየውን እንዲህ ሲል አሰናበተው፦+ +39 “ወደ ቤትህ ተመለስ፤ አምላክ ያደረገልህንም ነገር ተናገር።” ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ነገር በከተማው ሁሉ እያወጀ ሄደ። +40 ሕዝቡ እየጠበቁት ስለነበር ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ ሁሉም በደስታ ተቀበሉት።+ +41 በዚህ ጊዜ ኢያኢሮስ የሚባል አንድ የምኩራብ አለቃ መጣ። ኢየሱስ እግር ላይም ወድቆ ወደ ቤቱ እንዲገባ ይማጸነው ጀመር፤+ +42 ይህን ያደረገው 12 ዓመት ገደማ የሆናት አንዲት ልጁ ልትሞት ተቃርባ ስለነበር ነው። ኢየሱስ እየተጓዘ ሳለ ሕዝቡ እየተጋፋ ያጨናንቀው ነበር። +43 በዚያም፣ ለ12 ዓመት ደም ሲፈስሳት+ የኖረች አንዲት ሴት የነበረች ሲሆን ይህችን ሴት ሊፈውሳት የቻለ አንድም ሰው አልነበረም።+ +44 ከኋላም መጥታ የልብሱን ዘርፍ ነካች፤+ ይፈሳት የነበረውም ደም ወዲያውኑ ቆመ። +45 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፣ ጴጥሮስ “መምህር፣ ሕዝቡ ከቦህ እየተጋፋህ ነው የሚሄደው” አለው።+ +46 ኢየሱስ ግን “ኃይል+ ከእኔ እንደወጣ ስለታወቀኝ አንድ ሰው ነክቶኛል” አለ። +47 ሴትየዋም ሳይታወቅባት መሄድ እንዳልቻለች በተረዳች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ ከዚያም ለምን እንደነካችውና እንዴት ወዲያውኑ እንደተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት ተናገረች። +48 እሱ ግን “ልጄ ሆይ፣ እምነትሽ አድኖሻል። በሰላም ሂጂ” አላት።+ +49 ገና እየተናገረ ሳለ ከምኩራብ አለቃው ቤት የተላከ አንድ ሰው መጥቶ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታስቸግረው” አለው።+ +50 ኢየሱስ ይህን ሲሰማ “አትፍራ፤ ብቻ እመን፤ ልጅህ ትድናለች” አለው።+ +51 ወደ ኢያኢሮስ ቤት በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቷ አባትና እናት በስተቀር ማንም አብሮት ወደ ውስጥ እንዲገባ አልፈቀደም። +52 በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ ለልጅቷ እያለቀሱና በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ “በቃ አታልቅሱ፤+ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም”+ አላቸው። +53 ይህን ሲሰሙ ልጅቷ እንደሞተች ያውቁ ስለነበር በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። +54 እሱ ግን እጇን በመያዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” አለ።+ +55 የልጅቷም መንፈስ*+ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሳች፤+ የምትበላውም ነገር እንዲሰጧት አዘዘ። +56 ወላጆቿም የሚሆኑት ጠፋቸው፤ እሱ ግን የሆነውን ነገር ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።+ +11 አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ እየጸለየ ነበር፤ ጸሎቱንም ሲጨርስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ “ጌታ ሆይ፣ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው ሁሉ አንተም እንዴት እንደምንጸልይ አስተምረን” አለው። +2 በመሆኑም እንዲህ አላቸው፦ “በምትጸልዩበት ጊዜ ሁሉ እንዲህ በሉ፦ ‘አባት ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ።*+ መንግሥትህ ይምጣ።+ +3 የዕለቱን ምግባችንን* ለዕለቱ የሚያስፈልገንን ያህል ስጠን።+ +4 እኛ የበደሉንን* ሁሉ ይቅር ስለምንል+ ኃጢአታችንን ይቅር በለን፤+ ወደ ፈተናም አታግባን።’”+ +5 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ መካከል አንዱ፣ አንድ ወዳጅ አለው እንበል፤ በእኩለ ሌሊትም ወደ እሱ ሄዶ እንዲህ አለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ፣ እባክህ ሦስት ዳቦ አበድረኝ፤ +6 አንድ ወዳጄ ከመንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ነገር አጣሁ።’ +7 ወዳጁ ግን ከውስጥ ሆኖ ‘ባክህ አታስቸግረኝ። በሩ ተቆልፏል፤ ልጆቼም አብረውኝ ተኝተዋል። አሁን ተነስቼ ምንም ነገር ልሰጥህ አልችልም’ ይለዋል። +8 እላችኋለሁ፣ ወዳጁ ስለሆነ ተነስቶ ባይሰጠው እንኳ ስለ ውትወታው ሲል+ ተነስቶ የፈለገውን ሁሉ ይሰጠዋል። +9 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ደጋግማችሁ ለምኑ፣+ ይሰጣችኋል፤ ሳታሰልሱ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ ደጋግማችሁ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።+ +10 ምክንያቱም የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋል፤+ የሚፈልግ ሁሉ ያገኛል፤ የሚያንኳኳም ሁሉ ይከፈትለታል። +11 ደግሞስ ከመካከላችሁ ልጁ ዓሣ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ የሚሰጥ አባት ይኖራል?+ +12 ወይስ እንቁላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋል? +13 ታዲያ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ በሰማይ ያለው አባትማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸው!”+ +14 ከጊዜ በኋላ፣ ኢየሱስ ዱዳ የሚያደርግ ጋኔን አስወጣ።+ ጋኔኑ ከወጣ በኋላ ዱዳው ሰው መናገር ጀመረ፤ ሕዝቡም ተደነቀ።+ +15 ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ ግን “አጋንንትን የሚያስወጣው በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል* ነው” አሉ።+ +16 ሌሎች ደግሞ ሊፈትኑት ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ይጠይቁት ጀመር።+ +17 ኢየሱስም ሐሳባቸውን አውቆ+ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ እንዲሁም እርስ በርሱ የሚከፋፈል ቤት ይወድቃል። +18 በተመሳሳይም ሰይጣን እርስ በርሱ ከተከፋፈለ መንግሥቱ እንዴት ይቆማል? እናንተ አጋንንትን የማስወጣው በብዔልዜቡል እንደሆነ ትናገራላችሁና። +19 እኔ አጋንንትን የማስወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ የሚያስወጧቸው ታዲያ በማን ነው? ልጆቻችሁ ፈራጆች የሚሆኑባችሁ ለዚህ ነው። +20 ሆኖም አጋንንትን የማስወጣው በአምላክ ጣት+ ከሆነ የአምላክ መንግሥት ሳታስቡት ደርሶባችኋል ማለት ነው።+ +21 አንድ ብርቱ ሰው በደንብ ታጥቆ ቤቱን ከጠበቀ ንብረቱ ምንም አይነካበትም። +22 ይሁን እንጂ ከእሱ ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው ካጠቃውና ካሸነፈው ተማምኖበት የነበረውን መሣሪያ ሁሉ ይነጥቀዋል፤ ከእሱ የወሰደውንም ለሌሎች ያካፍላል። +23 ከእኔ ጎን ያልቆመ ሁሉ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ሁሉ ይበትናል።+ +24 “ርኩስ መንፈስ ከሰው ሲወጣ የሚያርፍበት ቦታ ፍለጋ ውኃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ የሚያርፍበት ቦታ ሲያጣ ግን ‘ወደለቀቅኩት ቤቴ እመለሳለሁ’ ይላል።+ +25 ሲመለስም ቤቱ ጸድቶና አጊጦ ያገኘዋል። +26 ከዚያም ሄዶ ከእሱ የከፉ ሌሎች ሰባት መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውም ይኖሩበታል። በመሆኑም የዚያ ሰው የኋለኛው ሁኔታ ከቀድሞው የከፋ ይሆንበታል።” +27 ይህን እየተናገረ ሳለ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “አንተን የተሸከመች ማህፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ደስተኞች ናቸው!” አለችው።+ +28 እሱ ግን “ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው!” አለ።+ +29 ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክትም ማየት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከዮናስ ምልክት በስተቀር ምንም ምልክት አይሰጠውም።+ +30 ምክንያቱም ዮናስ+ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደሆነ ሁሉ የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። +31 የደቡብ ንግሥት+ የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለመጣች በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነስታ ትኮንናቸዋለች። ነገር ግን ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።+ +32 የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሐ ስለገቡ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይኮንኑታል።+ ነገር ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ። +33 አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ በሰዋራ ቦታ አያስቀምጠውም ወይም እንቅብ* አይደፋበትም፤+ ከዚህ ይልቅ ወደ ቤት የሚገቡ ሁሉ ብርሃን እንዲያገኙ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል። +34 የሰውነት መብራት ዓይን ነው። ዓይንህ በአንድ ነገር ላይ ሲያተኩር* መላ ሰውነትህም ብሩህ * ይሆናል፤ ዓይንህ ምቀኛ* ሲሆን ግን መላ ሰውነትህም ጨለማ ይሆናል።+ +35 ስለዚህ በውስጥህ ያለ��� ብርሃን፣ ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። +36 እንግዲህ መላ ሰውነትህ ምንም ጨለማ ሳይኖርበት ብሩህ ከሆነ፣ ልክ ብርሃን እንደሚፈነጥቅልህ መብራት ሁለንተናህ ብሩህ ይሆናል።” +37 ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ አንድ ፈሪሳዊ አብሮት እንዲበላ ጋበዘው። እሱም ወደ ቤቱ ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። +38 ይሁን እንጂ ፈሪሳዊው ኢየሱስ ከምሳ በፊት እጁን እንዳልታጠበ* ባየ ጊዜ ተገረመ።+ +39 ጌታ ግን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ፈሪሳውያን ጽዋውንና ሳህኑን ከውጭ በኩል ታጸዳላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን በስግብግብነትና በክፋት የተሞላ ነው።+ +40 እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁ! የውስጡንስ የሠራው የውጭውን የሠራው አይደለም? +41 ስለዚህ በልባችሁ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ምጽዋት* አድርጋችሁ ስጡ፤ ያን ጊዜ በሁሉም ነገር ንጹሕ ትሆናላችሁ። +42 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ከኮሰረት፣ ከጤና አዳምና ከሌሎች አትክልቶች ሁሉ አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን የአምላክን ፍትሕና እሱን መውደድን ችላ ትላላችሁ። እርግጥ አሥራት የመስጠት ግዴታ አለባችሁ፤ ሆኖም ሌሎቹን ነገሮች ችላ ማለት አልነበረባችሁም።+ +43 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም በምኩራብ ከፊት መቀመጥ፣* በገበያ ቦታ ደግሞ ሰዎች እጅ እንዲነሷችሁ ትፈልጋላችሁ።+ +44 ሰዎች ሳያውቁ በላዩ ላይ የሚሄዱበትን የተሰወረ* መቃብር ስለምትመስሉ ወዮላችሁ!”+ +45 ከሕጉ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ “መምህር፣ እንዲህ ስትል እኮ እኛንም መስደብህ ነው” አለው። +46 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለ፦ “እናንተ የሕጉ አዋቂዎችም ወዮላችሁ! ምክንያቱም ለመሸከም የሚከብድ ሸክም በሰው ላይ ትጭናላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ ግን ሸክሙን በጣታችሁ እንኳ አትነኩትም።+ +47 “አባቶቻችሁ የገደሏቸውን ነቢያት መቃብሮች ስለምትሠሩ ወዮላችሁ!+ +48 እንግዲህ እናንተ ለአባቶቻችሁ ሥራ ምሥክሮች ናችሁ፤ ያም ሆኖ የእነሱን ሥራ ትደግፋላችሁ፤ ምክንያቱም እነሱ ነቢያትን ገደሉ፤+ እናንተ ደግሞ መቃብሮቻቸውን ትሠራላችሁ። +49 ስለዚህ የአምላክ ጥበብ እንዲህ አለች፦ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነሱ እልካለሁ፤ እነሱም አንዳንዶቹን ይገድላሉ በአንዳንዶቹም ላይ ስደት ያደርሳሉ፤ +50 በመሆኑም ይህ ትውልድ ዓለም ከተመሠረተበት* ጊዜ ጀምሮ ለፈሰሰው የነቢያት ደም ሁሉ ተጠያቂ ነው፤*+ +51 ከአቤል+ አንስቶ በመሠዊያውና በቤቱ* መካከል እስከተገደለው እስከ ዘካርያስ+ ድረስ ለፈሰሰው ደም ተጠያቂ ነው።’ አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ይህ ትውልድ ይጠየቅበታል።* +52 “እናንተ የሕጉ አዋቂዎች ወዮላችሁ! ምክንያቱም የእውቀትን ቁልፍ ነጥቃችሁ ወስዳችኋል። እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁም፤ ለመግባት የሚሞክሩትንም ትከለክላላችሁ።”+ +53 ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ ሲሄድ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ከበው እያጨናነቁት ስለተለያዩ ነገሮች በመጠየቅ ያዋክቡት ጀመር፤ +54 በሚናገረውም ነገር ሊያጠምዱት ያደቡ ነበር።+ +2 በዚያ ዘመን፣ አውግስጦስ ቄሳር የዓለም ሕዝብ ሁሉ እንዲመዘገብ አዋጅ አወጣ። +2 (ይህ የመጀመሪያ ምዝገባ የተካሄደው ቄሬኔዎስ የሶርያ አገረ ገዢ በነበረበት ጊዜ ነው።) +3 ሁሉም ሰው ለመመዝገብ ወደየራሱ ከተማ ሄደ። +4 ዮሴፍም+ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለነበር በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት ከተማ ተነስቶ በይሁዳ ወዳለች ቤተልሔም+ ተብላ ወደምትጠራ የዳዊት ከተማ ወጣ። +5 ለመመዝገብ የሄደውም በታጨችለት መሠረት+ ካገባትና የመውለጃ ጊዜዋ ከተቃረበው+ ከማርያም ጋር ነበር። +6 በዚያም እንዳሉ የምትወልድበት ጊዜ ደረሰ። +7 የበኩር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅም ወለደች፤+ በእንግዶች ማረፊያም፣ ቦታ ስላላገኙ ልጁን በጨርቅ ጠቅልላ በግርግም ውስጥ አስተኛችው።+ +8 በዚያው ክልል፣ ሌሊት* ሜዳ ላይ መንጎቻቸውን ሲጠብቁ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ። +9 በድንገት የይሖዋ* መልአክ መጥቶ በፊታቸው ቆመ፤ የይሖዋም* ክብር በዙሪያቸው አንጸባረቀ፤ እነሱም በታላቅ ፍርሃት ተዋጡ። +10 መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፤ እነሆ፣ ለሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚያስገኝ ምሥራች እነግራችኋለሁ፤ +11 በዛሬው ዕለት በዳዊት ከተማ+ አዳኝ+ ተወልዶላችኋልና፤ እሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።+ +12 ይህም ምልክት ይሁናችሁ፦ አንድ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ።” +13 በድንገት ብዙ የሰማይ ሠራዊት+ ከመልአኩ ጋር ታዩ፤ አምላክንም እያመሰገኑ እንዲህ አሉ፦ +14 “በሰማያት ለአምላክ ክብር ይሁን፤ በምድርም አምላክ ሞገስ ለሚያሳያቸው ሰዎች ሰላም ይሁን።” +15 መላእክቱም ከእነሱ ተለይተው ወደ ሰማይ ከሄዱ በኋላ እረኞቹ እርስ በርሳቸው “አሁኑኑ ወደ ቤተልሔም ሄደን ይሖዋ* በገለጠልን መሠረት በዚያ የተፈጸመውን ነገር ማየት አለብን” ተባባሉ። +16 በፍጥነትም ሄደው ማርያምንና ዮሴፍን አገኟቸው፤ ሕፃኑም በግርግም ተኝቶ ነበር። +17 ይህን ባዩ ጊዜ ስለ ሕፃኑ የተነገራቸውን መልእክት አወሩ። +18 ይህን የሰሙ ሰዎች ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር ተደነቁ፤ +19 ማርያም ግን የሰማቻቸውን ነገሮች በውስጧ ይዛ በልቧ ታሰላስል ነበር።+ +20 እረኞቹም የሰሙትና ያዩት ነገር ሁሉ ልክ እንደተነገራቸው ሆኖ ስላገኙት አምላክን እያከበሩና እያወደሱ ተመለሱ። +21 ከስምንት ቀን በኋላ፣ ሕፃኑ የሚገረዝበት ጊዜ ሲደርስ+ ከመፀነሱ በፊት መልአኩ ባወጣለት ስም ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።+ +22 በተጨማሪም በሙሴ ሕግ መሠረት+ የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ ሕፃኑን በይሖዋ* ፊት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት መጡ፤ +23 ይህን ያደረጉት “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* ለይሖዋ* የተቀደሰ መሆን አለበት”+ ተብሎ በይሖዋ* ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ነው። +24 ደግሞም የይሖዋ* ሕግ በሚያዘው መሠረት “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች”+ መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። +25 እነሆም፣ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እሱም አምላክ እስራኤልን የሚያጽናናበትን+ ጊዜ የሚጠባበቅ ጻድቅና ለአምላክ ያደረ ሰው ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእሱ ላይ ነበር። +26 በተጨማሪም ይሖዋ* የቀባውን* ሳያይ እንደማይሞት አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ገልጦለት ነበር። +27 እሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መጣ፤ ሕጉ ለልጁ* እንዲደረግ በሚያዘው የተለመደ ሥርዓት መሠረት+ ወላጆቹ ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘውት በገቡ ጊዜ +28 ስምዖን ሕፃኑን ተቀብሎ አቀፈውና አምላክን አወደሰ፤ እንዲህም አለ፦ +29 “ሉዓላዊው ጌታ ሆይ፣ በተናገርከው ቃል መሠረት አሁን ባሪያህን በሰላም እንዲያርፍ ታደርገዋለህ፤+ +30 ምክንያቱም ዓይኖቼ ሰዎችን የምታድንበትን መንገድ አይተዋል፤+ +31 ይህም በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፤+ +32 ደግሞም ብሔራትን የጋረደውን መሸፈኛ+ የሚገልጥ ብርሃን+ እንዲሁም የሕዝብህ የእስራኤል ክብር ነው።” +33 አባቱና እናቱም ስለ ልጁ በሚነገሩት ነገሮች ይደነቁ ነበር። +34 ስምዖንም እነሱን ከባረካቸው በኋላ እናቱን ማርያምን እንዲህ አላት፦ “እነሆ፣ ይህ ልጅ በእስራኤል ለብዙዎች መውደቅም+ ሆነ መነሳት+ ምክንያት ይሆናል፤ እንዲሁም ብዙዎች የሚቃወሙት ምልክት ይሆናል፤+ +35 ይህም የሚሆነው በብዙዎች ልብ ውስጥ ያለው ሐሳብ ይገለጥ ዘንድ ነው፤ በአንቺም ውስጥ* ትልቅ ሰይፍ ያልፋል።”+ +36 ከአሴር ነገድ፣ የፋኑኤል ልጅ የሆነች ሐና የምትባል ነቢዪት ነበረች። ይህች ሴት በዕድሜ የገፋች ነበረች፤ ካገባች በኋላ* ከባሏ ጋር የኖረችው ለሰባት ዓመት ብቻ ነበር፤ +37 በዚህ ጊዜ 84 ዓመት የሆናት መበለት ነበረች። ሌትና ቀንም በጾምና በምልጃ ቅዱስ አገልግሎት እያቀረበች ከቤተ መቅደስ ፈጽሞ አትጠፋም ነበር። +38 በዚያን ሰዓትም ቀርባ አምላክን ታመሰግን ጀመር፤ አምላክ ኢየሩሳሌምን ነፃ ያወጣል ብለው ለሚጠባበቁም ሁሉ ስለ ሕፃኑ መናገር ጀመረች።+ +39 የይሖዋ* ሕግ በሚለው መሠረት+ ሁሉንም ነገር ከፈጸሙ በኋላ በገሊላ ወደምትገኘው ወደ መኖሪያ ከተማቸው ወደ ናዝሬት+ ተመለሱ። +40 ሕፃኑም እያደገና እየጠነከረ እንዲሁም በጥበብ እየተሞላ ሄደ፤ የአምላክም ሞገስ በእሱ ላይ ነበር።+ +41 ወላጆቹም በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል* ወደ ኢየሩሳሌም የመሄድ ልማድ ነበራቸው።+ +42 ኢየሱስ የ12 ዓመት ልጅ ሳለ እንደተለመደው በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።+ +43 በዓሉ የሚከበርባቸው ቀናት ተጠናቀው መመለስ በጀመሩ ጊዜ ኢየሱስ እዚያው ኢየሩሳሌም ቀረ፤ ወላጆቹም ይህን አላስተዋሉም ነበር። +44 አብረዋቸው ከሚጓዙት ሰዎች ጋር ያለ ስለመሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፤ በኋላም ዘመዶቻቸውና የሚያውቋቸው ሰዎች ጋ ይፈልጉት ጀመር። +45 ባጡት ጊዜ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ እሱን ለማግኘትም ብዙ ደከሙ። +46 በመጨረሻም ከሦስት ቀን በኋላ ቤተ መቅደሱ ውስጥ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲያዳምጣቸውና ሲጠይቃቸው አገኙት። +47 በዚያ የነበሩት ሰዎችም ሁሉ በመረዳት ችሎታውና በመልሱ ተደንቀው ያዳምጡት ነበር።+ +48 ወላጆቹም ባዩት ጊዜ ተገረሙ፤ እናቱም “ልጄ፣ ምነው እንዲህ አደረግከን? እኔና አባትህ እኮ በጣም ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር” አለችው። +49 እሱ ግን “ለምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት መሆን እንደሚገባኝ አታውቁም?” አላቸው።+ +50 እነሱ ግን ምን እያላቸው እንዳለ አልገባቸውም። +51 ከዚያም ኢየሱስ አብሯቸው ወደ ናዝሬት ተመለሰ፤ እንደ ወትሮውም ይገዛላቸው* ነበር።+ እናቱም የተባሉትን ነገሮች ሁሉ በልቧ ትይዝ ነበር።+ +52 ኢየሱስም በአካልና በጥበብ እያደገ እንዲሁም በአምላክና በሰው ፊት ይበልጥ ሞገስ እያገኘ ሄደ። +4 ከዚያም ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ተመለሰ፤ በምድረ በዳም ሳለ መንፈስ ይመራው ነበር፤+ +2 በዚያም 40 ቀን ቆየ፤ ዲያብሎስም ፈተነው።+ በእነዚህም ቀናት ምንም ስላልበላ መጨረሻ ላይ ተራበ። +3 በዚህ ጊዜ ዲያብሎስ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ይህ ድንጋይ ዳቦ እንዲሆን እዘዝ” አለው። +4 ኢየሱስ ግን “‘ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰለት።+ +5 ዲያብሎስም ወደ አንድ ከፍ ያለ ቦታ አወጣውና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።+ +6 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ይህ ሁሉ ሥልጣንና የእነዚህ መንግሥታት ክብር ተሰጥቶኛል፤+ እኔ ደግሞ ለፈለግኩት መስጠት ስለምችል ለአንተ እሰጥሃለሁ። +7 ስለዚህ አንድ ጊዜ በፊቴ ተደፍተህ ብታመልከኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።” +8 ኢየሱስም መልሶ “‘ይሖዋ* አምላክህን ብቻ አምልክ፤ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው።+ +9 ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ከወሰደው በኋላ በቤተ መቅደሱ አናት* ላይ አቁሞ እንዲህ አለው፦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤+ +10 እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘አንተን እንዲጠብቁ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል።’ +11 እንዲሁም ‘እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው በእጃቸው ያነሱሃል።’”+ +12 ኢየሱስም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* አትፈታተነው’ ተብሏል” አለው።+ +13 ዲያብሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ትቶት ሄደ።+ +14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ።+ ዝናውም በዙሪያው ባለ አገር ሁሉ ተሰራጨ። +15 በ��ጨማሪም በምኩራቦቻቸው ማስተማር ጀመረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ያከብረው ነበር። +16 ከዚያም ወዳደገበት ቦታ ወደ ናዝሬት መጣ፤+ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገባ፤+ ሊያነብም ተነስቶ ቆመ። +17 የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልልም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም ተርትሮ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ቦታ አገኘ፦ +18 “የይሖዋ* መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ምክንያቱም ለድሆች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል። ለተማረኩት ነፃነትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቆኑትን ነፃ እንዳወጣ+ +19 እንዲሁም የይሖዋን* ሞገስ ስለሚያገኙበት ዓመት+ እንድሰብክ ልኮኛል።” +20 ከዚያም ጥቅልሉን ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኩራቡ ውስጥ ያሉት ሰዎችም ሁሉ ትኩር ብለው ይመለከቱት ነበር። +21 እሱም “ይህ አሁን የሰማችሁት የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል ዛሬ ተፈጸመ” አላቸው።+ +22 ሁሉም ስለ እሱ መልካም ነገር ይናገሩ ጀመር፤ ከአፉ በሚወጡት የሚማርኩ ቃላትም+ በመደነቅ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለም እንዴ?” ይሉ ነበር።+ +23 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “‘አንተ ሐኪም፣ እስቲ ራስህን አድን’ የሚለውን አባባል እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም። ‘በቅፍርናሆም+ እንደተደረገ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ አገርም አድርግ’ ትሉኛላችሁ።” +24 እንዲህም አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ነቢይ በገዛ አገሩ ተቀባይነት አያገኝም።+ +25 እውነቱን ልንገራችሁ፦ ለምሳሌ በኤልያስ ዘመን ሰማይ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር በተዘጋና በምድሪቱ ሁሉ ላይ ጽኑ ረሃብ በተከሰተ ጊዜ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ።+ +26 ሆኖም ኤልያስ በሲዶና አገር በሰራፕታ ትኖር ወደነበረች አንዲት መበለት ተላከ እንጂ ከእነዚህ ሴቶች ወደ አንዷም አልተላከም።+ +27 በተጨማሪም በነቢዩ ኤልሳዕ ዘመን በእስራኤል ብዙ የሥጋ ደዌ በሽተኞች ነበሩ፤ ሆኖም ከሶርያዊው ከንዕማን በስተቀር ከእነሱ መካከል አንድም ሰው አልነጻም።”*+ +28 በምኩራቡ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ይህን ሲሰሙ እጅግ ተቆጡ፤+ +29 ተነስተውም እያጣደፉ ከከተማው አስወጡት፤ ቁልቁል ገፍትረው ሊጥሉትም ፈልገው ከተማቸው ወደምትገኝበት ተራራ አፋፍ ወሰዱት። +30 እሱ ግን በመካከላቸው ሰንጥቆ ሄደ።+ +31 ከዚያም በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ወረደ። እዚያም በሰንበት ሕዝቡን ያስተምር ነበር፤+ +32 በሥልጣን ይናገር ስለነበረም ሕዝቡ በትምህርት አሰጣጡ እጅግ ተደነቁ።+ +33 በምኩራቡም ውስጥ ርኩስ መንፈስ ማለትም ጋኔን ያደረበት አንድ ሰው ነበር፤ ሰውየውም በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ጮኸ፦+ +34 “እንዴ! የናዝሬቱ ኢየሱስ፣+ እኛ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለን? የመጣኸው ልታጠፋን ነው? ማን እንደሆንክ በሚገባ አውቃለሁ፤ አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ ነህ።”+ +35 ሆኖም ኢየሱስ “ዝም በል፤ ከእሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም ሰውየውን በሕዝቡ ፊት ከጣለው በኋላ ምንም ሳይጎዳው ለቆት ወጣ። +36 በዚህ ጊዜ ሁሉም በመገረም “እንዴ! ይህ ምን ዓይነት አነጋገር ነው? ርኩሳን መናፍስትን በሥልጣንና በኃይል ያዛል፤ እነሱም ታዘው ይወጣሉ!” ሲሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር። +37 ስለ ኢየሱስ የሚወራው ወሬም በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተዳረሰ። +38 ኢየሱስ ከምኩራቡ ከወጣ በኋላ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት ኃይለኛ ትኩሳት ይዟት እየተሠቃየች ነበር፤ እነሱም እንዲረዳት ለመኑት።+ +39 እሱም አጠገቧ ቆመና ጎንበስ ብሎ ትኩሳቱን ገሠጸው፤ ትኩሳቱም ለቀቃት። ወዲያውም ተነስታ ታገለግላቸው ጀመር። +40 ፀሐይ ስትጠልቅም ሰዎች በተለያየ በሽታ የተያዙ ሕመምተኞቻቸውን ወደ እሱ አመጡ። እሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን በመጫን ፈወሳቸው።+ +41 አጋንንትም “አንተ የአምላክ ልጅ ነህ” እያሉና እየጮኹ+ ከብዙ ሰዎች ወጡ። እሱ ግን ገሠጻቸው፤ ክርስቶስ መሆኑንም አውቀው ስለነበር+ እንዳይናገሩ ከለከላቸው።+ +42 በነጋም ጊዜ ወጥቶ ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ።+ ሕዝቡ ግን ፈልገው ፈላልገው * ያለበት ቦታ ድረስ መጡ፤ እንዳይሄድባቸውም ለመኑት። +43 እሱ ግን “ለሌሎች ከተሞችም የአምላክን መንግሥት ምሥራች ማወጅ አለብኝ፤ ምክንያቱም የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው” አላቸው።+ +44 በመሆኑም በይሁዳ ምኩራቦች መስበኩን ቀጠለ። +16 ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ሀብታም ሰው አንድ መጋቢ* ነበረው፤ ይህ ሰው፣ መጋቢው ንብረቱን እያባከነበት እንዳለ የሚገልጽ ክስ ደረሰው። +2 ስለዚህ መጋቢውን ጠራውና ‘ይህ ስለ አንተ የምሰማው ነገር ምንድን ነው? ከዚህ በኋላ ቤቱን ማስተዳደር ስለማትችል በመጋቢነት ስትሠራበት የነበረውን የሒሳብ መዝገብ አስረክበኝ’ አለው። +3 በዚህ ጊዜ መጋቢው በልቡ እንዲህ አለ፦ ‘ጌታዬ የመጋቢነት ኃላፊነቴን ሊወስድብኝ ነው፤ ታዲያ ምን ባደርግ ይሻላል? እንዳልቆፍር አቅም የለኝም፤ እንዳልለምን ያሳፍረኛል። +4 ቆይ፣ ምን እንደማደርግ አውቃለሁ! ከመጋቢነት ኃላፊነቴ ስነሳ ሰዎች በቤታቸው እንዲቀበሉኝ አንድ ነገር አደርጋለሁ።’ +5 ከዚያም ከጌታው የተበደሩትን ሰዎች አንድ በአንድ በመጥራት የመጀመሪያውን ‘ከጌታዬ የተበደርከው ምን ያህል ነው?’ አለው። +6 እሱም ‘አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ* የወይራ ዘይት’ ሲል መለሰለት። መጋቢውም ‘የውል ሰነድህ ይኸውልህ፤ ቁጭ በልና ቶሎ ብለህ 50 ብለህ ጻፍ’ አለው። +7 ቀጥሎም ሌላውን ‘አንተስ፣ የተበደርከው ምን ያህል ነው?’ አለው። እሱም ‘አንድ መቶ የቆሮስ መስፈሪያ* ስንዴ’ አለው። መጋቢውም ‘የውል ሰነድህ ይኸውልህ፤ 80 ብለህ ጻፍ’ አለው። +8 ጌታውም መጋቢው ዓመፀኛ ቢሆንም እንኳ አርቆ በማሰብ* ባደረገው ነገር አደነቀው፤ ምክንያቱም የዚህ ሥርዓት* ልጆች በእነሱ ትውልድ ካሉት ሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ረገድ ከብርሃን ልጆች+ ይበልጥ ብልሆች ናቸው። +9 “ደግሞም እላችኋለሁ፦ በዓመፅ ሀብት ለራሳችሁ ወዳጆች አፍሩ፤+ እነሱም የዓመፅ ሀብት ሲያልቅ በዘላለማዊ መኖሪያ ይቀበሏችኋል።+ +10 በትንሽ ነገር ታማኝ የሆነ ሰው በብዙ ነገርም ታማኝ ነው፤ በትንሽ ነገር ታማኝ ያልሆነ ሰው ደግሞ በብዙ ነገርም ታማኝ አይሆንም። +11 ስለዚህ በዓመፅ ሀብት ታማኝ ሆናችሁ ካልተገኛችሁ እውነተኛውን ሀብት ማን በአደራ ይሰጣችኋል? +12 የሌላ ሰው በሆነው ነገር ታማኝ ሆናችሁ ካልተገኛችሁ ለእናንተ የታሰበውን ማን ይሰጣችኋል?+ +13 ለሁለት ጌቶች ባሪያ መሆን የሚችል አገልጋይ የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል ወይም አንዱን ደግፎ ሌላውን ይንቃል። ለአምላክም ለሀብትም በአንድ ጊዜ ባሪያ መሆን አትችሉም።”+ +14 ገንዘብ ወዳድ የሆኑት ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሲናገር ሰምተው ያፌዙበት ጀመር።+ +15 በመሆኑም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ በሰዎች ፊት ጻድቅ መስላችሁ ትቀርባላችሁ፤+ አምላክ ግን ልባችሁን ያውቃል።+ በሰዎች ፊት ከፍ ተደርጎ የሚታየው ነገር በአምላክ ፊት አስጸያፊ ነውና።+ +16 “ሕጉም ሆነ የነቢያት ቃል እስከ ዮሐንስ ድረስ ሲነገሩ ቆይተዋል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ የአምላክ መንግሥት ምሥራች እየታወጀ ነው፤ የተለያዩ ዓይነት ሰዎችም ወደዚያ ለመግባት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ነው።+ +17 እንደ እውነቱ ከሆነ ከሕጉ የአንዷ ፊደል ጭረት ሳትፈጸም ከምትቀር ሰማይና ምድር ቢያልፉ ይቀላል።+ +18 “ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ባሏ የፈታትንም ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።+ +19 “አንድ ሀብታም ሰው ���በር፤ ይህ ሰው ሐምራዊ* ልብስና በፍታ ይለብስ የነበረ ከመሆኑም በላይ ዕለት ተዕለት በደስታና በቅንጦት ይኖር ነበር። +20 ይሁን እንጂ እዚህ ሰው ደጃፍ ላይ እያመጡ የሚያስቀምጡት መላ ሰውነቱን ቁስል የወረሰው አልዓዛር የሚባል አንድ ለማኝ ነበር፤ +21 እሱም ከሀብታሙ ማዕድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ በልቶ ለመጥገብ ይመኝ ነበር። ውሾችም* ሳይቀር እየመጡ ቁስሉን ይልሱ ነበር። +22 ከጊዜ በኋላ ለማኙ ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ* ወሰዱት። “ሀብታሙም ሰው ሞተና ተቀበረ። +23 በመቃብርም* ሆኖ እየተሠቃየ ሳለ አሻቅቦ ሲመለከት ከሩቅ አብርሃምንና በእቅፉ ያለውን አልዓዛርን አየ። +24 በዚህ ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ‘አብርሃም አባት ሆይ፣ በዚህ የሚንቀለቀል እሳት እየተሠቃየሁ ስለሆነ እባክህ ራራልኝና አልዓዛር የጣቱን ጫፍ ውኃ ውስጥ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ ላከው’ አለ። +25 አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፣ አንተ በሕይወት ዘመንህ መልካም ነገሮችን ሁሉ እንደተቀበልክ፣ አልዓዛር ግን መጥፎ ነገሮች እንደደረሱበት አስታውስ። አሁን ግን እሱ እዚህ ሲጽናና አንተ ትሠቃያለህ። +26 ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ ከእኛ ወደ እናንተ መሻገር የሚፈልጉ መሻገር እንዳይችሉ እንዲሁም ሰዎች ከእናንተ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል ተደርጓል።’ +27 በዚህ ጊዜ ሀብታሙ ሰው እንዲህ አለ፦ ‘አባት ሆይ፣ እንደዚያ ከሆነ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤት እንድትልከው እለምንሃለሁ፤ +28 አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ እነሱም ወደዚህ የሥቃይ ስፍራ እንዳይገቡ በሚገባ ይመሥክርላቸው።’ +29 አብርሃም ግን ‘ሙሴና ነቢያት አሉላቸው፤ እነሱን ይስሙ’ አለው።+ +30 እሱም ‘አይ፣ እንደሱ አይደለም፤ አብርሃም አባት ሆይ፣ አንድ ሰው ከሞት ተነስቶ ወደ እነሱ ቢሄድ ንስሐ ይገባሉ’ አለ። +31 አብርሃም ግን ‘ሙሴንና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ+ አንድ ሰው ከሞት ቢነሳም አምነው አይቀበሉም’ አለው።” +6 በአንድ የሰንበት ቀን ኢየሱስ በእህል እርሻ መካከል እያለፈ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ እሸት ቀጥፈው በእጃቸው እያሹ+ ይበሉ ነበር።+ +2 በዚህ ጊዜ አንዳንድ ፈሪሳውያን “በሰንበት ቀን በሕግ የተከለከለ ነገር የምታደርጉት ለምንድን ነው?” አሏቸው።+ +3 ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ዳዊት እሱና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ነገር ፈጽሞ አላነበባችሁም?+ +4 ወደ አምላክ ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር ማንም እንዲበላው ያልተፈቀደውን በአምላክ ፊት የቀረበ ኅብስት ተቀብሎ እንደበላና ከእሱ ጋር ለነበሩት እንደሰጣቸው አላነበባችሁም?”+ +5 ከዚያም “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው” አላቸው።+ +6 በሌላ የሰንበት ቀን+ ወደ ምኩራብ ገብቶ ያስተምር ጀመር። በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለ* አንድ ሰው ነበር።+ +7 ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም ኢየሱስን የሚከሱበት ምክንያት ማግኘት ይፈልጉ ስለነበር በሰንበት ይፈውስ እንደሆነ ለማየት በትኩረት ይከታተሉት ነበር። +8 እሱ ግን ሐሳባቸውን አውቆ+ ስለነበር እጁ የሰለለበትን* ሰው “ተነሳና መሃል ላይ ቁም” አለው። ሰውየውም ተነስቶ በዚያ ቆመ። +9 ከዚያም ኢየሱስ “እስቲ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ፤ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ? ሕይወት* ማዳን ነው ወይስ ማጥፋት?” አላቸው።+ +10 በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ ሰውየውን “እጅህን ዘርጋ” አለው። ሰውየውም እንደተባለው አደረገ፤ እጁም ዳነለት። +11 እነሱ ግን እጅግ ተቆጡ፤ በኢየሱስ ላይ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉም እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር። +12 በዚያው ሰሞን ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤+ ሌሊቱንም ሙሉ ወደ አም��ክ ሲጸልይ አደረ።+ +13 በነጋ ጊዜም ደቀ መዛሙርቱን ወደ እሱ ጠርቶ ከመካከላቸው 12 ሰዎች መረጠ፤ ሐዋርያት ብሎም ሰየማቸው፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦+ +14 ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው ስምዖን፣ ወንድሙ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊልጶስ፣+ በርቶሎሜዎስ፣ +15 ማቴዎስ፣ ቶማስ፣+ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ “ቀናተኛው” የሚባለው ስምዖን፣ +16 የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና በኋላ ከሃዲ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ። +17 ከእነሱም ጋር ከተራራው ወርዶ ደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ የሆኑ እጅግ ብዙ ሰዎችም በዚያ ነበሩ፤ በተጨማሪም እሱን ለመስማትና ከበሽታቸው ለመፈወስ ከይሁዳ ሁሉና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አካባቢ ከሚገኙት ከጢሮስና ከሲዶና የመጡ በጣም ብዙ ሰዎች ነበሩ። +18 በርኩሳን መናፍስት ይሠቃዩ የነበሩ ሰዎችም እንኳ ተፈወሱ። +19 ኃይል ከእሱ እየወጣ+ ሁሉንም ይፈውስ ስለነበር ሕዝቡ ሁሉ ሊነካው ይፈልግ ነበር። +20 ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ቀና ብሎ በመመልከት እንዲህ ይል ጀመር፦ “እናንተ ድሆች የሆናችሁ ደስተኞች ናችሁ፤ የአምላክ መንግሥት የእናንተ ነውና።+ +21 “እናንተ አሁን የምትራቡ ደስተኞች ናችሁ፤ ኋላ ትጠግባላችሁና።+ “እናንተ አሁን የምታለቅሱ ደስተኞች ናችሁ፤ ኋላ ትስቃላችሁና።+ +22 “ሰዎች፣ በሰው ልጅ ምክንያት በሚጠሏችሁ፣+ በሚያገሏችሁ፣+ በሚነቅፏችሁና ክፉ እንደሆናችሁ አድርገው ያለስማችሁ ስም በሚሰጧችሁ* ጊዜ ሁሉ ደስተኞች ናችሁ። +23 በሰማይ ታላቅ ሽልማት ስለሚጠብቃችሁ በዚያን ቀን ሐሴት አድርጉ፤ በደስታም ፈንጥዙ፤ አባቶቻቸው በነቢያት ላይ እንዲሁ ያደርጉ ነበርና።+ +24 “ነገር ግን እናንተ ሀብታሞች ወዮላችሁ፤+ መጽናኛችሁን* በሙሉ አግኝታችኋልና።+ +25 “እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፤ ኋላ ትራባላችሁና። “እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፤ ኋላ ታዝናላችሁና፤ እንዲሁም ታለቅሳላችሁ።+ +26 “ሰዎች ስለ እናንተ መልካም ነገር በሚናገሩበት ጊዜ ሁሉ ወዮላችሁ፤+ አባቶቻቸው ለሐሰተኛ ነቢያት እንዲህ ያለ ነገር አድርገው ነበርና። +27 “ለእናንተ ለምትሰሙ ግን እላችኋለሁ፦ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ፤+ +28 የሚረግሟችሁን መርቁ፤ እንዲሁም ለሚሰድቧችሁ ጸልዩ።+ +29 አንዱን ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ስጠው፤ መደረቢያህን ለሚወስድብህ እጀ ጠባብህንም አትከልክለው።+ +30 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤+ ንብረትህን የሚወስድብህንም ሰው እንዲመልስ አትጠይቀው። +31 “በተጨማሪም ልክ ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ እንደምትፈልጉት ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው።+ +32 “የሚወዷችሁን ብቻ ብትወዱ ምን የሚያስመሰግን ነገር አለው? ኃጢአተኞችም እንኳ የሚወዷቸውን ይወዳሉና።+ +33 መልካም ለሚያደርጉላችሁ መልካም ብታደርጉስ ምን ዋጋ አለው? ኃጢአተኞችም እንኳ እንዲሁ ያደርጋሉ። +34 እንዲሁም ይመልስልኛል ብላችሁ ለምታስቡት ሰው ብታበድሩ* ምን ፋይዳ አለው?+ ኃጢአተኞችም እንኳ የሰጡትን ያህል መልሰው ለመቀበል ለኃጢአተኞች ያበድራሉ። +35 ከዚህ ይልቅ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ደግሞም በምላሹ ምንም ሳትጠብቁ አበድሩ፤+ ሽልማታችሁም ታላቅ ይሆናል፤ ደግሞም የልዑሉ አምላክ ልጆች ትሆናላችሁ፤ እሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ደግ ነውና።+ +36 አባታችሁ መሐሪ እንደሆነ ሁሉ እናንተም መሐሪዎች ሁኑ።+ +37 “በተጨማሪም በሌሎች ላይ አትፍረዱ፤* በእናንተም ላይ ፈጽሞ አይፈረድባችሁም፤+ ሌሎችን አትኮንኑ፤ እናንተም ፈጽሞ አትኮነኑም። ምንጊዜም ሌሎችን ይቅር በሉ፤* እናንተም ይቅር ትባላላችሁ።*+ +38 ለሰዎች ስጡ፤ እነሱም ይሰጧችኋል።+ ተትረፍርፎ እስኪፈስ ድረስ በተጠቀጠቀና ��ተነቀነቀ ጥሩ መስፈሪያ ሰፍረው በእቅፋችሁ ይሰጧችኋል። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሰው ይሰፍሩላችኋልና።” +39 ከዚያም እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላል? ሁለቱም ተያይዘው ጉድጓድ ውስጥ አይወድቁም?+ +40 ተማሪ* ከአስተማሪው አይበልጥም፤ በሚገባ የተማረ ሁሉ ግን እንደ አስተማሪው ይሆናል። +41 ታዲያ በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለምን ታያለህ?+ +42 በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ ወንድምህን ‘ዓይንህ ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? አንተ ግብዝ! መጀመሪያ በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አጥርተህ ማየት ትችላለህ። +43 “መልካም ዛፍ ሆኖ ሳለ የበሰበሰ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም፤ እንዲሁም የበሰበሰ ዛፍ ሆኖ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም።+ +44 እያንዳንዱ ዛፍ በፍሬው ይታወቃል።+ ለምሳሌ ሰዎች ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፤ ወይም ከእሾሃማ ቁጥቋጦ ወይን አይቆርጡም። +45 ጥሩ ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር ጥሩ ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰው ግን ካከማቸው መጥፎ ነገር ክፉ ነገር ያወጣል፤ አንደበቱ የሚናገረው በልቡ ውስጥ የሞላውን ነውና።+ +46 “ታዲያ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የምትሉኝ፣ የምለውን ግን የማታደርጉት ለምንድን ነው?+ +47 ወደ እኔ የሚመጣ፣ ቃሌን የሚሰማና የሚያደርግ ሁሉ ከማን ጋር እንደሚመሳሰል ልንገራችሁ፦+ +48 ቤት ለመሥራት በጥልቀት ቆፍሮ በዓለት ላይ መሠረቱን ከጣለ ሰው ጋር ይመሳሰላል። በኋላም ጎርፍ በመጣ ጊዜ ወንዙ ቤቱን በኃይል መታው፤ ሆኖም ቤቱ በደንብ ስለተገነባ ሊያነቃንቀው አልቻለም።+ +49 በሌላ በኩል ደግሞ ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ሰው+ ሁሉ መሠረት ሳይጥል፣ በአፈር ላይ ቤት ከሠራ ሰው ጋር ይመሳሰላል። ወንዙም ቤቱን በኃይል መታው፤ ወዲያውም ተደረመሰ፤ እንዳልነበረም ሆነ።” +10 ከዚህ በኋላ ጌታ ሌሎች 70* ሰዎችን ሾመ፤ እሱ ሊሄድበት ወዳሰበው ከተማና ቦታ ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱም ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው።+ +2 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “አዎ፣ አዝመራው ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂት ናቸው። ስለዚህ የመከሩ ሥራ ኃላፊ ወደ መከሩ፣ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።+ +3 እንግዲህ ሂዱ! እነሆ፣ በተኩላዎች መካከል እንዳሉ በጎች እልካችኋለሁ።+ +4 የገንዘብ ኮሮጆ ወይም የምግብ ከረጢት ወይም ትርፍ ጫማ አትያዙ፤+ በመንገድም ላይ ቆማችሁ ከማንም ጋር ሰላምታ አትለዋወጡ።* +5 ወደ ማንኛውም ቤት ስትገቡ በቅድሚያ ‘ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን’ በሉ።+ +6 በዚያም ሰላም ወዳድ ሰው ካለ ሰላማችሁ ያርፍበታል። ሰላም ወዳድ ሰው ከሌለ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል። +7 ለሠራተኛ ደሞዙ ስለሚገባው+ ያቀረቡላችሁን ነገር እየበላችሁና እየጠጣችሁ+ በዚያው ቤት ቆዩ።+ ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት አትዘዋወሩ። +8 “በተጨማሪም ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡ ሰዎቹ ከተቀበሏችሁ ያቀረቡላችሁን ብሉ፤ +9 እንዲሁም በዚያ ያሉትን በሽተኞች ፈውሱ፤ ደግሞም ‘የአምላክ መንግሥት ወደ እናንተ ቀርቧል’ በሏቸው።+ +10 ሆኖም ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡ ሰዎቹ ካልተቀበሏችሁ ወደ አውራ ጎዳናዎች ወጥታችሁ እንዲህ በሉ፦ +11 ‘በእግራችን ላይ ያለውን የከተማችሁን አቧራ እንኳ ሳይቀር አራግፈንላችሁ እንሄዳለን።+ ይሁንና የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ እወቁ።’ +12 እላችኋለሁ፦ በዚያ ቀን* ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶም ይቀልላታል።+ +13 “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ ውስጥ የተደረጉት ተአምራት በጢሮስና በሲዶና* ተደርገው ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ማቅ ለብሰውና አመድ ላይ ተቀምጠው ንስሐ በገቡ ነበር።+ +14 ስለዚህ በፍርድ ወቅት ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። +15 አንቺም ቅፍርናሆም ወደ ሰማይ ከፍ የምትዪ ይመስልሻል? በፍጹም! ወደ መቃብር* ትወርጃለሽ! +16 “እናንተን የሚሰማ ሁሉ እኔንም ይሰማል።+ እናንተን የማይቀበል ሁሉ ደግሞ እኔንም አይቀበልም። ከዚህም በላይ እኔን የማይቀበል ሁሉ የላከኝንም አይቀበልም።”+ +17 ከዚያም 70ዎቹ ደስ እያላቸው ተመልሰው “ጌታ ሆይ፣ አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዙልን” አሉት።+ +18 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ።+ +19 እነሆ፣ እባቦችንና ጊንጦችን እንድትረግጡ እንዲሁም የጠላትን ኃይል ሁሉ እንድትቋቋሙ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፤+ የሚጎዳችሁም አንዳች ነገር አይኖርም። +20 ይሁን እንጂ መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፤ ከዚህ ይልቅ ስማችሁ በሰማያት ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”+ +21 በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሴት አድርጎ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች+ ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ። አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ የአንተ ፈቃድ ነውና።+ +22 ሁሉንም ነገር አባቴ ሰጥቶኛል፤ ከአብ በስተቀር ወልድ ማን እንደሆነ የሚያውቅ የለም፤+ እንዲሁም ከወልድና ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በስተቀር አብ ማን እንደሆነ የሚያውቅ የለም።”+ +23 ከዚያም ብቻቸውን በነበሩበት ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ አሁን የምታዩትን ነገር የሚያዩ ዓይኖች ደስተኞች ናቸው።+ +24 እላችኋለሁ፣ ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ አሁን የምታዩትን ነገር ለማየት ተመኝተው ነበር፤ ግን አላዩም፤+ አሁን የምትሰሙትን ነገር ለመስማት ተመኝተው ነበር፤ ግን አልሰሙም።” +25 እነሆም አንድ ሕግ አዋቂ ኢየሱስን ሊፈትነው ተነስቶ “መምህር፣ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ አለብኝ?” አለው።+ +26 ኢየሱስም “በሕጉ ላይ የተጻፈው ምንድን ነው? አንተስ ምን ትረዳለህ?” አለው። +27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው። +28 ኢየሱስም “በትክክል መልሰሃል፤ ዘወትር ይህን አድርግ፤ ሕይወትም ታገኛለህ” አለው።+ +29 ሰውየው ግን ጻድቅ መሆኑን ለማሳየት ፈልጎ+ ኢየሱስን “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” አለው። +30 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በዘራፊዎች እጅ ወደቀ፤ እነሱም ከገፈፉትና ከደበደቡት በኋላ በሞትና በሕይወት መካከል ጥለውት ሄዱ። +31 እንደ አጋጣሚ አንድ ካህን በዚያ መንገድ ሲወርድ ሰውየውን አየውና ራቅ ብሎ አልፎት ሄደ። +32 በተመሳሳይም አንድ ሌዋዊ እዚያ ቦታ ሲደርስ አየውና ገለል ብሎ አልፎት ሄደ። +33 ሆኖም አንድ ሳምራዊ+ በዚያ መንገድ ሲጓዝ ሰውየው ወዳለበት ቦታ ደረሰ፤ ባየውም ጊዜ በጣም አዘነለት። +34 ስለሆነም ወደ ሰውየው ቀርቦ በቁስሎቹ ላይ ዘይትና የወይን ጠጅ አፍስሶ በጨርቅ አሰረለት። ከዚያም በራሱ አህያ ላይ ካስቀመጠው በኋላ ወደ አንድ የእንግዶች ማረፊያ በመውሰድ ተንከባከበው። +35 በማግስቱ ሁለት ዲናር* አውጥቶ ለእንግዶች ማረፊያ ቤቱ ባለቤት ሰጠውና ‘ይህን ሰው አስታመው፤ ከዚህ በላይ የምታወጣውን ተጨማሪ ወጪ ሁሉ ስመለስ እከፍልሃለሁ’ አለው። +36 ታዲያ ከእነዚህ ሦስት ሰዎች መካከል በዘራፊዎች እጅ ለወደቀው ሰው ባልንጀራ+ ሆኖ የተገኘው የትኛው ይመስልሃል?” +37 እሱም “ምሕረት በማሳየት የረዳው ነው” አለ።+ ከ���ያም ኢየሱስ “አንተም ሂድና እንዲሁ አድርግ” አለው።+ +38 እየተጓዙም ሳሉ ወደ አንድ መንደር ገባ። በዚያም ማርታ+ የምትባል አንዲት ሴት በቤቷ በእንግድነት ተቀበለችው። +39 እሷም ማርያም የምትባል እህት ነበረቻት፤ ማርያምም በጌታ እግር ሥር ተቀምጣ የሚናገረውን* ታዳምጥ ነበር። +40 ማርታ ግን በብዙ ሥራ ተጠምዳ ትባክን ነበር። በመሆኑም ወደ እሱ መጥታ “ጌታ ሆይ፣ እህቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ጥላ ስትቀመጥ ምንም ግድ አይሰጥህም? መጥታ እንድታግዘኝ ንገራት እንጂ” አለችው። +41 ጌታም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ማርታ፣ ማርታ፣ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ደግሞም ትጠበቢያለሽ። +42 ይሁንና የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድ ነገር ብቻ ነው። ማርያም በበኩሏ ጥሩ የሆነውን ድርሻ* መርጣለች፤+ ይህም ከእሷ አይወሰድም።” +14 በሌላ ወቅት ኢየሱስ በአንድ የሰንበት ቀን ከፈሪሳውያን መሪዎች ወደ አንዱ ቤት ምግብ ሊበላ በገባ ጊዜ በቤቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች በትኩረት ይከታተሉት ነበር። +2 በዚያም ሰውነት የሚያሳብጥ በሽታ* የያዘው አንድ ሰው ከፊት ለፊቱ ነበር። +3 ኢየሱስም ሕግ አዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን “በሰንበት መፈወስ በሕግ ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?” ሲል ጠየቃቸው።+ +4 እነሱ ግን ዝም አሉ። በዚህ ጊዜ በሰውየው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሰውና አሰናበተው። +5 ከዚያም “ከእናንተ መካከል ልጁ ወይም በሬው በሰንበት ቀን የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ቢወድቅ ወዲያውኑ ጎትቶ የማያወጣው ማን ነው?” አላቸው።+ +6 እነሱም ለዚህ መልስ ሊሰጡ አልቻሉም። +7 ኢየሱስ የተጋበዙት ሰዎች ለራሳቸው የክብር ቦታ ሲመርጡ+ ተመልክቶ እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ +8 “አንድ ሰው ወደ ሠርግ ሲጠራህ በክብር ቦታ አትቀመጥ።+ ምናልባት ከአንተ የበለጠ የተከበረ ሰው ተጠርቶ ሊሆን ይችላል። +9 በመሆኑም ሁለታችሁንም የጋበዘው ሰው መጥቶ ‘ቦታውን ለዚህ ሰው ልቀቅለት’ ይልሃል። በዚህ ጊዜ እያፈርክ ወደ ዝቅተኛው ቦታ ትሄዳለህ። +10 አንተ ግን ስትጋበዝ ሄደህ በዝቅተኛው ስፍራ ተቀመጥ፤ የጋበዘህም ሰው ሲመጣ ‘ወዳጄ ሆይ፣ ወደ ላይ ከፍ በል’ ይልሃል። በዚህ ጊዜ አብረውህ በተጋበዙት ሰዎች ሁሉ ፊት ክብር ታገኛለህ።+ +11 ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይደረጋልና፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ደግሞ ከፍ ይደረጋል።”+ +12 ቀጥሎ ደግሞ የጋበዘውን ሰው እንዲህ አለው፦ “የምሳ ወይም የራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ጓደኞችህን ወይም ወንድሞችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ሀብታም ጎረቤቶችህን አትጥራ። አለዚያ እነሱም ሊጋብዙህና ብድር ሊመልሱልህ ይችላሉ። +13 ሆኖም ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ አንካሶችንና ዓይነ ስውራንን ጥራ፤+ +14 ብድር ሊመልሱልህ ስለማይችሉ ደስተኛ ትሆናለህ። ምክንያቱም በጻድቃን ትንሣኤ+ ብድራት ይመለስልሃል።” +15 ከተጋበዙት መካከል አንዱ ይህን ሲሰማ “በአምላክ መንግሥት፣ ከማዕድ የሚበላ ደስተኛ ነው” አለው። +16 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “አንድ ሰው ትልቅ የራት ግብዣ አዘጋጅቶ+ ብዙ ሰዎች ጠራ። +17 የራት ግብዣው ሰዓት በደረሰ ጊዜ የተጋበዙትን ሰዎች ‘አሁን ሁሉም ነገር ስለተዘጋጀ ኑ’ ብሎ እንዲጠራቸው ባሪያውን ላከ። +18 ይሁን እንጂ ሁሉም ሰበብ ያቀርቡ ጀመር።+ የመጀመሪያው ‘እርሻ ስለገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝ፤ ስለዚህ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለው። +19 ሌላውም ‘አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ፤ ልፈትናቸው ስለሆነ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለ።+ +20 ሌላኛው ደግሞ ‘ገና ማግባቴ ስለሆነ መምጣት አልችልም’ አለ። +21 ባሪያውም መጥቶ ለጌታው ይህን ነገረው። በዚህ ጊዜ የቤቱ ጌታ ተቆጣ፤ ከዚያም ባሪያውን ‘ፈጥነህ ወደ ���ተማው አውራ ጎዳናዎችና ስላች መንገዶች ሄደህ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ ዓይነ ስውራንንና አንካሶችን ወደዚህ አምጣቸው’ አለው። +22 በኋላም ባሪያው ‘ጌታዬ፣ ያዘዝከው ተፈጽሟል፤ ያም ሆኖ አሁንም ቦታ አለ’ አለው። +23 በመሆኑም ጌታው ባሪያውን እንዲህ አለው፦ ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ጎዳናዎችና ወደ ስላች መንገዶች ሄደህ ያገኘሃቸውን ሰዎች በግድ አምጥተህ አስገባ።+ +24 እላችኋለሁ፣ ከእነዚያ ከተጋበዙት ሰዎች መካከል አንዳቸውም ያዘጋጀሁትን ራት አይቀምሱም።’”+ +25 ከዚያም እጅግ ብዙ ሕዝብ አብሮት እየተጓዘ ሳለ ወደ እነሱ ዞሮ እንዲህ አላቸው፦ +26 “ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱን፣ እናቱን፣ ሚስቱን፣ ልጆቹን፣ ወንድሞቹንና እህቶቹን ሌላው ቀርቶ የገዛ ራሱን ሕይወት* እንኳ የማይጠላ*+ ከሆነ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።+ +27 የራሱን የመከራ እንጨት* ተሸክሞ የማይከተለኝ ሁሉ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።+ +28 ለምሳሌ ከእናንተ መካከል፣ ግንብ ለመገንባት ፈልጎ ለመጨረስ የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳለው ለማወቅ በመጀመሪያ ተቀምጦ ወጪውን የማያሰላ ማን ነው? +29 እንዲህ ካላደረገ ግን መሠረቱን ከጣለ በኋላ ፍጻሜ ላይ ማድረስ ሊያቅተውና የሚያዩት ሰዎች ሁሉ ሊያፌዙበት ይችላሉ፤ +30 ‘ይህ ሰው መገንባት ጀምሮ ነበር፤ መጨረስ ግን አቃተው’ ይሉታል። +"31 ወይም ደግሞ አንድ ንጉሥ ሌላን ንጉሥ ጦርነት ለመግጠም በሚነሳበት ጊዜ 20,000 ሠራዊት አስከትቶ የመጣበትን ንጉሥ በ10,000 ሠራዊት ሊቋቋመው ይችል እንደሆነ ለማወቅ በቅድሚያ ተቀምጦ አይማከርም?" +32 መቋቋም የማይችል ከሆነ ሊገጥመው የሚመጣው ንጉሥ ገና ሩቅ ሳለ አምባሳደሮች* ልኮ እርቅ ለመፍጠር ይደራደራል። +33 እንደዚሁም ከእናንተ መካከል ያለውን ንብረት ሁሉ የማይሰናበት* ፈጽሞ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።+ +34 “ጨው ጥሩ ነገር እንደሆነ የታወቀ ነው። ሆኖም ጨው ራሱ የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን በምን መመለስ ይቻላል?+ +35 እንዲህ ያለ ጨው ለአፈር የሚሰጠው ጥቅም የለም፤ ማዳበሪያም ሊሆን አይችልም። በመሆኑም ሰዎች ወደ ውጭ ይጥሉታል። ስለዚህ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”+ +9 ከዚያም አሥራ ሁለቱን አንድ ላይ ጠርቶ አጋንንትን ሁሉ የማዘዝ+ እንዲሁም በሽታን የመፈወስ+ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው። +2 ደግሞም የአምላክን መንግሥት እንዲሰብኩና የታመሙትን እንዲፈውሱ ላካቸው፤ +3 እንዲህም አላቸው፦ “ለጉዟችሁ ምንም ነገር አትያዙ፤ በትርም ሆነ የምግብ ከረጢት፣ ዳቦም ሆነ ገንዘብ* እንዲሁም ሁለት ልብስ* አትያዙ።+ +4 ሆኖም ወደ አንድ ቤት ስትገቡ ከተማዋን ለቃችሁ እስክትሄዱ ድረስ እዚያው ቆዩ፤+ ከዚያም ተነስታችሁ ሂዱ። +5 በየትኛውም ከተማ የሚቀበላችሁ ሰው ካጣችሁ፣ ከዚያ ከተማ ስትወጡ ምሥክር እንዲሆንባቸው የእግራችሁን አቧራ አራግፉ።”*+ +6 እነሱም ወጥተው በሄዱበት ሁሉ ምሥራቹን እየተናገሩና የታመሙትን እየፈወሱ ከመንደር ወደ መንደር በመሄድ ክልሉን አዳረሱ።+ +7 በዚህ ጊዜ የአውራጃ* ገዢ የሆነው ሄሮድስ* የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ አንዳንዶች ዮሐንስ ከሞት ተነስቷል ይሉ ስለነበረም በጣም ግራ ተጋባ፤+ +8 ይሁንና ሌሎች ኤልያስ ተገልጧል፤ ሌሎች ደግሞ ከጥንት ነቢያት አንዱ ተነስቷል ይሉ ነበር።+ +9 ሄሮድስም “ዮሐንስን አንገቱን ቆርጬዋለሁ።+ ታዲያ እንዲህ ሲወራለት የምሰማው ይህ ሰው ማን ነው?” አለ። ስለሆነም ሊያየው ይፈልግ ነበር።+ +10 ሐዋርያቱም በተመለሱ ጊዜ ያደረጉትን ነገር ሁሉ ለኢየሱስ ተረኩለት።+ እሱም ቤተሳይዳ ወደምትባል ከተማ ብቻቸውን ይዟቸው ሄደ።+ +11 ሆኖም ሕዝቡ ይህን ስላወቁ ተከተሉት። እሱም በደግነት ተቀብሎ ስለ አምላክ መንግሥት ይነግራቸው ጀመር፤ ፈውስ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው።+ +12 ቀኑም መምሸት ሲጀምር አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ወደ እሱ መጥተው “ያለንበት ስፍራ ገለል ያለ ስለሆነ ሕዝቡ በአካባቢው ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት።+ +13 እሱ ግን “እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው።+ እነሱም “ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ምግብ ካልገዛን በስተቀር ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ ሌላ ምንም የለንም” አሉት። +"14 በዚያም 5,000 ያህል ወንዶች ነበሩ። እሱ ግን ደቀ መዛሙርቱን “ሕዝቡን በሃምሳ በሃምሳ ከፋፍላችሁ አስቀምጧቸው” አላቸው።" +15 እነሱም በታዘዙት መሠረት ሕዝቡ እንዲቀመጥ አደረጉ። +16 ከዚያም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ። ቆርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። +17 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ +18 በኋላም ብቻውን ሆኖ እየጸለየ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ መጡ፤ እሱም “ሕዝቡ እኔን ማን ይሉኛል?” ሲል ጠየቃቸው።+ +19 እነሱም መልሰው “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ከጥንት ነቢያት አንዱ ተነስቷል ይላሉ” አሉት።+ +20 እሱም “እናንተስ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ “የአምላክ መሲሕ ነህ”* አለው።+ +21 ከዚያም ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አስጠነቀቃቸው፤+ +22 ቀጥሎም “የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበሉ፣ እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት ተቀባይነት ማጣቱ ብሎም መገደሉና+ በሦስተኛው ቀን መነሳቱ+ አይቀርም” አላቸው። +23 ከዚያም ለሁሉም እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ፤+ የራሱን የመከራ እንጨት* በየዕለቱ ይሸከም፤ ያለማቋረጥም ይከተለኝ።+ +24 ሕይወቱን* ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔ ሲል ሕይወቱን* የሚያጣ ሁሉ ግን ያድናታል።+ +25 ደግሞስ አንድ ሰው ዓለምን ሁሉ የራሱ ቢያደርግ፣ ነገር ግን ሕይወቱን ቢያጣ ወይም ለጉዳት ቢዳረግ ምን ይጠቅመዋል?+ +26 በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅም በክብሩ እንዲሁም በአብና በቅዱሳን መላእክት ክብር ሲመጣ ያፍርበታል።+ +27 እውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆሙት መካከል አንዳንዶች የአምላክን መንግሥት እስኪያዩ ድረስ ፈጽሞ ሞትን አይቀምሱም።”+ +28 በመሆኑም ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ያህል በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ።+ +29 እየጸለየም ሳለ የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ነጭ ሆኖ አንጸባረቀ። +30 እነሆም ሁለት ሰዎች ይኸውም ሙሴና ኤልያስ ከእሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር። +31 እነሱም በክብር ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ስለሚፈጸመውና ከዚህ ዓለም ተለይቶ ስለሚሄድበት ሁኔታ ይነጋገሩ ጀመር።+ +32 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና አብረውት የነበሩት እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ነበር፤ ሙሉ በሙሉ ሲነቁ ግን የኢየሱስን ክብር እንዲሁም አብረውት የቆሙትን ሁለት ሰዎች አዩ።+ +33 ሰዎቹ ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ ጴጥሮስ ኢየሱስን “መምህር፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። ስለዚህ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴና አንድ ለኤልያስ ሦስት ድንኳኖች እንትከል” አለው፤ ምን እየተናገረ እንዳለ አላስተዋለም ነበር። +34 ይህን እየተናገረ ሳለ ግን ደመና መጥቶ ጋረዳቸው። ደመናው ሲሸፍናቸው ፍርሃት አደረባቸው። +35 ከዚያም ከደመናው “የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ መጣ።+ +36 ድምፁም በተሰማ ጊዜ ኢየሱስን ብቻውን ሆኖ አዩት። እነሱም ዝም አሉ፤ ያዩትንም ነገር በዚያን ወቅት ለማንም አልተናገሩም።+ +37 በማግስቱ ከተራራው ሲወርዱ ���ጅግ ብዙ ሕዝብ ከኢየሱስ ጋር ተገናኘ።+ +38 እነሆም ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “መምህር፣ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ፤ ምክንያቱም ያለኝ ልጅ አንድ እሱ ብቻ ነው።+ +39 እነሆም፣ ርኩስ መንፈስ ይይዘውና በድንገት ይጮኻል፤ ጥሎም በአፉ አረፋ እያስደፈቀ ያንፈራግጠዋል፤ ጉዳት ካደረሰበትም በኋላ በስንት መከራ ይለቀዋል። +40 ደቀ መዛሙርትህ እንዲያስወጡት ለመንኳቸው፤ እነሱ ግን አልቻሉም።” +41 ኢየሱስም መልሶ “እምነት የለሽና ጠማማ ትውልድ ሆይ፣+ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር መቆየትና እናንተን መታገሥ ሊኖርብኝ ነው? እስቲ ልጅህን ወደዚህ አምጣው” አለ።+ +42 ሆኖም ወደ እሱ እየመጣ ሳለ ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ በኃይል አንፈራገጠው። ይሁንና ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ገሠጸውና ልጁን ፈወሰው፤ ከዚያም ለአባቱ መልሶ ሰጠው። +43 በዚህ ጊዜ ሁሉም በአምላክ ታላቅ ኃይል ተደነቁ። ሰዎቹ ኢየሱስ ባደረገው ነገር ሁሉ እየተደነቁ ሳሉ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ +44 “ይህን የምነግራችሁን ቃል በጥሞና አዳምጡ፤ ደግሞም አስታውሱ፤ የሰውን ልጅ ለሰዎች አሳልፈው ይሰጡታልና።”+ +45 እነሱ ግን የነገራቸው ነገር አልገባቸውም። እንዲያውም እንዳያስተውሉት ነገሩ ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ጉዳይ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። +46 ከዚህ በኋላ ከመካከላቸው ማን እንደሚበልጥ እርስ በርሳቸው ይከራከሩ ጀመር።+ +47 ኢየሱስ የልባቸውን ሐሳብ ስላወቀ አንድ ትንሽ ልጅ አምጥቶ አጠገቡ አቆመ፤ +48 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ የላከኝንም ይቀበላል።+ ምክንያቱም ታላቅ የሚባለው ራሱን ከሁላችሁ እንደሚያንስ አድርጎ የሚቆጥር ነው።”+ +49 ዮሐንስም “መምህር፣ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያስወጣ አየን፤ ይሁንና ከእኛ ጋር ሆኖ አንተን ስለማይከተል ልንከለክለው ሞከርን” አለው።+ +50 ኢየሱስ ግን “የማይቃወማችሁ ሁሉ ከእናንተ ጋር ስለሆነ አትከልክሉት” አለው። +51 ኢየሱስ የሚያርግበት+ ጊዜ ሲቃረብ* ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቆርጦ ተነሳ። +52 ስለዚህ አስቀድሞ መልእክተኞች ላከ። እነሱም ሄደው ለእሱ የሚያስፈልገውን ነገር ለማዘጋጀት ወደ አንድ የሳምራውያን መንደር ገቡ። +53 ሕዝቡ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቆርጦ እንደተነሳ* ስላወቁ አልተቀበሉትም።+ +54 ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ+ ይህን ባዩ ጊዜ “ጌታ ሆይ፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝ ትፈልጋለህ?” አሉት።+ +55 እሱ ግን ዞር ብሎ ገሠጻቸው። +56 ስለዚህ ወደ ሌላ መንደር ሄዱ። +57 በመንገድ እየተጓዙም ሳሉ አንድ ሰው “ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው። +58 ኢየሱስ ግን “ቀበሮዎች ጉድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ቦታ የለውም” አለው።+ +59 ከዚያም ሌላውን “ተከታዬ ሁን” አለው። ሰውየውም “ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው።+ +60 እሱ ግን “ሙታን+ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው፤ አንተ ግን ሄደህ የአምላክን መንግሥት በየቦታው አውጅ” አለው።+ +61 አንድ ሌላ ሰው ደግሞ “ጌታ ሆይ፣ እኔ እከተልሃለሁ፤ በመጀመሪያ ግን ቤተሰቤን እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለው። +62 ኢየሱስም “ዕርፍ ጨብጦ በኋላው ያሉትን ነገሮች የሚመለከት ሰው+ ለአምላክ መንግሥት የሚገባ አይደለም” አለው።+ +13 በወቅቱ፣ በዚያ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስለደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች ለኢየሱስ አወሩለት። +2 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እነዚህ የገሊላ ሰዎች ይህ ስለደረሰባቸው ከሌሎቹ የገሊ�� ሰዎች ይበልጥ ኃጢአተኞች እንደሆኑ አድርጋችሁ ታስባላችሁ? +3 በፍጹም፤ ነገር ግን ንስሐ ካልገባችሁ ሁላችሁም እንደ እነሱ ትጠፋላችሁ።+ +4 ወይም ደግሞ የሰሊሆም ግንብ ተንዶባቸው የሞቱት 18 ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ይበልጥ በደለኞች የነበሩ ይመስላችኋል? +5 በፍጹም፤ ነገር ግን ንስሐ ካልገባችሁ ሁላችሁም ልክ እንደ እነሱ ትጠፋላችሁ።” +6 ከዚያም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ተናገረ፦ “አንድ ሰው በወይን እርሻው ውስጥ የተተከለች አንዲት የበለስ ዛፍ ነበረችው፤ እሱም ከዛፏ ፍሬ ሊለቅም መጣ፤ ሆኖም ምንም አላገኘባትም።+ +7 በዚህ ጊዜ የወይን አትክልት ሠራተኛውን ‘ከዚህች የበለስ ዛፍ ፍሬ ለማግኘት ሦስት ዓመት ሙሉ ተመላለስኩ፤ ሆኖም ምንም አላገኘሁባትም። ስለዚህ ቁረጣት! ለምን በከንቱ ቦታ ትይዛለች?’ አለው። +8 እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ ‘ጌታዬ፣ ዙሪያዋን ቆፍሬ ፍግ ላድርግባትና እስቲ ለአንድ ዓመት ደግሞ እንያት። +9 ወደፊት ፍሬ ካፈራች ጥሩ፤ ካልሆነ ግን ትቆርጣታለህ።’”+ +10 ኢየሱስ በሰንበት ቀን አንድ ምኩራብ ውስጥ እያስተማረ ነበር። +11 በዚያም ባደረባት ክፉ መንፈስ የተነሳ ለ18 ዓመት በበሽታ ስትማቅቅ የኖረች* አንዲት ሴት ነበረች፤ በጣም ከመጉበጧም የተነሳ ፈጽሞ ቀና ማለት አትችልም ነበር። +12 ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና “አንቺ ሴት፣ ከበሽታሽ ተገላግለሻል” አላት።+ +13 እጁንም ጫነባት፤ ወዲያውም ቀጥ አለች፤ አምላክንም ማመስገን ጀመረች። +14 የምኩራቡ አለቃ ግን ኢየሱስ በሰንበት ቀን በመፈወሱ ተቆጥቶ ሕዝቡን “ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤+ ስለዚህ በእነዚያ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይደለም” አላቸው።+ +15 ይሁን እንጂ ጌታ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እናንተ ግብዞች፣+ እያንዳንዳችሁ በሰንበት ቀን በሬያችሁን ወይም አህያችሁን ከጋጣው ፈታችሁ ውኃ ለማጠጣት ትወስዱ የለም?+ +16 ታዲያ የአብርሃም ልጅ የሆነችውና 18 ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ የኖረችው ይህች ሴት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራቷ መፈታት አይገባትም?” +17 ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ሁሉ በኀፍረት ተሸማቀቁ፤ ሕዝቡ በሙሉ ግን እሱ ባደረጋቸው አስደናቂ ነገሮች+ ሁሉ ይደሰቱ ጀመር። +18 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የአምላክ መንግሥት ከምን ጋር ይመሳሰላል? ከምንስ ጋር ላነጻጽረው? +19 አንድ ሰው ወስዶ በአትክልት ቦታው ከዘራት የሰናፍጭ ዘር ጋር ይመሳሰላል፤ ይህች ዘር አድጋ ዛፍ ሆነች፤ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎቿ ላይ ሰፈሩ።”+ +20 ደግሞም እንዲህ አለ፦ “የአምላክን መንግሥት ከምን ጋር ላነጻጽረው? +21 አንዲት ሴት ወስዳ ሊጡ በሙሉ እስኪቦካ ድረስ ከሦስት ትላልቅ መስፈሪያ* ዱቄት ጋር ከደባለቀችው እርሾ ጋር ይመሳሰላል።”+ +22 ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዘ ሳለ በየከተማውና በየመንደሩ እያስተማረ ያልፍ ነበር። +23 በዚህ ጊዜ አንድ ሰው “ጌታ ሆይ፣ የሚድኑት ጥቂቶች ናቸው?” ሲል ጠየቀው። እሱም እንዲህ አላቸው፦ +24 “በጠባቡ በር ለመግባት ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጉ፤+ እላችኋለሁ፦ ብዙዎች ለመግባት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን አይችሉም። +25 የቤቱ ባለቤት ተነስቶ አንዴ በሩን ከዘጋው በኋላ ውጭ ቆማችሁ ‘ጌታ ሆይ፣ ክፈትልን’+ እያላችሁ በሩን ብታንኳኩ ‘ከየት እንደመጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል። +26 በዚህ ጊዜ ‘አብረንህ እኮ በልተናል፤ ደግሞም ጠጥተናል፤ በአውራ ጎዳናዎቻችንም አስተምረሃል’ ማለት ትጀምራላችሁ።+ +27 እሱ ግን ‘ከየት እንደመጣችሁ አላውቅም። እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፣ ከእኔ ራቁ!’ ይላችኋል። +28 አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብንና ነቢያትን ሁሉ በአምላክ መንግሥት ውስጥ ስታዩና እናንተ ግን በውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ በዚያ ታለቅሳላችሁ፤ ጥርሳችሁንም ታፋጫላችሁ።+ +29 በተጨማሪም ሰዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ እንዲሁም ከሰሜንና ከደቡብ መጥተው በአምላክ መንግሥት በማዕድ ይቀመጣሉ። +30 ደግሞም ከኋለኞች መካከል ፊተኞች የሚሆኑ፣ ከፊተኞች መካከልም ኋለኞች የሚሆኑ አሉ።”+ +31 በዚያን ጊዜ አንዳንድ ፈሪሳውያን መጥተው “ሄሮድስ ሊገድልህ ስለሚፈልግ ከዚህ ውጣና ሂድ” አሉት። +32 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሄዳችሁ ያንን ቀበሮ ‘ዛሬና ነገ አጋንንትን አስወጣለሁ እንዲሁም ሰዎችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ሥራዬን አጠናቅቃለሁ’ በሉት። +33 ይሁንና ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ሊገደል ስለማይችል* ዛሬና ነገ እንዲሁም ከነገ ወዲያ ጉዞዬን መቀጠል አለብኝ።+ +34 ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም፣ ነቢያትን የምትገድል፤ ወደ እሷ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግር፤+ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግኩ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።+ +35 እነሆ፣ ቤታችሁ* ለእናንተ የተተወ ይሆናል።+ እላችኋለሁ፣ ‘በይሖዋ* ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!’ እስክትሉ ድረስ ፈጽሞ አታዩኝም።”+ +5 አንድ ቀን ኢየሱስ በጌንሴሬጥ ሐይቅ*+ ዳርቻ ቆሞ የአምላክን ቃል ሲያስተምር ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ያዳምጡት ነበር፤ ከዚያም ሰዎቹ እየተገፋፉ ያጨናንቁት ጀመር። +2 በዚህ ጊዜ ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ዳርቻ ቆመው ተመለከተ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ላይ ወርደው መረቦቻቸውን እያጠቡ ነበር።+ +3 ኢየሱስም አንደኛዋ ጀልባ ላይ ወጣ፤ የጀልባዋ ባለቤት የሆነውን ስምዖንንም ከየብስ ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ጠየቀው። ከዚያም ጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ጀመር። +4 ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ስምዖንን “ጥልቅ ወደሆነው አካባቢ ፈቀቅ በልና መረቦቻችሁን ጥላችሁ አጥምዱ” አለው። +5 ሆኖም ስምዖን መልሶ “መምህር፣ ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም አድረን ምንም አልያዝንም፤+ አንተ ካልክ ግን መረቦቹን እጥላለሁ” አለው። +6 እንደተባሉት ባደረጉም ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ። እንዲያውም መረቦቻቸው መበጣጠስ ጀመሩ።+ +7 በመሆኑም በሌላኛው ጀልባ ላይ የነበሩትን የሥራ ባልደረቦቻቸውን መጥተው እንዲያግዟቸው በምልክት ጠሯቸው፤ እነሱም መጡ፤ ሁለቱንም ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፤ ከዚህም የተነሳ ጀልባዎቹ መስጠም ጀመሩ። +8 ስምዖን ጴጥሮስ ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ እግር ሥር ተንበርክኮ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ስለሆንኩ ከእኔ ራቅ” አለው። +9 ይህን ያለው እሱና ከእሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ከያዙት ዓሣ ብዛት የተነሳ በጣም ስለተደነቁ ነው፤ +10 የስምዖን የሥራ ባልደረቦች የሆኑት የዘብዴዎስ ልጆች+ ያዕቆብና ዮሐንስም በጣም ተደንቀው ነበር። ኢየሱስ ግን ስምዖንን “አይዞህ አትፍራ፤ ከአሁን ጀምሮ ሰውን* የምታጠምድ ትሆናለህ” አለው።+ +11 ስለዚህ ጀልባዎቹን መልሰው ወደ የብስ ካስጠጉ በኋላ ሁሉን ነገር ትተው ተከተሉት።+ +12 በሌላ ጊዜ ደግሞ በአንድ ከተማ ውስጥ በነበረበት ጊዜ መላ ሰውነቱን የሥጋ ደዌ የወረሰው ሰው በዚያ ነበር። ሰውየውም ኢየሱስን ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ “ጌታ ሆይ፣ ብትፈልግ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” ሲል ለመነው።+ +13 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው። ወዲያውኑ የሥጋ ደዌው ለቀቀው።+ +14 ከዚያም ኢየሱስ ሰውየውን ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ሙሴ ባዘዘው መሠረት+ ስለ መንጻትህ መባ አቅርብ፤ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ” አለው።+ +15 ሆኖም ስለ እሱ የሚወራው ወሬ ይበልጥ እየተሰራጨ ሄደ፤ በጣም ብዙ ሰዎችም የሚናገረውን ለመስማትና ከበሽታቸው ለመፈወስ ይሰበሰቡ ነበር።+ +16 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ጭር ወዳሉ ስፍራዎች በመሄድ ይጸልይ ነበር። +17 አንድ ቀን ኢየሱስ እያስተማረ ሳለ ከገሊላ፣ ከይሁዳ መንደሮች ሁሉ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና የሕጉ መምህራን በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ ሰዎችንም ለመፈወስ የሚያስችለው የይሖዋ* ኃይል ከኢየሱስ ጋር ነበር።+ +18 በዚያን ጊዜም አንድ ሽባ ሰው በቃሬዛ የተሸከሙ ሰዎች መጡ፤ ሽባውን ወደ ውስጥ ለማስገባትና ኢየሱስ ፊት ለማስቀመጥ ጥረት አደረጉ።+ +19 ከሕዝቡም ብዛት የተነሳ መግቢያ ስላላገኙ ጣራው ላይ ወጥተው ጡቡን ካነሱ በኋላ የተኛበትን ቃሬዛ አሾልከው፣ ሽባውን ኢየሱስ ፊት በነበሩት ሰዎች መካከል አወረዱት። +20 ኢየሱስም እምነታቸውን በማየት “አንተ ሰው፣ ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው።+ +21 በዚህ ጊዜ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን “አምላክን የሚዳፈረው ይሄ ማን ነው? ከአምላክ በቀር ኃጢአትን ማን ይቅር ሊል ይችላል?” ይባባሉ ጀመር።+ +22 ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ተረድቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በልባችሁ የምታስቡት ምንድን ነው? +23 ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሏል’ ከማለትና ‘ተነስተህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀላል? +24 ይሁንና የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ . . .” አላቸውና ሽባውን “ተነስ፣ ቃሬዛህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።