diff --git "a/en-am/jw300-amharic-baseline/data/dev.am" "b/en-am/jw300-amharic-baseline/data/dev.am" new file mode 100644--- /dev/null +++ "b/en-am/jw300-amharic-baseline/data/dev.am" @@ -0,0 +1,1001 @@ +target_sentence +14 ለአባቶቼ ወግ ከፍተኛ ቅንዓት ስለነበረኝ ከወገኖቼ መካከል በእኔ ዕድሜ ካሉት ከብዙዎቹ የበለጠ በአይሁዳውያን ሃይማኖት የላቀ እድገት እያደረግኩ ነበር።+ +15 ሆኖም ከእናቴ ማህፀን እንድለይ* ያደረገኝና በጸጋው አማካኝነት የጠራኝ አምላክ+ +16 ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች ለአሕዛብ እንዳውጅ+ ልጁን በእኔ አማካኝነት ለመግለጥ በወደደ ጊዜ ከማንም ሰው* ጋር ወዲያው አልተማከርኩም፤ +17 በኢየሩሳሌም ወደሚገኙት ከእኔ በፊት ሐዋርያት ወደሆኑትም አልሄድኩም፤ ከዚህ ይልቅ ወደ ዓረብ አገር ሄድኩ፤ ከዚያም ወደ ደማስቆ+ ተመለስኩ። +18 ከዚያም ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋን*+ ለመጠየቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፤+ ከእሱም ጋር 15 ቀን ተቀመጥኩ። +19 ሆኖም ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ+ በስተቀር ከሌሎቹ ሐዋርያት መካከል ማንንም አላየሁም። +20 እንግዲህ እየጻፍኩላችሁ ያለሁት ነገር ውሸት እንዳልሆነ በአምላክ ፊት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። +21 ከዚያ በኋላ በሶርያና በኪልቅያ ወዳሉ ክልሎች ሄድኩ።+ +22 ሆኖም በይሁዳ ያሉ የክርስቲያን ጉባኤዎች በአካል አይተውኝ አያውቁም ነበር። +23 ይሁንና “ከዚህ ቀደም ያሳድደን የነበረው ሰው፣+ ሊያጠፋው ይፈልግ ስለነበረው እምነት+ የሚገልጸውን ምሥራች አሁን እየሰበከ ነው” የሚል ወሬ ብቻ ይሰሙ ነበር። +24 ስለዚህ በእኔ ምክንያት አምላክን ከፍ ከፍ ያደርጉ ጀመር። +2 ከዚያም ከ14 ዓመት በኋላ ዳግመኛ ወደ ኢየሩሳሌም ስወጣ በርናባስ አብሮኝ ነበር፤+ ቲቶንም ይዤው ሄድኩ።+ +2 ሆኖም የሄድኩት በተገለጠልኝ ራእይ መሠረት ነበር፤ ከዚያም በአሕዛብ መካከል እየሰበክሁ ያለሁትን ምሥራች ከፍ ተደርገው በሚታዩት ወንድሞች ፊት አቀረብኩ። ይሁን እንጂ እየሮጥኩ ያለሁት ወይም የሮጥኩት ምናልባት በከንቱ እንዳይሆን ስለሰጋሁ ይህን ያስታወቅኳቸው ለብቻቸው ነበር። +3 ይሁንና ከእኔ ጋር የነበረው ቲቶ+ እንኳ ግሪካዊ ቢሆንም እንዲገረዝ አልተገደደም።+ +4 ሆኖም ይህ ጉዳይ የተነሳው ሙሉ በሙሉ ባሪያዎች ሊያደርጉን በማሰብ+ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባለን አንድነት ያገኘነውን ነፃነት+ ሊሰልሉ ሾልከው በስውር በገቡት ሐሰተኛ ወንድሞች ምክንያት ነው፤+ +5 እኛ ግን የምሥራቹ እውነት በእናንተ ዘንድ ጸንቶ እንዲኖር በማለት ለአንድ አፍታ* እንኳ እሺ ብለን አልተገዛንላቸውም።+ +6 ወሳኝ ሰዎች ተደርገው የሚታዩትን+ በተመለከተ ግን እነዚህ ሰዎች ለእኔ የጨመሩልኝ አዲስ ነገር የለም። አዎ፣ አምላክ የሰውን ውጫዊ ማንነት አይቶ ስለማያዳላ እነዚህ ከፍ ተደርገው የሚታዩት ሰዎች ቀደም ሲል ምንም ይሁኑ ምን ለእኔ የሚያመጣው ለውጥ የለም። +7 በአንጻሩ ግን ጴጥሮስ ለተገረዙት እንዲሰብክ ምሥራቹ በአደራ እንደተሰጠው ሁሉ እኔም ላልተገረዙት እንድሰብክ ምሥራቹ በአደራ እንደተሰጠኝ በተገነዘቡ ጊዜ+ +8 (ጴጥሮስ ለተገረዙት ሐዋርያ ሆኖ እንዲያገለግል ኃይል የሰጠው አምላክ ለእኔም ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን እንዳገለግል ኃይል ሰጥቶኛልና፤)+ +9 እንዲሁም እንደ ዓምድ የሚታዩት ያዕቆብ፣+ ኬፋና* ዮሐንስ የተሰጠኝን ጸጋ በተረዱ ጊዜ+ እነሱ ወደተገረዙት እኛ ደግሞ ወደ አሕዛብ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ+ ቀኝ እጃቸውን በመስጠት አጋርነታቸውን* ገለጹልን። +10 ይሁንና ድሆችን ማሰባችንን እንዳናቋርጥ አደራ አሉን፤ እኔም ብሆን ይህን ለመፈጸም ትጋት የተሞላበት ጥረት ሳደርግ ነበር።+ +11 ይሁን እንጂ ኬፋ*+ ወደ አንጾኪያ+ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምኩት፤* ምክንያቱም ግልጽ የሆነ ስህተት ሠርቶ* ነበር። +12 የተወሰኑ ሰዎች ከያዕቆብ+ ዘንድ ከመምጣታቸው በፊት ከአሕዛብ ወገን ከሆኑ ሰዎች ጋር ይበላ ነበር፤+ እነሱ ከመጡ በኋላ ግ��� ከተገረዙት ወገን የሆኑትን በመፍራት ይህን ማድረጉን አቁሞ ራሱን ከአሕዛብ አገለለ።+ +13 የቀሩት አይሁዳውያንም በዚህ የግብዝነት ድርጊት* ከእሱ ጋር ተባበሩ፤ በርናባስም እንኳ በእነሱ የግብዝነት ድርጊት* ተሸንፎ ነበር። +14 ሆኖም ከምሥራቹ እውነት ጋር በሚስማማ መንገድ እየተጓዙ እንዳልሆኑ ባየሁ ጊዜ+ ኬፋን* በሁሉም ፊት እንዲህ አልኩት፦ “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለህ እንደ አይሁዳውያን ሳይሆን እንደ አሕዛብ የምትኖር ከሆነ ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰዎች እንደ አይሁዳውያን ልማድ እንዲኖሩ እንዴት ልታስገድዳቸው ትችላለህ?” +15 በትውልዳችን አይሁዳውያን እንጂ ከአሕዛብ ወገን እንደሆኑት ኃጢአተኞች ያልሆንነው እኛ፣ +16 አንድ ሰው የሚጸድቀው ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን+ ብቻ እንደሆነ እንገነዘባለን።+ ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ምክንያቱም ሕግን በመጠበቅ መጽደቅ የሚችል ሰው* የለም።+ +17 እኛ በክርስቶስ አማካኝነት መጽደቅ በመፈለጋችን እንደ ኃጢአተኞች ተደርገን ከታየን፣ ታዲያ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነው ማለት ነው? በጭራሽ! +18 በአንድ ወቅት እኔው ራሴ ያፈረስኳቸውን እነዚያኑ ነገሮች መልሼ የምገነባ ከሆነ ሕግ ተላላፊ መሆኔን አሳያለሁ ማለት ነው። +19 ለአምላክ ሕያው መሆን እችል ዘንድ በሕጉ በኩል ለሕጉ ሞቻለሁና።*+ +20 እኔ አሁን ከክርስቶስ ጋር በእንጨት ላይ ተቸንክሬአለሁ።+ ከዚህ በኋላ የምኖረው እኔ ሳልሆን+ ከእኔ ጋር አንድ ሆኖ የሚኖረው ክርስቶስ ነው። አሁን በሥጋ የምኖረውን ሕይወት የምኖረው በወደደኝና ለእኔ ሲል ራሱን አሳልፎ በሰጠው+ በአምላክ ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው።+ +21 የአምላክን ጸጋ+ወደ ጎን ገሸሽ አላደርግም፤* ጽድቅ የሚገኘው በሕግ አማካኝነት ከሆነማ ክርስቶስ የሞተው እንዲያው በከንቱ ነው።+ +4 እንግዲህ ይህን እላለሁ፦ ወራሹ የሁሉም ነገር ጌታ ቢሆንም እንኳ ሕፃን እስከሆነ ድረስ ከባሪያ በምንም አይለይም፤ +2 ይልቁንም አባቱ አስቀድሞ የወሰነው ቀን እስኪደርስ ድረስ በሞግዚቶችና በመጋቢዎች ሥር ሆኖ ይቆያል። +3 በተመሳሳይ እኛም ልጆች በነበርንበት ጊዜ በዓለም ውስጥ ላሉ ተራ ነገሮች ባሪያ ሆነን ቆይተናል።+ +4 ሆኖም ዘመኑ ሙሉ በሙሉ የሚጠናቀቅበት ጊዜ ሲደርስ አምላክ ከሴት የተወለደውንና+ በሕግ ሥር የነበረውን ልጁን ላከ፤+ +5 ይህን ያደረገው እኛን ልጆቹ አድርጎ መውሰድ ይችል ዘንድ+ በሕግ ሥር ያሉትን ዋጅቶ ነፃ ለማውጣት ነው።+ +6 አሁን እናንተ ልጆች ስለሆናችሁ አምላክ የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን+ ልኳል፤+ ይህም መንፈስ “አባ፣* አባት!” እያለ ይጣራል።+ +7 በመሆኑም ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅ ከሆንክ ደግሞ አምላክ ወራሽም አድርጎሃል።+ +8 ይሁንና አምላክን ከማወቃችሁ በፊት በእርግጥ አማልክት ላልሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ትገዙ ነበር። +9 አሁን ግን አምላክን አውቃችኋል፤ እንዲያውም አምላክ እናንተን አውቋችኋል፤ ታዲያ ደካማና ከንቱ ወደሆኑ ተራ ነገሮች መመለስና+ እንደገና ለእነዚህ ነገሮች ባሪያ መሆን ትፈልጋላችሁ?+ +10 ቀናትን፣ ወራትን፣+ ወቅቶችንና ዓመታትን በጥንቃቄ እየጠበቃችሁ ታከብራላችሁ። +11 የእናንተ ሁኔታ ያሳስበኛል፤ ምክንያቱም ለእናንተ የደከምኩት በከንቱ እንዳይሆን እሰጋለሁ። +12 ወንድሞች፣ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ፤ ምክንያቱም እኔም በአንድ ወቅት እንደ እናንተ ነበርኩ።+ እናንተ ምንም የበደላችሁኝ ነገር የለም። +13 በተጨማሪም ለመጀመሪያ ጊዜ ለእናንተ ምሥራቹን ለመስበክ አጋጣሚ ያገኘሁት በመታመሜ የተነሳ እንደነበር ታውቃላች���። +14 ሕመሜ ፈተና ሆኖባችሁ የነበረ ቢሆንም እንኳ አልናቃችሁኝም ወይም አልተጸየፋችሁኝም፤* ከዚህ ይልቅ እንደ አምላክ መልአክ ወይም እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ። +15 ታዲያ ያ ሁሉ ደስታችሁ የት ጠፋ? የሚቻል ቢሆን ኖሮ ዓይናችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደነበር እርግጠኛ ነኝ።+ +16 ታዲያ እውነቱን ስለምነግራችሁ ጠላት ሆንኩባችሁ ማለት ነው? +17 እነሱ ወደ ራሳቸው ሊስቧችሁ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፤ ይህን የሚያደርጉት ግን ለበጎ ሳይሆን እናንተን ከእኔ በማራቅ እነሱን አጥብቃችሁ እንድትከተሏቸው ለማድረግ ነው። +18 ይሁን እንጂ አንድ ሰው ምንጊዜም እናንተን አጥብቆ የሚፈልገው ለበጎ ዓላማ ከሆነ ጥሩ ነው፤ ይህም መሆን ያለበት እኔ ከእናንተ ጋር ስሆን ብቻ አይደለም፤ +19 የምወዳችሁ ልጆቼ፣+ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ በእናንተ ምክንያት እንደገና ምጥ ይዞኛል። +20 በእናንተ ግራ ስለተጋባሁ አሁን በመካከላችሁ ተገኝቼ ለየት ባለ መንገድ ላነጋግራችሁ ብችል ደስ ባለኝ ነበር። +21 እናንተ በሕግ ሥር መኖር የምትፈልጉ እስቲ ንገሩኝ፤ ሕጉ የሚለውን አትሰሙም? +22 ለምሳሌ ያህል፣ አብርሃም አንዱ ከአገልጋዪቱ፣+ ሌላው ደግሞ ከነፃዪቱ ሴት+ የተወለዱ ሁለት ወንዶች ልጆች እንደነበሩት ተጽፏል፤ +23 ሆኖም ከአገልጋዪቱ የተገኘው ልጅ የተወለደው በሥጋዊ መንገድ*+ ሲሆን ከነፃዪቱ ሴት የተገኘው ልጅ ደግሞ የተወለደው በተስፋ ቃል መሠረት ነው።+ +24 እነዚህ ሴቶች ሁለት ቃል ኪዳኖችን ስለሚወክሉ እነዚህ ነገሮች ምሳሌያዊ ትርጉም አላቸው፤ አንደኛው ቃል ኪዳን የተገባው በሲና ተራራ+ ሲሆን በዚህ ቃል ኪዳን ሥር ያሉት ልጆች ሁሉ ባሪያዎች ናቸው፤ ይህ ቃል ኪዳን ደግሞ አጋርን ያመለክታል። +25 አጋር፣ በዓረብ አገር የሚገኘውን የሲና ተራራ+ የምትወክል ሲሆን ዛሬ ካለችው ኢየሩሳሌም ጋር ትመሳሰላለች፤ ኢየሩሳሌም ከልጆቿ ጋር በባርነት ሥር ናትና። +26 ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን ነፃ ናት፤ እሷም እናታችን ናት። +27 “አንቺ የማትወልጂ መሃን ሴት፣ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ ምጥ የማታውቂ ሴት፣ እልል በይ፣ ጩኺም፤ ምክንያቱም ባል ካላት ሴት ይልቅ የተተወችው ሴት ልጆች እጅግ በዝተዋል” ተብሎ ተጽፏልና።+ +28 እንግዲህ ወንድሞች፣ እንደ ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ናችሁ።+ +29 ሆኖም ያን ጊዜ በሥጋዊ መንገድ* የተወለደው በመንፈስ የተወለደውን ማሳደድ እንደጀመረ+ ሁሉ አሁንም እንደዚያው ነው።+ +30 ይሁንና ቅዱስ መጽሐፉ ምን ይላል? “የአገልጋዪቱ ልጅ ከነፃዪቱ ልጅ ጋር በምንም ዓይነት አብሮ ስለማይወርስ አገልጋዪቱን ከነልጅዋ አባር።”+ +31 ስለዚህ ወንድሞች፣ እኛ የነፃዪቱ ልጆች እንጂ የአገልጋዪቱ ልጆች አይደለንም። +6 ወንድሞች፣ አንድ ሰው ሳያውቅ የተሳሳተ ጎዳና ቢከተል መንፈሳዊ ብቃት ያላችሁ እናንተ እንዲህ ዓይነቱን ሰው በገርነት* መንፈስ ለማስተካከል ጥረት አድርጉ።+ ይሁንና እናንተም ፈተና ላይ እንዳትወድቁ+ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።+ +2 አንዳችሁ የሌላውን ከባድ ሸክም ተሸከሙ፤+ በዚህ መንገድ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።+ +3 አንድ ሰው ምንም ሳይሆን ራሱን ከፍ አድርጎ የሚመለከት ከሆነ+ ራሱን እያታለለ ነው። +4 ከዚህ ይልቅ እያንዳንዱ ሰው የራሱን ተግባር ይመርምር፤+ ከዚያም ራሱን ከሌላ ሰው ጋር ሳያወዳድር+ ከራሱ ጋር ብቻ በተያያዘ እጅግ የሚደሰትበት ነገር ያገኛል። +5 እያንዳንዱ የራሱን የኃላፊነት ሸክም ይሸከማልና።+ +6 ከዚህም በተጨማሪ ቃሉን በመማር ላይ ያለ ማንኛውም ሰው፣ ይህን ትምህርት* ከሚያስተምረው ሰው ጋር መልካም ነገሮችን ሁሉ ይካፈል።+ +7 አትታለሉ፤ አምላክ አይዘበትበትም። አንድ ሰው ምንም ዘራ ምን ያንኑ መልሶ ያጭዳል፤+ +8 ምክንያቱም ለሥጋው ብሎ የሚዘራ ከሥጋው መበስበስን ያጭዳል፤ ለመንፈስ ብሎ የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለም ሕይወት ያጭዳል።+ +9 ካልታከትን* ጊዜው ሲደርስ ስለምናጭድ ተስፋ ቆርጠን መልካም ሥራ መሥራታችንን አንተው።+ +10 እንግዲያው ይህን ለማድረግ የሚያስችል አጋጣሚ* እስካገኘን ድረስ ለሁሉም፣ በተለይ ደግሞ በእምነት ለሚዛመዱን ሰዎች መልካም እናድርግ። +11 በራሴ እጅ እንዴት ባሉ ትላልቅ ፊደላት እንደጻፍኩላችሁ ተመልከቱ። +12 በሥጋ ተቀባይነት ለማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ* እንድትገረዙ ሊያስገድዷችሁ ይሞክራሉ፤ ይህን የሚያደርጉት ግን በክርስቶስ የመከራ እንጨት* ሳቢያ ስደት እንዳይደርስባቸው ነው። +13 እነሱ እንድትገረዙ የሚፈልጉት በእናንተ ሥጋ ለመኩራራት ብለው ነው እንጂ የተገረዙት ራሳቸውም እንኳ ሕጉን አይጠብቁም።+ +14 ይሁንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የመከራ እንጨት* ካልሆነ በስተቀር በሌላ ነገር ፈጽሞ መኩራራት አልፈልግም፤+ በእሱ የተነሳ፣ በእኔ አመለካከት ዓለም ሞቷል፤* በዓለም አመለካከት ደግሞ እኔ ሞቻለሁ።* +15 መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም፤+ ከዚህ ይልቅ የሚጠቅመው አዲስ ፍጥረት መሆን ነው።+ +16 ይህን የሥነ ምግባር ደንብ በመከተል በሥርዓት በሚመላለሱ ሁሉ ይኸውም በአምላክ እስራኤል+ ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን። +17 የኢየሱስ ባሪያ መሆኔን የሚያሳይ መለያ ምልክት በሰውነቴ ላይ ስላለ+ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አያስቸግረኝ። +18 ወንድሞች፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከምታሳዩት መንፈስ ጋር ይሁን። አሜን። +5 ክርስቶስ ነፃ ያወጣን እንዲህ ዓይነት ነፃነት እንድናገኝ ነው። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤+ ዳግመኛ ራሳችሁን በባርነት ቀንበር አታስጠምዱ።+ +2 እኔ ጳውሎስ፣ የምትገረዙ ከሆነ ክርስቶስ ለእናንተ ምንም እንደማይጠቅማችሁ አሳውቃችኋለሁ።+ +3 የሚገረዝ እያንዳንዱ ሰው መላውን ሕግ የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት ዳግመኛ አሳስበዋለሁ።+ +4 እናንተ በሕግ አማካኝነት ለመጽደቅ ስለምትጥሩ ከክርስቶስ ተለይታችኋል፤+ ከጸጋውም ርቃችኋል። +5 እኛ ግን ተስፋ የምናደርገውን በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ በመንፈስ አማካኝነት በጉጉት እንጠባበቃለን። +6 ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ላላቸው በፍቅር የሚመራ እምነት እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ ፋይዳ የለውም።+ +7 በአግባቡ ትሮጡ ነበር፤+ ታዲያ ለእውነት መታዘዛችሁን እንዳትቀጥሉ እንቅፋት የሆነባችሁ ማን ነው? +8 እንዲህ ያለው ማግባቢያ እየጠራችሁ ካለው የመጣ አይደለም። +9 ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ ያቦካል።+ +10 ከጌታ ጋር አንድነት ያላችሁ ሁሉ+ የተለየ ሐሳብ እንደማይኖራችሁ እተማመናለሁ፤ ሆኖም እያወካችሁ+ ያለው ማንም ይሁን ማን የሚገባውን ፍርድ ይቀበላል። +11 ወንድሞች፣ እኔ አሁንም ስለ መገረዝ እየሰበክሁ ከሆነ እስካሁን ለምን ስደት ይደርስብኛል? እንደዚያማ ቢሆን ኖሮ የመከራው እንጨት* እንቅፋት+ መሆኑ በቀረ ነበር። +12 ሊያውኳችሁ እየሞከሩ ያሉት ሰዎች ከናካቴው ቢሰለቡ* ደስታዬ ነው። +13 ወንድሞች፣ የተጠራችሁት ነፃ እንድትወጡ ነው፤ ብቻ ይህን ነፃነት የሥጋን ፍላጎት ለማርካት አትጠቀሙበት፤+ ይልቁንም አንዳችሁ ሌላውን በፍቅር አገልግሉ።+ +14 መላው ሕግ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ” በሚለው አንድ ትእዛዝ ተፈጽሟልና።*+ +15 ይሁንና እርስ በርሳችሁ መነካከሳችሁንና መባላታችሁን ካልተዋችሁ+ እርስ በርስ ልትጠፋፉ ስለምትችሉ ተጠንቀቁ።+ +16 እኔ ግን በመንፈስ መመላለሳችሁን ቀጥሉ እላለሁ፤+ እንዲህ ካደረጋችሁ የሥጋን ምኞት ከቶ አትፈጽሙም።+ +17 የሥጋ ፍላጎት ከመንፈስ ፍላጎት ጋር፣ የመንፈስ ፍላጎት ደግሞ ���ሥጋ ፍላጎት ጋር አይጣጣምም፤ እነዚህ እርስ በርሳቸው ይቃረናሉ። ስለሆነም ማድረግ የምትፈልጉትን አታደርጉም።+ +18 በተጨማሪም በመንፈስ የምትመሩ ከሆነ በሕግ ሥር አይደላችሁም። +19 የሥጋ ሥራዎች በግልጽ የታወቁ ናቸው፤ እነሱም፦ የፆታ ብልግና፣*+ ርኩሰት፣ ዓይን ያወጣ ምግባር፣*+ +20 ጣዖት አምልኮ፣ መናፍስታዊ ድርጊት፣*+ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣ ጭቅጭቅ፣ መከፋፈል፣ መናፍቅነት፣ +21 ምቀኝነት፣ ሰካራምነት፣+ መረን የለቀቀ ፈንጠዝያና እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው።+ እነዚህን በተመለከተ አስቀድሜ እንዳስጠነቀቅኳችሁ ሁሉ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽሙ* የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።+ +22 በሌላ በኩል ግን የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ደግነት፣ ጥሩነት፣+ እምነት፣ +23 ገርነት፣* ራስን መግዛት ነው።+ እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚከለክል ሕግ የለም። +24 ከዚህም በተጨማሪ የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከመጥፎ ምኞቱና ፍላጎቱ ጋር በእንጨት ላይ ቸንክረውታል።*+ +25 በመንፈስ የምንኖር ከሆነ መንፈስ የሚሰጠንን አመራር በመከተል ምንጊዜም በሥርዓት እንመላለስ።+ +26 በመካከላችን የፉክክር መንፈስ በማነሳሳትና+ አንዳችን ሌላውን በመመቅኘት በከንቱ አንመካ።+ +3 በዚህ ምክንያት እኔ ጳውሎስ ከአሕዛብ ወገን ለሆናችሁት ለእናንተ ስል የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ሆኛለሁ።+ +2 ለእናንተ ጥቅም ሲባል ስለተሰጠኝ የአምላክ ጸጋ መጋቢነት+ በእርግጥ ሰምታችኋል፤ +3 ቀደም ሲል በአጭሩ እንደጻፍኩት ቅዱሱ ሚስጥር ተገልጦልኛል። +4 በመሆኑም ይህን ስታነቡ ስለ ክርስቶስ ቅዱስ ሚስጥር+ ያለኝን ግንዛቤ መረዳት ትችላላችሁ። +5 ይህ ሚስጥር አሁን ለቅዱሳን ሐዋርያትና ነቢያት በመንፈስ እንደተገለጠው ባለፉት ትውልዶች ለነበሩ የሰው ልጆች አልተገለጠም ነበር።+ +6 ሚስጥሩ ይህ ነው፦ ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰዎች ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ በመሆን በምሥራቹ አማካኝነት አብረው ወራሾች፣ የአንድ አካል ክፍሎችና+ ከእኛ ጋር የተስፋው ተካፋዮች ይሆናሉ። +7 አምላክ የኃይሉ መግለጫ አድርጎ በሰጠኝ ነፃ ስጦታ ይኸውም በጸጋው አማካኝነት የዚህ ሚስጥር አገልጋይ ሆኛለሁ።+ +8 ከቅዱሳን ሁሉ ለማንስ+ ለእኔ ይህ ጸጋ ተሰጠኝ፤+ ይህም ሊደረስበት ስለማይችለው የክርስቶስ ብልጽግና የሚገልጸውን ምሥራች ለአሕዛብ እንዳውጅ +9 እንዲሁም ሁሉን ነገር የፈጠረው አምላክ ለብዙ ዘመናት ሰውሮት የቆየው ቅዱሱ ሚስጥር ሥራ ላይ የዋለበትን መንገድ ሰዎች ሁሉ እንዲያስተውሉ እረዳቸው ዘንድ ነው።+ +10 ይህ የሆነው በርካታ ገጽታዎች ያሉት የአምላክ ጥበብ በሰማያዊ ስፍራ ላሉት መስተዳድሮችና ባለሥልጣናት አሁን በጉባኤው አማካኝነት ግልጽ ይሆን ዘንድ ነው።+ +11 ይህም አምላክ ከጌታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ ባዘጋጀው ዘላለማዊ ዓላማ መሠረት ነው፤+ +12 በእሱም አማካኝነት ይህ የመናገር ነፃነት አለን፤ በክርስቶስ ላይ ባለን እምነት አማካኝነትም በልበ ሙሉነት ወደ አምላክ በነፃነት መቅረብ እንችላለን።+ +13 ስለዚህ ለእናንተ ስል እየደረሰብኝ ባለው መከራ የተነሳ ተስፋ እንዳትቆርጡ አደራ እላችኋለሁ፤ ይህ ለእናንተ ክብር ነውና።+ +14 በዚህም ምክንያት በአብ ፊት ለመጸለይ እንበረከካለሁ፤ +15 በሰማይና በምድር ያለ እያንዳንዱ ቤተሰብ ስያሜውን ያገኘው ከእሱ ነው። +16 እሱ ታላቅ ክብር ያለው እንደመሆኑ መጠን ውስጣዊውን ሰውነታችሁን የሚያጠነክር ኃይል+ በመንፈሱ አማካኝነት እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤ +17 ደግሞም በእምነታችሁ አማካኝነት ክርስቶስ ከፍቅር+ ጋር በልባችሁ ውስጥ እንዲያድር እጸልያለሁ�� ሥር እንድትሰዱና+ በመሠረቱ ላይ እንድትታነጹ+ ያስችላችሁ ዘንድ እለምናለሁ፤ +18 ይህም ስፋቱ፣ ርዝመቱ፣ ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደሆነ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር በሚገባ መረዳት እንድትችሉ +19 እንዲሁም አምላክ በሚሰጠው ሙላት ሁሉ ትሞሉ ዘንድ ከእውቀት በላይ የሆነውን የክርስቶስ ፍቅር እንድታውቁ ነው።+ +20 እንግዲህ በእኛ ውስጥ ከሚሠራው ኃይሉ ጋር በሚስማማ ሁኔታ፣+ ከምንጠይቀው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚችለው+ +21 ለእሱ በጉባኤው አማካኝነትና በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት በትውልዶች ሁሉ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። +1 በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ በኤፌሶን+ ላሉ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ላላቸው ታማኝ የሆኑ ቅዱሳን፦ +3 ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት* ሁሉ ስለባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይወደስ፤+ +4 በእሱ ፊት ፍቅር እንድናሳይ እንዲሁም ቅዱሳንና እንከን የለሽ ሆነን እንድንገኝ+ ዓለም ከመመሥረቱ* በፊት ከክርስቶስ ጋር አንድ እንድንሆን መርጦናልና። +5 ደግሞም እሱ እንደወደደና እንደ በጎ ፈቃዱ+ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የገዛ ራሱ ልጆች አድርጎ ሊወስደን+ አስቀድሞ ወስኗል፤+ +6 ይኸውም በተወደደው ልጁ+ አማካኝነት በደግነት ለእኛ በሰጠው ክቡር በሆነው ጸጋው+ የተነሳ እንዲወደስ ነው። +7 በተትረፈረፈ ጸጋው መሠረት በልጁ ደም አማካኝነት ቤዛውን በመክፈሉ ነፃ ወጥተናል፤+ አዎ፣ ለበደላችን ይቅርታ አግኝተናል።+ +8 ጸጋውንም ከጥበብና ከማስተዋል ሁሉ ጋር አትረፍርፎ ሰጥቶናል፤ +9 ይህን ያደረገው የፈቃዱን ቅዱስ ሚስጥር ለእኛ በማሳወቅ ነው።+ ይህ ሚስጥር ደግሞ እሱ ራሱ ካሰበው ዓላማው ጋር የሚስማማ ነው፤ +10 ዓላማውም በተወሰኑት ዘመናት ማብቂያ ላይ አንድ አስተዳደር ለማቋቋም ይኸውም ሁሉንም ነገሮች ማለትም በሰማያት የሚሆኑ ነገሮችንና በምድር የሚሆኑ ነገሮችን በክርስቶስ አንድ ላይ ለመሰብሰብ ነው።+ አዎ፣ በእሱ አማካኝነት ሁሉም ነገሮች ይሰበሰባሉ፤ +11 እኛም ከእሱ ጋር አንድነት ያለን ሲሆን ወራሾች እንድንሆንም ተመርጠናል፤+ ምክንያቱም ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ሁሉንም ነገር በወሰነው መንገድ የሚያከናውነው እሱ ከዓላማው ጋር በሚስማማ ሁኔታ አስቀድሞ መርጦናል፤ +12 ይህም የሆነው በክርስቶስ ተስፋ በማድረግ የመጀመሪያ የሆንነው እኛ አምላክን ከፍ ከፍ እንድናደርግና እንድናወድስ ነው። +13 ይሁንና እናንተም የእውነትን ቃል ማለትም ስለ መዳናችሁ የሚገልጸውን ምሥራች ከሰማችሁ በኋላ በእሱ ተስፋ አድርጋችኋል። ካመናችሁ በኋላ በእሱ አማካኝነት፣ ቃል በተገባው መንፈስ ቅዱስ ታትማችኋል፤+ +14 ይህም ለአምላክ ታላቅ ምስጋና ያስገኝ ዘንድ የራሱ ንብረት+ የሆኑትን በቤዛ+ አማካኝነት ነፃ ለማውጣት ለውርሻችን አስቀድሞ የተሰጠ ማረጋገጫ* ነው።+ +15 ስለዚህ በጌታ ኢየሱስ ላይ ስላላችሁ እምነት እንዲሁም ለቅዱሳን ሁሉ ስለምታሳዩት ፍቅር ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ +16 ስለ እናንተ ምስጋና ማቅረቤን አላቋረጥኩም። ወደፊትም ስለ እናንተ መጸለዬን እቀጥላለሁ፤ +17 የክብር አባት የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ስለ እሱ ትክክለኛ እውቀት ስትቀስሙ የጥበብ መንፈስ እንዲሰጣችሁና እሱ የሚገልጣቸውን ነገሮች መረዳት እንድትችሉ እጸልያለሁ።+ +18 የልባችሁ ዓይኖች እንዲበሩ አድርጓል፤ ይህን ያደረገው ለምን ዓይነት ተስፋ እንደጠራችሁ እንድታውቁ፣ ለቅዱሳን ውርሻ አድርጎ የሚሰጠው ታላቅ ብልጽግና ምን እንደሆነ እንድትረዱ+ +19 እንዲሁም ታላቅ ኃይሉ ለእኛ ለምናምነው ምን ያህል የላቀ እንደሆነ እንድታውቁ ነው።+ የዚህ ኃይል ታላቅነት፣ እጅግ ከፍተኛ የሆነው ብርታቱ በሚያከናውነው ሥራ ታይቷል፤ +20 ክርስቶስን ከሞት ባስነሳውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ባስቀመጠው+ ጊዜ ይህን ኃይሉን ተጠቅሟል፤ +21 በዚህ ሥርዓት* ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ጭምር ከየትኛውም መስተዳድር፣ ሥልጣን፣ ኃይልና ጌትነት እንዲሁም ከተሰየመው ከየትኛውም ስም በላይ እጅግ የላቀ ቦታ ሰጥቶታል።+ +22 በተጨማሪም ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዛለት፤+ ከጉባኤው ጋር በተያያዘም በሁሉ ነገር ላይ ራስ አደረገው፤+ +23 ጉባኤው የእሱ አካል+ ከመሆኑም በላይ በእሱ የተሞላ ነው፤ እሱ ደግሞ ሁሉንም ነገር በሁሉ የሚሞላ ነው። +2 በተጨማሪም፣ እናንተ በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ምክንያት ሙታን የነበራችሁ ቢሆንም አምላክ ሕያው አድርጓችኋል፤+ +2 በዚያን ጊዜ የዚህን ዓለም ሥርዓት* ተከትላችሁ፣+ የአየሩ ሥልጣን ገዢ+ በሚፈልገው መንገድ ትመላለሱ ነበር፤ ይህም አየር በማይታዘዙት ልጆች ላይ አሁን ተጽዕኖ እያሳደረ ያለ መንፈስ ነው።+ +3 አዎ፣ እኛ ሁላችን በአንድ ወቅት የሥጋችንንና የሐሳባችንን ፈቃድ እየፈጸምን+ ከሥጋችን ፍላጎት ጋር ተስማምተን በመካከላቸው እንኖር ነበር፤+ እንደ ሌሎቹ ሁሉ እኛም በተፈጥሯችን የቁጣ ልጆች ነበርን።+ +4 ሆኖም አምላክ ምሕረቱ ብዙ ነው፤+ እኛን ከወደደበት ታላቅ ፍቅሩ የተነሳ+ +5 በበደላችን ሙታን በነበርንበት ጊዜም እንኳ ሕያዋን አድርጎ ከክርስቶስ ጋር አንድ አደረገን፤+ እንደ እውነቱ ከሆነ የዳናችሁት በጸጋ ነው። +6 ደግሞም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ስላለን ከእሱ ጋር አስነሳን፤ እንዲሁም ከእሱ ጋር በሰማያዊ ስፍራ አስቀመጠን፤+ +7 ይህን ያደረገው ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ላለን ለእኛ በቸርነቱ* የገለጠውን ወደር የሌለውን የጸጋውን ብልጽግና በመጪዎቹ ሥርዓቶች* ያሳይ ዘንድ ነው። +8 እናንተ የዳናችሁት በእምነት አማካኝነት በዚህ ጸጋ ነው፤+ ይህም እናንተ በራሳችሁ ያገኛችሁት አይደለም፤ ይልቁንም የአምላክ ስጦታ ነው። +9 ማንም ሰው የሚኩራራበት ምክንያት እንዳይኖር ይህ በሥራ የሚገኝ አይደለም።+ +10 እኛ የአምላክ የእጁ ሥራዎች ነን፤ ደግሞም አምላክ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባለን አንድነት+ የፈጠረን፣+ እኛ እንድንሠራቸው አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራዎች እንድንሠራ ነው። +11 ስለዚህ በሰው እጅ በሥጋ “የተገረዙት፣” በአንድ ወቅት በትውልድ አሕዛብ የነበራችሁትን እናንተን “ያልተገረዙ” ይሏችሁ እንደነበር አስታውሱ። +12 በዚያን ጊዜ ከእስራኤል ብሔር ተገልላችሁና ለተስፋው ቃል ኪዳኖች+ ባዕዳን ሆናችሁ በዓለም ውስጥ ያለተስፋና ያለአምላክ እንዲሁም ያለክርስቶስ ትኖሩ እንደነበረ አስታውሱ።+ +13 ሆኖም እናንተ በአንድ ወቅት ርቃችሁ የነበራችሁ አሁን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ያላችሁ ሆናችኋል፤ እንዲሁም በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። +14 ሁለቱን ወገኖች አንድ ያደረገውና+ ይለያያቸው የነበረውን በመካከል ያለ ግድግዳ ያፈረሰው+ እሱ ሰላም አምጥቶልናልና።+ +15 ሁለቱን ወገኖች ከራሱ ጋር አንድነት እንዲኖራቸው በማድረግ አንድ አዲስ ሰው መፍጠርና+ ሰላም ማስፈን ይችል ዘንድ በሥጋው አማካኝነት ጠላትነትን ይኸውም ትእዛዛትንና ድንጋጌዎችን የያዘውን ሕግ አስወገደ፤ +16 እንዲሁም ይህን ያደረገው በመከራው እንጨት*+ ሁለቱን ወገኖች አንድ አካል አድርጎ ከአምላክ ጋር ሙሉ በሙሉ ለማስታረቅ ነው፤ ምክንያቱም በገዛ አካሉ ጠላትነትን አስወግዷል።+ +17 እሱም መጥቶ ከአምላክ ርቃችሁ ለነበራችሁት ለእናንተም ሆነ ወደ እሱ ቀርበው ለነበሩት የሰላምን ምሥራች አወጀ፤ +18 ምክንያቱም እኛ፣ የሁለቱም ወገን ሕዝቦች በእሱ አማካኝነት በአንድ መንፈስ ወደ አብ በነፃነት መቅረብ እንችላለን። +19 ስለዚህ እናንተ ከዚህ በኋላ እንግዶችና ባዕዳን አይደላችሁም፤+ ከዚህ ይልቅ ከቅዱሳን ጋር የአንድ አገር ዜጎችና+ የአምላክ ቤተሰብ አባላት ናችሁ፤+ +20 እንዲሁም በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ተገንብታችኋል፤+ ዋናው የመሠረት ድንጋይ* ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው።+ +21 ሕንጻው በሙሉ ከክርስቶስ ጋር አንድ ላይ በመሆን ልዩ ልዩ ክፍሎቹ ስምም ሆነው እየተገጣጠሙ+ የይሖዋ* ቅዱስ ቤተ መቅደስ ለመሆን በማደግ ላይ ነው።+ +22 እናንተም ከእሱ ጋር ባላችሁ አንድነት አምላክ በመንፈስ የሚኖርበት ቦታ ለመሆን አንድ ላይ እየተገነባችሁ ነው።+ +4 እንግዲህ በጌታ እስረኛ የሆንኩ+ እኔ ከተጠራችሁበት ጥሪ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤+ +2 በፍጹም ትሕትናና+ ገርነት፣ በትዕግሥት+ እንዲሁም እርስ በርሳችሁ በፍቅር በመቻቻል ኑሩ፤+ +3 አንድ ላይ በሚያስተሳስረው የሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ልባዊ ጥረት አድርጉ።+ +4 እናንተ የተጠራችሁበት አንድ ተስፋ+ እንዳለ ሁሉ አንድ አካልና+ አንድ መንፈስ+ አለ፤ +5 አንድ ጌታ፣+ አንድ እምነት፣ አንድ ጥምቀት አለ፤ +6 ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ፣ በሁሉም አማካኝነት የሚሠራና በሁሉም ላይ የሚሠራ የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ። +7 ደግሞም ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጥቶናል፤ ይህን የተቀበልነው ክርስቶስ ነፃ ስጦታውን ባከፋፈለን መሠረት ነው።+ +8 እንዲህ ይላልና፦ “ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮኞችን ወሰደ፤ ሰዎችንም ስጦታ አድርጎ ሰጠ።”+ +9 ታዲያ “ወደ ላይ ወጣ” የሚለው አነጋገር ምን ማለት ነው? ወደ ታች ይኸውም ወደ ምድርም ወርዷል ማለት ነው። +10 ሁሉንም ነገር ወደ ሙላት ያደርስ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ+ የወጣው+ ያው ወደ ታች የወረደው ራሱ ነው። +11 እንዲሁም አንዳንዶቹን ሐዋርያት፣+ አንዳንዶቹን ነቢያት፣+ አንዳንዶቹን ወንጌላውያን፣*+ አንዳንዶቹን ደግሞ እረኞችና አስተማሪዎች+ አድርጎ ሰጠ፤ +12 ይህን ያደረገው ቅዱሳንን እንዲያስተካክሉ፣* ሌሎችን እንዲያገለግሉና የክርስቶስን አካል* እንዲገነቡ ነው፤+ +13 ይህም ሁላችንም በእምነትና ስለ አምላክ ልጅ ትክክለኛ እውቀት በመቅሰም ወደሚገኘው አንድነት እንዲሁም ሙሉ ሰው ወደ መሆን*+ ይኸውም እንደ ክርስቶስ የተሟላ የጉልምስና ደረጃ ላይ እስክንደርስ ድረስ ነው። +14 በመሆኑም ከእንግዲህ ሕፃናት መሆን የለብንም፤ በማዕበል የምንነዳ ይመስል በማንኛውም የትምህርት ነፋስ፣+ በሰዎች የማታለያ ዘዴና በተንኮል በተወጠነ አሳሳች ሐሳብ የምንንገዋለልና ወዲያና ወዲህ የምንል መሆን የለብንም። +15 ከዚህ ይልቅ እውነትን በመናገር በሁሉም ነገር ወደ እሱ ይኸውም የአካሉ ራስ ወደሆነው ወደ ክርስቶስ+ በፍቅር እንደግ። +16 በእሱ አማካኝነት የአካል ክፍሎች ሁሉ+ አስፈላጊ የሆነውን ነገር በሚያሟላው በእያንዳንዱ መገጣጠሚያ አማካኝነት እርስ በርስ ተስማምተው ተገጣጥመዋል። እያንዳንዱ የአካል ክፍል በአግባቡ ሥራውን ማከናወኑ አካሉ ራሱን በፍቅር እያነጸ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያበረክታል።+ +17 ስለዚህ አሕዛብ በአእምሯቸው ከንቱነት*+ እንደሚመላለሱ እናንተም ከእንግዲህ እንዳትመላለሱ በጌታ እናገራለሁ እንዲሁም እመሠክራለሁ።+ +18 እነሱ በውስጣቸው ካለው ድንቁርናና ከልባቸው መደንደን የተነሳ አእምሯቸው ጨልሟል፤ እንዲሁም ከአምላክ ከሚገኘው ሕይወት ርቀዋል። +19 የሥነ ምግባር ስሜታቸው ስለደነዘዘ በስግብግብነት ማንኛውንም ዓይነት ርኩሰት ለመፈጸም ራሳቸውን ዓይን ላወጣ ምግባር*+ አሳልፈው ሰጥተዋል። +20 እናንተ ግን ክርስቶስ እንዲህ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፤ +21 ይህ ሊሆን የሚችለው በእርግጥ ኢየሱስ ካስተማረው እውነት ጋር በሚስማማ መንገድ እሱን ከሰማችሁና ከእሱ ከተማራችሁ ነው። +22 ከቀድሞ አኗኗራችሁ ጋር የሚስማማውንና አታላይ በሆነው ምኞቱ እየተበላሸ የሚሄደውን+ አሮጌውን ስብዕናችሁን* አውልቃችሁ እንድትጥሉ+ ተምራችኋል። +23 ደግሞም አእምሯችሁን የሚያሠራው ኃይል* እየታደሰ ይሂድ፤+ +24 እንዲሁም እንደ አምላክ ፈቃድ የተፈጠረውንና ከእውነተኛ ጽድቅና ታማኝነት ጋር የሚስማማውን አዲሱን ስብዕና* መልበስ ይኖርባችኋል።+ +25 ስለዚህ አሁን አታላይነትን ስላስወገዳችሁ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ* ጋር እውነትን ተነጋገሩ፤+ ምክንያቱም ሁላችንም የአንድ አካል ክፍሎች ነን።+ +26 ተቆጡ፤ ሆኖም ኃጢአት አትሥሩ፤+ ተቆጥታችሁ እያለ ፀሐይ አይጥለቅባችሁ፤+ +27 ዲያብሎስ አጋጣሚ እንዲያገኝ አታድርጉ።*+ +28 የሚሰርቅ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ከዚህ ይልቅ ለተቸገረ ሰው የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በእጆቹ መልካም ተግባር እያከናወነ በትጋት ይሥራ።+ +29 እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎቹን ሊጠቅም የሚችል መልካም ቃል ብቻ+ እንጂ የበሰበሰ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።+ +30 በተጨማሪም በቤዛው ነፃ ለምትወጡበት+ ቀን የታተማችሁበትን+ የአምላክን ቅዱስ መንፈስ አታሳዝኑ።+ +31 የመረረ ጥላቻ፣+ ቁጣ፣ ንዴት፣ ጩኸትና ስድብ ሁሉ+ እንዲሁም ክፋት ሁሉ ከእናንተ መካከል ይወገድ።+ +32 ይልቁንም አንዳችሁ ለሌላው ደጎችና ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ፤+ አምላክ በክርስቶስ አማካኝነት በነፃ ይቅር እንዳላችሁ ሁሉ እናንተም እርስ በርሳችሁ በነፃ ይቅር ተባባሉ።+ +6 ልጆች ሆይ፣ ከጌታ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤+ ይህ የጽድቅ ተግባር ነውና። +2 “አባትህንና እናትህን አክብር”+ የሚለው የመጀመሪያው ትእዛዝ እንዲህ የሚል የተስፋ ቃል ይዟል፦ +3 “ይህም መልካም እንዲሆንልህና* ዕድሜህ በምድር ላይ እንዲረዝም ነው።” +4 አባቶች ሆይ፣ ልጆቻችሁን አታስመርሯቸው፤+ ከዚህ ይልቅ በይሖዋ* ተግሣጽና+ ምክር* አሳድጓቸው።+ +5 እናንተ ባሪያዎች ሆይ፣ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ ሁሉ ለሰብዓዊ ጌቶቻችሁ ከልብ በመነጨ ቅንነት፣ በአክብሮትና በፍርሃት ታዘዙ፤+ +6 ሰዎችን ለማስደሰት+ እንዲሁ ለታይታ ሳይሆን እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች የአምላክን ፈቃድ በሙሉ ነፍስ*+ በመፈጸም ታዘዟቸው። +7 ሰዎችን ሳይሆን ይሖዋን* እንደምታገለግሉ አድርጋችሁ በማሰብ በፈቃደኝነት አገልግሉ፤+ +8 ባሪያም ሆነ ነፃ ሰው፣ እያንዳንዱ ለሚያደርገው ማንኛውም መልካም ነገር ከይሖዋ* ወሮታ እንደሚቀበል ታውቃላችሁና።+ +9 እናንተም ጌቶች ሆይ፣ ለእነሱ እንዲሁ ዓይነት አመለካከት ይኑራችሁ፤ የእነሱም ሆነ የእናንተ ጌታ በሰማያት እንዳለና+ እሱ ደግሞ እንደማያዳላ ስለምታውቁ አታስፈራሯቸው። +10 በተረፈ ከጌታና ከታላቅ ብርታቱ ኃይል+ ማግኘታችሁን እንድትቀጥሉ አሳስባችኋለሁ። +11 የዲያብሎስን መሠሪ ዘዴዎች* መቋቋም እንድትችሉ ከአምላክ የሚገኘውን ሙሉ የጦር ትጥቅ ልበሱ፤+ +12 ምክንያቱም የምንታገለው+ ከደምና ከሥጋ ጋር ሳይሆን ከመንግሥታት፣ ከሥልጣናት፣ ይህን ጨለማ ከሚቆጣጠሩ የዓለም ገዢዎች እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከክፉ መንፈሳዊ ኃይሎች ጋር ነው።+ +13 ስለሆነም ክፉው ቀን በሚመጣበት ጊዜ መቋቋም እንድትችሉና ሁሉንም ነገር ከፈጸማችሁ በኋላ ጸንታችሁ መቆም እንድትችሉ ከአምላክ የሚገኘውን ሙሉ የጦር ትጥቅ አንሱ።+ +14 እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ቀበቶ ታጥቃችሁና+ የጽድቅን ጥሩር ለብሳችሁ+ ጸንታችሁ ቁሙ፤ +15 እንዲሁም የሰላምን ምሥራች ለማወጅ ዝግጁ በመ���ን እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ።*+ +16 ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች* ሁሉ ማምከን የምትችሉበትን ትልቅ የእምነት ጋሻ አንሱ።+ +17 በተጨማሪም የመዳንን የራስ ቁር አድርጉ፤+ እንዲሁም የመንፈስን ሰይፍ ይኸውም የአምላክን ቃል ያዙ፤+ +18 ከዚህም በተጨማሪ በሁሉም ዓይነት ጸሎትና+ ምልጃ በማንኛውም ጊዜ በመንፈስ መጸለያችሁን ቀጥሉ።+ ለዚህም ሲባል ዘወትር ንቁ ሁኑ፤ እንዲሁም ስለ ቅዱሳን ሁሉ ምልጃ አቅርቡ። +19 የምሥራቹን ቅዱስ ሚስጥር በድፍረት ለሌሎች ማሳወቅ እንድችል አፌን በምከፍትበት ጊዜ የምናገረው ቃል እንዲሰጠኝ ለእኔም ጸልዩልኝ፤+ +20 በሰንሰለት የታሰረ አምባሳደር ሆኜ እያገለገልኩ+ ያለሁት ለዚሁ ምሥራች ነው፤ ስለ ምሥራቹ የሚገባኝን ያህል በድፍረት መናገር እንድችል ጸልዩልኝ። +21 እንግዲህ ስለ እኔ እንዲሁም እያከናወንኩ ስላለሁት ነገር እናንተም እንድታውቁ የተወደደ ወንድማችንና በጌታ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ቲኪቆስ+ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል።+ +22 በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለን እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያጽናና ለዚሁ ዓላማ ስል ወደ እናንተ እልከዋለሁ። +23 አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር ከእምነት ጋር ለወንድሞች ይድረስ። +24 ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የማይከስም ፍቅር ካላቸው ሁሉ ጋር የአምላክ ጸጋ ይሁን። +5 ስለዚህ የተወደዳችሁ ልጆቹ በመሆን አምላክን የምትመስሉ ሁኑ፤+ +2 ክርስቶስ እንደወደደንና*+ ጥሩ መዓዛ እንዳለው ሽታ ራሱን ስለ እኛ* መባና መሥዋዕት አድርጎ ለአምላክ እንደሰጠ+ ሁሉ እናንተም በፍቅር መመላለሳችሁን ቀጥሉ።+ +3 ለቅዱሳን የማይገባ ስለሆነ የፆታ ብልግናና* ማንኛውም ዓይነት ርኩሰት ወይም ስግብግብነት በመካከላችሁ ከቶ አይነሳ፤+ +4 አሳፋሪ ምግባር፣ የማይረባ ንግግርም ሆነ ጸያፍ ቀልድ የማይገቡ ነገሮች ናቸው፤+ ከዚህ ይልቅ አምላክን የምታመሰግኑ ሁኑ።+ +5 እንደምታውቁትና በሚገባ እንደምትገነዘቡት ሴሰኛ*+ ወይም ርኩስ ወይም ስግብግብ+ ማለትም ጣዖት አምላኪ የሆነ ማንኛውም ሰው በክርስቶስና በአምላክ መንግሥት ምንም ውርሻ የለውም።+ +6 በእነዚህ ነገሮች ምክንያት የአምላክ ቁጣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ ስለሚመጣ ማንም በከንቱ ንግግር አያታላችሁ። +7 ስለዚህ ከእነዚህ ሰዎች ጋር አትተባበሩ፤ +8 እናንተ በአንድ ወቅት ጨለማ ውስጥ ነበራችሁና፤ አሁን ግን የጌታ በመሆናችሁ+ ብርሃን ውስጥ ናችሁ።+ የብርሃን ልጆች ሆናችሁ መመላለሳችሁን ቀጥሉ፤ +9 የብርሃን ፍሬ ሁሉንም ዓይነት ጥሩነት፣ ጽድቅና እውነት የያዘ ነውና።+ +10 በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ምን እንደሆነ ምንጊዜም መርምራችሁ አረጋግጡ፤+ +11 ፍሬ ቢስ በሆኑ የጨለማ ሥራዎች ከእነሱ ጋር መተባበራችሁን አቁሙ፤+ ይልቁንም አጋልጧቸው። +12 በድብቅ የሚፈጽሟቸው ነገሮች ለመናገር እንኳ የሚያሳፍሩ ናቸውና። +13 ደግሞም ተጋልጠው ይፋ የሚወጡት ነገሮች ሁሉ እንዲገለጡ የሚደረገው በብርሃን ነው፤ ስለዚህ የተጋለጡት ነገሮች በሙሉ ብርሃን ይሆናሉ። +14 በመሆኑም እንዲህ ተብሏል፦ “አንተ እንቅልፋም፣ ንቃ፤ ከሞትም ተነሳ፤+ ክርስቶስ በአንተ ላይ ያበራል።”+ +15 ስለዚህ የምትመላለሱት ጥበብ እንደጎደላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኛ ሰዎች መሆኑን ምንጊዜም በጥንቃቄ አስተውሉ፤ +16 ቀኖቹ ክፉዎች ስለሆኑ ጊዜያችሁን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት።*+ +17 ከዚህ የተነሳ የይሖዋ* ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ የማመዛዘን ችሎታ የጎደላችሁ አትሁኑ።+ +18 በተጨማሪም መረን ለለቀቀ ሕይወት* ስለሚዳርጋችሁ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤+ ከዚህ ይልቅ በመንፈስ መሞላታችሁን ቀጥሉ። +19 በ���ዝሙርና በውዳሴ እንዲሁም በመንፈሳዊ ዝማሬ እርስ በርሳችሁ* ተነጋገሩ፤ በልባችሁም ለይሖዋ* የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤+ +20 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም+ ስለ ሁሉም ነገር አምላካችንን እና አባታችንን ሁልጊዜ አመስግኑ።+ +21 ክርስቶስን በመፍራት አንዳችሁ ለሌላው ተገዙ።+ +22 ሚስቶች ለጌታ እንደሚገዙ ሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ፤+ +23 ምክንያቱም ክርስቶስ አካሉ ለሆነውና አዳኙ ለሆነለት ጉባኤ ራስ እንደሆነ+ ሁሉ ባልም የሚስቱ ራስ ነው።+ +24 ደግሞም ጉባኤው ለክርስቶስ እንደሚገዛ ሁሉ ሚስቶችም በሁሉም ነገር ለባሎቻቸው ይገዙ። +25 ባሎች ሆይ፣ ክርስቶስ ጉባኤውን እንደወደደና ራሱን ለጉባኤው አሳልፎ እንደሰጠ+ ሁሉ እናንተም ሚስቶቻችሁን መውደዳችሁን ቀጥሉ፤+ +26 እሱ ይህን ያደረገው ጉባኤውን በቃሉ አማካኝነት በውኃ አጥቦ በማንጻት ይቀድሰው ዘንድ ነው፤+ +27 ይህም ጉባኤውን ጉድፍ ወይም የቆዳ መጨማደድ ወይም እንዲህ ያሉ ጉድለቶች የማይገኙበት+ ቅዱስና እንከን የለሽ አድርጎ ውበቱን እንደጠበቀ ለራሱ ለማቅረብ ነው።+ +28 በተመሳሳይም ባሎች ሚስቶቻቸውን እንደ ገዛ አካላቸው አድርገው ሊወዷቸው ይገባል። ሚስቱን የሚወድ ሰው ራሱን ይወዳል፤ +29 የገዛ አካሉን* የሚጠላ ማንም ሰው የለምና፤ ከዚህ ይልቅ ይመግበዋል እንዲሁም ይሳሳለታል፤ ክርስቶስም ለጉባኤው ያደረገው እንደዚሁ ነው፤ +30 ምክንያቱም እኛ የእሱ አካል ክፍሎች ነን።+ +31 “ከዚህ የተነሳ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤* ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።”+ +32 ይህ ቅዱስ ሚስጥር+ ታላቅ ነው። እኔም እየተናገርኩ ያለሁት ስለ ክርስቶስና ስለ ጉባኤው ነው።+ +33 ይሁንና ከእናንተ እያንዳንዱ ራሱን እንደሚወድ ሁሉ ሚስቱንም ይውደድ፤+ በሌላ በኩል ደግሞ ሚስት ባሏን በጥልቅ ታክብር።+ +3 በመጨረሻም ወንድሞቼ፣ ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ።+ ያንኑ ነገር ደግሜ ብጽፍላችሁ እኔን አይታክተኝም፤ ይህ ደግሞ ለእናንተ ጠቃሚ ነው። +2 ከውሾች ተጠንቀቁ፤ ጎጂ ነገር ከሚያደርጉ ሰዎች ተጠንቀቁ፤ ሥጋን ከሚቆርጡ* ሰዎች ተጠንቀቁ።