+ +25 በዚህ ጊዜ ሰውየው በፊታቸው ተነስቶ ተኝቶበት የነበረውን ቃሬዛ ተሸከመና አምላክን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ። +26 ይህን ሲያዩ ሁሉም በአድናቆት ተውጠው አምላክን ማመስገን ጀመሩ፤ ታላቅ ፍርሃትም አድሮባቸው “ዛሬ የሚያስደንቅ ነገር አየን!” አሉ። +27 ይህ ከሆነም በኋላ ኢየሱስ ወጥቶ ሲሄድ ሌዊ የሚባል ቀረጥ ሰብሳቢ በቀረጥ መሰብሰቢያው ቦታ ተቀምጦ አየና “ተከታዬ ሁን” አለው።+ +28 እሱም ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጎ በመተው ተነስቶ ይከተለው ጀመር። +29 ከዚያም ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ በግብዣውም ላይ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ሰዎች ከእነሱ ጋር ይበሉ ነበር።+ +30 ፈሪሳውያንና ከእነሱ ወገን የሆኑ ጸሐፍት ይህን ባዩ ጊዜ “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የምትበሉትና የምትጠጡት ለምንድን ነው?” በማለት በደቀ መዛሙርቱ ላይ ማጉረምረም ጀመሩ።+ +31 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።+ +32 እኔ የመጣሁት ኃጢአተኞች ንስሐ እንዲገቡ ለመጥራት እንጂ ጻድቃንን ለመጥራት አይደለም።”+ +33 እነሱም “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አዘውትረው ይጾማሉ፤ እንዲሁም ምልጃ ያቀርባሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ፣ ይጠጣሉ” አሉት።+ +34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው ከእነሱ ጋር እያለ የሙሽራው ጓደኞች እንዲጾሙ ልታደርጓቸው ትችላላችሁ? +35 ሆኖም ሙሽራው+ ከእነሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።”+ +36 በተጨማሪም እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “ከአዲስ ልብስ ላይ ቁራጭ ጨርቅ ወስዶ በአሮጌ ልብስ ላይ የሚጥፍ ሰው የለም። እንዲህ ቢያደርግ ግን አዲሱ ቁራጭ ጨርቅ ተቦጭቆ ይነሳል፤ ከአዲሱ ልብስ የተቆረጠው ጨርቅ ከአሮጌው ልብስ ጋር አይስማማም።+ +37 ደግሞም ባረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያስቀምጥ ሰው የለም። እንዲህ ቢያደርግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁ ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። +38 ስለዚህ አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ መቀመጥ አለበት። +39 አሮጌ የወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ አዲ��ን የሚፈልግ የለም፤ ምክንያቱም ‘አሮጌው ግሩም ነው’ ይላል።” +21 ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታሞች በመዋጮ ሣጥኖቹ* ውስጥ መባቸውን ሲከቱ አየ።+ +2 ከዚያም አንዲት ድሃ መበለት በጣም አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ትናንሽ ሳንቲሞች* ስትከት+ አይቶ +3 እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ የበለጠ የሰጠችው ይህች ድሃ መበለት ነች።+ +4 ሁሉም መባ የሰጡት ከትርፋቸው ነውና፤ እሷ ግን በድሃ አቅሟ ያላትን መተዳደሪያ ሁሉ ሰጥታለች።”+ +5 በኋላም አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ ውብ በሆኑ ድንጋዮችና ለአምላክ በተሰጡ ስጦታዎች እንዴት እንዳጌጠ+ በተናገሩ ጊዜ +6 “ይህ የምታዩት ነገር ሁሉ የሚፈርስበት ጊዜ ይመጣል፤ እንዲህ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ አይኖርም” አለ።+ +7 እነሱም “መምህር፣ እነዚህ ነገሮች በእርግጥ የሚፈጸሙት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙበትን ጊዜ የሚጠቁመው ምልክትስ ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+ +8 እሱም እንዲህ አለ፦ “እንዳያሳስቷችሁ ተጠንቀቁ፤+ ብዙዎች ‘እኔ እሱ ነኝ’ እንዲሁም ‘ጊዜው ቀርቧል’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና። እነሱን አትከተሉ።+ +9 በተጨማሪም ስለ ጦርነትና ብጥብጥ* ስትሰሙ አትሸበሩ። በመጀመሪያ እነዚህ ነገሮች መፈጸም አለባቸውና፤ ፍጻሜው ግን ወዲያው አይመጣም።”+ +10 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣+ መንግሥትም በመንግሥት ላይ+ ይነሳል። +11 ታላላቅ የምድር ነውጦች ይከሰታሉ፤ በተለያየ ስፍራም የምግብ እጥረትና ቸነፈር ይሆናል፤+ ደግሞም የሚያስፈሩ ነገሮች እንዲሁም ከሰማይ ታላላቅ ምልክቶች ይታያሉ። +12 “እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት ግን ሰዎች ይይዟችኋል፤ ስደት ያደርሱባችኋል+ እንዲሁም ለምኩራብና ለወህኒ ቤት አሳልፈው ይሰጧችኋል። በስሜም ምክንያት በነገሥታትና በገዢዎች ፊት ያቀርቧችኋል።+ +13 ይህም ለመመሥከር የሚያስችል አጋጣሚ ይከፍትላችኋል። +14 የምትሰጡትን መልስ አስቀድማችሁ መዘጋጀት እንደማያስፈልጋችሁ ልብ በሉ፤+ +15 ተቃዋሚዎቻችሁ ሁሉ በአንድነት ሆነው ሊቋቋሙት ወይም ሊከራከሩት የማይችሉት አንደበትና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።+ +16 ከዚህም በተጨማሪ ወላጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁና ጓደኞቻችሁ እንኳ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤* አንዳንዶቻችሁንም ይገድላሉ፤+ +17 በስሜ የተነሳም ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል።+ +18 ይሁን እንጂ ከራሳችሁ ፀጉር አንዷ እንኳ አትጠፋም።+ +19 ከጸናችሁ ሕይወታችሁን ታተርፋላችሁ።*+ +20 “ይሁንና ኢየሩሳሌም በጦር ሠራዊት ተከባ ስታዩ+ መጥፊያዋ እንደቀረበ እወቁ።+ +21 በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤+ በከተማዋ ውስጥ ያሉም ከዚያ ይውጡ፤ በገጠር ያሉም ወደ እሷ አይግቡ፤ +22 ምክንያቱም የተጻፈው ነገር ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይህ የፍትሕ እርምጃ የሚወሰድበት ጊዜ* ነው። +23 በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!+ ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቁጣ ይመጣል። +24 በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ተማርከውም ወደየአገሩ ይወሰዳሉ፤+ የተወሰኑት የአሕዛብ* ዘመናት እስኪፈጸሙ ድረስም ኢየሩሳሌም በአሕዛብ* ትረገጣለች።+ +25 “እንዲሁም በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ምልክቶች ይታያሉ፤+ በምድርም ላይ ሕዝቦች ከባሕሩ ድምፅና ነውጥ የተነሳ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ይጨነቃሉ። +26 የሰማያት ኃይላት ስለሚናወጡ ሰዎች ከፍርሃትና በዓለም ላይ የሚመጡትን ነገሮች ከመጠበቅ የተነሳ ይዝለፈለፋሉ። +27 ከዚያም የሰው ልጅ+ በኃይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።+ +28 ሆኖም እነዚህ ነገሮች መከሰት ሲጀምሩ መዳናችሁ እየቀረበ ስለሆነ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ፤ ራሳችሁንም ቀና አድርጉ��” +29 ከዚያም እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “የበለስ ዛፍንና ሌሎች ዛፎችን ሁሉ ተመልከቱ።+ +30 ዛፎቹ ሲያቆጠቁጡ ራሳችሁ አይታችሁ በጋ* እንደቀረበ ታውቃላችሁ። +31 በተመሳሳይ እናንተም እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ ስታዩ የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ እርግጠኞች ሁኑ። +32 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ ፈጽሞ አያልፍም።+ +33 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።+ +34 “ይሁንና ከልክ በላይ በመብላትና በመጠጣት+ እንዲሁም ስለ ኑሮ በመጨነቅ+ ልባችሁ ሸክም እንዳይበዛበት ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ አለዚያ ያ ቀን ድንገት ሳታስቡት +35 እንደ ወጥመድ+ ይመጣባችኋል። ይህ በመላው ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይደርስባቸዋልና። +36 እንግዲያው መፈጸማቸው ከማይቀረው ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ማምለጥና በሰው ልጅ ፊት መቆም እንድትችሉ+ ሁልጊዜ ምልጃ እያቀረባችሁ+ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ።”+ +37 ኢየሱስ ቀን ቀን በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር፤ ሲመሽ ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በተባለው ተራራ ያድር ነበር። +38 ሕዝቡም ሁሉ በቤተ መቅደስ እሱን ለመስማት በማለዳ ወደ እሱ ይመጡ ነበር። +15 አንድ ቀን ቀራጮችና ኃጢአተኞች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት በዙሪያው ተሰበሰቡ።+ +2 ፈሪሳውያንና ጸሐፍትም “ይህ ሰው ኃጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነሱም ጋር ይበላል” እያሉ አጉረመረሙ። +3 በዚህ ጊዜ የሚከተለውን ምሳሌ ነገራቸው፦ +4 “ከእናንተ መካከል 100 በጎች ያሉት ሰው አንዷ ብትጠፋበት 99ኙን በምድረ በዳ ትቶ የጠፋችውን እስኪያገኝ ድረስ አይፈልግም?+ +5 በሚያገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ላይ ይሸከማታል። +6 ቤት ሲደርስም ጓደኞቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋችውን በጌን ስላገኘኋት የደስታዬ ተካፋዮች ሁኑ’ ይላቸዋል።+ +7 እላችኋለሁ፣ ልክ እንደዚሁ ንስሐ መግባት ከማያስፈልጋቸው 99 ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል።+ +8 “ወይም ደግሞ አሥር ድራክማ ሳንቲሞች* ያሏት አንዲት ሴት አንዱ ድራክማ* ቢጠፋባት መብራት አብርታ ቤቷን በመጥረግ እስክታገኘው ድረስ በደንብ አትፈልገውም? +9 ሳንቲሙን ባገኘችው ጊዜም ጓደኞቿንና ጎረቤቶቿን* በአንድነት ጠርታ ‘የጠፋብኝን ድራክማ ሳንቲም* ስላገኘሁት የደስታዬ ተካፋዮች ሁኑ’ ትላቸዋለች። +10 እላችኋለሁ፣ ልክ እንደዚሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በአምላክ መላእክት ዘንድ ደስታ ይሆናል።”+ +11 ከዚያም እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት። +12 ታናሽየውም ልጅ አባቱን ‘አባቴ ሆይ፣ ከንብረትህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው። በመሆኑም አባትየው ንብረቱን ለልጆቹ አካፈላቸው። +13 ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሽየው ልጅ ያለውን ነገር ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ተጓዘ፤ በዚያም ልቅ የሆነ* ሕይወት በመኖር ንብረቱን አባከነ። +14 ያለውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ በዚያ አገር በሙሉ ከባድ ረሃብ ተከሰተ፤ በዚህ ጊዜ ችግር ላይ ወደቀ። +15 ከችግሩም የተነሳ ከዚያ አገር ሰዎች ወደ አንዱ ሄዶ የሙጥኝ አለ፤ ሰውየውም አሳማ+ እንዲጠብቅለት ወደ ሜዳ ላከው። +16 እሱም አሳማዎቹ የሚመገቡትን ምግብ በልቶ ለመጥገብ ይመኝ ነበር፤ ነገር ግን የሚሰጠው አልነበረም። +17 “ወደ ልቦናው ሲመለስ ግን እንዲህ አለ፦ ‘ስንቶቹ የአባቴ ቅጥር ሠራተኞች ምግብ ተርፏቸው እኔ እዚህ በረሃብ ልሞት ነው! +18 ተነስቼ ወደ አባቴ በመሄድ እንዲህ እለዋለሁ፦ “አባቴ ሆይ፣ በአምላክና* በአንተ ላይ በደል ፈጽሜአለሁ። +19 ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም። ከቅጥር ሠራተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ።”’ +20 ስለዚህ ተነስቶ ወደ አባቱ ሄደ። ገና ሩቅ ሳለም አባቱ አየው��� በዚህ ጊዜ አንጀቱ ተላወሰ፤ እየሮጠ ሄዶም አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ሳመው። +21 ከዚያም ልጁ ‘አባቴ ሆይ፣ በአምላክና በአንተ ላይ በደል ፈጽሜአለሁ።+ ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው። +22 አባትየው ግን ባሪያዎቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ቶሎ በሉ! ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጥታችሁ አልብሱት፤ ለእጁ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት። +23 የሰባውንም ጥጃ አምጥታችሁ እረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት። +24 ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል።+ ጠፍቶ ነበር፤ ተገኝቷል።’ ከዚያም ይደሰቱ ጀመር። +25 “በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ በእርሻ ቦታ ነበር፤ ተመልሶ መጥቶ ወደ ቤት በተቃረበ ጊዜ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ። +26 ስለዚህ ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ ነገሩ ምን እንደሆነ ጠየቀው። +27 አገልጋዩም ‘ወንድምህ መጥቷል፤ በደህና ስለመጣም አባትህ የሰባውን ጥጃ አርዶለታል’ አለው። +28 እሱ ግን ተቆጣ፤ ወደ ቤት ለመግባትም አሻፈረኝ አለ። ከዚያም አባቱ ወጥቶ ይለምነው ጀመር። +29 እሱም መልሶ አባቱን እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ እኔ ስንት ዓመት ሙሉ እንደ ባሪያ ሳገለግልህ ኖርኩ፤ መቼም ቢሆን ከትእዛዝህ ዝንፍ ብዬ አላውቅም፤ አንተ ግን ከጓደኞቼ ጋር እንድደሰት አንዲት የፍየል ጠቦት እንኳ ሰጥተኸኝ አታውቅም። +30 ሆኖም ሀብትህን ከዝሙት አዳሪዎች ጋር ያወደመው* ይህ ልጅህ ገና ከመምጣቱ የሰባውን ጥጃ አረድክለት።’ +31 በዚህ ጊዜ አባቱ እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ ደግሞም የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው። +32 ሆኖም ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶ ነበር፤ ተገኝቷል። ስለዚህ ልንደሰትና ሐሴት ልናደርግ ይገባል።’” +22 ፋሲካ የሚባለው የቂጣ* በዓል+ የሚከበርበት ጊዜ ተቃርቦ ነበር።+ +2 የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም ሕዝቡን ይፈሩ+ ስለነበር እሱን የሚገድሉበትን+ ከሁሉ የተሻለ መንገድ እየፈለጉ ነበር። +3 ከዚያም ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ሆኖ በተቆጠረውና አስቆሮቱ ተብሎ በሚጠራው በይሁዳ ሰይጣን ገባበት፤+ +4 ይሁዳም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደሱ ሹሞች ሄዶ ኢየሱስን ለእነሱ አሳልፎ መስጠት ስለሚችልበት መንገድ ተነጋገረ።+ +5 እነሱም በጉዳዩ ተደስተው የብር ገንዘብ* ሊሰጡት ተስማሙ።+ +6 እሱም በዚህ ተስማምቶ ሕዝብ በሌለበት እሱን አሳልፎ መስጠት የሚችልበትን ምቹ አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር። +7 የቂጣ በዓል የሚከበርበት ቀን ደረሰ፤ በዚህ ዕለት የፋሲካ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር፤+ +8 ስለዚህ ኢየሱስ “ሄዳችሁ ፋሲካን እንድንበላ አዘጋጁልን”+ ብሎ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላካቸው። +9 እነሱም “የት እንድናዘጋጅ ትፈልጋለህ?” አሉት። +10 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ከተማው ስትገቡ የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ። እሱን ተከትላችሁ ወደሚገባበት ቤት ሂዱ።+ +11 የቤቱንም ባለቤት ‘መምህሩ “ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሎሃል’ በሉት። +12 ሰውየውም የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል፤ በዚያ አዘጋጁ።” +13 እነሱም ሄዱ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ። +14 ሰዓቱ በደረሰ ጊዜም ከሐዋርያቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።+ +15 እንዲህም አላቸው፦ “መከራ ከመቀበሌ በፊት ይህን ፋሲካ አብሬያችሁ ለመብላት በጣም ስመኝ ነበር፤ +16 እላችኋለሁና፣ የዚህ ፋሲካ ትርጉም በአምላክ መንግሥት ፍጻሜውን እስኪያገኝ ድረስ ፋሲካን ዳግመኛ አልበላም።” +17 ከዚያም ጽዋ ተቀብሎ አምላክን ካመሰገነ በኋላ እንዲህ አለ፦ “እንኩ፣ ይህን ጽዋ እየተቀባበላችሁ ጠጡ፤ +18 እላችኋለሁና፣ ከአሁን ጀምሮ የአምላክ መንግሥት እስኪመጣ ድረስ ከዚህ ወይን ዳግመኛ አልጠጣም።” +19 በተጨማሪም ቂጣ+ አንስቶ አመሰገነ፣ ከቆረሰውም በኋላ ሰጣቸውና “ይህ ስለ እናንተ የሚሰጠውን+ ሥጋዬን ያመለክታል።+ ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት”+ አላቸው። +20 በተጨማሪም ራት ከበሉ በኋላ ጽዋውን አንስቶ ልክ እንደዚሁ አደረገ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ+ በሚፈሰው ደሜ+ አማካኝነት የሚመሠረተውን አዲሱን ቃል ኪዳን+ ያመለክታል። +21 “ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ ከእኔ ጋር በማዕድ ነው።+ +22 እርግጥ የሰው ልጅ አስቀድሞ በተወሰነው መሠረት ይሄዳል፤+ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት!”+ +23 ስለዚህ ከመካከላቸው በእርግጥ ይህን የሚያደርገው ማን ሊሆን እንደሚችል እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር።+ +24 ደግሞም ‘ከመካከላችን ታላቅ የሆነው ማን ነው?’ በሚል በመካከላቸው የጦፈ ክርክር ተነሳ።+ +25 እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “የአሕዛብ ነገሥታት በእነሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ፤ እንዲሁም በሕዝባቸው ላይ ሥልጣን ያላቸው ሰዎች በጎ አድራጊዎች ተብለው ይጠራሉ።+ +26 እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ።+ ከዚህ ይልቅ ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን፤+ አመራር የሚሰጥም እንደ አገልጋይ ይሁን። +27 ለመሆኑ በማዕድ ከተቀመጠና ቆሞ ከሚያገለግል ማን ይበልጣል? በማዕድ የተቀመጠው አይደለም? እኔ ግን በመካከላችሁ ያለሁት እንደ አገልጋይ ሆኜ ነው።+ +28 “ይሁን እንጂ እናንተ በፈተናዎቼ+ ከጎኔ ሳትለዩ ቆይታችኋል፤+ +29 አባቴ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን እንዳደረገ ሁሉ እኔም ከእናንተ ጋር ለመንግሥት ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+ +30 ይኸውም በመንግሥቴ ከማዕዴ እንድትበሉና እንድትጠጡ+ እንዲሁም በዙፋን ተቀምጣችሁ+ በ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ እንድትፈርዱ ነው።+ +31 “ስምዖን፣ ስምዖን፣ ሰይጣን ሁላችሁንም እንደ ስንዴ ያበጥራችሁ ዘንድ ጥያቄ አቅርቧል።+ +32 እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ምልጃ አቀረብኩ፤+ አንተም በተመለስክ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ።”+ +33 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ወደ ወህኒ ለመውረድም ሆነ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው።+ +34 እሱ ግን “ጴጥሮስ ሆይ፣ እውነት እልሃለሁ፣ ዛሬ ዶሮ ከመጮኹ በፊት፣ አላውቀውም ብለህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው።+ +35 በተጨማሪም እንዲህ አላቸው፦ “ያለገንዘብ ኮሮጆ፣ ያለምግብ ከረጢትና ያለትርፍ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ+ የጎደለባችሁ ነገር ነበር?” እነሱም “ምንም አልጎደለብንም” አሉ። +36 በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ግን የገንዘብ ኮሮጆ ያለው ኮሮጆውን ይያዝ፤ የምግብ ከረጢት ያለውም እንዲሁ፤ ሰይፍ የሌለው ደግሞ መደረቢያውን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ። +37 ይህን የምላችሁ ‘ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ’+ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ላይ መፈጸም ስላለበት ነው። ስለ እኔ የተነገረው ነገር ፍጻሜውን እያገኘ ነውና።”+ +38 እነሱም “ጌታ ሆይ፣ ይኸው ሁለት ሰይፎች አሉ” አሉት። እሱም “በቂ ነው” አላቸው። +39 ከዚያ ወጥቶም እንደ ልማዱ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት።+ +40 እዚያም በደረሱ ጊዜ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ” አላቸው።+ +41 እሱም የድንጋይ ውርወራ ያህል ከእነሱ በመራቅ ተንበርክኮ መጸለይ ጀመረ፤ +42 እንዲህም አለ፦ “አባት ሆይ፣ ፈቃድህ ከሆነ ይህን ጽዋ ከእኔ አርቅ። ይሁንና የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም።”+ +43 ከዚያም አንድ መልአክ ከሰማይ ተገልጦለት አበረታታው።+ +44 ሆኖም በከፍተኛ ጭንቀት ተውጦ ከበፊቱ ይበልጥ አጥብቆ መጸለዩን ቀጠለ፤+ ላቡም መሬት ላይ እንደሚንጠባጠብ ደም ሆኖ ነበር። +45 ከጸለየም በኋላ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲሄድ ከሐዘን የተነሳ ደክ��ቸው ስለነበር ሲያንቀላፉ አገኛቸው።+ +46 እሱም “ለምን ትተኛላችሁ? ተነሱ፤ ደግሞም ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ” አላቸው።+ +47 ገና እየተናገረ ሳለ ብዙ ሰዎች መጡ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ የተባለውም ሰው ይመራቸው ነበር፤ ሊስመውም ወደ ኢየሱስ ተጠጋ።+ +48 ኢየሱስ ግን “ይሁዳ፣ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጣለህ?” አለው። +49 በዙሪያው የነበሩትም አዝማሚያውን ሲያዩ “ጌታ ሆይ፣ በሰይፍ እንምታቸው?” አሉት። +50 እንዲያውም ከመካከላቸው አንዱ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው።+ +51 ኢየሱስ ግን መልሶ “ተዉ!” አለ። ጆሮውንም ዳሶ ፈወሰው። +52 ከዚያም ኢየሱስ እሱን ለመያዝ የመጡትን የካህናት አለቆች፣ የቤተ መቅደሱን ሹሞችና ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ መጣችሁ?+ +53 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ አብሬያችሁ ሳለሁ+ እኔን ለመያዝ እጃችሁን አላነሳችሁብኝም።+ ይሁንና ይህ የእናንተ ሰዓትና ጨለማ የሚነግሥበት ሰዓት ነው።”+ +54 ከዚያም ሰዎቹ ይዘው ወሰዱትና+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤት አመጡት፤ ጴጥሮስም በርቀት ይከተል ነበር።+ +55 በግቢው መካከል እሳት አንድደው አንድ ላይ ተቀምጠው ሳለ ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ተቀመጠ።+ +56 ይሁንና አንዲት አገልጋይ እሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሲሞቅ አየችውና ትኩር ብላ ከተመለከተችው በኋላ “ይህ ሰውም ከእሱ ጋር ነበር” አለች። +57 እሱ ግን “አንቺ ሴት፣ እኔ አላውቀውም” ሲል ካደ። +58 ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሌላ ሰው አየውና “አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ አይደለሁም” አለ።+ +59 አንድ ሰዓት ያህል ካለፈ በኋላ ደግሞ አንድ ሌላ ሰው “ይህ ሰው፣ የገሊላ ሰው ስለሆነ በእርግጥ ከእሱ ጋር ነበር!” በማለት አጥብቆ ይናገር ጀመር። +60 ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ ምን እንደምታወራ አላውቅም” አለ። ገና እየተናገረም ሳለ ዶሮ ጮኸ። +61 በዚህ ጊዜ ጌታ ዞር ብሎ ጴጥሮስን ትክ ብሎ አየው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” በማለት ጌታ የተናገረውን ቃል አስታወሰ።+ +62 ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ። +63 ኢየሱስን የያዙት ሰዎችም እየመቱት+ ያሾፉበት+ ጀመር፤ +64 ፊቱንም ከሸፈኑት በኋላ “እስቲ ትንቢት ተናገር! የመታህ ማን ነው?” እያሉ ይጠይቁት ነበር። +65 በእሱም ላይ ሌላ ብዙ የስድብ ቃል ይሰነዝሩ ነበር። +66 በነጋም ጊዜ የካህናት አለቆችንና ጸሐፍትን ጨምሮ የሕዝቡ ሽማግሌዎች ጉባኤ አንድ ላይ ተሰበሰበ፤+ ኢየሱስንም ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ አዳራሻቸው አምጥተው እንዲህ አሉት፦ +67 “አንተ ክርስቶስ ከሆንክ ንገረን።”+ እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ብነግራችሁም እንኳ ፈጽሞ አታምኑም። +68 ብጠይቃችሁም አትመልሱም። +69 ያም ሆነ ይህ ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ+ በኃያሉ አምላክ ቀኝ ይቀመጣል።”+ +70 በዚህ ጊዜ ሁሉም “ስለዚህ የአምላክ ልጅ ነህ ማለት ነው?” አሉት። እሱም “የአምላክ ልጅ መሆኔን እናንተው ራሳችሁ እየተናገራችሁ ነው” አላቸው። +71 እነሱም “ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ ያስፈልገናል? እኛ ራሳችን ከገዛ አፉ ሰምተነዋል” አሉ።+ +17 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “አባት ሆይ፣ ሰዓቱ ደርሷል። ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው፤+ +2 ይህም በሥጋ ለባሽ* ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደሰጠኸው+ ሁሉ እሱም አንተ ለሰጠኸው ሰው+ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲሰጥ ነው።+ +3 ብቸኛው* እውነተኛ አምላክ+ የሆንከውን አንተንና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ*+ የዘላለም ሕይወት+ ነው። +4 እንድሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ+ በምድር ላይ አከ���ርኩህ።+ +5 ስለዚህ አባት ሆይ፣ ዓለም ከመመሥረቱ በፊት በጎንህ ሆኜ ክብር እንደነበረኝ+ ሁሉ አሁንም በጎንህ አድርገህ አክብረኝ። +6 “ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገልጬላቸዋለሁ።*+ እነሱ የአንተ ነበሩ፤ አንተም ለእኔ ሰጠኸኝ፤ ደግሞም ቃልህን ጠብቀዋል።* +7 የሰጠኸኝ ነገር ሁሉ ከአንተ የተገኘ መሆኑን አሁን አውቀዋል፤ +8 ምክንያቱም የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁ፤+ እነሱም ተቀብለውታል፤ እንዲሁም የአንተ ተወካይ ሆኜ መምጣቴን በእርግጥ አውቀዋል፤+ አንተ እንደላክኸኝም አምነዋል።+ +9 ስለ እነሱ እለምንሃለሁ፤ የምለምንህ ስለ ዓለም ሳይሆን አንተ ስለሰጠኸኝ ሰዎች ነው፤ ምክንያቱም እነሱ የአንተ ናቸው፤ +10 ደግሞም የእኔ የሆነው ነገር ሁሉ የአንተ ነው፤+ የአንተ የሆነውም ሁሉ የእኔ ነው፤ እኔም በእነሱ መካከል ከብሬአለሁ። +11 “ከእንግዲህ እኔ በዓለም ውስጥ አልኖርም፤ እነሱ ግን በዓለም ውስጥ ናቸው፤+ እኔ ወደ አንተ መምጣቴ ነው። ቅዱስ አባት ሆይ፣ እኛ አንድ እንደሆንን* ሁሉ እነሱም አንድ እንዲሆኑ፣*+ ስለሰጠኸኝ ስለ ራስህ ስም ስትል ጠብቃቸው።+ +12 እኔ ከእነሱ ጋር ሳለሁ፣ ስለሰጠኸኝ ስለ ራስህ ስም ስል ስጠብቃቸው ቆይቻለሁ፤+ ደግሞም ጠብቄአቸዋለሁ፤ የቅዱስ መጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ+ ከጥፋት ልጅ በቀር+ አንዳቸውም አልጠፉም።+ +13 አሁን ግን ወደ አንተ መምጣቴ ነው፤ ደስታዬ በውስጣቸው ሙሉ እንዲሆን+ አሁን በዓለም ላይ እያለሁ እነዚህን ነገሮች እናገራለሁ። +14 ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ ሆኖም እኔ የዓለም ክፍል እንዳልሆንኩ ሁሉ እነሱም የዓለም ክፍል ስላልሆኑ ዓለም ጠላቸው።+ +15 “የምለምንህ ከዓለም እንድታወጣቸው ሳይሆን ከክፉው* እንድትጠብቃቸው ነው።+ +16 እኔ የዓለም ክፍል እንዳልሆንኩ+ ሁሉ እነሱም የዓለም ክፍል አይደሉም።+ +17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤*+ ቃልህ እውነት ነው።+ +18 አንተ ወደ ዓለም እንደላክኸኝ ሁሉ እኔም ወደ ዓለም ልኬአቸዋለሁ።+ +19 እነሱም በእውነት እንዲቀደሱ እኔ ራሴም ስለ እነሱ ስል ቅድስናዬን እጠብቃለሁ። +20 “የምለምንህ ስለ እነዚህ ብቻ ሳይሆን በእነሱ ቃል አማካኝነት በእኔ ለሚያምኑ ጭምር ነው፤ +21 ይህን ልመና የማቀርበውም ሁሉም አንድ እንዲሆኑ ነው፤+ ይኸውም ዓለም አንተ እንደላክኸኝ ያምን ዘንድ አባት ሆይ፣ አንተ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለህና እኔም ከአንተ ጋር አንድነት እንዳለኝ+ ሁሉ እነሱም ከእኛ ጋር አንድነት እንዲኖራቸው ነው። +22 እኛ አንድ እንደሆንን ሁሉ እነሱም አንድ እንዲሆኑ+ ለእኔ የሰጠኸኝን ክብር ሰጥቻቸዋለሁ። +23 እኔ ከእነሱ ጋር አንድነት አለኝ፤ አንተም ከእኔ ጋር አንድነት አለህ፤ ይህ ደግሞ እነሱም ፍጹም አንድ እንዲሆኑ* ነው፤ በተጨማሪም ዓለም አንተ እንደላክኸኝ እንዲሁም እኔን እንደወደድከኝ ሁሉ እነሱንም እንደወደድካቸው ያውቅ ዘንድ ነው። +24 አባት ሆይ፣ እነዚህ የሰጠኸኝ፣ እኔ ባለሁበት እነሱም ከእኔ ጋር እንዲሆኑ እፈልጋለሁ፤+ ይህም ዓለም ከመመሥረቱ* በፊት ስለወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብር እንዲያዩ ነው።+ +25 ጻድቅ አባት ሆይ፣ በእርግጥ ዓለም አላወቀህም፤+ እኔ ግን አውቅሃለሁ፤+ እነዚህ ደግሞ አንተ እንደላክኸኝ አውቀዋል። +26 እኔን የወደድክበት ፍቅር እነሱም እንዲኖራቸው እንዲሁም እኔ ከእነሱ ጋር አንድነት እንዲኖረኝ+ ስምህን አሳውቄአቸዋለሁ፤ ደግሞም አሳውቃለሁ።”+ +18 ኢየሱስ ስለ እነዚህ ነገሮች ከጸለየ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የቄድሮንን ሸለቆ*+ ተሻግሮ ወደ አንድ የአትክልት ስፍራ ሄደ፤ እሱና ደቀ መዛሙርቱም ወደ አትክልት ስፍራው ገቡ።+ +2 ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ብዙ ጊዜ በዚህ ስፍራ ይገናኝ ስለነበር አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም ቦታውን ያ���ቅ ነበር። +3 ስለዚህ ይሁዳ አንድ የወታደሮች ቡድን እንዲሁም ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን የተላኩ የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች አስከትሎ መጣ፤ እነሱም ችቦና መብራት እንዲሁም መሣሪያ ይዘው ነበር።+ +4 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የሚደርስበትን ነገር ሁሉ ስላወቀ ወደ ፊት ራመድ ብሎ “ማንን ነው የምትፈልጉት?” አላቸው። +5 እነሱም “የናዝሬቱን ኢየሱስ”+ ሲሉ መለሱለት። እሱም “እኔ ነኝ” አላቸው። አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም ከእነሱ ጋር ቆሞ ነበር።+ +6 ይሁን እንጂ ኢየሱስ “እኔ ነኝ” ሲላቸው ወደ ኋላ አፈግፍገው መሬት ላይ ወደቁ።+ +7 ዳግመኛም “ማንን ነው የምትፈልጉት?” ሲል ጠየቃቸው። እነሱም “የናዝሬቱን ኢየሱስ” አሉት። +8 ኢየሱስም መልሶ “እኔ ነኝ አልኳችሁ እኮ። የምትፈልጉት እኔን ከሆነ እነዚህን ተዉአቸው ይሂዱ” አለ። +9 ይህም የሆነው “ከሰጠኸኝ ከእነዚህ መካከል አንዱም እንኳ አልጠፋብኝም”+ ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። +10 በዚህ ጊዜ ሰይፍ ይዞ የነበረው ስምዖን ጴጥሮስ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው።+ የባሪያውም ስም ማልኮስ ነበር። +11 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ጴጥሮስን “ሰይፉን ወደ ሰገባው መልስ።+ አብ የሰጠኝን ጽዋ መጠጣት አይኖርብኝም?” አለው።+ +12 ከዚያም ወታደሮቹና የጦር አዛዡ እንዲሁም ከአይሁዳውያን የተላኩት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት። +13 በመጀመሪያም ወደ ሐና ወሰዱት፤ ምክንያቱም ሐና በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት+ የነበረው የቀያፋ+ አማት ነበር። +14 ቀያፋ ደግሞ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት ለእነሱ የተሻለ እንደሚሆን ለአይሁዳውያን ምክር የሰጠው ሰው ነው።+ +15 ስምዖን ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር ኢየሱስን እየተከተሉ ነበር።+ ይህን ደቀ መዝሙር ሊቀ ካህናቱ ያውቀው ስለነበር ከኢየሱስ ጋር ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ገባ፤ +16 ጴጥሮስ ግን ውጭ በር ላይ ቆሞ ነበር። ስለሆነም ሊቀ ካህናቱ የሚያውቀው ይህ ደቀ መዝሙር ወጥቶ በር ጠባቂዋን አነጋገራትና ጴጥሮስን አስገባው። +17 በር ጠባቂ የነበረችውም አገልጋይ ጴጥሮስን “አንተም ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ ነህ አይደል?” አለችው። እሱም “አይደለሁም” አለ።+ +18 ብርድ ስለነበር ባሪያዎቹና የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ባቀጣጠሉት ከሰል ዙሪያ ቆመው እየሞቁ ነበር። ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። +19 በዚህ ጊዜ የካህናት አለቃው ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀው። +20 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ። አይሁዳውያን ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኩራብና በቤተ መቅደሱ ሁልጊዜ አስተምር ነበር፤+ በስውር የተናገርኩት ምንም ነገር የለም። +21 እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? እኔ የነገርኳቸውን ነገር የሰሙትን ሰዎች ጠይቃቸው። እነዚህ የተናገርኩትን ያውቃሉ።” +22 ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ አጠገቡ ቆመው ከነበሩት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች አንዱ በጥፊ መታውና+ “ለካህናት አለቃው የምትመልሰው እንዲህ ነው?” አለው። +23 ኢየሱስም “የተሳሳተ ነገር ተናግሬ ከሆነ ስህተቴ ምን እንደሆነ ንገረኝ፤* የተናገርኩት ነገር ትክክል ከሆነ ግን ለምን ትመታኛለህ?” ሲል መለሰለት። +24 ከዚያም ሐና ኢየሱስን እንደታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው።+ +25 ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት እየሞቀ ነበር። በዚህ ጊዜ ሰዎቹ “አንተም ከእሱ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነህ አይደል?” አሉት። እሱም “አይደለሁም” ሲል ካደ።+ +26 ከሊቀ ካህናቱ ባሪያዎች አንዱ ይኸውም ጴጥሮስ ጆሮውን የቆረጠው+ ሰው ዘመድ “በአትክልቱ ስፍራ ከእሱ ጋር አይቼህ አልነበረም?” አለው። +27 ይሁን እንጂ ጴጥሮስ እንደገና ካደ፤ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።+ +28 ከዚያም ኢየሱስን ከቀያፋ ቤት ወደ ገዢው መኖሪያ ወሰዱት።+ ጊዜውም ማለዳ ነበር። ሆኖም እነሱ ፋሲካን መብላት ይችሉ ዘንድ እንዳይረክሱ+ ወደ ገዢው መኖሪያ አልገቡም። +29 ስለዚህ ጲላጦስ እነሱ ወዳሉበት ወጥቶ “በዚህ ሰው ላይ የምታቀርቡት ክስ ምንድን ነው?” አላቸው። +30 እነሱም መልሰው “ይህ ሰው ጥፋተኛ* ባይሆን ኖሮ ለአንተ አሳልፈን አንሰጠውም ነበር” አሉት። +31 ስለዚህ ጲላጦስ “እናንተ ራሳችሁ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት” አላቸው።+ አይሁዳውያኑም “እኛ ማንንም ሰው ለመግደል ሕግ አይፈቅድልንም” አሉት።+ +32 ይህ የሆነው ኢየሱስ በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚሞት ለማመልከት የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው።+ +33 ስለሆነም ጲላጦስ ወደ ገዢው መኖሪያ ተመልሶ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” አለው።+ +34 ኢየሱስም መልሶ “ይህ የራስህ ጥያቄ ነው ወይስ ሌሎች ስለ እኔ ነግረውህ ነው?” አለው። +35 ጲላጦስም “እኔ አይሁዳዊ ነኝ እንዴ? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ የራስህ ሕዝብና የካህናት አለቆች ናቸው። ያደረግከው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። +36 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦+ “መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም።+ መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል ቢሆን ኖሮ በአይሁዳውያን እጅ እንዳልወድቅ አገልጋዮቼ ይዋጉልኝ ነበር።+ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለም።” +37 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “እንግዲያው አንተ ንጉሥ ነህ?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ንጉሥ እንደሆንኩ አንተ ራስህ እየተናገርክ ነው።+ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመሥከር ነው።+ ከእውነት ጎን የቆመ ሁሉ ቃሌን ይሰማል።” +38 ጲላጦስም “እውነት ምንድን ነው?” አለው። ይህን ከተናገረ በኋላ እንደገና አይሁዳውያኑ ወዳሉበት ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።+ +39 ከዚህም በላይ በልማዳችሁ መሠረት በፋሲካ አንድ ሰው ለእናንተ መፍታቴ አይቀርም።+ ስለዚህ የአይሁዳውያንን ንጉሥ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” +40 እነሱም እንደገና በመጮኽ “ይህን ሰው አንፈልግም፤ በርባንን ፍታልን!” አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበር።+ +19 ከዚያም ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ ገረፈው።+ +2 ወታደሮቹም የእሾህ አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ ደፉበት፤ እንዲሁም ሐምራዊ ልብስ አለበሱት፤+ +3 ወደ እሱ እየቀረቡም “የአይሁዳውያን ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” ይሉት ነበር። ደግሞም በጥፊ ይመቱት ነበር።+ +4 ጲላጦስም ዳግመኛ ወደ ውጭ ወጥቶ “ምንም ጥፋት እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እነሆ ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ” አላቸው።+ +5 በመሆኑም ኢየሱስ የእሾህ አክሊል እንደደፋና ሐምራዊ ልብስ እንደለበሰ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም “እነሆ፣ ሰውየው!” አላቸው። +6 ይሁን እንጂ የካህናት አለቆቹና የቤተ መቅደስ ጠባቂዎቹ ባዩት ጊዜ “ይሰቀል! ይሰቀል!”*+ እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “እኔ ምንም ጥፋት ስላላገኘሁበት ራሳችሁ ወስዳችሁ ግደሉት”* አላቸው።+ +7 አይሁዳውያኑም “እኛ ሕግ አለን፤ ይህ ሰው ደግሞ ራሱን የአምላክ ልጅ ስላደረገ+ በሕጉ መሠረት መሞት አለበት”+ ሲሉ መለሱለት። +8 ጲላጦስ ያሉትን ነገር ሲሰማ ይበልጥ ፍርሃት አደረበት፤ +9 ዳግመኛም ወደ ገዢው መኖሪያ ገብቶ ኢየሱስን “ለመሆኑ ከየት ነው የመጣኸው?” አለው። ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም።+ +10 ስለሆነም ጲላጦስ “መልስ አትሰጠኝም? ልፈታህም ሆነ ልገድልህ* ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም?” አለው። +11 ኢየሱስም “ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን አይኖርህም ነበር። ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው የባሰ ኃጢ���ት ያለበት ለዚህ ነው” ሲል መለሰለት። +12 ከዚህ የተነሳ ጲላጦስ ኢየሱስን መፍታት የሚችልበትን መንገድ ያስብ ጀመር፤ አይሁዳውያኑ ግን “ይህን ሰው ከፈታኸው አንተ የቄሳር ወዳጅ አይደለህም። ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሰው ሁሉ የቄሳር ተቃዋሚ ነው” እያሉ ጮኹ።+ +13 ጲላጦስ ይህን ከሰማ በኋላ ኢየሱስን ወደ ውጭ አውጥቶ የድንጋይ ንጣፍ በተባለ ቦታ በፍርድ ወንበር ተቀመጠ፤ ይህ ቦታ በዕብራይስጥ ጋባታ ይባላል። +14 ጊዜው የፋሲካ* የዝግጅት ቀን+ ነበር፤ ሰዓቱ ደግሞ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር። ጲላጦስም አይሁዳውያኑን “እነሆ፣ ንጉሣችሁ!” አላቸው። +15 እነሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!”* እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልግደለው?” አላቸው። የካህናት አለቆቹም “ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ሲሉ መለሱ። +16 በዚህ ጊዜ እንጨት ላይ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው።+ እነሱም ኢየሱስን ይዘው ወሰዱት። +17 ኢየሱስም የመከራውን እንጨት* ራሱ ተሸክሞ የራስ ቅል ቦታ+ ወደተባለ ስፍራ ወጣ፤ ይህ ቦታ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ይባላል።+ +18 በዚያም በእንጨት ላይ ቸነከሩት፤+ ከእሱም ጋር ሁለት ሰዎችን የሰቀሉ ሲሆን ኢየሱስን በመካከል አድርገው አንዱን በዚህ ሌላውን በዚያ ጎን ሰቀሉ።+ +19 በተጨማሪም ጲላጦስ ጽሑፍ ጽፎ በመከራው እንጨት* ላይ አንጠለጠለው። ጽሑፉም “የአይሁዳውያን ንጉሥ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ነበር።+ +20 ኢየሱስ በእንጨት ላይ የተቸነከረበት ቦታ በከተማዋ አቅራቢያ የሚገኝ በመሆኑ ብዙ አይሁዳውያን ይህን ጽሑፍ አነበቡት፤ ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ፣ በላቲንና በግሪክኛ ነበር። +21 ይሁን እንጂ የአይሁድ የካህናት አለቆች ጲላጦስን “እሱ ‘የአይሁዳውያን ንጉሥ ነኝ’ እንዳለ ጻፍ እንጂ ‘የአይሁዳውያን ንጉሥ’ ብለህ አትጻፍ” አሉት። +22 ጲላጦስም “እንግዲህ የጻፍኩትን ጽፌአለሁ” ሲል መለሰ። +23 ወታደሮቹ ኢየሱስን በእንጨት ላይ ከቸነከሩት በኋላ መደረቢያዎቹን ወስደው እያንዳንዱ ወታደር አንድ አንድ ቁራጭ እንዲደርሰው አራት ቦታ ቆራረጧቸው፤ ከውስጥ ለብሶት የነበረውንም ልብስ ወሰዱ። ሆኖም ልብሱ ከላይ እስከ ታች አንድ ወጥ ሆኖ ያለስፌት የተሠራ ነበር። +24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው “ከምንቀደው ዕጣ ተጣጥለን ለማን እንደሚደርስ እንወስን” ተባባሉ።+ ይህም የሆነው “መደረቢያዎቼን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤ በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” የሚለው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።+ ወታደሮቹም ያደረጉት ይህንኑ ነበር። +25 ይሁንና ኢየሱስ በተሰቀለበት የመከራ እንጨት* አጠገብ እናቱ፣+ የእናቱ እህት፣ የቀልዮጳ ሚስት ማርያምና መግደላዊቷ ማርያም ቆመው ነበር።+ +26 ስለዚህ ኢየሱስ እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙር+ በአቅራቢያው ቆመው ሲያያቸው እናቱን “አንቺ ሴት፣ ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት። +27 ከዚያም ደቀ መዝሙሩን “እናትህ ይህችውልህ!” አለው። ደቀ መዝሙሩም ከዚያ ሰዓት አንስቶ ወደ ራሱ ቤት ወሰዳት። +28 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሁሉም ነገር እንደተፈጸመ አውቆ የቅዱስ መጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም “ተጠማሁ”+ አለ። +29 በዚያም የኮመጠጠ ወይን ጠጅ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር። በመሆኑም ወይን ጠጁ ውስጥ የተነከረ ሰፍነግ፣* በሂሶጵ* አገዳ ላይ አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት።+ +30 ኢየሱስ የኮመጠጠውን ወይን ጠጅ ከቀመሰ በኋላ “ተፈጸመ!”+ አለ፤ ራሱንም ዘንበል አድርጎ መንፈሱን ሰጠ።*+ +31 ዕለቱ የዝግጅት ቀን+ ስለነበር አይሁዳውያን በሰንበት (ያ ሰንበት ታላቅ ሰንበት* ስለነበር)+ አስከሬኖቹ በመከራ እንጨቶቹ ላይ ተሰቅለው እንዳይቆዩ+ ሲሉ እግራቸው ተሰብሮ እንዲወርዱ ጲላጦስን ጠየቁት። +32 ስለዚህ ወታደሮቹ መጥተው ከእሱ ጋር የተሰቀሉትን የመጀመሪያውን ሰውና የሌላኛውን ሰው እግሮች ሰበሩ። +33 ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን ቀደም ብሎ መሞቱን ስላዩ እግሮቹን አልሰበሩም። +34 ሆኖም ከወታደሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤+ ወዲያውም ደምና ውኃ ፈሰሰ። +35 ይህን ያየው ሰውም ምሥክርነት ሰጥቷል፤ ምሥክርነቱም እውነት ነው፤ እናንተም እንድታምኑ ይህ ሰው የሚናገራቸው ነገሮች እውነት እንደሆኑ ያውቃል።+ +36 ይህም የሆነው “ከእሱ አንድ አጥንት እንኳ አይሰበርም”+ የሚለው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። +37 ደግሞም ሌላ የቅዱስ መጽሐፉ ቃል “የወጉትን ያዩታል”+ ይላል። +38 ይህ ከሆነ በኋላ፣ የአርማትያሱ ዮሴፍ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጲላጦስን ጠየቀ፤ ዮሴፍ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር። ሆኖም አይሁዳውያንን* ይፈራ ስለነበር+ ይህን ለማንም አልተናገረም። ጲላጦስ ከፈቀደለት በኋላ መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን ወሰደ።+ +39 ቀደም ሲል በማታ ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስም+ 30 ኪሎ ግራም* ገደማ የሚሆን የከርቤና የእሬት* ድብልቅ * ይዞ መጣ።+ +40 የኢየሱስንም አስከሬን ወስደው በአይሁዳውያን የአገናነዝ ልማድ መሠረት ጥሩ መዓዛ ባላቸው በእነዚህ ቅመሞች ተጠቅመው በበፍታ ጨርቅ ገነዙት።+ +41 እሱ በተገደለበት* ቦታ አቅራቢያ አንድ የአትክልት ስፍራ ነበር፤ በአትክልት ስፍራው ውስጥ ደግሞ ገና ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበር።+ +42 ዕለቱ አይሁዳውያን ለበዓሉ የሚዘጋጁበት ቀን+ ስለነበርና መቃብሩም በአቅራቢያው ይገኝ ስለነበር ኢየሱስን በዚያ አኖሩት። +20 በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን መግደላዊቷ ማርያም በማለዳ፣ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብሩ መጣች፤+ መቃብሩ የተዘጋበትም ድንጋይ ተንከባሎ አየች።+ +2 ስለዚህ ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደነበረው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር+ እየሮጠች መጥታ “ጌታን ከመቃብሩ ውስጥ ወስደውታል፤+ የት እንዳኖሩትም አናውቅም” አለቻቸው። +3 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና ሌላው ደቀ መዝሙር ወደ መቃብሩ አመሩ። +4 ሁለቱም አብረው ይሮጡ ጀመር፤ ሆኖም ሌላው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ቀድሞ በመሮጥ መቃብሩ ጋ ደረሰ። +5 ጎንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት የበፍታ ጨርቆቹ እዚያ ተቀምጠው አየ፤+ ወደ ውስጥ ግን አልገባም። +6 ከዚያም ስምዖን ጴጥሮስ ተከትሎት መጥቶ መቃብሩ ውስጥ ገባ። የበፍታ ጨርቆቹም በዚያ ተቀምጠው አየ። +7 በራሱ ላይ የነበረው ጨርቅ፣ ከመግነዝ ጨርቆቹ ጋር ሳይሆን ለብቻው ተጠቅልሎ አንድ ቦታ ላይ ተቀምጦ አየ። +8 ከዚያም ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደርሶ የነበረው ሌላው ደቀ መዝሙርም ወደ ውስጥ ገባ፤ እሱም አይቶ አመነ። +9 ከሞት መነሳት እንዳለበት የሚናገረውን የቅዱስ መጽሐፉን ቃል ገና አልተረዱም ነበር።+ +10 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ። +11 ይሁን እንጂ ማርያም እዚያው መቃብሩ አጠገብ ቆማ ታለቅስ ነበር። እያለቀሰችም ወደ መቃብሩ ውስጥ ለማየት ጎንበስ አለች፤ +12 ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክትም+ የኢየሱስ አስከሬን አርፎበት በነበረው ቦታ አንዱ በራስጌው ሌላው በግርጌው ተቀምጠው አየች። +13 እነሱም “አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ?” አሏት። እሷም “ጌታዬን ወስደውታል፤ የት እንዳደረጉትም አላውቅም” አለቻቸው። +14 ይህን ካለች በኋላ ዞር ስትል ኢየሱስን በዚያ ቆሞ አየችው፤ ነገር ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቀችም።+ +15 ኢየሱስም “አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ? የምትፈልጊው ማንን ነው?” አላት። እሷም አትክልተኛው ስለመሰላት “ጌታዬ፣ አንተ ከዚህ ወስደኸው ከሆነ የት እንዳደረግከው ንገረኝ፤ እኔም እወስደዋለሁ” አለችው። +16 ኢየሱስም “ማርያም!” አላት። እሷም ዞ�� ብላ በዕብራይስጥ “ራቦኒ!” አለችው (ትርጉሙም “መምህር!” ማለት ነው)። +17 ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ጥብቅ አድርገሽ አትያዥኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግኩምና። ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ+ ‘ወደ አባቴና+ ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና+ ወደ አምላካችሁ ላርግ ነው’ ብለሽ ንገሪያቸው።” +18 መግደላዊቷ ማርያም መጥታ “ጌታን አየሁት!” ብላ ለደቀ መዛሙርቱ አበሰረቻቸው፤ እሱ ያላትንም ነገረቻቸው።+ +19 የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በነበረው በዚያው ቀን ምሽት ላይ ደቀ መዛሙርቱ አይሁዳውያኑን* በመፍራታቸው በሮቹን ቆልፈው ተቀምጠው ሳለ ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።+ +20 ይህን ካለ በኋላ እጆቹንና ጎኑን አሳያቸው።+ ደቀ መዛሙርቱም ጌታን በማየታቸው እጅግ ተደሰቱ።+ +21 ኢየሱስም ዳግመኛ “ሰላም ለእናንተ ይሁን።+ አብ እኔን እንደላከኝ፣+ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ”+ አላቸው። +22 ይህን ካለ በኋላ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፦ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።+ +23 የማንንም ሰው ኃጢአት ይቅር ብትሉ ኃጢአቱ ይቅር ይባላል፤ ይቅር የማትሉት ሰው ሁሉ ደግሞ ኃጢአቱ እንዳለ ይጸናል።” +24 ይሁን እንጂ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ዲዲሞስ* የሚባለው ቶማስ+ ኢየሱስ በመጣበት ጊዜ አብሯቸው አልነበረም። +25 ስለዚህ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት “ጌታን አየነው!” አሉት። እሱ ግን “በእጆቹ ላይ ምስማሮቹ የተቸነከሩበትን ምልክት ካላየሁ እንዲሁም ጣቴን ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ካላስገባሁና እጄን በጎኑ ካላስገባሁ+ ፈጽሞ አላምንም” አላቸው። +26 እንደገናም ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነሱ ጋር ነበር። በሮቹ ተቆልፈው የነበሩ ቢሆንም ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አለ።+ +27 ከዚያም ቶማስን “ጣትህን እዚህ ክተት፤ እጆቼንም ተመልከት፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አስገባ። መጠራጠርህን* ተውና እመን” አለው። +28 ቶማስም መልሶ “ጌታዬ፣ አምላኬ!” አለው። +29 ኢየሱስ “ስላየኸኝ አመንክ? ሳያዩ የሚያምኑ ደስተኞች ናቸው” አለው። +30 እርግጥ ኢየሱስ በዚህ ጥቅልል ውስጥ ያልተጻፉ ሌሎች ብዙ ተአምራዊ ምልክቶችም በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል።+ +31 ሆኖም እነዚህ የተጻፉት ኢየሱስ በእርግጥ ክርስቶስ እንዲሁም የአምላክ ልጅ እንደሆነ እንድታምኑና በማመናችሁም በስሙ አማካኝነት ሕይወት እንዲኖራችሁ ነው።+ +3 ከፈሪሳውያን ወገን፣ የአይሁዳውያን ገዢ የሆነ ኒቆዲሞስ+ የሚባል ሰው ነበር። +2 ይህ ሰው በማታ ወደ ኢየሱስ መጥቶ+ እንዲህ አለው፦ “ረቢ፣+ አንተ ከአምላክ ዘንድ የመጣህ አስተማሪ እንደሆንክ እናውቃለን፤ ምክንያቱም አምላክ ከእሱ ጋር ካልሆነ በቀር+ አንተ የምትፈጽማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች መፈጸም የሚችል አንድም ሰው የለም።”+ +3 ኢየሱስም መልሶ “እውነት እውነት እልሃለሁ፣ አንድ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ*+ በቀር የአምላክን መንግሥት ሊያይ አይችልም”+ አለው። +4 ኒቆዲሞስም “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ዳግም ወደ እናቱ ማህፀን ገብቶ ሊወለድ ይችላል?” አለው። +5 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ሰው ከውኃና+ ከመንፈስ+ ካልተወለደ በቀር ወደ አምላክ መንግሥት ሊገባ አይችልም። +6 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደ ደግሞ መንፈስ ነው። +7 ‘ዳግመኛ መወለድ አለባችሁ’ ስላልኩህ አትገረም። +8 ነፋስ ወደፈለገው አቅጣጫ ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ሆኖም ከየት እንደሚመጣና ወዴት እንደሚሄድ አታውቅም። ከመንፈስ የተወለደም ሁሉ እንደዚሁ ነው።”+ +9 ኒቆዲሞስም መልሶ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለው። +10 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አንተ የእስራኤል አስተማሪ ሆነህ ሳለህ እነዚህን ነገሮች አታውቅም? +11 እውነት እውነት እልሃለሁ፣ እኛ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሠክራለን፤ እናንተ ግን እኛ የምንሰጠውን ምሥክርነት አትቀበሉም። +12 ስለ ምድራዊ ነገሮች ነግሬአችሁ የማታምኑ ከሆነ ስለ ሰማያዊ ነገሮች ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? +13 ደግሞም ከሰማይ ከወረደው+ ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም።+ +14 ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደሰቀለ፣+ የሰው ልጅም እንዲሁ ሊሰቀል ይገባዋል፤+ +15 ይኸውም በእሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው።+ +16 “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ+ በልጁ የሚያምን* ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል።+ +17 ምክንያቱም አምላክ ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ላይ እንዲፈርድ ሳይሆን ዓለም በእሱ አማካኝነት እንዲድን ነው።+ +18 በእሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም።+ በእሱ የማያምን ሁሉ ግን በአምላክ አንድያ ልጅ ስም ስለማያምን ቀድሞውኑም ተፈርዶበታል።+ +19 እንግዲህ የሚፈረድባቸው በዚህ መሠረት ነው፦ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤+ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለነበረ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ። +20 መጥፎ ነገር የሚያደርግ* ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ እንዲሁም ሥራው እንዳይጋለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም። +21 ትክክል የሆነውን የሚያደርግ ሁሉ ግን ያደረገው ነገር ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ የተከናወነ መሆኑ እንዲታይ ወደ ብርሃን ይመጣል።”+ +22 ከዚህ በኋላ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ ገጠራማ ክልል ሄዱ፤ በዚያም ከእነሱ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ቆየ፤ ያጠምቅም ነበር።+ +23 ይሁንና ዮሐንስም በሳሊም አቅራቢያ በሄኖን ብዙ ውኃ በመኖሩ+ በዚያ እያጠመቀ ነበር፤ ሰዎችም እየመጡ ይጠመቁ ነበር፤+ +24 በዚህ ጊዜ ዮሐንስ ገና እስር ቤት አልገባም ነበር።+ +25 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት የመንጻት ሥርዓትን በተመለከተ ከአንድ አይሁዳዊ ጋር ተከራከሩ። +26 ከዚያ በኋላ ወደ ዮሐንስ መጥተው “ረቢ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረውና ስለ እሱ የመሠከርክለት ሰው+ እያጠመቀ ነው፤ ሰዉም ሁሉ ወደ እሱ እየሄደ ነው” አሉት። +27 ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በቀር አንዳች ነገር ሊያገኝ አይችልም። +28 ‘እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፤+ ከዚህ ይልቅ ከእሱ በፊት የተላክሁ ነኝ’+ እንዳልኩ እናንተ ራሳችሁ ትመሠክራላችሁ። +29 ሙሽራይቱ የሙሽራው ናት።+ ይሁን እንጂ የሙሽራው ጓደኛ በዚያ ቆሞ ሲሰማው በሙሽራው ድምፅ የተነሳ እጅግ ደስ ይለዋል። በመሆኑም የእኔ ደስታ ተፈጽሟል። +30 እሱ እየጨመረ መሄድ አለበት፤ እኔ ግን እየቀነስኩ መሄድ አለብኝ።” +31 ከላይ የሚመጣው+ ከሌሎች ሁሉ በላይ ነው። ከምድር የሆነው ምድራዊ ነው፤ የሚናገረውም ስለ ምድራዊ ነገሮች ነው። ከሰማይ የሚመጣው ከሌሎች ሁሉ በላይ ነው።+ +32 ስላየውና ስለሰማው ነገር ይመሠክራል፤+ ነገር ግን ምሥክርነቱን የሚቀበል ሰው የለም።+ +33 ምሥክርነቱን የተቀበለ ሰው ሁሉ አምላክ እውነተኛ መሆኑን አረጋግጧል።*+ +34 ምክንያቱም አምላክ የላከው የአምላክን ቃል ይናገራል፤+ አምላክ መንፈሱን ቆጥቦ* አይሰጥምና። +35 አብ ወልድን ይወዳል፤+ ደግሞም ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል።+ +36 በወልድ የሚያምን* የዘላለም ሕይወት አለው፤+ ወልድን የማይታዘዝ ግን የአምላክ ቁጣ በላዩ ይኖራል+ እንጂ ሕይወትን አያይም።+ +7 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በገሊላ መዘዋወሩን* ቀጠለ፤ ምክንያቱም አይሁዳውያን ሊገድሉት ይፈልጉ+ ስለነበር በይሁዳ ምድር መዘዋወር አልፈለ���ም። +2 ይሁን እንጂ የአይሁዳውያን በዓል የሆነው የዳስ በዓል+ ተቃርቦ ነበር። +3 ስለዚህ ወንድሞቹ+ እንዲህ አሉት፦ “ደቀ መዛሙርትህም የምታከናውነውን ሥራ ማየት እንዲችሉ ከዚህ ተነስተህ ወደ ይሁዳ ሂድ። +4 በይፋ እንዲታወቅ እየፈለገ በስውር የሚሠራ ሰው የለምና። እነዚህን ነገሮች የምትሠራ ከሆነ ራስህን ለዓለም ግለጥ።” +5 ወንድሞቹም ቢሆኑ አላመኑበትም ነበር።+ +6 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ጊዜዬ ገና አልደረሰም፤+ ለእናንተ ግን ማንኛውም ጊዜ ተስማሚ ነው። +7 ዓለም እናንተን የሚጠላበት ምንም ምክንያት የለውም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ እንደሆነ ስለምመሠክርበት ይጠላኛል።+ +8 እናንተ ወደ በዓሉ ሂዱ፤ እኔ ግን ገና ጊዜዬ ስላልደረሰ+ ወደ በዓሉ አልሄድም።” +9 ይህን ከነገራቸው በኋላ በገሊላ ቆየ። +10 ሆኖም ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ እሱም በግልጽ ሳይሆን በስውር ወደዚያው ሄደ። +11 በበዓሉም ላይ አይሁዳውያን “ያ ሰው የት አለ?” እያሉ ይፈልጉት ጀመር። +12 በሕዝቡም መካከል ስለ እሱ ብዙ ጉምጉምታ ነበር። አንዳንዶች “እሱ ጥሩ ሰው ነው” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “አይደለም። እሱ ሕዝቡን ያሳስታል” ይሉ ነበር።+ +13 እርግጥ አይሁዳውያንን* ይፈሩ ስለነበረ ስለ እሱ በግልጽ የሚናገር ሰው አልነበረም።+ +14 በበዓሉም አጋማሽ ላይ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሄዶ ያስተምር ጀመር። +15 አይሁዳውያንም በጣም ተገርመው “ይህ ሰው ትምህርት ቤት* ገብቶ ሳይማር ቅዱሳን መጻሕፍትን* እንዴት እንዲህ ሊያውቅ ቻለ?” አሉ።+ +16 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “የማስተምረው ትምህርት የራሴ ሳይሆን ከላከኝ የመጣ ነው።+ +17 ማንም የእሱን ፈቃድ ማድረግ የሚፈልግ ከሆነ ይህ ትምህርት ከአምላክ የመጣ+ ይሁን ከራሴ ለይቶ ያውቃል። +18 ከራሱ አመንጭቶ የሚናገር ሁሉ ራሱ እንዲከበር ይፈልጋል፤ የላከው እንዲከበር+ የሚፈልግ ሁሉ ግን እሱ እውነተኛ ነው፤ በእሱም ዘንድ ዓመፅ የለም። +19 ሕጉን የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም?+ ሆኖም አንዳችሁም ሕጉን አትታዘዙም። እኔን ለመግደል የምትፈልጉት ለምንድን ነው?”+ +20 ሕዝቡም “አንተ ጋኔን አለብህ። ሊገድልህ የፈለገው ደግሞ ማን ነው?” ብለው መለሱለት። +21 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ነገር ስለሠራሁ ሁላችሁም ተደነቃችሁ። +22 እስቲ ይህን ልብ በሉ፦ ሙሴ የግርዘትን ሕግ ሰጣችሁ+ (ይህ ሕግ የተሰጠው ከአባቶች ነው+ እንጂ ከሙሴ አይደለም)፤ እናንተም በሰንበት ሰው ትገርዛላችሁ። +23 የሙሴ ሕግ እንዳይጣስ ሲባል በሰንበት ቀን ሰው የሚገረዝ ከሆነ እኔ በሰንበት አንድን ሰው መፈወሴ ይህን ያህል ሊያስቆጣችሁ ይገባል?+ +24 የሰውን ውጫዊ ገጽታ በማየት አትፍረዱ፤* ከዚህ ይልቅ በጽድቅ ፍረዱ።”+ +25 በዚህ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መካከል አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፦ “ሊገድሉት የሚፈልጉት ሰው ይህ አይደለም እንዴ?+ +26 እሱ ግን ይኸው በአደባባይ እየተናገረ ነው፤ እነሱም ምንም አላሉትም። ገዢዎቹ ይህ ሰው በእርግጥ ክርስቶስ እንደሆነ አስበው ይሆን? +27 ሆኖም እኛ ይህ ሰው ከየት እንደመጣ እናውቃለን፤+ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከየት እንደመጣ ማንም አያውቅም።” +28 ከዚያም ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ እያስተማረ ሳለ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “እኔ ማን እንደሆንኩም ሆነ ከየት እንደመጣሁ ታውቃላችሁ። የመጣሁትም በራሴ ተነሳስቼ አይደለም፤+ ሆኖም የላከኝ በእውን ያለ ነው፤ እናንተም አታውቁትም።+ +29 እኔ ግን የእሱ ተወካይ ሆኜ የመጣሁ ስለሆንኩ አውቀዋለሁ፤+ የላከኝም እሱ ነው።” +30 በመሆኑም ሊይዙት ፈለጉ፤+ ሆኖም ሰዓቱ ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም።+ +31 ይሁንና ከሕዝቡ መካከል ብዙዎች በእሱ አምነው+ “ክ���ስቶስስ በሚመጣበት ጊዜ ይህ ሰው ካደረገው የበለጠ ብዙ ተአምራዊ ምልክት ያደርጋል እንዴ?” ይሉ ነበር። +32 ፈሪሳውያን ሕዝቡ በጉምጉምታ ስለ እሱ የሚያወራውን ነገር ሰሙ፤ የካህናት አለቆቹና ፈሪሳውያኑም ይይዙት* ዘንድ የቤተ መቅደስ ጠባቂዎችን ላኩ። +33 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ከእናንተ ጋር የምቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ከዚያም ወደ ላከኝ እሄዳለሁ።+ +34 እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ ወደምሄድበትም ልትመጡ አትችሉም።”+ +35 በዚህ ጊዜ አይሁዳውያን እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “ይህ ሰው ልናገኘው የማንችለው ወዴት ሊሄድ ቢያስብ ነው? በግሪካውያን መካከል ተበታትነው ወደሚገኙት አይሁዳውያን ሄዶ ግሪካውያንን ሊያስተምር አስቦ ይሆን እንዴ? +36 ‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ ወደምሄድበትም ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ይሆን?” +37 የበዓሉ+ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “የተጠማ ካለ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።+ +38 በእኔ የሚያምን ሁሉ ቅዱስ መጽሐፉ እንደሚለው ‘የሕያው ውኃ ጅረቶች ከውስጡ ይፈስሳሉ።’”+ +39 ይሁን እንጂ ይህን ሲል በእሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት መንፈስ መናገሩ ነበር፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ክብሩን ገና ስላልተጎናጸፈ+ መንፈስ አልተሰጠም ነበር።+ +40 ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶች ይህን ቃል ሲሰሙ “ይህ ሰው በእርግጥ ነቢዩ ነው” ይሉ ጀመር።+ +41 ሌሎችም “ይህ ክርስቶስ ነው”+ ይሉ ነበር። አንዳንዶች ግን እንዲህ አሉ፦ “ክርስቶስ የሚመጣው ከገሊላ ነው እንዴ?+ +42 ቅዱስ መጽሐፉ ክርስቶስ ከዳዊት ዘርና+ ዳዊት ከኖረበት መንደር+ ከቤተልሔም+ እንደሚመጣ ይናገር የለም?” +43 ስለዚህ እሱን በተመለከተ በሕዝቡ መካከል ክፍፍል ተፈጠረ። +44 ይሁንና አንዳንዶቹ ሊይዙት* ፈልገው ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አልያዘውም። +45 ከዚያም የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ወደ ካህናት አለቆቹና ወደ ፈሪሳውያኑ ተመልሰው ሄዱ፤ እነሱም ጠባቂዎቹን “ለምን ይዛችሁት አልመጣችሁም?” አሏቸው። +46 ጠባቂዎቹም “ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም” ብለው መለሱ።+ +47 ፈሪሳውያኑ ግን እንዲህ አሏቸው፦ “እናንተም ተታለላችሁ? +48 ከገዢዎች ወይም ከፈሪሳውያን መካከል በእሱ ያመነ አለ?+ +49 ሕጉን የማያውቀው ይህ ሕዝብ ግን የተረገመ ነው።” +50 ቀደም ሲል ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረውና ከእነሱ አንዱ የሆነው ኒቆዲሞስ እንዲህ አላቸው፦ +51 “ሕጋችን በመጀመሪያ ግለሰቡ የሚለውን ሳይሰማና ምን እያደረገ እንዳለ ሳያውቅ ይፈርድበታል?”+ +52 እነሱም “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህ? ከገሊላ አንድም ነቢይ እንደማይነሳ ቅዱሳን መጻሕፍትን መርምረህ ተረዳ” አሉት።* +12 የፋሲካ በዓል ከመድረሱ ከስድስት ቀን በፊት ኢየሱስ፣ ከሞት ያስነሳው አልዓዛር+ ወደሚኖርባት ወደ ቢታንያ መጣ። +2 በዚያም የራት ግብዣ አዘጋጁለት፤ ማርታ ታገለግላቸው የነበረ+ ሲሆን አልዓዛር ግን ከእሱ ጋር ከሚበሉት አንዱ ነበር። +3 ከዚያም ማርያም ግማሽ ሊትር ገደማ* የሚሆን እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ይኸውም ንጹሕ ናርዶስ አምጥታ በኢየሱስ እግር ላይ አፈሰሰች፤ እግሩንም በፀጉሯ አብሳ አደረቀች። ቤቱም በዘይቱ መዓዛ ታወደ።+ +4 ሆኖም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነውና አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ+ እንዲህ አለ፦ +5 “ይህ ዘይት በ300 ዲናር* ተሸጦ ገንዘቡ ለድሆች ያልተሰጠው ለምንድን ነው?” +6 እንዲህ ያለው ግን ለድሆች አስቦ ሳይሆን ሌባ ስለነበረ ነው፤ የገንዘብ ሣጥኑን ይይዝ የነበረው እሱ በመሆኑ ወደ ሣጥኑ ከሚገባው ገንዘብ የመስረቅ ልማድ ነበረው። +7 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ለቀብሬ ቀን ለማዘጋጀት+ ብላ ያደረገችው ስለሆነ ይህን ልማድ እንዳትፈጽም አትከልክሏት። +8 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤+ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።”+ +9 በዚህ ጊዜ ብዙ አይሁዳውያን ኢየሱስ እዚያ መኖሩን አውቀው መጡ፤ የመጡትም ኢየሱስን ለማየት ብቻ ሳይሆን እሱ ከሞት ያስነሳውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።+ +10 በመሆኑም የካህናት አለቆቹ አልዓዛርንም ለመግደል አሴሩ፤ +11 ምክንያቱም በእሱ የተነሳ ብዙ አይሁዳውያን ወደዚያ እየሄዱ በኢየሱስ ያምኑ ነበር።+ +12 በማግስቱም ወደ በዓሉ የመጡ እጅግ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየመጣ መሆኑን ሰሙ። +13 በመሆኑም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ። እንዲህ እያሉም ይጮኹ ጀመር፦ “እንድታድነው እንለምንሃለን!* በይሖዋ* ስም የሚመጣው የእስራኤል ንጉሥ+ የተባረከ ነው!”+ +14 ኢየሱስ የአህያ ውርንጭላ አግኝቶ ተቀመጠበት፤+ ይህም የሆነው እንዲህ ተብሎ በተጻፈው መሠረት ነው፦ +15 “የጽዮን ልጅ ሆይ፣ አትፍሪ። እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል።”+ +16 ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ እነዚህን ነገሮች አላስተዋሉም ነበር፤ ኢየሱስ ክብር በተጎናጸፈ ጊዜ+ ግን እነዚህ ነገሮች የተጻፉት ስለ እሱ እንደሆነና እነዚህን ነገሮች ለእሱ እንዳደረጉለት ትዝ አላቸው።+ +17 ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር ጠርቶ+ ከሞት ባስነሳበት ጊዜ አብረውት የነበሩት ሰዎች ስላዩት ነገር ይመሠክሩ ነበር።+ +18 ከዚህም የተነሳ ይህን ተአምራዊ ምልክት መፈጸሙን የሰማው ሕዝብ ሊቀበለው ወጣ። +19 ስለዚህ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው “ምንም ማድረግ እንዳልቻልን አያችሁ! ተመልከቱ፣ ዓለሙ ሁሉ ግልብጥ ብሎ ተከትሎታል” ተባባሉ።+ +20 ለአምልኮ ወደ በዓሉ ከመጡት ሰዎች መካከል አንዳንድ ግሪካውያን ነበሩ። +21 እነሱም በገሊላ የምትገኘው የቤተሳይዳ ሰው ወደሆነው ወደ ፊልጶስ+ ቀርበው “ጌታ ሆይ፣ ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” ብለው ጠየቁት። +22 ፊልጶስ መጥቶ ለእንድርያስ ነገረው። ከዚያም እንድርያስና ፊልጶስ መጥተው ለኢየሱስ ነገሩት። +23 ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የሰው ልጅ ክብር የሚያገኝበት ሰዓት ደርሷል።+ +24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አንዲት የስንዴ ዘር መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች አንድ ዘር ብቻ ሆና ትቀራለች፤ ከሞተች ግን+ ብዙ ፍሬ ታፈራለች። +25 ሕይወቱን የሚወድ ሁሉ* ያጠፋታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን* የሚጠላ+ ሁሉ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል።+ +26 እኔን ሊያገለግል የሚፈልግ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔ ባለሁበት አገልጋዬም በዚያ ይሆናል።+ የሚያገለግለኝንም ሁሉ አብ ያከብረዋል። +27 አሁን ተጨንቄአለሁ፤*+ እንግዲህ ምን ማለት እችላለሁ? አባት ሆይ፣ ከዚህ ሰዓት አድነኝ።+ ይሁንና የመጣሁት ለዚህ ሰዓት ነው። +28 አባት ሆይ፣ ስምህን አክብረው።” በዚህ ጊዜ “ስሜን አክብሬዋለሁ፤ ደግሞም አከብረዋለሁ”+ የሚል ድምፅ+ ከሰማይ መጣ። +29 በዚያ ቆመው የነበሩት ብዙ ሰዎች ድምፁን በሰሙ ጊዜ ‘ነጎድጓድ ነው’ አሉ። ሌሎች ደግሞ “መልአክ አናገረው” አሉ። +30 ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ድምፅ የተሰማው ለእኔ ሳይሆን ለእናንተ ሲባል ነው። +31 ይህ ዓለም የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ የዚህ ዓለም ገዢ+ አሁን ይባረራል።+ +32 እኔ ግን ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከተደረግኩ+ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ወደ ራሴ እስባለሁ።” +33 ይህን የተናገረው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምን ዓይነት አሟሟት እንደሚሞት ለማመልከት ነው።+ +34 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ “ክርስቶስ ለዘላለም እንደሚኖር ከሕጉ ሰምተናል።+ ታዲያ አንተ የሰው ልጅ ከፍ ማለት አለበት እንዴት ትላለህ?+ ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለሱለት። +35 ኢየሱስ�� እንዲህ አላቸው፦ “ብርሃኑ ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ይቆያል። ጨለማ እንዳይውጣችሁ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃን ሂዱ፤ በጨለማ የሚሄድ ሁሉ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።+ +36 የብርሃን ልጆች+ እንድትሆኑ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃኑ እመኑ።” ኢየሱስ ይህን ተናግሮ እንደጨረሰ ሄደ፤ ከእነሱም ተሰወረ። +37 በፊታቸው ብዙ ተአምራዊ ምልክቶች ቢፈጽምም በእሱ አላመኑም፤ +38 ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፦ “ይሖዋ* ሆይ፣ ከእኛ የሰማውን* ነገር ያመነ ማን ነው?+ የይሖዋስ* ክንድ ለማን ተገለጠ?”+ +39 ደግሞም ኢሳይያስ ሊያምኑ ያልቻሉበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ተናግሯል፦ +40 “በዓይናቸው አይተውና በልባቸው አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳይፈውሳቸው ዓይናቸውን አሳውሯል፤ ልባቸውንም አደንድኗል።”+ +41 ኢሳይያስ ይህን የተናገረው የክርስቶስን ክብር ስላየ ነው፤ ስለ እሱም ተናገረ።+ +42 ያም ሆኖ ከገዢዎችም እንኳ ሳይቀር ብዙዎች በእሱ አመኑ፤+ ይሁንና ፈሪሳውያን ከምኩራብ እንዳያባርሯቸው ስለፈሩ በእሱ ማመናቸውን በግልጽ አይናገሩም ነበር፤+ +43 ይህም የሆነው ከሰው የሚገኘውን ክብር ከአምላክ ከሚገኘው ክብር አስበልጠው ስለወደዱ ነው።+ +44 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “በእኔ የሚያምን ሁሉ በእኔ ብቻ ሳይሆን በላከኝም ጭምር ያምናል፤+ +45 እኔን የሚያይ ሁሉ የላከኝንም ያያል።+ +46 በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር+ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።+ +47 ይሁንና ማንም ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቅ ከሆነ የምፈርድበት እኔ አይደለሁም፤ እኔ የመጣሁት ዓለምን ለማዳን እንጂ በዓለም ላይ ለመፍረድ አይደለምና።+ +48 እኔን የሚንቀውንና ቃሌን የማይቀበለውን ሁሉ የሚፈርድበት አለ። በመጨረሻው ቀን የሚፈርድበት የተናገርኩት ቃል ነው። +49 እኔ የተናገርኩት በራሴ ተነሳስቼ አይደለምና፤ ከዚህ ይልቅ ምን እንደምልና ምን እንደምናገር ያዘዘኝ የላከኝ አብ ራሱ ነው።+ +50 ደግሞም የእሱ ትእዛዝ የዘላለም ሕይወት እንደሚያስገኝ አውቃለሁ።+ ስለዚህ ምንጊዜም የምናገረው ልክ አባቴ በነገረኝ መሠረት ነው።”+ +1 በመጀመሪያ ቃል+ ነበረ፤ ቃልም ከአምላክ ጋር ነበር፤+ ቃልም አምላክ*+ ነበር። +2 እሱም በመጀመሪያ ከአምላክ ጋር ነበር። +3 ሁሉም ነገሮች ወደ ሕልውና የመጡት በእሱ በኩል ነው፤+ ያለእሱ ወደ ሕልውና የመጣ አንድም ነገር የለም። +4 በእሱ አማካኝነት ሕይወት ወደ ሕልውና መጥቷል፤ ይህ ሕይወት ደግሞ የሰው ብርሃን ነበር።+ +5 ብርሃኑም በጨለማ እየበራ ነው፤+ ጨለማውም አላሸነፈውም። +6 ከአምላክ የተላከ አንድ ሰው ነበር፤ እሱም ዮሐንስ+ ይባላል። +7 ይህ ሰው ስለ ብርሃኑ ይመሠክር ዘንድ ምሥክር ሆኖ መጣ፤+ ይህን ያደረገው ሁሉም ዓይነት ሰዎች በእሱ በኩል እንዲያምኑ ነው። +8 ያ ብርሃን እሱ አልነበረም፤+ ከዚህ ይልቅ እሱ የመጣው ስለ ብርሃኑ ሊመሠክር ነው። +9 ለሁሉም ዓይነት ሰው ብርሃን የሚሰጠው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም የሚመጣበት ጊዜ ደርሶ ነበር።+ +10 እሱም በዓለም ነበረ፤+ ዓለምም ወደ ሕልውና የመጣው በእሱ በኩል ነው፤+ ሆኖም ዓለም አላወቀውም። +11 ወደ ገዛ አገሩ መጣ፤ ነገር ግን የገዛ ወገኖቹ አልተቀበሉትም። +12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ስላመኑ+ የአምላክ ልጆች+ የመሆን መብት ሰጣቸው። +13 እነሱም የተወለዱት ከአምላክ እንጂ+ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አይደለም። +14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤+ በመካከላችንም ኖረ፤ አንድያ ልጅ+ ከአባቱ እንደሚያገኘው ክብር ያለ ክብሩን አየን፤ እሱም መለኮታዊ ሞገስንና* እውነትን ተሞልቶ ነበር። +15 (ዮሐንስ ስለ እሱ መሥክሯል፤ ��ንዲያውም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “‘ከእኔ ኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለነበረ ከእኔ ይበልጣል’ ብዬ የተናገርኩት ስለ እሱ ነው።”)+ +16 ከእሱ የጸጋ ሙላት የተነሳ ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀብለናል። +17 ምክንያቱም ሕጉ የተሰጠው በሙሴ በኩል ነበር፤+ ጸጋና+ እውነት ግን የመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው።+ +18 በየትኛውም ጊዜ ቢሆን አምላክን ያየው አንድም ሰው የለም፤+ ስለ እሱ የገለጸልን+ ከአብ ጎን* ያለውና+ አምላክ+ የሆነው አንድያ ልጁ ነው። +19 አይሁዳውያን “አንተ ማን ነህ?”+ ብለው እንዲጠይቁት ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩ ጊዜ ዮሐንስ የሰጠው ምሥክርነት ይህ ነው፤ +20 “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም” ብሎ በግልጽ ተናገረ እንጂ ጥያቄውን ከመመለስ ወደኋላ አላለም። +21 እነሱም “ታዲያ ማን ነህ? ኤልያስ ነህ?”+ ሲሉ ጠየቁት። እሱም መልሶ “አይደለሁም” አለ። “ነቢዩ ነህ?”+ አሉት። እሱም “አይደለሁም!” ሲል መለሰ። +22 በዚህ ጊዜ “ለላኩን ሰዎች መልስ መስጠት እንድንችል ታዲያ አንተ ማን ነህ? ስለ ራስህስ ምን ትላለህ?” አሉት። +23 እሱም “ነቢዩ ኢሳይያስ እንደተናገረው ‘የይሖዋን* መንገድ አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኸው ሰው እኔ ነኝ” አለ።+ +24 ሰዎቹን የላኳቸውም ፈሪሳውያን ነበሩ። +25 በመሆኑም “ታዲያ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካልሆንክ ለምን ታጠምቃለህ?” ሲሉ ጠየቁት። +26 ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ በውኃ አጠምቃለሁ። እናንተ የማታውቁት ግን በመካከላችሁ ቆሟል፤ +27 እሱም ከኋላዬ ይመጣል፤ እኔ የጫማውን ማሰሪያ እንኳ ለመፍታት አልበቃም።”+ +28 ይህ የሆነው ዮሐንስ ሲያጠምቅ+ ከነበረበት ከዮርዳኖስ ማዶ በሚገኘው በቢታንያ ነበር። +29 በማግስቱ ኢየሱስ ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው+ የአምላክ በግ+ ይኸውላችሁ!+ +30 ‘ከኋላዬ አንድ ሰው ይመጣል፤ ከእኔ በፊት ስለነበረ ከእኔ ይበልጣል’ ያልኳችሁ እሱ ነው።+ +31 እኔም እንኳ አላውቀውም ነበር፤ እኔ በውኃ እያጠመቅኩ የመጣሁበት ምክንያት ግን እሱ ለእስራኤል እንዲገለጥ ነው።”+ +32 በተጨማሪም ዮሐንስ እንዲህ ሲል ምሥክርነት ሰጥቷል፦ “መንፈስ ከሰማይ ወጥቶ እንደ ርግብ ሲወርድ አይቻለሁ፤ በእሱም ላይ አረፈ።+ +33 እኔም እንኳ አላውቀውም ነበር፤ ሆኖም በውኃ እንዳጠምቅ የላከኝ ራሱ ‘በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው፣+ መንፈስ ሲወርድበትና ሲያርፍበት+ የምታየው ያ ሰው ነው’ አለኝ። +34 እኔም አይቻለሁ፤ እሱም የአምላክ ልጅ መሆኑን መሥክሬአለሁ።”+ +35 በማግስቱም ዮሐንስ ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደገና በዚያ ቆሞ ነበር፤ +36 ኢየሱስ ሲያልፍ አይቶም “የአምላክ በግ+ ይኸውላችሁ!” አለ። +37 ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ይህን ሲናገር በሰሙ ጊዜ ኢየሱስን ተከተሉት። +38 ከዚያም ኢየሱስ ዞር ብሎ ሲከተሉት አየና “ምን ፈልጋችሁ ነው?” አላቸው። እነሱም “ረቢ፣ የት ነው የምትኖረው?” አሉት (ረቢ ማለት “መምህር” ማለት ነው)፤ +39 እሱም “ኑና እዩ” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የት እንደሚኖር አዩ፤ ጊዜውም አሥር ሰዓት ገደማ ነበር፤ በዚያም ዕለት አብረውት ዋሉ። +40 ዮሐንስ የተናገረውን ከሰሙትና ኢየሱስን ከተከተሉት ሁለት ሰዎች አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ+ ነበር። +41 እንድርያስ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና “መሲሑን አገኘነው”+ አለው (መሲሕ ማለት “ክርስቶስ” ማለት ነው)፤ +42 ወደ ኢየሱስም ወሰደው። ኢየሱስም ባየው ጊዜ “አንተ የዮሐንስ ልጅ ስምዖን+ ነህ፤ ኬፋ ተብለህ ትጠራለህ” አለው (ኬፋ ማለት “ጴጥሮስ” ማለት ነው)።+ +43 በማግስቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ ፈለገ። ከዚያም ፊልጶስን+ አግኝቶ “ተከታዬ ሁን” አለው። +44 ፊልጶስም እንደ እንድርያስና እንደ ጴጥሮስ የቤተሳይዳ ከተማ ሰው ነበረ። +45 ፊልጶስ ናትናኤልን+ አግኝቶ “ሙሴ በሕጉ፣ ነቢያት ደግሞ በመጻሕፍት የጻፉለትን የዮሴፍን+ ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው” አለው። +46 ናትናኤል ግን “ደግሞ ከናዝሬት ጥሩ ነገር ሊገኝ ይችላል?” አለው። ፊልጶስም “መጥተህ እይ” አለው። +47 ኢየሱስም ናትናኤል ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እሱ “ተንኮል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ይኸውላችሁ!” አለ።+ +48 ናትናኤልም “እንዴት ልታውቀኝ ቻልክ?” አለው። ኢየሱስም መልሶ “ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይቼሃለሁ” አለው። +49 ናትናኤልም “ረቢ፣ አንተ የአምላክ ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” ሲል መለሰለት።+ +50 ኢየሱስም መልሶ “ያመንከው ከበለስ ዛፍ ሥር አየሁህ ስላልኩህ ነው? ከዚህ የሚበልጥ ነገር ገና ታያለህ” አለው። +51 ከዚያም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማይ ተከፍቶ የአምላክ መላእክት ወደዚያ ሲወጡና የሰው ልጅ ወዳለበት ሲወርዱ ታያላችሁ” አለው።+ +8 12 ደግሞም ኢየሱስ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ።+ እኔን የሚከተል ሁሉ በምንም ዓይነት በጨለማ አይሄድም፤ ከዚህ ይልቅ የሕይወት ብርሃን ያገኛል።”+ +13 ፈሪሳውያንም “አንተ ስለ ራስህ ትመሠክራለህ፤ ምሥክርነትህም እውነት አይደለም” አሉት። +14 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ስለ ራሴ ብመሠክር እንኳ ከየት እንደመጣሁና ወዴት እንደምሄድ ስለማውቅ+ ምሥክርነቴ እውነት ነው። እናንተ ግን ከየት እንደመጣሁና ወዴት እንደምሄድ አታውቁም። +15 እናንተ በሥጋዊ አስተሳሰብ* ትፈርዳላችሁ፤+ እኔ በማንም ላይ አልፈርድም። +16 እኔ ብፈርድ እንኳ ፍርዴ እውነተኛ ነው፤ ምክንያቱም የምፈርደው ብቻዬን አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው።+ +17 በሕጋችሁም ላይ ‘የሁለት ሰዎች ምሥክርነት እውነት ነው’+ ተብሎ ተጽፏል። +18 ስለ ራሴ የምመሠክር አንዱ እኔ ነኝ፤ ደግሞም የላከኝ አብ ስለ እኔ ይመሠክራል።”+ +19 በዚህ ጊዜ “አባትህ የት ነው?” አሉት። ኢየሱስም “እናንተ እኔንም ሆነ አባቴን አታውቁም።+ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር”+ ሲል መለሰላቸው። +20 ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቤተ መቅደስ፣ ግምጃ ቤቱ+ አካባቢ ሆኖ ሲያስተምር ነበር። ሆኖም ሰዓቱ ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም።+ +21 ኢየሱስም እንደገና “እኔ እሄዳለሁ፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ይሁንና ኃጢአተኛ እንደሆናችሁ ትሞታላችሁ።+ እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም”+ አላቸው። +22 አይሁዳውያኑም “‘እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ የሚለው ራሱን ሊገድል አስቦ ይሆን እንዴ?” አሉ። +23 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ከምድር ናችሁ፤ እኔ ከላይ ነኝ።+ እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም። +24 በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ ያልኳችሁ ለዚህ ነው። እኔ እሱ እንደሆንኩ ካላመናችሁ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ።” +25 እነሱም “ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ድሮውንም እኔ ከእናንተ ጋር የምነጋገረው እንዲያው በከንቱ ነው። +26 ስለ እናንተ ብዙ የምናገረው ነገር አለኝ፤ ፍርድ የምሰጥበትም ብዙ ነገር አለኝ። በመሠረቱ የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእሱ የሰማሁትን ያንኑ ነገር ለዓለም እየተናገርኩ ነው።”+ +27 እነሱ ግን ስለ አብ እየነገራቸው እንደሆነ አልተረዱም ነበር። +28 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰውን ልጅ ከሰቀላችሁት+ በኋላ እኔ እሱ+ እንደሆንኩና በራሴ ተነሳስቼ አንዳች ነገር እንደማላደርግ+ ከዚህ ይልቅ እነዚህን ነገሮች የምናገረው ልክ አብ እንዳስተማረኝ መሆኑን ታውቃላችሁ። +29 እኔን የላከኝ ከእኔ ጋር ነው፤ ሁልጊዜ እሱን ደስ የሚያሰኘውን ስለማደርግ+ ብቻዬን አልተወኝም።” +30 ይህን በተናገረ ጊዜ ብዙዎች በእሱ አመኑ። +31 ከዚያም ኢየሱስ በእሱ ላመኑት አይሁዳውያን እንዲህ አለ፦ “ቃሌን ጠብቃችሁ ብትኖሩ በእርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ +32 እውነትንም ታውቃላችሁ፤+ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል።”+ +33 እነሱም መልሰው “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ለማንም ባሪያዎች ሆነን አናውቅም። ታዲያ አንተ ‘ነፃ ትወጣላችሁ’ እንዴት ትለናለህ?” አሉት። +34 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው።+ +35 ደግሞም ባሪያ በጌታው ቤት ለዘለቄታው አይኖርም፤ ልጅ ከሆነ ግን ሁልጊዜ ይኖራል። +36 ስለዚህ ወልድ ነፃ ካወጣችሁ፣ በእርግጥ ነፃ ትሆናላችሁ። +37 የአብርሃም ዘር እንደሆናችሁ አውቃለሁ። ሆኖም ቃሌ በእናንተ ውስጥ ሥር ስለማይሰድ ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። +38 እኔ ከአባቴ ጋር ሳለሁ ያየሁትን ነገር እናገራለሁ፤+ እናንተ ግን ከአባታችሁ የሰማችሁትን ነገር ታደርጋላችሁ።” +39 እነሱም መልሰው “አባታችን አብርሃም ነው” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የአብርሃም ልጆች+ ብትሆኑ ኖሮ አብርሃም የሠራውን ትሠሩ ነበር። +40 እናንተ ግን ከአምላክ የሰማሁትን እውነት የነገርኳችሁን+ እኔን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። አብርሃም እንዲህ አላደረገም። +41 እናንተ እየሠራችሁ ያላችሁት የአባታችሁን ሥራ ነው።” እነሱም “እኛስ በዝሙት* የተወለድን አይደለንም፤ እኛ አንድ አባት አለን፤ እሱም አምላክ ነው” አሉት። +42 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አምላክ አባታችሁ ቢሆን ኖሮ እኔ ወደዚህ የመጣሁት ከእሱ ዘንድ ስለሆነ በወደዳችሁኝ ነበር።+ እሱ ላከኝ እንጂ እኔ በራሴ ተነሳስቼ አልመጣሁም።+ +43 እየተናገርኩት ያለው ነገር የማይገባችሁ ለምንድን ነው? ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው። +44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት መፈጸም ትሻላችሁ።+ እሱ በራሱ መንገድ መሄድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ* ነፍሰ ገዳይ ነበር፤+ በእሱ ዘንድ እውነት ስለሌለ በእውነት ውስጥ ጸንቶ አልቆመም። ውሸታምና የውሸት አባት ስለሆነ ውሸት ሲናገር ከራሱ አመንጭቶ ይናገራል።+ +45 በሌላ በኩል ግን እኔ እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም። +46 ከመካከላችሁ እኔን ኃጢአት ሠርተሃል ብሎ በማስረጃ ሊወነጅለኝ የሚችል ማን ነው? የምናገረው እውነት ከሆነ ደግሞ የማታምኑኝ ለምንድን ነው? +47 ከአምላክ የሆነ የአምላክን ቃል ይሰማል።+ እናንተ ግን ከአምላክ ስላልሆናችሁ አትሰሙም።”+ +48 አይሁዳውያኑም መልሰው “‘አንተ ሳምራዊ+ ነህ፤ ደግሞም ጋኔን አድሮብሃል’+ ማለታችን ትክክል አይደለም?” አሉት። +49 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ አባቴን አከብራለሁ እንጂ ጋኔን የለብኝም፤ እናንተ ግን ታቃልሉኛላችሁ። +50 እኔ ለራሴ ክብር እየፈለግኩ አይደለም፤+ ይሁንና ይህን የሚፈልግና የሚፈርድ አለ። +51 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ቃሌን የሚጠብቅ ከሆነ ፈጽሞ ሞትን አያይም።”+ +52 አይሁዳውያኑም እንዲህ አሉት፦ “አሁን በእርግጥ ጋኔን እንዳለብህ ተረዳን። አብርሃም ሞቷል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ‘ማንም ሰው ቃሌን የሚጠብቅ ከሆነ ፈጽሞ ሞትን አይቀምስም’ ትላለህ። +53 አንተ ከሞተው ከአባታችን ከአብርሃም ትበልጣለህ እንዴ? ነቢያትም ሞተዋል። ለመሆኑ አንተ ማን ነኝ ልትል ነው?” +54 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ራሴን የማከብር ከሆነ ክብሬ ከን�� ነው። እኔን የሚያከብረኝ እናንተ አምላካችን ነው የምትሉት አባቴ ነው።+ +55 ሆኖም እናንተ አላወቃችሁትም፤+ እኔ ግን አውቀዋለሁ።+ አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ውሸታም መሆኔ ነው። ይሁንና እኔ አውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ። +56 አባታችሁ አብርሃም ቀኔን እንደሚያይ ተስፋ በማድረግ እጅግ ተደሰተ፤ አይቶትም ደስ ተሰኘ።”+ +57 አይሁዳውያኑም “አንተ ገና 50 ዓመት እንኳ ያልሞላህ፣ አብርሃምን አይቼዋለሁ ትላለህ?” አሉት። +58 ኢየሱስም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ ነበርኩ” አላቸው።+ +59 በዚህ ጊዜ ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወረና ከቤተ መቅደሱ ወጥቶ ሄደ። +11 ማርያምና እህቷ ማርታ+ በሚኖሩበት መንደር በቢታንያ አልዓዛር የተባለ ሰው ታሞ ነበር። +2 ማርያም በጌታ ላይ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ያፈሰሰችውና በፀጉሯ እግሩን ያበሰችው+ ሴት ስትሆን የታመመውም፣ ወንድሟ አልዓዛር ነበር። +3 ስለዚህ እህቶቹ “ጌታ ሆይ፣ የምትወደው ሰው ታሟል” ሲሉ መልእክት ላኩበት። +4 ኢየሱስ ግን ይህን በሰማ ጊዜ “ይህ ሕመም ለአምላክ ክብር የሚያመጣ ነው+ እንጂ በሞት የሚያበቃ አይደለም፤ ይህም የአምላክ ልጅ በዚህ አማካኝነት ክብር ይጎናጸፍ ዘንድ ነው” አለ። +5 ኢየሱስ ማርታንና እህቷን እንዲሁም አልዓዛርን ይወዳቸው ነበር። +6 ይሁን እንጂ አልዓዛር መታመሙን ከሰማ በኋላ በዚያው በነበረበት ቦታ ሁለት ቀን ቆየ። +7 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን “ተመልሰን ወደ ይሁዳ እንሂድ” አላቸው። +8 ደቀ መዛሙርቱ ግን “ረቢ፣+ በቅርቡ እኮ የይሁዳ ሰዎች በድንጋይ ሊወግሩህ ፈልገው ነበር፤+ ታዲያ ወደዚያ ተመልሰህ ልትሄድ ነው?” አሉት። +9 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ብርሃን የሚሆንበት 12 ሰዓት አለ አይደል?+ ማንም ሰው በቀን ብርሃን የሚሄድ ከሆነ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ ምንም ነገር አያደናቅፈውም። +10 ሆኖም በሌሊት የሚሄድ ሰው በእሱ ዘንድ ብርሃን ስለሌለ ይደናቀፋል።” +11 ይህን ከነገራቸው በኋላም “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤+ እኔም ልቀሰቅሰው ወደዚያ እሄዳለሁ” አላቸው። +12 በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ “ጌታ ሆይ፣ ተኝቶ ከሆነ ይሻለዋል” አሉት። +13 ይሁንና ኢየሱስ የተናገረው ስለመሞቱ ነበር። እነሱ ግን ለማረፍ ብሎ እንቅልፍ ስለመተኛቱ የተናገረ መሰላቸው። +14 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ በግልጽ እንዲህ አላቸው፦ “አልዓዛር ሞቷል፤+ +15 ታምኑ ዘንድ በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል። ያም ሆነ ይህ ወደ እሱ እንሂድ።” +16 በዚህ ጊዜ ዲዲሞስ* የሚባለው ቶማስ ለተቀሩት ደቀ መዛሙርት “ከእሱ ጋር እንድንሞት አብረነው እንሂድ” አላቸው።+ +17 ኢየሱስ እዚያ በደረሰ ጊዜ አልዓዛር በመቃብር ውስጥ አራት ቀን እንደሆነው አወቀ። +18 ቢታንያ ለኢየሩሳሌም ቅርብ የነበረች ሲሆን ሦስት ኪሎ ሜትር ያህል* ርቀት ላይ ትገኝ ነበር። +19 ወንድማቸውን በሞት ያጡትን ማርታንና ማርያምን ለማጽናናት ብዙ አይሁዳውያን መጥተው ነበር። +20 ማርታ፣ ኢየሱስ እየመጣ መሆኑን ስትሰማ ልትቀበለው ወጣች፤ ማርያም+ ግን እዚያው ቤት ቀረች። +21 ማርታም ኢየሱስን እንዲህ አለችው፦ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር። +22 አሁንም ቢሆን አምላክ የጠየቅከውን ነገር ሁሉ እንደሚሰጥህ አምናለሁ።” +23 ኢየሱስም “ወንድምሽ ይነሳል” አላት። +24 ማርታም “በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንደሚነሳ አውቃለሁ” አለችው።+ +25 ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ።+ በእኔ የሚያምን* ሁሉ ቢሞት እንኳ እንደገና ሕያው ይሆናል፤ +26 በሕይወት ያለና በእኔ የሚያምን ሁሉ ደግሞ ፈጽሞ አይሞትም።+ ይህን ታምኛለሽ?” +27 እሷም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው የአምላክ ልጅ ክርስቶስ መሆንህን አምናለሁ” አለችው። +28 ይህን ካለች በኋላም ሄዳ እህቷን ማርያምን ለብቻዋ ጠርታት “መምህሩ+ መጥቷል፤ እየጠራሽ ነው” አለቻት። +29 ማርያምም ይህን ስትሰማ በፍጥነት ተነስታ ወደ እሱ ሄደች። +30 ይሁንና ኢየሱስ እዚያው ማርታ ያገኘችው ቦታ ነበር እንጂ ገና ወደ መንደሩ አልገባም ነበር። +31 እሷን እያጽናኑ በቤት አብረዋት የነበሩ አይሁዳውያንም ማርያም ፈጥና ተነስታ ስትወጣ ሲያዩ ወደ መቃብሩ+ ሄዳ ልታለቅስ መስሏቸው ተከተሏት። +32 ማርያምም ኢየሱስ የነበረበት ቦታ ደርሳ ባየችው ጊዜ እግሩ ላይ ተደፋች፤ ከዚያም “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር” አለችው። +33 ኢየሱስ እሷ ስታለቅስና አብረዋት የመጡት አይሁዳውያን ሲያለቅሱ ሲያይ እጅግ አዘነ፤* ተረበሸም። +34 እሱም “የት ነው ያኖራችሁት?” አለ። እነሱም “ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ” አሉት። +35 ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።+ +36 በዚህ ጊዜ አይሁዳውያኑ “እንዴት ይወደው እንደነበር ተመልከቱ!” አሉ። +37 ሆኖም ከእነሱ መካከል አንዳንዶች “የዓይነ ስውሩን ዓይን ያበራው ይህ ሰው+ ይሄኛውንም እንዳይሞት ማድረግ አይችልም ነበር?” አሉ። +38 ከዚያም ኢየሱስ ልቡ ዳግመኛ በሐዘን ታውኮ ወደ መቃብሩ መጣ። መቃብሩ ዋሻ ሲሆን በድንጋይም ተዘግቶ ነበር። +39 ኢየሱስ “ድንጋዩን አንሱት” አለ። የሟቹ እህት ማርታም “ጌታ ሆይ፣ አራት ቀን ስለሆነው አሁን ይሸታል” አለችው። +40 ኢየሱስም “ካመንሽ የአምላክን ክብር ታያለሽ ብዬ አልነገርኩሽም?” አላት።+ +41 ስለዚህ ድንጋዩን አነሱት። ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመልክቶ+ እንዲህ አለ፦ “አባት ሆይ፣ ስለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። +42 እውነት ነው፣ ሁልጊዜ እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፤ ይህን ያልኩት ግን እዚህ የቆሙት ሰዎች አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ ነው።”+ +43 ይህን ከተናገረ በኋላ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” አለ።+ +44 የሞተው ሰው እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው። +45 በመሆኑም ወደ ማርያም መጥተው ከነበሩትና ያደረገውን ነገር ካዩት አይሁዳውያን መካከል ብዙዎቹ በእሱ አመኑ፤+ +46 አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገር ነገሯቸው። +47 ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የሳንሄድሪንን ሸንጎ ሰብስበው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ብዙ ተአምራዊ ምልክቶች እያደረገ ስለሆነ ምን ብናደርግ ይሻላል?+ +48 እንዲሁ ብንተወው ሁሉም በእሱ ያምናሉ፤ ሮማውያንም መጥተው ቦታችንንና* ሕዝባችንን ይወስዱብናል።” +49 ሆኖም ከመካከላቸው አንዱ፣ በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ+ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ምንም አታውቁም፤ +50 ደግሞም ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ፣ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት እንደሚሻል ማሰብ ተስኗችኋል።” +51 ይሁንና ይህን የተናገረው ከራሱ አመንጭቶ አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት ስለነበረ ኢየሱስ ለሕዝቡ እንደሚሞት ትንቢት መናገሩ ነበር፤ +52 የሚሞተውም ለሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ተበታትነው ያሉትን የአምላክ ልጆችም አንድ ላይ መሰብሰብ ይችል ዘንድ ነው። +53 ስለዚህ ከዚያን ቀን አንስቶ ሊገድሉት አሴሩ። +54 በመሆኑም ኢየሱስ ከዚያን ጊዜ አንስቶ በአይሁዳውያን መካከል በይፋ መንቀሳቀስ አቆመ፤ ከዚህ ይልቅ በምድረ በዳ አቅራቢያ ወዳለ ስፍራ ሄደ፤ በዚያም ኤፍሬም+ ተብላ በምትጠራ ከተማ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ። +55 በዚህ ወቅት የአይሁዳውያን ፋሲካ+ ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም ከፋሲካ በፊት የ���ንጻት ሥርዓት ለመፈጸም ከገጠር ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ። +56 ኢየሱስንም ይፈልጉት ጀመር፤ በቤተ መቅደሱም ቆመው እርስ በርሳቸው “ምን ይመስላችኋል? ጭራሽ ወደ በዓሉ አይመጣ ይሆን?” ይባባሉ ነበር። +57 የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን መያዝ* እንዲችሉ እሱ ያለበትን ቦታ የሚያውቅ ሁሉ እንዲጠቁማቸው አዘው ነበር። +2 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ በምትገኘው በቃና የሠርግ ድግስ ነበር፤ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች። +2 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሠርጉ ተጠርተው ነበር። +3 የወይን ጠጁ እያለቀ ሲሄድ የኢየሱስ እናት “የወይን ጠጅ አልቆባቸዋል” አለችው። +4 ኢየሱስ ግን “አንቺ ሴት፣ ይህ ጉዳይ እኔንና አንቺን ምን ይመለከተናል?* ሰዓቴ ገና አልደረሰም” አላት። +5 እናቱም በዚያ የሚያገለግሉትን ሰዎች “የሚላችሁን ነገር ሁሉ አድርጉ” አለቻቸው። +6 የአይሁዳውያን የመንጻት ሥርዓት በሚያዘው መሠረት+ እያንዳንዳቸው ሁለት ወይም ሦስት የፈሳሽ መለኪያዎች* የሚይዙ ከድንጋይ የተሠሩ ስድስት የውኃ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር። +7 ኢየሱስም “ጋኖቹን ውኃ ሙሏቸው” አላቸው። እነሱም እስከ አፋቸው ድረስ ሞሏቸው። +8 ከዚያም “አሁን ቀድታችሁ ለድግሱ አሳዳሪ ስጡት” አላቸው። እነሱም ወስደው ሰጡት። +9 የድግሱ አሳዳሪም ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውኃ ቀመሰ፤ ሆኖም ከየት እንደመጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ +10 እንዲህ አለው፦ “ሰው ሁሉ በቅድሚያ ጥሩውን የወይን ጠጅ ያቀርብና ሰዎቹ ከሰከሩ በኋላ መናኛውን ያቀርባል። አንተ ግን ጥሩውን የወይን ጠጅ እስካሁን ድረስ አስቀምጠሃል።” +11 ኢየሱስ ከምልክቶቹ የመጀመሪያ የሆነውን ይህን ተአምር በገሊላ በምትገኘው በቃና ፈጸመ፤ ክብሩንም ገለጠ፤+ ደቀ መዛሙርቱም በእሱ አመኑ። +12 ከዚህ በኋላ እሱና እናቱ እንዲሁም ወንድሞቹና+ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆም+ ወረዱ፤ ሆኖም በዚያ ብዙ ቀን አልቆዩም። +13 በዚህ ጊዜ የአይሁዳውያን ፋሲካ*+ ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። +14 በቤተ መቅደሱ ውስጥ ከብት፣ በግና ርግብ+ የሚሸጡ ሰዎችን እንዲሁም በዚያ የተቀመጡ ገንዘብ መንዛሪዎችን አገኘ። +15 በዚህ ጊዜ የገመድ ጅራፍ ሠርቶ ሁሉንም ከበጎቻቸውና ከከብቶቻቸው ጋር አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ሳንቲሞች በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለባበጠ።+ +16 ርግብ ሻጮቹንም “እነዚህን ከዚህ አስወጡ! የአባቴን ቤት የንግድ ቤት* ማድረጋችሁ ይብቃ!” አላቸው።+ +17 ደቀ መዛሙርቱም “ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት ይበላኛል”+ ተብሎ የተጻፈው ትዝ አላቸው። +18 በዚህ ጊዜ አይሁዳውያን መልሰው “እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ የሚያረጋግጥ ምን ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት።+ +19 ኢየሱስም መልሶ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ እኔም በሦስት ቀን ውስጥ አነሳዋለሁ” አላቸው።+ +20 አይሁዳውያኑም “ቤተ መቅደሱን ለመገንባት 46 ዓመት ፈጅቷል፤ ታዲያ አንተ በሦስት ቀን ታነሳዋለህ?” አሉት። +21 እሱ ግን ቤተ መቅደስ ሲል ስለ ራሱ ሰውነት መናገሩ ነበር።+ +22 ከሙታን በተነሳ ጊዜም፣ ደቀ መዛሙርቱ ይህን ደጋግሞ ይናገር እንደነበር አስታወሱ፤+ ቅዱሳን መጻሕፍትንና ኢየሱስ የተናገረውንም ቃል አመኑ። +23 ይሁንና በፋሲካ በዓል፣ በኢየሩሳሌም በነበረበት ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚያከናውናቸውን ተአምራዊ ምልክቶች ሲያዩ በስሙ አመኑ። +24 ኢየሱስ ግን ሁሉንም ያውቃቸው ስለነበር አይተማመንባቸውም ነበር፤ +25 እንዲሁም በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ስለነበር ማንም ስለ ሰው እንዲመሠክርለት አላስፈለገውም።+ +4 ጌታ፣ ከዮሐንስ ይበልጥ ብዙ ደቀ መዛሙርት እያ��ራና እያጠመቀ+ መሆኑን ፈሪሳውያን እንደሰሙ ባወቀ ጊዜ፣ +2 (እርግጥ ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም) +3 ይሁዳን ለቆ እንደገና ወደ ገሊላ ሄደ። +4 ሆኖም በሰማርያ በኩል ማለፍ ነበረበት። +5 ስለሆነም ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው መሬት አጠገብ+ ወዳለችው ሲካር ወደተባለች የሰማርያ ከተማ መጣ። +6 ደግሞም በዚያ የያዕቆብ የውኃ ጉድጓድ ነበረ።+ ኢየሱስም ከጉዞው የተነሳ ደክሞት ስለነበር በውኃ ጉድጓዱ* አጠገብ ተቀመጠ። ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር። +7 አንዲት የሰማርያ ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም “እባክሽ፣ የምጠጣው ውኃ ስጪኝ” አላት። +8 (ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማዋ ሄደው ነበር።) +9 ሳምራዊቷም “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለ እኔን ሳምራዊቷን እንዴት የምጠጣው ውኃ ስጪኝ ትለኛለህ?” አለችው። (ይህን ያለችው አይሁዳውያን ከሳምራውያን ጋር ምንም ግንኙነት ስላልነበራቸው ነው።)+ +10 ኢየሱስም መልሶ “የአምላክን ነፃ ስጦታ+ ብታውቂና ‘የምጠጣው ውኃ ስጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብትረጂ ኖሮ አንቺ ራስሽ ትጠይቂው ነበር፤ እሱም ሕያው ውኃ ይሰጥሽ ነበር”+ አላት። +11 እሷም እንዲህ አለችው፦ “ጌታዬ፣ አንተ ውኃ መቅጃ እንኳ የለህም፤ ጉድጓዱ ደግሞ ጥልቅ ነው። ታዲያ ይህን ሕያው ውኃ ከየት ታገኛለህ? +12 አንተ ይህን የውኃ ጉድጓድ ከሰጠን እንዲሁም ከልጆቹና ከከብቶቹ ጋር ከዚህ ጉድጓድ ከጠጣው ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህ?” +13 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል። +14 እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ፈጽሞ አይጠማም፤+ ከዚህ ይልቅ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት የሚያስገኝ የውኃ ምንጭ ይሆናል።”+ +15 ሴትየዋም “ጌታዬ፣ እንዳልጠማም ሆነ ውኃ ለመቅዳት ወደዚህ ቦታ እንዳልመላለስ ይህን ውኃ ስጠኝ” አለችው። +16 እሱም “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ተመልሰሽ ነይ” አላት። +17 ሴትየዋም “ባል የለኝም” ብላ መለሰችለት። ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “‘ባል የለኝም’ ማለትሽ ትክክል ነው። +18 ምክንያቱም አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁን አብሮሽ ያለው ሰው ደግሞ ባልሽ አይደለም። ስለዚህ የተናገርሽው እውነት ነው።” +19 ሴትየዋም እንዲህ አለችው፦ “ጌታዬ፣ አንተ ነቢይ እንደሆንክ አሁን ተረዳሁ።+ +20 አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ አምልኳቸውን ያካሂዱ ነበር፤ እናንተ አይሁዳውያን ግን ሰዎች ማምለክ ያለባቸው በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ።”+ +21 ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “አንቺ ሴት፣ እመኚኝ፤ በዚህ ተራራም ሆነ በኢየሩሳሌም አብን የማታመልኩበት ሰዓት ይመጣል። +22 እናንተ የማታውቁትን ታመልካላችሁ፤+ እኛ ግን መዳን የሚጀምረው ከአይሁዳውያን ስለሆነ የምናውቀውን እናመልካለን።+ +23 ይሁንና እውነተኛ አምላኪዎች አብን በመንፈስና በእውነት የሚያመልኩበት ሰዓት ይመጣል፤ ያም ሰዓት አሁን ነው፤ ምክንያቱም አብ እንዲያመልኩት የሚፈልገው እንዲህ ያሉ ሰዎችን ነው።+ +24 አምላክ መንፈስ ነው፤+ የሚያመልኩትም በመንፈስና በእውነት ሊያመልኩት ይገባል።”+ +25 ሴትየዋም “ክርስቶስ የተባለ መሲሕ እንደሚመጣ አውቃለሁ። እሱ ሲመጣ ሁሉንም ነገር ግልጥልጥ አድርጎ ይነግረናል” አለችው። +26 ኢየሱስም “እያነጋገርኩሽ ያለሁት እኔ፣ እሱ ነኝ” አላት።+ +27 በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡ፤ ከሴት ጋር ሲነጋገር አይተውም ተደነቁ። ይሁን እንጂ “ምን ፈልገህ ነው?” ወይም “ከእሷ ጋር የምትነጋገረው ለምንድን ነው?” ያለው ማንም አልነበረም። +28 ሴትየዋም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማዋ በመሄድ ሰዎቹን እንዲህ አለቻቸው፦ +29 “ያደረግኩትን ሁሉ የነገረኝን ሰው መጥታችሁ እዩ። ��ህ ሰው ክርስቶስ ይሆን እንዴ?” +30 እነሱም ከከተማዋ ወጥተው ወደ እሱ መጡ። +31 በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ “ረቢ፣+ ብላ እንጂ” እያሉ ጎተጎቱት። +32 እሱ ግን “እናንተ የማታውቁት የምበላው ምግብ አለኝ” አላቸው። +33 ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው “ምግብ ያመጣለት ይኖር ይሆን እንዴ?” ተባባሉ። +34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና+ እንዳከናውነው የሰጠኝን ሥራ መፈጸም ነው።+ +35 እናንተ መከር ሊገባ ገና አራት ወር ይቀረዋል ትሉ የለም? እነሆ እላችኋለሁ፣ ዓይናችሁን ወደ ማሳው አቅንታችሁ አዝመራው እንደነጣ ተመልከቱ።+ +36 አሁንም እንኳ አጫጁ ደሞዙን እየተቀበለና ለዘላለም ሕይወት ፍሬ እየሰበሰበ ነው፤ ስለዚህ ዘሪውም ሆነ አጫጁ በአንድነት ደስ ይላቸዋል።+ +37 ከዚህም የተነሳ ‘አንዱ ይዘራል፤ ሌላኛውም ያጭዳል’ የሚለው አባባል እውነት ነው። +38 እኔም ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ። ሌሎች በደከሙበት እናንተ የድካማቸው ፍሬ ተካፋዮች ሆናችሁ።” +39 ሴትየዋ “ያደረግኩትን ሁሉ ነገረኝ”+ ብላ ስለመሠከረች ከዚያች ከተማ ብዙ ሳምራውያን በእሱ አመኑ። +40 ሳምራውያኑም ወደ እሱ በመጡ ጊዜ አብሯቸው እንዲቆይ ለመኑት፤ እሱም በዚያ ሁለት ቀን ቆየ። +41 በመሆኑም ሌሎች ብዙ ሰዎች ከተናገረው ቃል የተነሳ አመኑ፤ +42 ሴትየዋንም “ከእንግዲህ የምናምነው አንቺ ስለነገርሽን ብቻ አይደለም፤ ምክንያቱም እኛ ራሳችን ሰምተናል፤ እንዲሁም ይህ ሰው በእርግጥ የዓለም አዳኝ+ እንደሆነ አውቀናል” አሏት። +43 ከሁለት ቀናት በኋላ ከዚያ ተነስቶ ወደ ገሊላ ሄደ። +44 ይሁንና ኢየሱስ ራሱ፣ ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር+ ተናግሮ ነበር። +45 ገሊላ በደረሰ ጊዜም የገሊላ ሰዎች በጥሩ ሁኔታ ተቀበሉት፤ ምክንያቱም በኢየሩሳሌም በበዓሉ ላይ ተገኝተው+ በዚያ ያከናወናቸውን ነገሮች ሁሉ አይተው ነበር።+ +46 ከዚያም ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ ወደለወጠባት በገሊላ ወደምትገኘው ወደ ቃና በድጋሚ መጣ።+ በዚህ ጊዜ በቅፍርናሆም፣ ልጁ የታመመበት የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን የሆነ አንድ ሰው ነበር። +47 ይህ ሰው ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መምጣቱን ሲሰማ ወደ እሱ ሄደና ወደ ቅፍርናሆም ወርዶ በሞት አፋፍ ላይ ያለውን ልጁን እንዲፈውስለት ለመነው። +48 ኢየሱስ ግን “መቼም እናንተ ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ካላያችሁ ፈጽሞ አታምኑም” አለው።+ +49 የቤተ መንግሥት ባለሥልጣኑም “ጌታዬ፣ ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ በቶሎ ድረስ” አለው። +50 ኢየሱስም “ሂድ፤ ልጅህ ድኗል” አለው።+ ሰውየውም ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አምኖ ሄደ። +51 ሆኖም ሰውየው ወደዚያ እየወረደ ሳለ ባሪያዎቹ አገኙትና ልጁ በሕይወት እንዳለ* ነገሩት። +52 እሱም ልጁ ስንት ሰዓት ላይ እንደተሻለው ጠየቃቸው። እነሱም “ትናንት ሰባት ሰዓት ላይ ትኩሳቱ ለቀቀው” ብለው መለሱለት። +53 በዚህ ጊዜ አባትየው ልጁ የዳነው ልክ ኢየሱስ “ልጅህ ድኗል” ባለው ሰዓት ላይ መሆኑን አወቀ።+ እሱና መላው ቤተሰቡም አማኞች ሆኑ። +54 ይህም ደግሞ ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ ሲመጣ ያከናወነው ሁለተኛው ተአምራዊ ምልክት ነው።+ +16 “ይህን ሁሉ የነገርኳችሁ እንዳትሰናከሉ ብዬ ነው። +2 ሰዎች ከምኩራብ ያባርሯችኋል።+ እንዲያውም እናንተን የሚገድል+ ሁሉ ለአምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንዳቀረበ አድርጎ የሚያስብበት ሰዓት ይመጣል። +3 ሆኖም እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉት አብንም ሆነ እኔን ስላላወቁ ነው።+ +4 ይሁንና እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ የሚፈጸሙበት ሰዓት ሲደርስ አስቀድሜ ነግሬአችሁ እንደነበረ እንድታስታውሱ ነው።+ “ከእናንተ ጋር ስለነበርኩ እነዚህን ነገሮች በመጀመሪያ አልነገርኳችሁም። +5 አሁን ግን ወደ ላከኝ ልሄድ ነው፤+ ሆኖም ከመካከላችሁ ‘ወዴት ነው የምትሄደው?’ ብሎ የጠየቀኝ የለም። +6 እነዚህን ነገሮች ስለነገርኳችሁ ልባችሁ በሐዘን ተሞልቷል።+ +7 ይሁንና እውነቱን ለመናገር እኔ የምሄደው ለእናንተው ጥቅም ነው። ምክንያቱም እኔ ካልሄድኩ ረዳቱ*+ በምንም ዓይነት ወደ እናንተ አይመጣም፤ ከሄድኩ ግን እሱን ወደ እናንተ እልከዋለሁ። +8 እሱ ሲመጣ ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ለዓለም አሳማኝ ማስረጃ ያቀርባል፦ +9 በመጀመሪያ ደረጃ ስለ ኃጢአት+ የተባለው፣ ሰዎች በእኔ ስላላመኑ ነው፤+ +10 ከዚያም ስለ ጽድቅ የተባለው፣ እኔ ወደ አብ ስለምሄድና እናንተ ከእንግዲህ ስለማታዩኝ ነው፤ +11 ስለ ፍርድ የተባለው ደግሞ የዚህ ዓለም ገዢ ስለተፈረደበት ነው።+ +12 “ገና ብዙ የምነግራችሁ ነገር አለኝ፤ አሁን ግን ልትሸከሙት አትችሉም። +13 ይሁን እንጂ እሱ* ይኸውም የእውነት መንፈስ+ ሲመጣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ምክንያቱም የሚናገረው ከራሱ አመንጭቶ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሰማውን ይናገራል፤ እንዲሁም ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ያሳውቃችኋል።+ +14 የሚያሳውቃችሁ+ የእኔ ከሆነው ወስዶ ስለሆነ እሱ እኔን ያከብረኛል።+ +15 አብ ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ነው።+ የእኔ ከሆነው ወስዶ ያሳውቃችኋል ያልኳችሁ ለዚህ ነው። +16 ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤+ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ።” +17 በዚህ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው “‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ’ እንዲሁም ‘ወደ አብ ልሄድ ነውና’ ሲለን ምን ማለቱ ነው?” ተባባሉ። +18 ስለዚህ “‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ’ ሲል ምን ማለቱ ነው? ስለ ምን ነገር እየተናገረ እንደሆነ አልገባንም” አሉ። +19 ኢየሱስ ሊጠይቁት እንደፈለጉ ተረድቶ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሳችሁ ስለዚህ ጉዳይ የምትጠያየቁት ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ’ ስላልኩ ነው? +20 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ ታለቅሳላችሁ እንዲሁም ዋይ ዋይ ትላላችሁ፤ ዓለም ግን ይደሰታል፤ እናንተ ታዝናላችሁ፤ ሆኖም ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።+ +21 አንዲት ሴት የመውለጃዋ ሰዓት ደርሶ ስታምጥ ትጨነቃለች፤ ሕፃኑን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሰው ወደ ዓለም በመምጣቱ ከደስታዋ የተነሳ ሥቃይዋን ሁሉ ትረሳለች። +22 ስለዚህ እናንተም አሁን አዝናችኋል፤ ሆኖም እንደገና ስለማያችሁ ልባችሁ በደስታ ይሞላል፤+ ደስታችሁን ደግሞ ማንም አይነጥቃችሁም። +23 በዚያን ጊዜ እኔን ምንም ጥያቄ አትጠይቁኝም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አብን ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትጠይቁት+ ይሰጣችኋል።+ +24 እስካሁን ድረስ በስሜ አንድም ነገር አልጠየቃችሁም። ደስታችሁ የተሟላ እንዲሆን ጠይቁ፤ ትቀበላላችሁ። +25 “እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ በምሳሌ ነው። ይሁንና ለእናንተ በምሳሌ የማልናገርበት ሰዓት ይመጣል፤ ከዚህ ይልቅ ስለ አብ በግልጽ እነግራችኋለሁ። +26 በዚያ ቀን አብን በስሜ ትለምናላችሁ፤ ይህን ስል ስለ እናንተ አብን እጠይቃለሁ ማለቴ አይደለም። +27 ምክንያቱም እናንተ እኔን ስለወደዳችሁኝና+ የአምላክ ተወካይ ሆኜ እንደመጣሁ ስላመናችሁ+ አብ ራሱ ይወዳችኋል። +28 እኔ የአብ ተወካይ ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ። አሁን ደግሞ ዓለምን ትቼ ወደ አብ ልሄድ ነው።”+ +29 ደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አሉ፦ “አሁን እኮ በግልጽ እየተናገርክ ነው፤ በምሳሌም አልተናገርክም። +30 አሁን ሁሉን ነገር እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ እስኪጠይቅህ ድረስ መጠበቅ እንደማያስፈልግህ ተረዳን። ስለሆነም ከአምላክ ዘንድ እንደመጣህ እናምናለን።” +31 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “አሁን አመናችሁ? +32 እነሆ፣ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን ትታችሁ የምትሄዱበት ሰዓት ቀርቧል፤+ እንዲያውም ደርሷል። ይሁንና አብ ከእኔ ጋር ስላለ ብቻዬን አይደለሁም።+ +33 እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ በእኔ አማካኝነት ሰላም እንዲኖራችሁ ነው።+ በዓለም ሳላችሁ መከራ ይደርስባችኋል፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”+ +6 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የገሊላን ማለትም የጥብርያዶስን ባሕር* አቋርጦ ወደ ማዶ ተሻገረ።+ +2 ብዙ ሰዎችም ኢየሱስ የታመሙትን በመፈወስ+ የፈጸማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች ስላዩ ተከተሉት።+ +3 ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚያ ተቀመጠ። +4 በዚያን ጊዜ የአይሁዳውያን በዓል የሆነው ፋሲካ+ ተቃርቦ ነበር። +5 ኢየሱስም ቀና ብሎ ብዙ ሕዝብ ወደ እሱ እየመጣ እንዳለ ሲመለከት ፊልጶስን “እነዚህ ሰዎች የሚበሉት ዳቦ ከየት ብንገዛ ይሻላል?” አለው።+ +6 ሆኖም ይህን ያለው ሊፈትነው ብሎ እንጂ ለማድረግ ያሰበውን ያውቅ ነበር። +7 ፊልጶስም “እያንዳንዱ ሰው ትንሽ ትንሽ እንዲደርሰው ለማድረግ እንኳ የ200 ዲናር* ዳቦ አይበቃም” ሲል መለሰለት። +8 ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነው የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ እንዲህ አለው፦ +9 “አምስት የገብስ ዳቦና ሁለት ትናንሽ ዓሣ የያዘ አንድ ትንሽ ልጅ እዚህ አለ። ይህ ግን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ እንዴት ይበቃል?”+ +"10 ኢየሱስም “ሰዎቹ እንዲቀመጡ አድርጉ” አለ። በስፍራው ብዙ ሣር ስለነበር ሰዎቹ በዚያ ተቀመጡ፤ ወንዶቹም 5,000 ያህል ነበሩ።+" +11 ኢየሱስ ዳቦዎቹን ወስዶ ካመሰገነ በኋላ በዚያ ለተቀመጡት ሰዎች አከፋፈለ፤ ትናንሾቹን ዓሣዎችም ልክ እንደዚሁ አደለ፤ እነሱም የሚፈልጉትን ያህል ወሰዱ። +12 በልተው ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “ምንም እንዳይባክን የተረፈውን ቁርስራሽ ሁሉ ሰብስቡ” አላቸው። +13 ስለዚህ ከአምስቱ የገብስ ዳቦ ሰዎቹ በልተው የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ። +14 ሰዎቹም ኢየሱስ የፈጸመውን ተአምራዊ ምልክት ባዩ ጊዜ “ወደ ዓለም እንደሚመጣ ትንቢት የተነገረለት ነቢይ በእርግጥ ይህ ነው” አሉ።+ +15 ከዚያም ኢየሱስ ሰዎቹ መጥተው ሊይዙትና ሊያነግሡት እንዳሰቡ ስላወቀ ብቻውን ዳግመኛ ወደ ተራራ ገለል አለ።+ +16 በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕሩ ወረዱ፤+ +17 በጀልባም ተሳፍረው ባሕሩን በማቋረጥ ወደ ቅፍርናሆም ለመሻገር ተነሱ። በዚያን ሰዓት ጨልሞ የነበረ ቢሆንም ኢየሱስ ገና ወደ እነሱ አልመጣም ነበር።+ +18 በተጨማሪም ኃይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለነበረ ባሕሩ ይናወጥ ጀመር።+ +19 ይሁን እንጂ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ገደማ* እንደቀዘፉ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቃረብ ተመልክተው ፈሩ። +20 እሱ ግን “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ!” አላቸው።+ +21 ከዚያም ወዲያው ጀልባዋ ላይ አሳፈሩት፤ ጀልባዋም ሊሄዱ ወዳሰቡበት ቦታ በፍጥነት ደረሰች።+ +22 በማግስቱም፣ በባሕሩ ማዶ የቀሩት ሰዎች ባሕሩ ላይ ከአንዲት ትንሽ ጀልባ በስተቀር ሌላ ጀልባ እንዳልነበረና ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን በጀልባዋ እንደሄዱ፣ ኢየሱስ ግን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንዳልተሳፈረ ተረዱ። +23 ሆኖም ከጥብርያዶስ የተነሱ ጀልባዎች፣ ሕዝቡ ጌታ የባረከውን ዳቦ ወደበሉበት አካባቢ መጡ። +24 ሕዝቡ ኢየሱስም ሆነ ደቀ መዛሙርቱ በዚያ አለመኖራቸውን ባወቁ ጊዜ በጀልባዎቻቸው ተሳፍረው ኢየሱስን ፍለጋ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። +25 ከባሕሩ ማዶ ባገኙትም ጊዜ “ረቢ፣+ መቼ ወደዚህ መጣህ?” አሉት። +26 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እው��ት እላችኋለሁ፣ የምትፈልጉኝ ተአምራዊ ምልክት ስላያችሁ ሳይሆን ዳቦ ስለበላችሁና ስለጠገባችሁ ነው።+ +27 ለሚጠፋ ምግብ ሳይሆን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ዘላቂ ለሆነውና የዘላለም ሕይወት+ ለሚያስገኘው ምግብ ሥሩ፤ ምክንያቱም አብ ይኸውም አምላክ ራሱ እሱን እንደተቀበለው አሳይቷል።”*+ +28 እነሱም “ታዲያ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለውን ሥራ ለመሥራት ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት። +29 ኢየሱስም መልሶ “አምላክ የሚቀበለው ሥራማ እሱ በላከው ሰው ማመን ነው” አላቸው።+ +30 በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉት፦ “ታዲያ አይተን እንድናምንብህ ምን ተአምራዊ ምልክት ትፈጽማለህ?+ ምን ነገርስ ትሠራለህ? +31 ‘ይበሉ ዘንድ ከሰማይ ምግብ ሰጣቸው’+ ተብሎ በተጻፈው መሠረት አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ።”+ +32 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ከሰማይ የወረደውን ምግብ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ አባቴ ግን እውነተኛውን ምግብ ከሰማይ ይሰጣችኋል። +33 ምክንያቱም አምላክ የሚሰጠው ምግብ ከሰማይ የሚወርድና ለዓለም ሕይወት የሚያስገኝ ነው።” +34 እነሱም “ጌታ ሆይ፣ ይህን ምግብ ሁልጊዜ ስጠን” አሉት። +35 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሕይወት የሚያስገኘው ምግብ እኔ ነኝ። ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ ፈጽሞ አይራብም፤ እንዲሁም በእኔ የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አይጠማም።+ +36 ነገር ግን “አይታችሁኝም እንኳ አታምኑም” ብያችሁ ነበር።+ +37 አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ፈጽሞ አላባርረውም፤+ +38 ከሰማይ የመጣሁት+ የራሴን ፈቃድ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ነውና።+ +39 የላከኝም ፈቃድ፣ ከሰጠኝ ሁሉ አንዱም እንኳ እንዳይጠፋብኝና በመጨረሻው ቀን ሁሉንም ከሞት እንዳስነሳቸው+ ነው። +40 ምክንያቱም የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያውቅና በእሱ የሚያምን* ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፤+ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ።”+ +41 ከዚያም አይሁዳውያን “ከሰማይ የወረደው ምግብ እኔ ነኝ”+ በማለቱ በኢየሱስ ላይ ያጉረመርሙ ጀመር። +42 ደግሞም “ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለም? አባቱንና እናቱንስ እናውቃቸው የለም እንዴ?+ ታዲያ እንዴት ‘ከሰማይ ወረድኩ’ ይላል?” አሉ። +43 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ። +44 የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል ሰው የለም፤+ እኔም በመጨረሻው ቀን ከሞት አስነሳዋለሁ።+ +45 ነቢያት በጻፏቸው ጽሑፎች ላይ ‘ሁሉም ከይሖዋ* የተማሩ ይሆናሉ’+ ተብሎ ተጽፏል። ከአብ የሰማና የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል። +46 ከአምላክ ዘንድ ከመጣው በስተቀር አብን ያየ አንድም ሰው የለም፤+ እሱ አብን አይቶታል።+ +47 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው።+ +48 “ሕይወት የሚያስገኘው ምግብ እኔ ነኝ።+ +49 አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ፤ ይሁን እንጂ ሞቱ።+ +50 ከሰማይ የወረደውን ምግብ የሚበላ ሁሉ ግን አይሞትም። +51 ከሰማይ የወረደው ሕያው ምግብ እኔ ነኝ። ከዚህ ምግብ የሚበላ ሁሉ ለዘላለም ይኖራል፤ ምግቡ ደግሞ ለዓለም ሕይወት ስል የምሰጠው ሥጋዬ ነው።”+ +52 አይሁዳውያንም “ይህ ሰው እንዴት ሥጋውን እንድንበላ ሊሰጠን ይችላል?” በማለት እርስ በርሳቸው ይከራከሩ ጀመር። +53 በመሆኑም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁና ደሙን ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።+ +54 ሥጋዬን የሚበላና ደሜን የሚጠጣ ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በመጨረሻውም ቀን ከሞት አስነሳዋለሁ፤+ +55 ሥጋዬ እውነተኛ ምግብ፣ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። +56 ሥጋዬን የሚበላና ደሜን የሚጠጣ ሁሉ ከእኔ ጋር አንድነት ይኖረዋል፤ እኔም ከእሱ ጋር አንድነት ይኖረኛል።+ +57 ሕያው የሆነው አብ እንደላከኝና እኔም ከእሱ የተነሳ በሕይወት እንደምኖር ሁሉ የእኔን ሥጋ የሚበላም ከእኔ የተነሳ በሕይወት ይኖራል።+ +58 ከሰማይ የወረደው ምግብ ይህ ነው። ይህም አባቶቻችሁ በበሉበት ጊዜ እንደነበረው አይደለም፤ እነሱ ቢበሉም እንኳ ሞተዋል። ይህን ምግብ የሚበላ ሁሉ ግን ለዘላለም ይኖራል።”+ +59 ይህን የተናገረው በቅፍርናሆም በምኩራብ* እያስተማረ ሳለ ነበር። +60 ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ይህን ሲሰሙ “ይህ የሚሰቀጥጥ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል?” አሉ። +61 ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ጉዳይ እያጉረመረሙ እንዳሉ ስለገባው እንዲህ አላቸው፦ “ይህ ያሰናክላችኋል? +62 ታዲያ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደነበረበት ሲወጣ ብታዩ ምን ልትሉ ነው?+ +63 ሕይወትን የሚሰጠው መንፈስ ነው፤+ ሥጋ ምንም አይጠቅምም። እኔ የነገርኳችሁ ቃል መንፈስም ሕይወትም ነው።+ +64 ነገር ግን ከእናንተ መካከል የማያምኑ አንዳንዶች አሉ።” ኢየሱስ ይህን ያለው የማያምኑት እነማን እንደሆኑና ማን አሳልፎ እንደሚሰጠው ከመጀመሪያው ያውቅ ስለነበረ ነው።+ +65 ከዚያም “አብ ካልፈቀደለት በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም ያልኳችሁ ለዚህ ነው” አላቸው።+ +66 ከዚህም የተነሳ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ትተውት ወደነበረው ነገር ተመለሱ፤+ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም እሱን መከተላቸውን አቆሙ። +67 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን “እናንተም መሄድ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። +68 ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን?+ አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ።+ +69 አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ እንደሆንክ አምነናል፤ ደግሞም አውቀናል።”+ +70 ኢየሱስም መልሶ “አሥራ ሁለታችሁንም የመረጥኳችሁ እኔ አይደለሁም?+ ይሁንና ከመካከላችሁ አንዱ ስም አጥፊ* ነው” አላቸው።+ +71 ይህን ሲል የአስቆሮቱ ስምዖን ልጅ ስለሆነው ስለ ይሁዳ መናገሩ ነበር፤ ምክንያቱም ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆንም አሳልፎ የሚሰጠው እሱ ነበር።+ +10 “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በበሩ ሳይሆን በሌላ በኩል ዘሎ ወደ በጎቹ ጉረኖ የሚገባ ሌባና ዘራፊ ነው።+ +2 በበሩ በኩል የሚገባ ግን የበጎቹ እረኛ ነው።+ +3 በር ጠባቂውም ለእሱ ይከፍትለታል፤+ በጎቹም ድምፁን ይሰማሉ።+ የራሱን በጎች በየስማቸው ጠርቶ እየመራ ያወጣቸዋል። +4 የራሱ የሆኑትን ሁሉ ካወጣ በኋላ ከፊት ከፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ድምፁን ስለሚያውቁ ይከተሉታል። +5 እንግዳ የሆነውን ግን ይሸሹታል እንጂ በምንም ዓይነት አይከተሉትም፤ ምክንያቱም የእንግዳ ሰዎችን ድምፅ አያውቁም።” +6 ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነሱ ግን ምን እያላቸው እንዳለ አልገባቸውም። +7 ስለዚህ ኢየሱስ እንደገና እንዲህ አለ፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በጎቹ የሚገቡበት በር እኔ ነኝ።+ +8 አስመሳይ ሆነው በእኔ ስም የመጡ ሁሉ ሌቦችና ዘራፊዎች ናቸው፤ በጎቹ ግን አልሰሟቸውም። +9 በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል፤ ይገባል፤ ይወጣል፤ መሰማሪያም ያገኛል።+ +10 ሌባው ለመስረቅ፣ ለመግደልና ለማጥፋት ካልሆነ በቀር ለሌላ አይመጣም።+ እኔ የመጣሁት ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው ነው። +11 እኔ ጥሩ እረኛ ነኝ፤+ ጥሩ እረኛ ሕይወቱን* ለበጎቹ ሲል አሳልፎ ይሰጣል።+ +12 እረኛ ያልሆነና በጎቹ የራሱ ያልሆኑ ተቀጣሪ ሠራተኛ ተኩላ ሲመጣ ሲያይ በጎቹን ጥሎ ይሸሻል (ተኩላውም በጎቹን ይነጥቃል እንዲሁም ይበታትናል)፤ +13 ሠራተኛው እንዲህ የሚያደርገው ተቀጣሪ ስለሆነና ለበጎቹ ደንታ ስለሌለው ነው። +14 እኔ ጥሩ እረኛ ነኝ። በ��ቼን አውቃቸዋለሁ፤ በጎቼም ያውቁኛል፤+ +15 ይህም አብ እኔን እንደሚያውቀኝና እኔም አብን እንደማውቀው ነው፤+ ሕይወቴንም* ለበጎቹ ስል አሳልፌ እሰጣለሁ።+ +16 “ከዚህ ጉረኖ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤+ እነሱንም ማምጣት አለብኝ፤ ድምፄንም ይሰማሉ፤ ሁሉም አንድ መንጋ ይሆናሉ፤ አንድ እረኛም ይኖራቸዋል።+ +17 ሕይወቴን* መልሼ አገኛት ዘንድ አሳልፌ ስለምሰጣት+ አብ ይወደኛል።+ +18 በራሴ ተነሳስቼ አሳልፌ እሰጣታለሁ እንጂ ማንም ሰው ከእኔ አይወስዳትም። ሕይወቴን* አሳልፌ ለመስጠት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ ለመቀበልም ሥልጣን አለኝ።+ ይህን ትእዛዝ የተቀበልኩት ከአባቴ ነው።” +19 ከዚህ ንግግር የተነሳ በአይሁዳውያኑ መካከል እንደገና ክፍፍል ተፈጠረ።+ +20 ብዙዎቹም “ይህ ሰው ጋኔን አለበት፤ አእምሮውን ስቷል። ለምን ትሰሙታላችሁ?” አሉ። +21 ሌሎቹ ደግሞ “ጋኔን የያዘው ሰው እንዲህ አይናገርም። ጋኔን የዓይነ ስውራንን ዓይን ሊከፍት ይችላል እንዴ?” አሉ። +22 በዚያ ጊዜ በኢየሩሳሌም የመታደስ በዓል* ይከበር ነበር። ወቅቱም ክረምት ነበር፤ +23 ኢየሱስም በቤተ መቅደሱ በሚገኘውና መጠለያ ባለው የሰለሞን መተላለፊያ+ ውስጥ እያለፈ ነበር። +24 በዚህ ጊዜ አይሁዳውያን ከበውት “እስከ መቼ ድረስ ልባችንን* ታንጠለጥላለህ? አንተ ክርስቶስ ከሆንክ በግልጽ ንገረን” አሉት። +25 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ ነግሬአችኋለሁ፤ እናንተ ግን አታምኑም። በአባቴ ስም እየሠራኋቸው ያሉት ሥራዎች ስለ እኔ ይመሠክራሉ።+ +26 ሆኖም እናንተ በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።+ +27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ እነሱም ይከተሉኛል።+ +28 የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤+ መቼም ቢሆን ጥፋት አይደርስባቸውም፤ ከእጄ የሚነጥቃቸውም የለም።+ +29 አባቴ የሰጠኝ በጎች ከሌሎች ነገሮች ሁሉ ይበልጣሉ፤ እነሱንም ከአባቴ እጅ ሊነጥቃቸው የሚችል የለም።+ +30 እኔና አብ አንድ ነን።”*+ +31 በዚህ ጊዜም አይሁዳውያኑ ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ። +32 ኢየሱስም መልሶ “ከአብ ዘንድ ብዙ መልካም ሥራዎች አሳየኋችሁ። ታዲያ የምትወግሩኝ ከእነዚህ ሥራዎች መካከል በየትኛው የተነሳ ነው?” አላቸው። +33 አይሁዳውያኑም “እኛ የምንወግርህ ስለ መልካም ሥራህ ሳይሆን አንተ ሰው ሆነህ ሳለህ ራስህን አምላክ በማድረግ አምላክን ስለተዳፈርክ ነው”+ ሲሉ መለሱለት። +34 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በሕጋችሁ ላይ ‘“እናንተ አማልክት* ናችሁ” አልኩ’+ ተብሎ ተጽፎ የለም? +35 የአምላክ ቃል ያወገዛቸውን እሱ ‘አማልክት’+ ብሎ ከጠራቸውና ቅዱስ መጽሐፉ ሊሻር የማይችል ከሆነ +36 አብ የቀደሰኝንና ወደ ዓለም የላከኝን እኔን፣ ‘የአምላክ ልጅ ነኝ’+ ስላልኩ ‘አምላክን ትዳፈራለህ’ ትሉኛላችሁ? +37 እኔ የአባቴን ሥራ እየሠራሁ ካልሆነ አትመኑኝ። +38 የአባቴን ሥራ እየሠራሁ ከሆነ ግን እኔን ባታምኑኝ እንኳ ሥራዬን እመኑ፤+ ይህም አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው እንዲሁም እኔም ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝ እንድታውቁና ይህን ይበልጥ እያወቃችሁ እንድትሄዱ ነው።”+ +39 ስለዚህ እንደገና ሊይዙት ሞከሩ፤ እሱ ግን አመለጣቸው። +40 ከዚያም ዮሐንስ ቀደም ሲል ያጠምቅ ወደነበረበት ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳለው ቦታ+ ዳግመኛ ሄደ፤ በዚያም ለተወሰነ ጊዜ ቆየ። +41 ብዙ ሰዎችም ወደ እሱ መጥተው እርስ በርሳቸው “ዮሐንስ አንድም ተአምራዊ ምልክት አላደረገም፤ ሆኖም ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ነገር ሁሉ እውነት ነበር” ተባባሉ።+ +42 በዚያም ብዙዎች በእሱ አመኑ። +14 “ልባችሁ አይረበሽ።+ በአምላክ እመኑ፤+ በእኔም ደግሞ እመኑ። +2 በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ ቦታ አለ። ይህ ባይሆን ��ሮ በግልጽ እነግራችሁ ነበር፤ ለእናንተ ቦታ ለማዘጋጀት እሄዳለሁና።+ +3 ደግሞም ሄጄ ቦታ ባዘጋጀሁላችሁ ጊዜ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ እንደገና መጥቼ እኔ ወዳለሁበት እወስዳችኋለሁ።*+ +4 እኔ ወደምሄድበትም ቦታ የሚወስደውን መንገድ ታውቃላችሁ።” +5 ቶማስም+ “ጌታ ሆይ፣ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም። ታዲያ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?” አለው። +6 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እኔ መንገድ፣+ እውነትና+ ሕይወት+ ነኝ። በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።+ +7 እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ታውቁት ነበር፤ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ታውቁታላችሁ፤ ደግሞም አይታችሁታል።”+ +8 ፊልጶስም “ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። +9 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ፊልጶስ፣ ከእናንተ ጋር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ ኖሬም እንኳ አላወቅከኝም? እኔን ያየ ሁሉ አብንም አይቷል።+ ታዲያ እንዴት ‘አብን አሳየን’ ትላለህ? +10 እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝና አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው አታምንም?+ የምነግራችሁን ነገር የምናገረው ከራሴ አመንጭቼ አይደለም፤+ ሆኖም ሥራውን እየሠራ ያለው ከእኔ ጋር አንድነት ያለው አብ ነው። +11 እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝ አብም ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው እመኑኝ፤ ካልሆነ ደግሞ ከተሠሩት ሥራዎች የተነሳ እመኑ።+ +12 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ የሚያምን ሁሉ እኔ የምሠራቸውን ሥራዎች ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ+ እሱ ከእነዚህ የበለጡ ሥራዎች ይሠራል።+ +13 በተጨማሪም አብ በወልድ አማካኝነት እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።+ +14 ማንኛውንም ነገር በስሜ ከለመናችሁ እኔ አደርገዋለሁ። +15 “የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዛቴን ትጠብቃላችሁ።+ +16 እኔም አብን እጠይቃለሁ፤ እሱም ለዘላለም ከእናንተ ጋር የሚሆን ሌላ ረዳት* ይሰጣችኋል፤+ +17 እሱም የእውነት መንፈስ ነው፤+ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም።+ እናንተ ግን አብሯችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስላለ ታውቁታላችሁ። +18 ሐዘን ላይ* ትቻችሁ አልሄድም። ወደ እናንተ እመጣለሁ።+ +19 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም ከቶ አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤+ ምክንያቱም እኔ እኖራለሁ፤ እናንተም ትኖራላችሁ። +20 እኔ ከአባቴ ጋር አንድነት እንዳለኝ፣ እናንተ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳላችሁና እኔም ከእናንተ ጋር አንድነት እንዳለኝ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።+ +21 እኔን የሚወደኝ ትእዛዛቴን የሚቀበልና የሚጠብቅ ነው። እኔን የሚወደኝን ሁሉ ደግሞ አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” +22 የአስቆሮቱ ሳይሆን ሌላው ይሁዳ+ “ጌታ ሆይ፣ ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን ለመግለጥ ያሰብከው ለምንድን ነው?” አለው። +23 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ማንም ሰው እኔን የሚወደኝ ከሆነ ቃሌን ይጠብቃል፤+ አባቴም ይወደዋል፣ እኛም ወደ እሱ መጥተን መኖሪያችንን ከእሱ ጋር እናደርጋለን።+ +24 እኔን የማይወደኝ ሁሉ ቃሌን አይጠብቅም። ይህ እየሰማችሁት ያለው ቃል ደግሞ የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።+ +25 “አሁን ከእናንተ ጋር እያለሁ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ። +26 ሆኖም አብ በስሜ የሚልከው ረዳት* ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል እንዲሁም የነገርኳችሁን ነገር ሁሉ እንድታስታውሱ ያደርጋችኋል።+ +27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ።+ እኔ ሰላም የምሰጣችሁ ዓለም በሚሰጥበት መንገድ አይደለም። ልባችሁ አይረበሽ፤ በፍርሃትም አይዋጥ። +28 ‘እሄዳለሁ ወደ እናንተም ተመልሼ እመጣለሁ’ እንዳልኳችሁ ሰምታችኋል። ብትወዱኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ ከእኔ አብ ይበልጣልና።+ +29 በመሆኑም በሚፈጸምበት ጊዜ እንድታምኑ ከመፈጸሙ በፊት አሁን ነግሬአችኋለሁ።+ +30 የዚህ ዓለም ገዢ+ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር ብዙ አልነጋገርም፤ እሱም በእኔ ላይ ምንም ኃይል የለውም።+ +31 ይሁን እንጂ እኔ አብን እንደምወድ ዓለም እንዲያውቅ አብ ባዘዘኝ መሠረት+ እየሠራሁ ነው። ተነሱ ከዚህ እንሂድ። +9 በመንገድ እያለፈ ሳለም ሲወለድ ጀምሮ ዓይነ ስውር የሆነ አንድ ሰው አየ። +2 ደቀ መዛሙርቱም “ረቢ፣+ ይህ ሰው ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደው ማን በሠራው ኃጢአት ነው? በራሱ ኃጢአት ነው ወይስ በወላጆቹ?” ሲሉ ጠየቁት። +3 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እሱም ሆነ ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም፤ ሆኖም ይህ የሆነው የአምላክ ሥራ በእሱ እንዲገለጥ ነው።+ +4 ቀን ሳለ፣ የላከኝን የእሱን ሥራ መሥራት አለብን፤+ ማንም ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት ይመጣል። +5 በዓለም እስካለሁ ድረስ የዓለም ብርሃን ነኝ።”+ +6 ይህን ካለ በኋላ መሬት ላይ እንትፍ በማለት በምራቁ ጭቃ ለወሰ፤ ጭቃውንም በሰውየው ዓይኖች ላይ ቀባ፤+ +7 ሰውየውንም “ሄደህ በሰሊሆም ገንዳ ታጠብ” አለው (ሰሊሆም ማለት “ተላከ” ማለት ነው)። ሰውየውም ሄዶ ታጠበ፤ ዓይኑም በርቶለት መጣ።+ +8 ከዚያም ጎረቤቶቹና ቀደም ሲል ሲለምን ያዩት የነበሩ ሰዎች “ይህ ሰው ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለም እንዴ?” አሉ። +9 አንዳንዶች “አዎ፣ እሱ ነው” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “አይ፣ እሱን ይመስላል እንጂ እሱ አይደለም” ይሉ ነበር። ሰውየው ግን “እኔው ነኝ” ይል ነበር። +10 በመሆኑም “ታዲያ ዓይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” ሲሉ ጠየቁት። +11 እሱም “ኢየሱስ የተባለው ሰው ጭቃ ለውሶ ዓይኖቼን ቀባና ‘ወደ ሰሊሆም ሄደህ ታጠብ’ አለኝ።+ እኔም ሄጄ ታጠብኩ፤ ዓይኔም በራልኝ” ሲል መለሰ። +12 በዚህ ጊዜ “ሰውየው የት አለ?” አሉት። እሱም “እኔ አላውቅም” አለ። +13 እነሱም ዓይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። +14 እንደ አጋጣሚ ሆኖ ኢየሱስ ጭቃውን የለወሰበትና የሰውየውን ዓይኖች ያበራበት ቀን+ ሰንበት ነበር።+ +15 በዚህ ጊዜ ፈሪሳውያኑም እንዴት ማየት እንደቻለ ጠየቁት። እሱም “ሰውየው ዓይኖቼን ጭቃ ቀባ፤ እኔም ታጠብኩ፤ ከዚያም ማየት ቻልኩ” አላቸው። +16 ከፈሪሳውያንም መካከል አንዳንዶቹ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከአምላክ የመጣ አይደለም” አሉ።+ ሌሎቹ ደግሞ “ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እንዲህ ያሉ ተአምራዊ ምልክቶችን እንዴት ሊፈጽም ይችላል?” አሉ።+ በመሆኑም በመካከላቸው ክፍፍል ተፈጠረ።+ +17 በድጋሚም ዓይነ ስውሩን “ይህ ሰው ዓይኖችህን ስላበራልህ ስለ እሱ ምን ትላለህ?” አሉት። ሰውየውም “እሱ ነቢይ ነው” አለ። +18 ይሁን እንጂ አይሁዳውያኑ ማየት የቻለውን ሰው ወላጆች እስከጠሩበት ጊዜ ድረስ ሰውየው ዓይነ ስውር እንደነበረና በኋላ ዓይኑ እንደበራለት አላመኑም ነበር። +19 ወላጆቹንም “ዓይነ ስውር ሆኖ ተወልዷል የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነው? ታዲያ አሁን እንዴት ሊያይ ቻለ?” ሲሉ ጠየቋቸው። +20 ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ይህ ልጃችን እንደሆነና ዓይነ ስውር ሆኖ እንደተወለደ እናውቃለን። +21 አሁን ግን እንዴት ሊያይ እንደቻለ የምናውቀው ነገር የለም፤ ዓይኖቹን ማን እንዳበራለትም አናውቅም። እሱን ጠይቁት፤ ሙሉ ሰው ነው። ስለ ራሱ መናገር ያለበት እሱ ነው።” +22 ወላጆቹ ይህን ያሉት አይሁዳውያኑን* ስለፈሩ ነው፤+ ምክንያቱም አይሁዳውያን ኢየሱስን፣ ‘ክርስቶስ ነው’ ብሎ የተቀበለ ማንኛውም ሰው ከምኩራብ እንዲባረር አስቀድመው ወስነው ነበር።+ +23 ወላጆቹ “ሙሉ ሰው ነው። እሱን ጠይቁት” ያ���ት ለዚህ ነበር። +24 ስለዚህ ዓይነ ስውር የነበረውን ሰው ለሁለተኛ ጊዜ ጠርተው “እውነቱን በመናገር ለአምላክ ክብር ስጥ፤ እኛ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እናውቃለን” አሉት። +25 እሱም መልሶ “ኃጢአተኛ ይሁን አይሁን የማውቀው ነገር የለም። እኔ የማውቀው ዓይነ ስውር እንደነበርኩና አሁን ግን ማየት እንደቻልኩ ነው” አለ። +26 በዚህ ጊዜ “ምንድን ነው ያደረገልህ? ዓይንህን ያበራልህስ እንዴት ነው?” አሉት። +27 እሱም “ነገርኳችሁ እኮ፤ እናንተ ግን አትሰሙም። እንደገና መስማት የፈለጋችሁት ለምንድን ነው? እናንተም የእሱ ደቀ መዝሙር መሆን ፈለጋችሁ እንዴ?” ሲል መለሰላቸው። +28 እነሱም ሰውየውን በንቀት እንዲህ አሉት፦ “የዚያ ሰው ደቀ መዝሙር አንተ ነህ፤ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን። +29 አምላክ ሙሴን እንዳነጋገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደመጣ አናውቅም።” +30 ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ከየት እንደመጣ አለማወቃችሁ በጣም የሚያስገርም ነገር ነው፤ ያም ሆነ ይህ ዓይኖቼን አብርቶልኛል። +31 አምላክ ኃጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤+ ፈሪሃ አምላክ ያለውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን ሁሉ ግን ይሰማዋል።+ +32 ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደን ሰው ዓይኖች የከፈተ አለ ሲባል ከጥንት ዘመን ጀምሮ ተሰምቶ አይታወቅም። +33 ይህ ሰው ከአምላክ ባይሆን ኖሮ ምንም ነገር ሊያደርግ አይችልም ነበር።”+ +34 እነሱም መልሰው “አንተ ሁለመናህ በኃጢአት ተበክሎ የተወለድክ! እኛን ልታስተምር ትፈልጋለህ?” አሉት። ከዚያም አባረሩት!+ +35 ኢየሱስም ሰውየውን እንዳባረሩት ሰማ፤ ባገኘውም ጊዜ “በሰው ልጅ ላይ እምነት አለህ?” አለው። +36 ሰውየውም “ጌታዬ፣ አምንበት ዘንድ እሱ ማን ነው?” ሲል መለሰ። +37 ኢየሱስም “አይተኸዋል፤ ደግሞም እያነጋገረህ ያለው እሱ ነው” አለው። +38 እሱም “ጌታ ሆይ፣ በእሱ አምናለሁ” አለ። ከዚያም ሰገደለት።* +39 ኢየሱስም “የማያዩ ማየት እንዲችሉ፣+ የሚያዩም እንዲታወሩ፣+ ለዚህ ፍርድ ወደዚህ ዓለም መጥቻለሁ” አለ። +40 በዚያ የነበሩ ፈሪሳውያንም ይህን ሰምተው “እናንተም ዕውሮች ናችሁ እያልከን ነው?” አሉት። +41 ኢየሱስም “ዕውሮች ብትሆኑማ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባችሁ ነበር። አሁን ግን ‘እናያለን’ ትላላችሁ። ስለዚህ ኃጢአታችሁ እንዳለ ይኖራል” አላቸው።+ +13 የፋሲካ በዓል ተቃርቦ በነበረበት ወቅት ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት+ ሰዓት እንደደረሰ+ ስላወቀ በዓለም የነበሩትንና የወደዳቸውን ተከታዮቹን* እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።+ +2 በዚህ ጊዜ ራት እየበሉ ነበር። ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ+ ልብ ውስጥ ኢየሱስን አሳልፎ የመስጠት ሐሳብ አሳድሮ ነበር።+ +3 ኢየሱስ፣ አብ ሁሉን ነገር በእጁ እንደሰጠው እንዲሁም ከአምላክ እንደመጣና ወደ አምላክ እንደሚሄድ+ ያውቅ ስለነበር +4 ከራት ተነስቶ መደረቢያውን አስቀመጠ። ፎጣ ወስዶም ወገቡ ላይ አሸረጠ።+ +5 ከዚያም በመታጠቢያ ዕቃ ውስጥ ውኃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብና ባሸረጠው ፎጣ ማድረቅ ጀመረ። +6 ከዚያም ወደ ስምዖን ጴጥሮስ መጣ። ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ እግሬን ልታጥብ ነው?” አለው። +7 ኢየሱስም መልሶ “እያደረግኩት ያለውን ነገር አሁን አትረዳውም፤ በኋላ ግን ትረዳዋለህ” አለው። +8 ጴጥሮስም “በፍጹም እግሬን አታጥብም” አለው። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “ካላጠብኩህ+ ከእኔ ጋር ምንም ድርሻ አይኖርህም” ሲል መለሰለት። +9 ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንና ራሴንም እጠበኝ” አለው። +10 ኢየሱስም “ገላውን የታጠበ ሁለመናው ንጹሕ በመሆኑ ከእግሩ በስተቀር መታጠብ አያስፈልገውም። እና���ተ ንጹሐን ናችሁ፤ ሁላችሁም ግን አይደላችሁም” አለው። +11 ምክንያቱም አሳልፎ የሚሰጠው ሰው ማን እንደሆነ ያውቅ ነበር።+ “ሁላችሁም ንጹሐን አይደላችሁም” ያለው ለዚህ ነው። +12 እግራቸውን አጥቦ ካበቃና መደረቢያውን ለብሶ ዳግመኛ በማዕድ ከተቀመጠ በኋላ እንዲህ አላቸው፦ “ምን እንዳደረግኩላችሁ አስተዋላችሁ? +13 እናንተ ‘መምህር’ እና ‘ጌታ’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ እንደዚያ ስለሆንኩም እንዲህ ብላችሁ መጥራታችሁ ትክክል ነው።+ +14 ስለዚህ እኔ ጌታና መምህር ሆኜ ሳለሁ እግራችሁን ካጠብኩ+ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል።*+ +15 እኔ እንዳደረግኩላችሁ እናንተም እንደዚሁ እንድታደርጉ አርዓያ ሆኜላችኋለሁ።+ +16 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፤ የተላከም ከላከው አይበልጥም። +17 እነዚህን ነገሮች ስለምታውቁ ብትፈጽሟቸው ደስተኞች ናችሁ።+ +18 ይህን ስል ስለ ሁላችሁም መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኳቸውን አውቃለሁ። ይሁንና ‘ከማዕዴ ይበላ የነበረ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሳ’*+ የሚለው የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።+ +19 ገና ሳይፈጸም በፊት አሁን የምነግራችሁ፣ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ እሱ መሆኔን እንድታምኑ ነው።+ +20 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ የምልከውን የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤+ እኔን የሚቀበል ሁሉ ደግሞ የላከኝንም ይቀበላል።”+ +21 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ መንፈሱ ተረብሾ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል”+ ሲል በግልጽ ተናገረ። +22 ደቀ መዛሙርቱም ስለ ማን እየተናገረ እንዳለ ግራ ገብቷቸው እርስ በርሳቸው ይተያዩ ጀመር።+ +23 ከእነሱ አንዱ ይኸውም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር+ ኢየሱስ አጠገብ ጋደም ብሎ ነበር። +24 ስምዖን ጴጥሮስም ለዚህ ደቀ መዝሙር ምልክት በመስጠት “ስለ ማን እየተናገረ እንዳለ ንገረን” አለው። +25 እሱም ወደ ኢየሱስ ደረት ጠጋ ብሎ “ጌታ ሆይ፣ ማን ነው?” አለው።+ +26 ኢየሱስም “ይህን የማጠቅሰውን ቁራሽ ዳቦ የምሰጠው ሰው ነው” ሲል መለሰ።+ ከዚያም ዳቦውን አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው። +27 ይሁዳም ቁራሹን ከተቀበለ በኋላ ሰይጣን ገባበት።+ ስለዚህ ኢየሱስ “እያደረግከው ያለኸውን ነገር ቶሎ አድርገው” አለው። +28 ይሁን እንጂ በማዕድ ከተቀመጡት መካከል አንዳቸውም ለምን እንዲህ እንዳለው አልገባቸውም። +29 እንዲያውም አንዳንዶቹ ይሁዳ የገንዘብ ሣጥኑን ይይዝ ስለነበር+ ለበዓሉ የሚያስፈልጉትን ነገሮች እንዲገዛ ወይም ለድሆች የሆነ ነገር እንዲሰጥ ኢየሱስ ያዘዘው መስሏቸው ነበር። +30 ስለዚህ ይሁዳ ቁራሹን ዳቦ ከተቀበለ በኋላ ወዲያውኑ ወጣ። ጊዜውም ሌሊት ነበር።+ +31 ይሁዳ ከሄደ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “አሁን የሰው ልጅ ክብር ተጎናጸፈ፤+ አምላክም በእሱ አማካኝነት ከበረ። +32 አምላክ ራሱም ያከብረዋል፤+ ደግሞም ወዲያውኑ ያከብረዋል። +33 ልጆቼ ሆይ፣ ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ። እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁዳውያን ‘ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’+ እንዳልኳቸው ሁሉ አሁን ደግሞ ለእናንተ ይህንኑ እላችኋለሁ። +34 እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደወደድኳችሁ+ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።+ +35 እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ+ ሰዎች ሁሉ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።” +36 ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ ወዴት ልትሄድ ነው?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፤ በኋላ ግን ትከተለኛለህ” ሲል መለሰ።+ +37 ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ አሁን ልከተል��� የማልችለው ለምንድን ነው? ሕይወቴን* ስለ አንተ አሳልፌ ለመስጠት ፈቃደኛ ነኝ” አለው።+ +38 ኢየሱስም “ሕይወትህን* ስለ እኔ አሳልፈህ ትሰጣለህ? እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ሲል መለሰ።+ +5 ከዚህ በኋላ የአይሁዳውያን በዓል+ ስለነበረ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። +2 በኢየሩሳሌም በበጎች በር+ አጠገብ አምስት ባለ መጠለያ መተላለፊያዎች ያሉት በዕብራይስጥ ቤተዛታ ተብሎ የሚጠራ አንድ የውኃ ገንዳ ነበር። +3 በእነዚህ መተላለፊያዎች ውስጥ ብዙ ሕመምተኞች፣ ዓይነ ስውሮች፣ አንካሶችና ሽባዎች* ይተኙ ነበር። +4 *—— +5 በዚያም ለ38 ዓመት ሕመምተኛ ሆኖ የኖረ አንድ ሰው ነበር። +6 ኢየሱስ ይህን ሰው በዚያ ተኝቶ አየውና ለረጅም ጊዜ ሕመምተኛ ሆኖ እንደኖረ አውቆ “መዳን ትፈልጋለህ?”+ አለው። +7 ሕመምተኛውም “ጌታዬ፣ ውኃው በሚናወጥበት ጊዜ ገንዳው ውስጥ የሚያስገባኝ ሰው የለኝም፤ ወደ ገንዳው ስሄድ ደግሞ ሌላው ቀድሞኝ ይገባል” ሲል መለሰለት። +8 ኢየሱስም “ተነስ! ምንጣፍህን* ተሸክመህ ሂድ” አለው።+ +9 ሰውየውም ወዲያውኑ ተፈወሰ፤ ምንጣፉንም* አንስቶ መሄድ ጀመረ። ቀኑም ሰንበት ነበር። +10 በመሆኑም አይሁዳውያን የተፈወሰውን ሰው “ሰንበት እኮ ነው፤ ምንጣፍህን* እንድትሸከም ሕጉ አይፈቅድልህም” አሉት።+ +11 እሱ ግን “የፈወሰኝ ሰው ራሱ ‘ምንጣፍህን* ተሸክመህ ሂድ’ ብሎኛል” ሲል መለሰላቸው። +12 እነሱም “‘ምንጣፍህን* ተሸክመህ ሂድ’ ያለህ ሰው ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት። +13 ሆኖም ኢየሱስ ከቦታው ዞር ብሎ ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅሎ ስለነበር ሰውየው የፈወሰውን ሰው ማንነት ማወቅ አልቻለም። +14 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሰውየውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኘውና “አሁን ደህና ሆነሃል። የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ኃጢአት አትሥራ” አለው። +15 ሰውየውም ሄዶ የፈወሰው ኢየሱስ መሆኑን ለአይሁዳውያኑ ነገራቸው። +16 ከዚህም የተነሳ አይሁዳውያኑ በኢየሱስ ላይ ስደት ያደርሱበት ጀመር፤ ይህን ያደረጉት በሰንበት ቀን እነዚህን ነገሮች ይፈጽም ስለነበረ ነው። +17 እሱ ግን “አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው፤ እኔም እሠራለሁ”+ ሲል መለሰላቸው። +18 ከዚህም የተነሳ አይሁዳውያኑ ሰንበትን ስለጣሰ ብቻ ሳይሆን አምላክን የገዛ አባቱ እንደሆነ አድርጎ በመጥራት+ ራሱን ከአምላክ ጋር እኩል ስላደረገ+ እሱን ለመግደል ይበልጥ ተነሳሱ። +19 ስለሆነም ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ወልድ፣ አብ ሲያደርግ ያየውን ብቻ እንጂ በራሱ ተነሳስቶ አንድም ነገር ሊያደርግ አይችልም።+ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድም በተመሳሳይ መንገድ ያንኑ ያደርጋል። +20 ምክንያቱም አብ ወልድን ይወደዋል፤+ እንዲሁም እሱ ራሱ የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከእነዚህም የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።+ +21 አብ ሙታንን እንደሚያስነሳቸውና ሕያው እንደሚያደርጋቸው+ ሁሉ ወልድም እንዲሁ የፈለገውን ሰው ሕያው ያደርጋል።+ +22 አብ በማንም ላይ አይፈርድምና፤ ከዚህ ይልቅ የመፍረዱን ሥልጣን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶታል፤+ +23 ይህን ያደረገውም ሁሉም አብን እንደሚያከብሩ ሁሉ ወልድንም እንዲያከብሩ ነው። ወልድን የማያከብር ሁሉ እሱን የላከውን አብንም አያከብርም።+ +24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን የሚሰማና የላከኝን የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤+ ወደ ፍርድም አይመጣም፤ ከዚህ ይልቅ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግሯል።+ +25 “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ሙታን የአምላክን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ ያም ሰዓት አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ። +26 አብ በራሱ ሕ���ወት እንዳለው* ሁሉ፣+ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።+ +27 እሱ የሰው ልጅ+ ስለሆነ የመፍረድ ሥልጣን ሰጥቶታል።+ +28 በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤+ +29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ* ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።+ +30 በራሴ ተነሳስቼ አንድም ነገር ማድረግ አልችልም። እንደሰማሁ እፈርዳለሁ፤ የራሴን ፈቃድ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ+ መፈጸም ስለምፈልግ የምፈርደው የጽድቅ ፍርድ ነው።+ +31 “እኔ ብቻ ስለ ራሴ ብመሠክር ምሥክርነቴ እውነት አይደለም።+ +32 ስለ እኔ የሚመሠክር ሌላ አለ፤ ደግሞም እሱ ስለ እኔ የሚሰጠው ምሥክርነት እውነት እንደሆነ አውቃለሁ።+ +33 ወደ ዮሐንስ ሰዎች ልካችሁ ነበር፤ እሱም ለእውነት መሥክሯል።+ +34 ይሁን እንጂ እኔ የሰው ምሥክርነት አያስፈልገኝም፤ ይህን የምናገረው ግን እናንተ እንድትድኑ ነው። +35 ያ ሰው የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበር፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በእሱ ብርሃን እጅግ ለመደሰት ፈቃደኞች ነበራችሁ።+ +36 እኔ ግን ከዮሐንስ የበለጠ ምሥክር አለኝ፤ ምክንያቱም አባቴ እንዳከናውነው የሰጠኝ ሥራ ማለትም እየሠራሁት ያለው ይህ ሥራ አብ እንደላከኝ ይመሠክራል።+ +37 የላከኝ አብም ራሱ ስለ እኔ መሥክሯል።+ እናንተ መቼም ቢሆን ድምፁን አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤+ +38 እሱ የላከውንም ስለማታምኑ ቃሉ በልባችሁ ውስጥ አይኖርም። +39 “እናንተ በቅዱሳን መጻሕፍት የዘላለም ሕይወት የምታገኙ ስለሚመስላችሁ እነሱን ትመረምራላችሁ፤+ እነዚሁ መጻሕፍት ስለ እኔ የሚመሠክሩ ናቸው።+ +40 ሆኖም ሕይወት እንድታገኙ ወደ እኔ መምጣት አትፈልጉም።+ +41 እኔ ከሰው ክብር መቀበል አልፈልግም፤ +42 ይሁንና እናንተ የአምላክ ፍቅር በውስጣችሁ እንደሌለ በሚገባ አውቃለሁ። +43 እኔ በአባቴ ስም መጣሁ፤ እናንተ ግን አልተቀበላችሁኝም። ሌላው ግን በራሱ ስም ቢመጣ ትቀበሉታላችሁ። +44 እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትሰጣጡና ከአንዱ አምላክ የሚገኘውን ክብር የማትፈልጉ ሆናችሁ ሳላችሁ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?+ +45 እኔ በአብ ፊት የምከሳችሁ አይምሰላችሁ፤ የሚከሳችሁ ሌላ አለ፤ እሱም ተስፋ የጣላችሁበት ሙሴ ነው።+ +46 ደግሞም ሙሴን ብታምኑት ኖሮ እኔንም ታምኑኝ ነበር፤ እሱ ስለ እኔ ጽፏልና።