+ +3 እውነተኛውን ግርዘት የተገረዝነው እኛ ነንና፤+ እኛ በአምላክ መንፈስ፣ ቅዱስ አገልግሎት እናቀርባለን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ እንኩራራለን፤+ ደግሞም በሥጋ አንመካም፤ +4 ይሁንና በሥጋ የምመካበት ነገር አለኝ የሚል ማንም ቢኖር ያ ሰው እኔ ነኝ። በሥጋ የሚመካበት ነገር እንዳለው አድርጎ የሚያስብ ሌላ ማንም ሰው ቢኖር እኔ እበልጣለሁ፦ +5 በስምንተኛው ቀን የተገረዝኩና+ ከእስራኤል ብሔር፣ ከቢንያም ነገድ የተገኘሁ ስሆን ከዕብራውያን የተወለድኩ ዕብራዊ ነኝ፤+ ስለ ሕግ ከተነሳ ፈሪሳዊ ነበርኩ፤+ +6 ስለ ቅንዓት ከተነሳ በጉባኤው ላይ ስደት አደርስ ነበር፤+ ሕጉን በመታዘዝ ስለሚገኘው ጽድቅ ከተነሳ ደግሞ እንከን የማይገኝብኝ መሆኔን አስመሥክሬአለሁ። +7 ሆኖም ለእኔ ትርፍ የነበረውን ነገር ሁሉ ለክርስቶስ ስል እንደ ኪሳራ ቆጥሬዋለሁ።*+ +8 ከዚህም በላይ ስለ ጌታዬ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ከሚገልጸው የላቀ ዋጋ ያለው እውቀት አንጻር ሁሉንም ነገር እንደ ኪሳራ እቆጥረዋለሁ። ለእሱ ስል ሁሉንም ነገር አጥቻለሁ፤ ያጣሁትንም ነገር ሁሉ እንደ ጉድፍ* እቆጥረዋለሁ፤ ይህም ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ነው። +9 እንዲሁም ሕግ በመጠበቅ ባገኘሁት በራሴ ጽድቅ ሳይሆን በክርስቶስ በማመን+ በሚገኘው ጽድቅ+ ይኸውም በእምነት ላይ በተመሠረተው ከአምላክ በሚገኘው ጽድቅ+ ከክርስቶስ ጋር አንድ ለመሆን ነው። +10 ፍላጎቴ እሱንና የትንሣኤውን ኃይል+ ማወቅ እንዲሁም እሱ ለሞተው ዓይነት ሞት ራሴን አሳልፌ በመስጠት+ የሥቃዩ ተካፋይ+ መሆን ነው፤ +11 ደግሞም በተቻለ መጠን መ��መሪያ ላይ ትንሣኤ ከሚያገኙት መካከል መሆን ነው።+ +12 አሁን ሽልማቱን አግኝቻለሁ ወይም አሁን ወደ ፍጽምና ደርሻለሁ ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ እኔን የመረጠበትን ያን ነገር የራሴ ማድረግ እችል እንደሆነ ለማየት ጥረት እያደረግኩ ነው።+ +13 ወንድሞች፣ እኔ እንዳገኘሁት አድርጌ አላስብም፤ ነገር ግን ስለ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ፦ ከኋላዬ ያሉትን ነገሮች እየረሳሁ+ ከፊቴ ወዳሉት ነገሮች እንጠራራለሁ፤+ +14 አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የሚሰጠውን የሰማያዊውን ሕይወት+ ሽልማት አገኝ ዘንድ ግቡ ላይ ለመድረስ እየተጣጣርኩ ነው።+ +15 እንግዲህ ጎልማሳ+ የሆንነው እኛ ይህ አስተሳሰብ ይኑረን፤ በማንኛውም ረገድ ከዚህ የተለየ ሐሳብ ቢኖራችሁ አምላክ ትክክለኛውን አስተሳሰብ ይገልጥላችኋል። +16 ያም ሆነ ይህ ምንም ያህል እድገት ያደረግን ብንሆን በዚሁ መንገድ በአግባቡ ወደፊት መጓዛችንን እንቀጥል። +17 ወንድሞች፣ ሁላችሁም የእኔን ምሳሌ ተከተሉ፤+ እንዲሁም እኛ ከተውንላችሁ ምሳሌ ጋር በሚስማማ መንገድ የሚመላለሱትን ሁሉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። +18 የክርስቶስ የመከራ እንጨት* ጠላቶች ሆነው የሚመላለሱ ብዙዎች አሉና፤ ከዚህ በፊት ደጋግሜ እጠቅሳቸው ነበር፤ ሆኖም አሁን በእንባ ጭምር እጠቅሳቸዋለሁ። +19 መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሆዳቸው* አምላካቸው ነው፤ ሊያፍሩበት በሚገባው ነገር ይኩራራሉ፤ አእምሯቸው ደግሞ ያተኮረው በምድራዊ ነገሮች ላይ ነው።+ +20 እኛ ግን የሰማይ+ ዜጎች ነን፤+ ከዚያ የሚመጣውንም አዳኝ ይኸውም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በጉጉት እንጠባበቃለን፤+ +21 እሱም ክብር የተላበሰውን አካሉን እንዲመስል፣* ታላቅ ኃይሉን ተጠቅሞ ደካማውን አካላችንን ይለውጠዋል፤+ እንዲሁም ሁሉንም ነገር ለራሱ ያስገዛል።+ +1 የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያዎች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፣ ሽማግሌዎችንና የጉባኤ አገልጋዮችን+ ጨምሮ በፊልጵስዩስ+ ለሚገኙ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ላላቸው ቅዱሳን ሁሉ፦ +3 እናንተን ባስታወስኩ ቁጥር ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤ +4 ይህን የማደርገው ስለ እያንዳንዳችሁ ምልጃ ባቀረብኩ ጊዜ ሁሉ ነው። ደግሞም ምንጊዜም ምልጃ የማቀርበው በደስታ ነው፤+ +5 ምክንያቱም ምሥራቹን ከሰማችሁበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ለምሥራቹ አስተዋጽኦ* ስታደርጉ ቆይታችኋል። +6 በእናንተ መካከል መልካም ሥራ የጀመረው አምላክ፣ ሥራውን እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን+ ድረስ ወደ ፍጻሜ እንደሚያመጣው እርግጠኛ ነኝ።+ +7 ስለ እናንተ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ብዬ ማሰቤ ትክክል ነው፤ ምክንያቱም በእስራቴም+ ሆነ ለምሥራቹ ስሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን ለማድረግ ስጥር+ ከእኔ ጋር የጸጋው ተካፋዮች የሆናችሁት እናንተ በልቤ ውስጥ ናችሁ። +8 ክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ዓይነት ጥልቅ ፍቅር እናንተ ሁላችሁም በጣም እንደምትናፍቁኝ አምላክ ምሥክሬ ነው። +9 ፍቅራችሁ ከአምላክ ፈቃድ ትክክለኛ እውቀትና+ ጥልቅ ግንዛቤ+ ጋር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንዲሄድ መጸለዬን እቀጥላለሁ፤+ +10 ደግሞም ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ በማወቅ+ እስከ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንከን የማይገኝባችሁ እንድትሆኑና ሌሎችን እንዳታሰናክሉ+ +11 እንዲሁም ለአምላክ ክብርና ምስጋና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተትረፈረፈ የጽድቅ ፍሬ እንድታፈሩ እጸልያለሁ።+ +12 እንግዲህ ወንድሞች፣ እኔ ያጋጠመኝ ሁኔታ ምሥራቹ ይበልጥ እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ እንዳደረገ እንድታውቁ እወዳለሁ፤ +13 የታሰርኩት+ የክርስቶስ አገልጋይ በመሆኔ የተነሳ እንደሆነ በንጉሠ ነገሥቱ የክብር ዘብ ሁሉና በሌሎች ሰዎች ሁሉ ዘንድ ���ይፋ ታውቋል።+ +14 ጌታን የሚያገለግሉ አብዛኞቹ ወንድሞች በእኔ መታሰር ምክንያት የልበ ሙሉነት ስሜት አድሮባቸው የአምላክን ቃል ያለፍርሃት ለመናገር ከቀድሞው የበለጠ ድፍረት እያሳዩ ነው። +15 እርግጥ፣ አንዳንዶች ክርስቶስን እየሰበኩ ያሉት በቅናትና በፉክክር መንፈስ ነው፤ ይሁንና ሌሎች ይህን እያደረጉ ያሉት በጥሩ ዓላማ ነው። +16 እነዚህ፣ እኔ ለምሥራቹ ለመሟገት+ እንደተሾምኩ ስለሚያውቁ ስለ ክርስቶስ የሚያውጁት ከፍቅር ተነሳስተው ነው፤ +17 እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ ችግር ሊፈጥሩብኝ ስላሰቡ ይህን የሚያደርጉት በቅን ልቦና ሳይሆን በጥላቻ ተነሳስተው ነው። +18 ታዲያ ይህ ምን አስከተለ? በማስመሰልም ሆነ በእውነት፣ በሁሉም መንገድ ክርስቶስ እንዲሰበክ አስችሏል፤ በዚህ ደግሞ ደስተኛ ነኝ። ወደፊትም ቢሆን መደሰቴን እቀጥላለሁ፤ +19 ይህ በእናንተ ምልጃ+ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በሚሰጠኝ ድጋፍ+ መዳን እንደሚያስገኝልኝ አውቃለሁና። +20 ይህም በጉጉት ከምጠባበቀው ነገርና ከተስፋዬ ጋር በሚስማማ ሁኔታ በማንኛውም መንገድ እንዳላፍር ነው፤ ከዚህ ይልቅ በነፃነት በመናገር በሕይወትም ሆነ በሞት እንደ ወትሮው ሁሉ አሁንም ክርስቶስን በሰውነቴ አማካኝነት ከፍ ከፍ አደርገው ዘንድ ነው።+ +21 እኔ ብኖር የምኖረው ለክርስቶስ ነውና፤+ ብሞት ደግሞ እጠቀማለሁ።+ +22 በሥጋ መኖሬን የምቀጥል ከሆነ በማከናውነው ሥራ አማካኝነት ብዙ ፍሬ ማፍራት እችላለሁ፤ ይሁንና የትኛውን እንደምመርጥ አላሳውቅም። +23 በእነዚህ ሁለት ነገሮች አጣብቂኝ ውስጥ ገብቻለሁ፤ ምኞቴ ነፃ መለቀቅና ከክርስቶስ ጋር መሆን ነውና፤+ እርግጡን ለመናገር ይህ እጅግ የተሻለ ነው።+ +24 ይሁን እንጂ ለእናንተ ሲባል በሥጋ መኖሬ ይበልጥ አስፈላጊ ነው። +25 በመሆኑም በዚህ ጉዳይ እርግጠኛ ስለሆንኩ እድገት እንድታደርጉና በእምነት ደስታ እንድታገኙ ስል በሥጋ እንደምቆይና ከሁላችሁም ጋር መኖሬን እንደምቀጥል አውቃለሁ፤ +26 ይህም ዳግመኛ በእናንተ መካከል ስገኝ በእኔ ምክንያት ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ ደስታችሁ ይትረፈረፍ ዘንድ ነው። +27 ብቻ አኗኗራችሁ ስለ ክርስቶስ ከሚገልጸው ምሥራች ጋር የሚስማማ ይሁን፤*+ ይህም መጥቼ ባያችሁም ሆነ ከእናንተ ብርቅ አንድ ላይ ሆናችሁ በምሥራቹ ላይ ያላችሁን እምነት ጠብቃችሁ ለመኖር በአንድ ነፍስ* በመጋደል በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁን+ +28 እንዲሁም በምንም መንገድ በጠላቶቻችሁ አለመሸበራችሁን እሰማና አውቅ ዘንድ ነው። ይህ ነገር እነሱ እንደሚጠፉ+ እናንተ ግን እንደምትድኑ የሚያሳይ+ ማስረጃ ነው፤ ይህም ከአምላክ የተሰጠ ነው። +29 እናንተ በክርስቶስ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን ለእሱ ስትሉ መከራ እንድትቀበሉም መብት ተሰጥቷችኋል።+ +30 እኔ ስጋፈጥ ያያችሁትንና+ አሁንም እየተጋፈጥኩት እንዳለሁ የሰማችሁትን ያንኑ ትግል እናንተም እየተጋፈጣችሁ ነውና። +2 እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ባላችሁ አንድነት በመካከላችሁ ማንኛውም ዓይነት ማበረታቻ፣ ማንኛውም ዓይነት ፍቅራዊ ማጽናኛ፣ ማንኛውም ዓይነት መንፈሳዊ ኅብረት፣ ማንኛውም ዓይነት ጥልቅ ፍቅርና ርኅራኄ ካለ፣ +2 ፍጹም አንድነት ኖሯችሁና* አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ይዛችሁ በአንድ ሐሳብና በአንድ ፍቅር በመኖር ደስታዬን የተሟላ አድርጉልኝ።+ +3 ሌሎች ከእናንተ እንደሚበልጡ በትሕትና አስቡ+ እንጂ በጠበኝነት መንፈስ+ ወይም በትምክህተኝነት+ ምንም ነገር አታድርጉ፤ +4 ስለ ራሳችሁ ፍላጎት ብቻ ከማሰብ ይልቅ+ እያንዳንዳችሁ ለሌሎች ሰዎች ፍላጎትም ትኩረት ስጡ።+ +5 ክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ይህ አስተሳሰብ በእናንተም ዘንድ ይኑር፤+ +6 እሱ በአምላክ መልክ ይኖር የነበረ ቢሆንም+ የሥልጣን ቦታን ለመቀማት ማለትም ከአምላክ ጋር እኩል ለመሆን አላሰበም።+ +7 ከዚህ ይልቅ ራሱን ባዶ በማድረግ የባሪያን መልክ ያዘ፤+ ደግሞም ሰው ሆነ።*+ +8 ከዚህም በላይ ሰው ሆኖ በመጣ ጊዜ* ራሱን ዝቅ በማድረግ እስከ ሞት ድረስ ያውም በመከራ እንጨት*+ ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆኗል።+ +9 በዚህም ምክንያት አምላክ የላቀ ቦታ በመስጠት ከፍ ከፍ አደረገው፤+ እንዲሁም ከሌላ ከማንኛውም ስም በላይ የሆነ ስም በደግነት ሰጠው፤+ +10 ይህም በሰማይና በምድር እንዲሁም ከምድር በታች ያሉ ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ነው፤+ +11 ምላስም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ በመመሥከር+ አባት ለሆነው አምላክ ክብር ያመጣ ዘንድ ነው። +12 ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እኔ አብሬያችሁ ስሆን ብቻ ሳይሆን ይልቁንም አሁን አብሬያችሁ በሌለሁበት ወቅት ሁልጊዜ ታዛዥ እንደሆናችሁ ሁሉ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ከፍጻሜ ለማድረስ ተግታችሁ ሥሩ። +13 እሱ ደስ ለሚሰኝበት ነገር ፍላጎት እንዲያድርባችሁም ሆነ ለተግባር እንድትነሳሱ በማድረግ ኃይል የሚሰጣችሁ አምላክ ነውና። +14 ምንጊዜም ማንኛውንም ነገር ሳታጉረመርሙና+ ሳትከራከሩ አድርጉ፤+ +15 ይህም በጠማማና በወልጋዳ ትውልድ+ መካከል እንከንና እድፍ የሌለባችሁ ንጹሐን የአምላክ ልጆች እንድትሆኑ ነው።+ በዚህ ዓለም ውስጥ እንደ ብርሃን አብሪዎች ታበራላችሁ፤+ +16 ይህን የምታደርጉትም የሕይወትን ቃል አጥብቃችሁ በመያዝ ነው።+ ያን ጊዜ ሩጫዬም ሆነ ድካሜ ከንቱ ሆኖ እንዳልቀረ ስለምገነዘብ በክርስቶስ ቀን ሐሴት የማደርግበት ነገር ይኖረኛል። +17 ይሁንና በእምነት ተነሳስታችሁ በምታቀርቡት መሥዋዕትና+ ቅዱስ አገልግሎት* ላይ እንደ መጠጥ መባ ብፈስ+ እንኳ ደስ ይለኛል፤* እንዲሁም ከሁላችሁም ጋር ሐሴት አደርጋለሁ። +18 እናንተም ልክ እንደዚሁ ተደሰቱ፤ ከእኔም ጋር ሐሴት አድርጉ። +19 ስለ እናንተ በምሰማበት ጊዜ እንድበረታታ፣ ጌታ ኢየሱስ ቢፈቅድ ጢሞቴዎስን+ በቅርቡ ወደ እናንተ እንደምልከው ተስፋ አደርጋለሁ። +20 ስለ እናንተ ጉዳይ ከልብ የሚጨነቅ እንደ እሱ ያለ በጎ አመለካከት ያለው ሌላ ማንም የለኝምና። +21 ሌሎቹ ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት ይሯሯጣሉ። +22 እሱ ግን ከአባቱ ጋር እንደሚሠራ ልጅ+ ምሥራቹን በማስፋፋቱ ሥራ ከእኔ ጋር እንደ ባሪያ በማገልገል ማንነቱን እንዴት እንዳስመሠከረ ታውቃላችሁ። +23 በመሆኑም የእኔ ጉዳይ ምን ላይ እንደደረሰ ሳውቅ ወዲያውኑ ወደ እናንተ ልልከው ያሰብኩት እሱን ነው። +24 እንዲያውም የጌታ ፈቃድ ከሆነ እኔ ራሴም በቅርቡ እንደምመጣ እርግጠኛ ነኝ።+ +25 ለአሁኑ ግን በሚያስፈልገኝ ሁሉ በግል እንዲያገለግለኝ የላካችሁትን ወንድሜን፣ የሥራ ባልደረባዬንና አብሮኝ ወታደር የሆነውን አፍሮዲጡን ወደ እናንተ መላኩን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤+ +26 ምክንያቱም ሁላችሁንም ለማየት ናፍቋል፤ በተጨማሪም እንደታመመ መስማታችሁን ስላወቀ ተጨንቋል። +27 በእርግጥም በጠና ታሞ ሞት አፋፍ ደርሶ ነበር፤ ሆኖም አምላክ ምሕረት አደረገለት፤ ደግሞም ምሕረት ያደረገው ለእሱ ብቻ ሳይሆን በሐዘን ላይ ሐዘን እንዳይደራረብብኝ ለእኔም ጭምር ነው። +28 ስለዚህ ስታዩት ዳግመኛ እንድትደሰቱና የእኔም ጭንቀት እንዲቀል እሱን በተቻለ ፍጥነት ወደ እናንተ እልከዋለሁ። +29 ስለዚህ የጌታን ተከታዮች ወትሮ በምትቀበሉበት መንገድ በታላቅ ደስታ ተቀበሉት፤ እንዲሁም እንደ እሱ ያሉትን ሰዎች በአክብሮት ያዟቸው፤+ +30 ምክንያቱም እሱ፣ እናንተ እዚህ ሆናችሁ በግል ልትሰጡኝ ያልቻላችሁትን አገልግሎት በሚ��ባ ለማሟላት ሲል ከክርስቶስ ሥራ* የተነሳ ሕይወቱን* ለአደጋ በማጋለጥ ለሞት ተቃርቦ ነበር።+ +4 ስለዚህ የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ እንዲሁም ደስታዬና አክሊሌ+ የሆናችሁ ወንድሞቼና ወዳጆቼ፣ አሁን በገለጽኩላችሁ መሠረት ከጌታ ጋር ባላችሁ አንድነት ጸንታችሁ ቁሙ።+ +2 በጌታ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖራቸው+ ኤዎድያንን እመክራለሁ፤ ሲንጤኪንም እመክራለሁ። +3 አዎ፣ እውነተኛ የሥራ አጋሬ የሆንከው አንተም፣ ከቀሌምንጦስና ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ከሰፈረው+ ከቀሩት የሥራ ባልደረቦቼ ጋር ለምሥራቹ ሲሉ ከጎኔ ተሰልፈው ብዙ የደከሙትን* እነዚህን ሴቶች መርዳትህን እንድትቀጥል አደራ እልሃለሁ። +4 ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ። ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ!+ +5 ምክንያታዊነታችሁ*+ በሰው ሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ጌታ ቅርብ ነው። +6 ስለ ምንም ነገር አትጨነቁ፤+ ከዚህ ይልቅ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን ለአምላክ አቅርቡ፤+ +7 ከመረዳት ችሎታ ሁሉ በላይ የሆነው የአምላክ ሰላም+ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ልባችሁንና+ አእምሯችሁን* ይጠብቃል። +8 በመጨረሻም ወንድሞች፣ እውነት የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ቁም ነገር ያለበትን ነገር ሁሉ፣ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ በመልካም የሚነሳውን ነገር ሁሉ፣ በጎ የሆነውን ሁሉና ምስጋና የሚገባውን ነገር ሁሉ ማሰባችሁን* አታቋርጡ።+ +9 ከእኔ የተማራችሁትንም ሆነ የተቀበላችሁትን እንዲሁም የሰማችሁትንና ያያችሁትን ነገር ሁሉ ሥራ ላይ አውሉ፤+ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል። +10 አሁን ለእኔ እንደገና ማሰብ በመጀመራችሁ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል።+ ስለ እኔ ደህንነት ታስቡ የነበረ ቢሆንም ይህን በተግባር ለማሳየት የሚያስችል አጋጣሚ አላገኛችሁም። +11 ይህን ስል እንደተቸገርኩ መናገሬ አይደለም፤ ምክንያቱም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብሆን ባለኝ ረክቼ መኖርን ተምሬአለሁ።+ +12 በትንሽ ነገር እንዴት መኖር እንደሚቻልም+ ሆነ ብዙ አግኝቶ እንዴት መኖር እንደሚቻል አውቃለሁ። በማንኛውም ነገርና በሁሉም ሁኔታ ጠግቦም ሆነ ተርቦ፣ ብዙ አግኝቶም ሆነ አጥቶ መኖር የሚቻልበትን ሚስጥር ተምሬአለሁ። +13 ኃይልን በሚሰጠኝ በእሱ አማካኝነት ለሁሉም ነገር የሚሆን ብርታት አለኝ።+ +14 የሆነ ሆኖ የመከራዬ ተካፋዮች በመሆናችሁ መልካም አድርጋችኋል። +15 እንዲያውም እናንተ የፊልጵስዩስ ወንድሞች፣ ምሥራቹን መጀመሪያ ከሰማችሁ በኋላ ከመቄዶንያ ስወጣ በመስጠትም ሆነ በመቀበል ረገድ ከእናንተ በስተቀር ከእኔ ጋር የተባበረ አንድም ጉባኤ እንዳልነበረ ታውቃላችሁ፤+ +16 በተሰሎንቄ በነበርኩበት ጊዜ የሚያስፈልገኝን ነገር ከአንዴም ሁለቴ ልካችሁልኛልና። +17 ይህን ስል ስጦታ ለማግኘት በመፈለግ ሳይሆን እናንተ የምታገኙት ጥቅም እንዲጨምር የሚያደርገውን ፍሬ ለማየት በመፈለግ ነው። +18 ይሁን እንጂ የሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ፣ እንዲያውም ከሚያስፈልገኝ በላይ አለኝ። የላካችሁልኝን ከአፍሮዲጡ+ ስለተቀበልኩ ሞልቶ ተትረፍርፎልኛል፤ ይህም ጥሩ መዓዛ ያለው ሽታ፣+ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕትና አምላክ ደስ የሚሰኝበት ነገር ነው። +19 በአጸፋው ደግሞ አምላኬ እንደ ታላቅ ብልጽግናው መጠን በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አሟልቶ ይሰጣችኋል።+ +20 እንግዲህ ለአምላካችንና ለአባታችን ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። +21 ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ላላቸው ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታዬን አድርሱልኝ። ከእኔ ጋር ያሉ ወንድሞች ሰላምታ ልከውላችኋል። +22 ቅዱሳን ሁሉ በተለይ ደግሞ ከቄሳር ቤተሰብ+ የሆኑት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። +23 የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከምታሳዩት መንፈስ ጋር ይሁን። +3 ይሁን እንጂ ከክርስቶስ ጋር አብራችሁ ከተነሳችሁ+ ክርስቶስ በአምላክ ቀኝ+ በተቀመጠበት በላይ ያሉትን ነገሮች ፈልጉ። +2 አእምሯችሁ በምድር ባሉት ነገሮች ላይ ሳይሆን+ ምንጊዜም በላይ ባሉት ነገሮች ላይ እንዲያተኩር አድርጉ።+ +3 እናንተ ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ከክርስቶስ ጋር ተሰውሯል። +4 ሕይወታችን የሆነው ክርስቶስ+ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።+ +5 ስለዚህ በምድር ያሉትን የአካል ክፍሎቻችሁን ግደሉ፤+ እነሱም የፆታ ብልግና፣* ርኩሰት፣ ልቅ የሆነ የፍትወት ስሜት፣+ መጥፎ ፍላጎትና ጣዖት አምልኮ የሆነው ስግብግብነት ናቸው። +6 በእነዚህ ነገሮች ምክንያት የአምላክ ቁጣ ይመጣል። +7 እናንተም በቀድሞ ሕይወታችሁ በዚህ መንገድ ትኖሩ ነበር።+ +8 አሁን ግን ቁጣን፣ ንዴትን፣ ክፋትንና+ ስድብን+ ሁሉ ከእናንተ አስወግዱ፤ ጸያፍ ንግግርም+ ከአፋችሁ አይውጣ። +9 አንዳችሁ ሌላውን አትዋሹ።+ አሮጌውን ስብዕና* ከነልማዶቹ ገፋችሁ ጣሉ፤+ +10 እንዲሁም ከፈጣሪው አምሳል ጋር በሚስማማ ሁኔታ+ በትክክለኛ እውቀት አማካኝነት እየታደሰ የሚሄደውን አዲሱን ስብዕና ልበሱ፤+ +11 በዚህ ሁኔታ ግሪካዊ ወይም አይሁዳዊ፣ የተገረዘ ወይም ያልተገረዘ፣ የባዕድ አገር ሰው፣ እስኩቴስ፣* ባሪያ ወይም ነፃ ሰው ብሎ ልዩነት የለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉም ነገር ነው፤ እንዲሁም በሁሉም ነው።+ +12 እንግዲህ የአምላክ ምርጦች፣+ ቅዱሳንና የተወደዳችሁ እንደመሆናችሁ መጠን ከአንጀት የመነጨ ርኅራኄን፣+ ደግነትን፣ ትሕትናን፣+ ገርነትንና+ ትዕግሥትን+ ልበሱ። +13 አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖረው+ እንኳ እርስ በርስ መቻቻላችሁንና በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ።+ ይሖዋ* በነፃ ይቅር እንዳላችሁ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ።+ +14 ይሁንና በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ላይ ፍቅርን ልበሱ፤+ ፍቅር ፍጹም የሆነ የአንድነት ማሰሪያ ነውና።+ +15 በተጨማሪም አምላክ የጠራችሁ አንድ አካል እንድትሆኑና በሰላም እንድትኖሩ ስለሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ።*+ እንዲሁም አመስጋኝ መሆናችሁን አሳዩ። +16 የክርስቶስ ቃል ከጥበብ ሁሉ ጋር በተትረፈረፈ ሁኔታ በውስጣችሁ ይኑር። በመዝሙራት፣ ለአምላክ በሚቀርብ ውዳሴና በአመስጋኝነት መንፈስ* በሚዘመሩ መንፈሳዊ ዝማሬዎች ትምህርትና ማበረታቻ* መስጠታችሁን ቀጥሉ፤+ በልባችሁም ለይሖዋ* ዘምሩ።+ +17 በቃልም ሆነ በተግባር የምታደርጉት ነገር ምንም ሆነ ምን አባት የሆነውን አምላክ በኢየሱስ በኩል እያመሰገናችሁ ሁሉንም ነገር በጌታ ኢየሱስ ስም አድርጉት።+ +18 ሚስቶች ሆይ፣ የክርስቶስ ተከታዮች ሊያደርጉት የሚገባ ስለሆነ ለባሎቻችሁ ተገዙ።+ +19 ባሎች ሆይ፣ ሚስቶቻችሁን መውደዳችሁን ቀጥሉ፤+ መራራ ቁጣም አትቆጧቸው።*+ +20 ልጆች ሆይ፣ በሁሉም ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤+ እንዲህ ማድረጋችሁ ጌታን ያስደስተዋልና። +21 አባቶች ሆይ፣ ቅስማቸው እንዳይሰበር* ልጆቻችሁን አታበሳጯቸው።+ +22 ባሪያዎች ሆይ፣ ሰውን ለማስደሰት ብላችሁ ሰብዓዊ ጌቶቻችሁ በሚያዩአችሁ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በቅን ልብ ተነሳስታችሁ ይሖዋን* በመፍራት ጌቶቻችሁ ለሆኑት በሁሉም ነገር ታዛዥ ሁኑ።