+ +47 ሆኖም እሱ የጻፈውን ካላመናችሁ እኔ የምናገረውን እንዴት ታምናላችሁ?” +21 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ* ባሕር እንደገና ለደቀ መዛሙርቱ ተገለጠ።* የተገለጠውም በዚህ መንገድ ነበር፤ +2 ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዲዲሞስ* የሚባለው ቶማስ፣+ የገሊላ ቃና ሰው የሆነው ናትናኤል፣+ የዘብዴዎስ ልጆችና+ ሌሎች ሁለት ደቀ መዛሙርቱ አብረው ነበሩ። +3 ስምዖን ጴጥሮስ “ዓሣ ላጠምድ መሄዴ ነው” አላቸው። እነሱም “እኛም አብረንህ እንሄዳለን” አሉት። ወጥተው ሄዱና ጀልባ ላይ ተሳፈሩ፤ በዚያ ሌሊት ግን አንድም ዓሣ አልያዙም።+ +4 ይሁን እንጂ ጎህ ሲቀድ ኢየሱስ መጥቶ በባሕሩ ዳርቻ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቁም ነበር።+ +5 ከዚያም ኢየሱስ “ልጆቼ፣ የሚበላ ነገር* አላችሁ?” አላቸው። እነሱም “የለንም!” ብለው መለሱለት። +6 እሱም “መረቡን ከጀልባዋ በስተ ቀኝ ጣሉት፤ ዓሣ ታገኛላችሁ” አላቸው። እነሱም መረቡን ጣሉ፤ ከዓሣውም ብዛት የተነሳ መረቡን መጎተት አቃታቸው።+ +7 በዚህ ጊዜ፣ ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር+ ጴጥሮስን “ጌታ እኮ ነው!” አለው። ስምዖን ጴጥሮስም ጌታ መሆኑን ሲሰማ ከወገቡ በላይ ራቁቱን* ስለነበር መደረቢያውን ለበሰና* ዘሎ ባሕሩ ውስጥ ገባ። +8 ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ግን ከባሕሩ ዳርቻ ብዙም ሳይርቁ 90 ሜትር ��ደማ* ርቀት ላይ ስለነበሩ በዓሣዎች የተሞላውን መረብ እየጎተቱ በትንሿ ጀልባ መጡ። +9 ወደ ባሕሩ ዳርቻ በደረሱ ጊዜ በከሰል ፍም ላይ የተቀመጠ ዓሣ እንዲሁም ዳቦ አዩ። +10 ኢየሱስ “አሁን ከያዛችሁት ዓሣ የተወሰነ አምጡ” አላቸው። +11 ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጀልባዋ ላይ ወጥቶ በትላልቅ ዓሣዎች የተሞላውን መረብ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ጎተተው፤ የዓሣዎቹም ብዛት 153 ነበር። መረቡ ይህን ያህል ብዙ ዓሣ ቢይዝም አልተቀደደም። +12 ኢየሱስ “ኑ፣ ቁርሳችሁን ብሉ” አላቸው። ጌታ መሆኑን አውቀው ስለነበር ከደቀ መዛሙርቱ መካከል “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም። +13 ኢየሱስም መጥቶ ዳቦውን አነሳና ሰጣቸው፤ ዓሣውንም አንስቶ እንዲሁ አደረገ። +14 ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነበር።+ +15 ቁርስ በልተው ከጨረሱም በኋላ ኢየሱስ፣ ስምዖን ጴጥሮስን “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ ከእነዚህ አስበልጠህ ትወደኛለህ?” አለው። እሱም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም “ጠቦቶቼን መግብ” አለው።+ +16 ደግሞም ለሁለተኛ ጊዜ “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ ትወደኛለህ?” አለው። እሱም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም “ግልገሎቼን ጠብቅ” አለው።+ +17 ለሦስተኛ ጊዜም “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ በጣም ትወደኛለህ?” አለው። ጴጥሮስ ለሦስተኛ ጊዜ “በጣም ትወደኛለህ?” ብሎ ስለጠየቀው አዘነ። በመሆኑም “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ግልገሎቼን መግብ።+ +18 እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ወጣት ሳለህ ራስህ ለብሰህ ወደፈለግክበት ቦታ ትሄድ ነበር። ስታረጅ ግን እጅህን ትዘረጋለህ፤ ሌላ ሰውም ያለብስሃል፤ ወደማትፈልግበትም ቦታ ይወስድሃል።” +19 ይህን የተናገረው፣ ጴጥሮስ በምን ዓይነት አሟሟት አምላክን እንደሚያከብር ለማመልከት ነበር። ይህን ካለ በኋላ “እኔን መከተልህን ቀጥል” አለው።+ +20 ጴጥሮስ ዞር ሲል ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር+ ሲከተላቸው አየ፤ ይህ ደቀ መዝሙር ራት በበሉ ጊዜ ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ “ጌታ ሆይ፣ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነው። +21 ጴጥሮስም ባየው ጊዜ ኢየሱስን “ጌታ ሆይ፣ ይህስ ሰው ምን ይሆናል?” አለው። +22 ኢየሱስም “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲቆይ ብፈቅድ አንተ ምን ቸገረህ? አንተ እኔን መከተልህን ቀጥል” አለው። +23 በመሆኑም ይህ ደቀ መዝሙር አይሞትም የሚል ወሬ በወንድሞች መካከል ተሰራጨ። ይሁንና ኢየሱስ “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲቆይ ብፈቅድ አንተ ምን ቸገረህ?” አለው እንጂ አይሞትም አላለውም። +24 ስለ እነዚህ ነገሮች የሚመሠክረውና እነዚህን ነገሮች የጻፈው ይህ ደቀ መዝሙር ነው፤+ እሱ የሚሰጠው ምሥክርነትም እውነት እንደሆነ እናውቃለን። +25 እርግጥ ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮችም አሉ፤ እነዚህ ሁሉ በዝርዝር ቢጻፉ ዓለም ራሱ የተጻፉትን ጥቅልሎች ለማስቀመጥ የሚበቃ ቦታ የሚኖረው አይመስለኝም።+ +15 “እኔ እውነተኛው የወይን ተክል ነኝ፤ አትክልተኛው ደግሞ አባቴ ነው። +2 በእኔ ላይ ያለውን፣ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ቆርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ደግሞ ይበልጥ እንዲያፈራ ያጠራዋል።*+ +3 እናንተ ከነገርኳችሁ ቃል የተነሳ አሁን ንጹሐን ናችሁ።+ +4 ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ኑሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ያለኝን አንድነት ጠብቄ እኖራለሁ። ቅርንጫፉ ከወይኑ ተክል ጋር ተጣብቆ ካልኖረ በራሱ ፍሬ ማፍራት አይችልም፤ እናንተም ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ካልኖራችሁ+ ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም። +5 እኔ የወይኑ ተክል ነኝ፤ እናንተ ደግሞ ቅርንጫፎቹ ናችሁ። ማንኛውም ሰው ከእኔ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ ከኖረና እኔም ከእሱ ጋር አንድ ሆኜ ከኖርኩ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤+ እናንተ ከእኔ ተለይታችሁ ምንም ነገር ልታደርጉ አትችሉምና። +6 አንድ ሰው ከእኔ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ ካልኖረ እንደ ቅርንጫፍ ይጣልና ይደርቃል። ሰዎችም እንዲህ ያሉትን ቅርንጫፎች ሰብስበው እሳት ውስጥ በመጣል ያቃጥሏቸዋል። +7 እናንተ ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ከጠበቃችሁና ቃሌ በልባችሁ ከኖረ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ብትጠይቁ ይፈጸምላችኋል።+ +8 ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብታሳዩ በዚህ አባቴ ይከበራል።+ +9 አብ እኔን እንደወደደኝ፣+ እኔም እናንተን እንዲሁ ወድጃችኋለሁ። እናንተም በፍቅሬ ኑሩ። +10 እኔ የአብን ትእዛዛት ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም ትእዛዛቴን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ። +11 “እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ እኔ ያገኘሁትን ደስታ እንድታገኙና የእናንተም ደስታ የተሟላ እንዲሆን ነው።+ +12 ትእዛዜ ይህ ነው፤ እኔ እንደወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።+ +13 ሕይወቱን* ለወዳጆቹ ሲል አሳልፎ ከሚሰጥ ሰው የበለጠ ፍቅር ያለው ማንም የለም።+ +14 የማዛችሁን ነገር የምትፈጽሙ ከሆነ ወዳጆቼ ናችሁ።+ +15 ከእንግዲህ ባሪያዎች ብዬ አልጠራችሁም፤ ምክንያቱም ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን ነገር አያውቅም። እኔ ግን ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ ስላሳወቅኳችሁ ወዳጆች ብዬ ጠርቻችኋለሁ። +16 እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ፍሬ እንድታፈሩና ፍሬያችሁ ጸንቶ እንዲኖር ሾሜያችኋለሁ፤ የመረጥኳችሁ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ ነው።+ +17 “እነዚህን ነገሮች የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።+ +18 ዓለም ቢጠላችሁ፣ እናንተን ከመጥላቱ በፊት እኔን እንደጠላኝ ታውቃላችሁ።+ +19 የዓለም ክፍል ብትሆኑ ኖሮ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር። አሁን ግን እኔ ከዓለም መረጥኳችሁ እንጂ የዓለም ክፍል ስላልሆናችሁ+ ከዚህ የተነሳ ዓለም ይጠላችኋል።+ +20 ባሪያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን ቃል አስታውሱ። እኔን ስደት አድርሰውብኝ ከሆነ እናንተንም ስደት ያደርሱባችኋል፤+ ቃሌን ጠብቀው ከሆነ ደግሞ የእናንተንም ቃል ይጠብቃሉ። +21 ሆኖም የላከኝን ስለማያውቁት በስሜ ምክንያት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያደርጉባችኋል።+ +22 መጥቼ ባልነግራቸው ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር።+ አሁን ግን ለኃጢአታቸው የሚያቀርቡት ሰበብ የለም።+ +23 እኔን የሚጠላ ሁሉ አባቴንም ይጠላል።+ +24 ሌላ ማንም ያላደረገውን ነገር በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤+ አሁን ግን እኔን አይተዋል እንዲሁም እኔንም ሆነ አባቴን ጠልተዋል። +25 ይሁን እንጂ ይህ የሆነው ‘ያለምክንያት ጠሉኝ’+ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው። +26 ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ከአብ የሚወጣው ረዳት* ይኸውም የእውነት መንፈስ+ ሲመጣ እሱ ስለ እኔ ይመሠክራል፤+ +27 እናንተም ደግሞ ትመሠክራላችሁ፤+ ምክንያቱም ከመጀመሪያ አንስቶ ከእኔ ጋር ነበራችሁ። +17 ከዚያም በአምፊጶሊስና በአጶሎንያ በኩል ተጉዘው የአይሁዳውያን ምኩራብ ወዳለበት ወደ ተሰሎንቄ መጡ።+ +2 ጳውሎስም እንደ ልማዱ+ ወደ ምኩራብ ገባ፤ ለሦስት ሰንበትም ከቅዱሳን መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነሱ ጋር ተወያየ፤+ +3 ክርስቶስ መከራ መቀበሉና+ ከሞት መነሳቱ+ አስፈላጊ እንደነበር ማስረጃ እየጠቀሰ በማብራራትና በማስረዳት “ይህ እኔ የማውጅላችሁ ኢየሱስ እሱ ክር��ቶስ ነው” አላቸው። +4 ከዚህም የተነሳ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹ አማኞች በመሆን ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ፤+ ከግሪካውያንም መካከል አምላክን የሚያመልኩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እንዲሁም ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል የታወቁ ሴቶች እንዲሁ አደረጉ። +5 ሆኖም አይሁዳውያን ቅናት ስላደረባቸው+ በገበያ ስፍራ የሚያውደለድሉ አንዳንድ ክፉ ሰዎችን አሰባስበው አሳደሙ፤ ከተማዋንም በሁከት አመሷት። ጳውሎስንና ሲላስንም አምጥተው ለረብሻ የተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ለማቅረብ የያሶንን ቤት ሰብረው ገቡ። +6 ባጧቸው ጊዜም ያሶንንና አንዳንድ ወንድሞችን እየጎተቱ ወስደው የከተማዋ ገዢዎች ፊት በማቅረብ እንዲህ እያሉ ጮኹ፦ “ዓለምን ሁሉ ያናወጡት* እነዚያ ሰዎች እዚህም መጥተዋል፤+ +7 ያሶንም በእንግድነት ተቀብሏቸዋል። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሳርን ሕግ የሚቃረን ነገር ያደርጋሉ።”+ +8 ሕዝቡና የከተማዋ ገዢዎች ይህን ሲሰሙ ተሸበሩ፤ +9 ያሶንን እና ሌሎቹን የዋስትና ገንዘብ እንዲያስይዙ ካደረጓቸው በኋላ* ለቀቋቸው። +10 ወንድሞችም እንደመሸ ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ቤርያ ላኳቸው። እነሱም እዚያ እንደደረሱ ወደ አይሁዳውያን ምኩራብ ገቡ። +11 በቤርያ የነበሩት አይሁዳውያን በተሰሎንቄ ከነበሩት ይልቅ ቀና አስተሳሰብ ስለነበራቸው የሰሙት ነገር ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ በየዕለቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ በመመርመር ቃሉን በታላቅ ጉጉት ተቀበሉ። +12 ስለዚህ ከእነሱ መካከል ብዙዎቹ እንዲሁም ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል የተከበሩ ግሪካውያን ሴቶችና የተወሰኑ ወንዶች አማኞች ሆኑ። +13 ሆኖም በተሰሎንቄ ያሉት አይሁዳውያን ጳውሎስ የአምላክን ቃል በቤርያም እንዳወጀ ባወቁ ጊዜ ሕዝቡን ለማነሳሳትና ለማወክ ወደዚያ መጡ።+ +14 በዚህ ጊዜ ወንድሞች ወዲያውኑ ጳውሎስን ወደ ባሕሩ ዳርቻ ላኩት፤+ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው ቀሩ። +15 ጳውሎስን የሸኙት ሰዎችም እስከ አቴንስ አደረሱት፤ ከዚያም ጳውሎስ ‘ሲላስና ጢሞቴዎስ+ በተቻለ ፍጥነት ወደ እኔ እንዲመጡ ንገሯቸው’ የሚል መመሪያ ሰጣቸው፤ ሰዎቹም ተመልሰው ሄዱ። +16 ጳውሎስ በአቴንስ እየጠበቃቸው ሳለ ከተማዋ በጣዖት የተሞላች መሆኗን አይቶ መንፈሱ ተረበሸ። +17 ስለዚህ በምኩራብ ከአይሁዳውያንና አምላክን ከሚያመልኩ ሌሎች ሰዎች ጋር እንዲሁም በየዕለቱ በገበያ ስፍራ* ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይወያይ ጀመር። +18 ሆኖም ከኤፊቆሮስና ከኢስጦይክ ፈላስፎች መካከል አንዳንዶቹ ይከራከሩት ጀመር፤ ሌሎቹ ደግሞ “ይህ ለፍላፊ ምን ሊያወራ ፈልጎ ነው?” ይሉ ነበር። “ስለ ባዕዳን አማልክት የሚያውጅ ይመስላል” የሚሉም ነበሩ። ይህን ያሉት ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤ የሚገልጸውን ምሥራች ያውጅ ስለነበር ነው።+ +19 ስለዚህ ይዘው ወደ አርዮስፋጎስ* ከወሰዱት በኋላ እንዲህ አሉት፦ “ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ ልታስረዳን ትችላለህ? +20 ምክንያቱም ለጆሯችን እንግዳ የሆነ ነገር እያሰማኸን ነው፤ ይህ ነገር ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን።” +21 የአቴንስ ሰዎችና በዚያ የሚገኙ* የባዕድ አገር ሰዎች ትርፍ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ስለ አዳዲስ ነገሮች በማውራትና በመስማት ብቻ ነበር። +22 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ+ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፦ “የአቴንስ ሰዎች ሆይ፣ በሁሉም ነገር ከሌሎች ሰዎች ይበልጥ እናንተ አማልክትን እንደምትፈሩ* ማየት ችያለሁ።+ +23 ለአብነት ያህል፣ እየተዘዋወርኩ ሳለሁ የምታመልኳቸውን ነገሮች በትኩረት ስመለከት ‘ለማይታወቅ አምላክ’ የሚል ጽሑፍ የተቀረጸበት አንድ መሠዊያ አይቻለሁ። ስለዚህ ይህን ሳታው�� የምታመልኩትን እኔ አሳውቃችኋለሁ። +24 ዓለምንና በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረው አምላክ፣ እሱ የሰማይና የምድር ጌታ+ ስለሆነ በእጅ በተሠሩ ቤተ መቅደሶች ውስጥ አይኖርም፤+ +25 በተጨማሪም ሕይወትንና እስትንፋስንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለሰው ሁሉ የሚሰጠው+ እሱ ስለሆነ የሚጎድለው ነገር ያለ ይመስል በሰው እጅ አይገለገልም።+ +26 በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም+ የሰውን ወገኖች በሙሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤+ የተወሰኑትን ዘመናትና የሰው ልጆች የሚኖሩበትንም ድንበር ደነገገ፤+ +27 ይህን ያደረገው ሰዎች አምላክን እንዲፈልጉትና አጥብቀው በመሻት እንዲያገኙት ብሎ ነው፤+ እንዲህ ሲባል ግን እሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ ነው ማለት አይደለም። +28 ምክንያቱም ከእናንተ ባለቅኔዎች አንዳንዶቹ ‘እኛም የእሱ ልጆች ነንና’ ብለው እንደተናገሩት ሁሉ ሕይወት ያገኘነው፣ የምንንቀሳቀሰውና የምንኖረው በእሱ ነው። +29 “እንግዲህ እኛ የአምላክ ልጆች+ ከሆንን አምላክ በሰው ጥበብና ንድፍ ከወርቅ፣ ከብር ወይም ከድንጋይ የተቀረጸን ነገር ይመስላል ብለን ልናስብ አይገባም።+ +30 እርግጥ አምላክ ሰዎች ባለማወቅ የኖሩበትን ጊዜ+ ችላ ብሎ አልፎታል፤ አሁን ግን በየቦታው ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ እያሳሰበ ነው። +31 ምክንያቱም በሾመው ሰው አማካኝነት በዓለም ሁሉ ላይ በጽድቅ ለመፍረድ+ ዓላማ ያለው ሲሆን ይህን ለማድረግም ቀን ወስኗል፤ እሱንም ከሞት በማስነሳት ለሰዎች ሁሉ ዋስትና ሰጥቷል።”+ +32 እነሱም ስለ ሙታን ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ አንዳንዶቹ ያሾፉበት ጀመር፤+ ሌሎቹ ግን “ስለዚሁ ጉዳይ በድጋሚ መስማት እንፈልጋለን” አሉት። +33 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ ትቷቸው ሄደ፤ +34 አንዳንድ ሰዎች ግን ከእሱ ጋር በመተባበር አማኞች ሆኑ። ከእነሱም መካከል የአርዮስፋጎስ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆነው ዲዮናስዮስና ደማሪስ የተባለች ሴት እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ይገኙበታል። +18 ከዚህ በኋላ ከአቴንስ ተነስቶ ወደ ቆሮንቶስ መጣ። +2 በዚያም የጳንጦስ ተወላጅ የሆነ አቂላ+ የተባለ አይሁዳዊ አገኘ፤ ይህ ሰው ቀላውዴዎስ አይሁዳውያን ሁሉ ከሮም እንዲወጡ ባዘዘው መሠረት ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር በቅርቡ ከጣሊያን የመጣ ነበር። ጳውሎስም ወደ እነሱ ሄደ፤ +3 ሙያቸው አንድ ዓይነት በመሆኑ እነሱ ቤት ተቀምጦ አብሯቸው ይሠራ ነበር፤+ ሙያቸውም ድንኳን መሥራት ነበር። +4 በየሰንበቱ+ በምኩራብ+ ንግግር እየሰጠ* አይሁዳውያንንና ግሪካውያንን ያሳምን ነበር። +5 ሲላስና+ ጢሞቴዎስ+ ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ፣ ጳውሎስ ቃሉን በመስበኩ ሥራ በእጅጉ ተጠመደ፤ ኢየሱስ በእርግጥ ክርስቶስ መሆኑን እያስረዳ ለአይሁዳውያን ይመሠክር ነበር።+ +6 አይሁዳውያኑ እሱን መቃወማቸውንና መሳደባቸውን በቀጠሉ ጊዜ ግን ልብሱን አራግፎ*+ “ደማችሁ በራሳችሁ ላይ ይሁን።+ እኔ ንጹሕ ነኝ።+ ከአሁን ጀምሮ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ” አላቸው።+ +7 ከዚያም* ተነስቶ ቲቶስ ኢዮስጦስ ወደሚባል አምላክን ወደሚያመልክ ሰው ቤት ሄደ፤ የዚህ ሰው ቤት ምኩራቡ አጠገብ ነበር። +8 የምኩራብ አለቃው ቀርስጶስ+ ከቤተሰቡ ሁሉ ጋር በጌታ አመነ። መልእክቱን የሰሙ በርካታ የቆሮንቶስ ሰዎችም አምነው ይጠመቁ ጀመር። +9 ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፣ መናገርህን ቀጥል፤ ደግሞም ተስፋ አትቁረጥ፤ +10 እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ+ ማንም አንተን ሊያጠቃና ሊጎዳህ አይችልም፤ በዚህች ከተማ ብዙ ሰዎች አሉኝና።” +11 ስለዚህ በመካከላቸው የአምላክን ቃል እያስተማረ ለአንድ ዓመት ተኩል እዚያ ቆየ። +12 የሮም አገረ ገዢ* የሆነው ጋልዮስ አካይያን ያስተዳድር በነበረበት ጊዜ አይሁዳውያን ግንባር ፈጥረው በጳውሎስ ላይ ተነ��በት፤ በፍርድ ወንበር ፊት አቅርበውትም +13 እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ሕጉን በሚጻረር መንገድ ሰዎች አምላክን እንዲያመልኩ እያሳመነ ነው።” +14 ይሁንና ጳውሎስ ሊናገር ሲል ጋልዮስ አይሁዳውያንን እንዲህ አላቸው፦ “አይሁዳውያን ሆይ፣ አንድ ዓይነት በደል ወይም ከባድ ወንጀል ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ በትዕግሥት ላዳምጣችሁ በተገባኝ ነበር። +15 ነገር ግን ክርክራችሁ ስለ ቃላትና ስለ ስሞች እንዲሁም ስለ ሕጋችሁ+ ከሆነ እናንተው ጨርሱት። እኔ እንዲህ ላለ ነገር ፈራጅ መሆን አልፈልግም።” +16 ከዚያም ከፍርድ ወንበሩ ፊት አስወጣቸው። +17 በዚህ ጊዜ የምኩራብ አለቃ የሆነውን ሶስቴንስን+ ይዘው በፍርድ ወንበሩ ፊት ይደበድቡት ጀመር። ጋልዮስ ግን እንዲህ ባሉ ጉዳዮች እጁን አያስገባም ነበር። +18 ይሁንና ጳውሎስ በዚያ ለተወሰኑ ቀናት ከቆየ በኋላ ወንድሞችን ተሰናብቶ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋር በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። ስእለት ስለነበረበትም ክንክራኦስ+ በተባለ ቦታ ፀጉሩን በአጭሩ ተቆረጠ። +19 ኤፌሶን በደረሱም ጊዜ እነሱን እዚያው ተዋቸው፤ እሱ ግን ወደ ምኩራብ ገብቶ ከአይሁዳውያን ጋር ይወያይ ነበር።+ +20 ምንም እንኳ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲሰነብት አጥብቀው ቢለምኑትም ፈቃደኛ አልሆነም፤ +21 ከዚህ ይልቅ “ይሖዋ* ከፈቀደ ተመልሼ እመጣለሁ” ብሎ ተሰናበታቸው። ከዚያም ከኤፌሶን መርከብ ተሳፍሮ +22 ወደ ቂሳርያ ወረደ። ወጥቶም * ለጉባኤው ሰላምታ ካቀረበ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረደ።+ +23 በዚያም የተወሰነ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ከዚያ ወጥቶ በገላትያና በፍርግያ+ አገሮች ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ አበረታታ።+ +24 በዚህ ጊዜ የእስክንድርያ ተወላጅ የሆነ አጵሎስ+ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እሱም ጥሩ የመናገር ተሰጥኦ ያለውና ቅዱሳን መጻሕፍትን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነበር። +25 ይህ ሰው የይሖዋን* መንገድ የተማረ* ሲሆን በመንፈስ* እየተቃጠለ ኢየሱስን ስለሚመለከቱ ጉዳዮች በትክክል ይናገርና ያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ እሱ የሚያውቀው ዮሐንስ ይሰብከው ስለነበረው ጥምቀት ብቻ ነበር። +26 እሱም በምኩራብ ውስጥ በድፍረት መናገር ጀመረ፤ ጵርስቅላና አቂላም+ በሰሙት ጊዜ ይዘውት በመሄድ የአምላክን መንገድ ይበልጥ በትክክል አብራሩለት። +27 በተጨማሪም ወደ አካይያ መሄድ ፈልጎ ስለነበር ወንድሞች በዚያ የሚገኙት ደቀ መዛሙርት ጥሩ አቀባበል እንዲያደርጉለት የሚያሳስብ ደብዳቤ ጻፉለት። እዚያ በደረሰ ጊዜም በአምላክ ጸጋ አማኞች የሆኑትን ሰዎች በእጅጉ ረዳቸው፤ +28 ከአይሁዳውያን ጋር በይፋ በመወያየት ከቅዱሳን መጻሕፍት ላይ እያሳያቸው ኢየሱስ እሱ ክርስቶስ እንደሆነ በመግለጽ ትክክል እንዳልሆኑ በጋለ ስሜት ያስረዳቸው ነበር።+ +23 ጳውሎስ የሳንሄድሪንን ሸንጎ ትኩር ብሎ እየተመለከተ “ወንድሞች፣ እኔ እስከዚህ ቀን ድረስ በአምላክ ፊት ሙሉ በሙሉ ንጹሕ ሕሊና ይዤ ተመላልሻለሁ”+ አለ። +2 በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ፣ ጳውሎስ አጠገብ የቆሙት ሰዎች አፉን እንዲመቱት አዘዘ። +3 ጳውሎስም “አንተ በኖራ የተለሰንክ ግድግዳ! አምላክ አንተን ይመታሃል። በሕጉ መሠረት በእኔ ላይ ለመፍረድ ተቀምጠህ ሳለ አንተ ራስህ ሕጉን በመጣስ እንድመታ ታዛለህ?” አለው። +4 አጠገቡ የቆሙትም “የአምላክን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህ?” አሉት። +5 ጳውሎስም “ወንድሞች፣ እኔ እኮ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላወቅኩም። ምክንያቱም ‘በሕዝብህ ገዢ ላይ ክፉ ቃል አትናገር’ ተብሎ ተጽፏል” አላቸው።+ +6 ጳውሎስ ግማሾቹ ሰዱቃውያን ግማሾቹ ደግሞ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ስላወቀ በሳንሄድሪን ሸንጎ ውስጥ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ወንድሞች፣ እኔ ከፈሪሳውያን የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ።+ ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ ተስፋ በማመኔ ነው” ሲል ተናገረ። +7 ይህን በመናገሩ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ግጭት ተፈጥሮ ጉባኤው ለሁለት ተከፈለ። +8 ምክንያቱም ሰዱቃውያን ትንሣኤም፣ መልአክም፣ መንፈሳዊ ፍጥረታትም የሉም ይሉ የነበረ ሲሆን ፈሪሳውያን ግን በእነዚህ ነገሮች ያምኑ ነበር።+ +9 ስለዚህ ከፍተኛ ሁከት ተፈጠረ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ ጸሐፍት ተነስተው እንዲህ ሲሉ አጥብቀው ተከራከሩ፦ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘንም፤ መንፈስ ወይም መልአክ አናግሮት ከሆነ ግን+ . . . ።” +10 በመካከላቸው የተፈጠረው ግጭት እየከረረ ሲሄድ የሠራዊቱ ሻለቃ ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ወታደሮቹ ወርደው ከመካከላቸው ነጥቀው እንዲያመጡትና ወደ ጦር ሰፈሩ እንዲያስገቡት አዘዘ። +11 ሆኖም በዚያኑ ዕለት ሌሊት ጌታ በጳውሎስ አጠገብ ቆሞ እንዲህ አለው፦ “አይዞህ፣ አትፍራ!+ ምክንያቱም በኢየሩሳሌም ስለ እኔ በሚገባ እንደመሠከርክ* ሁሉ በሮምም ልትመሠክርልኝ ይገባል።”+ +12 በነጋም ጊዜ አይሁዳውያን በጳውሎስ ላይ በማሴር እሱን እስኪገድሉ ድረስ እህል ውኃ ላለመቅመስ ተማማሉ።* +13 ይህን ሴራ ለመፈጸም የተማማሉት ሰዎች ቁጥራቸው ከ40 በላይ ነበር። +14 እነሱም ወደ ካህናት አለቆቹና ወደ ሽማግሌዎቹ ሄደው እንዲህ አሉ፦ “ጳውሎስን እስክንገድል ድረስ አንዳች እህል ላለመቅመስ ጽኑ መሐላ ተማምለናል። +15 ስለዚህ እናንተ ከሳንሄድሪን ሸንጎ ጋር ሆናችሁ የጳውሎስን ጉዳይ ይበልጥ ማጣራት የምትፈልጉ በማስመሰል እሱን ወደ እናንተ እንዲያመጣው ለሠራዊቱ ሻለቃ ንገሩት። ይሁንና እኛ እዚህ ከመድረሱ በፊት እሱን ለመግደል ተዘጋጅተን እንጠብቃለን።” +16 ይሁን እንጂ የጳውሎስ የእህቱ ልጅ አድብተው ጥቃት ለመሰንዘር እንዳሰቡ በመስማቱ ወደ ጦር ሰፈሩ ገብቶ ጉዳዩን ለጳውሎስ ነገረው። +17 ጳውሎስም ከመኮንኖቹ አንዱን ጠርቶ “ይህ ወጣት ለሠራዊቱ ሻለቃ የሚነግረው ነገር ስላለው ወደ እሱ ውሰደው” አለው። +18 እሱም ወደ ሻለቃው ይዞት ሄደና “እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶኝ ይህ ወጣት የሚነግርህ ነገር ስላለው ወደ አንተ እንዳቀርበው ጠየቀኝ” አለው። +19 ሻለቃውም እጁን ይዞ ለብቻው ገለል ካደረገው በኋላ “ልትነግረኝ የፈለግከው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። +20 እሱም እንዲህ አለ፦ “አይሁዳውያን ስለ ጳውሎስ ጉዳይ በዝርዝር ማወቅ የፈለጉ በማስመሰል ነገ ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ እንድታመጣው ሊጠይቁህ ተስማምተዋል።+ +21 አንተ ግን በዚህ እንዳትታለል፤ ምክንያቱም ከመካከላቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች አድብተው በእሱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየጠበቁ ነው፤ ደግሞም እሱን እስኪገድሉ ድረስ እህልም ሆነ ውኃ ላለመቅመስ ተማምለዋል፤+ አሁንም ተዘጋጅተው የአንተን ፈቃድ እየተጠባበቁ ነው።” +22 በዚህ ጊዜ የሠራዊቱ ሻለቃ “ይህን ነገር ለእኔ መንገርህን ለማንም እንዳታወራ” ብሎ ካዘዘው በኋላ ወጣቱን አሰናበተው። +23 ከዚያም ከመኮንኖቹ መካከል ሁለቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ወደ ቂሳርያ የሚሄዱ 200 ወታደሮች እንዲሁም 70 ፈረሰኞችና ጦር የያዙ 200 ሰዎች አዘጋጁ። +24 በተጨማሪም ጳውሎስን ወደ አገረ ገዢው ወደ ፊሊክስ በደህና ለማድረስ የሚጓዝባቸው ፈረሶች አዘጋጁ።” +25 እንዲህ የሚል ደብዳቤም ጻፈ፦ +26 “ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ፤ ለክቡር አገረ ገዢ ለፊሊክስ፦ ሰላም ለአንተ ይሁን። +27 አይሁዳውያን ይህን ሰው ይዘው ሊገድሉት ነበር፤ ሆኖም የሮም ዜጋ መሆኑን ስላወቅኩ+ ወዲያውኑ ከወታደሮቼ ጋር ደርሼ አዳንኩት።+ +28 እሱን የከሰሱት ለምን እንደሆነ ለማወቅ ስለፈለግኩም ወደ ሳንሄድሪን ሸንጓቸው አቀረብኩት።+ +29 የተከሰሰውም ከሕጋቸው ጋር በተያያዘ በተነሳ ውዝግብ እንደሆነ ተረድቻለሁ፤+ ሆኖም ለሞት ወይም ለእስር የሚያበቃ አንድም ክስ አላገኘሁም። +30 ይሁንና በዚህ ሰው ላይ የተሸረበ ሴራ እንዳለ ስለተነገረኝ+ ወዲያውኑ ወደ አንተ ልኬዋለሁ፤ ከሳሾቹም ክሳቸውን በአንተ ፊት እንዲያቀርቡ አዝዤአቸዋለሁ።” +31 ስለዚህ ወታደሮቹ በታዘዙት መሠረት ጳውሎስን ይዘው+ በሌሊት ወደ አንቲጳጥሪስ ወሰዱት። +32 በማግስቱም ፈረሰኞቹ ከጳውሎስ ጋር ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ በማድረግ እነሱ ወደ ጦር ሰፈሩ ተመለሱ። +33 ፈረሰኞቹም ቂሳርያ በደረሱ ጊዜ ደብዳቤውን ለአገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳውሎስንም አስረከቡት። +34 እሱም ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ የየትኛው አውራጃ ሰው እንደሆነ ጠየቀ፤ የኪልቅያ ሰው መሆኑንም ተረዳ።+ +35 ከዚያም “ከሳሾችህ ሲመጡ ጉዳይህን በደንብ አየዋለሁ” አለው።+ በሄሮድስም ቤተ መንግሥት ውስጥ በጥበቃ ሥር ሆኖ እንዲቆይ አዘዘ። +19 ከጊዜ በኋላ፣ አጵሎስ+ በቆሮንቶስ በነበረበት ጊዜ ጳውሎስ በመሃል አገር አቋርጦ ወደ ኤፌሶን ወረደ።+ በዚያም አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን አገኘ፤ +2 እነሱንም “አማኞች በሆናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ተቀብላችሁ ነበር?” አላቸው።+ እነሱም “ኧረ እኛ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሰማነው ነገር የለም” ሲሉ መለሱለት። +3 እሱም “ታዲያ ምን ዓይነት ጥምቀት ነው የተጠመቃችሁት?” አላቸው። እነሱም “የዮሐንስን ጥምቀት” አሉት።+ +4 ጳውሎስም እንዲህ አላቸው፦ “ዮሐንስ ያጠምቅ የነበረው የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት ነበር፤+ ሰዎች ከእሱ በኋላ በሚመጣው+ ይኸውም በኢየሱስ እንዲያምኑ ይነግራቸው ነበር።” +5 እነሱም ይህን ሲሰሙ በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ። +6 ጳውሎስም እጁን በላያቸው በጫነ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤+ እነሱም በባዕድ ቋንቋዎች መናገርና መተንበይ ጀመሩ።+ +7 ሰዎቹም በአጠቃላይ 12 ገደማ ነበሩ። +8 ጳውሎስም ወደ ምኩራብ እየገባ+ ንግግር በመስጠትና ስለ አምላክ መንግሥት አሳማኝ በሆነ መንገድ በማስረዳት ለሦስት ወራት ያህል በድፍረት ሲናገር ቆየ።+ +9 ሆኖም አንዳንዶቹ ግትሮች ስለነበሩ ለማመን ፈቃደኞች አልሆኑም፤ የጌታን መንገድ+ በሕዝቡ ፊት ባጥላሉ ጊዜ ከእነሱ በመራቅ+ ደቀ መዛሙርቱን ለይቶ ወሰዳቸው፤ በጢራኖስ የትምህርት ቤት አዳራሽም በየዕለቱ ንግግር ይሰጥ ነበር። +10 ይህም ለሁለት ዓመት ያህል ቀጠለ፤ ከዚህም የተነሳ በእስያ አውራጃ የሚኖሩ አይሁዳውያንና ግሪካውያን ሁሉ የጌታን ቃል ሰሙ። +11 አምላክም በጳውሎስ እጅ በጣም አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን መፈጸሙን ቀጠለ፤+ +12 ሰዎችም የጳውሎስን ሰውነት የነኩ ጨርቆችንና ሽርጦችን ወደታመሙት ሰዎች ሲወስዱ+ ሰዎቹ በሽታቸው ይለቃቸው ነበር፤ ርኩሳን መናፍስትም ይወጡ ነበር።+ +13 ይሁንና እየዞሩ አጋንንትን ያስወጡ ከነበሩት አይሁዳውያን አንዳንዶቹም “ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ ስም እንድትወጣ አጥብቄ አዝሃለሁ”+ እያሉ ክፉ መናፍስት በያዟቸው ሰዎች ላይ የጌታ ኢየሱስን ስም ለመጥራት ሞከሩ። +14 አስቄዋ የተባለ የአንድ አይሁዳዊ የካህናት አለቃ ሰባት ወንዶች ልጆችም ይህን ያደርጉ ነበር። +15 ክፉው መንፈስ ግን መልሶ “ኢየሱስን አውቀዋለሁ፤+ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤+ እናንተ ደግሞ ማን ናችሁ?” አላቸው። +16 ከዚያም ክፉው መንፈስ ያደረበት ሰው ዘሎ ጉብ አለባቸው፤ አሸነፋቸውም፤ ስለዚህ ራቁታቸውን ሆነውና ቆስለው ከዚያ ቤት ሸሹ። +17 በኤፌሶን የሚኖሩት አይሁዳውያንና ግሪካውያን ሁሉ ይህን ሰሙ፤ በመሆኑም ሁሉም ፍርሃት አደረባቸው፤ የጌታ ኢየሱስ ስምም ይበልጥ እየገነነ ሄደ። +18 አማኞች ከሆኑ��� መካከል ብዙዎቹም እየመጡ ያደረጉትን ይናዘዙና በግልጽ ይናገሩ ነበር። +"19 ደግሞም አስማት ይሠሩ ከነበሩት መካከል ብዙዎች መጽሐፎቻቸውን አንድ ላይ ሰብስበው በማምጣት በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉ።+ የመጽሐፎቹንም ዋጋ ሲያሰሉ 50,000 የብር ሳንቲሞች* ሆኖ አገኙት።" +20 በዚህ መንገድ የይሖዋ* ቃል በኃይል እየተስፋፋና እያሸነፈ ሄደ።+ +21 ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና+ በአካይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ወሰነ።+ “እዚያ ከሄድኩ በኋላ ደግሞ ወደ ሮም ማቅናት አለብኝ” አለ።+ +22 ስለዚህ ከሚያገለግሉት መካከል ሁለቱን ማለትም ጢሞቴዎስንና+ ኤርስጦስን+ ወደ መቄዶንያ ላካቸው፤ እሱ ግን በእስያ አውራጃ ለተወሰነ ጊዜ ቆየ። +23 በዚህ ወቅት የጌታን መንገድ+ በተመለከተ ታላቅ ሁከት ተፈጠረ።+ +24 ምክንያቱም ድሜጥሮስ የተባለ አንድ የብር አንጥረኛ የአርጤምስን ቤተ መቅደስ የብር ምስሎች እየቀረጸ ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትርፍ ያስገኝ ነበር።+ +25 ድሜጥሮስ እነሱንና በተመሳሳይ ሙያ የተሰማሩ ሰዎችን ሰብስቦ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሰዎች፣ መቼም ብልጽግናችን የተመካው በዚህ ሥራ ላይ እንደሆነ ታውቃላችሁ። +26 አሁን ግን ይህ ጳውሎስ የተባለ ሰው በኤፌሶን+ ብቻ ሳይሆን በመላው የእስያ አውራጃ ማለት ይቻላል፣ በእጅ የተሠሩ አማልክት ሁሉ በፍጹም አማልክት አይደሉም እያለ ብዙ ሰዎችን አሳምኖ አመለካከታቸውን እንዳስለወጠ ያያችሁትና የሰማችሁት ጉዳይ ነው።+ +27 ከዚህም በላይ አሳሳቢ የሆነው ነገር የእኛ ሥራ መናቁ ብቻ ሳይሆን የታላቋ አምላክ የአርጤምስ ቤተ መቅደስ ዋጋ ቢስ ሆኖ ሊቀርና መላው የእስያ አውራጃም ሆነ ዓለም በሙሉ የሚያመልካት አርጤምስ ገናና ክብሯ ሊገፈፍ መሆኑ ጭምር ነው።” +28 ሰዎቹ ይህን ሲሰሙ በቁጣ ተሞልተው “የኤፌሶኗ አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ይጮኹ ጀመር። +29 በመሆኑም ከተማዋ በረብሻ ታመሰች፤ ሕዝቡም የመቄዶንያ ሰዎች የሆኑትን የጳውሎስን የጉዞ ጓደኞች ይኸውም ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን+ እየጎተቱ ግር ብለው ወደ ጨዋታ ማሳያው ስፍራ ገቡ። +30 ጳውሎስም ሕዝቡ ወዳለበት ሊገባ ፈልጎ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ከለከሉት። +31 የጳውሎስ ወዳጆች የነበሩ አንዳንድ የበዓላትና የውድድር አዘጋጆች እንኳ ሳይቀሩ ወደ ጨዋታ ማሳያው ስፍራ በመግባት ራሱን ለአደጋ እንዳያጋልጥ መልእክት በመላክ ለመኑት። +32 በተሰበሰበው ሕዝብ መካከል ከፍተኛ ትርምስ ተፈጥሮ ስለነበር አንዳንዶቹ አንድ ነገር ሲናገሩ ሌሎቹ ደግሞ ሌላ ነገር እየተናገሩ ይጯጯኹ ነበር፤ አብዛኛው ሰው ለምን እዚያ እንደተገኘ እንኳ አያውቅም ነበር። +33 አንዳንዶች እስክንድርን ከሕዝቡ መካከል ባወጡት ጊዜ አይሁዳውያን ወደ ፊት ገፉት፤ እስክንድርም የመከላከያ ሐሳቡን ለሕዝቡ ሊያቀርብ ፈልጎ በእጁ ምልክት ሰጣቸው። +34 ሆኖም አይሁዳዊ መሆኑን ባወቁ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ “የኤፌሶኗ አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ለሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። +35 በመጨረሻ የከተማዋ ዋና ጸሐፊ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አለ፦ “የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፣ የታላቋ አርጤምስ ቤተ መቅደስና ከሰማይ የወረደው ምስሏ ጠባቂ የኤፌሶናውያን ከተማ እንደሆነች የማያውቅ ማን አለ? +36 ይህ ፈጽሞ የማይታበል ሐቅ ስለሆነ ልትረጋጉና የችኮላ እርምጃ ከመውሰድ ልትቆጠቡ ይገባል። +37 ምክንያቱም እነዚህ ያመጣችኋቸው ሰዎች ቤተ መቅደስ የዘረፉ ወይም የምናመልካትን አምላክ የሰደቡ አይደሉም። +38 ስለዚህ ድሜጥሮስና+ አብረውት ያሉት የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች የሚከሱት ሰው ካለ ችሎት የሚሰየምባቸው ቀናት ያሉ ከመሆኑም ሌላ የሮም አገረ ገዢዎች* አሉ፤ እዚያ መሟገት ይችላሉ። +39 ከዚህ ያለፈ ልታቀርቡት የምትፈልጉት ክስ ካለ ግን በመደበኛ ጉባኤ መዳኘት ይኖርበታል። +40 አለዚያ ዛሬ በተፈጸመው ነገር የተነሳ ሕዝብ አሳድማችኋል ተብለን እንዳንከሰስ ያሰጋል፤ ለዚህ ሁሉ ሁከት መንስኤው ምን እንደሆነ ብንጠየቅ የምንሰጠው አጥጋቢ መልስ የለም።” +41 ይህን ከተናገረ በኋላ የተሰበሰበው ሕዝብ እንዲበተን አደረገ። +20 ሁከቱ ሲበርድ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስጠራቸው፤ ካበረታታቸውና ከተሰናበታቸው በኋላ ወደ መቄዶንያ ጉዞ ጀመረ። +2 በሚያልፍባቸው ስፍራዎች የሚያገኛቸውን ደቀ መዛሙርት በብዙ ቃል እያበረታታ ወደ ግሪክ መጣ። +3 በዚያ ሦስት ወር ቆየ፤ ይሁንና ወደ ሶርያ በመርከብ ለመሄድ ተነስቶ ሳለ አይሁዳውያን ሴራ ስለጠነሰሱበት+ ሐሳቡን ቀይሮ በመቄዶንያ አድርጎ ለመመለስ ወሰነ። +4 የጳይሮስ ልጅ የቤርያው ሶጳጥሮስ፣ የተሰሎንቄዎቹ አርስጥሮኮስና+ ሲኮንዱስ፣ የደርቤው ጋይዮስ፣ ጢሞቴዎስ+ እንዲሁም ከእስያ አውራጃ የመጡት ቲኪቆስና+ ጢሮፊሞስ+ አብረውት ነበሩ። +5 እነዚህም ወደ ጥሮአስ ቀድመውን በመሄድ እዚያ ጠበቁን፤ +6 እኛ ግን የቂጣ በዓል+ ካለፈ በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሳን፤ በአምስት ቀን ጊዜ ውስጥም እነሱ ወዳሉበት ወደ ጥሮአስ ደረስን፤ በዚያም ሰባት ቀን ቆየን። +7 በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ምግብ ልንበላ አንድ ላይ ተሰብስበን ሳለን ጳውሎስ በማግስቱ ይሄድ ስለነበር ንግግር ይሰጣቸው ጀመር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አስረዘመ። +8 በመሆኑም ተሰብስበንበት በነበረው ፎቅ ላይ ባለው ክፍል ውስጥ ብዙ መብራት ነበር። +9 ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ መስኮት ላይ ተቀምጦ የነበረ አውጤኪስ የሚባል አንድ ወጣት ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እንቅልፍ ስለጣለውም ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ወደቀ፤ ሲያነሱትም ሞቶ ነበር። +10 ጳውሎስም ከፎቅ ላይ ወርዶ በላዩ ላይ ተኝቶ አቀፈውና+ “በሕይወት ስላለ አትንጫጩ”* አላቸው።+ +11 ከዚያም ወደ ፎቅ ወጥቶ ማዕዱን ካስጀመረ* በኋላ በላ። እስከ ንጋትም ድረስ ሲነጋገር ቆየ፤ በኋላም ተነስቶ ሄደ። +12 ሰዎቹም ወጣቱን ወሰዱት፤ ሕያው በመሆኑም እጅግ ተጽናኑ። +13 እኛም ጳውሎስ በሰጠን መመሪያ መሠረት በመርከብ ተሳፍረን በቅድሚያ ወደ አሶስ ተጓዝን፤ ምክንያቱም ጳውሎስ በእግሩ ተጉዞ በዚያ ለመሳፈር አስቦ ነበር። +14 ስለዚህ አሶስ ላይ ከተገናኘን በኋላ አሳፍረነው ወደ ሚጢሊኒ ሄድን። +15 በነጋታውም ጉዟችንን በመቀጠል ከኪዮስ ትይዩ ወዳለው ስፍራ ደረስን፤ በሚቀጥለው ቀን ደግሞ ሳሞስ ላይ አጭር ቆይታ አደረግን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን። +16 ጳውሎስ በእስያ አውራጃ ምንም መቆየት ስላልፈለገ ኤፌሶንን+ አልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ምክንያቱም ቢችል በጴንጤቆስጤ በዓል ቀን ኢየሩሳሌም ለመድረስ ቸኩሎ ነበር።+ +17 ይሁን እንጂ ከሚሊጢን ወደ ኤፌሶን መልእክት ልኮ የጉባኤውን ሽማግሌዎች አስጠራ። +18 ወደ እሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “በእስያ አውራጃ እግሬ ከረገጠበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ በመካከላችሁ እንዴት እንደተመላለስኩ ታውቃላችሁ፤+ +19 በአይሁዳውያን ሴራ ምክንያት ብዙ መከራ ቢደርስብኝም እንኳ በታላቅ ትሕትናና+ በእንባ ጌታን አገለግል ነበር፤ +20 ደግሞም የሚጠቅማችሁን ማንኛውንም ነገር ከመንገርም ሆነ በአደባባይና+ ከቤት ወደ ቤት+ ከማስተማር ወደኋላ ብዬ አላውቅም። +21 ከዚህ ይልቅ አይሁዳውያንም ሆኑ ግሪካውያን ንስሐ እንዲገቡና+ ወደ አምላክ እንዲመለሱ እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ በተሟላ ሁኔታ* መሥክሬላቸዋለሁ።+ +22 አሁን ደግሞ እዚያ ምን እንደሚደርስብኝ ባላውቅም መንፈስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው፤ +23 እርግጥ ነው፣ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ በደረስኩበት ከተማ ሁሉ በተደጋጋሚ ያሳስበኛል።+ +24 ይሁንና ሩጫዬን እስካጠናቀቅኩ+ እንዲሁም ስለ አምላክ ጸጋ የሚገልጸውን ምሥራች በተሟላ ሁኔታ በመመሥከር* ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልኩትን አገልግሎት እስከፈጸምኩ ድረስ ሕይወቴ* ምንም አያሳሳኝም።* +25 “አሁንም እነሆ፣ የአምላክን መንግሥት የሰበክሁላችሁ እናንተ ሁላችሁ ዳግመኛ ፊቴን እንደማታዩ አውቃለሁ። +26 ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን ለማሳየት በዚህች ቀን እናንተን ምሥክር አድርጌ መጥራት እችላለሁ፤+ +27 ምክንያቱም የአምላክን ፈቃድ* ሁሉ ለእናንተ ከመንገር ወደኋላ አላልኩም።+ +28 ለራሳችሁም ሆነ አምላክ በገዛ ልጁ ደም+ የዋጀውን ጉባኤውን እረኛ ሆናችሁ እንድትጠብቁ+ መንፈስ ቅዱስ የበላይ ተመልካቾች+ አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ትኩረት ስጡ።+ +29 እኔ ከሄድኩ በኋላ ጨካኝ* ተኩላዎች በመካከላችሁ እንደሚገቡና+ መንጋውን በርኅራኄ እንደማይዙ አውቃለሁ፤ +30 ከእናንተ መካከል እንኳ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሳቸው ለመሳብ ጠማማ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ይነሳሉ።+ +31 “ስለዚህ ነቅታችሁ ጠብቁ፤ ሦስት ዓመት ሙሉ+ ሌሊትና ቀን እያንዳንዳችሁን በእንባ ከማሳሰብ ወደኋላ እንዳላልኩ አስታውሱ። +32 አሁንም ለአምላክ እንዲሁም ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው፣ ስለ እሱ ጸጋ ለሚገልጸው ቃል አደራ እሰጣችኋለሁ።+ +33 የማንንም ብር፣ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም።+ +34 እነዚህ እጆቼ ለእኔም ሆነ ከእኔ ጋር ለነበሩት የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለማሟላት እንዳገለገሉ+ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። +35 እናንተም እንዲሁ እየሠራችሁ ደካማ የሆኑትን መርዳት እንዳለባችሁ በሁሉም ነገር አሳይቻችኋለሁ፤+ እንዲሁም ‘ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል’+ በማለት ጌታ ኢየሱስ ራሱ የተናገረውን ቃል ማስታወስ ይኖርባችኋል።” +36 ይህን ተናግሮ ከጨረሰም በኋላ ከሁሉም ጋር ተንበርክኮ ጸለየ። +37 ከዚያም ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም እቅፍ አድርገው* ሳሙት፤ +38 ከሁሉ ይበልጥ ያሳዘናቸው ከዚህ በኋላ ፊቱን እንደማያዩ የተናገረው ቃል ነው።+ ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት። +3 አንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ሰዓት ይኸውም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደሱ እየወጡ ነበር፤ +2 ሰዎችም ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ ሽባ የሆነ አንድ ሰው ተሸክመው በማምጣት ወደ ቤተ መቅደሱ ከሚገባው ሰው ምጽዋት* እንዲለምን “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደሱ በር አጠገብ በየዕለቱ ያስቀምጡት ነበር። +3 ይህ ሰው ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሊገቡ ሲሉ አያቸውና ምጽዋት እንዲሰጡት ይለምናቸው ጀመር። +4 ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን ትኩር ብለው አዩት፤ ከዚያም ጴጥሮስ “ወደ እኛ ተመልከት” አለው። +5 ሰውየውም የሆነ ነገር ሊሰጡኝ ነው ብሎ በማሰብ ትኩር ብሎ ተመለከታቸው። +6 ይሁንና ጴጥሮስ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ። በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነስና ተራመድ!” አለው።+ +7 ከዚያም ቀኝ እጁን ይዞ አስነሳው።+ ወዲያውም እግሩና ቁርጭምጭሚቱ ጠነከረ፤+ +8 ዘሎም ተነሳ፤+ መራመድም ጀመረ፤ ደግሞም እየተራመደና እየዘለለ እንዲሁም አምላክን እያወደሰ ከእነሱ ጋር ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ። +9 ሰዎቹም ሁሉ ሲራመድና አምላክን ሲያወድስ አዩት። +10 ይህ ሰው “ውብ በር” በተባለው የቤተ መቅደሱ መግቢያ አጠገብ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው ሰው መሆኑን ስላወቁ በእሱ ላይ በተፈጸመው ሁኔታ እጅግ ተገረሙ፤+ በአድናቆትም ተዋጡ። +11 ሰውየው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዟቸው ሳለ በዚያ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ���ጅግ ተደንቀው እነሱ ወዳሉበት “የሰለሞን መተላለፊያ”+ ወደሚባለው ስፍራ ግር ብለው እየሮጡ መጡ። +12 ጴጥሮስ ይህን ባየ ጊዜ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በዚህ ለምን ትደነቃላችሁ? ደግሞስ በእኛ ኃይል ወይም እኛ ለአምላክ ያደርን በመሆናችን የተነሳ ይህን ሰው እንዲራመድ ያስቻልነው ይመስል ለምን ትኩር ብላችሁ ታዩናላችሁ? +13 የአባቶቻችን አምላክ ይኸውም የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ+ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና+ ጲላጦስ ሊፈታው ወስኖ የነበረ ቢሆንም በእሱ ፊት የካዳችሁትን አገልጋዩን ኢየሱስን አከበረው።+ +14 አዎ፣ እናንተ ይህን ቅዱስና ጻድቅ ሰው ክዳችሁ ነፍሰ ገዳይ የሆነን ሰው እንዲፈታላችሁ ጠየቃችሁ፤+ +15 በአንጻሩ ግን የሕይወትን “ዋና ወኪል”*+ ገደላችሁት። አምላክ ግን ከሞት አስነሳው፤ እኛም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን።+ +16 የኢየሱስ ስምና እኛ በስሙ ላይ ያለን እምነት ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን ሰው አጠነከረው። በኢየሱስ አማካኝነት ያገኘነው እምነት ይህ ሰው በሁላችሁም ፊት ፍጹም ጤናማ እንዲሆን አደረገው። +17 አሁንም ወንድሞች፣ ገዢዎቻችሁ እንዳደረጉት ሁሉ እናንተም ይህን ያደረጋችሁት ባለማወቅ እንደሆነ አውቃለሁ።+ +18 ይሁንና አምላክ፣ ክርስቶስ መከራ እንደሚቀበል በነቢያት ሁሉ አፍ አስቀድሞ ያሳወቀው ነገር በዚህ መንገድ እንዲፈጸም አድርጓል።+ +19 “ስለዚህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስ+ ንስሐ ግቡ፣+ ተመለሱም፤+ ከይሖዋም ዘንድ* የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ +20 እንዲሁም ለእናንተ የሾመውን ክርስቶስን ይኸውም ኢየሱስን ይልክላችኋል። +21 እሱም አምላክ በጥንቶቹ ቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገራቸው ነገሮች ሁሉ የሚታደሱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ በሰማይ መቆየት* ይገባዋል። +22 ደግሞም ሙሴ እንዲህ ብሏል፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ* ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል።+ እሱ የሚነግራችሁንም ነገር ሁሉ ስሙ።+ +23 ያንን ነቢይ የማይሰማ ሰው ሁሉ* ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።’+ +24 ከሳሙኤል ጀምሮ በተከታታይ የተነሱት ነቢያት ሁሉ ስለ እነዚህ ቀናት በግልጽ ተናግረዋል።+ +25 እናንተ የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ እንዲሁም አምላክ ለአብርሃም ‘የምድር ቤተሰቦች ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ይባረካሉ’+ ብሎ ከአባቶቻችሁ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ወራሾች ናችሁ።+ +26 አምላክ አገልጋዩን ካስነሳ በኋላ እያንዳንዳችሁን ከክፉ ሥራችሁ በመመለስ ይባርካችሁ ዘንድ በመጀመሪያ ወደ እናንተ ላከው።”+ +24 ከአምስት ቀን በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ+ ከተወሰኑ ሽማግሌዎችና ጠርጡለስ ከሚባል ጠበቃ ጋር ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ እነሱም በጳውሎስ ላይ ያላቸውን ክስ ለአገረ ገዢው አቀረቡ።+ +2 በተጠራም ጊዜ ጠርጡለስ እንዲህ ሲል ይከሰው ጀመር፦ “ክቡር ፊሊክስ ሆይ፣ በአንተ አማካኝነት ብዙ ሰላም አግኝተናል፤ አስተዋይነትህም ለዚህ ሕዝብ መሻሻል አስገኝቷል፤ +3 በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ለእነዚህ ነገሮች ሁሉ ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን። +4 ይሁንና አሁን ጊዜህን እንዳልወስድብህ በአጭሩ የምንነግርህን ጉዳይ መልካም ፈቃድህ ሆኖ እንድትሰማን እለምንሃለሁ። +5 ይህ ሰው መቅሰፍት* ሆኖብናል፤+ በዓለም ባሉት አይሁዳውያን ሁሉ መካከል ዓመፅ ያነሳሳል፤+ ከዚህም ሌላ የናዝሬታውያን ኑፋቄ ቀንደኛ መሪ ነው።+ +6 በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ መቅደሱን ለማርከስ ሲሞክር ስላገኘነው ያዝነው።+ +7 *—— +8 አንተ ራስህ ስትመረምረው በእሱ ላይ ያቀረብነው ክስ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ ትችላለህ።” +9 አይሁዳውያኑም የተባለው ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን በመግለጽ በክሱ ተባበሩ። +10 አገረ ገዢውም እንዲናገር በጭንቅላቱ ምልክት በሰጠው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ለብዙ ዓመታት ለዚህ ሕዝብ ፈራጅ ሆነህ ስታገለግል መቆየትህን አውቃለሁ፤ በመሆኑም ስለ ራሴ የመከላከያ መልስ የማቀርበው በደስታ ነው።+ +11 ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከ12 ቀን እንደማይበልጥ አንተው ራስህ ማረጋገጥ ትችላለህ፤+ +12 እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ከማንም ጋር ስከራከርም ሆነ በምኩራቦች ወይም በከተማው ውስጥ ሕዝቡን ለዓመፅ ሳነሳሳ አላገኙኝም። +13 በተጨማሪም አሁን ላቀረቡብኝ ክስ ሁሉ ምንም ማስረጃ ሊያቀርቡልህ አይችሉም። +14 ይሁን እንጂ በሕጉና በነቢያት የተጻፉትን ነገሮች ሁሉ+ ስለማምን እነሱ ኑፋቄ ብለው የሚጠሩትን የሕይወት መንገድ እንደምከተልና በዚህም መንገድ ለአባቶቼ አምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንደማቀርብ አልክድም።+ +15 ደግሞም እነዚህ ሰዎች ራሳቸው ተስፋ እንደሚያደርጉት ጻድቃንም ሆኑ ዓመፀኞች+ ከሞት እንደሚነሱ+ በአምላክ ተስፋ አደርጋለሁ። +16 በዚህ የተነሳ በአምላክም ሆነ በሰው ፊት ንጹሕ* ሕሊና ይዤ ለመኖር ሁልጊዜ ጥረት አደርጋለሁ።+ +17 ከብዙ ዓመታት በኋላም ለወገኖቼ ምጽዋት ለመስጠትና+ ለአምላክ መባ ለማቅረብ መጣሁ። +18 በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያገኙኝ የመንጻት ሥርዓት ፈጽሜ+ ይህንኑ ሳደርግ እንጂ ከብዙ ሕዝብ ጋር ሆኜ ሁከት ሳነሳሳ አልነበረም። ሆኖም ከእስያ አውራጃ የመጡ አንዳንድ አይሁዳውያን ነበሩ፤ +19 እነሱ እኔን የሚከሱበት ነገር ካላቸው እዚህ ፊትህ ተገኝተው ሊከሱኝ ይገባ ነበር።+ +20 ወይም እዚህ ያሉት ሰዎች በሳንሄድሪን ሸንጎ ፊት በቀረብኩበት ጊዜ ያገኙብኝ ጥፋት ካለ እነሱ ራሳቸው ይናገሩ፤ +21 በመካከላቸው ቆሜ በነበረበት ጊዜ ድምፄን ከፍ አድርጌ ‘ዛሬ በፊታችሁ ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ በማመኔ ነው!’ ብዬ ከመናገር በቀር ያደረግኩት ነገር የለም።”+ +22 ይሁን እንጂ ፊሊክስ ስለ ጌታ መንገድ+ በሚገባ ያውቅ ስለነበረ “የሠራዊቱ ሻለቃ ሉስዮስ ሲመጣ ለጉዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” በማለት ያቀረቡትን ክስ ለሌላ ጊዜ አስተላለፈው። +23 ከዚያም ጳውሎስ በቁጥጥር ሥር እንዲቆይ፣ ይሁንና መጠነኛ ነፃነት እንዲሰጠው መኮንኑን አዘዘው፤ ደግሞም ወዳጆቹ የሚያስፈልገውን ነገር ለማድረግ ሲመጡ እንዲፈቅድላቸው መመሪያ ሰጠው። +24 ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ፊሊክስ አይሁዳዊት ከሆነችው ሚስቱ ከድሩሲላ ጋር መጣ፤ ጳውሎስንም አስጠርቶ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ማመን ሲናገር አዳመጠው።+ +25 ጳውሎስ ስለ ጽድቅ፣ ራስን ስለ መግዛትና ስለሚመጣው ፍርድ+ ሲናገር ግን ፊሊክስ ፈርቶ “ለአሁኑ ይበቃል፤ አጋጣሚ ሳገኝ ግን እንደገና አስጠራሃለሁ” አለው። +26 በዚሁ አጋጣሚ ጳውሎስ ጉቦ ይሰጠኛል ብሎ ተስፋ ያደርግ ስለነበር ብዙ ጊዜ እያስጠራ ያነጋግረው ነበር። +27 ይሁንና ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፊሊክስ በጶርቅዮስ ፊስጦስ ተተካ፤ በዚህ ጊዜ ፊሊክስ በአይሁዳውያን ዘንድ ተወዳጅነት ማትረፍ ስለፈለገ+ ጳውሎስን እንደታሰረ ተወው። +7 ሊቀ ካህናቱም “ይህ የተባለው ነገር ልክ ነው?” አለው። +2 እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ ስሙ። አባታችን አብርሃም በካራን መኖር ከመጀመሩ በፊት በሜሶጶጣሚያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለት፤+ +3 እንዲህም አለው፦ ‘ከአገርህ ወጥተህ፣ ከዘመዶችህም ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።’+ +4 እሱም ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን መኖር ጀመረ። አባቱ ከሞተ+ በኋላ ደግሞ አምላክ ከዚያ ተነስቶ አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት ወደዚህ ምድር እንዲዛወር አደረገው።+ +5 ሆኖም በወቅቱ በዚህ ምድር ምንም ርስት፣ ሌላው ቀርቶ እግሩን ሊያሳርፍ የሚችልበት መሬት እንኳ አልሰጠውም፤ ይሁንና ገና ልጅ ሳይኖረው ለእሱም ሆነ ከእሱ በኋላ ለዘሮቹ ምድሪቱን ርስት አድርጎ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባለት።+ +6 ከዚህም በላይ አምላክ፣ ዘሮቹ በሰው አገር ባዕዳን ሆነው እንደሚኖሩ እንዲሁም የአገሩ ሰዎች ለ400 ዓመት በባርነት እንደሚገዟቸውና እንደሚያጎሳቁሏቸው* ነገረው።+ +7 ደግሞም አምላክ ‘በባርነት የሚገዛቸውን ብሔር እፈርድበታለሁ፤+ ከዚያም በኋላ ከነበሩበት አገር ወጥተው በዚህ ስፍራ ቅዱስ አገልግሎት ያቀርቡልኛል’ ሲል ተናግሯል።+ +8 “በተጨማሪም አምላክ ከእሱ ጋር የግርዘት ቃል ኪዳን አደረገ፤+ አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ፤+ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው።+ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤* ያዕቆብም 12ቱን የቤተሰብ ራሶች* ወለደ። +9 የቤተሰብ ራሶቹም በዮሴፍ ቀንተው+ ወደ ግብፅ ሸጡት።+ ሆኖም አምላክ ከእሱ ጋር ነበር፤+ +10 ከመከራውም ሁሉ ታደገው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስና ጥበብ አጎናጸፈው። ፈርዖንም በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ገዢ አድርጎ ሾመው።+ +11 ይሁንና በግብፅና በከነአን አገር ሁሉ ታላቅ መከራ ያስከተለ ረሃብ ተከሰተ፤ አባቶቻችንም የሚበሉት ነገር አጡ።+ +12 ሆኖም ያዕቆብ በግብፅ እህል መኖሩን ሲሰማ አባቶቻችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደዚያ ላካቸው።+ +13 ለሁለተኛ ጊዜ ሲሄዱ ዮሴፍ ማንነቱን ለወንድሞቹ ነገራቸው፤ ፈርዖንም ስለ ዮሴፍ ቤተሰብ ሰማ።+ +14 ስለዚህ ዮሴፍ መልእክት ልኮ አባቱን ያዕቆብንና ዘመዶቹን ሁሉ ከዚያ አገር አስጠራ፤+ እነሱም በአጠቃላይ 75 ሰዎች* ነበሩ።+ +15 ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ፤+ በዚያም ሞተ፤+ አባቶቻችንም በዚያ ሞቱ።+ +16 አፅማቸውም ወደ ሴኬም ተወስዶ አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በብር ገንዘብ* በገዛው መቃብር ውስጥ ተቀበረ።+ +17 “አምላክ ለአብርሃም የተናገረው የተስፋ ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ ሲቃረብ ሕዝባችን በግብፅ እየበዛና እየተበራከተ ሄደ፤ +18 ይህም የሆነው ዮሴፍን የማያውቅ ሌላ ንጉሥ በግብፅ እስከተነሳበት ጊዜ ድረስ ነው።+ +19 ይህ ንጉሥ በወገኖቻችን ላይ ተንኮል በመሸረብ ሕፃናት ልጆቻቸውን ለሞት አሳልፈው እንዲሰጡ አባቶቻችንን አስገደዳቸው።+ +20 በዚህ ወቅት በአምላክ ፊት እንኳ ሳይቀር እጅግ ውብ የነበረው ሙሴ ተወለደ። በአባቱም ቤት ሦስት ወር በእንክብካቤ ኖረ።*+ +21 በተጣለ ጊዜ+ ግን የፈርዖን ልጅ ወስዳ እንደ ራሷ ልጅ አድርጋ አሳደገችው።+ +22 ሙሴም የግብፃውያንን ጥበብ ሁሉ ተማረ። በንግግሩና በተግባሩም ብርቱ ሆነ።+ +23 “ሙሴ 40 ዓመት በሞላው ጊዜ ወንድሞቹ የሆኑት የእስራኤል ልጆች ያሉበትን ሁኔታ ለማየት* በልቡ አሰበ።*+ +24 እሱም አንድ ግብፃዊ በአንድ እስራኤላዊ ላይ በደል ሲፈጽም አየ፤ ለእስራኤላዊውም አግዞ ግብፃዊውን በመግደል ተበቀለለት። +25 ወንድሞቹ አምላክ በእሱ አማካኝነት እንደሚያድናቸው የሚያስተውሉ መስሎት ነበር፤ እነሱ ግን ይህን አላስተዋሉም። +26 በማግስቱም እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኛቸው፤ እሱም ‘ሰዎች፣ እናንተ እኮ ወንድማማቾች ናችሁ። ለምን እርስ በርሳችሁ ትጣላላችሁ?’ በማለት ሊያስታርቃቸው ሞከረ። +27 ይሁንና በባልንጀራው ላይ ጥቃት እየፈጸመ የነበረው ሰው ገፈተረውና እንዲህ አለው፦ ‘አንተን በእኛ ላይ ማን ገዢና ፈራጅ አደረገህ? +28 ትናንት ግብፃዊውን እንደገደልከው እኔንም ልትገድለኝ ትፈልጋለህ እንዴ?’ +29 ሙሴ ይህን ሲሰማ ሸሽቶ በምድያም አገር ባዕድ ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ።+ +30 “ከ40 ዓመትም በኋላ በሲና ተራራ አቅራቢያ በሚገኝ ምድረ በዳ፣ በሚነድ ቁጥቋጦ ነበልባል ውስጥ አንድ መልአክ ተገለጠለት።+ +31 ሙሴም ባየው ነገር ተደነቀ። ሆኖም ሁኔታውን ለማጣራት ወደዚያ ሲቀርብ የይሖዋ* ድምፅ እ���ዲህ ሲል ሰማ፦ +32 ‘እኔ የአባቶችህ አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ።’+ በዚህ ጊዜ ሙሴ ይንቀጠቀጥ ጀመር፤ ሁኔታውን ይበልጥ ለማጣራትም አልደፈረም። +33 ይሖዋም* እንዲህ አለው፦ ‘የቆምክበት ስፍራ ቅዱስ መሬት ስለሆነ ጫማህን አውልቅ። +34 በግብፅ ባለው ሕዝቤ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና በእርግጥ አይቻለሁ፤ የጭንቅ ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤+ ልታደጋቸውም ወርጃለሁ። አሁንም ና፣ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ።’ +35 ‘አንተን ማን ገዢና ፈራጅ አደረገህ?’ ብለው የተቃወሙትን ይህንኑ ሙሴን+ አምላክ በቁጥቋጦው ውስጥ በተገለጠለት መልአክ አማካኝነት ገዢና ነፃ አውጪ አድርጎ ላከው።+ +36 ይህ ሰው በግብፅ፣ በቀይ ባሕርና+ በምድረ በዳ ለ40 ዓመት+ ድንቅ ነገሮችንና ተአምራዊ ምልክቶችን በመፈጸም+ ከግብፅ እየመራ አወጣቸው።+ +37 “‘አምላክ ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል’ ብሎ ለእስራኤል ልጆች የተናገረው ይኸው ሙሴ ነው።+ +38 በሲና ተራራ ካነጋገረው መልአክና+ ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ በጉባኤው መካከል የነበረው እሱ ነው፤+ ደግሞም ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ሕያው የሆነውን ቅዱስ ቃል ተቀበለ።+ +39 አባቶቻችን ለእሱ ለመታዘዝ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ከዚህ ይልቅ እሱን በመቃወም በልባቸው ወደ ግብፅ ተመለሱ፤+ +40 አሮንንም ‘ፊት ፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን። ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት አናውቅምና’ አሉት።+ +41 ስለሆነም በዚያን ጊዜ ጥጃ ሠርተው ለጣዖቱ መሥዋዕት አቀረቡ፤ በእጃቸውም ሥራ ይደሰቱ ጀመር።+ +42 በዚህ ጊዜ አምላክ ፊቱን ከእነሱ አዞረ፤ በነቢያትም መጻሕፍት እንዲህ ተብሎ በተጻፈው መሠረት የሰማይ ሠራዊትን እንዲያመልኩ ተዋቸው፦+ ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ መባና መሥዋዕት ያቀረባችሁት ለእኔ ነበር? +43 ይልቁንም ልታመልኳቸው የሠራችኋቸውን ምስሎች ይኸውም የሞሎክን+ ድንኳንና ሮምፋ የሚባለውን አምላክ ኮከብ ተሸክማችሁ ተጓዛችሁ። ስለዚህ ከባቢሎን ወዲያ እንድትሰደዱ አደርጋችኋለሁ።’+ +44 “አባቶቻችን በምድረ በዳ የምሥክሩ ድንኳን ነበራቸው፤ ይህ ድንኳን የተሠራው አምላክ ሙሴን ባነጋገረው ወቅት በሰጠው ትእዛዝና ባሳየው ንድፍ መሠረት ነበር።+ +45 አባቶቻችንም ይህን ድንኳን በመረከብ ከኢያሱ ጋር ሆነው አምላክ ከአባቶቻችን ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይኖሩበት ወደነበረው ምድር+ ይዘውት ገቡ።+ እስከ ዳዊት ዘመን ድረስም በዚህ ምድር ቆየ። +46 ዳዊትም በአምላክ ፊት ሞገስ አገኘ፤ ለያዕቆብ አምላክም መኖሪያ ስፍራ የማዘጋጀት መብት እንዲሰጠው ጠየቀ።+ +47 ይሁን እንጂ ቤት የሠራለት ሰለሞን ነበር።+ +48 ሆኖም ልዑሉ አምላክ የሰው እጅ በሠራው ቤት አይኖርም፤+ ይህም ነቢዩ እንዲህ ሲል በተናገረው መሠረት ነው፦ +49 ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤+ ምድር ደግሞ የእግሬ ማሳረፊያ ናት።+ ለእኔ የምትሠሩልኝ ምን ዓይነት ቤት ነው? ይላል ይሖዋ።* ወይስ የማርፍበት ቦታ የት ነው? +50 እነዚህን ነገሮች ሁሉ የሠራው እጄ አይደለም?’+ +51 “እናንተ ግትሮች፣ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ፣ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን እንደተቃወማችሁ ነው፤ አባቶቻችሁ እንዳደረጉት እናንተም እንዲሁ ታደርጋላችሁ።+ +52 ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ስደት ያላደረሱበት ማን አለ?+ አዎ፣ እነሱ የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገድለዋቸዋል፤+ እናንተም አሁን ይህን ጻድቁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ደግሞም ገደላችሁት፤+ +53 በመላእክት አማካኝነት የተላለፈውን ሕግ ተቀበላችሁ፤+ ነገር ግን አልጠበቃችሁትም።” +54 እነሱም ይህን ሲሰሙ ልባቸው በንዴት በገነ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጩበት ጀመር። +55 እሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ትኩር ብሎ ወደ ሰማይ ሲመለከት የአምላክን ክብር እንዲሁም ኢየሱስ በአምላክ ቀኝ ቆሞ አየ፤+ +56 ከዚያም “እነሆ፣ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም+ በአምላክ ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ።+ +57 በዚህ ጊዜ በኃይል እየጮኹ ጆሯቸውን በእጃቸው ደፍነው በአንድነት ወደ እሱ ሮጡ። +58 ይዘውት ከከተማው ውጭ ካስወጡት በኋላ በድንጋይ ይወግሩት ጀመር።+ ምሥክሮቹም+ መደረቢያቸውን ሳኦል በተባለ ወጣት እግር አጠገብ አስቀመጡ።+ +59 እስጢፋኖስም እየወገሩት ሳለ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ መንፈሴን ተቀበል” ብሎ ተማጸነ። +60 ከዚያም ተንበርክኮ በታላቅ ድምፅ “ይሖዋ* ሆይ፣ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው” ብሎ ጮኸ።+ ይህን ከተናገረም በኋላ በሞት አንቀላፋ። +12 በዚያን ጊዜ ንጉሡ ሄሮድስ በአንዳንድ የጉባኤው አባላት ላይ ስደት ማድረስ ጀመረ።+ +2 የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን+ በሰይፍ ገደለው።+ +3 ይህ ድርጊቱ አይሁዳውያንን እንዳስደሰተ ባየ ጊዜ ጴጥሮስን ደግሞ በቁጥጥር ሥር አዋለው። (ይህም የሆነው በቂጣ* በዓል ሰሞን ነበር።)+ +4 ከያዘውና እስር ቤት ካስገባው+ በኋላ በአራት ፈረቃ፣ አራት አራት ሆነው እንዲጠብቁት ለተመደቡ ወታደሮች አስረከበው፤ ይህን ያደረገው ከፋሲካ* በኋላ ሕዝቡ ፊት ሊያቀርበው* አስቦ ነው። +5 ስለዚህ ጴጥሮስ እስር ቤት እንዲቆይ ተደረገ፤ ሆኖም ጉባኤው ስለ እሱ ወደ አምላክ አጥብቆ ይጸልይ ነበር።+ +6 ሄሮድስ ጴጥሮስን ሕዝቡ ፊት ሊያቀርበው ካሰበበት ቀን በፊት በነበረው ሌሊት፣ ጴጥሮስ በሁለት ወታደሮች መካከል በሁለት ሰንሰለቶች ታስሮ ተኝቶ ነበር፤ በር ላይ ያሉ ጠባቂዎችም እስር ቤቱን እየጠበቁ ነበር። +7 ይሁንና የይሖዋ* መልአክ ድንገት መጥቶ ቆመ፤+ በክፍሉም ውስጥ ብርሃን በራ። ጴጥሮስን ጎኑን መታ አድርጎ ከእንቅልፉ ቀሰቀሰውና “ቶሎ ብለህ ተነሳ!” አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጆቹ ላይ ወደቁ።+ +8 መልአኩም “በል ልብስህን ልበስ፤* ጫማህንም አድርግ” አለው። እሱም እንደተባለው አደረገ። ከዚያም “መደረቢያህን ልበስና ተከተለኝ” አለው። +9 እሱም ወጥቶ ይከተለው ጀመር፤ ይሁንና መልአኩ እያደረገ ያለው ነገር በእውን እየተከናወነ ያለ አልመሰለውም። እንዲያውም ራእይ የሚያይ መስሎት ነበር። +10 የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ አልፈው ከእስር ቤቱ ወደ ከተማዋ ወደሚያስወጣው የብረት መዝጊያ ደረሱ፤ መዝጊያውም በራሱ ተከፈተላቸው። ከወጡ በኋላ በአንድ ጎዳና አብረው ተጓዙ፤ ወዲያውም መልአኩ ተለይቶት ሄደ። +11 ጴጥሮስም የሆነውን ነገር ሲረዳ “ይሖዋ* መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና አይሁዳውያን በእኔ ላይ ይደርሳል ብለው ካሰቡት ነገር ሁሉ እንደታደገኝ አሁን በእርግጥ አወቅኩ” አለ።+ +12 ይህን ከተገነዘበ በኋላ ማርቆስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ዮሐንስ+ እናት ወደ ማርያም ቤት ሄደ፤ በዚያም በርከት ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ይጸልዩ ነበር። +13 የውጭውን በር ሲያንኳኳ ሮዳ የተባለች አንዲት አገልጋይ በሩን ለመክፈት መጣች። +14 የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑን ባወቀች ጊዜ በጣም ከመደሰቷ የተነሳ በሩን ሳትከፍት ሮጣ ወደ ውስጥ በመግባት ጴጥሮስ በር ላይ መቆሙን ተናገረች። +15 እነሱም “አብደሻል እንዴ!” አሏት። እሷ ግን ያንኑ አስረግጣ መናገሯን ቀጠለች። እነሱም “ከሆነም የእሱ መልአክ ይሆናል” አሉ። +16 ጴጥሮስ ግን እዚያው ቆሞ ማንኳኳቱን ቀጠለ። በሩን ከከፈቱም በኋላ ሲያዩት በጣም ተገረሙ። +17 እሱ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ምልክት ከሰጣቸው በኋላ ይሖዋ* ከእስር ቤት እንዴት እንዳወጣው በዝርዝር ነገራቸው፤ ከዚያም “ይህን ነገር ለያዕቆብና+ ለወንድሞች ንገሯቸው” አላቸው። ይህን ካለም በኋላ ወጥቶ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ። +18 በነጋም ጊዜ ወታደሮቹ ጴጥሮስ የት እንደደረሰ ግራ ስለተጋቡ በመካከላቸው ከፍተኛ ትርምስ ተፈጠረ። +19 ሄሮድስም ፈልጎ አፈላልጎ ባጣው ጊዜ ጠባቂዎቹን ከመረመረ በኋላ እርምጃ እንዲወሰድባቸው አዘዘ፤+ ከዚያም ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ወርዶ በዚያ የተወሰነ ጊዜ ተቀመጠ። +20 ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ በጣም ተቆጥቶ* ነበር። እነሱም በአንድ ልብ ሆነው ወደ እሱ በመምጣት የንጉሡ ባለሟል* የሆነውን ብላስጦስን ካግባቡ በኋላ ንጉሡን እርቅ ጠየቁ፤ ይህን ያደረጉት አገራቸው ምግብ የምታገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለነበረ ነው። +21 አንድ ልዩ ዝግጅት በተደረገበት ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ፤ ከዚያም ለሕዝቡ ንግግር መስጠት ጀመረ። +22 የተሰበሰበውም ሕዝብ “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ የሰው አይደለም!” እያለ ይጮኽ ጀመር። +23 በዚህ ጊዜ፣ ለአምላክ ክብር ባለመስጠቱ ወዲያውኑ የይሖዋ* መልአክ ቀሰፈው፤ በትል ተበልቶም ሞተ። +24 የይሖዋ* ቃል ግን እየተስፋፋ ሄደ፤ ብዙ ሰዎችም አማኞች ሆኑ።+ +25 በርናባስና+ ሳኦልም በኢየሩሳሌም እርዳታ ከሰጡ በኋላ ተመለሱ፤+ ማርቆስ ተብሎ የሚጠራውን ዮሐንስንም ይዘውት መጡ።+ +1 ቴዎፍሎስ ሆይ፣ ኢየሱስ ስላደረገውና ስላስተማረው ነገር ሁሉ በመጀመሪያው መጽሐፍ ላይ ጽፌልሃለሁ፤+ +2 ታሪኩም አምላክ እስከወሰደው ቀን ድረስ ያለውን ያካትታል።+ ለመረጣቸው ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት መመሪያዎች ከሰጣቸው በኋላ አረገ።+ +3 መከራ ከተቀበለ በኋላ ሕያው መሆኑን በብዙ አሳማኝ ማስረጃዎች አሳያቸው።+ እነሱም ለ40 ቀናት ያዩት ሲሆን እሱም ስለ አምላክ መንግሥት ይነግራቸው ነበር።+ +4 ከእነሱ ጋር ተሰብስቦ ሳለ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ከኢየሩሳሌም አትውጡ፤+ ከዚህ ይልቅ አብ ቃል የገባውንና እኔም ስለዚሁ ጉዳይ ስናገር የሰማችሁትን ቃል ፍጻሜ ተጠባበቁ፤+ +5 ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፤ እናንተ ግን ከጥቂት ቀናት በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ።”+ +6 እንደገና ተሰብስበው ሳሉ “ጌታ ሆይ፣ ለእስራኤል መንግሥትን መልሰህ የምታቋቁመው በዚህ ጊዜ ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+ +7 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጊዜያትንና ወቅቶችን የመወሰን ሥልጣን ያለው አብ ብቻ ስለሆነ* እናንተ ይህን ማወቅ አያስፈልጋችሁም።+ +8 ሆኖም መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኃይል ትቀበላላችሁ፤+ በኢየሩሳሌም፣+ በመላው ይሁዳና በሰማርያ+ እንዲሁም እስከ ምድር ዳር ድረስ+ ምሥክሮቼ ትሆናላችሁ።”+ +9 ይህን ከተናገረ በኋላም እያዩት ወደ ላይ ወጣ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰወረው።+ +10 እሱ ወደ ላይ እየወጣ ሳለ ትኩር ብለው ወደ ሰማይ ሲመለከቱ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች+ ድንገት አጠገባቸው ቆሙ፤ +11 እንዲህም አሏቸው፦ “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የተወሰደው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመጣል።” +12 ከዚያም ደብረ ዘይት ከተባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤+ ይህ ተራራ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን ርቀቱ የሰንበት መንገድ* ያህል ብቻ ነበር። +13 እዚያ በደረሱ ጊዜ ያርፉበት ወደነበረው ደርብ ወጡ። እነሱም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብና እንድርያስ፣ ፊልጶስና ቶማስ፣ በርቶሎሜዎስና ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ቀናተኛው ስምዖን እንዲሁም የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ነበሩ።+ +14 እነዚህ ሁሉ ከአንዳንድ ሴቶችና+ ከኢየሱስ እናት ከማርያም እንዲሁም ከወንድሞቹ+ ጋር በአንድ ልብ ተግተው ይጸልዩ ነበር። +15 በዚያው ሰሞን 120 የሚያህሉ ሰዎች አንድ ላይ ተሰብስበው ሳለ ጴጥሮስ በወንድሞች መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፦ +16 “ወንድሞች፣ ኢየሱስን የያዙትን ሰዎች እየመራ ስላመጣው ስለ ይሁዳ+ መንፈስ ቅዱስ በዳዊት በኩል በትንቢት የተናገረው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል መፈጸሙ የግድ ነበር።+ +17 ምክንያቱም እሱ ከእኛ እንደ አንዱ ተቆጥሮ የነበረ+ ከመሆኑም በላይ በዚህ አገልግሎት የመካፈል አጋጣሚ አግኝቶ ነበር። +18 (ይኸው ሰው ለዓመፅ ሥራው በተከፈለው ደሞዝ+ መሬት ገዛ፤ በአናቱም ወድቆ ሰውነቱ ፈነዳ፤* ሆድ ዕቃውም ተዘረገፈ።+ +19 ይህም በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ በመሆኑም መሬቱ በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፤ ትርጉሙም “የደም መሬት” ማለት ነው።) +20 በመዝሙር መጽሐፍ ላይ ‘መኖሪያው ወና ይሁን፤ በውስጡም ማንም ሰው አይኑርበት’+ እንዲሁም ‘የበላይ ተመልካችነት ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው’ ተብሎ ተጽፏልና።+ +21 ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል ሆኖ ሥራውን ያከናውን በነበረበት* ጊዜ ሁሉ ከእኛ ጋር ከነበሩት ወንዶች መካከል በአንዱ እሱን መተካት ያስፈልጋል፤ +22 የሚተካው ሰው ኢየሱስ በዮሐንስ ከተጠመቀበት ጊዜ አንስቶ+ ከእኛ እስከተወሰደበት ጊዜ+ ድረስ አብሮን የነበረ መሆን ይኖርበታል። በተጨማሪም ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምሥክር መሆን ያስፈልገዋል።”+ +23 ስለዚህ ሁለት ሰዎችን ዕጩ አድርገው አቀረቡ፤ እነሱም በርስያን ተብሎ የሚጠራው ዮሴፍ (ኢዮስጦስ ተብሎም ይጠራል) እና ማትያስ ነበሩ። +24 ከዚያም እንዲህ ብለው ጸለዩ፦ “የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቀው ይሖዋ* ሆይ፣+ ከእነዚህ ሁለት ሰዎች መካከል የመረጥከውን አመልክተን፤ +25 ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ለመሄድ ሲል የተወውን ይህን የአገልግሎትና የሐዋርያነት ቦታ የሚወስደውን ሰው ግለጥልን።”+ +26 ከዚያም በሁለቱ ሰዎች ላይ ዕጣ ጣሉ፤+ ዕጣውም ለማትያስ ወጣና ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቆጠረ።* +28 እኛም በደህና ወደ የብስ ደረስን፤ ደሴቲቱም ማልታ ተብላ እንደምትጠራ አወቅን።+ +2 የአካባቢው ነዋሪዎችም* የተለየ ደግነት* አሳዩን። ዝናብ መዝነብ ጀምሮ ስለነበረና ብርድ ስለነበር እሳት በማቀጣጠል ሁላችንንም በደግነት አስተናገዱን። +3 ይሁን እንጂ ጳውሎስ ጭራሮ ሰብስቦ እሳቱ ውስጥ ሲጨምር ከሙቀቱ የተነሳ እፉኝት ወጥታ እጁ ላይ ተጣበቀች። +4 ባዕድ ቋንቋ የሚናገሩትም ሰዎች እፉኝቷ እጁ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ መሆን አለበት፤ ከባሕሩ ተርፎ በደህና ቢወጣም እንኳ ፍትሕ* በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ይባባሉ ጀመር። +5 እሱ ግን እፉኝቷን እሳቱ ላይ አራገፋት፤ አንዳችም ጉዳት አልደረሰበትም። +6 ሆኖም ሰዎቹ ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል ወይም ድንገት ወድቆ ይሞታል ብለው ይጠባበቁ ነበር። ብዙ ጠብቀው ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ይህ ሰው አምላክ ነው ይሉ ጀመር። +7 በዚያ አካባቢ፣ ፑፕልዮስ የተባለ የደሴቲቱ አስተዳዳሪ ርስት ነበረው፤ እሱም በእንግድነት ተቀብሎን ሦስት ቀን በደግነት አስተናገደን። +8 የፑፕልዮስ አባት ትኩሳትና ተቅማጥ ይዞት ተኝቶ ነበር፤ ጳውሎስም ወደ እሱ ገብቶ ጸለየለት፤ እጁንም ጫነበትና ፈወሰው።+ +9 ይህ ከሆነ በኋላ በደሴቲቱ የሚኖሩ የታመሙ ሌሎች ሰዎችም ወደ እሱ እየመጡ ይፈወሱ ጀመር።+ +10 በተጨማሪም ብዙ ስጦታ በመስጠት አክብሮታቸውን ገለጹልን፤ በመርከብ ለመሄድ በተዘጋጀን ጊዜም የሚያስፈልጉንን ነገሮች ሁሉ ጫኑልን። +11 ከሦስት ወር በኋላም “የዙስ ልጆች” የሚል ዓርማ ባለው መርከብ ጉዞ ጀመርን። ይህ መርከብ ከእስክንድርያ የመጣ ሲሆን ክረምቱን ያሳለፈው በዚህች ደሴት ነበር። +12 በስራኩስ ወደሚገኘው ወደብ ከደረስን በኋላ በዚያ ሦስት ቀን ቆየን፤ +13 ከዚያም ተነስተን በመጓዝ ሬጊዩም ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላም የደቡብ ነፋስ ስለተነሳ በሁለተኛው ቀን ፑቲዮሉስ ደረስን። +14 በዚያም ወንድሞችን አገኘን፤ እነሱም ሰባት ቀን አብረናቸው እንድንቆይ ለመኑን፤ እነሱ ጋር ከቆየን በኋላ ወደ ሮም አመራን። +15 በዚያ የነበሩ ወንድሞች ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ እስከ አፍዩስ የገበያ ስፍራና ሦስት ማደሪያ* እስከሚባለው ቦታ ድረስ ሊቀበሉን መጡ። ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ አምላክን አመሰገነ፤ እንዲሁም ተበረታታ።+ +16 በመጨረሻም ሮም በደረስን ጊዜ ጳውሎስ አንድ ወታደር እየጠበቀው ብቻውን እንዲኖር ተፈቀደለት። +17 ይሁን እንጂ ከሦስት ቀን በኋላ የአይሁዳውያንን ታላላቅ ሰዎች አንድ ላይ ጠራ። ሰዎቹም በተሰበሰቡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች፣ ምንም እንኳ ሕዝቡን ወይም የአባቶቻችንን ልማድ የሚጻረር ነገር ያልፈጸምኩ+ ቢሆንም በኢየሩሳሌም አስረው ለሮማውያን አሳልፈው ሰጥተውኛል።+ +18 እነሱም ከመረመሩኝ+ በኋላ ለሞት የሚያበቃ ምንም ጥፋት ስላላገኙብኝ ሊፈቱኝ ፈልገው ነበር።+ +19 ሆኖም አይሁዳውያን ይህን በተቃወሙ ጊዜ ለቄሳር ይግባኝ ለማለት ተገደድኩ፤+ ይህን ያደረግኩት ግን ሕዝቤን የምከስበት ነገር ኖሮኝ አይደለም። +20 እናንተንም ለማየትና ለማነጋገር ጥያቄ ያቀረብኩት ለዚህ ነው፤ በዚህ ሰንሰለት የታሰርኩትም ለእስራኤል በተሰጠው ተስፋ ምክንያት ነው።”+ +21 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ስለ አንተ የተጻፈ ከይሁዳ የመጣ ምንም ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ከዚያ ከመጡት ወንድሞች መካከልም ስለ አንተ ክፉ ነገር የተናገረ ወይም ያወራ አንድም ሰው የለም። +22 ሆኖም ስለዚህ ኑፋቄ+ በየቦታው መጥፎ ነገር እንደሚወራ ስለምናውቅ+ የአንተን ሐሳብ ደግሞ መስማት ተገቢ ይመስለናል።” +23 በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ከእሱ ጋር ቀን ከወሰኑ በኋላ ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያ ስፍራው መጡ። እሱም በኢየሱስ እንዲያምኑ ለማድረግ+ ከሙሴ ሕግና+ ከነቢያት+ እየጠቀሰ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ* በመመሥከር ጉዳዩን አብራራላቸው። +24 አንዳንዶቹ የተናገረውን ነገር ሲያምኑ ሌሎቹ ግን አላመኑም። +25 እርስ በርስ ሊስማሙ ስላልቻሉም ለመሄድ ተነሱ፤ በዚህ ጊዜ ጳውሎስ የሚከተለውን የመጨረሻ ሐሳብ ተናገረ፦ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ለአባቶቻችሁ እንዲህ ሲል የተናገረው ቃል ትክክል ነበር፦ +26 ‘ወደዚህ ሕዝብ ሄደህ እንዲህ በላቸው፦ “መስማቱን ትሰማላችሁ፤ ግን በፍጹም አታስተውሉም፤ ማየቱን ታያላችሁ፤ ግን በፍጹም ልብ አትሉም።+ +27 ምክንያቱም በዓይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው እንዲሁም በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ እንዳይመለሱና እንዳልፈውሳቸው የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗል፤ በጆሯቸው ሰምተው ምላሽ አልሰጡም፤ ዓይናቸውንም ጨፍነዋል።”’+ +28 ስለዚህ አምላክ ሰዎችን ስለሚያድንበት መንገድ የሚናገረው ይህ መልእክት ለአሕዛብ እንደተላከ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤+ እነሱም በእርግጥ ይሰሙታል።”+ +29 *—— +30 ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ኖረ፤+ ወደ እሱ የሚመጡትንም ሁሉ በደግነት ያስተናግዳቸው ነበር፤ +31 ያለምንም እንቅፋት በታላቅ የመናገር ነፃነት* ስለ አምላክ መንግሥት ይሰብክላቸው የነበረ ከመሆኑም በላይ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምራቸው ነበር።+ +8 ሳኦልም በእሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።+ በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም በሚገኘው ጉባኤ ላይ ከባድ ስደት ተነሳ፤ ከሐዋርያት በስተቀር ደቀ መዛሙርቱ በሙሉ በይሁዳና በሰማርያ ክልሎች ሁሉ ተበተኑ።+ +2 ሆኖም ለአምላክ ያደሩ ሰዎች እስጢፋኖስን ወስደው ቀበሩት፤ ታላቅ ለቅሶም አለቀሱለት��� +3 ሳኦልም በጉባኤው ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረስ ጀመረ። በየቤቱ እየገባ ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን ጎትቶ በማውጣት ወህኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።+ +4 ይሁን እንጂ የተበተኑት ደቀ መዛሙርት በሄዱበት ቦታ ሁሉ የአምላክን ቃል ምሥራች ሰበኩ።+ +5 በዚህ ጊዜ ፊልጶስ ወደ ሰማርያ+ ከተማ* ሄዶ ስለ ክርስቶስ ይሰብክላቸው ጀመር። +6 ሕዝቡ ፊልጶስ የሚናገረውን ሲሰሙና የፈጸማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች ሲመለከቱ ሁሉም በአንድ ልብ በትኩረት ይከታተሉት ጀመር። +7 ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸው ብዙ ሰዎችም ነበሩ፤ ርኩሳን መናፍስቱም በከፍተኛ ድምፅ እየጮኹ ይወጡ ነበር።+ በተጨማሪም ሽባና አንካሳ የነበሩ በርካታ ሰዎች ተፈወሱ። +8 ከዚህም የተነሳ በዚያች ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። +9 በዚያች ከተማ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ከዚህ ቀደም አስማት እየሠራ የሰማርያን ሕዝብ ያስደምም የነበረ ሲሆን ታላቅ ሰው እንደሆነ አድርጎም ይናገር ነበር። +10 ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ፣ ሰዎች ሁሉ “ይህ ሰው ታላቅ ተብሎ የሚጠራ ‘የአምላክ ኃይል’ ነው” በማለት ትልቅ ቦታ ይሰጡት ነበር። +11 ረዘም ላለ ጊዜ በአስማት ሥራው ሲያስደንቃቸው ስለቆየ የሚለውን ሁሉ ይቀበሉ ነበር። +12 ይሁንና ስለ አምላክ መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምሥራች እያወጀ የነበረውን ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ+ ወንዶችም ሴቶችም ይጠመቁ ጀመር።+ +13 ስምዖን ራሱም አማኝ ሆነ፤ ከተጠመቀም በኋላ ከፊልጶስ+ አይለይም ነበር፤ ምልክቶችና ታላላቅ ተአምራት ሲፈጸሙ በማየት ይደነቅ ነበር። +14 በኢየሩሳሌም ያሉ ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የአምላክን ቃል እንደተቀበሉ ሲሰሙ+ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኩላቸው፤ +15 እነሱም ወደዚያ ወርደው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጸለዩላቸው።+ +16 ምክንያቱም በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ እንጂ መንፈስ ቅዱስ ገና በአንዳቸውም ላይ አልወረደም ነበር።+ +17 ከዚያም ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፤+ እነሱም መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። +18 ስምዖንም ሐዋርያት እጃቸውን የጫኑበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስ እንደሚቀበል አይቶ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ቃል በመግባት +19 “እጄን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበል ይህን ሥልጣን ለእኔም ስጡኝ” አላቸው። +20 ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ “የአምላክን ነፃ ስጦታ በገንዘብ ማግኘት እንደምትችል ስላሰብክ የብር ገንዘብህ ከአንተ ጋር ይጥፋ።+ +21 ልብህ በአምላክ ፊት ቀና ስላልሆነ በዚህ አገልግሎት ምንም ዓይነት ድርሻም ሆነ ዕድል ፋንታ የለህም። +22 ስለዚህ ከዚህ ክፋትህ ንስሐ ግባ፤ ምናልባት የልብህ ክፉ ሐሳብ ይቅር ይባልልህ እንደሆነ ይሖዋን* ተማጸን፤ +23 መራራ መርዝና* የክፋት ባሪያ እንደሆንክ አያለሁና።” +24 ስምዖንም መልሶ “ከተናገራችሁት ነገር አንዱም እንዳይደርስብኝ እባካችሁ ይሖዋን* ማልዱልኝ” አላቸው። +25 ጴጥሮስና ዮሐንስ የተሟላ ምሥክርነት ከሰጡና የይሖዋን* ቃል ከተናገሩ በኋላ የሰማርያ ሰዎች በሚኖሩባቸው በርካታ መንደሮች ምሥራቹን እያወጁ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።+ +26 ይሁንና የይሖዋ* መልአክ+ ፊልጶስን “ተነስተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ሂድ” አለው። (ይህ መንገድ የበረሃ መንገድ ነው።) +27 እሱም ተነስቶ ሄደ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ* ባለሥልጣንና የገንዘቧ ሁሉ ኃላፊ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባም* አገኘ። ይህ ሰው ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤+ +28 እየተመለሰም ሳለ በሠረገላው ውስጥ ተቀምጦ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያነብ ነበር። +29 መንፈስም ፊልጶስን “ሂድና ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው። +30 ፊልጶስ ከሠረገላው ጎን እየሮጠ ጃንደረባው የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ ጮክ ብሎ ሲያነብ ሰማና “ለመሆኑ የምታነበውን ትረዳዋለህ?” አለው። +31 እሱም “የሚመራኝ ሰው ሳይኖር እንዴት ልረዳው እችላለሁ?” አለው። ፊልጶስንም ሠረገላው ላይ ወጥቶ አብሮት እንዲቀመጥ ለመነው። +32 ያነበው የነበረው የቅዱስ መጽሐፉ ክፍል የሚከተለው ነበር፦ “እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤ በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል ጠቦት እሱም አፉን አልከፈተም።+ +33 ውርደት በደረሰበት ወቅት ፍትሕ ተነፈገ።+ ስለ ትውልዱ ማን በዝርዝር ሊናገር ይችላል? ምክንያቱም ሕይወቱ ከምድር ላይ ተወግዷል።”+ +34 ጃንደረባውም ፊልጶስን “እባክህ ንገረኝ፣ ነቢዩ ይህን የተናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነው ወይስ ስለ ሌላ ሰው?” አለው። +35 ፊልጶስም መናገር ጀመረ፤ ከዚህ ቅዱስ መጽሐፍ አንስቶም ስለ ኢየሱስ የሚገልጸውን ምሥራች ነገረው። +36 እየተጓዙም ሳሉ ውኃ ወዳለበት ቦታ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “ውኃ ይኸውና፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?” አለው። +37 *—— +38 ከዚያም ሠረገላው እንዲቆም አዘዘ፤ ሁለቱም ወርደው ውኃው ውስጥ ገቡ፤ ፊልጶስም ጃንደረባውን አጠመቀው። +39 ከውኃውም በወጡ ጊዜ፣ የይሖዋ* መንፈስ ወዲያውኑ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ፊልጶስን ከዚያ በኋላ አላየውም፤ ይሁንና ደስ ብሎት ጉዞውን ቀጠለ። +40 በኋላ ግን ፊልጶስ በአሽዶድ ታየ፤ ቂሳርያም እስኪደርስ ድረስ በሚያልፍበት ክልል በሚገኙ ከተሞች ሁሉ ምሥራቹን ያውጅ ነበር።+ +11 በይሁዳ የነበሩት ሐዋርያትና ወንድሞች፣ አሕዛብም የአምላክን ቃል እንደተቀበሉ ሰሙ። +2 ስለዚህ ጴጥሮስ ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ግርዘትን የሚደግፉ ሰዎች+ ይተቹት* ጀመር፤ +3 “ወዳልተገረዙ ሰዎች ቤት ሄደህ ከእነሱ ጋር በልተሃል” አሉት። +4 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ጉዳዩን በዝርዝር አብራራላቸው፦ +5 “በኢዮጴ ከተማ እየጸለይኩ ሳለ ሰመመን ውስጥ ሆኜ ራእይ አየሁ፤ አንድ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራቱም ጫፍ ተይዞ ከሰማይ ወረደና ወደ እኔ መጣ።+ +6 ይህን ነገር ትኩር ብዬ ስመለከት አራት እግር ያላቸው የምድር እንስሳት፣ የዱር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና የሰማይ ወፎች አየሁ። +7 በተጨማሪም አንድ ድምፅ ‘ጴጥሮስ፣ ተነሳና አርደህ ብላ!’ ሲለኝ ሰማሁ። +8 እኔ ግን ‘ጌታ ሆይ፣ በጭራሽ፤ ምክንያቱም ንጹሕ ያልሆነ ወይም የረከሰ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም’ አልኩ። +9 ለሁለተኛ ጊዜ ከሰማይ የመጣው ድምፅ ‘አምላክ ንጹሕ ያደረገውን ነገር ርኩስ ነው ማለትህን ተው’ ሲል መለሰልኝ። +10 ይህም ለሦስተኛ ጊዜ ተደገመ፤ ከዚያም ሁሉም ነገር እንደገና ወደ ሰማይ ተወሰደ። +11 ልክ በዚያው ሰዓት ደግሞ ከቂሳርያ ወደ እኔ የተላኩ ሦስት ሰዎች እኛ ወደነበርንበት ቤት ደረሱ።+ +12 በዚህ ጊዜ መንፈስ፣ ምንም ሳልጠራጠር አብሬያቸው እንድሄድ ነገረኝ። እነዚህ ስድስት ወንድሞችም አብረውኝ ሄዱ፤ ወደ ሰውየውም ቤት ገባን። +13 “እሱም በቤቱ ውስጥ መልአክ ቆሞ እንዳየና እንዲህ እንዳለው ነገረን፦ ‘ወደ ኢዮጴ ሰዎች ልከህ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራውን ስምዖንን አስጠራ፤+ +14 እሱም አንተና መላው ቤተሰብህ መዳን ልታገኙ የምትችሉበትን ነገር ሁሉ ይነግርሃል።’ +15 እኔም መናገር ስጀምር መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ በእኛ ላይ እንደወረደው ሁሉ በእነሱም ላይ ወረደ።+ +16 በዚህ ጊዜ፣ ‘ዮሐንስ በውኃ አጠመቀ፤+ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ’+ እያለ ጌታ ይናገር የነበረውን ቃል አስታወስኩ። +17 እንግዲህ አምላክ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላመንነው ለእኛ የሰጠውን ያንኑ ነፃ ስጦታ ለእነሱም ከሰጠ፣ ታዲያ አምላክን መከልከል* የምችል እኔ ማን ነኝ?”+ +18 እነሱም ይህን በሰሙ ጊዜ መቃወማቸውን ተዉ፤* ደግሞም “እንዲህ ከሆነማ አምላክ አሕዛብም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ንስሐ የሚገቡበት አጋጣሚ ሰጥቷቸዋል ማለት ነው” እያሉ አምላክን አከበሩ።+ +19 ከእስጢፋኖስ ሞት በኋላ በተቀሰቀሰው ስደት የተነሳ የተበተኑት ደቀ መዛሙርት+ እስከ ፊንቄ፣ ቆጵሮስና አንጾኪያ ድረስ ሄዱ፤ ቃሉን ይናገሩ የነበረው ግን ለአይሁዳውያን ብቻ ነበር።+ +20 ይሁን እንጂ ከእነሱ መካከል የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የሆኑ አንዳንዶች ወደ አንጾኪያ መጥተው ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎችን በማነጋገር የጌታ ኢየሱስን ምሥራች ይሰብኩላቸው ጀመር። +21 የይሖዋም* እጅ ከእነሱ ጋር ነበር፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም አማኝ በመሆን ጌታን መከተል ጀመሩ።+ +22 በኢየሩሳሌም የሚገኘው ጉባኤ ስለ እነሱ የሚገልጸው ወሬ ደረሰው፤ በዚህ ጊዜ በርናባስን+ ወደ አንጾኪያ ላኩት። +23 እሱም እዚያ ደርሶ አምላክ ለደቀ መዛሙርቱ ያሳየውን ጸጋ ባስተዋለ ጊዜ በጣም ተደሰተ፤ ሁሉም በጽኑ ልብ ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲቀጥሉም አበረታታቸው፤+ +24 በርናባስ መንፈስ ቅዱስ የሞላበትና ጠንካራ እምነት ያለው ጥሩ ሰው ነበር። ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም በጌታ አመኑ።+ +25 በመሆኑም ሳኦልን ፈልጎ ለማግኘት ወደ ጠርሴስ ሄደ።+ +26 ካገኘውም በኋላ ወደ አንጾኪያ አመጣው። ከዚያም አንድ ዓመት ሙሉ ከእነሱ ጋር በጉባኤ አብረው እየተሰበሰቡ ብዙ ሕዝብ አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርቱም በመለኮታዊ አመራር ለመጀመሪያ ጊዜ ‘ክርስቲያኖች’ ተብለው የተጠሩት+ በአንጾኪያ ነበር። +27 በዚያን ጊዜ ነቢያት+ ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ። +28 ከእነሱም መካከል አጋቦስ+ የተባለው ተነስቶ በምድሪቱ ሁሉ ታላቅ ረሃብ እንደሚከሰት መንፈስ አነሳስቶት ትንቢት ተናገረ፤+ ይህም በቀላውዴዎስ ዘመን ተፈጸመ። +29 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ እያንዳንዳቸው አቅማቸው በፈቀደ መጠን+ አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩ ወንድሞች እርዳታ ለመላክ ወሰኑ፤+ +30 እርዳታውንም በበርናባስና በሳኦል እጅ ለሽማግሌዎቹ ላኩ።+ +2 በጴንጤቆስጤ* በዓል ቀን+ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ነበር። +2 ድንገትም እንደ ኃይለኛ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ ተቀምጠውበት የነበረውንም ቤት ሞላው።+ +3 የእሳት ምላሶች የሚመስሉም ታዩአቸው፤ ተከፋፍለውም በእያንዳንዳቸው ላይ አረፉ፤ +4 ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤+ መንፈስም እንዲናገሩ ባስቻላቸው መሠረት በተለያዩ ቋንቋዎች* ይናገሩ ጀመር።+ +5 በዚያን ጊዜ በምድር ዙሪያ ካለ አገር ሁሉ የመጡ ለአምላክ ያደሩ አይሁዳውያን በኢየሩሳሌም ነበሩ።+ +6 ስለዚህ ይህ ድምፅ በተሰማ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ፤ እያንዳንዱም ሰው ደቀ መዛሙርቱ በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ በመስማቱ ግራ ተጋባ። +7 ደግሞም ሕዝቡ እጅግ ተደንቀው እንዲህ አሉ፦ “እንዴ፣ እነዚህ እየተናገሩ ያሉት የገሊላ ሰዎች አይደሉም?+ +8 ታዲያ እያንዳንዳችን በአገራችን ቋንቋ* ሲናገሩ የምንሰማው እንዴት ነው? +9 እኛ ከጳርቴና፣ ከሜዶን፣+ ከኤላም፣+ ከሜሶጶጣሚያ፣ ከይሁዳ፣ ከቀጰዶቅያ፣ ከጳንጦስ፣ ከእስያ አውራጃ፣+ +10 ከፍርግያ፣ ከጵንፍልያ፣ ከግብፅ፣ በቀሬና አቅራቢያ ካሉት የሊቢያ አውራጃዎችና ከሮም የመጣን አይሁዶችና ወደ ይሁዲነት የተለወጥን ሰዎች፣+ +11 የቀርጤስና የዓረብ ሰዎች ሁላችን ስለ አምላክ ታላቅ ሥራ በየቋንቋችን ሲናገሩ እየሰማናቸው ነው።” +12 ስለዚህ ሁሉም ተገርመውና ግራ ተጋብተው እርስ በርሳቸው “ይህ ነገር ምን ይሆን?” ይባባሉ ነበር። +13 ይሁን እንጂ ሌሎች “ያልፈላ የወይን ጠጅ* ተግተው ነው” በማለት አፌዙባቸው። +14 ጴጥሮስ ግን ከአሥራ አንዱ+ ጋር ተነስቶ በመቆም ድ��ፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ ተናገረ፦ “እናንተ የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ፣ አንድ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ስላለ ንግግሬን በጥሞና አዳምጡ። +15 ጊዜው ገና ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ስለሆነ እነዚህ ሰዎች እናንተ እንዳሰባችሁት አልሰከሩም። +16 ከዚህ ይልቅ ይህ የሆነው በነቢዩ ኢዩኤል በኩል እንዲህ ተብሎ በተነገረው መሠረት ነው፦ +17 ‘አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በመጨረሻው ቀን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ ወጣቶቻችሁ ራእዮችን ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤+ +18 በዚያ ቀን በወንዶች ባሪያዎቼና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ሳይቀር ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ እነሱም ትንቢት ይናገራሉ።+ +19 በላይ በሰማይ ድንቅ ነገሮች፣ በታች በምድር ደግሞ ተአምራዊ ምልክቶች አሳያለሁ፤ ደም፣ እሳትና የጭስ ደመናም ይታያል። +20 ታላቁና ክብራማው የይሖዋ* ቀን ከመምጣቱ በፊት ፀሐይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ። +21 የይሖዋን* ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”’+ +22 “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ፦ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት፣ አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት በመካከላችሁ የፈጸማቸው ተአምራት፣ ድንቅ ነገሮችና ምልክቶች የናዝሬቱ ኢየሱስ በአምላክ የተላከ ሰው እንደሆነ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ናቸው።+ +23 ይህ ሰው ለሞት አልፎ ተሰጠ። ይህም አምላክ አስቀድሞ የወሰነው ፈቃዱና* የሚያውቀው ነገር ነበር።+ እናንተም በክፉ ሰዎች እጅ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።+ +24 አምላክ ግን ከሞት ጣር* አላቆ አስነሳው፤+ ምክንያቱም ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለም።+ +25 ዳዊትም ስለ እሱ እንዲህ ይላል፦ ‘ይሖዋን* ሁልጊዜ በፊቴ* አደርገዋለሁ፤ እሱ በቀኜ ስለሆነ ፈጽሞ አልናወጥም። +26 ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሴት አደረገ። እኔም በተስፋ እኖራለሁ፤* +27 ምክንያቱም በመቃብር* አትተወኝም፤* ታማኝ አገልጋይህም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም።+ +28 የሕይወትን መንገድ አሳውቀኸኛል፤ በፊትህ በታላቅ ደስታ እንድሞላ ታደርገኛለህ።’+ +29 “ወንድሞች፣ ከቀድሞ አባቶች አንዱ የሆነው ዳዊት እንደሞተና እንደተቀበረ+ እንዲሁም መቃብሩ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደሚገኝ ለእናንተ በግልጽ እንድናገር ፍቀዱልኝ። +30 እሱ ነቢይ ስለነበረና አምላክ ከዘሮቹ አንዱን* በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ በመሐላ ቃል እንደገባለት ስላወቀ+ +31 አምላክ ክርስቶስን በመቃብር* እንደማይተወውና ሥጋውም እንደማይበሰብስ* አስቀድሞ ተረድቶ ስለ ትንሣኤው ተናገረ።+ +32 ይህን ኢየሱስን አምላክ ከሞት አስነሳው፤ እኛ ሁላችንም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን።+ +33 ስለዚህ ወደ አምላክ ቀኝ ከፍ ከፍ ስለተደረገና+ ቃል የተገባውን ቅዱስ መንፈስ ከአብ ስለተቀበለ+ ይህን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው። +34 ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፤ ሆኖም እሱ ራሱ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ ‘ይሖዋ* ጌታዬን እንዲህ ብሎታል፦ “በቀኜ ተቀመጥ፤ +35 ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ሁን።”’+ +36 ስለዚህ ይህን እናንተ በእንጨት ላይ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን+ አምላክ ጌታም+ ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ቤት ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።” +37 ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ልባቸው እጅግ ተነክቶ ጴጥሮስንና የቀሩትን ሐዋርያት “ወንድሞች፣ ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሏቸው። +38 ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፦ “ንስሐ ግቡ፤+ እያንዳንዳችሁም ለኃጢአታችሁ ይቅርታ እንድታገኙ+ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤+ የመንፈስ ቅዱስንም ነፃ ስጦታ ትቀበላላችሁ። +39 ምክንያቱም የተስፋው ቃል+ ለእናንተና ለልጆቻችሁ እንዲሁም ይሖዋ* አምላካችን ወደ ራሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነው።”+ +40 በሌላ ብዙ ቃልም በሚገባ* መሠከረላቸው፤ “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ” እያለም አጥብቆ አሳሰባቸው።+ +"41 ስለዚህ ቃሉን በደስታ የተቀበሉ ተጠመቁ፤+ በዚያም ቀን 3,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች* ተጨመሩ።+" +42 የሐዋርያቱንም ትምህርት በትኩረት መከታተላቸውን ቀጠሉ፤ አንድ ላይ ይሰበሰቡ፣* ምግባቸውንም አብረው ይበሉ+ እንዲሁም በጸሎት ይተጉ ነበር።+ +43 ሰው ሁሉ* ፍርሃት አደረበት፤ ሐዋርያቱም ብዙ ድንቅ ነገሮችና ተአምራዊ ምልክቶች ያደርጉ ጀመር።+ +44 ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤ ያላቸውም ነገር ሁሉ የጋራ ነበር፤ +45 በተጨማሪም ያላቸውን ሀብትና ንብረት በመሸጥ+ ገንዘቡን ለሁሉም አከፋፈሉ። ለእያንዳንዱም ሰው የሚያስፈልገውን ያህል ሰጡ።+ +46 በየዕለቱም በአንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅደሱ አዘውትረው ይገኙ ነበር፤ ምግባቸውንም በተለያዩ ቤቶች ይበሉ የነበረ ሲሆን የሚመገቡትም በታላቅ ደስታና በንጹሕ ልብ ነበር፤ +47 አምላክንም ያወድሱ የነበረ ከመሆኑም በላይ በሰው ሁሉ ፊት ሞገስ አግኝተው ነበር። ይሖዋም* የሚድኑ ሰዎችን በየዕለቱ በእነሱ ላይ ይጨምር ነበር።+ +26 አግሪጳ+ ጳውሎስን “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው። በዚህ ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ እንዲህ ሲል የመከላከያ መልሱን ይሰጥ ጀመር፦ +2 “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ አይሁዳውያን በእኔ ላይ ያቀረቡትን ክስ+ ሁሉ በተመለከተ ዛሬ በአንተ ፊት የመከላከያ መልስ መስጠት በመቻሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ፤ +3 በተለይ ደግሞ አንተ የአይሁዳውያንን ልማዶችና በመካከላቸው ያሉትን ክርክሮች ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ስለዚህ በትዕግሥት እንድታዳምጠኝ እለምንሃለሁ። +4 “ገና ከልጅነቴ በሕዝቤ መካከልም ሆነ በኢየሩሳሌም እንዴት እንደኖርኩ አይሁዳውያን ሁሉ በሚገባ ያውቃሉ፤+ +5 ከድሮ ጀምሮ የሚያውቁኝ ሰዎች ሊመሠክሩ ፈቃደኞች ቢሆኑ ኖሮ በሃይማኖታችን ውስጥ ወግ አጥባቂ የሆነውን ቡድን በመከተል+ ፈሪሳዊ ሆኜ እንደኖርኩ ያውቃሉ።+ +6 አሁን ግን እዚህ ለፍርድ የቀረብኩት አምላክ ለአባቶቻችን የገባውን ቃል ተስፋ በማድረጌ ነው፤+ +7 ደግሞም 12ቱ ነገዶቻችን ለአምላክ ቀንና ሌሊት በትጋት ቅዱስ አገልግሎት በማቅረብ እየተጠባበቁ ያሉት የዚህኑ ተስፋ ፍጻሜ ነው። ንጉሥ ሆይ፣ አይሁዶች የከሰሱኝ በዚህ ተስፋ ምክንያት ነው።+ +8 “አምላክ ሙታንን የሚያስነሳ መሆኑ ሊታመን የማይችል ነገር እንደሆነ አድርጋችሁ የምታስቡት* ለምንድን ነው? +9 እኔ ራሴ የናዝሬቱ ኢየሱስን ስም በተቻለኝ መጠን መቃወም እንዳለብኝ አምን ነበር። +10 ደግሞም በኢየሩሳሌም ያደረግኩት ይህንኑ ነው፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ+ ብዙ ቅዱሳንን ወህኒ ቤት አስገብቻለሁ፤+ እንዲገደሉም የድጋፍ ድምፅ ሰጥቻለሁ። +11 ብዙ ጊዜም በየምኩራቡ እነሱን እየቀጣሁ እምነታቸውን በይፋ እንዲክዱ ለማስገደድ ሞክሬአለሁ፤ በእነሱ ላይ እጅግ ተቆጥቼ በሌሎች ከተሞች ያሉትን እንኳ ሳይቀር እስከ ማሳደድ ደርሻለሁ። +12 “ይህን እያከናወንኩ በነበረበት ወቅት ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ተልእኮ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ እየተጓዝኩ ሳለ +13 ንጉሥ ሆይ፣ እኩለ ቀን ሲሆን በመንገድ ላይ ከፀሐይ ብርሃን የበለጠ ድምቀት ያለው ከሰማይ የመጣ ብርሃን በእኔና አብረውኝ በሚጓዙት ሰዎች ዙሪያ ሲያበራ አየሁ።+ +14 ሁላችንም መሬት ላይ በወደቅን ጊዜ አንድ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ‘ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ? መውጊያውን* መቃወምህን ከቀጠልክ ለአንተው የባሰ ይሆንብሃል’ ሲለኝ ሰማሁ። +15 እኔም ‘ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?’ አልኩ። ጌታም እንዲህ አለኝ��� ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ። +16 ይሁንና አሁን ተነስተህ በእግርህ ቁም። የተገለጥኩልህ እኔን በተመለከተ ስላየኸው ነገርና ወደፊት ስለማሳይህ ነገር አገልጋይና ምሥክር እንድትሆን አንተን ለመምረጥ ነው።+ +17 ወደ እነሱ ከምልክህ ከዚህ ሕዝብና ከአሕዛብ እታደግሃለሁ፤+ +18 የምልክህም የኃጢአት ይቅርታ ያገኙና+ በእኔ ላይ ባላቸው እምነት አማካኝነት በተቀደሱት መካከል ርስት ይቀበሉ ዘንድ ዓይናቸውን እንድትገልጥ+ እንዲሁም ከጨለማ+ ወደ ብርሃን፣+ ከሰይጣን ሥልጣንም+ ወደ አምላክ እንድትመልሳቸው ነው።’ +19 “በመሆኑም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ከሰማይ ለተገለጠልኝ ራእይ አልታዘዝም አላልኩም፤ +20 ከዚህ ይልቅ በመጀመሪያ በደማስቆ+ ላሉ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና+ በመላው የይሁዳ አገር ሁሉ ለሚገኙ ከዚያም ለአሕዛብ ንስሐ እንዲገቡና ለንስሐ የሚገባ ሥራ+ በመሥራት ወደ አምላክ እንዲመለሱ የሚያሳስበውን መልእክት ማዳረሴን ቀጠልኩ። +21 አይሁዳውያኑ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የያዙኝና ሊገድሉኝ የሞከሩት በዚህ የተነሳ ነው።+ +22 ይሁን እንጂ ከአምላክ እርዳታ በማግኘቴ እስከዚህ ቀን ድረስ ለትንሹም ሆነ ለትልቁ መመሥከሬን ቀጥያለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ ይፈጸማል ብለው ከተናገሩት በስተቀር ምንም የተናገርኩት ነገር የለም፤+ +23 እነሱም የተናገሩት ክርስቶስ መከራ እንደሚቀበልና+ ከሙታን የመጀመሪያ ሆኖ በመነሳት+ ለዚህ ሕዝብም ሆነ ለአሕዛብ ስለ ብርሃን እንደሚያውጅ ነው።”+ +24 ጳውሎስ የመከላከያ መልሱን እየሰጠ ሳለ ፊስጦስ ጮክ ብሎ “ጳውሎስ አሁንስ አእምሮህን ልትስት ነው! ብዙ መማር አእምሮህን እያሳተህ ነው!” አለ። +25 ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፦ “ክቡር ፊስጦስ ሆይ፣ አእምሮዬን እየሳትኩ አይደለም፤ እኔ እየተናገርኩ ያለሁት እውነተኛ እንዲሁም ከጤናማ አእምሮ የሚመነጭ ቃል ነው። +26 እንደ እውነቱ ከሆነ በነፃነት እያናገርኩት ያለሁት ንጉሥ ስለ እነዚህ ነገሮች በሚገባ ያውቃል፤ እነዚህ ነገሮች በድብቅ የተፈጸሙ ባለመሆናቸው አንዳቸውም ቢሆኑ ከእሱ የተሰወሩ እንዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ።+ +27 ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ በነቢያት ታምናለህ? እንደምታምን አውቃለሁ።” +28 አግሪጳም ጳውሎስን “በአጭር ጊዜ ውስጥ አሳምነህ ክርስቲያን ልታደርገኝ እኮ ምንም አልቀረህም” አለው። +29 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “በአጭርም ሆነ በረጅም ጊዜ አንተ ብቻ ሳትሆን ዛሬ እየሰሙኝ ያሉት ሁሉ ከእስራቴ በስተቀር እንደ እኔ እንዲሆኑ አምላክን እለምናለሁ” አለ። +30 ከዚያም ንጉሡ ተነሳ፤ አገረ ገዢው፣ በርኒቄና አብረዋቸው ተቀምጠው የነበሩት ሰዎችም ተነሱ። +31 እየወጡ ሳሉም እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃ ምንም ነገር አላደረገም” ተባባሉ።+ +32 ከዚያም አግሪጳ ፊስጦስን “ይህ ሰው ወደ ቄሳር ይግባኝ ባይል ኖሮ ሊፈታ ይችል ነበር” አለው።+ +4 ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ እየተናገሩ ሳሉ ካህናቱ፣ የቤተ መቅደሱ ሹምና ሰዱቃውያን+ ድንገት ወደ እነሱ መጡ። +2 እነሱም ሐዋርያቱ ሕዝቡን እያስተማሩና ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ በግልጽ እየተናገሩ+ ስለነበር እጅግ ተቆጡ። +3 በመሆኑም ያዟቸው፤ መሽቶም ስለነበር እስከ ማግስቱ ድረስ እስር ቤት አቆዩአቸው።+ +"4 ይሁን እንጂ ንግግሩን ሰምተው ከነበሩት መካከል ብዙዎቹ አመኑ፤ የወንዶቹም ቁጥር 5,000 ገደማ ሆነ።+ " +5 በማግስቱም የሕዝቡ ገዢዎች፣ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ +6 የካህናት አለቃው ሐና፣+ ቀያፋ፣+ ዮሐንስ፣ እስክንድርና የካህናት አለቃው ዘመዶችም ሁሉ ከእነሱ ጋር ነበሩ። +7 ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከላቸው አቁመው “ይህን ያደረጋችሁት በምን ሥልጣን ወይም በማን ስም ነው?” ብለው ጠየቋቸው። +8 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ+ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሕዝቡ ገዢዎችና ሽማግሌዎች፣ +9 ዛሬ በእኛ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ያለው ለአንድ ሽባ ሰው በተደረገ መልካም ሥራ+ የተነሳ ከሆነና ይህን ሰው ያዳነው ማን እንደሆነ ማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ፣ +10 ይህ ሰው ጤናማ ሆኖ እዚህ ፊታችሁ የቆመው፣ እናንተ በእንጨት ላይ በሰቀላችሁት+ ሆኖም አምላክ ከሞት ባስነሳው+ በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣+ ይኸውም በኢየሱስ አማካኝነት እንደሆነ እናንተም ሆናችሁ መላው የእስራኤል ሕዝብ ይወቅ። +11 ‘እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፣ የማዕዘን ራስ የሆነው ድንጋይ’ እሱ ነው።+ +12 ደግሞም መዳን በሌላ በማንም አይገኝም፤ ምክንያቱም ልንድንበት የምንችል ከሰማይ በታች ለሰዎች የተሰጠ ሌላ ስም የለም።”+ +13 ሰዎቹ ጴጥሮስና ዮሐንስ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ ያልተማሩና* ተራ ሰዎች+ መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ። ከኢየሱስ ጋር እንደነበሩም ተገነዘቡ።+ +14 የተፈወሰውንም ሰው ከእነሱ ጋር ቆሞ ሲያዩት+ ምንም መልስ መስጠት አልቻሉም።+ +15 ስለዚህ ከሳንሄድሪን ሸንጎ አዳራሽ እንዲወጡ አዘዟቸው፤ ከዚያም እርስ በርሳቸው ይማከሩ ጀመር፤ +16 እንዲህም ተባባሉ፦ “እነዚህን ሰዎች ምን ብናደርጋቸው ይሻላል?+ ምክንያቱም በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ የታወቀ አስደናቂ ነገር እንደፈጸሙ የማይታበል ሐቅ ነው፤+ ይህን ደግሞ ልንክድ አንችልም። +17 ይሁንና ይህ ነገር በሕዝቡ መካከል ይበልጥ እንዳይስፋፋ ከዚህ በኋላ በዚህ ስም ለማንም ሰው እንዳይናገሩ በማሳሰብ እናስፈራራቸው።”+ +18 ከዚያም ጠርተዋቸው በኢየሱስ ስም ፈጽሞ እንዳይናገሩ ወይም እንዳያስተምሩ አዘዟቸው። +19 ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው እንዲህ አሏቸው፦ “አምላክን ከመስማት ይልቅ እናንተን መስማት በአምላክ ፊት ተገቢ እንደሆነና እንዳልሆነ እስቲ እናንተው ፍረዱ። +20 እኛ ግን ስላየነውና ስለሰማነው ነገር ከመናገር ወደኋላ ማለት አንችልም።”+ +21 በመሆኑም እንደገና ካስፈራሯቸው በኋላ ለቀቋቸው፤ ይህን ያደረጉት እነሱን ለመቅጣት የሚያስችል ምንም ተጨባጭ ነገር ስላላገኙና ሕዝቡን ስለፈሩ ነው፤+ ምክንያቱም ሕዝቡ ሁሉ በተፈጸመው ሁኔታ አምላክን እያከበረ ነበር። +22 በዚህ ተአምር* የተፈወሰውም ሰው ዕድሜው ከ40 ዓመት በላይ ነበር። +23 ከተለቀቁ በኋላ ወደ ወንድሞቻቸው ሄደው የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ ያሏቸውን ሁሉ ነገሯቸው። +24 እነሱም ይህን በሰሙ ጊዜ በአንድ ልብ ሆነው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እንዲህ ሲሉ ወደ አምላክ ጸለዩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ሆይ፣ ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ የፈጠርክ አንተ ነህ፤+ +25 በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለሃል፦+ ‘ብሔራት ለምን ታወኩ? ሕዝቦችስ ለምን ከንቱ ነገር ያውጠነጥናሉ? +26 የምድር ነገሥታት ተሰለፉ፤ ገዢዎችም በአንድነት ተሰብስበው በይሖዋና* እሱ በቀባው* ላይ ተነሱ።’+ +27 በእርግጥም ሄሮድስና ጳንጥዮስ ጲላጦስ+ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው አንተ በቀባኸው+ በቅዱስ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሱ፤ +28 ይህም የሆነው እጅህና ፈቃድህ አስቀድመው የወሰኑት እንዲፈጸም ነው።+ +29 አሁንም ይሖዋ* ሆይ፣ ዛቻቸውን ተመልከት፤ ባሪያዎችህም ቃልህን በፍጹም ድፍረት መናገራቸውን እንዲቀጥሉ እርዳቸው፤ +30 ለመፈወስም የዘረጋኸውን እጅህን አትጠፍ፤ በቅዱስ አገልጋይህ በኢየሱስ ስም+ ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ማድረግህንም ቀጥል።”+ +31 ምልጃ ካቀረቡም* በኋላ ተሰብስበውበት የነበረው ቦታ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው+ የአምላክን ቃል በድፍረት መናገር ጀመሩ።+ +32 በተጨማሪም ከፍተኛ ቁጥር የነበራቸው ያመኑት ሰዎች አንድ ልብና ነፍስ* ነበራቸው፤ አንዳቸውም ቢሆኑ ያላቸው ማንኛውም ንብረት የግላቸው እንደሆነ አድርገው አይቆጥሩም ነበር፤ ከዚህ ይልቅ ያላቸው ነገር ሁሉ የጋራ ነበር።+ +33 ደግሞም ሐዋርያቱ ስለ ጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ በታላቅ ኃይል መመሥከራቸውን ቀጠሉ፤+ ሁሉም የአምላክን ታላቅ ጸጋ አግኝተው ነበር። +34 ከመካከላቸውም አንድም ችግረኛ አልነበረም፤+ ምክንያቱም መሬት ወይም ቤት የነበራቸው ሁሉ እየሸጡ ገንዘቡን በማምጣት +35 ለሐዋርያት ያስረክቡ ነበር።+ ከዚያም ለእያንዳንዱ ሰው በሚያስፈልገው መጠን ይከፋፈል ነበር።+ +36 የቆጵሮስ ተወላጅ የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበር፤ ሐዋርያት በርናባስ+ ብለውም ይጠሩት የነበረ ሲሆን ትርጉሙም “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው፤ +37 እሱም መሬት ስለነበረው መሬቱን ሸጦ ገንዘቡን በማምጣት ለሐዋርያት አስረከበ።+ +16 ከዚያም ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ+ ሄደ። በዚያም አማኝ የሆነች አይሁዳዊት እናትና ግሪካዊ አባት ያለው ጢሞቴዎስ+ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ +2 እሱም በልስጥራና በኢቆንዮን ባሉ ወንድሞች፣ በመልካም ምግባሩ የተመሠከረለት ነበር። +3 ጳውሎስ፣ ጢሞቴዎስ አብሮት እንዲሄድ እንደሚፈልግ ገለጸ፤ አባቱ ግሪካዊ መሆኑን ሁሉም ሰው ያውቅ ስለነበረም በእነዚያ አካባቢዎች ስላሉት አይሁዳውያን ሲል ወስዶ ገረዘው።+ +4 በየከተሞቹ ሲያልፉም በዚያ ለሚያገኟቸው ሁሉ በኢየሩሳሌም ያሉት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ያስተላለፏቸውን ውሳኔዎች እንዲጠብቁ ጉዳዩን ያሳውቋቸው ነበር።+ +5 ጉባኤዎቹም በእምነት እየጠነከሩና ከዕለት ወደ ዕለት በቁጥር እየጨመሩ ሄዱ። +6 ከዚህም ሌላ መንፈስ ቅዱስ ቃሉን በእስያ አውራጃ እንዳይናገሩ ስለከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አድርገው አለፉ።+ +7 ደግሞም ወደ ሚስያ በወረዱ ጊዜ ወደ ቢቲኒያ+ ሊገቡ ሞከሩ፤ ሆኖም የኢየሱስ መንፈስ አልፈቀደላቸውም። +8 ስለዚህ በሚስያ በኩል አልፈው* ወደ ጥሮአስ ወረዱ። +9 ጳውሎስም ሌሊት በራእይ አንድ የመቄዶንያ ሰው በዚያ ቆሞ “ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን” ብሎ ሲለምነው አየ። +10 ጳውሎስ ይህን ራእይ እንዳየም ‘አምላክ ምሥራቹን እንድንሰብክላቸው ጠርቶናል’ የሚል መደምደሚያ ላይ ስለደረስን ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ሞከርን። +11 ስለዚህ ከጥሮአስ መርከብ ተሳፍረን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ ሄድን፤ በማግስቱ ደግሞ ወደ ኔያጶሊስ ተጓዝን፤ +12 ከዚያም ተነስተን የሮማውያን ቅኝ ግዛትና የመቄዶንያ አውራጃ ቁልፍ ከተማ ወደሆነችው ወደ ፊልጵስዩስ+ መጣን። በዚህች ከተማም ለተወሰኑ ቀናት ቆየን። +13 በሰንበት ቀን የጸሎት ስፍራ ይገኝበታል ብለን ወዳሰብነው ከከተማው በር ውጭ ወዳለ አንድ ወንዝ ዳር ሄድን፤ በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩት ሴቶች መናገር ጀመርን። +14 ከትያጥሮን+ ከተማ የመጣች፣ ሐምራዊ ጨርቅ የምትሸጥና* አምላክን የምታመልክ ሊዲያ የተባለች አንዲት ሴት እያዳመጠች ነበር፤ ይሖዋም* ጳውሎስ የሚናገረውን በማስተዋል እንድትሰማ ልቧን በደንብ ከፈተላት። +15 እሷና በቤቷ የሚኖሩ ሰዎች ከተጠመቁ+ በኋላ “ለይሖዋ* ታማኝ እንደሆንኩ አድርጋችሁ ከቆጠራችሁኝ ወደ ቤቴ ገብታችሁ እረፉ” ብላ ተማጸነችን። እንድንገባም አስገደደችን። +16 አንድ ቀን ወደ ጸሎት ስፍራ እየሄድን ሳለ መንፈስ ይኸውም የጥንቆላ+ ጋኔን ያደረባት አንዲት አገልጋይ አገኘችን። እሷም በጥንቆላ ሥራዋ ለጌቶቿ ብዙ ትርፍ ታስገኝላቸው ነበር። +17 ይህች ሴት ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች “እነዚህ ሰዎች የመዳንን መንገድ የሚያውጁላችሁ የልዑሉ አምላክ ባሪያዎች ናቸው” በማለት ትጮኽ ነበር።+ +18 ለብዙ ቀናት እየደጋገመች ይህንኑ ትናገር ነበር። በመጨረሻም ጳውሎስ በዚህ ነገር በመሰላቸቱ ዞር ብሎ ያን መንፈስ “ከእሷ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ” አለው። መንፈሱም በዚያው ቅጽበት ወጣ።+ +19 ጌቶቿ የገቢ ምንጫቸው መቋረጡን+ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው እየጎተቱ ገዢዎቹ ወደሚገኙበት ወደ ገበያ ስፍራው* ወሰዷቸው።+ +20 ከዚያም የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች ፊት አቅርበዋቸው እንዲህ አሉ፦ “እነዚህ ሰዎች ከተማችንን ክፉኛ እያወኩ ነው።+ እነሱ አይሁዳውያን ናቸው፤ +21 ደግሞም እኛ ሮማውያን ልንቀበለውም ሆነ ልንፈጽመው የማይገባንን ልማድ እያስፋፉ ነው።” +22 ሕዝቡም በአንድነት በእነሱ ላይ ተነሳ፤ የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎችም ልብሳቸውን ከገፈፏቸው በኋላ በበትር እንዲደበደቡ አዘዙ።+ +23 በጣም ከደበደቧቸው በኋላ እስር ቤት አስገቧቸው፤ የእስር ቤቱንም ጠባቂ በደንብ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።+ +24 እሱም እንዲህ ያለ ትእዛዝ ስለተሰጠው ወደ እስር ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን በእግር ግንድ አሰረው። +25 ይሁንና እኩለ ሌሊት ገደማ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና አምላክን በመዝሙር እያወደሱ ነበር፤+ ሌሎቹ እስረኞችም ያዳምጧቸው ነበር። +26 ድንገት ከባድ የምድር ነውጥ በመከሰቱ የእስር ቤቱ መሠረት ተናጋ። በተጨማሪም በሮቹ ወዲያውኑ የተከፈቱ ሲሆን ሁሉም የታሰሩበት ማሰሪያ ተፈታ።+ +27 የእስር ቤቱ ጠባቂም ከእንቅልፉ ነቅቶ የእስር ቤቱ በሮች መከፈታቸውን ሲያይ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ለመግደል ሰይፉን መዘዘ።+ +28 ጳውሎስ ግን ድምፁን ከፍ አድርጎ “በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ! ሁላችንም እዚህ አለን” ሲል ተናገረ። +29 በዚህ ጊዜ የእስር ቤቱ ጠባቂ መብራት እንዲያመጡለት ጠይቆ ወደ ውስጥ ዘሎ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ ፊት ተደፋ። +30 ወደ ውጭ ካወጣቸውም በኋላ “ጌቶቼ፣ ለመዳን ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” አለ። +31 እነሱም “በጌታ ኢየሱስ እመን፤ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ ትድናላችሁ” አሉት።+ +32 ከዚያም ለእሱና በቤቱ ላሉት ሰዎች ሁሉ የይሖዋን* ቃል ነገሯቸው። +33 ጠባቂውም ሌሊት በዚያው ሰዓት ይዟቸው ሄዶ ቁስላቸውን አጠበላቸው። ከዚያም እሱና መላው ቤተሰቡ ወዲያውኑ ተጠመቁ።+ +34 ወደ ቤቱም ወስዶ ማዕድ አቀረበላቸው፤ በአምላክ በማመኑም ከመላው ቤተሰቡ ጋር እጅግ ተደሰተ። +35 ሲነጋም የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች “እነዚያን ሰዎች ልቀቃቸው” ብለው እንዲነግሩት መኮንኖቹን ላኩበት። +36 የእስር ቤቱ ጠባቂ የላኩትን መልእክት እንዲህ ሲል ለጳውሎስ ነገረው፦ “የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች ሁለታችሁ እንድትፈቱ ሰዎች ልከዋል። ስለዚህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ።” +37 ጳውሎስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እኛ የሮም ዜጎች+ ሆነን ሳለ ያለፍርድ በሕዝብ ፊት ገርፈው እስር ቤት ወረወሩን። ታዲያ አሁን በድብቅ አስወጥተው ሊጥሉን ይፈልጋሉ? እንዲህማ አይሆንም! እነሱ ራሳቸው መጥተው ይዘውን ይውጡ።” +38 መኮንኖቹም ይህን ነገር ለከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች ነገሯቸው። እነሱም ሰዎቹ የሮም ዜጎች መሆናቸውን ሲሰሙ ፍርሃት አደረባቸው።+ +39 በመሆኑም መጥተው ለመኗቸው፤ ከእስር ቤቱም ይዘዋቸው ከወጡ በኋላ ከተማዋን ለቀው እንዲሄዱ ጠየቋቸው። +40 እነሱ ግን ከእስር ቤቱ ወጥተው ወደ ሊዲያ ቤት አመሩ፤ እዚያም ወንድሞችን አግኝተው ካበረታቷቸው+ በኋላ ከተማዋን ለቀው ሄዱ። +6 በዚያን ወቅት የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ አይሁዳውያን በየዕለቱ በሚከናወነው ምግብ የማከፋፈል ሥ�� መበለቶቻቸው ቸል ስለተባሉባቸው ዕብራይስጥ ተናጋሪ በሆኑት አይሁዳውያን ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ።+ +2 ስለዚህ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ደቀ መዛሙርቱን በሙሉ ጠርተው እንዲህ አሏቸው፦ “በማዕድ ምግብ ለማከፋፈል ስንል የአምላክን ቃል የማስተማር ሥራችንን ብንተው ተገቢ አይሆንም።+ +3 ስለዚህ ወንድሞች፣ ለዚህ አስፈላጊ ጉዳይ እንድንሾማቸው ከእናንተ መካከል መልካም ስም ያተረፉ፣*+ በመንፈስና በጥበብ የተሞሉ+ ሰባት ወንዶች ምረጡ፤+ +4 እኛ ግን በጸሎትና ቃሉን በማስተማሩ ሥራ* ላይ ሙሉ በሙሉ እናተኩራለን።” +5 የተናገሩት ነገር ሁሉንም ደስ አሰኛቸው፤ ስለሆነም ጠንካራ እምነት የነበረውንና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን እንዲሁም ፊልጶስን፣+ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞንን፣ ፓርሜናስንና ወደ ይሁዲነት ተለውጦ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ። +6 ሐዋርያትም ፊት አቀረቧቸው፤ እነሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።+ +7 ከዚህም የተነሳ የአምላክ ቃል መስፋፋቱን ቀጠለ፤+ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሄደ፤+ በጣም ብዙ ካህናትም ይህን እምነት ተቀበሉ።+ +8 እስጢፋኖስም ጸጋና ኃይል ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ድንቅ ነገሮችና ተአምራዊ ምልክቶች ይፈጽም ነበር። +9 ይሁን እንጂ ‘ነፃ የወጡ ሰዎች ምኩራብ’ ተብሎ የሚጠራው ቡድን አባላት የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ከተወሰኑ የቀሬና፣ የእስክንድርያ፣ የኪልቅያና የእስያ ሰዎች ጋር መጥተው እስጢፋኖስን ተከራከሩት። +10 ይሁንና ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም።+ +11 ስለዚህ “ይህ ሰው በሙሴና በአምላክ ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተነዋል” ብለው እንዲናገሩ አንዳንድ ሰዎችን በድብቅ አግባቡ። +12 በተጨማሪም ሕዝቡንና ሽማግሌዎችን እንዲሁም ጸሐፍትን ቀሰቀሱ፤ ከዚያም ድንገት መጡና በኃይል ይዘው ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ ወሰዱት። +13 የሐሰት ምሥክሮችም አቀረቡ፤ እነሱም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ይህን ቅዱስ ስፍራና ሕጉን የሚቃወም ነገር ከመናገር ሊቆጠብ አልቻለም። +14 ለምሳሌ ያህል፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያፈርሰውና ሙሴ ያስተላለፈልንን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተነዋል።” +15 በሳንሄድሪን ሸንጎ ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ ትኩር ብለው ሲያዩት ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ታያቸው። +25 ፊስጦስም+ ወደ አውራጃው ከመጣና ኃላፊነቱን ከተረከበ ከሦስት ቀን በኋላ ከቂሳርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። +2 የካህናት አለቆችና አንዳንድ የታወቁ አይሁዳውያንም በጳውሎስ ላይ ያላቸውን ክስ ለእሱ አቀረቡ።+ ከዚያም ፊስጦስን ይለምኑት ጀመር፤ +3 ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም በማስመጣት እንዲተባበራቸው* ጠየቁት። ይህን ያሉት ግን መንገድ ላይ አድፍጠው ጳውሎስን ሊገድሉት አስበው ስለነበር ነው።+ +4 ይሁን እንጂ ፊስጦስ፣ ጳውሎስ እዚያው ቂሳርያ ታስሮ እንደሚቆይና እሱ ራሱም በቅርቡ ወደዚያ እንደሚመለስ ነገራቸው። +5 “በመሆኑም ከእናንተ መካከል ሥልጣን ያላቸው ከእኔ ጋር ይውረዱና ሰውየው ያጠፋው ነገር ካለ ይክሰሱት” አላቸው።+ +6 ስለዚህ ፊስጦስ ከስምንት ወይም ከአሥር ቀን ያልበለጠ ጊዜ ከእነሱ ጋር ካሳለፈ በኋላ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በማግስቱም በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ። +7 ጳውሎስ በቀረበ ጊዜ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁዳውያን በዙሪያው ቆመው በማስረጃ ያልተደገፉ በርካታ ከባድ ክሶች አቀረቡበት።+ +8 ጳውሎስ ግን “እኔ በአይሁዳውያን ሕግ ላይም ሆነ በቤተ መቅደሱ ወይም በቄሳር ላይ ምንም የፈጸምኩት በደል የለም” ሲል የመከላከያ መልሱን ሰጠ።+ +9 ፊስጦስም በአይሁዳውያን ዘንድ ተወዳጅነት ማትረፍ ስለፈለገ+ ጳውሎስን “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ጉዳይ እዚያ እኔ ባለሁበት መዳኘት ትፈልጋለህ?” ሲል ጠየቀው። +10 ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፦ “እኔ ልዳኝበት በሚገባኝ በቄሳር የፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተ ራስህ በሚገባ እንደተገነዘብከው በአይሁዳውያን ላይ የፈጸምኩት ምንም በደል የለም። +11 በእርግጥ ጥፋተኛ ሆኜ ከተገኘሁና ለሞት የሚያበቃ ነገር ፈጽሜ ከሆነ+ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ ሰዎች ያቀረቡብኝ ክስ ሁሉ መሠረተ ቢስ ከሆነ ግን እነሱን ለማስደሰት ብሎ ማንም ሰው እኔን ለእነሱ አሳልፎ የመስጠት መብት የለውም። ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ!”+ +12 በዚህ ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ከተመካከረ በኋላ “ወደ ቄሳር ይግባኝ ስላልክ ወደ ቄሳር ትሄዳለህ” ሲል መለሰለት። +13 የተወሰኑ ቀናት ካለፉ በኋላ ንጉሥ አግሪጳና* በርኒቄ ለፊስጦስ ክብር ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቂሳርያ መጡ። +14 በዚያም ብዙ ቀናት ስለቆዩ ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለንጉሡ በማቅረብ እንዲህ አለው፦ “ፊሊክስ እስር ቤት የተወው አንድ ሰው አለ፤ +15 ኢየሩሳሌም በነበርኩበት ጊዜ የካህናት አለቆቹና የአይሁዳውያን ሽማግሌዎች ይህን ሰው በመክሰስ+ እንዲፈረድበት ጥያቄ አቅርበው ነበር። +16 እኔ ግን ክስ የቀረበበት ሰው ከከሳሾቹ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ለቀረበበት ክስ የመከላከያ መልስ መስጠት የሚችልበት አጋጣሚ ሳያገኝ እንዲሁ ሰውን ለማስደሰት ተብሎ ብቻ አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት እንዳልሆነ ገለጽኩላቸው።+ +17 ስለዚህ ከሳሾቹ ወደዚህ በመጡ ጊዜ ምንም ሳልዘገይ በማግስቱ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጬ ሰውየውን እንዲያመጡት አዘዝኩ። +18 ከሳሾቹም ቆመው በተናገሩ ጊዜ እኔ የጠበቅኩትን ያህል ከባድ በደል እንደፈጸመ የሚያሳይ ክስ አላቀረቡበትም።+ +19 ከዚህ ይልቅ ከእሱ ጋር ይከራከሩ የነበረው ስለ ገዛ አምልኳቸውና*+ ስለሞተው፣ ጳውሎስ ግን ሕያው ነው ስለሚለው ኢየሱስ ስለተባለ ሰው ነው።+ +20 እኔም ይህን ክርክር እንዴት እንደምፈታው ግራ ስለገባኝ ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ስለዚህ ጉዳይ እዚያ መፋረድ ይፈልግ እንደሆነ ጠየቅኩት።+ +21 ጳውሎስ ግን አውግስጦስ* ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ታስሮ እንዲቆይ ይግባኝ ጠየቀ፤+ በመሆኑም ወደ ቄሳር እስከምልከው ድረስ በእስር ቤት እንዲቆይ አዘዝኩ።” +22 በዚህ ጊዜ አግሪጳ ፊስጦስን “እኔም ይህ ሰው ሲናገር ብሰማው ደስ ይለኝ ነበር” አለው።+ እሱም “እንግዲያውስ ነገ ትሰማዋለህ” አለው። +23 ስለዚህ በማግስቱ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ክብር ደምቀው እንዲሁም በሻለቃዎችና በከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ታጅበው ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ ገቡ፤ ፊስጦስም ትእዛዝ በሰጠ ጊዜ ጳውሎስ እንዲቀርብ ተደረገ። +24 ፊስጦስም እንዲህ አለ፦ “ንጉሥ አግሪጳና ከእኛ ጋር እዚህ የተሰበሰባችሁ ሁሉ፣ ይህ የምታዩት ሰው በኢየሩሳሌምም ሆነ እዚህ፣ አይሁዳውያን ሁሉ ከእንግዲህ በሕይወት ሊኖር አይገባውም እያሉ በመጮኽ ለእኔ አቤቱታ ያቀረቡበት ሰው ነው።+ +25 እኔ ግን ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር እንዳልፈጸመ ተረድቻለሁ።+ በመሆኑም እሱ ራሱ ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ ልልከው ወስኛለሁ። +26 ይሁንና ስለ እሱ ወደ ጌታዬ የምጽፈው ምንም የተረጋገጠ ነገር አላገኘሁም። ስለዚህ አሁን በችሎቱ ፊት ከተመረመረ በኋላ ልጽፈው የምችለው ነገር አገኝ ዘንድ በእናንተ ሁሉ ፊት በተለይ ደግሞ በአንተ በንጉሥ አግሪጳ ፊት አቀረብኩት። +27 ምክንያቱም አንድን እስረኛ የተከሰሰበትን ምክንያት ሳይገልጹ መላክ ተገቢ አልመሰለኝም።” +10 በቂሳርያ “የጣሊያን ክፍለ ጦር”* ተብሎ በሚጠራ ሠራዊት ውስጥ ቆርኔሌዎስ የሚ��ል አንድ የጦር መኮንን* ነበር። +2 እሱም ከመላው ቤተሰቡ ጋር ለአምላክ ያደረና ፈሪሃ አምላክ የነበረው ሰው ሲሆን ለሰዎች ምጽዋት የሚሰጥና ዘወትር ወደ አምላክ የሚማልድ ሰው ነበር። +3 ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት+ ገደማ አንድ የአምላክ መልአክ ወደ እሱ ሲመጣ በራእይ በግልጽ አየ፤ መልአኩም “ቆርኔሌዎስ!” አለው። +4 ቆርኔሌዎስም በድንጋጤ ትኩር ብሎ እያየው “ጌታ ሆይ፣ ምንድን ነው?” በማለት ጠየቀው። እሱም እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህና ምጽዋትህ በአምላክ ፊት መታሰቢያ እንዲሆን አርጓል።+ +5 ስለዚህ አሁን ወደ ኢዮጴ ሰዎች ልከህ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራውን ስምዖንን አስጠራው። +6 ይህ ሰው፣ ቤቱ በባሕሩ አጠገብ በሚገኘው በቆዳ ፋቂው በስምዖን ቤት በእንግድነት አርፏል።” +7 ያነጋገረው መልአክ ተለይቶት እንደሄደ ከአገልጋዮቹ ሁለቱን እንዲሁም እሱን በቅርብ ከሚያገለግሉት ወታደሮች መካከል ለአምላክ ያደረ አንድ ወታደር ጠራ፤ +8 የሆነውንም ነገር ሁሉ ከነገራቸው በኋላ ወደ ኢዮጴ ላካቸው። +9 በማግስቱም የተላኩት ሰዎች ተጉዘው ወደ ከተማዋ ሲቃረቡ ጴጥሮስ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ገደማ ሊጸልይ ወደ ሰገነት ወጣ። +10 ይሁን እንጂ በጣም ከመራቡ የተነሳ መብላት ፈለገ። ምግብ እየተዘጋጀ ሳለም ሰመመን ውስጥ ገባ፤+ +11 ሰማይም ተከፍቶ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራቱም ጫፍ ተይዞ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፤ +12 በላዩም የተለያዩ በምድር ላይ የሚኖሩ አራት እግር ያላቸው እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታት እንዲሁም የሰማይ ወፎች ነበሩ። +13 ከዚያም አንድ ድምፅ “ጴጥሮስ፣ ተነሳና አርደህ ብላ!” አለው። +14 ጴጥሮስ ግን “ጌታ ሆይ፣ በጭራሽ፤ ምክንያቱም እኔ ንጹሕ ያልሆነና የረከሰ ነገር በልቼ አላውቅም” አለ።+ +15 ያም ድምፅ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ “አምላክ ንጹሕ ያደረገውን ነገር ርኩስ ነው ማለትህን ተው” አለው። +16 ይህም ለሦስተኛ ጊዜ ተደገመ፤ ወዲያውኑም ጨርቅ የሚመስለው ነገር ወደ ሰማይ ተወሰደ። +17 ጴጥሮስ ‘የራእዩ ትርጉም ምን ይሆን’ በማለት በጣም ግራ ተጋብቶ እያለ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች የስምዖንን ቤት አጠያይቀው መጡና የውጭው በር ላይ ቆሙ።+ +18 ከዚያም ተጣርተው ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራው ስምዖን በዚያ በእንግድነት አርፎ እንደሆነ ጠየቁ። +19 ጴጥሮስ ያየውን ራእይ በሐሳቡ እያወጣና እያወረደ ሳለ መንፈስ+ እንዲህ አለው፦ “እነሆ፣ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል። +20 ስለዚህ ተነስተህ ወደ ታች ውረድ፤ የላክኋቸው እኔ ስለሆንኩ ምንም ሳትጠራጠር አብረሃቸው ሂድ።” +21 ጴጥሮስም ሰዎቹ ወዳሉበት ወርዶ “የምትፈልጉት ሰው እኔ ነኝ። ወደዚህ የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አላቸው። +22 እነሱም እንዲህ አሉ፦ “በአይሁዳውያን ሁሉ የተመሠከረለት ቆርኔሌዎስ+ የተባለ ጻድቅና አምላክን የሚፈራ አንድ የጦር መኮንን፣ ወደ አንተ መልእክተኞች ልኮ ወደ ቤቱ እንዲያስመጣህና የምትለውን ነገር እንዲሰማ አንድ ቅዱስ መልአክ መለኮታዊ መመሪያ ሰጥቶታል።” +23 እሱም ወደ ቤት አስገብቶ አስተናገዳቸው። በማግስቱም ተነስቶ ከእነሱ ጋር ሄደ፤ በኢዮጴ ያሉ አንዳንድ ወንድሞችም አብረውት ሄዱ። +24 በሚቀጥለው ቀንም ወደ ቂሳርያ ገባ። ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን ሰብስቦ እየጠበቃቸው ነበር። +25 ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተቀበለውና እግሩ ላይ ወድቆ ሰገደለት።* +26 ጴጥሮስ ግን “ተነስ፣ እኔም እንደ አንተው ሰው ነኝ” ብሎ አስነሳው።+ +27 ከእሱ ጋር እየተነጋገረ ወደ ውስጥ ሲገባም ብዙ ሰዎች ተሰብስበው አገኘ። +28 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ አይሁዳዊ ከሌላ ዘር ጋር ይወዳጅ ወይም ይቀራረብ ዘንድ ሕጉ እንደማይፈቅድ በሚገባ ታውቃላችሁ፤+ ሆ���ም አምላክ ማንንም ሰው ንጹሕ ያልሆነ ወይም ርኩስ ማለት እንደማይገባኝ ገልጦልኛል።+ +29 በመሆኑም በተጠራሁ ጊዜ ምንም ሳላንገራግር መጣሁ። ስለዚህ ለምን እንዳስጠራችሁኝ ማወቅ እፈልጋለሁ።” +30 ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለ፦ “ከአራት ቀን በፊት በዚሁ ሰዓት ይኸውም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በቤቴ ሆኜ እየጸለይኩ ሳለ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው ድንገት ፊቴ ቆሞ +31 እንዲህ አለኝ፦ ‘ቆርኔሌዎስ፣ ጸሎትህ ተሰምቶልሃል፤ ምጽዋትህም በአምላክ ፊት ታስቦልሃል። +32 ስለዚህ ወደ ኢዮጴ ሰዎች ልከህ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራውን ስምዖንን አስጠራው። ይህ ሰው፣ ቤቱ በባሕሩ አጠገብ በሚገኘው በቆዳ ፋቂው በስምዖን ቤት በእንግድነት አርፏል።’+ +33 እኔም ወዲያውኑ ሰዎች ላክሁብህ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። ስለዚህ አሁን እኛ ይሖዋ* እንድትናገር ያዘዘህን ነገር ሁሉ ለመስማት ይኸው ሁላችንም በአምላክ ፊት ተገኝተናል።” +34 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፦ “እነሆ፣ አምላክ እንደማያዳላ በእርግጥ አስተዋልኩ፤+ +35 ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና ትክክል የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።+ +36 አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለእስራኤል ልጆች የሰላም ምሥራች ለማወጅ ቃሉን ላከላቸው፤+ ይህም ምሥራች ኢየሱስ የሁሉ ጌታ+ እንደሆነ የሚገልጽ ነው። +37 ዮሐንስ ስለ ጥምቀት ከሰበከ በኋላ ከገሊላ አንስቶ በመላው ይሁዳ ይወራ ስለነበረው ጉዳይ ታውቃላችሁ፤+ +38 የተወራውም ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ ነው። አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ቀባው፤+ ደግሞም ኃይል ሰጠው፤ ኢየሱስም አምላክ ከእሱ ጋር ስለነበር መልካም ነገር እያደረገና+ በዲያብሎስ ቁጥጥር ሥር የወደቁትን እየፈወሰ+ በዚያ አገር ሁሉ ተዘዋወረ። +39 እሱ በአይሁዳውያን አገርም ሆነ በኢየሩሳሌም ላደረጋቸው ነገሮች ሁሉ እኛ ምሥክሮች ነን፤ እነሱ ግን በእንጨት* ላይ ሰቅለው ገደሉት። +40 አምላክ እሱን በሦስተኛው ቀን አስነሳው፤+ ከዚያም ለሰዎች እንዲገለጥ* አደረገው፤ +41 የተገለጠው ግን ለሁሉም ሰው ሳይሆን አምላክ አስቀድሞ ለመረጣቸው ምሥክሮች ይኸውም ከሞት ከተነሳ በኋላ አብረነው ለበላንና ለጠጣን ለእኛ ነው።+ +42 በተጨማሪም አምላክ እሱን በሕያዋንና በሙታን ላይ ፈራጅ አድርጎ እንደሾመው+ ለሰዎች እንድንሰብክና በተሟላ ሁኔታ* እንድንመሠክር አዘዘን።+ +43 በእሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአት ይቅርታ እንደሚያገኝ+ ነቢያት ሁሉ ስለ እሱ ይመሠክራሉ።”+ +44 ጴጥሮስ ስለዚህ ጉዳይ ገና እየተናገረ ሳለ ቃሉን እየሰሙ በነበሩት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።+ +45 ከጴጥሮስ ጋር የመጡት የተገረዙ አማኞች* የመንፈስ ቅዱስ ነፃ ስጦታ ከአሕዛብ ወገን በሆኑ ሰዎችም ላይ በመፍሰሱ ተገረሙ። +46 ምክንያቱም በባዕድ ቋንቋዎች* ሲናገሩና አምላክን ሲያወድሱ ይሰሟቸው ነበር።+ በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እንዲህ አለ፦ +47 “እንደ እኛው መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉትን እነዚህን ሰዎች በውኃ እንዳይጠመቁ ሊከለክላቸው የሚችል አለ?”+ +48 ይህን ካለ በኋላ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ አዘዛቸው።+ ከዚያም የተወሰነ ቀን አብሯቸው እንዲቆይ ለመኑት። +14 በኢቆንዮን ጳውሎስና በርናባስ አብረው ወደ አይሁዳውያን ምኩራብ ገቡ፤ በዚያም ጥሩ ንግግር ስለሰጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አይሁዳውያንና ግሪካውያን አማኞች ሆኑ። +2 ሆኖም ያላመኑት አይሁዳውያን ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን ሰዎች* በማነሳሳት በወንድሞች ላይ ጥላቻ እንዲያድርባቸው አደረጉ።+ +3 በመሆኑም ከይሖዋ* ባገኙት ሥልጣን በድፍረት እየተናገሩ በኢቆንዮን ረዘም ላለ ጊዜ ቆዩ፤ እሱም ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች በእነሱ አማካኝነት እንዲከናወኑ በማድረግ ስለ ጸጋው የሚነገረው መልእክት ትክክል መሆኑን ያረጋግጥላቸው ነበር።+ +4 ይሁንና የከተማዋ ሕዝብ ተከፋፈለ፤ አንዳንዶቹ ከአይሁዳውያን ጎን ሲቆሙ ሌሎቹ ደግሞ ከሐዋርያት ጎን ቆሙ። +5 አሕዛብና አይሁዳውያን ከገዢዎቻቸው ጋር ሆነው ሊያንገላቷቸውና በድንጋይ ሊወግሯቸው በሞከሩ ጊዜ+ +6 ጳውሎስና በርናባስ ይህን ስላወቁ ልስጥራና ደርቤ ወደሚባሉት የሊቃኦንያ ከተሞች እንዲሁም በዙሪያቸው ወዳሉት መንደሮች ሸሹ።+ +7 በዚያም ምሥራቹን ማወጃቸውን ቀጠሉ። +8 በልስጥራም አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር። እሱም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ሽባ የነበረ ሲሆን ፈጽሞ በእግሩ ሄዶ አያውቅም። +9 ይህ ሰው ጳውሎስ ሲናገር ያዳምጥ ነበር። ጳውሎስም ትኩር ብሎ አየውና ለመዳን የሚያበቃ እምነት እንዳለው ተመልክቶ+ +10 ከፍ ባለ ድምፅ “ተነስና በእግርህ ቁም” አለው። ሰውየውም ዘሎ ተነሳና መራመድ ጀመረ።+ +11 ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ በሊቃኦንያ ቋንቋ “አማልክት በሰው አምሳል ሆነው ወደ እኛ ወርደዋል!” በማለት ጮኹ።+ +12 በርናባስን ዙስ፣ ጳውሎስን ደግሞ ዋና ተናጋሪ ስለነበር ሄርሜስ ብለው ይጠሯቸው ጀመር። +13 በከተማዋ መግቢያ ላይ ይገኝ የነበረው የዙስ ቤተ መቅደስ ካህን፣ ኮርማዎችና የአበባ ጉንጉን ወደ ከተማዋ መግቢያ በማምጣት ከሕዝቡ ጋር ሆኖ መሥዋዕት ሊሠዋላቸው ፈለገ። +14 ይሁን እንጂ ሐዋርያቱ በርናባስና ጳውሎስ ይህን ሲሰሙ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ሮጠውም ሕዝቡ መሃል በመግባት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፦ +15 “እናንተ ሰዎች፣ እንዲህ የምታደርጉት ለምንድን ነው? እኛም እንደ እናንተው ድክመት ያለብን ሰዎች ነን።+ ምሥራቹን እያወጅንላችሁ ያለነውም እነዚህን ከንቱ ነገሮች ትታችሁ ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ የፈጠረውን ሕያው አምላክ እንድታመልኩ ነው።+ +16 ባለፉት ትውልዶች፣ ሕዝቦች ሁሉ በራሳቸው መንገድ እንዲሄዱ ፈቀደላቸው፤+ +17 ይሁንና ለራሱ ምሥክር ከማቅረብ ወደኋላ አላለም፤+ ከሰማይ ዝናብ በማዝነብና ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠት+ እንዲሁም የተትረፈረፈ ምግብ በማቅረብና ልባችሁን በደስታ በመሙላት መልካም ነገር አድርጓል።”+ +18 ይህን ሁሉ ተናግረው እንኳ ሕዝቡ እንዳይሠዋላቸው ያስጣሉት በብዙ ችግር ነበር። +19 ሆኖም አይሁዳውያን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጥተው ሕዝቡን አግባቡ፤+ ጳውሎስንም በድንጋይ ከወገሩት በኋላ የሞተ መስሏቸው ጎትተው ከከተማዋ አወጡት።+ +20 ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በከበቡት ጊዜ ግን ተነስቶ ወደ ከተማዋ ገባ። በማግስቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤ ሄደ።+ +21 በዚያች ከተማ ምሥራቹን ሰብከው በርካታ ደቀ መዛሙርት ካፈሩ በኋላ ወደ ልስጥራ፣ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ። +22 በዚያም “በብዙ መከራ አልፈን ወደ አምላክ መንግሥት መግባት አለብን”+ እያሉ በእምነት ጸንተው እንዲኖሩ በማበረታታት ደቀ መዛሙርቱን* አጠናከሩ።+ +23 ከዚህም በተጨማሪ በየጉባኤው ሽማግሌዎችን ሾሙላቸው፤+ ከጾሙና ከጸለዩም በኋላ+ ላመኑበት ለይሖዋ* አደራ ሰጧቸው። +24 ከዚያም በጵስድያ በኩል አልፈው ወደ ጵንፍልያ+ መጡ፤ +25 በጴርጌ ቃሉን ካወጁ በኋላ ወደ አታሊያ ወረዱ። +26 ከዚያም ተነስተው በመርከብ ወደ አንጾኪያ ሄዱ፤ ጳውሎስና በርናባስ አሁን ያጠናቀቁትን ሥራ እንዲያከናውኑ ለአምላክ ጸጋ በአደራ የተሰጡት በአንጾኪያ ነበር።+ +27 እዚያም ደርሰው ጉባኤውን ከሰበሰቡ በኋላ አምላክ በእነሱ አማካኝነት ያከናወናቸውን በርካታ ነገሮች እንዲሁም ለአሕዛብ የእምነትን በር እንደከፈተላቸው ተረኩላቸው።+ +28 በዚያም ከደቀ መዛሙ��ቱ ጋር ረዘም ያለ ጊዜ አሳለፉ። +9 ሳኦል ግን አሁንም በጌታ ደቀ መዛሙርት ላይ በመዛትና እነሱን ለመግደል ቆርጦ በመነሳት+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤ +2 የጌታን መንገድ የሚከተሉትን+ በዚያ የሚያገኛቸውን ወንዶችና ሴቶች ሁሉ አስሮ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደማስቆ ለሚገኙ ምኩራቦች ደብዳቤ እንዲጽፍለት ጠየቀው። +3 እየተጓዘም ሳለ ወደ ደማስቆ ሲቃረብ ድንገት ከሰማይ የመጣ ብርሃን በዙሪያው አንጸባረቀ፤+ +4 እሱም መሬት ላይ ወደቀ፤ ከዚያም “ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ። +5 ሳኦልም “ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም እንዲህ አለው፦ “እኔ አንተ የምታሳድደኝ+ ኢየሱስ ነኝ።+ +6 አሁን ተነስተህ ወደ ከተማዋ ግባ፤ ምን ማድረግ እንዳለብህም ይነገርሃል።” +7 አብረው እየተጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምፅ የሰሙ ቢሆንም ማንንም ባለማየታቸው የሚናገሩት ጠፍቷቸው ዝም ብለው ቆሙ።+ +8 ሳኦልም ከወደቀበት ተነሳ፤ ዓይኖቹ ቢገለጡም ምንም ነገር ማየት አልቻለም። በመሆኑም እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ ወሰዱት። +9 ለሦስት ቀንም ምንም ሳያይ+ እንዲሁም ሳይበላና ሳይጠጣ ቆየ። +10 በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤+ ጌታም በራእይ “ሐናንያ!” አለው። እሱም “ጌታ ሆይ፣ እነሆኝ” አለ። +11 ጌታም እንዲህ አለው፦ “ተነስተህ ‘ቀጥተኛ’ ወደተባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳም ቤት ሳኦል የሚባለውን የጠርሴስ ሰው+ ፈልግ። እሱም አሁን እየጸለየ ነው፤ +12 ሐናንያ የሚባል ሰው እንደሚመጣና ዓይኑ ይበራለት ዘንድ እጁን እንደሚጭንበት በራእይ አይቷል።”+ +13 ሐናንያ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ፣ ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ባሉ ቅዱሳን አገልጋዮችህ ላይ ምን ያህል ጉዳት እንዳደረሰ ከብዙዎች ሰምቻለሁ። +14 ወደዚህ ስፍራ የመጣው ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተሰጥቶት ነው።”+ +15 ጌታ ግን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሰው በአሕዛብ እንዲሁም በነገሥታትና በእስራኤል ልጆች ፊት ስሜን እንዲሸከም+ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ+ ስለሆነ ወደ እሱ ሂድ። +16 እኔም ስለ ስሜ ሲል ምን ያህል መከራ መቀበል እንዳለበት በግልጽ አሳየዋለሁ።”+ +17 ስለዚህ ሐናንያ ሄደ፤ ወደተባለውም ቤት ገባ፤ እጁንም በላዩ ጭኖ እንዲህ አለው፦ “ወንድሜ ሳኦል፣ ወደዚህ ስትመጣ መንገድ ላይ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ የዓይንህ ብርሃን እንዲመለስልህና በመንፈስ ቅዱስ እንድትሞላ እኔን ልኮኛል።”+ +18 ወዲያውም ከዓይኖቹ ላይ ቅርፊት የሚመስሉ ነገሮች ወደቁ፤ እሱም እንደገና ማየት ቻለ። ከዚያም ተነስቶ ተጠመቀ፤ +19 እንዲሁም ምግብ በልቶ ብርታት አገኘ። በደማስቆ ካሉ ደቀ መዛሙርት ጋር የተወሰኑ ቀናት ቆየ፤+ +20 ወዲያውም ስለ ኢየሱስ እሱ የአምላክ ልጅ እንደሆነ በምኩራቦቹ ውስጥ መስበክ ጀመረ። +21 የሰሙት ሁሉ ግን እጅግ በመደነቅ እንዲህ ይሉ ነበር፦ “ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሲያጠፋ የነበረው አይደለም?+ ወደዚህስ የመጣው እነሱን እያሰረ ለካህናት አለቆች ለማስረከብ አልነበረም?”+ +22 ሳኦል ግን ይበልጥ እየበረታ ሄደ፤ በደማስቆ የሚኖሩ አይሁዶችን ኢየሱስ እሱ ክርስቶስ እንደሆነ አሳማኝ ማስረጃ እያቀረበ አፋቸውን ያስይዛቸው ነበር።+ +23 በርካታ ቀናት ካለፉ በኋላ አይሁዳውያን እሱን ለመግደል አሴሩ።+ +24 ይሁን እንጂ ሳኦል ሴራቸውን አወቀ። እነሱም ሊገድሉት ስለፈለጉ ቀን ከሌት የከተማዋን በሮች ነቅተው ይጠብቁ ነበር። +25 ስለዚህ የእሱ ደቀ መዛሙርት ሳኦልን ወስደው በሌሊት በከተማዋ ቅጥር ላይ ባለ መስኮት በማሾለክ በቅርጫት አወረዱት።+ +26 ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ+ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመቀላቀል ጥረት ���ደረገ፤ እነሱ ግን ደቀ መዝሙር መሆኑን ስላላመኑ ሁሉም ፈሩት። +27 ስለዚህ በርናባስ+ ረዳው፤ ሳኦልንም ወደ ሐዋርያት ወስዶ በመንገድ ላይ ጌታን እንዴት እንዳየውና+ እሱም እንዴት እንዳናገረው እንዲሁም በደማስቆ በኢየሱስ ስም እንዴት በድፍረት እንደተናገረ በዝርዝር ነገራቸው።+ +28 እሱም በኢየሩሳሌም በነፃነት እየተንቀሳቀሰና በጌታ ስም በድፍረት እየተናገረ አብሯቸው ቆየ። +29 ግሪክኛ ተናጋሪ ከሆኑ አይሁዳውያን ጋር ይነጋገርና ይከራከር ነበር፤ እነሱ ግን ሊገድሉት ሞከሩ።+ +30 ወንድሞች ይህን ሲያውቁ ወደ ቂሳርያ ይዘውት ወረዱ፤ ከዚያም ወደ ጠርሴስ ላኩት።+ +31 በዚያ ወቅት በይሁዳ፣ በገሊላና በሰማርያ ያለው ጉባኤ+ ሁሉ ሰላም አገኘ፤ በእምነትም እየጠነከረ ሄደ፤ መላው ጉባኤ ይሖዋን* በመፍራትና መንፈስ ቅዱስ ከሚሰጠው ማጽናኛ+ ጋር በመስማማት ይኖር ስለነበር በቁጥር እየበዛ ሄደ። +32 ጴጥሮስም በየቦታው እየተዘዋወረ በነበረበት ወቅት በልዳ ወደሚኖሩት ቅዱሳን ደግሞ ወረደ።+ +33 በዚያም ሽባ በመሆኑ የተነሳ ለስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኛ የሆነ ኤንያስ የተባለ አንድ ሰው አገኘ። +34 ጴጥሮስም “ኤንያስ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል።+ ተነሳና አልጋህን አንጥፍ” አለው።+ እሱም ወዲያውኑ ተነሳ። +35 በልዳ እና በሳሮን ሜዳ የሚኖሩ ሁሉ እሱን አይተው በጌታ አመኑ። +36 በኢዮጴ ጣቢታ የምትባል አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟም ትርጉም “ዶርቃ”* ማለት ነው። እሷም መልካም በማድረግና ምጽዋት በመስጠት የምትታወቅ ነበረች። +37 በዚያን ጊዜም ታማ ሞተች። ሰዎችም አጠቧትና በደርብ ላይ በሚገኘው ክፍል ውስጥ አስቀመጧት። +38 ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለነበረች ደቀ መዛሙርቱ ጴጥሮስ በዚያች ከተማ እንዳለ ሲሰሙ “እባክህ ፈጥነህ ወደ እኛ ና” ብለው እንዲለምኑት ሁለት ሰዎች ወደ እሱ ላኩ። +39 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ተነስቶ አብሯቸው ሄደ። እዚያም ሲደርስ ደርብ ላይ ወደሚገኘው ክፍል ይዘውት ወጡ፤ መበለቶቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው እያለቀሱ ዶርቃ ከእነሱ ጋር በነበረችበት ጊዜ የሠራቻቸውን በርካታ ልብሶችና ቀሚሶች* ያሳዩት ነበር። +40 ጴጥሮስም ሁሉም እንዲወጡ ካደረገ በኋላ+ ተንበርክኮ ጸለየ። ከዚያም ወደ አስከሬኑ ዞር ብሎ “ጣቢታ፣ ተነሽ!” አለ። እሷም ዓይኖቿን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች።+ +41 እሱም እጇን ይዞ አስነሳት፤ ቅዱሳኑንና መበለቶቹንም ጠርቶ ሕያው መሆኗን አሳያቸው።+ +42 ይህ ነገር በመላው ኢዮጴ ታወቀ፤ ብዙዎችም በጌታ አመኑ።+ +43 ጴጥሮስም በኢዮጴ ስምዖን በተባለ አንድ ቆዳ ፋቂ ቤት ለበርካታ ቀናት ተቀመጠ።+ +27 እኛም በመርከብ ወደ ጣሊያን እንድንሄድ ስለተወሰነ+ ጳውሎስንና የተወሰኑ እስረኞችን የአውግስጦስ ክፍለ ጦር አባል ለሆነ ዩልዮስ ለሚባል አንድ የጦር መኮንን አስረከቧቸው። +2 ከአድራሚጢስ ተነስቶ በእስያ አውራጃ የባሕር ዳርቻ ላይ ወደሚገኙት ወደቦች ሊሄድ በተዘጋጀ መርከብ ተሳፍረን ጉዞ ጀመርን፤ በተሰሎንቄ የሚኖረው የመቄዶንያው አርስጥሮኮስም+ አብሮን ነበር። +3 በማግስቱ ሲዶና ደረስን፤ ዩልዮስም ለጳውሎስ ደግነት* በማሳየት ወደ ወዳጆቹ እንዲሄድና እንክብካቤ እንዲያደርጉለት ፈቀደለት። +4 ከዚያም ተነስተን በባሕር ላይ ጉዟችንን ቀጠልን፤ ነፋሱ ከፊት ለፊታችን ይነፍስ ስለነበር ቆጵሮስን ተገን አድርገን አለፍን። +5 ከዚያም በኪልቅያና በጵንፍልያ ዳርቻ በኩል ያለውን ባሕር አቋርጠን በሊቂያ ወደሚገኘው የሚራ ወደብ ደረስን። +6 በዚያም መኮንኑ ወደ ጣሊያን የሚሄድ ከእስክንድርያ የመጣ መርከብ አግኝቶ አሳፈረን። +7 ከዚያም ለብዙ ቀናት በዝግታ ተጉዘን በስንት ችግር ቀኒዶስ ደረስን። ነፋ��� እንደ ልብ እንድንጓዝ ስላልፈቀደልን በስልሞና በኩል ቀርጤስን ተገን አድርገን አለፍን። +8 የባሕሩን ዳርቻ ይዘን በብዙ ችግር በመጓዝ በላሲያ ከተማ አቅራቢያ ወዳለው “መልካም ወደብ” ወደተባለ ስፍራ ደረስን። +9 ረጅም ጊዜ በመቆየታችንና የስርየት ቀን+ ጾም እንኳ ሳይቀር በማለፉ፣ ወቅቱ በባሕር ላይ ለመጓዝ አደገኛ ነበር፤ በመሆኑም ጳውሎስ አንድ ሐሳብ አቀረበ፤ +10 እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ሰዎች፣ ይህ ጉዞ በጭነቱና በመርከቡ ላይ ብቻ ሳይሆን በሕይወታችንም* ላይ እንኳ ሳይቀር ከፍተኛ ጉዳትና ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል ይታየኛል።” +11 ይሁን እንጂ መኮንኑ ጳውሎስ የተናገረውን ከመቀበል ይልቅ የመርከቡ መሪና የመርከቡ ባለቤት የተናገሩትን ሰማ። +12 ወደቡ የክረምቱን ጊዜ በዚያ ለማሳለፍ አመቺ ስላልነበረ አብዛኞቹ ከዚያ ተነስተው ጉዟቸውን በመቀጠል እንደ ምንም ፊንቄ ወደተባለው የቀርጤስ ወደብ ደርሰው ክረምቱን እዚያ ለማሳለፍ ሐሳብ አቀረቡ፤ ይህ ወደብ ወደ ሰሜን ምሥራቅም ሆነ ወደ ደቡብ ምሥራቅ ለመሄድ የሚያስችል ነበር። +13 የደቡብ ነፋስ በቀስታ እየነፈሰ እንዳለ ባዩ ጊዜ እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሏቸው መልሕቁን ነቅለው የቀርጤስን የባሕር ዳርቻ ይዘው መጓዝ ጀመሩ። +14 ይሁንና ብዙም ሳይቆይ አውራቂስ* የሚባል ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ከደሴቲቱ ቁልቁል ነፈሰ። +15 መርከቡ እንቅስቃሴው ስለተገታና ነፋሱን ሰንጥቆ መሄድ ስላልቻለ ዝም ብለን በነፋሱ እየተነዳን ሄድን። +16 ከዚያም ቄዳ የተባለችውን ትንሽ ደሴት ተገን አድርገን በፍጥነት ተጓዝን፤ ሆኖም በመርከቡ ኋለኛ ክፍል የነበረችውን ትንሿን ጀልባ* መቆጣጠር የቻልነው በብዙ ችግር ነበር። +17 ጀልባዋ ወደ ላይ ተጎትታ ከተጫነች በኋላ መርከቡን ዙሪያውን በማሰር አጠናከሩት፤ ከስርቲስ* አሸዋማ ደለል ጋር እንዳይላተሙ ስለፈሩም የሸራውን ገመዶች በመፍታት ሸራውን ዝቅ ካደረጉ በኋላ በነፋስ እየተነዱ ሄዱ። +18 አውሎ ነፋሱ ክፉኛ እያንገላታን ስለነበር በማግስቱ የመርከቡን ጭነት ያቃልሉ ጀመር። +19 በሦስተኛውም ቀን ለመርከቡ የሚያገለግሉትን ቁሳቁሶች በገዛ እጃቸው ወደ ባሕሩ ወረወሩ። +20 ለብዙ ቀናት ፀሐይንም ሆነ ከዋክብትን ማየት ስላልቻልንና ውሽንፍሩ ስለበረታብን በመጨረሻ በሕይወት የመትረፍ ተስፋችን እየተሟጠጠ ሄደ። +21 ሰዎቹ እህል ሳይቀምሱ ብዙ ቀን ከቆዩ በኋላ ጳውሎስ በመካከላቸው ቆሞ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሰዎች፣ ምክሬን ሰምታችሁ ቢሆን ኖሮ ከቀርጤስ ባልተነሳችሁና ይህ ጉዳትና ኪሳራ ባልደረሰ ነበር።+ +22 አሁንም ቢሆን አይዟችሁ! ምክንያቱም መርከቡ ብቻ እንጂ ከእናንተ አንድም ሰው* አይጠፋም። +23 ቅዱስ አገልግሎት የማቀርብለትና ንብረቱ የሆንኩለት አምላክ የላከው መልአክ+ ትናንት ሌሊት አጠገቤ ቆሞ +24 ‘ጳውሎስ ሆይ፣ አትፍራ። ቄሳር ፊት መቅረብ ይገባሃል፤+ አምላክ ለአንተ ሲል ከአንተ ጋር የሚጓዙት ሰዎች ሁሉ እንዲተርፉ ያደርጋል’ ብሎኛል። +25 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ አይዟችሁ! ምክንያቱም ይህ የተነገረኝ ነገር በትክክል እንደሚፈጸም በአምላክ ላይ እምነት አለኝ። +26 ይሁን እንጂ ከአንዲት ደሴት ዳርቻ ጋር መላተማችን የግድ ነው።”+ +27 በ14ኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር ላይ ወዲያና ወዲህ እየተንገላታን ሳለ እኩለ ሌሊት ላይ መርከበኞቹ ወደ አንድ የብስ የተቃረቡ መሰላቸው። +28 ጥልቀቱንም ሲለኩ 36 ሜትር ገደማ* ሆኖ አገኙት፤ ጥቂት ርቀት ከተጓዙም በኋላ በድጋሚ ሲለኩ 27 ሜትር ገደማ* ሆኖ አገኙት። +29 ከዓለት ጋር እንላተማለን ብለው ስለፈሩ ከመርከቡ የኋለኛ ክፍል አራት መልሕቆች ጥለው የሚነጋበትን ጊዜ በጉጉት መጠባበቅ ጀመሩ። +30 ሆኖም መርከበኞቹ ከመርከቡ የፊተኛ ክፍል መልሕቅ የሚጥሉ አስመስለው ትንሿን ጀልባ ወደ ባሕር በማውረድ ከመርከቡ ለማምለጥ ሲሞክሩ +31 ጳውሎስ መኮንኑንና ወታደሮቹን “እነዚህ ሰዎች መርከቡን ጥለው ከሄዱ ልትድኑ አትችሉም” አላቸው።+ +32 በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ የትንሿን ጀልባ ገመዶች ቆርጠው ብቻዋን ተንሳፋ እንድትቀር አደረጓት። +33 ሊነጋ ሲል ጳውሎስ እንዲህ በማለት ምግብ እንዲቀምሱ ሁሉንም አበረታታቸው፦ “እህል የሚባል ነገር ሳትቀምሱ እንዲሁ ልባችሁ ተንጠልጥሎ ስትጠባበቁ ይኸው ዛሬ 14ኛ ቀናችሁ ነው። +34 ስለዚህ ለራሳችሁ ደህንነት ስለሚበጅ እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋለሁ፤ ምክንያቱም ከእናንተ መካከል ከራስ ፀጉሩ አንድ እንኳ የሚጠፋበት የለም።” +35 ይህን ካለ በኋላ ዳቦ ወስዶ በሁሉ ፊት አምላክን አመሰገነ፤ ቆርሶም ይበላ ጀመር። +36 በዚህ ጊዜ ሁሉም ተበረታተው ምግብ እየወሰዱ ይበሉ ጀመር። +37 መርከቡ ላይ በአጠቃላይ 276 ሰዎች* ነበርን። +38 በልተው ከጠገቡ በኋላ ስንዴውን ወደ ባሕሩ በመጣል የመርከቡን ጭነት አቃለሉ።+ +39 ሲነጋም የደረሱበትን አገር ለይተው ማወቅ አልቻሉም፤+ ሆኖም አሸዋማ የሆነ የባሕር ወሽመጥ ተመለከቱ፤ ስለዚህ እንደ ምንም ብለው መርከቡን ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለማድረስ ወሰኑ። +40 በመሆኑም መልሕቆቹን ቆርጠው ባሕሩ ውስጥ ጣሉ፤ በዚያው ጊዜም የመቅዘፊያዎቹን ገመዶች ፈቱ፤ የፊተኛውንም ሸራ ነፋስ እንዲያገኘው ከፍ ካደረጉ በኋላ ወደ ባሕሩ ዳርቻ አመሩ። +41 ሆኖም ድንገት በባሕር ውስጥ ካለ የአሸዋ ቁልል ጋር ተላተሙ፤ በዚህ ጊዜ መርከቡ መሬት ስለነካ የፊተኛው ክፍሉ ሊንቀሳቀስ በማይችል ሁኔታ አሸዋው ውስጥ ተቀረቀረ፤ የመርከቡ የኋለኛ ክፍል ግን በማዕበል እየተመታ ይሰባበር ጀመር።+ +42 በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ ከእስረኞቹ አንዳቸውም እንኳ ዋኝተው እንዳያመልጡ ሊገድሏቸው ወሰኑ። +43 መኮንኑ ግን ጳውሎስን ለማዳን ቆርጦ ስለነበር ያሰቡትን እንዳይፈጽሙ ከለከላቸው። ከዚያም መዋኘት የሚችሉ ወደ ባሕሩ እየዘለሉ እንዲገቡና ቀድመው ወደ የብስ እንዲደርሱ አዘዘ፤ +44 የቀሩትም ሰዎች አንዳንዶቹ በሳንቃዎች፣ ሌሎቹ ደግሞ በመርከቡ ስብርባሪዎች ላይ እየተንጠላጠሉ እንዲወጡ አዘዘ። በዚህ መንገድ ሁሉም በደህና ወደ የብስ ደረሱ።+ +13 በአንጾኪያ ባለው ጉባኤ ውስጥ ነቢያትና አስተማሪዎች ነበሩ፤+ እነሱም፦ በርናባስ፣ ኒጌር ማለትም ጥቁር ተብሎ የሚጠራው ሲምዖን፣ የቀሬናው ሉክዮስ፣ የአውራጃ ገዢ ከሆነው ከሄሮድስ ጋር የተማረው ምናሔና ሳኦል ናቸው። +2 እነዚህ ይሖዋን* እያገለገሉና* እየጾሙ ሳሉ መንፈስ ቅዱስ “በርናባስንና ሳኦልን አንድ ሥራ እንዲሠሩ ስለመረጥኳቸው ለዩልኝ”+ አለ። +3 እነሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ ከዚያም አሰናበቷቸው። +4 ሰዎቹም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዙ። +5 ስልማና በደረሱ ጊዜም የአምላክን ቃል በአይሁዳውያን ምኩራቦች ማወጅ ጀመሩ። ዮሐንስም እንደ አገልጋይ ሆኖ ይረዳቸው ነበር።+ +6 ደሴቲቱን ከዳር እስከ ዳር አዳርሰው እስከ ጳፎስ ተጓዙ፤ በዚህ ጊዜ በርያሱስ የተባለ ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ የነበረ አንድ አይሁዳዊ አገኙ። +7 እሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አስተዋይ የሮም አገረ ገዢ* ጋር ነበር። ይህ አገረ ገዢ የአምላክን ቃል ለመስማት ስለጓጓ በርናባስንና ሳኦልን ጠራቸው። +8 ይሁን እንጂ ጠንቋዩ ኤልማስ* አገረ ገዢው ይህን እምነት እንዳይቀበል ለማከላከል ፈልጎ ይቃወማቸው ጀመር። (ኤልማስ የተባለው ስም ትርጉም ጠንቋይ ማለት ነው።) +9 በዚህ ጊዜ፣ ጳውሎስ ተብሎ የሚጠራው ሳኦል በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ትኩር ብሎ ተመለከተው፤ +10 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “አንተ ተንኮልና ክፋት ሁሉ የሞላብህ፣ የዲያብሎስ ልጅ፣+ የጽድቅም ሁሉ ጠላት! ቀና የሆነውን የይሖዋን* መንገድ ማጣመምህን አትተውም? +11 እነሆ፣ የይሖዋ* እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዓይነ ስውር ትሆናለህ፤ ለተወሰነ ጊዜም የፀሐይ ብርሃን አታይም።” ወዲያውኑም ጭጋግና ጨለማ ዓይኑን ጋረደው፤ እጁን ይዞ የሚመራው ሰው ለማግኘትም ዙሪያውን መፈለግ ጀመረ። +12 አገረ ገዢውም ስለ ይሖዋ* በተማረው ነገር ተደንቆ ስለነበር ይህን ባየ ጊዜ አማኝ ሆነ። +13 ጳውሎስና ባልደረቦቹ ከጳፎስ ተነስተው በባሕር ላይ በመጓዝ ጵንፍልያ ውስጥ ወዳለችው ወደ ጴርጌ ሄዱ። ዮሐንስ+ ግን ከእነሱ ተለይቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።