+ +23 የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለይሖዋ* እንደምታደርጉት በማሰብ በሙሉ ነፍሳችሁ* አድርጉት፤+ +24 ከይሖዋ* ዘንድ እንደ ሽልማት የምትቀበሉት ውርሻ እንዳለ ታውቃላችሁና።+ ጌታችንን ክርስቶስን እንደ ባሪያ አገልግሉ። +25 መጥፎ ነገር የሚሠራ የእጁን እንደሚያገኝ የተረጋገጠ ነው፤+ ደግሞም አድልዎ የለም።+ +1 በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፣+ +2 በቆላስይስ ለሚገኙ ከክርስቶስ ጋር አንድነት ላላቸው ታማኝ የሆኑ ቅዱሳን ወንድሞች፦ አባታችን ከሆነው አምላክ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። +3 ስለ እናንተ ስንጸልይ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት የሆነውን አምላክ ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ +4 ምክንያቱም በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ስላላችሁ እምነትና ለቅዱሳን ሁሉ ስለምታሳዩት ፍቅር ሰምተናል፤ +5 ይህም የሆነው በሰማይ ከሚጠብቃችሁ ተስፋ የተነሳ ነው።+ ይህን ተስፋ በተመለከተ ቀደም ሲል የሰማችሁት፣ በተነገራችሁ የእውነት መልእክት ይኸውም በምሥራቹ አማካኝነት ሲሆን +6 ይህም ምሥራች ወደ እናንተ ደርሷል። ምሥራቹ በመላው ዓለም እየተስፋፋና ፍሬ እያፈራ+ እንደሆነ ሁሉ የአምላክን ጸጋ እውነት ከሰማችሁበትና በትክክል ካወቃችሁበት ቀን አንስቶ በእናንተም መካከል እያደገና ፍሬ እያፈራ ነው። +7 የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ ሆኖ በእኛ ምትክ ከሚሠራውና አብሮን ባሪያ ከሆነው ከተወዳጁ ኤጳፍራ+ የተማራችሁት ይህን ነው። +8 ደግሞም ስለ መንፈሳዊ ፍቅራችሁ ነግሮናል። +9 ከዚህም የተነሳ ይህን ከሰማንበት ቀን አንስቶ ከጥበብና ከመንፈሳዊ ግንዛቤ+ ሁሉ ጋር በፈቃዱ ትክክለኛ እውቀት+ ትሞሉ ዘንድ ስለ እናንተ መጸለያችንንና መለመናችንን አላቋረጥንም፤+ +10 ይህም በመልካም ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁና ስለ አምላክ ትክክለኛ እውቀት በመቅሰም+ እያደጋችሁ ስትሄዱ ለይሖዋ* በሚገባ ሁኔታ እንድትመላለሱና እሱን ሙሉ በሙሉ እንድታስደስቱ ነው፤ +11 በትዕግሥትና በደስታ ሁሉንም ነገር በጽናት እንድትቋቋሙ የአምላክ ታላቅ ኃይል የሚያስፈልጋችሁን ብርታት ሁሉ ይስጣችሁ፤+ +12 ደግሞም በብርሃን ውስጥ ያሉት ቅዱሳን ከሚያገኙት ውርሻ+ ለመካፈል ያበቃችሁን አባት አመስግኑ። +13 እሱ ከጨለማው ሥልጣን ታድጎን+ ወደሚወደው ልጁ መንግሥት አሻግሮናል፤ +14 ልጁም ቤዛውን በመክፈል ነፃ እንድንወጣ ይኸውም የኃጢአት ይቅርታ እንድናገኝ አድርጎናል።+ +15 እሱ የማይታየው አምላክ አምሳልና+ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው፤+ +16 ምክንያቱም በሰማያትና በምድር ያሉ ሌሎች ነገሮች በሙሉ፣ የሚታዩትና የማይታዩት ነገሮች፣ ዙፋኖችም ሆኑ ጌትነት፣ መንግሥታትም ሆኑ ሥልጣናት የተፈጠሩት በእሱ አማካኝነት ነው።+ ሌሎች ነገሮች በሙሉ የተፈጠሩት በእሱ በኩልና+ ለእሱ ነው። +17 በተጨማሪም እሱ ከሌሎች ነገሮች ሁሉ በፊት ነው፤+ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ወደ ሕልውና የመጡትም በእሱ አማካኝነት ነው፤ +18 እሱ የአካሉ ማለትም የጉባኤው ራስ ነው።+ በሁሉም ነገር ቀዳሚ መሆን እንዲችልም እሱ የመጀመሪያ፣ ከሙታን መካከልም በኩር ነው፤+ +19 ይህም የሆነው እሱ በሁሉም ነገር ሙሉ እንዲሆን አምላክ ስለፈለገ ነው፤+ +20 እንዲሁም በመከራው እንጨት* ላይ ባፈሰሰው ደም+ አማካኝነት ሰላም በመፍጠር ሌሎቹን ነገሮች ሁሉ ይኸውም በምድርም ሆነ በሰማያት ያሉትን ነገሮች ሁሉ በእሱ በኩል ከራሱ ጋር ለማስታረቅ ስለወደደ ነው።+ +21 በእርግጥ እናንተ በአንድ ወቅት አእምሯችሁ በክፉ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ስለነበር ከአምላክ የራቃችሁና ጠላቶች ነበራችሁ፤ +22 አሁን ግን እሱ ቅዱሳንና እንከን የሌለባችሁ እንዲሁም ከማንኛውም ክስ ነፃ የሆናችሁ አድርጎ በፊቱ ሊያቀርባችሁ ስለፈለገ+ ራሱን ለሞት አሳልፎ በሰጠው ሰው ሥጋዊ አካል አማካኝነት ከራሱ ጋር አስታርቋችኋል፤ +23 በእርግጥ ይህ የሚሆነው በእምነት መሠረት ላይ ታንጻችሁና+ ተደላድላችሁ በመቆም፣+ የሰማችሁት ምሥራች ካስገኘላችሁ ተስፋ ሳትወሰዱ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ነው፤+ ይህም ምሥራች ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ* ተሰብኳል።+ እኔም ጳውሎስ የዚህ ምሥራች አገልጋይ ሆኛለሁ።+ +24 ለእናንተ ስል በተቀበልኩት መከራ+ አሁን እየተደሰትኩ ነው፤ በክርስቶስ የተነሳ በአካሌ ላይ የሚደርሰው መከራ በዚህ ብቻ አያበቃም። ይህ መከራ እየደረሰብኝ ያለው ለአካሉ+ ይኸውም ለጉባኤው+ ስል ነው። +25 የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ እሰብክ ዘንድ ለእናንተ ጥቅም ሲባል ከአምላክ ከተሰጠኝ የመጋቢነት ሥራ+ ጋር በሚስማማ መንገድ የዚህ ጉባኤ አገልጋይ ሆኛለሁ፤ +26 ይህም ቃል ካለፉት ሥርዓቶችና* ካለፉት ትውልዶች አንስቶ ተሰውሮ+ የቆየው ቅዱስ ሚስጥር+ ነው። አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጧል።+ +27 በተጨማሪም አምላክ በአሕዛብ መካከል የዚህን ቅዱስ ሚስጥር ታላቅ ብልጽግና ለቅዱሳኑ ያሳውቅ ዘንድ ወዷል፤+ ይህ ቅዱስ ሚስጥር የክብሩ ተስፋ+ የሆነውና ከእናንተ ጋር አንድነት ያለው ክርስቶስ ነው። +28 እያንዳንዱን ሰው የጎለመሰ* የክርስቶስ ደቀ መዝሙር አድርገን ለአምላክ ማቅረብ እንድንችል ሰውን ሁሉ እያሳሰብንና በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምናውጀው ስለ እሱ ነው።+ +29 ይህን ዳር ለማድረስ፣ በውስጤ እየሠራ ባለው በእሱ ብርቱ ኃይል አማካኝነት አቅሜ በሚፈቅደው ሁሉ በትጋት እየሠራሁ ነው።+ +2 ለእናንተና በሎዶቅያ+ ላሉት እንዲሁም በአካል አይተውኝ ለማያውቁ* ሁሉ ስል ምን ያህል ብርቱ ትግል እያደረግኩ እንዳለሁ እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ። +2 ይህም ልባቸው እንዲጽናና+ እንዲሁም ስምም ሆነው በፍቅር እርስ በርስ እንዲተሳሰሩ ነው።+ በዚህ መንገድ ታላቅ የሆነውን ብልጽግና ይኸውም ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ የሆኑበትን የእውነት ግንዛቤ ማግኘት ብሎም የአምላክ ቅዱስ ሚስጥር ስለሆነው ስለ ክርስቶስ+ ትክክለኛ እውቀት መቅሰም ይችላሉ። +3 የጥበብና የእውቀት ውድ ሀብት ሁሉ በሚገባ ተሰውሮ የሚገኘው በክርስቶስ ውስጥ ነው።+ +4 ይህን የምለው ማንም ሰው አግባብቶ እንዳያታልላችሁ ነው። +5 በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ግን ከእናንተ ጋር ስለሆንኩ ሥርዓት ያለውን አኗኗራችሁንና+ በክርስቶስ ላይ ያላችሁን ጽኑ እምነት+ በማየት እየተደሰትኩ ነው። +6 ስለዚህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደተቀበላችሁት ሁሉ ከእሱ ጋር በአንድነት መመላለሳችሁን ቀጥሉ፤ +7 በተማራችሁት መሠረት በእሱ ላይ ሥር ሰዳችሁና ታንጻችሁ ኑሩ፤+ እንዲሁም በእምነት ጸንታችሁ መኖራችሁን ቀጥሉ፤+ ብዙ ምስጋናም አቅርቡ።+ +8 በክርስቶስ ላይ ሳይሆን በዓለም መሠረታዊ ነገሮች እንዲሁም በሰው ወግ ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማታለያ+ ማንም ማርኮ* እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ፤ +9 ምክንያቱም መለኮታዊው ባሕርይ በተሟላ ሁኔታ በአካል የሚኖረው በእሱ ውስጥ ነው።+ +10 በመሆኑም የገዢነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ+ በሆነው በእሱ አማካኝነት ሁሉንም ነገር አግኝታችኋል። +11 ከእሱ ጋር ባላችሁ ዝምድና የተነሳ በእጅ ባልተከናወነ ግርዘት ተገርዛችኋል፤ ይህም ኃጢአተኛውን ሥጋዊ አካል በማስወገድ+ የሚከናወን የክርስቶስ አገልጋዮች ግርዘት ነው።+ +12 የእሱን ዓይነት ጥምቀት በመጠመቅ ከእሱ ጋር ተቀብራችሁ ነበርና፤+ ከእሱ ጋር ባላችሁ ዝምድና የተነሳም አብራችሁ ተነስታችኋል፤+ ይህም የሆነው እሱን ከሞት ያስነሳው+ አምላክ ባከናወነው ታላቅ ሥራ ላይ ባላችሁ እምነት አማካኝነት ነው። +13 በተጨማሪም በበደላችሁና በሥጋችሁ አለመገረዝ የተነሳ ሙታን የነበራችሁ ቢሆንም አምላክ ከእሱ ጋር ሕያዋን አድርጓችኋል።+ በደላችንን ሁሉ በደግነት ይቅር ብሎናል፤+ +14 ድንጋጌዎችን የያዘውንና+ ይቃወመን የነበረውን+ በእጅ የተጻፈ ሰነድም ደመሰሰው።+ በመከራው እንጨት* ላይ ቸንክሮም ከመንገድ አስወገ��ው።+ +15 በመከራው እንጨት* አማካኝነት መንግሥታትንና ባለሥልጣናትን ገፎ በድል ሰልፍ እየመራ እንደ ምርኮኛ በአደባባይ እንዲታዩ አድርጓቸዋል።+ +16 ስለዚህ በምትበሉትም ሆነ በምትጠጡት ወይም በዓልን፣ የወር መባቻንና*+ ሰንበትን በማክበር+ ረገድ ማንም ሰው አይፍረድባችሁ።+ +17 እነዚህ ለሚመጡት ነገሮች ጥላ ናቸው፤+ እውነተኛው ነገር* ግን የክርስቶስ ነው።+ +18 በውሸት ትሕትናና በመላእክት አምልኮ* የሚደሰት ማንኛውም ሰው ሽልማቱን እንዲያሳጣችሁ አትፍቀዱ።+ እንዲህ ያለ ሰው ባያቸው ነገሮች ላይ ተመሥርቶ “ጥብቅ አቋም የሚይዝ”* ከመሆኑም በላይ ሥጋዊ አስተሳሰቡ በከንቱ እንዲታበይ ያደርገዋል። +19 እነዚህ ሰዎች ራስ+ ከሆነው ጋር በጥብቅ የተቆራኙ አይደሉም፤ መላው አካል በመገጣጠሚያዎችና በጅማቶች አማካኝነት የሚያስፈልገውን ነገር የሚያገኘውና እርስ በርስ ስምም ሆኖ የተያያዘው እንዲሁም የሚያድገው ራስ በሆነው አማካኝነት ነው። ይህም እድገት የሚገኘው ከአምላክ ነው።+ +20 የዚህን ዓለም መሠረታዊ ነገሮች በመተው ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ+ ለድንጋጌዎቹ+ ራሳችሁን በማስገዛት አሁንም የዓለም ክፍል የሆናችሁ በሚመስል ሁኔታ ለምን ትኖራላችሁ? +21 ድንጋጌዎቹም “አትውሰድ፣ አትቅመስ፣ አትንካ” የሚሉ ናቸው። +22 እነዚህ ሁሉ የሰው ትእዛዛትና ትምህርቶች ስለሆኑ ሁሉም ጥቅም ላይ ውለው እንዲጠፉ የተወሰነባቸው ናቸው።+ +23 እነዚህ ነገሮች በገዛ ፈቃድ በሚቀርብ አምልኮና በውሸት ትሕትና፣ ሰውነትን በማሠቃየት+ የሚገለጹ ጥበብ ያለባቸው ነገሮች ቢመስሉም የሥጋን ፍላጎት በማሸነፍ ረገድ አንዳች ፋይዳ የላቸውም። +4 ጌቶች ሆይ፣ እናንተም በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ በመገንዘብ ባሪያዎቻችሁን በጽድቅና በፍትሕ አስተዳድሯቸው።+ +2 በጸሎት ረገድ ዘወትር ንቁ በመሆንና ምስጋና በማቅረብ+ በጽናት ጸልዩ።+ +3 ደግሞም ለእኔ መታሰር ምክንያት የሆነውን ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ቅዱስ ሚስጥር ማወጅ እንድንችል+ አምላክ የቃሉን በር እንዲከፍትልን ለእኛም ጸልዩልን፤+ +4 ቅዱሱን ሚስጥር የሚገባኝን ያህል በግልጽ እንዳውጅም ጸልዩልኝ። +5 ጊዜያችሁን በተሻለ መንገድ በመጠቀም* በውጭ ካሉት ጋር* ባላችሁ ግንኙነት በጥበብ መመላለሳችሁን ቀጥሉ።+ +6 ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ምንጊዜም በጨው+ የተቀመመ ያህል ለዛ ያለው ይሁን።+ +7 በጌታ ታማኝ አገልጋይና አብሮኝ ባሪያ የሆነው የተወደደው ወንድሜ ቲኪቆስ+ ስለ እኔ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል። +8 እሱን ወደ እናንተ የምልከው ስላለንበት ሁኔታ እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያጽናና ነው። +9 እናንተ ጋ ከነበረው ከታማኙና ከተወደደው ወንድሜ ከአናሲሞስ+ ጋር ይመጣል፤ እነሱም እዚህ እየተከናወነ ስላለው ነገር ሁሉ ያሳውቋችኋል። +10 አብሮኝ የታሰረው አርስጥሮኮስ+ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ የበርናባስ ዘመድ* የሆነው ማርቆስም+ ሰላም ብሏችኋል (እሱን በተመለከተ ወደ እናንተ ከመጣ እንድትቀበሉት+ መመሪያ ደርሷችኋል)፤ +11 ኢዮስጦስ ተብሎ የሚጠራው ኢየሱስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ እነዚህ ከተገረዙት ወገን ናቸው። ለአምላክ መንግሥት አብረውኝ የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነሱም የብርታት ምንጭ ሆነውልኛል።* +12 ከእናንተ ጋር የነበረው የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያ የሆነው ኤጳፍራ+ ሰላምታ ልኮላችኋል። በአምላክ ፈቃድ ሁሉ ፍጹምና* ጽኑ እምነት ያላችሁ ሆናችሁ እስከ መጨረሻው እንድትቆሙ ዘወትር በጸሎቱ ስለ እናንተ እየተጋደለ ነው። +13 ስለ እናንተ እንዲሁም በሎዶቅያና በሂራጶሊስ ስላሉት ብዙ እንደሚደክም እኔ ራሴ እመሠክርለታለሁ። +14 የተወደደው ሐ���ም ሉቃስ+ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ ዴማስም+ ሰላም ብሏችኋል። +15 በሎዶቅያ ላሉት ወንድሞችና ለንምፉን እንዲሁም በቤቷ ላለው ጉባኤ+ ሰላምታዬን አቅርቡልኝ። +16 እንዲሁም ይህ ደብዳቤ እናንተ ጋ ከተነበበ በኋላ በሎዶቅያውያን ጉባኤ እንዲነበብና ከሎዶቅያ የሚደርሳችሁ ደብዳቤ ደግሞ እናንተ ጋ እንዲነበብ ዝግጅት አድርጉ።+ +17 በተጨማሪም አርክጳን+ “በጌታ የተቀበልከውን አገልግሎት ከፍጻሜ እንድታደርስ ለአገልግሎቱ ትኩረት ስጥ” በሉት። +18 እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ የጻፍኩላችሁ ሰላምታ ይድረሳችሁ።+ በሰንሰለት ታስሬ+ እንዳለሁ አስታውሱ። የአምላክ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። +3 ስለዚህ ከዚህ በላይ መታገሥ ስላልቻልን* በአቴንስ+ ብቻችንን መቅረት እንደሚሻል ተሰማን፤ +2 በመሆኑም እምነታችሁ ይጠነክር ዘንድ እንዲያጸናችሁ እንዲሁም እንዲያበረታታችሁ ጢሞቴዎስን+ ላክንላችሁ፤ እሱ ወንድማችንና ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች የሚያውጅ የአምላክ አገልጋይ* ነው፤ +3 የላክነውም ማንም በእነዚህ መከራዎች እንዳይናወጥ* ነው። እንዲህ ካሉ መከራዎች ማምለጥ እንደማንችል እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና።+ +4 አብረናችሁ በነበርንበት ጊዜ መከራ መቀበላችን እንደማይቀር አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ ደግሞም እንደምታውቁት ይኸው ነገር ደርሷል።+ +5 ስለዚህ ከዚህ በላይ መታገሥ ባልቻልኩ ጊዜ ስለ ታማኝነታችሁ ለመስማት እሱን ላክሁት፤+ ይህን ያደረግኩት ምናልባት ፈታኙ+ በሆነ መንገድ ፈትኗችሁ ድካማችን ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ስለሰጋሁ ነው። +6 ይሁንና ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ አሁን ወደ እኛ መጥቶ+ ስለ ታማኝነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ ምሥራች አብስሮናል፤ ደግሞም እኛን ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ እናንተን ለማየት እንደምንናፍቅ ሁሉ እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁ ነግሮናል። +7 ወንድሞች፣ በችግራችንና በመከራችን ሁሉ በእናንተና ባሳያችሁት ታማኝነት የተነሳ የተጽናናነው ለዚህ ነው።+ +8 ምክንያቱም ከጌታ ጋር ባላችሁ ዝምድና ጸንታችሁ የምትቆሙ ከሆነ ሕይወታችን ይታደሳል።* +9 በእናንተ የተነሳ በአምላካችን ፊት ለተሰማን ታላቅ ደስታ በአጸፋው ስለ እናንተ ምስጋናችንን ለአምላክ ለመግለጽ ምን ማድረግ እንችላለን? +10 ፊታችሁን ማየትና ከእምነታችሁ የጎደለውን ነገር ማሟላት እንችል ዘንድ አቅማችን በሚፈቅደው መጠን ሌት ተቀን ምልጃ እናቀርባለን።+ +11 አሁንም አምላካችንና አባታችን እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅኑልን። +12 በተጨማሪም እኛ ለእናንተ ፍቅር እንዳለን ሁሉ እርስ በርስም ሆነ ለሰዎች ሁሉ የምታሳዩትን ፍቅር ጌታ ያብዛላችሁ ብሎም ያትረፍርፍላችሁ፤+ +13 ይህም ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚገኝበት ጊዜ+ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁን እንዲያጸናና ያላንዳች እንከን ቅዱስ እንዲያደርግ ነው።+ +1 ከጳውሎስ፣ ከስልዋኖስና*+ ከጢሞቴዎስ፤+ አባት ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድነት ላለው የተሰሎንቄ ሰዎች ጉባኤ፦ የአምላክ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። +2 ሁላችሁንም በጸሎታችን+ በጠቀስን ቁጥር ሁልጊዜ አምላክን እናመሰግናለን፤ +3 የእምነት ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨ ድካማችሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተስፋ በማድረጋችሁ+ የተነሳ የምታሳዩትን ጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን። +4 አምላክ የሚወዳችሁ ወንድሞች፣ እሱ እንደመረጣችሁ እናውቃለን፤ +5 ምክንያቱም የሰበክንላችሁ ምሥራች ወደ እናንተ የመጣው በቃል ብቻ ሳይሆን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ እንዲሁም በጠንካራ እምነት ነው። ደግሞም ለእናንተ ስንል በመካከላችሁ ምን ዓይነት ሰዎች ሆነን እንደኖርን ታውቃላችሁ። +6 ብዙ መከራ ቢደርስባችሁም+ቃሉን ከመንፈስ ቅዱስ በሚገኝ ደስታ ስለተቀበላችሁ የእኛንም+ ሆነ የጌታን+ አርዓያ ተከትላችኋል፤ +7 በመሆኑም በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ አማኞች ሁሉ ምሳሌ ሆናችኋል። +8 የይሖዋ* ቃል ከእናንተ ወጥቶ የተሰማው በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በአምላክ ላይ ያላችሁ እምነት በሌሎች ቦታዎችም ሁሉ ተሰራጭቷል፤+ ስለዚህ እኛ ምንም መናገር አያስፈልገንም። +9 ምክንያቱም መጀመሪያ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደተገናኘን እንዲሁም ሕያው የሆነውንና እውነተኛውን አምላክ ለማገልገል ጣዖቶቻችሁን በመተው+ እንዴት ወደ አምላክ እንደተመለሳችሁ እነሱ ራሳቸው ሁልጊዜ ይናገራሉ፤ +10 በተጨማሪም ወደ አምላክ የተመለሳችሁት ከሞት ያስነሳውንና ከሚመጣው ቁጣ+ የሚታደገንን የልጁን ይኸውም የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት ለመጠባበቅ ነው።+ +2 ወንድሞች፣ የእኛ ወደ እናንተ መምጣት ፍሬ ቢስ ሆኖ እንዳልቀረ እናንተ ራሳችሁ እንደምትገነዘቡ ምንም ጥርጥር የለውም።+ +2 እንደምታውቁት በመጀመሪያ በፊልጵስዩስ+ መከራና እንግልት ደርሶብን ነበር፤ ይሁንና ከባድ ተቃውሞ እያለም* የአምላክን ምሥራች ለእናንተ ለመንገር+ በአምላካችን እርዳታ እንደ ምንም ብለን ድፍረት አገኘን። +3 የምንሰጠው ምክር ከተሳሳተ ሐሳብ ወይም ከመጥፎ ዓላማ የመነጨ ወይም ደግሞ ማታለያ ያዘለ አይደለም፤ +4 ሆኖም ምሥራቹን በአደራ ለመቀበል በአምላክ ዘንድ ብቁ ሆነን የተቆጠርን እንደመሆናችን መጠን የምንናገረው ሰዎችን ለማስደሰት ሳይሆን ልባችንን የሚመረምረውን+ አምላክ ለማስደሰት ብለን ነው። +5 እንዲያውም የሽንገላ ቃል የተናገርንበት ወይም ስግብግብነት የሚንጸባረቅበትን ፍላጎታችንን ለመሸፈን ብለን በማስመሰል የቀረብንበት ጊዜ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤+ ለዚህም አምላክ ምሥክር ነው! +6 በተጨማሪም የክርስቶስ ሐዋርያት እንደመሆናችን መጠን እናንተን ብዙ ወጪ በማስወጣት ሸክም ልንሆንባችሁ እንችል የነበረ ቢሆንም እንኳ ከእናንተም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ክብር ለማግኘት አልሞከርንም።+ +7 ከዚህ ይልቅ የምታጠባ እናት ልጆቿን በፍቅር እንደምትንከባከብ እኛም በመካከላችሁ በነበርንበት ጊዜ በገርነት ተንከባከብናችሁ። +8 በመሆኑም ለእናንተ ጥልቅ ፍቅር ስላለን የአምላክን ምሥራች ለማካፈል ብቻ ሳይሆን ራሳችንን* ጭምር ለእናንተ ለመስጠት ቆርጠን ነበር፤+ ምክንያቱም እናንተ በእኛ ዘንድ እጅግ የተወደዳችሁ ነበራችሁ።+ +9 ወንድሞች፣ ድካማችንንና ልፋታችንን እንደምታስታውሱ ጥርጥር የለውም። የአምላክን ምሥራች በሰበክንላችሁ ጊዜ፣ ማናችሁንም ብዙ ወጪ በማስወጣት ሸክም እንዳንሆንባችሁ+ በማሰብ ሌት ተቀን እንሠራ ነበር። +10 አማኞች ከሆናችሁት ከእናንተ ጋር በነበረን ግንኙነት ታማኞች፣ ጻድቃንና ነቀፋ የሌለብን ሆነን እንደተመላለስን ምሥክሮች ናችሁ፤ አምላክም ምሥክር ነው። +11 አባት+ ለልጆቹ እንደሚያደርገው ሁሉ እያንዳንዳችሁን እንዴት እንመክራችሁ፣ እናጽናናችሁና አጥብቀን እናሳስባችሁ+ እንደነበረ በሚገባ ታውቃላችሁ፤ +12 ይህን ያደረግነው ወደ መንግሥቱና+ ወደ ክብሩ+ በጠራችሁ አምላክ ፊት በአግባቡ መመላለሳችሁን እንድትቀጥሉ ነው።+ +13 በእርግጥም አምላክን ያለማቋረጥ የምናመሰግነው ለዚህ ነው፤+ ምክንያቱም የአምላክን ቃል ከእኛ በሰማችሁ ጊዜ እንደ ሰው ቃል ሳይሆን እንደ አምላክ ቃል አድርጋችሁ ተቀብላችሁታል፤ ደግሞም የአምላክ ቃል ነው፤ አማኞች በሆናችሁት በእናንተም ላይ በእርግጥ እየሠራ ነው። +14 ወንድሞች፣ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ያላቸውን በይሁዳ የሚገኙትን የአምላክ ጉባኤዎች ምሳሌ ተከትላችኋል፤ ምክንያቱም እነሱ በአይሁዳውያን እጅ መከራ እየተቀበሉ እንዳሉ ሁሉ እናንተም በገዛ አገራችሁ ሰዎች እጅ ተመሳሳይ መከራ ተቀብላችኋል፤+ +15 አይሁዳውያን ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ሳይቀር የገደሉ+ ከመሆኑም በላይ በእኛ ላይ ስደት አድርሰዋል።+ ከዚህም በተጨማሪ አምላክን እያስደሰቱ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሰውን ሁሉ ጥቅም የሚጻረሩ ናቸው፤ +16 አሕዛብ ይድኑ ዘንድ ለእነሱ እንዳንሰብክ ሊከለክሉን ይሞክራሉ።+ በዚህ መንገድ ሁልጊዜ ብዙ ኃጢአት ይፈጽማሉ። ይሁንና ቁጣው የሚገለጽበት ጊዜ ደርሷል።+ +17 እኛ ግን ወንድሞች፣ (በልብ ሳይሆን በአካል) ለአጭር ጊዜ ከእናንተ ለመለየት በተገደድንበት ወቅት እጅግ ስለናፈቅናችሁ ከእናንተ ጋር በአካል ለመገናኘት* ብርቱ ጥረት አደረግን። +18 በመሆኑም ወደ እናንተ መምጣት ፈልገን ነበር፤ አዎ፣ እኔ ጳውሎስ ከአንዴም ሁለቴ ሞክሬ ነበር፤ ሆኖም ሰይጣን መንገድ ዘጋብን። +19 ጌታችን ኢየሱስ በሚገኝበት ጊዜ በእሱ ፊት ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም የሐሴታችን አክሊል ምንድን ነው? እናንተ አይደላችሁም?