+ +14 እነሱ ግን ጉዟቸውን በመቀጠል ከጴርጌ ተነስተው በጵስድያ ወደምትገኘው ወደ አንጾኪያ መጡ። በሰንበት ቀንም ወደ ምኩራብ ገብተው+ ተቀመጡ። +15 የሕጉና የነቢያት መጻሕፍት በሕዝቡ ፊት ከተነበበ+ በኋላ የምኩራቡ አለቆች “ወንድሞች ሆይ፣ ሕዝቡን የሚያበረታታ የምትናገሩት ቃል ካላችሁ ተናገሩ” የሚል መልእክት ላኩባቸው። +16 ስለዚህ ጳውሎስ ተነስቶ በእጁ ምልክት በመስጠት እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሰዎችም ሆናችሁ አምላክን የምትፈሩ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፣ ስሙ። +17 የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መረጠ፤ በግብፅ ምድር ባዕዳን ሆነው ይኖሩ በነበረበት ጊዜም ሕዝቡን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ በኃያል ክንዱም ከዚያ አወጣቸው።+ +18 ለ40 ዓመት ያህልም በምድረ በዳ ታገሣቸው።+ +19 በከነአን ምድር የነበሩትን ሰባት ብሔራት ካጠፋ በኋላ ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሰጣቸው።+ +20 ይህ ሁሉ የሆነው በ450 ዓመት ያህል ጊዜ ውስጥ ነው። “ይህ ከሆነ በኋላ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ድረስ መሳፍንትን ሰጣቸው።+ +21 ከዚያ በኋላ ግን ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ጠየቁ፤+ አምላክም ከቢንያም ነገድ የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን+ ለ40 ዓመት አነገሠላቸው። +22 እሱን ከሻረው በኋላ ‘እንደ ልቤ የሆነውን+ የእሴይን+ ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤ እሱ የምፈልገውን ነገር ሁሉ ያደርጋል’ ሲል የመሠከረለትን ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ አስነሳላቸው።+ +23 አምላክ በገባው ቃል መሠረት ከዚህ ሰው ዘር ለእስራኤል አዳኝ የሆነውን ኢየሱስን አመጣ።+ +24 ዮሐንስ፣ ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት በይፋ ሰብኮ ነበር።+ +25 ይሁንና ዮሐንስ ተልእኮውን በማጠናቀቅ ላይ ሳለ ‘እኔ ማን እመስላችኋለሁ? እኔ እኮ እሱ አይደለሁም። ይሁን እንጂ ከእኔ በኋላ ሌላ ይመጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ ለመፍታት እንኳ አልበቃም’ ይል ነበር።+ +26 “ወንድሞች፣ እናንተ ከአብርሃም ዘር የተወለዳችሁ እንዲሁም በመካከላችሁ ያሉ አምላክን የሚፈሩ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፣ ይህ የመዳን ቃል ለእኛ ተልኳል።+ +27 የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና የሃይማኖት መሪዎቻቸው* የእሱን ማንነት አልተገነዘቡም፤ በእሱ ላይ በፈረዱበት ጊዜ ግን በየሰንበቱ ከፍ ባለ ድምፅ የሚነበበውን ነቢያት የተናገሩትን ቃል ፈጸሙ።+ +28 ለሞት የሚያበቃ አንድም ምክንያት ባያገኙበትም እንኳ+ ያስገድለው ዘንድ ጲላጦስን ወተወቱት።+ +29 ስለ እሱ የተጻፈውን ነገር ሁሉ ከፈጸሙ በኋላም ከእንጨት* ላይ አውርደው መቃብር ውስጥ አኖሩት።+ +30 ሆኖም አምላክ ከሞት አስነሳው፤+ +31 እሱም ከገሊላ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ አብረውት ለሄዱት ሰዎች ለብዙ ቀናት ታያቸው። እነሱም አሁን ስለ እሱ ለሕዝቡ እየመሠከሩ ነው።+ +32 “ስለሆነም እኛ ለአባቶቻችን ስለተገባው ቃል የሚገልጸውን ምሥራች እያወጅንላችሁ ነው። +33 አምላክ ኢየሱስን ከሞት በማስነሳት+ ለእነሱ የገባውን ቃል ለእኛ ለልጆቻቸው ሙሉ በሙሉ ፈጽሞታል፤ ይህም የሆነው በሁለተኛው መዝሙር ላይ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ’ ተብሎ በተጻፈው መሠረት ነው።+ +34 አምላክ ኢየሱስን የማይበሰብስ አካል ሰጥቶ ከሞት አስነስቶታል፤ ይህን አስቀድሞ በትንቢት ሲናገር ‘ለዳዊት ቃል የተገባውን የማይከስም * ታማኝ ፍቅር አሳያችኋለሁ’ ብሏል።+ +35 ስለዚህ በሌላም መዝሙር ላይ ‘ታማኝ አገልጋይህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ ብሏል።+ +36 በአንድ በኩል፣ ዳዊት በሕይወት ዘመኑ አምላክን ካገለገለ* በኋላ በሞት አንቀላፍቷል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮ መበስበስን አይቷል።+ +37 በሌላ በኩል ግን አምላክ ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ መበስበስን አላየም።+ +38 “ስለዚህ ወንድሞች፣ በእሱ በኩል የሚገኘው የኃጢአት ይቅርታ አሁን እየታወጀላችሁ እንዳለ እወቁ፤+ +39 በኢየሱስ የሚያምን ማንኛውም ሰው፣ በእሱ አማካኝነት ‘ከበደል ነፃ ነህ’ ሊባል ይችላል፤+ የሙሴ ሕግ ግን እናንተን ከበደል ነፃ ሊያደርጋችሁ አልቻለም።+ +40 ስለዚህ በነቢያት መጻሕፍት እንዲህ ተብሎ የተነገረው ነገር በእናንተ ላይ እንዳይደርስ ተጠንቀቁ፦ +41 ‘እናንተ ፌዘኞች፣ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፤ ጥፉም፤ ማንም በዝርዝር ቢነግራችሁ እንኳ ፈጽሞ የማታምኑትን ሥራ በእናንተ ዘመን እያከናወንኩ ነውና።’”+ +42 እየወጡ ሳሉም ሰዎቹ ስለዚሁ ጉዳይ በሚቀጥለው ሰንበትም እንዲነግሯቸው ለመኗቸው። +43 በምኩራቡ የተደረገው ስብሰባ ከተበተነ በኋላ ከአይሁዳውያንና ወደ ይሁዲነት ተለውጠው አምላክን ከሚያመልኩት መካከል ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሏቸው፤ እነሱም ሰዎቹን በማነጋገር የአምላክን ጸጋ አጥብቀው እንደያዙ እንዲቀጥሉ አሳሰቧቸው።+ +44 በቀጣዩ ሰንበት የከተማዋ ሕዝብ ሁሉ ማለት ይቻላል፣ የይሖዋን* ቃል ለመስማት አንድ ላይ ተሰበሰበ። +45 አይሁዳውያንም ሕዝቡን ባዩ ጊዜ በቅናት ተሞልተው ጳውሎስ የተናገረውን ቃል በመቃወም ይሳደቡ ጀመር።+ +46 በዚህ ጊዜ ጳውሎስና በርናባስ በድፍረት እንዲህ አሏቸው፦ “የአምላክ ቃል በመጀመሪያ ለእናንተ መነገሩ አስፈላጊ ነበር።+ እናንተ ግን ወደ ጎን ገሸሽ እያደረጋችሁትና የዘላለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ላይ እየፈረዳችሁ ስለሆነ እኛም ለአሕዛብ እንሰብካለን።+ +47 ይሖዋ* ‘እስከ ምድር ዳር ድረስ መዳንን እንድታመጣ ለብሔራት ብርሃን አድርጌ ሾሜሃለሁ’ በማለት ትእዛዝ ሰጥቶናልና።”+ +48 ከአሕዛብ ወገን የሆኑት ይህን ሲሰሙ እጅግ በመደሰት የይሖዋን* ቃል አከበሩ፤ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ያላቸው ሁሉ አማኞች ሆኑ። +49 ከዚህም በተጨማሪ የይሖዋ* ቃል በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ እየተስፋፋ ሄደ። +50 ይሁንና አይሁዳውያን ፈሪሃ አምላክ ያላቸውን የተከበሩ ሴቶችና በከተማዋ የሚኖሩትን ታላላቅ ወንዶች በመቀስቀስ በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ስደት አስነሱ፤+ ከክልላቸውም አስወጧቸው። +51 እነሱም የእግራቸውን አቧራ አራግፈው* ወደ ኢቆንዮን ሄዱ።+ +52 ደቀ መዛሙርቱም በደስታና+ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። +5 ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው ከሚስቱ ከሰጲራ ጋር መሬት ሸጠ። +2 ይሁንና ከገንዘቡ የተወሰነውን ደብቆ አስቀረ፤ ሚስቱም ይህን ታውቅ ነበር፤ የቀረውንም አምጥቶ ለሐዋርያት አስረከበ።+ +3 ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለ፦ “ሐናንያ፣ ሰይጣን መንፈስ ቅዱስን እንድትዋሽና+ ከመሬቱ ሽያጭ የተወሰነውን ደብቀህ እንድታስቀር ያደፋፈረህ ለምንድን ነው? +4 ሳትሸጠው በፊት ያንተው አልነበረም? ከሸጥከውስ በኋላ ገንዘቡን የፈለግከውን ልታደርግበት ትችል አልነበረም? እንዲህ ያለ ድርጊት ለመፈጸም በልብህ ለምን አሰብክ? የዋሸኸው ሰውን ሳይሆን አምላክን ነው።” +5 ሐናን�� ይህን ቃል ሲሰማ ወደቀና ሞተ። ይህን የሰሙ ሁሉ እጅግ ፈሩ። +6 ወጣት ወንዶችም ተነስተው በጨርቅ ከጠቀለሉት በኋላ ተሸክመው አውጥተው ቀበሩት። +7 ይህ ከሆነ ከሦስት ሰዓት ገደማ በኋላ ደግሞ የተፈጸመውን ነገር ያላወቀችው ሚስቱ መጣች። +8 ጴጥሮስም “እስቲ ንገሪኝ፣ መሬቱን የሸጣችሁት በዚህ ዋጋ ነው?” አላት። እሷም “አዎ፣ በዚሁ ዋጋ ነው” አለች። +9 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ሁለታችሁ የይሖዋን* መንፈስ ለመፈተን የተስማማችሁት ለምንድን ነው? እነሆ፣ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር ደጃፍ ላይ ነው፤ እነሱም ተሸክመው ያወጡሻል” አላት። +10 ወዲያውም እግሩ ሥር ወድቃ ሞተች። ወጣቶቹ ሲገቡም ሞታ አገኟት፤ ተሸክመው አውጥተውም ከባሏ አጠገብ ቀበሯት። +11 በመሆኑም መላው ጉባኤ እንዲሁም ይህን የሰሙ ሰዎች ሁሉ በከፍተኛ ፍርሃት ተዋጡ። +12 በተጨማሪም ሐዋርያት በሕዝቡ መካከል ብዙ ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች መፈጸማቸውን ቀጥለው ነበር፤+ ሁሉም አንድ ላይ ሆነው መጠለያ ባለው “የሰለሞን መተላለፊያ”+ ይሰበሰቡ ነበር። +13 እርግጥ ከሌሎቹ መካከል ከእነሱ ጋር ሊቀላቀል የደፈረ አንድም ሰው አልነበረም፤ ሆኖም ሕዝቡ ያሞግሳቸው ነበር። +14 ከዚህም በላይ በጌታ ያመኑ እጅግ በርካታ ወንዶችና ሴቶች በየጊዜው በእነሱ ላይ ይጨመሩ ነበር።+ +15 ደግሞም ጴጥሮስ በዚያ ሲያልፍ በአንዳንዶቹ ላይ ቢያንስ ጥላው ቢያርፍባቸው በማለት ሕመምተኞችን አውራ ጎዳናዎች ላይ አውጥተው በትናንሽ አልጋዎችና በምንጣፎች ላይ ያስተኟቸው ነበር።+ +16 በተጨማሪም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ ከተሞች ብዙ ሰዎች ሕመምተኞችንና በርኩሳን መናፍስት የሚሠቃዩ ሰዎችን ተሸክመው መምጣታቸውን ቀጠሉ፤ የመጡትም ሁሉ ይፈወሱ ነበር። +17 ይሁንና ሊቀ ካህናቱና አብረውት የነበሩት የሰዱቃውያን ሃይማኖታዊ ቡድን አባላት ሁሉ በቅናት ተሞልተው ተነሱ። +18 ሐዋርያትንም ይዘው እስር ቤት ከተቷቸው።+ +19 ይሁን እንጂ ሌሊት የይሖዋ* መልአክ የእስር ቤቱን በሮች ከፍቶ+ አወጣቸውና እንዲህ አላቸው፦ +20 “ሂዱና በቤተ መቅደሱ ቆማችሁ ስለዚህ ሕይወት የሚገልጸውን ቃል ሁሉ ለሕዝቡ መናገራችሁን ቀጥሉ።” +21 እነሱም በተነገራቸው መሠረት ንጋት ላይ ወደ ቤተ መቅደሱ ገብተው ያስተምሩ ጀመር። ሊቀ ካህናቱና ከእሱ ጋር የነበሩት በመጡ ጊዜም የሳንሄድሪንን ሸንጎና መላውን የእስራኤል ልጆች ሽማግሌዎች ጉባኤ በአንድነት ሰበሰቡ፤ ሐዋርያቱንም ወደ እነሱ እንዲያመጧቸው ሰዎችን ወደ እስር ቤቱ ላኩ። +22 የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች እዚያ በደረሱ ጊዜ ግን እስር ቤቱ ውስጥ አላገኟቸውም። ስለዚህ ተመልሰው መጥተው ነገሯቸው፤ +23 እንዲህም አሏቸው፦ “እስር ቤቱ በሚገባ ተቆልፎ ጠባቂዎቹም በሮቹ ላይ ቆመው አገኘናቸው፤ በሮቹን ስንከፍት ግን ውስጥ ማንንም አላገኘንም።” +24 የቤተ መቅደሱ ሹምና የካህናት አለቆቹም ይህን ሲሰሙ ‘የዚህ ነገር መጨረሻ ምን ይሆን?’ በማለት በነገሩ ግራ ተጋቡ። +25 በዚህ ጊዜ አንድ ሰው መጥቶ “እስር ቤት ያስገባችኋቸው ሰዎች በቤተ መቅደሱ ቆመው ሕዝቡን እያስተማሩ ነው” ብሎ ነገራቸው። +26 ከዚያም የቤተ መቅደሱ ሹም ከጠባቂዎቹ ጋር ሄዶ አመጣቸው፤ ሆኖም ሕዝቡ በድንጋይ እንዳይወግራቸው ስለፈሩ ያመጧቸው በኃይል አስገድደው አልነበረም።+ +27 አምጥተውም በሳንሄድሪን ሸንጎ ፊት አቆሟቸው። ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ይጠይቃቸው ጀመር፤ +28 እንዲህም አለ፦ “በዚህ ስም ማስተማራችሁን እንድታቆሙ በጥብቅ አዘናችሁ ነበር፤+ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋታል፤ የዚህንም ሰው ደም በእኛ ላይ ለማምጣት ቆርጣችሁ ተነስታችኋል።”+ +29 ጴጥሮስና ሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ከሰው ይልቅ አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል።+ +30 እናንተ በእንጨት* ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሳው።+ +31 እስራኤል ንስሐ እንዲገባና የኃጢአት ይቅርታ እንዲያገኝ+ አምላክ እሱን “ዋና ወኪል”+ እና “አዳኝ”+ አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።+ +32 ለዚህም ጉዳይ እኛ ምሥክሮች ነን፤+ እንዲሁም አምላክ እሱን እንደ ገዢያቸው አድርገው ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ምሥክር ነው።”+ +33 እነሱም ይህን ሲሰሙ እጅግ ተቆጡ፤ ሊገድሏቸውም ፈለጉ። +34 ሆኖም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ የተከበረ፣ የሕግ አስተማሪ የሆነ ገማልያል+ የሚባል አንድ ፈሪሳዊ በሳንሄድሪኑ ሸንጎ መካከል ተነስቶ ሰዎቹን ለጊዜው ወደ ውጭ እንዲያስወጧቸው አዘዘ። +35 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በእነዚህ ሰዎች ላይ ልታደርጉ ያሰባችሁትን ነገር በተመለከተ ልትጠነቀቁ ይገባል። +36 ለምሳሌ ያህል፣ ከዚህ ቀደም ቴዎዳስ ራሱን እንደ ታላቅ ሰው በመቁጠር ተነስቶ ነበር፤ ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎችም ከእሱ ጋር ተባብረው ነበር። ነገር ግን እሱም ተገደለ፤ ተከታዮቹም ሁሉ ተበታትነው እንዳልነበሩ ሆኑ። +37 ከእሱ በኋላ ደግሞ የሕዝብ ቆጠራ በተካሄደበት ወቅት የገሊላው ይሁዳ ተነስቶ ተከታዮች አፍርቶ ነበር። ይሁንና እሱም ጠፋ፤ ተከታዮቹም ሁሉ ተበታተኑ። +38 ስለዚህ አሁን የምላችሁ፣ እነዚህን ሰዎች አትንኳቸው፤ ተዉአቸው። ይህ ውጥን ወይም ይህ ሥራ ከሰው ከሆነ ይጠፋል፤ +39 ከአምላክ ከሆነ ግን ልታጠፏቸው አትችሉም።+ እንዲያውም ከአምላክ ጋር ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል።”+ +40 እነሱም ምክሩን ተቀበሉ፤ ሐዋርያትንም ጠርተው ገረፏቸው፤*+ ከዚያም በኢየሱስ ስም መናገራቸውን እንዲያቆሙ አዘው ለቀቋቸው። +41 እነሱም ስለ ስሙ ውርደት ለመቀበል ብቁ ሆነው በመቆጠራቸው ደስ እያላቸው+ ከሳንሄድሪን ሸንጎ ወጡ። +42 ከዚያም በየቀኑ በቤተ መቅደስም ሆነ ከቤት ወደ ቤት+ እየሄዱ ስለ ክርስቶስ ይኸውም ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን ምሥራች ያለማሰለስ ማስተማራቸውንና ማወጃቸውን ቀጠሉ።+ +21 ከእነሱ በግድ ከተለያየን በኋላ በመርከብ ተሳፍረን በቀጥታ በመጓዝ ቆስ ደረስን፤ በማግስቱ ደግሞ ወደ ሮድስ አመራን፤ ከዚያም ወደ ጳጥራ ሄድን። +2 ወደ ፊንቄ የሚሻገር መርከብ ባገኘን ጊዜ ተሳፍረን ጉዟችንን ቀጠልን። +3 የቆጵሮስ ደሴት በታየችን ጊዜ በስተ ግራ ትተናት ወደ ሶርያ አመራን፤ መርከቡ ጭነቱን በጢሮስ ማራገፍ ስለነበረበት እኛም እዚያ ወረድን። +4 ደቀ መዛሙርቱን ፈልገን ካገኘን በኋላ በዚያ ሰባት ቀን ቆየን። እነሱም በመንፈስ ተመርተው ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ደጋግመው ነገሩት።+ +5 የቆይታ ጊዜያችን ባለቀ ጊዜ ከዚያ ተነስተን ጉዟችንን ጀመርን፤ ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ከከተማዋ እስክንወጣ ድረስ ሸኙን። ከዚያም በባሕሩ ዳርቻ ተንበርክከን ጸለይን፤ +6 በኋላም ተሰነባበትን። ከዚያም እኛ ወደ መርከቡ ገባን፤ እነሱ ደግሞ ወደ ቤታቸው ተመለሱ። +7 ከጢሮስ ተነስተን በመርከብ በመጓዝ ጴጤሌማይስ ደረስን፤ እዚያም ለወንድሞች ሰላምታ ካቀረብን በኋላ አብረናቸው አንድ ቀን ቆየን። +8 በማግስቱ ከዚያ ተነስተን ቂሳርያ ደረስን፤ በዚያም ከሰባቱ ወንዶች አንዱ ወደሆነው ወደ ወንጌላዊው ፊልጶስ+ ቤት ገብተን እሱ ጋ አረፍን። +9 ይህ ሰው ትንቢት የሚናገሩ አራት ያላገቡ* ሴቶች ልጆች ነበሩት።+ +10 ለብዙ ቀናት እዚያ ከተቀመጥን በኋላ አጋቦስ+ የሚባል አንድ ነቢይ ከይሁዳ ወረደ። +11 ወደ እኛም መጥቶ የጳውሎስን ቀበቶ በመውሰድ የራሱን እግርና እጅ ካሰረ በኋላ እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ‘አይሁዳውያን የዚህን ቀበቶ ባለቤት በኢየሩሳሌም እንዲህ አድርገው ያስሩታል፤+ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል።’”+ +12 ይህን ስንሰማ እኛም ሆንን በዚያ የነበሩት ደቀ መዛሙርት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ እንለምነው ጀመር። +13 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “እያለቀሳችሁ ልቤን ለምን ታባባላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም እንኳ ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ።+ +14 እሱን ለማሳመን ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱ “እንግዲህ የይሖዋ* ፈቃድ ይሁን” ብለን ዝም አልን።* +15 ከዚህ በኋላ ለጉዞው ተዘጋጅተን ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ ጀመርን። +16 በቂሳርያ ከሚኖሩት ደቀ መዛሙርት አንዳንዶቹ ወደምናርፍበት ሰው ቤት እኛን ለመውሰድ አብረውን ሄዱ፤ ይህ ሰው ምናሶን የተባለ የቆጵሮስ ሰው ሲሆን ከቀድሞዎቹ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነበር። +17 ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን። +18 በማግስቱም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ሄደ፤+ ሽማግሌዎቹም ሁሉ በዚያ ነበሩ። +19 ሰላምታ ካቀረበላቸውም በኋላ፣ እሱ ባከናወነው አገልግሎት አማካኝነት አምላክ በአሕዛብ መካከል የፈጸማቸውን ነገሮች በዝርዝር ይተርክላቸው ጀመር። +20 እነሱም ይህን ከሰሙ በኋላ አምላክን አመሰገኑ፤ እሱን ግን እንዲህ አሉት፦ “ወንድም፣ ከአይሁዳውያን መካከል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማኞች እንዳሉ ታውቃለህ፤ ደግሞም ሁሉም ለሕጉ ቀናተኞች ናቸው።+ +21 እነሱም አንተ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁዳውያን ሁሉ ልጆቻቸውን እንዳይገርዙም ሆነ የቆየውን ልማድ እንዳይከተሉ በመንገር የሙሴን ሕግ እንዲተዉ ስታስተምር እንደቆየህ ስለ አንተ የሚወራውን ወሬ ሰምተዋል።+ +22 እንግዲህ ምን ማድረግ ይሻላል? መምጣትህን እንደሆነ መስማታቸው አይቀርም። +23 ስለዚህ አሁን የምንነግርህን ነገር አድርግ፦ ስእለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ። +24 እነዚህን ሰዎች ይዘህ በመሄድ ከእነሱ ጋር የመንጻት ሥርዓት ፈጽም፤ ራሳቸውንም እንዲላጩ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ክፈልላቸው። ይህን ካደረግክ በአንተ ላይ የተወራው ሁሉ ከንቱ መሆኑንና አንተም ሕጉን እያከበርክ በሥርዓት እንደምትኖር ሁሉም ሰው ያውቃል።+ +25 ከአሕዛብ የመጡትን አማኞች በተመለከተ ግን ለጣዖት ከተሠዋ፣+ ከደም፣+ ታንቆ ከሞተ* እንስሳ ሥጋና+ ከፆታ ብልግና* እንዲርቁ+ ወስነን ደብዳቤ ጽፈንላቸዋል።” +26 ከዚያም ጳውሎስ በማግስቱ ሰዎቹን ይዞ በመሄድ አብሯቸው የመንጻት ሥርዓቱን ፈጸመ፤+ የመንጻት ሥርዓቱ የሚያበቃበትን ቀንና ለእያንዳንዳቸው መባ የሚቀርብበትን ጊዜ ለማሳወቅም ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ። +27 ሰባቱ ቀናት ሊጠናቀቁ በተቃረቡበት ጊዜ ከእስያ የመጡ አይሁዳውያን ጳውሎስን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያዩት ሕዝቡን ሁሉ ለሁከት በማነሳሳት ያዙት፤ +28 እንዲህ እያሉም ጮኹ፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እርዱን! በሄደበት ቦታ ሁሉ ለሚያገኛቸው ሰዎች ሕዝባችንን፣ ሕጋችንንና ይህን ስፍራ የሚቃወም ትምህርት የሚያስተምረው ይህ ሰው ነው። በዚህ ላይ ደግሞ የግሪክ ሰዎችን ወደ ቤተ መቅደሱ ይዞ በመምጣት ይህን ቅዱስ ስፍራ አርክሷል።”+ +29 ይህን ያሉት ቀደም ሲል የኤፌሶኑን ሰው ጢሮፊሞስን+ ከእሱ ጋር ከተማው ውስጥ አይተውት ስለነበር ነው፤ ደግሞም ጳውሎስ ይህን ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ ይዞት የገባ መስሏቸው ነበር። +30 በመሆኑም ከተማዋ በሙሉ ታወከች፤ ሕዝቡም ግር ብለው እየሮጡ በመምጣት ጳውሎስን ያዙት፤ እየጎተቱም ከቤተ መቅደሱ አወጡት፤ በሮቹም ወዲያው ተዘጉ። +31 ሊገድሉትም እየሞከሩ ሳለ መላዋ ኢየሩሳሌም እንደታወከች የሚገልጽ ወሬ ለሠራዊቱ ሻለቃ ደረሰው፤ +32 እሱም ወዲያውኑ ወታደሮችንና የጦር መኮንኖችን ይዞ እየሮጠ ወደ እነሱ ወረደ። እነሱም ሻለቃውንና ወታደሮቹን ሲያዩ ጳውሎስን መደብደባቸውን ተዉ። +33 በዚህ ጊዜ የሠራዊቱ ሻለቃ ቀርቦ በቁጥጥር ሥር አዋለውና በሁለት ሰንሰለት እንዲታሰር አዘዘ፤+ ከዚያም ማን እንደሆነና ምን እንዳደረገ ጠየቀ። +34 ከሕዝቡም መካከል አንዳንዶች አንድ ነገር ሲናገሩ ሌሎቹ ደግሞ ሌላ ነገር ይናገሩ ነበር። ስለዚህ ሻለቃው ከጫጫታው የተነሳ ምንም የተጨበጠ ነገር ማግኘት ስላልቻለ ወደ ጦር ሰፈሩ እንዲወሰድ አዘዘ። +35 ሆኖም ጳውሎስ ወደ ደረጃው በደረሰ ጊዜ ከሕዝቡ ዓመፅ የተነሳ ወታደሮቹ ተሸክመውት ለመሄድ ተገደዱ፤ +36 ብዙ ሕዝብም እየተከተለ “ግደለው!” እያለ ይጮኽ ነበር። +37 ጳውሎስ ወደ ጦር ሰፈሩ ሊያስገቡት በተቃረቡ ጊዜ ሻለቃውን “አንዴ ላናግርህ?” አለው። ሻለቃውም እንዲህ አለው፦ “ግሪክኛ መናገር ትችላለህ እንዴ? +"38 አንተ ከዚህ ቀደም ዓመፅ አነሳስተህ 4,000 ነፍሰ ገዳዮችን ወደ ምድረ በዳ ያሸፈትከው ግብፃዊ አይደለህም?”" +39 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “እኔ እንኳ በኪልቅያ የምትገኘው የታወቀችው የጠርሴስ+ ከተማ ነዋሪ የሆንኩ አይሁዳዊ ነኝ።+ ስለዚህ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ” አለ። +40 ከፈቀደለት በኋላ ጳውሎስ ደረጃው ላይ ቆሞ ለሕዝቡ በእጁ ምልክት ሰጠ። ታላቅ ጸጥታ በሰፈነ ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ+ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ መናገር ጀመረ፦ +15 አንዳንድ ሰዎች ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ወርደው “በሙሴ ሥርዓት መሠረት ካልተገረዛችሁ+ በቀር ልትድኑ አትችሉም” እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ጀመር። +2 በዚህ የተነሳ ጳውሎስና በርናባስ ከሰዎቹ ጋር የጦፈ ክርክርና ጭቅጭቅ ውስጥ ገቡ። በመሆኑም ጳውሎስና በርናባስ እንዲሁም አንዳንድ ወንድሞች ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው+ ጉዳዩን* በዚያ ለሚገኙት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች እንዲያቀርቡ ተወሰነ። +3 በዚህም መሠረት ጉባኤው የተወሰነ መንገድ ከሸኛቸው በኋላ በፊንቄና በሰማርያ በኩል በማለፍ ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰዎች ተለውጠው አምላክን ማምለክ እንደጀመሩ በዝርዝር ተናገሩ፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኟቸው። +4 ኢየሩሳሌም ሲደርሱም በዚያ የሚገኘው ጉባኤ እንዲሁም ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ጥሩ አቀባበል አደረጉላቸው፤ የተላኩትም ወንድሞች አምላክ በእነሱ አማካኝነት ያከናወናቸውን በርካታ ነገሮች ተረኩላቸው። +5 ይሁንና ከፈሪሳውያን ሃይማኖታዊ ቡድን መካከል አማኞች የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ከመቀመጫቸው ተነስተው “እነዚህን ሰዎች መግረዝና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ማዘዝ አስፈላጊ ነው” ሲሉ ተናገሩ።+ +6 ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ይህን ጉዳይ ለመመርመር ተሰበሰቡ። +7 ከብዙ ክርክር በኋላ ጴጥሮስ ተነስቶ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች፣ አሕዛብ የምሥራቹን ቃል ከእኔ አፍ ሰምተው እንዲያምኑ አምላክ ገና ከመጀመሪያው ከእናንተ መካከል እኔን እንደመረጠኝ በሚገባ ታውቃላችሁ።+ +8 ልብን የሚያውቀው አምላክ+ ለእኛ እንዳደረገው ሁሉ ለእነሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሠከረላቸው።+ +9 ደግሞም በእኛና በእነሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም፤+ ከዚህ ይልቅ በእምነታቸው የተነሳ ልባቸውን አነጻ።+ +10 ታዲያ አባቶቻችንም ሆኑ እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን+ ቀንበር በደቀ መዛሙርቱ ጫንቃ ላይ በመጫን+ አሁን አምላክን ለምን ትፈታተናላችሁ? +11 በአንጻሩ ግን እኛ የምንድነው በጌታ ኢየሱስ ጸጋ አማካኝነት እንደሆነ እናምናለን፤+ እነሱም ቢሆኑ ይህንኑ ያምናሉ።”+ +12 በዚህ ጊዜ የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ጸጥ አለ፤ በርናባስና ጳውሎስ፣ አምላክ በእነሱ አማካኝነት በአሕዛብ መካከል ያከናወናቸውን በርካታ ተአምራዊ ���ልክቶችና ድንቅ ነገሮች ሲናገሩም ያዳምጥ ጀመር። +13 እነሱ ተናግረው ካበቁ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞች፣ ስሙኝ። +14 አምላክ ከአሕዛብ መካከል ለስሙ የሚሆኑ ሰዎችን ለመውሰድ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት ለእነሱ ትኩረት እንደሰጠ ሲምዖን*+ በሚገባ ተርኳል።+ +15 እንዲህ ተብሎ የተጻፈው የነቢያት ቃልም ከዚህ ጋር ይስማማል፦ +16 ‘ከዚህ በኋላ ተመልሼ የፈረሰውን የዳዊትን ድንኳን* ዳግመኛ አቆማለሁ፤ ፍርስራሹንም አድሼ ዳግም እገነባዋለሁ፤ +17 ይህን የማደርገው የቀሩት ሰዎች፣ ከብሔራት ከመጡት በስሜ የተጠሩ ሰዎች ጋር አንድ ላይ ሆነው ይሖዋን* ከልብ እንዲፈልጉ ነው በማለት እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው ይሖዋ* ተናግሯል፤+ +18 እነዚህም ነገሮች ከጥንት ዘመን ጀምሮ ይታወቃሉ።’+ +19 ስለዚህ እንደ እኔ ሐሳብ ከሆነ፣* ተለውጠው አምላክን ማምለክ የጀመሩትን አሕዛብ ባናስቸግራቸው ይሻላል፤+ +20 ከዚህ ይልቅ በጣዖት+ ከረከሱ ነገሮች፣ ከፆታ ብልግና፣*+ ታንቆ ከሞተ* እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከደም እንዲርቁ+ እንጻፍላቸው። +21 ምክንያቱም ከጥንት ዘመን ጀምሮ በየከተማው በሰንበት ቀናት ሁሉ በምኩራቦች ውስጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ከሙሴ መጻሕፍት በማንበብ በውስጡ የሰፈረውን ቃል የሚሰብኩ ሰዎች ነበሩ።”+ +22 ከዚያም ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከመላው ጉባኤ ጋር ሆነው ከመካከላቸው የተመረጡ ሰዎችን ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ በወንድሞች መካከል ግንባር ቀደም የሆኑትን በርስያን የሚባለውን ይሁዳንና ሲላስን+ ላኩ። +23 ደግሞም የሚከተለውን ደብዳቤ ጽፈው በእነሱ እጅ ላኩላቸው፦ “ከወንድሞቻችሁ ከሐዋርያትና ከሽማግሌዎች፣ በአንጾኪያ፣+ በሶርያና በኪልቅያ ለምትኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆናችሁ ወንድሞች፤ ሰላምታችን ይድረሳችሁ! +24 ከእኛ መካከል አንዳንዶች ወጥተው እኛ ምንም ሳናዛቸው በሚናገሩት ነገር እንዳስቸገሯችሁና+ ሊያውኳችሁ* እንደሞከሩ ስለሰማን +25 ሰዎች መርጠን ከተወደዱት ወንድሞቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ ለመላክ በአንድ ልብ ወሰንን፤ +26 በርናባስና ጳውሎስ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሕይወታቸውን* አሳልፈው የሰጡ ናቸው።+ +27 ስለዚህ ይህንኑ ነገር በቃልም እንዲነግሯችሁ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል።+ +28 ከሚከተሉት አስፈላጊ ነገሮች በስተቀር፣ ሌላ ተጨማሪ ሸክም እንዳንጭንባችሁ መንፈስ ቅዱስና+ እኛ ወስነናል፦ +29 ለጣዖት ከተሠዉ ነገሮች፣+ ከደም፣+ ታንቆ ከሞተ እንስሳ* ሥጋና+ ከፆታ ብልግና* ራቁ።+ ከእነዚህ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ከራቃችሁ መልካም ይሆንላችኋል። ጤና ይስጣችሁ!”* +30 የተላኩትም ሰዎች ከተሰናበቱ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ እዚያ የሚገኙትንም ደቀ መዛሙርት በአንድነት ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጧቸው። +31 እነሱም ካነበቡት በኋላ ባገኙት ማበረታቻ እጅግ ተደሰቱ። +32 ይሁዳና ሲላስም ራሳቸው ነቢያት ስለነበሩ ብዙ ቃል በመናገር ወንድሞችን አበረታቷቸው፤ እንዲሁም አጠናከሯቸው።+ +33 በዚያም የተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ወደላኳቸው ሰዎች እንዲመለሱ ወንድሞች በሰላም አሰናበቷቸው። +34 *—— +35 ይሁን እንጂ ጳውሎስና በርናባስ እያስተማሩና ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋር ሆነው ምሥራቹን ይኸውም የይሖዋን* ቃል እየሰበኩ በአንጾኪያ ቆዩ። +36 ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “የይሖዋን* ቃል ባወጅንባቸው ከተሞች ሁሉ ያሉት ወንድሞች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተመልሰን እንጠይቃቸው”* አለው።+ +37 በርናባስ፣ ማርቆስ ተብሎ የሚጠራው ዮሐንስ+ አብሯቸው እንዲሄድ ወስኖ ነበር። +38 ጳውሎስ ግን ማርቆስ በጵንፍልያ ተለይቷቸው ስለነበረና ያከናውኑት ወደነበረው ሥራ ከእነሱ ጋር ስላልሄደ አሁን አብሯቸው እንዲሄድ አልፈለገም።+ +39 በዚህ ምክንያት በመካከላቸው ኃይለኛ ጭቅጭቅ ስለተፈጠረ ተለያዩ፤ ስለዚህ በርናባስ+ ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። +40 ጳውሎስ ደግሞ ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለይሖዋ* ጸጋ በአደራ ከሰጡት በኋላ ከዚያ ተነስቶ ሄደ።+ +41 ጉባኤዎችንም እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ በኩል አለፈ። +22 “ወንድሞችና አባቶች፣ አሁን ለእናንተ የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ።”+ +2 እነሱም በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገር በሰሙ ጊዜ ይበልጥ ጸጥ አሉ፤ እሱም እንዲህ አለ፦ +3 “እኔ ኪልቅያ ውስጥ በምትገኘው በጠርሴስ+ የተወለድኩ አይሁዳዊ ነኝ፤+ ሆኖም የተማርኩት በዚህችው ከተማ በገማልያል+ እግር ሥር ተቀምጬ ሲሆን የአባቶችን ሕግ በጥብቅ እንድከተል የሚያስችል ትምህርት ቀስሜአለሁ፤+ ዛሬ እናንተ ሁላችሁ እንዲህ እንደምትቀኑ ሁሉ እኔም ለአምላክ እቀና ነበር።+ +4 ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን በማሰርና ለወህኒ ቤት አሳልፌ በመስጠት የጌታን መንገድ የሚከተሉትን እስከ ሞት ድረስ ስደት አደርስባቸው ነበር፤+ +5 ይህን በተመለከተም ሊቀ ካህናቱና መላው የሽማግሌዎች ጉባኤ ሊመሠክሩ ይችላሉ። ከእነሱም በደማስቆ ላሉ ወንድሞቻችን የተጻፈ ደብዳቤ ተቀብዬ በዚያ ያሉትን አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም በማምጣት ለማስቀጣት በጉዞ ላይ ነበርኩ። +6 “ሆኖም በጉዞ ላይ ሳለሁ ወደ ደማስቆ ስቃረብ፣ እኩለ ቀን ገደማ ላይ ድንገት ከሰማይ የመጣ ኃይለኛ ብርሃን በዙሪያዬ አንጸባረቀ፤+ +7 እኔም መሬት ላይ ወደቅኩ፤ ከዚያም ‘ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ?’ የሚል ድምፅ ሰማሁ። +8 እኔም መልሼ ‘ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?’ አልኩት። እሱም ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ’ አለኝ። +9 ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች ብርሃኑን አይተዋል፤ ሆኖም እሱ ሲያነጋግረኝ ድምፁን አልሰሙም።* +10 በዚህ ጊዜ ‘ጌታ ሆይ፣ ምን ባደርግ ይሻላል?’ አልኩት። ጌታም ‘ተነስተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ እዚያም ልታደርገው የሚገባህ ነገር ሁሉ ይነገርሃል’ አለኝ።+ +11 ይሁንና ከብርሃኑ ድምቀት የተነሳ ዓይኔ ማየት ስለተሳነው አብረውኝ የነበሩት ሰዎች እጄን ይዘው እየመሩ ደማስቆ አደረሱኝ። +12 “ከዚያም ሕጉን በሚገባ በመጠበቅ ለአምላክ ያደረ እንዲሁም እዚያ በሚኖሩት አይሁዳውያን ሁሉ የተመሠከረለት ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው +13 ወደ እኔ መጣ። አጠገቤም ቆሞ ‘ወንድሜ ሳኦል፣ ዓይኖችህ ይብሩልህ!’ አለኝ። እኔም በዚያው ቅጽበት ቀና ብዬ አየሁት።+ +14 እሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን እንድታውቅ፣ ጻድቁን እንድታይና+ ድምፁን እንድትሰማ መርጦሃል፤ +15 ይህን ያደረገው ስላየኸውና ስለሰማኸው ነገር በሰው ሁሉ ፊት ለእሱ ምሥክር እንድትሆን ነው።+ +16 ታዲያ አሁን ምን ትጠብቃለህ? ተነስና ተጠመቅ፤ ስሙንም እየጠራህ+ ኃጢአትህን ታጠብ።’+ +17 “ሆኖም ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለስኩ በኋላ+ በቤተ መቅደሱ ውስጥ እየጸለይኩ ሳለ ሰመመን ውስጥ ገባሁ፤ +18 ጌታም ‘ስለ እኔ የምትሰጠውን ምሥክርነት ስለማይቀበሉ ፍጠን፤ ከኢየሩሳሌም ቶሎ ብለህ ውጣ’ ሲለኝ አየሁት።+ +19 እኔም እንዲህ አልኩት፦ ‘ጌታ ሆይ፣ በየምኩራቡ እየዞርኩ በአንተ የሚያምኑትን አስርና እገርፍ እንደነበረ እነሱ ራሳቸው በሚገባ ያውቃሉ፤+ +20 ደግሞም የአንተ ምሥክር የነበረው የእስጢፋኖስ ደም ሲፈስ እኔ በድርጊቱ በመስማማት እዚያ ቆሜ የገዳዮቹን ልብስ ስጠብቅ ነበር።’+ +21 እሱ ግን ‘በሩቅ ወዳሉ አሕዛብ ስለምልክህ ተነስተህ ሂድ’ አለኝ።”+ +22 ሕዝቡ ይህን እስኪናገር ድረስ ጸጥ ብለው ሲያዳምጡት ቆዩ። ከዚያም “ይህ ሰው መኖር የማይገባው ስለሆነ ከምድር ገጽ ይወገድ!” ብለው ጮኹ። +23 ደግሞም እየጮኹ መደረቢያቸውን ይወረውሩና አፈር ወደ ላይ ይበትኑ ስለነበር+ +24 የሠራዊቱ ሻለቃ ጳውሎስን ወደ ጦር ሰፈሩ እንዲያስገቡት ትእዛዝ ሰጠ፤ ደግሞም በጳውሎስ ላይ እንዲህ የሚጮኹት ለምን እንደሆነ በትክክል ማወቅ ስለፈለገ እየተገረፈ እንዲመረመር አዘዘ። +25 ሆኖም ሊገርፉት ወጥረው ባሰሩት ጊዜ ጳውሎስ አጠገቡ የቆመውን መኮንን “አንድን ሮማዊ* ሳይፈረድበት* ለመግረፍ ሕግ ይፈቅድላችኋል?” አለው።+ +26 መኮንኑ ይህን ሲሰማ ወደ ሠራዊቱ ሻለቃ ሄዶ “ምን ለማድረግ ነው ያሰብከው? ይህ ሰው እኮ ሮማዊ ነው” አለው። +27 ሻለቃውም ወደ ጳውሎስ ቀርቦ “ሮማዊ ነህ እንዴ?” አለው። እሱም “አዎ” አለው። +28 ሻለቃውም መልሶ “እኔ ይህን የዜግነት መብት የገዛሁት ብዙ ገንዘብ አውጥቼ ነው” አለው። ጳውሎስ ደግሞ “እኔ ግን በመወለድ አገኘሁት” አለ።+ +29 ስለዚህ እያሠቃዩ ሊመረምሩት የነበሩት ሰዎች ወዲያውኑ ከእሱ ራቁ፤ የሠራዊቱ ሻለቃም በሰንሰለት አስሮት ስለነበር ሮማዊ መሆኑን ሲገነዘብ ፈራ።+ +30 በመሆኑም በማግስቱ አይሁዳውያን የከሰሱት ለምን እንደሆነ በትክክል ማወቅ ስለፈለገ ፈታውና የካህናት አለቆቹ እንዲሁም መላው የሳንሄድሪን ሸንጎ እንዲሰበሰቡ አዘዘ። ከዚያም ጳውሎስን አውርዶ በመካከላቸው አቆመው።+ +3 ታዲያ አይሁዳዊ መሆን ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው? ግርዘትስ ፋይዳው ምንድን ነው? +2 በሁሉም መንገድ ትልቅ ጥቅም አለው። በመጀመሪያ ደረጃ የአምላክ ቅዱስ ቃል+ በአደራ ተሰጥቷቸዋል። +3 አንዳንድ አይሁዳውያን እምነት ቢጎድላቸውስ? የእነሱ እምነት ማጣት ሰዎች በአምላክ እንዳይታመኑ ሊያደርግ ይችላል? +4 በፍጹም! ከዚህ ይልቅ “በቃልህ ጻድቅ ሆነህ ትገኝ ዘንድ፣ በፍርድም ፊት ትረታ ዘንድ”+ ተብሎ እንደተጻፈ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ሆኖ ቢገኝ+ እንኳ የአምላክ እውነተኝነት የተረጋገጠ ነው።+ +5 ይሁን እንጂ የእኛ ክፋት የአምላክን ጽድቅ አጉልቶ የሚያሳይ ከሆነ ምን ማለት እንችላለን? አምላክ ቁጣውን መግለጹ ኢፍትሐዊ ያሰኘዋል እንዴ? (አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ማለት ነው።) +6 በፍጹም! አለዚያ አምላክ በዓለም ላይ እንዴት ይፈርዳል?+ +7 ይሁንና በእኔ ውሸት የተነሳ የአምላክ እውነት ለእሱ ክብር በሚያመጣ መንገድ ይበልጥ ጎልቶ የሚወጣ ከሆነ ታዲያ እኔ ለምን ኃጢአተኛ ተብዬ ይፈረድብኛል? +8 እንዲህ ከሆነማ አንዳንድ ሰዎች “ጥሩ ነገር እንዲገኝ መጥፎ ነገር እንሥራ” ይላሉ በማለት በሐሰት እንደሚያስወሩብን ለምን አንልም? በእነዚህ ሰዎች ላይ የሚበየነው ፍርድ ፍትሐዊ ነው።+ +9 እንግዲህ ምን ማለት ይቻላል? እኛ የተሻልን ነን ማለት ነው? በፍጹም! ምክንያቱም አይሁዳውያንም ሆኑ ግሪካውያን ሁሉም የኃጢአት ተገዢዎች+ እንደሆኑ በመናገር አስቀድመን ከሰናቸዋል፤ +10 ይህም እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈው ነው፦ “ጻድቅ ሰው የለም፤ አንድም እንኳ የለም፤+ +11 ማስተዋል ያለው አንድም ሰው የለም፤ ደግሞም አምላክን የሚፈልግ አንድም ሰው የለም። +12 ሁሉም መንገድ ስተዋል፤ ሁሉም የማይረቡ ሆነዋል፤ ደግነት የሚያሳይ አንድም ሰው የለም፤ አንድም እንኳ አይገኝም።”+ +13 “ጉሮሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ።”+ “ከከንፈራቸው ሥር የእባብ መርዝ አለ።”+ +14 “አፋቸውም በእርግማንና በምሬት የተሞላ ነው።”+ +15 “እግሮቻቸው ደም ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው።”+ +16 “በመንገዳቸው ላይ ጥፋትና መከራ አለ፤ +17 የሰላምንም መንገድ አያውቁም።”+ +18 “በዓይኖቻቸው ፊት አምላክን መፍራት የሚባል ነገር የለም።”+ +19 እንግዲህ አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለም በሙሉ በአምላክ ፊት ተጠያቂ እንዲሆን+ ሕግ የሚናገ���ው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሆነ እናውቃለን። +20 ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ማንም ሰው* በፊቱ ጻድቅ ነህ ሊባል አይችልም፤+ ምክንያቱም ስለ ኃጢአት ትክክለኛ ግንዛቤ* የሚገኘው በሕጉ አማካኝነት ነው።+ +21 አሁን ግን ሕግ ሳያስፈልግ፣ በሕጉና በነቢያት የተመሠከረለት+ የአምላክ ጽድቅ ግልጽ ሆኗል፤+ +22 እምነት ያላቸው ሁሉ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት አማካኝነት የአምላክን ጽድቅ ያገኛሉ። ይህም የሆነው በሰዎች መካከል ምንም ልዩነት ስለሌለ ነው።+ +23 ምክንያቱም ሁሉም ኃጢአት ሠርተዋል፤ የአምላክንም ክብር ማንጸባረቅ ተስኗቸዋል፤+ +24 ይሁንና ክርስቶስ ኢየሱስ የከፈለው ቤዛ+ በሚያስገኘው ነፃነት አማካኝነት በጸጋው+ ጻድቃን ናችሁ መባላቸው እንዲሁ የተገኘ ነፃ ስጦታ ነው።+ +25 በኢየሱስ ደም የሚያምኑ+ ሁሉ ማስተሰረያ ያገኙ*+ ዘንድ አምላክ እሱን መባ አድርጎ አቅርቦታል። አምላክ ይህን ያደረገው የራሱን ጽድቅ ለማሳየት ነው፤ ምክንያቱም አምላክ ቻይ በመሆን በቀደሙት ዘመናት የተፈጸሙትን ኃጢአቶች ይቅር ብሏል። +26 ይህን ያደረገው በዚህም ዘመን የራሱን ጽድቅ ለማሳየት ነው፤+ ይህም በኢየሱስ የሚያምነውን ሰው ጻድቅ ነህ በማለት እሱ ራሱ ጻድቅ ይሆን ዘንድ ነው።+ +27 ታዲያ እንድንኮራ የሚያደርገን ነገር ይኖራል? ምንም ነገር የለም። እንዳንኮራ የሚያደርገን ሕግ የትኛው ነው? የሥራ ሕግ ነው?+ በፍጹም አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ እንዳንኮራ የሚያደርገን የእምነት ሕግ ነው። +28 ምክንያቱም አንድ ሰው ጻድቅ ነህ የሚባለው የሕግን ሥራ በመፈጸም ሳይሆን በእምነት እንደሆነ እንረዳለን።+ +29 ወይስ አምላክ የአይሁዳውያን አምላክ ብቻ ነው?+ የአሕዛብስ አምላክ አይደለም?+ አዎ፣ የአሕዛብም አምላክ ነው።+ +30 አምላክ አንድ ስለሆነ+ የተገረዙትን ከእምነት የተነሳ ጻድቃን ይላቸዋል፤+ ያልተገረዙትንም በእምነታቸው አማካኝነት ጻድቃን ናችሁ ይላቸዋል።+ +31 ታዲያ በእምነታችን አማካኝነት ሕግን እንሽራለን ማለት ነው? በፍጹም! እንዲያውም ሕግን እንደግፋለን።+ +7 ወንድሞች፣ (እየተናገርኩ ያለሁት ሕግ ለሚያውቁ ሰዎች ነው፤) ሕጉ በአንድ ሰው ላይ ሥልጣን የሚኖረው በሕይወት እስከኖረ ድረስ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? +2 ለምሳሌ ያህል፣ ያገባች ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ በሕግ ለእሱ የታሰረች ናት፤ ባሏ ከሞተ ግን ከባሏ ሕግ ነፃ ትወጣለች።+ +3 በመሆኑም ባሏ በሕይወት እያለ የሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች።+ ባሏ ከሞተ ግን ከእሱ ሕግ ነፃ ስለምትሆን የሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አትባልም።+ +4 ስለዚህ ወንድሞቼ፣ እናንተም የሌላ ይኸውም ከሞት የተነሳው+ የክርስቶስ እንድትሆኑ+ በእሱ አካል አማካኝነት ለሕጉ ሞታችኋል፤* ይህም የሆነው ለአምላክ ፍሬ እንድናፈራ ነው።+ +5 ምክንያቱም እንደ ሥጋ ፍላጎት እንኖር በነበረበት ጊዜ ሕጉ ይፋ ያወጣቸው የኃጢአት ምኞቶች ለሞት ፍሬ እንድናፈራ በሰውነታችን* ውስጥ ይሠሩ ነበር።+ +6 አሁን ግን አሮጌ በሆነው በተጻፈው ሕግ+ ሳይሆን በአዲስ መልክ በመንፈስ ባሪያዎች+ እንሆን ዘንድ አስሮ ይዞን ለነበረው ሕግ ስለሞትን ከሕጉ ነፃ ወጥተናል።+ +7 እንግዲህ ምን እንበል? ሕጉ ጉድለት አለበት ማለት ነው?* በፍጹም! እንደ እውነቱ ከሆነ ሕጉ ባይኖር ኖሮ ኃጢአት ምን እንደሆነ ባላወቅኩ ነበር።+ ለምሳሌ ሕጉ “አትጎምጅ”+ ባይል ኖሮ መጎምጀት ምን እንደሆነ ባላወቅኩ ነበር። +8 ሆኖም ኃጢአት፣ ይህ ትእዛዝ ባስገኘው አጋጣሚ ተጠቅሞ ማንኛውንም ዓይነት ነገር የመጎምጀት ፍላጎት በውስጤ እንዲያድር አደረገ፤ ሕግ ባልነበረበት ጊዜ ኃጢአት የሞተ ነበርና።+ +9 በእርግጥ ሕግ ባልነበረበት ጊዜ ሕያው ነበርኩ። ትእዛዙ ሲመጣ ግን ኃጢአት ዳግመኛ ሕያው ሆነ፤ እኔ ግን ሞትኩ።+ +10 ወደ ሕይወት እንዲመራ የታሰበውም ትእዛዝ+ ሞት እንዳመጣ ተገነዘብኩ። +11 ምክንያቱም ኃጢአት ትእዛዙ ባስገኘው አጋጣሚ ተጠቅሞ አታሎኛል፤ እንዲሁም በትእዛዙ አማካኝነት ገድሎኛል። +12 ስለዚህ ሕጉ በራሱ ቅዱስ ነው፤ ትእዛዙም ቅዱስ፣ ጻድቅና ጥሩ ነው።+ +13 ታዲያ ይህ ጥሩ የሆነው ነገር* ሞት አመጣብኝ ማለት ነው? በፍጹም! ከዚህ ይልቅ የገደለኝ ኃጢአት ነው። የኃጢአት ምንነት እንዲገለጥ ጥሩ በሆነው ነገር አማካኝነት ሞት ያመጣብኝ ኃጢአት ነው።+ ትእዛዙም ኃጢአት ምን ያህል ክፉ እንደሆነ አሳይቷል።+ +14 ሕጉ መንፈሳዊ* እንደሆነ እናውቃለንና፤ እኔ ግን ለኃጢአት የተሸጥኩ ሥጋዊ ነኝ።+ +15 ለምን እንዲህ እንደማደርግ አላውቅም። ለማድረግ የምፈልገውን ነገር አላደርግምና፤ ከዚህ ይልቅ የማደርገው የምጠላውን ነገር ነው። +16 ይሁን እንጂ የማደርገው የማልፈልገውን ከሆነ ሕጉ መልካም ነው በሚለው እስማማለሁ። +17 ሆኖም አሁን ይህን የሚያደርገው በእኔ ውስጥ የሚኖረው ኃጢአት ነው+ እንጂ እኔ አይደለሁም። +18 ምክንያቱም በውስጤ ማለትም በሥጋዬ ውስጥ የሚኖር ምንም ጥሩ ነገር የለም፤ መልካም የሆነውን ነገር የማድረግ ፍላጎት እንጂ የመፈጸም ችሎታ የለኝም።+ +19 የምመኘውን መልካም ነገር አላደርግምና፤ የማልፈልገውን መጥፎ ነገር ግን አደርጋለሁ። +20 እንግዲህ የማደርገው የማልፈልገውን ነገር ከሆነ ይህን የማደርገው እኔ ሳልሆን በውስጤ የሚኖረው ኃጢአት ነው። +21 እንግዲያው ይህ ሕግ በራሴ ላይ ሲሠራ አያለሁ፦ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ስፈልግ ከእኔ ጋር ያለው ግን መጥፎ ነገር ነው።+ +22 በውስጤ በአምላክ ሕግ እጅግ ደስ ይለኛል፤+ +23 በሰውነቴ* ውስጥ ግን ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና+ በሰውነቴ* ውስጥ ላለው የኃጢአት ሕግ ምርኮኛ አድርጎ የሚሰጠኝን+ ሌላ ሕግ አያለሁ። +24 እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! እንዲህ ወዳለው ሞት ከሚመራኝ ሰውነት ማን ይታደገኛል? +25 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚታደገኝ አምላክ የተመሰገነ ይሁን! ስለዚህ እኔ ራሴ በአእምሮዬ ለአምላክ ሕግ ባሪያ ስሆን በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ ባሪያ ነኝ።+ +12 እንግዲህ ወንድሞች፣ ሰውነታችሁን ሕያው፣ ቅዱስና+ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት አድርጋችሁ እንድታቀርቡ+ በአምላክ ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም የማሰብ ችሎታችሁን ተጠቅማችሁ የምታቀርቡት ቅዱስ አገልግሎት ነው።+ +2 በተጨማሪም ይህ ሥርዓት* እንዲቀርጻችሁ አትፍቀዱ፤ ከዚህ ይልቅ ጥሩ የሆነውን፣ ተቀባይነት ያለውንና ፍጹም የሆነውን የአምላክ ፈቃድ መርምራችሁ ማረጋገጥ ትችሉ ዘንድ+ አእምሯችሁን በማደስ ተለወጡ።+ +3 እያንዳንዱ ሰው ከሚገባው በላይ ስለ ራሱ በማሰብ ራሱን ከፍ አድርጎ አይመልከት፤+ ከዚህ ይልቅ አምላክ ለእያንዳንዱ በሰጠው* እምነት መሠረት ጤናማ አስተሳሰብ እንዳለው በሚያሳይ መንገድ እንዲያስብ፣ በመካከላችሁ ያለውን እያንዳንዱን ሰው በተሰጠኝ ጸጋ እመክራለሁ።+ +4 በአንድ አካል ላይ ብዙ የአካል ክፍሎች አሉን፤+ ደግሞም ሁሉም የአካል ክፍሎች አንድ ዓይነት ተግባር አያከናውኑም፤ +5 ልክ እንደዚሁ እኛም ብዙ ብንሆንም እንኳ ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት አንድ አካል ነን፤ ደግሞም አንዳችን የሌላው የአካል ክፍል ነን።+ +6 በመሆኑም በተሰጠን ጸጋ መሠረት+ የተለያዩ ስጦታዎች ስላሉን ስጦታችን ትንቢት መናገር ከሆነ በተሰጠን እምነት መሠረት ትንቢት እንናገር፤ +7 ማገልገል ከሆነ ማገልገላችንን እንቀጥል፤ የሚያስተምርም ቢሆን ማስተማሩን ይቀጥል፤+ +8 የሚያበረታታም* ቢሆን ማበረታቻ መስጠቱን ይቀጥል፤+ የሚሰጥ* በል���ስና ይስጥ፤+ የሚያስተዳድር* በትጋት ያስተዳድር፤+ የሚምር በደስታ ይማር።+ +9 ፍቅራችሁ ግብዝነት የሌለበት ይሁን።+ ክፉ የሆነውን ተጸየፉ፤+ ጥሩ የሆነውን አጥብቃችሁ ያዙ። +10 በወንድማማች ፍቅር እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ። አንዳችሁ ሌላውን ለማክበር ቀዳሚ ሁኑ።*+ +11 ታታሪዎች* ሁኑ እንጂ አትስነፉ።*+ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ።+ ይሖዋን* እንደ ባሪያ አገልግሉ።+ +12 በተስፋው ደስ ይበላችሁ። መከራን በጽናት ተቋቋሙ።+ ሳትታክቱ ጸልዩ።+ +13 ለቅዱሳን እንደየችግራቸው ያላችሁን አካፍሉ።+ የእንግዳ ተቀባይነትን ባሕል አዳብሩ።+ +14 ስደት የሚያደርሱባችሁን መርቁ፤+ መርቁ እንጂ አትርገሙ።+ +15 ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ። +16 ለራሳችሁ ያላችሁ ዓይነት አመለካከት ለሌሎችም ይኑራችሁ፤ የትዕቢት ዝንባሌ እንዳያድርባችሁ ተጠንቀቁ፤ ትሕትና የሚንጸባረቅበት አስተሳሰብ ይኑራችሁ።+ ጥበበኞች እንደሆናችሁ አድርጋችሁ አታስቡ።+ +17 ለማንም በክፉ ፋንታ ክፉ አትመልሱ።+ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ጥረት አድርጉ። +18 ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ።+ +19 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ከዚህ ይልቅ “‘በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ’ ይላል ይሖዋ”*+ ተብሎ ስለተጻፈ ለቁጣው* ዕድል ስጡ።+ +20 ነገር ግን “ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህ።”*+ +21 በክፉ አትሸነፍ፤ ከዚህ ይልቅ ምንጊዜም ክፉውን በመልካም አሸንፍ።+ +1 የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያ ከሆነው፣ ሐዋርያ እንዲሆን ከተጠራውና የአምላክን ምሥራች እንዲያውጅ ከተሾመው* ከጳውሎስ፤+ +2 ይህ ምሥራች አምላክ በነቢያቱ አማካኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አስቀድሞ የሰጠው የተስፋ ቃል ሲሆን +3 በሥጋ ከዳዊት ዘር+ ስለተወለደው ልጁ የሚገልጽ ነው፤ +4 ይሁንና እሱ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የአምላክ ልጅ+ መሆኑ እንዲታወቅ ተደርጓል። ይህም የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በተነሳ+ ጊዜ ነው። +5 ለስሙ ክብር በብሔራት ሁሉ መካከል+ በእምነት የሚታዘዙ ሰዎች እንዲገኙ ሲባል በእሱ አማካኝነት ጸጋና ሐዋርያነት+ ተቀብለናል፤* +6 የኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሆኑ ከአሕዛብ ከተጠሩት መካከል እናንተም ትገኙበታላችሁ። +7 ቅዱሳን እንድትሆኑ ለተጠራችሁና በአምላክ ለተወደዳችሁ በሮም ለምትኖሩ ሁሉ፦ አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። +8 ከሁሉ አስቀድሜ፣ ስለ እምነታችሁ በመላው ዓለም ስለሚወራ ስለ ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለአምላኬ ምስጋና አቀርባለሁ። +9 ያለማቋረጥ ዘወትር በጸሎቴ እናንተን ሳልጠቅስ እንደማላልፍ፣+ ስለ ልጁ የሚገልጸውን ምሥራች በማወጅ በሙሉ ልቤ ቅዱስ አገልግሎት የማቀርብለት አምላክ ምሥክሬ ነው፤ +10 ደግሞም በአምላክ ፈቃድ አሁን በመጨረሻ እንደ ምንም ተሳክቶልኝ ወደ እናንተ መምጣት እንድችል ልመና እያቀረብኩ ነው። +11 ለመጽናት የሚያስችላችሁን መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እጓጓለሁና፤ +12 ይህን ስል እኔ በእናንተ እምነት እናንተም በእኔ እምነት እርስ በርሳችን እንድንበረታታ+ ነው። +13 ይሁንና ወንድሞች፣ በሌሎች አሕዛብ መካከል ፍሬ እንዳፈራሁ ሁሉ በእናንተም መካከል ፍሬ አፈራ ዘንድ ወደ እናንተ ለመምጣት ብዙ ጊዜ አቅጄ እንደነበር እንድታውቁ እፈልጋለሁ። ሆኖም ለመምጣት ባሰብኩ ቁጥር የሆነ እንቅፋት ያጋጥመኛል። +14 ለግሪካውያንም ሆነ ግሪካውያን ላልሆኑ* እንዲሁም ለጠቢባንም ሆነ ላልተማሩ ዕዳ አለብኝ፤ +15 በመሆኑም በሮም ላላች���ት ለእናንተም ምሥራቹን ለማወጅ እጓጓለሁ።+ +16 እኔ በምሥራቹ አላፍርምና፤+ እንዲያውም ለሚያምን ሁሉ+ ይኸውም በመጀመሪያ ለአይሁዳዊ+ ከዚያም ለግሪካዊ+ ምሥራቹ መዳን የሚያስገኝ የአምላክ ኃይል ነው። +17 ምክንያቱም “ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል”+ ተብሎ እንደተጻፈ ሁሉ እምነት ያላቸው+ ሰዎች፣ አምላክ በምሥራቹ አማካኝነት ጽድቁን እንደሚገልጥ ይረዳሉ፤ ይህ ደግሞ እምነታቸውን ያጠነክርላቸዋል። +18 እውነትን ለማፈን+ የተንኮል ዘዴ የሚጠቀሙ ሰዎች በሚፈጽሙት አምላክን የሚጻረር ድርጊትና ክፋት ሁሉ ላይ የአምላክ ቁጣ+ ከሰማይ እየተገለጠ ነው፤ +19 ምክንያቱም ስለ አምላክ ሊታወቅ የሚችለው ነገር በእነሱ ዘንድ በግልጽ የታወቀ ነው፤ ይህም የሆነው አምላክ ይህን ግልጽ ስላደረገላቸው ነው።+ +20 የማይታዩት ባሕርያቱ ይኸውም ዘላለማዊ ኃይሉና+ አምላክነቱ+ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በግልጽ ይታያሉ፤+ ምክንያቱም ባሕርያቱን ከተሠሩት ነገሮች ማስተዋል ይቻላል፤ ስለሆነም የሚያመካኙበት ነገር የላቸውም። +21 አምላክን የሚያውቁ ቢሆኑም እንኳ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም ብሎም አላመሰገኑትም፤ ከዚህ ይልቅ አስተሳሰባቸው ከንቱ ሆነ፤ የማያስተውለው ልባቸውም ጨለመ።+ +22 ጥበበኞች ነን ቢሉም ሞኞች ሆኑ፤ +23 ሊጠፋ የማይችለውን አምላክ ክብር ጠፊ በሆነው ሰው፣ በወፎች፣ አራት እግር ባላቸው እንስሳትና በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት ምስል ለወጡት።+ +24 ስለሆነም አምላክ እንደ ልባቸው ምኞት የገዛ ራሳቸውን አካል እንዲያስነውሩ ለርኩሰት አሳልፎ ሰጣቸው። +25 እነዚህ ሰዎች የአምላክን እውነት በሐሰት ለውጠዋል፤ በፈጣሪ ፋንታ ለፍጥረት ክብር ሰጥተዋል፤* እንዲሁም ቅዱስ አገልግሎት አቅርበዋል፤ ይሁንና ለዘላለም ሊወደስ የሚገባው ፈጣሪ ብቻ ነው። አሜን። +26 አምላክ አሳፋሪ ለሆነ የፆታ ምኞት+ አሳልፎ የሰጣቸው በዚህ ምክንያት ነው፤ ሴቶቻቸውም ተፈጥሯዊ የሆነውን ግንኙነት ከተፈጥሮ ውጭ በሆነ ግንኙነት ለወጡ፤+ +27 ወንዶቹም ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከሴቶች ጋር መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው ኃይለኛ በሆነ የፆታ ስሜት ተቃጠሉ፤ ወንዶች ከወንዶች ጋር አስነዋሪ ነገር ፈጸሙ፤+ እነሱ ራሳቸውም ለጥፋታቸው የሚገባውን ቅጣት* እየተቀበሉ ነው።+ +28 ለአምላክ እውቅና መስጠት ተገቢ መስሎ ስላልታያቸው* መደረግ የማይገባውን ነገር እንዲያደርጉ አምላክ በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ለሌለው አስተሳሰብ አሳልፎ ሰጣቸው።+ +29 ደግሞም እነዚህ ሰዎች በዓመፅ፣+ በኃጢአተኝነት፣ በስግብግብነት፣*+ በክፋት፣ በቅናት፣+ በነፍሰ ገዳይነት፣+ በጥል፣ በማታለልና+ በተንኮል+ የተሞሉ ናቸው፤ እንዲሁም ስም አጥፊዎች፣* +30 ሐሜተኞች፣+ አምላክን የሚጠሉ፣ ተሳዳቢዎች፣ ትዕቢተኞች፣ ጉረኞች፣ ክፋት ጠንሳሾች፣ ለወላጆች የማይታዘዙ፣+ +31 የማያስተውሉ፣+ ቃላቸውን የማይጠብቁ፣ ተፈጥሯዊ ፍቅር የሌላቸውና ምሕረት የለሾች ናቸው። +32 እነዚህ ሰዎች ‘እንዲህ ያሉ ነገሮችን የሚያደርጉ* ሁሉ ሞት ይገባቸዋል’+ የሚለውን የአምላክን የጽድቅ ሕግ በሚገባ የሚያውቁ ቢሆኑም በዚህ ድርጊታቸው መግፋት ብቻ ሳይሆን ይህን የሚያደርጉትንም ይደግፋሉ። +8 ስለዚህ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ያላቸው ኩነኔ የለባቸውም። +2 ምክንያቱም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ላላቸው ሰዎች ሕይወት የሚያስገኘው መንፈስ ሕግ፣ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ አውጥቷችኋል።+ +3 ሕጉ ከሰብዓዊ አለፍጽምና የተነሳ ደካማ በመሆኑ+ ሊፈጽመው ያልቻለውን+ ነገር አምላክ ኃጢአትን ለማስወገድ የገዛ ራሱን ልጅ ኃጢአተኛ በሆኑ ሰዎች አምሳል+ በመላክ+ ፈጽሞታል። እንዲህ በማድረግም የሥጋን ኃጢአት ኮንኗል፤ +4 ይህም የሆነው የሕጉ የጽድቅ መሥፈርት እንደ ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ መንፈስ ፈቃድ+ በምንመላለሰው በእኛ እንዲፈጸም ነው።+ +5 እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ አእምሯቸው በሥጋዊ ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው፤+ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን አእምሯቸው በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው።+ +6 በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ሞት ያስከትላልና፤+ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ግን ሕይወትና ሰላም ያስገኛል፤+ +7 ሥጋ ለአምላክ ሕግ ስለማይገዛና ደግሞም ሊገዛ ስለማይችል በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር የአምላክ ጠላት ያደርጋል።+ +8 ስለሆነም እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚመላለሱ አምላክን ማስደሰት አይችሉም። +9 ይሁን እንጂ የአምላክ መንፈስ በእርግጥ በውስጣችሁ የሚኖር ከሆነ ከሥጋ ጋር ሳይሆን ከመንፈስ+ ጋር ስምም ናችሁ። ሆኖም አንድ ሰው የክርስቶስ መንፈስ ከሌለው ይህ ሰው የክርስቶስ አይደለም። +10 ይሁንና ክርስቶስ ከእናንተ ጋር አንድነት ካለው፣+ ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ቢሆንም እንኳ መንፈስ ከጽድቅ የተነሳ ሕይወት ያስገኛል። +11 እንግዲህ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው የአምላክ መንፈስ በእናንተ ውስጥ የሚኖር ከሆነ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው+ እሱ በእናንተ ውስጥ በሚኖረው መንፈሱ አማካኝነት ሟች ሰውነታችሁንም ሕያው ያደርገዋል።+ +12 ስለዚህ ወንድሞች ግዴታ አለብን፤ ይሁንና ግዴታችን እንደ ሥጋ ፈቃድ መኖር አይደለም፤+ +13 እንደ ሥጋ ፈቃድ የምትኖሩ ከሆነ መሞታችሁ የማይቀር ነውና፤ ይሁን እንጂ ሰውነታችሁ የሚፈጽመውን ሥራ በመንፈስ ብትገድሉ+ በሕይወት ትኖራላችሁ።+ +14 በአምላክ መንፈስ የሚመሩ ሁሉ በእርግጥ የአምላክ ልጆች ናቸውና።+ +15 ዳግመኛ ለፍርሃት የሚዳርጋችሁን የባርነት መንፈስ አልተቀበላችሁም፤ ከዚህ ይልቅ አምላክ ልጆቹ አድርጎ እንዲወስዳችሁ የሚያስችል መንፈስ አግኝታችኋል፤ ይህም መንፈስ “አባ፣* አባት!”+ ብለን እንድንጣራ ይገፋፋናል። +16 የአምላክ ልጆች+ መሆናችንን ይህ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ሆኖ ይመሠክራል።+ +17 እንግዲህ ልጆች ከሆን ወራሾች ነን፤ ይኸውም ከአምላክ ውርሻ እንቀበላለን፤ ይሁንና የምንወርሰው ከክርስቶስ ጋር ነው፤+ አሁን አብረነው መከራ ከተቀበልን፣+ በኋላ ደግሞ አብረነው ክብር እንጎናጸፋለን።+ +18 በአሁኑ ጊዜ የሚደርስብን መከራ በእኛ ላይ ከሚገለጠው ክብር ጋር ሲነጻጸር ከምንም ሊቆጠር እንደማይችል አምናለሁ።+ +19 ፍጥረት የአምላክን ልጆች መገለጥ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠባበቀ ነው።+ +20 ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቷልና፤+ የተገዛው ግን በገዛ ፈቃዱ ሳይሆን በተስፋ እንዲገዛ ባደረገው በእሱ አማካኝነት ነው፤ +21 ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከመበስበስ ባርነት ነፃ ወጥቶ+ የአምላክ ልጆች የሚያገኙት ዓይነት ክብራማ ነፃነት ማግኘት ነው። +22 ፍጥረት ሁሉ እስካሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በመሠቃየት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን። +23 ይህም ብቻ ሳይሆን የውርሻችንን በኩራት ይኸውም መንፈስን ያገኘን እኛ ራሳችንም በቤዛው አማካኝነት ከሥጋዊ አካላችን ነፃ በመውጣት አምላክ ልጆቹ አድርጎ እንዲወስደን+ በጉጉት እየተጠባበቅን በውስጣችን እንቃትታለን።+ +24 በዚህ ተስፋ ድነናል፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረገው ነገር የሚታይ ከሆነ ተስፋ መሆኑ ይቀራል፤ ደግሞስ አንድ ሰው የሚያየውን ነገር ተስፋ ያደርጋል? +25 የማናየውን ነገር+ ተስፋ የምናደርግ ከሆነ+ ግን ጸንተን በጉጉት እንጠባበቀዋለን።+ +26 በተመሳሳይም መንፈስ በድካማችን ይረዳናል።+ ምን ብለን መጸለይ እንዳለብን ግራ የምንጋባበት ጊዜ ሊኖር ይችላል። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥመንና ስሜታችንን በቃላት መግለጽ ተስኖን ስንቃ���ት መንፈስ ራሱ ስለ እኛ ይማልዳል። +27 ይሁንና ልብን የሚመረምረው+ አምላክ የመንፈስን ዓላማ ያውቃል፤ ምክንያቱም መንፈስ ለቅዱሳን የሚማልደው ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ነው። +28 አምላክ ለሚወዱት ይኸውም ከእሱ ዓላማ ጋር በሚስማማ መንገድ ለተጠሩት ሥራውን ሁሉ አቀናጅቶ ለበጎ እንዲሆንላቸው እንደሚያደርግ እናውቃለን፤+ +29 ምክንያቱም መጀመሪያ እውቅና የሰጣቸው ሰዎች የልጁን መልክ እንዲመስሉ+ አስቀድሞ ወስኗል፤ ይኸውም ልጁ ከብዙ ወንድሞች+ መካከል በኩር+ እንዲሆን ነው። +30 ከዚህም በተጨማሪ አስቀድሞ የወሰናቸውን+ እነዚህን ጠራቸው፤+ የጠራቸውን እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው።+ በመጨረሻም ያጸደቃቸውን እነዚህን አከበራቸው።+ +31 እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንበል? አምላክ ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?+ +32 ለገዛ ልጁ እንኳ ያልሳሳው፣ ከዚህ ይልቅ ለእኛ ለሁላችን አሳልፎ የሰጠው+ አምላክ፣ ከእሱ ጋር አብሮ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ እንዴት በደግነት አይሰጠንም? +33 አምላክ የመረጣቸውን ማን ሊከሳቸው ይችላል?+ ምክንያቱም የሚያጸድቃቸው አምላክ ራሱ ነው።+ +34 እነሱን የሚኮንን ማን ነው? ምክንያቱም የሞተው ብሎም ከሞት የተነሳውና በአምላክ ቀኝ የተቀመጠው+ እንዲሁም ስለ እኛ የሚማልደው+ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። +35 ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል?+ መከራ ወይስ ጭንቀት ወይስ ስደት ወይስ ረሃብ ወይስ ራቁትነት ወይስ አደጋ ወይስ ሰይፍ?+ +36 ይህም “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ሞትን እንጋፈጣለን፤ እንደ እርድ በጎችም ተቆጠርን”+ ተብሎ እንደተጻፈው ነው። +37 ከዚህ ይልቅ በወደደን በእሱ አማካኝነት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ሙሉ በሙሉ በድል አድራጊነት እንወጣለን።+ +38 ምክንያቱም ሞትም ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣ መንግሥታትም ቢሆኑ፣ አሁን ያሉት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ወደፊት የሚመጡት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ማንኛውም ኃይል+ ቢሆን፣ +39 ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን፣ ሌላ ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ከተገለጸው የአምላክ ፍቅር ሊለየን እንደማይችል ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነኝ። +11 እንግዲያው ‘አምላክ ሕዝቡን ትቷል ማለት ነው?’ ብዬ እጠይቃለሁ፤+ በፍጹም! ምክንያቱም እኔም ራሴ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከአብርሃም ዘር፣ ከቢንያም ነገድ ነኝ። +2 አምላክ መጀመሪያ እውቅና የሰጣቸውን ሰዎች አልተዋቸውም።+ ቅዱስ መጽሐፉ ኤልያስ እስራኤልን በአምላክ ፊት በከሰሰበት ጊዜ የሆነውን ነገር በተመለከተ ምን እንደሚል አታውቁም? +3 “ይሖዋ* ሆይ፣ ነቢያትህን ገድለዋል፤ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋል፤ እኔ ብቻ ቀረሁ፤ አሁንም ሕይወቴን* ለማጥፋት ጥረት እያደረጉ ነው።”+ +"4 ይሁንና አምላክ የሰጠው መልስ ምን ነበር? “ለባአል ያልተንበረከኩ 7,000 ሰዎች አሉኝ።”+" +5 ስለዚህ በዚህ መንገድ በጸጋ የተመረጡ ቀሪዎች+ በአሁኑ ዘመንም አሉ። +6 የተመረጡት በጸጋ+ ከሆነ በሥራ መሆኑ ቀርቷል፤+ አለዚያ ጸጋው ጸጋ መሆኑ በቀረ ነበር። +7 እንግዲህ ምን ማለት እንችላለን? እስራኤል አጥብቆ ይፈልገው የነበረውን ነገር አላገኘም፤ የተመረጡት ግን አገኙት።+ የቀሩት የማስተዋል ስሜታቸው ደነዘዘ፤+ +8 ይህም “አምላክ እስከ ዛሬ ኃይለኛ የእንቅልፍ መንፈስ ጣለባቸው፤+ የማያይ ዓይንና የማይሰማ ጆሮ ሰጣቸው” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +9 በተጨማሪም ዳዊት እንዲህ ብሏል፦ “ማዕዳቸው ወጥመድና አሽክላ እንዲሁም እንቅፋትና ቅጣት ይሁንባቸው። +10 ዓይኖቻቸው ማየት እንዳይችሉ ይጨልሙ፤ ጀርባቸውም ጎብጦ እንዲቀር አድርግ።”+ +11 በመሆኑም ‘የተሰናከሉት ወድቀው እንዲቀሩ ነው?’ ብዬ እጠይቃለሁ፤ በፍጹም! ከዚህ ይልቅ እነሱ ሕጉን በመተላለፋቸው ለአሕዛብ የመዳን መንገድ ተከፈተ፤ ይህም የሆነው እነሱን ለማስቀናት ነው።+ +12 እነሱ ሕጉን መተላለፋቸው ለዓለም በረከት ከሆነና የእነሱ ማነስ ለአሕዛብ በረከት ካስገኘ+ ቁጥራቸው መሙላቱማ ምን ያህል ታላቅ በረከት ያስገኝ ይሆን! +13 አሁን ደግሞ የምናገረው ከአሕዛብ ወገን ለሆናችሁት ነው። ለአሕዛብ የተላክሁ ሐዋርያ+ እንደመሆኔ መጠን አገልግሎቴን አከብራለሁ፤*+ +14 ይህን የማደርገው የገዛ ወገኖቼ* የሆኑትን በማስቀናት ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹን ማዳን እችል እንደሆነ ብዬ ነው። +15 የእነሱ መጣል+ ለዓለም እርቅ ካስገኘ፣ ተቀባይነት ማግኘታቸውማ ከሞት ወደ ሕይወት መሻገር ማለት አይሆንም? +16 በተጨማሪም በኩራት ተደርጎ የተወሰደው የሊጡ ክፍል ቅዱስ ከሆነ ሊጡ በሙሉ ቅዱስ ነው፤ እንዲሁም ሥሩ ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹም ቅዱሳን ናቸው። +17 ይሁን እንጂ ከቅርንጫፎቹ መካከል አንዳንዶቹ ቢሰበሩና አንተ የዱር ወይራ ሆነህ ሳለህ በእነሱ መካከል ከተጣበቅክ እንዲሁም ከወይራው ዛፍ ሥር ከሚገኘው በረከት ተካፋይ ከሆንክ +18 በተሰበሩት ቅርንጫፎች ላይ አትታበይ።* በእነሱ ላይ የምትታበይ+ ከሆነ ግን አንተን የተሸከመህ ሥሩ ነው እንጂ አንተ ሥሩን እንዳልተሸከምከው አስታውስ። +19 ይሁንና “ቅርንጫፎቹ የተሰበሩት እኔ በቦታቸው እንድጣበቅ ነው”+ ብለህ ታስብ ይሆናል። +20 እውነት ነው! እነሱ ባለማመናቸው ተሰብረዋል፤+ አንተ ግን በእምነት ቆመሃል።+ ቢሆንም መፍራት እንጂ መታበይ አይገባህም። +21 አምላክ በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት ካልራራ ለአንተም አይራራምና። +22 ስለዚህ አምላክ ደግም+ ጥብቅም እንደሆነ ተመልከት። በወደቁት ላይ ጥብቅ ይሆናል፤+ አንተ ግን የአምላክ ደግነት የሚገባህ ሆነህ እስከተገኘህ ድረስ ደግነቱን ያሳይሃል፤ አለዚያ ግን አንተም ተቆርጠህ ትጣላለህ። +23 እነሱም እምነት የለሽ ሆነው ካልቀጠሉ ይጣበቃሉ፤ አምላክ መልሶ ሊያጣብቃቸው+ ይችላልና። +24 አንተ በተፈጥሮ የዱር ከሆነው የወይራ ዛፍ ተቆርጠህ፣ ከተፈጥሮ ውጭ በሆነ መንገድ በጓሮ የወይራ ዛፍ ላይ መጣበቅ ከቻልክ እነዚህ ተፈጥሯዊ የሆኑት ቅርንጫፎችማ በራሳቸው የወይራ ዛፍ ላይ ተመልሰው መጣበቅ እንደሚችሉ የታወቀ ነው! +25 ወንድሞች፣ በራሳችሁ ዓይን ጥበበኞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ቅዱስ ሚስጥር እንድታውቁ እፈልጋለሁ፦+ የአሕዛብ ቁጥር እስኪሞላ ድረስ የእስራኤል ሕዝብ በከፊል ስሜቱ ደንዝዟል፤ +26 በዚህም መንገድ እስራኤል ሁሉ+ ይድናል። ይህም እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈው ነው፦ “አዳኝ* ከጽዮን ይወጣል፤+ የያዕቆብም ዘሮች የክፋት ድርጊታቸውን እንዲተዉ ያደርጋል። +27 ኃጢአታቸውንም በማስወግድበት ጊዜ+ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው።”+ +28 እርግጥ ከምሥራቹ ጋር በተያያዘ ለእናንተ ጥቅም ሲባል የአምላክ ጠላቶች ናቸው፤ በአምላክ ምርጫ መሠረት ግን ለአባቶቻቸው በተገባው የተስፋ ቃል የተነሳ በአምላክ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።+ +29 አምላክ በስጦታውና በጠራቸው ሰዎች አይጸጸትምና። +30 በአንድ ወቅት እናንተ አምላክን የማትታዘዙ ነበራችሁ፤+ አሁን ግን በእነሱ አለመታዘዝ+ ምክንያት ምሕረት አግኝታችኋል።+ +31 ስለዚህ አይሁዳውያን ሳይታዘዙ በመቅረታቸው አምላክ ለእናንተ ምሕረት አሳይቷችኋል፤ ከዚህም የተነሳ ለእነሱም ምሕረት ሊያሳያቸው ይችላል። +32 አምላክ ለሁሉም ምሕረት ያሳይ ዘንድ+ ሁሉም ያለመታዘዝ እስረኞች+ እንዲሆኑ ፈቅዷልና። +33 የአምላክ ብልጽግና፣ ጥበብና እውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱም ፈጽሞ የማይመረመር ነው! መንገዱም የማይደረስበት ነው! +34 እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ “የይሖዋን* ሐሳብ ማወቅ የቻለ ማን ነው? አማካሪውስ የሆነ ማን ነው?”+ +35 ወይስ “መልሶ ይከፍለው ዘንድ ለእሱ ያበደረ ማን ነው?”+ +36 ምክንያቱም ሁሉም ነገር የተገኘው ከእሱ፣ በእሱና ለእሱ ነው። ለእሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። +2 ስለዚህ አንተ ሰው፣ ማንም ሆንክ ማን+ በሌላው ላይ የምትፈርድ ከሆነ ምንም የምታመካኝበት ነገር የለህም፤ በሌላው ላይ ስትፈርድ ራስህንም ኮነንክ ማለት ነው፤ ምክንያቱም በሌላው ላይ የምትፈርድ አንተ ራስህ እነዚያኑ ነገሮች በተደጋጋሚ ታደርጋለህ።+ +2 አምላክ እንዲህ ያሉትን ነገሮች በሚፈጽሙ ሰዎች ላይ እንደሚፈርድ እናውቃለን፤ ፍርዱ ደግሞ ከእውነት ጋር የሚስማማ ነው። +3 ይሁን እንጂ አንተ ሰው፣ እንዲህ ያሉትን ነገሮች በሚፈጽሙ ሰዎች ላይ እየፈረድክ አንተ ግን እነዚያኑ ነገሮች የምታደርግ ከሆነ ከአምላክ ፍርድ አመልጣለሁ ብለህ ታስባለህ? +4 ወይስ አምላክ በደግነቱ ወደ ንስሐ ሊመራህ+ እየሞከረ እንዳለ ሳታውቅ የደግነቱን፣+ የቻይነቱንና+ የትዕግሥቱን+ ብዛት ትንቃለህ? +5 እንግዲህ በግትርነትህና ንስሐ በማይገባው ልብህ የተነሳ በራስህ ላይ ቁጣ ታከማቻለህ። ይህ ቁጣ አምላክ የጽድቅ ፍርድ በሚፈርድበት ቀን ይገለጣል።+ +6 እሱም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍለዋል፦+ +7 በመልካም ሥራ በመጽናት ክብርን፣ ሞገስንና ሊጠፋ የማይችል ሕይወትን+ ለሚፈልጉ የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ +8 ይሁን እንጂ ጠብ ወዳዶች በሆኑትና ለእውነት ከመታዘዝ ይልቅ ለዓመፅ በሚታዘዙት ላይ ቁጣና መዓት ይወርድባቸዋል።+ +9 ክፉ ሥራ በሚሠራ ሰው ሁሉ* ላይ ይኸውም በመጀመሪያ በአይሁዳዊ ከዚያም በግሪካዊ ላይ መከራና ጭንቀት ይመጣል፤ +10 ሆኖም መልካም ሥራ የሚሠራ ሁሉ ይኸውም በመጀመሪያ አይሁዳዊ+ ከዚያም ግሪካዊ+ ክብር፣ ሞገስና ሰላም ያገኛል። +11 በአምላክ ዘንድ አድልዎ የለምና።+ +12 ሕግ ሳይኖራቸው ኃጢአት የሠሩ ሁሉ ያለሕግ ይጠፋሉና፤+ ሆኖም ሕግ እያላቸው ኃጢአት የሠሩ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል።+ +13 ምክንያቱም በአምላክ ፊት ጻድቅ የሆኑት ሕግን የሚሰሙ አይደሉም፤ ከዚህ ይልቅ ጻድቃን ናችሁ የሚባሉት ሕግን የሚፈጽሙ ናቸው።+ +14 ሕግ የሌላቸው+ አሕዛብ በተፈጥሮ በሕጉ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሲያደርጉ እነዚህ ሰዎች ሕግ ባይኖራቸውም እንኳ እነሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና። +15 የሕጉ መሠረታዊ ሐሳብ በልባቸው እንደተጻፈ የሚያሳዩት እነሱ ራሳቸው ናቸው፤ ሕሊናቸው ከእነሱ ጋር ሆኖ በሚመሠክርበት ጊዜ ሐሳባቸው በውስጣቸው* እየተሟገተ አንዴ ይከሳቸዋል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጥፋተኛ አይደላችሁም ይላቸዋል። +16 ይህ የሚሆነው እኔ በማውጀው ምሥራች መሠረት አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ሰዎች በስውር በሚያስቧቸውና በሚያደርጓቸው ነገሮች ላይ በሚፈርድበት+ ቀን ነው። +17 አንተ አይሁዳዊ ተብለህ የምትጠራ፣+ በሕጉ የምትመካ፣ ከአምላክ ጋር ባለህ ዝምድና የምትኩራራ፣ +18 ፈቃዱን የምታውቅ፣ በሕጉ ውስጥ ያለውን ነገር የተማርክ*+ በመሆንህ የላቀ ዋጋ ያላቸውን ነገሮች በሚገባ የምትገነዘብ፣ +19 ለዕውር መሪ፣ በጨለማ ላሉት ብርሃን ነኝ ብለህ የምታምን፣ +20 ማስተዋል የጎደላቸውን የማሠለጥንና ሕፃናትን የማስተምር ነኝ የምትል እንዲሁም በሕጉ ውስጥ ያሉትን የእውቀትና የእውነት መሠረታዊ ገጽታዎች የምታውቅ ከሆንክ፣ +21 ታዲያ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርም?+ አንተ “አትስረቅ”+ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህ? +22 አንተ “አታመንዝር”+ የምትል ታመነዝራለህ? አንተ ጣዖትን የምትጸየፍ ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህ? +23 አንተ በሕግ የምትኩራራ ሕጉን በመተላለፍ አምላክን ታዋርዳለህ? +24 ይህም “በእናንተ ምክንያት የአምላክ ስም በአሕ���ብ መካከል ይሰደባል” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +25 መገረዝ+ ጥቅም የሚኖረው ሕጉን እስካከበርክ ድረስ ነው፤+ ሕጉን የምትተላለፍ ከሆነ ግን መገረዝህ እንደ አለመገረዝ ይቆጠራል። +26 ያልተገረዘ ሰው+ በሕጉ ውስጥ ያሉትን የጽድቅ መሥፈርቶች የሚጠብቅ ከሆነ አለመገረዙ እንደ መገረዝ አይቆጠርም?+ +27 እንግዲህ አንተ የተጻፈ ሕግ ያለህና የተገረዝክ ሆነህ ሳለ ሕግን የምትጥስ ከሆነ በሥጋ ያልተገረዘ ሆኖ ሕግን የሚፈጽም ሰው ይፈርድብሃል። +28 ምክንያቱም እውነተኛ አይሁዳዊነት በውጫዊ ገጽታ የሚገለጽ አይደለም፤+ ግርዘቱም ውጫዊና ሥጋዊ ግርዘት አይደለም።+ +29 ከዚህ ይልቅ በውስጡ አይሁዳዊ የሆነ እሱ አይሁዳዊ ነው፤+ ግርዘቱም በተጻፈ ሕግ ሳይሆን በመንፈስ+ የሆነ የልብ ግርዘት ነው።+ እንዲህ ዓይነቱ ሰው ውዳሴ የሚያገኘው ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው።+ +4 እንዲህ ከሆነ ታዲያ በሥጋ አባታችን የሆነው አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? +2 ለምሳሌ አብርሃም ጻድቅ የተባለው በሥራ ቢሆን ኖሮ የሚመካበት ነገር በኖረው ነበር፤ ሆኖም በአምላክ ፊት ሊመካ አይችልም። +3 የቅዱስ መጽሐፉስ ቃል ምን ይላል? “አብርሃም በይሖዋ* አመነ፤ ይህም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።”+ +4 ይሁንና ለሚሠራ ሰው ደሞዙ እንደ ሥራው ዋጋ* እንጂ እንደ ጸጋ ስጦታ ተደርጎ አይቆጠርለትም። +5 በሌላ በኩል ግን በራሱ ሥራ ከመመካት ይልቅ ኃጢአተኛውን ጻድቅ ነህ ብሎ በሚጠራው አምላክ የሚያምን እምነቱ እንደ ጽድቅ ይቆጠርለታል።+ +6 ይህም ዳዊት፣ አምላክ ያለሥራ እንደ ጻድቅ አድርጎ የሚቆጥረው ሰው ስለሚያገኘው ደስታ እንዲህ ብሎ እንደተናገረው ነው፦ +7 “የዓመፅ ሥራቸው ይቅር የተባለላቸው፣ ኃጢአታቸውም የተሸፈነላቸው* ደስተኞች ናቸው፤ +8 ይሖዋ* ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ደስተኛ ነው።”+ +9 ታዲያ ይህን ደስታ የሚያገኙት የተገረዙ ሰዎች ብቻ ናቸው ወይስ ያልተገረዙትም ጭምር?+ ምክንያቱም “አብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት” ብለናል።+ +10 ታዲያ እምነቱ እንደ ጽድቅ የተቆጠረው በምን ዓይነት ሁኔታ እያለ ነው? ተገርዞ እያለ ነው ወይስ ከመገረዙ በፊት? ተገርዞ እያለ ሳይሆን ከመገረዙ በፊት ነው። +11 ገና ከመገረዙ በፊት በነበረው እምነት ላገኘው ጽድቅ ምልክት ሆኖ የሚያገለግለውን+ ግርዘትን እንደ ማኅተም* ተቀበለ፤ ስለዚህ ባይገረዙም እንኳ በእምነታቸው የተነሳ እንደ ጻድቃን ለተቆጠሩት ሁሉ አባት ሆኗል፤+ +12 ለተገረዙት ዘሮቹም አባት ነው፤ ይሁንና ግርዘትን አጥብቀው ለሚከተሉት ብቻ ሳይሆን አባታችን አብርሃም+ ከመገረዙ በፊት የነበረውን እምነት ተከትለው በሥርዓት ለሚመላለሱ ሰዎችም ሁሉ አባት ነው። +13 ምክንያቱም አብርሃም ወይም ዘሩ የዓለም ወራሽ+ እንደሚሆን ተስፋ የተሰጠው በሕግ አማካኝነት ሳይሆን በእምነት በሚገኘው ጽድቅ ነው።+ +14 ወራሾች የሚሆኑት ሕጉን በጥብቅ የሚከተሉ ቢሆኑ ኖሮ እምነት ከንቱ በሆነ ነበርና፤ የተስፋውም ቃል ባከተመ ነበር። +15 እንደ እውነቱ ከሆነ ሕጉ ቁጣ ያስከትላል፤+ ሆኖም ሕግ ከሌለ ሕግን መተላለፍ የሚባል ነገር አይኖርም።+ +16 በመሆኑም ተስፋው በእምነት የተገኘ ነው፤ ይህም የሆነው ተስፋው በጸጋ+ ላይ የተመሠረተ እንዲሆንና ለዘሩ ሁሉ+ ይኸውም ሕጉን በጥብቅ ለሚከተል ብቻ ሳይሆን የሁላችንም አባት+ የሆነውን የአብርሃምን እምነት በጥብቅ ለሚከተል ጭምር የተረጋገጠ እንዲሆን ነው። +17 (ይህም “ለብዙ ብሔራት አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።)+ ይህ የሆነው እሱ ባመነበት ማለትም ሙታንን ሕያው በሚያደርገውና የሌለውን እንዳለ አድርጎ በሚጠራው* አምላክ ፊት ነው። +18 ተስፋ ለማድረግ የሚያበቃ ምንም መሠረት ባይኖርም እንኳ “የአ���ተም ዘር እጅግ ይበዛል”+ ተብሎ በተነገረው መሠረት የብዙ ብሔራት አባት እንደሚሆን በተሰጠው ተስፋ አምኗል። +19 እምነቱ ባይዳከምም እንኳ 100 ዓመት ገደማ+ ሆኖት ስለነበር የሞተ ያህል ስለሆነው የገዛ ራሱ አካል እንዲሁም ሙት* ስለሆነው የሣራ ማህፀን አሰበ።+ +20 ሆኖም አምላክ ከሰጠው የተስፋ ቃል የተነሳ ለአምላክ ክብር በመስጠት በእምነት በረታ እንጂ እምነት በማጣት አልወላወለም፤ +21 ደግሞም አምላክ የሰጠውን ተስፋ መፈጸም እንደሚችል ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነበር።+ +22 በመሆኑም “ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።”+ +23 ሆኖም “ተቆጠረለት” ተብሎ የተጻፈው ስለ እሱ ብቻ አይደለም፤+ +24 ከዚህ ይልቅ እንደ ጻድቃን ስለምንቆጠረው ስለ እኛም ጭምር ነው፤ ምክንያቱም ጌታችንን ኢየሱስን ከሞት ባስነሳው በእሱ እናምናለን።+ +25 ኢየሱስ ስለ በደላችን ለሞት አልፎ ተሰጠ፤+ አምላክ ጻድቃን ናችሁ ብሎ እንዲያስታውቅልንም ከሞት ተነሳ።+ +16 በክንክራኦስ+ ጉባኤ የምታገለግለውን እህታችንን ፌበንን ላስተዋውቃችሁ እወዳለሁ፤ +2 በጌታ የእምነት ባልደረባችሁ እንደመሆኗ መጠን ለቅዱሳን በሚገባ ሁኔታ* ተቀበሏት፤ የምትፈልገውንም እርዳታ ሁሉ አድርጉላት፤+ ምክንያቱም እሷ እኔን ጨምሮ ለብዙ ወንድሞች ድጋፍ ሆናለች። +3 በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩት ለጵርስቅላና ለአቂላ+ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ +4 እነሱ ለእኔ* ሲሉ ሕይወታቸውን* ለአደጋ አጋልጠዋል፤+ እኔ ብቻ ሳልሆን በአሕዛብ መካከል የሚገኙ ጉባኤዎችም ሁሉ ያመሰግኗቸዋል። +5 በቤታቸው ላለው ጉባኤም ሰላምታ አቅርቡልኝ።+ በእስያ ከመጀመሪያዎቹ የክርስቶስ ተከታዮች አንዱ የሆነውን የምወደውን ኤጲኔጦስን ሰላም በሉልኝ። +6 ለእናንተ ብዙ የደከመችውን ማርያምን ሰላም በሉልኝ። +7 ዘመዶቼ+ የሆኑትንና አብረውኝ የታሰሩትን እንዲሁም በሐዋርያት ዘንድ ስመጥር የሆኑትንና ከእኔ ቀደም ብለው የክርስቶስ ተከታዮች የሆኑትን አንድሮኒኮስንና ዩኒያስን ሰላም በሉልኝ። +8 በጌታ ለምወደው ለአምጵልያጦስ ሰላምታዬን አቅርቡልኝ። +9 በክርስቶስ አብሮን የሚሠራውን ኡርባኖስንና የምወደውን እስጣኩስን ሰላም በሉልኝ። +10 በክርስቶስ ዘንድ መልካም ስም ያተረፈውን አጵሌስን ሰላም በሉልኝ። የአርስጦቡሉስ ቤተሰብ ለሆኑት ሰላምታ አቅርቡልኝ። +11 ዘመዴን ሄሮድዮንን ሰላም በሉልኝ። የጌታ ተከታዮች የሆኑትን የናርኪሰስን ቤተሰቦች ሰላም በሉልኝ። +12 በጌታ ሆነው በትጋት የሚሠሩትን ጥራይፊናና ጥራይፎሳ የተባሉትን ሴቶች ሰላም በሉልኝ። የምንወዳትን ጰርሲስን ሰላም በሉልኝ፤ በጌታ ሥራ ብዙ ደክማለችና። +13 የጌታ ምርጥ አገልጋይ ለሆነው ለሩፎስ እንዲሁም እኔም እንደ እናቴ ለማያት ለእናቱ ሰላምታ አቅርቡልኝ። +14 አሲንክሪጦስን፣ ፍሌጎንን፣ ሄርሜስን፣ ጳጥሮባን፣ ሄርማስንና ከእነሱ ጋር ያሉትን ወንድሞች ሰላም በሉልኝ። +15 ፊሎሎጎስንና ዩልያን፣ ኔርዩስንና እህቱን፣ ኦሊምጳስን እንዲሁም ከእነሱ ጋር ያሉትን ቅዱሳን ሁሉ ሰላም በሉልኝ። +16 በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ። የክርስቶስ ጉባኤዎች በሙሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። +17 እንግዲህ ወንድሞች፣ ክፍፍል ከሚፈጥሩና ለእንቅፋት ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ከሚያመጡ ሰዎች እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች የተማራችሁትን ትምህርት የሚጻረሩ ናቸው፤ ይህን ከሚያደርጉ ሰዎች ራቁ።+ +18 እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ለጌታችን ለክርስቶስ ሳይሆን ለራሳቸው ፍላጎት* ባሪያዎች ናቸው፤ በለሰለሰ አንደበትና በሽንገላ ቃላት የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ። +19 ታዛዥነታችሁ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ሆኗል፤ ስለዚህ እኔ በእናንተ እጅግ እደሰታለሁ። ይሁንና ለመልካም ነገር ጥበበኞች እንድትሆኑ፣ ለክፉ ነገር ደግሞ አላዋቂዎች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።+ +20 ሰላም የሚሰጠው አምላክ በቅርቡ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ይጨፈልቀዋል።+ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። +21 የሥራ አጋሬ ጢሞቴዎስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ ዘመዶቼ+ የሆኑት ሉክዮስ፣ ያሶንና ሶሲጳጥሮስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። +22 ይህን ደብዳቤ በጽሑፍ ያሰፈርኩት እኔ ጤርጥዮስም በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ። +23 እኔንም ሆነ መላውን ጉባኤ የሚያስተናግደው ጋይዮስ+ ሰላም ይላችኋል። የከተማዋ የግምጃ ቤት ሹም* ኤርስጦስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ ወንድሙ ቁአስጥሮስም ሰላም ይላችኋል። +24 *—— +25 አምላክ ለረጅም ዘመናት ተሰውሮ ከቆየው ቅዱስ ሚስጥር+ መገለጥ ጋር በሚስማማ ሁኔታ እኔ በማውጀው ምሥራችና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰበከው መልእክት መሠረት ሊያጸናችሁ ይችላል። +26 አሁን ግን ሕዝቦች ሁሉ እምነት እንዲኖራቸውና እሱን እንዲታዘዙ ቅዱሱ ሚስጥር፣ በዘላለማዊው አምላክ ትእዛዝ መሠረት ትንቢታዊ በሆኑ ቅዱሳን መጻሕፍት አማካኝነት በሕዝቦች ሁሉ መካከል እንዲገለጥና እንዲታወቅ ተደርጓል፤ +27 እሱ ብቻ ጥበበኛ+ ለሆነው አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። +6 እንግዲህ ምን እንበል? ጸጋ እንዲበዛ ኃጢአት መሥራታችንን እንቀጥል? +2 በፍጹም! እኛ ለኃጢአት የሞትን+ ሆነን ሳለን ከእንግዲህ እንዴት በኃጢአት ውስጥ መኖራችንን እንቀጥላለን?+ +3 ወይስ ክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ የተጠመቅን+ ሁላችን እሱ ሞት ውስጥ እንደተጠመቅን+ አታውቁም? +4 ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደተነሳ ሁሉ እኛም አዲስ ሕይወት እንድንኖር+ እሱ ሞት ውስጥ በመጠመቅ ከእሱ ጋር ተቀብረናል።