+ +20 በእርግጥም እናንተ ክብራችንና ደስታችን ናችሁ። +4 በመጨረሻም ወንድሞች፣ አምላክን ማስደሰት እንድትችሉ እንዴት መመላለስ እንዳለባችሁ አስተምረናችኋል፤+ ደግሞም በዚሁ መንገድ እየተመላለሳችሁ ነው፤ በመሆኑም ይህንኑ ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ በጌታ ኢየሱስ ስም እንጠይቃችኋለን እንዲሁም እንለምናችኋለን። +2 በጌታ ኢየሱስ ስም የሰጠናችሁን መመሪያዎች ታውቃላችሁና። +3 የአምላክ ፈቃድ እንድትቀደሱና+ ከፆታ ብልግና* እንድትርቁ ነው።+ +4 ከእናንተ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን አካል* በመቆጣጠር+ እንዴት በቅድስናና+ በክብር መያዝ እንዳለበት ሊያውቅ ይገባል። +5 ይህም አምላክን እንደማያውቁት አሕዛብ+ ስግብግብነት በሚንጸባረቅበት ልቅ የፍትወት ስሜት አይሁን።+ +6 ማንም ሰው በዚህ ጉዳይ ከገደቡ ማለፍና ወንድሙን መጠቀሚያ ማድረግ አይኖርበትም፤ ምክንያቱም አስቀድመን እንደነገርናችሁና በጥብቅ እንዳስጠነቀቅናችሁ ይሖዋ* በእነዚህ ነገሮች ሁሉ የተነሳ የቅጣት እርምጃ ይወስዳል። +7 አምላክ የጠራን ለቅድስና ነው እንጂ ለርኩሰት አይደለም።+ +8 እንግዲህ ለዚህ ንቀት የሚያሳይ ሰው የሚንቀው ሰውን ሳይሆን ቅዱስ መንፈሱን የሚሰጣችሁን+ አምላክ ነው።+ +9 ይሁን እንጂ እናንተ ራሳችሁ እርስ በርስ እንድትዋደዱ ከአምላክ ስለተማራችሁ+ የወንድማማች ፍቅርን በተመለከተ+ እንድንጽፍላችሁ አያስፈልግም። +10 ደግሞም በመላው መቄዶንያ ለሚገኙ ወንድሞች ሁሉ ይህን እያደረጋችሁ ነው። ሆኖም ወንድሞች፣ ይህን ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ እናሳስባችኋለን። +11 ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁ በሰላም ለመኖር፣+ በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባትና+ በገዛ እጃችሁ ለመሥራት ተጣጣሩ፤+ +12 ይህም በውጭ ባሉት* ሰዎች ፊት ሥርዓት ባለው መንገድ እንድትመላለሱና+ ምንም ነገር የሚጎድላችሁ እንዳትሆኑ ነው። +13 በተጨማሪም ወንድሞች፣ ተስፋ እንደሌላቸው+ እንደ ሌሎቹ ሰዎች እንዳታዝኑ በሞት አንቀላፍተው ስላሉት+ ሳታውቁ እንድትቀሩ አንፈልግም። +14 ኢየሱስ እንደሞተና ከሞት እንደተነሳ የምናምን ከሆነ+ ከኢየሱስ ጋር አንድነት ኖሯቸው በሞት ያንቀላፉትንም አምላክ ሕይወት ሰጥቶ ከእሱ ጋር እንዲሆኑ ያደርጋል።+ +15 የይሖዋን* ቃል መሠረት አድርገን የምንነግራችሁ ይህ ነውና፤ ጌታ እስከሚገኝበት ጊዜ ድረስ በሕይወት የምንኖር በሞት አንቀላፍተው ያሉትን በምንም መንገድ አንቀድምም፤ +16 ምክንያቱም ጌታ ራ�� በትእዛዝ ድምፅ፣ በመላእክት አለቃ+ ድምፅና በአምላክ መለከት ድምፅ ከሰማይ ይወርዳል፤ ከክርስቶስ ጋር አንድነት ኖሯቸው የሞቱትም ቀድመው ይነሳሉ።+ +17 ከዚያም በሕይወት ቆይተን የምንተርፈው እኛ በአየር ላይ ከጌታ ጋር ለመገናኘት+ ከእነሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤+ በዚህም መንገድ ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።+ +18 ስለሆነም በእነዚህ ቃላት ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ። +5 እንግዲህ ወንድሞች፣ ጊዜያትንና ወቅቶችን በተመለከተ ምንም ነገር እንዲጻፍላችሁ አያስፈልግም። +2 የይሖዋ* ቀን+ የሚመጣው ሌባ በሌሊት በሚመጣበት መንገድ+ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁና። +3 “ሰላምና ደህንነት ሆነ!” ሲሉ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት ያልታሰበ ጥፋት ድንገት ይመጣባቸዋል፤+ ደግሞም በምንም ዓይነት አያመልጡም። +4 እናንተ ግን ወንድሞች፣ በጨለማ ውስጥ ስላልሆናችሁ ሌሊቱ ድንገት እንደሚነጋበት ሌባ፣ ያ ቀን ድንገት አይደርስባችሁም፤ +5 እናንተ ሁላችሁ የብርሃን ልጆችና የቀን ልጆች ናችሁና።+ እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ልጆች አይደለንም።+ +6 ስለዚህ ነቅተን እንኑር+ እንዲሁም የማስተዋል ስሜታችንን እንጠብቅ+ እንጂ እንደ ሌሎቹ አናንቀላፋ።+ +7 የሚያንቀላፉ ሰዎች፣ የሚያንቀላፉት በሌሊት ነው፤ የሚሰክሩም ቢሆኑ የሚሰክሩት በሌሊት ነው።+ +8 የቀን ልጆች የሆንነው እኛ ግን የማስተዋል ስሜታችንን እንጠብቅ፤ ደግሞም የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እንድፋ፤+ +9 ምክንያቱም አምላክ የመረጠን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መዳን እንድናገኝ+ ነው እንጂ ለቁጣ አይደለም። +10 እሱ በሕይወት ብንኖርም ሆነ ብናንቀላፋ* አብረነው እንድንኖር+ ለእኛ ሞቶልናል።+ +11 ስለዚህ አሁን እያደረጋችሁት እንዳለው እርስ በርስ ተበረታቱ* እንዲሁም እርስ በርስ ተናነጹ።+ +12 እንግዲህ ወንድሞች፣ በመካከላችሁ በትጋት እየሠሩና በጌታ ሥራ አመራር እየሰጧችሁ ያሉትን እንዲሁም ምክር እየለገሷችሁ ያሉትን እንድታከብሯቸው እንለምናችኋለን፤ +13 በተጨማሪም በሚያከናውኑት ሥራ የተነሳ በፍቅር ለየት ያለ አሳቢነት እንድታሳዩአቸው እንለምናችኋለን።+ እርስ በርሳችሁ ሰላማዊ ግንኙነት ይኑራችሁ።+ +14 በሌላ በኩል ደግሞ ወንድሞች፣ ይህን እናሳስባችኋለን፦ በሥርዓት የማይሄዱትን አስጠንቅቋቸው፤*+ የተጨነቁትን* አጽናኗቸው፤ ደካሞችን ደግፏቸው፤ ሁሉንም በትዕግሥት ያዙ።+ +15 ማንም ሰው በማንም ላይ በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤+ ከዚህ ይልቅ እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ ምንጊዜም መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።+ +16 ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ።+ +17 ዘወትር ጸልዩ።+ +18 ለሁሉም ነገር አመስግኑ።+ አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ያለው ፈቃድ ይህ ነው። +19 የመንፈስን እሳት አታጥፉ።+ +20 ትንቢቶችን አትናቁ።+ +21 ሁሉንም ነገር መርምሩ፤+ መልካም የሆነውን አጥብቃችሁ ያዙ። +22 ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ራቁ።+ +23 የሰላም አምላክ ራሱ ሙሉ በሙሉ ይቀድሳችሁ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኝበት ጊዜ መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና* አካላችሁ በማንኛውም ረገድ ጤናማ ይሁን፤ ደግሞም ነቀፋ አይገኝበት።+ +24 የጠራችሁ ታማኝ ነው፤ ይህን በእርግጥ ያደርገዋል። +25 ወንድሞች፣ ስለ እኛ መጸለያችሁን አታቋርጡ።+ +26 ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው። +27 ይህ ደብዳቤ ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አደራ እላችኋለሁ።+ +28 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። +3 በመጨረሻም ወንድሞች፣ በእናንተ ዘንድ እንደሆነው ሁሉ የይሖዋ* ቃል በፍጥነት መስፋፋቱን ���ንዲቀጥልና+ እንዲከበር ስለ እኛ መጸለያችሁን አታቋርጡ፤+ +2 ደግሞም ከመጥፎና ከክፉ ሰዎች እንድንድን+ ጸልዩልን፤ እምነት ሁሉም ሰው የሚኖረው ነገር አይደለምና።+ +3 ጌታ ግን ታማኝ ነው፤ እሱ ያጠነክራችኋል፤ እንዲሁም ከክፉው ይጠብቃችኋል። +4 ከዚህም በላይ እኛ የጌታ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን፣ ያዘዝናችሁን እያደረጋችሁ እንዳለና ወደፊትም ማድረጋችሁን እንደምትቀጥሉ በእናንተ እንተማመናለን። +5 አምላክን እንድትወዱና+ ክርስቶስን በጽናት+ እንድትከተሉ ጌታ ልባችሁን በትክክለኛው አቅጣጫ መምራቱን ይቀጥል። +6 ወንድሞች፣ በሥርዓት ከማይሄድና+ ከእኛ የተቀበላችሁትን* ወግ* ከማይከተል+ ማንኛውም ወንድም እንድትርቁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። +7 የእኛን አርዓያ እንዴት መከተል እንዳለባችሁ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤+ ምክንያቱም በመካከላችሁ ሳለን ሥርዓት በጎደለው መንገድ አልተመላለስንም፤ +8 እንዲሁም የማንንም ምግብ በነፃ አልበላንም።+ እንዲያውም ብዙ ወጪ በማስወጣት በማናችሁም ላይ ሸክም ላለመሆን ሌት ተቀን በመሥራት እንደክምና እንለፋ ነበር።+ +9 ይህን ያደረግነው የእኛን አርዓያ እንድትከተሉ+ ራሳችንን ለእናንተ ምሳሌ አድርገን ለማቅረብ ብለን እንጂ ሥልጣን ሳይኖረን ቀርቶ አይደለም።+ +10 እንዲያውም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “መሥራት የማይፈልግ ሁሉ አይብላ” የሚል ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበር።+ +11 አንዳንዶች ሥራ ፈት በመሆን በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ+ ሥርዓት በጎደለው መንገድ በመካከላችሁ እንደሚመላለሱ እንሰማለንና።+ +12 እንዲህ ያሉ ሰዎች አርፈው ሥራቸውን በመሥራት በድካማቸው ያገኙትን እንዲበሉ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛቸዋለን፤ እንዲሁም አጥብቀን እንመክራቸዋለን።+ +13 እናንተ ግን ወንድሞች፣ መልካም የሆነውን ከማድረግ አትታክቱ። +14 ሆኖም በዚህ ደብዳቤ አማካኝነት ላስተላለፍነው ቃል የማይታዘዝ ሰው ቢኖር ይህን ሰው ምልክት አድርጉበት፤* ያፍርም ዘንድ ከእሱ ጋር አትግጠሙ።+ +15 ይሁን እንጂ እንደ ጠላት አትመልከቱት፤ ከዚህ ይልቅ እንደ ወንድም አጥብቃችሁ መምከራችሁን ቀጥሉ።+ +16 የሰላም ጌታ ራሱ በሁሉም መንገድ ዘወትር ሰላም ይስጣችሁ።+ ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን። +17 እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ የጻፍኩላችሁ ሰላምታ ይድረሳችሁ፤+ ይህ የእጅ ጽሑፍ የደብዳቤዎቼ ሁሉ መለያ ነው፤ አጻጻፌ እንዲህ ነው። +18 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን። +1 አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድነት ላለው የተሰሎንቄ ሰዎች ጉባኤ፣ ከጳውሎስ፣ ከስልዋኖስና* ከጢሞቴዎስ+ የተላከ ደብዳቤ፦ +2 አባት ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። +3 ወንድሞች፣ ስለ እናንተ አምላክን ሁልጊዜ ለማመስገን እንገፋፋለን። እምነታችሁ እጅግ እያደገ በመሄዱና ሁላችሁም እርስ በርስ የምታሳዩት ፍቅር እየጨመረ በመምጣቱ ይህን ማድረጋችን ተገቢ ነው።+ +4 ስለዚህ እየደረሰባችሁ* ያለውን ስደትና መከራ ሁሉ ችላችሁ በመኖር+ ባሳያችሁት ጽናትና እምነት የተነሳ በአምላክ ጉባኤዎች መካከል እኛ ራሳችን ስለ እናንተ በኩራት እንናገራለን።+ +5 ይህ ሁሉ አምላክ ትክክለኛ ፍርድ እንደፈረደ የሚያሳይ ማስረጃ ከመሆኑም በተጨማሪ መከራ እየተቀበላችሁለት ላለው የአምላክ መንግሥት ብቁ ሆናችሁ እንድትቆጠሩ የሚያደርግ ነው።+ +6 ከዚህ አንጻር አምላክ መከራን ለሚያመጡባችሁ በአጸፋው መከራን መክፈሉ የጽድቅ እርምጃ ነው።+ +7 መከራን የምትቀበሉት እናንተ ግን ጌታ ኢየሱስ ከኃያላን መላእክቱ ጋር+ ከሰማይ በሚገለጥበት ��ዜ+ ከእኛ ጋር እረፍት ይሰጣችኋል፤ +8 የሚገለጠውም በሚንበለበል እሳት ነው፤ በዚያን ጊዜ አምላክን በማያውቁትና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ለሚገልጸው ምሥራች በማይታዘዙት ላይ የበቀል እርምጃ ይወስዳል።+ +9 እነዚህ ሰዎች ዘላለማዊ ጥፋት ተፈርዶባቸው ከጌታ ፊት ይወገዳሉ፤+ ክብራማ ኃይሉንም አያዩም፤ +10 በዚያን ጊዜ ከቅዱሳኑ ጋር ሊከበር ይመጣል፤ በእሱ የሚያምኑም ሁሉ በአድናቆት ያዩታል፤ እናንተም የሰጠናችሁን ምሥክርነት በእምነት ስለተቀበላችሁ ከእነሱ መካከል ትቆጠራላችሁ። +11 በዚህ ምክንያት አምላካችን ለጥሪው+ ብቁዎች አድርጎ እንዲቆጥራችሁ እንዲሁም የወደደውን መልካም ነገር ሁሉና በእምነት ተገፋፍታችሁ የምታከናውኑትን ሥራ በኃይሉ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ እንዲፈጽም ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን። +12 ይህም በአምላካችንና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ መሠረት የጌታችን የኢየሱስ ስም በእናንተ እንዲከበርና እናንተም ከእሱ ጋር ባላችሁ አንድነት እንድትከበሩ ነው። +2 ይሁን እንጂ ወንድሞች፣ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገኘትና+ ከእሱ ጋር ለመሆን አንድ ላይ መሰብሰባችንን+ በተመለከተ ይህን እንለምናችኋለን፤ +2 በመንፈስ በተነገረ ቃል* ወይም በቃል መልእክት ወይም ደግሞ ከእኛ የተላከ በሚመስል ደብዳቤ አማካኝነት የይሖዋ* ቀን+ ደርሷል ብላችሁ በማሰብ የማመዛዘን ችሎታችሁ በቀላሉ አይናወጥ፤+ ደግሞም አትደናገጡ። +3 ማንም ሰው በምንም መንገድ አያሳስታችሁ፤ ምክንያቱም በመጀመሪያ ክህደቱ+ ሳይመጣና የጥፋት ልጅ የሆነው የዓመፅ ሰው+ ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣም።+ +4 እሱ አምላክ ነኝ እያለ በማወጅ በአምላክ ቤተ መቅደስ ይቀመጥ ዘንድ አምላክ ተብሎ ከሚጠራ ወይም ከሚመለክ ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው። +5 ያኔ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ እነዚህን ነገሮች እነግራችሁ እንደነበር አታስታውሱም? +6 በገዛ ራሱ ጊዜ ይገለጥ ዘንድ አሁን የሚያግደው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ። +7 እርግጥ ሚስጥራዊ የሆነው ይህ ዓመፅ አሁንም እየሠራ ነው፤+ ሆኖም ሚስጥር ሆኖ የሚቆየው አሁን አግዶት ያለው ነገር ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ ብቻ ነው። +8 ከዚያ በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ+ የሚያስወግደውና የእሱ መገኘት ይፋ በሚሆንበት ጊዜ+ እንዳልነበረ የሚያደርገው ዓመፀኛ ይገለጣል። +9 ሆኖም የዓመፀኛው መገኘት የሰይጣን ሥራ+ ሲሆን ይህም የሚፈጸመው በተአምራት፣ በሐሰተኛ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ሁሉ+ +10 እንዲሁም ለማታለል ማንኛውንም ዓይነት የክፋት ዘዴ+ በመጠቀም ነው። ወደ ጥፋት እያመሩ ያሉት ሰዎች ይድኑ ዘንድ የእውነት ፍቅር በውስጣቸው ስለሌለ ይህ ሁሉ እንደ ቅጣት ይደርስባቸዋል። +11 በዚህም ምክንያት አምላክ ሐሰት የሆነውን ያምኑ ዘንድ አታላይ በሆነ ተጽዕኖ ተሸንፈው እንዲስቱ ይፈቅዳል፤+ +12 ይህን የሚያደርገው እውነትን ከማመን ይልቅ በዓመፅ ስለሚደሰቱ ሁሉም እንዲፈረድባቸው ነው። +13 ይሁን እንጂ በይሖዋ* የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ አምላክ እናንተን በመንፈሱ በመቀደስ+ እንዲሁም በእውነት ላይ ባላችሁ እምነት መዳን እንድታገኙ ከመጀመሪያው አንስቶ ስለመረጣችሁ+ አምላክን ስለ እናንተ ሁልጊዜ ለማመስገን እንገፋፋለን። +14 የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር እንድታገኙ፣ እኛ በምናውጀው ምሥራች አማካኝነት ለዚህ ዓላማ ጠርቷችኋል።+ +15 ስለዚህ ወንድሞች ጸንታችሁ ቁሙ፤+ እንዲሁም ከእኛ በተላከ የቃል መልእክትም ሆነ ደብዳቤ የተማራችኋቸውን ወጎች አጥብቃችሁ ያዙ።+ +16 በተጨማሪም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንዲሁም የወደደን፣+ በጸጋም አማካኝነት ዘላለማዊ መጽናኛና መልካም ተ��ፋ+ የሰጠን አባታችን የሆነው አምላክ +17 ልባችሁን ያጽናኑ፤ እንዲሁም ምንጊዜም መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉና እንድትናገሩ ያጽኗችሁ።* +3 ይህ ቃል እምነት የሚጣልበት ነው፦ የበላይ ተመልካች+ ለመሆን የሚጣጣር ሰው መልካም ሥራን ይመኛል። +2 ስለዚህ የበላይ ተመልካች የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ በልማዶቹ ልከኛ የሆነ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው፣*+ ሥርዓታማ፣ እንግዳ ተቀባይ፣+ የማስተማር ብቃት ያለው፣+ +3 የማይሰክር፣*+ ኃይለኛ ያልሆነ፣* ይልቁንም ምክንያታዊ የሆነ፣+ የማይጣላ፣+ ገንዘብ ወዳድ ያልሆነ፣+ +4 ታዛዥና ቁም ነገረኛ የሆኑ ልጆች ያሉትና የራሱን ቤተሰብ በተገቢው ሁኔታ የሚያስተዳድር ሊሆን ይገባዋል፤+ +5 (ደግሞስ አንድ ሰው የራሱን ቤተሰብ እንዴት እንደሚያስተዳድር ካላወቀ የአምላክን ጉባኤ እንዴት ሊንከባከብ ይችላል?) +6 በትዕቢት ተነፍቶ ዲያብሎስ የተፈረደበት ዓይነት ፍርድ እንዳይፈረድበት አዲስ ክርስቲያን አይሁን።+ +7 ከዚህም በተጨማሪ እንዳይነቀፍና* በዲያብሎስ ወጥመድ ውስጥ እንዳይወድቅ በውጭ ባሉት* ሰዎች ዘንድ በመልካም የተመሠከረለት* ሊሆን ይገባል።+ +8 የጉባኤ አገልጋዮችም በተመሳሳይ ቁም ነገረኞች፣ በሁለት ምላስ የማይናገሩ፣* ብዙ የወይን ጠጅ የማይጠጡ፣ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የማይስገበገቡ፣+ +9 የእምነትን ቅዱስ ሚስጥር በንጹሕ ሕሊና አጥብቀው የሚይዙ መሆን ይገባቸዋል።+ +10 በተጨማሪም ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በቅድሚያ ይፈተኑ፤ ከዚያም ከክስ ነፃ ሆነው+ ከተገኙ አገልጋይ ሆነው ያገልግሉ። +11 ሴቶችም እንደዚሁ ቁም ነገረኞች፣ የሰው ስም የማያጠፉ፣+ በልማዶቻቸው ልከኞችና በሁሉም ነገር ታማኞች ሊሆኑ ይገባል።+ +12 የጉባኤ አገልጋዮች የአንዲት ሚስት ባል እንዲሁም ልጆቻቸውንና የራሳቸውን ቤተሰብ በተገቢው ሁኔታ የሚያስተዳድሩ ሊሆኑ ይገባል። +13 በተገቢው ሁኔታ የሚያገለግሉ ወንዶች ለራሳቸው መልካም ስም የሚያተርፉ ከመሆናቸውም በላይ በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ስላላቸው እምነት አፋቸውን ሞልተው ለመናገር የሚያስችል ነፃነት ያገኛሉና። +14 በቅርቡ ወደ አንተ እንደምመጣ ተስፋ ባደርግም እነዚህን ነገሮች ጽፌልሃለሁ፤ +15 ይህን ያደረግኩት ምናልባት ብዘገይ በአምላክ ቤተሰብ+ ይኸውም የእውነት ዓምድና ድጋፍ በሆነው የሕያው አምላክ ጉባኤ ውስጥ ምን ዓይነት ምግባር ማሳየት እንዳለብህ ታውቅ ዘንድ ነው። +16 በእርግጥም ይህ ለአምላክ የማደር ቅዱስ ሚስጥር ያለጥርጥር ታላቅ ነው፦ ‘በሥጋ እንዲገለጥ ተደረገ፤+ በመንፈስ ጻድቅ ተባለ፤+ ለመላእክት ታየ፤+ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፤+ በዓለም ያሉ አመኑበት፤+ በክብር አረገ።’ +1 አዳኛችን በሆነው አምላክና ተስፋችን+ በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ትእዛዝ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ +2 በእምነት እውነተኛ ልጄ+ ለሆነው ለጢሞቴዎስ፦*+ አባት ከሆነው አምላክና ከጌታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ለአንተ ይሁን። +3 ወደ መቄዶንያ ልሄድ በተነሳሁበት ጊዜ በኤፌሶን እንድትቆይ እንዳበረታታሁህ ሁሉ አሁንም አንዳንዶች የሐሰት ትምህርት እንዳያስፋፉ ታዛቸው ዘንድ በዚያው እንድትቆይ አበረታታሃለሁ፤ +4 በተጨማሪም ለፈጠራ ወሬዎችና+ ለትውልድ ሐረግ ቆጠራ ትኩረት እንዳይሰጡ እዘዛቸው። እንዲህ ያሉ ነገሮች ለግምታዊ ሐሳቦች በር ከመክፈት ውጭ የሚያስገኙት ፋይዳ የለም፤+ አምላክ እምነትን ለማጠናከር ከሚሰጠው ነገር ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም። +5 የዚህ ትእዛዝ* ዓላማ ከንጹሕ ልብ፣ ከጥሩ ሕሊናና ግብዝነት ከሌለበት እምነት+ የሚመነጭ ፍቅር+ እንዲኖረን ነው። +6 አንዳንዶች እነዚህን ነገሮች በመተው ���ሬ ቢስ ወደሆነ ወሬ ፊታቸውን አዙረዋል።+ +7 የሕግ አስተማሪዎች+ መሆን ይፈልጋሉ፤ ሆኖም የሚናገሯቸውን ነገሮችም ሆነ አጥብቀው የሚሟገቱላቸውን ነገሮች አያስተውሉም። +8 አንድ ሰው በአግባቡ ሥራ ላይ እስካዋለው ድረስ ሕጉ መልካም ነው፤ +9 ደግሞም ሕግ የሚወጣው ለጻድቅ ሰው ሳይሆን ሕግ ለሚተላለፉና+ ለዓመፀኞች፣ ፈሪሃ አምላክ ለሌላቸውና ለኃጢአተኞች፣ ታማኞች ላልሆኑና* ቅዱስ የሆነውን ለሚንቁ፣ አባትንና እናትን ለሚገድሉ እንዲሁም ለነፍሰ ገዳዮች መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል፤ +10 በተጨማሪም ለሴሰኞች፣* ግብረ ሰዶም ለሚፈጽሙ ወንዶች፣* ለአፋኞች፣ ለውሸታሞችና በሐሰት ለሚምሉ* እንዲሁም ትክክለኛውን* ትምህርት+ ለሚጻረሩ ነገሮች ሁሉ ነው፤ +11 ይህ ትምህርት ደስተኛው አምላክ ከገለጸው ክብራማ ምሥራች ጋር የሚስማማ ሲሆን እሱም ምሥራቹን በአደራ ሰጥቶኛል።+ +12 ለአገልግሎቱ በመሾም ታማኝ አድርጎ ስለቆጠረኝ ኃይል የሰጠኝን ጌታችን ክርስቶስ ኢየሱስን አመሰግናለሁ፤+ +13 ምንም እንኳ ቀደም ሲል አምላክን የምሳደብ፣ አሳዳጅና እብሪተኛ የነበርኩ ብሆንም ይህን አድርጎልኛል።+ ደግሞም ባለማወቅና ባለማመን ስላደረግኩት፣ ምሕረት ተደርጎልኛል። +14 የጌታችን ጸጋም ከእምነት እንዲሁም የክርስቶስ ኢየሱስ ተከታይ በመሆኔ ምክንያት ካገኘሁት ፍቅር ጋር እጅግ ተትረፍርፎልኛል። +15 ‘ክርስቶስ ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳን+ ወደ ዓለም መጣ’ የሚለው ቃል እምነት የሚጣልበትና ሙሉ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚገባው ነው። ከኃጢአተኞች ደግሞ እኔ ዋነኛ ነኝ።+ +16 ይሁንና ለእኔ ምሕረት የተደረገው ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ዋነኛ ኃጢአተኛ የሆንኩትን እኔን ምሳሌ አድርጎ በመጠቀም የዘላለም ሕይወት ለማግኘት እምነታቸውን በእሱ ላይ ለሚጥሉ ሰዎች ትዕግሥቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ነው።+ +17 እንግዲህ ለማይጠፋውና+ ለማይታየው፣+ እሱ ብቻ አምላክ ለሆነው+ ለዘላለሙ ንጉሥ+ ክብርና ግርማ ለዘላለም ይሁን። አሜን። +18 ልጄ ጢሞቴዎስ፣ ከዚህ ቀደም ስለ አንተ በተነገሩት ትንቢቶች መሠረት ይህን ትእዛዝ* በአደራ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም ከእነዚህ ጋር በሚስማማ መንገድ መልካሙን ውጊያ መዋጋትህን እንድትቀጥል ነው፤+ +19 ይህን የምታደርገው እምነትንና ጥሩ ሕሊናን+ አጥብቀህ በመያዝ ነው፤ አንዳንዶች ሕሊናቸውን ወደ ጎን ገሸሽ በማድረጋቸው ባሕር ላይ አደጋ ደርሶበት እንደተሰባበረ መርከብ እምነታቸው ጠፍቷል። +20 ከእነሱም መካከል ሄሜኔዎስና+ እስክንድር ይገኙበታል፤ እነሱ ከተግሣጽ ተምረው በአምላክ ላይ የስድብ ቃል ከመናገር እንዲቆጠቡ ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቻቸዋለሁ።*+ +2 እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች በተመለከተ ምልጃ፣ ጸሎት፣ ልመናና ምስጋና እንዲቀርብ አሳስባለሁ፤ +2 በተጨማሪም ነገሥታትንና በሥልጣን ላይ ያሉትን ሁሉ በተመለከተ እንዲሁ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤+ ይህም ሙሉ በሙሉ ለአምላክ በማደርና ሁሉንም ነገር በትጋት በማከናወን* በጸጥታና በተረጋጋ ሁኔታ መኖራችንን እንቀጥል ዘንድ ነው።+ +3 ይህም አዳኛችን በሆነው አምላክ+ ፊት መልካምና ተቀባይነት ያለው ነው፤ +4 የእሱ ፈቃድ ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲድኑና+ የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ ነው። +5 አንድ አምላክ አለና፤+ በአምላክና በሰው መካከል+ ደግሞ አንድ መካከለኛ አለ፤+ እሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤+ +6 ራሱን ለሁሉ* ተመጣጣኝ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤+ በተወሰነለት ጊዜም የምሥክርነት ቃል የሚነገርለት ነገር ይህ ነው። +7 ሰባኪና ሐዋርያ+ ይኸውም እምነትንና እውነትን በተመለከተ የአሕዛብ አስተማሪ+ ሆኜ የተሾምኩት ለዚህ ምሥክርነት ሲባል ነው፤+ ይህን ስል እውነቱን እየተናገርኩ ነው እንጂ እየዋሸሁ አይደለም። +8 ስለዚህ በሁሉም ቦታ ወንዶች ቁጣንና+ ክርክርን+ አስወግደው ታማኝ እጆችን ወደ ላይ በማንሳት+ አዘውትረው እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ። +9 በተመሳሳይም ሴቶች ፀጉር በመሸረብና በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ደግሞ በጣም ውድ በሆነ ልብስ ሳይሆን በልከኝነትና በማስተዋል፣* ተገቢ በሆነ* ልብስ ራሳቸውን ያስውቡ፤+ +10 ለአምላክ ያደርን ነን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉት እንደሚገባ በመልካም ሥራ ይዋቡ።+ +11 ሴት ሙሉ በሙሉ በመገዛት+ በጸጥታ* ትማር። +12 ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም።+ +13 በመጀመሪያ የተፈጠረው አዳም ነውና፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች።+ +14 በተጨማሪም አዳም አልተታለለም፤ ከዚህ ይልቅ ፈጽሞ የተታለለችውና+ ሕግ የተላለፈችው ሴቷ ናት። +15 ይሁን እንጂ ሴት ጤናማ አስተሳሰብ በመያዝ* በእምነት፣ በፍቅርና በቅድስና ብትጸና ልጅ በመውለድ+ ደህንነቷ ተጠብቆ* ትኖራለች።+ +4 ይሁን እንጂ በመንፈስ መሪነት የተነገረው ቃል በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች ከመናፍስት ለሚመነጩ አሳሳች ቃሎችና*+ ለአጋንንት ትምህርቶች ጆሯቸውን በመስጠት ከእምነት መውጣታቸው እንደማይቀር በግልጽ ይናገራል፤ +2 ይህም የሚሆነው በጋለ ብረት የተተኮሰ ያህል ሕሊናቸው የደነዘዘባቸው ግብዝ ሰዎች በሚናገሩት ውሸት የተነሳ ነው።+ +3 እነዚህ ሰዎች ጋብቻን ይከለክላሉ፤+ እንዲሁም እምነት ያላቸውና እውነትን በትክክል የተረዱ ሰዎች ምስጋና አቅርበው እንዲበሏቸው+ አምላክ የፈጠራቸውን ምግቦች+ ‘አትብሉ’ ብለው ያዛሉ።+ +4 ይሁንና አምላክ የፈጠረው ነገር ሁሉ መልካም ነው፤+ በምስጋና እስከተቀበሉት ድረስ ምንም የሚጣል ነገር የለም፤+ +5 በአምላክ ቃልና በጸሎት ተቀድሷልና። +6 ይህን ምክር ለወንድሞች በመስጠት የእምነትንና አጥብቀህ የተከተልከውን የመልካም ትምህርት ቃል በሚገባ የተመገብክ የክርስቶስ ኢየሱስ ጥሩ አገልጋይ ትሆናለህ።+ +7 ነገር ግን አሮጊቶች እንደሚያወሯቸው ካሉ አምላክን የሚጻረሩ የውሸት ታሪኮች ራቅ።+ ከዚህ ይልቅ ለአምላክ ማደርን ግብ አድርገህ ራስህን አሠልጥን። +8 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ* በጥቂቱ ይጠቅማል፤ ለአምላክ ማደር ግን ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ ሕይወት ተስፋ ስለሚሰጥ ለሁሉም ነገር ይጠቅማል።+ +9 ይህ ቃል እምነት የሚጣልበትና ሙሉ በሙሉ ሊቀበሉት የሚገባ ነው። +10 ጠንክረን በመሥራትና ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ ያለነውም ለዚህ ነው፤+ ምክንያቱም ሁሉንም ዓይነት ሰዎች+ በተለይ ደግሞ ታማኝ የሆኑትን በሚያድነው+ ሕያው አምላክ ላይ ተስፋችንን ጥለናል። +11 እነዚህን ትእዛዛት መስጠትህንና ማስተማርህን ቀጥል። +12 ወጣት በመሆንህ ማንም ሰው ሊንቅህ አይገባም። ከዚህ ይልቅ ታማኞች ለሆኑት በንግግር፣ በምግባር፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርዓያ ሁን። +13 እኔ እስክመጣ ድረስ ለሰዎች ለማንበብ፣+ አጥብቀህ ለመምከርና* ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ። +14 የሽማግሌዎች አካል እጁን በአንተ ላይ በጫነበት+ ጊዜ በትንቢት የተሰጠህን ስጦታ ቸል አትበል። +15 እድገትህ በሁሉም ሰዎች ዘንድ በግልጽ እንዲታይ በእነዚህ ነገሮች ላይ አሰላስል፤* እንዲሁም ትኩረትህ ሙሉ በሙሉ በእነዚህ ነገሮች ላይ ያረፈ ይሁን። +16 ለራስህና ለምታስተምረው ትምህርት ምንጊዜም ትኩረት ስጥ።+ በእነዚህ ነገሮች ጽና፤ ይህን በማድረግ ራስህንም ሆነ የሚሰሙህን ታድናለህና።+ +6 የአምላክ ስምና ትምህርት ፈጽሞ እንዳይሰደብ በባርነት ቀንበር ሥር ያሉ ሁሉ ጌቶቻቸው ሙሉ ክብር እንደሚገባቸው ይገንዘቡ።+ +2 በተጨማሪም አማኝ የሆኑ ጌቶች ያሏቸው ባሪያዎች፣ ጌቶቻቸው ወንድሞች ስለሆኑ ብቻ አክብሮት አይንፈጓቸው። ከዚህ ይልቅ እነሱ ከሚሰጡት ጥሩ አገልግሎት እየተጠቀሙ ያሉት፣ የእምነት ባልንጀሮቻቸውና የተወደዱ ወንድሞቻቸው ስለሆኑ ይበልጥ በትጋት ያገልግሏቸው። እነዚህን ነገሮች ማስተማርህንና እነዚህን ማሳሰቢያ +3 አንድ ሰው የተለየ ትምህርት ቢያስተምርና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካስተማረው ትክክለኛ* ትምህርትም+ ሆነ ለአምላክ ማደርን ከሚያበረታታው ትምህርት+ ጋር የማይስማማ ቢሆን +4 ይህ ሰው በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያስተውል ነው።+ ስለ ቃላት የመጨቃጨቅና የመከራከር አባዜ* የተጠናወተው ነው።+ እንዲህ ያሉ ነገሮች ቅናት፣ ጠብ፣ ስም ማጥፋትና* መጥፎ ጥርጣሬ ያስከትላሉ፤ +5 በተጨማሪም ለአምላክ ማደር ጥቅም ማግኛ እንደሆነ አድርገው በሚያስቡ፣+ አእምሯቸው በተበላሸና+ እውነትን መረዳት ባቆሙ ሰዎች መካከል ተራ በሆኑ ጉዳዮች የማያባራ ጭቅጭቅ ያስነሳሉ። +6 እንደ እውነቱ ከሆነ ለአምላክ ያደርን+ መሆናችንና ባለን ነገር ረክተን መኖራችን ትልቅ ጥቅም ያስገኛል። +7 ወደ ዓለም ያመጣነው ምንም ነገር የለምና፤ ምንም ነገር ይዘን መሄድም አንችልም።+ +8 ስለዚህ ምግብና ልብስ* ካለን በእነዚህ ነገሮች ረክተን መኖር ይገባናል።+ +9 ሀብታም ለመሆን ቆርጠው የተነሱ ግን ፈተናና ወጥመድ+ ውስጥ ይወድቃሉ፤ እንዲሁም ሰዎችን ጥፋትና ብልሽት ውስጥ በሚዘፍቁ ከንቱና ጎጂ በሆኑ ብዙ ምኞቶች ይያዛሉ።+ +10 የገንዘብ ፍቅር የብዙ ዓይነት ጎጂ ነገሮች ሥር ነውና፤ አንዳንዶች በዚህ ፍቅር ተሸንፈው ከእምነት ጎዳና ስተው ወጥተዋል፤ እንዲሁም ሁለንተናቸውን በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።+ +11 የአምላክ ሰው ሆይ፣ አንተ ግን ከእነዚህ ነገሮች ሽሽ። ከዚህ ይልቅ ጽድቅን፣ ለአምላክ ማደርን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ጽናትንና ገርነትን+ ተከታተል። +12 መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ የተጠራህለትንና በብዙ ምሥክሮች ፊት በጥሩ ሁኔታ በይፋ የተናገርክለትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ። +13 ሁሉንም ነገሮች ሕያው አድርጎ በሚያኖረው አምላክና ለጳንጥዮስ ጲላጦስ+ በይፋ ግሩም ምሥክርነት በሰጠው በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት ይህን አዝሃለሁ፦ +14 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ+ ድረስ ትእዛዙን ያለእንከንና ያለነቀፋ ጠብቅ፤ +15 ደስተኛውና ብቸኛው ኃያል ገዢ በተወሰነለት ጊዜ ራሱን ይገልጣል። እሱ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ነው፤+ +16 ያለመሞትን ባሕርይ+ የተላበሰው እሱ ብቻ ነው፤ ሊቀረብ በማይችል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤+ እሱን ያየ ወይም ሊያየው የሚችል አንድም ሰው የለም።+ ክብርና ዘላለማዊ ኃይል ለእሱ ይሁን። አሜን። +17 አሁን ባለው ሥርዓት* ሀብታም የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ እንዲሁም ተስፋቸውን አስተማማኝነት በሌለው ሀብት+ ላይ ሳይሆን የሚያስደስቱንን ነገሮች ሁሉ አትረፍርፎ በሚሰጠን አምላክ ላይ እንዲጥሉ እዘዛቸው።+ +18 በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፤+ +19 እውነተኛ የሆነውን ሕይወት አጥብቀው መያዝ ይችሉ ዘንድ+ ለራሳቸው ውድ ሀብት ማከማቸታቸውን ይኸውም ለወደፊቱ ጊዜ የሚሆን መልካም መሠረት መጣላቸውን ይቀጥሉ።+ +20 ጢሞቴዎስ ሆይ፣ ቅዱስ የሆነውን ነገር ከሚጻረሩ ከንቱ ንግግሮችና በውሸት “እውቀት” ተብለው ከሚጠሩ እርስ በርሳቸው ከሚቃረኑ ሐሳቦች በመራቅ+ በአደራ የተሰጠህን ነገር ጠብቅ።+ +21 አንዳንዶች እንዲህ ዓይነቱ እውቀት እንዲታይላቸው ለማድረግ ሲጣጣሩ ከእምነት ጎዳና ወጥተዋል። የአምላክ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። +5 ሽማግሌ የሆነውን በኃይለ ቃል አትናገ���ው።+ ከዚህ ይልቅ እንደ አባት ቆጥረህ በደግነት ምከረው፤ ወጣት ወንዶችን እንደ ወንድሞች፣ +2 አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ወጣት ሴቶችን ደግሞ እንደ እህቶች አድርገህ በፍጹም ንጽሕና ያዛቸው። +3 በእርግጥ መበለት ለሆኑ መበለቶች*+ አሳቢነት* አሳያቸው። +4 ሆኖም አንዲት መበለት ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ካሏት እነዚህ ልጆች በመጀመሪያ በራሳቸው ቤተሰብ+ ውስጥ ለአምላክ የማደርን ባሕርይ ማንጸባረቅን እንዲሁም ለወላጆቻቸውና ለአያቶቻቸው የሚገባቸውን ብድራት መክፈልን ይማሩ፤+ ይህ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ነውና።+ +5 በእርግጥ መበለት የሆነችና ምንም የሌላት ሴት ተስፋዋን በአምላክ ላይ ትጥላለች+ እንዲሁም ሌት ተቀን ያለማሰለስ ምልጃና ጸሎት ታቀርባለች።+ +6 ለሥጋዊ ፍላጎቷ ያደረች መበለት ግን በሕይወት ብትኖርም የሞተች ናት። +7 ስለዚህ ከነቀፋ ነፃ መሆን ይችሉ ዘንድ እነዚህን መመሪያዎች* መስጠትህን ቀጥል። +8 በእርግጥም አንድ ሰው የራሱ ለሆኑት በተለይ ደግሞ ለቤተሰቡ አባላት የሚያስፈልጋቸውን ነገር የማያቀርብ ከሆነ እምነትን የካደ ከመሆኑም በላይ እምነት የለሽ ከሆነ ሰው የከፋ ነው።+ +9 አንዲት መበለት ከ60 ዓመት በላይ ከሆነች በመዝገብ ላይ ትጻፍ፤ ደግሞም የአንድ ባል ሚስት የነበረች ልትሆን ይገባል፤ +10 እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፣+ እንግዶችን በመቀበል፣+ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣+ የተቸገሩትን በመርዳትና+ ማንኛውንም በጎ ተግባር በትጋት በማከናወን በመልካም ሥራ ጥሩ ስም ያተረፈች+ ልትሆን ይገባል። +11 በዕድሜ ያልገፉ መበለቶች ግን መዝገብ ላይ መጻፍ የለባቸውም፤ የፆታ ፍላጎታቸው በክርስቲያናዊ አገልግሎታቸው ላይ እንቅፋት በሚፈጥርበት ጊዜ ማግባት ይፈልጋሉና። +12 ደግሞም የመጀመሪያውን የእምነት ቃላቸውን* ስላፈረሱ በራሳቸው ላይ ፍርድ ያመጣሉ። +13 ከዚህ በተጨማሪ በየቤቱ እየዞሩ ሥራ ፈት ይሆናሉ፤ ሥራ ፈት መሆን ብቻ ሳይሆን ማውራት ስለማይገባቸው ነገሮች እያወሩ ሐሜተኞችና በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።+ +14 ስለዚህ በዕድሜ ያልገፉ መበለቶች እንዲያገቡ፣+ ልጆች እንዲወልዱ፣+ ቤታቸውን እንዲያስተዳድሩና ተቃዋሚው ትችት ሊሰነዝር የሚችልበት አጋጣሚ እንዲያገኝ ከማድረግ እንዲቆጠቡ እፈልጋለሁ። +15 እንዲያውም አንዳንዶቹ ከዚህ በፊት ሰይጣንን ለመከተል ዞር ብለዋል። +16 አንዲት አማኝ የሆነች ሴት፣ መበለት የሆኑ ዘመዶች ቢኖሯት ጉባኤው ሸክም እንዳይበዛበት እሷ ትርዳቸው። በዚህ መንገድ ጉባኤው በእርግጥ መበለት የሆኑትን* መርዳት ይችላል።+ +17 በመልካም ሁኔታ የሚያስተዳድሩ+ በተለይ ደግሞ በመናገርና በማስተማር ተግተው የሚሠሩ+ ሽማግሌዎች እጥፍ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል።+ +18 የቅዱስ መጽሐፉ ቃል “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር”፤+ እንዲሁም “ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋል” ይላልና።+ +19 በሁለት ወይም በሦስት ምሥክሮች+ ማስረጃ ካልሆነ በቀር በሽማግሌ ላይ የሚቀርብን ክስ አትቀበል። +20 ለሌሎቹ ማስጠንቀቂያ እንዲሆን* ኃጢአት የመሥራት ልማድ ያላቸውን ሰዎች+ በሁሉ ፊት ውቀሳቸው።+ +21 እነዚህን መመሪያዎች መሠረተ ቢስ ከሆነ ጥላቻና ከአድልዎ በራቀ መንገድ እንድትጠብቅ በአምላክ፣ በክርስቶስ ኢየሱስና በተመረጡት መላእክት ፊት በጥብቅ አዝሃለሁ።+ +22 በማንም ሰው ላይ እጅህን ለመጫን አትቸኩል፤*+ እንዲሁም በሌሎች ኃጢአት ተካፋይ አትሁን፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ። +23 ከእንግዲህ ውኃ አትጠጣ፤* ከዚህ ይልቅ ለሆድህና በተደጋጋሚ ለሚነሳብህ ሕመም ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ። +24 የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት በይፋ የታወቀ ስለሚሆን ወዲያውኑ ፍርድ ያስከትላል፤ የሌሎቹ ሰዎች ኃጢአት ደግሞ ውሎ አድሮ መታወቁ አይቀርም።+ +25 በተመሳሳይም መልካም ሥራዎች በይፋ የታወቁ ናቸው፤+ በይፋ ያልታወቁትም ቢሆኑ ተደብቀው ሊቀሩ አይችሉም።+ +3 ነገር ግን በመጨረሻዎቹ ቀናት+ ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን እንደሚመጣ ይህን እወቅ። +2 ምክንያቱም ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ ጉረኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ታማኝ ያልሆኑ፣ +3 ተፈጥሯዊ ፍቅር የሌላቸው፣* ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ፣ ስም አጥፊዎች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ ጥሩ ነገር የማይወዱ፣ +4 ከዳተኞች፣ ግትሮች፣ በኩራት የተወጠሩ፣ ከአምላክ ይልቅ ሥጋዊ ደስታን የሚወዱ ይሆናሉ፤ +5 ለአምላክ ያደሩ መስለው ይታያሉ፤ በሥራቸው ግን ኃይሉን ይክዳሉ፤+ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። +6 በየቤቱ ሾልከው የሚገቡ ሰዎች የሚነሱት ከእነዚህ መካከል ነው፤ እነዚህ ሰዎች በተለያዩ ምኞቶች የሚነዱትን፣ በኃጢአት የተተበተቡትን ደካማ ሴቶች ይማርካሉ፤ +7 እንደነዚህ ያሉት ሴቶች ሁልጊዜ ይማራሉ፤ ሆኖም ትክክለኛውን የእውነት እውቀት መረዳት አይችሉም። +8 እንግዲህ ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደተቃወሙት ሁሉ እነዚህም እውነትን ይቃወማሉ። እንዲህ ያሉ ሰዎች አእምሯቸው ሙሉ በሙሉ የተበላሸ ከመሆኑም ሌላ በእምነት ጎዳና ስለማይመላለሱ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አጥተዋል። +9 ይሁንና የእነዚያ ሁለት ሰዎች ሞኝነት ለሰው ሁሉ በጣም ግልጽ እንደነበረ ሁሉ የእነዚህ ሰዎች ሞኝነትም ግልጽ ስለሚሆን በአካሄዳቸው ብዙም ሊገፉበት አይችሉም።+ +10 አንተ ግን ትምህርቴን፣ አኗኗሬን፣+ ዓላማዬን፣ እምነቴን፣ ትዕግሥቴን፣ ፍቅሬንና ጽናቴን በጥብቅ ተከትለሃል፤ +11 እንደ አንጾኪያ፣+ ኢቆንዮንና+ ልስጥራ+ ባሉ ቦታዎች የደረሰብኝን ስደትና መከራ ታውቃለህ። ይህን ሁሉ ስደት በጽናት አሳልፌአለሁ፤ ጌታም ከዚህ ሁሉ ታደገኝ።+ +12 በእርግጥም የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በመሆን ለአምላክ ያደሩ ሆነው መኖር የሚፈልጉ ሁሉ ስደት ይደርስባቸዋል።+ +13 ሆኖም ክፉ ሰዎችና አስመሳዮች እያሳሳቱና እየተሳሳቱ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ።+ +14 አንተ ግን በተማርካቸውና አምነህ በተቀበልካቸው ነገሮች ጸንተህ ኑር፤+ ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች እነማን እንዳስተማሩህ ታውቃለህ፤ +15 እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ እንድታገኝ የሚያስችሉህን ቅዱሳን መጻሕፍት+ ከጨቅላነትህ+ ጀምሮ አውቀሃል።+ +16 ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው፤+ እንዲሁም ለማስተማር፣+ ለመውቀስ፣ ነገሮችን ለማቅናትና* በጽድቅ ለመገሠጽ ይጠቅማሉ፤+ +17 ይኸውም የአምላክ ሰው ለማንኛውም መልካም ሥራ በሚገባ በመታጠቅ ሙሉ በሙሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው። +1 በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የሚገኘውን ሕይወት+ በተመለከተ ከተገባው ቃል ጋር በሚስማማ ሁኔታ በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ +2 ለተወዳጁ ልጄ ለጢሞቴዎስ፦+ አባት ከሆነው አምላክና ከጌታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ለአንተ ይሁን። +3 የቀድሞ አባቶቼ እንዳደረጉት ቅዱስ አገልግሎት የማቀርብለትንና በንጹሕ ሕሊና የማገለግለውን አምላክ አመሰግናለሁ፤ ደግሞም ሌት ተቀን አንተን ዘወትር በምልጃዬ አስታውሳለሁ። +4 እንባህን ሳስታውስ፣ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ። +5 በአንተ ውስጥ ያለውን ግብዝነት የሌለበት እምነት+ አስታውሳለሁና፤ ይህ እምነት በመጀመሪያ በአያትህ በሎይድ እንዲሁም በእናትህ በኤውንቄ ዘንድ ነበር፤ ይሁንና በአንተም ውስጥ እንዳለ እርግ���ኛ ነኝ። +6 ስለዚህ በአንተ ላይ እጄን በጫንኩበት+ ጊዜ የተቀበልከውን የአምላክ ስጦታ በቅንዓት እንድትጠቀምበት* አሳስብሃለሁ። +7 አምላክ የኃይል፣+ የፍቅርና የጤናማ አእምሮ መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።+ +8 ስለሆነም ስለ ጌታችን መመሥከር አያሳፍርህ፤+ ደግሞም ለእሱ ስል እስረኛ በሆንኩት በእኔ አትፈር፤ ከዚህ ይልቅ በአምላክ ኃይል በመታመን+ አንተም ለምሥራቹ የበኩልህን መከራ ተቀበል።+ +9 እሱ በእኛ ሥራ ሳይሆን በራሱ ዓላማና ጸጋ የተነሳ አዳነን፤+ እንዲሁም ቅዱስ በሆነ ጥሪ ጠራን።+ ይህን ጸጋ ከረጅም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ሰጠን፤ +10 አሁን ግን ይህ ጸጋ አዳኛችን የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ በመገለጡ ግልጽ ሆኖ ታይቷል፤+ እሱ ሞትን አስወግዶ+ በምሥራቹ አማካኝነት+ ሕይወትንና አለመበስበስን+ በተመለከተ ብርሃን ፈንጥቋል፤+ +11 እኔም ለዚህ ምሥራች ሰባኪ፣ ሐዋርያና አስተማሪ ሆኜ ተሹሜአለሁ።+ +12 አሁን መከራ እየተቀበልኩ ያለሁትም ለዚሁ ነው፤+ ሆኖም አላፍርበትም።+ ያመንኩበትን እሱን አውቀዋለሁና፤ በአደራ የሰጠሁትንም እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ጠብቆ ማቆየት እንደሚችል እተማመናለሁ።+ +13 ከእኔ የሰማኸውን የትክክለኛ* ትምህርት+ መሥፈርት* ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባለህ አንድነት ካገኘኸው እምነትና ፍቅር ጋር አጥብቀህ ያዝ። +14 ይህን መልካም አደራ በእኛ ውስጥ በሚኖረው መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ጠብቅ።+ +15 ፊጌሎስንና ሄርሞጌኔስን ጨምሮ በእስያ አውራጃ+ ያሉት ሁሉ ትተውኝ እንደሄዱ ታውቃለህ። +16 ጌታ ለኦኔሲፎሮስ+ ቤተሰብ ምሕረትን ይስጥ፤ እሱ ብዙ ጊዜ መንፈሴን አድሶልኛልና፤ በታሰርኩበት ሰንሰለትም አላፈረም። +17 እንዲያውም ሮም በነበረ ጊዜ አፈላልጎ አገኘኝ። +18 ጌታ ይሖዋ* በዚያ ቀን ምሕረቱን ይስጠው። ደግሞም በኤፌሶን ያከናወነውን አገልግሎት ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ። +2 እንግዲህ ልጄ+ ሆይ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በሚገኘው ጸጋ አማካኝነት በርታ፤* +2 ከእኔ የሰማኸውንና ብዙዎች የመሠከሩለትን ነገር፣+ ታማኝ ለሆኑ ሰዎች አደራ ስጥ፤ እነሱም በበኩላቸው ሌሎችን ለማስተማር ብቃቱን ያሟላሉ። +3 የክርስቶስ ኢየሱስ ምርጥ ወታደር+ እንደመሆንህ መጠን አንተም በበኩልህ መከራ ተቀበል።+ +4 ወታደር ሆኖ የሚያገለግል ማንኛውም ሰው ለውትድርና የመለመለውን ሰው ደስ ማሰኘት ስለሚፈልግ ራሱን በንግድ ሥራ* አያጠላልፍም። +5 በውድድር የሚሳተፍ ማንኛውም ሰው የውድድሩን ደንብ ጠብቆ ካልተወዳደረ የድሉን አክሊል አይሸለምም።+ +6 ጠንክሮ የሚሠራ ገበሬ ከፍሬው የመጀመሪያው ተቋዳሽ መሆን አለበት። +7 ለምናገረው ነገር ምንጊዜም ትኩረት ስጥ፤ ጌታም በሁሉም ነገር ማስተዋል ይሰጥሃል። +8 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ+ እንዲሁም የዳዊት ዘር+ እንደሆነ አስታውስ፤ እኔም የምሰብከው ምሥራች ይህ ነው፤+ +9 ከዚህም የተነሳ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሬ መከራ እየተቀበልኩ ነው፤ ደግሞም ታስሬአለሁ።