+ +5 ሞቱን በሚመስል ሞት ከእሱ ጋር አንድ ከሆንን+ ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ+ ደግሞ ከእሱ ጋር አንድ እንደምንሆን ጥርጥር የለውም። +6 ምክንያቱም ኃጢአተኛው ሰውነታችን በእኛ ላይ ምንም ኃይል እንዳይኖረውና+ ከእንግዲህ የኃጢአት ባሪያዎች ሆነን እንዳንኖር+ አሮጌው ስብዕናችን ከእሱ ጋር በእንጨት ላይ እንደተቸነከረ እናውቃለን።+ +7 የሞተ ከኃጢአቱ ነፃ ወጥቷልና።* +8 በተጨማሪም ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእሱ ጋር እንደምንኖር እናምናለን። +9 ክርስቶስ አሁን ከሞት እንደተነሳና+ ዳግመኛ እንደማይሞት+ እናውቃለን፤ ከእንግዲህ ሞት በእሱ ላይ እንደ ጌታ ሊሠለጥን አይችልም። +10 ምክንያቱም እሱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኃጢአት ሞቷል፤*+ ሆኖም አሁን እየኖረ ያለውን ሕይወት የሚኖረው ለአምላክ ነው። +11 በተመሳሳይም እናንተ ለኃጢአት እንደሞታችሁ ሆኖም በክርስቶስ ኢየሱስ ለአምላክ እንደምትኖሩ አድርጋችሁ አስቡ።+ +12 በመሆኑም ኃጢአት ለሰውነታችሁ ምኞት ተገዢ እንድትሆኑ በማድረግ ሟች በሆነው ሰውነታችሁ ላይ መንገሡን እንዲቀጥል አትፍቀዱ።+ +13 በተጨማሪም ሰውነታችሁን* የክፋት መሣሪያ* አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፤ ከዚህ ይልቅ ከሞት ወደ ሕይወት እንደተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለአምላክ አቅርቡ፤ ሰውነታችሁንም* የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለአምላክ አቅርቡ።+ +14 ምክንያቱም በጸጋ+ ሥር እንጂ በሕግ ሥር ስላልሆናችሁ+ ኃጢአት በእናንተ ላይ ጌታ ሊሆን አይገባም። +15 እንግዲህ ከዚህ በመነሳት ምን ማለት እንችላለን? በጸጋ ሥር እንጂ በሕግ ሥር ስላልሆንን ኃጢአት እንሥራ ማለት ነው?+ በፍጹም! +16 ለማንም ቢሆን ታዛዥ ባሪያዎች ሆናችሁ ራሳችሁን ካቀረባችሁ ለዚያ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች+ እንደሆናችሁ አታውቁም? በመሆኑም ሞት+ ለሚያስከትለው ለኃጢአት+ አለዚያም ጽድቅ ለሚያስገኘው ለታዛዥነት ባሪያዎ�� ናችሁ። +17 ሆኖም እናንተ በአንድ ወቅት የኃጢአት ባሪያዎች የነበራችሁ ቢሆንም እንድትከተሉት ለተሰጣችሁ ለእንዲህ ዓይነቱ ትምህርት ከልብ ስለታዘዛችሁ አምላክ የተመሰገነ ይሁን። +18 አዎ፣ ከኃጢአት ነፃ ስለወጣችሁ+ የጽድቅ ባሪያዎች ሆናችኋል።+ +19 እኔ ሰዎች በሚረዱት ቋንቋ የምናገረው በሥጋችሁ ድክመት የተነሳ ነው፤ የአካል ክፍሎቻችሁን ክፉ ድርጊት ለመፈጸም ለርኩሰትና ለክፋት ባሪያዎች አድርጋችሁ አቅርባችሁ እንደነበረ ሁሉ አሁን ደግሞ የአካል ክፍሎቻችሁን ቅዱስ ሥራ ለመሥራት የጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ።+ +20 የኃጢአት ባሪያዎች በነበራችሁበት ጊዜ በጽድቅ ሥር አልነበራችሁምና። +21 ታዲያ በዚያን ጊዜ ታፈሯቸው የነበሩት ፍሬዎች ምን ዓይነት ነበሩ? አሁን የምታፍሩባቸው ነገሮች ናቸው። የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነውና።+ +22 ይሁን እንጂ አሁን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችሁ የአምላክ ባሪያዎች ስለሆናችሁ በቅድስና ጎዳና ፍሬ እያፈራችሁ ነው፤+ የዚህም መጨረሻ የዘላለም ሕይወት ነው።+ +23 የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና፤*+ አምላክ የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ+ የዘላለም ሕይወት ነው።+ +10 ወንድሞች፣ ለእስራኤላውያን ከልቤ የምመኘውና ስለ እነሱ ለአምላክ ምልጃ የማቀርበው እንዲድኑ ነው።+ +2 ለአምላክ ቅንዓት እንዳላቸው እመሠክርላቸዋለሁና፤+ ሆኖም ቅንዓታቸው በትክክለኛ እውቀት ላይ የተመሠረተ አይደለም። +3 የአምላክን ጽድቅ ሳያውቁ+ የራሳቸውን ጽድቅ ለመመሥረት+ ስለፈለጉ ራሳቸውን ለአምላክ ጽድቅ አላስገዙም።+ +4 የሚያምን* ሁሉ መጽደቅ ይችል ዘንድ+ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።+ +5 ሙሴ በሕጉ አማካኝነት ስለሚገኘው ጽድቅ ሲገልጽ “እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል” ሲል ጽፏል።+ +6 ሆኖም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ በተመለከተ እንዲህ ተብሏል፦ “በልብህ+ ‘ወደ ሰማይ ማን ይወጣል?’ አትበል፤+ ይህም ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ +7 ወይም ‘ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል?’ አትበል፤+ ይህም ክርስቶስን ከሞት ለማስነሳት ነው።” +8 ይሁንና ቅዱስ መጽሐፉ ምን ይላል? “ቃሉ ለአንተ ቅርብ ነው፤ ደግሞም በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው”፤+ ይህም እኛ የምንሰብከው የእምነት “ቃል” ነው። +9 ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ በይፋ ብትናገር+ እንዲሁም አምላክ ከሞት እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና። +10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና፤ በአፉ ደግሞ እምነቱን በይፋ ተናግሮ ይድናል።+ +11 ቅዱስ መጽሐፉ “በእሱ ላይ እምነት የሚጥል ሁሉ አያፍርም” ይላል።+ +12 በአይሁዳዊና በግሪካዊ መካከል ምንም ልዩነት የለምና።+ የሁሉም ጌታ አንድ ነው፤ እሱም የሚለምኑትን ሁሉ አብዝቶ ይባርካል።* +13 “የይሖዋን* ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።”+ +14 ይሁንና ካላመኑበት እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ስለ እሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምኑበታል? ደግሞስ የሚሰብክላቸው ሳይኖር እንዴት ይሰማሉ? +15 ካልተላኩስ እንዴት ይሰብካሉ?+ ይህም “የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ምሥራች የሚናገሩ ሰዎች እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው!”+ ተብሎ እንደተጻፈው ነው። +16 ሆኖም ምሥራቹን የታዘዙት ሁሉም አይደሉም። ኢሳይያስ “ይሖዋ* ሆይ፣ ከእኛ የሰማውን* ነገር ያመነ ማን ነው?” ብሏልና።+ +17 ስለዚህ እምነት የሚገኘው ቃሉን ከመስማት ነው።+ ቃሉን መስማት የሚቻለው ደግሞ ስለ ክርስቶስ የሚናገር ሰው ሲኖር ነው። +18 ይሁንና ‘ሳይሰሙ ቀርተው ይሆን?’ ብዬ እጠይቃለሁ። በእርግጥ ሰምተዋል፤ “ጩኸታቸው ወደ መላው ምድር ወጣ፤ መልእክታቸውም እስከ ዓለም ዳርቻዎች ተሰማ” ተብሏልና።+ +19 ይሁንና ‘እስራኤላውያን ሳያውቁ ቀርተው ይሆን?’ ���ዬ እጠይቃለሁ።+ ሙሴ አስቀድሞ “እናንተን፣ ሕዝብ ባልሆኑት አስቀናችኋለሁ፤ ሞኝ በሆነ ብሔር አማካኝነትም ክፉኛ አስቆጣችኋለሁ” ብሏል።+ +20 ኢሳይያስም በድፍረት “ያልፈለጉኝ ሰዎች አገኙኝ፤+ እኔን ለማግኘት ባልጠየቁ ሰዎችም ዘንድ የታወቅኩ ሆንኩ” ብሏል።+ +21 እስራኤልን በተመለከተ ግን “ወደማይታዘዝና ልበ ደንዳና ወደሆነ ሕዝብ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ” ብሏል።+ +14 በእምነቱ ጠንካራ ያልሆነውን ሰው ተቀበሉት+ እንጂ በአመለካከት ልዩነት* ላይ ተመሥርታችሁ አትፍረዱ። +2 አንድ ሰው እምነቱ ማንኛውንም ነገር እንዲበላ ይፈቅድለታል፤ በእምነቱ ጠንካራ ያልሆነ ሰው ግን አትክልት ብቻ ይበላል። +3 ማንኛውንም ነገር የሚበላ የማይበላውን አይናቅ፤ የማይበላው ደግሞ በሚበላው ላይ አይፍረድ፤+ ይህን ሰው አምላክ ተቀብሎታልና። +4 በሌላው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?+ እሱ ቢቆምም ሆነ ቢወድቅ ለጌታው ነው።+ እንዲያውም ይሖዋ* እንዲቆም ሊያደርገው ስለሚችል ይቆማል። +5 አንድ ሰው አንዱ ቀን ከሌላው ቀን የበለጠ እንደሆነ አድርጎ ያስባል፤+ ሌላው ደግሞ አንዱ ቀን ከሌሎቹ ቀናት ሁሉ የተለየ እንዳልሆነ ያስባል፤+ እያንዳንዱ ሰው ሙሉ በሙሉ ያመነበትን ውሳኔ ያድርግ። +6 አንድን ቀን የሚያከብር ለይሖዋ* ብሎ ያከብራል። ማንኛውንም ነገር የሚበላም አምላክን ስለሚያመሰግን ለይሖዋ* ብሎ ይበላል፤+ የማይበላም ለይሖዋ* ብሎ አይበላም፤ ይሁንና አምላክን ያመሰግናል።+ +7 እንዲያውም ከመካከላችን ለራሱ ብቻ ብሎ የሚኖር የለም፤+ ለራሱ ብቻ ብሎም የሚሞት የለም። +8 ብንኖር የምንኖረው ለይሖዋ* ነውና፤+ ብንሞትም የምንሞተው ለይሖዋ* ነው። ስለዚህ ብንኖርም ሆነ ብንሞት የይሖዋ* ነን።+ +9 ክርስቶስ የሞተውና ዳግም ሕያው የሆነው ለዚህ ዓላማ ይኸውም በሙታንም ሆነ በሕያዋን ላይ ጌታ ይሆን ዘንድ ነውና።+ +10 ታዲያ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ?+ አንተ ደግሞ ወንድምህን ለምን ትንቃለህ? ሁላችንም በአምላክ የፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።+ +11 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’+ ይላል ይሖዋ፣* ‘ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ እኔ አምላክ መሆኔን በይፋ ይመሠክራል’” ተብሎ ተጽፏልና።+ +12 ስለዚህ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለአምላክ መልስ እንሰጣለን።+ +13 ስለሆነም ከእንግዲህ አንዳችን በሌላው ላይ አንፍረድ፤+ ከዚህ ይልቅ በአንድ ወንድም ፊት የሚያደናቅፍ ወይም የሚያሰናክል ነገር ላለማስቀመጥ ቁርጥ ውሳኔ እናድርግ።+ +14 የጌታ ኢየሱስ ተከታይ እንደመሆኔ መጠን ማንኛውም ነገር በራሱ ርኩስ እንዳልሆነ አውቄአለሁ ደግሞም አምኛለሁ፤+ አንድ ነገር ለአንድ ሰው ርኩስ የሚሆነው ያ ነገር ርኩስ ነው ብሎ ሲያስብ ብቻ ነው። +15 አንተ በምግብ የተነሳ ወንድምህ ቅር እንዲሰኝ ካደረግክ በፍቅር መመላለስህን ትተሃል ማለት ነው።+ ስለዚህ ክርስቶስ የሞተለት ይህ ሰው በምትበላው ምግብ ምክንያት እንዲጠፋ አታድርግ።*+ +16 በመሆኑም መልካም ነው ብላችሁ የምታደርጉት ነገር በሌሎች ዘንድ በመጥፎ እንዳይነሳ ተጠንቀቁ። +17 የአምላክ መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ ነው እንጂ የመብልና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም።+ +18 በዚህ መንገድ ክርስቶስን እንደ ባሪያ የሚያገለግል ሁሉ በአምላክ ፊት ተቀባይነት፣ በሰዎችም ዘንድ ሞገስ ያገኛልና። +19 ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና+ እርስ በርሳችን የምንተናነጽበትን+ ነገር ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናድርግ። +20 ለምግብ ብለህ የአምላክን ሥራ ማፍረስ ተው።+ እርግጥ ነው፣ ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ሆኖም አንድ ሰው መብላቱ ሌሎችን የሚያደናቅፍ ከሆነ ጎጂ* ነው።+ +21 ወንድምህ ��ሚሰናከልበት ከሆነ ሥጋ አለመብላት፣ የወይን ጠጅ አለመጠጣት ወይም ማንኛውንም የሚያሰናክል ነገር አለማድረግ የተሻለ ነው።+ +22 እንግዲህ እምነትህ በአንተና በአምላክ መካከል ያለ ጉዳይ ይሁን። ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ካደረገ በኋላ መልሶ ራሱን የማይኮንን ሰው ደስተኛ ነው። +23 እየተጠራጠረ ከበላ ግን የበላው በእምነት ስላልሆነ ቀድሞውንም ተኮንኗል። ደግሞም በእምነት ያልተደረገ ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው። +9 የክርስቶስ ተከታይ እንደመሆኔ መጠን የምናገረው እውነት ነው፤ ሕሊናዬ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚመሠክር አልዋሽም፤ +2 ታላቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ሥቃይ በልቤ ውስጥ አለ። +3 የሥጋ ዘመዶቼ ስለሆኑት ስለ ወንድሞቼ ስል እኔ ራሴ የተረገምኩ ሆኜ ከክርስቶስ ብለይ በወደድኩ ነበርና። +4 እነሱ እስራኤላውያን ናቸው፤ አምላክ ልጆቹ አድርጎ የወሰዳቸው፣+ ክብር ያገኙት፣ ቃል ኪዳን የተገባላቸው፣+ ሕግ የተሰጣቸው፣+ ቅዱስ አገልግሎት የማቅረብ መብት ያገኙትና+ ተስፋ የተሰጣቸው+ እነሱ ናቸው። +5 አባቶችም የእነሱ ናቸው፤+ ክርስቶስም በሥጋ የተገኘው ከእነሱ ነው።+ የሁሉ የበላይ የሆነው አምላክ ለዘላለም ይወደስ። አሜን። +6 ይሁን እንጂ የአምላክ ቃል ከንቱ ሆኖ ቀርቷል ማለት አይደለም። ከእስራኤል የተወለደ ሁሉ በእርግጥ “እስራኤል” አይደለምና።+ +7 በተጨማሪም የአብርሃም ዘር ስለሆኑ+ ሁሉም ልጆቹ ናቸው ማለት አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ “ዘርህ የሚጠራልህ በይስሐቅ በኩል ይሆናል” ተብሎ ተጽፏል።+ +8 ይህም ሲባል በሥጋ ልጆች የሆኑ በእርግጥ የአምላክ ልጆች አይደሉም፤+ በተስፋው ልጆች+ የሆኑት ግን ዘሩ እንደሆኑ ተደርገው ይቆጠራሉ። +9 የተስፋው ቃል “የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ እመጣለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች” ይላልና።+ +10 ተስፋው የተሰጠው በዚያን ጊዜ ብቻ ሳይሆን ርብቃ ከአባታችን ከይስሐቅ መንታ ልጆች በፀነሰች ጊዜ ጭምር ነው፤+ +11 ምርጫውን በተመለከተ የአምላክ ዓላማ በሥራ ሳይሆን በጠሪው ላይ የተመካ ሆኖ ይቀጥል ዘንድ ልጆቹ ከመወለዳቸውና ጥሩም ሆነ ክፉ ከማድረጋቸው በፊት +12 ርብቃ “ታላቁ የታናሹ ባሪያ ይሆናል” ተብሎ ተነግሯት ነበር።+ +13 ይህም “ያዕቆብን ወደድኩ፤ ኤሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +14 እንግዲህ ምን እንበል? አምላክ ፍትሕ ያዛባል ማለት ነው? በፍጹም!+ +15 ሙሴን “ልምረው የምፈልገውን እምረዋለሁ፤ ልራራለት የምፈልገውን ደግሞ እራራለታለሁ” ብሎታልና።+ +16 ስለዚህ ይህ የተመካው በአንድ ሰው ፍላጎት ወይም ጥረት* ሳይሆን ምሕረት በሚያደርገው አምላክ ላይ ነው።+ +17 ቅዱስ መጽሐፉ ስለ ፈርዖን ሲናገር “በሕይወት ያቆየሁህ ኃይሌን በአንተ ለማሳየትና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ለማድረግ ነው” ይላል።+ +18 ስለዚህ አምላክ የፈለገውን ይምራል፤ የፈለገውን ደግሞ ግትር እንዲሆን ይፈቅዳል።+ +19 በመሆኑም “እንደዚህ ከሆነ ታዲያ ሰዎችን ለምን ይወቅሳል?* ደግሞስ ፈቃዱን ማን መቃወም ይችላል?” ትለኝ ይሆናል። +20 ለመሆኑ ለአምላክ የምትመልሰው አንተ ማን ነህ?+ አንድ ዕቃ ቅርጽ አውጥቶ የሠራውን ሰው “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋል?+ +21 ሸክላ ሠሪው ከዚያው ከአንዱ ጭቃ፣ አንዱን ዕቃ ክቡር ለሆነ አገልግሎት ሌላውን ዕቃ ደግሞ ክብር ለሌለው አገልግሎት ለመሥራት በጭቃው ላይ ሥልጣን እንዳለው+ አታውቅም? +22 አምላክ ቁጣውን ለማሳየትና ኃይሉ እንዲታወቅ ለማድረግ ቢፈልግም እንኳ ጥፋት የሚገባቸውን የቁጣ ዕቃዎች በብዙ ትዕግሥት ችሏቸው እንደሆነስ ምን ታውቃለህ? +23 ይህን ያደረገው ታላቅ ክብሩን አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው የምሕረት ዕቃዎች+ ላይ ለመግለጥ +24 ይኸውም ከአይሁዳውያን ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብም+ በጠራን በእኛ ላይ ታላቅ ክብሩን ለመግለጥ ቢሆንስ? +25 ይህም በሆሴዕ መጽሐፍ ላይ እንዲህ ብሎ እንደተናገረው ነው፦ “ሕዝቤ ያልሆኑትን+ ‘ሕዝቤ’ ብዬ፣ ያልተወደደችውንም ‘የተወደደች’+ ብዬ እጠራለሁ፤ +26 ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብሎ በተነገራቸው ስፍራም በዚያ ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።”+ +27 ከዚህም በተጨማሪ ኢሳይያስ ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፦ “የእስራኤል ልጆች ቁጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም እንኳ የሚድኑት ቀሪዎች ብቻ ናቸው።+ +28 ይሖዋ* በምድር የሚኖሩትን ይፋረዳልና፤ ይህን ደግሞ ሳይዘገይ* ይፈጽመዋል።”+ +29 ደግሞም ኢሳይያስ አስቀድሞ እንደተናገረው “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ* ዘር ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን፣ ገሞራንም በመሰልን ነበር።”+ +30 እንግዲህ ምን እንበል? አሕዛብ ጽድቅን ባይከታተሉም እንኳ ጽድቅን ይኸውም በእምነት አማካኝነት የሚገኘውን ጽድቅ አገኙ፤+ +31 ሆኖም እስራኤል የጽድቅን ሕግ ቢከታተልም ግቡ ላይ አልደረሰም፤ ይኸውም ሕጉን አልፈጸመም። +32 ይህ የሆነው ለምንድን ነው? በእምነት ሳይሆን በሥራ የሚገኝ እንደሆነ አድርገው ስለተከታተሉት ነው። ስለዚህ “በማሰናከያ ድንጋይ” ተሰናከሉ፤+ +33 ይህም “እነሆ፣ በጽዮን የሚያደናቅፍ ድንጋይና የሚያሰናክል ዓለት አኖራለሁ፤+ በእሱ ላይ እምነት የሚጥል ግን አያፍርም”+ ተብሎ እንደተጻፈው ነው። +13 ሰው* ሁሉ ለበላይ ባለሥልጣናት ይገዛ፤+ ሥልጣን ሁሉ የሚገኘው ከአምላክ ነውና፤+ ያሉት ባለሥልጣናት አንጻራዊ ቦታቸውን ያገኙት ከአምላክ ነው።+ +2 ስለዚህ ባለሥልጣንን የሚቃወም ሁሉ አምላክ ያደረገውን ዝግጅት ይቃወማል፤ ይህን ዝግጅት የሚቃወሙ በራሳቸው ላይ ፍርድ ያመጣሉ። +3 ገዢዎች የሚያስፈሩት ክፉ ለሚያደርጉ እንጂ መልካም ለሚያደርጉ አይደለምና።+ እንግዲያው ባለሥልጣንን መፍራት የማትፈልግ ከሆነ መልካም ማድረግህን ቀጥል፤+ ከእሱም ምስጋና ታገኛለህ፤ +4 ለአንተ ጥቅም ሲባል የተሾመ የአምላክ አገልጋይ ነውና። ክፉ የምታደርግ ከሆነ ግን ልትፈራ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ሰይፍ የሚታጠቀው እንዲያው በከንቱ አይደለም። ክፉ የሚሠራን በመቅጣት* የሚበቀል የአምላክ አገልጋይ ነው። +5 ስለዚህ ቁጣውን በመፍራት ብቻ ሳይሆን ስለ ሕሊናችሁ ስትሉም መገዛታችሁ አስፈላጊ ነው።+ +6 ቀረጥ የምትከፍሉትም ለዚሁ ነው፤ ምክንያቱም እነሱ ሕዝባዊ አገልግሎት የሚያከናውኑ የአምላክ አገልጋዮች ናቸው፤ የዘወትር ተግባራቸውም ይኸው ነው። +7 ለሁሉም የሚገባውን አስረክቡ፤ ቀረጥ ለሚጠይቅ ቀረጥ፣+ ግብር ለሚጠይቅ ግብር ስጡ፤ መፈራት የሚፈልገውን ፍሩ፤+ መከበር የሚፈልገውን አክብሩ።+ +8 እርስ በርስ ከመዋደድ በቀር በማንም ላይ ምንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤+ ሰውን የሚወድ ሁሉ ሕጉን ፈጽሟልና።+ +9 ምክንያቱም “አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ አትጎምጅ”+ የሚሉት ሕጎችና ሌሎች ትእዛዛት በሙሉ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ በሚለው በዚህ ቃል ተጠቃለዋል። +10 ፍቅር በባልንጀራው ላይ ክፉ አያደርግም፤+ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።+ +11 ምን ዓይነት ዘመን ላይ እንደምንገኝ ስለምታውቁም ይህን አድርጉ፤ አማኞች ከሆንበት ጊዜ ይልቅ አሁን መዳናችን ይበልጥ ስለቀረበ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን ነው።+ +12 ሌሊቱ እየተገባደደ ነው፤ ቀኑም ቀርቧል። ስለዚህ ከጨለማ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን አውልቀን+ የብርሃንን የጦር ዕቃዎች እንልበስ።+ +13 መረን በለቀቀ ፈንጠዝያና በስካር፣ ልቅ በሆነ የፆታ ግንኙነትና ዓይን ባወጣ ምግባር*+ እንዲሁም በጠብና በቅናት+ ሳይሆን በቀን ብርሃን እንደምንመላለስ በጨዋነት እንመላለስ።+ +14 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤+ የሥጋ ፍላጎታችሁን ለማርካት ዕቅድ አታውጡ።+ +5 ስለዚህ አሁን በእምነት አማካኝነት ጻድቃን ናችሁ+ ስለተባልን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል+ ከአምላክ ጋር ያለንን ሰላም ጠብቀን እንኑር፤* +2 ደግሞም በኢየሱስ አማካኝነት የአምላክን ጸጋ ለማግኘት በእምነት ወደ እሱ መቅረብ የቻልን ሲሆን ይህን ጸጋ አሁን አግኝተናል፤+ የአምላክንም ክብር እንደምናገኝ ተስፋ በማድረግ እጅግ እንደሰት።* +3 በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራ ውስጥ እያለንም እጅግ እንደሰት፤*+ ምክንያቱም መከራ ጽናትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን፤+ +4 ጽናትም በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንድናገኝ+ ያስችለናል፤ ተቀባይነት ማግኘት ደግሞ ተስፋን+ ያጎናጽፋል፤ +5 ተስፋውም ሳይፈጸም ቀርቶ ለሐዘን* አይዳርገንም፤+ ምክንያቱም የአምላክ ፍቅር፣ በተሰጠን መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በልባችን ውስጥ ፈሷል።+ +6 ገና ደካሞች ሳለን+ ክርስቶስ አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ ለኃጢአተኞች ሞቷልና። +7 ለጻድቅ ሰው የሚሞት ማግኘት በጣም አዳጋች ነው፤ ለጥሩ ሰው ለመሞት የሚደፍር ግን ምናልባት ይገኝ ይሆናል። +8 ሆኖም አምላክ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እንዲሞትልን በማድረግ ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር አሳይቷል።+ +9 ከእንግዲህ በደሙ ጻድቃን ናችሁ ስለተባልን+ በእሱ አማካኝነት ከአምላክ ቁጣ እንደምንድን ይበልጥ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።+ +10 ጠላቶች ሆነን ሳለን በልጁ ሞት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ከታረቅን አሁን ታርቀን ሳለንማ+ በእሱ ሕይወት እንደምንድን የተረጋገጠ ነው። +11 ይህም ብቻ ሳይሆን አሁን እርቅ ባገኘንበት+ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በአምላክ ሐሴት እያደረግን ነው። +12 ስለሆነም በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤+ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።+ +13 ሕጉ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በዓለም ላይ ነበርና፤ ሆኖም ሕግ በሌለበት ማንም በኃጢአት አይጠየቅም።+ +14 ይሁንና አዳም ትእዛዝ በመተላለፍ የሠራውን ዓይነት ኃጢአት ባልሠሩት ላይም እንኳ ሳይቀር ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት በሁሉ ላይ ነገሠ፤ አዳም በኋላ ለሚመጣው አምሳያ ነበር።+ +15 ሆኖም ስጦታው ያስገኘው ነገር በደሉ ካስከተለው ነገር የተለየ ነው። ምክንያቱም በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ሞተዋል፤ ይሁንና የአምላክ ጸጋና ነፃ ስጦታው በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ+ አማካኝነት ለብዙ ሰዎች ወደር የሌለው* ጥቅም አስገኝቷል!+ +16 በተጨማሪም ነፃ ስጦታው ያስገኘው ውጤት የአንዱ ሰው ኃጢአት+ ካመጣው ውጤት የተለየ ነው። ምክንያቱም አንድን በደል ተከትሎ የመጣው ፍርድ ኩነኔን አስከትሏል፤+ ብዙዎች በደል ከፈጸሙ በኋላ ግን አምላክ ጻድቃን እንዲባሉ የሚያስችል ስጦታ ሰጥቷል።+ +17 በአንድ ሰው በደል የተነሳ ሞት በዚህ ሰው በኩል ከነገሠ+ የአምላክን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅን ነፃ ስጦታ የሚቀበሉትማ+ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት+ ሕይወት አግኝተው ነገሥታት+ ሆነው እንደሚገዙ ይበልጥ የተረጋገጠ ነው! +18 ስለዚህ አንድ በደል ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲኮነኑ እንዳደረገ ሁሉ+ አንድ የጽድቅ ድርጊትም* ሁሉም ዓይነት ሰዎች ጻድቃን ናችሁ ተብለው ለሕይወት እንዲበቁ ያስችላል።+ +19 ምክንያቱም በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደሆኑ ሁሉ+ በአንዱ ሰው መታዘዝም ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።+ +20 ሕጉ የመጣው ሰዎች ብዙ በደል እንደሚፈጽሙ ለማሳየት ነው።+ ይሁን እንጂ ሰዎች ብዙ ኃጢአት ሲፈጽሙ አምላክ ታላቅ ጸጋ ��ሳያቸው። +21 ይህ የሆነው ለምንድን ነው? ኃጢአት ከሞት ጋር እንደነገሠ+ ሁሉ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የዘላለም ሕይወት ይገኝ ዘንድ ጸጋ በጽድቅ አማካኝነት እንዲነግሥ ነው።+ +15 እኛ በእምነት ጠንካሮች የሆን ጠንካሮች ያልሆኑትን ሰዎች ድክመት ልንሸከም ይገባል+ እንጂ ራሳችንን የምናስደስት መሆን የለብንም።+ +2 እያንዳንዳችን ባልንጀራችንን* የሚጠቅመውንና የሚያንጸውን ነገር በማድረግ እናስደስተው።+ +3 ክርስቶስ እንኳ ራሱን አላስደሰተምና፤+ ይህም “ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋ በእኔ ላይ ደረሰ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +4 በምናሳየው ጽናትና+ ከቅዱሳን መጻሕፍት በምናገኘው መጽናኛ ተስፋ ይኖረን ዘንድ+ ቀደም ብሎ የተጻፈው ነገር ሁሉ ለእኛ ትምህርት እንዲሆን ተጽፏልና።+ +5 ጽናትንና መጽናኛን የሚሰጠው አምላክ፣ ሁላችሁም ክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖራችሁ ያድርግ፤ +6 ይኸውም በኅብረትና+ በአንድ ድምፅ* የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት እንድታከብሩ ነው። +7 ስለዚህ ክርስቶስ እኛን እንደተቀበለን+ ሁሉ አምላክ እንዲከበር እናንተም አንዳችሁ ሌላውን ተቀበሉ።+ +8 ክርስቶስ፣ አምላክ እውነተኛ መሆኑን ለማሳየት ሲል ለተገረዙት አገልጋይ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ፤+ በተጨማሪም አገልጋይ የሆነው፣ አምላክ ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ለማረጋገጥ+ +9 እንዲሁም ብሔራት አምላክን ስለ ምሕረቱ ያከብሩት ዘንድ ነው።+ ይህም “ስለዚህ በብሔራት መካከል በይፋ አወድስሃለሁ፤ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +10 ደግሞም “እናንተ ብሔራት፣ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ” ይላል።+ +11 እንደገናም “ብሔራት ሁሉ፣ ይሖዋን* አወድሱት፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያወድሱት” ይላል።+ +12 እንዲሁም ኢሳይያስ “የእሴይ ሥር ይገለጣል፤+ ብሔራትንም የሚገዛው ይነሳል፤+ ብሔራትም ተስፋቸውን በእሱ ላይ ይጥላሉ” ይላል።+ +13 በእሱ በመታመናችሁ የተነሳ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተስፋ እንዲትረፈረፍላችሁ* ተስፋ የሚሰጠው አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ።+ +14 ወንድሞቼ ሆይ፣ እናንተ ራሳችሁ በጥሩነት የተሞላችሁ እንደሆናችሁ፣ የተሟላ እውቀት እንዳላችሁና አንዳችሁ ሌላውን መምከር* እንደምትችሉ እኔ ራሴ ስለ እናንተ እርግጠኛ መሆን ችያለሁ። +15 ይሁን እንጂ አንዳንድ ጉዳዮችን ግልጥልጥ አድርጌ የጻፍኩላችሁ ተጨማሪ ማሳሰቢያ ልሰጣችሁ ስለፈለግኩ ነው። ይህን የማደርገው ከአምላክ በተሰጠኝ ጸጋ የተነሳ ነው። +16 ይህ ጸጋ የተሰጠኝም ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው።+ የአምላክን ምሥራች በማወጁ ቅዱስ ሥራ+ የምካፈለው እነዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰ፣ ተቀባይነት ያለው መባ ሆነው ለአምላክ እንዲቀርቡ ነው። +17 ስለዚህ ለአምላክ ከማቀርበው አገልግሎት ጋር በተያያዘ በክርስቶስ ኢየሱስ ሐሴት የማደርግበት ምክንያት አለኝ። +18 አሕዛብ ታዛዦች እንዲሆኑ ክርስቶስ በእኔ አማካኝነት ስላከናወነው ነገር ካልሆነ በቀር ስለ ሌላ ነገር ለመናገር አልደፍርም። ይህን ያከናወነው እኔ በተናገርኩትና ባደረግኩት ነገር +19 እንዲሁም በተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች+ ደግሞም በአምላክ መንፈስ ኃይል ነው፤ በመሆኑም ከኢየሩሳሌም አንስቶ ዙሪያውን እስከ እልዋሪቆን ድረስ ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች በተሟላ ሁኔታ ሰብኬአለሁ።+ +20 በዚህ መንገድ የክርስቶስ ስም አስቀድሞ በታወቀበት ቦታ ምሥራቹን ላለመስበክ የተቻለኝን ሁሉ ጥረት አድርጌአለሁ፤ ይህን ያደረግኩት ሌላ ሰው በጣለው መሠረት ላይ መገንባት ስላልፈለግኩ ነው፤ +21 ይህም “ከ��ህ በፊት ስለ እሱ ምንም ያልተነገራቸው ያያሉ፤ ያልሰሙም ያስተውላሉ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +22 በተደጋጋሚ ጊዜያት ወደ እናንተ መምጣት ሳልችል የቀረሁትም በዚህ ምክንያት ነው። +23 አሁን ግን በዚህ አካባቢ ባሉት አገሮች ያልሰበክሁበት ክልል የለም፤ ደግሞም ለብዙ ዓመታት* ወደ እናንተ ለመምጣት ስጓጓ ቆይቻለሁ። +24 በመሆኑም ወደ ስፔን በምጓዝበት ጊዜ እንደማገኛችሁና እናንተ ጋ ለተወሰነ ጊዜ ቆይቼ ናፍቆቴን ከተወጣሁ በኋላ ጥቂት መንገድ እንደምትሸኙኝ ተስፋ አደርጋለሁ። +25 አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል* ወደ ኢየሩሳሌም ልጓዝ ነው።+ +26 በመቄዶንያና በአካይያ ያሉት ወንድሞች በኢየሩሳሌም ባሉት ቅዱሳን መካከል ለሚገኙት ድሆች መዋጮ በመስጠት ያላቸውን ነገር በደስታ አካፍለዋልና።+ +27 አዎ፣ ይህን ያደረጉት በፈቃደኝነት ነው፤ ደግሞም የእነሱ ዕዳ ነበረባቸው፤ ምክንያቱም አሕዛብ የእነሱን መንፈሳዊ ነገር ከተካፈሉ እነሱ ደግሞ ለሚያስፈልጓቸው ቁሳዊ ነገሮች የማዋጣት ዕዳ አለባቸው።+ +28 ስለሆነም ይህን ሥራ ካከናወንኩና መዋጮውን ካስረከብኳቸው* በኋላ በእናንተ በኩል አድርጌ ወደ ስፔን እሄዳለሁ። +29 ደግሞም ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ የክርስቶስን የተትረፈረፈ በረከት ይዤላችሁ እንደምመጣ አውቃለሁ። +30 እንግዲህ ወንድሞች፣ ስለ እኔ አምላክን በመለመን ከእኔ ጋር አብራችሁ በጸሎት እንድትተጉ+ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና ከመንፈስ በሚገኘው ፍቅር አበረታታችኋለሁ፤ +31 በይሁዳ ካሉት የማያምኑ ሰዎች እጅ እንድድንና+ በኢየሩሳሌም ለሚገኙት ቅዱሳን+ የማቀርበው አገልግሎት* በእነሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጸልዩልኝ፤ +32 ይኸውም አምላክ ከፈቀደ ወደ እናንተ በደስታ እንድመጣና ከእናንተ ጋር በመሆን መንፈሴ እንዲታደስ ነው። +33 ሰላም የሚሰጠው አምላክ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።+ አሜን። +3 በመሆኑም ወንድሞች፣ ከክርስቶስ ጋር በተያያዘ ገና ሕፃናት+ እንደሆኑ እንደ ሥጋውያን ሰዎች እንጂ እንደ መንፈሳውያን ሰዎች+ ላነጋግራችሁ አልቻልኩም። +2 ጠንካራ ስላልነበራችሁ ወተት እንጂ ጠንካራ ምግብ አልመገብኳችሁም። አሁንም ቢሆን ገና አልጠነከራችሁም፤+ +3 ደግሞም ገና ሥጋውያን ናችሁ።+ ቅናትና ጠብ በመካከላችሁ ስላለ ሥጋውያን መሆናችሁ፣+ ደግሞም በዓለም እንዳሉ ሰዎች መመላለሳችሁ አይደለም? +4 አንዱ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፣” ሌላው ደግሞ “እኔ የአጵሎስ+ ነኝ” ሲል እንደ ማንኛውም ሰው መሆናችሁ አይደለም? +5 ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? ጌታ የሰጣቸውን ሥራ የሚያከናውኑ አገልጋዮች+ ናቸው፤ እናንተም አማኞች የሆናችሁት በእነሱ አማካኝነት ነው። +6 እኔ ተከልኩ፤+ አጵሎስ አጠጣ፤+ ያሳደገው ግን አምላክ ነው፤ +7 ስለዚህ ምስጋና የሚገባው የሚያሳድገው አምላክ እንጂ የሚተክለውም ሆነ የሚያጠጣው አይደለም።+ +8 የሚተክለውም ሆነ የሚያጠጣው በኅብረት የሚሠሩ ናቸው፤* ሆኖም እያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የራሱን ወሮታ ይቀበላል።+ +9 እኛ ከአምላክ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። እናንተ በመልማት ላይ ያለ የአምላክ እርሻ ናችሁ፤ የአምላክ ሕንፃ ናችሁ።+ +10 በተሰጠኝ የአምላክ ጸጋ መሠረት በሙያው እንደተካነ ግንበኛ* እኔ መሠረት ጣልኩ፤+ ሌላው ደግሞ በዚያ ላይ ይገነባል። ሆኖም እያንዳንዱ በዚያ ላይ እንዴት እንደሚገነባ በጥንቃቄ ሊያስብ ይገባል። +11 ማንም ሰው ከተጣለው መሠረት ሌላ አዲስ መሠረት መጣል አይችልምና፤ ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።+ +12 ማንም በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮች፣ በእንጨት፣ በሣር ወይም በአገዳ ቢገነባ +13 የፈተናው ቀን ሲመጣ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ እሳቱ+ ሁሉንም ነገር ይገልጣልና፤ እንዲሁም እያንዳንዱ ሰው ምን ዓይነት ግንባታ እንዳከናወነ እሳቱ ራሱ ፈትኖ ያሳያል። +14 ማንም በመሠረቱ ላይ የገነባው ነገር ቢጸናለት ወሮታ ያገኛል፤ +15 ይሁንና ማንም ሰው የሠራው ሥራ ቢቃጠል ኪሳራ ይደርስበታል፤ እሱ ግን ይተርፋል፤ ሆኖም በእሳት ውስጥ አልፎ የመትረፍ ያህል ይሆናል። +16 እናንተ ራሳችሁ የአምላክ ቤተ መቅደስ+ እንደሆናችሁና የአምላክ መንፈስ በእናንተ ውስጥ እንደሚያድር አታውቁም?+ +17 ማንም የአምላክን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ አምላክ ያፈርሰዋል፤ የአምላክ ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፤ ቤተ መቅደሱም እናንተ ናችሁ።+ +18 ማንም ራሱን አያታል፤ ከእናንተ መካከል ማንም በዚህ ሥርዓት* ጥበበኛ እንደሆነ ቢያስብ፣ ጥበበኛ መሆን ይችል ዘንድ ሞኝ ይሁን። +19 ምክንያቱም የዚህ ዓለም ጥበብ በአምላክ ፊት ሞኝነት ነው፤ “ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኮል ይይዛቸዋል” ተብሎ ተጽፏልና።+ +20 ደግሞም “ይሖዋ* የጥበበኞች ሐሳብ ከንቱ እንደሆነ ያውቃል” ተብሏል።+ +21 በመሆኑም ማንም በሰዎች አይኩራራ፤ ሁሉም ነገር የእናንተ ነውና፤ +22 ጳውሎስም ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም*+ ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን አሁን ያሉት ነገሮችም ቢሆኑ የሚመጡትም ነገሮች ቢሆኑ ሁሉም ነገር የእናንተ ነው፤ +23 እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፤+ ክርስቶስ ደግሞ የአምላክ ነው። +7 በደብዳቤያችሁ ላይ ያነሳችኋቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ፣ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ባይነካ* ይሻላል፤ +2 ይሁንና የፆታ ብልግና* ስለተስፋፋ እያንዳንዱ ወንድ የራሱ ሚስት ትኑረው፤+ እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት።+ +3 ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ ሚስትም ብትሆን ለባሏ እንደዚሁ ታድርግለት።+ +4 ሚስት በራሷ አካል ላይ ሥልጣን የላትም፤ ሥልጣን ያለው ባሏ ነው፤ በተመሳሳይም ባል በራሱ አካል ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሥልጣን ያላት ሚስቱ ናት። +5 አንዳችሁ ለሌላው የሚገባውን አትከልክሉ፤ እንዲህ ማድረግ የምትችሉት በጋራ ስምምነት የተወሰነ ጊዜ ለጸሎት ለማዋል ካሰባችሁ ብቻ ነው፤ ደግሞም ራሳችሁን መግዛት አቅቷችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ። +6 ይሁን እንጂ ይህን ያልኩት እንዲህ ማድረግ እንደሚቻል ለመግለጽ ነው እንጂ ለማዘዝ አይደለም። +7 ይሁንና ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን ደስ ባለኝ ነበር። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ከአምላክ ያገኘው የራሱ ስጦታ አለው፤+ አንዱ አንድ ዓይነት ስጦታ ሲኖረው ሌላው ደግሞ ሌላ ዓይነት ስጦታ አለው። +8 ሆኖም ላላገቡና መበለት ለሆኑ እንደ እኔ ሆነው ቢኖሩ የተሻለ ነው እላለሁ።+ +9 ራሳቸውን መግዛት ካቃታቸው ግን ያግቡ፤ በፍትወት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና።+ +10 ላገቡት ሰዎች ይህን መመሪያ እሰጣለሁ፤ ይህ መመሪያ የጌታ እንጂ የእኔ አይደለም፤ ሚስት ከባሏ አትለያይ።+ +11 ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባሏ ጋር ትታረቅ፤ ባልም ሚስቱን መተው የለበትም።+ +12 ለሌሎች ደግሞ እንዲህ እላለሁ፤ ይህን የምለው እኔ እንጂ ጌታ አይደለም፦+ አንድ ወንድም አማኝ ያልሆነች ሚስት ካለችውና አብራው ለመኖር ከተስማማች አይተዋት፤ +13 እንዲሁም አንዲት ሴት አማኝ ያልሆነ ባል ካላትና ባሏ አብሯት ለመኖር ከተስማማ አትተወው። +14 አማኝ ያልሆነ ባል ከሚስቱ ጋር ባለው ዝምድና የተነሳ ተቀድሷልና፤ አማኝ ያልሆነች ሚስትም ከወንድም ጋር ባላት ዝምድና የተነሳ ተቀድሳለች፤ እንዲህ ባይሆን ኖሮ ልጆቻችሁ ርኩሳን በሆኑ ነበር፤ አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው። +15 ይሁንና አማኝ ያልሆነው ወገን ለመለየት ከመረጠ ይለይ፤ እንዲህ ያለ ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ አንድ ወንድም ወይም ���ንዲት እህት ምንም ዓይነት ግዴታ የለባቸውም፤ አምላክ የጠራችሁ ለሰላም ነውና።+ +16 አንቺ ሚስት፣ ባልሽን ታድኚው እንደሆነ ምን ታውቂያለሽ?+ ወይስ አንተ ባል፣ ሚስትህን ታድን እንደሆነ ምን ታውቃለህ? +17 ያም ሆነ ይህ እያንዳንዱ ሰው ይሖዋ* በሰጠው ድርሻና አምላክ ሲጠራው በነበረበት ሁኔታ ይመላለስ።+ ለጉባኤዎችም ሁሉ ይህን መመሪያ እሰጣለሁ። +18 አንድ ሰው የተጠራው ተገርዞ እያለ ነው?+ እንዳልተገረዘ ሰው አይሁን። አንድ ሰው የተጠራው ሳይገረዝ ነው? ከሆነ አይገረዝ።+ +19 መገረዝ ምንም ማለት አይደለም፤ አለመገረዝም ቢሆን ምንም ማለት አይደለም፤+ ዋናው ነገር የአምላክን ትእዛዛት መጠበቅ ነው።+ +20 እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በዚያው ይቀጥል።+ +21 የተጠራኸው ባሪያ እያለህ ነው? ይሄ አያስጨንቅህ፤+ ሆኖም ነፃ መውጣት የምትችል ከሆነ አጋጣሚውን ተጠቀምበት። +22 ባሪያ እያለ የተጠራ ማንኛውም የጌታ ደቀ መዝሙር ነፃ የወጣ የጌታ ሰው ነውና፤+ በተመሳሳይም ነፃ እያለ የተጠራ ሰው የክርስቶስ ባሪያ ነው። +23 በዋጋ ተገዝታችኋል፤+ የሰው ባሪያ መሆናችሁ ይብቃ። +24 ወንድሞች፣ እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በአምላክ ፊት በዚያው ሁኔታ ይቀጥል። +25 ድንግል የሆኑትን* በተመለከተ ከጌታ የተቀበልኩት ትእዛዝ የለኝም፤ ይሁን እንጂ ጌታ ካሳየኝ ምሕረት የተነሳ እንደ ታማኝ ሰው የራሴን ሐሳብ እሰጣለሁ።+ +26 ስለዚህ አሁን ካለው ችግር አንጻር አንድ ሰው ባለበት ሁኔታ ቢቀጥል የተሻለ ይመስለኛል። +27 በሚስት ታስረሃል? ከሆነ መፈታትን አትሻ።+ ሚስት የሌለህ ነህ? ከሆነ ሚስት ለማግባት አትፈልግ። +28 ይሁንና ብታገባም ኃጢአት ይሆንብሃል ማለት አይደለም። እንዲሁም ድንግል የሆነ ሰው ቢያገባ ኃጢአት ይሆንበታል ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ የሚያገቡ ሰዎች በሥጋቸው ላይ መከራ ይደርስባቸዋል። ነገር ግን የእኔ ምኞት ከዚህ እንድትድኑ ነው። +29 ከዚህም በላይ ወንድሞች፣ የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን ልነግራችሁ እወዳለሁ።+ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስት ያላቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፤ +30 የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፣ የሚደሰቱም እንደማይደሰቱ፣ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው +31 እንዲሁም በዓለም የሚጠቀሙ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ፤ የዚህ ዓለም ትእይንት እየተለዋወጠ ነውና። +32 በመሆኑም ከጭንቀት ነፃ እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። ያላገባ ሰው ጌታን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚችል በማሰብ ስለ ጌታ ነገር ይጨነቃል። +33 ያገባ ሰው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚችል በማሰብ ስለ ዓለም ነገር ይጨነቃል፤+ +34 በመሆኑም ሐሳቡ ተከፋፍሏል። በተጨማሪም ያላገባች ሴትም ሆነች ድንግል በአካሏም ሆነ በመንፈሷ ቅዱስ መሆን ትችል ዘንድ ስለ ጌታ ነገር ትጨነቃለች።+ ይሁን እንጂ ያገባች ሴት ባሏን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደምትችል በማሰብ ስለ ዓለም ነገር ትጨነቃለች። +35 ይህን የምለው ግን ለእናንተው ጥቅም ብዬ ነው እንጂ ነፃነት ላሳጣችሁ* ብዬ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ተስማሚ የሆነውን ነገር እንድታደርጉና ሐሳባችሁ ሳይከፋፈል ዘወትር ለጌታ ያደራችሁ እንድትሆኑ ላነሳሳችሁ ብዬ ነው። +36 ይሁንና አንድ ሰው ሳያገባ ቀርቶ ራሱን መቆጣጠር* እንደተሳነው ከተሰማው፣ በተለይ ደግሞ አፍላ የጉርምስና ዕድሜን ያለፈ ከሆነና ማግባቱ የሚመረጥ ከሆነ የፈለገውን ያድርግ፤ ኃጢአት አይሆንበትም። እንዲህ ያሉ ሰዎች ያግቡ።+ +37 ሆኖም አንድ ሰው ልቡ ከቆረጠና ይህን ማድረግ እንደማያስፈልገው ከተሰማው፣ ደግሞም ራሱን መግዛት የሚችል ከሆነና ሳያገባ* ለመኖር በልቡ ከወሰነ መልካም ያደር��ል።+ +38 ስለዚህ የሚያገባ* ሁሉ መልካም ያደርጋል፤ ሳያገባ የሚኖር ሁሉ ደግሞ የተሻለ ያደርጋል።+ +39 አንዲት ሚስት ባሏ በሕይወት ባለበት ዘመን ሁሉ የታሰረች ናት።+ ባሏ በሞት ካንቀላፋ ግን በጌታ ብቻ ይሁን እንጂ ከፈለገችው ሰው ጋር ለመጋባት ነፃ ናት።+ +40 እንደ እኔ ከሆነ ግን እንዳለች ብትቀጥል ይበልጥ ደስተኛ ትሆናለች፤ እኔ ደግሞ የአምላክ መንፈስ እንዳለኝ እርግጠኛ ነኝ። +12 ወንድሞች፣ አሁን ደግሞ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች+ በሚገባ እንድታውቁ እፈልጋለሁ። +2 አሕዛብ* በነበራችሁበት ጊዜ ድምፅ የሌላቸው ጣዖቶች+ ካሳደሩባችሁ ተጽዕኖ የተነሳ ወደመሯችሁ ቦታ ሁሉ በመሄድ እነሱን ተከትላችሁ ትባዝኑ ነበር። +3 ስለዚህ ይህን እንድታውቁ እወዳለሁ፦ በአምላክ መንፈስ ተመርቶ “ኢየሱስ የተረገመ ነው!” የሚል ማንም የለም፤ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ካልሆነ በቀር ማንም “ኢየሱስ ጌታ ነው!” ብሎ ሊናገር አይችልም።+ +4 ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ፤ ምንጩ ግን ያው መንፈስ ነው፤+ +5 ልዩ ልዩ አገልግሎቶች አሉ፤+ ሁሉም አገልግሎት የሚቀርበው ግን ለአንድ ጌታ ነው፤ +6 በተጨማሪም ልዩ ልዩ ሥራዎች* አሉ፤ ሆኖም ሁሉም ሰዎች እነዚህን ሁሉ ነገሮች እንዲያከናውኑ የሚያስችለው አንድ አምላክ ብቻ ነው።+ +7 ይሁን እንጂ መንፈስ በእያንዳንዱ ሰው አማካኝነት ጠቃሚ ለሆነ ዓላማ ይገለጣል።+ +8 ለአንዱ በመንፈስ አማካኝነት በጥበብ የመናገር ችሎታ* ይሰጠዋልና፤ ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ በእውቀት የመናገር ችሎታ ይሰጠዋል፤ +9 ለሌላው በዚያው መንፈስ እምነት ይሰጠዋል፤+ ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ፣ የመፈወስ ስጦታ ይሰጠዋል፤+ +10 እንዲሁም ለሌላው ተአምራት የመሥራት፣+ ለሌላው ትንቢት የመናገር፣ ለሌላው በመንፈስ መሪነት የተነገረን ቃል የመረዳት፣+ ለሌላው በተለያዩ ልሳኖች* የመናገር፣+ ለሌላው ደግሞ ልሳኖችን የመተርጎም ችሎታ ይሰጠዋል።+ +11 ሆኖም ለእያንዳንዱ በግለሰብ ደረጃ እነዚህን ስጦታዎች እንደፈቀደ በማከፋፈል እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚያከናውነው ያው አንድ መንፈስ ነው። +12 አካል አንድ ቢሆንም ብዙ የአካል ክፍሎች እንዳሉትና የዚህ አካል ክፍሎች በሙሉ ብዙ ቢሆኑም አንድ አካል+ እንደሆኑ ሁሉ ክርስቶስም እንደዚሁ ነው። +13 አይሁዳውያንም ሆን ግሪካውያን፣ ባሪያዎችም ሆን ነፃ ሰዎች ሁላችንም አንድ አካል ለመሆን በአንድ መንፈስ ተጠምቀናልና፤ እንዲሁም ሁላችንም አንድ መንፈስ እንድንጠጣ ተሰጥቶናል። +14 አካል በአንድ ብቻ ሳይሆን በብዙ የአካል ክፍሎች የተገነባ ነውና።+ +15 እግር “እኔ እጅ ስላልሆንኩ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ አይቀርም። +16 እንዲሁም ጆሮ “እኔ ዓይን ስላልሆንኩ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ አይቀርም። +17 አካል በሙሉ ዓይን ቢሆን ኖሮ እንዴት መስማት ይቻል ነበር? አካል በሙሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮስ እንዴት ማሽተት ይቻል ነበር? +18 ሆኖም አምላክ እያንዳንዱን የአካል ክፍል እሱ በፈለገው ቦታ መድቦታል። +19 የአካል ክፍሎች ሁሉ አንድ ዓይነት ቢሆኑ ኖሮ ሙሉ አካል ከየት ይገኝ ነበር? +20 አሁን ግን የአካል ክፍሎች ብዙ ቢሆኑም አካል ግን አንድ ነው። +21 ዓይን እጅን “አንተ አታስፈልገኝም” ሊለው አይችልም፤ ወይም ደግሞ ራስ እግርን “አንተ አታስፈልገኝም” ሊለው አይችልም። +22 እንዲያውም ደካማ የሚመስሉት የአካል ክፍሎች በጣም አስፈላጊ ናቸው፤ +23 እምብዛም ክብር የላቸውም ብለን የምናስባቸውን የአካል ክፍሎች የበለጠ ክብር እንሰጣቸዋለን፤+ በመሆኑም የምናፍርባቸውን የአካል ክፍሎች ይበልጥ በክብር እንይዛቸዋለን፤ +24 በአንጻሩ ደግሞ ���ሚያምሩት የአካል ክፍሎቻችን ምንም አያስፈልጋቸውም። ይሁንና አምላክ ክብር የሚጎድለውን የአካል ክፍል ታላቅ ክብር በማልበስ አካልን ገንብቷል፤ +25 ይህን ያደረገው በአካል መካከል ክፍፍል እንዳይኖር፣ ከዚህ ይልቅ የአካል ክፍሎች በእኩል ደረጃ አንዳቸው ለሌላው አሳቢነት እንዲያሳዩ ነው።+ +26 አንድ የአካል ክፍል ቢሠቃይ ሌሎቹ የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረውት ይሠቃያሉ፤+ ወይም አንድ የአካል ክፍል ክብር ቢያገኝ ሌሎቹ የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረውት ይደሰታሉ።+ +27 እንግዲህ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤+ እያንዳንዳችሁም በግለሰብ ደረጃ የአካሉ ክፍል ናችሁ።+ +28 አምላክ የተለያዩ የአካል ክፍሎችን ይኸውም አንደኛ ሐዋርያትን፣+ ሁለተኛ ነቢያትን፣+ ሦስተኛ አስተማሪዎችን፣+ ከዚያም ተአምር የሚፈጽሙትን፣+ ከዚያም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፣+ ጠቃሚ አገልግሎት የሚያከናውኑትን፣ የመምራት ችሎታ ያላቸውንና+ በተለያዩ ልሳኖች የሚናገሩትን+ በጉባኤ ውስጥ መድቧል። +29 ሁሉ ሐዋርያት ናቸው? ሁሉስ ነቢያት ናቸው? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸው? ሁሉስ ተአምር ይሠራሉ? +30 ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸው? ሁሉስ በልሳን ይናገራሉ?+ ሁሉስ ተርጓሚዎች ናቸው?+ +31 ይሁንና ብልጫ ያላቸውን ስጦታዎች ለማግኘት ጥረት* ማድረጋችሁን ቀጥሉ።+ ደግሞም ከሁሉ የላቀውን መንገድ አሳያችኋለሁ።+ +1 በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ+ እንዲሆን ከተጠራው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከሶስቴንስ፣ +2 በቆሮንቶስ ለሚገኘው የአምላክ ጉባኤ+ ይኸውም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባላችሁ አንድነት ለተቀደሳችሁ፣+ እንዲሁም የእነሱም ሆነ የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም+ በየስፍራው ሆነው ከሚጠሩ ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠራችሁ፦ +3 ከአባታችን ከአምላክና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። +4 በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ በሰጠው ጸጋ የተነሳ አምላኬን ሁልጊዜ ስለ እናንተ አመሰግናለሁ፤ +5 ምክንያቱም በሁሉም ነገር ይኸውም በመናገር ችሎታ ሁሉና በእውቀት ሁሉ በክርስቶስ በልጽጋችኋል፤+ +6 ደግሞም ስለ ክርስቶስ የተሰጠው ምሥክርነት+ በእናንተ መካከል በሚገባ ሥር ሰዷል፤ +7 ስለዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ ማንኛውም ስጦታ ፈጽሞ አይጎድልባችሁም።+ +8 በተጨማሪም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን+ ከማንኛውም ክስ ነፃ መሆን እንድትችሉ እስከ መጨረሻው ያጸናችኋል። +9 ከልጁ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ* የጠራችሁ አምላክ ታማኝ ነው።+ +10 እንግዲህ ወንድሞች፣ ሁላችሁም ንግግራችሁ አንድ እንዲሆንና በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳይኖር፣+ ከዚህ ይልቅ በአስተሳሰብም ሆነ በዓላማ ፍጹም አንድነት እንዲኖራችሁ+ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አጥብቄ አሳስባችኋለሁ። +11 ወንድሞቼ ሆይ፣ የቀሎኤ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አንዳንዶች በመካከላችሁ አለመግባባት እንዳለ ነግረውኛል። +12 ይኸውም እያንዳንዳችሁ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፣” “እኔ ግን የአጵሎስ+ ነኝ፣” “እኔ ደግሞ የኬፋ* ነኝ፣” “እኔ የክርስቶስ ነኝ” ትላላችሁ። +13 ታዲያ የክርስቶስ ጉባኤ ተከፋፍሏል ማለት ነው? ጳውሎስ ለእናንተ ሲል በእንጨት ላይ ተሰቅሏል እንዴ? ወይስ የተጠመቃችሁት በጳውሎስ ስም ነው? +14 ከቀርስጶስና+ ከጋይዮስ+ በስተቀር ከእናንተ አንዳችሁንም ባለማጥመቄ አምላክን አመሰግናለሁ፤ +15 በመሆኑም ከእናንተ መካከል በእኔ ስም እንደተጠመቀ ሊናገር የሚችል ማንም የለም። +16 እርግጥ የእስጢፋናስን+ ቤተሰብም አጥምቄአለሁ። ከእነዚህ ሌላ ግን ያጠመቅኩት ሰው መኖሩን አላስታውስም። +17 ክርስቶስ የላከኝ እንዳጠምቅ ሳይሆን ምሥራቹን እንዳውጅ ነው፤+ ደግሞም የክርስቶስ የመከራ እንጨት* ከንቱ እንዳይሆን ምሥራቹን የማውጀው በንግግር ጥበብ* አይደለም። +18 ስለ መከራው እንጨት* የሚነገረው መልእክት ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ሞኝነት፣+ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ላለነው ለእኛ ግን የአምላክ ኃይል መገለጫ ነው።+ +19 “የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የሊቃውንትንም ማስተዋል ወዲያ እጥላለሁ” ተብሎ ተጽፏልና።+ +20 የዚህ ሥርዓት* ጥበበኞች የት አሉ? ጸሐፍትስ* የት አሉ? ተሟጋቾችስ የት አሉ? አምላክ የዓለምን ጥበብ ሞኝነት አላደረገም? +21 ዓለም በራሱ ጥበብ+ አምላክን ሊያውቀው ስላልቻለ+ አምላክ በጥበቡ፣ እንደ ሞኝነት በሚቆጠረውና+ እየተሰበከ ባለው መልእክት አማካኝነት የሚያምኑትን ሰዎች ለማዳን መርጧል። +22 አይሁዳውያን ተአምራዊ ምልክቶች ማየት ይፈልጋሉ፤+ ግሪካውያን ደግሞ ጥበብን ይሻሉ፤ +23 እኛ ግን በእንጨት ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁዳውያን መሰናክል ለአሕዛብ ደግሞ ሞኝነት ነው።+ +24 ይሁን እንጂ ክርስቶስ ለተጠሩት፣ ለአይሁዳውያንም ሆነ ለግሪካውያን የአምላክ ኃይልና የአምላክ ጥበብ ነው።+ +25 ምክንያቱም የአምላክ ሞኝነት እንደሆነ ተደርጎ የሚታሰበው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል፤ የአምላክ ድክመት እንደሆነ ተደርጎ የሚታሰበው ነገር ደግሞ ከሰዎች ብርታት ይበልጣል።+ +26 ወንድሞች፣ ከራሳችሁ ሁኔታ መረዳት እንደምትችሉት በሰብዓዊ አመለካከት* ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፣+ ኃያላን የሆኑ ብዙዎች እንዲሁም ከትልቅ ቤተሰብ የተወለዱ ብዙዎች አልተጠሩም፤+ +27 ከዚህ ይልቅ አምላክ ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱውንም ነገር ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤+ +28 አምላክ በሰዎች ዘንድ ትልቅ ግምት የሚሰጠውን ነገር ከንቱ ያደርግ ዘንድ በዚህ ዓለም ዝቅ ተደርጎ የሚታየውንና የተናቀውን ነገር ይኸውም ከንቱ መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ፤+ +29 ይህን ያደረገው ማንም ሰው* በአምላክ ፊት እንዳይኩራራ ነው። +30 ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ሊኖራችሁ የቻለው በእሱ ምክንያት ነው፤ ክርስቶስ ደግሞ ለእኛ ከአምላክ የመጣ ጥበብ፣ ጽድቅና+ ቅድስና+ ሆኖልናል፤ እንዲሁም በቤዛው ነፃ አውጥቶናል፤+ +31 ይህም “የሚኩራራ በይሖዋ* ይኩራራ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +8 ለጣዖቶች የቀረበን ምግብ በተመለከተ፣+ ሁላችንም እውቀት እንዳለን እናውቃለን።+ እውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።+ +2 አንድ ሰው ስለ አንድ ነገር አውቃለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ስለዚያ ነገር ማወቅ የሚገባውን ያህል ገና አያውቅም። +3 ሆኖም አንድ ሰው አምላክን የሚወድ ከሆነ በእሱ ዘንድ የታወቀ ነው። +4 ለጣዖቶች የቀረበ ምግብ መብላትን በተመለከተ፣ በዓለም ላይ ጣዖት ከንቱ እንደሆነና+ ከአንዱ በቀር አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።+ +5 ብዙ “አማልክት” እና ብዙ “ጌቶች” እንደመኖራቸው መጠን በሰማይም ሆነ በምድር አማልክት ተብለው የሚጠሩ+ ቢኖሩም እንኳ +6 እኛ ግን ሁሉም ነገር ከእሱ የሆነ እኛም ለእሱ የሆን+ አንድ አምላክ+ አብ+ አለን፤ እንዲሁም ሁሉም ነገር በእሱ በኩል የሆነና እኛም በእሱ በኩል የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለ።+ +7 ይሁንና ይህ እውቀት ያላቸው ሁሉም ሰዎች አይደሉም።+ አንዳንዶች ግን ቀደም ሲል ጣዖት ያመልኩ ስለነበር የሚበሉት ምግብ ለጣዖት የተሠዋ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ፤+ ሕሊናቸው ደካማ ስለሆነም ይረክሳል።+ +8 ይሁን እንጂ ምግብ ከአምላክ ጋር አያቀራርበንም፤+ ባንበላ የሚጎድልብን ነገር የለም፤ ብንበላም የምናተርፈው ነገር የለም።+ +9 ነገ�� ግን የመምረጥ መብታችሁ፣ ደካማ የሆኑትን በሆነ መንገድ እንዳያሰናክላቸው ተጠንቀቁ።+ +10 አንተ እውቀት ያለህ በጣዖት ቤተ መቅደስ ውስጥ ስትበላ አንድ ሰው ቢያይህ ደካማ የሆነው ይህ ሰው ሕሊናው ለጣዖት የቀረበውን ምግብ እንዲበላ አያደፋፍረውም? +11 እንግዲህ ክርስቶስ የሞተለት ይህ ደካማ የሆነው ወንድምህ በአንተ እውቀት ሳቢያ ጠፋ* ማለት ነው።+ +12 በዚህ መንገድ ወንድሞቻችሁን ስትበድሉና ደካማ የሆነውን ሕሊናቸውን ስታቆስሉ+ በክርስቶስ ላይ ኃጢአት እየሠራችሁ ነው። +13 ስለዚህ ምግብ ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ ወንድሜን ላለማሰናከል ስል ከእንግዲህ ፈጽሞ ሥጋ አልበላም።+ +11 እኔ የክርስቶስን አርዓያ እንደምከተል እናንተም የእኔን አርዓያ ተከተሉ።+ +2 በሁሉም ነገር ስለምታስቡኝና ለእናንተ ያስተላለፍኳቸውን ወጎች አጥብቃችሁ ስለያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ። +3 ይሁንና የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፣+ የሴትም ራስ ወንድ፣+ የክርስቶስ ራስ ደግሞ አምላክ እንደሆነ እንድታውቁ እወዳለሁ።+ +4 ራሱን ሸፍኖ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ ሁሉ የእሱን ራስ ያዋርዳል፤ +5 ራሷን ሳትሸፍን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር+ ሴት ሁሉ ደግሞ የእሷን ራስ ታዋርዳለች፤ እንዲህ የምታደርግ ሴት ራሷን እንደተላጨች ሴት ትቆጠራለች። +6 አንዲት ሴት ራሷን የማትሸፍን ከሆነ ፀጉሯን ትቆረጥ፤ ፀጉሯን መቆረጧ ወይም መላጨቷ የሚያሳፍራት ከሆነ ግን ትሸፈን። +7 ወንድ የአምላክ አምሳልና+ ክብር ስለሆነ ራሱን መሸፈን የለበትም፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት። +8 ሴት ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘምና።+ +9 ከዚህም በተጨማሪ ሴት ለወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም።+ +10 ከዚህ የተነሳም ሆነ ለመላእክት ሲባል ሴት በሥልጣን ሥር መሆኗን የሚያሳይ ምልክት በራሷ ላይ ታድርግ።+ +11 ይሁንና በጌታ ተከታዮች ዘንድ ሴት ያለወንድ አትኖርም፤ ወንድም ያለሴት አይኖርም። +12 ሴት ከወንድ እንደተገኘች ሁሉ+ ወንድም የተገኘው በሴት አማካኝነት ነውና፤ ሆኖም ሁሉም ነገሮች የተገኙት ከአምላክ ነው።+ +13 እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ፦ ሴት ሳትሸፈን ወደ አምላክ ብትጸልይ ተገቢ ይሆናል? +14 ወንድ ፀጉሩን ቢያስረዝም ውርደት እንደሚሆንበት ተፈጥሮ ራሱ እንኳ አያስተምራችሁም? +15 ሴት ግን ፀጉሯን ብታስረዝም ለእሷ ክብር አይደለም? ፀጉሯ የተሰጣት በመሸፈኛ ምትክ ነውና። +16 ይሁን እንጂ ማንም ሰው ሌላ ልማድ መከተል አለብን በሚል ለመከራከር ቢፈልግ እኛም ሆን የአምላክ ጉባኤ ከዚህ የተለየ ልማድ የለንም። +17 ሆኖም ስብሰባችሁ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እነዚህን መመሪያዎች ስሰጣችሁ ላመሰግናችሁ አልፈልግም። +18 በመጀመሪያ ደረጃ፣ በጉባኤ በምትሰበሰቡበት ጊዜ በመካከላችሁ ክፍፍል እንዳለ እሰማለሁ፤ ደግሞም ይህ በተወሰነ መጠን እውነትነት እንዳለው አምናለሁ። +19 በዚህ ሁኔታ በእናንተ መካከል ኑፋቄዎች ብቅ ማለታቸው አይቀርም፤+ ይህም መሆኑ ከእናንተ መካከል ተቀባይነት የሚያገኙት ሰዎች ተለይተው እንዲታወቁ ያስችላል። +20 አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ የሚኖረው ሁኔታ የጌታ ራትን+ በአግባቡ ለማክበር የሚያስችል አይደለም። +21 የጌታ ራትን በምትበሉበት ጊዜ አንዳንዶች አስቀድመው የራሳቸውን ራት ስለሚበሉ አንዱ ይራባል ሌላው ደግሞ ይሰክራል። +22 የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁም? ወይስ የአምላክን ጉባኤ በመናቅ ምንም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁ? እንግዲህ ምን ልበላችሁ? ላመስግናችሁ? በዚህ ነገርስ አላመሰግናችሁም። +23 እኔ ከጌታ የተቀበልኩትን ለእናንተ አስተላልፌአለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት ሌሊት+ ቂጣ አንስቶ +24 ካመሰገነ በኋላ ቆርሶ “ይህ ስለ እናንተ የሚሰጠውን ሥጋዬን ያመለክታል።+ ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።+ +25 በተጨማሪም ራት ከበሉ በኋላ ጽዋውን+ አንስቶ ልክ እንደዚሁ አደረገ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ጽዋ በደሜ+ አማካኝነት የሚመሠረተውን አዲሱን ቃል ኪዳን+ ያመለክታል። ከዚህ ጽዋ በጠጣችሁ ቁጥር ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት።”+ +26 ይህን ቂጣ በበላችሁና ከዚህ ጽዋ በጠጣችሁ ቁጥር ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ታውጃላችሁ። +27 እንግዲህ የማይገባው ሆኖ ሳለ ከቂጣው የሚበላ ወይም ከጌታ ጽዋ የሚጠጣ ከጌታ አካልና ደም ጋር በተያያዘ ተጠያቂ ይሆናል። +28 አንድ ሰው የሚገባው እንደሆነ ለማወቅ በቅድሚያ ራሱን ይመርምር፤+ ቂጣውን መብላትና ጽዋውን መጠጣት የሚችለው ይህን ካደረገ ብቻ ነው። +29 ምክንያቱም አካሉ ምን ትርጉም እንዳለው ሳይገነዘብ የሚበላና የሚጠጣ በራሱ ላይ ፍርድ የሚያመጣበትን ነገር መብላትና መጠጣት ይሆንበታል። +30 ከእናንተ መካከል ብዙዎቹ የተዳከሙትና ታማሚ የሆኑት እንዲሁም ጥቂት የማይባሉት በሞት ያንቀላፉት* በዚህ ምክንያት ነው።+ +31 ሆኖም ራሳችንን መርምረን ብናውቅ ኖሮ ባልተፈረደብን ነበር። +32 ይሁን እንጂ በሚፈረድብን ጊዜ፣ ከዓለም ጋር አብረን እንዳንኮነን+ ሲል ይሖዋ* ይገሥጸናል።+ +33 ስለዚህ ወንድሞቼ፣ ይህን ራት ለመብላት በምትሰበሰቡበት ጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ። +34 የምትሰበሰቡት ለፍርድ እንዳይሆን የራበው ሰው ካለ እዚያው ቤቱ ይብላ።+ የቀሩትን ጉዳዮች ግን ስመጣ አስተካክላለሁ። +2 ስለዚህ ወንድሞች፣ የአምላክን ቅዱስ ሚስጥር+ ለእናንተ ለመግለጽ በመጣሁ ጊዜ በንግግር ችሎታ+ ወይም በጥበብ እናንተን ለማስደመም አልሞከርኩም። +2 ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ትኩረቴን በኢየሱስ ክርስቶስና በእሱ መሰቀል ላይ ብቻ ለማድረግ ወስኜ ነበርና።+ +3 ወደ እናንተም የመጣሁት ደካማ ሆኜ እንዲሁም በፍርሃትና እጅግ በመንቀጥቀጥ ነበር፤ +4 ንግግሬም ሆነ የሰበክሁላችሁ መልእክት የሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ የአምላክን መንፈስና ኃይል የሚያሳይ ነበር፤+ +5 ይኸውም እምነታችሁ በአምላክ ኃይል ላይ እንጂ በሰው ጥበብ ላይ የተመሠረተ እንዳይሆን ነው። +6 በመሆኑም በጎለመሱት+ መካከል ስለ ጥበብ እንናገራለን፤ ሆኖም የምንናገረው የዚህን ሥርዓት* ጥበብ ወይም የሚጠፉትን የዚህን ሥርዓት ገዢዎች+ ጥበብ አይደለም። +7 ከዚህ ይልቅ የምንናገረው በቅዱስ ሚስጥር+ የተገለጠውን የአምላክ ጥበብ ይኸውም አምላክ ለእኛ ክብር ከዘመናት በፊት* አስቀድሞ የወሰነውን የተሰወረ ጥበብ ነው። +8 ይህን ጥበብ ከዚህ ሥርዓት* ገዢዎች መካከል አንዳቸውም አላወቁትም፤+ ቢያውቁትማ ኖሮ ታላቅ ክብር ያለውን ጌታ ባልሰቀሉት* ነበር። +9 ይሁንና “አምላክ ለሚወዱት ያዘጋጃቸውን ነገሮች ዓይን አላየም፣ ጆሮም አልሰማም፣ የሰውም ልብ አላሰበም” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +10 አምላክ እነዚህን ነገሮች በመንፈሱ+ አማካኝነት የገለጠው ለእኛ ነውና፤+ ምክንያቱም መንፈስ ሁሉንም ነገሮች አልፎ ተርፎም የአምላክን ጥልቅ ነገሮች ይመረምራል።+ +11 ከሰዎች መካከል በአንድ ሰው ውስጥ ያለውን ነገር በውስጡ ካለው የሰውየው መንፈስ በቀር ማን ሊያውቅ ይችላል? በተመሳሳይም በአምላክ ውስጥ ያለውን ነገር ከአምላክ መንፈስ በቀር ማንም አያውቅም። +12 እኛ አምላክ በደግነት የሰጠንን ነገሮች ማወቅ እንድንችል ከአምላክ የሆነውን መንፈስ+ ተቀበልን እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። +13 ደግሞም እነዚህን ነገሮች እንናገራለን፤ የምንናገረው ግን ከሰው ጥበብ+ በተማርነው ቃል አይደለም፤ ከዚህ ���ልቅ መንፈሳዊ ጉዳዮችን በመንፈሳዊ ቃል ስናብራራ* ከመንፈስ በተማርነው ቃል እንናገራለን።+ +14 ዓለማዊ ሰው ግን ከአምላክ መንፈስ የሆኑትን ነገሮች አይቀበልም፤ እንዲህ ያሉት ነገሮች ለእሱ ሞኝነት ናቸውና፤ በመንፈስ የሚመረመሩ ስለሆኑም ሊረዳቸው አይችልም። +15 ይሁን እንጂ መንፈሳዊ ሰው ሁሉንም ነገር ይመረምራል፤+ እሱ ራሱ ግን በማንም ሰው አይመረመርም። +16 “ያስተምረው ዘንድ የይሖዋን* አስተሳሰብ ያወቀ ማን ነው?” ተብሏልና፤+ እኛ ግን የክርስቶስ አስተሳሰብ አለን።+ +4 እንግዲህ ሰው እኛን የክርስቶስ አገልጋዮችና* የአምላክ ቅዱስ ሚስጥር በአደራ የተሰጠን መጋቢዎች እንደሆን አድርጎ ሊቆጥረን ይገባል።+ +2 በዚህ ረገድ መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል። +3 በእናንተም ሆነ በሰዎች ሸንጎ* ብመረመር ለእኔ ምንም ትርጉም የለውም። እኔም እንኳ ራሴን አልመረምርም። +4 ምክንያቱም ሕሊናዬ በሁሉም ነገር ንጹሕ ነው። ሆኖም ይህ ጻድቅ መሆኔን ያረጋግጣል ማለት አይደለም፤ እኔን የሚመረምረኝ ይሖዋ* ነው።+ +5 ስለዚህ ጊዜው ከመድረሱ በፊት በምንም ነገር ላይ አትፍረዱ፤+ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጠብቁ። እሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ነገር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ እንዲሁም በልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ይገልጣል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ከአምላክ ምስጋናውን ይቀበላል።+ +6 እንግዲህ ወንድሞች፣ አንዱን ከሌላው በማስበለጥ እንዳትታበዩ፣+ ለእናንተው ጥቅም ራሴንና አጵሎስን+ ምሳሌ አድርጌ በማቅረብ እነዚህን ነገሮች የተናገርኩት “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ደንብ እንድትማሩ ነው። +7 ለመሆኑ አንተን ከሌላው የተለየህ እንድትሆን ያደረገህ ማን ነው? ደግሞስ ያልተቀበልከው ምን ነገር አለ?+ ከተቀበልክ ደግሞ እንዳልተቀበልክ ሆነህ የምትኩራራው ለምንድን ነው? +8 እንግዲህ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችኋል ማለት ነዋ! ባለጠጎች ሆናችኋላ! ያለእኛ ነግሣችኋል+ ማለት ነዋ! እኛም ከእናንተ ጋር መንገሥ እንድንችል ነገሥታት ሆናችሁ መግዛት ጀምራችሁ ቢሆን ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር!+ +9 አምላክ እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደተፈረደባቸው+ ሰዎች መጨረሻ ላይ ወደ መድረክ እንድንወጣ ያደረገን ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ለዓለም፣ ለመላእክትና ለሰዎች ትርዒት ሆነናል።+ +10 እኛ በክርስቶስ የተነሳ ሞኞች ነን፤+ እናንተ ግን በክርስቶስ የተነሳ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ጠንካሮች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን ተዋርደናል። +11 እስከዚህ ሰዓት ድረስ እየተራብንና+ እየተጠማን፣+ እየተራቆትን፣ እየተደበደብንና*+ ቤት አጥተን እየተንከራተትን እንገኛለን፤ +12 እንዲሁም በገዛ እጃችን እየሠራን እንለፋለን።+ ሲሰድቡን እንባርካለን፤+ ስደት ሲያደርሱብን በትዕግሥት እናሳልፋለን፤+ +13 ስማችንን ሲያጠፉ በለዘበ አንደበት እንመልሳለን፤*+ እስካሁን ድረስ የዓለም ጉድፍና* የሁሉ ነገር ጥራጊ እንደሆንን ተደርገን እንታያለን። +14 እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ላሳፍራችሁ ብዬ ሳይሆን እንደተወደዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልመክራችሁ ነው። +"15 ምንም እንኳ በክርስቶስ 10,000 ሞግዚቶች* ሊኖሯችሁ ቢችልም ብዙ አባቶች እንደሌሏችሁ ግን የተረጋገጠ ነው፤ በምሥራቹ አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ እኔ አባታችሁ ሆኛለሁና።+" +16 ስለዚህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ።+ +17 በጌታ ልጄ የሆነውን የምወደውንና ታማኝ የሆነውን ጢሞቴዎስን የምልክላችሁ ለዚህ ነው። እሱም በየስፍራው በሚገኙ ጉባኤዎች ሁሉ ሳስተምር የምጠቀምባቸውን ይኸውም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቴን የማከናውንባቸውን ዘዴዎች* ያሳስባችኋል።+ +18 አንዳንዶች እኔ ወደ እናንተ የማልመጣ መስሏቸው በኩራት ተወጥረዋል። +19 ይሁንና ይሖዋ* ከፈቀደ በቅርቡ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜም እነዚህ በኩራት የተወጠሩ ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ሳይሆን የአምላክ ኃይል ይኖራቸው እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ። +20 የአምላክ መንግሥት የወሬ ጉዳይ ሳይሆን የኃይል ጉዳይ ነውና። +21 ለመሆኑ የትኛው ይሻላችኋል? ዱላ+ ይዤ ልምጣ ወይስ በፍቅርና በገርነት መንፈስ ልምጣ? +16 ለቅዱሳን መዋጮ ማሰባሰብን በተመለከተ+ ደግሞ በገላትያ ለሚገኙ ጉባኤዎች የሰጠሁትን መመሪያ መከተል ትችላላችሁ። +2 መዋጮ የሚሰባሰበው እኔ በምመጣበት ጊዜ እንዳይሆን ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን አቅሙ በሚፈቅድለት መጠን የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጥ። +3 ስመጣም የመረጣችኋቸውንና የድጋፍ ደብዳቤ የጻፋችሁላቸውን ሰዎች+ የልግስና ስጦታችሁን ኢየሩሳሌም እንዲያደርሱ እልካቸዋለሁ። +4 ይሁን እንጂ የእኔም መሄድ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አብረውኝ ይሄዳሉ። +5 ይሁንና በመቄዶንያ በኩል ማለፌ ስለማይቀር በዚያ ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤+ +6 ወደምሄድበትም ቦታ የተወሰነ መንገድ እንድትሸኙኝ ምናልባት እናንተ ጋ ልቆይ እችላለሁ፤ እንዲያውም ክረምቱን ከእናንተ ጋር አሳልፍ ይሆናል። +7 ይሖዋ* ቢፈቅድ ከእናንተ ጋር የተወሰነ ጊዜ አሳልፋለሁ ብዬ ተስፋ ስለማደርግ አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ላያችሁ አልፈልግም።+ +8 ይሁንና እስከ ጴንጤቆስጤ በዓል ድረስ በኤፌሶን+ እቆያለሁ፤ +9 ምክንያቱም ትልቅ የሥራ በር ተከፍቶልኛል፤+ ሆኖም ብዙ ተቃዋሚዎች አሉ። +10 ጢሞቴዎስ+ ከመጣ በመካከላችሁ በሚቆይበት ጊዜ ፍርሃት እንዳይሰማው ተባበሩት፤ እሱም እንደ እኔ የይሖዋን* ሥራ የሚሠራ ነውና።+ +11 ስለዚህ ማንም አይናቀው። ከወንድሞች ጋር እየጠበቅኩት ስለሆነ ወደ እኔ እንዲመጣ በሰላም ሸኙት። +12 ወንድማችንን አጵሎስን+ በተመለከተ ደግሞ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር። እሱ አሁን የመምጣት ሐሳብ የለውም፤ ሆኖም ሁኔታው ሲመቻችለት ይመጣል። +13 ነቅታችሁ ኑሩ፤+ በእምነት ጸንታችሁ ቁሙ፤+ ወንድ ሁኑ፤*+ ብርቱዎች ሁኑ።+ +14 የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በፍቅር አድርጉ።+ +15 እንግዲህ ወንድሞች ይህን አሳስባችኋለሁ፦ የእስጢፋናስ ቤተሰብ በአካይያ የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት* እንደሆኑና ቅዱሳንን ለማገልገል ራሳቸውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ። +16 እናንተም እንደ እነሱ ላሉት እንዲሁም ከእኛ ጋር ለሚተባበሩትና በትጋት ለሚሠሩት ሁሉ ተገዙ።+ +17 እስጢፋናስ+ እና ፈርጡናጦስ እንዲሁም አካይቆስ እዚህ በመገኘታቸው እጅግ ተደስቻለሁ፤ ምክንያቱም የእናንተ እዚህ አለመኖር በእነሱ ተካክሷል። +18 እነሱ የእኔንም ሆነ የእናንተን መንፈስ አድሰዋልና። ስለዚህ እንዲህ ላሉት ሰዎች እውቅና ስጡ። +19 በእስያ ያሉ ጉባኤዎች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ እንዲሁም በቤታቸው ያለው ጉባኤ+ ሞቅ ያለ ክርስቲያናዊ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። +20 ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ። +21 እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ የጻፍኩላችሁ ሰላምታ ይድረሳችሁ። +22 ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፣ ና! +23 የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። +24 የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሆናችሁ ሁሉ፣ ፍቅሬ ይድረሳችሁ። +6 ከእናንተ መካከል አንዱ ከሌላው ጋር የሚከራከርበት ጉዳይ ቢኖረው፣+ ጉዳዩን በቅዱሳን ፊት በማቅረብ ፋንታ በዓመፀኛ ሰዎች ፊት ለማቅረብ ፍርድ ቤት ለመሄድ እንዴት ይደፍራል? +2 ወይስ ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁም?+ ታዲያ እናንተ በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ በጣም ተራ የሆኑ ጉዳዮችን ለመዳኘት አትበቁም? +3 በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁም?+ ታዲያ በአሁኑ ሕይወት በሚያጋጥሙ ጉዳዮች ላይ ለምን አትፈርዱም? +4 ደግሞስ በአሁኑ ሕይወት የሚያጋጥሙ ዳኝነት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ካሉ+ ጉባኤው የሚንቃቸው ሰዎች እንዲዳኙት ታደርጋላችሁ? +5 ይህን የምለው ኀፍረት እንዲሰማችሁ ብዬ ነው። ወንድሞቹን መዳኘት የሚችል አንድ እንኳ ጥበበኛ ሰው በመካከላችሁ የለም? +6 አንድ ወንድም ሌላውን ወንድም ፍርድ ቤት ይወስዳል፤ ያውም የማያምኑ ሰዎች ፊት! +7 እንግዲህ እርስ በርስ ተካስሳችሁ ፍርድ ቤት መሄዳችሁ ለእናንተ ትልቅ ሽንፈት ነው። ከዚህ ይልቅ እናንተ ራሳችሁ ብትበደሉ አይሻልም?+ ደግሞስ እናንተ ራሳችሁ ብትታለሉ አይሻልም? +8 እናንተ ግን ትበድላላችሁ እንዲሁም ታታልላላችሁ፤ ያውም የገዛ ወንድሞቻችሁን! +9 ወይስ ዓመፀኞች የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁም?+ አትታለሉ፤ ሴሰኞችም*+ ሆኑ ጣዖት አምላኪዎች+ ወይም አመንዝሮች+ ወይም ቀላጮች*+ ወይም ግብረ ሰዶማውያን*+ +10 ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች+ ወይም ሰካራሞች+ ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ቀማኞች የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+ +11 አንዳንዶቻችሁም እንደዚህ ነበራችሁ። ሆኖም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ታጥባችሁ ነጽታችኋል፣+ ተቀድሳችኋል+ እንዲሁም ጻድቃን ተብላችኋል።+ +12 ሁሉም ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ሆኖም ሁሉም ነገር ይጠቅማል ማለት አይደለም።+ ሁሉም ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ሆኖም ለምንም ነገር ተገዢ መሆን አልሻም። +13 ምግብ ለሆድ፣ ሆድም ለምግብ ነው፤ አምላክ ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋል።+ አካል ለጌታ ነው እንጂ ለፆታ ብልግና* አይደለም፤+ ጌታ ደግሞ ለአካል ነው። +14 ይሁን እንጂ አምላክ በኃይሉ+ አማካኝነት ጌታን እንዳስነሳው+ እኛንም ከሞት ያስነሳናል።+ +15 ሰውነታችሁ የክርስቶስ አካል ክፍል እንደሆነ አታውቁም?+ ታዲያ የክርስቶስ አካል ክፍል የሆነውን ወስጄ ከዝሙት አዳሪ ጋር ላጣምረው? በፍጹም! +16 ከዝሙት አዳሪ ጋር የሚጣመር ሁሉ ከእሷ ጋር አንድ አካል እንደሚሆን አታውቁም? አምላክ “ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” ብሏልና።+ +17 ሆኖም ከጌታ ጋር የተቆራኘ ሁሉ በመንፈስ ከእሱ ጋር አንድ ነው።+ +18 ከፆታ ብልግና* ሽሹ!+ አንድ ሰው የሚፈጽመው ሌላ ኃጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ የፆታ ብልግና የሚፈጽም ሁሉ ግን በራሱ አካል ላይ ኃጢአት እየሠራ ነው።+ +19 የእናንተ አካል ከአምላክ ለተቀበላችሁት፣ በውስጣችሁ ላለው መንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ+ እንደሆነ አታውቁም?+ በተጨማሪም እናንተ የራሳችሁ አይደላችሁም፤+ +20 በዋጋ ተገዝታችኋልና።+ ስለዚህ በሰውነታችሁ+ አምላክን አክብሩ።+ +10 እንግዲህ ወንድሞች፣ አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች+ እንደነበሩና ሁሉም በባሕር መካከል እንዳለፉ+ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ +2 ሁሉም ከሙሴ ጋር በመተባበር በደመናውና በባሕሩ ተጠመቁ፤ +3 ደግሞም ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ ምግብ ተመገቡ፤+ +4 በተጨማሪም ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ።+ ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዓለት ይጠጡ ነበርና፤ ይህም ዓለት ክርስቶስን ያመለክታል።*+ +5 ይሁንና አምላክ በአብዛኞቹ ስላልተደሰተ በምድረ በዳ ወድቀው ቀርተዋል።+ +6 እነሱ ጎጂ የሆኑ ነገሮችን እንደተመኙ እኛም እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ለእኛ ምሳሌ ሆነውልናል።+ +7 “ሕዝቡ ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ። ከዚያም ሊጨፍሩ ተነሱ” ተብሎ እንደተጻፈው ከእነሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖት አምላኪዎች አትሁኑ።+ +"8 ከእነሱ አንዳንዶቹ የፆታ ብልግና* ፈጽመው ከመካከላቸው 23,000 የሚሆኑት በአንድ ቀን እንደረገፉ እኛም የፆታ ብልግና* አንፈጽም።+" +9 ከእነሱ አንዳንዶቹ ይሖዋን* ተፈታትነው በእባቦች እንደጠፉ እኛም አንፈታተነው።+ +10 በተጨማሪም ከእነሱ አንዳንዶቹ በማጉረምረማቸው+ በአጥፊው እንደጠፉ+ አጉረምራሚዎች አትሁኑ። +11 እነዚህ ነገሮች ምሳሌ ይሆኑ ዘንድ በእነሱ ላይ ደረሱ፤ የተጻፉትም የሥርዓቶቹ ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅ ነው።+ +12 በመሆኑም የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።+ +13 በሰው ሁሉ ላይ ከሚደርሰው ፈተና የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም።+ ይሁንና አምላክ ታማኝ ነው፤ ልትሸከሙት ከምትችሉት በላይ ፈተና እንዲደርስባችሁ አይፈቅድም፤+ ከዚህ ይልቅ ፈተናውን በጽናት መቋቋም እንድትችሉ ፈተና ሲደርስባችሁ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።+ +14 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ከጣዖት አምልኮ ሽሹ።+ +15 ይህን የምናገረው ማስተዋል ላላቸው ሰዎች ነው፤ የምናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ። +16 የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም መቋደስ አይደለም?+ የምንቆርሰውስ ቂጣ ከክርስቶስ አካል መቋደስ አይደለም?+ +17 ምክንያቱም እኛ ብዙ ብንሆንም ቂጣው አንድ ስለሆነ አንድ አካል ነን፤+ ሁላችንም የምንካፈለው ከዚሁ አንድ ቂጣ ነውና። +18 እስቲ ሥጋዊ እስራኤላውያንን ተመልከቱ፦ መሥዋዕቱን የሚበሉት ከመሠዊያው ጋር ተቋዳሾች አይደሉም?+ +19 እንግዲህ ምን እያልኩ ነው? ለጣዖት የተሠዋ ነገር የተለየ ፋይዳ አለው ማለቴ ነው? ወይስ ጣዖት ዋጋ አለው ማለቴ ነው? +20 እንዲህ ማለቴ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ አሕዛብ መሥዋዕት አድርገው የሚያቀርቧቸውን ነገሮች የሚሠዉት ለአምላክ ሳይሆን ለአጋንንት ነው ማለቴ ነው፤+ ከአጋንንት ጋር እንድትተባበሩ ደግሞ አልፈልግም።+ +21 የይሖዋን* ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ መጠጣት አትችሉም፤ “ከይሖዋ* ማዕድ”+ እና ከአጋንንት ማዕድ መካፈል አትችሉም። +22 ወይስ ‘ይሖዋን* እያስቀናነው ነው’?+ እኛ ከእሱ ይበልጥ ብርቱዎች ነን እንዴ? +23 ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፤ ሆኖም ሁሉም ነገር ይጠቅማል ማለት አይደለም። ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፤ ሆኖም ሁሉም ነገር ያንጻል ማለት አይደለም።+ +24 እያንዳንዱ ሰው ምንጊዜም የራሱን ጥቅም ሳይሆን የሌላውን ሰው ጥቅም ይፈልግ።+ +25 ከሕሊናችሁ የተነሳ ምንም ጥያቄ ሳታነሱ በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ማንኛውንም ነገር ብሉ፤ +26 “ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ የይሖዋ* ነውና።”+ +27 አማኝ ያልሆነ ሰው ቢጋብዛችሁና መሄድ ብትፈልጉ ከሕሊናችሁ የተነሳ ምንም ጥያቄ ሳታነሱ የቀረበላችሁን ሁሉ ብሉ። +28 ይሁንና አንድ ሰው “ይህ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበ ነው” ቢላችሁ ይህን ለነገራችሁ ሰውና ለሕሊና ስትሉ አትብሉ።+ +29 እንዲህ ስል ስለ ራሳችሁ ሕሊና ሳይሆን ስለ ሌላው ሰው ሕሊና መናገሬ ነው። ነፃነቴ በሌላው ሰው ሕሊና ለምን ይፈረድበት?+ +30 አመስግኜ የምበላ ከሆነ ባመሰገንኩበት ነገር ለምን እነቀፋለሁ?+ +31 ስለዚህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ ሁሉንም ነገር ለአምላክ ክብር አድርጉ።+ +32 ለአይሁዳውያንም ሆነ ለግሪካውያን እንዲሁም ለአምላክ ጉባኤ እንቅፋት አትሁኑ፤+ +33 እኔ ብዙዎች እንዲድኑ የእነሱን እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በማደርገው ነገር ሁሉ፣+ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት እንደምጥር እናንተም እንዲሁ አድርጉ።+ +14 ፍቅርን ተከታተሉ፤ ሆኖም መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይልቁንም ትንቢት የመናገር ስጦታን ለማግኘት ጥረት* አድርጉ።+ +2 በልሳን የሚናገር ለአምላክ እንጂ ለሰው አይናገርምና፤ በመንፈስ አማካኝነት ቅዱስ ሚስጥሮችን ቢናገርም+ እንኳ ማንም አይሰማውም።+ +3 ይሁን እንጂ ትንቢ��� የሚናገር በንግግሩ ሰዎችን ያንጻል፣ ያበረታታል እንዲሁም ያጽናናል። +4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢት የሚናገር ግን ጉባኤን ያንጻል። +5 ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወድ ነበር፤+ ሆኖም ትንቢት ብትናገሩ እመርጣለሁ።