+ ሆኖም የአምላክ ቃል አልታሰረም።+ +10 ከዚህም የተነሳ የተመረጡትም በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የሚገኘውን መዳን ከዘላለማዊ ክብር ጋር ያገኙ ዘንድ ለእነሱ ስል ሁሉንም ነገር በጽናት ተቋቁሜ እኖራለሁ።+ +11 የሚከተለው ቃል እምነት የሚጣልበት ነው፦ አብረን ከሞትን አብረን ደግሞ በሕይወት እንደምንኖር የተረጋገጠ ነው፤+ +12 ጸንተን ከኖርን አብረን ደግሞ እንነግሣለን፤+ ብንክደው እሱም ይክደናል፤+ +13 ታማኞች ሆነን ባንገኝ እሱ ምንጊዜም ታማኝ ሆኖ ይኖራል፤ እሱ ራሱን ሊክድ አይችልምና። +14 ስለ ቃላት እንዳይነታረኩ በአምላክ ፊት እየመከርክ* እነዚህን ነገሮች ዘወትር አሳስባቸው፤ እንዲህ ያለው ነገ�� በሚሰሙት ሰዎች ላይ ጉዳት ከማስከተል* በስተቀር ምንም ጥቅም የለውም። +15 የእውነትን ቃል በአግባቡ በመጠቀም፣ ተቀባይነት ሊያገኝ እንደሚገባውና ምንም የሚያፍርበት ነገር እንደሌለው ሠራተኛ አድርገህ ራስህን በአምላክ ፊት ለማቅረብ የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ።+ +16 ሆኖም ቅዱስ የሆነውን ነገር ከሚጻረሩ ከንቱ ንግግሮች ራቅ፤+ እንዲህ ያሉ ንግግሮች* ሰዎች ይበልጥ ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው እየሆኑ እንዲሄዱ ያደርጋሉና፤ +17 እንዲህ ያሉ ንግግሮችን የሚናገሩ ሰዎች ቃላቸው እንደተመረዘ ቁስል ይሰራጫል። ከእነሱም መካከል ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ይገኙበታል።+ +18 እነዚህ ሰዎች ‘ትንሣኤ ቀደም ብሎ ተከናውኗል’ ብለው በመናገር ከእውነት ርቀዋል፤+ ደግሞም የአንዳንዶችን እምነት እያፈረሱ ነው። +19 ይሁን እንጂ “ይሖዋ* የእሱ የሆኑትን ያውቃል”+ እንዲሁም “የይሖዋን* ስም የሚጠራ ሁሉ+ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት ጠንካራው የአምላክ መሠረት ጸንቶ ይኖራል። +20 በአንድ ትልቅ ቤት ውስጥ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ ሳይሆን የእንጨትና የሸክላ ዕቃም ይኖራል፤ አንዳንዱ ክብር ላለው ዓላማ የሚያገለግል ሲሆን ሌላው ግን ክብር ለሌለው ዓላማ ያገለግላል። +21 እንግዲህ ማንም ከእነዚህ ከኋለኞቹ ነገሮች ቢርቅ ክብር ላለው ዓላማ የሚያገለግል፣ የተቀደሰ፣ ለባለቤቱ የሚጠቅምና ለመልካም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ መሣሪያ* ይሆናል። +22 ስለዚህ ከወጣትነት ምኞቶች ሽሽ፤ ከዚህ ይልቅ በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩት ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ለማግኘት ተጣጣር። +23 በተጨማሪም ጠብ ሊያስከትል እንደሚችል በመገንዘብ ሞኝነትና አላዋቂነት ከሚንጸባረቅበት ክርክር ራቅ።+ +24 የጌታ ባሪያ ሊጣላ አይገባውምና፤ ከዚህ ይልቅ ለሰው ሁሉ ገር፣*+ ለማስተማር ብቁ የሆነና በደል ሲደርስበት ራሱን የሚገዛ፣+ +25 እንዲሁም ቀና አመለካከት የሌላቸውን በገርነት* የሚያርም ሊሆን ይገባዋል።+ ምናልባትም አምላክ ትክክለኛ የእውነት እውቀት ያገኙ ዘንድ+ ለንስሐ* ያበቃቸው ይሆናል፤ +26 እነሱም ዲያብሎስ ፈቃዱን ያደርጉ ዘንድ በሕይወት እንዳሉ አጥምዶ እንደያዛቸው+ በመረዳት ወደ ልቦናቸው ተመልሰው ከእሱ ወጥመድ ሊወጡ ይችላሉ። +4 በአምላክ ፊት እንዲሁም በሕያዋንና በሙታን+ ላይ በሚፈርደው+ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አጥብቄ አሳስብሃለሁ፤ ደግሞም በእሱ መገለጥና+ በመንግሥቱ+ አማካኝነት አዝሃለሁ፦ +2 ቃሉን ስበክ፤+ አመቺ በሆነ ጊዜም ሆነ በአስቸጋሪ ጊዜ በጥድፊያ ስሜት አገልግል፤ በብዙ ትዕግሥትና በማስተማር ጥበብ ውቀስ፣+ ገሥጽ እንዲሁም አጥብቀህ ምከር።+ +3 ትክክለኛውን ትምህርት* የማይታገሡበት ጊዜ ይመጣልና፤+ ከዚህ ይልቅ ከራሳቸው ፍላጎት ጋር በሚስማማ ሁኔታ ጆሯቸውን እንዲኮረኩሩላቸው* በዙሪያቸው አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ።+ +4 እውነትን ከመስማት ጆሯቸውን ይመልሳሉ፤ ለተረትም ጆሮ ይሰጣሉ። +5 አንተ ግን በሁሉም ነገር የማስተዋል ስሜትህን ጠብቅ፣ መከራን በጽናት ተቋቋም፣+ የወንጌላዊነትን ሥራ አከናውን* እንዲሁም አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ ፈጽም።+ +6 እኔ እንደ መጠጥ መባ እየፈሰስኩ ነውና፤*+ ደግሞም ነፃ የምለቀቅበት ጊዜ+ በጣም ቀርቧል። +7 መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤+ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤+ እምነትን ጠብቄአለሁ። +8 ከዚህ በኋላ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤+ ጻድቅ ፈራጅ+ የሆነው ጌታ በፍርድ ቀን ይህን እንደ ሽልማት አድርጎ ይሰጠኛል፤+ ይሁንና ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእሱን መገለጥ ለሚናፍቁ ሁሉ ነው። +9 ወደ እኔ ቶሎ ለመምጣት የተቻለህን ሁሉ አድርግ። +10 ዴማስ+ በአሁኑ ጊዜ ያለውን ሥርዓት* ወዶ፣ ትቶኝ ወደ ተሰሎንቄ ሄዷልና፤ ቄርቂ��� ወደ ገላትያ፣ ቲቶ ደግሞ ወደ ድልማጥያ ሄደዋል። +11 አብሮኝ ያለው ሉቃስ ብቻ ነው። ማርቆስ በአገልግሎት ስለሚረዳኝ ከአንተ ጋር ይዘኸው ና። +12 ቲኪቆስን+ ግን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ። +13 ስትመጣ በጥሮአስ፣ ካርጶስ ጋ የተውኩትን ካባ እንዲሁም የመጽሐፍ ጥቅልሎቹን በተለይም ብራናዎቹን* አምጣልኝ። +14 የመዳብ አንጥረኛው እስክንድር ብዙ ጉዳት አድርሶብኛል። ይሖዋ* እንደ ሥራው ይከፍለዋል።+ +15 አንተም ከእሱ ተጠንቀቅ፤ መልእክታችንን ክፉኛ ተቃውሟልና። +16 የመጀመሪያ መከላከያዬን ባቀረብኩበት ወቅት ሁሉም ትተውኝ ሄዱ እንጂ ከእኔ ጎን የቆመ ማንም አልነበረም፤ አምላክ ይህን አይቁጠርባቸው። +17 ሆኖም የስብከቱ ሥራ በእኔ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ እንዲፈጸምና ብሔራት ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ አጠገቤ ቆሞ ኃይል ሰጠኝ፤+ ከአንበሳ አፍም ዳንኩ።+ +18 ጌታ ከክፉ ሥራ ሁሉ ይታደገኛል፤ እንዲሁም አድኖኝ ለሰማያዊ መንግሥቱ ያበቃኛል።+ ለእሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። +19 ለጵርስቅላና ለአቂላ+ እንዲሁም ለኦኔሲፎሮስ+ ቤተሰብ ሰላምታ አቅርብልኝ። +20 ኤርስጦስ+ በቆሮንቶስ ቀርቷል፤ ጢሮፊሞስ+ ግን ስለታመመ በሚሊጢን ትቼዋለሁ። +21 ክረምቱ ከመግባቱ በፊት ለመምጣት የተቻለህን ሁሉ አድርግ። ኤውቡሉስ ሰላም ብሎሃል፤ እንዲሁም ጱዴስ፣ ሊኖስ፣ ቅላውዲያና ወንድሞች ሁሉ ሰላምታቸውን ልከውልሃል። +22 ጌታ ከምታሳየው መንፈስ ጋር ይሁን። ጸጋው ከእናንተ ጋር ይሁን። +3 ለመንግሥታትና ለባለሥልጣናት እንዲገዙና እንዲታዘዙ+ እንዲሁም ለመልካም ሥራ ሁሉ ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስባቸው፤ +2 ደግሞም ስለ ማንም ክፉ ነገር እንዳይናገሩ፣ ጠበኞች እንዳይሆኑ ከዚህ ይልቅ ምክንያታዊ እንዲሆኑና+ ለሰው ሁሉ ገርነትን በተሟላ ሁኔታ እንዲያንጸባርቁ አሳስባቸው።+ +3 እኛም በአንድ ወቅት የማናመዛዝን፣ የማንታዘዝ፣ የምንስት፣ ለተለያየ ምኞትና ሥጋዊ ደስታ የምንገዛ፣ በክፋትና በቅናት የምንኖር፣ በሰዎች ዘንድ የምንጠላና እርስ በርስ የማንዋደድ ነበርን። +4 ይሁን እንጂ አዳኛችን የሆነው አምላክ ደግነትና+ ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር በተገለጠ ጊዜ +5 (እኛ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን+ በምሕረቱ)+ እኛን አጥቦ ሕያው በማድረግና በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በማደስ+ አዳነን።+ +6 ይህን መንፈስ አዳኛችን በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በእኛ ላይ አትረፍርፎ* አፈሰሰው፤+ +7 ይህን ያደረገው በእሱ ጸጋ አማካኝነት ከጸደቅን+ በኋላ ከተስፋችን ጋር በሚስማማ ሁኔታ የዘላለም ሕይወትን+ እንድንወርስ ነው።+ +8 እነዚህ ቃላት እምነት የሚጣልባቸው ናቸው፤ ደግሞም በአምላክ ያመኑ ሁሉ መልካም ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንዲያተኩሩ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ዘወትር አስረግጠህ እንድትናገር እፈልጋለሁ። እነዚህ ነገሮች መልካምና ለሰዎች ጠቃሚ ናቸው። +9 ሆኖም ሞኝነት ከሚንጸባረቅበት ክርክር፣ ከትውልድ ሐረግ ቆጠራ፣ ከጭቅጭቅና ሕጉን በተመለከተ ከሚነሳ ጠብ ራቅ፤ እነዚህ ነገሮች ምንም የማይጠቅሙና ከንቱ ናቸው።+ +10 ኑፋቄ+ የሚያስፋፋን ሰው ከአንዴም ሁለቴ አጥብቀህ ምከረው።*+ ካልሰማህ ግን ከእሱ ራቅ፤+ +11 እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከትክክለኛው መንገድ የወጣና ኃጢአት እየሠራ ያለ ከመሆኑም ሌላ በራሱ ላይ እንደፈረደ እወቅ። +12 አርጤማስን ወይም ቲኪቆስን+ ወደ አንተ ስልክ፣ እኔ ወዳለሁበት ወደ ኒቆጶሊስ ለመምጣት የተቻለህን ሁሉ አድርግ፤ ክረምቱን በዚያ ለማሳለፍ ወስኛለሁና። +13 ሕጉን ጠንቅቆ የሚያውቀው ዜናስም ሆነ አጵሎስ ለጉዟቸው የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እንዲሟላላቸው የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ።+ +14 ይሁን እንጂ አሳሳቢ ችግር ሲፈጠር መርዳት እን��ችሉና+ ፍሬ ቢሶች እንዳይሆኑ የእኛም ሰዎች በመልካም ሥራ መጠመድን ይማሩ።+ +15 አብረውኝ ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል። ለሚወዱን የእምነት ባልንጀሮቻችን ሰላምታ አቅርብልኝ። የአምላክ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን። +1 የአምላክ ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ። ይህ ሐዋርያ፣ አገልግሎቱ ከአምላክ ምርጦች እምነትና ከእውነት ትክክለኛ እውቀት ጋር የሚስማማ ሲሆን ይህ እውነት ለአምላክ ያደሩ ሆኖ ከመኖር ጋር የተቆራኘ ነው፤ +2 ደግሞም ሊዋሽ የማይችለው አምላክ+ ከረጅም ዘመናት በፊት በሰጠው የዘላለም ሕይወት+ ተስፋ ላይ የተመሠረተ ነው፤ +3 ይሁንና አዳኛችን በሆነው አምላክ ትእዛዝ በአደራ በተሰጠኝ+ የስብከቱ ሥራ አማካኝነት ራሱ በወሰነው ጊዜ ቃሉ እንዲታወቅ አደረገ፤ +4 የጋራችን በሆነው እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነው ለቲቶ፦ አባት ከሆነው አምላክና አዳኛችን ከሆነው ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለአንተ ይሁን። +5 አንተን በቀርጤስ የተውኩህ ያልተስተካከሉትን* ነገሮች እንድታስተካክልና በሰጠሁህ መመሪያ መሠረት በየከተማው ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው፤ +6 ይኸውም ከክስ ነፃ የሆነ፣ የአንዲት ሚስት ባል እንዲሁም በስድነት* ወይም በዓመፀኝነት የማይከሰሱ አማኝ የሆኑ ልጆች ያሉት ማንም ሰው ካለ እንድትሾም ነው።+ +7 ምክንያቱም የበላይ ተመልካች በአምላክ የተሾመ መጋቢ እንደመሆኑ መጠን ከክስ ነፃ መሆን አለበት፤ በራሱ ሐሳብ የሚመራ፣+ ግልፍተኛ፣+ ሰካራም፣ ኃይለኛና* አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚስገበገብ ሊሆን አይገባም፤ +8 ከዚህ ይልቅ እንግዳ ተቀባይ፣+ ጥሩ የሆነውን ነገር የሚወድ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው፣*+ ጻድቅ፣ ታማኝ፣+ ራሱን የሚገዛ፣+ +9 እንዲሁም ትክክለኛ* በሆነው ትምህርት+ ማበረታታትም* ሆነ ይህን ትምህርት የሚቃወሙትን መውቀስ+ ይችል ዘንድ የማስተማር ጥበቡን+ ሲጠቀም የታመነውን ቃል* በጥብቅ የሚከተል ሊሆን ይገባል። +10 ዓመፀኞች፣ በከንቱ የሚለፈልፉና አታላዮች የሆኑ በተለይም ግርዘትን በጥብቅ የሚከተሉ ብዙ ሰዎች አሉና።+ +11 እነዚህ ሰዎች አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ማስተማር የማይገባቸውን ትምህርት በማስተማር የመላውን ቤተሰብ እምነት እያፈረሱ ስለሆነ አፋቸውን ማዘጋት ያስፈልጋል። +12 ከእነሱ መካከል የሆነ የገዛ ራሳቸው ነቢይ “የቀርጤስ ሰዎች ምንጊዜም ውሸታሞች፣ አደገኛ አውሬዎችና ሥራ ፈት ሆዳሞች ናቸው” ብሏል። +13 ይህ የምሥክርነት ቃል እውነት ነው። ለዚህም ሲባል እነሱን አጥብቀህ መውቀስህን ቀጥል፤ ይኸውም በእምነት ጠንካሮች* እንዲሆኑ +14 እንዲሁም ለአይሁዳውያን ተረቶችና ከእውነት የራቁ ሰዎች ለሚሰጡት ትእዛዝ ትኩረት እንዳይሰጡ ነው። +15 ንጹሕ ለሆኑ ሰዎች ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤+ ለረከሱና እምነት ለሌላቸው ሰዎች ግን ንጹሕ የሆነ ነገር የለም፤ አእምሯቸውም ሆነ ሕሊናቸው የረከሰ ነውና።+ +16 አምላክን እንደሚያውቁ በይፋ ይናገራሉ፤ ሆኖም በሥራቸው ይክዱታል፤+ ምክንያቱም አስጸያፊና የማይታዘዙ እንዲሁም ለማንኛውም ዓይነት መልካም ሥራ የማይበቁ ናቸው። +2 አንተ ግን ምንጊዜም ከትክክለኛ* ትምህርት ጋር የሚስማማ ነገር ተናገር።+ +2 አረጋውያን ወንዶች በልማዶቻቸው ረገድ ልከኞች፣ ቁም ነገረኞች፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያላቸው እንዲሁም በእምነት፣ በፍቅርና በጽናት ጤናሞች ይሁኑ። +3 በተመሳሳይም አረጋውያን ሴቶች ለቅዱሳን ሰዎች የሚገባ ባሕርይ ያላቸው፣ ስም የማያጠፉ፣ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ እንዲሁም ጥሩ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤ +4 ይህም ወጣት ሴቶችን በመምከር* ባሎቻቸውን የሚወዱ፣ ልጆቻቸውን የሚወዱ፣ +5 ጤናማ አስተሳሰብ ያላቸው፣ ንጹሐን፣ በቤት ውስጥ የሚሠሩ፣* ጥሩዎችና ለባሎቻቸው የሚገዙ+ እንዲሆኑ ለማድረግ ያስችላቸዋል፤ ይህም የአምላክ ቃል እንዳይሰደብ ነው። +6 በተመሳሳይም ወጣት ወንዶች ጤናማ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው አሳስባቸው፤+ +7 በማንኛውም ሁኔታ መልካም ሥራ በመሥራት አርዓያ መሆንህን አሳይ። ንጹሕ የሆነውን ነገር* በቁም ነገር አስተምር፤+ +8 ደግሞም ሊነቀፍ የማይችል ጤናማ* አነጋገር በመጠቀም አስተምር፤+ ይኸውም ተቃዋሚዎች ስለ እኛ የሚናገሩት መጥፎ ነገር አጥተው እንዲያፍሩ ነው።+ +9 ባሪያዎች ጌቶቻቸውን ለማስደሰት ጥረት በማድረግ በሁሉም ነገር ይገዙላቸው፤+ የአጸፋ ቃልም አይመልሱላቸው፤ +10 ደግሞም ሊሰርቋቸው አይገባም፤+ ከዚህ ይልቅ አዳኛችን የሆነው አምላክ ትምህርት በሁሉም መንገድ ውበት እንዲጎናጸፍ ያደርጉ ዘንድ ሙሉ በሙሉ እምነት የሚጣልባቸው ይሁኑ።+ +11 የአምላክ ጸጋ ተገልጧልና፤ ጸጋው ለሁሉም ዓይነት ሰዎች መዳን ያስገኛል።+ +12 ይህም ጸጋ ፈሪሃ አምላክ በጎደለው መንገድ መኖርና ዓለማዊ ምኞቶችን+ መከተል ትተን አሁን ባለው በዚህ ሥርዓት* ውስጥ ጤናማ አስተሳሰብ በመያዝ፣ በጽድቅና ለአምላክ በማደር እንድንኖር ያሠለጥነናል፤+ +13 በዚህ ሁኔታ አስደሳች የሆነውን ተስፋ+ እንዲሁም የታላቁን አምላክና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በክብር መገለጥ እንጠባበቃለን፤ +14 ክርስቶስ ከማንኛውም ዓይነት የዓመፅ ሕይወት እኛን ነፃ ለማውጣትና*+ ለመልካም ሥራ የሚቀና+ ልዩ ንብረቱ የሆነ ሕዝብ ለራሱ ለማንጻት ሕይወቱን ለእኛ ሰጥቷል።+ +15 እነዚህን ነገሮች፣ በሙሉ ሥልጣን መናገርህን፣ አጥብቀህ መምከርህንና* መውቀስህን ቀጥል።+ ማንም ሰው ፈጽሞ አይናቅህ። +1 ለክርስቶስ ኢየሱስ ሲል እስረኛ ከሆነው ከጳውሎስና+ ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፣+ ለተወደደው የሥራ ባልደረባችን ለፊልሞና፣ +2 ለእህታችን ለአፍብያና አብሮን የክርስቶስ ወታደር ለሆነው ለአርክጳ+ እንዲሁም በቤትህ ላለው ጉባኤ፦+ +3 አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። +4 አንተን በጸሎቴ በጠቀስኩ ቁጥር ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤+ +5 ስለ እምነትህ እንዲሁም ለጌታ ኢየሱስና ለቅዱሳን ሁሉ ስላለህ ፍቅር እሰማለሁና። +6 ከሌሎች ጋር የምትጋራው እምነት በክርስቶስ አማካኝነት መልካም ነገሮችን ሁሉ እንደተቀበልን እንድትገነዘብ ይረዳህ ዘንድ እጸልያለሁ። +7 ወንድሜ ሆይ፣ ስለምታሳየው ፍቅር በመስማቴ እጅግ ተደስቻለሁ እንዲሁም ተጽናንቻለሁ፤ ምክንያቱም የቅዱሳን ልብ* በአንተ አማካኝነት ታድሷል። +8 ስለዚህ ተገቢ የሆነውን ነገር እንድታደርግ አንተን ለማዘዝ ከክርስቶስ ጋር በተያያዘ ሙሉ ነፃነት ቢኖረኝም፣ +9 እኔ ጳውሎስ አረጋዊና አሁን ደግሞ ለክርስቶስ ኢየሱስ ስል እስረኛ እንደመሆኔ መጠን ፍቅርን መሠረት በማድረግ እለምንሃለሁ። +10 በእስር ላይ እያለሁ እንደ አባት የሆንኩለትን+ ልጄን አናሲሞስን+ በተመለከተ እለምንሃለሁ። +11 እሱ ቀደም ሲል ምንም አይጠቅምህም ነበር፤ አሁን ግን ለአንተም ሆነ ለእኔ የሚጠቅም ሰው ሆኗል። +12 እሱን፣ አዎ ከልቤ የምወደውን እሱን ወደ አንተ መልሼ ልኬዋለሁ። +13 ለምሥራቹ ስል እዚህ ታስሬ ሳለሁ+ በአንተ ፋንታ እኔን እንዲያገለግል ለራሴ እዚሁ ባስቀረው ደስ ይለኝ ነበር። +14 ነገር ግን የምታደርገው መልካም ነገር በራስህ ፈቃድ እንጂ በግዴታ እንዳይሆን አንተ ሳትስማማ ምንም ነገር ማድረግ አልፈልግም።+ +15 ምናልባት ለአጭር ጊዜ* ከአንተ ጠፍቶ የሄደው፣ ተመልሶ ለዘለቄታው የአንተ ሆኖ እንዲኖር ይሆናል፤ +16 ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ+ ሳይሆን ከባሪያ ይበልጥ እንደተወደደ ወን���ምህ ነው፤+ በተለይ ለእኔ ተወዳጅ ወንድም ነው፤ ሆኖም በሰብዓዊ ግንኙነታችሁም ሆነ ከጌታ ጋር ባላችሁ ዝምድና ለአንተ ይበልጥ ተወዳጅ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። +17 ስለዚህ እኔን እንደ ወዳጅ አድርገህ ከቆጠርከኝ እኔን እንደምትቀበለኝ አድርገህ እሱን በደግነት ተቀበለው። +18 ከዚህም በተጨማሪ የበደለህ ነገር ካለ ወይም የአንተ ዕዳ ካለበት ዕዳውን በእኔ ላይ አስበው። +19 እኔ ጳውሎስ ይህን በራሴ እጅ ጽፌልሃለሁ፦ ያለበትን ዕዳ እኔ እከፍልሃለሁ፤ ደግሞም ከሕይወትህ ጋር በተያያዘም እንኳ የእኔ ባለዕዳ እንደሆንክ መናገር አያስፈልገኝም። +20 ወንድሜ ሆይ፣ ሁለታችንም የጌታ ደቀ መዛሙርት በመሆናችን በዚህ ረገድ እንድትተባበረኝ እፈልጋለሁ፦ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንደመሆንህ መጠን ልቤን* አድስልኝ። +21 ይህን የምጽፍልህ በዚህ እንደምትስማማ በመተማመንና ከምጠይቅህም በላይ እንደምታደርግ በማወቅ ነው። +22 ከዚህም ሌላ ጸሎታችሁ ተሰምቶ ወደ እናንተ እንደምመለስ*+ ተስፋ ስለማደርግ ማረፊያ አዘጋጅልኝ። +23 በክርስቶስ ኢየሱስ የተነሳ አብሮኝ እስረኛ የሆነው ኤጳፍራ+ ሰላምታ ያቀርብልሃል፤ +24 የሥራ ባልደረቦቼ የሆኑት ማርቆስ፣ አርስጥሮኮስ፣+ ዴማስና+ ሉቃስም+ ሰላም ብለውሃል። +25 የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እናንተ ከምታሳዩት መንፈስ ጋር ይሁን። +3 ስለሆነም የሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች+ የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች፣ በእሱ እንደምናምን በይፋ የምንናገርለትን፣ ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ።+ +2 ሙሴ በመላው የአምላክ ቤት ላይ ታማኝ እንደነበረ ሁሉ+ እሱም ለሾመው ታማኝ ነበር።+ +3 ቤቱን የሠራው፣ ከቤቱ የበለጠ ክብር ስላለው እሱ* ከሙሴ የበለጠ ክብር ይገባዋል።+ +4 እያንዳንዱ ቤት ሠሪ እንዳለው የታወቀ ነው፤ ሁሉን ነገር የሠራው ግን አምላክ ነው። +5 ሙሴም በመላው የአምላክ ቤት ላይ ታማኝ አገልጋይ ነበር። አገልግሎቱም ከጊዜ በኋላ ለሚነገሩ ነገሮች ምሥክር ነው። +6 ክርስቶስ ግን በአምላክ ቤት ላይ የተሾመ ታማኝ ልጅ ነበር።+ እኛም አፋችንን ሞልተን የመናገር ነፃነታችንንና የምንደሰትበትን ተስፋችንን እስከ መጨረሻው አጥብቀን ከያዝን የአምላክ ቤት ነን።+ +7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦+ “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ +8 በምድረ በዳ እጅግ የሚያስቆጣ ድርጊት በተፈጸመበት በፈተና ቀን እንደሆነው ልባችሁን አታደንድኑ፤+ +9 በዚያ፣ አባቶቻችሁ ያደረግኩትን ሁሉ ለ40 ዓመት ቢያዩም እኔን በመፈተን ተገዳደሩኝ።+ +10 በዚህም ምክንያት በዚያ ትውልድ በጣም ተንገሸገሽኩ፤ እንዲህም አልኩ፦ ‘ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፤ መንገዴንም ሊያውቁ አልቻሉም።’ +11 በመሆኑም ‘ወደ እረፍቴ አይገቡም’ ብዬ በቁጣዬ ማልኩ።”+ +12 ወንድሞች፣ ሕያው ከሆነው አምላክ በመራቅ እምነት የለሽ የሆነ ክፉ ልብ ከእናንተ መካከል በማናችሁም ውስጥ እንዳያቆጠቁጥ ተጠንቀቁ፤+ +13 ከዚህ ይልቅ ከእናንተ መካከል አንዳችሁም ኃጢአት ባለው የማታለል ኃይል እንዳትደነድኑ “ዛሬ”+ ተብሎ የሚጠራ ጊዜ እስካለ ድረስ በየዕለቱ እርስ በርሳችሁ ተበረታቱ። +14 የክርስቶስ ተካፋዮች የምንሆነው* በመጀመሪያ የነበረንን ትምክህት እስከ መጨረሻው አጽንተን ከያዝን ብቻ ነውና።+ +15 ይህም “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ እጅግ የሚያስቆጣ ድርጊት በተፈጸመበት ጊዜ እንደሆነው ልባችሁን አታደንድኑ” እንደተባለው ነው።+ +16 ድምፁን ቢሰሙም እንኳ እጅግ ያስቆጡት እነማን ነበሩ? ይህን ያደረጉት ሙሴ እየመራቸው ከግብፅ የወጡት ሁሉ አይደሉም?+ +17 ከዚህም ሌላ ለ40 ዓመት አምላክ በእነሱ እንዲንገሸገሽ ያደረጉት እነማን ናቸው?+ እነዚያ ኃጢአት የሠሩትና ��ሳቸው በምድረ በዳ ወድቆ የቀረው አይደሉም?+ +18 ደግሞስ ወደ እረፍቴ አይገቡም ብሎ የማለው ስለ እነማን ነው? እነዚያን ያልታዘዙትን በተመለከተ አይደለም? +19 ስለዚህ ሊገቡ ያልቻሉት እምነት በማጣታቸው የተነሳ እንደሆነ እንረዳለን።+ +7 አብርሃም ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሳሌም ንጉሥና የልዑሉ አምላክ ካህን የሆነው ይህ መልከጼዴቅ አግኝቶት ባረከው፤+ +2 አብርሃም ደግሞ ከሁሉ ነገር አንድ አሥረኛ ሰጠው።