+ ደግሞም ትንቢት የሚናገር በልሳን ከሚናገር ይበልጣል። ምክንያቱም በልሳን የሚናገር የተናገረውን ካልተረጎመው ጉባኤው ሊታነጽ አይችልም። +6 አሁን ግን ወንድሞች፣ ወደ እናንተ መጥቼ ራእይን በመግለጥ+ ወይም በእውቀት+ ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኳችሁ በስተቀር በልሳን ብነግራችሁ ምን እጠቅማችኋለሁ? +7 እንደ ዋሽንትና በገና ካሉ ድምፅ የሚያወጡ ግዑዝ ነገሮች ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። የሚያወጡት የድምፅ ቃና ግልጽ የሆነ ልዩነት ከሌለው ከዋሽንቱም ሆነ ከበገናው የሚወጣው ዜማ እንዴት ይለያል? +8 ደግሞም መለከት ለመለየት የሚያስቸግር ድምፅ ቢያሰማ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል? +9 ልክ እንደዚሁም ከአንደበታችሁ የሚወጣው ቃል በቀላሉ የሚገባ ካልሆነ ስለ ምን እየተናገራችሁ እንዳለ ማን ሊያውቅ ይችላል? እንዲህ ከሆነ ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁ። +10 በዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎች አሉ፤ ሆኖም ትርጉም የሌለው ቋንቋ የለም። +11 አንድ ሰው የሚናገረውን ቋንቋ ትርጉም ካላወቅኩ እኔ ለሚናገረው ሰው የባዕድ አገር ሰው እሆንበታለሁ፤ እሱም ለእኔ የባዕድ አገር ሰው ይሆንብኛል። +12 ስለዚህ እናንተም የመንፈስን ስጦታዎች እጅግ ስለምትፈልጉ ጉባኤውን የሚያንጹ ስጦታዎች በብዛት ለማግኘት ጥረት አድርጉ።+ +13 ስለሆነም በልሳን የሚናገር ሰው የሚናገረውን መተርጎም እንዲችል ይጸልይ።+ +14 ምክንያቱም በልሳን የምጸልይ ከሆነ፣ የሚጸልየው የተቀበልኩት የመንፈስ ስጦታ ነው፤ አእምሮዬ ግን ምንም የሚያከናውነው ነገር የለም። +15 ታዲያ ምን ማድረግ ይሻላል? በመንፈስ ስጦታ እጸልያለሁ፤ ሆኖም የምጸልየው ትርጉሙ ገብቶኝ ነው። በመንፈስ ስጦታ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤ ሆኖም የምዘምረው ትርጉሙ ገብቶኝ ነው። +16 እንዲህ ካልሆነ በመንፈስ ስጦታ ውዳሴ ብታቀርብ በመካከልህ ያለው ምንም የማያውቅ ሰው ምን እየተናገርክ እንዳለህ ስለማይገባው ላቀረብከው ምስጋና እንዴት “አሜን” ሊል ይችላል? +17 እርግጥ አንተ ግሩም በሆነ መንገድ ምስጋና ታቀርብ ይሆናል፤ ሌላው ሰው ግን እየታነጸበት አይደለም። +18 ከሁላችሁ የበለጠ በብዙ ልሳኖች ስለምናገር አምላክን አመሰግናለሁ። +19 ይሁንና በጉባኤ ውስጥ አሥር ሺህ ቃላት በልሳን ከምናገር ሌሎችንም ማስተማር* እችል ዘንድ አምስት ቃላት በአእምሮዬ* ብናገር እመርጣለሁ።+ +20 ወንድሞች፣ በማስተዋል ችሎታችሁ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤+ ለክፋት ግን ሕፃናት ሁኑ፤+ በማስተዋል ችሎታችሁም የጎለመሳችሁ ሁኑ።+ +21 በሕጉ ላይ “‘በባዕዳን አንደበትና እንግዳ በሆኑ ሰዎች ቋንቋዎች ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ እነሱ ግን በዚያን ጊዜም እንኳ አይሰሙኝም’ ይላል ይሖዋ”* ተብሎ ተጽፏል።+ +22 በመሆኑም ልሳን ለአማኞች ሳይሆን አማኝ ላልሆኑት ምልክት ነው፤+ ትንቢት ግን አማኝ ላልሆኑት ሳይሆን ለአማኞች ነው። +23 ስለዚህ ጉባኤው በሙሉ አንድ ላይ ተሰብስቦ ባለበት ወቅት ሁሉም በልሳኖች ቢናገሩና በዚህ መሃል ምንም የማያውቁ ሰዎች ወይም አማኞች ያልሆኑ ቢገቡ እነዚህ ሰዎች ‘አእምሯችሁን ስታችኋል’ አይሏችሁም? +24 ሆኖም ሁላችሁም ትንቢት እየተናገራችሁ ሳለ አማኝ ያልሆነ ወይም ምንም የማያውቅ ሰው ቢገባ ሁላችሁም የምትናገሩት ቃል እንደ ወቀሳ የሚያገለግለው ከመሆኑም በላይ ራሱን በሚገባ እንዲመረምር ያነሳሳዋል። +25 በዚህ ጊዜ በልቡ የተሰወረው ነገር ይገለጣል፤ በመ��ኑም “አምላክ በእርግጥ በመካከላችሁ ነው” እያለ በግንባሩ ተደፍቶ ለአምላክ ይሰግዳል።+ +26 እንግዲህ ወንድሞች፣ ምን ማድረግ ይሻላል? አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ አንዱ ይዘምራል፣ ሌላው ያስተምራል፣ ሌላው ራእይን ይገልጣል፣ ሌላው በልሳን ይናገራል፣ ሌላው ደግሞ ይተረጉማል።+ ሁሉም ነገር ለማነጽ ይሁን። +27 በልሳን የሚናገሩ ካሉ ከሁለት ወይም ከሦስት አይብለጡ፤ በየተራም ይናገሩ፤ የሚናገሩትንም ሌላ ሰው ይተርጉም።+ +28 የሚተረጉም ሰው ከሌለ ግን በጉባኤ መካከል ዝም ይበሉና ለራሳቸውና ለአምላክ ይናገሩ። +29 ሁለት ወይም ሦስት ነቢያት+ ይናገሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ ትርጉሙን ለመረዳት ይጣሩ። +30 ሆኖም አንድ ሰው እዚያ ተቀምጦ ሳለ ራእይ ቢገለጥለት የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል። +31 ሁሉም እንዲማሩና ሁሉም እንዲበረታቱ ሁላችሁም በየተራ ትንቢት መናገር ትችላላችሁ።+ +32 ነቢያት የመንፈስ ስጦታዎችን በአግባቡ ሊጠቀሙባቸው ይገባል። +33 አምላክ የሰላም እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና።+ በቅዱሳን ጉባኤዎች ሁሉ እንደሚደረገው +34 ሴቶች በጉባኤ ውስጥ እንዲናገሩ ስላልተፈቀደላቸው ዝም ይበሉ።+ ከዚህ ይልቅ ሕጉም እንደሚለው ይገዙ።+ +35 ያልገባቸው ነገር ካለ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው። +36 የአምላክ ቃል የመጣው ከእናንተ ነው? ወይስ የአምላክ ቃል የደረሰው ወደ እናንተ ብቻ ነው? +37 ነቢይ እንደሆነ ወይም የመንፈስ ስጦታ እንዳለው የሚያስብ ሰው ካለ እነዚህ የጻፍኩላችሁ ነገሮች የጌታ ትእዛዛት መሆናቸውን አምኖ ይቀበል። +38 ሆኖም ይህን ችላ የሚል ካለ እሱም ችላ ይባላል።* +39 ስለዚህ ወንድሞቼ፣ ትንቢት ለመናገር ጥረት አድርጉ፤+ ይሁንና በልሳኖች መናገርንም አትከልክሉ።+ +40 ሆኖም ሁሉም ነገር በአግባብና በሥርዓት ይሁን።+ +9 እኔ ነፃ ሰው አይደለሁም? ሐዋርያስ አይደለሁም? ደግሞስ ጌታችንን ኢየሱስን አላየሁትም?+ እናንተ በጌታ የሥራዬ ውጤት አይደላችሁም? +2 ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ለእናንተ ሐዋርያ እንደሆንኩ የተረጋገጠ ነው! እናንተ የጌታ ሐዋርያ መሆኔን የሚያረጋግጥ ማኅተም ናችሁና። +3 ለሚመረምሩኝ የማቀርበው የመከላከያ መልስ ይህ ነው፦ +4 እኛ የመብላትና የመጠጣት መብት* የለንም እንዴ? +5 እንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች+ እንዲሁም እንደ ኬፋ*+ አማኝ የሆነች ሚስት ይዘን የመዞር መብት የለንም?+ +6 ወይስ ሰብዓዊ ሥራ የመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ+ ብቻ ነን? +7 ለመሆኑ በራሱ ወጪ ወታደር ሆኖ የሚያገለግል ማን ነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው?+ ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የተወሰነ ድርሻ የማያገኝ ማን ነው? +8 ይህን የምለው ከሰብዓዊ አመለካከት አንጻር ነው? ሕጉስ ቢሆን እንዲህ አይልም? +9 በሙሴ ሕግ “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር” ተብሎ ተጽፏልና።+ አምላክ ይህን የተናገረው ስለ በሬዎች ተጨንቆ ነው? +10 እንዲህ ያለው ስለ እኛ በማሰብ አይደለም? እንዲህ ተብሎ የተጻፈው በእርግጥ ስለ እኛ ነው፤ ምክንያቱም አራሹም ሆነ የሚያበራየው ሰው ሥራቸውን የሚያከናውኑት ከምርቱ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተስፋ በማድረግ ነው። +11 እኛ በእናንተ መካከል መንፈሳዊ ነገሮች ከዘራን ከእናንተ ሥጋዊ ነገሮች ብናጭድ ትልቅ ነገር መሆኑ ነው?+ +12 ሌሎች የእናንተን ድጋፍ የማግኘት መብት ካላቸው እኛ ከእነሱ የበለጠ መብት የለንም? ይሁንና እኛ በዚህ መብት* አልተጠቀምንም፤+ ከዚህ ይልቅ ስለ ክርስቶስ የሚሰበከውን ምሥራች የሚያደናቅፍ ምንም ነገር ላለመፍጠር ሁሉን ችለን እንኖራለን።+ +13 ቅዱስ አገልግሎት የሚያከናውኑት ሰዎች ከቤ��� መቅደስ የሚያገኙትን ምግብ እንደሚመገቡ እንዲሁም ዘወትር በመሠዊያው የሚያገለግሉ ከመሠዊያው የራሳቸውን ድርሻ እንደሚያገኙ አታውቁም?+ +14 በተመሳሳይም ምሥራቹን የሚያውጁ ሰዎች በምሥራቹ አማካኝነት በሚያገኙት ነገር እንዲኖሩ ጌታ አዟል።+ +15 ይሁን እንጂ እኔ ከእነዚህ ዝግጅቶች በአንዱም አልተጠቀምኩም።+ እርግጥ ይህን የጻፍኩት እንዲህ ሊደረግልኝ ይገባል ለማለት አይደለም፤ ማንም ሰው የምኮራበትን ነገር ከሚያሳጣኝ ብሞት ይሻለኛልና!+ +16 አሁን ምሥራቹን እየሰበክሁ ብሆንም ለመኩራራት ምክንያት አይሆነኝም፤ እንዲህ የማድረግ ግዴታ ተጥሎብኛልና። እንዲያውም ምሥራቹን ባልሰብክ ወዮልኝ!+ +17 ይህን በፈቃደኝነት ካከናወንኩ ሽልማት አለኝ፤ ይሁንና ሳልወድ ባደርገውም እንኳ የመጋቢነት አደራ ተጥሎብኛል።+ +18 ታዲያ ሽልማቴ ምንድን ነው? ከምሥራቹ ጋር በተያያዘ ሥልጣኔን* አላግባብ እንዳልጠቀምበት ምሥራቹን በምሰብክበት ጊዜ ምሥራቹን ያለክፍያ ማቅረብ ነው። +19 እኔ ከሰው ሁሉ ነፃ ነኝ፤ ሆኖም በተቻለ መጠን ብዙዎችን እማርክ ዘንድ ራሴን ለሁሉ ባሪያ አደረግኩ። +20 አይሁዳውያንን እማርክ ዘንድ ለአይሁዳውያን እንደ አይሁዳዊ ሆንኩ፤+ እኔ ራሴ በሕግ ሥር ባልሆንም እንኳ በሕግ ሥር ያሉትን እማርክ ዘንድ በሕግ ሥር ላሉት በሕግ ሥር እንዳለሁ ሆንኩ።+ +21 በአምላክ ፊት ከሕግ ነፃ ያልሆንኩና በክርስቶስ ፊት በሕግ ሥር ያለሁ ብሆንም እንኳ ሕግ የሌላቸውን እማርክ ዘንድ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደሌለው ሰው ሆንኩ።+ +22 ደካሞችን እማርክ ዘንድ ለደካሞች ደካማ ሆንኩ።+ በተቻለ መጠን የተወሰኑ ሰዎችን አድን ዘንድ ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ሁሉንም ነገር ሆንኩ። +23 ምሥራቹን ለሌሎች አካፍል ዘንድ ለምሥራቹ ስል ሁሉን ነገር አደርጋለሁ።+ +24 በሩጫ ውድድር ሁሉም እንደሚሮጡ፣ ሽልማቱን የሚያገኘው ግን አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? እናንተም ሽልማቱን እንድታገኙ በዚሁ ሁኔታ ሩጡ።+ +25 በውድድር የሚሳተፍ ማንኛውም ሰው* በሁሉም ነገር ራሱን ይገዛል። እነሱ ይህን የሚያደርጉት የሚጠፋውን አክሊል+ ለማግኘት ሲሆን እኛ ግን የማይጠፋውን አክሊል ለማግኘት ነው።+ +26 ስለዚህ እኔ ያለግብ አልሮጥም፤+ ቡጢ የምሰነዝረውም አየር ለመምታት አይደለም፤ +27 ከዚህ ይልቅ ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ እኔ ራሴ በሆነ መንገድ ተቀባይነት እንዳላጣ* ሰውነቴን እየጎሰምኩ*+ እንደ ባሪያ እንዲገዛልኝ አደርገዋለሁ። +13 በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ በኃይል እንደሚጮኽ ደወል* ወይም ሲምባል* ሆኛለሁ። +2 የመተንበይ ስጦታ ቢኖረኝ፣ ቅዱስ ሚስጥርን ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ+ እንዲሁም ተራራን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማንቀሳቀስ የሚያስችል እምነት ቢኖረኝ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።*+ +3 ሌሎችን ለመመገብ ያለኝን ሁሉ ብሰጥ+ እንዲሁም እኩራራ ዘንድ ሰውነቴን አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ+ ምንም የማገኘው ጥቅም የለም። +4 ፍቅር+ ታጋሽና+ ደግ+ ነው። ፍቅር አይቀናም።+ ጉራ አይነዛም፣ አይታበይም፣+ +5 ጨዋነት የጎደለው ምግባር አያሳይም፣*+ የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም፣+ በቀላሉ አይበሳጭም።+ ፍቅር የበደል መዝገብ የለውም።+ +6 ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም፤+ ከዚህ ይልቅ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል። +7 ሁሉን ችሎ ያልፋል፣+ ሁሉን ያምናል፣+ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣+ ሁሉን ነገር በጽናት ይቋቋማል።+ +8 ፍቅር ለዘላለም ይኖራል።* ሆኖም የመተንበይ፣ በልሳን የመናገርም* ሆነ የእውቀት ስጦታ ይቀራል። +9 እውቀታችን ከፊል ነውና፤+ ትንቢት የምንናገረውም በከፊል ነው፤ +10 የተሟላው ሲመጣ ግን ከፊል የሆነው ይቀራል። +11 ልጅ በነበርኩበት ጊዜ እንደ ልጅ እናገ��፣ እንደ ልጅ አስብ እንዲሁም እንደ ልጅ አመዛዝን ነበር፤ አሁን ሙሉ ሰው ከሆንኩ በኋላ ግን የልጅነትን ጠባይ ትቻለሁ። +12 አሁን በብረት መስተዋት ብዥ ያለ* ምስል ይታየናል፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት የማየት ያህል በግልጽ ይታየናል። አሁን ስለ አምላክ የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን እሱ እኔን በትክክል የሚያውቀኝን ያህል የተሟላ* እውቀት ይኖረኛል። +13 ይሁን እንጂ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እነዚህ ሦስቱ ይቀጥላሉ፤ ከእነዚህ መካከል የሚበልጠው ግን ፍቅር ነው።+ +5 በመካከላችሁ የፆታ ብልግና*+ እንደተፈጸመ ይወራል፤ እንዲህ ዓይነቱ ብልግና* ደግሞ በአሕዛብ መካከል እንኳ ታይቶ አይታወቅም፤ ከአባቱ ሚስት ጋር የሚኖር ሰው አለ ተብሏል።+ +2 ታዲያ በዚህ ትኩራራላችሁ? ይልቁንም በዚህ ማዘንና+ ድርጊቱን የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ማስወጣት አይገባችሁም?+ +3 ምንም እንኳ እኔ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ደግሞም እንዲህ ያለ ድርጊት በፈጸመው ሰው ላይ አብሬያችሁ ያለሁ ያህል ሆኜ ፈርጄበታለሁ። +4 በጌታችን በኢየሱስ ስም አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በጌታችን በኢየሱስ ኃይል በመንፈስ ከእናንተ ጋር እንደምሆን በመገንዘብ +5 እንዲህ ያለውን ሰው ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል፤+ ይህም እሱ በጉባኤው ላይ ያሳደረው መጥፎ ተጽዕኖ እንዲወገድና* የጉባኤው መንፈስ በጌታ ቀን ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ነው።+ +6 መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው አታውቁም?+ +7 አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ ምክንያቱም የፋሲካችን በግ+ የሆነው ክርስቶስ ስለተሠዋ+ ከእርሾ ነፃ ናችሁ። +8 ስለዚህ በዓሉን+ በአሮጌ እርሾ እንዲሁም በክፋትና በኃጢአት እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት በቅንነትና በእውነት ቂጣ እናክብር። +9 ከሴሰኞች* ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ* በደብዳቤዬ ላይ ጽፌላችሁ ነበር፤ +10 እንዲህ ስል ግን በአጠቃላይ ከዚህ ዓለም+ ሴሰኞች፣* ስግብግብ ሰዎች፣ ቀማኞች ወይም ጣዖት አምላኪዎች ጋር አትገናኙ ማለቴ አይደለም። እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ ጨርሶ ከዓለም መውጣት ያስፈልጋችሁ ነበር።+ +11 አሁን ግን የጻፍኩላችሁ፣ ወንድም ተብሎ እየተጠራ ሴሰኛ* ወይም ስግብግብ+ ወይም ጣዖት አምላኪ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም+ ወይም ቀማኛ+ ከሆነ ማንኛውም ሰው ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ*+ አልፎ ተርፎም እንዲህ ካለው ሰው ጋር ምግብ እንኳ እንዳትበሉ ነው። +12 በውጭ ባሉ* ሰዎች ላይ የምፈርደው እኔ ምን አግብቶኝ ነው? በውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱም? +13 በውጭ ባሉት ላይ አምላክ ይፈርዳል።+ “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱት።”+ +15 አሁን ደግሞ ወንድሞች፣ የነገርኳችሁን ምሥራች ላስታውሳችሁ እወዳለሁ፤+ ይህ ምሥራች እናንተም የተቀበላችሁትና የቆማችሁለት ነው። +2 በተጨማሪም እኔ የነገርኳችሁን ምሥራች አጥብቃችሁ የምትይዙ ከሆነ በምሥራቹ ትድናላችሁ፤ አለዚያ አማኝ የሆናችሁት በከንቱ ነው ማለት ነው። +3 እኔ የተቀበልኩትን ከሁሉ በላይ የሆነውን ነገር ለእናንተ አስተላልፌአለሁና፤ ይኸውም ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤+ +4 ደግሞም ተቀበረ፤+ ቅዱሳን መጻሕፍት+ እንደሚሉትም በሦስተኛው ቀን+ ተነሳ፤+ +5 ለኬፋ*+ ከዚያም ለአሥራ ሁለቱ ታየ።+ +6 በኋላ ደግሞ በአንድ ጊዜ ከ500 ለሚበልጡ ወንድሞች የታየ+ ሲሆን አንዳንዶቹ በሞት ቢያንቀላፉም አብዛኞቹ ግን አሁንም ከእኛ ጋር አሉ። +7 ከዚያም ለያዕቆብ ታየ፤+ ቀጥሎም ለሐዋርያቱ በሙሉ ታየ።+ +8 በመጨረሻ ደግሞ እንደ ጭንጋፍ ለምቆጠር ለእኔ ተገለጠልኝ።+ +9 እኔ የአም��ክን ጉባኤ አሳድድ ስለነበር ከሐዋርያት ሁሉ የማንስና ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነኝ።+ +10 ሆኖም አሁን የሆንኩትን ለመሆን የበቃሁት በአምላክ ጸጋ ነው። አምላክ ለእኔ ያሳየው ጸጋም ከንቱ ሆኖ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሁሉም የበለጠ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ይሁንና ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የአምላክ ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። +11 እንግዲህ እኔም ሆንኩ እነሱ የምንሰብከው በዚህ መንገድ ነው፤ እናንተም ያመናችሁት በዚህ መንገድ ነው። +12 ታዲያ ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ እየተሰበከ ከሆነ+ ከእናንተ መካከል አንዳንዶቹ እንዴት የሙታን ትንሣኤ የለም ይላሉ? +13 የሙታን ትንሣኤ ከሌለማ ክርስቶስም አልተነሳም ማለት ነዋ! +14 ክርስቶስ ካልተነሳ ደግሞ ስብከታችን ከንቱ ነው፤ እምነታችሁም ከንቱ ነው። +15 ከዚህም በተጨማሪ ሙታን በእርግጥ የማይነሱ ከሆነ አምላክ ክርስቶስን ከሞት ስላላስነሳው፣ ክርስቶስን አስነስቶታል+ ብለን ስንመሠክር ሐሰተኞች የአምላክ ምሥክሮች ሆነን ተገኝተናል ማለት ነው።+ +16 ምክንያቱም ሙታን የማይነሱ ከሆነ ክርስቶስም ከሞት አልተነሳም ማለት ይሆናል። +17 ክርስቶስ ካልተነሳ ደግሞ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም ከነኃጢአታችሁ ትኖራላችሁ።+ +18 የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሆነው በሞት ያንቀላፉትም ለዘላለሙ ጠፍተዋል ማለት ነው።+ +19 በክርስቶስ ተስፋ ያደረግነው ለዚህ ሕይወት ብቻ ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን። +20 ይሁንና ክርስቶስ በሞት ካንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሞት ተነስቷል።+ +21 ሞት የመጣው በአንድ ሰው በኩል+ ስለሆነ የሙታን ትንሣኤም በአንድ ሰው በኩል ነው።+ +22 ሁሉም በአዳም እንደሚሞቱ+ ሁሉም በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉና።+ +23 ሆኖም እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፦ ክርስቶስ በኩራት ነው፤+ በመቀጠል ደግሞ ክርስቶስ በሚገኝበት ጊዜ የእሱ የሆኑት ሕያዋን ይሆናሉ።+ +24 ከዚያም ማንኛውንም መስተዳድር እንዲሁም ሥልጣንን ሁሉና ኃይልን አጥፍቶ መንግሥቱን ለአምላኩና ለአባቱ በሚያስረክብበት ጊዜ ፍጻሜ ይሆናል።+ +25 አምላክ ጠላቶችን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግለት ድረስ ንጉሥ ሆኖ ሊገዛ ይገባዋልና።+ +26 የመጨረሻው ጠላት፣ ሞት ይደመሰሳል።+ +27 አምላክ “ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዝቶለታልና።”+ ሆኖም ‘ሁሉም ነገር ተገዝቷል’+ ሲል ሁሉንም ነገር ያስገዛለትን እንደማይጨምር ግልጽ ነው።+ +28 ይሁንና ሁሉም ነገር ከተገዛለት በኋላ ወልድ ራሱ ሁሉን ነገር ላስገዛለት ራሱን ያስገዛል፤+ ይህም አምላክ ለሁሉም ሁሉንም ነገር እንዲሆን ነው።+ +29 አለዚያማ ለመሞት ብለው በመጠመቅ ምን የሚያተርፉት ነገር ይኖራል?+ ሙታን ፈጽሞ የማይነሱ ከሆነ እነሱም ለመሞት ብለው የሚጠመቁበት ምን ምክንያት አለ? +30 እኛስ ሁልጊዜ ለአደጋ ተጋልጠን የምንኖረው ለምንድን ነው?+ +31 እኔ በየቀኑ ሞትን እጋፈጣለሁ። ወንድሞች፣ ይህ እውነት መሆኑን የጌታችን የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በሆናችሁት በእናንተ ላይ ባለኝ ትምክህት አረጋግጥላችኋለሁ። +32 እንደ ሌሎች ሰዎች* በኤፌሶን ከአውሬዎች ጋር ከታገልኩ፣+ እንዲህ ማድረጌ ለእኔ ምን ይጠቅመኛል? ሙታን የማይነሱ ከሆነማ “ነገ ስለምንሞት እንብላ፣ እንጠጣ።”+ +33 አትታለሉ። መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን አመል* ያበላሻል።+ +34 ጽድቅ የሆነውን በማድረግ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአት መሥራትን ልማድ አታድርጉ፤ አንዳንዶች ስለ አምላክ አያውቁምና። ይህን የምላችሁ ላሳፍራችሁ ብዬ ነው። +35 ይሁንና አንድ ሰው “ሙታን የሚነሱት እንዴት ነው? ከሞት የሚነሱትስ ምን ዓይነት አካል ይዘው ነው?” ይል ይሆናል።+ +36 አንተ ማስተዋል የጎደለህ! የምትዘራው መጀመሪያ ካልሞተ ሕያው ሊሆን አይችልም። +37 ደግሞም ስንዴም ሆነ ሌላ ዓይነት እህል ስትዘራ የምትዘራው ዘሩን እንጂ በኋላ የሚያድገውን አካል አይደለም፤ +38 ሆኖም አምላክ የፈለገውን አካል ይሰጠዋል፤ ለእያንዳንዱም ዘር የራሱን አካል ይሰጠዋል። +39 ሥጋ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም፤ በመሆኑም የሰው ሥጋ አለ፣ የከብት ሥጋ አለ፣ የወፎች ሥጋ አለ እንዲሁም የዓሣ ሥጋ አለ። +40 በተጨማሪም ሰማያዊ አካላት አሉ፤+ ምድራዊ አካላትም አሉ፤+ ሆኖም የሰማይ አካላት የራሳቸው ክብር አላቸው፤ የምድር አካላት ደግሞ ሌላ ዓይነት ክብር አላቸው። +41 ፀሐይ የራሷ ክብር አላት፤ ጨረቃ ደግሞ ሌላ ዓይነት ክብር አላት፤+ ከዋክብትም ሌላ ዓይነት ክብር አላቸው፤ እንዲያውም የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ክብር ይለያል። +42 ስለዚህ የሙታን ትንሣኤም እንደዚሁ ነው። የሚዘራው የሚበሰብስ ነው፤ የሚነሳው የማይበሰብስ ነው።+ +43 የሚዘራው በውርደት ነው፤ የሚነሳው በክብር ነው።+ የሚዘራው በድካም ነው፤ የሚነሳው በኃይል ነው።+ +44 የሚዘራው ሥጋዊ አካል ነው፤ የሚነሳው መንፈሳዊ አካል ነው። ሥጋዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካልም አለ። +45 ስለዚህ “የመጀመሪያው ሰው አዳም ሕያው ሰው* ሆነ” ተብሎ ተጽፏል።+ የኋለኛው አዳም ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።+ +46 ይሁንና የመጀመሪያው መንፈሳዊው አይደለም። የመጀመሪያው ሥጋዊው ነው፤ የኋለኛው ደግሞ መንፈሳዊው ነው። +47 የመጀመሪያው ሰው ከምድር የተገኘና ከአፈር የተሠራ ነው፤+ ሁለተኛው ሰው ደግሞ ከሰማይ ነው።+ +48 ከአፈር የተሠሩት ከአፈር እንደተሠራው ናቸው፤ ሰማያዊ የሆኑትም ከሰማይ እንደመጣው ናቸው።+ +49 ከአፈር የተሠራውን ሰው መልክ እንደመሰልን ሁሉ+ የሰማያዊውንም መልክ እንመስላለን።+ +50 ይሁን እንጂ ወንድሞች ይህን እነግራችኋለሁ፦ ሥጋና ደም የአምላክን መንግሥት አይወርስም፤ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም። +51 እነሆ፣ አንድ ቅዱስ ሚስጥር እነግራችኋለሁ፦ በሞት የምናንቀላፋው ሁላችንም አይደለንም፤ ነገር ግን ሁላችንም እንለወጣለን፤+ +52 የመጨረሻው መለከት በሚነፋበት ወቅት ድንገት፣ በቅጽበተ ዓይን* እንለወጣለን። መለከት ይነፋል፤+ ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሳሉ፤ እኛም እንለወጣለን። +53 ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይገባዋልና፤+ ይህ ሟች የሆነው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋል።+ +54 ሆኖም ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስና ይህ ሟች የሆነው የማይሞተውን ሲለብስ “ሞት ለዘላለም ተዋጠ” ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።+ +55 “ሞት ሆይ፣ ድል አድራጊነትህ የት አለ? ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ?”+ +56 ለሞት የሚዳርገው መንደፊያ ኃጢአት ነው፤+ ለኃጢአት ኃይል የሚሰጠው ደግሞ ሕጉ ነው።+ +57 ሆኖም አምላክ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ድል ስለሚያጎናጽፈን የተመሰገነ ይሁን!+ +58 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ጸንታችሁ ቁሙ፤+ አትነቃነቁ፤ እንዲሁም ከጌታ ጋር በተያያዘ በትጋት የምታከናውኑት ሥራ ከንቱ አለመሆኑን አውቃችሁ+ ምንጊዜም የጌታ ሥራ የበዛላችሁ ሁኑ።+ +3 ብቁ መሆናችንን ለማሳየት ራሳችንን ለእናንተ እንደ አዲስ ማስተዋወቅ ያስፈልገናል? ወይስ እንደ አንዳንድ ሰዎች ለእናንተ ወይም ከእናንተ የምሥክር ወረቀት ያስፈልገን ይሆን? +2 ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነብቡት በልባችን ላይ የተጻፈ ማስረጃችን እናንተ ራሳችሁ ናችሁ።+ +3 ምክንያቱም እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው አምላክ መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላቶች+ ላይ ሳይሆን በሥጋ ጽላቶች ይኸውም በልብ ላይ፣+ አገልጋዮች+ በሆንነው በእኛ አማካኝነት የተጻፋችሁ የክርስቶስ ደብዳቤ እንደሆናችሁ ���ግልጽ ታይቷል። +4 በክርስቶስ በኩል በአምላክ ፊት እንዲህ ያለ እምነት አለን። +5 ብቃታችንን በገዛ ራሳችን ያገኘነው እንደሆነ አድርገን አናስብም፤ ከዚህ ይልቅ አስፈላጊውን ብቃት ያገኘነው ከአምላክ ነው፤+ +6 እሱም የአዲስ ቃል ኪዳን+ አገልጋዮች ይኸውም የተጻፈ ሕግ+ ሳይሆን የመንፈስ አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አድርጎናል፤ የተጻፈው ሕግ ለሞት ፍርድ ይዳርጋልና፤+ መንፈስ ግን ሕያው ያደርጋል።+ +7 የእስራኤል ልጆች፣ ከፊቱ ክብር የተነሳ የሙሴን ፊት ትኩር ብለው ማየት እስኪሳናቸው ድረስ+ የሞት ፍርድ የሚያስከትለውና በድንጋይ ላይ በፊደል የተቀረጸው ሕግ+ በክብር ይኸውም በሚጠፋ ክብር ከመጣ +8 የመንፈስ አገልግሎት+ እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም?+ +9 ኩነኔ የሚያስከትለው የሕግ አገልግሎት+ ክብራማ+ ከሆነ ጽድቅ የሚያስገኘው አገልግሎትማ እንዴት እጅግ የላቀ ክብር አይኖረውም!+ +10 እንዲያውም በአንድ ወቅት ክብራማ የነበረው፣ ከእሱ የላቀ ክብር ያለው በመምጣቱ ምክንያት ክብሩ ተገፏል።+ +11 የሚጠፋው በክብር ከመጣ+ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም!+ +12 እንዲህ ዓይነት ተስፋ ስላለን+ ታላቅ የመናገር ነፃነት አለን፤ +13 ደግሞም የእስራኤል ልጆች የዚያን የሚሻረውን ነገር መጨረሻ እንዳይመለከቱ ሙሴ ፊቱን በመሸፈኛ ይሸፍን+ በነበረበት ጊዜ ያደርግ እንደነበረው አናደርግም። +14 ሆኖም እነሱ አእምሯቸው ደንዝዟል።+ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አሮጌው ቃል ኪዳን ሲነበብ ያው መሸፈኛ እንደጋረዳቸው ነውና፤+ ምክንያቱም መሸፈኛው የሚወገደው በክርስቶስ አማካኝነት ብቻ ነው።+ +15 እንዲያውም እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቁጥር+ ልባቸው በመሸፈኛ እንደተሸፈነ ነው።+ +16 ሆኖም አንድ ሰው ወደ ይሖዋ* ሲመለስ መሸፈኛው ይወገዳል።+ +17 ይሖዋ* መንፈስ ነው፤+ የይሖዋ* መንፈስ ባለበት ደግሞ ነፃነት አለ።+ +18 እኛ ሁላችንም ባልተሸፈነ ፊት የይሖዋን* ክብር እንደ መስተዋት ስናንጸባርቅ ያንኑ መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር* እንለወጣለን፤ በዚህ መንገድ መንፈስ የሆነው ይሖዋ* ራሱ* እንደሚያደርገን እንሆናለን።+ +7 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እነዚህ ተስፋዎች ስላሉን+ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፤+ እንዲሁም አምላክን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ። +2 በልባችሁ ውስጥ ቦታ ስጡን።+ እኛ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም አላበላሸንም፤ ማንንም መጠቀሚያ አላደረግንም።+ +3 ይህን የምለው ልኮንናችሁ አይደለም። ከዚህ በፊት እንደነገርኳችሁ በልባችን ውስጥ ስለሆናችሁ ብንሞትም ሆነ ብንኖር አብረን ነን። +4 እናንተን በግልጽ ለማናገር ነፃነት ይሰማኛል። በእናንተ በጣም እኮራለሁ። እንዲሁም እጅግ ተጽናንቻለሁ፤ በመከራችንም ሁሉ ደስታዬ ወሰን የለውም።+ +5 መቄዶንያ+ በደረስን ጊዜ በሁሉም አቅጣጫ መከራ ደረሰብን እንጂ ሰውነታችን* ምንም እረፍት አላገኘም፤ በውጭ ጠብ፣ በውስጥ ፍርሃት ነበረብን። +6 ይሁንና ያዘኑትን የሚያጽናናው አምላክ፣+ ቲቶ በመካከላችን በመገኘቱ እንድንጽናና አደረገን፤ +7 የተጽናናነውም እሱ በመካከላችን በመገኘቱ ብቻ ሳይሆን እሱ በእናንተ ምክንያት ባገኘው መጽናኛ ጭምር ነው፤ ተመልሶ በመጣ ጊዜ እኔን ስለመናፈቃችሁ፣ ስለተሰማችሁ ጥልቅ ሐዘንና ለእኔ ስላላችሁ ልባዊ አሳቢነት* ነግሮናል፤ ስለዚህ ከበፊቱ ይበልጥ ደስ ብሎኛል። +8 በደብዳቤዬ አሳዝኛችሁ ቢሆን እንኳ+ በዚህ አልጸጸትም። መጀመሪያ ላይ ብጸጸት እንኳ፣ ደብዳቤው እንድታዝኑ ያደረጋችሁ ለአጭር ጊዜ ብቻ እንደሆነ ስለተረዳሁ +9 አሁን የምደሰተው እንዲያው በማዘናችሁ ሳይሆን ሐዘናችሁ ለንስሐ ���ላበቃችሁ ነው። ያዘናችሁት ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ነውና፤ በመሆኑም በእኛ የተነሳ ምንም ጉዳት አልደረሰባችሁም። +10 ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ማዘን ለመዳን የሚያበቃ ንስሐ ያስገኛልና፤ ይህ ደግሞ ለጸጸት አይዳርግም፤+ የዚህ ዓለም ሐዘን ግን ሞት ያስከትላል። +11 አምላካዊ በሆነ መንገድ ማዘናችሁ እንዴት ለተግባር እንዳነሳሳችሁ ተመልከቱ! አዎ፣ አቋማችሁን ለማስተካከል እርምጃ እንድትወስዱ አነሳስቷችኋል፤ ደግሞም እንዴት ያለ ቁጣ፣ እንዴት ያለ ፍርሃት፣ እንዴት ያለ ጉጉት፣ እንዴት ያለ ቅንዓት እንዳስገኘ ተመልከቱ! በእርግጥም ስህተታችሁን ለማረም እርምጃ እንድት +12 ምንም እንኳ ለእናንተ ብጽፍም የጻፍኩት በደል ለሠራው+ ወይም በደል ለተፈጸመበት ሰው ብዬ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ለመልእክታችን በጎ ምላሽ ለመስጠት የምታደርጉት ጥረት በእናንተ ዘንድና በአምላክ ፊት ግልጽ ሆኖ እንዲታይ ነው። +13 እኛም የተጽናናነው ለዚህ ነው። ይሁን እንጂ ከመጽናናታችንም በተጨማሪ ሁላችሁም የቲቶ መንፈስ እንዲታደስ ስላደረጋችሁ በእሱ ደስታ እኛም ይበልጥ ተደስተናል። +14 ምክንያቱም ስለ እናንተ ለእሱ በኩራት ተናግሬ ቢሆን እንኳ አላሳፈራችሁኝም፤ ይሁንና ለእናንተ የተናገርነው ነገር በሙሉ እውነት እንደሆነ ሁሉ ለቲቶ በኩራት የተናገርነውም ነገር እውነት እንደሆነ ተረጋግጧል። +15 በተጨማሪም ሁላችሁም ያሳያችሁትን ታዛዥነት እንዲሁም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደተቀበላችሁት ሲያስታውስ ለእናንተ ያለው ጥልቅ ፍቅር ጨምሯል።+ +16 እኔም በሁሉም መንገድ በእናንተ መተማመን* በመቻሌ እጅግ ደስ ብሎኛል። +12 ልኩራራ ይገባኛል። ምንም ጥቅም ባይኖረውም እንኳ ከጌታ የተቀበልኳቸውን ተአምራዊ ራእዮችና+ ጌታ የገለጠልኝን መልእክቶች+ እናገራለሁ። +2 የክርስቶስ ደቀ መዝሙር የሆነ አንድ ሰው አውቃለሁ፤ ይህ ሰው ከ14 ዓመት በፊት ወደ ሦስተኛው ሰማይ ተነጠቀ፤ የተነጠቀው በሥጋ ይሁን ከሥጋ ውጭ አላውቅም፤ አምላክ ግን ያውቃል። +3 አዎ፣ እንዲህ ያለ ሰው አውቃለሁ፤ በሥጋ ይሁን ከሥጋ ውጭ አላውቅም፤ አምላክ ግን ያውቃል፤ +4 ይህ ሰው ወደ ገነት ተነጥቆ በአንደበት ሊገለጹ የማይችሉና ሰው እንዲናገራቸው ያልተፈቀዱ ቃላት ሰማ። +5 እንዲህ ባለው ሰው እኩራራለሁ፤ ሆኖም በድክመቶቼ ካልሆነ በስተቀር በራሴ አልኩራራም። +6 ልኮራ ብፈልግ እንኳ የምናገረው እውነት ስለሆነ ምክንያታዊነት እንደሚጎድለኝ ሆኜ ልቆጠር አይገባም። ይሁንና ማንም በእኔ ላይ ከሚያየውና ከእኔ ከሚሰማው በላይ እንደሆንኩ አድርጎ እንዳይገምተኝ ይህን ከማድረግ እቆጠባለሁ፤ +7 እንዲህ ያሉ አስደናቂ ነገሮች ስለተገለጡልኝ ብቻ ማንም ሰው ለእኔ ከፍ ያለ ግምት ሊኖረው አይገባም። እንዳልታበይ ሥጋዬን የሚወጋ እሾህ ተሰጠኝ፤+ ይህም እንዳልታበይ ዘወትር የሚያሠቃየኝ* የሰይጣን መልአክ* ነው። +8 ይህ ነገር ከእኔ እንዲርቅ ጌታን ሦስት ጊዜ ለመንኩት። +9 እሱ ግን “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ምክንያቱም ኃይሌ ፍጹም የሚሆነው በምትደክምበት ጊዜ ነው” አለኝ።+ እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል በእኔ ላይ እንደ ድንኳን እንዲኖር እጅግ ደስ እያለኝ በድክመቴ እኩራራለሁ። +10 ስለሆነም ስለ ክርስቶስ ስል በድክመት፣ በስድብ፣ በእጦት፣ በስደትና በችግር ደስ እሰኛለሁ። ስደክም ያን ጊዜ ብርቱ ነኝና።+ +11 ምክንያታዊነት የሚጎድለኝ ሆኛለሁ። እንዲህ እንድሆን ያስገደዳችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ እናንተ ስለ እኔ ብቃት መመሥከር መቻል ነበረባችሁና። ምንም እንኳ እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆንም ከእናንተ የተራቀቁ ሐዋርያት በአንዲት ነገር እንኳ አላንስም።+ +12 ደግሞም የሐዋ��ያነቴን ማስረጃዎች በታላቅ ጽናት+ እንዲሁም ምልክቶችን፣ ድንቅ ነገሮችንና ተአምራትን በመፈጸም አሳይቻችኋለሁ።+ +13 እናንተ ከሌሎች ጉባኤዎች ያነሳችሁት በምንድን ነው? ምናልባት እኔ በእናንተ ላይ ሸክም ሳልሆን በመቅረቴ ሊሆን ይችላል፤+ እንዲህ ከሆነ ይህን ጥፋቴን በደግነት ይቅር በሉኝ። +14 እነሆ ወደ እናንተ ለመምጣት ስዘጋጅ ይህ ሦስተኛ ጊዜዬ ነው፤ በእናንተ ላይ ሸክም አልሆንም። እኔ የምፈልገው እናንተን እንጂ ንብረታችሁን አይደለምና፤+ ደግሞም ለልጆቻቸው+ ሀብት ማከማቸት የሚጠበቅባቸው ወላጆች ናቸው እንጂ ልጆች ለወላጆቻቸው አያከማቹም። +15 በእኔ በኩል ስለ እናንተ* ያለኝን ሁሉ፣ ራሴንም ጭምር ብሰጥ እጅግ ደስ ይለኛል።+ እኔ ይህን ያህል አጥብቄ ከወደድኳችሁ እናንተ ለእኔ ያላችሁ ፍቅር ከዚህ ያነሰ ሊሆን ይገባል? +16 የሆነ ሆኖ ሸክም አልሆንኩባችሁም።+ ነገር ግን እናንተ “መሠሪ” እንደሆንኩና “አታልዬ” እንዳጠመድኳችሁ ትናገራላችሁ። +17 ለመሆኑ ወደ እናንተ ከላክኋቸው ሰዎች መካከል በአንዱ እንኳ ተጠቅሜ ከእናንተ አላግባብ ጥቅም ለማግኘት ሞክሬአለሁ? +18 ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ገፋፋሁት፤ ከእሱም ጋር ወንድምን ላክሁት። ለመሆኑ ቲቶ ከእናንተ አላግባብ ጥቅም ለማግኘት ሞክሮ ነበር?+ ከእሱ ጋር በአንድ መንፈስ አልተመላለስንም? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረም? +19 እስካሁን ድረስ የምታስቡት እኛ ለእናንተ የመከላከያ መልስ እየሰጠን እንዳለን አድርጋችሁ ነው? እኛ የክርስቶስ ተከታዮች ሆነን የምንናገረው በአምላክ ፊት ነው። ይሁንና የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ሁሉንም ነገር የምናደርገው እናንተን ለማነጽ ነው። +20 እኔ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ምናልባት እኔ እንደምፈልገው ሳትሆኑ እንዳላገኛችሁ፣ እናንተም እኔን እንደምትፈልጉት ሆኜ ሳታገኙኝ እንዳትቀሩ እሰጋለሁ፤ እንዲያውም ጠብ፣ ቅናት፣ ኃይለኛ ቁጣ፣ ንትርክ፣ ስም ማጥፋት፣ ሐሜትና ብጥብጥ እንዲሁም በኩራት የተወጠሩ ሰዎች እንዳይኖሩ እሰጋለሁ። +21 እንደገና በምመጣበት ጊዜ ምናልባት አምላኬ በፊታችሁ ያሳፍረኝ ይሆናል፤ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ኃጢአት ፈጽመው ከሠሩት ርኩሰት፣ የፆታ ብልግናና* ዓይን ያወጣ ምግባር* ንስሐ ባልገቡት በርካታ ሰዎች አዝን ይሆናል ብዬ እፈራለሁ። +1 በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፣+ በቆሮንቶስ ለሚገኘው የአምላክ ጉባኤ እንዲሁም በመላው አካይያ+ ለሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ፦ +2 አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። +3 የምሕረት* አባትና+ የመጽናናት+ ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት+ ይወደስ፤ +4 እኛ ከአምላክ በምናገኘው መጽናኛ+ በማንኛውም ዓይነት መከራ* ውስጥ ያሉትን ሰዎች ማጽናናት እንድንችል+ እሱ በሚደርስብን መከራ ሁሉ ያጽናናናል።*+ +5 ስለ ክርስቶስ ብለን የምንቀበለው መከራ ብዙ እንደሆነ ሁሉ+ በክርስቶስ በኩል የምናገኘው መጽናኛም የዚያኑ ያህል ብዙ ነው። +6 ስለዚህ እኛ መከራ ቢደርስብን ለእናንተ መጽናኛና መዳን ያስገኛል፤ መጽናኛ ብናገኝ ደግሞ በእኛ ላይ የደረሰው መከራ በእናንተም ላይ ሲደርስ እንድትጸኑ የሚረዳ መጽናኛ ይሆንላችኋል። +7 እናንተን በተመለከተ ያለን ተስፋ የማይናወጥ ነው፤ ይህም የሆነው መከራውን ከእኛ ጋር እንደምትካፈሉ ሁሉ መጽናኛውንም እንደምትካፈሉ ስለምናውቅ ነው።+ +8 ወንድሞች፣ በእስያ አውራጃ ስለደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንፈልጋለን።+ ከአቅማችን በላይ የሆነ ከባድ ጫና ደርሶብን ስለነበር በሕይወት የመትረፍ ተስፋችን እንኳ ተሟጦ ነበር።+ +9 እንዲያ���ም የሞት ፍርድ ተፈርዶብናል የሚል ስሜት አድሮብን ነበር። ይህ የሆነው ግን በራሳችን ሳይሆን ሙታንን በሚያስነሳው አምላክ እንድንታመን ነው።+ +10 እሱ እንዲህ ካለ ለሞት ሊዳርግ የሚችል አደገኛ ሁኔታ አድኖናል፤ ደግሞም ያድነናል፤ ወደፊትም እንደሚያድነን በእሱ ተስፋ እናደርጋለን።+ +11 እናንተም ስለ እኛ ምልጃ በማቅረብ ልትረዱን ትችላላችሁ።+ ይህን ማድረጋችሁ ብዙዎች በሚያቀርቡት ጸሎት የተነሳ ለሚደረግልን ቸርነት ብዙዎች ስለ እኛ የምስጋና ጸሎት እንዲያቀርቡ ያነሳሳቸዋል።+ +12 የምንኮራበት ነገር ይህ ነው፦ በዓለም ውስጥ በተለይም በእናንተ መካከል በቅድስናና አምላካዊ ቅንነት በማሳየት እንደኖርን ሕሊናችን ይመሠክራል፤ ይህን ያደረግነው በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን+ በአምላክ ጸጋ ነው። +13 ልታነብቡትና* ልትረዱት ከምትችሉት በቀር ስለ ሌላ ነገር አንጽፍላችሁም፤ ይህን ነገር በተሟላ ሁኔታ* መረዳታችሁን እንደምትቀጥሉ ተስፋ አደርጋለሁ፤ +14 አንዳንዶቻችሁ በእኛ መኩራት እንደምትችሉ እንደተገነዘባችሁ ሁሉ እኛም በጌታችን በኢየሱስ ቀን በእናንተ እንኮራለን። +15 በመሆኑም በዚህ በመተማመን ዳግመኛ እንድትደሰቱ* በመጀመሪያ ወደ እናንተ ለመምጣት አቅጄ ነበር፤ +16 ወደ መቄዶንያ ስሄድ እግረ መንገዴን እናንተን ለማየት፣ ከዚያም ከመቄዶንያ ተመልሼ ከእናንተ ጋር ለመገናኘትና ወደ ይሁዳ እንድትሸኙኝ ለማድረግ አስቤ ነበር።+ +17 እንዲህ ዓይነት ዕቅድ አውጥቼ የነበረው እንዲሁ ሳላስብበት ይመስላችኋል? ወይስ ማንኛውንም ነገር ሳቅድ በሥጋዊ አስተሳሰብ ተነድቼ በማቀድ አንዴ “አዎ፣ አዎ” ከዚያ ደግሞ “አይሆንም፣ አይሆንም” የምል ይመስላችኋል? +18 አምላክ እምነት የሚጣልበት እንደመሆኑ መጠን እኛ ለእናንተ የምንናገረውም ነገር እውነት ነው። መጀመሪያ ላይ “አዎ” ብለን ከዚያ ደግሞ “አይሆንም” አንልም። +19 ምክንያቱም እኛ ማለትም እኔ፣ ስልዋኖስና* ጢሞቴዎስ+ የሰበክንላችሁ የአምላክ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ “አዎ” ሆኖ እያለ “አይደለም” ሊሆን አይችልም፤ ከዚህ ይልቅ ከእሱ ጋር በተያያዘ “አዎ” የተባለው “አዎ” ሆኗል። +20 አምላክ የሰጣቸው ተስፋዎች የቱንም ያህል ብዙ ቢሆኑም በእሱ አማካኝነት “አዎ” ሆነዋል።+ ስለዚህ እኛ ለአምላክ ክብር እንድንሰጥ በእሱ አማካኝነት ለአምላክ “አሜን” እንላለን።+ +21 ይሁንና እኛም ሆን እናንተ የክርስቶስ ለመሆናችን ዋስትና የሰጠንና የቀባን አምላክ ነው።+ +22 በተጨማሪም በማኅተሙ ያተመን+ ሲሆን ወደፊት ለሚመጣውም ነገር ማረጋገጫ* ሰጥቶናል፤ ይህም በልባችን ውስጥ ያለው መንፈስ ነው።+ +23 ወደ ቆሮንቶስ እስካሁን ያልመጣሁት ለባሰ ሐዘን እንዳልዳርጋችሁ ብዬ ነው፤ ይህ እውነት ካልሆነ አምላክ በእኔ* ላይ ይመሥክርብኝ። +24 ጸንታችሁ የቆማችሁት በራሳችሁ እምነት ስለሆነ እኛ ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር የምንሠራ ነን እንጂ በእምነታችሁ ላይ የምናዝ አይደለንም።+ +8 ወንድሞች፣ በመቄዶንያ+ ላሉት ጉባኤዎች ስለተሰጠው የአምላክ ጸጋ እንድታውቁ እንፈልጋለን። +2 ከባድ ፈተና ደርሶባቸው በመከራ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ታላቅ ደስታ የነበራቸው ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ* ልግስና አሳይተዋል፤ ይህን ያደረጉት በጣም ድሆች ሆነው ሳለ ነው። +3 እንደ አቅማቸው+ እንዲያውም ከአቅማቸው በላይ እንደሰጡ እመሠክርላቸዋለሁና፤+ +4 ምክንያቱም እነዚህ ወንድሞች ለቅዱሳን በልግስና በመስጠት፣ በእርዳታ አገልግሎቱ ለመካፈል መብት እንዲሰጣቸው በራሳቸው ፍላጎት ተነሳስተው ይለምኑን እንዲያውም ይማጸኑን ነበር።+ +5 ደግሞም ከጠበቅነው በላይ አድርገዋል፤ ምክንያቱም ራሳቸውን በመጀመሪያ ለጌታ ከዚያም በአምላክ ፈቃድ ለእኛ ሰጥተዋል። +6 ስለዚህ ቲቶ+ ቀደም ሲል በእናንተ መካከል የልግስና ስጦታችሁን የማሰባሰቡን ሥራ እንዳስጀመረ ሁሉ ይህንኑ ሥራ ወደ ፍጻሜ እንዲያደርስ አበረታታነው። +7 ስለዚህ በሁሉም ነገር ይኸውም በእምነት፣ በቃል፣ በእውቀት፣ በትጋት ሁሉና እኛ ለእናንተ ባለን ፍቅር ባለጸጋ እንደሆናችሁ ሁሉ በልግስና በመስጠት ረገድም ባለጸጋ ሁኑ።+ +8 ይህን የምላችሁ እናንተን ለማዘዝ ሳይሆን ሌሎች የሚያሳዩትን ትጋት እንድታውቁ ለማድረግና የፍቅራችሁን እውነተኝነት ለመፈተን ነው። +9 የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በእሱ ድህነት እናንተ ባለጸጋ ትሆኑ ዘንድ እሱ ባለጸጋ ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድሃ ሆኗል።+ +10 በዚህ ረገድ የምሰጠው ሐሳብ አለ፦+ ይህን ሥራ መሥራታችሁ ይጠቅማችኋል፤ ምክንያቱም ከአንድ ዓመት በፊት ሥራውን መጀመር ብቻ ሳይሆን ዳር ለማድረስም ፍላጎት እንዳላችሁ አሳይታችኋል። +11 ስለዚህ የጀመራችሁትን ሥራ ዳር አድርሱት፤ ሥራውን ለመጀመር ጓጉታችሁ እንደነበር ሁሉ፣ አሁንም እንደ አቅማችሁ በመስጠት ከፍጻሜ እንዲደርስ አድርጉ። +12 ለመስጠት ፈቃደኝነቱ ካለ ስጦታው ይበልጥ ተቀባይነት የሚኖረው አንድ ሰው ባለው መጠን ሲሰጥ+ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለምና። +13 ይህን የምለውም ሌሎች እንዲቀላቸው አድርጌ እናንተ እንዲከብዳችሁ ለማድረግ አይደለም፤ +14 ከዚህ ይልቅ በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነሱን ጉድለት እንዲሸፍን ነው፤ የእነሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጉድለት ይሸፍናል፤ ይህም ሸክሙን እኩል እንድትጋሩ ያስችላል። +15 ይህ ደግሞ “ብዙ የሰበሰበ ብዙ አላተረፈም፤ ጥቂት የሰበሰበም ምንም አልጎደለበትም” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +16 እኛ ለእናንተ ያለንን ዓይነት ልባዊ አሳቢነት በቲቶ+ ልብ ውስጥ ያሳደረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤ +17 ምክንያቱም ቲቶ ወደ እናንተ የሚመጣው የእኛን ማበረታቻ በመቀበል ብቻ ሳይሆን በታላቅ ጉጉት፣ በራሱ ፈቃድ ተነሳስቶ ነው። +18 ይሁንና ከምሥራቹ ጋር በተያያዘ እያከናወነ ባለው ሥራ በጉባኤዎች ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ከእሱ ጋር እንልከዋለን። +19 ከዚህም በላይ ጌታን ለማስከበርና ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ መሆናችንን ለማሳየት ይህን የልግስና ስጦታ በምናከፋፍልበት ጊዜ ይህ ወንድም የጉዞ አጋራችን እንዲሆን በጉባኤዎች ተሹሟል። +20 ስለዚህ እኛ ከምናከፋፍለው የልግስና መዋጯችሁ ጋር በተያያዘ ማንም ሰው ምንም ዓይነት ስህተት እንዳያገኝብን እንጠነቀቃለን።+ +21 ምክንያቱም ‘በይሖዋ* ፊት ብቻ ሳይሆን በሰዎችም ፊት ሁሉንም ነገር በሐቀኝነት እናከናውናለን።’+ +22 በተጨማሪም በተደጋጋሚ ጊዜ በብዙ ነገር ተፈትኖ ትጉ ሆኖ ያገኘነውን ወንድማችንን ከእነሱ ጋር እንልከዋለን፤ እንዲያውም አሁን በእናንተ ላይ ባለው ጠንካራ እምነት የተነሳ ትጋቱ እጅግ ጨምሯል። +23 ይሁን እንጂ ቲቶን በተመለከተ ጥያቄ የሚያነሳ ካለ እሱ ለእናንተ ጥቅም አብሮኝ የሚሠራ ባልደረባዬ ነው፤ ወይም ደግሞ ስለ ወንድሞቻችን ጥያቄ ካለ እነሱ የጉባኤዎች ሐዋርያትና የክርስቶስ ክብር ናቸው። +24 ስለሆነም ለእነሱ ያላችሁን ፍቅር እውነተኝነት በተጨባጭ አስመሥክሩ፤+ እንዲሁም በእናንተ የምንኮራው ለምን እንደሆነ ለጉባኤዎቹ አሳዩ። +11 በመጠኑ ምክንያታዊነት ቢጎድለኝ እንድትታገሡኝ እፈልጋለሁ። ደግሞም እየታገሣችሁኝ ነው! +2 በአምላክ ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፤ እኔ ራሴ እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል ለክርስቶስ አቀርባችሁ ዘንድ ለአንድ ባል አጭቻችኋለሁ።+ +3 ሆኖም እባቡ ሔዋንን በተንኮሉ እንዳታለላት+ ሁሉ እናንተም አስተሳሰባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ልታሳዩ ���ሚገባውን ቅንነትና ንጽሕና በሆነ መንገድ እንዳታጡ እፈራለሁ።+ +4 አንድ ሰው መጥቶ እኛ የሰበክንላችሁን ሳይሆን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክላችሁ ወይም ከተቀበላችሁት መንፈስ የተለየ ዓይነት መንፈስ ቢያመጣ ወይም ከተቀበላችሁት ምሥራች የተለየ ሌላ ምሥራች ቢናገር+ እንዲህ ያለውን ሰው በቸልታ ታልፉታላችሁ ማለት ነው። +5 እኔ ከእናንተ የተራቀቁ ሐዋርያት በምንም ነገር የማንስ አይመስለኝም።+ +6 የተዋጣልኝ ተናጋሪ ባልሆን እንኳ+ እውቀት አይጎድለኝም፤ ይህን በሁሉም መንገድ እንዲሁም በሁሉም ነገር አሳይተናችኋል። +7 ወይስ እናንተ ከፍ እንድትሉ ራሴን ዝቅ አድርጌ የአምላክን ምሥራች ለእናንተ ያለዋጋ በደስታ መስበኬ እንደ ኃጢአት ተቆጥሮብኝ ይሆን?+ +8 እናንተን ለማገልገል ከሌሎች ጉባኤዎች ቁሳዊ እርዳታ በመቀበሌ እነሱን አራቁቻለሁ።+ +9 ከእናንተ ጋር ሳለሁ ተቸግሬ በነበረበት ጊዜ ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የጎደለኝን ነገር በሙሉ በሚገባ ስላሟሉልኝ ለማንም ሸክም አልሆንኩም።+ አዎ፣ እስካሁን ድረስ በእናንተ ላይ በምንም መንገድ ሸክም አልሆንኩም፤ ወደፊትም ሸክም አልሆንም።+ +10 የክርስቶስ እውነት በውስጤ እስካለ ድረስ በአካይያ ክልሎች ሁሉ በዚህ ነገር እንዳልኩራራ ምንም ነገር ሊያግደኝ አይችልም።+ +11 ይህን ያደረግኩት ለምንድን ነው? ስለማልወዳችሁ ነው? እንደምወዳችሁ አምላክ ያውቃል። +12 ይሁንና ከእኛ ጋር እኩል ለመሆን የሚፈልጉትና እኛም ሐዋርያት ነን ብለው የሚኩራሩት ሰዎች ለዚህ የሚሆን መሠረት* እንዳያገኙ አሁን እያደረግኩት ያለሁትን ወደፊትም አደርጋለሁ።+ +13 እንዲህ ያሉት ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት ለመምሰል ራሳቸውን የሚለውጡ ሐሰተኛ ሐዋርያትና አታላይ ሠራተኞች ናቸውና።+ +14 ይህም ምንም አያስደንቅም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋውጣልና።+ +15 ስለዚህ አገልጋዮቹም የጽድቅ አገልጋዮች ለመምሰል ራሳቸውን ቢለዋውጡ ምንም አያስገርምም። ሆኖም ፍጻሜያቸው እንደ ሥራቸው ይሆናል።+ +16 አሁንም ዳግመኛ እናገራለሁ፦ ማንም ሰው ምክንያታዊ እንዳልሆንኩ አድርጎ አያስብ። እንደዚያ አድርጋችሁ የምትመለከቱኝ ከሆነ ግን እኔም እንደ እነሱ በመጠኑ መኩራራት እንድችል ምክንያታዊነት እንደሚጎድለው ሰው አድርጋችሁ ተቀበሉኝ። +17 እንደዚህ የምናገረው የጌታን ምሳሌ በመከተል ሳይሆን ምክንያታዊ ያልሆነ ሰው እንደሚያደርገው በኩራትና በትምክህት ነው። +18 ብዙዎች በሥጋዊ ነገር ስለሚኩራሩ* እኔም እኩራራለሁ። +19 እናንተ በጣም “ምክንያታዊ” ስለሆናችሁ ምክንያታዊ ያልሆኑ ሰዎችን በደስታ ትታገሣላችሁ። +20 እንዲያውም ማንም እንደ ባሪያ ቢያደርጋችሁ፣ ማንም ንብረታችሁን ሙልጭ አድርጎ ቢወስድባችሁ፣ ማንም ያላችሁን ቢቀማችሁ፣ ማንም ራሱን ከፍ ከፍ ቢያደርግባችሁ ወይም ማንም በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሣላችሁ። +21 ይህን መናገር ለእኛ አሳፋሪ ነው፤ ምክንያቱም አንዳንዶች በሥልጣናችን በአግባቡ መጠቀም የማንችል ደካሞች እንደሆን አድርገው ሊያስቡ ይችላሉ። ሆኖም ምክንያታዊነት እንደሚጎድለው ሰው ልናገርና ማንም ሰው በሆነ ነገር የልብ ልብ የሚሰማው ከሆነ እኔም የልብ ልብ ሊሰማኝ ይችላል። +22 ዕብራውያን ናቸው? እኔም ነኝ።+ እስራኤላውያን ናቸው? እኔም ነኝ። የአብርሃም ዘር ናቸው? እኔም ነኝ።+ +23 የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸው? እንደ እብድ ሰው ልናገርና እኔ ከሁሉ በላቀ ደረጃ የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ፦ ከሁሉም ይበልጥ ሠርቻለሁ፣+ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፣+ ብዙ ጊዜ ተደብድቤአለሁ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ሞት አፋፍ ደርሻለሁ።+ +24 አይሁዳውያን ለ40 ጅራፍ አንድ የቀረው ግርፋት አምስት ጊዜ ገርፈውኛል፤+ +25 ሦስት ጊዜ በዱላ ተደብድቤአለሁ፤+ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወግሬአለሁ፤+ ሦስት ጊዜ የመርከብ መሰበር አደጋ አጋጥሞኛል፤+ አንድ ሌሊትና አንድ ቀን በባሕር ላይ አሳልፌአለሁ፤ +26 ብዙ ጊዜ ተጉዣለሁ፤ ደግሞም በወንዝ ሙላት ለሚመጣ አደጋ፣ ዘራፊዎች ለሚያደርሱት አደጋ፣ የገዛ ወገኖቼ ለሚያደርሱት አደጋ፣+ ከአሕዛብ ለሚሰነዘር አደጋ፣+ በከተማ፣+ በምድረ በዳና በባሕር ላይ ለሚያጋጥም አደጋ እንዲሁም በሐሰተኛ ወንድሞች መካከል ለሚያጋጥም አደጋ ተጋልጬ ነበር፤ +27 ብዙ ጥሬአለሁ፤ ብዙ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ ሳልተኛ አድሬአለሁ፤+ ተርቤአለሁ፤ ተጠምቻለሁ፤+ ብዙ ጊዜ ምግብ በማጣት ተቸግሬአለሁ፤+ በብርድ ተቆራምጃለሁ፤ በልብስ እጦትም ተቸግሬአለሁ። +28 ከእነዚህ ውጫዊ ችግሮች በተጨማሪ ዕለት ዕለት የሚያስጨንቀኝ* የጉባኤዎች ሁሉ ሐሳብ ነው።+ +29 ድካም የሚሰማው አለ? እኔስ ብሆን ድካም አይሰማኝም? የተሰናከለ አለ? ይህ እኔን በጣም አያናድደኝም? +30 መኩራራት ካስፈለገ ድክመቴን በሚያሳዩ ነገሮች እኩራራለሁ። +31 ለዘላለም የሚመሰገነው የጌታ ኢየሱስ አምላክና አባት እየዋሸሁ እንዳልሆነ ያውቃል። +32 በደማስቆ የንጉሥ አሬጣስ የበታች የሆነው ገዢ ሊይዘኝ ፈልጎ የደማስቆ ሰዎችን ከተማ ያስጠብቅ ነበር፤ +33 ሆኖም በከተማዋ ግንብ ላይ በሚገኘው መስኮት በኩል በቅርጫት አውርደውኝ+ ከእጁ አመለጥኩ። +2 እንደገና በምመጣበት ጊዜ ለሐዘን ምክንያት የሚሆን ነገር እንዳይፈጠር ወስኛለሁ። +2 ምክንያቱም የደስታዬ ምንጭ የሆናችሁትን እናንተን ካሳዘንኳችሁ እንግዲህ እኔን ማን ሊያስደስተኝ ነው? +3 ባለፈው ጊዜ የጻፍኩላችሁ በምመጣበት ጊዜ ልደሰትባቸው በሚገባ ሰዎች እንዳላዝን ነው፤ ምክንያቱም የእኔ ደስታ የእናንተ የሁላችሁም ደስታ እንደሚሆን እተማመናለሁ። +4 ልቤ በብዙ መከራና ጭንቀት ተውጦ በብዙ እንባ የጻፍኩላችሁ እንድታዝኑ ሳይሆን+ ለእናንተ ያለኝን ጥልቅ ፍቅር እንድታውቁ ነው። +5 ለሐዘን የሚዳርግ ነገር ያደረገ ማንም ቢኖር+ ያሳዘነው እኔን ሳይሆን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሁላችሁንም ነው፤ እንዲህ ያልኩት ግን ነገሩን ለማክበድ ብዬ አይደለም። +6 እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከእናንተ አብዛኞቻችሁ የሰጣችሁት ተግሣጽ ይበቃዋል፤ +7 አሁን ይህ ሰው ከልክ በላይ በሐዘን እንዳይዋጥ+ በደግነት ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባል።+ +8 ስለዚህ ለእሱ ያላችሁን ፍቅር እንድታረጋግጡለት አሳስባችኋለሁ።+ +9 የጻፍኩላችሁም በሁሉም ነገር ታዛዥ መሆናችሁን ታሳዩ እንደሆነ ለማረጋገጥ ነው። +10 በደሉ ምንም ይሁን ምን እናንተ ይቅር ያላችሁትን ማንኛውንም ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ። እንዲያውም ሁሉንም ነገር በክርስቶስ ፊት ይቅር ያልኩት (ይቅር ያልኩት ነገር ካለ) ለእናንተ ስል ነው፤ +11 ይህም ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ* ነው፤+ እሱ የሚሸርበውን ተንኮል* እናውቃለንና።+ +12 ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች ለማወጅ ጥሮአስ+ በደረስኩ ጊዜ የጌታን ሥራ ለማከናወን በር ተከፍቶልኝ ነበር፤ +13 ይሁንና ወንድሜን ቲቶን+ ስላላገኘሁት መንፈሴ ተረብሾ ነበር። በመሆኑም በዚያ ያሉትን ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ+ ሄድኩ። +14 በድል ሰልፍ ከክርስቶስ ጋር አብረን እንድንጓዝ በማድረግ ዘወትር ለሚመራንና የእውቀቱ መዓዛ በእኛ አማካኝነት በሁሉም ቦታ እንዲናኝ ለሚያደርገው አምላክ ምስጋና ይድረሰው! +15 እኛ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ባሉት መካከልና ወደ ጥፋት እያመሩ ባሉት መካከል ለአምላክ የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤ +16 ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ለሞት የሚዳርግ የሞት ሽታ፣*+ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ላሉት ደግሞ ወደ ሕይወት የሚመራ የሕይ��ት መዓዛ ነን። እንዲህ ላለው አገልግሎት ብቃት ያለው ማን ነው? +17 እኛ ነን፤ ምክንያቱም እኛ እንደ ብዙዎቹ ሰዎች የአምላክን ቃል አንሸቃቅጥም፤*+ ከዚህ ይልቅ በአምላክ የተላክን እንደመሆናችን መጠን በቅንነት እንናገራለን፤ ይህን የምናደርገው በአምላክ ፊት ሆነን እንዲሁም ከክርስቶስ ጋር በመተባበር ነው። +4 ስለዚህ በተደረገልን ምሕረት የተነሳ ይህ አገልግሎት ስላለን ተስፋ አንቆርጥም። +2 ከዚህ ይልቅ አሳፋሪ የሆኑትን ስውር ነገሮች ትተናል፤ በተንኮል አንመላለስም፤ የአምላክንም ቃል አንበርዝም፤+ ነገር ግን እውነትን በመግለጥ በአምላክ ፊት የሰውን ሁሉ ሕሊና በሚማርክ መንገድ ራሳችንን ብቁ አድርገን እናቀርባለን።+ +3 እንግዲህ የምናውጀው ምሥራች በእርግጥ የተሸፈነ ከሆነ የተሸፈነው ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ነው፤ +4 የአምላክ አምሳል ስለሆነው ስለ ክርስቶስ+ የሚገልጸውና ክብራማ የሆነው ምሥራች የሚፈነጥቀው ብርሃን በእነሱ ላይ እንዳያበራ+ የዚህ ሥርዓት* አምላክ+ የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ አሳውሯል።+ +5 እኛ የምንሰብከው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ስለ ኢየሱስ ስንል የእናንተ ባሪያዎች መሆናችንን እንጂ ስለ ራሳችን አይደለምና። +6 “በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይብራ” ያለው አምላክ ነውና፤+ ስለሆነም በክርስቶስ ፊት አማካኝነት፣ በልባችን ውስጥ ስለ አምላክ አስደናቂ እውቀት ይፈነጥቅ ዘንድ በልባችን ላይ ብርሃን አብርቷል።+ +7 ይሁን እንጂ ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነው ኃይል ከእኛ ሳይሆን ከአምላክ የመነጨ መሆኑ ይታወቅ ዘንድ+ ይህ ውድ ሀብት+ በሸክላ ዕቃ+ ውስጥ አለን። +8 በየአቅጣጫው ብንደቆስም መፈናፈኛ አናጣም፤ ግራ ብንጋባም መውጫ ቀዳዳ አናጣም፤*+ +9 ስደት ቢደርስብንም አልተተውንም፤+ በጭንቀት ብንዋጥም* አንጠፋም።+ +10 የኢየሱስ ሕይወት በእኛም ሰውነት እንዲገለጥ በኢየሱስ ላይ የደረሰውን ለሞት ሊዳርግ የሚችል መከራ ዘወትር በሰውነታችን እንሸከማለን።+ +11 የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችንም ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆን ለኢየሱስ ስንል ዘወትር ከሞት ጋር እንፋጠጣለንና።+ +12 ስለሆነም በእኛ ላይ ሞት፣ በእናንተ ላይ ግን ሕይወት እየሠራ ነው። +13 “አመንኩ፤ ስለዚህም ተናገርኩ” ተብሎ ተጽፏል።+ እኛም እንዲህ ዓይነት የእምነት መንፈስ ስላለን እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን፤ +14 ኢየሱስን ያስነሳው እሱ፣ እኛንም ከኢየሱስ ጋር እንደሚያስነሳንና ከእናንተ ጋር አንድ ላይ በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን።+ +15 ይህ ሁሉ የሆነው ለእናንተ ሲባል ነውና፤ ይኸውም ብዙ ሰዎች ለአምላክ ክብር ምስጋና እያቀረቡ ስለሆነ የተትረፈረፈው ጸጋ ይበልጥ እንዲበዛ ነው።+ +16 ስለዚህ ተስፋ አንቆርጥም፤ ምንም እንኳ ውጫዊው ሰውነታችን እየመነመነ ቢሄድም ውስጣዊው ሰውነታችን ከቀን ወደ ቀን እየታደሰ እንደሚሄድ ምንም ጥርጥር የለውም። +17 የሚደርስብን መከራ* ጊዜያዊና ቀላል ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድና ዘላለማዊ የሆነ ክብር ያስገኝልናል፤+ +18 ስለዚህ ዓይናችን እንዲያተኩር የምናደርገው በሚታዩት ነገሮች ላይ ሳይሆን በማይታዩት ነገሮች ላይ ነው።+ የሚታዩት ጊዜያዊ ናቸውና፤ የማይታዩት ግን ዘላለማዊ ናቸው። +6 ደግሞም ከእሱ ጋር አብረን የምንሠራ+ እንደመሆናችን መጠን የአምላክን ጸጋ ከተቀበላችሁ በኋላ ዓላማውን እንዳትስቱ እናሳስባችኋለን።+ +2 እሱ “ሞገስ በማሳይበት ጊዜ ሰምቼሃለሁ፤ በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ” ይላልና።+ እነሆ፣ አምላክ ሞገስ የሚያሳይበት ልዩ ጊዜ አሁን ነው። እነሆ፣ የመዳን ቀን አሁን ነው። +3 አገልግሎታችን እንከን እንዳይገኝበት በምንም መንገድ ማሰናከያ እ���ዲኖር አናደርግም፤+ +4 ከዚህ ይልቅ በሁሉም ነገር ራሳችንን ብቁ የአምላክ አገልጋዮች አድርገን እናቀርባለን፤+ ይህን የምናደርገው በብዙ ነገር በመጽናት፣ በመከራ፣ በእጦት፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች፣+ +5 በድብደባ፣ በእስር፣+ በሁከት፣ በከባድ ሥራ፣ እንቅልፍ አጥቶ በማደርና ጾም በመዋል ነው።+ +6 የአምላክ አገልጋዮች መሆናችንን በንጽሕና፣ በእውቀት፣ በትዕግሥት፣+ በደግነት፣+ በመንፈስ ቅዱስ፣ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፣+ +7 እውነት የሆነውን በመናገርና በአምላክ ኃይል እናሳያለን።+ እንዲሁም በቀኝ እጅና* በግራ እጅ* የጽድቅ መሣሪያዎችን በመያዝ፣+ +8 ክብርንም ሆነ ውርደትን እንዲሁም ነቀፋንም ሆነ ምስጋናን በመቀበል የአምላክ አገልጋዮች መሆናችንን እናስመሠክራለን። እውነተኞች ሆነን ሳለን እንደ አታላዮች ተቆጥረናል፤ +9 በሚገባ የታወቅን ሆነን ሳለን እንደማንታወቅ ተቆጥረናል፤ የምንሞት ስንመስል* እነሆ፣ ሕያዋን ነን፤+ ብንቀጣም ለሞት አልተዳረግንም፤+ +10 ሐዘንተኞች ተደርገን ብንታይም ምንጊዜም ደስተኞች ነን፤ እንደ ድሆች ብንቆጠርም ብዙዎችን ባለጸጋ እያደረግን ነው፤ ምንም የሌለን ብንመስልም ሁሉ ነገር አለን።+ +11 የቆሮንቶስ ወንድሞች ሆይ፣ በግልጽ ነግረናችኋል፤ ልባችንም ወለል ብሎ ተከፍቶላችኋል። +12 እኛ ፍቅራችንን አልነፈግናችሁም፤+ እናንተ ግን ጥልቅ ፍቅራችሁን ነፍጋችሁናል። +13 ስለዚህ ልጆቼን እንደማናግር ሆኜ አናግራችኋለሁ፤ እናንተም በአጸፋው ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱ።+ +14 ከማያምኑ ጋር አቻ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ።*+ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ኅብረት አለው?+ ወይስ ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ያገናኘዋል?+ +15 በተጨማሪም በክርስቶስና በቤልሆር* መካከል ምን ስምምነት አለ?+ ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ድርሻ አለው?+ +16 እንዲሁም የአምላክ ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው?+ እኛ የሕያው አምላክ ቤተ መቅደስ ነንና፤+ አምላክ “በመካከላቸው እኖራለሁ፤+ ከእነሱም ጋር እሄዳለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፣ እነሱ ደግሞ ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደተናገረው ነው።+ +17 “‘ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡና ራሳችሁን ለዩ’ ይላል ይሖዋ፤* ‘ርኩስ የሆነውንም ነገር አትንኩ’”፤*+ “‘እኔም እቀበላችኋለሁ።’”+ +18 “‘እኔ አባት እሆናችኋለሁ፤+ እናንተ ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትሆኑኛላችሁ’+ ይላል ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ።”* +10 በመካከላችሁ ሆኜ ፊት ለፊት ስታይ እንደ ደካማ የምቆጠረውና+ ከእናንተ ስርቅ እንደ ደፋር የምታየው+ እኔ ጳውሎስ በክርስቶስ ገርነትና ደግነት+ እለምናችኋለሁ። +2 በመካከላችሁ በምገኝበት ጊዜ በሥጋዊ አስተሳሰብ እንደምንመላለስ አድርገው በሚቆጥሩን አንዳንድ ሰዎች ላይ በድፍረት ከባድ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስገድድ ሁኔታ እንደማይፈጠር ተስፋ አደርጋለሁ። +3 ምንም እንኳ በሥጋ የምንኖር ቢሆንም የምንዋጋው በሥጋዊ መንገድ አይደለም። +4 የምንዋጋባቸው የጦር መሣሪያዎቻችን ሥጋዊ አይደሉምና፤+ ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደርመስ የሚያስችል መለኮታዊ ኃይል ያላቸው ናቸው።+ +5 ስለ አምላክ የሚገልጸውን እውቀት የሚጻረሩ የተሳሳቱ ሐሳቦችንና ይህን እውቀት የሚያግድን ማንኛውንም ከፍ ያለ ነገር እናፈርሳለን፤+ እንዲሁም ማንኛውንም ሐሳብ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን፤ +6 ሙሉ በሙሉ ታዛዦች መሆናችሁን ካሳያችሁ በኋላ በማንኛውም መንገድ ታዛዥ በማይሆን ግለሰብ ላይ የቅጣት እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተናል።+ +7 እናንተ የምትመለከቱት ውጫዊውን ነገር ብቻ ነው። ማንም ሰው የክርስቶስ ነኝ ብሎ በራሱ የሚተማመን ከሆነ እሱ የክርስቶስ እንደሆነ ሁሉ እኛም የክርስቶስ እንደሆን በድጋሚ ሊያጤን ይገባዋል። +8 ጌታ እናንተን ለማፍረስ ሳይሆን ለማነጽ በሰጠን ሥልጣን እጅግ ብኮራም እንኳ+ ለኀፍረት አልዳረግምና። +9 እናንተን በደብዳቤዎቼ ለማስፈራራት እየሞከርኩ ያለሁ ሆኖ እንዲሰማችሁ አልፈልግም። +10 አንዳንዶች “ደብዳቤዎቹ ከባድና ኃይለኛ ናቸው፤ በመካከላችን በአካል ሲገኝ ግን ደካማ ከመሆኑም በላይ ንግግሩ የተናቀ ነው” ይላሉና። +11 እንዲህ ያለው ሰው፣ በአካል ሳንኖር በደብዳቤዎቻችን የምንናገረው ቃልና በአካል ስንገኝ የምናደርገው ነገር ምንም ልዩነት እንደሌለው መገንዘብ ይገባዋል።+ +12 እኛ ራሳቸውን ብቁ አድርገው ከሚያቀርቡ ሰዎች ጋር ራሳችንን ለመመደብ ወይም ለማነጻጸር አንደፍርምና።+ ይሁንና እነሱ ራሳቸውን በራሳቸው ሲመዝኑና ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያነጻጽሩ ማስተዋል እንደሌላቸው ያሳያሉ።+ +13 እኛ ግን ከተሰጠን ወሰን ውጭ ባለው ነገር አንኩራራም፤ ከዚህ ይልቅ የምንኮራው አምላክ ለክቶ በሰጠን ክልል ውስጥ ባለው ነገር ብቻ ነው፤ ይህ ክልል ደግሞ እናንተንም ያጠቃልላል።+ +14 እናንተ ከክልላችን ውጭ ያላችሁ ይመስል እናንተ ጋር ለመድረስ ከክልላችን ውጭ መሄድ አላስፈለገንም፤ ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች በመጀመሪያ እናንተ እስካላችሁበት ድረስ ይዘን የመጣነው እኛ ነንና።+ +15 ከተመደበልን ወሰን ውጭ ሌላ ሰው በደከመበት ነገር እየተኩራራን አይደለም፤ ሆኖም እምነታችሁ እያደገ ሲሄድ በክልላችን ውስጥ ያከናወንነውን ሥራ በሚገባ እንደምትገነዘቡ ተስፋ እናደርጋለን። ይህም ይበልጥ እንድንሠራ ያደርገናል፤ +16 በመሆኑም በሌላው ሰው ክልል፣ አስቀድሞ በተሠራ ሥራ ከመኩራራት ይልቅ ከእናንተ ወዲያ ባሉት አገሮች ምሥራቹን እንሰብካለን። +17 “ሆኖም የሚኩራራ በይሖዋ* ይኩራራ።”+ +18 ተቀባይነት የሚያገኘው ራሱን ብቁ እንደሆነ አድርጎ የሚያቀርብ ሳይሆን+ ይሖዋ* ብቁ ነው የሚለው ሰው ነውና።+ +9 ለቅዱሳን የሚደረገውን አገልግሎት* በተመለከተ+ ልጽፍላችሁ አያስፈልግም፤ +2 እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆናችሁን አውቃለሁና፤ በመሆኑም “የአካይያ ወንድሞች ሌሎችን ለመርዳት ለአንድ ዓመት ያህል ዝግጁ ሆነው ሲጠባበቁ ቆይተዋል” ብዬ ለመቄዶንያ ወንድሞች በኩራት ተናግሬአለሁ፤ የእናንተ ቅንዓት ደግሞ አብዛኞቹን አነሳስቷል። +3 ይሁንና በዚህ ረገድ በእናንተ ላይ ያለን ትምክህት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር አስቀድሞ ስለ እናንተ እንደተናገርኩት ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ ወንድሞችን እልካለሁ። +4 አለዚያ የመቄዶንያ ወንድሞች ከእኔ ጋር መጥተው ዝግጁ ሳትሆኑ ቢያገኟችሁ፣ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ እኛም በእናንተ በመተማመናችን እናፍራለን። +5 ስለዚህ ቀደም ሲል ልትሰጡ ቃል የገባችሁትን የልግስና ስጦታ አስቀድመው ያዘጋጁ ዘንድ ወንድሞች ቀደም ብለው ወደ እናንተ እንዲመጡ ማበረታታት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እንዲህ ከሆነ ስጦታው ተዘጋጅቶ ይጠብቀናል፤ ይህ ደግሞ ስጦታ የሰጣችሁት አስገድደናችሁ ሳይሆን በልግስና እንደሆነ ያሳያል። +6 ይሁንና ጥቂት የሚዘራ ሁሉ ጥቂት ያጭዳል፤ በብዛት የሚዘራ ሁሉ ደግሞ በብዛት ያጭዳል።+ +7 አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ+ እያንዳንዱ ሰው ቅር እያለው* ወይም ተገዶ ሳይሆን በልቡ ያሰበውን ይስጥ።+ +8 በተጨማሪም ምንጊዜም የሚያስፈልጋችሁ ነገር በበቂ ሁኔታ እንዲኖራችሁ እንዲሁም መልካም ሥራን ሁሉ ለመሥራት የሚያስችላችሁን ነገር በብዛት እንድታገኙ አምላክ ጸጋውን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።+ +9 (ይህም “በብዛት* አከፋፈለ፤ ለድሆችም ሰጠ። ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ +10 እንግዲህ ለዘሪ ዘርን፣ ለ��ብል እህልን አትረፍርፎ የሚሰጠው እሱ የምትዘሩትን ዘር አትረፍርፎ ይሰጣችኋል፤ እንዲሁም የጽድቃችሁን ፍሬ ያበዛላችኋል።) +11 በሁሉም መንገድ በልግስና መስጠት እንድትችሉ አምላክ አትረፍርፎ ይባርካችኋል፤ እኛ በምናከናውነው ሥራ የተነሳ እንዲህ ያለው ልግስና ሰዎች ለአምላክ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያነሳሳቸዋል፤ +12 ምክንያቱም ይህ የምታከናውኑት ሕዝባዊ አገልግሎት* ቅዱሳን የሚያስፈልጓቸው ነገሮች በሚገባ እንዲሟሉላቸው+ ከማድረጉም በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ለአምላክ ብዙ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያደርጋል። +13 በዚህ የእርዳታ አገልግሎት አማካኝነት የሚያዩት ማስረጃ አምላክን እንዲያከብሩ ያደርጋቸዋል፤ ምክንያቱም እናንተ በይፋ ለምታውጁት ስለ ክርስቶስ ለሚገልጸው ምሥራች ተገዢዎች ናችሁ፤ እንዲሁም ለእነሱም ሆነ ለሁሉም በምታደርጉት መዋጮ ለጋሶች ናችሁ።+ +14 ደግሞም አምላክ ከሰጣችሁ የላቀ ጸጋ የተነሳ ስለ እናንተ ምልጃ እያቀረቡ ለእናንተ ያላቸውን ፍቅር ይገልጻሉ። +15 በቃላት ሊገለጽ ለማይችለው ነፃ ስጦታው አምላክ የተመሰገነ ይሁን። +13 ወደ እናንተ ለመምጣት ሳስብ ይህ ሦስተኛ ጊዜዬ ነው። “ማንኛውም ጉዳይ የሚጸናው ሁለት ወይም ሦስት ምሥክሮች በሚሰጡት የምሥክርነት ቃል* ነው።”+ +2 ምንም እንኳ አሁን ከእናንተ ርቄ ያለሁ ቢሆንም ለሁለተኛ ጊዜ አብሬያችሁ እንዳለሁ አድርጋችሁ በማሰብ ቃሌን ተቀበሉ። ደግሞም ዳግመኛ ከመጣሁ ማንንም ሳልገሥጽ እንደማላልፍ ከዚህ በፊት ኃጢአት የሠሩትንም ሆነ የተቀሩትን ሁሉ አስቀድሜ አስጠነቅቃለሁ፤ +3 ይህም የሆነው በእናንተ መካከል በድካም ሳይሆን በኃይል የሚሠራው ክርስቶስ በእኔ አማካኝነት እንደሚናገር የሚያሳይ ማስረጃ ስለፈለጋችሁ ነው። +4 እርግጥ ነው፣ እሱ በእንጨት ላይ የተሰቀለው በድካም የተነሳ* ነው፤ ይሁንና በአምላክ ኃይል የተነሳ ሕያው ሆኗል።+ እርግጥ እኛም ከእሱ ጋር ደካሞች ነን፤ ሆኖም በእናንተ ላይ እየሠራ ባለው የአምላክ ኃይል+ ከእሱ ጋር እንኖራለን።+ +5 በእምነት ውስጥ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ዘወትር ራሳችሁን ፈትሹ፤ ማንነታችሁን ለማወቅ ዘወትር ራሳችሁን መርምሩ።+ ተቀባይነት አጥታችሁ ካልሆነ በስተቀር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር አንድነት እንዳለው አትገነዘቡም? +6 እኛ ግን ተቀባይነት ያለን መሆናችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ አደርጋለሁ። +7 መጥፎ ነገር እንዳትሠሩ ወደ አምላክ እንጸልያለን፤ ይህን የምናደርገው እኛ ተቀባይነት ያለን ሆነን እንድንታይ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ እኛ ተቀባይነት ያላገኘን መስለን ብንታይም እንኳ እናንተ መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው። +8 እኛ ለእውነት የቆምን ነን እንጂ እውነትን የሚጻረር ምንም ነገር ማድረግ አንችልምና። +9 እኛ በደከምንበት ጊዜ ሁሉ እናንተ ብርቱዎች ብትሆኑ ምንጊዜም ደስተኞች ነን። ደግሞም መስተካከላችሁን እንድትቀጥሉ እንጸልያለን። +10 ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ በመካከላችሁ በምሆንበት ጊዜ ጠበቅ ያለ እርምጃ እንዳልወስድ ነው፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ+ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም። +11 በተረፈ ወንድሞች፣ መደሰታችሁን፣ መስተካከላችሁን፣ ማጽናኛ መቀበላችሁን፣+ በሐሳብ መስማማታችሁንና+ በሰላም መኖራችሁን ቀጥሉ፤+ የፍቅርና የሰላም አምላክም+ ከእናንተ ጋር ይሆናል። +12 እርስ በርስ በመሳሳም* ሰላምታ ተለዋወጡ። +13 ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። +14 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና የአምላክ ፍቅር እንዲሁም በጋራ የምንቀበለው መንፈስ ቅዱስ ከሁላችሁ ጋር ይሁን። +5 ምድራዊ ቤታችን* የሆነው ይህ ድንኳን ቢፈርስ+ በሰው እጅ የተሠራ ቤት ሳይሆን በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ ሕንፃ ከአምላክ እንደምናገኝ እናውቃለን።+ +2 ከሰማይ የሆነውን መኖሪያችንን ለመልበስ እየናፈቅን በዚህ ቤት* ውስጥ ሆነን እንቃትታለን፤+ +3 ስለዚህ ይህን ስንለብስ ራቁታችንን ሆነን አንገኝም። +4 እንዲያውም በዚህ ድንኳን ውስጥ ያለነው እኛ ከባድ ሸክም ተጭኖን እንቃትታለን፤ ምክንያቱም ዘላለማዊው ሕይወት ሟች የሆነውን አካል እንዲተካ+ ይህን ድንኳን ማውለቅ ሳይሆን ሰማያዊውን መኖሪያ መልበስ እንፈልጋለን።+ +5 ለዚህ ነገር ያዘጋጀን አምላክ ነው፤+ ለሚመጣው ነገር ማረጋገጫ* አድርጎ መንፈሱን የሰጠን እሱ ነው።+ +6 በመሆኑም ስለዚህ ጉዳይ ምንጊዜም እርግጠኞች ነን፤ በተጨማሪም መኖሪያችን በሆነው በዚህ አካል እስካለን ድረስ ከጌታ ጋር አብረን እንዳልሆን እናውቃለን፤+ +7 የምንመላለሰው በእምነት እንጂ በማየት አይደለምና። +8 ሆኖም እኛ እርግጠኞች ነን፤ ደግሞም ከዚህ አካል ተለይተን መኖሪያችንን ከጌታ ጋር ብናደርግ እንመርጣለን።+ +9 ስለዚህ ከእሱ ጋር አብረን ብንኖርም ሆነ ባንኖር ዓላማችን በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ነው። +10 ምክንያቱም እያንዳንዱ በሥጋ እያለ ላደረገው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር፣ እንደ ሥራው ብድራት እንዲቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ልንቀርብ* ይገባል።+ +11 እንግዲህ ጌታን መፍራት እንደሚገባን ስለምናውቅ ሰዎች የምንናገረውን እንዲቀበሉ ለማሳመን ምንጊዜም እንጥራለን፤ ሆኖም አምላክ በሚገባ ያውቀናል።* የእናንተም ሕሊና እኛን በሚገባ እንድታውቁ እንደረዳችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። +12 እኛ ብቃታችንን ለእናንተ እንደ አዲስ ማቅረባችን አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በልብ ውስጥ ባለው ነገር ሳይሆን በውጫዊ መልክ ለሚኩራሩ+ መልስ መስጠት ትችሉ ዘንድ በእኛ እንድትኮሩ እያነሳሳናችሁ ነው። +13 አእምሯችንን ብንስት+ ለአምላክ ብለን ነውና፤ ጤናማ አእምሮ ቢኖረን ደግሞ ለእናንተ ብለን ነው። +14 አንድ ሰው ለሁሉም መሞቱን+ ስለተረዳን ክርስቶስ ያለው ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም ሁሉም ቀድሞውኑ ሞተዋል። +15 በሕይወት ያሉትም ከእንግዲህ ለራሳቸው ከመኖር ይልቅ ለእነሱ ለሞተውና ለተነሳው እንዲኖሩ እሱ ለሁሉም ሞቷል።+ +16 ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ሰዎችን የምናውቀው ከሥጋዊ አመለካከት አንጻር አይደለም።*+ ክርስቶስን በሥጋዊ ሁኔታ እናውቀው የነበረ ቢሆንም ከዚህ በኋላ በዚህ መንገድ አናውቀውም።+ +17 በመሆኑም ማንም ከክርስቶስ ጋር አንድ ከሆነ አዲስ ፍጥረት ነው፤+ አሮጌዎቹ ነገሮች አልፈዋል፤ እነሆ፣ አዳዲስ ነገሮች ወደ ሕልውና መጥተዋል! +18 ሆኖም ሁሉም ነገሮች የተገኙት በክርስቶስ አማካኝነት ከራሱ ጋር ካስታረቀንና+ የማስታረቅ አገልግሎት ከሰጠን አምላክ ነው።+ +19 ይህም፣ አምላክ በክርስቶስ አማካኝነት ዓለምን ከራሱ ጋር ከማስታረቁም በላይ+ በደላቸውን አልቆጠረባቸውም ማለት ነው፤+ ለእኛ ደግሞ የእርቁን መልእክት በአደራ ሰጥቶናል።+ +20 ስለዚህ እኛ ክርስቶስን ተክተን+ የምንሠራ አምባሳደሮች ነን፤+ አምላክ በእኛ አማካኝነት እየተማጸነ ያለ ያህል ነው። ክርስቶስን ተክተን የምንሠራ እንደመሆናችን መጠን “ከአምላክ ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን። +21 እኛ በእሱ አማካኝነት በአምላክ ፊት ጻድቅ እንድንሆን+ ኃጢአት የማያውቀው+ እሱ ለእኛ የኃጢአት መባ ተደረገ። +3 እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁ የገላትያ ሰዎች! ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በእንጨት ላይ ተቸንክሮ ፊት ለፊት ያያችሁት ያህል በዓይነ ሕሊናችሁ ተስሎ ነበር፤+ ታዲያ አሁን አፍዝ አደንግዝ ያደረገባችሁ ማን ነው?+ +2 እስቲ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ፦ መንፈስን የተቀበላችሁት ሕግን በመጠበቅ ነው ወይ�� የሰማችሁትን በማመን?+ +3 ይህን ያህል ማስተዋል የጎደላችሁ ናችሁ? በመንፈሳዊ መንገድ መጓዝ ከጀመራችሁ በኋላ በሥጋዊ መንገድ ልታጠናቅቁ ታስባላችሁ?+ +4 ብዙ መከራ የተቀበላችሁት እንዲያው በከንቱ ነው? መቼም በከንቱ ነው ብዬ አላስብም። +5 መንፈስን የሚሰጣችሁና በመካከላችሁ ተአምራት የሚፈጽመው+ እሱ ይህን የሚያደርገው ሕግን በመጠበቃችሁ ነው ወይስ የሰማችሁትን በማመናችሁ? +6 ይህም አብርሃም “በይሖዋ* አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት” እንደተባለው ነው።+ +7 የአብርሃም ልጆች የሆኑት እምነትን አጥብቀው የሚከተሉት መሆናቸውን እንደምታውቁ የተረጋገጠ ነው።+ +8 ቅዱስ መጽሐፉ፣ አምላክ ከብሔራት ወገን የሆኑ ሰዎችን በእምነት አማካኝነት ጸድቃችኋል እንደሚላቸው አስቀድሞ ተረድቶ “ብሔራት ሁሉ በአንተ አማካኝነት ይባረካሉ” በማለት ምሥራቹን ለአብርሃም አስቀድሞ አስታውቆታል።+ +9 በመሆኑም እምነትን አጥብቀው የሚይዙ በእምነት ከተመላለሰው ከአብርሃም ጋር የበረከቱ ተካፋዮች ሆነዋል።+ +10 ሕግን በመጠበቅ የሚታመኑ ሁሉ የተረገሙ ናቸው፤ “በሕጉ የመጽሐፍ ጥቅልል የተጻፉትን ነገሮች ሁሉ በመፈጸም እነሱን ተግባራዊ ማድረጉን የማይቀጥል ሰው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ተጽፏልና።+ +11 በተጨማሪም “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ ስለተጻፈ+ በአምላክ ፊት ማንም በሕግ አማካኝነት ጻድቅ ሊባል እንደማይችል ግልጽ ነው።+ +12 ሕጉ በእምነት ላይ የተመሠረተ አይደለም። ከዚህ ይልቅ “ትእዛዛቱን የሚጠብቅ ማንኛውም ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል” ይላል።+ +13 ክርስቶስ በእኛ ፋንታ የተረገመ ሆኖ እኛን ከሕጉ እርግማን ነፃ በማውጣት+ ዋጅቶናል፤+ ምክንያቱም “በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሰው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ተጽፏል።+ +14 ይህም የሆነው ለአብርሃም ቃል የተገባው በረከት በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ለብሔራት እንዲደርስና+ እኛም በእምነታችን አማካኝነት ቃል የተገባውን መንፈስ ማግኘት እንድንችል ነው።+ +15 ወንድሞች፣ በሰው ዕለታዊ ሕይወት የተለመደ አንድ ምሳሌ ልጠቀም፦ አንድ ቃል ኪዳን፣ በሰውም እንኳ ቢሆን አንዴ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሊሽረው ወይም ምንም ነገር ሊጨምርበት አይችልም። +16 የተስፋው ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነው።+ ቅዱስ መጽሐፉ ስለ ብዙዎች እንደሚናገር “ለዘሮችህ” አይልም። ከዚህ ይልቅ ስለ አንድ እንደሚናገር “ለዘርህ” ይላል፤ እሱም ክርስቶስ ነው።+ +17 በተጨማሪም ይህን እላለሁ፦ ከ430 ዓመታት በኋላ+ የተሰጠው ሕግ ቀደም ሲል አምላክ የገባውን ቃል ኪዳን አፍርሶ የተስፋውን ቃል አይሽርም። +18 ውርሻው የሚገኘው በሕግ አማካኝነት ቢሆን ኖሮ በተስፋ ቃል አማካኝነት መሆኑ በቀረ ነበርና፤ ሆኖም አምላክ ውርሻውን ለአብርሃም በደግነት የሰጠው በተስፋ ቃል አማካኝነት ነው።+ +19 ታዲያ ሕግ የተሰጠው ለምንድን ነው? ሕጉ የተጨመረው፣ ቃል የተገባለት ዘር እስኪመጣ ድረስ+ ሕግ ተላላፊነትን ይፋ ለማድረግ ነው፤+ ሕጉ የተሰጠውም በመላእክት አማካኝነት+ በአንድ መካከለኛ እጅ ነው።+ +20 ይሁንና አንድ ወገን ብቻ ባለበት መካከለኛ አይኖርም፤ አምላክ ደግሞ አንድ ወገን ብቻ ነው። +21 ታዲያ ሕጉ የአምላክን የተስፋ ቃል ይጻረራል ማለት ነው? በጭራሽ! ሕይወት ሊያስገኝ የሚችል ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ጽድቅ የሚገኘው በሕግ አማካኝነት በሆነ ነበር። +22 ሆኖም ቅዱስ መጽሐፉ ሁሉም ነገሮች የኃጢአት እስረኛ እንዲሆኑ አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፤ ይህም የሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ ሁሉ ይሰጥ ዘንድ ነው። +23 ይሁን እንጂ እምነት ከመምጣቱ በፊት፣ ሊገለጥ ያለውን እምነት እየተጠባበቅን ��ሕግ ጥበቃ ሥር እስረኞች እንድንሆን አልፈን ተሰጥተናል።+ +24 በመሆኑም በእምነት አማካኝነት መጽደቅ እንችል ዘንድ+ ሕጉ ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ ሞግዚታችን* ሆኗል።+ +25 አሁን ግን ያ እምነት ስለመጣ+ ከእንግዲህ ወዲህ በሞግዚት* ሥር አይደለንም።+ +26 እንደ እውነቱ ከሆነ ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ባላችሁ እምነት የተነሳ+ የአምላክ ልጆች ናችሁ።+ +27 ወደ ክርስቶስ የተጠመቃችሁ ሁላችሁም ክርስቶስን ለብሳችኋልና።*+ +28 ሁላችሁም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት በመፍጠር አንድ በመሆናችሁ+ በአይሁዳዊና በግሪካዊ፣+ በባሪያና በነፃ ሰው+ እንዲሁም በወንድና በሴት+ መካከል ልዩነት የለም። +29 በተጨማሪም የክርስቶስ ከሆናችሁ በእርግጥም የአብርሃም ዘር ናችሁ፤+ በተስፋውም ቃል መሠረት+ ወራሾች ናችሁ።+ +1 ከሰዎች ወይም በሰው ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ+ እንዲሁም እሱን ከሞት ባስነሳውና አባታችን በሆነው አምላክ+ አማካኝነት ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ +2 እንዲሁም አብረውኝ ካሉት ወንድሞች ሁሉ፣ በገላትያ ላሉት ጉባኤዎች፦ +3 አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። +4 ኢየሱስ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ+ አሁን ካለው ክፉ ሥርዓት*+ እኛን ለመታደግ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ፤+ +5 ለዘላለም ለአምላክ ክብር ይሁን። አሜን። +6 አምላክ በክርስቶስ ጸጋ ከጠራችሁ በኋላ እንዲህ በፍጥነት ከእሱ ዞር ማለታችሁና* ለሌላ ዓይነት ምሥራች ጆሯችሁን መስጠታችሁ ደንቆኛል።+ +7 እንደ እውነቱ ከሆነ ሌላ ምሥራች የለም፤ ሆኖም እናንተን የሚረብሹና+ ስለ ክርስቶስ የሚናገረውን ምሥራች ለማጣመም የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ። +8 ይሁን እንጂ ከመካከላችን አንዱ ወይም ከሰማይ የወረደ መልአክ፣ እኛ ከሰበክንላችሁ ምሥራች የተለየ ምሥራች ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። +9 ቀደም ሲል እንደተናገርነው፣ አሁንም ደግሜ እላለሁ፣ ማንም ይሁን ማን ከተቀበላችሁት የተለየ ምሥራች ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። +10 አሁን እኔ ጥረት የማደርገው የሰውን ሞገስ ለማግኘት ነው ወይስ የአምላክን? ደግሞስ ሰዎችን ለማስደሰት እየሞከርኩ ነው? አሁንም ሰዎችን እያስደሰትኩ ከሆነ የክርስቶስ ባሪያ አይደለሁም ማለት ነው። +11 ወንድሞች፣ እኔ የሰበክሁላችሁ ምሥራች ከሰው የመነጨ ምሥራች እንዳልሆነ ላሳውቃችሁ እወዳለሁ፤+ +12 ኢየሱስ ክርስቶስ በራእይ ገለጠልኝ እንጂ የተቀበልኩትም ሆነ የተማርኩት ከሰው አይደለምና። +13 በእርግጥ፣ በአይሁዳውያን ሃይማኖት+ ሳለሁ ምን ዓይነት ሰው እንደነበርኩ ሰምታችኋል፤ የአምላክን ጉባኤ ክፉኛ* አሳድድና ለማጥፋት ጥረት አደርግ ነበር፤+