* በመጀመሪያ ስሙ “የጽድቅ ንጉሥ” ማለት ነው፤ ደግሞም የሳሌም ንጉሥ ማለትም “የሰላም ንጉሥ” ነው። +3 አባትና እናትም ሆነ የዘር ሐረግ እንዲሁም ለዘመኑ መጀመሪያ፣ ለሕይወቱም መጨረሻ የለውም፤ ከዚህ ይልቅ የአምላክን ልጅ እንዲመስል በመደረጉ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።+ +4 እንግዲህ የቤተሰብ ራስ* የሆነው አብርሃም ምርጥ ከሆነው ምርኮ ላይ አንድ አሥረኛውን የሰጠው+ ይህ ሰው ምን ያህል ታላቅ እንደነበረ ተመልከቱ። +5 እርግጥ የክህነት ኃላፊነት የሚቀበሉ ከሌዊ ልጆች ወገን የሆኑት ሰዎች+ ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከገዛ ወንድሞቻቸው አሥራት እንዲሰበስቡ ሕጉ ያዛል።+ +6 ሆኖም ከእነሱ የትውልድ ሐረግ ያልመጣው ይህ ሰው ከአብርሃም አሥራት የተቀበለ ሲሆን የተስፋ ቃል የተሰጠውን ሰው ባርኮታል።+ +7 እንግዲህ አነስተኛ የሆነው ከእሱ በሚበልጠው እንደተባረከ ምንም ጥርጥር የለውም። +8 በአንድ በኩል አሥራት የሚቀበሉት ሟች የሆኑ ሰዎች ሲሆኑ በሌላ በኩል ግን አሥራት የሚቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሠከረለት ሰው ነው።+ +9 እንግዲህ አሥራት የሚቀበለው ሌዊ እንኳ በአብርሃም በኩል አሥራት ከፍሏል ማለት ይቻላል፤ +10 መልከጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ ሌዊ ገና በአባቱ በአብርሃም አብራክ ውስጥ* ነበርና።+ +11 እንግዲህ ፍጽምና ሊገኝ የሚችለው በሌዊ ክህነት አማካኝነት ቢሆን ኖሮ+ (ክህነቱ ለሕዝቡ የተሰጠው ሕግ አንዱ ገጽታ ስለሆነ)፣ እንደ አሮን ሥርዓት ሳይሆን እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት+ ያለ ተብሎ የተነገረለት ሌላ ካህን መነሳቱ ምን ያስፈልግ ነበር? +12 ክህነቱ ስለሚለወጥ ሕጉም የግድ መለወጥ ያስፈልገዋልና።+ +13 ይህ ሁሉ ነገር የተነገረለት ሰው ከሌላ ነገድ የመጣ ነውና፤ ከዚህ ነገድ ማንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ያገለገለ የለም።+ +14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የታወቀ ነውና፤+ ይሁንና ሙሴ ከዚህ ነገድ ካህናት እንደሚገኙ የተናገረው ነገር የለም። +15 ደግሞም እንደ መልከጼዴቅ ያለ ሌላ ካህን+ ሲነሳ ይህ ጉዳይ ይበልጥ ግልጽ ይሆናል፤+ +16 እሱ ካህን የሆነው በሥጋዊ ትውልድ ላይ በተመካውና ሕጉ በያዘው መሥፈርት ሳይሆን የማይጠፋ ሕይወት+ እንዲኖረው ባስቻለው ኃይል ነው። +17 “እንደ መልከጼዴቅ፣ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ተብሎ ተመሥክሮለታልና።+ +18 እንግዲህ የቀድሞው ትእዛዝ ደካማና ፍሬ ቢስ በመሆኑ ተሽሯል።+ +19 ሕጉ የትኛውንም ነገር ወደ ፍጽምና አላደረሰምና፤+ ወደ አምላክ የምንቀርብበት የተሻለ ተስፋ+ መሰጠቱ ግን ይህን ማድረግ ችሏል።+ +20 በተጨማሪም ይህ ያለመሐላ እንዳልሆነ ሁሉ +21 (ያለመሐላ ካህናት የሆኑ ሰዎች አሉና፤ እሱ ግን በመሐላ ካህን ሆኗል፤ ይህም የሆነው “ይሖዋ* ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ’ ብሎ ምሏል፤ ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም”* በማለት ስለ እሱ የተናገረው አምላክ በማለው መሐላ መሠረት ነው፤)+ +22 እንደዚሁም ኢየሱስ ለተሻለ ቃል ኪዳን ዋስትና* ሆኗል።+ +23 ከዚህም በተጨማሪ ካህናት አገልግሎታቸውን እንዳይቀጥሉ ሞት ስለሚያግዳቸው አንዱ ሌላውን እየተካ እንዲያገለግል ብዙዎች ካህናት መሆን ነበረባቸው፤+ +24 እሱ ግን ለዘላለም+ ሕያው ሆኖ ስለሚኖር ክ���ነቱ ተተኪ የለውም። +25 ስለሆነም ለእነሱ ለመማለድ ሁልጊዜ ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእሱ አማካኝነት ወደ አምላክ የሚቀርቡትን ፈጽሞ ሊያድናቸውም ይችላል።+ +26 እኛ የሚያስፈልገን ታማኝ፣ ቅን የሆነ፣ ያልረከሰ፣+ ከኃጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው።+ +27 እነዚያ ሊቃነ ካህናት ያደርጉ እንደነበረው፣ በመጀመሪያ ለራሱ ኃጢአት ከዚያም ለሕዝቡ ኃጢአት+ በየዕለቱ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤+ ምክንያቱም ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ ይህን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፈጽሞታል።+ +28 ሕጉ ድክመት ያለባቸውን ሰዎች ሊቃነ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤+ ከሕጉ በኋላ የመጣው የመሐላ ቃል+ ግን ለዘላለም ፍጹም የተደረገውን ልጅ+ ይሾማል። +12 እንግዲያው እንዲህ ያለ ታላቅ የምሥክሮች ደመና በዙሪያችን ስላለልን እኛም ማንኛውንም ሸክምና በቀላሉ ተብትቦ የሚይዘንን ኃጢአት+ ከላያችን አንስተን እንጣል፤ ከፊታችን የሚጠብቀንን ሩጫም በጽናት እንሩጥ፤+ +2 የምንሮጠውም የእምነታችን “ዋና ወኪል”* እና “ፍጹም አድራጊ” የሆነውን ኢየሱስን በትኩረት በመመልከት ነው።+ እሱ ከፊቱ ለሚጠብቀው ደስታ ሲል፣ የሚደርስበትን ውርደት ከምንም ሳይቆጥር በመከራ እንጨት* ላይ እስከ መሞት ድረስ ጸንቷል፤ እንዲሁም በአምላክ ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።+ +3 እንግዲህ እንዳትደክሙና ተስፋ እንዳትቆርጡ*+ ኃጢአተኞች የራሳቸውን ጥቅም በመጻረር የሚያሰሙትን እንዲህ ዓይነቱን የተቃውሞ ንግግር በጽናት የተቋቋመውን+ እሱን በጥሞና አስቡ። +4 እናንተ ከዚህ ኃጢአት ጋር እያደረጋችሁ ባላችሁት ትግል ደማችሁ እስኪፈስ ድረስ ገና አልታገላችሁም። +5 ደግሞም ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን የተሰጣችሁን የሚከተለውን ማሳሰቢያ ሙሉ በሙሉ ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ* የሚሰጥህን ተግሣጽ አቅልለህ አትመልከት፤ በሚያርምህም ጊዜ ተስፋ አትቁረጥ፤ +6 ይሖዋ* የሚወዳቸውን ይገሥጻልና፤ እንዲያውም እንደ ልጁ አድርጎ የሚቀበለውን ሁሉ ይቀጣል።”*+ +7 ተግሣጽ የምትቀበሉበት* አንዱ መንገድ ይህ ስለሆነ መከራ ሲደርስባችሁ መጽናት ያስፈልጋችኋል። አምላክ የያዛችሁ እንደ ልጆቹ አድርጎ ነው።+ ለመሆኑ አባቱ የማይገሥጸው ልጅ ማን ነው?+ +8 ሆኖም ሁላችሁም ይህን ተግሣጽ ካልተቀበላችሁ ዲቃላዎች ናችሁ እንጂ ልጆች አይደላችሁም። +9 ከዚህም በላይ ሰብዓዊ አባቶቻችን ይገሥጹን ነበር፤ እኛም እናከብራቸው ነበር። ታዲያ የመንፈሳዊ ሕይወታችን አባት ለሆነው ይበልጥ በፈቃደኝነት በመገዛት በሕይወት ልንኖር አይገባም?+ +10 እነሱ መልካም መስሎ በታያቸው መንገድ ለጥቂት ጊዜ ገሥጸውናል፤ እሱ ግን ከቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን+ ለጥቅማችን ሲል ይገሥጸናል። +11 እርግጥ ነው፣ ማንኛውም ተግሣጽ ለጊዜው የሚያስደስት አይመስልም፤ ይልቁንም ያስከፋል፤* በኋላ ግን በተግሣጽ ሥልጠና ላገኙ ሰዎች የጽድቅን ሰላማዊ ፍሬ ያፈራላቸዋል። +12 ስለዚህ የዛሉትን እጆችና የተብረከረኩትን ጉልበቶች አበርቱ፤+ +13 የተጎዳው የአካል ክፍል እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ እግራችሁ ዘወትር ቀና በሆነ መንገድ እንዲጓዝ አድርጉ።+ +14 ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ፤+ ቅድስናንም ፈልጉ፤+ ያለቅድስና ማንም ሰው ጌታን ማየት አይችልም። +15 ማንም የአምላክን ጸጋ እንዳያጣ ብሎም መርዛማ ሥር በቅሎ ችግር እንዳይፈጥርና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ፤+ +16 በተጨማሪም በመካከላችሁ ሴሰኛ* ሰውም ሆነ ለአንድ ጊዜ መብል ሲል የብኩርና መብቱን አሳልፎ እንደሰጠው እንደ ኤሳው ቅዱስ ነገሮችን የማያደንቅ ሰው እንዳይገኝ ተጠንቀቁ።+ +17 ኤሳው የኋላ ኋላ በረከቱን ለመውረስ በፈለገ ጊዜ እንደተከለከለ ታውቃላችሁና፤ ሐሳብ ለማስቀየር* እያለቀሰ ብርቱ ጥረት ቢያደርግም+ እንኳ አልተሳካለትም። +18 እናንተ እኮ የቀረባችሁት ሊዳሰስ ወደሚችለውና+ በእሳት ወደተያያዘው ተራራ፣+ ወደ ጥቁሩ ደመና፣ ወደ ድቅድቁ ጨለማ፣ ወደ አውሎ ነፋሱ፣+ +19 ወደ መለከት ድምፁና+ ቃል ያሰማ ወደነበረው ድምፅ+ አይደለም፤ ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዳይነገራቸው ለምነው ነበር።+ +20 “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት” የሚለው ትእዛዝ በጣም አስፈርቷቸው ነበርና።+ +21 በተጨማሪም በዚያ ይታይ የነበረው ነገር በጣም አስፈሪ ስለነበረ ሙሴ “ፈራሁ፤ ተንቀጠቀጥኩም” ሲል ተናግሯል።+ +22 እናንተ ግን የቀረባችሁት ወደ ጽዮን ተራራና+ የሕያው አምላክ ከተማ ወደሆነችው ወደ ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም፣+ አንድ ላይ ወደተሰበሰቡ አእላፋት* መላእክት፣ +23 በሰማያት ወደተመዘገበው የበኩራት ጉባኤ፣+ የሁሉ ፈራጅ ወደሆነው አምላክ፣+ ፍጽምና እንዲያገኙ ወደተደረጉት+ ጻድቃን መንፈሳዊ ሕይወት፣+ +24 የአዲስ ቃል ኪዳን+ መካከለኛ ወደሆነው ወደ ኢየሱስና+ ከአቤል ደም በተሻለ ሁኔታ ወደሚናገረው ወደተረጨው ደም ነው።+ +25 እየተናገረ ያለውን እሱን ከመስማት ወደኋላ እንዳትሉ* ተጠንቀቁ። በምድር ላይ መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸው የነበረውን ከመስማት ወደኋላ ያሉት ሰዎች ከቅጣት ካላመለጡ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረውን እሱን ከመስማት ዞር ብንል እንዴት እናመልጣለን?+ +26 በዚያን ጊዜ ድምፁ ምድርን አናውጦ ነበር፤+ አሁን ግን “ምድርን ብቻ ሳይሆን ሰማይን ጭምር እንደገና አናውጣለሁ” ሲል ቃል ገብቷል።+ +27 እንግዲህ “እንደገና” የሚለው አባባል የማይናወጡት ነገሮች ጸንተው ይኖሩ ዘንድ የሚናወጡት ይኸውም የተሠሩት ነገሮች የሚወገዱ መሆናቸውን ያመለክታል። +28 ስለዚህ እኛ ሊናወጥ የማይችል መንግሥት ልንቀበል እንደሆነ ስለምናውቅ ጸጋውን መቀበላችንን እንቀጥል፤ ይህም በጸጋው አማካኝነት በአምላካዊ ፍርሃትና በጥልቅ አክብሮት፣ ተቀባይነት ባለው መንገድ ለአምላክ ቅዱስ አገልግሎት ማቅረብ እንችል ዘንድ ነው። +29 አምላካችን የሚባላ እሳት ነውና።+ +1 በጥንት ዘመን አምላክ በተለያዩ ጊዜያትና በብዙ መንገዶች በነቢያት አማካኝነት ለአባቶቻችን ተናግሯል።+ +2 አሁን ደግሞ በእነዚህ ቀናት መጨረሻ የሁሉም ነገር ወራሽ+ አድርጎ በሾመውና የተለያዩ ሥርዓቶችን* በፈጠረበት+ በልጁ+ አማካኝነት ለእኛ ተናገረ። +3 እሱ የአምላክ ክብር+ ነጸብራቅና የማንነቱ ትክክለኛ አምሳያ ነው፤+ እሱም በኃያል ቃሉ ሁሉንም ነገር ደግፎ ያኖራል። እኛን ከኃጢአታችን ካነጻ+ በኋላም በሰማይ በግርማዊው ቀኝ ተቀምጧል።+ +4 ስለዚህ ከመላእክት ስም እጅግ የላቀ ስም+ የወረሰ በመሆኑ ከእነሱ የተሻለ ሆኗል።+ +5 ለምሳሌ፣ አምላክ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ”+ ደግሞም “አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል”+ ብሎ ከመላእክት መካከል ስለ የትኛው መልአክ ተናግሮ ያውቃል? +6 ሆኖም የበኩር ልጁን+ እንደገና ወደ ዓለም* የሚያመጣበትን ጊዜ በተመለከተ “የአምላክ መላእክት ሁሉ ይስገዱለት”* ይላል። +7 በተጨማሪም ስለ መላእክት ሲናገር “መላእክቱን መናፍስት፣ አገልጋዮቹን*+ ደግሞ የእሳት ነበልባል ያደርጋል”+ ይላል። +8 ስለ ልጁ ሲናገር ግን እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው፤+ የመንግሥትህ በትርም የቅንነት* በትረ መንግሥት ነው። +9 ጽድቅን ወደድክ፤ ዓመፅን ጠላህ። ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ* ይበልጥ በደስታ ዘይት ቀባህ።”+ +10 ደግሞም እንዲህ ይላል፦ “ጌታ ሆይ፣ አንተ በመጀመሪያ የምድርን መሠረት ጣልክ፤ ���ማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። +11 እነሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ +12 እንደ ካባ፣ እንደ ልብስም ትጠቀልላቸዋለህ፤ ደግሞም እንደ ልብስ ትለውጣቸዋለህ። አንተ ግን ያው ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።”+ +13 ይሁንና “ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ”+ ብሎ ከመላእክት መካከል ስለ የትኛው መልአክ ተናግሮ ያውቃል? +14 ሁሉም መዳን የሚወርሱትን እንዲያገለግሉ የሚላኩ ቅዱስ አገልግሎት* የሚያከናውኑ መናፍስት አይደሉም?+ +8 እንግዲህ የምንናገረው ነገር ዋና ነጥብ ይህ ነው፦ በሰማያት በግርማዊው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ+ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤+ +2 እሱም የቅዱሱ ስፍራና*+ የእውነተኛው ድንኳን አገልጋይ* ነው፤ ይህም ድንኳን በሰው ሳይሆን በይሖዋ* የተተከለ ነው። +3 እያንዳንዱ ሊቀ ካህናት የሚሾመው ስጦታና መሥዋዕት ለማቅረብ ነውና፤ በመሆኑም ይሄኛው ሊቀ ካህናትም የሚያቀርበው ነገር ያስፈልገዋል።+ +4 እሱ ምድር ላይ ቢሆን ኖሮ ካህን ባልሆነ ነበር፤+ ምክንያቱም ሕጉ በሚያዘው መሠረት ስጦታ የሚያቀርቡ ሰዎች አሉ። +5 እነዚህ ሰዎች ለሰማያዊ ነገሮች+ ዓይነተኛ አምሳያና ጥላ+ የሆነ ቅዱስ አገልግሎት ያቀርባሉ፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኑን ለመሥራት በተዘጋጀ ጊዜ “በተራራው ላይ ተገልጦልህ ባየኸው ንድፍ መሠረት ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ ሥራ” ተብሎ ከተሰጠው መለኮታዊ ትእዛዝ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ነው።+ +6 ይሁንና ኢየሱስ እጅግ የላቀ አገልግሎት* ተቀብሏል፤ ልክ እንደዚሁም ለተሻለ ቃል ኪዳን+ መካከለኛ ሆኗል፤+ ይህም ቃል ኪዳን በተሻሉ ተስፋዎች ላይ በሕግ የጸና ነው።+ +7 የመጀመሪያው ቃል ኪዳን ምንም ጉድለት ባይኖረው ኖሮ ሁለተኛ ቃል ኪዳን ባላስፈለገ ነበር።+ +8 አምላክ በሕዝቡ ላይ ጉድለት ስላገኘ እንዲህ ብሎ ተናግሯልና፦ “‘እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።* +9 ‘ይህም ቃል ኪዳን አባቶቻቸውን እጃቸውን ይዤ ከግብፅ ምድር እየመራሁ ባወጣኋቸው ቀን+ ከእነሱ ጋር እንደገባሁት ዓይነት ቃል ኪዳን አይሆንም፤ ምክንያቱም እነሱ በቃል ኪዳኔ አልጸኑም፤ በመሆኑም ችላ አልኳቸው’ ይላል ይሖዋ።* +10 “‘ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና’ ይላል ይሖዋ።* ‘ሕግጋቴን በአእምሯቸው ውስጥ አኖራለሁ፤ በልባቸውም ላይ እጽፋቸዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።+ +11 “‘እነሱም እያንዳንዳቸው የአገራቸውን ሰው፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን “ይሖዋን* እወቅ!” ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም። ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና። +12 ለክፉ ሥራቸው ምሕረት አደርግላቸዋለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም።’”+ +13 “አዲስ ቃል ኪዳን” ሲል የቀድሞውን ቃል ኪዳን ጊዜ ያለፈበት አድርጎታል።+ ስለዚህ ጊዜ ያለፈበትና እያረጀ ያለው ቃል ኪዳን ሊጠፋ ተቃርቧል።+ +11 እምነት ተስፋ የተደረጉትን ነገሮች በእርግጠኝነት መጠበቅ ማለት ነው፤+ በተጨማሪም የምናምንበት ነገር በዓይን የሚታይ ባይሆንም እውን መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። +2 በጥንት ዘመን የኖሩት ሰዎች* የተመሠከረላቸው በዚህ አማካኝነት ነው። +3 ሥርዓቶቹ* የተቋቋሙት በአምላክ ቃል መሆኑን የምንረዳው በእምነት ነው፤ በመሆኑም የሚታየው ነገር ወደ ሕልውና የመጣው ከማይታዩ ነገሮች ነው። +4 አቤል፣ ቃየን ካቀረበው የበለጠ ዋጋ ያለው መሥዋዕት ለአምላክ በእምነት አቀረበ፤+ አምላክ ስጦታውን ስለተቀበለ* በዚህ እምነቱ የተነሳ ጻድቅ እንደሆነ ተመሥክሮለታል፤+ ቢሞትም እንኳ በእምነቱ አማካኝነት አሁንም ይናገራል።+ +5 ሄኖክ+ ሞትን እንዳያይ በእምነት ወደ ሌላ ቦታ ተወሰደ፤ አምላክ ወደ ሌላ ቦታ ስለወሰደውም የትም ቦታ ሊገኝ አልቻለም፤+ ከመወሰዱ በፊት አምላክን በሚገባ ደስ እንዳሰኘ ተመሥክሮለት ነበርና። +6 በተጨማሪም ያለእምነት አምላክን በሚገባ ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ አምላክ የሚቀርብ ሁሉ እሱ መኖሩንና ከልብ ለሚፈልጉትም ወሮታ ከፋይ መሆኑን ማመን ይኖርበታልና።+ +7 ኖኅ+ ገና ስላልታዩት ነገሮች መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ከተቀበለ በኋላ+ አምላካዊ ፍርሃት ያሳየውና ቤተሰቡን ለማዳን መርከብ የሠራው በእምነት ነበር፤+ በዚህ እምነት አማካኝነትም ዓለምን ኮንኗል፤+ እንዲሁም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ለመውረስ በቅቷል። +8 አብርሃም+ በተጠራ ጊዜ ወደፊት ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ በመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ይኖርበት የነበረውን ስፍራ ለቆ ወጣ።+ +9 በባዕድ አገር እንደሚኖር እንግዳ በተስፋይቱ ምድር በእምነት ኖረ፤+ ደግሞም አብረውት የዚሁ ተስፋ ቃል ወራሾች ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር+ በድንኳን ኖረ።+ +10 አምላክ ንድፍ ያወጣላትንና የገነባትን፣ እውነተኛ መሠረት ያላትን ከተማ ይጠባበቅ ነበርና።+ +11 ሣራም የተስፋን ቃል የሰጠው እሱ ታማኝ* እንደሆነ አድርጋ ስላሰበች ዕድሜዋ ካለፈ በኋላም እንኳ ዘር ለመፀነስ በእምነት ኃይል አገኘች።+ +12 ከዚህም የተነሳ እንደሞተ ያህል ከሚቆጠረው+ ከአንድ ሰው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዙና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የማይቆጠሩ ልጆች ተወለዱ።+ +13 እነዚህ ሁሉ የተስፋውን ቃል ፍጻሜ ባያዩም እምነታቸውን እንደጠበቁ ሞቱ፤+ ሆኖም ከሩቅ አይተው በደስታ ተቀበሉት፤+ በምድሩም ላይ እንግዶችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች መሆናቸውን በይፋ ተናገሩ። +14 እንዲህ ብለው የሚናገሩት ሰዎች የራሳቸው የሆነ ቦታ ለማግኘት ከልብ እንደሚሹ ያሳያሉ። +15 ይሁንና ትተውት የወጡትን ቦታ ሁልጊዜ ቢያስቡ ኖሮ+ መመለስ የሚችሉበት አጋጣሚ በኖራቸው ነበር። +16 አሁን ግን የተሻለውን ይኸውም ከሰማይ የሆነውን ስፍራ ለማግኘት ይጣጣራሉ። ስለዚህ አምላክ፣ እሱን አምላካችን ብለው ቢጠሩት አያፍርባቸውም፤+ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና።+ +17 አብርሃም በተፈተነ ጊዜ+ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ እስከ ማቅረብ ድረስ እምነት አሳይቷል፤ የተስፋን ቃል በደስታ የተቀበለው ይህ ሰው አንድያ ልጁን መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ተዘጋጅቶ ነበር፤+ +18 ይህን ያደረገው “ዘርህ የሚጠራልህ በይስሐቅ በኩል ይሆናል” ተብሎ ተነግሮት እያለ ነው።+ +19 ይሁንና አምላክ ከሞት እንኳ ሳይቀር ሊያስነሳው እንደሚችል ተገንዝቦ ነበር፤ ልጁንም ከሞት አፋፍ መልሶ አገኘው፤ ይህም እንደ ምሳሌ ሆኖ አገልግሏል።+ +20 ይስሐቅም ወደፊት ከሚሆኑት ነገሮች ጋር በተያያዘ ያዕቆብንና+ ኤሳውን+ በእምነት ባረካቸው። +21 ያዕቆብ መሞቻው በተቃረበ ጊዜ+ የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን የባረካቸውና+ የበትሩን ጫፍ ተመርኩዞ ለአምላክ የሰገደው በእምነት ነበር።+ +22 ዮሴፍ ሊሞት በተቃረበ ጊዜ ስለ እስራኤል ልጆች ከግብፅ መውጣት* በእምነት ተናገረ፤ ስለ አፅሙም* መመሪያ* ሰጣቸው።+ +23 ሙሴ ከተወለደ በኋላ ወላጆቹ መልኩ የሚያምር ሕፃን+ መሆኑን ስላዩ የንጉሡን ትእዛዝ ሳይፈሩ+ ለሦስት ወር የሸሸጉት+ በእምነት ነበር። +24 ሙሴ ካደገ በኋላ+ የፈርዖን የልጅ ልጅ* ተብሎ ለመጠራት በእምነት እንቢ አለ፤+ +25 በኃጢአት ከሚገኝ ጊዜያዊ ደስታ ይልቅ ከአምላክ ሕዝብ ጋር መንገላታትን መረጠ፤ +26 ምክንያቱም ቅቡዕ* ሆኖ የሚደርስበት ነቀፋ በግብፅ ከሚገኝ ውድ ሀብት የላቀ እንደሆነ አስቧል፤ የሚከፈለውን ወሮታ በትኩረት ተመልክቷልና። +27 ደግሞም በእምነት ግብፅን ለቆ ወጣ፤+ ሆኖም ይህን ያደረገው የንጉሡን ቁጣ ፈርቶ አይደለም፤+ የማይታየውን አምላክ+ እንደሚያየው አድርጎ በጽናት ቀጥሏልና። +28 አጥፊው የበኩር ልጆቻቸውን እንዳይገድል* ሙሴ ፋሲካን* ያከበረውና መቃኖቹ ላይ ደም የረጨው በእምነት ነው።+ +29 እስራኤላውያን በደረቅ ምድር የሚሄዱ ያህል ቀይ ባሕርን በእምነት ተሻገሩ፤+ ይሁንና ግብፃውያን እንዲህ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሰመጡ።+ +30 እስራኤላውያን የኢያሪኮን ግንብ ሰባት ቀን ከዞሩት በኋላ በእምነት ወደቀ።+ +31 ዝሙት አዳሪዋ ረዓብ ታዛዥ ሳይሆኑ ከቀሩት ሰዎች ጋር ከመጥፋት የዳነችው በእምነት ነው፤ ምክንያቱም ሰላዮቹን በሰላም ተቀብላለች።+ +32 እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን እላለሁ? ስለ ጌድዮን፣+ ስለ ባርቅ፣+ ስለ ሳምሶን፣+ ስለ ዮፍታሔ፣+ ስለ ዳዊት+ እንዲሁም ስለ ሳሙኤልና+ ስለ ሌሎቹ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ ያጥረኛል። +33 እነዚህ ሰዎች በእምነት መንግሥታትን ድል አድርገዋል፤+ ጽድቅን አስፍነዋል፤ የተስፋን ቃል ተቀብለዋል፤+ የአንበሶችን አፍ ዘግተዋል፤+ +34 የእሳትን ኃይል አጥፍተዋል፤+ ከሰይፍ ስለት አምልጠዋል፤+ ደካማ የነበሩት ብርታት አግኝተዋል፤+ በጦርነት ኃያላን ሆነዋል፤+ ወራሪ ሠራዊትን አባረዋል።+ +35 ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀብለዋል፤+ ሌሎች ወንዶች ግን ቤዛ ተከፍሎላቸው ነፃ መሆን ስላልፈለጉ ከባድ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፤ ይህን ያደረጉት የተሻለ ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ ነው።